diff --git "a/data/amh/train.tsv" "b/data/amh/train.tsv" new file mode 100644--- /dev/null +++ "b/data/amh/train.tsv" @@ -0,0 +1,1312 @@ +category headline text url +sports የስፖርት ኮከቦች እና የንግድ ምልክቶቻቸው- ከቦልት እስከ ክርስቲያኖ ሮናልዶ "የአትሌቲክሱ ዓለም ኮከብ እና ፈጣኑ ሰው ዩሴን ቦልት ከውድድር በፊት እና በኋላ የሚያሳየውን ታዋቂ የሆነውን ምልክት ለንግድ ምልክትነት ለመጠቀም ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛል። እሱ ብቻ ግን አይደለም የሚለይበትን ምልክት የሚያሳይ ኮከብ። የአሜሪካ የፓተንት እና የንግድ ምልክት ቢሮ እንደገለጸው ቦልት ታዋቂውን ምልክቱን በንግድ ምልክትነት ለማስመዝገብ ማመልከቻውን ነሐሴ 2014 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ አስገብቷል። መቀመጫቸውን ዋሽንግተን ያደረጉት የንግድ ምልክት ጠበቃው ጆሽ ገርበን “አንድ እጁ ታጥፎ ወደ ጭንቅላቱ ሲጠቆም ሌላኛው እጁ በተመሳሳይ አቅጣጫ ወደ ላይ ከፍ ብሎ  እንደሚዘረጋ” ያሳያል ብለዋል። ቦልት ይህን የሚያደርገው ዝነኛ የድል አድራጊነቱን የሚያሳየውን አርማ የንግድ ምልክት በማድረግ ልብሶችን እና የፋሽን ዕቃዎችን ለመሸጥ በማሰቡ ነው። ታዋቂዋ የአሜሪካ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሜጋን ራፒኖ ጎል ካስቆጠረች በኋላ ደስታዋን በምትገልጽበት የተለየ መንገድ ትታወቃለች። ከአሜሪካ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫ እና የኦሎምፒክ ወርቅ አሸናፊ ለመሆን የበቃችው ሜጋን እጆቿን ዘርግታ በምታሳየው ፈገግታ ወይም እርካታ ትለያለች። እአአ በ2019 በፊፋ ኮከብ ተጫዋች ለመሆን የበቃችው ተጫዋቿ ቀላል እና በአድናቂዎች የተወደደ የደስታ አገላለጽ ነው ያላት። ሞ ፋራህ የበርካታ የኦሎምፒክ፣ የዓለም እና የአውሮፓ የረዥም ርቀት ሩጫዎች ሻምፒዮን ነው።  ብዙዎችም ""የእንግሊዝ የምንግዜም ታላቅ አትሌት"" እያሉ ይጠሩታል። ውድድሮችን ሲያሸንፍ ""ሞቦት"" በማሳየት በጣም ታዋቂ ነው። የሁለቱን አጅቹን ጣቶች በማገናኘት የጭንቅላቱ አናት ላይ በማድረግ የስሙ መነሻ የሆነውን ‘M’ የእንግሊዘኛ ፊደል ይሠራል። ታዋቂው ፖርቹጋላዊ የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ጎል ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን የሚገልጽበት መንገድ አዘጋጅቷል። ይሮጥና ይዘላል፣ አየር ላይ እያለ ይዞርና እጆቹን ወደ ጎን እየወረወረ “ሲ” እያለ ይጮሃል። “ሲ” በፖርቹጋል ቋንቋ አዎ እንደማለት ነው። ደቡብ ኮሪያዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሶን ሄንግ-ሚን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለሚሳተፈው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ይጫወታል። አጥቂው ጎል ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን የሚገልጽበት የራሱን ልዩ ምልክት አዘጋጅቷል። አውራ እና ጠቋሚ ጣቶቹን በማገናኘት ያንን ቅጽበት ለመቅረጽ የሚረዳውን ካሜራን የሚወክል ቅርጽ ይሠራል። ስለእነዚህ ምልክተቶች ምን ያስባሉ? ቦልት ዝነኛ ምልክት ያለው ብቸኛው ሰው ባይሆንም በዓለም ዙሪያ በጣም ታዋቂው ነው ማለት ግን ይቻላል። የንግድ ምልክት ማመልከቻው ከተሳካ ደግሞ ምናልባት የበለጠ ዕውቅና ያገኛል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/ceknk30j2xxo +sports እግር ኳስ፡ ዩናይትድ፣ አርሴናል፣ ቼልሲ . . . ምን አስበዋል? የስፖርት ጋዜጦች ስለ እግር ኳስ ምን እያሉ ነው? በሚቀጥለው ጥር የሚከፈተው የዝውውር መስኮትስ ምን ያሳየን ይሆን?ዋና ዋናዎቹን በዚሀች አጭር ዘገባ እንዳስሳለን። አላንድ፡ የቦሩሲያ ዶርትመንዱ አጥቂ ኧርሊንግ ብራውት አላንድ ፈላጊው በዝቷል። አሁን ደግሞ ቼልሲዎች ተጫዋቹን ለማስፈረም ዕቅድ እንዳላቸው እየተነገረ ነው። ነገር ግን ማንቸስተር ሲቲዎች ተጫዋቹ የእኛ ነው እያሉ ነው። ይህን የዘገበው '90 ሚኒት' ጋዜጣ ነው። ቼልሲ አላንድንና የዌስትሃሙን ዴክሌን ራይስ ለማስፈረም ሰባት ተጫዋቾቹን ሊሸጥ እንደሚችል ስካይ ስፖርት ዘግቧል። ባርክሌይ፣ አሎንሶ፣ ሩዲገር፣ ክሪስቴንሰን፣ ጆርጊንሆ፣ ድሪንክዎተርና ሞሰስ ለገበያ ሊቀርቡ እንደሚችሉ ተነግሯል። በሌላ በኩል ማንቸስተር ዩናይትድም አላንድን ማስፈረም ይፈልጋል። ነገር ግን የተጫዋቹ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ከዩናትድ ጋር ያለው ግንኙነት ሰላማዊ ስላልሆነ ችግር ሊፈጥር ይችላል እየተባለ ነው ይላል ሚረር ባወጣው ዘገባ። ዩናይትድ አላንድን ማስፈረም ካልቻለ ፊቱን ወደ ኤቨርተኑን ዶሞኒክ ካልቨርት-ሌዊን ሊያዞር ይችላል። ሩዲገር፡ ቼልሲ ሊሸጣቸው ካሰባቸው ተጫዋቾች መካከል የሆነው ጀርመናዊው አንቶኒዮ ሩዲገር በፓሪስ ሴይንት ዠርሜይን ይፈለጋል። ይህን ያተመው የፈረንሳዩ 'ለ ፓሪዚያ' ነው። ሊቨርፑል፡ ቀያዮቹ የሪያል ማድሪዱን ብራዚላዊ ተከላካይ ኤደር ሚሊቶን ለማስፈረም አቅደዋል። አርጀንቲናዊው የ34 ዓመት ተጫዋች እዝቄል ጋሬይም በሊቨርፑሎች እየተፈለገ ነው። ይህን ዜና ያሰማው የስፔኑ ቶዶፊቻሄስ ነው። አርሴናል፡ የመድፈኞቹ አሠልጣኝ ማይክል አርቴታ የሪያል ማድሪዱን ብራዚላዊ አጥቂ ቪኒሺዬስ ጁኒዬርን ወደ ኤሜሬትስ ለማምጣት አቅደዋል። የ22 ዓመቱ አጥቂ ወደ ኤሜሬትስ በሚቀጥለው ጥር ወር በውሰት ሊመጣ ይችላል ተብሏል። አርቴታ ከወጣቱ አጥቂ በተጨማሪ የ28 ዓመቱን ስፔናዊ አማካይ ኢስኮ፤ ይፈልገዋል። ነገር ግን ተጫዋቹ ወደ ዩቬንቱስ መሄድን ይመርጣል - 'የደይሊ ስታር' እንደዘገበው። ባርሴሎና፡ የካታሎኑ ክለብ የአርሴናሉን ተከላካይ ሹከርዳን መስጣፊን ይፈልገዋል ይላል 'ስፖክስ' ጋዜጣ። የ28 ዓመቱ ሙስጣፊ ከአርሴናል ጋር ያለው ውል እየተገባደደ ነው። ጆንስ፡ የደርቢ ካውንቲ አሠልጣኝ የሆነው ዋይኒ ሩኒ የቀድሞ የቡድን አጋሩ ፊል ጆንስን ማስፈረም ይሻል። እንደ 'ሜትሮ' ዘገባ ከሆነ በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት ዕድል ያጣው ጆንስ በዌስትብሮምም ይፈለጋል። የአውሮፓ እግር ኳስ የዝውውር መስኮት በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ጥር ወር ይከፈታል። ማን ወደ የት ይሄዳል? ጊዜ ይፈታዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-55435608 +business ዓለምን ካስጨነቃት የዋጋ ንረት ተጠቃሚዎቹ እነማን ናቸው? ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተጽእኖ ሳያገግም የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት የገጠመው የዓለም ምጣኔ ሃብት ከቀውስ አዙሪት ውስጥ አልወጣም። የነዳጅ እና የምግብ ምርቶች የዋጋ ንረት በመላው ዓለም በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ከባድ አድርጎታል። ታዲያ ዓለም በዋጋ ንረት በምትጨነቅበት በአሁኑ ወቅት በተለየ ሁኔታ ትርፍ እያጋበሱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ዘርፎች አሉ። እነዚህ ከዋጋ ንረት የሚያተርፉ ድርጅቶች የትኞቹ ናቸው? https://www.bbc.com/amharic/articles/crgj31l8mzzo +health ኮሮናቫይረስ፡ በቫይረሱ የሞቱት የሮማኒያው ከንቲባ በምርጫ አሸነፉ "በኮሮናቫይረስ የሞቱት የሮማኒያው ከንቲባ በቅርቡ የተደረገውን ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ አሸንፈዋል። 64 በመቶ የመራጮችንም ድምፅ ማግኘት ችለዋል። በደቡባዊቷ ሮማኒያ በምትገኘው ግዛት ዴቬሴሉ ከንቲባ የነበሩት ኢዮን አሊማን ለሶስተኛ ጊዜም አሸንፈዋል። ከሁለት ሳምንታት በፊት በመዲናዋ ቡካሬስት ህይወታቸው ያለፈው የቀድሞው ከንቲባ ስም ከተመራጮች ዝርዝር ውስጥ ነበር። የተመራጮች ዝርዝር ቀድሞ በመታተሙ ስማቸውን ማስወገድ እንዳልተቻለም ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል። በዚህም ምክንያት የሞተ ሰው ከንቲባ ሆኖ እንደተመረጠም ተገልጿል። ሌላ ምርጫ እንደሚደረግም ባለስልጣናቱ ለሮይተርስ የተናገሩ ሲሆን በርካታ የግዛቲቷ ነዋሪዎች የቀድሞ ከንቲባቸውን ቀብር በመጎብኘት ሃዘናቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው። በርካታ የመንደሪቷ ሰዎችም በመካነ መቃብሩ ተሰባስበው መታየታቸውን በማህበራዊ ሚዲያ የተጋሩ ቪዲዮዎች አሳይተዋል። ""ይህ የአንተ ድል ነው"" ሲል አንድ ግለሰብ ሲናገር ተሰምቷል። ""እውነተኛ ከንቲባችን ነበ��"" በማለት ሌላ ግለሰብ ለአካባቢው የቴሌቪዥን ጣቢያ መናገሯን ሮይተርስ ዘግቧል። ""ሁሉንም የግዛቲቷን ነዋሪ በእኩል አይን ያይ የነበረ፤ ህግንም ያከብር ነበር። እንደሱ አይነት ከንቲባ መቼም አይኖረንም"" ግለሰቧ ማለቷንም ሮይተርስ አስነብቧል። የቀድሞ የባህር ኃይል አባል የነበሩት ኢዮን የግራ ክንፍ የሚያዘመው የሶሺያል ዲሞክራት ፓርቲ (ፒኤስዲ) አባል ነበሩ፤ በትናንትናው ዕለትም 57 አመታቸው ይሆን ነበር። በከንቲባነታቸው በህዝባቸው በከፍተኛ ሁኔታ መወደዳቸውም በፓርቲያቸው ዘንድ ጥሩ ስም አስገኝቶላቸዋል። ፓርቲያቸው በአሁኑ በተደረገው አገራዊ ምርጫ በተለያዩ ከተሞችና የምክር ቤቶች መቀመጫቸውን ለቀኝ ክንፍ አክራሪው ዩኤስ አር ፕላስ አሊያስና የአገሪቱን የመንግሥት ስልጣን በበላይነት ለተቆጣጠረው ሴንትሪስት ሊበራል አጥተዋል። በበርካታ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት የፍትህ ስርአቱ እንዲሻሻልና የሰፈነው ሙስና እንዲቆም የሚጠይቁ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፎችን ተከትሎም ነው ፒኤስዲ በርካታ መቀመጫዎችን በፖርላመንት በድምፅ እንዲያጣ የተደረገው። የቀድሞ ከንቲባው ኢዮን ከሞቱ በኋላ በምርጫ ማሸነፍ በአገሪቷ የመጀመሪያው ክስተት አይደለም በጎሮጎሳውያኑ 2008 ኔኩላይ ኢቫስኩ የተባሉት ከንቲባም በጉበት በሽታ ከሞቱ በኋላ የቮይነስቲ ግዛት ከንቲባ ሆነዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54336166 +health ኮሮናቫይረስ፡ አውሮፕላኖች እንዴት ነው በፀረ- ተህዋሲያን የሚፀዱት? "የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ቀጥ ብሎ የነበረውን የአለም የንግድ እንቅስቃሴን ለመመለስ በርካታ ጥረቶች እየተደረገ ነው። በተለያዩ አገራትም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጥለዋቸው የነበሩ መመሪያዎችን እያላሉ ይገኛሉ። የወረርሽኝ ስርጭቱን ለመግታት አገራት አስተላልፈዋቸው ከነበሩ መመሪያዎች መካከል ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማቆም፣ አየር ማረፊያዎቻቸውንና ድንበሮቻቸውን መዝጋት ይገኙበታል። በዚህም የተነሳ በርካታ የኢንዱስትሪ ዘርፎች በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ሲሆን በተለይም የአየር ትራንስፖርት ዘርፉ እንዲሽመደመድ ምክንያት ሆኗል። ከሰሞኑ አገራቱ ዘግተዋቸው የነበሩ ድንበሮቻቸውን ከፍተዋል፤ አለም አቀፍ አየር መንገዶቹም በረራዎችን ጀምረዋል። የአለም አቀፉ አቪየሽን ድርጅት የአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ እንዲያንሰራራና ተጓዦችም ደህንነታቸቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲጓዙ ለማድረግ እንደ መመሪያነት የሚያገለግል አንድ ሰነድ አውጥቷል። በዚህም መመሪያ ውስጥ ከተካተቱት ጉዳዮች መካከል አውሮፕላኖች በምን መንገድ በፀረ- ተህዋሲያን መፀዳት እንዳለባቸውና የፅዳት ድግግሞሽንም ይመለከታል። እንዲሁ ከላይ ከላይ ሲታይ የአየር በረራና አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የሚጣጣሙ አይመስሉም ። ነገር ግን ተቆጣጣሪ አካላት የተለያዩ ፕሮቶኮሎችን በማውጣት አስፈላጊ የሚባሉ የፅዳት መመሪያዎችን ለመተግበር ቀን ተሌት ደፋ ቀና በማለት ላይ ናቸው። ለአየር በረራዎች በዋነኝነት የሚያስፈልገው ፈጣንና፣ በቅልጥፍና የተሞላ ውጤታማ ፀረ- ተህዋሲያን የፅዳት ስርዓት መዘርጋት ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ፍቃድ ያላቸው የፀረ- ተህዋሲያን ፅዳት በሚታዩና፣ ተደራሽ በሆኑ አካላት ላይ ጨርቅን እንዲሁም ተንቀሳቃሽ መርጫን በመጠቀም ማፅዳት ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ። ነገር ግን ሁለቱም የማፅጃ መንገዶች በሰዎች አማካኝነት የሚካዱ ከመሆናቸው አንፃር ውጤታማነታቸውን የሚቀንስ ሲሆን መደረስ የማይችሉ የአውሮፕላኑ አካላትም ላይ ክፍተትን ይፈጥራሉ ተብሏል። ኦክስጅንና ኦዞን በሌላ መልኩ ""አቶሚክ ኦክስጅንን"" እንደ ፀረ-ተህዋሲያነት በመጠቅም አካባቢን ለማፅዳት ተጀምሯል። ከዚህም በተጨማሪ አምቡላንሶችን ለማፅዳት የሚጠቀሙበትን ፀረ ተህዋሲያንንም ለአውሮፕላን የውስጥ ክፍል ለማፅዳት እየታሰበበት ነው። ነገር ግን እነዚህ ማፅጃዎች ባላቸው የንጥረ ነገር በተለይም 'ኦክሳይድ' ባለው ባህርይ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ላይ ጉዳት ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆን በሚለው ስምምነት ላይ አልተደረሰም። መቶ በመቶ ውጤታማ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ በሌለበት ሁኔታ ሌላኛው አማራጭ ""የኦዞን"" ንጥረ ነገሮችን መጠቀም ነው። በአሁኑ ወቅት ኦዞን በአውሮፕላን አካላት ላይ አገልግሎት ላይ ባይውልም በመጠጥ ቤቶችና በተለያዩ የንግድ ተቋማት ላይ በፀረ-ተህዋሲያን ማፅጃነት እያገለገለ ይገኛል። አካባቢውን የኦዞን ንጥረ ነገሮችን በመርጨት ውጤታማ የሆነ ፅዳትን ማግኘት ይቻላል። ነገር ግን ይህ ንጥረ ነገር በከፍተኛ መጠን ሲሆን ለሰዎች ጎጅ በመሆኑ ባለሙያን በመጠቀም መንገደኞች በሌሉበት ሁኔታ ሊረጭ ይገባል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ኦዞን ላይ ያለው ዋነኛ ጥያቄም የኦክሳይድ ንጥረ ነገር መጠኑ ነው፤ 'በአውሮፕላን የውስጥ አካልና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ላይ ያለው ተፅእኖ ላይ መስማማት አልተቻለም። 'አየኖችና የአልትራቫዮሌት ጨረር ' በላብራቶሪ ውስጥ ተሞክሮ ውጤታማ የሆነው ከከባቢ አየር የሚለቀቀውን የውሃ ትነት ውስጥ የኦክስጅንና ሃይድሮጅን ንጥረ ነገሮችን ለይቶ በማውጣት ፀረ ተህዋሲያንን መፍጠር ነው። ይህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ መንገድ በጣም አድካሚና ለሁለት ሰዓታት ያህልም የሚወስድ ጊዜን ይፈጃል። ሆኖም ይሄ መንገድ በከፍተኛ ሁኔታ ውጤታማና መቶ በመቶ የሚተማመኑበት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ፀረ ተህዋሲያኑ ቀላልና ተንቀሳቃሽ በሆነ መልኩ ትልልቅ የአውሮፕላን አካሎችን ማፅዳት ቢቻልም ለማፅዳት ግን ረዘም ያለ ጊዜ መውሰድ ያስፈልጋል። ሌላኛው ደግሞ ሲ የሚባለው የአልትራቫዮሌት ጨረር ሲሆን ይህ ጨረር ሳርስ የተባለውን የኮሮናቫይረስ አይነት ማጥፋት ይችላል። ለዚያም ነው ከፍተኛ ወጪ የሌላቸው ጨረሮች የአውሮፕላን አካላትን ለማፅዳት እየተነደፉ እንዲሁም እየተመረቱ ያሉት። ይህንም ተከትሎ በገበያው ላይ የነዚህ ጨረሮች ፍላጎት በመጨመሩ ምክንያት የአልትራቫዮሌት ጨረሮችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች ምርታቸው በሚቀጥሉት አራት አመታት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምርም ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በርካታ አማራጮች በርካታ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ አማራጮች ከመኖራቸው አንፃር በተለያየ ሂደትም ላይ ናቸው። አሁንም ቢሆን የትኛው የበለጠ ተስማሚ እንደሆነም እስካሁንም አይታወቅም። የትኛው የፀረ ተህዋሲያን ስርአት የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ከተቻለ በኋላ ምን ያህል ጊዜም ይወስዳል የሚለውን ማየት አስፈላጊ እንደሆነም እየተነገረ ነው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አሁንም ስጋት ሆኖ ባለበት ወቅት በርካታ አየር መንገዶች በረራ መጀመራቸው ጋር ተያይዞ ቫይረሱ እንዳይሰራጭ የማድረግ ከፍተኛ ኃላፊነትና ሸክም ተጥሏባቸዋል። የአውሮፕላኑ ሰራተኞች፣ መንገደኞችን ደህንነት በሚያስጠብቅ መልኩ አውሮፕላኖቹ በፀረ ተህዋሲያን መፀዳትም ግዴታ ነው። እነዚህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ ዘዴዎች ቫይረሱን መግታት ብቻ ሳይሆን የአየር መንገድ ኃላፊዎችም ሆነ ተቆጣጣሪዎች የሚያስወጣቸውን ዋጋና እንዲሁም ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መንገድ መፅዳት የሚችሉበትን ሁኔታ መገምገም ይጠበቅባቸዋል። በአንድ መልኩ የአየር ትራንስፖርቱ ወደቀደመ ሁኔታ እንዲመለሱ ግፊት እያደረጉ ሲሆን በሌላ መልኩ በዚህ ወረርሽኝ መካከል የተጓዦች ደህንነት በተጠበቀ መልኩ አገልግሎታቸውን መመለስና በወረርሽኙ ምክንያት ያጡትን ገቢ ለማግኘትም አጣጥመው መሄድ ይጠበቅባቸዋል። በተለይም አውሮፕላኖቹ የሚፀዱበትን ደረጃና ያለውን የስጋት መጠንን መቀነስና፤ የሚፀዳበትን ጊዜ አጣጥመው መሄድም ይጠበቅባቸዋል። የመንገደኞችን ጤንትና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠትም አየር መንገዶቹ እነዚህን ተግባራት እንዲያከናውኑም አለም አቀፉ አቪየሽንም መመሪያ ሰጥቷል። ከአለም አቀፉ አቪየሽን ቡድንና፣ የትራንስፖርት ዘርፍ ተመራማሪዎች የተውጣጡ ግለሰቦችም ውጤታማ የሆኑትን የፀረ ተህዋሲያን የማፅጃ ዘዴዎችንም ለመቀየስ ከፍተኛ ምርምሮችን እያደረጉም ነው፤ የተለያዩ መመሪያዎችንም በማውጣትም ላይ ይገኛሉ።" https://www.bbc.com/amharic/53627279 +politics ቤኒቶ ሙሶሊኒ ላይ የተኮሰችው አየርላንዳዊት "ጊዜው በፈረንጆቹ ሚያዝያ 7 1926 ነበር። ቦታው ደግሞ የጣልያኗ መዲና ሮም። የሃገሬው ሰው በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከነበሩ ኃያላን መካከል አንዱ የነበረውን ግለሰብ ለማየት ተኮልኩሏል። አንዲት አየርላንዳዊት ሴት ግን በሰውዬው ወሬ ብዙም አልተማረከችም። ዓላማዋ ሌላ ነበር። ድንገት የተኩስ ድምፅ ተሰማ። ሰው ወዲያ ወዲህ ተበታተነ። ለተሰበሰበው ሰው መልዕክቱን ሲያስተላልፍ የነበረው ቤኒቶ ሙሴሊኒም ወደኋላ ተዘረጋ። ጥይቷ የፈለቀችው ከአየርላንዳዊቷ ሴት አፈሙዝ ነበር። ዒላማዋን አልሳተችም። የሙሶሊኒን አፍንጫ ቦረሸችው። ሙሶሊኒ ግን አልሞተም። የጣልያኑ መሪ ከተቃጣበት የግድያ ሙከራ መትረፍ ቻለ። አውሮፓውያን በ20ኛው ክፍለ ዘመን ፋሺስታዊነትን ለመከላከል ከፈፀሟቸው ድርጊቶች መካከል የቫዮሌት ጊብሰን ድርጊት ሁሌም ይነሳል። ሙሶሊኒን ለመግደል ጥረት ካደረጉ አራት ሰዎች መካከል የተሻለ ሙከራ ያደረገችው እሷ ናት። አየርላንዳዊቷ ሙሶሊኒን ለመግደል ሙከራ ካደረገች እነሆ መቶ ዓመት ሊደፍን ጥቂት ዓመታት ይቀሩታል። ይህን ለማሰብ ደብሊን ውስጥ መታሰቢያ እንዲቆምላት ሥራዎች ተጀምረዋል። ቫዮሌት ሙሶሊኒ ላይ ሶስት ጥይቶች ተኩሳለች። አራተኛውን ልትለቀው ስትል ግን ሽጉጧ ነከሰ። ይሄኔ የሙሶሊኒ ጠባቂዎች የከበቧት። የከተማዋ ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ በቁጥጥር ሥር ባያውሏት ኖሮ የጠባቂዎቹ ጡጫ ሲሳይ ትሆን ነበር። ጣልያን ውስጥ ታሥራ ከቆች በኋላ ወደ እንግሊዝ እንድትሄድ ተደረገ። ይህ የሆነው ጣልያን ውስጥ የፍርድ ሂደቱ ቢካሄድ ውርደት ይሆናል በሚል ነው ይባላል። ቫዮሌት እንግሊዝ ውስጥ ባለው የቅዱስ አንድሩ የአእምሮ ሕሙማን መታከሚያ ማዕከል ገብታ በስተመጨረሻ በፈረንጆቹ 1956 ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ከእንግሊዛዊ አየርላንዳዊ ከበርቴ ቤተሰብ የተወለደችው ቫዮሌት ክዊን ቪክቶሪያ ውስጥ ነበር የምትኖረው። አሁን የደብሊን ከተማ በስሟ መታሰቢያ እንዲቆም ረቂቅ አፅድቆ ወደ ሥራ ገብቷል። የከተማዋ አስተዳደር የሴትዬዋ ድርጊት በታሪክ መዝገብ ብዙም ባለመዘገቡ የሠራችውን 'ፀረ-ፋሺስት' ሥራ የሚዘክር መታሰቢያ ሊቆምላት ይገባል ብሏል። ""የብሪታኒያ መንግሥትና ቤተሰቦቿ የሷን ድርጊት እንደ 'እብድ ሰው' ተግባር ሳይሆን እንደ ፖለቲካ ሊያዩት ይገባል"" ይላል ረቂቁ። በጀግንነቷ ምክንያት የተሰቃየችው ረቂቁን ለደብሊን ከተማ ምክር ቤት ያቀረቡት ገለልተኛው የከተማው ምክር ቤት አባል ማኒክስ ፍሊን ""ቫዮሌት ጊብሰን በአየርላንድና እንግሊዝ መንግሥታት የተረሳች ናት"" ሲሉ ይከራከራሉ። ""ልክ እንደበርካታ ሴቶች እጅግ ድፍረት የተሞላበት ድርጊት ብትፈፅምም ተገፍታለች"" ሲሉ ለቢቢሲ ሰሜን አየርላንድ ጣቢያ ይናገራሉ። ""ቫዮሌት ጊብሰን የሠራችው ሥራ የሚያሳፍር ነው' 'እብድ ናት' በማለት እንድትደበቅ ተደርጋለች።"" የቫዮሌት ቤተሰቦች ለመታሠቢያ ኃውልቱ ፈቀድ ሰጥተዋል። በሚቀጥሉ��� ሳምንታትም ረቂቁ ፀድቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ይጠበቃል። መታሰቢያ በልጅነቷ ያደገችበት ደብሊን ውስጥ የሚገኘው የሜሪዬን አደባባይ እንዲሆንም ሐሳብ ቀርቧል። ደብዳቤ ለቸርችል የቫዮሌት ታሪክ ወደ አደባባይ ብቅ ያለው በፈረንጆቹ 2014 አርቲኢ የተሰኘው ራድዮ ጣቢያ በሠራው ዘጋቢ ቅንብር ምክንያት ነው። ዘገባው 'ሙሶሊኒ ላይ የተኮሰችው ሴት' ከተሰኘው መፅሐፍ ላይ የተወሰደ ነው። ታሪኳ ላይ እንደተመዘገበው ቫዮሌት ከቅዱስ አንድሩ ሆስፒታል እንድትለቀቅ በወቅቱ ለነበሩ ኃያላን መሪዎች ደብዳቤ ፅፋ ነበር። ከእነዚህ መካከል የአሁኗ የእንግሊዝ ንግሥት ኤሊዛቤት ይገኙበታል። ሌላኛው ደብዳቤ የተላከው በወቅቱ የእንግሊዝ መሪ ለነበሩት ዊንስተን ቸርችል ነበር። ቸርችል በደብሊን ከተማ ባደጉ ወቅት ከቫዮሌት ጋር እውቅና ሳይኖራቸው አይቀርም ይላል ታሪኳን የሚዘግበው መፅሐፍ። ለዊንስተን ቸርችል የተፃፈው ደብዳቤ አሁንም አለ። ነገር ግን በወቅቱ ደብዳቤው ለቸርችል ሊደርስ አልቻለም። የራድዮ ዘገባው አዘጋጆች ወደ ጣልያን ሄደው በሠሩት ጥናት መሠረት ሙሶሊኒ ላይ ከተሞከሩ ግድያዎች መካከል ብዙ መረጃ የተሰበሰበው በቫዮሌት ዙሪያ ነው። ""ይህን ድርጊት የፈፀመው ወንድ ቢሆን ኖሮ ይሄን ሃውልት ወይም ሌላ መታሰቢያ ተሠርቶለት ነበር። እሷ ሴት ስለነበረች ታሠረች። እኛ ታሪኩን ለሕዝብ ይፋ በማድረጋችን ደስተኞች ነን"" ይላሉ የዘገባው አዘጋጆች። ቤኒቶ ሙሶሊኒ ማነው? የሙሶሊኒ ብሔራዊ ፋሺስት ፓርቲ ጣልያን ውስጥ ወደ ሥልጣን የመጣው ከአንደኛው ዓለም ጦርነት በኋላ ነው። 'ብላክሸርትስ' በተሰኙ ታጣቂዎች የሚደገፈው ፖርቲ ተቀናቃኞችን በኃይል ያስፈራራ ነበር። ፋሺስቱ ፓርቲ በ1920ዎቹ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ዴሞክራሲያዊ የሚባሉ ተቋማትን አፈራረሰ። ሙሶሊኒ የጣልያን አምባገነናዊ መሪ ሆነው የተሾሙት በፈረንጆቹ 1925 ነበር። ሙሶሊኒ በስፔን የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት የጁኔራል ፍራንቺስኮ ፍራንኮ ደጋፊ ነበር። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ደግሞ የአዶልፍ ሂትለር ቀኝ እጅ ነበር። ሙሶሊኒ የሂትለርን አንዳንድ ፖሊሲዎች ወስዶ በ1938 የጣልያኑ አይሁዳዊያን ሙሉ በሙሉ መብታቸው እንዲገፈፍ አድርጎ ነበር። በአይሁዶች ጅምላ ጭፍጨፋ [ሆሎኮስት] ወቅት ከ7 ሺህ 500 በላይ የጣልያን አይሁዶች እንደተገደሉ ይታመናል። ኢትዮጵያ በጣልያን ለሁለተኛ ጊዜ የተወረረችው በሙሶሊኒ አምባገነናዊ ሥርዓት ወቅት ነበር። ሙሶሊኒ ከምዕራባዊያን ጦር ለማምለጥ ሲሞክር በጣሊያን ነፃ አውጭዎች ተይዞ የተገደለው በፈረንጆቹ 1945 ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-56145284 +business ኮሮናቫይረስና የነዳጅ ዘይት ምን አገናኛቸው? "ኮሮናቫይረስ የማይነካው ነገር እንደሌለ እየታየ ነው። በየሰበብ አስባቡ እያሻቀበ የነበረውን ነዳጅ ዘይትን ሊነካው ዳርዳር እያለ ነው። በሽታው አሳሳቢ ደረጃ ላይ በደረሰበት በአሁኑ ጊዜ የዓለማችን ትልልቆቹ የነዳጅ አምራች አገራት በሽታው ካስከተለው ችግር ለመቋቋም በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ምርታቸው ሊቀንስ ይችላል እየተባለ ነው። የነዳጅ ዋጋን ለመደገፍ እርምጃ እንዲወሰድ እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት የነዳጅ አምራች አገራት ማህበር የሆነው ኦፔክ እና አጋሮቹ በዚህ ሳምንት ስብሰባ እንደሚቀመጡ እየተጠበቀ ነው። • ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በቻይና • አባቱ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠረው አካል ጉዳተኛ ታዳጊ ሞተ በጥር ወር መጀመሪያ ላይ የነዳጅ ዋጋ በዓመት ውስጥ ከታየው ከፍ ብሎ በ20 በመቶ ካሻቀበ በኋላ አሽቆልቁሎ ዝቅተኛው ዋጋው ላይ ይገኛል። ስለምን ይህ የቫይረስ ወረርሽኝ እንዲህ ያለው ከፍተኛ ተጽእኖን በዓለም አቀፉ የኃይል ���በያ ላይ ሊያስከትል ቻለ? የቻይናዊያን አዲስ ዓመት የበዓል ጊዜ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል በበሽታው ምክንያት በመራዘሙና የጉዞ እገዳ በመደረጉ ፋብሪካዎች፣ ቢሮዎችና መደብሮች ዝግ ሆነው ይገኛሉ። ይህም ማለት አስከ 14 ሚሊዮን በርሜሎችን በቀን ውስጥ የምትጠቀመውና የዓለማችን ትልቋ የድፍድፍ ነዳጅ ገዢ አገር የሆነችው ቻይና ማሽኖቿን ለማንቀሳቀስ፣ ለተሽከርካሪዎችና ለኤሌክትሪክ ኃይል ወትሮ ከምትፈልገው ነዳጅ ዘይት በእጅጉ የቀነሰውን እንድትጠቀም አድርጓታል። በወረርሽኙ ምክንያት በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጓቸውን በረራዎች በማቋረጣቸው የተነሳና በቻይና ውስጥ ባለው የጉዞ እገዳ ሳቢያ በረራዎች በመቀነሳቸው ለአውሮፕላን ነዳጅ ያለው ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል ተብሎ ይታሰባል። • ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? • ካሜሮናዊው በኮሮናቫይረስ በመያዝ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ ብሉምበርግ በዚህ ሳምንት እንደዘገበው የቻይና ዕለታዊ የድፍድፍ ነዳጅ ፍጆታ በ20 በመቶ ቀንሷል። ይህም ማለት ብሪታኒያና ጣሊያን በአንድ ላይ በቀን የሚያስፈልጋቸውን ነው። በዚህም ሳቢያ በቻይና መንግሥት የሚተዳደረው የእስያ አህጉር ትልቁ የነዳጅ ማጣሪያ ሲኖፔክ በየቀኑ የሚያጣራውን የድፍድፍ ነዳጅ መጠን በ600 ሺህ በርሜሎች ቀንሷል። ይህም ከሥራው 12 በመቶው አቁሟል ማለት ሲሆን ከ10 ዓመታት በላይ ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛው ቅናሽ ነው። በነዳጅ ዘይት ላይ የታየው ከፍተኛ ቅናሽ የኃይል ኢንዱስትሪውን በከፍተኛ ደረጃ እንዳሳሰበው የዘርፉ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው። በነዳጅ ፍላጎት ላይ የተከሰተው ከፍተኛ ቅናሽ በቻይና ውስጥ የተከሰተውን የሥራ መቀዛቀዝን የሚያሳይ ግልጽ ምልክት ነው። በተጨማሪም ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ቻይናን ካጋጠማት የኢኮኖሚ ዕድገት መቀነስ ክስተት ውስጥ ዝቅተኛው ማጋጠሙ ደግሞ የነዳጅ ፍጆታዋን የበለጠ ይቀንሰዋል ተብሏል። የተባሉት በቻይና የሳይንስ አካዳሚ ውስጥ ተመራማሪ የሆኑነት ዣንግ ሚንግ እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ባሉት ሦስት ወራት የአገሪቱን ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ከ5 በመቶ በታች ሊያወርደው ይችላል። • ""ኮሮናቫይረስ በአሜሪካ የሥራ ዕድልን ሊያሳድግ ይችላል"" ያደጉት አገራት እድገታቸውን ለማጠናከር ትግል በሚያደርጉበት ጊዜ ቻይና የዓለማችን ሁለተኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚና ለዓለም የኢኮኖሚ ዕድገት አንቀሳቃሽ ሞተር ናት። የዓለም ገንዘብ ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ክሪስታሊና ጆርጂዮቫ ባዚህ ሳምንት እንዳሉት ወረርሽኙ ቢያንስ ለአጭር ጊዜ የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን ያቀዛቅዘዋል፤ ነገር ግን የወደፊቱን ለመናገር አሁን ጊዜው ገና እንደሆነም አመልክተዋል። እያሽቆለቆለ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ለማሳደግ ታላላቆቹ የዓለም ነዳጅ ዘይት አምራቾች ለገበያ የሚያቀርቡትን ምርት በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ እንደሚወያዩ እየተነገረ ነው። የኮሮናቫይረስ ክስተት ለነዳጅ የለውን ፍላጎት እንዲቀንስ በማድረጉ ምክንያት የነዳጅ አምራችና ላኪ አገራት ማኅበር የሆነው ኦፔክ አባል የሆነችው ኢራን ሰኞ ዕለት እየወደቀ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ለመደገፍ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በይፋ ጠይቃለች። የኦፔክ አባል አገራትና ሩሲያ በዚህ ሳምንት ያደርጉታል ተብሎ በሚጠበቀው ስብሰባ ላይ በቀን ለገበያ ከሚያርቡት የነዳጅ ምርት ከ500 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን በርሜል የሚደርሰውን ለመቀነስ ይወያያሉ ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-51368390 +sports በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚጠበቁበት የቤልግሬዱ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና "ሰርቢያ ቤልግሬድ ውስጥ ዛሬ ከ���ጋቢት 9 ተጀምሮ አስከ 11/2014 ዓ.ም በሚቆየው የዓለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና አፍሪካዊያን አትሌቶች ሜዳሊያ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኬንያዊው አትሌት ፈርዲናንድ ኦሙርዋ ኦማንያላ ከእነዚህ መካከል አንዱ ሲሆን የዩሴይን ቦልትን የ100 ሜትር የዓለም ክብረወሰን መስበር እንደሚችል ተናግሯል። ኬንያዊው አትሌት በሰርቢያው ሻምፒዮና ውድድሩን 60 ሜትር ይጀምራል። የ26 ዓመቱ አትሌት በ9.77 በሆነ ሰከንድ የአፍሪካን የ100 ሜትር ክብረወሰን በእጁ አስገብቷል። በአጭር ርቀት መሻሻል ካሳየ የቦልትን ክብረ ወሰን (9.58 ሰከንድ) ለመስበር እንደሚረዳው ያምናል። ""ምንም የማይቻል ነገር የለም ብዬ አምናለሁ። የዓለም ክብረ ወሰን የሚሳካ ነገር ነው"" ሲል ኦማንያላ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ተናግሯል። ""ይህን ክብረ ወሰን መስበር የሚችል ሰው ካለ እኔ ነኝ ብዬ አምናለሁ።'' ""የአፍሪካን ክብረ ወሰን ተመልከቱ። ሩጫ ስጀምር ሰዎች በቅርቡ አይሰበርም ብለው አስበው ነበር። ይህን ግን ባለፈው ዓመት አሳክቻለሁ።'' ይህም የኦማንያላ ክብረወሰን የምንጊዜም ፈታኝ ሰዓቶች ስምንተኛው አድርጎታል። ይህን ግን ያሳካው የ14 ወራት የአበረታች መድኃኒት እገዳ በ2017 ከተጣለበት በኋላ ነው። መድኃኒቱ የተገኘበት በውስጡ ስቴሮይድ አለበት ያለውን የህመም ማስታገሻ ከወሰደ በኋላ መሆኑን ጠቅሶ ""በሁኔታው ተጎድቻለሁ"" ብሏል። ሻምፒዮን ለመሆን ጣሊያናዊውን የ100 ሜትር የኦሊምፒክ ሻምፒዮን ማርሴል ጃኮብስን እና የወቅቱን የቤት ውስጥ ሻምፒዮን አሜሪካዊውን ክርስቲያን ኮልማንን ማሸነፍ ይኖርበታል። በቤልግሬድ የሚወዳደሩ ሌሎች አፍሪካውያንስ? በ2022ቱ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከ137 አገራት የተውጣጡ 680 አትሌቶች ይሳተፋሉ። ውድድሩ ከመጋቢት 9 እስከ 11/2014 ሰርኒያ ቤልግሬድ ውስጥ ይካሄዳል። ስድስቱ ተጠባቂ አፍሪካዊያን ሰለሞን ባረጋ (ኢትዮጵያ) - የ22 ዓመቱ አትሌት የ10,000 ሜትር የኦሊምፒክ ሻምፒዮን ነው። በ2018 በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በ3000 ሜትር ያገኘውን የብር ሜዳሊያ ለማሻሻል ይወዳደራል። ለሜቻ ግርማ (ኢትዮጵያ) - በ3000 ሜትር መሰናክል የዓለም እና የኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ነው። የ21 ዓመቱ አትሌት የ3000 ሜትር አሸናፊ ለመሆን ከሰለሞን ጋር ይፎካከራል። ሳሙኤል ተፈራ (ኢትዮጵያ) - የ1500ሜ የዓለም የቤት ውስጥ ክብረ ወሰን ባለቤት ሲሆን በ2018 በርሚንግሃም ላይ ያገኘውን የወርቅ ሜዳሊያ ለማስጠበቅ ይወዳደራል። ጉዳፍ ፀጋይ (ኢትዮጵያ) - የ5,000 ሜትር የኦሊምፒክ እና የ1500 ሜትር የዓለም ሻምፒዮና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊዋ 24 ዓመቷ አትሌት በ1500 ሜትር ትጠበቃለች። ኢሴ ብሩሜ (ናይጄሪያ) - የኦሊምፒክ እና የዓለም ሻምፒዮና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊዋ የ26 ዓመቷ አትሌት፣ የአፍሪካ ሻምፒዮን ናት። በሴቶች የአግድሞሽ ዝላይ ውድድር ትሳተፋለች። ሃሊማ ናካዪ (ኡጋንዳ) - የ27 ዓመቷ አትሌት በ2019 ዶሃ ላይ ባስመዘገበችው የ800 ሜትር የዓለም ሻምፒዮና ወርቅ ላይ ተጨማሪ ድል ለማስመዝገብ ትፎካከራለች። ያሲር ትሪኪ (አልጄሪያ) - ባለሦስትዮሽ ዝላይ (ትሪፕል ጃምፕ) በ16.95 ሜትር በመዝለል ከወቅቱ የዓለም ምርጥ 5ቱ ውስጥ ተካቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60788088 +politics ምርጫ 2013፡ የምርጫ ውጤት በምርጫ ክልል ደረጃ ረቡዕና ሐሙስ ይገለጻል ተባለ "ሰኞ ዕለት የተካሄደው ምርጫ ውጤት በምርጫ ክልል ደረጃ ረቡዕና ሐሙስ ይፋ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ቆጠራ በተጠናቀቀባቸው ምርጫ ጣቢዎች ውጤቶች ከማክሰኞ ንጋት ጀምሮ ይፋ ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን፤ የምርጫ ጣቢያ ውጤቶች ወደ ምርጫ ክልሎች ከተላኩ በኋላ ""ነገ [ረቡእ] እና ከነገ ወዲያ [ሐሙስ] የምርጫ ክልል ው��ት ይፋ ይደረጋል"" ሲሉ የቦርዱ የኮምዩኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ተናግረዋል። የምርጫ ክልል ውጤቶች ደግሞ ከመላው አገሪቱ ወደ ማዕከል ገብተው አስፈላጊው ማጣራት ከተካሄደ በኋላ ቦርዱ አጠቃላይ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማክሰኞ ከሰዓት በበኋላ በሰጠው መግለጫ እስከ ቀጣይ 10 ቀናት ድረስ ቢያንስ ጊዜያዊ የሆነ የአጠቃላይ የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጋለሁ ብሏል። ከዚህ ባሻገር የተለያዩ ግለሰቦች የምርጫ ጣቢያ ውጤቶችን በመያዝ የመጨረሻ ውጤት በማስመሰል ይፋ ከማድረግ ተግራባቸው እንዲቆጠቡ ቦርዱ ጠይቋል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮምዩኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ በርካታ አክቲቪስቶች እና ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከአንድ ምርጫ ጣቢያ የተገኘ ውጤን መሠረት በማድረግ 'የዚህ ምርጫ ክልል አሸናፊ እከሌ ነው' እያሉ ሲውጁ ተመልክተናል ብለዋል። የምርጫ ውጤቶችን ይፋ ማድረግ የሚችለው ምርጫ ቦርድ ብቻ መሆኑን ያስታወሱት ሶሊያና፤ መሰል ተግባራት ""ተቀባይነት የሌለው እና ወንጀል ጭምር ነው"" ብለዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምን ያክል ሰዎች ድምጽ ለመስጥት ወጡ የሚለው አሃዝ እስካሁን እንደሌለው በመጥቀስ በርካታ ቁጥር ያለው ሰው ግን ድምጽ ለመስጥ መውጣቱን መገንዘቡ ተገልጿል። ""በከተማም በገጠርም በርካታ ሕዝብ ድምጽ ለመስጥት ወጥቷል። ይህም በጣም አስደሳች ነበር"" ብለዋል የቦርዱ የኮምዩኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ። ሰኞ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች በተካሄደው ምርጫ የተሰጡትን ድምጾች በመቁጠር ከማክሰኞ ጠዋት ጀምሮ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ውጤቶች ይፋ እየተደረጉ ሲሆን በበርካታ ቦታዎች ውጤቶች ታውቀዋል። ከዚህ ባሻገር በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠሙ መስተጓጎሎች ሰኞ ዕለት ድምጽ ሳይሰጥባቸው በቀሩ አካባቢዎች ዛሬ ማክሰኞ ዕለት መራጮች ድምጽ ሰሰጡ ውለዋል። ከምርጫው ጋር በተያያዘ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ በሆቴል ክፍላቸው ውስጥ ሕይወታቸው አልፎ ስለተገኙት አሜሪካዊ ግለሰብን በተመለከተም ቦርዱ ክስተቱን ከፖሊስ መስማቱን ተናግረዋል። ""ግለሰቡ በሆቴል ክፍላቸው ሕይወታቸው አልፎ መገኘቱን ሰምተናል። ሆቴል ክፍላቸው ወድቀው ነው የተገኙት። እጅግ አሳዛኝ አጋጣሚ ነው"" ካሉ በኋላ የግለሰቡ አሟሟት ከምርጫው ጋር የተገናኘ አለመሆኑን ተናግረዋል። ሶሊያና ግለሰቡ ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢ አለመሆናቸውን ጠቅሰው በእንግድነት ከምርጫ ቦርድ ባጅ ወስደው እንደነበረ ተናግረዋል። ""የመታዘብ ሥራን የሚሰሩ አልነበሩም። ለእንግዶች የሚሰጥ ባጅ ነው የወሰዱት። ከካርተር ሴንተር ለመታዘብ የመጣ የለም"" ብለዋል። ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታስቦ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደዚህ ዓመት ተሸጋግሮ በሁለት ዙሮች ምርጫው እንዲካሄድ በተወሰነው መሰረት የመጀመሪያው ዙር ምርጫ ሰኞ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ተካሂዷል። ሁለተኛው ዙር ምርጫ በሶማሌና በሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በሌሎች አንዳንድ አካባቢዎች ከሁለት ወራት በኋላ ጳጉሜ 01/2013 ዓ.ም ይካሄዳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57554222 +health በኒው ዚላንድ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው "በኒው ዚላንድ በጠና የታመሙ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው። ባለፈው ወር በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ 65.2% መራጮች የፍቃድ ሞትን ደግፈዋል። ዩትኔዝያ ወይም የፈቃድ ሞት በጠና የታመሙ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖሩ የተነገራቸው ሰዎች በህክምና እርዳታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ የሚደረግበት ሂደት ነው። ሕጉ በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ጸድቆ ይተገበራል ተብሎ ይጠበቃል። ኒው ዚላንድ ሕጉን ካጸደቀች የፈቃድ ሞት ከሚ���ገበርባቸው ጥቂት አገሮች አንዷ ትሆናለች። ዩትኔዝያ ከተፈቀደባቸው አገሮች ኔዘርላንድ እና ካናዳ ይጠቀሳሉ። ኒው ዚላንዳውያን ባለፈው ወር መሪያቸውን ሲመርጡ ስለ ፈቃድ ሞት እና ዕጸ ፋርስ ሕዝበ ውሳኔ አድርገዋል። ዕጸ ፋርስን ለመዝናኛ መጠቀም ሕጋዊ እንዲሆን ድምጽ የሰጡት 46.1% ብቻ ሲሆኑ፤ 53.1% ተቃውመዋል። የፈቃድ ሞትን ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደን እንዲሁም ተቀናቃኛቸው ጁዲት ኮሊንስም ይደግፉታል። ሕዝቡም ሕጋዊ ይሁን ብሎ እንደሚመርጥ ይጠበቅ ነበር። ባለቤቱ የሞተችበት ማት ቪከርስ ""ርህራሄ እና ደግነት አሸንፈዋል። በጠና የታመሙ ኒው ዚላንዳውያን ሕይወታቸውን ማሳለፍ ስለሚችሉ ደስ ብሎኛል"" ሲል የተሰማውን ገልጿል። ጠበቃ የነበረችው ባለቤቱ የአንጎል እጢ ሲገኝባት በፈቃዷ ለመሞት ክስ ብትመሠረትም ሳታሸንፍ በጠና ታማ ከአምስት ዓመታት በፊት ሞታለች። ""ባለቤቴ መሞት አትሻም ነበር። ማንም ሰው መሞት አይፈልግም። ነገር ግን መኖር የምርጫ ጉዳይ ነው። ስቃይ እየበረታ ሲሄድ መሞት አንዱ ምርጫ መሆን አለበት"" ብሏል። አንድ ሰው በፈቃዱ ለመሞት በጠና የታመመ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖር የተረጋገጠ መሆን አለበት። ሰውነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ እንደሄደና ውሳኔው ላይ ለመድረስ በቂ መረጃ እንዳለው ማረጋገጥም ተገቢ ነው። ሂደቱ የሚመራው በዶክተር ወይም በነርስ ነው። አንድ ሰው እድሜው ስለገፋ፣ የአእምሮ ህመም ስላለበት ወይም የአካል ጉዳት ስላለበት የፍቃድ ሞት ሕግን መተግበር አይችልም። ሕጉን የሚቃወሙ ሰዎች ""እንድንኖር እንጂ እንድንሞት አትርዱን"" ሲሉ ምክር ቤት ሄደው ተቃውሞ አሰምተዋል። ሕጉ ለማኅበረሰቡ አስጊ እንደሆነ እና ራስን ማጥፋትን ለመግታት ከወጣ መርህ ጋር እንደሚቃረን ይናገራሉ። ሌላው መከራከሪያ ነጥብ በጠና የታመሙ ሰዎች የቤተሰብ ሸክም ላለመሆን ብለው በፈቃዳቸው ሊሞቱ ይችላሉ የሚለው ነው። ዩትኔዝያን አጥብቆ ሲተች የነበረ ቡድን ""የኒው ዚላንድ ዜጎች የተሳሳተ ሕግ እንዲጸድቅ ድምጽ በመስጠታቸው አዝነናል"" ሲል መግለጫ አውጥቷል። የፈቃድ ሞትን ሕጋዊ ያደረጉ አገሮች የኒው ዚላንድን ሕዝበ ውሳኔ በቅርበት ሲከታተሉ ነበር። ከነዚህ መካከል ቤልጄም፣ ካናዳ፣ ኮሎምቢያ፣ ሉግዘምበርግ እና ኔዘርላንድስ ይጠቀሳሉ። በኔዘርላንድስ በህክምና ታግዞ ራስን ማጥፋት ይቻላል። በአሜሪካ ያሉ ብዙ ግዛቶች እና የአውስትራሊያዋ ቪክቶሪያ በህክምና የታገዘ ሞትን ፈቅደዋል።" https://www.bbc.com/amharic/54744271 +business """የቻይናና የአሜሪካ ቀዝቃዛው ጦርነት ከኮሮናቫይረስ በላይ ለዓለም ያሰጋል""" "በመጪዎቹ ዓመታት በአሜሪካና በቻይና መካከል ሊከሰት የሚችለው ቀዝቃዛ ጦርነት ዓለምን ከኮሮናቫይረስ በላይ ሊያስጨንቅ እንደሚገባ ዕውቁ የምጣኔ ሀብት ሊቅ ጄፍሪ ሳክስ ተናገሩ። የኮሎምቢያው ዩኒቨርስቲ ዕውቅ ፕሮፌሰር ጄፍ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ዓለም ወደ አንዳች መደነቃቀፍ እያመራች ነው፤ መሪ አልባም ሆናለች ብለዋል። እንዲሁም የዓለም ሁኔታ መልክ ባልያዘበት ሁኔታ በሁለቱ የዓለም ኃያላን መካከል ያለው ቁርሾና ቅራኔ እየባሰ ከሄደ ሁኔታዎችን ያባብሳል፤ ጦሱም ለተቀረው ዓለም ይተርፋል ብለዋል። እኚህ ፕሮፌሰር ለዚህ ሁሉ ተጠያቂዋ አሜሪካና አመራሯ ነው ብለዋል። • አገራዊ መድረክ ማዘጋጀት እንጂ ከህወሓት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይትን አንቀበልም፡ ደብረፅዮን (ዶ/ር) • ""አባላቶቻችን በአካባቢው ይህን የደንብ ልብስ መልበስ ካቆሙ ስድስት ወራት አልፈዋል"" የኦሮሚያ ፖሊስ አሁን ያለው የአሜሪካ አመራር ከትብብር ይልቅ ክፍፍልን የሚያፋፍም ነው ሲሉም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""አመራሩ አዲስ ቀዝቃዛ ጦርነ��� ከቻይና ጋር ለመፍጠር እየሞከረ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ዓለምን ዳግም ወደ ሰላም ለመመለስ በጣም ይቸገራል"" ብለዋል ፕሮፌሰሩ። የፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስ አስተያየት የመጣው ሰሞኑን ቻይናና አሜሪካ ከምጣኔ ሀብት ጦርነት ጋር ብቻም ሳይሆን ፖለቲካዊ መቆራቆዝ ውስጥ እየገቡ ስለመሆኑ ምልክቶች መታየታቸውን ተከትሎ ነው። በያዝነው ሳምንት ለምሳሌ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በቻይና ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ የሚጥለው ሰነድ ላይ ይፈርማሉ ተብሏል። ማዕቀቡን የሚጥሉት በዢንጂያንግ ግዛት የቻይና ሙስሊሞችን ለርዕዮተ ዓለም ጥምቀት ማጎርያ ውስጥ መከተታቸውን ተከትሎ ነው። ያም ሆኖ የዶናልድ ትራምፕ የቀድሞው የደኅንነት አማካሪ ሰሞኑን ለአንባቢዎች ያደርሱታል በተባለው አዲስ መጽሐፋቸው እንደጠቀሱት፤ ፕሬዝዳንቱ ቻይና ይህንን የሙስሊሞች ማጎርያ እንድትገነባ አበረታተው ነበር። ዶናልድ ትራምፕ ከሰሞኑ ከዎልስትሪት ጆርናል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ቻይና ኮሮናቫይረስን ለዓለም ያቀበለችውና ብሎም ያሰራጨችው ሆን ብላ የአሜሪካንን ምጣኔ ሀብት ለማንኮታኮት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የቻይናና የአሜሪካንን የኢኮኖሚ ጦርነት ካመላከቱ ነገሮች አንዱ አሜሪካ በቻይናው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ ላይ የጣለችው እቀባ ነው። አሜሪካ እንደምትለው ሁዋዌ የደንበኞችን መረጃ ለመሰለል የተቋቋመ ነው። ቻይና ይህንን ክስ ታስተባብላለች። የቀድሞው የዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ የደኅንነት አማካሪ ጆን ቦልተን አዲስ በጻፉት መጽሐፍ እንዳጋለጡት ከሆነ ዶናልድ ትራምፕ ህዋዌ ላይ እቀባ ያደረጉት በድጋሚ የመመረጥ ዕድላቸውን ለማስፋት ብቻ ነው። • ትራምፕ እንዳይታተም ባሉት መጽሐፍ ይፋ የሚደረጉ 6 ምስጢሮች • በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚደረገው ድርድር፡ የግብፅ ፍላጎትና የኢትዮጵያ ውሳኔ ፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስም በዚህ የቦልተን ሐሳብ ይስማማሉ። ሁዋዌን ትራምፕ ያገዱት የምርም የደኅንነት ጉዳይ አሳስቧቸው ሊሆን አይችልም። ""አሜሪካ በ5ጂ የሞባይል ቴክኖሎጂ ተቀድማለች። ሁዋዌ ደግሞ የዓለምን የገበያ ድርሻ ተቀራምቶታል፤ ይህ ነው አሜሪካንን የረበሻት"" ይላሉ። ከቻይና ጋር ፍጥጫ ላይ ያለችው አገር አሜሪካ ብቻ አይደለችም። ቻይና ባለፈው ሳምንት ከሕንድ ጋር የድንበር ግጭት ውስጥ ገብታ 20 የሕንድ ወታደሮችን መገደላቸው አይዘነጋም። ይህ በእንዲህ እናዳለ ቻይና በፓኪስታን፣ በምያንማር፣ በሲሪሊንካና በኔፓል በርካታ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን እያገዘች ነው። እነዚህ አገራት ደግሞ የሕንድ ጎረቤቶች ናቸው። ሕንድ ቻይና የአካባቢው ተጽእኖ ፈጣሪ አገር የመሆኗን ጉዳይ ማስቆም ትፈልጋለች። ፕሮፌሰር ሳክስ እንደሚያምኑት ቻይና በአካባቢው አገራት ላይ የትብብር መንፈስ ካሳየች ነገሮች የተሻሉ ይሆናሉ። ቻይና እድሏ ያለው በእጇ ነው። ቻይና ተባባሪ ከሆነች፣ በዲፕሎማሲ ችግሮችን ለመፍታት ከፈለገችና የትብብር መንፈስ ካሳየች ጉልበት ያላት አገር ስለሆነች ብዙ ነገር መቀየር ትችላለች፤ የእሲያ አህጉርም የተሻለ መጻኢ እድል ይኖረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53135326 +health በኮሮና የተያዙ ሰዎች በድባቴ እና የመርሳት በሽታ የመጠቃት እድላቸው እንደሚጨምር ጥናት አመለከተ ባለፈው ስድስት ወራት ውስጥ የኮሮናቫይረስ የያዛቸው ሰዎች በድባቴ፣ የመርሳት በሽታ፣ ስትሮክ እና በሳይኮሲስ ህመሞች የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን በኦክስፎርድ ተመራማሪዎች የተሰራ ጥናት አመላከተ። ከእነዚህ ውስጥ አንድ ሶስተኛው ቀድመው የነበሩባቸው የስነ ልቦና እና የነርቭ ችግሮች ያገረሽባቸዋል ወይም እንደ አዲስ ሕመሞቹ ያጠቋቸዋል ሲል ጥናቱ አመልክ��ል። በቫይረሱ ተይዘው ሆስፒታል የገቡ ወይም በፅኑ ህሙማን ማቆያ ከነበሩ ደግሞ የመያዝ እድላቸው የበለጠ ይሰፋል ሲል ጥናቱ አመላክቷል። እነዚህ ጫናዎችም ጭንቀትን በማስከተል ወይም ቫይረሱ አዕምሮ ላይ በሚያስከትለው ቀጥተኛ ጫና ላይ ሊመሰረት እንደሚችልም አክሏል። እንግሊዛዊያን ሳይንቲስቶቹ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎችን የኤሌክትሮኒክ መረጃ በመመልከት እና በተለይም 14 ለሚሆኑ የስነ-ልቦና እና የነርቭ ችግሮች የመጋለጥ እድሎችን መርምረዋል። ከእነዚህም መካከል የአዕምሮ ውስጥ የደም መፍሰስ፣ ስትሮክ፣ ፓርኪንሰን፣ የመርሳት በሽታ፣ ሳይኮሲስ፣ የስሜት መቃወስ እና የጭንቀት ችግሮች ይገኙበታል፡፡ በጣም መታመምን ወይም ወደ ሆስፒታል መወሰድ ከሚያስከትለው የጭንቀት ጫና የተነሳ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ለጭንቀት እና የስሜት መቃወስ መዳረግ በተደጋጋሚ የታዩባቸው ችግሮች ናቸው ሲል ገልጿል። እንደ ስትሮክ እና የመርሳት በሽታ ያሉት ደግሞ ቫይረሱ በራሱ በሚያስከትለው አካላዊ ጉዳት ላይ ተመስርተው የሚከሰቱ ወይም ሰውነታችን ለቫይረሱ በሚሰጠው ምላሽ ምክንያት ሊከሰቱ ይችላሉ ሲልም አስረድቷል። ጥናቱ የኮሮናቫይረስ በቀጥታ ለፓርኪንሰን ወይም ለጊላይን-ባሬ ሲንድሮም የማጋለጥ እድሉን አላረጋገጠም። ምርምሩ ሁለት በጉንፋን የተያዙ ሰዎችን የያዙ ቡድኖችን በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ጋር በማነፃፀር የተሰራ ሲሆን፣ ጥናቱን ያካሄዱት የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ኮሮና ከሌሎች የመተንፈሻ ህመሞች በበለጠ ከአዕምሮ ጉዳቶች ጋር እንደሚያያዝ ገልፀዋል። ቫይረሱ ወደ አዕምሮ ውስጥ እንደሚገባ እና ጉዳቶችን እንደሚያደርስ የሚያሳዩ ማስረጃዎች ተገኝተዋል ሲሉ ከተመራማሪዎቹ አንዱ የሆኑት የኦክስፎርዱ የኑሮሎጂ ፕሮፌሰር መሱድ ሃሰን አብራርተዋል፡፡ ከቀጥተኛ ጉዳቶችም ባሻገር የደም መርጋትን በማስከተሉ እና ይህም ስትሮክን ሊያመጣ እንደሚችል አክለዋል፡፡ በአጠቃላይም ሰውነታችን ቫይረሱን ለመከላከል ሲል የሚያደርገው ግብ ግብ አእምሮን ሊጎዳ ይችላል ሲሉም ገልፀዋል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-56664358 +sports ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከሁሉ ቀድመው ካሜሮን የገቡት ዋሊያዎች "በኮሮናቫይረስ ምክንያት በአንድ ዓመት የዘገየው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሁንም በወረርሽኙ ስጋት ውስጥ ሆኖ በመጪው ወር ጥር 01/2014 ዓ.ም ካሜሩን ውስጥ መካሄድ ይጀምራል። በዚሁ ውድድር መሳተፋቸውን ያረጋገጡት ዋልያዎቹም ባለፈው ሳምንት እሁድ ከሁሉም የአፍሪካ አገራት ቀድመው ካሜሩን በመድረስ ዝግጅታቸውን ጀምረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ጌታነህ ከበደን ጨምሮ 25 ተጫዋቾች በቡድኑ ውስጥ የተካተቱ ሲሆን፣ ካፍ ካስቀመጠው ገደብ በተጨማሪ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሦስት ተጫዋቾች እንዲካተቱ ተደርጓ። ታኅሣሥ 14/ 2014 ይፋ ከተደረገው የብሔራዊ ቡድኑ 25 ተጫዋቾች ዝርዝር ከዚህ ቀደም በተጠባባቂነት ተይዘው የነበሩት ሱራፌል ዳኛቸው፣ ፍሬው ጌታሁን እና ይሁን እንደሻው ብሔራዊ ቡድኑን ተቀላቅለው ዋሊያዎቹ 28 ተጫዋቾችን በመያዝ ወደ ካሜሩን አቅንተዋል። የኢትዮጵያ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈው ከ8 ዓመታት በፊት ደቡብ አፍሪካ ባስተናገደችው ውድድር ላይ ነበር። ባለፈው እሁድ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ የተነሳው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ልዑክ በቀዳሚነት የካሜሩን ሁለተኛ ከተማ ወደሆነችው ዱዋላ ደርሶ ለአንድ ሰዓት ከቆየ በኋላ ወደ ዋና ከተማዋ ያውንዴ ደርሷል። ብሔራዊ ቡድኑ ያውንዴ አየር ማረፊያ እንደደረሰ ���ኮቪድ-19 ምርመራን ያደረገ ሲሆን በመቀጠል ወደ ሆቴል ዴ ዴፕዩቴ አምርቶ ማረፊያውን ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያሳያል። ብሔራዊ ቡድኑ እስካሁን ቀላል እና ጠንከር ያሉ አራት ልምምዶችን አከናውኗል። በዋሊያዎቹ ከሁሉ ቀድመው ለምን ወደ ካሜሩን ሄዱ? የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን እንደሚሉት የመጀመሪያ እቅድ ተደርጎ የነበረው በመካከለኛው ምሥራቅ ከሚገኙ አገራት መካከል በአንዱ ውስጥ ዝግጅት ለማድረግ ነበር። ""ከሳዑዲ አረቢያ እግር ኳስ ማኅበር ጋር ንግግሮች ነበሩ። እንዲያውም ሙሉ ወጪያችንን ሸፍነው እነሱ ጋር ሄደን እንድንዘጋጅ ተነጋግረን ነበር።"" ነገር ግን የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የጉዞ እግዳዎችን ከጣለባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ በመሆኗ ሀሳቡ ሳይሳካ እንደቀረ ኃላፊው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የሳዑዲ አረቢያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ቢሆን በተፈጠረው ነገር ማዘኑን እንደገለጸና ይቅርታ እንደመጠየቀም ኃላፊው አመልክተዋል። የመጀመሪያው እቅድ አለመሳካቱን ተከትሎ ደግሞ ፌደሬሽኑ ወደ ሁለተኛ እቅዱ ፊቱን ለማዞር ተገዷል። ይህም ደግሞ ወደ ምዕራብ አፍሪካ አገራት በመሄድ ልምምድ ማካሄድ ነበር። በስተመጨረሻም ወደ አዘጋጇ አገር ካሜሩን በመሄድ ልምምድ ለማድረግ ውሳኔ ላይ ተደርሷል። በተጨማሪም ብሔራዊ ቡድኑ ቀድሞ ወደ ካሜሩን ማቅናቱ የአገሪቱን የአየር ጸባይ ለመልመድ ይእንደሚረዳ የገለጹት አቶ ባሕሩ፣ የአፍሪካ ዋንጫ ዘንድሮ እንዳይካሄድ ከተለያዩ ወገኖች ግፊት ይደረግ ስለነበረ ያን በመቃወም ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ እንዲከናወን ኢትዮጵያ ያላትን ድጋፍ ለማሳየት መሆኑን ጠቅሰዋል። ፊፋንና የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበርን ጨምሮ አንዳንድ የእግር ኳስ ማኅበራት የወረርሽኙን ስርጨት ተከትሎ የአፍሪካ ዋንጫ በዚህ ጊዜ መካሄድ የለበትም የሚል አስተያየት ሲሰጡ እንደነበር ዋና ፀሐፊው ተናግረዋል። ""እኛ ደግሞ የፓንአፍሪካኒዝም ጀማሪዎች እንዲሁም የካፍ መስራች እንደመሆናችን ይሄ ውድድር በተያዘለት ጊዜ በካሜሩን እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ለመስጠትና ይህንን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ቀድመን ወደ ካሜሩን ለማቅናት የወሰንነው።"" ኦሚክሮን የተባለው አዲሱን የኮቪድ-19 ዝርያ በስፋት መሰራጨትን ተከትሎ በርካቶች ውድድሩ ላይካሄድ ይችላል በሚል ስጋታቸውን ቢገልጹም፣ የየካሜሩን መንግሥት እና የእግር ኳስ ማኅበሩ እንዲሁም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ግን ጨዋታው በወጣለት መረሃ ግብር መሠረት እንደሚከናወን አረጋግጠዋል። ነገር ግን በካሜሩን በሚካሄደው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ላይ መታደም የሚችሉት የኮቪድ-19 ክትባትን ሙሉ ለሙሉ የወሰዱ እና ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው የተረጋገጠ ደጋፊዎች ብቻ እንደሚሆኑ አዘጋጆቹ ገልጸዋል። የካሜሩን ቆይታና ዝግጅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሁን የሚገኘው የፊፋ ወኪል በሆነ ኤጀንት አማካይነት በተመቻቸ የስልጠና ካምፕ አገልግሎት መስጫ ውስጥ ነው። ይህ የስልጠና አገልግሎት መስጫ ካምፕ ሆቴል፣ መስተንግዶ፣ የስልጠና ቦታና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ ያሟላ እንደሆነ አቶ ባህሩ ይገልጻሉ። ""አሁን ብሔራዊ ቡድኑ ያለበት ቦታ ሁሉንም ፍላጎታቸውን የሚያሟላ ነው። አሁን ላይም ተጫዋቾቹ አስፈላጊውን ስልጠናና ዝግጅት በዚህ ማዕከል እያደረጉ ነው'' ሲሉ ዋሊያዎቹ ለውድድሩ አስፋለጊውን ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን አመልክተዋል። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዝግጅት ያውንዴ ከከተመ ሳምንት ሊሆነው ተቃርቧል። በቆይታውም መደበኛ ልምምድ በማድረግ ከ���ምንት ለሚጀመረው ውድድር እየተዘጋጀ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞም ከዋሊያዎቹ ቀጥሎ ካሜሩን ከደረሰው የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር ሐሙስ ዕለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አድርጓል። በምድብ 'መ' ከግብፅ፣ ከናይጄሪያ እና ከጊኒ ቢሳዎ ጋር ከተደለደለችው ሱዳን ጋር በተደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታው አማኑኤል ገ/ሚካኤል ሁለት፣ ሽመልስ በቀለ ደግሞ አንድ ግቦችን አስቆጥረው ዋሊያዎቹ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ለማሸነፍ ችለዋል። ዋሊያዎቹ በካሜሩን በሚኖራቸው ቆይታ አጠቃላይ ወጪያቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ እንደሚሸፍን የፌደሬሽኑ ዋና ፀሐፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የአፍሪካ አህጉር ትንቁ የእግር ኳስ ውድድር በሆነው ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ ለሚቀርበው ቡድን የሚያስፈልገውን ገንዘብ ፌዴሬሽኑ ከመንግሥት አግኝቷል። ""ለዚህ ውድድር 51 ሚሊየን ብር እንዲመድብ ጠይቀን 35 ሚሊየን ብር ጸድቆልናል። በዚህ ገንዘብ ነው ብሔራዊ ቡድኑ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው። በዚህ አጋጣሚ መንግሥት ላደረገው ነገር በሙሉ ፌዴሬሽኑ ያመስግናል'' ብለዋል አቶ ባሕሩ። ከዋሊያዎቹ ምን እንጠብቅ? የአፍሪካ እግር ኳስ ውድድር መስራች የሆነችው ኢትዮጵያ ከውድድሩ ርቃ ከመቆየቷ በተጨማሪ ከአንድ ጊዜ በላይ የጎላ ውጤትን ሳታስመዘገብ ቆይታለች። በዚህ 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሚሳታፈው ቡድን ግን ይህንን ታሪክ የመቀየር ከፍ ያለ ፍላጎት አለው። ለዚህም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋሊያዎቹ በምድብ ጨዋታዎች ጥሩ ውጤት አስመዝግበው ከምድባቸው ማለፍን በቀዳሚነት የሚጠበቅ ውጤት እንደሆነ አቶ ባህሩ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ካሜሩን፣ ከቡርኪና ፋሶ እና ኬፕ ቬርድ ጋር ተደልድሏል። በዚህ ሂደትም ዋሊያዎቹ ከምድባቸው ወደቀጣይ ዙር ማለፍን የመጀመሪያ ግብ ከመሆኑ ጎን ለጎን ""በስፖርት ዲፐሎማሲው ዘርም ሌሎች ኃላፊነቶችን እንመዲወስዱም"" አቶ ባሕሩ ጠቅሰው ""ኢትዮጵያን ለዓለም ሕዝብ በደንብ ማስተዋወቅና ማሳየት እንፈልጋለን። በዚህ ትልቅ አጋጣሚ አንድነታችንን ለመላው ዓለም በደንብ አድርገን እናሳያለን"" ብለዋል። በተጨማሪም ካሜሩን ውስጥ 20 የሚደርሱ የኢትዮጵያውያን ስብስቦች እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ባህሩ እነዚህን ኢትዮጵያውያን በማሰባብ ለብሔራዊ ቡድኑ ድጋፍ እንዲያደርጉ፣ እንዲሁም ከ500 በላይ የሚሆኑ ደጋፊዎች ከኢትዮጵያ ወደ ካሜሩን ለመጓዝ እየተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። የዋሊያዎቹ ስብስብ ግብ ጠባቂዎች፡ ተክለማርያም ሻንቆ ከሲዳማ ቡና፣ ፋሲል ገብረሚካኤል ከባሕር ዳር ከተማ፣ ጀማል ጣሰው ከአዳማ ከተማ እንዲሁም ፍሬው ጌታሁን ከድሬዳዋ ከተማ ናቸው። ተከላካዮች፡ አስራት ቱንጆ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ሱሌማን ሐሚድ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ረመዳን የሱፍ ከወልቂጤ ከተማ፣ ደስታ ዮሐንስ ከአዳማ ከተማ፣ አስቻለው ታመነ ከፋሲል ከነማ፣ ያሬድ ባየህ ከፋሲል ከነማ፣ ምኞት ደበበ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና መናፍ አወል ከባሕር ዳር ከተማ። አማካዮች፡ አማኑኤል ዮሐንስ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ጋቶች ፓኖም ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሽመልስ በቀለ ከአል ጎውና፣ መስዑድ መሐመድ ከጅማ አባጅፋር፣ ሱራፌል ዳኛቸው ከፋሲል ከነማ፣ ፍጹም ዓለሙ ከባሕር ዳር ከተማ፣ ፍሬው ሰለሞን ከሲዳማ ቡና፣ በዛብህ መላዮ ከፋሲል ከነማ እንዲሁም ይሁን እንደሻው ከፋሲል ከነማ። አጥቂዎች፡ አቡበክር ናስር ከኢትዮጵያ ቡና፣ ጌታን ከበደ ከወልቂጤ ከተማ፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሽመክት ጉግሳ ከፋሲል ከነማ፣ ሙጂብ ቃሲም ከጄይኒስ ስፖርቲቭ ዲ ካቢሌ፣ መስፍ�� ታደሰ ከሐዋሳ ከተማ እንዲሁም ዳዋ ሁጤሳ ከአዳማ ከተማ ተመርጠዋል። ዋሊያዎቹ በካሜሩን ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ የደረሰችው ከዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ ነው። በ1962 (እአአ) የአህጉሪቱን ትልቁን ዋንጫ ያነሱት ዋሊያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ሲሳተፉ ይህኛው ለ11ኛ ጊዜ ነው። በዓለም እግር ኳስ 137ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በአሠልጣኝ ውበቱ አባተና በአምበሉ ጌታነህ ከበደ እየተመራች ወደ ያውንዴ አቅንታለች። ይህ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለአሠልጣኝ ውበቱ አባቱና ለቡድኑ አባላት ከአፍሪካ ዋንጫ መሥራቾች አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ያላትን ተሰጥዖ የሚያሳዩበት መድረክ እንደሚሆን ይገመታል። ውበቱ ለዓይን ገዥ የሆነውን ኳስ እግር ላይ ሳይቆዩ እየተቀባበሉ መጫወትን የሚመርጥ አሠልጣኝ ነው። የመሃል ሜዳው ሞተር ሽመልስ በቀለና አጥቂው ጌታነህ ከበደ ከወጣቱ የኢትዮጵያ ቡና አጥቂ አቡበከር ናስር ጋር በመጣመር ለተቀናቃኞቻቸው አደጋ ሊሆኑ ይችላሉ። ውበቱ በሚመርጠው የ4-3-3 አሠላለፍ ማለትም 4 የኋላ ደጀን ሦስት አማካዮችና ሦስት አጥቂዎች ተመርቶ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይገመታል። ብሔራዊ ቡድኗን በውበቱ አባተ እያጠናከረች ያለችው ኢትዮጵያ ወደ ዙር 16 መሻገር እንደ ትልቅ ውጤት ቢታይ የሚገርም አይሆንም። አልፎም ብሔራዊ ቡድናቸው በአፍሪካ ትልቁ ውድድር ሲሳተፍ ማየት ለጓጉ ኢትዮጵያዊያን ይህ ትልቅ ዕድል ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-59840259 +health የተከተቡ ሰዎች ለምን በድጋሚ ኮሮናቫይረስ ይይዛቸዋል? "ኮቪድ የሰው ልጅን የሙጥኝ እንዳለ አለ። አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ አርጀንቲና፣ ብራዚል እና ሌሎም አገራት ውስጥ ኦሚክሮን ተመልሶ እያመሳቸው ነው። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሆስፒታል አልጋን እየያዙ ነው። ከእነዚህ የሚበዙት የተከተቡ ናቸው። ታዲያ መከተብ ከተህዋሲው ካልተከላከለ ምንድነው ፋይዳው? እርግጥ ነው ተከተቡ በተባሉ ሰዎች የሚታይ የጎንዮሽ ጉዳት ዝቅተኛ ነው። ብዙ ሰዎች በድኅረ ክትባት ጊዜ ከትኩሳት፣ ከራስ ምታት፣ ከክንድ መለስተኛ ሕመም፣ ከድካምና ከማቅለሽለሽ የከፋ ስሜት አይሰማቸውም። በክትባቱ ታይተዋል የሚባሉት አናፊላክሲስ፣ ቶምቦሲስ፣ ሚዮካርዲቲስ (የልብ አካባቢ መለብለብ) ወዘተ እጅግ ቁጥሩ ባነሱ ተከታቢ ሰዎች ዘንድ ብቻ ነው የተስተዋሉት። አሁን ድፍን ዓለም እየጠየቀ ያለው ጥያቄ ግን አንድ ነው። መከተብ ከተህዋሲው መያዝ ካላዳነ ምንድነው ፋይዳው? የሚል። ቢቢሲ ከሕጻናት ሕክምና አዋቂና የተላላፊ በሽታዎች አጥኚ ሬናቶ ክፎሪ ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ ቆይታ አድርጎ ነበር። እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ በመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ እነ ፋይዘር እና አስትራዜኒካ እንዲሁም ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባታቸውን ሲያበለጽጉ ግብ የነበረው ተህዋሲው ሰዎችን ለከፋ የጤና ችግር እንዳይዳርጋቸው፣ ሲከፋ ደግሞ ለሞት እንዳያበቃቸው እንጂ ተህዋሲው እንዳይዛቸው ለማድረግ አልነበረም። ሐኪሙ ይህ ግባቸው ተሳክቷል ብለው ያምናሉ። ""ክትባቶቹ እጅግ ለከፋው የጤና ችግር አጋላጭ ሁኔታ በቂና አስተማማኝ ምላሽ ይሰጣሉ። ቀላልና መለስተኛ ለሆኑ የተህዋሲው ምልክቶች ደግሞ ክትባቶቹ እምብዛምም ናቸው።"" እንደ ሐኪሙ ማብራሪያ መጀመሪያውኑም እኮ ክትባቶቹ ሥሪታቸው ወረርሽኙን ማቆም ወይም ሰው በተህዋሲው መልሶ እንዳይያዝ ማድረግ አልነበረም ይላሉ። ""ዋናው የክትባቶቹ ተልዕኮ አንድ ነው። ተህዋሲው ሰውነትን ለከፋ አደጋ ብሎም ለሞት እንዳያበቃ ጉዳቱን መቀነስ ነበር፤ ይህም ስኬታማ ነው"" ይላሉ። እንደ ምሳሌ የሚያቀርቡት በተለምዶ የጉንፋን ማስታገሻ የምንለው ክትባትን ነው። ያ ክትባት ለዘመናት ሲሰጥ ነው የተኖረው። አንድም ጊዜ ግን ጉንፋኑን ለማጥፋት ተብሎ አግልግሎት ላይ አልዋለም። ሰዎች በጉንፋን የተነሳ ወደከፋ ደዌ እንዳይወደቁ ማገዝ ነው ተግባሩ። ይህ ክትባት ኢንፍሌዌንዛን ለማጥፋት አልተመረተም። ነገር ግን ልጆች፣ ነፍሰጡሮች፣ ሽማግሌዎች እና ገመምተኞች ይህ የኢንፍሌውዛ ተህዋሲዊ ችግር ውስጥ እንዳይጥላቸው ያደርጋቸዋል። የኮቪድ-19 ክትባትም ተመሳሳይ ነው። ወረርሽኝ የማቆም ተልዕኮ የለውም ይላሉ። የኮቪድ-19 ክትባቶች ምን ያህል ሞትን ታድገዋል የሚለውን ብንመለከት ይህን የሐኪሙን ሙግት የሚደግፍ ሆኖ እናገኘዋለን። የኮመንዌልዝ ፈንድ ባወጣው አንድ ሰነድ ላይ እንደተመላከተው ኮሮናቫይረስ ክትባቶች ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት ብቻ አንድ ሚሊዮን ሞትን ተከላክሏል። ነገር ግን 10 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ ሆስፒታል እንዳይገቡና አልጋ እንዳይዙ የሆኑት ክትባት በመውሰዳቸው ነው። ይህ አሐዝ የአሜሪካንን ሕዝብ ብቻ ግምት ውስጥ ያስገባ ነው። የዓለም ጤና ድርጅትና የአውሮፓ የተላላፊ በሽታ ቁጥጥጥር ማዕከል እንደሚገምቱት ደግሞ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ፣ በ33 የአውሮፓ አገራት የሚኖሩ ዜጎች ክትባቱ ከሞት ታድጓቸዋል። ይህ በሌላ አነጋገር ሲገለጽ እነዚህ ሰዎች ክትባቱን በወቅቱ ባይከተቡ ኖሮ የመሞት ዕድላቸው ሰፊ ነበር። ከእነዚህ መካከል ምናልባትም በርካታ ሰዎች ተህዋሲው መልሶ አልያዛቸውም ባይባልም፣ ለከፋ ጉዳት እንዳያደርሳቸው የሆነው ግን በመከተባቸውና በመከተባቸው ብቻ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተከተቡ ሰዎች ለምን በተህዋሲው በብዛት መያዝ ጀመሩ? ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙሉ ክትባት የወሰዱ ሰዎች ሳይቀር በኦሚክሮን እየተያዙ እንደሆነ የሚስተባበል ጉዳይ አይደለም። ይህ በሦስት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። በተለይ በምዕራቡ ዓለም ገና እና አዲስ ዓመት ክብረ በዓል ላይ በርካታ ሰዎች በጋራ ብዙ ተቀራርበዋል። ይህ መቀራረብ ተህዋሲው እንደልብ እንዲዛመት ሳያስችለው አልቀረም። ሁለተኛው ምክንያት ክትባቱ ለተቀረው ዓለም ከተሰራጨ ከዓመት በኋላ ተመራማሪዎች የደረሱበት አንድ ፍንትው ያለ ሐቅ ቢኖር፣ ክትባቱ አንድ ጊዜ ተወስዶ በቃ ከዚህ ወዲያ እምብዛም አያስፈልግም የሚባል እንዳልሆነ ነው። ""በጊዜ ሂደት የክትባቱ የመከላከል አቅም እንደሚወርድ ደርሰንበታል። አቅሙ የመውረዱ ፍጥነት ደግሞ ከተከታቢው ዕድሜና የተፈጥሮ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው"" ይላሉ ሐኪም ክፎሪ። ይህም ሐቅ ነው ሦስተኛ ዙር የማጠናከሪያ ክትባት ዘመቻ እንዲከፈት ምክንያት የሆነው። ይህ ዘመቻ በቅድሚያ ዕድሜያቸው ለገፋ ብቻ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ሌሎች ሰዎችም ቢወስዱት ጥቅም እንጂ ጉዳት እንደሌለው ተደርሶበታል። ያም ሆኖ አሁንም የተከተቡ ሰዎች በተህዋሲው እየተያዙ ነው ያሉት። በዚህ ጉዳይ ላይ ሐኪሙ የሚሉት ይህንን ነው። ""ነገሩ እንደ ኢንፍሌዎንዛ ክትባት ነው። ከዚህ ሁኔታ ጋር፣ ከሐቁ ጋር ተስማምተን መኖር መቀጠል ነው የሚኖርብን። ሌላ ነገር የለም።"" መልካሙ ነገር ተከትበው ሳለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመጣው ልውጥ የኮሮናቫይረስ ምክንያት ወደ ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑ ነው። ይህም የሚያሳየው ክትባቱ ይነስም ይብዛ ሥራውን እየሠራ መሆኑን ነው። ይህን ሐቅ ለማስረዳት ኒውዮርክ ከተማን እንደ ማሳያ መውሰድ ብቻ በቂ ነው። በታኅሣሥ ወር ወደ ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎች እና የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ አሻቀበ። ከእነዚህ ውስጥ እጅግ የበዙት ክትባት ያልወሰዱ ናቸው። ክትባት የወሰዱ ሰዎች ግን በተህዋሲው ቢያዙም ለሆስፒታል የሚያበቃ ችግር ላይ አልወደቁም። የዩናይትድ ኪንግደም ጤና ቢሮም ቢሆን ከዚህ የተለየ ድምዳሜ ላይ አልደረሰም። የኬምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ባወጣው አንድ የጥናት አሐዝ አንድ ሙሉ ጠብታ የተከተበ ሰው በኦሚክሮን ቢያዝ ወደ ሆስፒታል የማይመጣበት ዕድል 81 ከመቶ በላይ ነው። ሐኪሙ የመጨረሻ መልዕክታቸው ይህ ነው። ""ብከተብም ባልከተብም ያው በቫይረሱ መያዜ አይቀርምና ቢቀርብኝስ የሚሉት ሰዎች ፍጹም የተሳሳቱ ናቸው። እውነት ነው፣ የተከተበም ያልተከተበም በተህዋሲው ሊያዝ ይችላል። ነገር ግን ውጤታቸው አንድ አይደለም። የተከተቡት በቤታቸው ያልፉታል፤ ያልተከተቡት ግን ይሞታሉ።""" https://www.bbc.com/amharic/news-59925005 +politics ኡጋንዳ ከሙዚቀኛው ተቃዋሚ ጋር ግንኙነት ያላቸው የዩቲዩብ ቻናሎች እንዲታገዱ ጠየቀች "የኡጋንዳ መንግሥት ከታዋቂው ሙዚቀኛና ተቃዋሚ ቦቢ ዋይን ግንኙነት ያላቸው የዩቲዩብ ቻናሎች እንዲታገዱ ጠይቋል። በኡጋንዳ የኮሚዩኒኬሽን ዘርፉን በዋነኝነት የሚቆጣጠረው አካል አስራ አራት የዩቲየብ ቻናሎች እንዲዘጉ ጠይቋል። ተቆጣጣሪው አካል ደብዳቤውን የፃፈው የዩቲዩብ ባለቤት ለሆነው ጉግል ሲሆን በባለፈው ወር ከደረስው ነውጥም ጋር ግንኙነት ያላቸውና ለ50 ሰዎችም መሞት ተጠያቂ ናቸው ያላቸው እንደሆነም አስፍሯል። በአገሪቱ ውስጥ ዋነኛ ተቃዋሚ የሚባለው ሮበርት ካያጉላንይ ወይም ቦቢ ዋይን እስር ተከትሎም በመዲናዋም ካምፓላም ሆነ በዋነኞቹ ከተሞች ነውጥ ተከስቷል። ሙዚቀኛው ቦቢ ዋይን የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን ጥሷል በሚልም ነው ለእስር የተዳረገው። እንዲታገዱ የተወሰኑት የዩቲዩብ ቻናሎች ከሙዚቀኛው ጋር ግንኙነት አላቸው ቢባልም የኡጋንዳ ኮሚዩኒኬሽን የህግ ጉዳዮች ኃላፊ በበኩላቸው ""የአጋጣሚ ጉዳይ ነው"" ማለታቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል። ኮሚሽኑ ለጉግል በፃፈው ደብዳቤ የዩቲብ ቻናሎቹን ነውጡን ለማነሳሳት ተጠቅመውበታል፤ ከህግ ውጭ ያላቸውንም ይዘቶች አሳይተዋል በማለትም ዴይሊ ሞኒተር ጋዜጣ ፅፏል። ኡጋንዳ በጥር ወር ምርጫዋን ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ናት። አገሪቷን ከሶስት አስርት አመታት በላይ የመሯት ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪንም በምርጫው ይወዳደራሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-55329580 +sports እግር ኳስ፡ አምስት ቁልፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ ኢትዮጵያ ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ከኒጀር ጋር ለምታደርገው የደርሶ መልስ ጨዋታ ተጠርተው ከነበሩት ተጫዋቾች መካከል አምስት ቁልፍ ተጫዋቾች ኮቪድ-19 እንደተገኘባቸው ተነገረ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ለብሔራዊ ቡድኑ ተጠርተው ከነበሩት 36 ተጫዋቾች መካከል ለቡድኑ ወሳኝ የሆኑት አምስት ተጫዋቾች በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። አቶ ባህሩ ለውድድሩ 41 ተጫዋቾች መጠራታቸውን አስታውሰው፣ አምስቱ በተለያየ ምክንያት ቡድኑን አለመቀላቀላቸውን አመልክተዋል። ከአምስቱ መካከል ሁለቱ በአሁን ሰዓት በውጭ አገር በሙከራና በመጫወት ላይ የሚገኙ ተጫዋቾች ናቸው ብለዋል። ኃላፊው አክለውም ሁለት ተጫዋቾች ዘግይተው ቡድኑን መቀላቀላቸውን ገልፀው፤ አንደኛው ደግሞ ከዚህ ቀደም በነበረበት ጉዳት ምክንያት ቡድኑን መቀላለቀል ያልቸለ መሆኑን ተናግረዋል። ለእግር ኳስ ቡድኑ አባላት የኮቪድ-19 ምርመራ ከመደረጉ በፊት የልብ ምርመራን ጨምሮ አጠቃላይ የጤና ምርመራ መደረጉን የተናገሩት ኃላፊው፤ የኮቪድ-19 ምርመራውም ለሁሉም መሰጠቱን ገልጸዋል። በዚህም መሠረት ለብሔራዊ ቡድኑ ለተጠሩት ለአጠቃላዩ 36 ተጫዋቾች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎ አምስት ተጫዋቾች ላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸ��ል ብለዋል አቶ ባሕሩ። ቫይረሱ ከተገኘባቸው ተጫዋቾች ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉትን የመለየት ሥራ እየተሰራም መሆኑን ጨምረው አመልክተዋል። እነዚህ ቫይረሱ የተገኘባቸው አምስት ተጫዋቾች በአሁኑ ጊዜ በሆቴል ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ መደረጉን በመግለጽ፣ ልምምድ እየሰሩ በቶሎ እንዲያገግሙ ፌዴሬሽኑ የተቻለውን ሁሉ እያደረገ መሆን አብራርተዋል። የአምስቱ ተጫዋቾች ውጤት እንደተሰማ በቡድኑ አባላት መካከል ድንጋጤ ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ከኅብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት የመጡ ባለሙያዎች ሙያዊ ምክር እንደሰጧቸውም ተገልጿል። እነዚህ በኮቪድ-19 የተያዙ አምስት ተጫዋቾች ለለይቶ ማቆያነት ፈቃድ ወደ ተሰጣቸው ሆቴሎች ዛሬ፣ ሰኞ፣ እንደሚዛወሩም ኃፊው አክለው ተናግረዋል። አምስቱ ተጫዋቾች በቡድኑ ውስጥ ቁልፍ ሚና እንደነበራቸው ያስታወሱት አቶ ባሕሩ በቡድኑ ላይ የሥነ ልቦና ጫና ቢኖረውም ቶሎ አገግመው ወደ ቡድኑ እንዲቀላቀሉ ይደረጋል ብለዋል። ተጫዋቾቹ ከ14 ቀን ለይቶ ማቆያ በኋላ ለጨዋታው ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚገመት ተናግረው፣ እነዚህን ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ የመቀላቀል ውሳኔ ግን የአሰልጣኙ መሆኑን አስረድተዋል። ቀሪ የቡድኑ አባላትን ከኮሮናቫይረስ ለመጠበቅ የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑንም አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ከኒጀር ጋር የሚኖራት ጨዋታ የሚካሄደው ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም መሆኑ ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል። በተያያዘ ዜና ከኮሮናቫይረስ ስጋት ጋር በተያያዘ ተቆርጠው የቆዩት ከፍተኛ ሊግ፣ አንደኛ ሊግና የሴቶች ፕሪሚየር ሊግን ኅዳር አጋማሽ ላይ ለመጀመር የእግር ስ ፌዴሬሽኑ አቅዶ ለቡድኖች ማሳወቁንና እነርሱም ዝግጅት ማድረጋቸውን አክለው ተናግረዋል። ውድድሮቹ የሚካሄዱት በዝግ ስታዲየም መሆኑን ገልፀው በሂደት አማራጮች እየታዩ ደጋፊዎች የሚገቡበት ሁኔታ ይፈቀዳል ብለው እንደሚያስቡ ለቢቢሲ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ተናግረዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54417243 +health ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስጂን እጥረት በርካቶች በሚሞቱባት ሕንድ ሆስፒታል ላይ በተነሳ እሳት 13 ህሙማን ሞቱ "ዛሬ አርብ በሕንዷ ከተማ ሙምባይ አቅራቢያ ባለ ኮቪድ-19 ህክምና ሆስፒታል ላይ በተነሳ ቢያንስ 13 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ። አርብ ጠዋት የተቀሰቀሰው እሳት ለበርካቶች ሞት ምክንያት ከሆነ በኋላ በቁጥጥር ሰር የዋለ ሲሆን ከአደጋው ተረፉት ህሙማን በአቅራቢያ ወደሚገኝ ሆስፒታል ተዘዋውረዋል። በርካታ ሰዎች በወረርሽኙ እየተያዙባት ባለችው ሕንድ በዛሬው ዕለት ብቻ 332,730 ሰዎች ላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ይህም በዓለም በአንድ ቀን የተመዘገበው የህሙማን ቁጥር ነው ተብሏል። በበሽታው ሰበብ ህይወታቸው ሚያልፍ ሰዎች አሃዝም እጅግ ከፍተኛ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓታት 2,263 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። በሕንድ ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተከትሎ በዋና ከተማዋ ኒው ደልሂ ያሉ ሆስፒታሎች ከፍተኛ የኦክስጂን እጥረት አጋጥሟቸዋል። በዚህም ኦክስጂን በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ታማሚዎች ህይወት እያለፈ መሆኑን እና በሕንድ ምርጥ የተባለ የጤና መሰረተ ልማት ባያላት ኒው ደልሂ ከተማ ለጽኑ ህሙማን የሚሆኑ አልጋዎች ሞልተዋል ተብሏል። እስከ አሁን ድረስ 16 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ሕንድ አረጋግጣለች። ትናንት ሐሙስ ይፋ የተደረገው የ24 ሰዓታት የምርመራ ውጤት ብቻ ከ314 ሺህ በላይ ሰዎች በአንድ ቀን በወረርሽኙ መያዛቸውን እና ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸውን ያሳያል። የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ናሬንድራ ሞዲም በቫይረሱ ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው ግዛቶች መሪዎች እና ከኦክስጂን አምራቾች ጋር ዛሬ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከኒው ደልሂ ውጪ ጉጃራት፣ ኡታር ፕራዴሽ እና ሃርያና የተሰኙት ግዛቶች ተመሳሳይ የኦክስጂን እጥረት ገጥሟቸዋል። ግዛቶች የኦክስጂን መያዣ ጋኖች ወደ ሌሎች ግዛቶች እንዳይዘዋወሩ በማገድ ላይ ሲሆኑ፤ የተወሰኑ ተቋማት ምርቶቻቸውን ማከማቸት መጀመራቸውን የደልሂ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በኮቪድ-19 ተይዞ በህክምና ላይ ያለው የሕንድ ፖለቲከኛ ሳውራህ ባራድዋጅ በትዊተር ገጹ የተገጠመለት ኦክስጂን ሊያልቅ የቀረው ሦስት ሰዓታት ብቻ መሆኑን አጋርቶ ነበር። ""ብዙ ሰዎች በኦክስጅን ላይ ጥገኛ ሆነው ነው ያሉት። የተገጠመላቸው ኦክስጂን ሲጠናቀቅ ህይወታቸው ያልፋል። ይህ ጊዜ በጋራ ተባብረን የምንሰራበት ነው"" ሲል ተማፅኗል። በበሽታው ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በሕንድ ባህል መሰረት የሞቱ ሰዎች አስከሬንን ለማቃጠል ከፍተኛ ወረፋ መኖሩን ቤተሰቦች ገልጸዋል። አንድ ሐኪም በሆስፒታ ውስጥ ተራ የሚጠብቁ በርካታ አስከሬኖች መኖራቸውንም ገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56827449 +sports የጀርመን ቡንደስሊጋ ቡድኖች ለ'ብላክ ላይቭስ ማተር' ያላቸውን ድጋፍ አሳዩ "የጀርመን ቡንደስሊጋ የእግር ኳስ ቡድኖች ለ'ብላክ ላይቭስ ማተር' እንቅስቃሴ ያላቸውን ድጋፍ በትናንትናው ዕለት በተለያዩ ተቃውሞዎች አሳይተዋል። የብሮሲያ ዶርትሙንድና ሄርታ በርሊን ተጫዋቾች በሲግናል ኢዱና ፓርክ በመገኘት ሜዳውን በመክበብም በጉልበታቸው ተንበርክከው ነበር። የዶርትሙንድ ተጫዋቾች ከውድድሩ በፊት ሲያሟሙቁ ""ፍትህ ከሌለ ሰላም የለም"" እንዲሁም ""ተባብረን እንቁም"" የሚሉ መልእክቶች በተፃፈባቸው ማሊያዎች (ካናቴራዎች) ነው። የባየር ሙኒክ ተወዳዳሪዎች ""ለዘረኝነት ቀይ ካርድ"" የሚል ማሊያ (ካናቴራ) ለብሰው የነበረ ሲሆን፤ በዛኑ ዕለት ባየር ሌቨርኩሰንን 4 ለ2 በሆነ ውጤት ረትተዋል። የቡንደስሊጋ ቡድኑ አመራሮችም እንዲሁም የቡድኑ አባላት በጨዋታዎች ላይ 'ብላክ ላይቭስ ማተር' የሚል ፅሁፍ ያለበት እጃቸው ላይ አጥልቀው ነበር ተብሏል። የሜይንዝ ቡድን አጥቂ ካሜሮናዊው ፒየር ኩንዴ ከኤይንትራችት ፍራንክፈርት ጋር ባደረጉት ጨዋታም ላይ ጎል ካስቆጠረ በኋላ በጉልበቱ ተንበርክኳል። በግጥሚያው ቡድኑ 2 ለ0 ረትቷል። በዚህ ሳምንትም ታዋቂዎቹ የስፖርት ሰዎች ሴረና ዊልያምስ፣ ፓውል ፖግባና ሊውስ ሃሚልተን በአሜሪካ በጥቁሮች ላይ የሚፈፀመውን የፖሊስ ጭካኔ አስመልክቶ ድምፃቸውን አሰምተዋል። ባለፈው ሳምንት በሚኒያፖሊስ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ እጁ ከኋላ እንደተጠፈረ ከመሬት ላይ ተጣብቆ ነጭ ፖሊስ አንገቱን በጉልበቱ ለዘጠኝ ደቂቃ ተጭኖት ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ በበርካታ ግዛቶች ተቃውሞች ተቀጣጥለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-52954511 +health የአውሮፓ ዕለታዊ የኮቪድ ሞት ካለፈው ሳምንት አንጻር 40 በመቶ ከፍ ብሏል "በአውሮፓ በየቀኑ የሚመዘገበው የሞት መጠን ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በ40 በመቶ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ለቢቢሲ ገለጸ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ዶ/ር ማርጋሬት ሃሪስ እንደተናገሩት ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ እንግሊዝ፣ ኔዘርላንድስ እና ሩሲያ በአንድ ሦስተኛ ባደገው ቁጥር ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል። ""በሆስፒታሎች ውስጥ የጽኑ ህሙማን የህክምና ክፍሎች በጣም በታመሙ ሰዎች መሞላት ጀምረዋል"" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ በቀን 320 የሆነ ከፍተኛ ሞት በማስመዝገብ በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ26ሺህ በላይ አድርሶታል። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በ 221 ሰዎች ሞት ምክንያት በጣሊያን ውስጥም እንዲሁ ከፍተኛ ጭማሪ ታይቷል። በአጠቃላይ በኦስትሪያ የሟቾች ቁጥር ማክሰኞ ከ 1000 በላይ ሆኗል። ጣሊያን ውስጥም ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ወደ 22,000 ደርሰዋል። አዲስ የተጣለውን ገደብ በመቃወም ሰኞ አመሻሽ ላይ የተቃውሞ ሰልፎች በጣሊያን ተካሂደዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ምን አለ? ከቢቢሲ ወርልድ ጋር ቆይታ ያደረጉት ያደረጉት ዶ/ር ሃሪስ ""በመላው አውሮፓ የከፋ እና አስደንጋጭ በሆነ መልኩ በቫይረሱ የሚያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ጭማሪ እያየን ነው"" ብለዋል። ከቀደመው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በየቀኑ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንድ ሦስተኛ ሲጨምር የሚመዘገበው የሞት መጠን በ40 በመቶ ከፍ ብሏል። ""የሆስፒታሎችን አቅም በተሻለ መንገድ ማስተዳደር ቢቻልም በበርካታ አገራት የሚገኙ ሆስፒታሎች አልጋዎች በፍጥነት እየተያዙ ነው"" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ""በተወሰኑ የአውሮፓ አገራት ውስጥ የተጣሉ አዳዲስ ገደቦች ውጤታማነት የሚታወቀው በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው"" ብለዋል። ሩሲያ ከዛሬ ጀምሮ ሰዎች በሚበዙባቸው እንደ ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ታክሲ እና አሳንሰር ያሉ ቦታዎች ላይ የአፍና አፍኝጫ መሸፈኛዎችን ማድረግን አስገዳጅ አድርጋለች። የፈረንሳይ መንግሥት በፓሪስ እና በሌሎች ከተሞች ውስጥ ቀድሞ የተጣሉትን እገዳዎች ማራዘምን ጨምሮ ጥብቅ እርምጃዎችን በመተግበር ላይ እየተወያየ ነው። ጣሊያን ካለፈው አርብ ጀምሮ ምግብና እና መጠጥ ቤቶች፣ የስፖርት መዝወተሪያ ስፍራዎች ና ሲኒማዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መዘጋታቸውን በመቃወም በቱሪን ሰልፍ ያደረጉ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው ፖሊስ በሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ለመተኮስ ተገዷል።" https://www.bbc.com/amharic/54708506 +health የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት ላይ የተደረገ ሙከራ ከፍተኛ ውጤት አሳየ "በኦክስፎርድ የኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እና በቡርኪናፋሶ ሳይንቲስቶች በጋራ የተሰራ አዲስ የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት በተደረገለት ሙከራ ውጤታማ መሆነ ተገለጸ። በክትባቱ ላይ በተደረጉት መጀመሪያ ሙከራዎች 77 በመቶ በሆነ ውጤት ስኬታማ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ይህም አሁን ለህክምና ከሚውሉ መድኃኒቶች አንጻር ውጤታማነቱ በእጅጉ የላቀ ነው ተብሏል። የህክምና ጉዳዮች መጽሔት በሆነው 'ላንሴት' ላይ የታተመው የጥናቱ ውጤት 450 ከቡርኪናፋሶ የተወጣጡ ህጻናት የተሳተፉበት ሲሆን ከዚህ በኋላ በርከት ያሉ ሰዎች የሚሳተፉበት ሙከራ ይደረግበታል። በቀጣዩ የሙከራ ሂደትም 4,800 ህጻናት የሚሳተፉ ሲሆን እነዚህም ከቡርኪናፋሶ፣ ከማሊ እና ከኬንያ ናቸው። ""ይህ ሙከራ በጣም አስደሳች የሆነ ውጤታማነት ነው ያሳየው። ክትባቱ ከዚህ በፊት ከነበሩ ህክምናዊች አንጻር የተሻለ የመከላከል ብቃት አሳይቷል። ""በመቀጠል የምናካሂዳቸውን ሁለተኛና ሦስተኛ ዙር ሙከራዎች እየተጠባበቅን ነው። በእነዚህ ሙከራዎች በርከት ያሉ ሰዎች የሚሳተፉ ሲሆን በስፋት ቢመረት ምን አይነት ውጤት እንደሚኖረው ለማወቅ ይረዳናል"" ብለዋል በቡርኪናፋሶ የጤና ሳይንስ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ሃሊዶ ቲንቶ። ለወባ በሽታ የሚሆን ክትባት ማግኘት በህክምና ምርምር ውስጥ እግጅ ትልቅ ዜና ነው የሚሆነው። ሙከራው በስኬት የሚጠናቀቅ ከሆነ ትልቅ ግኝት እንደሚሆን ይጠበቃል። የወባ በሽታ በዓመት ከ400 ሺህ በላይ ሰዎችን የሚገድል ሲሆን አብዛኛዎቹ ከሰሀራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገራት ውስጥ የሚኖሩ ህጻናት ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ለወባ በሽታ የሚሆን አንድ ክትባት ያለ ሲሆን ውጤታማነቱ ደግሞ 50 በመቶ ብቻ ነው። በአዲሱ ክትባት የመጀመሪያ ዙር ሙከራ ላይ 77 በመቶ ውጤታማነት የታየ ሲሆን በሌሎች አገራትም ላይ ለመሞከር ታቅዷል። በጊዜ ብዛት ደግሞ ቢያንስ በአራት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ይሞከራል። በሙከራው የሚሳተፉት 5 ሺህ የሚሆኑ ህጻናት ደግሞ እድሜያቸው ከሦስት ዓመት በታች የሆኑ ናቸው። አሁን በሙከራ ላይ የሚገኘው አዲሱ ክትባት ሙሉ ፈቃድ አላገኘም። ነገር ግን ውጤታማነቱ በሙከራዎች በተገቢ ሁኔታ የሚረጋገጥ ከሆነ የበርካቶችን ህይወት የማትረፍ ትልቅ አቅም አለው ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56827450 +business መንግሥት በኦሮሚያ ባለው ታጣቂ ቡድን ላይ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገለጸ "የመንግሥት ኃይል በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ላይ የተጠናከረ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ዛሬ ረፋድ በሰጡት መግለጫ፣ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ሲል የሚጠራውንና መንግሥት 'ሸኔ' ሲል በአሸባሪነት የፈረጀውን ታጣቂ ኃይል ለማስወገድ ፀረ ሽምቅ ውጊያ ኮማንዶ በማሰማራት ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል። ዘመቻው በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ እና በምሥራቅ ወለጋ፣ በምዕራብ እና በምሥራቅ ጉጂ፣ በሰሜን፣ በምሥራቅ እና በምዕራብ ሸዋ እንዲሁም በቦርና ዞኖች እየተካሄደ እንደሆነም ሚኒስትሩ ገልጸዋል። እየተደረገ ባለው ዘመቻ ""በሺዎች የሚቆጠሩ"" የታጣቂው ቡደኑ አባላት መገደላቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ ፣ የቡድኑ አመራሮች፣ ታጣቂዎች፣ የስንቅና የሥልጠና ማዕከል ""ከጥቅም ውጪ እንዲሆን ተደርጓል፤ መሳሪያዎችም ተማርከዋል ብለዋል። ለገሰ ቱሉ ( ዶ/ር) ታጣቂው ኃይል በተቀናጀው ኦፕሬሽን እየደረሰበት ያለውን ጉዳት መቋቋም ባለመቻሉ እየተበተነ ነው ሲሉም በመግለጫቸው አመልክተዋል። ሆኖም ከትናንት በስቲያ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ( ኦፌኮ) በሰጠው መግለጫ በኦሮሚያ ዞኖች ከዓለም ዓይን የተሰወረ ጦርነት እየተካሄደ ነው ሲል በጦርነቱ በርካታ ዜጎች በጅምላ መገደላቸውን ገልጿል። ኦፌኮ እየተፈጸሙ ነው ያላቸው ""የጅምላ ግድያዎች""ም ገለልተኛ በሆነ ዓለም አቀፍ አካልም እንዲጣራ ጠይቋል። እንደ ፓርቲው መግለጫ ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ንጹሃን ናቸው ያላቸው ከ297 በላይ ሰዎች በክልሉ በመንግሥት ኃይሎች ተገድለዋል፤ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። የተባበሩት መንግሥታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ( ኦቻ) በዚህ ሳምንት ባወጣው ሪፖርት በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር እና ግጭቶች ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው እንደወጡ አመልክቷል። ቀደም ብሎም መንግሥት በዘመቻው ድል እየቀናኝ ነው ማለቱን ተከትሎ ፣ ታጣቂ ቡድኑ በታጣቂዎቹ ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለና የመንግሥት እርምጃ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን በቃል አቀባዩ በኩል ለቢቢሲ ገልጾ ነበር። በክልሉ በታጣቂ ቡድኑና በመንግሥት መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ ሰላማዊ ሰዎች ሰለባ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለሥልጣናትም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ለቢቢሲ እንደተናገሩት መንግሥት ታጣቂ ቡድኑ በስፋት በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎችም በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃትም ፈጽሟል። መንግሥት ግን እነዚህን ክሶች ያጣጣላቸው ሲሆን ዘመቻው በክልሉ እየደረሰ ያለውን ሞት፣ መፈናቀልና የንብረት ውድመት ለማስቀረት የተጀመረ ነው ብሏል። ባለፉት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ እና ምዕራብ ሸዋ አካባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት ታጣቂዎች ፈፀሙት በተባለ ጥቃት በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፤ ከቤት ንብረታቸውም ተፈናቅለዋል። ለገሰ (ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ይህንን ""ዘመቻ ለማጠልሸት የሚጥሩ ኃይሎች አሉ"" ያሉ ሲሆን፣ እነዚህ ኃይሎች መን��ሥት በታጣቂ ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰድ ሲጀምር ንጹሃን ዜጎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጉዳት እየደረሰባቸው ነው በሚል የሚጮሁ ናቸው"" ሲሉ ማንነታቸውን ያልገለጿቸውን አካላት ከሰዋል። ይሁን እንጂ ለተከታታይ ሳምንታት እየተካሄደ ባለው ዘመቻ በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ""እፎይታ እየተሰማቸው ነው"" ብለዋል። በመግለጫው የተነሱ ሌሎች ጉዳዮችስ ? ስለጎንደሩ ግጭት በጎንደር በቀብር ስፍራ በተወሰኑ ሰዎች አለመግባባት በተፈጠረ ግጭት ጉዳት ቢከሰትም ታቅዶ ነበር ያሉት 'ሴራ' መክሸፉን ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ተናግረዋል። በግጭቱ የወደሙ መስጊዶችና አብያተ ክርስቲያናትን በጋራ ለመገንባት፣ ንብረታቸው የወደመባቸውና የተዘረፈባቸውን ግለሰቦች መልሶ ለማቋቋምም እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ግጭት እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ አካላትም ጉዳያቸው ፍርድ ቤት ቀርቦ እየታየ ነው ብለዋል። ከሳምንታት በፊት በጎንደር በቀብር ሥፍራ ላይ በተከሰተ ሃይማኖታዊ መልክ ያለው ግጭት ቢያንስ የ21 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ150 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ መገለጹ ይታወሳል። ይህ ግጭት ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተዛምቶም በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል። ሚኒስትሩ ይህንን በተመለከተ የፌደራል ፖሊስ የመርማሪ ቡድን እስካሁን የተሰሩ ሥራዎችን በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። 'አልሸባብ' የኮሚዩኒኬሽ አገልግሎት ሚኒስትሩ በመግለጫቸው የአልሻባብ የሽብር ቡድን ከሸኔ እና ከህወሓት ጋር በመቀናጀት በመሃል አገር፣ በምሥራቅና በምዕራብ የአገሪቱ ክፍሎች የሽብር ጥቃቶችን ለመፈፀም የወጠኑትን እቅድ መንግሥት በወሰደው እርምጃ ሳይሳካ መቅረቱን ተናግረዋል። በተወሰደው እርምጃም ቀደም ብሎ በርካታ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፣ ባለፉት ቀናት በሶማሌ ክልል የተለያዩ ዞኖች፣ በኦሮሚያ፣ በምዕራብ ሐረርጌ እና በአርሲ፣ በምዕራብና ምሥራቅ ባሌ በርካታ የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጸዋል። እስካሁንም 45 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ሚኒስትሩ ገልጸው፣ ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በርካታ የጦር መሣሪያዎች መያዛቸውንና በየቤተ እምነቶች የተቀበሩ መሣሪያዎችም በሕዝብ ጥቆማ እየተለቀሙ ነው ብለዋል። በዚህም 105 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 13 ብሬል፣ 25 አርፒጂ፣ 25 ሳጥን የተለያዩ መጠን ያላቸው ጥይቶች፣ አራት ስናይፐር መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አመልክተዋል። በአማራ ክልል ስላለው የፀጥታ ሁኔታ የአማራ ክልል እና አጎራባች ክልሎችን ለማጋጨት እና ሕገ ወጥነት ለማስፋፋት ሆነ ብለው የሚሰሩ ኃይሎች ላይ የሚወሰድ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ ውስጥ ያሉ ""ኢ መደበኛ አደረጃጀቶች"" ሕግ በማስከበርና ክልሉን ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ለመመለስ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የሚያስችል አሰራር ተነድፎ አሳታፊ ውይይቶች እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል። ሚኒስትሩ አክለውም በክልሉ ላይ ሊቃጣ የሚችልን ማንኛውም ጥቃት ለመመከት የሚደረግ እንቅስቃሴ ለመግታት የሚሰሩ ኃይሎች ላይም ምህረት እንደማይኖር አስጠንቅቀዋል። ሰብዓዊ እርዳታ ለትግራይ ሚኒስትሩ ከሰሜኑ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ጋር በተያያዘም ወደ ትግራይ በየብስም፣ በአየርም የሚጓጓዘው ሰብዓዊ እርዳታ እንደቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ሚኒስትሩ መግለጫ ከሆነ ባለፈው ሳምንት 165 ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቀለ ገብተዋል። የእርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ማቅረብ የሚችሉት እርዳታ ያህል እንዲያቀርቡ መንግሥትም የተቻለውን እያደረገ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ነገር ግን የትግራይ ኃይሎች ለእርዳታ ማጓጓዝ ሥራው እንቅፋት ሆነዋል ብለዋል። ""ህወሓት ከአፋር ክልል መውጣቱን ቢገልጽም፣ አሁንም በአፋር ክልል ከበርሃሌ፣ ከኮነባ፣ ከአብአላ እና ከመጋሌ ወረዳዎች አልወጣም። በአማራ ክልልም፣ አድርቃይ፣ ጠለምት፣ አበርገሌ እና ሌሎች አካባቢዎችን ይዞ ይገኛል"" ሲሉ ከሰዋል። ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ ያለገደብ ትግራይ እንዲደርስ ሙሉ በሙሉ ከአፋር ክልል መውጣቱን ያስታወቀ ቢሆንም የክልሉ የፀጥታ ባለሥልጣናት ኃይሎቹ አሁንም በክልሉ እንደሚገኙ ለቢቢሲ መግለጻቸው የሚታወስ ነው። መንግሥት ከህወሓት የሚቃጣን ጥቃት ለመመከት በየትኛውም ጊዜና ሰዓት ሙሉ ዝግጁነትና አቅም ያለው መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ግጭት ቀስቃሽ በሆኑ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች ተነሳስቶ ወደ ግጭት እንደማይገባ ግን በአጽንኦት ተናግረዋል። የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ የምግብ ዋጋ ንረትና ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳሳቢ ሆኗል። ሚኒስትሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫም የሸቀጦች ዋጋ ግሽበት ከምርት አቅርቦት ጋር የሚያያዝ መሆኑን ጠቅሰው፣ ስኳር፣ ዘይት፣ የህጻናት አልሚ ምግቦች እና ሌሎች ምግብ ነክ ፍጆታዎችን በፍራንኮ ቫሉታ አገር ውስጥ እንዲገቡ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። ፍራንኮ ቫሉታ ሕጋዊ ከሆነ ምንጭ የሚገኝ የውጭ ምንዛሬ ሲሆን የባንክ ቤት ፈቃድ ሳያስፈልገው ከውጪ አገር ዕቃ ለማስገባት የሚያስችል ፈቃድ ነው። ባለፉት ወራት በ700 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በመስኖ የለማ ስንዴ ውጤት በማስገኘቱ ከ25 ሚሊየን ኩንታል በላይ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና ተጨማሪ ምርት ለማግኘት ጥረት እየተደረገ እንደሆነም ሚኒስትሩ አክለዋል። ከዚህ ባሻገርም በግንባታው ዘርፍ ላይ እና በሲሚንቶ ላይ የሚታየውን ችግር ለመፍታትም እየተሠራ ነው ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61435712 +business ‘ፓትሪዮት’፡ አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጣት ብዙ የተነገረለት አየር መቃወሚያ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ምዕራባዊያንን አጥብቀው ሲጠይቁ የነበረው አንድ ነገር የአየር መቃወሚያ እንዲሰጣቸው ነበር። ምክንያቱም ሩሲያ በአየር ኃይሏ ኪዬቭን ጨምሮ ዋና ዋና ከተሞችን በጨለማ እንዲዋጡ አድርጋለች። በካሚካዚ ድሮንና በተወንጫፊ ሚሳኤሎች ብዙ ጥፋት አድርሳለች። ውሃና መብራት ለሚሊዮኖች ቅንጦት ሆኖ እንዲሰማቸው ሆኗል። ዩክሬናውያን የውርጩን ዘመን ያለማሞቅያ በብርድ እየተንዘፈዘፉ እንዲኖሩ ተደርገዋል። በዩክሬን ብዙ ከተሞች መብራት በፈረቃ ነው የሚከፋፈለው። ከዚህም የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ በዩክሬን ሰማይ ላይ የሚፈነጩትን ድሮኖችና ሚሳኤሎች ጭጭ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗል። አንድ ነገር መደረግ ነበረበት። ዜሌንስኪ ምዕራባዊያን ድረሱልን አሉ። ይነስም ይብዛ ደርሰውላቸዋል። ይሁንና እስከዛሬ የደረሳቸው የአየር መቃወሚያ ዘመናዊ ቢሆንም ከሩሲያ አቅም አንጻር ሲታይ የልብ አያደርስም። ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ወደ አሜሪካ ማማተር ጀመሩ። ጆ ባይደን አላሳፈሯቸውም። ባይደን ለዜሌንስኪ አንድ ያረጋገጡላቸው ነገር ቢኖር ከሰሞኑ እጅግ የላቁ ናቸው የሚባሉትን የአየር መቃወሚያዎች እንደሚልኩላቸው ነው። ፓትሪዮት ይባላል ስማቸው። ይህ እርዳታ አሜሪካ ለዩክሬን 66 ቢሊዮን ዶላር ከለገሰች በኋላ የመጣ ትልቁ ስጦታ ሆኗል። ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያዎች ውድ፣ በጣም ውጤታማ እና የልብ አድርስ ናቸው ይባላል። አንድ ፓትሪዮት ሚሳኤል ዋጋው ይጠራ ከተባለ ዋጋው 3 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል። ይህ ማለት በምሕጻረ ቃል ኤንኤኤምኤስ (NASAMS) የሚባሉትን ዘመናዊ የአየር መቃወሚያዎች በሦስት እጥፍ በዋጋ ይበልጣቸዋል። ፓትሪዮት ሚሳኤሎች የተሠሩ�� በኢራቅ ጦርነት ጊዜ ነበር፤ የሩሲያ ሠራሽ ሚሳኤሎችን ለመቃወም። ይህም እንደ አውሮፓዊያኑ በ1980ዎቹ መጀመርያ ማለት ነው። ነገር ግን ከዚያ ወዲህ ብዙ ማሻሻያዎች ተደርገውለት አሁን ወደደረሰበት ወደ ላቀ ደረጃ ደርሷል። ብዙ ያደጉ አገሮች አየር ክልላቸውን የሚጠብቁት በዚህ የአየር መቃወሚያ ነው። በቀላሉ ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ ይቻላል። በአንድ ጊዜ በርካታ የአየር ጥቃቶችን መመከት ይችላል። የኤሌክትሮኒክ የግንኙነት እቀባ (ጃሚንግ) ቢሰነዘርበት ራሱ ይህን መመከት የሚያስችል መሣሪያ ተገጥሞለታል። 24 ሰዓት የራዳር ቅኝት ያደርጋል። ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያዎችን ለመጠቀም የራዳር ጣቢያ፣ የዕዝ ጣቢያና ማስወንጨፊያ ማማ ያስፈልጋሉ። ከ40-160 ኪሎ ሜትር የጠላት ዒላማን ተምዘግዝገው ማደባየት ይችላሉ። በዋናነት አገልግሎታቸው የዋርዲያ ነው። ጥበቃ የማድረግ። ከተማን፣ ወይም አንድ አካባቢን፣ ወይም አንድ ግዙፍ መሠረተ ልማትን ከየትኛውም ዓይነት የአየር ጥቃት መጠበቅ። አሜሪካዊያን ወይም የኔቶ አባል አገራት ዩክሬን ገብተው እነዚህን መሣሪያዎች መጠቀም አይችሉም። ስለዚህ ዩክሬናዊያን ለዚሁ ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያ ሚሳኤል ሲባል ልዩ ስልጠና መውሰድ ነበረባቸው። አሜሪካ በጀርመን ባላት የጦር ሰፈር ይህንኑ ሥልጠና ለተመረጡ ዩክሬናዊያን ሰጥታቸዋለች ተብሏል። ዛሬ ሐሙስ ሞስኮ ባወጣችው መግለጫ ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያን ለዩክሬን ማስታጠቅ “የምዕራባዊያን ጠብ አጫሪነት” መቀጠሉን ማሳያ ነው ስትል ድርጊቱን አውግዛለች። ከዛሬ ጀምሮ እነዚህ መሣሪያዎች ዋንኛ ዒላማዋ እንደሚሆኑም ዝታለች። የጦር ባለሙያዎች ይህን ፓትሪዮት የአየር መቃወሚያ ለዩክሬን ከተሰጡ ስጦታዎች ትልቁ ብለው ያወድሱታል። ምክንያት ሲጠቅሱም በተለይ ኼርሶን ከተማን የዩክሬን ወታደሮች ከሩሲያ ወታደሮች ከነጠቁ በኋላ የዩክሬን ሰማይ ክፍት ሆኖ መቆየቱን ያወሳሉ። በዚህ የተነሳ ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ክፉኛ ውድመት ሲደርስባቸው ቆይቷል። የዕለት ተዕለት ኑሮ በዩክሬን ፈተና የሆነውም ለዚሁ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው የሩሲያ ሚሳኤሎችንና ድሮኖችን ማቆም የሚችል ቴክኖሎጂ በመጥፋቱ ነበር። አሁን ፓትሪዮት እንደ ስሙ አርበኝነቱን ያሳይ ይሆናል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c3g43d1n4dko +politics ሩሲያ እና ዩክሬን: ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዴት ፈጠረች? "ሩሲያ በቅርብ አመታት በአፍሪካ ተጽዕኖዋን እያሰፋች ነው። ከዩክሬን ወረራ በኋላ አዳዲሶቹ አጋሮቿ ድጋፍ እንዲሰጧት ወይም እንደተባበሩት መንግሥታት ባሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቢያንስ ገለልተኛ ሆነው እንዲቆዩ ትጠብቃለች። ከሊቢያ እስከ ማሊ፣ ሱዳን፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ በሞዛምቢክ እና ሌሎችም ሃገራት ሩሲያ ይበልጥ እየተሳተፈች ነው። አብዛኛው ተሳትፎዋ ደግሞ በወታደራዊ ኃይል ሲሆን አማፂያንን ወይም የጂሃዲስት ታጣቂዎችን መዋጋትን ይጨምራል። ኬንያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል ባትሆንም ሩስያ በዩክሬን የወሰደችውን እርምጃ አስመልክቶ ተቃውሞዋን በግልፅ አሳይታለች። ይህን የኬንያን አቋም የሚደግፉ ሌሎች ሃገራት ግን ብዙም አልታዩም። የአፍሪካ ህብረት ግጭቱ ""እጅግ እንዳሳሰበው"" ቢገልጽም በሩሲያ ላይ የሰነዘረው ትችት የለም። በብሪክስ ቡድን ውስጥ የሩሲያ አጋር የሆነችው ደቡብ አፍሪካ ሃገሪቱ ጦሯን ከዩክሬን እንድታስወጣ ስትጠይቅ በድርድር መፍትሄ እንዳለም ጨምራ ገልጻለች። ሩሲያ የዶኔስክ እና የሉሃንስክ ክልሎችን እንደ ገለልተኛ ሃገር ዕውቅና መስጠቷን እንደሚደግፉ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን-አርቻን��� ቱዋዴራ መናገራቸው ተዘግቧል። ረቡዕ ደግሞ የሱዳኑ ምክትል መሪ መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ የልዑካን ቡድን እየመሩ ወደ ሞስኮ አቅንተዋል። ይህም በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ያሳያል። በአፍሪካ ያለው አጋርነት እየተቀየረ ስለመሆኑ ከሚያሳዩት ምሳሌዎች አንዱ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጥቃት ከመሰንዘሯ ከአንድ ሳምንት በፊት ፈረንሳይ በማሊ ጂሃዲስቶችን በመዋጋት ላይ የነበራት ተሳትፎ ማብቃቱ ነው። የማሊው ጠቅላይ ሚኒስትር ቾጌል ማይጋ ከፍራንስ 24 ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሃገራቸው ከሩሲያ ጋር ወታደራዊ ስምምነቶች መፈራረሟን አረጋግጠዋል። አወዛጋቢው የሩሲያ የግል ወታደራዊ ኩባንያ ዋግነር ግሩፕ እጁ እንደሌለበትም ገልጸዋል። ይህ ለማሊ የሚደረገው የሩስያ እርዳታ ለቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግሥት ከቀረበው ድጋፍ ጋር ተደምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት ሩሲያ ይፋዊ እና መደበኛ ባልሆነ መልኩ በአፍሪካ ላይ ያላትን ተጽዕኖ ለማሳደግ እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑን ያሳያል። የታደሰው የሩስያ-አፍሪካ ግንኙነት እየተጠናከረ መጥቶ እአአ በ2019 በደቡባዊ ሩሲያ ሶቺ ከተማ የተካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ከ50 በላይ የሃገራት ልዑካን ሲሳተፉ 43ቱ ርዕሳነ ብሔሮች ናቸው። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለመሪዎቹ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር የነፃነት እንቅስቃሴዎችን የመደገፍ ታሪክን ለመጠበቅ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ቃል ገብተዋል። ሩሲያ ለበርካታ የአፍሪካ መንግሥታት ግልጽ ያልሆነ የፀጥታ ጥበቃ፣ በስልጠና፣ በስለላ፣ በመሳሪያ እንዲሁም የሩሲያ ቅጥረኞችን በአካባቢው ግጭቶች ውስጥ በማሳተፍም ትታወቃለች። ፑቲን እንዳመለከቱት ታሪካዊ ግንኙነቱ ከሩሲያ በፊት ከነበረችው የሶቪየት ህብረት (ዩኤስኤስአር) ዘመን ድረስ የሚሄድ ሲሆን በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ካሉት በርካታ የውድድር ቦታዎች መካከል አንዷ አፍሪካ ነበረች። እአአ በ 1991 የሶቭየት ህብረት ስትፈራርስ ጀምሮ እስካለፉት ጥቂት ዓመታት ድረስ ሩሲያ የሽግግር ጊዜ ውስጥ እያለፈች የነበረ ሲሆን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነትም ዋነኛ አጀንዳ አልነበረም ። በድጋሚ የልዕለ ኃያልነት ደረጃን እንደገና ማግኘት ለሩሲያ ፕሬዚዳንት የውጭ ፖሊሲ ቅድሚያ የሚሰጡት ሆነ። እአአ በ 2014 ሩሲያ የክሬሚያን ሰርጥ ወደ ግዛቷ መቀላቀሏን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ማዕቀቦችን ማስተናገድ ብቻ ሳይሆን ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላት ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ተበላሽቷል። ከዓለም አቀፍ መገለል ስጋት ጋር በተያያዘ ሞስኮ አዳዲስ አጋሮችን መፈለግ ጀመረች። በሩሲያ ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር የሆኑት ኢሪና አብራሞቫ ""በእገዳው ምክንያት ሩሲያ ወደ ውጭ ለሚላከው ምርቷ አዲስ ገበያ መፈለግ አለባት"" ብለዋል። ሩሲያ የምትፈልገው ገበያ ብቻ አይደለም። እየጨመረ ያለውን ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖ ትፈልግ ነበር እአአ በ 2014 በሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የተሳተፈችው ፕሬዚደንት በሽር አል አሳድን ደግፋ ምዕራባውያን እያደረጉ ያሉትን ትርምስ ለማጉላት እና ሩሲያ እንዴት ማስተካከል እንደምትችል ለማሳየት ነው። ከሶሪያ በኋላ ደግሞ ወደ አፍሪካ አህጉር አቀናች። በደቡብ አፍሪካ የኩዋዙሉ-ናታል ዩኒቨርሲቲ የክብር ፕሮፌሰር ኢሪና ፊላቶቫ እንደሚሉት ሩሲያ በአፍሪካ ውስጥ የነበራት ቁልፍ ተግባር እንደሶሪያ ሁሉ የምዕራባውያንን ተጽዕኖ ማቃለል ነበር። ለምሳሌ አውሮፓውያን በሳህል ያለውን የጂሃዲስት ስጋት መቆጣጠር እንዳልቻሉ ለማሳየት ፈልጋ ነበር። ይህንንም በአፍሪካ ውስጥ ለማሳካት ሁለት ፖሊሲ ተጠቀመች። የመጀመሪያው በአንዳንድ ሃገራት ይፋዊ ወታደራዊ ስልጠናዎችን መስጠት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ መደበኛ ያልሆኑ እንደ ዋግነር ግሩፕ ያሉ ድርጅቶች ደግሞ በመዋጋት ጭምር እየተሳተፉ ነው። በ2017 ከዋግነር ግሩፕ የሩስያ ቅጥረኛ ገዳይ ቡድን የታየባት የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ነበረች። በኋላም እነሱን ተከትሎ ኦፊሴላዊ የሩሲያ ወታደራዊ አማካሪዎች ቡድን ገባ። ዓላማቸው ፕሬዝደንት ቱዋዴራን በስልጣን እንዲቆዩ መርዳት ነበር። በቅጥረኞቹ የሚፈጸሙት የጭካኔ ወንጀሎች እየተለመደ መጣ። ሩሲያ ግን አንድም ዜጋዋ በጦር ወንጀሎች እና በሠላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም ውስጥ እንዳልተሳተፉ በተደጋጋሚ ገልጻለች። የሩስያ ቅጥረኞች በሊቢያ፣ ሱዳን፣ ሞዛምቢክ እና ማሊ የተለያዩ በተለያዩ ደረጃዎችን ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል። ሌላው የአህጉሪቱ ጠቀሜታ እያደገ መሄዱን የሚያመለክተው አፍሪካ ለሩሲያ የጦር መሳሪያ ኢንዱስትሪ ዋና ገበያ መሆኗ ነው። ወደ አፍሪካ ከሚገባው የጦር መሳሪያ ግማሽ ያህሉ ከሩሲያ መሆኑን የሀገሪቱ የመንግስት የጦር መሳሪያ ላኪ ኤጀንሲ አስታውቋል። ዋና መሣሪያ ገዢዎች አልጄሪያ እና ግብፅ ናቸው። ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ እና ካሜሩንም አዲስ ደንበኞች ሆነዋል። በዲፕሎማሲው ግንባርም ለጠበቀው ግንኙነት የቀረበ ሽልማት አለ። አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከሩብ በላይ ድምጽ ያላት ሲሆን በሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ድምጽ ልትሆን ትችላለች። በሞስኮ ከፍተኛ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት የታተመውና ስለ አፍሪካ እና ሩሲያ ትብብር የሚገልጸው የ 2021 ዘገባ እንደሚያመለክተው ከዚህ ቀደም የሩሲያ ድርጊትን በተመለከተ የአፍሪካ ሀገራት ገለልተኛ የመሆን አዝማሚያ አሳይተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60543495 +politics የፑቲንን አስተዳደር ሙስና የሚታገሉት የሩስያ ሴቶች "ወንዶች ጎልተው የወጡበትን የሩስያ ፖለቲካ ለመለወጥ ሙስናን የሚቃወሙ ሴቶች ቆርጠው ተነስተዋል። እነዚህ ሴቶች የለውጥ ተምሳሌት ተብለዋል። ከተቃዋሚው አሌክሲ ናቫልኒ ጋር ይሠራሉ። ናቫልኒ የጸረ ሙስና ንቅናቄን ማዕከል ያደረገው ኤፍቢኬ ፓርቲውን ለፓርላማ ምርጫ ሲያዘጋጅ የእነዚህ ሴቶች ሚና ጉልህ ነው። የሩስያ ፓርላማ ለፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታማኝ ነው። አብላጫውን ቁጥር የያዙትም ወንዶች ናቸው። ከታህታይ ምክር ቤቱ የሴቶች ድርሻ 16% ሲሆን ከላዕላይ ምክር ቤቱ ደግሞ 17% መቀመጫ አላቸው። በናቫልኒ ፓርቲ ወንዶችም ሴቶችም ቁልፍ ሚና አላቸው። በንቅናቄው ጎልተው የወጡ ሴቶች እነማን እንደሆኑ እናስተዋውቃችሁ። ዩሊያ ናቫልኒያ እአአ በ2000 ከናቫልኒ ጋር ትዳር የመሠረተችው ዩሊያ ሕይወቷ ፖሊስ ጣቢያና ፍርድ ቤት በመመላለስ የተሞላ ሆኗል። ቤቷም በተደጋጋሚ ተበርብሯል። ቱርክ የተዋወቁት ጥንዶች ሁለቱም 44ኛ ዓመታቸውን ይዘዋል። ዩሊያ ያጠናችው ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሲሆን፤ ባንክ ውስጥ ሠርታለች። ቤታቸው ሞስኮ ሲሆን፤ ሴት ልጃቸው ዳርያ አሜሪካ እየተማረች ነው። ዩሊያ አሁን ከመገናኛ ብዙኃንና ከመንግሥት ስለላ ሸሽታ ጀርመን ነች። በመላው ሩስያ እሷን የሚደግፉ ሴቶች ቀይ ለብሰው ፎቶ በመነሳት ኢንስታግራም ላይ ለጥፈዋል። ባለቤቷ የሁለት ዓመት ከስምንት ወር እስር ሲፈረድበት ቀይ ለብሳ ነበር ፍርድ ቤት የተገኘችው። የፋሽን ጋዜጠኛዋ ካይታ ፌዶሮቫ ይህንን በማስመልከት ቀይ ከለበሰች ወዲህ ነው ሌሎች ሴቶች ቀይ በማድረግ ድጋፋቸውን ማሳየት የጀመሩት። ""አትዘኚ። የከፋ ነገር አይከሰትም"" በማለት ነበር ባለቤቷ ናቫልኒ ከመታሰሩ በፊት የተሰናበታት። ወደ ፓለቲካ ተሳትፎ የገባችው ባለፈው ነሐሴ ባለቤቷ ተመርዞ ለሞት በተቃረበበት ወቅት ነበር። ባለቤቷ ከተመረዘ በኋላ ከሰርቢያ ወደ ጀርመን እንዲወሰድ የወሰነችው እሷ ነበረች። ከሰመመን ሲነቃ ""ትራሴን ታስተካክልልኝ የነበረችው እሷ እንደነበረች አስታውሳለሁ። እስክትመጣ እጠብቃት ነበር"" ብሏል ናቫልኒ። ባለቤቷ አገግሞ ከጀርመን ወደ ሩስያ ሲመለስ ታስሯል። እስሩን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ካደረጉ አንዷ ደግሞ እሷ ነበረች። የባለቤቷን ጸረ ሙስና ተቃውሞ የምትደግፈው ዩሊያ፤ ሰልፍ ከወጣች በኋላ 270 ዶላር ተቀጥታለች። ሊቦቭ ሶቦል የ33 ዓመቷ ጠበቃ በናቫልኒ ቡድን ውስጥ ከሚታወቁ አንዷ ናት። አሁን በቁም እስር ላይ ትገኛለች። እሷና ሌሎችም የናቫልኒ ደጋፊዎች ከተቃውሞ ሰልፉ በኋላ ታስረዋል። ለመታሰራቸው ምክንያት የተባለው የኮቪድ-19 መከላከያ መርህን መጣስ ነው። ናቫልኒ ሙስናን የሚያጋልጥበትን የዩቲዩብ ገጽ ፕሮዲውስ የምታደርገው ሊቦቭ ናት። ገጹ በሚሊዮኖች የሚቆጡ ተከታዮች አሉት። እአአ በ2019 ባለሥልጣኖች ከሞስኮ የምርጫ ኮሚቴ ጎትተው ሲያስወጧት የሚያሳይ ቪድዮ ካሰራጨች ወዲህ ታዋቂነቷ ጨምሯል። ከዚያ በኋላ ለአንድ ወር የረሀብ አድማ አድርጋለች። እሷና ሌሎችም የግል እጩዎች በሞስኮ ከተማ አስተዳደር ምርጫ እንዳይሳተፉ ታግደዋል። መስከረም ላይ ለሩስያ ፓርላማ ምርጫ የመወዳደር እቅድ አላት። ከ2011 ጀምሮ በናቫልኒ የጸረ ሙስና ፕሮጀክት ውስጥ ሠርታለች። 2014 ላይ ሚሮሳለቫ የተባለች ልጅ የወለደች ሲሆን፤ በሥራዋ ምክንያት በ2016 ባለቤቷ ጥቃት እንደደረሰበት ትናገራለች። በጸረ ሙስና ንቅናቄ ምክንያት እሷም ናቫልኒም በተደጋጋሚ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ከከሰሷቸው መካከል ዩቭጌኒ ፕሪጎዚን የተባለው ባለሀብት ይጠቀሳል። ለክሬምሊን ቅርብ የሆነው ባለጸጋው ""የፑቲን ሼፍ"" በሚል ይታወቃል። አንስቲዥያ ቫስሌይቫ ዶክተር ናት። በዚህ ወር ፖሊሶች ቤቷን ሲበረብሩ ችላ ብላቸው የቤትሆቨንን ሙዚቃ ስትጫወት የሚያሳይ ቪድዮ ተለቆ ዝነኛ ሆናለች። የ36 ዓመቷ አንስቴዥያ ለናቫልኒ ቅርብ የሆነ የሀኪሞች ቡድን ትመራለች። 2017 ላይ ናቫልኒ አይኑ ላይ ጉዳት ሲደርስበት እሷ ነበረች ያከመችው። የሁለት ልጆች እናት ስትሆን፤ ናቫልኒን የሚደግፍ ሰልፍ በማካሄዷ የቁም እስር ላይ ትገኛለች። ከዚህ ቀደም ከሞስኮ ታይምስ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ የሩስያ መንግሥት ለኮሮናቫይረስ የሰጠውን ምላሽ ተችታለች። እናቷ ሀኪም እንደነበሩና የፖለቲካ ተሳትፎ ለማዳበር የተነሳሳችውም በዚህ ምክንያት እንደሆነ ትናገራለች። ""የአገራችን ጤና ሥርዓት ውስጥ ያለውን እያዩ ፖለቲካ ውስጥ አለመሳተፍ አይቻልም"" ትላለች። ኪራ ያርሚሽ ከ2014 ጀምሮ የናቫልኒ ቃል አቀባይ ስትሆን፤ በቁም እስር ላይ ትገኛለች። ወደተለያዩ አገሮች ሲጓዝ አብራው ትሄዳለች። ነሐሴ ላይ አውሮፕላን ውስጥ ሳለ ተመርዞ ራሱን ሲስትም አብረው እየተጓዙ ነበር። የሞስኮ ዓለም አቀፍ ተቋምን የተቀላቀለችው የቴሌቭዥን የተሰጥኦ ውድድር አሸንፋ ሲሆን፤ ያጠናችው ጋዜጠኝነት ነው። በጸረ ሙስና ንቅናቄ ከታሰረች በኋላ በማረሚያ ቤት ስለሚገኙ ሴቶች የሚያትት ረዥም ልቦለድ ጽፋለች። በናቫልኒ የዩቲዩብ ገጽም ብዙ መሰናዶዎች መርታለች። ኦልጋ ሚካሎቫ የናቫልኒ ጠበቃ ናት። በአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ልምድ አላት። 2017 ላይ ሩስያ ናቫልኒን እና ወንድሙን ገንዘብ አጭበርብራችኋላ ብላ ከሳ ነበር። ፍርድ ቤቱ ግን ክሱን ውድቅ አድርጎ የሩስያ የፍትሕ ሚንስትር በሺዎች የሚቆጠር ዶላር ካሳ እንዲከፍል ወስኗል። ናቫልኒ ከጀርመን ወደ ሩስያ ሲመለስ በቁጥጥር ሥር የዋለው ከዚህ ክስ ጋር በተያያዘ ነው። ኢኮ ሞስኪቭ ከተባለ የራድዮ ጣቢያ ጋር ባደረገችው ቆይታ ሕገ አ��ጪውና ሕግ አስፈጻሚው መካከል ልዩነት የለም ስትል ተችታለች። የአውሮፓ ትልቁ የሰብዓዊ መብት ፍርድ ቤት በሆነው ካውንስል ውስጥ ለናቫልኒ ጥብቅና የምትቆመውም ኦልጋ ናት።" https://www.bbc.com/amharic/56066793 +health ለ15 ወራት ደሞዛቸው ያልተከፈላቸው የትግራይ የሕክምና ባለሙያዎች "የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ኃይሎች ወደ ጦርነት ከመግባታቸው በፊት ማጀታቸው የሞላ፣ ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት የሚልኩ፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው የሚተርፉ ነበሩ። በመቀለ የሚገኙ እና ቢቢሲ ያነጋገራቸው መምህራን፣ የሕክምና ባለሙያዎች እና ሌሎች የመንግሥት ተቀጣሪዎች ከሁለት ዓመት በፊት የነበራቸው ሕይወት የዛሬውን አይመስልም ነበር። ዛሬ በትግራይ ያለው ጦርነት ተባብሶ፣ በክልሉ የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ሥራ አቁመው፣ የሰብዓዊ እርዳታ ተመናምኖ ሁሉም የሰው እጅ ጠባቂ እንደሆነ ይናገራሉ። ለሌሎች ይዘረጋ የነበረ እጅ ዛሬ ለምጽዋት ደጅ ይጠናል። ለገባ ለወጣ ይቆረስበት የነበረ መሶብ ጦሙን አድሯል። ዕድለኛ የሆነ 15 ኪሎ ግራም የእርዳታ ስንዴ ዱቄት ተቀብሎ ልጆቹን ያበላል። የተቀረው እና ምንም ማድረግ የማይችለው ደግሞ የተሻለ ቀን እንዲመጣ፣ ጦርነቱ እንዲያበቃና ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ይጸልያል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ኅብረት እና አሜሪካ እየተባባሰ የመጣው ከባድ ውጊያ ያለውን ሁኔታ አስከፊ ሊያደርገው እንደሚችል በመግለጽ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል። ወደ ትግራይ ክልል ጋዜጠኞች እንዲገቡ ባለመፍቀዱ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ምክንያት፣ የግጭቱ መጠን እና ያስከተለው ሰብአዊ ቀውስ ስፋት በዝርዝር ለመረዳት አስቸጋሪ አድርጎታል። ቢቢሲ ያነጋገራቸውን የሕክምና ባለሙያዎች ሕይወት እናንተ ቤት ምን ይመስላል ሲል ጠይቋቸዋል። በአይደር ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ባለሞያ የሆኑት ዶ/ር ፋሲካ ዓምደሥላሴ ለረዥም ወራት ደሞዝ እንዳልተቀበሉ እና ከብዙ ወራት በኋላ “ዕድል ቀንቶ” የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች የሚሰጡትን የእርዳታ ስንዴ መቀበላቸውን ይናገራሉ። “ሕይወት አድን ምግብ ካላገኙ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ህጻናት ጋር ሲነጻጸር ልጆቼ ዕድለኞች ናቸው” በማለት ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር የሰጣቸውን እርዳታ የሚያሳይ ምስልና ጽሑፍ በትዊተር ገጻቸው ላይም አስፍረው ነበር። “እርዳታ ሳገኝ በጣም ተደሰትኩ፤ ከዚህ የባሰ መጥፋት፣ ህመም እና ሞት ነው የሚመጣው። በርካታ መልካም ሕይወት የነበራቸው ሰዎች፣ አስተማሪዎች . . . ወደ ጎዳና ወጥተው እያየናቸው ነው። የጉልበት ሥራ የሚሰሩ፣ መንገድ ላይ ሳሙና የሚሸጡ ብዙ የመንግሥት ሠራተኞች አሉ” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሆስፒታሉ ሠራተኞች በግንቦት ወር 2013 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ደሞዛቸው እንደተከፈላቸው ገልፀው፣ ነገር ግን በዚያው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የትግራይ ኃይሎች ከተማዋን ከተቆጣጠሩ በኋላ የወር ደሞዛቸው አልተከፈላቸውም። ዶ/ር ፋሲካ፣ አክለውም በባሕር ማዶ ወዳጅ ዘመድ ያላቸው የእነርሱን ድጋፍ እየጠበቁ አንደሚኖሩ አስታውሰው፣ ነገር ግን ሁሉም የሚደግፈው ዘመድ አለው ማለት እንዳልሆነ ያብራራሉ። አክለውም “በሰብአዊ እርዳታ የሚመጣው ስንዴ ተቀብለው ለወፍጮ ቤት የሚሆን ገንዘብ የሚቸገሩ አሉ” ሲሉ የችግሩን ግዝፈት ለማሳየት ይጥራሉ። በአይደር ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ውስጥ የሚሰራ እና ከሰኔ 30 ጀምሮ ወርሃዊ ደሞዙን ያላገኘው ስሜን አትግለፁ ያለን ዶክተር “ባልደረቦቼ በሙሉ ችግር ውስጥ ናቸው” ይላል። ይህ ዶክተር ላለፉት ሦስት ዓመታት በሆስፒታሉ ውስጥ ያገለገለ ሲሆን፣ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነው። “ከዚህ በ��ት ሕይወቴን እየመራሁ ወላጆቼን ጭምር እረዳ ነበር። አሁን ግን ለአካለ መጠን እንዳልደረሰ ልጅ ተመልሰው ወላጆቼ እየረዱኝ ነው። እነሱ ገጠር ሆነው የሚያገኟትን እህል እየተካፈልን ነው የምንኖረው።” አብዛኛዎቹ የሆስፒታሉ ሠራተኞች እንደሌላው ማኅበረሰብ እርዳታ ይጠብቃሉ የምትለው ነርስ ፍሬ በበኩሏ፣ “ከገበሬ ዘመዶቼና ወዳጆቼ የሚላክልኝን እየጠበቅኩ ቀን እገፋለሁ” ትላለች። ከጦርነቱ በፊትም ቢሆን በክልሉ ውስጥ በነበሩ ማኅበራዊ ችግሮች እና ዝቅተኛ የሥራ ዕድል ምክንያት በርካታ የቤተሰብ አባላት እርስ በእርስ በመተጋገዝ ላይ ነበር የሚኖሩት። “የቤተሰብና የዘመድ ኃላፊነት የተሸከምን ዜጎች እንደመሆናችን መጠን ያለ ክፍያ ልጆችን ማሳደግ ከባድ ነው። ምግብ ተበልቶ በሕይወት መቆየት ከባድ ሆኖ ሳለ በህክምና ሥነ-ምግባር ስለ ሌሎች ሕይወት መጨነቅ ስላለብን፣ ሥራ መቋረጥ የለበትም በሚል በባዶ ሆዱ ወደ ሥራ ቦታ መጥቶ ነው እየሰራ ያለው” ስትል ነርስ ፍሬ ትገልጻለች። የመቀለ ዩኒቨርስቲ አካል የሆነው አይደር ሪፈራል ሆስፒታል በትምህርት ሚኒስቴር ስር የሚተዳደር ነው። ቢቢሲምለሠራተኞቹ የደመወዝ አልተከፈለንም ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በስልክና በጽሑፍ መልዕክት ብንሞክርም ጥረታችን አልተሳካም። በትግራይ ከአንድ ዓመት በላይ የባንክ እና የትራንስፖርት አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን መሠረታዊ ሸቀጦች ከአፋር እና ከአማራ ክልሎች ""በሕገ-ወጥ"" መንገድ እንደሚገቡ የቢቢሲ ምንጮች ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የመሠረታዊ ሸቀጦች የዋጋ ንረት እና የገንዘብ እጥረት እንዳለ፣ ካለው የነዳጅ እጥረት የተነሳም የትራንስፖርት ዋጋ በመናሩ የዕለት ኑሯቸው መክበዱን ነዋሪዎች ያስረዳሉ። “ለራስና ለልጆች መሆን አለመቻል ሕይወት ዓላማ እንዲያጣ ያደርጋል። በአሁኑ ጊዜ መኮረኒ፣ ሩዝ፣ ዘይት ውድ ናቸው” ሲሉ ሌላ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የሕክምና ባለሙያ ተናግረዋል። አብዛኞቹ የመንግሥት ሠራተኞች የሚኖሩት በኪራይ ቤት በመሆኑ፣ ገንዘብ አለማግኘት አከራይና ተከራይ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል የሚለው ደግሞ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና የጤና ባለሙያ የሆነው ዶክተር ነው። “አብዛኛው ሠራተኛ አይደለም ለቤት ኪራይ ለታክሲም መክፈል አይችልም። እኔ የሰው ፊት ላለማየት ስል የሞቀ ቤት ባይሆንም 70 ካሬ መንደር በሚገኘው ያላለቀ ቤት ውስጥ ነው የምኖረው። ኤሌክትሪክ እና ውሃ በጭራሽ አይታሰቡም፤ ከጉድጓድ የሚመጣ ውሃ ነው የምንጠጣው። ውሃ ማከሚያ መድኃኒት እንኳ አናገኝም።” የትግራይ ክልል ከአንድ ዓመት በላይ ከበባ ላይ በመቆየቱ ምክንያት የሕክምና ባለሞያዎች እና ታካሚዎች የሚያደርጉት ግራ ገብቷቸዋል የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ “የሰብአዊ እርዳታ እንዲሁም የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ተከትሎ በርካታ ታካሚዎች እጃችን ላይ እየሞቱ ይገኛሉ” ይላሉ። ህጻናት በምግብ እጥረት ዋነኛ ተጠቂዎች መሆናቸውን የገለፁት የሕክምና ባለሙያዎቹ፣ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በትግራይ 2,500 የሚጠጉ ህጻናት በምግብ እጥረት መሞታቸውን ቢቢሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ይህ አኃዝ ግን መሬት ላይ ያለውን እውነታ እንደማያሳይ የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ። የሰብአዊ እርዳታ ሰጪ ተቋማት ጦርነቱ አስከፊ የሆነ ሰብአዊ ቀውስ ማስከተሉና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሎ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች አፈናቅሏል ሲሉ ይገልጻሉ። “ሁኔታው በጣም አሳሳቢ ከመሆኑ የተነሳ ደሞዛችን ሳይከፈለን መስራታችን ብቻ ሳይሆን ችግሩ ታካሚዎች ላይ ጭምር ሲታይ ከባድ ያደ��ገዋል። ተርበን መጥተንም የተራቡ ሰዎች ማከም፣ እንዲህ አይነት ምግብ ብሉ ማለት ይከብዳል። የምንሰራበት ሆስፒታል ሳይቀር የሚዘጋበት ደረጃ ላይ ደርሷል” ሲል ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀው ዶክተር ተናግሯል። አክሎም “ብዙውን ጊዜ የምናሳልፈው በሥራ ላይ ነው፤ ባለን ጊዜ ደግሞ ዛሬ ወይም ነገ እርዳታ እናገኛለን ብለን ስንጠብቅ እንውላለን። ገጠር የሚኖሩ ወላጆቼ እርሻ ስላላቸው አሁን እየረዱኝ ነው” ብሏል። “በእግዚአብሔር ጸጋ ነው የምኖረው” የምትለው ነርስ ፍሬ፣ ከሰባት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ልጆች እንዳሏትና ልጆቿ የለመዱት ምግብ እንድታቀርብላቸው ሲጠይቋት እንደምትጨነቅ ትናግራለች። “ምግብ ሳይበሉ የሚያድሩበት ጊዜም ስላለ፣ ለጥያቄያቸው መልስ ማጣት የሚፈጥረው ህመም ከባድ ነው። በጭንቀት ራሴን እንዳልጎዳ እፈራለሁ።” በሰኔ ወር መጀመሪያ 2022 የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ክብሮም ገብረሥላሴ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በክልሉ ትልቁ ሆስፒታል በመብራት መቆራረጥ እና በመድኃኒት እጦት ምክንያት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት አቁሟል ብለው ነበር። ነገር ግን በጦርነቱ ምክንያት በተፈጠሩ ተደራራቢ ችግሮች ምክንያት፣ ሆስፒታሉ የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት የሚፈለገው ያህል ባይሆንም ሠራተኞች በግል ችግራቸው ምክንያት ሥራ ለማቆም አስበው አያውቁም ስትል ነርስ ፍሬ ገልጻለች። “መንግሥት ግዴታውን እንዳልተወጣ አውቃለሁ፤ ሆኖም እኔ ወደ ሥራ ገበታ ባለመምጣቴ የሚጠፋ ሕይወት አለ ብዬ ስለማስብ ነው ወደ ሥራ የምመጣው። እኛ አገልግሎት ካቆምን ነገ እዚህ አገር ማን ይኖራል? ብዙ ታማሚዎች በመድኃኒት፣ በምግብ እና በኦክሲጅን እጦት ሞተዋል። ነገር ግን ሊተርፍ የሚችለውን ሰው ማዳን በመቻሌ ውጤታማ ነኝ ብዬ አስባለሁ።” ዶ/ር ፋሲካ ዓምደሥላሴ ሕክምና ባለሙያዎቹ እየሰሩ የሚገኙበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያስረዱ “ቁርስ ሳይበሉ ወደ ሥራ ቦታ መጥተው የወደቁ ነርሶች አሉ፤ በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ላይ ነን። አንድ ሰው ያመጣው ምግብም ቅመሺ ተብላ ልጆቼን ቁርስ ሳልሰጣቸው ነው የመጣሁት ብላ ያለቀሰች ነርስ አለች። በችግር ምክንያት የሚለምኑና ወደ ቤተሰቦቻቸው የተመለሱ አሉ” ይላሉ። “የምንኖረው ሕይወት፣ ይሆናል ብለን አስበነው የማናውቅ ነው” የሚለው ሌላው በሆስፒታሉ ውስጥ መምህርና የጤና ባለሙያ የሆነው ዶክተር በበኩሉ፣ በትራንስፖርት እና በገንዘብ ችግር ምክንያት ቤተሰቦቹ ያሉበት ሁኔታ እንደማያውቅ ይናገራል። “ሕይወታችን በቃላት ከሚገለጸው በላይ ነው፤ ነገር ግን ሥራ አላቆምንም። ለማንኛውም እኛ የምንሄደው መድኃኒት ቢያጡም ‘አይዟችሁ’ ለማለት ከታካሚዎች መራቅ ስለሌለብን ነው። ሙያችን ገንዘብ አልተከፈለንም በሚል የሚተው አይደለም። እዚህ የታመሙትን ትተን ቤት እንድንቀመጥ ህሊናችን አይፈቅድልንም። የተራቡትን ማብላት ባልችልም የታመሙትን መድኃኒቱን ሰጥቼ በሕይወት ማኖር እችላለሁ።” የሆስፒታሉ ሠራተኞች በፌደራል መንግሥት ተቋም ተቀጥረው የሚሰሩ በመሆናቸው በጦርነቱ ምክንያት “ሆን ተብሎ” የወር ደሞዛችን ተይዟል የሚል ቅሬታ አላቸው። “ብዙ የሰብአዊ እርዳታ ኤጀንሲዎች ገንዘብ አምጥተው ለሠራተኞቻቸው ይከፍላሉ፤ የቀጠረን አካል ግን ዝም አለ። ባንክ ዝግ ነው፤ ከዚህ በፊት የቆጠብኩት በችግር ጊዜ እንዳልጠቀምበት ጭምር ነው የተከለከልኩት። ይግባኝ የማይባል ፍርድ” በማለት አንድ ሠራተኛ ቅሬታውን ለቢቢሲ ገልጿል። እስከ አሁን ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች አልተሳኩም። “በጣም የሚያሳስበኝ ነገር ይህ ሁኔታ መቼ እንደሚያበቃ ነው። ልጆቻችን ይዘን እንዳንወጣ የስደት መንገዱ በእግር የሚኬድ ስለሆነ በወታደሮች እንዳንገደል እንፈራለን። ሙሉ ለሙሉ ተከባችሁ በረሃብ ጥፉ የሚያስብል ሁኔታ ነው ያለው” ብሏል ዶክተሩ።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cgegl7dd8k7o +sports እግር ኳስ ፡ የዲያጎ ማራዶና የአስከሬን ምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ "ከአንድ ወር በፊት በልብ ችግር ምክንያት ያረፈው የቀድሞው የዓለም የእግር ኳስ ኮከብ በዲያጎ አርማንዶ ማራዶና አስከሬን ላይ የተደረገው ምርምራ ይፋ ሆነ። የአርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ የአስከሬን ምርመራ እንዳረጋገጠው ህይወቱ ባለፈበት ጊዜ ምንም አይነት አልኮልም ሆነ ዕጽ መውሰዱን የሚያሳይ ምልክቶች እንዳልተገኙ ተገልጿል። በአውሮፓውያኑ 1986 ላይ በተደረገው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ላይ ኮከብ በመሆን አገሩ አርጀንቲና በአሸናፊነት ዋንጫ እንድትነሳ ያስቻለው ማራዶና በኅዳር ወር ላይ ነበር በድንገት ህይወቱ ያለፈው። ማራዶና በሞተበት ጊዜ ለህይወቱ ማለፍ በርካታ መላምቶች ሲቀርቡ የነበረ ሲሆን፤ በአስከሬኑ ላይ በተደረገው ምርመራ ተገኘው ውጤት ግን ከብዙዎች ግምት የተለየ ሆኗል። ምርመራው እንዳመለከው የ60 ዓመቱ ማራዶና በኩላሊቱ፣ በልቡ ላይና በሳምባው ላይ ችግሮች ነበሩበት ተብሏል። በእግር ኳስ ኮከቡ አስከሬን ላይ ምርመራ እንዲደረግ የታዘዘው በተለይ ማራዶና ህይወቱ ከማለፉ በፊት በተደረገለት የህክምና ድጋፍ ዙሪያ ለሞቱ ምክንያት ሊሆን የሚችል ማንኛውም አይነት ቸልተኝነት ከነበረ ለማጣራት ነበር። የምን ጊዜም የእግር ኳስ ኮከብ ተደርጎ የሚታሰበው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኅዳር ወር መጀመሪያ ላይ በአንጎሉ ውስጥ ላጋጠመው የደም መርጋት የተሳካ የቀዶ ህክምና ተደርጎለት የነበረ ሲሆን፤ በተጨማሪም ለነበረበት የአልኮል ሱስ ህክምና ለመጀመር እየተዘጋጀ ነበር። ከአገሩ አርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ባሻገር ለቦካ ጁኒየርስና ለናፖሊ ክለቦች የተጫወተው ማራዶና ህይወቱ ባለፈበት ዕለት በአስከሬኑ ላይ ምርመራ በተደረገበት ጊዜ በከባድ የልብ ችግር ምክንያት መሞቱን ለመወቅ ተችሎ ነበር። ከማራዶና ሞት ጋር በተያያዘ በመጨረሻው ሰዓት የህክምና ድጋፍ ያደረገለት ዶክተር ህይወቱን ለማዳን ተገቢውን ድጋፍ አላደረገም በሚሉና በሌሎችም ጉዳዮች ሲወቀስ የቆየ ቢሆንም በመጨረሻ የተገኘው የአስከሬን ምርመራ ውጤት ግን ነጻ ያወጣዋል ተብሏል። ከማራዶና ሞት በኋላ የሦስት ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀናት በመላዋ አርጀንቲና ታውጆ አስከሬኑ በዋና ከተማዋ ቦነስ አይስ ውስጥ በሚገኘው የፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት ውስጥ ተቀምጦ፤ አገሬው በከፍተኛ ቁጥር በመገኘት ሐዘኑን በመግለጽ እንደተሰናበተው ይታወሳል። ይሁን እንጂ የማራዶና አስከሬን እስካሁን እንደተቀመጠ ይገኛል ለዚህም ምክንያቱ ከተደረገው ምርመራ ባሻገር ከማራዶና ሞት በኋላ ኮከቡን የእግር ኳስ ተጫዋች አባትነት የሚጠይቅ አቤቱታ ለፍርድ ቤት በመቅረቡ ነው። ለዚህም የአርጀንቲና አንድ ፍርድ ቤት የማራዶና አስከሬን ለዘረ መል (DNA) ምርመራ ስለሚፈለግ ""ባለበት ይጠበቅ"" የሚል በሰጠው ውሳኔ መሰረት አስከሬኑ ለጊዜው ቦነስ አይረስ ውስጥ በሚገኝ አንድ የግል የአስከሬን ማቆያ ውስጥ እንዲቆይ ተወስኗል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55458658 +health በአፍሪካ የተፈራውን ያክል ድህነት ሰዎችን ለኮሮናቫይረስ አጋልጧል? ከአፍሪካ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚዋ ደቡብ አፍሪካ ናት። አሁን ላይ ግን በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው። በሌሎች የአፍሪካ አገራት ያለው ስርጭት መጠንም በአንጻራዊነት ዝግ ያለ ነው። አፍሪካ ውስጥ በርካታ የተጨናነቁ መንደሮች አሉ። በእነዚህ መንደሮች ንጽህናና አካላዊ ርቀት መጠበቅ ከባድ ነው። በአንጻራዊነት ደህና በሚባሉ ከተማ ቀመስ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ቫይረሱን በፍጥነት ሊያሰራጩት እንደሚችሉ የጤና ባለሙያዎች ሲያስጠነቅቁ ተደምጠዋል። በደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 አማካሪ ቡድን ኃላፊ ሳሊም አብዱል ካሪም እንደሚሉት፤ ሰዎች በብዛት፣ ተጨናንቀው በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ቫይረሱ በፍጥነት ይሰራጫል። እውነታው ከዚህ የባለሙያዎች መላ ምት ተቃራኒ ቢሆንስ? የተጨናነቁ መንደሮች እንደተገመተው ለበሽታው መሰራጨት ምክንያት ሳይሆኑ እንዲያውም ቫይረሱ በስፋት እንዳይስፋፋ አድርገው ቢሆንስ? የአህጉሪቱ ድህነት እንደተፈራው ለወረርሽኙ ተጋላጭ ሳያደርጋት ቀርቶ ቢሆንስ? ሚሥጥሩ ምንድን ነው? ኮሮናቫይረስ መሰራጨት ሲጀምር ሁሉም ባለሙያዎች አፍሪካ አደጋ ውስጥ ትወድቃለች ብለዋል። የደቡብ አፍሪካው ቫይሮሎጂስት ሻቢር ማህዲ “ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደምንገባ አስቤ ነበር። አበቃልን ብዬም ነበር” ይላሉ። በጣም ተስፋ ሰጪ ናቸው የተባሉ መላ ምቶች ሳይቀሩ ለህሙማን አልጋ እንደሚጠፋ፣ የጤና ሥርዓቱ እንደሚቃወስ ሲጠቁሙ ነበር። ሆኖም ግን በደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዩናይትድ ኪንግደም በሰባት እጥፍ ያንሳል። ደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳትሆን ሌሎች አገራትም የተፈራው ያህል ቫይረሱ ጉዳት እያደረሰባቸው አይደለም። ሆስፒታሎች እንደተሰጋው አልተጨናነቁም። በተቀረው ዓለም እንደተከሰተው የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ጫፍ ላይ ደርሶም አልታየም። ፕ/ር ሻቢር፤ “በአብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት የቫይረሱ ስርጭት ጫፍ አልታየም። ለምን እንደሆነ አልገባኝም። ግልጽ ያልሆነና ለማመን የሚያስቸግር ነው” ይላሉ። አፍሪካ ውስጥ ኮሮናቫይረስ በአስጊ ሁኔታ ያልተሰራጨው አብዛኛው የአህጉሪቱ ነዋሪ ወጣት ስለሆነ ነው የሚሉ ባለሙያዎች አሉ። የአፍሪካውያን አማካይ እድሜ ከአውሮፓውያኑ በግማሽ ያንሳል። የቶኒ ብሌር ተቋም የአፍሪካ ዳይሬክተር ቲም ብሮምፊልድ እንደሚሉት፤ አፍሪካ የወጣቶች አህጉር መሆኗ ከበሽታው ተከላክሏታል። ነገር ግን በበሽታው የተያዙ ሰዎችን እድሜ ከግምት ያስገቡ የስታትስቲክስ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ እድሜ ከበሽታው የሚከላከል ብቸኛ ነገር አይደለም። ፕ/ር ሳሊም “ትልቁ ነጥብ እድሜ አይደለም” የሚሉትም ለዚህ ነው። በደቡብ አፍሪካ እና በሌሎችም አገራት ወረርሽኙ መሰራጨት እንደጀመረ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ሚናው ቀላል አይደለም። ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉም ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል። በሌላ በኩል የአህጉሪቱ ከፍታ እና ሙቀት የበሽታውን ስርጭት ይቀንሳል የሚለው መላ ምት እንደማይሠራ ተገልጿል። በቂ የመሠረተ ልማት ዝርጋት ባለመኖሩ ለወደፊት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት ያላቸው አሉ። “አፍሪካ ክፉውን ጊዜ አልፋለች ማለት አልችልም። አንድ ቀን ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምር ይሆናል” ሲሉ ፕ/ር ሳሊም ያስረዳሉ። ሌሎቹ ኮሮናቫይረሶች በሶዌቶ የክትባት ቤተ ሙከራ ውስጥ ሳይንቲስቶች ምርምር እያደረጉ ይገኛሉ። በቤተ ሙከራው ለአምስት ዓመታት የቆየ የሰው ደም ናሙና አለ። ይህም የኢንፍሉዌንዛ ክትባት ላይ ምርምር ሲካሄድ የተገኘ ናሙና ነው። ተመራማሪዎቹ፤ ሰዎች በሌሎች አይነት ኮሮናቫይረሶች መያዛቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እየፈለጉ ነው። ይህ ማለት ሰውነት ራሱን ከኮቪድ-19 የሚከላከልበት አቅም አዳብሯል ማለት ነው። “ከዚህ ቀደም በሽታን የመከላከል አቅም ማዳበር ተችሎ ሊሆን ይችላል። ቫይረሱ በሌሎች የዓለም ክፍሎች የተስፋፋው ያህል በአፍሪካ ያልተ��ራጨውም ለዚህ ይሆናል” ይላሉ ፕ/ር ሻቢር። በተጨናነቀ መንደር የሚኖሩ ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ስለሆኑ ምናልባትም በጊዜ ሂደት ኮቪድ-19ን መከላከል የሚያስችል አቅም አዳብረው ሊሆን እንደሚችል የደቡብ አፍሪካ ሳይንቲስቶች ይገምታሉ። “በከፍተኛ ሁኔታ በተጨናነቁ አካባቢዎች በሽታውን የመከላከል አቅም ሊፈጠር ይችላል። ብዙ ሰዎች ምንም የበሽታው ምልክት የማይታይባቸው ወይም መጠነኛ ምልክት የሚያሳዩት ለዚህ ይሆናል” ሲሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። የአፍሪካ ድህነት የኮሮናቫይረስ ተጋላጭነትን ቀንሶት ሊሆን እንደሚችልም ያምናሉ። በሌላ በኩል እንደ ብራዚል ባሉ ዜጎች ተጨናንቀው የሚኖሩባቸው አገሮች በርካቶች በቫይረሱ እየተያዙ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-54009884 +business 'ገበሬው አምርቶ የማይጠቀምባት ኢትዮጵያ' የኑሮ ውድነቱን እንዴት መቀነስ ትችላለች? "በምጣኔ ሃብታዊ ቋንቋ የአቅርቦት ሰንሰለት ይባላል። በእንግሊዝኛው 'ሰፕላይ ቼይን' የሚባለው ማለት ነው። የአቅርቦት ሰንሰለት ሸማቹ ወይም ተገልጋዩ የሚፈልገው ነገር ለገበያ እስኪቀርብ ድረስ ያለው ሂደት ነው። የምጣኔ ሃብት ሰዎች የአቅርቦት ሰንሰለት የአንዲት ሃገር ዕድገት ምሰሶ ወይም ከምሰሶዎች አንዱ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም ይላሉ። የአቅርቦት ሰንሰለትን በቀላል ቋንቋ ለማስረዳት ወደ አርባምንጭ እንሂድ። አርባምንጭ የፍራፍሬ ሃገር ናት። በተለይ ደግሞ ሙዝ። አንድ ፍሬ ሙዝ አርባምንጭ ላይ ያለው ዋጋ እና አዲስ አበባ ተመሳሳይ አይደለም። እንዲሆንም ላይጠበቅ ይችላል። ለምሳሌ አንድ ፍሬ አርባምንጭ ከተማ 20 ሳንቲም ተሸጠ እንበል፤ አዲስ አበባ ሲደርስ ደግሞ 1 ብር [ምሳሌ ነው]። ሙዝ አርባምንጭ በቅሎና አድጎ አዲስ አበባ አሊያም ሌሎች ከተሞች የሚደርሰው የአቅርቦት ሰንሰለትን ተሳፍሮ ነው። አምራች አለ። ከአምራች ተቀብሎ የሚያከፋፍል አለ። ከአከፋፋይ ተቀብሎ የሚቸረችር ይኖራል። ከዚያ ገዥ። ስለ አቅርቦት ሰንሰለት ይህን ካልን ከለት'ተዕለት ኑሯችን ጋር ያለውን ቁርኝት እንይ። አንድ የኢትዮጵያ ኑሮ ሁኔታ የሚያሳስባቸው ግለሰብ፣ አማራ ክልል ውስጥ ያለች አንድ ሽንኩርት አምራች ሥፍራ ያለው የሽንኩርት ዋጋና ከተማ ሲደርስ ያለው ዋጋ እጅግ የተለያየ መሆኑ ያሳስባል ሲሉ በትዊተር ገፃቸው አሥፍረው ነበር። ለመሆኑ የአቅርቦት ሰንሰለትና የኑሮ ውድነት ግንኙነት አላቸው? የአቅርቦት ሰንሰለቱ የተቃና ቢሆን ኖሮ ለውጥ ይመጣል? ""እርግጥ ነው ግንኙነት አላቸው። ነገር ግን ሌሎች ምክንያቶች የበለጠ ተፅዕኖ አላቸው"" ይላሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ። ""ያለፈውን አሥር ዓመት ብናይ ኢሕአዴግ በገጠርም በከተማም መንገድ ሠርቷል። ግን ከአሥር ዓመት በፊት ያለውን ንረትና አሁን ያለውን ስታየው የዛሬው በጣም ትልቅ ነው። ስለዚህ ሌሎች ገፊ ምክንያቶች ናቸው ለዋጋ ንረቱ ምክንያት የሆኑት እንጂ ሰንሰለቱ ብቻ አይደለም።"" ፕሮፌሰር አለማየሁ እነዚህ 'ገፊ' ያሏቸውን ምክንያቶች ያስረዳሉ። ባደረግኩት ጥናት እነዚህ ምክንያቶች አራት ናቸው ይለሉ። ""አንደኛው ምርታማነት ነው። ምርታማነታችን በሄክታር ሲሰላ በጣም የሞተ ነው። ለምሳሌ በአማካይ የእርሻ ምርታማነቱ የሚያድገው በዓመት በ2.5 ነው። ይህ ከሕዝብ ቁጥር ጋር ሲነፃፀር ዝቅ ያለ ነው። በእያንዳንዱ የሰብል ዓይነት ሊለያይ ይችላል። ነገር ግን በአጠቃላይ በቂ አይደለም። በጥናቴ መሠረት ቁጥር አንድ ምክንያት ይህ ነው። ""ቁጥር ሁለት ያገኘሁት ምክንያት ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 12/13 ዓመታት ከተገቢው በላይ ብር ይታተም ነበር። ለምሳሌ 2000 ዓ.ም. ላይ የቁጠባ ሒሳብና የቼክ ሒሳብ ውስጥ ያለን ጨምሮ ጠቅላላ ኢት��ጵያ ውስጥ የነበረው ብር 67 ቢሊየን ነበር። አሁን 870 ቢሊየን ደርሷል። ይህ ማለት በአማካይ በ30 በመቶ ያድግ ነበር ማለት ነው ላለፉት 13 ዓመታት።"" ፕሮፌሰር ዓለማየሁ የብር መጠኑ ከ4 እና 5 በመቶ መብለጥ አልነበረበትም ሲሉ ይሞግታሉ። ሶስተኛው ምክንያትም ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነው የሚሉት ምሁሩ የኢትዮጵያ ብር አቅም ከዓመት ዓመት እየተዳከመ መምጣቱ ሌላኛው ሰበብ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። ""በተለይ አዲሱ መንግሥት ከመጣ በኋላ የገንዘባችን አቅም እየወረደ ወይም እየረከሰ መጥቷል። የቀደመው መንግሥት ብዙ ብር ያትም ነበር። አዲሱ መንግሥት ደግሞ ብሩን እያረከሰው ነው። 80 በመቶ የሚሆኑ ከውጭ የምንገዛቸው ነገሮች የኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ነዳጅ የመሳሰሉ ናቸው። ስለዚህ ብሩ በረከሰ ቁጥር እነዚህ ዕቃዎች ይወደዳሉ። በ21 ብር የምትገዛው የነበረው አሁን በ40 ብር ነው የምትገዛው ማለት ነው።"" ፕሮፌሰር አለማየሁ ወደ አራተኛው ምክንያት ሲመጡ ከላይ ካነሳነው የአቅርቦት ሰንሰለት ጋር የተያያዘ ርዕስ ያነሳሉ። ""አራተኛው ምክንያት የነጋዴዎች አለአላግባብ ትርፍ ማጋበስ ነው። ለምሳሌ አንድ ሽንኩርት የሚያመርት ገበሬ የሚያገኘው ገቢና አዲስ አበባ ያንን ሽንኩርት የሚሸጠው ነጋዴ የሚያገኘው ሲነፃፀር ይዘገንናል። ገበሬው ምንም አያገኝም። ባደጉ ሃገራት አንድ ነጋዴ 20 በመቶ ካተረፈ ትልቅ ነገር ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ እኮ መቶ ሁለት መቶ 'ፐርሰንት' ነው የምታተርፈው። መፍትሄውስ? ምሁሩ መፍትሄው ችግሮቹን 'መገልበጥ ነው' ይላሉ። እንዴት ማለት? በዝርዝር ያስረዳሉ። ""ለምሳሌ የመጀመሪያው መፍትሄ የሚሆነው ምርታማነትን ማሳደግ ነው። ለምሳሌ ስንዴ ኢትዮጵያ ምን ያክል ታመርታለች? በቆሎስ? ደቡብ አፍሪካ በቆሎ የኛን እጥፍ ነው የምታመርተው። ስለዚህ ምርታማነት ላይ መሥራት ነው አንዱ መፍትሄ።"" የምጣኔ ሃብት አስተማሪው ምርታማነት ማሳደግ ትልቅ 'ኢንቨስትመንት' ይጠይቃል ይላሉ። ነገር ግን በአጭር ጊዜ መፍትሄ ለማምጣት ሊደረግ የሚችለው በትናንሽ መስኖዎች ምርት ማምረት ነው ይላሉ። ""ጠቅላላ ምርታማነት እንኳ ባይጨምር በዓመት ሁለቴ አመርትን ማለት ነው። ለምሳሌ 5 ኩንታል የምታመርት ከሆነ በዓመት፤ በመስኖ ሁለት ጊዜ አመርትክ ማለት 10 ኩንታል ሆነ ማለት ነው። ስለዚህ የአጭር ጊዜ መፍትሄ ሆኖ የሚታየኝ ይሄ ነው።"" ፕሮፌሰር አለማየሁ ካለው የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር አንፃር ወጣቶች በዚህ መስክ ላይ እንዲሰማሩ ያሻል ይላሉ። እንደ ምሁሩ ከሆነ ሁለተኛው መፍትሄ ጥብቅ የሆነ የገንዘብ ፖሊሲ ማውጣት ነው። ካልሆነ ደግሞ የሚወሰደውን ብድር ከላይ ለተጠቀሰው መፍትሄ ማዋል ይገባል ይላሉ። ""የሚታተመው ብር ባለፉት ሶስት ዓመታት እየቀነሰ መጥቷል። ይሄ ቆንጆ እርምጃ ነው። ግን ከዚህ በተጓዳኝ የሚታተመው ብር የት ነው የሚገባው የሚለው ነው። የሚታተመው ብር ምርታማነት ላይ ቢጠፋ ችግር አልነበረውም ነበር። የመጀመሪያውን ችግር በፈታ ነበር።"" የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ከጠ/ሚ ኃይለማርያም ዘመን ጀምሮ ብር 'ዲቫሉዌት' አልያም አቅሙ መውረድ የለበትም በማለት ሲሞግቱ እንደነበር ይናገራሉ። ""ፈረንጆቹ የሚነግሯቸው 'ኤክስፖርት' [የወጪ ንግድ] ይጨምራል፤ 'ኢምፖርትን' [የገቢ ንግድ] ይቀንሳል እያሉ ነው። ባለፉት ሶስት ዓመታት እኛ ማየት አንደቻልነው ኤክስፖርት አልጨመረም፤ ያው ባለፉት አስር ዓመታት በነበረበት [3 ቢሊዮን ዶላር] እንዳለ ነው። ኢምፖርቱ አይቀንስም [ወደ 17 ቢሊዮን ዶላር ነው]። ብርን የማርከስ ጎንዮሽ ጉዳት ከውጭ የሚመጣ ነገር በሙሉ ድሮ በ20 ብር የነበረው አሁን ወደ 40 ከፍ ማለቱ ነው። ይህ ለዋጋ ንረቱ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል።"" ፕሮፌሰሩ ���ደ አራተኛው መፍትሄ ሲመጡ የአቅርቦት ሰንሰለቱ የተስተካከለ ቢሆን ኖሮ የምርት ዋጋ እጅጉን ይቀንስ ነበር ይላሉ። ""ያለው አማራጭ መቆጣጠር ነው። ነገር ግን ነጋዴን ተቆጣጥረህ አትዘልቀውም። አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ከ200 ሺህ በላይ ነጋዴዎች አሉ። ይሁንና ልቆጣጠር ብትል ችግር ሊፈጠር ይችላል። ""ስለዚህ እኔ የሚታየኝ መፍትሄ ምንድነው፤ በግልና በመንግሥት ትብብር በየቀበሌው ገበያዎችን መመሥረት ነው። በተለይ መሠረታዊ ዕቃዎችን ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ። የአምራቾችና የሸማቾች ማሕበር የሚባሉ አሉ። ነገር ግን በሌብነትና በሙስና የተዘፈቁ ናቸው። ስለዚህ የትርፍ ህዳጉን ወስነህ 'ፕሮፌሽናል' የሆነ በግልና በመንግሥት የሚተዳደር [ፐብሊክ ኤንድ ፕራይቬት ፓርትነርሺፕ] ብትመሠርት አንድ መፍትሄ የሚሆን ይመስለኛል።"" ምሁሩ እነዚህ ገበያዎች መሠረታዊ ለሆኑ ነገሮች ብቻ ነው መሆን ያለባቸው ይላሉ። ""ለዚህ ቆንጆ ምሳሌ 40ና 50 ዓመታት ያገለገሉ ልብ የማንላቸው ተቋማት አሉ። ኢትፍሩትና ከነማ ፋርማሲ የሚባሉ። የእነዚህን ተቋማት 'ስትራክቸር' ማጥናትና በዚያ መሠረት ማቋቋም ይቻላል።"" የአቅርቦት ሰንሰለት በኢትዮጵያና በጎረቤት ሃገራት ጎረቤት ሃገር ኬንያ ሁለተኛ ሃገሬ ናት የሚሉት ፕሮፌሰር አለማየሁ የኬንያ መንግሥት ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ በገበሬውና በሸማቹ መካከል ያለውን የዋጋ ክፍተት በማጥበብ ትርፉን መልሶ ለገበሬ ማድረግ የሚያስችል ሥርዓት እየዘረጋ እንደሆነ ይናገራሉ። ""ዓላማው ትርፉን ወስዶ ለገበሬው ጥቅም ማዋል ነው። ለምሳሌ የጤና ተቋማትን መገንባት፤ ትምህርት ቤት ማሠራት የመሳሰሉትን ለማቋቋም ነው የሚተልመው ይህ ሥርዓት።"" ይህን እየቀረፁ ያሉት ኬንያዊ ባለሙያ ልክ እንደ ራይድ ወይም ኡበር ያለን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሥርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከሩ እንዳሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። ""ይህ 'ሲስተም' በኤሌክትሮኒክ አማካይነት ምርቶችንና ሸማቹን ማገናኘት ነው ዓላማው።"" ኬንያ ከኛ የሚለያት ቁጥሩ አነስተኛ የሆነና የተደራጀ ነጋዴ መኖሩ ነው ይላሉ ምሁሩ። ስለዚህ ይህ ለቁጥጥር ይመቻል ሲሉ ልዩነቱን ያስረዳሉ። ""እኛ አንድ 15-20 ዓመት አይቀረንም ብለህ ነው ኬንያ አሁን ያለችበት ለመድረስ?"" የሚሉት ፕሮፌሰር አለማየሁ ኢትዮጵያ መወዳደር ያለባት ከነ ሩዋንዳና ማላዊ ጋር ነው ይላሉ። ምሁሩ ሐሳባቸውን ሲያጠቃልሉ 'ኋላ ቀር መሆናችን ገብቶን ወደ መፍትሄው በፍጥነት ማምራት አለብን' ይላሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-56920410 +politics የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የዘ ኢኮኖሚስት ዘጋቢን ፈቃድ ሰረዘ "የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በኢትዮጵያ የዘ ኢኮኖሚስት ጋዜጣ ዘጋቢ የሆነውን ቶም ጋርድነር ፈቃድ መሰረዙን አስታወቀ። ዘጋቢው ""የሙያ ስነ ምግባርና የሃገሪቱን ህግና መመሪያ መጣሱንም"" በመግለፅ ባለስልጣኑ ለፈቃዱ መሰረዝ ምክንያት እንደሆነ በዛሬው ዕለት ግንቦት 5፣ 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። ባለስልጣኑ ጥሰቶች ብሎ ያሰፈራቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አልገለጸም። ባለስልጣኑ እዚህ ውሳኔ ላይ ከመደረሱ በፊት ከዚህ ቀደም ከዘጋቢው ቶም ጋርድነር ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች አድርገናል ብሏል። ባለስልጣኑ ከሳምንታት በፊት ለዘ ኢኮኖሚስት ዘጋቢው ቶም ጋርድነር የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሰጥቷል። ጋዜጠኛው በግል የማህበራዊ ሚዲያው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የህወሃት መሪ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ጋር በስልክ ተወያይተዋል የሚል መልዕክት ማስፈሩን ተከትሎ ባለስልጣኑ በሪፖርቱ ላይ በተለይም በብሔራዊ ጥቅም ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስጠንቅቋል። ቶም ጋርድነርም ሆነ ዘ ኢኮኖሚስት በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ምላሽ አልሰጡም። ነገር ግን ይህ እርምጃ በባለስልጣናቱ የሚዲያ ሽፋንን ለመቆጣጠር የተደረገ ሙከራ ነው በሚል ትችት ቀርቦበታል። በባለፈው አመት ጥቅምት ወር መጨረሻ በትግራይ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት ለጋዜጠኞች እና ለተቃዋሚዎች አስቸጋሪ ሁኔታን በመፍጠር ይወቀሳል። ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች፣ ጅምላ ግድያዎች፣ ደፈራዎች፣ እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠሩ የሚችሉ መጠነ ሰፊ ጥሰቶች ተፈፅመውባቸዋል በሚባሉ የጦርነቱ ስፍራዎች ደርሰን መዘገብ ተከልክለናል በሚልም ጋዜጠኞች ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ይሰማል። የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪው ድርጅት (ሲፒጄ) የጸጥታ ኃይሎች በጦርነት ጊዜ የወጣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋዜጠኞችን በዘፈቀደ ለማሰር ተጠቅመዋል ሲል ከቅርብ ወራት በፊት መተቸቱ ይታወሳል። በወቅቱ በእስር ላይ የዋሉ በርካታ ጋዜጠኞች ከእስር ቢለቀቁም ከአገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁለት ጋዜጠኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ናቸው። ሲፒጄ በተጨማሪም ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት ጋዜጠኞችን በማሰር ኢትዮጵያ ሁለተኛ ናት በሚል ሪፖርት አውጥቷል። በቅርቡም ድርጅቱ በእስር ላይ ያሉት ደሱ ዱላ እና ቢቂላ አመኑ የተሰኙ ጋዜጠኞች እንዲፈቱና ክሳቸው እንዲቋረጥ ጠይቋል። የማኅበራዊ ሚዲያ የሆነው የኦሮሚያ ኒውስ ኔትወርክ ጋዜጠኞቹ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ቢሆንም የታሰሩት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳም ደሱ እና ቢቂላ በእስር ቤት እንዳሉና ህገ መንግሥቱን በመፃረር በቀረበባቸው እስከ ሞት የሚያደርስ ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጠብቃቸውም ገልጿል። ከ12 ወራት በፊት በተመሳሳይ መልኩ ኢትዮጵያ የኒውዮርክ ታይምስ ዘጋቢን 'ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ አቅርቧል' በሚል የፕሬስ ፈቃዱን የነጠቀች ሲሆን ይህንን እርምጃም ጋዜጣው 'አምባገነናዊ አካሄድ' እና 'እጅጉን ተስፋ አስቆራጭ' ብሎታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61441551 +politics በአማራ ክልል የፀጥታ ተቋማት ባልደረቦች የነበሩትን ጨምሮ በርካቶች መታሰራቸውን የደኅንነት ምክር ቤት አስታወቀ "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፣ በአማራ ክልል የፀጥታ ተቋማትን “የከዱ” የተባሉ አባሎችን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ አካላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገለጸ። ምክር ቤቱ ትላንት ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ ላይ “ከፀጥታ ተቋማት የከዱ አባላትን የመያዝ፣ በተለያዩ ወንጀሎች የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ሥር የማዋል” ሥራ መከናወኑ ተገልጿል። በአማራ ክልል ባለፉት ሳምንታት መንግሥት “የሕግ ማስከበር” በሚል በወሰደው እርምጃ፣ “ተበትነው የፀጥታ ስጋት ሲሆኑ የቆዩ የጦር መሣሪያዎች የመሰብሰብ፣ በሕገ ወጥ ተግባራት ተሰማርተው የነበሩ አክቲቪስቶችን ሥርዓት የማስያዝ” ሥራ መካሄዱንም የደኅንነት ምክር ቤቱ መግለጫ ይጠቁማል። እነዚህንም “ሕዝቡን ለእፎይታ ያበቁ ተግባሮች” ሲል ምክር ቤቱ ገልጿቸዋል። የፌደራል መንግሥት እና የአማራ ክልል መንግሥት በአማራ ክልል የጦር መሣሪያን በመመዝገብ የጀመሩት ዘመቻ ኋላ ላይ ከ4000 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉበት እንደሆነ ተገልጿል። መንግሥት ዘመቻውን “የሕግ ማስከበር” ቢለውም፣ ዘመቻው መንግሥትን የሚተቹ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ማኅበረሰብ አንቂዎችን እንዲሁም ፋኖ የተባለውን ኢ-መደበኛ አደረጃጀት ኢላማ ያደረገ ነው ብለው የሚከራከሩም አሉ። ምክር ቤቱ የፋኖን ታጣቂዎች በስም ባይጠቅስም ከመንግሥት ፀጥታ መዋቅሮች ውጭ ያሉ የታጠቁ አደረጃጀቶች ""እንደፈለጉ"" ሊሆኑ እንደማይችሉ በመግለጫው አስፍሯል። “በአገር ውስጥ ኃይልን በብቸኝነት የመጠቀም መብት ለመንግሥት የተሰጠ መብት ነው። ዜጎች በሰላም ጊዜ አልሚ፣ በጦርነት ጊዜ ተፋላሚ መሆናቸውም ከጥንት የነበረ ነው። ያ ማለት አገር ስትወረር ሁሉም ለአገሩ ተፋላሚ ይሆናል። አገር ሰላም ስትሆን ደግሞ ሁሉም ወደ ሕጋዊ ማዕቀፍ ይገባል ማለት ነው” ብሏል። ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ሚያዝያ 14 ቀን 2014 ዓ. ም. ስለ አገር አቀፍ የፀጥታና ደኅንነት ያደረገውን ግምገማ ተከትሎ ባስቀመጠው አቅጣጫ፣ ከአማራ ክልል በተጨማሪ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝም የተወሰዱ እርምጃዎች እንዳሉ በትናንትናው መግለጫ አትቷል። በመግለጫው መሠረት በኦሮሚያ ክልል “በሺዎች የሚቆጠሩ የሸኔ አባላት ተገድለዋል”። “የሸኔን ልዩ ልዩ ቡድኖች የመደምሰስ፣ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን የማምከን፣ በጠላት እጅ የነበሩ አካባቢዎችን መልሶ የመቆጣጠር፣ መንግሥታዊ መዋቅሩን የማጥራት” እርምጃዎች እንደተወሰዱ ጠቅሶ፣ እነዚህንም “ውጤታማ” ሲል ገልጿቸዋል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚለው እና መንግሥት ‘ሸኔ’ የሚለው ታጣቂ ቡድን መካከል ውጊያ ሲካሄድ መሰንበቱ አይዘነጋም። መንግሥት በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ታግዞ በተካሄደው በዚህ ውጊያ ንጹሐን ዜጎች ሰለባ መሆናቸውን የኦሮሚያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ መክሰሳቸው ይታወሳል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ “የታጠቁ ሽፍቶችን ሥርዓት ማስያዝና መደምሰስ” መከናወኑን ጠቅሶ እነዚህን ሥራዎች “አበረታች” ሲል ምክር ቤቱ ገልጿቸዋል። በክልሉ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያን የመሰብሰብ እንዲሁም ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለሥ ሥራ መሠራቱን አክሏል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ በክልሉ መንግሥትና በተለይም የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) መካከል ዘላቂ ሰላም ለማውረድ የሚደረጉ ጥረቶች በተደጋጋሚ መሰናክል ሲገጥማቸው ቆይቷል። ከቀናት በፊት በካማሺ ዞን በምትገኘው ምዥጋ ወረዳ በክልሉ ልዩ ኃይሎችና በጉሕዴን ታጣቂዎች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ 19 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። በሌላ በኩል በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች “ሊደረግ ታስቦ የነበረው የአል-ሸባብ እንቅስቃሴ በፀጥታ አካላት ቅንጅት ከሽፏል” ሲል ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ገልጿል። በደቡብ እና በጋምቤላ ክልሎች “የታጠቁና የተደራጁ ሽፍቶችን መልክ የማስያዝ እንቅስቃሴ” መከናወኑን ጠቅሶ፣ በተጨማሪም የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመግታትና በተለያዩ ማኅበረሰቦች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን የመፍታት ሥራ መሠራቱን መግለጫው አትቷል። ምክር ቤቱ “ዓለም አቀፍ የሚዲያ ትኩረትን ለመሳብ የሚፈልጉ” ያላቸው ቡድኖች በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ የቃጡትን ጥቃት የፀጥታና ደኅንነት መዋቅሩ ማክሸፉን አያይዞ ገልጿል። መንግሥት በአማራ ክልልና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ፣ የሕግ የበላይነትን ማስከበር የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት እንዲሁም የአገርን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ብቸኛው መፍትሄ ነው ማለቱ ይታወሳል። በተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ሕገ ወጥነትና የሰላም መደፍረስን መንግሥት እንዲቆጣጠር ሕዝቡ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ነበር ያለው መግለጫው፣ ብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤት አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ መወሰኑን አስታውሷል። በዚህ መግለጫውም በአጠቃላይ የተጀመረው ሰላምና ጸጥታ የማስፈን እንዲሁም ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አፅንኦት ሰጥቷል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cx87elvg9j7o +sports እግር ኳስ ፡ የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ማልያ በልካቸው አለመሰፋቱ ቁጣን ቀሰቀሰ "የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች የቡድኑ ማልያ በሴቶች ልክ የለም መባሉን ተከትሎ ቁጣቸውን እያሰሙ ነው። የብሔራዊ ቡድኗ ከሜዳ ውጭ የምትጫወትበት ማልያ በአዲስ መልክ ቢሰራም ለሴቶች የሚሆን የለም ተብለዋል ደጋፊዎች። መቶ በመቶ ከፖሊስተር ጨርቅ የተሠራው አዲሱ ማልያ ባለፈው አርብ ከወንዶቹ ማልያ ጋር ነበር ለገበያ የቀረበው። ነገር ግን የሴቶች ብሔራዊ ቡድኗ በትዊትር ገጿ እንዳስታወቀችው አዲሱ ማልያ በሴቶች ልክ አልተሰራም፤ በወንዶች እንጂ በማለት ያጋጠመውን ችግር ገልጸዋል። 'ማቲልዳስ' በተሰኘ ቅፅል ስም የምትታወቀው ቡድን ይፋ እንዳደረገችው አዲሱ ማልያ እስከ 2022 [በአውሮፓውያኑ] ድረስ በሴቶች ልክ አይሠራም። የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ሰባተኛ ናት። የአውስትራሊያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ናይኪ የተሰኘው የስፖርት አልባሳት አምራች ያመረቱት አዲሱ ቢጫ ማልያ ገበያ ላይ ፈላጊው በዝቷል። ነገር ግን ማልያው በሴቶች ልክ ባለመሠራቱ ሴቶቹም የሚለብሱት ለወንዶቹ የተሠራውን ነው ተብሏል። ምንም እንኳ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት ማልያውን ለብሰው ፎቶ በመነሳት ማስታወቂያ ቢሰሩም ደጋፊዎች ግን ይህ አላስደሰታቸውም። ብሔራዊ ቡድኗ ችግሩ የሚቀረፈው በአውሮፓውያኑ 2022 አዲስ ማልያ ሲተዋወቅ ነው ብላለች። ደጋፊዎችን ጨምሮ የብሔራዊ ቡድኑ አባላት በሁኔታው የተሰማቸውን ቅሬታ በማኅበራዊ ድር አምባ ገፆቻቸው ላይ ገልፀዋል። አውስትራሊያ 2023 ላይ የሚካሄደውን የሴቶች ዓለም ዋንጫ ታዘጋጃለች። የአገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አፈ ቀላጤ ስለጉዳዩ በአንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተጠይቀው ""ተጨማሪ አስተያየት መስጠት አልችልም"" ብለዋል። የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 'ማቲልዳስ' አባላት በአውሮፓውያኑ 2019 ከወንዶቹ እኩል ደመወዝ እንዲከፈላቸው መወሰኑ ይታወሳል። በስምምነቱ መሠረት ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች እኩል ደመወዝና የማስታወቂያ ገቢ ያገኛሉ። አልፎም በአውሮፕላን ሲጓዙ የሚደርግላቸው እንክብካቤና የልምምድ ሜዳ ቁሳቁስ አቅርቦት ከወንዶቹ እኩል እንዲሆን ሆኗል። ነገር ግን አሁንም ወንዶቹ በሚወዳደሩባቸው ውድድሮች ካሸነፉ እንዲሁም ዋንጫ ካገኙ ከሴቶቹ የተሻለ ገንዘብ ያገኛሉ። የወንዶቹ ብሔራዊ ቡድን በዓለም 41ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54216906 +health የወባ በሽታን 70 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል አንድ ጥናት አመለከተ "በአንድ ጥናት መሰረት አዲስ አይነት የመከላከል መንገዶችን በመጠቀም አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ህጻናት በወባ በሽታ የመያዝና የመሞት ዕድላቸውን በ70 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል ተጠቆመ። የወባ በሽታ በተደጋጋሚ የሚከሰትባቸው ወራት ከመድረሳቸው በፊት ክትባቱን እንዲወስዱ ማድረግና በተጨማሪ ደግሞ ሌሎች መከላከያ መድኃኒቶችን እንዲጨምሩበት በማድረግ ሙከራው ከፍተኛ የሆነ ውጤት ማስገኘቱን በለንደን የሚገኙ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል። የዚህ የወባ በሽታን የመከላከል ሙከራው የተደረገው ከቡርኪናፋሶ እና ከማሊ የተወጣጡ ከ17 ወራት በታች የሆኑ 6 ሺህ ህጻናት ላይ ነው ተብሏል። አፍሪካ በየዓመቱ በወባ በሽታ ምክንያት እስከ 400 ሺህ ሞቶችን የምታስመዘግብ ሲሆን አብዛኞቹ ደግሞ እድሜያቸው ከአምስት ወራት በታች ነው። ይህ ጥናት 'በኒው ኢንግላንድ ጆርናል ኦፍ ሜድሲን' የህክምና መጽሔት ላይ የታተመ ሲሆን በሙከራው ላይ ለህጻናቱ አሁን ላይ የሚገኙ የወባ ክትባቶችን ቀድሞ መስጠትና የወባ በሽታ በብዛት በሚከሰትባቸው ወራት ደግሞ (አብዛኛውን ጊዜ የዝናብ ወራት ናቸው) ሌሎች የወባ መከላከያ መድኃኒቶችን በመስጠት ነው ከፍተኛ ውጤት የተገኘው። ""እኛ እናገኘዋለን ብለን ካሰብነው ውጤት በጣም የተሻለ ነገር ነው ያገኘነው"" ብለዋል የምርምር ቡድኑ አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ብራያን ግሪንዉድ። ""በሁለቱም አገራት ሙከራውን ከጀመርን በኋላ በወባ በሽታ ምክንያት ሆስፒታል የሚገቡና ህይወታቸው የሚያልፍ ህጻናት ቁጥር በእጅጉ ቀንሷል።"" ባለፉት ሦስት ዓመታት በተሰራው ሙከራ የዝናብ ወራት ከመድረሳቸው በፊት ሦስት የወባ ክትባቶች ለህጻናቱ የተሰጣቸው ሲሆን የዝናብ ወቅት ሲገባ ደግሞ የተለያዩ አይነት የወባ መከላከያ መድኃኒቶችን እንዲወስዱ ተደርጓል። በዚህም የወባ በሽታ ስርጭትን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ታይቶበታል። የዚህ ሙከራ ውጤትም ከየትኛውም አይነት ክትባትና መድኃኒት በተሻለ መልኩ ውጤት ያስገኘ ሲሆን በአፍሪካ በወባ በሽታ የሚጠቁ ህጻናትን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ይህም ሚሊየኖችን ህይወት እንደሚታደግ ከወዲሁ ተገምቷል። በሙከራው ላይ ክትባቱን ቀደም ብለው ከወሰዱትና በዝናብ ወቅት ደግሞ ሌሎች መከላከያዎችን ከወሰዱት ህጻናት መካከል 624ቱ በወባ በሽታ የተያዙ ሲሆን 11 ህጻናት ደግሞ ሆስፒታል ገብተው ህክምና ወስደዋል። በተጨማሪም የሟቾች ቁጥር በእጅጉ ቀንሶ 3 ብቻ ነበር። በዚህ ሙከራ እንዳይካተቱ ከተደረጉት ተመሳሳይ ቁጥር ካላቸው ህጻናት መካከል ደግሞ 1661 ህጻናት በወባ በሽታ የተያዙ ሲሆን 37 ህጻናት ደግሞ ሆስፒታል ገብተዋል። የሟቾች ቁጥር ደግሞ 11 ነበር። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ይህ አዲስ ሙከራ በጣም ውጤታማ ስለመሆኑ ማሳያ ነው። ከዚህ በፊት በሚደረጉ ሙከራዎች ጉንፋንን ቀድሞ ለመከላከል መሰል ጥረቶች ቢደረጉም በወባ በሽታ ላይ ሲሞከር ግን ይህ የመጀመሪያው ነው። የዓለም ጤና ድርጅት የወባ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ፔድሮ አሎንሶ ደግሞ ""ይህን አዲስ አይነት የወባ በሽታ ክትባትና መከላከል ሥራ በመልካም ጎኑ ነው የምንመለከተው። አፍሪካ ውስጥ በርካታ ሞትን ማስቀረት እንደሚያስችል እንገምታለን"" ብለዋል። የወባ በሽታ ክትባቱ እስካሁን 740 ሺህ ለሚሆኑ ጋና፣ ኬንያ እና ማላዊ ውስጥ ለሚገኙ ህጻናት የተሰራጨ ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅት ይሁንታውን እስኪሰጥ እየተጠበቀ ነው። በዚህ ሙከራ ላይ የትኛውም ህጻን ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንዳላስተናገደ ተመራማሪዎቹ አስታውቀዋል። በዚህም መሰረት ህጻናት ክትባቱን እና መከላከያ መድኃኒቶቹን እስከ 5 ዓመታቸው ድረስ እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን በዚያውም ሌሎች የተሻሉ አማራጮች ከመጡ አብረው እንደሚካተቱ ተገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58345206 +business ቢሊየን ዓመት ያስቆጠረው ጥቁር አልማዝ በ4.3 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ "የዓለማችን ትልቁ የተቆረጠ አልማዝ ነው ተብሎ የሚታመነውና የቢሊየን ዓመት ዕድሜ ያለው ጥቁር አልማዝ በ4.3 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ። ዘ ኢኒግማ ተብሎ የተሰየመው የ555.55 ካራት አልማዝ ከአንድ ሙዝ ክብደት ጋር ተነጻጽሯል። በበይነ መረብ ግብይትም ከ4.4 ሚሊየን ፓውንድ በላይ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ከአስትሮይድ ጋር ወደ ምድር መምጣቱን ጨምሮ ስለ አልማዙ አመጣጥ ብዙ መላ ምቶች አሉ። አጫራቹ ሶዝባይ እንዳለው፤ ገዢው ክፍያውን በክሪፕቶከረንሲ ለማድረግ መርጧል። ሶዝባይ የገዢውን ማንነት ሳይገልጽ ቆይቶ፤ ከጨረታው በኋላ የክሪፕቶከረንሲ ባለሙያው ሪቻርድ ኸርት የዘ ኢኒግማ ገዢ መሆኑን በማኅበራዊ ገጹ ገልጿል። ሶዝባይ ከ180,000 በላይ ለሚሆኑት የትዊተር ተከታዮቹ፤ የአልማዙ ክፍያ እንደተጠናቀቀ እና ንብረቱን እንደተረከበ አልማዙ ሄክስ.ኮም ዳይመንድ (HEX.com Diamond) የሚል ስያሜ እንደሚሰጠው ገልጿል። ስያሜው የክሪፕቶከረንሲ ባለሙያው ሪቻርድ ከመሠረተውን ብሎክቼይን የተገኘ ነው። አልማ�� ካርቦንዶስ ነው ተብሏል። ይህም በጣም ጠንካራ ከሆኑ የተፈጥሮ አልማዞች አንዱ ነው። ካርቦናዶስ የሚባሉት የአልማዝ አይነቶች ጥቂት ሲሆኑ አልፎ አልፎ የተገኙትም በብራዚል እና በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ብቻ ነው። በሜትሮዎች ውስጥ ብቻ የሚገኘው ኦስቦርኔት የተባለውን ማዕድን ስላላቸው ከጠፈር እንደመጡ ይታመናል። ሶዝባይ ዘ ኢኒግማን ""በሰው ልጅ ዘንድ ከሚታወቁት ብርቅዬ፣ ከቢሊየን ዓመታት በላይ ካስቆጠሩት የጠፈር ድንቅ ስጦታዎች አንዱ ነው"" ሲል ገልጾታል። የጥቁር አልማዝ ትክክለኛ አመጣጥ በምስጢር የተሞላ ነው። ጥቁር አልማዞች ከ2.6 እስከ 3.2 ቢሊየን ዓመታት መኖራቸው ይገመታል። ይህም ዳይኖሰር ከመፈጠሩ በፊት መሆኑ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-60329211 +politics ሩሲያ ለዩክሬን ተገንጣይ ክልሎች ዕውቅና ሰጠች "የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሲካሄድ የቆየው የሰላም ድርድር ማብቃቱን በመግለጽ በዩክሬን ምሥራቃዊ ክፍል ተገንጥለው ለሚገኙ አማፂ ክልሎችን ዕውቅና ሰጡ። ለራሳቸው ነጻነታቸውን ያወጁት የዶኔስክ እና የሉሃንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊኮች በሩሲያ የሚደገፉ አማፂያን ሲሆኑ እአአ ከ2014 ጀምሮ ከዩክሬይን ጦር ጋር ሲዋጉ ነበር። የሩሲያ ወታደሮች በሁለቱም ክልሎች ""የሰላም ማስከበር ሚናቸውን"" እንዲወጡ ታዘዋል። ሩሲያ ሆን ብላ ሉዓላዊነታችንን እየጣሰች ነው ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከሰዋል። ፕሬዚደንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ በቴሌቭዥን ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር ዩክሬን ሰላም እንደምትፈልግ ገልጸዋል። አክለውም ""አንፈራም"" ካሉ በኋላ ""ለማንም አሳልፈን የምንሰጠው ነገር አይኖርም"" ብለዋል። ኪዬቭ ከዓለም አቀፍ አጋሮቿ ""ግልጽ እና ውጤታማ የድጋፍ እርምጃዎች"" እንደሚያስፈልጋት ጨምረው ጠቅሰዋል። ""አሁን እውነተኛ ወዳጃችን እና አጋራችን ማን እንደሆነ እና የሩስያ ፌዴሬሽንን በቃላት ብቻ ማስፈራራትን የሚቀጥል ማን እንደሆነ ማየት በጣም አስፈላጊ ነው"" ብለዋል። የምዕራቡ ኃያላን አገራት ፑቲን በአማፂያኑ ቁጥጥር ሥር ላሉ አካባቢዎች ዕውቅና መስጠታቸው የሩስያ ወታደሮች ወደ ዩክሬን ምሥራቃዊ ክፍል በይፋ እንዲገቡ መንገድ ይከፍታል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲያ የሩስያ ፓስፖት በዶኔስክ እና በሉሃንስክ ለብዙ ሰዎች ተሰጥቷል። የምዕራባውያኑ ስጋትም ሩሲያ ዜጎቼን ለመጠበቅ በሚል ሽፋን ወታደሮቿን ልታንቀሳቅስ ትችላለች የሚል ነው። ከሰኞው መግለጫ በኋላ አንድ ሰዓት የሚፈጅ ንግግር ያደረጉት ፑቲን ዘመናዊዋ ዩክሬን በሶቪየት ሩሲያ ""የተፈጠረች"" ናት ብለው ""የጥንታዊት ሩሲያ መሬት"" በማለትም ገልጸዋታል። እአአ በ1991 በተካሄደው የሶቭየት ኅብረት ውድቀት ወቅት ሩሲያ ""ተዘርፋለች"" ብለዋል። ዩክሬንን በአሻንጉሊት መንግሥት የምትመራ ""የአሜሪካ ቅኝ ግዛት ናት"" በማለት የጠቀሱ ሲሆን፤ አሁን ባለው አመራር ዜጎች እየተሰቃዩ ነው ሲሉም ተናግረዋል። እአአ በ2014 የተካሄደውን እና በሩሲያ የሚደገፍ የነበረውን አመራር ከሥልጣን ያወረደውን ተቃውሞ መፈንቅለ መንግሥት ሲሉ ገልጸውታል። 'ተቀባይነት የሌለው ነው' ዩናይትድ ስቴትስ የፑቲንን እርምጃ በፍጥነት አውግዛለች። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም መገንጠል በሚፈልጉት ክልሎች የአሜሪካውያንን አዲስ ኢንቨስትመንት፣ ንግድ እና ፋይናንስን የሚከለክል ትዕዛዝ ፈርመዋል። እርምጃዎቹ ""ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች"" ለመጣል ዝግጁ ከሆኑት የምዕራባውያን ማዕቀቦች የተለዩ መሆናቸውን ኋይት ኃውስ አስታውቋል። የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የሩስያ ድርጊት ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጻረር ""የዩክሬንን ሉዓላዊነትን በግልፅ የጣሰ ነው"" ብለ���ል። ""ጥሩ ያልሆነ ምልክት እና ጥቁር ምልክት"" ነው ሲሉም ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትሩስ በበኩላቸው እንግሊዝ ማክሰኞ ዕለት በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ እንደምትጥል አስታውቀዋል። የአውሮፓ ኅብረት ""ከዩክሬን ጎን በመቆም በአንድነት፣ በጥንካሬ እና በቁርጠኝነት ምላሽ ለመስጠት"" ቃል ገብቷል ። የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን በበኩላቸው የሩስያ ወታደሮችን የሰላም ማስከበር መግለጫ ሐሳብ ውድቅ በማድረግ ""ተቀባይነት የሌለው፣ ያልተመጣጠነ፣ ያልተገባ፣ ከንቱ ሐሳብ ነው"" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የቭላድሚር ፑቲን እርምጃ ከ150,000 በሚበልጡ የሩስያ ወታደሮች ድንበሯ ለተከበበው ዩክሬን የነበረውን ቀውስ የበለጠ ያጠናክረዋል። ሩሲያ ለመውረር አቅዳለች መባሉን ውድቅ ስታደርግ አሜሪካ ደግሞ ጥቃት አይቀሬ እንደሆነ ታምናለች። የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ሾልስ እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከመግለጫቸው በፊት የሩስያውን መሪ አነጋግረዋል። ምዕራባውያን አገራት ከዩክሬን ጀርባ በመሆን ሩሲያ ወረራ ከፈጸመች ከባድ ማዕቀብ እንደሚጠብቃት ቃል ገብተዋል። ለአሁኑ የሩሲያ እርምጃ ምላሹ ምን እንደሆነ እስካሁን ግልጽ አይደለም። ከአወዛጋቢው ውሳኔ ቀደም ብሎ ፑቲን የሩሲያን የፀጥታ ምክር ቤት ሰብስበው ክልሎቹ ራሳቸውን የቻሉ ነጻ ሪፐብሊካኖች መሆናቸውን በማረጋገጥ ጉዳይ ሲወያዩ ነበር። የፑቲን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሐሳባቸውን ለመስጠት ወደ መድረክ የተጠሩ ሲሆን ሁሉም እርምጃውን እንደሚደግፉ ተናግረዋል። በቴሌቭዥን የተሰራጨው የሰኞው ስብሰባ ግን ሙሉ በሙሉ የተሳካ አልነበረም። ከፑቲን ጋር በተደረገው ውይይት ወቅት ሁለት ባለሥልጣናት ክልሎቹን ወደ ሩሲያ ""የማካተት"" ዕድልን የሚጠቅሱ መስለው ነበር። በሁለቱም አጋጣሚዎች ፑቲን አርመዋቸዋል። ""እየተነጋገርን ያለነው ለነፃነታቸው ዕውቅና ስለመስጠት ወይም ስላለመስጠት ነው"" ሲሉ ለተደመጡት አንድ ባለሥልጣን ""እኛ ስለእሱ እየተወያየን አይደለም"" በማለት አንገታቸውን ነቅንቀዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60474353 +business የመንደር ውል ሕጋዊ ነው? በመንደር ውል ቤት ስንሻሻጥ ልብ ልንላቸው የሚገቡን ቁልፍ ነጥቦች "የአገሪቱ አዋዋይ በተለምዶ 'ውልና ማስረጃ' የምንለው መሥሪያ ቤት ነው። የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ኤጀንሲ ደግሞ ሙሉ ስሙ ነው። አሁን ግን አገልግሎት እየሰጠ አይደለም። ነገሩ ከወቅቱ የአገሪቱ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ሳይሆን አይቀርም። ከሐምሌ ወዲህ ይኸው እስከዛሬም አገልግሎት እየሰጠ ያለው በከፊል ነው። የተንቀሳቃሽ ንብረት ሽያጭን ጨርሶውኑ እያዋዋለ አይደለም። ይህን ተከትሎ ዜጎች በስፋት በመንደር ውል ተጠምደዋል። ""ላልከዳህ-ላልክድህ ቃል አለኝ"" እያሉ በየመንደሩ እየተፈጣጠሙ ነው። ለመሆኑ በውልና ማስረጃ ያልተረጋገጡ የመንደር ውሎች በሕግ ፊት ተቀባይነት አላቸው? በዚህ ጉዳይ ላይ ቢቢሲ ሁለት ከፍተኛ የሕግ አማካሪና ጠበቆችን አነጋግሯል። ጠበቃ ሚካኤል ተሾመ እና ጠበቃ ታምራት ኪዳነማርያም ይባላሉ። ሕጉን እያመሳከሩ፣ በሥራ ተሞክሮ የሚገጥሟቸውን እያጣቀሱ ጉዳዩን በየፈርጁ ይተነትኑልናል። ውል የሚጸናው ምን ሲሟላ ነው? አራት ነገር ካልተሟላ ውል አይጸናም ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። 1ኛ• ፈቃድ (Consent) ነው። ተዋዋዩ ፈቃዱን የሰጠው ወዶና ፈቅዶ በማያሻማ ሁኔታ መሆን ይኖርበታል። ምን ማለት ነው ይሄ፣ በመታለል/በማታለል የተፈጸመ ውል ዋጋ አይሰጠውም። 2ኛ• ተዋዋዮቹ በሕግ 'ችሎታ ያላቸው' መሆን አለባቸው። 'ችሎታ' የሕግ ትርጉሙ ሁለት ነው። የተዋዋዮች ዕድሜ ከ18 ዓመት በላይ መሆን እና የአእምሮ ጤ�� ነው። 3ኛ• የውሉ ዋና ጉዳይ በሕግ የሚፈጸም መሆን አለበት። ለምሳሌ ባዶ መሬት መሸጥ አይቻልም። ስለዚህ የባዶ መሬት ሽያጭ ውል ቢደረግም በፍርድ ቤት ውድቅ ነው። ሌላስ? 4ኛ• የውል አቀራረጽ ወይም ፎርም ነው። ይህም ማለት ለምሳሌ ለማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሸጥ 2 ምስክሮች መኖራቸው፣ በውል አዋዋይ ፊት መረጋገጥ፣ ሕጉ ያስቀመጣቸው ዝርዝሮች መሟላት ማለት ነው። የሆነስ ሆኖ፣ የመንደር ውል ሕጋዊ ነው? ጠበቃ ሚካኤል፣ ለዚህ ጥያቄ በአጭሩ ""ሕጋዊ አይደለም"" የሚል መልስ ይሰጣሉ። ጠበቃ ታምራት ደግሞ ""ነውም፣ አይደለምም"" የሚል ምላሽ ይሰጣሉ። ይህን ያሉበትን ምክንያት ወደ ኋላ ላይ ያስረዱናል። አሁን ወደ ጠበቃ ሚካኤል ነጥቦች እንመለስ። ጠበቃ ሚካኤል ለዚህ ድምዳሜ ያበቃቸውን ነጥብ ሲያስረዱ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፣ ማለትም ቤትና መሬት በርካታ ሰዎች በመንደር ውል የሚሻሻጡ ቢሆንም በርካታ ሰዎች ተግባሩን ስላደረጉት ግን ሕጋዊ አያሰኘውም ይላሉ። ይህ የመንደር ውል በሕግ ተቀባይነት የማይኖረው የሰነድ ማረጋገጥ ዋና ዓላማን የሚጥስ መሆኑ ነው ይላሉ። ሰነድ ለምን ይረጋገጣል? ባይረጋገጥስ ምን ችግር አለው? ከሚለው እንጀምር። ጠበቃ ሚካኤል 'ሰነድ ለሁለት ዓላማ ነው የሚረጋገጠው' ብለው የክርክሩን ፍሬ ነገር ያሲዙናል። አንደኛ በተዋዋዮቹ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግዛት ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሦስተኛ ወገን ለሚያነሳው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። ሦስተኛ ወገን የሚባሉት እነማን ናቸው ያልን እንደሁ፣ ከገዥና ሻጭ ውጪ ያሉ የትኛውንም ወገኖችን ያካትታል። ለምሳሌ የመንግሥት አካል፣ የክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር፣ ባንክ፣ ለምሳሌ ሽያጩ ይፍረስልኝ የምትል/የሚል ሚስት/ባል . . . ወዘተ እነዚህ ሁሉ 3ኛ ወገን ይባላሉ። ከእነዚህ አካላት አንዱ፣ እንበልና በመንደር ውል በተፈጸመ ንብረት ላይ ጥያቄ ቢያነሱ ሙግቱን ያለምንም እሰጥ አገባ አሸነፉ ማለት ነው። በመንደር ውል ቤት የገዛ ሰው ቀለጠ ማለት ነው። በአጭሩ ውል የሚረጋገጥበት ዋንኛ ዓላማ ሦስተኛ ወገኖች ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። ""የመንደር ውል ችግሩም ይሄ ነው"" ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። እርግጥ ውል በሰነዶች ሲረጋገጥ መንግሥት ቴምብር ያሳርፍበታል። ገቢ ያገኛል። ገዥና ሻጭ ሰነዱን ይዘው ክፍለ ከተማ ሲሄዱ የመንግሥት አካል ቀረጥ ይጥላል። ከዚያም ገቢ ይገኛል። ተዋዋዮች ሕጋዊ ሰነድ ይዘው ስለቀረቡ፣ ሕጋዊ አገልግሎት አግኝተው የስም ማዞርያ አሹራ ይከፍላሉ። ይህም ሌላ ገቢ ነው። ለዚህም ነው ውሉ በሕጉ ላይ የተቀመጠውን ፎርም ስላሟላ እንደ ሕጋዊ ውል ተቆጥሮ ተፈጻሚነት የሚኖረው ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። ተፈጻሚነት ይኖረዋል ማለት ግን ምን ማለት ነው? በአጭሩ ለምሳሌ ሻጭ ለገዢ ስም አላዞርልህም ቢል ፍርድ ቤት ከሶ በግዴታ ስም እንዲያዞር፣ ገዥ ላይ ለደረሰው ኪሳራም ካሳ እንዲያገኝ ይሆናል ማለት ነው። ይህን ዕድል ግን በመንደር ውሎች ላይ ለማሳካት አስቸጋሪ ይሆናል። በመንደር ውል የተሸጠ ንብረት እጣ ፈንታው ምንድነው? በፍርድ ቤት ቀርቦ ያልተመዘገበ ውል፣ ወይም በውል አዋዋዮች ፊት ያልተረጋገጠ የመንደር ውል እንደ ሕጋዊ ተቆጥሮ አፈጻጸም ሊቀርብበት አይችልም። በዚህ ላይ ምንም ብዥታ መኖር የለበትም ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። ሆኖም ግን የመንደር ውሎች አሁንም በብዙ ሰዎች ዘንድ ይሠራባቸዋል። ውልና ማስረጃ አገልግሎት ስላቆመ ብቻ ሳይሆን ድሮም ይሠራባቸዋል። የሚገርመው ፍርድ ቤትም በብዛት እነዚህን በመንደር ውል የተፈጣጠሙ አቤቱታዎች ይመለከታል። ለምን? የመንደር ውል ሕጋዊ ካልሆነ ለምን ፍርድ ቤት ይመለከተዋል? ለምን ""ወዲያልኝ! ሲጀመር፣ ይሄ ሕጋ��� ውል አይደለም"" ብሎ አሽቀንጥሮ አይጥለውም? ጠበቃ ሚካኤል ""ሕግ በባህሪው አስተናጋጅ (Flexible) መሆን ስላለበት ነው"" ይላሉ። ጉዳዩን ሲያብራሩም፣ የመንደር ውል ተዋዋዮች፣ 'አዎ የመንደር ውል አድርገናል' ብለው ሳይካካዱ የሚያነሱት ጉዳይ ውሉ የመንደር ውል ነውና 'ፎርምን ብቻ አላሟላም' ተብሎ ውድቅ አይደረግም የሚል መረዳት በፍርድ ቤት አካባቢ ስላለ ነው ይላሉ። ጠበቃ ታምራት በዚህ በአቶ ሚካኤል ነጥብ ይስማሙና ነገር ግን በመንደር ውል ሕጋዊነት ዙርያ ያለው ብዥታ ""እኛ የሕግ ባለሞያዎችም እርግጠኛ ሆነን ምክር መስጠት እስክንቸገር የሚያደርሰን ሆኗል"" ይላሉ፡፡ ነገሩን ሲያፍታቱት፣ በመርኅ ደረጃ አንድ ውል በመንደርም ይደረግ በውል አዋዋይ ፊትም ይደረግ፣ በቃልም ይደረግ ሕጋዊ መሆኑን በማስመር ይጀምራሉ። ሆኖም ሕግ የግድ በጽሑፍ መሆን አለባቸው የሚላቸው የውል ዓይነቶች አሉ። ከእነዚህ አንዱ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ነው። የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በጽሑፍ መሆን አለበት፣ በሁለት ምስክሮች ፊት መሆን አለበት። በአዋዋይ ፊት መሆን አለበት። አሁንም ጥያቄውን እንድገመው። ውሉ በመንደር ቢደረግ እጣ ፈንታው ምንድነው የሚሆነው? ጠበቃ ታምራት ""እውነት ለመናገር በዚህ ረገድ ሕጉ የተረጋጋ አይደለም"" ይላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት በዚህ ላይ ቁርጥ፣ ጥርት ያለ መልስ እስከዛሬ ፍርድ ቤቶች አልሰጡም። የአገሪቱ የመጨረሻ ፍርድ ቤት የሆነው ሰበርም ቢሆን ከውል አዋዋይ (ውልና ማስረጃ) ውጪ የተደረጉ የመንደር ውሎች ይፀናሉ ወይስ አይፀኑም በሚለው ላይ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ውሳኔ መስጠቱን ያወሳሉ። በአንድ በኩል፣ ሰዎች በመንደር ከተዋዋሉና ነገር ግን ፊርማቸውን ካልተካካዱ ውሉ በተዋዋዮቹ መካከል ብቻ ይጸናል ብሎ የወሰነበት ፍርድ አለ። ይህ ማለት ውሉ የሚጸናው በእነሱ ላይ ብቻ ነው። ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብ ግን አይችልም። ምን ማለት ነው፣ አንድ ሰው ቤቱን በመንደር ውል ቢሸጥና ውል ለማፍረስ ፍርድ ቤት ቢሄድ ገዥ ገንዘቡን ለመክፈል ይገደዳል። ሻጭም ቤቱን ለመስጠት ይገደዳል። ሆኖም ግን፣ ለምሳሌ ባንክ በቤቱ ላይ ጥያቄ ቢኖረው የመንደር ውሉ አይጸናበትም። ወይም ደግሞ ሻጭ ላይ ባለ ዕዳ የሆነ ሰው ዕዳዬ ቤቱ ተሸጦ ይከፈለኝ ቢል ቤቱ ተሸጧልና አይከፈልህም ሊባል አይችልም። ምክንያቱም በመንደር ውል ስለተሸጠ። አደጋውም እዚህ ላይ ነው። ገዢው የመንደር ውሉን ይዞ ""እኔ እኮ ይሄን ቤት ገዝቼዋለሁ"" ብሎ ጥያቄ ያነሱ ሦስተኛ ወገኖችን ዝም ሊያሰኛቸው አይችልም። ስለዚህ ገዢ በመንደር ውል መፈጣጠሙ ""ወዶና ፈቅዶ በራሱ ላይ አደገኛ አደጋን ጋብዟል"" ይላሉ ጠበቃ ታምራትና ጠበቃ ሚካኤል። ተዋዋዮች የመንደር ውልን ለምን ተመራጭ ያደርጋሉ? አሁን አሁን የተለመደው አሰራር ገዥና ሻጭ ውል የሚፈጽሙት በሁለት ዙር ነው። መጀመሪያ በመንደር ውል ይፈጣጠሙና ነው ወደ ሁለተኛ ውል አዋዋይ ዘንድ የሚመጡት። ብዙውን ጊዜ አንድ ቤት ስንት እንደተሸጠ በትክክል የሚታወቀውም በመንደር ውል ላይ እንጂ በትክክለኛው ውል ላይ አይደለም። ተዋዋዮች ወደ መንግሥት ተቋማት ሄደው የሚዋውሉት በ2ኛ ደረጃ ነው። ይህን ሲያደርጉም ብዙውን ጊዜ ዋጋ ቀንሰው ነው። ""…ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ትክክለኛ ዋጋ ተናግረው የሚዋዋሉት። መንግሥት ቢቸግረው ተመን አውጥቶ ያስክፍላል። 6 በመቶ አሹራ ትከፍላለህ። የተዋዋልከው ከተመኑ ከፍ ካለ በተዋዋልከው ያስከፍላል። ዝቅ ካለ ደግሞ በተመኑ ያስከፍላል"" ይላሉ ጠበቃ ታምራት። ጠበቃ ሚካኤል በበኩላቸው ይህ የሁለት ጊዜ ውል ብዙ ሰው ልብ ባይለውም አደጋ አለው ይላሉ። እንዴት? በሁለት ዓይነ�� ዋጋ መፈራረም የሚያመጣው አደጋ ስምምነት ሲፈርስ ነው። አንድ ሰው ለምሳሌ ውል ይፍረስልኝ ብሎ ፍርድ ቤት ሲሄድ ውል ይፈርሳል። ውል ሲፈርስ ደግሞ ወደነበረበት ነው የሚመለሰው። ሻጭ ገንዘብ ይመልሳል፣ ገዥ ንብረቱን ይመልሳል። በአሥር ሚሊዮን ብር የተሸጠ ቤት ውልና ማስረጃ ባረጋገጠው ውል፣ ፍርድ ቤት ተሂዶ ውል ቢፈርስ ተዋዋዮቹ ዋጋ ዝቅ አድርገው ስለሚዋዋሉ [ለምሳሌ 6ሚሊዮን ብር] ሻጭ ገንዘብ መልስ ይባላል። ይህን ጊዜ እንዲመልስ የሚገደደው በውልና ማስረጃ በገዛበትን ገንዘብ ነው። ይህ ማለት ገዥ 4 ሚሊዮን ብር መክሰሩም አይደል? ጠበቃ ታምራት በበኩላቸው ዜጎች የመንደር ውልን የሚመርጡት በዋናነት ቀላልና ምቹ ስለሆነ ነው ይላሉ። ሕጋዊው አሠራሩ ጥብቅ ነው፤ በርካታ ሰነዶች መሟላትን ይፈልጋል፤ ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አስቸጋሪ ነው። ለዚህም እንደ ማስረጃ የሚያነሱት ካርታን ነው። ""አይደለምና በገጠር፣ በአዲስ አበባ ስንቱ ቤት ነው የተሟላ ካርታ፣ የተሟላ ሰነድ ያለው? ስንቱ ከተማ ነው ማዘጋጃ ቤትስ ያለው?"" ካርታው ስሙ ባንተ ነው ወይ? ዕዳና ዕገዳ የለበትም ወይ? ይሄ ሁሉ ነገር ከክፍለ ከተማ መጣራት አለበት። አቶ ታምራት ""መጣራቱ በጎ ነው፣ ክፋት የለውም"" ካሉ በኋላ፣ ነገር ግን ሰዎች በተለያየ ምክንያት የሚጠየቁትን ሁሉ ለማሟላት ይቸገራሉ ይላሉ። ""አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ችግሩን እያወቁም ከነጉድለቱ ንብረቱን መግዛት ይፈልጋሉ። አትግዙ ልንላቸው ነው? ገዢ የፍርድ ቤት ዕግድ መኖሩን እያወቅኩ ልግዛ ቢልስ? ልንከለክለው ነው?"" ልብ የማንላቸው የመንደር ውል አደጋዎች የመንደር ውል ሕጋዊ ነው አይደለም የሚለውን ሙግት እረፍት እንስጠውና ወደ አንድ ቁልፍ ነጥብ እንሻገር። የመንደር ውል ይዞብን የሚመጣው ፈተና ምንድነው? ሁለቱ ጠበቆች የነገሩንን በአጭር በአጭሩ እናካፍላችሁ። አንድ የቤት ገዥ በመንደር ውል ከተዋዋለ በኋላ ያን ይዞ ክፍለ ከተማ ሄዶ ስም ይዙርልኝ ቢል ተቀባይነት የለውም። አንድ ቤት ገዥ ቤቱን በመንደር ውል ገዝቶ አገር ሰላም ብሎ እየኖረ ድንገት የ3ኛ ወገን ጥያቄ ቤቱ ላይ ቢነሳ ለከፍተኛ ቀውስ ይጋለጣል። ይህም ከሻጭ ባል/ሚስት የሚመጣ፣ ""ውሉ ውድቅ ይደረግልኝ"" የሚል ጥያቄ ሊሆን ይችላል። በመንደር ውል ያገባ/ያላገባ ሰነዶች ጋር ተያይዞም ብዙ አሳሳቢ ጉዳዮች አሉ። ኋላ ላይ በሚመጣ መቃቃር ፍቺ ቢኖር ገዢ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ይገባል። አንድ ቤት ገዥ አገር ሰላም ብሎ ቤት በመንደር ውል ገዝቶ እየኖረ፣ የሻጭ ባል/ሚስት ሽያጩ አይመለከተኝም ይፍረስልኝ ብትል/ቢል፣ ቤት ገዢ ከፍተኛ የፋይናንስና የሥነ ልቡና ጉዳት ይደርስበታል። የመንደር ውሉን ይዞ ፍርድ ቤት ቢሄድም አትስተናገድም ባይባልም፣ ከሻጭ ገንዘቡን መልሶ የማግኘት ዕድሉ ጠባብ ነው የሚሆነው። ""እንዲህ ዓይነት በርካታ ጉዳዮች ያጋጥሙናል፣ ሽያጭ ውሉ አይመለከትኝ የሚሉ የትዳር አጋሮች ይኖራሉ። በቤተሰብ ሕጉ ከ500 ብር በላይ የሚደረግ ሽያጭ የሁለቱንም ይሁንታ ማግኘት አለበት፤ በዚህ የተነሳ የመንደር ውል ያልታሰበ ጣጣ ይዞ ይመጣል"" ይላሉ አቶ ሚካኤል። ለምሳሌ መንግሥት ይህን ክልከላ ሲያነሳ ሥራ በቆመበት ወቅት በመንደር ውል የተዋዋላችሁ በሙሉ ውላችሁ ውድቅ ነው ቢል በርካታ ሰዎች ገንዘብ መልስልኝ-አልመልስም አተካራ ውስጥ ሊከታቸው ይችላል። ይህ ባይሆን እንኳ እነዚህ ሰዎች የመንደር ውላቸውን ለማጽደቅ ውልና ማስረጃ ሲሄዱ ገንዘብ በባንክ ያስተላለፋችሁበትን ሰነድ አምጡ ይባላሉ። በዚህን ጊዜ ሻጭ የተቀበለው ገንዘብ ተመናምኖበት ይሆናል። ገዥ ያን ከፍተኛ ገንዘብ በድጋሚ በባንክ ለማስተላለፍ ይቸገር ይሆናል። እጁ ላይ አይኖረውም ይሆናል። የቤት ዋጋ በየጊዜው ከመናሩ ጋር ተያይዞ ደግሞ ሻጭ በአዲሱ የዋጋ ተመን ሊማልልና ሐሳቡን ሊቀይር ይችላል። የከፈልኩን ቀብድ መልስልኝ አልመልስም ጣጣ ሊከተል ይችላል። በዚህ መካካድ መካከል የመንደር ውል ተይዞ ፍርድ ቤት ሲኬድ፣ ፍርድ ቤት ተዋዋዮቹ ውል ማድረጋቸውን እስካልተካካዱ ድረስ ያስተናግዳቸዋል። ነገር ግን ሻጭ በውሉ የሚገደደው በመንደር ውሉ የተመላከተውን የገንዘብ መጠን ብቻ ነው። በሐሰተኛ የብድር ውል የሚፈጸሙ የመንደር ውሎችም ዘርፈ ብዙ ጣጣን ያስከትላሉ። የብር የመግዛት ዋጋ መውረድና የቤት ዋጋ መጨመር ሻጭ በጊዜ ሂደት ሽያጩን ክዶ፣ ገንዘብ እንዲመልስ የሚያማልል ነው። ""…ብቻ በአጠቃላይ በመንደር ውል ገዥው በራሱ ላይ የሚጋብዘው አደጋ የትየሌሌ ነው"" ይላሉ ጠበቃ ሚካኤል። አቶ ታምራት በበኩላቸው በመንደር ውል ስንዋዋል አንዳንድ ጊዜ ይሆናሉ ብለን የማንጠብቃቸው ነገሮችም እንደሚከሰቱ መዘንጋት የለብንም ሲሉ ያስገነዝባሉ። ""…ለምሳሌ በመሀል ሞት አለ። ከአገር መውጣት አለ። ውክልና ማንሳት አለ። በሰው ላይ ነገ ምን እንደሚደርስ ማን ያውቃል?"" አቶ ሚካኤል በበኩላቸው፣ ""በመንደር ውል የተፈጣጠመ ሻጭ ቢሞት የውርስ ጉዳይ ይከተላል፣ ጋብቻ ቢፈርስ የቤተሰብ ክርክር ውስጥ ይገባል፣ ወራሾች ቤቱ በሕገ ወጥ ውል የተፈጸመ ነው ብለው ሊያሳግዱት ይችላሉ። ጣጣው ብዙ ነው።"" ጠበቃ ታምራት እንዲያውም ነገሩ ከዚህም የከፋ የሚሆንበት ጊዜ እንዳለ ጠቅሰዋል። ""አንዳንድ መጥፎ ሰዎች ያጋጥማሉ። አንድን ቤት በመንደር ውል ለሁለት እና ለሦስት ሰው ከሸጡ በኋላ 'በሉ ሥራችሁ ያውጣችሁ' ብለው የሚሰወሩ።"" ታዲያ ምን ይሻላል? ጠበቃ ሚካኤል፣ ምክራቸው አንድ ነው። ""በቃ፣ የመንደር ውል ይቅርብን"" የሚል። የግድ ከሆነስ? የግድ ከሆነም ውሉ መዘጋጀት ያለበት በሕግ አዋቂዎች ነው ይላሉ። ምክንያቱም አሁን ያሉ ውሎች ከጫፍ እስከ ጫፍ አንድና-ወጥ (standard) ናቸው። በጠበቃ ቢዘጋጁ ግን የሻጭና ገዢ ግዴታን በማያሻማ ሁኔታ ያስቀምጣሉ። ከዚያም ባሻገር ነገ ሊመጣ የሚችልን የሕግ ክፍተትን መድፈን ይቻላል። ጠበቃ ታምራት በበኩላቸው የውሎች ወጥ መሆን በራሱ ችግር አይደለም ብለው ያምናሉ። ነገር ግን ወጥ ተደርገው የተበጁ ውሎች በየጊዜው ክፍተቶቻቸው እየተሞሉ መሄድ አለባቸው ባይ ናቸው። ዞሮ ዞሮ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የመንደር ውልን ጨርሶ ማቆም እንደማይቻል ያምናሉ። ተዋዋዮች አውቀው እስከገቡበት ድረስ አታድርጉት ሊባሉም አይችሉም። ሆኖም ውል ማዋዋል በውጭ አገር እንደሚደረገው በጠበቆች በኩል (ፕራይቬታይዝ) ቢደረግ የሚል አዲስ ሐሳብ አላቸው። ይህ ሐሳብ ራሱን ችሎ መፍታታት የሚፈልግ ስለሆነ በሌላ ጊዜ እንመለስበት ይሆናል። አሁን ጥያቄው የመንደር ውል ይቅርብን ወይስ? የሚለው ነው። አቶ ታምራት ሐሳባቸውን የሚጠቀልሉት በምሳሌ ነው። ""የመንደር ውልን እንደ ሕክምና እንውሰደው። እጃችንን ሳንታጠብ ብንበላ ልንታመመም እንችላለን፤ ላንታመም እንችላለን። ታጥበን ብንበላ ግን ጥሩ ነው።""" https://www.bbc.com/amharic/59633486 +health ስትወለድ በክብደት የዓለማችን ትንሿ ጨቅላ የነበረችው ከዓመት በኋላ ከሆስፒታል ወጣች ስትወለድ ከአንድ ብርቱካን ያነሰ ክብደት ትመዝን የነበረችው የዓለማችን ጨቅላ ከ13 ወራት የሆስፒታል ቆይታ በኋላ ወደ ቤቷ ገባች። እምቦቅቅላዋ በሲንጋፖር ሆስፒታል ባለፉት 13 ወራት በጽኑ ሕሙማን ክፍል ክትትል ሲደረግላት ቆይቷል። ዌክ ዩ ዥዋን ትባላለች። ስትወለድ የምትመዝነው 212 ግራም ነበር። ይህ ክብደት ማለት በአማካይ የአንድ ትንሽ ብርቱካን ክብደት ማለት ነው። ቁመቷ 24 ደግሞ ሴትቲ ሜትር ብቻ ነበር። አንድ ጤ��ማ ልጅ የሚወለደው በአማካይ ከ40 ሳምንታት ቆይታ በኋላ መሆኑ ይታወቃል። ይህቺ ልጅ የተወለደችው ግን ያለ ጊዜው በ25 ሳምንቷ ነበር። እስከዛሬ ስትወለድ የዓለማችን በኪሎ ትንሿ ትባል የነበረችው ልጅ አሜሪካዊት ነበረች። ይህች ልጅ ስትወለድ 245 ግራም ነበር የምትመዝነው። ይህ ክብረ ወሰን አሁን በሲንጋፖሯ ጨቅላ ተሻሽሏል። የዚህች ደቃቃ ልጅ እናት ልጇን የተገላገለቻት በቀዶ ህክምና ነበር። ለመውለድም ገና አራት ወራት ሲቀራት ነበር የተገላገለቻት። ከ13 ወራት ከፍተኛ ክትትል በኋላ አሁን የጨቅላዋ ክብደት 6.3 ኪሎ ግራም ሆኗል። የሲንጋፖር ብሔራዊ ሆስፒታል ይህቺ ልጅ በተወለደች ወቅት በሕይወት የመኖር ዕድሏ በጣም ጠባብ ነበር ይላል። በሆስፒታል ቆይታዋ በሕይወት እንድትቆይ የተለያዩ ሕክምናዎች እና የሕክምና ድጋፎች አስፈልገዋት ነበር። ዶክተሮች ጨቅላዋ እድገቷ አጥጋቢ በመሆኑ ከሆስፒታል እንድትወጣ መወሰኑን ተናግረዋል። ጨቅላዋ ዌክ ዩ ዥዋን አሁንም ቢሆን የከፋ የሳምባ ሕመም ያለባት ሲሆን ወደቤት ከተሰወደችም በኋላ ለመተንፈስ ድጋፍ ያስፍልጋታል ተብሏል። ሐኪሞች ጨቅላዋ ከሳምባ ሕመሟ እንደምታገግም ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል። የልጅቷ እናት ከዚህ ቀደም የወለዱት ልጅ ጤናማና መደበኛ ኪሎ የሚያሟላ ነበር። የዚህች ደቃቃ አራስ ልጅ የሆስፒታል ወጪ ከፍተኛ ሲሆን ገንዘቡን የሸፈኑት ግን ከሕዝብ በተሰበሰበ ዘመቻ ነው። ለዚህች በኪሎ ዝቅተኛ ለተባለችው የዓለማችን እንቦቀቅላ በአጭር ጊዜ 270ሺህ ዶላር ተሰብስቦላታል። https://www.bbc.com/amharic/news-58142407 +sports ኮሮናቫይረስ፡ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች 419 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍሉ ይችላሉ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ሊጉ በቅርቡ ጀምሮ በዝግ ስታዲየም ቢጫወቱም እንኳን ለአገር ውስጥና ለዓለማቀፍ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እስከ 419 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍሉ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል። ቢቢሲ ስፖርት ባገኘው መረጃ መሰረት ሊጉ ከነጭራሹ የሚቋረጥ ከሆነ አልያም ከሊጉ የሚወርዱ ቡድኖች የሚኖሩ ካልሆነ ክለቦቹ ከተገለጸው ገንዘብ ተጨማሪ ሊከፍሉም ይችላሉ። • የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በገለልተኛ ሜዳ ሊጠናቀቅ ይሆን? • ኮሮናቫይረስን ለማሸነፍ ከኢቦላ በሽታ ምን ልምድ መውሰድ ይቻላል? የፕሪምረየር ሊግ ክለቦች ደግሞ ሊጉን ማስቀጠል በሚቻለበት ሁኔታ ላይ የሚያደርጉትን ውይይት ትናንት አስቀጥለዋል። የ2019/20 ወድድር ዘመን 92 ጨዋታዎች ይቀሩታል። እነዚህን ጨዋታዎች እንዴት እናጠናቅ በሚለው ዙሪያ የሊጉ ክለቦች ላለፉት ሳምንታት የቪድዮ ስብሰባ ሲያደርጉ ነበር። የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ደግሞ ሊጉን ለማጠናቀቅ ቆርጠው ተነስተዋል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ቢያንስ 10 ገለልተኛ ሜዳዎች ያስፈለጋሉ ነው የሚሉት። ገለልተኛ ሜዳዎችን መጠቀም ያስፈለገው ደጋፊዎች ከሜዳ ውጪም ቢሆን እንዳይሰበሰቡ በማሰብ ነው ተብሏል። አልፎም የሚመረጡት ሜዳዎች ከፖሊስና የስፖርት ሜዳዎችን ደህንነት ከሚመረምር አካል ይሁንታ ያገኙ መሆን አለባቸው ተብሏል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መጋቢት ወር መግቢያ ላይ ነበር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲቆም የተደረገው። ሁሉም የሊጉ ክለቦች የቀሩትን 92 ጨዋታዎች ለመጫወት ተስማምተዋል። የዚህ ዓመት ወድድር ይቋረጥ የሚል ሐሳብ ከየትኛውም ክለብ አልመጣም ተብሏል። የገንዘብ ክፍያው የተጠየቀው የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች በታሰበላቸው ጊዜ ባለመካሄዳቸው ነው። በተጨማሪም ሊጉ የሚቀጥል ቢሆን እንኳን ጨዋታዎቹ ያለ ተመልካች መካሄዳቸውና ከቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጋር ስምምነት ከተደረሰበት ጊዜ ውጪ ስለሚካሄዱ ነው። • በኮሮናቫይረስ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊነታቸው የ���መረ 6 ምርቶች • በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች የፕሪምየር ሊግ ዋና ስራ አስፈጻሚው ሪቻርድ ማስተርስ በቅርቡ እንደገለጹት ደግሞ የዘንድሮው ሊግ የሚቋረት ከሆነ ክለቦች በአጠቃላይ እስከ 1 ቢሊየን ፓውንድ ኪሳራ ሊያጋጥማቸው ይችላል። ገለልተኛ ሜዳዎች ላይ ጨዋታዎቹን መቀጠል በሚለው ሀሳብ አንዳንድ ክለቦች አልተስማሙም። የሊጉ ኃላፊዎችም ቡድኖቹን ለማሳመንና በተቻለ መጠን ጨዋታዎቹን በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ለማስጀመር እየሞከሩ ነው። እስካሁን ዋትፎርድ፣ አስቶን ቪላ እና ብራይተን ጨዋታዎቹን በገለልተኛ ሜዳ ማካሄድ የሚለውን ሀሳብ በይፋ የተቃወሙ ሲሆን በሜዳቸው ደህንነቱ የተጨበቀ ጨዋታ ማካሄድ እንደሚችሉ መንግስትን ማሳመን ይጠበቅባቸዋል። የሊቨርፑል ከተማ ከንቲባ ደግሞ ጨዋታዎቹ በገለልተኛ ሜዳ ተካሂደውም ሊቨርፑል የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ የሚያነሳ ከሆነ ደጋፊዎች በአንፊል ስታዲየም ዙሪያ ተሰባስበው ደስታቸውን ሊገልጹ እንደሚችሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-52629957 +business በአዲስ አበባ ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ በሚያደርጉ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ "በአዲስ አበባ ተገቢ ያልሆነ ጫና እና የትምህርት ክፍያ ጭማሪ በሚፈፅሙ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቤት ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በርካታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን ተረድቻለሁ ብሏል። እነዚህ ትምህርት ቤቶች ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለትምህርት አገልግሎት እና ምዝገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ፣ የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ ባለስልጣን ባወጣዉ የማስፈጸሚያ ማኑዋል መስረት እየሰሩ አይደለም ብሏል። በአሁኑ ወቅት ያለውን ወሳኝና አስቸጋሪ ወቅት መሆኑን አስታውቆ ይህንንም በጋራ ለማለፍ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል። ""አሁን ባለንበት ወቅት ተደጋግፈን የምናልፍበት እንጂ አንዱ በሌላዉ ላይ ጫና የሚፈጥርበት አይደለም"" ብሏል። በዚህም መሰረት የግል ትምህርት ቤት ከደንበኞቻቸው ጋር በመነጋገር እና በመግባባት እንዲሰሩ አሳስቧል። ነገር ግን ይህንን ተላልፈው በሚሰሩና በሚቀርበው ጥቆማ መሰረት ፈጣንና የማያዳግም እርምጃ ቢሮ ለመውሰድም እንደሚገደድ አሳስቧል። ከዚህ ቀደም ለቢሮው እና ለወላጅ ምላሽ በመስጠታቸዉ እና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰዳቸዉ በ41 ትምህርት ተቋማት ላይ ተጥሎ የነበረዉ እገዳ እንዲነሳላቸዉ እና አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን አስታውሷል። ቢሮው የግል ትምህርት ተቋማቱ የትምህርት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ እና ለከተማው ነዋሪ የስራ እድል ከመፍጠር ረገድ ሚናቸው ላቅ ያለ ነው ብሏል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት የተቀመጡትን መመሪያዎች በማክበር ላከናወኑት ተግባርም እውቅና ሰጥቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58391132 +health ኮሮናቫይረስ ፡ ስንት ተስፋ ሰጪ የኮቪድ-19 ክትባቶች ተገኝተዋል? የተለያዩ ተቋሞች የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት መቃረባቸውን እያስታወቁ ነው። ይህም ለመላው ዓለም ተስፋ የሰጠ ዜና ሆኗል። ከሳምንት በፊት ፋይዘር እና ባዮቴክ የተባሉ ተቋሞች ውጤታማነቱ አስተማማኝ የሆነ ክትባት ማግኘታቸውን ማሳወቃቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ ሞዴርና የተባለ ድርጅት ውጤታማ የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራ ማድረጉን ይፋ አድርጓል። በኦክስፎርድ የሚካሄደው የክትባት ምርምር በ60ዎቹ እና 70ዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ላይ በሽታ የመከላከል አቅምን ከማዳበር አንጻር ውጤታማ መሆኑ ተገልጿል። ሌለው በክትባት ምርምር ውጤታማ እየሆነ የሚገኘው የቤልጄሙ ጃንሰን ሲሆን፤ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ሦስተኛ ደረጃ ሙከራ ላይ ይገኛል። ክትባት ሰውነት በሽታ የመከላከል አቅም እንዲያዳብር በማገዝ፤ ሕይወት ወደቀደመው ገጽታ እንዲመለስ ይረዳል። ሰዎች በወረርሽኙ እንዳይያዙም ያግዛል። ወይም ደግሞ የበሽታውን አደገኛንት ይቀንሳል። ክትባቶቹ ምን ልዩነት አላቸው? ክትባት የሚሠራው ሰውነት በሽታውን የሚከላከልበትን አቅም ለማዳበር ሲሆን፤ ሰውነት ቫይረሱ እንግዳና አደገኛ እንደሆነ ተገንዝቦ እንዲዋጋ ያግዛል። ፋይዘር እና ባዮቴክ እንዲሁም ሞዴርና ያገኙት አርኤንኤ የተባለ ክትባት ነው። ይህም የቫይረሱን የዘረ መል ቅንጣቶች ሰውነት ውስጥ በመክተት፤ ሰውነት በሽታውን ለይቶ የመከላከል አቅም እንዲያዳብር የሚደረግበት መንገድ ነው። በጃንሰን የሚሠራው ክትባት ደግሞ ዘረ መሉ የተሻሻለ የጉንፋን ቫይረስን በመጠቀም፣ ኮሮናቫይረስን እንዲመስል አድርጎ ጎጂነቱን ለመቀነስ ይሞክራል። በዚህ መንገድ ሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም አዳብሮ ወረርሽኙን እንዲከላከል ይደረጋል። በኦክስፎር እና በሩስያ የሚሠሩት ክትባቶች ጉዳት አልባ ቫይረስን ዝንጀሮ ላይ ይሞክራሉ። ከዚያም ዘረ መሉን አሻሽሎ ከኮሮናቫይረስ ጋር እንዲመሳሰል በማድረግ ውጤት ለማግኘት ይሞከራል። በቻይና የተሠሩት ሁለት ክትባቶች የተጠቀሙት ራሱን ቫይረሱን ነው። ቫይረሱ ጉዳት እንዳያስከትል ካከሰሙት በኋላ ነው ምርምሩ የተሠራው። ሰዎችን ለቫይረሱ በማጋለጥ የሚሠሩ ምርምሮች የትኛው ክትባት የተሻለ ውጤታማ እንደሆነ ለመረዳት ያግዛሉ። ክትባት መቼ እናገኛለን? ፋይዘር በዚህ ዓመት መጨረሻ 50 ሚሊዮን ጠብታዎችን በመላው ዓለም እንደሚያከፋፍል ተናግሯል። በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ 1.3 ቢሊዮን ጠብታዎች ይገኛሉ። ለምሳሌ ዩናይትድ ኪንደም በዓመቱ መጨረሻ 10 ሚሊዮን የክትባት ጠብታ እንደምታገኝ ይጠበቃል። ተጨማሪ 30 ሚሊዮን ክትባቶች ማዘዟንም አስታውቃለች። ሌለው ጥያቄ ክትባቱን በቅድሚያ ማን ያገኛል? የሚለው ነው። ይህ የሚወሰነው ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ በሚሰራጭባቸው እና የበለጠ ውጤታማ በሆነባቸው አካባቢዎች ነው። ዩናይትድ ኪንግደም በቅድሚያ ክትባቱን የምትሰጠው በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ለሆኑት በእድሜ የገፉ ሰዎችና እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ነው። ክትባቱ ውጤታማ መሆኑ የሚታወቀው ሁሉም የሙከራ ደረጃዎች ታልፈው ክትባቱ በሽታን እንደሚከላከል ወይም በበሽታው ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር እንደሚቀንስ ሲታወቅ ነው። ክትባቶች ፍቃድ አግኝተው፤ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ጠብታዎች መመረትም አለባቸው። ቫይረሱን ከምድር ላይ ለማስወገድ ከ60 እስከ 70 የሚሆነው የዓለም ሕዝብ በሽታውን የመካከል አቅም ማዳበር አለበት። https://www.bbc.com/amharic/news-55003274 +sports ሊቨርፑል ከ ማድሪድ፡ ታላቁ የአውሮፓ እግር ኳስ ፍልሚያ ዛሬ ምሽት አራት ሰዓት ላይ የፈረንሳይዋ ዋና ከተማ ፓሪስ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የኃያላኑን ሪያል ማድሪድና ሊቨርፑል ፍልሚያ ታስተናግዳለች። ሁለቱ ቡድኖች ከአራት ዓመታት በፊት በዚሁ መድረክ ለፍጻሜ ተገናኝተው ማድሪዶች ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው። እግር ኳስ የሚወድ ማንኛውም ሰው ይህ ጨዋታ እንዲያመልጠው አይፈልግም። እግር ኳስ ለምኔ የሚሉት እንኳን ስለነዚህ ቡድኖች ፍልሚያ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ሰምተዋል። በአውሮፓ ቻምፒየንስ ታሪክ ዋንጫውን 13 ጊዜ በማንሳት ተወዳዳሪ የሌላቸው ማድሪዶች ስድስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ከቻሉት ሊቨርፑሎች ጋር ነው የሚፋለሙት። የስፔን ኃያላኑ ማድሪዶ��� በዘንድሮው ውድድር ከምድብ ድልድል ጀምሮ አበቃላቸው እየተባለ ነው እዚህ የደረሱት። ቼልሲን፣ ፒኤስጂን እንዲሁም ለዋንጫው ለማለፍ ደግሞ ማንቸስተር ሲቲን ባለቀ ሰዓት ባስቆጠሯቸው ግቦች በመታገዝ ነው እዚህ የደረሱት። አጥቂው ካሪም ቤንዜማ ከምን ጊዜው በበለጠ በምርጥ አቋም ላይ ይገኛል። በዘንድሮው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ 15 ግቦችን በማስቆጠር ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ቤንዜማ፣ በስፔን ላሊጋም ቢሆን 27 ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ነው የጨረሰው። ሌላኛው የቡድን አጋሩ ቪኒሺየስ ጁኒየርም ቢሆን እንደ ዘንድሮ ብዙ ግቦችን አስቆጥሮ አያውቅም። በዛሬው ምሽት ጨዋታ እነዚህ ኮከቦች የሊቨርፑልን የተከላካይ መስመር በእጅጉ እንደሚፈትኑ ይጠበቃል። በሌላ በኩል የሊቨርፑሉ አምበል ጆርዳን ሄንደርሰን በስታ ዴ ፍራንስ ስታዲየም “ማድሪድን ዝም እናሰኛለን” ሲል ተደምጧል። በዘንድሮው ውድድር ኤፍኤ ካፕ እና ካራባዎ ካፕ ያሸነፉት ሊቨርፑሎች በፕሪምየር ሊጉ ዋንጫውን በማንቸስተር ሲቲ ተነጥቀዋል። አራት ዋንጫ ለማሸነፍ አልመው የነበሩት አሰልጣኙ የርገን ክሎፕ አሁን ላይ የመጨረሻ ተስፋቸው ቻምፒየንስ ሊግ ሆኗል። የርገን ክሎፕ ስለቡድናቸው ስብስብ ሲናገሩ ይህ ቡድን በእውነት ልዩ ነው ብለዋል። ዋንጫውን አሸንፈው ደጋፊዎቻቸውን በደስታ ለማስፈንጠዝ መዘጋጀታቸውን አክለዋል። ስለጨዋታው ተጠይቆ የነበረው የማድሪዱ ቤንዜማ ሊቨርፑሎች ምናልባት ይህንን ዋንጫ ያሸነፉ ያህል ሊያስቡ ይችላሉ። እኛም እሱን ነው የምንፈልገው ብሏል። አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ በበኩላቸው የዓመታት ልምድ ባላቸው ሞድሪች እና ክሩዝ የሚመራው የመሀል ሜዳው ቤንዜማ እና ቪኒሺየስ ሲጨመሩበት ቡድናቸው አስፈሪ እንደሚሆን ዝተዋል። ከአራት ዓመት በፊት ሊቨርፑል በማድሪድ በፍጻሜው ሲሸነፍ ተጎድቶ የወጣው ሞሐመድ ሳላህ በዚህ ፍልሚያ ግብ ማስቆጠር እንደሚፈልግ ተናግሯል። ማድሪድ ለዋንጫው ማለፉን ሳያረጋግጥ በፊት እንኳን በፍጻሜው ማድሪድን መግጠም እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ ተናግሮ ነበር። በቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ሊቨርፑል ከ ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ሲገናኙ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ከአራት ዓመታት በፊት እአአ 2018 ሁሉቱ ኃያል ቡድኖች ለፍጻሜ ተጋጥመው ነበር። በጨዋታው መጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ የሊቨርፑሉ ኮከብ ሞ ሳላህ የተፈጸመበትን ጉዳት ተከትሎ ከሜዳ ወጣ። ይህም ለሊቨርፑል ትልቅ ጉዳት ነበር። ከዚያም የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ ሎሪስ ካሪየስ ቡድኑን ትልቅ ዋጋ ያስከፈሉ ሁለት ጥፋቶችን ሰራ። የመጨረሻም ማድሪድ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ሊቨርፑልን መርታት ቻለ። ሊቨርፑሎች ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ግን ሌላ ቀን ነው እያሉ ነው። የእንግሊዙ 'ዴይሊ ሜይል ኦንላይ' ከሊቨርፑል አምበል ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ በስፋት አስነብቧል። ጆርዳን ሄንደርሰን በስታ ዴ ፍራንስ ስታዲየም “ማድሪድን ዝም እናሰኛለን” ብሏል። የሊቨርፑሉ አሰልጠኝ የርገን ክሎፕ ደግሞ በቡድናቸው ስብስብ መተማመን እንዳላቸው ለቢቢሲ ብሬክፋት ተናግረዋል። ክሎፕ “ይህ ቡድን በእውነት ልዩ ነው” በማለት የቡድን አባሎቻቸውን አሞካሽተዋል። ማድሪድ ልዩ አቋም ላይ ይገኛል። ጎል አዳኙ ካሪም ቤንዜማ ከመቼም ጊዜ በላይ ድንቅ አቋም ላይ ነው። ማድሪድ ከእዚህ የፍጻሜ ውድድር የደረሰው በፒኤስ ጂ፣ ቼልሲ እና ማንችስተር ሲቲ ቀድሞ የተያዘበትን ብልጫ ቀልብሶ ነው። የስፔኑ እውቅ ጋዜጣ 'ማርካ' ቤንዜማን በፊት ገጽ አውጥቶታል። ለማድሪዱ አሰልጣኝ አንቼሎቲም ቢሆን የነገው ጨዋታ ሊቨርፑልን የሚበቀሉበት አጋጣሚን ይፈጥርላቸዋል። እአአ 2005 ላይ በቱርክ ኢስታንቡል በነበረው የቻምፒየን�� ሊግ ፍጻሜ ጨዋታ፣ ሊቨርፑል ከኤስ ሚላን መገናኘታቸው ይታወሳል። በዚያ ጨዋታ ሊቨርፑል 3ለ0 ከመመራት ተነስቶ ኤስ ሚላንን ሲያሸንፍ አንቼሎቲ የኤስ ሚላን አሰልጣኝ ነበሩ። በነገው ጨዋታ ደግሞ ከ90ኛው ደቂቃ በኋላ ሊቨርፑል የበላይነቱን ይዞ ያጠናቅቃል የሚለው ግምት ሚዛን ደፍቷል። ሊቨርፑል 46 በመቶ የማሸነፍ ዕድል ተሰጥቶታል። ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑልን ሊረታ የሚችልበት አጋጣሚ ደግሞ 28 በመቶ የተገመተ ሲሆን፣ 26 በመቶ ጨዋታው ከ90ኛው ደቂቃ መጠናቀቅ በኋላ ሁለቱ ቡድኖች አቻ ይሆናሉ ተብሎ ተገምቷል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c10g9zzgd11o +politics ዶናልድ ትራምፕ በአምሳያቸው የተሠሩ የኤንኤፍቲ ስብስቦችን ለገበያ አቀረቡ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእሳቸው ፊት አምሳያ የተሰሩ የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሥራዎችን ይፋ በማድረግ ለገበያ አቀረቡ። ትራምፕ እነዚህ ውስን የሆኑት ዲጂታል ካርዶች የሥራ እና የጥበብ ሕይወቴን የሚያንጸባርቁ ናቸው ብለዋል። ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ይፋ የማደርገው ጉዳይ አለ ማለታቸውን ተከትሎ፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዳግም ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ምክትላው አድርገው የሚያቀርቡትን ዕጩ ይፋ ሊያደርጉ ነው ተብሎ በስፋት ተጠብቆ ነበር። ይሁን እንጂ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ አዲስ ይፋ ያደረጉትን የኤንኤፍቲ ስብስብ በቪዲዮ መልክ አስተዋውቀዋል። እያንዳንዳቸው በ99 ዶላር ለገበያ ከቀረቡት የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሥራዎች መካከል አንዱ ልዕል ኃያል ሆነው የሚያሳየው ይገኝበታል። NFT የሚለው Non-fungible token የሚለው ምሕጻረ ቃል የሚወክል ነው። የnon-fungible (ነን-ፈንጀብል) ምጣኔ ሃብታዊ ትርጉም ደግሞ መተኪያ የሌለው፤ በሌላ የማይቀየር ነገር ማለት ነው። ሰዎች የዶናልድ ትራምፕን ኤንኤፍቲ በ99 ዶላር ሲገዙ የገዙት ዲጂታል ካርድ ብቸኛው ባለቤት ይሆናሉ። ከክሪፕቶከረንሲ ተቀባይነት መጨመር ጋር ተያይዞ የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሥራዎች በኤንኤፍቲ በስፋት መሸጥ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። የዲጂታል ጥበብ ብቸኛ ባለቤት የመሆን ፍላጎት እንዲሁም ኤንኤፍቲ የኢንቨስትመንት አማራጭ ነው የሚሉ ምክንያቶች የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሥራዎች በኤንኤፍቲ አማካይነት ግብይታቸው እንዲጨምር አድርገዋል። ዶናልድ ትራምፕ እነዚህን ዲጂታል ካርዶች ሲያስተዋውቁ ጥሩ የገና ስጦታ ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል። ያልተጠበቀው የትራምፕ አካሄድ ከትችት አላመጠም። ተጽዕኖ ፈጣሪ ሪፐብሊካኖችን ጨምሮ በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የትራምፕን ውሳኔ አብጠልጥለዋል። የትራምፕ የቀድሞ ስትራቴጂስት ስቲቭ ባነን፤ “ከዚህ በላይ መታገስ አልችልም” ካሉ በኋላ በትራምፕ ዲጂታል ካርዶች ላይ ተሳትፎ ያደረጉ “ዛሬውኑ ከሥራቸው መባረር አለባቸው” ብለዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ደግሞ ለዶናልድ ትራምፕ ምላሽ በሚመስል መልኩ በቅርብ ቀናት ያከናወኗቸውን ሥራዎች ዘርዝረዋል። ፕሬዝዳንቱ የዋጋ ንረትን ማረጋጋታቸውን፣ አዳዲስ የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ሳምንታት የከናወኗቸውን በትዊተር ገጻቸው ዝርዝረዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cpeq0e92qveo +health ኦሚክሮን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው- የዓለም ጤና ድርጅት "አዲሱ የኮሮናቫይረስ ልውጥ አሚክሮን በዓለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ። ይህ ልውጥ ዝርያ በ77 አገራት ውስጥ መኖሩ ተረጋግጧል። ነገር ግን በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረእየሱስ እንዳሉት ምናልባት እስካሁን ያልታወቁ በሌሎች አገራት ውስጥ ሊኖር ይችላል ብ��ዋል። ዶክተር ቴዎድሮስ ልውጡን ዝርያ ለመጋፈጥ በቂ ስራ አለመሰራቱ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል። ""በእርግጥ እስካሁን ድረስ ይህ ቫይረስ የጋረጠውን አደጋ አቅልለን እንደምንመለከተው ተረድተናል ። ምንም እንኳን ኦሚክሮን ብዙም የከፋ በሽታ ባያመጣም፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ብዛት እንደገና ያልተዘጋጁ የጤና ስርዓቶችን ሊያሽመደምድ ይችላል"" ብለዋል። ኦሚክሮን የተሰኘው ልውጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በደቡብ አፍሪካ በህዳር ወር ላይ ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሃገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር አሳይቷል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ባደረጉት ምርመራ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ከሚታይባቸው ቀለል ካሉ ምልክቶች ለማገገም ራሳቸውን ለይተው ይገኛሉ። ኦሚክሮን መከሰቱን ተከትሎ ደቡብ አፍሪካን እና ጎረቤቶቿን የሚጎዳ የጉዞ እቀባ በርካታ ሃገራት ቢጥሉም ይህ ግን በመላው አለም እንዳይስፋፋ ማድረግ አልቻለም። በትናንትናው ዕለት፣ ማክሰኞ ዶክተር ቴድሮስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አንዳንድ ሃገራት ለኦሚክሮን ምላሽ ለመስጠት የክትባት መርሃ ግብራቸውን ያጠናከሩ ሲሆን ከዚህም ጋር ተያይዞ ስለ ክትባት ኢ-ፍትሃዊነት ያላቸውን ስጋት በድጋሜ አንፀባርቀዋል። የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የፋይዘር ክትባት በኦሚክሮን ላይ ከዋናው ዝርያ ሲነፃፀር ውጤታማነቱ በጣም ያነሰ ቢሆንም ይህ ጉድለት በሶስተኛና በማበረታቻ ክትባት ሊቀለበስ እንደሚችል አሳይቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59662932 +health ኮሮናቫይረስ፡ የስፔን ቀብር አስፈጻሚዎች የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ በስፔን የሚገኙ የቀብር አስፈጻሚ ድርጅቶች ሰራተኞች በኮሮረናቫይረስ የሚሞሩ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ የሰራተኛ ቁጥር ይጨመርልን በማለት የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተሰምቷል። የሰራተኞች ማህበራት እንደገለጹት ወረርሽኙ መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ ሲከሰት ቀብር አስፈጻሚዎቹ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው የአንዳንድ ሰዎችን ቀብር ሳይፈልጉ እንዲያራዝሙ ተገድደዋል። በአሁኑ ሰአት ደግሞ አውሮፓ በሁለተኛ ዙር የቫይረሱ ስርጭት እየተፈተነች ትገኛለች። በርካታ አገራት ቫይረሱ እንደ አዲስ መሰራጨት መጀመሩን ተከትሎ የሰአት እላፊዎችና የእንቅስቃሴ ገደቦችን ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከሩ ሲሆን የሟቾችም ቁጥር ቢሆን እያንሰራራ መጥቷል። ቅዳሜ ዕለት ኦስትሪያ እና ፖርቹጋል አዳዲስ መመሪያዎችን ማስተዋወቃቸው ይታወሳል። በመላው ስፔን የሚገኙ የቀብር አስፈጻሚ ድርጅቶች ሰራተኞች ዕሁድ ዕለት አድማውን መትተዋል። አድማው የተካሄደው ደግሞ ፈረንሳያውያን የሞቱባቸውን ሰዎች መቃብር ስፍራ በሚጎበኙበት ቀን ነው። አንድ በዋና ከተማዋ ማድሪድ የሚገኝ የቀብር አስፈጻሚ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ሲናገር በአሁኑ ሰአት እየጨመረ የመጣውን የሟቾች ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት ከ15 እስከ 20 ሰራተኞች እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። አርብ ዕለት ብቻ በስፔን 239 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ባሳለፍነው መጋቢት ወር ላይ የበርካታ ሰዎች አስክሬን ሳይቀበር ለተጨማሪ አንድ ሳምንት እንዲቆዩ የተገደዱ ሲሆን የቀብር ስነስርአቱም ቢሆን ከከተማዎች አካባቢ ራቅ ባሉ ቦታዎች ነበር የሚካሄደው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ ስፔን እስካሁን ከ1.1 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን 35 ሺ 800 ደግሞ የሟቾች ቁጥር ነው። በሌሎች የአውሮፓ አገራትም ቢሆን የሁለተኛ ዙር ስርጭቱን ተከትሎ በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰአታት ብቻ 46 ሺ 290 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የገለጸች ሲሆን ትናንት ከትናንት በስቲያ ደግሞ 35 ሺ 641 ሰዎች መያዛቸውን አስታውቃ ነበር። በአጠቃላይ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 37 ሺ 19 ደርሷል። ጣልያን ደግሞ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር አዳዲስና ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምሪያለው ብላለች። የአገሪቱ የጤና ሚኒስትሩ ሮቤርቶ ስፔራንዛ በጣልያን ያለውን ስርጭት ለመቆጣጠር ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴን መገደብ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54776071 +politics የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው የኡጋንዳው የትራንስፖርት ሚንስትር ቆሰሉ የኡጋንዳ የትራንስፖርት ሚንስትር በታጣቂዎች የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው የቆሰሉ ሲሆን የሚንስትሩ ልጅና ሹፌር ግን በጥቃቱ መገደላቸው ተገለጸ። የቀድሞው የመከላከያ ኃላፊና የአሁኑ የትራንስፖርት ሚንስትር ጄነራል ካቱምባ ዋማላ የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ካምፓላ የሚገኘው ቤታቸው አቅራቢያ መሆኑን የአይን እማኞች ገልጸዋል። በሞተርሳይክል ይጓዙ የነበሩ ታጣቂዎች የሚንስትሩ መኪና ላይ ደጋግመው መተኮሳቸው ነው የተነገረው። ከግድያ ሙከራው ጋር የተያያዙ ናቸው የተባሉ የስልክ ጥሪዎች ላይ ምርመራ እየተካሄ እንደሆነ መከላከያ ኃይሉ አስታውቋል። ጄነራል ካቱምባ የደረሰባቸው ጉዳት ለሕይወታቸው አስጊ እንዳልሆነና ሕክምና እያገኙበት ያለው ሆስፒታል በወታደሮች እየተጠበቀ እንደሆነ ተገልጿል። ኡጋንዳ ውስጥ እጅግ ከሚከበሩ ፖለቲከኞችና ወታደራዊ ግለሰቦች አንዱ ናቸው። የአገሪቱ መከላከያ ኮማንደር እንዲሁም የፖሊስ ኃላፊም ሆነው አገልግለዋል። የቢቢሲዋ የኡጋንዳ ዘጋቢ ፔሸንስ አቲሬ እንደምትለው፤ መሰል ጥቃቶች የተለመዱ ቢሆኑም የግድያ ሙከራው አስደንጋጭ ነው። ዛሬ ጥቃት ሲፈጸምባቸው በወታደር መኪና ውስጥ ነበሩ። መኪናው ላይ ከጎን እና ከፊት ተተኩሶበታል። ልጃቸው ብሬንዳ ዋማላ እና ሹፌራቸው ሀሩና ካዮንዶ ሕይወታቸው አልፏል። ጄነራሉ ደም በደም ሆነው፣ በፍርሀት ሲንቀጠቀጡና ከዚያም በሞተርሳይክል ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቷል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሞተርሳይክል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተኩስ እየከፈቱ አገሪቱን እየናጧት እንደሆነ የቢቢሲ ዘጋቢ ትናገራለች። እአአ ሰኔ 2018 ላይ ኢብራሒም አቢርጋ የተባለ ፖለቲከኛና የፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ቀንደኛ ደጋፊ ቤቱ አቅራቢያ ተተኩሶበት ተገድሏል። የቀድሞው የፖሊስ ቃል አቀባይ አንድሪው ፌሊክስ ካውሲም በሚያዝያ 2017 ተገድሏል። የእስልምና መምህራንም በተመሳሳይ ሁኔታ ተገድለዋል። እስካሁን ድረስ ግድያዎቹ ተመርምረው ውጤት ሲገኝ ወይም ተጠያቂዎች ለፍርድ ሲቀርቡ አልታየም። https://www.bbc.com/amharic/57318950 +politics በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ የጂቡቲ ወታደሮችን ማስለቀቁን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ ስድስት የጂቡቲ ወታደሮችን አስለቅቆ ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ወታደሮቹ ፍሩድ (ዘ ፍሮንት ፎር ዘ ሪስቶሬሽን ኦፍ ዩኒቲ ኤንድ ዲሞክራሲ) በተሰኙ የጂቡቲ ታጣቂዎች ታግተው እንደነበርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረቡዕ ታኅሣሥ 12/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አመላክቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮቹን ከታጣቂዎቹ እገታ ማስለቀቅ የቻለው በተቀናጀ ስለላ እና የፖሊስ ዘመቻ መሆኑንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ፍስሐ ሻወል መናገራቸው ሰፍሯል። ወታደሮቹን በማስለቀቅ ሂደት የማኅበረሰቡ አመራሮች እና የአፋር ክልል አስተዳደር ከፍተኛ ሚና መጫወቱ ቢገለጽም ወታደሮ�� በየትኛው ስፍራ ታግተው እንደነበር አልተገለጸም። ከእገታ የተለቁትን ወታደሮች ለጂቡቲ መንግሥት ማስረከባቸውን እና በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ያለውን ትብብርን አጽንኦት መሰጠቱንም አምባሳደሩን ዋቢ አድርጎ መግለጫው አመላክቷል። የታጣቂ ቡድኑ ፍሩድ መስከረም 26/2015 ዓ.ም. ጂቡቲ ታድጁራ ክልል ውስጥ በሚገኘው ጋራብቲሳን የጦር ሰፈር ጥቃት ካደረሱ በኋላ ወታደሮቹ መታገታቸው ተገልጿል። በጋራብቲሳን ጦር ሰፈር በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ ሰባት ወታደሮች ሕይወታቸውን እንዳጡና ተጠያቂውም “የአሸባሪ ቡድን” የተባለው ፍሩድ ነው ሲል የጂቡቲ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር። በዚሁም መግለጫ ላይ ከሞቱት በተጨማሪ አራት ወታደሮች መቁሰላቸው እና ስድስቱ መጥፋታቸው ተገልጿል። ፍሩድ በበኩሉ ከጦር ሰፈሩ አስራ አምስት ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ የጂቡቲ ጦር ላደረሰበት ጥቃት ምላሽ እንደሆነም መግለጹ ተዘግቧል። ፍሩድ ታጣቂዎቹ የጦር ሰፈሩን ተቆጣጥረው መቆየታቸውን እና መሳሪያ እና ጥይቶችም መውሰዳቸውን ቢገልጹም የጂቡቲ ባለሥልጣናት ግን ውድቅ የቡድኑን የጦር መሳሪያ ምርኮ ጉዳይ ውድቅ አድርጎታል። ይህንንም ጥቃት ተከትሎ የጂቡቲ ፓርላማ ቡድኑን በአሸባሪነት ፈርጆታል። ቡድኑ በጂቡቲ ጦር ሰፈር ላይ የፈጸመውንም ጥቃት የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ተቋም (ኢጋድ) እና የጅቡቲ ዋና የንግድ አጋር የሆነችውን ኢትዮጵያን ጨምሮ ክልላዊ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አውግዘውታል። በአውሮፓውያኑ 1991 የተቋቋመው ፍሩድ በጂቡቲ መንግሥታዊ ሥርዓት መገለል ደርሰቦቸዋል የሚለውን የአፋር ሕዝብ ጥያቄን ይዞ የተነሳ እንደሆነ ይነገራል። ከበርካታ ውጣ ውረዶች በኋላ በአውሮፓውያኑ 2001 ፍሩድ ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራርሞ ነበር። ነገር ግን የታጣቂው ክንፍ ስምምነቱን ውድቅ በማድረግ በትጥቅ ትግሉ እቀጥላለሁ ያለ ሲሆን፣ ለረጅም ጊዜም ይህ ነው የማይባል  ጉልህ ወታደራዊ እርምጃ ሳይወስድ ቆይቷል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cyek0y9zw80o +sports እስራኤል ፡ አረቡ ባለሃብት በእስራኤሉ ዘረኛ ክለብ ላይ ገንዘባቸውን ለማፍሰስ ለምን መረጡ? "ከቀናት በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ ፅንፈኛ የሚባለው የእስራኤሉ ቤይታር ጄሩሳሌም እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች የቡድኑን ልምምድ በማቋረጥ ሜዳውን ወረሩት። ደጋፊዎቹ በቁጣና በንዴት ሜዳውን የወረሩት ክለቡ ከሚወዳደርበት የእስራኤል ሊግ ወደታች ለመውረድ እየተንገታገተ በመሆኑ አይደለም። ነገሩ ወዲህ ነው። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ንጉሣዊ ቤተሰብ አባል የሆኑት ቱጃር በክለቡ ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ ነው ቁጣቸውን የገለፁት። ክለቡም ከሁለት ቀናት በፊት ከሼክ ሃማድ ቢን ካሊፋ አል ናይን ጋር የኢንቨስትመንት ስምምነቶች ላይ መድረሱን አስታውቆ ነበር። የቤይታር ደጋፊዎች በፀረ-አረብ፣ ፀረ-ሙስሊም፣ እብሪተኛና ፀበኛ ባህርያቸው የታወቁና ስምም አትርፈዋል። ከሰሞኑም ሜዳውን ብቻ መውረር ሳይሆን በቤይታር ስታዲየምም ላይ አፀያፊ የሚባሉ የግራፊቲ ምስሎችን በግድግዳዎች ላይ ስለዋል። ምንም እንኳን የቤይታር ደጋፊዎች ምላሽ የከፋ ቢሆን በአንዳንድ አረብ አስተያየት ሰጭዎች ዘንድ ስምምነቱ ተቀባይነት አላገኘም። በሬድዮ የስፖርት ፕሮግራም አቅራቢው ሳይድ ሃስን ለኒውዮርክ ታይምስ እንደተናገረው ስምምነቱ ""አሳፋሪ"" ነው በማለት ነበር። በተለይም የክለቡ ደጋፊዎች ፀረ-አረብ አቋም እንዳላቸው እየታወቀ ክለቡ ላይ ኢንቨስት መደረጉን ተችቷል። በስምምነቱም መሰረት አል ናህያን በሚቀጥሉት አስር ዓመታት 92 ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ ሲሆን 50 በመቶም የክለቡ የባለቤትነት ድርሻ ይኖራቸዋል። ክለቡ በአሁኑ ወቅት በሊጉ ባለው ደረጃ ከአስራ አራት ቡድኖች መካከል አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የእስራኤል መንግሥትና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማደስ በመስከረም ላይ ፊርማ ማኖራቸውን ተከትሎ እንዲህ አይነት የንግድ ስምምነቶች በሁለቱ አገራት መካከል እየጎረፉ ነው ተብሏል። ባለ መጥፎ ስሙ ክለብ የአሁኑ በሁለቱ አገራት መካከል የተከናወነ ቁልፍ ስምምነት ባያደርገውም የቤይታር ስምምነት በከፍተኛ ሁኔታ አወዛጋቢ ነው። በእስራኤል ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ በተለያዩ ክለቦች የይሁዲና አረብ ተጫዋቾች በአንድ ላይ ቢኖሩም ቤይታር አንድም አረብ ተጫዋች በታሪኩ አስፈርሞ አያውቅም። ሆኖም በክለቡ ታዳጊ ቡድን ውስጥ አረቦች አሉ። በጎሮጎሳውያኑ 2013 ክለቡ ሁለት ሙስሊም ተጫዋቾችን ከቺቺንያ ማስፈረሙን ተከትሎ የቤይታር ቢሮ በደጋፊዎቹ ተቃጥሏል። ክለቡ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎችም ላይ ""ሞት ለአረቦች"" የሚሉ መፈክሮችና ዝማሬዎች እንዲሁም አፀያፊ የሚባሉ ፅሁፎችን ከደጋፊዎቹ በኩል መሰስማትና ማየት የተለመደ ነው። የክለቡ ባለቤት ይህንን ባህርይ ለመቀየር ቢሞክሩም ብዙ ፍሬ አላፈራም ተብሏል። አዲስ ባለቤት፣ ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፉ ሚሊዮነር የሆኑት ሞሼ ሆጌግ የተባሉት ግለሰብ ከሁለት ዓመት በፊት ክለቡን ገዙት። ሞሼ የተወለዱት እስራኤል ቢሆንም አባታቸው ቱኒዝያዊ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ የሞሮኮም ዝርያ አላቸው ተብሏል። ከዓመት በፊት የክለቡ ባለቤት ሞሼ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ዘረኛ የሆኑ ጉዳዮችን እንደማይታገሱና ዘረኛ በሆኑ ደጋፊዎችም ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ""የማንንም ህይወት ማበላሸት እየሞከርኩ አይደለም። የአባታቸውና እናታቸውንም ሚና እየወሰድኩ አይደለም። ለማስተማርም እየሞከርኩ አይደለም ያ የኔ ሥራ አይደለም"" ብለዋል ሞሼ። አክለውም ""ነገር ግን ያን ባህርይ ወደ ስታዲየም ሲያመጡት በተሰበሰበውም ሕዝብ ላይ ሆነ በአገራችን ላይ መጥፎ ነፀብራቅ ነው። ያንን ደግሞ አልቀበለውም"" ብለዋል። ሞሼም ቢሆኑ ""ነጥብ ለማስቆጠር"" በሚል አረብ ተጫዋች እንደማያስፈርሙ ቢናገሩም፤ ለስፖርታዊ ምክንያቶች ሲሉ ግን ለማስፈረም ወደኋላ እንደማይሉና ፍራቻም እንደሌላቸው አሳውቀዋል። ""የተጫዋች እምነቱ፣ ቀለሙ ምንም ይሁን ግድ አይሰጠኝም። ቡድኑን መርዳት ይችላል ወይ? ጥሩ ተጫዋች ነው የሚለው ጉዳይ ነው የሚያሳስበኝ"" ብለዋል። ""የአረቦቹ ተጫዋቾች ይፈርሙም አይፈርሙም እስራኤላዊ የሆጉ ጎበዝ አረብ ተጫዋቾች አሉ። አንደኛውን ልናስፈርም እንችላለን"" ብለዋል ሞሼ። በተለይም ከአረቡ ቱጃር አልናህያን ጋር የተረደገውን ስምምነት ሞሼ ይበል የሚያሰኝ ነው ብለውታል። ""በአንድ ላይ ሆነን ክለቡን በአዲስ መልክ በመተባበር፣ ስኬትና ወንድማማችነት በተሞላበት መልኩ እናድሰዋለን"" በማለትም ተናግረዋል። ንግድና ጓደኝነት አልናህያን በቤይታር ኢንቨስት እንዲያደርጉ ዋነኛ ምክንያታቸውም ከሞሼ ጋር ያላቸው የዓመታት የንግድ ሽርክናውና ወዳጅነት እንደሆነ ተናግረዋል። ስምምነቱ መፈረሙንም ተከትሎ አል ናህያ የክለቡ አጋር በመሆናቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል። ""ክለቡ እያከናወነው ስላለው ለውጥ ሰምቻለሁ። በዚህም ተሳታፊ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ"" ብለዋል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁን ግለ ህይወት የፃፈው ጋዜጠኛው አንሸል ፊፈር በበኩሉ የቤይታር ደጋፊዎች ከእስራኤል ገዢ ፓርቲ ሊኩዊድ ጋር ፅኑ ቁርኝት እንዳላቸው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁም በጨዋታዎች ወቅት ከፅንፈኞቹ ደጋፊዎች ጋር አንድ ላይ ፎቶም ተነስተዋል። ""አል ናህያ በቤይታር ጄሩሳሌም ኢንቨስት ለማድረግ መወሰናወች ምንም ተቃርኖ የለውም። ቤተሰባቸው በአጠቃላይ ከእስራኤል መሪዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ቁልፍ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል"" በማለትም ጋዜጠኛው ይናገራል። ይሄ ብቻ አይደለም አል ናህያ ከሁለት ቀናት በፊት በተድበሰበሰ መልኩ ኢየሩሳሌም የእስራኤል መዲና እንደሆነች የሚጠቁም ንግግር አድርገዋል። ለአስርት ዓመታት በዘለቀው የእስራኤልና ፍልስጥኤም ግጭትና የእየሩሳሌም ሁኔታ ዋነኛና አወዛጋቢ ጉዳያቸውም ነው። እስራኤል መላው ኢየሩሳሌም ግዛቴና መዲናዬ ናት የምትል ሲሆን ይህ በአሜሪካ ቢደገፍም በርካታ አገራት ይቃወሙታል። ፍልስጥኤማውያን በበኩላቸው እስራኤል በጎሮጎሳውያኑ 1967 በተካሄደው ጦርነት በወረራ የያዘችውን ምሥራቅ እየሩሳሌም መጪዋ መዲናችን ናት ይላሉ። እስራኤልና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ግንኙነታቸውን ለማደስ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ ፍልስጥኤም መዲናዋን ምሥራቅ እየሩሳሌም ባደረገ መልኩ ግዛቷን የምትመሰርትበትን ሁኔታም እንደምታግዝ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አስታውቃለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-55241937 +business ሕንድ ውስጥ ከ2.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያውጣ ኮኬይን ተያዘ "የሕንድ ባለሥልጣናት ጉጃራት በምትባለው ግዛት ወደ 3ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተባለውን አደንዛዥ ዕጽ መያዛቸውን አስታወቁ። ይህ በጉጃራት በሚገኝ ወደብ ላይ የተያዘው ከፍተኛ መጠን ያለው ይህ ኮኬይን ለገበያ ቢቀርብ ከ2.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያወጣል ተብሏል። ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው እና በርካታ ሰዎች ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑም ተነግሯል። የኮኬይኑ መነሻ አፍጋኒስታን መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ በይፋዊ ሰነዶች ላይ እቃው 'ታልክ' የተሰኘ የማዕድን ድንጋይ መሆኑ ነበር የተመለከተው። ዕጹ በቅድሚያ ከአፍጋኒስታን ወደ ኢራን ከተጓጓዘ በኋላ ነበር በሕንድ ጉጃራት ሙንደራ ወደብ የተያዘው። የሕንድ የገቢዎች ደኅንነት ዳይሬክቶሬት እንዳለው ከሆነ፤ ኢራን ከሚገኘው ባዳር አባስ ወደብ አደንዛዥ ዕጹ ወደ ሕንድ መላኩን የሚጠቁም መረጃ ደርሶን ነበር ብሏል። ዳይሬክቶሬቱ እቃውን ወደ ሕንድ ያስገባው ተቋምም በሕንድ የሚገኝ ኩባንያ ስለመሆኑ የቀደመ መረጃ እንዳለ አመልክቷል። ""ባለሙያዎቻችን እቃውን በቁጥጥር ሥር አውለው ምርመራ ሲያደርጉ፤ በኮንቴነሮቹ ውስጥ ዕጽ ተገኝቷል። ኮኬይን መሆኑም ተረጋግጧል"" ብሏል ዳይሬክቶሬቱ በመግለጫው። ባለሥልጣናት እንዳሚሉት ከሆነ ከአደንዛዥ ዕጹ ዝውውር ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በመዲናዋ ዴልሂ ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ዘመቻ መካሄዱን አስታውቀዋል። ""እስካሁን የተካሄዱ ምርመራዎች በቁጥጥር ስር ላይ ያሉት የአፍጋኒስታን ዜጎች በዕጹ ዝውውር ውስጥ መሳተፋቸውን አሳይቷል"" ብሏል ኤጀንሲው። ኮኬይንን ጨምሮ በርካታ አደንዛዥ ዕጾችን ለማምረት የሚውለው ኦፒየም ፖፒይ የተባለውን ተክል በማምረት አፍጋኒስታን ቁጥር አንድ አገር ነች። እንደ ተባበሩት መንግሥታት የዕጽ እና ወንጀል ቢሮ መረጃ ከሆነ ለዓለም ገበያ ከሚቀርበው የኦፒየም ምርት 80 በመቶው የሚመረተው በአፍጋኒስታን ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-58640077 +sports በአከራካሪው የ3ሺህ ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አገኘች "ኳታር ዶሃ ላይ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክ��� ሻምፒዮና ውድድር ላይ በወንዶች የሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው ለሜቻ ግርማ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አሸነፈ። ይህ በሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ውድድር በለሜቻ ግርማ የተገኘው የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ በዘርፉ የመጀመሪያ ሲሆን የተመዘገበው ሰዓትም ለአገሪቱ ክብረ ወሰን ነው ተብሏል። ኬንያዊው አትሌት የወርቅ ሜዳሊያውን በወሰደበት በዚህ የመሰናክል ሩጫ ውድድር ላይ ለሜቻ የተቀደመው ከአንድ ሰከንድ በታች በሆነ ጠባብ ልዩነት ነው። ለሜቻ አንደኛ ሆኖ የወርቅ ሜዳሊያን ካገኘው ኬንያዊው ሯጭ ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ ጋር እኩል የመጨረሻውን መስመር በማለፋቸው አሸናፊው ማን እንደሆነ በውድድሩ ማብቂያ ላይ ወዲያውኑ አልታወቀም ነበር። • ""ቤተ መንግሥቱን ለማስዋብ ለሙያችን የሚከፈለን ገንዘብ የለም"" መስከረም አሰግድ • ተማሪዎች መገረፍ አለባቸው የሚሉት የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት • 10 ሚሊዮን ሕዝብ ይታደምበታል የተባለው ኢሬቻ በአዲስ አበባ የውድድሩ ዳኞች በቪዲዮ (ፎቶ ፊኒሽ) ታግዘው ከአንድ ሰከንድ ባነሰ የሰከንዶች ቅንጣት የመጨረሻውን መስመር ኬንያዊው ለሜቻን ቀድሞ እንዳለፈ ከለዩ በኋላ ነው አሸናፊው ሊታወቅ የቻለው። በስፍራው የሚገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለስልጣናት ለሜቻ አንደኛ ወጥቷል ብለው አምነው ሰለነበር ይፋ የተደረገውን ውጤት በመቃወም ቅሬታ ለማቅረብ አስበው የነበረ ቢሆንም፤ የመጨረሻውን ሰከንድ የውድድሩን ቪዲዮና ምስሎችን ተመልክተው ካጣሩ በኋላ ቅሬታቸውን ማንሳታቸውን የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል። 19 ዓመት ሊሆነው ሁለት ወራት የቀሩት ወጣቱ ለሜቻ በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ መሳተፍ የጀመረው በቅርቡ ሲሆን በኬንያዊያን የበላይነት ስር በነበረው የሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ውድድር ላይ የብር ሜዳሊያ ያስገኘበት የዶሃው ውድድር ሦስተኛው ዓለም አቀፍ ተሳትፎው ነው። በውድድሩ አሸናፊ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነው ኬንያዊው ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ በዚህ በፈረንጆች ዓመት በሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል አራት ጊዜ ተሳትፎ የነበረ ቢሆንም በአራቱም ለማሸነፍ ሳይችል ቀርቶ በዓለም ሻምፒዮና ላይ እንደተሳካለት ተነግሯል። በዚህ ውድድር ላይ በማሸነፍ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ይገባል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው የዳይመንድ ሊግ አሸናፊው ጌትነት ዋሌ አራተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል። ለሜቻ ውድድሩን ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀበት ሰዓት እስካሁን በተካሄዱት የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ላይ ከተመዘገቡት ለአንደኛው ከቀረቡት ውጤቶች ሁሉ የበለጠ እንደሆነም ተነግሯል። እስካሁን በተካሄዱ ዓለም አቀፍ የሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ ውድድር ላይ ኢትዮጵያ ሜዳሊያ አግኝታ የማታውቅ ሲሆን ይህ በዶሃ እየተካሄደ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በለሜቻ ግርማ የተገኘው ሜዳሊያ የመጀመሪያ ነው። የብር ሜዳሊያ አሸናፊው ለሜቻ ከውድድሩ በኋላ ለቢቢሲ እንደተናገረው በውጤቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል። አንደኛ በመሆን ያሸነፈው ኬንያዊው አትሌት ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ ውድድሩ ላይ ከኢትዮጵያዊያኑ በኩል ከባድ ፈተና እንደገጠመው ተናግሯል። • ""የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም"" ዱቤ ጂሎ ""ኢትዮጵያዊያኑ በደንብ ተዘጋጅተው ነበር የገቡት። ውድድሩን ለመቆጣጠርና ከፊት ከፊት ሆኜ ለመምራት እቅዱ ነበረኝ ነገር ግን ሊሆን አልቻለም። ለሜቻና ጌትነት ግን እቅዴን እንዳላሳካ አድርገውታል"" ሲል ገጥሞት የነበረውን ፈተና ለጋዜጠኞች ተናገሯል። ኢትዮጵያዊያን ከኬንያዊያን በተሻለ ተዘጋጅተው መግባታቸውን የሚናገረው ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ ለማሸነፍ የ��በረው ጽኑ ፍላጎት በውድድሩ የወርቅ ሜዳሊያውን እንዲወስድ እንደረዳው ገልጿል። በዚህ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ እስከ ዛሬ ጠዋት ኢትዮጵያ አንድ ወርቅና ሦስት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ላይ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኬንያ በሦስት ወርቅና በሁለት የነሃስ ሜዳሊያ ሦስተኛ ስትሆን አሜሪካና ቻይና አንደኛና ሁለተኛ ሆነው የሜዳሊያ ሰንጠረዡን እየመሩ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/49944141 +sports የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራር ምርጫ ያስከተለው ውዝግብ "ካለፈው ሳምንት ማብቂያ ወዲህ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ ጋር በተያያዘ ውዝግብ መከሰቱ ሲነገር ቆይቶ ሰኞ ዕለት በኮሚቴው ጽህፈት ቤት ውስጥ ተካሄደ የተባለን ስብሰባ ተከትሎ በአካባቢው ተቃውሞ እንደነበር ተሰምቷል። ይህ በኦሊምፒክ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ደጃፍ የተደረገው የተቃውሞ ሠልፍ የተጠራው የኮሚቴው አባል በሆነው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንደነበረ የፌዴሬሽኑ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ብስራት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የተቃውሞ ሠልፉን ያደረጉበትን ምክንያት ሲያስረዱም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እያደረገ ይገኛል ያሉትን ሕገ ወጥና አግባብ ያልሆነ አሰራርን በመቃወም ነው ብለዋል። በዚህ ተቃውሞ ላይ በቶኪዮ 2020 ኢትዮጵያን በአትሌቲክ የሚወክሉ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ የቀድሞ አትሌቶች፣ የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና የሌሎች አገር አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽን አመራሮች መገኘታቸውን አቶ ስለሺ ጨምረው አስረድተዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴም መጋቢት 20/2013 ዓ.ም የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ለማድረግ ከሚገኝበት አቢጃ ኮትዲቯር ውስጥ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ፤ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውክልና ሳይሰጣቸው በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ተገኝተዋል ያላቸው ግለሰቦች ላይ እገዳ መጣሉን አሳውቋል። በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮችን ምላሽ ለማካተት ቢቢሲ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ለአሁን አልተሳካለትም። ነገር ግን ትናንት ማምሻውን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ኮሚቴውን ለቀጣይ አራት ዓመታት እንዲመሩ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በፕሬዝደንትነት፣ አትሌት ብርሃኔ አደሬ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት፣ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው መመረጣቸውን አስፍረዋል። ቢቢሲ ይህንን መረጃ ከኮሚቴውም ሆነ መመረጣቸው ከተነገረው ሰዎች ለማረጋገጥ አልቻለም። የሁለቱ አትሌቶች በምርጫው ውስጥ መካተትን በተመለከተ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ ላይ ሂደቱ ሕጋዊ መስመርንና አሰራርን ያልተከተለ ነው በማለት ተቃውሞታል። ፌዴሬሽኑ በመግለጫው ላይ የኃይሌ ገብረሥላሴና የብርሃኔ አደሬ በኦሎምፒክ ኮሚቴው ከፍተኛ አመራርነት ውስጥ መግባታቸው ለአገር ካበረከቱት አስተዋጽኦ አንፃር ተገቢ መሆኑን ጠቅሶ፤ ነገር ግን ""በማኅበር ወይም በፌዴሬሽን የተወከሉ ባለመሆናቸው ህጋዊ መስመሩን ያልተከተለ ነው"" ብሏል። የአሁኑ ውዝግብ መነሻ የሆነው ከዚህ ቀደም አዲስ አመራሮችን መሰየምን በተመለከተ በኮሚቴው የተሰጠው ውሳኔ ባላከበረ ሁኔታ ምርጫ እንዲካሄድ መደረጉ እንደሆነ ይነገራል። የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ ላይ እንደሰፈረውና አቶ ስለሺ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም በታኅሣሥ ወር ሐዋሳ ላይ በተደረገ ጉባኤ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ከቶኪዮ ኦሎምፒክ ማግስት በመስከረም 2014 ዓ.ም ላይ እንዲደረግ መወሰኑን በማስታወስ፣ ይህንን የጣሰ ተግባር በኮሚቴው መፈፀሙን ይናገራሉ። እንደ አቶ ስለሺ ከሆነ የኦሎምፒክ ኮሚቴው ይህንን ስምምነት መጣሱ ብቻ ሳይሆን የዓለም ዓቀፉን ኦሎምፒክ ቻርተር እየተገበረ አይደለም ሲሉም ይከሳሉ። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለአባልነት የትምህርት ዝግጅት እንደመስፈርት ማስቀመጡን በተጨማሪም የኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራር በተለይም ፕሬዝዳንቱ የስልጣን ዘመናቸው ስምንት ዓመት እንዲሆን መደረጉንም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በቻርተሩ አንድ ግለሰብ ለመመረጥ የትምህርት ዝግጅት እንዲኖረው ማድረጉ ለአባልነት እና ለሥራ አስፈፋሚነት አስፈላጊ አይደለም በማለት ይከራከራሉ። በዚህም የተነሳ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ አባላት ይህ አሰራር መስተካከል አለበት የሚል አቋም እንዳላቸውና ይሀንንም አቋም ሌሎቹ ፌዴሬሽኖች እንደሚጋሩት ይገልጻሉ። የኦሎምፒክ ኮሚቴ ሰሞኑን በባሕር ዳር ከተማ ተሰብስቦ ምርጫ ለማከናወን ቢሞከርም ፈቃድ ባለማግኘቱ ወደ ሐዋሳ መሻገሩን እዚያም ፈቃድ ባለማግኘታቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ሰኞ መጋቢት 20/2013 ዓ.ም ኦሎምፒክ ኮሚቴ ቅጥር ግቢ ውስጥ ምርጫ አደርገው መጠናቀቁ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም 13 የስፖርት አገር አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች ተቃውሟቸውን ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና ለሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት በጽሁፍ ማሳወቃቸው በማስታወስ ምላሽ እየጠበቁ መሆኑን ተናግረዋል። በአገር አቀፍ ደረጃም የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም ባህልና ቱሪዝም ሁለቱ አካላት በጉዳዩ ላይ በጋራ ውይይት ይኖራቸዋል በማለት ሁለቱን አካላት አቀራርቦ በማወያየት ውሳኔያቸውን እንደሚጠበቅ ይናገራሉ። ይህንን የኦሎምፒክ ኮሚቴ ምርጫን በመቃወምም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማኅበር፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አሰልጣኞች ማኅበር መግለጫ ሰጥተዋል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ጃፓን ቶኪዮ ውስጥ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው የ2020 የኦሊምፒክ ውድድር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት በዚህ ዓመት ማብቂያ ላይ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮጵያም በሐምሌ ወር አጋማሽ ላይ በሚካሄደው የዓለማችን ትልቁ የስፖርት ውድድር ላይ የምትሳታፍ ሲሆን፤ ነገር ግን ይህ በኦሊምፒክ ኮሚቴውና በፌዴሬሽኖች እንዲሁም በማኅበራት መካከል ተከሰተው ውዝግብ በቶሎ መፍትሔ ካላገኘ በአገሪቱ ተሳትፎ ላይ ምን ውጤት እንደሚኖረው ወደፊት የሚታይ ይሆናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56554166 +politics መንግሥት ከህወሓት ጋር በሚደረገው የድርድር ሂደት እንደሚገፋበት ተገለጸ የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላም ለማውረድ ከህወሓት ጋር በሚደረገው የድርድር ሂደት እንደሚገፋበት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ። ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ. ም. ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ላይ ፕሬዝዳንቷ መንግሥት በዚህ ዓመት ትኩረት የሚያደርግባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ባደረጉት ንግግር ነው ይህንን ያሉት። “የአገሪቱን ጥቅም ባስከበረ” እንዲሁም “ዘለቄታን ባማከለ” መልኩ ከህወሓት ጋር የሚደረገውን ድርድር የፌደራል መንግሥቱ እንደሚቀጥልበት ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቷ እንዳሉት መንግሥት የድርድር ሂደቱን ቢገፋበትም “የሰላም አማራጭ ተትቶ ትንኮሳ ከተደረገ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል” ሲሉ ተናግረዋል። ጨምረውም መንግሥት “ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር” ያለውን ፍላጎት በንግግራቸው ጠቅሰው “የሰላም በር አይዘጋም” ሲሉ አስምረውበታል። አያይዘውም ማንኛውንም ልዩነት ለመፍታት “ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመወያየት አሁንም ጥሪ ያቀርባል” ሲሉ ፕሬዝዳንቷ ተናግረዋል። የባለፈው ሳምንት የአፍሪካ ኅብረትን የድርድር ጥሪ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታና ጊዜ ንግግር ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በመግለጽ ግብዣውን መቀበሉ ይታወሳል። በተመሳሳይም ህወሓት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት ይደረጋል በተባለው ንግግር ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆኑን ገልጿል። ነገር ግን በአህጉራዊው ድርጅት አማካይነት ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ይደረጋል ተብሎ የነበረው ንግግር የሎጂስቲክስ በተባለ ችግር ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መዘዋወሩ ተነግሯል። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ፣ በዚህ ዓመት መንግሥት አገሪቱ ከጦርነት የምትወጣበት እንዲሆን ያለውን ፍላጎት ጠቁመው፣ የአፍሪካ ኅብረትም ለሰላም የሚያደርገውን ጥረት እንደሚቀጥል ተስፋ እንዳለ ጠቅሰዋል። ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝዳንቷ በዓመቱ የምክር ቤቶቹ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ከህወሓት ጋር ከሚደረገው ድርድር ባሻገር አገር አቀፍ የምክክር ኮሚሽኑ የሐሳብ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት መንግሥት እንደሚደግፍ ገልጸዋል። “ደም አፋሳሽ ጦርነት ከሚፈጥረው ቂምና ቁርሾ እንዲሁም ከግጭት አዙሪት ለመውጣት” ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ጎን መቆም እንደሚያሻ ተናግረዋል። ከሰዓት በኋላ በተደረገው ስብሰባ የ2014 ዓ. ም. ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና የምጣኔ ሀብት ዳሰሳ አቅርበው፣ ለ2015 ዓ. ም. የተያዙ ዕቅዶችን ርዕሰ ፕሬዝዳንቷ በንግግራቸው ዳሰዋል። በጦርነቱ ሳቢያ የወደሙ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት መስጫዎችን መልሶ ለማቋቋም በ2014 ዓ. ም. ሥራዎች እንደተጀመሩና በያዝነው ዓመትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። ጦርነት፣ የኮሮናቫይረስ፣ ጎርፍ እና ድርቅ በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ ጫና ቢያሳድርም፣ ውጤቶች እንደተመዘገቡም ርዕሰ ብሔሯ ሳይጠቅሱ አላለፉም። ያለፈው ዓመት ከውጭ ንግድ ከፍተኛ የሚባለው ገቢ የተመዘገበበት እንደሆነ ጠቅሰው፣ የታክስ ገቢ 93.5% እንዳደገ እንዲሁም ለ2.38 ሚሊዮን ሕዝብ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረ ተናግረዋል። ግብርናው 43% ድርሻውን እንደያዘና የአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ 32% ድረሻ እንደያዘ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። መንግሥት በተያዘው በጀት ዓመት ትኩረት ከሚሰጣቸው ምጣኔ ሀብታዊ ማሻሻያዎች መካከል የታክስ ገቢ ማሻሻል፣ የሀብት ብክነት መቀነስ እንዲሁም የመንግሥትን በጀት ድህነትን የሚቀንስ ዘርፍ ላይ እንደሚያተኩር ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ጠቅሰዋል። አያይዘውም በግጭት ሳቢያ ለተፈናቀሉ ሰብአዊ እርዳታ ለማድረግ እንዲሁም ማኅበራዊ አገልግሎት መስጫዎችን መልሶ ለማቋቋም ፋይናንስ በማሰባሰቡ መንግሥት እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን በመሥራ እና አሮጌ ትምህርት ቤቶች በማደስ እንዲሁም ደግሞ ለአቅመ ደካሞች ቤት በመሥራት ማኅበራዊ በጎ አገልግሎቶች 1 ሚሊዮን ዜጋ እንደተሳተፈ ገልጸዋል። በምጣኔ ሀብት ረገድ ማኅበረሰቡን እየፈተነ ያለውን የዋጋ ንረት ለማርገብ የምግብ ምርትን በማሳደግ፣ የንግድ ሰንሰለትን አዘምኖ ምርትን ወደ ገበያ በማምጣት እና አነስተኛ ገቢ ላላቸው ድጎማ በማድረግ እንደሚሠራ አክለዋል። በ2014 ዓ. ም. ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን እንደ ስኬት የጠቀሱት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ፣ ግድቡን በተያዘለት ጊዜ አጠናቆ የሚመነጨውን ኃይል ከኢትዮጵያ ባሻገር ለጎረቤት አገራትም የመሸጥ ዕቅድን በንግግራቸው አንስተዋል። መንግሥት በተያዘው የበጀት ዓመት አገሪቱን አማራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ በማድረግ እንዲሁም የተቀዛቀዘውን የቱሪዝም ዘርፍ በማነቃቃት እንደሚሠራ ጠቁመዋል። በሕዝቡ ዘንድ በፍትሕ እጦት እና መዘግየት የተፈጠረውን ቅሬታ ለመቅረፍ እንደሚሠራ እንዲሁም የአገር አቀፍ ተቋማትን አሠራር ግልጽና ቀልጣፋ ለማድረግ እንደሚሠራም ጠቅሰዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cn453yyr27eo +health ካናዳ ፋይዘር የተሰኘው ክትባት ለሕፃናት እንዲሰጥ ፈቀደች ካናዳ ፋይዘር የተሰኘውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ከ12 እስከ 15 ዓመት ላሉ ህጻናት እንዲሰጥ ፈቃድ ሰጠች። ይህ ውሳኔ የኮሮናቫይረስ ክትባት በዚህ ዕድሜ ላሉ ህጻናት እንዲሰጥ የፈቀደች የመጀመሪያዋ ሀገር አድርጓታል። የሶስተኛ ምዕራፍ ‘የክሊኒካል’ ሙከራ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ነው የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ፋይዘር የተሰኘው ክትባትከ 12 እስከ 15 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ያሉ ህጻናት እንዲከተቡ ይሁንታውን የሰጠው። “በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ላይ የተሞከረው ክትባቱ አስተማማኝና ውጤታማ ነው” ሲሉ የሚኒስቴሩ አማካሪ ገልጸዋል። ፋይዘር ቀደም ብሎ በሀገሪቱ ከ16 ዓመት በላይ ያሉ ሰዎች እንዲወስዱት ካናዳ ፈቅዳ ነበር። በሀገሪቱ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባት የአልቤርታ ግዛት ከ9 ቀናት በኃላ ከ12 እስከ 15 የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ታዳጊዎች ክትባቱን መውሰድ ይጀምራሉ። በካናዳ እስካሁን 1.2 ሚሊዮን ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የያዛቸው ሲሆን 20 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ19 ዓመት በታች ነው። የክትባት አሰጣጡ በአንጻራዊነት የዘገየ እንደሆነ በሚነገርባት ካናድ 34 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ቢያንስ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ወስዷል። https://www.bbc.com/amharic/news-57029733 +health ኮሮናቫይረስ፡ አፍሪካ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የኮቪድ ክትባት መስጠት ትጀምራለች ተባለ "የዓለም ጤና ድርጅት ሁሉም የአፍሪካ አገራት እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ ""ከፍተኛ ቅድሚያ"" ለሚሰጣቸው ሰዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት መከተብ አለባቸው አለ። ኮቫክስ 90 ሚሊዮን ክትባቶችን ወደ አፍሪካ በቅርቡ ማሰራጨት ይጀምራል ያለው የዓለም ጤና ድርጅት፣ የስርጭት መጠኑም የሚወሰነው አገራት ባላቸው የሕዝብ ብዛት መጠን መሆኑ ተመልክቷል። ለእያንዳንዱ አገር የሚከፋፈለው ክትባት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከፊት ተሰልፈው እየሰሩ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ብቻ የሚያገኙት ሳይሆን፣ ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አካላትንም ለመከተብ ያስችላል ብሏል። ሁሉም የአፍሪካ አገራት የኮቪድ-19 ክትባት እንዲያገኙ የሚሰራው ኮቫክስ የተሰኘው ጥምረት ክትባቱን መቼ እነደሚያጓጉዝ እና የትኛው አገር ምን ያህል እና መቼ ያገኛል የሚለውን ዝርዝር አውጥቶ መጨረሱ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት ሁሉም የአፍሪካ አገራት የኮሮናቫይረስ ክትባትን በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ መስጠት መጀመር አለባቸው ብሏል። በዓለም ጤና ድርጅት ከክትባት ጋር በተያያዘ የሚሰሩት ዶ/ር ሪቻርድ ሚሂንጎ ክትባቱ በሚቀጥሉት አንድና ሁለት ሳምንታት መሰጠት እንዲጀምር ""አገራት የመጀመሪያውን ደረጃ ዝግጁነት ያሟላሉ ብለን ተስፋ አእናደርጋለን"" ካሉ በኋላ በየካቲት ወር መጨረሻ ክትባቱ መሰጠት እነደሚጀምር ገልፀዋል። ይህ ኮቫክስ ለአፍሪካ አገራት የሚሰጠው 90 ሚሊዮን ክትባት የመጀመሪያው ዙር ሲሆን እስከ ፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ድረስ 600 ሚሊዮን ያህል ክትባቶች ለአፍሪካ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠብቅ ተገልጿል። ይህ ክትባት አገራት ካላቸው የሕዝብ ብዛት ውስጥ እስከ 20 በመቶ ድረስ መከተብ ያስችላቸዋል ተብሏል። በፈረንጆች 2022 እያንዳንዱ አፍሪካዊ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ያገኛል ተብሎ እቅድ መቀመጡንም ጤና ድርጅቱ አስታውቋል። ከኮቫክስ በአቻነት የአፍሪካ ሕብረት የጀመረው ጥረት መኖሩን የተናገረው የዓለም ጤና ድርጅት በእነዚህ ሁለት መን���ዶች በሚገኝ ክትባት በ2021 መጨረሻ እስከ 40 በመቶ የሚደርሱ አፍሪካውያን ክትባቱን ያገኛሉ ተብሎ ታቅዷል። ይህም በ2022፣ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑ አፍሪካውያን ክትባቱን ማግኘት ያስችላቸዋል ማለት ነው። ኮቫክስ (COVAX) ምጣኔ ኀብታቸው ደካማና መካከለኛ ለሆኑ አገራት ክትባቱን ለማቅረብ ያለመ፣ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የተመሰረተ ኢኒሼቲቭ (ጅማሮ) ነው። ሁሉም የአፍሪካ አገራት ይህንን ጅማሪ ተቀብለውታል። ይህም ማለት አፍሪካ በዚህ ጅማሮ በኩል ክትባቱ ፍቃድ ካገኘና ከፀደቀ በኋላ፣ 220 ሚሊዮን ክትባቶችን ታገኛለች። እኤአ በ2021 መጨረሻ ላይ ኮቫክስ 2 ቢሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመግዛት እቅድ ይዟል። ይህ አገራቱ የኮቪድ-19 ክትባትን ስርጭት እንዴት ለማካሄድ በሚወስኑት ውሳኔ ላይ ይመሰረታል። የዓለም ጤና ድርጅት መመሪያ የጤና ባለሙያዎች የኮሮና መካለከል ላይ ከፊት ያሉ በመሆኑ ክትባቱን ቅድሚያ ማግኘት እንዳለባቸው ያስቀምጣል። በመቀጠል ደግሞ ወደ አገራት መግቢያና መውጫ ላይ የሚሰሩ ግለሰቦች፣ በእድሜ የገፉ ሰዎችና የተለያዩ ተያያዥ የጤና ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ክትባቱን ከሌሎች ዜጎች ቀድመው ያገኛሉ ሲል አስቀምጧል። ቀሪው ሕዝብ እነዚህ ዜጎች ከተከተቡ በኋላ ይሰጠዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት በመመሪያ ላይ አመልክቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55950980 +business የአሜሪካ ሴኔት ቦይንግ አብራሪዎችን በተሳሳተ መልኩ አሰልጥኖ ነበር አለ የአሜሪካ ሴኔት መርማሪዎች የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ የ737 ማክስ አውሮፕላኖችን የሚፈትሹ አብራሪዎችን 'ተገቢ ባልሆነ መልኩ' ስልጠና እንዲያገኙ አድርጓል ሲሉ ከሰሱ። በወራት ልዩነት ሁለት አደጋዎች ማጋጠማቸውን ተከትሎ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በአውሮፓውያኑ መጋቢት 2019 ላይ እንዳያበሩ ታግደው ነበር። መርማሪዎቹ እንደሚሉት ቦይንግ እና የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር (FAA) በመመሳጠር ስለአውሮፕላኖቹ ወሳኝ መረጃዎችን ሆን ብለው ለመደበቅ ሞክረዋል። ቦይንግ በበኩሉ በምርመራው የተገኙትን መረጃዎች በሙሉ እየተመለከታቸው እንደሆነና ጉዳዩን በጥብቅ የሚያው እንደሆነ የገለጸ ሲሆን የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር በበኩሉ ምንም ስህተት አልሰራሁም ብሎ ነበር። ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲበር በነበረው ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕን የደረሰው አደጋ ከመከሰቱ በፊት የአሜሪካ አውሮፕላን አብራሪዎች ቡድን በዚህ መሰል አውሮፕላኖች የደህንነት ስጋት እንዳለ ለኩባንያው አሳውቀው እንደነበር መገለጹ ይታወሳል። ግንቦት 2019 ላይ በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከዚህ ቀደም በኢንዶኔዥያ ከደረሰው አደጋ በኋላ ኤምካስ (MCAS) ተብሎ በሚጠራው መቆጣጠሪያ ስርዓት ላይ ችግር እንደነበረበትና በአፋጣኝ እንዲፈታ አሳስበው እንደነበርም ተገልጾ ነበር። በወቅቱ ቦይንግ ግን አብራሪዎች ያነሱትን ጥያቄ ወደጎን በመተው ወደ ፊት የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌሩን ለማስተካከል ቃል መግባቱ ተገልጿል። የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር የአሜሪካ ሴኔት በመረጃ የልተደገፈ ውንጀላ እያደረገ እንደሆነ በመግለጽ በ737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ያደረገው ምርመራ በጥልቀት የተካሄደ መሆኑን አስታውቋል። ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ የአንዶኔዥያው ላየን ኤይር ንብረት የሆነው 737 ማክስ 8 ተከስክሶ በአውሮፕላኑ ተሳፍረው ነበሩት 189 ሰዎች ማለቃቸው ይታወሳል። አደጋው በተከሰተበት ወቅት የኢንዶኔዥያ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አደጋው አውሮፕላኑ ላይ በነበረ እክል ምክንያት ነው የተከሰተው ቢሉም ድርጅቱ እጄ የለበትም ማለቱ ይታወሳል። ከአምስት ወራት በኋላ ደግሞ መጋቢት 1 ቀን ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲበር የነበረው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ ለ157 ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆኗል። ትናንት አርብ ዕለት የሴኔት መርማሪ ኮሚቴው ባወጣው ሪፖርት ላይ ከድርጅቱ በሚስጥራዊ መንገድ አገኘሁት ባለው መረጃ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር እና ቦይንግ ከምርመራው ቀደም ብለው የምርመራው ውጤት እነሱ በሚፈልጉት መንገድ እንዲሆን አድርገዋል ብሏል። ይህ ሪፖርት የአሜሪካ ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ባሳለፍነው ወር ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በድጋሚ መብረር እንዲጀምሩ ከፈቀደ በኋላ መሆኑ ቦይንግን ያስደሰተው አይመስልም። በያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢ የብራዚሉ ጎል አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ በረራ እንደሚመልስ ማስታወቁ የሚታወስ ነው። የብራዚል ግዙፉ አየር መንገድ ጎል እንዳለው፤ 140 የሚሆኑ አውሮፕላን አብራሪዎቹ በአውሮፕላኑ አሜሪካ ውስጥ ሥልጠና ወስደዋል። ሰባት 737 ማክስ አውሮፕላኖቹን ለ27 የአገር ውስጥ መዳረሻዎች ማዘጋጀቱን አየር መንገዱ ገልጿል። እስካሁን 737 ማክስ ወደ በረራ እንዲመለስ የፈቀዱት አሜሪካ እና ብራዚል ናቸው። https://www.bbc.com/amharic/news-55375186 +business መርዛማ ሊድን አጋልጣ 423 ሚሊዮን ብር ያገኘችው ፊሊስ ኦሚዶ ፊሊስ ኦሚዶ ኬንያዊት የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ናት። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2009 ላይ ለምትሠራበት ድርጅት ስጋቷን ስትገልጽ፤ ይህን ጉዳይ ዳግመኛ እንዳታነሺ ተብላ ነበር። ፊሊስ ትሠራበት የነበረው ድርጅት የሚያካሂደው የባትሪ መልሶ ጥቅም ላይ (ሪሳይክሊንግ) ሂደት የሰዎችን ሕይወት ሊቀጥፍ እንደሚችል ነበር ለአሠሪዎቿ የተናገረችው። ነገር ግን ሰሚ ጆሮ አላገኘችም። በአሠሪዎቿ “ዝም በይ” ብትባልም ፊሊስ አልሰማቻቸውም። ያኔ 31 ዓመቷ ነበር። ገና ከዩኒቨርስቲ እንደተመረቀች ሞምባሳ የሚገኝ ‘ኬንያ ሜታል ሪፈረንስስ’ የሚባል ድርጅት ውስጥ ተቀጠረች። ድርጅቱ የመኪና ባትሪን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ሊድ የተሰኘውን ንጥረ ነገር ያመርታል። መርዛማ ጭስ ፊሊስ የድርጅቱ ክንውኖች አካባቢ ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ተጽዕኖ እንድታጠና ተጠይቃ ነበር። ሆኖም ግን ግኝቷን ለድርጅቱ ስታሳውቅ እርምጃ ከመውሰድ ይቆጠባሉ። ባትሪ የማቅለጥ ሂደቱ አየር ከመበከሉም በላይ ተረፈ ምርቱ የሚጣለው በድርጅቱ አቅራቢያ የሚገኘው የኦዊኖ ማኅበረሰብ መኖሪያ አካባቢ ነው። ድርጅቱ የአካባቢውን አየርም ውሀም እየበከለ ነበር። ሠራተኞቹ ላይም ጉዳት ደርሷል። • ዶናልድ ትራምፕ 'ቲክቶክ' አሜሪካ ውስጥ እንዳይሰራ ሊያግዱ ነው ከልጅነቷ ጀምሮ ተፈጥሮን የምትወደው ፊሊስ፤ 2009 ላይ ችግሩ ምን ያህል ስር የሰደደ እንደሆነ አልተረዳችም ነበር። ፊሊስ የ15 ዓመት ወጣት ሳለች እናቷ ከሞቱ በኋላ ወደ ሞምበሳ አቀናች። ዩኒቨርስቲ ስትገባ መማር የምትፈልገው የአካባቢ ጥናት ነበር። ሆኖም የቢሮ ሠራተኛ የሚያደርጋት ዘርፍን ማጥናት ግድ ሆነባት። ምንነቱ ያልታወቀው ህመም በቢሮ ሠራተኛነት የተቀጠረችበት ድርጅት እሷ ለምትወደው ነገር ደንታ አልነበረውም። ፊሊስም ቅሬታዋን ይዛ በድርጅቱ መሥራት ቀጠለች። 2010 ላይ የሁለት ኣመት ልጇ ታመመ። የተለያዩ ሕክምናዎች ቢሰጡትም፤ ህመሙ ሊታወቅለች፣ ሊያገግምም አልቻለም። የልጇ ህመም ተባብሶ ሆስፒታል አልጋ ያዘ። ያኔ አንድ ጓደኛዋ ልጇ በሊድ ተመርዞ ከሆነ እንድታስመረምረው መከረቻት። • ፌስቡክ እና ጉግል ለሚያወጡት ዜና እንዲከፍሉ ሊገደዱ ነው ምርመራ ሲደረግለት ደሙ ውስጥ ከፍተኛ የሊድ መጠን ተገኘ። ልጇ ጡት ሲጠባ ለንጥረ ነገሩ ተጋልጦ እንደሆነ ስትረዳ እጅግ ተደናገጠች። ተበሳጭታ ሥራዋን ለቀቀች። ከዛም ድርጅቱ የልጇን የሕክምና ወጪ እንዲሸፍን መጎትጎት ጀመረች። ማኅበረሰቡ ውስጥ ከሚኖሩ ልጆች ሦስቱ ምርመራ እንዲደረግላቸው ገፋፍታ ያገኘችው ውጤት ፍርሀቷን እውን ያደረገ ነበር። “ውሸትሽን ነው” ፊሊስ የምርመራ ውጤቶቹን ይዛ የመንግሥት ተቋሞች ጣልቃ እንዲገቡ ደብዳቤ መጻፍ ጀመረች። ቢሆንም ምላሽ እንዳልሰጧት ትናገራለች። “ብሔራዊ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም የማወራው ነገር ውሸት እንደሆነና ፍርድ ቤት ብሄድም ራሳቸውን ለመከላከል ዝግጁ እንደሆኑ ጻፉልኝ” ስትል ትገልጻለች። ለድርጅቱ ፍቃድ እንዲሰጥ ያደረገው ይህ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም ነው። • ከኮሮናቫይረስ በእጅጉ እያተረፉ ያሉት ትልልቅ ድርጅቶች ፊሊስ ያላት እውነተኛ መረጃ እንደሆነ ለማሳየት ከአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ድርጅት ጋር በመጣመር ተጨማሪ ምርመራዎች እንዲካሄዱ አደረገች። ማስረጃ ቢኖራትም የመንግሥት ባለሥልጣኖች ጫና ሊያሳድሩባት ሞክረዋል። “ቀስ በቀስ ነበር የምንቀሳቀሰው። ሥራችን በበጎ ፍቃድ ላይ የተመሠረተ ነበር። በኢ-ፍትሐዊ መንገድ ስታሰር ለዋስ የምከፍለው ገንዘብ እንኳን አልነበረኝም። 17 ሰዎች በዋስ እንድወጣ አደረጉ።” 2012 ላይ ሞምባሳ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ካስተባበች በኋላ፤ ግጭት ለመቀስቀስ ሞክረሻል ተብላ ለአንድ ምሽት ታስራ ነበር። ‘ፍሮንት ላይን ዲፌንደርስ’ እና ‘ኢስት አፍሪካን ሎው ሶሳይቲ’ የተባሉ የሕግ ጉዳዮች የተራድኦ ድርጅቶች ፊሊስ ክሱን እንድትከላከል የገንዘብ ድጋፍ ሰጥተዋል። ኋላ ላይ የሰልፉ አስተባባሪዎች ላይ ማስረጃ ባለመገኘቱ ክሱ ተቋረጠ። ድብደባ ፊሊስ ከ204 በፊት የነበረውን ጊዜ “በጣም ከባድ” ስትል ትገልጸዋለች። ትግሏን ለማቀረጥ የተቃበረችበት ወቅት እንደነበረም ታስታውሳለች። ከመንግሥት ባለሥለጣኖች የሚደርሳት ማስፈራሪያ ያስጨንቃት ነበር። ቤቷ በር ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ወንዶች ድብደባ ደርሶባት ለአንድ ወር ተደብቃም ነበር። “ሲደበድቡኝ ጎረቤቴ ስለደረሰ ነው የተረፍኩት። ተደብድቤ የተጣልኩበት ቦታ የመኪናው መብራት ሲበራ ልጄ እየጮኸ ነበር።” • ኮሮናቫይረስ ለምን ጥቁሮች ላይ እንደሚበረታ ሊጠና ነው የፊሊስ ቤተሰቦች ልጇ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነገር ውስጥ እንደገባች በማሰብ፤ በተፈጠረው ነገር ደስተኛ አልነበሩም። እሷ ግን የሚተማመኑባትን የማኅበረሰቡ አባላት ችላ ማለት አልፈለገችም። በተለይ 2011 ላይ ማኅበረሰቡ ውይይት አድርጎ ሲጨርስ ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ የተኮሱባቸውን ጊዜ አትዘነጋም። “አደገኛ እፅ እየፈለግን ነው በሚል ሰበብ የሰዎች ቤት ላይ ጉዳት አደረሱ። ትንሽ ገቢ ያላቸው ድሆች አሉ። የነሱን ቤት ከሚጎዱ እኔን ቢያስሩኝ ይሻለኝ ነበር።” ካሳ ፊሊስን መሰናክሎቹ አላስቋሟትም። ማኅበረሰቡን ለመታደግ ለዓሥር ዓመታት ያለመታከት ፍድድ ቤት ቆማ ታግላለች። በስተመጨረሻም ድል ቀንቶት፤ ፍርድ ቤቱ 12 ሚሊዮን ዶላር (423 ሚሊዮን ዶላር ገደማ) ካሳ አግኝታለች። ካሳውን የሚከፍሉት አካባቢ ያለ እየደረሰ የነበረውን ጉዳት ችላ ያሉ የመንግሥት ተቋሞች እና የመኪና ባትሪ መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውለው ድርጅት ነው። ፍርድ ቤቱ አካባቢው በአራት ወር ውስጥ እንዲጸዳም ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔው ካልተተገበተ ሌላ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። “ገንዘቡ 3000 የሚሆኑት የማኅበረሰቡ አባለት ያዩትን ስቃይ አይተካም። ሆኖም ግን ገንዘቡ ለሕምናና መድኃኒት መግዣ ይውላል” ብላለች። ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት የተበየኑ የካሳ ክፍያዎች በአፋጣኝ ተጎጂዎች እጅ እንዳልገቡ ስለምታውቅ፤ ፊልሰን ትግሉ እንዳልተቋጨ ትናገራለች። እስከ መስከረም አጋማሽ የካሳ ገንዘቡ እጃቸው ካልገባ ዝም እንደማትልም ታስረግጣለች። https://www.bbc.com/amharic/news-53620643 +politics የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ለአምስተኛ ጊዜ የሚወዳደሩበት ምርጫ ድምፅ መስጠት ተጀመረ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ለአምስተኛ ጊዜ የሚወዳደሩበት ምርጫ ዛሬ ድምፅ መስጠት ተጀምሯል፡፡ ከአረብ ሊግ የተወከሉ የምርጫው ታዛቢ ሁሉም ነገር በሰላም እየተካሄደ ነው ሲሉ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ ከ 200 ሺህ በላይ ድምፅ ሰጪዎች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ምርጫ ምሽት ላይ ይዘጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፕሬዚዳንት ጉሌህ ለ 22 አመታት አገሪቷን አስተዳድረዋል፡፡ የበቢሲው ዘጋቢ መሃመድ አብዲራሂም እንዳለው ዋና ዋና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ምርጫው የማስመሰል ምርጫ ነው በሚል ጥለው ወጥተዋል፡፡ ብቸኛ ተፎካካሪያቸው ዘካሪያ ኢስማኤል እምብዛም የማይታወቁ ነጋዴ ሲሆኑ ከዚህ ቀደም በመከላከያ ሰራወት ውስጥ አባልም ነበሩ፡ ተፎካካሪያቸው የፅዳት እቃዎችን ከውጪ አገራት የሚያስገቡ ሲሆን ባለፈው ጥር ለምርጫ እንደሚወዳደሩ ይፋ እስከሚያደርጉ ድረስ በሕዝቡ ዘንድ የሚያውቃቸው አልነበረም፡፡ የ 57 አመት ጎልማሳው ለጉሌህ ስጋት እንደማይሀኑ እና ፕሬዘዳንት ጉሌህ ምርጫውን እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል፡፡ በስትራቴጂያዊ አቀማመጧ ለቀጠናው ቁልፍ ከሚባሉ አገራት መካከል የሆነችው ትንሿ አገር ጂቡቲ ከአንድ ሚሊዮን የሚያንስ ህዝብ ያላት ሲሆን አሜሪካ እና ቻይናን ጨምሮ የሃያላን አገራት የወታደራዊ መቀመጫ መሆኗ ይታወቃል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-56686721 +health የዓለም ጤና ድርጅት አውሮፓን በድጋሚ የወረርሽኙ ማዕከል ናት ሲል አስጠነቀቀ "በአውሮፓ እየተባባሰ በመጣው ስርጭት ምክንያት አህጉሪቱ በድጋሚ የኮቪድ ወረርሽኝ ""ማዕከል"" ሆናለች ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ኃላፊ ሃንስ ክሉጅ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንዳሉት አህጉሪቱ በየካቲት ወር ግማሽ ሚሊዮን ተጨማሪ ሞት ልታስመዘግብ ትችላለች። ለስርጭቱ መጨመር በበቂ ሁኔታ ክትባት አለመሰጠቱን በማንሳት ትችቱን ሰንዝሯል። ""ለኮቪድ-19 መስፋፋት ምላሽ ከመስጠት ቀድሞውኑ እንዳይከሰት ወደሚያግዙ ስልቶች መለወጥ አለብን"" ብለዋል። ከቅርብ ወራት ወዲህ በመላው አህጉሪቱ ክትባቱን የመስጠት ምጣኔው ቀንሷል። በስፔን ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ሁለቱን ዙር ክትባት ወስደዋል። ይህ ቁጥር በፈረንሳይ እና በጀርመን ዝቅተኛ በሚባል ደረጃ፣ 68 በመቶ እና 66 በመቶ ላይ ይገኛል። የአንዳንድ የመካከለኛው እና የምስራቅ አውሮፓ ሃገሮች አሃዝ ደግሞ ከዚህም ዝቅተኛ ነው። እአአ ጥቅምት 2021 ሙሉ ለሙሉ ክትባቱን የወሰዱ ሩሲያውያን 32 በመቶ ብቻ ናቸው። ክሉጅ የማዕከላዊ እስያ ክፍልን ጨምሮ 53 ሃገሮችን በሚሸፍነው የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ዞን የህዝብ ጤና እርምጃዎችን መላላትን ለበሽታው መባባስ እንደተጨማሪ ምክንያት አንስተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በአካባቢው እስካሁን 1.4 ሚሊዮን ሰዎች መሞታቸውን መዝግቧል። የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ቴክኒካል ኃላፊ ማሪያ ቫን ኬርክሆቭ ምንም እንኳን ""በቂ የክትባት እና የመሳሪያ አቅርቦት"" ቢኖርም ወረርሽኙ ባለፉት አራት ሳምንታት በመላው አውሮፓ ከ 55 በመቶ በላይ ከፍ ብሏል ብለዋል። ባልደረባቸው ዶክተር ማይክ ሪያን የአውሮፓ ተሞክሮ ""ለዓለም የማስጠንቀቂያ ደወል ነው"" ሲሉ ገልጸውታል። በጀርመን ስርጭቱ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ወደ 34000 የሚጠጉ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ተመዝግበዋል። በጀርመን ያለው የኮቪድ ስርጭት በዕለት ከ 37000 የሚበልጡ ሰዎች በቫይረሱ ከሚያዙባት የዩኬ የቅርብ ጊዜ ቁጥሮች በታች ነው። የህብረተሰብ ጤና ባለሥልጣናት ግን አራተኛው ማዕበል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሞት ሊያስከትል እና በጤና ስርዓቱ ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 165 ሰዎች መሞታቸው የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከአንድ ሳምንት በፊት ከነበረው 126 ሞት ጨማሪ አሳይቷል። የጀርመን አርኬአይ ኢንስቲትዩቱ ሎተር ዊለር ስለ አስፈሪ ቁጥሮች ተናግረዋል። ""አሁን የመከላከያ እርምጃዎችን ካልወሰድን አራተኛው ማዕበል የበለጠ አደጋ ያመጣል"" ብለዋል። ክትባቱን ካልወሰዱት ጀርመናውያን መካከል ከ60 በላይ ዕድሜ ያላቸው ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሲሆን እነዚሀም ለበለጠ አደጋ የተጋለጡ ናቸው። ሃንስ ክሉጅ እንደሚሉት የቫይረሱ መጨመር በጀርመን ብቻ የተገደበ አይደለም። ባለፈው ሳምንት የሟቾች ቁጥር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው በሩሲያ ሲሆን ከ 8,100 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። በዩክሬን ደግሞ 3800 ሰዎች ሞተዋል። ሁለቱም ሀገራት በጣም ዝቅተኛ ክትባት የሰጡ ሲሆን ዩክሬን ባለፉት 24 ሰዓታት 27377 አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አስመዝግባለች። ሮማኒያ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ የሆነውን የ591 ሰዎችን ሞት አስመዝግባለች። በሃንጋሪ በየዕለቱ በኮቪድ የሚያዙ ሰዎች ከእጥፍ በላይ አድጎ ባለፈው ሳምንት 6268 ደርሷል። ጭንብል መልበስ አስገዳጅ የሆነው በሕዝብ ማመላለሻዎች እና በሆስፒታሎች ብቻ ነው። ዶክተር ሪያን ""በአሁን ተጨማሪ ጥቂት ሰዎችን ከከተብን ወረርሽኙ አብቅቷል የሚል ሃሳብ ላይ ነን። ጉዳዩ እንደዚያ አይደለም"" ብለው ሃገራት ቀዳዳቸውን እንዲደፍኑ ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል። የደች መንግሥት ጭንብል መልበስ እና አካላዊ መራራቅን ህዝብ በሚሰባሰብበት ቦታዎች ላይ እንደሚጀምር በዚህ ሳምንት ተናግሯል። ምክንያቱ ያለው ደግሞ በሳምንት ውስጥ የሆስፒታል አልጋዎች የመያዝ ምጣኔ በ 31 በመቶ ከፍ በማለቱ ነው ። የኮቪድ ስርጭት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ላትቪያ ከሰኞ ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥታለች። ክሮሺያ ሐሙስ ዕለት 6310 አዳዲስ በቫእረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባለች። ይህ ቁጥር እስካሁን ድረስ ከታየው ከፍተኛው ቁጥር ነው። ስሎቫኪያ ሁለተኛውን ከፍተኛ ቁጥር መዝግባለች። የቼክ ስርጭት በፀደይ ወቅት ወደ ነበረበት ደረጃ ተመልሷል። የእንግሊዝ ምክትል ዋና የህክምና መኮንን ፕሮፌሰር ጆናታን ቫን ታም በበኩላቸው በጣም ብዙ ሰዎች ወረርሽኙ እንዳበቃ ያምናሉ ብለዋል። ከፍተኛ የክትባት መጠን በደረሰባቸው ሃገሮች የስርጭት መጠኑ አሁንም በአንጻራዊነት ሁኔታ ዝቅተኛ ነው። ጣሊያን ከ12 አመት በላይ ለሆኑት ዜጎቿ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ክትባት ብትሰጥም ባለፈው ሳምንት ውስጥ አዳዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በ16.6 በመቶ ጨምሯል። ከመስከረም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፖርቹጋል የስርጭት መጠን ከ 1000 በላይ ሆኗል። ረቡዕ 2287 ሰዎች በቫይረሱ የታዩዛበት ስፔን የስርጭት መጨመር ካላዩት ጥቂት ሃገሮች አንዷ ሆናለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-59165910 +politics በሶማሌ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አባላት መካከል የተከሰተው ምንድን ነው? "የሶማሌ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የቀድሞ አባላት ነን ያሉ አካላት የክልሉን ብልጽግና ፓርቲ 'ለማረም እና ለማስተካከል' በሚል እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ይናገራሉ። እነዚህ ጅግጅጋ ላይ የተሰባሰቡ የፓርቲው የቀድሞ አመራሮች በቁጥር ከ10 በላይ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የአገሪቱ ከተሞችም ሌሎች የፓርቲው የቀድሞ አባላትና አመራሮች አብረዋቸው መኖራቸውን ገልፀዋል። ቡድኑ እንቅስቃሴውን 'የክልሉን ሕዝብ ለማዳን' በሚል መጀመሩን ጨምረው ተናግርዋል። የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኑኬሽን ኃላፊ የነበሩት እና አሁን የተቃዋሚው ቡድኑ ውስጥ እየተሳተፉ የሚገኙት አቶ ሐቢብ ሐጂ መሐሙድ ለቢቢሲ ሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት፣ 'የብልጽግና ፓርቲ መስመሩን ስቷል' ሲሉ ተናግረዋል። እንደ አቶ ሐቢብ ገለጻ አሁን ያለውን የብልጽግና አመራር በመቃወም የተሰባሰቡት አካላት ከዚህ ቀደም የቢሮ ኃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባላት የነበሩ እና ክልሉን ከ15 እስከ 20 ዓመት በተለያዩ የፖለቲካ ዘርፎች ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸው። የክልሉ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር መሐመድ ሻሌ በበኩላቸው እነዚህ ተሰባስበው ተቃውሟቸውን እያሰሙ ያሉ አካላት ""ከድርጅቱ አባልነት የተባረሩና ከኃላፊነታቸው የተነሱ ግለሰቦች ናቸው"" ሲሉ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። ""ከኃላፊነታቸው የተባረሩ እና ያኮረፉ ግለሰቦች ስብሰብ ነው"" ሲሉ የተናገሩት የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ በፓርቲው ውስጥ ያለውን ስህተት ለማስተካከል እንደ ድርጅት ዝግጅት ላይ ነን ሲሉ አክለዋል። ኢንጂነር መሐመድ አክለውም በማኅበራዊ ሚዲያዎች የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ተከፋፍሏል በሚል የሚናፈሰው መረጃ ""ስህተት እና ተቀባይነት የሌለው"" መሆኑን ጨምረው ያስረዳሉ። አቶ ሐቢብ በበኩላቸው ተቃውሞ እያሰሙ ያሉት የተባረሩ የብልጽግና የቀድሞ አባላት ናቸው የሚለው የጽህፈት ቤት ኃላፊውን ምላሽ ""ሐሰት"" ሲሉ አጣጥለውታል። አቶ ሐቢብ አክለውም በፓርቲው ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲሁም በሁሉም ደረጃ ሙስና መኖሩንም ይናገራሉ። አክለውም የክልሉ መንግሥት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን አስሯል በሚል ተጨማሪ ክስ ያቀርባሉ። አቶ መሐመድ በበኩላቸው ፓርቲው በቅርቡ ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚያካሄድ እና አስፈላጊውን ማስተካከያ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። አቶ መሐመድ ሻሌ የተቃዋሚ አባላት ታስረዋል የሚለውን ክስ ውድቅ አድርገዋል። በገዢው ፓርቲ ውስጥ አሉ ያሏቸውን ችግሮች አንስተው ተቃውሞ እያሰሙ ያሉት ግለሰቦች በፓርቲው ውስጥ ያሉ ጉዳዮችን ከማንሳታቸው ባሻገር ሌሎችም ነገሮችን ጠቅሰዋል። በዚህም በድርቅ የተጎዳው የክልሉ ሕዝብ በቂ ድጋፍ እየተደረገለት አይደለም የሚሉት አቶ ሐቢብ፣ የኑሮ ውድነት በሕዝብ ላይ እያስከተለ ስላለው ጫና፣ በክልሉ ስላለው የወጣቶች ሥራ አጥነት ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል እንደሚገኙበት ይናገራሉ። በአጠቃላይ ሕዝቡ 'የወደፊት ራዕዩ' የጨለመ አካሄድ በክልሉ ሰፍኗል ሲሉ የሚናገሩት አቶ ሐቢብ፣ በስልጣን ላይ ያሉት የፓርቲው አባላት በቂ ልምድ እና እውቀት የላቸውም ሲሉ ይተቻሉ። የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር መሐመድ ሻሌ ግን ከፓርቲው እራሳቸውን የነጠሉት ግለሰቦች ያቀረቧቸው ክሶች ተቀባይነት የሌላቸውና ክልሉ ለተጠቀሱትን ችግሮች መፍትሔ ለማበጀት ፓርቲውና የክልሉ መስተዳደር የሚጠበቅባቸውን እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60333655 +politics የኡጋንዳ ምርጫ 2021፡ ኡጋንዳ በምርጫው ዋዜማ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ አደረገች "በዛሬው ዕለት ምርጫ በምታካሂደው ኡጋንዳ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ከዋዜማው ጀምሮ እንዲቋረጥ መደረጉ ተገልጿል። የኢንተርኔትን ሁኔታ በበላይነት የሚቆጣጠር ኔት ብሎክስ የተሰኘው ቡድን በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው ከትናንትና ምሽት አንድ ሰዓት ጀምሮ በመላው አገሪቱ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠ ነው። ይህ የባለስልጣናቱ ኢንተርኔት የማቋረጥ ውሳኔም በቅርቡ የትኛውም የትኛውም አይነት ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲዘጉ የተላለፈውንም ይከተላል። ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኑ እንዳሉት ፌስቡክ የፓርቲያቸውን ደጋፊዎች አካውንት እንዲታገድ በማድረጉ ይህ ውሳኔ እንደተላለፈ አስታውቀዋል። በአፍሪካ ውስጥ ለረዥም ዘመናት ስልጣን ከተቆጣጠሩ�� አንዱ በሆኑት ዩዌሪ ሙሴቪኒና በታዋቂው ሙዚቀኛ ቦቢ ዋይን መካከል ከፍተኛ ፉክክር እንደሚጠበቅም እየተነገረ ነው። ሙዚቀኛውና ለእጬ ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደረው ቦቢ ዋይን በበኩሉ የኢንተርኔት መቋረጥ ምርጫውን የማጭበርበር አካልም እንደሆነ በትዊተር ገፁ አስፍሯል። ""የኡጋንዳ ህዝብ በከፍተኛ ፅናትና ውሳኔ ላይ ነው። ይህንን ጨቋኝ መንግሥትም ከስልጣን ለማውረድ የሚያግደው ኃይል አይኖርም"" በማለትም አስፍሯል። የምርጫ ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር መሰረት ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ የሚከፈቱ ሲሆን ውጤቱም እስከ ቅዳሜ ድረስ ይፋ እንደማይሆንም ተገልጿል። አገሪቱ ዘንድሮ ልታካሂደው ያሰበችው ምርጫ ከፍተኛ ሁከቶችን አስተናግዷል። በተለይም በምርጫው ቅስቀሳ ወቅት በተነሱ አመፆችና ሁከቶች የበርካታ ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል። ለ35 አመታት በስልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ ለስድስተኛ ጊዜም አገሪቷን ለማስተዳደር ይወዳደራሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-55657685 +health በአሜሪካ የኮቪድ ክትባት ያልተከተበው ግለሰብ የልብ ንቅለ ተከላ ተሰረዘ "በአሜሪካ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ታካሚው የኮቪድ-19 ክትባት ባለመውሰዱ የልብ ንቅለ ተከላውን ሰረዘ። ዲጄ ፈርጉሰን የተሰኘው የ31 ዓመት ታካሚ አንገብጋቢ የሆነ የልብ ንቅለ ተከላ የሚያስፈልገው ቢሆንም በቦስተን የሚገኘው ሆስፒታል ግን ግለሰቡን ከታካሚዎች ዝርዝር ውስጥ አስወጥቶታል። የብሪንግሃም እና የሴቶች ሆስፒታል የልብ ንቅለ ተከላውን የሰረዘው ታካሚው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ባለመውሰዱ ነው። የታካሚው ወላጅ አባት ዴቪክ፤ የኮቪድ ክትባት ከልጃቸው መሠረታዊ መርሆች ጋር የሚቃረን መሆኑን በመግለጽ ልጃቸው በክትባት እንደማያምን ገልጸዋል። ሆስፒታሉ በበኩሉ ንቅለ ተከላውን የሰረዝኩት መመሪያ በመከተል ነው ብሏል። ""በውስጥ አካላት ጉዳት ምክንያት በንቅለ ተከላ አዲስ የውስጥ አካል የተቀበለ ታካሚ በሕይወት የመትረፍ እድሉ ከፍተኛ እንዲሆን የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን"" ሲል የብሪግሃም እና የሴቶች ሆስፒታል ለቢቢሲ ገልጿል። የሆስፒታሉ ቃል አቀባይ ሆስፒታላቸው የታካሚዎችን በሽታ የመከላከል አቅም ከግምት በማስገባት ንቅለ ተከላው የመሳካት እድሉን እና ታካሚዎች ከቀዶ ጥገናው በኋላ የመትረፍ እድላቸው ከፍ ለማድረግ ከንቅለ ተከላ በፊት የኮቪድ-19 ክትባት እና የአኗኗር ዘይቤዎችን እንደሚመለከቱ ገልጸዋል። በሆስፒታሉ የአካል ክፍሎችን ለመተካት በተጠባባቂ መዝገብ ውስጥ ከሚገኙት 100,000 ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በአምስት ዓአመት ጊዜ ውስጥ የውስጥ አካል እንደማያገኙ እና የአካል ክፍሎች እጥረት ከፍተኛ መሆኑንም ገልጿል። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ፈርጉሰን ባጋጠመው የልብ ሕመም ምክንያት ላለፉት አራት ወራት ሆስፒታል ተኝቶ በመታከም ላይ ይገኛል። ለግለሰቡ ገንዘብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው የጎ ፈንድ ሚ አካውንት ላይ አዘጋጆቹ እንደገለጹት ፈርጉሰን ክትባቱን ከወሰደ በልቡ ላይ ተጨማሪ ሕመሞች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ሰግተዋል። የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ኤጄንሲ ሲዲሲ በበኩሉ የንቅለ ተከላ ተቀባዮች እና በአቅራቢያቸው ያሉ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንዲከተቡ እንዲሁም ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባት እንዲወስዱ ያበረታታል። ዶ/ር አርተር ካፕላን በኒዩ ግሮስማን የሕክምና ትምህርት ቤት የሕክምና ሥነ ምግባር ኃላፊ ናቸው። ለሲቢኤስ ኒውስ እንደተናገሩት፤ ማንኛውም የሰውነት አካል ከተቀየረ በኋላ የታካሚው በሽታ የመከላከል ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ይዘጋል። በተጨማሪም በተራ ጉንፋን እንኳን ለሞት ሊዳርግ ይችላል። ""የውስጥ አካል ክፍሎቹ በጣም አነስተኛ ቁጥር ስላላቸው አናሳ የመዳን እድል ላለው ሰው ላለመስጠት እንሞክራለን። ሌሎች ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች ከንቅለ ተከላው በኋላ የመዳን እድላቸው ከፍተኛ ነው"" ሲሉ ተናግረዋል። ወላጅ አባቱም ልጃቸው በራሱ ሰውነት ላይ የመወሰን መብት እንዳለው እና ሕመሙንም በጀግንነት እየታገለ እንደሆነ ተናግረዋል። በዚህ አስቸጋሪ ግዜ ውስጥ ባሳየው ቁርጠኝነትም ለልጃቸው ያላቸው ክብር መጨመሩን ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60136750 +business ኮሮናቫይረስ ፡ አርጀንቲና በኮቪድ-19 ሰበብ ባለሀብቶች ላይ አዲስ ግብር ጣለች "አርጀንቲና ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ሕክምና የሚያስፈልጉ የሕክምና አቅርቦቶችን ለማሟላትና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችላትን ወጪ ለመሸፈን ሀብታም ዜጓቿ ላይ አዲስ ግብር ጣለች። ይህ አንድ ጊዜ የሚከፈለውና ""የሚሊየነሮች ግብር"" የተባለውን ታክስ ለመጣል የወጣው ረቂቅ ለአርጀንቲና ምክር ቤት አባላት ቀርቦ 26 እንደራሴዎች ቢቃወሙትም የ42ቱን ድጋፍ በማግኘቱ ጸድቋል። ይህ ግብር ይመለከታቸዋል የተባሉት የአርጀንቲና ባለጸጋዎች ሀብታቸው ከ25 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሲሆን ብዛታቸውም 12 ሺህ እንደሚሆኑ ታውቋል። አርጀንቲና እስካሁን 1.5 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያረጋገጠች ሲሆን 40 ሺህ የሚደርሱት ደግሞ በበሽታው ሳቢያ ለሞት ተዳርገውባታል። አርጀንቲና በወረርሽኙ ክፉኛ ከተመቱ የዓለም አገራት መካከል አንዷ ስትሆን ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህሙማን በማስመዝገብ አምስተኛዋ አገር ሆናለች። አገሪቱ ያላት አጠቃላይ ሕዝብ 45 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን ከቁጥር አንጻር በበሽታው የተያዙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከተገኙባቸው አገራት መካከል ትንሽ የሕዝብ ቁጥር ያላት አገር ሆናለች። ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ የምትገኘው አርጀንቲና የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት በሚል የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ በሥራ አጥነት፣ በድህነትና በመንግሥት ዕዳ ላይ ተጨማሪ ጫናን ፈጥሯል።. በአገሪቱ ባለሀብቶች ላይ የተጣለው አዲሱ ግብር ከአጠቃላዩ ግብር ከፋይ 0.8 በመቶውን ብቻ የሚመለከት መሆኑን የግብሩን ደንብ ካረቀቁት ሰዎች መካከል አንዱ ተናግረዋል። ግብሩን ይከፍላሉ ተብለው የሚጠበቁት ሚሊየነሮች በአገር ውስጥ ካላቸው ሀብት እየጨመረ በሚሄድ ሁኔታ አስከ 3.5 በመቶ እንዲሁም በውጪ አገር ካላቸው ሀብት ደግሞ 5.25 በመቶ እንደሚሆን ተገልጿል። የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ እንደዘገበው፤ በአዲሱ ግብር አማካይነት ከሚሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ 20 በመቶው ለሕክምና አቅርቦቶች፣ 20 በመቶው ለአነስተኛና መካከለኛ የንግድ ተቋማት ድጋፍ፣ 20 በመቶው ለተማሪዎች የነጻ ትምርት ዕድል ድጋፍ፣ 15 በመቶው ለማኅበራዊ ልማትና ቀሪው 25 በመቶው ደግሞ ለተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ሥራ ይውላል። በአዲሱ ታክስ አማካይነት በፕሬዝዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ የሚመራው የአርጀንቲና መንግሥት 300 የአርጀንቲና ፔሶ ወይም ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ነገር ግን ተቃዋሚዎች አዲሱ ግብር እንደተባለው የአንድ ጊዜ ብቻ ላይሆን እንደሚችልና የውጭ መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾችን ሊያሸሽ ይችላል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል። አንደኛው ተቃዋሚ ፓርቲ አዲሱን ሕግ ሀብት ""የመውረስ"" ድርጊት ሲል ተቃውሞታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55200359 +politics ተጨማሪ ሁለት ፓርቲዎች በሶማሌ ክልል ከሚደረገው ምርጫ እራሳቸውን አገለሉ "በ6ኛው አገራዊ ምርጫ በሶማሌ ክልል ተሳታፊ የነበሩ ሁለት ተጨማሪ ፓርቲዎች እራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን አስታወቁ። በሶማሌ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤት እጩዎችን አቅርበው የነበሩት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) እና የነፃነትና የእኩልነት ፓርቲ (ነዕፓ) ከመጪው ምርጫ እራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል። ከሁለቱ ፓርቲዎች በተጨማሪ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) መስከረም 20 ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ እንደማይሳተፍ ማስታወቁ ይታወሳል። ኦብነግ በምርጫው አልሳተፍም ያለው፤ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባና ሌሎች ችግሮችን በተመለከተ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ መፍትሄ ባለማግኘቱ እንደሆነ፣ የኦብነግ የአዲስ አበባ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ አብዱላሂ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ኢዜማ እና ነዕፓ በተመሳሳይ በሶማሌ ክልል በተካሄደው የመራጮች ምዝገባ ሂደት እንዲሁም ከአጠቃላይ የምርጫ ሕግ እና ሥርዓት ጋር በተያያዘ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረብናቸው ቅሬታዎች ሊፈቱ ባለመቻላቸው እራሳችንን ከምርጫው አግልለናል ብለዋል። ሁለቱ ፓርቲዎች፤ ከዚህ በፊት ተሰርቆ የነበረው የምርጫ ቁሳቁስ በአዲስ እንዲተካ የጠየቅን ቢሆንም አሁን ግን ቀድሞ ተዘርፎ በነበረው ካርድ ወደ ምርጫ በመገባቱ ምርጫው ተዓማኒነት አይኖረውም"" ብለዋል በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ። ከዚህ በተጨማሪም ፓርቲዎቹ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መዋቅር ከመንግሥት መዋቅር ጋር የተዋሀደ በመሆኑ የምርጫውን ፍትሀዊነት እና ተዓማኒነት ያሳጣል የሚሉ እና ሌሎች ምክንያቶችን በመዘርዘር ከምርጫው እራሳቸውን ማግለላቸውን ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ መስከረም 20 የሚካሄደውን ምርጫ በተመለከተ ትናንት ለጋዜጠኞች ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ምርጫ ባልተደረገበት የሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ በነበረበት ወቅት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ለቦርዱ አቤቱታ ቀርቦ እንደነበር ቦርዱ አስታውሷል። ይህን ተከትሎም በክልሉ በሰባት ምርጫ ክልሎች በድጋሚ የመራጮች ምዝገባ ተከናውኗል ብሏል ቦርዱ። የመራጮች ምዝገባ የተካሄደውም ቦርዱ ባሰማራው አጣሪ ቡድን ውሳኔ ላይ መስረት በማድረግ መሆኑም ተገልጿል። መስከረም 20 2014 ዓ.ም. በሶማሌ፣ በሐረሪ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ምርጫ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዚሁ ዕለትም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የመሆን ሕዝበ ውሳኔ ይካሄዳል። በዚህ ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ ድምጽ ለመስጠት 7.6 ሚሊዮን ሕዝብ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቋል። በፀጥታ ችግር፣ በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ በታዩ ግድፈቶች፣ በመራጮች ምዝገባ ላይ የቀረቡ አቤቱታዎችን ለማጣራት ጊዜ በማስፈለጉ የድምፅ መስጫው ቀን በአንዳንድ ክልሎች የምርጫ ክልሎች እንዲራዘም መወሰኑ ይታወቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58640081 +politics የትግራይ ኃይሎች አላማጣና ኮረምን መቆጣጠራቸው ተነገረ "የትግራይ ኃይሎች በደቡባዊ ትግራይ የምትገኘውን ኮረም ከተማን መቆጣጠራቸው ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ። ክልሉ ከጦርነቱ በፊት የነበረ ግዛቶችን በሙሉ ለማስመለስ እየተካሄደ ነው የተባለውም ጦርነት ወደ ደቡብ ክፍል መቀጠሉንም ሮይተርስ በዘገባው አስነብቧል። ሮይተርስ የህወሓት ቃለ አቀባይ ጌታቸው ረዳን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የትግራይ ኃይሎች ከመቀለ በስተደቡብ በኩል 170 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ኮረም ከተማ መቆጣጠራቸውን ነው። ሰኞ ዕለት አመሻሽ ላይ የወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በደቡባዊ ትግራይ ዋነኛዋ ከተማ የሆነችውና ከኮረም 20 ኪሎሜትር ርቀት የምትገኘውን አላማጣንም መቆጣጠራቸው እየተነገረ ነው። ሁለት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአላማጣ ነዋሪዎች የትግራይ ኃይሎች ከትናንት ምሽት አምስት ሰዓት ጀምሮ የአላማጣ ���ተማን መቆጣጠራቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። የዓይን እማኞቹ እንደሚሉት ከከተማ ወጣ ብሎ በሶስት የገጠር መንደሮችም ከፍተኛ የሆነ ውጊያ መስማታቸውን አስረድተዋል። ከአይን እማኞቹ በተጨማሪ የትግራይ ኃይል ተዋጊዎችም ኮረምና አላማጣ ከተሞችን እንደተቆጣጠሩ ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት በአላማጣ ከተማ የስልክ አገልግሎት የሚሰራ ሲሆን፤ በከተማዋም መረጋጋት እየታየ እንደሆነና በርካታዎችም በጎዳናዎች ወጥተው ደስታቸውን እየገለፁ እንደሆነ አኚሁ እማኞቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መንግሥት እነዚህ ከተሞች በትግራይ ኃይሎች ስር ቁጥጥር ስለመሆናቸው የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ከሮይተርስ የኮረም ከተማ በማን ቁጥጥር ስር ነው ያለችው ተብሎ የቀረበላቸውን ጥያቄ ቀጥታ ባይመልሱም ""የተኩስ አቁም አውጀናል"" የሚል የጽሁፍ መልዕከት ልከዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮቹን ከመቀለ እንዳስወጣና የተናጠል ተኩስ አቁም እንዳወጀ ይታወሳል። በወቅቱም ህወሓት የተኩስ አቁሙን ""ቀልድ ነው"" ብሎ ነበር። ሮይተርስ የኮረምን በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋል በግል ባያረጋግጥም በአዲስ አበባ የሚገኙና የኮረም የቀድሞ ነዋሪ ከሆኑ ሰው ውጊያ እንደነበር ሰምቷል። በአሁኑ ወቅት ኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ቢቋረጥም የእኚህ የቀድሞ ነዋሪ የቤተሰብ አባል የሆኑ ግለሰብ ውጊያውን ሸሽተው ስልክ ወዳለበት ቦታ ደርሰው ነግረውኛል ብለዋል። በትግራይ ክልል ጦርነቱ የተነሳው በማዕከላዊ መንግሥትና በክልሉ አስተዳዳሪ ህወሓት መካከል ከስምንት ወራት በፊት ነበር። የማዕከላዊ መንግሥቱ ከሦስት ሳምንታት በኋላ መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ድል መቀዳጀቱን በማወጅ ውጊያው ቆሟል ብሎ ነበር። ህወሓት በበኩሉ ውጊያውን እንደቀጠለ በተደጋጋሚ ሲናገር ነበር። ህወሓት የክልሉን መዲናን ጨምሮ በርካታ የክልሉ ግዛቶችን ቢቆጣጠርም በምዕራብና በደቡብ በኩል ያሉ ግዛቶች በአማራ ክልል ኃይሎች በመያዛቸው ጦርነቱ መፋፋሙ እየተነገረ ነው። ህወሃትና የአማራ ክልል ከሰሞኑ ምን አሉ? የህወሓት ቃለ አቀባይ ጌታቸው እንደሚናገሩት የትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት የነበራት ወሰን እንዲከበርና ሰዎችና ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ የትራንስፖርት መንገዶች ክፍት እንዲሆኑ በማለት መናገራቸውን ሮይተርስ አስነብቧል። ከሰሞኑ ህወሓት ምዕራብ ትግራይ የሚላቸውን ግዛቶች በተመለከተ የአማራ ክልል ቀደም ሲል የተወሰዱብኝ አካባቢዎች ናቸው በማለት የሚነሳው ጥያቄ ተቀባይነት የሌላቸውና የአማራ አካባቢዎች ናቸው የሚል ምላሽ ተሰጥቷል። የአማራ ብልጽግና ጽ/ቤት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ ""ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሰቲት ሁመራ፣ ጠለምትና ራያ በራሳቸው መስዋዕትነት ነፃነታቸውን ያስከበሩ የአማራ አካባቢዎች መሆናቸውን በድጋሚ እናሳውቃችኋለን"" በማለት አስፍሯል። ህወሓት በበኩሉ የትግራይ መንግሥት በሚል ባወጣው መግለጫ ""በትግራይ መሬት እና የትግራይ ክልል ያሉ የአማራ ልዩ ኃይል ይሁኑ ሚሊሻዎችና ታጣቂዎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ ከትግራይ ለቀው እንዲወጡ"" ብሏል። ይህ ካልሆነ ግን አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድም ገልጿል። የአማራ ክልል መንግሥት ""የአማራን ሕዝብ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ደም ለማቃባት በሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሕዝቡን እያነሳሳሱ ይገኛሉ። የአማራ ሚሊሻዎችንም ወደ ትግራይ መሬት እያስጠጉ ነው"" ብሏል። የአማራ ክልል በበኩሉ ""ለህልውና የማስከበር ዘመቻ"" በሚልም የክልሉ የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ በከፈታቸው የባንክ ሂሳብ ቁጥሮችም ነዋሪዎች የተቻላቸውን እንዲረዱ ጥሪ ቀርቧል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር በትናንትናው ዕለት ""የህልውና ዘመቻ"" ብለው የጠሩትን እንዲደግፉ ለሕዝቡ ጥሪ አቅርበዋል። ""ኢትዮጵያውያንና የአማራ ተወላጆች በአሁኑ ጊዜ ህወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ ግልፅ ጦርነት አውጆብን የህልውና ትግል በማካሄድ ላይ እንገኛለን ይህንን ዘመቻ በቻላችሁት ሁሉ እንድትደግፉ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ"" በማለት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። አሜሪካ የውጊያው መቀጠል ያሳደረባት ስጋት የአሜሪካ መንግሥት በውጭ ጉዳይ ቃለ አቀባዩ ኔድ ፕራይስ በኩል በሰጠው መግለጫ በምዕራብ ትግራይ የቀጠለው ውጊያ ሪፖርቶች ስጋት እንዳጫሩባቸው ገልጸዋል። የውጊያዎች መቀጠል በክልሉ ያሉ በረሃብ የተጎዱ ነዋሪዎችን ለመድረስ የሚደረገውን የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያደናቅፈውም ቃለ አቀባዩ ተናግረዋል። ቃለ አቀባዩ የትግራይ መከላከያ ኃይል፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይልና የአማራ ልዩ ኃይል ለንፁሃኑ ሕዝብ ጥቅምና የአገሪቱን አንድነት ለመጠበቅ በስምምነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጠይቀዋል። ሁሉም የታጠቁ አካላት ንፁሃንን መጠበቅን ጨምሮ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተጣለባቸውን የሰብዓዊ ሕግጋዊ ግዴታ እንዲወጡም አሳስበዋል፥። በዚህም መግለጫ የሰብዓዊ እርዳታ መብቶችን የጣሱና ሰብዓዊ መብት ጥሰትን የፈፀሙ አካላት ሊጠየቁ ይገባል ተብሏል። ""ከዚህ ቀደም ደጋግመን እንዳልነው የኢትዮጵያን ውስጣዊ ወሰኖችን በኃይል ለመቀየር መሞከር ተቀባይነት የለውም። እንዲህ አይነት ጉዳዮችን የመሰሉ ብሔራዊ ጥያቄዎች ሊፈቱ የሚገቡት በሕዝቡ ነው። ሕዝቡ ብሔራዊ ውይይትና መግባባት ላይ ሲደርስ ነው። በጠመንጃ አፈሙዝ አይደለም"" ብለዋል። በክልሉ ያለው ቀውስና የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት በትግራይ ክልል የተነሳው ጦርነት 2 ሚሊዮን ነዋሪውን ከክልሉ ሲያፈናቅል 400 ሺህ ደግሞ ለረሃብ ተጋልጠዋል። በያዝነው ሳምንት ሰኞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለትግራይ ክልል የላካቸው ሰብዓዊ እርዳታ ጭነት መቀለ መግባታቸው ተገልጿል። በሁለት ሳምንት ውስጥ ለመጀሪያ ጊዜ የደረሰው ይህ እርዳታ በ50 የጭነት መኪኖች የተጓጓዘ ነው። በመቀለ የደረሰው እርዳታ 900 ሜትሪክ ቶን ምግብና አስፈላጊ ቁሳቁስ ቢሆንም በክልሉ ካለው ችግር አንፃር ይህ ቁጥር በእጥፍ ማደግ አለበት ተብሏል። ከአራት ሚሊዮን ሕዝብ በላይ አስቸኳይ እርዳታ በሚፈልግባት ትግራይ 10 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብና 150 ሺህ ሊትር ነዳጅ በየሳምንቱ መድረስ አለበት በማለት ድርጅቱ አፅንኦት ሰጥቷል። በትግራይ ያሉ ዋነኛ መንገዶች የተዘጉ ሲሆን ሁለት ድልድዮችም ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። መቀለ በትግራይ ኃይሎች ከተያዘች ጀምሮ መብራት የቴሌኮምዩኒኬሽን አገልግሎት፣ ባንክና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች ተቋርጠዋል። ህወሓት ማዕከላዊው መንግሥት እርዳታን እያገደ ነው በሚል የሚወቅስ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ መሰረተ ልማቶችን እየገነባሁ ነው ብሏል። በትግራይ ክልል ከግንቦት 22/2013 ዓ.ም ጀምሮ ምንም አይነት በረራዎች የተቋረጡ ቢሆንም መንግሥት ከሰሞኑ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ለሚፈልጉ ሁሉ ልዩ ፈቃድ እንደሚሰጥና በረራዎችም ከሰኔ 28/2013 ዓ.ም እንደሚጀመሩ ተገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት በልዩ ሁኔታ የፈቀደውን የሰብዓዊ እርዳታ በረራ አለመከልከሉንና በአሁኑም ወቅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም መንገደኞችን ወደ ትግራይ ክልል ለማጓጓዝ ሁለት በረራዎች እንዲፈቀዱለት መጠየቁን ተገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ ባደረጉት ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችና ቁጥራቸው የማይታወቅ ተዋጊዎች ተገድለዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም በማወጅ ወታደሮቹን ከመዲናዋ መቀለ እንዳስወጣ ቢገልፅም ህወሓት በበኩሉ መቀለን በኃይል እንደተቆጣጠረ ተናግሯል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን በኩል ኢትዮጵያ የተኩስ አቁሙን ለማወጅ የወሰነችበት ሁኔታም ከሰሞኑ ተገልጿል። ከዚህም መካከል አብዛኛዎቹ የህወሓት የፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪዎች በመገደላቸውና በመታሰራቸው እንዲሁም የቀሩትን ጥቂት የህወሓት አመራሮች ለመያዝ ሲባል ጦርነቱን መቀጠል አስፈላጊ ባለመሆኑ ነው ተብሏል። በክልሉ ያሉ ነዋሪዎች የግብርና ወቅታቸውን እንዳይስተጓጎል፣ የረድዔት ድርጅቶች የበርካቶችን ህይወት እንዲያድኑ እድል ለመስጠት እንዲሁም የግጭቱ የመጀመሪያ ገፈት ቀማሽ የትግራይ ሕዝብ ሰላም የሚያስፈልገው በመሆኑ እና ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሄ የሚፈልግ በመሆኑ ከጠቀሷቸው ምክንያቶች ናቸው። ህወሓት በስምምነት ላይ የተደረሰ የተኩስ አቁም እንደሚቀበል ያስታወቀ ሲሆን ካስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ከክልሉ የኤርትራ ወታደሮችና የአማራ ክልል ኃይሎች ወጥተው ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት እንዲመለሱ የሚጠይቀው ይገኝበታል። ባለፉት ወራት ጦርነቱን ተከትሎ በክልሉ ውስጥ ተፈጽመዋል የተባሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ ወገን እንዲመረመሩ እንዲሁም ቴሌኮም፣ መብራትና የአውሮፕላን በረራን ጨምሮ የተቋረጡ የመሠረተ ልማት አገልግሎቶች እንዲጀመሩም ጠይቋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57816164 +business ሮማን አብራሞቪች፡ ከማደጎ እስከ ቢሊየነርነት "ገና በሦስት ዓመቱ ወላጆቹን በሞት የተነጠቀው ዛሬ ላይ ከዓለማችን እጅግ ከናጠጡ ባለጸጎች መካከል ተጠቃሹ ነው፤ ሮማን አብራሞቪች። ሮማን አብራሞቪች ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያለው የጠበቀ ግንኙነት የገነባውን ገናና ስምና ንግድ እያሳጣው ይገኛል። ''እርግጠኛ ሰዎች ለሦስት ወይም አራት ቀናት እኔ ላይ ትኩረት ያደርጉ እና ከዛ ያልፋል። እኔ ላይ ትኩረት አያደርጉም። ማን እንደሆንኩኝ ቶሎ ይረሳሉ። እኔ ደግሞ ይሄ በጣም ነው የሚስማማኝ'' ብሎ ነበር ቢሊየነሩ የለንደኑን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ቡድን ቼልሲን በገዛ ወቅት። ነገር ግን በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ዓለም ሁሉ የሚያወራው ስለዚህ ቢሊየነር ሆኗል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በአብራሞቪች ንብረት ላይ እግድ ጥሏል። ይህ እግድ ቼልሲ እግር ኳስ ክለብ እና መኖሪያ ቤቶቹን ይጨምራል። ከንብረት እግዱ በተጨማሪ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ)መንግሥት የጉዞ እገዳም ጥሎበታል። የዩኬ መንግሥት ይህንን ያደረግኩት አብራሞቪች በዩክሬን ላይ ወረራ ከፈጸሙት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የቀረበ ትስስር ስላለው ነው ብሏል። አብራሞቪች ስመ ጥር የንግድ ሰው ለመሆን ብዙ ፈተናዎችን አልፏል። ገና ከጨቅላ እድሜው ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፎ ነው ዓለማችን ላይ ተጽእኖ መፍጠር ከሚችሉ ቢሊየነሮች መካከል ተጠቃሽ መሆን የቻለው። ከወላጅ አልባነት ወደ ቢሊየነርነት ሮማን አብራሞቪች እአአ 1966 በደቡብ ምዕራባዊ ሩሲያ ከዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ሳራቶቭ በተባለች ከተማ ነበር የተወለደው። አብራሞቪች ገና የአንድ ዓመት ልጅ ሳለ ነበር ወላጅ እናቱ ኤእሪ በደም መመረዝ ምክንያት ሕይወቷ ያለፈው። ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ አባቱ በግንባታ ሥራ ላይ ባጋጠመው አደጋ ሕይወቱ አለፈ። ከዚህ በኋላ አብራሞቪች እድገቱ የአየሩ ሁኔታ እጅግ ቀዝቃዛ እና ሕይወት ከባድ በሆነች የሩሲያ ክፍል ውስጥ በዘመዶች እጅ ሆነ። ""እውነቱን ለመናገር ልጅነቴ በጣም መጥፎ ነበር አልልም። በልጅነታችን ነገሮችን መለየት ላይ እስከዚህም ነን። አንዱ ህጻን ካሮት ይበላል፤ ሌላኛው ደግሞ ከረሜላ ይበላል። ሁለቱም ለልጆች ጣፋጭ ናቸው። በልጅነታችን እነዚህን ልዩነቶች አናስተውላቸውም'' ብሎ ነበር አብራሞቪች ከጋርዲያን ጋር ቆይታ ባደረገ ወቅት። በ16 ዓመቱ ትምህርቱን በማቋረጥ በመካኒክነት የሥራ ሲሆን ሞስኮ ውስጥ ደግሞ ከፕላስቲክ የተሰሩ የህጻናት መጫወቻዎችን ይሸጥ ነበር። የሶቪየት ሕብረት መከላከያ ኃይልንም ተቀላቅሎ ነበር። የወቅቱ የሶቪየት ሕብረት መሪ የነበሩት ሚኻኤል ጎርባቾቭ ለሥራ ፈጣሪዎች የሚመች አስተዳደር መዘርጋታቸውን ተከትሎ አብራሞቪች ሽቶ በመሸጥ ጠቀም ያለ ገንዘብ መሰብሰብ ጀመረ። የሶቪየት ሕብረት መበተንን ተከትሎ የነዳጅ ኩባንያዎች ከመንግሥት እጅ ወጥተው ለባለሀብቶች መሸጥ ተጀመረ። ገና በሀያዎቹ አጋማሽ የእድሜ ክልል ውስጥ የነበረው አብራሞቪች አጋጣሚውን ከመጠቀም አልቦዘነም። በተጭበረበረ ነው በተባለ የጨረታ ሂደት አብራሞቪች 'ሲብኔፍት' የተባለውን የነዳጅ ኩባንያ በአውሮፓውያኑ 1995 ላይ ከመንግሥት በ250 ሚሊየን ዶላር ገዛ። ከአስር ዓመታት በኋላ ማለትም እአአ 2005 ላይ መልሶ ይህንኑ ኩባንያ ለመንግሥት በ13 ቢሊየን ዶላር ሸጠው። ምንም እንኳን የአብራሞቪች ጠበቆች ቢሊየነሩ የነዳጅ ድርጅቱን በሚገዛበት ወቅት ምንም አይነት ሕገ ወጥ ነገር አልፈጸመም ብለው ቢከራከሩም፤ 2012 ላይ በአንድ የዩኬ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ግን አብራሞቪች እራሱ የኩባንያውን ግዢ ለማቀላጠፍ ክፍያ መፈጸሙን አምኗል። በ1990ዎቹ አካባቢ ደግሞ በሩሲያ የአልሙኒየም ንግድ ዘርፍን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ፍትጊያ ነበር። ''በየሦስት ቀኑ የሆነ ሰው ይገደል ነበር'' ይላል አብራሞቪች። ግድያው የሚፈጸመው በተፎካካሪ የአልሙኒየም ነጋዴዎች ላይ ነበር። ይህንን ያስተዋለው አብራሞቪች የራሱንና የቤተሰቦቹን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲል ከዚህ ንግድ እራሱን በሂደት አግልሏል። ይሁን እንጂ ባልተረጋጋ የንግድ ሥርዓት ውስጥ ሆኖ እንኳ አብራሞቪች ብዙ ቢሊዮን ዶላሮችን መሰብሰብ ችሏል። ጉዞ ወደ ፖለቲካ የሩሲያ ፕሬዝዳንት የነበሩት ቦሪስ ዬልሲን ጥሩ ወዳጁ ነበሩ። እንዲያውም በአንድ ወቅት በሞስኮ የፖለቲካ ዓለም ውስጥ ተሳትፎው ጠንክሮ በክሬምሊን መኖሪያ ቤት እንዲሰጠው ተደርጎም ነበር። 1999 ላይ ፕሬዝዳንት ቦሪስ ዬልሲን ከሥልጣናቸው ሲወርዱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትና የቀድሞው የሩሲያ የስለላ ተቋም ኬጂቢ ሰላይ ቭላድሚር ፑቲን ቦሪስ ዬልሲንን እንዲተኩ ከደገፏቸው ሰዎች መካከል አብራሞቪች አንዱ ነበሩ። ፑቲን ሥልጣን በያዙ በመጀመሪያዎቹ ወራት የሶቪየት ሕብረት መፍረስን ተከትሎ ቢሊየኖችን መሰብሰብ የቻሉ ባለሃብቶች ላይ ትኩረት አድርገው ነበር። ለፑፒን አጋርነታቸውን ማሳየት ያልቻሉት ከአገር የወጡ ሲሆን ገሚሶቹ ደግሞ ወደ እስር ቤት እንዲወረወሩ ተደርጓል። አብራሞቪች ከፑቲን ጎን መሰለፍን መርጧል። እንደውም እአአ 2000 ላይ አብራሞቪች በሰሜን ምሥራቃዊ ሩሲያ የተጎዳ የሚባለው ቹኮትካ ግዛት አስተዳዳሪ ሆኖ ተሹሞ ነበር። አብራሞቪች የራሱን ገንዘብ በመጠቀም ዜጎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ማድረጉን ተከትሎ ከፍተኛ ተቀባይነት ቢያገኝም፣ በ2008 ላይ በገዛ ፈቃዱ ከሥስልጣኑ ወርዷል። ሥልጣን ይበቃኝ ቢልም፤ የንግድ ሥራውን ግን አቀላጥፎ ቀጥሏል። መኪኖችን፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ውድ የጥበብ ሥራዎችን በመሰብሰብም ይታወቃል። እግር ኳስና አብራሞቪች በአውሮፓውያኑ 2003 ዝምተኛውና አይናፋር ነው የሚባለው አብራሞቪች የእንግሊዙን ቼልሲ የእግር ኳስ ክ��ብ በ140 ሚሊዮን ፓዎንድ በመግዛት በእግር ኳስ ወዳጆች ዘንድ ዝናው ናኘ። አብራሞቪች ቼልሲን ከገዛ በኋላ ቡድኑ አምስት ጊዜ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ መሆን የቻለ ሲሆን፣ ሁለት ቻምፒየንስ ሊግ እንዲሁም አምስት የኤፍኤ ዋንጫዎችን አሸንፏል። የዩኬ መንግሥት ማዕቀብ ከመጣሉ 8 ቀናት አስቀድሞ አብራሞቪች ቼልሲን ለሽያጭ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። ""አንድ ቀን በአካል በስታምፎርድ ብሪጅ ተገኝቼ እሰናበታችኋለሁ"" ሲል መልዕክቱን ለቼልሲ ደጋፊዎች አስተላልፏል። አብራሞቪች በለንድን የእግር ኳስ ክለብ ብቻ ሳይሆን ከ150 ሚሊዮን ፓዎንድ በላይ የሚገመት ባለ15 ክፍል የተንጣለለ መኖሪያ ቤት አለው። ሦስት ጊዜ ትዳሩን የፈታው አብራሞቪች፤ በዓለማችን ግዙፍ ከሚባሉ ቅንጡ የመዝናኛ መርከቦች መካከል የሚዘረዘሩት ሶላሪስ እና ኢክሊፕስ የተባሉት የግሉ ናቸው። የአብራሞቪች አጠቃላይ ሀብት 13.7 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሲሆን፣ በዓለማችን 128ኛው ሀብታም ሰውም ነው ሲል ብሉምበርግ ብሏል። ፎርብስ ግን የአብራሞቪች አጠቃላይ ሀብት ከ12.3 ቢሊየን እንደማይበልጥና በዓለማችን ካሉ ባለሀብቶች አንጻር 142ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አመልክቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60899537 +business ነዳጅ አምራች አገራት የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ ከስምምነት ደረሱ "ነዳጅ አምራች አገራት የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ እና በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ የሚደርሰውን ጫና ለማቃለል ምርታቸውን ለማሳደግ ተስማሙ። በሁለት ዓመት ተኩል ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ዋጋዎች ከጨመሩ በኋላ የነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት (ኦፔክ) አባላት እና እንደ ሩሲያ ያሉ ከድርጅቱ ውጭ ያሉ አገራት ከነሐሴ ጀምሮ አቅርቦትን ያሳድጋሉ። እርምጃው የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ላይም ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሏል። የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በዚህ ዓመት በ43 በመቶ ገደማ ጨምሮ በበርሜል ወደ 74 ዶላር ከፍ ብሏል። ባለፈው ዓመት ኦፔክ እና አጋሮቻቸው በወረርሽኙ የተነሳ የፍላጎት ማሽቆልቆል በመኖሩ እና ዋጋው በመቀነሱ ከምርታቸው በቀን 10 ሚሊዮን በርሜል ቀንሰው ነበር። ይሁን እንጂ በዚህ ዓመት የዓለም ምጣኔ ሃብት እያንሰራራ በመሆኑ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል። ይህም በአንዳንድ አገራት የዋጋ ግሽበት እንዲጨምር አስተዋጽኦ በማድረጉ እና በዓለም የኢኮኖሚ መሻሻል ላይ እንቅፋት እንዳይሆን አስግቷል። የነዳጅ አምራቾች ዋጋ ለመቀነስ ፍላጎት ቢያሳዩም በሳዑዲ አረቢያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በሐምሌ ወር መጀመሪያ ዕቅዱን እንዲደናቀፍ ምክንያት ሆኗል። በሪያድ እና በሞስኮ የቀረበውን ተጨማሪ ነዳጅ የማምረት ዕቅድ ፍላጎት አቡዳቢ ውድቅ አድርጋ ነበር። በቅርብ አጋሮች መካከል ያልተለመደ ውዝግብ ከ50 በመቶ በላይ የነዳጅ አቅርቦቶችን የሚቆጣጠረውን ኦፔክና አጋሮቹ መረጋጋት ላይ ጥያቄ አስነስቷል። በአዲሱ ስምምነት መሠረት ኦፔክ እና አጋሮቹ ገበያውን ለማረጋጋት ከነሐሴ እስከ ታህሳስ 2021 ድረስ በቀን ተጨማሪ ሁለት ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ለማምረት ተስማምተዋል። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ሩሲያ፣ ኩዌት እና ኢራቅን ጨምሮ በርካታ አባል ሃገራት ከግንቦት 2022 ጀምሮ ከፍተኛ የምርት ኮታ ከስምምነት ላይ ተደርሷል። ባለፈው ዓመት ወደ ሥራ የገባው የነዳጅ ምርት ቅነሳ እስከ መስከረም 2022 ድረስ ያበቃል ብሏል። የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ አባላቱ ""ገንቢ"" እና ""መግባባት"" ላይ ደርሰዋል ብለዋል። ""ወረርሽኙ እስካ አሁን በቁጥጥር ስር ባይውልም በመላው ዓለም በክትባት ምክንያት እንደ መኪኖች እና የአውሮፕላን ነዳጅ በመጨመ�� ምርታችን እያገገመ መሆኑን እያየን ነው"" ብለዋል። ""ኃላፊነታችንን መወጣት እና የዓለም ኢኮኖሚ እንዲረጋጋ ማድረግ በጣም አስፈላጊያችን ነው"" ሲሉ ገልጸዋል፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-57884491 +politics ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ የተገደሉባት የቻድ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? "የሟቹ የቻድ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ መጨረሻ አነሳሳቸውን የሚያስታውስ ነው። ዴቢ በ1990 (እአአ) በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ነበር ስልጣን ከሄስኔ ሃበሬ የቀሙት። በተመሳሳይም ፕሬዝዳንት ዴቢ ከስልጣን ሊያወርዷቸው በሚፈልጉት አማጽያን ጉዳት ደርሶባቸው ህይወታቸው አለፈ። ከስልጣን ሊያወርዷቸው በሚታገሉት አማጽያን እጅ ሞትን ተቀበሉ። ዴቢ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላም ጦር ሜዳ እየተገኙ ወታደሮቻቸውን ይጎበኛሉ። ""ተዋጊው መሪ"" በመባል የሚታወቁት ዴቢ ነሐሴ 2020 ከገዢው ከፓትሪዮቲክ ሳልቬሽን ሙቭመንት ፓርቲ 'ማርሻል ኦፍ ቻድ' የሚል ማዕረግ ተሰጣቸው። ሠራዊቱ በመንግሥታዊው 'ቴሌ ቻድ' ቴሌቪዥን በሰጠው መግለጫ ዴቢ ""በመጨረሻ በጦር ሜዳ ተገኝተው የአገሪቱን አንድነት ሲያስጠብቁ አልፈዋል"" ብሏል። ""በጦር ሜዳ ላይ የደረሰባቸውን ጉዳት ተከትሎ የቻድ ማርሻል ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ ህይወታቸው ማሉን ለቻዳውያን ስናሳውቅ በታላቅ ሀዘን ነው።"" ዴቢ ""ከሊቢያ ከመጡ አሸባሪ ቡድኖች ጋር የተካሄደ ውጊያ በጀግንነት ሲመሩ እንደነበር"" እና ወደ ዋና ከተማዋ ንጃሜና ህክምና ሲያቀኑ ህይወታቸው ማለፉን አክሏል። ቱቡ ሚዲያ በትዊተር ገጹ እንደዘገበው ዴቢ በሰሜን ንጃሜና በምትገኘው ካኔም ግዛት ከፍሮንት ቼንጅ ኤንድ ኮንኮርድ ኢን ቻድ (ፋክት) ጋር በነበረ ግጭት ነው የቆሰሉት። ወታደር ስልጣኑን ይቆጣጠራል ዴቢ አገሪቱን በኃይል መርተዋል። ተቺዎቻቸውን እና ተቀናቃኞቻቸውን ያለ ርህራሄ አፍነዋል። ለምሳሌ ቻድ በ2018 ከተሞከረው የመፈንቅለ መንግሥት ወዲህ ጠቅላይ ሚኒስትር አልነበራትም። ታኅሣሥ 2020 ይፋ የተደረገው አዲስ ሕገ-መንግሥት የምክትል ፕሬዝዳንትነት ቦታን ቢፈጥርም ዴቢ እስከተገደሉበት ጊዜ ማንም አልተሾመበትም። የቅርቡ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የተቃናቃኞቻቸውን ጥያቄ ""የዲሞክራሲ ሥርዓት ማለት ሥርዓት አልበኝነት አይደለም"" በማለት ዴቢ ውድቅ አደርገዋል። ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን ላይ ዘመዶቻቸውን እና የሚቀርቧቸውን በመሾም ስልጣን ዘመናቸውነ ሲያራዝሙ ቆዩ። ልጃቸው ጄኔራል ማሐማት ኢድሪስ ዴቢ የፕሬዚዳንታዊው ጥበቃ ኃላፊ ነበሩ። የአገሪቱ አመራር ቦታ በፕሬዚዳንቱ ዘመዶች በመታጠሩ ለዴቢ የሚሆን የፖለቲካ ተተኪ የለም ማለት ነው። የዴቢን ሞት ተከትሎ ሠራዊቱ ስልጣኑን መቆጣጠሩ አያስደንቅም። ሠራዊቱ እንደገለጸው ፓርላማውና መንግሥት አስተዳደሩ መበተኑንና በመሐማት ዴቢ የሚመራ 15 አባላት ያሉት የሽግግር ወታደራዊ ምክር ቤት ""የአገሪቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ"" መሾሙን አስታውቋል። አዲስ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ወታደራዊው ቡድን ጁንታ ለ18 ወራት አገሪቱን ያስተዳድራል። ሕገ መንግሥቱ ተሰርዞ በመሐማት ዴቢ በሚተላለፍ የሽግግር ቻርተር ይተካል። ወታደራዊ ኃይል በአገር አቀፍ ደረጃ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ንጋት 11 ሰዓት የሚቆይ የሰዓት እላፊ ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል። መሐማት ኢድሪስ ዴቢ ማሐማት ከ2014 ጀምሮ የፕሬዚዳንታዊ ጥበቃ ኃላፊ፣ የመንግሥት ተቋማት የደኅንነት አገልግሎቶች ዋና ዳይሬክቶሬት ሆነው አገልግለዋል። በ2013 በማሊ የቻድ ኃይሎች ምክትል ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን አዲሱን ኃላፊነት በመረከብ ወደ አገራቸው ከመመለሳቸው በፊት ከፈረንሳይ ኃይሎች ጎን በተለያዩ ተልዕኮዎች ላይ ተሳትፈዋል ተብሏል። ማሐማት ከአማጽያን ጋር በምዕራባ��ው የካኔም ግዛት በተደረገው ፍልሚያ አባታቸው ሲቆስሉ አብረዋቸው ነበሩ። ""ጄኔራል ካካ"" በመባል የሚታወቁት ማሐማትም ከአንዳንድ ወንድሞቹ በተቃራኒ ብልህነት እና ታዋቂነትን በማሳየት ዝና አላቸው። ልክ እንደ አባታቸው በጦርነት ከጥቃት የተረፉ ወታደር ናቸው። ""ፕሬዚዳንቱ [ኢድሪስ ዴቢ] ከታዋቂ ቻዳውያን እና ከሚግቧቧቸው መንግሥታት ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ጋር ማሐማት እንዲገናኙ አድርገዋል። ለሥልጣን አንዲበቁም በአባታቸው በሚሰጣቸው መንገድ ነበር"" ሲል ጁን እፍሪክ ዘግቧል። ሟቹ ዴቢ ብዙ ወንድ ልጆች ነበሯቸው። አንዳንዶቹም በመንግሥታቸው ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል። በማሐማት እና በአንዳንድ ወንድሞቹ መካከል ውዝግብ ሊፈጠር ይችላል። ተቃዋሚዎች የሽግግር ወታደራዊ ምክር ቤቱን ውድቅ አድርገዋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሳሌህ ኬብዛቦ እና የተቃዋሚ ፓርቲው ፍሪደምስ ኤንድ ዴቨሎፕመንት መሐመድ አህመድ አልሃቦ በበኩላቸው የሽግግር መንግሥቱ በብሔራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲመራ መጠየቃቸውን 'ሌ ጆርናል ደ ቻድ' ዘግቧል። ተቃዋሚዎች የተዳከሙ እና የተከፋፈሉ በመሆናቸው ለወታደራዊው ጁንታ ከፍተኛ ተግዳሮት የመሆን ዕድል የላቸውም። ለአማጽያን የሞራል ማሻሻያ በካኔም ጦርነት ከባድ ኪሳራ እንደደረሰባቸው የተዘገበው አማጽያኑ የዴቢ ሞት ሁኔታውን ሊያሳምርላቸው ይችላል። ሠራዊቱ ከአማጽያኑ ጋር በካኔም በተደረገው ውጊያ ከ300 በላይ አማጽያን የተገደሉ ሲሆን 150 ደግሞ ቆስለዋል። የአማጽያኑ መሪ ማሐማት መሃዲ አሊ ከፈረንሳዩ አርኤፍአይ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የደረሰባቸው ኪሳራ እውነት መሆኑን አምነዋል። ""ያልተለመደው ዓይነት ግጭት ነበር። ከሁኔታዎች አንጻር ታክቲካዊ ማፈግፈግ አደረግን"" ያሉት መሪው የቻድ ጦር በፈረንሣይ አየር ኃይል የተደገፈ መሆኑን ቢገልጹም ፓሪስ ውድቅ አደርጋዋለች። አማጺው ከ2016 ጀምሮ ከደቡብ ሊቢያ እየተነሳ ጥቃት ያደርስ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ ወደ ንጃሜና ለማቅናት ጥረቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። ቡድኑ በሁለት ቀናቱ የካኔም ውጊያ 15 ከፍተኛ የቻድ ወታደራዊ መኮንኖችን ገድያለሁ ወይም አቁስያለሁ ብሏል። ኪሳራ ቢደርስበትም ከ1,500 በላይ ተዋጊዎችን እንዳሉት የሚዘገበው የፋክት አማጽያን ቻድ በዴቢ ሞት በምታዝነበት በዚህ ወቅት አዳዲስ ጥቃቶችን ሊያደርስ ይችላል። የዴቢ ሞት ለቻድ ታጠቂ ቡድኖች የመሰባሰቢያ ጥሪ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ሌላኛው አማጺ ቡድን ከአገሪቱ ሠራዊት ጋር የሚፋለመውን አማጺ ያወደሰ ሲሆን ሁሉም የቻድ አማጺያን ቡድኖች በአንድ ተሰባስበው የዴቢን አገዛዝ እንዲከስልጣን እንዲያወርዱ ጠይቋል። ቀጣናዊ የፀረ-ሽምቅ አንቅስቃሴዎች የዴቢ ሞት በሳሀል እና በቻድ ሐይቅ አካባቢ በጂሃዳዊ አማጽያን ላይ የቻድን መንግሥት ወታደራዊ ዘመቻ መቀጠል ጥርጣሬ ውስጥ ጥሎታል። ቻድ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ በማሰማራት አገራቱን እና የፈረንሣይን በአልቃይዳ እና በኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) ታጣቂዎች ላይ የምታደርገውን ውጊያ እየረዱ ነው። የቻድ ወታደሮች ቦኮ ሃራምን እና ኢስላሚክ ስቴት በምዕራብ አፍሪካ በቻድ አቅራቢያ ከሚገኙት ናይጄሪያ፣ ኒጀር፣ ካሜሩን እና ቻድ ጋር በመተባበር ላይ ይገኛሉ። ዴቢ በክልላዊ የፀረ-ሽምቅ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍ የቻድን ዓለም አቀፋዊ ገጽታ ከፍ ያደረገ ሲሆን ከምዕራቡ ዓለም በተለይም ከፈረንሳይ፣ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ወታደራዊ እና የገንዘብ ድጋፍን እንድታገኝ አድርጓል። ለምሳሌም 5,200 የወታደሮች በማሊ ቢሰማሩም የኦፕሬሽን ባርካኔ ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጫው ቻ�� ነው። የፋክት አማጽያን ንጃሜናን ኢላማ ያደረጉ ሲሆን ዴቢንም ገድለዋል። ወታደራዊው ምክር ቤት በአገር ውስጥ በሚካሄደው አመጽ ላይ በማተኮር የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቀንስ ስለመሆኑ ጊዜ የሚፈታው ይሆናል። በነሐሴ ወር 2020 በማሊ የተካሄደውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በጭፍን መደገፏን ከሚገልጹ መረጃዎች አንፃር ፈረንሳይ ቻድ ውስጥ ለሠራዊቱ ስልጣን መያዝ የምትሰጠው ምላሽ ትኩረትን የሚስብ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/56828901 +sports ዋልያዎቹ ከምድባቸው የማለፍ እድላቸው ምን ያህል ነው? በካሜሮን እዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እየተሳተፈ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ያደርጋል። በመጀመሪያዎቹ ሁለት የምድብ ጨዋታዎች ሽንፈትን ያስተናገዱት ዋልያዎቹ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋቸውን ከቡርኪና ፋሶ ጋር ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ያደርጋሉ። ዋልያዎቹ በመጀመሪያው ጨዋታቸው በኬፕ ቬርድ 1 ለ 0፤ በሁለተኛው ግጥሚያ ደግሞ በአዘጋጇ ካሜሩን 4 ለ 1 መሸነፋቸው ይታወሳል። ለመሆኑ ዋልያዎቹ ከምድባቸው የማለፈ እድላቸውም ምን ያህል ነው? መልሱ - ጠባብ ነው። ዋልያዎቹ ሁለት ጊዜ ተሸንፈው 4 የጎል እዳን በመያዝ በምድቡ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ቡርኪና ፋሶ በውድድሩ መክፈቻ ጨዋታ አዘጋጇን 1ለ0 ስትመራ ቆይታ ተከታትሎ በተቆጠሩባት ሁለት የፍጹም ቅጣት ምቶች በካሜሮን 2 ለ 1 ተሸንፋለች። ቡርኪና ፋሶ በቀጣይ የምትጋጠመው ከኬፕ ቬርድ ነው። ኬፕ ቬርድን 1 ለ 0 በማሸነፍ በምድብ ሀ ኬፕ ቬርድን በጎል ልዩነት በመብለጥ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። የምድቡን ሁለቱንም ጨዋታዎች ያሸነፈችው ካሜሮን በአንደኝነት እየመራች ነው። ዋልያዎቹ ያለባቸውን 4 የግብ እዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ከምድቡ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ ቡርኪና ፋሶን 5 ለ 0 እና ከዚያ በላይ በሆነ ውጤት አሸንፈው፤ የኬፕ ቬርድ ቡድን በካሜሮን የማይበገሩ አናብስት መሸነፍን መጠበቅ አለባቸው። ነገር ግን በእግር ኳስ ሜዳ የሚከሰተውን መተንበይ ባይቻልም ዋልያዎቹ የምድቡ ሁለተኛ በሆነችው ቡርኪና ፋሶ ላይ በርካታ ጎሎችን አስቆጥረው ማሸነፍ የዋዛ አይሆንላቸውም። በፈረንጆቹ 2013 በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት ኢትዮጵያ እና ቡርኪና ፋሶ በአንድ ምድብ ተደልድለው እንደነበረ ይታወሳል። በዚህ ውድድርም ቡርኪና ፋሶ ዋልያዎቹን 4 ለ 0 አሸንፈው እንደነበር ይታወሳል። ምርጥ ሦስተኛ? የአፍሪካ ዋንጫ 24 ብሔራዊ ቡድኖችን እያሳተፈ ይገኛል። ይህ ማለት እያንዳንዳቸው አራት ቡድኖችን ያቀፉ ስድስት ምድቦች አሉት ማለት ነው። ከእነዚህ መካከል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን የሚይዙ ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር በቀጥታ ሲያልፉ፤ አራት ምርጥ ሦስተኛ ቡድኖችም ቀጣዩን የ16ቱን ዙር ይቀላቀላሉ። ዋልዮቹም ከምድባቸው ምርጥ ሦስተኛ ሆኖ ለመጨረስ ቡርኪና ፋሶን አሸንፈው የኬፕ ቬርድ በካሜሮን መሸነፍን መጠበቅ አለባቸው። ከዚህ በተጨማሪም ዋልያዎቹ ከሌሎች ምድቦች ምርጥ ሦስተኛ ሆኖ የመጨረስ እድል ያላቸውን አገራት ውጤት መጠበቅ ግድ ይላቸዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-60020563 +business ከኢንጅነር ስመኘው ሞት በኋላ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ምን ላይ ደረሰ? "የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከጅማሮው በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩት የነበሩት ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ አንድ ዓመት አስቆጠሩ። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በመስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው በድንገት አልፎ ከተገኘ በኋላ፤ በወቅቱ የፌደራል ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ኢንጅነሩ ራሳቸውን እንዳጠፉ በምርመራው እንደደረሰበት ማሳወቁ ይታወሳል። መኪናቸው ውስጥ የተገኘውም ሽጉጥ የኢንጂ���ሩ እንደነበር በምርመራው አረጋግጫለሁ ብሏል። •ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? •ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጥቂት እንንገርዎ የግድቡ ምልክት ተደርገው የሚወሰዱት ኢንጅነር ስመኘው ሞት፣ በርካቶችን ያስደነገጠ እና ኃገሪቱ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ የፈሰሰበት የህዳሴ ግድብ ከየት ይደርሳል? የሚል ስጋትን የፈጠረም ነበር። በኢንጅነር ስመኘው ቦታ የተተኩት የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ፤ ''አንድ ሰው በግሉ የሚቻለውን ያክል ነው አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችለው እንጂ የጀመረውን ሁሉ ይጨርሳል ማለት አይደለም'' በማለት የቀድሞውን የፕሮጀክቱን መሪ ያስታውሳሉ። አክለውም ''ህዳሴ ግድብ የህዝብ ነው። እኔም አሻራዬን ትቼ ላልፍ እችላለሁ የኢንጅነር ስመኘውን አስተዋጽኦንም እንዲሁ ነው የምመለከተው'' ይላሉ። የቀድሞው የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መሪ ከሞቱ በኋላ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት የህዳሴ ግድብ አፈጻጸም እንዴት ነው? ምን ተለወጠ? ምን ችግር አጋጠመው? ከኢንጅነር ክፍሌ ጋር ቆይታ አድርገናል። • ''የሚፈርስ የግድቡ አካል የለም'' የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፕሮጀክቱ ለምን ዘገየ? ኢንጅነር ክፍሌ ፕሮጀክቱ በታቀደለት የጊዜ ገደብ ባይሄድም በአሁኑም ወቅት ህዝብ እና መንግሥት ለአባይ ግድብ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዳላቋረጡ ይናገራሉ። በዋናነት ከፕሮጀክቱ ጋር በተያያዘ ያጋጠሙ ሁለት ፈተናዎች አሉ የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ የመጀመሪያው ከስነ-ምድር (Geology) ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይገልጻሉ። የአባይ ወንዝ የሚሄድበት መሬት ሥሩ ጠንካራ ነው ተብሎ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀው፤ ወደ ስራ ከተገባ በኋላ ግን መሬቱ እንደተጠበቀው ሳይሆን እንደቀረና መሬቱን ቆፍሮ በኮንክሪት የመሙላቱ ሥራ ብዙ ጊዜ መውሰዱን ኢንጅነር ክፍሌ ያስረዳሉ። ለህዳሴ ግድብ መዘግየት እንደ ሁለተኛ ምክንያትነት የሚጠቅሱት ደግሞ ከብረታብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር የተያያዘ ነው። እንደ ኢንጅነር ክፍሌ ከሆነ መንግሥት የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ግንባታው ሲገባ በተቻለ መጠን በግድቡ ላይ ሃገር በቀል ተቋማት አስተዋጽኦዋቸውን እንዲያበረክቱ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ነበር። በዚሁ መንፈስ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ሥራውን እንዲያከናውን በንዑስ ተቋራጭነት እንዲሰራ መወሰኑን ያስረዳሉ። ተቋሙ የኤክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን የመገንባት አቅምም ሆነ ልምድ ስለሌለው የግንባታ ስራውን ወደፊት ማስኬድ አልቻለም ብለዋል። ""ፕሮጀክቱ ላይ ብዙ ቢሊየን ብር ቢፈስም፤ መልክ አልያዘም"" ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት የሲቪል ሥራው ወደ 84 በመቶ በላይ ቢጠናቀቅም፤ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው 28 በመቶ የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ወደ ስልሳ ስምንት በመቶ መድረሱን ተናግረዋል። መጋቢት 10፣ 2011ዓ.ም በነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክርቤት ጽሕፈት ቤት፣ ከሚዲያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በነበረው የውይይት መድረክ የግድቡ የግንባታ ቡድን ተወካይ አቶ ኤርሚያስ ውብሸት የግድቡ የሲቪል ሥራ 85 በመቶ፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ 25በመቶ እና የብረታ ብረት ስራ 13 መድረሱንና በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ 66.24 በመቶ ደርሷል ብለዋል። መንግሥት ለሜቴክ ተሰጥቶ የነበረውን ውል ካቋረጠ በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እና ልምድ ላላቸው ለአዳዲስ ተቋራጮች በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ የማድረግ ተግባርም ተከናውኗል ። በግንባታ ስራው ተሰማርተው የሚገኙት ስድስትተቋራጮች እንደሆነ የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ፤ ከእነዚህም መካከል የፈረን���ይ፣ ጀርመን እና ቻይና ኩባንያዎች ይገኙበታል ይላሉ። በውይይት መድረኩ ላይም እንደተጠቀሰው ከተቋራጮቹም መካከል ሲጂጂሲ፣ ሳይኖ ሃይድሮ፣ ቮይት፣ ጂኦ ሃይድሮ ፍራንስና ኤክሲዲ ይገኙበታል በማለት በስም ይዘረዝራሉ። •ስለኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እስካሁን ምን እናውቃለን? እንደ ተርባይን ያሉ ከውሃ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግንባታዎች ከፍተኛ ልምድ የሚጠይቁ ሥራዎች መሆናቸውን ኢንጅነር ክፍሌ ገልፀው አዳዲሶቹ ተቋራጮች የግንባታ ሥራውን በተቀላጠፈ ሁኔታ እየሠሩ እንደሚገኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሳሊኒ ቅሬታ እና የፕሮጀክቱ ክንውን የሲቪል ሥራውን ለማከናወን ኮንትራት ወስዶ ሲሰራ የቆየው የጣሊያኑ ሳሊኒ ከግንባታ ክፍያ መዘግየት ጋር ተያይዞ ቅሬታዎችን ሲያሰማ ነበር። ኢንጅነር ክፍሌ እንደሚሉት ሳሊኒ ያነሳቸው ቅሬታዎች አግባብነት ከተጠና በኋላ መንግሥት እና ሳሊኒ ከመግባባት ላይ ደርሰዋል ይላሉ። ""ሳሊኒ ሲያነሳው የነበረው ቅሬታ 'ፕሮጀክቱ የዘገየው እኔ በፈጠርኩት ችግር አይደለም። ሜቴክ የሚጠበቅበትን የተርባይን እና ሌሎች ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ብረቶችን በወቅቱ ማቅረብ ቢችል ኖሮ ሥራውን በሰዓቱ ማጠናቀቅ እችል ነበር። ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ለኪሳራ ተጋልጫለሁ' የሚል ነበር"" በማለት ኢንጅነር ክፍሌ ያስረዳሉ። ሳሊኒ በዚህ ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ መንግሥት ካሳ እንዲከፍለው ጥያቄ አቅርቦ ነበር። •ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ "" ከሳሊኒ ጋር ያለው ጉዳይ አልተፈታም። በመንግሥት የተወሰደው እርምጃ በዚህ የመዘግየት ምክንያት ኪሳራ ደርሶበት አስጊ የሆነ የገንዘብ ደረጃ ላይ በመድረሱ፤ ሳሊኒ ይገባኛል የሚለው ጥያቄ እልባት እስኪያገኝ ድረስ በታሳቢነት 124 ሚሊዮን ብር እንዲከፈለው ተወስኗል። ይህ የተወሰነው ስራውን ከማስቀጠል አንፃር ነው። የሳሊኒ ያቀረበው የኪሳራ ይገባኛል ካሳ ሙሉ በሙሉ መቀበል ማለት አይደለም። እየታየ እንዲሁም እየተጠና ነው። እውነት ይህ ሁሉ ኪሳራ ይደርስበታል ለሚለውም በዝርዝር እየታየ ነው""ይላሉ ኢንጅነር ክፍሌ። ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ሳሊኒ ብቻ ሳይሆን ጉዳቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ጭምር ነው የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ ""እውነት ለመናገር ህዝቡ በግንባታው ሞራሉ ተነክቷል። ግንባታው የደረሰበትን ደረጃ በማስመልከት ለህዝብ የሚሰጠው መረጃ የተሳሳተ ነበር። እውነቱ ተደብቆ ቆይቶ በአንዴ እውነቱ ሲገለጥ ህዝቡ ማዘኑ አልቀረም"" ይላሉ። ፕሮጀክቱ በተጀመረበት ወቅት በአራት ዓመት ውስጥ በሁለት ተርባይኖች አማካኝነት ኃይል ማመንጨት ይጀምራል መባሉን እና በሰባት ዓመታት ውስጥ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደነበረ ኢንጅነር ክፍሌ ያስታውሳሉ። ይህን መሰል ግዙፍ ፕሮጀክት በሰባት ዓመታት ውሰጥ መጨረስ ይቻላል ተብሎ መጀመሩ በራሱ ስህተት ነው የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ ሜቴክ ""የሚጠበቅበትን በወቅቱ ማድረግ ቢችል ኖሮ ቢያንስ በ2009 ላይ ኃይል ማመንጨት መጀመር ይቻል ነበር"" ይላሉ። ከሁለት አመታት በኋላ ኃይል የማመንጨት ጅማሮ እቅድ እንዳለ የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ በአራት ዓመታት ውስጥ ደግሞ ግንባታው ሙሉ በሙሉ የማጠናቀቅ እቅድም እንደተያዘ ይናገራሉ። ነገር ግን ተግዳሮቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አልደበቁም። በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ ሁሉም ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ ማለት ሳይሆን በመጀመሪያ ግድቡ ውሃ የሚሞላበት ሁኔታ ላይ የታችኛው የተፋሰስ ሃገራትን ማወያየት ዋናው ስራ እንደሆነ ይናገራሉ። ""ተርባይኖቹ በሙሉ አቅም ኃይል የሚያመነጩት በግድቡ ውሃ መሙላት ላይ ተሞርኩዞ ነው። የተርባይኖቹ ስራ ግን ሙሉ በሙሉ ለመጨረስ ታቅዷል"" ይላሉ። የፕሮጀክቱ ተጨማሪ ወጪ ሃሳብ ሆኗል? የዚህ ፕሮጀክት ወጪ ከህዝብ ከሚሰበሰበው እና መንግሥት ከሚመድበው በጀት ሲሆን፤ መንግሥት ተጨማሪ በጀት እየመደበ የግንባታ ሥራው እንዲቀጥል እያደረገ መሆኑንም ይናገራሉ። ህዝቡም ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ በማዋጣት ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ጠቅሰዋል። የውጪ ምንዛሬ እጥረት እና ከግንባታው መጓተት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ወጪ ፕሮጀክቱን እንደጎዳው የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ ""ህዝብ እና መንግሥት አሁንም ፕሮጀክቱን ከግብ ማድረስ ያለስለሰ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ"" ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-49027549 +business ህንድ አሜሪካን ይጎዳል የተባለ የንግድ ታሪፍ ልታስተዋውቅ ነው "ህንድ ከእሁድ ጀምሮ የለውዝና የአፕል ምርቶችን ጨምሮ 28 የአሜሪካ ምርቶች ላይ አዲስ ታሪፍ ልታስተዋውቅ መሆኑን ገልፃለች። አዲሱ ታሪፍ ህንድ የብረትና አሉሚኒየም ምርቶችን ወደ አሜሪካ በምትልክበት ወቅት ለጫነችባት ከፍተኛ ግብር ምላሽ ነው ተብሏል። አሜሪካ ግብሩን ዝቅ አድርጊ ብትባል በእምቢተኝነቷ ቀጥላለች። በዚህ ወር ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ ለህንድ በንግዱ ዘርፍ የምታደርግላትን የተለየ ጥቅማጥቅም እንደምታቆም ገልፀው ነበር። •ኢሳያስን ለመጣል'#ይበቃል' የተሰኘው የኤርትራውያን እንቅስቃሴ •ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት በምላሹም ህንድ እስከ 120% የሚደርስ ታሪፍ በአሜሪካ ምርቶች እንደሚጫን በባለፈው አመት ህንድ አስታውቃ የነበረ ቢሆንም በውይይቶች ምክንያት አተገባበሩ ዘግይቶ ነበር። በባለፈው አርብ ግን የህንድ የገንዘብ ሚኒስትር ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ሲባል ውሳኔው ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል። በአሜሪካና በህንድ ያለው የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት በባለፈው አመት 142 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን ይህም ከአስራ ሰባት አመት በፊት ከነበረው ቁጥር ጋር ሲወዳደር ሰባት እጥፍ ነው ተብሏል። ነገር ግን 5.6 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው የህንድ ወጪ ንግድ አሜሪካ ከቀረጥ ነፃ አድርጋላት የነበረ ሲሆን አሜሪካ ይህንን የንግድ ግንኙነት ማቆሟ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ተፅእኖ ሊያደርስ እንደሚችል ተንታኞች ይናገራሉ። •የትራምፕ እና የለንደኑ ከንቲባ ሳዲቅ ካህን እሰጣገባ የትራምፕ አስተዳደር ""ኢፍትሐዊ"" የንግድ ስርአትን ለማስተካከል በሚል እንቅስቃሴያቸው ነው እንዲህ አይነት የንግድ መጠቃቀም ግንኙነት እንዲቀሩ ያደረጉት። ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ ኃገራት ያለው የንግድ ግንኙነት የሻከረ ሲሆን በባለፈው አመትም ህንድ ለዚህ ምላሽ የሚሆን የታሪፍ ጫናን አስተዋውቃለች። ትራምፕ በበኩላቸው ህንድ ከኢራን ነዳጅ እንዲሁም ከሩሲያ ኤስ 400 ሚሳይል ለመግዛት የያዘችውን እቅድ የማታቆም ከሆነ ማእቀብ ይጣልባታል ሲሉ አስፈራርተዋል። •የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ልጆቻቸው 'ሞባይል' እንዳይጠቀሙ የሚያግዱት ለምን ይሆን? የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራሃማንያም ጃይሻንካርና አቻቸው ማይክ ፖምፔዮ ጃፓን በሚካሄደው የጂ-20 ጉባኤ ላይ የሚወያየዩ ሲሆን፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕና ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በቅርቡ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-48652222 +politics የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት፡ በወታደራዊው ኃይል ተቃውሞ ሦስት ሰዎች ተገደሉ "በሱዳን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን በመደገፍና ወታደራዊ ኃይሉን በመቃወም አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች በቀጥታ በተኮሱት ጥይትና አስለቃሽ ጭስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን የሐኪሞች ኮሚቴ አስታወቀ። ቅዳሜ ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ���ደ ሥልጣን እንዲመለሱ በዋና መዲናዋ ካርቱም እና በሌሎች ከተሞች አደባባይ በመውጣት ጠይቀዋል። የአገሪቷ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የጸጥታ ኃይሎች በቀጥታ በተቃዋሚዎች ላይ ተኩሰዋል መባሉን ሀሰት ነው ብሏል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ግን ሌሎች ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎችም ለጉዳት እንደተዳረጉ ተናግረዋል። መፈንቅለ መንግሥቱን የመሩት ጀነራል አብደል ፈታህ ቡርሃን የሲቪል አስተዳደሩን የበተኑት በዚህ ሳምንት ነበር። ጀነራሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጁ ሲሆን ""መፈንቅለ መንግሥቱን ያደረኩት በአገሪቷ የእርስ በርስ ጦርነትንና ፖለቲካዊ ሽኩቻን ለማስወገድ ነው"" ብለዋል። መፈንቅለ መንግሥቱ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ውግዘትን አስከትሏል። ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣን መቆጣጠሩን በመቃወም አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች የሱዳንን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ እንዲሁም ""ወታደራዊ አገዛዝ አንፈልግም"" በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል። በካርቱም 'የሬዚስታንስ' ኮሚቴ አባል የሆኑት ሻህን አል ሻህፍ ""ሰዎች ሰላማዊ ናቸው። ምንም እንኳን ከጸጥታ ኃይሎች ጥይት ቢተኮስባቸውም ተቃውሞው በሰላማዊ መንገድ ይቀጥላል"" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አሁን ላይ ጀነራል ቡርሃን ሁሉንም ደጋፊዎቹን እንዳጣ ተረድተናል ሲሉም ሻህን አክለዋል። "" ይህ አንድ ሰው ያካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ነው ። የሚደግፈው ማንም የለም"" ብለዋል ሻህን። ገለልተኛ የሆነው የሱዳን ሴንትራል ሐኪሞች ኮሚቴ በኦምዱርማን በተቃዋሚዎች ላይ በተተኮሰ ጥይት ተመትተው ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል። የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን በተቃዋሚዎች ላይ ጥይት ተተኩሷል መባሉን ሀሰት ነው ያለ ሲሆን የተወሰኑ ተቃዋሚዎች ፖሊስ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል ሲል ከሷል። በዚህ ሳምንት ብቻ በተቃዋሚዎችና በጸጥታ ኃይሎች መካከል በነበረ ግጭት ከ10 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። የሱዳን ባለሥልጣናት የኢንተርኔትና ሌሎች የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎቶችን ያቋረጡ ሲሆን የእንቅስቃሴ ገደብም ጥለዋል። እአአ 2019 አገሪቷን ለረዥም ዓመታት የመሩት ኦማር ሀሰን አል ባሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ባሳለፍነው ሰኞ መፈንቅለ መንግሥቱ እስከሚካሄድ ድረስ የሲቪልና ወታደራዊ ኃይሎች ሥልጣን በመጋራት ሱዳንን ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59066441 +politics በአገር ውስጥ ጉዳይ የተወጠሩት ባይደን ስብሰባ ለመሳተፍ አውሮፓ ገቡ "የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን 2.75 ትሪሊየን ዶላር የሃገር ውስጥ አጀንዳቸውን በዋሽንግተን በመተው ለሁለት ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች አውሮፓ ገብተዋል። ባይደን በዩናይትድ ኪንግደም የአየር ንብረት ኮንፈረንስ ላይ ለሌሎች የዓለም መሪዎች የአካባቢ ጥበቃ ዕቅዳቸውን ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል። የተሰሚነት ደረጃቸው እየቀነሰ የመጣው ባይደን፤ የስልጣን ዘመናቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ፕሬዚዳንቱ ራሳቸው ተናግረዋል ። ባይደን ለጂ20 ስብሰባ ዓርብ ጠዋት ሮም ደርሰዋል። በስብሰባው የዓለም ዝቅተኛ የግብር መጠን ዋነኛ አጀንዳ ይሆናል። ካቶሊክ የሆኑት ሁለተኛው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አርብ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋርም በቫቲካን ይገናኛሉ። ቀጥሎ እሁድ ምሽት ለተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት (COP26) ኮንፈረንስ ወደ ግላስጎው ስኮትላንድ ያመራሉ። ባይደን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት ከወጡ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመዋጋት ተመልሳለች የሚለውን መልዕክት ማስተላለፍ ይፈልጋሉ ። ባይደን ከዋይት ሃውስ ወደ ሮም ከማቅናታቸው በፊት ለወራት የውዝግብ ውጤት የሆነውን የወጪ ቅነሳ ዕቅድን ይፋ አድርገዋል። የዩናይትድ ���ቴትስ ዲሞክራሲ አሁንም እንደሚሠራ በሁለቱ ጉባኤዎች ወቅት ማረጋገጥ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ""የተቀረው ዓለም መስራት እንችል እንደሆነ ይጠራጠራል"" ማለታቸው አንድ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የባይደን የወጪ ዕቅዱ ምን ይዟል? 555 ቢሊዮን ዶላር፡ ታዳሽ ኃይልን ለሚጠቀሙ እና ዝቅተኛ ልቀትን ለሚያመነጬ በግብር ማበረታቻ መስጠት። 400 ቢሊዮን ዶላር፡ ለሦስት እና አራት ዓመት ህጻናት ነጻ ትምህርት። 150 ቢሊዮን ዶላር፡ አንድ ሚሊዮን ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ባይደን በአንድ ትሪሊየን ዶላር የመሠረተ ልማት ፓኬጅ ዙሪያ ዲሞክራቶችን ለማሰባሰብ መጀመሪያ እየሞከሩ ነው። ይህም ቀደም ብሎ በሴኔቱ ጸድቋል ። አረንጓዴው ወጪ በ2030 የአሜሪካን የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀትን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ፣ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አዲስ የግብር እፎይታ ለመስጠት እና በአሜሪካ ቤቶች ላይ የፀሐይ ፓነሎች መትከልን አቅዷል። በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬ ያላቸው አካላት ሕጉን በጽሁፍ ለማየትም በመጠየቃቸው የተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ ዕለት 1,684 ገጾች ያሉትን ሰነድ ይፋ አድርጓል። ምክር ቤቱ በመሠረተ ልማት ረቂቅ ህግ ላይ እስከሚቀጥለው ሳምንት ድረስ ድምጽ አይሰጥም። ባይደን ረቡዕ ወደ ዋሽንግተን የሚመለሱ ይሆናል። የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ አሁንም ቢሆን ባይደን ከሮም በስልክ ሕግ አውጭውን ለማግባባት ሊሞክሩ ይችላሉ ብለዋል ። እንደ ሪልክሊርፖሊቲክስ ከሆነ የፕሬዝዳንቱ የሥራ ተቀባይነት ደረጃ አማካይ ወደ 42.5 በመቶ ዝቅ ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/59074461 +business በዓመት 2ሚሊዮን ብር የሚያስከፍለው ትምህርት ቤት ጥቁሮችን ይቅርታ ጠየቀ "የኢትን ትምህርት ቤት በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኝና በትምህርት ጥራቱ የገነነ ሥመ ጥር እንዲሁም ውድ ትምህርት ቤት ነው፡፡ በዚህ ትምህርት ቤት የአሁኑን ጠቅላይ ሚኒትር ቦሪስ ጆንሰንን ጨምሮ ንጉሣዊያን ቤተሰቦችና ሌሎች ሥመ ጥር ፖለቲከኞች ተምረውበታል፡፡ የዚህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ታዲያ ለመጀመርያው የትምህርት ቤቱ ጥቁር ተማሪ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ናይጄሪያዊው ደራሲ ዲሊቤ ኦኒያማ ከኢትን ኮሌጅ ለመመረቅ የመጀመርያው ጥቁር ነው፡፡ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና (ማትሪክ) የወሰደው እንደ አውሮፓዊያኑ በ1969 ዓ. ም ነበር፡፡ በኢትን ኮሌጅ ተማሪ ሳለ ይደርስበት የነበረው ዘረኝነት በተመለከተ መጽሐፍ ጽፎ አሳትሞ ነበር፡፡ ይህን በማድረጉም ትምህርት ቤቱ ‹‹እኔ ዘንድ ዝር እንዳትል›› በሚል ለረዥም ዘመን አግዶት ቆይቷል፡፡ የዚህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ሳይመን ሄንደርሰን ""ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ነገሮች ከዚያ በኋላ ተሻሽለዋል፡፡ ነገር ግን ብዙ ይቀረናል"" ብለዋል፡፡ ‹‹ከኛ ትምህርት ቤት የወጡ ጥቁሮች ተማሪ ሳሉ በዘረኝነት ችግር ይደርስባቸው እንደነበር ይጠቅሳሉ፡፡ ይህን መቀበልና ማሻሻል ይኖርብናል፡፡›› ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡ የዚህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ዲሊቤ ኦኒያማንም ቢሆን ይቅርታ መጠየቅ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ‹‹በአካል አግኝቼው ወደ ተማረበት ትምህርት ቤት ጋብዤው ይቅርታ ማለት እፈልጋለሁ ብለዋል የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ለቢቢሲ። ዝነኛው ደራሲ ኦኒይማን ለቢቢሲ እንደተናገረው ‹‹አሁን እሱን ይቅርታ መጠየቅ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ስለ ኢተን ያለኝ አመለካከትንም አይቀይረውም፡፡›› ብለዋል፡፡ ናይጄሪያዊው ደራሲ በየቀኑ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ዘረኝነትን ያስተናግድ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግሯል፡፡ ‹‹ለምንድነው ጥቁር የሆንከው፣ ጸጉርህ ውስጥ ምን ያህል ዝንብና ቅማል ነው ያለው? እናትህ ለመሆኑ አፍንጫዋ ውስጥ አጥንት አለ?›› ይሉኝ ነበር ሲል ይደርስበት የነበረውን ዘረኝነት ጠቅሷል፡፡ ኦኒያማን በትምህርቱ ደከም ሲል ወይም በስፖርት የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግብ መምህራኑ ‹‹ይህ በዘሩ ምክንያት የመጣ ነው›› ይሉት እንደነበር ያስታውሳል፡፡ በትምህርቱ ጥሩ ውጤት ባመጣ ጊዜ ደግሞ ‹‹እንዴት ጥቁር ሆነው እንዲህ አይነት ውጤት አገኘህ፤ ኮርጀህ መሆን አለበት›› ይሉታል፡፡ ትምህርት ቤቱን ከለቀቀ በኋላ በዚያ ትምህርት ቤት የገጠመውን ሁሉ ጽፎ በማሳተሙ ነበር በ1972 ትምህርት ቤቱ ደብዳቤ የላከለት፡፡ መጽሐፍ በመጻፉም መቼም ቢሆን የተማረበትን ትምህርት ቤት ዳግም መጎብኘት እንደማይችል የሚገልጽ ደብዳቤ ነበር የተላከለት፡፡ አሁን የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ይቅርታ ያሉት የጆርጅ ፍሎይድን በነጭ ፖሊስ ግድያ ተከትሎ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ ከተቀጣጠለ በኋላ ነው፡፡ በእንግሊዝ ባለፉት ሳምንታት ሁለት ግዙፍ ኩባንያዎች በተመሳሳይ ጥቁሮችን ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ ባሪያ ያመላልሱ ለነበሩ የመርከብ ድርጅቶች የመድን ዋስትና ይሰጥ የነበረው ሎይድስ ኦፍ ሎንደን ኩባንያ በባሪያ ንግድ ላይ ለነበረው ሚና ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፣ ቢራ ጠማቂው ግሪን ኪንግ የኩባንያው መስራች ድሮ በካሪቢያን በባሪያዎች ጉልበት ላይ ላደረሰው መከራ ይቅርታ ጠይቋል፡፡. ኢተን ትምህርት ቤት በንጉሥ ሄነሪ ስድስተኛ የተመሰረተ ሲሆን ይህም እንደ አውሮፓዊያኑ በ1440 የሆነ ነው፡፡ በኢተን የትምህርት ጥራት የላቀ ሲሆን አሁን እዚያ ለመማር በዓመት 50ሺህ ዶላር ክፍያን ይጠይቃል፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-53148768 +sports ደራርቱ ቱሉ፡ ከ30 ዓመት በፊት ለአፍሪካ ሴቶች የተተከለ የድል ችቦ ደራርቱ ቱሉ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ነግሳ ከቆየች ድፍን 30 ዓመታት ተቆጠሩ። ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ገብታ መኖር የጀመረችው የባርሴሎና ኦሊምፒክን ተከትሎ ነው። በባርሴሎና ደግሞ ለእርሷ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያንም ፈር የቀደደ ድል ነበር ያስመዘገበችው። ሳቂታዋ ደራርቱ በሩጫው ሜዳ ብቻ ሳይሆን በስፖርት አስተዳደርም ስሟ በበጎ ይነሳል። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት፣ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ በምክት ፕሬዝዳንትነት እና በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንግረስ ደግሞ ኢትዮጵያን ወክላ የምክር ቤቱ አባል የሆነችው ደራርቱ ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቃለ ምልልስ ባርሴሎናን አስታውሳለች። ሩጫ እንዴት ጀመርሽ? ሩጫ የጀመርኩት በቆጂ  ትምህርት ቤት እያለሁ ነው። ሩጫ እወድ ነበር። እረኛም ስለሆንኩኝ ከብትም ለመመለስ ስሄድ፣ ውሃም ስቀዳ፣ ጎረቤትም ስላክ ገበያም ስላክ ሁሌ በሩጫ ነው። ውሃ ስቀዳ ትንሿን ገንቦዬን ተሸክሜ እሮጥ ነበር። ከሩጫ ጎን ለጎን ደግሞ ፈረስ መጋለብ እወድ ነበር። ትምህርት ቤት ውስጥ ሩጫ የጀመርኩት በ15 ዓመቴ ነበር። ሩጫ እና ፈረስ ግልቢያ የኔ መዝናኛዎች ናቸው። በሩጫ እታወቃለሁ ብዬ ሳይሆን እንዲሁ ስለምወድ ነበር የምሮጠው። እግዚአብሔር ፈቅዶ ደግሞ እንጀራዬ አደረገው። በሩጫ ለመጀመርያ ግዜ መወዳደር የጀመርሽው የት ነው? ለምን? ሩጫን የጀመርኩት አርሲ ውስጥ በትንሿ በቆጂ ከተማ በትምህርት ቤቴ ነው። በትምህርት ቤት ውስጥ ለስፖርት ክፍለ ጊዜ፣ ለማርክ ሲባል የተለያዩ ስፖርቶችን እንሰራ እና እንጫወት ነበር። በዚያውም በውድድሮች ላይ መሳተፍ ጀመርኩኝ። ለትምህርት ቤት፣ ለወረዳ፣ ለአውራጃ ከዚያ ለክፍለ አገር ለመወዳደር በቃሁ። እኤአ በ1992 ኦሊምፒክ ላይ ስትሳተፊ ምን ተሰማሽ? እስካሁንም ድረስ ለባርሴሎና ኦሊምፒክ ያለኝ ስሜት ትልቅ ነው። ምክንያቱም እስካሁንም ከአገሬ ሕዝብ እንዲሁም ከዓለም ማኅበረሰብ ጋር ያስተዋወቀኝ ውድድር ነው። ከእኔ መታወቅ፣ ከእኔ ደስታ በላይ ደግሞ በባርሴሎና ኦሊምፒክ ላይ የእኔ ማሸነፍ ለኢትዮጵያ ሴቶች በር ከፋች በመሆኑ በጣም ደስ ይለኛል። ሁልጊዜም የምደሰትበት ነው። ለካ ሴቶችም ከሰሩ፣ ወደ ስፖርቱ መድረክ ከመጡ በእንደዚህ ዓይነት የአደባባይ ውድድሮች ላይ ማሸነፍ ይችላሉ ብለው የኢትዯጵያ ሴት አትሌቶች ተነሱ። በዚያ ነው እስካሁን ድረስ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ሴቶች የበረከቱት። ስለዚህ የባርሴሎና ድል ለእኔ ሁለት ስሜት፣ ሁለት ደስታ አለው። ባርሴሎና ላይ በወቅቱ ስትሳተፊ አሸንፋለሁ የሚል የራስ መተማመን ነበረሽ? እንዲህ ዓይነት ዝግጁነት ነበረሽ? ከዚያ በፊት በተወሰኑ ውድድሮች ላይ ተሳትፌአለሁ። ኦሊምፒክ ግን የመጀመሪያዬ ነበር። ባርሴሎናን እንደ ማንኛውም ውድድር ነበር ያየሁት። ምክንያቱም በዚያን ወቅት ኦሊምፒክ ከሌሎች ውድድሮች ምን ያህል እንደሚለይ ለይቼ ስለማላውቅ እንደማንኛውም ውድድር ነበር ያየሁት። ነገር ግን የውድድሩን ትልቅነት የሚያውቁት፣ ዓለም አቀፍ ልምድ ያላቸው አሰልጣኜ አስፈላጊውን ልምምድ አድርገን በከፍተኛ ሁኔታ ነበር ያዘጋጁን። በወቅቱ ምንም ዓይነት የፍርሃት ስሜት አልነበረኝም፤ ምክንያቱም በእድሜ ልጅ ነበርኩ። የመጀመሪያዬ የኦሊሎምፒክ ውድድርም ስለሆነ መሸነፍና ማሸነፉ ብዙም አላስጨነቀኝም። ግን ጥሩ አቋም ላይ ነበርኩኝ። ከዚያ ውድድር በፊት ጃፓን ቶኪዮ ላይ ተወዳድሬ ነበር ስምንተኛ ነበር የወጣሁት። ስለዚህ ባርሴሎና ላይ እንደ ቶኪዮው መጨረሻ ላይ ሄደሽ እንዳትቆሚ ከፊት ከሚሄዱት ጋር እግር በእግር እየተከተልሽ ሂጂ ተብዬ ነበር። በወቅቱ 10 ሺህ ማጣሪያ ነበረው። እዚያ ላይ ፉክክሩን ስታዬ ምን ነበር ስሜትሽ? ጥሩ አቋም ላይ ስለነበርኩኝ፣ ጥሩ ስለተዘጋጀሁኝ ማጣሪያውም ፍጻሜውም አልከበደኝም። አሰልጣኜ በቂ ልምምድ እና ዝግጅት እንድሰራ በማድጋቸው ብዙ አልተቸገርኩም። ሌላው ደግሞ አብረውን የሚወዳደሩትን ብዙዎቹን አላውቃቸውም ነበር። እኔ የማውቀው ሁለት አትሌቶችን ብቻ ነበር። ሌሎቹን አላውቃቸውም። እናም ብዙ አልከበደኝም። በወቅቱ በተካሄዱት የማጣሪያ እና የፍጻሜ ውድድር መካከል ምን ታደርጊ በር? (ሳቅ) አሰልጣኜ ዓለም አቀፍ አሰልጣኝ ናቸው። እርሳቸው ከውድድር በፊት ምን እንደምንሰራ፣ በውድድር መካከል ደግሞ ምን እንደምናደርግ ያውቃሉ። የረዥም ጊዜ ውድድር ፕሮግራም ምን እነደሆነ፣ በዚያ መካከል ደግሞ በማጣሪያ እና በፍጻሜ መካከል ደግሞ ያለውን ስለሚያውቁ እርሳቸው የሚሰጡንን ልምምድ ነበር የምንሰራው። እንግዲህ አሁን ብዙ አላስታውስም ግን እርሳቸው የሚሰጡንን ስሰራ ደስተኛ ሆኜ ነበር የምሰራው። ግን ከማጣሪያው በኋላ ለፍጻሜውም አልተጨናነኩም ነበር። ከውድድር በፊት የምታደርጊው የተለየ ነገር አለ? ሌላ ጊዜ አንደማደርገው ልምምዴን ከቁርስ በፊት ወይንም ደግሞ በኋላ ልሰራ እችላለሁ። ከሰራሁም በኋላ ደግሞ እተኛለሁ። ስለዚህ እበላለሁ፣ እጠጣለሁ፣ ከዚያ ደግሞ አርፋለሁ። ከዚያ ውጪ የተለመደው ምግብ፣ የተለመደው እረፍት፣ የተለመደውን ልምምድ ነው ያደረግኩት። ማታ ራሱ ማሟሟቂያ ሰዓቴ እስኪደረስ ድረስ ስታዲየም ውስጥ መተኛቴ ትዝ እለኛል። ማማሟቂያ ሜዳ ላይ በጣም ጥሩ እንቅልፍ መተኛቴ ትዝ ይለኛል። ትዝ ይለኛል አሰልጣኜ ነበረ የቀሰቀሱኝ። ብዙ ነገር ስለባርሴሎና ይረሳኛል ይህ ግን አይረሳኝም። ስለ ፍጻሜው ውድድር ትዝ የሚልሽ ነገር ምንድን ነው? ሳስብ የነበረው አሰልጣኜ ልክ የቶኪዮው ዓይነት ነገር እንዳይገጥመኝ የመከሩኝን ነበር። እሱም ተጠንቅቀሽ ሩጪ፣ ከከበደሽ በራስሸ ጊዜ ሩጪ፣ እንዳትደነዝዢ ነበር ያሉኝ። እርሳቸውም እነዳሉኝ፣ ቀስ ��ያልኩ ነበር ዙሩን የሄድኩት። ምክንያቱም እርሳቸው ልጆቹ ፈጥነው የሚሄዱብሽ ከሆነ ራስሽን ጠብቀሽ ሂጂ ብለውኝ ነበር። ደቡብ አፍሪካዊቷ ኤለና ሜየር አስር ዙር ሲቀር ነበር የሄደችው እና እኔ ቀረት ብዬ ቀስ ብዬ ነበር የደረስኩባት። ምክንያቱም እኔ አሰልጣኜን በጣም አከብራለሁ። በጣም እወዳቸዋለሁ። የሚሉኝንም ስለምሰማ እና ቃላቸውን ስለማከብር እርሳቸው የመከሩኝን ነበር እያሰብኩ ስሮጥ የነበረው። ከሦስት፣ ከአራት ዙር በኋላ ነበር የደረስኩባቸው። ልክ አሰልጣኜ የመከሩኝን ነበረ የማደርገው። ስታሸንፊ ምን ተሰማሽ? በወቅቱ የስፔኗ ባርሴሎና በጣም ሞቃት ነበረች፣ በዚያ ሙቀት ቲሸርት ደርቤ ነበር ስሮጥ የነበረው። ነገር ግን አቋሜ ጥሩ ነበረ። ልክ 400 ሜትር ሲቀር እንደምወጣ እና በአጨራረስ እንደማሸንፋቸው ነበር የማስበው እና ጥሩ ስሜት ነበር የተሰማኝ። ደስታውም ወደር አልነበረውም። ውድድሩን በአሸናፊነት ካጠናቀቅሽ በኋላ ከኤላና ሜየር ጋር ደስታችሁን በጋራ ነበር የገለጻችሁት፤ ለምን? ይሄማ ሁል ጊዜ የሚደረግ ነገር ነው። ምክንያቱም አሸንፈን ሁለታችንም አንደኛ እና ሁለተኛ ነው የወጣነው። አንደኛው ሁለታችንም ከአፍሪካ ነበርን። ሁለተኛው ደግሞ አፓርታይድ ያበቃበት ወቅት ነበር። ደቡበን አፍሪካውያን በዚያን ጊዜ ከአፓርታይድ ሥርዓት ማብቃት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ኦሊምፒክ ስለነበር በጋራ ደስታችንን ገለጽን። ከኤሌና ጋር ባንተዋወቅም እንግዲህ ስፖርት ለእህትማማችንት፣ ለሰላም፣ ለፍቅር የሚለው እዚያ ሜዳ ላይ ታየ ማለት ነው። በዚህ ምክንያት ነበር ደስታችንን ነው የገለጽነው ማለት ነው። ከድል በኋላ በአገር ቤት የነበረው አቀባበል ምን ይመስል ነበር? (ሳቅ) በጣም የተለየ ነበር። በጣም በጣም የተለየ እና እስከዛሬም ድረስ ልዩ ስሜት የሚፈጥርብኝ አቀባበል ነበር። ቤተሰቤ፣ ፌዴሬሽናችን፣ አገራችን፣ መሥሪያ ቤቴ (ማረሚያ ቤቶች)፣ ጓደኞቼ ሁሉም በአጠቃላይ እንደ አገር ጀግና ነበር የተቀበሉኝ። እና ሁሌም በጣም በጣም ሁሌም የማይረሳ አቀባበል ነው ያደረጉልኝ። በጣም ነበር ደስ ያለኝ። በተጨማሪም እኔ ወታደር ስለሆንኩ ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ ያገኘሁበትም ነው። በወቅቱ ከፍተኛ ገንዘብ የተሸለምኩበት፣ እንደገና ደግሞ በአገሬ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያወቀኝ፣ እና ብቻ ለእኔ ልዩ ነበር ያ ጊዜ። አሸናፊነትሽ ጥሎ ያለፈው ነገር ምንድን ነው? እንዴት እታወሳለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ? (ሳቅ) እንግዲህ ጥሎ ያለፈው እንደገለጽኩት ከሕዝበ ጋር ያስተዋወቀኝ ይህ የባርሴሎና ድል ነው። ሁለተኛ ደግሞ የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ምሳሌ መሆኔ የእኔ ውርስ [ሌጋሲ] ነው ብዬ አስባለሁ። የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሴት የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ በመሆንሽ እና ለአገርሽ እና ለአፍሪካ ፈር ቀዳጅ የሆነውን ውጤት ማስመዝገብሽ ምን ስሜት ፈጥሮብሽ ነበር? (ሳቅ) እንግዲህ ባርሴሎና የመጀመሪያዬ ይሁን አንጂ ብዙ ውድድሮችን አድርጌያለሁ። ከአገር አቋራጭ ጀመሮ የተለያዩ ውድድሮችን አሸንፌያለሁ። ብዙ የተለየ ነገር አይሰማኝም። እንዲያውም ምንድን ነው አሁን ከአትሌትነት ወጥቼ ወደ ስፖርት አመራርነት ስመጣ እና በቅርቡ ደግሞ ከአሜሪካ ኦሪገን በድል ስንመለስ ልክ የባርሴሎናው እና የሲድኒው ጊዜ ድል ነው ትዝ ያለኝ። በሩጫ ዘመኔ እንደዚህ ዓይነት አቀባበል ሲደረግ ማየቴ በጣም ነው ያስደሰተኝ። ምከንያቱም አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ነው እንደዚህ ዓይነት ዕድል የሚሰጠው። እኔ ያሳለፍኩባቸው ጊዜያት ወርቃማ ናቸው። ምክንያቱም ያለውንም ጊዜ በደንብ ነበር የተጠቀምኩበት። በጣም ነው ደስ የሚለኝ። በጣም በጣም ወርቃማ ጊዜያት ነበሩ። ���እኔም ለቤተሰቤም ልዩ ጊዜ ነበር። የዛሬ 30 ዓመትን ዛሬ ላይ ቆሜ ሳስታውሰው በጣም ደስ ይለኛል። ሦስት የቤተሰቦችሽ አባልም በሩጫው ዘርፍ ውጤታማ አትሌቶች ናቸው። ቤተሰቦችሽ በሩጫው ውጤታማ የመሆናቸው ሚስጥሩ ምንድን ነው? (ረዥም ሳቅ) ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ምንም የተለየ ምስጢር የለውም። አንዱ ደግሞ ወደዚህ እስከመጣሁ ድረስ እኔ በጣም ሥራዬን አክባሪ ነኝ። ታታሪ ነኝ። የሚጠበቅብኝን በሚገባ እሰራለሁ። ልምምዴን በደንብ እሰራለሁ። አንድ ሰው ሥራው በእግዚአብሔር እንዲባረክልት በተቻለ መጠን መልፋት፣ መጣር አለበት። ከዚያ ደግሞ ባለው ዕምነት እግዚአብሔር ጥረቱን እንዲባርክለት ፀሎት ማድረግ አለበት። ዋናው ጠንክሮ መስራት፣ መታገስ፣ ለሥራ ያለን ፍቅር ማሳየት ነው። ይኸው ነው ሌላ የተለየ ነገር የለውም። የስፖርት ቡድንን ለመቀላቀል ብለሽ ለእናትሽ ሳትናገሪ መሄድሽ እውነት ነው? ከዛሬ 35 ዓመት በፊት እኔ ሩጫ ስጀምር አገር ቤት የነበረው አመለካከት፣ ሴት ልጅ ረዥም ቀሚስ ለብሳ፣ በሥነ ሥርዓት ትምህርቷን ተምራ፣ ትዳርም የምትይዝ ከሆነ በሥርዓቱ ተድራ ቤተሰብ ትመሠርታለች እንጂ በቁምጣ መታየት ነውር ነው። ስለዚህ እናቴም እንደ አንድ እናት ጥሩ ልጅ ሆኜ፣ ጨዋ ልጅ ሆኜ እንዳድግ ትፈልጋለች። ስለዚህ በዚያ ጊዜ ከወንድ ጋር መሮጥ፣ በቁምጣ መሮጥ፣ እንደ ባለጌ ልጅ፣ ሥነ ምግባር እንደ ሌላት ልጅ ያስቆጥራል። ስለዚህ ለእናቴ ፍላጎቴን ብነግራት ስለማትፈቅድልኝ ለአባቴ እና ለእህቶቼ፣ ለአክስቶቼ ነግሬ ነበር የመጣሁት። በዚያው ወቅት ባርሴሎና ከሩጫ ሜዳው ውጪ ምን ተሰማሽ? ከተማውን ጎበኘሽ? (ሳቅ) በዚያ ወቅት ምንም አላየሁም። ምክንያቱም ሁልጊዜ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች፣ አሁንም ድረስ የምናደርገው የግል ውድድር ካልሆነ በስተቀር፣ አገር ወክለን ስንሄድ ውድድራችን እና ልምምዳችን ላይ ነው የምናተኩረው። ውድድር የጨረሰ ውድድር ያልጨረሰውን መደገፍ ማበረታታት እንጂ እንደዚህ ከተማ የመዞር፣ ገበያ የመሄድ ብዙም ልምድ የለንም። እስከዛሬ ድረስም የኢትዮጵያን አትሌቶች፣ አንዱ የማመሰግንበት ነገር ይሄ ነው። ስለዚህም የዚያን ጊዜ ባርሴሎናን ተዘዋውሬ አላየኋትም። ነገር ግን የማስታውሰው ልምምድ በምሰራበት ወቅት፣ የልምምድ ስታዲየም መኖሩ፣ ምግብ ቤቶቹ 24 ሰዓት ክፍት መሆናቸው እርሱ እርሱ ለእኔ ይገርመኝ ነበር። የሚስተናገደው ሰው ብዛት ይገርመኝ ነበር። በቁርስ ሰዓት፣ በምሳ ሰዓት በእራት ሰዓት ሰዉ አይቀንስም እና ወጪ ወራጁ መብዛቱ ይገርመኝ ነበር። በወቅቱ ከተማዋን ተዘዋውሬ ባላያትም የባርሴሎና ኦሊምፒክ ለእኔ አሁንም ድረስ የተለየ ነው። ከባርሴሎና በኋላ ከኤለና ሜየር ጋር ግንኙነታችሁ ቀጥሏል? እርሷ ናት ከእኔ ቀድማ ሩጫ ያቆመችው። ሩጫ እስክታቆም ድረስ እንገናኝ ነበር። ከዚያ በኋላ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ በአጋጣሚ እንገናኝ ነበር። የደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክተሬት ሲሰጠኝ የክብር እንግዳ ሆና መጥታ ተገናኝተናል። ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኘነው ያኔ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c891j8lrn81o +politics ባይደን እና ፑቲን በዩክሬን ጉዳይ 'ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ' ፍለጋ ሊወያዩ ነው "የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዩክሬን ያለውን ውጥረት ለማርገብ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዚህ ወር ለሁለተኛ ጊዜ ሊወያዩ ነው። መሪዎቹ ሐሙስ ዕለት በስልክ ይነጋገራሉ ተብሏል። እንደዋይት ሐውስ ባለሥልጣን ከሆነ ፕሬዝዳንቶቹ በአገሮቹ መካከል በቀጣይ ስለሚደረጉ የፀጥታ ውይይቶች እና በአውሮፓ ባለው ሁኔታ ላይ ይወያያሉ። ከዩክሬን ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ ጦር ያሰፈረችው ሩሲያ አገሪቱ�� ለመውረር አላቀድኩም ስትል አስተባብላለች። ሩሲያ ወታደሮቿ በቦታው ለልምምድ መገኘታቸውን ጠቅሳ ጦሯን በአገሯ በነጻነት የማንቀሳቀስ መብት እንዳላት ተናግራለች። ለጉዳዩ የጋራ ምላሽን ለመስጠት ከሐሙሱ ውይይት በፊት አሜሪካ፣ የአውሮፓ መሪዎችን አማክራለች ሲል የዋይት ሐውስ መግለጫ አስታውቋል። የዩክሬን የደኅንነት ባለሥልጣናት ከ100 ሺህ የሚበልጡ የሩሲያ ወታደሮች ወደሚጋሩት ድንበር መላካቸውን ገልጸዋል። ዩክሬን ጥቃት ከደረሰባት ፑቲንን ""አይተውት የማያውቁት"" ማዕቀብ እንደሚጠብቃቸው አሜሪካ ዝታለች። አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደገለጹት ባይደን ለሩሲያ አቻው ""ዲፕሎማሲያዊ መንገድ"" የሚያቀርቡ ቢሆንም በድንበር ላይ ያለው የሩሲያ ጦር መጠናከር ""በጣም ያሳስባቸዋል"" ብለዋል። ሩሲያ ""ዩክሬን ላይ ተጨማሪ ወረራ"" ከፈጸመች አሜሪካ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ባይደን ለፑቲንን ይነግራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪን ጋር ረቡዕ ዕለት ተነጋግረዋል። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ እንዳሉት ብሊንከን ""ሩሲያ በዩክሬን ድንበሮች ላይ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ዩናይትድ ስቴትስ በመቃወም ለዩክሬን ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ያላትን የማይናወጥ ድጋፍ በድጋሚ ገልጸዋል።"" በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች በስልክ ባደረጉት ውይይት ባይደን ለዩክሬን ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ድጋፋቸውን ገልጸዋል። ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ባትሆንም ከሕብረቱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላት። ሩሲያ በበኩሏ ኔቶ ወደ ምሥራቅ እንደማይንቀሳቀስ እና የጦር መሳሪያ ዩክሬንን ጨምሮ ወደ የትኛውም የጎረቤት አገር እንደማይላክ በሕጋዊ መንገድ ዋስትና እንደምትፈልግ ተናግራለች። የኔቶ ዋና ፀሐፊ የንስ ስቶልተንበርግ በበኩላቸው የዩክሬን የሕብረቱ አባልነት የኔቶ እና የኪየቭ ጉዳይ ነው ሲሉ አበክረው ገልጸዋል። ""ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ማንኛውም ውይይት የአውሮፓ ደኅንነት የተመሰረተባቸውን ዋና መርሆች በማክበር መሆን አለበት"" ሲሉ ቀደም ብለው ተናግረዋል። የሊቱዌኒያው ፕሬዝዳንት ጊታናስ ናውሴዳ ደግሞ አሁን ያለውን ሁኔታ ምናልባትም ""በ30 ዓመታት ውስጥ ከታዩት እጅግ አደገኛው"" ሲሉ ገልጸውታል። የሩሲያ ባለሥልጣናት በአውሮፓውያኑ ጥር 10 ከአሜሪካ አቻዎቻቸው ጋር በጄኔቫ ሊገናኙ ቀጠሮ ይዘዋል። በዕለቱ ከፑቲን ጋር ይገናኙ እንደሆነ የተጠየቁት ባይደን ""እስቲ እናያለን"" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ሆኖም በጄኔቫ በሚደረገው ድርድር ላይ ይገኛሉ ተብሎ አይጠበቅም።" https://www.bbc.com/amharic/news-59825257 +business በሩሲያዊው አሌክሴ መታሰር ምክንያት የ11 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ሊቋረጥ ይችላል ተባለ "ሩሲያና አውሮፓን የሚያስተሳስረው ንግድ በዋዛ የሚታይ አይደለም። አውሮፓ 40 ከመቶ ጋዝ የምታገኘው ከሩሲያ ነው። አሁን ደግሞ እጅግ ግዙፉ የጋዝ ማስተላለፍያ ቧንቧ ከሩሲያዋ ኪንጊሴፐን እስከ ግራስዋልድ ጀርመን ድረስ የሚዘረጋ ነው። ይህ ፕሮጀክት በርካታ አገራትን የሚያቋርጥና በባልቲክ ባህር ስምጥ ተቀብሮ የሚያልፍ ውስብስብ ፕሮጀክት ነው። ፕሮጀክቱ ጀርመንን የሩሲያ የኢኮኖሚ እስረኛ ሊያደርጋት ይችላል የሚለው ስጋት ገና ከፕሮጀክቱ መጠንሰስ ጀምሮ ሲነገር የነበረ ነው። አሁን ደግሞ ጀርመንና ሩሲያ በአሌክሴ ናቫልንሊ ጉዳይ እየተነታረኩ ነው የሚገኙት። በርካታ አገራት ጀርመን በሩሲያ ላይ ማዕቀብ እንደትጥል እየገፏፏት ይገኛሉ። በተለይም ከሩሲያ እስከ ጀርመን እየተዘረጋ ያለውን ዘመናዊ የጋዝ ማስተላለፍያ ቧንቧ ሥራ እንዲቋረጥ እንድታደርግ ነው በዋናነት ግፊቱ እየበረታ ያለው። ""ኖርድ ስትሪም 2"" የሚል ስም የተሰጠው ይህ ፕሮጀክት በአውሮፓ እጅግ ግዙፍ ከሆኑት ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ ነው። በአውሮፓ ኅብረት የፓርላማ አባላት፣ አባል አገራት በሩሲያ ላይ ማናቸውን ዓይነት ማዕቀብ በመጣል ጫና እንዲፈጥሩ ጥሪ አድርገዋል። አሌክሴ ናቫልኒ በሩሲያ ከተመረዘ በኋላ በጀርመን ሕክምና አድርጎ ወደ አገሩ ሲመለስ በፕሬዚዳንት ፑቲን ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ እስር ቤት መወሰዱ አይዘነጋም። አሜሪካ በዚህ የጋዝ ማስተላለፍያ ቧንቧ ፕሮጀክት ላይ ቀደም ብላ ማዕቀብ ጥላለች። ማዕቀቡ የተጣለው ቧንቧዎቹን እየቀበረ ባለው የሩሲያ ግዙፍ መርከብ ላይ ነው። አሜሪካ በተደጋጋሚ እንደምትለው ይህ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ሩሲያ በአውሮፓ ላይ የሚኖራትን ተጽእኖ ፈጣሪነት በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። የአሜሪካ ግምጃ ቤት ማዕቀብ የጣለባት የሩሲያ መርከብ ፎርቹና የምትባለዋ ስትሆን ይህ ማዕቀብ የተጣለው ትራምፕ ሥልጣን ሊለቁ በነበሩባቸው የመጨረሻ ቀናት ነው። ሆኖም ይህን ማዕቀብ ጆ ባይደንም የሚደግፉት እንጂ የሚቀለብሱት አይሆንም ተብሏል። የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ስምምነት ለአውሮፓ መጥፎ ስምምነት ነው ሲሉም ነበር። በቅርቡ ሥልጣን የሚለቁት የጀመርኗ መራሂት መንግሥት አንጌላ መርከል በማዕቀቡ ጉዳይ ተጠይቀው ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ፕሮጀክቱ ሩሲያ ለጀርመን የምትልከውን የጋዝ መጠን በእጥፍ እንደሚጨምር እጅግ ቁልፍ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸው ሆኖም መንግሥታቸው ጉዳዩን ከባይደን አስተዳደር ጋር እንደሚመክርበት ተናግረዋል። ይህን የጋዝ ማስተላለፍያ ቧንቧ 2ሺህ 460 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን 94 ከመቶ ተጠናቋል። ሥራው በ2019 መጨረሻ ላይ ለአንድ ዓመት የቆመው በአሜሪካ ማዕቀብ የተነሳ ነበር። ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ ዋናው የቧንቧዎቹን መቅበር ሥራ የሚሰራው ኩባንያ ሥራውን ለማቆም ተገዶ ነበር። ባለፈው ወር ግን ፎርቹና መርከብ በጀርመን የውሀ አካል ሥር የመቅበሩን ሥራ ጨርሳ በዴንማርክ ውስጥ ሥራውን ለመቀጠል በዝጅግጀት ላየዕ ነበረች። ሆኖም ማዕቀቡ ሥራውን እንዲቆም አስደርጓታል። አሁን ፎርቹና መርከብ በባልቲክ ባህር ላይ ነው የምትገኘው። የ44 ዓመቱ የፑቲን ተቺ አሌክሴ ናቫልኒ ኖቪቾክ በሚባል የነርቭ መርዝ ከተመረዘ በኋላ ሕይወቱ በተአምር የተረፈችው የጀርመን ሐኪሞች ባደረጉለት ርብርብ ነው። ሆኖም ማገገሙን ተከትሎ ወደ እናት አገሩ ሩሲያ በድፍረት ለመመለስ መወሰኑ ብዙዎችን አስደንቋል። በርካታ ጋዜጠኞች እሱ በተሳፈረባት አውሮፕላን አብረውት ወደ ሩሲያ የተጓዙ ሲሆን እንደተፈራውም ከበርሊን ሩሲያ እንደገባ በቁጥጥር ሥር ውሏል። የሱን መታሰር ተከትሎ በርካታ አገራት ቁጣቸውን በሩሲያ ላይ ሰንዝረዋል። የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ የአሌክሴ መታሰር በጀርመንና በሩሲያ መካከል ችግር የሚፈጥር ነው ካሉ በኋላ በዚህ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት ላይም የራሱ አሉታዊ ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል ጠቁመው ነበር። በዚህ ሳምንት ሃይኮ ማስ ወደ ዋሺንግተን ተጉዘው አቻቸውን አንቶኒ ብሊንከንን ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55761773 +politics በሊባኖስ ጉዳት ባደረሰው ፍንዳታ የተቆጡ ተቃዋሚዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ መኖሪያ ቤት ጥቃት ፈጸሙ "ሊባኖስ ውስጥ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ፈንድቶ ሞትና ጉዳት ካደረሰ በኋላ ተቃዋሚዎች በአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤት ላይ ጥቃት ፈጸሙ። እሁድ ዕለት በደረሰው ���ዳጅ ፍንዳታ 27 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 79 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ይህንን ተከትሎም በርካታ ተቃዋሚዎች ናጂብ ሚካቲ ከሥልጣናቸው እንዲለቁ ጠይቀዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤትም ላይ ድንጋይ በመወርወር ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል። ሚካቲ የተቃዋሚዎቹን ሐዘን እንደተረዱ የገለጹ ሲሆን ""ተቀባይነት የሌለው ጥፋት"" ያሉትን የተቃዋሚዎቹን ድርጊት አውግዘዋል። የአገሪቱ ሠራዊት እንዳስታወቀው የነዳጅ ማጠራቀሚያው ፍንዳታ ያጋጠመው በአካር ክልል ወታደሮች ከጥቁር ገበያ ነጋዴዎች የያዙትን ነዳጅ ሲያስተላልፉ ነበር። የፍንዳታው መንስኤ እስካሁን ግልጽ አይደለም፤ ነገር ግን በወቅቱ በነዳጅ ማጠራቀሚያው አካባቢ በርካታ ሰዎች ተሰብስበው እንደነበር ጦሩ አስታውቋል። ""ጦሩ ቤንዚኑን እያከፋፈለ እንደሆነ ሰማን፤ ሰዎችም ነዳጁን በጀሪካን ለመቅዳት ሲጎርፉ ነበር"" ስትል እስማኤል የተባለ ወንድሟ በአደጋው ክፉኛ የተጎዳባት ማረዋ አል ሼይክ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ተናግራለች። ማርዋ አክላም ፍንዳታው የተከሰተው አንድ ሰው ላይተር ሲጠቀም እንደሆነ ከዓይን ምስክሮች መስማቷን ገልጻ፤ ""ሌሎች ደግሞ 'በአካባቢው ተኩስ ነበር' ብለዋል"" ብላለች። ""ሟቾቹ የዚህ ግድየለሽ መንግሥት ሰለባዎች ናቸው"" ብላለች ማርዋ። ከአንድ ዓመት በፊት በቤይሩት የተከሰተውን ፍንዳታ ተከትሎ አስተዳደራቸው ሥልጣን የለቀውና በፖለቲካ አለመግባባት ምክንያት በሌላ ያልተተኩት፤ ነገር ግን አገሪቷን በባለአደራነት የሚያስተዳድሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሰን ዲያብ ""ፍንዳታው አሳዛኝ አደጋ ነው"" በማለት ሰኞ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሆኖ እንዲውል አውጀዋል። ጦሩ በበኩሉ የአደጋውን መንስዔ እያጣራሁ ነው ብሏል። በአል ቴሊል የነዳጅ ማጠራቀሚያው የነበረበትን ቦታ ባለቤትም በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ጦሩ አክሏል። የአካባቢው ነዋሪዎችም የግለሰቡ ቤት በእሳት እንዳቃጠሉት ተገልጿል። በሊባኖስ የነዳጅ እጥረት ያለ ሲሆን፤ በዓለም በከባድ የምጣኔ ሐብት ቀውስ እየተፈተኑ ካሉ አገራት አንዷ ናት። የአገሪቷ ገንዘብ የመግዛት አቅም ባለፉት ሁለት ዓመታት ወድቋል። ይህም በአገሪቷ ያለውን ግሽበት ከነበረበት የበለጠ አባብሶታል። ባለፈው ሳምንት የአገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በማጋጠሙ የነዳጅ ድጎማዎችን ለማቆም ወስኗል። መንግሥት በበኩሉ የነዳጅ ዋጋ መለወጥ የለበትም ሲል ውሳኔውን ተቃውሟል። የፀጥታ አካላትም በነዳጅ ማደያዎችና በግለሰብ የነዳጅ ማጠራቀሚያዎች የተከማቸ ነው ያሉትን ነዳጅ ቅዳሜ እለት ማከፋፈል ጀምረዋል። አብዛኞቹ ሊባኖሳውያን በግል ጀኔሬተር (ኃይል ማመንጫ) ላይ ጥገኛ በመሆናቸው የነዳጅ እጥረቱ በርካታ ሰዎችና ተቋማት በቀን ለሁለት ሰዓታት ያህል ብቻ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓቸዋል። እሁድ ዕለት ባጋጠመው ፍንዳታ የተጎዱ ሰዎችን የሚያክሙ አንዳንድ ሆስፒታሎችም መደበኛ የነዳጅ አቅርቦት ከሌለ ለመዝጋት ሊገደዱ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58223897 +business ሮበርት ሙጋቤ በባንካቸው ውስጥ ያልተናዘዙት አስር ሚሊዮን ዶላር ተገኘ "የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አስር ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችም በመዲናዋ ሐራሬ ትተው ማለፋቸውን የሃገሪቱ የመንግሥት ጋዜጣ 'ሔራልድ' ዘግቧል። ባለፈው ዓመት መስከረም በዘጠና አምስት ዓመታቸው ያረፉት ሙጋቤ ለገንዘቡም ሆነ ለቀሪው ንብረታቸው ወራሽ ማን እንደሆነ ኑዛዜ ባለማስቀመጣቸው የመንግሥት ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ጣልቃ እንዲገቡ ሆኗል። ይህንን ጉዳይ ለመወሰን ስብሰባ ተቀምጠው ነበር። •ሮበርት ሙጋቤ የሞቱት ""በካንሰር"" ነው ተባለ •ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ���ስከተለው ውጤት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ልጅ ቦና ቺኮዎሬ በጥቅምት ወር ላይ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት በፃፈችው ደብዳቤ አስር ሚሊዮን ዶላር በሃገሪቱ ባንክ፣ በሌሎች ገጠራማ ቦታዎች ካሏቸው ቤቶች በተጨማሪ ደግሞ አራት ቤቶች በሐራሬ እንዳላቸውም መጥቀሷን ሔራልድ ልጃቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። አስር መኪኖችም እንዳላቸው ጋዜጣው ጨምሮ አትቷል። •ጃፓኖች ከሰውና ከእንስሳት የተዳቀሉ የሰው አካላትን ለመፍጠር ሙከራ ላይ ናቸው ዚምባብዌ ነፃ ከወጣችበት ጀምሮ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ሃገሪቱን የመሩት ሙጋቤ ከስልጣን የተነሱት ከሁለት ዓመታት በፊት ነው። ሙጋቤ አራት ልጆችም ትተው ነው ይህችን ዓለም የተሰናበቱት። በዚምባብዌ ህግ መሰረት ባለቤታቸው እንዲሁም ልጆቻቸው ሃብታቸውን የሚወርሱ ይሆናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-50640487 +politics ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ የጣሉትን የነዳጅ ዋጋ ገደብ ደካማ ነው አሉ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ምዕራባውያን በሩሲያ ወጪ ንግድ ላይ የጣሉትን የነዳጅ ዋጋ ገደብ “ደካማ” ነው ሲሉ ተቹ። አርብ ዕለት የጸደቀው የዋጋ ገደብ የሩሲያን ድፍድፍ ነዳጅ የሚገዙ አገራት በበርሜል ከ60 ዶላር በላይ እንዳይከፍሉ ለማድረግ ያለመ ነው። ሩሲያ በነዳጅ ምርቶች ወጪ ንግድ ላይ የተጣለውን የዋጋ ገደብ እንደማትቀበል አሳውቃለች። በመጪው ሰኞ ተግባራዊ የሚሆነው የዋጋ ጣሪያ ምዕራባውያን ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፈጸመችው ወረራ ጋር ተያይዞ እያደረጉት ያለው ጫና አካል ነው። ነገር ግን ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ የዋጋ ጣሪያውን የምዕራባውያንን ደካማ አቋም ያንጸባረቀ ነው ሲሉ ተችተዋል። የሩሲያ ምጣኔ ኃብትም ላይ የረባ የሚባል ጫናም አያሳርፍም፤ ጉዳትም አያደርስም ብለዋል። “ሩሲያ ሆን ብላ የዓለምን የገበያ ስርዓት በማወክ በሁሉም የአለም ሃገራት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሳለች” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። “በአሁኑ ወቅት ጠንከርና ጠበቅ ያሉ እርምጃዎች ጥቅም ላይ የሚውሉበት ነው” ሲሉም አክለዋል። የዋጋ ጣሪያው ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደውን ጦርነት የገንዘብ አቅም ለማዳከም አልሟል። ይህንንም ፕሮፖዛል ያቀረቡት በኢንዱስትሪ የበለጸጉት የቡድን ሰባት አገራት (አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓን እና የአውሮፓ ህብረት) ናቸው። የቡድን ሰባት አገራት ባወጡት የጋራ መግለጫ የአውሮፓ ህብረት እና አውስትራሊያ እርምጃው የተወሰደው ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከምታካሂደው ወራራ ትርፍ እንዳታገኝ ለማድረግ ነው ማለታቸው ሰፍሯል። ቅዳሜ ዕለት የክሬምሊን ቃለ አባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሩሲያ ለዚህ እርምጃ ዝግጁ መሆናቸውን ቢያሳውቁም አገራቸው የዋጋ ጣሪያውን አትቀበለውም ብለዋል ። የሩሲያ ነዳጅ ላይ የሚደረገው የምዕራባውያኑ ጫና ሞስኮ ላይ ተጽእኖ ቢኖረውም፣ በአሁኑ ወቅት የሩሲያ ድፍድፍ ነዳጅ ቀዳሚ ገዢዎች በሆኑት እንደ ሕንድ እና ቻይና ባሉ ገበያዎች ይካካሳል ተብሏል። የዋጋ ጣሪያው ስምምነት ተግባራዊ የሚሆነው የአውሮፓ ህብረት በባህር በሚገባው የሩሲያ ድፍድፍ ነዳጅ ላይ የተጣለው እገዳ ተፈጻሚ በሚሆንበት በተመሳሳይ ዕለት ነው። አዲሱ የዋጋ ጣሪያ እርምጃ በዓለም ዙሪያ ያለውን የነዳጅ ወጪ ንግድ ላይ ተፅእኖ የሚያሳድር ነው። በቡድን 7 አማካኝነት የቀረበውን የነዳጅ ዋጋ ጣሪያ ውሳኔን የፈረሙ አገራት በባሕር በኩል የሚያስገቡትን ነዳጅ መግዛት የሚችሉት በስምምነቱ በተቀመጠው ወይም ከዚያ በታች በሆነ ዋጋ ነው። የዩክሬን ምዕራባውያን አጋሮች በዋጋ ጣሪያው ስምምነት ላይ ያልፈረሙ አገራት የሩሲያን ነዳጅ ለሚያደርሱላቸው ተሽከርካሪዎች የሚሰጠውን መድህን እንደሚከለክሉ ገልጸዋል። ይህም ሩሲያ ነዳጇን ከተቀመጠው ዋጋ በላይ እንዳትሸጥ የሚያደርግ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c1ve0drlrzvo +business የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ብድር ለመልቀቅ እያቅማሙ ነው ተባለ "ለኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ የሚባሉ የፋይናንስ ተቋማት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ብድር ለመልቀቅ እያቅማሙ ነው። ይህም የሆነበት ዋነኛው ምክንያት ተጨማሪ ብድር ለአገሪቱ መስጠት የመክፈል አቅሟን የበለጠ ሊያዳክም ይችላል ከሚል ስጋት ነው። በገንዘብ ሚኒስትር አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሮይተርስ እንደተናገሩት ለምሳሌ የቻይናው ኤክዚም ባንክ እሰጣለው ብሎ የነበረውን ከፍተኛ ገንዘብ ለመልቀቅ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ይህም ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጵያ ከመስጠት የታቀበው የብድር መጠን 339 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይህን ያሉት የገንዘብ ሚኒስቴር የቻይና ትብብር ዳይሬክተር ደምሱ ለማ ናቸው። ነገር ግን የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጵያ ብድር ለመልቀቅ በማቅማማት ላይ ያለ ብቸኛው የፋይናንስ ተቋም አይደለም። ሰኔ ወር ላይ በገንዘብ ሚኒስቴር የታተመ አንድ ሰነድ እንዳመለከተው የውጭ አበዳሪዎች አስከ መጋቢት መጨረሻ ድረስ 11 ቢሊዮን ዶላር ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። የዓለም ባንክ አንድ አካል የሆነው የዓለም አቀፉ የልማት ትብብር ማኅበር (ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን) ለምሳሌ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ይለቃል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን ይህን እስከአሁን ተግባራዊ አላደረገም። ሚኒስቴሩ በሰነዱ ከጠቀሳቸው ሌሎች አበዳሪ ተቋሟት አንዱ ግዙፉ የዓለም የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ሲሆን ተቋሙ 2.7 ቢሊዮን ዶላር እስከ አሁን ለኢትዮጵያ አለቀቀም። ከውጭ አበዳሪዎች ትልቅ የምትባለው ቻይና 1.4 ቢሊዮን ዶላር ብድር አልለቀቀችም። ከላይ ከተጠቀሱት አበዳሪዎች ሌላ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና ሌሎች የንግድ ባንኮች ይገኙበታል። ይህ የውጭ አበዳሪዎች ተጨማሪ ብድር ለኢትዮጵያ ለመልቀቅ አለመፍቀዳቸው አገሪቱ ላይ እየተካሄዱ ያሉ መጠነ ሰፊ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ሊያስተጓጉል እንደሚችል ይገመታል። በውጭ ብድር ተጠቃሚ እየሆኑ ከቆዩት ፕሮጀክቶች መካከል እርሻ፣ ትራንስፖርት፣ ኮሚዩኒኬሽን፣ አውራ ጎዳናዎች እና የባቡር ፕሮጀክቶች ይገኙበታል። እነዚህ በድምሩ 675 ቢሊዮን ዶላር ብድር ያገኙ ፕሮጀክቶች ናቸው። ይህም እንደ አውሮፓውያኑ ከሐምሌ 2020 እስከ መጋቢት 2021 ያለውን የሚያመላክት አሐዝ ነው። አሁን የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ገንዘብ ለማበደር ታቅበው ሁኔታውን ቆም ብለው እያጤኑት የሚገኙት አገሪቱ የብድር እፎይታን በተመለከተ በዓለም አቀፍ ደረጃ ንግግር የጀመረች በመሆኑ ነው። ባለፈው ሐምሌ ወር የአይኤምኤፍ ቃል አቀባይ ጌሪ ራይስ በኢትዮጵያ የብድር ጉዳይ ላይ አንድ ከሚቴ በፍጥነት እንዲቋቋም ጥሪ አድርገው ነበር። ይህም ከቡድን 20 እና ከፓሪስ ክለብ አበዳሪዎች ዘንድ ኢትዮጵያ ያቀረበችውን የብድር እፎይታ ጥያቄ እንዲመለከት ነበር። መንግሥት የብድር መመለሻ እፎይታ ለማግኘት ንግግር መጀመሩ ስህተት አይደለም ይላሉ ባለሙያዎች። በተለይም የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ ብዙ አገራት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸው ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል ብለዋል። በጉዳዩ ላይ ለቢቢሲ አስተያየታቸውን የሰጡት የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ እንደሚሉት ""ኢትዮጵያ ኮቪድን አልፈጠረችውም፡፡ … ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራት የብድር እፎይታ ጊዜን መጠየቃቸው ምክንያታዊ አይደለም ማለት አልችልም"" ሲሉ የኢትዮጵያን የብድር እፎይታ ጥያቄ አግባብነት ደግፈዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ የተበደረችው ዕዳ እስከ መጋቢት ወር ብቻ 29 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም የጥቅል አገር ውስጥ ምርት እድገት (ጂዲፒ) 27 ከመቶ የያዘ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-58246656 +politics እስራኤል-ጋዛ፡ ኔታንያሁ የሃማስ ታጣቂዎች ለዓመታት ወደ ኋላ ተመልሰዋል አሉ "እስራኤል በጋዛ ያደረገችው የዘጠኝ ቀናት ድብደባ የሃማስ ታጣቂዎችን በበርካታ ዓመታት ወደ ኋላ የመለሰ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ ተናገሩ። የእስራኤልና የፍልስጥኤም ግጭት አሁንም ጋብ አላለም። በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ወደ ደቡባዊ እስራኤል በተኮሱት ሮኬት ሁለት የውጭ አገር የእርሻ ሠራተኞች ተገድለዋል። እስራኤልም በጋዛ የምታደርገውን የአየር ድብደባ ቀጥላለች። በዌስት ባንክ በራማላህ አቅራቢያ በተደረገ ተቃውሞ ቢያንስ ሦስት ፍልስጥኤማዊያን በእስራኤል ፖሊሶች ተገድለዋል። ግጭቱ እንዲቆም የተደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችም ያን ያህል ውጤት አላመጡም። ፈረንሳይ ከግብጽ እና ጆርዳን ጋር በመተባበር ግጭቱን ለመፍታት የሚያስችል ረቂቅ ሃሳብ ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት አቅርባለች። አገራቱ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበዋል። ማክሰኞ ዕለት እስራኤል እርዳታ እንዲገባ ለመፍቀድ ወደ ጋዛ የሚወስደውን ድንበር የከፈተች ቢሆንም ከፍልስጤም ወታደሮች ሮኬቶች በመተኮሱ በድጋሜ ድንበሩ ተዘግቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ምንድን ነው ያሉት? ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ ""ጋዛን የሚያስተዳድረው የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኑ ሃማስ ያልተጠበቀ ዱብ ዳ አጋጥሞታል፤ ይህ ዘመቻም በእስራኤል ዜጎች ዘንድ መረጋጋት እስከሚመጣ ድረስ ይቀጥላል"" ብለዋል። እንደ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በጋዛ ቢያንስ 215 ሰዎች ተገድለዋል። ከእነዚህ መካከል 100 የሚሆኑት ሴቶችና ህጻናት ናቸው። የጤና አገልግሎት ተቋም እንዳለው በእስራኤል ደግሞ ሁለት ህጻናትን ጨምሮ 12 ሰዎች ተገድለዋል። ማክሰኞ ዕለት እስራኤል በጋዛ ከተገደሉት መካከል ቢያንስ 150 የሚሆኑት ታጣቂዎች እንደሆኑ አስታውቃለች። ይሁን እንጅ ሃማስ በወታደሮቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት በአሃዝ አልጠቀሰም። ግጭቱ ከተከሰተ ጀምሮ እስራኤል ሁለቱ የፍልስጤም ታጣቂዎች ክንፍ 120 ሺህ የሚደርሱ ሮኬቶች በጋዛ እንደነበራቸው ግምቷን አስቀምጣለች። ታጣቂዎቹ ከማክሰኞ ዕለት ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ 3 ሺህ 300 የሚሆኑ ሮኬቶችን እስራኤል ላይ ተኩሰዋል። ከእነዚህ መካከል ከ450 እስከ 500 የሚደርሱት ከታለመው ሳይደርሱ በአጭር ቀርተው በጋዛ ጉዳት ማድረሳቸውን የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ተናግረዋል። በዌስት ባንክ የተፈጠረው ምንድን ነው? በዌስት ባንክ እና በምስራቅ እየሩሳሌም ያሉ በርካታ ፍልስጥኤማዊያን እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ድብደባ በመቃወም አድማ መትተዋል። በእስራኤል የሚገኙና የእስራኤል አረቦች በብዛት በሚኖሩባቸው እንደ ሃይፋ ያሉ አካባቢዎች ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል። የሕዝብ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች እና በርካታ የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል። በተለያዩ አካባቢዎችም ግጭቶች ነበሩ። በዌስት ባንክ ከተማ ራማላህ ሰላማዊ ባልሆነው ተቃውሞ ወቅት መተኮሳቸውን የእስራኤል ፖሊስ ተናግሯል። በአካባቢው የነበሩ ሦስት ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በሄብሮን ወታደሮችን ለማጥቃት የሞከረ ሌላ ፍልስጤማዊ መገደሉንም የእስራኤል ጦር አስታውቋል። በእየሩሳሌም የደማስቆ መግቢያም ግጭቶች የነበሩ ሲሆን የእስራኤል ወታደሮች በርካቶችን አስረዋል። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ድርጅት- ኦቻ ���ጋዛ 52 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ከእነዚህ መካከል 47 ሺህ የሚሆኑት ወደ ተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤቶች መሸሻቸውን አስታውቋል። ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በኒውዮርክ በቅርቡ በተደረገው ስብሰባ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ በድጋሚ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ ቀርቷል። ፈረንሳይ ያቀረበችው የመፍትሔ ሃሳብ የተዘጋጀው ከግብፁ መሪ አብደል ፈታህ አል ሲሲ እና ከጆርዳኑ ንጉስ አብዱላህ ሁለተኛ ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ወቅት መሆኑን አስታውቃለች። አሜሪካ ከዚህ ቀደም የጸጥታው ምክር ቤት የተኩስ አቁም ጥሪ የሚያቀርብ የጋራ መግለጫ ለማውጣት የተደረጉ ጥረቶች ላይ ሳትስማማ ቀርታለች። አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት እና ሌሎች ኃያላን ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። ግብጽ እስራኤልና ሃማስን ለማሸማገል እንደምትፈልግ ገልጻለች። ይሁን እንጅ እስራኤል ሃማስን እና እስላማዊ ጅሃድን ለማጥፋት ጥቃት መፈፀሟን እንደምትቀጥል አስታውቃለች። በተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም አምባሳደር ሪያድ ማንሱር የጸጥታው ምክር ቤት ወጥ አቋም አለማሳየቱን ""አሳፋሪ"" ብለውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ የቱርኩ ፕሬዚደንትን ሬሲብ ታይፕ ኤርዶዋንን ስለ እስራኤል ተናግረዋል ባለችው 'ጸረ አይሁዳውያን' ንግግር ከሳለች። ፕሬዚደንቱ በንግግራቸው በፍልስጥኤማውያን ላይ በምትፈጽመው ጥቃት እስራኤልን ከሰዋል። በቅርቡም ""ይህ ተፈጥሯቸው ነው"" በማለት ""እስራኤል ገዳይ ናት"" በማለት 'ጸረ አይሁዳውያን' ተደርጎ በስፋት የሚታይ ንግግር ተናግረዋል። የአሜሪካ የፕሬዚደንት የታይፕ ኤርዶዋንን ንግግር በጥብቅ አውግዛለች። ፕሬዚደንት ኤርዶዋንና ሌሎች የቱርክ መሪዎች ተጨማሪ ግጭት ሊቀሰቅስ ከሚችል መሰል ንግግርም እንዲታቀቡ አሳስባለች። ግጭቱን የቀሰቀሰው ምንድን ነው? በእስራኤልና በሃማስ መካከል የተከሰተው ግጭት የተነሳው በፍልስጤማውያን እና እስራኤላውያን ፖሊስ መካከል በምሥራቅ እየሩሳሌም ቅዱስ ሥፍራ ለቀናት በተፈጠረ ግጭት ነው። ሥፍራው በሙስሊሞችም ክብር የሚሰጠው ሲሆን ሃራም አል ሻሪፍ እያሉ ይጠሩታል። አይሁዳውያን ደግሞ የተራራው ቤተ መቅደስ ይሉታል። ሃማስ እስራኤል ፖሊሶቿን ከአካባቢውና በርካታ ሙስሊሞች ከሚኖሩበት የአረቦች ግዛት ሼክ ጃራህ እንድታነሳ ትፈልጋለች። ሼክ ጃራህ በርካታ የፍልስጥኤም ቤተሰቦች በአይሁድ ነዋሪዎች የተገደሉበት ነው። ሃማስ ለዚህ ጥያቄው መልስ ሳያገኝ ቀረ። ከዚያም ሮኬት መተኮስ ጀመረ። በእርግጥ የፍልስጤማውያን ቁጣ ለሳምንታት በእየሩሳሌም በነበረው ውጥረት ታምቆ የቆየ ነበር። ከሚያዝያ ወር አጋማሽ ጀምሮም ከፖሊሶች ጋር ግቶች ነበሩ። ከዚያም እስራኤል እአአ1967 በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት፤ ምስራቅ እየሩሳሌምን በተቆጣጠረችበትና 'የእየሩሳሌም ቀን' ተብሎ በሚጠራው ዓመታዊ በዓል ላይ ሌላ ችግር ተቆሰቆሰ። ግጭቱ ለዓመታት የነበረ ይሁን እንጅ የሰሞኑ ግጭት መነሻ ግን ይኸው ነው። ለሁለቱም ወገኖች ሃይማኖታዊና ብሔራዊ መሠረት ያላት የከተማዋ እጣ ፈንታም ለአስርት ዓመታት በዘለቀው የእስራኤልና ፍልስጤም ግጭት ላይ የወደቀ ነው። እስራኤል እአአ በ1980 ምሥራቅ እየሩሳሌምና ጠቅላላ ከተማዋን እአአ በ2017 ዋና መዲናዋ አድርጋለች። ነገር ግን ይህ በአብዛኛው አገራት እውቅና አልተሰጠውም። ፍልስጤም ደግሞ እመሰርተዋለሁ ብላ ላሰበችው ለራሷ አገር ዋና መዲናነት የምሥራቃዊ እየሩሳሌም ግማሹ ክፍል ይገባኛል ትላለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-57167680 +politics አንዳንድ ነጥቦች አዲስ ስለሚቋቋመው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን "ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉ��ዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ይህንን ሂደት የሚመራና የሚያስተባብር አካል ለማቋቋም የሚያስችሉ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። የተለያዩ አላማዎችን አንግበው በፖለቲካው መድረኩ ላይ ያሉ ኃይሎችና ልሂቃን እንዲሁም ሕዝቡ ውስጥ ያሉ ጥያቄዎችና ሐሳቦችን መሠረት በማድረግ እንዲቀራረቡ በማድረግ ለአገራዊ አንድነት ገንቢ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አገራዊ ምክክሩ አውንታዊ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። የሚቋቋመው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለአስርታት ምላሽ ሳያገኙ መግባባት ያልተደረሰባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮችን በማንሳት ታላላቅና ተከታታይ አገራዊ ምክክሮችን አሳታፊ በሆነ መንገድ በማካሄድ መግባባትን መገንባት ዋነኛ አላማው ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረቡዕ ታኅሣሥ 20/2014 ዓ.ም ያጸደቀው እና ላለፉት ሁለት ወራት ሲረቀቅ ብሎም ውይይቶች ሲደረጉበት የቆየው ""የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን"" አዋጅ መነጋጋሪያ ሆኖ ሰንብቷል። ቢያንስ ሁለት ጊዜ መሠረታዊ ማሻሻያዎችን ያለፈው አዋጁ በርካታ አስተያየቶችና ትችቶችን ሲያስተናግድ ቆይቶ ነው ወደ ሥራ እንዲገባ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቀው። በቀድሞው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአሁኑ የፍትሕ ሚኒስቴር አርቃቂነት፣ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መሪነት እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ሥራ ለመግባት በዝግጅት ላይ ስላለው አዲሱ ኮሚሽን አንዳንድ ነጥቦች። የኮሚሽነሮች ሹመት በአዋጁ የዜሮ ረቂቅ ላይ ሰባት ኮሚሽነሮች ይሾሙለታል ተብሎ የተጠቀሰ ሲሆን ቀጥሎም ተሻሽሎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ ላይ የኮሚሽነሮች ቁጥር ወደ 11 ከፍ ተደርጓል። የመጀመሪያው ረቂቅ ዋና ኮሚሽነር እና ሌሎች ኮሚሽነሮች የሰላም ሚኒስቴር ከሕዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶችና ከሲቪል ማኅበራት ጥቆማ በመቀበል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚያቀርብ ያወሳ ነበር። በመቀጠልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ አካላት ጋር በመወያየት ዕጩዎቹን ለተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ያሾማሉ ሲል የመጀመሪያው ረቂቅ ያትት ነበር። ነገር ግን የጸደቀው አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት የዕጩ ኮሚሽነሮችን ጥቆማ ከሕዝብ፣ ከሲቪል ማኅበራት እና ከፖለቲካ ድርጅቶች እንደሚቀበል እና አፈ ጉባኤው ለምክር ቤቱ ዕጩ ኮሚሽነሮችን እንደሚያቀርብ ያትታል። ""ምክንያቱም የዕጩዎችን ጥቆማ መቀበል እና ለምክር ቤቱ አቅርቦ የማሾም ሥልጣን የአፈ ጉባኤው እና የጽህፈት ቤታቸው ሲሆን ይህ የኮሚሽነሮቹ ገለልተኝነት የተሻለ እንዲሆን ያደርጋል"" ሲል የጸደቀው የውሳኔ ሃሳብ ይጠቅሳል። በቅድሚያ በረቂቅ ሕጉ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው ሥልጣን ሊሰጥ የነበረው ሐሳብም በመጨረሻ ውድቅ ተደርጎ የአፈ ጉባኤው ሥልጣን አንዲሆን ተደርጓል። የኮሚሽነሮቹ መብቶች በአዋጁ አንቀጽ 15 መሰረት በኮሚሽነርነት የሚሾሙት አባላት ያለመከሰስ መብት አግኝተዋል። እንዲሁም ""የኮሚሽነሮች ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም ለመንግሥት ከፍተኛ ተሿሚዎች በተፈቀደው ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም አግባብ ይፈፀማል"" ሲል አዋጁ ያስቀምጣል። በኮሚሽኑ ሥራ ላይ ድምጽ የመስጠት ብሎም ለሥራቸው የሚያስፈልጉ ሰነዶቸን እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን የማግኘት እና የመመልከት መብት አላቸው። ይህንንም በሥራ ላይ ያገኙትን ምስጢር የመጠበቅ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ስለ ኮሚሽኑ ሥራዎች ኮሚሽኑ በጀቱ በመንግሥት የሚመደብ ሲሆን የመንግሥትን የፋይናንስ አስተዳደር መርሆዎችን መሰረት በማድረግ በበጀቱ ላይ ሙሉ ነጻነት እንደሚኖረው አዋጁ ያደርጋል። ኮሚሽነሮቹ አባል የሆኑበት ምክር ቤት ዋናውን የኮሚሽኑን ሥራዎች የሚ���ከናውን ይሆናል። ምክር ቤቱ ለምክክር የሚሆኑ አጀንዳዎችን መምረጥ፣ ከኮሚቴዎችም ሆነ ከሕዝብ የሚገኙ ምክረ ሐሳቦችን ለመንግሥት ማቅረብ፣ ለኮሚሽኑ እንቅስቃሴ የሚያስፈለጉ የውስጥ ደንብ እና መመሪያዎችን ማውጣትን ጨምሮ መሠረታዊ የአስተዳዳራዊ ተግባራትን ጨምሮ በበላይነት ይመራል። በሕብረተሰቦች መካከል የሚታዩ መሠረታዊ ልዩነቶች ምክንያቶችን በመለየት እና ለውይይትም ርዕሰ ጉዳዮችን በመለየት ምክክር እንዲደረግባቸው የሚለየው ይሔው ኮሚሽን ነው። እንዲሁም እነዚህ ምክክሮች ""ብቃት ባለው ገለልተኛ በሆነ አካል የሚመሩ፤ ያለመግባባት መንስኤዎችን በትክክል የሚዳስስ አጀንዳ ላይ የሚያተኩ፣ ግልጽ ብሎም ለማስፈጸም የሚያስችሉ ውጤታማ አገራዊ ውይይትን የሚያስተናግድ ሥርዓትን የመዘርጋት"" ሥልጣንም ተሰጥቶታል። የኮሚሽኑ የሥራ ጊዜ በአዋጁ ዜሮ ረቂቅ ላይ ለሁለት ዓመት የሚቆይ እድሜ ይኖረዋል የተባለው ኮሚሽኑ በአንድ ዓመት ከፍ ብሎ የሦስት ዓመት የቆይታ ዘመን እንዲኖረውም ተደርጓል። ነገር ግን እንዳስፈላጊነቱ በተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ጊዜው ሊራዘም እንደሚችል እና እድሜው መሰላት የሚጀምረው ኮሚሽነሮቹ ከተሾሙበት ዕለት ጀምሮ መሆኑም በአዋጁ ተካቷል። ዋና መስሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ሆኖ እንዳስፈላጊነቱ በክልሎች ቅርንጫፎች ሊኖረው እንደሚችል ተገልጿል። የኮሚሽኑ ሥልጣን ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ አላማ መንግሥታዊ በሆኑም ሆነ ባልሆኑ ተቋማት የተደረጉ የምክክር ሂደቶችን እና የተገኙ ውጤቶችን በማጥናት በቀጣይ ለሚያካሂዳቸው አገራዊ ውይይቶች በግብአትነት እንደሚጠቀም አዋጁ ያስረዳል። በልሂቃኖች መካከል አገራዊ ጉዳዮችን አስመልከቶ ያሉ ልዩነቶችን የመለየት፣ ምክክሮችን የማሳለጥ እንዲሁም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚወከሉ ተሳታፊዎች ያሉባቸውን የምክክር ስብሰባዎችን ያካሂዳል። ኮሚሸኑ ተወካዮችን የመምረጥ ብሎም ኮሚሽነሮቹ እነዚህን ምክክሮችን የመምራት ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። እንዲሁም የምክክር አጀንዳዎችን፣ የምክክሮቹን ሂደት፣ በምክክሮቹ የተገኙ ምክረ ሐሳቦችን ተግባር ላይ ሊውሉ ስለሚችሉበት መንገድ ሪፖርቶችን በማሰናዳት ለመንግሥት እና ለሕዝብ የማቅረብ ግዴታም ተጥሎበታል። መንግሥት ምክረ ሐሳቦችን እንዲተገብር የማገዝ ብሎም ተግባራዊነታቸውን የመከታተል ሥልጣንም አግኝቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59822579 +business በህንድ በመጠጥ መመረዝ የበርካቶች ህይወት አለፈ በህንድ በመጠጥ መመረዝ የ86 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል። ግለሰቦቹ በህገወጥ መንገድ የተመረተ አልኮል በመጠጣታቸው ህይወታቸው ማለፉን የሰሜን ህንዷ ግዛት ፑንጃብ ኃላፊዎች አስረድተዋል። በትናንትናው ዕለት ፖሊስ አካባቢውን በመቆጣጠር ህገወጥ የተባለውን መጠጥ የያዘ ሲሆን መጠጡን ያመርታሉ የተባሉ 25 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። የሟቾችም ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ነው ተብሏል። በህንድ በመጠጥ መመረዝ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሲሞቱ አዲስ አይደለም፤ በተደጋጋሚም የሚከሰት ችግር ነው ተብሏል። በየአመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ህንዳውያን በጓዳ ጎድጓዳው ንፅህናው ባልተጠበቀ መልኩ የሚጠመቁ መጠጦችን በመጠጣት ህይወታቸው ያልፋል። በተለይም በገጠሯ ህንድ ታዋቂ ስም ያላቸውን መጠጦች ከመግዛት ይልቅ በህገ ወጥ መንገድ የተመረቱና ዋጋቸው ርካሽ የሆኑ መጠጦችን ይገዛሉ፤ በዚህም በርካቶች መመረዛቸው ሪፖርት ይደረጋል። መጠጥ ጠማቂዎች ሜታኖል የሚባለው ንጥረ ነገር ይጨምሩበታል። ይህ ንጥረ- ነገር ከፍተኛ መርዛማነት ያለው ሲሆን የመጠጡን ጥንካሬም ለመጨመርም ነው ሜታኖልን የሚጨምሩበት ተብሏል። በትንሽም መጠን ቢሆን ይህ ንጥረ ነገር ከተወሰደ አይነ ስውርነት፣ የጉበት ህመም እንዲሁም ባስ ሲል ሞት እንደሚያስከትልም ባለሙያዎች ይናገራሉ። በዚህ ሳምንት አርብም የፑንጃብ ግዛት አስተዳዳሪ ሚኒስትር አማሪንደር ሲንግ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ላይ ምርመራ እንዲጀመር አዘዋል። በርካታ ሪፖርቶች እንደሚያስረዱት መጠጡ በከፍተኛ መጠን እንደተጠመቀና ጎዳናዎች ላይ ላሉ የካፌ ባለቤቶች እንደተሸጠና የአካባቢው ማህበረሰብም መጠጡን ማግኘቱ ተገልጿል። ከሰሞኑም በሕንድ ውስጥ በምትገኘው አንድራ ፕራዴሽ ግዛት የመጠጥ መሸጫ ሱቆች መዘጋታቸውን ተከትሎ በርከት ባለ አልኮል የተሰራ ሳኒታይዘር የጠጡ ቢያንስ አስር ግለሰቦች ሕይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል። የአካባቢው ፖሊስ ኃላፊ እንደተናገሩት ሰዎቹ ሕይወታቸው ሊያልፍ የቻለው ሳኒታይዘሩን ከውሃ እና ከለስላሳ መጠጦች ጋር ቀላቅለው በመጠጣታቸው ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-53627129 +health "ፕሬዝደንት ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ ""ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው"" አሉ" "በአሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች የአፍ እና አፍንጫ ጭምብል የማድረግ ግዴታ የለባቸውም መባሉን ተከትሎ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው ብለዋል። ባለስልጣናት በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ከውስን ቦታዎች በስተቀር ያለጭምብል መንቀሳቀስ ይችላሉ ብለዋል። አካላዊ ርቀትን መጠበቅም አይጠበቅባቸውም ተብሏል። ከዚህ ውሳኔ በኋላ ""ኦቫል"" ቢሮ ከሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች ጋር ፕሬዝዳንቱ ራሳቸው ያለጭምብል ታየተዋል። ይሁን እንጂ እንደ አወቶብስ፣ አውሮፕላንና ሆስፒታል ባሉ መሰባሰብን በሚጠይቁ ከበር መለስ አገልግሎቶች የሚሰጡባቸው ቦታዎች ላይ ግን ክትባት የተከተቡትም ቢሆኑ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታቸው ነው። ሙሉ በሙሉ ክትባቱን ላገኙ ሰዎች የኮቪድ ክልከላዎች እንዲነሱላቸው በባይደን አስተዳደር ላይ ጫና ሲደረግበት ቆይቷል። በሌላ በኩል ደግሞ የአሜሪካ የመምህራን ፌዴሬሽን ለፕሬዝዳንት ባይደን ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከፈቱ ጥሪ አቅርቧል። ይህ ጥሪ የተላለፈው ፋይዘር ያመረተውን ከትባት ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 ያሉ ህጻናት መከተብ እንዲችሉ ፍቃድ ከተሰጠ በኃላ ነው። አሁን ላይ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ተሰምቷል። የአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅም ግዴታቸ እንዳልሆነ አስታውቋል። በቲውተር ገጻቸው ያልተከተቡ ሰዎች 'ማስክ' ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ያሳሰቡት ባይደን ""ህጉ ቀላል ነው መከተብ ወይም እስከትከተቡ ጭምብል ማደረግ። ምርጫው የእናንተ ነው"" ብለዋል። በአሜሪካ 35 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ክትባት ያገኘ ሲሆን የ ጆ ባይደን አስተዳደር ይሄ ቁጥር እስከ ሀምሌ ደረስ በእጥፍ አሳድጎ 70 በመቶ ለማደረስ አቅዷል።" https://www.bbc.com/amharic/57111329 +sports ለንደን ማራቶን፡ አትሌት ሹራ ቂጣታ ከኬንያዊው ኪፕቾጌ የማራቶን ድል እንዲነጥቅ የረዳው ምንድን ነው? "ኤሉድ ኪፕቾጌን ለማሸነፍ እንዴት ያለ ወኔ ይበቃ ይሆን? ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች የሮጠውን ብርቱ አትሌት ለማሸነፍ ምን ሲደረግ ይቻላል? ጥብቅ ልምምድ ወይስ ተሰጥኦ? ለለንደን ማራቶን አሸናፊው ሹራ ቂጣታ ግን ጥሩ ቁርስ በቂ ነው። ባለፈው ዓመት በዩኬ ዋና ከተማ አራተኛ በመሆን ነው ያጠናቀቀው። ያኔ ኬኒያዊው ኪፕቾጌ ነው ያሸነፈው። በወቅቱ ሹራ በትዊተር ሰሌዳው ላይ ባዶ ሆዱን መሮጡን፣ ለቁርስ ፍራፍሬ ብቻ መመገቡን ገልጾ ነበር። ሹራ በወቅቱ 35 ኪሎ ሜትሮች ከሮጠ በኋላ የተሰማውን ሲያሰፍር ""ሆዴ ከጀርባዬ ጋር የተጣበቀ መስሎኝ ነበር፤ ሞርሙሮኝ ነበር"" ብሏል። በዚህ ዓመት ከስህተቱ የተማረው ሹራ ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት ጥሩ ምግብ ወሳስዷል። ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ "" ሁሉንም ነገር ተመግቤያለሁ"" ብሏል። ""ሾርባ፣ ዳቦ፣ እንቁላል እና እርጎ ወስጃለሁ፤ አቅም የሚሆነኝንና ውድድሩን በጥሩ ጉልበት መፎካከር የሚያስችለኝን ሁሉ ወስጃለሁ።"" ውድድሩ ደግሞ ከ2014 ጀምሮ በማራቶኑ መስክ አልበገር ያለውን ኬንያዊ ማንበርከክን ያካተተ ነበር። ኪፕቾጌ የዋዛ አትሌት አይደለም። በኦሎምፒክ መንደር ስሙ በደማቅ ተጽፏል። የዓለም ክብረ ወሰን በእጁ ነው። የ35 ዓመቱ ኪፕቾጌ በለንደን ለአምስተኛ ጊዜ ድልን ለመቀዳጀት ጉልበቱን አበርትቶ ሞራሉን አደርጅቶ ነው የተገኘው። የዓለም መገናኛ ብዙኃንም ስሙን ደጋግመው ያነሳሉ። ምስሉን ደጋግመው ያሳያሉ። ጋዜጦች የፊት ገጻቸው ላይ አትመውታል። ለንደን ለኪፕቾጌ፣ ኪፕቾጌም ለለንደን መሃላ ያላቸው ይመስላል። ኪፕቾጌና ለንደን ግን ያላቸው ቃል ኪዳን ፈረሰ። መፍረስ ብቻ ሳይሆን ስምንተኛ ወጣ። ከፊት የፈለጉት ከኋላ አገኙት። በኋላም ጆሮውን አሞት እንደነበር አስረዳ። ለረዥም ርቀት ሩጫ እርጥበታማ አየርና ቅዝቃዜ ምቹ አይደለም። ሹራ የገባበት ሰዓትም፣ ሁለት ሰዓት ከአምስት ደቂቃ ከ41 ሰከንድ የሚያሳየው ይህንኑ ነው። ሹራ ግን እንደውም አየሩ ረድቶኛል ሲል ያምናል። እኤአ ከ2013 ወዲህ የለንደን ማራቶንን ሲያሸንፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሆነው ሹራ ""ሲዘንብ በጣም ደስ አለኝ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በከባድ ዝናብ ውስጥ ነው ልምምድ ስሰራ የነበረው"" ይላል። ""አንድ ቀን ሶደሬ ለልምምድ ሄድኩኝ፣ ከባድ ዝናብ እየዘነበ ከተማው በጎርፍ ተጥለቅልቋል። አሰልጣኜ እኔን ለማዳን መምጣት ሁሉ ነበረበት"" ሲል የነበረውን የልምምድ ሁኔታም ያስታውሳል። ""የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሲከሰት፣ ቤት አልተቀመጥኩም። ለአምስት ወራት ያህል ከአሰልጣኜ ጋር ልምምድ ስሰራ ነበር። ይህን ድል ኪፕቾጌን ማሸነፌ ልዩ አያደርገውም፤ ጠንክሬ መስራቴ ነው ልዩ የሚያደርገው።"" ቀነኒሳ በቀለ ባጋጠመው ጉዳት የተነሳ ከውድድሩ መውጣቱን ካሳወቀ በኋላ በኪፕቾጌና በቀነኒሳ መካከል ይኖራል ተብሎ የታሰበው ፍልሚያ ሳይሳካ ቀረ። ስለዚህ ማንም የቀነኒሳን አገር ልጅ፣ ሹራን ከኪፕቾጌ ጋር አነጻጽሮ ለማወዳደርና የዜና ፍጆታ ለማድረግ ፍላጎት አላሳየም። ሹራም ቢሆን ""ሁሉም ትኩረቱ የነበረው ኪፕቾጌ እና ቀነኒሳ ላይ ነበር፤ እኔን ዞርም ብሎ ያየኝ አልነበረም"" ሲል ይገልጻል። ""ለራሴ ለዓለም ሌላ ሻምፒዮን መኖሩን አሳያለሁ ብዬ ነገርኩት፤ እናም ይህ ስሜት ነው እስከመጨረሻው ድረስ በራስ መተማመንና በሙሉ አቅም እንድቀጥል የረዳኝ።"" ሹራ በበርካታ የስፖርቱ አድናቂዎች ዘንድ የሚታወቅ ስም አይደለም። ነገር ግን በለንደን ሁለት ጊዜ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቅቋል፣ በ2018 ደግሞ በኒውዮርክ ሁለት ሰዓት ከአራት ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በመግባት የራሱን ምርጥ ሰዓት አስመዝግቧል። በዙሪያው ያሉ አትሌቶች የ24 ዓመቱን ሹራ ዝምተኛ ግን በራስ መተማመን ያለው ሲሉ ይገልፁታል። የሹራ ወኪል ሁሴን ማኬ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ፤ "" በጣም መልካም፣ የሚፈልገውን የሚያውቅ፣ ቤተሰቡን የሚያስቀድም ሰው ነው። እናም የእርሱ ምርጥ ነገሩ በራስ መተማመኑ ነው"" ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል። ""በለንደን በራሱ በብርቱ ተማምኖ ነበር፤ እናም ወደ ውድድር ሲገባ ውድድሩ ውስጥ ስላሉት አትሌቶች ግድ አልሰጠውም፤ ያም አሁን ላገኘው ሻምፒዮናነት ረድቶታል። ተስፋ አደርጋለሁ በዚሁ ይቀጥላል።"" ሹራ አትሌቲክስን የተዋወቀው በትምህርት ቤት ���ስጥ ነው። ኋላም እኤአ ከ2015 ጀምሮ አሰልጣኝ ሃጂ አዲሎ በአዲስ አበባ እያሰለጠኑት ይገኛሉ። ""በጣም ደፋር አትሌት ነው፤ እናም ሁልጊዜ አቅሙን እስከቻለ ድረስ ይጠቀማል"" ይላሉ አሰልጣኙ። አሰልጣኝ ሃጂ ወደ እንግሊዝ ለመሄድ ቀናት ሲቀራቸው የኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው በምርመራ በመረጋገጡ ድሉን በአካል ተገኝተው ለማጣጣም አልታደሉም። ቢቢሲ ሹራን እንዴት ማሰልጠን እንደጀመሩ ሲጠይቃቸው ""ሹራ ከመጣበት አካባቢ የሆነ ሰው ከኔ ጋር አብሮ ይሮጥ ነበር። እናም እኔ ወዳለሁበት ካምፕ አምጥቶት እስቲ እየው አለኝ። ሞከርነው፤ ጥሩ ነበር ግን ፅናቱንና ፍጥነቱን ማሻሻል ነበረበት"" በማለት ሁኔታውን ያስታውሳሉ። ""በሶስት ወር ውስጥ፣ በጣም በርካታ ነገር አሻሻለ፤ እናም የመጀመሪያውን ማራቶን እንዲካፈል ወደ ሻንጋይ ላክነው።"" ሹራ የተገኘው ሰባት ልጆች ካሏቸው ገበሬ ቤተሰቦች ነው። ""ትምህርት በጣም እወድ ነበር፤ ዶክተር አልያም ፓይለት ነበር መሆን የምፈልገው። ነገር ግን ከድሃ ቤተሰብ ስለሆነ የተገኘሁት ቤተሰቦቼን ለመርዳት ትምህርቴን ማቋረጥ ነበረብኝ"" በማለት ልጅነቱን ያስታውሳል። ""አንድ ቀን ዝነኛ እሆናለሁ፤ አለምን እዞራለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም"" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ስለ እርሱ እና ስለድሉ በትዊተር ሰሌዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ መጻፋቸውን በመግለጽ፤ ""አስቤ የማላውቀውን ህይወት ነው እየኖርኩ ያለሁት"" ይላል። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ሹራ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን ለሁለት አስርታት ያጣችውን ድል መመለስ ይፈልጋል። ""ለአገሬ እና ለልጆቼ ጥሩ ትዝታ እንዲሆን የወርቅ ሜዳሊያ ማምጣት እፈልጋለሁ። ከዚያም 'አባታችን የኦሎምፒክ ሜዳሊያ አሸናፊ ነው' ይላሉ።""" https://www.bbc.com/amharic/54546131 +business የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት ለምን ተስተጓጎለ? "በመላው ሃገሪቱ ባሉት ቅርንጫፎችና በትልቅነቱ ቀዳሚ እንደሆነ የሚነገርለት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአራት ተከታታይ ቀናት ተስተጓጉሎ የነበረውን አገልግሎት አስተካክሎ መደበኛ አገልግሎቱን መስጠት እንደጀመረ የባንኩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የአብሥራ ከበደ ለቢቢሲ ገለፁ። • በሴት ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የባንክ ቅርንጫፍ ተከፈተ • የአማራ ክልል ተፈናቃዮች ስለ ንግድ ባንክ እርዳታ ምን ይላሉ? ከሰሞኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የተለመደውን አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ ተገልጋዮች ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ22 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችና ከ1450 በላይ ቅርንጫፎች እንዳሉት የገለፁት ኃላፊው፤ ከባለፈው ሳምንት አርብ ጀምሮ ሲስተሙ የመዘግየት ችግር እንዳጋጠመውና ሙሉ በሙሉ ተስተጓጉሎ እንደነበር አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ባሳለፍነው እሁድ ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሶ የኤትኤም ማሽኖች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር ገልጸዋል። ይኽው አገልግሎት እንደገና ሰኞ ጠዋት ጀምሮ በድጋሚ መስተጓጎል ገጥሞት የነበረ ቢሆንም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መደበኛ አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል። ""በአጠቃላይ ለአንድ ቀን ተኩል ያህል ነበር አገልግሎቱ የተቋረጠው"" የሚሉት ኃላፊው አገልግሎቱ ከተስተካከለ በኋላ በየቅርንጫፎቹ የደንበኞች ቁጥር ጨምሮ ነበር ይላሉ። ስለ ሲስተሙ መጨናነቅ የተጠየቁት አቶ የአብሥራ ""እንዲህ ነው ተብሎ የሚገለፅ ነገር የለም፤ ግን ቴክኖሎጂ በባህሪው ድንገት የሚፈጠሩ ችግሮችን ያስተናግዳል"" ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። የሲስተም መጨናነቅ በባንኩ ውስጥ አሊያም በውጭ በሚፈጠሩ የኢንተርኔትና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት ሊፈጠር እ��ደሚችል የሚያስረዱት ኃላፊው፤ አሁን ያጋጠመው ችግር ግን በራሱ በባንኩ ሲስተም መጨናነቅ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ባንኩ ለሚመጡት 10 ዓመታት የሚያገለግል ዘመናዊ የመረጃ ቋት ያለው ቢሆንም ያጋጠመው እክል አንዳንድ ጊዜ በቴክኖሎጂ ላይ በሚፈጠሩ ጊዜያዊ ችግሮች ነው። በነበረው መስተጓጎል የደረሰውን ኪሳራ አስመልክተን ጥያቄ ያነሳንላቸው አቶ የአብሥራ ""ባንኩ የደንበኞች አገልግሎት ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ ነበር እንጂ፤ ባጋጠመው መስተጓል ያጋጠመው ኪሳራ ስሌት ውስጥ አልገባም""ብለዋል። ኃላፊው አክለውም ወደፊት ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም እየሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። የደንበኞች ቁጥር በጨመረ ቁጥርም እንዲህ ዓይነት መጨናነቆች እንዳይከሰቱ ባንኩ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንክ፣ የኢንተርኔት፣ ሲቢኢ ብር፣ በካርድ አገልግሎት ክፍያ መፈፀሚያ ማቅረቡን በመግለፅ ደንበኞች ሳይንገላቱና ሳይደክሙ አገልግሎቱን መጠቀም እንደሚችሉ ጠቁመዋል። እንደ አማራጭ የቀረቡት መንገዶች ከኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። በኢትዮጵያ ያለው የኢንተርኔት ተደራሽነትና ፍጥነት በርካቶች የሚማረሩበት ነው። እንዲያም ሲል በተለያዩ ምክንያቶች በተለያዩ ጊዜያት መዘጋቱ ጉዳዩን የከፋ ያደርገዋል። በመሆኑም እነዚህ ንግድ ባንክ ያስቀመጣቸው አማራጭ አገልግሎቶች የበለጠ ጫናው ላይ አይወድቁም ወይ? ስንል ለኃላፊው ጥያቄ አንስተን ነበር። ኃላፊውም ችግሮች መኖራቸውን አምነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለችግሮቹ እልባት ለመስጠት ሃገሪቱ ውስጥ ያለውን እንዲሁም የራሱንም መሠረተ ልማት አጣምሮ እንደሚጠቀም ገልፀዋል። በዚህ መካከል የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ደንበኞች ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል። ""እስካሁን ከ5 ሚሊዮን በላይ የኤትኤም ካርድ ተጠቃሚዎች እና ከ2 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ባንክ ተጠቃሚዎች አሉ"" የሚሉት ኃላፊው በኢትዮጵያ ካለው የሕዝብ ብዛት ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ በአገሪቱ የሚፈጠሩ ክፍተቶቹን ባንኩ እየሞላ አገልግሎት መስጠታቸውን እንደሚቀጥሉ ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያጋጠመው መስተጓጎል ተፈታ ካለ በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ ተጠቃሚዎችና የባንኩ ሠራተኞችን በመጠየቅ ለማረጋገጥ ባደረግነው ሙከራ የነበረው ችግር መፈታቱን የገለጹ ሲሆን በተወሰኑ ቦታዎች ላይ የሲስተም ዘገምተኛ መሆን እንዳለ ገልጸዋል። ስለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኃላፊው እንደነገሩን... • ከ22 ሚሊየን በላይ ደንበኞች አሉት • የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 542 ቢሊየን ብር ደርሷል • አጠቃላይ ሃብቱ ከ660 ቢሊየን ብር በላይ ነው • ከ5 ሚሊየን በላይ የኤ ቲ ኤም ካርድ ተጠቃሚዎች አሉት • ከ2 ሚሊየን በላይ የሞባይል ባንክ ተጠቃሚዎችን ያስተናግዳል • 38 ሺህ ሠራተኞች አሉት • ከ1450 በላይ ቅርንጫፎች አሉት • የደበኞች ቁጥር በየዓመቱ በ2 እና 3ሚሊየን ብልጫ ያሳያል።" https://www.bbc.com/amharic/news-49260745 +politics የአውሮፓ ሕብረት የአውሮፕላን እስርን ተከትሎ በቤላሩስ ላይ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ተስማማ "የአውሮፓ ሕብረት የቤላሩስ አየር መንገድ በአውሮፓ ሰማይ ላይ እንዳይበር ለማድረግ ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታወቀ። ሕብረቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው እሁድ ዕለት በበረራ ላይ የነበረ አውሮፕላን አንድ ጋዜጠኛን ለመያዝ ሲል አቅጣጫውን እንዲለውጥ ተገዶ ሚንስክ እንዲያርፍ መደረጉን ተከትሎ ነው። በብራስልስ በተካሄደው ስብሰባ የ27ቱ አባል አገራት መሪዎች የአው��ፓ ሕብረት አየር መንገዶችም በቤላሩስ ሰማይ ላይ ድርሽ እንዳይሉ ተናግረዋል። ሕብረቱ ሌሎች ተጨማሪ ምጣኔ ሃብታዊ ማዕቀቦችን እንደሚጥልም አስታውቋል። የ26 ዓመቱ ሮማን ፕሮታሴቪች ከግሪክ ወደ ሊቱያኒያ እየበረረ ሳለ ነበር አውሮፕላኑ ውስጥ ቦምብ ሊኖር ይችላል በሚል አውሮፕላኑ አቅጣጫውን ለውጦ ሚንስክ እንዲያርፍ የተገደደው። ይህንን ተከትሎ ምዕራባውያን አገራት ቤላሩስን በራየንኤር አውሮፕላን ጠለፋ ከሰዋል። አሁን ላይ የወጣ ተንቀሳቃሽ ምሥል ጋዜጠኛ ፕሮታሴቪች በምንስክ አየር ማረፊያ ከተያዘበት ጊዜ አንስቶ ያለ ፈቃዱና ጫና ተደርጎበት ምሥሉ መቀረጹን ያሳያል። ሰኞ ዕለት በወጣው በዚሁ ተንቀሳቃሽ ምሥል ጋዜጠኛው በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝና በቤላሩስ ግዛት የተከሰሰበትን ወንጀል እንደሠራ ተናዟል። ይሁን እንጅ የአገሪቷን ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ መሪን ጨምሮ የመብት ተሟጋቾች ጋዜጠኛ ፕሮታሴቪች ስህተቱን እንዲያምን ጫና ተደርጎበታል ሲሉ ተንቀሳቃሽ ምሥሉን ተችተዋል። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የቤላሩስ ባለሥልጣናት ድርጊት ""አስደንጋጭ ነው፤ በፖለቲካ ልዩነት እና በፕሬስ ነጻነት ላይ የተፈጸመ አሳፋሪ ጥቃት ነው"" ብለዋል። የጋዜጠኛ ፕሮታሴቪች አባት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ልጃቸው ድብደባ ሊፈጸምበት እንደሚችል ሰግተዋል። አባት ድሚትሪ ፕሮታሴቪች ሰኞ ዕለት ለቢቢሲ ሲናገሩ ልጃቸው ""በገዛ አገሩ ባለሥልጠናት እንዴት እንደሚያዝ በጣም ተጨንቄያለሁ"" ብለዋል። ""እንደሚወጣው ተስፋ እናደርጋለን። ሁኔታው ለማሰብም ያስፈራል። ድብደባ እና እንግልት ሊደርስበት ይችላል። በጣም ነው የሰጋነው"" ሲሉ ተናግረዋል። ድሚትሪ አክለውም "" በጣም ደንግጠናል ፤ ተበሳጭተናልም። እንዲህ ዓይነት ነገር በ21ኛው ክፍለ ዘመን ያውም በአውሮፓ እምብርት ላይ መፈፀም አይገባውም ነበር"" ብለዋል። የአውሮፓ ሕብረትን ጨምሮ ሁሉም የዓለም ማሕበረሰብ በባለሥልጣናቱ ላይ ታይቶ የማይታወቅ ጫና እንደሚያሳድር ተስፋ አለን ብለዋል ዲሚትሪ። ጫናውም እንደሚሰራና ባለሥልጣናቱ የሰሩት ተግባር ትልቅ ስህተት እንደሆነ እንደሚገነዘቡም ተስፋ እንደሚያደርጉ አባት ዲሚትሪ ገልጸዋል። ጋዜጠኛው ማነው? የ26 ዓመቱ ጋዜጠኛ ከቤላሩስ የወጣው እአአ በ2019 ነው። ኔክስታ ለተባለው መገናኛ ብዙኃን የቤላሩስም የ2020 ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ዘግቧል። ኔክስታ በዋነኛነት በቴሌግራም የሚሠራጭ መገናኛ ብዙኃን ሲሆን፤ በትዊተር እና በዩቲዩብ ላይም ይገኛል። በምርጫው ወቅትና ከምርጫው በኋላም የቤላሩስን የተቃውሞ ድምጽ በማሰማት ከፍተኛ ሚና አለው። ጋዜኛው ከምርጫ ዘገባው በኋላ ቤላሩስ ከሳዋለች። ቤላሩስ ውስጥ በሽብርተኝነት ስለተፈረጀ የሞት ቅጣት እንደሚጠብቀው ተቃዋሚዋ ስቪትና ቲካንቫክያ ተናግረዋል። ተቃዋሚዋ በምርጫው ማሸነፋቸውን ይናገራሉ። ሆኖም ግን ከቤላሩስ መንግሥት ሸሽተው ሊቱዋንያ ለመሸሸግ ተገደዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57230080 +health ኢትዮጵያ፡ ‘የማይናገሩት’ እና ‘የማይነገርለት’ የተንሰራፋው የወጣቶች ጭንቀት በብዙ ምክንያቶች ማንነቷ እንዲታወቅ አትፈልግም። እኛም እንዳትታወቅ በሚል ‘ቅድስት’ በሚል ስም እንጠራታለን። ቅድስት ዘንድሮ ነው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናዋን የወሰደችው። ከቢቢሲ ጋር ዛሬ ያገናኛት ጉዳይ ግን የተከሰተው ከሁለት ዓመት በፊት ነው። ገና አስረኛ ክፍል እያለች። “አንድ እኛ ትምህርት ቤት ከሚማር ልጅ ጋር የዐይን ፍቅር ይዞኝ ነበር” ስትል ትጀምራለች። አፍላ ፍቅር። በጓደኞቿ ግፊት ፈራ ተባ እያለች ‘የልቤን’ ያለችውን ነገረችው። ምላሹ ግን የልቧን አላደረሰውም። አዘነች። ተከፋች። የማዘን እና የመከፋቱ ጉዳይ መልከ ብዙ ነው። “አንዳንዴ ለምን ለጓደኞቼ ነገርኳቸው? እላለሁ” ትላለች። ጓደኞቿ እሷን ሲያዩ ርዕሰ ጉዳይ የሚሆነው የእሷ ‘የፍቅር ጥያቄ’ ሆኗል። ጓደኞቿ እሱን ሲያዩም ርዕስ የሚሆነው አሁንም የእሷ ‘የፍቅር ጥያቄ’ ነው። ጭንቀቱ ትምህርት ቤት ተወልዶ ቤት ድረስ ዘለቀ። “ቤተሰቦቼ ስለጉዳዩ አያውቁም” ትላለች። ቤተሰቦቿ የማያውቁትን ጉዳይ ግን የቤተሰቡ አባል አደረገችው። ስታጠናም አልጋ ላይ ተጋድማም ስለ ‘ትምህርት ቤቱ ልጅ’ ብቻ ሆነ ሃሳቧ። እንዳሁኑ አይሁን እንጂ ሌላም ሃሳብ ነበረባት። በትምህርቷ ጥሩ የምትባል ናት። ቤተሰቦቿም ለትልቅ ደረጃ የሚጠብቋት። በትምህርት ጥሩ ራመድ ካለ ቤተሰብም ነው የተገኘችው። በተለይ አባት ዲግሪውን አንድ ሁለት ሦስት እያሉ ደራርበውታል። ለዚህም ነው አባት የእኔን መንገድ ትከተላለች ብለው የሚኮሩባት ጭምር የሆነችው። ይህ በቀጥታም ሆነ በዘወርዋራ ትምህርትሽ ላይ አተኩሪ የሚል ግፊ ነበረው። ለእሷ ግን ሌላ የምታብሰለስለው ሌላ ምትጨነቅበት ጉዳይ ሆነባት። የምትወደውን ልጅ ማጣቷን እና ቤተሰቦቿ በሚፈልጓት ደረጃ አለመራመዷ ያስጨንቋት ገቡ። ቤትም ትምህርት ቤትም የሚያሳስቧት ነገሮች ሆኑ። ከቤት ትምህርት ቤት ከትምህርት ቤት ደግሞ ቤት ለምትለው ቅድስት ሌላ ማምለጫ መንገድ ጠፋ። “ሌላ ሰው የሆንኩ ያህል ተሰማኝ። የሚያስደስተኝ ነገር አጣሁ። እንቅልፍ በዓይኔ አልዞር አለ። ሌላ ሰው ሆንኩኝ” ትላለች። በዚህ ጊዜ ትንሽ እረፍት የሚሰጣት ‘የእኔ’ ከምትላቸው ጓደኞቿ ጋር መሆን ነው። ይህ ደግሞ ሁሌም አይሳካም። እሷ ብዙም እንድትወጣ አይፈቀድላትም። ጓደኞቿ ቤታቸው ሲሄዱ ደግሞ የልባቸውን ለማውራት አይመቻቸውም። በዚህ ውጣ ውረድ ሳምንታት ከነፉ። ቤተሰቦቿ ሳይሰሙ መፍትሔ ያመጡልኛል ያለቻቸውን መንገዶች አማተረች። መፍትሔ የለም። መጽሐፍትን አነበበች። መፍትሔ የለም። ዩቲዩብ ላይ ተጣደች። አሁንም መፍትሔ የለም። * * * የመጨረሻው መፍትሔ ወደ ህክምና ማዕከል ለመሄድ ሆነ። ይህም ግን ቀላል ውሳኔ አልነበረም። ለቤተሰብ ሳይናገሩ ህክምና መሄድ ከባድ ነው። ብዙ መዘዞችም አሉት። ብዙ ጥያቄ ያስከትላል። እሷ ደግሞ አንኳን ለብዙ ለአንድም ጥያቄ መልስ የላትም። ያለቤተሰብ ሐኪም ዘንድ መሄድ የድጋፍ ማጣት ስሜት ይፈጥራል። ለተማሪ ደግሞ ሌላ ፈተና አለው - ገንዘብ አለማግኘት። ‘ቁጥጥር ለሚበዛባት’ ቅድስት ከትምህርት ቤት ቀርቶ ሐኪም ዘንድ መሔድ በራሱ ከባድ ነበር። አውጥታ አውርዳ ግን አንድ ውሳኔ ላይ ደረሰች። ለብቻዋ ወደ ህክምና መሔድ። “እኔም የሚሰጠኝን [የኪስ ገንዘብ] አጠራቅሜ ጓደኞቼም ሰጥተውኝ ሐኪም ቤት ሄድኩኝ” ትላለች። ሐኪሙ ጭንቀት እንዳለባት ነገራት። አሁን ወደ አቶ ብርሃኑ ራቦ እናቅና። አቶ ብርሃኑ የሞሽን የማማከር እና የሥልጠና ድርጅት  ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው። “በብዙ ፀሐፊዎች ወይም ፈላስፋዎች አረዳድ ውጥረት ወይም ጭንቀት ሰው አሁን ያለበት እና በመድረሻው መካከል ያለው ርቀት ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ በሚፈጠር ተስፋ ማጣት የሚከሰት ነው ይላሉ” ሲሉ ይገልጻሉ። ቅድስት ስላሳለፈችበት የሕይወት መስመር ለአቶ ብርሃኑ ስናጫውታቸውም “ውጥረት ወይም ጭንቀት በተለይ ዕድሜያቸው 20 እና ከዚያ በታች የሆኑ ልጆች ዘንድ እየጨመረ ነው። ቤተሰብ፣ መምህራን እና ማኅበረሰቡ ሳያውቁ ስር እየሰደደ እየተሰቃዩበት ነው። ማንም ስለማይረዳቸውም በራሳቸው መንገድ መፍትሔ ለመፈለግ ይጥራሉ” ብለዋል። ምክንያቱ ምን ይሆን ሲባሉ መልከ ብዙ መሆኑን ይጠቁማሉ ባለሙያው። አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ችግሮች ፍርሃት እንዲያድርባቸውና ተስፋ እንዲቆርጡ ያደርጋቸዋል። “ጤና፣ ችግር፣ የሠላም እጦት ችግር አለ። የሰዎችን ሞት መስማት ኖርማል (የተለመደ) ሆኗል” የሚሉት አማካሪው አቶ ብርሃኑ፣ ስለዚህ ወጣቶች ተስፋ የማይታያቸው በጣም የሚጨነቁ እና ውጥረት ውስጥ የሚገቡ ሆነዋል ሲሉ ያስረዳሉ። ማን ከጎኔ አለ ሳይባል ስለዘረኝነት፣ ስለሃይማኖት. . . ጦርነት ይወራል። ወጣቶችን እና ህጻናትና ሳያማክል መኖራቸውን እንኳን ከግምት ሳይገባ ይወራል። ትርፉ ልጆችን መጉዳት ነው ሲሉ አቶ ብርሃኑ ያስረዳሉ። በተጨማሪ ደግሞ የቴክኖሎጂ በረከት የትዬ ለሌ ነው። ከህጻን እስከ አዋቂ መዳፍ ላይ ፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቲዩብ . . .  በቀላሉ የሚገኝበት ዘመን ነው። የሚታጨደው በረከት ግን መልካሙም ብቻ አይደለም። እንክርዳዱም ጥቂት አይደለም። አቶ ብርሃኑ ሩብ ክፍለ ዘመን በማማከር እና በማሠልጠን አሳልፈዋል። ዓመት ዓመትን ሲተካ በጭንቀት እና ድባቴ የሚሰቃዩ ሰዎች ቁጥር መናሩን ይናገራሉ። ምክንያቱን ለማወቅ ደግሞ አነስተኛ ጥናት አከናውነዋል። “ዘመኑ ሰዎች የማይረኩበት። በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ ነገሮች የፈጣሪን ህላዌ ራሱ የሚጠራጠሩበት፤ ‘ፈጣሪ እያለ ለምን ይሔ ሆነ?’ የሚል ሊመልሷቸው የማይችሏቸው ጥያቄዎች ውስጥ የመግባት ዕድል አለ።” “ቤተሰብ፣ እናት እና አባት እያለኝ ለምን ይሔ ደረሰብኝ? ለምን ይሔ ሆነብኝ? መንግሥት እያለ ለምን ይሔ ሆነ?” እያሉ ከሚተማመኑበት ነገር እየራቁ ሲሄዱ መፍትሔ፣ ረዳት እና አቅም የማጣት ሁኔታ ይመጣል። “በተስፋ ከመሞላት ወደ ተስፋ መቁረጥ ይሄዳሉ።” መፍትሔ የሚሉት ደግሞ ከባህል፣ ከእምነት እና ከእሴት የወጡ ነገሮችን ማድረግ ነው። “በመቀጠል በራሳቸውም በሌላውም ላይ መጨከን ነው” ይላሉ። በቅርቡ በማኅበራዊ ሚዲያ ራሳቸውን እንደሚያጠፉ ተናግረው ራሳቸውን ያጠፉ መኖራቸውን አስታውሰው “ይህ አስደንጋጭ ነው” ሲሉ አቶ ብርሃኑ ያስረዳሉ። “ሞትን የመሰለ ከባድ ነገር በቀጠሮ ወስነህ ስታደርገው ውጥረታችን እና ጭንቀታችን በሰው፣ በምድር እና በሰማይ ተስፋ መቁረጣችን ምን ያህል እንደሆነ በትክክል ይገለጻል። ልጆችን ተሰናብቶ ወደ ሞት መሄድ ወደየት እየሄድን እንደሆነ ያሳያል” ሲሉ ያክላሉ። “እንደተከታታይ ፊልም በላያችን ላይ የሚመላለሰው ጦርነት፣ አካላዊ እና ቁሳዊ ጉዳቱን እንጂ ሥነልቦናዊ አደጋው ታስቦ እየተሠራበት አይደለም” ይላሉ። ይህም ልጆች ተስፋ እንዲቆርጡ፣ ነገን እንዳያስቡ፣ እንዳያልሙ፣ የሰውነት ክብርን እና ሰብዓዊነትን እንዲያጡ ያደርጋቸዋል በሚል ይገልጻሉ። “የሰብዓዊ እና ማኅበራዊ ቀውስ በኢኮኖሚው ላይ ተደምሮ የምንይዘው የምንጨብጠው አጥተናል” በማለት የእለት ከዕለት ሕይወት ጫናም የእራሱ አሉታዊ ውጤት አለው ይላሉ። “የመኖር ትርጉም ሲያጣባቸው የማያውቁትን ዓለም መሞትን ወደ መምረጥ ይሄዳሉ” የሚሉት አቶ ብርሃኑ “ከዚህ አንጻር እንደባለሙያ የሚያሳስበን ትኩረት ማጣት ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። ይህ ‘ጊዜ ቦንብ’ ነው የሚሉት አቶ ብርሃኑ ያውም ‘ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ’ ይላሉ። ቤተሰብ በሙሉ ቴክኖሎጂ ላይ ተጥዶ ሰው አፍ ለአፍ የማይነጋገርበት ሁኔታ እያደገ ነው። ሰው ችግሩን የሚነግረው ለሚሰማው ለሚያዳምጠው ነው። ወላጆች የራሳቸውን ችግር ለማለፍ ወይም ዓላማቸውን ለማሳካት እንጂ ልጆችን ለመስማት ጊዜ የላቸውም። “ወላጆች ልጆቻቸውን፣ መምህራን የተማሪዎቻቸው ችግር ከማዳመጥ የራሳቸውን ችግር ነው የሚያሰላስሉት። ‘እኔ ለመግባችሁ ስሯሯጥ’ በሚል የልጆቹን ችግር እንደምቾት እና ድሎት ነው የሚያዩት” ይላሉ አቶ ብርሃኑ። ልጆቹ ችግራቸውን ያጠራቅሙና ከወላጆች። ከመ���ህራን እና ከማኅበረሰቡ ደብቀው በራሳቸው መንገድ ለመፍታት ይሞክራሉ። ያውም “ጥሩ ባልሆነ፣ በማይመከር እና ችግሩን በሚያባበስ መልኩ ለመፍታት ይሯሯጣሉ።” “ይህንን አድርገው ሲያቅታቸው ደግሞ ራሳቸውን ይጠላሉ፣ እንቅለፍ ያጣሉ። እያደረ ፍርሃት ውስጥ ይከታቸዋል። ሁሉም እያወቀበቸው መሆኑን ከፍተኛ እርምጃ ይወስዳሉ” ይላሉ። የቅድስት ወላጆች ልጃቸው ያላትን ለውጥ መከታተል ነበረባቸው። ለእሷም ከባድ ቢሆንም ችግሩን ለቤተሰቦቿ ማሳወቅ የተሻለ ቀላል ያደርግላት ነበር። “እነዲህ ዓይነት ነገር በብዛት ያጋጥማል። ከትንንሽ ልጆች ጀምሮ በማይታወቅ ድባቴ ውስጥ ያሉ አሉ” ይላሉ ባለሙያው። ስለ ቅድስት ያጫወትናቸው አቶ ብርሃኑ እሳቸውም በርካታ ተመሳሳይ ታሪክ እንደሚያውቁ ይናገራሉ። ከእነዚህም መካከል አንዱን አውግተውናል። “አንድ በጣም ጎበዝ ወጣት ነበር። በጥሩ ቤተሰብ ውስጥ ያደገ ነው። ዩኒቨርሲቲ ሲገባ ችግሩን የሚሰማው ስለሌለ ይጨነቅ ጀመረ። ቤተሰቡ ለእሱ ያላቸው ግምት ትልቅ በመሆኑ፣ ትምህርቱን መከታታል አልቻለም። በኋላም ትምህርቱን አቋረጠ። ወላጆቹ ይህን ሁሉ አያውቁም።” ነጻ አገልግሎትም የሚሰጡት አቶ ብርሃኑ ተማሪው ቢሯቸው ሲደርስ ፊታቸውን አላዞሩበትም። “እና ተገቢውን ድጋፍ ሰጥተነው ወደ ትምህርቱ ተመልሶ ዓላማው እንዲያሳካ እገዛ አደረግንለት” ሲሉ ያስታውሳሉ። “ብዙ ወላጅ ልጆቼ ጥሩ ናቸው። ጎበዝ እና ሥነ ምግባር ያላቸው ናቸው ይላሉ እንጂ ብዙ ወጣቶች በከፍተኛ ሁኔታ ድባቴ ውስጥ ነው ያሉት።” “በአገራችን ብዙ ነገር ተስፋ የሚያስቀርጥ ይሆንባቸዋል። ወላጆች ትልልቅ ርዕሶችን ቤት እና መኪና ውስጥ ያወራሉ። ቲቪው እና ስልካቸው የሚዘገንን መረጃ ይሰጣል። ልጆቹ ትምህርት ቤት ሌላ፣ ቤት ሌላ ናቸው። ጓደኞቻው ጋርም ሌላ ናቸው። በዚህ ምክንያትም የተለያየ ስብዕና ያዳብራሉ” ይላሉ አቶ ብርሃኑ። ለአቶ ብርሃኑ እነዚህን ከፍተኛ ችግሮች በአነስተኛ ድርጅቶች ብቻ መፍታት ከባድ ነው። “ከቁስ እና ኢኮኖሚው በላይም በዘመቻ ከምንም በላይ መሠራት አለበት ብለን የምናምነው የሰው አዕምሮ ላይ ነው” ይላሉ። ይህ ሕብረተሰቡ እና መንግሥት ኃላፊነት ነው። ወጣቶች ደግሞ ሌላ ኃላፊነት አለባቸው። “ወጣቶች እውቀት ላይ ትኩረት ያድረጉ። አካላዊ እንቅስቃሴ አለባቸው። ከዲጂታል ይልቅ መጽሐፎችን በእጅ ይዞ እያገላበጡ ማንበብ። በተቻለ መጠንም ከቴክኖሎጂ ጋር የሚቆዩበትን ጊዜ መቀነስ አለባቸው” ይላሉ አቶ ብርሃኑ። በተጨማሪም በቀን ስንት ሰዓት ማየት እንዳለባቸው መለየት እና ከቻሉ በሳምንት አንድ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ከቴክኖሎጂ ውጪ መሆን ያስፈልጋል። ከተፈጥሮ ጋር መገናኘት፣ ስፖርት መስራት፣ በበጎ አድራጎት መሳተፍ እና  ህይወታቸውን በተቻለ መጠን መንፈሳዊ ማድረግ እንደሚያስፈለግ ባለሙያው አጥብቀው ይመክራሉ። “ዘመኑ ፈጣን ነው። ይህን ሊታደግ የሚችል ፈጣሪ እንዳላቸው በማየት ለሕይወታቸው ቅርጽ መስጠት። በሕይወት ክህሎት ሥልጠናዎች እንዲሳተፉ ማድረግ ያስፈልጋል። በተለይ ደግሞ ወጣቶች የትምህርት፣ የሥራ እና ሌሎች መከወን ያለባቸው ነገሮች መብዛት ሳይሆን ለበርካቶች የጭንቀት ምንጭ የሚሆነው፣ እያንዳንዱን ሥራ በጊዜ አለመሥራት መሆኑን እንዲገነዘቡ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለዚህ ወላጆች እና ልጆች ያላቸውን ጊዜ እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው መልመድ ይገባል የሚሉት አቶ ብርሃኑ “የሰዓት አስተዳርን ከቤት ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል።” ወደተነሳንበት ታሪክ እንመለስ። አሁን ቅድስት በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ህክምናዋን በደንብ ተከታትላለች። “ሐኪም ቤት ደርሼ የተመለስኩ ቀን ነው የሆነ ነገር የቀለለኝ” ስትል ታስታውሳለች። “ቤት የደረስኩት ፈገግ ብዬ ነበር። ከረዥም ጊዜ በኋለ ጥሩ እንቅልፍም ተኛሁኝ” ብላለች። ሕክምናውም ቢሆን ግን መዘዝ ነበረው። በተለይ ቤተሰብ ሳያውቅ መድኃኒት ደብቆ መዋጥ ፈተና ነው። አንዴ ወስና የገባችበት በመሆኑ ግን ተወጣችው። ዘንድሮ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለመግባት በመዘጋጀት ላይ ትገኛለች። ቤተሰቦቿ እንደሚጠብቋት በትምህርቷ መግፋት ትፈልጋለች። ያውም አባቷ በሚፈልጉት የትምህርት ዘርፍ ነው መቀጠል የምትፈልገው። አባት እና ልጅ በአንድ የትምህርት መስክ ሊጓዙ ነው። አሁንም ግን ከስጋት ነጻ አይደለችም። ጉዳዩን ለቤተሰቦቿ አለመንገሯ ያሳስባታል። ቢያውቁስ የሚል ስጋት አለባት። ግን ከቀድሞው የተሻለ ጥንካሬ ስላላት ምንም ቢመጣ ከቤተሰቦቿ ጋር እንደምታልፈው ታምናለች። https://www.bbc.com/amharic/articles/c5152vjxv3no +health ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ የተከተቡ ዜጎቿ ጭምብል ሳያደርጉ መሰባሰብ ይችላሉ አለች "የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) የኮሮናቫይረስ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ወደቀደመ ህይወታቸው መመለስ ይችላሉ የሚል መመሪያ አውጥቷል። በዚህም መሰረት ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ጭምብል (ማስክ) ሳያደርጉ በቤት ውስጥ መሰብሰብ ይችላሉ ተብሏል። ሲዲሲ እንዳስታወቀው የመጨረሻውን ክትባት ከተከተቡ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከኮሮናቫይረስ ስጋት ነፃ ናቸው ብሏል። እስካሁን ድረስ አሜሪካ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿን ከትባለች። የአገሪቱ የጤና ባለስልጣናት አዲሱን የደህንነት መመሪያ ይፋ ያደረጉት በትናንንትናው እለት ዋይት ሃውስ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ግብረ- ኃይል መግለጫ ላይ ነው። መመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ማድረግ ይችላሉ ብሎ ካስቀመጣቸው መካከል፦ ""ከኮቪድ-19 በኋላ ሊኖር የሚችለውን አለም ማየት ጀምረናል። የበለጠ ዜጎቻችን በተከተቡ ቁጥር ማከናወን የምንችላቸውን ተግባራትም ይጨምራሉ"" በማለት የዋይት ሃውስ ከፍተኛ አማካሪ አንዲ ስላቪት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ህዝባዊ በሆነ ቦታ ላይ ጭምብል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ እንዲሁም አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማስወገድና የተጣሉ የጉዞ ገደቦችን መከተል ይኖርባቸዋል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ መመሪያው ያልተከተቡና ለኮሮናቫይረስ በበለጠ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦችም በተለይ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስቀምጧል። አሜሪካ በቅርቡ የምትከትባቸውን ዜጎቿን ቁጥር በከፍተኛ እየጨመረ መሆኑን ያስታወቀች ሲሆን እስካሁን ድረስ 90 ሚሊዮን ሰዎች ተከትበዋል። በተለይም የጆንሰን ጆንሰን የአንድ ጊዜ ክትባት እውቅና ማግኘቱ አቅርቦቱን ጨምሮታል ተብሏል። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ ኮቪድ-19 የማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ መሆኑ ቀጥሏል። አገሪቱ እስካሁን ድረስ 29 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን 525 ሺህ ዜጎቿንም አጥታለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-56330257 +politics እነ አቶ ጀዋር መሐመድ ለሁለተኛ ጊዜ በራሳቸው ፍቃድ ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ "አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ እና አቶ ደጀኔ ጣፍ ለሁለተኛ ጊዜ በራሳቸው ፍላጎት ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የዛሬውን ቀጠሮ ይዞ የነበረው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በሚሰሙበት ሁኔታ ላይ ክርክር ለማድመጥ እና ከዚህ ቀደም ችሎት ሳይገኙ የቀሩት ተከሳሾች ከችሎት የቀሩበትን ምክንያት እንዲያብራሩ ነበር። በዛሬው ችሎት በእነ አቶ ጀዋር የክስ መዝገብ ስ��� ከተዘረዘሩ ተከሳሾች መካከል ከላይ ስማቸው የተጠቀሱት አራት ግለሰቦችን ጨምሮ አቶ አማን ቃሉ የተባሉ ተከሳሽ ችሎት ሳይገኙ ቀርተዋል። አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ እና አቶ ደጀኔ ጣፋ ችሎት ያልተገኙበትን ምክንያት በጠበቃቸው በኩል ለችሎቱ አድርሰዋል። ዐቃቤ ሕግ ግን ተከሳሾች ችሎት የማይቀርቡበትን ምክንያት በጠበቃቸው በኩል መናገር የሚፈቅድ የሕግ አካሄድ የለም በማለት ፍርድ ቤቱ ለተከሳሾች ጠበቃ እድል እንዳይሰጥ ጠይቋል። ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾች ጠበቃ ሐሳባቸውን እንዲያቀርቡ እድል ሰጥቷል። በዚሁ መሠረት ""የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚው አካል የፍርድ ቤት ውሳኔን እያከበረ አይደለም፤ ከእስር የወጡ ጓደኞቻችን የት እንዳሉ አናውቅም"" ሲሉ እነ አቶ ጀዋር በጠበቃቸው በኩል ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል። ተከሳሾቹ በፍርድ ቤት ነጻ ተብለው ከእስር ቢወጡ ተመሳሳይ እጣ ሊገጥመን ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው አራቱ ተከሳሾች በጠበቃቸው በኩል አስታውቀዋል። እነ አቶ ጀዋር በጠበቃቸው በኩል ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ፤ አራት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ከእስር ከወጡ በኋላ የደረሱበት አልታወቀም ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ተከሳሾቹ ችሎት ሳይቀርቡ የቀሩበት ምክንያት አጥጋቢ አይደለም ብሏል። በዚህም መሠረት ማረሚያ ቤቱ አራቱን ተከሳሾች ""ሌሎች ተከሳሾችን ችሎት እንደሚያቀርበው እነዚህንም ያቀርብ"" ሲል ትዕዛዝ በመስጠት ለሐምሌ 21/2013 ዓ. ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57737839 +health ኮሮናቫይረስ፡ ዶ/ር ፋውቺ ለክትባት መጣደፉ ቢቀርብን ይሻላል አሉ የአሜሪካ ዕውቅ የማኅበረሰብ ጤናና የተላላፊ በሽታዎች ጉዳይ ኃላፊ ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ‹‹እኔ ተናግሪያለሁ! ይሄ ለክትባት የምንጣደፈው ነገር አላማረኝም›› እያሉ ነው፡፡ ይህን የተናገሩት ዶናልድ ትራምፕ የመጪው ምርጫ በለስ እንዲቀናቸው በሙከራ ላይ ያለን ክትባት ያለጊዜው ወደ ሕዝብ በማውጣት ‹ክትባት ደርሷልና ተከተቡ› እንዳይሉ ስጋት መፈጠሩን ተከትሎ ነው፡፡ ዶ/ር ፋውቺ በአሜሪካ ህዝብ ከትራምፕ የበለጠ ተሰሚነትና የመታመን ፀጋን ያገኙ ጎምቱ የጤና ባለሞያ ናቸው፡፡ ከሮይተርስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት አንድን ክትባት የሕክምና ደንብና መርሆችን ሳይከተሉ ወደ ሕዝብ ማውጣት የሌሎች ክትባቶችን ተስፋ ያጨልማል፡፡ ትራምፕ አንድን ክትባት ሙሉ ሒደቱን ሳይጨርስና በብዙ ሰዎች ላይ ሙከራ ሳይደረግበት ይፋ ለማድረግ እየተዘጋጁ ነው የሚሉ መረጃዎች እየወጡ የሚገኙት ካለፈው ሳምንት ወዲህ ነው፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይህን ለማድረግ የተበረታቱት በሕዝብ ዘንድ ያላቸውን ቅቡልነት በኅዳር ከሚደረገው ምርጫ በፊት ለመጨመር በመሻት ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ትራምፕ ከጆ ባይደን ያነሰ ቅቡልና እንዳላቸው የሕዝብ ፖለቲካዊ ሙቀት መመተሪያ ዳሰሳ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ዲሞክራቶች ‹‹እኚህ ትራምፕ የሚባሉ ሰውዬ ለዝናቸው ሲሉ የአሜሪካውያንን ሕይወት ለፖለቲካ ቁማር እያዋሉት ይገኛሉ›› ብለው ከሰዋቸዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትዊተር ሰሌዳቸው እንደጻፉት ከሆነ የአሜሪካ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ለመድኃኒት አምራቾች ሥራቸውን እያደናቀፈባቸው ነው፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይህን የሚሉት የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ‹ክትባት አምራቾች ትክክለኛውን የመድኃኒት አመራረት ሒደት ተከትለው እንዲሄዱ› በተደጋጋሚ በማሳሰቡ ነው፡፡ ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ዶናልድ ትራምፕ በኦክስፎድና በአስትራዜኔካ አማካኝነት እየተሞከረ ያለው ክትባት ለአስቸኳይ የሕክምና አገልግሎት በአቋራጭ ለሕዝብ እንዲቀርብ የሚቻልበትን መንገድ እየፈለጉ እንደሆነ ዘግቦ ነበር፡፡ እነ ኦክስፎርድ እየሞከሩት ባለው ክትባት ለመሳተፍ 10 ሺ አሜሪካዊያን ፈቃደኝነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ነገር ግን የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን 30ሺህ ፈቃደኞች ካልተሟሉ ይሁንታን አልሰጥም እያለ ነው፡፡ የኦክስፎርድ ክትባት አሁን ዓለም ላይ እየተሞከሩ ካሉ በዐሥራዎቹ ከሚገኙ ምርምሮች እጅግ ተስፋ የተጣለበት ነው፡፡ ባለፉት ሳምንታት ታዋቂ መድኃኒት ፋብሪካዎች መድኃኒቶቻቸውን በመሞከር ላይ ተጠምደው ቆይተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የኤሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር የወባ መድኃኒት የሆነው ሀይድሮክሲክሎሮኪዩን ለኮሮና ታማሚዎች ቢሰጥ እንደማይቃወም ተናግሮ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን መድኃኒቱ ከጥቅሙ ጉዳት ማመዘኑ በምርመራ በመረጋገጡ እውቅና ነፍጎታል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ይህን መድኃኒት ለሳምንታት መውሰዳቸውንና ፍቱን እንደሆነ እንደደረሱበት በተደጋጋሚ ይናገራሉ፡፡ ዶ/ር ፋውቺ እንደሚሉት ክትባቶች ትክክለኛውን አካሄድ ካልተከተሉ አደጋ ማስከተላቸው ብቻም ሳይሆን ሰዎች በቀጣይ በሚወጡ መድኃኒቶች እምነት ያጣሉ፣ እንዲመከርባቸው የሚፈቅዱ በጎ ፈቃደኞችንም ማሸሽ ይሆናል፡፡ ዶ/ር ፋውቺ ፖለቲካ ሕክምና ውስጥ ገብቶ መፈትፈት የለበትም፡፡ ሕክምና የራሱን መንገድ እንዲከተል ሊተው ይገባል የሚል አቋም አላቸው፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-53900469 +politics የኢትዮጵያ መንግሥት በደቡብ አፍሪካ ለሚካሄደው ድርድር የቀረበለትን ጥሪ ተቀበለ የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት አማካይነት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለሚካሄደው የሰላም ድርድር የቀረበለትን ግብዣ መቀበሉን አስታወቀ። በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማብቃት እንዲቻል የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ መንግሥትን እና የትግራይ ኃይሎችን ድርድር እንዲጀምሩ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ነበር ጥሪ ያቀረበው። መንግሥት በኮሙኒኬሽን አገልግሎት በኩል የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፣ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ይፋዊ ጥሪ ማቅረቡን አረጋግጧል። የአፍሪካ ኅብረት ግብዣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ በፊት ያቀረባቸውን አቋሞች የጠበቁ ናቸው በማለት፤ ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ብቻ እንዲሆን እና ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲደረግ መንግሥት አቋሙን ሲገልጽ መቆየቱን አመልክቷል። ስለዚህም መንግሥት ግጭቱን ለመፍታት ሲወስዳቸው የቆዩትን ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ እርምጃዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። በተመሳሳይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት የኢትዮጵያ መንግሥት የሰላም ንግግር  ጥሪውን መቀበሉን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የድርድር ጥሪውን የተቀበለው “ግጭቱን በሰላም ለማብቃት እና ካለቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር ካለው አቋም ጋር የሚጣጣም” በመሆኑ ነው ብለዋል። በኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሐማት ተፈርሞ ቅዳሜ መስከረም 21/2015 ዓ.ም. በተጻፈው የንግግር የግብዣ ጥሪ ላይ የመጀመሪያ ደረጃው ንግግር በመጪው ቅዳሜ ወይም እሁድ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እንደሚጀመር ይጠበቃል። ቢቢሲ የተመለከተው ከአፍሪካ ኅብረት ተጽፏል የተባለው ደብዳቤ ድርድሩ የሚጀመርበት ቀንን በተመለከተ ስህተት እንዳለ ያሳያል። ደብዳቤው እሁድ መስከረም 28 የሚል ቢሆንም እሁድ ግን መስከረም 29 ነው። ሮይተርስ የዜና ወኪል በበኩሉ ከዲፕሎማቲክ ምንጮች አረጋገጥኩ እንዳለው፣ የአፍሪካ ኅብረት ለህወሓት ሊቀ መንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የግ���ዣ ደብዳቤ መጻፉን ዘግቧል። የዜና ወኪሉ ስለ ግባዣው የህወሓት ቃል አቀባይ ከሆኑት ከአቶ ጌታቸው ረዳ ማረጋገጫ ለማግኘት ጥያቄ አቅርቦ፣ በቅርቡ ይካሄዳል ስለሚባለው ንግግር የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል ብሏል። በኅብረቱ ተጻፈ የተባለው ደብዳቤ እንደሚለው በሁለቱ ወገኖች መካከል ከቀናት በኋላ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ንግግር ለቀጣይ ድርድር አስፈላጊ በሆኑ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ አመልክቷል። የጦርነቱ መባባስን ተከትሎ የአፍሪካ ኅብረት የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆን ለአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካዩ አድርጎ ሰላም ለማውረድ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል። ከቀናት በኋላ ለማድረግ የታሰበው ይህ የሰላም ንግግር በኦሉሴጉን ኦባሳንጆ የሚመራ ሲሆን፣ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ጨምሮ ሌሎች አሸማጋዮች እንደሚሳተፉበት ተነግሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሐመር ከሰኞ መስከረም 23/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ አፍሪካ በመምጣት ሰላም እንዲወርድ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መግለጹ ይታወሳል። ልዩ መልዕክተኛው ከሚጎበኟቸው አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ አንዷ ስትሆን፣ ከሰኞ መስከረም 23 አስከ ጥቅምት 08/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ በፕሪቶሪያ እና በናይሮቢ በሚኖራቸው ቆይታ ከየአገራቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር እንደሚነጋገሩ ተገልጿል። ባለፈው መጋቢት ወር የሰብአዊ እርዳታን ለማቅረብ ተደርሶ የነበረው የተኩስ አቁም ነሐሴ 18/2014 ዓ.ም. በተቀሰቀሰው ጦርነት ፈርሶ በበርካታ የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ውጊያዎች ከተቀሰቀሱ በኋላ፣ የአሁኑ የማይክ ሐመር ጉዞ ሁለተኛው ነው። ከአንድ ወር በኋላ ሁለት ዓመት የሚሞላው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ አሜሪካ ለአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኝነት የሰየመቻቸው ሦስተኛው ዲፕሎማት የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሐመር፣ ባለፉት አራት ወራት በአዲስ አበባ እና በመቀለ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እና ከትግራይ አመራሮች ጋር ተገናኝተዋል። ግብ ብሎ የነበረው ጦርነት ማገርሸቱን ተከትሎ አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲታቀቡ ጠይቀው፣ ውጥረቱን በማርገብ በተለይ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ሁሉ እንዲደርስ ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ይህ ጦርነት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. ትግራይ ክልል ውስጥ ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ተስፋፍቶ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱበት የሚታመን ሲሆን፣ በመቶ ሺዎች ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ሁሉም የጦርነቱ ተሳታፊዎች ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንደፈጸሙ በተደጋጋሚ ሲከሰሱ የነበረ ሲሆን፣ በተጨማሪም ቁሳዊ ውድመትን ባስከተለው በዚህ ጦርነት ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ ነዋሪዎች እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል። አስተማማኝ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ በሆነበት በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢ አሁንም ጦርነቶች እንደሚካሄዱ ከተለያዩ ምንጮች የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ሁለቱም ወገኖች ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸውን ከገለጹ ወራት የተቆጠሩ ቢሆንም፣ አስካሁን በይፋ ንግግር ጀምረው ተጨባጭ እርምጃዎች አልታዩም። ይልቁንም ጋብ እያለ የሚቀሰቀሰው ጦርነት በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን አለመረጋጋት በማባባስ ለነዋሪዎች መፈናቀል እና ለእንቅስቃሴዎች መስተጓጎል ምክንያት ሆኗል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cgrd55vr82go +sports ኢትዮጵያ ጫፍ በደረሰችበት የአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ሰባት አገራት ትላንት ተለዩ "ትላንት በተካሄደ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ወደ በካሜሮን አዘጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ ተጨማሪ ሰባት አገራት ተለዩ። ጋምቢያ፣ ኮሞሮስ፣ ጋቦን፣ ጋና፣ ግብጽ፣ ዚምባብዌ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ናቸው ወደ አህጉራዊው ውድድር ማለፋቸውን ያረጋገጡት አገራት ናቸው። ጋምቢያ አንጎላን በሜዳዋ 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አልፋለች። በምድብ አራት የምትገኘው ጋምቢያ ከሁለቱ አላፊ ቡድኖች አንዷ የሚያደርጋትን ወሳኝ ጎል አሳን ሴሳይ ከዕረፍት መልስ አስገኝቷል። በዚህ ምድብ የምትገኘው ጋቦን ዲሞክራቲክ ኮንጎን 3 ለ 0 በማሸነፍ ሌላኛዋ አላፊ አገር ሆናለች። በዚህም ጋቦን የ2019ኙ ውድድር ካመለጣት በኋላ ወደ ውድድር መድረኩ ለመመለስ በቅታለች። ፒየር-ኤሚሪክ ኦባሜያንግ፣ ዴኒስ ቡዋንጋ እና አሮን ቡውፔንዛ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው። ባለፉት 4 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተሳትፋ የነበረውች ኮንጎ፤ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። በካሜሩን አዘጋጅነት ለመኪሄደው ውድድር ለማለፍ በምድብ 6 የምትገኘው ግብጽ የሚያስፈልጋትን አንድ ነጥብ ለማግኘት ከኬንያ ጋር ተጫውታ 1 ለ 1 አቻ ተለያይታለች። ፈርኦኖቹ ከኮሞሮስ ጋር እኩል ዘጠኝ ነጥብ ይዘዋል። ኬንያ አራት ነጥብ ሲኖራት ቶጎ በሁለት ነጥብ በምድቡ ግርጌ ላይ ትገኛለች። በናይሮቢ በተካሄደው ጨዋታ ማግዲ አፍሻ በሁለተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ግብጽ ቀዳሚ ሆናለች። ከእረፍት መልስ ኬንያ በአብደላህ ሃስ አማካኝነት አቻ ለመሆን ችላለች። ቀድም ብላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ መሳተፏን ያረጋገጠችው ኮሞሮስ ከሜዳዋ ውጪ ከቶጎ ጋር 0 ለ 0 ተለያይታለች። ከዚህ በፊት በውድድሩ መሳተፍ ያልቻሉት ቡድኖች ከ2019 ጀምሮ 16 የነበረው የተወዳዳሪ አገራት ቁጥር ወደ 24 በማደጉ ተጠቃሚ ለመሆን ችለዋል። ከምድብ ሦስት ለማለፍ ከደቡብ አፍሪካ ጋር 1 ለ 1 በሆነ ውጤት አቻ በመውጣት ጋና ወደ ውድድሩ የሚያስገባትን ትኬት ቆርጣለች። መሐመድ ቁዱስ ከ2010 የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በኡራጓይ ተሸንፈው በወጡበት ስታዲየም ቀዳሚ የሚያደርጋቸውን ጎል ቢያስቆጥርም በደቂቃዎች ልዩነት ፐርሲ ታው ደቡብ አፍሪካን አቻ አድርጓል። ካለፉት 15 ውድድሮች በአንዱ ብቻ ያልተካፈሉት ጥቁሮቹ ከዋክብት አስር ነጥብ በመያዝ ከደቡብ አፍሪካ እኩል ሆነዋል። በስድስተኛው እና በመጨረሻው የምድቡ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ ዘጠኝ ነጥብ ካላት ሱዳን ጋር ትጫወታለች። ጋና ከሱዳንም ሆነ ከባፋና ባፋናዎች ጋር በነበራት ጨዋታ ያላት ውጤት የተሻለ በመሆኑ የአራት ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮኗ ከውድድሩ ውጭ የምትሆንበት ሁኔታ የለም። ዚምባብዌ ከሜዳዋ ውጪ ቦትስዋናን 1 ለ 0 አሸንፋለች። አልጄሪያ በሌላ የምድቡ ጨዋታ ከዛምቢያ ጋር 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቃለች። በዚህም ዚምባብዌ እና አልጄሪያ ተያይዘው ሲያልፉ የ2012ቱ ውድድር አሸናፊ ዛምቢያ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ኤሚሊዮ ንሱ በመጨረሻው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ኢኳቶሪያል ጊኒ ታንዛኒያን 1ለ 0 በማሸነው ማለፏን አረጋግጣለች። ሊቢያን 5 ለ 2 በሆነ ውጤት ያሸነፈችው ቱኒዚያ ከምድብ አንድ ቀድማ ነበረ ለውድድሩ ማለፏን ያረጋገጠችው። በከፍተኛ ጎል ልዩነት ቢሸነፉም ሊቢያውያን ከሰባት ዓመታት እገዳ በኋላ ብሔራዊ ቡድናቸውን በሜዳው ሲጫወቱ ለማየት በመቻላቸው ተደስተዋል። በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ውድድር ላይ ከሚሳተፉ ቡድኖች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተለይተዋል። ኮሞሮስ፣ ጋቦን፣ ጋምቢያ፣ ጋና፣ ግብጽ፣ ዚምባብዌ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ አልጄሪያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ��ኒ፣ ማሊ፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዝያ እና አስተናጋጇ ካሜሩን በውድድሩ መሳተፋቸውን አረጋግጠዋል። ኢትረዮጵያስ ምን ተስፋ አላት? በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኮትዲቯር፣ ማደጋስካር እና ኒጀር ጋር የተመደበችው ኢትዮጵያ፤ በመጀመሪያው ጨዋታ በማደጋስካር አንድ ለባዶ ተሸንፋ የነበረ ሲሆን፤ በቀጣይ በባሕር ዳር በተደረገ ጨዋታ ኮትዲቯርን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። በመቀጠል ዋልያዎቹ ወደ ኒጀር ተጉዘው፤ አንድ ለባዶ ቢሸንፉም በመልሱ ጨዋታ ሦስት ለባዶ ማሸነፍ ችለዋል። ዋልያዎቹ ከማደጋስካር ጋር በነበራቸው የምድብ ጨዋታ ደግሞ አራት ለባዶ በማሸነፍ ነው ምድቡን በዘጠኝ ነጥብ መምራት የቻሉት። በምድቡ ወሳኝ ጨዋታ ዛሬ ኮትዲቯር ከኒጀር የሚያደርጉት ሲሆን ጨዋታው በኮትዲቯር አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ ኢትዮጵያ በምድቡ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ ትላለች። ጨዋታው በኒጀር አሸናፊነት አልያም አቻ የሚጠናቀቅ ከሆነ ደግሞ ዋልያዎቹ መሪነታቸውን አስጠብቀው ወደ መጨረሻው የምድብ ጨዋታ ይጓዛሉ ማለት ነው። ዋልያዎቹ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታቸውን መጋቢት 21/2013 ዓ.ም በኮትዲቯር የሚያደርጉ ሲሆን ማደጋስካር ከኒጀር የሚያደርጉትም ጨዋታ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። ኢትዮጵያ ኮትዲቯርን የምታሸንፍ ከሆነ በካሜሩን አዘጋጅነት በሚካሄደው ጨዋታ ተሳታፊነቷን የምታረጋግጥ ሲሆን፤ ማደጋስካር ከኒጀር የሚያደርጉት ጨዋታ በኒጀር አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ ደግሞ ሰፊ የማለፍ ዕድል ይኖራታል። ዋሊያዎቹ ለመጨረሻው የምድቡ ቸዋታ ዛሬ ኮትዲቯር አቅንተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም የብሔራዊ ቡድን አባላት ""ከተለያዩ አካባቢዎች እና ቡድኖች የመጡ ተጨዋቾች በአንድ ዓላማ ተጫውተው ያስገኙት ድል ትልቅ አርአያነት አለው"" በማለት እስካሁን ያስመዘገቡትን ውጤት አድንቀው ለቀጣዩ ጨዋታ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። 33ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለአንድ ዓመት መራዘሙ ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56539796 +business ኤሎን መስክ ለትዊተር ሰማያዊ ምልክት በወር ስምንት ዶላር እንደሚያስከፍል ተናገረ ኤሎን መስክ የተረጋገጠ የትዊተር አካውንት (ገጽ) መሆኑን የሚያመለክተውን ሰማያዊ ምልክት በስማቸው ለሚፈልጉ የትዊተር ተጠቃሚዎች ወርሃዊ ስምንት ዶላር እንደሚያስከፍል ተናገረ። በ44 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ የማህበራዊ ድረ-ገጹን ትዊተርን የገዛው ኤሎን መስክ ይህንን የወሰነው “የማያስፈልጉ መረጃዎችንና ማጭበርበሮችን ለመቆጣጠር ነው” ብሏል። በትዊተር አካውንት ከተጠቃሚዎች ስም ቀጥሎ ያለው ሰማያዊ ምልክት በዋነኝነት ታዋቂ የሆኑ ሰዎች ገጻቸውን ለማረጋገጥ የሚጠቀሙበት ሲሆን ክፍያም የለውም። ይህ እርምጃ አስተማማኝ ምንጮችን ለመለየት ፈታኝ እንደሚያደርገው ተቺዎች ተናግረዋል። የዓለማችን ባለጸጋ የሆነው ኤሎን መስክ አክሎ እንደተናገረው የሚከፍሉ ተጠቃሚዎች ምላሽ ለማግኘት፣ ለፍለጋዎች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸውና ከሌሎች በተለየ መልኩ ግማሽ ማስታወቂያ ብቻ በገፃቸው ላይ እንደሚደርስ ተናግሯል። “ስልጣን ለህዝቡ! ለሰማያዊ ስምንት ዶላር በወር!” በማለት ቢሊዮነሩ በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሮ “የጌቶችና የጭሰኞች” ስርዓት በማለት የቀድሞውን የሰማያዊ ምልክት (ብሉ ቲክ) የማረጋገጫ ዘዴን ተችቷል። ከዚህ ቀደም ተጠቃሚዎች ብሉ ቲክ እንዲኖራቸው ለማድረግ አጠር ያለ የኦንላይን ማመልከቻ ቅጽን መሙላት አለባቸው። ብዙዎቹም ማንነታቸውን በማስመሰል ኢላማ ለሆኑ ታዋቂ ሰዎች ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች የታሰበ ነበር። ትዊተር ይህንን ያስተዋወቀው በአውሮፓውያኑ 2009 ነበር። ለዚህም መነሻ የሆነው ኩባንያው ታዋቂ ሰዎችን በማስመሰል የሚያጭበረብሩ አካላትን ለመከላከል በቂ ጥራት አላደረገም በሚል ክስ መቅረቡን ተከትሎ ነው። ኤሎን መስክ ለዓመታት ትርፍ ያላስገኘውን የትዊተርን የቢዝነስ አሰራር ለማደስ እየሰራ ባለበት ወቅት ከባድ ፈተና ገጥሞታል። ትዊተር በማስታወቂያ ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ እንደሚፈልግም ተናግሯል። ከወዲሁ አንዳንድ ኩባንያዎች በእርሳቸው አመራር በትዊተር ገጽ ላይ የማስተዋወቁ ጉዳይ እንዳሳሰባቸው እየገለጹ ነው። የመስክ የኤሌክትሪክ መኪና ኩባንያ ቴስላ ተቀናቃኝ የሆነው ጄኔራል ሞተርስ ባለፈው ሳምንት በትዊተር ላይ የሚያደርገውን ማስታወቂያዎችን ማቆሙን ተናግሯል ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c72z7eg9600o +sports የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መጠሪያውን እና የብሮድካስት መብቱን ሊሸጥ ነው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተላለፍ እንዲችሉ ጨረታ ማውጣቱን ገለፀ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ፤ ማህበሩ ሁለት ዋና ዋና ነገሮችን ለመሸጥ አቅዶ ጨረታ ማውጣቱን ተናግረዋል። አንደኛው፤ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድሮችን በቴሌቪዥን ለማሰራጨት የብሮድካስቲንግ መብቱን ለመሸጥ በማሰብ የዓለም አቀፍ እንዲሁም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃኖች እንዲወዳደሩ ጨረታ ማውጣቱን ገልፀዋል። ሁለተኛው ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ኩባንያ የሚጠራበትን ስም ለመሸጥ ጨረታ ማውጣታቸውን አቶ ክፍሌ ሰይፈ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፉ 16 ቡድኖች በጋራ ያቋቋሙትና በንግድ ድርጅትነት የተመዘገበ ማህበር መሆኑን ሥራ አስኪያጁ አቶ ክፍሌ ጨምረው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምከንያት በዝግ ስታድየም የሚታይ ከሆነ፣ እንዲሁም ምርመራ እንዲደረግ ግዴታ የሚቀመጥ ከሆነ ተጨማሪ ወጪ ስለሚጠይቅ እነዚህን ነገሮች ለመሸፈን በማሰብ የተለየ አማራጭ ማሰባቸውን ጨምረው ተናግረዋል። ከሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ የአክሲዮን ማህበሩ አባል ቡድኖች ከመንግሥት ድጎማ ተላቅቀው ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ እንዲሁም በአፍሪካም ሆነ በአውሮፓ ደረጃ ያሉ የስፖርት ቡድኖች እንደሚያደርጉት የስፖርት ኢንቨስትመንት ውስጥ እንዲገቡ መነሻ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል። ከጨረታው የሚገኘው አብዛኛው ገቢ የሚሰጠው ለእግርኳስ ቡድኖቹ መሆኑን የተናገሩት አቶ ክፍሌ፣ ቀሪው የድርጅቱ ሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመሸፈን ይውላል ብለዋል። ማሕበሩ የተቋቋመው የእግር ኳስ ቡድኖቹ ከመንግሥት ድጎማ ነፃ እንዲወጡ ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ በፕሪሚየር ሊጉ ከሚሳተፉ 16 ክለቦች መካከል ሁለቱ ቡድኖች ብቻ የራሳቸውን ወጪ በመሸፈን የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ደጋፊ አካላት (ስፖንሰርሺፕ) እንዳላቸው ገልፀዋል። ቀሪዎቹ 14 የእግር ኳስ ቡድኖች የከተማ ክለቦች ወይም ስፖንሰር የሌላቸው መሆናቸውን በመጥቀስ እነዚህን ቡድኖች በገቢ ራስን ማስቻል የዚህ ማህበር ቀዳሚ ዓላማ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ቡድኖች ችግሮች እንዳለባቸው የሚጠቅሱት ኃላፊው፣ በአመራር ችግር ደሞዝ የማይከፈላቸው በመኖራቸው ከጨረታው የሚገኘው ገንዘብ አብዛኛው ለክለቦች እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። ይህንን የገቢ ክፍፍልን በሚመለከት የማስፈፀሚያ ሰነድ ተዘጋጅቶ 16ቱም ክለቦች መስከረም ወር ላይ ውይይት ካደረጉበት በኋላ የሚፀድቅ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል። ማህበሩ በርካታ ተጫራቾች ���ናገኛለን ብሎ ያሰበው ከዓለም አቀፍ ተጫራጮች መሆኑንም ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጨረታው ላይ የአገር ውስጥ ድርጅቶችም እንደሚሳተፉ የገለፁት አቶ ክፍሌ በሚወዳደሩበት ወቅት ምክረ ሃሳብ አዘጋጅተው ገቢ የሚያገኙበትን መልክ እና የድርሻ ክፍፍሉ ምን እንደሚመስል ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፟። በኢትዮጵያ እግርኳስ ረዥም ታሪክ ቢኖረውም፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ከማይሸጥባቸው የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት። https://www.bbc.com/amharic/53864758 +politics የትራምፕ መኖርያ ቤት በፖሊስ መፈተሹን ተከትሎ የፀጥታ አካላት እንዳይገደሉ ተፈርቷል ባለፈው ሳምንት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት (ማር ኤ ላጎ) ላይ ድንገተኛ አሰሳና ፍተሻ ተደርጎበት ነበር። ይህን ተከትሎ በአሜሪካ የፀጥታ አካላት ላይ ስጋት ነግሷል። በድርጊቱ የተቆጡ የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ ኃይል አባላትን እያስፈራሩ ነው። የአሜሪካ የፀጥታ እና ደኅንነት መሥሪያ ቤቶች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለባልደረቦቻቸው ባስተላለፉት የተጠንቀቁ መልዕክት ‘አደጋ እንደተደቀነባችሁ አውቃችሁ በጥንቃቄ ተንቀሳቀሱ’ ሲል ያሳስባል። ከዚህ የትራምፕ መኖሪያ ቤት ፍተሻ በኋላ በተለይም በፖሊሶች፣ በዳኞች፣ በዐቃቤ ሕግ ሠራተኞች ላይ እየደረሰ ያለው የግድያ ዛቻ በእጥፍ ጨምሯል። ባለሥልጣናቱ በዚህ የተጠንቀቁ ማሳሰቢያቸው ሁሉም የፀጥታ አባላት ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል አካባቢያቸውን በንቃት እንዲከታተሉ አሳስበዋል። ኤፍቢአይ የአንድን የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ቤት ዘልቆ ገብቶ ብርበራ ሲያደርግ ትራምፕ የመጀመሪያው ናቸው። በፍሎሪዳ ፓልም ቢች የባሕር ዳርቻ የሚገኘው የዶናልድ ትራምፕ ማር ኤ ላጎ መኖርያ ቤት ድንገተኛ ብርበራ ከተደረገበት በኋላ በርካታ ሰነዶች ማግኘቱን የአሜሪካ ፖሊስ ይፋ አድርጓል። ከእነዚህ ተገኙ ከተባሉ ሰነዶች መካከል በዶናልድ ትራምፕ ቤት በፍጹም መገኘት ያልነበረባቸው ጥብቅ የአገር ምሥጢሮች ይገኙበታል ተብሏል። የአገር ምሥጢሮች ‘ጥብቅ ምሥጢር’፣ ምሥጢር እና ለሕዝብ ያልተፈቀደ በሚል ይከፈላሉ። ጥብቅ የአገር ምሥጢር ተደርገው ከተቀመጡ ሰነዶች መካከል ደግሞ እጅግ ጥብቅ የአገር ምሥጢር ተብለው የተሰነዱ ይገኙበታል። እነዚህ ሰነዶች በአሜሪካ አስተዳደር ውስጥ ሦስት እና አራት የተመረጡ የደኅንነት ሰዎች ብቻ ሊያውቋቸው የሚገቡ ፍጹም ምሥጢር ሆነው መቆየት የነበረባቸው ናቸው ተብሏል። እነዚህ ሰነዶች ለምን በዶናልድ ትራምፕ ቤት ተገኙ የሚለውን ፖሊስ እየመረመረ ነው። ትራምፕ በበኩላቸው እነዚህ ዶሴዎች ቀድሞውንም ከምሥጢራዊ ሰነድነት ሰንዱቅ እንዲወጡ መደረጋቸውን ይናገራሉ። ይህን ውዝግብ ተከትሎ የዶናልድ ትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ትራምፕ ራሳቸውን በሚያስተዳድሩት የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጾች ጭምር በመጠቀም ለፖሊሶችና የፀጥታ አካላት የግድያ ዛቻ እያደረሱ ነው። እነዚህ ዛቻዎች ዛቻ ብቻ አይደሉም። ለምሳሌ ባለፈው አርብ በኦሃዮ ግዛት የኤፍቢአይ ቢሮን ጥሶ ጥቃት ሊፈጽም የነበረ አንድ ወጣት በፖሊስ ተገድሏል። ሟች ይህን የግድያ ሙከራ ከማድረጉ በፊት 'ትሩዝ ሶሻል' በሚባለው የትራምፕ ማኅበራዊ የትስስር መድረክ ላይ የፀጥታ አካላትን ለመግደል እንደተዘጋጀ ጽፎ ነበር። አንዳንድ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ይህ በትራምፕ ላይ እየተደረገ ያለው ማሳደድ እሳቸውን በቀጣይነት ዳግም ወደ ሥልጣን እንዳይመጡ ለማሸማቀቅ በዲሞክራቶች የተጎነጎነ ሴራ ነው ብለው ሲተቹ ቆይተዋል። ይህ ትችት እየሰፋ በመሄዱ ፖሊስ በፍርድ ቤት የብርበራ ፈቃድ ያገኘበትን ማስረጃ ለሕዝብ ይፋ ለ��ድረግ ተገዷል። ከዚህ ቀደም ፖሊስ አንድ ምርመራ ሳይገባደድ ለፍርድ ቤት ብርበራ እንዲያካሄድ እንዲፈቀድለት ያቀረባቸውን መረጃዎች ለሕዝብ ይፋ አያደርግም ነበር። ዶናልድ ትራምፕ ብርበራውን ተከትሎ ሦስት ፓስፖርቶቼ ተወስደውብኛል ብለዋል። ብርበራውን ተከትሎ በተገኙ ሰነዶች ትራምፕ አዲስ ክስ ይከፈትባቸው እንደሆነ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። ትናንት ሰኞ ምሽት ዐቃቤ ሕግ የዶናልድ ትራምፕ ወዳጅና ጠበቃ ሩዲ ጁሊያኒን ለመክሰስ ሰነዶች እየሟሉ እንደሆነ ተዘግቧል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c03z223d85no +politics ኡሁሩ ኬንያታ በአገራቸውና በአካባቢው አገራት እንዴት ይታወሳሉ? ከኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት ጋር ተያይዞ በሚነሱ የሰላም ድርድሮች ላይ ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከሌሎች የአፍሪካ መሪዎች በበለጠ ሲጠቀሱ ይሰማል። በተለይም የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ወገንተኝነትን አሳይተዋል በሚል በትግራይ ኃይሎች የሚወቀሱ ሲሆን፣ በትግራይ ያለውን ሁኔታ እንደተከታተሉት የተነገራላቸው ኡሁሩም አደራዳሪ ይሁኑ ሲሉም ተሰምተዋል። ከአምስት ወራት የተኩስ አቁም አዋጅ በኋላ ያገረሸው ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ የተለያዩ ተቋማትና አገራት ጥረት እያደረጉ ሲሆን፣ ኡሁሩ ከሥልጣን ከለቀቁ በኋላ ምን አይነት ሚና ሊኖራቸው ይችል ይሆን የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተው ነበር። በአሁኑ ወቅት ይህ ጥያቄ ምላሽ ያገኘ ሲሆን አዲሱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በኢትዮጵያ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ኡሁሩ የሚያከናውትን ተግባር እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል። ሩቶ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ እና በታላላቅ ሐይቆች ቀጠና (ግሬት ሌክስ) ሰላም ለማምጣት የሚያስመሰግን ተግባር አከናውነዋል ብለዋል። “በኢትዮጵያ እና በታላላቅ ሐይቆች ቀጠና የተጀመሩ የሰላም ጥረቶች ለማጠናከር ቁርጠኛ ነኝ” ያሉት አዲሱ ፕሬዝዳንት ሩቶ፤ የቀድሞው ፕሬዝዳንት የጀመሩትን ሰላም የማምጣት ጥረት ለመቀጠል ተስማምተዋል ብለዋል። በኢትዮጵያ እና በቀጣናው ያከናወኑት ተግባር እንዳለ ሆኖ በአገራቸው ኬንያስ እንዴት ይታወሳሉ? ወቅቱ ከአራት ዓመት በፊት ነበር። አንድ ተማሪ የኬንያውን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከሥልጣን ሲሰናበቱ እንዴት መታወስ ይፈልጋሉ? ብሎ ጠየቃቸው። ለአሁሩ ያልጠበቁት ነገር ቢሆንም ሁለት ጉዳዮች ላይ አትኩሮት ሰጥተው ተናግረዋል። “አንደኛ አንድነቱን የጠበቀ፣ የተቀናጀ ማኅበረሰብን ማምጣት ችያለሁ። ሁለተኛ በሙስና ላይ የከፈትነውን ጦርነት ማሸነፍ ችለናል” ሲሉም ከፍተኛ ጭብጨባ ነው የጠበቃቸው። ከሁለት የሥልጣን ዘመናቸው በኋላ መንበራቸውን ለቀድሞ አጋራቸውና ለአሁኑ ተቃናቃኛቸው ዊሊያም ሩቶ ሥልጣን ባስረከቡበት ወቅት አሁሩ የጠቀሷቸውን ስኬቶች አሳክተው ይሆን? ሌሎች የሚጠቀሱባቸው ተግባራትስ ምን ይሆኑ? ኡሁሩ ለአገራዊ አንድነት ትልቅ ትርጉም ያለው እርምጃ ወስደዋል ከሚባልላቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ በአውሮፓውያኑ 2018 ከተቃዋሚ መሪ እና ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ጋር ፖለቲካ እርቅ ማሳያ የተባለው መጨባበጥ ነበር። በአውሮፓውያኑ 2017 የተደረገው ምርጫ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጎ በድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን፣ በዚህም ድጋሚ ምርጫ ኦዲንጋ ሳይሳተፉ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ራሳቸውን የሕዝብ መሪ በማለት የይስሙላ ቃለ ሐላ ሥነ ሥርዓት አካሂደው ነበር። ይህንንም ተከትሎ ለወራት የዘለቀ አለመረጋጋት የተከተለ ሲሆን፣ የሁለቱ ፖለቲከኞች “የእጅ መጨባበጥ” ይህንን እንዲቋጭ አድርጎታል። ነገር ግን የኡሁሩ እና የኦዲን��� ስምምነት በወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት በነበሩት ዊሊያም ሩቶ በጥሩ መልኩ አልታየም። ዊሊያም ሩቶ የምግብ ዋስትናን የማሳደግ፣ ሁለንተናዊ የጤና አገልግሎትን ለማስፈን፣ መኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረብ እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማሳደግ የነበራቸውን ትልልቅ አጀንዳዎች እንዳይሳኩ ምክንያት ሆኗል ይላሉ የሁለቱ ፖለቲከኞች ጥምረት። ይህንንም ተከትሎ የኡሁሩ ኬንያታ እና የዊሊያም ሩቶ ግንኙነት የሻከረ ሲሆን፣ ኡሁሩ ለዊሊያም ሩቶ ያላቸውን ድጋፍ በማቆም በምትኩ ተቀናቃኛቸው የነበሩትን ራይላ ኦዲንጋን በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋቸዋል። በኡሁሩ ኬንያታ እና በምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ መካከል ያለው ውጥረት ከምርጫው በኋላም ቀጥሏል። ዊሊያም ሩቶ በመመረጣቸው ደስተኛ አለመሆናቸውን የተናገሩት ኡሁሩ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት ያስተላለፉትም ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሰየማቸው አንድ ቀን በፊት ነው። ኡሁሩ ኬንያታ አስበውት የነበረው አንድነት ይህንን ላይሆን ቢችልም፣ በአውሮፓውያኑ 2007 የተከሰተውን የምርጫ ውዝግብ ተከትሎ በነበረ የብሔር ግጭት 1200 ሰዎችን በሞቱባትና እንዲሁም በርካታ ሺዎች በተፈናቀሉባት አገር ወሳኝ ነበር ተብሏል። በተለይም በቅርቡ የነበረው ምርጫ በሰላም መጠናቀቅ ተንታኞች እንደሚያምኑት ኡሁሩ የራሳቸው ዕጩ ራይላ ኦዲንጋ ቢሸነፉም አንድነትን ለማምጣት እና የጋራ ማኅበረሰብ ለመገንባት ያደረጉትን ጥረት አሳክቷል። የሁለቱ ፓለቲከኞች መጨባበጥ ሁሉም የሚሳተፉበት እና የመገለልም ስሜትን ያስወገደ እንደሆነ በማሲንዴ ሙሊሮ ዩኒቨርስቲ የሥነ ጽሁፍ እና ኮሚዩኒኬሸን ፕሮፌሰር የሆኑት ኤጋሪ ካባጂ ይናገራሉ። ሆኖም በኡሁሩ እና በራይላ ኦዲንጋ መካከል የተደረገው እርቅ በተቃዋሚ ዘንድ ክፍተትን ፈጥሯል። የመንግሥትን ኃላፊነት የሚቆጣጠር፣ መንግሥት ያልተገባ ተግባር ሲፈፅም የሚፈትሽ ጠንካራ ተቃዋሚ እንዳይኖር ምክንያት ሆኗል ይላሉ የፖለቲካ ተንታኟ ኔሪማ ዋኮ ኦጂዋ። ይህም ኡሁሩ ኬንያታ ሙስናን እና የሕዝብ ሃብት ምዝበራን ማስቆም ያለመቻላቸው ሚና ሳይጫወት እንዳልቀረም ተንታኝዋ ያስረዳሉ። ለራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ቅስቀሳ በሚያካሂዱበት ወቅት ሙሰኞችን ለመቆጣጠር ችላ ብለው እንደነበር አምነዋል። እንዲሁም በአውሮፓውያኑ 2012 አገሪቱ በየቀኑ 2 ቢሊዮን የኬንያ ሸልንግ (17 ሚሊዮን ዶላር) በሙስና በየቀኑ ታጣለች ብለዋል። ይህንንም አስመልክቶ “ፕሬዝዳንቱ ካወቁ በዚህ ጉዳይ ላይ ለምን አንድ ነገር አላደረጉም? በርካታ ጉዳዮች ፍርድ ቤት ቢሆኑም ፍርድ ማግኘት አልተቻለም” ሲሉ በኮዲ አፍሪካ የግብር ኤክስፐርት የሆኑት ኒኪል ሂራ ይጠይቃሉ። የኡሁሩ አስተዳደር በአገሪቱ ውስጥ ግድቦች እና ስታዲየም በመገንባት፣ የኤሌክትሪክ መስመሮች ዝርጋታ፣ የናይሮቢ ፈጣን የባቡር መንገድን ጨምሮ የባቡር ሃዲዶች ግንባታ በመሳሰሉ ፕሮጀክቶች ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ አፍስሷል። እነዚህ ኢንቨስትመንቶች የተከናወኑት በከፍተኛ ብድር ሲሆን ፈሶባቸዋል የተባለው ወጪም ጥያቄ አስነስቷል። ለምሳሌ በቻይና የተገነባው ከሞምባሳ እስከ ናይሮቢ የተዘረጋው የባቡር መስመር 3.2 ቢሊዮን ዶላር የፈጀ ሲሆን፣ ይህም  በጎረቤት አገራት ታንዛንያ እና ኢትዮጵያ ከተከናወኑ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ጋር ሲነፃፀሩ ዋጋው እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ። በቀጣዮቹ ዓመታት መመለስ ያለባት ብድርም ጣራ እንዲነካ አድርጎታል። በአውሮፓውያኑ 2021 መገባደጃ ላይ የአገሪቱ እዳ 72.6 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን፣ ይህም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ውስጥ 68 በመቶ ነው። ኡሁሩ በአውሮፓውያኑ 2013 ���ደ ሥልጣን ሲመጡ 38 በመቶ ነበር። የምሥራቅ አፍሪካ ግዙፉን ኢኮኖሚ ለማፋጠን አገሪቱ አዳዲስ መሠረተ ልማቶችን መገንባት እንደሚያስፈልጋት ታዛቢዎች ቢስማሙም፣ የገንዘብ አያያዝ በአግባቡ ጥቅም ላይ አልዋለም የሚለው ስጋት ፈጥሯል። ከፖሊሲዎች ባሻገር የኡሁሩ ቀለል ያለ ስብዕና በርካቶች የሚናፍቁት ነው። ፕሬዚዳንቱ በአደባባይ ላይ በሚታዩበት ሁሉ ከሰዎች ጋር እንደ ጓደኛ ነው የሚያወሩት። ኡሁሩ ጥበቃዎቻቸው ራቅ ብለው እየተከታተሏቸው በናይሮቢ ጎዳናዎች ላይ በእግራቸው ሲዘዋወሩ ማየት፣ ኛማ ቾማ ብለው ኬንያውን የሚጠሩትን የሥጋ ጥብስ በገበያ ላይ በአካባቢው ሰዎች ተከብቦ መብላት እና የጎልፍ ጨዋታን ከታዳሚዎች ጋር እያወሩ ይከታተሉ ነበር። ለህፃናት እና ለታዋቂ ሰዎችም ቤተ መንግሥታቸው በመጋበዝና እንዲጎበኙ በማድረግ ሥልጣን ብቻ ያላቸው ብቻ የሚገቡበት የሚለውንና እንደ ብርቅና ድንቅ የነበረውን ሁኔታ ለመሻር ሞክረዋል። በተጨማሪም ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ከተጻፈው ውጪ በመውጣት ለሕዝብ ከመጋረጃው በስተጀርባ ያለውን ፍንጭም ይሰጡ ነበር። ምንም እንኳን በአገር አቀፍ ደረጃ ሁለንተናዊ የጤና አገልግሎትን ለመዘርጋት የነበራቸው ሰፊ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባይሆንም፣ የሆስፒታል አልጋዎች አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ተሻሽሏል፤ እንዲሁም አዳዲስ ሆስፒታሎች ተገንብተዋል። ከአገር ውስጥ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኬንያ የምትታይበት ሁኔታ ባለፉት አስር አመታት ተሻሽሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተዘዋዋሪ ሊቀ መንበርነቱን የተረከበችው ኬንያ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረገችውን ወረራ አውግዛለች። በተባበሩት መንግሥታት የኬንያ አምባሳደር ማርቲን ኪማኒ በማኅበራዊ ሚዲያ በሰፊው ባሰራጩት መግለጫቸው፣ አፍሪካ በቅኝ ግዛት ቀንበር ያሳለፈችውን ታሪክ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ካደረገችው ወረራ  ጋር አነጻጽረውታል። በሩሲያና እና በዩክሬን ግጭት ውስጥ ቀጥታ አስተያየት ከመስጠት ይልቅ ሌሎች በርካታ የአፍሪካ አገራት ዝምታን መርጠዋል። ኡሁሩ ኬንያታ የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ሊቀመንበር በመሆን በኢትዮጵያ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭቶችን ለመፍታት አደራዳሪ ሆነውም ሰርተዋል። በአጠቃላይ ኬንያ በኡሁሩ ኬንያታ የሥልጣን ዘመን ያልተጠበቁ ተግዳሮቶች ገጥሟት ነበር። ከእነዚህም መካከል በናይሮቢ እና በሌሎች ቦታዎች ታጣቂዎች ያደረሱት ጥቃት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዲሁም በከፊል በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ምክንያት የተከሰተው የኑሮ ውድነት ይጠቀሳሉ። ኡሁሩ ሥልጣናቸውን በሚያስረክቡበት ወቅት ለቀጣዩ መንግሥት የቤት ሥራዎች የሆኑት በምርጫ ዘመቻ ወቅት ተወዳዳሪዎቹ ቃል የገቡት የዜጎችን አንገብጋቢ ችግሮች መፍታት ነው። ከእነዚህም መካከል ከፍተኛ የሥራ አጥነት እና የኑሮ ውድነት መጨመርን የሚጠቀስ ሲሆን በነሐሴ ወር የዋጋ ግሽበት ወደ 8.5 በመቶ ከፍ ብሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/crg2q0dv1gvo +business አልጄሪያ ለሥራ አጦች ወርሃዊ ክፍያ ልትሰጥ ነው ከፍተኛ የሥራ እጦት ባለባት አልጄሪያ መንግስት ለወጣቶች የሥራ አጥነት ድጎማ እንደሚጀምር ፕሬዝዳንቱ ተናገሩ። ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ተቡን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ከ19 እስከ 40 ዓመት ለሆናቸው ሥራ ፈላጊዎች ከመጋቢት ጀምሮ ወርሃዊ ክፍያ ያገኛሉ። ለክፍያው ብቁ የሆኑ ዜጎች ሥራ እስኪያገኙ ድረስ በወር ወደ 100 ዶላር የሚጠጋ ክፍያ እና አንዳንድ የሕክምና ጥቅማጥቅሞችን ያገኛሉ። ተቡን አክለውም ይህን መሰሉን ጥቅማ ጥቅም በማስተዋወቅ ከአውሮፓ ውጪ አልጄሪያ የመጀመሪያዋ ሀገር መሆኗን አስታውቀዋል። በአልጄሪያ ከ600 ሺህ በላይ ስራ አጦች እንዳሉም አክለዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-60387663 +health የካንሰር ህዋስን የሚገድለው ቫይረስ ለካንሰር ሕሙማን ተስፋ እንደሚሰጥ ተገለጸ ቫይረስ በመጠቀም የካንሰር ሕዋሳትን የሚገድለው ሕክምና ለካንሰር ሕሙማን ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ተገለጸ። የዩናይትድ ኪንግደም ሳይንቲስቶች እንደሚሉት፣ በዚህ ሕክምና አንድ ካንሰር ታማሚ ሲፈወስ ሌላ ታማሚ ደግሞ ከፍተኛ ማገገም አሳይቷል። ለሕክምና የዋለው ቫይረስ በዋናነት የጉሮሮ መከርከር የሚያስከትለው ኸርፕስ ሲምፕሊክስ ሲሆን፣ ቫይረሱ እንዲዳከም ተደርጎ ነው ጥቅም ላይ የዋለው። በሕክምናው ዙሪያ ተጨማሪ ጥናቶች ቢያስፈልጉም፣ ለካንሰር ሕሙማን ተጨማሪ ዕድሜ የመስጠት ተስፋ እንዳለው ሳይንቲስቶች ገልጸዋል። የ39 ዓመቱ ክሪስቶፍ ዎጂኮስኪ በሕክምናው የሙከራ ደረጃ ከተሳተፉ አንዱ ነው። ምዕራብ ለንደን የሚኖረው ክሪስቶፍ በሮያል ማርስደን ኤንኤችኤስ ፋውንዴሽን ትረስት በሚገኘው የካንሰር ምርምር ማዕከል ለምርምር በጎ ፈቃደኛ ሆኗል። እአአ በ2017 ነበር የምራቅ አመንጪ ሕዋስ ካንሰር እንዳለበት የተነገረው። ቀዶ ሕክምና ቢደረግለትም አልተሻለውም። “የመኖር ተስፋ የለህም ተብዬ ነበር። የሕይወት ማገባደጃ እንክብካቤ እየተደረገልኝ ነበር። እጅግ ልብ ይሰብራል። አሁን ግን ተስፋ የሚሰጥ ምርምር ውስጥ መግባቴ ተስፋ አጭሮብኛል” ብሏል። የካንሰር ሕዋሳትን የሚገድለው ቫይረስ ሙከራ ከተደረገለት በኋላ ክሪስቶፍ ካንሰሩ ጠፍቶለታል። ለተከታታይ አምስት ሳምንታት በየሁለት ሳምንቱ መርፌ ይሰጠው ነበር። ሰውነቱ ውስጥ ያለው በካንሰር የተጎዳ ሕዋስ ላይ አነጣጥሮ ነው ቫይረሱ የሚሠራው። ይህም በሽታ የመከላከል አቅሙ እንዲዳብር አግዟል። በሙከራ ደረጃ አርፒ2 የተባለውን ቫይረስ በመርፌ ይወስዱ የነበሩት 40 ሰዎች ናቸው። ከመካከላቸው ከመርፌው በተጨማሪ ኒቮሎማብ የተባለ የካንሰር መድኃኒት በተጨማሪ ሲሰጣቸው የነበሩም ይገኙበታል። ክሪስቶፍን ጨምሮ አርፒ2 ከተሰጣቸው ዘጠኝ ሕሙማን ሦስቱ ሰውነታቸው ውስጥ ያለው ካንሰር ተመናምኗል። አርፒ2 መርፌን ከኒቮሎማብ መድኃኒት ጋር አጣምረው ከወሰዱ 30 ሰዎች ሰባቱም አገግመዋል። እንደ ድካም ያሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ውስን ነበሩ። ዋና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ኬቨን ሀሪንግተን ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ የምርምሩ ውጤት “እጅግ አስደናቂ” ነው። በተለያየ የካንሰር ደረጃ ላይ ላሉ ሕሙማን ተስፋ ሰጭ እንደሆነ አክለዋል። ሕክምናው እምብዛም ለማይታየው የዐይን ካንሰር እና የኢሶፎገስ ካንሰር እንደሚውልም ተመራማሪው ተናግረዋል። “በሕክምና ምርምር የመጀመሪያ ደረጃ እንዲህ ያለ ተስፋ ሰጭ ውጤት ማግኘት አልተለመደም። በርካታ የካንሰር ሕሙማንን ማከም ስንጀምር ምን ውጤት ልናገኝ እንደምንችል እስከማይ ጓጉቻለሁ” ብለዋል። ዶ/ር ማሪን ቤከር የተባሉት የካንሰር ተመራማሪ፣ የካንሰር ሕክምና አንድ ደረጃ ከፍ እንዲል ያገዘ ጥናት መሆኑን ተናግረዋል። “ሳይንቲስቶች ቫይረስን ተጠቅመው ካንሰርን መዋጋት እንደሚችሉ የደረሱበት ከ100 ዓመታት በፊት ነበር። ነገር ግን ደኅንነቱ በተጠበቀና በውጤታማ መንገድ ሕክምናውን ማስኬድ ቀላል አልሆነም። ይህ አዲሱ ሕክምና በጥቂት ሰዎች ሲመረመር ተስፋ ፈንጥቋል። ወደ ሰፊ ምርምር ማደግ አለበት” ሲሉ አስረድተዋል። ሳይንቲስቶች ቫይረስ ተጠቅመው ካንሰርን ለመዋጋት ሲሞክሩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ከዚህ ቀደም የቆዳ ካንሰርን ለማከም ቫይረስ ጥቅም ላይ የሚውልበት ሕክምና ፈቃድ ተሰጥቶታል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c19jrd08nl2o +sports የቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020፡ የትኞቹ አገራት የቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020 የሜዳሊ�� ሰንጠረዥ የ2020ው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ውድድር ከዚህ በፊት ከተካሄዱት በበለጠ በ33 የስፖርት አይነቶች ውድድሮች የሚካሄድበት ነው። ባለፈው ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ይህ የኦሊምፒክ ውድድር በኮሮናቫይረስ ምክንያት ወደዚህኛው ዓመት የተሸጋገረ ሲሆን ውድድሩ ጃፓን ውስጥ በሚገኙ 42 የተለያዩ ስፍራዎች ላይ ይካሄዳል። ይህ የቢቢሲ አማርኛ ገጽም በቶኪዮ ኦሊምፒክ በሚደረጉ ውድድሮች አገራት የሚያገኙትን የሜዳሊያ ዝርዝሮች የያዘ ሰንጠረዥ ነው። በዚህ ሰንጠረዥ ላይ ተወዳዳሪዎች የሚያገኙት ሜዳሊያ ከሚወክሉት አገር እና ከሚይዙት ደረጃ ጋር በየደቂቃው እየተከታተልን የምናቀርብበት ነው። በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ላይ በውድድሩ የሚሳተፉ ብሔራዊ የኦሊምፒክ ቡድኖች የሚያስመዘግቧቸው የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያዎች በዝርዝር ይቀመጣሉ። https://www.bbc.com/amharic/57662275 +politics ባይደንን ከሞት ያተረፏቸው አፍጋናዊ አስተርጓሚ አሜሪካ ገቡ "ጆ ባይደን ሴናተር እያሉ አፍጋኒስታን ውስጥ ከአደጋ ያተረፏቸው አስተርጓሚና ቤተሰቦቻቸው ጓዛቸውን ጠቅልለው ከሃገራቸው መውጣታቸው ተሰምቷል። ጊዜው 2008 ነበር። በፈረንጆቹ። የአሁኑ ፕሬዝደንት ጆ ባይደንና ሌሎች ሴናተሮችን የያዘ ሄሊኮፕተር በከባድ አየር ምክንያት ከአንዲት የአፍጋኒስታን መንደር ለማረፍ ይገደዳል። ሥፍራው ለወትሮው የበረዶ ጥጥ የሚዘንብበትና ታጣቂዎች ጥቃት አከታትለው የሚያደርሱበት ነው። አማን ካሊል በአሜሪካ መንግሥት ተቀጥረው ከሚሠሩ አፍጋናዊያን መካከል ነበሩ። አሜሪካዊያኑን ሴናተሮች በመኪናቸው አሳፍረው ወደ ድብቅ ሥፍራም ወስደዋል። አስተርጓሚው ከባለፈው ነሐሴ ጀምሮ ወደ አሜሪካ የሚያስገባ ቪዛ ማግኘት አቅቷቸው ላይ ታች ሲኳትኑ ቆይተዋል። ነገር ግን አሁን በታሊባን ቁጥጥር ሥር ያለችውን ሃገራቸውን እንደ ሌሎች በርካታ ሺህ አፍጋናዊያን ወደኋላ ጥለው ወጥተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ፤ አስተርጓሚው ካሊልና ቤተሰቦቻቸው ከአፍጋኒስታን በሰላም ወጥተዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""አስተርጓሚው ከአፍጋኒስታን የወጡት በአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ ነው። ይህ ጉዳይ እንዲሳካ ድጋፍ ላደረጉልን ምስጋና እናቀርባለን"" ብለዋል ቃል አቀባዩ። ካሊል የአሁኑን የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጨምሮ ሴናተር ቻክ ሄግልና ሴናተር ጆን ኬሪን በአካል ካገኙ ከ13 ዓመታት በኋላ ወደ አሜሪካ የሚያስገባቸውን ቪዛ ለማግኘት እየጣሩ ነው። አሜሪካ አፍጋኒስታንን ለታሊባን ጥላ ከወጣች በኋላ ካሊል ፕሬዝደንት ባይደን እንዲያድኗቸው ጥሪ ማቅረባቸው አይዘነጋም። እሳቸውንና ሚስታቸውን እንዲሁም አምስት ልጆቻቸውን ከአፍጋኒስታን እንዲያስወጣቸው በሲኤንን ጥሪ ያቀረቡት ካሊል ""አምናቸዋለሁ። ሁሉን የማድረግ አቅም እንዳላቸው አምናለሁ"" ብለው ነበር። ባለፈው መስከረም ስለ አቶ ካሊል ጉዳይ የተጠየቁት የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ አስተርጓሚው ላደረጉት ነገር አመስግነው መንግሥታቸው ሰውዬው ከአፍጋኒስታን ለማስወጣት ቁርጠኛ መሆኑን መናገራቸው አይዘነጋም። ካሊል አሁን ከአፍጋኒስታን ወጥተው ፓኪስታን እንደሚገኙ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። ሂዩማን ፈርስት ኮአሊዥን የተሰኘውና አሁን ፓኪስታን የሚገኙ 200 አፍጋናዊያንን ከካቡል ያስወጣው የተራድዖ ድርጅት የባይደን አስተርጓሚ በሕይወት በመውጣታቸው ደስተኛ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግሯል። አሜሪካ በአፍጋኒስታን በኢራቅ በነበሩት ጦርነቶች አሜሪካዊያን ወታደሮችን በማስተርጎምና በሌሎች መስኮች ላገዙ ዜጎች ልዩ ቪዛ አዘጋጅታለች። ካሊል ወደ ዋሺንግተን የሚያስገባቸ���ን ቪዛ አግኝተው ወደ አሜሪካ ያቀኑ እንደሆነ እስካሁን ግልፅ አይደለም። ከፈረንጆቹ 2008 ጀምሮ 70 ሺህ አፍጋኒስታናዊያን በአሜሪካ እርዳታ ሃገራቸውን ለቀው ወጥተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58880580 +sports አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በትናንትናው እና በዛሬው እለት ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አቶ ኢሳያስ ጅራ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ። ላለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸንን በፕሬዚዳንትነት የመሩት አቶ ኢሳያስ ጅራ 94 ድምፅ በማግኘት እንደተመረጡ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ሶስት እጩዎች ቀርበው የነበረ ሲሆን በእጩ ተወዳዳሪነት የቀረቡት አቶ መላኩ ፈንታ 27 ድምፅ እንዲሁም አቶ ቶኪቻ ዓለማየሁ 17 ድምፅ አግኝተዋል። ሦስቱ ለፕሬዚዳንትነት የቀረቡት ዕጩዎች ሁለት ክልልን እና አንድ የከተማ አስተደደርን ወክለው ነው የተወዳደሩት። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዳኛቸው ነገሮን (ዶ/ር) የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል። በዛሬው ምርጫ በተጨማሪም ስድስት ወንዶችና ሶስት ሴቶች፣ ዘጠኝ የስራ አስፈጻሚዎች የተመረጡ ሲሆን እነዚህም አዲሱ ቃሚሱ፣ ዳኛቸው ነገሮ፣ ሸረፋ ደለቾ፣ ሙራዶ አብዶ፣ አሰር አብርሃም፣ ሃቢባ ሲራጅ፣ ፋይዛ ረሻድ፣ብዙአየሁ ጀንበሩ ናቸው። ፌዴሬሽኑን በቀጣይነት የሚመሩት ፕሬዝዳንት ስፖርቱን ማሳደግ፣ ማዘመን እንዲሁም ብሔራዊ ቡድኑ ደረጃውን የጠበቀ መጫወቻ ሜዳ እንዲኖረው ማድረግ ከሚጠበቁበት ዐበይት ተግባራት መካከል ይጠቀሳሉ። ይህ ጠቅላላ ጉባኤ መጀመሪያ ጎንደር ከተማ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ተደርጓል። አቶ ኢሳያስ ጅራ ላለፉት አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንት የመሩ ሲሆን፣ ለቀጣይ አራት ዓመታት እንዲመሩ በድጋሜ ተመርጠዋል። ከፌደሬሽኑ ውጪ የሴካፋ፣ የምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ውድድር ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። አቶ ኢሳያስ የኦሮሚያ ክልልን ወክለው ነው የተወዳደሩት። ከአራት ዓመት በፊት በ2010 ዓ.ም፣ የጂማ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ሥራ አስኪያጅ በመሆን እያገለገሉ ባለበት ወቅት ነው ተወዳድረው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት የሆኑት። ከ20 ዓመታት በላይ በስፖርት አመራርነት የቆዩት አቶ ኢሳያስ፣ በጂማ እና በሰበታ እግር ኳስ ቡድኖች በአመራርነት ሠርተዋል። ባለፉት ዓመታት “ደረት የሚያስነፋም ባይሆን አንገት የማያስደፋ ሥራ” መስራታቸውን ከአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቆይታ ወቅት ተናግረው ነበር። “ተጨባጭና በአይን የሚታይ ሥራ ሰርተናል” የሚሉት አቶ ኢሳያስ ዳግም ቢመረጡ የጀመሯቸውን መልካም ነገሮች ማስቀጠል፣ ሊሰሯቸው አቅደው በተለያየ ምክንያት ያልተሳኩትን ደግሞ ማከናወን እቅዳቸው ነው። ከእቅዳቸው መካከል ዐቢይ የሆነው “የክለቦች አደረጃጀት ላይ መሥራት” መሆኑን ተናግረዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1q65nw626o +sports የፀረ-አበረታች ኤጀንሲ በአትሌቲክስ ውስጥ የካናቢስን መታገድ ሊመረምር ነው "የዓለም ፀረ-አበረታች ንጥረ ነገሮች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የሆነው ዋዳ በአትሌቲክስ ውስጥ የካናቢስን መከልከል ዳግም ሊመረምር ነው። ኤጀንሲው ይህን የሚያደርገው አሜሪካዊቷ የአጭር ርቀት ተወዳዳሪ የካናቢስ ምርመራ ማለፍ ባለመቻሏ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ሳትሳተፍ ከቀረች በኋላ ነው። የ21 ዓመቷ ሻካሪ ሪቻርደሰን የወላጅ እናቷን ሞት ተከትሎ ሐዘኗን ለመቋቋም ካናቢስ መጠቀሟን ይፋ አድርጋ ነበር። የዓለም ፀረ-አበረታች ንጥረ ��ገሮች ኤጀንሲ በካናቢስ ዙሪያ ሳይንሳዊ ምርመራ በቀጣይ የፈረንጆች ዓመት እንደሚጀመር ገልጾ፤ ካናቢስ በአትሌቲክስ ውስጥ የተከለከለ ሆኖ አስከ 2022 ይቀጥላል ብሏል። የፀረ-አበረታች ኤንጀንሲው በካናቢስ ላይ ያለው ሕግ ዳግም ማጤን ያስፈለው ""ከሚመለከታቸው በርካታ አካላት ጥያቄዎች በመቅረባቸው ነው"" ብሏል። ሪቻርድሰን ሰኔ ወር ላይ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ በአሜሪካ በተደረገ ውድድር በ100 ሜትር ማሸነፍ ችላ ነበር። በዚህም በማጣሪው ግማሽ ፍጻሜ ውድድር ላይ ያጠናቀቀችበት ሰዓት 6ኛው በሴቶች የተመዘገበ ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦ ነበር። የአትሌቷ የካናቢስ ምርመራ ውጤት 'ፖዘቲቭ' የሆነው በኦሊምፒክ ማጣሪያ ላይ ሲሆን፤ በማጣሪያ ውድድር ላይ ያስመዘገበችው ፈጣኑ ሰዓትም ውድቅ ተደርጎባታል። የአንድ ወር እገዳም ተጥሎባታል። ሪቻርድሰን የተካፈለችበት ማጣሪያ ውድድር የተካሄደው ከወላጅ እናቷ ሞት ከአንድ ሳምንት በኋላ ነበር። የአሜሪካ የትራክ እና መስክ እንዲሁም የአሜሪካ ፀረ-አበረታች ኤጀንሲ በአትሌቷ ወላጅ እናት ሞት ሐዘናቸውን በመግለጽ፤ አትሌቷ ዕጹን የተጠቀመችው የውድድር አቅሟን ከፍ ለማድረግ ባይሆንም ሕጉን ከመከተል ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ካናቢስ ተጠቅሞ የተገኘ አትሌት እስካ አራት ዓመት እግድ ሊጣልበት ይችላል። ይሁን እንጂ እግዱ የተላለፈበት አትሌት ዕጹን ተጠቅመው ከተገኙ የውድድር አቅምን ከፍ ለማድረግ አለመሆኑን ማረጋገጥ የሚችሉ ከሆነ ቅጣቱ ወደ ሦስት ወራት ዝቅ ሊደረግ ይችላል። ከዚህ ውጪ አንድ አትሌት ለሕክምና ክትትል ፍቃደኛ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ የትኛውም አይነት እግድ ወደ አንድ ወር ዝቅ ሊደረግ ይችላል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58571965 +politics ቻይና 'ወኪሏን' ወደ ዩኬ ፓርላማ አስገብታለች መባሉን አስተባበለች "የዩናይትድ ኪንግደም የደህንነት ተቋም (ኤምአይ5) ቻይና ወኪሏን የዩኬ ፓርላማ ውስጥ አስርጋ አስገብታለች ማለቱን ተከትሎ ቤይጂንግ ክሱን አጣጣለች። የደህንነት መስሪያ ቤቱ እንዳለው ክሪስቲን ቺንግ ኩይ የፓርላማ አባላት እና በቀጣይ አባል ለመሆን የሚፈልጉ ግለሰቦች ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ጋር ""ግንኙነት እንዲመሠርቱ"" አግዛለች ብሏል። ከ420,000 ፓውንድ በላይ ከግለሰቧ ድጋፍ የተደረገለት የሌበር ፓርቲ ተወካዩ ባሪ ጋርዲነርን ጨምሮ ለሌሎች ፖለቲከኞችም ድጋፍ አድርጋለች። መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የቻይና ኤምባሲ ኤምአይ5 በእንግሊዝ በሚገኙ የቻይና ማህበረሰብ አባላትን 'ስም እያጠፋ እና እያስፈራራ ነው' ሲል ከሷል። የኤምባሲው ቃል አቀባይ በኤምባሲው ድረ-ገጽ ላይ በሰጡት መግለጫ ""ቻይና በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት የሚለውን መርህ ሁሌም ትከተላለች"" ብለዋል። ""በማንኛውም አገር ፓርላማ ውስጥ 'ተጽዕኖ ለመፍጠር' ምንም ፍላጎት የለንም። በእንግሊዝ የቻይና ማህበረሰብ አባላት ላይ የሚደረገውን ስም ማጥፋት እና ማስፈራራት አጥብቀን እንቃወማለን"" ብሏል። እንደ ኤምአይ5 ማስጠንቀቂያው ከሆነ ሊ ከፓርላማው ጋር የነበራት ግንኙነት ""እንግሊዛዊ የሆኑ ቻይና ዝርያ ያላቸውን ለመወከል እና ብዝሃነትን ለማሳደግ"" ነበር። ኤምአይ5 በኩሉ እንቅስቃሴው ""ከዩናይትድ ፍሮንት ዎርክ ዲፓርትመንት (የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ አካል ነው) ጋር በድብቅ መካሄዱን አሰስታውቆ የገንዘብ ድጋፍ በቻይና እና ሆንግ ኮንግ በሚገኙ የውጭ አገር ዜጎች ተደርጓል"" ብሏል። ዲፓርተመንቱ የዩናይትድ ኪንግደም የፖለቲካ ምህዳር ለኮሚኒስት ፓርቲው ምቹ መሆኑን ለማረጋገጥ እና የሰብዓዊ መብቶችን ጨምሮ በፓርቲው ላይ ስጋቶችን የሚያነሱትን ለመቃወም ""ከተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች"" ጋር ""ግ���ኙነትን ለማዳበር"" ያለመ ነው ተብሏል። የደህንነት ቢሮው እንዳለው ግለሰቧ ቻይናዊያን በብሪታንያ ተብሎ የሚጠራውንና አሁን የተበተነውን ኦል ፓርቲ ፓርላመንተሪ ግሩፕን ጨምሮ ""በዩናይትድ ኪንግደም ፖለቲካ ውስጥ ካሉ ግለሰቦች ጋር ሰፊ ግንኙነት ነበራት"" ብሏል። ኤምአይ5 አክሎም ""የቻይናን የኮሚኒስት ፓርቲን አጀንዳ ለማራመድ የፓርላማ ቡድኖችን ለማቋቋም ልትፈልግ ትችላለች"" በማለት አስጠንቅቋል። ወግ አጥባቂ የህዝብ እንደራሴ እና የቀድሞ የፓርቲ ሊቀመንበር ሰር ኢይን ደንካን ስሚዝ ሐሙስ በፓርላማው ስለማስጠንቀቂያው ያነሱ ሲሆን ይህም በአፈ ጉባኤው ለፓርላማ አባላት እንደተላከ አረጋግጠዋል። ""በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው"" ያሉ ሲሆን ሊ ከሃገራቸው እንድትባረር እና መንግሥት ለምክር ቤቱ መግለጫ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ፕሪቲ ፓቴል ""የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን ወክላ በፖለቲካ ጣልቃገብነት ተግባር ላይ የተሠማራች ግለሰብ የፓርላማ አባላት ላይ ማነጣጠሯ በጣም አሳሳቢ ነው"" ብለዋል። ዩናይትድ ኪንግደም ""የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለመለየት"" እርምጃዎች እንዳሏት ተናግረዋል። የሌበር ፓርቲ የህዝብ እንደራሴ ባሪ ጋርዲነር ከክርስቲን ቺንግ ኩይ ሊ የህግ ቢሮ ድጋፍ ማግኘት የጀመሩት እአአ ከ2014 ጀምሮ ነው። የሊ ልጅ ለህዝብ እንደራሴው በበጎ ፈቃደኝነት መሥራቱን እና በኋላም ቃለ ጉባኤ ያዥ ሆኖ ተቀጠሯል። ዠርሚ ኮርቢ የሌበር መሪ በነበሩበት ጊዜ የትይዩ ካቢኔ አባል የነበሩት ጋርዲነር ስለግለሰቧ ""ለተወሰኑ ዓመታት ከደህንነት አገልግሎታችን ጋር ግንኙነት ሳደርግ ነበር"" ብለዋል። ሊ የጥናት ባለሙያ ሆኖ በተሾመበት ወቅት ምንም ሚና ያልነበራት ሲሆን ሁሉም ልገሳዎችም ""በትክክል ሪፖርት የተደረጉ ናቸው"" ብለዋል። ጋርዲነር በኋላ ላይ ለስካይ ኒውስ ""በእኔ እይታ ገንዘቡ በፓርላማ ውስጥ መሥራት የቻልኩትን ሥራ ለማሻሻል እና ለምርጫ ክልሌ ልሠራው የቻልኩትን ለማሻሻል የዋለ ነበር። ለግል ጥቅሜ የዋለ ገንዘብ የለም"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/59991402 +sports በኢትዮጵያና ታንዛኒያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ግጥሚያ የተከሰተው ምንድን ነው? ኡጋንዳ እየተካሄደ በሚገኘው የሴካፋ ውድድር የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የታንዛኒያ አቻዋን 2 ለ1 ረትታለች። የዚህ ጨዋታ ማብቂያ ግን እንደ ሌሎች ግጥሚያዎች ተጫዋቾች ተጨባብጠው የተለያዩበት አይደለም። ለመሆኑ የተፈጠረው ምንድን ነው? ኢትዮጵያ ሰኞ ዕለት ባደረገችው የመጀመሪያው ጨዋታዋ ጅቡቲን 7 ለምንም መርታቷ ይታወሳል። ቀጣይ ከጎረቤት ሃገር ኤርትራ ጋር ግጥሚያ የነበራት የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 5 ለባዶ አሸንፋለች። ሶስተኛው የኢትዮጵያ ጨዋታ ከታንዛኒያ ጋር ትናንት ረቡዕ በኡጋንዳ ንጄሩ የተደረገ ሲሆን የዚህ ጨዋታ የመጀመሪያ አጋማሽ ጎል አላስተናገደም። በሁለተኛው አጋማሽ ተነቃቅታ የገባችው ኢትዮጵያ በ10 ደቂቃ ውስጥ ሁለት ጎል በማስቆጠር መሪነቱን ያዘች። ሁለቱን የኢትዮጵያ ጎሎች መሳይ ተመስገንና ይየን ኒያቦኒ ናቸው ያስቆጠሩት። ነገር ግን የታንዛንያዋ ሉቫንጋ አንድ ጎል አስቆጥራ የሃገሯን የጎል ዕዳ ወደ አንድ ዝቅ አደረገች። በዚህ ጎል የተነቃቁት ታንዛኒያዎች በተደጋጋሚ የጎል ማግባት ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም። የጎል ሙከራቸውን የቀጠሉት ታንዛኒያዎች በጭማሪ ሰዓት ቅጣት ምት ያገኛሉ። ቅጣት ምቱ ወደ ጎል ከተሰነዘረ በኋላ የኢትዮጵያዋ ግብ ጠባቂ ቤቴልሄም በቀለ ኳሱን መቆጣጠር ባለመቻሏ የታንዛኒያዋ አጥቂ አይሻ ማሳካ ወደጎል ትቀይራታለች። ነገር ግን ይህ ጎል ከጨዋታ ውጪ ነው በማለት የመስመር ዳኛዋ አሊ��� ኢራዱካንዳ ባንዲራቸውን ያውለበልባሉ። በዚህ ውሳኔ ደስተኛ ያልሆኑት የታንዛኒያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አባላት ወደ መስመር ዳኛዋ በመሄድ ይከቧትና ይገፏት ጀመር። የታንዛኒያዋ ተከላካይ ፉሙካዚ የመስመር ዳኛዋን ገፍትራ በመጣሏ በቀይ ካርድ ከጨዋታው ታግዳለች። የታንዛኒያ ተጫዋቾች የመስመር ዳኛዋን በመግፋት በማዋከብ ብቻ ሳያልፉ ባንዲራዋን በመንጠቃቸው የካርድ ሰለባ ሆነዋል። የጨዋታው ማብቂያ ፊሽካ ከተነፋ በኋላም የታንዛኒያ ተጫዋቾች የጨዋታውን ዳኞች በማዋከባቸው ከሴካፋ ቅጣት ይጠብቃቸዋል እየተባለ ነው። በኡጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ በምሕፃሩ ሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ባለፈው ቅዳሜ ነው የተጀመረው። ታንዛንያ፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ ቡሩንዲና ኡጋንዳ እየተሳተፉ ሲሆን ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያና ሶማሊያ በውድድሩ አልተሳተፉም። ኢትዮጵያ እስካሁን ያደረገቻቸውን 3 ጨዋታዎች በማሸነፍ በ9 ነጥብ ውድድሩን እየመራች ትገኛለች። ሌላኛው በኡጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው ቀጣናዊው የእግር ኳስ ውድድር አነጋጋሪ የሆነው ጉዳይ 5 ኤርትራዊያን መጥፋታቸው ነው። አምስቱ ተጫዋቾች ባለፈው ማክሰኞ ጠዋት ካረፉበት ሆቴል የተሰወሩ ሲሆን በሴካፋ ከ20 አመት በታች የሴቶች ሻምፒዮና የኤርትራ ብሄራዊ ቡድን አባል ነበሩ። የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ማህበራት ምክር ቤት ሴካፋ] ባወጣው መግለጫ ጉዳዩ ለፖሊስ ሪፖርት እንደተደረገና ምርመራም በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልጻል። ሴካፋ ከኡጋንዳ የእግር ኳስ ባለስልጣን ጋር የጠፉ ተጫዋቾችን ለማግኘት እንደሚሰራም ተናግረዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-59161580 +sports ለ39 ዓመታት እራሱን ስቶ የቆየው የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አረፈ "ላለፉት 39 ዓመታት ኮማ ውስጥ የነበረው የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋች ዣን ፒየር አዳምስ በ73 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ሆስፒታል የገባው እአአ ግንቦት 1982 ለጉልበት ቀዶ ሕክምና ነበር። ማደንዘዣ ሲሰጠው በተፈጠረ ስህተት ምክንያት እራሱን ከሳተ በኋላ ለ39 ዓመታት ከኮማ አልነቃም። ሴኔጋል የተወለደው አጥቂው ዣን ፒየር፤ ለፓሪስ ሴንት ዠርሜን እና ኒይስ ቡድን ከ140 ጊዜ በላይ ተሰልፏል። ፓሪስ ሴንት ዠርመን (ፒኤስጂ) ባወጣው መግለጫ፤ ""ግርማ ሞገስ ያለው፣ ልምድ ያካበተው እና የተከበረው"" ሲል ነው ተጫዋቹን የገለጸው። ኒይስ በበኩሉ ለተጨዋቹ መታሰቢያ መርሃ ግብር እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል። ዣን ፒየር እአአ ከ1972 እስከ 1976 ፈረንሳይ 22 ዋንጫዎችን እንድታገኝ አስችሏል። 84 ጊዜ ተጫዋቹን ያሰለፈው ኒምስ ቡድን ""ለቤተሰቦቹና ለሚወዱት ሰዎች በአጠቃላይ መጽናናት እንመኛለን"" ሲል የሐዘን መግለጫ አውጥቷል። ዣን ፒየር በልምምድ ላይ ሳለ ጉልበቱ ላይ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ነበር ወደ ሆስፒታል የተወሰደው። በእለቱ በሆስፒታሉ የነበሩ አብዛኞቹ ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ላይ ነበሩ። ማደንዘዣ የሚሰጡት ሐኪም ዣን ፒየርን ጨምሮ ለስምንት ህሙማን አገልግሎት እየሰጡ ነበር። ማደንዘዣ የሚሰጡትን ሐኪም የሚረዳ ተለማማጅ ባለሙያም ሆስፒታሉ ውስጥ ነበር። ተለማማጁ ባለሙያ ኋላ ላይ ለዣን ፒየር ሕክምና የመስጠት አቅም እንዳልነበረው ተናግሯል። ""የተሰጠኝ ኃላፊነት ከአቅሜ በላይ ነበር"" ብሏል። ማደንዘዣ የሚሰጡት ሐኪም እና ተለማማጁ ባለሙያ በሠሩት ስህተት ምክንያት ዣን ፒየር የልብ እና የአዕምሮ ጉዳት ደርሶበታል። ሁለቱ ባለሙያዎች እስከ 199ዎቹ አጋማሽ ድረስ ለስህተታቸው ሳይቀጡ ቢቆዩም፤ ኋላ ላይ 750 ዩሮ ቅጣት እንዲከፍሉ ���ና ለአንድ ወር እንዲታገዱ ተወስኗል። ዣን ፒየር ከ15 ወራት በኋላ ከሆስፒታል ወጥቶ ባለቤቱ በርንዴት በቤታቸው ውስጥ ስትንከባከበው ቆይታለች። ለአራት አስርት ዓመታት እራሱን ስቶ ቢቆይም፤ ባለቤቱ ግን እስትንፋስ የሚሰጠው መሣሪያ እንዲቋረጥ አልፈቀደችም። በየቀኑ ልብሱን እየቀየረችለት፣ ምግብ እያዘጋጀችለት፣ ስጦታ እየሰጠችው እና እያዋራችው 39 ዓመታትን አሳልፋለች። በእርግጥ ዣን ፒየር ኮማ ውስጥ ስለነበረ ለባለቤቱ ምንም ምላሽ አልሰጣትም። ይረዱት የነበሩ ነርሶች እንደሚሉት ከሆነ፤ በርንዴት ከአጠገቡ ስትለይ እራሱን ስቶ የቆየው ዣን ፒየር አንዳች የስሜት ለውጥ ይታይበት ነበር። የሕክምና ስህተት የሠራው ሆስፒታል እስከ ዛሬ ድረስ ይቅርታ አለመጠየቁ የዣን ፒየርን ባለቤት ዘወትር ያበሳጫታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58468255 +politics የጀርሲ ፍርድ ቤት የሮማን አብራሞቪችን 7 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ንብረቶች አገደ ከሩሲያዊው ቢሊየነር ሮማን አብራሞቪች ጋር የተያያዙ እና 7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ ንብረቶች በጀርሲ ፍርድ ቤት ታግደዋል። ከቀናት በፊት የጀርሲ ፖሊስ በደሴቲቱ ላይ ከባለሀሃብቱ አብራሞቪች የንግድ እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ በተጠረጠሩ ቦታዎች ፈተሻ ማድረጉን የጀርሲ የህግ መኮንኖች ጽህፈት ቤት አሳውቋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ጦርነት ምክንያት ቢሊየነሩ አብራሞቪች በዩኬ ማዕቀብ ውስጥ ከተካተቱበት ውስጥ ይገኛሉ። የደሴቲቱ ሀገር ጀርሲ የዩኬን በመከተል በተመሳሳይ ሰዎች ላይ ማዕቀብ ጥላለች። የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ከ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመቱት ከአብራሞቪች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በተጠረጠሩት እና በጀርሲ የሚገኙ ወይም በባለቤትነት በተያዙ ንብረቶች እንዳይንቀሳቀሱ ትእዛዝ አስተላልፏል ሲል የደሲቲቱ የሕግ መኮንኖች ክፍል ገልጿል። ሮማን አብራሞቪች ባለፈው ወር ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ወረራ ምክንያት በዩኬ እና በአውሮፓ ህብረት ማዕቀብ ከተጣለባቸው በርካታ ባላሃብቶች መካከል አንዱ ናቸው። መንግስታትም የባለሃብቶቹን ውድ ጀልባዎች እና ሌሎች የቅንጦት ንብረቶችን ለመውሰድ እርምጃዎቸውን እያጠናከሩ ነው። ቢሊየነሩ ከወራት በፊት የቼልሲ እግር ኳስ ክለብን ለመሸጥ እንቅስቃሴ ጀምረው የነበረ ቢሆንም ማዕቀብ ከተጣለባቸው በኋላ ሂደቱ በመንግስት በእንግሊዝ መንግሥት እንዲቀጥል ተደርጓል። ከካሪቢያን ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው አንቲጓ እና ባርቡዳ ዩናይትድ ኪንግደም በአብራሞቪች ባለቤትነት የተያዙ ቅንጡ ጀልባዎችን እንድትይዝ ለመርዳት ፈቃደኛ ብላ ነበር። ባለሃብቱ በድምሩ በ1.2 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ዋጋ ያላቸው ቅንጡ ጀልባዎቻቸው በደቡብ ምዕራብ ቱርክ፣ በአውሮፓ ህብረት እና በዩኬ ስር ይገኛሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-61103519 +sports "ጉዬ አዶሎ፡ ""ቀነኒሳን ከመሰለ ጀግና ጋር በመወዳደሬ ትልቅ ደስታ ይስማኛል""" "የበርሊን ማራቶን አሸናፊው አትሌት ጉዬ አዶላ ""ቀነኒሳን ከመሰለ ጀግና ጋር መወዳደሬ ትልቅ ደስታ ይስማኛል"" ሲል ተናገረ። አትሌት ጉዬ ውድድሩ እንደ አጠቃላይ ቆንጆ ነበር ያለ ካለ በኋላ፤ ""በሰዓቱ ደስተኛ ባልሆነም አንደኛ በመውጣቴ ደስ ብሎኛል"" ብሏል። በውድድሩ ጥሩ ሰዓት ያልተመዘገበው በበርሊን የነበረው ከፍተኛ ሙቀት እንደምክንያት ያነሳው አትሌቱ፤ በውድድር ላይ የሚያጋጥሙ ስህተቶችን በማራም በቀጣይ ውድድር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። ""የማስበው የኤሊዩድ ሪኮርድ መስበር ነው"" ትናንት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን ላሌኛው ክስተት የሆነው ኢትዮጵያዊው ወጣት አትሌት አባቴ ታዱ ነው። አትሌት አባቴ ታዱ 4ኛ ደ��ጃን ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ ""እንደ ጉዬ አዶላ እና ቀነኒሳ በቀለ ያሉ ልምድ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ነበሩ። ከእነርሱ ጋር ተወዳድሬ ልምድ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ"" ብሏል። አትሌት አባቴ ታዱ ""የወደፊት እቅዴ በደንብ ሰርቼ ይሄን የኤሊይድ ኪፕቾጌን ሪኮርድ መስበር አለብኝ ብዬ ነው ማስበው"" ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58704717 +politics የአዲስ ዓመት ተስፋዬ 'ይህ በቃን' ብለን ወደ አዲስ ምዕራፍ የምንሸጋገርበት እንዲሆን ነው "የቀድሞው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በመስከረም ወር 2005 ዓ. ም. ነበር የአቶ መለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ ኢትዮጵያን እንዲመሩ የተሾሙት። ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመሾማቸው በፊት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደርነትን ጨምሮ በበርካታ የክልል ብሎም የፌደራል የሥራ ኃላፊነቶች ላይ ቆይተዋል። በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በቦርድ አመራርነት ያገለግላሉ። እንዲሁም ከባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ጋር ባቋቋሙት ፋውንዴሽን አማካኝነት በተለያዩ ተግባራትን ላይ እየተሳተፉ ነው። አቶ ኃይለማሪያም በአፍሪካ ምርጫዎችን የመታዘብ ሂደቶችን መርተዋል። ቢቢሲ ከአቶ ኃይለማሪያም ጋር የ2015 አዲስ ዓመት አስመልክቶ አጭር ቆይታ አደርጓል። ቢቢሲ፡ ጡረታ ወጥተዋል ወይስ አሁንም መደበኛ ሥራዎች አለዎት? ኑሮዎትስ የት ነው? አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የምኖረው። ነገር ግን የሥራዬ ሁኔታ ወደ ተለያዩ አገራት በተደጋጋሚ ያመላልሰኛል። በሁለት መስኮች በዋናነት እሳተፋለሁ። የመጀመሪያው ሥራዬ በኃይለማሪያም እና ሮማን ፋውንዴሽን ከባለቤቴ ጋር በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ እንሰራለን። ቅድሚያ የሚሰጣቸው የአየር ንብረት ለውጥ፣ ብሎም የተፈጥሮ ሃብት እና የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ላይ እንሰራለን። ይህም የደን፣ የአፈር እና የውሃ፣ የእጽዋት እንዲሁም የዱር እንስሳት ጥበቃ ሥራዎች ላይ እናተኩራለን። አገራችን በዚህ ጉዳይ በጣም የተጎዳች ናት። ከፍተኛ የሆነ የአየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች አሉባት። ድርቅ እና ጎርፍ ተመላልሰው ያጠቋታል። ሥራችንን በኦሞ ስምጥ ሸለቆ ላይ እንጀምር ብለን እዚያ ጀምረናል። የአካባቢው ኅብረተሰብ በአብዛኛው አርብቶ አደር ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሕጻናት፣ የልጆች፣ የሴቶች ብሎም የወጣቶች ጉዳይ በጣም አንገብጋቢ ነው። ስለዚህም የጤና፣ የትምህርት እና የሥርዓተ ምግብ ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ በዚሁ በኦሞ ስምጥ ሸለቆ አካባቢ እየሰራን እንገኛለን። ሌላኛው ግን የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ የማደርገው ተሳትፎ ነው። ይህ ከልጅነቴ ጀምሮ የሚያሳስበኝ ጉዳይ ስለሆነ ነው የትምህርት መስኬን ስመርጥ ወደዛው ያዘነበልኩት። ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ መፍትሔዎች ላይ የቅስቀሳ ሥራዎች (Advocacy) ላይ በሰፊው እሳተፋለሁ። እንዲሁም በሰላም እና ፀጥታ አጀንዳ ላይ በተለይም በአፍሪካ  ውስጥ የሚደረጉ ውይይቶች ላይም ወረቀቶችን አቀርባለሁ እንዲሁም እሳተፋለሁ። በአንድ ወቅት የዓለም አቀፉ ክራይሲስ ግሩፕ የቦርድ አባል ሆኜ እሰራ ነበር። አሁን በሥራ መደራረብ ምክንያት ትቼዋለሁ። እንዲሁም በአፍሪካ የኢኮኖሚ ለውጥ ላይ፣ የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ፣ ዴሞክራሲ እና የአመራር ሥራን የማቀላጠፍ ሥራዎች ላይ እሳተፋለሁ። ቢቢሲ፡  አውደ ዓመትን እንዴት ያሳልፋሉ? አቶ ኃይለማሪያም ፡ ብዙ ጊዜ ከአውደ ዓመት በፊት በቤተክርስትያን ጾሞች አሉ። አዲሱም ዓመት ከመግባቱ 15 ቀናት ቀደም ብለን የጾም ጸሎት እናካሂዳለን። አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የልማት፣ የብልጽግና እን��ሆን ብሎም የተረጋጋ ሆኖ እንዲያልፍ እንጸልያለን። ነገር ግን በየትኛውም በዓል ወቅት ግርግር ሲኖር ብዙም ደስተኛ አይደለሁም። በእርግጥ በባሕሪዬ ብዙ ግርግር አልወድም። ይልቁንም ወደ ጫካ፣ ወንዝ ወይም ፓርኮች የመሄድ ልምድ አለኝ። ቤት ውስጥ የምናሳልፍ ከሆነ ግን ቁጭ ብለን የምንጫወትበት ነው። ከሁሉም በላይ ዋናው የቤተሰብ ነውና፤ ቤተሰብ አንድ ላይ ይሰበሰባል። በተለይም ማምሻ አካባቢ ሁሉም ሰው ከቸርችም ሆነ ከየቤታቸው ይሰበሰባሉ፤ እንጫወታለን። ቢቢሲ፡ ከዚህ በፊት አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ቁርጥ ሥጋ በጣም እንደሚወዱ ተናግረው ነበር። በአውደ ዓመት ላይ ቁርጥ ሥጋ እንዴት ነዎት? አቶ ኃይለማሪያም፡ አዎ በተገኘ መጠን ቁርጥ ሥጋ እመገባለሁ። በርግጥ ውፍረትን ለመቀነስም ሆነ ጤናማ የምግብ ሥርዓት ለመከተል ጭምር እንደ ሥጋ ያሉ ፕሮቲኖች ይመከራሉ። ከመጠን በላይ ሆነው ወደ ዩሪክ አሲድ እንዳይቀየሩ ጥንቃቄ ከተደረገ ማለት ነው። ከልጆቼም አንዷ በጣም ትወዳለች። ቢቢሲ፡ ስለዚህ በዓመት በዓል ወቅት ጥሬ ሥጋ ከቤታችሁ አይጠፋም? አቶ ኃይለማሪያም፡ አይጠፋም! ቢቢሲ፡ ለአዲስ ዓመት ለቤተሰብ ስጦታ መስጠት ላይ እንዴት ነዎት? አቶ ኃይለማሪያም ፡ በአውደ ዓመት እንኳን ብዙም ስጦታ በባሕላችንም አልተለመደም። ምናልባት ፖስት ካርድ ካልሆነ። ነገር ግን በተለያየ ጊዜ ስጦታ እንሰጣጣለን። ለእኛም ስጦታ ይመጣልናል። ከሚመጡልን ስጦታዎች መካከል አበባ፣ በግ እና መጠጦች ይገኛሉ። ነገር ግን እኛ መጠጥ ስለማንጠጣ አጠራቅመን ሸጠን ለሌላ ዓላማ እናውለዋለን። ቢቢሲ፡ በአዲሱ ዓመት ተስፋ እና ስጋትዎት ምንድን ነው? አቶ ኃይለማሪያም ፡ እኔ ሁልግዜ ተስፋዬ በእግዚአብሔር ላይ ነው። በእርሱ ተስፋ አደርጋለሁ፤ መቼም ተስፋ አልቆርጥም። መልካም ነገር ያደርጋል ብዬ አምናለሁ። ስጋት እና ተስፋ ግን የሰው ልጅ ዕለት ተቀን የሚፈራረቁበት ጉዳዮች ናቸው። ከእነሱ ውጪ ሆኖ መኖር የሚችል ሰው የለም። አንዳንዴ ተስፋ ያይላል አንዳንዴ ስጋት ያይላል። በአገራችንም ሆነ በግል ብዙ ተስፋ የሚሰጡ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ፣ በዚያው ልክም ስጋት የሚያጭሩ፣ መፍታት ሲገባን ያልፈታናቸው የተጠራቀሙ ችግሮች አሉ። እነዚያን ከስሜት በጸዳ፣ በሰከነ ሁኔታ፣ አርቆ በማሰብ እንደዚሁም ፍቅርን ሰላምን እና መተሳሰብን ማዕከል አድርጎ ጥላቻን እና ምሬትን መፍታት ያስፈልጋል። በርካታ አገራት ብዙ ስጋቶች በተፈጠሩባቸው ጊዜ ያንን ትምህርት አድርገው ከእንግዲህ በቃኝ የሚሉበት ወቅት አለ። የአውሮፓ አገራት ሲመሰረቱ በብዙ ጣጣዎች ውስጥ አልፈው ነበር፤ ግን ያንን በቃን ብለው ነው ያመለጡት። እኛም አሁን ባለንበት ሁኔታ በቃን፣ ሰለቸን ከዚህ በኋላ አይደገም ብሎ ሕዝቡ በምሬት ያንን የሚስማማበት ወቅት እየደረሰ ይሆን? በሁሉም አቅጣጫ ያሉ መሪዎች የሚስማሙበት ጊዜ እየደረሰ ይሆን? ብዬ እጠይቃለሁ። ይህ ከሆነ ያለፈውን ለታሪክ አስቀምጦ ወደ አዲስ ምዕራፍ የመሸጋገር እድል አለ። ያ ካልሆነ ወደ ጥፋት የመሸጋገር ዕድል ይኖረዋል። ለእኔ ግን ተስፋዬ 'ይህ በቃን' ብለን ወደ አዲስ ምዕራፍ የምንሸጋገርበት ይሆናል የሚል ነው። ቢቢሲ፡ ኢትዮጵያ እና ሕዝቦቿ  አሁን ያሉበት አስቸጋሪ  ሁኔታ ይታወቃል። ይህንን ለማሻሻል ምን ሚና ይጫወታሉ? አቶ ኃይለማሪያም ፡ የእኔ ሚና ትልቅ ነው ብዬ ባልወስድም በታሪክ አጋጣሚ ኢትዮጵያን የሚያክል ትልቅ አገር እንደመራ ሰው ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ ጥረቶችን አደርጋለሁ። የሰላም፣ የመተባበር እና የፍቅር መንፈስ እንጂ የጥላቻ እና የጥሎ ማለፍ ስሜት የሚመራው እንዳይሆን ለማሳሰብ እና ለመምከር እሞክራለሁ። ይሄ በቃል ይባላል እንጂ በተግባር ሲተገበር ከባድ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያ ላይ ተጸዕኖ ማሳደር የሚችሉ ሰዎችን አገኛለሁ። በተለይም አፍሪካዊያን እና ምዕራባዊያን መሪዎችን በማግኘት ትክክለኛውን ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ለማብራራት እሞክራለሁ። አገሪቱ ካለችበት ችግር እንድትወጣ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥረት አደርጋለሁ። ያልተረዱት እውነታ ካለም ለማስረዳት እና በተለይም ደግሞ ትኩረታቸው ተፋላሚ ወገኖች ላይ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንዲሆን ለማድረግ እሞክራለሁ። ሕዝቡ ላይ ትኩረታቸውን ካላደረጉ ተፋላሚ ወገኖች በሚፈጥሩት ችግር ሕዝቡ ከፍተኛ ቅጣት እንዲደርስበት ይሆናል። ያ እንዳይሆን ሁሌም ሕዝቡን እንዲመለከቱ እና መንግሥታትንም እንዲመክሩ፤ ከሚያባብስ ነገር ይልቅ የሚያግባባ ነገር እንዲያደርጉ እመክራለሁ። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከስቃይ የሚያስወጣ እንጂ ስቃዩን የሚያበዛ እርምጃ እንዳይወስዱ አሳስባቸዋለሁ። በተለይም ኢትዮጵያን የመሰለች ትልቅ አገር መሰረቷ የተናጋ እንደሆነ መላው አፍሪካ፣ ብሎም መካከለኛው ምሥራቅም ሆነ የአውሮፓ አገራት ድረስ የሚደርስ ቀውስ እንደሚመጣ አውቀው የተረጋጋ ፖሊሲ እንዲይዙ ጥረት አደርጋለሁ። ቢቢሲ፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በርካቶች ወደኋላ ሄደው ልጅነታቸውን ያስባሉ። እርስዎ አዲስ ዓመት ሲመጣ ወደ አዕምሮዎት የሚመጡ ትዝታዎች ምንድን ናቸው? አቶ ኃይለማሪያም ፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በተለይም አንድ መጥፎ ትዝታ አለኝ። ልክ 12ኛ ክፍል እንደጨረስኩ በነሐሴ ወር መጨረሻ ነበር አባቴ ሕይወቱ ያለፈው። አዲሱ ዓመት በለቅሶ ላይ ሳለን ነበር የደረሰው። ዩኒቨርሲቲም መግቢያ ወቅት ነበር እና ከለቅሶ እንደተነሳሁ ነበር ለምዝገባ የሄድኩት። ያ አዲስ ዓመት ለእኔ የከፋ አዲስ ዓመት ነበር። እሱን ሁልጊዜ ነው የማስታውሰው። አባታችን ለእኛ ሁሉም ነገር ስለነበረ ያ ስብራት የነበረ አዲስ ዓመት አልረሳውም። በሌላ በኩል ደግሞ ከባለቤቴ ጋር ሠርጋችን በነሐሴ መጨረሻ ላይ ነበር።  እና በወጣትነት በአዲስ ዓመት ያሳለፍነው ሁልጊዜም ትዝ የሚለን መልካም ትዝታችን ነው። እና ሁለቱም ነገሮች ተፈራርቀው አይቻለሁ። ከዚያ በተረፈ ግን በእኛ አካባቢ በልጅነታችን አሁን በተለምዶ መስቀል የሚባለው ዓመት በዓል አለ። በእርግጥ በብሔሩ አጠራር 'ጊፋታ' ነው የሚባለው፤ ኋላ ከመስቀል ጋር ተገጣጠመ እንጂ። የዘመን መለወጫ ነው። መስከረም 17 ከሚውልበት ሳምንት ጀምሮ ለወራት ነው የሚከበረው። ያንን በጣም ከልቤ ያከበርኩበት ጊዜ ነው፤ እስከ 15 ዓመቴ ድረስ። ከዚያ በኋላ እሱም በተለያየ ምክንያት እየቀዘቀዘ መጥቷል። ቢቢሲ፡ ምንም አንኳን በአውደ ዓመት ዙሪያ ቢሆንም ቆይታችን ለማሳረጊያ አንድ ጥያቄ ላንሳ። ራስዎን ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ካገለሉ በኋላ፣ ለኢትዮጵያ ይመጣል ብለው ያሰቡት ለውጥ መጥቷል ብለው ያምናሉ? አቶ ኃይለማሪያም ፡ የእኔ ራሴን ከሥልጣን ማግለል በወቅቱ ተፈጥሮ የነበረውን ውጥረት እና ስጋት በማርገብ እና ሕዝቡ ተስፋ እንዲሰንቅ በማድረግ የራሱን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ከሥልጣን ወርዶ በሰላም የኖረ ሰው በአገራችን ባልነበረበት ሁኔታ ይህ እንደሚቻል አንድ ተምሳሌት መፈጠሩ አንድ ነገር ነው። እኔም የታደልኩ ነኝ ብዬ አምናለሁ። ይሄ በሁሉም መስክ የሚያስተላልፈው የራሱ መልዕክት አለው። አሁን በአመራር ላሉትም ይህ እንደሚቻል አሳይቷል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይም ""ልክ እንዳንተ ዕድል ቢገጥመኝ እና እኔም በጊዜዬ አስረክቤ በሰላም ከሕዝቡ ጋራ የምኖርበት ሁኔታ ቢፈጠርልኝ"" ሲል ሰምተሽ ይሆናል። ከእኔ በኋላ ያሉ መሪዎች ሥልጣን የመጨረሻው ሕይወት እንዳልሆነ እና ��ሥልጣን ወርዶ መኖር እንደሚቻል ያሳየ ነው ብዬ አስባለሁ። እንዲያውም የተሻለ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚቻል ያሳያል። ምንም እንኳን አስተዋጽኦ የምናደርገበት መንገድ ቢለያይም። ነገር ግን የአገራችን የኢትዮጵያ ችግር በጣም ጥልቅ ነው። በእኔ ወይም በአንድ ሰው ከሥልጣን መውረድ የሚፈታ አይደለም። የተወሰነ የራሱን መደላድል የሚፈጥር ሊሆን ይችላል። እኔ አሁን ወጥቼም ቢሆን ሳስበው የአገራችን ችግር ጥልቀቱን ባለመረዳት ብዙ እንጎዳለን። ኢትዮጵያ መግለጽ ከምችለው በላይ እጅግ የተወሳሰበ፣ የተደራረበ፣ እጅግ በጣም የቆየ፣ እንዲሁም አሁን የተፈጠሩ ችግሮች ውስጥ ያለች አገር ነገር ነች። ይሄ መፍትሄው እና መፍቻው ምንድን ነው ብሎ ማሰብን ይጠይቃል። ሌላው ቀርቶ አሁን ያለው አመራር ሁሉ ወረድኩ ቢል እንኳን የሚፈታ አይደለም። ችግሩ ከአመራር መለዋወጥ በላይ ነው። ይልቁንም አንድ ከፍተኛ የሥርዓት ለውጥ ይጠይቃል። በርካታ ቅሬታ እና ቁርሾ የሞላው ሕብረተሰብ ነው ያለን። ወጣቱ የራሱ አስተሳሰብ አለው፤ የቆየው ሰው የራሱ አሰተሳሰብ አለው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በጣም ብዙ ምልክቶች አሳርፈው ያለፉ ትውልዶች አሉ። በእኛ አጠራር የ1960ዎቹ ትውልድ አሁንም በተለያዩ ፓርቲዎች ውስጥ ሆኖ እስካሁን ለሥልጣን እየተፎካከሩ ያሉ ሰዎችም ያሉበት ማለት ነው። ይሄ ትውልድ በወቅቱ የያዛቸው አቋሞች ኢትዮጵያን በመልካምም ሆነ በመጥፎው ጠባሳ ጥለው ያለፉ ናቸው። ከእነዚያ ውስጥ አንዱ የብሔር ጥያቄ የተመለሰበት መንገድ ነው። አሁን በደንብ እንደገባን ሁላችንም እንዳሰብነው የብሔሮችን መብት እና እኩልነት ከማምጣት አልፎ የመጠፋፊያ መንገድ ብሎም የጽንፈኝነት አዝማሚያ እያሳየ ነው። ከዚህ የተነሳ ብዙ መከራ ውስጥ ነው ያለነው። ይህንን በግልጽ ተወያይተን መካከለኛውን መንገድ መፈለግ አለብን። ከጽንፈኝነት የራቀ ነገር ግን የሃይማኖት እና የብሔር መብቶችን ጨምሮ የቡድን መብቶች ከዜግነት መብት በማይበልጡበት መንገድ መፍቻ አማራጮችን ቁጭ ብለን መፈለግ አለብን። ይህ በተለያየ መንገድ የተመሰረቱ እንደ ሶቪየት ኅብረት ያሉ አገራት በሚፈጠሩበት ጊዜ የመጣ ሃሳብ ነው። ኋላ ወደ ራሳችን ስናመጣው ሕዝባችን የተቀላቀለ መሆኑን በሚረሳ መንገድ ነበር ያስገባነው። እያንዳንዱ ብሔር ወጥ ነው ብለን በማሰብ ያስገባነው ነገር አሁን መላወሻ አሳጥቶናል። እንግዲህ እንደዚህ አይነት እና መሰል ያልተፈቱ ጥያቄዎች አሉ። የጋራ ፍቺ ለመስጠት የሃይማኖት እና የፖለቲካ መሪዎች እንዲሁም የሚመለከታቸውን በሙሉ ያሳተፈ ውይይት ተደርጎ ለእነዚህ ችግሮች መፍተሄ ማፈላለግ ያስፈልጋል። ለምሳሌ የእኔን ብሔር ወስደሽ ወላይታዎች በአጼ ምኒሊክ አገር የመመስረት ሂደት ውስጥ ተጨፍልቀናለን፣ በመቶ ሺዎች ተጨፍጭፈናል ብለው እስካሁን ይናገራሉ። እውነት ነው፤ ይሄ አልተደረገም አልልም። ነገር ግን ከአንድ ፊውዳል ንጉሥ ዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት ጥበቃ የምናስብ ከሆነ ከታሪክ ጋር ግጭት እንገባለን። በወቅቱ ንጉሥ ጦናም ቢሆኑ ይሄንን ዕድል ቢያገኙ ንጉሥ ምኒሊክ ያደረጉትን ሊያደርጉ ይችላሉ ብዬ ነው የማምነው። ንጉሥ ጦናም በራሱ አካካቢ የፊውዳል ሥርዓት ጫና ፈጥሯል። ስለዚህ ሁሉም የፊውዳል ሥርዓቶች የሚፈጽሙት ነገር ነው። ነገር ግን ልክ አልነበረም። ያንን ቁርሾ ይዞ እርሳቸው የተፈጠሩበትን ጭቁኑ የአማራ ብሔር ይሄንን ችግር እንደፈጠረ ተደርጎ የሚሳልበት እና የተለያየ ስያሜ የሚሰጥበት መንገድ መፈታት አለበት። ይሄ አሁን ባለንበት ሁኔታ ያልተፈታ ቁርሾ ጥሎ ንጹሁ ሕዝብ እንዲጎዳ እና እንዲሞት ያደርጋል። የአገራችንን የበፊት ታሪክ በጎውን ይዘን፣ ሌላውን ደግሞ ሁለተኛ በማይደገምበት ሁኔታ እንዴት ነው መሻገር የሚቻለው የሚለው ላይ መስራት አለብን። ሁሉም የራሱን ያልሻረ ቁስል ተንፍሶ እና አንዳንዱን ደግሞ ልክ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ላይ ተስማምቶ ማለፍን ይጠይቃል። ጥልቅ እና አካታች የማኅበረሰብ ውይይት እና መግባባት መፈጠር አለበት። ይሄ ካልሆነ ግን ስጋታችን የበለጠ እየጨመረ መሄዱ አይቀርም። እናም የእኔ መውጣት ሁሉን ነገር የሚፈታ አይደለም። በወቅቱ የተወሰነ ተስፋ ጭሮ ነበር። ያ ተስፋ በሂደት እየቀዘቀዘ እና እየቀነሰ መምጣቱን ሁላችንም የምናየው ነገር ነው። ነገር ግን ወደ ትክክለኛው መንገድ እንድንገባ አሁንም ዕድል አለን።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cl5845y7v53o +health በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱ ተገለጸ "በኢትዮጵያ በየዓመቱ በኤችአይቪ ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱ ተገለጸ። በፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግነኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዳንኤል በስረ በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱን ጥናቶች ያመላክታሉ ብለዋል። በአገር አቀፍ ደረጃ አጠቃላይ የቫይረሱ የስርጭት ምጣኔ 0.86 በመቶ መሆኑን አቶ ዳንኤል ያስረዳሉ። ""ይሄ ማለት በመላው አገሪቱ፤ በሁሉም ማሕበረሰብ ክፍል ተመሳሳይ ነው ማለት አይደለም። በገጠር እና በከተማ የስርጭት ምጣኔው የተለያየ ነው"" የሚሉት ዳንኤል፤ በጋምቤላ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስርጭት ምጣኔው ከፍተኛ መሆኑን ይናገራሉ። ዳንኤል የቫይረሱ ስርጭት በጋምቤላ 4.1 በመቶ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከ3 በመቶ በላይ መሆኑን ያስረዳሉ። 3 በመቶ ምጣኔ ምን ማለት እንደሆን ሲያስረዱ፤ በቀላል ቋንቋ ከመቶ ሰዎች ሦስት ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው አለ ማለት ነው ይላሉ። በሶማሌ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በታች መሆኑን ይናገራሉ። የሶማሌ ክልል 0.01 በመቶ አነስተኛ የቫይረሱ ስርጭት የሚገኘበት ክልል መሆኑን ይናገራሉ። በአገሪቱ ክልሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የቫይረሱ ስርጭት ልዩነት እንዴት ሊፈጠረ ቻለ? ተብለው የተጠየቁት አቶ ዳንኤል፤ ለዚህ ጥያቄ ቁርጥ ያለ ምላሽ ለመስጠት በዝርዝር ጥናት ላይ መመርኮዝ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የተሰራ ሥራ ልዩነት ፈጥሮ ሳይሆን ዋናው ምክንያት ከባህል እና ሃይማኖታዊ ጉዳይ ጋር ሊያያዝ ይችላል ይላሉ። አቶ ዳንኤል ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ አጠቃላይ የቫይረሱ ስርጭት ምጣኔ ከ6 በመቶ በላይ ደርሶ የሚያውቅበት አጋጣሚ እንዳለ ይናገራሉ። በከተሞች አካባቢ ደግሞ የስርጭት ምጣኔው እስከ 10 በመቶ ስለመድረሱ ተመዝግቦ ነበር ይላሉ። ""በአንድ አገር አጠቃላይ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫይረሱ ስርጭት ወረርሽኝ ነው የሚባለው"" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ምንም እንኳ በአገር ደረጃ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በታች ቢሆንም የስርጭት መጠኑ ከ1 በመቶ በላይ የሆነባቸው ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች መኖራቸውን ይናገራሉ። የቫይረሱ ስርጭት በጾታ ተከፍሎ ሲታይ ደግሞ፤ ሴቶች ከወንዶች በላይ ተጋላጭ መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሽታውን በመከላከል ረገድ የሚሰሩ ሥራዎች መቀነሳቸውን ዳንኤል አስረድተዋል። መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ቀደም ሲል ሲሰሩ በነበሩበት ልክ ቫይረሱን የመከላከል ሥራ እየሰሩ አይደለም ይላሉ። ለዚህም ምክንያቱ የስርጭቱ መጠን በየዓመቱ መቀነስ በማሳየቱ እና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከመከላከሉ ይልቅ ሕክምናው ላይ ትኩረት በመሰጠቱ ነው ይላሉ። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በአሁኑ ወቅት ከ622 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ይገኛል። ከእነዚህ መካከል ወደ 500 ሺህ የሚሆኑ ጸረ-ኤችአይቪ መድሃኒት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጥናቶች ያሳያሉ ብለዋል ዳንኤል። በየዓመቱ ከ11 ሺህ በላይ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች አሉ። ""ይህን የከፋ የሚያደርገው ከእነዚህ ውስጥ 67 በመቶ ድርሻ የሚይዙት እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች መሆናቸው ነው"" ይላሉ ዳንኤል። የቫይረሱን ስርጭት መከላከል አስፈላጊነትን ከሚያረጋግጡት መካከል አንዱ በበሽታው የሚያዙት አብዛኛዎቹ ወጣቶች መሆናቸው ነው ይላሉ። ""አምራች ኃይል ነው። እንደ ሀገር ተስፋ የሚጣልበት ነው። በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ላይ የስርጭት ምጣኔው ከፍ ብሎ መታየቱ እንደ አገር አደጋ ውስጥ እንዳለን የሚያሳይ ነው"" ብለዋል። ዳንኤል፤ ሴተኛ አዳሪዎች፣ ባሎቻቸውን በሞት ያጡ እና ትዳራቸውን የፈቱ ሴቶች ዘንድ የቫይረሱ ስርጭት መጠን ከፍተኛ ነው ይላሉ። ""በሴተኛ አዳሪዎች የስርጭት ምጣኔው 18 በመቶ ነው። ባሎቻቸውን በሞት ያጡ እና ትዳራቸውን የፈቱ ሴቶች አካባቢ የስርጭት ምጣኔው ወደ 20 በመቶ ሆኖ እናያለን"" ይላሉ። ሕይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ከ12 ሺህ ባለይ ሰዎች ደግሞ በየዓመቱ በኤድስ እና ተያያዥ በሽታዎች ሕይወታቸው እያለፈ ነው። በአገሪቱ ቫይረሱ በደማቸው ይገኘባቸዋል ከተባለው ከ622 ሺህ ባለይ ሰዎች 61 በመቶውን የሚይዙት ሴቶች ናቸው ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት የስርጭት ምጣኔው ከ1 በታች መሆኑ የስርጭት መጠኑ አነስተኛ እንደሆነ ነው የሚያሳየን የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ የስርጭት መጠኑ ግን ሊያዘናጋን አይገባም ይላሉ። ""መዘናጋቱ እና ቸልተኝነቱ በዚህ መንግድ የሚቀጥል ከሆነ፤ እንደ አገር ያልተገባ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል"" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ የልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ይላሉ። ኮቪድ እና ኤችአይቪ የኮሮናቫይረስ መከሰት ኤችአይቪ በደማቸው በሚገኝባቸው እና መድሃኒት በሚወስዱ ሰዎች ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል ይላሉ። ""ትልቁ ችግር የነበረው ስነ-ልቦናዊ ተጽእኖ ነው"" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ኮቪድ-19 ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸውን ሰዎችን ይጎዳል በሚል በስጋት ወደ ጤና ተቋም ያለመምጣት ሁኔታዎች እንደነበሩ ይናገራሉ። ከዚህ በተጨማሪም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በማሰብ በመንግሥት የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን ተከትሎ ከሚኖሩበት ርቀው መድሃኒት ይወስዱ የነበሩ ሰዎች የትራንስፖርት አማራጭ ባለማግኘት መድሃኒታቸውን መውሰድ የማይችሉት ሁኔታ ነበር። ""ለምሳሌ አዲስ አበባ ላይ ያለ ሰው አዳማ ሄዶ የሚወስድ ከሆነ . . . መንቀሳቀሱ ሲቆም መድሃኒቱን በትክክል ለመወሰድ መቸገር ነበር"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59515396 +sports አሜሪካ አበረታች መድኃኒት የሚጠቀሙ ስፖርተኞችን በወንጀል ልትከስ ነው የአሜሪካ ምክር ቤት ሴኔት በዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች ላይ የአበረታች መድኃኒት የተጠቀመ ማንኛውንም ሰው የወንጀል ክስ እንዲመሰረትበት የሚያስችልን ረቂቅ ህግ አፀደቀ። የአበረታች መድኃኒት ጥሰቶችን ባጋለጠው በሩሲያዊው ግሪጎሪ ሮድቼንኮቭ ስም የሮድቼንኮቭ ፀረ-አበረታች አዋጅ ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሲፈርሙበት ሕግ ይሆናል ተብሏል፡፡ የአሜሪካ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ዋና ኃላፊ ትራቪስ ታይጋርት ውሳኔውን “ንፁህ ስፖርት ለመፍጠር በሚደረገው ትግል ትልቅ” ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡ የዓለም ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (ዋዳ) ግን ጉዳዩ እንዳሳሰበው አስታውቋል። ቀደም ሲል በተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ከፀደቀ በኋላ ሰኞ ዕለት ሴኔቱ ያለተቃውሞ ያፀደቀው ሕግ ስፖርተኞችን፣ ስፖንሰር አድራጊዎችን እና ከአበረታች መድኃኒት መስፋፋት ጀርባ ያሉት ላይ አሜሪካ ክስ መመስረት ያስችላታል። ሕጉ ቀድም ሲል በዋዳ ቅጣት ካልተላፈባቸውን ስፖርተኞች ይልቅ አሰልጣኞች፣ ወኪሎች፣ ሥራ አስኪያጆች እና ባለሥልጣናትን ላይ ዒላማ ያደርጋል፡፡ ህጉን ተከላለፉ አካላት እስከ አንድ ሚሊዮን ዶላር ወይም እስከ 10 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣትን ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡ “ሕጉ ንፁህ ስፖርተኞችን ለመከላከል እንዲሁም ስፖርትን፣ ስፖንሰሮችን የሚያታልሉ እና ስፖርተረኞችን የሚጎዱ ዓለም አቀፍ የአበረታች መድኃኒት አሰራጮችን ተጠያቂ ያደርጋል” ብለዋል ታይጋርት፡፡ “በዓለም ዙሪያ ለንጹህ ስፖርት ለሚደረገው ትግል ታላቅ ቀን ነው። በቅርቡ ህግ ሆኖ ለማየት እና ለንጹህ ስፖርት በመፍጠር በኩል ለውት ያመጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል። ዋዳ በበኩሉ ዓለም አቀፋዊ የፀረ-አበረታች መድኃኒት እርምጃዎችን ሊያዳክም ይችላል በሚል “ሥጋቶች” እንዳሉት ገልጿል። ሕጉ በረቂቁ ውስጥ ያካተታቸውን የአሜሪካ ፕሮፌሽናል እና የኮሌጅ ስፖርተኞችን ሳያካትት ለምን ቀረ ሲል ጠይቋል፡፡ “ለአሜሪካውያን ስፖርቶች ጥሩ ካልሆነ ለሌላው ዓለም ጥሩ የሆነው ለምንድነው?” ሲልም ያክላል። በተጨማሪ ይህ ረቂቅ ሕጉ መረጃ ሰጪዎች ወደ ፊት እንዳይመጡ ሊያግደው ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ዋዳ ገልጿል። ታይጋር ግን ህጉ “መረጃ ሰጪዎችን ይጠብቃል” ብሏል፡፡ የቀድሞው የሞስኮ የፀረ-አበረታች መድኃኒቶች ቤተ ሙከራ ኃላፊ የነበረው ሮድቼንኮቭ እ.ኤ.አ. በ2015 በሩሲያ መንግስት የተደገፈውን አበረታች መድኃኒት አጠቃቀም ዝርዝር ማስረጃ ይዘው ከሩስያ ተሰደዋል፡፡ በዚህ ምክንያትም ሩሲያ ከ2018ቱ ክረምት ኦሎምፒክ ታግዳለች። https://www.bbc.com/amharic/news-54978864 +politics የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት፡ ቢያንስ ሦስት ተቃዋሚዎች ሲገደሉ በርካቶች ለጉዳት ተዳረጉ "በሱዳን ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣን መቆጣጠሩን ተቃውመው አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ ወታደሮች በተኮሱት ተኩስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ 80 የሚሆኑ ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸው ተዘገበ። ተቃዋሚዎቹ አደባባይ የወጡት ወታደራዊ ኃይሉ የሲቪል አስተዳደሩን ከበተነ፣ የፖለቲካ መሪዎችን ካሰረ እና በአገሪቷ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ በኋላ ነው። ወታደሮች የተቃውሞውን አስተባባሪዎች ለመያዝ በዋና መዲናዋ ካርቱም የቤት ለቤት አሰሳ እያደረጉ እንደሆነም ተነግሯል። በሱዳን የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት በዓለም ዙሪያ የተወገዘ ሲሆን አሜሪካ ለእርዳታ የምትሰጠውን 700 ሚሊየን ዶላር አቁማለች። መፈንቅለ መንግሥቱን የመሩት ጀነራል አብደል ፈታህ ቡርሃን በአገሪቷ ለተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ ተጠያቂ ተደርገዋል። የሲቪል መሪዎችና አቻቸው የወታደራዊ መሪዎች ከሁለት ዓመት በፊት አገሪቷን ለረዥም ጊዜ ሲመሩ የነበሩት ኦማር አልበሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ የፖለቲካ ሽኩቻ ውስጥ ገብተዋል። ሰኞ ምሽት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎች በካርቱምና በሌሎች ከተሞች ጎዳናዎች ላይ በመውጣት የሲቪል አስተዳደሩ እንዲመለስ መጠየቃቸውን የቢቢሲ አረብኛ ዘጋቢ መሀመድ ኦስማን ዘግቧል። አንድ ጉዳት የደረሰበት ተቃዋሚ ከወታደራዊ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውጭ እግሩ ላይ መመታቱን ለቢቢሲ የተናገረ ሲሆን ሌላኛው ተቃዋሚም ጦሩ መጀመሪያ ላይ ቦንብ እንደወረወረ እና ከዚያም በቀጥታ ጥይት መተኮሱን ተናግሯል። "" ሁ���ት ሰዎች ሞተዋል ፤ ይህንንም በዐይኔ ተመልክቻለሁ"" ብሏል አል ታይብ መሀመድ አህመድ። የሱዳን ሐኪሞች ማሕበር እና የማስታወቂያ ሚኒስቴር የተተኮሰው ከጦሩ መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውጭ መሆኑን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። በከተማዋ ካሉ ሆስፒታሎች የወጡ ምሥሎችም ሰዎች ልብሳቸው በደም ተነክሮ እና በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸው ያሳያሉ። ተቃዋሚዎች የመኪና ጎማዎችን በማቃጠልና ድንጋይ በማስቀመጥ መንገድ ዘግተዋል። በርካታ ሴቶችም ""ወታደራዊ አገዛዝ አንፈልግም"" በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል። የከተማዋ አውሮፕላን ማረፊያም የተዘጋ ሲሆን ዓለም አቀፍ በረራዎችም ታግደዋል። ኢንተርኔትና የስልክ መስመሮችም ተዘግተዋል። የሴንትራል ባንክ ሰራተኞች በመላ አገሪቷ አድማ መትተዋል። ሒሞችም በጦሩ በሚመሩ ሆስፒታሎች ከድንገተኛ ሕክምና በስተቀር አንሰራም ብለዋል። የዓለም መሪዎች ጦሩ አገሪቷን መቆጣጠሩን ተከትሎ ስጋታቸውን ገልጸዋል። አሜሪካ በሱዳን በቁም እስር ላይ ያሉና የት እንዳሉ የማይታወቁ የፖለቲካ መሪዎች እንዲፈቱ በመጠየቅ ዩናይትድ ኪንግደምን፣ አውሮፓ ሕብረትን ፣ የተባበሩት መንግሥታት እና ሱዳን አባል የሆነችበትን የአፍሪካ ሕብረትን ተቀላቅላለች። በቤት ውስጥ እስር እንደሚገኙ ከተነገረው የፖለቲካ መሪዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ እና ባለቤታቸው እንዲሁም የካቢኔ አባላቶቻቸው እና ሌሎች የሲቪል መሪዎች ይገኙበታል። የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳለው ሰኞ ጠዋት ልዩ የደህንነት አባላት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤት በመሄድ ሃምዶክ በመፈንቅለ መንግሥቱ እንዲስማሙ ሞክረው የነበሩ ቢሆንም እርሳቸው ግን ሳይስማሙ ቀርተዋል። ሱዳን እአአ 2019 አገሪቷን ለረዥም ጊዜ የመሩት ኦማር አል ባሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ የሲቪልና የወታደራዊ መሪዎች ሥልጣን በመጋራት ስምምነት አገሪቷን እየመሩ ነበር። ስምምነቱ አገሪቷን ወደ ዲሞክራሲ ለማሸጋገር ያለመ ቢሆንም ቀደም ብሎ በርካታ መፈንቅለ ሙከራዎች ተደርገዋል። ለመጨረሻ ጊዜ የተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የተካሄደውም ከአንድ ወር በፊት ነበር። የሥልጣን መጋራት ስምምነቱን መሪ የነበሩት ጀነራል አብደል ፈታህ አልቡርሃን የአሁንን መፈንቅለ መንግሥት የመሩ ሲሆን መፈንቅለ መንግሥቱ በፖለቲካ ሽኩቻ ምክንያት የተፈጠረውን ""የአብዮቱን አካሄድ ለማስተካከል"" አስፈላጊ ነበር ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59042602 +sports ኢትዮጵያውያኑ የሴቶችና የወንዶች የ5ሺህ ሜትር ውድድር ክብረ ወሰንን ሰበሩ ኢትዮጵያውያኑ እጅጋየሁ ታዬ እና በሪሁ አረጋዊ የዓለም የአምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ክብረ ወሰን መስበራቸውን የዓለም አትሌቲክስ የበላይ አካል አስታወቀ። ትናንት አርብ በፈረንጆቹ አቆጣጠር የዓመቱ የመጨረሻ ዕለት በአውሮፓዊቷ ስፔን ባርሴሎና ከተማ በኩርሳ ዴልስ ናሶስ በተካሄደ ውድድር ነው ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ክብረ ወሰን የሰበሩት። በሴቶቹ እጅጋየሁ ታዬ ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ እንዲሁም በወንዶቹ በሪሁ አረጋዊ በ12 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በማጣናቀቅ ነው ቀደም ሲል በርቀቱ የተያዙትን ክብረ ወሰኖች ያሻሻሉት። በሴቶቹ የአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት የዓለምን ክብረ ወሰን ያሻሻለችው እጅጋየሁ ታዬ ቀደም ሲል ከነበረው ሰዓት ላይ በ24 ሰከንዶች ቀድማ ገብታለች። በሪሁ አረጋዊም ክብረ ወሰኑን ያሻሻለው በሁለት ሰከንዶች መሆኑን የዓለም አትሌቲስ አስታውቋል። የዓለም አትሌቲክስ በድረ ገጹ ላይ ባወጣው መረጃ የ21 ዓመቷ እጅጋየሁ ታዬ የኢትዮጵያ የ3ሺህ ሜትር ርቀት ባለ ክብረ ወሰን መሆኗን አስታውሶ፤ ክብረ ወሰኑን አስክታሻሽል ድረስም በአምስት ሺህ ሜትር ውድ���ር የዓለም ሁለተኛዋ ፈጣን ሯጭ ሆና ቆይታለች ብሏል። እጅጋየሁ የአምስት ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰንን ያሻሻለችበት የባርሴሎናው ውድድር በሩጫ ዘመኗ ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ የውድድር ተሳትፎዋ ነው። የሃያ ዓመቱ በሪሁ አረጋዊ በኅዳር ወር ሊል ውስጥ በተደረገው ተመሳሳይ ውድድር ላይ በኬንያዊው ጆሽዋ ቼፕቴጌ ተይዞ የቆየውን ክብረ ወሰን ለመስበር በአንድ ሰከንድ ተቃርቦ ነበር። ነገር ግን የፈረንጆቹ 2021 ከመጠናቀቁ በመጨረሻዋ ዕለት በመጨረሻው ውድድር በሪሁ ከወር በፊት ተቃርቦ የነበረውን ክብረ ወሰን ለማሻሻል ችሏል። በተለመደው የዓለም አትሌቲክስ አሰራር መሠረት ይህ በሁለቱ ኢትዮጵየውያን አትሌቶች የተሻሻለው ክብረ ወሰን የሚጸድቀው አስፈላጊው የማጣራት ሂደት ከተካሄደ በኋላ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-59845516 +sports ለኢትዮጵያውያንና ለአፍሪካውያን ፈር ቀዳጅ ድል ያስመዘገበችው ፋጡማ ሮባ "ፋጡማ ሮባ የመጀመሪያውን የሴቶች ማራቶን ፈር ቀዳጅ ድሏን እ.ኤ.አ. በ1996 በሞሮኮ ማራክሽ ነበር የተቀዳጀችው። በመቀጠልም ከሁለት ወር በኋላ በሮም ማራቶን አሸናፊ ሆነች። ከሮም አሸናፊነት በኋላም በ1996 በአትላንታ አሜሪካ በሚደረገው የኦሊምፒክ ውድድር በ2:26:05 በሆነ ሰዓት አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች። በወቅቱ ፋጡማን በመከተል ሁለት ደቂቃ ዘግይተው የሩሲያዋ ቫለንቲና ይጎሮቫና ጃፓናዊቷ ዩኩ አርሞሪ 2ኛና 3ኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል። ከ1997 እስከ 1999 የተካሄዱ የቦስተን ማራቶን ውድድሮች በተከታታይ ያሸነፈችውን ፋጡማ የ'ቦስተኗ ንግሥት' የሚል ቅጽል ስም አግኝታበታለች። ለአትሌት አበበ ቢቂላ ትልቅ ፍቅር እንደላት የምትናገረው አትሌት ፋጡማ ሮባ ""አቤን በደንብ እወደዋለሁ፤ አደንቀዋለሁ። አቤን እኔ ብቻ ሳልሆን መላው ዓለም ያደንቀዋል"" ትላለች። ለዓመታት ከአገርና ከአትሌቲክሱ መድረክ ርቃ የቆችው የኦሊምፒኳ ኮከብ አትሌት ፋጡማ ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ ስለ ህይወቷ እንዲህ ብላለች። [የተጠቀሱት ዓመታት በሙሉ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ናቸው] ስለ አትሌቲክስ ምንም የማውቀው ነገር የለኝም በ1970 ዓ.ም በአርሲ ዞን ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ፣ ሁሉሌ ካራ በሚባል ስፍራ ተወለድኩ። ገጠር ውስጥ ከአርሶ አደር ቤተሰብ ነው የወጣሁት። ኑሮዬና ትምህርቴም እንደ ማንኛውም የገጠር ልጅ ነበር። በገጠር እንዳደጉት ልጆች ከብቶችን ስጠብቅና ቤተሰብን ስረዳ ስለቆየሁ ቶሎ ትምህርት ቤት አልገባሁም። ትምህርት ቤቱም ከቤተሰቤ ርቆ ስለሚገኝ በደንብ ካደግሁ በኋላ በደርሶ መልስ 14 ኪሎ ሜትር በእግር ተጉዤ እማር ነበር። ያደግኩበት ገጠር ቴሌቪዥንም ሆነ ሬዲዮ አልነበረም። ስለዚህ ስለአትሌቲከስ የማውቀው ነገር አልነበረም። ይሁን እንጂ በትምህርት ቤት ውስጥ እኣወዳደሩ ነጥብ ይይዙልን ነበር። አስተማሪያችን መሃረብ ይዞልን ""ማን ቀድሞ ይነካል"" እያለ ያወዳድረን ነበር። እኔ ከሴቶች ጋር ተወዳድሬ አሸንፋለሁ። ወንዶችንም ቢያመጡ አሸንፍ ነበር። ከዚያ በኋላ ከትምህርት ቤቴ ተመርጬ በወቅቱ አውራጃ ወደሚባለው፣ ከዚያ ደግሞ ክፍለ አገር ለሚባለው ተወክዬ መወዳደር ጀመርኩኝ። በዚሁ ነው እንግዲህ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ የተለያዩ የስፖርት ቡድኖች መኖራቸውን ያወቅኩት። ክፍለ አገርን ወክዬ በተወዳደርኩበት ጊዜ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ቡድን አይቶኝ ሃጂ ቡልቡላ የሚባለል ሰው ላከብኝ። እርሱም ቡድኑ እንደሚፈልገኝ፣ ትምህርቴንም እንድማር፣ ደሞዝም እንደሚከፍሉኝ ነገረኝ። እኔም ቤተሰቤን ሳማክር ብዙም ደስተኛ ስላልነበሩ ሊከለክሉኝ አሰቡ። ይሁን እንጂ ሃጂን ካዩ በኋላ ፈቀዱልኝ፤ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጣሁ። በ1994 እኤአ ቤልጂየም አገር ነበርኩኝ። እዚያም በአገር አጭር ውድድሮች ላይ በመሮጥ ተሳተፍኩኝ። ቤልጂየም በቆሁበት ወቅት አንድ ማራቶን የምትሮጥ ሴትን በፓሪስ ማራቶን ለምን ካንቺ ጋር አልሮጥም ብዬ ጠየቅኳት። እርሷም ነይ አብረን እንሂድ አለችኝ። ከዚያም በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1994 በተካሄደው የፓሪስ ማራቶን ሳልዘጋጅ ተወዳደርኩ። ውድድሩ ሲጀመር ከሌሎች አትሌቶች ጋር መሮጥ አቃተኝ። ጥለውኝ ሄዱ፤ ይሁን እንጂ ወደ 35ኛው ኪሎ ሜትር ላይ ደረስኩባቸው። ከእነርሱ ጋር ግን መቀጠል አልቻልኩም ጥለውኝ ሄዱ። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ውሃ ጠጣሁ። ውሃውም ሆዴን ወጥሮ ያዘኝ። ውድድሩንም ብጨርስም ሁለተኛ አልሮጥም ብዬ ነበር። ወደ አገር ቤት ስመለስ ግን ዶ/ር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ማራቶን እንድሮጥ ጠየቁኝ። ከዚያ በኋላ ስልጠና ወስጄ እንዴት ማራቶን እንደምሮጥ ተማርኩ። ወደ ሞሮኮ ሄጄም ማራካሽ ላይ ማራቶን ተወዳደርኩ። በ1996 የማራካሽ ማራቶን ላይ ብዙም ስልጠናና ልምምድ ሳላደርግ ነበር የተሳተፍኩት። በውድድሩም 'ቢ ካታጎሪ' የሚባለውን አምጥቼ ተመለስኩ። ከሁለት ወር በኋላ በሮም ማራቶን ተወዳድሬ፣ 'ኤ ካታጎሪ' የሚባለውን ውጤት አምጥቼ በኦሊምፒክ ውድድር ለመሳተፍ የሚያስችለኝን ነጥብ አገኘሁ። በዚሁ ልምምድ አድርጌ በ1996 በተካሄደው የአትላንታ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ሄድኩኝ። ኦሊምፒክ ትልቅ ውድድር ነው። የአትላንታ ኦሊምፒክ ለእኔ ከተሳተፍኩባቸው ሁሉ ትልቁ ውድድር ነበር። ለውድድሩ በበቂ ተዘጋጅቼ ነበር። ግን ፍርሃት በውስጤ ስለነበረ አሸንፋለሁ የሚል ግምት አልነበረኝም። ካሸነፍኩ በኋላ ግን ትልቅ ደስታ ነው የተሰማኝ። አሰልጣኞቼም በውድድሩ ታሸንፋለች ብለው አልጠበቁም ነበረ። በኦሊምፒክ ማራቶን ውድደድር ላይ በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሴት አፍሪካዊት መሆኔ በጣም አስደሰተኝ። የሚረሳም አይደለም። ከአትላንታ በኋላ በ1997፣ 98፣ 99 በቦስተን ማራቶን ውድድሮች በተከታትዬ ለሦስት ጊዜ አሸንፌያለሁ። በ2004 ነበር ሩጫ ያቆምኩት። በዚያ ጊዜ ለመውለድ ብዬ ነበር ሩጫ ያቆምኩት፤ ከዚያ በኋላ ግን አልተመለስኩበትም። አሁን የሁለት ልጆች እናት ነኝ። የመጀመሪያው ልጄ 15 ዓመት ሁለተኛዋ ደግሞ 13 ዓመቷ ናቸው። ሩጫ ካቆምኩ በኋላ ምንም እየሰራሁ አልነበረም። ልጆቼን እያሳደኩ ነበር። ይሁን እንጂ እነርሱ ካደጉልኝ በኋላ አንደንድ ሥራዎችን ለመስራት እያሰብኩ ነው። የአሁኑን አትሌትክስ ብዙም አልከታተልም። ይሁን እንጂ በተለያዩ ውድድሮች ላይ ስመለከት ጠንካራ አትሌቶች አሉ። እኛ ስንገባበት የነበረውንም ሰዓት እያሻሻሉ ነው። ከአሰልጣኞቻቸው ጋር ከተስማሙ እና በደንብ ከሰሩ ከዚህ የበለጠ ነጥብ ማምጣት እንደሚችሉ ተስፋ አደርጋለሁ።" https://www.bbc.com/amharic/news-56156447 +politics ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ሦስት የተቃዋሚ አባላትን በካቢኔያቸው ውስጥ አካተቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲሱ ካቢኔያቸው ውስጥ ሦስት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በሚኒስተርነት እንዲያገለግሉ ለሕዝብ ተወካዮች አቅርበው አስሹመዋል። በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ቀጀላ መርዳሳ በሚኒስትር ተሹመዋል። ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር፣ አቶ በለጠ ሞላ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፣ እንዲሁም አቶ ቀጀላ መርዳሳ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ ውስጥ ተካተዋል። ኢዜማ ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ የቀረበውን የአብረን እንሥራ ጥያቄ አሁን ኢትዮጵያ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ጥያቄውን ተቀብሎ አብሮ ለመሥራት በአብላጫ ድምጽ መወሰኑን ባሳለፍነው እሁድ አስታውቋል። ኢዜማ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ አራት መቀመጫዎች ያሉት ሲሆን አብን ደግሞ አምስት መቀመጫዎችን ለማሸነፍ ችሏል። በአቶ ዳውድ ኢብሳ በሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ውስጥ በተፈጠረ አለመግባባት ከግንባሩ ተለይቶ በመውጣት በአቶ አራርሳ ቢቂላ የሚመራው ግንባር በምርጫው ባይሳተፍም ምክትሩ በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ ተካተዋል። በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ባለፈው ሳምንት ሥራውን በጀመር ወቅት በከንቲባነት የተሾሙት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ 26 የካቢኔ አባሎቻቸውን አቅርበው ሲያስሾሙ ሁለቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን አመራሮችን አካተው ነበር። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅብራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲሾሙ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር የሱፍ ኢብራሂም ደግሞ የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን ሆነው ተሹመዋል። የኦሮሚያ ክልልም ከሳምንት በፊት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ አራርሳ ቢቂላን የቢሮ ኃላፊ አድርጎ የሾመ ሲሆን የአማር ክልልም ከተቃዋሚዎቹ አብንና ከአዴኃን ሁለት ሰዎችን በቢሮ ኃላፊነት ሹመት ሰጥተዋል። ከተፎካካሪ ፓርቲዎች በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕመድ እጩ የካቢኔ አባላቶቻቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው አስሾሙ። የጠቅላይ ሚንስትሩ የካቢኔ አባላት እና ኃላፊነቶቻቸው የሚከተሉት ናቸው። https://www.bbc.com/amharic/58814095 +business የዩክሬኑ ጦርነት ባለፉት 50 ዓመታት ያልታየ የዋጋ ንረት እንደሚያስከትል ተገለጸ "የዩክሬን ጦርነት ከአውሮፓውያኑ 1970ዎቹ ወዲህ በዓለማችን ታይቶ የማይታወቅ የሸቀጦች እጥረት ሊያስከትል እንደሚችል የዓለም ባንክ አሳስቧል። የዓለም ባንክ ባወጣው ትንበያ መሠረት የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በበርካታ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያስከተለ ሲሆን ከነዚህ መካከል በዋነኛነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ስንዴ እንዲሁም ጥጥ ይገኙበታል። ""የዋጋ ጭማሪው ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊና ሰብአዊ ጫናዎችን እያስከተለ ነው"" ብለዋል ሪፖርቱን ካዘጋጁት መካከል አንደኛው የሆኑት ፒተር ኔግል። አክለውም ""በመላው ዓለም የሚገኙ ቤተሰቦች ጫናውን በደንብ እያስተዋሉት ነው። እኛን በጣም የሚያሳስበን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ጉዳይ ነው። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ናቸው ምግብ ለማግኘት ከፍተኛ ጉልበትና ገንዘብ የሚያወጡት። የዋጋ ንረት ተከሰተ ማለት እነዚህን ቤተሰቦች ነው በቀጥታ የሚመለከተው"" ብለዋል። የኃይል አቅራቢ ድርጅቶች ዋጋ ከ50 በመቶ በላይ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህ ደግሞ ለድሃ ቤተሰቦችና አነስተኛ የንግድ ተቋማት መጥፎ ዜና ነው ይላል የዓለም ባንክ። ከፍተኛው የዋጋ ጭማሪ የሚኖረው አውሮፓ ውስጥ ሲሆን በዚህም ምናልባት ዋጋዎች ከሁለት እጥፍ በላይ ጨምረው ልንመለከት እንችላለን። የዋጋ ንረቱ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ዓመት እንዲሁም በ2024 ቅናሽ እንደሚያሳይ ተገምቷል። ነገር ግን ምንም እንኳን ቅናሽ ቢስተዋል ከዚህ በፊት ከነበሩት ዋጋዎች አንጻር እስከ 15 በመቶ የሚደርስ ጭማሪ ይኖረዋል ብሏል የዓለም ባንክ። የነዳጅ ዋጋም ቢሆን ጭማሪ እያሳየ እስከ 2024 ድረስ ሊቀጥል እንደሚችል የተገመተ ሲሆን ያልተጣራ ድፍድፍ በርሜል ነዳጅ በዚህ ዓመት እስከ 100 ዶላር ሊያወጣ ይችላል። ይህ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ የዋጋ ንረትን ያባብሰዋል። ሩሲያ ዓለማችን ከምትጠቀመው ነዳጅ 11 በመቶ የሚሆነውን ታቀርባለች። ነገር ግን ጦርነቱ ቢቆም እንኳን ጦርነቱን ተከትሎ በርካታ ያደጉ አገራት ሩሲያ ላይ ማዕቀብ መጣላቸውና ትልልቅ የአውሮፓና አሜሪካ ድርጅቶች ሩሲያን ጥለው መውጣታቸው ለወደፊቱ በርካታ መዘዞችን ይዘው ይመጣሉ። በሌላ በኩል አውሮፓውያን ከሚጠቀሙት ጋዝ 40 በመቶ የሚሆነው ከሩሲያ ሲሆን፣ የሚመጣው 27 በመቶ የነዳጅ ፍላጎታቸውም ቢሆን የሚሟላው በሩሲያ ነው። ይህ ደግሞ በተለይ በአውሮፓ የዋጋ ንረቱ ከዕለት ወደ ዕለት እንዲጨምርና እጥረት እንዲከሰትም እያደረገ ነው። የዓለም ባንክ እንደሚለው ከነዳጅና ጋዝ በተጨማሪ የምግቦች ዋጋም ቢሆን በእጅጉ ይጨምራል። የተባበሩት መንግሥታትም ቢሆን በ60 ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የምግቦች ዋጋ ንረት መከሰቱን አስታውቋል። የስንዴ ዋጋ የ42 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ገብስም ቢሆን የ33 በመቶ ጭማሪ ታይቶበታል። የዶሮ ምርቶች የ41̇.8 በመቶ ጭማሪ እንዲሁም ሌሎች ጥራጥሬዎች የ29.8 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ተስተውሎባቸዋል። እነዚህ ሁሉ ቁጥሮች የሚያሳዩት ደግሞ ሩሲያና ዩክሬን ምን ያህል ለዓለማችን ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ አገራት እንደሆኑ ነው። ከጦርነቱ በፊት ሁለቱ አገራት የዓለም ሕዝብ ከሚመገበው ስንዴ 28.9 በመቶ የሚሆነውን ያቀርቡ የነበረ ሲሆን፣ ዓለም ለማብሰል ይጠቀመው የነበረው የሱፍ ዘይትም ቢሆን 60 በመቶው የሚመጣው ከነዚሁ አገራት ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/61240082 +sports ዛየን አሊ ሰልማን፡ በአርሰናል የእግር ኳስ ቡድን የተመለመለው የአራት ዓመቱ ታዳጊ ዛየን አሊ ሰልማን የእንግሊዝ ትልቅ የእግር ኳስ ቡድንን ቀልብ ሲስብ ዕድሜው ገና አራት ነበር። ዛየን ያለው ችሎታ ከእድሜው በሁለት እጥፍ የላቀ ነው ሲሉ ይናገራሉ፤ አሰልጣኞቹ። የአርሰናል ቅድመ መደበኛ አካዳሚ እያሰለጠነው የሚገኘው ዛየን ገና ከአሁኑ ከሌሎች ስመ ገናና የእግር ኳስ ቡድኖች ጥሪ እየቀረበለት ይገናል። https://www.bbc.com/amharic/59047067 +sports ሴቶች ስታዲየም እንዲገቡ በቅርቡ የፈቀደችው ሳዑዲ የሴቶች ሊግን ልታስጀምር ነው ሴቶች ስታዲየም ገብትው ኳስ እንዳይመለከቱ ትከለክል የነበረችው ሳዑዲ አራቢያ የሴቶች የእግር ኳስ ሊግን ልታስጀምር ነው። በሊጉ የሚሳተፉ ቡድኖች በመዲናዋ ሪያድ እና በሌሎች ሁለት ከተሞች ውድድሮችን ያካሂዳሉ። አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን በሳዑዲ እያካሄዱ ካለው የለውጥ እርምጃ መካከል ይህ ውሳኔ ተጠቃሽ ነው። የሰብዓ መብት ተሟጋቾች ግን አሁንም በሳዑዲ የሴቶች መብት ላይ ገደብ ተጥሏል ይላሉ። ባለስልጣናት የሴቶች የእግር ኳስ ሊግን ማቋቋም ያስፈለገው ሴቶች በስፖርት ያላቸው ተሳትፎ ለማሳዳግ ነው ብለዋል። ሴቶች ስታዲየም ገብትው እግር ኳስ እንዲመለከቱ የተፈቀደላቸው የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ነበር። በተመሳሳይ ዓመት ሳዑዲ ሴቶች መኪና ማሽከርከር አይችሉም የሚለውን ክልከላዋን አስቁማለች። ባሳለፍነው ዓመት ደግሞ ሴቶች ያለ ወንድ ጥበቃ ከአገር ውጪ ጉዞ ማድረግ እንዲችሉ እንደተፈቀደላቸው ይታወሳል። ይህ ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን በርካታ የሴቶች መብት ተከራካሪዎች በሳዑዲ እስር ቤቶች ውስጥ እየማቀቁ ይገኛሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-51641657 +sports ተጠባቂውን የሊቨርፑል እና የማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ ማን በበላይነት ያጠናቅቃል? በዚህ ሳምንትስ ከሊቨርፑል እና ከማንቸስተር ሲቲ ማን ያሸንፋል? “ወደ ኤሚሬትስ ስታዲም ከማቅናታቸው በፊት ሊቨርፑሎች ወደ ቀድሞ ብቃታቸው ይመለሳሉ በሚል ግምቴን ስሰጣቸው ቆይቻለሁ” ይላል ሱቶን። “ግን አልተሳካም። በቻምፒዮንስ ሊግ ሬንጀርስን 7 ለ 1 ማሸነፍ ቢችሉም ከፊታቸውን ከባድ ጨዋታ አለ።” ሱቶን ይህንን ጨዋታ ጨምሮ የ11ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን ግምት አስቀምጧል። ብሬንትፎርድ ከ ብራይተን ውድድር ዓመቱን በድንቅ መንገድ የጀመሩት ብሬንትፎርዶች ከሰሞኑ ውጤት አልቀናቸውም። ባለፈው ሳምንት በኒውካስል ተደቁሰዋል። አዲስ አሰልጣኝ የሾሙት ብራይተኖች ደግሞ ምን ዓይነት ጉዞ እንደሚኖራቸው መገመት ከባድ ነው። ሁሌም ግን ጠንካራ ሆነው ስለሚቀርቡ ይህንን ጨዋታ ያሸንፋሉ ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 1 - 2 ሌስተር ከ ክሪስታል ፓላስ ሌስተሮች በሜዳቸው ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ባደረጉት ጨዋታ ድንቅ ሆነው ቢያመሹም ከብርንማውዝ ጋር ደግሞ ደካማ ነበሩ። ነገሮች የሚቀየሩ አይመስለኝም። የኋላ መስመራቸው ደካማ ሲሆን እነዊልፍሬድ ዛሃ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ፓላሶችም ሊድስ እስኪያሸንፉ ድረስ መንሸራተት ጀምረው ነበር። ሁለቱም ቡድኖች ነጥብ ተጋርተው ይወጣሉ ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 - 2 ቶተንሃም ከ ኤቨርተን ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በተለይም ጎል ካስቆጠሩ በኋላ ኤቨርተኖች ከሚገባቸው በታች ነበር የተንቀሳቀሱት። የቶፊዎቹ ተከላካይ መስመር መሻሻል ቢያሳይም አሁንም ክፍት መሆኑን ዩናይትድ አሳይቷል። ስፐርስን ማቆም ቀላል ቢሆንም ሃሪ ኬን እና ሶን ሄዩንግ-ሚን በጥሩ አቋም ላይ ይገኛሉ። ስለዚህ ቶተንሃም የሚሳካለት ሲሆን የጎሉ መጠን የሚወሰነው ግን የመጀመሪያወን ጎል በሚያስቆጥሩበት ደቂቃ ይሆናል። ግምት፡ 3 – 1 ፉልሃም ከ በርንዝማውዝ ፉልሃሞች ከዌስትሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ ነበሩ። አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ፍጹም ቅጣት ምት በመሰጠቱ ቢበሳጩም መናደድ ካለባቸው በተደጋጋሚ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ አልሰማ ብሎ ስህተት በሠራው አንድሪያስ ፔሬራ ላይ መሆን ነበረበት። ሁሌም በርንማውዝን ይሸነፋል እያልኩ ትክክል አለመገመቴን ያሳዩኛል። ደጋፊዎችም ይህን ይወዱታል። በጋሪ ኦኒዬል ስር ብርንማውዞች ጥሩ ቢሆኑም ሦስቱን ነጥብ ለፉልሃም አሰጠላሁ። ግምት፡ 2 – 1 ዎልቭስ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት ዎልቭሶች እስካሁን አሰልጣኝ ባይኖራቸውም በሚገባቸው መጠን መንቀሳቀስ ያልቻሉ ድንቅ ተጫዋቾችን ይዘዋል። በወራጅ ቀጠና ውስጥ ቢሆንም ብቃቱን ማሳየት እንዳልቻለ ቡድን ነው የምመለከተው። ኖቲንግሃም ፎረስትን ደግሞ ከዚህ በተለየ መልኩ የምመለከተው ሲሆን ባለፈው ሳምንት ከአስቶንቪላው ጨዋታ ነጥብ ማግኘታቸው ዕድለኛ ያደርጋቸዋል። የፎረስት ተጫዋቾች ያልተዋሃዱ ሲሆን  በራሳቸው ላይ ያለቸው እምነትም እየተሸረሸረ ይመስለኛል። ግምት፡ 2 – 0 አስቶን ቪላ ከ ቼልሲ የአስልጣኝ ስቴቨን ዤራርድ ጉዳይ በአስቶን ቪላ ደጋፊዎች ዘንድ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ያገኘ አይመስልም። ዋናው ምክንያት ደግሞ የሚመርጡት አጨዋወት ነው። ፒየር-ኤመሪክ ኦባሚያንግ ጎል እያስቆጠረ ሲሆን አሰልጣኝ ግርሃም ፖተርም የመላመድ ብቃታቸውን እያሳዩ ነው። ቪላ በሜዳው የማሸነፍ ጫና ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ተጫዋቾቹም ተጽዕኖው ያገኛቸዋል። ግምት፡0 – 2 ሊድስ ከ አርሴናል ሊድሶች ከፓላስ ጋር በነበራቸው ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ድንቅ ቢሆኑም አልዘለቁበትም። በዚህ ጨዋታም ሊድስ መጀመሪያ ላይ ተጭኖ ለመጫወት ቢሞክርም አይዘልቅበትም። ካላቸው ጥሩ እንቅስቃሴ እና ካለፈው ሳምንት ውጤት በኋላ አርሴናሎች ጨዋታውን በበላይነት እንደሚያጠናቅቁ እገምታለሁ። እንደምገምተው ሊድሶች አጥቅተው ለመጫወት ከሞከሩ ጋብርኤል ማርቲኔሊ እና ቡካዮ ሳካ የመጫወቻ ክፍተት ይገኛሉ። ለጋብርኤል ጂሰስም ዕድሎችን ይፈጥራል። ግምት፡ 1 – 3 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ኒውካስል ይህን ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ያሸንፋል ብዬ አልገምትም። ጥያቄው ኒውካስል አንድ ነጥብ ያገኛል ወይስ ሦስት ነጥብ የሚለው ነው። ማንቸስተር በኤሪክ ቴን ሃግ ስር እየተሻሻለ መሆኑን እቀበላለሁ። ከዚህ ይልቅ ኒውካስል በማጥቃት መጫወት በመጀመራቸው እና ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ዘጠኝ ጎሎችን ማስቆጠራቸው ነው። አሰልጣኝ ኤዲ ሃዊ በኦልትራፎርድ አጨዋወታቸውን ይቀይራሉ ብዬ አልገምትም። ይህ ደግሞ ቸዋታው ክፍት እንዲሆን ሲያደርግ ማንቸስተርንም ተጠቃሚ ያደርጋል። ግምት፡ 1 – 1 ሳውዝሃምፕተን ከ ዌስት ሃም ይህም ከባድ ጨዋታ ነው። ሳውዝሃምፕተንን በማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ መገምገም ከባድ ነው። አሰልጣኝ ራልፍ ላይ ያንዣበበው ጫና ባለመቀነሱ ከዚህ ጨዋታ ውጤት ይጠብቃሉ። ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ብዬ ብገምትም ነገሮች ወደ ዌስት ሃም ያደሉብኛል። ጂያንሉካ ስካማካን እወደዋለሁ። ዌስት ሃሞችም ወደ ድል መስመር ተመልሰዋል። ግምት፡ 1 – 2 ሊቨርፑል ከ ማንቸስተር ሲቲ ሊቨርፑልን ከዋንጫው ፉክክር ውጭ ማድረግ ከባድ ቢሆንም ሲቲ ወደ አንፊልድ አቅንቶ ማሸነፍ ከቻል ዕድል አይኖራቸውም። ሲቲዎች ይህንን ስለሚያውቁ ይጠቀሙበታል። ኤርሊንግ ሃላንድ በሳምንቱ አጋማሽ እረፍት በማግኘቱ ለዚህ ጨዋታ ዝግጁ ይሆናል። የሊቨርፑል አጨዋወት ለሃለንድ ስለሚመች ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ሊቨርፑሎች ዕድል መፍጠር ቢችሉም ማንቸስተር ሲቲ ባለው አቋም በላይ መሆኑ ግልጽ ነው። በ2021 የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን አራት ያስቆጠረ ሲሆን በዚህ ጨዋታም ተመሳሳይ ጎል እጠብቃለሁ። ግምት፡ 1 - 4 https://www.bbc.com/amharic/articles/c72d77v22xwo +business ትግራይ ውስጥ በረሃብ ሳቢያ ሰዎችና እንስሳት እየሞቱ ነው ተባለ "በጦርነት በተጎዳችው ትግራይ ክልል ሰዎች እና እንስሳት በረሃብ እና በመሠረታዊ የህክምና እንክብካቤ እጥረት እየሞቱ መሆኑን የክልሉ ግብርና ኃላፊ ገለጹ። ""በመንደሮች እና በከተሞች ውስጥ የምግብ እና የመድኃኒት እጥረት አለ። እናም በክልሉ ውሰጥ እየተከሰተ ያለው ቀውስ እኛ ከምናውቀው የበለጠ ሊሆን ይችላል"" ሲሉ ዶ/ር አትንኩት መዝገቦ ለቢቢሲ ትግርኛ ተናግረዋል። ህወሓትም ባወጣው መግለጫ ላይ የክልሉን አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኤጀንሲን ዋቢ አድርጎ በነሐሴ ወር 150 ሰዎች በረሃብ መሞታቸው ተመዝግቧል ብሏል። ረሃቡ የተከሰተው ማይ ቅኔጣል፣ ቆላ ተምቤን፣ ሃውዜን፣ በማዕከላዊ ዞን ታንኳ ምላሽ እንዲሁም ሽረ ውስጥ ባለ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ውስጥ እንደሆነም ተገልጿል። በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ በተቀሰቀው ጦርነት ሳቢያ ከባድ ሰብአዊ ቀውስ ተከስቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታንም አስመልክቶ ""በአስርት ዓመታት ውስጥ በዓለም ላይ አስከፊው የረሃብ ሁኔታ"" እንዲቀለበስ ከተፈለገ 5.2 ሚሊዮን ሰዎች የአስቸኳይ እርዳታ ሊቀርብላቸው እንደሚገባ አስታውቋል። ቀደም ሲልም 400 ሺህ የሚሆን ሕዝብ በረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸውን አስታውቋል። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በክልሉ የደረሱትን 152 የጭነት መኪኖችን ጨምሮ 500 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባታቸውን ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ የእርዳታ አቅርቦቱን ለማፋጠን የፍተሻ የደኅንነት ኬላዎች ቁጥርም መቀነሱ ተነግሯል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከነሐሴ 16 ጀምሮ አንድም እርዳታ የጫነ መኪና ወደ ትግራይ አልደረሰም ሲል ቅሬታ ያቀረበ ሲሆን በየቀኑም በ100 መኪኖች የተጫነ የእርዳታ አቅርቦት ለክልሉ ያስፈልጋሉ ብሏል። የግብርና ኃላፊው በተጨማሪ ምን አሉ? የግብርና ኃላፊው ዶ/ር አትንኩት መዝገቦ እንደሚናገሩት በምግብ ዕርዳታ ዕጥረት ምክንያት ረሃብ በመላው ክልሉ እየተስፋፋ ነው። ""ከዚህ ቀደም ነዋሪዎች የነበረቻቸውን ይቋደሱ ነበር ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የሚበሉት የላቸውም"" ብለዋል። ለዚህም ደግሞ ነዳጅ አቅርቦት አለመኖሩ እንዲሁም የባንክ አገልግሎትና መብራት መቋረጥ ችግሩን በዋነኝነት እንዳባባሰው ያስረዳሉ። በዚህም የምግብ እጥረት ዋነኞቹ ተጠቂዎችና ከፍተኛ ድርሻውን የያዙት ሴቶችና ህፃናት መሆናቸውንም ይናገራሉ። በትግራይ ክልል በተጣለው መገናኛ አገልግሎት እገዳ ምክንያት እየተፈጠረ ያለውን የቀውስ መጠን በዝርዝር መረዳት አዳጋች ቢሆንም ""ግለሰቦች በረሃብ ምክንያት ሲሞቱ በአይናችን እያየን ነው"" ብለዋል። ""በምግብ እና በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ሰዎች እየሞቱ እና የህመም እባጭ ምልክቶችን እያሳዩ ነው"" በማለትም ያስረዳሉ። የግብርና ቢሮ ኃላፊው እንደሚናገሩት በክልሉ ውስጥ እየተከሰተ ያለውን ቀውስ ለመግታት የምግብ ዕርዳታ እንደሚጠብቁ አስረድተዋል። ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት ያለው የዝናብ ጥሩ ቢሆንም አርሶ ለማምረት ከሦስት እስከ አራት ወራት ይወስዳል እንዲሁም በአንዳንድ አካባቢዎች የአንበጣ ወረራ መገኘቱንም እንደ ስጋት አንስተዋል። በተለይም የአንበጣ ወረራውን ለመግታት በሚደረገው ትግል የመገናኛ ዘዴዎች መዘጋታቸው አሳሳቢ አድርጎታል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ እንስሳቱ ክትባት ባለማግኘታቸው በተለያዩ በሽታዎች እየሞቱ እንደሆነም አስረድተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የእርዳታ ቁሳቁስ የጫኑ 100 የጭነት መኪናዎች ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቀለ መግባታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትናንትናው ዕለት አስታውቋል። 3500 ቶን ይመዝናሉ የተባሉት የጭነት መኪናዎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ሕይወት አድን ቁሶችን ጭነው ነው ወደ ክልሉ የገቡት። ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ መንግሥት ለትግራይ የእርዳታ አቅርቦቶችን በጠበቀ መንገድ ዘግቷል ሲል ከሷል። በዚህም ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለአደጋ እየተጋለጡ መሆኑን አስጠንቅቋል። የፌደራሉ መንግሥት በበኩሉ ወደ ክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ እንዳይገባ እክል የሆኑት የህወሓት አማጺያን ናቸው ይላል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58472069 +sports ለዓለም ዋንጫ ዝግጅት በርካታ የውጭ አገር ሠራተኞች የሞቱባት ኳታር የሠራተኞች አያያዝ በጉጉት የሚጠበቀው የዓለም ዋንጫ ውድድሮች እሁድ ኅዳር 11/2015 ዓ.ም. ይጀመራል። ከተለያየ የዓለማችን ክፍሎች የሚተሙ የእግር ኳስ ደጋፊዎችም በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ ስደተኛ ሠራተኞች አማካኝነት በተገነቡ ስታዲየሞች ጨዋታዎችን ይመለከታሉ። በሠራተኞች ላይ ሞትን ጨምሮ በርካታ የመብት ጥሰቶች ደርሰዋል በሚልም ኳታር ተደራራቢ ውግዘቶችን እያስተናገደች ትገኛለች። ኳታር ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ውድድር ሰባት ስታዲየሞችን እንዲሁም አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ፣ በርካታ መንገዶችን የሚያገናኝ መስመር እና 100 ያህል አዳዲስ ሆቴሎችን ገንብታለች። የፍጻሜዎቹን ጨዋታ በሚያስተናግደው ስታዲየም ዙሪያ አንድ ሙሉ ከተማ ተገንብቷ። የኳታር መንግሥት ስታዲየሞቹን ለመገንባት ብቻ 30 ሺህ የውጭ አገር ሠራተኞች መቀጠራቸውን አስታውቋል። አብዛኛዎቹ ከባንግላዴሽ፣ ከሕንድ፣ ከኔፓል እና ከፊሊፒንስ የመጡ ናቸው። በኳታር ስንት የውጭ አገር ሠራተኞች ሞተዋል? ኳታር የዓለም ዋንጫ አዘጋጅነት ካሸነፈች በኋላ ከሕንድ፣ ከፓኪስታን፣ ከኔፓል፣ ከባንግላዲሽ እና ከስሪላንካ የመጡ 6 ሺህ 500 ስደተኛ ሠራተኞች መሞታቸውን ዘጋርዲያን በዘገባው አስነብቧል። ይህ አሃዝ በኳታር የሚገኙ የየአገራቱ ኤምባሲዎች ያወጡትን መረጃ የተመሠረት ያደረገ ነው። ይሁን እንጂ የኳታር መንግሥት የሞቱት ግለሰቦች በሙሉ ከዓለም ዋንጫ ጋር በተያያዙ ፕሮጄክቶች ላይ የሚሰሩ ስላልሆኑ መረጃው የተሳሳተ ነው ብሏል። ከሟቾቹ መካከል ብዙዎቹ በኳታር ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ሲሰሩ እንደቆዩ እና በእርጅና ወይም በሌሎች የተፈጥሮ ምክንያቶች ሊሞቱ እንደሚችሉ ተናግሯል። ከ2014 እስከ 2020 ባለው ወቅት ውስጥ በዓለም ዋንጫ ስታዲየሞች ግንባታ ላይ የነበሩ 37 የጉልበት ሠራተኞች መሞታቸውን የገለጸው የኳታር መንግሥት፣ ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ሞቶች ብቻ “ከሥራ ጋር የተገናኙ” መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ ብሏል። ይሁን እንጂ ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት በዚህ አይስማማም፣ በማለት በመንግሥት የቀረበው አሃዝ በጣም ዝቅተኛ ግምት ነው ይላል። ኳታር በሥራ ላይ እያሉ በልብ ድካም እና በተንፈስ ችግር የሚሞቱትን ከሥራ ጋር በተገናኘ አድርጎ አድርጋ አትቆጥርም። ሆኖም እነዚህ የህመም ምልክቶች ከፍተኛ በሆነ ሙቀት እና በከባድ የጉልበት ሥራ ምክንያት በሙቀት ወላፈን ሲመቱ የሚመጣ ነው። ተቋሙ ከዓለም ዋንጫ ጋር የተያያዙ አደጋዎችን በተመለከተ በኳታር ውስጥ በመንግሥት ከሚተዳደሩ ሆስፒታሎች እና የአምቡላንስ አገልግሎቶች የተሰበሰቡ መረጃዎች ላይ በመመስረት የራሱን አሃዝ አዘጋጅቷል። በአውሮፓውያኑ 2021 ብቻ 50 የውጭ አገር ሠራተኞች መሞታቸውን እና ከ500 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት፣ 37 ሺህ 600 ደግሞ ቀላል እና መካከለኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል። ቢቢሲ አረብኛም የኳታር መንግሥት የውጭ አገር ሠራተኞችን ሞት አሃዝ መቀነሱን የሚጠቁሙ መረጃዎችን ሰብስቧል። በአውሮፓውያኑ 2010  ኳታር ዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት ውድድሩን ካሸነፈች በኋላ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በውጭ አገር ሠራተኞች አያያዟ ላይ ከፍተኛ ወቀሳ አሰምተዋል። በአውሮፓውያኑ 2016 ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኳታር ኩባንያዎችን የግዳጅ የጉልበት ሥራን ይጠቀማሉ ሲል ከሷል። በርካታ ሠራተኞች በማያፈናፍንና በተጨናነቀ መጠለያ ውስጥ እንደሚኖሩ፣ ከፍተኛ የቅጥር ክፍያ እንዲከፍሉ መደረጋቸውን፣ ደመወዝ እንደተከለከሉ እና ፓስፖርታቸውም እንደተቀማ አስታውቋል። ከአውሮፓውያኑ 2017 ጀምሮ መንግሥት የውጭ አገር ሠራተኞችን በጣም በሞቃታማ የአየር ሁኔታ ውስጥ እንዳይሰሩ ለመከላከል፣  የሥራ ሰዓታቸውን ለመቀነስ እና በሠራተኞች ካምፖች ውስጥ ያለውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል አንዳንድ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አሳውቆ ነበር። ሆኖም ባለፈው ዓመት ሌላኛው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን ሂውማን ራይትስ ዎች የውጭ አገር ሠራተኞች አሁንም “በቅጣት እና ሕገወጥ በሆነ የደመወዝ ቅነሳ” እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጿል። ለረጅም ሰዓታት አድካሚና የሚያንገላታ ሥራ ሰርተው ለወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸውም አስታውቋል። የኳታር ኩባንያዎች ከባርነት አይተናነስም በሚባልለት ካፋላ በተሰኘው የዓረብ አገራት ሕግን ተከትለው ይሰሩ ነበር። በዚህም አሰራር መሰረት ሠራተኞች ስፖንሰር ቢደረጉም ሥራቸውን መልቀቅ አይችሉም፤ ፖስፖርታቸውንም ይነጠቃሉ። እንደ ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (አይኤልኦ) ባሉ ተቋማት ጫና ምከንያት የኳታር መንግሥት ካፋላን ቢያስቀርም፤ ነገር ግን አምነስቲ አሁንም ኩባንያዎች የጉልበት ሠራተኞች ቀጣሪዎች እንዳይቀይሩ ጫና ያደርጋሉ ብሏል። በሠራተኛ ሕጉ ላይ ያለው ማሻሻያ የዓለም ዋንጫ ካለቀ በኋላም መቆም እንደሌለበት አስጠንቅቋል። ከዓለም አቀፉ ሠራተኞች ተቋም ጋር በመተባበር የኳታር መንግሥት በርካታ ማሻሻያዎችን አድርጓል። ከእነዚህም መካከል አሠሪዎች ለሠራተኞቻቸው በወቅቱ ክፍያ እንዲከፍሉ ለማድረግ የተነደፈ የደመወዝ ጥበቃ ዘዴን ያጠቃልላል። የኳታር መንግሥት ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ማሻሻያው በኳታር የሚገ��� አብዛኞቹን የውጭ አገር ሠራተኞችን የሥራ ሁኔታ የለወጠ ነው። “ማሻሻያዎቹ ተግባራዊ መሆናቸውንም ለማረጋገጥ እርምጃዎች ተወስደዋል” ብለዋል ቃል አቀባዩ ። “እነዚህ እርምጃዎች በቀጠሉ ቁጥር ሕግን የሚጥሱ ኩባንያዎች ቁጥር ማሽቆልቆሉን ይቀጥላል” ሲሉም አስረድተዋል። ይህ ጉዳይ እስከ ፍጻሜዎቹ ጨዋታዎች ድረስ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚችል አመላካች ነው። ዓለም አቀፉን እግር ኳስ የሚመራው ፊፋ ለዓለም ዋንጫ ተሳታፊ 32 ቡድኖች “ትኩረት ሰጥተው በእግር ኳስ ላይ እንዲያተኩሩ” የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፏል። ስፖርቱን ወደ ርዕዮተ ዓለም ወይም ፖለቲካዊ “ጦርነት” መወሰድ ወይም “የሞራል ትምህርቶችን ለመስጠት መጠቀሚያ” መሆን የለበትም ብሏል። ለፊፋ ደብዳቤም በምላሹ አሥር የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበራት “ሰብአዊ መብቶች ሁሉን አቀፍ እና በሁሉም ቦታ የሚተገበሩ ናቸው” ብለዋል። የአውስትራሊያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ኳታር በስደተኛ ሠራተኞች ላይ በደል እየፈፀመች ነው በሚል ነቅፎ ቪዲዮ አውጥቷል። የዴንማርክ ተጫዋቾች የኳታርን የሰብአዊ መብት አያያዝ ለመቃወም ሙሉ ለሙሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cj594vzzzj5o +sports ሊቨርፑል ከሪያል ማድሪድ በነበረው ጨዋታ የተፈጠሩ ክስተቶች እንዲመረመሩ ጠየቀ "ሊቨርፑል ከሪያል ማድሪድ ጋር ያደረጉትን የቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታን እንዲዘገይ ያደረገውና ደጋፊዎች ያጋጠሟቸው ""ተቀባይነት የሌላቸው ጉዳዮች"" ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ። የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበራት ኅብረት የደህንንት ምክንያቶችን ጠቅሶ ጨዋታውን እንዲዘገይ ያደረገው ሲሆን በዚህም ጨዋታው ከ30 ደቂቃ በላይ መዘግየት አጋጥሞታል። በፈረንሳይዋ መዲና ፓሪስ ስታድ ዴ ፍራንስ ስታዲየም የተደረገው የቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ እስከ ምሽቱ አራት ተኩል ድረስ ያልተጀመረ ሲሆን በዚህ ጨዋታም ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑልን 1 ለ0 ረትቷል። ጥቂት ደጋፊዎችም በግንብ አጥሮች ላይ ለመውጣት ሲሞክሩ ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ ተኩሰዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ደጋፊዎች በተጨናነቁ ሰልፎች ወደ ስታዲየሙ ለመግባት ሲሞክሩ የሚያሳዩ ምስሎችም መውጣት ጀምረዋል። በርካቶች ጨዋታው ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት ወደ ስታዲየሙ እንደደረሱ ቢናገሩም ወደ ስታዲየሙ ግቢ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ተናግረዋል። ""የሊቨርፑል ደጋፊዎች ወደ ስታድ ዴ ፍራንስ ስታዲየም ለመግባት ሲሞክሩ ባጋጠሟቸው ጉዳዮች እንዲሁም የጸጥታው ብልሽት በደጋፊዎቻችን ላይ የፈጠረው እክል በጣም አሳዝኖናል"" ሲል የአንፊልድ ክለብ መግለጫ አውጥቷል። ""ይህ በአውሮፓ እግር ኳስ ታላቅ ውድድር ነው እና ደጋፊዎች ዛሬ ማምሻውን ያየናቸው ትዕይንቶች ሊያጋጥማቸው አይገባም። የእነዚህ ተቀባይነት የሌላቸው ጉዳዮች መንስኤዎች ላይ መደበኛ ምርመራ እንዲደረግ በይፋ ጠይቀናል"" ብሏል። የአውሮፓ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ዩኤፋ በበኩሉ ""በእነዚህ በተፈጠሩት ክስተቶች ለተጎዱት እናዝናለን። የተፈጠሩትንም ጉዳዮች ከፈረንሳይ ፖሊስ እና ባለስልጣናት እንዲሁም ከፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ እንመረምራለን"" ብሏል። ሆኖም ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት በሊቨርፑል ደጋፊዎች መግቢያ በኩል ሃሰተኛ ትኬቶችን የያዙ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ለማለፍ ሲሞክሩ ቲኬቱ ባለመስራቱ መታገዳቸውንም ገልጿል። በዚህም ወደ ስታዲየሙ ለመግባት የሚሞክሩ በርካታ ደጋፊዎች ላይ መጨናነቅ መፍጠሩንና እውነተኛ ቲኬት የያዙ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየሙ እንዲገቡ ለማድረግ በነበረውም ሙከራ ጨዋታው በ35 ደቂቃ መዘግየቱን አስታውቋል። ጨዋታው ከተጀመረም በኋላ ከስታዲየም ውጭ የነበሩ ደ���ፊዎች ቁጥር መበራከቱ የቀጠለ ሲሆን ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ከስታዲየሙ እንዲርቁም አድርገዋቸዋል ብሏል። የፈረንሳይ ፖሊስ በበኩሉ ሃሰተኛ ትኬቶችን የያዙ ደጋፊዎች በግድ ወደ ስታዲየሙ ለመግባት እንደሞከሩና ""ፖሊስ በሰጠው ፈጣን ምላሽ ሁኔታው እንደተረጋጋ"" ገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61612597 +politics በሶማሊያ ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ማን ናቸው? "የመሪነት ሥልጣንን ሲጨብጡ የመጀመሪያቸው አይደለም። እአአ ከ2012 እስከ 2017 የሶማሊያ ስምንተኛው ፕሬዝዳንት ነበሩ። በ2017 በድጋሚ ሲወዳደሩ ግን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ረቷቸው። በቀውስ በምትናጠው የአፍሪካ ቀንድ አገር ሶማሊያ በድጋሚ በመመረጥ ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ታሪክ ሠርተዋል። የትላንቱ ምርጫ በአገሪቷ ታሪክ ፉክክር የበዛበት ነበር። የምርጫ ሂደቱ በሦስት ዙር ተካሂዷል። አዲሱ ፕሬዝዳንት በትምህርት ዘርፍ ይታወቃሉ። የምረጡኝ ቅስቀሳቸው ማጠንጠኛ ሶማሊያን ከተቀረው ዓለም ማስታረቅና የሕዝቡን አንድነት ማረጋገጥ ነው። በበዓለ ሲመታቸው የተናገሩትም ይህን ሕልማቸውን ነው። ""ከቀጠናውና ከዓለም አቀፍ አካላት ጋር በቅርበት እንደምንሠራ ቃል እገባለሁ"" ብለዋል። ከድምጻቸው እርቅ ይስተጋባል። ለእያንዳንዱ የሶማሊያ ዜጋ እንደሚሠሩም ተናግረዋል። በሦስተኛው የድምጽ መስጫ ደረጃ በ214 አብላጫ ድምጽ፣ 110 ድምጽ ያገኙትን ፋርማጆ አሸንፈዋል። 2017 ላይ ያሸነፏቸው ፋርማጆን በ2022 መልሰው አሸንፈዋቸዋል። ያለፉትን ሁለት ዓመታት ያሳለፉት በሞቃዲሾ የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ነው። ፋርማጆ ሥልጣናቸውን ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለማራዘም ሲሞክሩ ከተቃወሙ መካከል ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ አንዱ ናቸው። አምና የፀጥታ ኃይል አባላት ቤታቸውን ከፈተሹ በኋላ መነጋገሪያ ሆነዋል። ፍተሻው የተካሄደው ተቃዋሚዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ በወጠኑበት ወቅት ነበር። ሶማሊያ ለ30 ዓመታት በእርስ በእርስ ጦርነት ስትናጥ አገሪቱን ጥለው ካልሄዱ ጥቂት መሪዎች መካከልም አንዱ ናቸው። ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ከፍተኛ ድርቅን ጨምሮ በበርካታ ችግሮች የተሸበበች አገር ነው ከፋርማጆ የሚረከቡት። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው፣ ድርቁ ካልተገታ ወደ ረሃብ ከፍ ሊል ይችላል። ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሩሃብ አፋፍ ላይ ሆነው አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ይጠብቃሉ። ሶማሊያን የኑሮ ውድነትና የዩክሬን ጦርነት ያባባሰው የዋጋ ግሽበትም ይፈትናታል። በፌደራል መንግሥቱና በክልሎች መካከል እየሰፋ ያለው ልዩነትም ሌላው የሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ የቤት ሥራ ይሆናል። ሙስና ሌላው የሶማሊያ ማነቆ ነው። ተንታኞች እንደሚሉት አዲሱ ፕሬዝዳንት አገራቸው ከኬንያ፣ ጂቡቲ እና ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር ያላትን ግንኙነት የማደስ ኃላፊነትም ተጥሎባቸዋል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት የሶማሊያ እና ኬንያን ግንኙነት ቆርጠዋል። አገራቱ በባሕር ወሰንም ይወዛገባሉ። ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ 2012 ላይ ሲመረጡ አገራቸው ከምዕራባውያን እና ከአፍሪካ አገራት ጋር መደበኛ የዲፕሎማሲ ትስስተሯን እንድታድስ አስችለዋል። በሌላ በኩል በአስተዳደራቸው ስር ያለውን ሙስና ማስወገድ አልቻሉም ተብለው ይታማሉ። የተወለዱት እአአ በ1955 ሂራን ግዛት ነው። በሞቃዲሾ በመካከለኛው መደብ ሰፈር አድገው ከሶማሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርስቲ በምህንድስና በ1981 ተመርቀዋል። በቅርብ የሚያውቋቸው ዝምተኛና የማይታበዩ ሰው ናቸው ይሏቸዋል። ሁለተኛ ዲግሪ ከመሥራታቸው በፊት በሕንድ ቦሆፓል ዩኒቨርስቲ አስተማሪ ነበሩ። ወደ ሶማሊያ ሲመለሱ በተባበሩት መንግሥታት የተዘረጋውን የመምህራን ሥልጠና ለመምራት በትምህርት ሚኒስቴር ተቀጠሩ። በ1991 ማዕከላዊው መንግሥት ሲንኮታኮት፣ በዩኒሴፍ የትምህር ኃላፊ ሆነው ተቀጠሩ። በደቡብና ማዕከላዊ ሶማሊያ ይዘዋወሩ ነበር። ወቅቱ በትምህርት ዘርፍ ያለውን ውድቀት በቅርበት ያስተዋሉበት ነበር። ከሦስት ዓመታት በኋላ፣ በሞቃዲሾ ጦርነቱ ከተነሳ ወዲህ ግንባር ቀደም ከሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አንዱን ከፈቱ። የሙስሊም ወንድማማችነት (Muslim Brotherhood) የሶማሊያ ቅርንጫፍ የሆነው አል-ኢላህ ጋር ግንኙነት አላቸው። የጎሳ ግጭት በተነሳበት ወቅት ለማኅበረሰቡ የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ቡድኑ በግብፅና ሱዳን ጋር በተመሳሳይ በሆነ የእስልምና አስተምህሮት የሚተዳደር ትምህርት ቤቶች ከፍቷል። እንደ አል-ሸባብ እና አል-ቃይዳ ያሉ አክራሪዎችንም ያወግዛል። ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ""ለዘብተኛ ሙስሊም"" ተብለው ይታወቃሉ። በጦርነት የደቀቀችውን ሶማሊያ ለመደገፍ በንግድ ሰዎች የተቋቋመው 'ዩኒየን ኦፍ ኢስላሚክ ኮርትስ' ከተባለው ፍርድ ቤት ጋርም ትስስር አላቸው። ፍርድ ቤቱ በ2006 ለአገሪቱ አንጻራዊ ሰላም አምጥቷል። አል-ሸባብ በፍርድ ቤቱ ያለው ጫና እየጨመረ መሄድ ያሰጋት ኢትዮጵያ ፍርድ ቤቱን የሚቀለብስ እርምጃ መውሰዷ ይታወሳል። የአዲሱ ፕሬዝዳንት ደጋፊዎች እንደሚሉት፣ ሰላምና መረጋጋትን ለመመለስ የሚሠሩ መሪ ናቸው። በ1990ዎቹ የሲቪል ማኅበራት ውስጥ ከፍተኛ ንቅናቄ ያደርጉ ነበር። የጎሳ ግጭትን በማርገብም ይታወቃሉ። ሞቃዲሾን ለሁለት ሰንጥቆ በሁለት ተፎካካሪ ጎሳዎች እንድትመራ ያደረጋት ""ግሪን ላየን"" የተባለውን አካሄድ ለማፍረስ በተደረገው ድርድር ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ይህ አካሄድ ""የሞቃዲሾ ካንሰር"" ተብሎ ይጠራ ነበር። ለነዋሪዎችና ለፖለቲከኞችም ሕይወትን ፈታኝ አድርጓ ቆይቷል። በሽግግር አስተዳደር ወቅት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካሪ ነበሩ። በ2001 ከግጭት በኋላ እርቅ ለማውረድ የሚጥረው የ'ሴንተር ፎር ሪሰርች ኤንድ ዳያሎግ' አጥኚ ሆነው ተቀጥረዋል። ይህ ማዕከል ከምዕራቡ ዓለም ጋር ባለው ቅርርብ ይተቻል። ሆኖም ጥናቶቻቸው ሶማሊያን ከ30 ዓመታት የእርስ በእርስ ጦርነት ለማውጣት ያግዛሉ ተብሎ ይታመናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61468546 +health በአውስትራሊያ በአፍንጫ የሚወሰድ የኮቪድ-19 መከላከያ ላይ ሙከራ እየተደረገ ነው "የደም መርጋት ሲያጋጥም ጥቅም ላይ የሚውለው መድኃኒት (blood thinner) ኮሮናቫይረስን ለመከላከል እንዲውል የአውስትራሊያ አጥኚዎች ምርምር እያደረጉበት ይገኛሉ። ሙከራ የተደረገበት መድኃኒት በአፍንጫ የሚሳብ (nasal spray) ነው። አጥኚዎቹ እንዳሉት፤ መድኃኒቱ የኮሮናቫይረስ የፕሮቲን መጠን እንዳይጨምር በማድረግ የበሽታውን ስርጭት ይከላከላል ተብሎ ይታመናል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በአፍንጫቸው መድኃኒቱን ሲወስዱ በሽታውን ማስተላለፍ ማቆማቸውን ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል። ሙከራው እአአ በ2022 አጋማሽ ነው የሚጠናቀቀው። ውጤታማ ከሆነ ለክትባት አጋዥ ይሆናል። ይህ ዘዴ በቫይረሱ የተያዘን ሰው ለማከም እንዲሁም በአፍንጫ ከተወሰደ በኋላ ቫይረሱን ለመከላከለም እንደሚውል ተጠቁሟል። የምርምሩ መሪ ፕ/ር ዶን ካምቤል ""መድኃኒቱ ሰው በሚበዛበት አካባቢ ለሚሆኑ ሰዎች ይረዳል"" ብለዋል። ሰዎች ወደ መደብር ወይም ሌላ ቦታ ከመሄዳቸው በፊት መድኃኒቱን አፍንጫቸው ላይ ነፍተው ከቤታቸው መውጣት እንደሚችሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። በሌሎች አገሮችም በአፍንጫ የሚወሰዱ መድኃኒቶች ላይ ምርምር እየተደረገ ሲሆን፤ የአውስትራሊያውን ልዩ የሚያደርገው ኸፕሪን ከተባለው የደም መርጋት መድኃኒት መሠራቱ ነው። ኸፕሪን በአፍንጫ ሲወሰድ ወደ ደም ሳይገባ አፍንጫ ላይ ይቆያል። ስለዚህም ቫይረሱ ወደ ሰውነት እንዳይገባ ይከላከላል። ሙከራው ከመንግሥት 3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ተደርጎለት በ400 ኮሮናቫይረስ የያዛቸው ሰዎች ያሉባቸው ቤቶች ይተገበራል ተብሎ ይጠበቃል። እያንዳንዱ ሰው በቀን ሦስት ጊዜ መድኃኒቱን በአፍንጫው ይስባል። ሙከራ በሚደረግባቸው ቤቶች መድኃኒቱ የቫይረሱን ስርጭት መግታት አለመግታቱ ይፈተሻል። በሙከራው ከሚሳተፉት መካከል ሜልበርን ዩኒቨርስቲ፣ ሞናሽ ዩኒቨርስቲ፣ ሜልበርነስ ኖርዘን ኸልዝ፣ ፒተር ዶርቲ ኢንስትቲትዩት፣ መርዶክ ችልድረንስ ሪሰርች እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ይገኙበታል። የምርምሩ ተሳታፊ ፕሮፌሰር ሚቼል መክቶስ እንዳሉት፤ ኸፕሪን ለታካሚዎች እንዲሰጥ ፈቃድ ተሰጥቶት በስፋት ገበያ ላይ የሚገኝ መድኃኒት መሆኑ ጥናቱን ያፋጥነዋል። ፕሮፌሰር ዶን በበኩላቸው በአፍንጫ የሚወሰደውን መድኃኒት ላለፉት 20 ወራት እንደተጠቀሙትና ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንዳላስከተለባቸው ገልጸዋል። ጨምረውም ""መድኃኒቱ ውጤታማ ይሆናል ብለን እናምናለን"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59770888 +sports የአውስትራሊያ ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች በስፖርቱ ውስጥ ጾታዊ ጥቃት መኖሩን ተናገሩ "የቀድሞዋ የአውስትራሊያ ሴት የእግር ኳስ ተጫዋች ሊሳ ዴ ቫና በስፖርቱ ውስጥ ስላለው የጾታዊ ጥቃት ባህል ለአንድ ጋዜጣ የሰጠችው ቃለ ምልልስ አነጋጋሪ ሆኗል። የ36 ዓመቷ የቀድሞ የማቲልዳስ የእግር ኳስ ቡድን አጥቂ በይፋ መናገሯን ተከትሎም ሌሎች የሃገሪቱ ሴት ተጫዋቾች ተመሳሳይ ሃሳቦችን ማንጸባረቅ ጀምረዋል። የአውስትራሊያ የእግር ኳስ ባለስልጣን እንዲህ ያሉ ቅሬታዎች ቀርበውለት እንደማያውቁ በመግለጽ እነዚህን ክሶች ተከትሎ ግን ሊሳን ጨምሮ ሌሎች ተጫዋቾች የሚያሰሙትን አቤቱታ ተቀብሎ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ለመመስረት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። ""በእግር ኳስ ጨዋታ ከሚሳተፉ ሰዎች የሚጠበቁ ስነምግባሮችን ለሚጥስ ማንኛውም ዓይነት ተግባርም ሆነ ጾታዊ ጥቃት ምንም አይነት ትዕግስት የለንም"" ሲል ባለስልጣኑ ተናግሯል። ሊሳ ባለፈው ወር ጫማዋን እስከምትሰቅል ድረስ ለሃገሯ 150 ጊዜ ተሰልፋ ተጫውታለች። ለማቲልዳስ በምትጫወትበት ወቅት በአንድ የቡድን አጋሯ ወሲባዊ ጥቃት እንደተፈጸመባት በአውስትራሊያ ለሚታተመው ሲድኒ ቴሌግራፍ ተናግራለች። ""ወሲባዊ ጥቃት ደርሶብኝ ነበር ወይ? አዎ። የማሸማቀቅ ድርጊቶች ተፈጽመውብኝ ነበር ወይ? አዎ። ተገልያለሁ? አዎ። ምቾት የሚነሱ ነገሮችን ተመልክቼ ነበር ወይ? አዎ"" ስትል ተናግራለች። በየትኛውም ስፖርታዊ ጨዋታዎች ውስጥ ያሉ ስነምግባር የጎደላቸው ተግባራት በሙሉ እንደሚረብሿትም አክላለች። ሊሳን የሚደግፉ ምስክርነቶች በቀድሞ የቡድን አጋሯ ኤሊሲያ ካርናቫስ እና በቀድሞ ማናጀሯ ሮዝ ጋሮፋኖ መሰጠታቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። ራሄል ዶብሶን የተሰኘች የቀድሞ የቡድን አጋሯም መጀመሪያ ቡድኑን ስትቀላቀል ጥቃት ለመፈጸም የታሰቡ ግንኙነቶች ውስጥ ማለፏን ተናግራለች። ""ይህ አሁንም በከፍተኛዎቹ ሰዎች ደረጃም የቀጠለ ነገር ነው። ይህንን ለመግታት አንዳች ነገር ካልተደረገ ምንም የሚቀየር ነገር የለም"" ስትል ለጋዜጣው ተናግራለች። የአሜሪካ ሴት የእግር ኳስ ተጫዋቾች ተመሳሳይ መልዕክቶችን ካስተላለፉ በኋላ ነው የአውስትራሊያ ተጫዋቾችም ጥቃቶቹን ማጋለጥ የጀመሩት። ይህ በጂምናስቲክ ብሎም በዋና ስፖርት ውስጥ ያሉ ሴት ስፖርተኞችም በተለያየ ወቅት ይፋ እያወጡት ያለ ክስተት ሆኗል።" https://www.bbc.com/amharic/58814088 +business ኮሮና ቫይረስ፡ የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አገራት ኢኮኖሚያዊ ድቀት እንደሚያጋጥማቸው ተ��በየ የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ከግማሽ ምዕተዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 ምክንያት የኢኮኖሚ ድቀት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ተነበየ። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በዚህ ዓመት ብቻ በ2.1 በመቶ የሚጎዳ ሲሆን ይህ ጉዳት እስከ 5.1 ድረስ ሊደርስ ይችላል ብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በ52 የአፍሪካ አገሮች የተከሰተ ሲሆን እስካሁን ድረስ በመላ አህጉሪቱ 10,250 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችም ቁጥርም 492 ደርሷል። የዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ አበዳሪ አገራት ለአፍሪካ እዳቸውን ለተወሰነ ጊዜ እንዲያራዝሙ እና አገራት ያላቸው ገንዘብ ወደ ሕይወት ማዳንና ኑሮን ማሻሻል ላይ ማዋል እንዲችሉ ጥሪ አቅርበዋል። አፍሪካ በኮቪድ-19 ከተጠቁ አህጉራት የመጨረሻዋ ስትሆን፣ አገራት ድንበራቸውን መዝጋት፣ ዜጎቻቸው ከቤት ውጪ እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ፣ መንገደኞችን በለይቶ ማቆያ ማስቀመጥ ርምጃዎችን የወሰዱት በፍጥነት ነበር። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የመጀመሪያው ጉዳት ንግድን ማስተጓጎል ነበር። የዓለም ባንክ እንደሚለው ከሆነ የግብርና ምርቶች አቅርቦት መቀነስ፣ የአቅርቦት መስተጓጎል፣ እና የሕይወት መጥፋት ወደ ምግብ እጥረት ሊመራ ይችላል። በአፍሪካ በምጣኔ ሃብታቸው ግዙፍ የሆኑት ናይጄሪያና አንጎላ በወረርሽኙ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መውረድ ምጣኔ ሃብታቸው ክፉኛ ከተጎዳ አገራት መካከል ይገኙበታል። ደቡብ አፍሪካም ብትሆን የማዕድን ገቢዋ አሽቆልቁሏል። • በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው ከኢትዮጵያና ኬንያ የሚላኩ የግብርና ምርቶች ሁሉም ተዘግተዋል። ከባህርማዶ ወደ አገር ውስጥ ይደረግ የነበረው የጎብኚዎች ፍሰት፣ የሚላክ የውጪ ምንዛሪ፣ እንዲሁም የቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ቆሟል። በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ፣ የእርስ በእርስ ግጭት፣ እንዲሁም በደቡባዊ አፍሪካ ያለው ድርቅ በአፍሪካ ያለውን ችግር ተደራራቢ አድርጎታል። የዓለም ባንክ ብድር መክፈል ለተወሰነ ጊዜ እንዲቆም የሚል ምክረ ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን፣ ይህም በዓመት ለብድር ክፍያ የሚውለውን ወደ 35 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም ለወለድ ክፍያ የሚውለውን 44 ቢሊየን ዶላር ነፃ ያደርጋል ተብሏል። ድርጅቱ አክሎም የአፍሪካ አገራት ለድሃ ዜጎቻቸው ምግብ እንዲያከፋፍሉ፣ መሰረታዊ ግልጋሎቶች ላይ የተጣሉ ክፍያዎችን እንዲያነሱ መክሯል። https://www.bbc.com/amharic/news-52230764 +health ኦሚክሮን፡ በፍጥነት በሚዛመተው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ? "እንሆ ሁለት ትላልቅ ጥያቄዎች፡ ኦሚክሮን በምን ያህል ፍጥነት ሊዛመት ይችላል? በኦሚክሮን ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ? እኒህን ሁለት ጥያቄዎች መልስ አገኘንላቸው ማለት ኦሚክሮን የተሰኘው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምን ያህል አደገኛ ነው የሚለውን መለስን ማለት ነው። የምድራችን ሳይንቲስቶች እኒህን ጥያቄዎች ለመመለስ ደፋ ቀና እያሉ ነው። ትንሽ ፍንጭ የሚሰጥ ነገር ያገኙም ይመስላል። የመከላከል አቅም በጣም አስፈላጊ ነው። ኦሚክሮን ሁሉን ነገር ወደኋላ መልሶ እንደአዲስ እንድንድህ ሊያደርገን ነው ባይባልም አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ምን ያህል አስጊ ነው የሚለውን መመልስ ጥቂት ሳምንታትን ሊጠይቅ ይችላል። ኦሚክሮን በምን ያህል ፍጥነት እየተዛመተ ይሆን? መልሱ ""በፍጥነት"" የሚል ነው። ይህ ዝርያ በክትባትም ይሁን በርካታ ሰዎች በመያዛቸው ምክንያት የተሻለ የመከላከል አቅም አዳብረዋል በሚባሉ ሥፍራዎችም በፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል። ለምሳሌ ደቡብ አፍሪ�� ከአንድ ወር በፊት ዴልታ ከተሰኘው የኮቪድ ዝርያ ጋር ተላምዳ በቀን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 300 ወርዶ ነበር። አሁን ግን አራተኛው የኮቪድ ማዕበል ከ10 ሺህ በላይ ሰዎችን አዳርሷል። ዩናይትድ ኪንግደምም ብትሆንም ኦሚክሮን እንደሰደድ እሣት እየተዛመተባት ይገኛል። ሳይንቲስቶች የኦሚክሮንን ዱካ እያገኙ ያሉት ዝርያው የኮቪድ ምርመራ በሚደረግበት ወቅት ትቶ በሚያልፋቸው አሻራዎች አማካይነት ነው። ይህ አሻራ ኤስ-ጂን ይሰኛል። ይህ ከኮቪድ ምርምራ ላይ የሚገኝ ቅንጣት ባለፈው ወር መጨረሻ ወደ 0.1 በመቶ ወርዶ ነበር። አሁን ግን ወደ 5 በመቶ አድጓል። ይህ በቁጥር ሲገለጥ በቀን 2500 ሰዎች በአዲሱ ዝርያ ይያዛሉ ማለት ነው። ይህ ስሌት ሙሉ በሙሉ ትክክል ነው ማለት ባይቻልም በአራተኛው የኮቪድ ማዕበል የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ የማይታበይ ሐቅ ነው። ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም የኦሚክሮን ቁጥር በየሦስት ቀኑ እጥፍ እየሆነ እንደሚሄድ መረጃዎች ጠቋሚ ናቸው። ኦሚክሮን የሚዛመትበት ፍጥነት ዴልታ ከተሰኘው ዝርያ በላይ ሲሆን ኮሮናቫይረስ ባለፈው ዓመት መባቻ ሲጀምር ሲስፋፋ የነበረውን ዓይነት ፍጥነት እንዳለው ተደርሶበታል። በዚህ ፍጥነቱ መዛመቱን ከቀጠለ በቀን 2500 የነበረው ቁጥር ከአንድ ወር በኋላ በቀን 100 ሺህ ይሆናል ማለት ነው። እኔን ይይዘኝ ይሆን? በሽታው ምን ያህል ከባድ ነው? ሳይንቲስቶች እስካሁን ድረስ ባደረጉት ጥናት ጭንቀት ውስጥ የከተተታቸው የኦሚክሮን ዝርያ የኮቨድ ክትባትን የመቋቋም አቅሙ ነው። ኦሚክሮን አሠራሩ ክትባቱ እንዲከላከል ከተሠራለት የመጀመሪያው የኮቪድ ዝርያ ለየት ያለ ነው። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የኮቪድ ክትባት ሁለት ጊዜ የወሰዱ ሰዎች አዲሱን ዝርያ የመከላከል አቅማቸው ከ20 እስከ 40 እጥፍ ሊቀንስ ይችላል። እርግጥ ነው እስካሁን በአዲሱ ዝርያ ዙሪያ አጠንጥነው የተሠሩ ጥናቶች ቁጥር ትንሽ ነው። ነገር ግን እኒህ ጥናቶች የአዲሱን ዝርያ የመዛመት ኃይል የሚያሳዩ ናቸው። ቢሆንም ስለ አዲሱ ዝርያ መልካም ዜናም አልጠፋም። ፋይዘር-ባዮንቴክ የሠራው ሙከራ እንደሚያመለክተው ማጠናከሪያ ክትባት [ሦስተኛ ክትባት] የወሰዱ ሰዎች ኦሚክሮንን የመከላከል አቅማቸው ከፍ ይላል። ለኦሚክሮን ሦስት ዙር መከተብ ማለት ለዋናውና የቀደመው ቫይረስ ሁለት ዙር እንደመከተብ ማለት ነው። የኤደንብራ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ኤሌኖር ራይሊ ይህን ሙከራ ""አበረታች"" ሲሉ ይገልፁትና ""ማጠናከሪያው ክትባት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚያሳይ ነው"" ይላሉ። ኦሚክሮን ምን ያህል ከባድ የኮሮናቫይረስ ዝርያ እንደሆነ ግን እስካሁን የምናውቀው ጥቂት ነው። በዝርያው ተይዘው ሆስፒታል የገቡ ሰዎች ጥናት እስኪደርግባቸው ድረስ ስለበሽታው ኃያልነት ያለው እውቀት እፍኝ አይሞላም። እርስዎ ሁለት ጊዜ ክትባት ወሰዱ ማለት አሊያም ከዚህ በፊት ኮቪድ ይዞዎት ነበር ማለት ኦሚክሮንን የመከላከል አቅምዎ የተሻለ ነው ይላሉ ሳይንቲስቶች። እና ወደፊት ምን ሊሆን ይችላል? ኮሮናቫይረስን እንዲከላከሉ ተብለው የተዘጋጁት ክትባቶች ኦሚክሮንን ሊከላከሉ እንደሚችሉ ግምት አለ። ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ጤና ብንሆን እንኳ ሁላችንም ደህና ላንሆን እንችላለን። አንዳንድ ሰዎች የመከላከል አቅማቸው እጅግ የደከመ ነው። አንዳንዶች ቢከተቡም ላይከላከሉ ይችላሉ። አንዳንዶች ክትባት መውሰድ አይችሉ ይሆናል። አንዳንዶች ደግሞ በውዴታ ክትባት አንወስድም እያሉ ነው። በዴልታ ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ሆስፒታል እስከመግባት ደርሰዋል። አዲሱ ዝርያ ብዙ ሰዎች በአንድ ጊዜ ወደ ሆስፒታል እንዲገቡ ካደረገ ችግር ሊፈጠር ይችላል። የዋርዊክ ዩኒቨርሲቲው ፕሮ��ሰር ማይክል ቲልደስሊ ""ማዕበል ትልቅ ከሆነ ባለፈው ጥር እንደተመለከትነው ዓይነት ሊሆን ይችላል። ሆስፒታሎችም ሊጨናነቁ ይችላሉ"" ባይ ናቸው። ነገር ግን አሁን ያለን መረጃ ጥቂት ስለሆነ ይህ ነው ብሎ መናገር እንደሚከብድ ያስረዳሉ። የዓለም ሳይንቲስቶች የተስማሙበት ይህ ነው የሚባል ኦሚክሮን እየተዛመተበት ያለ ፍጥነት የለም። በሽታው ምን ያህል ከባድ ሊሆን እንደሚችልም በውል አይታወቅም። ክትባቱን ሊፈታተነው ይችላል ወይ የሚለውም ምላሽ አላገኘም። ማድረግ የሚቻለው ራስን ከበሽታው እየጠበቁ በቀጣይ ሳምንታት የሚሆነውን በቅርበት መከታተል ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-59596054 +politics የሚየንማር ዜጎች ሥራ አቁመው ተቃውሞውን ተቀላቀሉ "በሚየንማር በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተወገዱት አን ሳን ሱ ቺ እንዲለቀቁ የሚጠይቀው አገራዊ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። ሠራተኞችም የሥራ ማቆም አድማ በመምታት ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመዲናዋ ፒ ታው በሚገኙት ያንጎን እና ማንዳሊ አደባባዮች ተቃውሞ እያካሄዱ ነው። ሚየንማር እንደዚህ ያለ ተቃውሞ ካየች ከአስር ዓመት በላይ ይሆኗታል። ወታደራዊ ሃይሉ የሚየንማርን መሪ በመፈንቅለ መንግሥት አስወግዶ ለአንድ ዓመት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል። መሪዋ፣ ፕሬዘዳንት ዊን ሚንት እንዲሁም ሌሎችም የገዢው ፓርቲ ኤንኤልዲ አባላት የቁም እስር ላይ ይገኛሉ። ""አንሠራም"" በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በኔይ ፒ ታው የተቃውሞ ሰልፍ እያካሄዱ ነው። በሌሎች ከተሞችም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል። መምህራን፣ ጠበቃዎች፣ የባንክ ሠራተኞችና የመንግሥት ተቀጣሪዎች ከተቃዋሚዎቹ መካከል ይገኙበታል። በሺዎች የሚቆጠሩ መምህራን ያንጎን ከተባለ ከተማ ሱሌ ፓጎንዳ ወደተባለው ማዕከላዊ ሚየንማር አቅንተዋል። ሠራተኞች የተቃውሞው አካል እንዲሆኑ ሥራ እንዲያቆሙም በበይነ መረብ ንቅናቄ እየተደረገ ነው። የ28 ዓመቱ የፋብሪካ ሠራተኛ ሂኒን ታዚን ""ዛሬ የሥራ ቀን ነው። እኛ ግን አንሠራም። ደሞዛችን ቢቆረጥም አንሠራም"" ሲል ለኤኤፍፒ ተናግሯል። በኔይ ፒይ ታው ፓሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን ውሃ እንደተጠቀመና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እንዳሉም ተዘግቧል። ተቃዋሚዎች እርስ በእርስ ሲረዳዱና አይናቸውን ሲያሹ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ያሳያል። በየጎዳናው መፈክር ይዘው ድምጻቸውን የሚያሰሙ ተቃዋሚዎችም ታይተዋል። የሚየንማሩ ኤንኤልዲ ፓርቲ ብሔራዊ ምርጫ አሸንፏል መባሉን ተከትሎ መከላከለያው መፈንቅለ መንግሥት አካሂዷል። ወታደራዊ ሀይሉ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ተቃዋሚዎችን ደግፏል። ሆኖም ግን የአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ምርጫው ስለመጭበርበሩ ምንም ማስረጃ የለም ብሏል። መከላከያው የገንዘብ፣ የጤና፣ የአገር ውስጥ እና የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮችን አንስቶ ሌሎች ባለሥልጣኖች ሾሟል። ፌስቡክ፣ ትዊተር እና ኢንስታግራም የመሳሰሉትን ወታደራዊ ሀይሉ አግዷል። ከቅዳሜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ተቃውሞ እየተካሄደ ይገኛል። ሚየንማር ውስጥ እንዲህ ያለ ተቃውሞ የተካሄደው እአአ በ2007 ነበር። በያኔው የሻፍሮን አብዮት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወታደራዊ አገዛዙን ለመቃወም አደባባይ ወጥተው ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/55976538 +health በአፍሪካ በሕይወት መቆያ ዕድሜ በ10 ዓመት ጨመረ በአፍሪካ በሕይወት የመቆያ ዕድሜ በ10 ዓመት መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ። አፍሪካ ውስጥ ሰዎች በሕይወት ይቆዩበት የነበረው አማካይ ዕድሜ ከዚህ ቀደም 46 የነበረ ሲሆን፣ አሁን ወደ 56 ከፍ ብሏል። ሰዎች ዘለግ ያሉ ዓመታት መኖር የጀመሩት የተሻለ የሕክምና አቅርቦት በመዘርጋቱ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ነገር ግን የዕድሜ ልኬቱ ከተቀረው ዓለም ጋር ሲነጻጸር አሁንም ከአማካዩ ያነሰ እንደሆነ አክሏል። ሰዎች በሕይወት የሚቆዩበት ዕድሜ የሚሰላው ዕድሜያቸውን፣ ጾታቸውን እና የሚኖሩበትን አገር ከግምት በማስገባት ነው። የዓለም ጤና ድርጅት አሁን ያወጣው መረጃ ላይ ለመድረስ እአአ ከ2000 እስከ 2019 ከ47 የአፍሪካ አገራት የሰበሰበውን መረጃ ገምግሟል። “በሌሎች አካባቢዎች ካለው መሻሻል የአፍሪካ ይበልጣል። ግን ኮሮናቫይረስ ያሳደረው ተጽዕኖ ለውጡን ሊቀለብስ ይችላል” ብሏል የዓለም ጤና ድርጅት። የተባበሩት መንግሥታት፣ የዓለም ጤና ድርጅትም መረጃ ጠቅሶ በድረ ገጹ እንዳሰፈረው፣ በአፍሪካ ለታየው በሕይወት መቆያ ዕድሜ መሻሻል የጤና ሚኒስትሮች ምስጋና ይገባቸዋል። እአአ በ2000 የሕክምና ሽፋን 24 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2019 ወደ 46 በመቶ አድጓል። በአፍሪካ በሕይወት መቆያ ዕድሜ ከጨመረባቸው ምክንያቶች አንዱ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት መሻሻሉ ነው። እንደ ኤችአይቪ፣ ቲቢ እና ወባ ያሉ በሽታዎችን ለመቆጣጠር ከ2005 ወዲህ ከፍተኛ ጥረት እየተደረ መሆኑ ይጠቀሳል። ተመድ እንደሚለው፣ ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት አበረታች ቢሆንም በተቃራኒው እንደ ስኳርና ደም ግፊት ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በቁጥር እየጨመሩ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ማትሺዲሶ ሞይቲ “ሰዎች ጤናማ ሆነው ለረዥም ዓመታት እየኖሩ ነው። በሽታን ለመከላከልም አበረታች ጥረት ተጀምሯል። ነገር ግን የታየው ለውጥ መገታት የለበትም። አገራት እንደ ካንሰር ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመቅረፍ ጥረት ካላደረጉ የታየው ለውጥ ይከስማል” ብለዋል። ኮሮናቫይስ በሕክምና መስጫ ተቋማት ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ በሕይወት መቆያ ዕድሜ ላይ ጫና ሊያሳድር እንደሚችል አያይዘው አንስተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የዳሰሳ ጥናት ሲሠራ ምላሽ ከሰጡ 36 የአፍሪካ አገራት መካል ወደ 90 በመቶው የሕክምና አገልግሎት መስተጓጎል እንደገጠማቸው ተናግረዋል። መንግሥታት ለዜጎች ጤና ጥበቃ የሚመድቡት በጀት ከፍ ማለት እንዳለበት የዓለም ጤና ድርጅት መክሯል። በአብዛኛው የአፍሪካ አገራት ከብሔራዊ የጤና በጀት 50 በመተo ብቻ ነው የሚያቀርቡት። ይህም ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ፈጥሯል። ከግማሽ በላይ በጀት የሚመድቡ አገራት አልጄሪያ፣ ቦትስዋና፣ ኬፕ ቨርዴ፣ ኢስዋቲኒ፣ ጋቦን፣ ሲሸልስ እና ደቡብ አፍሪካ ናቸው። ዜጎች ከኪሳቸው ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው ለሕክምና መክፈል እንደሌለባቸው የጠቀሰው የዓለም ጤና ድርጅት፣ የመንግሥት በጀት የግድ መሻሻል እንዳለበት ምክረ ሐሳቡን አስቀምጧል። ከደመወዛቸው ከ10 በመቶ በላዩን ለሕክምና የሚያውሉ ሰዎች አስጊ ደረጃ የደረሱ ይባላሉ። ባለፉት 20 ዓመታት በ15 የአፍሪካ አገራት ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ የራሳቸውን የሕክምና ወጪ ሲሸፍኑ ተስተውሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cml9zd8vngmo +health ኮሮናቫይረስ፡ ሙሉ ሕዝቧን እየከተበች ያለችው እስራኤል በክትባቱ ፍቱንነት ጥርጣሬ የገባት ለምንድነው? "ሕዝቧን በብዙ ቁጥር እየከተበች ያለችው እስራኤል የክትባቱን ፈዋሽነት የሚጠራጠሩ ዜጎቿ አሳስበዋታል። ተራ ዜጎች ብቻም ሳይሆኑ የጤና ባለሙያዎቿም ስለ ክትባቱ ፈዋሽነት መጠነኛ ጥርጣሬ የገባቸው ይመስላል። እስራኤል የኮቪድ ክትባትን በብዛት በመግዛት አገሯ አከማችታለች። በርካታ ሕዝቧን ክትባቱን ለመክተብ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ትገኛለች። ዝጅግት ላይ ብቻም ሳይሆን ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧን ክትባት እንዲደርሰው አድርጋለች። የእስራኤል ግብ ሙሉ በሙሉ ሕዝቧን መ���ተብና ተህዋሲውን ታሪክ ማድረግ ነው። እንዲያው አንዳንዶች ይቺ አገር እስራኤል ሕዝቧን ""የቤተሙከራ አይጥ"" ልታደርገው ነው ወይ? እስከማለት ደርሰዋል። ይህን ስታደርግ ታዲያ ብዙ የጤና አዋቂ ሳይንቲስቶች ዐይናቸውን በዚያች አገር ላይ ጥለዋል። ለምን? ዋናው ምክንያት በእስራኤል የሚታየው የክትባት ውጤት ለተቀረው ዓለም ብዙ ተስፋ ስለሚኖረው ነው። ሳይንቲስቶች እስራኤል ላይ ዓይናቸውን የጣሉበት አንዱ ምክንያትም ይኸው ነው። አንድ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ክትባት ሲከተብ በዚያች አገር ተህዋሲው ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አጓጉቷቸዋል። ይህንን የክትባቱን ዘመቻ እያስተባበሩ ከሚገኙት ዋናው ሰው የፋይዘር ክትባት እንደተባለው ፍቱን ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም በሚል ጥርጣሬ እንደገባቸው በይፋ ተናግረዋል። ይህን እንዲሉ ያደረጋቸው ታዲያ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የፋይዘር ክትባትን ከወሰዱ በኋላም ተህዋሲው ስለተገኘባቸው ነው። ጥርጣሬው መፈጠር የጀመረውም አንድም በዚህ የተነሳ ነው። ሌሎች ሳይንቲስቶች ግን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ጊዜው ገና ነው ይላሉ። እኚህ በክትባቱ ላይ ጥርጣሬን ያነሱት ፕሮፌሰር ናችማን አሽ በጤና ጥበቃ ሚኒስትር ጥርጣሪያቸው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። ""የፕሮፌሰሩ አስተያየት ከአውድ ውጭ የተነገረና ትክክል ያልሆነ ነው"" ብሏል የእስራኤል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ። ""በጽኑ የሚታመሙ ዜጎቻችን ቁጥር መቀነስ አለበት ብለዋል ፕሮፌሰሩ፣ ገና 2ኛው ዙር ብልቃጥ በመሰጠት ላይ ያለው አሁን ስለሆነ ይህ ውጤቱ በቀጣይነት የሚታይ እንጂ አሁን ምንም ማለት የሚቻልበት ደረጃ ላይ አይደለንም"" ብሏል ይኸው መግለጫው። እርግጥ ነው ክትባቱ የራሱ ባህሪ አለው። አንድ ሰው ክትባት ከወሰደ በኋላ ሰውነቱ የተህዋሲውን ጄኔቲክ አውቆ ወራሪ ኃይል እንደመጣ ተገንዝቦ ለዚህ የሚሆን መከላከያ ለማዘጋጀት ጊዜ ይፈልጋል። አንቲቦዲና ቲ'ሴል አምርቶ ተህዋሲውን ለመጋፈጥ ጊዜ ይፈልጋል። ይህ እስኪሆን የተከተበ ሰውም ቢሆን ሊታመም ይችላል። ቢመረመር ተህዋሲው ሊገኝበት ይችላል። ይህ ሂደት ታዲያ እስከ 2 ሳምንት ሊወስድ እንደሚችል ፕሮፌሰር ዳኔ አልትማን፣ የኢምፔሪያል ኮሌጅ ለንደን ኢሚኑሎጂስት ይናገራሉ። ክላት በእስራኤል ትልቁ የጤና ሽፋን ሰጪ ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት ከተከተቡ 200 ሺህ፣ እድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑት ውስጥ በዚሁ እድሜ ላይ ያሉ ክትባቱን ግን ካልወሰዱ ሰዎች ጋር በማወዳደር በሰራው ጥናት በሁለት ሳምንት ውስጥ የተከተቡትም ያልተከተቡትም ላይ ተመጣጣኝ ቁጥር ያለው ሰው በተህዋሲው መያዙን ይፋ አድርጓል። ይህ ነው በፋይዘር ክትባት ላይ ጥርጣሬ እንዲነግስ ምክንያት የሆነው። ከዚያ በኋላ ቆይቶ ግን የተከተቡት ካልተከተቡት በ33 ከመቶ ባነሰ በተህዋሲው መያዛቸው እየተስተዋለ መምጣቱ ተነግሯል። ""ይህ ገና ጅምር ላይ ያለ የጥናት ውጤት ነው፤ በዚህ ደረጃ ራሱ በ33 በመቶ የተህዋሲው መዛመት ቀንሷል። ስለዚህ የሚያሳስብ ነገር የለም"" ብለዋል የክላት ድርጅት የጤና መኮንን ራን ባሊቸር። በፋይዘር የክሊኒክ የሙከራ ጊዜም ቢሆን ተመሳሳይ ነገር ታይቷል። ክትባቱን በወሰዱና ባልወሰዱት መሀል በተደረገ ጥናት ግልጽ ልዩነት ለማየትና የመዛመት ፍጥነት ሲቀንስ ለመታዘብ 100 ቀናት ያስፈልጋሉ ነው የሚለው መድኃኒት አምራቹ ፋይዘር። እስራኤል ዜጎቿን መከተብ የጀመረችው በታህሣሥ 19 ነበር። አሁን የሕዝቧን 10 ከመቶ ከከተበች 2 ሳምንት አልፏታል። ዛሬ ላይ ደግሞ ከ9 ሚሊዮን ሕዝቧ ውስጥ ግማሽ ሚሊዮኑ ክትባት ደርሶታል። ነገር ግን በአገሪቱ ውስጥ በተህዋሲው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነ�� በጉልህ አልታየም። ለምን? ክትባት የወሰደ ሰው የመከላከል አቅም ለማዳበር ከሚወስድበት ጊዜ አንጻር ቢያንስ ለአንድ ወራት ያህል ክትባቱ ያመጣውን ለውጥ ለማወቅ ከባድ ይሆናል ተብሏል። ፕሮፌሰር ባሊቸር ግን በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ወደ ጽኑ ሕሙማን የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣት አለበት ይላሉ። ፋይዘር መድኃኒት አምራች ሁለት ጠብታ ክትባቱን የወሰደ ሰው 95% በተህዋሲው ያለመያዝ እድሉ የሰፋ ነው ይላል። ነገር ግን በብዙ ክትባቶች እንደታየው ከዚህ ያነሰ መቶኛ እንኳ የፈውስ እድል ብዙ ለውጥ ያመጣል። አመታዊው የፍሉ ክትባት ለምሳሌ ፈዋሽነቱ ከ40-60% ብቻ ነው። ሆኖም በየዓመቱ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን ከሞት ይታደጋል። አንዱ አሁን እያነጋገረ ያለው አንድ ጠብታ የወሰዱ ዜጎችን ሁለተኛውን ጠብታ እየሰጡ ቀስ በቀስ ሕዝቡን ማዳረስ ነው ወይስ አንዱን ጠብታ ለሰፊው ሕዝብ ካዳረሱ በኋላ ለ2ኛው ዙር እንደገና መጀመር ይሻላል የሚለው ነው። ታላቋ ብሪታኒያ እንዳመነችው ብዙ ሰዎችን የመጀመርያውን ጠብታ ካዳረሱ በኋላ ለ2ኛው መመለስ ይሻላል የሚል ነው። በዚህ ዘዴ በተህዋሲው የሚጋለጡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ይቻላል ብላ አምናለች። ትንሽ ቁጥር ያለውን ሕዝብ 2 ጠብታ ሰጥቶ ትንሽ ቁጥር ያለውን ሕዝብ ከተህዋሲው በደንብ መከላከል የተሻለ ነው የሚሉም አሉ። ጠብታው መሰጠት ያለበት በ2 ሳምንት ልዩነት መሆኑም ሌላው ፈተና ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው አንድ ጠብታ ከወሰደ በኋላ ሌላ ሁለት ሳምንት መጠበቅ ተህዋሲው ከጋረጠው ፈተና አንጻር ትእግስትን የሚፈታተን በመሆኑ ነው። ፕሮፌሰር ኢቫንስ ማጠቃለያ ሐሳብ ሲሰጡ ይህን ይላሉ፡ ""ከእስራኤል አሁን የሚመጡ ሪፖርቶች ያልተሟሉ ብቻ ሳይሆን መረጃን የሚሰጡ፥ እንዲሁም አጥጋቢ ሆነው አላገኘናቸውም። በታላቋ ብሪታኒያ ሁለተኛውን ጠብታ አዘግይቶ የመጀመርያውን ጠብታ ማዳረስ የሚለውን አሰራር ሊያስቀይር የሚችል ነገርም አላገኘንባቸውም"" ዞሮ ዞሮ በቀጣይ ወራት በእስራኤል ተህዋሲው ድራሹ እየጠፋ ካልመጣ ዓለም መደንገጡ አይቀርም።" https://www.bbc.com/amharic/news-55745103 +health የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት በኮቪድ ተያዙ የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት አንድሬ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር ኮቪድ ተመርምረው ተህዋሲው እንደተገኘባቸው ይፋ አደረጉ። የ67 ዓመቱ ፕሬዝዳንት በትዊተር ሰሌዳቸው እንደጻፉት አሁን የበሽታውን ቀላል ምልክቶችን ማሳየት ጀምረዋል። የፕሬዝዳንቱ በተህዋሲው የመያዝ ዜና የመጣው ሜክሲኮ በወረርሽኝ እየታመሰች ባለችበት ወቅት ነው። ሜክሲኮ እስከዛሬ ከ150ሺህ ባላይ ዜጎቿን በተህዋሲው አጥታለች። ሎፔዝ ኦብራዶር አገሪቱን ከቤቴ ሆኜ መምራቴን እቀጥላለሁ ብለዋል። ሩሲያ ሰራሹን ክትባት ለማግኘትም ከፑቲን ጋር እነጋገራለሁ ብለዋል። ትናንት ሁለቱ መሪዎች ዛሬ ሰኞ በስልክ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ዙርያ ይነጋገራሉ የሚሉ ዘገባዎች ወጥተው ነበር። ዋናው አጀንዳ የሚሆነውም ሰፑትኒክ የተሰኘውን ሩሲያ ሰራሽ ክትባት ሜክሲኮ የምታገኝበትን ዘዴ መቀየስ ነው። ባለፈው ዓመት ፕሬዝደንት ሎፔዝ ሩሲያ ሰራሹን የኮቪድ ክትባት ፈዋሽነቱ እንደተረጋገጠ 12 ሚሊዮን ጠብታ ወደ አገሬ አስገባለሁ ብለው ተናግረው ነበር። ሜክሲኮ ሩሲያ ሰራሹን ክትባት ፈዋሽነት ለጊዜው አላረጋገጠችም። ሆኖም ግን 128 ሚሊዮን ለሚሆነው ሕዝቧ ክትባቱን ለማዳረስ የፋይዘር ባዮንቴክ መዘግየት ታክሎበት ወደ ሩሲያ ለማማተር ተገዳለች። አሁን ለሩሲያው ስፑትኪን ክትባት አውቅና የሰጡ ዋና ዋና አገራት ብራዚል፣ አርጀንቲናና ሀንጋሪ ናቸው። ጆስ ሉዊስ አሎሚያ ዛጋራ የተባለ አንድ የጤና ረዳት የፕሬዝዳንቱን ጤንነት ከገመገመ በኋላ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፤ የሚያሳስብ ነገር የለም ብሏል። የጤና ባለሙያዎች ቡድን ለፕሬዝዳንቱ የቅርብ ክትትል እያደረጉላቸው ይገኛሉ። ሜክሲኮ በተህዋሲው የተያዙባት ዜጎች ቁጥር ወደ 2 ሚሊዮን እየተጠጋ ይገኛል። በ150ሺ ሟቾች ቁጥርም ግማሽ ሚሊዮን እየተጠጋ ያለ ሕዝብ ከሞተባት አሜሪካ፣ እንዲሁም ከብራዚልና ሕንድ ቀጥሎ ከዓለም በ4ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። https://www.bbc.com/amharic/55792459 +health በፈረንሳይ የፌስቡክ ተጽእኖ ፈጣሪዎች የኮቪድ-19 ክትባትን እንዲያጥላሉ ገንዘብ ቀረበላቸው በፈረንሳይ ማንነቱ ያልታወቀ አንድ አካል በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን እያደነ የኮቪድ-19 ክትባትን ካጥላላችሁልኝ ከፍተኛ ገንዘብ እሰጣችኋለሁ እያለ በማባበል ላይ ነው፡፡ ደለብ ያለ ገንዘብ እንደቀረበላቸው ያመኑ በርካታ የፌስቡክ፣ የዩትዩብና የኢኒስታግራም ዝነኞች ጉዳዩን አደባባይ አውጥተውታል፡፡ ማንነቱ ያልታወቀው ይህ ገንዘብ ከፋይ አካል/ድርጅት መቀመጫውን በዩኬ እንዳደረገ ቢገመትም ሊደረስበት ግን አልቻለም፡፡ ዝነኞቹን በገንዘብ የሚያማልለው ኢሜይል እየላከ ሲሆን በተለይም ፋይዘር የተባለውን የክትባት ዓይነት ዘዴኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲከፍቱበት ዝነኞችን ያባብላል፡፡ ለምሳሌ በዩትዩብ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮች ያሉት ሊዮ ግራሴት እጅግ የሚያማልል ገንዘብ እንደቀረበለት በትዊተር ሰሌዳው አጋልጧል፡፡ ገንዘብ ያቀረበለት ድርጅት በሊክንድኢን ገጹ ሠራተኞቹ በሩሲያ እንደሚገኙ እንደሚያመላክትም አስረድቷል፡፡ ሊዮ ጨምሮ እንዳጋለጠው ድርጅቱ ክትባቱን ሲያጥላላ በፍጹም ገንዘብ እንደተከፈለው እንዳይናገር እና ቪዲዮም ስፖንሰር እንደተደረገ እንዳይገልጽ በዚህ ድርጅት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል፡፡ ‹‹የስም ማጥፋት ማስታወቂያ ሲሰራ ቪዲዮውን በራሴ እንደሰራሁት እንድናገር ገፋፍተውኛል›› ብሏል ሊዮ፡፡ ሊዮ ይኸው ድርጅት ፋይዘር የተባለውን ክትባት የሚወስዱ ሰዎች አስትራዜኒካ ከወሰዱት ጋር ሲነጻጸሩ በሦስት እጥፍ ሞታቸው እንደተፋጠነ እንዲናገር ጠይቆታል፡፡ ከሊዮ በተጨማሪ በርካታ የፈረንሳይ የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ዝነኞች በተመሳሳይና ለተመሳሳይ እኩይ ተግባር ከፍ ያለ ገንዘብ እንደቀረበላቸው መናገር ጀምረዋል፡፡ በኢናስታግራም 85 ሺህ ተከታዮች ያሉት ሌላ ዝነኛ ለፈረንሳይ ቲቪ እንደተናገረው ለ30 ሰከንድ የስም ማጥፋት ቪዲዮ 2 ሺህ ዩሮ ቀርቦልኛል ብሏል፡፡ የፈረንሳይ የጤና ሚኒስትር ኦሊቪየር ቬራን ይህ ገንዘብ ለዝነኞች የሚረጨው ድርጅት የት እንደሆነ የምናውቀው ነገር የለም፡፡ ድርጊቱ ግን አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡ በሁለት ዙር የሚሰጠው ፋይዘር ክትባት ሙሉ ስሙ ፋይዘር እና ባዮንቴክ ሲሆን በፈረንሳይ ለሕዝብ በብዛት እየተሰጠ ያለ የክትባት ዓይነት ነው፡፡ ክትባቱን የፈጠሩት የአሜሪካው ፋይዘርና የጀርመኑ ባዮንቴክ በሽርክና ነው፡፡ ሌላው በሁለት ዙር የሚሰጠው አስትራዜኒካ በፈረንሳይ በ2ኛ ደረጃ እየተሰጠ ሲሆን የሚያመርተው ደግሞ የዩኬና ስዊድሽ ጥምረት የሆነ ፋርማሱቲካል ኩባንያ ነው፡፡ ባለፈው መጋቢት የአውሮጳ ኅብረት አንድ ሪፖርት የሩሲያና የቻይና ሚዲያዎች በምዕራቡ ዓለም እየተሰጡ ያሉ የኮቪድ-19 ክትባቶችን ኅብረተሰቡ በጥርጣሬ እንዲያያቸው ለማድረግ ውስጥ ውስጡን ይሰራሉ ሲል ከሶ ነበር፡፡ ሞስኮ ይህንን ክስ አጣጥላዋለች፡፡ https://www.bbc.com/amharic/57251178 +health ወረርሽኙ መቀጠሉ የዙምን ሽያጭ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለፀ "የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በርካታ የአለማችን ህዝብ በቤት መገደቡ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ለስብሰባዎችና ለሌሎች ዝግጅቶች መገልገያ የሆነው የድምፅና የቪዲዮው መተግበሪያው ዙም ከፍተኛ ሽያጭ እንዳስመዘገበና ትርፉም በዚሁም ሊቀጥልም እንደሚችል ኩባንያው አስታውቋል። በካሊፎርኒያ መቀመጫውን ያደረገው የዙም ኩባንያ 2.5 ቢሊዮን ዶላርም ትርፍ አገኛለሁ ብሎ የተነበየ ሲሆን ይህም በመጋቢት ወር አገኘዋለሁ ብሎ ካሰበው እጥፍ ነው ተብሏል። ወረርሽኙን ተከትሎም ስሙ የገነነው ዙም አገራት ሁለተኛ ዙር ወረርሽኝን በማስተናገዳቸውም በርካታ ሰዎች ለየእለት ግንኙነታቸው ተመራጭ መተግበሪያ አድርጎታል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአለማችን ህዝቦችም መተግበሪያውን ከቤተሰብና ከጓደኞች ጋር ለመጫወት፣ በመማር ማስተማር ሂደት፣ ጉባኤዎችና የተለያዩ ዝግጅቶችን ለማካሄድና፣ ለስብሰባዎችም ተመራጭ አድርገውታል። የዙም መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤሪክ ዩዋን እንደሚሉት ""ሰራተኞች ከየትኛውም ቦታ መስራትን በቀጠሉበት ወቅት"" የከፋይ ኩባንያ ደንበኞች ቁጥር እየጨመረ ነው ብሏል። በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ዙም 434 ሺህ ከአስር ሰራተኞች በላይ ያሉት ከፋይ ኩባንያ ደንበኞች እንዳሉት የተዘገበ ሲሆን ይህም ከባለፈው አመት ጋር 485 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ነው ተብሏል። በዚህም ምክንያት ኩባንያው ከጠበቀው በላይ ሽያጭና ትርፍም እየተንበሸበሸ እንደሆነም ተነግሯል፥ ዙም ከባለፈው አመት ነሐሴ እስከ ጥቅምት ባለው የሩብ አመት ሽያጭ 777 ሚሊዮን ዶላር የመዘገበ ሲሆን ይህም ከሁለት አመት በፊት በዚህ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር 367 በመቶ ጭማሬ አሳይቷል። ትርፉም በዚሁ ሩብ አመት 198.4 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን ከሁለት አመት በፊት የነበረው የሩብ አመት ትርፍ 2.2 ሚሊዮን ዶላር ነበር። በዚህ ሳምንት ሰኞ ሽያጩንና ትርፉን እንደገና በመገምገም ለሶስተኛ ጊዜ አዲስ ትንበያን ያወጣ ሲሆን በመጪው አውሮፖውያኑ አዲስ አመትም 2.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆንም ለኢንቨስተሮች አሳውቋል። በነሐሴ ወር ላይ ኩባንያው ተንብዮት የነበረው 2.37 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት የነበረው ሽያጭ 622̌.7 ሚሊዮን ዶላርም ነበር ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55141283 +sports ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ደምቀውበት ያለፈው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን በአሜሪካዋ ግዛት ኦሪገን፣ ዩጂን ከተማ ውስጥ ሲካሄድ በሰነበተው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ሴት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ታሪክ በማስመዝገብ ደምቀው ታይተዋል። ኢትዮጵያ በውድድሩ ካስመዘገበቻቸው 10 ሜዳሊያዎች 7ቱ የተመዘገቡት በተለያዩ ርቀቶች በተሳተፉ ሴት አትሌቶች አማካይነት የተገኙ ናቸው። ኢትዮጵያ በ4 የወርቅ፣ በ4 የብር እና በ2 የነሐስ ሜዳሊያዎች ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ደግሞ ከአሜሪካ በመቀጠል ሁለተኛ ሆና ውድድሩን አጠናቃለች። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮን በርካታ ሜዳሊያዎች ሲያስመዘግቡ ይህ የመጀመሪያው ነው። ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር፣ ለተሰንበር ግደይ በ10 ሺህ ሜትር እንዲሁም ጎተይቶም ገ/ሥላሴ በማራቶን ኢትዮጵያ ካስመዘገበቻቸው 4 የወርቅ ሜዳሊያዎች ሦስቱን ማስገኘት ችለዋል። ቀሪ አንድ የወርቅ ሜዳሊያ የተገኘው በወንዶች የማራቶን ውድድር በታምራት ቶላ አማካይነት ነው። ከ4ቱ የብር ሜዳሊያዎች ሁለቱን ያጠለቁት ጉዳፍ ፀጋይ እና ወርቅውሃ ጌታቸው ናቸው። ይህም ጉዳፍ በ1 ሺህ 500 ሜትር፤ ወርቅውሃ ደግሞ በ3 ሺህ ሜትር መስናክል። የተቀሩትን ሁለት የብር ሜዳሊያዎች ለሜቻ ግርማ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል እንዲሁም ሞሰነት ገረመው በማራቶን ለአገራቸው አስመዝግበዋል። ሁለቱ የነሐስ ሜዳሊያዎች የተመዘገቡት በሁለት ሴት አትሌቶች ነው። ዳዊት ስዩም በ5 ሺህ ሜትር እንዲሁም መቅደስ አበበ በ3 ሺህ ሜትር። ወርቅ ያስመዘገቡት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በውድድሩ ከፍተኛ ብቃታቸውን ከማሳየታቸው ባሻገር የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናንም ክብረ ወሰን ለማሻሻል በቅተዋል። ደራርቱ ቱሉ ያለፉትን ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሽንን በበላይነት ስትመራ ቆይታለች። በተለያዩ የአትሌቲክስ መድረኮች ላይ የአገሯን ስም ያስጠራችው ደራርቱ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆና ከተመረጠች በኋላ፣ ይህ የኦሪገኑ ሻምፒዮና ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ዓለም አቀፍ ውድድር ነው። ደራርቱ ፌዴሬሽኑን መምራት ከጀመረች ወዲህ ሁለት ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና፤ አንድ ጊዜ በኦሊምፒክ መድረክ፤ አንድ ጊዜ ደግሞ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያ ተሳታፊ ሆናለች። በኳታር ዶሃ በተሰናደው የ2019 የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብርና አንድ ነሐስ ይዛ ተመልሳለች። በዚህ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በሚታወቁበት የመካከለኛና ረዥም ርቀት ውድድር ተለመደውን ወርቅ ማስመዝገብ ባይችሉም ተስፋ ያላቸው አትሌቶች ታይተው ነበር። ኢትዮጵያ በመድረኩ በስምንት ሜዳሊያ አምስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች። ከዚህ በኋላ በደራርቱ የተመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ታላቅ ወደ ሚባለው የኦሊምፒክ መድረክ ነው ያቀናው። በ2022 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ያገኘችው ሜዳሊያ ብዛት አራት ነው። ይህ ውጤት ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ ካመጣቻቸው ዝቅተኛ ከተባሉት የሚመደብ ነው። ቀጥሎ ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ዓለም አቀፍ መድረክ ባለፈው መጋቢት የተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ፍልሚያ ነው። ይህ መድረክ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ነበር። ኢትዮጵያ፤ በአራት ወርቅ፣ በሦስት ብርና በሁለት የነሐስ አሜሪካን አስከትላ ከዓለም ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች። https://www.bbc.com/amharic/articles/cyep9eld3deo +sports በአንድ ቀን የተወለዱ ልጆች በስሟ እንዲጠሩ ስለተደረገላት አትሌት ያውቃሉ? ናዋል ኤል ሞውታዋኬል ሞሮኳዊት አትሌት ናት። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ነሐሴ 8፣ 1984 በሎስ አንጀለስ ኦሎምፒክ ድል ተቀዳጅታለች። ማሸነፏ እጅግ ያስደሰታቸው ሞሮኳዊው ንጉሥ ሐሰን በእለቱ የተወለዱ ሴቶች ባጠቃላይ ናዋል ተብለው እንዲጠሩ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ሰሞኑን 36ኛ ዓመት ልደታቸውን የሚያከብሩ የሞሮኮ ሴቶች ስማቸው ናዋል የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ናዋል በኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ያገኘች የመጀመሪያዋ ሞሮኳዊት ናት። በ400 ሜትር የመሰናክል ዝላይ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ሴትም ናት። በሎስ አንጀለሱ ኦሎምፒክ ላይ የተገኘች ብቸኛዋ ሞሮኳዊት ሴት ናዋል ነበረች። በኦሎምፒክ ታሪክ ድል የተቀዳጀች የመጀመሪያዋ ሴት አረብ አፍሪካዊትም ናት። የውድድሩ ተካፋይ የነበረው ሰዒድ አዊታ በ500 ሜትር ሩጫ ያሸነፈው ምናልባትም በናዋል ድል ተነሳስቶ ይሆናል። “ስለውድድሩ ሳስብ ሌሊቱን በሙሉ እንቅልፍ አልወሰደኝም” ናዋል ከውድድሩ አንድ ቀን በፊት ሲያቃዣት ነበር። መሰናክል ዘላ አንዳች ጉድጓድ ውስጥ እንደምትገባ ይሰማት እንደነበር ታስታውሳለች። “በጣም ፈርቼ ነበር። ብቸኛዋ ሞሮኳዊት ሴት ስለነበርኩ ሁሉም የቡድኑ አባላት ተስፋ ጥለውብኝ ነበር።” ውድድሩን ከማሸነፏ በፊት የነበረውን ምሽት እንዲህ ታስታውሰዋለች። “ስለ ውድድሩ ሳስብ ሌሊቱን በሙሉ እንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር። ሲያቃዠኝ፣ ሲያልበኝ ስለነበር መተኛት አልቻልኩም። ዝግ ብዬ ስሮጥ ይታየኝ ነበር።” በችሎታዋ አምና በውድድሩ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ትፈልግ ነበር። “ያሰብኩት ከመጨረሻዎቹ ስምንት ተወዳዳሪዎች አንዷ እንደምሆን ነበር። አሰልጣኞቼ እንደማሸንፍ ስላሰቡ በራሴ እንድተማመን ደጋግመው ይነግሩኝ ነ��ር።” ናዋል እና አሰልጣኞቿ ከመጨረሻው ውድድር በፊት የሷና የተፎካካሪዎቿን ያለፉ ውድድሮች ቪድዮ ይመለከቱ እንደነበር ታስታውሳለች። የሷን ደካማና ጠንካራ ጎኖች ከተፎካካሪዎቿ ጋር ያነጻጽሩም ነበር። “ላሸንፍ ስለምችል ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ጠንካራ መሆን እንዳለብኝ ይነግሩኝ ነበር” ትላለች። ናዋል እንደምታሸንፍ ማመኗ የስኬቷ ሚስጥር ነበር። እራሷን “ያንቺ ጊዜ ነው። ድል ሊያመልጥሽ አይገባም” እያለችም ነበር። የናዋል አሜሪካዊት ጓደና ጁዲ ብራውንም የውድድሩ ተሳታፊ ነበረች። በእርግጥ የውድድሩ ተመልካቾች የ22 ዓመቷ ናዋል ደጋፊ አልነበሩም። ጋዜጠኞች ውድድሩን በአንክሮ ይከታተላሉ ነበር። ውድድሩ በይፋ ከመከፈቱ በፊት ናዋል በስህተት የጀመረች መስሏት ተደናግጣ ነበር። ኋላ ላይ ግን ተረጋጋች። “የመጀሪያውን፣ ሁለተኛውንና ሦስተኛውን መሰናክል በግራ እግሬ ዘለልኩ። ከዛ እስከ መጨረሻው ድረስ ቀኝና ግራ እግሬን መለዋወጥ ጀመርኩ።” ተፎካካሪዎቿን በቅርብ ርቀት ማየት ስላልቻለች ግራ ተጋብታ እንደነበር ታስታውሳለች። “ሌሎቹ ሯጮች የት ገቡ? ብዬ አሰብኩ። ለካ በጣም ቀድሜያቸዋለሁ። የመጨረሻውን ነጥብ ከማለፌ በፊት እኔ ብቻ እያለፍኩ መሆኑን ለማረጋገጥ ወደ ግራና ቀኝ ተመለከትኩ።” “አባቴ በቦታው ባለመኖሩ ከፍቶኝ ነበር” ናዋል ወርቅ ስታገኝ ጓደኛዋ ጁዲ ብራውን ብር አግኝታለች። “ሳሸንፍ በጣም ነው ደስ ያለኝ። ግን አባቴ በቦታው ባለመኖሩ ከፍቶኝ ነበር። ሁሌም ይደግፈኝ የነበረው አባቴ ከውድድሩ ከወራት በፊት ሕይወቱ አልፏል።” የናዋል ቤተሰቦች ስፖርት ወዳጅ ናቸው። አባቷ የጁዶካ ተጫዋች (እንደ ማርሻል አርት አይነት ውድድር) እናቷ ደግሞ መረብ ኳስ ተጫዋች ነበሩ። ናዋል ህልሟን እንድታሳካ ቤተሰቦቿ ይደግፏት ነበር። “ማሸነፌ ለአገሬ ትልቅ ዜና ነበር። ማንም ያልጠበቀው ድል ነው። አንዲት ታዳጊ ሞሮኳዊት ከምርጥ አትሌቶች ጋር ተፎካክራ አሸንፋ ወርቅ ታገኛለች ብሎ ማንም አላሰበም። በልቤና በአዕምሮዬ እስከወዲያኛው የሚኖር ታሪካዊ ቅጽበት ነው።” የናዋል ድል በወግ አጥባቂ አረብና ሙስሊም አገሮች ለሚኖሩ ብዙ ሴቶች በር ከፍቷል። “ከዛ በኋላ ብዙ ሞሮኳዊ ሴቶች አሸንፈዋል። በአልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ግብፅ እና ባህሬን የሚኖሩ ሴቶችም እንዲሁ። በኦሎምፒክስ ላይ ሴቶች አሳትፈው የማያውቁ አገሮች፤ ሴቶችን ለተሳትፎ ብቻ በቡድናቸው ከማካተት አልፈዋል። ሴቶች የሚካተቱት ለተሳትፎ ሳይሆን ለማሸነፍ ሆኗል” ትላለች አትሌቷ። https://www.bbc.com/amharic/news-53740809 +politics በጣሊያን ኤምባሲ የሚገኙ የቀድሞ ባለስልጣናት በቀናት ውስጥ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ "ሠላሳ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ በጥገኝነት የሚገኙት ሁለት የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቀጣይ ቀናት ይቅርታ ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ። እነዚህ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና ሌፍተናንት ጄነራል አዲስ ተድላ ከደርግ መንግሥት መውደቅ በኋላ በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ላለፉት ሦሰት አስርት ዓመታት ቆይተዋል። የኢህአዴግ ሠራዊት አዲስ አበባን ከመያዙ አንድ ቀን ቀደም ብለው በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ከተጠለሉት አራት የወቅቱ ከፍተኛ ባለስልጣንት መካከል የነበሩት ብርሃኑ ባይህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ሌፍተናንት ጀነራል አዲስ ተድላ የሠራዊቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ነበሩ። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ አወል ሱልጣን ለቢቢሲ እንደገለጹት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለቱ የቀድሞ ባለስልጣናት፤ የሞት ፍርዳቸው ወደ እድ�� ልክ እስራት በርዕሰ ብሔሯ ተቀንሶላቸዋል። ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በደርግ መንግሥት ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ ወቅት ተፈጽመዋል በተባሉ የተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው ነው የሞት ቅጣት የተበየነባቸው። አቶ አወል እንዳሉት የጣሊያን ኤምባሲ ሁለቱ ግለሰቦች እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ ለበርካታ ዓመታት በመቆየታቸው እና እድሜያቸው መግፋቱን ተከትሎ ከእድሜ ጋር ተያይዘው በሚመጡ ሕመሞችም ችግር ላያ ያሉ መሆኑን በመጥቀስ ግለሰቦቹ ነጻ እንዲወጡ ሃሳብ መቅረቡን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""እኛ ያሉበትን ሁኔታ አናውቅም። የሚታመሙ ሰዎች መሆናቸውን ከኤምባሲው ተገልጾልናል። ኤምባሲው ግለሰቦቹ ቢወጡ የሚል ምክረ ሃሳብ አቅርቧል"" ብለዋል። ዐቃቤ ሕግም በተመሳሳይ የተላለፈባቸው የሞት ፍርድ ወደ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀነስ በይቅርታ እና የምህርት ቦርድ በኩል ለርዕሰ ብሔሯ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል። ""ግለሰቦቹ ጥፋተኛ የተባሉበት ወንጀል በይቅርታ የሚያስለቅቅ ባይሆንም፤ ግለሰቦቹ ባለፉት 30 ዓመታት በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ እስር በሚመስል ሁኔታ ነጻነታቸውን አጥተው ቆይተዋል"" ብለዋል። የጣሊያን ኤምባሲ ለዐቃቤ ሕግ ባስታወቀው መሠረት ግለሰቦቹ ከኤምባሲው ምንም አይነት ድጋፍ ሲደረግላቸው አልነበረም። ከቤተሰባቸው ይቀርብላቸው የነበረውን ቀለብ እየተጠቀሙ ነው እስካሁን የቆዩት ብለዋል አቶ አወል። በዐቃቤ ሕግ ጥያቄ መሠረት ፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የሞት ቅጣቱን ወደ እድሜ ልክ እስራት እንዲቀነስ ካደረጉ በኋላ በቀጣይም ዐቃቤ ሕግ ግለሰቦቹ በአመክሮ እንዲለቀቁ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥያቄ እንደሚያቀርቡ አቶ አወል አስታውቀዋል። ""ፕሬዝደንቷ የሞት ቅጣቱን ወደ የእድሜ ልክ ቅጣት ቀይረውታል። በቀጣይ ግለሰቦቹ እስካሁን የቆዩበት ሁኔታ ከጥፋታቸው እንዲማሩ ስላደረጋቸው እና ከዚህ በኋላ ባሉበት ሁኔታ እንዲቆዩ ማደረግ የፍትሕ ዓላማ ስላማይሆን ሊወጡ የሚችሉበትን ሁኔታ ከሕግ አግባብ ነገሮችን ለማየት ጥረት አድርገናል። በዚህ መሠረትም ሰዎቹ በአመክሮ እንዲላቀቁ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ዛሬ ወይም ሰኞ እንልካለን"" ብለዋል። ፍርድ ቤቱ ደግሞ ይህን ከመረመረ በኋላ ግለሰቦቹ በቀጣይ ቀናት በአመክሮን እንዲለቀቁ ያጸድቃል ብለን እናስባለን ሲሉ አቶ አወል ለቢቢሲ ተናግረዋል። የግለሰቦቹን ጉዳይ የሚመለከተው በተከሰሱበት ወንጀል ከዚህ ቀደም ጥፋተኛ ብሎ በፈረደባቸው ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑንም ተናግረዋል። የኤርትራ ነጻነት ግንባር አሥመራን ሲቆጣጠርና የኢህአዴግ ኃይሎች ድል እየቀናቸው ወደ አዲስ አበባ ለመግባት አንድ ሳምንት ሲቀራቸው የወቀቱ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪያም ስልጣናቸውንና አገራቸውን ለቀው አስካሁን ድረስ በጥገኝነት ወደሚገኙባት ዚምባብዌ ካቀኑ ከሳምንት በኋላ ነበር ባለስልጣናቱ ወደ ጣሊያን ኤምባሲ የገቡት። ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እንዲሁም ሌፍተናንት ጄነራል አዲስ ተድላ በውቅቱ ተይዘው ከነበሩ ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር በስልጣን ዘመናቸው ወቅት ተፈጽመዋል በተባሉ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸው በሌሉበት የሞት ቅጣት ተወስኖባቸው ነበር። መንግሥትም የጣሊያን መንግሥት ተፈላጊዎቹን አሳልፎ እንዲሰጠው በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ጣሊያን ጥያቄውን ሳትቀበለው ግለሰቦቹን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ኤምባሲዋ ውስጥ አስጠግታ 30 ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ለቀሩት ጊዜ ጠብቃ አቆይታቸዋለች። በወቅቱ በኤምባሲው ውስጥ ጥገኝነት በመጠየቅ ገብተው የነበሩት ከፍተኛ ባለስልጣናት ስምንት የነበሩ ሲሆን አራቱ በእራሳቸው ፈቃድ ኤምባሲውን ለቀው መውጣታቸው ይነገራል። ���ሁን ኤምባሲው ውስጥ ከሚገኙት ከኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና ሌፍተናንት ጀነራል አዲስ ተድላ በተጨማሪ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪያም አገር ለቀው ሲሄዱ ለቀናት የመሪነት ቦታውን ይዘው የነበሩት ሌ/ጀኔራል ተስፋዬ ገብረኪዳን እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ኃይሉ ይመኑ ይገኙ ነበር። እነዚህ ከፍተኛ የቀድሞ ባለስልጣናት በኤምባሲው ውስጥ ጥገኝነት አግኝተው ለተለያዩ ጊዜያት ከቆዩ በኋላ እዚያው እንዳሉ በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸው እንዳለፈ ይታወቃል። ዚምባብዌ የሚገኙትንና በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ያሉትን ጨምሮ በወቅቱ እጃቸውን ሰጥተው በነበሩ የቀድሞው መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በስልጣን ዘመናቸው ተፈጽመዋል በተባሉ ጥፋቶች የከባድ ክስ ተመስርቶባቸው የፍርድ ሂደቱ ለዓመታት ከተካሄደ በኋላ አብዛኞቹ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል። ነገር ግን በእስር ላይ ሳሉ ህይወታቸው ካለፈው ውጪ ያሉት ባለስልጣናት ከ20 ዓመታት እስር በኋላ በምህረት ነጻ መውጣታቸው ይታወቃል።" https://www.bbc.com/amharic/55314978 +business በፈረንሳይ በአዲስ ዓመት ዋዜማ 874 መኪናዎች ተቃጠሉ ፈረንሳይ ውስጥ በአዲስ ዓመት ዋዜማ በአጠቃላይ 874 መኪናዎች ዶግ አመድ መሆናቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ቢሆንም የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው ይህ ቁጥር ከ2019 ጋር ሲነፃፀር የወረደ ነው። ባለሥልጣናቱ ጨምረው እንደጠቆሙት በዘንድሮው የአዲስ ዓመት በርካታ ሰዎች ለጥቂት ሰዓታት በሕግ ጥላ ሥር እንዲቆዩ ተደርገዋል። ባለፈው ዓመት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል ሲባል የተጣለውን ሰዓት እላፊ ተከትሎ ፈረንሳይ ምንም ዓይነት ረብሻ አላስተናገደችም። ከፈረንጆቹ 2005 ጀምሮ መኪና ማቃጠል ፈረንሳይ እየተለመደ የመጣ የከተሜዎች ባሕል መሆን ጀምሯል። በቅርብ ዓመታት ይህንን ድርጊት ለመከላከል ሲባል ቢያንስ 95 ሺህ ፖሊሶች ወደ መንገድ ወጥተው ሲያስሱ ነበር። የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በየዓመቱ ቢያንስ 32 ሺህ የእሣት አደጋ ሠራተኞች በተጠንቀቅ ቆመው ይጠብቃሉ። በዋና ከተማዋ ፓሪስ የአፍና አፍንጫ መከላከያ ማድረግ የዜጎችና ጎብኚዎች ግዴታ ነው። ነገር ግን ይህንን ተላልፈው ተገኝተዋል የተባሉ 779 ሰዎች በከተማዋ ባለሥልጣናት ቅጣት ተላልፎባቸዋል። ምንም እንኳ ፈረንሳይ የተወሰኑ የኮቪድ-19 ገደቦችን ብታነሳም ከሰሞኑ በተቀሰቀሰው የኦሚክሮን ዝርያ ምክንያት ሕግጋቱ ተመልሰው ተግባራዊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከሰኞ ጀምሮ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች ዝግ በሆነ አዳራሾች መሰባሰብ አይችሉም። ከዚህም አልፎ ከቤታቸው ሆነው መሥራት የሚችሉ ሰዎች ወደ ቢሮ እንዳይገቡ እግድ ይጣልባቸዋል። ፈረንሳይ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት የመጀመሪያዋ ቅዳሜ መቶ ሺህ ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንደተያዙባት ይፋ ማድረጓ ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/news-59850637 +business የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ያለሙት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች "በተለያዩ ምክንያቶች በኢትዮጵያ በሚገኙ ከተሞች የመሠረታዊ ምርቶች ዋጋ ያለማቋረጥ እያሻቀበ ዜጎች ላይ ጫና እየፈጠረ ነው። ለዋጋ ግሽበቱ ምክንያት በመሆን ከሚጠቀሱት መካከል በአገሪቱ ያለው ጦርነት እና ያስከተላቸው ጊዜያዊ ችግሮች እንዲሁም በወጪ ንግድ ያለው መዛነፍ ይጠቀሳሉ። በሌላ በኩል በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ እና በሌሎች ዓለም አቀፋዊ የምጣኔ ሀብት ምክንያቶች በኢትዮጵያ ኑሮ 'የማይቀመሰ' ሆኗል የሚለውን ብዙዎች የሚጋሩት ነው። ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው የኅዳር ወር 2014 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ33 በመቶ ጭማሪ አለው። ከዚህ ውስጥ የምግብ ነክ ምርቶች የኅዳር ወር በ38.9 በመቶ የጨመረ ሲሆን አምና በተመሳሳይ ወቅት ተንከባላይ የምግብ ነክ ዋጋ ግሽበት 23.2 ሆኖ ተመዝግቦ ነበር። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተብ ክፍሎች ደግሞ በዋጋ ግሽበቱ በቀዳሚነት ተጎጂ ሆነዋል። እነዚህን የኅብረተብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ የቅዳሜ እሁድ ገበያዎች ከሳምንታት በፊት ሥራ ጀምረዋል። ገበያዎቹ ለምን ተቋቋሙ? ገበያዎቹ በአንድ በኩል ለሸማቾች ምክንያታዊ በሆነ ዋጋ ምርት የማቅረብ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለአምራቾች ገበያ የመፍጠር ዓላማ ያላቸው ናቸው። የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ላለፉት ዘጠኝ ሳምንታት በአዲስ አበባ የተለያዩ አከባቢዎች የተከናወኑት የእሁድ ገበያዎች ቀዳሚ ዓላማ በከተማው የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ""ለመከላከል እና ለመቆጣጠር"" እንዲሁም ሸማቾችን እና አምራቾችን በቀጥታ ለማገናኘት ያለመ እንደሆነ ይናገራሉ። ""በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተብ ክፍሎች በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን ማግኘት እንዲችሉ እና ከዚያ ጎን ለጎን ደግሞ ለአምራች፣ አርሶ አደሮችም፣ ፋብሪካዎችም የገበያ ችግሮቻቸውን ለመፍታት ያለመ ነው።...ከተማችን ላይ ያለውን የምርት አቅርቦት መጠን ማሳደግም"" ዓላማው ነው ሲሉ ለቢቢሲ አብራርተዋል። በአዲስ አበባ ይህ ገበያ በየሳምንቱ እሁድ የሚደረግ ሲሆን በድሬዳዋ ደግሞ ቅዳሜንም ያካትታል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የድሬዳዋ ከተማ የንግድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሚኑ ጠሃ፣ የገበያዎቹ ""ዋና ዓላማ የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ ነው። በተለይ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያለው የኅብረተሰብ ክፍል ዋጋ ሳይጨመርበት የግብር ምርቶችን እና የፋብሪካ ምርቶችን በቀላሉ በተመጣጣኝ ዋጋ አግኝቶ ከኑሮ ጫናው እንዲላቀቅ የተጀመረ ነው"" ሲሉ ገልጸዋል። ገበያዎቹ ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባሉ የሚሉት አቶ አሚኑ፣ የሽንኩርትን ገበያ ለአብነት በማንሳት ""በመደበኛው ገበያ እስከ አርባ ብር የሚሸጠው ሽንኩርት እኛ ባዘጋጀነው የቅዳሜ እና የእሁድ ገበያ እስከ 28 ብር የሚሽጥ ነው"" ብለዋል። በገበያዎቹ ምን እና ማን ያቀርባል? በአዲስ አበባ በአስራ አንድ፣ በድሬዳዋ ደግሞ በአራት ቦታዎች የተዘረጉት እነዚህ የእረፍት ቀናት ገበያዎች የግብርና እና የፋብሪካ ምርቶች የሚቀርቡበት ነው። በሁለቱም ከተሞች ያሉ የከተማ ግብርና ውጤቶች እንዲሁም በከተሞቹ ዙሪያ ያሉ አርሶ አድሮች የሚያመርቷቸው የእህል ምርቶች በገበያዎቹ አማካኝነት ለነዋሪዎች ይቀርባል። በድሬዳዋ ከተማ እነዚህ ገበያዎች በአብዛኛው ጤፍን ጨምሮ አትክልት እና ፍራፍሬ፤ ከቃሪያ እስከ ሽንኩርት ያሉ የጓሮ አትክልቶችን እንዲሁም በከተማ ውስጥ ያሉ ፋብሪካዎች የሚያመርቷቸው ዘይት፣ ዱቄት፣ መኮሮኒ፣ ፓስታ፣ ብስኩትን እና ሳሙናን የመሰሉ ምርቶች ይቀርቡበታል። የፋብሪካ ምርቶቹ ""በተመጣጣኝ ዋጋ ኅብረተሰቡ ማግኘት እንዲችል ነው፤ አከፋፋይ እና ቸርቻሪ እጅ ሳይገባ ማለት ነው። በፋብሪካ ዋጋ ኅብረተሰብ እንዲያገኝ የተደረገ ነው"" ሲሉ አቶ አሚኑ ተናግረዋል። እንደ ድሬዳዋ ሁሉ በአዲስ አበባም በገበያዎቹ መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ይቀርቡበታል። ገበያዎቹ እንደ ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ ድንች፣ ጎመን ያሉ አትክልቶች፤ ሙዝ እና ብርቱካንን የመሳሰሉ ፍራፍሬዎች፤ ጤፍ እና ስንዴን ጨምሮ የሰብል ምርቶች፤ ዘይት፣ ፓስታ፣ የዳቦ ዱቄት አይነት የኢንዱስትሪ ውጤቶችንም የሚያካትት ነው። ""በዋናነት ምርቶቹ ትኩረት ያደረጉት ኅብረተሰቡ በየዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ለምግብነት የሚያውላቸው እና የሚጠቀምባቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በአቅራቢያው እንዲያገኝ ያለመ"" እንደሆነ አቶ መስፍን ጠቅሰዋል። ለገበያዎቹ ምርት የሚያቀርቡት በከተማ ግብርና የተሰማሩ በግልም ይሁን ተደራጅተው የሚሰሩ አምራቾች ናቸው። በተጨማሪም በከተሞቹ ዙሪያ ያሉ አርሶ አደሮች እና ፋብሪካዎች ናቸው። ከተሞቹ ከኦሮሚያ፣ ከአማራ፣ ከደቡብ ክልል የሚገኙ ምርቶችን በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች አማካኝነት ያቀርባሉ። ገበያዎቹ እስከመቼ ይቀጥላሉ? በድሬዳዋ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያ በተጀመረ በአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ውስጥ ወይም እስከ 6ኛው ሳምንት አርባ ሚሊዮን ብር የሚያህል ግብይት መፈጸሙን አቶ አሚኑ ተናግረዋል። ""በዚህ ስድስት ሳምንት ውስጥ አርባ ሚሊዮን ግብይት ቢካሄድም ግን በመደበኛ የገበያ ዋጋ ሊያወጣ ይችል የነበረው ከአስር ሚሊዮን ብር በላይ ኅብረተሰቡን አድነነዋል"" ብለዋል ኃላፊው። የገበያ ልውውጡን ትክክለኛው አሀዝ መረጃ ለጊዜው የለኝም ያሉት አቶ መስፍን ደግሞ ልውውጡ ""ሰፊ ቁጥር ያለው እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ"" መምጣቱን ጠቅሰው በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል። ""ዘመናዊ የንግድ ሥርዓት እየገነባን እስክንሄድ፣ የቁጥጥር ሥርዓታችን ውጤታማ እየሆነ ሲሄድ፣ ምርታማነታችንን በምንፈልገው ደረጃ እስኪደርስ ... ገበያዎቹ ተጠናክረው ይቀጥላሉ"" የሚሉት አቶ መስፍን እነዚህ የመገበያያ አማራጮች የሚይዟቸው ምርቶች እያደጉ ቦታዎቹም እየጨመሩ እንደሚሄዱም አመላክተዋል። በድሬዳዋ ደግሞ በስሩ ያሉ ሁሉም ቀበሌዎች ለእነዚህ የገበያ አማራጮች ስፍራዎችን እንዲያዘጋጁ እየተደረገ መሆኑን አቶ አሚኑ ተናግረዋል። ገበያዎቹ አሁን በያዙት ቅርጽ ወይም ተጨማሪ አማራጮችን በማካተት በዘላቂነት እንሚቀጥሉም አንስተዋል። ኃላፊዎቹ እነዚህ ገበያዎች የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የቀረቡ አማራጮች መሆኑን ጠቅሰው፣ ሰፊው ገበያ ላይ የሚስተዋሉ እና ዜጎች ላይ ጫና እንዲፈጠር ምክንያት የሆኑ የንግድ ሥርዓቱ ችግሮችን ለመቅረፍ የተጀመሩ ቁጥጥሮች እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59839436 +health ኮቪድ-19፡ በስህተት የ16 ሺህ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ውጤት ሳይገለጽ ቀረ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በገጠመ የቴክኒክ ስህተት ወደ 16 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሳይገለጽ ቀረ። ይህም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት የሚደረገውን ጥረት አጓቷል። የአገሪቱ የሕብረተሰብ ጤና ተቋም እንዳለው ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 2 ድረስ 15,841 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በእለታዊ ሪፖርት ሳይካተት ቀርቷል። ሪፖርት ያልተደረጉት ሰዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ በወጡት እለታዊ ሪፖርቶች ተካተዋል። • የኮቪድ-19 ፀር ሳሙና ወይስ ፀረ-ቫይረስ ፈሳሽ? • ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን ለማየት ሆስፒታል ጥለው ወጡ • ልብስ ሳያረጥብ በፀረ ተህዋስ የሚያፀዳው የኢትዮጵያዊው ፈጠራ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ውጤታቸው ቢነገራቸውም ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች መረጃው እንዳልደረሳቸው ተቋሙ አስታውቋል። በገጠመው የቴክኒክ ስህተት ምክንያት ባለፈው ሳምንት የወጡ ሪፖርቶች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን አሳንሰዋል። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በቫይረሱ እንደተያዙ የተገለጸው 7,000 ሰዎች ቢሆንም፤ ትክክለኛው ቁጥር ወደ 11,000 ይጠጋል። ሪፖርት ካልተደረጉት ሰዎች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የሰሜን ምዕራብ ኢንግላንድ ነዋሪዎች ናቸው። በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የሚኖሩት በሊቨርፑል እና በማንችስተር ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች በአጠቃላይ እንደተነገራቸው ገልጸዋል። የክትባት ምርምር ግብረ ኃይል ኃላፊ ኬት ቢንግሀም ለፋይናንሽያል ታይምስ እንደተናገሩት፤ ከዩኬ ዜጎች ከፊሉ ይከተባሉ። “ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ሰዎች ክትባት አይሰጥም። ክትባቱ ከ50 ዓመት በላይ ለሆኑና በዋናነትም ለጤና ባለሙያዎችና አረጋውያንን ለሚንከባከቡ ሰዎች ይሰጣል” ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወረርሽኙን የማሸነፍ ተስፋ እንዳለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ማኅበረሰቡ “ጥንቃቄ ማድረግ እንጂ መፍራት የለበትም” ሲሉም አክለዋል። በአገሪቱ የምርመራ ውጤት መዘግየቱ መንግሥትን እያስተቸ ባለበት ወቅት፤ በስህተት ውጤታቸው ያልተገለጸ ሰዎች የመኖራቸው ዜና ነገሮችን አባብሷል። በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች መረጃውን አለማግኘታቸው ሌላው አሳሳቢ ነገር ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦች በ48 ሰዓታት ውስጥ ሊነገራቸው ይገባል። ስህተቱ የኮምፒውተር እንደሆነና አሁን መስተካከሉ ተገልጿል። መንግሥት ትላንት ባወጣው ሪፖርት ተጨማሪ 22,961 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸውና አጠቃላይ በበሽታው የተያዙ ቁጥር 502,978 መድረሱን ገልጿል። የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ኃላፊው ማይክል ብሮይድ እንዳሉት፤ አብዛኞቹ ሪፖርት ያልተደረጉ ቁጥሮች የቅርብ ጊዜ የምርመራ ውጤት ናቸው። “ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍና የምርመራ ውጤቶቹን ለመግለጽ ሞክረናል። ስህተቱ ሊፈጥር የሚችለውን ስጋት እንረዳለን። በቀጣይ ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጠር ጥብቅ እርምጃ ወስደናል” ብለዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54423275 +health ለሁለተኛ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዘው ከመጀመሪያው በባሰ በጠና ታመመ አሜሪካ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተያዘው ሰው፤ ከመጀመሪያው በባሰ ሁኔታ በጠና መታመሙን ሐኪሞች ተናገሩ። የ25 ዓመቱ ግለሰብ ከሳምባው በቂ ኦክስጅን ወደ ሰውነቱ መዘዋወር ስላልቻለ ሆስፒታል ገብቷል። በድጋሚ በቫይረሱ የመያዝ እድል አነስተኛ ሲሆን፤ ግለሰቡም እያገገመ ይገኛል። የኔቫዳ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ በተለየ ሁኔታ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ የሚያደርገው ህመም ወይም በሽታ የመቋቋም ኃይል ውስንንነት የለበትም። ግለሰቡ ከመጋቢት እስከ ሰኔ ድረስ ያሳየው የበሽታው ምልክቶች ቀጣዮቹ ናቸው፦ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ግለሰቡ ሁለት ጊዜ በቫይረሱ ተይዟል። መጀመሪያ የያዘው ቫይረስ ተደብቆ በድጋሚ አላገረሸበትም። የሁለቱ ቫይረሶች የዘረ መል ቅንጣት የተለያየ ነው። በኔቫዳ ዩኒቨርስቲ መመህር የሆኑት ዶ/ር ማርክ ፓንዶሪ “ቀደም ያለ ኢንፌክሽን ለሁለተኛ ጊዜ በበሽታው ከመያዝ እንደማያድን ግኝታችን ይጠቁማል። ለሁለተኛ ጊዜ በቫይረሱ የመያዝ እድል መኖሩ በሽታን ስለመከላከል አቅም ያለንን አመለካከት ይለውጣል” ብለዋል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ፣ እጃቸውን አዘውትረው መታጠብ እና አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸውም ዶክተሩ መክረዋል። ሁሉም ሰው በሽታውን የመከላከል አቅም ያዳብራል? መጠነኛ ምልክት ያሳዩ ሰዎች በሽታውን መከላከል ይችላሉ? በሽታውን የመከላከል አቅም ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል? የሚሉት ገና መልስ ያልተገኘላቸው ጥያቄዎች ናቸው። በሽታው በጊዜ ሂደት የሚያሳድርብንን ተጽዕኖ ለመረዳት እንዲሁም ክትባት ለማግኘትም እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ያሻል። እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙ ከ37 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ዳግመኛ በሽታው የያዛቸው እጅግ ጥቂቶቹ ናቸው። ከሆንግ ኮንግ፣ ቤልጄም እና ኔዘርላንድ የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው፤ ለሁለተኛ ጊዜ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ከመጀመሪያው በበለጠ አልታመሙም። ኢኳዶር ውስጥ ግን ከመጀሪያው በላቀ የታመመ ሰው ነበር። ሰውነት ቫይረሱን የመቋቋም አቅም ስለሚያዳብር ለሁለተኛ ጊዜ በሽታው ሲከሰት ቀለል ይላል የሚል መላ ምት ነበር። አሜሪካ ያለው ግለሰብ በሁለተኛው ዙር ለምን በሽታው እንደጠናበት አልታወቀም። ምናልባትም ከመጀመሪያው በላቀ ከፍተኛ መጠን ላለው ቫይረስ ተጋልጦ ሊሆን ይችላል። ለመጀመሪያው ቫይረስ የዳበረው በሽታ የመከላከል አቅም ሁለተኛውን ዙር ከባድ አድርጎት እንደሆነም ይገመታል። የኢስት አንጅሊያው ፕ/ር ፖል ሀንተር “በሁለቱ ህመም መካከል ያለው ጊዜ አጭር መሆኑና ሁለተኛው ዙር ከመጀመሪያው መባሱ አሳሳቢ ነው” ይላሉ። የአሜሪካውን ግልሰብ የተመለከተው ጥናት ምን ይጠቁማል? ለሚለው ምላሽ ለመስጠት ገና ነው ብለዋል ፕ/ር ፖል። https://www.bbc.com/amharic/news-54527534 +sports ሮማን አብራሞቪች ቼልሲን ለመሸጥ ወሰኑ "የቼልሲው ባለቤት ሮማን አብራሞቪች ክለቡን ለመሸጥ ማቀዳቸውን ገለጹ። ባለሃብቱ አብራሞቪች በፕሪሚየር ሊጉ ክለብ ድረ-ገጽ ላይ ባወጡት መግለጫ ""በጣም ከባዱን እና የሚያመውን ውሳኔ"" መወሰናቸውን ተናግረዋል። ሩሲያዊው ""ምንም ዓይነት ብድር እንዲመለስ"" ያልጠየቁ ሲሆን የሽያጩ ገቢም ለጦርነት ተጎጂዎች ይውላል ብለዋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፈጸመችው ወረራ በኋላ አብራሞቪች ቅዳሜ ዕለት እንዳስታወቁት የቼልሲን ""ኃላፊነት እና ተጠሪነት"" ለፋውንዴሽኑ እንደሚሰጡ ተናግረው ነበር። ይህም ክለቡን ከ 1.5 ቢሊየን ፓውንድ በላይ ብድር ውስጥ የዘፈቁት አብራሞቪች ቼልሲን ለሽያጭ ያቀርባሉ የሚል ግምት ፈጠረ። ይህንን ተከትሎም ቢሊየነሩ ሃንስ ጆርጅ ዊስ ክለቡን የመግዛት ዕድል እንደቀረበላቸው ረቡዕ ዕለት ለስዊዘርላንዱ ብሊክ ጋዜጣ ተናግረዋል። ዊስ እንዳስታወቁት አብራሞቪች በፓርላማው የማዕቀብ ስጋት ""ቼልሲን በፍጥነት ለመሸጥ"" እንደፈለጉ ተናግረዋል። የ55 ዓመቱ አብራሞቪች ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ቢነገርም እሳቸው ግን አስተባብለዋል። ""ከሽያጩ የሚገኘው የተጣራ ገንዘብ በሙሉ ለዩክሬን ጦርነት ተገጎጂዎች"" እንደሚሰጥ ተናግረዋል። ቼልሲን ለመግዛት ለአብራሞቪች ጥያቄ እንደቀረበላቸው ቢቢሲ ስፖርት የተረዳ ሲሆን ክለቡም እስከ ሦስት ቢሊዮን ፓውንድ ይገመታል። አብራሞቪች በመግለጫቸው ""ሁሌም ውሳኔዎችን የምወስነው የክለቡን ፍላጎት ከግምት በማስገባት ነው"" ብለዋል። ""አሁን ባለው ሁኔታ ለክለቡ፣ ለደጋፊው፣ ለሠራተኞቹ እንዲሁም ለክለቡ ስፖንሰሮች እና አጋር አካላት ይጠቅማል ብዬ ስለማምን ክለቡን ለመሸጥ ወስኛለሁ።"" በማለት ገልጸዋል። ""የክለቡ ሽያጭ ፈጣን ሳይሆን ተገቢውን ሂደት የሚከተል ነው። ምንም ዓይነት ብድር እንዲከፈልም አልጠይቅም።"" ""ከሽያጩ የተገኘው ገንዘብ በሙሉ የሚለግስበት የበጎ አድራጎት ድርጅት እንዲያቋቁም ለቡድኔ መመሪያ ሰጥቻለሁ። ፋውንዴሽኑ በዩክሬን በጦርነት ተጎጂ ለሆኑ ጥቅም ላይ ይውላል።"" ቢቢሲ ስፖርት እንደተረዳው ከሆነ የቼልሲ ፋውንዴሽን ክለቡን ለመቆጣጠር እስካሁን አልተስማማም። አብራሞቪች ቅዳሜ ዕለት ባወጡት መግለጫ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈፀመችውን ወረራ ባለመጥቀሳቸው ተወቅሰዋል። የቡድኑ ተጫዋቾች ዜናው ቀደም ብሎ እንዲደርሳቸው አልተደረገም ተብሏል። ተጫዋቾች ዜናውን የሰሙት ከሉተን ታውን ከሚያደርጉት የአምስተኛው ዙር የኤፍኤ ካፕ ጨዋታ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ ነው። በጨዋታው ቡድኑ ከመመራት ተነስቶ 3 ለ 2 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜው ተቀላቅሏል። አብራሞቪች ቼልሲን እአአ በ2003 በ140 ሚሊዮን ፓውንድ መግዛታቸው ይታወሳል። ባለሃብቱ በመግለጫቸው ግዢው ""ለንግድም ሆነ ለገንዘብ ሲባል የተደረገ አልነበረም። ለስፖርቱ እና ለክለቡ ንጹህ ፍቅር ሲባል የተደረገ ነ��"" ብለዋል። አብራሞቪች በክለቡ ውጤታማ ነበሩ? ክለቡን ከገዙበት ጊዜ ጀምሮ ቼልሲ ከመለወጥ ባለፈ በፕሪሚየር ሊጉ በትልቅ ደረጃ ለመወዳደር ገንዘብ ምን ያህል እንደሚያስፈልግ ምሳሌ ሆኗል። አብራሞቪች ለክለቡ ከ 1.5 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ብድር የወሰዱ ሲሆን ይህም ትልቅ ስኬት አስመዝግቧል። በእርሳቸው የባለቤትነት ክለቡ የሚቻለውን ሁሉ ትልልቅ ዋንጫ ማንሳት ችሏል። የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ሁለት ጊዜ፣ ፕሪሚየር ሊግ እና ኤፍኤ ካፕ አምስት አምስት ጊዜ፣ ዩሮፓ ሊግ ሁለት ጊዜ እና የሊግ ዋንጫን ሦስት ጊዜ ማንሳት ችሏል። ባለፈው ነሐሴ የዩኤፋ ሱፐር ካፕን ያሸነፉ ሲሆን በየካቲት ደግሞ የመጀመሪያውን የዓለም የክለቦች ዋንጫን አንስተዋል። 13 የተለያዩ አሰልጣኞችን የሾመ ሲሆን ክለቡ በዝውውር ገበያው ሁለት ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ወጪ አድርጓል። የቼልሲ ሴቶች ቡድንም በአብራሞቪች ስር ውጤማ መሆን ችሏል። የሴቶችን ሱፐር ሊግ አራት ጊዜ ሲያነሳ የሴቶችን ኤፍ ኤ ካፕ ሦስት ጊዜ ማሸነፍ ችሏል። ባለለፈው ዓመትም ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ደርሷል። የክለቡ ስም በመግነኑ እንደ አውስትራሊያዊቷ ሳም ኬር እና ዴንማርካዊው አጥቂ ፔርኒል ሃርደር ያሉ የዓለም ኮከቦች ወደ ክለቡ ሊዘዋወሩ ችለዋል። አብራሞቪች ለምን መሸጥ መረጡ? ሌሎች የሩሲያ ቢሊየነሮች ንብረታቸው ከመታገድ ባለፈ የአውሮፓ ህብረት ማዕቀብ ዒላማ ሆነዋል። ይህ ደግሞ ከኤቨርተን ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሩሲያዊው ቢሊየነር አሊሸር ኡስማኖቭንም ያጠቃልላል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት በአብራሞቪች ወይም በኡስማኖቭ ላይ እስካሁን እገዳ አልጣለም። የሌበር ፓርቲ ተወካይ የሆኑት ክሪስ ብራያንት ማክሰኞ ዕለት ለህዝብ እንደራሴዎች አራርሞቪች ""ማዕቀብ በጣም በመፍራቱ ቤቱን ነገ ሊሸጥ ነው። ሌላውም የመኖሪያ አፓርታማው ይቀጥላል"" ብለዋል። ረቡዕ ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጥያቄዎችን ባስተናገዱበት ወቅት የሌበር ፓርቲ መሪው ኬይር ስታርመር አብራሞቪች ለምን ማዕቀብ እንዳልተጣለባቸው ጠይቀው ነበር። ""አሁን ባለው ደረጃ በማንኛውም ግለሰብ ጉዳዮች ላይ አስተያየት መስጠት ተገቢ አይደለም"" ሲሉ ጆንሰን ምላሽ ሰጥተዋል። የሩሲያዊው ቃል አቀባይ ግን የሌበር ፓርቲ መሪውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ አብራሞቪች ምንም ማእቀብ የሚያስጥል ነገር አላደረጉም ብለዋል። ዊስ አክለውም ""አብራሞቪች በእንግሊዝ ያሏቸውን ቪላዎቻቸውን በሙሉ ለመሸጥ እየሞከሩ ነው። ቼልሲንም በፍጥነት መሸት ይፈልጋሉ"" ብለዋል። ""እኔ እና ሌሎች ሶስት ሰዎች ቼልሲን ከአብራሞቪች ለመግዛት ማክሰኞ ቀርቦልን ነበር።"" የአብራሞቪች ቃል አቀባይ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።" https://www.bbc.com/amharic/news-60596117 +sports እግር ኳስ፡ ህይወቱ በሱስ ምክንያት የተመሳቀለው የፕሪምየር ሊግ ቡድን አምበል """በጣም ብዙ እርዳታ አስፈልጎኝ ነበር። ወደ ሌላ አይነት ሕይወት ለመሸጋገር ከብዶኝ ነበር፤ ምክንያቱም ህይወቴን በሙሉ እግር ኳስን ብቻ ነበር የማውቀው። ከእንደዚያ አይነት ቦታ መውደቅ ከባድ ነው።"" ክላውስ ሉንደክቫም ቁርጭምጭሚቱ ላይ ባጋጠመው ተደጋጋሚ ጉዳት ምክንያት በአውሮፓውያኑ 2008 ከእግር ኳስ እራሱን እንዲያገል መገደዱን በተመለከተ የተናገረው ነው። ጫማውን ከሰቀለ በኋላ ደግሞ የአልኮልና የአደንዛኝ እጽ ሱሰኛ ሆነ። ክላውስ በወቅቱ የ35 ዓመት እግር ኳስ ተጫዋች የነበረ ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በሚጫወተው ሳውዝሃምፕተን ውስጥ እጅግ የላቀ ብቃት አላቸው ከሚባሉት ተጫዋቾች መካከል ነበር። ለቡድኑ ከ400 በላይ ጨዋታዎች ላይ የተሰለፈ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 1996 ነበር ከ���ስኬ በርገን ሳውዝህምፕተንን የተቀላቀለው። በሳውዝህምፕተን ደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ክብርና መወደድን ማግኘት ችሏል። ክልጅነቱ ጀምሮ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መጫወት ህልሙ እንደነበር በተደጋጋሚ ይገልጻል። ""የመጀመሪያም የመጨረሻም ፍላጎቴ በእንግሊዝ እግር ኳስ መጫወት ነበር"" ይላል። ""የልጅነት ህልሜ ነው እውን የሆነው። እውነቱን ለመናገር ያንን ያክል ጊዜ ተፎካካሪ ሆኜ እቆያለሁ ብዬ አላስብኩም ነበር"" ይላል የኖርዌይ ዜግነት ያለው ክላውስ። ከኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን ጋር በመሆንም 40 ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችሏል። ''ለእኔ ከሌላ አገር መጥቶ ለሳውዝህምፕተን ለ12 ዓመታት መጫወትና የቡድኑ አምበል ለመሆን መቻል ልዩ እና ትልቅ ቦታ ያለው ነገር ነው"" ይላል። በ2008 (እአአ) 18 ሺህ የሳውዝሀምፕተን ደጋፊዎች በተገኙበት ቡድኑ ሴልቲክን ገጥሞ ነበር። በወቅቱ ክላውስ ከነጉዳቱ ነበር ወደ ሜዳ ገባው። ነገር ግን የመጀመሪያዎቹን ጥቂት ደቂቃዎች ከተጫወተ በኋላ ተቀይሮ ሲወጣ በከፍተኛ ጭብጨባ ነበር የተሸኘው። ያቺ ዕለት ለክላውስ የእግር ኳስ ሕይወቱ ማብቂያ የመጀመሪያዋ ነበረች። ከመጨረሻው ጨዋታ አንድ ዓመት በኋላ ደግሞ ክላውስ ሉንደክቫም ሙሉ በሙሉ ሌላ ዓለም ውስጥ ገብቶ በሱስ የተጠመደ ሰው ሆኖ ነበር። የቀን ተቀን ሕይወቱን ይመራበት የነበረው የታቀደና በስልጠና የታገዘ የኑሮ ዘይቤው ሲቀየር እግር ኳስ ከህይወቱ ወጣ። ለበርካታ ዓመታት የሚያውቀው ስልጠና ማድረግ፣ ለጨዋታ መጓዝ፣ እግር ኳስ መጫወት፣ ከጉዳት ማገገም የሚባሉት ነገሮች ታሪክ ሆነው ቀሩ። ከእግር ኳስ በኋላ በሳውዝሃምፕተን የነበረው ቆይታ በተስፋ መቁረጥና በጭንቀት የተሞላ ነበር። ይህንን አስጨናቂ ጊዜ ለማለፍም ፊቱን ወደ አልኮልና ወደ አደንዛዥ እጽ አዞረ። ""በሕይወቴ በርካታ ስህተቶችን ሰርቻለሁ። አሁን መለስ ብዬ ሳስበው በጣም ከባድ ጊዜ ነበር። በተለይ እግር ኳስ ተጫዋቾች ጠዋት ከእንቅልፋቸው ሲነሱ ተስፋና ትርጉም የሚሰጣቸው ነገር ሊኖር ይገባል። ከእግር ኳስ በኋላም ቢሆን የሚሰሩት ነገር መኖር አለበት።"" ''እኔ በወቅቱ ሁሉም ነገር ነበረኝ። በጣም ብዙ ገንዘብ ነበረኝ፣ በጣም ምርጥ ቤተሰብ እና መኖሪያ ቤት ነበረኝ። ኖርዌይ ውስጥም የራሴ መኖሪያ ቤት ነበረኝ። ጀልባዎች፣ መኪናዎች፤ ሁሉም ነገር ነበረኝ። ነገር ግን በደግንገት ድብርት ውስጥ ገባሁና ብቸኝነት ተሰማኝ። የሚፈልገኝ ሰው እንደሌለ ተሰማኝ።"" ""የእግር ኳስ መልበሻ ክፍሉን ናፈቅኩት። በየሳምንቱ ከቡድን ጓደኞቼ ጋር መሰልጠንና መጫወት አማረኝ። ይሄ ሁሉ ነገር በድንገት ከህይወቴ ሲጠፋ በጣም ከባድ ጊዜን እንዳሳልፍ አደረገኝ።"" በርካታ እግር ኳስ ተጫዋቾች ጫማቸውን ከሰቀሉ በኋላ በተመሳሳይ የህይወት መስመር ውስጥ ሲገቡ ይታያሉ። እጅግ በተራቀቀውና ትንሿ ስህተት እንኳን ትልቅ ዋጋ በምታስከፍልበት የእግር ኳስ ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን በየቀኑ መጣርና መልፋት ግድ ይላል። ይሄ ሁሉ ልፋትና የዕለት ተዕለት ስልጠና በአንድ ጊዜ ሲቋረጥ ተጨዋቾች ከፍተኛ ድብርትና የህይወት መመሰቃቀልና ትርጉም ማጣት ውስጥ ይገባሉ። ምንም እንኳን ልክ እንደ ክላውስ አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች የሚፈልጉት ነገር በሙሉ የተሟላላቸው ቢሆንም ከድብርት ግን ማምለጥ አይችሉም። ""በየቀኑ ስኬታማ ለመሆን መጣር፣ የውስጥ አቅምን አሟጥጦ መጠቀም፣ በየቀኑ እና በየሳምንቱ ምርጥ ሆኖ ለመገኘትና በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎችን ለማስደስት የሚደረገው ትግል በጣም አስደሳችና ሰውነትን የሚያነቃቃ ነው"" ይላል ክላውስ። ክላውስ ሉንደክቫም ከኖርዌዩ ኤስኬ ብራን ወደ ሳውዝሃምፕተን የተቀላቀለው በ350 ሺህ ፓውንድ ነበር። በነበረው የእግር ኳስ ህይወትም ሁሉም ተጫዋት ሊተማመንበት የሚችል አይነት ሰው ነበር። ምርጥና ቀጣይነት ያለው አቋም የሚያሳይ ተጫዋች ነበር። ነገር ግን ከእግር በኋላ የነበረው ማንነት ከመጀመሪያው በፍጹም የተለየ ነበር። በአንድ ወቅት እንደውም በፖሊስ ቁጥጥር ስር እስከመዋልና በሱሱ ምክንያት ሆስፒታል እስከመግባት ደርሶ ነበር። ""እግር ኳስ ካቆምኩኝ በኋላ ምናልባት ለትንሽ ዓመታት ቀለል ያለ ሕይወት መኖር አለብኝ ብዬ ለእራሴ ነገርኩት። በወቅቱ በርካታ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ እሳተፍ ነበር። በሄድኩበት ቦታ ሁሉ መጠጥ ነበር። በዚያውም ለመዝናናት እየተባለ መጠጥ ቤት መሄድ ተጀመረ።"" ""ወዲያው እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ። ከባድ ድብርት ውስጥም ገባሁ። ሳላስበው ከዚህ በፊት አይቼው በማላውቀው ሁኔታ እራሴን ተስፋ ቆርጬ አገኘሁት። ፊቴንም ወደ መጠጥና ኮኬይን አዞርኩኝ። ነገር ግን የአልኮልና የኮኬይን ጥገኛ ስሆን ነገሮች እንደውም እየከፉ መጡ።"" ""በየቀኑ መጠጣትና አደንዛዥ እጽ መጠቀም ጀመርኩ። ባለቤቴ እና ሁለት ሴት ልጆቼ ወደ ኖርዌይ ተመለሱ።"" ""ከአንዴም ሁለት ጊዜ እራሴን ለማጥፋት ሞክሬያለው። በጣም ከባድ ጭንቀት ውስጥ ገባሁና ሁሉም ነገር ትርጉም አጣብኝ። ድሮ የማውቀው ማንነቴ ጠፋብኝ። በወቅቱ የመረጥኩት ሁሉንም ለመርሳት አልኮል መጠጣት ነበር። ጥፋተኝነቴንና ሃፍረቴን ለመደበቅ ሁሌም መስከር ነበረብኝ።"" ምንም እንኳን ክላውስ ሉንደክቫም በጣም አስቸጋሪ የህይወት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ለመረዳት ብዙ ጊዜ ቢፈጅበትም እርዳታ ለመጠየቅ ግን አልቦዘነም ነበር። የቀድሞው የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ፒተር ኬይ ወዳቋቋመው የስፖርተኞች ክሊኒክ ገባ። ""የቀድሞው ሳውዝሀምፕተን አምበል እና በርካቶች እንደ ጀግናቸው የሚቆጥሩት የነበረው ሰው እንደዚህ ተሰብሮ ማየት ከባድ ነው። በወቅቱ በጣም ከባድ ቢሆንም አብረውኝ ለነበሩ ሰዎች ስሜንና ያለብኝን ችግር ስናገር ብዙዎቹ ይደነግጡ ነበር።"" ረጅም ጊዜ የፈጀው የማገገም ሂደት ቀላል አልነበረም። ተመልሶ አልኮል መጠጣትና ኮኬይን መጠቀምን ጨምሮ ሌሎች አስቸጋሪ ፈተናዎች ነበሩ በመሀል ላይ። ነገር ግን ቆራጥ መሆንና ሕይወትን ለመቀየር እራስን ማሳመን ወሳኝ መሆኑን ክላውስ ይናራል። ""በጣም ብዙ ውጣ ውረዶች ነበሩ። ሁለት ጊዜ ወደ ሱሴ ተመልሼ ነበር። አሁን ጥቂት ዓመታት አልፎታል ግን ሱሰኛ መሆኔን አምኜ ለመቀበል ትንሽ ጊዜ ፈጅቶብኝ ነበር።"" ""በነበረኛ ቆይታ ያለ አልኮልና አደንዛኝ እጽ ጥሩ ሕይወት መኖር እንደሚቻል እየገባኝ መጣ። በጣም ደስተኛ ሆንኩኝ፤ በእራሴም ኮራሁ። ምንም እንኳን ያሳለፍኩት ጊዜ ቀላል ባይሆንም አሁን ካለሁበት ሁኔታ ላይ በመገኘቴ በጣም እድለኛ ነኝ።"" ምንም እንኳን ክላውስ ሉንደክቫም እና ባለቤቱ በአውሮፓውያኑ 2014 ላይ ትዳራቸውን አፍርሰው ፍቺ ቢፈጽሙም አሁን ጥሩ የሚባል ግንኙነት ያላቸው። ከሁለቱ ሴት ልጆቹ ጋር ያለውም ግንኙነት ከምን ጊዜውም በበለጠ ጥሩ የሚባል ነው። ክላውስ ለሳውዝሀምፕተን በሚጫወትበት ወቅት ስለ አእምሮ ጤና እና ጭንቀት ማውራት ብዙም የተለመደ ነገር አልነበረም። ነገር ግን አሁን ነገሮች በፍጥነት እየተቀየሩ ይመስላል። ሰዎች በህይወታቸው የሚገጥማቸውን ጭንቀትና አስቸጋሪ ነገር ማጋራት ጀምረዋል። ክላውስ በአሁኑ ጊዜ አደንዛዥ እጽ የሚጠቀሙና ሱሰኛ የሆኑ ሰዎችን በመርዳት ላይ ተሰማርቶ ይገኛል። ከቀድሞ ክለቡ ሳውዝሀምፕተን ጋር በተመሳሳይ ጉዳዮች ዙሪያ ለመስራትም ፍላጎት አለው። ከቀድሞ ቡድኑም ጋር ግንኙነት የፈጠረ ሲሆን በቡድኑ ታሪክ ስማቸው ከሚጠቀስ ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደመሆኑ፤ ተጫዋቾች ሊያጋጥሟችው ስለሚችሉ ፈተናዎች ግንዛቤ ማስጨጥ ደግሞ ህልሙ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-55287481 +health ኮሮናቫይረስ፡ በኖርዌይ የአንዲት መርከብ ተሳፋሪዎችና ሠራተኞች በቫይረሱ ተያዙ "በኖርዌይ የመዝናኛ መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ቢያንስ 40 መንገደኞችና ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ኤምኤስ ሮልስ አሙንድሰን በተባለችው መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች መንገደኞች ደግሞ ለይቶ ማቆያ ገብተው የምርመራ ውጤታቸውን እየተጠባበቁ እንደሆነ የመርከቧ ባለንብረት ተናግረዋል። ሁርቲግሩትን የተባለ የኖርዌይ ድርጅት ንብረት የሆነችው መርከብ በትሮምሶ ወደብ ያረፈችው ባሳለፍነው አርብ ነበር። በዚህም ሳቢያ ድርጅቱ ሁሉንም የመዝናኛ መርከቦቹን እንዳይንቀሳቀሱ አግዷል። የድርጅቱ ኃላፊ ዳንኤል ስካይልዳም ""አሁን ትኩረት ያደረግነው ባልደረቦቻችንና እንግዶቻችንን ለመንከባከብ የምንችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ነው"" ሲሉ በመግለጫቸው ተናግረዋል። አራት የመርከቡ ሠራተኞች የኮሮናቫይረስ ምልክት ታይቶባቸው አርብ ዕለት መርከቧ ወደብ ላይ ካረፈች በኋላ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በኋላ ላይ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ158 ሠራተኞች መካከልም ሌሎች 32ቱ በቫይረሱ መያዛቸው የምርመራ ውጤታቸው አመላክቷል። ይሁን እንጂ 180 የሚሆኑ መንገደኞች ከመርከቧ እንዲወጡ የተፈቀደላቸው ሲሆን በባለሥልጣናት ቁጥጥር እንዲመረመሩ ተደርጓል። ሁሉም መንገደኞች ራሳቸውን እንዲለዩ መደረጉንም የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ከሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ በመርከቧ ጉዞ ላይ ከነበሩ 387 ተሳፋሪዎች መካካልም እስካሁን በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠው አምስት እንደሆኑ ተገልጿል። የጤና ባለሥልጣን የሆኑት ሊን ቮልድ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት አሁን ከተከሰተው የቫይረስ ሥርጭት ጋር ተያይዞ በርካታ ሰዎች ቫይረሱ ሊገኝባቸው እንደሚችል ገልፀዋል። መርከቧ በአርክቲክ በሚገኘው ስቫልባርድ ለአንድ ሳምንት የቆየች ሲሆን በኢንግላንድና ስኮትላንድ የሚገኙ ወደቦችን ደግሞ መስከረም ላይ ለመጎብኘት እቅድ ይዛ ነበር ተብሏል። ይሁን እንጂ ኢንዱስትሪው በወረርሽኙ በመመታቱ ሁሉም የወደፊት ጉዞዎች ስለመኖራቸው የታወቀ ነገር እንደሌለ ተገልጿል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ወረርሽኙ በመርከቦች ላይ በመዛመቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በባሕር ላይ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ መቆየታቸው ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/53640749 +sports በካሜሮን ዕድሜያቸውን ያጭበረበሩ እግር ኳስ ተጫዋቾች ሊቀጡ ነው በካሜሮን ዕድሜያቸውን አጭበርብረዋል ተብለው የተጠረጠሩ አርባ አራት የእግር ኳስ ተጫዋቾች ምርመራ ተከፍቶባቸዋል። ተጫዋቾቹ ከዕድሜያቸው በተጨማሪ ማንነታቸውንም አጭበርብረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ከአማተር ክለቦች የተውጣጡ ሲሆን ጥቂቶቹ ደግሞ የብሄራዊ ሊጎች ተጫዋቾች መሆናቸውን የካሜሮን እግር ኳስ አስተዳዳሪ ፌካፉት አስታውቋል። ተጫዋቾቹ በማጭበርበር ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ለስድስት ወር ያህል ከየትኛውም ጨዋታ የመታገድ  ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የፌካፉት ባለስልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ተጫዋቾቹ እድሜያቸውንና ማንነታቸውን ሲያጭበረብሩ ተባባሪ ናቸው ተብለው የተከሰሱ በርካታ የክለብ ፕሬዚዳንቶች ፌካፉት በሚያደርገው ማጣራት እንዲገኙ ተጠርተዋል። ፌዴሬሽኑ ምርምሩንና መረጃዎችን የሚሰማው በዝግ ነው ተብሏል። በካሜሮን የዕድሜ ማጭበርበር ክስ የተለመደ ነው። በአውሮፓውያኑ 2016፣ 14 የካሜሮን  ተጫዋቾች በአመት ሁለት ጊዜ በሚደረገው የዩ 17 የአፍሪካ ዋንጫ ከመካሄዱ ጥቂት ቀናት በፊት ታግደዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cl7gxeyvdggo +health አስትራዜኒካ የደም መርጋት ያስከትላል? የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱን ሊገመግም ነው የዓለም ጤና ድርጅት ብዙ እየተወራበት ያለውን የኦክስፎርድ አስትራዜኒካን ውጤታማነትን በተለይም ከደም መርጋት ጋር ያለውን ተያያዥነት በክትባት ሊቃውንት ሊያስገመግም ነው፡፡ ክትባቱ ውጤታማ ነው ከተባለ በኋላ ብዙ አገራት ለሕዝባቸው ማደል ጀምረው ነበር፡፡ ሆኖም ደም እንዲረጋ ያደርጋል የሚል መረጃ መውጣቱን ተከትሎ ብዙ የአውሮፓ አገራት ለጊዜው የክትባት እደላው እንዲቆም ወስነዋል፡፡ አንዳንድ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ደማቸው የመርጋት ምልክት በማሳየቱ ነው ስጋት የተፈጠረው፡፡ እነዚህ የክትባት ሊቃውንት ለግምገማ የሚቀመጡት ዛሬ ማክሰኞ ነው፡፡ በተመሳሳይ የአውሮጳ መድኃኒት ኤጀንሲ ኃላፊዎችም ዛሬ በጉዳዩ ላይ ለመምከር ይሰበሰባሉ ተብሏል፡፡ የክትባት ሊቃውንት ቡድን ሁኔታዎችን ከገመገመ በኋላ ኦክስፎርድ አስትራዜኒካ ክትባት ለሰዎች ቢሰጥ የከፋ ጉዳት እንደሌለው የሚያትት መግለጫ ሐሙስ ያወጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ በአውሮፓ ኅብረትና በታላቋ ብሪታኒያ በድምሩ 17 ሚሊዮን ዜጎች አስትራዜኒካ ክትባትን የወሰዱ ሲሆን ከዚህ ሁሉ ተከታቢ መሀል የደም መርጋት አጋጠማቸው የተባሉትን ሰዎች ቁጥር ከ40 አይበልጥም፡፡ አሁን ይህ ክትባት በእርግጥ የደም መርጋትን ያመጣል ወይ የሚለው በተጨባጭ የታወቀ ባይሆንም ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን እና ስፔንን ጨምሮ በርካታ አገራት ክትባቱን ለጊዜው ይቆየን ብለዋል፡፡ ቤልጂየም፣ ፖላንድ፣ ቼክ ሪፐብሊክና ዩክሬን ግን ክትባቱን ለሕዝባቸው ማደላቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ክትባቱ በእርግጥ የደም መርጋት ያስከትላል በሚለው ላይ አዲስ ምርመራ መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡ ባለፈው ማክሰኞ የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ክትባቱ ደም እንደሚያረጋ የተገኘ አንዳችም ተጨባጭ መረጃ የለም ብለው ነበር፡፡ በርከት ያሉ የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት ክትባቱን መውሰድ የጎንዮሽ ጉዳቱን በመፍራት ካለመውሰድ የተሻለ ነው፡፡ ክትባቱ ደም እንዲረጋ ያደርጋል የሚሉት አጋጣሚዎችም ከጠቅላላው ተከታቢ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ይላሉ፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-56411449 +business የጓቲማላ ተቃዋሚዎች ምክር ቤቱን በእሳት አቃጠሉ "በመቶዎች የሚቆጠሩ ጓቲማላውያን ተቃዋሚዎች የአገሪቱን ምክር ቤት ህንፃ መዝብረው እሳት ለቀውበታል ተብሏል። ፖሊስም ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ተጠቅሟል። የተወሰነው የህንፃው ክፍልም በቃጠሎው ጉዳት ደርሶበታል። የእሳት አደጋ አገልግሎት ሰራተኞች እሳቱን ማጥፋት ቢችሉም በርካታ ሰዎችም በጭሱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ህክምናም እየተደረገላቸውይገኛሉ። ከሰሞኑ ምክር ቤቱ ያፀደቀውን በጀት በመቃወምም ነው ተቃውሟቸውን እየገለፁ ያሉት። በጀቱ ትልልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ከመንግሥት ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባንያዎች እንዲሰሯቸው በማድረግ ቅድሚያ ሰጥቷል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ የማህበራዊና ምጣኔ ኃብታዊ ጫና የደረሰባቸውን የማህበረሰቡ አካላትን ችላ ብሏልም በማለት እየወቀሱ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ በትምህርትና በጤና ላይ ከፍተኛ የሆነ የበጀት ቅነሳ መደረጉም ተቃዋሚዎችን ያበሳጨ ጉዳይ ሆኗል። ሌላው ተቃዋሚዎቹ ዋነኛ ቁልፍ ጉዳይ ብለው የሚያነሱት ጓቲማላ በኤታና ኢዮታ በተባሉት አውሎ ንፋስ መመታቷን ተከትሎ ህዝቧ እንዲህ አይነት ውርጅብኝ ባለበት ወቅት ፓርላማው ሆን ብሎ የወሰነው ውሳኔ ነው ይላሉ። ፓርላማው ህዝቡ በተደናገረበት ወ���ት ይህንን ውሳኔ መወሰኑም አስተችቶታል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት አሌሃንድሮ ጊማቴይ ከስልጣናቸው እንዲለቁ ተቃዋሚዎች በመጠየቅ ላይ ናቸው። በትናንትናውም እለት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተሳተፈበት የተቃውሞ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን በአንፃራዊነትም ሰላማዊ ነው ተብሏል። ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጉይሌርሞ ካስቲሎ በበኩላቸው በጀቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ የገለፁ ሲሆን እሳቸውም ሆነ ፕሬዚዳንቱ ""ለአገሪቱ ደህንነት ሲባል ከስልጣን መውረድ አለብን"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55033851 +health ኮሮናቫይረስ፡ ብዙ ያልተነገረለት ኮቪድ-19 በአንጎላችን ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ምንድን ነው? "ስትሮክ፣ ቅዠት፣ ጭንቀት፣ ግራ መጋባት፣ ድካም ፣ እያለ ይቀጥላል። ኮቪድ-19 የመተንፈሻ አካላት ላይ ብቻ ጉዳት የሚያደርስ ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል። እያንዳንዱ ሳምንት ባለፈ ቁጥር ኮሮናቫይረስ ዘርፈ ብዙ አእምሯዊና አካላዊ ጉዳቶችን ማስከተል ይጀምራል። ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጡ በርካታ ሰዎች በመጀመሪያ አካባቢ ብዙም የሚሰጋ ህመም የማይሰማቸው ሲሆን፤ ቀስ በቀስ ግን ማስታወስ አለመቻልና ድካምን የመሳሰሉ ጠንከር ያሉ ምልክቶች ማሳየት ይጀምራሉ። ፖል ማይልሪያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሁለት ከባድ የሚባሉ ስትሮኮች [የአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ] አጋጥመውታል። የ64 ዓመቱ ፖል በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የኮምዩኒኬሽንስ ኃላፊ ሲሆን እምብዛም ስጋት ውስጥ ሊከተው ሚችል የጤና እክል አልነበረበትም። በለንደኑ የአንጎልና የአንጎል ቀዶ ህክምና ብሔራዊ ሆስፒታል ውስጥ እጅግ ከፍተኛ የጤና መሻሻል ያሳየ የኮሮረናቫይረስ ታማሚ ሆኗል። ካጋጠመው ስትሮክ በኋላም ፖል ጥሩ የሚባል መሻሻል ታይቶበታል። የመጀመሪያው ስትሮክ ያጋጠመው በሆስፒታል የጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እያለ ነበር። በዚህ ምክንያት ሕይወቱ ልታልፍበት የምትችለበት እድልም ከፍተኛ ነበር። ለዚህም ሲባል ደም የሚያቀጥን መድኃኒት እንዲወስድ ተደርጎ ነበር። ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ስትሮክ አጋጠመው። ሁለተኛው ግን በጣም የከፋና ሕይወቱን ትልቅ አደጋ ውስጥ የከተተ ነበር። አማካሪ የአንጎል ሐኪም ሆኑት ዶክተር አርቪንድ ቻንድራቴቫ፤ ፖል በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታሉ ሲመጣ ሥራቸውን ጨርሰው እየወጡ ነበር። ''ፖል ፊቱ ላይ ግራ መጋባት ይስተዋልበት ነበር። መመልከት የሚችለው በአንድ አቅጣጫ በኩል ብቻ ነበር፤ ተንቀሳቃሽ ስልኩን ለመጠቀምም ሲቸገርና የይለፍ ቃሉን ማስታወስ አቅቶት ግራ ሲጋባ ነበር'' ብለዋል ዶክተሩ። ዶክተር አርቪንድ እንደሚሉት በፖል ጭንቅላት ውስጥ አጋጥሞ የነበረው የደም መርጋት ከዚህ በፊት አይተውት የማያውቁት አይነት እንደሆነ ይናገራሉ። ፖል በተደረገለት ምርመራ የደም መርጋት ምልክቶች ታይተውበታል። በምርመራው የተገኘው ውጤትም አጋትሟቸው በማያውቁት ሁኔታ እጅግ የተለየና አሳሳቢ ነበር። ""በሕይወቴ እንዲህ ያለ ውስብስብና ከፍተኛ ከፍተኛ ደም መርጋት ሁኔታ ተመልክቼ አላውቅም"" የሚሉት ዶክተር አርቪንድ ኮሮረናቫይረስ የፖል ደም በእጅጉ የተጣበቀ እንዲሆን እንዳደረግ ይገልጻሉ። በእንቅስቃሴ ገደቡ ጊዜ ስትሮክ አጋጥሟቸው ድንገተኛ ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ቀንሶ ነበር። ነገር ግን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የአንጎል ህክምና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ስትሮክ ያጋጠማቸው ስድስት ሕመምተኞችን አክመዋል። ለአደጋው መንስኤ የነበረው በሰውነት እና በአንጎል ውስጥ እብጠት የሚያስከትሉ የሰውነት በሽታ ተከላካይ ሕዋሳት በጣም ከመጠን በላይ መበራከት ነው። ዶክተር አርቪንድ የፖልን አንጎል የውስጥ ክፍልን የሚያሳዩ ምስሎችን ሲመለከቱ በቫይረሱ ምክንያት የማየት አቅሙ መዳከሙን፣ ማስታወስ እንደሚቸግረው፣ መናገር እንደሚከብደውና ነገሮችን ማስተዋል ከባድ እንደሚሆንበት አስተውለዋል። ያጋጠመው ስትሮክ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ሐኪሞች በሕይወት አይተርፍም ወይም የአካል ጉዳተኛ ይሆናል ብለዋ ገምተው ነበር። ፖልም ቢሆን ""ከሁለተኛው ስትሮክ በኋላ ባለቤቴ እና ሴት ልጆቼ አበቃለት ብለው እንደገና ደግመው እንደማያዩኝም ገምተው ነበር'' ሲል ተናግሯል። ''ዶክተሮቹ ምንም ማድረግ የሚችሉት ነገር እንደሌለና ያለው አማራጭ መጠበቅ ብቻ እንደሆነ ነገሯቸው። ነገር ግን እኔ በሆነ መንገድ ተረፍኩኝ፤ ጤናዬም ቀስ በቀስ መስተካከል ጀመረ።'' ፖል እየተሻለው መሆኑን ካሳዩ ነገሮች መካከል ከነርሶቹ ጋር በእንግሊዝኛ የጀመረውን ንግግር በፖርቹጊዝ መጨረስ መጀመሩ ነበር። ፖል ስድስት ቋንቋዎችን የሚናገር ሲሆን ከስትሮኩ በኋላ ጭንቅላቱ ቀድሞ የተማራቸውን ነገሮችና በዚህ ሁኔታ ውስጥ ቋንቋዎችን ማስታወስ መጀመሩ ለዶክተሩ አበረታች ውጤት ነበር። ፖል እንደሚለው ከስትሮኩ በኋላ እንደቀድሞው በፍጥነት ማንበብ ያቃተው ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ነገሮችን ይዘነጋል። ነገር ግን ካጋጠሙት ሁለት ስትሮኮች አንጻር በጭንቅላቱ ላይ የደረሰው ጉዳት ከታሰበው በታች ትንሽ ነው። አካላዊ የማገገም ሂደቱም ቢሆን ተስፋ ሰጪ ነበር። ዶክተሮች ለዚህ በምክንያትነት ያስቀመጡት ደግሞ ከዚህ በፊት የነበረው አካላዊ ብቃት ጥሩ መሆኑን ነው። ""በየቀኑ ለአንድ ሰዓት ያህል ብስክሌት እነዳለሁ፣ በሳምንት ውስጥ የስፖርት ማዘውተሪያ እሄዳለሁ፣ በአቅራቢያ ባለ ወንዝ ውስጥም እዋኛለሁ። ከዚህ በኋላ ግን ሳይክል መንዳት የምችል አይመስለኝም። ነገር ግን መዋኘት መቀጠል የምችል ይመስለኛል'' ብሏል ፖል። በላንሴት የሥነ አእምሮ ክፍል ባደረገው ጥናት መሰረት በዩናይትድ ኪንግደም ሆስፒታሎች ውስጥ 125 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት የአንጎል ውስጥ ችግር አጋጥሟቸዋል። ግማሽ የሚሆኑት ደግሞ ስትሮክ ያጋጠማቸው ሲሆን የደም መርጋት ችግርና የአንጎል እብጠት እንዲሁም እብደት መሰል ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል። ካናዳዊው የአንጎል ህክምና ተመራማሪው ፕሮፌሰር አድሪያን ኦዊን እንደሚሉት በኮሮረናቫይረስ ምክንያት ከባድ የጤና እክል ካጋጠማቸው በኋላ ሲሻላቸው ወደቤታቸው የሚላኩ ሰዎች ድነዋል ማለት አይደለም። ታማሚዎቹ ወደቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ለበርካታ ሳምንታት ሊቆይ የሚችል የማገገም ሂደት ይጠብቃቸዋል ብለዋል። በዚህም ምክንያት የኮቪድ-19 ታማሚዎች የሚያሳዩት ምልክቶችና አንጎላቸው ላይ የሚስተዋለውን የአጭርና የረጅም ጊዜ ጉዳት በአግባቡ መመርመር ወደፊት ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ፕሮፌሰር አድሪያን ያሳስባሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-53282426 +sports ፊፋ በእንግሊዝ ተጫዋቾች ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት መመርመር ጀመረ "እንግሊዝ ሃንጋሪን 4 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ላይ በተጫዋቾች ላይ የተሰነዘረውን የዘረኝነት ጥቃት ለመመርመር ፊፋ ሥራ መጀመሩ ተነገረ። ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በሃንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ውስጥ በተካሄደው የእግር ኳስ ግጥሚያ ላይ የእንግሊዝ ተጫዋቾቹ ራሂም ስተርሊንግ እና ጁድ ቤሊንግሃም የዘረኝነት ጥቃት ኢላማ ሆነው ነበር። ቡዳፔስት ውስጥ በሚገኘው ፑስካስ አሬና ስታዲየም በተደረገውና እንግሊዝ በሰፊ የግብ ልዩነት ባሸነፈችበት ጨዋታ ወቅት ተጨዋቾቹ ላይ የተለያዩ ነገሮች ከተመልካቾቹ ተወርውሮባቸዋል። ይህም የተከሰተው በጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ነበር። ከክስተቱ በኋላ ተጫዋቾቿ ላይ ጥቃት የተሰነዘረባት እንግሊዝ ድርጊቱን ""ፈጽሞ ተቀ���ይነት የሌለው"" ስትል አውግዛዋለች። ለጀርመኑ ቡድን ቦሪሲያ ዶርትሙንድ የመሃል መስመር ተጫዋች የሆነው የ18 ዓመቱ ቤሊንግሃም ከጥቃቱ በኋላ የዘረኝነት ጥቃቱን በተመለከተ ትዊተር ላይ እንዳሰፈረው ""የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ተገቢውን የቅጣት እርምጃ ካልወሰዱ ድርጊቱ የጨዋታው አካል ሆኖ ይቀጥላል። ጥላቻ እንዲሰፍን ማድረግ የለብንም።"" ብሏል። የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንም ""እንዲህ አይነቱ አሳፋሪ ድርጊት እስከ መጨረሻው ከእግር ኳስ ሜዳዎች እንዲወገዱ በአጥፊዎች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መወሰድ አለበት"" ሲሉ የዓለም እግር ኳስ የበላይ አካል የሆነውን ፊፋን ጠይቀዋል። አርብ ከሰዓት በኋላ ፊፋ እንዳስታወቀው በእግሊዝና በሃንጋሪ ግጥሚያ ወቅት የነበረውን የጨዋታውን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ በድርጊቱ ላይ የሥነ ሥርዓት እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ሂደት መጀመሩን አስታውቋል። ጨምሮም ፊፋ የትኛውንም አይነት ዘረኝነት፣ መድልዎና ጥቃትን አጥብቆ የሚቃወምበት አቋሙ አሁንም ጽኑ እንደሆነ ገልጿል። ""በእግር ኳስ ውስጥ የሚከሰቱ እንዲህ አይነት ተቀባይነት የሌላቸው ተግባራትን ፈጽሞ አይታገስም"" ሲል አቋሙን አሳውቋል። የአውሮፓ የእግር ኳስ ማኅበር (ዩኤፋ) የሃንጋሪ ደጋፊዎች ቀደም ሲል አሳይተውት በነበረው የዘረኝነት ድርጊት ምክንያት ብሔራዊ ቡድኑ ሦስት ጨዋታዎችን በዝግ ስታዲየም እንዲያደርግ ወስኖ ነበር። ነገር ግን የሐሙስ ዕለቱ ጨዋታ በፊፋ አማካይነት የሚደረግ በመሆኑ የዩኤፋ ውሳኔ ተግባራዊ ሳይደረግ ደጋፊዎች በስታዲየም ተገኝተው ጨዋታውን ለመከታተል ችለው ነበር። የአውሮፓ የእግር ኳስ ማኅበር በሃንጋሪ ላይ ቅጣት ጥሎ የነበረው ባለፈው ሰኔ ወር ላይ በነበረ ጨዋታ ወቅት ካጋጠሙ የዘረኝነትና የመድልዎ ተግባራት ጋር በተያያዘ ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-58386459 +politics ክልልነት በጠየቁ የደቡብ አካባቢዎች ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ "በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ስር ያሉ 6 ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ክልል እንሁን ጥያቄ ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 12/2014 ዓ.ም. ባካሄደው 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ በ1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በአንድ ክልል እንጠቃለል ጥያቄ ተቀብሎ ከመረመረ በኋላ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ውሳኔ ተላልፏል። በዚህም የወላይታ፣ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የደቡብ ኦሞ፣ የጌዴኦ፣ የኮንሶ ዞኖች፣ እንዲሁም የደራሼ፣ የአማሮ፣ የቡርጂ፣ የአሌ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በጋራ ''የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል''ን የመመስረት ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠትም የህዝብ ይሁንታ መገኘት ስላለበትም ነው ሕዝብ ውሳኔ የሚካሄደው። በዚህም መሠረት ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አማካኝነት በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ሕዝበ ውሳኔ እንዲያደራጅ እና የሕዝበ ውሳኔው ውጤትም ሪፖርት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲቀርብም ጠይቋል። በተጨማሪም የሕዝበ ውሳኔው ሂደት ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና የሕዝብን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ እንዲጠናቀቅ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ አስተላልፏል። ሌሎቹ የሃድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ ዞኖች እና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል አንድ ላይ እንደሚቀጥሉም ተገልጿል። የስድስት ዞኖች እና የአምስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል የመሆን ጥያቄ በየደረጃው ባሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳ በየብሔረሰብ ምክር ቤቶች ውይይት ተደርጎበትና ጸድቆ የመጣ ሲሆ���፣ ይህንንም ጥያቄ አስመልክቶ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰን እና የሰላም ግንባታ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሲመክርና ሲመረምር ቆይቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል። በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 46/2 ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝበ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ ማንነትና ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን የሚጠቅስ ሲሆን ኮሚቴው ዞኖቹና ወረዳዎቹ ያቀረቡት ጥያቄ ሕገ መንግሥቱን የተከተለ መሆኑንም መርምሯል። በተጨማሪም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በማንኛውም ጊዜ ክልል የመመስረት መብት እንዳላቸው የተደነገገ በመሆኑ የቀረበው ጥያቄ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት አካል እንደሆነ ሕገ መንግሥቱን በመጥቀስ ውሳኔው መተላለፉ ተጠቅሷል። በርካታ የሕዝብ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ባለማግኘታቸው ለግጭት ለሰዎች ሕይወት መጥፋት ለንብረት መውደም መንስኤ ሆኖ የቆየ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር መናገራቸው ተገልጿል። ""ሰላምን ለማስፈን፣ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማኅበረሰብ ለመገንባትና በፍትሃዊነት ላይ የተመሠረተ ልማት ለማፋጠን የሕዝቦች ጥያቄዎች በአፋጣኝ ሊመለሱ ይገባል"" ማለታቸውም ተጠቅሷል። በቅርብ ዓመታት በደቡብ ክልል በተናጠል ክልል የመመስረት ጥያቄ በክልሉ ካሉ ዞኖች እየቀረበ ይገኛል። አለመረጋጋት እና ለሰው ሕይወት መጥፋት ምክንያት ከሆኑት መካከል በሲዳማ እና በወላይታ መከሰቱ ይታወሳል። ሲዳማ በክልልነት በመደራጀት ከደቡብ ክልል የወጣ የመጀመሪያው ዞን በመሆን 10ኛው የአገሪቱ ክልል ለመሆን ችሏል። በማስከተልም የምዕራብ ኦሞ፣ የቤንች ሸኮ፣ የከፋ፣ የዳውሮ፣ የሸካ ዞኖች እና የኮንታ ልዩ ወረዳ በአንድ ላይ ተጣምረው በሕዝበ ውሳኔ 11ኛው፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ተመስርቷል። ከዚህም በኋላ ቢሆን በቀሩት የክልሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ውስጥ በጥምረት አልያም በተናጠል ክልል የመሆን ጥያቄዎች የደቡብ ክልል ዋነኛው ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል። በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስር የሆኑ እና ራሳቸውን የቻሉ ክልሎች ሆነው ለመደራጀት የተለያዩ ጥያቄዎች ሲያቀርቡ የነበሩ ዞኖችን እና ልዩ ወረዳዎች በተለያዩ ክልሎች ስር ለመደራጀት የሚያስችላቸውን ውሳኔ በምክር ቤቶቻቸው አማካኝነት እያሳለፉ ነው። ከ50 በላይ ብሔር ብሔረሰቦችን የያዘው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ከአገሪቱ ትልቅ ከሚባሉት ክልሎች መካከል አንዱ ሆኖ ቆይቷል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c0v4j8l3yqyo +health ኮሮናቫይረስ፡ በቱርክ የኦክስጅን ቬንትሌተር ፈንድቶ የኮሮና ህሙማንን ገደለ "በቱርክ በሚገኝ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ማዕከል የኦክስጅን ቬንትሌተር ፈንድቶ ዘጠኝ የኮሮና ህሙማንን ገድሏል። አደጋው ያጋጠመው ጋዚንቴፕ በምትባለው ግዛት የሚገኘው የሳንኮ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ነው። የቬንትሌተሩም መፈንዳትም በፅኑ ህሙማኑ ክፍል ውስጥ እሳት ማስነሳቱንም የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። አንደኛው ህመምተኛም ወደ ሌላ ሆስፒታል ሊዛወር ሲል ነው የሞተው ተብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ 2 ሚሊዮን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን 17 ሺህ 610 ሰዎችም ህይወታቸውን ማጣታቸውን ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ፍንዳታው ባስከተለው እሳት የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ወዲያውም እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ ተደርጓል። ሟቾቹ ከ56-85 እድሜ የሚገመቱ መሆኑንም ከሆስፒታሉ የወጣው መግለጫ ያሳያል። የኦክስጅን ቬንትሌተር ፍንዳታው እንዴት ተከሰተ ለሚለውም ምርመራ ተከፍቷል። በፅኑ ህሙማን የሚገኙ በርካታ ሌሎች ህመምተኞችም አቅ���ቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታልም ህክምና እንዲያገኙ መወሰዳቸውንም የጋዚያንቴፕ አስተዳደር ቢሮ በመግለጫው ጠቅሷል። ""ባለስልጣናቱ የሚያስፈልገውን እርምጃም እየወሰዱ ነው"" ብሏል መግለጫው። አክሎም በሞቱ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ፣ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝቷል። የቱርክ ፕሬዚዳንት ኢብራሒም ካሊን ቃለ አቀባይም በትዊተር ገፃቸው ""ለቆሰሉት በቶሎ እንዲያገግሙ እንመኛለን"" በማለት ምኞታቸውን አስተላልፈዋል። በባለፈው ወር እንዲሁ በሮማንያ በተነሳ እሳት 10 የኮሮናቫይረስ ህሙማን ህይወታቸው አልፏል። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ለእሳቱ መነሻ የሆነው አንድ የህክምና ቁሳቁስ በእሳት ተያይዞ አቅራቢያ የነበረውን የኦክስጅን ሲሊንደር በማቀጣጠሉ ነው። በጥር ወርም እንዲሁ በሩሲያዋ ቼልያቢንስክ ግዛት በሚገኝ ጊዜያው የኮሮናቫይረስ ሆስፒታል ውስጥ የኦክስጅን ክፍሉ ውስጥ ፍንዳታ በመነሳቱ እሳት አስከትሏል። በቦታው የነበሩ 150 የኮሮናቫይረስ ህመምተኞችም በአስቸኳይ እንዲወጡ መደረጋቸውንም የሩሲያ ድንገተኛና አስከቸኳይ ሚኒስቴር ገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55383518 +health ኮሮናቫይረስ: እስራኤል የፋይዘር ክትባት ውጤታማ ሆኖ ማግኘቷን ገለፀች "ከእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የፋይዘር ክትባት የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን 94 በመቶ የመከላከል አቅም አለው። ይህም ክትባቱ በክሊኒክ ውስጥ በተደረጉለት ሙከራዎች ወቅት የነበረውን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ባለው ህዝብ ውስጥም ውጤታማ መሆኑን ያሳያል፡፡ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ከፍተኛ ውጤታማነት እያስገኘ መሆኑን የማህበረሰብ ጤና ሐኪሙ ፕሮፌሰር ሀጋይ ሌቪን ተናግረዋል። ""በጣም ተጋላጭ ለሆኑት ቡድኖች ከፍተኛ የክትባት ሽፋን መስጠት ወሳኝ"" ነበር ብለዋል፡፡ የእስራኤል ትልቁ የጤና ፈንድ ክላሊት በተመሳሰይ ዕድሜ እና የጤና ሁኔታ በሚገኙ 600,000 ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ መልካም የሚባል ውጤት መገኘቱን፣ ክትባት ካልወሰዱ ሰዎች አንጻር እንደታየባቸው አመልክቷል፡፡ ክትባቱን በወሰዱት ዘንድ 94% ያነሰ ኢንፌክሽኖችን አግኝቷል፡፡ በተጨማሪም ክትባቱ ሁሉንም ማለት በሚቻል ሁኔታ ከባድ ህመሞችን ተከላክሏል፡፡ ውጤቱ ከ70 ዎቹ በላይ የሆኑትን ጨምሮ በሁሉም የዕድሜ ቡድኖች ውስጥ ተመሳሳይ ነበር፡፡ ይህ ""እንደ እንግሊዝ ላሉት ሌሎች ሀገሮች"" ስለ ክትባቱ ጠቃሚ መልዕክት ከማስተላለፉም በተጨማሪ፣ በቫይረሱ በጣም ሊታመሙ የሚችሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች ""በከፍተኛ"" ሁኔታ ክትባቱን እንዲያገኙ ያግዛል ብለዋል ፕሮፌሰር ሌቪን፡፡ ፕሮፌሰሩ አክለውም የእንቅስቃሴ ገደቦችን ከማላላት በፊት ምን ያህል ቁጥር መከተብ እንደሚያስፈልግ መናገር አልችልም ብለዋል፡፡ ""በመተላለፍ ላይ ያለው ተጽዕኖ ምን እንደሆነ እስካሁን አናውቅም"" ብለዋል፡፡ ሆኖም ቢያንስ ""ክትባቱ ግለሰብን ለመጠበቅ ጠቃሚ ነው"" ሲሉም አክለዋል፡፡ የእስራኤል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃን በመተንተን ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር ኤራን ሴጋል በበኩላቸው ክትባቱ በኮቪድ -19 ጉዳዮች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመረዳት ሃገሪቱ ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ ከሆኑት መካከል 80 በመቶውን መከተብ እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ እስራኤል የክትባት መርሃግብሩ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመመልከት በዓለም ላይ የመጀመሪያዋ ሀገር ብትሆንም፣ ወደዚህ ደረጃ ለመድረስ ከፍተኛ የሆነ ህዝብን ማዳረስ እና በርካታ ሳምንታትን ሊፈጅባት ይችላል፡፡ በመጀመሪያ ክትባት በተወሰዱ እና ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ በሆናቸው እና ከዚያ ቀደም ነዋሪዎቻቸውን ባስከተቡ ከተሞች ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት ሲቀንስ ታይቷል። ይህም ቀደም ባሉት የእንቅስቃሴ ገደቦች ወቅት ያልታየ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ከእገዳው ይልቅ ክትባቱ ለቁጥሩ መቀነስ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠንካራ ማስረጃ ይሰጣል፡፡ ፕሮፌሰር ሴጋል እንደሚያስጠነቀቁት ከሆነ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በላይ በዝግታ የቀነሰ ሲሆን ምናልባትም በእስራኤል ውስጥ ዋነኛው የቫይረሱ ዝርያ በሆነው እና በብሪታንያ በተገኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ""በጣም ፈጣን"" በሆነው በእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር እንኳን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊከላከሉት የማይችሉ ሲሆን በበሽታው ከተያዙም በጠና ሊታመሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ""አሁንም ቢሆን ከእንቅስቃሴ እገዳው ለመውጣት በጥንቃቄ መውጣት አለብን"" ወይም ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሆስፒታል መተኛት ሊገደዱ ይችላሉ ይላሉ፡ እስራኤል ከፍተኛ የሆነ የኢንፌክሽን ማዕበል እያጋጠማት እና በጥብቅ እገዳዎች ውስጥ ብትቆይም ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆኑ ሁሉ የመከተብ መብት ስላላቸው ትምህርት ቤቶች የመከፈት ተስፋ አላቸው ተብሏል፡፡ በፍልስጤም ግዛቶች ክትባቱን ማን መስጠት አለበት በሚለው ጥያቄ ሃገሪቱ ትችት ደርሶባታል፡፡ ለጤና ሠራተኞች እንዲደርስ እስራኤል በዌስት ባንክ እና በጋዛ ላሉት ፍልስጤሞች የተወሰነ መጠን ያለው ክትባት ማሳለፍ የጀመረችው ገና አሁን ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከነዋሪዎቿ ለሩብ ያህሉ ሁለቱንም ዙር ክትባት ሰጥታለች፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-56073530 +health ኮሮናቫይረስ፡ሪፐብሊካኖች በሚያደርጉት እጩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሚዲያዎች እንዳይሳተፉ ተወሰነ "የአሜሪካ የሪፐብሊካን ፓርቲ በዚህ ወር እጩ ፕሬዚዳንቱን በይፋ ለመምረጥ እቅድ ይዟል። ይህ ምርጫም ሚዲያዎች እንዳይሳተፉበትና በዝግም እንደሚካሄድ ተገልጿል። የሪፐብሊካን ቃለ አቀባይ እንደተናገሩት ሚዲያ እንዳይሳተፍ የተወሰነው ከኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ጋር በተያያዘ መሆኑንም አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። በሰሜን ካሮላይና የሪፐብሊካን ልዑካን ተሰባስበውም እጩ ፕሬዚዳንቱን ዶናልድ ትራምፕን በይፋ እንደገና ይመርጣሉ። 336 የሚሆኑ ልዑካን በሰሜን ካሮላይና ግዛት፣ ቻርሎቴ ከተማ በዚህ ወር ይሰባሰባሉ። እነዚህ ልዑካን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቁጥሩ በመገደቡ መገኘት ያልቻሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ አባላትን ወክለው ይገኛሉ። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፓርቲያቸው ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ሲሆኑ፤ እንደገና በይፋ መመረጣቸውም የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸውንም እንዲሁ በይፋ መጀመሩን የሚያበስር ነው ተብሏል። ""ፓርቲያችን በፌደራል እንዲሁም በተለያዩ ግዛቶች የወጡ የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን በመከተልም ነው ስብሰባውን የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥርን የወሰንነው"" በማለት ቃለ አቀባይዋ ተናግረዋል። ይህ ውሳኔ ከዚህ በፊት ይደረጉ የነበሩ ስብሰባዎቸን አካሄድ የቀየረ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነቱ ስብሰባ የበርካታ ሚዲያዎችን ቀልብ የሚስብና ለህዝቡም መልዕክቶች ይፋ የሚሆኑበት ነበር። የሰሜን ካሮላይና አስተዳዳሪ በሚገኙት ሰዎች ብዛትና አካላዊ ርቀት ጋር ተያይዞ ስብሰባውን ወደ ሌላ ቦታ እንዲያደርጉት መጠየቀቻውን ተከትሎ ግንቦት ወር ላይ ወደ ጃክሰን፣ ፎሎሪዳ እንደሚደረግ ትራምፕ ተናግረው ነበር። ነገር ግን ወደ በኋላ ፍሎሪዳ ሊደረግ የነበረውን ስብሰባ በመሰረዝ ወደቀደመው እቅድ በመመለስ ሰሜን ካሮላይና እንዲካሄድ ተወስኗል።ግዛቲቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ያለምክንያት እያቀጣጠሉ ነው በማለት ወንጅለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53627157 +sports ዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች፡ ፈረንሳይ ድል ሲቀናት አርጀንቲና እጅ ሰጥታለ��� የአምናዋ የዓለም ሻምፒዮና ፈረንሳይ ከመመራት ተነስታ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አውስትራሊያን በማሸነፍ አጀማመሯን አሳምራለች። ፈረንሳይ እንደካሪም ቤንዜማ፣ ንጎሎ ካንቴ እና ፖል ፖግባ ያሉ ኮከቦቿን በጉዳት አጥታ ነው ወደ ዓለም ዋንጫው ያቀናችው። ትላንት በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታዋ በአውስትራሊያ ቀድሞ ጎል ተቆጥሮባታል። ክሬግ ጉድዊን ነው ጎሏን ለቢጫ ለባሾቹ ያስቆጠረው። አድሪዬ ራቢዮ ሰማያዊዎቹን በ27ኛው ደቂቃ አቻ አደረገ። ኦሊቨር ዥሩ ሁለተኛዋን ጎል አስቆጥሮ ፈረንሳይ 2 ለ 0 በምምራት ወደ መልበሻ ክፍ አመሩ። ምሽቱን ድንቅ ሆኖ ያመሸው ክሊያን ምባፔ ሦስተኛዋን ጎል አስቆጥሯል። ዥሩ አራተኛዋን ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው 4 ለ 1 ተጠናቋል። ዥሩ ለብሔራዊ ቡድኑ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ቁጥር 51 አድርሷል። በዚህም ከቲዬሪ ሄነሪ እኩል ለመሆን በቅቷል። በዚሁ ምድብ አራት የሚገኙት ቱኒዝያ እና ዴንማርክ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይተዋል። በርካታ የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ተጫዋቾችን ያሰለፉት ዴንማርኮች በኤጁኬሽን ስታዲየም ጠንካራ ፉክክር ገጥሟቸዋል። ሁለቱም ቡድኖች ያስቆጠሯቸው ጎሎች ከጨዋታ ውጪ በሚል ተሽረዋል። በ95 ደቂቃ ኳስ ፍጹም ቅጣት ክልል ውስጥ በእጅ ተነክቷል በሚል ዳኛው ሜዳ ዳር የሚገኘውን ቴሌቪዥን ደጋግመው ቢመለከቱም ፍጹም ቅጣት ምቱን ለዴንማርክ ሳይሰጡ ቀርተዋል። የምድብ ሦስት ጨዋታዎችም ትላንት ነው የተከናወኑት። በእግር ኳስ ታሪክ የጎላ ስም የሌላት ሳዑዲ አረቢያ ለዋንጫው የምትገመተውን አርጀንቲናን ማሸነፍ ችላለች። ሳዑዲዎች በሉሳይል ስታዲየም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታቸው አንድ ለባዶ ከመመራት በመነሳት ሁለት ግቦችን አስቆጥረው ምድብ ሦስትን መምራት ጀምረዋል። አርጀንቲና ያገኘችውን ፍጹም ቅጣት ምት ሊዮኔል ሜሲ አስቆጥሮ አገሩን ቀዳሚ ማድረግ ችሎ ነበር። በአርጀንቲና በኩል በርካታ ግቦችን ለማስቆጠር ባደረጓቸው ተደጋጋሚ ጥረቶች ሦስት ግቦችን ማስቆጠር ቢችሉም ከጨዋታ ውጪ በመሆናቸው ተሰርዘዋል። ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሮ በ10 ደቂቃ ውስጥ ሳዑዲ ውጤት ቀያሪውን ግብ አስቆጠረች። ሳሌህ አል-ሼህሪ የመጀመሪያዋን ጎል ሲያስቆጥር ሳሌም አል ዳወሳሪ ያስቆጠራት ግብ ቡድኑን አሸናፊ አድርጋለች። የምድቡ ደካማ ቡድን በሆነችው ሳዑዲ የተሸነፈችው አርጀንቲና ቀጣይ ሁለት የምድብ ጨዋታዎች በውድድሩ የሚኖራትን ዕጣ ፈንታ ይወስናሉ። ሳዑዲ በታሪኳ ለዓለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ የበቃችው በ1994 ነበር። ሪያድ ደስታዋን ለመግለጽ አንድ ቀን አይበቃኝም ብላለች። ልዑል ሳልማን ረቡዕም ብሔራዊ በዓል ነው ሲሉ ደስታው እንዲራዘም ፈቃዳቸው ሆኗል። ሜሲ እና አርጀንቲና ቀጣይ ጨዋታቸውን በሐዘን ለመጠበቅ ተገደዋል። በምድቡ ሌላ ጨዋታ ሜክሲኮ እና ፖላንድ ያለ ጎል አቻ ተለያይተዋል። የፖላንዱ አምበል እና የጎል ቀበኛ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ አገሩን ለድል ልታበቃ የምትችል ፍጹም ቅጣት ምት አግኝቶ ሳይጠቀምባት ቀርቷል። በስታዲየም 974 በተደረገው ጨዋታ የሜክሲኮው ግብ ዘብ ጉሌርሞ ኦቾአ ፍጹም ቅጣት ምቱን አድኗል። በርካታ የሜክሲኮ ደጋፊዎች የታደሙበት ጨዋታ ይህ ነው የሚባል ፉክክር ሳይታይበት ተጠናቋል። ምድቡን ሳዑዲ ስትመራ ፖላንድ እና ሜክሲኮ ይከተላሉ። ምድቡ ግርጌ ላይ የምትገኘው አርጀንቲና በቀጣይ ከሜክሲኮ ትጫወታለች። የዓለም ዋንጫው ዛሬም ቀጥሎ ይካሄዳል። የምድብ አምስት እና ስድስት ጨዋታዎች ዛሬ ይከናወናሉ። ምድብ አምስት ላይ ጀርመን እና ጃፓን ይገናኛሉ። ሁለቱ ቡድኖች በኻሊፋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም 10 ሰዓት ጨዋታቸውን ይጀምራሉ። በዚሁ ምድብ የሚገኙት ስፔን እና ኮስታሪካም ጨዋታቸውን ያከና���ናሉ። የአል ቱማማ ስታዲየም የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ አንድ ሰዓት ላይ ያስተናግዳል። በምድብ ስድስት አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ከክሮሽያ ትጫወታለች። ጨዋታው ቀን ሰባት ሰዓት በአል ባይት ስታዲየም ይከናወናል። ቤልጂየም ደግሞ ካናዳን ትገጥማለች። ምሽት አራት ሰዓት የሚከናወነው ጨዋታ በአህማድ ቢን አሊ ስታዲየም ይደረጋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0491jyxz8o +sports አሠልጣኝ ኤሪክሰንን ጨምሮ ታዋቂ ተጫዋቾችን ያጭበረበረው ደላላ "ለእግር ኳስ ደጋፊዎች እንደ መጀመሪያዋ የውድድር ዘመን ጨዋታ ጣፋጭ የለም። በጉጉት የጠበቁት ሊግ አሊያም የዋንጫ ፍልሚያ ሲጀምር የምትታየው የመጀመሪያዋ ጨዋታ እንደ ጨቅላ የሚያስቦርቅ ነገር አላት። ጊዜው 2009 በፈረንጆቹ። በእንግሊዝ ሊግ ሁለት የሚጫወተው ኖትስ ካውንቲ የ09/10 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ጨዋታውን እያካሄደ ነው። ኖትስ ካውንቲ ከዚህ ጨዋታ አንድ ወር ቀድሞ ሙንቶ ፋይናንስ በሚባል ጥምር ተቋም ተገዝቷል። ሙንቶ፤ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ኖትስ ካውንቲን ከፕሪሚዬር ሊጉ ዝቅ ብሎ ለሚደረው የቻምፒዮንሺፕ ውድድር ለማድረስ ቃል ገብቷል። እኔን ጨምሮ የዕድሜ መሰሎቼ ወጣት የኖትስ ደጋፊዎች የከተማ ተቀናቃኛችን ኖቲንግሃም ፎረስትን ጥለን ወደላይኛው ሊግ ስናል እያለምን ነው። ነገር ግን ነባር የቡድኑ ደጋፊዎች ይህ የአዲሱ የክለቡ ባለቤት ቃል ብዙም የተዋጠላቸው አይመስልም። ከጥቂት ቀናት በኋላ እውቁ አሠልጣኝ ስቬን-ጎራን ኤሪክሰን የክለቡ ዳይሬክተር ሆነው ተቀጠሩ። እንግሊዝን ለዓለምና አውሮፓ ዋንጫ ያደረሱት አሠልጣኝ ካሜራው መብራቱን እየለቀቀባቸው ለዓለም ሕዝብ ስለክለቡ መግለጫ ሰጡ። ይሄኔ የክለቡ ጥንታዊ ደጋፊዎች ሳይቀሩ ሕልማቸው ለመለመ። ኖትስ ካውንቲ አይደለም ለቻምፒዮን ሺፕ ለፕሪሚዬር ሊግ የመወዳደር አቅም አለው ሲሉ ይፎክሩ ጀመር። አዎ፤ የምናወራው ከሊግ 2 ላለመውረድ ስለሚታገለው፤ የደረጃ ሠንጠረዡ አጋማሽ ለመድረስ ስለሚንጠራራው ኖትስ ካውንቲ ነው። እነሆ ኖትስ ካውንቲ በኤሪክሰን እየተመራ ወደ ፕሪሚዬር ሊግ ሊገሰግስ ነው። 9 ሺህ ሰው የሚያስተናግደው ሜዶው ሌን ጠጠር ቢወረወር መሬት እንዳያደርፍ ሆኖ ሞልቷል። ኤሪክሰን በተዘጋጀለቻው የክብር መንበር ተሰይመው ቡድናቸውን ይመለከታሉ። አዲሱ ፈራሚ ሊ ሂዩስ ብቃቱን ለማሳየት ቋምጧል። ኖትስ ካውንቲ ከብራድፈርድ ሲቲ። ጨዋታው ተጀመረ። የመጀመሪያው ጎል - ኖትስ ካውንቲ። ስታድየሙ በአንድ እግሩ ቆመ። ሊ ሂዩስ ጎል አገባ። ደገመ። ደጋገመ። በመጀመሪያ ጨዋታ ሶስታ [ሃትሪክ] ሠራ። ፍልሚያው በኖትስ ካውንቲ 5 ለምንም አሸናፊነት ተጠቀቀ። በኖትስ ካውንቲ ደጋፊነቴ ከተደስትኩባቸው ቀናት መካከል ይህ ከቤተሰቦቼ ጋር ያየሁት ፍልሚያ በፍፁም ከአእምሮዬ አይጠፋም። ነገር ግን ሁሉም ነገር ሕልም ነበር። ምንም እንኳ የዛኔ ነገሩ ባይገባኝም ከመካከለኛው ምስራቅ ናቸው የተባሉት ቱጃር የክለቡ ባለቤቶች ሐሰት ነበሩ። ባለቤቶቹ ካዝና ውስጥ አሉ የተባሉት ሚሊዮኖች ረብጣዎች የውሃ ሽታ ሆኑ። የደጋፊዎች ሕልም መክኖ ቀረ። ክለቡ፣ ደጋፊዎቹ እንዲሁም ኤሪክሰን የአጭበርባሪው ረስል ኪንግ የቅጥፈት ስልት ሰለባ ሆኑ። እነሆ ይህ ከሆነ ከአስር ዓመት በኋላ እኔና ሌሎቹ የሙያ አጋሮቼ ምንድነው የተፈጠረው የሚለውን ለመመርመር ተነሳን። ያገኘነውን ነገር ግን ካሰብነውም በላይ ውስብስብ ነው። ዓመታት የወሰደ፤ ከኖቲንግሃም በጀርዚ አድርወጎ ባህሬይንን ተሻግሮ በዱባይ በኩል ሰሜን ኮሪያ የዘለቀ የሐሰት፣ ስግብግብነት ታሪክ። ደጋፊዎቹ ክለቡ ሲሸጥ ባለቤቱ ማነው ከየትስ ነው የመጣው፤ ሚሊዮን ዶላሮቹስ የማናቸው፤ ብለው አልጠየቁም። ይባስ ብሎ ኤሪክሰን የክለቡ የእግር ኳስ ዳይሬክተር ሆነው ሲፈርሙ ሁሉም ጮቤ ረገጠ። ስዊድናዊው አሠልጣኝ ቀጥታ ወደ ሥራ ነው የገቡት። ጊዜ ሳይፈጁ ተጫዋቾች ማስፈረም ጀመሩ። አንድ ካስፐር ሽማይክል የሚባል ወጣትና ተስፈኛ ግብ ጠባቂ ለማምጣት እንዳቀዱም ተናገሩ። ሽማይክል ሊድስ ዩናይትድን ከመቀላቀሉ በፊት ለኖትስ ካውንቲ አንድ ዓመት ተጫውቷል። ኤሪክሰን ወደ ኖትስ ካውንቲ ከመምጣታቸው በፊት ማንቸስተር ሲቲን አሠልጥነዋል። ይሄኔ ነው የዝነኛው ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ፒተር ሽማይክል ልጅ ካስፐር ሽማይክልን የተመለከቱት። ካስፐር በወቅቱ እንደአሞራ ተወርውሮ ኳስ የሚቀልበው ጆ ሃርትን ረትቶ ቋሚ ተሰላፊ መሆን ባለመቻሉ ወደሌላ ክለብ መዛወርን ያልማል። ኤሪክሰን ካስፐርና አባቱን ፒተር ሽማይክልን ካሳመኑ በኋላ ዓመታዊ ደሞዝ 1.5 ሚሊዮን ዩሮ እንዲባለ አስማምተው ለአምስት ዓመት አስፈረሙት። ምን ሽማይክል ብቻ ኖትስ ካውንቲ ማስፈረም የማይችለው እግር ኳሰኛ እንደሌለ ይወራ ጀመር። ብራዚላዊው ተከላካይ ሮቤርቶ ካርሎስ፤ ፖርቹጋላዊው ኮከብ ሉዊዝ ፊጎ የጡረታ ዘመናቸውን በኖትስ ካውንቲ ሊያሳልፉ ይችላሉ የሚሉ ወሬዎች ይናፈሱ ጀመር። ነገር ግን የብዙዎችን ቀልብ ገዝቶ የነበረው የ34 ዓመቱ እንግሊዛዊ ዴቪድ ቤካም ኤልኤ ጋላክሲን ጥሎ ሊመጣ ነው የሚለው የከተማው ወሬ ነበር። በዚህ ሁሉ ወሬ መሃል የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ካያቸው ድንቅ ተከላካዮች መካከል አንዱ ሆነው የ34 ዓመቱ ሶል ካምፕቤል ወደ ሜዶው ሌን ዘለቀ። ካምፕቤል ከአንድ ወር በኋላ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሞርካምቤ ጋር በነበረው ፍልሚያ አደረገ። ከቤተሰቦቼ ጋር ወደ ተፋላሚዎቻችን ሜዳ ሄደን ጨዋታውን ተመለከትን። ውጤቱ ግን አስካፊ ነበር። ኖትስ ካውንቲ 2-1 ተረታ። ደጋፊዎች መቸም ሽንፈት ያለ ነው፤ ካምፕቤልን ወደ አቋሙ መመለሱ አይቀሬ ነው ብለው ተስፋ ሰንቀው ወደ ቤታቸው ገቡ። ቢሆንም ከጥቂት ቀናት በኋላ ሶል ካምፕቤል ከኖትስ ጋር ያለውን ስምምነት አፍርሶ መልቀቁ ተሰማ። ይህ ዜና ከመሰማቱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ ዘ ሰን የተባለው ጋዜጣ ኖትስ ካውንቲን የደለለው ረስል ኪንግ የተባለው ግለሰብ በ1990ዎቹ በማጭበርበር ወንጀል ተከሶ ሁለት ዓመት ከርቸሌ ከርሞ እንደወጣ አስነበበ። ክለቡ፤ ኪንግ ""ስትራቴጂያዊ አማካሪ"" ነው እንጂ ከዚያ ዘለለ ሚና የለውም ሲል ዘገባውን አጣጣለ። ነገር ግን እውነታው ይህ አልነበረም። ኪንግ፤ የባህሬይን ንጉሣዊ ቤተሰብ የውጭ ሃብት ተቆጣጣሪ ነኝ በማለት ከለንደን ኢንቨስትመን ባንክን ያታልል ኖሯል። ረስል ኪንግ ከዚሁ ባንክ ማረጋገጫ አስፅፎ ነው የኖትስ ካውንቲ ባለቤትነቱን ያረጋገጠው። በተመሳሳይ ሰዓት የአንድ ግዙፍ የማዕድን አውጭ ኩባንያ ባለቤት ነኝ በማለት ከሰሜን ኮሪያ መንግሥት ጋር የድንጋይ ከሰልና ወርቅ ለማውጣት ስምምነት ይገባል። ይሄን የምርመራ ዘገባ ስናዋቅር ያገኘናቸው ኤሪክሰን ግለሰቡ አግባብቶ ወደ ሰሜን ኮሪያ እንደወሰዳቸውና የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ለ2010 ዓለም ዋንጫ እንድናልፍ ደካማ ምድብ ውስጥ መድቡን ብለው እንደጠየቋቸው ነግረውናል። ኤሪክሰን ይህን በፍፁም ማድረግ እንደማይችሉ ለሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣናት እንደነገራቸው ያክላሉ። ከሰሜን ኮሪያ ጋር የማዕድን ማውጣት ስምምነት የገባው ኪንግ ይህን ተጠቅሞ ኩባንያው በአክሲዮን ገበያ እንደሚዘገብ መጣር ይጀምራል። ነገር ግን ይህ አልተሳካለትም። ይሄኔ ኪንግ ወደ ባሕሬይን ይበርና በመካከለኛው ምስራቅ እንደ ፋይናንሻል ታይምስ ያለ ጋዜጣ ለመመሥረት ያቅዳል። ኪንግ የኋላ ኋላ የማጭበርበር ሂደቱ አልሳካ ብሎት በፖሊስ ይፈለግ ጀመረ። በስተመጨረሻም የካ���ና ሲሳይ ሆኖ በአሜሪካዋ ከተማ ጀርዚ በፈፀመው ወንጀል ምክንያት ወደ ከርቸሌ ይላካል። ሰውየው ባለፈው ዓመት ከእሥር ተለቋል። ስለሰራነው የምርመራ ዘገባ ምላሽ ካለው በሚል ጥያቄ ብናቀርብለትም ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም። በኪንግ ተጭበርብሮ ብሩን ሲዘራ የነበረው ኖትስ ካውንቲ ሁለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ታሪክ ሆኖ ከመቅረት ተርፎ አሁን በአዲስ ባለቤት እጅ ወድቋል። እኔን ጨምሮ በርካታ ደጋፊዎች ክለባችን ባለመሸጡ ደስተኛ ብንሆንም ያንን የስድስት ወር የደስታ የሃዘን ጊዜ መቼም አንረሳውም። ምንድነው የሆነው? ሕልም ነው? ወይስ እውነት? ኖትስ አሁን በናሽናል ሊግ ውድድር ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61037984 +politics በምሥራቅ ወለጋ ታጣቂዎች ጥቃት ሰንዝረው እስረኞችን ማስመለጣቸው ተነገረ "በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ ታጣቂዎች በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በፈጸሙት ጥቃት እስረኞችን አስመልጠው በርካታ የፖሊስ አባላትን ማቁሰላቸው ተነገረ። ቢቢሲ ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ከሆስፒታል ምንጮች ማረጋገጥ እንደቻለው ጥቃቱ የተፈጸመው ማክሰኞ ዕለት ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም ነው። የአካባቢው ባለስልጣናት ጥቃቱን በተመለከተ ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቢቢሲ ጥያቄያ ቢቀርብላቸውም አስካሁን ያሉት ነገር የለም። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራውና ከወራት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪ ድርጅትነት የተፈረጀው መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጥቃቱን ስለመፈጸሙ አስታውቋል። በሳሲጋ ወረዳ የጋሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ ግለሰብ ጥቃቱን በተመለከተ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ማከሰኞ ረፋድ 3፡30 አካባቢ በከተማዋ የተኩስ ድምጽ መሰማት እንደጀመረ ገልጸዋል። የተኩስ ልውውጡም በአካባቢው በነበሩ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና ታጣቂዎቹ መካከል መሆኑን እና ይህም እስከ እኩለ ቀን መቀጠሉን ይናገራሉ። ታጣቂ ቡድኑ ጥቃት የፈጸመው በሳሲጋ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ሲሆን በዚህም ጥቃት እስረኞችን ማስመለጡን ነዋሪው ይናገራሉ። ""ከእስር ቤቱ ያመለጡ ስድስት ሰዎች እኔ ወደ ምሠራበት ቦታ ሸሽተው ገብተው ነበር። ክፍት በር ሲያገኙ ነው ዘልቀው የገቡት። ከዚያ በኋላ ወጥተው ሄዱ። እኔም የሥራ ቦታዬን ዘግቼ ከአካባቢው ሄድኩ"" በማለት የገጠማቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ በተረጋገጠው የትዊተር ገጽ ላይ ቡድኑ በሳሲጋ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ስለመፈጸሙ አስፈሯል። በዚህም ጥቃት ""ከ100 በላይ የፖለቲካ እስረኞች ተለቀዋል"" ብሏል። ቢቢሲ ከእስር ያመለጡ እስረኞችን ትክክለኛ ቁጥር ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አልቻለም። ጥቃቱን ተከትሎ በቁጥር ከ40 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው የፖሊስ አባላት ላይ የተለያየ ጉዳት ደርሶባቸው ለሕክምና ወደ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል መምጣታቸውን ከሆስፒታሉ ማረጋገጥ ተችሏል። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሆስፒታሉ ሠራተኛ ""ከሳሲጋ ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላት ይመጣሉ ተብለን ስንጠባበቅ ነበር"" ብለዋል። በተጨማሪም፤ ""በጥይት እንደተመቱ ነው የሚናገሩት (ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላት)፤ እኛም ጉዳት የደረሰባቸው በጥይት ተመትተው መሆኑን አረጋግጠናል"" ይላሉ። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት የፖሊስ አባላት ቀዶ ሕክምና እንደተደረገላቸው እና ሌሎች ስምንት የፖሊስ አባላትም የቀዶ ሕክምና እንደሚደረግላቸው መሆኑን የሆስፒታሉ ሠራተኛ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተጨማሪም ""ስድስት ሰዎች ደግሞ ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ተብለዋል"" በማለት ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ሌላ የጤና ተቋም የ��ላኩ የፖሊስ አባላት መኖራቸውንም ጨምረው ተናግረዋል። በዚህ ጥቃት ሕይወቱ ያለፈ የፖሊስ አባል ስለመኖሩ እስካሁን ማወቅ አልተቻለም። የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ስለጉዳዩ ተጠይቀው ""እኔ አላውቅም። በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ የለኝም"" በማለት ዛሬ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራው እና መንግሥት ""ሸኔ"" የሚለው ታጣቂ ቡድን በምዕራብ ኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ባለሥልጣናት እና የጸጥታ አካላት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲሰነዝር ቆይቷል። ከጥቂት ወራት በፊት የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዚህ ታጣቂ ቡድን 112 የፖሊስ አባላት፣ 57 የሚሊሻ አባላት እና በተለያየ ደረጃ የሚገኙ 18 ባለሥልጣናት መገደላቸውን አስታውቆ ነበር። በተጨማሪም በአካባቢዎቹ በተለያዩ ጊዜያት በንጹሃን ነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ከተፈጸሙ የጅምላ ግድያዎች ጋር በተለያያዘ ክስ ሲቀርብበት ቆይቷል። ከሳምንት በፊት በምስራቅ ወለጋ ኪራሙ ወረዳ ከ100 በላይ ንጹሃን ሰዎች የቡድኑ ታጣቂዎች ናቸው በተባሉ ጥቃት ፈጻሚዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣት መግለጫ አስታውቆ ነበር። እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጣራውና መንግሥት ሸኔ የሚለው ይህ ታጣቂ ቡድን ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በሰሜን ኢትዮጵያ ከባድ ጦርነት ውስጥ ከሚገኘው ከህወሓት ጋር በጋር ጸረ መንግሥት እንቅስቃሴ ለማድረግ መስማማቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58424823 +sports 95 ለ 0 እና 91 ለ 1 የተጠናቀቁ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ ምርመራ ተጀመረ የሴራ ሊዮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን 95 ለ 0 እና 91 ለ 1 በተጠናቀቁ ሁለት የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ። የአገሪቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በሁለት ጨዋታዎች ሊታመን የማይችል 187 ጎሎች መቆጠራቸውን ‘አሳፋሪ’ ብሎታል። በሴራ ሊዮን በሁለተኛ ደረጃ የእግር ኳስ ሊግ በተደረጉት ግጥሚያዎች ካሁንላ ሬንጀርስ እና ገልፍ ኮኖ ክለቦች ተጋጣሚዎቻቸውን በከፍተኛ የጎል ብልጫ አሸንፈዋል። ካሁንላ ክለብ ሉምቤቡ ዩናይትድ የተሰኘውን ቡድን 95 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን፤ ገልፍ ኮኖ ደግሞ ኮኪየም ሌበናን 91 ለ 1 አሸንፏል። በእነዚህ ጨዋታዎች የተመዘገቡት የጎል ብዛቶች በሴራ ሊዮን ታሪክ ታይተው የማይታወቁ ሲሆን፣ የአገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ውጤቱን ሰርዞታል። ሁለቱ ቡድኖች ከፍተኛ ወደሆነው የአገሪቱ ፕሪሚየር ሊግ ለማለፍ ተጋጣሚዎቻቸውን ማመን በማይቻል ውጤት ቢያሸንፉም የሁለቱም ጨዋታ ውጤቶች ተሰርዘዋል። በመጀመሪያው አጋማሽ አሸናፊዎቹ ተጋጣሚዎቻቸውን 2 ለ 0 እና 7 ለ 1 ብቻ እየመሩ ነበር። ከእረፍት መልስ ግን በሁለቱም ጨዋታዎች ከፍተኛ ጎሎች መቆጠራቸው ሆነ ተብሎ ጎሎች እንዲቆጠሩ ሳይደረግ አይቀርም የሚል ጥርጣሬን ፈጥሯል። “ይህን መሰል አሳፋሪ ተግባር ሲፈጸም ዝም ብለን አንመለከትም፤ ተገቢው ቅጣት ይተላለፋል” ሲሉ የአገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ቶማስ ብሪማ ለቢቢሲ ስፖርት ተናግረዋል። “አስቸኳይ የሆነ ምርመራ በመክፈት ለዚህ ተጠያቂ የሆኑትን እንለያለን። . . .ጥፋተኛ ሆነው የሚገኙት በሴራ ሊዮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ይቀጣሉ፤ ለአገሪቱ ፀረ-ሙስና ኮሚሸንም ተላልፈው ይሰጣሉ” ብለዋል የአገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት። ተጋጣሚያቸውን በሰፊ የጎል ልዩነት ያሸነፉት የሁንላ ሬንጀርስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ “ስፖርታዊ ጨዋነትን ያልጠበቀ” ያሉትን ባህሪ አጥብቀው እንደሚያወግዙ ተናግረዋል። በዚሁ ክለብ በከፍተኛ ውጤት የተሸነፈው ሉምቤቡ ዩናይትድ ክለብ አሰልጣኝ በበኩላቸው ሆነ ተብሎ የጨዋታ ውጤት ለማስቀየር የተደረገ ጥረት ስለመኖሩ የማውቀው ነገር የለም ብለዋል። አሰልጣኝ ሞሐመድ ጃን ጃሎህ የሚያሰለጥኑት ቡድን 95 ለ 0 ከመሸነፉም በላይ ሦስት ተጫዋቾቻቸው ከሜዳ ተወግደዋል። “የጨዋታ ውጤት ለማስቀየር ሆነ ተብሎ የተደረገ ነገር ስለመኖሩ የማውቀው ነገር የለም። ስለ ሌሎች ግን መናገር አልችልም” ሲሉ እራሳቸውን ተከላክለዋል። “በሁለተኛው አጋማሽ በርካታ ጎሎች ተቆጥረውብናል። በጣም ተበሳጭቼ ነበር. .  . ምን ያክል ጎሎች እንደተቆጠሩብን እንኳ ማወቅ አልቻልኩም ነበር” ብለዋል። የሴራ ሊዮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአራቱንም ክለቦች ተጫዋቾች እና አስተዳዳሪዎች፣ ጨዋታውን የመሩ ዳኞችን እና የአካባቢውን እግር ኳስ ማኅበር አባላት ላይ ምርመራ አደርጋለሁ ብሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cw4pjl34k13o +business ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደረገ የኬንያው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መስከረም 26/2015 ዓ.ም. በአገሪቱ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደረገ። ኩባንያው በነሐሴ ወር ከአዲስ አበባ በ500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የድሬዳዋ ከተማ ነበር የሙከራ አገልግሎቱን የጀመረው። በቀጣይ በነበሩ ሳምንታት ደግሞ በአስር ከተሞች ማለትም በሐረር፣ በሐረማያ፣ በአዳማ፣ በባሕር ዳር፣ በቢሾፍቱ፣ በደብረ ብርሃን፣ በጎንደር እና በሌሎች ከተሞች የሙከራ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ከእነዚህ ሙከራዎች በኋላ ዛሬ በይፋ አገልግሎቱን በአዲስ አበባ መጀመሩን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ያስታወቀ ሲሆን፣ በዚህ ሥነ ሥርዓትም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ተገኝተዋል። በቅርቡ የነበረውን የኬንያ ምርጫ ያሸነፉት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለመጀመሪያ ጉብኝታቸው አዲስ አበባ ገብተዋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዛሬ በመላው አገሪቱ የኔትወርክ አገልግሎት ከጀመረም በኋላ ለተጨማሪ 14 ከተሞች አገልግሎቱን እንደሚያዳርስም ተገልጿል። “በሁለገብ የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃዳችን ግዴታዎች መሰረት በከተማ የደንበኞቻችን ሙከራዎቻችን የምንቀጥል ሲሆን፣ ለተጨማሪ ከተሞች እና የተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ኔትወርካችንን እና አገልግሎታችንን ማቅረብ እንቀጥላለን” ሲሉ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሱሳ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለ125 ዓመታት በላይ በመንግሥት የልማት ድርጅት በብቸኝነት ተይዞ የነበረውን የቴሌኮም ዘርፍ ክፍት በማድረግ የቴሌኮም ፈቃድ የሰጠችው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር። በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ለመሰማራት በተደረገው ዓለም አቀፍ ጨረታ በኬንያው ሳፋሪኮም የሚመራው ጥምረት በ850 ሚሊዮን ዶላር ማሸነፉ ይታወሳል። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የተሰኘው ይህ ጥምረት በዘርፉ አሉ የሚባሉ ስመ ጥር የቴሌኮም ኩባንያዎችን እና ተቋማትን በቅንጅት የያዘ ሲሆን፣ እነዚህም ሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕና ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽን እንዲሁም ሲዲሲ ግሩፕ የተካተቱበት ነው። ዋነኛው የአገሪቱ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ ድርሻውን ለውጭ ባለሀብቶች፣ 5 በመቶውን ለኢትዮጵያውያን እና 55 በመቶውን በመንግሥት ይዞታ ይቀጥላል ተብሎ ነበር። ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች አንዱ የሆነው ኢትዮቴሌኮም ገቢው ትርፋማ ከሚባሉ ድርጅቶች አንዱ ቢሆንም ከሌሎች የቀጠናው ኩባንያዎች ጋር ሲወዳዳር ዝቅተኛ ነበር ይላሉ በዘርፉ ያሉ ተንታኞች። ኢትዮጵያ ኢትዮቴሌኮምን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ድርሻ ለመሸጥ የወሰነችው በዋነኝነት ያላትን ከፍተኛ ዕዳ ለመክፈል እንደሆነ ተንታኞች የሚናገሩ ሲሆን፤ በተጨማሪነት የቴሌኮ��ን ተደራሽነት ለመጨመርና አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ እንደሆነም ይጠቀሳል። ከሳፋሪኮም ከሚመራው ጥምረት በተጨማሪ በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ለመግባት የሚያስችል ሁለተኛ ፈቃድ እንደሚሰጥ መንግሥት መግለጹ ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2p31gzlryo +health ኮሮናቫይረስ ፡ ወደ ታይዋን ኮቪድ-19 ቫይረስ አስገብቷል የተባለው አብራሪ ከሥራ ተባረረ "የኮሮናቫይረስን ወደ ታይዋን ይዞ ገብቷል የባለ ኒው ዚላንዳዊው የአውሮፕላን አብራሪ ከሥራ ተሰናብቷል። ሰውዬው ታይዋን ውስጥ ከወራት በኋላ ለተከሰተው የኮሮናቫይረስ የማኅበረሰብ ሥርጭት ተጠያቂ ነው ተብሎ ነው ከሥራው የተባረረው። አብራሪው ኢቫ ኤይር ለተሰኘው የታይዋን አየር መንገድ ይሰራ የነበረ ሲሆን፤ ባለፈው ማክሰኞ ከአብራሪው ጋር ግንኙነት የነበረው ግለሰብ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘበት ተገልጿል። ታይዋን ለ253 ቀናት አንድም በአገር ውስጥ ያለ ሰው በኮቪድ-19 አልተያዘባትም ነበር። ይህ ዜና ከተሰማ ወዲህ መንግሥት ሕዝቡ የገና በዓል ግርግሩን ገታ እንዲያደርገው አሳስቧል። ከገና ተከትሎ የሚከበረው የአዲስ ዓመት ዋዜማ ቀንም ሰዎች ከቤታቸው ንቅንቅ እንዳይሉ ተነግሯቸዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ማናወጥ ከጀመረ ወዲህ ታይዋን 777 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ሲሆን ሰባት ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን አሳውቃለች። የአውሮፕላን አብራሪው በቫይረሱ የተያዘው በያዝነው የታኅሣሥ ወር መግቢያ ላይ ቢሆንም ምንም የበሽታው ምልክት ግን አልነበረውም ተብሏል። አብራሪዎች ወደ ታይዋን ሲመጡ ለሦስት ቀናት ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩ የሚገደዱ ቢሆንም ምልክት ካላሳዩ ምርመራ እንዲያደርጉ አይመከሩም። ሰውዬው ምልክት ባይኖረውም ከዩናይትስ ስቴትስ አውሮፕላኑን እያበረረ ሲመጣ ግን ሲያስል ነበር ተብሏል። ይህንንም ተከትሎ አብራሪው መሬት እንዳረፈ ምርመራ ተደርጎለት ቫይረሱ እንዳለበት ተደርሶበታል። የታይዋን ባለሥልጣናት አንድ ሰው ቫይረሱ እንደተገኘበት ካረጋገጡ በኋላ ከየት ነው የመጣውን የሚለውን ሲያጣሩ ነበር አብራሪው ላይ የደረሱበት። ኒው ዚላንዳዊው አብራሪ ከመመርመሩ በፊት ከማን ጋር ግንኙነት እንደነበረው ባለማሳወቁ ነው ሥራውን ያጣው። ሰውዬው በዚህ ጥፋቱ 300 ሺህ የታይዋን ዶላር [415 ሺህ ብር ገደማ] እንዲቀጣ ተወስኖበታል። ኢቫ ኤይር አብራሪው ከሥራው የተሰናበተው የአየር መንገዱን ደንብ ባለማክበሩና የአውሮፕላኑ ጋቢና [ኮክፒት] ውስጥ ሳለ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ባለማድረጉ ነው ብሏል። ሰውዬው ከአንዲት ሴት በተጨማሪ ሁሉት የሥራ አጋሮቹንም በበሽታው እንዲያዙ አድርጓል ተብሎ ተወቅሷል። ስሙ ያልተጠቀሰው ይህ አብራሪ ""ወረርሽኙን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት"" ችላ ብሏል የሚል ትችት ገጥሞታል። ታይዋን ኮሮናቫይረስ በአውሮፕላን ተሳፍሮ ወደ አገሯ መግባቱን ከሰማች ወዲህ ጥብቅ የመከላከያ መንገዶች እንደ አዲስ ለመዘርጋት አቅዳለች። ቫይረሱን ከአብራሪው ተላልፎባታል ከተባለችው ሴት ጋር በአንድም ሆነ በሌላም መንገድ ግንኙት አላቸው የተባሉ 170 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው። የቻይና ጎረቤት የሆነችው ታይዋን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ጥብቅ እርምጃ ከወሰዱና ከተሳካላቸው ጥቂት የዓለማችን ግዛቶች መካከል ናት። የታይዋን 23 ሚሊዮን ነዋሪዎችም በሽታውን ለመከላከል ከባለሥልጣናት የሚሰጡ መመሪያዎችን በማክበር አስተዋፅዖ አበርክተዋል ተብለው ይመሰገናሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-55435035 +politics """ባሌን በብርሃን ፍጥነት ነው የገደሉት"" የሃይቲ ፕሬዝደንት ባለቤት" "በቅርቡ የተገደሉት የሃይቲ ��ሬዝደንት ባለቤት ገዳዮች ወደቤታቸው መጥተው ባላቸውን በእኩለ ለሊት ሲገድሉባቸው የነበረውን ሁኔታ ተናግረዋል። ማርቲን ሞይዝ እንዳሉት ጥቃቱ በጣም በፍጥነት የተፈፀመ ከመሆኑ የተነሳ ባላቸው ጆቨኔል ""አንድም ቃል መተንፈስ"" አልቻሉም። ፕሬዝደንት ሞይዝ ባፈለው ረቡዕ ነው የተገደሉት። ገዳዮች ተብለው የተጠረጠሩት ደግሞ 28 የውጭ ሃገር ዜጎች ናቸው። ሚስታቸው ማርቲን ሞይዝ ተጎድተው በአሜሪካዋ ከተማ ማያሚ ሕክምና ሲያገኙ ቆይተው አሁን አገግመዋል። ቅዳሜ ዕለት በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት የድምፅ መልዕክት የባላቸውን ሥራ ለመጨረስ ቃል ገብተዋል። ""ከብርሃን በፈጠነ ጊዜ ሰርጎ ገቦች ወደ ቤታቸውን ዘልቀው ባሌን በጥይት ገድለውታል"" ብለዋል በድምፅ መልዕክታቸው። ""ይህ ድርጊት ስም የለውም። ምክንያቱም ጆቨኔል ሞይዝን የመሰለ ፕሬዝደንትን አንድም ቃል ሳይተነፍስ ለመግደል አጥር አልባ ወንጀለኛ መሆን አለብህ።"" ማርቲን ባላቸው የተገደለው በፓለቲካዊ ምክንያት እንደሆነ ይገምታሉ። በተለይ ደግሞ ለፕሬዝደንቱ የተሻለ ሥልጣን የሚሰጣቸው የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ለማድረግ ማሰባቸውን ተከትሎ ነው። እኒህ ስም የሌላቸው ገዳዮች ""የፕሬዝደንቱን ሕልም መግደል ነው የሻቱት"" ይላሉ። ""አዎ እያለቀስኩ ነው። ነገር ግን ሃገራችን መንገዷን እንድትስት መፍቀድ የለብንም። የፕሬዝደንት ጆቨኔል ሞይዝ፣ ባሌ፣ የምንወደው ፕሬዝደንታችን ደም በከንቱ እንዲፈስ መፍቀድ የለብንም።"" የ53 ዓመቱ ሞይዝ በደቡብ፣ ሰሜንና መካከለኛው አሜሪካ ካሉ ሃገራት ድህንት አቆራምዷታል የምትባለውን ሃይቲን ለአራት ዓመታት መርተዋል። የሥልጣን ዘመናቸው ወጣ ገባ ነበር። በሙስናና ብልሹ አስተዳደር ምክንያት በርካታ ተቃውሞ ተነስቶባቸው ያውቃል። ከሁለት ዓመት በፊት የሕዝብ ተወካዮች ምርጫ ማከናወን የነበረባት ሃይቲ ባለመግባባት ምክንያት አራዝማዋለች። በሚቀጥለው መስከረም የሕገ መንግሥት ማሻሻያ እንዲደረግ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ አቅደው ነበር የተገደሉት ፕሬዝደንት። ባለፈው የካቲት ፕሬዝደንቱ እሳቸውን ሊገሏቸው ያሰቡ ሰዎች ሐሳብ መክሸፉን ተናግረው ነበር። የገዳዮቹ ዓላማ ምንድነው? እንዴትስ የፕሬዝደንቱን ጥበቃዎች ዘልቀው ገቡ የሚሉት ጥያቄዎች እስካሁን አልተመለሱም። የሃይቲ ፖሊስ አብዛኛዎቹ የገዳዩ ቡድን አባላት ኮሎምቢያዊያን ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ አሜሪካዊያን ናቸው ብሏል። 17 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ፤ ሶስት ሰዎች ከፖሊስ ጋር በነበረ የተኩስ ልውውጥ ተገድለዋል፤ ስምንት ተጠርጣሪዎች ደግሞ እየታሰሱ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-57794473 +business ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ በክሪፕቶከረንሲ ያጭበረበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተያዙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በክሪፕቶከረንሲ አማካይነት 575 ሚሊዮን ዶላር አጭበርብረዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች መያዙን የኢስቶኒያ ፖሊስ አስታወቀ። የኢስቶኒያ ፖሊስ ከአሜሪካው የፌደራል መርምራ ቢሮ (ኤፍቢይ) ጋር በመተባበር ሁለቱን ተጠርጣሪዎች ሲከታተል ቆይቶ ነው በቁጥጥር ስር የዋላቸው። የኢስቶኒያ ዜግነት ያላቸው የ37 ዓመት ጎልማሶቹ ሰርጌይ ፓታፔንኮ እና ኢቫን ቱሮጊን ተላለፈው እንዲሰጧቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንደሚፈልጉ ተነግሯል። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ፖሊቢየስ በተባለ የበይነ መረብ ሐሰተኛ ባንክ እና ሃሽፍሌር በተሰኘ የክሪፕቶከረንሲ ግብይት አገልግሎት አማካይነት ነው በመቶዎቹ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያጭበረበሩት። ከዚሁ ጋር በተያያዘም አሜሪካ በግለሰቦቹ ላይ መደበኛ ክስ ከፍታለች። ከአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት የወጣ መግለጫ፣ ሁለቱ ሰዎች አስከ 20 ዓመት ሊያሳስሩ በሚችሉት ���ገንዘብ ዝውውር ማጭበርበር እና ሕገ ወጥ ገንዘብን ሕጋዊ ለማድረግ በማሴር ክስ ተመስርቶባቸዋል ብሏል። ተጠርጣሪዎቹ ኢስቶኒያ ዋና ከተማ ታሊን ውስጥ በሚገኝ ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበርና፣ ለአሜሪካ ተላልፈው አስኪሰጡ ድረስ በእስር ላይ እንደሚቆዩ መግለጫው አመልክቷል። እስካሁን ሁለቱ ግለሰቦች ከጠበቆች ስለጉዳዩ የተሰጠ አስተያየት የለም። የአሜሪካ ፍትሕ መሥሪያ ቤት እንዳለው ሁለቱ ተጠርጣሪዎች፣ ማጭበርበር መሆኑን ያላወቁ ሰዎችን በሃሽፍሌር ክሪፕቶከረንሲ ማውጣት ሥራ ውስጥ እንዲሳተፉ እንደሚያደርጉ በመግለጽ ገንዘብ ሰብስበዋል። ክሪፕቶ ማውጣት ማለት ኮምፒውተሮችን በመጠቀም ትርፍ የሚያስገኝ ተጨባጭ ያልሆነ ገንዘብ ማምረት ነው። ይህ ሂደትም በጣም ከፍተኛ መጠን ያለው የኮምፒውተር ኃይልን ይጠቀማል። በዓለም ዙሪያ ያሉ በርካታ ሰዎች ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋን የሚያወጣ የሃሽፍሌር ክሪፕቶከረንሲ ኮንትራቶችን በአራት ዓመታት ውስጥ ገዝተዋል። ነገር ግን ግለሰቦቹ የተስማሙትን ሥራ እውን ለማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል። የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት እንዳለው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ከክሪፕቶው በተጨማሪ ሰዎች ፖሊቢየስ በተባለው የበይነ መረብ ባንክ ላይ መዋዕለ ነዋያቸውን ካፈሰሱ ትርፍ እንደሚያገኙ ቃል ገብተውላቸው ነበር። በዚህም አማካይነትም 25 ሚሊዮን ዶላር ቢሰበስቡም የተባለው ባንክ ግን የት እንዳለ አይታወቅም። ተከሳሾቹ በተጨባጭ የሌሉ ኩባንያዎችን በመጠቀም በወንጀል የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አድርገዋል። በዚህም ቢያንስ 75 ንብረቶችን እና የቅንጦት መኪኖችን መግዛታቸውን የአሜሪካ መንግሥት ገልጿል። በኢስቶኒያ ፖሊስ የበይነ መረብ ወንጀል ቡድን እና በአሜሪካው ኤፍቢአይ አማካይነት በተካሄደው በዚህ ምርመራ 15 አሜሪካውያንን ጨምሮ 100 ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል። በግለሰቦቹ ተፈጽሟል የተባለው ወንጀል በኢስቶያ ውስጥ ካጋጠሙ ግዙፍ የማጭበርበር ድርጊቶች መካከል አንዱ መሆኑን ፖሊስ የገለጸ ሲሆን፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናትም ሕዝቡ እየሰፋ ከመጣው በቴክኖሎጂ የታገዘ ማጭበርበር እራሱን እንዲጠብቅ አስጠንቅቋል። በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላሮችን ማጭበርበር የተጠረጠሩት ሁለቱ ግለሰቦች የተየዙት ኤፍቲኤክስ የተባለው የዓለም ሁለተኛው የክሪፕቶ ግብይት መድረክ ከስሮ የክሪፕቶከረንሲው ገበያ ቀውስ ውስጥ በወደቀበት ጊዜ ነው። ኤፍቲኤክስ ባለፈው ሳምንት ኪሳራ እንደገጠመው አሜሪካ ውስጥ ያሳወቀ ሲሆን፣ በዚህም 50 የሚደርሱ የዋነኛ አበዳሪዎቹ 3.1 ቢሊዮን ዶላር እዳ እንዳለበት የፍርድ ቤት ሰነዶች አመልክተዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c9e1nv2lv8zo +health በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ ሦስት ሰዎች ሞቱ "በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ 3 ሰዎች ሞቱ። ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ ተቅማጥ፣ ማስመለስና የመድማት ምልክቶችን እያሳዩ እንደሆነ ተነግሯል። አራቱ ሰዎች እነዚህን ምልክቶች ማሳየት የጀመሩት የአንድ በኢቦላ የሞተችን ነርስ ቀብር ከታደሙ በኋላ ነበር። ባለሥልጣናት አዲስ የተሰራ ክትባት በዓለም ጤና ድርጅት በኩል እንደሚገኝ እየተናገሩ ነው። በፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2016 ብቻ በምዕራፍ አፍሪካ ኢቦላ ወረርሽኝ የ11ሺ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። ወረርሽኙ ጊኒን ጨምሮ ጎረቤቶቿን ላይቤሪያንና ሴራሊዮንን በከፍተኛ ሁኔታ አጥቅቶ ነበር። ይህን ተከትሎም በርካታ ክትባቶች ተሞክረዋል። ክትባቶቹ ወረርሽኞቹን ለማቆም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ አገልግሎት ላይ ሲውሉ ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት የጊኒ ተወካይ አልፍሬድ ጆርጅ ኪ ዜርቦ ""አስፈላጊውን ክትባት ለማቅረብ የዓለም ጤና ድርጅት ከመድኃኒት አም���ቾች ጋር እየተነጋገረ ነው ብለዋል። የኢቦላ ክትባት ለመጀመርያ ጊዜ በ2015 በጊኒ ሙከራ ተደርጎ ውጤት ማስገኘቱ ይታወሳል። ከክትባቱ ሌላ ታማሚው የመዳን እድሉን የሚጨምሩ መድኃኒቶች መፈብረካቸውም ይታወቃል። አሁን በጊኒ የተቀሰቀሰው ኢቦላ በአንድ ጤና ጣቢያ ትሰራ የነበረች ነርስ ታማ ከሞተች በኋላ በቀብሯ ላይ የተገኙ ሰዎች በተህዋሲው መጠቃታቸው ነው የተነገረው። ነርሷ ከሞተች ከ4 ቀናት በኋላ ነበር የተቀበረችው። ምናልባት አስክሬን በማጠብ ላይ የነበሩ ሰዎች ተህዋሲውን እንዳዛመቱ ይገመታል። ብዙውን ጊዜ በኢቦላ የሞቱ ሰዎች አስክሬን አደገኛና መርዛማ የኢቦላ ተህዋሲን የመሸከም አቅም አለው። የተህዋሲው እድሜም ከ2 ቀን እስከ 3 ሳምንት ይቆያል። ኢቦላ ቺምፓዚን ከመሰሉ እንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ተህዋሲ ነው። ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውም በደም፣ በሰውነት ፈሳሽ ወይም ተህዋሲው ከነካው አካባቢ ሊሆን ይችላል። አሁን ሁሉም በተህዋሲው የተለከፉት እድሜያቸው ከ25 ዓመት በላይ የሆኑና የነርሷን ቀብር የታደሙት ናቸው። የወረርሽኙን መቀስቀስ ተከትሎ ሴራሊዯንና ላይቤሪያ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ። የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ለጤና ሚኒስትሮቻቸው ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተሉ አዘዋል። የቢቢሲ ዘጋቢ ከሴራሊዯን እንደጻፈችው በአገሪቱ ከኮቪድ ተህዋሲ በላይ ሕዝቡ ስጋት ያለበት ለኢቦላ ወረርሽኝ ነው። ኢቦላ ተህዋሲ ድንገቴ ትኩሳት በመፍጠር በአጭር ሰዓት ታማሚውን በማዳከም የጡንቻ ከባድ ሕመም ፈጥሮ ጉሮሮን አቁሱሎ የሚገድል በሽታ ነው። ከዚህም ባሻገር ማስመለስ፣ ማስቀመጥ እና የውስጥና የውጭ መድማትን ያስከትላል። ታማሚዎች የሚሞቱት ብዙውን ጊዜ ፈሳሽ ከሰውነታቸው ተሟጦ ስለሚያልቅ ነው። ይህም የአንዳች ሰውነት አካል ሥራ ማቆምን ያስከትልና ለሞት ይዳርጋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56066789 +health “ክትባት ቢገኝም ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ” የዓለም ጤና ድርጅት ክትባት በስፋት ከመሰራጨቱ በፊት በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ሁለት ሚሊዮን ሊደርሱ ይችላሉ አለ። የድርጅቱ የድንገተኛ ቡድን መሪ ዶ/ር ማይክ ራየን እንዳሉት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ካልተባበረ የሟቾች ቁጥር ሊጨምርም ይችላል። ወረርሽኙ መሰራጨት ከጀመረ ወዲህ ወደ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ሞተዋል። 32 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተይዘዋል። በአንዳንድ አገራት በሽታው እያገረሸ ሲሆን፤ አሜሪካ፣ ሕንድ እና ብራዚል ውስጥ በአጠቃላይ ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰው ታሟል። በሽታው ባገረሸባቸው የአውሮፓ አገራት ዳግመኛ የእንቅስቃሴ ገደብ የመጣል እቅድ አለ። አውሮፓ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ማይክ፤ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣል በፊት ምርመራ በማካሄድና በሽታው ካለባቸው ጋር ንክኪ ያላቸውን በመለየት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት መሞከር ያዋጣል ብለዋል። ስለ ሟቾች ቁጥር ምን ተባለ? ክትባት መሰራጨት ከመጀመሩ በፊት ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ዶ/ር ማይክ “ሊሆን ይችላል” ብለዋል። ለበሽታው የሚሰጠው ህክምና እየተሻሻለ መምጣቱ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር መቀነሱን ቢናገሩም፤ ውጤታማ ክትባት ቢገኝም እንኳን የሟቾች ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን እንደሚያልፍ አስረድተዋል። መንግሥታት ኃላፊነታቸውን በመወጣት የሰዎችን ሕይወት እንዲታደጉም አሳስበዋል። በተለያዩ አገራች ጥብቅ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ለምሳሌ በስፔን በሽታው በበረታበት ማድሪድ በከፊል እንቅስቃሴ የመግታት እቅድ ነበር። ተቃውሞ ስለገጠመው ተግባራዊ አልሆነም። ፈረንሳይ ውስጥም የባርና ሬስ���ራንት ተቀጣሪዎች ንግዳቸው እንዳይዘጋ ተቃውመዋል። ዩናይትድ ኪንግደም አዳዲስ የጥንቃቄ እርምጃዎች ወስዳለች። እስራኤልም ንግድና በረራ ላይ ጥብቅ ገደብ ጥላለች። በሌላ በኩል በሽታው የከፋባት አሜሪካ ንግድ ተቋሞች ላይ ተጥሎ የነበረውን ገደብ አንስታለች። የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ እንደሚሉት፤ አሜሪካ የወረርሽኙን የመጀመሪያ ዙር ስርጭት ገና አላለፈችም። https://www.bbc.com/amharic/news-54306899 +business የጥቁር ገበያው ምንዛሪ መናር በኢኮኖሚው ላይ ምን ጫና ይዞ ይመጣል? "በአዲስ አበባ መደበኛ ባልሆነው የውጭ ምንዛሬ መስመር በሕገወጥ መንዛሪዎች የሚመራው የጥቁር ገበያ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ አንድ ዶላር በጥቁር ገበያው ከ64 እስከ 68 ብር ድረስ በመመንዘር ላይ እንደሚገኝ እና በተለያዩ ሁኔታዎች ይህ ዋጋ እስከ 72 ብር ድረስ ከፍ እንደሚል በዚሁ ሥራ ላይ ያለ ግለሰብ ለቢቢሲ ተናግሯል። በመደበኛው የምንዛሪ ገበያ አንድ ዶላር በ45 ብር እየተመነዘረ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ በጥቁር እና መደበኛ ገበያው መካከል ያለው ልዩነት ከ20 ብር በላይ ሆኗል። ይህም ከዛሬ ሦስት ዓመት ሐምሌ 2010 ከነበረበት ጋር ሲነጻጸር የእጥፍ ልዩነት አለው። በወቅቱ አንድ ዶላር በጥቁር ገበያው በ31 ብር ይመነዘር ነበር። በመደበኛ ገበያውም ላይም ቢሆን ቀላል የማይባል ከፍተኛ ማሻቀብ ታይቶበታል። ከሰባት ወራት በፊት ከ40 ብር ያልተሻገረው የመደበኛው ገበያ ምንዛሪ አሁን የአምስት ብር ጭማሪ አሳይቷል። እንዲሁም በ13 ዓመታት ውስጥ የአምስት እጥፍ ጭማሪ ታይቷል። ""የጥቁር ገበያው ምንዛሪ መናር እየተባባሰ እንጂ እየተቃለለ ይሄዳል የሚል እምነት የለኝም"" የሚሉት ለዓመታት የኢትዯጵያን የምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ሲተነትኑ የቆዩ ባለሞያ ናቸው። በሥራቸው ጠባይ ምክኒያት ስማቸው እንዳይጠቀስ የመረጡት እኚሁ የምታኔ ሀብት ባለሞያ መንግሥት የብርን ምንዛሪ ለማዳከም የሚከተለውን ፖሊሲ ለክርክራቸው እንደማስረጃነት ያቀርባሉ። ""ይህ ሰዎች ቁጠባቸውን በዶላር እንዲያደርጉ ስለሚያበረታታ የጥቁር ገበያውን ዋጋ ይጨምረዋል። እንደተለመደው ወደ ውጪ ከምንልከው ከውጭ የምናስገባው ጋር ሲነጻጸር እጅግ ያነሰ ስለሆነ በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት እጅግ የተጋነነ ሆኖ ይቀጥላል"" ሲሉ አክለዋል። ""ግጭቶች እና ተዛማጅ ብቅ ብቅ እያሉ ያሉ ፍላጎቶች የመንግሥትን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ይጨምሩታል። ይህ ማለት መንግሥት የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ከግሉ ዘርፍ ጋር ይወዳደራል ማለት ነው። ስለዚህ የግሉ ዘርፍ ብቸኛ አማራጩ ወደሆነው የትይዩ ገበያ ይሸጋገራል"" ሲሉ የምጣኔ ሀብት ተንታኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ኢኮኖሚው ላይ የሚጣሉ ማዕቀቦች መንግሥት ከውጭ አገራት በሚያገኛቸውን የምንዛሪ ፈሰሶች ላይ ጫና ይኖራቸዋል ያሉት ባለሙያው፤ ግጭቶች ሲኖሩ ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እና ይዞት የሚመጣው ጥሬ ምንዛሬም አብሮ ቀሪ ነው ሲሉ ያስረዳሉ። በባንክ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ትንታኔዎችን በመስጠት የሚታወቁት እና መቀመጫቸውን በእንግሊዝ ለንደን ያደረጉት አብዱልመናን መሐመድ በመደበኛ እና በጥቁር ገበያው መካከል ያለው ልዩነት ለዓመታት በ20 እና 30 በመቶ መካከል መቆየቱን ያስታውሳሉ። አሁን ይህ ልዩነት ወደ 50 በመቶ አሻቅቧል ይላሉ። የዚህ ቀጥተኛ ውጤትም አሁንም በከፍተኛ መጠን እየጨመረ በመጣው የዋጋ ግሽበት ላይ እንደሚበረታ አብዱልመናን ይናገራሉ። ለዚህም ምክኒያቱ አስመጪዎች የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች ስለማያገኙ ከዚሁ የጥቁር ገበያ በሚያገኙት ምንዛሪ እቃዎችን በማስመጣታቸው ነው ሲሉም ይከራከራሉ። በተጨማሪም መንግሥት ይህንን በጥቁር እና በመደበኛው ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ለመሙላት ሲል በፍጥነት የብርን ዋጋ ማዳከሙ አይቀሬ ነው ሲሉ አብዱልመናን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተጨማሪም የኢኮኖሚው አይገመቴነት ባለሀብቶች ሀብታቸውን እንዳያፈሱ ያግዳል ብለዋል። ""የብር በፍጥነት ዋጋ ማጣት ከውጭ የሚገኙ ብድሮችን የመክፈል አቅምን ያዳክማል። ይህ የመንግሥትም ሆነ የግል ተበዳሪዎችን ኪሳራ ውስጥ ሊከት ይችላል። ብድሩንም ሆነ ወለዱን በውጭ ምንዛሪ የመቀየር ኃላፊነት የሚወድቅበት መንግሥትም ከፍተኛ ጫና ውስጥ ይወድቃልል"" ሲሉም አክለዋል። ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ከተሰኘ ድረ-ገጽ የተገኘ መረጃ እንደሚያመላክተው ባለፉት 10 ዓመታት በባንኮች የዶላር ዋጋ በ28 ብር ገዳማ ጭምሯል። 2003 ዓ.ም. ላይ በባንክ 1 የአሜሪካ ዶላር በ16 የኢትዮጵያ ብር ይመነዘር ነበር። ይህ አሳሳቢ ጉዞ ወዴት ያመራል ለሚለው ምላሽ የሰጡት የምጣኔ ሀብት ተንታኙ ""ትንበያዎች የሚያሳዩት እኤአ 2022 መደበኛው ምንዛሪ ወደ 47̂ ነጥብ 7 ብር እንደሚያመራ ብሎም በ 2023 ወደ 54 ነጥብ 1 ብር ከፍ እንደሚል ነው። ቁጥሮቹን ብንተዋቸው እንኳን አሁን ያለው አካሄድ የሚያሳየን በእርግጠኝነት የብር ምንዛሪ እየተዳከመ እንደሚሄድ ነው"" ሲሉ አስረድተዋል። የኑሮ ውድነት፣ የአገር ውስጥ ኢኮኖሚው በዶላር መንቀሳቀስ (dollarization of domestic economy) እንዲሁም የድህነት መባባስ፣ የብር ዋጋ መውደቅ የአጭር ጊዜ ጫናዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተንታኙ ገልጸዋል። እንዲሁም ይህ በጊዜ ካልተገታ ወደ ሕዝባዊ አመጽ የሚያመራበት እድል እንዳለም አሳስበዋል። በረጅም ጊዜ ኢኮኖሚው ሙሉ በሙሉ የመውደቅ ቀውስ (Full blown economic crisis) ሊጋረጥበት እንደሚችል ጠቅሰው ይህም ኢኮኖሚው ከተለያዩ አቅጣጫ ቀውሶች ሲገጥሙት የሚከሰት መሆኑን ያስረዳሉ። ""የውጭ ንግድ፣ የገንዘብ ፖሊሲው፣ ምርት፣ የብድር አስተዳደር ብሎም በኢንቨስትመንት ላይ የሚያሳድረው ጫና የኢኮኖሚ ውድቀት (Full blown economic crisis) ሊያጋጥም የሚችልበት እድል አለ"" ሲሉም ገልጸዋል። የባንክ ዘርፍና እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አብዱልመናን በበኩላቸው መንግሥት ይህንን ችግር ለመፍታት ወይም ለማቃለል የብርን በፍጥነት መዳከምን ጨምሮ በርካታ የአስተዳደር እርምጃዎችን መውሰድ አለበት ብለው ያምናሉ። በተጨማሪም ጥብቅ የሆነ የሞኒተሪ ፖሊሲን መተግበር ከመፍትሄዎቹ መካከል እንደሆኑም ገልጸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58089453 +politics ሳይፍ ጋዳፊ - የቀድሞው የሊቢያ መሪ ልጅ 'ፕሬዝደንታችሁ አርጋችሁ ምረጡኝ' እያሉ ነው የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአማር አል-ጋዳፊ ልጅ በሚቀጥለው ወር በአገሪቱ በሚካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ለመሳተፍ መመዝገቡ ተሰምቷል። ሳይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ በአንድ ወቅት ከአባቱ ሥልጣን ለመረከብ ጫፍ የደረሰ ሰው ነበር። ነገር ግን ከ10 ዓመት በፊት ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን በደል መደገፉ ስሙ እንዲጠለሽ አድርጎታል። ከዚህ ተቃውሞ በኋላ ሊቢያ ወደ ቀድሞ ሰላምና መረጋጋቷ መመለስ ፈጽሙ አልቻለችም። የመብት ተሟጋች ቡድኖች በሚወጥለው ወር የሚካሄደው ምርጫ ነፃና ፍትሐዊ ላይሆን ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ኃያላን የሚባሉ አገራትና የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ምርጫውን ለማደናቀፍ የሚሞክር አሊያም ውጤት የሚያዛባ አካል ከባድ እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በይነ መረብ ላይ የተሰቀሉ ፎቶዎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎች፤ ሳይፍ ጋዳፊ ከአንድ የማስታወቂያ 'ፖስተር' ፊት ቆሞ በምርጫው ለመሳተፍ ሲመዘገብ አሳይተዋል። ፊቱ በፂም የተወረረውና በሊቢያ ባሕላዊ ልብስ ያሸበረቀው ሳይፍ ከቁርዐን ላይ ምዕራፎችን ���የመዘዘ ለከበቡት ካሜራዎች ተናግሯል። ሳይፍ አሁን ያለው አቋምና አባቱ ጋዳፊ ሥልጣን ላይ እያሉ ያሳይ የነበረው አቋም ፍፁም የተለያዩ ሆነው ተስተውለዋል። አባቱ በፈረንጆቹ 2011 ከሥልጣን ሲወገዱ ሳይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ በሚሊሻዎች ቁጥጥር ሥር ውሎ ነበር። በሚሊሻዎች ቁጥጥር ስድስት ዓመታትን ካስቆጠረ በኋላ ሞት ተፈርዶበት ነገር ግን ይህ ፍርድ የኋላ ኋላ ሊቀለበስ ችሏል። የጋዳፊ ልጅ ሳይፍ አሁንም በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት [አይሲሲ] በጦር ወንጀሎች ይፈለጋል። ሳይፍ ብቅ ብቅ ማለት የጀመረው ቀስ በቀስ ሲሆን በተለይ ዚንታን ከሚገኘው ቪላ ቤቱ ሆኖ ከኒው ዮርክ ታይምስ ጋር ያደረገው ቃል ምልልስ ብዙ ተመልካች አግኝቷል። እንደ ቢቢሲ ሞኒተሪንግ ባልደረባ አሚራ ፋታላ ዘገባ ከሆነ የጋዳፊ ልጅ በምርጫው ለመሳተፍ መመዝገብ ሊቢያዊያንን ለሁለት ከፍሏል። ነገር ግን ለዓመታት አባቱን ይተካል እየተባለ ሲጠበቅ ስለነበር ወደ ሥልጣን ለመምጣት ማሰቡ ብዙም አስገራሚ አልሆነም። ቢሆንም የቀጣዩን ወር ምርጫ ለማሸነፍ ቀላል እንደማይሆንለት የቢቢሲ መካከለኛው ምሥራቅ አርታኢ ሴባስቲያን አሸር ይናገራል። አርታኢው ወትሮውንም በቋፍ ላይ የሚገኘው የሊቢያ ምርጫ በጋዳፊ ልጅ ወደፊት መምጣት ምክንያት እንዳይናወጥ ስጋት አለው። ለዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት ስትታመስ የቆየችው ሊቢያ አሁን በጊዜያዊ መንግሥት አስተዳደር ሥር ብትሆንም አሁንም አለመረጋጋት አለ። በሊቢያ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በምርጫው ሕግና ቀነ ቀጠሮ ምክንያት የተነሳው አለመግባባት ፕሬዝደንታዊውን ምርጫ እንዳያመክነው ስጋት ጭሯል። በምርጫው ለመሳተፍ ከተመዘገቡት መካከል የአገሪቱን ምሥራቃዊ ክፍል የተቆጣጠረውን አማፂ ቡድን ይመሩ የነበሩት ኻሊፋ ሐፍጣርና በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈውን መንግሥት የሚያስተዳድሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አል-ድቤባህ ይገኙበታል። https://www.bbc.com/amharic/news-59284872 +business በኢትዮጵያ ለወራት የቆየው የብድር እቀባ በምጣኔ ሀብቱ ላይ ምን ውጤት ነበረው? "ላለፉት አራት ወራት ተግባራዊ ተደርጎ የነበረው የብድር ክልከላ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዚህ ሳምንት አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ ኅዳር 20/2014 ዓ.ም ባንኮች የብድር አገልግሎት ለሁሉም ደንበኞቻቸው እንዲሰጡ ትዕዛዝ ማስተላለፉን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የብድር ክልከላው 'የምጣኔ ሀብትን አሻጥር' ለመከላከል በማለምና በጥቁር ገበያና በመደበኛ የባንኮች የውጭ ምንዛሪ ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት መስፋቱን ተከትሎ የተጣለው ባለፈው ነሐሴ ወር ነበር። ለመሆኑ ይህ ለወራት የቆየ የብድር እቀባ ምጣኔ ሀብቱን እንዴት ጎድቶታል? ""ብድር የምጣኔ ሀብት ሞተር ነው"" የሚሉት በኩዌት የሳይንስና ምርምር ተቋም የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ ዶ/ር አየለ ገላን እቀባው ቀድሞውኑም መጣል አልነበረበትም ይላሉ። ተመራማሪው እንደሚሉት ""ከአገር ደኅንነትና ሕገ ወጥ ገንዘብን ለመቆጣጠር ጭራሽኑ ገንዘብ ምጣኔ ሀብቱ ውስጥ አይግባ፤ ከምንጩ እናድርቀው ማለት አግባብ አይደለም"" ብለዋል። ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎችም ብሔራዊ ባንክ በአብዛኛው የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች ምንን መሠረት እንደሚያደርጉ ግልጽ አለመሆኑን በማንሳት ውሳኔዎቹ ውጤት አስገኝተዋል፤ አላስገኙም ለማለት እንደሚያስቸግር ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ባለበት አገር ባንኮች መሠረታዊ ሥራቸውን እንዳይሠሩ ማገድ ምጣኔ ሀብቱን እንዲቆም ማድረግ ነው ይላሉ። ባለሙያዎቹ እያንዳንዱ የሚዘዋወረው ገንዘብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በብድር መልክ ከባንክ የሚመጣ ነው ��ማለትም እቀባው በተጣለባቸው ጊዜያት ""ብዙ ነገር ጠፍቷል"" ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ይህንን ሃሳብ የሚጋሩት ዶ/ር አየለም በምጣኔ ሀብቱ ላይ ጠቅላላ ጉዳት የሚያመጣ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ቁጥጥሩን ማጥበቅ ይቻል ነበር ብለዋል። ""ብድር አይነኬ መሆን አለበት፤ ብድር ማቆም ማለት የአንድን ሰው የደም ዝውውርን እንደማቆም ነው"" ብለዋል ተመራማሪው። የብድር ክልከላው በምጣኔ ሀብቱ ላይ ያደረሰው ጉዳት እንዴት ይገለጻል? በሚል ለቀረበለቸው ጥያቄም ዶ/ር አየለ ""ምጣኔ ሀብቱን ካለበት ወደ ኋላ የመለሰ፣ በምንም መለኪያ የማይገለጽ አጠቃላይ ውድቀት ነው"" ሲሉ ገልጸውታል። የብድር አገልግሎት ሳይከለከልም የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ችግር እንደነበረበት ያስታወሱት ተመራማሪው፤ እቀባው መጣሉ በእሳት ላይ ቤንዚን እንደመጨመር መሆኑን አስረድተዋል። ተጥሎ የነበረው የብድር እቀባ ምን የሚል ነበር? ነሐሴ ወር ላይ በብሔራዊ ባንክ ተላልፎ የነበረው የብድር ክልከላ ባንኮች ሕንጻ፣ መሬትና ቤቶችን መያዣ በማድረግ የሚሰጡ ብድሮችን በጊዜያዊነት እንዲያቆሙ ያዛል። ከማስያዣ ውጭ የሚሰጡና ከወጪ ንግድ ጋር የተያያዙ የብድር ዓይነቶችም ተቋርጠው ነበር። ይሁን እንጂ እቀባው በሌሎች ተንቀሳቃሽ ንብረቶች የሚሰጥን ብድር የሚከለክል አልነበረም። በወቅቱ የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔው የተላለፈው ""በምጣኔ ሀብቱ ውስጥ እየታየ ያለውን አሻጥር"" ለመቆጣጠር በማሰብ መሆኑን ገልጾ ነበር። ብሔራዊ ባንኩ ባለፍነው መስከረም ወር ላይ ባስተላለፈው የብድር ክልከላ ላይ ማሻሻያ በማድረግ ባንኮች አምስት የብድር ዓይነቶችን መፍቀድ እንደሚችሉ አስታውቆ ነበር። ከእነዚህም መካከል ባንኮች የሰጡትን ብድር ለማስመለስ በሐራጅ ያወጧቸውን ንብረቶች ለመግዛት ለሚጠይቁ ገዥዎች፣ ባንኩ ብድር መውሰድ ያስችላሉ ያላቸው በሁለተኛ እና ሦስተኛ ወገኖች መካከል የሚደረግ ግብይትና ለባንክ ሠራተኞች የሚሰጥ አስቸኳይ ብድር ይገኙበታል። ከዚህም ባሻገር በጎንደር አካባቢ ለሚገኙ ሰሊጥ አምራቾች የፀደቀ የብድር ዓይነት እንዲለቀቅም ባንኩ ባወጣው ማሻሻያ መገለፁ ተዘግቧል። የብድር ክልከላው መነሳቱ ምን ፋይዳ ይኖረው ይሆን? ብዙ ጊዜ ብሔራዊ ባንክ መሠል ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ መነሻው እንደማይታወቅና ለውይይትም ክፍት አለመሆኑን የሚያስታውሱት የዘርፉ ባለሙያዎች፤ እቀባው መነሳቱ ምን አስገኘ የሚለውን ለመናገር መጀመሪያ የተፈለገው ምን እንደሆነ መታወቅ እንዳለበት ይናገራሉ። ""በመሆኑም በውሳኔው ምን እንደተገኘ ሊያብራራ የሚችለው ብሔራዊ ባንክ ነው"" ይላሉ። ብሔራዊ ባንክ የብድር ክልከላው መነሳቱን ከመግለፅ ያለፈ በጉዳዩ ላይ የሰጠው ማብራሪያ የለም። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ከብሔራዊ ባንክ ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራም አልተሳካም። በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ለበርካቶች መተዳደሪያ ነው። ባንኮችም ብድር በመስጠት ከፍተኛ ገቢ ያገኛሉ። ሌሎችም ብድርን የተንተራሱ በርካታ ዘርፎች አሉ። በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፉ የበርካቶች መተዳደሪያ እንደሆነ እንደ አብነት በመጥቀስ፤ እቀባው መነሳቱ ይህን ዘርፍ እንዲያንሰራራ ያደርገው ይሆን? ተብለው የተጠየቁት የምጣኔ ሀብት ተመራማሪው ዶ/ር አየለ፤ የኮንስትራክሽን ዘርፉም ሆነ ሌላው ከባንክ ከሚገኝ ብድርና ራሱ ካለው ጋር አዋህዶ ነው የሚንቀሳቀሰው ይላሉ። ነገር ግን የኮንስትራክሽን ዘርፉ ብዙ ሰዎችን ቢቀጥርም፤ እርሱን ""እንደ ኢኮኖሚ ሞተር"" አድርጎ መውሰድ ስህተት መሆኑን ተናግረዋል። ""ትልቁ የኢኮኖሚ በሽታ ኮንስትራክሽንን እንደ ኢኮኖሚ ሞተር ማሰብ ነው"" ይላሉ ዶ/ር አየለ። ላለፉት 30 ዓመታት ���ርካታ የኮንስትራክሽን ሥራዎች መሠራታቸውን ያስታወሱት ተመራማሪው፤ ይህ ግን የኢኮኖሚ መረጋጋትን እንዳላመጣና የኑሮ ውድነትን እንዳልቀነሰም ያስረዳሉ። በመሆኑም ብሔራዊ ባንክ ለኮንስትራክሽን የሚሰጠውን ብድር ቀንሶ ወደ ግብርና ወይም ጥቃቅን ኢንደስትሪዎች እንዲዞር ማድረግ አለበት ሲሉም ይመክራሉ። ""ብድር ለእንስሳት እርባታ፣ ለፍራፍሬ ምርት፣ ለወተት፣ ለአልባሳት ምርት እና ምርት ለሚገኝባቸው ዘርፎች ቢዛወር፤ ከባንክ የተሰጠው ብድር ወደ ዋጋ ግሽበት (ኢንፍሌሽን) ሳይሆን የተረጋጋ ገበያ እንዲኖር ያደርግ ነበር"" ብለዋል ዶ/ር አየለ። የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለፈው ዓመት በ2020 ከነበረበት 6 በመቶ በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት በ2021 ሁለት በመቶ ብቻ እንደሚያድግ ተገምቷል። ይህም በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከታየው በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርክት (አይኤምኤፍ) መረጃ አሳይቷል። አገሪቱ በዓመት ወደ 14 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እቃዎችን ከውጭ የምታስገባ ሲሆን ወደ ውጪ የምትልከው 3.4 ቢሊዮን ዶላር ብቻ የሚያወጡ ምርቶችን ነው። ከዚህም በተጨማሪ የአገሪቱ ብሔራዊ ዕዳ በዚህ ዓመት 60 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) 70 በመቶ ይደርሳል ተብሏል። በርካታ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችም ""ይህ የሚያሳስብ ነው"" ብለዋል። በኢትዮጵያ የሰሜኑ ክፍል እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ የቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት እድል ማገዷ፣ የአበዳሪዎች ብድር ለመስጠት ማቅማማት እንዲሁም በጦርነቱ ሳቢያ የአገር ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች መስተጓጎል በምጣኔ ሀብቱ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59463389 +sports የዱባይ ማራቶን በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት ተጠናቀቀ "ትናንት ሌሊት በተከናወነው የዱባይ ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀዋል። በወንዶች አትሌት ኦሊቃ አዱኛ ቢቂላ ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ ወርቅነሽ ደገፋ የመጀመሪያ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። አትሌት ኦሊቃ ውድድሩን በአንደኝነት ለማጠናቀቅ 02፡06፡15 የፈጀበት ሲሆን፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሦስተኛ እስከ 10 ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኬኒያዊው ኤሪክ ኪፕታኑ ነው። በሴቶች በተካሄደው ውድድር አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ 02፡19፡37 በመግባት በአንደኝነት ስትጨርስ፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሁለተኛ እስከ ዘጠነኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። አትሌት ጉተኒ ሾኔ ሁለተኛ ስትሆን አትሌት በዳቱ ሂርጳ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። አትሌት ወርቅነሽ ትናንት ከውድድሩ በፊት ለቢቢሲ ለዚህ ውድድር ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጓን ተናግራለች። አትሌት ወርቅነሽ ""የዱባይ አቀማመጥ ለኔ በጣም ምቹ ነው አሸንፋሁ"" ብላ ነበር። አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ የ2017ቱን የዱባይ ማራቶን ማሸነፏ ይታወሳል። ሁለተኛ ደረጃን የያዘችው አትሌት ጉተኒ ሾሜ 02፡20፡11 የገባች ሲሆን አትሌት በዳቱ ደግሞ 02፡21፡54 በሆነ ሰዓት አጠናቃለች። የዱባይ ማራቶን መዘጋጀት ከጀመረ ወዲህ ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች 15 ጊዜ በወንዶች ደግሞ 14 ጊዜ አሸንፈዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-51232629 +health ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ ኮርያ ለድመት እና ውሾች የኮቪድ-19 ምርመራ ልታደርግ ነው "ደቡብ ኮሪያ በዋና ከተማዋ ሶል የሚገኙ ውሾች እና ድመቶች የኮቪድ-19 ምልክት ካሳዩ ምርመራ እንደሚደረግላቸው የሶል ሜትሮፖሊታን አስተዳደር አስታወቀ። የከተማዋ አስተዳደር እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኮቪድ-19 የተያዘች ድመት መገኘቷን ተከትሎ ነው። ምልክቱን የሚያሳዩ የቤት እንሰሳት ብቻ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ይደረግላቸዋል ተብሏል። በተጨማሪም ቫይረሱ ለያዘው ሰው የተጋለጡና ትኩሳት ወይንም ደግሞ የመተንፈስ ችግር የገጠማቸው ድመትና ውሾች ምርመራ እንደሚደረግላቸው ተገልጿል። እነዚህ የቤት እንስሳት ተመርምረው ተህዋሲው እንዳለባቸው ከተረጋገጠ በቤት ውስጥ ራሳቸውን አግልለው እንዲቀመጡ ይደረጋል። እንደ ዩንሃፕ የተሰኘ መገናኛ ብዙኀን ዘገባ ከሆነ የደቡብ ኮሪያ በሽታ መቆጣጣር ኃላፊ የሆኑት ፓርክ ዮ ሚ እነዚህ የቤት እንስሳት መንግሥት ወዳዘጋጃቸው ለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባት አይጠበቅባቸውም። ነገር ግን የእነዚህ እንስሳት ባለቤት በኮቪድ-19 ታምሞ ሆስፒታል ከገባ፣ በጠና ከታመመ ወይንም ደግሞ በእድሜ መግፋት ምክንያት ለመንከባከብ ካልቻለ የከተማ አስተዳደሩ ወደሚያስተዳድረው የለይቶ ማቆያ ይወሰዳሉ ተብሏል። እስካሁን ድረስ የኮሮናቫይረስ ከቤት እንስሳት ወደ ሰው ስለመተላለፉ የተገኘ ማረጋገጫ የለም። ኃላፊዋ አክለውም ነዋሪዎች ""የቤት እንስሳቶቻቸውን በሚያንሸራሽሩበት ወቅት ከሰዎችም ሆነ ከሌሎች እንስሳት ቢያንስ ሁለት ሜትር እንዲያርቋቸው"" አደራ ብለዋል። ባለፈው ወር በአንድ የሃይማኖት ተቋም ውስጥ የተገኘች ድመት በኮሮናቫይረስ መያዟ በምርመራ መረጋገጡን ዮንሃብ የዜና ወኪል ዘግቧል። የጤና ባለሙያዎች በሃይማኖት ተቋሙ ውስጥ የነበሩ እናትና ልጅ ቫይረሱን ወደ ድመቷ ማስተላለፋቸውን ጠርጥረዋል። እናትና ልጅ በኮቪድ 19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ባለሙያዎች ድመትም ሆነ ውሻ ቫይረሱን ወደ ሰው የማስተላለፍ እድላቸው በጣም የጠበበ ነው ያሉ ሲሆን ድመቶች ግን እርስ በእርስ ቫይረሱን ሊያስተላልፉ ይችላሉ ብለዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በተደጋጋሚ የቤት አንስሳት በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጦ ያውቃል። ባለፈው ወር በሳንዲያጎ መካነ አንስሳት ሁለት ጎሬላዎች ይንከባከባቸው ከነበረ ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ተይዘው ተገኝተዋል። በኒውዮርክ ብሮንክስ መካነ አንስሳት ደግሞ ዝሆን እና ታይገር፣ በስፔን ባርሴሎና መካነ እንስሳት አንበሳ በኮሮና ተህዋሲ ተይዘዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55984271 +health ልጅን አቅፎ መተኛት ወይስ ለብቻ በተዘጋጀ አልጋ ላይ ማስተኛት? "ወላጆች ስለ ልጆቻቸው የሚያሳስቧቸው ጉዳዮች በርካታ ናቸው። ይህ ግን ከአገር አገር፣ ከባህል ባህል፣ ከኑሮ ደረጃ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ሊለያይ ይችላል። ""ልጄ ክፍሉ ውስጥ ይሆን?"" የሚለው ጥያቄ በበርካታ የምዕራቡ ዓለም ወላጆች ጭንቅላት ውስጥ የሚመላለስ ሃሳብ ነው። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ይህ እየተለወጠ የመጣ ይመስላል። የህጻናት አስተዳደግና ሁኔታም እየተቀያየረ ነው። ይህ ደግሞ በምዕራባውያኑ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የዓለማችን ከፍል እየሆነ ያለ ነው። በአንዳንድ ባህሎች ከልጆች ጋር አንድ ክፍል መጋራት አንዳንዴም አንድ አልጋ ላይ መተኛት የተለመደ ቢሆንም የምዕራቡ ዓለም ወላጆች ግን ልጆቻቸውን የሚያሳድጉበት የራሳቸው የሆነ መንገድ አላቸው። በእቅድ የሚመራ የእንቅልፍ ሥርዓትና የእንቅልፍ ልምምድ ስልጠና እስከመስጠትም ተደርሷል። ምናልባት እነዚህ ነገሮች ዘመናዊና አዲስ ዓይነት ልጆችን የማሳደጊያ መንገዶች መስለው ሊታዩ ይችላሉ። በአሜሪካና ዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ወላጆች ልጆቻቸው ከተወለዱ በኋላ ቢያንስ ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት አብረዋቸው አንድ ክፍል ውስጥ እንዲያስተኟቸው ይመከራሉ። በመላው ዓለም በሚገኙ በርካታ ማሕበረሰቦች፤ ልጆች ከዚህ ረዘም ላለ ጊዜ ከወላጆቻቸው ጋር ያሳልፋሉ። በአውሮፓውያኑ 2016 ላይ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት በተለይ የእስያ አገራት የሚገኙ ወላጆች ረዘም ላለ ጊዜ ከልጆቻቸው ጋር አንድ ክፍል ውስጥ አልያም በአንድ አልጋ ላይ ይተኛሉ። ለምሳሌ እንደ ሕንድ እና ኢንዶኔዢያ ባሉ አገራት 70 በመቶ የሚሆኑት ወላጆች እንዲሁም በስሪላንካ እና ቪዬትናም 80 በመቶ የሚሆኑት ወላጆች ረዘም ላለ ጊዜ ከልጆቻቸው ጋር በአንድ አልጋ ላይ ይተኛሉ። በአፍሪካ ደግሞ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ረዘም ላለ ጊዜ በአንድ ክፍል ውስጥ አልያም በተመሳሳይ አልጋ መተኛት ብዙም የተለመደ አይደለም ይላል ጥናቱ። ከዚህ መረዳት የሚቻለው ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ቢያንስ በመጀመሪያዎቹ ወራት በአንድ አልጋ ላይ መተኛት የተለመደ ነገር መሆኑን ነው። ዴብሚታ ዱታ በሕንዷ ባንጋሎር ዶክተር እና የልጆች አስተዳደግ አማካሪ ሲሆኑ ምንም እንኳን የምዕራባውያን ተጽዕኖዎች ቢኖሩም የአልጋ መጋራት አሁንም ሕንድ ውስጥ ጠንካራ ባህል ነው ይላሉ። ሌላው ቀርቶ በርካታ ልጆች ያሉበት ቤት ቢሆንም አልያም ልጆቹ ሲያድጉ የራሳቸው ክፍል የሚሰጣቸው ቢሆንም በመጀመሪያዎቹ ወራት (እስከ 12 ወራት) ግን ከወላጆቻቸው ጋር በአንድ አልጋ ላይ እንዲተኙ ይደረጋሉ። ''በአንድ አልጋ ላይ መተኛት ዋነኛው ጥቅሙ ልጆች ሌሊት ላይ ከእንቅልፋቸው እንዳይነሱ እና ወላጆቻቸውን እንዳይረብሹ ነው'' ይላሉ ዶክተር ዴብሚታ። አክለውም ''ሴት ልጄ ሰባት ዓመት እስከሚሞላት ድረስ ከእኛ ጋር ነበር አልጋ የምትጋራው። ጡት መጥባት ካቆመች በኋላ እንኳን ከእኛ ጋር መተኛት ትወድ ነበር'' ይላሉ። ልጆች ከልጅነታቸው ጀምሮ ነጻነታቸውን አውጀው እንዲያድጉ ማድረግ የምዕራቡ ዓለም ፍልስፍና ተደርጎ ይቆጠራል። በዚህ ምክንያት ከወላጆች ጋር አልጋ መጋራት ልጆች በራሳቸው ነገሮችን ማድረግ የማይችሉ እንዲሆኑ እንደሚያደርጋቸው ይታመናል። በተጨማሪም ልጆች ከወላጆች ጋር አብረው የሚተኙ ከሆነ ሁሉም ፍላጎታቸው ያለገደብ ይሟላል ተብሎ ይታሰባል። ይህ ደግሞ የልጆች አስተዳደግ ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል ይላሉ ምዕራባውያኑ። እንደ ዶክተር ዴብሚታ ያሉ ወላጆች ግን በዚህ ሀሳብ አይስማሙም። '' ትንሽ በራስ መተማመን እንዲኖራቸውና መጠኑን ያላለፈ ነጻነት ከሰጠናቸው ልጆች በራሳቸው ጊዜ ከወላጆቻቸው መለየት ይጀምራሉ። ለዘለአለም ከወላጆቻቸው ጋር መቆየት አይፈልጉም'' ይላሉ ዶክተር ዴብሚታ። በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ በርካታ ወላጆች ግን ልጆችን እንቅልፍ ማለማመድ ላይ ተጠምደዋል። ልጆች ቢያለቅሱ እንኳን እዚያው ትንሿ አልጋቸው ላይ ሆነው ለቅሷቸውን እስኪጨርሱ እስከመጠበቅ ደርሰዋል። በዚህ ሂደት ውስጥ ልጆች ለረጅም ጊዜ እንቅልፋቸውን መተኛት እንደሚማሩ ይታሰባል። በዚህ መካከልም ወላጆች በቂ የሆነ እረፈት ያገኛሉ ማለት ነው። በአውስትራሊያ በመንግሥት ድጋፍ የሚደረግላቸው እንቅልፍ ማስተማሪያ ማዕከላት ጭምር አሉ። ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ እነዚህ ማዕከላት ይዘው በመሄድ ልጆቻቸው ረዘም ላለ ጊዜ እንቅልፍ መተኛት እንዲማሩ ማድረግ ይችላሉ። በመሆኑም በተለያዩ አገራት ያለው የባህል ልዩነት ልጆች የት መተኛት አለባቸው የሚለውን ብቻ ሳይሆን መቼ እና እንዴት መተኛት አለባቸው የሚለውን ይወስናል ማለት ነው። በቶክዮ ቤይ ኡራያሱ ኢቺካዋ ሜዲካል ማዕከል ውስጥ በተሰራ ጥናት መሰረት፤ ጃፓን ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ሦስተኛ ወራቸው ላይ ሲደርሱ ከሌሎች የእስያ አገራት ያነሰ እንቅልፍ እንደሚተኙ ተገልጿል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ጃፓን ውስጥ እንቅልፍ የስንፍና ምልክት ተደርጎ ስለሚቆጠር ሊሆን እንደሚችል ይነገራል። በእስያ አገራት የሚገኙ ህጻናት ለምሳሌ ከምዕራቡ ዓለም ህጻናት ጋር ሲነጻጸር እንቅልፍ ሳይተኙ ረዘም ላለ ጊዜ ይቆያሉ። ይህ ደግሞ የሚሆነው ወላጆች ከሥራ ሲመለሱም ይሁን በየትኛውም አጋጣሚ ከልጆቻቸው ጋር እንደ ልብ መጫወትና ጊዜ ማሳለፍ ስለሚፈልጉ ነው ይላል ጥናቱ። በዩናይትድ ኪንግደም ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲተኙ ይመከራል። ልክ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም በአሜሪካም የዘርፉ ባለሙያዎች ተመሳሳይ ምክር ይሰጣሉ። ምክንያቱ ደግሞ ልጆች ብቻቸውን ሆነው የሆነ እክል ቢያጋጥማቸው ሊከሰት የሚችለውን የሞት ቁጥር ለመቀነስ ብቻ ነው። ይሁን እንጅ ባለሙያዎቹ ከልጆች ጋር አንድ ላይ መተኛትን አጥብቀው ይቃወማሉ። ለዚህ በምክንያትነት የተቀመጠው ደግሞ ልጆች ታፍነው ሊሞቱ ይችላሉ የሚል ነው። ነገር ግን በጉዳዩ ላይ በቂና ጥልቅ የሆነ ምርምር ባለመካሄዱ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር አልጋ መጋራታቸው ጠቃሚ ነው ወይስ ጎጂ የሚለው ላይ ጥርት ያለ አቋም መያዝ ከባድ ነው ይላሉ- የህጻናት ህክምና ባለሙያው ዶክተር ራሽሚ ዲያዝ። በዚህ ጉዳይ የተሰሩት ጥናቶችም ቢሆኑ አብዛኛዎቹ ካደጉት አገራት በተሰበሰበ መረጃ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። በእነዚህ አገራት ደግሞ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር አልጋ የመጋራት ባህላቸው ዝቅተኛ ነው። በሌላ በኩል ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ከልጆች ጋር አልጋ መጋራት የተለመደ ባህል ሲሆን በእነዚህ አገራት በእንቅልፍ ላይ እያሉ የሚሞቱ ህጻናት ቁጥር በእጅጉ ዝቅተኛ ነው። ልክ ከልጆች ጋር አልጋ መጋራት ሌሊት ላይ ቅርብ ለመሆን እንደሚያስችለው ሁሉ፤ ልጆች ቀን ላይ እንዳይተኙ ማድረግ ደግሞ ወላጆች ሥራቸውን እየሰሩ ከልጆቻቸው ጋር ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ ሊረዳቸው ይችላል። ሌላኛው ከልጆች አስተዳደግ ጋር የሚነሳው ነጥብ ልጆችን አቅፎ መንቀሳቀስ ብዙ እንዳያለቅሱ ያደርጋቸዋል ወይ የሚለው ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ ምርምር የሰራችው ኩሮዳ እንደምትለው ወላጆች ልጆቻቸውን አቀፏቸው፣ አዘሏቸው ወይም አላዘሏቸው ማልቀሳቸው አይቀርም። ''ልጆችን ማቀፍ እና እንዳያለቅሱ ማድረግ ምንም አይነት ግንኙነት የላቸውም። በዚህ ላይ ልስማማ አልችልም'' ትላለች። በኩሮዳ ጥናት መሰረት ልጆችን ማቀፍ የልብ ምታቸውና እንቅስቃሴያቸው እንዲቀንስ እንደሚያደረግ የተስተዋለ ሲሆን ከለቅሷቸው ጋር ግን የሚገናኘው ነገር የለም። ነገር ግን ልጆችን አቅፎ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ትኩረታቸው በሌላ ነገር ላይ እንዲሆን ሲደረግ የማልቀሳቸው መጠን የሚቀንስ ሲሆን እያለቀሱም ከሆነ የማቆም እድላቸው ከፍተኛ ነው። ከልጆች ጋር ዐይን ለዐይን መተያየት ሁሌም ቢሆን ከህጻናቱ በኩል የሚጠበቅ ነገር ነው። ከዚህ በተጨማሪ ለመጀመሪያዎቹ ወራት ህጻናት ያለማቋረጥ ምግብ መመገብ አለባቸው። ሌላው ቀርቶ ከአዋቂዎች የእንቅልፍ ሥርዓት ጋር መላመድ በሚጀምሩበት ወቅት እንኳን እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ሌሊት ላይ ከእንቅልፋቸው ሊነቁ ይችላሉ። ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው። ነገር ግን ምዕራባውያን ወላጆች ከጓደኞቻቸውና ቤተሰቦቻቸው የሚነገራቸው ነገር ለየት ያለ ነው። ልጆች ሌሊት ላይ የሚነቁ ከሆነ ችግር ውስጥ እንደሆኑ ነው የሚነገራቸው። ይህ ደግሞ ከባህል ጋር የሚገናኝ ነገር ነው። ልጆች ሌሊት መነሳታቸው የተለመደና ጤናማ ነገር ቢሆንም፤ ቀን ላይ ረዥም ሰዓት የማይተኙ ከሆነ ግን ሌሊት ላይ ሳይነቁ ሊተኙ ይችላሉ። ልጆች ሌሊት ላይ ለጥ ብለው መተኛት አለባቸው የሚለው ብሂል የመጣው በአውሮፓውያኑ 1950ዎቹ አካባቢ በተሰራ አንድ ጥናት ላይ ተመስርቶ ነው። በጥናቱ መሰረት ከእንግሊዟ ለንደን ከተማ ከተውጣጡ ከ160 ህጻናት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት በሦስተኛ ወራቸው ላይ ሌሊቱን ሙሉ ነበር የሚተኙት። ነገር ግን ተመራማሪዎቹ ሌሊቱን ሙሉ መተኛት ���ለው የገለጹት ህጻናቱ ሌሊት ላይ ወላጆቻቸውን አለመረበሻቸውንና ድምጻቸው አለመሰማቱን ብቻ ነው። ምናልባት ህጻናቱ ወላጆቻቸውን አይረብሹ እንጂ ቢያንስ አንድ ጊዜ እንኳን መንቃታቸው አይቀርም። አሁንም ቢሆን ከህጻናት እንቅልፍና አስተዳደግ ጋር በተያያዘ የሚሰሩት ጥናቶች በጣም ጥቂት የሚባል የዓለማችንን ማህበረሰብ ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው። አብዛኛዎቹ ጥናቶች የተሰሩት 'ባደጉት' በሚባሉት ምዕራባውያን አገራት ውስጥ በሚገኙ ህጻናት ላይ ብቻ ነው። ምንም እንኳን በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ያለው የልጆች አስተዳደግ በተለያዩ ባህሎች ላይ የተመሰረተ ቢሆንም፤ ልጆች ሁልጊዜም ከወላጆቻቸው ተገቢውን ጊዜና እንክብካቤ ማግኘት አለባቸው የሚለው ግን አጠያያቂ ጉዳይ አይደለም።" https://www.bbc.com/amharic/news-56549405 +health በአፍሪካ የተፈራውን ያክል ድህነት ሰዎችን ለኮሮናቫይረስ አጋልጧል? ከአፍሪካ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚዋ ደቡብ አፍሪካ ናት። አሁን ላይ ግን በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው። በሌሎች የአፍሪካ አገራት ያለው ስርጭት መጠንም በአንጻራዊነት ዝግ ያለ ነው። አፍሪካ ውስጥ በርካታ የተጨናነቁ መንደሮች አሉ። በእነዚህ መንደሮች ንጽህናና አካላዊ ርቀት መጠበቅ ከባድ ነው። በአንጻራዊነት ደህና በሚባሉ ከተማ ቀመስ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ቫይረሱን በፍጥነት ሊያሰራጩት እንደሚችሉ የጤና ባለሙያዎች ሲያስጠነቅቁ ተደምጠዋል። በደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 አማካሪ ቡድን ኃላፊ ሳሊም አብዱል ካሪም እንደሚሉት፤ ሰዎች በብዛት፣ ተጨናንቀው በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ቫይረሱ በፍጥነት ይሰራጫል። እውነታው ከዚህ የባለሙያዎች መላ ምት ተቃራኒ ቢሆንስ? የተጨናነቁ መንደሮች እንደተገመተው ለበሽታው መሰራጨት ምክንያት ሳይሆኑ እንዲያውም ቫይረሱ በስፋት እንዳይስፋፋ አድርገው ቢሆንስ? የአህጉሪቱ ድህነት እንደተፈራው ለወረርሽኙ ተጋላጭ ሳያደርጋት ቀርቶ ቢሆንስ? ሚሥጥሩ ምንድን ነው? ኮሮናቫይረስ መሰራጨት ሲጀምር ሁሉም ባለሙያዎች አፍሪካ አደጋ ውስጥ ትወድቃለች ብለዋል። የደቡብ አፍሪካው ቫይሮሎጂስት ሻቢር ማህዲ “ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደምንገባ አስቤ ነበር። አበቃልን ብዬም ነበር” ይላሉ። በጣም ተስፋ ሰጪ ናቸው የተባሉ መላ ምቶች ሳይቀሩ ለህሙማን አልጋ እንደሚጠፋ፣ የጤና ሥርዓቱ እንደሚቃወስ ሲጠቁሙ ነበር። ሆኖም ግን በደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዩናይትድ ኪንግደም በሰባት እጥፍ ያንሳል። ደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳትሆን ሌሎች አገራትም የተፈራው ያህል ቫይረሱ ጉዳት እያደረሰባቸው አይደለም። ሆስፒታሎች እንደተሰጋው አልተጨናነቁም። በተቀረው ዓለም እንደተከሰተው የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ጫፍ ላይ ደርሶም አልታየም። ፕ/ር ሻቢር፤ “በአብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት የቫይረሱ ስርጭት ጫፍ አልታየም። ለምን እንደሆነ አልገባኝም። ግልጽ ያልሆነና ለማመን የሚያስቸግር ነው” ይላሉ። አፍሪካ ውስጥ ኮሮናቫይረስ በአስጊ ሁኔታ ያልተሰራጨው አብዛኛው የአህጉሪቱ ነዋሪ ወጣት ስለሆነ ነው የሚሉ ባለሙያዎች አሉ። የአፍሪካውያን አማካይ እድሜ ከአውሮፓውያኑ በግማሽ ያንሳል። የቶኒ ብሌር ተቋም የአፍሪካ ዳይሬክተር ቲም ብሮምፊልድ እንደሚሉት፤ አፍሪካ የወጣቶች አህጉር መሆኗ ከበሽታው ተከላክሏታል። ነገር ግን በበሽታው የተያዙ ሰዎችን እድሜ ከግምት ያስገቡ የስታትስቲክስ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ እድሜ ከበሽታው የሚከላከል ብቸኛ ነገር አይደለም። ፕ/ር ሳሊም “ትልቁ ነጥብ እድሜ አይደለም” የሚሉትም ለዚህ ነው። በደቡብ አፍሪካ እና በሌሎችም አገራት ወረርሽ��� መሰራጨት እንደጀመረ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ሚናው ቀላል አይደለም። ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉም ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል። በሌላ በኩል የአህጉሪቱ ከፍታ እና ሙቀት የበሽታውን ስርጭት ይቀንሳል የሚለው መላ ምት እንደማይሠራ ተገልጿል። በቂ የመሠረተ ልማት ዝርጋት ባለመኖሩ ለወደፊት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት ያላቸው አሉ። “አፍሪካ ክፉውን ጊዜ አልፋለች ማለት አልችልም። አንድ ቀን ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምር ይሆናል” ሲሉ ፕ/ር ሳሊም ያስረዳሉ። ሌሎቹ ኮሮናቫይረሶች በሶዌቶ የክትባት ቤተ ሙከራ ውስጥ ሳይንቲስቶች ምርምር እያደረጉ ይገኛሉ። በቤተ ሙከራው ለአምስት ዓመታት የቆየ የሰው ደም ናሙና አለ። ይህም የኢንፍሉዌንዛ ክትባት ላይ ምርምር ሲካሄድ የተገኘ ናሙና ነው። ተመራማሪዎቹ፤ ሰዎች በሌሎች አይነት ኮሮናቫይረሶች መያዛቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እየፈለጉ ነው። ይህ ማለት ሰውነት ራሱን ከኮቪድ-19 የሚከላከልበት አቅም አዳብሯል ማለት ነው። “ከዚህ ቀደም በሽታን የመከላከል አቅም ማዳበር ተችሎ ሊሆን ይችላል። ቫይረሱ በሌሎች የዓለም ክፍሎች የተስፋፋው ያህል በአፍሪካ ያልተሰራጨውም ለዚህ ይሆናል” ይላሉ ፕ/ር ሻቢር። በተጨናነቀ መንደር የሚኖሩ ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ስለሆኑ ምናልባትም በጊዜ ሂደት ኮቪድ-19ን መከላከል የሚያስችል አቅም አዳብረው ሊሆን እንደሚችል የደቡብ አፍሪካ ሳይንቲስቶች ይገምታሉ። “በከፍተኛ ሁኔታ በተጨናነቁ አካባቢዎች በሽታውን የመከላከል አቅም ሊፈጠር ይችላል። ብዙ ሰዎች ምንም የበሽታው ምልክት የማይታይባቸው ወይም መጠነኛ ምልክት የሚያሳዩት ለዚህ ይሆናል” ሲሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። የአፍሪካ ድህነት የኮሮናቫይረስ ተጋላጭነትን ቀንሶት ሊሆን እንደሚችልም ያምናሉ። በሌላ በኩል እንደ ብራዚል ባሉ ዜጎች ተጨናንቀው የሚኖሩባቸው አገሮች በርካቶች በቫይረሱ እየተያዙ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-54009884 +health ኮሮናቫይረስ፡ 'የኮቪድ-19 የመጀመሪያውን ዙር ክትባት መውሰድ ቫይረሱ እንዳይስፋፋ ያደርጋል' "የመጀመሪያውን ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት መወጋት የበሽታውን ሥርጭት በግማሽ እንደሚቀንስ አንድ ጥናት አመለከተ። የፋይዘርና የአስትራዜኔካ የመጀመሪያው ዙር ክትባት የተሰጣቸውና ከሦስት ሳምንታት በኋላ በቫይረሱ እንዲያዙ የተደረጉ ሰዎች ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው የማስተላለፍ ዕድላቸው ዝቅ ያለ ነው ብሏ ጥናቱ። የዩናይትድ ኪንግድ ጤና ሚኒስትር ማት ሃንኮክ የጥናቱን ውጤት ""አስደናቂ ዜና"" ሲሉ ገልፀውታል። ሚኒስትሩ ሰዎች የክትባት ተራቸው ከደረሰ ሳያመነቱ ሄደው እንዲከተቡም አሳስበዋል። በጥናቱ ላይ የተሳተፉ ሰዎች ክትባቱ ከተሰጣቸው ከ14 ቀናት በኋላ በቫይረሱ ቢጋለጡም ብዙም ምልክት አላሳዩም። ምንም እንኳ የጥናቱ ውጤት ""የሚበረታታ"" ቢሆን ሰዎች ልክ ቫይረሱ እንዳለባቸው እያሰቡ መንቀሳቀስ አለባቸው ይላሉ ዶክተር ሜሪ ራምሴ። ክትባቱ በተለይ በጋራ የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን ከአንድ ወደ ሌላ እንዳያስተላልፉ ፍቱን ነው ይላሉ የጤና ሙያተኞች። የዋርዊክ ዩኒቨርሲቲ ምሁሩ ማይክ ቲልደስሊ ጥናቱ ክትባቶች ምን ያክል ውጤታማ እንደሆኑ ያሳያል፤ ሰዎች ክትባት መውሰድ እንዳለባቸውም ይጠቁማል ይላሉ። ይህ ጥናት የኮሮናቫይረስ ክትባት ምን ያክል የወረርሽኙን ሥርጭት እየገታው እንዳለ ማሳያ ነው ተብሏል። ጥናቱን ያሠራው 'ፐብሊክ ሄልዝ ኢንግላንድ' የተሰኘው የመንግሥት ድርጅት እንደሚለው ክትባቶች ሰዎች ተሰባስበው ለሚኖሩባቸው እንደ ማረሚያ ቤት ላሉ ቦታዎች ፍቱን ነው ይላል። አሁን ምናልባት አስጊ የሚሆነው ነ���ር አዲስ ዓይነት የኮሮናቫይረስ ዝርያ ቢመጣ ክትባቱ መከላከል ይችላል ወይ የሚለው ነው። ነገር ግን የዘርፉ ሰዎች ክትባቶቹ አዲስ ዓይነት የኮቪድ-19 ዝርያ ቢመጣ እንኳ መከላከል ያስችላሉ ይላሉ። ክትባት ምንድነው? ክትባት ማለት ለአንድ ኢንፌክሽን፣ በሽታ ወይም ተህዋሲ ሰውነታችን እንዲከላከል የሚዘጋጅ ጠብታ ነው። ክትባት በይዘቱ የተዳከመ የተህዋሲ ቅንጣትን የያዘ ሊሆን ይችላል። ይህም ማለት በሽታውን፣ ቫይረሱን አሊያም ክትባቱን ነው ሰዎች የሚወጉት ማለት ነው። ወይም ደግሞ በሽታው በሽታ እንዳያስከትል በሚያስችል ደረጃ ራሱን ለሰውነታችን ብቻ እንዲያጋልጥ አድርጎ ማንነቱን ማሳጣት ማለት ነው። በዚህ ሂደት የሰውነታችን በሽታ ተከላካይ ሠራዊት ለጠላት ኃይል እንዳይሸነፍ፣ እጅ እንዳይሰጥ፣ እንዲነቃ፣ የማንቃት ትጥቅና ስንቅን የማቀበል ያህል ነው የክትባቱ ሁነኛ ተግባር። ክትባት ለሕመም አያጋልጥም። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎችን ሊያዳክማቸው፣ ወይም መጠነኛ የጎንዮሽ ጉዳት ሊያደርስባቸው ይችላል። ከእነዚህም ምልክቶች መካከል ክንድ ላይ ቁስለት ወይም ደግሞ ጊዜያዊ ትኩሳት የተለመዱ ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/news-56926149 +sports አርሰናል ቼልሲን አሸንፎ መሪነቱን ሲያስቀጥል ኒውካስል በግስጋሴው ቀጥሏል ትናንት እና ከትናንት በሰቲያ የተከናወኑት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ባማረ ጨዋታ ታጅበው አስደናቂ ውጤቶች ተዘምግቦባቸው ተጠናቀዋል። አርሰናል፣ ኒውካስትል ዩናይትትድ እና ሊቨርፑል ከሜዳቸው ውጪ ተጉዘው ወሳኝ ሦስት ነጥቦችን ይዘው ተመልሰዋል። ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ በቪላ ፓርክ የበላይነት ተይዞበት 3 ለ 1 ሲሸነፍ ዌስትሃም ዩናይትድ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት በተጨማሪ ሰዓት በተቆጠረበት ጎል በክርስታል ፓላስ 2 ለ 1 ተሸንፏል። አርሰናል ትናንት በስታንፎርድ ብሪጅ ሄዶ ያገኘው ሦስት ነጥብ በትክክልም የሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪ መሆኑን ያስመሰከረበት ነበር። ቀደም ሲል ቶተንሃምን፣ ቀጥሎ ሊቨርፑልን ከዚያም ቼልሲ በመርታት የዋንጫ ተፎካካሪ መሆኑን አሳይቷል። በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይም ማንችስተር ሲቲን በሁለት ነጥብ በመብለጥ መሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ድል በኋላ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድኑ “ወደ አዲስ ደረጃ ከፍ ብሏል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። ወደ ሴንቲ ሜሪ ያቀነው ኒውካስል ደግሞ በተጋጣሚው ላይ አራት ጎሎችን በማስቆጠር በአስደናቂ ግስጋሴው ቀጥሏል። ኒውካስል የትናንት ድሉን ተከትሎ ከቶተነሃም በላይ ከሲቲ በታች ሆኖ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ፓራጓዊው የፊት መስመር ተጫዋቹ ሚጉኤል አልሚሮን በትናንቱ ጨዋታው ጎል በማስቆጠር ቡድኑን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል። ለኒውካስል የተቀሩትን ጎሎች ክሪስ ውድ፣ ጆ ዊልሎክ እና ብሩኖ ጉሜሬሽ አስቆጥረዋል። ሳውዝሃምፕተን በሜዳው እና በደጋፊው ፊት በሰፊ የጎል ልዩነት በመሸነፉ አሰልጣኝ ራልፍ ሃሳንሃትል ከሰራቸው ሊነሱ ይችላሉ የሚሉ መረጃዎች በስፋት እየወጡ ይገኛሉ። ሳውዝሃምፕተን ከባለፉት 8 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንዱን ብቻ ነው። አሰልጣኙ ግን ከኒውካስል ጨዋታ በኋላ በሰጡት አስተያየት ትኩረታቸው የወደፊት ጨዋታዎች ላይ እንጂ ስለ ሥራቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል። ክርስቲያኖ ሮናልዶን በቋሚ አሰላልፍ ይዘው የገቡት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ በቪላ ፓርክ ሽንፈትን ተከናንበው ተመልሰዋል። ስፔናዊው አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ቪላን መርተው በሜዳቸው ቀያይ ሴጣኞቹን ከ23 ዓመታት በኋላ ማሸነፍ ችለዋል። ቴን ሃግ ተጫዋቾቻው ያሳዩት አቋም “መጥፎ” ነበር ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። አሰልጣኙ ለፊት መስመር ተጫዋቹ ሮናልዶ ኳስ ለማድረስ ሲባል በረዥሙ ሲሻሙ የነበሩት ኳሶች ውጤታማ እንዳልነበሩ ተናግረዋል። 15ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የተጠናቀቀው በቶተነሃም እና ሊቨርፑል ጨዋታ ነበር። ሞ ሳላህ በመጀመሪያው አጋማሽ ያስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ቡድኑ ወሳኝ ሦስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ረድቶታል። በሁለተኛው አጋማሽ ቶተነሃም አጥቅቶ በመጫወት ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ያደረገ ቢሆንም ከአንድ ጎል የዘለለ ማስቆጠር አልቻለም። ሊቨርፑል ቶተነሃምን ያሸነፈው በኖቲንግሃም ፎረስት እና በሊድስ ዩናይትድ ተከታታይ ሽንፈቶች ከደረሰበት በኋላ ነው። ሊጉን አርሰናል፤ ማንችስተር ሲቲ፣ ኒውካስል እና ቶተነሃምን አስከትሎ እየመራ ሲሆን ማንችስተር ዩናትድ እና ብራይተን 5ኛ እና 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ቼልሲ እና ሊቨርፑል ደግሞ 7ኛ እና 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በወራጅ ቀጠናው ላይ ደግሞ ሳውዝሃምፕተን፣ ዎልቭስ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ይገኛሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c723012gr2go +health 'በስምምነት' እግሩ በመጋዝ የተቆረጠው አውስትራሊያዊ ሕይወቱ አለፈ "በሰሜን ምሥራቅ አውስትራሊያ 'በስምምነት' እግሩ በመጋዝ የተቆረጠው አውስትራሊያዊ አዛውንት ሕይወቱ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። እንደፖሊስ መረጃ ከሆነ ሟች እና የ36 ዓመቱ ተጠርጣሪ እግር የሚቆርጥበት ሁኔታን በተመለከተ አንዳች አይነት ስምምነትና 'ቅድመ ዝግጅት' ነበራቸው። የ66 ዓመቱን አዛውንት እግር በባትሪ ኃይል በሚሰራ መጋዝ ቆርጧል የተባለው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ በግድያ ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል። እንደ ፖሊስ ከሆነ ሁለቱ ግለሰቦች ቀድሞ የሚተዋወቁ ሲሆን፤ ሟቹ እግሩ በመጋዝ ሲቆረጥ እራሱን ለመከላከል ያደረገው ጥረት የለም። መርማሪ ፖሊስ ጋሪ ሃንተር ""ፖሊስ ሆኜ በሠራሁባቸው 34 ዓመታት ውስጥ እንዲህ አይነት ሁኔታ አጋጥሞኝ አያውቅም"" ሲሉ ለአውስትራሊያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። መርማሪው ፖሊስ ድርጊቱን ""አሳዛኝ"" በማለት ገልጸው የሟች እግር ለምን እንደተቆረጠ እስካሁን ግልጽ አይደለም ብለዋል። ፖሊስ ክስተቱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የ66 ዓመቱ ግለሰብ እና በግድያ ወንጀል ክስ የተመሰረተበት የ36 ዓመት ተጠርጣሪ ቅዳሜ ማለዳ በሰሜን ኩዊንስላንድ በምትገኘው በኢንስፌይል መናፈሻ ስፍራ ተገኝተው ነበር። ቀድሞውኑ ይተዋወቁ የነበሩት ሁለቱ ሰዎች፤ አብረው በመኪና ወደ ፓርኩ አቅንተው ለ20 ደቂቃዎች ያክል ዛፍ ስር ተቀምጠው ከቆዩ በኋላ የ36 ዓመቱ ግለሰብ የሌላኛውን እግር በመጋዝ ከጉልበቱ በታች ቆርጦታል ብሏል ፖሊስ። ተጠርጣሪው እግሩ የተቆረጠውን ግለሰብ መኪና ውስጥ ተመልሶ እንዲገባ ከረዳው በኋላ ከአካባቢው በእግሯ ተሰውሯል። መንገደኛ የተጎዳውን ሰው ተመልክቶ ለድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ቢደውልም የ66 ዓመቱ አዛውንት ብዙም ሳይቆዩ ሕይወታቸው አልፏል። ተጠርጣሪው ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60459117 +sports የአውሮፓ ታላላቅ አሰልጣኞች መልቀቅ እና ቀጣይ እጣ ፈንታቸው "አንቶኒዮ ኮንቴ ሴሪ አን ካሸነፈ በኋላ ኢንተር ሚላንን በቃኝ ብሏል። ዚኔዲን ዚዳን ከሪያል ማድሪድ ኃላፊነቱን ሲለቅ ቶተንሃም የፓሪስ ሴንት ዠርሜኑን አለቃ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን ለማስኮበልል እየሞከረ ነው። የሊግ 1 አሸናፊነት ክሪስቶፍ ጋልቲየርን በሊል ማቆየት አልቻለም። ጁቬንቱሶች አንድሪያ ፒርሎን በማሰናበት በማሲሚሊያኖ አሌግሪ ሊተኩት እየሠሩ ነው። በጀርመን ዮሃንስ ፍሊክ ከባየር ሙኒክ መነሳት ተመሳሳይ ውሳኔ በሌሎች ክለቦችም ዘንድ እንዲተገበር መንገድ ከፍቷል። የ2020 - 21 የውድድር ዘመን አቧራ ገና አልሰከነም። ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ ብዛት ያላቸው ታላላቅ አሰልጣኞች ከሥራቸው ሲለቁ ተመልክተናል። ከገንዘብ ነክ ጉዳዮች እስከ አድካሚው ዓመት ያለውን ዝርዝር ሁኔታ የቢቢሲ ሬዲዮ 5 ባለሙያዎች ለምን እንደሆነ ይተነትኑታል። ""በከፍተኛ ሁኔታ የተፈጠሩ አለመግባባቶች"" የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የእግር ኳስ ክለቦችን ፋይናንስ አሽመድምዷል። ኬፒኤምጂ እንደተባለው የገበያ ኩባንያ ከሆነ በአውሮፓ ኃያላኑ 32 ክለቦች ከየካቲት 2020 ጀምሮ 6.1 ቢሊዮን ዩሮ አጥተዋል። በጀርመን ፍሊክ ባየርን ለቀቀ። ጁሊያን ናጌልስማን በቦታው ተተካ። ጄሲ ማርች ደግሞ አር ቢ ላይፕዚግን በመረከቡ በርካታ ለውጦች ተከታትለው መጡ። ከዚያን ጊዜ ወዲህ በጣሊያን፣ በስፔን፣ በእንግሊዝ እና በፈረንሳይ ያለው ተመሳሳይ ታሪክ ነው። ጀርመናዊው የእግር ኳስ ጋዜጠኛ ራፋኤል ሆኒግስቴይን በቢቢሲ ራዲዮ 5 ቀጥታ ስርጭት ላይ ""መልቀቂያዎቹ የሚያመሳስላቸው በኮቪድ-19 ወቅት ስለ ገንዘብ ብዙ ውስጣዊ ክርክሮችን በመመልከታችን ነው"" ብሏል። ""ከእነዚህ አሰልጣኞች ብዙዎቹ ለቀዋል። ምክንያቱም ለሌላ ሥራ ለመሰለፍ ሳይሆን ስለበቃቸው ነው"" ሲል ተናግሯል። አክሎም ""ከዚህ ቀደሙ በተለየ በእነዚህ ትላልቅ ክለቦች ትላልቅ አሰልጣኞች በዚህ ቁጥሮች ሲለቁ አላየንም"" ብሏል። ""ፍሊክ በተጫዋቾች ዝውውር ላይ ከፍተኛ አለመግባባት ከተፈጠረ በኋላ ነው የለቀቀው። ምክንያቱ ደግሞ ኮቪድ-19 ነው። ፍሊክ የሚፈልገውን ያህል ገንዘብ ሙኒክ ማውጣት አልቻለም። በዚህም አለመግባባቱ ተጀመረ"" ሲል አስረድቷል። በላሊጋው 2ኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ሪያል ማድሪድ በኬፒኤምጂ ጥናት የአውሮፓ ውዱ ክለብ በመሆን አጠናቋል። ዚዳን ግን በቦርዱ እና በፕሬዚዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ስለመደገፉ አልተሰማውም ሲል የስፔን እግር ኳስ ባለሙያው ጊየም ባላጌ አስታውቋል። ኮንቴ በ11 ዓመታት የመጀመሪያውን የጣሊያን ዋንጫ ለክለቡ ቢያሳካም በኢንተርም ተመሳሳይ ታሪክ ነው ያለው። ምክንያቱም በክለቡ የፋይናንስ ችግር የተነሳ በዚህ ክረምት የደመወዝ ክፍያን በ 20 በመቶ ለመቀነስ ተዘጋጅቷል። ጣሊያናዊው ጋዜጠኛ ጋብሪኤል ማርኮቲ ""ኮንቴ ገንዘብ ፈለገ፤ ጥያቄዎችንም አቀረበ። ነገር ግን አንድ ወይም ሁለት ታላላቅ ተጫዋቾችን ከማግኘት ይልቅ አንድ ወይም ሁለት ታላላቅ ተጫዋቾችን መሸጥ ሊኖርበት ነው"" ብሏል። ""ስሜቱ ተለውጧል፡፡ ፔፕ ጋርዲዮላ ወይም የርገን ክሎፕን ካልሆንክ እነዚያን ጥያቄዎች ማንሳት በጣም ከባድ ነው"" ይላል፡፡ ማርኮቲ አክሎም ""አዳዲስ ተጨዋቾችን ከመግዛት ይልቅ አዲስ አሰልጣኝ ማምጣት ይረክሳል። በግልጽ እንደሚታየው ተያያዥ ምላሽ ስለመኖሩ አይካድም። አብዛኛው ከድህረ ኮሮናቫይረስ ገንዘብ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚ ጋር የተያያዘ ነው"" ብሏል፡፡ ""ለዚህም ነው ዚዳን ከማድሪድ የለቀቀው፣ ኮንቴ ኢንተርን የተሰናበተው። ይህ የዝውውር መስኮት ለአሰልጣኞች እና ለተጫዋቾች በጣም የተለየ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው"" ሲል ያስረዳል፡፡ አንዳንዶቹ ደክመዋል፣ ሌሎች ደግሞ አዲስ ፈተናዎች አስፈልጓቸዋል ያለፈው ዓመት በወረርሽኙ ከተስተጓጎለ በኋላ በመላው አውሮፓ ያሉ ክለቦች በተጨናነቀ የጊዜ ሰሌዳዎች እንዲጫወቱ ማስገደዱን ተከትሎ ውስጣዊ ውጥረቶች መኖራቸው የተጠበቀ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደ ኮንቴ ያሉት አንዳንዶቹም ችግሮች ቢኖሩም፣ በዝውውር ገንዘብ ላይ አለመግባባት ቢፈጠርም ስኬት አስመዝግበዋል። ዚዳን ዋንጫ ማንሳት ቢሳነውም በዕድሜ የገፋውን የሪያል ቡድን ይዞ የላሊጋው ሻምፒዮንነትን ለጥቂት ሲያጣ በቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ደርሶ በቼልሲ ተሸንፏል። የፈረንሣዊው የእግር ኳስ ጋዜጠኛ ጁሊየን ሎረን እንደተናገረው ""በ���ፈጠረው ነገር በሙሉ ይህ ለዚዳን ልዩ ዓመት ነበር። በኮሮናቫይረስ ተያዘ፡፡ ቡድኑን እስከደረሰበት ደረጃም ለማብቃት ችሏል።"" ""ምናልባትም ከዚህ የተሻለ ማድረግ ከባድ እንደሚሆን ተሰምቶት ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባትም ብዙዎች አሰልጣኞች ሲለቁ በልባቸው ውስጥ ያለው ይህ ነው - 'በዚህ ዓመት ካደረግነው የበለጠ ልንሠራ እንችላለን?' የሚል፡፡ ""ጋልቲየ በሚቀጥለው ዓመት ሊል የሊግ 1 ን በድጋሚ የሚያሸንፍበት ዕድል እንደሌለ አስቦ ይሆናል። ሌሎች አማራጮች እያሉ ለምን ይቆያሉ? ለኮንቴም ምናልባት ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፡፡"" ባላጌ አክሎም ""ትላልቅ ክለቦች አሰልጣኞቻቸውን እየቀያየሩ ነው። ትላልቅ ሥራዎች ክፍት ስለሆኑ ለመመረጥ ዝግጁ የሆኑ ሁለት ወይም ሦስት አሰልጣኞች አሉ"" ብሏል፡፡ ""በእርግጥ ዚዳን ወደ ሌላ ሥራ እንደሚሄድ ቢጠበቅም፤ ዝሎና ተዳክሞ ነበር፡፡ ብዙ አሰልጣኞችንም ነክቷል።"" ማን ወዴት እያመራ ነው? በጣም ስመ ገናና የሆኑ አሰልጣኞች ከአንዱ ወደ ሌላው ክለብ በመንቀሳቀስ ላይ በመሆናቸው ማን ወዴት ያመራል የሚሉ ግምቶች እጥረት የለም፡፡ ኮንቴ ከሪያል ማድሪድ እና በፕሪሚየር ሊጉ ደግሞ ክፍት ከሆነው የቶተንሃም ሥራ ጋር ስሙ ተገናኝቷል፡፡ የቀድሞው አሰልጣኙ ፖቸቲኖን በተመለከተ ስፐርስ ከፓሪስ ሴንት ጀርሜን ጋር ግንኙነት አድርገዋል። ማርኮቲ በበኩሉ ለቢቢሲ ራዲዮ 5 እንደገለጸው ፖቸቲኖ የማድሪድ ዋነኛ ዒላማ ነው፡፡ ሲሞኔ ኢንዛጊ ሐሙስ ዕለት ከሌላው የሴሪ ኤ ቡድን ላዚዮ መሰናበቱን ተከትሎ በኢንተር የኮንቴ ተተኪ ሆኖ የተሰለፈ ይመስላል፡፡ የቀድሞው አለቃቸውን አሌግሪን እንደሚተኩ የሚነገርላቸው ጁቬንቱሶች የሚያሰናበቱት አንድሪያ ፒርሎ መጨረሻ ምን እንደሚሆን ለመገመት ይከብዳል፡፡ ሊልን ለመልቀቅ ""ጊዜዬ አሁን ደርሷል"" የሚል ጥልቅ እምነት ያለው ጋልቲየ በቀጣይ ከኒስ እና ሊዮን አሰልጣኝት ጋር ስሙ ተያይዟል። የቀድሞው የዎልቭሶች አለቃ ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶም እንዲሁ አዲስ ክለብ እየፈለገ ነው፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-57278702 +politics የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ ሕግን አጸደቀ የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በጦር መሣሪያ ቁጥጥር ላይ አዲስ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ። ይህ ሲሆን ከ30 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ወትሮም የዲሞክራቶችና የሪፐብሊካንን ጎራ የሚለየው የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ጉዳይ ከረዥም ዘመን ትግል በኋላ ነው ለዚህ የበቃው። 15 የሪፐብሊካን ፓርቲ እንደራሴዎች ረቂቁን ደግፈው ድምጽ ሰጥተዋል። ረቂቁ በ65 ድጋፍና በ33 ተቃውሞ አልፏል። ይህ የሆነው ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የተኩስ እሩምታን የከፈቱ ግለሰቦችን ተከትሎ በርካቶች ሕይወታቸውን ካጡ በኋላ ነው። በኒውዮርክ፣ ቡፋሎ ባለፈው ወር በአንድ ሱፐርማርኬት ውስጥ ጥቁሮችን እየነጠለ ተኩስ የከፈተው ወጣት እንዲሁም በቴክሳስ፣ ዩቫልዲ ከተማ፣ በአንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በርካታ ሕጻናትን ጨምሮ በድምሩ 31 ሰዎች መገደላቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ይህ ረቂቅ በሚቀጥለው ሳምንት የታችኛው ምክር ቤት ከመከረበት በኋላ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፈርመውበት ሕግ ይሆናል። ይህም በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የሚፈጸም ተግባር ነው። ምንም እንኳ ይህ ረቂቅ እዚህ ለመድረሱ ብዙ ውጣ ውረድ ቢያይም የታሰበውን ያህል አንጀት አርስ እንዳልሆነ በጉዳዩ ላይ ብዙ ሕዝባዊ ንቅናቄን ሲመሩ የነበሩ ተሟጋቾች እየተናገሩ ነው። ረቂቁ አያሌ ውስንነቶች አሉበት የሚሉ የሕግ አዋቂዎችም ጥቂት አይደሉም። ይህ ረቂቅ ሕግ ሆኖ በቅርቡ ሲጸድቅ የጦር መሣሪያ ገዝቼ ማንገት እፈልጋለሁ የሚል ሰው በተለይ ዕድሜው ከ21 በታች ከሆነ የጀርባ ታሪኩ በብርቱ እንዲጠና ይደረጋል። ከዚህ ሌላ 15 ቢሊዮን ዶላር ከፌዴራል መንግሥት ለግዛቶች ይመደባል። ይህም ከጦር መሣሪያ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ለሚከናወኑ ሥራዎች በሚል ፈሰስ የሚደረግ ነው። በተለይም በትምህርት ቤቶች አካባቢ የጥበቃ ቁጥጥርን ለማጠናከር እና ለአእምሮ ጤና ማጎልበቻ መርሐ ግብር ማስፈጸሚያ የሚውል ይሆናል። ከዚህ ሌላ ግዛቶች የደኅንነት ስጋት ናቸው ብለው ለሚያምኗቸው ግለሰቦች አስቀድመው ትጥቅ ማስፈታትን ያበረታታል። ይህ “ሬድ ፍላግ” ተብሎ የሚጠራው የሕግ ሐሳብ ፖሊስ፥ ቤተሰብ ወይም የሥራ ባልደቦችም ሊሆኑ ይችላሉ አንድ ግለሰብ ለደኅንነት ስጋት ነው ብለው በጽኑ ካሰቡ፣ የታጠቀውን መሣሪያ እንዲፈታ ጥያቄ የሚያቀርቡበት ዘዴ ነው። ሌላው በዚህ ረቂቅ የተካተተው “ቦይፍሬንድ ሉፕሆል” በሚል በይበልጥ የሚታወቀው ሐሳብ ሲሆን ይህም ያልተጋቡ ፍቅረኛሞች፣ በመጠናናት ዘመናቸው ምናልባትም ከሁለቱ አንዱ ቀደም ብሎ የጾታ ጥቃት ታሪክ ያለው ሰው ከሆነ ከዚያ ወዲህ መሣሪያ እንዳይታጠቅ የሚከለክል ነው። ከዚህ በፊት የፌዴራል ሕግ ያገቡ፣ ወይም ልጅ ያላቸው ወይም በእጮኛነት ደረጃ ያሉ እና በጾታ ጥቃት ታሪክ ያላቸው ሰዎችን ብቻ መሣሪያ እንዳይታጠቁ ክልከላ ያደርግ ነበር። አሁን በአዲሱ ረቂቅ ግን ይህ ሕግ አዲስ እየተጠናኑ ያሉ አፍላ ፍቅረኛሞች ጭምር እንዲያካትቱ ተደርጓል። አሁን በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የመሣሪያ ቁጥጥር ረቂቁ በሰፊ ድጋፍ ማለፉ ልዩ ያደረገው። በርካታ ሪፐብሊካን እንደራሴዎች ለመሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ ይህን ያህል ድጋፍ ሲሰጡ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። በታሪክ ለዘመናት በዲሞክራቶች ይቀርብ የነበሩ የመሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ የሕግ ሐሳቦች ወዲያውኑ በሪፐብሊካን ተወካዮች ውድቅ ሲደረጉ ኖረዋል። የዲሞክራት እንደራሴዎች ተጠሪ ቸክ ሹመር “ይህ ረቂቅ ሕግ ማለፉ ሁሉን ችግር ይቀርፋል ባንልም ሐቀኛውን መንገድ መያዛችንን አመላካች ነው” ብለዋል። የብሔራዊ ጠመንጃ ማኅበር (NRA) ረቂቅ ሕጉን በጽኑ ተቃውሞታል። ጆ ባይደን ውሳኔው የሚበረታታ ነው ቢሉም እሩምታ ተኩስ መክፈት የሚያስችሉ ዘመናዊ ጠመንጃዎች ላይ ዕቀባ እንዲደረግ የነበራቸውን ፍላጎት አለማሟላቱ ግን ቅር አሰኝቷቸዋል። በቡፋሎም ሆነ በቴክሳሱ ጥቃት 31 ሰዎች የተገደሉት አከታትለው ጥይት በሚተፉ አውቶማቲክና ከፊል አውቶማቲክ መሣሪያዎችን ገዝተው በታጠቁ ወጣቶች ነበር። በአሜሪካ አሁን በአማካይ በግለሰቦች እጅ 390 ሚሊዮን ጠመንጃና ሽጉጦች ይገኛሉ። በ2020 ብቻ 45 ሺህ አሜሪካዊያን በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በጦር መሣሪያ ተገድለዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c728rg65jkgo +business የዋጋ ግሽበት እጅግ የሚያሰጋቸው አገራት የትኞቹ ናቸው? "የዋጋ ግሽበት ዓለምን ከጥግ ጥግ አስግቷል። ከኢትዮጵያ እስከ ሲሪ ላንካ ከብራዚል እስከ ደቡብ አፍሪካ። ምግብ ተወዷል። ነዳጅ ተወዷል። ምን ያልተወደደ አለ? የተለይ የመሠረታዊ አቅርቦቶች ዋጋ መናር ዓለምን አስጨንቋል። በእርግጥ የዋጋ ግሽበት ከሌላው የዓለም ክፍል በላይ የሚያንገዳግዳቸው አገሮች አሉ። ለዚህ ምክንያቱ ሰብል አለመሰብሰቡ፣ ወረርሽኙ መክፋቱ እና የተፈጥሮ ጋዝ መጥፋቱ ነው። በዚህ ደግሞ በአፍሪካ ከሰሀራ በታች ያሉ አገራት ዋነኛ ተጎጂ ናቸው። ቱርክ፣ ብራዚል እና ሲሪ ላንካም ይጠቀሳሉ። ከሰሀራ በታች ያሉ አገራት አብዛኞቹ ከሰሀራ በታች ያሉ አገራት ምግብ ለማብሰል የተጣራ ፈሳሽ ጋዝ (በሲሊንደር የሚታሸግ ቡታ ጋዝ) ይጠቀማሉ። የጋዝ ዋጋ ደግሞ እያሻቀበ ይገኛል። ባለፈው ዓመት በአንዳንድ የናይጄሪያ ግዛቶች ጋዝ በእጥፍ ጨምሯል። ብዙዎች ወደ ማገዶ እንጨት፣ ��ሰል እና ኬሮሲን ፊታቸውን ለማዞር ተገደዋል። እነዚህ አማራጭ ኃይል ምንጮች ደግሞ አካባቢን ይበክላሉ። የተጠቃሚዎቹን ሳምባም ይጎዳሉ። የነዳጅ ዋጋ መጨመር፤ የማዳበሪያ ዋጋ እንዲሁም ምግብ ከእርሻ ወደ መደብር የሚጓጓዝበት ዋጋም እንዲንር ምክንያት ሆኗል። የናሳ የመሬት ምልከታ እንደሚጠቁመው በበርካታ የአፍሪካ አገሮች ዝናብ ከጠፋ ሰነባብቷል። ይህም የዋጋ ግሽበት አስከትሏል። በአንጎላ ባለፈው ዓመት የምግብ ዋጋ 36.4 በመቶ መጨመሩን የአገሪቱ የስታትስቲክስ ተቋም ይፋ አድርጓል። በማላዊ የኑሮ ውድነት ፀረ መንግሥት ሰልፎችን አስከትሏል። በአፍሪካ 282 ሚሊዮን ሰዎች ተመጣጣኝ ምግብ እንደማያገኙ የተባበሩት መንግሥታት ገልጿል። ቱርክ ጥቅምት ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በኢስታንቡል እና ዲያርባሪክ ከተሞች ሰልፍ መውጣታቸው ይታወሳል። አምና የዋጋ ግሽበት በ36 በመቶ ከፍ ብሏል። የአገሪቱ የስታትስቲክስ ተቋም እንዳለው የምግብ ዋጋ በዓመት 44 በመቶ ጨምሯል። በኢስታንቡል በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመንግሥት ሱቆች ለዳቦ ሰልፍ ይዘው ማየት ተለምዷል። የግል ዳቦ ቤቶች ዋጋ ስለማይቀመስ ከእነሱ መግዛት አይታሰብም። ነዳጅና ማዳበሪያ ከመወደዱ ባሻገር የቱርክ መንግሥት የስንዴ ዋጋን መጨመሩ ዳቦ እንዲወደድ አድርጓል። የአውቶብስና ባቡር ክፍያም በእጥፍ ጨምሯል። የመብራት ክፍያ 50 በመቶ፣ የጋዝ ክፍያ 25 በመቶ ከፍ ብሏል። መንግሥታት የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የወለድ መጠንን የሚጨምሩበት አሠራር አለ። ይህም ገንዘብን ለማግኘት አስቸጋሪ ያደርጋል። ፕሬዘዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ""ወለድን መጨመር ሀብታምን የበለጠ ሀብታም የሚያደርግ፣ ድሃን የባሰ የሚያደኸይ ሰይጣናዊ አካሄድ ነው"" ብለዋል። የአገሪቱ ብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠንን እንዲቀንስም አዘዋል። ይህ ውሳኔ የቱርክ መገበያያ ሊራ ከዶላር አንጻር ዋጋው በ45 በመቶ እንዲያሽቆለቁል አድርጓል። መንግሥት ለዋጋ ግሽበት መፍትሔ ያለው የደመወዝ መጠንን በ50 በመቶ ማሳደግ ነው። የምጣኔ ሀብት ተንታኞች የቱርክ የዋጋ ግሽበት በመጪው ፀደይ 50 በመቶ ይደርሳል ብለው ተንብየዋል። ብራዚል የብራዚል የስታትስቲክስ ተቋም እንደሚለው የሸቀጥ ዋጋ በ10 በመቶ፣ የነዳጅ ዋጋ በ50 በመቶ ጨምሯል። አምና በድርቅ ሳቢያ መሠረታዊ ሰብል የሆኑት ሩዝ እና ባቄላ ጠፍተው ነበር። የምግብ ዋጋም በ14 በመቶ አሻቅቧል። ብራዚል በቀንድ ከብት ከዓለም አንደኛ ብትሆንም የሥጋ ዋጋ እጅግ ከፍ ብሏል። ሥጋ የሚገዙ ዜጎች ቁጥርም በ67 በመቶ አሽቆልቁሏል። በድርቁ ሳቢያ ኃይል አመንጪዎችም እየተንገዳገዱ ነው። ለምሳሌ የአገሪቱ ከውሃ ኤሌክትሪክ ኃይል አመንጪ ተቋም ተዘግቷል። በዚህ ምክንያት የመብራት ክፍያ በአንድ አምስተኛ ጭማሪ አሳይቷል። ከ213 ሚሊዮን ብራዚላውያን 27 ሚሊዮኑ ከድህነት ወለል በታች እንደሚኖሩ ጉቴሮ ቫርጋስ የተባለ ድርጅት ገልጿል። እነዚህ ሰዎች በወር በ49 ዶላር ይኖራሉ። ሲሪ ላንካ አምና ከነበረው የምግብ ዋጋ አንጻር የዘንድሮው 20 በመቶ ንሯል። ደሴቷ ሲሪ ላንካ አምና መሠረታዊ የምግብ አቅርቦትን ከውጭ ለማስገባት ስትሞክር የምግብ ዋጋ በጣም ተወዶባታል። ዋነኛ ገቢዋን ከቱሪዝም ታገኝ ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ግን ለሁለት ዓመታት የአገሪቱን የእንጀራ ገመድ በጥሷል። በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት ተመናምኗል። ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ስለሌላቸው መንግሥት ምግብ ጫኝ መርከቦች እንዳይገቡ አግዷል። ይህም በመደብሮች የምግብ አቅርቦት ውስን እንዲሆን፣ የሸቀጥ ዋጋም እንዲንር አድርጓል። በተለይም ሩዝ፣ ስንዴ እና የዱቄት ወተት ዋጋቸው አይቀመስም። ነዳጅም በ85 በመቶ ጨምሯ���። የተቆጣውን ሕዝብ ለማረጋጋት መንግሥት 1 ቢሊዮን ዶላር መድቦ፤ በሠራተኞችን ደመወዝ እና ጡረታ ላይ ማሻሻያ አድርጓል። ከአንዳንድ የምግብ ዓይነቶች እና መድኃኒት ላይም ቀረጥ ተነስቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60165449 +business ምጣኔ ሃብት ፡ አዲሶቹ የብር ኖቶች እና የያዟቸው የደኅንነት ገጽታዎች "ኢትዮጵያ ከሁለት አስር ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50፣ እናየ100 የገንዘብ ዓይነቶችን ሙሉ ለሙሉ በመተካት አዲስ የገንዘብ ኖቶች ይፋ አድርጋለች። በቅርቡ ይፋ የተደረጉት የብር ኖቶች ቀደም ሲል ከነበሩት በተሻለ አጠቃቀም ምቹና ረዥም ጊዜ እንዲያገለግሉ ተደርገው መሰራታቸው የተገለጸ ቢሆንም ተጠቃሚዎች አንዳንድ ቅሬታዎች ሲያሰሙ ተደምጧል። በአዲሱ የ100 እና የ10 ብር ኖቶች ላይ ከላይ ወደ ታች የተዘረጋው መስመር ብሔራዊ ባንክ አስቀድሞ እንደገለፀው በአንበሳው መካከል አያልፍም። አንዳንዱ ላይ በአንበሳው ጆሮ፣ አንዳንዶቹ ላይ ደግሞ በአንበሳው ላይ ተሰምሮ ይታያል። ነጠብጣቡም የሚጀምረው አንዳንዱ ላይ ከብሩ ጫፍ ሌሎቹ ላይ ደግሞ ትንሽ ወረድ ብሎ እንደሆነ ማስተዋል ይቻላል። ይህንን ተከትሎ እነዚህ የገንዘብ ኖቶች የተጭበረበሩ ናቸው የሚል አሉባልታ በማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን ተጠቃሚዎች ዘንድ ሲሰራጭም እየተሰማ ነው። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የብሔራዊ ባንክ የከረንሲ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አበበ ሰንበቴ ግን አዲሶቹ የብር ኖቶች ላይ የሚታየው ልዩነት ተራ የሕትመት ችግር እንጂ ተመሳስሎ የተሠራ እንዳልሆነ ገልፀዋል። አክለውም ይህ በገንዘቡ አጠቃቀም ላይ የሚያመጣው ለውጥ እንደሌለ አስረግጠው ይናገራሉ። ይህንን በኅብረተሰቡ ውስጥ እየተነገሩ ያሉ ሁኔታዎችን ሲያብራሩም በአዲስ የገንዘብ ኖቶች ላይ ለደኅንነት የተቀመጡ ምልክቶች ላይ የተወሰነ ልዩነት ሊኖር እንደሚችልም ምክንያቱን አስቀምጠዋል። በተቻለ መጠን መስመሮች መኖር ካለባቸው ስፍራ ፈቀቅ ሊሉ እንደሚችሉ ጠቅሰው፣ ""የሕትመት ችግሩ ባይኖር ይመከራል፤ አይኖርም ግን ተብሎ አይጠበቅም"" ብለዋል። እነዚያ ምልክቶች በትክክል በአዲሱ የገንዘብ ኖት ላይ እስከተገለፀ ድረስ ያን ያህል ችግር ነው ተብሎ ሊወሰድ እንደማይችል አብራርተዋል። ብሔራዊ ባንክ ገንዘቡ ሲታተም በቅድሚያ ያየው መኖሩን የገለፁት አቶ አበበ፣ ሕትመቱን ለሚሰሩት አካላት ያንን በተቻለ መጠን እንዲያጠቡትም ገለፃ እንደተደረገላቸው ያስታውሳሉ። ነገር ግን ባለው ሁኔታ ማሽኑ ላይ ለህትመት ሲገባ መዛነፉ እንደተፈጠረ ይናገራሉ። አቶ አበበ አዲሶቹን ብሮች ከቀደመው ጋር በማነጻጸርም ኀብረተሰቡ እነዚህን የደኅንነት መለያ ምልክቶች የሆኑ መስመሮች የተሰሩት ወረቀቱ ላይ በመታተም ሳይሆን ወረቀቱ ውስጥ ተሰርተው ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም በባለ 50 ብር እና በባለ 100 ብር ኖቶች ላይ ያለው መስመር የታተመው በገንዘቡ ላይ መሆኑን አስታውሰው የአሁኑ ግን በወረቀቱ ውስጥ መሰራቱን ይናገራሉ። የሚጠራጠር ተገልጋይ ካለ ብሩን በብርሃን ላይ ወስዶ በሚመለከትበት ወቅት ቀጥታ ከላይ ወደ ታች የሚወርድ መስመር እንደሚመለከት ያስረዳሉ። አቶ አበበ እንደሚሉት ይህም ሁኔታ ብርን አስመስለው የሚሰሩ ግለሰቦች በጭራሽ ሊሰሩት በማይችሉበት ሁኔታ ዲዛይን ተደርጓል። ሆኖም እንዲህ ዓይነት የመስመር መዛነፍ በሁሉም ኖቶች ላይ ሳይሆን ባበለ መቶ በተወሰኑ ቅጠሎች ላይ የተከሰተ መሆኑን ተናግረዋል። ሌላው ለአቶ አበበ ቢቢሲ ኣቀረበላቸው ጥያቄ በሁለት መቶ ብር ኖቶች ላይ የታየውን የእንግሊዝኛ ፊደላት ግድፈት ነው። በብሩ ላይ መቶ ወይም በእንግሊዝኛው hundred ተብሎ ከተፃፉ ፊደላት መካከል ዲ(d) ኦ (0) እንደሚመስል ማስተዋል ይቻላል። አቶ አበበ ሲመልሱም የተመረጠው ፎንት መሆኑን በማንሳት ይህ ተጠቃሚዎችን በሚያሳስት ደረጃ አለመቀመጡን አብራርተዋል። ከዚህ ቀደም የነበረው ባለ መቶ ብሮች ላይ ካለው ጋር ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነው ያሉት አቶ አበበ ፊደላቶቹ 'ፎንት' ሲመረጡ የተከሰተ መሆኑን ይናገራሉ። እነዚህ የፊደል አጣጣሎች የተመረጠው መሆኑ ጠቅሰው የሚያመጣው ምንም አይነት ችግር እንደማይኖርም ይገልፃሉ። ሁለት መቶ የሚለው የአማርኛ ፊደልና ቁጥሩ በአግባቡ መቀመጡን ገልፀው፣ ይህ የብር ተጠቃሚው ላይ የሚፈጥረው ችገር አለመኖሩን አረጋግጠዋል። የአይነ ስውራን ብሔራዊ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ወሰን አለሙ በቀድሞው ብር ላይም ሆነ በአሁኑ የብር ኖቶች ላይ የሚዳሰሱ ምልክቶች መኖራቸውን በማንሳት የአሁኑ ከቀድሞው የተሻለ መሆኑን ያነሳሉ። ምልክቶቹ በቀኝና በግራ ጫፍ ላይ እንዳሉ የሚገልፁት አቶ ወሰን፣ ብሔራዊ ባንኩ እንዳለው ነጥቦቹ ከአስር ብር ጀምሮ እስከ ሁለት መቶ ብር ድረስ ብዛታቸው እየተለያየ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል። የአይነስውር ማህበሩ ፕሬዝዳንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት የተቀመጡት ምልክቶች በጣም የተጠጋጉ በመሆናቸው በእጅ ለመለየት አስቸጋሪ ናቸው። ብሮቹን ለመለየት ከዚህ ቀደም ስፋቱና ቁመታቸውን ይጠቀሙ እንደነበር ገልፀው፣ የአሁኖቹ መቶ እና ሁለት መቶ ብሮች ያላቸው የመጠን ልዩነት በጣም አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ። አቶ አበበ በበኩላቸው ለብሔራዊ ባንኩ የመጣ እንዲህ አይነት አስተያየት እስካሁን ድረስ አለመኖሩን ገልፀው ፤ የተቀመጡት ምልክቶች ሌሎች አገራትም የሚጠቀሙባቸው መሆናቸውን አስረድተዋል። ቴክኖሎጂው በትክክል ማየት የተሳናቸው ሰዎች ሊጠቀሙበት ይችላሉ ተብሎ መቀመጡን በመግለጽ በባለመቶው ላይ ስድስት፣ በባለ ሁለት መቶው ላይ ደግሞ ስምንት ምልከቶች መኖራቸውን ገልፀዋል። አቶ ወሰን እነዚህ ምልክቶች ብሩ የወረቀት በመሆኑ ሊፈገፈጉ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። አቶ አበበ ግን የገንዘቡ ጥራትም ቢሆን ሌሎች አገራት የሚጠቀሙባቸው ጥራቱን የጠበቀ ወረቀት መሆኑን ያስረዳሉ። በርግጥ በሌሎች አገራት ላይ የፕላስቲክ ገንዘቦች ያሉ ቢሆኑም ኢትዮጵያ ግን በአሁኑ ሰዓት እነዚያን ለመጠቀም የማትችልባቸው የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን አንስተዋል። የገንዘብ ሕትመት ሚስጥራዊነቱን በጠበቀ መልኩ እንደሚካሄድ ተናግረው የሚኖሩ ጉድለቶች በሚመጡ አስተያየቶች በሂደት እንደሚስተካከሉ ገልፀዋል። ሕትመት የአንድ ጊዜ ክንውን አይደለም በማለትም ባንኩ የሚቀርቡ አስተያየቶችን ካመነባቸው በሂደት ማስተካከያ እንደሚደርግ ተናግረዋል። ገንዘቡ ላይ የሚታዩ የደኅንነት መጠበቂያ ምልክቶች ምንድን ናቸው? አዳዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች አስመስለው የሚሰሩ ሐሰተኛ የብር ኖቶችን ለመከላከልና ለመለየት በሚያስችል ሁኔታ የተለያዩ የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታዎች እንዲኖሯቸው ተደርጓል። ለአይነ ስውራንም የእውቅና ምልክት ያላቸው ሲሆን የብሩን ዋጋ በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደኅንነት መጠበቂያ ያለው ነው። በተመሳሳይ ገንዘቡ ወደ ላይ ወይንም ወደታች ሲዞር የሚንቀሳቀስ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ የደኅንነት መጠበቂያ ምልክት እንዳለውም ተነግሯል። እንደ ብሔራዊ ባንክ ገለፃ ከሆነ አዳዲሶቹ ገንዘቦች የሚሽከረከር ደማቅ ቀለም ኮኮብ አዲስ የደህንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ውስጥም NBET፣ ኢብባ እና ገንዘቡ አይኖቶች ተፅፈው ይገኙበታል ነው የተባለው። ገንዘቡ ወደ ብርሃን አቅጣጫ ተደርጎ ሲታይ በላይ ላይ ከሚገኘው ምስል ፊት ለፊት ተመሳሳይ ደብዛዛ ውሃ መልክ ያለው ምልክት እንደሚታይ ተጠቁሟል። የብር ኖቶቹ በብርሃን አቅጣጫ ሲታይ ኳስ መሳይ ምልክት ከኖቶቹ በስተኋላ ካለው ተመሳሳይ ምልክት ጋር በፍፁም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ። እንዲሁም አንበሳው ምስል ራስ ላይ 'አልትራቫዮሌት ጨረር' ሲበራበት ወደ ቢጫነት የሚለወጥ' ፍሎረሰንት' ምልክት አለው ተብሏል። ኖቶቹን በመቀየሩ ሥራ ለህትመት ብቻ በአጠቃላይ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገ ተነግሯል። ከቀለም አንጻር አዲሱ ባለ 200 ብር ኖት ሐምራዊ፣ ባለ100 ብር ኖት ውሃ ሰማያዊ፣ ባለ50 ብር ኖት ቀይ ብርቱካናማ፣ ባለ10 ብር ኖት ደግሞ አረንጓዴ ቀለም አላቸው።" https://www.bbc.com/amharic/54297291 +business ከባንክ አገልግሎት ወደ ተቆራረጠችው ትግራይ ገንዘብ ለመላክ የሚከፈለው ከባድ ዋጋ ላለፉት ሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ በቆየችው ትግራይ መሠረታዊ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ሕይወት ከባድ ሆኗል። በርካቶች ከጦርነቱ በፊት የነበራቸውን ሕይወት እና ጓደኝነት፣ ትምህርት እና ሥራ፣ ከምንም በላይ ሰላምን ይናፍቃሉ። የታመሙ ሮጥ ብለው የሚታከሙበት የሕክምና ተቋም ህንጻው ብቻ ቀርቷል። ሮጥ ብለው ያገኙትን የሚሸምቱበት ሱቅ ባዶውን ያዛጋል። ያለቻቸውን በውድ ዋጋ የሚሸጡ ነጋዴዎች ጋር ለመሄድ ደግሞ ገንዘብ ወሳኝ፤ ግን ከየት ይምጣ። የሁለት ልጆች አባት የሆነው አቶ አብርሃ ይሕደጎ፣ በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ የመዝገብ ቤት ሠራተኛ ነበር። አሁን ላይ ግን የሚከፈለው ገንዘብ እንደሌለና ሥራውን እንዳቆመ ገልጿል። “ጦርነቱ ያስጨንቀናል፤ የምንኖረው ሕይወትን እንኳ ምን ብዬ እንደምገልጸው አላውቅም - እየባሰበት ነው። እኔ፤ አልፎ አልፎ የሚላክልኝን ገንዘብ ጠብቄ ልጆቼን ለመቀለብ እየጣርኩ ነው። እዚህ ሁሉንም ነገር ስለተወደደ ገንዘቡ ጥቅም የለውም፤ ምንም ነገር መግዛት አይቻልም” ይላል። በባሕር ማዶ ወዳጅ ዘመድ ያላቸው ችግራቸውን ጠቅሰው የድጋፍ ተማጽኖ ድምጽ ያሰማሉ። ገንዘብ ግን ወደ ትግራይ ለማስገባት ውጣ ውረዱ ከባድ ነው። ለዚህም ነው የትግራይ ተወላጅ የሆኑት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ሳይቀር ለቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ለመላክ መቸገራቸውን የተናገሩት። ጦርነቱ ባንክን ጨምሮ የተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ምክንያት በመሆኑ በሚሊዮን የሚቆጠር የክልሉ ሕዝብ የባንክ አገልግሎት አያገኝም። የፋይናንስ አገልግሎቶች መቋረጥ ደግሞ ወደ ክልሉ ገንዘብ መላክን እጅግ አስቸጋሪ እና ብዙ ወጪ የሚጠይቅ እንዲሆን አድርጎታል። ይሄንን ተከትሎ አንዳንድ ቤተሰቦች ገንዘብ ለማግኘት ንብረታቸውንና ሌላ አለኝ የሚሉትን ነገር ሸጠዋል። አንዳንዶች ደግሞ በውጭ አገራት የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው እጅ ይጠባበቃሉ። ሰላም ባለኸኝ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የሥርዓተ-ጾታ ባለሞያ ስትሆን፣ በትግራይ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በነበሩት ጥቂት ወራት ነጻ የትምህርት ዕድል አግኝታ ነው ወደ ቤልጅም የሄደችው። አሁን ግን በጦርነቱ ምክንያት ወደ ትግራይ መመለስ እንዳልቻለች ትናገራለች። እንደ ሰላም ያሉ በውጭ አገር ሆነው ቤተሰቦቻቸውንና ጓደኞቻቸውን በገንዘብ እያገዙ የሚገኙ ሰዎች፣ ወደ ትግራይ ገንዘብ ለመላክ እጅግ የተወሳሰበና ዋስትና የሌላቸው መንገዶችን ይጠቀማሉ። ሰላም “በሕይወት ለመቆየት፣ እንባ እየተናነቃቸው ገንዘብ ላኩልን ስለሚሉን፣ የምንልከው ገንዘብ ከግማሽ በላይ እየተወሰደብንም ቢሆን ሕጋዊ ያልሆነ መንገድ እንድንጠቀም ተገደናል” ትላለች። እሷ፣ ከአንድ ዓመት በላይ ገንዘብ ለመላክ የተለያዩ መንገዶችን ስትጠቀም መቆየቷን ትናገራለች። የመጀመሪያው አዲስ አበባ ያሉ ሰዎችን መጠቀም ነው። አዲስ አበባ ያሉ አቀባባዮች መቀለ ከሚ��ሩ ገንዘብ ካላቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት አላቸው። አዲስ አበባ ለሚገኙት ሰዎች በስማቸው በባንክ አካውንታቸው ውስጥ ገንዘብ ካስገቡ በኋላ፣ ለማን እንደሚሰጥ እና የላኪ ስም በስልክ ይነገራቸዋል። ከባንክ አገልግሎት ከራቀች ረዥም ወራትን ባስቆጠረችው መቀለ የሚኖሩ ባለሀብቶች ጋር ደውለው ምን ያህል ገንዘብ እንደተላከ፣ መቼ መውሰድ እንደሚቻል ይነጋገራሉ። ከዚያም መልሰው ለገንዘቡ ላኪ መረጃውን በማስተላለፍ ኮሚሽናቸውን ተቀብለው ሥራቸውን ይጨርሳሉ። እዚህ ላይ ገንዘብ ላኪ እና ተቀባይ መረጃ የመለዋወጥ ድርሻውን ራሳቸው ይወጣሉ። ሌላኛው ገንዘብ መቀባበያ መንገድ ደግሞ በአፋር እና በአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ እና ገንዘብ በማዘዋወር ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መጠቀም ነው። ይህ የገንዘብ ዝውውር ግን አንድ ስምምነት ይፈልጋል። መጀመሪያ ላኪው ከገንዘብ አዘዋዋሪዎቹ ጋር በሚያደርገው ስምምነት መሰረት ከ30 እስከ 50 በመቶ የድለላ ዋጋ [ኮሚሽን] እንዲከፍል ይስማማል። ሁለቱም የሚያስማማቸው መጠን ላይ ከደረሱ በኋላ ተቀባዩ ቀሪው ገንዘብ ይደርሰዋል። በአፋር ክልል ያለው እንቅስቃሴ የሚከፈለው ገንዘብ አዲስ አበባ ካለው ዝቅ ያለ ቢሆንም፣ ገንዘቡ ተቀባዩ ጋር እስኪ ደርስ እስከ ሦስት ወር ሊወስድ እንደሚችል ተጠቃሚዎች ይናገራሉ። ተራ በቃል የሚፈጸም ንግግር ብቸኛው ገንዘብ ላኪው ያለው መተማመኛ ሲሆን፣ አንዳንድ የገንዘብ አዘዋዋሪዎች ገንዘቡን ካደረሱ በኋላ የተቀባዩን ድምጽ ወይም ምስል ቀርጸው ላኪው ጋር በመላክ ድርሻቸውን እንደተወጡ ያረጋግጣሉ። ሰላም እነዚህ ሁሉንም አማራጮች ተጠቅማባቸዋለች። አንድ ጊዜ “ወንድሜ ታሞ ስለነበረ፣ የሚታከምበት ገንዘብ ቶሎ ብላችሁ ላኩ ስለተባልን 67 ሺህ ብር ላኩኝ። ቤተሰቦቼ የደረሳቸው ግን 30 ሺህ ብር ብቻ ነበር። በዚህ በጣም ተበሳጭቻለሁ” ትላለች። የዚህ ምክንያት የገንዘብ አዘዋዋሪዎቹ መስመር ከአዲስ አበባ ጀምሮ እስከ ትግራይ የተዘረጋ ስለሆነ፣ የሚላከው ገንዘብ ተቀባዩ እጅ እስኪደርስ በርካታ የጥቅም ተካፋይ ሰዎች ስላሉ እንደሆነ ይነገራል። ከዚህ ቀደም ቢቢሲ ያነጋገረው በዚህ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ አንድ ግለሰብ “የምንወስደው ኮሚሽን ሁሉ ወደ ኪሳችን አይገባም። አንድ ገንዘብ ከባንክ ስናወጣ ለበርካታ ሰዎች የሚሆን ስለምናወጣ እነሱም የሻይ ይፈልጋሉ። በተጨማሪም ወደ ትግራይ ብዙ ገንዘብ ይዞ መግባት ከባድ እና መሰናክሎች የበዛበት ነው። እነዚህን በገንዘብ እየሸፈንን ነው የምንሄደው” ብሎ ነበር። ትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ 616 የባንክ ቅርንጫፎች በመዘጋታቸው ምክንያት ወደ ባንኮቹ ገንዘብ መላክም ሆነ፣ በትግራይ ክልል ከተከፈቱ የሂሳብ ቁጥሮች ገንዘብ ማንቀሳቀስ አይቻልም። አሁን ያለው የገንዘብ ዝውውር ሰንሰለት እጅግ አደገኛ እና የከተማ አስተዳደሮች እና የፀጥታ አካላት ቁጥጥር የሚያደርጉበት ስለሆነ፣ በርካታ ሰዎች ገንዘባቸው በተለያየ መንገድ ጠፍቶ መቅረቱን ይናገራሉ። ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ የቆቦ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በኩል ሲያልፍ የነበረ ሦስት ሚሊዮን ብር በፀጥታ አካላት ቁጥጥር ላይ መዋሉን አስታውቆ ነበር። በዚህ መሠረት የገንዘብ አዘዋዋሪዎቹ መንገድ ላይ ፍተሻ ሲኖር የያዙት ገንዘብ እንደሚወረስባቸው ይናገራሉ። ሰላም ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር በአፋር ክልል በኩል ያለውን የገንዘብ ዝውውር ተጠቅማ ወደ ትግራይ የላከቸው ስድስት ሺህ ዩሮ፣ ገንዘቡን እንዲያደርስ የተቀበለው ግለሰብ እጅ ላይ መቅረቱን ትናገራለች። ይህ የበርካታ ሰዎች ላይ ደርሷል። “ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ��ይ አስተማሪ ነው፤ አንዱ ጓደኛችን በእሱ በኩል የላከው አንድ ሺህ ዩሮ በሦስት ቀን መቀለ ደረሰ። የሚያስከፍለው ኮሚሽን 22 በመቶ ስለነበረ፣ የሚቀንስልን በማግኘታችን ደስ አለን። ‘በርከት አድርጋችሁ የምትልኩ ከሆነ ለእናንተም የምትከፍሉት ይቀንስላችኋል፣ እኔም አልመላለስም’ ስላለን የተለያዩ ሰዎች ጠይቄ 6 ሺህ ዩሮ ላኩለት” ትላለች። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 3 ሺህ ዩሮ የራሷ ሲሆን ቀሪውን የጓደኞቿ ነበር። ገንዘቡ በወቅቱ በነበረው የባንክ ምንዛሪ ከ327 ሺህ ብር በላይ ይገመታል። “ባንኮች ቢሰሩ እንዲህ ላለ ችግር አንዳረግም ነበር፤ ግን ደግሞ ቤተሰቦቻችን በሕይወት እንዲቆዩልን ስለምንፈልግ የጭንቅ አማራጮች እንድንወስድ ተገደናል” ስትል ትናገራለች። ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ቀናት የቀሩት ጦርነት እንዲያበቃ በተለያዩ ወገኖች ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን በክልሉ ተቋርጠው የሚገኙት ባንክን ጨምሮ ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ወደ ሥራ እንዲመለሱ የሚደረገው ግፊት ይጠቀሳል። በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ እንደ ሳተላይት ስልክ ያሉ መሣሪያዎች በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የእርዳታ ተቋማት የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች ሆነው ቆይተዋል። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር እነዚህ የሳተላይት ስልኮችን ተጠቅሞ ነዋሪዎች ከክልሉ ውጪ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው ጋር ለማገናኘት ሲሰራ ቆይቷል። እስከ አሁን ማኅበሩ “በጦርነት እና ግጭት የተለያዩ” ሰዎች 115 ሺህ የሚጠጉ የስልክ ጥሪዎች እና መልዕክቶች እንዲያስተላልፉ ማድረጉን ይገልጻል። ወደ ክልሉ እርዳታ የጫነ መኪና ሲያመላልስ የነበረ ለደኅንነቱ ሲል ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈቀደ አሽከርካሪ የፌደራል ኃይሎች በትግራይ ከነበሩበት ጊዜ አንስቶ ሦስተኛው ዙር ጦርነት እስከተነሳበት ወቅት በነበሩ የተለያዩ ግዜያት እርዳታ ሲያደርስ ነበር። “መንገድ ላይ ብዙ ነገሮች አሉ፤ በጦርነቱ ምክንያት የደረሰው ውድመት በየቦታ ይታያል። የተቃጠሉ መኪኖች፣ የወደሙ መኖሪያ ቤቶች በርካታ ናቸው። ጦርነቱ መንገድ ላይ የሚታይ ነው የሚመስለው” ይላል። በክልሉ በተንቀሳቀሰባቸው አካባቢዎች ያጋጠመ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውስ መኖሩን የሚናገረው አሽከርካሪው፣ አንዳንድ አሽከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ሲነሱ ገንዘብ አድርሱልን ከሚሉ ሰዎች ገንዘብ ተቀብለው እንደሚሄዱ ይገልጻል። “በትግራይ ሁለንታዊ ችግር አለ፤ መንገድ ላይ ‘እባክህን ገንዘብ ወይ መድኃኒት አምጣልን’ ብሎ የሚጠይቅ ሰው ብዙ ነው፤ በተለይ የካንሰር ህሙማን። ከእዚያው ለመግዛትም አቅም የላቸውም፤ ሁሉም ሰው ግን ገንዘብ ይጠይቃል።” የጦርነቱን ዳግም ማገርሸት ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ወደ ትግራይ ሲያደርሰው የነበረው ሰብአዊ እርዳታን እንዳቆመ ባለፈው የነሐሴ ወር አስታውቆ ነበር። በዚህ ወቅት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ይገልጻል። “እንዲህ አይነት ጦርነት ይኖራል ብዬ አስቤ አላውቅም፤ በዚህ ዘመን እናትህ በሕይወት እያለች ለአንድ ቀንም ቢሆን ድምጿ በስልክ አለመስማት ከባድ ነው። በየቀኑ ሰዎች ሞቱ፣ የአየር ጥቃት ተፈጸመ፣ ህጻናት በረሃብ እየሞቱ ነው የሚሉ ዜናዎች ስሰማ ይጨንቀኛል” የምትለው ሰላም ጦርነቱ የሚቆምበትን ጊዜ በጉጉት እየጠበቀች መሆኗን ትናገራለች። https://www.bbc.com/amharic/articles/ce5g410x6j0o +politics በምንጃር እና ፈንታሌ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተው ምንድን ነው? "ከአዲስ አበባ ሰሜን ምሥራቅ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል በሚዋሰኑበት አካባቢ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ነዋሪዎችና የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት ገለጹ። የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞኖች በሚዋሰኑበት አካባቢ ጥቃት መፈጸሙንም የሁለቱም ዞኖች አስተዳዳሪዎች ገልጸው በጥቃቱ የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ የአካባቢ ሚሊሻዎችና በነዋሪዎች ላይ ሞትና ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል። ጥቃቱ በማን እንደተፈጸመ በግልጽ ባይነገርም በሁለቱም አካባቢዎች ያሉ አስተዳዳሪዎች ግን አንዳቸው ከአንዳቸው ተጎራባች ወረዳ የመጡ ታጣቂዎች እንደሆኑ ገልጸዋል። የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች ይህንን ከስተት በተመለከተ ባወጡት መግለጫ ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት ""ጽንፈኛ ኃይሎች"" መሆናቸውን ገልጸው፣ ይህም በማኅበረሰቦች መካከል ግጭትን ለመፍጠር የታቀደ ነው ብለዋል። ከዚህ በፊትም በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በይዞታ ይገባኛል ምክንያት አልፎ አልፎ ግጭቶች ያጋጥሙ የነበረ ሲሆን፣ የአሁኑ ጥቃት ግን የፀጥታ ኃይሎች ላይ ያነጣጠረ ነው። የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች ጥቃት ፈጻሚዎቹን ተከታትሎ በመያዝ ለሕግ ለማቅረብ በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን ባወጡት መግለጫ አመልክተዋል። የተከሰተው ምነድን ነው? ማከሰኞ መጋቢት 20/2014 ዓ.ም በተከሰተው ጥቃት የሰሜን ሸዋ የምንጃር ሸንኮራ እና በምሥራቅ ሸዋ የፈንታሌ ኃላፊዎች እንደሚሉት ታጣቂዎቹ ከሌላኛው አካባቢ እንደመጡና ጉዳት እንዳደረሱ ይናገራሉ። በአማራ ክልል ባለው የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ቦሰት እንዳሉት ከኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሆነዉ አሞራቤት ቀበሌ አውራ ጎዳና መንደር ላይ ታጣቂዎቹ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ዋና አስተዳዳሪው ከአጎራባቹ የኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ መጡ ያሏቸው ጥቃት ፈጻሚዎቹ ""የተደራጁ እና የቡድንና በከባድ መሳሪያ የታጠቁ"" መሆናቸውን አመልክተው፣ በጥቃቱ የሰው ሕይወት መጥፋቱንና ንብረት መጎዳቱን በወረዳው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ አመልክተዋል። በአካባቢው ከዚህ ቀደምም የተለያዩ ጥቃቶች ያጋጥሙ እንደነበር የገለጹት አቶ ታደሰ ከቀናት በፊት የተፈጸመው ጥቃት መነሻ በግልጽ እንደማይታወቅ ገልጸው ""ምናልባትም ማንነታቸው ያልታወቁ ፀረ ሰላም ኃይሎች አቅደው አካባቢውን በማውደም ነዋሪዎችን ለማፈናቀል አልመው"" የፈጸሙት ሊሆን እንደሚችሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ በበኩላቸው ከአጎራባቹ የአማራ ክልል አካባቢ የመጣ ታጣቂ ቡድን በዞኑ የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት ፈጽሞ ጉዳት አድርሷል ብለዋል። ነገር ግን በቀጣይ ቀናት ጥቃቱን የፈጸመው አካል ማነው? ከየት የመጣነው? የሚለው ይጠራል ያሉት አቶ አባቡ ""የብሔር ግጭት መፍጠር የሚፈልጉ በኦሮሚያ እና አማራ ድንበር ላይ የሚንቀሳቀስ የተደራጀ ጽንፈኛ ኃይል ሊሆን ይችላል"" የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል። አስተዳዳሪው ጥቃት ፈጻሚው ቡድን ማንነቱ የማይታወቅ መሆኑን አመልክተው፣ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ እንደሆነና ባለፈው ማክሰኞ በአካባቢው የሚሊሻ አባላት ላይ በፈጸመው ጥቃትም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። በጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሏቸው የፀጥታ አባላት ለሥራ ተሰማርተው በቡድን እየተመለሱ ሳለ በተፈጸመባቸው ድንገተኛ ጥቃት ከመካከላቸው 18ቱ መገደላቸውንና 15 ደግሞ መቁሰላቸውን ረቡዕ ከሰዓት በኋላ ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የምሥራቅ ሸዋ ፖሊስ አዛዥ ኤቢሳ አሰፋ ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ኦቢኤን እንደተናገሩት በጥቃቱ የተገደሉት 26 ሰዎች ናቸው ብለዋል። የፖሊስ አዛዡ ጥቃቱ ያደረሰው ቡድንን ማንነት ያልገለጹ ሲሆን፣ ነገር ግን ""የተደራጀ እና ዘመናዊ ጦ�� መሳሪያ የታጠቀ ነው"" ሲሉ ከተፈጸመው ጥቃት ተነስተው ግምታቸውን አስቀምጠዋል። የኦሮሚያ ክልል ጥቃቱን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር ባወጣው መግለጫ ጥቃቱን የፈጸሙት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኘው ምንጃር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መሆናቸውን አመልክቷል። ክልሉ እንዳለው በምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ቆርኬ/አውራ ጎዳና በሚባለው ልዩ ሥፍራ ""በምንጃር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎች በጉዞ ላይ በነበሩት የሕዝብ ሚሊሻና የፌዴራል ፖሊስ ላይ"" ጥቃት ማድረሳቸውን አስታውቆ ሐዘኑን ገልጿል። ጥቃቱ ""የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች ዘላቂ አብሮነትና ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞን ለማደናቀፍ በጽንፈኛ ኃይሎች የተወጠነ የጥፋት ዕቅድ አካል"" ነው በማለት፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለሕግ ለማቅረብ እንደሚሰራ የኦሮሚያ ክልል አመልክቷል። ጨምሮም የኦሮሚያ ክልል ከአማራ ክልል ጋር በመሆን ጥቃቱ በደረሰበት ቦታ ላይ ተገቢውን ክትትል በማድረግ ወንጀለኞችን ህግ ፊት ለማቅረብ በጋራ እየሠራ መሆኑን አመልክቷል። የአማራ ክልል ይህንን ጥቃት ተከትሎ የአማራ ክልል ባወጣው መግለጫ ተመሳሳይ ጥቃቶች በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ መፈጸማቸውን አስታውሶ፣ የክልሉ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በሰውና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሐዘን ገልጿል። ጨምሮም ""ተስፈኛ ጽንፈኞችና አሸባሪዎች"" ያለቸው ኃይሎች በአማራ ክልል ሕዝብ እና በአጎራባች ክልል ሕዝብ መካከል ግጭት ለመፍጠር እንዲሁም የክልሉን ሕዝብ ""ማኅበራዊ እረፍት ለመንሳት በክልላችን አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት ለማጫር ተንቀሳቅሰዋል፤ እየተንቀሳቀሱም ይገኛሉ"" ይገኛሉ ብሏል። መግለጫው ""ከጽንፈኛና ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ የጥፋት ትስስር በመፍጠር የአማራ ክልልን የቀውስ ሜዳ ለማድረግ"" የጠላት እቅድ በመፈጸምም ሆነ በማስፈጸም ተግባር ላይ ተሳታፊ ናቸው ያላቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቋል። የክልሉን ሕዝብ ሰላምና ደኅንነት አደጋ ላይ ለመጣል በግልፅም ሆነ በህቡዕ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከዚህ ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነም በማንኛውም አይነት ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል። የመንገድ መዘጋት ጥቃቱን ተከትሎ መሃል ኢትዮጵያን ከጂቡቲ ወደብ ጋር በሚያገናኘው መስመር ላይ የሚገኘው ከመተሐራ ወደ ወለንጪቲ ከተማ የሚወስደው ዋነኛ መንገድ ለረጅም ሰዓታት ተዘግቶ እንደነበር የአካባቢው ኃላፊዎች ተናግረዋል። በዚህም ሳቢያ በሁለቱም በኩል የሚያልፉ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ባሉበት ለመቆም ተገደው የነበረ ሲሆን የመከላከያ ሠራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተሰማርተው አካባቢውን ካረጋጉ በኋላ መንገዱ ለተሽከርካሪ ክፍት ሆኗል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60930010 +health ኮሮናቫይረስ፡ ድመትና ውሾች ኮቪድ እንደሚይዛቸው ተደረሰበት "የኮቪድ ቫይረስ በለማዳ የቤት ውስጥ እንሰሳት በተለይም በውሾችና በድመቶች ላይ በስፋት እንደሚገኝ አንድ ጥናት አመለከተ። ጥናቱ እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው 196 የኮቪድ ተህዋሲ የጎበኘው ቤተሰብ ላይ ባደረገው ምርምር ነው። በ196 አባወራዎች ላይ በተደረገው ይህ ምርምር 310 ድመቶችና ውሾች የተካተቱበት ነው። ከነዚህ ውስጥ ስድስት ድመቶችና ሰባት ውሾች ተህዋሲውን ተሸክመው ተገኝተዋል። 54ቱ ደግሞ ከዚህ ቀደም ተህዋሲው ይዞ እንደለቀቃቸው የሚያሳይ የበሽታ ተከላካይ ቅንጣት ተገኝቶባቸዋል። ዶ/ር ኤልስ ብሮንስ በኡትሬች ዩኒቨርስቲ ተመራማሪና መምህር ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት ኮቪድ ያለባቸው ሰዎች ከድመትና ውሾቻቸው ��ር ምንም ዓይነት ንክኪ ባያደርጉ ይመረጣል። ""እዚህ ጋ ዋናው ነጥብ የእንሰሳቱ ጤና አይደለም"" ይላሉ ዶ/ር ኤልስ። ዋናው ነጥብ የቤት እንሰሳቱ ""ቫይረሱን ተሸካሚና አዘዋዋሪ ከመሆናቸው ላይ ነው።"" አጥኚዎቹ ከቤት እንሰሳቱ ወደ ሰው ቫይረሱ ስለመተላለፉ በእርግጥ ያሉት ነገር ባይኖርም በውሻና በድመት ላይ ግን ተህዋሲው ጎልቶ የማይታይና እነሱም ቢሆን ምንም ዓይነት የበሽታ ምልክቶችን እንደማያሳዩ ደርሰውበታል። ካሳዩም እጅግ ዝቅተኛ የሆኑ ምልክቶቹን ብቻ ነው የሚሆነው። በጥናቱ የተሳተፉ ተመራማሪዎች በርካታ የቤት እንሰሳት ቫይረሱን ያገኙት ከሰው ልጆች እንደሆነና ነገር ግን በተቃራኒው እንዳልሆነ ገምተዋል። የቤት እንሰሳቱ ባለቤቶች ተህዋሲውን ከድመትና ከውሻ የማግኘታቸው ዕድል ዜሮ ነው ልንል አንችልም፤ ነገር ግን ይህ የመሆን ዕድሉ አነስተኛ ነው ብለዋል የእንሰሳት ሐኪምና የማይክሮባዮሎጂካል ዳያግኖስቲክ ሴንተር ባልደረባ ዶ/ር ብራውንስ። በሩሲያ የእንሰሳት ሐኪሞች ለቤት እንሰሳት የተህዋሲውን ክትባት መውጋት መጀመራቸው መዘገቡ ይታወሳል። ዶ/ር ብራውን ግን ይህን ማድረጉ ጥቅሙ አልታይ ብሏቸዋል። ""ለጊዜው እንሰሳቱ ተህዋሲውን ወደ ሰው ስለማስተላለፋቸው አስተማማኝ የሆነ ሳይንሳዊ መረጃ አላገኘንም"" ይላሉ።" https://www.bbc.com/amharic/57662274 +business ጠ/ሚንስትር ዐብይ አህመድ ግንባታውን ከጎበኙት የላሙ ወደብ ምን ይጠበቃል? "ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የላሙ ወደብ ግንባታን ጎበኙ። መሪዎቹ በተጨማሪም ዛሬ ሐሙስ በሞምባሳ የተገኝተው ሊኮኒ የእግረኞች መሻገሪያ ድልድይን በይፋ ይመርቃሉ። 1.2 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የሞምባሳው ሊኮኒ ድልድይ ለቀጠናው የመጀመሪያው ሲሆን፤ ድልድዩ በ1.9 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ ወጪ የተገነባ ነው። ሁለቱ መሪዎች ትላንት በመርሳቤት ግዛት የተገነባውን የድንበር መተላለፊያ መርቀዋል። ከዚያም ወደ ላሙ ግዛት አቅንተው የወደብ ግንባታ ሂደቱን ቃኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅት፤ ኢትዮጵያ እና ኬንያ በድንበር ተሻጋሪ የመሠረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ እንደሚተባበሩ መሪዎቹ ተናግረዋል። በግንባታ ላይ የሚገኘውን ባለ 32 ክፍል የላሙ ወደብ በጎበኙበት ወቅት፤ ከሞምባሳ በናይሮቢ አድርጎ አዲስ አበባ የሚገባውን አውራ ጎዳና ለማፋጠን ተስማምተዋል። ይህ አውራ ጎዳና የቀጠናውን ንግድ ያሳልጣል ተብሎ ይጠበቃል። ፕሬዝደንት ኡሁሩ ""የሞምባሳ-ናይሮቢ-አዲስ አበባ አውራ ጎዳና አካል የሆነውን የላሙ ወደብ ግንባታ ቃኝተናል። በዚህ የላፕሴት ፕሮጀክት አማካይነት ኢትዮጵያ አስተማማኝ እና ቀጥተኛ የሆነ መንገድ ታገኛለች። ሞያሌን፣ ኢሲኦሎን እና የላሙ ወደብን የሚያገናኝ ነው"" ብለዋል። ላፕሴት (LAPSSET) የተባለው ፕሮጀክት የላሙ ወደብን፣ ደቡብ ሱዳንን እና የኢትዮጵያ የትራንስፖርት መተላለፊያን የሚወክል ነው። ይህ ፕሮጀክት የኬንያ፣ የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ነው። ፕሮጅክቱ ሦስቱን አገራት እርስ በእርስ የሚያስተሳስር ሲሆን፤ ከሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ጋርም እንደሚያገናኛቸው ተገልጿል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የላሙ ወደብ ለኢትዮጵያ እና ለደቡብ ሱዳን እንደሚጠቅም ተናግረዋል። የሁለቱ አገሮች ትብብር መላው አፍሪካን ለማስተሳሰር የሚደረገው ጥረት አካል እንደሆነም ገልጸዋል። ""የላሙ ወደብ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለደቡብ ሱዳንም ይጠቅማል። በቀጠናችን የምጣኔ ሀብት ትስስር ለመፍጠርና የሕዝባችንን ሕይወት ለመለወጥ ያለን ራዕይ እውነት እንዲሆን ያግዛል"" ብለዋል። ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆኗና የአውራ ጎዳና መሠረተ ልማት ውስንነት አገሪቱ ላይ ያሳ��ረውን ተጽዕኖ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ""በ21ኛው ክፍለ ዘመን ያለ መሠረተ ልማት እና የምጣኔ ሀብት ትስስር መኖር አይቻልም። ምሥራቅ አፍሪካን መቀየር የምንችለው ወንድሜ [ኡሁሩ ኬንያታ] ኬንያ ውስጥ እንዳደረጉት ሁሉ እያንዳንዱ መንግሥት ጊዜና አቅሙን መሠረተ ልማት ላይ ለማፍሰስ ቁርጠኛ ሲሆን ነው"" ብለዋል። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ በበኩላቸው፤ ኬንያ እና ኢትዮጵያ የትራንስፖርት ትስስር ለመፍጠር ከተስማሙ በኋላ የላሙ ወደብ ግንባታ በአመርቂ ሁኔታ እየተገነባ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የመጀመሪያው ክፍል እንደተጠናቀቀና የሁለት ተጨማሪ ክፍሎች ግንባታ 86 በመቶ ማለቁን ተናግረዋል። ""በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ላይ እርስዎን እና የደቡብ ሱዳኑን ፕሬዝዳንት ጋብዤ የወደቡን ሦስት ክፍሎች እንደምናስጀምር ተስፋ አደርጋለሁ"" ሲሉ ኡሁሩ፤ ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ተናግረዋል። ላሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ወደብ ሆኖ የምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የንግድ መዳረሻ እንደሚሆንም ኡሁሩ አመልክተዋል። ኢትዮጵያ እና ኬንያ በምን መንገድ በቀጠናው የትራንስፖርት ቢዝነስ እንደሚጣመሩ የሚጠቁም ዝርዝር እቅድ ይፋ እንደሚያደርጉም አክለዋል። ይህም ምሥራቅ አፍሪካን በቀጠናው እንዲሁም በአፍሪካም የሎጅስቲክስ ዘርፍ ግንባር ቀደም የሚያደርግ ነው ብለዋል። ፕሬዘዳንት ኡሁሩ አያይዘውም የላሙ-ዊቱ-ጋሪሰን አውራ ጎዳና 80 በመቶ ተጠናቋል ብለዋል። ይህ አውራ ጎዳና በጋሪሳ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት አመቺ መሆኑ ተጠቁሟል። ከዚህ ቀደም የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን የጎበኙት ፕሬዝዳንቱ፤ ሁለቱ አገሮች ልዩ የምጣኔ ሀብት ማዕከል ሞያሌ ውስጥ ለመገንባት መወሰናቸውን ተናግረዋል። ይህም ድንበር ተሻጋሪ ንግድን ከማሳደጉ ባሻገር የአካባቢውን ነዋሪዎች እንደሚጠቅም ተገልጿል። የላሙ ወደብ ይህ ወደብ የሚገነባው በኬንያዋ ላሙ ግዛት ውስጥ ሲሆን 32 መርከቦች በተመሳሳይ ሰዓት መልህቃቸውን እንዲጥሉ የሚያስችል ነው። የዚህ ወደብ ግንባታ አጠቃላይ ወጪ ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል። የመጀመሪያዎቹ ሦስት መርከብ ማረፊያዎች ግንባታ ወጪ በኬንያ መንግሥት የሚሸፍን ይሆናል ተብሏል። የመጀመሪያው መርከብ ማቆሚያ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ሁለተኛው እና ሦስተኛዎቹ የመርከብ ማቆሚያዎች ግንባታ ደግሞ በቀጣይ ወራት ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይገመታል። ይህንንም ተከትሎ የላሙ ወደብን ወደ ሥራ ለማስገባ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55255792 +sports 'ሴቶች ብዙ ያወራሉ' ያሉት የቶክዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ሥራ ሊለቁ ነው "የቶክዮ ኦሊምፒክስ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊ የሆኑት ግለሰብ ሴቶችን አስመልክተው የሰጡትን ፆተኛ አስተያየት ተከትሎ በደረሰባቸው ከፍተኛ ወቀሳ ሥልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ሊለቁ ነው። የኮሚቴው ኃላፊው የ83 ዓመቱ ዮሺሮ ሞሪ ሴቶች በስብሰባዎች ላይ ""በጣም ብዙ ያወራሉ፤ ሴት የቦርድ ኃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል"" ሲሉ ተናግረዋል ተብሏል። ዮሺሮ ሞሪ ለሰጡት አስተያየት ይቅርታ ጠይቀው በሰጠሁት አስተያየት ግን ስልጣኔን አለቅም ብለው ነበር። ይሁን እንጂ ሞሪ ጫናው በርትቶባቸው ሥልጣናቸውን ሊለቁ ከጫፍ ተቃርበዋል። . ጭንቅላቱን ከአዞ አፍ ፈልቅቆ በማውጣት ራሱን ያተረፈው አውስትራሊያዊ . ""ለምን ስሜን ለ20 ዓመታት ደበቅኩ?""የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ነገ አርብ በይፋ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊነት እንደሚነሱ ይጠበቃል ሲሉ የጃፓን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሞሪ ሴቶችን በማስመልከት ብዙ ያስወቀሳቸውን ፆተኛ አስተያየት የሰጡት ከአንድ ሳምንት በፊት በተካሄደው የጃፓን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስ��ሰባ ላይ ነበር።በስበሰባው ላይ ""ሴት የቦርድ አባላትን ቁጥር ለመጨመር ካሰብን ለሚያደርጉት ንግግር የሚሰጣቸው ሰዓት የተወሰነ ሊሆን ይገባል። እነሱ እንደሆነ ቶሎ ተናግሮ የመጨረስ ችግር አለባቸው። በጣም ያናድዳል"" ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል በማለት የጃፓኑ አሳሂ ሺምቡን ጋዜጣ ዘግቧል።የኦሊምፒክ ኮሚቴ በአሁኑ ወቅት 24 አባላት ያሉት ሲሆን አምስቱ ሴቶች ናቸው።ከትናንት በስቲያ የሴቶች የሕግ ባለሙያዎች ስብስብ የሞሪን አስተያየት ለመቃወም ባለ ነጭ ቀለም ልብስ ለብሰው ታይተዋል። የሴት የሕግ ባለሙያዎቹን ሃሳብ በመደገፈም በርካቶች ነጭ የመልበስ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል። በርካቶችም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሞሪ ስልጣናቸው እንዲለቁ እየጠየቁ እና ፊርማ እያሰበሰቡ ነው። በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ በነጻ አገልግሎት ለመስጠት ከተመዘገቡ ከ400 በላይ ሰዎች የሰውዬውን ንግግር ተከትሎ ፍቃደኝነታቸውን ስርዘዋል ተብሏል። በፈረንጆቹ ከ2000 እስከ 2001 ለአንድ ዓመት ብቻ ጃፓን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያስተዳደሩት ዮሪ ዲፕሎማሲ በራቃቸው አስተያየቶቻቸው ይታወቃሉ።" https://www.bbc.com/amharic/56027725 +health በአውስትራሊያ አረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት በየሳምንቱ 50 ወሲባዊ ጥቃቶች ይደርሳሉ ተባለ "በአውስትራሊያ የሚገኙ የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት ውስጥ በየሳምንቱ አምሳ ያህል ወሲባዊ ጥቃቶች እንደሚደርሱ ከሰሞኑ ብሔራዊ አጣሪ ኮሚቴ ይፋ አድርጓል። ለሁለት አመታት ያህልም በአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶችንና መንገላቶችን ይፋ ባደረገበት መረጃ ነው ሮያል ኮሚሽን ይህንንም ያካተተው። መርማሪዎቹ እንዳሉት በጎሮጎሳውያኑ 2018-2019 ጊዜ 2 ሺህ 520 አረጋውያን ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። ""ይህ ሁኔታ ብሔራዊ እፍረት ነው"" ብለውታል የምክር ቤት አባሉ ፒተር ሮዝን ኪው ሲ ለአጣሪው ኮሚቴ ""ቁጥሮቹ የሚረብሹትን ያህል እነዚህን መረጃዎች ያገኘው የመንግሥት አካል ክትትትልና ቁጥጥር አለማድረጉ የበለጠ የከፋ ነው"" ብለዋል። በአረጋውያኑ የእንክብካቤ ማዕከል ላይ የሚታየው ቸልተኝነት ከፍተኛ ውዝግብና ጥያቄ ያስነሳ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በአውስትራሊያ በኮሮናቫይረስ ከሞቱት አብዛኛዎቹ በአረጋውያን ማዕከል የሚገኙ ናቸው። አውስትራሊያ በኮሮናቫይረስ ሞተዋል ብላ ከመዘገበችው 903 ሰዎች መካከል 75 በመቶ በነዚህ ማዕከላት የሚገኙ ናቸው። በእነዚህ ማዕከላት ላይ የሚደርሱ ወሲባዊ ጥቃቶች የቀደመ ስጋት ሆነው የቆዩ መሆናቸውን ያመኑት ፒተር ሮዝን ቁጥሩም በአገሪቱ ያሉትን 13-18 በመቶ ጥቃት እንደደረሰባቸው ያሳያል። በርካቶች በዕድሜያቸው የበለፀጉ ወይም ተጋላጭ የሆኑ ቤተሰቦቻቸውን በአረጋውያኑ ማዕከል የሚያስገቡት ደህንነታቸው ይጠበቃል በሚል ዕምነትም እንደሆነም የምክር ቤት አባሉ አስረድተዋል። ""በአረጋውያን ማዕከላት የሚገኙ ሰዎች ከማህበረሰቡ በበለጠ ለወሲባዊ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸው ተቀባይነት የለውም"" ብለዋል ፒተር ሮዝን በአጠቃላይ መርማሪዎች እንደሚገምቱት 32 ሺህ ያህል ወሲባዊ፣ አካላዊና የስነልቦናዊ ጥቃቶች መድረሳቸውን ነው። ይህም ቁጥር በአንድ አመት ያህል እንደደረሰ መረጃው ጠቁሟል። ወሲባዊ ጥቃቱ እንክብካቤ በሚሰጡ ግለሰቦች እንዲሁም እዛው ባሉ ነዋሪዎች እንደሚፈፀምም መረጃው ይፋ አድርጓል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54637492 +health የእሲያ-ፓሲፊክ አገራት በኮቪድ ምክንያት የተጣሉ ዓለም አቀፍ የጉዞ ገደቦችን ማንሳት ጀመሩ ሲንጋፖር፣ አውስትራሊያ እና ጃፓንን ጨምሮ የእሲያ-ፓሲፊክ አገራት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዓለም አቀፍ ጎዞዎች ላይ ተጥለው የነበሩትን ክልካላዎች ማንሳት መጀመራቸው��� ሬውተርስ ዘገበ። አገራቱ የዓለም አቀፍ በረራዎች መጀመር በቫይረሱ ስርጭት የተጎዳውን ምጣኔ ሃብታቸውን እንደሚያነቃቃው ታምኖበታል። እንደ እሲያ ፓሲፊክ አየር መንገደኞች ማህበር አሃዝ ከሆነ በእሲያ ብቻ በኮቪድ-19 ምክንያት ሰኔ ወር ላይ የዓለም አቀፍ ተጓዦች ቁጥር 97 በመቶ ቀንሶ ነበር። አሁንም ቢሆን በርካታ የእሲያ አገራት ተጓዦች ከኮቪድ ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት፣ የህክምና መድህን እና አንዳንዶች ደግሞ ወደ ለይቶ መቆያ መግባትን ግዴታ ስለሚያደርጉ የተጓዦች ቁጥር በቅርቡ ላያንሰራራ ይችላል። ይህም ለአየር መንገዶች እና ለቱሪዝም ዘረፉ ሌላ ፈተና ሆኖ ይቀጥላል። ሲንጋፖር እና ኢንዶኔዢያ በአገራቱ መካከል የኮሮናቫይረስ ምርመራ በማድረግ ለይፋዊ የመንግሥት ሥራ ጉዞ እንዲደረግ ከስምምነት ደርሰዋል። ሲንጋፖር ከዚህ ቀደም ከቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና ማሌዢያ ጋር ተመሳሳይ ስምምነትን የደረሰች ሲሆን ከኒው ዚላንድ እና ቪዬትናም ግን ማንኛው ተጓዥ ወደ ሲንጋፖር መግባት ይችላል ተብሏል። የኒው ዚላንድ ዜጎች ደግሞ ወደተወሰኑት የአውስትራሊያ ግዛቶች ከአርብ ጀምሮ ወደ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ መግባት ሳይጠበቅባቸው መጓዝ ይችላሉ። ይሁን እንጂ የኒው ዚላንድ ዜጎች ከአውስትራሊያ ሲመለሱ እራሳቸውን ለሁለት ሳምንት ለይተው የመቆየት ግዴታ ይኖርባቸዋል። ከአምስት ቀናት በኋላ አጠቃላይ ምርጫ የምታከናውነው ኒው ዚላንድ ድንበሮቿን ለአውስትራሊያ ክፍት ለማድረግ እቅድ እንደሌላት ተጠቁሟል። አውስትራሊያ በበኩሏ ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለመጀመር ከጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ሲንጋፖር ጋር ምክክር እያካሄደች ትገኛለች። ጃፓን እና ቪዬትናም ደግሞ ለንግድ የሚደረጉ ጉዞዎች እንዲከናወኑ ተስማምተዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54506852 +sports ሴቶች 'ብዙ ያወራሉ' ያሉት የቶክዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ሥራቸውን ለቀቁ "የቶክዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊ የሆኑት ግለሰብ ሴቶችን አስመልክተው የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ በደረሰባቸው ከፍተኛ ወቀሳ ሥልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ለቀዋል። የኮሚቴው ኃላፊው የ83 ዓመቱ ዮሺሮ ሞሪ ሴቶች በስብሰባዎች ላይ “በጣም ብዙ ያወራሉ፤ ሴት የቦርድ ኃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል' ሲሉ ተናግረዋል ተብሏል። ዮሺሮ ሞሪ ለሰጡት አስተያየት ይቅርታ ጠይቀው በሰጠሁት አስተያየት ግን ስልጣኔን አለቅም ብለው ነበር። ነገር ግን ዛሬ አርብ ዕለት ለሰነዘርኩት ያልተገባ አስተያየት ይቅርታ እጠይቃለው በማለት ከስራቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ይፋ አድርገዋል። ''በአሁኑ ሰአት ዋናው ነገር ሐምሌ ወር ላይ ኦሎምፒክ መካሄዱ ነው። የእኔ በእዚህ አካባቢ መገኘት የዝግጅቱን ስራ ከባድ እንዲያደርገው አልፈልግም'' ብለዋል ዛሬ በተካሄደው የኮሚቴው ልዩ ስብሰባ ላይ። የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ነገ አርብ በይፋ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊነት እንደሚነሱ ይጠበቃል ሲሉ የጃፓን መገናኛ ብዙሃን ዘግበው ነበር። ሞሪ ሴቶችን በማስመልከት ብዙ ያስወቀሳቸውን አስተያየት የሰጡት ከአንድ ሳምንት በፊት በተካሄደው የጃፓን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነበር። በስበሰባው ላይ ""ሴት የቦርድ አባላትን ቁጥር ለመጨመር ካሰብን ለሚያደርጉት ንግግር የሚሰጣቸው ሰዓት የተወሰነ ሊሆን ይገባል። እነሱ እንደሆነ ቶሎ ተናግሮ የመጨረስ ችግር አለባቸው። በጣም ያናድዳል"" ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል በማለት የጃፓኑ አሳሂ ሺምቡን ጋዜጣ ዘግቧል። የኦሊምፒክ ኮሚቴ በአሁኑ ወቅት 24 አባላት ያሉት ሲሆን አምስቱ ሴቶች ናቸው።ከትናንት በስቲያ የሴቶች የሕግ ባለሙያዎች ስብስብ የሞሪን አስተያ���ት ለመቃወም ባለ ነጭ ቀለም ልብስ ለብሰው ታይተዋል። የሴት የሕግ ባለሙያዎቹን ሃሳብ በመደገፈም በርካቶች ነጭ የመልበስ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል። በርካቶችም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሞሪ ስልጣናቸው እንዲለቁ እየጠየቁ እና ፊርማ አሰባስበው ነበር። በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ በነጻ አገልግሎት ለመስጠት ከተመዘገቡ ከ400 በላይ ሰዎች የሰውዬውን ንግግር ተከትሎ ፍቃደኝነታቸውን ስርዘዋል ተብሏል። በፈረንጆቹ ከ2000 እስከ 2001 ለአንድ ዓመት ብቻ ጃፓን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያስተዳደሩት ዮሪ ዲፕሎማሲ በራቃቸው አስተያየቶቻቸው ይታወቃሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-56038533 +health የዓለም ጤና ድርጅት አውሮፓን በድጋሚ የወረርሽኙ ማዕከል ናት ሲል አስጠነቀቀ "በአውሮፓ እየተባባሰ በመጣው ስርጭት ምክንያት አህጉሪቱ በድጋሚ የኮቪድ ወረርሽኝ ""ማዕከል"" ሆናለች ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ኃላፊ ሃንስ ክሉጅ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንዳሉት አህጉሪቱ በየካቲት ወር ግማሽ ሚሊዮን ተጨማሪ ሞት ልታስመዘግብ ትችላለች። ለስርጭቱ መጨመር በበቂ ሁኔታ ክትባት አለመሰጠቱን በማንሳት ትችቱን ሰንዝሯል። ""ለኮቪድ-19 መስፋፋት ምላሽ ከመስጠት ቀድሞውኑ እንዳይከሰት ወደሚያግዙ ስልቶች መለወጥ አለብን"" ብለዋል። ከቅርብ ወራት ወዲህ በመላው አህጉሪቱ ክትባቱን የመስጠት ምጣኔው ቀንሷል። በስፔን ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ሁለቱን ዙር ክትባት ወስደዋል። ይህ ቁጥር በፈረንሳይ እና በጀርመን ዝቅተኛ በሚባል ደረጃ፣ 68 በመቶ እና 66 በመቶ ላይ ይገኛል። የአንዳንድ የመካከለኛው እና የምስራቅ አውሮፓ ሃገሮች አሃዝ ደግሞ ከዚህም ዝቅተኛ ነው። እአአ ጥቅምት 2021 ሙሉ ለሙሉ ክትባቱን የወሰዱ ሩሲያውያን 32 በመቶ ብቻ ናቸው። ክሉጅ የማዕከላዊ እስያ ክፍልን ጨምሮ 53 ሃገሮችን በሚሸፍነው የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ዞን የህዝብ ጤና እርምጃዎችን መላላትን ለበሽታው መባባስ እንደተጨማሪ ምክንያት አንስተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በአካባቢው እስካሁን 1.4 ሚሊዮን ሰዎች መሞታቸውን መዝግቧል። የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ቴክኒካል ኃላፊ ማሪያ ቫን ኬርክሆቭ ምንም እንኳን ""በቂ የክትባት እና የመሳሪያ አቅርቦት"" ቢኖርም ወረርሽኙ ባለፉት አራት ሳምንታት በመላው አውሮፓ ከ 55 በመቶ በላይ ከፍ ብሏል ብለዋል። ባልደረባቸው ዶክተር ማይክ ሪያን የአውሮፓ ተሞክሮ ""ለዓለም የማስጠንቀቂያ ደወል ነው"" ሲሉ ገልጸውታል። በጀርመን ስርጭቱ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ወደ 34000 የሚጠጉ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ተመዝግበዋል። በጀርመን ያለው የኮቪድ ስርጭት በዕለት ከ 37000 የሚበልጡ ሰዎች በቫይረሱ ከሚያዙባት የዩኬ የቅርብ ጊዜ ቁጥሮች በታች ነው። የህብረተሰብ ጤና ባለሥልጣናት ግን አራተኛው ማዕበል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሞት ሊያስከትል እና በጤና ስርዓቱ ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 165 ሰዎች መሞታቸው የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከአንድ ሳምንት በፊት ከነበረው 126 ሞት ጨማሪ አሳይቷል። የጀርመን አርኬአይ ኢንስቲትዩቱ ሎተር ዊለር ስለ አስፈሪ ቁጥሮች ተናግረዋል። ""አሁን የመከላከያ እርምጃዎችን ካልወሰድን አራተኛው ማዕበል የበለጠ አደጋ ያመጣል"" ብለዋል። ክትባቱን ካልወሰዱት ጀርመናውያን መካከል ከ60 በላይ ዕድሜ ያላቸው ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሲሆን እነዚሀም ለበለጠ አደጋ የተጋለጡ ናቸው። ሃንስ ክሉጅ እንደሚሉት የቫይረሱ መጨመር በጀርመን ብቻ የተገደበ አይደለም። ባለፈው ሳምንት የሟቾች ቁጥር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው በሩሲያ ሲሆን ከ 8,100 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ���ልፏል። በዩክሬን ደግሞ 3800 ሰዎች ሞተዋል። ሁለቱም ሀገራት በጣም ዝቅተኛ ክትባት የሰጡ ሲሆን ዩክሬን ባለፉት 24 ሰዓታት 27377 አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አስመዝግባለች። ሮማኒያ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ የሆነውን የ591 ሰዎችን ሞት አስመዝግባለች። በሃንጋሪ በየዕለቱ በኮቪድ የሚያዙ ሰዎች ከእጥፍ በላይ አድጎ ባለፈው ሳምንት 6268 ደርሷል። ጭንብል መልበስ አስገዳጅ የሆነው በሕዝብ ማመላለሻዎች እና በሆስፒታሎች ብቻ ነው። ዶክተር ሪያን ""በአሁን ተጨማሪ ጥቂት ሰዎችን ከከተብን ወረርሽኙ አብቅቷል የሚል ሃሳብ ላይ ነን። ጉዳዩ እንደዚያ አይደለም"" ብለው ሃገራት ቀዳዳቸውን እንዲደፍኑ ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል። የደች መንግሥት ጭንብል መልበስ እና አካላዊ መራራቅን ህዝብ በሚሰባሰብበት ቦታዎች ላይ እንደሚጀምር በዚህ ሳምንት ተናግሯል። ምክንያቱ ያለው ደግሞ በሳምንት ውስጥ የሆስፒታል አልጋዎች የመያዝ ምጣኔ በ 31 በመቶ ከፍ በማለቱ ነው ። የኮቪድ ስርጭት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ላትቪያ ከሰኞ ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥታለች። ክሮሺያ ሐሙስ ዕለት 6310 አዳዲስ በቫእረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባለች። ይህ ቁጥር እስካሁን ድረስ ከታየው ከፍተኛው ቁጥር ነው። ስሎቫኪያ ሁለተኛውን ከፍተኛ ቁጥር መዝግባለች። የቼክ ስርጭት በፀደይ ወቅት ወደ ነበረበት ደረጃ ተመልሷል። የእንግሊዝ ምክትል ዋና የህክምና መኮንን ፕሮፌሰር ጆናታን ቫን ታም በበኩላቸው በጣም ብዙ ሰዎች ወረርሽኙ እንዳበቃ ያምናሉ ብለዋል። ከፍተኛ የክትባት መጠን በደረሰባቸው ሃገሮች የስርጭት መጠኑ አሁንም በአንጻራዊነት ሁኔታ ዝቅተኛ ነው። ጣሊያን ከ12 አመት በላይ ለሆኑት ዜጎቿ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ክትባት ብትሰጥም ባለፈው ሳምንት ውስጥ አዳዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በ16.6 በመቶ ጨምሯል። ከመስከረም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፖርቹጋል የስርጭት መጠን ከ 1000 በላይ ሆኗል። ረቡዕ 2287 ሰዎች በቫይረሱ የታዩዛበት ስፔን የስርጭት መጨመር ካላዩት ጥቂት ሃገሮች አንዷ ሆናለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-59165910 +sports አሜሪካ፡ ፖሊሶች ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሳቸውን በመቃወም ቴኒስ ተጫዋቿ ኦሳካ ራሷን ከውድድር አገለለች ጃፓናዊቷ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ናዮሚ ኦሳካ ፖሊሶች ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሳቸውን በመቃወም ከታላቁ የኒው ዮርክ ቴኒስ ውድድር ራሷን አገለለች። “ጥቁር ሴት እንደመሆኔ እኔ ቴኒስ ስጫወት ከማየት በበለጠ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች እንዳሉ አምናለሁ” ብላለች በትዊተር ገጿ። ምንም መሣሪያ ያልታጠቀው ጥቁር አሜሪካዊው ጄኮብ ላይ ፖሊሶች ከጀርባው ተኩሰውበታል። እሁድ በኪኖሻ ግዛት ከተተኮሰበት በኋላ በመላው ዊስኮንሰን ተቃውሞ ተቀጣጥሏል። በፖርትላንድ፣ ሚኒሶታና ሌሎችም ግዛቶች ተቃውሞው ቀጥሏል። ከወራት በፊት ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ መገደሉን በመቃወም በመላው አገሪቱ የ ‘ብላክ ላይቭስ ማተር’ [የጥቁሮች ሕይወት ዋጋ አላት] ሰልፎች መካሄዳቸው አይዘነጋም። ደብሊውቲኤ የተባለው የሜዳ ቴኒስ ውድድር አዘጋጆች እስከ አርብ ድረስ ጨዋታው እንደተሰረዘ አስታውቀዋል። “የዘር መድልዎና ኢፍትሐዊነትን የቴኒስ ስፓርት እንደሚቃወም ማሳየት እንፈልጋለን” የሚል መግለጫም አውጥተዋል። ናዮሚ ኦሳካ ከግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ መውጣቷን መግለጿን ተከትሎ ነበር ይህ መግለጫ የወጣው። በጃፓንኛና በእንግሊዘኛ በጻፈችው ትዊት “ቴኒስ ስላልተጫወትኩ ትልቅ ነገር ይፈጠራል ብዬ አልጠብቅም። ነገር ግን ነጭ ተጫዋቾች በሚበዙበት ስፖርት ውስጥ አንዳች ውይይት እንዲጀመር ምክንያት ከሆንኩኝ ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ እየተራመድን ነው” ብላለች። ናዮሚ አያይዛም “ጥቁሮች በፖሊሶች እየተገደሉ መሆኑን ሳይ ያመኛል” ስትል ሀዘኗን ገልጻለች። ጃፓናዊና የሄይቲ ውህድ የሆነችው ናዮሚ፤ ጃፓን ውስጥ የዘረኝነት ሰለባ ናት። ማስታወቂያዎች ላይ የቆዳ ቀለሟን ሲያነጡ፤ ቆዳዋን ነጭ ማድርግ አለባት እያሉ የሚሳለቁ ኮሜዲያኖችም አሉ። በስፓርቱ ዓለም ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሱን የተቃወሙ ሌሎችም አሉ። የቅርጫት ኳስ ቡድኑ ሚልዋኪ ባክስ ከውድድር መውጣታቸውን ተከትሎ ኤንቢኤ ሦስት ግጥሚያዎች ሰርዟል። ሁለት የቤዝቦል ጨዋታዎችም ተሰርዘዋል። ፖሊሶች ጄኮብ ላይ የተኮሱት ያሳለፍነው እሁድ ሦስት ልጆቹ ወደ ነበሩበት መኪና ሲገባ ነው። አሁን ሆስፒታል ውስጥ እያገገመ ሲሆን፤ ጠበቃው ከዚህ በኋላ መራመድ ከቻለ ተዓምር ነው ብለዋል። ፖሊሶች ጄኮብ ላይ ሰባት ጊዜ መተኮሳቸውን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-53929600 +health ረመዳን፡ ጾም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥና የሚሰጠው ጥቅም "ታላቁ የረመዳን ጾም ወቅት እነሆ ተጀምሯል። በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ በጉጉት የሚተበቀው ይህ ወቅት ቀኑ በጾም ምሽት ላይ ደግሞ ከቤተሰብና ከዘመድ ጋር ተሰብስቦ በአንድነት ማፍጠር የተለመደ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በገጠማት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ላይ ተሰብስቦ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶችን መካፈልና ከተለያዩ ሰዎች ጋር መሰባሰብ እንዲቀር ይመከራል። ስለዚህም በሐይማኖት አባቶች የሚሰጠውን ምክር ተግባራዊ በማድረግ ይህንን ቅዱስ የጾም ወቅት እራሳችንንና ሌሎችን በመጠበቅ ልናሳልፈው ይገባል። በወረርሽኙ ምክንያት ምዕመናን ቀደም ሲል ሲያከናውኗቸው የነበሩ የጋር ሥርዓቶችን ማድረግ ባይችሉም፤ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ከቅርብ የቤተሰብ አባላቸው ጋር የተለመደውን ሥርዓት መፈጸም ይችላሉ ተብሏል። መጾም ታላቅ መንፈሳዊ ጸጋ እንደሚያስገኝ የሐይማኖት አባቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገር ደግሞ የጤና ባለሙያዎች ጾም ከሚያስገኘው መንፈሳዊ በረከት በተጨማሪ ለአካላዊ ጤንነት የሚሰጠው ጠቀሜታ አለው ይላሉ። ዝርዝሩን እነሆ. . . በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ረመዳንን በጾም ያሳልፋሉ። ጀንበር ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ። ሰውነታችን ከጾም ጋር የሚተዋወቀው ለመጨረሻ ጊዜ ምግብ ከቀመስን ከስምንት ሰዓታት በኋላ ነው። ይህም ማለት አንጀታችን ከተመገብነው ምግብ የሚያገኛቸውን ንጥረ ነገሮች በሙሉ አሟጦ ከጨረሰ በኋላ ነው የሚሆነው። ከዚህ በኋላ ሰውነታችን ተስፋ ይቆርጥና ፊቱን ጡንቻችንና ጉበታችን ውስጥ ወደተከማቸ ጉሉኮስ ያዞራል። የተቀረው የሰውነታችን አካል ጉልበት የሚያገኘውም ከዚህ የመጠባበቂያ 'ግምጃ ቤት' ከሚያገኘው ኃይል ይሆናል ማለት ነው። ከጡንቻና ከጉበት የጉሉኮስ ክምችት ሲያልቅ ሰውነታችን ሌላ አማራጭ ስለማይኖረው ስብን (Fat) ማቃጠል ይጀምራል። ከዚህ በኋላ ሙቀትና ጉልበትን የሚያገኘውም ከሌላ ሳይሆን ስብን በማቃጠል ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ታዲያ መልካም ነገሮች ይከሰታሉ። የሚቃጠለው ስብ በመሆኑ ክብደት መቀነስ፣ የኮሌስትሮል መጠን መውረድ ይኖራል። የስኳር መጠናችን በዚህ ወቅት ዝቅ ማለቱ አይቀርም። ሆኖም በደማችን ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን ስለሚቀንስ ድካምና መዛልን ያስከትልብናል። ይህን ተከትሎ መጠነኛ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና መልካም ያልሆነ የአፍ ጠረን ሊከተል ይችላል። ይህ የሚሆነው በረሀብ ምክንያት ሆዳችንን ሲሞረሙረንና ያለ ምግብ መቆየቱ ለሰውነታችን እየከበደው ሲመጣ ነው። ከ3-7ኛ ቀን፤ ሰውነታችን በፈሳሽ እጥረት የሚጎዳበት ጊዜ ሰውነታችሁ ጾሙን እየተለማመደ ሲመጣ በውስጣችን የሚገኘው የስብ ክምችት እየተሰባበረ ራሱን ወደ የደም ስኳርነት (Blood sugar) ይለውጣል። የምንወስደው ፈሳሽ መጠን እየቀነሰ መምጣቱ በሰውነታችን ውስጥ ያለው ፈሳሽ ወደመሟጠጥ (ዲሃይድሬሽን) ስለሚያመራ በ""ማፍጠሪያ"" ሰዓትና ከዚያም በኋላ ባለው የሌሊቱ ክፍለ ጊዜ በርከት ያሉ ፈሳሾችን መውሰድ ይመከራል። በጾም መግደፊያ ሰዓት የምትወስዱት የምግብ መጠን ጉልበት ሰጪ የሆኑ ተመጣጣኝ ምግቦችን ማግኘት ይኖርበታል። በፕሮቲን ከበለጸጉ ምግቦች ባሻገር ጨው እና በርከት ያለ ውኃ ከሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦች ጋር ማግኘት ለሰውነታችን መልካም ሁኔታን ይፈጥራል። ከ8ኛ-15ኛ ቀናት በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጾሙን ተላምዶታል። በዚህም የተነሳ ድካምና መዛሉ እንደመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም። ዶክተር ራዚን ማህሩፍ የአኔስቴሺያና የጽኑ ሕሙማን ሕክምና አማካሪ ናቸው። በኬምብሪጅ አዴንብሩክ ሆስፒታል ውስጥ ነው የሚሠሩት። እርሳቸው እንደሚሉት በዚህ ጊዜ ጾሙ ለሰውነታችን ሌላም በጎ ጎን ይዞ ይመጣል። ለምሳሌ በሌላው ጊዜ በርከታ ያለ ካሎሪ ያላቸው ምግቦችን የምንወስድ ከነበረ ሰውነታችን ሥራዎችን በአግባቡ ለመፈፀም ፈተና ውስጥ ይወድቅ ነበር። ወይም ደግሞ እክል ይገጥመዋል። በጾም ጊዜ ግን ይህ ሁኔታ ይስተካከላል። ""ምክንያቱም የካሎሪ ክምችት ስለማይበዛበት ሰውነታችን ወደ ሌሎች ሥራዎች ትኩረቱን ያደርጋል"" ይላሉ ሐኪሙ። ለዚህም ነው ""ጾም ኢንፌክሽን በመዋጋትና ጤናን በመመለስ አስተዋጽኦ የሚኖረው።"" ከ16ኛ- 30ኛ ያሉ ቀናት በረመዳን ሁለተኛው ምዕራፍ (ከ15ኛው ቀን ጀምሮ) ሰውነት ሙሉ በሙሉ ጾሙን ይላመዳል። በዚህ ጊዜ እነ ደንዳኔ፣ ጉበት፣ ኩላሊት እንዲሁም ቆዳ ሁሉም ራሳቸውን በማጽዳት ሂደት (ዲቶክሲፊኬሽን) ውስጥ ነው የሚሆኑት። ዶክተር ማህሩፍ እንደሚሉት በዚህ ወቅት ጤና ተመልሶ፣ ሰውነታችን የቀድሞውን ጉልበቱን የሚያገኝበትና የማስታወስ አቅምና ትኩረት የማድረግ ብቃት ወደ ቀድሞው ሁኔታ የሚመለስበት ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጉልበት ለማግኘት ወደ ፕሮቲን መሄድ አይኖርበትም። ይህ የሚሆነው ብዙውን ጊዜ ረሀብ ሲሰማንና ሰውነታችን ከጡንቻዎቻችን እየቀሰመ የሚወስደውን ምግብ ማደን ሲጀምር ነው። በዚህ መንገድ የሚቀጥለው ግን ለቀናትና ለሳምንታት በተከታታይ ስንጾም ነው። የረመዳን ጾም የሚጸናው የየዕለቱ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ብቻ ስለሆነ ሰውነታችን ጉልበት ከምግብ እንዲያገኝ የ""ኢፍጣር"" ሰዓት ዕድል ይሰጠዋል። ፈሳሽም እንደልብ ያገኛል። ይህ ጡንቻዎቻችን ውስጥ ያለን ክምችት ለመጠባበቂያነት ያቆይልናል። የተወሰነ ኪሎ እንድንቀንስም ይረዳናል። ይህም ለሰውነት መልካም ነገር ነው። ጾም ጤናን ይጎዳል? የካምብሪጁ አዲንብሩክ ሆስፒታል ሐኪም ዶክተር ማሕሩፍ ምላሻቸው ""እንደሁኔታው"" የሚል ነው። እንደርሳቸው አመለካከት በርከት ያሉ ሁኔታዎች ጾምን ለሰውነታችን ጎጂም ጠቃሚም ሊያደርጉት ይችላሉ። ጾም ለሰውነታችን መልካም የሚሆንበት አንዱ ምክንያት መቼ ምን መብላት እንዳለብን ትኩረት እንድናደርግ ስለሚያስችለን ነው። ሁለተኛው ክብደታችንን መቆጣጠርና፣ የካሎሪ መጠን መወሰን ስለሚያስችል ነው። ለወር ያህል መጾም እምብዛምም የሚያመጣው የጤና እክል ባይኖርም ከዚያ በኋላ ግን ለተከታታይ ጊዜ ያለማቋረጥ መጾም ግን አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ሐኪሙ ሳይጠቁሙ አያልፉም። እንደ ሐኪሙ ማብራሪያ ያለማቋረጥ መጾም በቋሚነት ኪሎ ለመቀነስ አይረዳም። ምክንያቱም ከሆነ ጊዜ በኋላ ሰውነታችን ስብን ወደ ጉልበት መቀየር ያቆምል። ከዚያ ይልቅ ፊቱን ወደ ጡንቻዎቻችን ነው የሚያ���ረው። ይህ ደግሞ ጤናማ አይደለም። ምክንያቱም ሰውነታችን ከሆነ ወቅት በኋላ ""በመራብ ስሜት"" ላይ ስለሚቆይ ነው። ሐኪሙ እንደሚሉት ከረመዳን ውጭ መጾም ቢያስፈልግ እንኳ በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ እያፈራረቁ መጾም በመደዳ ለተከታታይ ቀናት ከመጾም እጅግ የተሻለ ጤናማ ተግባር ነው። ""ረመዳን በአግባቡ ከተጾመና በቂ ፈሳሽ በቀን ውስጥ ማግኘት ከተቻለ፣ ጠቃሚ የጡንቻ ክምችቶች ሳይቃጠል ኪሎ መቀነስ ስለሚያስችል የጤና በረከትም ያስገኛል"" ይላሉ እኚሁ ሐኪም።" https://www.bbc.com/amharic/news-44128047 +business የኤሎን መስክ ኩባንያ የነበረውን አብዛኛውን ቢትኮይን መልሶ ሸጠ ከአንድ ዓመት በፊት በክሪፕቶከረንሲ ላይ ብዙ ኢንቨስት አድርጎ የነበረው የኤሎም መስክ ተቋም ቴስላ፤ ገዝቶት የነበረውን አብዛኛውን ቢትኮይን መልሶ ሸጠ። የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ ከነበረው ቢትኮይን 75 በመቶ የሚሆነውን መሸጡ ተገልጿል። ቴስላ የሸጠው ቢትኮይን እአአ 2021 መጨረሻ ላይ 2 ቢሊዮን ዶላር ያወጣ ነበር። ኩባንያው ዋጋው እየወደቀ ካለው የክሪፕቶካረንሲ ኢንቨስትመንት እራሱን እያራቀ ነው ተብሏል። የቢትኮይን ዋጋ በጥቂት ወራት ውስጥ 50 በመቶ በላይ ዋጋውን አጥቷል። ትልቅ ስም ካላቸው የክሪፕቶከረንሲ ወዳጆች መካከል የቴስላ ኩባንያ ባለቤት ኤሎን መስክ ተጠቃሽ ነው። ቴስላ እአአ 2021 መጀመሪያ ላይ 1.5 ቢሊዮን ዶላር አውጥቶ ቢትኮይን ላይ ኢንቨስት ማድረጉ የክሪፕቶከረንሲ ዋጋን ከፍ አድርጎት ነበር። ቴስላ ለሚሸጣቸው የኤሌክትሪክ መኪኖች ቢትኮይንን በክፍያ መልክ እቀባላለሁ ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ የቢትኮይን ግብይት የሚሳለጥበት ሥርዓት ከፍተኛ ኃይል እንደሚፈልግ በማስታወስ ቴስላ የከባቢ አየርን ለመጠበቅ ሲባል ቢትኮይንን እንደ ክፍያ አማራጭ ማቅረቤን ትቼዋለሁ ብሏል። ቢትኮይን ከስምንት ወራት ገደማ በፊት ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ አንድ ቢትኮይን 70 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ጋር ተጠግቶ ነበር። ዛሬ ላይ ግን የአንድ የቢትኮይን ዋጋ ከ25 ሺህ ዶላር በታች እየተሸጠ ነው። ቴስላ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥቶ የሸመተውን ክሪፕቶከረንሲ መልሶ እንደማይሸጥ የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ኤሎን መስክ በወቅቱ በትዊተር ጉጹ ላይ ጽፎ ነበር። ኩባንያው ገዝቶት የነበረውን ቢትኮይን መልሶ እንደሸጠ ያሳወቀው የሩብ ዓመት ሪፖርቱን ይፋ ባደረገበት ጊዜ ነው። ቴስላ ትርፋማነቴን ከጎዱት ምክንያቶች መካከል አንዱ ቢትኮይን ነው ብሏል። በአውሮፓውያኑ 2022 የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ኩባንያ የገበያ ድርሻ በ40 በመቶ ወርዷል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cev51ryzz9xo +sports የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ፡ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚጠበቁ ኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ተወዳዳሪዎች እነማን ናቸው? አፍሪካውያን ሯጮች በተለይም ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን አትሌቶች በመካከለኛ እና በረጅም ርቀት የሩጫ መስኮች በኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ የበላይ ናቸው። ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታቅዶ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ወደዚህ ዓመት የተሸጋገረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ከዚህ በፊት በውድድሩ ውስጥ ያልነበሩ ስፖርቶችን በማካተት በዚህ ሳምንት መካሄድ ይጀምራል። በዚህም መሰረት አምስት የስፖርት አይነቶች በውድድሩ ውስጥ እንደተካተቱ ታውቋል፤ እነሱም የውሃ ላይ ሸርተቴ (ሰርፊንግ)፣ ተራራ መውጣት (ክላይምቢንግ)፣ ቤዝቦል፣ ስኬት ቦርዲንግ እና ካራቴ ሲሆኑ የተወሰኑ አፍሪካውያን በእነዚህ ዘርፎቹ ይወዳደራሉ። አርብ ሐምሌ 16/2013 ዓ.ም የቶኪዮው ኦሊምፒክ ሲጀምር በተለያዩ ስፖርት ውድድሮች የሚሳተፉ በርካታ አፍሪካውያን ሲኖሩ ኢትዮጵያም በኦሊምፒክ ስሟ በሚጠራባቸው ዘርፎች የሚሳተፉ ስፖርተኞችን ልካለች። ከኢትዮጵያውያን በ��ጨማሪ በርካታ አገራት በተለያዩ ዘርፎች በውድድሩ ይሳተፋሉ ከእነዚህ መካከል በቶኪዮው ኦሊምፒክ ላይ ትኩረት ከተደረገባቸው መካከል ከስኬታማዎቹ እና ከአዲሶቹ መካከል የተወሰኑትን ወድድር ዘርፎቹ እንዲህ አቅርበናል። ሥነ ዘዴ እነዚህ የአፍሪካ ስፖርተኞች የተለያዩ የአህጉሪቱን ክልሎች ይወክላሉ ተብለው ነው የቀረቡት። የተመረጡትም በኦሊምፒክ ተሳትፏቸው፣ ባገኙት ሜዳሊያ ብዛት እና ከሚወዳደሩበት የተለየ የስፖርት አይነት አንጻር ነው። ተሳታፊዎች የአርትኦት ዝግጅት፡ ንኬቺ ኦግቦና፣ ፕሪንሰስ አቡሜሬ እና ሙቶኒ ሙቺሪ። ዲዛይን፡ ኦላኒዬ አዴቢምፔ እና ሚሊሰንት ዋቺራ። የድረ ገጽ ዝግጅት፡ ፒዩሪቲ ቢሪር። ተጨማሪ፡ ሳሊ ሞራሌስ እና ሴሌስቲን ካሮኔይ ምስሎች፡ ጌቲ ኢሜጅስ፣ የዓለም ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን፣ ኤኤፍፒ፣ ናይጄሪያን ኒውስ፣ የናይጄሪያ የውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን፣ መክሰብ ደበሳይ፣ የሞዛምቢክ የውሃ ቀዘፋ ቡድን፣ ጊያና ፋሩክ፣ ኢፒኤ፣ ፕሬስፎከስ/ኒውስ ፒክስ እና ፒኤ፣ ኤርዊዘርየት ትዊተር፣ ብሩስ ቫይን እና ኦሊምፒክ፣ ክላይምብ ዛምቢያ፣ ዲደብሊው እና የሞዛምቢክ ቡድን። https://www.bbc.com/amharic/news-57911750 +business የኬንያና የሶማሊያ እሰጥ አገባ የጫት ንግድን እየጎዳው ነው ተባለ ኬንያ እና ሶማሊያ የገቡበት ዲፕሊማሲያዊ እስጥ አገባ በጫት ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ተነገረ። የሶማሊያ መንግሥት ከኬንያ በሚገባ የጫት ምርት ላይ እግድ መጣሉን ተከትሎ ጫት አምራች ኬንያውያን ገበሬዎች ከፍተኛ ኪሰራ እየገጠማቸው መሆኑ ተግልጿል። ሶማሊያ ከወራት በፊት ከኬንያ በሚገባው የጫት ምርት ላይ እግድ የጣለችው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ምክንያት በማድረግ ነበር። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የኬንያ የጫት ምርት ወደ ሶማሊያ ከመግባቱ በፊት ኬንያ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባታል ትላለች ሶማሊያ። ሶማሊያ የኬንያን የጫት ምርት ወደ አገሬ ከማስገባቴ በፊት ኬንያ በውስጣዊ ጉዳዬ ጣልቃ ከመግባት መቆጠብ ይኖርባታል፣ የሶማሊያን አየር ክልል ማክበር ይኖርባታል፤ እንዲሁም እንደ ስኳር፣ ወተት እና ማር ያሉ የሶማሊያ ምርቶችን እንድትቀበል ጠይቃለች። ኬንያ በበኩሏ በሶማሊያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባቷን እና ፍትሃዊ ከሆነ የንግድ ስምምነት ለመድረስ ዝግጁ መሆኑኗን ትገልጻለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ሶማሊያ ከኢትዮጵያ የጫት ምርት ማስገባቷን ቀጥላለች። ሶማሊያ በአብዛኛው የጫት ምርትን የምታገኘው ከኢትዮጵያና ከኬንያ ነው። በምስሥቃዊ ኬንያ የምትገኘው ሜሩ ጫት በማብቀል ትታወቃለች። ወደ ሶማሊያ ይላክ የነበረው የጫት ምርት ላይ እግድ መጣሉን ተከትሎ ጫት አምራች ገበሬዎች ለችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው። የዘጠኝ ልጆች እናት የሆነችው ሜሪ ናቶንጃ “አረንጓዴው ወርቅ” የምትለውን ጫት ለበርካታ ዓመታት ስታመርት ቆይታለች። የጫት ምርት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሶማሊያ በሚላክበት ወቅት ጥሩ ገቢ ታገኝ እንደነበረም ሜሪ ታስታውሳለች። ከስድስት ዓመታት በፊት ዩናይትድ ኪንግደም ጫት ወደ አገሬ አይገባም ስትል ወሰነች። ባሳለፍነው ዓመት ሕዳር ወር ላይም ሶማሊያ ከኬንያ በሚገባ የጫት ምርት ላይ ገደብ ጣለች። ይህን ጊዜ ሜሪ እሷ እና መሰል በሺዎች የሚቆጠሩ ጫት አምራች ገበሬዎች ሕይወታቸው መፈተኑን ትናገራለች። “ሕይወት ፈተና ሆኖብናል። ገንዘብ በእጃችን የለም። መልበስ እና መብላት ከባድ ሆኖብናል። ልጆቻችን ጾማቸውን እያደሩ ነው። በየሦስት ወሩ ምርት እየሰበሰብን ከአንድ እስከ አምስት ሺህ ዶላር እናገኝ ነበር። አሁን ግን አንድ ዶላር እንኳን ማግኘት አንችልም።” የኬንያ የጫት ነጋዴዎች ማኅበር እንደሚለው ከሆነ የኬንያ ጫት አምራች ገበሬዎች ከዚህ ቀደም እስከ 50 ቶን የሚመዝን ጫት ወደ ሶማሊያ በመላክ እስከ 140 ሺህ ዶላር ድረስ ገቢ ያስገኙ ነበር። አሁን ላይ ገበሬዎች ከምርታቸው እጅግ አነስተኛ የሚሆነውን ለኬንያ ገበያ ካቀረቡ በኋላ ሌላው ፈላጊ ስለሌለው ምርቱ እየተጣለ ነው ይላል ማኅበሩ። ባሳለፍነው ወር በሶማሊያ እና በኬንያ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት ተካሮ ሶማሊያ የኬንያን አምባሳደር አባራ በናይሮቢ የሚገኘውን አምባሳደሯን መጥራቷ ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/news-55212239 +politics በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የያዙት የቡርኪናፋሶ መሪ መፈንቅለ መንግሥት ተደረገባቸው የቡርኪናፋሶ የጦር መኮንኖች በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ሌተናል ኮሎኔል ፖል ሄንሪ ዳምቢባ ከሥልጣን መወገዳቸውን አስታወቁ። የቡድኑ መሪ ሻምበል ኢብራሂም ትራኦሬ እንደተናገሩት የወታደራዊ መሪው ሌትናል ኮሎኔል ዳምቢባ ከመሪነት የተወገዱት፣ በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱትን እስላማዊ አማጺያንን በአግባቡ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ነው። መኮንኑ ጨምረውም ላልተወሰነ ጊዜ ሁሉም የአገሪቱ ድንበሮች ዝግ እንደሚሆኑ እና የትኛውም አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መከልከሉን አሳውቀዋል። አሁን ከሥልጣን መወገዳቸው የተገለጸው ዳምቢባ የሚመሩት ቡድን፣ ባለፈው ዓመት ጥር ላይ ነበር በሕዝብ የተመረጠውን አስተዳደር በመፈንቅለ መንግሥት ገልብጦ ወደ ሥልጣን የመጣው። በወቅቱም ወታደራዊ ቡድኑ መንግሥት የእስላማዊ ቡድኖችን ጥቃት ማስቆም አልቻለም በሚል ነበር መፈንቅለ መንግሥት ማድረጉን ያሳወቀው። ትናንት አርብ ጠዋት ላይ በዋና ከተማዋ ዋጋዱጉ ውስጥ ከባድ ተኩስ ከተሰማ በኋላ ሕዝቡ እንዲረጋጋ ሌተናል ኮሎኔል ዳምቢባ ጠይቀው ነበር። ትናንት ምሽት ላይ ከ20 በላይ የሚሆኑ አብዛኞቹ ፊታቸው የተሸፈነ የታጠቁ ወታደሮች በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የቡድኑ መሪ ናቸው በተባሉት ትራኦሬ የተፈረመ መግለጫ አቅርበዋል። “እየተባባሰ የሚሄድ ችግር በገጠመን ጊዜ ዳምቢባ በደኅንነት ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ በተደጋጋሚ ሞክረናል፤ ነገር ግን የዳምቢባ ተግባር ለማድረግ ካቀድነው ውጪ በመሆኑ አሁን ከሥልጣን እንዲወገድ ወስነናል” ብሏል መግለጫው። ከዚህ በኋላም በመላዋ አገሪቱ ከምሽት 3 ሰዓት እስከ ንጋት 11 የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ የተጣለ ሲሆን፣ ሌተናል ኮሎኔል ዳምቢባ የት እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም። አሜሪካ ቡርኪናፋሶ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ነገር “በእጅጉ እንዳሳሰባት” በመግለጽ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ዜጎቿ እንቅስቃሴያቸውን እንዲቆጥቡ መክራለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ “መረጋጋት እንዲሰፍንና ሁሉም ወገኖች ከየትኛውም ድርጊት እንዲቆጠቡ” ጥሪ አቅርበዋል። የምዕራብ አፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ ማኅበር የሆነው ኤኮዋስ “ሥልጣንን ሕገ መንግሥታዊ ከሆነ መንገድ ውጪ መያዝና በሥልጣን ላይ መቆየትን አጥብቄ እቃወማለሁ” በማለት በቡርኪናፋሶ የተካሄደውን የመንግሥት ግልበጣውን አውግዞታል። አርብ ዕለት አጥቢያ በፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት እና በዋና ከተማዋ ዋጋዱጉ ውስጥ ባለ ጦር ሰፈር አቅራቢያ የተኩስ ድምጽና ፍንዳታ መጀመሪያ ላይ ተሰምቶ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ጠዋት ላይ ወታደሮች አንዳንድ መንገዶችን በመዝጋት ቁልፍ የከተማ ክፍሎች ላይ በመሰማራታቸው ለወትሮ ግርግር የሚበዛበት ከተማ ጭር ብሎ ነበረ። ቀን ላይ የተኩስ ድምጽ የተሰማ ሲሆን የአገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያም ስርጭቱን ለሰዓታት አቋርጦ ቆይቶ ነበር። የመፈንቅለ መንግሥት ወሬ በስፋት በተናፈሰበት አርብ ከሰዓት በኋ�� ፕሬዝዳንቱ ሌ/ኮሎኔል ዳምቢባ፣ በአንዳንድ ወታደሮች ዘንድ የተፈጠረ ስሜታዊነት “ግራ መጋባትን” መፍጠሩን በመግለጽ “ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ድርድር እየተካሄደ ነው” በማለት ሕዝቡ እንዲረጋጋ ጠይቀው ነበር። አሁን ከሥልጣን መባረራቸው የተነገረው ዳምቢባ ባለፈው ዓመት ጥር ፕሬዝዳንት ሮች ካቦሬን እየጨረ የመጣውን የእስላማዊ ታጣቂዎች ጥቃትን መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ነበር በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ያስወገዱት። ነገር ግን ዳምቢባ ወደ ሥልጣን ከመጡም በኋላ በርካታ ዜጎች ደኅንነት እንደማይሰማቸው በመግለጽ በዚህ ሳምንት በተለያዩ የቡርኪናፋሶ ክፍሎች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል። አርብ ከሰዓት በኋላ አንዳንዶች በዋና ከተማዋ ዋጋዱጉ ውስጥ ሌተናል ኮሎኔል ዳምቢባ ከሥልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር። በቡርኪናፋሶ የእስላማዊ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ ከሰባት ዓመት በፊት የጀመረ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ፣ ሁለት ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች ደግሞ ከቤታቸው ለመፈናቀል ተገደዋል። ቡርኪናፋሶ በአውሮፓውያኑ 1960 ነጻ አገር ከሆነች በኋላ እስካሁን ድረስ ስምንት የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥቶች ተካሂዶባታል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c9enzkkp0k8o +business ቻይና የከፋ ድህነትን ከግዛቷ ማስወገዷን አወጀች "የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ አገራቸውን ""በተዓምርዊ"" ሁኔታ ከከፋ ድህነት መውጣቷን ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ መንግሥታቸው ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ100 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ከድህነት ማውጣት መቻሉን ገልፀዋል። ዢ ጂንፒንግ ቤይጂንግ ውስጥ በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት ""የተሟላ ድል"" በማለት ስኬቱን አንቆለጳጵሰው ""በታሪክ ውስጥ የሚመዘገብ"" ብለውታል። ነገር ግን ይህ የፕሬዝዳንቱ ንግግር ያልተዋጠላቸው ባለሙያዎች ድህነት በቻይና እንዴት እንደተለካ ጠይቀዋል። በቻይና የከፋ ድህነት ተብሎ የሚገለፀው በዓመት ገቢው ከ620 ዶላር በታች የሆነ ግለሰብ ነው። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ""የከፋ ድህነትን የማስወገድ ተግባሩ ተጠናቅቋል"" ብለዋል። አሁን ባለው መስፈርት በገጠራማ የአገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ 98.99 ሚሊዮን ድሆች በሙሉ ከድህነት ወጥተዋል፤ 832 በድህነት የተጎዱ አካባቢዎች እና 128 ሺህ መንደሮች ደግሞ ከድህነት ዝርዝር ውስጥ ስማቸው ተፍቋል"" ሲሉ አክለዋል። ዢ ጂንፒንግ ወደ ስልጣን ከመጡበት 2012 (እኤአ) ጀምሮ በገጠር ያለን ድህነትን ማስወገድ ቁልፍ ተግባራቸው አድርገው ሲሰሩ ነበር። ቻይና ባለፈው ዓመት የመጨረሻዎቹን ድሃ የተሰኙ አካባቢዎችን ከድህነት ዝርዝር ውስጥ ስማቸውን አንስታለች። በዚህም የተነሳ ቻይና በ2020 የከፋ ድህነትን ማስወገድ ችላለች። ዛሬ፣ ሐሙስ በተካሄደ ክብረ በዓል ላይ ዢ ጂንፒንግ ድህነትን በመዋጋት ተግባር ውስጥ ለተሳተፉ አካላት ሜዳሊያ ሸልመዋል። ነገር ግን ባለሙያዎች ቻይና ድህነትን የምትበይንበትን መስፈርት ዝቅ አድርጋ አስቀምጣለች፤ አሁንም በድሃ አካባቢዎች ተጨማሪ ሃብት ማፍሰስ ያስፈልጋል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በቻይና አንድ ሰው የከፋ ድህነት ውስጥ ይኖራል ለመባል የቀን ገቢው 1.69 ዶላር መሆን አለበት። እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የዓለም ባንክ ግን 1.90 ዶላር የሚያገኝን ሰው የከፋ ድህነት ውስጥ ይገኛል ሲል ይበይናል። በቻይና አሁንም በዜጎች መካከል የሰፋ የሃብት ልዩነት ይታያል።" https://www.bbc.com/amharic/56201582 +sports የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባለድሎች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን አመርቂ ድል ያስመዘገቡት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ደማቅ አቀባበል ተደረገላ���ው። በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያ ከአዘጋጇ አሜሪካ በመከተል የሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በአጠቃላይ 10 ሜዳሊያዎችን አግኝተዋል። እነዚህም አራት ወርቅ፣ አራት ብር እና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች ናቸው። በአሜሪካዋ ኦሪጎን ግዛት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተገኘው የሜዳሊያ ብዛት በታሪክ የላቀ ውጤት የተመዘገበበት ነው ተብሏል። ረቡዕ ምሽት አዲስ አበባ የገቡት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላት ሐሙስ ጠዋት አዲስ አበባ ውስጥ ደማቅ የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ደስተቻቸውን ለመግለጽ ወደ ዋና ዋና መንገዶች የወጡ ሲሆን፣ አትሌቶቹም በከፍት መኪናዎች ላይ ሆነው ታይተዋል። ቡድኑ ወደ ታላቁ ቤተ-መንግሥት በማቅናት በአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ እና በሌሎችም ታዋቂ ግለሰቦች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ታላቅ ድልን ያስመዘገበውን ቡድን አባል የነበረችው እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆነችው አትሌት ደራርቱ ቱሉ ለሰጠችው አመራርም አድናቆት ተችሯታል። ደራርቱ በአትሌቶቹ ውጤት እንደኮራች በመግለጽ፤ በቀጣዩ ውድድር ከባድ ፉክክር እንደሚጠብቃቸው አውቀው እንዲዘጋጁ አትሌቶቹን አሳስባለች። ጨምራም ጦርነት ከተካሄደበት የትግራይ ክልል የመጡ አትሌቶች ቤተሰቦቻቸውን ማግኘት እንዲችሉ የፌደራል መንግሥት ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ጠይቃለች። “ከትግራይ የመጡት አትሌቶች አስካሁን ቤተሰቦቻቸውን የማግኘት ዕድል አላገኙም” ስትል በቤተ-መንግሥት ውስጥ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ተናግራለች። በውድድሩ ላይ ሦስት ወርቅ ሜዳሊያ ያመጡት ለተሰንበት ግደይ፣ ጎተይቶም ገብረሥላሴ እና ጉዳፍ ፀጋይ ከትግራይ ክልል የመጡ አትሌቶች ናቸው። በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ ክልል የግንኙነት መስመሮች ከተቋረጡ ከአንድ ዓመት በላይ እንደሆነው ይታወቃል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሜዳሊያ ላስገኙ አትሌቶች ከ700ሺህ እስከ 2.5 ሚሊዮን ብር ድረስ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል። በ5 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ እና በ1 ሺህ 500 ሜትር የብር ሜዳሊያ ያስገኘቸው አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ የ2.5 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆናለች። አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ በማስገኘቷ 1.5 ሚሊየን ብር እንዲሁም በ5 ሺህ ሜትር ላበረከተችው ውጤታማ የቡድን ሥራ 500 ሺህ ብር በድምሩ የ2 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆናለች። በማራቶን ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ላመጡት አትሌት ጎተይቶም ገብረ ሥላሴ እና ታምራት ቶላ እያንዳንዳቸው የ1 ሚሊዮን 750 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል። በወንዶች ማራቶን የብር ሜዳሊያ ያስገኘው ሞስነት ገረመው፣ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ ላስገኘቸው ወርቅውሃ ጌታቸው እንዲሁም በወንዶች 3 ሺህ መሰናክል የብር ሜዳሊያ ላስገኘው ለሜቻ ግርማ ለእያንዳንዳቸው የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በ5ሺህ ሜትር እና በ3ሺህ ሜትር መሰናክል የነሐስ ሜዳሊያ ያስገኙት አትሌት ዳዊት ስዩም እና መቅደስ አበበ የ700 ሺህ ብር ሽልማት ተሰጥቷል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c2934kd1kw7o +sports በሙስና ተፈርዶባቸው የነበሩት የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ኃላፊ አረፉ "የቀድሞ የዓለም አትሌቲክስ ኃላፊ ላሚን ዲያክ በ88 ዓመታቸው ሴኔጋል ውስጥ ማረፋቸው ተሰማ። ባለፈው ዓመት በሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት ዲያክ ከአውሮፓውያኑ 1999 እስከ 2015 የዓለም አትሌቲክስ (የቀድሞው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር-አይኤኤፍ) ፕሬዝዳንት ነበሩ። በአውሮፓውያኑ 2020 ከሩሲያ አበ��ታች መድኃኒት ቅሌት ጋር ተያይዞ በሙስና እና በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል። የፈረንሳይ ፍርድ ቤት በአራት ዓመት እስራት እንዲቀጡ የበየነባቸው ሲሆን ሁለት ዓመቱ ተቀንሶላቸዋል። ነገር ግን ሳይታሰሩ ወደ ሴኔጋል ተመልሰው እንዲሄዱ ተፈቅዶላቸው በቁም እስረኛነት ቆይተዋል። በኋላም በዋስ ተለቀዋል። ልጃቸው ፓፓ ማሳታ ዲያክ ""በተፈጥሯዊ ምክንያት ቤት ውስጥ ህይወቱ አልፏል"" በማለት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በዛሬው ዕለት እንደሚፈጸም ተነግሯል። ቀደም ሲል ዲያክ ጠበቆች በጤና እጦት ላይ እንዳሉ እና ከታሰሩ እንደሚሞቱ ተናግረው ነበር። የቀድሞው ኃላፊ ጥፋተኛ ቢባሉም በሴኔጋል ድጋፍ አላቸው። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ዲያክ ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ያስቻለውን 565 ሺህ ዶላር ዋስትና የከፈሉት ጃራፍ የተባለው የሴኔጋሉ እግር ኳስ ክለብ ባለቤት ቼክ ሴክ ናቸው። ሴክ የቀድሞ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ሲሆኑ አሁን በንግድ ሥራ ይተዳደራሉ። ""ጥሩ ሰውና ታላቅ መሪ ነበር። ወደ አገሩ እንዲመለስ እንፈልጋለን። 565 ሺህ ዶላር ለመሰብሰብ አንድ ወር ፈጅቶብናል"" ሲሉ ከዲያክ ህልፈት በኋላ ተናግረዋል። ""ህይወቱ ሌላ ቦታ እንዲያልፍ አስበን አለማወቃችን በጣም አስፈላጊ ነበር።"" ""ተወዳጅ የአገሩ ልጅ፣ ሁለንተናዊ አስደናቂ ዜጋ"" ሲሉ ሴክ ቀደም ሲል ዲያክን ገልጸዋቸው ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-59521751 +politics የትራምፕን የዋይት ሐውስ ሰነዶች መርማሪዎች እንዲመለከቱ ፍርድ ቤት ፈቀደ "አንድ የአሜሪካ ዳኛ የካፒቶል አመጽን ከትትሎ ምርመራ የሚያደርገው የኮንግረስ ኮሚቴ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዋይት ሐውስ ሰነዶችን እንዲመለከት ፈቃድ ሰጡ። ትራምፕ ሰዶቹን መርማሪ ኮሚቴው እንዳይመለከተው ያስችለኛል ያሉትን ሕጋዊ መብት አንስተው ተከራክረው ነበር። ምርመራውን የሚያካሂደው ኮሚቴ ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ መንግሥት ምክር ቤት ህንጻ (ካፒቶል ሂል) ላይ ባለፈው ዓመት ጥር ወር የተካሄደውን አመጽ ቀደመው ያውቁ ነበር የሚለውን ለመለየት ለሚያደርገው ጥረት መልስ ለማግኘት ነው። የአሜሪካ ኮንግረስ በምርጫ ያሸነፉትን የጆ ባይደንን ፕሬዝደንትነት ለማጽደቅ በተቀመጠበት ወቅት የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሂል ላይ ወረራ መፈጸማቸው ይታወሳል። ትራምፕ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርቡ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚል መከራከሪያ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ምርመራ እያካሄደ የሚገኘው ኮሚቴ በኮንግረሱ ላይ በትራምፕ ደጋፊዎች ጥቃት ከመሰንዘሩ በፊት የዋይት ሐውስ የስልክ ልውውጦች እና ትራምፕ ከማን ጋር ተገናኝተዋል ነበር የሚለውን ለማወቅ ነው ስነዶቹን የሚመለከተው። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ደግሞ ሰነዶቹ ለማንም ይፋ እንዳይሆኑ ሲቃወሙ ነበር። ነገር ግን ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኛ ታንያ ቹትካን ማክሰኞ ዕለት የዋይት ሐውስ ሰነዶችን የሚጠብቀው ብሔራዊ የማህደር መስሪያ ቤት ትብበር እንዲያደርግና ሰነዶቹን ለመርማሪ ኮሚቴው እንዲሰጥ አዝዘዋል። ዳኛ ታንያ በቀድሞው ፕሬዝዳነት ባራክ ኦባማ የተሾሙ ሲሆን የዶናልድ ትራምፕን ጥያቄም ውድቅ አድርገዋል። ""ፕሬዝዳንቶች እኮ ንጉሥ አይደሉም። ቅሬታ ያቀረቡት ግለሰብም አሁን ላይ ፕሬዝዳንት አይደሉም"" ብለዋል ዳኛዋ ታንያ ባስተላለፉት ባለ 39 ገጽ የውሳኔ ሀሳብ። ነገር ግን ይህ ውሳኔ ወደ ፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንደሚሄድ ይጠበቃል። እስካሁን ድረስ 16 የዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ረዳቶች ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዘዋል። ከእነዚህም መካከል የቀድሞ የዋይት ሐውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ኬይሊ ማክናኒ፣ የትራምፕ ���ፍተኛ አማካሪ የነበሩት ስቴፈን ሚለር፣ የቀድሞ የቅስቀሳ ኃላፊው ቢል ስቴፈን፣ የቀድሞ የዋይት ሐውስ ከፍተኛ ኃላፊ ማርክ ሚዶውስ እና የቀድሞ የፕሬዝዳንቱ የደኅንነት አማካሪ ማይክል ፍሊን ይገኙበታል። ከካፒቶል ሂል ጥቃት ጋር ተያይዞ እስካሁን ድረስ 670 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በወቅቱም አንድ የካፒቶል ሒል የፖሊስ አባልን ጨምሮ አምስት ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59230353 +sports ጉዳፍ ጸጋይ በ5ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆነች በአሜሪካዋ ኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ ባለቤት ሆናለች። ጉዳፍ በዚህ ድሏ ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ያገኘቻቸውን የወርቅ ቁጥሮች አራት ማድረስ ችላለች። ከፍተኛ ፉክክር በነበረበት ውድድር ጉዳፍ 14፡46: 29 በመግባት ነው ባለክብር የሆነችው። ኬንያዊቷ ቢትሪስ ቺቤት ሁለተኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ ባለቤት ለመሆን በቅታለች። ሌላኛው ኢትዮጵያዊት ዳዊት ስዩም ሦስተኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ለድሉ መሳካት ትልቅ ድርሻ የነበራት ለተሰንበት ግደይ አምስተኛ በመውጣት አጠናቃለች። ለተሰንበት በዚሁ የኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቷ ይታወሳል። ከእኩለ ሌሊት በኋላ በተካሄደው የ5ሺህ ሜትር ውድድር የመጨረሻዎቹ 100 ሜትሮች ድረስ አሸናፊዋን መለየት አስቸጋሪ የሆነበት ነበር። በ1500 ሜትር ልምድ ያላት ጉዳፍ ትንቅንቁን የኋላ ኋላ በበላይነት አጠናቃለች። ጉዳፍ ከወራት በፊት በ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ክብረ ወሰኑን መስበሯ ይታወሳል። በኦሪገኑ ውድድርም ከቀናት በፊት በዚሁ ዘርፍ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ ባለቤት ለመሆን በቅታለች። ጉዳፍ ከውድድሩ በኋላ “በመጎዳቴ ምክንያት የቶክዮው ኦሎምፒክ በጣም ከባዱ ጊዜ ነበር” ማለቷን ወርልድ አትሌቲክስ አስነብቧል። “ለ1500 ሜትር በደንብ ስዘጋጅ ቆይቻለሁ። ይህም በጨረሻዎቹ ሜትሮች ላይ በፍጥነት እንድሄድ ጠቅሞኛል። ሲፋን ትልቅ እና እሷም የ1500 ሜትር አትሌት መሆኗን አውቃለሁ። ስለዚህ እሷም ፍጥነቱ አላት። እሷ ስትቀደም እኔ ፍጥነቴን በመጨመር ሜዳሊያውን ለማግኘት በቅቻለሁ” ብላለች። ዳዊት በበኩሏ ከዓመታት የጉዳት ቆይታ በኋላ ነው ወደ ድል የተመሰለችው። “የሜዳሊያ አሸናፊ ሆኜ መድረክ ላይ ለመውጣት ተስፋ አድርጌያለሁ” ትላለች ዳዊት። “በዚህ ዘርፍ የሜዳሊያ ባለቤት ለመሆን አልሜያለሁ። ለአምስት ዓመታት ከጉዳት ጋር ስታገል ቆይቻለሁ። ስለዚህ ይህ ድል ለእኔ ልዩ ነው” ብላለቸ። ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በእስካሁን ቆይታ አራት የወርቅ፣ አራት የብር እና ሁለት የነሃስ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። በኦሪጎን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል። ኢትዮጵያ ሜዳሊያ የምትጠበቅብትን የወንዶች 5000 ሜትርን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎችም ቀሪ ውድድሮችን ታከናውናለች። https://www.bbc.com/amharic/articles/c1vg3ew6y76o +sports ኬንያዊው አትሌት ኪፕቾጌ የዓመቱ የዓለም የስፖርት ኮከብ ሆኖ ተመረጠ የማራቶኑ ጀግና ኤሉድ ኪፕቾጌ ቢቢሲ በሚያደርገው ምርጫ የአመቱ የዓለም የስፖርት ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በማጠናቀቅ ታሪክ የሰራ የመጀመሪያው ሯጭ መሆን ችሏል። የ35 አመቱ ኬንያዊ በኦስትሪያዋ መዲና ቪየና በተደረገው የማራቶን ወይም የ42.2 ኪሎሜትር ርቀትን በ1 ሰዓት ከ 59 ደቂቃ ከ 40 ሰኮንዶች በመግባት አለምን አስደምሟል። • ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች አጠናቀቀ • ኬኒያዊው አትሌት የዓለምን የማራቶን ክብረ ወሰን ሰበረ • ኪፕቾጌ ማራ���ንን ከ2 ሰዓት በታች ለመሮጥ ዝግጅቱን አጠናቀቀ ይህንንም ውድድር ከማሸነፉ ከስድስት ወራት በፊት የለንደንን ማራቶን ለአራተኛ ጊዜ አሸንፏል። ከሶስት ዓመት በፊት ሪዮ በተደረገው የኦሎምፒክ ውድድር አሸንፎ የነበረው ኪፕቾጌ፤ ለንደን ላይ ባደረገው ውድድርም በሃያ ስምንት ሰኮንዶች የሪዮ ሰአቱን አሻሽሎታል። ለህዝብ ክፍት በነበረው በዚህ የኮከብነት ምርጫም አሜሪካዊቷን የጂምናዝየም ስፖርተኛ ሲሞን ቢሌስ፣ የደቡብ አፍሪካ የራግቢ ተጫዋቹን ሲያ ኮሊሲ፣ የክሪኬት ተጫዋቹን ስቲቭ ስሚዝ፣ አሜሪካዊው ጎልፍ ተጫዋች ታይገር ውድስና አሜሪካዊቷ እግር ኳሰኛ ሜጋን ራፒኖን በመርታት ኪፕቾጌ አሸንፏል። በባለፈው አመት ጣልያናዊው የጎልፍ ተጫዋች ፍራንቸስኮ ሞሊናሪ ማሸነፉ ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/news-50798738 +health ኮሮናቫይረስ፡ ሳይታወቅ ለዓመታት በሌሊት ወፎች ውስጥ ነበር የሰው ልጆች ላይ ጉዳት እያስከተለ ያለው ኮሮናቫይረስ ለበርካታ ዓመታት ሳይታወቅ በሌሊት ወፎች ሰውነት ውስጥ እንደነበር ጥናቶች ያሳያሉ። ኮቪድ-19ን የሚያስከትለው ቫይረስ በሌሊት ወፎች ላይ ከታየ ከ40 እስከ 70 ዓመታት አልፈዋል። ወደ ሰው ልጆች ከተሻረገ ጥቂት ጊዜው መሆኑን ሳይንቲስቶች ይናገራሉ። መረጃው፤ ኮቪድ-19 በሰው የተሠራና ከቤተ ሙከራ አምልጦ የወጣ ነው የሚለው የሴራ ትንተና ላይ እውነትን የተመረኮዘ ስለመሆኑ ጥያቄ ያጭራል። ፕ/ር ዴቪድ ሮበርትሰን በግላስጎው ዩኒቨርስቲ ነው የሚሠሩት። የሳቸው ጥናት ‘ኔቸር ማይክሮባዮሎጂ’ በተባለ መጽሔት ላይ ታትሟል። ፕ/ር ዴቪድ እንደሚናገሩት፤ ሳርስ-ኮቭ-2 ከሌሊት ወፎች ቫይረስ ጋር የዘረ መል ተመሳሳይነት ቢኖረውም፤ አንዳቸው ከሌላቸው የበርካታ ዓሠርታት ልዩነት አላቸው። “እነዚህ ሰውን ሊይዙ የሚችሉ ቫይረሶች ዘለግ ላለ ጊዜ እንደኖሩ ጥናቱ ያሳያል” ይላሉ። ቫይረሱ መቼ እና እንዴት ወደ ሰው ልጆች እንደተሸጋገረ መታወቅ እንዳለበት ተመራማሪው ያስረዳሉ። “በሌሊት ወፎች ላይ ቫይረሱ እንዳለ ካወቅን ለመቆጣጠር መሞከር አለብን።” ለወደፊቱ ወረርሽኞች እንዳይቀሰቀሱ፤ ሰዎች የሚገጥሟቸው ህመሞች የቅርብ ክትትል እንደሚያሻቸው ጥናቱ ያሳያል። ከዱር የሌሊት ወፎች ላይ ናሙና ተወስዶ ምርመራ መካሄድም አለበት። ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት፤ “እነዚህ ቫይረሶች ዓመታት አስቆጥረዋል ማለት ሰዎችን ጨምሮ ሌላም መኖሪያቸው የሚያደርጉት አካል አግኝተዋል ማለት ነው።” በጥናቱ፤ የሳርስ-ኮቭ-2 ዘረ መል ተቀራራቢው ከሆኑ የሌሊት ወፍ ላይ ያሉ ቫይረሶች ማለትም አርኤቲጂ13 እንዲሁም ከሌሎች ጋር ንጽጽር ተደርጓል። ሁለቱ አይነቶች በምን ወቅት ላይ ተመሳሳይ የዘር ግንድ እንደነበራቸውም ተጠንቷል። በዚህ መሠረትም ሁሉቱ ዓይነቶች ከአስርታት በፊት በተለያየ የእድገት ሁኔታ ማለፋቸው ተደርሶበታል። በሪዲንግ ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ፕ/ር ማርክ ፓጌል በጥናቱ ባይሳተፉም፤ ሰዎችን ሊጎዱ የሚችሉ ኮሮናቫይረሶች ሳይታወቁ በሌሊት ወፎች ላይ ከ40 እስከ 70 ዓመታት መኖራቸውን ምርምሩ እንደሚያሳይ ይስማማሉ። “ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ በሽታዎች ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ ጥናቱ ያሳያል። እንስሳት ውስጥ በጥገኝነት የሚኖሩና ለሰው ልጅ ጎጂ የሆኑ፤ እስካሁን ድረስ ግን ያልታወቁ ሌሎች ቫይረሶችም ሊኖሩ ይችላሉ።” ቫይረሶቹ ወደ ሌሎች የዱር እንስሳት ተላልፈው ሊሆን ይችላል። በተለይም በሕገ ወጥ የእንስሳት ዝውውር ሳቢያ እርስ በእርስ የተቀራረቡ እንስሳት የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። እስካሁን ድረስ ያለው መረጃ እንደሚያሳየው ግን የቫይረስ ዋነኛ ተሸካሚ የሆኑት የሌሊት ወፎች ናቸው። ከዚህ ቀደም የሰሠሩ ጥናቶች ፓንጎሎኖች ��ሳርስ-ኮቭ-2 ዝግመተ ለውጥ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ያሳያል። አሁን ግን ይህ ትክክል እንዳልሆነ ተደርሶበታል። ቻይናን መዳረሻው ባደረገ ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ ወቅት ፓንጎሊኖች ከሌሎች እንስሳት ጋር ንክኪ ነበራቸው። ስለዚህም ፓንጎሊኖች ለቫይረሱ የተጋለጡት በቅርቡ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-53600806 +business የአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ‘የማይቀመስ’ የሆነው ለምንድን ነው? ወደፊትስ ይቀንስ ይሆን? በቅርቡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ መዲና፣ ናይሮቢ የበረሩ ሦስት ተሳፋሪዎች በነፍስ ወከፍ 28 ሺህ ብር ከፍለናል ይላሉ። ሦስቱ ጓደኛሞች በአማካኝ 1፡45 ሰዓት ለሚወስደው የኢኮኖሚ ክፍል በረራ ደርሶ መልስ በድምሩ 84 ሺህ ብር ከፍለዋል። እርግጥ ነው የአውሮፕላን በረራ ዋጋ በተሳፋሪ የበረራ ቀን እና ሰዓት እንዲሁም ‘በኢኮኖሚ እና በቢዝነስ ክፍሎች’ ምርጫ ይለያያል። ቢሆንም በተለይ ከኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ በአህጉረ አፍሪካ የአውሮፕላን በረራ አቅሙ ያላቸው የሚጓዙበት እየሆነ ነው። ስሙን እንድንጠቅስ ያልፈለገ አንድ ኢትዮጵያዊ፣ ከናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ የበረራ ዋጋ የማይቀመስ በመሆኑ “በሞያሌ በኩል በባስ አገር ቤት ደርሼ መጥቻለሁ” ይላል። የኬንያ አየር መንገድ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ለበረራ ብዙ በማስከፈል ከአፍሪካ ቁንጮው ሆኖ ብቅ ብሏል። አየር መንገዱ አፍሪካ ውስጥ አሉ ከሚባሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ እንዲሁም ከፈረንሳዩ ኤር ፍራንስ የላቀ ገንዘብ ለቲኬት ያስከፍላል ተብሏል። ኬኪው (KQ) በተሰኘ ምሕፃረ ቃል የሚታወቀው የጎረቤት አገር ኬንያ አየር መንገድ ውድ ነው የተባለው ወደ 24 የአፍሪካ አገራት ሲበር የሚያስከፍለው ዋጋ ተጠንቶ ነው። አፍሪካን ኮምፒቲሽን ፎረም የተሰኘው ድረ ገጽ የኬንያ አየር መንገድ ለአገር ውስጥ እና ለዓለም አቀፍ በረራ ከፍተኛ ገንዘብ ይጠይቃል ሲል ፅፏል። ነገር ግን የደቡብ አፍሪካው እና የኢትዮጵያ አየር መንገድም እንዲሁ እጅግ ብዙ ለቲኬት ከሚያስከፍሉ የአፍሪካ አየር መንገዶች መካከል ናቸው። የኮቪድ ወረርሽኝ እና የዩክሬንን ጦርነት ተከትሎ የአውሮፕላን በረራ ዋጋ ጭማሪ ቢያሳይም በተለይ የአፍሪካ በረራዎች እጅግ መወደዳቸው ብዙዎችን ያነጋገረ ጉዳይ ሆኗል። በቅርቡ በዩናይትድ ኪንግደሙ ብሪቲሽ ኤርዌይስ ወደ ናይሮቢ ደርሶ መልስ የቆረጠው ዙሪች 800 ፓውንድ ገደማ እንደከፈለ ይናገራል። በተቃራኒው በቅርቡ የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫን ለመታደም ወደ ኢትዮጵያ ለማቅናት ያቀደችው ሚሼል የቲኬት ዋጋው ከ800 ዶላር በላይ እንደሆነባት በትዊተር ገጿ ፅፋለች። ይህ አሁን ባለው የምንዛሪ ዋጋ 97 ሺህ ሽልንግ ገደማ ነው። ከኮቪድ ወረርሽኝ በፊት ከናይሮቢ አዲስ አበባ ደርሶ መልስ በኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን በኬንያ ኤርዌይስ ለመብረር ከ19 ሺህ እስከ 25 ሺህ ሽልንግ ይጠይቅ ነበር። አሁን ግን ከ80 ሺህ ሽልንግ በላይ ይጠይቃል። ይህ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው? የነዳጅ ዋጋ ወይስ ሌላ ተጨማሪ ምክንያት? የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና የኦፕሬሽን ኦፊሰር [ሲኦኦ] ለማ ያደቻ፣ ለዚህ አንዱ ምክንያት የሌሎች አገራት መንግሥታት የሚጡልብን “ግብር” ነው ይላሉ። አቶ ለማ እንደሚሉት የአየር በረራ ዋጋ የሚተመነው በሚያስወጣው ወጪ ላይ ተመርኩዞ ነው። ለዚህም አየር መንገዳቸው ወደ ተለያዩ አገራት ሲጓዝ የሚያወጣውን ወጪ አስልቶ እንዲሁም አየር መንገዱ የሚያቀርበውን አገልግሎት ከግምት አስገብቶ ዋጋ ይተምናል። ይህንን በምሳሌ ሲያብራሩ አንድ ሰው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀጥታ ከደቡብ አፍሪካ ሲመጣና ከደቡብ አፍሪካ ተነስቶ ናይሮቢ አርፎ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣ ምቾቱ አንድ አይደለም ይላሉ። “አውሮፕላኑ ቀጥታ ከመምጣት ይልቅ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ እያቆራረጠ የሚጓዝ ከሆነ ይህ አንድን መንገደኛ ምቾት ይነሳል። ስለዚህ ቀጥታ ሲመጣ ዋጋው ይጨምራል፤ እያቆራረጠ ሲመጣ ደግሞ ዋጋው ሊቀንስ ይችላል” ይላሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብዛኛውን ጊዜ ከአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና የአሜሪካ አገራት ቀጥታ በረራ እንደሚያደርግ የሚናገሩት ኃላፊው፣ ይህ ማለት ደንበኞች ሳይጉላሉ በምቾት ይመጣሉ ማለት ነው። ስለዚህ በገበያው መሠረት ላቅ ያለ ክፍያ ሊከፍሉ ይችላሉ ሲሉ ያስረዳሉ። ኦፕሬሽን ኦፊሰሩ ሌላው ለበረራ ቲኬት ዋጋ መወደድ እንደ ምክንያት የሚያነሱት በዓለም አቀፍ ገበያ የነዳጅ ዋጋ መናሩን ነው። አልፎም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ የአየር ማረፊያ የአገልግሎት ክፍያ ከፍ ማለቱን ኃላፊው ይጠቅሳሉ። አቶ ለማ፤ በአየር መንገዶች አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች መንገደኛ ከመመዝገብ ጀምሮ ለማሳፈር፣ ምግብ ለማቅረብ፣ ነዳጅ ለመሙላት፣ ለፅዳት ሥራ እና ለሌሎችም አገልግሎቶች የሚያስከፍሉት ዋጋ መጨመሩ ለቲኬት ዋጋ መናር ምክንያት ነው ይላሉ። “እነዚህ ወጪዎች እየጨመሩ በሚመጡበት ጊዜ እኛ ደግሞ የሚያካክስ ክፍያ እንጠይቃለን።” የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራሱን የሚያስተዳድረው ራሱ በሚያገኘው ገንዘብ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ለማ፤ “ሠርቶ ከሚያገኘው ገቢ ደግሞ ወጪውን መሸፈን ይኖርበታል” ይላሉ። በፈረንጆቹ 2022 የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው የቲኬት ዋጋ ጭማሪ ያሳየው በተለያዩ ምክንያቶች ነው ሲሉ የኬንያ ኤርዌይስ ኃላፊ ለቢቢሲ ይናገራሉ። በኢትዮጵያ የኬንያ ኤርዌይስ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ፌሊክስ ምዋንጋንጊ የቲኬት ዋጋ ገበያ ላይ ባለው ፍላጎትና አቅርቦት ላይ የተወሰነ ነው ይላሉ። ፌሊክስ እንደሚሉት ከኮቪድ በፊት ኢንዱስትሪው ድጎማ ያገኝ ነበር። ነገር ግን በድኅረ-ኮቪድ ይህ ድጎማ እምብዛም አይደለም። ኃላፊው እንደሚገልጹት በተለይ በአህጉረ አፍሪካ ያለው አቅርቦት በተወሰኑ አየር መንገዶች ላይ የተመረኮዘ በመሆኑ የቲኬት ዋጋው ላይ ለውጥ ታይቷል። “አፍሪካ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አየር መንገዶች ጥቂት ናቸው። ይህ ማለት አቅርቦቱ የተወሰነ ነው ማለት ነው። ይህ በተዘዋዋሪ የበረራ ዋጋ እንዲወደድ ያደርጋል።” ኃላፊው ከኮቪድ በኋላ የፍላጎት ጭማሪ መታየቱን ጠቅሰው፣ ይህን ተከትሎ የቲኬት ዋጋ ከፍ ማለቱን ይናገራሉ። አክለው ደንበኞች አፍሪካ ውስጥ ለሚደረግ በረራ ከየትኛው የዓለም ክፍል ሆነው ቲኬት ቢቆርጡ ዋጋው ተመሳሳይ ነው ይላሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገዱ ኃላፊ አንደኛው የድርጅቱ ዓላማ “ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ደንበኞችንና ኢትዮጵያውያንን ማገልገል ነው” ካሉ በኋላ “በአጠቃላይ ኦፕሬሽኑ ትርፋማ ሲሆን በአንዳንድ የበረራ መስመሮች በኪሳራም ይሁን ከሌሎች መስመሮች በሚገኘው ትርፍ እንሠራለን” ይላሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወዳዳሪዎች አንዳንድ ጊዜ ዝቅተኛ ዋጋ ሊያቀርቡ እንደሚችሉ የሚያምኑት ኃላፊው “ብሔራዊ አየር መንገድ ከሆነ በአገሩ መንግሥት ሊደገፍ ይችላል።” “እንደምታውቁት በኮቪድ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድና አንድ ሌላ ድርጅት ናቸው ከኪሳራ ማገገሚያ ገንዘብ [bailout] ያልተቀበሉት። እኛ ወጨያችንና ገቢያችንን በደንብ አመዛዝነን ነው የምንሠራው።” ኃላፊው፤ የቲኬት ዋጋ ቲኬቱ በሚቆርጥበት ወቅት ላይ የተመሠረት ሊሆን እንደሚችልም ይገልጣሉ። ለምሳሌ አንድ ደንበኛ ቲኬቱን የገዛው በረራው ከሚደረግበት ጊዜ ከስድስት ወራት በፊት ከሆነ ዋጋው የሚቀንሰው አየር መንገዱ ብሩን ተቀብሎ ስለሚሠራበት ይህ ታሳቢ ተደርጎ ቅናሽ እንደሚኖረው ያብራራሉ። በተቃራኒው ቲኬቱ የተቆረጠው ለበረራው ቅርብ በሆነ ጊዜ ከሆነ ‘ቢድ ፕራይሲንግ’ በተባለው መንገድ እንደሚሸጥ ይጠቅሳሉ። ‘ቢድ ፕራይሲንግ’ ምን እንደሆነ የሚያብራሩት አቶ ለማ፤ ይህ ማለት ደንበኞች በቀሩት ወንበሮች ይወዳደሩ እና የተሻለ ዋጋ የከፈለ ያገኘዋል ማለት ነው። ፌሊክስ፤ ልክ እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር ለማ ያደቻ ሁሉ ደንበኞች የጉዞ ቀን ሲቃረብ ቲኬት የሚቆርጡ ከሆነ ዋጋው ከፍ ሊልባቸው እንደሚችል ይገልጻሉ። ማኔጀሩ አክለው ‘አይታክስ’ [አይ ገቨርንመንት] ታክስ ተብሎ የሚታወቀው የግብር ዓይነት ለቲኬት ዋጋ መወደድ አስተዋፅዖ እንዳለው ለቢቢሲ ይናገራሉ። ይህ ማለት አየር መንገዶች ለሚያርፉበት አገር መንግሥት የሚከፍሉት የአገልግሎት ክፍያ ነው። “ለምሳሌ ከናይሮቢ ወደ ኢንቴቤ [ኡጋንዳ] ሲኬድ ለመንግሥት የሚከፈል የመነሻ ክፍያ አለ። ይህ የበረራ ዋጋ ላይ ለውጥ ያመጣል። አንዳንድ ጊዜ የመንግሥት ግብር ከቲኬቱ ዋጋ አስከ 30 በመቶ ይደርሳል።” እየተገባደደ ያለው የፈረንጆቹ 2022 በአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ በጉዞ መሠረዝ፣ በዕቃዎች መጥፋት እና በበረራዎች መዘግየት ምክንያት ደንበኞች እጅግ የተጉላሉበት ዓመት ሆኖ ተመዝግቧል። በርካታ አየር መንገዶች ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት የነበራቸውን ገቢ እና የበረራ ቁጥር ለማሳደግ በሚል በወሰዱት እርምጃ ኢንዱስትሪው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል። ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ማኅበር [IATA] ዋና ሥራ አስኪያጅ ዊሊ ዌልሽ የነዳጅ ዋጋ በመጨሩ ምክንያት የበረራ ቲኬት ዋጋ “ያለጥርጥር ይጨምራል” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ማኅበሩ እንደሚለው በፈረንጆቹ 2021 የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከስሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር እንደጠቀሱት ድጎማ ካለገኙ ጥቂት አየር መንገዶች መካከል የሆነ አየር መንገደዱ [ኢቲ]፣ በወረርሽኙ ወቅት በጭነት አውሮፕላኖች ምክንያት ትርፋማ መሆኑን አውጆ ነበር። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአፍሪካ ቁንጮ የሚባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ ሌሎች ዋና ዋና አየር መንገዶች የቲኬት ዋጋቸው የማይቀመስ ሆኗል። የበርካታ ደንበኞች ቅሬታ የሆነው የቅርብ ርቀት በረራዎች ዋጋ እጅግ መናር ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዚህ ማብራሪያ ይኖረው ይሆን? ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰሩ አቶ ለማ ለዚህ ምክንያቱ ‘ፌቬኒው ማኔጅመንት’ ነው ይላሉ። “ለምሳሌ ከአዲስ አበባ ወደ አሥመራ ስንበር፣ አሥመራ ላይ የምንከፍላቸው ክፍያዎች አሉ። መንግሥት የሚጥለው ግብር ማለት ነው።” እንግሊዝ ውስጥ የአየር ማረፊያ ታክስ በጣም ከፍተኛ ነው የሚሉት ኃላፊው ውሃ መቀየር፣ ነዳጅ መሙላት እና ሌሎች መሬት ላይ የሚከናወኑ ሥራዎችን የሚሠሩ ድርጅቶች ክፍያቸው ላቅ ያለ እንደሆነ ይናገራሉ። አብዛኛውን ጊዜ አየር መንዱ ራቅ ወዳሉ፣ እንደ አውሮፓ እና አሜሪካ ሲጓዝ አማራጮች ስላሉት ዋጋቸው ተመጣጣኝ ከሆኑ ድርጅቶች ጋር እንደሚሠራ የሚናገሩት ኃላፊው፣ በአፍሪካ አገራት ግን ‘በሞኖፖሊ’ ስለተያዘ የዋጋ ልዩነት ያመጣል ይላሉ። “እንዳለመታደል ሆኖ አየር መንገዱ በቀዳሚነት በሚሠራባቸው የአፍሪካ አገራት ወጪው (ኮስት ኦፍ ቢዝነስ) በጣም ከፍተኛ ነው የሚሉት ኃላፊው፣ በዚህ ምክንያት የቲኬት ዋጋ እንደተወደደ ያስረዳሉ። በተለያዩ አገራት ያሉ የታክስ ሕጎች ለቲኬት ዋጋ መጨመር ሚና እንዳላቸው በማንሳት፣ አንዳንድ አገራት የገቢ ግብር ጭምር እንደሚያስከፍሉ ይናገራሉ። “በኢትዮጵያ መንግሥት እና በረራው በሚደረግበት አገር መንግሥት መካከ��� ታክስ አለመጠየቅ ስምምነት ካለ ታክሱ ኢትዮጵያ ውስጥ እንጂ ውጪ አገር አንከፍልም።” ነገር ግን ይህ ስምምነት ከሌለ የቲኬት ዋጋው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ኃላፊው ያብራራሉ። በኢትዮጵያ የኬንያ ኤርዌይስ ኃላፊ የሆኑት ፌሊክስም፣ አንዳንድ ጊዜ አጭር ርቀት የሚጓዝ በረራ ከረዥሙ የሚወደድበትን ምክንያት ያስረዳሉ። ለምሳሌ ይላሉ ኃላፊው፤ “ወደ ዱባይ የሚደረግ በረራ ረዥም ሰዓት ይወስዳል። ስለዚህ አንድ አሊያም ሁለት ሰዓት ከሚወስድ በረራ የላቀ ዋጋ ሊኖረው ይገባል ማለት አይደለም።” የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከናይሮቢ ዱባይ የሚያደርገው በረራ፤ ከናይሮቢ አዲስ አበባ ከሚያደርገው ያነሰ የቲኬት ዋጋ ነው ያለው። ከናይሮቢ አዲስ አበባ በአማካኝ ከአንድ ሰዓት ተኩል እስከ ሁለት ሰዓት ሲወስድ፣ ከናይሮቢ ዱባይ የሚደረግ በረራ 6 ሰዓታት ሊፈጅ ይችላል። የኬንያ ኤርዌይስ በረራም በተመሳሳይ ለአጭር ርቀት በረራ የሚያስከፍለው ክፍያ ላቅ ያለው ነው የሚል ወቀሳ ይደርስበታል። ፌሊክስ፤ ይህ የሚሆነው ‘ቫሊዩ ቤዝድ ፕራይሲንግ’ ስለምንጠቀም ነው ሲሉ ያስረዳሉ። “እኔ የማቀርበው አገልግሎት ዋጋ እና ገበያው ላይ ያለው ዋጋ ምን ያህል ነው? የሚለው ይታያል። ይህ ዋጋ ገበያ ላይ ባለው ውድድር የሚወሰን ይሆናል። ስለዚህ ረዥም ርቀት ያላቸው በረራዎች ከአጭር ርቀቱ በተነፃፃሪ ዝቅተኛ ዋጋ እንዲኖራቸው የሚያደርገው ያለው የአቅርቦት አቅም ነው።” ኃላፊው ሌላው ለአጭር ርቀት በረራዎች መወደድ ምክንያት ነው የሚሉት አገልግሎቱን የሚሰጡት ድርጅቶች ቁጥር ውሱን መሆኑ ነው። ከአዲስ አበባ-ናይሮቢ፤ ከናይሮቢ-አዲስ አበባ፤ የሚደረገውን በረራ በምሳሌነት የሚያነሱት ፌሊክስ ይህን አገልግሎት የሚሰጡት ‘ኬኪው’ እና ‘ኢቲ’ ብቻ ናቸው ይላሉ። ከሌሎች አገራት የሚነሱ አየር መንገዶች ይህ አገልግሎት ሊሰጡ ቢችሉም የሚወስዱት ሰዓት ግን ረዥም ሊሆን እንደሚችል ይጠቅሳሉ። አጭር ርቀት በረራ የሚሰጡ አየር መንገዶች ጥቂት መሆናቸው ውድድር ስለማይኖር ዋጋ ከፍ እንዲል እንደሚያደርገው ነው የሚገልጹት። ደንበኞች ወደ መዳረሻቸው ቀጥታ ሳይሆን አቆራርጠው ሲሄዱ ዋጋ የሚቀንሰው የሚወስድባቸው ሰዓት ከቀጥታ በረራ ከፍ ያለ ስለሆነ ነው የሚል ትንታኔ ይሰጣሉ። አሁን ባለው ሁኔታ የአውሮፕላን ቲኬት ዋጋ የመቀነሱ ነገር ከባድ እንደሆነ የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ተንታኞች ይናገራሉ። ኤሜሬትስ፣ የጃፓን አየር መንገድ፣ ኤር ኤዥያ. . . በቲኬቶቻቸው ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ካሳዩ አየር መንገዶች መካከል ይጠቀሳሉ። በኮሮናቫይረስ ወረረሽኝ፣ በነዳጅ ዋጋ መናር እና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት ባሉ ግጭቶች ምክንያት የተሰቀለው የበረራ ዋጋ በቅርቡ ይወርዳል ተብሎ አይገመትም። ፌሊክስ ግን ምናልባት “ከአንድ ዓመት በኋላ” የሚል ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። “አየር መንገዶች አሁን ያለው ዋጋ ባለበት ይቀጥል ወይስ ገበያው ላይ ሌሎች አየር መንገዶች ይጨመሩ የሚል ጫና አለባቸው።” ፌሊክስ፤ ገበያው ላይ ተጨማሪ አየር መንገዶች እንዲመጡ ማድረጉ ዋጋውን ያረጋጋዋል የሚል እምነት አላቸው። “ይህ በዓመት ሁለት ጊዜ ይጓዝ የነበረ መንገደኛ በእጥፍ እንዲጓዝ ያስችለዋል ማለት ነው። ነገር ግን የበረራ ዋጋ ምናልባት ለአንድ ዓመት ባለበት የሚቀጥል ይመስለኛል። ምክንያቱም አየር መንገዶች ኪሳራታቸውን መመለስ ይፈልጋሉ።” ነገር ግን ደንበኞች ሁለት አማራጮችን ተጠቅመው የተሻለ የበረራ ዋጋ ሊያገኙ እንደሚችሉ ኃላፊው ይጠቁማሉ። አንደኛው ‘ፕሮሞሽናል ፌር’ [የማስታወቂያ ቅናሽ] መጠቀም ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ጉዞን አስቀድሞ በማቀድ በቅናሽ ቲኬት መቁረጥ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cn41y4nn9jdo +politics ተመድ በወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኙት የማሊ ፐሬዚዳንት ባስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አቀረበ "የማሊ መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ፕሬዝደንት ባህ ንዳዋና ጠቅላይ ሚኒስተር ሞክታር ኦዋኔ በቁጥጥር ስር አዋለ መባሉን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ተልዕኮ መሪዎቹ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል። ተልዕኮው በፈረንሳኛ ቋንቋ በትዊተር አማካኝነት ባቀረበው ጥሪ የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ማሊ ነገሮችን ""እንድታረጋጋ""ም ጠይቋል። ይህ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥሪ የሀገሪቱ የሽግግር መንግስት ጊዜያዊ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር በዋና ከተማዋ አቅራቢያ በሚኝ ወታደራዊ ካምፕ መወሰዳቸውን ተከትሎ የመጣ ነው። የመከላከያ ሚንስትሩም በወታደሩ ቁጥጥር ስር እንደዋሉም ተዘግቧል። ታዲያ ይህ ድርጊት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሀገሪቱ ሁለተኛ መፈንቅለ መንግስት እንዳያስከትል ስጋት ጭሯል። ትላንት - ሰኞ የጊዜያዊ መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኤ ኤፍ ፒ የዜና ተቋም በስልክ ወታደሮች ""ሊይዟቸው መምጣታቸውን"" ተናግረው ነበር ታዲያ ሀሳባቸውን ሳይቆጩ ስልኩ መቋረጡንም ነው ኤ ኤፍ ፒ የዘገበው። የአፍሪካ ህብረት፣ የሰሜን አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ፣ የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካም ድርጊቱን አውግዘው ፖለቲከኞቹ ያለቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱም ጠይቀዋል። የመሪዎቹ እስር የተሰማው የሀገሪቱ መንግስት በባለፈው መፈንቅለ መንግስት የተሳተፉ ሁለት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ላይ የስልጣን ሽግሽግ ማድረጉ ከታወቀ ከአንድ ሰዓት በኋላ ነው። ከ ዘጠኝ ወራት በፊትም በተደረገ መፈንቅለ መንግስት በስልጣን የነበሩት ፕሬዝዳንት ከተነሱ በኋላ ማሊ መረጋጋት ርቋት ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-57237154 +politics የኢራንን የኑክሊየር ሳይንቲስቶች እያደነ የሚገድላቸው ማን ነው? ባለፈው ሳምንት የእስራኤል ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑት ሰው ድንገት ተነስተው ወደ ቱርክ በረሩ። አንድ የኢራን ህቡዕ ቡድን የእስራኤል ቱሪስቶችን ለመግደል ተንቀሳቅሷል የሚል መረጃ ስለደረሳቸው ነው ፈጥነው ቱርክ የገቡት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእስራኤልና ኢራን መካከል የጦፈ ግን ደግሞ ድብቅ ውጊያ እየተደረገ ነው፤ ከመጋረጃ በስተጀርባ። ይህ ነገር ወደለየለት ጦርነት እንዳያመራ መፈራቱ አልቀረም። ለበርካታ ዓመታት ሁለቱ አገራት በምሥጢራዊ ጥቃት ተጠምደው ነው የኖሩት። እስራኤል በምድር ላይ የኢራንን ያህል ጠላት የለኝም ትላለች። ኢራን በበኩሏ በይፋ እስራኤል ከመካከለኛው ምሥራቅ መጥፋት ያለባት አገር ናት እስከማለት ደፍራ ተናግራለች። በዋናነት ደግሞ ከአሜሪካ ጋር በማበር በአካባቢው ገናና አገር ሆኜ እንዳልወጣ፣ ዕድገቴን እንዳላፋጥን አንቃ ይዛኛለች በማለት ትከሳታለች። አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጣት ሲጠቋቆሙ ቆይተው ነገሮች ከፈረንጆች 2020 ወዲህ ጀምሮ መልካቸውን እየቀየሩ መጡ። ኢራን የእስራኤል ምሥጢራዊ ቡድን ታላቁን የኑክሊየር ሳይንቲስቴን ገደለብኝ ስትል ከሰሰች። ሳይንቲስቱ ሞህሲን ፋኽሪዛድ ናቸው። የተገደሉት በቴህራን ጎዳና ላይ መኪናቸውን እያሽከረከሩ ሳለ በርቀት መቆጣጠሪያ በሚታዘዝ መትረየስ ተደብድበው ነበር። እስራኤል ድርጊቱን ስለመፈጸሟ አላመነችም፣ አላስተባበለችም። ሁልጊዜም እንደምታደርገው ዝምታን መርጣለች። ሞህሲን ፋኽሪዛድ እንዲህ በህቡዕ ቡድን ሲገደሉ የመጀመሪያው የኢራን ሳይንቲስት አይደሉም። ከፈረንጆቹ 2007 ወዲህ ብቻ አምስት የኢራን ቁንጮ ሳይንቲስቶች ተገድለዋል። ኒውዮርክ ታይምስ እኚህ ባለሥልጣን በምን ዝግጅትና ሁኔታ እንደተገደሉ ምንጮቹን ሳይጠቅስ በዝርዝር ዘግቦ ነበር። የቀድሞው የሞሳድ አለቃ በኋላ ላይ እንደተናገሩት እኚህ የኑክሊየር ሳይንቲስት ለዓመታት የእሰራኤል ራስ ምታት ሆነው ቆይተዋል። በኑክሊየር ሳይንስ ዘርፍ ያላቸው ዕውቀት እስራኤልን ሲያሳስባት ነው የኖረው። “በክትትላችን ውስጥ ነው የኖሩት” ብለዋል እኚህ የሞሳድ የቀድሞ ባለሥልጣን። የምዕራብ አገራት የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች እንደሚሉት ከሆነ ሞህሲን ፋኽሪዛድ ኢራን በምሥጢር ልትገነባው ለምትሞክረው የኒክሊየር ኃይል ዋናው አዛዥ ነበሩ። ከዚህ ወዲያ ኢራንና እስራኤል ከመጋረጃ ጀርባ በተለያዩ ኦፕሬሽኖች ተጠምደው ነው የቆዩት። ጆ ባይደን በቀዳሚያቸው ዶናልድ ትራምፕ እንደ መናኛ ተቀዳዶ የተጣለውን ሰላማዊ የኑክሊየር ስምምነት ለመመለስ እየጣሩ ነው። ስምምነቱን ለመመለስ አንድ ዋና ማነቆ ሆኖ የያዛቸው ጉዳይ በሽብር ቡድን ዝርዝር የገባውን የኢራን አብዮታዊ ዘብ ስሙ ከሽብርተኞች መዝገብ ይፋቅ የሚለው ሐሳብ አሜሪካንን ስላላስማማት ነው። እስራኤል በቅርብ ጊዜ በኢራን ተደግሶልኝ ነበር ያለችውን የግድያ ሙከራ ማክሸፏን ተናግራለች። ኢራን በበኩሏ በእስራኤል ውስጥ የድሮን ጥቃት ኦፕሬሽን ማድረጓን በኩራት ገልጻለች። ሆኖም ዝርዝር ሁኔታው አልተብራራም። ሁለቱ አገራት አንዱ የሌላውን  የመርከብ ጭነት በማጥቃት ይወነጃጀላሉ። ኢራን ከምድር በታች ባለት የኑክሊየር ማብሊያ ማዕከል ላይ ለተፈጸመባት አሻጥር እስራኤልን ተጠያቂ አድርጋለች። ከቀናት በፊት ኢራን ሦስት ከሞሳድ ጋር ግንኙነት ነበራቸው ያለቻቸውን፣ ሌላ ተጨማሪ የኢራን ኒክሊየር ሳይንቲስት ሊገድሉ እንደሆነ እንደደረሰችባቸው የከሰሰቻቸውን ሰዎች ፍርድ ቤት ልታቀርብ እንደሆነ ተናግራለች። ኢራን ከዚህ ሌላ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሯ በማይታወቅ ሁኔታ እየሞቱ ያሉ ቁልፍ ሰዎች እያጋጠሟት እንደሆነ አምናለች። ከእነዚህ መካከልም ሁለት የኤሮስፔስ ኃላፊዎች በሥራ ላይ ሳሉ “ተሰውተዋል” ብላለች። አሟሟታቸው ግን ምሥጢራዊ ነው። ሌላ በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ይሠራ የነበረ መሐንዲስም እንዲሁ በአሻጥር ተገድሎብኛል ብላለች። ይሁንና ለእነዚህ ግድያዎች እስራኤልን በቀጥታ ተጠያቂ እስከማድረግ አልሄደችም። ከመጋረጃው ጀርባ በሁለቱ አገራት መካከል እየተደረገ ባለው ጦርነት እስራኤል እና ኢራን ይበልጥ ወደ መድረክ እየወጡ ይመስላል። ይህ ነገር ወደ ሆሊውድም ዘልቆ በአፕል የቴሌቪዥን የቲቪ ትዕይንት ላይ አንድ የሞሳድ ሰላይ የኢራንን አብዮታዊ ጥበቃን በጣጥሶ ሲገባ ያሳያል። የሆሊውድ ፊልም ግን በመሬት ላይ የማይታይ ነገር አይደለም። ለምሳሌ ከቅርብ ቀናት በፊት እስራኤል ዜጎቼ ሆይ! እባካችሁ ወደ ቱርክ አትሂዱ፤ በቱርክ አገር ያላችሁም ከሆነ ቶሎ ውጡ ስትል አስታውቃለች። ይህም አንድ የኢራን ህቡዕ ቡድን በአንዳች ስፍራ የእስራኤል ዜጎችን ኢላማ ለማድረግ እየተሰናዳ መሆኑን ስለደረሰችበት ነው። መሐመድ ሙራንዲ የቴህራን ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ናቸው። የኢራን የኑክሊየር ድርድር የሚዲያ ጉዳዮች አማካሪም ናቸው። በምዕራባዊያን ከለላ ሰላማዊ ዜጎችን እያደኑ መግደል ማስገደል ለእስራኤል የተለመደ ተግባር ነው ይላሉ። “ይሁንና እስራኤል እንደምትለው ያህል በኢራን ውስጥ ኦፕሬሽን አታስፈጽምም። በድንገት የሞቱ የኢራን ዜጎችም የእስራኤል ልዩ ኦፕሬሽን የሥራ ውጤት አድርጎ የማቅረብ አዝማሚያ አለ” ባይ ናቸው። ፕሮፌሰሩ ጨምረውም “አትጠራጠሩ፣ ኢራን እያንዳንዱን ጥቃት ትበቀላለች” ብለዋል። ኢራን ልዩ ኃይሏ 'ቁዱስ' ይባላል። ቁዱስ የአብዮታዊ ዘብ አንድ ክንፍ ነው። ዓላማና ተግባሩ ደግሞ ከኢራን ውጪ ምሥጢራዊ ግዳጆችን መወጣት ነው። የቁዱስ ብርጌድ ዋና አለቃ ጄኔራል ኢስማኢል ቃኒ፣ ኢራን ማንኛውንም የአሜሪካና የእስራኤል ጠላት የሆነ ቡድንን መደገፏን ትቀጥልበታለች ብለዋል። ጄኔራል ኢስማኢል ማናቸው? ከተባለ ቃሲም ሱለይማኒን የተኩ ሰው ናቸው። ቃሲም ሱለይማኒ ደግሞ ከሁለት ዓመት በፊት በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ፣ በጥር ወር፣ አሜሪካ በድሮን ጥቃት እንደገደለቻቸው ይታወሳል። ሱለይማኒ አሜሪካ በዐይነ ቁራኛ ስትከታተላቸው የነበሩ ሰው ናቸው። ዶናልድ ትራምፕ እርምጃ ይወሰደብት እስኪሉ ድረስ በአሜሪካ የስለላ ቡድን መነጽር ሥር ነበር። ትራምፕ እርምጃው ከተወሰደ በኋላ “ሱለይማኒ የዓለማችን ቁጥር አንድ አሸባሪ ነበር” ሲሉ ተናግረዋል። ትራምፕ ሱለይማኒ እንዲገደሉ የወሰኑት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ማይክ ፓምፔዎ ግፊት ነው ተብሏል። ዶናልድ ትራምፕ በመካከለኛው ምሥራቅ የኢራን ሚና እንዲኮሰምን ትልቁን ሚና የተጫወቱ የእስራኤል ባለውለታ ተደርገው ይወስዳሉ። በተለይ አስራኤል ከመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል የቀየሰችወን ‘አብረሃም አኮርድ’ የተባለውን ዕቅዷን በማስተዋወቅ እስራኤልን ከአረብ አገራት ጋር አወዳጅተው ነው የሄዱት። የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና ባህሬይን ከእስራኤል ጋር ግንኙነታቸውን እንዲያድሱ በማገዝ ‘አብረሃም አኮርድ’ ስምምነትን በማፈጣጠም ይበልጥ ኢራንን የመነጠል ሥራም ሠርተዋል። “ኢራን የአብረሃም አኮርድ ስምምነቶችን እጅግ ትጸየፋለች” ይላሉ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የአረብ ዲፕሎማት። አንድ የኢራን የቀድሞ ባለሥልጣን ግን ይህን ያሰተባብላሉ። “ስምምነቱን ባንወደውም ዘላቂ እንደማይሆን እናውቃለን፤ ጊዜያዊ እፍ እፍ ነው፤ የትም አያደርስም” ብለዋል ለቢቢሲ። የጆ ባይደን የሰሞኑ የሳዑዲ አረቢያና የእስራኤል ጉብኝት እንዳለ ሆኖ፣ አንድ በባይደን አስተዳደር ውስጥ ያሉ ባለሥልጣን የእስራኤልና ኢራን ፍጥጫ ወደከፋ ደረጃ እንደማይሸጋገር እናውቃለን፤ ቢያንስ በአጭር ጊዜ ያ እንደማይሆን እንረዳለን ይላሉ። ሪች ጎልድበርግ ደግሞ መቀመጫውን ዋሺንግተን ያደረገ የመከላከያ ጉዳዮች የጥናትና ምርምር ቡድን ባልደረባ ናቸው። እሳቸው እንደሚያምኑት እስራኤል የምታደርጋቸው ምሥጢራዊ ኦፕሬሽኖች ከመበርከታቸው የተነሳ አሁን አሁን ተራ ዕለታዊ ጉዳዮች እንዲመስሉ እያደረገች ነው። “...አንድ ቀን ግን ዓለም ከመንቃቱ በፊት እስራኤል በኢራን ኑክሊየር ማበልጸጊያ ማዕከል ላይ ድንገተኛ የአየር ጥቃት ማድረሷ አይቀርም፤ ዓለም ጥቃቱን እናስቁመው ከማለቱ በፊት ጥቃቱ ተገባዶ እናገኘው ይሆናል” ብለዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c29xn1dj09zo +health ኮሮናቫይረስ፡ የላቲን አሜሪካው ቁጥር-1 ቢሊዮነር በኮቪድ ተያዙ በመላው ላቲን አሜሪካ የናጠጡ ሀብታም የሚባሉት ካርሎስ ስሊም በኮቪድ ተህዋሲ መያዛቸው ታወቀ፡፡ የ80 ዓመቱ ቢሊዮነር ካርሎስ ሜክሲኳዊ ሲሆኑ በቴሌኮሚኒኬሽን ቢዝነስ እውቅ ናቸው፡፡ ለጊዜው መጠነኛ የኮቪድ ምልክቶችን ብቻ እያሳዩ ነው ተብሏል፡፡ ልጃቸው በትዊተር ሰሌዳው እንደጻፈው ‹አባቴ ደህና ነው አታስቡ› ብሏል፡፡ የቢሊየነሩ በኮቪድ መያዝ ዜና የተሰማው የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት የ67 ዓመቱ አንድሬስ ማኑል ሎፔዝ ኦብራዶር በኮቪድ መያዛቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሜክሲኮ ከዓለም አገራት ክፉኛ በኮቪድ ከተጎዱ አገራት ተርታ የምትመደብ ናት፡፡ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በተህዋሲው የተያዙ ሲሆን 150ሺህ ዜጎች ደግሞ ሕይወታቸው በዋዛ አልፏል፡፡ ዛሬ ሰኞ የካርሎስ ስሊም ልጅ ዶሚት ካርሎስ ስሊም እንደጻፈው ‹አባቴ ለአንድ ሳምንት መጠነኛ ምልክቶችን ካሳየ በኋላ አሁን ሻል እያለው ነው፤ ለውጥ አለው›› ብሏል፡፡ ቢሊየነሩ ካርሎስ ስሊም ዋንኛውን የሜክሲኮ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሰጪ፣ ሞቪል ኩባንያን በባለቤትነት ያስተዳድራሉ፡፡ ፎርብስ መጽሔት የዚህ ቴሌኮም ኩባንያቸው ግምት 52 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል ሲል ገምቶታል፡፡ ሜክሲኮ አሁን ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ በመስፋፋቱ በዋና ከተማዋ ሜክሲኮ ሲቲ ሆስፒታሎች እየሞሉ ነው ብሏል በሜክሲኮ የቢቢሲ ዘጋቢ ዊል ግራንት፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ ያገኛቸውና አሁን ከቤታቸው ሆነው ሥራ እየሠሩ ያሉት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሎፔዝ ኦብራዶር የሩሲያ ሠራሹን ስፑትኪን ክትባትን ወደ አገራቸው ለማስገባት ከፑቲን ጋር እንደተነጋገሩ ተዘግቧል፡፡ በዚህም መሠረት 24 ሚሊዮን ጠብታዎች በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ሜክሲኮ ይደርሳሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-55807195 +business አውስትራሊያ ፡ የሒትለርን ቪዲዮ በመጠቀም ፌስቡክ ላይ በአለቆቹ የተሳለቀው ሠራተኛ 200 ሺህ ዶላር ተሰጠው ስኮት ትሬሲ ይባላል፡፡ የግዙፉ የብሪቲሽ ፔትሮሊየም ኩባንያ (ቢፒ) ሠራተኛው ነበር፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት ከዕለታት በአንዱ ከሥራ ይባረራል፡፡ የተባረረው አርፍዶ ሥራ በመግባቱ ወይም እንዝህላል ሆኖ አይደለም፡፡ የገዛ መሥሪያ ቤቱ ላይ በመሳለቁ እንጂ፡፡ የተሳለቀበት መንገድ ግን ሳያስበው ዝነኛ አድርጎታል፡፡ ሰውየው በፌስቡክ ለቅርብ ጓደኞቹ አንድ ቪዲዮ ያጋራል፡፡ ቪዲዮው የተወሰደው 2004 ዓ.ም ላይ ዝነኛ ከነበረው ዳውንፎል (Downfall) የሆሊውድ ፊልም ላይ የተቀናበረ ነው፡፡ በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ በሰራተኛውና በአለቆች መካከል የነበረውን የደመወዝ ይጨመርልን ጥያቄና አታካራ ተመርኩዞ አለቆቹ ልክ እንደ ሂትለር ሆነው ሲቆጡ የሚያሳይ ቅንብር ነበር የሰራው፡፡ ይህንን ስላቀ-ምሥል (meme) ለቅርብ የፌስቡክ ጓደኞቹ ብቻ በማጋራቱ አለቆቹ ሰምተው በመቆጣታቸው መሥሪያ ቤቱ ሰውየውን ከሥራ ያባርረዋል፡፡ ሰውየው በዚህ ይናደድና ኩባንያውን ፍርድ ቤት ይገትረዋል፡፡ እንዴት በፌስቡክ ላይ ለጓደኞቼ በቀለድኩት ጥሩ ቀልድ ከሥራ እባረራለሁ ሲል ይከሳል፡፡ በቅድሚያ የመሥሪያ ቤቱ የሰራተኛ ማኅበር ጉዳዩ በሽምግልናና ግልግል ዳኝነት ይታይ ይልና ይኸው ይደረጋል፡፡ የግልግል ዳኝነቱ የሰውየው መባረር ትክክል ነው ብሎ ይፈርዳል፡፡ ሚስተር ትሬሲ ድሮም እናንተን ማመን ይልና ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዞት ይሄዳል፡፡ ለሁለት ዓመት ያህል ጠበቃ አቁሞ ሽንጡን ገትሮ ከተከራከረ በኋላ ፍርድ ቤት ሰውየው ያለ አግባብ ነው የተባረረው ሲል ይበይንለታል፡፡ በዚህም የተነሳ የብሪታኒያ ፔትሮል ኩባንያ (ቢፒ) ለሰራተኛው 200ሺህ ዶላር እንዲከፍለው ይወስንለታል፡፡ ይህም ላለፉት ሁለት ዓመታት ያጣውን ደመወዙንና ጥቅማጥቅሙን ጨምሮ የጡረታ አበሉንና የሞራል ጉዳት ካሳን ያካተተ ነው፡፡ ቢፒ የሚለው ሰውየው የሂትለርን ቪዲዮ (ምንም እንኳ ከፊልም የተወሰደ ቢሆንም) ተጠቅሞ በመሥሪያ ቤቱ ላይ ምሥለ-ስላቅ ሰርቶ በፌስቡክ ገጽ መለጠፉ ‹አሳፋሪም ነውርም› ነው፡፡ ከአንድ ትጉህ፣ ጨዋ ሠራተኛም የሚጠበቅ አይደለም፡፡ ሚስተር ትሬሲ በበኩሉ እኔ ይህን ያደረኩት መጥፎ ልቦና ይዤ ሳይሆን ለቀልድ ነው፤ ቀልድ ደግሞ ለጤና ጥሩ ነው ብሏል፡፡ ፌዴራል ፍርድ ቤት በሰጠው ብይን ምሥለ-ስላቁ ላይ ያለው ሂትለር የቢፒ መሥሪያ ቤት አለቆችን አይወክልም፡፡ ስለዚህ ሚስተር ትሬሲ ነውረኛ ሊባል አይችልም ብሏል፡፡ ሰኞ ወደ ሥራ የተመለሰው የነዳጅ አውጪ ሰራተኛው ሚስተር ትሬሲ አካውንቱ ውስጥ 200ሺህ ዶላሩ ከገባለት በኋላ ዘንጦ ነው፡፡ ቢፒ ለሚስተር ትሬሲ 150 ሺህ ዶላር ብቻ ይበቃዋል፣ ምክንያቱም ሰራተኛው ባሰራጨው ቪዲ�� ስማችን ጎድፏል፣ በዚያ ላይ በፍርድ ቤት ክርክር ላይ ሳለ ሥራ ፈልጎ ማግኘት ይችል ነበር። በዚያን ጊዜ ለቦዘነው እኛ የመክፈል እዳ የለብንም ቢልም የሰራተኛው ጠበቃ በበኩሉ በዚያን ጊዜ ሥራ እንዳልፈለገ በምን አወቃችሁ ሲል ተከራክሯል፡፡ የግራ ቀኙን የሰማው ፍርድ ቤት ‹በቃ 200 ሺህ ዶላር› ለሰውየው ክፈሉት ብሏል፡፡ ገንዘቡ ሲሰላ ወደ ሳባት ሚሊዮን ብር ይጠጋል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-53732694 +health ኤርትራውያን በካንሰር ለሚሰቃይ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር አሰባሰቡ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን እና ትውልደ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች በሕመም ለሚሳቃይ አንድ ኤርትራዊ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን የካናዳ ዶላር በላይ አሰባሰቡ። በኤርትራ ነዋሪ የሆነው እና የስድስት ልጆች አባት የሆነው ዮናስ ፀጋይ፤ ባለፈው አንድ ዓመት ሆድኪን ሊምፎማ በተባለ የደም ካንሰር አይነት ሲሰቃይ ቆይቷል። 'ዮናስ ፀጋይን እና ቤተሰቡን ይርዱ' በሚል በተከፈተው የጎፈንድሚ አካውንት በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የካናዳ ዶላር ማሰባሰብ ተችሏል። ለዮናስ የተሰባሰበው መዋጮ ማክሰኞ ጥር 09 ከሰዓት ላይ 637 ሺህ የካናዳ ዶላር (ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ) ደርሷል። በጎፈንድሚ ገጽ ላይ ተያይዞ በወጣው የእርዳታ ተማጽኖ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ፤ ዮናስ ፀጋይ በደም ካንሰር ምክንያት ከፍተኛ ሕመም ውስጥ እንደሚገኝ እና ሰዎች ለሕክምና ወጪ መዋጮ እንዲያደርጉለት ሲማጸን ይታያል። በስድስት ልጆቹ ተከቦ የሚታየው ዮናስ፤ በሕመሙ ምክንያት ሰውነቱ አብጦ እና እጆቹን በኃይል ሲያሽ ይታያል። ለዮናስ የቀረበው የእርዳታ አድርጉ ጥሪ በርካታ ምላሾችን በማግኘት በጎፈንዲሚ ገጽ ላይ ቀዳሚ ደረጃን ይዟል። ዮናስ በኤርትራ ወደ ጤና ተቋማት ቢሄድም ለተጨማሪ ሕክምና ከአገር ውጭ መጓዝ እንዳለበት ተነግሮታል። በድህነት ውስጥ የሚኖረው ዮናስ የሕክምና ወጪውን መሸፈን አለመቻሉን በመግለጽ አንድ የዩቲዩብ ገጽ የስድስት ልጆቹ አባት የሆነው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ለሌሎች አጋርቷል። ዮናስን ለማገዝ የጎፈንድሚ ገጽ በተከፈተ በመጀመሪያዎቹ 12 ሰዓታት ውስጥ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን ከ350 ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ በማዋጣት ፈጣን ምላሽ ሰጥተዋል። የእርዳታ ገንዘብ አሰባሳቢዎች መካከል አንዱ የሆነው ዮሴፍ ወርቄ እንዲህ በፍጥነት በርካቶችን ያሳተፈ መዋጮ አጋጥሞት እንደማያውቅ ለቢቢሲ ትግርኛ ክፍል ተናግሯል። አስተባባሪው እንደሚለው በሕመም የሚሰቃየው የዮናስ ተማጽእኖ የበርካታ ሰዎችን ልብ ተነክቷል። እንድ የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የጤና አግልግሎት (ኤንኤችኤስ) ድረ-ገጽ ከሆነ ዮናስ የሚሰቃይበት ሆድኪን ሊምፎማ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥም ከነጭ የደም ሴል ጋር የተገናኘ የደም ካንስር አይነት ነው። ተቋሙ እንደሚለው ከሆነ ይህ የካንሰር ሕመም በጨረር ሕክምና (በኬሞቴራፒ) እንዲሁም በራዲዮቴራፒ ሕክምና ሊድን ይችላል። https://www.bbc.com/amharic/news-60041868 +business ኤለን መስክ የማይክሮሶፍቱን ቢል ጌትስን በልጦ የዓለማችን 2ኛው ቢሊየነር ሆነ "የቴክኖሎጂ ፈጣሪው ኤለን መስክ በአጭር ጊዜ ውስጥ የዓለማችን 2ኛው ቢሊየነር ሆነ። መስክ የማይክሮሶፍቱን ቢል ጌትስን በልጦ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የተቀመጠው። የኤለን መስክ ሀብት በአጭር ጊዜ የተምዘገዘገው ቴስላ የተባለው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያው በስቶክ ገበያ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ተከትሎ ነው። ይህ ድንገተኛ የሀብት ጭማሪ የኤለን መስክን የሀብት መጠን ከ7 ቢሊዮን ወደ 128 ቢሊዮን አድርሶታል። የቢሊየነሮችን ዝርዝር የሚያስቀምጠው ብሉምበርግ እንደሚለው ከሆነ በዚህ ሰዓት ኤለ��� መስክን የሚበልጠው የዓለማችን ቁንጮ ሀብታም የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ ብቻ ነው። ቴስላ የአሌክትሪክ አምራች በአሜሪካ የስቶክ ገበያ ትልልቆቹን 500 ኩባንያዎች ደረጃ በሚያስቀምጠው ኤስ ኤንድ ፒ (S&P 500) ዝርዝር እንደሚገባ ባስታወቀ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው የሀብት ግስጋሴው በአስደንጋጭ መልኩ ሽቅብ የወጣው። የዚህን ዜና መውጣት ተከትሎ በርካታ ሰዎች የቴስላ መኪናን ድርሻ ለመግዛት ሽሚያ እንዲፈጠር አድርጓል። የቴስላ ኩባንያ ጠቅላላ ግምትም ግማሽ ትሪሊዮን ዶላር አድርሶታል። ይህን ተከትሎ ምንም እንኳ የኤለን መስክ ድርሻ በቴስላ ኩባንያ ውስጥ አነስተኛ ቢሆንም የሰውየው ሀብት ጣሪያ እንዲነካ ምክንያት ሆኗል። ቴስላ ኩባንያው በዓለም ላይ ከፍተኛ ዋጋ ከሚሰጠው መኪና አምራች ኩባንያ ዋንኛው ነው። ሆኖም ከቶዮታ፣ ቮልስ ዋገን እና ጄኔራል ሞተርስ ጋር ሲነጻጸር የሚያመርታቸው መኪናዎች ብዛት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ማክሰኞ ዕለት መስክ ጀርመን በነበረ ጊዜ የአውሮጳ የመኪና ገበያ ውስጥ መኪና በገፍ የማምረት ሥራ ውስጥ መግባት እንዴት አዋጭ እንደሆነ ሲያስረዳ ነበር። አሜሪካ ብዙ ሰዎች ትልልቅ መኪና መንዳት ነው ምርጫቸው፤ እዚህ አውሮጳ ግን ትንንሽ ናቸው መኪናዎች፥ ቴስላ በርከት ያለ መኪና በማምረት የዋጋ ተፎካካሪ መሆን የሚችል ይመስለኛል ብሏል መስክ። ቴስላ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ለተከታታይ ዓመታት ኪሳራን ሲያስመዘግብ ቆይቶ ከዚያ በኃላ ግን ላለፉት ለ5 ተከታታይ ሩብ ዓመታት ትርፋማ እየሆነ ቆይቷል። የትርፍ እድገቱንየኮቪድ ወረርሽኝም አልበገረውም። መቀመጫውን ካሊፎርኒያ ያደረገው ቴስላ በኤስ ኤንደ ኤስ የስቶክ ማርኬት ግማሽ ትሪሊዮን የሀብት ግምት ዋጋ ይዞ በመግባት የመጀመርያው ነው። ቢልጌትስ በዓለም የቢሊየኖች ተርታ ለዘመናት ይዞት የቆየውን መሪነት የተነጠቀው በፈረንጆች 2017 ሲሆን አዲሱ ቢሊየነር ደግሞ የአማዞኑ ቤዞስ ነበር። የቢል ጌትስ ሀብት 127.7 ቢሊየን ዶላር ነው፤ ሆኖም ገንዘቡን በብዛት ለበጎ አድራጎት ስለሚሰጥ እንጂ ከዚህ በላይ የሀብት ግምት ይኖረው ነበር ይላል ብሉምበርግ። የጄፍ ቤዞስ ሀብት አሁን ላይ 182 ቢሊየን ደርሶለታል። ቤዞስም እንደ መስክ ሁሉ በዚህ ዓመት ገቢው በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮለታል። ይህም ወረርሽኙ የበይነ መረብ ግዢ እንዲፋፋም እድል በመፍጠሩ ነው። ኤለን መስክ ባለፈው ሳምንት የኮቪድ ተህዋሲ ሳይዘኝ አልቀረም ብሎ በትዊተር ሰሌዳው ጽፎ ነበር። መጠነኛ ምልክቶችን ሲያሳይ ነበር። ኤሎን መስክ በፈጠራት የጠፈር ታክሲ ""ስፔስ ኤክስ"" 4 የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ወደ ዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ የተሳፈሩት በቅርብ ሳምንት ነበር። ኤሎን መስስ ተወልዶ ያደገው በፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪካ ሲሆን በ17 ዓመቱ ወደ ካናዳ ካቀና በኃላ ለትምህርት በልውውጥ የስኮላርሺፕ ፕሮግራም ወደ አሜሪካ ፔኒሲልቬኒያ ዩኒቨርስቲ ገባ። በዚያው አጋጣሚ ነው አሜሪካ የቀረው። አሁን ነዋሪነቱ በአሜሪካ ሎሳአንጀለስ ካሊፎርኒያ ውስጥ ነው። 49 ዓመቱ ሲሆን የ7 ልጆች አባትም ነው።" https://www.bbc.com/amharic/55056387 +health እንቅልፍ በመቀነስ የሥራ ጫናን ‘የመበቀል’ ልማድ "ማ ራዎ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት፤ በሳምንት ለስድስት ቀናት ትሠራ ነበር። ቻይና፣ ሻንጋይ ውስጥ ለሚገኝ መድኃኒት አምራች ትሠራ የነበረው ማ፤ በአጭር ጊዜ ነበር ሕይወቷ በሥራ የተዋጠው። ለመመገብ አጭር ሰዓት ብቻ ነበራት። ለመተኛትም እንዲሁ። ""ከሥራ ውጪ ምንም የግል ሕይወት አልነበረኝም። ድብርት ይዞኝ ነበር"" ትላለች። ሥራዋ ለግል ሕይወት ጊዜ ስላሳጥት እንቅልፏን መስዋዕት እያደረገች ለራሷ ጊዜ ለመስጠት ትሞክር ነበር። ካላት አጭር የመኝ�� ጊዜ ቀንሳ ዜና ማንበብ፣ ቪድዮ ማየት ጀመረች። ብዙዎች እንደ ማ እንቅልፍ ትተው የተለያየ ተግባር ያከናውናሉ። ቀናቸው በሥራ ስለሚዋጥ ከምሽት ውጪ ክፍተት አያገኙም። ምሽት ላይ ከመተኛት ይልቅ ጊዜ በማጣት ሳቢያ ያልሠሩትን ነገር ያገባድዳሉ። ጋዜጠኛዋ ዳፊን ኪ ሊ ""ቀናቸውን ባሻቸው መንገድ ማሳለፍ ያልቻሉ ሰዎች ማታ ከመጠን በላይ በማምሸት ለማካካስ ይሞክራሉ"" ስትል ትዊተር ላይ ጽፋ ነበር። ጽሑፉን ከ4,500 በላይ ሰዎች ወደውታል። አንድ ሌላ ሰው ደግሞ ""ቀኖቼ በኔ ሳይሆን በሌሎች ቁጥጥር ሥር ናቸው። ምሽቱ ግን የእኔ ነው"" ሲል ጽፏል። በእንግሊዘኛ 'revenge bedtime procrastination' ይባላል። የሥራ ጫና የሚበዛባቸው ሰዎች ለእንቅልፍ ጊዜ ሲያገኙ ከመተኛት ይልቅ የተለያየ ሥራ ይሠራሉ። መጽሐፍ ያነባሉ፣ ቲቪ ያያሉ፣ ከሰዎች ጋር ያወራሉ ወዘተ. . . እንቅልፍን መበቀል እንደማለት ነው። እንቅልፍ ለምን እምቢ ይለናል? በቂ እንቅልፍ አለማግኘት የጤና ቀውስ ነው። እአአ 2019 ላይ በ12 አገሮች የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው ከ11,000 በላይ ሰዎች መተኛት ከሚገባቸው ሰዓት ባነሰ 6.8 ሰዓት ብቻ ይተኛሉ። በየቀኑ በአማካይ ስምንት ሰዓት መተኛት ይመከራል። አንዳንዶች መተኛት የማይችሉት ስለሚጨነቁ ወይም በዙሪያቸው ያሉ ነገሮች ስለሚረብሿቸው ነው። አብላጫውን ቁጥር የሚይዙ ሰዎች የማይተኙት ግን በሥራ ጫና ወይም በትምህርት ምክንያት ነው። ቻይና የተሠራ ጥናት ከ1990ዎቹ ወዲህ የተወለዱ ሰዎች በአግባቡ እንደማይተኙ ያሳያል። በተለይም በግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋሞች የሚሠሩ እምብዛም አይተኙም። የ33 ዓመቷ ጉ ቢንግ የምትሠራው ዲጂታል ኤጀንሲ ውስጥ ነው። ከሌሊት ስምንት ሰዓት በፊት አትተኛም። እሷ ብቻ ሳትሆንም ጓደኞቿም ከእኩለ ሌሊት በኋላ ነው የሚተኙት። ጉ ልተኛ ብትል እንኳን አምሽታ መሥራት ስላለባት መተኛት አትችልም። ለእንቅልፍ ጊዜ ስታገኝ ደግሞ የራሷን ሥራ መሥራት ስለምትጀምር ሳትተኛ ትቀራለች። ""ጊዜዬን መሥሪያ ቤቱ ቀምቶኛል። ያለኝ ጊዜ ከሥራ ውጪ ያለው ሰዓት ብቻ ነው። ስለዚህ እንቅልፍ ትቼ የተሰረቅኩትን ሰዓት አካክሳለሁ"" ትላለች። በሥራና በግል ሕይወት መካከል መስመር ጠፍቷል በሼፈልድ ዩኒቨርስቲ የሥነ ልቦና መምህርቷ ሲያራ ኬሊ፤ በሥራ እና በግል ሕይወት መካከል ያለው መስመር እየጠፋ ነው ይላሉ። አንድ ሰው ከሥራ ባልደረባው ጋር በማንኛውም ጊዜ ይነጋገራል። ይህ ግንኙነት ደግሞ ሥራና የግል ሕይወትን እያደበላለቀ ነው። ሥራ ሲበዛ የመዝናኛ ጊዜን እንደሚቀንስ እሙን ነው። መዝናኛ ጊዜ ለማግኘት ብሎ እንቅልፍን መስዋዕት ማድረግ ግን ጤናማ እንዳልሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ዘለግ ላለ ጊዜ እንቅልፍ ማጣት ለተለያየ የአዕምሮ ህመም ያጋልጣል። የሥነ ልቦና መምህርቷ ሲያራ ሰዎች መዝናኛ ሰዓት የግድ ማግኘት አለባቸው። የሥራ ጫና መዝናኛ ሰዓት ሲያሳጣቸው እንቅልፍ ትተው የሚዝናኑትም ለዚያ ነው። ""ሠራተኞች መንፈሳቸውን የሚያዝናኑበት መንገድ ሊያገኙ ይገባል"" ሲሉ አሠሪዎች ጉዳዩን እንዲያስቡበት ይመክራሉ። የሠራተኞች መብት ላይ የሚሠሩት የማኅበረሰብ ባለሙያ ሂውንግ ቹንግ፤ ሠራተኞች የእንቅልፍ እንዲሁም የመዝናኛ ሰዓት በሚያሳጣቸው መንገድ ሥራ ሊደራረብባቸው አይገባም ይላሉ። ይህንን ማድረግም የቀጣሪዎች ኃላፊነት ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-56051981 +sports ኳታር ለዓለም ዋንጫ እንዴት ተመረጠች፣ ውድድሩ ለምን ኅዳር ላይ ሆነ? "ሚሊዮኖች. . . ቢሊዮኖችም ሊሆን ይችላል፤ በጉጉት የሚጠብቁት የዓለም እግር ኳስ ፍልሚያ በቀጣይ ዓመት ኅዳር ላይ መካሄድ ይጀምራል። የዓለም ዋንጫ ውድድር ኅዳር ወር ላይ ሲሆን ይህ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። አዘጋጇ ደግሞ የመካከለኛ ምሥራቋ ቱጃር አገር ኳታር ናት። የዓለም ዋንጫ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሲያመራም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። አስካሁን ከሁለት አገራት በስተቀር በዚህ ተወዳጅ ፍልሚያ ላይ መሳተፋቸውን አረጋግጠዋል። ሁለቱ አገራት ደግሞ በዚህ ሳምንት በሚደረገው ኢንተርኮንቲኔንታል ጥሎ ማለፍ ይለያሉ። ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ ፊፋ፣ ኳታር የዓለም ዋንጫን እንደትደግስ ወስኛለሁ ሲል ወሳኔው ብዙ አወዛግቦ ነበር። የዓለም ዋንጫ ይህ የፈረንጆች ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት በኢትዮጵያ ቀጣይ ዓመት ኅዳር 12 ጀምሮ ታኅሣሥ 09 ይቋጫል። ለወትሮው የዓለም ዋንጫ በኢትዮጵያ ክረምት ነበር የሚሰናዳው። ዘንድሮ ግን ሙቀቱ ከምላስ ላብ በሚያመነጭባት ዶሃ ሊካሄድ በመሆኑ የጊዜ ሰሌዳውን ማሻሻል ግድ ብሏል። ዶሃ ኅዳርና ታኅሣሥ ገደማ ቀዝቀዝ ትላለች። ሙቀቱ ወደ 18 ሴሊሺየስ ይወርዳል ማለት ነው? ብለው ካሰቡ ተሳስተዋል። ኳታር ብርድ ብድር የሚሰማዎት ሙቀቱ ወደ 25 ሴሊሺየስ ሲደርስ ነው። ለወይናደጋ ሰው 25 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ማለት ልብስ አስወልቆ ዛፍ ጥላ ሥር የሚያስተኛ ነው። ዶሃ እንደሌላው አገር ወግ ደርሷት የዓለም ዋንጫን ሰኔና ሐምሌ ላዘጋጅ ብትል ሙቀቱ 40 ባስ ሲል ደግሞ 50 ዲግሪ የሚደርስ ሙቀት ያቃጥላታል። መቼም እግር ኳስ ወዳዱ ማኅበረሰብ ሮናልዶና ሜሲ ጥብስ እንዳሸተተ ውሻ ሲያለከልኩ ማየት አይሻም። እርግጥ ነው ዶሃ የዓለም ዋንጫን ላዘጋጅ ያለችው ረብጣዋን ተማምና ነው። ዶሃ ""ግድ የለም በኔ ይሁንባችሁ፤ ሙቀቱ ተፈጥሮን በሚያስንቅ ማቀዝቀዣ በተገጠመለት ስታድዬም አጫውታችኋለሁ"" ብላ ነበር። ነገር ግን ፊፋ በዚህ እንኳ አንስማማም አለ። ታድያ ውድድሩ ኅዳር ወር ላይ ቢካሄድ ምን ችግር አለው? ኅዳር እና ታኅሣሥ የአውሮፓ እግር ኳስ የሚደምቅበት ወቅት ነው። ነገር ግን ዘንድሮ በርካታ ተጫዋቾች አገራቸውን ወክለው ለመፋለም ወደ ኳታር የሚያመሩበት ወቅት ይሆናል። ዘንድሮ ኅዳር እና ታኅሣሥ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግን ለማየት ካሰቡ ውሳኔዎን ለመቀየር ጊዜው አልረፈደም። የጣልያን ሴሪ አ እንዲሁም የስፔን ላሊጋም ኅዳር እና ታኅሣሥ እረፍት ይወጣሉ። የአውሮፓ እግር ኳስ ወደ ወትሮ ፕሮግራሙ የሚመለሰው ከዓለም ዋንጫ በኋላ ነው። ጊዜው በፈረንጆቹ 2010 ዓመተ ምህረት። አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና አውስትራሊያ እንዲሁም ኳታር የዓለም ዋንጫን እንድናሰዳ ዕድሉ ይሰጠን ሲሉ አመለከቱ። ፊፋ ጊዜ ወስዶ ጥያቄያቸውን ማጤን ጀመረ። ከዚያም ጊዜው ደርሶ 22 የፊፋ ሥራ አስፈፃሚ አባላት መጥተው እነሆ ምርጫችን ዶሃ ሆናለች አሉ። አንዲት የአራብ አገር የዓለም ዋንጫን ስትደግ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ነገር ግን ብዙ አገራት ኳታር 'በእጇ ተራምዳ' ይሆናል እንጂ እንዴት ልትመረጥ ቻለች ይሉ ጀመር። የኋላ ኋላ ኳታር ለፊፋ ሰዎች 3.7 ሚሊዮን ዶላር ለግሳለች ተብላ በይፋ ተከሰሰች። ነገር ግን ሁለት ዓመት ከፈጀ ምርመራ በኋላ ስሟ ነፃ ወጣ። በወቅቱ የፊፋ አለቃ የነበሩት ሴፕ ብላተር ለኳታር ድምፃቸውን ቢሰጡም፣ ትንሽ ቆይተው ተሳስተናል ማለት ጀመሩ። ብላተር አሁን ስዊትዘርላንድ ውስጥ በማጭበርበርና ሙስና ወንጀል ተከሰው ፍርዳቸውን እየጠበቁ ይገኛሉ። ለረዥም ዓመታት ፊፋን የመሩት ብላተር፣ እኔ ጥፋት የለብኝም ሲሉ ያስተባብላሉ። ኳታር ከአምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎችም ክስ ቀርቦባታል። እኒህ የመብት ተሟጋች ተቋማት ስታድዬም ለመገንባት የመጡ የውጭ አገራት ዜጎች መብታቸው ተረግጧል ይላሉ። አገራት ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ማጣሪያ ማድረግ የጀመሩት ከሦስት ዓመታት በፊት ነው። ማጣሪያው የተደረገው በአህጉር ተከፋፍሎ ነበር። አህጉራት ምድብ መድበው ብሔራዊ ቡድኖችን ካፋለሙ በኋላ አሸናፊዎች ወደ ኳታር ያቀናሉ። ያለፈውን የዓለም ዋንጫ ያነሳችው ፈረንሳይ ወደ ኳታር ታቀናለች። የአውሮፓ ዋንጫን ያነሳችው ጣልያን ግን ዶሃ ላይ አትታይም። የሞሐመድ ሳላህ ግብፅም ወደ ዶሃ የሚወስዳትን ቲኬት መቁረጥ አልቻለችም። 32 አገራት በዚህ ውድድር ይሳተፋሉ። ከአንድ አህጉር የመጡ አገራት በአንድ ምድብ አይደለደሉም። ነገር ግን ይህ ሕግ ለአውሮፓ አይሠራም። ምክንያቱ ደግሞ ለአውሮፓ የተሰጠው ኮታ ከፍ ማለቱ ነው። ብራዚል፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይና ስፔን የዓለም ዋንጫን ለማንሳት ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው አገራት መካከል ናቸው። የኳታር የሕዝብ ቁጥር 2.9 ሚሊዮን ነው። ዕድሜ ለነዳጅ ምርቷ ይሁንና ኳታር ከባለፀጋ የዓለማችን አገርት መካከል ናት። ኳታር ለዓለም ዋንጫ ብላ ሰባት አዳዲስ ዘመናዊ ስታድዬሞች አቁማለች። ትንሿ አገር በዚህ አላበቃችም። የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ እንዲከናወንበት ብላ አንድ ከተማ ገንብታለች። ከ100 በላይ አዳዲስ ሆቴሎች፣ የባቡር ጣቢያ እንዲሁም መንገድ ለዓለም ዋንጫ በሚል የተገነቡ ናቸው። የዓለም ዋንጫ አዘጋጆች 1.5 ሚሊዮን ሰዎች ውድድሩን ለመታደም ዶሃ ይገባሉ ይላሉ። ኳታር ወግ አጥባቂ ሙስሊም አገር በመሆኗ ደጋፊዎች ባሕሪያቸውን እንዲያጤኑ ይመከራሉ። አንድ ቢራ እስከ 13 ዶላር [በአሁናዊ ገበያ 670 ብር] ሊሸጥ ይችላል። አልኮል መቅመስ የፈለገ ሰው ቅንጡ ወደሆኑ ሆቴሎች አቅንቶ ነው መጠቀም የሚችለው። አዘጋጆቹ ግን ደጋፊዎች እንደፈለጉ መጠጥ የሚጎነጩበት ሥፍራ እናሰናዳለን እያሉ ነው። ኳታር ውስጥ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ሕገ-ወጥ ነው። ለተመሳሳይ ፆታ ፍቅር እንሟገታለን የሚሉ ቡድኖች መንግሥታት ይህን እንዲቃወሙ ይጠይቃሉ። አንዳንድ የዌልስ ደጋፊዎች ደግሞ ወደ ዶሃ አንሄድም በማለት እየዛቱ ነው። የዓለም ዋንጫ አዘጋጆች ""ሁሉም ሰው መምጣት ይችላል"" ቢሉም ኳታር ግን በተመሳሳይ ፆታ ላይ ያላትን አቋም እንደማታላላ ግልጽ አደርጋለች።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c51wglqrq46o +business ከኑሮ ውድነት ጋር ግብ ግብ የገጠሙት የመንግሥት ሠራተኞች "ረድኤት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኝ የሥራ እድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት ውስጥ ሠራተኛ ነች። በዚህ ዘገባ ውስጥ የተካተቱ ሁለቱም የመንግሥት ሠራተኞች ስማቸው ተቀይሯል። ሥራቸውን እንዳያጡ ሰግተዋል። ትውልድ እና እድገቷ አዲስ አበባ ነው። ""ከቤተሰቤ ጋር ባይሆን በ 2700 ብር ደሞዝ ተቀጥሬ እንዴት እኖር ነበር?"" ስትል ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት የነበራትን የመነሻ ደመወዝ ትናገራለች። አሁን እንደምንም አምስት ሺህ ብር ይደርሳታል። በቅርቡ ትዳር ይዛ ከቤተሰቦቿ ቤት የወጣችው ረድኤት የቤት ኪራይ ወጪዋ ሰባት ሺህ ብር ነው። እቁብም ትጥላለች፤ ሦስት ሺህ ብር። ይህ ከምግብ፣ ከጤና ከድንገተኛ ወጪዎች ውጪ ነው። ""ከባለቤቴ ጋር ተጋግዘን ነው እንጂ ብቻዬን ብሆን እንዴት ይቻላል"" ትላለች። ""ደመወዝ ከተቀበልኩ በኋላ ከ15 ቀን በኋላ እጄ ላይ ገንዘብ አይቀርም"" ትላለች። በምትሰራበት የሥራ እድል ፈጠራ ቢሮ የሥራ እድል ተፈጥሮላቸው የገቡ አዲስ ሠራተኞች በተለይም ቤት ተከራይተው የሚኖሩ ባልደረቦቿ እጅግ ከባድ የሚባል ኑሮ እንደሚገፉ ትናገራለች። ""ለእነሱ ምንም ከምንም አይሆንም። በጣም ያሳዝነኛል። ኪራይ እና ምግብ ችለው ለመኖር በጣም በችግር ነው የሚኖሩት"" ስትል ረድኤት ታስረዳለች። በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛው ቀጣሪ እና የሥራ እድል ምንጭ መንግሥት ነው። የመንግሥት ሠራተኞች ቁጥር አንድ ሚሊዮን ከተሻገረ 10 ዓመት ሊሞላው ነው። እንደ የአለም ባንክ መረጃ ከሆነ የደርግ ስርዓት ሲወድቅ 300 ሺህ የማይሞሉ ከ 200 ሺ�� የማያንሱ የመንግሥት ሠራተኞች በኢትዮጵያ ነበሩ። ታዲያ ይህ ኃይል የዋጋ ግሽበት ወይም በተለምዶ የኑሮ ውድነት በሚባል ቀውስ ምክንያት እየተፈተነ ይገኛል። የዋጋ ግሽበት የገንዘብ የመግዛት አቅም ሲቀንስ የሚከሰት ነው። የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያሳየው እኤአ ከ 1970 እስከ 2019 ባለው ግዜ ውስጥ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት የተከሰተው በኢትዮጵያ ሚሌኒየም ወቅት ነበር። በወቅቱ የዋጋ ግሽበቱ 44 ነጥብ 4 ሆኖ ተመዝግቧል። እንዲሁም ደርግ በወደቀበት ዓመት የዋጋ ግሽበቱ 36 በመቶ ደርሶ እንደነበር የዓለም ባንክ መረጃ ያመላክታል። ከ 2005 ዓም ጀምሮ ለሶስት ዓመታት በአንድ ዲጂት ተወስኖ እና ተረጋግቶ የቆየው የዋጋ ግሽበት በ 2009 ዓ.ም አስር በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። በተለይ በመገባደድ ላይ ባለው ዓመት የተተኮሰው ግሽበት በተለይም የምግብ ምግብ ነክ ቁሶች ላይ የ 28̌ በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ይህንን ጭማሪ በቀላል ቋንቋ የሚያብራሩት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ተንታኙ አብዱልመናን መሃመድ «የመንግሥት ሰራተኞች ባለፈው ሁለት ዓመታት ብቻ የደመወዛቸውን 40 በመቶ ለዋጋ ግሽበት አስረክበዋል» ይላሉ። ይህ ማለት ከሁለት አመት በፊት 10 ሺህ ብር ደመወዝ የነበረው ሰው አሁን ላይ ባለው ግሽበት ሲሰላ ደመወዙ ወደ ስድስት ሺህ ብር አሽቆልቁሏል ማለት ነው። በመንግሥት መዋቅር ""የስራ ሂደት አስተባባሪ"" ማለት ዋና አለቃ ማለት ነው። ""የእነርሱ ደመወዝ ኪስ የሚሞላ፤ ተለቅ ያለ ነው"" ሲሉ ከስራቸው ያሉ ባለሞያዎች ያስባሉ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ባለ አንድ ተቋም ቡድን መሪ የሆነችው እመቤት ግን ""የያዝነው ቦታማ ትልቅ ነው፤ ግን እኛም በችግር ነው የምንኖረው"" ትላለች። እሷም የወር ደመወዟ 15 ቀን አይቆይላትም። እጇ ላይ 7500 ብር ቢደርስም አምስት ሺህ ብር ""በጣም ጠባብ"" ለምትላት ባለ ሁለት ክፍል ቤቷ ትከፍላለች። ሁለት ልጆች አሏት። ""ቀነስ ያለ ትምህርት ቤት"" ፈልጋ በወር 750 ብር ለአንድ ልጅ ትከፍላለች። ልጁን የሚያመላልስ ሰርቪስም ከፍያ ይጠይቃል። ""የመንግሥት ሠራተኛ ከሆንሽ ልጅሽን የሚይዝ ሞግዚት ያስፈልጋል። የዘይት፣ የጤፍ ዋጋ ሰማይ ነው። ምን ያልተወደደ ነገር አለ?"" በማለት ""መኖር አዳግቶኛል"" ስትል እመቤት ኑሮዋን ትገልጸዋለች። ከስምንት ዓመት ጀምሮ ቤት ለማግኘት ብትቆጥብም ህልም ሆኖ መቅረቱም ያስቆጫታል። ነገር ግን ደመወዝ ይጨመር ይሆን ብላ ትጠብቃለች። ረድኤትን እና እመቤትን የሚያስማማቸው አንድ ነገር አለ። በትምህርታቸው ለመግፋት ቢያቅዱም በገቢ እጥረት ምክንያት ትተውታል። ረድኤት እንደውም ጀምራ መክፈል ሲያቅታት ትታዋለች። እንደ እመቤት ሁሉ ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች የላባቸውን ውጤት ለዋጋ ግሽበት ሲያስረክቡ ውጤቱ አሳሳቢ መሆኑን የኢኮኖሚ ተንታኙ አብዱልመናን ይናገራሉ። ""ይህ በኑሮ ደረጃ ላይ ከፍተኛ ጫና አለው። በተጨማሪም በሥራቸው ላይ ተነሳሽነት እና ደስታ ወይም እርካታ ማጣት ያጋጥማቸዋል። ይህ ለዝቅተኛ አፈጻጸም ብሎም ለሙስና በር ከፋች ነው"" ሲሉ ባለሞያው ያብራራሉ። ለበርካታ ዓመታት የኑሮ ውድነቱ መሰረት የንግድ ሰንሰለቱ እንደሆነ ባለሞያዎች በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል። ይህም በተለይ ምርት ከገበሬው እስከ ሸማቹ እስከሚደርስ ባለው ሠንሰለት መሃል ያሉ ደላላዎችን ተወቃሽ ያደረገ ነበር። መንግሥት በተለይም ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች ላይ የሚታየውን ጭማሪ «ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለው፣ የጥቂቶች አሻጥር» ሲል በተደጋጋሚ ይሰማል። ከሁለት ዓመታት በፊት ጀምሮ በ 2013 የተባባሰው ግሽበት ግን ምክንያቶቹ ከተለመደው የዘለሉ እንደሆኑ የኢኮኖሚ ባለሞያው አብዱል መናን ይናገራሉ። ""አሁን ያጋጠመው የዋጋ ግሽበት ዋና መሰረቱ ብር ከሌሎች የውጪ ገንዘቦች አንጻር ዋጋው እንዲቀንስ በመደረጉ ምክንያት ነው። እንግዲህ ይህ የሆነው ለአስርት ዓመታት በዋጋ ግሽበት ሲናጥ ብሎም በፖለቲካ ያለመረጋጋት ውስጥ ባለ ኢኮኖሚ ላይ ነው"" ሲሉ አዲስ ያሉትን ምክንያት ያብራራሉ። ይህ እንዲቆም ካስፈለገም መንግሥት የብርን ዋጋ የመቀነስ ፖሊሲውን ማቆም አለበት ሲሉም አብዱልመናን ይመክራሉ። እንዲሁም የባንኮችን ተቀማጭ ገንዘብ በመጨመር እና በሂደት የቁጠባ ወለድን ከፍ ማድረግን ጨምሮ የገንዘብ ፖሊሲውን ቆንጠጥ ማድረግ ችግሩን ያቃልለዋልም ይላሉ። ገንዘብ ዋጋ ለማጣቱ ምክንያት ከሚባሉት ነገሮች መካከል አንዱ መንግሥት እንዳሻው ከብሔራዊ ባንክ በመበደር ፈሰስ ማድረጉ ነው። ይህ ክስም አላግባብ የብር ኖት በማተም ኢኮኖሚው ውስጥ መክተት ሌላው ለዋጋ ግሸበቱ መሰረት እንደሆነ በባለሞያዎች ለአመታት ሲነሳ የቆየ ምክንያት ነው። አብዱልመናን ይህንን ችግር ለመቆጣጠር ቁልፍ የሚሉት ሌላው መፍትሄም ይሄንን ይመለከታል። ""መንግስት ከብሔራዊ ባንክ የሚበደረውን ገንዘብ መጠን መቀነስ ይገባዋል"" ሲሉ ያክላሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-58215116 +politics ባልደራስ አቶ እስክንድር ነጋ በእስር ቤት 'የደኅንነት ስጋት ገጥሞታል' አለ "አዲስ አበባ በሚገኝ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፕሬዘዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ""ደኅንነታቸው አደጋ ላይ ወድቋል"" ሲል ፓርቲያቸው ስጋቱን ገለጸ። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ገለታው ዘለቀ፤ አቶ እስክንድር ቃሊቲ ከሚገኘውና በተለምዶው 'ዋይታ' ተብሎ ከሚጠራው የማረሚያ ቤቱ ክፍል ወይም ዞን ወደ ሌላ እንዲዘዋወሩ በመደረጉ ስጋቱ መፈጠሩን ለቢቢሲ ገልጸዋል። አቶ ገለታው በስም ያልጠቀሷቸው ""ከእስር ቤቱ ውጪ ያሉ"" ባሏቸው ወገኖች አማካይነት ""በተቀናጀ ዘመቻ"" ምክንያት አቶ እስክንድር ወደ ዞን ስምንት እንዲዘዋወሩ መደረጋቸውን ገልጸዋል። ይህ ሁኔታ የተከሰተው ፓርቲው በእስር ላይ የሚገኙ አመራሮቹና አባላቱ በመጪው ምርጫ ላይ በዕጩነት እንዲቀርቡ የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ መሆኑንም አቶ ገለታው ተናግረዋል። በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ በሚገኘው 'ዋይታ' ተብሎ በሚታወቀው ዞን ውስጥ ስምንት ሰዎች እንደሚገኙ የጠቀሱት አቶ ገለታው፤ አቶ እስክንድር አሁን የሚገኙበት ዞን ከቀደመው የተለየ መሆኑንና የደኅንንት ስጋት እንደገጠማቸው ተናግረዋል። ጨምረውም ""አቶ እስክንድር ከእስረኞች ማስፈራሪያ እና ማስጨነቅ ደርሶባቸዋል"" በማለት የፓርቲው ፕሬዝዳንት ባሉበት የእስር ቤት ክፍል ውስጥ የገጠማቸውን ችግር አመልክተዋል። አቶ እስክንድር አሁን ያሉበት ዞን ስምንት በከፍተኛ ወንጀል ተጠጥረው የታሰሩ ሰዎች የሚታሰሩበት መሆኑን የገለጹት አቶ ገለታው፤ ""እስክንድር ተቸግሬአለሁ ብሎ አያውቅም፤ ቢብስበት ነው ከዋይታ ለመውጣት ያመለከተው። አሁን ግን የባሰ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው"" ሲሉ አክለዋል። አቶ እስክንድር ለደኅንነታቸው ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው፣ እስካሁን ግን ምንም አይነት አካላዊ ጥቃት እንዳልደረሰባቸው ጠቅሰው፤ ""[የጥቃት] ሙከራ እንደተደረገባቸው እና ከአንድ የማረሚያ ቤቱ የጥበቃ ኃላፊ ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው እንደተነገራቸው ገልጸዋል"" ብለዋል አቶ ገለታው። ያለው ሁኔታ ""ለሕይወቴ አደጋ እደሆነ ከጠባቂዎች ተነግሮኛል፤ እኔም ይህንን ታዝቤአለሁ"" በሚል አቶ እስክንድር እንደነገሯቸው አቶ ገለታው አክለዋል። ይህንንም በተመለከተ ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ጋር መፍትሄ ለመፈለግ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን አመልክተው፤ ዛሬም ለማረሚ�� ቤቱ ደብዳቤ ጽፈው እንደሚያስገቡ ተናረግዋል። ቢቢሲ በዚህ ጉዳይ ላይ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረገው ጥረት ስልካቸው ባለመነሳቱ ሳይሳካለት ቀርቷል። በተያያዘ ዜና በእስር ላይ ያሉት ከፍተኛ አመራሮችና በመጪው ምርጫ እጩ የሆኑት ተወዳዳሪዎች የሆኑት እነ አቶ አስክንድር ነጋ ያለመከሰስ መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲለቀቁ ጠበቆቻቸው ጠይቀዋል። ጠበቆቻቸው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ፍትኃብሔር ቸሎት በትናንትናው ዕለት ሰኔ 1፣ 2013 ዓ.ም ባስገቡት የአቤቱታ ደብዳቤ ነው ይህንነ የጠየቁት። በአቤቱታ ደብዳቤው መሰረት የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ፣ አስቴር ስዩም ፣ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ ለመጪው ምርጫ እጩ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የምርጫው ውጤት እስኪታወቅ ድረስ በእስር መቆየት ስለማይችሉ በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታሉ ጠይቀዋል። አዲስ ነገር አለ በሚል ከመደበኛው ቀጠሮ በፊት የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ጉዳያቸው በውጪ ሆነው እንዲከታተሉ መጠየቃቸው በደብዳቤው ላይ ሰፍሯል። አመራሮቹ ያለመከሰስ መብታቸው ተጠብቆ ክሱ ተቋርጦ ከእስር እንዲለቀቁ ለፍርድቤቱ የቀረበው አቤቱታ ላይ ዐቃቤ ሕግ መልስ እንዲሰጥበት ለዓርብ ሰኔ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ቀጠሮ እንደተሰጠ የባልደራስ የሕግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሄኖክ አክሊሉ መግለፃቸው በፓርቲው ማህበራዊ ትስስር ገፅ ሰፍሯል። አቶ እስክንድር ነጋና ሌሎች የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላት ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በታዋቂው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ከተፈጸመ በኋላ ከተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ ይገኛሉ። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከጥቂት ወራት በፊት በእስር ላይ የሚገኙት አባላቱ በዚህ ወር በሚካሄደው ምርጫ ላይ ዕጩ ሆነው እንዲቀርቡ ምርጫ ቦርድን ጠይቆ ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ታሳሪዎቹ በዕጩነት እንዲመዘገቡ መወሰኑ ይታወሳል። በእስር ላይ ሆነው ፓርቲውን ወክለው በዕጩነት ከተመዘገቡት አባላቱ መካከል አቶ እስክንድር አንዱ ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/news-57397740 +sports ኢንተር ሚላን የማንችስተር ዩናይትዱን ጄሲ ሊንጋርድ ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተነገረ በዘንድሮው የጥር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ክለቦች የሚያተኩሩባቸውን ተጫዋቾች እየጠቀሱ ነው። ምንም እንኳ እስካሁን በዝውውሩ ስማቸው የሚነሳ ትልልቅ ተጫዋቾች ቁጥር አናሳ ቢሆንም በርከት ያሉ ተጫዋቾች ግን በዝውውሩ ክለብ የቀይራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የጣሊያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን፤ የማንችስተር ዩናይትድና የአንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የሆነውን የ28 ዓመቱን ጄሲ ሊንጋርድን ለመውሰድ ፍላጎት ማሳየቱን ሚረር ዘግቧል። ይህ የሚሆነው ግን ኢንተር ሚላን ዴንማርካዊው ክርስቲያን ኤሪክሰንን ካሰናበተ ነው ተብሏል። ሌላኛውን የዩናይትዱን አማካይ ፖል ፖግባን ደግሞ የፓሪስ ሴይንት ዠርሜኑ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቺቲኖ አጥብቀው እንደሚፈልጉት እና ቡድናቸውንም በ27 ዓመቱ ፈረንሳያዊ አማካይ ላይ መመስረት እንደሚፈልጉ ዴይሊ ስታር መረጃ ደርሶኛል ብሏል። ሜይል እንደጻፈው ከሆነ የአር ቢ ሌፕዚጉን ፈረንሳያዊ ተከላካይ ዳዮት ኡፓሜካኖ ለማስፈረም የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ውድድሩ ውስጥ ገብቷል። ይህንን ተጫዋች ማንችስተር ዩናይትድም እንደሚፈልገው ማንችስተር ኢቭኒንግ ኒውስ ዘግቧል። ላለፉት ወራት ከቡድን ስብስቡ ውስጥ ያልተካተተው የአርሰናሉ አማካይ ሜሱት ኦዚል፣ ምናልባት ወደ ቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ ሊያመራ እ���ደሚችል ሰን ጽፏል። የ32 ዓመቱ ኦዚል በአርሰናል ቆይታው ሊኖረው የሚችለውን 350 ሺህ ሳምንታዊ ደመወዙን ለሦስት ዓመታት ተቀናንሶ እየተከፈለው ወደ ፌነርባቼ ሊያመራ ይችላል ተብሏል። ሌላኛው የአርሰናሉ አማካይ ሉካስ ቶሬራ ወደ ፊዮረንቲና ሊያመራ እንደሚችል የስፔኑ ሙንዶ ዲፖርቲቮ ዘግቧል። የ24 ዓመቱ ኡራጓያዊ አማካይ፣ ለስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ በውሰት ተሰጥቶ እየተጫወተ ቢቆይም እንደታሰበው ስኬታማ አልሆነለትም ተብሏል። ፉትቦል ኢንሳይደር እንደዘገበው የሊዮኑ ፈረንሳያዊ አጥቂ ሙሳ ደምበሌ ከዌስትሃም የቀረበለትን የጥር ወር ዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። ከአሁን በፊት ለሴልቲክ የተጫወተው ፈረንሳያዊው አጥቂ ምናልባትም የስፔኑን አትሌቲኮ ማድሪድ ለመቀላቀል ሳይቃረብ እንዳልቀረ የስፔኑ ማርካ ጋዜጣ አስነብቧል። ብራዚላዊው የማንችስተር ሲቲ አማካይ ፈርናንዲንሆ ከሲቲ ጋር ያለው ኮንትራት በውድድር ዓመቱ ይጠናቀቃል። በመሆኑም የ35 ዓመቱ ተጫዋች ወደ አገሩ ብራዚል ወይም ወደ ሌሎች የአውሮፓ ክለቦች ሊሄድ እንደሚችል ጎል አስነብቧል። ቱቶ መርካቶ እንደሚለው ደግሞ ግሪካዊውን የአርሰናል የመሃል ተከላካይ ለማስፈረም ጂንዋ ከስፔኑ ሪያል ቤቲስ ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል ተብሏል። ዌስትሃም ሴኔጋላዊውን የ22 ዓመት የዋትፎርድ አጥቂ እስማየላ ሳርን ለማስፈረም 30 ሚሊዮን ፓውንድ ማዘጋጁን ሰን ሰምቻለሁ ብሏል። የዌስትሃም አለቃ ዴቪድ ሞይስ የሪያል ማድሪዱን የፊት መስመር ተሰላፊ የ27 ዓመቱን ማሪያኖ ዲያዝን በውሰት ለማምጣት ፍላጎት እንዳላቸውም ሜይል ዘግቧል። https://www.bbc.com/amharic/news-55608009 +health “እስክሞት ልታገል”፡ የኩላሊት ህሙማን መርጃ ያቋቋመው የኩላሊት ታማሚ "የህክምና ምርመራ ውጤት! ሕይወታችንን ባላሰብነው፣ ባልጠበቅነው መንገድ ይገለባብጣል። ለኢዮብ ተወልደመድኅን ያ ክፉ ጊዜ ጥቅምት 2006 ዓ.ም ነበር። የኩላሊት ታማሚ እንደሆነ ሐኪሞች ሲገሩት። የሁለት ሴት ልጆች አባት የሆነው ኢዮብ ይህን ዜና ሲሰማ የሚገባበት ጠፋው። ባለቤቱ በድንጋጤ ከፍተኛ ሐዘን ተጫናት። አዲስ አበባ ውስጥ የተክለሐይማኖት ሰፈር ልጅ ነው። ከ1979 ዓ. ም. ጀምሮ ግን ለአምስት ዓመታት አሰበ ተፈሪ ኖሯል። ዘጠነኛ ክፍልን አብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት ተምሮ 10ኛ ክፍል ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት በማታ ፈረቃ ገባ። የግድ ታናናሾቹን ማሳደግ ስለነበረበት ከ11ኛ ክፍል በላይ መቀጠል አልቻለም። ትምህርቱን አቋርጦ እንጨት ሥራ ያዘ። በእንጨትና አልሙንየም ሥራ ተቀጥሮ ለሦስት ዓመታት ሠራ። ጥሩ ገቢ ያገኝ ስለነበር ታናናሽ ወንድሞቹን፣ እናትና አባቱንም ያስተዳድር ጀመር። 1991 ዓ.ም. ላይ ከብድርና ቁጠባ ተቋም አነስተኛ ገንዘብ ተበድሮ ቤቱ የእንጨት ሥራ ከፈተ። ገቢው እያደገ መጣ። ንግዱ ሲጦፍ ከመንግሥት ቦታ ወስዶ እንጨት ሥራውን አስፋፋ። በልደታ ክፍለ ከተማ በከፈተው እንጨት ቤት ሙያውን ያስተምርም ነበር። ጥቅምት 2006 ዓ.ም. ላይ የኩላሊት ህመም አለብህ ሲባል ግን ነገሮች መስመር ሳቱ። ሥራውን ወዲያው አላቋረጠም። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከበደው መምጣቱ ግን አልቀረም። ከታመመ ከሁለት ዓመት በኋላ አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከጥቃቅንና መካከለኛ የንግድ ሰዎች አንዱ ብሎ ሸልሞታል። የኩላሊት ህመም አቅም ይነሳል። አካልን፣ ሥነ ልቦናን፣ ቤተሰብን፣ ጓደኛን፣ ሥራን ይፈትናል። ኢዮብ የገጠመውም ይኸው ነው። የኩላሊት ህክምና እድሜ ልክ የሚወስድ፣ ገንዘብንም የሚያሟጥጥ እንደሆነ ሲገነዘብ የባለቤቱና የሕጻናት ልጆቹ እጣ ፈንታ እንቅልፍ ነሳው። ቤተሰቤን ድሃ አድርጌ ከምሞት ምነው እኔው ቀድሜ ብሞት ሲል ያስብ እንደነበር ይናገራል። በአንድ ወር ውስ�� የኩላሊት እጥበት [ዳያለሲስ] ካላደረገ እንደሚሞት ሲነገረው ቤተሰቡና ጓደኞቹ ተረበሹ። በአፋጣኝ ኮርያ ሆስፒታል ወስደውት የኩላሊት እጥበት ጀመረ። ህመሙም ጋብ አለለት። ያኔ ሆስፒታሉ ውስጥ ያየው ነገር የሕይወት አቅጣጫውን እንዲቀይር እንዳደረገው ያስታውሳል። ""አቅም የሌለው፣ መካከለኛ ገቢ ያለው፣ ባለ ሀብት ታካሚም አለ። ልዩነቱ በግልጽ ይታያል። በርካቶች ህክምናውን ለማድረግ አቅም አልነበራቸውም። እኔ ታክሜ ነጻነት ሳገኝ ለምኖ ያልሞላለት ሰው ግን ምን ያህል ነጻነቱን ያጣል? ስል አሰብኩ።"" ለወራት የኩላሊት እጥበት ሲያደርግ የህክምናው ወጪ ከብዷቸው የሚያቋርጡ እንዳሉ ይሰማ ነበር። ወጪው ከአቅማቸው በላይ ሆኖ የሚሞቱትንም ቤቱ ይቁጠራቸው። ""እስክሞት ልታገል"" ኩላሊት መሥራት ሲያቆም የኩላሊት እጥበት ማድረግ ግዴታ ነው። ህመሙ የሌለባቸው ሰዎች ሰውነታቸው ውስጥ የሚከማች ቆሻሻን ሽንት በመሽናት ያስወግዳሉ። ታማሚዎች የኩላሊት እጥበት ካላደረጉ ቆሻሻው አይወጣም ማለት ነው። እናም ሰውነታቸው ይታፈናል፣ ያብጣል፣ ሲከፋም ሕይወታቸውን ያጣሉ። በሳምንት ሦስቴ የኩላሊት እጥበት ማድረግ የሚጠበቅበት ሰው በሳምንት አንዴ ብቻ ቢያደርግ ወይም ቢያቋርጥ ይህ መታፈን ይገጥመዋል። ምግብ መብላትም አይችልም። ኢዮብ በህመሙ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎችን ሲያይ በቀረኝ ሕይወት የአቅሜን መርዳት አለብኝ ብሎ ወሰነ። ህሙማን የገንዘብ እርዳታ የሚያገኙበት እና መንግሥት ከህመሙ ጋር በተያያዘ የሚያወጣቸው ውሳኔዎች ላይ ጫና ማሳደር የሚቻልበት ማኅበር አቋቋመ። 'ሞት በኩላሊት ይብቃ' የተጀመረው በ2007 ዓ.ም. ነው። በታመመበት ጊዜ በመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት አልነበረም። በግል ሆስፒታልም በውስን ቦታ፣ በውድ ገንዘብ ይከናወናል። ህክምናውን ለማግኘት የሚደረገው ጥረት አሁንም ድረስ ከባድ ነው። በመንግሥት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት በአንድ ዙር 500 ብር ያስከፍላል። በግል ሆስፒታሎች ደግሞ ከ1500 እስከ 3500 ብር ያወጣል። ""መሞቴ አይቀርም እስክሞት ልታገል ብዬ ወሰንኩ። ለመንግሥት አካላት እና ለአንዳንድ ተቋማት ድምጼን ማሰማት ጀመርኩ። በመኪና እየዞሩ መቀስቀስ፣ ብሮሸር መለጠፍም ቀጠልኩ። ይኸው 8 ዓመት ኖርኩኝ። በጥቂት ቦታም ቢሆን በመንግሥት ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ተጀምሯል። ይሄ በኩራት የምናገረው የልፋቴ ውጤት ነው።"" ማኅበሩ ከምስረታው ጀምሮ ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ120 በላይ ህሙማንን ደግፏል። ቁጥሩ ለቀን፣ ለሳምንት፣ ለአንድ ወር ወይም ለሁለት ወር የኩላሊት እጥበት ገንዘብ የሚከፈልላቸውን ይጨምራል። ወርሀዊ መዋጮ በማድረግ እና በጉልበት ሥራ የሚደግፉ የማኅበሩ አባላት አሉ። ደበበ እሸቱ፣ ስዩም ተፈራ፣ ዳንኤል ተገኝ ታዋቂ የማኅበሩ አባላት ናቸው። ኢዮብ ""አምባሳደሮቻችን"" ይላቸዋል። ከ2007 ወዲህ ድጎማ ከተደረገላቸው ህሙማን መካከል አምስቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሞት በኩላሊት ይብቃ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በምኒሊክ እና በዘውዲቱ ሆስፒታሎች ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ ለሁለት ዓመት ነጻ የኩላሊት እጥበት ከሚሰጣቸው 105 ህመምተኞች አንዱ ኢዮብ ነው። ያቋቋመው ማኅበር ከያዛቸው ፕሮጀክቶች አንዱ የኩላሊት ህሙማን ተደራጅተው ሥራ እንዲሠሩ ከክፍለ ከተሞች ጋር መነጋገር ነው። ይህም ለህክምና ገንዘብ ሲሉ ጎዳና ወጥተው ለመለመን የተገደዱ ወገኖችን ለመደገፍ ያለመ ነው። ፕሮጀክቱን የጤና ሚንስትር እና የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ድጋፍ ሰጥቶት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለአንድ ህመምተኛ የሥራ እድል ተፈጥሯል። በሌሎች ክፍለ ከተሞችም እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ወ���ገን ባንክ ለህመምተኞች መርጃ ገንዘብ የሚሰበሰብበት ሳጥን ተቀምጧል። በቋሚነት በሳምንት ለአንድ ህመምተኛ የኩላሊት እጥበት ክፍያ የሚያደርጉ የማኅበሩ አባላት አሉ። ማኅበሩ በሰበሰበው ገንዘብ ሦስት ህሙማን የኩላሊት ንቅለ ተከላ የተደረገላቸው ሲሆን፤ ነጻ ህክምና የሚያገኙ እንዳሉም ይናገራል። ""ኢትዮጵያ ውስጥ የኩላሊት እጥበት ክፍያ ከፍተኛ ስለሆነ ከ70 እስከ 80 በመቶ ያሚሆነው የኩላሊት ህመምተኛ በሳምንት አንዴ ወይም ሁለት ቀን ነው የሚያደርገው"" ይላል። ማኅበሩ በሠራው ስሌት መሠረት አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ከ700 ያላነሱ የኩላሊት ህመምተኞች በግል ሆስፒታል ነው ህክምና የሚከታተሉት። ዝቅተኛ የሚባለውን የአንድ ዙር የኩላሊት እጥበት ወጪ 1500 ብር መክፈል የሚችሉ ውስን ናቸው። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጎዳና ላይና በየሐይማኖት ተቋማት ከመለመን ውጪም አማራጭ የለውም። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የኢዮብ ማኅበር የመዋጮ ፕሮጀክት ቀርጿል። ሐሳቡ በወር 10 ብር፣ በዓመት 120 ብር የሚያዋጡ አንድ ሚሊዮን ሰዎችን በማኅበሩ አባልነት መመዝገብ ነው። ፕሮጀክቱ ከሦስት ዓመት በፊት ሲጀመር ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጀምሮ፣ ታዋቂ ሰዎችና ሌሎች ሰዎችን ጨምሮ ወደ 3000 ሰዎችን መመዝገብ ተችሏል። ከአባላቱ የሚሰበሰበውን ገንዘብ የሚከታተል መተግበሪያ እያሠሩ ነው። ኢትዮ-ቴሌኮም አጭር የጽሑፍ መልዕክት (ኤስኤምኤስ) እየላከ ገንዘቡን ሰብስቦ በቀጥታ ወደ ጤና ሚንስትር እንዲያስገባ ለማድረግ ወጥነዋል። አንድ ሚሊዮን ሰዎች በወር 10 ብር፣ በዓመት 120 ብር ቢያዋጡ፤ በአንድ ዓመት በአጠቃላይ 120 ሚሊዮን ብር ይገኛል። ይህም ለነጻ የኩላሊት ህክምና እንዲውል እንደሚፈልግ ኢዮብ ይናገራል። ""ይህ ገንዘብ በመሀል ምንም ሂደት ሳይኖር ከቴሌ ወደ ጤና ሚንስትር በቀጥታ ስለሚገባ ተአማኒነት ይኖረዋል"" ይላል። ከጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር በጉዳዩ ላይ ከስድስት ወር በፊት እንደተነጋገረ ይገልጻል። ""ሚንስትሯ በሐሳቡ ደስተኛ እንደሆኑና ለመደገፍ ፍቃደኛ እንደሆኑ ነግረውኛል። ገንዘቡ ከቴሌ ወደ ጤና ጥበቃ በቀጥታ እንዲገባ እንደምንፈልግ ስነግራቸው የሕግ አግባቡን ልይ ብለዋል።"" የቀድሞው የጤና ሚንስትር ዶ/ር አሚር አማን ሐሳቡን ደግፈው የአባልነት መታወቂያ አውጥተዋል። የኢዮብ ውጥን ተሳክቶ በአንድ ዓመት 120 ሚሊዮን ብር ማግኘት ከተቻለ እስከ 500 ሰዎች ለዓመት በመንግሥት ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት በነጻ ያገኛሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲደግፏቸው ለማድረግ መልዕክት እንደላኩና እስካሁን እንዳላገኟቸው የሚናገረው ኢዮብ በድጋሚ ጥያቄ እንደሚያቀርብላቸው ገልጿል። ሐሳቡ እውን ከሆነ ""መዋጮው ኪስ አይጎዳም። ብንኖርም ባንኖርም ቋሚና ቀጣይ ይሆናል። ጤናማው ሰው የሚያዋጣው ገንዘብ ወደ ኋላ መገልገያው እንዲሆን የጤና መድኅን አካል ማድረግም ይቻላል"" ሲል ተስፋውን ይናገራል። እንደ ኩላሊት፣ ካንሰር እና ልብ ያሉ ህመሞች ህክምና ሊሰጥባቸው እየተገባ ብዙዎች የሚሞቱባቸው ናቸው። ምናልባትም እንዲህ ባሉ የረድኤት ፕሮጀክቶች ችግሩን መቅረፍ ይቻላል ብሎ ያምናል። ""ባለቤቴ- ጀግናዬ"" ኢዮብ ከመታመሙ በፊት ለራሱና ለቤተሰቡ ሕይወት መለወጥ የሚተጋ ሰው ነበር። አሁን ግን የብዙዎችን ኃላፊነት ለመሸከም መርጧል። የማኅበሩ መስራች፣ ሥራ አስኪያጅ ብቻ ሳይሆን ሹፌር፣ ቀስቃሽ፣ ገንዘብ ሰብሳቢ የሆነባቸውን ጊዜያት ያስታውሳል። ሥራውን ""ፈጣሪ እና ህሊናዬ የተደሰቱበት ስለሆነ ኩራት እና ደስታ ይሰማኛል"" ሲል ይገልጸዋል። ለስምንት ዓመታት የኩላሊት እጥበት ሲያደርግ ወገቡ እና እግሩ ላይ ጉዳት ስለደረሰበት በድጋፍ ነው የሚንቀሳቀሰው። እንደ ቀድሞው የማኅበሩን ሥራዎች እንዳያከናውንም አድርጎታል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የሰውነት ክብደቱ ከ56 ወደ 46 ኪሎ ቀንሷል። ብርታት ከሚሰጡት በዋነኛነት የሚጠቅሰው ""ጀግናዬ"" የሚላት ባለቤቱን ነው። ""በጤናማነቴ ጊዜ ያፈራሁትን ከ1.5 ሚልዮን ብር በላይ ለማኅበሩ ሳውል ነገ ይሞታል ብላ ቅር አላላትም። ብር አንሶን የልጆቼን መኖርያ ቤት ስሸጥ እሷ የነበረንን ንግድ ቤት በመሸጥ ሹፌር ሆና ልጆቹን አስተማረች። ለዛሬ አብቅታኛለችና ጀግናዬ ናት።"" ሲታመም የሩቅና የቅርብ ቤተሰብ፣ ጓደኛም በአብዛኛው እንደሸሸው ይናገራል። ከልጆቹ ጋር ሰፊ ጊዜ ባለማሳለፉ፣ እንዳሻቸው ባለማዝናናቱም ያዝናል። ከኩላሊት ታማሚዎች ጋር ስቴድየም ዙርያ፣ ባዛሮች ላይ እንዲሁም ወደ መንግሥትና የግል ተቋማት እየሄደ እርዳታ ለማሰባሰብ ይሞክራል። ህክምናውን ትቶ የማኅበሩን ጉዳይ የሚከታተልባቸው ጊዜያትም አሉ። የኩላሊት ህመም ""ሳቄን፣ ደስታዬን፣ እግሬን አሳጥቶኛል"" ይላል። ከዚህ በተቃራኒው ""እውነተኛ ታጋይና ለወገን ቶርቋሪ አድርጎኛል"" ሲል ያለበት ሁኔታ ይገልጻል። በእሱ ማኅበር ውስጥ ይረዱ ከነበሩ ህሙማን መካከል ኋላ ላይ በራሳቸው ማኅበር መስርተው መንቀሳቀስ የጀመሩ ሰዎች መኖራቸው ያስደስተዋል። ህሙማንን ሲረዳ ከሚያገኘው እፎይታ በተጨማሪ ቤተሰቡ ሐሴት ይሰጠዋል። ""ሁሌም ሚስቴና ልጆቼ የተቃጠልኩትን ማቀዝቀዣዎቼ ናቸው"" ይላቸዋል። ሐኪሞች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ እንዳለበት ነግረውታል። ኩላሊት የሚሰጠው የቤተሰብ አባል ቢያገኝም የወጪው ነገር አሳሳቢ ነው። የማኅበሩ ስኬት ከሚላቸው መካከል ብዙ ገንዘብ ባይኖራቸውም ለህሙማን ገንዘብ ለመለገስ የሚፈቅዱ ሰዎች ማግኘታቸውን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን የሚያስደነግጥ ምስል ወይም የተጎዳ ሰው ቁስል ካልታየ በስተቀር በማኅበረሰቡ ዘንድ እምብዛም ሰዎችን የመርዳት ተነሳሽነት እንደሌለ አስተውሏል። የተጎዱ ሰዎችን ለይቶ በቀጥታ የመርዳት ልማድ ባለመኖሩ ማኅበረሰቡ እርዳታ የሚሰጠው ባገኘው አጋጣሚ፣ በየመንገዱ ለሚያገኘው ገንዘብ ጠያቂ ነው። ይህም በእርዳታ ስም የሚያጭበረብሩ እንዲበራከቱ መንገድ እንደከፈተም ያምናል። ሰዎች ባላቸው አቅም ተጎጂዎችን በእቅድ የመርዳት ባህል እንዲዳብሩ ይመኛል። የኩላሊት ህክምና በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሕግ አንድ ሰው ኩላሊቱ መሥራት ካቆመ ከቤተሰቡ ውጪ ኩላሊት ከሌላ ሰው መውሰድ አይችልም ይላል። ይህ ሕግ ቤተሰብ የሌላቸው ወይም ከቤተሰቦቻቸው ጋር የደም አይነታቸው የማይመሳሰል ሰዎችን ሕይወት አደጋ ውስጥ ጥሏል ይላል። ዘመድ፣ አብሮ አደግ ወይም ሌላ ለጋሽ ኩላሊት የሚሰጥበት አሠራር እንዲዘረጋ ለጤና ሚንስቴር ማሳሰቡንም ኢዮብ ይናገራል። ሌላው ክፍተት የኩላሊት ንቅለ ተከላ የሚከናወነው በጳውሎስ ሆስፒታል ብቻ መሆኑ ነው። ይህ አገልግሎት ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መነሳት ወዲህ መቋረጡም ሌላ ችግር ነው። በሌላ በኩል ንቅለ ተከላ ያደረጉ ሰዎች የመድኃኒት እጥረት ይገጥማቸዋል። የኩላሊት እጥበት የሚያደርጉ ሰዎችም እንዲሁ ተጓዳኝ የሰውነት መጠገኛ መድኃኒቶች ያጣሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ መድኃኒቶቹን ማግኘት ከባድ ነው። ያሉትም በጣም ውድ ናቸው። ኢዮብ ከታመመበት ከስምንት ዓመታት ወዲህ ብዙ ነገሮች እየተሻሻሉ መምጣታቸውን አይክድም። ""ትላንት የነበረውን ጨለማ ስለማውቀው የዛሬው የተሻለ ነው እላለሁ"" ይላል። ሆኖም ግን አሁንም ያሉ ክፍተቶች እንዲሸፈኑ ይጠይቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58126744 +health ኮሮናቫይረስ፡ በካናዳ አንዲት ጨቅላ ሕጻን ጭምብል ባለማጥለቋ በረራ ተሰረዘ "ነገሩ አስገራሚ ነው፡፡ በካናዳ አንዲት ጨቅላ ��ጻን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ባለማድረጓ ብቻ ፖሊስ ተጠርቷል፣ በረራውም ተሰርዟል፡፡ ሕጻኗ ከተወለደች ገና 19 ወሯ ነው፡፡ ዌስት ጄት ደግሞ ሁሉም ተሳፋሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማጥለቅ እንዳለባቸው ያሳስባል፡፡ ጨቅላዋ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሲደረግላት እሪታዋን ታቀልጠዋለች፡፡ ብትባል ብትሰራ እምቢኝ ትላለች፡፡ እናትና አባት ያልሞከሩት ነገር የለም፡፡ ሕጻኗ ሞቼ እገኛለሁ አለች፡፡ የአየር መንገዱ አስተናጋጆችና ቤተሰብ አንድ ሁለት ሲባባሉ ነገሩ ተካሮ በረራ እስከመሰረዝ ደርሷል፡፡ አየር መንገዱ ግን ታሪኩ ሌላ ነው ይላል፡፡ የ19 ወር ጨቅላዋ አይደለችም ችግር የፈጠረችብኝ ብሏል ዌስትጄት፡፡ እንዲያውም በሷ ደረጃ ያሉ ሕጻናት ጭምብል እንዲያጠልቁም አይገደዱም ብሏል፡፡ ታዲያ ለምን በረራውን ሰረዛችሁ ሲባል ሌላ የጨቅላዋ ታላቅ እህት አለች፤ 3 ዓመቷ ነው፡፡ እሷ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አጥልቂ ስትባል እምቢ በማለቷ ነው በረራውን እንድንሰርዝ የተገደድነው ብሏል፣ ዌስትጄት፡፡ የሕጻናቱ እናትና አባት፣ እንዲሁም ተሳፋሪዎች ግን"" ዌስትጄት ቀጣፊ ነው፣ ዋሽቷል፤ የ3 ዓመቷ ልጅ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጋ ነበር ሲሉ ""ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ግርግር በሞባይል የተቀረጸ ቪዲዮም የ3 ዓመቷ ልጅ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጋ ነው የምትታየው፡፡ ፖሊስም በበኩሉ እኔ ስደርስ ታላቅየው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጋ ነበር ብሏል፡፡ ይህ የሆነው ማክሰኞ ነው፤ ከትናንት በስቲያ፡፡ በረራው ከካልጋሪ ተነስቶ ቶሮንቶ የሚደርስ ነበር፡፡ በረራ 652 ግን ከመነሻው ሳይሳካ ቀርቶ ሁሉም ተሳፋሪዎች ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ተደርገዋል፡፡ የልጆቹ አባት አቶ ኮድሀሪ እንዲህ ዓይነት ጉድ በፍጹም ያጋጥመኛል ብዬ በሕልሜም በእውኔም አስቤም ጠብቄም አላውቅም ብሏል ለቢቢሲ፡፡ ‹‹እኔና ባለቤቴ ከሁለቱ ሴት ልጆቻችን ጋር ነበርን፤ አውሮፕላኑ ሊነሳ ሲል የሦስት ዓመቷ ልጄ ቁርስ ቢጤ እየበላች ነበር፡፡ የበረራ አስተናጋጇ መጥታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንድታጠልቅ ነገረቻት፡፡ እኔና እናቷ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርገናል፤ የ3 ዓመቷ ልጃችን ደግሞ እየበላች ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ ‹‹የበረራ አስተናጋጇ ዌስትጄት በአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጉዳይ ጥብቅ ፖሊሲ እንደሚከተልና ልጃቸው ቁርሱ መብላቷን ትታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ካላጠለቀች በረራው እንደማይደረግ ነገረችን›› ይላል አባት፡፡ ‹‹ልጆች ደግሞ በአንድ ጊዜ መታዘዝ እሺ ስለማይሉ ማባበል ጀመርኩ፡፡ የ3 ዓመቷ ልጄ ትንሽ ካስቸገረችን በኋላ እሺ ብላ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዋን አጠለቀች፡፡›› ‹‹ታናሽየው ግን እምቢኝ አለች፤ እንዲያውም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛውን ስናደርግላት ወደላይ አላት›› ይላል አባት፡፡ ‹‹ዌስትጄት ትእግስት አልፈጠረባቸውም፡፡ ትንሽዋ ልጄ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ስላላጠለቀች አውሮፕላኑ እንደማይበር ነገሩን፡፡›› እንዲያውም ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ እንደታዘዙና አንወርድም ካሉ ግን እንደሚታሰሩ እንደተነገራቸው ለቢቢሲ አስታውቋል፡፡ በዚህ ጊዜ ከአውሮፕላኑ ለመውረድ ተስማማን ብሏል አባት ለቢቢሲ፡፡ አባት በረራው ከተሰረዘ በኋላ ተረዳሁ እንደሚለው ከሆነ ‹‹በካናዳ ትራንስፖርት ፖሊሲ መሰረት የ19 ወሯ ጨቅላ ልጃቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማጥለቅ አትገደድም ነበር፡፡›› ዌስትጄት ባወጣው መግለጫ ግን በረራው የተሰረዘው የ19 ወሯ ጨቅላ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ስላላጠለቀች ሳይሆን የሷ ታላቅ የ3 ዓመቷ ህጻን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኗ ነው ብሏል፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-54098154 +sports አትሌቲክስ ፌደሬሽን፡ 'በ��ሊምፒክ የሚሳተፉ ሯⶐች የሚመረጡት በቴክኒክ ኮሚቴ ነው' አለ በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው በማራቶን የሚወደዳሩ አትሌቶችን የሚመርጠው ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ እንዲሆን ከስምምነት መደረሱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ። ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ በኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት በሆኑት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የሚመራ ሲሆን የአትሌቲክስ አሰልጣኞች የኮሚቴው አባላት ናቸው። ይህንን በሚመለከት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ማክሰኞ መግለጫ ሰጥቷል። የዛሬው መግለጫ የአትሌቲክ ፌዴሬሽን፣ የኦሊምፒክ፣ የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን እና ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር በጋራ ይሰጣሉ ተብሎ ነበር። ይሁን እንጂ ይህን መግለጫ የኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ብቻ እንዲሰጥ ከስምምነት መደረሱ በመግለጫው ተጠቅሷል። አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሚያዚያ 23 በሰበታ ከተማ በተካሄደው የማራቶን ማጣሪያ ውድድር የተሻለ ሰዓት ያስመዘገቡ አትሌቶችን ይፋ አድርጎ እንደነበረ ይታወሳል። ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በተካሄደው ማጣሪያ ከ1 እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁት አትሌቶች ሹራ ቂጣታ፣ ሌሊሳ ዴሲሳ፣ ሲሳይ ለማ እና ጫሉ ዳሶ መሆናቸው ይታወሳል። በሴቶች ደግሞ ትዕግስት ግርማ፣ ብርሀኔ ዲባባ፣ ሮዛ ደረጄ እና ዘይነባ ይመር የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። ፌዴሬሽኑ የማራቶን ተሳትፎ በቴክኒክ ኮሚቴው የሚወሰን ነው ከማለት ውጪ ሰበታ ከተማ ተካሂዶ በነበረው ማጣሪያ ውጤታ ያስመዘገቡ አትሌቶች እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ያለው ነገር የለም። በሌላ በኩል ይህ ማጣሪያ አግባባ አይደለም በማለት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በማጣሪያው ላይ ሳይሳተፍ መቅረቱ ይታወሳል። አትሌት ቀነኒሳ 2016 በተካሄደው የሪዮ ኦሊምፒክ ተሳታፊ እንዳልነበር አስታውሶ፤ በኦሊምፒክ መድረክ አገሬን እንዳልወክል በፌደሬሸኑ እየተከለከልኩ ነው ሲል ቅሬታ አቅርቦ ነበር። በማራቶን የሚወዳደሩ አትሌቶችን በተመለከተ የቴክኒክ ኮሚቴው ውሳኔ ወደፊት ይፋ እንደሚደረግም ተነግሯል። በሌላ በኩል ከ800 ሜትር እስ 10ሺህ ያሉ ወድድሮች ኢትዮጵያ ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶችን ለመምረጥ 73 አትሌቶችን የሚያሳትፍ ማጣሪያ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። ይህ የማጣሪያ ውድድር በስዊትዘርላንድ ሄንግሎ ከተማ ከአንድ ወር ገደማ በኋላ እንደሚካሄድና ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ብቻ የሚያሳትፍ መሆኑም ተጠቅሷል። በዚህ መሠረት በሄንግሎ በሴቶች እና በወንዶች የ800፣ 1ሺህ 500፣ 3ሺህ፣ 5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ማጣሪያዎች ይከናወናሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-57076979 +business ባይደን ለችግር ጊዜ ከተከማቸው ነዳጅ በርካታ ሚሊዮን በርሜል እንዲቀዳ አዘዙ "የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አሜሪካ ለችግር ጊዜ በሚል ካከመቻችው ነዳጅ በገፍ እንዲቀዳ አዘዋል። ፕሬዝደንቱ ይህን ትዕዛዝ ያስተላለፉት እየናረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ለመዋጋት ነው። ባይደን እንዲወጣ ያዘዙት 180 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ በማከማቻው ታሪክ ትልቁ ነው። ዩክሬን ባለው ጦርነት ምክንያት ጣራ እየነካ የነበረው የነዳጅ ዋጋ ከባይደን ትዕዛዝ በኋላ ትንሽ ረገብ ብሏል። ነገር ግን አሜሪካ በየቀኑ ለመከራ ጊዜ ካስቀመጠችው ነዳጅ አንድ ሚሊዮን በርሜል ብትቀዳም ችግሩን ሙሉ በሙሉ አይቀርፈውም ይላሉ የዘርፉ ሰዎች። ባይደን፤ ከማከማቻው እንዲቀዳ የታዘዘው ነዳጅ አሜሪካ ""የራሷን የነዳጅ ምርት እስክታሳልጥ ድረስ"" እንዲያግዝ በሚል ነው ብለዋል። ፕሬዝደንቱ ኩባንዎች ነዳጅን ከመንግሥት መውሰድ የመጨረሻ አማራጭ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ባይደን አረንጓዴ የኃይል ምንጭ የሚከተሉ ኩባንያዎች እንዲበረታ��� መክረዋል። በሚቀጥለው ኅዳር የግማሽ ዓመት ምርጫ ለማካሄድ ደፋ ቀና እያለች ያለችው አሜሪካን ጨምሮ የዓለም ሃገራት የኑሮ መወደድ እያማረራቸው ነው። ባይደን፤ ስትራቴጂክ ፔትሮሊዬም ሪዘርቭ ከተሰኘው የችግር ቀን ገንዳ ነዳጅ ለመቅዳት የወሰንነው ""ያለዕቅዳችን"" ነው ብለዋል። ይህ ግዙፍ የነዳጅ ማከማቻ ገንዳ የተመሠረተው በፈረንጆቹ 1974 ነው። ማከማቻው ቴክሳስና ሉዊዚያና መካከል በሚገኘው የገልፍ ኮስት ላይ በተንጣለለው የጨው ክምር አካባቢ ይገኛል። ይህ ገንዳ በፈረንጆቹ 2009 700 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ አቅፎ ነበር። ባለፈው መጋቢት ሲለካ ግን የነዳጅ ክምችቱ ወደ 568 ሚሊዮን በርሜል ወርዷል። አሜሪካ ከሳዐዲ ቀጥሎ ሁለተኛዋ ግዙፍ የነዳጅ አምራች ከሆነችው ሩሲያ ነዳጅ አልገዛም ካለች ወዲህ የነዳጅ እጥረት እያንገላታት ይመስላል። የነዳጅ ዋጋ መለከያ የሆነው ብሬንት ክሩድ ባለፈው የፈረንጆቹ ወር መጀመሪያ ዋጋ አሜሪካና አጋሮቿ ሩሲያ ላይ ማዕቀብ ከጣሉ በኋላ አሿቅቧል። ምንም እንኳ የኃይል ዋጋ ቀስ በቀስ ቢወርድም ነዳጅ ግን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዋጋው 70 በመቶ ጨምሯል። አሜሪካ ውስጥ እየናረ የመጣው ኑሮ ሪፐብሊካን ጮቤ እንዲረግጡ እያደረጋቸው ነው። የባይደን ተቃዋሚዎች የኑሮ ውድነቱን በባይደን አስተዳደር አላከዋል። አሁን ደግሞ ነዳጅ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዋጋው ሲያሻቅብ የባይደን አስተዳደርን ከድጡ ወደ ማጡ መርቷቸዋል። ባለፈው ሐሙስ ሩሲያን ጨምሮ የነዳጅ አምራች ሃገራት ማሕበሩ ኦፔክ አባላት የነዳጅ ምርታቸውን ለመጨመር ተስማምተዋል። የኃይል ዋጋ ከዩክሬን ጦርነት በፊትም ቢሆን የዓለም ምጣኔ ሃብትን ሊፈታተነው እንደሚችል ግምት ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-60950886 +politics በሆሮ ጉድሩ በታጣቂዎች የተገደሉ ሰላማዊ ነዋሪዎች ከ100 በላይ እንደሆኑ ኢሰመኮ ገለጸ በባለፉት ሳምንታት በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች የተገደሉ ሰላማዊ ነዋሪዎች ከ100 በላይ እንደሆኑ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። በሰላማዊነዋሪዎች ላይ ግድያውን የፈጸሙት መንግሥት ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ የአማራ ኢመደበኛ ታጣቂ ኃይሎችና ግለሰቦች ባደረሱት ተከታታይ ጥቃት መሆኑንም ኢሰመኮ በትናንትናው ዕለት መስከረም 16፣ 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። በዞኑ ኡሙሩ፣ ሆሮ ቡልቅ እና ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳዎች ከነሐሴ 25 ቀን 2014ዓ.ም ባሉት ሶስት ሳምንታት በደረሰው ተከታታይ ጥቃትም ከግድያ በተጨማሪ ዘረፋዎችም ተፈፅሟል ብሏል። የግል ንብረት እና የቁም ከብቶች በነዚህ ታጣቂ ኃይሎች ተዘርፈዋል ያለው ኢሰመኮ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለው ያለ በቂ እርዳታ በፈታኝ ሁኔታ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች በሰላማዊ ነዋሪዎች እና በአካባቢው የሚሊሻ አባላት ላይ ግድያ መፈጸማቸውን ገልጿል።   የመንግሥት መግለጫ ስለተገደሉት ሰዎች ብዛት ያለው ነገር የለም። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትም ሆነ የአማራ ኢ-መደበኛ ተብለው የተጠቀሱት ታጣቂዎች ስለ ጥቃቱ እስካሁን ያሉት የለም። በባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ኡሙሩ ወረዳ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰን ግድያ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ለመከላከል በትኩረት እንዲሰራ ማሳሰቡን አስታውሷል። ኮሚሽኑ እንዳለው ከነሐሴ 23 እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በታጣቂዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ60 በላይ ሰዎች መገደላቸውን፤ ከ70 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን እና ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጾ ነበር��� በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ተጨማሪ የጸጥታ ስጋት እስካሁን በመቀጠላቸውም በአካባቢው ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች ተስፋፍተው መቀጠላቸው እጅግ አሳሳቢ መሆኑንም ገልጿል። ኢሰመኮ በዚሁ መግለጫ ላይ መንግሥት የሲቪል ሰዎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታውን በአግባቡ መወጣት እንደሚኖርበትም አሳስቧል። “የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥታት በአካባቢው ብሔርን መሰረት አድርገው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል በመወሰድ ላይ የሚገኙትን እርምጃ ችግሩን በሚመጥን ደረጃ በማሳደግ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል” በማለት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ  አሳስበዋል። በአሁኑ ወቅት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈጽሞበታል የተባለውን የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞንን ጨምሮ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ይንቀሳቀስባቸዋል በሚባሉት የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ባለፉት ዓመታት ሰላማዊ ነዋሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና ባለሥልጣናት እንዲሁም ተቋማት ጥቃት ሲፈጸምባቸው ቆይቷል። በተለይ ካለፈው ዓመት አጋማሽ ወዲህ በአካባቢው ነዋሪ በሆኑ የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ተደጋጋሚ ጥቃቶች መፈጸማቸው ይታወሳል። በእነዚህ ጥቃቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር አባላት የተገደሉ ሲሆን በርካታ ኦሮሞዎችም በታጣቂዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ተገድለዋል። መንግሥት እና ከጥቃቶቹ የተረፉ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች የበርካቶችን ሕይወት ለቀጠፉት ጥቃቶች የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ተጠያቂ ሲያደርጉ ቡድኑ ግን ድርጊቱን ሲያስተባብብል ቆይቷል። በተከታታይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከተገደሉትና ጉዳት ከደረሰባቸው ነዋሪዎች ባሻገር በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንበረታቸው ተፈናቅለዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c2q4ex3k0n1o +sports በኮቪድ ምክንያት 11 ተጫዋቾች እንኳን ቢቀሩ ጨዋታ እንደማይሰረዝ ካፍ ገለጸ "በአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ሃገራት የኮቪድ1-9 ወረርሽኝ ቢያጋጥማቸውና 11 ተጫዋች ብቻ ቢቀራቸው እንኳ ጨዋታው እንደማይሰረዝ ካፍ ገልጿል። የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪው ካፍ ከአስራ አንዱ ተጫዋቾች አንዱም ግብ ጠባቂ ባይሆን ጨዋታው እንደማይሰረዝ አስታውቋል። ይህንን ማሟላት የማይችል ቡድን በተለምዶ ፎርፌ በሚባለው ሕግ መሠረት የ2-0 ሽንፈት ይጣልበታል ይላል ካፍ። ካፍ ይህንን ትዕዛዝ ያስተላለፈው ዛሬ ምሽት [እሑድ] ከሚጀምረው ውድድር በፊት በርካታ ሃገራት ተጫዋቾቻችን በኮቪድ ተይዘዋል ብለው ካማረሩ በኋላ ነው። ካፍ አክሎም ""ለየት ያለ ምክንያት"" ላላቸው ሃገራት የውድድሩ አጋጅ ኮሚቴ ""አስፈላጊውን ውሳኔ ይሰጣል"" ብሏል። ከሁሉም ቀድማ ካሜሩን የገባችው ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት የተወሰኑ ተጫዋቾቿ በኮቪድ ተይዘውባት እንደነበር ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቦ ነበር። ተጫዋቾችን ጨምሮ የአሠልጣኝ ቡድን አባላት በኮቪድ ተይዘው ለቀናት ካገገሙ በኋላ መመለሳቸውን ድረ-ገፁ ዘግቧል። ባለፈው አርብ ወደ ካሜሩን ማቅናት የነበረባት ግብፅ በኮቪድ ምክንያት ወደ አዘጋጇ ሃገር የምታደርገውን በረራ አራዝማ ነበር። አልፎም የግብፅ ብሔራዊ ቡድን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ልምምድ አለመሥራቱም ተሰምቷል። ዘጠኝ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን በማንሳት ክብረ ወሰን የጨበጡት ፈርዖኖቹ ቅዳሜ ዕለት ወደ ካሜሩን መብረራቸው ተሰምቷል። የአርሰናሉ አጥቂ ፒዬር-ኤሜሪክ ኦባሜያንግ በኮቪድ ከተያዙ ሁሉት የጋቦን ብሔራዊ ቡድን አባላት መካከል አንዱ ሆኗል። ጊኒ ደግሞ ተከላካዩ ሚካኤል ድሬስታምን፣ አማካዩ ሞርላዬ ሲላን እንዲሁም አጥቂው ሶማን ሩዋንዳ ጥላ ነው ወደ ካሜሩን ያቀናችው። ኬፕ ቨርድና ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የምትሳተፈው ጋምቢያ ባለፈው ሳምንት በርካታ ተጫዋቾቻቸው በኮቪድ መያዛቸውን ይፋ አድርገው ነበር። ቱኒዚያም እንዲሁም የተወሰኑ ተጫዋቾቿ በኮቪድ መጠቃታቸውን አሳውቃለች። ዛሬ ምሽት የሚጀምረው የአፍሪካ ዋንጫ በመጀመሪያው ጨዋታ አዘጋጇ ካሜሩን ከቡርኪና ፋሶ ሲያፋልም በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ ከኬፕ ቨርድ ትገጥማለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-59926712 +sports አርሰናል 5 ሲያስቆጥር፤ ዩናይትድ በዴ ሂያ ጥረት 3 ነጥብ ይዞ ወጥቷል ትናንት በተከናወኑ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች አርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። አርሰናል በኢሚሬትስ ስታዲየም በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ መጨረሻ ላይ የሚገኙትን ኖቲንግሃም ፎረስተን አስተናግደው አምስት ጎሎዎችን አከናንበዋቸዋል። ገብርኤል ማርቲኔሊ፣ ሪስ ኔልሰን፣ ቶማስ ፓርቴ እና ማርቲን ኦዴጋርስ ለአርሰናል ጎል ያስቆጠሩ ተጨዋቾች ናቸው። መድፈኞቹ በድንቅ የጨዋታ ብቃት ያገኙት ሦስት ነጥብ በ31 ነጥቦች በሊጉ መሪነት እንዲቀጥሉ አስቸሏቸዋል። የመጀረሚያውን ጎል ለገርኤል ማርቲኔሊ አመቻቸቶ ያቀበለው ቡካዮ ሳካ በመጀመሪያው አጋማሽ በጉዳት ምክንያት ተቀይሮ ወጥቷል። ቡካዮ ሳካ ያጋጠመው ጉዳት ዝርዝር ይፋ ባይደረግም ተጨዋቹን ከኳታር የዓለም ዋንጫ የሚያስቀረው አይሆንም ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። የአርሰናል ቁልፍ ተጫዋች የሆነው የ21 ዓመቱ ቡካዮ ሳካ፤ በጋርዝ ሳውጌት ቡድን አባል በመሆን ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር ወደ ኳታር ያቀናል ተብሎ ይገመታል። የ14ኛው ሳምንት የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች የተጠናቀቁት በማንችስተር ዩናይትድ እና ዌስት ሃም ግጥሚያ ነበር። ማርከስ ራሽፎርድ ለማንስተር ዩናይትድ ያስቆጠራት 100ኛ ጎል ቡድኑ ሦስት ነጥብ እንዲሰበስብ አስችላለች። ከራሸፎድ ጎል እኩል የግብ ጠባቂው ዴቪድ ዴ ሂያ ድንቅ አቋም ክለቡ ሦስት ነጥቦችን ማሳካት ችሏል። ዴቪድ ዴ ሂያ በጨዋታው ማጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ የዌስት ሃም ተከላካዩ ከርትስ ዙማ የጭንቅላት ኳስ እንዲሁም የሚካሂል አንቶኒዮን እና የደክለን ራይስ ጠንካራ ምት ግብ ጠባቂው ይህን አቋም ያሳየው በኳታር የዓለም ዋንጫ ለስፔን ብሔራዊ ቡድን አለመመረጡ በስፋት ከተዘበ በኋላ ነው። ባለፈው ሳምንት በርካታ የሰፔን ጋዜጦች  ዴ ሂያበእግሩ መጨዋት አይችልም በሚል በአሰልጣኝ ሉዊስ ኤነሪኬ ስብስብ ውስጥ አለመካተቱን ዘግበዋል። የስፔን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ከዴ ሂያ ይልቅ የብራይተኑን ሮበርት ሳንቼዝ፣ የብሬንት ፎርዱን ዴቪድ ራያ እና የቼልሲውን ኬፓ አሪዛባላጋን ይዘው ወደ ኳታር እንደሚያቀኑ የአገሪቱ ጋዜጦች በስፋት ዘግበዋል። የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ግን የግብ ጠባቂ ዋነኛ ስራ ጎል እንዳይቆጠር ማድረግ እንጂ በእግር የመጫወት ችሎታ አይደለም ሲሉ ግብ ጠባቂያቸውን ተከላክለዋል። “ሁሉም የራሱ አመለካከት አለው ለእኔ ግን ለግብ ጠባቂ የመጀመሪያው ነገር ጎሎች እንዳይቆጠሩ መከላከል ነው” ብለዋል። በሳምንት 375ሺህ ፓወንድ የሚከፈለው ዴ ሂያ የዓለማችን ከፍተኛ ተከፋዩ ግብ ጠባቂ እንደሆነ ይታመናል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2nk0077d3o +politics ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን ሒደቱ ተቀባይነት ያለው መሆን አለበት አሉ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “አካታች ብሔራዊ ምክክሩ” ስኬታማ እንዲሆን ሒደቱ ተቀባይነት ያለው ሆኖ መከናወን አለበት አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ መጋቢት 23/2014 ባወጡት መግለጫ ብሔራዊ ምክክሩ የፖለቲካ ፈተናዎቻችንን መቅረፍ የሚያስችለን ወርቃማ እድል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ብለዋል። “ይህን ወርቅ የሆነ አጋጣሚ . . . እንደ ዕንቁ አክብረንና ተከባክበን ከተጠቀምንበት ዋጋው ከፍ ያለና ታሪክ ቀያሪ ዕድል ይሆናል” ብለዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚደረግ ሂደትን የሚመራና የሚያስተባብር ኮሚሽን መመሥረቱ ይታወሳል። ይህ ኮሚሽን የተለያዩ አላማዎችን አንግበው በፖለቲካው መድረኩ ላይ ያሉ ኃይሎችን እንዲሁም ሕዝቡ ውስጥ ያሉ ጥያቄዎችን መሠረት በማድረግ ልዮነቶች ጠበው አገራዊ መግባባት ላይ አንዲደረስ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ ይታመናል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው መግለጫቸው የብሔራዊ ምክክሩ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ የምክክር ሂደቱን በበላይነት የሚመራውን የምክክር ኮምሽን በተለያዩ መንገዶች መደገፍ፣ ማትጋትና ማጽናት አለብን ብለዋል። “በዚህ ጉዳይ ዳር ቆሞ መገኘት በታሪክ ፊት የሚያስወቅስ ተግባር ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሁሉም በባለቤትነት ስሜት ለምክክር ሂደቱ አስተዋጽዖ ማድረግ አለበት ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አስተዳደራቸው የምክክር ኮሚሽኑ በቅልጥፍና መሥራት እንዲችል አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም ብለዋል። ተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የውይይቱ ተሳታፊ ብቻ ሳይሆኑ “የሂደቱ ባለቤት ለሂደቱ ቅልጥፍናና ስኬት አስፈላጊውን ሁሉ እንድታደርጉ በትኅትና እጠይቃለሁ"" ብለዋል። ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በዚህ የምክክር ሂደት ተሳትፎ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን 11 ኮሚሽነሮችን መሾሙ ይታወሳል። ምክር ቤቱ ከእነዚህ መካከል ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ እንዲሆኑ ሰይሟል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60954318 +business ቱርክ፡ ፕሬዝደንቱ የማዕከላዊ ባንክ ገዢውን ካባረሩ በኋላ የሃገሪቱ ገንዘብ 14 በመቶ ላሸቀ የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን የሃገሪቱን ማዕከላዊ ባንክ አስተዳደሪ ማበረራቸውን ተከትሎ የቱርክ መገበያየ ሊራ 14 በመቶ ላሸቀ። የቀድሞ የባንክ ገዢ ናሲ አግባል፤ ሊራ በጣም ዘቅጦ ከነበረበት ከፍ አድርገው ለዚህ ያበቁ ሰው ናቸው የሚል ሙገሳ ይቸራቸዋል። ነገር ግን ፕሬዝደንት ኤርዶዋን ሳይታሰብ ባለፈው ቅዳሜ ሰውዬውን አንስተው በሌላ ተክተዋቸዋል። ቱርክ የማዕከላዊ ባንክ አስተዳዳሪ ስታባርር በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይህ ሶስተኛው ነው። ባለፈው ኅዳር የተሾሙት አግባል ከ15 በመቶ በላይ እየሆነ የመጣውን የዋጋ ንረት ለማቀዛቀዝ የወለድ መጠንን ከፍ አድርገው ነበር። የሰውዬው መባረር የሃገር ቤትና የውጭ ኢንቨስተሮችን አስደንግጧል። አግባል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በወሰዷቸው እርምጃዎች በብዙዎች ዘንድ አድናቆት እንዲቸራቸው አድርጓቸው ነበር። ሊራ አንድ ወቅት ላይ በፈረንጆቹ 2021 አዳጊው የመገበያያ ገንዘብ ተብሎ ከአሜሪካ ዶላር ጋር ሲነፃፀር ያለውን ዝቅጠት በአምስት አሻሽሎ ነበር። ባለፈው ሳምንት ሰውዬው የወለድ መጠን 2 በመቶ እንዲጨምር ማድረጋቸውን ተከትሎ የቱርክ ሊራ ወደላይ ተመንድጎ ነበር። በሃገሪቱ መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ ባለሃብቶች ቱርክ ጠበቅ ያለ የገንዘብ ፖሊሲ እንድትቀርፅ ሲወተውቱ ቆይተዋል። አሁን ፕሬዝደንት ኤርዶዋን የማዕከላዊ ባንኩን አስተዳደር በሌላ ለመተካት በማሰባቸው ምክንያት የሊራ ዋጋ እንዳሽቆለቆለ ሊቀር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። አዲሱ የማዕከላዊ ባንኩ ኃላፊ የባንኪንግ ፕሮፌሰር ናቸው። አልፎም የገዢው ፓርቲ የቀድሞ ሕግ አውጭ ነበሩ። ሰውዬው ከተባረሩት ኃላፊ በተቃራኒ የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ወለድ መጨመር አ��ፈላጊ ነው ብለው አያምኑም። የቱርክ የወለድ መጠን 19 በመቶ ደርሷል። ይህም የውጭ ሃገር ኢንቨስተሮች ገንዘባቸው በሃገሪቱ እንዲያከማቹ አድርጓቸዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-56480620 +health የጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ወደ ውጪ የሚደረገውን ጉዞ ያስቀር ይሆን? የሰበታ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አሕመድ አባዲ የሦስት ዓመት ልጃቸው በጭንቅላት ካንሰር በመታመሙ ከሰባት ወራት በፊት ታይላንድ ባንግኮክ ከተማ ወስደው አሳክመዋል። “ከዚያ ተመልሰን በሦስተኛው ወር ስናስመረምረው በአከርካሪ አጥንቱ ላይ ካንሰር ተገኘበት” ይላሉ አቶ አሕመድ። የልጃቸው የጤና በጣም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደነበር የሚናገሩት አቶ አህመድ፣ “መቀመጥ፣ መሄድ፣ መተኛት እና ምግብ መዋጥም አይችልም ነበር” ይላሉ። በዚህ ሰዓት ነበር አቶ አሕመድ ልጃቸውን እና ቤተሰባቸውን ይዘው ወደ ጅማ ከተማ የሄዱት። ወደ ጅማ ያቀኑት በጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ልጃቸውን ለማሳየት እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለካንሰር ሕክምና ወደ ጅማ ያቀኑት አቶ አሕመድ ብቻ አይደሉም። የባቱ ከተማ ነዋሪው አቶ ሙላቱም ጅማ ድረስ ያመጣቸው ሕክምናውን በመፈለግ ነው። ከዚህ ቀደም በካንሰር እንደታመሙ የሄዱት ወደ ሐዋሳ ነበር። በሐዋሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለካንሰር የሚያስፈልገውን የኬሞቴራፒ ሕክምና ከወሰዱ በኋላ ለጨረር ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተልከው ነበር። በጥቁር አንባሳ ለጨረር ሕክምና ተመዝግበው ወረፋ እስኪደርሳቸው እየጠበቁ እነደነበር የሚናገሩት አቶ ሙላቱ “በጥቁር አንባሳ ሰው ይበዛል፣ ለጨረር ሕክምና ከተመዘገብኩ ከአንድ ዓመት ከሁለት ወር በኋላ በቀደም’ለታ ጠሩኝ” ይላሉ። ዶ/ር አብዩ ለገሰ በጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ስፔሻሊስት እና ኃላፊ ናቸው። “አገልግሎቱን ከጀመረ ወደ አራት ዓመት ይሆናል። ስንጀምር በመርፌ የሚሰጠውን ወይንም የካንሰር ሜዲካል አንኮሎጂ በመስጠት ነበር። በእርሱ ጀምረን ከተጠናከረ ከሁለት ዓመት ተኩል በኋላ የጨረር ሕክምና ማሽን አስመርቀን አገልግሎቱን መስጠት ጀመርን” ይላሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ የካንሰር ጨረር ሕክምና (ራዲዮ ቴራፒ) የሚሰጠው በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ብቻ ነበር። የጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ይህንን አገልግሎት የሚሰጥ ሁለተኛው ማዕከል ነው። “እኛ የምንሰጠው አገልግሎት ለጅማ አካባቢ ማኀበረሰብ ብቻ ሳይሆን ከመላው አገሪቱ ለሚመጡ ታካሚዎች ነው” ይላሉ ዶ/ር አብዩ። ከዚህ በፊት ወደ ውጭ አገራት በመሄድ ሕክምና ያገኙ የነበሩ ታማሚዎች በአሁኑ ጊዜ ወደ ማዕከሉ በመምጣት አገልግሎት እያገኙ መሆኑን የሚገልጹት ኃላፊው፣ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥም 4500 ለሚሆኑ ታካሚዎች የካንሰር ሕክምና መስጠታቸውን ይናገራሉ። አገልግሎት መሰጠት ከጀመረ ሰባት ወር የሆነው የሆስፒታሉ የጨረር ሕክምና (ራዲየሸን) ደግሞ 725 የሚሆኑ ታካሚዎችን አስተናግዷል። የካንሰር ሕክምና አገልግሎት ካለመስፋፋቱ ጋር በተያያዘ የካንሰር ሕሙማን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለወራት የሕክምና ቀጠሮን ይጠብቃሉ። በተሻለ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙት ደግሞ እንደ ቱርክ፣ ሕንድ እና ታይላንድ ወዳሉ አገራት በመጓዝ ሕክምና ያገኛሉ። የሰበታ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አሕመድ አባዲ፣ ልጃቸው የጭንቅላት ካንሰር መያዙን በተነገራቸወ ወቅት ታይላንድ ወስደው ነበር ያሳከሙት። ይሁን እንጂ ወደ አገር ቤት ተመልሰው የተወሰኑ ወራት ከቆዩ በኋላ በአከርካሪ አጥንቱ ላይ ካንሰር በመገኘቱ ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ይዘውት መጥተዋ��። የልጃቸው የጤና ሁኔታ በአስጊ ሁኔታ ላይ ደርሶ እንደነበር የሚያስታውሱት አቶ አህመድ፣ “አርብ እነርሱ ጋር ሄጄ፣ በልዩ ሁኔታ ካዩት በኋላ በሦስተኛው ቀን ማክሰኞ ዕለት የጨረር ሕክምና እንዲያገኝ አደረጉልኝ” ይላሉ። “15 የጨረር ሕክምና ነው የታዘዘለት። ከዚያም መካከል እስካሁን ሰባቱን ወስዷል። በእነዚሁ በወሰዳቸው ሰባቱ ሕክምና አስገራሚ ውጤት ነው ያየነው። አንደኛ በእግሩ እና በመቀመጫው ላይ የነበረው ችግር ተፈትቷል” በማለት ስለልጃቸው ጤንነት መሻሻል ይናገራሉ። ለሕክምና ከአገር መውጣት ኪስንም ስነ ልቦናንም እንደሚፈታተን አቶ አህመድ አልሸሸጉም። “አንደኛ የአውሮፕላን ቲኬት ራሱ በጣም ውድ ነው። ሌላው ደግሞ ከእኛ አገር ባህል ወጥተህ በሌላ አገር ውስጥ ትቸገራለህ። ክፍያውን የምትፈጽመው በውጭ ምንዛሪ ነው። ከህክምናው ውጪ ለሌሎች ወጪዎች የሚሆን የውጪ ምንዛሪ ማግኘት አስቸጋሪ ነው።” እንደ ቱርክ፣ ሕንድ እና ታይላንድ ባሉ የውጭ አገራት የሚሰጡ ሕክምናዎች ውድ መሆናቸውን የሚናገሩት የካንሰር ስፔሻሊስቱ ዶ/ር አብዩ፣ ማዕከላቸው ከፍተኛ ደረጃ ያለው ሕክምና እየሰጠ መሆኑን ያስረዳሉ። ይህም ዜጎች ወደ ውጭ አገር በመሄድ የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚደርስባቸውን እንግልት የሚያስቀር መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል። በተጨማሪም የውጭ ምንዛሪን ከማስቀረት አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ያብራራሉ። ከዚህ በፊት ከመላው አገሪቱ ለሚመጡት ታካሚዎች የካንሰር ሕክምናን ሲሰጥ የነበረው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ከታካሚዎች ቁጥር መብዛት የተነሳ ለጨረር ሕክምና የረዥም ጊዜ ቀጠሮ እንዲጠብቁ ይደረግ ነበር። ዶ/ር አብዩ ይህንን ሲገልፁ፣ ቢያንስ አንድ ዓመት ያህል የሚወስድ ቀጠሮ እንደሚሰጥ ያስረዳሉ። በዚህም የቀጠሮ ጊዜያቸው ሳይደርስ እና ህክምናውን ሳያገኙ፣ ሕይወታቸው የሚያልፍ ነበሩ። በአሁኑ ወቅት በጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ታካሚዎች የጨረር ሕክምናን ለማግኘት ከሦስት እስከ አራት ወር ድረስ ብቻ ቀጠሮ ሊሰጣቸው እንደሚችል ኃላፊው ይናገራሉ። ይህም ሊሆን የቻለው፣ ከአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚመጡ ታካሚዎች ወደ ጅማ ለሕክምና በመሄዳቸው የተነሳ መሆኑን ይናገራሉ። በተቻለን መጠን እስከ አንድ ዓመት ቀጠሮ የሚያዝላቸው ህሙማን እንዳይኖሩ ጥረት እያደረግን ነው የሚሉት ዶ/ር አብዩ፣ የካንሰር ታማማዎችም ቢሆኑ የበሽታው ምልክቶች እንደታየባቸው ወዲያውኑ ሕክምና መጀመር አለባቸው ሲሉ ይመክራሉ። የካንሰር ህመምን ለማከም የሚሰጡት ሕክምናዎች ዋና ዋናዎቹ ሦስት መሆናቸውን ባለሙያው ይናገራሉ። እነርሱም ቀዶ ሕክምና፣ በመርፌ የሚሰጥ መድኃኒት እና የጨረር ሕክምና ናቸው።። የጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ከእነዚህ መካከል ሁለቱን፣ ማለትም በመርፌ የሚሰጠውን ሕክምና እና የጨረር ሕክምና (ራዲዮቴራፒ) አገልግሎቶችን ይሰጣል። በማዕከሉ  ለጨረር ሕክምናው የሚሆነው መሳርያ በጅማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ 20 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ ነው የተደራጀው። “አንድ ማሽን ነው ያለን። የማሽን እና እቃዎች ጉድለት አለብን” የሚሉት ዶ/ር አብዩ፣ በአሁኑ ሰዓትም ተጨማሪ ማሽን ለመግጠም የሚያስችል ተስማሚ ቦታ እንዳላቸው ይናገራሉ። ማዕከሉ ሁለት የካንሰር ስፔሻሊስቶች፣ የጨረር ማሽን ባለሙያ፣ አንድ ሜዲካል ፊዚስት፣  እንዲሁም ነርሶች እና የሬዲዮ ቴራፒ ባለሙያዎች ጋር የተደራጀ ነው። ዶ/ር አብዩ ወደ ማዕከላቸው በብዛት የሚመጡ የካንሰር ታማሚዎችን ሲያስረዱ፣  የማህፅን ጫፍ፣ የጡት እና የአንጀት ካንሰር ታማሚዎች ከፍተ��ውን ቁጥር እንደሚይዙ ይናገራሉ። ከእነዚህም በተጨማሪ የጡንቻ፣ የአጥንት እንዲሁም የደም ካንሰር ቀጥሎ በብዛት የሚስተዋሉ መሆናቸውን ስፔሻሊስቱ ይናገራሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cx80yr27ezqo +health ኮሮረናቫይረስ፡ ጃፓናዊቷ የኮቪድ-19 ታማሚ በህይወት ካለ ሰው የሳንባ ንቅለ ተከላ በማድረግ የመጀመሪያ ሆነች አንዲት የኮቪድ-19 ታማሚ ጃፓናዊት በህይወት ካሉ ሰዎች ሳንባ በመቀበል በዓለማችን የመጀመሪያዋ የኮሮናቫይረስ ህመምተኛ ለመሆን በቃች። ግለሰቧ በቀዶ ህክምና በአካሏ ላይ እንዲገባ የተደረገውን የሳንባ ክፍል ከልጇና ከባሏ የተበረከተ ነው ተብሏል። ታማሚዋ ሳንባው የተለገሳት በኮሮናቫይረስ ምክንያት የመተንፈሻ አካሏ እንደ አንድ የሰውነት ክፍሏ መደበኛውን ሥራውን መሥራት በማቆሙ ነው። በኪዮቶ የሚገኙ ሐኪሞች እንዳሉት ሴትየዋ በቅርብ ወራት ውስጥ አገግማ ወደ ሙሉ ጤናዋ ትመለሳለች። ጃፓን ውስጥ ከሞቱ ሰዎች ላይ የሚገኝን የሳንባ ልገሳ ለማግኘት ያለው ወረፋ ብዙ ጊዜን መጠበቅን ይጠይቃል። በሕይወት ካሉ ሰዎች ሳንባ ንቅለ ተከላ ለኮቪድ-19 በሽተኛ ሲለገስ ግን ይህ የመጀመሪያው ነው። ንቅለ ተከላው የተደረገበት የኪዮቶ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል የሳንባ መተካቱን ሂደት 11 ሰዓታት በፈጀ የቀዶ ህክምና ሂደት አጠናቆታል። ሐኪሞቹ እንዳሉት ሳንባውን የለገሱት ባልና ልጅ እንዲሁም ሳንባ የተለገሳት ታማሚ ሦስቱም በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። በቻይና፣ በአውሮፓና በአሜሪካ በተመሳሳይ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሳንባቸው ከጥቅም ውጪ የሆነባቸው ታማሚዎች የሞቱ ሰዎችን ሳንባ በመቀበል እየዳኑ ይገኛሉ። ነገር ግን ከሞቱ ሰዎች ሳንባ ማግኘት ተራን የመጠበቁ ሂደት በጃፓን ዓመታትን የሚወስድ ነው። ሌላ ተያያዥ በሽታ ያልነበረባት ይህች ጃፓናዊት ታካሚ ኮቪድ-19 ከተያዘች በኋላ በሕይወት ለመቆየት የግድ የሳንባ ንቅለ ተከላ እንደሚያስፈልጋት ከታወቀ በኋላ ባሏና ልጇ ይህን ልገሳ ለማድረግ አላቅማሙም። በሕይወት ከሚገኘው ልጇና ከባለቤቷ ለግለሰቧ የተሰጠው የተወሰነ የሳንባ ክፍላቸው ነው። የሚቀራቸው ሳንባ አነስተኛ በመሆኑ ሊፈጥርባቸው የሚችለው የጤና እክል ልገሳውን ከማድረጋቸው በፊት ተብራርቶላቸዋል። ንቅለ ተከላውን የመሩት ፕሮፌሰር ለጃፓኑ ኪዮዶ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ይህ በሕይወት ካሉ ሰዎች ሳንባን ወስዶ ለሌላ ሰው የመትከል ሂደት ትልቅ የሕክምና አምርታ ነው ብለዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-56674361 +politics የአፍሪካ አገራት መሪዎች በመንግሥት ምስረታ በዓለ ሲመት ላይ ምን አሉ? "ዛሬ መስከረም 24/2014 ዓ.ም እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ አዲስ መንግሥት መስረታ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ንግግር አድርገው ለኢትዮጵያና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ላይ የተጋበዙት የኡጋንዳው ፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፤ በኡጋንዳ ሕዝብ ስም የኢትዮጵያን ሕዝብ እና ጠቅላይ ሚንስትሩን ""እንኳን ደስ አላችሁ"" ብለዋል። በኡጋንዳ የጎሳ እና የሃይማኖት ክፍፍል ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረ ገልጸው፤ የማንነት ፖለቲካ የሚፈጥረውን ልዩነት መቅረፍ ወደ ለውጥ ጎዳና እንደሚያሻግር ተናግረዋል። የደቡብ ሱዳኑ ሳልቫ ኪር በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰላም ለማለት እና እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ነው የመጣሁት። ""ያለ እናንተ ድምጽ ወንድሜ ዐብይ ወደ ሥልጣን አይመጣም ነበር። ከጎኑ ቆማችሁ ወደ ሰላም ተሻገሩ"" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያን ""ታላቋ እናታችን"" ሲሉ አንቆለጳጵሰዋል። ��ደቡብ ሱዳን የተፈጠረው ቀውስ በኢትዮጵያ እንዲደገም እንደማይሹ እና ግጭቱ በሰላማዊ ውይይት እንዲፈታ ጠይቀዋል። በደቡብ ሱዳን እና ሱዳን መካከል ሰላም እንዲወርድ ኢትዮጵያ ያደረገችውን ጥረት ከታሪክ አጣቅሰዋል። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፣ በኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያም፣ በአቶ መለስ ዜናዊ ዘመነ መንግሥትም ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ላይ ፊቷን እንዳላዞረችም ሳልቫ ኪር ሳይጠቅሱ አላለፉም። የጂቡቲው ፕሬዘዳንት እስማኤል ጊሌ በበዓለ ሲመቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ማየት አስደስቶኛል ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን ""ከጂቡቲ ሕዝብ የተላከ የሚያበረታታ እና ተስፋ ሰጪ መልዕክት ይዤ ነው የመጣሁት"" ብለዋቸዋል። ኢትዮጵያን የፓን አፍሪካኒዝም ተምሳሌት ብለው ካሞገሱ በኋላ፤ በምጣኔ ሀብት ረገድ በቀጠናው ያላትን ሚና ጠቅሰው ""ኢትዮጵያ ከራሷ ጋር ሰላም እንድታወርድ፣ የቀድሞ ትልቅነቷን ዳግም እንድታድስ"" ጠይቀዋል። ጦርነት በቀጠናው ያስከተለውን አስከፊ ገጽታ ከታሪክ አጣቅሰው፤ ኢትዮጵያም ""ከልጆቿ ጋር እንድትታረቅ"" እና ወደ ሰላም እንድትመለስ አሳስበዋል። እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፣ እንኳን ለኢሬቻ አደረሳችሁ፣ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ሲሉም በአማርኛ ንግግራቸውን አጠናቀዋል። የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በመስቀል አደባባይ ባደረጉት ንግግር፤ ""ወንድሜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነህ ስለተመረጥክ እንኳን ደስ አለህ"" ብለዋል። ኬንያ የኢትዮጵያን እድገት እና ሰላም ለመደገፍ ዝግጁ ናት ሲሉም ድጋፋቸውን ገልጸዋል። ""ወንድሜ ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንድትመራ፣ ሰላም እንድታመጣ፣ መረጋጋትን እንድታረጋግጥ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድ እንድታደርግ ሥልጣን ሰጥተውሀል። የመረጡህም ያልመረጡህም ያንተ ሕዝቦች ናቸው"" ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። የአፍሪካ ሕዝቦች ከቅኝ ግዛት ነጻ እንዲሆኑ የረዳችው ኢትዮጵያ ""እናታችን ናት"" ካሉ በኋላ ""እናት ሰላም ካጣች ቤተሰቧም ይታወካል"" ሲሉ ኢትዮጵያ ወደ ሰላም እንድትመጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የናይጄሪያው ፕሬዝደንት ሙሐመዱ ቡሀሪ፤ በበዓለ ሲመቱ ላይ በመገኘቴ ኩራት ይሰማኛል ብለዋል። በሰኔ ወር የተካሄደው ምርጫ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ""በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ እንደሚያምን አሳይቶኛል"" ሲሉም ተናግረዋል። አይይዘውም በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ጠቅላይ ሚንስትሩ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። ናይጄሪያ የኢትዮጵያን አንድነት እና ሉዓላዊነት መከበር እንደምትደግፍም ቡሀሪ ገልጸዋል። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ በበዓለ ሲመቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያውያን ፍላጎታቸውን የሚያስጠብቅ አስተዳደር በመምረጣችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ጨምሮ ሌሎችም ፈተናዎችን ለማለፍ አስተዳደሩ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስባል። አያይዘውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉን አቀፍ እድገት እንዲጎናጸፍ ጠቅላይ ሚንስትሩ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ እምነቴ ነው ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58792454 +business ከጉሊት እስከ ቅንጡ ሆቴል ግብይትን ያሳለጠው ኤም-ፔሳ ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣል? ከሁለት ወራት በኋላ በኢትዮጵያ ሥራ እንደሚጀምር ያስታወቀው ሳፋሪኮም፤ ኤም-ፔሳ የተባለውን የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት በአገሪቱ እንዲዘረጋ መንግሥት ፍላጎት እንዳለው ተዘግቧል። የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝን ጠቅሰው የአገር ውስጥ እና የኬንያ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ሳፋሪኮም ኤ���-ፔሳን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲጀምር ይፈልጋል። ከዚህ ቀደም መንግሥት የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓትን ለውጭ አገራት ኩባንያዎች ክፍት እንደማያደርግ መግለጹ አይዘነጋም። አሁን ግን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለሳፋሪኮም የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ኤም-ፔሳ ፈቃድ እንዲሰጥ የሚያስችል ሕጋዊ አሠራር እየተነደፈ እንደሚገኝ ተገልጿል። ሚኒስትር ዴኤታውን ያጣቀሱ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት፤ ሳፋሪኮም ለኤም-ፔሳ የፊታችን ግንቦት ፈቃድ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። መንግሥት ከዚህ ቀደም ባወጣው የቴሌኮም ጨረታ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ዝርጋታ አልተካተተም ነበር። በኬንያው ሳፋሪኮም የሚመራው እና የኢትዮ-ቴሌኮምን ጨረታ ያሸነፈው ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ ጥምረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት በተፈራረመበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ የተገኙት የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ኢትዮጵያ ገበያውን ለኤም-ፔሳ ክፍት እንድታደርግ በተዘዋዋሪ መጠቆማቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለተኛውን የቴሌኮም ጨረታ ላልተወሰነ ጊዜ ቢያራዝመውም፤ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ዝርጋታን ከዝርዝሩ እንዳስወጣው ተገልጿል። ሳፋሪኮም ይህንን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለው ፈቃድ በቅርቡ እንደሚሰጠውም ታክሏል። ኤም-ፔሳ የሚሠራው እንዴት ነው? ኤም-ፔሳ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ነው። መሥራቹ የኬንያው የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ሲሆን፤ አሁን ላይ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት እየተተገበረ ይገኛል። ኤም-ፔሳ ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ ከተጫነ በኋላ ገንዘብ ማስቀመጥ፣ ገንዘብ መቀበል፣ ክፍያ መፈጸም፣ የባንክ ተቀማጭ ገንዘብን ወደ ስልክ ማዘዋወር፣ ገንዘብ ለሌላ ኤም-ፔሳ ተጠቃሚ መላክ እና ሌላም የገንዘብ ልውውጥ ማካሄድ ይቻላል። እአአ በ2007 በሳፋሪኮም እና ቮዳፎን የተጀመረው ኤም-ፔሳ ኬንያ ውስጥ የሚተዳደረው በኬንያ ብሔራዊ ባንክ ነው። ኤም-ፔሳ የሚለው መጠሪያ ውስጥ ኤም ሞባይልን ሲወክል፣ ፔሳ ደግሞ በስዋሂሊ ገንዘብ ማለት ነው። የገንዘብ ልውውጥን የሚያሳልጡ የሳፋሪኮም ተወካዮች በተለያዩ መደብሮች ይገኛሉ። ለእነዚህ ተወካዮች ጥሬ ገንዘብ በመስጠት ወደ ኤም-ፔሳ ገንዘቡን እንዲያዘዋውሩ ማድረግ ይቻላል። በኤም-ፔሳ ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ ያለ ገንዘብን በጥሬ ገንዘብ ከተወካዮቹ የመውሰድ አማራጭም አለ። በተለይ ኬንያ ውስጥ ከጉሊት አንስቶ እስከ ቅንጡ ሆቴሎች ድረስ ክፍያ የሚፈጸመው በኤም-ፔሳ ነው። አገልግሎቱ በሚገኝባቸው ሌሎች አገራትም የውሃ እና መብራት ክፍያን ጨምሮ ለምርት እንዲሁም ለአገልግሎት ክፍያ ለመፈጸም ሁነኛ አማራጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በኤም-ፔሳ የገንዘብ ልውውጥ ሲደረግ ወይም ከሳፋሪኮም ተወካይ ገንዘብ ሲወሰድ በገንዘቡ ልክ የሚወሰን የአገልግሎት ክፍያ ይጠየቃል። ኤም-ፔሳን የትኞቹ አገራት ይጠቀማሉ? ወደ ዲጂታል የገንዘብ ልውውጥ እየተሻገረ ባለው ዓለም ውስጥ ከፍተኛ እውቅና ካተረፉ ተሞክሮዎች አንዱ ኤም-ፔሳ ነው። እአአ በ2010 በታዳጊ አገራት እጅግ ስኬታማው የሞባይል ገንዘብ መለዋወጫ ተብሎ ተሞካሽቷል። ከኬንያ አልፎ በታንዛንያ፣ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ በግብፅ፣ በጋና፣ በሌሴቶ እና በሞዛምቢክ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የሳፋሪኮም ድረ ገጽ ይጠቁማል። ጀርመን፣ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና ቻይና ወዳሉ ባንኮች ገንዘብ ማዘዋወር ይቻላል። የቮዳፎን ድረ ገጽ እንደሚለው ኤም-ፔሳ ከ50 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት። ከአፍሪካ ትልቁ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት እንደሆነ የሚነገርለት ኤም-ፔሳ፤ የባንክ ደብተር ላላቸው ብቻ ሳይሆን የባንክ ተጠቃሚ ላልሆኑ ሰዎችም አገልግሎት በመስጠት ይታወቃል። በተለይም የባንክ አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ኤም-ፔሳ ተደራሽ መሆኑ ለንግድ ብቻ ሳይሆን ለገንዘብ ቁጠባም መንገድ እንደከፈተ ይገለጻል። ከገጠር እስከ ከተማ ጥሬ ገንዘብ ይለዋወጥ የነበረን ማኅበረሰብ ወደ ስልክ የገንዘብ ዝውውር በስኬታማ ሁኔታ እንዳሻገረ ይነገርለታል። ኤም-ፔሳ ጥቃቅን እና አነስተኛ ነጋዴዎችን የሚያበረታታ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት እንደሆነ የሳፋሪኮም ገጽ ይጠቁማል። ከተንቀሳቃሽ ስልክ የአየር ሰዓት ግዥ አንስቶ በተለያዩ አገልግሎት መስጫዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያዘዋውራል። ገንዘብ ለመቆጠብ እና ገንዘብ ለመበደር ኤም-ሸዋሪ የተባለ አዲስ አሠራርም ለተጠቃሚዎቹ ዘርግቷል። የቮዳፎን ድረ ገጽ እንደሚጠቁመው፤ ኤም-ፔሳ እንደ ዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ወርልድሬሚት፣ ሬሚትሊ እና ኤምኤፍኤስ አፍሪካ ያሉ ዓለም አቀፍ የገንዘብ መለዋወጫዎች ጋር ትስስር ፈጥሯል። በየዓመቱ ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከውጭ አገራት የሚነሳ የገንዘብ ዝውውር (remittance) ያስገኛል። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው፤ የገንዘብ ልውውጥ ዲጂታል ቅርጽ ሲይዝ ተደራሽነቱ ይሰፋል፤ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ያማለከም ይሆናል። ኤም-ፔሳ እና ኤም-ብር ምን ያመሳስላቸዋል? ኤም-ብር ኢትዮጵያ ውስጥ ተንቀሳቃሽ ስልክን የተመረኮዘ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ነው። በኤም-ብር ተጠቃሚዎች መካከል ገንዘብ ለማስተላለፍ፣ በኤም-ብር ተወካይ በኩል ጥሬ ገንዘብን ወደ ስልክ ለመውሰድ ወይም ከስልክ ተቀማጭ ጥሬ ገንዘብ ለማውጣትም ይውላል። የተንቀሳቃሽ ስልክ የአየር ሰዓት መግዛትን ጨምሮ ውሃ እና መብራት ለመክፈል እንዲሁም ለሌሎችም የምርት እና የአገልግሎት ግዢዎች ኤም-ብርን መጠቀም ይቻላል። ኤም-ፔሳ እና ኤም-ብርን ጨምሮ ሌሎች ዓለም ላይ ያሉ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓቶች መሠረታዊ ሐሳባቸው ተመሳሳይ ቢሆንም በአገልግሎት ዓይነት እና ቅልጥፍና ይለያያሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮ-ቴሌኮምን ድርሻ ለተለያዩ የቴሌኮም ኩባንያዎች ግዥ ክፍት ሲያደርግ ከተነሱ ነጥቦች አንዱ፤ የውጭ ቴሌኮሞች ወደ ኢትዮጵያ መግባት በዘርፉ ውድድር በመፍጠር የአገልግሎት ጥራትን ያስጠብቃል የሚለው ነው። ወደ ዲጂታል የፋይናንስ ሥርዓት የሚደረገውን ሽግግር ለማፋጠን በተለያዩ አገራት የተፈተሸ የሥራ ልምድ ያላቸው ተቋሞችን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ማስገባትን በአወንታዊ ጎኑ የወሰዱት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች አሉ። ኤም-ፔሳ ኢትዮጵያን ያሰጋል? ኤም-ፔሳ የኢትዮ-ቴሌኮምን ጨረታ ያሸነፈው ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ ጥምረት በሚመራው ሳፋሪኮም ከሚሰጡ የቴሌኮም አገልግሎቶች አንዱ ነው። ሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕ፣ ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽንና ሲዲሲ ግሩፕን የያዘው ጥምረት 850 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦ ነበር ጨረታውን ያሸነፈው። በመንግሥት የሚተዳደሩ እንደ ኢትዮ-ቴሌኮም ያሉ ተቋሞችን ለውጭ ኩባንያዎች ወይም የግል ባለሀብቶች የመክፈት ሐሳብ ደጋፊዎች እንዳሉት ሁሉ ነቃፊዎችም አያጣም። ለመንግሥት ከፍተኛ ዓመታዊ ገቢ የሚያስገኙ ድርጅቶችን ለሽያጭ ማቅረብ መንግሥት የሚያገኘውን ትርፍ እንደሚቀንስ እንዲሁም በአገር ውስጥ የገበያ ተወዳዳሪዎች ላይ አሉታዊ ጫና እንደሚያሳድርም የሚከራከሩ ይጠቀሳሉ። ለውጭ ኩባንያዎች ሁሉንም ዘርፎች ክፍት ከማድረግ ይልቅ እንደ ፋይናንስ ያዙ ዘርፎች በማዕከላዊ መንግሥት ሥር ሆነው እንዲዘልቁ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ነው የሚል አስተያየት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይሰነዝራሉ። እንደ ሳፋሪኮም ያሉ ተቋሞች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን የሞባይልና የኢንተርኔት አገልግሎት ቢሰጡም፤ እንደ ኤም-ፔሳ ባለ አገልግሎት የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ የመግባታቸውን ጉዳይ በጥያቄ ምልክት የሚያስተናግዱት አሉ። ኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍን ለግል ባለሀብቶች ከከፈቱ የመጨረሻዎቹ አገራት አንዷ እንደሆነች ይነገራል። በሳፋሪኮም የሚመራው ጥምረት፤ ለኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር ድጋፍ እንደሚያደርግ፣ ለበርካቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርና የዜጎችን ሕይወት በበጎ እንደሚቀይር በምሥረታው ወቅት አስታውቋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት በመታገዝ ከያዘችው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያዎች መካከል የቴሌኮምን ድርሻ መሸጥ እንደሚገኝበት ገልጻለች። https://www.bbc.com/amharic/60329210 +politics ኬንያ ከሰሃራዊ አረብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጋር ግንኙነቷን ማቋረጧን አስታወቀች ከተሾሙ ቀናትን ያስቆጠሩት የኬንያው ፕሬዘዳንት ዊልያም ሩቶ አገራቸው ከሰሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ (ሳዲአር)ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ገለጹ። ፕሬዚዳንቱ ትላንት ረቡዕ በትዊተር ገጻቸው ላይ ይህንኑ መልዕክት አስፍረው የነበረ ሲሆን ከሰአታት በኋላ ግን ልጥፉን አንስተዋል። የቀድሞ የስፔን ቅኝ ግዛት የነበረው ይህ የምዕራብ ሰሃራ አካባቢ እ.ኤ.አ በ1975 ከቅኝ ግዛት ከተላቀቀ በኋላ ሞሮኮ ግዛቴ ነው በሚል በቁጥጥሯ ስር ለማድረግ ሙከራዎችን አድርጋለች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሰሃራዊ ነባር ሕብረተሰቦች እና የሞሮኮ መንግስት መካከል ዘላቂ የግጭት ምክንያት ሆኖ ዘልቋል። ታዲያ የኬንያ አዲሱ ፕሬዘዳንት ዊሊያም ሩቶ ሰሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በኬንያ ያላትን ሕጋዊ ቆይታ እና ግንኙነት እንዲያበቃ ለማድረግ እርምጃዎች መጀመራቸውን ተናግረዋል። በምዕራብ ሰሃራ ያሉትን ያለመግባባቶች ዘላቂ መፍትሄ የሚያገኙት የተባበሩት መንግስታት በሚያዘጋጀው ማዕቀፍ ብቻ ውስጥ ነው ብላ ኬንያ እንደምታምንም ተናግረዋል። የሰሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ መሪ ብራሂም ጋሃሊ ማክሰኞ በተካሄደው የፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በአለ ሲመት ላይ ተገኝተው ነበር። ፕሬዘዳንት ሩቶ ይህንን ውሳኔያቸውን ይፋ ያደረጉት የሞሮኮው ንጉስ መሀመድ ስድስተኛ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ከደረሳቸው ከጥቂት ሰአታት በኋላ ነበር። ከአርባ አመታት በላይ ሕጋዊ ቅቡልነት ያላት አገር ለመሆን እየሰራች የምትገኘው ሰሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የአፍሪካ ሕብረት ሙሉ አባል ስትሆን በርካታ አገራት ዕውቅና ሰጥተዋታል። በአሁን ሰአትም ከፊል ቅቡልነት ያላት አገር ናት። ሞሮኮ በበኩሏ ምዕራብ ሰሃራ ግዛቴ ነው የሚል ጠንካራ አቋሟን የምታራምድ ሲሆን በአካባቢው የሚኖሩ ሕዝቦች ፍላጎታቸውን እንዲያሳዩ የሕዝበ ውሳኔ ይደረግ የሚለውን ሃሳብም አትቀበልም። ይህ የሰሀራ በረሃ አካል የሆነው ክፍል እስካሁን ድረስ ያልተነካ የነዳጅ ዘይት ክምችት ያለበትን የባሕር ክፍል እንደሚይዝ ይታመናል። ከዛም ባሻገር ከፍተኛ የፎስፌት ክምችት ያለው ሲሆን በአሳ ሃብቱ የበለጸገ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cn3rvr7v2e2o +politics ከሰሞኑ የጋምቤላ ጥቃት ጀርባ ያለው ቡድን ማን ነው? ማክሰኞ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም ማለዳ ላይ የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት-ሸኔ በጋራ በመሆን በጋምቤላ ከተማ ላይ ጥቃት በመክፈት ከተማዋ ለቀናት ከተለመደ እንቅስቃሴዋ ውጪ ሆና ቆይታለች። የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ጋትሉክ ቡኦም ፓል ጥቃታቸው የጀመረው ከከተማው 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ደምቢዶሎ መውጫ ላይ ከሚገኝ ጫካ በመነሳት እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለተወሰኑ ሰዓታት በርካታ የከተማዋን ክፍሎች ተቆጣጥረው እንደነበር የሚናገሩት ሊቀመንበሩ የመንግሥት ኃይሎች ወደ ከተማው በማፈግፈግ ውጊያው “በሕዝብ መካከል” ስለነበር፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና እርሳቸው በመነጋገር ከከተማው መውጣታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። በወቅቱ የክልሉ መስተዳደርም ታጣቂዎቹ የተወሰነውን የከተማዋን ክፍል ተቆጣጥረው እንደነበርና ፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት ጠንካራ እርምጃ አማጺያኑን በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ከተማዋ ማስወጣት መቻሉን አሳውቋል። አቶ ጋትሉክ  እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቃል አቀባይ ዕቅዳቸውን አሳክተው በወታደራዊ ካምፕ ላይ ጉዳት አድርሰው በርካታ መሣርያም መማረካቸውን ቢናገሩም፤ የክልሉ ባለሥልጣናት እና ነዋሪዎች ግን በርካታ የታጣቂዎቹ ቡድን አባላት በከተማዋ ውስጥ መገደላቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከማክሰኞው ጥቃት በኋላ ረቡዕ ዕለትም የጋምቤላ መደበኛ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሎ ቆይቶ፣ ሐሙስ ዕለት ነዋሪው ወደ ተለመደ ሥራው እየተንቀሳቀሰ መሆኑን እና ፀጥታ ኃይሉም ከጥቃቱ በኋላ በሕዝቡ ውስጥ ተደብቀዋል ያላቸውን የታጣቂ ቡድኑ አባላትን አድነው በመያዝ ላይ ናቸውን የክልሉ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጋምቤላ ነጻነት ግንባር በኮንፌዴሬሽን በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያ ለመመስረት እንደሚታገሉና አሁን የፈጸሙት ጥቃት ዓላማ ከተማዋን መቆጣጣር እንደነበር አቶ ጋትሉክ ገልጸዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ላይ የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ በታጣቂዎቹ ላይ “ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን፣ በወገን ጦር ላይም መጠነኛ ጉዳት መድረሱን” ተናግረው ነበር። የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር በበኩላቸው ትልቅ ኪሳራ የደረሰው በመንግሥት ወገን ላይ እንደሆነና ከእነርሱ ወገን ሦስት ተዋጊዎቻቸው ሲሞቱ፣ ሌሎች ቁጥራቸውን ያልገለጿቸው ደግሞ መቁሰላቸውን አረጋግጠዋል። የከተማው ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩትና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጩ ምስሎች እንዳሳዩት በርካታ የታጠቂው ቡድን አባላት ናቸው የተባሉ አስከሬኖች በጋምቤላ ከተማ መንገዶች ላይ ታይተዋል። መንግሥት በሽብርተኛ ቡድንነት የፈረጀው እና ሸኔ በሚል የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ የሕዝብ ግንኙነት እንደሆነ የሚነገረው ኦዳ ተርቢ፣ የቡድኑ ታጣቂዎች ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር የተሳካ የመቀናጅት ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጾ ነበር። በክልሉ ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑ እና ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ግለሰብ ይህን ጥቃት የፈፀሙት ከውጪ የመጡ አካላት ብቻቸውን ሳይሆን በሕዝቡ እና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚገኙ እገዛ አድርገዋል ሲሉ ይወነጅላሉ። የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ከከተማው በቅርብ ርቀት፣ አንፊሎ እና ድንበር አካባቢ መሽገው ይገኛሉ ያሉት ግለሰቡ፣ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ተፈናቃዮች ጋርም በመቀላቀል እገዛ እንደሚያገኙ ይናገራሉ። በጋምቤላ ከተማ ማክሰኞ ዕለት በነበረው ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ከተለያዩ ምንጮች አጣርቷል። ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ከተደረገው ብሔራዊ ምርጫ በኋላ መመስረቱ የሚነገረው የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ጋነግ) በሺዎች የሚቆጠሩ አባላትና ታጣቂዎች እንዳሉት ይናገራል። የድርጅቱ ሊቀ መንበርና ምክትል፣ የኢህአዴግ አጋር ድርጅት በመሆን ክልሉን ሲያስተዳድር የነበረው የጋምቤላ ሕዝቦች አንድነት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባል ሆነው በክልሉ በተለያየ የመንግሥት ኃላፊነት ላይ አገልግለዋል። በዚህም ሊቀ መንበሩ በተለያዩ የክልሉ መንግሥት ቢሮዎች ከምክትል ኃላፊነት እስከ የክልሉ ኮሌጅ ዲንነት ድረስ መስራታቸውንም ለቢቢሲ ገልፀዋል። ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ኃላፊነቶች ውስጥ ያገለገሉት አቶ ጋልዋክ፣ በባሕልና ቱሪዝም ቢሮ፣ በከተማና ልማት፣ በትምህርት ቢሮዎች ውስጥ በምክትል ኃላፊነቶች እንዲሁም በክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ እና ጥቃቅን እና አነስተኛ በከፍተኛ አመራርነት መስራታቸውን ይናገራሉ። ጋነግ “በዲሞክራሲ እና በፍትሕ የሚያምን፣ ለጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት የሚታገል ድርጅት ነው” እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን፣ ፓርቲው ከሌሎች በአገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ጋር አጋርነት በመፍጠር የፌደራሊስት ኃይሎች ግንባር ተሳታፊ ነበር። ይህ የፌደራሊስት ኃይሎች የተባለው ስብስብ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት በተደጋጋሚ ወደ መቀለ በመመላለስ ከህወሓት ጋር ሲመክር እንደነበር ሊቀመንበሩ ያስታውሳሉ። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ጦርነቱ ሲቀሰቀስ አዲስ አበባ ውስጥ የነበሩት የግንባሩ ሊቀመንበር ጋትሉክ “ከሦስት ወራት በላይ ከህወሓት ጋር ግንኙነት ጋር አለህ በሚል” ታስረው መቆየታቸውን ይናገራሉ። ሊቀመንበሩ “የተጭበረበረ ነው” በሚሉት በ2013 ሰኔ ወር ላይ በተካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ላይ መሳተፋቸውንና፣ “ከዚያ በኋላ ሊያስሩኝ ሲሞክሩ ወደ በረሃ ገባሁ” የሚሉት ጋልቶክ ለጋምቤላ ሕዝብ እኩልነት ትግል መጀመራቸውን ተናግረዋል። የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ከቀናት በፊት በጋራ ሆኖ ጥቃት ከሰነዘረው የኦሮሞ የነጻነት ሠራዊት የመሣርያ እና ሥልጠና ድጋፍ እንደሚያገኝ ሊቀመንበሩ አረጋግጠዋል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አዛዥ የሆነው ኩምሳ ድሪባም (ጃል መሮ) ለቢቢሲ ከግንባሩ አመራሮች ጋር የረዥም ጊዜ ትውውቅ እንዳላቸውና ለታጣቂዎቻቸውም ስልጠና ሲሰጡ እንደነበርም ገልጿል። ሊቀመንበሩ የሌላ አገር ዜግነት እንዳላቸውና በጋምቤላ ክልል ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ በሰሩባቸው ጊዜያት የሕዝብና የመንግሥት ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉ ክስ የሚቀርብባቸው ሲሆን፣ ይህ ጉዳይ እንደማይመለከታቸው ይናገራሉ። ሁለቱም ክሶች ከሊቀመንበሩ ጋር በተመሳሳይ ስም የሚታወቁት ምክትላቸውን የሚመለከት መሆኑንና ግለሰቡ የአሜሪካ ዜግነት እንዳለው አምነው፣ ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት ፈጽመዋል መባሉን “መሠረተ ቢስ ውንጀላ ነው” ሲሉ አጣጥለውታል። የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ጋትሉክ ተብለው የሚጠሩ ሲሆን፣ ሊቀመንበሩ ጋትሉክ ቡኦም ፓል ምክትላቸው ደግሞ ጋትሉክ ፓልቴርጋር ይባላሉ። የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር እንጂ በቀጥታ ከህወሓት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደሌለው ሊቀ መንበሩ ጠቅሰው ነገር ግን “ከህወሓት ጋር ያለን የዓላማ አንድነት ነው” በማለት ተናግረዋል። ከአንድ ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንግሥት ሸኔ የሚለውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን እና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይን (ህወሓት) በሽብርተኛነት በመፈረጅ ሕገ ወጥ ቡድኖች ማድረጉ ይታወሳል። በምዕራብኢትዮጵያ የሚገኘው የጋምቤላ ክልል ዋና ከተማው ጋምቤላ ሲሆን ከደቡብ ሱዳን፣ ከኦሮሚያ እና ከደቡብ ክልል ሕዝቦች ጋር ይዋሰናል። አኝዋክ፣ኮሞ፣መዠንገር፣ኑዌር እና ኦፖ የሚባሉ አምስት ብሔረሰቦች አሉት። በተጨማሪም ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የተወጣጡ ሌሎች ብሔረሰቦችም የሚኖሩበት ክልልነው። ከዚህ ቀደም ባለው መረጃ የክልሉ ሕዝብ ብዛት ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠ�� ሲሆን በኢትዮጵያ ትንሽ ሕዝብ ከሚኖርባቸው ክልሎች አንዱ ነው። ለእርሻተስማሚ ለም መሬት ያለው የጋምቤላ ክልል፣ በተጨማሪም ከዓመት ዓመት የሚፈሱ ሁለት ግዙፍ ወንዞች ባለቤት ነው። ክልሉ በተለያዩ ጊዜያት ብሔርን መሠረት ያደረጉ ተደጋጋሚ ጥቃቶችና ግጭቶች ያጋጠሙት ሲሆን፣ በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን ሰርገው የሚገቡ ታጣቂዎችም ጥቃት ይፈጽሙበታል። እንደ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት መረጃ ከሆነ ክልሉ ከ480 ሺህ በላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መኖርያ ነው። ክልሉን የሚመራው የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕዴን) የተለያዩትን የክልሉ ብሔሮች ይወክሉ የነበሩ ቡድኖችን በማዋሃድ የተመሰረተ ነው። ጋሕዴን ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢህአዴግ አጋር ድርጅት የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ አባል ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2mp4jrdzmo +business የምዕራባውያንን ማዕቀብ ለሚሸሹት ሩሲያውያን መሸሸጊያ የሆነችው ዱባይ "የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ከቭላድሚር ፑቲን አስተዳደር ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የሩሲያ ባለጸጎች ከምዕራባውያን ማዕቀበ ለማምለጥ ዱባይን መዳረሻቸው እያደረጉ ነው። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቢሊየነር ሩሲያዊያን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትሷ ዱባይ እየገቡ ነው። አንድ ሪፖርት በመጀመሪያዎቹ የ2022 ሦስት ወራት ዱባይ ውስጥ በሩሲያ ባለሀብቶች የተገዙ ንብረቶች መጠን በ67 በመቶ ጨምሯል ብሏል። ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ እስካሁን ድረስ የዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ አልጣለችም። ሩሲያ 'ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን' የምትለውን ወረራንም አላወገዘችም። ማዕቀብ ላልተጣለባቸው ሩሲያዊወያንም ቪዛ እየሰጠች ነው። የሞስኮ ወረራን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ወራት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሩሲያውያን አገራቸውን ጥለው ሳይወጡ አይቀርብም ይባላል። አንድ የሩሲያ ዜግነት ያለው የምጣሄ ሀብት ባለሙያ ጦርነቱ በተጀመረ በመጀመርያዎቹ 10 ቀናት ከ200ሺህ ያላነሱ ሩሲያውያን አገራቸውን ጥለው ተሰደዋል ብሎ ነበር። አዳዲስ ኩባንያዎች በዱባይ ሲቋቋሙ ድጋፍ የሚያደርገው ቨርቱዞን በቅርብ ወራት ገበያው እንደደራላት ይገልጻል። ""ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ከሩሲያውያን የሚቀርብልን የአግልግሎት ፍላጎት በአምስት እጥፍ ጨምሯል"" ብለዋል የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ጆርጅ ሆጄኢግ። ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደሚሉት ከሆነ ሩሲያውያኑ ከአገራቸው እየሸሹ ያሉት ጦርነቱን ተከትሎ በሩሲያ ሊያጋጥም የሚችለው የምጣሄ ሀብት ድቀት ስለሚያሳስባቸው ነው። ""ለአንጡራ ሀብታቸው ማረጋገጫ ስለሚፈልጉ ነው ወደዚህ የሚዘዋወሩት"" ብለዋል። የሩሲያውያን ባለሀብቶች ወደ ዱባይ መትመም በከተማዋ የቅንጡ ቪላ እና አፓርትመንት ቤቶች ፍላጎትን ጣራ አድርሶታል። የቤት አሻሻጮችም የዋጋ ጭማሪ ሪፖርት እያደረጉ ነው። ሞደርን ሊቪንግ የተባለ ቤት አሻሻጭ ኩባንያ የሩሲያውያንን የቤት ፍላጎት ለማርካት የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪ የሽያጭ ባለሙያዎችን መቅጠሩን ለቢቢሲ ገልጿል። የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቲያጎ ካለዳስ ወደ ዱባይ በአስቸኳይ መዘዋወር የሚፈልጉ ሩሲያውያን የሰልክ ጥሪ እንደሚደርሳቸው ይገልጻሉ። ""ወደዚህ የሚመጡት ሩሲያውያን ግዢ የሚፈጽሙት ለኢንቨስትመንት ብቻ ሳይሆን ዱባይን ሁለተኛ ቤታቸው ለማድረግ ነው"" ብለዋል። በግለሰብ ደረጃ ያሉ ባለሀብቶች ብቻ አይደሉም ወደ ዱባይ እያቀኑ ያሉት፤ ኩባንያዎች ከነሠራተኞቻቸው ወደ ዱባይ እየተመሙ ነው። ፉአድ ፋቱሌቭ ከዊዌይ ኩባንያ መሥራቾች መካከል አንዱ ነው። ፉአድ የብሎክቼይን ኩባንያው በሩሲያ እና ዩክሬን ቅርንጫፎች እንዳሉት ���ናገራል። ከጦርነቱ በኋላ ግን እርሱ እና አጋሮቹን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቹን ወደ ዱባይ ማዘዋወራቸውን ይገልጻል። ""ጦርነቱ በሥራችን ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሯል።"" ፉአድ ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ የጣሏቸው ማዕቀቦች ሥራቸውን ለመሥራት ስላላስቻላቸው አገር ለመቀየር መገደዳቸውን ያስረዳል። እንደ ጄፒ ሞርጋን እና ጉግል ያሉ ዓለም አቀፍ ስም ያላቸው ኩባንያዎችም በሩሲያ ያላቸውን ቢሮ በመዝጋት ሠራተኞቻቸውን ወደ ዱባይ እያዘዋወሩ ነው። የባህረ ሰላጤው አገራት ዩኤኢ እና ሳዑዲ አረቢያ፣ ምዕራባውያኑ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ያቀረቡላቸውን ተደጋጋሚ ጥሪ ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም። የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ከወራት በፊት የሩሲያን ወረራ ለማውገዝ ድምጽ በሰጠበት ወቅት ጉዳዩን በድምጸ ታዕቅቦ ካለፉት አገራት መካከል ዩኤኢ አንዷ ነበረች። ከዚህ በተጨማሪም ሩሲያን ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ለማገድ የወጣው ውሳኔ ላይ አቡ ዳቢ በድምጸ ታዕቅቦ አልፋለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-61330372 +business ባለፈው ዓመት ለኑሮ መወደድ ምክንያት የሆኑት ዋነኛ ክስተቶች የትኞቹ ናቸው? ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ ከዚህ በፊት ከታየው በከፍተኛ ሁኔታ የናረ የምርት እና የአገልግሎቶች ዋጋ መናር ተከስቷል። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች የሚቀርቡ ሲሆን፣ ይህ ቪዲዮ የዓለምን ሕዝብን ክፉኛ ላስጨነቀው የዋጋ ንረት ሰበብ ለሆኑት መካከል ዋናዎቹን ይዳስሳል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cgr0n57lp2xo +health ዋነኛ ምልክቱ የጀርባ ሕመም የሆነው የደም ካንሰር ዓይነት "መልቲፕል ማይሎማ (Multiple myeloma) የደም ሥርዓትን የሚያጠቃ እና በብዛት ያልተለመደ የደም ካንሰር ዓይነት ነው። በብዛት በኩላሊት እና በአጥንት ላይ የተለያዩ እክሎችን ያስከትላል። በዚህም የተነሳ የሕመም ምልክቶቹ ከሌላ ሕመም ለመለየት አስቸጋሪ ያደርገዋል። ይህ ሕመም በሽታ ተከላካይ የሆኑትን ነጭ የደም ህዋሳትን፣ ፕላዝማ ህዋሳትን ያጠቃል። እነዚህ የተጠቁ ህዋሳት ደግሞ የተበላሹ ህዋሳትን በመፈጠር እየተባዙ፣ ጤናማ ያልሆነ የሰውነት በሽታ ተከላካይ ህዋሳትን ያመርታሉ። ይህም ኤም ፕሮቲን ( M-protein) ወይንም ሞኖክሎናል ፕሮቲን (monoclonal protein) ይሰኛል። እነዚህ ፕሮቲኖች የተለያዩ የሰውነት ክፍላችን ላይ ጉዳት ስለሚያደርሱ 'መልቲፕል' የሚል ስያሜን አግኝተዋል። በዚህ ካንሰር የተያዙ ሰዎች ተጨማሪ ምልክት ከማሳየታቸው በፊት ቀድሞ የጀርባ ሕመም ይኖራቸዋል። ይህ ምናልባት በሚተኙበት ወቅት ምቾት በማጣት የሚፈጠር ሊሆን ይችላል። ካልሆነም በስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ ጠንካራ ልምምድ ከማድረግ ወይንም ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ። በንግድ ሥራ የተሰማራው የ37 ዓመቱ ሉዊዝ ፈርናንዶ ፎንቴኔል በርካታ የህክምና ምርመራዎችን እና ክትትሎችን ካደረገ በኋላ ነው በዚህ የካንሰር ዓይነት መያዙ የታወቀው። “በጣም ነበር ሕመም የሚሰማኝ። ነገር ግን የመጀመሪያው ስብራት ከሰባት ወር በፊት ካጋጠመኝ በኋላ ነው ሕክምና ያገኘሁት።  ስለ ሕመሜ ያለኝን ጥርጣሬ ያነሳሁት እኔ ራሴው ነኝ። ኢንተርኔት ላይ የተወሰነ ነገር አንብቤ ስለነበር"" በማለት ያስታውሳል። ልክ ሉዊዝ ፈርናንዶ እንዳጋጠመው ሁሉ፣ ይህ የካንሰር ዓይነት የአጥንትን ጥንካሬ በማዳከም ስብራት ሊከተል ይችላል። ይህ ደግሞ የሚከሰተው ከፍተኛ የፕላዝማ ሴሎች በመቅኒ ውስጥ እንዲፈጠሩ በማድረግ የሄማቶፖየቲክ ህዋሳት ሲቀንሱ ነው። በዚህ የካንሰር ዓይነት የተነሳም የኩላሊት ሥራ ሊስተጓጎል ይችላል። ምንም እንኳ ይህ የካንሰር ዓይነት በብዛት የሚያጋጥም ባይሆንም፣ ከደም የካንሰር ዓ���ነቶች መካከል በመከሰት ሁለተኛው ነው። በብራዚል ከ100 ሺህ ሰዎች መካከል አራቱ በዚህ የካንሰር ዓይነት ሊያዙ ይችላሉ ተብሎ ይገመታል። ይህም ማለት በየዓመቱ 7600 አዳዲስ በዚህ ካንሰር የሚያዙ ሰዎች ይኖራሉ። ይህ የካንሰር ዓይነት እድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑ ሰዎቸን የሚያጠቃ ቢሆንም በወጣቶችም ላይ ታይቶ ይታወቃል። መልቲፕል ማይሎማ በሽንት አልያም በደም ምርመራ ሊታወቅ እችላል። መልቲፕል ማይሎማ ፈጽሞ የሚፈውስ መድኃኒት ባይኖርም፣ ነገር ግን በዚህ የካንሰር ዓይነት የተያዙ ግለሰቦች ረዥም ጊዜ ጤናቸው ተሻሽሎ መኖር እንዲችሉ ማድረግ እንደሚቻል የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። በይበልጥ ቀድሞ የተደረሰበት ከሆነ የግለሰቦችን ጤና የበለጠ አደጋ ላይ ከመጣሉ በፊት ለመከላከል እንደሚቻል ያስረዳሉ። ይህንን የካንሰር ዓይነት ለማከም ኬሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን የመቅኒ ንቅለ ተከላ በማካሄድ ሕክምናው ይሰጣል። ሉዊዝ ፈርናንዶ የመቅኒ ንቅለ ተከላ ቢያካሄድም ሕመሙ ዳግም አገርሽቶበት መሰቃየቱን ያስታውሳል። ከ28 ዓመቴ ጀምሮ ከሕመም ውጪ ያሳለፍኩበትን ቀን አላስታውስም የሚለው ሉዊዝ፣ 28 ቀናት በሆስፒታል 21 ቀናት ደግሞ ቤቱ ሆኖ የተለያዩ መድኃኒቶችን ቅንብር እየወሰደ እና ክትትል እየተደረገለት ሕክምናውን አካሂዷል። በዓመታት ውስጥ ከበሽታው ጋር ተዋውቆ እንዴት መኖር እንዳለበት የተረዳው ሉዊዝ አሁን በተሻለ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ያስረዳል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cw4pxx87kyeo +sports ሁለቱንም እጆቹን ያጣው ቻይናዊ አራት የፓራ ኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎችን ሰበሰበ ቻይናዊው የፓራ ዋናተኛው ዤንግ ታኦ በቶኪዮ ፓራ ኦሎምፒክ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማሸነፉና ክብረ ወሰኖችን መስበሩ በርካቶችን እያስገረመ ይገኛል። ዤንግ አካል ጉዳተኛ ሲሆን ሁለቱንም እጀቹን አጥቷል። ''ልጄ ተመልከቺ፤ ምንም እንኳን እጆች ባይኖሩኝም በጣም ፈጣን ዋናተኛ ነኝ'' ብሏል ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ ለሴት ልጁ በላከው የተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክት። ዤንግ ገና ታዳጊ ሳለ ነበር በኤሌክትሪክ ሾክ ምክንያት ሁለቱንም እጆቹን ያጣው። በቶኪዮ ፓራ ኦሎምፒክ ድሞ በነጻ ቀዘፋ፣ ባክስትሮክ እንዲሁም በተርፍላይ ዘርፎች የበላይነትን መውሰድ ችሏል። ሁሉም ድሎቹ ደግሞ በዓለም እና በፓራ ኦሎምፒክ ክብረ ወሰን ሆነው ተመዝግበዋል። ረቡዕ ዕለት በ50 ሜትር ነጻ ቀዘፋ በማሸነፍ የውድድሩን ክብረ ወሰን በእጁ ማስገባት የቻለ ሲሆን ያሸነፈውም የወርቅ ሜዳሊያ ለአገሩ ቻይና በፓራ ኦሎምፒክ ያገኘችው 500ኛ የወርቅ ሜዳሊያ ሆኖ ተመዝግቧል። በዚህም በርካታ ቻይናውያን በማህበራዊ ሚዲያዎች በኩል ለዤንግ ያላቸውን ክብርና ፍቅር ሲገልጹለት ነበር። ቻይና የመጀመሪያውን የፓራ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊኦኣ ማግኘት የቻለችው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1984 ላይ ኒው ዮርክ ውስጥ በተካሄደው ውድድር ነበር። ዤንግ ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃል '' ይህ ውድድር የቶኪዮ የመጨረሻዬ ስለሆነ ያለኝን አቅም ሁሉ ሰብስቤ እንዲሁም ያለምንም ቁጭት ነው የተፎካከርኩት። እንደሚመስለኝ በህይወቴ ምርጡ ውድድር ነበር'' ብሏል። ሰኞ ዕለት ደግሞ ዤንግ በ50 ሜትር የጀርባ ቀዘፋ የፍጻሜ ውድድርን በ31.42 ሰከንዶች በሆነ ሰአት በማጠናቀቅ የዓለም ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ችሏል። ድሉን ተከትሎም ዤንግ ለሁለት ዓመት ሴት ልጁ ባስተላለፈው ስሜታዊ የተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክት ተከትሎ በርካቶች ማበረታቻና አድናቆታቸውን እያጎረፉለት ይገኛሉ። ዤንግ ውድድሩን ለመጀመርና በኃይል ለመወርወር ከገንዳው ፊትለፊት ከሚገኝ ብረት ጋት የተያያዘ ፎጣ በጥርሱ በመያዝ የተጠቀመ ሲሆን በርካታ የምህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም ድፍረቱን እና ጥንካሬውን እየገለጹ አድናቆታቸውን አጉርፈውለታል። አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ደግሞ ዤንግ ለቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅት በሚያደርግበት ወቅት በየቀኑ የ10 ኪሎሜትር ዋና ያደርግ ነበር። ገና የ13 ዓመት ታዳጊ ሳለ ወደ ውሃ ዋና ስፖርት የገባው ዤንግ በዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደር የጀመረው ደግሞ ከስድስት በኋላ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ በፓራ ኦሎምፒክ የተሳተፈው ደግሞ በአውሮፓውያኑ 2012 በተካሄደው የለንደን ኦሎምፒክ ሲሆን እስካሁን ድረስ ደግሞ 9 ሜዳሊያዎችን ሰብስቧል። https://www.bbc.com/amharic/news-58452725 +politics በሞቃዲሾ የተከሰተው ውጊያ የለየለት ጦርነት እንዳይቀሰቅስ አስግቷል በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በሁለት ተጻራሪ ኃይሎች መካከል ውጊያ ተካሄደ። ትናንት እሁድ ከአገሪቱ ቤተ መንግሥቱት አቅራቢያ የከባባድ መሣሪያዎች ድምጽና የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አመላክተዋል። ሞርታር ጭምር የፕሬዝዳንቱ መቀመጫ ወደሆነው ቤተ መንግሥት ስለመተኮሱ ተሰምቷል። ውጊያው ምናልባትም ፕሬዝዳንት ፋርማጆን በሚደግፉና በሚቃወሙ የሠራዊት አካላት አልያም በታጣቂዎች መካከል ሳይካሄድ እንዳልቀረ ተጠርጥሯል። ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ወይም (ይበልጥ የሚታወቁበት ስማቸው ፋርማጆ) የሥልጣን ዘመናቸውን በሁለት ዓመት ማራዘማቸው እያነጋገረ ነበር። የፋርማጆ የሥልጣን ዘመን ባለፈው የካቲት ወር ማብቃት ነበረበት። የፋርማጆ ሥልጣናቸውን ማራዘም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ እየተወገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ሕብረትም ሆነ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፋርማጆ ውሳኔ እንዳሳሰባቸው ከመግለጽ አልተቆጠቡም። ትናንት እሁድ በወጡ አንዳንድ ዘገባዎች እንደተመላከተው በአንዳንድ አካባቢዎች የተነሱ አለመግባባቶች እየሰፉ ሄደው ማዕከላዊ ሞቃዲሾን ሲያምሱ ውለዋል። አንዳንድ የአገሬው መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ ግጭቱ በዋናነት የፋርማጆን መንግሥት በሚደግፉና በሚቃወሙ ታጣቂ ኃይሎች መካከል የተደረገ ነበር። የጎሣ መሪዎችም በግጭቱ ተሳትፎ ነበራቸው። እስከአሁን በትናንቱ ግጭት ስለደረሰው ጉዳት የተባለ ነገር የለም። የግል የሆነው 'ካሲማዳ' የወሬ ድረ ገጽ እንዳለው ጸረ ፋርማጆ ሰልፈኞች ወደ ጎዳና ወጥተው ጎማ ያቃጠሉ ሲሆን፤ አማጺ ወታደሮችም የተወሰኑ የሞቃዲሾ ሰሜናዊ ሰፈሮችን መቆጣጠር ችለው ነበር። የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ማህሙድ እና የተቃዋሚ መሪው አብዱራህማን አብዲሺኩር የመንግሥት ደጋፊ ታጣቂዎች ቤቶቻቸው ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ተናግረዋል። በተለይ አብዱሺኩር በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ እንደጻፉት መከላከያ ኃይሉን ፖለቲካ ውስጥ ማስገባት አደጋ አለው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ትናንት ከሰዓት የሶማሊያ ደኅንነት ሚኒስትር ሐሰን ሐነደበይ ጂማሌ ስማቸውን ያልጠቀሷቸው አገሮች ከግጭቱ ጀርባ እንዳሉ አስታውቀዋል። እጃቸውን እንዲሰበስቡም አሳስበዋል። የደኅንነት ሚኒስትሩ በቴሌቪዥን ወጥተው እንደተናገሩት ታጣቂ ቡድን ወደ ሞቃዲሾ ተሰማርቶ አገሪቱን ለማመስ ተልዕኮ ተሰጥቶት ነበር። ሆኖም አክሽፈነዋል ብለዋል። ሶማሊያ ለአስርታት በጦርነት ስትታመስ የቆየች አገር ናት። ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ ግን የመረጋጋት ዝንባሌን ስታሳይ ቆይታለች። የፋርማጆ መንግሥትም የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ ያለው ሆኖ ቆይቷል። ሆኖም የፋርማጆ ሕጋዊ የግዛት ዘመን በየካቲት ማብቃቱን ተከትሎ ምርጫ መዘግየቱ ያቺን አገር ወደለየለት ግጭት ውሰጥ እንዳይከታት ተሰግቷል። በሶማሊያ ምርጫ የሚካሄድበት መ��ገድ ከተመለደው ወጣ ያለና የተወሳሰበ ነው። በሶማሊያ የቀጥታ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሳይሆን የሚደረገው የጎሳ መሪዎች የሕዝብ ተወካዮችን ከመረጡ በኋላ የተመረጡት የሕዝብ ተወካዮች ናቸው ፕሬዝዳንቱን የሚመርጡት። https://www.bbc.com/amharic/news-56884281 +health ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በድጋሚ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆኑ "ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለማችንን ትልቁን የጤና ተቋም የዓለም የጤና ድርጅትን ለሁለተኛ ዙር እንዲመሩ ዳግም ተመረጡ። የዶ/ር ቴድሮስ ብቸኛ ዕጩ ሆነው ዳግም መመረጣቸው የተረጋገጠው በጄኔቫ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የዓለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉብዔ ላይ ነው። ዶክተር ቴድሮስ ያለተፎካካሪ በብቸኛ ዕጩነት በቀረቡበት መድረክ ላይ ከተለያዩ የድርጅቱ አባል አገራት ለዕጪነት ለተሰጣቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። የዋና ዳይሬክተሩ ምርጫን በመደገፍ በቦትሰዋናው ተወካይ በኩል የአፍሪካ አገራት ቡድንን በመወከል ሊቀርብ የነበረውን መግለጫ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተቃውመውታል። በዚህም 45 የአፍሪካ አገራት ድጋፍ በሚል ቦትሰዋና ለዶ/ር ቴድሮስ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት እና የመልካም የሥራ ጊዜ ምኞት አስተላልፈዋል። ዶ/ር ቴድሮስ ያለፉት አምስት ዓመታት የተባበሩት መንግሥት ጤና ድርጅት ሲመሩ ቆይተዋል። በዚህ ወቅት የኮቪድ-19 ስርጭት እና ተቋማቸው ከቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የገባው ውዝግብ የሥልጣን ዘመናቸውን ፈታኝ ከዳረጉት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። የዓለም ጤና ዳይሬክተሩ መመረጣቸውን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ""በእኔ ላይ ላላችሁ መተማመን እና ለጣላችሁብኝ እምነት አመሰግናለሁ"" ብለዋል። ዶ/ር ቴድሮስ ተቋሙን በይፋ ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ለሁለተኛ ዙር መምራት ይጀምራሉ። ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከመመረጣቸው በፊት እአአ ከ2012 እስከ 2016 ድረስ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከዚያ ቀደም ብሎ ደግሞ ለበርካታ ዓመታት የአገሪቱ የጤና ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። ዶ/ር ቴድሮስ የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር ሆነው ባገለገሉባቸው ዓመታት በኢትዮጵያ የጤና መሠረታዊ አገልግሎቶች መስፋፋታቸው እና የሕጻናት እና እናቶች ሞት መጠን መቀነሱ ይገለጻል። ዋና ዳይሬክተሩ በመጀመሪያው ዙር የዓለም ጤና ድርጅት የመሪነት ዘመናቸው ከገጠሟቸው ፈተናዎች መካከል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋር ጦርነት በገጠመበት ጊዜ ለቡድኑ ድጋፍ ይሰጣሉ በሚል ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ከሰዋቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61568901 +health በአሜሪካ ሲካሄድ የነበረ የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ተቋረጠ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ሲያካሂድ የነበረውን ምርምር አንድ በጎ ፍቃደኛ መታመሙን ተከትሎ ማቋረጡን አስታወቀ። ኩባንያው እንዳለው በክትባት ሙከራው ላይ እየተሳተፈ የነበረው በጎ ፍቃደኛ የጤና እክል የገጠመው ክትባት ለማግኘት ከሚደረገው ምርምር ጋር ተያይዞ ስለመሆኑ ይጣራል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፍቃደኞች በሚሳተፉበት ምርምር ላይ በጎ ፍቃደኞች የጤና እክል ሊገጥማቸው እንደሚችል ኩባንያው አስታውሶ፤ ለጥንቃቄ ሲባል ሶስተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው የሙከራ ምርምሩ እንቋዲረጥ ተደርጓል ብሏል። የበጎ ፍቃደኛውን ግላዊ መብት ለመጠበቅ ሲባል የተሳታፊው ማንነት እና ያጋጠመው ህመም እንደማይገለጽ ተጠቁሟል። የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ እንዲቋረጥ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በዩናይትድ ኪንግደም በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና አስትራ ዜኔካ ጥምረት ሲካሄድ የነበረው ም��ምር ላይ አንድ በጎ ፍቃደኛ ላይ የጤና መቃወስ ማጋጠሙን ተከትሎ ሙከራው ከተቋረጠ በኋላ ምርምሩ እንደገና መጀመሩ ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ከ180 በላይ የኮሮናቫይረስ ክትባት ምርምሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ አንዳቸውም የክሊኒካል ሙከራቸውን ማጠናቀቅ አልቻሉም። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ኩባንያ እያካሄደ ያለው የኮሮናቫይረስ ምርምር ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና አስትራ ዜኔካ የደረሱበት ደረጃ ላይ መድረስ የቻለ ነበር። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ሲያካሂድ በነበረው የምርምር ስራ ላይ በጎ ፍቃደኞችን መመልመል የጀመረው መስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ነበር። ሙከራው 60ሺህ ተሳታፊዎችን በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ያሳትፋል ተብሎ ነበር። https://www.bbc.com/amharic/54526621 +sports የዓለማችን ኮከብ አትሌት ሞ ፋራህ ለዘመናት የደበቀውን ምስጢር ይፋ አወጣ ከዓለማችን ኮከብ አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው ሞ ፋራህ በህፃንነቱ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መወሰዱን እና ለአስገዳጅ የጉልበት ብዝበዛ መጋለጡን ይፋ አደረገ። በስፖርቱ ዘርፍ ለዩናይትድ ኪንግደም ባበረከተው አስተዋጽኦ በአገሪቱ ከፍተኛ ማዕረግ የሆነውን ‘ሰር’ የሚለውን መለያ ያገኘው ሞ ፋራህ ስሙ በወላጆቹ የተሰጠው ሳይሆን ሐሰተኛ ነው ብሏል። ፋራህ በህጻናት ላይ የሚደርሰውን የጉልበት ብዝባዛ ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት እውነተኛ ታሪኩን ይፋ በማውጣወት ያለፈበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለቢቢሲ ተርኳል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cyrkz71kx1do +health የታንዛኒያው ፕሬዝደንት የኮቪድ-19 ክትባት ለታንዛኒያውያን አያስፈልግም አሉ "የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ የአገሪቱ ጤና ባለስልጣናት የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመጠቀም ከመወሰናቸው በፊት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው አሉ። ማጉፉሊ ምንም አይነት ማረጋገጫ ሳያቀርቡ የኮቪድ-19 ክትባት ሕዝቡን ሊጎዳ ይችላል ብለዋል። ""የጤና ሚንስቴር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ጥናቶችን ሳያከናውኑ እነዚህን ክትባቶች ለመሞከር መፍጠን የለባቸውም። ሁሉም ክትባት ለእኛ ጠቃሚ አይደሉም፤ መጠንቀቅ አለብን። መሞከሪያ መሆን የለብንም"" ሲሉ ማጉፉሊ ተናግረዋል። ""ክትባቶች አደገኛ ናቸው። ነጩ ሰውዬ ክትባት አገኘሁ ካለ፤ ለኤድስ፣ ለካንሰር እና ለቲቢ እስካሁን ክትባት ሊኖረው ይገባል።"" ፕሬዝደንቱ ይህን ይበሉ እንጂ የኮቪድ-19 ክትባቶች ለሰው ልጆች እንዲሰጡ የተፈቀደው በርካታ ምርመሮች እና ሙከራዎች ከተከናወነባቸው በኋላ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ተሞክረው፣ ደህንነታቸው ተረጋግጦ፣ በመድሃኒት ተቆጣጣሪ አካላት ፍቃድ በማግኘታቸው ነው ለሰዎች እየተሰጡ ያሉት በማለት የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ ፊሊፓ ሮክስቢይ ትናገራለች። ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ግን ዜጎቻቸውን ይህን ክትባት ከመውሰዳቸው በፊት ጥንቃቄ አድርጉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ከክትባት ይልቅ ጸሎት ማድረግ እና ለባህላዊ መድሃኒት ቅድሚያ መስጠት የተሻለ አማራጭ ነው ሲሉ ታንዛኒያውያንን መክረዋል። ""በርካታ አገራት የእንቅስቃሴ ገደቦችን አስተዋውቀዋል። በታንዛኒያ ግን የሰዎችን እንቅስቃሴ የመገደብ እቅድ የለንም። ፈጣሪያችን በሕይወት አለ፤ እርሱ ይጠብቀናል"" ሲሉ ተደምጠዋል። ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ከወራት በፊት ታንዛኒያ ከኮቪድ-19 ነጻ ሆናለች ብለው ያወጁ ሲሆን፤ በከተሞች አከባቢ ስለጨመረው የሰዎች ሞት ቁጥር ላይ ግን ያሉት ነገር የለም። ማጉፉሊ አባል የሆኑበት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ባወጣው መግለጫ ግን፤ ታንዛኒያ መጀመሪያ ላይ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር ቢቻላትም አሁን ላይ ግን የቫይረሱ ስርጭት እንደ አዲስ መስፋፋቱን አስታውቋል። የታንዛኒያ ጤና ሚንስቴር በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ፣ የሚሞቱ እና የሚያገግሙ ሰዎች አሃዝን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ካቆመ ወራቶች አልፈዋል።" https://www.bbc.com/amharic/55825410 +health ሲዲሲ የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰራጭበት መንገድ ላይ የአሜሪካ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ አሳሰበ የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) የአሜሪካ ግዛቶች የጤና ኃላፊዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት የበለጠ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ቀድሞ የሚታደልበት አማራጭ ላይ ቀድመው እንዲዘጋጁ ማሳሰቡ ተነገረ። ሲዲሲ ትናንት በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው ጽሑፍ ላይ ክትባቱ ለበሽታው የበለጠ ተጋለጭ ለሆኑ ሰዎች እስከ ጥቅምት አጋማሽ ሊሰራጭ እንደሚችል ጠቁሟል። “ሲዲሲ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ በማሰብ ዝግጁ ሊሆን የሚችል የክትባት መጠን እና ጊዜን ለግዛቶች አሳውቋል። ከጥቅምት አጋማሽ እስከ ሕዳር መጨረሻ ድረስ መጠናቸው አነስተኛ ቢሆንም የክትባት ስርጭት ሊኖር ይችላል” ሲሉ የሲዲሲ ቃል አቀባይ ለሬውተርስ ተናግረዋል። ኒው ዮርክ ታይመስ ደግሞ ቀደም ሲል ሲዲሲ ከሁሉም 50 የአሜሪካ ግዛቶች እና አምስት ግዙፍ ከተሞች ከስርጭት ጋር ተያይዞ ያሉ የእቅድ መረጃዎችን ጠይቋል። በኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ላይ ሲዲሲ ጥቅምት አጋማሽ ላይ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ አንድ ወይም ሁለት የኮቪድ-19 ክትባቶች ለስርጭት ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል። ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ ናቸው ለተባሉ እንደ የጤና ባለሙያዎች፣ ለደህንነት ሰራተኞች እና እድሜያቸው የገፉ ሰዎችን የሚንከባከቡ ነርሶች እና ባልደረቦች ክትባቱ ያለ ክፍያ ይሰጣቸዋል ይላል የሲዲሲው ዶክመንት። የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒዮ ፋውቺ ለኤምኤስኤንቢሲ ቴሌቪዥን ትናንት ሲናገሩ፤ ለኮቪድ-19 ክትባት ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥርን ከግምት በማስገባት እስከ ሕዳር ወር ድረስ የትኛው የኮቪድ-19 ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ይቻላል ብለዋል። ሞደርና፣ አስትራዜኔካ እና ፐፊዘር የተሰኙ መድሃኒት አምራቾች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ የሆነ የኮቪድ-19 ክትባት ለማዘጋጀት ጥረት ላይ ይገኛሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-54012503 +sports ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕሪምየር አሸናፊ ሆነ "ማንችስተር ሲቲ በአራት ዓመታት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆኗል። ትናንት ምሽት በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ በሌስተር ሲቲ መሸነፉን ተከትሎ ነው ሲቲዎች አሸናፊነታቸውን ያረጋገጡት። የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን አሸናፊነቱን ያረጋገጠው ሦስት ጨዋታዎች እየቀሩ ከማንችስር ዩናትድ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት10 በመሆኑ ነው። ማንችስተር ሲቲ የዘንድሮውን ጨምሮ በአጠቃላይ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሰባት ጊዜ አሸናፊ መሆን ችለዋል። ይህ ደግሞ በዘጠኝ ዓመት ውስጥ አምስተኛ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫቸው ነው። ''በጣም አስገራሚና ከሌሎች ጊዜዎች በጣም የተለየ ድል ነው'' ብሏል ጋርዲዮላ። ''የዘንድሮው በጣም ከባድ ነበር። መቼም ቢሆን የዘንድሮውን ድላችንን እናስታውሰዋለን። የዚህ ቡድን እና የነዚህ ተጫዋቾች አሰልጣኝ በመሆኔ በጣም ኩራት ይሰማኛል። . . . 'ከዚህ በፊት ስፔን አሰልጥኛለሁ፣ ጀርመንም አሰልጥኛለሁ፤ ነገር ግን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በጣም ከባዱ ነው'' ብሏል ጋርዲዮላ። 50ኛ ዓመቱን የደፈነው ፔፕ ጋርዲዮላ በአውሮፓውያኑ 2016 የጀርመኑን ባየርን ሙኒክ ለቆ ነበር ወደ እንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ የመጣው። በእነዚህ ስምንት ዓመታት ደግሞ 8 ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል። ሲቲዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ የነበራቸውን ጨዋታ አሸንፈው ቢሆን ቀደም ብለው ዋንጫውን ማንሳተቸውን ማረጋገጥ ይችሉ የነበረ ቢሆንም በቼልሲ ሁለት ለአንድ ተሸንፈዋል። ማንችስተር ሲቲዎች ከሳምንታት በፊት በካራባዎ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ቶተንሀምን በማሸነፍ ዋንጫውን ማንሳት የቻሉ ሲሆን በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ደግሞ ከቼልሲ ጋር ይገናኛሉ። ሲቲዎች በሚቀጥለው ሳምንት ከኤቨርተን ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ የሚያነሱ ሲሆን በአዲሱ መመሪያ መሰረት ደግሞ እስከ 10 ሺ የሚደርሱ ደጋፊዎች ገብተው ጨዋታውንና ስነ-ስርአቱን መከታተል ይችላሉ። የማንችስተር ሲቲ አምበል ብራዚላዊው ፈርናንዲንሆነ ቡድኑን መምራት 'ትልቅ ክብር' እንደነበር ገልጿል። ''ይህን ዋንጫ በማንሳታችን በጣም ኮርቻለሁ፤ በጣም ተደስቻለሁ። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከዓለማችን በጣም ከባዱ ሊግ ነው። እያንዳንዱ ጨዋታ በጣም ከባድ ነው። ዋንጫውን ማንሳታችን ለእኔም ሆነ ለመላው ቡድኑ ትልቅ ስኬት ነው'' ብሏል። ሲቲን በቅርብ ርቀት ሲከታተል የነበረው የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኙ ሶልሻየር በበኩሉ ""የውድድር ዓመቱ ሊጠናቀቅ 10 እና 12 ቀናት እስከሚቀሩት ድረስ ተፎክረናል። ማንችስተር ሲቲ በጣም ምርጥ ቡድን ነበር'' ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/57084282 +health የታንዛኒያው ፕሬዝደንት የኮቪድ-19 ክትባት ለታንዛኒያውያን አያስፈልግም አሉ "የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ የአገሪቱ ጤና ባለስልጣናት የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመጠቀም ከመወሰናቸው በፊት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው አሉ። ማጉፉሊ ምንም አይነት ማረጋገጫ ሳያቀርቡ የኮቪድ-19 ክትባት ሕዝቡን ሊጎዳ ይችላል ብለዋል። ""የጤና ሚንስቴር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ጥናቶችን ሳያከናውኑ እነዚህን ክትባቶች ለመሞከር መፍጠን የለባቸውም። ሁሉም ክትባት ለእኛ ጠቃሚ አይደሉም፤ መጠንቀቅ አለብን። መሞከሪያ መሆን የለብንም"" ሲሉ ማጉፉሊ ተናግረዋል። ""ክትባቶች አደገኛ ናቸው። ነጩ ሰውዬ ክትባት አገኘሁ ካለ፤ ለኤድስ፣ ለካንሰር እና ለቲቢ እስካሁን ክትባት ሊኖረው ይገባል።"" ፕሬዝደንቱ ይህን ይበሉ እንጂ የኮቪድ-19 ክትባቶች ለሰው ልጆች እንዲሰጡ የተፈቀደው በርካታ ምርመሮች እና ሙከራዎች ከተከናወነባቸው በኋላ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ተሞክረው፣ ደህንነታቸው ተረጋግጦ፣ በመድሃኒት ተቆጣጣሪ አካላት ፍቃድ በማግኘታቸው ነው ለሰዎች እየተሰጡ ያሉት በማለት የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ ፊሊፓ ሮክስቢይ ትናገራለች። ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ግን ዜጎቻቸውን ይህን ክትባት ከመውሰዳቸው በፊት ጥንቃቄ አድርጉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ከክትባት ይልቅ ጸሎት ማድረግ እና ለባህላዊ መድሃኒት ቅድሚያ መስጠት የተሻለ አማራጭ ነው ሲሉ ታንዛኒያውያንን መክረዋል። ""በርካታ አገራት የእንቅስቃሴ ገደቦችን አስተዋውቀዋል። በታንዛኒያ ግን የሰዎችን እንቅስቃሴ የመገደብ እቅድ የለንም። ፈጣሪያችን በሕይወት አለ፤ እርሱ ይጠብቀናል"" ሲሉ ተደምጠዋል። ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ከወራት በፊት ታንዛኒያ ከኮቪድ-19 ነጻ ሆናለች ብለው ያወጁ ሲሆን፤ በከተሞች አከባቢ ስለጨመረው የሰዎች ሞት ቁጥር ላይ ግን ያሉት ነገር የለም። ማጉፉሊ አባል የሆኑበት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ባወጣው መግለጫ ግን፤ ታንዛኒያ መጀመሪያ ላይ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር ቢቻላትም አሁን ላይ ግን የቫይረሱ ስርጭት እንደ አዲስ መስፋፋቱን አስታውቋል። የታንዛኒያ ጤና ሚንስቴር በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ፣ የሚሞቱ እና የሚያገግሙ ሰዎች አሃዝን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ካቆመ ወራቶች አልፈዋል።" https://www.bbc.com/amharic/55825410 +sports ስኮትላንድ እግር ኳ�� ተጫዋቾች ‘የቴስታ’ ኳሶችን እንዳይመቱ ልታግድ ነው በስኮትላንድ ያሉ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ከጨዋታ አንድ ቀን በፊት እና በኋላ ኳስ በጭንቅላት (በቴስታ) እንዳይመቱ ሊታገዱ ነው። ክለቦችም የጭንቃላት ኳስ የሚበዛባቸው የልምምድ ቀኖችን በሳምንት ወደ አንድ እንዲቀንሱ ተጠይቀዋል። ውሳኔው የግላስጎው ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ጥናት እግር ኳስ ተጫዋቾች ከሦስት እጥፍ በላይ ከጭንቅላት ጋር በተያያዘ በሽታ እንደሚሞቱ ማሳየቱን ተከትሎ የመጣ ነው። ባለሙያዎች ችግሩ ኳስን በተደጋጋገሚ በጭንቅላት ከመምታት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ጠቁመዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ ማኅበር ከ12 ዓመት በታች ቡድኖች በልምምድ ወቅት ኳስ በጭንቅላት እንዳይመቱ የሚያግድ ሕግ አለው። አዲሱ ሕግ በአገሪቱ ካሉ 50 የወንዶች እና የሴቶች የእግር ኳስ ክለቦች ጋር ውይይት በማድረግ እና የእግር ኳስ ማኅበሩ በጭንቅላት ኳስ ዙሪያ መረጃ ከሰበሰበ በኋላ ይተገበራል ተብሏል። ክለቦችም በልምምድ ወቅት የጭንቅላት ኳሶችን ሁኔታ በድንብ እንዲያጤኑ ተነግሯቸዋል። ዶክተር ጆን ማሊን ከ20 ዓመታት በላይ የስኮትላንድ እግር ኳስ ማኅበር ሐኪም ሆነው አገልግለዋል። በ2019 በተካሄደው እና የቀድሞ ተጫዋቾችን ከዲሜንሺያ (የጭንቅላት ህመም ሲሆን ከመርሳት እና ከማንነት ለውጥ ጋር ይያያዛል) ጋር ባያያዘው ጥናት ተሳትፈዋል። “ጥናቶቹ እየተጠናከሩ ቢሆንም እስካሁን ባለው ከ24 እስከ 48 ሰዓታት የሚቆይ የመርሳት ችግርን ያስከትላል። ኳስ በጭንቅላት ከተመታ በኋላ የአዕምሮ ፕሮቲኖች በደም ናሙና ውስጥ ተገኝተዋል።” “የጭንቅላት ኳስ የሚመቱ ተጫዋቾች የአዕምሮ ስካን ላይ ለውጥም ታይቷል። ስለዚህ ዋና ዓላማው በልምምድ ቦታ የጭንቅላት ኳሶችን በመቀነስ በጊዜ ሂደት የሚመጣውን ጉዳት መቀነስ ነው” ብለዋል። በአዲሱ ሕግ መሠረት ከጨዋታ በፊት የሚኖሩ የቅጣት ምትን ጨምሮ የጭንቅላት ኳስን የሚያካትቱ ልምምዶች ላይ ለውጥ ያመጣል። “ባለድርሻ አካላትን ለማካተት በሚል ጊዜ ወስደናል” ብለዋል ዶ/ር ማክሊን። “መሠረታዊ መረጃ ለማግኘት በልምምድ ወቅት ምን ያህል የጭንቅላት ኳስ እንደሚኖር ለማወቅ እንፈልጋለን።” “በቀመጠልም ከማኅበሩ፣ ከክለቦች እና ከአሰልጣኞች ጋር በመሆን ተጫዋቾችን እናሳትፋለን” ብለዋል። “ይህ የጋራ ኃላፊነት ሲሆን የተጫዋቾችንም ጤና ለመጠበቅ ያለመ ነው” ሲሉ አስረድተዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ ማኅበር ዋና ኃላፊ አንዲ ጎልድ እንዳሉት በጨዋታ ወቅት ስላለው የጭንቅላት ኳስ በቂ መረጃ አለ። የቅርብ ጊዜው ምርምር ግን “በልምምድ ወቅት የጭንቅላት ላይ ያለውን ጫና ለመረዳት በጣም ጠቃሚ ነው” ብለዋል። አክለውም “ለተጫዋቾቻን ጤና ሲባል በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውይይት ለማመቻቸት የሚያስፈልጉ መረጃዎችን እና አመለካከቶችን ስለሰጡን ክለቦችን፣ አሰልጣኞችን እና ተጫዋቾችን አመሰግናለሁ።” በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት መጀመሪያ ላይ የእንግሊዝ የእግር ኳስ ማኅበር በልምምድ ወቅት ተጫዋቾች በሳምንት 10 ከፍተኛ ተፅእኖ ያላቸውን የጭንቅላት ኳሶች ብቻ እንዲጠቀሙ የሚገድብ መመሪያ ለክለቦች አውጥቷል። የቀድሞ የሴልቲክ አምበል ቢሊ ማክኔል እና ከእንግሊዝ ጋር የዓለም ዋንጫን አነስቶ የነበረውና በኋላም የአየርላንድ ሪፐብሊክ አሰልጣኝ ለመሆን የቻለው ጃክ ቻርልተንን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ የቀድሞ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በዲሜንሽያ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0jy82pyl2o +politics ሩሲያ በዩክሬን ላይ 'መጠነ ሰፊ ጥቃት ልትፈፅም' እንደምትችል አሜሪካ አስታወቀች "የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን ከፍተኛ ውጥረት የነገሰባት ዩክሬንን በተመለከተ በመጪው ማክሰኞ በቪዲዮ እንደሚነጋገሩ ዋይት ሃውስ አስታውቋል። ከሰሞኑ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሩሲያ በዩክሬን ላይ ""መጠነ ሰፊ ጥቃት ለመፈጸም"" እቅድ እንዳወጣች የሚያሳይ ማስረጃ አገራቸው እንዳገኘች ገልጸዋል። ነገር ግን ፕሬዚዳንት ፑቲን ዩክሬንን ለመውረር የመጨረሻ ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ግልጽ አይደለም ሲሉም አክለዋል። ሩሲያ በበኩሏ የማጥቃትም ሆነ የመውረር ሃሳብን ውድቅ አድርጋ ዩክሬን ሰራዊቷን በከፍተኛ ሁኔታ እያጠናከረች ነው ስትል ከሳታለች። የዋይት ሀውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ጄን ፓሳኪ ቅዳሜ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ ፕሬዚዳንት ባይደን ""ሩሲያንና ዩክሬንን በሚያዋስነው ድንበር ላይ ሩሲያ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ አሜሪካ ያላትን ስጋት እንዲሁም አሜሪካ ለዩክሬን ሉዓላዊነትና ግዛታዊ አንድነት የምታደርገውን ድጋፍ"" በተመለከተ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ጋር በሚያደርጉት የስልክ ልውውጥ ያነሳሉ ብለዋል። ዩክሬን በበኩሏ ሃገራቱ በሚዋሰኑበት ድንበር ላይ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች፣ የኤሌክትሮኒክ የጦር መሳሪያዎችን እና 94 ሺህ ወታደሮችን ሩሲያ ማሰማራቷን ገልጻለች። በአውሮፓውያኑ 2014 ሩሲያ የክሪሚያን ግዛት ከዩክሬን ከወሰደች በኋላ ከፍተኛ የጦር መሳሪያና ወታደር በጋራ ድንበሩ ላይ ስታሰማራ የመጀመሪያው ነው። የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር ኦሌክሲይ ሬዝኒኮቭ የደህንነት ዘገባዎችን በመጥቀስ ሩሲያ በጥር ወር መጨረሻ ወታደራዊ ጥቃትን ልትፈፅም እንደምትችል ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ያለው የሩስያ ጦር እንቅስቃሴ በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ቀደም ሲል ሻክሮ የነበረውን ግንኙነት የበለጠ ውጥረት እንዲነግስ አድርጎታል። በያዝነው ሳምንት አርብ ዕለት ፕሬዚዳንት ባይደን ""በርካቶችን እያስጨነቀ ያለውንና ሊያደርግ ይችላል ብለው እየጠበቁት"" ያለውን ጉዳይ ""አስቸጋሪ፣ በጣም ፈታኝ እንዲሆን አደርገዋለሁ"" ሲሉ ፑቲንን አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ ጠንከር ያለ እርምጃ ከወሰደች አሜሪካ እና የአውሮፓ አጋሮቿ ማዕቀብ ለመጣል ተወያይተዋል። ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ባትሆንም ከህብረቱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላት እና የአሜሪካ ጄቭሊን ፀረ ታንክ ሚሳኤሎችን ጨምሮ ከምዕራባውያን በርካታ የጦር መሳሪያዎች ድጋፎችን ታገኛለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-59537669 +health ለህሙማን ሌላ ህመም የሆነባቸው የመንግሥት ጤና ተቋማት ዋጋ ጭማሪ "ሠላማዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ናት። እናቷ ባለባቸው ህመም ምክንያት በየጊዜው ሐኪም ቤት ይመላለሳሉ። ሁሌም እንደምታደርገው እናቷ ላለባቸው ቀጠሮ በቅርቧ ወደሚገኘው ጤና ጣቢያ ይዛቸው ታቀናለች። ጤና ጣቢያውን ከቅርበቱም በላይ በዋጋውም ተመራጭ ነው። ስትደርስ የገጠማት ግን ከከዚህ በፊቱ የተለየ ነው። ዋጋው አይቀመስም። ካላቸው አቅም አንጻር ያልጠበቁትም ነው። ""5 ብር የነበረው የካርድ ዋጋ 50 ብር ደርሷል።"" ""ካርድ ብቻም አይደለም። ሁሉም የአገልግሎቶች ዋጋ ጨምሯል"" ትላለች ሠላማዊት። ህክምና ላይ ያለው ምርጫ ደግሞ አንድ ብቻ ነው፤ መታከም። ሠላማዊትም ወደ ግል የጤና ተቋም እንዳትሄድ ዋጋው ከዚህም ይብሳል። ""ያለኝ አማራጭ ስልክ ደውዬ ተጨማሪ ብር በብድር እንዲያመጡልኝ ማድረግ ነው"" ትላለች። ነጻ የነበሩ አገልግሎቶችም ዋጋ ተቆርጦላቸዋል። የመንግሥት የህክምና ተቋማት ዋጋ መናር አዲስ አበባ ላይ ብቻ አልታጠረም። ዶክተር ሱራፌል አየለ ይባላሉ። የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ሐኪም ናቸው። በሆስፒታሉ የአገልግሎት እና የህክምና ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ይ���ሉ። 'ትዕዛዙ ከፌዴራል የመጣ ነው' ያሉት ጭማሪ 'አስገራሚ' መሆኑን ለቢቢሲ አስረድተዋል። ""ካርድ ማውጫ 5 ብር ነበር፣ አሁን 60 ብር ነው። ተኝቶ ለመታከም የአልጋ ክፍያ በቀን ከ10 ብር ወደ 180 ብር አድጓል። የላብራቶሪ እና ሌሎች ወጪዎችም በተመሳሳይ ጨምሯል"" ብለዋል። እንደ ዶ/ር ሱራፌል ከሆነ ከዚህ ቀደም ነጻ የነበሩ አገልግሎቶችም ዋጋ ተቆርጦላቸዋል። ""በነጻ ተኝተው ይታከሙ የነበሩ የምግብ እጥረት ያለባቸው ታካሚዎች (SAM Patients) አሁን ከሌላው እኩል ለአልጋ 180 ብር እየከፈሉ ነው። ልጁ በድህነቱ ምክንያት ምግብ አጥቶ የቀጨጨበት ወላጅም በቀን 180 ብር እንዲከፍል ይደረጋል"" ይላሉ። ቢቢሲ ከተለያዩ ምንጮች ባደረገው ማጣራት በመንግሥት የህክምና ተቋማት የሚሰጡ ዋጋዎች ጭማሪ የተለያየ መሆኑን አረጋግጧል። ትኩረቱን በህክምና ባለሙያዎች ላይ ባደረገው ሐኪም በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ሐሳባቸውን ያሰፈሩት የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ዮናስ ላቀው 'የአማኑኤል ሆስፒታል የዋጋ ጭማሪ' በሚል ርዕስ የሚከተለውን አስቀምጠዋል። ""በፊት የካርድ 5 ብር የነበረው 50 ብር ሆኗል። ለተኝቶ ህክምና ማስያዣ 400 ብር የነበረው 9,000 ብር ሆኗል። ለአልጋ በቀን 3 ብር የነበረው 118 ብር ሆኗል።"" ከአዲስ አበባ የአማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ወደ ደግሞ ወራቤ እናቅና። ዶ/ር ፈድሉ ጀንፋ በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪም ናቸው። እርሳቸው በሚሠሩበት ሆስፒታሉም በተመሳሳይ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ይገልጻሉ። የዋጋ ጭማሪው በተለያዩ ደረጃ የሚገለጽ መሆኑን ጠቁመው ለምሳሌ ""የአልትራሳውንድ ዋጋ ከ150 ብር ወደ 300 ብር ከፍ ብሏል። ተኝቶ ታካሚዎች በቀን ለአልጋ ይከፍሉት የነበረው 47 ብር አሁን ወደ 170 ብር ከፍ ብሏል"" ይላሉ። የዋጋ ጭማሪው ሁሉንም አይመለከትም ይህንን የዋጋ ክለሳ ያደረገው ጤና ጥበቃ ሚንስትር መሆኑን የሚገልጹት ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ የኢትዮጵያ ጤና መድኅን ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ናቸው። ""ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው ዋጋ ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ እና ከቆይታ፣ ከዋጋና ከብር የመግዛት አቅም አንጻር መስተካከል እንደነበረበት ይጠበቃል"" ብለዋል። በተጨማሪም [በመንግሥት የጤና ተቋማት ላይ] አገልግሎት ላይ የሚቀርብ ቅሬታ አለ። ""ቅሬታውን ለመፍታት ደግሞ ሃብት ያስፈልጋል"" ይላሉ ወይዘሮ ፍሬይህይወት። ""በነበረው አሠራር ለህክምናው ዘርፍ ከሚወጣው ወጪ 60 ወይንም 70 በመቶ የሚሆነው በመንግሥት ነበር የሚሸፈነው። ቀሪው ነው በኅብረተሰቡ"" ብለዋል። የዋጋ ጭማሪው በጤና መድኅን ስር የታቀፉትን አይመለከትም። ዶ/ር ዮናስ ላቀው ""ይህ ለውጥ የጤና ሚኒስትር በደነገገው መመሪያ መሠረት ነው። የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ያላቸው ታካሚዎች አሁንም በነጻ አገልግሎት ያገኛሉ። የሌላቸው ግን አገልግሎት ለማግኘት ክፍያ መፈፀም ይጠበቅባቸዋል"" ብለዋል። በዚህ ምክንያት ህክምና ማግኘት የሚገባቸው ሰዎች እያገኙ አይደለም። ""የህሙማን ቁጥር መቀነስ እንዳለ ጠቅላላ ሐኪሞች (ጀነራል ፕራክቲሽነርስ) ይነግሩናል። ሆስፒታል ገብተው በመተኛት መታከም የሚገባቸው በገንዘቡ ምክንያት አልገቡም እንደሚባል ሰምቻለሁ"" ያሉት ዶ/ር ፈድሉ ናቸው። የታካሚዎች ቁጥር በመቀነሱ የሚስማሙት ዶ/ር ሱራፌል ""[ዋጋውን ሲያውቁ] በር ላይ ደርሰው ይመለሳሉ። አሁን አብዛኛዎቹ ታካሚዎች በዋጋ ጭማሪው ምክንያት እየተቸገሩ፣ ህክምና አቋርጠው ለመውጣት እየተገደዱ፣ አስፈላጊ መድሃኒቶችን ለመግዛት እና ምርመራዎችን ለማድረግ እየተቸገሩ ሲሆን የጤና መድኅን ተጠቃሚ የሆኑ ታካሚዎች ግን ያለ ምንም ችግር እየታከሙ ይገኛል"" ብለዋል። በጤና መድኅ�� እጦት ምክንያት ወደ ህክምና ተቋማት የሚመጣ ሰው በመቅረቱ ወይም በክፍያው ምክንያት ተገቢውን ህክምና ባለማግኘቱ ህይወት ልናጣ እንችላለን ሲሉ ሃሳቡን የሚደግፉት ዶ/ር ፈድሉ ናቸው። የጤና መድኅን ያላቸውም በፈለጉት ቦታ መታከም አልቻሉም ሌላው በህክምና ባለሙያዎች የተነሳው አሠራሩ ሊተገበር ስለመሆኑ ቀደም ተብሎ ለኅብረተሰቡ ማሳወቅ እና ዝግጅት እንዲኖር መደረግ ነበረበት የሚል ነው። አሠራሩን ተግባራዊ ከማድረግ በፊት ኅብረተሰቡ እንዲያውቅ እና እንዲዘጋጅ የስድስት ወር ቅድመ ዝግጅ ቢደረግበት የተሻለ ይሆን ነበር ይላሉ ዶ/ር ፈድሉ። ወ/ሮ ፍሬህይወት ግን ኅብረተሰቡን ዝግጁ የማድረግ ሥራ የእነርሱ መሥሪያ ቤት አለመሆኑን በመጥቀስ ይህ የሚመለከተው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መሆኑን ጠቁመዋል። ሌላው የተነሳው ችግር የጤና መድኅን ያላቸው ሰዎችም ቢሆኑ በሁሉም የመንግሥት የጤና ተቋማት ላይ መጠቀም አለመቻላቸው ነው። ""ያለው ዞናዊ አሠራር ነው። [በኛ ዞን የወጣ የጤና መድኅን] የሚሠራው በእኛ ዞን ብቻ ነው። ከአጎራባች ዞን ለሚመጡት አገልግሎት አይሰጥም። ስለዚህ ለመክፈል ይገደዳሉ። በዞን ብቻ መሆን የለበትም በክልል ደረጃ ወይንም በአገር አቀፍ ደረጃ መሆን አለበት"" ይላሉ ዶ/ር ፈድሉ። ተመሳሳይ ችግር እንዳስተዋሉ ዶ/ር ሱራፌልም ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንድ ታካሚ ጎንደር ላይ ማግኘት ያልቻለውን ህክምና ለማግኘት ወደ ባህርዳር ቢያቀና ባለው የጤና መድኅን የሚሸፈን ባለመሆኑ ለመክፈል ይገደዳል ብለዋል። ይህ ደግሞ የጤና መድኅኑም ቢሆን ለሁሉም ነጻ ህክምና አያስገኝም ማለት መሆኑን አስረድተዋል። የጤና መድኅኑ በሁሉም የጤና ተቋማት አገልግሎት እንደማያስገኝ የሚስማሙት ወ/ሮ ፍሬህይወት ""አሁን ያለው አሠራር የሪፈራል ሰንሰለቱን ጠብቆ ነው የሚሄደው"" ይላሉ። ይህም ማለት አንድ ታካሚ የጤና መድኅኑን ካገኘበት አካባቢ ካለ የጤና ተቋም በመሄድ ህክምና ያገኛል። ህክምናው ነጻ ነው። ህክምናው ከዚያ ተቋም በላይ ከሆነ ሪፈር ተጽፎለት ወደሚቀጥለው የጤና ተቋም ሄዶ መታከም ይችላል። በዚህ መልኩ ሲኬድም ህክምናው ነጻ ነው። ስለዚህ የሪፈር ሰንሰለቱን ይዞ እንጂ በራሱ መንገድ ሁሉም ጋር በመሄድ ነጻ መታከም አይችልም ማለት ነው። ይህን ለመፍታት የጤና ተቋማት ከብዙ የጤና ተቋማት ጋር ውል እንዲገቡ እና አብረው እንዲሠሩ ለማድረግ እየተሠራ እንደሚገኝ ወ/ሮ ፍሬህይወት ተናግረዋል። የጤና መድኅኑ ምዝገባ በዲጂታላይዝ አለመሆኑንም በምክንያትነት አቅርበዋል። ምዝገባው ዲጂታላይዝ አለመሆኑ ታካሚዎች በተለያዩ የጤና ተቋማት ሄደው ለመታከም ካርዱን ሲጠቀሙ ለማመሳከር እንቅፋት መሆኑ ነው የችግሩ መነሻ። ለሁሉም ያልተዘጋጀ የጤና መድኅን ሌላው ችግር ደግሞ የጤና መድኅኑ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ብቻ ያማከለ መሆኑ ነው። የመንግሥት ሠራተኞች እና የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ በጤና መድኅኑ የማይታቀፉ መኖራቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ሱራፌል እነዚህ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለችግሩ ተጋላጭ ናቸው ብለዋል። የጤና መድኅኑ መደበኛ ባልሆነ የሥራ ዘርፍ የተሠማሩ እና ወር ጠብቀው ቋሚ ደመወዝ የማያገኙ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። ""አሁን ተግባራዊ የተደረገው የጤና መድኅን መደበኛ ባልሆነ ሥራ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ እና ከ10 በታች በሚቀጥሩ የሥራ ዘርፎች እና ዝቅተኛ የኑሮ መጠን ላይ ያሉትን እንደሚያቅፍ"" ወይዘሮ ፍሬህይወት አረጋግጠዋል። በቅርቡ ደግሞ ሌሎችንም ለማካተት የሚያስችል አሠራር በመዘርጋት ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ ችግሩ እንደሚፈታ ተናግረዋል። የጠየቅናቸው የህክምና ባለሙያዎች በዋጋ ጭማሪው ላይ ብዙም ቅሬታ ያላቸው አይመስሉም። ���ማይስማሙት በተጨመረው ዋጋ መጠን እና በተጨመረበት ጊዜ ላይ ነው። ካነሷቸው ችግሮች ጎን ለጎን ""አጠቃላይ ሃሳቡ ኅብረተሰቡን ወደ ጤና መድኅን ለማስገባት ይመስላል። ምክንያቱም ከኪስ ተከፍሎ አይቻልም። ሁሉም ሰው በከፈለው ገንዘብ ይታከማል። የሴክተሩ ገንዘብም ይሻሻላል። ዕቅዱ እንደ ምዕራባውያኑ እና አሜሪካ ለማድረግ ነው። በአጠቃላይ አሠራሩን እደግፈዋለሁ። ዕቅዱ የጤና ሴክተሩን ለማሳደግ ነው። የጤናውን ዘርፍ ለማሳደግም ያለመ ነው"" የሚሉት ዶ/ር ፈድሉ ናቸው። ""ለምን በዚህ መጠን ዋጋ እንደጨመረ ለማወቅ ባደረኩት ጥረት ሆስፒታሎች ከዚህ በፊት ከመጠን ባነሰ ዋጋ አገልግሎት ሲሰጡ ስለነበር ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተዳረጉ እና አሁን የወጣው ዋጋ ግን ተገቢው ክፍያ እንደሆነ ነው። በተጨማሪም በገጠር የሚኖረው ማኅበረሰብ የጤና መድኅን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማበረታታት ነው"" ይላሉ ዶ/ር ሱራፌል። ""ሌላው ጥያቄ የሆነብኝ ነገር 'ሆስፒታሎች ይህን የዋጋ ጭማሪ ሲያደርጉ የሚሰጠው አገልግሎት ጥራትና ፍጥነቱ ከድሮው በተለየ ይጨምራል ወይ?' የሚለው ነው። ይህን በሂደት የምናየው ይሆናል። የታካሚዎቻችን መቸገር እና መንገላታት ግን ለህክምናውም ለሃኪሙም ከባድ ራስ ምታት ነው። ተገቢው ትኩረት እና መፍትሄ ያስፈልገዋል"" ብለዋል። የሠላማዊት እናት ህክምናቸውን ተከታትለው አገግመዋል። እሷም በቀጣዩ ቀን ዓመታዊ ክፍያ ፈጽማ የጤና መድኅን አባል ሆነዋል። በየጊዜው በእናቷ ምክንያት ሐኪም ቤት የምትመላለሰው ሠላማዊት አሁን ""እፎይ ብያለሁ"" ብላለች። 40 ሚሊዮን ሰዎች በጤና መድን ታቅፈዋል የጤና መድህን ማለት አንድ ቤተሰብ በአመት የተወሰነ ብር በመክፈል የቤተሰቡ አባል ሲታመም በነጻ አገልግሎት የሚያገኝበት መንገድ ነው።የጤና መድኅን የተጀመረው ኅብረተሰቡ ባልተጠበቀ ወጪ ወዳልታሰበ ድህነት እንዳይገባ ለማድረግ ነው ይላሉ ፍሬህይወት። መደበኛ ያልሆነ የሥራ ዘርፍ እና በወር ቋሚ ደመወዝ የማይከፈላቸው ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። አሠራሩ ተግባራዊ ከተደረገ 10 ዓመት ይሆነዋል። 40 ሚሊዮን ያህል አባላት እንዳሉትም ለማወቅ ተችሏል። ካሉት አባላቱ መካከል 24 በመቶ ከድህነት ወለል በታች በመሆናቸው (8 ሚሊዮን ያህሉ መሆኑ ነው) ወጪያቸውን የሚሸፈነው በመንግሥት ነው። እንደ የአካባቢው በሚለያይ ክፍያ በዓመት አንድ ጊዜ በሚደረግ ክፍያ አባል መሆን ይቻላል። ለምሳሌ ባለፈው ዓመት አዲስ አበባ ላይ አንድ አባወራ በዓመት 350 ብር በመክፈል ይመዘገባል። የጥቅም ማዕቀፉም የልብ እና የአዕምሮ ህክምናን ጨምሮ እስከ አዲስ አበባ ድረስ በመንግሥት የህክምና ተቋማት የሚሰጥ ይሆናል። አሁን በጤና ጥበቃ በመንግሥት የጤና ተቋማት ላይ ተደረገውን ጭማሪን ተከትሎ የጤና መድኅኑ ዓመታዊ ክፍያ ላይ ክለሳ በማድረግ ጭማሪ ሊኖር አንደሚችልም ወ/ሮ ፍሬህይወት ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የጤና ጥበቃን ሃሳብ ለማካተት በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።" https://www.bbc.com/amharic/news-58220082 +health "ፕሬዝደንት ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ ""ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው"" አሉ" "በአሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች የአፍ እና አፍንጫ ጭምብል የማድረግ ግዴታ የለባቸውም መባሉን ተከትሎ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው ብለዋል። ባለስልጣናት በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ከውስን ቦታዎች በስተቀር ያለጭምብል መንቀሳቀስ ይችላሉ ብለዋል። አካላዊ ርቀትን መጠበቅም አይጠበቅባቸውም ተብሏል። ከዚህ ውሳኔ በኋላ ""ኦቫል"" ቢሮ ከሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች ጋር ፕሬዝዳንቱ ራሳቸው ያለጭምብል ታየተ��ል። ይሁን እንጂ እንደ አወቶብስ፣ አውሮፕላንና ሆስፒታል ባሉ መሰባሰብን በሚጠይቁ ከበር መለስ አገልግሎቶች የሚሰጡባቸው ቦታዎች ላይ ግን ክትባት የተከተቡትም ቢሆኑ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታቸው ነው። ሙሉ በሙሉ ክትባቱን ላገኙ ሰዎች የኮቪድ ክልከላዎች እንዲነሱላቸው በባይደን አስተዳደር ላይ ጫና ሲደረግበት ቆይቷል። በሌላ በኩል ደግሞ የአሜሪካ የመምህራን ፌዴሬሽን ለፕሬዝዳንት ባይደን ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከፈቱ ጥሪ አቅርቧል። ይህ ጥሪ የተላለፈው ፋይዘር ያመረተውን ከትባት ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 ያሉ ህጻናት መከተብ እንዲችሉ ፍቃድ ከተሰጠ በኃላ ነው። አሁን ላይ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ተሰምቷል። የአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅም ግዴታቸ እንዳልሆነ አስታውቋል። በቲውተር ገጻቸው ያልተከተቡ ሰዎች 'ማስክ' ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ያሳሰቡት ባይደን ""ህጉ ቀላል ነው መከተብ ወይም እስከትከተቡ ጭምብል ማደረግ። ምርጫው የእናንተ ነው"" ብለዋል። በአሜሪካ 35 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ክትባት ያገኘ ሲሆን የ ጆ ባይደን አስተዳደር ይሄ ቁጥር እስከ ሀምሌ ደረስ በእጥፍ አሳድጎ 70 በመቶ ለማደረስ አቅዷል።" https://www.bbc.com/amharic/57111329 +politics ቦክሰኛው ማኒ ፓኪዮ ለፕሬዘዳንትነት እንደሚወዳደር ይፋ አደረገ "በዓለም የቦክስ ውድድር መድረኮች ኮከብ የሆነው ፊሊፒንሳዊው ማኒ ፓኪዎ በቀጣይ ዓመት በሚደረገው ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደር ይፋ አደረገ። ፓኪዮ ገዢውን ፓርቲ በሚቀናቀነው ፒዲፒ-ላባን ፓርቲ አማካኝነት ነው ዕጩ ተወዳዳሪ ሆኖ ለምርጫው የሚቀርበው። በበርካታ ድሎች ከታጀበው ቦክሰኝነቱ ባሻገር የ42 ዓመቱ ፓኪዎ በፊሊፒንስ ፓርላማ ውስጥ ሴናተርም ነው። በስልጣን ላይ የሚገኙት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ለሌላ የስልጣን ዘመን መወዳደር ባይችሉም አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ዕጩ አድርጎ አቅርቧቸዋል። ሂደቱን በቅርበት የሚከታተሉ ተቺዎች የዱቴርቴ ተግባር ስልጣንን የሙጥኝ የማለት ሙከራ ሲሉ ትችት እያቀረቡባቸው ይገኛሉ። ዱቴርቴ ከቅርብ ወዳጃቸው ክሪስቶፈር ቦንግ ጎ ጋር ለምርጫው እንዲቀርቡ የተመረጠ ቢሆንም ክሪስቶፈር ግን ወዳጃቸውን ዱተርቴንን ለመተካት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት የፕሬዚዳንት ዱቴርቴ ሴት ልጅ ሳራ ዱቴርቴ-ካርፒዮ አባቷን ለመተካት ለውድድር ልትቀርብ እንደምትችል ፍንጮች አሉ። ቦክሰኛው ማኒ ፓኪዮ በውድድር ሕይወቱ በስምንት የተለያዩ የክብደት ምድቦች አሸንፏል። በቅርቡም ከኩባዊ ተቀናቃኙ ጋር ባደረገው ግጥሚያ መሸነፉን ተከትሎ ከቦክሱ አለም ራሱን ለማግለል ማሰቡን አስታውቋል። የቀረበለትን የፕሬዘዳንትነት ጥያቄ በተቀበለበት ግዜም ""እኔ ታጋይ ነኝ፤ በግጥሚያ መድረክ (ቦክስ) ሆነም ውጪ ታጋይ ሆኜ ቀጥላለሁ""ብሏል። በድቡብ ምስራቅ ኢሲያ በምትገኘው ፊሊፒስ እጅግ ዝነኛ የሆነው ፓኪዮ በምርጫው አሸንፎ ስልጣን የሚይዝ ከሆነ ድህነትን እና ሙስናን አዋጋለሁ ሲል ቃል ገብቷል።" https://www.bbc.com/amharic/58621504 +sports ቶኪዮ ኦሊምፒክ፡ አውስትራሊያ የኦሊምፒክ ተሳታፊዎችን ለማስተዋወቅ የለቀቀችው ፎቶ አወዛገበ የአውስትራሊያ ኦሊምፒክ ቡድን ተወዳዳሪዎችን ለማስተዋወቅ የለጠፈው ፎቶ ውግዘት ገጥሞታል። የአውስትራሊያን የኦሎምፒክ ቡድን ለማስተዋወቅ ይፋ የተደረገው ፎቶ ብዝሃነትን አያንጸባርቅም በሚል አንዲት ጥቁር ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ራሷን ከውድድሩ ልታቅብ እንድምትችል አስጠንቅቃለች። የአውስትራሊያን የኦሊምፒክ�� ፓራሊምፒክ [የአካል ጉዳተኞች የሚሳተፉበትን] ተሳታፊዎች ትጥቅን ለማስተዋወቅ የተለቀቀው ምስል ላይ የሚታዩ ሰዎች በሙሉ ተመሳሳይ የቆዳ ቀለም ያላቸው ናቸው። እናም በሀገሪቱ እውቅና ያላት ጥቁር የቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ ሊዝ ካምቤጅ ፎቶውን “ነጭ የተቀባ” ብላዋለች። የኦሎምፒክ ቡድኑን ብዛሃነትን ለማንጸባርቅ ከዚህ የተለየ ነገር መስራት ነበረበት ያለው ደግሞ የአውስትራሊያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ነው። በ2012 ኦሊምፒክ የነሀስ ሜዳሊያ ያገኘችው ካምቤጅ ጉዳዮ ቅር እንዳሰኛት መጀመሪያ የገለጸችው በኢንስታግራም ገጿ ነበር። ናይጄሪያዊ አባትና አውስትራሊያዊት እናት ያላት ቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ የተወለደችው ለንደው ውስጥ ነው። ይህ አነጋጋሪ ምስል ማሕበራዊ ድር አምባ ላይ ሲለጠፍ ከስሩ የተቀመጠው የመጀመሪያው አስተያየት “እኔን የማይወክልኝ ሀገርን እንዴት ሊወክል ይችላል?” ሲል ይጠይቃል። ከዚህ በፊት የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች የቡድኑ ማልያ በሴቶች ልክ የለም መባሉን ተከትሎ ቁጣቸውን አሰምተው ነበር። የሃገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለወንዶች ያደላል ተብሎም የማሕበራዊ ድር አምባ ግርግር ተነስቶ ነበር። https://www.bbc.com/amharic/news-57027326 +sports በኳታር የዓለም ዋንጫ ተጫዋቾች እና ተመልካቾች እንዳያደርጉ የተከለከሉት ነገሮች የትኞቹ ናቸው? እየተካሄደ ያለው የኳታር የዓለም ዋንጫ ውድድር በርካታ ድንቅ ነገሮች እየታዩበት ከመሆኑ በተጨማሪ ውዝግቦችንም እያስተናገደ ነው። ኳታር በባሕረ ሰላጤረው በረሃ ውስጥ አጀብ ያሰኙ ስታዲየሞችን ገንብታ በአረቡ ዓለም የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ በማስተናገድ ታሪክ አስመዝግባለች። በተጫማሪም ይህ የዓለም ዋንጫ ከቀደሙት በተለየ በርካታ ትችቶች የተሰነዘሩበት ነው። ኳታር ከእምነት እና ከሕጓ አንጻር የተለያዩ ክልከላዎችን የጣለች ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ ድጋፍ እና ውግዘት ከተለያዩ ወገኖች እየተሰነዘሩባት ነው። ታዲያ በዚህ የዓለም ዋንጫ ደጋፊዎች እና ተጫዋቾች ፈጽሞ እንዳያደርጉት የተከለከሉት ነገሮች የትኞቹ ናቸው? https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1kg2n80jqo +business ኤሚሬትስ ገንዘቤን አላገኘሁም በሚል ወደ ናይጄሪያ የሚደርገውን በረራ ሊያቋርጥ ነው ግዙፉ የዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ አየር መንገድ ወደ ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ናይጄሪያ የማደርገውን በረራ ሊያቋርጥ መሆኑን አስታወቀ። ዋና መቀመጫውን ዱባይ ያደረገው ኤሚሬትስ አየር መንገድ የናይጄሪያ በረራውን ከነሐሴ 26/2014 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚያቆም ገልጿል። ኤሚሬትስ ወደ ናይጄሪያ እና ከናይጄሪያ የሚያደርገውን በረራውን ለማቆም የወሰነው በአገሪቱ ያለውን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻሉ መሆኑን አስታውቋል። ኢሚሬትስ አየር መንገድ በአገሪቱ ሲሰጥ ለቆየው የአየር ትራንስፖርት አገለግሎቱ ከናይጄሪያ ማግኘት ያልቻለው 85 ሚሊዮን ዶላር እንዳለው አመልክቷል። አየር መንገዱ ገንዘቡን ማግኘት ባለመቻሉ ወደ ናይጄሪያ የሚያደርገውን የበረራ ቁጥር እንደሚቀንስ ለአገሪቱ አቪዬሽን ሚኒስቴር በደብዳቤ አስታውቆ ነበር። በደኅንነት እና ለመንገደኞች በሚሰጠው ምቾች የ2022 የዓለማችን ምርጥ 20 አየር መንገዶች ውስጥ መካተት የቻለው ኤሚሬትስ፤ ነሐሴ 2014 አጋማሽ ላይ የበረራ ቁጥሩን ከመቀነሱ በፊት በሳምንት ለ11 ጊዜ ያህል ወደ ናይጄሪያ መዳረሻዎች ይበር ነበር። ኤሚሬትስ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪ ላለመብረር መውሰኑን ተከትሎ መጉላለት ሊገጥማቸው የሚችሉ ደንበኖቹ የአየር ቲኬታቸውን በመሰረዝ ገንዘባቸውን ተመላሽ ማድረግ እንደሚችሉ አልያም ከሌሎች የአፍሪካ መዳረሻዎች መነሳት ወይም መብረር እንደሚችሉ አማራጭ ሰጥቷል። ከኤሚሬትስ በተጨማሪ ሌሎ��� ግዙፍ አየር መንገዶች በአፍሪካ ግዙፍ ከሚባሉት መዳረሻዎች መካከል አንዷ ከሆነችው ናይጄሪያ ያላቸውን ገንዘብ ማንቀሳቀስ አለመቻላቸውን በመግለጽ ቅሬታ ያሰማሉ። ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ወደ ናይጄሪያ የሚበሩ ሌሎች አየር መንገዶችም የኤሚሬትስን ውሳኔ ሊከተሉ ይችላሉ። አየር መንገዶች በናይጄሪያ ማንቀሳቀስ ያልቻሉት የገንዘብ መጠን 600 ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተጠቅሷል። በአፍሪካ የሕዝብ ቁጥር ቀዳሚ የሆነችው ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ናይጄሪያ ባጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ የውጭ ኩባንያዎች ላቀረቡት ምርትና አገልግሎት ከአገሪቱ በሚያውጡት የውጭ ምንዛሬ መጠን ላይ ገደብ ጥላለች። https://www.bbc.com/amharic/articles/c848nyg3rplo +politics ሊዝ ትረስ፡ ስልጣን እንዲለቁ ያስገደዷቸው 3 መሠረታዊ ጉዳዮች ሊዝ ትረስ ወደ ዶውኒንግ ስትሪት ከመጡ በ6ኛው ሳምንታቸው ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል። ገና በ45ኛ ቀናቸው ስልጣን መልቀቃቸው በዩኬ ታሪክ ለአጭር ጊዜ ስልጣን ላይ የቆዩ ሰው ያደርጋቸዋል። ሊዝ ትረስ የወግ አጥባቂ መሪነት ቦታን ከቦሪስ ጆንሰን ተረክበው ለ6 ሳምንታት የዩኬ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነዋል። ከዚህ ቀደም ዩኬን ለአጭር ጊዜ በጠቅላይ ሚንስትርነት የመሩት ጆርጅ ካኒንግ ነበሩ። ጆርጅ ካኒንግ ሞት ሳይቀድማቸው እአአ 1872 ላይ ዩኬን ለ119 ቀናት መርተው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትሯን ስልጣን እንዲለቁ ያስገደዷቸውን ሦስት ምክንያቶች እንመልከት። ሊዝ ገና ወደ ስልጣን እንደመጡ ነበር ፈተና የበዛባቸው። ሊዝ ስልጣን በያዙ ሦስተኛ ሳምንታቸው ከፋይናንስ ሚንስትሩ ጋር በመሆን የ45 ቢሊዮን ፓዎንድ የታክስ ቅነሳ እቅድ አስተዋወቁ። ይህ ግን ብዙ ምጣኔ ሃብታዊ ችግሮችን ይዞ በመምጣቱ ትችት አስከተለባቸው። ይህ እቅድ ሙሉ በሙሉ የተተወ ሲሆን የፋይንስ ሚንስትሩም ከስልጣናቸው ተባረዋል። ሊዝ ከበርካታ ቁጥር ካላቸው የፓርቲ አጋሮቻቸው ትችት በዝቶባቸው ነበር። አንዳንዶች ስልጣን እንዲለቁ ጭምር በአደባባይ ጥሪ ሲያቀርቡ ነበር። የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሴኡላ ብሬቨርማን ስልጣናቸውን ለቀቁ። ሊዝ የተፈጠረባቸውን ክፍተቶች ለመሙላት የቀድሞ ተቀናቃኞቻቸውን ግራንት ሻፕስ እና ጄረሚ ሃንትን መሾም ነበረባቸው። ትረስ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪነትን ቦታ ሲይዙ ቀጥሎ ደግሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ሲሆኑ ፈጽማቸዋለሁ ያሏቸውን ማድረግ አልቻሉም። በጽሐፍት ቤታቸው በር ላይ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ባስታወቁበት አጭሩ መግለጫቸው፤ “ወግ አጥባቂ ፓርቲ ለመረጠኝ ኃላፊነት መወጣት እንደማልችል ተረድቻለሁ” ብለዋል። ሊዝ ትረስን ለመተካት በቀጣይ ሳምንት የመሪነት ውድድር ይካሄዳል ይባል እንጂ ተሰናባቿን ጠቅላይ ሚንስትር ማን ሊተካ እንደሚችል እስካሁን አልታወቀም። አንድ ነገር ግን ግልጽ ነው። ጀረሚ ሃንት የዩኬ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን እንደማይወዳደሩ አስታውቀዋል። ሊዝ ትረስም እርሳቸውን የሚተካ መሪ እስኪገኝ ድረስ በስልጣን ላይ እንደሚቆዩ በዛሬው መግለጫቸው አስታውቀዋል። ዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤት ከሕልፈታቸው በፊት ለመጨረሻ ጊዜ የጠቅላይ ሚንስትርነት ሹመትን ያጸደቁት የሊዝ ትረስን ነበር። ንግሥት ኤልዛቤጥ በ70 ዓመት የንግሥና ዘመናቸው ሊዝ ትረስ 15ኛ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ነበር። https://www.bbc.com/amharic/articles/cerd038x0yro +sports የሱዳኑ ክለብ ከጊዮርጊስ ጋር ያለው ግጥሚያ ከኢትዮጵያ ውጪ ይሁንልኝ አለ የሱዳኑ እግር ኳስ ክለብ ከኢትዮጵያው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርገው የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከኢትዮጵያ ውጪ ይሁንልኝ ሲል ካፍን ጠየቀ። አል-ሂላል ኦምዱርማን እግር ��ስ ክለብ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሊደረግ የታሰበው ውድድር ከኢትዮጵያ ውጪ እንዲሆን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንን (ካፍ) የጠየቀው በደኅንነት ስጋት ነው። በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ዳግም ማገርሸቱ የደኅንነት ስጋት እንዳሳደረበት ክለቡ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ የገለጸ ሲሆን ካፍም ለጥያቄው ምላሽ እንደሚሰጠኝ ተስፋ አለኝ ብሏል። ከአንድ ሳምንት ገደማ በፊት ለወራት ከዘለቀ ውጥረት በኋላ የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት ለሦስተኛ ዙር ዳግም መቀስቀሱ ይታወሳል። ምንም እንኳ የሱዳኑ ክለብ የደኅንነት ስጋት ስላለብኝ ጨዋታው ከኢትዮጵያ ውጪ ይሁን ብሎ ይጠይቅ እንጂ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን በቀለ በባህር ዳር ጨዋታ ለማድረግ ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት የለም ብለዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው በሱዳኑ ክለብ የቀረበው ጥያቄ በይፋዊ መንገድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ የደረሰው ነገር እንደሌለ ከገለጹ በኋላ፤ መስከረም 1/2015 ዓ.ም. ለማድረግ ከታቀደው ጨዋታ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት የለም ብለዋል። “ኤልሜሪክ የተባለው የሱዳን ክለብ ከጂቡቲ ክለብ ጋር ያለው የመልስ ጨዋታ በባህር ዳር ስታዲየም እንዲደረግለት እየጠየቀ ያለው” ካሉ በኋላ ጨዋታውን ለማካሄድ ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት እንደሌለ ተናግረዋል። ከአገር ውጪ የሚጫወቱ ኢትዮጵያን ተጫዋችን ለብሔራዊ ቡድን በመመልመል የሚታወቁት ፋርሃን ሞሐመድ ደግሞ የሱዳኑ ክለብ ይህን ጥያቄ ለካፍ ያቀረበው በኢትዮጵያ መጫወት ስላልፈለገ እንጂ በትክክል የደኅንነት ስጋት ኖሮበት አይደለም ብለዋል። “ግብጾች ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት በኢትዮጵያ ላለመጫወት ፍላጎት ስለሌላቸው እንጂ ትክክለኛ ስጋት ኖሯቸው አይደለም” ብለዋል። በተመሳሳይ ፋርሃን ከአል-ሂላል ጋር የአንድ ከተማ ክለብ የሆነው አልሜሪክ ከጂቡቲው ክለብ ጋር ግጥሚያውን በጂቡቲ ካደረገ በኋላ በሜዳው ማድረግ የነበረበትን የመልስ ጨዋታውን በባህር ዳር ስታዲየም ለማድረግ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረው የአል-ሂላል ክለብ ጥያቄ ምክንያታዊ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ፋርሃን ሞሐመድ ለክለቡ ጥያቄ ምላሽ ይሰጣል ብዬ አልጠብቅም ብለዋል። የባለፈው ዓመት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ቻምፒዮንሲ ሊግ ተሳታፊ ሲሆን፤ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ፋሲል ከነማ ደግሞ አፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ተሳታፊ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cw9d804p33lo +health ዩናይትድ ኪንግደም ጤነኛ ሰዎችን በኮቪድ ተህዋሲ 'ልትለክፋቸው' ነው የኮቪድ ክትባትን በማግኘት ጥረት ውስጥ ከፊት ከሆኑ አገራት አንዷ የሆነችው ዩናይትድ ኪንግደም የተለየ አይነት የክትባት ሙከራ ለማድረግ ቀዳሚዋ አገር ልትሆን ነው። በጥር ወር ላይ 90 ጤነኛ ሰዎች ሆን ተብለው ለኮቪድ ተህዋሲ እንዲጋለጡ በማድረግ ነው አዲሱ ሙከራ የሚደረገው። ይህም ቶሎ ክትባት ለማግኘት ይረዳል ተብሏል። መንግሥት ከወዲሁ 33.6 ሚሊዮን ፓውንድ ለዚሁ ሙከራ መድቧል። ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግበታል የተባለው ይህ አዲስ የሙከራ ዘዴ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ከአገሪቱ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ይሁንታን ማግኘት ይኖርበታል። በመድኃኒት ቅመማ ሂደት ‹ሂዩማን ቻሌንጅ› በሚል የሚታወቀው ይህ ጤነኞች ላይ በሽታ አምጪ ተህዋስን ሆን ብሎ በማጋባት ሙከራ ማድረግ ብዙም የተለመደ አይደለም። ነገር ግን ከዚህ ቀደም በወባና በኢንፍሉዌዛ የመድኃኒት ግኝቶች ሂደት ውስጥ ተሞክሮ ውጤት ማስገኘቱን ኔቸር መጽሔት ዘግቧል። ሳይንቲስቶች በጥር ወር መጀመርያ ተግባራዊ ያደርጉታል በተባለው በዚህ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉ�� ሰዎች ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 30 የሚሆን ፍጹም ጤነኛ የሆኑ በጎ ፈቃደኞች ብቻ ናቸው። ሙከራው አንድን ሰው ምን ያህል የተህዋሲው መጠን ነው ለበሽታ የሚያጋልጠው የሚለውንም ለማወቅ ይረዳል ተብሏል። ለበጎ ፈቃደኞቹ በቅድሚያ ተህዋሲው በትንሽ መጠን ይሰጣቸዋል። ፍጹም ጤነኛ ሰዎችን እንደ አይጥ መሞከርያ ማድረግ ቶሎ ውጤት ለማግኘት አስፈላጊ ነው የሚሉ በርካታ ቢሆንም መድኃኒት በሌለው በሽታ ሰዎችን ሆን ብሎ መበከል ከሕክምና ሥነ ምግባር አንጻር ተገቢ አይደለም ሲሉ ነገሩን የሚተቹትም በርካታ ናቸው። ተህዋሲው ለበጎ ፈቃደኞቹ የሚሰጣቸው በአፍንጫቸው በኩል ይሆናል ተብሏል። ለ24 ሰዓታትም ጥብቅ ክትትል ይደረግላቸዋል። በጎ ፈቃደኞቹ ለከፋ አደጋ የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ ነው፤ ምክንያቱም ጤነኞችና ወጣቶች በመሆናቸውና በጥንቃቄ ስለሚመረጡ ነው ይላሉ ተመራማሪዎች። ቅድመ ጥንቃቄው አስተማማኝ በሚባል ደረጃ ላይ ሲደርስ በበጎ ፈቃደኞቹ በአንዳንዶቹ ላይ ሙከራ ላይ የሚገኙ ክትባቶች ይሰጧቸዋል። ለኮቪድ ተህዋሲው ከመገላጣቸው በፊትም ክትባት እንዲወስዱ የሚደረጉ ይኖራሉ። ክትባቱን የወሰዱት ለተህዋሲው ተጋልጠው ተህዋሲው ይይዛቸዋል ወይስ አይዛቸውም የሚለውም ምላሽ ያገኛል። የዚህ ምርምር መሪ የኢምፔሪያል ኮሌጁ ዶ/ር ክሪስ ቺዩ ሰዎች ያን ያህልም ሐሳብ ሊገባቸው አይገባም ይላሉ። ‹‹እኔና ባልደረቦቼ በዚህ መንገድ ላለፉት 10 ዓመታት በርካታ ጤነኛ ሰዎች ላይ ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ ቫይረሶችን በመስጠት ስንሰራ ቆይተናል። እርግጥ ነው የትኛውም ጥናት ቢሆን የራሱ አደጋ የለውም አይባልም። ነገር ግን አደጋውን ለመቀነስ እንታገላለን›› ብለዋል። ረዳታቸው ፕሮፌሰር ፒተር ኦፔን ሻው በበኩላቸው ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲ ሆን ብሎ በመበከል ምርምር ማካሄድ በቀላሉ የሚታይ ነገር ባይሆንም ውጤት ለማግኘት ግን ወሳኝ ነው፤ ያግዛል ብለዋል። በአሁን ሰዓት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኮቪድ ክትባቶች በመጨረሻ ምዕራፍ ሙከራ ላይ ሲሆኑ ውጤት ያስገኛሉ ተብለው በጉጉት እየተጠበቁ ካሉት መካከል የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው ተጠቃሽ ነው። በጥር ወር ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲው በመበከል የሚደረገው ምርምር ሌላ ፍቱን መድኃኒት ቀድሞ ቢገኝም የሚቋረጥ አይሆንም። ክትባቶች ከተገኙ በኋላ የትኛው ክትባት እጅግ ውጤታማ ነው የሚለው ጥናት ይቀጥላል። ተህዋሲውን በገዛ ፈቃዳቸው ለመውሰድ የፈቀዱ የታላቋ ብሪታኒያ ዜጎች ለጊዜያቸውና ለደፋር ውሳኔያቸው የሚመጥን ነው የሚባል ገንዘብ ይከፈላቸዋል። ሙከራው ከተደረገባቸው በኋላም ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያለማቋረጥ የቅርብ ክትትል ይደረግባቸዋል። https://www.bbc.com/amharic/54617479 +politics ባይደን የሚቀለብሷቸው የትራምፕ ውሳኔዎች የትኞቹ ናቸው? "አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን 50 ዓመታት በፖለቲካው ውስጥ አሳልፈዋል። በአስተዳደር ዘመናቸው ይወስዷቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ እርምጃዎች አንዱ አሜሪካን ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት መመለስ ነው። የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያስተላለፏቸው አወዛጋቢ ውሳኔዎችን ባይደን ይቀለብሳሉ ተብሎም ይጠበቃል።ከነዚህ መካከል በሙስሊም አገራት ዜጎች ላይ ተጥሎ የነበረው የጉዞ እገዳ ይገኝበታል። ከባይደን አጀንዳዎች አንዱ አሜሪካን ወደ ዓለም ጤና ድርጅት አባልነቷ መመለስ ነው። ትራምፕ ድርጅቱ ለቻይና የወገነ ነው ብለው ከድርጅቱ መውጣታቸው አይዘነጋም። ባይደን ከዓለም ጤና ድርጅት በተጨማሪ አሜሪካን ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነትም ይመልሳሉ ተብሏል። ከሙስሊም አገራት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ሰዎች ላይ ተጥሎ የነበረውን ክልከ�� ባይደን ያነሳሉ። ከነዚህ ባሻገር በወረርሽኙ ሳቢያ ከቤታቸው እንዲወጡ የተገደዱ ዜጎች ተጨማሪ የመኖሪያ ጊዜ ይፈቀድላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። ከባይደን ተጠባቂ እርምጃዎች ዋና ዋናዎቹን እንመልከት፦ ጭምብል ማድረግ ግዴታ ይሆናል በወረርሽኙ ሳቢያ በአሜሪካ ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል። አዲሱ አስተዳደር በቀዳሚነት ከሚያተኩርባቸው ጉዳዮች አንዱም ኮሮናቫይረስ ነው። ባይደን ወረርሽኙን ""አስተዳደራችን ከሚገጥመው ፈተናዎች አንዱ ነው"" ብለውታል። ቫይረሱን ለመከላከል የጥንቃቄ እርምጃዎችን ለመተግበርም ቃል ገብተዋል። የመንግሥት ይዞታ በሆኑ ቦታዎችና በጉዞ ወቅት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ከሚያስተላልፉት ውሳኔ አንዱ ይሆናል። በእርግጥ ባይደን ይህንን ውሳኔ የሚተገብሩበት የሕግ ማዕቀፍ የለም። ስለዚህም አገረ ገዢዎችን በግል ጥረታቸው ለማሳመን አቅደዋል። ባይደን ሥልጣን በያዙ በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ ለ100 ሚሊዮን ሰዎች ክትባት ለመስጠት ወጥነዋል። ይህንን የሚተገብሩት ያሏቸውን ክትባቶች ባጠቃላይ ለዜጎች በማከፋፈል ሲሆን፤ ለሁለተኛ ዙር ክትባት ተብሎ የሚቀመጥ ጠብታ አይኖርም ማለት ነው። የምጣኔ ሀብት ውሳኔዎች ከቤታቸው በግድ እንዲወጡ ተወስኖባቸው ለነበሩ ሰዎች ጊዜ መስጠት ከባይደን አስተዳደር ከሚጠበቁ ውሳኔዎች ዋነኛው ነው። መንግሥት ለተማሪዎች የሚሰተውን የገንዘብ ድጋፍ ያስቀጥላሉም ተብሏል ካቢኔያቸው ለሠራተኛው ማኅበረሰብ እፎይታ የሚሰጥ የምጣኔ ሀብት ውሳኔ እንዲያሳልፍ ያዛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኮሮናቫይረስ ጫና ላሳደረበት የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት የ1.9 ትሪሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ መታቀዱ ይታወሳል። ምክር ቤቱ እቅዱን ካጸደቀ አሜሪካውያን በነፍስ ወከፍ 1 ሺህ 400 ዶላር ያገኛሉ። በቀጣይ 100 ቀናት ውስጥ ትምህርት ቤቶች ጥንቃቄ በተሞላው መንገድ ይከፈታሉ። የትራምፕን አወዛጋቢ የግብር ቅነሳ ባይደን እንደሚቀለብሱ ተገልጿል። እአአ 2017 ላይ ትራምፕ ያሳለፉት የግብር ቅነሳ ባልተገባ መንገድ ሀብታሞችን የጠቀመ ነው ሲሉ ባይደን ይተቻሉ። ከዚህ ባሻገር ባይደን የአሜሪካ ድርጅቶች በውጪ አገራት በሚያደርጓቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚጣለውን ግብር ለመጨመር ወጥነዋል። ይህ እውን እንዲሆን የግብር ፖሊሲያቸውን ምክር ቤቱ ማጽደቅ አለበት። የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ባይደን ሥልጣን በያዙበት የመጀመሪያው ቀን አሜሪካን ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ እንደሚመልሱ አስታውቀዋል። የፓሪሱ ስምምነት የዓለምን የሙቀት መጠን ከ2.0 ሴንቲ ግሬድ በታች ማድረግን ያካትታል። ትራምፕ አሜሪካን ከዚህ ስምምነት አስወጥተዋት ነበር። ባይደን የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ጥብቅ እርምጃዎች እንደሚወስዱ ይጠበቃል። ይህም በመጀሪያዎቹ 100 የሥልጣን ቀናት ውስጥ የአየር ንብረት ለውጥ ውይይት ማካሄድን ያካትታል። በ2050 የአሜሪካን የካርቦን ልቀት ዜሮ የማድረስ እቅድም አላቸው። የስደተኞች ፖሊሲ ለውጥ ትራምፕ ሥልጣን በያዙ በሰባተኛ ቀን ነበር በሙስሊም አገራት ዜጎች ላይ የጉዞ እገዳ የጣሉት። እገዳው የኢራን፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ፣ ሶርያ፣ የመን ዜጎችን እንዲሁም የቬንዝዌላ እና የሰሜን ኮርያ ዜጎችን የሚያግድ ነው። ይህ ውሳኔ በባይደን አስተዳደር ዘመን ይሻራሉ ተብለው ከሚጠበቁ መካከል ይጠቀሳል። ከ11 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰነድ አልባ ስደተኞች ዜግነት ማግኘት የሚችሉበትን ሥርዓት ለምክር ቤት እንደሚልኩ ተገልጿል። ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ህጻናት ዜግነት የሚያገኙበት ዝርዝር ውስጥ የሚገቡበት አሠራር በባይደን ዘመነ መንግሥት እውን ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት አንዱ ነው። ባይደን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ 545 ስደተኛ ልጆችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመመለስ ቃል ገብተው ነበር። ትራምፕ በተደጋጋሚ ያወሩለት የነበረውን በአሜሪካና ሜክሲኮ መካከል የሚገነባውን የድንበር ግድግዳ ፕሮጀክት ባይደን ያስቆሙታል። ዘረኛና ኢፍትሐዊ ውሳኔዎችን መሰረዝ ዘረኛና ኢፍትሐዊ የተባሉና በርካቶችን ከቤት ባለቤትነት እንዲሁም ከጤና መድህን ተጠቃሚነት ያገዱ ውሳኔዎችን ባይደን ይሰርዛሉ ተብሏል። በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ከሚወስዷቸው እርምጃዎች መካከል የፖሊስ ተቋምን ዳግመኛ ማዋቀር ቀዳሚው ነው። በወንጀል ተጠርጥረው በሚታሰሩ ሰዎች አነስተኛ የእስራት ጊዜ እንዲፈረድባቸው የሚያስችልና ማኅበረሰብ አቀፍ ፓሊስን የሚያስተገብር ፓሊሲም ከባይደን ይጠበቃል። የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች መብት ባይደን የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎችን ከጥቃት የሚከላከሉ እንዲሁም በትምህርት ቤትና በወታደራዊ አገልግሎት ዘርፍ ያለውን መድልዎ የሚገቱ ውሳኔዎች ለማስተላለፍ ቃል ገብተዋል። ይህንን ውሳኔ በምክር ቤቱ አማካይነት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ እንደሚያሳልፉ ግን ግልጽ አይደለም። ከባይደን ከሚጠበቁ ለውጦች ሌላው አሜሪካ ከወዳጅ አገሮቿ ጋር ያላትን ግንኙነት ማደስ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/55735398 +sports እውቁ የቴኒስ ተጫዎች ጆኮቪች ከአውስትራሊያ ተባረረ "የዓለማችን ቁጥር አንድ የሜዳ ቴኒስ ኮኮብ ኖቫክ ጆኮቪች በአውስትራሊያ ለመቆየት ባደረገው የመጨረሻ ፍርድ ቤት ክርክር ተረትቶ አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ። ክትባት ለመቀበል አሻፈረኝ ያለው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቹ፤ የአገሪቱ መንግሥት ""በጤና እና ባልተገባ ስነምግባር"" ምክንያት ቪዛውን መሰረዙን ተከትሎ ጆኮቪች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ቢወስደውም ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ውድቅ አርጎበታል። በውሳኔው ""በጣም ቅር ብሎኛል"" ያለው ጆኮቪች ውሳኔው ተቀበሎ ወደ ዱባይ አቅንቷል። አገሩ ሰርቢያ 'በአውስትራልያ ኦፕን' የቴኒስ ውድድር ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ያደረገችው ጥረትም ፍሬ አልባ ሆኗል። የጆኮቪች ደጋፊዎች ከውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታውን አንድ ቀን ቀደም ብሎ የተወሰነውን ውሳኔ ከችሎቱ ውጪ ሆነው በቁዘማ ተከታትለዋል። ከደጋፊዎቹ መካከል አንዷ በውድድሩ ላይ የዚህ ዝነኛ ተጫዎች አለመኖር የእረፍት ጊዜዋን ""ባዶ"" እንደሚያደርግባት ተናግራለች። የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ""ድንበሮቻችንን ለማጠናከር እና አውስትራሊያውያንን ለመጠበቅ የተደረገ ውሳኔ ነው"" ሲሉ ውሳኔውን በአውንታ መቀበላቸው ገልጸዋል። ሆኖም ጠቅላይ ሚንስትሩ እና አስተዳደራቸው የጆኮቪችን ጉዳያ የያዙበት መንገድ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ እያስተቻቸው ነው። የጆኮቪች ጉዳይ መነሻ የአውስትራሊያ ኢሚግሬሽን ሚኒስትር አሌክስ ሃውክ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ቪዛውን ከሰረዙ በኋላ ነው። ምክንያት ያሉት ደግሞ በአገሪቱ የፀረ-ክትባት እንቅስቃሴን ሊያስፋፋ የሚችል ስሜት አንጸባርቋል በሚል ነው። ትላንት እሁዱ በተደረገው የፍርድ ቤት ችሎት የጆኮቪች ጠበቃ ተጫዋቹን ቪዛ ለመቀማት በመንግስት የተሰጡት ማብራሪያዎች ምክንያታዊ አይደሉም ያሉ ሲሆን የቴኒስ ኮከቡን ከአገር ማባረር የፀረ-ክትባት እንቅስቃሴን ያባብሳል ሲሉ አስረድተዋል። ዕውቁ ጆኮቪች በመጀመሪያ በፈረንጆቹ ታህሳስ ወር አጋማሽ ላይ በኮቪድ መያዙ ተረጋግጦ ነበር። ሆኖም ከዛ በኋላ በአውስትራሊያ የቴኒስ አስተዳደር እና በቪክቶሪያ የግዛት አስተዳደር ወደ አውስትራሊያ መግባት እንዲችል ፍቃድ ተሰጥቶት ነበር። ሆኖም የአውስትራሊያ የድንበር ዘብ የፌደራል የኮሮናቫይረስ መስፈርቶችን አላሟላም በሚል በፈረንጆቹ ጥር መግቢያ ላይ ቪዛው ተሰርዟል። የጠቅላይ ሚኒስትር ሞሪሰን መንግሥት ""የአገሪቱን የግዛት አንድነት ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎች እና እርምጃዎችን ለመውሰድ ተዘጋጅቷል"" ብሏል። ሆንም የተቃዋሚው ሌበር ፓርቲ አመራር እና ሴናተር የሆኑት ክሪስቲና ኬኔሊ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጆኮቪች ጉዳይን በተሳሳተ መንገድ በመምራት እራሳቸውን ""በዓለም ፊት መሳቂያ"" አድርገዋል ሲሉ ተችተዋቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/60020796 +politics የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ከመንግሥት ባለሥልጣንና ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ተወያዩ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሐመር አርብ አዲስ አበባ በመግባት ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር ተወያዩ። በቅርቡ የተሾሙት ልዩ መልዕክተኛው ካለፈው ሳምንት ማብቂያ በጀመሩት ጉዟቸው በቀዳሚነት ወደ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና ግብፅ ከተጓዙ በኋላ ነው አዲስ አበባ ያቀኑት። ልዩ መልዕክተኛው አዲስ አበባ እንደገቡ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ከኦነግ እና ከኦፌኮ ሊቃነ መናብት ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል። አምባሳደር ማይክ ሐመር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛነት ኃላፊነት ከተቀበሉ በኋላ የመጀመሪያ በሆነው ጉዟቸው አርብ ዕለት አዲስ አበባ መግባታቸውን ያመለከተው የአሜሪካ ኤምባሲ፣ በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ከመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ይገናኛሉ ብሏል። ልዩ መልዕክተኛው በቀዳሚነት የተነጋገሩት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ሲሆን፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ስለሚደረገው ጥረት፣ የእርዳታ አቅርቦት እና በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አመልክቷል። ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት መሪነት ለተጀመረው የሰላም ጥረት ቁርጠኛ መሆኑን እና ለዚህም ተደራዳሪ ቡድን አቋቁሞ ሥራ መጀመሩን፣ ያልተገደበ ሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መቀጠሉን እና የመብት ጥሰት ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ለማድረግ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አብራርተዋል። አቶ ደመቀ ጨምረውም መንግሥት ለሰላም ንግግር ያለውን ዝግጁነት በሚያሳይበት ጊዜ “በህወሓት በኩል የሚታየው ወላዋይ አቋም በአፍሪካ ኅብረት የሚካሄደውን የሰላም ጥረት ስጋት ላይ የሚጥል ነው” በማለት የተገኙ ውጤቶች ወደኋላ እንዳይመለሱ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቡድኑ ላይ አስፈላጊውን ጫና እንዲያሳርፍ መጠየቃቸውን ሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ ገልጿል። ከልዩ መልዕክተኛው ጋር በተደረገው ውይይት ግንባታው እየተጠናቀቀ ያለውን ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ፣ ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ከሚያስማማ መፍትሄ ላይ ለመድረስ በመርኅ ላይ የተመሠረተ አቋም እንዳለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል። ውይይቱን በተመለከተ ከልዩ መልዕክተኛው በኩል የተባለ ነገር ባይኖርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ማይክ ሐመር መንግሥት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እና በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እያስገኘ ያለውን ውጤት ማድነቃቸውን አመልክቷል። በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አርብ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳመለከተው ሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ፣ ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጋር በመሆን ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር መወያየተቻውን ገልጿል። አዲስ አበባ በሚገኘው በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ውስ��� የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከሌሎች ዲፕሎማቶች ጋር ሆነው ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ ጋር በተደረገው ውይይት ላይ በአጠቃላዩ የአገሪቱ ሰላም፣ በኢኮኖሚ እና በፓርቲዎቹ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን ኦነግ በፌስቡክ ገጹ አመልክቷል። ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያለው ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት በተመለከተ ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c80dpn08pn1o +sports እግር ኳስና ኮሮናቫይረስ፡ የኢትዮጵያን ስም በአውሮፓ ያስጠራችው ሎዛ ሎዛ አበራ በማልታ በሴቶች ዘርፍ የ2019/2020 የውድድር ዘመን ምርጥ ተጫዋች በመሆን በማልታ የእግርኳስ ተጫዋቾች ማህበር ተሸልማለች። ሎዛ ለቢቢሲ አዲስ አይደለችም። የማልታውን ቡድን ቢርኪርካራ እንደተቀላቀለች እንዴት ነው ሕይወት በአውሮፓ ስንል አናግረናት ነበር። ከዚያ ቃለ ምልልስ በኋላ ሎዛ ብዙ ታሪክ ፅፋለች። ሪከርድ ሰብራለች። ሎዛ ለሌሎች አንጋፋ የስፖርት መገናኛ ብዙሃንም አዲስ አይደለችም። ከጎል ዶት ኮም ጀምሮ እስከ ካፍ ኦንላይን ስለሎዛ አውርተው አይጠግቡም። ቡድኗ ቢርኪርካራ ተቃናቃኙ ሂበርኒያንስን በማልታ ታሪክ ከፍተኛ በሆነ ጎል 17 ለምንም ሲረታ ሎዛ 7 ጎል መረብ ላይ አሳርፋለች። የተወሰኑ ኳሶችንም ለጎል አመቻችታ አቀብላለች። ሎዛ ከዚህ ታሪካዊ ጨዋታ በፊትና በኋላ በርካታ ጎሎችን በማስቆጠር ቡድኗ የማልቲዝ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ እንዲሆን አድርጋለች። ሎዛአሁንየትነች? ሎዛ አሁን ያለችው ትውድል ቀዬዋ ነው። ከምባታ ዞን የምትገኘው ዱራሜ ከተማ። አጥቂዋ ለእረፍት ወደ ኢትዮጵያ በመጣችበት ነው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተከሰተው። በዚህ ምክንያት ወደ ማልታ ተመልሳ ማቅናት አልቻለችም። ለነገሩ የማልቲዝ ሊግ በወረርሽኙ ምክንያት ተቋርጦ ነበር። ሎዛ ኢትዮጵያ እያለች ቡድኗ ቢርኪርካራ የማልታ የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑ ይፋ ሆነ። ኢትዮጵያዊት ተስፈኛ አጥቂ በማልታ ሊግ የመጀመሪያ ዓመት ቆይታዋ በ12 ጨዋታዎች 30 ጎሎች በማስቆጠር ኮከብ ጎል አግቢ ሆናለች። 'ከቢርኪርካራ ጋር ባለድል በመሆኔ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም ነገር በመልካም ሁኔታ ተጠናቋል' ትላለች ሎዛ። የወደፊት ዕቅድ የማልታ የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ የቀጣዩ ዓመት ውድድር በመጪው ጥቅምት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ከአዳማ ከነማ ቢርኪርካራን መስከረም 2012 ላይ የተቀላቀለችው ሎዛ ከቡድኑ ጋር ያላት ውል ተጠናቋል። ለመሆኑ ውሏን ለማራዘም አስባ ይሆን? 'ከቢርኪርካራ ጋር የነበረኝ ውል የአንድ ዓመት ነው። እሱ ተጠናቋል። እርግጥ ነው ቢርኪርካራ ውሌን ለማራዘም ጥያቄ አቅርበዋል። እኔም ያቀረብኩላቸው ቅድመ ሁኔታ አለ። በእሱ የምንስማማ ከሆነ ልቀጥል እችላለሁ።' ሎዛ ከቢርኪርካራ ጋር የነበረኝ ቆይታ በጣም መልካም ነበር ትላለች። 'እርግጥ ነው አንድ ነገር ሲጀመር ሊከብድ ይችላል። ነገር ግን የማይለመድ የለም። ቡድኑ የነበረው ጥንካሬ ነበር። እዚያ ላይ የሁላችንም ጥረት ሲታከልበት ውጤታማ መሆን ችለናል።' እውን የማልታ የሴቶች ሊግ ለተጫዋቾች ጥሩ ክፍያ ይከፍላል ወይ የሚል ጥያቄ ከቢቢሲ የቀረበላት ሎዛ፤ ክፍያው እንኳ ቢቀር የማልታ ልምዱ ለወፊት የተሻለ ውድድር ውስጥ ራሷን እንድታገኝ እንደሚረዳት ትናገራለች። 'አንድን ነገር ለማሳካትስ ስታስብ ብዙ ነገሮችን ከግምት ታስገባለህ። እኔ ክፍያን እዚህ ውስጥ አልከተውም። የክፍያ ማነስ አለ እያልኩ ሳይሆን አላማዬ በዚህ ጉዞ ራሴን ለማሳየት፤ ወጥቼ መጫወት እንደምችል ለማሳየትና ፕሮፋይሌን ከፍ ለማድረግ ስለሆነ ተሳክቶልኛል ብዬ ነው የማስበው።' 'እርግጥ ነው የሃገሬ ምግብ ናፍቆኝ ነበር' ትላለች ከግማሽ ዓመት በላይ በአውሮጳዊቷ ትንሽዬ የጠረፍ ሃገር የቆየችው ሎዛ። ኮሮናቫይረስና እግር ኳስ ባለፈው ታኅሣሥ ድምፁ የተሰማው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሰው ልጅ ከጠበቀው በላይ ጥፋት አድርሷል፤ የተለመዱ የሕይወት መስተጋብሮችን እንዳይሆኑ አድርጓል። ወረርሽኙ ካመሰቃቀላቸው መስኮች አንዱ እግር ኳስ ነው። ይህ ወረርሽኝ በሎዛ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ሕይወት ላይ ያመጣው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? 'በጣም ከባድ ነው። እግር ኳስን ብቻ ሳይሆን ሌሎች መስኮችንም የጎዳና ለዓለም የመጣ ስለሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም።' ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ ከውድድር ርቀው የነበሩ እግር ኳስ ተጫዋቾች አንዱ ፈተናቸው በያሉበት ሆነው የአካል ብቃታቸውን ጠብቀው መቆየት ነው። ሎዛስ? 'በአቅራብያዬ በሚገኙ ቦታዎች እየሄድኩ እሠራ ነበር። ሠፈር ውስጥም ቤትም ነው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የማደርገው። ራቅ ብሎ ሄዶ እንቅስቃሴ ለማድረግ ጊዜው ስለማይፈቅድ በምችለው መልኩ በአቅራቢያዬ ነበር እንቅስቃሴ ሳደርግ የነበረው።' ሎዛ እሷ ብቻ ሳትሆን የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድንና የቀድሞ ቡድኗ አዳማ ከነማ ተጫዎቾችን አልፎ አልፎ በስልክ እንደምታገኛቸው በታቻላቸው መጠን በአካባቢዎች እንቅስቃሴ እያደረጉ እንዳሉ ትናገራለች። አልፎም ሎዛ 'እንቅስቃሴ ማድረግ ከወረርሽኙ ሊታደገን ስለሚችል ሁሉም ሰው በያለበት የተቻለውን ያክል እንቅስቃሴ ቢያደርግ' ስትል ምክሯን ትለግሳለች። የሎዛ የአዲስ ዓመት ምኞት 'ሁላችንም ከምንወደው ሙያ ርቀን በቤታችን ነው ያለነው። ፈጣሪ ይህን ዓመት በሰላም አሻግሮ ይህንን ወረርሽኝ ያርቅልን፤ እንዲሁም ሁላችንንም ወደ ሥራ ይመልሰን ብዬ እመኛለሁ።' 'ስፖርተኛውም በስፖርቱ፤ ሌላውም በተሰማራበት መስክ በአዲሱ ዓመት የተሻለ ነገር እንሠራለን ብዬ ነው የማስበው።' ቢቢሲ፡ እናመሰግናለን ሎዛ፤ ለአንቺና ለቤተቦችሽ መልካም አዲስ ዓመት ማለት እንወዳለን። ሎዛ፡ እኔም አመሰግናለሁ። ለእናንተም መልካም አዲስ ዓመት! https://www.bbc.com/amharic/news-54101682 +business ፓኪስታን ዜጎቿ የሻይ ፍጆታቸውን እንዲቀንሱ ጠየቀች የፓኪስታን ዜጎች በአገሪቱ ያለውን የምጣኔ ሃብት ቀውስ ለማረጋጋት የሚጠጡትን የሻይ መጠን እንዲቀንሱ ተጠየቁ። የፓኪስታን ከፍተኛ ሚኒስትር አህሳን ኢቅባል፣ በቀን ጥቂት ብርጭቆ ሻይ መጎንጨት ፓኪስታን የሻይ ቅጠል ምርትን ከውጪ ለማስገባት የምታወጣውን ወጪ ይቀንሳል ብለዋል። በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከውጭ የሚገባ ማንኛውም ምርት ለመግዛት የሚበቃው ከሁለት ወር ላነሰ ጊዜ ብቻ ነው ተብሏል። ይህም አገሪቷን አስቸኳይ የገንዘብ እርዳታ እንድትፈልግ አስገድዷታል። ፓኪስታን ባለፈው ዓመት ከ600 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ ሻይ ቅጠል ከውጭ በማስገባት ከዓለም ከፍተኛውን ሻይ ቅጠል አስመጪነት ቦታን ይዛለች። እንደ ፓኪስታን ሚዲያ ከሆነ ሚኒስትር ኢቅባል “የአገሬው ሰው የሻይ ፍጆታውን ወደ አንድ ወይም ሁለት ብርጭቆ እንዲቀንስ እጠይቃለሁ። ምክንያቱም ሻይ ቅጠል የምናስገባው በብድር ነው” ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የንግድ ተቋማት የሚጠቀሙትን የኤሌክትሪክ ኃይል ለመቆጠብ የንግድ ቦታቸውን ምሽት 2፡30 ላይ እንዲዘጉ ሚኒስትሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ተማፅኖው ለፓኪስታን ሕዝብ የቀረበው የአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት በተከታታይ እና በፍጥነት እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ ነው። ይህም በአገሪቱ፣ መንግሥት ምርቶችን ከውጭ ለማስገባት የሚያወ��ቸውን ወጪዎች በመቀነስ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ይዞ እንዲያቆይ አስገድዶታል። የአገሪቷ ሕዝቦች የሻይ ፍጆታቸውን እንዲቀንሱ መጠየቃቸው በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል። አብዛኛው ሰውም አገሪቷ የገጠማት ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ቀውስ የሻይ ፍጆታን በመቀነስ ይፈታል የሚል እምነት የለውም። የፓኪስታን የውጭ ምንዛሬ ክምችት የካቲት ወር ላይ ከነበረው 16 ቢሊየን ዶላር በሰኔ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ወደ ከ10 ቢሊየን ዶላር በታች አሽቆልቁሏል። ባለፈው ወር የካራቺ ባለሥልጣናት በአገሪቷ ያለውን የውጪ ምንዛሬ ክምችት ለመጠበቅ በርካታ መሠረታዊ ያልሆኑ የቅንጦት እቃዎች እንዳይገቡ ገደብ ጥለው ነበር። በአገሪቷ ያለው የምጣኔ ሃብት ቀውስ፣ ባለፈው ሚያዝያ ወር በተደረገው የምክር ቤት ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህንን ለተኩት ሸህባዝ ሸሪፍ መንግሥት ትልቅ ፈተና ሆኗል። ሸሪፍ ሥልጣን ተረክበው ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ የአገሪቷ ምጣኔ ሃብት በአግባቡ አልተመራም፤ ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመመለስም ከባድ ነው ሲሉ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ከሰዋል። ባለፈው ሳምንት ካቢኔው፣ የተቋረጠውን የ6 ቢሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም እንዲጀመር ዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት(አይኤምኤፍ)ን ለማሳመን የ47 ቢሊየን ዶላር በጀት አጽድቋል። አይኤምኤፍ እአአ በ2019 በውጭ ምንዛሬ እጥረት እና ለዓመታት በዘገየ እድገት ምክንያት የሚፈጠር የምጣኔ ሃብት ቀውስን ለማቃለል የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም፣ አበዳሪዎች አገሪቷ ብድሩን ለመክፈል ያላትን የፋይናንስ አቅም ከጠየቁ በኋላ ቆሟል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1zzww9vrpo +politics ንግሥቲቱ እና አፍሪካ: ረጅም ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት "የያኔዋ ልዕልት ኤልዛቤጥ በኬንያ ገጠራማ ሥፍራ በሚገኘውና በአረንጓዴ ተክሎች፣ በረጃጅም ዛፎች እና በዱር አራዊት በተከበበው ትሬቶፕስ ሆቴል ሲደርሱ አባታቸው ንጉስ ጆርጅ ስድስተኛ አረፉ።በዚያም በ25 ዓመታቸው የንግሥትነት ሥፍራውን ያዙ። ንግሥት ኤልዛቤጥ ሁለተኛ በሰባ ዓመት የንግሥና ዘመናቸው ከ20 በላይ የአፍሪካ አገሮችን ጎብኝተዋል። በአንድ ወቅት ለቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ ከማንኛውም ሰው በላይ የአፍሪካ አገራትን ጎብኝቻለሁ በማለት በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችን ፈገግ አሰኝተው ነበር። ንግሥት ሲሆኑም በርካታ አገራትን ያካተተ የአፍሪካ አህጉርን በግዛትነት ጠቅልለው ወርሰው ነበር። በግዛት ዘመናቸውም በአውሮፓውያኑ 1957 ነጻነቷን ካገኘችው ጋና ጀምሮ 14ቱም የአፍሪካ አገራት የእንግሊዝ ቅኝ ግዛቶች ነጻነታቸውን አግኝተዋል። ንግሥቲቷ ነፃነታቸውን ካገኙ አገራትም ጋር ሞቅ ያለ ግንኙነትን መፍጠር ችለዋል፤ ይህን ማድረግ የቻሉትም በከፊል የብሪታንያ ግዛት ተተኪ የሆነውን የኮመንዌልዝ ድርጅትን በመመስረት ነው። በአውሮፓውያኑ 1961 ጋና ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ እንድትሆን ከመሩት እና የመጀመሪያዋ ፕሬዚዳንት ክዋሜ ንክሩማህ ጋር ሲደንሱም ታይተዋል። በተለይም ኢምፓየር (ግዛት) የሚለው ቃል በአውሮፓውያኑ 1953 በነበረው የንግሥና በዓለ ሲመትና መሃላ ወቅት እንዲቀር ተደርጓል። ንግሥቲቱ ማረፋቸውን ተከትሎ ከአህጉሪቱ የተውጣጡ መሪዎች ብሪታንያ እና ኮመንዌልዝን ለረጅም ዓመታት በንግሥና ለመሩትን ንግሥት ኤልዛቤጥ ሃዘናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ንግሥናቸው የተጀመረበት ኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ “ከራስ ባለፈ ለሰው ልጅ የሚያገለግሉ ትልቅ ተምሳሌት የሆኑና እና የዩናይትድ ኪንግደም ብቻ ሳይሆን ኬንያ የተከበረች አባል የሆነችበት የኮመንዌልዝ ኅብረት ቁልፍ መሪ ናቸው” ሲሉ ገልጸ���ቸዋል። የዚምባብዌ እና የዩናይትድ ኪንግደም ግንኙነት ለረጅም ዓመታት ሻክሮ የቆየ ሲሆን ሟቹ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ አገራቸው ከኮመንዌልዝ ኅብረት አባልነት ለቃ እንድትወጣ አድርገዋል። ሆኖም ተተኪያቸው ኤመርሰን ምናንጋግዋ “የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለንጉሳዊው ቤተሰብ፣ ለዩናይትድ ኪንግደም እና ኮመንዌልዝ” በትዊተር ገጻቸው በፍጥነት ገልጸዋል። በአፍሪካ ትልቋ ግዛት የነበረችው ናይጄሪያ መሪ ሙሃማዱ ቡሃሪ በበኩላቸው፣ ረዘም ያለ የሀዘን መግለጫ በትዊተር ገጻቸው ያሰፈሩ ሲሆን “ከፍተኛ ሃዘንም ተሰምቶኛል” ብለዋል። ""የዘመናዊቷ ናይጄሪያ የታሪክ ምዕራፍ፣ ዓለም አቀፋዊ ስብዕና እና የላቀ መሪ ከሆኑት ያለ ንግሥት ኤልዛቤጥ ሙሉ አይሆንም። ሕይወታቸውን ለሕዝባቸው፣ ለኮመንዌልዝ እንዲሁም መላው ዓለምን የተሻለ ቦታ ለማድረግ ሰጥተዋል” ብለዋል። የግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቻርለስ ሳልሳዊ ወደ ዙፋኑ መምጣታቸውንም ፕሬዚዳንቱ በደስታ ተቀብለውታል። አዲሷ የኮመንዌልዝ አባል የሆነችውና የፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ግዛት የነበረችው ጋቦን ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎም ሀዘናቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። የአህጉሪቱ መሪዎች የሀዘን መግለጫቸውን ቢያስተላልፉም ሌሎች አፍሪካውያን በበኩላቸው በብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ወቅት የደረሰባቸውን ስቃይና በደል እየተናገሩ ሲሆን፣ ይህም በንጉሳዊ ቤተሰቦች ስም ተፈጽሟል እያሉ ነው። አንዳንድ የአፍሪካ ንጉሶችና ቤተሰቦችም ሀዘናቸውን ገልጸዋል። ልዑል ማንጎሱቱ ቡተሌዚ፣ በደቡብ አፍሪካ ዙሉ ሕዝብ መሪ ንጉስ ሚሱዙሉ ካዝዌሊቲኒ ስም ሀዘናቸውን ገልጸዋል። ከንጉሥ ቻርልስ ሳልሳዊ ጋር ያላቸውን ወዳጅነትም በመጥቀስ ለእርሳቸውም በግላቸው የሀዘን መግለጫ ልከዋል። ንጉሥ ሚሱዙሊ፣ አባታቸው ዝዌሊቲኒ ከ50 ዓመታት ንግሥና በኋላ በቅርብ ጊዜ ያረፉ ሲሆን የንጉሥ ቻርለስንም ሁኔታ በቅርበት ይረዳሉ። ንግሥቲቱ ከደቡብ አፍሪካ ጋር የረጅም ጊዜ ታሪክ አላቸው። በአውሮፓውያኑ 1947 የ21ኛ ዓመት ልደታቸውን ያከበሩት በደቡብ አፍሪካ በጉብኝት ላይ ነበር። በኬፕታውን በሬድዮ ላይ በሰጡት መግለጫ ሕይወታቸውን ለኮመንዌልዝ ኅብረት እንደሰጡና ደቡብ አፍሪካም ሙሉ ሕይወታቸውን የኖሩበትን ያህል “በአገሬ ያለሁ ያህል ይሰማኛል” ብለዋል። የፖለቲካ አቋማቸውን በማንጸባረቅ የማይታወቁት ንግሥት ኤልዛቤጥ ለአስርት ዓመታት በአገሪቱ ውስጥ የነጮች ጥቂቶች አገዛዝ ካበቃ ከአንድ ዓመት በኋላ በአውሮፓውያኑ 1995 ደቡብ አፍሪካን ሲጎበኙ ጠንከር ያለ ንግግር አድርገዋል። “የእርቅ መንፈሱ ለዓለም ተምሳሌት የሆነ የሕዝብን አንድነት አምጥቷል። እኔም ተመልሼ መጥቼ ይህንን ተአምር ለመመልከት ችያለሁ” በማለት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። ንግሥቲቱ ከኔልሰን ማንዴላ ጋር መልካም ግንኙነት ነበራቸው። የንግሥቲቱን ማረፍ ተከትሎ የኔልሰን ማንዴላ ፋውንዴሽን፣ “[ ከኔልሰን ማንዴላ] ጋር በተደጋጋሚ በስልክ ያወሩ ነበር። ያለ ቅጥያ ክብር ስም በመጀመሪያ ስማቸው ነበር የሚጠራሩት ይህም የመከባበር እና የመውደድ ምልክት ነው” በማለት መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው አክሎም ማንዴላ ለንግሥቲቷ ልዩ ስም ነበራቸው “ሞትላሌፑላ፣ የሚል ሲሆን ትርጉሙም ከዝናብ ጋር መምጣት ማለት ነው” ለዚህም በአውሮፓውያኑ 1995 ሲመጡ ዝናብ ከመዝነቡ ጋር በመገጣጠሙ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c514xy2zzqqo +health የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝ አዲስ አይነት የአእምሮ ጤና እክል ይዞ መጥቷል ተባለ "በኮሮናቫይረስ ከሚያዙ ሰዎች በእያንዳንዱ 17 ሰው አንድ ሰው ከባድ ጭንቀት፣ ድብርት እና እንቅልፍ ማጣት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚያጋጥመው አንድ አሜሪካ ውስጥ የተሰራ ጥናት ጠቁሟል። ይህ ቁጥር ታዲያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸው እንዲህ አይነት የጤና እክል ከሌሎች በሽታዎች ጋር ሲነጻጸር እጥፍ እንደሆነ ደርሰንበታል ይላሉ ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎች። በጥናቱ መሰረት ባልተጠበቀ ሁኔታ የቀደም የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች በኮሮናቫይረስ የመያዝ እድላቸው ከጤናማ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር 65 በመቶ ከፍ ያለ እንደሆነ ደርሰንበታል ብለዋል። ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያትነት የተቀመጠው የአእምሮ ጤና ችግር ኣላባቸው ታማሚዎች ሰውነታቸው የሚገኝበት አካላዊ ጥንካሬ፣ የሚወስዷቸው መድሀኒቶችና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ናቸው። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑትና የጥናቱ መሪው ፖል ሀሪሰን እንደሚሉት ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ ለከባድ የአእምሮ ጤና እክል የመጋለጣቸው እድል አብሮ ይጨምራል። ''ሌላው ቀርቶ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጦ ነገር ግን ሆስፒታል ሳይሄዱ በቤታቸው የዳኑት እንኳን ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው'' ይላሉ። ተመራማሪዎቹ 62 ሺህ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ፈቃደኛ ሰዎችን ለሶስት ወራት ያክል ሲከታተሉ የነበረ ሲሆን ከእነሱ የሚያገኙትን መረጃ እንደ ጉንፋን፣ የኩላሊት ህመም እንዲሁም የአጥንት ስብራት ካጋጠማቸው ሰዎች ጋር አወዳድረውታል፥። በዚህም መሰረት በኮሮናቫይረስ የተያዙት ሰዎች ከፍተኛ የአእምሮ ጤና መቃወስ ታይቶባቸዋል ተብሏል። በኮሮናቫይረስ የተያዙት ሰዎች በከባድ ጭንቀት፣ ድብርት እና እንቅልፍ ማጣት የመጠቃት ዕድላቸው ከሌሎቹ አንጻር 18 በመቶ ከፍ ብሎ ታይቷል። እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች መጠራጠርን እና ፍርሃትን መቋቋም አለመቻል የተለመደ የአእምሮ ህመም ባህሪ እንደሆነ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። ""ብዙ ጊዜ የጭንቀት ህመም ገና ባልተፈጠረና ባልታወቀ ነገር ላይ ይሆናል ብሎ አብዝቶ በመጨነቅ የሚመጣ ነው። ከዚህ አንፃር ኮሮናቫይረስ ከባድ ነገር ነው"" ፕሮፌሰር ፖል ሀሪሰን አዲስ ነገር በሚያጋጥመን ጊዜ አዕምሯችን ለተፈጠረው ነገር በተለያየ መንገዶች ምላሽ ይሰጣል። በአሁኑ ወቅት መላውን ዓለም እያስጨነቀ ያለው ኮሮናቫይረስም በኑሯችን፣ በሥራችናና በአጠቃላይ ህይወታችን ላይ ከዚህ በፊት ያልነበረ ሁኔታን ፈጥሯል። በዚህም ሳቢያ አዕምሯችን ወረርሽኙን በተመለከተና ተያያዥ ነገሮችን በተለየ ሁኔታ ለመገንዘብ ተገዷል። ይህም ክስተት ነው በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን ለተለያዩ የአእምሮ ጤና ችግሮች እያጋለጣቻው የሚገኘው። ሰዎች አይደለም እንዲህ ነገሮች ከበድ ባሉበት ወቅት አይደለም በደህናው ዘመን እንኳን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በአካል ማግኘት አስቸጋሪ ሲሆንና ሃሳብ ጭንቀታቸውን አይን አይናቸውን እያዩ ማካፈል ሳይችሉ ሲቀሩ ቀላል የማይባል ሥነ ልቦናዊ ጫና ይደርስባቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54885168 +politics ሊዝ ትረስ ከንግሥቲቱ ጋር ከተገናኙ በኋላ በይፋ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ ትናንት ሰኞ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ሆነው የተመረጡት ሊዝ ትረስ ዛሬ ማክሰኞ ከንግሥት ኤልዛቤጥ ሁለተኛ ጋር ከተገኙ በኋላ በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ። ሊዝ ትረስ ወደ ባልሞራል ቤተ-መንግሥት ተጉዘው ንግሥት ኤልዛቤጥን ያገኙት በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የተለመደ አካሄድን መከተል ስላለባቸው ነው። የዩኬ እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤጥ ዳግማዊት በ70 ዓመት የንግሥና ዘመናቸው ሊዝ ትረስ 15ኛ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው። አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ንግሥቲቱን ያገኙት ቀደም ሲል ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለንግሥቲቱ የመልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ካስገቡ በኋላ ነው። ሊዝ ትረስ ከባኪንግሃም ይልቅ ስኮትላንድ ወደ ሚገኘው ባልሞራል ቤተ-መንግሥት መሄድ ያስፈለጋቸው ንግሥቲቱ ለመንቀሳቀስ የጤና እክል ስለገጠማቸው ነው ተብሏል። አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር በመጀመሪያው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቀናቸው ቀሪ የሥልጣን ዘመናቸውን የሚጀመሩት በሚከተሉት ተግባራት ይሆናል። በቅድሚያ ንግሥት ኤልዛቤት፣ ሊዝ ትረስ ካቢኔያቸውን አዋቅረው መንግሥት እንዲመሰርቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ግብዣ ያቀርባሉ። ሊዝ ትረስም ‘እጅ መሳም’ ተብሎ በሚጠራው ሥርዓት ግብዣውን ይቀበላሉ። ከዚያም በይፋ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ሊዝ ትረስ ወደ መኖሪያ እና የሥራ ቦታቸው ወደሚሆነው 10 ዶውኒንግ ስትሪት በማቅናት ከጥቁሩ በር ፊትለፊት የመጀመሪያ ንግግራቸውን ያደርጋሉ። ሊዝ ትረስ በዚህ ንግግራቸው የአስተዳደራቸው ዋና ዓላማዎች ምን እንደሆኑ ያብራራሉ። ቀጥሎ ባሉት ቀናት ሊዝ ትረስ ከሚተገብሯቸው ተግባራት መካከል አንዱ ለዩኬ ጦር ኃላፊዎች ደብዳቤ መጻፍ ነው። በዚህ ጽሑፋቸው ዩናይትድ ኪንግደም የኒውክለር ጥቃት ቢፈጸምባት ምላሿ ምን ይሆናል የሚል ነው። ይህ ደብዳቤ ታዲያ የሚከፈተው ጦሩ ከዩኬ መንግሥት ጋር ግንኙነቱ ከተቋረጠ ነው። ሊዝ ትረስ ዛሬ በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት የዩኬ ወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ነው። ባለፉት ዓመታት የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ሊዝ ትረስ፤ የወግ አጥባቂ መሪ ለመሆን ከቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ብርቱ ፉክክር ገጥሟቸው ነበር። ይሁን እንጂ የኋላ ኋላ ሊዝ ትረስ በሰፊ የድምጽ ብልጫ ሪሺ ሱናክን በመብለጥ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ እንዲሆኑ በፓርቲው አባላት ተመርጠዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cx9g7ydydlzo +business ዓለም ባንክ ለኮሮናቫይረስ ድንገተኛ እርዳታ 12 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባ "የዓለም ባንክ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ትግል ውስጥ ያሉ አዳጊ አገራትን ያግዝ ዘንድ የ12 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብቷል። ዓለም ባንክ ገንዘቡን የሚሰጠው በብድር፣ በእርዳታና በቴክኒክ ድጋፍ መልክ ሲሆን ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የዓለም መሪዎች ኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚያቸውን እንዳያሽመደምድ ብርቱ ዝግጅት ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ነው። ኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚዎች ላይ የሚያስከትለው መቀዛቀዝ አገራትን ችግር ውስጥ ሊከት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል። ይህ የዓለም ባንክ እርዳታ አገራት የኮሮናቫይረስን ስርጭት በመከላከል ረገድ የጤና አገልግሎት ስርዓቶቻቸውን እንዲያጠናክሩና ቫይረሱ የሚያሳድረውን ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ለመቀነስ ከግል ዘርፍ ጋር እንዲሰሩ ለማስቻል ነው። ""ለማድረግ እየሞከርን ያለነው የቫይረሱ ስርጭት እንዲገታ ነው"" ብለዋል የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ። ዓለም ባንክ እንዳስታወቀው እርዳታውን በቅድሚያ የሚሰጠው በጣም ድሃ ለሆኑ አገራትና ለቫይረሱ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ለሆኑ አገሮች ነው። • ትዊተር በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሠራተኞቹ ከቤት እንዲሠሩ ፈቀደ • ጣልያን ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው አካባቢዎችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ዘጋች • ኮሮናቫይረስ የአእምሮ መረበሽን እያስከተለ ነው ተባለ ኮሮናቫይረስ በ70 አገራት ላይ እንደተሰራጨ የሚታወቅ ነው። ዓለም ባንክ ቃል የገባው ገንዘብ ግማሽ ያህሉ ከባንኩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን የሚገኝ ሲሆን አራት ቢሊዮን የሚሆነው ደግሞ ቀደም ሲል ከነበሩ ፈንዶች ተዘዋውሮ የሚመጣ እንደሆነ ተገልጿል። እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ 92 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ��ኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን 80 ሺህ የሚሆኑት ኬዞዎች የተመዘገቡት ቻይና ውስጥ ነው። በሌላ በኩል ሶስት ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ የሞቱ ሲሆን በተመሳሳይ ብዙዎቹ ሞቶች የተመዘገቡት በቻይና ነው። በዛሬው እለት 38 ሞቶች በቻይና የተመዘቡ ቢሆንም የቻይና መንግሥት እንቅስቃሴን የሚገቱ ጥብቅ እገዳዎችን በመጣሉ ላለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ አዳዲስ በኮሮናቫይረስ የመያዝ ሪፖርቶች ቀንሰዋል እየተባለ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/51716797 +sports የስፖርት ውርርድ አዲሱ የወጣቶች ሱስ ይሆን? "ሄኖክ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚኖር ወጣት ነው። ከስድስት ወር በፊት በጓደኞቹ ገፋፊነት የጀመረው በስፖርት ውድድሮች ላይ ገንዘብ ማስያዝ መወራረድ ሱስ እየሆነበት እንደመጣ ይናገራል። ''ከገንዘብ ጋር የተያያዘ እንደመሆኑ መጠን እራስን ለመቆጣጠር ትንሽ ይከብዳል። በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረጉ በተለይ የእንግሊዝና ሌሎች የአውሮፓ ሊጎች ላይ ሳላስይዝ አላልፍም''ይላል። • ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ በትንሹ ከ10 ብር ጀምሮ እስከ 200 ብር ድረስ በአንድ ጊዜ እንደሚያስይዝ የሚናገረው ሄኖክ የጨዋታዎቹን ውጤት ለማየትና ምን ያህል እንደበላ አልያም እንደተበላ ለማረጋገጥ ቁጭ ብሎ ሌሊቱን የሚያሳልፍበት ጊዜም እንዳለ ይናገራል። ሌላው ቢቀር ይላል ሄኖክ ''ማህበራዊ ሚዲያዎችን በተንቀሳቃሽ ስልኬ በመመልከት የማጠፋውን ጊዜ እንኳን ቀንሻለው። አጋጣሚው ሲኖረኝ ሁሌም የአቋማሪ ድርጅቱን መተግበሪያ ከፍቼ ማየት ነው የሚቀናኝ።'' በስፖርት ውድድሮች ውጤት ላይ ተመስርቶ መወራረድ በኢትዮጵያ እምብዛም የተለመደ ነገር አልነበረም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እንደ አቢሲኒያ፣ አክሱምና ሃበሻን የመሳሰሉ የስፖርት አወራራጅ ድርጀቶች የብዙ ወጣቶችን ቀልብ መሳብ ጀምረዋል። ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነው የአቢሲኒያ አወራራጅ ድርጅት መስራችና ባለቤት የሆነው አሸናፊ ንጉሤ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፈቃድ አግኝተው መስራት የጀመሩት ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ መሆኑን ይናገራል። አሸናፊ ""ብዙ ሰዎች ከስፖርታዊ ውርርዶች ጋር በተያያዘ የተሳሳተ አመለካከት አላቸው"" ብሎ ያምናል። በስፖርታዊ ውድድሮች ገንዘባቸውን ለማስያዝ የሳምንቱ መጨረሻ ቀናትን በጉጉት ከሚጠብቁት እንደ ሄኖክ ካሉ ተቋማሪዎች በተለየ ሱስ የማስያዝም ሆነ አላግባብ ወጪ ውስጥ አያስገባም ይላል። ''በስፖርት ውድድሮች ይሄኛው ቡድን ያሸንፋል ሌላኛው ይሸነፋል እያሉ መወራረድ የተለመደና ሁሌም የነበረ ነገር ነው'' የሚለው አሸናፊ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ፈቃድ አግኝቶ ተሳታፊዎች ልኩን ባላለፈ መልኩ እንዲወራረዱ ማድረጉ ከጉዳቱ ጥቅሙ እንደሚበልጥ ያስረዳል። ''በአሁኑ ጊዜ ወጣቶች ከሚታሰበው በላይ የስፖርት እውቀታቸው ጨምሯል። በዚህም ምክንያት ገንዘባቸውን ሲያስይዙ እራሱ በእውቀት ላይ ተመስርተው ነው። ገንዘባቸውን ከማስያዛቸው በፊት ሬድዮና ስፖርታዊ ድረገጾችን ተከታትለው ስለሆነ የሚመጡት ከውርርዱ በተጨማሪ መረጃ ቶሎ ቶሎ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል'' ይላል። በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቴድሮስ ነዋይ በበኩላቸው የስፖርት ውርርድ ድርጀቶች ተገቢውን ቅድመ ሁኔታዎች እስካሟሉ ድረስ ማህበረሰቡ ላይ የሚያሳድሩት ጫና እንደሌለ ይናገራሉ። እስካሁን አስተዳደሩ 28 የሚሆኑ አወራራጅ ድርጅቶችን በህጋዊ መንገድ የመዘገበ ሲሆን 23 የሚሆኑት ፍቃድ ባገኙበት ዘርፍ ሥራቸውን እያከናወኑ ነው። ከነዚህ መካከል አራቱ በያዝነው 2012 ዓ.ም ፍቃድ ያገኙ ናቸው። አቶ ቴዎድሮስ እንደሚሉት የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባለፈው ዓመት ከአወራራጅ ድርጅቶች ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢም አግኝቷል። ''በመጀመሪያ መረሳት የሌለበት በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩትን ድርጅቶች አቋማሪ አንላቸውም። የስፖርት ውድድር አወራራጅ ድርጅቶች ብለን ነው የምንጠራቸው'' ይላሉ። ''ቁማር ሲሆን አንዱ የሚጎዳበት አንዱ ብቻ ደግሞ የሚጠቀምት ነው። ስለዚህ ምንም ማህበራዊ ፋይዳ ሊኖረመው አይችልም። እኛ ፈቃድ የምንሰጠው የስፖርት ውርርድ ባህሪው የሎተሪ ነው። ማህበረሰቡ በተለይም ወጣቶች ጊዜያቸውን በሌሎች ነገሮች ላይ ከሚያሳልፉ እየተዝናኑ እድላቸውን የሚሞክሩበት ነው።'' ''ማህበራዊ ፋይዳ ከሌለው እኛም ፈቃድ አንሰጥም'' የሚሉት አቶ ቴድዎሮስ ለዚህም ድርጅቶቹ ከውርርድ ከሚያገኙት ገቢ 20 በመቶውን በመረጡት ማህበራዊ የበጎ አድራጎት ተቋም ላይ እንዲያውሉ እንደሚገደዱ ጠቅሰዋል። ከዚህ በተጨማሪ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከድርጅቶቹ ገቢ 15 በመቶውን በኮሚሽን መልክ የሚወስድ ሲሆን ድርጅቶቹ ከደንበኞቻቸው ግብር ሰብስበውም ለመንግሥት ገቢ ያደርጋሉ። በተጨማሪ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውንም ይከፍላሉ። እነዚህ ሁሉ ሂደቶች ድርጅቶቹ ብዙ ትርፍ እንዳይግበሰብሱና የሚገኘው ገቢ ለተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች መዋላቸውን ማረጋገጫ እንደሚሰጣቸው አቶ ቴድሮስ ይናገራሉ። ሌላኛው ያነጋገርነውና በስፖርት ውድድሮች ገንዘብ ማስያዝ ከጀመረ ብዙ ጊዜ እንዳልሆነው የሚናገረው አሰግድ በሳምንት ቢያንስ አምስት ጨዋታዎች ላይ ገንዘቡን እንደሚያስይዝ ይናገራል። አብዛኛዎቹ ድርጅቶች ዘመናዊ አሰራር ስለሌላቸው በአካል ሄዶ ገንዘብ ማስያዝና መቀበል አድካሚ መሆኑን ይገልጻል። ''ብዙ ጊዜ በስሜ ገንዘብ ለማስገባትም ሆነ ካሸነፍኩኝ ገንዘቤን ለመቀበል ወደ አቋማሪ ድርጅቶቹ ቢሮ ድረስ መሄድ አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ ወደ ቢሮው የሚሄድ ጓደኛዬ ካለ ለእኔም እንዲያስገባልኝ የማደርግብትም ጊዜ አለ'' ይላል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ ምንም እንኳን ውርርድን በተመለከተ ስለኢትዮጵያ በቂ የሆነ መረጃ ባይበኖርም በኬንያ፣ በደቡብ አፍሪካ ወይንም በናይጄሪያ የሚገኙ እድሜያቸው ከ18 እስከ 40 የሚደርሱ ሰዎች በአማካይ በቀን እስከ 15 ዶላር ድረስ እንደሚያስይዙ ጥናቶች ይጠቁማሉ። በሌሎቹ የአፍሪካ ሀገራት ከሚስተዋለው በተለየ ሄኖክ ገንዘቡን የሚያስይዝባቸው ድርጅቶ የሀገር ውስጥ ውድድሮችን እምብዛም እንደማያካትቱና በብዛት የአውሮፓ ሊጎች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ይናገራል። እስከ 14 ሺህ ብር ድረስ ሁለት ጊዜ በውርርድ እንዳሸነፈ የሚናገረው ሄኖክ ገንዘቡን ከማስያዙ በፊት የተለያዩ መረጃዎችን እንደሚሰበስብና አማራጮቹን ለማብዛት እንደሚሞክር ነግሮናል። በስፖርታዊ ውድድሮች መወራረድ ጋር አብሮ የሚነሳ አንድ ችግር አለ። እሱም እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችና ተማሪዎች በዚሁ ተግባር ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን ሊያጠፉ መቻላቸው ነው። አሰግድ አብዛኛዎቹ አወራራጅ ድርጅቶች ለመወራረድ ከሚመጡት ሰዎች መካከል ምን ያህሉ ""እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መሆኑን የሚቆጣጠሩ አይመስለኝም"" ይላል። ''እኔ በግሌ ገንዘብ ለማስያዝ ስሄድ ትንንሽ ልጆችን እመለከታለው። ልክ እንደ ማንኛውም ሰው ተስተናግደው ነው የሚሄዱት። በስልካቸው መተግበሪያዎችን አውርደው ሲጠቀሙም እምለከታለው"" ሲል አሳሳቢ መሆኑን ይተቅሳል። የአቢሲኒያ አወራራጅ ድርጅት ባለቤት አሸናፊ ንጉሤ ግን እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች በስፖርታዊ ውድድሮች እንዳይሳተፉ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርጉ ይናገራል። ''ማንኛውም ሰው ገንዘብ ለማስያዝም ሆነ አባል ለመሆን ወደ ቢሮዎቻችን ሲመጣ መታወ���ያ እንጠይቃለን። በድረ ገጽና በስልክ መተግበሪያዎች ለሚጫወቱት ደግሞ የገንዘብ ዝውውር ለማድረግ በባንክ በኩል የሂሳብ ደብተር መክፈት ስላለባቸው የእድሜያቸውን ነገር በዚው እንቆጣጠረዋለን።'' ''ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንዲጫወቱ አንፈቅድም፤ አብረውት ሊመጡ የሚችሉትንም ጉዳቶች ጠንቅቀን እናውቃቸዋለን'' ይላል። • አብረሃም መብራቱ፡ የየመንን ብሔራዊ ቡድን ለትልቅ ውድድር ያበቃ ኢትዮጵያዊ የስፖርታዊ ውድድሮች ላይ የሚደረግ ውርርድ ዙሪያ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችን ድርጅቶቹ እንዳያጫውቱ የሚከለክል መመሪያ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባይኖረውም ውርርዱ ላይ ህጻናት እንዳይሳተፉ ስምምነት እንዳላቸው የአስተዳደሩ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ገልጸዋል። ''እድሜያቸው ያልደረሰ ህጻናት የሚጫወቱ ከሆነ ተገቢውን እርምጃ ከመውሰድ ግን ወደኋላ አንልም። ጥቆማ ከደረሰንም የምንከታተል ሲሆን እስካሁን ግን ምንም የደረሰን ቅሬታም ሆነ ጥቆማ የለም'' ይላሉ። ውርርድ ሱስ የማስያዝ ባህሪ ሊኖረው ስለሚችል ወደፊት የዘርፉን አካሄድ በመመልከትና ተያይዘው የሚመጡ ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ አስተዳደሩ ዝግጁ መሆኑን አቶ ቴድሮስ ገልጸዋል። ለአሁኑ ግን በኢትዮጵያ ያለው የውርርድ ዘርፍ ገና ጀማሪ በሚባልበት ደረጃ በመሆኑ አካሄዱን መከታተልና ማህበረሰቡ እየተዝናና ሃላፊነቱን የሚወጣበትን መንገድ ማማቻቸት ላይ ትኩረት እንዳደረጉም አክለዋል። ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ መወራረድ ሙሉ በሙሉ መከልክል የለበትም የሚለው ሃሳብ ያሚያስማማቸው አሰግድና ሄኖክ አወራራጅ ድርጅቶችም ሆነ መንግሥት ውርርድ ሱስ ሊያስይዝ እንደሚችል በደንብ መረጃ ቢሰጡና ዘርፉ ጠበቅ ያለ ክትትል ቢደረግብት መልካም እንደሆነ ግን ያምናሉ። ከስፖርታዊ ውርርዶች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የወጣቶች ሥራ አጥነት፣ ለስፖርታዊ ውድድሮች ያለ ከፍተኛ ፍቅር፣ የላላ የቁማር ህግና ቀላል የተንቀሳቃሽ ስልክ ክፍያ መንገዶች መብዛት እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ ሃገራት ትልቅ ፈተና ሊደቅኑ እንደሚችሉ አንዳንዶች ስጋታቸውን ይገልጻሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-49835538 +business ኮሮናቫይረስ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ምን አሉ? "ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ትናንት አርብ አመሻሽ ላይ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በተመለከተ በጽህፈት ቤታቸው መግለጫ ሰጥተወው ነበር። በዚህ መግለጫቸው ላይም የኢኮኖሚ፣ የጸጥታ፣ የጤና እና የማህበራዊ ጉዳዮች ኮሚቴ ተቋቁሞ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ሲከታተል መቆየቱን አስታውቀዋል። በዚህም መሠረት አዳዲስ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ተወስኗል በማለት ውሳኔዎቹን ገልፀዋል።. ማንኛውም ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ሰው ለ14 ቀናት በራሱ ወጪ ወደ ለይቶ ማቆያ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ከ 30 በላይ አገራት የሚያደርገውን በረራ እንዲያቋርጥ መወሰኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አየር መንገዱ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት አስታውቀዋል። ""አየር መንገዱ 190 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ አጋጥሞታል። በዚህም ወደፊት ከፍተኛ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል ይጠበቃል"" ብለዋል። የአምልኮ ስርዓቱ እና ልምዱ ለበሽታው ተጋላጭ ያደርጋል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከኦርቶዶክስ ኃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት መደረጉን ተናግረዋል። በዚህም ""በእነሱ [ኦርቶዶክስ ኃይማኖት አባቶች] በኩል መልዕክት እንደሚተላለፍ ይጠበቃል"" ያሉ ሲሆን፤ የፕሮቴስታንት መሪዎችም ቴክኖሎጂን በመታገዝ አገልግሎት እንዲሰጡ አማራጭ መ���መጡን ተናግረዋል። በእስልምናም የሚደረጉ ሰላቶች ንክኪ ስለሚኖራቸው፤ የሃይማኖት መሪዎች እርምጃ እንደሚወስዱ እና መግለጫ እንዲሰጡ መንግሥት ጥሪ አስተላልፏል ብለዋል። በማረሚያ ቤቶች በሽታው ከገባ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ታራሚዎችን ወደ ሌሎች ቦታዎች ወስዶ ዘርዘር ለማድረግ ተጨማሪ ቦታዎች ተዘጋጅቷል ብለዋል። አክለውም አዳዲስ ታራሚዎች ምርመራ ሳይደረግላቸው ወደ ማረሚያ ቤት አይገቡም ብለዋል። እንዲሁም የቤተሰብ ጥየቃ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም መደረጉን ጠቅሰዋል። ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፤ ህጻናትን የያዙ፣ የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰ እና ቀለል ያለ ክስ ያለባቸው እንዲለቀቁ መወሰኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከሰሞኑ የወረርሽኙን ስርጭት ተከትሎ በአዲስ አበባ በውጪ አገር ዜጎች ላይ የደረሰው ጥቃት ''ኢትዮጵያዊ ባህሪ የሌለው ነው'' በማለት ጥቃቱን አውግዘዋል። ከሰሞኑ በርካታ ወጣቶች ሰዎችን እጅ ማስታጠብ ጨምሮ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ሲያከናውኑ ነበር። መንግሥት የበጎ አድራጎት ሥራዎቹን በአክብሮት የሚመለከተው ነው ካሉ በኋላ፤ ነገር ግን አገልግሎቱን የሚሰጡ ሰዎች ተገቢውን ጥንቃቄ መውሰድ እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የእስካሁኑን የሕክምና ባለሙያዎችን ጥረት አድንቀዋል። የቫይረሱ ስርጭት የሚስፋፋ ከሆነም በሽታውን ለማሸነፍ ብዙ ጥረት ይጠበቅባችኋል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ከጃክ ማ፣ ከቢል ጊቴስ እና ከዓለም ባንክ በተገኙ ድጋፎች የዜጎች ሕይወት እንዳያልፍ እንደሚሰራ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የመሽት መዝናኛ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ይሆናሉ ብለዋል። በጠባብ ቦታ ላይ በርካታ ሰዎች ስለሚያስተናግዱ የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ዝግ ይደረጋሉ ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። ""በሽታውን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠራችንን እስክናረጋግጥ ድረስ የምሽት መዝናኛዎች እንዲዘጉ ተወስኗል"" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ ያልተገባ ትርፍ ለማግኘት በሞከሩ ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታውሰው አሁንም ሕጋዊ የማስተካከያ እርምጃዎች መውሰድ ይቀጥላል ብለዋል። በክልሎች የሚገኙ ዋና ዋና ሆስፒታሎች ምረመራ የማድረግ አቅማቸውን ለማሳደግ ስራዎች ሲከናወኑ እንደነበረ አስታወሰዋል። ለዚህም የሚረዳ የምረመራ እና የማዳን ሥራ እንዲሰራ ተግባብተናል ብለዋል። ወረርሽኙ ከወራት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ስለሚኖረው ጫና ሲያስረዱ፤ ""ምርጫ ቦርድ የራሱን ግምገማ እያካሄደ ነው፤ ግምገማውን መሰረት በማድረግ የመጨረሻው ውጤት ይፋ ይደረጋል"" ብለዋል። የመጠጥ ውሃ እጥረት ባለባቸው ቦታዎች በቦቴ የማቅረብ ሠራዎች እየተካሄዱ እንደሆነ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። በተለይ በከተማ አከባቢ ከፍተኛ የውሃ እጥረት መኖሩን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በመግለጫቸው መጨረሻ ላይ ""የብልጽግና ፓርቲ የገንዘብ መዋጮ ላይ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችን እና የፖለቲካ ምሁሮችን በተመለከተ ባደረጉት ንግግር በርካቶች ማዘናቸውን ሰምቻለሁ"" ብለዋል። ""ጉዳዩ የማይመለከታችሁ እና በንግግሬ እንድትከፉ የሆናችሁ፣ የተማራችሁ እና በተማራችሁበት ዘርፍ አገራችሁን በቅንነት የምታገለግሉ፣ ውጤትም ያመጣችሁ ሰዎች ጉዳዩ እናንተን የማይመለከት ቢሆንም፤ ጉዳዩ እናንተን የማይመለከት መሆኑን በግልጽ ባለማስቀመጤ እናንተን ይቅርታ እጠይቃለሁ"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/51986050 +health ኮሮናቫይረስ፡ የአሜሪካውያን የኮቪድ-19 ክትባት ምርጫ ለምን የተለያየ ሆነ? "አሜሪካ ሦስት ክትባቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የፈቀደች ሲሆን ሰዎች የሚፈልጉትን እየመረጡ ነው። ሦስቱም የኮቪድ-19 ክትባቶች በቫይረሱ መያዝና ተይዞ ሆስፒታል መግባትን እንዲሁም ሞትን በመከላከል ረገድ ውጤታማ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ የጤና ባለሥልጣናት ለዜጎች የሚሰጠው የተሻለው ክትባት ነው ብለዋል። ቢሆንም ከጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ይልቅ ፋይዘር እና ሞደርና ክትባቶችን የሚመርጡ ብዙዎች ናቸው። በመጋቢት መጀመሪያ የዲትሮይት ከንቲባ ማይክ ዱጋን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባትን ውድቅ አድርገው በአሜሪካ የቀረቡት ሌሎች ሁለት ክትባቶች የተሻሉ መሆናቸውን ለከተማዋ ነዋሪዎች ጠቁመዋል። በጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት ""የዲትሮይት ከተማ ነዋሪዎች የተሻለውን እንዲያገኙ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ"" ብለዋል። የጤና ባለሙያዎች አስተያየት ከሰጡ በኋላ ከንቲባው ክትባቱ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ስለመሆኑ ""ሙሉ እምነት አለኝ"" በማለት ገልጸዋል። እንደ ዱጋን ሁሉ አንዳንድ አሜሪካውያን ስለ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት እና ስለ አጠቃላይ ውጤታማነቱ ጥያቄ አንስተዋል። የጤና ባለሥልጣናት ግን እነዚህ ቁጥሮች ሙሉውን ገጽታ እንደማያሳዩ አስጠንቅቀዋል። አንዳንዶች ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን ከመውሰድ ሳይከተቡ ቢዘገዩ እንደሚመርጡ ይናገራሉ። አንድ የዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ ለቢቢሲ ሲናገሩ ""የክትባት ቀጠሮ በነበረኝ ጊዜ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን እየሰጡ እንደሆነ ስለሰማሁ ሰርዤዋለሁ። ያንን ክትባት በጭራሽ አልወስድም"" ብለዋል። እንደ ዶ/ር ማይክል አንድራሲክ ያሉ የጤና ባለሥልጣናት ማንኛውንም ፈቃድ ያገኘ ክትባት መውሰድ ጥሩ መሆኑን አሜሪካውያንን ለማሳመን እየሞከሩ ነው። ""በአንድ በኩል ሰዎች ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ በጣም ተደስተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ውጤታማነቱን በተመለከተ ብዙ ግራ መጋባት አለ። ይህ ደግሞ ጥሩ አይደለም"" ሲሉ በፍሬድ ሃች የክትባትና ተላላፊ በሽታ ክፍል ከፍተኛ የሳይንስ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አንድራሲክ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአሜሪካ ተቆጣጣሪዎች አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠውን ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት በይፋ ያጸደቁት በየካቲት ነው። ይህም ፍቃድ ያገኘ የመጨረሻው ክትባት አድርጎታል። አዲስ የኤም አር ኤን ኤ ክትባት ቴክኖሎጂን ከሚጠቀሙት እና ሁለት ጊዜ ከሚሰጡት ከፋይዘር እና ከሞዴርና ክትባቶች በተለየ መልኩ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ጉዳት እንዳያደርስ የተደረገ ቫይረስን ይጠቀማል። ከዚያ የኮሮናቫይረስን ዘረ መል በከፊል ወደ ሰውነት ይወስዳል። ይህም ሰውነት አደጋውን ለይቶ እንዲያውቅ እና ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት እንዲዘጋጅ ያደርጋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በክትባቱ ላይ እምነት እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡ በዚህ ወር ለአሜሪካኖች ከቀረበው በእጥፍ 100 ሚሊዮን ተጨማሪ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባቶች እንደምታዝ አስታውቀዋል። የብሔራዊ አለርጂ እና ተላላፊ በሽታዎች ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ በበኩላቸው በአሜሪካ የሚገኙ ሁሉም ክትባቶች ጥሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባትም ""ደካማ ክትባት አይደለም"" ብለዋል። አሳሳቢው ነገር ከሙከራዎች የሚወጣው የውጤታማነት መረጃ መለያየት ነው። የጤና ባለሥልጣናት ሦስቱም ክትባቶች መቶ በመቶ ቫይረሱን የመከላከል አቅም አላቸው ሲሉ አሳስበዋል። የፋይዘር እና የሞደርና ክትባቶች አዳዲሶቹ የቫይረሱ ዝርያዎች ከመስፋፋታቸው በፊት የተሞከሩ ሲሆን አዳዲሶቹ ዝርያዎች በሙከራዎች ላይ ልዩነት ይፈጥራሉ። በተጨማሪም የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣ���ሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) ሁሉም ክትባቶች ከዓመታዊው የጉንፋን ክትባት የበለጠ ውጤታማ ናቸው ሲል ይገልጻል። እንደ ዶ/ር አንድራስክ ከሆነ ""ዋናው ነገር ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን፣ ሞደርና እና ፋይዘር ከባድ በሽታን በመከላከል፣ ሆስፒታል መተኛትን በመቀነስ፣ ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን በመቀነስ ወይም መሞትን በመከላከል በማይታመን ሁኔታ ውጤታማ ናቸው።"" የማኅበረሰብ ጤና ተሟጋቾች እንደሚሉት ከሆነ ሌላው የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ጠቃሚ ጎን በአሜሪካ ውስጥ ብቸኛው አንድ ጊዜ የሚሰጥ ክትባት መሆኑን ነው። ራቅ ወዳሉ እና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎችም ለማሰራጨት የበለጠ ምቹ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ያንን ክትባት ብቻ ወደ አካባቢዎቹ መላክ መገለልን ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አለ። አክለውም ""ሁሉም ክትባቶች ለሁሉም ሊደርሱ ይገባል ብዬ አስባለሁ። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን ወደ ገጠር እና ድሃ ማኅበረሰቦች የመላክ ምክንያታዊነት በእንክብካቤ ተደራሽነት ምክንያት ነው ብዬ አስባለሁ"" ብለዋል ዶ/ር አንድራስክ። እንደ ዶ/ር አንድራስክ ያሉ የማኅበረሰብ አመራሮች እና የጤና ባለሙያዎች በክትባቱ ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ለማስፋፋት እና የተሳሳተ መረጃን ለመከላከል ጥረት እያደረጉ ነው። በአሜሪካ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ ""የእኔ ተራ ሲደርስ ማንኛውንም ክትባት እወስዳለሁ"" ይላሉ። ሌሎቹ አሳሳቢ ጉዳዮችስ ምንድን ናቸው? ዩ ኤስ ኮንፈረንስ ኦፍ ካቶሊክ ቢሾፕስ የተባለው እና በአሜሪካ የሚገኘውን ቤተክርስትያን የሚወክለው ጉባኤ በክትባቱ ዙሪያ ""የሞራል ስጋት"" መኖሩን መግለጹ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። የስጋቱ ምንጭ ጽንስ በማስወረድ ከሚገኙ ሕዋሶች ክትባቱ ተመርቷል መባሉ ነው። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኢቦላ ክትባትን ለማዘጋጀት የዋለውን ተመሳሳይ ዘዴ ተጠቅሟል። በተጨማሪም የትኛውም የኮቪድ -19 ክትባት ምንም ዓይነት የሰው ህዋሳትን አልያዘም። ጉባኤው ምርጫ እስካለ ድረስ ካቶሊኮች አማራጭ ክትባቶች መውሰድ እንዳለባቸው መክሯል። በአሜሪካ ጉባኤ የተሰጠው ምክር ከቫቲካን አቋም ጋር የሚቃረን ይመስላል። ምክንያቱም ቫቲካን እንዲህ ያሉት ክትባቶች ""ከሞራል አንጻር ተቀባይነት አላቸው"" ስለምትል ነው። ሌሎች የካቶሊክ መሪዎችም የቤተክርስቲያኗ አባላት ከዚህ ክትባት መራቅ አለባቸው የሚለውን ሐሳብ እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል። የሐርትፎርድ ሊቀ ጳጳስ እና ሌሎች የአካባቢው የሐይማኖት አባቶች በሰጡት መግለጫ ሁሉም ነዋሪዎች ለራሳቸው ጤና እና ለጋራ ጥቅም ሲሉ ""ማንኛውንም ክትባት ለመቀበል የህሊና ነፃነት ሊሰማቸው ይገባል"" ሲሉ ተናግረዋል። እንደ ዶሮ በሽታ እና ሩቤላ ያሉ ሌሎች ብዙ ክትባቶች በተመሳሳይ መልኩ የተሠሩ ቢሆንም የካቶሊክ መሪዎች ስለ ለጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ያሰሙት ስጋት በአንዳንድ አሜሪካውያን ዘንድ ጥርጣሬ እንዲጨምር አድርጓል። ስጋቶችን የሚጋፈጠው የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ብቻ አይደለም። አሜሪካ ጥቅም ላይ እንዲውል ለመፍቀድ እየተዘጋጀችበት የሚገኘው የኦክስፎርድ-አስትራዛኔካ ክትባት ከደም መርጋት ችግር ጋር በተያያዘ የአውሮፓ አገራት ታግዶ ነበር። የአውሮፓ ሕብረት የመድኃኒት ተቆጣጣሪ ባሥልጣን ክትባቱ ""ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ነው"" ብሎ መግለጹን ተከትሎ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን እና ስፔን ክትባቱን መጠቀም መጀመራቸውን ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56498267 +business ዩናይትድ ኪንግደም ለታዳጊ አገራት ምርቶች የቀረጥ ቅነሳ ልታደርግ ነው "ዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ግንኙነቷን ለማሳደግ ከታዳጊ አገራት ከምታስገባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ምርቶች ላይ ቀረጥ ልትቀንስ ነው። ይህ ለታዳጊ አገራት የታሰበው የንግድ ዕቅድ በጥር ወር ተግባራዊ ይሆናል። ይህም ዩናይትድ ኪንግደም የአውሮፓ ኅብረት አባል በነበረችበት ጊዜ በነበረው ዕቅድ ላይ ይመሠረታል ተብሏል። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በስፋት የማይመረቱ እንደ ልብስ፣ ጫማ እና ምግቦች ያሉ ዕቃዎች ዝቅተኛ ወይም ዜሮ ታሪፍ ይጣልባቸዋል። ዕቅዱ 65 ታዳጊ አገራትን ያጠቃልላል ተብሏል። ዕቅዱ በማደግ ላይ ያሉ አገራት ያለ ታሪፍ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ከሚልኳቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ምርቶች በተጨማሪ ሲሆን፣ ከአፍሪካ ወደ አገሪቱ የሚገቡ 99 በመቶ ሸቀጦችን የሚመለከት ነው። የዓለም አቀፍ ንግድ ቢሮ እንደገለጸው ዕቅዱ ንግድን “ዕድገት ለማስመዝገብ እና ድህነትን ለማጥፋት"" እንዲሁም የእርዳታ ጥገኝነትን ለመቀነስ ዩናይትድ ኪንግደም የምታደርገው ጥረት አካል ነው። ዕቅዱ አገራት በሰብዓዊ መብት፣ በጉልበት ብዝበዛ ወይም በአየር ንብረት ለውጥ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ምክንያት የማገድ ሥልጣንን ያካትታል። የዓለም አቀፍ ንግድ ኃላፊ የሆኑት አን-ማሪ ትሬቬሊያን እንዳሉት ""የንግድ ፖሊሲያችንን እንደገና እየተቆጣጠርን የዩናይትድ ኪንግደም ንግዶችን የሚደግፉ ውሳኔዎችን ከመውሰድ ባለፈ በኑሮ ውድነት እና የታዳጊ አገራትን ኢኮኖሚ ​​ይደግፋል።"" ከ65 ድሃ አገራት ከጨርቃ ጨርቅ እስከ ፍራፍሬ የሚደርሱ ምርቶች በዩናይትድ ኪንግደም ሲሸጡ፣ የአነስተኛ ወይም የዜሮ ታሪፍ ተጠቃሚ ይሆናሉ። ይህም ይበልጥ ተፎካካሪ ያደርጋቸዋል። አዲሱ ዕቅድ የተወሰኑትን ተጨማሪ ክፍያዎችም ይቀንሳል ተብሎም ይጠበቃል። ለውጦቹ አስመጪዎችን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ፓውንድ እንዲያድኑ ያግዛሉ። ሆኖም ሙሉ በሙሉ ቢተገበር እንኳን ለተጠቃሚዎች የሚደርሰው የዋጋ ቅናሽ አነስተኛ ሊሆን ይችላል። ለታዳጊ አገራት የሚሰጠው ዕርዳታን በመቀነሱ በምትኩ መንግሥት በንግድ የመደገፍ ፖሊሲ እንዳለው ያሳያል ተብሏል። ከወቅቶች መለዋወጥ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ምርቶች ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ መመረት በማይችሉበት ወቅት በምርቶቹ ላይ የሚጣለው አነስተኛ ታሪፍም ይነሳል። አንዳንድ ደንቦችም ቀላል ይሆናሉ፤ ለምሳሌ አንድ ምርት አብዛኛውን ግብዓቶቹን ከየት ነው የሚያገኘው በሚል የምርቱን መነሻ አገር የመወሰን ጉዳይም አንዱ ነው። በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ የተሰማራው የባንግላዲሹ የዲቢኤል ግሩፕ ሥራ አስኪያጅ መሐመድ ጃባር ዕቅዱ ለድርጅታቸው ""ትልቅ ለውጥ"" መሆኑን ጠቅሰዋል። “በለውጦቹ ምክንያት ጥጥ ቀድም ሲል ከምናገኝባቸው አገራት በተጨማሪ ከሌሎችም በርካታ አገራት ማግኘት እንችላለን ማለት ነው። ይህም ንግዱን የበለጠ ተወዳዳሪ እና የአቅርቦት ሰንሰለቶቻችንን በጣም ጠንካራ ያደርገዋል” ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/crg7pp8x210o +politics የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስልጣን አስረከበ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አዲስ ለተመሰረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዛሬው ዕለት ስልጣን አስረክቧል። ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 24፣ 2014 ዓ.ም በስድስተኛው ዙር 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው የስልጣን ርክክቡን አዲስ ከተቋቋመው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋር ያደረገው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል በመሆን በፌዴሬሽን ምክር ቤት እውቅናን ያገኘው በባለፈው ሳምንት መስከረም 20፣ 2014 ዓ.ም ነው። 11ኛውን ክልል ያቋቋሙት የምዕራብ ኦሞ ፣ የቤንች ሸኮ፣ የከፋ ፣ የዳውሮ ፣ የሸካ ዞኖችና የኮንታ ልዩ ወረ��� አፈ ጉባኤዎችም በስልጣን ርክክቡ ወቅትም ተገኝተው ነበር። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በምክር ቤቱ ተገኝተው ባደረጉትም ንግግር የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመሆን ጥያቄ ሂደት ዲሞክራሲያዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መካሄድ እንዲችል ክልላቸው ሲሰራ መቆየቱን መናገራቸውም ተዘግቧል። ርእሰ መስተዳድሩ አዲስ የተቋቋመው ክልል በፍጥነት አዲሱ ክልል በፍጥነት ወደ መሬት እንዲወርድ ለማድረግ በትኩረት መሰራት እንዳለበትና ከፋይናንስ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በኮሚቴ የሚታይና ለመንግስት የሚቀርብ መሆኑንም አስረድተዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እንዲመሠረት በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ላይ ድምጽ ለመስጠት ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመዝግበው ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ድምጽ መስጠታቸው ይታወሳል። በምርጫው ከተሳተፉት መካከልም አምስቱ ዞኖች እና አንዱ ልዩ ወረዳ ከደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰብ እና ሕዝቦች ክልል ሥር ወጥተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በመባል መዋቀራቸውን በመደገፍ 1 ሚሊዮን 221 ሺህ 92 ሰዎች ድምጽ ሰጥተዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-59151038 +business መዳብ ተብሎ ድንጋይ የተሸጠለት ድርጅት 36 ሚሊዮን ዶላር ተጭበረበረ "ባለፈው የፈረንጆች ዓመት 36 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት መዳብ ከቱርክ ኩባንያ የገዛው ድርጅት ቀለም የተቀባ ድንጋይ እንደደረሰው አስታወቀ። አንድ የሸቀጣ ሸቀጥ ነጋዴ በ36 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት የገዛውን መዳብ፤ አቅራቢ ኩባንያው ቀለም በተቀቡ ድንጋዮች ቀይሮ እንዳስረከበው ገልጿል። መቀመጫውን ጄኔቫ ያደረገው ሜርኩሪያ ኢነርጂ ግሩፕ 10,000 ቶን የመዳብ ግዢ መፈጸሙን ተከትሎ በጭነት ማጓጓዝ (ካርጎ) ወቅት ተጭበርብሬያለሁ ብሏል። ጭነቶቹ ቻይና ሲደርሱ በመዳቡ ምትክ ቀለም በተቀቡ ድንጋዮች የተሞሉ ኮንቴይነሮችን ሆነው ተገኝተዋል። የደኅንነት እና የፍተሻ ቁጥጥሮች ቢከናወኑም መጭበርበሩ መፈጸሙ ተነግሯል። ባለፈው ዓመት ሜርኩሪያ መዳረሻው ቻይና እንዲሆን ያቀደውን መዳብ ለመግዛት ተስማምቶ ከ300 በላይ ኮንቴይነሮች ውስጥ 6,000 ቶን ያህል መዳብ በስምንት መርከቦች ተጭነውለታል። ኢስታንቡል አቅራቢያ ከሚገኘው ወደብ ጭነቱ መጓጓዝ ከመጀመሩ በፊት፣ በከፊል የተጣራውን መዳብ በሚመስሉ ቀለም በተቀቡ የተጠረቡ ድንጋዮች ተቀይሯል። በዓለም ላይ ካሉ አምስት ታላላቅ የነዳጅ ነጋዴዎች አንዱ የሆነው ሜርኩሪያ በመዳብ አቅራቢው በቢኤትሳን ባኪር ላይ በቱርክ እና በእንግሊዝ ፍርድ ቤቶች ፍትህ ለማግኘት እየጣረ ነው። የቱርክ ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር የሚያያዙ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል። ኩባንያው በመግለጫው ላይ ""በዚህ የተደራጀ ወንጀል ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል"" ካለ በኋላ ኢስታንቡል የፋይናንስ ወንጀሎች መምሪያን አመስግኗል። ቁልፎች ተሰብረዋል በአጣሪ ኩባንያ ምርመራ ከመካሄዱ በፊት መዳቦቹ ወደ መጀመሪያዎቹ ኮንቴነሮች የተጫኑ ይመስላል። ማጭበርበርን ለመከላከል ጥቅም ላይ የዋሉ ማህተሞች በዕቃዎቹ ላይ ተደርገዋል። ነገር ግን ኮንቴነሮቹ ተከፍተው መዳቦቹ በድንጋዮች ተተክተዋል ሲል የኢስታንቡል የሕግ ኩባንያ ኬዋይቢ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግሯል። አጭበርባሪዎቹ እንዳይታወቅባቸው እውነተኛዎቹን ማህተሞች በሐሰተኞቹ ቀይረዋል። መርከቦቹ በባሕር ላይ በነበሩት ወቅት ለአምስት ጭነቶች ሜርኩሪያ ከ36 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከፍሏል። መርከቦቹ በዚያው ወር መጨረሻ በቻይናው ሊያንጉንግ ወደብ እስኪደርሱ ድረስ መጭበርበሩ አልታወቀም። ""ገዢው በሻጩና በሁለት ተባባሪዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድ አቤቱታ አቅርቧ��� ድርጊቱ በተደራጀ መንገድ የተከናወነ የማጭበርበር ውጤት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል"" ብሏል የቱርክ ፖሊስ በሰጠው መግለጫ። አንድ ነጋዴ የገዛቸው ንብረቶች ካልደረሱት በጭነት ኢንሹራንሱ ፖሊሲ መሠረት ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል። የቱርኩ ኩባንያ ከሰባት ስምምነቶች በአንዱ ብቻ ጭነቱን ለመካስ የሚውል እውነተኛ ኢንሹራንስ እንደሚገባ ሜርኩሪያ ደርሶበታል። የተቀረው በሙሉ የተጭበረበረ ነበር። ሮይተርስ ለሜርኩሪያ መዳቡን የሸጠውን የቱርክ ኩባንያ ቢኤትሳን ባኪርን ለማነጋገር ቢሞክርም ምላሽ አላገኘም። በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ችሎቶች በዚህ ሳምንት ይሰማሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-56343133 +politics ምርጫ ቦርድ ‘ኢሠፓ’ በሚል ስም የቀረበውን የፓርቲ ምዝገባ ጥያቄ ውድቅ አደረገ "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ)” በሚል ስያሜ የቀረበውን የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ምዝገባ ጥያቄን ውድቅ አደረገ። ከ30 ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ብቸኛው ገዢ ፓርቲ የነበረው ኢሠፓ፣ ሕገወጥ ተብሎ ከአገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ከተገለለ በኋላ በስሙ ለመደራጀት ጥያቄ የቀረበው ባለፈው ግንቦት ወር ነበር። ቦርዱ የኢ.ሕ.ድ.ሪ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ከመሠረቱ ፓርቲ ጋር በተመሳሳይ ስም ለመመዝገብ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገባቸውን ሕጋዊ ምክንያቶች ዘርዝሯል። ቦርዱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ መሠረት ለምዝባ ጥያቄ የቀረበበት የፓርቲ ስያሜ ቀድሞ ሕጋዊ ሰውነት ከነበረው ፓርቲ ስያሜ ጋር በመመሳሰል፣ በመራጮች ዘንድ ግርታን የሚፈጥር ሆኖ ከተገኘ ቦርዱ ሊቀበለው አይገባም ብሏል። ከዚህ በተጨማሪ ከደርግ ከሥልጣን መወገድ በኋላ የወጣው እና ያልተሻረው ‘ሰላማዊ ሰልፍ እና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት አዋጅ’ ኢሠፓ የተባለው ድርጅት ፀረ-ዲሞክራሲ እና ወንጀለኛ ደርጅት ነው በሚል በሕግ አፍርሶታል ብሏል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምዝገባ ጥያቄ የቀረበበት የፓርቲ ስያሜ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ከነበረ ፓርቲ ጋር ብቻ ሳይሆን የተመሳሰለው፣ ""አሁንም ጸንቶ ባለ ሕግ ወንጀለኛ ተብሎ ከተፈረጀ እና ከፈረሰ ድርጅት ጋር ጭምር ነው"" ብሏል ቦርዱ በደብዳቤው። ቦርዱ በዚህ ስያሜ የቀረበለትን የፓርቲ ምዝገባ ጥያቄ ቢቀበል ያልተሻረ ሕግን እንደተሻረ፤ እንዲሁም የፈረሰ ድርጅት ገደቡ ተላልፎ እንደገና እንደተቋቋመ የሚመስል ግንዛቤን የሚፈጥር በመሆኑ እንዳልተቀበለው ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም የስሙ መመሳሰል በምርጫ ወቅት ምራጮችን ሊያምታት ስለሚችል ቦርዱ በመቋቋሚያ በአዋጁ ቁጥር መሠረት “የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ)” በሚል ስያሜ የቀረበለትን የፓርቲ ምዝገባ ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል። በቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ተፈርሞ የቦርዱን ውሳኔ በተላለፈበት ደብዳቤ ላይ፤ አስተባባሪዎቹ በሌላ ስያሜ ፓርቲ አቋቋመው የመደራጀት እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ የማድረግ መብታቸው የተጠበቀ መሆኑን አስታውሰዋል። ከንጉሣዊው ሥርዓት መውደቅ በኋላ በወታደሮች ቁጥጥር ስር የገባው የኢትዮጵያ መንግሥት በእርስ በርስ ጦርነት፣ በድረቅና  በከባድ የረሃብ አደጋ ስትናጥ የቆየችውን አገር ለ17 ዓመታት የመራው አስተዳደር በተለያዩ ቅርጾች መቆየቱ ይታወቃል። ንጉሡ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ከተለያዩ የአገሪቱ የጦር ክፍሎች የተዋቀረው ወታደራዊ ኮሚቴ ደርግ፣ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር መስርቶ ከቆየ በኋላ፣ ርዕዮት ዓለሙን ሶሻሊዝም በማድረግ ወደ መደበኛ መዋቅር ለመሸጋገር ዓመታት ወስዶበታል። በዚህም የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ አደራጅ ��ሚሽን (ኢሠፓአኮ) በማቋቋም ዝግጅት ሲያደርግ ከቆ በኋላ፣ ከ10ኛው የአብዮት በዓል ጋር በተያያዘ በመስከረም 1977 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲን (ኢሠፓ) የአገሪቱ ብቸኛው ገዢ ፓርቲ ሆኖ ተመስርቶ ነበር። ፓርቲው አሁን በስደት ላይ በሚገኙት በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም የሚመራ የነበረ ሲሆን፣ በመላው አገሪቱ ሰፊ መዋቅር ዘርግቶ አገሪቱን ሲመራ ቆይቷል። ነገር ግን ይህ ፓርቲ ከተመሰረተ ከአምስት ዓመት በላይ በሥልጣን ላይ ሳይቆይ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ለዓመታት የዘለቀውን የትጥቅ እንቅስቃሴ ሲያካሄዱ የነበሩት የኤርትራ ነጻነት ግንባር እና ህወሓት በጦር ሜዳው የበላይነት አግኝተው ፓርቲውን ከሥልጣን አስወግደውታል። ይህንንም ተከትሎ በ17 ዓመቱ የደርግ የሥልጣን ዘመን በተፈጸሙት የመብት ጥሰቶች ምክንያት ኢሠፓ ሕገ-ወጥ ፓርቲ ተብሎ፣ አባላት እና አመራሮቹ ለዓመታት በእስር ቆይተዋል። አብዛኞቹ የፓርቲው አመራሮችም በእድሜ እና በተለያዩ ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለያዩ ሲሆን፣ ጥቂት የማይባሉት ደግሞ ከ20 ዓመታት እስር በኋላ ነጻ ወጥተው በኢትዮጵያና በተለያዩ አገራት ይገኛሉ። ከጥቂት ወራት በፊትም አስካሁን ማንነታቸው ይፋ ያልወጣ ግለሰቦች ተሰባስበው ከሦስት አስርት ዓመት በኋላ፣ በኢሠፓ ስም አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረባቸው በአውንታዊ እንዲሁም በአሉታዊ መልኩ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። እስካሁም ድረስ ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት ግለሰቦች የቀድሞ የፓርቲው አባላት እና አመራሮች መሆን አለመሆናቸው በይፋ የታወቀ ነገር የለም።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cg656qpdgypo +politics የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት ከግድያ ሙከራ ለጥቂት አመለጡ "የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት ክርስቲና ፈርናንዴዝ ዴ ኪርችነር ትላንት ሃሙስ ምሽት ከግድያ ሙከራ ለጥቂት አመለጡ። ምክትል ፕሬዝዳንቷ በጥይት ከመመታት የዳኑት የተኳሹ መሳሪያ በመንከሱ ነው ተብሏል። ዴ ኪርችነር ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ሰላምታ በመስጠት ላይ ሳሉ ነበር አንድ ግለሰብ ከሕዝቡ መካከል ወጥቶ ፊታቸው ላይ ሽጉጡን አነጣጥሮ ለመተኮስ የሞከረው። የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ ምክትል ፕሬዝዳንቷ ፊት ላይ ተነጣጥሮ የነበረው ጦር መሳሪያ አምስት ጥይቶች ጎርሶ የነበረው ቢሆንም ቃታው ሲሳብ ግን ሳይተኩስ ቀርቷል ብለዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቷ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ክሳቸውን በመከታተል ላይ ባሉበት በዚህ ወቅት ነው የግድያ ሙከራ የተፈጸመባቸው። የቀረበባቸውን ክስም ፖለቲካዊ አላማ የያዘ በሚል በተደጋጋሚ ውድቅ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ፖሊስ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የ35 አመቱ ብራዚላዊ ምክትል ፕሬዘዳንቷን ለመግደል በመሞከር በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል። ግለሰቡ ምክትል ፕሬዝዳንቷን ለመግደል ምን እንዳነሳሳው ለመረዳት ምርመራ እየተደረገ እንደሆነም ተገልጿል። ትላንት ምሽት ንግግር ያደረጉት ፕሬዘዳንት ፈርናንዴዝ ጥቃቱን ያወገዙ ሲሆን በምክትላቸው ላይ የተደረገው የግድያ ሙከራ አርጀንቲና እእአ በ1983 ወደ ዲሞክራሲ ስርዓት ከተመለሰች ወዲህ ካጋጠሙ ""እጅግ አሳሳቢ"" ክስተቶች መካከል አንዱ ነው ብለዋል። ‘’ከምክትል ፕሬዘዳንቷ ጋር አለመስማማት እና ልዩነቶች ሊኖሩን ይችላሉ። ነገር ግን የጥላቻ ንግግሮች ሁከትን ይወልዳሉ። አመጽ እና ዴሞክራሲ ደግሞ አብረው የመሄድ እድል የላቸውም"" ሲሉ ፕረዘዳንት ፈርናንዴዝ ተናግረዋል። ፕሬዘዳንቱ አክለውም አርብ ቀን ብሔራዊ በዓል ሆኖ እንዲውል እና አርጀንቲናዊያን በሕይወት የመኖር መብትን በመደገፍ ብሎም ምክትል ፕሬዝዳንቷ ላይ የተቃጣውን ጥቃት የሚያወግዙበት ቀን እንዲሆን አውጀዋል። በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጩ ምስሎች እንደሚያሳዩት ተጠርጣሪው ወደ ግለሰቧ ጭንቅላት ሽጉጡን በማነጣጠር ለመተኮስ ሲሞክር ይታያል። ከዚያም ምክትል ፕሬዘዳንቷ ጎንበስ ብለው ወደ ታች ሲመለከቱ ይታያል። ነገር ግን ምንም ጥይት አልተተኮሰም። እ.ኤ.አ. ከ2007 እስከ 2015 መካከል ፕሬዝዳንት የነበሩት ዴ ኪርቸነር በስልጣን ዘመናቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በተጭበረበሩ ጨረታዎች አሸናፊዎችን በመምረጥ ክስ ቀርቦባቸዋል። አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ መሰረት ጥፋተኛ የሚባሉ ከሆነ የ12 አመት እስራት እና እድሜ ልክ ከፖለቲካ የመታገድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ሆኖም ዴ ኪርችነር የፓርላማው ጸሃፊ እና አባል በመሆናቸው ምክንያት ያለመከሰስ መብት አላቸው። እንዲሁም ቅጣት ቢጣልባቸው እንኳን በአገሪቱ ህግ መሰረት ቅጣቱ በሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ካልፀደቀ ወይም ከአንድ አመት ተኩል በኋላ በሚደረገው ምርጫ የሴኔት መቀመጫቸውን ካላጡ በስተቀር አይታሰሩም።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1lk573xk7o +business ክሪፕቶከረንሲዎች ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተጋለጡ የግብይት ባለሙያዎች አስጠነቀቁ ክሪፕቶከረንሲን ጨምሮ ሌሎችም የበይነ መረብ ገንዘብ ማዘዋወሪያዎች አደጋ እንዳንዣበበባቸው የሆንግ ኮንግን የግብይት ተንታኞች ማስጠንቀቂያ ሰጡ። “ኢንቨስተሮች ከፍተኛ አደጋ ማንዣበቡን ይገንዘቡ” ሲል 'ሴኪውሪቲስ ኤንድ ፊውቸርስ' ኮሚሽን የተባለው የባለሙያዎች ማኅበር አሳውቋል። ማስጠንቀቂያውን የተሰጠው የክሪፕቶከረንሲ ገበያ በውዝግብ በተሞላበት ጊዜ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኤፍቲኤክስ ክሪፕቶከረንሲ መሥራች ሳም ባንክማን-ፍሬድ በዚህ ሳምንት ታስሮ ክስ ተመሥርቶበታል። “አንዳንድ የበይነ መረብ ሀብት ማከማቻዎች [virtual asset] በመርኅ አይመሩም። እንደ ባንክ ተቀማጭ ሒሳብም አይወሰዱም። ስለዚህ ኢንቨስተሮች ለገንዘባቸው ከለላ የላቸውም” ሲሉ ባለሙያዎቹ አስጠንቅቀዋል። “ኢንቨስተሮች እነዚህን አሠራሮች የማይረዷቸው ከሆነ ኪሳራ ሊገጥማቸው ስለሚችል ኢንቨስት እንዲያደርጉ አይመከርም” ሲሉም አክለዋል። የኤፍቲኤክስ ክሪፕቶከረንሲ መሥራች ሳም ባንክማን-ፍሬድ ባህማስ ውስጥ በተያዘ በሰዓታት ውስጥ የአሜሪካ አመራሮች በአገሪቱ ታሪክ “ከፍተኛው የፋይናንስ ማጭበርበር” ክስ መስርተውበታል። የሆንግ ኮንጉ ማኅበር ሊቀ መንበር ጌሪ ጊንስለር “ሳም በማጭበርበር ነው ቢዝነሱን ያዳበረው” ብለዋል። ሳም በዋስ ለመለቀቅ ቢጠይቅም አልተፈቀደለትም። የኤፍቲኤክስ ክሪፕቶከረንሲ ተፎካካሪ የሆነው ቢናንስ፣ ለተወሰነ ጊዜ መቋረጡን ተከትሎ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በክሪፕቶከረንሲው ኢንቨስት ተደርጎ የነበረ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ተነስቷል። የብሎክቼይን መረጃ ተቋም የሆነው ናንሳን እንደሚለው፣ የዓለም ትልቁ ክሪፕቶከረንሲ 1.9 ቢሊዮን ዶላር ተቀንሶበታል። የቢናንስ ዋና ኃላፊ ቻንፔንግ ዛሆ ግን የተቀነሰው ገንዘብ ወደ 1.4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ነው ብሏል። “አንዳንድ ቀን ገንዘብ ይቀነሳል (ወጪ ይደረጋል)። በሌላ ቀን ደግሞ ገንዘብ ይጨመራል (ገቢ ይደረጋል)። ይሄ የተለመደ የንግድ አካሄድ ነው” ሲል አክሏል። የበይነ መረብ ገንዘቡ ክሪፕቶከረንሲ በተለዋዋጭ የገቢ ሁኔታ ዋጋው ከፍና ዝቅ ሲል ቆይቷል። ትልቁ ክሪፕቶከረንሲ የሆነው ቢትኮይን ዘንድሮ 60 በመቶ ኪሳራ ገጥሞታል። ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎችም ገቢያቸው አሽቆልቁሏል። የገንዘብ ምንጭና ገንዘቡ የሚቀመጥበት ቦታ አለመታወቅ እንዲሁም ከመንግሥታት ቁጥጥር ውጪ መሆኑ፣ እንደ አደንዛዥ እጽ እና እገታ ያሉ ወንጀሎችን ያበረታታል የሚል ስ���ት ይደመጣል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c72nyeppxm0o +health ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ ኮርያ የኮቪድ-19 ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ሕጓን አጠበቀች "በደቡብ ኮርያ ዋና ከተማ የኮቪድ-19 ስርጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ሙዚየሞች፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ እንዲሁም መጠጥ ቤቶች ተዘግተዋል። ማክሰኞ ዕለት የቫይረሱ ስርጭት ለአምስተኛ ቀን ወደ ሶስት ዲጂት ከፍ ያለ ሲሆን በአብዛኛው እድሜያቸው በ40ዎቹ ውስጥ የሆኑ ሰዎች መጠቃታቸው ታውቋል። ደቡብ ኮርያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በፍጥነት በመቆጣጠር ስሟ በተደጋጋሚ ሲነሳ ነበር። ነገር ግን ከቤተ እምነቶች ጋር በተያያዘ የተቀሰቀሰው ዳግም ወረርሽኝ ስጋትን አጭሯል። ደቡብ ኮርያ ማክሰኞ ዕለት 246 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን በምርመራ ስታረጋግጥ በአገሪቷ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 15,761 ደርሷል። አብዛኛዎቹ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ግለሰቦች በሳራንግ ዤይል ቤተ ክርስትያን ጋር የሚገናኙ ሲሆን፣ የቤተ እምነቷ ፓስተር የፕሬዝዳንት ሙን ዤ-ኢን ቀንደኛ አብጠልጣይ ናቸው። ይህ በደቡብ ኮርያ የተከሰተው አዲስ ወረርሽኝ በሌላ እምነት ስፍራም ይዛመታል የሚል ፍራቻ ቀስቅሷል። በደቡብ ኮርያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱ ሲታወቅ መነሻው የነበረው ሺንቼዮንጂ ቸርች ኦፍ ጂሰስ ነበር። ከዚህ ቤተ እምነት ጋር ግንኙነት ያላቸው 5,200 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው መገኘታቸው ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ 457 ከሳራንግ ዤይል ቤተክርስትያን ጋር ይያያዛል ተብሏል። ከእነዚህ መካከል አስር ግለሰቦች ባለፉት ሁለት ሳምንታት በዋና ከተማዋ ሶል በተደረገ መንግሥትን በሚቃወም ሰልፍ ላይ ተሳትፈው እንደነበር ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። የደቡብ ኮርያ ባለሥልጣታናት ማንኛውም ቤተ እምነት የአምልኮ ስርዓቱን በቤተ እምነቶች ውስጥ እንዳያካሂድ ያገዱ ሲሆን የቫይረሱ ስርጭት ታይቶባቸዋል የተባሉ ቤተ እምነቶችን ምዕመናን፣ ራሳቸውን ለይተው እንዲቀመጡ እና ምርመራ እንዲያደርጉ የመለየት ስራ እየሰሩ ነው። ""አሁን ያለው ስርጭትን መቆጣጠር ካልቻልን ቀውስ ውስጥ እየገባን ነው፣ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ያደርጋል፣ ይህ ደግሞ ህክምና ስርዓታችን እንዲንኮታኮትና ከፍተኛ የሆነ የምጣኔ ሃብት ድቀት እንዲደርስ ያደርጋል"" ብለዋል የኮሪያ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ድርጅት ዳይሬክተር ዢዮንግ ኢኡን ኬኦንግ። ከዛሬ ረብዑ ጀምሮም 12 ለአደጋ ተጋላጭ የተባሉ የንግድ ዘርፎች በዋና ከተማዋ ሶል፣ ኢንቺዮን እና በተጎራባች የጊዮንጊ ግዛት እንዲዘጉ ተወስኗል፤ ከእነዚህም መካከል ፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች፣ አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ሙዚየሞችም የተዘጉ ሲሆን በቤት ውስጥ ከ50 ሰው በላይ፣ ከቤት ውጪ ደግሞ ከ100 ሰው በላይ ሆኖ መሰብሰብ ታግዷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53831241 +health ኮሮናቫይረስ፡ 33 ሚሊዮን ፓውንድ ያሰባሰቡት የ100 አመቱ ሽማግሌ በኮቪድ-19 ሞቱ "በእንግሊዝ ለጤና ባለሙያዎች ያላቸውን ክብር ለመቸር 33 ሚሊዮን ፓውንድ በማሰባሰብ ከፍተኛ ስም ያተረፉት ካፕቴን ቶም ሙር በመቶ አመታቸው በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አልፏል። 33 ሚሊዮን ፓውንድ ለአገሪቱ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት ወይም ኤንኤችኤስ ማሰባሰብ የቻሉት የ100 አመቱ የዕድሜ ባለፀጋ በባለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ከመተንፈሻ እክል ጋር በተያያዘ ቤድፎርድ ወደተባለ ሆስፒታል ተወስደው ነበር። ልጃቸው፣ ሃና ኢንግራም ሙር በባለፉት ሳምንታት በሳንባ ምች ህመም ሲሰቃዩ እንደነበርና በዚህ ሳምንት በኮሮናቫይረስ እንደተያዙ ተናግራለች። ግለሰቡ የ2ኛው የዓለም ጦርነት ተዋጊ ሲሆ��� ከቤታቸው ጓሮ በሚገኘው ሜዳ 100 ዙር በመሮጥም ነው የእርዳታ ገንዘብ ያሰባሰቡት። ይህንንም ያደረጉት ከመቶኛ አመት ልደታቸው በፊት ነው። ልጆቻቸው ሃና ኢንግራም ሙርና ሉሲ ቲየክሴራ እንዳሉት ""ውድ አባታችን ካፕቴን ሰር ቶም ሙር መሞታቸውን በታላቅ ሃዘን ነው የምንናገረው"" ብለዋል። በመጨረሻው ሰዓትም ከአባታቸው ጎን በመሆናቸው ትልቅ ክብር እንደነበር ገልፀዋል። ""ለሰዓታት ያልህ ስለ ልጅነታችን፣ ስለ ውዷ እናታችን ስናወራ ነበር። ረዥም ሰዓት ሳቅን፣ አለቀስን። አባታችን በባለፈው አመት አስቦትና አልሞት የማያውቀው ነገር ተሳክቶለታል። ""ብለዋል አክለውም ""ምንም እንኳን ለአጭር ወቅት ቢሆን በብዙዎች ልቦና ዘንድ የማይረሳ ነገርን ጥሏል። ለኛ አስደናቂ አባት፣ አያት ነው፤ ሁልጊዜም ቢሆን በልባችን ይኖራል"" በማለት ኃዘናቸውን አጋርተዋል። የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ለአባታቸው ያደረጉላቸውን እንክብካቤ አድንቀዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55909539 +health ኖርዌይ ፡ በአንድ ዋሻ ውስጥ ሲዝናኑ የነበሩ ሰዎች በጭስ ታፍነው ሆስፒታል ገቡ "በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ውስጥ በሚገኝ በአንድ ከመሬት በታች ባለ ዋሻ ውስጥ ተሰባስበው እየተዝናኑ ከነበሩ ሰዎች መካከል ከ20 የሚበልጡት በካርበን ሞኖክሳይድ ጭስ ታፍነው በመመረዛቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ። ግለሰቦቹ ሊገኙ የቻሉት በአካባቢው ቅኝት ሲያደርጉ የነበሩ ፖሊሶች በዋሻው ውስጥ ከነበሩት መካከል የተወሰኑት ራሳቸውን ስተው ወደ ጎዳና በመውጣት ወዲያ ወዲህ ሲሉ ካገኟቸው በኋላ ነው። ከዚህም በኋላ ሌሎቹ ጓደኞቻቸው በጭሱ ታፍነው ከዋሻው ውስጥ በመውጣታቸው አምቡላንስ ተጠርቶ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ ተደርጓል። ባለስልጣናቱ የፓርቲው ታዳሚዎችን ለመመረዝ ያበቁት ወደ ዋሻው ይዘው ከገቡት አነስተኛ ጄኔሬተር በሚወጣ ጭስ ምክንያት ነው ብለው ያምናሉ። በጭሱ የመመረዝ ጉዳት ካጋጠማቸው 25 ሰዎች መካከል ሁለቱ በዋሻው ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ለማውጣት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ፖሊሶች ናቸው። ግለሰቦቹ አሁን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተም ""እድለኞች ናቸው፤ የሁሉም የጤና ሁኔታ እየተሻሻለ ነው። በጤናቸው ላይ ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም"" ሲሉ በኦስሎ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ዋና ሐኪም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ከ20 በላይ ሰዎች በጭስ በታፈኑበት በዚህ ዝግጅት ላይ 200 የሚደርሱ ሰዎች ታድመውበት እንደነበር የኦስሎ ፖሊስ አስታውቋል። በተጨማሪም ታምመው ወደ ሆስፒታል ከገቡት የፓርቲው ታዳሚዎች ውጪ ያሉት ማቅለሽለሽ፣ የራስ ምታት፣ ራስን የመሳት ስሜት ካጋጠማቸው ወደ ሐኪም ቤት እንዲሄዱ ፖሊስ መክሯል። ፖሊሶች በአደጋው ስፍራ ከመድረሳቸው በፊት ከዋሻው ወጥቶ የሄደ የዝግጅቱ ታዳሚ እንዳለው በስፍራው በነበረው የታፈነ አየር ምክንያት በተደጋጋሚ ወደ ውጪ እየወጣ አየር ሲወስድ ነበር። የኦስሎ ፖሊስ በዋሻው ውስጥ ስለተካሄደው ዝግጅት ቀድሞ ጥቆማ የደረሰው ቢሆንም በወቅቱ ለምን እርምጃ መውሰድ እንዳልቻለ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53967065 +business ከ20 ሺህ ብር በላይ የሚወጣበት የኢትዮጵያ ዘመናዊ የንቅሳት ገበያ "ሰውነታቸው ላይ ንቅሳት ለማሳረፍ ወደ ንቅሳት ቤቶች ጎራ ከሚሉ ሰዎች መካከል በፍቅር ወይም በትዳር የተጣመሩ ጥንዶች ይገኙበታል። ""ጥንዶቹ ፍቅራቸውን ለመግለጽ ሴቷ የወንዱን፣ ወንዱ ደግሞ የሴቷን ስም አሊያም የስም መጀመሪያ ፊደላትን መነቀስ የተለመደ ሆኗል"" ይላል የንቅሳት ባለሙያው (ታቱ አርቲስት) ሔኖክ ጥላሁን። ሆኖም በጥንዶቹ መካከል ንፋስ ገብቶ መራራቅ ሲመጣ ""ለየብቻ ይመጡና ንቅሳቱን ቀይርልኝ"" ብለው እንደሚጠይቁት ይናገራል። ይህን��� በመሰሉ አጋጣሚዎች የተሞላውን የንቅሳት ሥራ፤ ሰዎች ሐሳባቸውን ለማንጸባረቅ ያውሉታል። ዮሴፍ ተስፍዬ ይባላል። 28 ሺህ ብር አውጥቶ በሁለቱም እጆቹ ከትከሻው እስከ መዳፉ አንጓ 'የውስጤን ሐሳብ ይገልጹልኛል' ያላቸውን የተለያዩ ምስሎችና ጽሁፎች ተነቅሷል። ለእሱ የደስታ ምንጭ የሆነው ንቅሳቱ በተመልካቾች ዘንድ ሁለት ዓይነት አስተያየት ይቀርብበታል። አንዱ ""ምን ነካህ?"" ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ""ያምራል"" የሚል ነው ይላል። ነገር ግን በሚሠራበት አካባቢ ንቅሳቱ እንዳይታይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግም ይናገራል። ሳምራዊት ተስፋዬ እና ኤልኤዘር ሙሴም በተመሳሳይ መነሻ የተለያዩ የሰውነት ክፍላቸውን ተነቅሰዋል። ለመሆኑ በአዲስ አበባ ምን አይነት ንቅሳቶች ይዘወተራሉ? ምን ያህል ገንዘብስ ይወጣባቸዋል? የንቅሳቶች ይዘት እና ምክንያት የንቅሳት ባለሙያው ሔኖክ ጥላሁን ቀደም ሲል ሥዕሎችን ይስል እንደነበር ይናገራል። እንደ ባለሙያው ገለጻ ንቅሳትም አንድ የጥበብ ዘርፍ በመሆኑ 'ሄና ታቱ' የሚል ድርጅት በመክፈት ንቅሳትን መተዳዳሪያው ካደረገ ከስምንት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል። ንቅሳት የሚፈልጉ ሰዎች ከተዘጋጀ የንቅሳት ዝርዝር ውስጥ መርጠው ወይም የፈለጉትን ማንኛውንም አይነት ምስል አሊያም ጹሁፍን ወደ ንቅሳት መቀየር ይቻላል ይላል። በብዛት ወደ እሱ የሚመጡ ሰዎች ሰውነታቸው ላይ እንዲያርፍ የሚርጡት ይዘት ሐይማኖታዊ መሆኑን ይናገራል። በተጨማሪም ጥንዶች ፍቅራቸውን ለመግለጽ ተመሳሳይ ንቅሳት ወይም አንዱ የሌላውን ስም ይነቀሳሉ። የእናታቸውን ወይም የአባታቸውን ምስል ወይም ስም የተነቀሱ ደንበኞች እንዳሉት የሚጠቅሰው ሔኖክ፤ በሌላ በኩል መስቀል፣ የቅዱሳን ሥዕሎችና መሰል ሐይማኖታዊ ይዘቶች በብዛት እንደሚዘወተሩ ያስረዳል። ብዙዎች ንቅሳትን ""የሚወዱትን ነገር መግለጫና ማሳያ አድርገው ነው የሚያዩት"" ሲል ይጠቅሳል። ሳምራዊት የግራ እጇ ከክንዷ በታች ያለው ክፍል ሙሉ በሙሉ በንቅሳት የተሸፈነ ነው። ""ስለ ወደደኝ አዳነኝ"" እና ""Be Happy"" የሚሉ ጽሁፎች፣ ሳቅን የሚገልጽ የስሜት ነጸብራቅ ምስል (emoji)፣ አበባ እንዲሁም ሌሎች ምስሎች አሉ። ደረቷ ላይ ""blessed"" የሚል ጽሁፍና አንገቷ ላይ ደግሞ መስቀል ተነቅሳለች። ኤልዜር የደረቱ አብዛኛው ክፍል ንቅሳት ያረፈበት ሲሆን፤ የነብርና ንስር ምስሎችን ነው የተነቀሰው። ዮሴፍ ደግሞ ሰዓት፣ አበባ፣ ኮምፓስና መሰል ምስሎችን በቀይና ጥቁር ቀለሞች በእጆቹ ላይ ተነቅሷል። ሳምራዊት ለሐይማኖቷ ያላትን ፍቅር ለመግለጽና ውስጧ ያለውን የተለያየ ሰሜት ለማንጸባረቅ እንደተነቀሰች ትገልጻለች። ዮሴፍ እና ኤልኤዘር ውስጣቸው የሚያምንበትና የሚወዱት ሐሳብ ሰውነታቸው ላይ እንዲታይ በማለም ነው አካላቸውን በንቅሳት የሸፈኑት። በተለይ ኤልኤዘር ለቤተሰቦቹ ያለውን ፍቅር ለመግለጽ መነቀሱን ተናግሯል። እነ ሳምራዊት በጠቀሷቸው ምክንያቶች ይነቀሱ እንጂ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጠባሳን ለመሸፈን ወይም ባህላዊ ንቅሳቶችን ወደ ዘመነኛ ለመቀየር ወደ ንቅሳት ቤቶች የሚያመሩ ሰዎች እንዳሉም ሔኖክ ይገልጻል። የንቅሳት ገበያ ኤልኤዘር ንቅሳቱን በተለያየ ጊዜ ማድረጉን ያስረዳል። ለዚህም እስከ 20 ሺህ ብር አውጥቷል። ሳምራዊት ደግሞ 15 ሺህ ብር በመክፈል ነው ንቅሳቷን ያሠራችው። ዝቅተኛው የንቅሳት ርዝመት አምስት ወይም ስድስት ሴንቲ ሜትር እንደሚረዝምና 500 ብር እንደሚያስወጣ ሔኖክ ይገልጻል። ንቅሳቱ ከፍ እያለ ሲሄድ ዋጋ እንደሚጨምር እንዲሁም ጀርባ ላይ የሚሠሩ ንቅሳቶች በአንድ ጊዜ እንደማያልቁና እስከ ሦስት ቀናት ሊፈጁ እንደሚችሉ ተናግሯል። ይህም እስከ 15 ሺህ ብር የሚወጣበት ነው። ታዲያ ይህ ሥራ ዋና የገቢ ምንጬ ነው የሚለው ሔኖክ ""በየቀኑ ሥራ አለ"" ሲል አስረድቷል። ንቅሳት ለመሥራት የሚውሉ መሣሪያዎች ከዘመኑ ጋር እየተጓዙ ነው የሚለው የንቅሳት ባለሙያው፤ ግብዓቶችን አገር ውስጥ ማግኘት ግን ፈታኝ መሆኑን እና የንቅሳት መርፌ ሳይቀር ከውጪ አገራት እንደሚገባ ይገልጻል። ""ንቅሳት ላይ ከቴክኖሎጂው በላይ የአርቲስቱ ጉዳይ [የባለሙያው አቅም] ነው ትልቁ ነገር"" ሲልም ጨምሯል። የተመልካቾች አስተያየት እና ልዩ ገጠመኞች ዮሴፍ ንቅሳቴን ሲያዩ ""የሚያማትቡ አሉ"" ይላል። ኤልኤዘር ደግሞ ""አንዳንድ ሰው የሚያየኝ እንደ ዱርዬ ነው። ባንክ ስገባ አንዳንድ ሰዎች ቦርሳቸውን የሚደብቁበት ጊዜ አለ"" ሲል ገልጾታል። ""ሁሉም ሰው አንድ አይደለም። ወጣቶቹ ይወዱታል። 'በጣም ያምራል' ይላሉ። ሌላው ደግሞ 'ኔጌቲቭ' አስተያየት ነው የሚሰጠው። 'ለምን እንዲህ አደርግሽ?' 'በሐይማኖት አይፈቀድም' ይላሉ"" ያለችው ደግሞ ሳምራዊት ናት። የንቅሳት ባለሙያው ሔኖክም በሥራው ብዙ ነገሮች እንደሚገጥሙት ይገልጻል። ፍቅረኞች ወይም ባለትዳሮች ፍቅራቸውን 'ለማጠንከር' በማሰብ ለመነቀስ ወደኛ ይመጣሉ የሚለው ሔሄኖክ፤ ከተሠራላቸው በኋላ ግን ተመልሰው የሚመጡ እንዳሉ ጠቅሷል። ""ይመጡና ይሄን ነገር አልፈለኩትም። የዚያን ጊዜ በደንብ አላሰብኩበትም። ይሄን ነገር ማጥፋት እፈልጋለሁ ይላሉ። ያው ማጥፋት ከባድ ስለሆነ በሌላ ዲዛይን ይሸፈናል።"" በሌላ በኩል ፊታቸው ላይ ንቅሳት ለማሠራት መጥተው እድሜያቸው ትንሽ ከሆነ ""በኋላ እንዳይጸጽታቸው"" ብለን እንመክራለንም ብሏል። ""አንዳንዴ ሰዎች ንቅሳተቱን ሳይጨርሱ የሚሄዱበት አጋጣሚ አለ - አመመኝ በሚል"" ሲልም ተናግሯል። አንዱን አጋጣሚ ሲያስታውስ፤ አንድ ደንበኛው ""የቅዱስ ሚካኤልን ምስል ጀርባው ላይ ለመነቀስ መረጠ"" ይላል። እናም ንቅሳቱ ተጀመረ። ""ሥዕሉ መልአኩ ሰይጣኑን ሲረግጥ የሚያሳየው ነው። እኛ ከሥር እየሠራን ነው ወደ ላይ የምንሄደው። ሰይጣኑን ወደ ማገባደድ ደርሰን ወደ ላይ እየወጣን ስንሄድ 'በቃ አልቻልኩም ይቅርብኝ' አለ። ለመጨረስ በተከታታይ ብደውልለትም አልመጣም። እስካሁን ሰይጣኑን ይዞ ነው የሚዞረው"" ሲል ያስታውሳል። ንቅሳቱ ሲሠራ በሚፈጠረው ህመም ምክንያት ንቅሳት ጀምረው ከሚያቋርጡ በተቃራኒው የንቅሳቱ መሣሪያ በሚፈጥው መጠነኛ ህመም 'እንደሚደሰት' ዮሴፍ አስረድቷል። ኤልኤዘር ደግሞ ""አንድ ጊዜ ፀበል ለጠመቅ ሄጄ ቄሱ አልጠምቅህም ብለውኝ ነበር [ንቅሳቱን አይተው]"" ብሏል። በሌላ በኩል ዮሴፍ ""ሰዎች እንደ ቁም ነገረኛ ስለማይቆጥሩኝ፤ ሥራ ቦታ 'ታቱ' እንዳለኝ የማያውቅ ብዙ ሰው አለ"" ሲል ገልጿል። ሳምራዊት በመነቀሷ ከቤተሰቧ አሉታዊ አስተያየት እንዳልገጠማትና እንዲያውም ስትነቀስ 15 ሺህ ብሩን ቤተሰቧ እንደከፈለላት ስትናገር፤ ከዚህ በተቃራኒ ኤልኤዘርና ዮሴፍ ቤተሰቦቻቸው ብዙም በአወንታዊ መንገድ አልተቀበሏቸውም። ንቅሳት እና ጤና የቆዳና የአባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ሐኪሙ ዶክተር ድጋፌ ጸጋዬ ""ዘመናዊም ይሁን ባህላዊ ንቅሳት ሹል በሆኑ ነገሮች እየወጉ ቀለምን ቆዳ ውስጥ በመጨመር ጌጦችን የመፍጠር ልምድ ነው ብለን ልንገልጸው እንችላለን"" ሲሉ ያስረዳሉ። ታዲያ ይህ ልምድ ከጤና አኳያ ሊታዩ የሚችሉ ጉዳዮች አሉትም ብለዋል። እንደ ዶ/ር ድጋፌ ገለጻ፤ ንቅሳት ቋሚ ሲሆን ሰዎች ግን ቀድመው ለንቅሳት የተነሱበት ፍላጎትና ስሜት በጊዜ ብዛት ሊቀየር ይችላል። በዚህም ምክንያት የተነቀሱ ሰዎች ከ40 ዓመታቸው በኋላ የሚጸጸቱበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል። በሌላ በኩል ""ንቅሳት ያለበት ሰው ደም እንዲሰጥ አይመከርም"" ያሉት ሀኪሙ፤ ለዚህም ምክንያቱ ���ንቅሳት መሣሪያዎች ለተላላፊ በሽታ ስለሚያጋልጡ ነው ብለዋል። ንቅሳት የቆዳ መቆጣት [allergic reactions] ሊፈጥር እንደሚችል ዶ/ር ድጋፌ ጠቅሰዋል። ""የሰውነት አለርጂው ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመጣል። ከተነቀሱ ከሳምንታት ብሎም ከ10 ወይም ከ15 ዓመታት በኋላ የቆዳ መቆጣት፣ የማሳከክ ወይም የማበጥ ስሜትን ሊያመጣ ይችላል"" ብለዋል። ንቅሳት የሚደረግበት ስፍራና የመሣሪያው ንጽህና ካልተጠበቀ ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ሊዳርግም ይችላል። ""ንቅሳት ያደረገ ሰው ኤምአርአይ የሚባለውን ምርመራ ማድረግ ቢፈልግ እንደ ንቅሳቱ አይነትና የቀለም አይነት ንቅሳቱ ባለት ቦታ ላይ የቃጠሎ ቁስል ሊያጋጥም ይችላል"" ሲሉም ያክላሉ። ቋሚ ንቅሳት መጥፋት ይችላል? አዎ መጥፋት ይችላል። ""አብዛኛውን ንቅሳት በሌዘር [በጨረር] ማሽን ማጥፋት የሚቻልበት ዕድል አለ"" ሲሉ ገልጸዋል - ዶ/ር ድጋፌ። ሕክምናው የብርሃንን ኃይል ወደ ሙቀት በመቀየር የሚሠራ መሆኑን የሚስረዱት ሐኪሙ፤ ጨረሩ ቆዳው ውስጥ ያለውን ቀለም በመሰባበር በደም አማካይነት እንዲወገድ ያደርጋል ብለዋል። ሕክምናው ተከታታይ ሲሆን፤ ለዘመናዊ ንቅሳት ከ6 እስከ 10 ጊዜ ቢሰጥ ""ከፍተኛ ለውጥ ሊመጣ የሚችልበት አጋጣሚ አለ"" ብለዋል - ቆዳን ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት ባይመልሰውም። ሕክምናው በእያንዳንዱ የክትትል ዙር እስከ 2500 ብር ሊያስወጣ እንደሚችል የሚገልጹት ሐኪሙ፤ ሰዎች ንቅሳት ከማሠራታቸው በፊት ደጋግመው እንዲያስቡበት መክረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57390536 +business በቱኒዝያ በሺዎች የሚቆጠሩ የተፎካካሪ የፓርቲ አባላት ፕሬዚዳንት ሳዒድን ለመቃወም አደባባይ ወጡ "በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በቱኒዚያ ዋና ከተማ ጎዳናዎች ላይ የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት ለመቃወም አደባባይ  ወጥተዋል። እርስ በእርስ ጭምር የሚቃረኑ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የተቃውሞ ሰልፎቹን በመዲናዋ ቱኒዝ አካሂደዋል። የተቀናቃኝ ፓርቲዎቹ ከ2011 ህዝባዊ አመጽ በኋላ የተገኘውን ዲሞክራሲያዊ ጉዞ እየቀለበሱ ነው ያሏቸውን ካይስ ሰኢድን ""አምባገነን"" ሲሉ አውግዘዋል። የምግብ እና የነዳጅ እጥረት ለፈጠረው የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስም ተጠያቂነት አለባቸው ብለዋል። የፕሬዝዳንት ሰኢድ ተቺዎች መፈንቅለ መንግሥት ከማድረግ ባለፈ ቱኒዚያን ወደ በአንድ ሰው የሚመራ ፍጹም አምባገነናዊነት  ለመመለስ ሞክረዋል ሲሉ ይከሷቸዋል። በአውሮፓውያኑ 2021 ጠቅላይ ሚኒስትሩን አሰናብተው ፓርላማውን ካገዱ በኋላ፣ ከአንድ ዓመት በኋላ ፕሬዝዳንቱ የአንድ ሰው አገዛዛቸውን የሚያፀድቀውን ህገ-መንግስት እንዲያልፍ ቢሞክሩም በተቃዋሚ ፓርቲዎች ድምጽ ውድቅ ተደርጓል። አዲሱ ህገ መንግስት በአውሮፓውያኑ 2011 ከተካሄደው የአረብ አብዮት በኋላ የተረቀቀውንና የቱኒዚያ የቀድሞ አምባገነን መሪውን ዚነ አል-አቢዲን ቤን አሊን ከስልጣን ያስወገደውን ተክቷል። ይህ የሃገሪቱ መሪ ሙሉ የሥራ አስፈጻሚውን እንዲቆጣጠር፣ የሠራዊቱ የበላይ አዛዥ እንዲሆን እና ያለ ፓርላማው እውቅና መንግስትን የመሾም አቅም ሰጥቷቸዋል። ፕሬዚዳንት ሰኢድ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ውድቀትን ለመስበር አስፈላጊ ነበር ብለው ይሞግታሉ። ማሻሻያዎቹም የ2011 አብዮትን መንፈስ ያማከሉ እና ወደፊትም የተሻለ እንደሚሆን ተናግረዋል። ደጋፊዎቹ ውሳኔውን በደስታ ተቀብለዋል። ሃገሪቱ ብልሹ አሠራርን እና ሙስናን ለመቅረፍ ጠንካራ መሪ ትፈልጋለች በማለት ነው የሚደግፉት። ቅዳሜ ዕለት በማእከላዊ ቱኒዝ ሰልፈኞች “ውረድ፣ ውረድ” ሲሉ ተደምጠዋል። የተቃውሞ ሰልፉን ከጠሩት መካከል አንዱ የሆነው ናሽናል ሳልቬሽን ፎሮንት የተባለው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት የቱኒዚያን ፓርላማ ከፍተኛ ወንበር የያዘውን ኤናህዳን የያዘ ነው። ​​ሰኢድ  ፓርላማውን በኋላ ላይ በትነዋል። የቱኒዚያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኤናሃዳ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አሊ ላራይድ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ሰልፉ “በካይስ ሰኢድ የስልጣን ዘመን ላይ ያለው ቁጣ” የሚያሳይ ነው። “ስልጣን እንዲለቁ እየነገርናቸው ነው።“ አክለውም ተስፋ መቁረጥ፣ ድህነት እና ሥራ አጥነት እያደገ መሆኑን ጠቅሰው ሰኢድ በስልጣን ላይ ከቆዩ ""ቱኒዚያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አይኖራትም” ብለዋል። ናሽናል ሳልቬሽን ፍሮንትስልጣኑ የተገደበ አዲስ አዲስ ፓርላማ ለመምረጥ በታህሳስ ወር በሚካሄደው ምርጫ እንደማይሳተፍ አስታውቋል። የኢናሃዳ ርዕዮተ ዓለም ጋር ተቀናቃኝ የሆነው የፍሪ ዴስቶሪያን ፓርቲም በተመሳሳይ ቅዳሜ በዋና ከተማዋ የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጅቷል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች በመስከረም ወር 9.1 በመቶ የደረሰውን የዋጋ ግሽበት ምክንያት የውሃ ወጪን መጨመሩን ለማስመልከት ባዶ ጀሪካኖችን ይዘው ነበር። በ60ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ጡረተኛው ሰኢድ “ምንም እየሠራ አይደለም፣ ነገሮችም እየባሱ ነው”  ብለዋል። በኤንናዳ የሚመራውን ሰላማዊ ሰልፍ ወደ 1 ሺህ 500 የሚጠጉ ሰዎች የተቀላቀሉ ሲሆን ወደ 1 ሺህ 000 የሚጠጉት ደግሞ በፒዲኤል ተቃውሞ ላይ ተገኝተዋል ሲል የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኤኤፍፒተናግሯል። በአውሮፓውያኑ 2011 የተካሄደው የቱኒዚያ አብዮት ከአረብ አብዮት ብቸኛው እና ስኬታማው እንደሆነ ቢነገርም ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መረጋጋትን አላመጣም።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1jj288gqvo +health ኮሮናቫይረስ፡ ስለ አዲሱ የኮቪድ ዝርያ እስከ አሁን የምናውቃቸው 10 ነጥቦች ኮቪድ-19 ክትባት ተገኘለት እፎይ መባል በጀመረ ገና በሳምንቱ ከወደ ብሪታኒያ መጥፎ ዜና ተሰምቷል፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ አዲስ ዝርያ ያለባቸው ሰዎች መገኘት ነው ዜናው፡፡ በፈረንጆች ገና ይህ ያልተጠበቀ ዜና መሰማቱ ለጊዜው አውሮጳን እያመሳት ነው፡፡ ከብሪታኒያ የሚመጡ አውሮፕላኖች ላይ እግድ እያወጡ ያሉት የአውሮጳ አገራት ድንበራቸውን ጠርቅመው እየዘጉት ነው፡፡ 1ኛ፡- በብሪታኒያ በተለይም በሎንደንና አካባቢው እስከዛሬ ታይቶ የማይታወቅ የተህዋሲው ናሙና ተገኝቷል፡፡ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን በታመሙ ሰዎች ላይ በብዛት የሚታየው የቫይረስ ዓይነትም ይኸው ዝርያ መሆኑ ድንጋጤን ፈጥሯል፡፡ 2ኛ፡- ይህ የቫይረስ ዝርያ ሌሎች የተህዋሲ ዝርያዎችን በፍጥነት እየተካ ቦታውን እየያዘ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ 3ኛ፡- ራሱን የሚያባዛበት መንገድ ለየቅል መሆኑ ምናልባት ለቁጥጥር ያስቸግር ይሆን የሚል ስጋትን ጨምሯል፡፡ ከመተንፈሻ አካል ውጭ ያሉ ሴሎችንም ራሱን እየለወጠ የማጥቃት አቅም ሊኖረው ይችል ይhoን የሚል ስጋትም አለ፡፡ 4ኛ፡- ለመጀመርያ ጊዜ ይህ የተህዋሲ ዝርያ የተገኘው በመስከረም ወር ነበር፡፡ በጥቅምት ወር ሎንዶን አካባቢ በኮቪድ ከተያዙት ሲሶዎቹ የዚህ ተህዋሲ መልክ ተገኘባቸው፡፡ በታኅሣሥ ወር ደግሞ 75 ከመቶዎቹ ታማሚዎችን የለከፈው ይህ ልዩ ተህዋሲ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ 5ኛ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ቅዳሜ ዕለት በሰጡት መግለጫ ይህ ተህዋሲ እስከዛሬ ከነበረው ቫይረስ ጋር ሲወዳደር የመዛመት ዕደሉ በ70 ከመቶ የፈጠነ ነው ብለዋል፡፡ 6ኛ፡- አዲሱ የተህዋሲ ዝርያ በጊዜ ሂደት ራሱን ቀይሮ ይሁን ወይም ከሌላ ቦታ መጥቶ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። 7ኛ፡- አዲሱ የተህዋሲ ዝርያ በመላው ብሪታኒያ የተሰራጨ ቢሆንም አሁን ክምችቱ በብዛት የሚኘው በለንደንና አካባቢው ነው፡፡ ከለንደን በተጨማሪ በደቡብ ምሥራቅና በምሥራቅ ኢንግላንድም እንዲሁ በስፋት ተመዝግቧል፡፡ 8ኛ፡- ኔክስትስትሬይን የተሀዋሲ ዝርያዎችን የዘረ መል ኮድ የሚመዘግብ ድርጅት ሲሆን፣ ይህ ልዩ የተህዋሲ ዝርያ ከብሪታኒያ ወደ ዴንማርክና አውስትራሊያ መዛመቱን ተናግሯል፡፡ ኔዘርላንድና ጣሊያንም ይህ አዲሱ የተህዋሲው ዝርያ አገራቸው መግባቱን አረጋግጠዋል፡፡ 9ኛ፡- ይህ ልዩ የተህዋሲ ዝርያ ቅንጣት በደቡብ አፍሪካም ተገኝቷል የተባለ ሲሆን በኋላ ላይ የወጡ መረጃዎች ግን ከዚህ ብሪታኒያ ተገኘ ከተባለው ተህዋሲ ጋር የዝርያ ተመሳሳይነት የላቸውም ብለዋል፡፡ 10ኛ፡- ተህዋሲው ራሱን ቆርጦ እየቀጠለና እያባዛ ሊያመልጥ ቢችልም አሁን ወደ ገበያ እየገቡ ያሉ ክትባቶች ግን ማንነቱን ያጠፉታል፣ ፈውስም ይሆናል ተብሎ በስፋት ታምኗል፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ እስከዛሬ ሌሎች ዝርያዎች ኖረውት ያውቃሉ? አዎ! ዛሬ በተለያየ ዓለም የምናገኘው የቫይረስ ዝርያ ቅንጣት ቻይና ዉሃን ከተማ ከተገኘው ዝርያ ጋር አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ አሁን በብዙ የአውሮጳ አገሮች የሚገኘው D614G የሚባል የተህዋሲ ዝርያ ዓይነት ነው። ተህዋሲው ራሱን እየቀየረ ሊመጣ ይችላል፡፡ ምናልባት መነሻው ሊሆን የሚችለው ደካማ የመከላከል አቅም ካለው በሽተኛ ራሱን ቀይሮ የተነሳ ተህዋሲ ነው የሚሆነው፡፡ አንድ ታማሚ ተህዋሲውን ማሸነፍ ሲሳነው ሰውነቱ የተህዋሲው መራቢያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡ እስከአሁን በዚህ ረገድ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ገና በደንብ መጠናት ይኖርበታል፡፡ ለጊዜው የሚታወቀው በከፍተኛ ፍጥነት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ ብቻ ነው፡፡ ያም ሆኖ ብዙ ሰዎችን ማዳረስ ከቻለ ብዙ ሰዎች አልጋ ይይዛሉ፡፡ ይህ ደግሞ በተዘዋዋሪ ሞትን ሊጨምር ይችላል፡፡ መቶ በመቶ ባይሆንም አሁን የሚገመተው ክትባቶቹ ለዚህ ተህዋሲም ፈውስ እንደሆኑ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው አሁን ተሳኩ የተባሉት ክትባቶች የተህዋሲውን መላ አካሉንና ባህሪውን ሁሉ እንዲያጠቁ የተዘጋጁ ስለሆኑ ተህዋሲው ራሱን እያባዛ ራሱን ሊቀያይር ቢሞክርም እንኳ ከክትባቶቹ ያመልጣል ማለት ዘበት ነው ይላሉ ተመራማሪዎች፡፡ https://www.bbc.com/amharic/55391884 +sports ከእነዚህ 7 ‘ውድ’ ተጨዋቾች ዝውውራቸውን የሚያጠናቅቁ ይኖሩ ይሆን? የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ ሌሎች የአውሮፓ ዝነኛ ሊጎች የወድድር ዘመናቸውን መጀመራቸውን ተከትሎ ክለቦች በየትኛው የሜዳ ክፍል ራሳቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው እየለዩ ነው። ቢቢሲ ስፖርት ወደ ሌሎች ክለቦች ሊዘዋወሩ የሚችሉ “ውድ” ያላቸውን 7 ተጫዋቾችና ያሏቸውን አማራጮች ተመልክቷል። ሮናልዶ ክለቡን መልቀቅ መፈለጉ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ተጫዋቹ ከአንዴም ሁለቴ ልቀቁኝ ሲል ተናግሯል። ሮናልዶ ክለቡን የሚለቀው በቻምፒየንስ ሊግ መጫወት ስለምፈልግ ነው ይበል እንጂ በቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ የሆነ አንድም ቡድን በሮናልዶ ላይ ፍላጎት አላሳየም። የ37 ዓመቱ ተጫዋች የሚጠይቀው ከፍተኛ ክፍያ ለክለቦች የሚቀመስ አልሆነም። የውድድር ዓመቱን አሳፋሪ በተባሉ ሽንፈቶች ለጀመረው ዩናይትድ ሮናልዶ በመልበሻ ክፍል ውስጥ አሉታዊ ተጽእኖ ፈጣሪ ነው የሚል ሪፖርት ዘ አትሌቲክ ይዞ ወጥቷል። አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ሮናልዶ አይሸጥም ይበሉ እንጂ ክለቡ ትናንት ማክሰኞ ነሐሴ 10/2014 ዓ.ም. በሮናልዶ ላይ የነበረውን አቋም በመቀየር ክለቡን እንዲለቅ እንደሚፈቅድ ተገልጿል። ይህን ተከትሎ የሮናልዶ ወኪል ተጫዋቹን ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ለማዘዋወር ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፉት ወራት የዲ ዮንግ ስም ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል። ዩናይትድ ለዲ ዮንግ 56 ሚሊዮን ፓዎንድ ለመክፈል ከባርሴሎና ጋር ከተስማማ በርካታ ሳምንታት ቢያልፉም የዝውውር ስምምነቱ ግን ፈቀቅ አላለም። የኔዘርላንዱ አማካይ ኑ ካምፕን የመልቀቅ ፍላጎት ባይኖረውም ባርሴሎና ግን ከገባበት የፋይናንስ ቀውስ እፎይታ ለማግኘት ዲ ዮንግን ሊሸጥ ይችላል። ይህ የዝውውር ስምምነት ተፈጻሚ እንዳይሆን ማነቆ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ ዲ ዮንግ በባርሴሎና ሳይከፍለው የቆየው ገንዘብ አንዱ መሆኑ ሪፖርት ተደርጓል። አሁን ላይ ደግሞ ቼልሲ ዲ ዮንግን ለመወሰድ ጥረት ጀምሯል። ቼልሲ በዚህ የዝውውር መስኮት ከ150 ሚሊዮን ፓዎንድ በላይ ወጪ በማድረግ በርካታ ተጫዋቾችን ሰብስቧል። ክለቡን በቅርቡ የተረከቡት አሜሪካዊው ባለሃብት አሁንም በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ለንደን ከማምጣት የቦዘኑ አይመስልም። ሮበርት ሎዋንዶውስኪ ወደ ባርሳ ማምራቱን ተከትሎ ኦባሚያንግ ወደ ቼልሲ ሊዘዋወር ይችላል። ቼልሲ ለቀድሞ የአርሰናል አምበል ኦባ እስከ 25 ሚሊዮን ፓዎንድ ሊጠየቅ ይችላል። ባርሳን ሊሰናበት የሚችለው ሌላኛው ተጫዋች ሜምፊስ ዴፓይ ነው። ባርሴሎና ራፊንሃን ከሊድስ ዩናይትድ ካዘዋወረ በኋላ፤ ዴፓይ በነጻ ዝውውር ወዳሻው ክለብ መሄድ እንደሚችል ክለቡ አሳውቆታል። የ28 ዓመቱ ሆላንዳዊ የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ የክንፍ ተጫዋች ወደ ጣሊያኑ ጁቬንቱስ ሊያመራ ይችላል። አሁንም ቼልሲ ነው። ቼልሲ የሌስተሩን ተከላካይ በውድ ዋጋ ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ለመውስደ የሚያመነታ አይመስልም። የመሃል ተከላካዩን ኩሊባሊን ከናፖሊ እንዲሁም የቀኝ ክንፍ ተመላላሹን ማርከ ኩከሪያልን ከብራይተን ያዘዋወሩት ሰማያዎዎቹ ለሌላ ተከላካይ ከፍተኛ ገንዘብ ለመክፈል ዝግጁ ይመስላሉ። ቼልሲ ለ21 ዓመቱ ፈረንሲያዊ 80 ሚሊዮን ፓዎንድ ሊያወጣ ይችላል የሚሉ ሪፖርቶች ወጥተዋል። ኤቨርተን የፊት መስመር አጥቂያቸውን ሪቻርልሰንን በቶተነሃም ተነጥቀዋል። ደካማ አቋም እያሳየ ባለው ኤቨርተን ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለው አንቶኒ ጎርደንም ወደ ቼልሲ ሊያመራ ይችላል። ቼልሲ ለአንቶኒ ጎርደን ያቀረበው የ40 እና የ45 ሚሊዮን ፓዎንድ የዝውውር ጥያቄዎች በኤቨርተን ውድቅ ተደርጎበታል። ቼልሲ ግን ዳግም ተጫዋቹን ለመውሰድ ሌላ ጥረት እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት በውሰት በቆየበት ሳውዛምፕተን 9 ጎሎችን በማስቆጠር ጥሩ ግዜን ያሳለፈው አጥቂው ብሮጃ የብዙ ክለቦችን ትኩረት ስቧል። አልባናዊው አጥቂ ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ከተመለሰ በኋላ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ የመካተት እድልን አላገኘም። ይህም ወደ ሌላ ክለብ እንዲያማትር ሊያደርገው ይችላል የሚሉ ግምቶች አሉ። ዌስት ሃም፣ ኤቨርተን እና ኒው ካስትል የ20 ዓመቱን አጥቂ የመውሰድ ጽኑ ፍላጎት ካላቸው ክለቦች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c51vzkg0ng0o +sports ለወራት በሩሲያ ቁጥጥር ስር የምትገኘው አሜሪካዊቷ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች በምን ሁኔታ ነው ያለችው? በሚቀጥለው ወር አሜሪካ የሴቶች የቅርጫት ኳስ ውድድር ሲጀመር በሊጉ ውስጥ ደምቀው መውጣት ከቻሉት ኮከቦች መካከል አንደኛዋ አትኖርም። የፊኒክስ ሜርኩሪ ተጨዋቿ ብሪትኒ ግራይነር ካሳለፍነው የካቲት ወር ጀምሮ ሩሲያ ውስጥ ተይዛ የምትገኝ ሲሆን ዋይት ሀውስ እስካሁን በጉዳዩ ላይ ምንም መረጃ መስጠት አልቻለም። የ31 ዓመቷ ብሪትኒ ገሪነር ሩሲያ ውስጥ ከአደንዛዥ እጽ ጋር በተያያዘ እስር ቤት እንደምትገኝ ይታመናል። ሩሲያ በምትገባበት ወቅት የአየር ማረፊያው ሰራተኞችች ባደረጉባት ምርመራ በቦርሳዋ ውስጥ የእጸ ፋርስ ዘይት ተገኝቷል የሚል ጥርጣሬም አለ። የተባለው ነገር እውነት ሆኖ ከተገኘና ብሪትኒ ግራይነር ጥፋተኛ የምትባል ከሆነ እስከ 10 ዓመት የሚደርስ እስር እንደሚጠብቃት ተገልጿል። ብሪትኒ ግራይነር በዓለማችን ምርጧ ሴት የቅርጫት ኳስ እንደሆ��ች በርካቶች ይስማማሉ። በቅርጫት ኳስ ሕይወቷም የኮሌጅ ቻምፒየንሺፕ፣ የአሜሪካ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ውድድር፣ ዩሮሊግ እንዲሁም የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፍ የቻለች ድንቅ ስፖርተኛ ነች። ከአውሮፓውያኑ 2015 ጀምሮ ደግሞ የአሜሪካ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ሊግ ለእረፍት ሲቋረጥ ወደ ሩሲያ በመሄድ ለአንድ ቡድን ትጫወታለች። ምንም እንኳን በርካቶች ብሪትኒ ግራይነር ዓለማችን ካየቻቸው ምርጥ የቅርጫት ኳስ ኮከቦች መካከል አንዷ እንደሆነች ቢስማሙም አሁን ላይ ላይ ግን ስላለችበት ሁኔታ ምንም አለመታወቁ ጥቂት የማይባሉ አሜሪካውያንን አስቆጥቷል። በሩሲያ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ከዋለች ሁለት ወር የሞላት አሜሪካዊቷ ስፖርተኛ ቤተሰቦችም ሆነ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት እና የአሜሪካ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ሊግ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት አስተያየት አለመስጠትን መርጠዋል። ባሳለፍነው ወር የሞስኮ ፍርድ ቤት እንዳስታወቀው የብሪትኒ ግራይነርን ጉዳይ ለመከታተል ሲባል እስከ ግንቦት አጋማሽ ድረስ እንድትቆይ መወሰኑን አስታውቋል። የዋይት ሀውስ ፕረስ ሰክረተሪዋ ጄን ሳኪ ሰⶉ ዕለት በጉዳዩ ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ብዙም መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡ ሲሆን ''በሌላ አገር በእስር ላይ ስለሚገኙ አሜሪካውያን ማውራት ብዙም ጠቃሚ አይደለም'' በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። ''ምናልባት ዜጋችንን ለማስመለስ የምናደርገውን ጥረት ሊያደናቅፈው ይችላል'' ብለዋል። '' በሩሲያ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ሁሉም አሜሪካውያንን ቀጣይነት ባለው እና ጊዜውን በጠበቀ መልኩ መጎብኘት እንድንችል በተደጋጋሚ እየጣርን ነው። የብሪትኒ ጉዳይንም በተመለከተ በቅርበት እየተከታተልነው ነው'' ሲሉም አክለዋል። ብሪትኒ ገራይነር በዘንድሮው የቅርጫት ኳስ ሊግ ብትሳተፍ ኖሮ ለስምነተኛ ተከታታይ ዓመቷ ይሆነ የነበረ ሲሆን በሊጉም ከፍተኛ ድምቀትን ትፈጥር እንደነበር አድናቂዎቿ እና የቡድን አጋሮቿ ገልጸዋል። ልክ እንደ ብሪትኒ ሁሉ ሌሎች የአሜሪካ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ሊጎች ውስጥ የሚሳተፉ ስፖርተኞች ሊጉ ሲዘጋ ወደ ሌሎች አገራት በመሄድ ይጫወታሉ። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ተጨማሪ ገቢን ለማግኘት ነው። ለምሳሌ ሩሲያ አሜሪካ ከሚከፈላቸው አምስት እጥፍ ትከፍላለች። https://www.bbc.com/amharic/news-61058593 +sports የሴቶች ዓለም ዋንጫ፡ ሴት እግር ኳሰኞች ስንት ይከፈላቸዋል? ዓለም ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ ሃገራትስ? የሴቶች እግር ኳስ ከጊዜ ጊዜ እያደገ የመጣ ይመስላል፤ ትኩረት መሳብም ጀምሯል። የዘንድሮውን የዓለም የሴቶች ዓለም ዋንጫ ጨዋታ 1 ቢሊዮን ተመልካቾች ይታደሙታል የሚል ግምት አለ። የሉሲዎቹ አምበል የሆነችው ሎዛ አበራ ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር የሴቶች ክፍያ እዚህ ግባ የማይባል ነው ትላለች። በዓለም አቀፍ ደረጃስ? የባለፈው ዓለም ዋንጫ አሸናፊ የአሜሪካ አጥዊ የሆነችው ሆፕ ሶሎ የሴቶች እና የወንዶች ክፍያ ልዩነት ፊፋ ውስጥ ያለውን 'የወንድ የበላይነት' ያሳያል ስትል ትወቅሳለች። እስቲ ክፍያውን በቁጥር ከፋፍለን እንመልከተው። • እግር ኳስ ተጫዋቹ ወንድወሰን ዮሐንስ እንዴት ተገደለ? ፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው የዘንድሮው የሴቶች የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ላይ አሸናፊ የምትሆነው ብሔራዊ ቡድን 4 ሚሊዮን ዶላር [115 ሚሊዮን ብር ገደማ] ታገኛለች። ከባለፈው ዓለም ዋንጫ ክፍያ እጥፍ ማለት ነው። እያንዳንዳቸው ተሳታፊ ቡድኖች ደግሞ ከ750 ሺህ ዶላር [22 ሚሊዮን ብር ገደማ] ጀምሮ በነብስ ወከፍ ይቀበላሉ። ከሽልማት ወጪው በተጨማሪ ለዝግጅት በሚል እያንዳንዷ ቡድን 800 ሺህ ዶላር ከፊፋ ትቀበላለች። በጠቅላላው ፊፋ ለዘንድሮው ዓለም ዋንጫ 30 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል። ሩስያ አዘጋ���ታ ፈረንሳይ በወሰደችው የ2018ቱ የወንዶች ዓለም ዋንጫ ፊፋ ለሽልማት ብሎ ያዘጋጀው ጠቅላላ ገንዘብ 400 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ነው፤ ከሴቶቹ ከአስር እጥፍ በላይ ማለት ነው። ለዝግጅት ተብሎ ለእያንዳንዱ ቡድን በነብስ ወከፍ የተሰጠው ደግሞ 1̋ሚሊዮን ዶላር ነው፤ ከሴቶቹ እጥፍ በላይ ማለት ነው እንግዲህ። አጀብ! የሚያስብል ሆኖ እንዳገኙት እንጠራጠርም። የወንዶቹ ክፍያ ከሴቶቹ በልጦ የመገኘቱ ጉዳይ ከሚያመጡት ገቢ ጋር መገናኘቱ ነው ብለው የሚከራከሩ አልጠፉም። ቢሆንም በፊፋ ሕግ መሠረት ከሴቶች እግር ኳስ የሚገኘው ገንዘብ ለሴቶች እግር ኳስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ወጪዎች የሚውል ነው። ፊፋ ለሃገራት የሚከፍለው ገንዘብ የተጨዋቾች ኪስ ሳይሆን ወደ ፌዴሬሽን ካዝና የሚገባ ነው። የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ድርሻ ቆንጠር አድርጎ ለተጨዋቾች መስጠትና የቀረውን ደግሞ ሌሎች መስኮች ላይ በተን በተን ማድረግ ይሆናል። ታድያ በፌዴሬሽኖች እና በእግር ኳስ ተጨዋቾች ማሕበር መካከል የሚደረግ ድርድር አለ። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ የአውስትራሊያ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን የትኛውንም ገንዘብ በሽልማት መልክ ሲያገኝ ተጨዋቾች 30 በመቶ እንዲያገኙ ተደራድሯል። ወደ ክለቦች ስንወርድ ደግሞ የተሻለ ክፍያ የሚያገኙት [ከወንዶች ሲነፃፀር ቁጥሩ እጅግ አናሳ ቢሆንም] በምዕራብ አውሮፓ የሚጫወቱቱ ናቸው። ገንዘቡ ደግሞ ከ1 ሺህ እስከ 2 ሺህ ዩሮ ይደርሳል፤ ጨዋታ ባለ ቁጥር ደግሞ የላብ መተኪያ የሚሆን ከ50-100 ዩሮ ያገኛሉ። እርግጥ ነው ስም ያላቸው ተጨዋቾች ከዚህ የተሻለ ይከፈላቸዋል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ክፍያው ምን ያህል ዝቅ ያለ እንደሆነ መገመት አያዳግትም። ፊፋ የሴቶች ዓለም የዋንጫ አሸናፊ ሽልማትን ከባለፈው ዓለም ዋንጫ እጥፍ ማድረጉ አንድ እርምጃ ወደፊት ነው የሚሉ ባይጠፉም 'አሁንም ትንሽ ነው' ብለው የሚከራከሩ አልጠፉም። በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ፊፋ የሴቶች እግር ኳስ ላይ ከ400-500 ሚሊዮን ዶላር አፈሳለሁ ይላል። የአሜሪካ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን የሃገሪቱን እግር ኳስ ማሕበር እኩል ክፍያን እውን አላደረገም በሚል ከሶታል። የአውስትራሊያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማሕበር ፊፋ የሴቶች እና የወንዶች የዓለም ዋንጫ ሽልማት እኩል መሆን አለበት ሲል እየሞገተ ነው። 2016 ላይ የአፍሪካ ዋንጫን የበላችው የናይጄሪያ ሴቶች ቡድን በክፍያ ጉዳይ ከፌዴሬሽን ጋር በነረው እሰጥ-አገባ አድማ አድርጋ ነበር። የኒው ዚላንድ ወንዶች እና ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት ከ2018 ጀምሮ ማንኛውም ዓይነት ክፍያ እኩል እንዲያገኙ የሚያደርግ ውል ደርሰዋል፤ በኖርዌይም እንዲሁ። ምንም እንኳ ልዩነቱ አሁንም የሰማይና ምድርን ያክል [የሎዛ አበራን አገላለፅ ለመጠቀም] ቢሆንም ከጊዜ ጊዜ ግን ለውጥ መምጣቱ አይካድም። https://www.bbc.com/amharic/48591305 +health የኮሮናቫይረስ በአንዳንድ ምግቦች ላይ ለቀናት እንደሚቆይ ጥናት አረጋገጠ የኮሮናቫይረስ በተለይም ታሽገው በሚሸጡ ምግቦች ላይ እንደሚቆይ የዩናትድ ኪንግደም ተመራማሪዎች ገለጹ። የአገሪቱ የምግብ ጥራት ኤጀንሲ ባሰራው ጥናት ሳይንቲስቶች ቫይረሱን ሆነ ብለው በተወሰኑ የምግብ ማሸጊያዎች ላይ በማድረግ ሙከራውን አድረገዋል። ይህም በአትክልት እና ፍራፍሬ፣ ኬክ እና ዳቦ እንዲሁም የታሸጉ መጠጦች ሙከራው ተደርጎባቸዋል። ሳይንቲስቶቹ ሳይታጠቡ ወይም ሳይበስሉ ሊበሉ የሚችሉ ምግቦችን በመምረጥ ነው ጥናቱን ያካሄዱት። ነገር ግን ይህ ሸማቾች ላይ የሚያመጣው አደጋ ያነሰ መሆኑን ገልጸዋል። በአብዛኛው የምግብ ምርቶች ላይ ሳይንቲስቶቹ ያስቀመጡት የቫይረስ መጠን በ24 ሰአት ውስጥ ከፍተኛ ማሽቆልቆል ታይቶበታል። ነገር ግን በአንዳንድ ማሸጊያዎች ላይ ቫይረሱ ለአንድ ሳምንት ያህል እንደሚቆይ የሳውዝ ሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ተናግረዋል። ሳርስ ኮቭ 2 የተሰኘውን የቫይረስ አይነት ወስደው ምርምሩን ያደረጉት አጥኚዎች እንደሚሉት ''እንደዚህ ያለ በንክኪ ብቻ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭ የቫይረስ አይነትን በተመለከተ ያገኘነው ግኝት ትኩረት የሚገባው ነው'' ሲሉ ተናግረዋል። ሳይንቲስቶች ሸማቾች በተለይም ምግብ በሚያዘጋጁበት ወቅት እጃቸውን እንዲታጠቡ እና በጥሬው የሚበሉ ምግቦችን አጥበው እንዲመገቡ አሳስበዋል። ተመራማሪዎች በጥናታቸው የኮሮናቫይረስ በንክኪ ከሚተላለፈው ይልቅ በምራቅ ፍንጣቂዎች በአየር አማካይነት የበለጥ እንደሚተላለፍ አረጋግጠዋል። ጥናቱ እንዳረጋገጠው ቫይረሱ በተለይም ሸካራ ገጽ ባላቸው እንደ ብሮኮሊ ባሉ አትክልቶች ላይ እንደ ፖም ባሉ ልሙጥ ከሆኑት በበለጠ እንደሚቆዩም አረጋግጧል። ጥናቱ አክሎም ፖም በቅርፊቱ ላይ በያዘው ኬሚካል አማካኝነት በቂቃዎች ወይም በሰዓታት ውስጥ በላዩ ላይ ያረፈውን ቫይረስ መግደል እንደሚጀምርም አረጋግጧል። በኬክ እና ዳቦ ላይ በተደረጉ ሙከራዎችም በአንዳንድ ደረቅ ገጽ በላቸው ኬኮች ላይ ቫይረሱ በሰአታት ውስጥ ቁጥሩ መቀነሱን ተናግረዋል። ለዚህም ምናልባት ኬኮቹ በሚበስሉበት ወቅት እንቁላል ስለሚቀቡ እና ይህም እንቁላል ውስጥ ካለ አሲድ አማካኝነት ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል። በቺዝ እና ቀዝቃዛ ስጋ ቫይረሱን ለቀናት አንዳንዴም ለሳምንት ሊያቆዩ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ኮቪድ በፕላስቲካ እቃዎች ላይ እስከ አንድ ሳምንት ድረስ ሊቆይ ይችላል። በካርቶን ላይ ለተወሰኑ ቀናት ብሎም በአልሙኒየም ማሸጊያዎች ላይ የተወሰኑ ሰአታትን ሊቆይ እንደሚችል ሳይንቲስቶቹ ተናግረዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0j54rpdryo +health ኮሮናቫይረስ፡ ኒውዚላንድ 14 በከሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች አገኘች የኒውዚላንዷ ትልቋ ከተማ ኦክላንድ በድጋሚ የእንቅስቃሴ ገደብ ከተጣለባት በኋላ አዲስ 14 በኮሮረናቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተገለጸ። በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ አራት አንድ የቤተሰብ አባላት የሆኑ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲሰማ መላው ኒውዚላንድ በድንጋጤ ተውጦ የነበረ ሲሆን የአሁኑ ደግሞ ነገሮችን አባብሷል። ከውጭ አገራት በቫይረሱ ተይዘው ከሚመጡ ሰዎች ውጪ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ አገሪቱ ላለፉት ሶስት ወራት ምንም በቫይረሱ የተያዘ ሰው አላገኘችም ነበር። ዛሬ ከተገኙት ተጨማሪ 14 ሰዎች መካከል 13ቱ ከዚሁ ቤተሰብ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን አንደኛው ግለሰብ ደግሞ ከሌላ አገር ወደ ኒውዚላንድ ገብቶ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ እንደሆነ ተገልጿል። ከትላንት ረቡዕ ጀምሮ ደግሞ በኦክላንድ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። '' ሁኔታው ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ማየት እንችላለን'' ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጃሲንዳ አርደርን። በሰጡት ጋዜታዊ መግለጫ ላይ አክለውም '' ጉዳዩ በተገቢው መንገድ ክትትል እየተደረገበት ነው፤ ፈጣንና ተገቢው እርምጃም ይወሰዳል'' ሲሉ ተደምጠዋል። ሁሉም ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን ኃላፊዎች ያስታወቁ ሲሆን ከነሱ ጋር በማንኛውም መንገድ ንክኪ የነበራቸው ሰዎችም ክትትል እንደሚደረግባቸው ገልጸዋል። ኒውዚላንድ እስካሁን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በወሰደቻቸው ፈጣንና ውጤታማ እርምጃዎች ከመላው ዓለም ምስጋናና ሙገሳ ሲጎርፍላት ነበር። ይህ ዜና ከተሰማ በኋላም በመላው አገሪቱ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ግዴታ የተደረገ ሲሆን ቫይረሱ በተገኘባት ኦክላንድ ደግሞ ጠንከር ያለ የእንቅ��ቃሴ ገደብ ተጥሏል። ከማክሰኞ በፊት በኒው ዚላንድ በአገር ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ሳታገኝ 102 ቀናት መቆየት የቻለች አገር ነበረች። የአገሪቱ የጤና ኃላፊዎችና ሰራተኞች ቫይረሱ ከየት እንደተነሳ ለማወቅ በፍጥነት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ተገልጿል። በኮቪድ-19 የተያዙት ሰዎች ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና የስራ ባልደረቦችም ተለይተው ምርመራ ይደረግላቸዋል ተብሏል። '' ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት ያለእረፍት እየሰራን ነው። ምንጩ ከየት እንደሆነም ለማወቅ የምንችለውን ነገር በሙሉ እያደረግን ነው'' ብለዋል ብሄራዊ የጤና ኃላፊው አሽሊ ብሉምፊልድ። ቫይረሱ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በድጋሚ ሲያገረሽ ይሄ የመጀመሪያው አይደለም። በርካታ የአውሮፓ አገራት ሁኔታዎች መሻሻል ሲያሳዩ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ማንሳታቸውን ተከትሎ ቫይረሱ ሁለተኛ ዙር መስፋፋት ጀምሯል። ቪየትናም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሳታገኝ 99 ቀናት ሳታገኝ ከቆየች በኋላ ዳ ናንግ በተባለችው ከተማ ስርጭቱ በድጋሚ መጀመሩ የሚታወስ ነው። በኒውዚላንድ ወረርሽኙ በድጋሚ መቀስቀሱ ምናልባት በሌሎች ከተሞችም የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ሊያስገድድ እንደሚችል ተፈርቷል። አገሪቱ ደግሞ በሳምንታት ልዩነት ውስጥ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ነበረች። ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ምን አይነት ውሳኔዎች እንሚተላለፉ ነገ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። https://www.bbc.com/amharic/news-53761579 +health “እስክሞት ልታገል”፡ የኩላሊት ህሙማን መርጃ ያቋቋመው የኩላሊት ታማሚ "የህክምና ምርመራ ውጤት! ሕይወታችንን ባላሰብነው፣ ባልጠበቅነው መንገድ ይገለባብጣል። ለኢዮብ ተወልደመድኅን ያ ክፉ ጊዜ ጥቅምት 2006 ዓ.ም ነበር። የኩላሊት ታማሚ እንደሆነ ሐኪሞች ሲገሩት። የሁለት ሴት ልጆች አባት የሆነው ኢዮብ ይህን ዜና ሲሰማ የሚገባበት ጠፋው። ባለቤቱ በድንጋጤ ከፍተኛ ሐዘን ተጫናት። አዲስ አበባ ውስጥ የተክለሐይማኖት ሰፈር ልጅ ነው። ከ1979 ዓ. ም. ጀምሮ ግን ለአምስት ዓመታት አሰበ ተፈሪ ኖሯል። ዘጠነኛ ክፍልን አብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት ተምሮ 10ኛ ክፍል ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት በማታ ፈረቃ ገባ። የግድ ታናናሾቹን ማሳደግ ስለነበረበት ከ11ኛ ክፍል በላይ መቀጠል አልቻለም። ትምህርቱን አቋርጦ እንጨት ሥራ ያዘ። በእንጨትና አልሙንየም ሥራ ተቀጥሮ ለሦስት ዓመታት ሠራ። ጥሩ ገቢ ያገኝ ስለነበር ታናናሽ ወንድሞቹን፣ እናትና አባቱንም ያስተዳድር ጀመር። 1991 ዓ.ም. ላይ ከብድርና ቁጠባ ተቋም አነስተኛ ገንዘብ ተበድሮ ቤቱ የእንጨት ሥራ ከፈተ። ገቢው እያደገ መጣ። ንግዱ ሲጦፍ ከመንግሥት ቦታ ወስዶ እንጨት ሥራውን አስፋፋ። በልደታ ክፍለ ከተማ በከፈተው እንጨት ቤት ሙያውን ያስተምርም ነበር። ጥቅምት 2006 ዓ.ም. ላይ የኩላሊት ህመም አለብህ ሲባል ግን ነገሮች መስመር ሳቱ። ሥራውን ወዲያው አላቋረጠም። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከበደው መምጣቱ ግን አልቀረም። ከታመመ ከሁለት ዓመት በኋላ አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከጥቃቅንና መካከለኛ የንግድ ሰዎች አንዱ ብሎ ሸልሞታል። የኩላሊት ህመም አቅም ይነሳል። አካልን፣ ሥነ ልቦናን፣ ቤተሰብን፣ ጓደኛን፣ ሥራን ይፈትናል። ኢዮብ የገጠመውም ይኸው ነው። የኩላሊት ህክምና እድሜ ልክ የሚወስድ፣ ገንዘብንም የሚያሟጥጥ እንደሆነ ሲገነዘብ የባለቤቱና የሕጻናት ልጆቹ እጣ ፈንታ እንቅልፍ ነሳው። ቤተሰቤን ድሃ አድርጌ ከምሞት ምነው እኔው ቀድሜ ብሞት ሲል ያስብ እንደነበር ይናገራል። በአንድ ወር ውስጥ የኩላሊት እጥበት [ዳያለሲስ] ካላደረገ እንደሚሞት ሲነገረው ቤተሰቡና ጓደኞቹ ተረበሹ። በአፋጣኝ ኮርያ ሆስፒታል ወስደውት የኩላሊት እጥበት ጀመረ። ህመሙም ጋብ አለለት። ያኔ ሆስፒታሉ ውስጥ ያየው ነገር የሕይወት አቅጣጫውን እንዲቀይር እንዳደረገው ያስታውሳል። ""አቅም የሌለው፣ መካከለኛ ገቢ ያለው፣ ባለ ሀብት ታካሚም አለ። ልዩነቱ በግልጽ ይታያል። በርካቶች ህክምናውን ለማድረግ አቅም አልነበራቸውም። እኔ ታክሜ ነጻነት ሳገኝ ለምኖ ያልሞላለት ሰው ግን ምን ያህል ነጻነቱን ያጣል? ስል አሰብኩ።"" ለወራት የኩላሊት እጥበት ሲያደርግ የህክምናው ወጪ ከብዷቸው የሚያቋርጡ እንዳሉ ይሰማ ነበር። ወጪው ከአቅማቸው በላይ ሆኖ የሚሞቱትንም ቤቱ ይቁጠራቸው። ""እስክሞት ልታገል"" ኩላሊት መሥራት ሲያቆም የኩላሊት እጥበት ማድረግ ግዴታ ነው። ህመሙ የሌለባቸው ሰዎች ሰውነታቸው ውስጥ የሚከማች ቆሻሻን ሽንት በመሽናት ያስወግዳሉ። ታማሚዎች የኩላሊት እጥበት ካላደረጉ ቆሻሻው አይወጣም ማለት ነው። እናም ሰውነታቸው ይታፈናል፣ ያብጣል፣ ሲከፋም ሕይወታቸውን ያጣሉ። በሳምንት ሦስቴ የኩላሊት እጥበት ማድረግ የሚጠበቅበት ሰው በሳምንት አንዴ ብቻ ቢያደርግ ወይም ቢያቋርጥ ይህ መታፈን ይገጥመዋል። ምግብ መብላትም አይችልም። ኢዮብ በህመሙ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎችን ሲያይ በቀረኝ ሕይወት የአቅሜን መርዳት አለብኝ ብሎ ወሰነ። ህሙማን የገንዘብ እርዳታ የሚያገኙበት እና መንግሥት ከህመሙ ጋር በተያያዘ የሚያወጣቸው ውሳኔዎች ላይ ጫና ማሳደር የሚቻልበት ማኅበር አቋቋመ። 'ሞት በኩላሊት ይብቃ' የተጀመረው በ2007 ዓ.ም. ነው። በታመመበት ጊዜ በመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት አልነበረም። በግል ሆስፒታልም በውስን ቦታ፣ በውድ ገንዘብ ይከናወናል። ህክምናውን ለማግኘት የሚደረገው ጥረት አሁንም ድረስ ከባድ ነው። በመንግሥት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት በአንድ ዙር 500 ብር ያስከፍላል። በግል ሆስፒታሎች ደግሞ ከ1500 እስከ 3500 ብር ያወጣል። ""መሞቴ አይቀርም እስክሞት ልታገል ብዬ ወሰንኩ። ለመንግሥት አካላት እና ለአንዳንድ ተቋማት ድምጼን ማሰማት ጀመርኩ። በመኪና እየዞሩ መቀስቀስ፣ ብሮሸር መለጠፍም ቀጠልኩ። ይኸው 8 ዓመት ኖርኩኝ። በጥቂት ቦታም ቢሆን በመንግሥት ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ተጀምሯል። ይሄ በኩራት የምናገረው የልፋቴ ውጤት ነው።"" ማኅበሩ ከምስረታው ጀምሮ ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ120 በላይ ህሙማንን ደግፏል። ቁጥሩ ለቀን፣ ለሳምንት፣ ለአንድ ወር ወይም ለሁለት ወር የኩላሊት እጥበት ገንዘብ የሚከፈልላቸውን ይጨምራል። ወርሀዊ መዋጮ በማድረግ እና በጉልበት ሥራ የሚደግፉ የማኅበሩ አባላት አሉ። ደበበ እሸቱ፣ ስዩም ተፈራ፣ ዳንኤል ተገኝ ታዋቂ የማኅበሩ አባላት ናቸው። ኢዮብ ""አምባሳደሮቻችን"" ይላቸዋል። ከ2007 ወዲህ ድጎማ ከተደረገላቸው ህሙማን መካከል አምስቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሞት በኩላሊት ይብቃ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በምኒሊክ እና በዘውዲቱ ሆስፒታሎች ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ ለሁለት ዓመት ነጻ የኩላሊት እጥበት ከሚሰጣቸው 105 ህመምተኞች አንዱ ኢዮብ ነው። ያቋቋመው ማኅበር ከያዛቸው ፕሮጀክቶች አንዱ የኩላሊት ህሙማን ተደራጅተው ሥራ እንዲሠሩ ከክፍለ ከተሞች ጋር መነጋገር ነው። ይህም ለህክምና ገንዘብ ሲሉ ጎዳና ወጥተው ለመለመን የተገደዱ ወገኖችን ለመደገፍ ያለመ ነው። ፕሮጀክቱን የጤና ሚንስትር እና የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ድጋፍ ሰጥቶት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለአንድ ህመምተኛ የሥራ እድል ተፈጥሯል። በሌሎች ክፍለ ከተሞችም እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ወጋገን ባንክ ለህመምተኞች መርጃ ገንዘብ የሚሰበሰብበት ሳጥን ተቀምጧል። በቋሚነት በሳምንት ለአንድ ህመምተኛ የኩላሊት እጥበት ���ፍያ የሚያደርጉ የማኅበሩ አባላት አሉ። ማኅበሩ በሰበሰበው ገንዘብ ሦስት ህሙማን የኩላሊት ንቅለ ተከላ የተደረገላቸው ሲሆን፤ ነጻ ህክምና የሚያገኙ እንዳሉም ይናገራል። ""ኢትዮጵያ ውስጥ የኩላሊት እጥበት ክፍያ ከፍተኛ ስለሆነ ከ70 እስከ 80 በመቶ ያሚሆነው የኩላሊት ህመምተኛ በሳምንት አንዴ ወይም ሁለት ቀን ነው የሚያደርገው"" ይላል። ማኅበሩ በሠራው ስሌት መሠረት አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ከ700 ያላነሱ የኩላሊት ህመምተኞች በግል ሆስፒታል ነው ህክምና የሚከታተሉት። ዝቅተኛ የሚባለውን የአንድ ዙር የኩላሊት እጥበት ወጪ 1500 ብር መክፈል የሚችሉ ውስን ናቸው። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጎዳና ላይና በየሐይማኖት ተቋማት ከመለመን ውጪም አማራጭ የለውም። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የኢዮብ ማኅበር የመዋጮ ፕሮጀክት ቀርጿል። ሐሳቡ በወር 10 ብር፣ በዓመት 120 ብር የሚያዋጡ አንድ ሚሊዮን ሰዎችን በማኅበሩ አባልነት መመዝገብ ነው። ፕሮጀክቱ ከሦስት ዓመት በፊት ሲጀመር ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጀምሮ፣ ታዋቂ ሰዎችና ሌሎች ሰዎችን ጨምሮ ወደ 3000 ሰዎችን መመዝገብ ተችሏል። ከአባላቱ የሚሰበሰበውን ገንዘብ የሚከታተል መተግበሪያ እያሠሩ ነው። ኢትዮ-ቴሌኮም አጭር የጽሑፍ መልዕክት (ኤስኤምኤስ) እየላከ ገንዘቡን ሰብስቦ በቀጥታ ወደ ጤና ሚንስትር እንዲያስገባ ለማድረግ ወጥነዋል። አንድ ሚሊዮን ሰዎች በወር 10 ብር፣ በዓመት 120 ብር ቢያዋጡ፤ በአንድ ዓመት በአጠቃላይ 120 ሚሊዮን ብር ይገኛል። ይህም ለነጻ የኩላሊት ህክምና እንዲውል እንደሚፈልግ ኢዮብ ይናገራል። ""ይህ ገንዘብ በመሀል ምንም ሂደት ሳይኖር ከቴሌ ወደ ጤና ሚንስትር በቀጥታ ስለሚገባ ተአማኒነት ይኖረዋል"" ይላል። ከጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር በጉዳዩ ላይ ከስድስት ወር በፊት እንደተነጋገረ ይገልጻል። ""ሚንስትሯ በሐሳቡ ደስተኛ እንደሆኑና ለመደገፍ ፍቃደኛ እንደሆኑ ነግረውኛል። ገንዘቡ ከቴሌ ወደ ጤና ጥበቃ በቀጥታ እንዲገባ እንደምንፈልግ ስነግራቸው የሕግ አግባቡን ልይ ብለዋል።"" የቀድሞው የጤና ሚንስትር ዶ/ር አሚር አማን ሐሳቡን ደግፈው የአባልነት መታወቂያ አውጥተዋል። የኢዮብ ውጥን ተሳክቶ በአንድ ዓመት 120 ሚሊዮን ብር ማግኘት ከተቻለ እስከ 500 ሰዎች ለዓመት በመንግሥት ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት በነጻ ያገኛሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲደግፏቸው ለማድረግ መልዕክት እንደላኩና እስካሁን እንዳላገኟቸው የሚናገረው ኢዮብ በድጋሚ ጥያቄ እንደሚያቀርብላቸው ገልጿል። ሐሳቡ እውን ከሆነ ""መዋጮው ኪስ አይጎዳም። ብንኖርም ባንኖርም ቋሚና ቀጣይ ይሆናል። ጤናማው ሰው የሚያዋጣው ገንዘብ ወደ ኋላ መገልገያው እንዲሆን የጤና መድኅን አካል ማድረግም ይቻላል"" ሲል ተስፋውን ይናገራል። እንደ ኩላሊት፣ ካንሰር እና ልብ ያሉ ህመሞች ህክምና ሊሰጥባቸው እየተገባ ብዙዎች የሚሞቱባቸው ናቸው። ምናልባትም እንዲህ ባሉ የረድኤት ፕሮጀክቶች ችግሩን መቅረፍ ይቻላል ብሎ ያምናል። ""ባለቤቴ- ጀግናዬ"" ኢዮብ ከመታመሙ በፊት ለራሱና ለቤተሰቡ ሕይወት መለወጥ የሚተጋ ሰው ነበር። አሁን ግን የብዙዎችን ኃላፊነት ለመሸከም መርጧል። የማኅበሩ መስራች፣ ሥራ አስኪያጅ ብቻ ሳይሆን ሹፌር፣ ቀስቃሽ፣ ገንዘብ ሰብሳቢ የሆነባቸውን ጊዜያት ያስታውሳል። ሥራውን ""ፈጣሪ እና ህሊናዬ የተደሰቱበት ስለሆነ ኩራት እና ደስታ ይሰማኛል"" ሲል ይገልጸዋል። ለስምንት ዓመታት የኩላሊት እጥበት ሲያደርግ ወገቡ እና እግሩ ላይ ጉዳት ስለደረሰበት በድጋፍ ነው የሚንቀሳቀሰው። እንደ ቀድሞው የማኅበሩን ሥራዎች እንዳያከናውንም አድርጎታል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የሰውነት ክብደቱ ከ56 ወደ 46 ኪሎ ቀንሷል። ብርታት ከሚሰጡት በዋነኛነት የሚጠቅሰው ""ጀግናዬ"" የሚላት ባለቤቱን ነው። ""በጤናማነቴ ጊዜ ያፈራሁትን ከ1.5 ሚልዮን ብር በላይ ለማኅበሩ ሳውል ነገ ይሞታል ብላ ቅር አላላትም። ብር አንሶን የልጆቼን መኖርያ ቤት ስሸጥ እሷ የነበረንን ንግድ ቤት በመሸጥ ሹፌር ሆና ልጆቹን አስተማረች። ለዛሬ አብቅታኛለችና ጀግናዬ ናት።"" ሲታመም የሩቅና የቅርብ ቤተሰብ፣ ጓደኛም በአብዛኛው እንደሸሸው ይናገራል። ከልጆቹ ጋር ሰፊ ጊዜ ባለማሳለፉ፣ እንዳሻቸው ባለማዝናናቱም ያዝናል። ከኩላሊት ታማሚዎች ጋር ስቴድየም ዙርያ፣ ባዛሮች ላይ እንዲሁም ወደ መንግሥትና የግል ተቋማት እየሄደ እርዳታ ለማሰባሰብ ይሞክራል። ህክምናውን ትቶ የማኅበሩን ጉዳይ የሚከታተልባቸው ጊዜያትም አሉ። የኩላሊት ህመም ""ሳቄን፣ ደስታዬን፣ እግሬን አሳጥቶኛል"" ይላል። ከዚህ በተቃራኒው ""እውነተኛ ታጋይና ለወገን ቶርቋሪ አድርጎኛል"" ሲል ያለበት ሁኔታ ይገልጻል። በእሱ ማኅበር ውስጥ ይረዱ ከነበሩ ህሙማን መካከል ኋላ ላይ በራሳቸው ማኅበር መስርተው መንቀሳቀስ የጀመሩ ሰዎች መኖራቸው ያስደስተዋል። ህሙማንን ሲረዳ ከሚያገኘው እፎይታ በተጨማሪ ቤተሰቡ ሐሴት ይሰጠዋል። ""ሁሌም ሚስቴና ልጆቼ የተቃጠልኩትን ማቀዝቀዣዎቼ ናቸው"" ይላቸዋል። ሐኪሞች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ እንዳለበት ነግረውታል። ኩላሊት የሚሰጠው የቤተሰብ አባል ቢያገኝም የወጪው ነገር አሳሳቢ ነው። የማኅበሩ ስኬት ከሚላቸው መካከል ብዙ ገንዘብ ባይኖራቸውም ለህሙማን ገንዘብ ለመለገስ የሚፈቅዱ ሰዎች ማግኘታቸውን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን የሚያስደነግጥ ምስል ወይም የተጎዳ ሰው ቁስል ካልታየ በስተቀር በማኅበረሰቡ ዘንድ እምብዛም ሰዎችን የመርዳት ተነሳሽነት እንደሌለ አስተውሏል። የተጎዱ ሰዎችን ለይቶ በቀጥታ የመርዳት ልማድ ባለመኖሩ ማኅበረሰቡ እርዳታ የሚሰጠው ባገኘው አጋጣሚ፣ በየመንገዱ ለሚያገኘው ገንዘብ ጠያቂ ነው። ይህም በእርዳታ ስም የሚያጭበረብሩ እንዲበራከቱ መንገድ እንደከፈተም ያምናል። ሰዎች ባላቸው አቅም ተጎጂዎችን በእቅድ የመርዳት ባህል እንዲዳብሩ ይመኛል። የኩላሊት ህክምና በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሕግ አንድ ሰው ኩላሊቱ መሥራት ካቆመ ከቤተሰቡ ውጪ ኩላሊት ከሌላ ሰው መውሰድ አይችልም ይላል። ይህ ሕግ ቤተሰብ የሌላቸው ወይም ከቤተሰቦቻቸው ጋር የደም አይነታቸው የማይመሳሰል ሰዎችን ሕይወት አደጋ ውስጥ ጥሏል ይላል። ዘመድ፣ አብሮ አደግ ወይም ሌላ ለጋሽ ኩላሊት የሚሰጥበት አሠራር እንዲዘረጋ ለጤና ሚንስቴር ማሳሰቡንም ኢዮብ ይናገራል። ሌላው ክፍተት የኩላሊት ንቅለ ተከላ የሚከናወነው በጳውሎስ ሆስፒታል ብቻ መሆኑ ነው። ይህ አገልግሎት ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መነሳት ወዲህ መቋረጡም ሌላ ችግር ነው። በሌላ በኩል ንቅለ ተከላ ያደረጉ ሰዎች የመድኃኒት እጥረት ይገጥማቸዋል። የኩላሊት እጥበት የሚያደርጉ ሰዎችም እንዲሁ ተጓዳኝ የሰውነት መጠገኛ መድኃኒቶች ያጣሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ መድኃኒቶቹን ማግኘት ከባድ ነው። ያሉትም በጣም ውድ ናቸው። ኢዮብ ከታመመበት ከስምንት ዓመታት ወዲህ ብዙ ነገሮች እየተሻሻሉ መምጣታቸውን አይክድም። ""ትላንት የነበረውን ጨለማ ስለማውቀው የዛሬው የተሻለ ነው እላለሁ"" ይላል። ሆኖም ግን አሁንም ያሉ ክፍተቶች እንዲሸፈኑ ይጠይቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58126744 +sports የሞ ፋራህ የቀድሞ አሠልጣኝ ለአራት ዓመት ከአትሌቲክስ ታገዱ የሞ ፋራህ ቀድሞ አሠልጣኝ፣ አልቤርቶ ሳላዛር፣ ከአበረታች መድሀኒት ጋር በተያያዘ ከስፖርት ለአራት ዓመት ታገዱ። የ61 ዓመቱ ሳላዛር የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን የሆነው ፋራህን ማፍራት ���ቻለው የናይክ ኦሪጎን ፕሮጀክት ከ2011 እስከ 2017 ድረስ ሲመሩ ቆይተዋል። ውሳኔው የተላለፈው በአሜሪካው የፀረ አበረታች መድሃኒት ኤጀንሲ ለአራት ዓመት ያህል ምርመራ ሲደረግ ከቆየና ለሁለት ዓመት ያህል በፍርድ ቤት ክርክር ከተካሄደ በኋላ ነው። ምርመራው የተጀመረው ቢቢሲ በ2015 ፓናሮማ የተሰኘ ፕሮግራሙ ላይ ጉዳዩን ካቀረበ በኋላ ነው። • የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች • የጤፍ ቢራ አሜሪካ ውስጥ ገበያ ላይ ዋለ • ከአንደኛ ክፍል ዲግሪ እስኪጭኑ ከልጃቸው ጋር የተማሩት አባት ይህ የቢቢሲ ፕሮግራም ከአሜሪካው ፕሮፑብሊካ ድረገፅ ጋር በጋራ በመሆን በአሜሪካ ኦሪጎን ውስጥ በሚገኘው የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ስፍራ የሚሰጡ አበረታች መድሃኒቶችንና የሚካሄዱ ተገቢ ያልሆነ ተግባራትን አጋልጧል። የዩኬ ስፖርቶችን የሚቆጣጠረው ዩኬ አትሌቲክስ፣ የራሱን ምርመራ ያካሄደ ሲሆን ለስድስት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮናው፣ እንግሊዛዊው ፋራህ፣ ከ አሜሪካዊው ሳላዛር ጋር እንዲሰራ ይሁንታውን ሰጥቶት ነበር። በናይክ እየተከፈላቸው በርካታ የሳላዛር አትሌቶችን የሚያክሙት ዶክተር ጄፍሪ ብራውን ደግሞ ለአራት ዓመት ታግደዋል። ፋራህ ከሳላዛር ጋር የተለያየው በ2017 መሆኑን ጠቅሶ ከአበረታች መድሃኒት ጋር በተያያዘ አለመሆኑን ግን ገልጿል። https://www.bbc.com/amharic/news-49889111 +sports የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ ሊያግድ ነው "የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ከአንጎል ጤንነት ጋር በተያያዘ የወጣ ሪፖርትን ተከትሎ ከ12 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ እገዳ ለመጣል እያሰበ መሆኑ ተነገረ። በግላስጎው ዩኒቨርስቲ የሚገኙ ባለሙያዎች እንደደረሱበት የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች አንጎልን እያዳከመ ለሞት በሚያበቃ የአንጎል በሽታ የመጋለጥ እድላቸው ከሦስት ጊዜ በላይ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ ከህክምና ባለሙያዎች ጋር ከተነጋገረ በኋላ ያሉ አማራጮች ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ ተነግሯል። አሜሪካ ውስጥ ከአምስት ዓመት በፊት ጀምሮ ታዳጊ ህጻናት ኳስ በጭንቅላታቸው እንዳይመቱ እገዳ ተጥሏል። • ''ብሔርተኝነት'' እያጠላበት ያለው እግር ኳስ • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ' በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ በጭንቅላት (በቴስታ) ኳስ መምታት በአንጎል ደህንነት፣ በተለይም በህጻናት ላይ የሚኖረውን ውጤት በተመለከተ ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክር ተከትሎ ስኮትላንድ ውስጥ ክልከላ ሊቀመጥ እንደሚችል እየተነገረ ነው። አንድ ውስጥ አዋቂ እንዳሉት ""ጉዳዩ ታዳጊዎች በእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት ኳስ በጭንቅላታቸው የመግጨት አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን በልምምድ ወቅት በተደጋጋሚ ኳስን በጭንቅላት መምታትን ይመለከታል"" ብለዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ዋና የህክምና አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጆን ማክሊን ባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ ኳስን በጭንቅላት በመምታት በታዳጊ ተጫዋቾች ላይ የሚፈጠረውን ጫና ለመቀነስ እርምጃ እንዲወሰድ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ዶክተሩ እንዳሉት ""ከስኮትላንድና ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ጋር በመሆን ተቀባይነት ያለው መመሪያ ለማዘጋጀት ሥራ ጀምረናል። "" • አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ • ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ? ""ለምሳሌም ለታዳጊዎች የሚሰጠውን ኳስ በጭንቅላት የመምታት ልምምድ የተወሰነ እንዲሆንና አንጎላቸው ለማገገም እንዲችል በሳምንት የሚሰጣቸው ስልጠና አንድ ጊዜ ብቻ እንዲሆን ማድረግን የመሰለ ቀላል እርምጃ ሊሆን ይችላል"" ብለዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ውስጥ አዋቂ እንዳሉት የማ���በሩ አመራር ቡድን ታዳጊዎች ኳስ በጭንቅላታቸው መምታትን በተመለከተ የቀረበውን የባለሙያ አስተያየት ይደግፈዋል ብለዋል። በግላስጎው ዩኒቨርስቲ ለተደረገው ጥናት መነሻ የሆነው የቀድሞው ዌስት ብሮም አጥቂ ጄፍ አስቴል ለህልፈት የተዳረገው በተደጋጋሚ በጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ ነው የሚል አስተያየት ከተሰነዘረ በኋላ ነው። በ2002 (እኤአ) አስቴል ከሞተ በኋላ፣ በጥናቱ መዘግየት ቤተሰቦቹ ቁጣቸውን በመግለጻቸው፣ በእግር ኳስ ማህበሩና በፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር አነሳሽነት ጥናቱ ተደርጓል። የሟቹ እግር ኳስ ተጫዋች ሴት ልጅ የሆነችው ዳውን ጥናቱ ይፋ ከተደረገ በኋላ በውጤት ""እንደደነገጠች"" ተናግራለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-50198595 +business ኢትዮጵያ ከግዙፉ የወደብ አስተዳዳሪ ድርጅት ጋር ውል ገባች "ኢትዮጵያ ከዓለማችን ግዙፍ የወደብ አንቀሳቃሾች መካከል አንዱ ከሆነው ዲፒ ዎርልድ ጋር የስምምነት ውል ገብታለች። ስምምነቱ ኢትዮጵያን ከሶማሊንዱ በርበራ ወደብ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ነው ተብሏል። የዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ ንብረት የሆነው ዲፒ ዎርልድ ፕሮጀክቱ ""ቀጣናውን ለማበልፀግና ምጣኔ ሃብታዊ አቅምን ለማሳደግ ውይይት እንዲደረግ መንገድ ይከፋታል"" ብሏል። ፕሮጀክቱ ከራስ ገዟ የሶማሊላንድ በርበራ ወደብ ሁለቱን ሃገራት እስከሚያገናኘው የዋጃሌ ከተማ ድረስ ይዘረጋል። የወደቡን ፕሮጀክት በትብብር የሚገነቡት የአቡ ዳቢ ዕድገት ፈንድና የዩናይትድ ኪንግደም ዓለም አቀፍ ዕድገት ናቸው። ግንባታው በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ዲፒ ዎርልድ ከኢትዮጵያ ጋር በተገባው ውል [ሜሞራንደም ኦፍ አንደርስታንዲንግ] ውል መሠረት ዕቃ አስመጪና ላኪ ድርጅቶች በጥምረት እንዲሰሩ ያስችላል ይላል። ድርጅቱ 1 ቢሊዮን ዶላር አፍስሶ ደረቅ ወደብ፣ ጎተራ፣ መጋዘን እንዲሁም ማቀዝቀዣ የተገጠመላቸው ማከማቸዎች ለመገንባት አቅዷል። ""በርካታ ሥራዎች ይፈጥራል፤ አዳዲስ ቢዝነሶችና ኢንቨስተመንቶች ወደ ኮሪደሩ እንዲመጡ ያስችላል፤ አልፎም ሃገሪቱ ከዓለም አቀፍ ንግድ ጋር ያላትን ግንኙነት ያጠናክራል"" ብለዋል የዲፒ ዎርልድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሱልጣን አሕመድ ቢን ሱሌይማን። በርበራ ወደብ በቅርቡ ሰፊ የመልሶ ግንባታ እንደተሰራለት ይታወሳል። በፈረንጆቹ 2016 ሶማሊላንድ ዲፒ ዎርልድን ቀጥራ ወደቧን ሰፋ አድርጎ እንዲገናባላት የ30 ዓመት ስምምነት መፈራረሙ አይዘነጋም። በወቅቱ በየብስ የተከበበችው ኢትዮጵያ ከፕሮጀክቱ 19 በመቶ ድርሻ መጋራቷ ይታወሳል። 30 በመቶው ድርሻ የተያዘው በሶማሊላንድ ሲሆን የተቀረው 51 በመቶ ድርሻ የዲፒ ወርልድ ነው። ዲፒ ዎርልድ በ442 ሚሊዮን ዶላር ወደቡን ለማስፋፋትና በዓመት 2 ሚሊዮን 20 ቻማ ርዝማኔ ያላቸውን ኮንቴነሮች ለመትከል ተስማምቷል። ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከሁሉም ጎረቤት ሃገራት ጋር የንግድ መስመር ለመዘርጋት እንቅስቃሴ ጀምራለች። ይህ እንቅስቃሴ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ላላት ኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት አጋዥ ነው እየተባለ ነው። በስምምነቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ሃገራቸው ""የወደብ መንገዶቿን የተሰባጠረ ለማድረግና ዕቃና አገልግሎት የሚመላለስበትን አማራጭ ለማስፋት እየሠራች ነው"" ሲሉ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከ95 በመቶ በላይ ዕቃዎችን የምታመላልሰው በጎረቤት ሃገር ጅቡቲ ወደብ በኩል ነው። በፈረንጆቹ 2018 ኢትዮጵያ 750 ኪሎ ሜትር የሚዘረጋ በኤሌክትሪክ የሚሠራ ባቡር ወደ ጅቡቲ ወደብ መዘርጋቷ ይታወሳል። የባቡር ግንባታው 4.5 ሚሊዮን ዶላር አውጥቷል። አሁን የተገባው የበርበራ ወደብ ስምምነት በጅቡቲ በኩል ያለውን የዕቃዎች ምልልስ ወደ 50 በመቶ ዝቅ ሊያደርገው ይችላል ሲሉ ባለሙያዎች ይገምታሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-57029652 +health ኮሮናቫይረስ፡ የዓለም ጤና ድርጅት ለአዲሶቹ የኮቪድ ዝርያዎች የግሪክ ስያሜዎችን ሰጠ የዓለም ጤና ድርጅት ለአዳዲሶቹ የኮቪድ-19 ዝርያዎች ስም ለመስጠት የሚያስችል ስርአት ማዘጋጀቱን አስታወቀ። ከዚህ በኋላም ድርጅቱ የቫይረሱን አይነቶች ለመለየት የግሪክ ፊደላትን የሚጠቀም ሲሆን በዩናይትድ ኪንግደም፣ ደቡብ አፍሪካና ሕንድ ውስጥ የታዩት አዳዲስ ዝርያዎች መጀመሪያ ስያሜ ይሰጣቸዋል። ለምሳሌም በዩናይትድ ኪንግደም የታየው አዲሱ ቫይረስ ዝርያ 'አልፋ' የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። የደቡቡ አፍሪካው 'ቤታ' የተባለ ሲሆን በሕንድ በርካቶችን ያጠቃው የቫይረስ አይነት ደግሞ 'ዴልታ' ተብሎ እንደሚጠራ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ስያሜዎቹን ያስተዋወቅኩት አንደኛ በንግግር ወቅት ቀላል ለማድረግና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በቫይረሱ ዙሪያ የሚኖሩ የተለያዩ ማግለሎችን ለማስቀረት ነው ብሏል። ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ወር መጀመሪያ አካባቢ የሕንድ መንግሥት በአገሪቱ የተገኘውን የኮቪድ-19 አዲስ ቫይረስ 'ቢ.1.617.2' የሚል ስያሜ መስጠቱን ተከትሎ በርካታ ትችቶችን አስተናግዶ ነበር። ''የትኛውም አገር አዲስ የቫይረሱ አይነቶችን ሪፖርት በማድረጉ መገለል ሊደርስበት አይገባም'' ብለዋል የዓለም ጤና ደርጅት ቴክኒካል መሪ የሆኑት ማሪያ ቫን ኬርኮቭ። አክለውም አገራት አዲሶቹ ቫይረሶች ላይ ጠበቅ ያለ የክትትልና የምርመራ ስራ እንዲያከናውኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። አዲሱ የቫይረሶቹ ስያሜ ከተለያዩ ነገሮች አንጻር ከግምት ውስጥ እንደገባ የተገለጸ ሲሆን የሁሉም ቫይረሶች ስም ዝርዝር በዓለም ጤና ድርጅት ድረገጽ ላይ ይፋ ተደርጓል። እነኚህ የግሪክ ፊደላት አሁን በጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙትን ሳይንሳዊ ስሞች የሚተኩ አይደለም። አዲሶቹ የኮሮናቫይረስ አይነቶች ከ24 የሚበልጡ ከሆነ የተዘጋጀው ስርአት ፊደላት ያልቁበታል። በዚህም መሰረት አዲስ ስያሜ የመስጠት ስርአት ይዘረጋል ብለዋል ማሪያ ቫን ኬርኮቭ። ''እኛ እያልን ያለነው እንደ ቢ.1.617.2 ያሉ ሳይንሳዊ ስያሜዎችን ሙሉ በሙሉ መቀየር ሳይሆን ሁሉም ሰው የሚረዳው አይነት ስያሜ እንስጠው ነው። ስያሜው ቀለል ሲል ማህበረሰቡ በዕለት ተዕለት ግንኙነቱ ይጠቀማቸዋል'' ብለዋል። ሰኞ ዕለት የዩናይትድ ኪንግደም መንግስትን የሚያማክሩ ተመራማሪዎች አገሪቱ በሶስተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል። በዋነኛነት ሰዎችን እያጠቃ የሚገኘውም 'ዴልታ' የሚል ስያሜ የተሰጠው የሕንዱ ዝርያ ነው። ይህ ዝርያ 'አልፋ' የሚል ስያሜ ከተሰጠው የዩኬው ዝርያ በበለጠ መልኩ በቶሎ መሰራጨት የሚችል ሲሆን በዩኬ ለጨመረው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ምክንያት ነው። በሌላ በኩል በቬትናም የተስተዋለው አዲሱ የቫይረስ አይነት በሕንድ እና ዩናይትድ ኪንግደም ከታዩት የቫይረሱ ዝርያዎች የተቀላቀለ ሲሆን በቀላሉ በአየር መተላለፍ የሚችል ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-57313043 +politics ምርጫን ተከትሎ የተቀሰቀሰው የሶማሊያ ውዝግብ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ያመራ ይሆን? "በሶማሊያ ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ መዘግየቱ አለመግባባትን እና በፖለቲከኞች መካከል አለመተማመንን አባብሷል። ይህንንም ተከትሎ በመዲናዋ ሞቃዲሾ የሰዎች ሕይወት የጠፋበት አመጽ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አገሪቱን ወደ ከፋ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። በመዲናዋ ሞቃዲሾ በፌዴራል ኃይሎች እና በታጠቁ የተቃዋሚ ታማኝ ኃይሎች መካከል ከቀና�� በፊት በተነሳ ግጭት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገድለዋል። ግጭቱ ይቀጥላል በሚል በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች 'ሠላማዊ' ወደሚሏቸው መንደሮች ተሰደዋል። ክፍተቱ ለአል-ሻባብ የአፍሪካ ቀንዷን አገር የበለጠ ለማተራመስ መልካም አጋጣሚ ሊሆነው ይችላል። ታጣቂዎቹ ከቅርብ ወራት ወዲህ ብቻ በምርጫው ዙሪያ ውይይቶች በተካሄዱባቸው ቦታዎች ላይ በርካታ ጥቃቶችን አካሂደዋል። የአገሪቱ የታችኛው ምክር ቤት የፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆን የስልጣን ዘመን በሁለት ዓመት ይራዘም ሲል ወሰነ። ከሁለት ሳምንት በፊት ከተላለፈው ውሳኔ በኋላ የአገሪቱ የፖለቲካ ክፍተቶች ተባብሰዋል። ከወራት ውይይቶች በኋላ ውሳኔው ሲጸድቅ የፌዴራል መንግሥቱ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሕዝባዊ ምርጫዎችን እንዲያደራጅ ቢያዝም የአገሪቱን የምርጫ ቀውስ ማስቆም አልቻለም። የሶማሊያ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና የተቃዋሚ ፖለቲከኞች የሥልጣን ማራዘሙን ውድቅ በማድረግ ፋርማጆን ሥልጣንን የሙጥኝ ብለዋል ሲሉ ከሰዋል። የተነሳባቸው ተቃውሞና ሊከተል የሚችለው ቀውስ ያሰጋቸው ፕሬዝዳንቱ የሥልጣን ዘመናቸውን የማራዘም ፍላጎታቸውን እንዲተዉ አስገድዷቸዋል። ነገር ግን ውጥረቱ በጎሳ ፉክክር ይበልጥ እየከረረ ነው። ከአስርት ዓመታት የእርስ በእርስ እና የታጣቂዎች ግጭት በኋላ የተገኘውን አንፃራዊ መረጋጋት ሊቀለበስ የሚችልም ነው። ቁልፍ ተዋናዮች እና ምላሾች ተቃዋሚዎች የፋርማጆ ሥልጣን የካቲት 8 ስላበቃ ከእንግዲህ ለፕሬዝዳንትነታቸውን እውቅና አንሰጥም ብለዋል። ናሽናል ሳልቬሽን ፎረም (ብሔራዊ አገርን የማዳኛ መድረክ እንደማለት ነው) ተቋቁሟል። ፎረሙ ተሰሚ በሆኑ ተቃዋሚዎች የተቋቋመ ነው። የፋርማጆ ቀንደኛ ተቃዋሚ የሆኑት የምክር ቤት አፈ ጉባኤ አብዲ ሀሺ አብዱላሂ፣ የጁባላንድ እና ፑንትላንድ መሪዎችን ያካተተ ጥምረት ነው። ሕገ መንግሥታዊ ባልሆነው የሥልጣን ማራዘሚያ ላይ ""አስፈላጊ እርምጃዎችን እንወስዳለን"" ሲሉም ዝተዋል። የሴኔቱ አፈ ጉባኤ አብዱላሂ እንዳሉት፤ ፕሬዚዳንቱ የውሳኔ ሐሳቡን ለማጽደቅ የላይኛውን ምክር ቤት ሳያቀርቡ ማራዘማቸው ሕገ መንግሥቱን የሚፃረር ነው። የፑንትላንድ ፕሬዝዳንት ሰኢድ አብዱላሂ ዴኒ እና የጁባው አቻቸው አህመድ መሐመድ ኢስላም በሞቃዲሾ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ነበር። ""ሶማሊያን ከማይቀረው የትርምስ አዘቅት ውስጥ እንዳትገባ እንዲያድኑ"" ጠይቀዋል። የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ምክር ቤት ፋርማጆን ለመተካት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ጥምረት ነው። በቀድሞው ፕሬዝዳንት ሻሪፍ ሼህ አህመድ የሚመራ ሲሆን ፕሬዚዳንቱን ""የጦር አበጋዝ"" ብለዋቸዋል። የሃውያ ንዑስ ጎሳ አባላት ተደማጭነት ካላቸው ጎሳዎች መካከል ነው። ለአንድ ቀን በመዲናዋ ሞቃዲሾ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ ሥልጣን የማራዘሙን ውሳኔ ውድቅ አድርገውታል። አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና የአውሮፓ ሕብረት ሥልጣን የማራዘሙ ውሳኔ ሶማሊያ ወደ ሰላምና መንግሥት ግንባታ የምታደርገውን ጉዞ የሚያደናቅፍ ነው ብለዋል። ግንኙነታቸውን በድጋሚ እንደሚያጤኑትም አስጠንቅቀዋል። አሜሪካ ""ሰላምና መረጋጋትን በማደናቀፍ"" በሥልጣን ማራዘሙ በተሳተፉት ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል ዝታለች። የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ሥልጣን ማራዘሙን ውድቅ አድርጎታል። የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የሶማሊያ መሪዎች በምርጫ ውዝግቡ ዙሪያ ውይይት እንዲቀጥሉ ያቀረበውን ሐሳብ እንደሚደግፍ አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ከፍተኛ ተቃውሞ ቢቀርብባቸውም በታችኛው ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴዎች እና ���ጋልሙዱግ፣ በሂውማሌ እና በደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ሰፊ ድጋፍ አላቸው፡፡ በቋፍ ላይ ያለ የፌዴራል ሥርዓት የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሥርዓት ሥር የሰደደውን የጎሳ ግጭት ለማቆም እና የአንድነት መንግሥት ለመመስረት የሚደረገውን ጥረት በመሰናከሉ የተመሠረተ ነው። ይህን ተከትሎም የተቆራረጠ እና ደካማ ቢሆንም ብሔራዊ ደኅንነት ግንባታው እያዘገመም ቢሆን እንዲጓዝ መንገዱን ጠርጓል። አገሪቱ ከ30 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሀብት ሥርዓት ለመቀላቀል የፋይናንስ ተቋማቷን እንደገና አደራጅታለች። ምርጫው ያስከተለው አለመረጋጋት በማዕከላዊ መንግሥት እና ቀድሞውንም የፋርማጆን ሥልጣን 'በሚያኮስሱት' አንዳንድ የክልል መንግሥታት መካከል ውዝግቡን አጡዞታል። እአአ በመስከረም 2018 አምስት የአገሪቱ የክልል ፕሬዚዳንቶች በሥልጣን እና በሀብት ክፍፍል አለመግባባት ምክንያት ከፌዴራል መንግሥት ጋር እንደማይተባበሩ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ለምላሽ አልዘገዩም። ክልሎችን በራሳቸው ቁጥጥር ስር ማድረግ ጀመሩ። ተቀናቃኝ ሊሆኑ የሚችሉትን በመንቀል አጋሮቻቸውን በጋልሙዱግ እና በደቡብ ምዕራብ ግዛቶች አስቀመጡ። የፌዴራሉ መንግሥት በፑንትላንድ እና በጁባላንድ ባሉ ምርጫዎች ላይ ተመሳሳይ ተጽዕኖ ማሳደር አልቻለም። የእነዚህ አካባቢ መሪዎች ፋርማጆ እንደገና እንዳይመረጡ እየሠሩ ነው። የፖለቲካ ህልውናቸው የተመሠረተው በዚሁ ላይ ነው። የመስከረም 17ቱ ስምምነት ብሔራዊው የምርጫ ኮሚሽን ቀጥተኛ ተሳትፎ ያለው ሕዝባዊ ምርጫ ለማድረግ እንደማይቻል አስታውቋል። ተዓማኒነት ያለው ምርጫ ለማዘጋጀት እስከ 13 ወር ድረስ እንደሚያስፈልገው እአአ ሰኔ 2020 ለሕዝብ እንደራሴዎች ገልጿል። የጁባላንድ፣ ፑንትንትላንድ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫውን መዘግየት ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆኑም። እአአ ሐምሌ 2020 አስደንጋጭ ነበር የተባለለት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ኬይሬ ከሥልጣን መነሳት በምርጫው ሂደት ላይ ያላቸውን እምነት ይባስ ሸረሸረው። የጁባላንድ እና የፑንትላንድ መሪዎች በማዕከላዊው ዱሳማሬብ ከተማ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልነበሩም። በስብሰባው ላይ ከምርጫ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ስምምነት ተደርሷል። የአማጺያኑ አመራሮች አድሏዊ ነው ሲሉ የምርጫ ኮሚሽኑ እንዲፈርስ ጠይቀዋል። እአአ መስከረም 17 ቀን 2020 ከሳምንታት የዓለም አቀፍ ግፊት በኋላ በምርጫ ሁኔታዎች ላይ ስምምነት ተፈረመ። በስምምነቱ መሠረት ሁለት የምርጫ ክልሎች በእያንዳንዱ ክልል ይኖራሉ። ምርጫዎች የሚካሄዱት በየክልል ተሰብሳቢዎች ላይ ተመስርቶ ሲሆን በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ውስጥ 101 የምርጫ ልዑካን ድምጽ ይሰጣሉ። በአማጽያን ጥያቄ መሠረት ምርጫውን በበላይነት የሚቆጣጠር ብሔራዊ እና ክልላዊ የምርጫ ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙ ተወሰነ። የጁባላንዱ ማዶቤ እና የፑንትላንዱ ዴኒ በፌዴራል መንግስት የተቋቋመውን የምርጫ ኮሚሽን ባለመቀበላቸው የስምምነቱ ትግበራ እንቅፋት ገጠመው። የጸጥታ አዛዦች እንዲነሱ እና ፓርላማው እንዲበተንም ጠይቀዋል። የምርጫውን መዘግየት አስቀድሞ የገመተው የፌዴራሉ ፓርላማ እአአ ኅዳር 2020 አዲስ ተመራጮች እስኪተኩ ድረስ ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላልፏል። የዘር ፖለቲካ እና ግጭት በምርጫው ላይ በተፈጠረው ክፍፍል ላይ ብሔራዊ ማንነት እና የጎሳ ማንነት ልዩነትም ሚና ተጫውተዋል። አለመተማመን እየጠነከረ ሲሄድ ፖለቲከኞች እና ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣናት ወደ ጎሳቸው መመሸግ ጀመሩ። እነዚህም በጎሳ ሚሊሻዎች፣ በጎበ��� አለቆች እና በቀድሞ የጦር መሪዎች የሚጠበቁ ናቸው። የተወሰኑ የተቃዋሚ የፓርቲ አመራሮች ለትጥቅ ትግል መዘጋጀት ያዙ። የጦር መሣሪያዎችና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የገዙም አሉ። በመዲናዋ ሞቃዲሾ የዘገየውን ምርጫ የሚቃወሙ ሰልፈኞችን በሚደግፉ ወታደሮች እና በፖሊስ መካከል መጋቢት 15 ቀን ግጭት ተፈጥሯል። የፖሊስ መኮንኖቹ በቱርክ የሰለጠነው ልዩው የሃርማድ የፖሊስ ኃይል አባላት ነበሩ። ከዚህ በፊት መንግሥት ፍላጎቱን በክልል መንግሥታት ላይ ለመጫን ልዩ ኃይሉን ይጠቀም ነበር። የቀድሞው የሞቃዲሾ የፖሊስ አዛዥ ሳዲቅ ኦማር ሃሰን (ሳዳቅ ጆን) በምርጫ ውዝግብ ላይ ለመወያየት የተዘጋጀውን የፓርላማ ስብሰባ በማገድ እአአ ሚያዝያ 13 ፊታቸውን መንግሥት ላይ አዞሩ። ከኃላፊነት ተነስተው ማዕረጋቸውም ተገፈፈ። የቀድሞው የፖሊስ አዛዥ ከቀናት በኋላ በጎበዝ አለቆች እና ከጎሳቸው በተገኙ ሚሊሺያዎች እየተጠበቁ በከተማው በዳይናል አካባቢ ካምፕ መሠረቱ። መንግሥት የታጠቁ የጸጥታ ኃይሎችን በአቅራቢያው ወደሚገኙ አካባቢዎች በማሰማራቱ ውጥረቱ ዋና ከተማዋን አዳርሷል። በኋላ ላይ ሁኔታው ተረጋጋ። በፋርማጆ ላይ የተጀመረው አዲስ አመጽ የጎሳ ጦርነት ቀስቅሶ አገሪቱን በቀላሉ ወደ የእርስ በእርስ ግጭት እንዳያስገባ ያሰጋል። የፖለቲካ እና የደኅንነት አንድምታዎች የአልሻባብ ታጣቂዎች በ2011 ከሞቃዲሾ ከተባረሩ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦርነት ድባብ በከተማዋ ሰፍሯል። ጂሃዳዊው ቡድን ከአብዛኞቹ ዋና ዋና ከተሞች ተጠራርጎ ተባሯል። ብሔራዊው ጦር፣ በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት ልዑክ እና በአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ ጥረት ቢያደረጉም ቡድኑም አሁንም በማዕከላዊ እና በደቡባዊ ክልሎች ኃይሉ እንዳለ ነው። አል-ሸባብ በሞቃዲሾ በርካታ ጥቃቶችን ፈጽሟል። የተፈጠረውን ሁከት በመጠቀምም እንቅስቃሴዎቹን ለማጠናከር ሊጠቀምበት ይችላል። እንደመገናኛ ብዙሃን ከሆነ አዲስ ጉዳት የደረሰባቸው ሕንፃዎች፣ ታንኮች እና የጦር ተሽከርካሪዎች ላይ የታጠቁ ወታደሮች እና ዋና ዋና መንገዶች ተዘግተዋል። በግል በሚተዳደረው ራዲዮ ኩልሚዬ የሚሠራ አንድ ጋዜጠኛ እንደተናገረው፤ ትራፊክ እና የማዘጋጃ ቤት ፖሊሶች በጎዳናዎች የሉም። የአል-ሸባብ ጥቃትን ለመከላከል በዋና ዋና መንገዶች ላይ የተተከሉ የደኅንነት ካሜራዎችም ወድመዋል። በትጥቅ የተደገፈው አመጽ የፕሬዚዳንት ፋርማጆን የእውቅና ጥያቄ የከድጡ ወደ ማጡ የወሰደው ሲሆን፤ በምርጫ ውዝግብ ላይ የተከፈተውን የውይይት መስኮትም የሚዘጋ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/56916800 +health በኢትዮጵያ የተካሄደው እና አስር ባለሙያዎች የተሳተፉበት ተደራራቢ የልብ ቀዶ ሕክምና "የልብ ቀዶ ህክምና ከፍ ያለ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ህክምና ሲሆን በተለይ ተደራራቢ ችግር ሲኖር ደግሞ ሥራው በእጅጉ የተወሳሰበ ስለሚሆን ከፍ ያለ ልምድና ቴክኖሎጂ ባላቸው አገራት ውስጥ እንዲካሄድ ይመከራል። ሰኞ እሁድ 18/2013 ዓ.ም ከዚህ በፊት 'ኢትዮጵያ ውስጥ አልተደረገም' የተባለ እና ስድስት ሰዓታትን የፈጀ የልብ ቀዶ ጥገና በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ኤሎዚየር የልብ ህክምና ማዕከል ውስጥ በአንድ ጊዜ ሁለት የቀዶ ህክምናው የተደረገላቸው ግለሰብ የ55 ዓመት ጎልማሳ ናቸው። በህመምተኛው ግለሰብ ልብ ላይ በአንድ ጊዜ የተሰራው ሁለት ቀዶ ህክምና ሲሆን፣ አንደኛው የልብ የደም ቧንቧዎች በሚዘጉበት ጊዜ የደም ቧንቧን ከሌላ የሰውነት ክፍል በመውሰድ የተዘጋው ቦታ ላይ በመተካት የተከናወነ የልብ የደም ስር ነቅሎ መትከል (ሲኤቢጂ) ነው። ሌላኛው ደግሞ 'ኦርቲክ ቫልቭ' ወይም ደግሞ አንደኛው የግራ የልብ ክፍል በር ሙሉ በሙሉ ተ��ግቶ ደም ከቀኝ የልብ ክፍል ወደ አኦርታ (Aorta) መውጣት ሲቸገር የልብ በር ቀዶ ህክምና (ቫልቭ) የሚባለው ነው። በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተከናወነው ይህንን ስኬታማ የቀዶ ህክምና ካከናወኑት ሐኪሞች መካከል አንዱና በኢትዮጵያ የልብ ሕክምና ማዕከል ውስጥ የሚሰሩት ዶ/ር ፈቃደ አግዋር ለቢቢሲ እንደተናገሩት ""እነዚህን ሁለት ቀዶ ህክምናዎች እኚህ ግለሰብ ላይ በአንድ ጊዜ ተደርገዋል። ይህ በቀዶ ሕክምና ሙያ በጣም ትልቅ የሚባል ስኬት ነው። ቀዶ ህክምናው በአገራችን ባለሙያዎች ሲሰራ የመጀመሪያው ነው።"" ለስድስት ሰዓታት የተካሄደውን የቀዶ ህክምና ሂደት የመሩት ዶ/ር ፈቃደ እንደሚሉት አሁን በአንድ ህመምተኛ ላይ በአንድ ጊዜ የተከናወነው ቀዶ ህክምና በተናጠል ከሚሰራው ውስብስብና አስቸጋሪ ነው። በዚህ ሂደት ሁለቱን ቀዶ ህክምናዎች በአንድ ልብ ላይ ሲሰራ የልብንና የሳንባን ሥራ ተክቶ የሚሰራው ማሽን አገልግሎቱን አብቅቶ ወደተፈጥሯዊው ሂደት ሲመለስ እንዴት ይሆናል? የሚለው ዋነኛው አሳሳቢ ጉዳይ ሲሆን ባለሙያዎቹም አስፈላጊውን ጥንቃቄና ክትትል አድርገዋል። ይህ ተደራራቢ ቀዶ ህክምና አደጋን የሚያስከትል በመሆኑ እያንዳንዱን ለውጥ ባለሙያዎቹ በቅርበት ሲከታተሉት ነበር። ""ከኦፕራሲዮን ስንወጣ ሐዘን ይዘን ልንወጣ እንችላለን። የማይነሳ ልብ ሊሆን ይችላል። በ24 ሰዓት ውስጥ ማንኛውም አደገኛ ነገር ሊከሰት ይችላል። ይህንን ሁሉ ነገር ከአዕምሯችን ጓዳ ውስጥ አድርገን ነበር የሰራው። ነገር ግን ሁሉም ነገሮች አልተከሰቱም"" ብለዋል ዶ/ር ፈቃደ። ከመነሻው ቀዶ ህክምናው እስከ ሰባት ሰዓት የሚደርስ ጊዜን ሊወስድ ይችላል ተብሎ የታሰበ ቢሆንም በስድስት ሰዓታት ውስጥ በስኬት መጠናቀቁ ተነግሯል። ይህ እጅግ ከፍ ያለ ጥንቃቄን የሚፈልገው ተደራራቢ የልብ ቀዶ ህክምና ሂደት ሲከናወን ውጥረት የተሞላበት ቢሆንም ምንም አይነት ችግር እንዳላጋጠማቸው ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። ""ምንም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ አልተፈጠረም ነበር። ጮክ ብለን እንኳን የተነጋገርንበት ጊዜ እንኳ አልነበረም። በስድስት ሰዓቱ ውስጥ በተቻለን አቅም ተረጋገግተን የአስቴር ዘፈንን እየሰማን ነበር የሰራነው"" ብለዋል ዶ/ር ፈቃደ። የልብ ቀዶ ህክምና በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የልብ ቀዶ ህክምና መከናወን ከተጀመረ ጥቂት ዓመታት ብቻ ነው የተቆጠሩት። ከዚያ ውጪ ልብ ቀዶ ህክምና ይከናወን የነበረው ከውጪ አገር በሚመጡ ባለሙያዎች በተመላላሽነት፣ ለአጭር ጊዜ ነበር። የልብ ቀዶ ህክምና በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ሲከናወንባቸው በቆዩት አራት ዓመታት ውስጥ፣ አሁን በአንድ ጊዜ በተሳካ ሁኔታ በአንድ የልብ ታማሚ ላይ የተደረገው ቀዶ ህክምና ተደርጎ አይታወቅም። ነገር ግን ሁለቱንም ቀዶ ህክምናዎች በተናጠል ሲከናወኑ መቆየታቸውን ያስታወሱት ዶ/ር ፈቃደ፣ ሁለቱንም አንድ ላይ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ልምዱ ስላልነበረና ውስብስብ በመሆኑ ሳይደረግ መቆየቱን ይናገራሉ። ስለዚህም እንዲህ አይነቱ ተደራራቢ ቀዶ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎችም የነበራቸው አማራጭ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው ወደ ውጪ አገር ሂዶ መታከም ነበር። ለዚህም ከ50 ሺህ ዶላር በላይ መክፈልን ይጠይቃል። በርካታ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ ተደራራቢ የልብ ችግር ሲያጋጥማቸው ህክምና ለማግኘት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ወደ ሕንድ፣ ቱርክና ታይላንድ ይሄዳሉ። ዶ/ር ፈቃደ እንደሚሉት በስኬት የተከናወነው ቀዶ ህክምና ለዘርፉ ታላቅ ዕመርታ ነው ""የመጀመሪያው የቀዶ ህክምና ፈተናዎች ይኖሩታል። ነገር ግን አንድ ጊዜ በስኬት ከተከናወነ ለቀጣይ ህክምና መንገዱ ይከፈታል"" በማለት ሰዎች ህክምናውን ለማግኘት ወደ ውጭ አገር መሄድ አይጠበቅባቸውም ብለዋል። የልብ ህመም በኢትዮጵያ ከአኗኗር ዘይቤ መለወጥ ጋር ተያይዞ ተላላፊ ካልሆኑ የጤና ዕክሎች መካከል የሚጠቀሱት የልብ ህመሞች እየተስፋፉ መሆናቸው ይነገራል። በተለይ ከፍ ያለ ሙያ፣ ጥንቃቄና ወጪን የሚጠይቁት የልብ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መሆናቸውን ባለሙያዎች ይናገራሉ። በኢትዮጵያም የተለያዩ የልብ ችግሮች የሚያጋጥማቸው ሰዎች ቁጥር ቀላል የሚባል እንዳልሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ፈቃደ፣ በስፋት የሚያጋጥመው ዋነኛው የልብ ቫልቭ ችግር መሆኑን ይገልጻሉ። የልብ በሮች መጥበብ ወይም ወደ ኋላ ማፍሰስ ደግሞ ሌላኛው እክል ነው። በተጨማሪም ""የልብ የደም ቧንቧዎች መደፈን በአሁኑ ወቅት እየበዛ የመጣ ነው"" ሲሉ ያክላሉ። ""ከደም ግፊት እና ከስኳር ህመም ጋር ተያይዞ የሚመጣ የልብ የደም ስሮች መዘጋት ወይም ደግሞ 'ኮሮናሪ አርተሪ ዲዚዝ' የምንለው በአሁኑ ወቅት እየጨመረ ይገኛል።"" የተሳካው ቀዶ ህክምና የተደረገላቸው ታካሚ ላይ ሁለት ተደራራቢ የልብ ችግሮች በአንድ ላይ በመከሰታቸው ችግሩን የተወሳሰበ በማድረግ ታማሚውን ለከፍተኛ ችግር እንዳጋለጣቸው ዶ/ር ፈቃደ ይናገራሉ። በ55 ዓመቱ ጎልማሳ ላይ በተደራራቢነት ያጋጠሙት የልብ ችግሮች በተለያዩ ሰዎች ላይ በተናጠል መከሰታቸው የተለመደ መሆኑን ሕክምና ባለሙያው ያስረዳሉ። ነገር ግን ሁለቱም አንድ ታካሚ ላይ በተደራራቢነት መከሰታቸው አልፎ አልፎ የሚያጋጥ ነው ሲሉም አክለዋል። ታካሚውና ቤተሰባቸው ታማሚው ወደ ህክምና ሲመጡ የገጠማቸው የልብ ችግር አንድ ብቻ እንደሆነ ነበር ያሰቡት። ነገር ግን ሐኪሞቹ ሰፋ ያለ ምርመራ ሲያደርጉ ሌላ ተደራቢ ችግር መኖሩ ተረዱ። ያለውን ሁኔታ የተገነዘቡት የታማሚው ቤተሰቦቹ ሁለቱንም ችግሮች በአንድ ጊዜ በቀዶ ህክምና ማስተካከል እንደሚያስፈልግ በተነገራቸው ጊዜ ""እውነታውን ተቀብለው እምነታቸውን በእኛ ላይ ጣሉ"" ይላሉ ዶ/ር ፈቃደ። ቀዶ ህክምናው ከቀኑ 8 ሰዓት ተጀምሮ ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ተጠናቀቀ። ታካሚውም ከኦፕራሲዮኑ ከወጡ በኋላ በ4 ሰዓት ውስጥ መንቃት ቻሉ። ""ሲቀጥልም ሰውነታቸው ሙሉ በሙሉ እንደሚሰራ ካረጋገጥን በኋላ ማሽኑን ከሰውነታቸው መንቀል ችለናል። በሚቀጥለው 24 ሰዓት ውስጥም ያስገባናቸውን ጎማዎች ሙሉ በሙሉ በማስወጣት ከአልጋ እንዲወጡ ተደረገ"" ይላሉ ዶ/ር ፈቃደ። ""ሁሉም ነገር የተሳካ ነበር። ታካሚውም ያስገባንላቸው ሁሉም ጎማዎች ወጥተውላቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመሳሳቅ እና ለመጨዋወት በቁ"" በማለት የቀዶ ህክምናውን ስኬት በደስታ ይገልጹታል። ባለሙያዎች እንደሚሉእት ደረት ተከፍቶ የልብ ቀዶ ህክምና ከተደረገ በኋላ አጥንት እስኪገጥም ድረስ 12 ሳምንት ይፈልጋል። ታካሚው በሰባት ቀናት ውስጥ ከሆስፒታል እንደሚወጡና ምናልባት በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው ይመለሳሉ። የመጨረሻው ስኬት ይህ የልብ የቀዶ ጥገና በርካታ ሙያተኞች የተሳተፉበት ተግባር ነበር። የልብ ቀዶ ህክምና ሐኪም፣ የልብ ቀዶ ህክምና አጋዥ፣ ሰመመን ሰጪ ሐኪሞች፣ የልብና የሳንባን ሥራ ተክቶ የሚሰራውን ማሽን የሚያንቀሳቅሱ ባለሞያዎች እና ሌሎችም በቡድኑ ውስጥ የተካተቱ ናቸው። በአጠቃላይ ከ10 በላይ ኢትዮጵያውያን ሙያተኞች ተሳትፈውበታል። በዚህ በአገሪቱ ውስጥ ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው በተባለው የተሳካ ተደራራቢ የልብ ቀዶ ህክምና የተሳተፉት ባለሙያዎች ሥራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ታካሚያቸው በደህና ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል። በዚህም ታካሚውን ከቀዶ ህክምና ጠረጴዛ ላይ አስነስተው የልብ ምታቸውን፣ የልብ የደም ግፊት መጠናቸውን፣ የሽ���ት በበቂ ሁኔታ መምጣትን፣ የልብ የኤሌክትሪካዊ ተግባርን፣ የሳንባ የኦክስጂን አቀባበል እና የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት መወሰን ነበር። ""በሚገርም ሁኔታ እኚህ የመጀመሪያ ታካሚያችን የልባቸውን ሥራ የሚያግዝ ምንም አይነት መድኃኒት አላስፈለጋቸውም"" የሚሉት ዶ/ር ፈቃደ ""ስለዚህ በተመለከትነው ውጤት ስለተደሰትን አንድ ላይ ተቃቅፈን ፎቶ ተነሳን።""" https://www.bbc.com/amharic/news-58024877 +politics የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አደገኛ ዕፅ አልተጠቀምኩም አሉ ከዓለማችን ወጣት የአገር መሪዎች አንዷ የሆኑት የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የአደገኛ ዕፅ ምርመራ ማድረጋቸውን ይፋ አደረጉ። የ36 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ምርመራውን እንዲያደርጉ የተገደዱት በዚህ ሳምንት መባቻ በመሸታ ቤት መስመር ባለፈ ሁኔታ ሲጨፍሩ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል መውጣቱን ተከትሎ ነው። ትናንት ዐርብ አዲስ በወጣ ሌላ ተንቀሳቃሽ ምሥል ደግሞ፣ ሳና ማሪን ከአንድ የፊንላንድ ዕውቅ የሙዚቃ አቀንቃኝ ጋር ተጠጋግተው ሲደንሱ ይታያል። እነዚህ ተንቀሳቃሽ ምሥሎች ለሕዝብ ከታዩ በኋላ ተቃዋሚዎች ጠቅላይ ሚኒስትሯ የደም ምርመራ እንዲያደርጉ ሲወተውቱ ነበር። ሳና ማሪን ይህንኑ ጥያቄ በመቀበል የአደገኛ ዕፅ ምርመራ በማድረግ ውጤት እየተጠባበቁ ነው። የምርመራ ውጤት በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ ይደረጋል። ወጣቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና በተደጋጋሚ ‘አንዳችም ሕገ ወጥ ተግባር አልፈጸምኩም’ ሲሉ በሔልሲንኪ ለሚገኙ ዘጋቢዎች ተናግረዋል። ‘እንኳንስ አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኜ ይቅርና በአፍላ ዕድሜዬም አደገኛ ዕፅ ያለበት ቦታ ድርሽ ብዬ አላውቅም’ ነው ያሉት፣ ሳና። ምርመራውን ያደረጉትም በሕዝብ ዘንድ ያለውን ብዥታ ለማጥራት እንደሆነም ተናግረዋል። በተጨማሪም የምርመራ ውጤቱ ይፋ እስኪደረግ ንጹህ ሆኖ የመገመት መብታቸው እንዲጠበቅም ተማጽነዋል። አንዳንድ ጋዜጠኞች ለጠቅላይ ሚኒስትሯ በምሽት በሚጨፍሩባቸው ጊዝያት አስቸኳይ የመንግሥት ውሳኔዎች አስፈልገው ቢሆን በስካር መንፈስ ውሳኔ ሰጥተው ያውቁ እንደሆን ጠይቀዋቸው ነበር። ማሪን ሲመልሱም እንዲህ ዓይነት አስቸኳይ ነገር በሌሊት መጥቶ አያውቅም ብለዋል። ማሪን በዚህ መሸታ ቤት እየጨፈሩ በነበረበት ወቅት እየተቀረጹ እንደሆነ ያውቁ እንደነበረም ይፋ አድርገዋል። ነገር ግን ተንቀሳቃሽ ምሥሉ ለሕዝብ ይፋ መደረጉ እንዳላስደሰታቸው አልሸሸጉም። ‘እኔ የመሰለኝ ሰዎች የሥራ ሰዓትንና የመዝናኛ ሰዓትን ለይተው ይመለከታሉ፤ የሰው የግል ድንበር የት ጋ እንደሆነም ይረዳሉ ብዬ አስቤ ነበር’ ብለዋል። ከዓለም ወጣት መሪዎች አንዷ የሆኑት ማሪን በስፋት የሙዚቃ ፌስቲቫሎች ላይ እየተገኙ ሲጨፍሩ በተደጋጋሚ ታይተው ያውቃሉ። ባለፈው ሳምንት እንዲያውም ባይልድ የተሰኘ የጀርመን ሚዲያ ጠቅላይ ሚኒስትሯን ‘የዓለም አራዳዋ መሪ’ በሚል መርጧቸው ነበር። ባለፈው ሐሙስ ከተለቀቀው ቪዲዮ በኋላ ዐርብ ዕለት ደግሞ ከፊንላንዱ ሞዛቂ ኦላቪ ኡዚቪርታ ጋር ተቀራርበው ሲጨፍሩ የሚያሳይ ሌላ ምሥል ተለቆባቸው ነበር። አንድ ጋዜጠኛ ጠቅላይ ሚኒስትሯ በዚህ ሞዛቂ እየተሳሙ እንደነበረ ጠይቋቸው ይህንኑ አስተባብለዋል። ‘እየሳመኝ አልነበረም፤ ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብሎ እያወራኝ ነበር፤ ምናልባት ጉንጬን ሳም አድርጎት ሊሆን ይችላል’ ብለዋል። አክለውም፣ ‘አንድ ወንድ ጉንጬ ላይ ቢስመኝ ጉድ የሚያስብል ነገር አይደለም፤ ለባለቤቴ የምነግረው ትልቅ ጉዳይም ሊሆን አይችልም’ ሲሉ ክስተቱ ይህን ያህል በሚዲያ መራገቡን አጣጥለውታል። የጠቅላይ ሚኒስትሯ የሰሞኑ ውዝግብ በፊንላድ አዲስ ክርክርን አስነስቷል። ሚዲያዎች ጉዳዩን ለጥጠውታል ከሚለው ክርክር አንስቶ  የአንድ መሪ የግል መብት እስከምን ደረጃ ሊሄድ ይችላል የሚሉት ጉዳዮች በስፋት መነጋገሪያ ሆነዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c9eydv2mdn1o +health በህንድ የተከሰተው የጥቁር ፈንገስ በሽታ በወረርሺኝነት እንዲታወጅ ጥሪ ቀረበ በህንድ የሚገኙ ክልሎች ‹‹የጥቁር ፈንገስ›› አማካኝነት የሚከሰተው በሽታ በከፍተኛ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ በወረርሺኝነት እንዲታወጅ የአገሪቱ የጤና ሃላፊዎች ጠየቁ። ከዚህ ቀደም እንብዛም የማይታየው እና በዚህ ፈንገስ አማካኝነት የሚከሰተው የሚውኮርማይኮሲስ በሽታ እስከ 50 በመቶ ድረስ ገዳይ ሲሆን የሚተርፉ ሰዎችም አይናቸውን ወይም የመንጋጋ አጥንት ያጣሉ። ከቅርብ ወራት ጀምሮ ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ከ ኮቪድ ያገገሙ እና በማገገም ላይ ያሉ ሰዎች በሚውኮርማይኮሲስ ተይዘው ተገኝተዋል። የኮቪድ ህመምተኞችን ለማከም ከዋሉ መድሃኒቶች ጋር ግንኙነት ሊኖረው እንደሚችል ሃኪሞች ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል። በተለይም የስኳር ህመምተኞች ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ከሆኑ ከ 12 እስከ 15 ባሉት ቀናት ውስጥ ተጋላጭ ሳይሆኑ እንዳልቀረ ሃኪሞቹ ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። የህንድ የጤና ሚኒስትር የጽህፈት ቤት ሃላፊ ላቭ አጋርዋል በህንድ ላሉ 29 ክልሎች ይህንን ህመም ወረርሺኝ ብለው እንዲያወጁ በደብዳቤ ጠይቀዋል። ህመሙ ወረረሺኝ ተብሎ የሚታወጅ ከሆነ ከጤና ሚኒስቴር የተሸለ ትብብር አና ህክምና ለመስጠት ብሎም በእያንዳንዱ ክልል ያለውን ሁኔታ ለመከታተል ያስችላል ተብሏል። በኮሮና ቫይረስ እየተናጠች ባለችው ህንድ እስካሁን ድረስ ምን ያህል ሰዎች በሚውኮርማይኮሲስ እንደተያዙ በውል አይታወቅም። በህንድ ባጋጠመው ሁለተኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ የስርጭት ማእበል በሁለተኛ ደረጃ ተጠቂ የሆነችው ማሃራሽትራ ክልል እስካሁን 1500 የሙኮርሚኮሲስ ታማሚዎችን ለይታለች። በህንድ ዋና ከተማ ሙምባይ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል በሁለት ወር ውስጥ 24 ህመምተኞችን መመልከቱ እና ይህ ባለፈው አመት ከታየው ስድስት ህመምተኛ ቁጥር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል። ሃኪሞችም ፈንገሱ ወደ አእምሮ ሳይሰራጭ የህመምተኞችን ህይወት ለማትረፍ የመንጋጋ አጥንትን ወይም አይናቸውን ለማስወገድ መገደዳቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። በበርካታ የህንድ የመድሃኒት አምራቾች የሚመረተው እና ይህንን ህመም ለማከም የሚለው አምፎተሪሰን የተሰኘው መድሃኒት እጥረት መከሰቱም ታውቋል። https://www.bbc.com/amharic/news-57197231 +business ልደት ፤ ወጣቱ ለልደቱ የተሰጠውን ውስኪ በመሸጥ የ40ሺህ ፖውንድ ቤት ሊገዛ ነው "ማቲው ሮብሰን ይባላል፡፡ አባቱ አንድ ነገር አስለምደውታል፡፡ በየዓመቱ ልደቱ ሲሆን 18 ዓመት ዕድሜ ያለው ውስኪ ገዝተው ይሰጡታል፡፡ ልጁ ውስኪውን ያጠራቅማል፡፡ አሁን 28 ዓመት ደርሷል፡፡ ሮብሰን የተወለደው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1992 ነው። በእነዚህ ሁሉ ዓመታት አባቱ በድምሩ 5ሺህ ፓውንድ አውጥተዋል፡፡ በየዓመቱ አንድ ውስኪ ለልደቱ ለመግዛት፡፡ እስከዛሬ 28 የውስኪ ጠርሙሶችን ገዝተውለታል፡፡ የውስኪው ዓይነት ማካላን የሚባል ነው፡፡ አሁን ዋጋው ንሯል፡፡ አባትየው ለ28 ጠርሙስ ውስኪ በ28 ዓመታት ውስጥ በድምሩ 5ሺህ ፓውንድ ብቻ ያውጡ እንጂ አሁን ላይ ውስኪዎቸ እስከ 40ሺህ ፓውንድ ይሸጣሉ፡፡ ሮብሰን እንደሚለው ውስኪ ለልጅ ተገቢ የልደት ስጦታ ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን አባቴ ውስኪዎቹን በፍጹም እንዳልከፍታቸው ያስጠነቅቀኝ ስለነበር ለዚህ በቅቻለሁ ብሏል፡፡ የሮብሰን አባት ፒት ይባላሉ፡፡ ስኮትላንድ ነው የሚኖሩት፡፡ በ1974 የተመረተው ዊስኪ ለመጀመርያ ጊዜ የገዙለት እንዲሁ እንደዋዛ ነበር፡��� ""እንደቀልድ በየዓመቱ አንድ ውስኪ ብሰጠው 18 ዓመት ሲሆነው 18 ዊስኪ ይኖረዋል ብዬ አሰብኩ፡፡ ነገሩን ለማድመቅ ነው እንጂ ለልጄ የምሰጠው ስጦታ ግን ዊስኪ ብቻ አልነበረም"" ብለዋል፡፡ አሁን ማካላን ዊስኪዎች ተፈላጊ ናቸው፡፡ እንደ ቅርስ የሚሰበሰቡ የዊስኪ አይነቶች ናቸው፡፡ የነበራቸው ዋጋም በጣም ጨምሯል፡፡ አሁን ዊስኪዎቹን ማርክ ሊትለር የተባለ እሳት የላሰ የዊስኪ ደላላ ሊሸጣቸው ነው፡፡ ምርጥ ስብስቦች ናቸው ብሏል ለቢቢሲ፡፡ ባለፉት ዓመታት የእነዚህ ውስኪዎቹ ዋጋ እጥፍ በእጥፍ ነው የጨመረው፡፡ ብናጣ ብናጣ እስከ 40ሺህ ፓውንድ እንሸጣቸዋለን ይላል፡፡ ዊስኪዎቹ የሚሸጡት ለኒውዮርክ ወይም ለእሲያ ገበያ ነው፡፡ ሮብሰን በ40ሺህ ፓውንዱ ቤት ለመግዛት እያሰበ ነው፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-54053425 +health በኔዘርላንድስ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመቀነስ ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ የኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት በአገራቸው የክረምት መግባትን ተከትሎ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ ለሦስት ሳምንታት የመገበያያ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና ምግብ አቅራቢዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ እገዳ መጣሉን ገለጹ። ይህም በምዕራብ አውሮፓ የመጀመሪያዋ ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ የጣለች አገር አድርጓታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጨናቂ እና ከባድ ውሳኔ ነው ያሉት እገዳ፤ መነሻው በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እና ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ነው ብለዋል። ሆኖም የአገሪቱን መንግሥት ውሳኔ ተቃውመው አደባባይ የውጡ ዜጎች ታይተዋል። በዚህም ሳቢያ ፖሊስ በሄግ በመቶዎች በሚቆጠሩ ተቃዋሚዎችን ለመበተን ውሃ ረጭቷል። በአሁኑ ወቅት በበርካታ የአውሮፓ አገራት የኮሮናቫይረስ ስርጭት እየጨመረ ሲሆን ለዚህ ከተሰጡ ምክንያቶች አንዱ በብዙ አገራት ክትባት በብዛት እየተወሰደ አለመሆኑ ነው። በኔዘርላንድስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ክትባት ማግኘቱን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሦስት ሳምንቱ ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል። በኔዘርላንድስ ባለፈው አርብ የተመዘገበው ዕለታዊ የኮቪድ-19 አሐዝ 16 ሺህ 287 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ያመላክታል። ይህ ቁጥር ከሐሙስ ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ቢሆንም ካለፈው ሳምንት ጋር ሲወዳደር ግን በአንድ ሦስተኛ ከፍ ያለ ነው። የኔዘርላንድስ የክትባት ምጣኔ በአንጻራዊነት ከፍተኛ የሚባል ነው። በአገሪቱ ከ12 ዓመት በላይ ካሉ ሰዎች 82.4 በመቶ የሚሆኑት ሁለት ዙር የወረርስኙ መከላከያ ክትባት ያገኙ ሲሆን፤ ይህም ከጠቅላላው ሕዝብ 73 በመቶውን የሚይዝ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-59272479 +sports በግማሽ ጨዋታ ጡት ማጥባት፡ የሴት ስፖርተኞች ታሪክ """የተወሰኑ የቡድናችን አባል ነበሩ፤ ግማሽ ጨዋታ ሲሆን ወይ ጡት ለማጥባት ወይም ጡታቸውን ለማለብ ይሄዳሉ። ከዚያም ወደሜዳ ይመለሳሉ"" ትላለች አንጎላዊ-አሜሪካዊቷ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኢታሊ ሉቃስ። ""ይህንን ቀርቦ ማየትም ሆነ በዚህ ማለፍ የሚያስደምም ነው፤ ለየት ያለ ጥንካሬ ያስፈልጋል"" በማለት ታስረዳለች። እናት መሆንና ታዋቂ ለሆነ የቅርጫት ኳስ ቡድን መጫወት እንዲሁም ለሁለቱም የሚሆን ጊዜ ማግኘት ቀላል አይደለም። እናትነትና ስፖርተኝነትን አመጣጥኖ መሄድም ፈታኝ ነው። በተለይም ሴት ስፖርተኞች በሚያረግዙበት ወቅት እርግዝናው በአካላቸው ላይ ሊያመጣ የሚችለው ለውጥ፣ አሰሪዎች ነፍሰጡር መሆናቸውን በሚያውቁበት ወቅት ሊከተል የሚችለው ጫና እንዲሁም አዲስ ህይወትን ወደ ስፖርቱ ዓለም ማምጣት የራሱ የሆኑ ፈታኝ ችግሮች አሉት። በዚህም ምክንያት ሴት ስፖርተኞች እናት ���ሆንን በከፍተኛ ሁኔታ ይፈሩታል። ለምሳሌ ባለፈው ዓመት 'አፍሮ ባስኬት' ተብሎ በሚጠራው የአፍሪካውያን የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ውድድር በሴኔጋል ሲካሄድ ከ144ቱ ቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች መካከል እናት የሆኑት 25ቱ ብቻ ናቸው። ይህ ቢሰላ አስራ ሁለት ቡድን ከሚይዝ ቡድን ውስጥ እናት የሆኑት ሁለት ብቻ ናቸው እንደማለት ነው። ምናልባት በስፖርቱ ዓለም ውስጥ እርጉዝ ሆነው ስፖርቱን ከቀጠሉት መካከል የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቿ ሴሪና ዊልያምስ ትገኝበታለች። ከሦስት ዓመት በፊትም የዓለም አቀፉን ሻምፒዮና ለ23ኛ ጊዜ ስታሸንፍ ልጇን አሌክሲስ ኦሎምፒያ ኦሃኒያን ነፍሰ ጡር ሆና ነው። ካሜሮናዊቷ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ባሌታ ሙኮኮ ነፍሰጡር መሆኗን አታውቅም ነበር፤ እርጉዝ መሆኗን የተረዳችው በጣም ዘግይታ ነው። ለፈረንሳዩ ቡድን ትጫወት በነበረበት ወቅት አንድ ቀን ጀርባዋን በፀና ታመመችና ወደ ሆስፒታል ሄደች፤ ዶክተሩም የሰባት ወር ነፍሰጡር እንደሆነች ነገራት። ""ዓመቱን በሙሉ ቅርጫት ኳስ ተጫውቻለሁ። መጋፋት መውደቅ እንዲሁም መመታት ነበር። እርጉዝ መሆኔን አላወቅኩም። ልክ መጫወት ሳቆም ሆዴም እየገፋ መምጣት ጀመረ"" ትላለች። አክላም ""ልጅ ለመውለድ እንዲሁም ለመታረስ ጊዜው ነበረኝ። የወለድኩት ሰኔ ወር ነበር እናም እስከ ነሐሴ ድረስ ምንም አይነት ጨዋታ አልነበረኝም እናም ለማረፍ ጊዜ አግኝቻለሁ"" በማለት ታስረዳለች። ምንም እንኳን እንደ ሴሪና ባሌታ ወደ ስፖርቱ ዓለም መመለስ ብትችልም፤ ነገር ግን እናት መሆንና ስፖርተኛ መሆን ከፍተኛ መስዋዕትነትን ይጠይቃል። በባለፈው ዓመት በዓለም አቀፉ ሻምፒዮን ውድድር ላይ የዱላ ቅብብል የወርቅ ሜዳሊያዋን ያገኘችው ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ ደስታዋን የገለፀችው ልጇን ዛየንን በውድድሩ ቦታ ላይ በማምጣት ነበር። በወቅቱም ምን ያህል መስዋዕትነት እንደከፈለች ስትናገር የልጇ ዛየን ትምህርት እንዲሁም ስፖርት ነክ ውድድሮች ላይ መገኘት አለመቻሏን ነው። ምክንያቱም መቋረጥ የማይችሉ ስልጠናዎች ስለነበሯት ነው፤ ይህም በወቅቱ ፈታኝ ነበር ብላለች። ፅናትና ቁርጠኝነት ብቻ ሳይሆን ታዋቂ አትሌት ለመሆን መስዋዕትነት እንደሚያስፈልግ ባሌታ የተማረችው ነገር ነው። ""የመጀመሪያ ልጄ የሚኖረው ከእናቴ ጋር ነው ምክንያቱም ስፖርቱ አብዛኛውን ጊዜዬን ስለሚወስድብኝ ብዙም አላየውም"" የምትለው ባሌታ፤ ""የማገኘው በበዓላት ወቅት እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ቅዳሜና እሁድ ብቻ ነው። የሚቀጥለውን ልጄን በምወልድበት ጊዜ ግን ለአንድ ዓመት ቢሆን ስፖርቱን ቀጥ አደርገዋለሁ"" በማለት እቅዷን አስረድታለች። ለሴት ስፖርተኞች በሚወልዱበት ወቅት ሥራ ማቋረጥ ግዴታ ይሆን? ሥራ ማቋረጡስ ለስፖርተኞች ምን አይነት ሁኔታን ያስከትል ይሆን? ቀድሞ ይከፈላቸው የነበረውን የገንዘብ መጠን ከወለዱ በኋላ ያገኙት ይሆን? ስድስት ጊዜ በመቶና ሁለት መቶ ሜትር ሩጫ የኦሊምፒክ ሻምፒዮና መሆን የቻለችው አሊሰን ፌሊክስ፤ እናት መሆኗን ተከትሎ ስፖንሰር የሚያደርጋት ናይክ ይከፍላት ከነበረው 70 በመቶ ቀንሶ ልክፈልሽ እንዳላት ገልፃለች። ምንም እንኳን ፌሊክስ ናይክ ያደረገውን ኢፍትሃዊነት በማጋለጥና በመሞገት ማሸነፍ ብትችልም ብዙ ሴት ስፖርተኞች ይህ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያስጨንቃቸው ቢቢሲ ያናገራቸው አትሌቶች ገልፀዋል። ይህ ብቻ አይደለም ልጅ ከወለዱ በኋላ ከአካላዊ ሁኔታ መቀያየር ጋር ተያይዞ መጫወትም ሆነ መወዳደር ቢከብዳቸውስ? የአይቮሪኮስቷ ቅርጫት ኳስ አምበል ማሪያማ ካዩቴ ይህ ነው ያጋጠማት። ""በውድድር ላይ ተጎድቼ ሁለቱም ጉልበቴ ላይ ቀዶ ጥገና አደረግኩኝ። እናም የመጀመሪያ ጉልበቴን ቀዶ ጥገና ሳደርግ ለምን ልጅ አልወልድም እና ወደ ቅርጫት ኳሱ አልመለስም አልኩኝ። እና አሁን ማለት የምችለው ልጅ በመውለዴ እኮራለሁ"" በማለት ጉዞዋን አስረድታለች። በሴቶች የስፖርት ዓለም ውስጥ እናትነት እንደ አንድ ችግር መታየቱ መቆም አለበት የምትለው የባሌታ አሰልጣኝ ናቶሻ ከሚንግስ፤ ይህም ጥያቄ ሊሆን አይገባም በማለት ትከራከራለች። ""ኮሌጅ ውስጥ ስፖርተኞች የነበሩ ወልደው እንደገና ተመልሰው የሚወዳደሩ ስፖርተኞችን አውቃለሁ"" በማለት የቅርጫት ኳስ አሰልጣኟ ናቶሻ አፅንኦት ሰጥታ ትናገራለች። ""ሴት አትሌቶች በእናትነትና በስፖርት ህይወታቸው መካከል እንዲመርጡ መገደድ የለባቸውም። ዋናው ነገር በደንብ ጠንክረው መስራትና ቁርጠኝነትን ማሳየት አለባቸው። ምክንያቱም ለብዙ ሴቶች ከባድ የሚሆነው በእርግዝና ወቅት የሚፈጠረውን አካላዊ ሁኔታ ወደነበረበት መመለስ ነው። ለመጫወት ወደሚያበቃቸው አካላዊ ቅርፅም ሆነ ብቃት መመለስ አለባቸው።"" የምትለው አሰልጣኟ ""ቤተሰብ መመስረት ለሚፈልጉትም ምርጫቸው ነው። እኛም እናበረታታቸዋለን ቤተሰብ መመስረት የሚፈልጉትን የአትሌትነት ህይወታቸውን እንዳያቋርጡ የምንጎተጉታቸው ጉዳይ ነው።"" አትሌቶች ልጅ ከወለዱ በኋላ ወደ ስፖርቱ መመለስ ለሚፈልጉትም ሆነ ቤተሰብ መመስረት ለሚሹ ዋናው ጉዳይ ከአሰልጣኞች ዘንድ የሚያገኙት ድጋፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አሰልጣኟ ታስረዳለች። ""ከአሰልጣኞች እንዲሁም ከአስተዳደሩ ዘንድ የሚያገኙት ድጋፍ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል። ድጋፍ እስካለ ድረስ ቅርጫት ኳስ መጫወት የሚፈልጉ ስፖርተኛ እናቶች የትም መድረስ ይችላሉ"" በማለት ሃሳቧን ታጠቃልላለች።" https://www.bbc.com/amharic/sport-52284120 +politics ጆ ባይደንና ፑቲን በነገር እየተቆራቆሱ ነው ጆ ባይደን የሩሲያውን ኃያል ቭላድሚር ፑቲንን ‹ነፍሰ በላ› ብለው ከጠሩ በኋላ በሁለቱ መሪዎች መሀል አንድ ሁለት መባባሉ አይሏል፡፡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለተሰበቀባቸው የቃላት ጦር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ‹ሌባን ሌባ ቢሰርቀው ምን ሊደንቀው› ዓይነት ይዘት ያለው ምላሽ በመስጠት የጀመሩት ቭላድሚር ፑቲን ጆ ባይደን ፍቃዳቸው ከሆነ በቲቪ በቀጥታ ስርጭት ይግጠሙኝ ብለዋል፡፡ ቭላድሚር ፑቲን በቴሌቪዥን በሰጡት በዚህ ቃለ ምልልስ ባላንጣቸውን አሌክሴ ናቫልኒን በመርዝ ለመግደል እንዳልሞከሩ አስተባብለዋል፡፡ የአሜሪካው ፐሬዝዳንት ጆ ባይደን ለኤቢሲ ኒውስ ቴሌቪዥን ቀደም ብለው እንደተናገሩት ‹ነፍሰ በላው› ፑቲን በ2020 የአሜሪካ ምርጫ እጁን አስገብቶ መዶለቱን ጠቅሰው ለዚህም ‹ዋጋ መክፈሉ አይቀርም› ሲሉ ጠጠር ያለ ሂስ አቅርበዋል፡፡ ሩሲያ ይህን የጆ ባይደንን ንግግር ተከትሎ አምባሳደሯን ወደ አገር ቤት መጥራቷ ይታወሳል፡፡ ሩሲያ አምባሳደሯን አናቶሊ አንቶኖቭን ወደ ሞስኮ ከጠራች በኋላ እንዳለችው አሜሪካ ለሩሲያ ጋር ያላት ግንኙነት ተበላሽቶ ዳግም የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል ስትል ለችግሩ መባባስ ባይደንን ተችታለች፡፡ ጆ ባይደን በበኩላቸው የአሜሪካ የደኅንነት መሥሪያ ቤት ሪፖርትን መሠረት በማድረግ እንደገለጹት ፑቲን በአሜሪካ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ ወቅት እጃቸውን አስገብተው ሊፈተፍቱ ሞክረዋል ሲሉ ሩሲያን ወቅሰዋል፡፡ ይህ የአሜሪካ የስለላ መሥሪያ ቤት ሪፖርታዥ እንደሚያትተው ሩሲያ ባለፈው ኅዳር የተካሄደውን የአሜሪካ ምርጫ የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ እንዲያሸንፉ ያልፈነቀለችው ድንጋይ አልነበረም፡፡ አሜሪካ ይህን የስለላ መሥሪያ ቤት ሪፖርት ተከትሎ በሚቀጥለው ሳምንት በሩሲያ ላይ ጫን ያለ ማዕቀብ እንደምትጥል እየተጠበቀ ነው፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-56441604 +sports ሜሲ ለስድ��ተኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ የባርሴሎና እና የአርጀንቲናው የፊት መስመር ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች በመባል ለስድሰተኛ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ሆነ። የ32 ዓመቱ ሜሲ ባሎንዶርን ሲያሸንፍ እ.አ.አ. ከ 2015 በኋላ የመጀመሪያው ሲሆን ለክለቡና ለአገሩ 54 ግቦችን በማስቆጠር ባለፈው ዓመት ደግሞ ከባርሴሎና ጋር የላሊጋው አሸናፊ መሆን ችሏል። • ማንችስተር ዐይኑን የጣለባቸው የአቶ ምሥጢረ ኃይለሥላሴ ልጆች • ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች የሊቨርፑሉ ተከላካይ ቨርጂል ቫን ዳይክ ደግሞ በዚህ ዓመት ሁለተኛውን ቦታ መያዝ ችሏል። አምስት ጊዜ ባሎንዶርን ማሸነፍ የቻለው የጁቬንቱስና የፖርቹጋር አጥቂው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሦስተኛ መሆኑ ታውቋል። በሴቶች ደግሞ ከአሜሪካ ጋር የዓል ዋንጫን ማሸነፍ የቻለችው ሜገን ራፊኖ የባሎንዶር አሸናፊ ስትሆን እንግሊዛዊቷ ሉሲ ብሮንዝ ሁለተኛ ሆናለች። የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ ብራዚላዊው አሊሴን ቤከር ምርጥ በረኛ ሲባል ጀርመናዊው የባርሴሎና ግብ ጠባቂ ማርክ ቴር ስቴገን እና ብራዚላዊው የማንቸስተር ሲቲ በረኛ ኤደርሰን ሁለተኛና ሦስተኛውን ቦታ ይዘዋል። የጁቬንቱሱ የመሀል ተከላካይ ደ ሊክት ከ21 ዓመት በታች ምርጥ ተጫዋች ተብሎ በቀድሞ ባሎንዶር አሸናፊዎች ተመርጧል። ሜሲ ዘንድሮ የባሎንዶር አሸናፊ ሲሆን ውድድሩን ለ11ኛ ተከታታይ ጊዜ ከስፔን ላሊጋ የመጡ ተጫዋቾች እንዲያሸንፉ አድርጓል። • ከመጠጥ ቀጅነት ወደ እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ሜሲ በሽልማቱ ወቅት ''ምንም እንኳን ባሎንዶርን ያሸነፍኩት ለስድስተኛ ጊዜ ቢሆንም በጣም የተለየ ደስታ ተሰምቶኛል። ባለቤቴ ሁሌም ቢሆን ትልቅ ህልም እንዲኖረን ትነግረኛለች፤ ለዚህም እራሴን በጣም ዕድለኛ አድርጌ ነው የምቆጥረው።'' ሜሲ ለባርሴሎና እስካሁን 700 ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን በስሙም 614 ግቦችን አስቆጥሯል። ከቡድኑም ጋር 10 የላሊጋና አራት ቻምፒየንስ ሊግን ጨምሮ 34 ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል። https://www.bbc.com/amharic/news-50640646 +health ኮሮናቫይረስ ፡ የአውሮፓ ሕብረት የክትባት አቅርቦት ውዝግብ ቀጥሏል "ሁለተኛው የኮሮናቫይረስ ክትባት አምራች አቅርቦትን አስመልክቶ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ የአውሮፓ ሕብረት የክትባት ስርጭትን ተስፋ አስቆራጭ አድርጎታል ተባለ፡፡ የዩናይትድ ኪንግደም መድኃኒት አምራች የሆነው አስትራዜኔካ የምርት ችግር መኖሩን መጥቀሱ አቅርቦቱ ከሚጠበቀው በታች ይሆናል ማለት ነው፡፡ የአውሮፓ ኮሚሽን በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እየሞከርኩ ነው ብሏል፡፡ በአንዳንድ የአውሮፓ ክፍሎች የፋይዘር-ባዮኤንቴክ ክትባት አቅርቦት በመቀነሱ ምክንያት ክትባቱ በመቆም ላይ ነው፡፡ ከኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ጋር ክትባቱን የሚሠራው አስትራዜኔካ በመግለጫው ስለ ሁኔታውን ቢጠቅስም ዝርዝር ጉዳዮችን አልሰጠም፡፡ ""በአውሮፓው የአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ባለው የማምረቻ ጣቢያ ምክንያት ምርቱ መጀመሪያ ከሚጠበቀው በታች ይሆናል"" ብሏል፡፡ ሮይተርስ ስማቸው ያልተጠቀሰ የአውሮፓ ሕብረት ባለሥልጣንን ዋቢ አድርጎ እንደገለጸው፤ ኩባንያው በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ወደ ሕብረቱ ሊያደርስ ካሰበው የክትባት ብዛት ወደ 60 በመቶ የሚሆነውን ቅናሽ እንደሚያደርግ ለአውሮፓ ሕብረት ተናግሯል። የአስትራዜኔካ ክትባት በአውሮፓ ሕብረት የመድኃኒት ተቆጣጣሪ ዘንድ ገና ፈቃድ ባያገኝም በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚያገኝ ይጠበቃል፡፡ አስትራዜኔካ ቢያንስ 300 ሚሊዮን ክትባት ለማቅረብ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ተፈራርሟል፡፡ በመጋቢት ወር መጨረሻ ቃል ከተገባላቸው ሁለት ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባቶች፤ 600,000 ብቻ ማግኘቷን የኦስትሪያ ሚዲያዎች የዘገቡ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ከወራት በኋላ ይደርሰሉ ተብሏል። መዘግየቱ ""ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የለውም"" ሲሉ የኦስትሪያው የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሩዶልፍ አንሾበር ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካው ኩባንያ ፋይዘር፤ በቤልጅየም ያለው ፋብሪካውን አቅም ለማሳደግ እየሠራ በመሆኑ ለሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት የሚልከውን የክትባት መጠን እንደሚቀንስ አስታውቋል። የአውሮፓ ሕብረት 600 ሚሊዮን ጠብታ ከፋይዘር ለመግዛት ተስማምቷል፡፡ የፋይዘር ክትባት መቀነስ በጀርመን እና በጣሊያን ውስጥ የሚገኙ በርካታ ክልሎች የመጀመሪያዎቹን ክትባቶች እንዲያቆሙ አስገድዷቸዋል፡፡ በማድሪድ ለህክምና ባለሙያዎች የሚሰጠው ክትባትም ቆሟል፡፡ የክትባት ቅነሳን አስመልክቶ ጣልያን እና ፖላንድ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን ብለው አስፈራርተዋል፡፡ የአውሮፓ ሕብረት የኦክስፎርድ-አስትራዛኔካ ክትባትን ሳያጸድቅ መቆየቱ ያማረረው የሃንጋሪ መንግሥት፤ የአውሮፓ ሕብረትን ይሁንታ ባያገኝም በርካታ የስፑትኒክ ቪ ክትባ ለመግዛት ከሩሲያ ጋር ተስማምቷል።" https://www.bbc.com/amharic/55777884 +politics የኬንያ ፕሬዚዳንት የምርጫ አስፈጻሚዎችን አገዱ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ነሐሴ የተካሄደውን ምርጫና አሸናፊ ያደረጋቸውን ውጤት ያልተቀበሉ አራት የምርጫ ኮሚሽነሮችን ከስራ አገዱ። ፕሬዚዳንት ሩቶ ዛሬ አርብ እንዳስታወቁት ፍርድ ቤት አራቱን ባለስልጣናት ህግ በመጣስ፣ በከባድ ስነ ምግባር ጉድለትና በብቃት ማነስ እንደሚመረምራቸውና ከስልጣናቸውም እንደሚባረሩ ገልጸዋል። ነገር ግን የተቃዋሚ ፓርቲው አመራርና ለአምስት ጊዜ በምርጫ የተወዳደሩት ራይላ ኦዲንጋ ውሳኔውን አውግዘው በመጪው 2027 ምርጫንም መንግሥት ለማጭበርበር ያለመ ነው ብለዋል። “አራቱ ኮሚሽነሮች እንዲባረሩ የተደረጉት ሩቶና አስተዳደራቸው የምርጫ ኮሚሽኑን እንደ አዲስ ለማዋቀርና በራሳቸው ሹመኞች ለመሙላት ነው። ሩቶ በ2022 እያቀደ ያለው በ2027 ምርጫ ለማጭበርበር ነው” ብለዋል ኦዲንጋ ፕሬዚዳንት ሩቶ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ያስታወቁት ነሐሴ በተደረገው ምርጫ ኮሚሽነሮቹ ባሳዩት ባህርይ ምክንያት እንዲታገዱ በብሔራዊ ምክር ቤቱ የቀረበውን ሃሳብ ተከትሎ ነው። ዊሊያም ሩቶ ተፎካካሪያቸውን ራይላ ኦዲንጋን 50.5 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸው ይታወሳል። ነገር ግን የምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀ መንበሩን ጨምሮ ከሰባት ኮሚሽነሮች ውስጥ አራቱ የምርጫው አኃዝ የተሳሳተ እና ውጤቱም “ግልጽ ያልሆነ” ብለውታል። https://www.bbc.com/amharic/articles/crgj5g616y5o +politics የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላዎችን ለመዝጋት መወሰን የሚኖረው አንድምታ "ባለፈው ረቡዕ ኢትዮጵያ በአልጄሪያ ዋና ከተማዋ አልጀርስ የሚገኘው ኤምባሲዋን ለመዝጋት እንወደሰነችና ከአገሪቱ ጋር የሚኖራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ግን እንደሚቀጥል ኤምባሲው አስታውቋል። በተጨማሪም ኢምባሲው የሚዘጋው እየተካሄደ ባለው ማሻሻያና ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ እንደሆነም ገልጿል። በአልጀርስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ ካሏት ኢምባሲዎችና ቆንስላዎች መካከል ግማሽ ያህሉን እንደምትዘጋ ካሳወቁ በኋላ በይፋ መዘጋቱ የታወቀ የመጀመሪያው ኤምባሲ ነው። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ""አሁን በየቦታው ዶላር ከምንበትን ለስድስት ወር ወይም ለአንድ ዓመት ካሉን ኤምባሲዎች ቢያንስ 30ዎቹ መዘጋት አለባቸው። እነዚህ ተዘግተው አምባሳደራቸው እዚህ ሆኖ ይሰራል"" በማለት ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ሊዘጉ እንደሚችሉ ጠቁመው ነበር። ከሰባት ዓመት በፊት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተቀላቀሉት እና አልጄሪያ በነበረው ኤምባሲ ለሦስት ዓመታት ያገለገሉት የዲፕሎማሲ ባለሙያው ሰመረ ኪዳነ ውሳኔው ድንገተኛና አስደንጋጭ ነው ይላሉ። ይህ ውሳኔ ከመምጣቱ ከአራት ወር በፊት ሥራቸውን መልቀቃቸውን ገልፀው፣ ""ይህንን ስሰማ ግን ደንግጫለሁ፤ አልጠበቅኩትም። ብዙ የሰራሁበት ኤምባሲ ስለሆነ እና ጉዳቱም ከፍተኛ ስለሆነ ውሳኔው ከብዶኛል"" ሲሉ የተፈጠረባቸውን ስሜት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ወር ለሁሉም ሚስዮኖች በጻፈው ደብዳቤ 'ሠራተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ስለተወሰነ በተመደቡበት ቦታ ሲገለገሉበት የነበረውን ንብረት አስረክበው እስከ ነሐሴ 15፣ 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ወደ ዋና መሥሪያ ቤት [አዲስ አበባ] ሪፖርት እንዲያደርጉ' አሳስቧል። ሆኖም የተለያዩ የኤምባሲና የቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ይሰሩ የነበሩ ሠራተኞች በኤምባሲዎች መዘጋትና በድንገተኛው ጥሪ ምክንያት ሥራቸውን አቁመው ወደ አገራቸው እንደማይመለሱ እየተነገረ ነው። ከእነዚህም መካከል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት በብራሰልስ የአውሮፓ ሕብረት ጉዳዮችን ሲከታተሉ የቆዩት መርከብ ነጋሽ አንዱ ናቸው። አቶ መርከብ ሲሰሩበት የነበረው በብራሰልስ የሚገኘው ኤምባሲ ሠራተኞች በአጠቃላይ ወደ አገር ቤት ተመልሰው ሪፖርት እንዲያደርጉ ደብዳቤ ደርሷቸዋል። በዚህም መሰረት አብዛኛው ዲፕሎማት ተመልሶ ስልጠና ተሰጥቶት እንደ አስፈላጊነቱ እንደገና ሊመደብም ላይመደብም ይችላል የሚል ማብራሪያ እንደተሰጣቸው የሚናገሩት አቶ መርከብ፣ ""ይህ አሳማኝ አይደለም"" ይላሉ። በዚህ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለሱና ሥራ እንዳቆሙ ተናግረዋል። ነገር ግን በመንግሥት እንዲዘጉ ከተወሰኑ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች መካከል የብራሰልሱ ኤምባሲ እንደማይገኝበት ቢቢሲ አረጋግጧል። አቶ መርከብ ""ሪፖርት አላደረግኩም፤ ግን እዚህ የነበረኝን ኃላፊነት እና እቃ አስረክቤያለሁ። አልመለስም"" በማለት ለዚህ መነሻ ሆኖኛል የሚሏቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣሉ። በትግራይ ክልል ያለው ጦርነት አንዱ ነው የሚሉት አቶ መርከብ፣ በክልሉ የተፈጠረው ቀውስ በቀጥታ ጫና እንደሚያደርስበት በመግለጽ ""አገሪቷ ላይ ያለው ሁኔታ ስለሚታወቅ ከአሁን በኋላ ለዚህች አገር ለማገልገል ፍላጎት የለኝም"" ብለዋል። ባለፉት ወራት እስከ 'መሰወር' የሚደርስ እስራትና እንግልት በትግራይ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ነው የሚለውን የአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጓቾች ሪፖርቶች በመጥቀስም ""ለራሴና ለቤተሰቦቼ ደኅንነት ስለሚያሰጋኝ ላለመመለስ ወስኛለሁ"" ሲሉ ተናግረዋል። መንግሥት ግን ለዚህ ውንጀላ ምላሽ ሲሰጥ 'ማንም በማንነቱ ምክንያት' እንዳልታሰረ በመግለጽ፤ መንግሥት አሸባሪ ብሎ ከፈረጀው ከህወሓት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎችን ተጠያቂ የማድረግ ሥራዎች እንደሆኑ መግለጹ ይታወሳል። እስከ ባለፈው የሐምሌ ወር ለዘጠኝ ዓመታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጂቡቲና አቡዳቢ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የተለያዩ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን ሲሰራ የቆየው ዳዊት ንጉሤ በበኩሉ ውሳኔውና እየቀረቡ ያሉ ምክንያቶች አጥጋቢ አይደሉም ይላል። በዚህም የተነሳ ""ጥቂት የማይባሉ ባሉበት አገር ወይም ወደ ሌላ አገር በመሄድ የመቅረት አዝማሚያ"" እንዳላቸውም ተናግሯል። ""እኔ የማውቃቸው የሥራ ባልደረቦቼ ደንግጠዋል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ የመመለስ ፍላጎት የላቸውም። የጠራ ነገር ስለሌለ ወደ አገር ቤት ተመልሰንም ሥራ ላይ መቀጠል ላይኖር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።"" ብሏል። እነዚህ ወደ አገራቸው አንመለስም የሚሉ የሚስዮኖቹ ልዑካን ከዚህ በፊት በፖለቲካዊ ውሳኔ የተመደቡና ልምድ የሌላቸው እንደሆኑ የሚተቹ ወገኖች አሉ። ወደ አገራቸው እንደማይመለሱ ለቢቢሲ የተናገሩት ሁለቱ ግለሰቦች ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው በቀጥታ ወደ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ በመቀላቀል በተለያዩ የወደብ፣ ሕዝብ ለሕዝብ፣ የኢንቨስትመንትና ሌሎች የዲፕሎማሲ ሥራዎች የሰለጠኑና ሲሰሩበት የነበረ መሆናቸውን ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ ላይ ኤምባሲዎች ብዙ ገንዘብ እንደሚወጣባቸው በመግለጽ ሚንስቴሩን፣ እንደ አዲስ በማጠናከር ብዙ አዲስ ወጣቶች ሰልጥነው ወደ መሥሪያ ቤቱ እንደተቀላቀሉ ተናግረዋል። ከዚህ ውጪ ""ከኤምባሲዎች በማይተናነስ መልኩ ከአምባሳደር በላይ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን አሉ። ውጪ ያላችሁ ኢትዮጵያውያንም ለዚህ ተዘጋጁ፤ ኢትዮጵያ ከዚህ በላይ አትችልም"" የሚል መልዕክት አስተላልፈው ነበር። የኤምባሲዎች መዘጋት ምክንያት ምንድን ነው? ከቀናት በፊት መዘጋቱን ያሳወቀው በአልጄሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳስታወቀው ለመዘጋቱ ምክንያት የሆነው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ያስከተለው አሉታዊ ጫና፣ የገንዘብ እጥረትና የምጣኔ ሀብት ቀውስ ነው ይላል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ማሻሻያዎችን በማካሄድ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዓለም የበለጠ የምትወከልበትን መንገድ እንደገና ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑ በመታመኑ እንደሆነ ኤምባሲው አስታውቋል። መንግሥት በአገሪቷ ካለው ለውጥ ጋር በተያያዘ መንግሥት በመሥሪያ ቤቱ የተሻሻለ የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት ለመዘርጋት የሁሉም ተቋማት አደረጃጀትና አሰራር እየተፈሸ መሆኑን በመጥቀስ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ላይ ለውጥ ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል። በዋናነት ግን በዓለም ደረጃ ያጋጠሙ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ግምት ውስጥ በማስገባት ማሻሻያ ለማድረግ መወሰኑንም ምንጮቻችን ገልጸዋል። ገንዘብ የለም ስለተባለ ብዙ ኤምባሲና ቆንስላ ጽህፈት ቤት አያስፈልግም በሚል የሚዘጉ፣ በአንድ አምባሳደር እንዲሰሩ የተደረጉ፣ ከአዲስ አበባ ይሸፈናሉ የተባሉና አንዳንዶቹም የሰው ኃይላቸው ተቀይሮ አልያም ተቀንሶ እንዲሰሩ የሚደረጉ እንዳሉ ተነግሯል። እስከ አሁን ግን ይህንን በተመለከተ የተሰጠ ዝርዝር ይፋዊ መረጃ የለም። ቢቢሲ ግን በሙስካት፣ ዘ-ሄግ፣ ደብሊን፣ ሎስ አንጀለስ፣ ሚኒሶታ፣ ፍራንክፈርት፣ ኢስታንቡል፣ ጓንጁ፣ ሻንጋይ፣ ቾንቺን፣ ሙምባይ፣ አቢጃን፣ ኩዌት፣ ጃካርታ፣ ካምቤራ፣ ብራዚሊያ፣ ኦታዋ፣ ሃቫና፣ ሐራሬ፣ ራባት፣ አልጀርስ፣ ካይሮ፣ ዳካር፣ አክራ፣ ኪጋሊ፣ ኪንሻሳ፣ ሴዑል፣ ዶሃ፣ ባህሬን፣ ስቶክሆልም የሚገኙ ሚስዮኖች እስከ ጥቅምት ወር ባለው ጊዜ እንደሚዘጉ ከምንጮቹ ካገኘው ሰነድ ላይ ተመልክቷል። እነዚህ ሚሲዮኖች ሲገለገሉባቸው የነበሩ እቃዎች ወደ አገር ቤት እንዲመለሱና ባሉበት እንዲታቀቡ ሲል፤ በአንዳንዶቹ ሚሲዮኖች የነበሩ እቃዎች ግን ረጅም ዓመታት ያገለገሉ ስለሆኑ የፌደራል መንግሥት ንብረት ማስወገድ መመሪያና የአገራቱን ሕግ በመከተል እንዲወገዱ አሳስቧል። ከዚህ በተጨማሪ ቢቢሲ ያገኘው ሰነድ፤ በኪጋሊ እና ታንዛኒያ ዶዶማ የነበሩ ኤምባሲዎች በ'ላፕቶፕ አምባሳደር' እና ከዋና መስሪያ ቤት [አዲስ አበባ] ሆኖው እንዲሰሩ መወሰኑን በመግለጽ ለሁሉም ሠራተኞች ስልጠና መዘጋጀቱን ያስረዳል። የትግራይ ጦርነት እና የኤምባሲዎች መዘጋት ጦርነቱ ብዙ ኪሳራ አድርሷል የሚሉት ሰመረ ""የሁሉም ጦርነት ኪሳራ ብዙ ስለሆነ ያጋጠመው ኢኮኖሚያዊ ችግርም ከዚህ የሚመነጭ ይመስለኛል"" ይላሉ። በሌላ በኩል መንግሥት በጦርነቱ ምክንያት ዓለም አቀፍ ጫና ሲደርስበት፣ በተለይ በአሜሪካና አውሮፓ ከባድ የዲፕሎማሲ ጫና አጋጥሞታል የሚለው ዳዊት በበኩሉ ይህንን ለመመከት ግን ""ከዋና መሥሪያ ቤት በሚሰጠን መመሪያ መሠረት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማስረዳት ስንሰራ ነበር"" ብሏል። ሆኖም ውጤታማ አልሆነም የሚል ድምዳሜ እንዳለው በመግለጽ ""በእኔ ግምት የኤምባሲዎቹ መዘጋት ምክንያት ካለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት በተጨማሪ መንግሥት ተገቢውን የዲፕሎማሲ ሥራ አልሰሩም ያላቸውን በአሜሪካና አውሮፓ የሚገኙትን ጨምሮ እንዲዘጉና ዲፕሎማቶቹም እንዲመለሱ አድርጓል"" ሲል ያስረዳል። በዚህ ጉዳይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም። ሆኖም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ወደ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች በላከው ደብዳቤ ለሠራተኞቹ አዲስ ስልጠና ለመስጠት እንዲሁም በተሻሻለ አደረጃጀትና የሰው ኃይል ለማጠናከር እንደሆነ ይገልጻል። ኤምባሲዎችን መዝጋት እና ማዘዋወር ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አዲስ አደለም የሚሉት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ከሳምንት በፊት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ መንግሥት በተለያዩ ዘርፎች የተሃድሶ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ጠቅሰዋል። አሁን መንግሥት እየወሰዳቸው ያላቸው የተሃድሶ እርምጃዎች ብቃትን መጨመር ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆናቸውንም አክለው ተናግረዋል። እነዚህ ማሻሻያዎች በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እና በኤምባሲዎች እየተካሄደ መሆኑንም ያነሳሉ። በኤምባሲዎች ውስጥ የሚካሄደው ማሻሻያ ወጪን መቆጠብ እና 'ዲጂታላይዝ' ማድረግ ላይ ያተኮረ መሆኑን አምባሳደሩ ጨምረው ተናግረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሁን እያዳረገ ያለው የተሃድሶ እርምጃ ""ውጤታማ ዲፕሎማሲያዊ ተቋም"" መገንባት መሆኑን በማንሳት አሁን ካለው የትግራይ ጦርነት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው አብራርተዋል። የኤምባሲዎቹ መዘጋት የሚፈጥረው ጫና አለ? ኢትዮጵያ ከኃይለሥላሴ ዘመን ጀምሮ በትልልቅ ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች የምትታወቅ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት መስራችና አባል አገር ናት። በርካታ ዓለም ዓቀፋዊ ስምምነቶች ከፈረሙት መካከል እና በእነዚህም ስምምነቶች የምትገዛ ሆና ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት በማምጣት እውቅ ዲፕሎማቶች በማፍራት ትጠራለች። የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶች ባለሙያው ዳዊት ""አሁን ይሄን ሁሉ ስኬት በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ታች ወርዷል፤ ያጋጠመን ችግር ከ50 ዓመታት በላይ የተገነባውን ዲፕሎማሲ የሚያፈርስ ነው"" የሚል ቅሬታ አለው። መሥሪያ ቤቱ በሚቀጥሉት ዓመታት የዲፕሎማሲ አድማስ የማስፋት፣ ተጨማሪ ኤምባሲዎች የመከፈት እንጂ ይሄንን ያክል ቁጥር ያላቸው ሚስዮኖች የመዝጋት ዕቅድ ኖሮት አያውቅም የሚሉት ደግሞ መርከብ ነጋሽ ናቸው። ሆኖም ""አገሪቷ ይሄንን የሚሸከም ኢኮኖሚያዊ አቅም የላትም፤ ይሁን እንጂ ለስብሰባዎችና ሌሎች ጉዳዮች ብዙ ገንዘብ የሚያወጣ መንግሥት ነው"" በማለት ውሳኔውን ይተቻሉ። ሚሲዮኖቹ የአገር ጥቅም ለማስከበር የሚያግዙ ሥራዎች በመስራት እንደቆዩ የሚገልጹት ባለሙያዎቹ ውሳኔው ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የሕዝብ ጥቅም ማስከበር ላይ አሉታዊ ጫና እንዳያሳድር ስጋት አላቸው። ኤምባሲዎቹ የውጭ ኢንቨስትመንት በመሳብ፣ የአገር ውስጥ ምርቶች በመሸጥና ቱሪዝም መሳብ ላይ ትኩረት አድርገው ሲንቀሳቀሱ ነበሩም ይላሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ ብዙ ጥቅም የማታገኝባቸው ኤምባሲዎች እንዲሁም ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸው ሚስዮኖች የሉም ማለት ይቻላል? ስንል ጠይቀናል። የዲፕሎማሲ ባለሙያው ሰመረ፣ ሲጠ��� ክፍተት ያለበት አንድ ወይም ሁለት ሊኖር ይችላል፤ በአንዴ 30 ኤምባሲዎች መዝጋት ግን ሌላ ትርጉም ነው ያለው ይላሉ። ""ብዙ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም አይገኝባቸውም የተባሉ አሉ፤ ብዙ ዜጋም የሌላቸው። ሆኖም እነዚህ ጽህፈት ቤቶች በመዝጋት ከሩቅ ውጤታማ ሥራ መስራት አይቻልም። ከዚህ ይልቅ እንዲጠናከሩ በማድረግ መፍትሄ ማምጣት ይቻል ነበር፤ የሚል እምነት አለኝ"" ብለዋል። ይህ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ አለው የሚሉት ባለሙያው፡ ""ምክንያቱም እንደምትፈልገው የውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ፣ መሸጥ ወይም ከውጭ ማስገባት አይቻልም"" ይላሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-58386457 +health በዩኬ የበረራ ሰልጣኝ በወባ ትንኝ ከተነከሰች በኋላ ሕይወቷ ማለፉ በምርመራ ተረጋገጠ በዩናይትድ ኪንግደም የንግድ አየር መንገድ አውሮፕላን ሰልጣኝ አብራሪ የነበረችው ግለሰብ በወባ ትንኝ ከተነከሰች በኋላ ወደ አንጎል በተሰራጨ ኢንፌክሽን ሳቢያ ሕይወቷ ማለፉ በምርመራ ተረጋገጠ። ነዋሪነቷ ሰፎልክ፣ በሪይ ሴንት ኤድመንድስ የነበረው የ21 ዓመቷ ኦሪያና ፔፐር፣ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር በቤልጂየም፣ አንትወርፕ እያለች በወባ ትንኝ ከተነከሰች ከአምስት ቀናት በኋላ ሕይወቷ ማለፉ ተገልጿል። የሰፎልክ ከፍተኛ የወንጀል መርማሪ የሆኑት ናይጀል ፓርስሊይ፣ ወደፊት ጥሩ ሥራ የሚጠብቃት ወጣት ሞት እጅግ አሳዛኝ ነው ብለዋል። በኢፕስዊች ከተማ የሚገኘው የሰፎልክ መርማሪ ፍርድ ቤት፣ ኦሪያና በኦክስፎርድ በኢዚጄት የአብራሪ ሥልጠና ፕሮግራምን የጽሁፍ ፈተናዋን አልፋ የበረራ ብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት ወደ ቤልጂየም ማቅናቷን አስረድቷል። ሰልጣኝ አብራሪዋ በአውሮፓውያኑ ሐምሌ መጀመሪያ ቀኝ ዐይኗ ላይ በወባ ትንኝ ከተነከሰች በኋላ በሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ገብታ እንደነበርና የተነከሰችበት አካባቢ እብጠትና መመረዝ እንደታየበት ተነግሯል። የፀረ ተህዋስ መድኃኒት ቢታዘዝላትም ከሁለት ቀናት በኋላ ራሷን በመሳቷ የፍቅር ጓደኛዋ መልሶ ወደ ሆስፒታል ወስዷታል። ከዚያም ከሦስት ቀናት በኋላ ሕይወቷ ሊያልፍ ችሏል። የሞቷ ምክንያት በነፍሳት ንክሻ ምክንያት በሚፈጠር ኢንፌክሽን ሳቢያ ወደ አንጎል የሚሄደው የደም ሥር መዘጋት [ሴፕቲክ ኢምቦሊ] መሆኑን የሕክምና ማስረጃዎች አመልክተዋል። መርማሪው ፓርስሊይ፣ ኦሪያና የሞተችበትን ምክንያት ገለጻ ሲያደርጉ፣ ኦሪያና ሕይወቷ ሊያልፍ የቻለው ግንባሯ ላይ ባጋጠማት የነፍሳት ንክሻ በኋላ በተከሰተ አደገኛ የሆነ ኢንፌክሽን ነው ብለዋል። መርማሪው እንደዚህ ዓይነት አደጋ ከዚህ በፊት አይተው እንደማያውቁም ተናግረዋል። የምርመራ ውጤቱ በተነበበት ወቅትም የኦሪያና አባት ትሪስታን ልጃቸው “ከአባቷ እና ከወንድሟ ኦሊቨር ጋር እንደመብረር የሚያስደስታት ነገር አልነበረም” ብለዋል። ኦሪያና የምትወደውን ሰው አግኝታ፣ ሕልሟን ለማሳካት “የአውሮፕላን አብራሪነት ሥልጠና እየወሰደች ነበር” ሲሉም አክለዋል። የልጃቸው ሞት ምርመራ ከተሰማ በኋላ እናቷ ሉዊዛ በበኩላቸው፣ ለኦሪያና መታሰቢያ ከእንግሊዝ ሴት አብራሪዎች ማኅበር ጋር በመተባበር “ሌሎች ሴት አብራሪዎች ሙያውን እንዲቀላቀሉ ለማበረታታት ነጻ የትምህርት እድል ተዘጋጅቷል” ብለዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cy7q2xzyp3jo +business ሊባኖሳውያን የራሳቸውን ገንዘብ ለማውጣት በባንኮች ላይ የሚፈጽሙት ዘረፋ በሊባኖስ ለዓመታት በዘለቀው የምጣኔ ሃብት ቀውስ ምክንያት፣ ባንኮች ደንበኞቻቸው በሚያወጡት የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ጥለዋል። ይህ ደግሞ ተጠቃሚዎች ገንዘባቸውን ለማግኘት ኃይል እንዲጠቀሙ እያደረጋቸው ነው። ባለፉት ሳምንታት ዜጎች ካስቀመጡት ገንዘብ የፈለጉት�� ያህል ለማውጣት ሽጉጥ ታጥቀወ ወደ ባንኮች በመሄድ ያራሳቸውን ገንዘብ በመሳሪያ በማስገደድ ለማውጣት እየሞከሩ ነው። ይህ ቪዲዮ በዚህ መንገድ ገንዘብ ለማውጣት በሞከሩ ሁለት ሊባኖሳውያን ታሪክ አማካይነት የችግሩን መባባስ ያሳያል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cglg1k2np17o +health ኮሮናቫይረስ፡ ድመትና ውሾች ኮቪድ እንደሚይዛቸው ተደረሰበት "የኮቪድ ቫይረስ በለማዳ የቤት ውስጥ እንሰሳት በተለይም በውሾችና በድመቶች ላይ በስፋት እንደሚገኝ አንድ ጥናት አመለከተ። ጥናቱ እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው 196 የኮቪድ ተህዋሲ የጎበኘው ቤተሰብ ላይ ባደረገው ምርምር ነው። በ196 አባወራዎች ላይ በተደረገው ይህ ምርምር 310 ድመቶችና ውሾች የተካተቱበት ነው። ከነዚህ ውስጥ ስድስት ድመቶችና ሰባት ውሾች ተህዋሲውን ተሸክመው ተገኝተዋል። 54ቱ ደግሞ ከዚህ ቀደም ተህዋሲው ይዞ እንደለቀቃቸው የሚያሳይ የበሽታ ተከላካይ ቅንጣት ተገኝቶባቸዋል። ዶ/ር ኤልስ ብሮንስ በኡትሬች ዩኒቨርስቲ ተመራማሪና መምህር ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት ኮቪድ ያለባቸው ሰዎች ከድመትና ውሾቻቸው ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ ባያደርጉ ይመረጣል። ""እዚህ ጋ ዋናው ነጥብ የእንሰሳቱ ጤና አይደለም"" ይላሉ ዶ/ር ኤልስ። ዋናው ነጥብ የቤት እንሰሳቱ ""ቫይረሱን ተሸካሚና አዘዋዋሪ ከመሆናቸው ላይ ነው።"" አጥኚዎቹ ከቤት እንሰሳቱ ወደ ሰው ቫይረሱ ስለመተላለፉ በእርግጥ ያሉት ነገር ባይኖርም በውሻና በድመት ላይ ግን ተህዋሲው ጎልቶ የማይታይና እነሱም ቢሆን ምንም ዓይነት የበሽታ ምልክቶችን እንደማያሳዩ ደርሰውበታል። ካሳዩም እጅግ ዝቅተኛ የሆኑ ምልክቶቹን ብቻ ነው የሚሆነው። በጥናቱ የተሳተፉ ተመራማሪዎች በርካታ የቤት እንሰሳት ቫይረሱን ያገኙት ከሰው ልጆች እንደሆነና ነገር ግን በተቃራኒው እንዳልሆነ ገምተዋል። የቤት እንሰሳቱ ባለቤቶች ተህዋሲውን ከድመትና ከውሻ የማግኘታቸው ዕድል ዜሮ ነው ልንል አንችልም፤ ነገር ግን ይህ የመሆን ዕድሉ አነስተኛ ነው ብለዋል የእንሰሳት ሐኪምና የማይክሮባዮሎጂካል ዳያግኖስቲክ ሴንተር ባልደረባ ዶ/ር ብራውንስ። በሩሲያ የእንሰሳት ሐኪሞች ለቤት እንሰሳት የተህዋሲውን ክትባት መውጋት መጀመራቸው መዘገቡ ይታወሳል። ዶ/ር ብራውን ግን ይህን ማድረጉ ጥቅሙ አልታይ ብሏቸዋል። ""ለጊዜው እንሰሳቱ ተህዋሲውን ወደ ሰው ስለማስተላለፋቸው አስተማማኝ የሆነ ሳይንሳዊ መረጃ አላገኘንም"" ይላሉ።" https://www.bbc.com/amharic/57662274 +health ኮሮናቫይረስ፡ በታንዛኒያ 'የኮቪድ-19 ምልክቶችን ያሳዩ' በርካታ መነኮሳትና ካህናት መሞታቸው ተሰማ "በታንዛኒያ ስድሳ መነኮሳትና 25 ካህናት ባለፉት ሁለት ወራት መሞታቸውን የአገሪቱ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስታወቀች። እነዚህ ካህናትና መነኮሳት የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ታይቶባቸው ነበር ተብሏል። በአገሪቱ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ህሙማን መረጃ ይፋ በማይሆንባት ታንዛኒያ ቤተ ክርስቲያኗ የአገሬው ሰው ከወረርሽኙ እንዲጠነቀቅ ምክሯን ለግሳለች። የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ወረርሽኙን ሲያጣጥሉ የተሰሙ ሲሆን ባለፈው ወር የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ታንዛኒያ ወረርሽኙን ለመከላከል ክትባት የመስጠት ዕቅድ የላትም ብለዋል። በተቃራኒው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ያላትን ስጋት ስትገልፅ ቆይታለች። የታንዛኒያ የካቶሊክ ኤፒስኮፓል ጉባኤ ፀሐፊ ቄስ ቻርለስ ኪቲማ እንዳስታወቁት የኮቪድ-19 ስጋት በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል። ""ራሳችንንም ሆነ ሌሎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑትን ጥንቃቄዎች ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው። በተለይም የእድሜ ባለፀጎችንና ተጓዳኝ ህመም ያለባቸውን ሰዎች ትኩረት ልንሰጣቸው ይገባ���"" በማለት በዳሬሰላምከተማ በተደረገ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ቄስ ቻርለስ እንዳሉት መነኮሳቱና ካህናቱ ምርመራ ባለማድረጋቸው በኮሮናቫይረስ ሞተዋል ብላ ለማወጅ ቤተ ክርስቲያኗ ብትቸገርም ሁሉም የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ታይቶባቸዋል ተብሏል። በርካቶችም በከፍተኛ ሁኔታ ለመተንፈስ ተቸግረው እንደነበር ተገልጿል። ""ዜጎች እየተመረመሩ አይደለም። ይሄ ትልቁ ፈተና ነው። ቤተ ክርስቲያኗ በአገሪቱ ውስጥ 500 የጤና ማዕከላት ቢኖሯትም ኮሮናቫይረስ መመርመር አልተፈቀደላትም። እንዲሁም የመመርመሪያ መሳሪያውም የለንም"" ብለዋል። ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን በተመለከተ ከመንግሥታቸው በኩል የሚሰጡ አስተያየቶች በቅርቡ እንደተቀየረ ቢናገርም፤ ነገር ግን ታንዛኒያ ግልፅ የሆኑ መመሪያዎችን ባለማስቀመጧ ብዙዎች እንደማይጠነቀቁ ተናግረዋል። ቤተ ክርስቲያኗ የወረርሽኙን አስከፊነት በተመለከተ በተደጋጋሚ የምትናገር ሲሆን ጥር ወር ላይ የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡን ገልፃለች። ታንዛኒያ ካለፈው ዓመት የግንቦት ወር በኋላ የታማሚዎችን ቁጥር ማሳወቅ አቁማለች። የዓለም ጤና ድርጅት የታማሚዎችን ቁጥር እንድታሳውቅና በክትባቱ ላይ ያላትን አቋም እንድትቀይር ተማፅኗል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56272129 +health ጃዋር መሐመድ፡ እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸው ተገለፀ "የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በትናንት ውሎው በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና 14 ተጠርጣሪዎች የቅድመ ምርመራ መዝገብ ባለፈው ቀጠሮ የተሰጡ ትዕዛዞችን አፈፃፀምና የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ነበር ትናንት፣ ሐሙስ (ነሐሴ 14 2012) ቀጠሮ የያዘው። በትናንትናው ዕለትም ባለፈው ቀጠሮ ተሰጥተው ከነበሩ ትዕዛዞች አንደኛው ተጠርጣሪዎች የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግላቸው የሚል ነበር። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም ከኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲትዩት የተላከ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት ማስረጃን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል። በማስረጃው መሠረት አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ ሃምዛ አዳነ (ቦረና) እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸው በችሎቱ ላይ ተነግሯል። በሌላ በኩል፣ በሌላ ቀጠሮ ትዕዛዝ ተሰጥቶበት የነበረው የአቶ ጃዋር መሐመድ የሕክምና ጉዳይ ነበር። ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሐመድ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። አቶ ጃዋር መሐመድ በትናንቱ ችሎት ሕክምና እንዳላገኙ እና አሁንም እየታመሙ እንደሆነ ""ምግብ ስበላ ያስመልሰኛል፤ ያስቀምጠኛል"" በማለት የጤንነታቸውን ሁናቴ አስረድተዋል። አቶ ጃዋር ለህይወታቸው ካላቸው ስጋት የተነሳ በማያውቁት ሃኪም መታከም እንደማይፈልጉ ጨምረው ተናግረዋል። በተለይ ""ሃጫሉ ሞቷል፤ ጃዋር ነው የቀረው እየተባለ ነበር። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም ህይወቴ ላይ ስጋት ስላለ ነው ጥብቅ ጥበቃ እያደረገልኝ ያለው፤ እኔም የመንግሥት የሕክምና ተቋማትን ንቄ ሳይሆን ለሕይወቴ ካለኝ ስጋት አንጻር ነው በግል ሀኪሜ መታከም የፈለግሁት"" ሲሉ አስረድተዋል። ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጀዋር መሐመድ ሰኞ ዕለት መርማሪ ፖሊስ እና አቃቤ ሕግ እርሳቸው ጋር በመገኘት የግል ሐኪማቸውን ጠርተው መታከም እንደሚችሉ ነግረዋቸው የነበረ ቢሆንም በወቅቱ ግን የሐኪማቸው ስልክ ስላልነበራቸው በነጋታው መጥተው እንዲያክሟቸው ቢጠሯቸውም እንዲያክሟቸው እንዳልተፈቀደ እና እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ አቃቤ ሕግ ""በወቅቱ አስቸኳይ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ከነበር ሐኪማቸውን ጠርተው እንዲታከሙ ነግረናቸው ነበር። ይሁን እንጂ ስልካቸው የለኝም በማለት ሊ��ከሙ አልቻሉም። ከዚያ ውጪ ግን ባለው ደንብ መሰረት ነው መታከም ያለባቸው"" በማለት ለችሎቱ አስረድቷል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም አቶ ጃዋር መሐመድ በፌደራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል ሁኔታዎችን ማመቻቸቱንና እዚያ የሚታከሙ ከሆነም ""ለሕይወታቸው ዋስትና"" እንደሚሰጥ ተናግሯል። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ የሕገ-መንግሥቱን አንቀጽ 21 በመጥቀስ፣ አቶ ጃዋር መሐመድ በግል ሐኪማቸው የመታከም መብት እንዳላቸው ይህም እንዲፈፀም ትዕዛዝ ሰጥቷል። በሌላ በኩል በተጠርጣሪዎች በጠበቆቻቸው በኩል እንደ ቅሬታ ሲነሳ የነበረው የካሜራ ጉዳይ ነው። ይህም ጠበቆች ደንበኞቻቸውን የሚያናግሩበት ስፍራ ላይ ምስልና ድምጽ የሚቀርጽ ካሜራ በመገጠሙ ምስጢራቸው በተጠበቀ መልኩ ደንበኞቻቸውን ማናገር እንዳልቻሉ ነሐሴ 11 2012 በነበራው የችሎት ውሎ ላይ ተናግረው ነበር። ፍርድ ቤቱም ጠበቆች ደንበኞቻቸውን ምስጢራቸው በተጠበቀ መልኩ ማግኘት እንዲችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ ጠበቆች ትናንት ለችሎቱ እንዳስረዱት፣ ደንበኞቻቸውን ለማነጋገር ሰኞ፣ ረብዑ እና አርብ ቀጠሮ እንደተያዘላቸው ገልፀው ረብዑ እለትም ወደ ስፍራው ባመሩበት ወቅት ካሜራው እንደተገጠመ መሆኑን መመልከታቸውን ገልፀው ስልክ ቁጥራቸውን ትተው ሲስተካከል እንዲጠሯቸው በመንገር መመለሳቸውን ገልፀዋል። በእለቱም (ረብዑ 13/2012) ወደ አስር ሰዓት አካባቢ ተደውሎላቸው መጠራታቸውን፣ ይሁን እንጂ በመምሸቱ የተነሳ ደንበኞቻቸውን ሳያነጋግሩ መመለሳቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለችሎቱ ተናግረዋል። ""ዛሬ እንዳነጋግራቸው ነው ተነጋግረን የተመለስነው፤ ዛሬ ጠዋት ስንሄድ ደግሞ ያለ ቀናችሁ ነው የመጣችሁት ገብታችሁ ማናገር አትችሉም ተብለን ተመልሰናል እና ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እያከበረ አይደለም"" በማለት እንዲስተካከልላቸው በመጠየቅ ለችሎቱ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። ፖሊስ በበኩሉ የተገጠመው ካሜራ ቤተ መጻህፍትን ለመጠበቅ እንደሆነ በመናገር፣ ጠበቆች ከደንበኞቻቸው ጋር እንዲገናኙ ሌላ ስፍራ ማመቻቸታቸውንና መገናኘታቸውን ለዚህም ደግሞ ጠበቆች ወደ ቅጽር ግቢው ገብተው ደንበኞቻቸውን ሲያናግሩ የፈረሙበትን መዝገብ ማቅረብ እንደሚችሉ ለችሎቱ ተናግሯል። ይሁን እንጂ ጠበቆች ""ከዚህ በፊት በነበረው አሰራር ገብተን ደንበኞቻችንን አናግረን ስንወጣ ነው የምንፈርመው አሁን ገና ደንበኞቻችንን ሳናገኝ እንድንፈርም ይደረጋል፤ ገና ወደ ውስጥ ስንገባ፥ ሳናገኛቸው እየተመለስን ነው"" ብለዋል። ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አድምጦ፣ ጠበቆች ደንበኞቻቸውን ምስጢሩ በተጠበቀበት ስፍራ ማግኘት አለባቸው። ይህም መፈፀም አለበት፤ ይህ ካልተፈፀመ ግን ሕጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ በመግለጽ ውሳኔ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የቅድመ ምርመራ መዝገብ ሥራ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች በሙሉ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ የኦኤምኤን ጋዜጠኛው አቶ መለሰ ዲሪብሳን ጨምሮ በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ስር ለሚገኙ ለአራት ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራው አለመካሄዱን ጠበቃው አቶ ዋቤ ሐጂ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ መለሰ፤ ""ከእኛ ጋር ታስረው የነበሩ ሰዎች በኮሮና ተይዘዋል። ፍርድ ቤቱም ከዚህ ቀደም ምርመራ እንዲደረግልን አዞ ነበር። ይሁን እንጂ እስካሁን ምርመራ አልተደረገልንም። ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እያከበረ አይደለም"" ሲሉ ለችሎቱ አቤቱታቸውን አቅርበዋል። ከዚህ በተጨማሪም አቶ መለሰ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ቤተሰቦቻቸውን በስልክ እያገኙ መሆኑን እና እርሳቸው ግን ይህን መከልከላቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። በስተመጨረሻም ችሎቱ የተጠርጣሪዎች እንዲሁም የአቃቤ ሕግ አቤቱታ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት እንዲሁም ደግሞ የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለነሐሴ 18 2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።" https://www.bbc.com/amharic/53852370 +health የአሜሪካ ግዛቶች የኮቪድ-19 ክልከላዎችን ማንሳት ጀመሩ የቴክሳስ፣ ሚሺጋን፣ ሉዊዚያና እና ሚሲሲፒ ግዛቶች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይሆንም አሉ። የግዛቶቹ አስተዳዳሪዎች ከዚህ ውሳኔ የደረሱት ኮቪድ-19 በአሜሪካ ለአራተኛ ዙር ሊሰራጭ ይችላል የሚል ስጋት ባለበት ወቅት ነው። ሪፓብሊካኑ የቴክሳስ ገዢ ግሬግ አቦት፤ “ቴክሳስን 100% ለመክፈት ጊዜ አሁን ነው” ብለዋል። ቴክሳስ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይደለም በማለት ያወጀች ትልቋ የአሜሪካ ግዛት ነች። በዚህም መሰረት ከአንድ ሳምንት በኋላ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይሆንም። ዜጎችም በመንግሥት ተቋማት ማስክ ሳያደርጉ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፤ በገበያ ስፍራዎችም ማስክ ሳያደርጉ መገበያየት ይችላሉ። የሚሲሲፒ ገዢ በበኩላቸው በቀጣይ ቀናት የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይሆንም ብለዋል። ታቴ ሪቭስ፤ “ማስክ የማድረግ ግዴታ እናነሳለን። የንግድ ተቋማትም ከነገ ጀምሮ በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ” ሲሉ ተናግረዋል። የባይደን አስተዳደር ግን አሁንም ቢሆን የኮሮናቫይረስ ክልከላዎች መተግበር አለባቸው የሚል ጽኑ አቋም አለው። የኮሮናቫይረስ ክትባት በአሜሪካ በስፋት በመከፋፈሉ፤ በርካታ አሜሪካውያን ክትባቱን በመውሰዳቸው ሕይወት ወደቀደመ መልኩ ለመመለስ ፍላጎት እንዲጨምር አድርጓል ተብሏል። ባይደን ትናንት አሜሪካ ለሁሉም አዋቂ አሜሪካውያን እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የኮቪድ-19 ክትባት ማቅረብ ይቻላታል ብለዋል። በቅርብ ሳምንታት በቫይረሱ የሚያዙ እና የሚሞቱ አሜሪካውያን ቁጥር ቀንሷል። ይሁን እንጂ የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) አገሪቱ አስፈላጊውን ጥንቃቄ የማታደርግ ከሆነ ወረርሽኙ ለ4ኛ ዙር ሊከሰት ይችላል ሲል አስጠንቅቋል። አሜሪካ እስካሁን 28 ሚሊዮን ሕዝቧ በቫይረሱ መያዙን በምርመራ ያረጋገጠች ሲሆን፤ 516 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከበሽታው ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን አጥተዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-56262360 +business ኢቲ 302 ቦይንግ 737፡ ልክ የዛሬ አንድ ዓመት በኢትዮጵያው አውሮፕላን ላይ ምን ተከሰተ? "ዕሑድ መጋቢት 1 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ለኢትዮጵያዊያን አስደንጋጭ ዕለት ነበር። እርግጥ 'የኢትዮጵያ'' ታሪኩ የከፍታ ነው። የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ሲንደፋደፍ 'ET' ከፍ ብሎ በሯል፤ያውም ለዘመናት። በትርፍም፣ በአውሮፕላን ብዛትም፣ በበረራ ስፋትም፣ በመስተንግዶ ጥራትም ሞገስ ተለይቶት አያውቅም። በጥቅሉ ከፍ እንጂ ዝቅ ብሎ አያውቅም። በዚያች ሰንበት ግን 'ማክስ-8' ጎንበስ ካለበት ቀና አልል አለ። አብራሪዎቹ የቻሉትን ሞከሩ። አልሆነም። • ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በመግለጫ ምልልስ እየተወዛገቡ ነው የአውሮፕላኑ ሠሪዎች ጥፋቱን በአብራሪዎች ለመደፍደፍ የቀደማቸው አልነበረም። መጀመርያ ጥርጣሪያቸውን አስቀደሙ፤ ቀጥለው የሚዲያ ዘመቻ ከፈቱ። ችግሩ ከአብራሪዎቹ ካልሆነ ከአውሮፕላኑ ፈጣሪዎች እንደሚሆን አላጡትም። ጣት ወደነርሱ ሲቀሰር ደግሞ ሌላ ቁስል ይቀሰቅሳል፤ ኢንዶኒዢያ። ያን ቁስል መልሶ መነካካት የቦይንግን ስምና ዝና ጠራርጎ የሚወስድ ችግር ያስከትላል። ስለዚህ በቻሉት ሁሉ ነገሩን ከነገርሱ ማራቅ ነበረባቸው። ያን ዕለት ማለዳ ምን ሆነ? ከራሱ አልፎ ለአህጉሪቱ አየር መንገዶች በክፉ ጊዜ ደርሶላቸዋል። በዚህ ከፍታ ላይ እያለ ነበር ክፉው አጋጣሚ የተከሰተው። በማለዳ ዘመናዊውን ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ወደ ናይሮቢ አሰማራ። ብዙ ጊዜ ሙሉ በሚባል ደረጃ ተጓዦችን የሚያስተናግደው የናይሮቢው በረራ 149 መንገደኞችን አሳፍሮ ነበር። ተጨማሪ 8 የአውሮፕላኑ ሠራተኞችም ነበሩበት። የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ወደ ናይሮቢ ኬንያ ለመብረር እንዲያኮበኩብ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን መልካም ፈቃድ ያገኘው ከጠዋት 02 ሠዓት ከ37 ደቂቃ ነበር። አውሮፕላኑ ክንፉን ዘርግቶ ተንደርድሮ ተነሳ። ልክ ከአንድ ደቂቃና ከ10 ሰከንዶች በኋላ ከተለመደው የተለየ ሁኔታ እንዳጋጠመ በአብራሪዎቹ ታወቀ። ረዳት አብራሪው ለዋና አብራሪው ይህንኑ አሳወቀ። ዋና አብራሪውም ችግሩን ለማስወገድ በማለት አውሮፕላኑ በራሱ ሥርዓት እንዲበር ጥረት ማድረግ ጀመረ። አብራሪዎቹ የገጠማቸውን ችግር ለማስተካከል ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም እንዳሰቡት ሊሳካላቸው አልቻለም። ወዲያውኑ ረዳት አብራሪው ስላጋጠማቸው ነገር ለአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ሪፖርት አደረገ። ረዳት አብራሪው ለአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አውሮፕላኑን የመቆጣጠር ችግር እንደገጠመው አሳወቁ። ብዙም ሳይቆዩ አውሮፕላኑ ከአብራሪዎቹ ቁጥጥር ውጪ እየሆነ መጣ። አፍንጫውን ወደ ምድር እያገደለ አስቸገረ። አብራሪዎቹ ይህንን ለማስተካከል በከፍተኛ ጥድፊያ ጥረት እያደረጉ ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር በመገናኘት 14ሺህ ጫማ ላይ መቆየት እንደሚሹ ገለጹ። አውሮፕላኑ ቀና ሊል አልቻለም። ጭራሽ አልታዘዝ አለ። የጀመሩት በረራ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ስላጋጠመው ወደ ተነሱበት ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ መመለስ እንደሚፈልጉ አሳወቁ። ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ወዲያውኑ ፍቃድ አገኙ። ይህ ሁሉ የሆነው በደቂቃዎች ልዩነት ነበር። አሁንም አብራሪዎቹ አውሮፕላኑ ካዘቀዘቀበት ከፍ ለማድረግ ጥረታቸው አልተቋረጠም፤ አውሮፕላኑ ግን በስሪቱ ግድፈት እንደሆነ በሚገመት መልኩ አሻገረኝ አለ። ይባስ ብሎ ቁልቁል መምዘገዘግ ጀመረ። በመጨረሻም አብራሪዎቹ ከበረራ ተቆጣጣሪዎች ጋር የነበራቸው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ። የአቶ ተወልደ ትዝታ ከ150 በላይ ሰዎችን የያዘው የኢቲ302 የአውሮፕላን ሳይከሰከስ እንዳልቀረ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስጋት ቢገባቸውም ለደቂቃዎች ተስፋ አልቆረጡም ነበረ። ከደቂቃዎች በኋላም የአሰቃቂው አደጋ መከሰት የማይሸሹት እውነት ሆነ። የአደጋውን መከሰት ቀድመው የሰሙት የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሰንበት ቅዳሴን እየታደሙ ነበር። ""የአደጋውን መድረስ ዜና የሰማሁት ጧት ነው። በእርግጥም በጣም ክው አድርጎኛል። በጣም፤ እጅግ በጣም ነው ያሳዘንኩት"" ሲሉ መጋቢት አንድ ቀን ጠዋት የተፈጠረባቸውን ስሜት ያስታውሳሉ። እሁድ ረፋድ ላይ የአደጋውን መከሰት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጽህፈት ቤት በማኅበራዊ ገጹ ላይ አረዳ። በደረሰው አደጋም ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም ሐዘኑን ገለጸ። ከዚህ በኋላ አደጋው የዓለም መገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ርእስ ሆነ፤ የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ብርክ ያዘው። ተመሳሳይ አውሮፕላን የገዛ ሐሳብ ገባው። ሊገዛ ያሰበ ቀብዴን መልሱልኝ ማለት ጀመረ። የቦይንግ ገበያ ምስቅልቅል ውስጥ ገባ። በተለይ ከዚህ አደጋ ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ የኢንዶኔዢያ ላየን ኤር አየር መንገድ አሰቃቂና በባህሪው ተመሳሳይ አደጋ አጋጥሞት እንደነበር ሲታወስ ነገሮች ወዴት እያመሩ እንደሆነ ግልጽ ነበር። ለአደጋው ምክንያት ተለያዩ መላ ምቶች ቢቀርቡም በአውሮፕላኑ ላይ ያለ ችግር ሊሆን እንደሚችል በመገለጹ ጥያቄዎች በአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ ላይ በረታ። ይህንንም ተከትሎ ሌላ አደጋን ለማስቀረት እጅግ ዘመናዊ እንደሆኑ የተነገረላቸው ቦይንግ 737 ማክስ 8 ስሪት አውሮፕላኖች ከበረራ ውጪ የማድረግ እርምጃን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ አየር መንገዶች ወሰዱ። በኢትዮጵያ አውሮፕላን ላይ የደረሰው አደጋ እጅግ የከፋ ስለነበረ አንድም ሰው ከአደጋው አልተረፈም። ከአዲስ አበባ በ40 ኪሎ ሜትሮች አካባቢ ርቀት ላይ ከምትገኘው ቱሉ ፈራ ሜዳ ላይ የወደቀውን የአውሮፕላኑን ስብርባሪና የአደጋውን ሰለባዎች አካል ለማግኘት የቀናት ቁፋሮ አስፈልጎ ነበር። ለሟች ቤተሰቦች ሐዘኑ ድርብ ሆነ። ከአደጋው ጋር በተያያዘ አንዳንድ ወገኖች የአብራሪዎች ችግር አድርገው ለማቅረብ ቢሞክሩም የአደጋው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ግን አብራሪዎቹ ክስተቱን ለማስቀረት መጣራቸውንና በአውሮፕላኑ ላይ የተገጠመው የመቆጣጠሪያ ሥርዓት ለአደጋው ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አመልክቶ ነበር። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማሪያምም ከመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ጋር በተያያዘ ""ፓይለቶቹ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው የሚጠበቅባቸውን ተገቢ እርምጃ በመውሰድ ያላቸውን ከፍ ያለ ሙያዊ ብቃት በማስመስከራቸው"" አየር መንገዱ እንደሚኮራባቸው መስክረዋል። አደጋው በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ሕይወት ከማሳጣቱ ባሻገር ዘመናዊ የተባለውን አውሮፕላን ባመረተው ቦይንግ ኩባንያ ላይ ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎችን አስከትሏል። በኩባንያው ላይ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ዋና ሥራ አስፈጻሚውም ከሥራቸው ተባረዋል። ተመሳሳዩን አውሮፕላን እንዲያመርትላቸው ያዘዙ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶችም ትዕዛዛቸውን ከመሰረዝ አልፈው ሥራ ላይ የነበሩትን ከበረራ ውጪ አደረጓቸው። በዚህም ባለዝናው የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ በወራት ጊዜ ውስጥ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ኪሳራ አጋጠመው። ጉዳዩም ዛሬም ድረስ መቋጫ አላገኘም።" https://www.bbc.com/amharic/news-51797891 +health የዝንጀሮ ፈንጣጣ ለኢትዮጵያ ምን ያህል ስጋት ነው? "በአሁኑ ጊዜ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ ቢያንስ በ13 አገራት ከ90 በላይ ሰዎች ላይ መከሰቱ የዓለም ጤና ድርጅት አረጋግጧል። በሽታው በስፋት የታየው በአሜሪካ እና በአውሮፓ አገራት ውስጥ ነው። በንክኪ የሚተላለፈው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከኮቪድ-19 ጋር ሲነጻጸር የመዛመት ፍጥነቱ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ እንደ ዩናይትድ ኪንግድም ያሉ አገራት ""ችላ የምንለው አይደለም"" ብለው በልዩ ትኩረት እየሰሩ ነው። ለመሆኑ ይህ በሽታ ኢትዮጵያን ያሳስባታል? በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲቲዩት የበሽታዎች ቅኝት እና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ወሰን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በኢትዮጵያ የመከሰት ""ከፍተኛ ዕድል አለው ብለን እናስባለን"" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ዳይሬክተሩ የወርርሽኞች አቅም እና የመተላለፊያ መንገዶቻቸው የበሽታውን አሳሳቢነቱን እንደሚወስኑ ያብራራሉ። ""ብዙ አገራትን የሚያዳርሱ በሽታዎች ብዙ ጊዜ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚዛመቱት በትንፋሽ የሚተላለፉት በሽታዎች ናቸው"" የሚሉት አቶ መስፍን ቀጥሎ ያለውን ደረጃ የሚይዙት ደግሞ በንክኪ የሚተላለፉት መሆኑናቸውን ጠቁመዋል። በንክኪ የሚተላለፉ በሽታዎች በፍጥነት የመዛመት ዕድላቸው ዝቅ ያለ ነው። ""ያ ማለት ግን ከአገር ወደ አገር አይተላለፍም ማለት አይደለም።"" እዚህ ጋር የዝንጀሮ ፈንጣጣ በንክኪ እንደሚተላለፍ ልብ በሉ። ዳይሬክተሩ በሽታው እስካሁን በኢትዮጵያ እንዳልተከሰተ ገልጸዋል። በኢት���ጵያ በታሪክም በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው ተመዝግቦ አያወቅም። ሆኖም በሽታው ከተከሰተባቸው አገራት የሚነሳ ማንኛውም ሰው የዝንጀሮ ፈንጣጣን ""በቀላሉ"" ወደ ኢትዮጵያ ይዞት ሊመጣ እንደሚችል ነው አቶ መስፍን የሚናገሩት። ""የኢትዮጵያ ሁኔታ ከአፍሪካ አገሮች ወደ አውሮፓ እና ከአውሮፓ ወደ አፍሪካ አገራት ብዙ ትራንዚት እና ከፍተኛ የሰዎች ዝውውር ስላለ ከፍተኛ የመከሰት ዕድል አለው... ለሌሎችም አገራት ስጋት እስከሆነ ድረስ ለእኛም ስጋት መሆኑ አይቀርም፤ እኛም እየተንቀሳቀስን ያለነው ለአገራችንም ስጋት ነው ብለን ነው"" ብለዋል። አቶ መስፍን ይህ በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓ አገራት በስፋት እየታየ ያለው በሽታ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ""በተቻለ መጠን"" አስፈላጊውን ተግባር እያከናወኑ መሆናቸውን አመልክተዋል። ራስ ምታት እና ከ35.5 በላይ የሆነ የሰውነት ሙቀት [ትኩሳት] ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ምልክቶች ውስጥ መካከል ይካተታሉ። በዚህም መነሻ በአገሪቱ በሁሉም ዓለምአቀፍ የየብስ እና የአየር በሮች ላይ የሙቀት ልኬት እየተከናወነ ነው። ከሚጠበቀው በላይ የሆነ የሰውነት ሙቀት ያላቸው ሰዎች ለዚሁ ዓላማ ወደተዘጋጁ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት ተወስደው ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚደረግላቸው ያነሱት ኃላፊው፣ ለባለሙያዎች ሥልጣና እየተሰጠ እና በሽታው ቢያጋጥም የሚወሰዱ እርማጃዎችን በሚመለከት ""የምላሽ መመሪያ"" እየተዘጋጀ ነው ብለዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢከሰትስ? አቶ መስፍን እንደሚሉት በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢከሰት በሚል መነሻ አስፈላጊ ግብአቶችን የሟሟላት እና አቅም የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። በሁሉም ክልሎች ይህንን በሽታ የሚቆጣጠሩ ግብረ ኃይሎችን ማቋቋም፣ የተያዙ ሰዎችን ጉዳይ ለመከታተል የሚስችሉ ሥርዓቶችን ማጎልበት፣ የፈጣን ምላሽ ቡድን ማዋቀር እና የአቅም ግንባታ ተግባራትን በክልሎች ለማከናወን ""የዓለም ጤና ድርጀትን ጨምሮ ከሌሎች አጋሮች ጋር እየሰራን ነው"" ሲሉም አክለዋል። ወደ አገሪቱ መግቢያ እና መውጫ በሆኑ በሮች በሚደረጉ ምርመራዎች እስካሁን ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር የተያያዘ አሳሳቢ ሁኔታ አለመከሰቱን ኃላፊው አመላክተዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድን ነው? የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በተሰኘ ቫይረስ የሚከሰተው በሽታው 'ስሞልፎክስ' ተብሎ የሚጠራው የፈንጣጣ ዝርያ ውስጥ የሚካተት ነው። ከሰው ብቻ ሳይሆን ከእንስሳት እና ቫይረሱ ካለባቸው ቁሶች ጋር በሚኖር ንክኪ የሚተላለፈው በሽታው ለምጀመሪያ ጊዜ እንደ አውሮፓውያኑ በ1958 በዝንጀሮ ላይ የተገኘ ነው። በ1978 ደግሞ በዲሞክራቲክ ኮንንጎ በሰው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘቱ ተረጋግጧል። በገጠራማ የማዕከላዊ እና ምዕራባዊ አፍሪካ አገራት በፋት የሚያጠቃው የዝንጀሮ ፈንጣጣ እጅግ አሳሳቢ የሚባል አይደለም። በሽታውን 85 በመቶ መከላከል እንደሚችል የተረጋገጠ ክትባትም አለው። አንዳንድ ጊዜ ያለምንም ህክምና በራሱ ጊዜ ሊጠፋ የሚችል ነው ። ሆኖም በምዕራብ አፍሪካ በበሽታው ምክንያት ህይወት አልፏል። የበሽታው የሞት ምጣኔ ከ3 እስከ 6 በመቶ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጀት ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል። ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የሰውነት እብጠት፣ የጀርባ እና የጡንቻ ህመም ደግሞ የበሽታው ምልክቶች ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/news-61564071 +health በቀጣይ በዓለም ላይ የሚከሰቱ ወረርሸኞች ከኮቪድ በላይ ገዳይ ሊሆኑ ይችላሉ ተባለ "በዓለማችን ከዚህ በኋላ የሚከሰቱ ወረርሽኞች ከኮሮረናቫይረስ በላይ የከፉ ገዳይ ሊሆኑ እንደሚችሉ የኦክስፎርድ አስትራዜኔካ ክትባትን ከፈጠሩት ተመራማሪዎች መካከል አንዷ ባለሙያ ተናገሩ። ፕሮፌሰር ሳራ�� ጊልበርት እንደሚሉት ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ዝግጁነት ለመደገፍ መንግሥታት በቂ ድጋፍ ማድረግ ያለባቸው ሲሆን አሁን የተገኙ ስኬቶችንም ማስቀጠል አስፈላጊ ነው። ፕሮፌሰሯ አክለውም ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት ክትባቶች አዲሱን የቫይረስ አይነት ኦሚክሮን ለመከላከል ብዙም አቅም ላይኖራቸው እንደሚችልም ጠቁመዋል። ስለአዲሱ ቫይረስ በቂ መረጃ እስከሚገኝ ድረስ ሰዎች በጥንቃቄ እንዲንቀሳቀሱም መክረዋል። ""ወረርሽኝ ሕይወታችንን እና አኗኗራችንን አደጋ ላይ ሲጥል ይህ የመጨረሻው የሚሆን አይመስለኝም። እውነታው ቀጣዩ ወረርሽኝ በጣም ከባድ ሊሆን እንደሚችል ነው። በፍጥነት የሚዛመት፣ በከፍተኛ ሁኔታ ገዳይ አልያም ሁለቱንም ያጣመረ ሊሆን ይችላል"" ብለዋል። ""በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ያለፍነውን ችግር መርሳት የለብንም። ወረርሽኙ በምጣኔ ሀብታችን ላይ ያሳደረው ጫና ወደፊት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን እንዳንቆጣጠር ሊያደርገን አይገባም'' ሲሉ ያሳስባሉ። ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት ስለአዲሱ ኦሚክሮን ቫይረስ ሲናገሩ ""አዲሱ ቫይረስ እራሱን አሻሽሎ ስለመጣ በክትባት መልክ ወይም በኮሮረናቫይረስ ስንያዝ የምናዳብረው በሽታ የመከላከል አቅም ብዙም ላይጠቅመን ይችላል"" ብለዋል። አክለውም ስለአዲሱ ቫይረስ በቂ መረጃ እስከሚገኝና ምርምሮች እስከሚደረጉ ድረስ ሰዎች ስርጭቱን ለመቀነስ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። በኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የተገኘው ትምህርትና ክትባቶችን በፍጥነት የማድረስ ልማድ ሊቀጥል እንደሚገባ ያሳሰቡት ፕሮፌሰሯ ከዚህ በኋላ መሰል እርምጃዎች የተለመዱ መሆን አለባቸው ብለዋል። የኦሚክሮን ስርጭትን ለመቆጣጠር እንዲቻል በማለት ቅዳሜ ዕለት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚጓዙ ሰዎች ከበረራቸው አስቀድመው የኮሮረናቫይረስ ምርምራ እንዲያደርጉ መንግሥት አሳስቧል። በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እስካሁን 246 ሰዎች በአዲሱ ኦሚክሮን መያዛቸው የተረጋተጠ ሲሆን ትናንት ዕሁድ ዕለት ብቻ 86 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መንግሥት አስታውቋል። ነገር ግን የዩኬን መንግሥት የሚያማክሩ አንድ ተመራማሪ የጉዞ እገዳውና ሌሎች መመሪያዎች የዘገዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕሮፌሰር ማርክ ዉልሐውስ እንደሚሉት የመንግሥት ውሳኔ የዘገየ ሲሆን እዚህ ግባ የሚባል ለውጥ ያመጣል ብለው እንደማያምኑም ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59545549 +politics የነዳጅ አምራች አገራት ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ምርታቸውን እምብዛም እንደማይጨምሩ አስታወቁ ምንም እንኳን የዓለም የነዳጅ ዋጋ በሰባት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ በሚባል ደረጃ ከፍ ቢልም ትልልቅ የሚባሉት ነዳጅ አምራች አገራት ግን የነዳጅ ምርታቸውን መጠን በትንሹ ብቻ እንደሚጨምሩ አስታውቀዋል። በሩሲያ የሚመራው የነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት ኦፔክ እና አጋሮቹ በምንም አይነት ሁኔታ ከድንበራቸው የሚወጣ ነዳጅ እምብዛም ከፍ እንደማያደርጉ ነው የተገለጸው። 23 አባል አገራት ያሉት ድርጅቱ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በየቀኑ ተጨማሪ 400 ሺ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ብቻ ለገበያ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል። ድርጅቱ በአውሮፓውያኑ 2021 አባል አገራት በተስማሙበት የምርት ሂደትን ይከተላል። አገራቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቀንሶ የነበረውን ምርት ቀስ በቀስ ለማስተካከል ነበር የተስማሙት። በወቅቱ የነዳጅ ፍላጎት በመቀነሱ አገራት የምርት መጠናቸውን ለመቀነስ ተገድደው ነበር። ነገር ግን ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ የአንድ ድፍድፍ በርሜል ነዳጅ ዋጋ 113 ዶላር ደርሷል። ኦፔክ+ የሰሞኑን የነዳጅ ዋጋ መጨመርና ስጋት በተመለ��ተ ባወጣው መግለጫ ላይ በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ምርት እጥረት እንደሌለ ገልጿል። በሌላ በኩል የዓለም አቀፉ ኢነርጂ ኤጀንሲ አባል አገራት በበኩላቸው ከወሳኝ መጠባበቂያዎቻቸው ተጨማሪ ነዳጅ 60 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ለመልቀቅ ተስማምተዋል። ከዚህ ነዳጅ ግማሽ የሚሆነው የሚመጣው ከአሜሪካ እንደሚሆን ይጠበቃል። ነገር ግን ይህ ውሳኔ እንኳን የስቶክ ገበያውንም ሆነ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ግሽበት በአፋጣኝ ያስተካክለዋል ተብሎ አይጠበቅም። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት የነዳጅ ዋጋ በቅርብ ወራት ውስጥ ወደነበረበት የመመለስ ዕድሉ ጠባብ ነው። እንደ ቢፒ እና ሼል ያሉ ትልልቅ የነዳጅ አጣሪና አከፋፋይ ድርጅቶች ከሩሲያ ለቅቀው እንደሚወጡ ማስታወቃቸው ደግሞ ገበያው እንዳይረጋጋ እንደሚያደርገው ተገልጿል። እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት የሩሲያ የነዳጅ ደንበኞች ትልቅ ችግር እየገጠማቸው ነው። የምዕራቡ ዓለም አገራት ሩሲያ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ተከትሎ ድርጅቶቹ ክፍያ መፈጸም ሆነ መቀበል እንዲሁም የነዳጅ ዝውውር ላይ ከፍተኛ ጫና እያጋጠማቸው ነው። ''በአጭር ጊዜ ውስጥ የነዳጅ ዋጋ ሲጨምር እየተመለከትን ነው። ከሩሲያ ጋር በተያያዘ ያለው ግራ መጋባት የነዳጅ ገበያው እንዳይረጋጋ አድርጎታል'' ይላሉ በዋሽንግተን የስትራቴጂክ እና ዓለም አቀፍ ጥናት ባለሙያው ቤን ካሂል። ነዳጅ አምራች አገራት ምርታቸውን ለምን መጨመር አልፈለጉም? ቁልፍ የሚባሉት ነዳጅ አምራች አገራት አሁን ላይ ያለውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር በሚል ምርት ብንጨምር በሚቀጥለው ዓመት ላይ ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ ምርት ገበያው ላይ ሊትረፈረፍ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ይህ ደግሞ የነዳጅ ዋጋና በእጅጉ ያወርደዋል። ምንም እንኳን አንዳንድ የነዳጅ ላኪ ድርጅቶች ከሩሲያ የሚመጣውን አንደኛ ደረጃ ነዳጅ በርካሽ ዋጋ ለማሸጥ ቢሞክሩም ገዢ እንደጠፋ እየተነገረ ነው። ሩሲያ ከአሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ በመቀጠል የዓለማችን ሶስተኛዋ የነዳጅ አምራች አገር ነች። በዚህም ከዓለማችን የነዳጅ ፍላጎት ከ8 እስከ 10 በመቶ የሚሆነውን የምታሟላው ሩሲያ ነች። ከዚህ በተጨማሪ አብዛኛው አውሮፓ 40 በመቶ የሚሆነውን የተፈጥሮ ጋዝ የሚያገኘው ከሩሲያ ነው። ለዚህም ይመስላል የምዕራቡ ዓለም አገራት ሩሲያ ላይ ከነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ጋር በተያያዘ ጠንካራ ማዕቀብ መጣል የከበዳቸው። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት የኦፔክ+ አባል አገራት በዩክሬን ሩሲያ ቀውስ ምክንያት ወደፊት ሊከሰት የሚችለውን ቀውስ ከማየት ይልቅ አሁን ላይ ገበያው ምን ይመስላል የሚለውን ከግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚፈልጉ ይገልጻሉ። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እየጨመረ በመጣው የነዳጅ ዋጋ ምክንያት ትንሽ የተደናገጡ ይመስላል። እንደ ሳኡዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያሉ የኦፔክ+ አባል አገራት ላይ ጫና ለማሳደር ቢሞክሩም እምብዛም አልተሳካለቸውም። በሌላ በኩል ደግሞ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአቡ ዳቢ ልዑል ሼክ ሞሀመድ ቢን ዛይድ ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም የኦፔክ+ አባል አገራት የወሰኑት በወሰኑት ውሳኔ ላይ ስለመጽናት ተነጋግረዋል። እስካሁን ድረስ በርካታ የመካከለኛው ምስራቅ ነዳጅ አምራች አገራት ከዩክሬን ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዝምታን የመረጡ ይመስላል። ባሳለፍነው ሳምንት የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የሩሲያን ወረራ የሚቃወም የአቋም መግለጫ ሲያወጣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በድምጸ ታቅቦ አልፋለች። ተንታኞች እንደሚሉት ዩኤኢ እና ሳኡዲ አረቢያ በጉዳዩ ላይ የገለልተኝነት ውሳኔ እየተከተሉ ነው ብለዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-60598934 +health ከአራስ እስከ 114 ዓመት ዕድሜ የኮቪድ-19 ሕሙማንን ያከመው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ውለታ "ላለፉት ሁለት ዓመታት መላውን ዓለም አዳርሶ 15 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት የመጀመሪያ ወቅት ሥራ የጀመረው ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በኢትዮጵያ የወረርሽኑ ጥረት ውስጥ ጉልህ ቦታን ይዟል። ስለ ወረርሽኙ ምንነትና አጠቃላይ ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ባልነበረበት ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕሙማንን ተቀብሎ ያስተናገደው ሆስፒታሉ፣ ባለፈው ሐሙስ በእንክብካቤው ስር የነበሩት ብቸኛ ታካሚ አገግመው ወደ ቤታቸው በመሄዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ሆስፒታሉ ውስጥ የኮቪድ ታማሚ እንደሌለ አሳውቋል። የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ታካሚው አገግመው ወደ ቤታቸው በመሸኘታቸው ላለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ የኮቪድ-19 የሕክምና ማዕከል ሆኖ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለው ሆስፒታል ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ታካሚ ውሎ አድሯል። የሕክምና ማዕከሉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽን በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በሁሉም የበሽታው ማዕበል ደረጃዎች ወቅት ሕምና የሚያስፈልጋቸውን ሕሙማን ሲያገለግል ቆይቷል። አገሪቱን ባጋጠሟት አራት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማዕበሎች ውስጥ ባለፉት ሁለት ዓመታት ምንም ታካሚ ሳይኖር ያሳለፉበት ጊዜ እንዳልነበረ ዶ/ር ያሬድ አስታውሰዋል። በአራተኛው ማዕበል ተቀብለው ሕክምና ሲሰጧቸው ከነበሩ ሕሙማን መካከል የሕክምና ባለሙያ የሆኑት ታካሚ አስፈላጊውን ድጋፍ አግኝተው በማገገማቸው ነው ሐሙስ መጋቢት 27/2041ዓ. ም. ከሆስፒታሉ የተሸኙት። በዚህም ሆስፒታሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሕክምና የሚያስፈልገው አንድም ታማሚ ሳይረኖረው 24 ሰዓታትን አሳልፏል። ""ሕክምናውን በተሳካ ሁኔታ ጨርሶ የተሸኘው ሰው፣ በወረርሽኙ አራተኛ ማዕበል አገግሞ ከሆስፒታሉ የወጣ የመጨረሻው ሰው ይሆናል ብለን ተስፋ እንዳርጋለን"" ሲሉ ዶ/ር ያሬድ ለቢቢሲ ምኞታቸውን ተናግረዋል። ኮቪድ-19 መጋቢት 04/2012 ዓ. ም. በኢትዮጵያ ውሰጥ መገኘቱ ሲረጋገጥ በአገሪቱ የተገኘ የመጀመሪያውን ጃፓናዊ ታማሚ በመቀበል ሥራ የጀመረው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል፣ ከሁለት ዓመታት ያልተቋረጠ አገልግሎት በኋላ ስማቸው ያልተገለጹትን ለአሁኑ የመጨረሻው ሊባሉ የሚችሉትን ሕመምተኛ አክሞ ለመሸኘት በቅቷል። በሁለት ዓመታት ውስጥ ሐሙስ ዕለት አገግመው እስከወጡት ታካሚ ድረስ ሆስፒታሉ 6546 የኮሮናቫይረስ ሕሙማንን ያስተናገደ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ ወይም 87 በመቶ የሚሆኑት ባገኙት ሕክምና አገግመው መውጣታቸውን ዶ/ር ያሬድ ገልጸዋል። ከዚህ ባሻገር ከ800 በላይ የሚሆኑት ወይም አጠቃላይ ሆስፒታሉ ካስተናገዳቸው ሕሙማን መካከል 13 በመቶው ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ለህልፈት ተዳርገዋል። የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ይህንን አገልግሎት በሰጠባቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ወረርሽኙ የተለያዩ ጫናዎች ባለሙያዎች ላይ አሳድሮ እንደነበር የሚያስታውሱት ዶ/ር ያሬድ ""በተለይ በመጀመሪያው ጊዜ ላይ ስለ በሽታው ዝርዝር ሁኔታ ከነበረው ዝቅተኛ መረጃ አንጻር ባለሙያዎች ከፍተኛ የሥነ ልቦና ጫና ገጥሟቸው ነበር"" ይላሉ። ነገር ግን የሕክምና ባለሙያዎቹ ቃል ኪዳናቸውን ጠቀብቀው አገራቸውንና ሕዝባቸውን በማስቀደም በዚያ አስፈሪና አስቸጋሪ ወቅት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ባለፉት ሁለት ዓመታት ያለማቋረጥ ለመወጣት ችለዋል። በተለይ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሕሙማን ወደ ሆስፒታሉ በብዛት መምጣት በጀመሩበት በሁለተኛው እና በሦስተኛ ዙር የወረርሽኑ ማዕበል ወቅት፣ የሰው ሠራሽ መተንፈሻ ��ጋፍ የሚፈልጉ እና ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች መጨመሩ ከባድ ጫናን በሆስፒታሉ ላይ አስከትሎ ነበር። በተጨማሪ ደግሞ ለሌሎች ሕክምናዎች ከሚሰጡ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች መካከልም በበሽታው የሚያዙ ስለነበሩ ከባድ ሥራና ኃላፊነትን ከሚወጡት ባለሙያዎች ሲቀነሱ የሰው ኃይል እጥረት ገጥሟቸው የነበረበት ጊዜ እንደነበር ዶ/ር ያሬድ ይጠቅሳሉ። ከባለሙያዎቹ መካከል በተደጋጋሚ ጭምር በበሽታው የመያዝ ሁኔታ የገጠማቸው ቢኖሩም ለሞት የተዳረገ የሆስፒታሉ ባልደረባ አልነበረም። የመጀመሪያው የኮቪድ-19 ሕክምና ማዕከል የሆነው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከወረርሽኙ መከሰት ጀምሮ በሆስፒታል ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን፣ የመተንፈሻ ድጋፍ የሚያሻቸውን እንዲሁም የጽኑ ሕሙማን ሕክምና ድጋፍ የሚፈልጉ የኮቪድ-19 ሕሙማንን አስተናግዷል። በተጨማሪም በኮሮናቫይረስ ተይዘው ተጓዳኝ ሕመም ኖሮባቸው የሐኪም የቅርብ ክትትልና ድጋፍ የሚያስፍለጋቸው፣ ነፍሰ ጡሮችና የመውለጃ ጊዜያቸው የደረሱ ሕሙማንን ጭምር በመቀበል ከወረርሽኙ ጋር የተያያዙ ዘርፈ ብዙ የሕክምና አገልግሎቶችን ሲሰጥ ቆይቷል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ሆስፒታሉ በሰጠው አገልግሎት ከወረርሽኙ የዳኑ ሰዎች በተለያየ የዕድሜ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። እዚያው የተወለዱ የአንድ ቀን ዕድሜ ካላቸው አራስ ሕጻናት አንስቶ አስከ 114 ዓመት ዕድሜ ያላቸው አዛውንት ድረስ የኮቪድ ሕሙማንን ሆስፒታሉ አስተናግዷል። ከአንድ ወር በታች ዕድሜ ያላቸው በበሽታው ተይዘው ለሕክምና የገቡት ሁሉም ጨቅላ ሕጻናት አገግመው እንደወጡ ዶ/ር ያሬድ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በሁለት ዓመታት ውስጥ በርካታ መልካምና አሳዛኝ አጋጣሚዎች በሆስፒታሉ ውስጥ ማጋጠሙን በመጥቀስ፣ እነዚህን የሆስፒታሉን ክስተቶች እና ሌሎች የሚነገሩ ታሪኮችን በመጽሐፍ የማቅረብ ሐሳብ እንዳላቸው ዶ/ር ያሬድ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ መገኘቱን ተከትሎ በአገሪቱ ውስጥ በተደረጉ ምርመራዎች ከ470 ሺህ በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ከ7500 በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ለሞት መዳረጋቸውን ከጤና ሚኒስቴር የወጣው ወቅታዊ መረጃ ያመለክታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61346541 +health ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች ሥራውን ማቋረጡን አስታወቀ "የፈረንሳዩ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ኤምኤስኤፍ ሠራተኞቹ ትግራይ ውስጥ ከተገደሉ በኋላ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚያከናውነውን ሥራ ማቋረጡን ገለጸ። ሰኔ 17/2013 ዓ.ም ትግራይ ክልል ውስጥ ለሥራ እየተጓዙ ሳለ ማንነታቸው ባልታወቁ ጥቃት ፈጻሚዎች የተገደሉት የእርዳታ ድርጅቱ ሠራተኞች ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዷ ደግሞ የስፔን ዜግነት ያላት ናት። ድርጅቱ እንዳለው በሠራተኞቹ ላይ በተፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ዙሪያ አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግና በክልሉ ውስጥ የእርዳታ ሠራተኞች ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ እንዲፈቀድ ጠይቋል። በሠራተኞቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም ኤምኤስኤፍ በትግራይ ክልል ማዕከላዊና ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኙት አቢ አዲ፣ አዲግራትና አክሱም ውስጥ የሚያከናውነውን ሥራ ማቋረጡን አስታውቋል። ነገር ግን ከእነዚህ አካባቢዎች ውጪ ባሉ ሌሎች አካባቢዎች አባላቱ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ነዋሪዎች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ሥራቸውን ማከናወን እንደሚቀጥሉ ገልጿል። ""በባልደረቦቻችን ላይ ግድያው ከተፈጸመ ሁለት ሳምንት ሊሆነው ቢቃረብም ማንም ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የሌለ ሲሆን በተጨማሪም በግድያው ዙሪያ ስላለው ሁኔታ ምንም ግልጽ ያለ ነገር የለም"" ሲሉ የድርጅቱ ኃላፊ ቴሬሳ ሳንክሪስቶቫል ተናግረዋል። ጨምረውም በባልደረቦቻቸው ላይ በተፈጸመው ግድያ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ምርመራ አድርገው ምን እንደተከሰተና ተጠያቂው ማን እንደሆነ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። በዚህም ሳቢያ ""በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ በጣም ከባድ ነገር ግን አስፈላጊ የሆነውን በበርካታ የትግራይ አካባቢዎች የምናካሂዳቸውን ሥራዎቻችንን ለማቋረጥ ወስነናል"" ብለዋል። የእርዳታ ሠራተኞቹ ሰኔ ወር አጋማሽ ላይ በትግራይ ክልል ውስጥ በጉዞ ላይ እንዳሉ የነበራቸው ግንኙነት መቋረጡንና በተከታዩ ቀን የሁለቱ ኢትዮጵያውያንና የስፔናዊቷ አስከሬን ይጓዙበት ከነበረው መኪና ጥቂት ሜትሮች ራቅ ብሎ መገኘቱንም የድንበር የለሽ ሐኪሞች በወቅቱ ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቶ ነበር። በጥቃቱ የተገደሉት የህክምና እርዳታ ድርጅቱ ባልደረቦች በየካቲት ወር ላይ በድርጅቱ በረዳት አስተባባሪነት ሥራ የጀመረው የ31 ዓመቱ ዮሐንስ ሃለፎም፣ በግንቦት ወር ለግብረ ሰናይ ድርጅቱን መሥራት የጀመረው የ31 ዓመቱ ሹፌር ቴድሮስ ገብረ ማሪያም እና ለዓመታት በድንገተኛ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪነት የሠራችው የ34 ዓመቷ ስፔናዊት ማሪያ ኽርናንዴዝ ናቸው። አስካሁን ድረስ ለሦስቱ የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ሠራተኞች ግድያ ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የሌለ ሲሆን ስለግድያው የወጣ ምንም አይነት ተጨመሪ መረጃ የለም። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግድያውን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ የተሰማውን ሐዘን ገልጾ፤ ጥቃቱ የተፈጸመው አቢ አዲ ተብሎ በሚጠራ ""ህወሓት በሚንቀሳቀስበት አካባቢ"" መሆኑን አመልክቷል። ጨምሮም እንዲህ አይነቱን ""ኃላፊነት በማይሰማው ቡድን የሚፈጸምን ጥቃት ለማስቀረት የእርዳታ ድርጅቶች በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ወታደራዊ እጀባ እንዲደረግላቸው መንግሥት ያቀረበው ጥሪ ትክክል መሆኑን ያመለክታል"" ብሏል። ከመንግሥት ሠራዊት ጋር ለስምንት ወራት በጦርነት ውስጥ የቆየው የህወሓት ኃይልም በበኩሉ በእርዳታ ሠራተኞቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ አውግዞ ድርጊቱ በመንግሥት ወታደሮች የተፈጸመ ነው ሲል ገልጾ ነበር። ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) በትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት በመደገፍና በማቋቋም እንዲሁም የህክምና ድጋፍ ለሚሹ ሰዎች እርዳታን እያደረገ ያለ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው። ድርጅቱ በባልደረቦቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም አገልግሎቱን አሁን ለማቋረጥ በወሰነባቸው አካባቢዎች ውስጥ ለሚገኙ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የተለያየ አይነት የጤና አገልግሎቶች ሲያርብ መቆየቱን ገልጿል። የአገልግሎቱ መቋረጥም በርካታ ሰዎች ከረድኤት ድርጅቱ ሲያገኙት የነበረውን የሰብአዊና የጤና ድጋፎችን እንዲያጡ ያደርጋቸዋል ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57714392 +health ኤርትራውያን በካንሰር ለሚሰቃይ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር አሰባሰቡ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን እና ትውልደ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች በሕመም ለሚሳቃይ አንድ ኤርትራዊ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን የካናዳ ዶላር በላይ አሰባሰቡ። በኤርትራ ነዋሪ የሆነው እና የስድስት ልጆች አባት የሆነው ዮናስ ፀጋይ፤ ባለፈው አንድ ዓመት ሆድኪን ሊምፎማ በተባለ የደም ካንሰር አይነት ሲሰቃይ ቆይቷል። 'ዮናስ ፀጋይን እና ቤተሰቡን ይርዱ' በሚል በተከፈተው የጎፈንድሚ አካውንት በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የካናዳ ዶላር ማሰባሰብ ተችሏል። ለዮናስ የተሰባሰበው መዋጮ ማክሰኞ ጥር 09 ከሰዓት ላይ 637 ሺህ የካናዳ ዶላር (ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ) ደርሷል። በጎፈን��ሚ ገጽ ላይ ተያይዞ በወጣው የእርዳታ ተማጽኖ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ፤ ዮናስ ፀጋይ በደም ካንሰር ምክንያት ከፍተኛ ሕመም ውስጥ እንደሚገኝ እና ሰዎች ለሕክምና ወጪ መዋጮ እንዲያደርጉለት ሲማጸን ይታያል። በስድስት ልጆቹ ተከቦ የሚታየው ዮናስ፤ በሕመሙ ምክንያት ሰውነቱ አብጦ እና እጆቹን በኃይል ሲያሽ ይታያል። ለዮናስ የቀረበው የእርዳታ አድርጉ ጥሪ በርካታ ምላሾችን በማግኘት በጎፈንዲሚ ገጽ ላይ ቀዳሚ ደረጃን ይዟል። ዮናስ በኤርትራ ወደ ጤና ተቋማት ቢሄድም ለተጨማሪ ሕክምና ከአገር ውጭ መጓዝ እንዳለበት ተነግሮታል። በድህነት ውስጥ የሚኖረው ዮናስ የሕክምና ወጪውን መሸፈን አለመቻሉን በመግለጽ አንድ የዩቲዩብ ገጽ የስድስት ልጆቹ አባት የሆነው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ለሌሎች አጋርቷል። ዮናስን ለማገዝ የጎፈንድሚ ገጽ በተከፈተ በመጀመሪያዎቹ 12 ሰዓታት ውስጥ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን ከ350 ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ በማዋጣት ፈጣን ምላሽ ሰጥተዋል። የእርዳታ ገንዘብ አሰባሳቢዎች መካከል አንዱ የሆነው ዮሴፍ ወርቄ እንዲህ በፍጥነት በርካቶችን ያሳተፈ መዋጮ አጋጥሞት እንደማያውቅ ለቢቢሲ ትግርኛ ክፍል ተናግሯል። አስተባባሪው እንደሚለው በሕመም የሚሰቃየው የዮናስ ተማጽእኖ የበርካታ ሰዎችን ልብ ተነክቷል። እንድ የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የጤና አግልግሎት (ኤንኤችኤስ) ድረ-ገጽ ከሆነ ዮናስ የሚሰቃይበት ሆድኪን ሊምፎማ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥም ከነጭ የደም ሴል ጋር የተገናኘ የደም ካንስር አይነት ነው። ተቋሙ እንደሚለው ከሆነ ይህ የካንሰር ሕመም በጨረር ሕክምና (በኬሞቴራፒ) እንዲሁም በራዲዮቴራፒ ሕክምና ሊድን ይችላል። https://www.bbc.com/amharic/news-60041868 +politics ፑቲን በአገራቸው ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ከጦርነት አዋጅ ጋር አመሳሰሉ "የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ወረራ ምክንያት በምዕራባውያን ሀገራት የተጣሉትን ማዕቀቦች ""ጦርነት ከማወጅ ጋር ተመሳሳይ ነው"" ሲሉ ገልጸዋል ። ""ነገር ግን አምላክ ይመስገን ወደዛ አልደረሰም"" ሲሉም አክለዋል። ዩክሬን ከበረራ ቀጠና ውጭ መደረግ አለባት በሚል የዩክሬን ባለስልጣናት ከፍተኛ ግፊት እያደረጉ ሲሆን ይህንንም አስመልክቶ ፕሬዚዳንት ፑቲን የበረራ ክልከላ ሙከራ በጦርነቱ ውስጥ ቀጥታ ተሳትፎ እንደሚታይ አስጠንቅቀዋል። ከጦርነቱም ጋር ተያይዞ በሩሲያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጁ ይችላሉ የሚለውን ሃሳብ ውድቅ አድርገውታል። ፕሬዚዳንት ፑቲን ይህንን ያሉት በሞስኮ አቅራቢያ በሚገኘው የኤሮፍሎት ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ ሴት የበረራ አስተናጋጆች ቡድን ባነጋገሩበት ወቅት ነው። አስራ አንደኛ ቀኑን ባስቆጠረው የሩስያ ወረራን ተከትሎ ምዕራባውያን ሃገራት በሩስያ የሚያደርጉትን ማዕቀብ አጠናክረው ቀጥለዋል። እስካሁን ከተጣሉ ማዕቀቦች መካከል የፕሬዚዳንት ፑቲን የውጭ ሃብት ማገድን ጨምሮ የሩስያ ባንኮችን ስዊፍት ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ማስወጣት ይገኙበታል። በተጨማሪም በርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በሩሲያ ውስጥ ያለውን ሥራቸውን አቁመዋል ። በያዝነው ሳምነት ቅዳሜ ፣ ዛራ ፣ ፔይፓል እና ሳምሰንግ የተሰኙት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በሩሲያ ያለውን ንግዳቸውን በቅርብ ጊዜ ያቆሙ ድርጅቶች ሆነዋል። በአገሪቱ ላይ የተጣለው ማዕቀብ የአገሪቱን መገበያያ ገንዘብ ሩብል በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሽቆለቆል ያደረገው ሲሆን የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የወለድ ተመኖችን በእጥፍ እንዲጨምር አስገድዶታል። ፕሬዚዳንት ፑቲን በቅርቡ በሰጡት አስተያየት፣ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስረዳት ሞክረዋል። የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪ ማህበረሰቦችን በሀገሪቱ እ��ተደረገ ካለው ""ከፍተኛ ወታደራዊነትና ናዚነት"" ጥፋት ለመከላከል እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። የምዕራባውያን የመከላከያ ተንታኞች የሩሲያ ወታደራዊ ዘመቻ እንደተጠበቀው እየሄደ አይደለም ለሚሉት አስተያየትም ፕሬዚዳንቱ ምላሽ ሰጥተዋል ""ሠራዊታችን ሁሉንም ተግባራት ይፈጽማል። ምንም ጥርጥር የለኝም። ሁሉም ነገር በእቅድ እየሄደ ነው"" ብለዋል። በጦርነቱ ላይ የሚሳተፉት በሙያቸው ወታደሮች የሆኑ ብቻ መሆናቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ ምንም አይነት ተቃራኒ ዘገባዎች ቢኖሩም ዜጎች በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ውትድርና አለመግባታቸውን ገልጸዋል። የሩሲያው መሪ በዩክሬን ሰማይ ላይ በረራ ለመከልከል የሚደረገው ጥረት ወታደራዊ ግጭቱን አንድ እርምጃ ወደፊት እንደሚወስደውና ተሳታፊዎቹም እንደ ጠላት ተዋጊ እንደሚወሰዱ ተናግረዋል። ""አሁን ያለው አመራር በአሁኑ ተግባራቸው ከቀጠሉ የዩክሬንን የወደፊት እድል አደጋ ላይ እንደሚጥሉ ሊገነዘቡ ይገባል"" ሲሉም አክለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60636847 +health በዩኬ ኮቪድ-19 በህሙማን ላይ የቆየበት ረጅሙ ጊዜ ከ16 ወር በላይ መሆኑን ምርመራዎች አመለከቱ "የዩናይትድ ኪንግደም ሐኪሞች ኮቪድ-19 በህሙማን ላይ የቆየበትን ረጅም ጊዜ መዝገበዋል። ሐኪሞቹ በኮቪድ-19 ተይዘው ሕክምና ያደረጉላቸው ህመምተኛ ከቫይረሱ ነጻ ሳይሆኑ በአጠቃላይ ለ16 ወራት ወይም ለ505 ቀናት እንደቆዩ ምርመራዎች እንዳመለከቱ ገልጸዋል። ስማቸው ያልተጠቀሰው እኝህ ግለሰብ ሌላ ተጓዳኝ በሽታዎች የነበሩባቸው ሲሆን እአአ በ2021 ሆስፒታል ውስጥ ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ይህችን ዓለም ተሰናብተዋል። እኝህ ግለሰብ ለ16 ወራት ያህል በተመረመሩ ቁጥር ቫይረሱ ይገኝባቸው ነበር። የለንደን የሕክምና ባለሙያዎች ለረጅም ጊዜ በቫይረሱ ተይዞ መቆየት እምብዛም የተለመደ አይደለም ይላሉ። አብዛኛው ሰው በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም ከቫይረሱ ነጻ ይሆናሉ። ነገር ግን ቀደም ሲል የተጠቀሱት ግለሰብ የነበራቸው በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም እጅግ የተዳከመ ነበር። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደዚህ ያሉ ስር የሰደዱ የሰውነት መቆጣቶችን ስለኮቪድ ያለን ግንዛቤ እና ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ ለማሻሻል ጥናት እንደሚያስፈልግ ይጠቁማሉ ብለዋል። ህመምተኛው ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዙት በ2020 መጀመሪያ ላይ ነበር። የበሽታው ምልክትም የነበራቸው ሲሆን በፒሲአር ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ72 ሳምንታት ለሚበልጥ በርካታ ጊዜ ለመደበኛ ምርመራ እና ለእንክብካቤ ሆስፒታል ሲገቡ እና ሲወጡ ነበር። በአጠቃላይ ለ50 ጊዜ ያህል ምርመራ አድርገው ከቫይረሱ ነጻ አለመሆናቸው በምርመራ ተረጋግጧል። የኪንግስ ኮሌጅ ለንደን እና ጋይስ ኤንድ ሴንት ቶማስ ኤንኤችኤስ ፋውንዴሽን ትረስት ሐኪሞች እንዳሉት ግለሰቡ በተደጋጋሚ በቫይረሱ የተያዙ ሳይሆን አንድ ጊዜ ተይዘው ለረዥም ጊዜ ከቫይረሱ ሳያገግሙ መቆየታቸውን ዝርዝር የሆነ ላብራቶሪ ምርምራ ትንታኔ አሳይቷል። ህመምተኛው የፀረ ቫይረስ መድሃኒቶች ከወሰዱ በኋላ እንኳን ከበሽታው ማገገም አልቻሉም ነበር። ይህ አንድ ግለሰብ ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ ተረጋግጦ ምልክቶቹ ከማይጠፉበትና በቫይረሱ ለረዥም ጊዜ ተይዞ መቆየት ጋር የተለየ ነው። በሕክምና ጉባዔ ላይ ስለግኝቶቹ ከሚያቀርቡት ሐኪሞቹ አንዱ በአውሮፓ ኮንግረንስ ክሊኒካል ማይክሮባዮሎጂ እና ተላላፊ በሽታዎች ሐኪም የሆኑት ዶክተር ሉኬ ብላግዶን ስኔል ናቸው። ዶክተር ሉኬ ""ከጉሮሮ የሚወሰድ ናሙና ምርመራ ይደረግ ነበር። ግለሰቡ ሁል ጊዜ በተመረመሩ ቁጥር ከቫይረሱ ነጻ አለመሆናቸውን ያሳይ ነበር። ህመምተኛው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው��� የሚያሳይ የምርመራ ውጤት ኖሯቸው አያውቅም። እናም ይህ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ በሽታ እንደሆነ መናገር እንችላለን። ምክንያቱም የቫይረሱ ዘረ መል ላይ ያደረግነው ተከታታይ ምርመራ ቫይረሱ በህመምተኛው ላይ የተለየ እና ወጥ የሆነ እንደሆነ አመላክቷል"" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዶክተር ሉኬ ""ሰዎች ለረጅም ጊዜ በቫይረሱ ተይዘው ሲቆዩ ቫይረሱ ከሰውነታቸው ጋር ይላመዳል። ይህም አዳዲስ ዝርያዎችን ለመከላከል አቅም እንዲያዳብሩ ሊያግዝ ይችላል"" ብለዋል። ምርመራ ካደረጉላቸው ዘጠኝ ታካሚዎች መካከልም አንዳቸውም በሌላ የቫይረስ ዝርያ አለመያዛቸውን ዶክተር ሉኬ ተናግረዋል። ስር በሰደደ ኢንፌክሽን የተያዘ ሰው ቫይረሱን ለሌሎች ላያስተላልፍ እንደሚችልም ዶክተር ሉኬ አክለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/61132951 +health ከ 1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን 8 ሰዎችን ብቻ የሚያጠቃው አስገራሚ በሽታ አንዳንድ በሽታዎች ግራ ናቸው። ለታማሚም ለአስታማሚም፤ ለአካሚም ለታካሚም። ሐኪሞች እንዲህ ግራ የሆኑትን ደዌዎች ኢዲዮፓቲክ (idiopathic) ሲሉ ይጠሯቸዋል። ግራ የሚባሉት ግራ ስለሚያጋቡ ነው። መንስኤያቸው ስለማይታወቅ። ይህ ዛሬ የምንነግራችሁ በሽታ ከዚህ ይመደባል። 60 ከመቶ በምን እንደሚመጣ አይታወቅም። ሲመጣ ግን እግር ተወርች ያስራል። አስሮ ቤት ያስቀምጣል። የአማርኛ ስም የለውም። በእንግሊዝኛ ‘ትራንስቨረስ ማያሊቲስ’ ይባላል። በቅጽል ስሙ (TM) ይሉታል። በደምሳሳው የሕብለ ሰረሰር (የነርቭ) በሽታ ነው። ቀደም ሲል እንዳልነው 60 ከመቶው በምን እንደሚመጣ አይታወቅም። በቃ አያድርስ ነው የሚባለው። 40 ከመቶ ግን ምንጩ ይታወቃል። ይህን ዘርዘር አድርገው የሚያስረዱን ዶ/ር ዳዊት ክብሩ ናቸው። ዶ/ር ዳዊት የነርቭ ሕክምና ከፍተኛ ስፔሻሊስት ናቸው። አሁን በሰሜን አሜሪካ፣ በዊስኮንስን እና በሚቺጋን ግዛቶች በተለያዩ ሆስፒታሎች ይሠራሉ። “በሽታው የሕብለ ሰረሰር አንዱን ክፍል በድንገት ያጠቃል” ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ቀጥሎ ከተጠቃው ሕብለ ሰረሰር በታች ያለውን የነርቭ ሥርዓት ይስተጓጎላል። ይስተጓጎላል ሲባል ምን ማለት ነው? ለምሳሌ እጅና እግርን ማዘዝ ይቸግራል። ሽንት መቆጣጠርም ሊያስቸግር ይችላል። “ከእንቅልፌ ስነሳ ድንገት መራመድ አቃተኝ፤ እግሬ ሰነፈብኝ” የሚሉ ታማሚዎች ያጋጥማሉ። ማንኛውም ነገር ሲነካን ቆዳችን ንክኪን የሚረዳበትን መንገድም ይቀየራል። ይህ የሚሆነው ከአእምሮ የሚላክ መልዕክት እየተቀየረ ለነርቭ ጫፍ ስለሚደርስ ነው። ለምሳሌ አንሶላ ጣል ቢደረግብን አሸዋ የተደፋብን ያህል ሊሰማን ይችላል። የሸሚዝ ቁልፍ ሲነካን በመርፌ የተወጋን ያህል ሊሰማን ይችላል። “በሽታው ያልተለመደ የሚባል ነው’’ ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ያልተለመደ ያስባለው ደግሞ ምልክቶቹ አይደሉም። ጥቂት ሰዎችን ብቻ ስለሚያጠቃ ነው። በዓለም ከአንድ ሚሊዮን ሰው ቢበዛ 8 ሰዎችን ቢይዝ ነው። ይህን አሃዝ ወደ እኛ አገር እንመንዝረው። ለስሌት እንዲመቸን የኢትዮጵያን ሕዝብን 100 ሚሊዮን ነው እንበል። በዓመት በዚህ በሽታ የሚያዙት 800 ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ እንደማለት ነው። ምንም ስላደረግን አይደለም የሚመጣው። ምንም ሳላላደረግንም አይደለም። በቃ አንዳንድ ጊዜ መከላከያችን በስህተት ራሱን ያጠቃል። ይህ ከባዕድ ተህዋሲዎች ጋር የሚያያዝ ሊሆን ይችላል። በሽታው በምን በምን ይመጣል? ስንል ዶ/ር ዳዊትን ጠየቅን። “ብዙውን ጊዜ ያለምንም ምክንያት በድንገት ይመጣል።” “ሌላ ጊዜ ደግሞ የአንጀት መቁሰል (ጋስትሮ ስትራይተስ) ሲያመን ሊመጣ ይችላል” ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። “አንዳንድ ሰዎች በአንጀት መቁሰል ከታመሙ ከ2 ሳምንት ወይም ከ3 ሳምንት በኋላ በዚህ በሽታ ይያ���ሉ።” እንደ ጉንፋን ዓይነት ወይም ኮቪድ ወይም ኤችአይቪም ይህን ድንገቴ በሽታ ሊስከትሉ ይችላል። አንዳንድ ሰዎች አንዳች ቫይረስ ከያዛቸው ከ2 እና ከ3 ሳምንት በኋላ ይህ በሽታ ይከሰትባቸዋል። ክሮኒክ በሽታዎች የሚባሉ በቋሚነት ሰውን የሚያጠቁ በሽታዎች አሉ። ለምሳሌ የመገጣጠሚያ ሕመም ያለባቸው ሰዎች ይህ በሽታ አንዳንዴ ይከሰትባቸዋል። በአመዛኙ ግን ይህ በሽታ ግራ የሚያጋባና ምክንያቱ የማይታወቅ፣ መነሻው በውል የማይለይ እና ያልተለመደ ደዌ ነው። ዶ/ር ዳዊት እንደሚሉት ይህ በሽታ የሚያሳያቸው ምልክቶች ውስን ናቸው። አንዱና ዋንኛው የእግር መስነፍ ነው። የጡንቻ መልፈስፈስ ነው። ታማሚዎች አንድ እርምጃ መራመድ ተራራ የመውጣት ያህል ሊሰማቸው ይችላል። ይህ የሚሆነው ደግሞ በብዛት በአጭር ቀናት ውስጥ ነው። ፋታም አይሰጥም። የእግር መስነፍ ብቻ ሳይሆን ከአንገት በታች ወይም ከወገብ በታች ያለ የሰውነት ክፍል በጠቅላላ አለመታዘዝ ይኖራል። ሽንት እምቢኝ፣ አልወጣ ሊል ይችላል። ቀስ ብሎ ደግሞ የሽንት እና ሰገራ ሙሉ ቁጥጥር ማጣት ይመጣል። ምልክቶቹ በትንሹ እንኳ ሲታዩ ቶሎ ሐኪም ማየት እንጂ ሌላ መላ የለም። “ቶሎ ከታከመ ነው ማገገም የሚቻለው። ከዘገዩ አደጋ ነው” ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። በዚህ በሽታ ድንገተኛ (acute) እና መለስተኛ ድንገተኛ (sub-acute) የሚባሉ ደረጃዎች አሉ። ድንገተኛ የምንለው በቀናት ውስጥ የሚመጣ ነው። መለስተኛ ድንገተኛ የሚባለው ደግሞ በ2 ሳምንት አካባቢ የሚባባስ ነው። ድንገተኛው በቀናት ውስጥ አጣድፎ ለሞት ሊያደርስ ይችላል። በተለይ ቶሎ ሐኪም ዘንድ ካልተሄደ አደገኛ ነው። ከፊል ድንገቴ ከሆነ ግን ፋታ ይሰጣል። ይህ የሚታወቀው በኤምአይአር እና በተጨማሪ ደም ምርመራዎች ነው። ዶ/ር ዳዊት በሽታውን በቀላሉ ለማስረዳት የኤሌክትሪክ መስመርን እንደ ምሳሌ ይጠቀማሉ። ነርቮች የእኛ የኤሌክትሪክ መስመር ሽቦዎች ናቸው። ሕብለ ሰረሰር ውስጥ ልክ እንደ ኤሌክትሪክ መስመር ሽቦዎች የሚያልፉበት አንድ የነርቭ መስመር አለ። እሱ የነርቭ መስመር ብግነት ሲገጥመው ነው ይህ በሽታ የሚጀምረው። የነርቭ መስመሩ ብግነት ደረጃ ደግሞ የበሽታውን ደረጃ ይወስናል። ብግነቱን ማቆም ነው የመጀመሪያው ጥረት። ሁለት ዓይነት ሕክምናዎች ይሰጣሉ። የመጀሪመያው ሕክምና ስቴሮይድ ይባላል። በደም ሥር ይሰጣል። ለተወሰኑ ቀናት። ይህም ብግነቱን ይቀንሳል። ሌላኛው ደግሞ ‘ኢሚኖሞግሎቢን’ የሚባለው ነው። የተቀመሙ አንቲቦዲዎች በደም ሥር ይሰጣል። ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ አይገኝም። ውድም ነው። ከዚህ በኋላ ኦኮፔሽናልናል ፊዚዮቴራፒ ነው የሚቀጥለው። ጡንቻ መሰልጠን የሚችል ነገር ነው። አገልግሎቱን አቁሞ ከቀረ በዚያው ይሰንፋል፤ ይረሳል ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ስለዚህ ሰውነታችን በፊዚካል ቴራፒ መሰልጠን አለበት። ይህ በሽታ በዘር አይተላለፍም። አንዳንድ ጊዜ ግን ክትባት ያመጣዋል። በኮቪድ በተያዙ ሰዎች ላይም አልፎ አልፎ ሊከሰት ይችላል። ሆኖም ግን ከስንት አንዴ ነው ይህ የሚሆነው። የኮቪድ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ተህዋስ ይህን የሕብለ ሰረሰር ብግነትን ሊያመጡ ይችላሉ። ሰውነታችን ባክቴሪያዎቹንና ቫይረሶቹን ለማጥፋት ከሰውነታችን የሚሠራቸው አንቲቦዲ የምንላቸው ንጥረ ነገሮች አሉ። እነርሱ በስህተት የራሳችንን መከላከያ ሲያጠቁ ይህ በሽታ ይከሰታል። በተመሳሳይ ኮቪድም ቫይረስ ነው። ይህን በሽታ ሊያመጣ ይችላል። እስካለፈው ዓመት መጨረሻ ድረስ በ22 አገሮች እንዲህ ዓይነት አጋጣሚዎች ሪፖርት ተደርገዋል። ግን ብዙ አይደሉም። በመቶ ሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ በኮቪድ ከተያዙ ሰዎች ውስጥ ይህ የተከሰተባቸው ሰዎች ከመቶ በታች ናቸው። “ከ140 ሚሊዮን ሰው ነው 100 ሰዎች ሪፖርት የተደረገው። የኮቪድ ክትባትም ተመሳሳይ ነው። ክትባቶች ለዚህ የሕብለ ሰረሰር በሽታ ቢያጋልጡም ቁጥራቸው ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም” ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ስለዚህ የኮቪድ ክትባት ይህን ሕመም ያመጣል ወይስ አያመጣም? ዶ/ር ዳዊት ለዚህ የሚሰጡት ምላሽ ጥንቃቄ የተሞላበት ነው። “የኮቪድ ክትባት ይህን በሽታ ያመጣል ብሎ መናገር ትክክል አይሆንም።” ይህ ሲባል የሕብለ ሰረሰር በሽታው ከከትባት ጋር አይያያዝም ማለት ሳይሆን፣ በዚህ የመከሰት አጋጣሚው እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው። “እንደ ሕብረተሰብ ሦስትና አራት አጋጣሚዎች (cases) ስላሉ ክትባት በሽታውን ያመጣል ብለን መናገር ፍጹም ስህተት ነው” ይላሉ። ዶ/ር ዳዊት እንደሚያወሱት ከሆነ ይህ በሽታ በእኛ አገር በብዛት ከቲቢ ጋር እንደሚምታታ ይናገራሉ። ብዙ ሰው ቲቢ በአገራችን ከሳምባ ጋር ብቻ አያይዞ ነው የሚያየው። ነገር ግን ቲቢ ሳንባን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ያጠቃል። ከእነዚህም መካከል ሕብለ ሰረሰር ይገኝበታል። ይህን በሽታ ከሌሎች ተመሳሳይ በሽታዎች የሚለየው ታዲያ በቀናት ውስጥ ነገሮች መባባሳቸው ነው። በተለይ ዶ/ር ዳዊት አገር ቤት ለሚገኙ ጠቅላላ ሐኪሞች ማስገንዘብ የሚሹት አንድ ነገር አለ። በሽተኞቻቸው ላይ ምልክቶችን ካዩ ሳይውሉ ሳያድሩ በፍጥነት ወደ ነርቭ ሐኪም እንዲልኳቸው። ይህም በተለይ በገጠርና ጤና ጣቢያ አካባቢ መዘግየት ሊኖር ከቻለ በሽታው ወዲያው ስለሚባባስ ነው። ከአንድ ወር እስከ ሦስት ወር ባለ ጊዜ ታማሚዎች ለውጥ ማየት ይጀምራሉ። ይሁንና ነገሮች በአንድ እና በሁለት ቀን ውስጥ ከተከሰቱ የማገገም ዕድሉም እየጠበበ ይመጣል። ረዘም ያለ ቀን የታመመ ሰው የማገገም ዕድሉ ከፍ ይላል። በዚህ ሕመም የ 1/3ኛ ሕግ የሚባል ነገር አለ ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። ከታማሚዎቹ ውስጥ አንድ እጁ ሙሉ በሙሉ ይድናሉ። ይህም እስከ ሦስት ወራት ሊወስድ ይችላል። አንድ ሦስተኛዎቹ ደግሞ አዝጋሚ ለውጥ ያያሉ። ይህ ለውጥ ዓመታት ሊወስድም ይችላል። ቀሪዎቹ አንድ ሦስተኞቹ ደግሞ ቋሚ ችግር ይኖርባቸዋል ማለት ነው። እንደ ዶ/ር ዳዊት መረዳት ከሆነ ከዚህ በሽታ ለማገገም ጊዜ ይወስዳል። የማገገም ዕድሎችን የሚጨምሩ ሌሎች ነገሮች ግን አሉ። ለምሳሌ በአፋጣኝ ሕክምና ማግኘት፤ ለምሳሌ አጋዥ ሕክምናዎች ኦኮፔሽናል እና ፊዚካል ቴራፒን ቶሎ መጀመር። በተለይ በሽተኞቹ ወጣት ከሆኑ ደግሞ የማገገም ዕድላቸው በዚያው ደረጃ ይጨምራል። ዶ/ር ዳዊት የነርቭን ተግባር በቀላል ቋንቋ ለማስረዳት የኤሌክትሪክ መስመርን ማሰብ ይበጃል እንዳሉ ከላይ ገልጠናል። በቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ ሽቦዎችን የሚሸፍን ኮንዲት አለ። በሰውነት ደግሞ ነርቮችን የሚሸፍን ነገር አለ፤ ማይሊን ይባላል። ብዙ ጊዜ ብግነቱ ይህን ሽፋኑን ነው የሚያጠቃው። ብግነቱ ከፍተኛ ሲሆን ግን ወደ ነርቭም ይገባል። በዚህ ጊዜ ነርቮች መልዕክት ለማስተላለፍ ይቸገራሉ። መልዕክት የሚተላለፈው በኬሚካል መስተጋብር ነው። ለምሳሌ ጭንቅላታችን “ተራመድ!” ብሎ ሲያዝ እኛ አናውቀውም እንጂ በነርቭ በኩል በሕብለ ሰረሰር አልፎ ወደ እግር ይሄዳል። ሕብለ ሰርሰር ላይ ብግነት ሲኖር መልዕክቱ በትክክል አይተላለፍም። በዚህን ጊዜ የነርቭ ሥራ ተስተጓጎለ እንላለን። በዚህ በሽታ ሦስት ዓይነት ምልክቶች አሉ ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። አንደኛ ‘ሞተር’ የምንለው የእንቅስቃሴ መስተጓጎል ነው። በቅጽበት ሰውነት ድንዝዝ ይላል። ስንፍ ይላል። እግር ታጥፎ አለመዘርጋት፣ ተዘርግቶ አለመታጠፍ ወይም ግትር የማለት ፀባይ ያሳያል። ሁለተኛ ‘ሴንሰሪ’ የምንለው ነው። ይህም የውሸት ምልክቶች እና ስሜቶች ማየት ስንጀምር ነው። እግሬ ትልቅ የሆነ ይመስለኛል። እግሬ በረዶ ውስጥ የገባ ይመስለኛል፤ የምንለው ለዚህ ነው። በሕክምና ዲስቴዥያ እንለዋለን። የተሳሳተ መልዕክት ሲተላለፈ እንደማለት ነው። ሦስተኛው ደግሞ ‘ኦቶኖሚክ ዲስፈንክሽን’ የሚባለው ነው። ይህም ማለት የእኛ ቁጥጥር ሳይኖረው አእምሯችን ካለማወቅ በራሱ የሚሠራቸው ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ሽንታችን እንደመጣ የምናውቀው መሽናት እንዳለብን አስበንበት አብሰልስለን ሳይሆን ሰውነታችን ስለሚነግረን ነው። የ‘ሰብ ኮንሽየስ’ አእምሮ ክፍል “ሽንት ወጥሮሃል ሂድና ሽና” ይለናል። ይህ በሽታ እሱን መልዕክት ያዛባውና ሽንት እንደመጣብን አይነግረንም። ከዚያ ፊኛችን ተጠራቅሞ ተጠራቅሞ በራሱ ጊዜ ይወጣል። እኛ ሳናውቀው። ይህን ክስተት ‘ኦቶኖሚክ ዲስፈንክሽን’ እንለዋለን ይላሉ ዶ/ር ዳዊት። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ በዚህ በሽታ ስንፈተ ወሲብ ይገጥማቸዋል። ዶ/ር ዳዊት ይህን በሽታ በተለየ ሁኔታ መከላከል እንደማይቻል ይጠቁማሉ። ይልቅ ደጋግመው የሚያሰምሩበት ምልክት በታየ ፍጥነት ቶሎ ሐኪም ማየትን ነው። ለታመሙ ሰዎች የሚሰጡት ምክር ሁለት ነው። አንዳንድ ታማሚዎች ካገገሙ በኋላ በተራዘመ ጊዜ የኩላሊት ኢንፌክሽን ሊገጥማቸው ይችላል። ይህን መከታተል ይኖርባቸዋል። ሌሎች ታማሚዎች ደግሞ መንቀሳቀስ ስለሚያቅታቸው አልጋ ላይ ይውላሉ። ይህንን ተከትሎ መቀመጫና ጀርባ አካባቢ ቁስል ይከሰታል። ይህ ሌላ ኢንፌክሽን ሊመጣ ይችላል። በዚህ ሁኔታ በሽተኛውን በየሁለት ሰዓቱ ማገላበጥ ያስፈልጋል ይላሉ። ከዚህ ሁሉ በላይ የሚያሰምሩበት ግን አንድ ነገር ነው። ሰዎች ምልክት ካዩ ሐኪም ለማየት መዘግየት እንደሌለባቸው። በዚህ በሽታ መዘግየት ማለት ሞት ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c16xpxknlw6o +health ኮሮናቫይረስ፡ በእንግሊዝ 10 አዳዲስ የኮቪድ-19 ክትባት መስጫ ማዕከላት ሊከፈቱ ነው እንግሊዝ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ አዳዲስ የኮሮናቫይረስ ክትባት መስጫ ማዕከላትን ልትከፍት እንደሆነ አስታውቃለች። ይህ የሆነው መንግሥት ከአንድ ወር በኋላ በዩናይትድ ኪንግደም 15 ሚሊዮን ሕዝብ ለመከተብ ያቀደውን ግብ ለማሳካት ነው። ብላክበርን ካቴድራል እና ቅዱስ ሄለንስ ራግቢ ግራውንድ (ሜዳ) አሁን አገልግሎት እየሰጡ ያሉትን ሰባት ማዕከላት ይቀላቀላሉ። የእንግሊዝ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት [ኤንኤችኤስ] ማዕከላቱ በሳምንት በሺዎች የሚቆጠሩ ክትባቶችን እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በብሔራዊ የክትባት ዘመቻው የተሳተፉትን አመስግነዋል። በዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙት 3.3 ሚሊዮን ሰዎች ቁጥር በላይ ማለትም 3.5 ሚሊዮን ሰዎች ክትባቱን ወስደዋል። ሆኖም ከተመዘገበው ቁጥር በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እንደሚኖሩ ይታመናል። መንግሥት ቁጥራቸው 15 ሚሊዮን ለሚሆኑ፤ ከ70 ዓመት ዕድሜ በላይ ለሆኑ፣ ለበሽታው ተጋላጭ ለሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች እና የእንክብካቤ ማዕከላት ሰራተኞችን በሙሉ በየካቲት ወር አጋማሽ ክትባቱን ለመስጠት ቃል ገብቷል። በእንግሊዝ ታሪክ ሰፊው በሆነው በዚህ የክትባት መርሃ ግብር ሕዝቡ አረጋዊያንን በመርዳትና በቀጠሯቸው እንዲገኙ በማገዝ ድርሻውን እንዲወጣ መንግሥት አሳስቧል። https://www.bbc.com/amharic/news-55693948 +health ኮሮናቫይረስ፡ የትኞቹ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት ጀመሩ? ሌሎቹስ መች ይጀምራሉ? "በአህጉረ አፍሪካ ቢያንስ 100 ሺህ ያክል ሰዎች እስካሁን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። አህጉሪቱ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በተገቢው መንገድ እየሰጠች አይደለም እየተባለች ትታማለች። ለመሆኑ የትኞቹ የአህጉሪቱ ሃገራት ናች ክትባት መስጠት የጀመሩት? የዓለም ሃገራት የኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት ፉክክር ላይ ናቸው። የአፍሪካ ሃገራት ግን ሃብታም ከሚባሉት ሃገራት ጋር ሲነፃፀር ወደኋላ የቀሩ ይመስላሉ። ""በጣም ተጋላጭ የሆኑ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት የማግኘት ተራቸው እስኪደርስ ድረስ እየጠቁ ነገር ግን እምብዛም ተጋላጭ ያልሆኑ ሃብታም ሃገራት ክትባቱን ሲያገኙ ማየት ፍትሃዊ አይደለም"" ይላሉ በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ማትሺዲሶ ሞዬቲ። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማኽሮ የአውሮፓና ሃገራትና አሜሪካ ከክትባቶቻቸው ቀንሰው ለአፍሪካ ሃገራት መስጠት አለባቸው ሲሉ ምክረ ሐሳብ አመንጭተው ነበር። የተወሰኑ ክትባቶች ለአፍሪካ ሃገራት በፍጥነት ሊዳረሱ ይገባል ይላሉ ፕሬዝደንቱ። አፍሪካ ውስጥ እስካሁን ድረስ ክትባት ማግኘት የቻሉት ከፋብሪካዎች በቀጥታ መግዛት የቻሉና ከሩስያ፣ ቻይና፣ ሕንድና ዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ በእርዳታ መልክ ያገኙ ሃገራት ናቸው። የአፍሪካ ሃገራት በዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ፕሮግራሞች ክትባት ለማግኘት ተስፋ አድርገዋል። አንደኛው ፕሮግራም ኮቫክስ የተሰኘው ነው። ይህ ፕሮግራም ሁሉም ሃገራት ክትባት ያገኙ ዘንድ ያለመ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ከያዝነው የፈረንጆች ወር መጨረሻ ጀምሮ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት ማግኘት ይጀምራሉ ብሎ ይገምታል። በዚህ ወቅት የሚሠራጩ 90 ሚሊዮን ክትባቶች የአህጉሪቱን 3 በመቶ ሕዝብ ይከትባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ክትባት በጣም ተጋላጭ ለሆኑና በቫይረሱ ምክንያት የበለጠ አደጋ ለሚደርስባቸው እንደ ጤና ባለሙያዎች ላሉ የሕብረተሰብ አካላት የሚከፋፈል ነው። የኮቫክስ ዓላማ 600 ሚሊዮን ክትባት ማግኘት ነው። ይህ የክትባት መጠን በፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ባለው የአህጉሪቱን 20 በመቶ ሰው ይከትባል። የአፍሪካ በሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል ኃላፊ ጆን ንኬንጋሶንግ ግን ይህ የክትባት መጠን በሽታውን ከአፍሪካ ነቅሎ ለማስወጣት በቂ ነው ብለው አያምኑም። እሳቸው እንደሚሉት የአፍሪካ ሃገራት ቢያንስ 60 በመቶ የሚሆነውን ሕዝባቸውን መከተብ አለባቸው። የአፍሪካ ሕብረትም በሃምሳ አምስቱ የአፍሪካ ሃገራት ስም ክትባት ለማግኘት ደፋ ቀና እያለ ነው። የአፍሪካ ሞባይል ኔትወርክ አቅራቢ ድርጅት የሆነው ኤምቲኤን 25 ሚሊዮን ዶላር በማዋጣት ለአፍሪካ የጤና ባለሙያዎች የሚሆን ሰባት ሚሊዮን ክትባት ለማግኘት እየጣረ ነው። የበሽታ ቁጥጥር ማዕከሉ እንደሚለው በኤምቲኤን በኩል የተገኘ አንድ ሚሊዮን ክትባት ለ20 ሃገራት በያዝነው ወር መጨረሻ ይከፋፈላል። የትኞቹ ሃገራት ቀድመው ክትባቱን እንደሚያገኙ ግን የተባለ ነገር የለም። ዜጎቻቸውን መከተብ የቻሉ ሃገራት የትኞቹ ናቸው? ምንም እንኳ ጥቂት ሃገራት ባለፈው ወር ክትባት መስጠት ቢጀምሩም አብዛኛዎቹ ሃገራት ግን ገና አልጀመሩም። በሰሜን አፍሪካ ክትባት መስጠት የጀመሩት ሃገራት ሞሮኮ፣ አልጄሪያና ግብፅ ናቸው። ከሰሃራ በታች ባሉ አፍሪካ አገራት ደግሞ ደቡብ አፍሪካ፣ ሲሼልስ፣ ሩዋንዳ፣ ሞሪሺዬስና ዚምባቡዌ ይገኛሉ። እንደ ኢኳቶሪያል ጊኒና ሴኔጋል ያሉ ሃገራት የመጀመሪያውን ዙር የሳይኖፋርም ክትባት ተቀብለዋል፤ መከተብ ግን አልጀመሩም። በአህጉሪቱ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጠቃችው ደቡብ አፍሪካ አስትራዜኔካ የተሰኘውን ክትባት ለመከተብ ዕቅድ ይዛ ነበር። ነገር ግን ክትባቱ በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ላይ ያለው ኃያልነት አናሳ ነበው በሚል ሰርዛዋለች። ነገር ግን አሁን ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ከተሰኘው ፋብሪካ የተገኘው ክትባት ለአዲሱ ዝርያ ፍቱን ነው በሚል መከተብ ጀምራለች። ደቡብ አፍሪካ ከሕንዱ አቅራቢ ያገኘችውን አድን ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባት ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት መጠቀም ከፈለጉ በሚል ለአፍሪካ ሕብረት ሰጥታለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-56144583 +sports ማንቸስተር ሲቲ ከቶተንሃም፣ አርሴናል ከኤቨርትን. . . የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት ባለፈው ሳምንት ዌስት ሃም እና ኒውካስል በአወዛጋቢው በቪዲዮ በታገዘ ዳኝነት (ቫር) መጎዳታቸውን የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን ይገልጻል። እንደሱቶን ከሆነ ዌስትሃም ከቼልሲ ጋር አቻ መለያየት ይችል ነበር። ከፓላስ ጋር በነበረው ጨዋታ ኒውካስልም ሦስት ነጥባ ማሳካት ይችል ነበር። “ያለፈው ሳምንት ለእኔ ጥሩ አይደለም። ያለፈው ሳምንት ግምቴ በቫር ውሳኔ ሳይሳካ ቀርቷል” ብሏል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ፣ እሑድ እና ሰኞ ይከናወናሉ። ለዚህ ሳምንትም ሱቶን የሊጉን ጨዋታዎች  ግምት አስቀምጧል። ፉልሃም ከ ቼልሲ ቼልሲ በዚህ ውድድር ዓመት ወጥ አቋም ማሳየት አልቻለም። ከአሰልጣኝ ቶማስ ቱህል መሰናበት በኋላስ ቡድኑ ምን ዓይነት አቋም ያሳያል? አዲሱ አሰልጣኝ ግርሃም ፖተር ቡድኑን ለማዘጋጀት በቂ ጊዜ ያላቸው አይመስልም። ቼልሲ ከፉልሃም የተሻሉ ተጫዋቾችን ይዟል። ቢሆንም ፉልሃም በሜዳው ማግኘት ከነበረበት ዘጠኝ ነጥብ ሰባቱን ማሳካት ችሏል። ግምት፡ 1 – 1 የግራም ፖተርን መልቀቅ ተከትሎ ብራይተን ወዴት ያመራ ይሆን? ብርንማውዝም አሰልጣኙ ስኮት ፓርከርን ካሳበተ በኋላ በጊዜያዊው አሰልጣኝ ጋሪ ኦኔል ይመራል። ኖቲንግሃም ፎረስትን ካሸነፉ በኋላ ሥራውን በቋሚነት ለመያዝ ማለሙ ጥፋት አይደለም። ፓርከር አንዳንድ ተጫዋቾቹ ለሊጉ ይመጥናሉ ብሎ የሚያስብ አይመስለኝም። ኦኔል ግን በተቃራኒው የሚያስብ ይመስለኛል። ይህ ነው ልዩነቱም። የፖተር መልቀቅም የተጫዋቾችን እምነት በመሸርሸር ለበርንማውዝ የሚጠቅም ይመስለኛል። ከፖተር ውጭም በራይተን ይህን ጨዋታ በበላይነት የሚያጠናቅቅ ይመስለኛል። ግምት፡ 1 – 2 ይህ ጨዋታ በመሰናበት አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኙ ሁለት አሰልጣኞች የሚገናኙበት ነው። በብራይተን ከተሸነፉ በኋላ ብሬንዳን ሮጀርስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ከቡድኑ ጋር መቀጠል የሚፈልጉ አይመሰልም። ስቴቨን ዤራርድም ጫና ውስጥ ቢወድቅም ከማንቸስተር ሲቲ ጋር አቻ መውጣቱ ቡድን እየገነባ ለመሆኑ ምልክት ሊሆን ይችላል። ሮጀርስ አሰልጣኝ ሆነው ዤራርድ ተጫዋች ሆነው በሊቨርፑል ይተዋወቃሉ። ሁለቱም አሰልጣኞች የተለያዩ ቡድኖችን ይዘውም በስኮትላንድ ሊግ ተገናኝተዋል። ይህን ሁሉ ከግምት በማስገባት ቡድኖቹ ለመፋለም ብዙ ምክንያት እንዳላቸው አምናለሁ። ሆኖም ቪላ የሚያሽነፍ ይሰምለኛል። ግምት፡ 1 – 2 የሊቨርፑል ተከላካይ መስመር እንደቀድሞው አይደለም። ረቡዕ ምሽት በናፖሊ በተደጋጋሚ ሲፈተን አምሽቷል። ከዚህ ቀደም ሊቨርፑል ከመጥፎ ውጤቱ እንደሚያገግም በተደጋጋሚ እገምት ነበር። አሁን ግን በተቃራኒው እቆማለሁ። ሊቨርፑል ጎል እንደሚያስቆጥር ባምንም ዎልቭስ ጫና ያሳድርባቸዋል። ዎልቭሶች ችግራቸው ጎል ማስቆጠር ነው። ዲዬጎ ኮስታ ለዚህ መፍትሔ ስለመሆኑ ብጠራጠርም አንፊልድ ላይ የተወሰኑ ዕድሎችን እንደሚፈጥሩ አምናለሁ። ግምት፡ 1 – 2 ይህንን ጨዋታ ለመገመት ከባድ ነው። ባለፈው ዓመት ሴንት ሜሪ ላይ ሳውዝሃምፕት 4-1 ሲያሸንፍ በመልሱ ጨዋታ ብሬንትፎርድ 3-0 አሸንፏል። ጫና ያለው በአሰልጣኝ ራልፍ ሃሰንሃልት ላይ ቢሆን ጨዋታዎችን አሸንፈው በሊጉ እንደሚቆዩ አምናለሁ። ብሬንትፎርድ ጎል የማስቆጠር ችግር እንደሌለበት በሊድስ ጨዋታ አሳይቷል። አቻ ብዬ መገመት ባልወድም ከዚህ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች አንድ አንድ ነጥብ ያገኛሉ። ግምት፡ 2 – 2 በሊ��� ምርጡ የመልሶ ማጥቃት ቡድን ቶተንሃም ነው። የሲቲ አጨዋወት ለቶተንሃም እንደሚመች ባለፈው የካቲት ኢትሃድ ላይ ተመልክተናል። የቅዳሜው ጨዋታ ክፍት እንደሚሆን እጠበቃለሁ። ሶን በዚህ ጨዋታ ጎል ያስቆጥራል ብዬ አስባለሁ። ሃላንድም ኳስና መረብን ያገናኛል። ግምት፡ 3 – 3 አርሴናል ከ ኤቨርትን አርሴናል ባለፈው ሳምንት በማንቸስተር ዩናይትድ ከደረሰበት ሽንፈት አንድ ነገር ማግኘት ነበረበት። አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአንድ ጊዜ ሦስት ተጫዋቾችን በቀየረበት አጋጣሚ ሲተች ተመልክቻለሁ። ለእኔ ግን ተገቢ ውሳኔ ነበር። ይህ ጨዋታ ለአርሴናል ቀላል አይሆንም። ኤቨርተን በጥሩ መንፈስ ላይ ይገኛል። ይህ የላምፓርድ ቡድን ነጥብ እንዲያገኝ በቂው ነው? ቡድኑ ጥሩ ኳስ ፈጣሪ ተጫዋቾች ያሉት ሲሆን ጋብርኤል ጄሱስን ካሰለፈ የእሑዱን ጨዋታ በድል ያጠናቅቃል። ግምት፡ 2 - 1 ዌስት ሃም በቼልሲ ሜዳ ባጋጠመው ነገር አዝኛለሁ። ማክስዌል ኮርኔት ያስቆጠረው ኳስ መሻሩ ከመጥፎ ውሳኔዎች አንዱ ነው። ኒውካስልም በተመሳሳይ መጥፎ ውሳኔ ተላልፎበታል። ሁለቱም ቡድኖች ማስመስከር የሚፈልጉት ጉዳይ ስላለ ጥሩ ጨዋታ ይሆናል። ኒውካስል ማጥቃትን የሚመርጥ ሲሆን ይህ አጨዋወት ለዌስት ሃም መልሶ ማጥቃት የተመቸ ነው። ግምት፡ 2 – 1 በሦስት ሳምንታት ውስጥ ማንቸስተር ዩናይትድ ለብዙዎች ከዓለማችን መጥፎው ቡድን ወደ ሃገሪቱ ድንቅ ቡድንነት ተቀይሯል። እውነታውን ካየበደረጃ ሰንጠረዡ መሐል ላይ ነው የሚገኙት። ያለፉትን አራት ጨዋታዎች ሲያሸንፉ ጥሩ ቢሆኑም በመሐል መሰናክል ያጋጥማቸዋል። ባለፈው ዓመት ዩናይትድን በሜዳው ያሸነፈው ክሪስታል ፓላስ በዚህም ጨዋታ ጥሩ ውጤት የሚያመጡለት ድንቅ ተጫዋቾች አሉት። የዩናይትድ ተከላካይ ክፍል ጫናን የሚቋቋምበት መንገድ የተመቸኝ ሲሆን በዚህ ጨዋታም የማሸነፍ ጉዟቸውን ይቀጥላሉ። ግምት፡ 0 – 1 ሊድስ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት በእነዚህ ሁለት ቡድኖች ምክንያት ከደጋፊዎች ከፍተኛ ትችት ገጥሞኛል።  ይህ የሆነው ደግሞ ሁለቱም እንደሚወርዱ እና ፎረስት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች እንደሚሸነፍ በመገመቴ ነበር። በዚህ ጨዋታ ምን እንደሚፈጠር እንመልከት። በሜዳቸው እንደመጫወታቸው ሊድሶች የሚጠቀሙ ይሆናል። ፎረስት ያስመጣቸውን ተጫዋቾች እስኪያዋህድ ጊዜ ያስፈልገዋል። ፎረስት ባለፈው ሳምንተ 2 ለ 0 ከመምራት በበርንማውዝ መሸነፉ ቡድኑን ይጎዳዋል። ግምት፡ 3 – 1 https://www.bbc.com/amharic/articles/cw0njlx21x3o +health ኮሮናቫይረስ፡ አውሮፕላኖች እንዴት ነው በፀረ- ተህዋሲያን የሚፀዱት? "የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ቀጥ ብሎ የነበረውን የአለም የንግድ እንቅስቃሴን ለመመለስ በርካታ ጥረቶች እየተደረገ ነው። በተለያዩ አገራትም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጥለዋቸው የነበሩ መመሪያዎችን እያላሉ ይገኛሉ። የወረርሽኝ ስርጭቱን ለመግታት አገራት አስተላልፈዋቸው ከነበሩ መመሪያዎች መካከል ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማቆም፣ አየር ማረፊያዎቻቸውንና ድንበሮቻቸውን መዝጋት ይገኙበታል። በዚህም የተነሳ በርካታ የኢንዱስትሪ ዘርፎች በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ሲሆን በተለይም የአየር ትራንስፖርት ዘርፉ እንዲሽመደመድ ምክንያት ሆኗል። ከሰሞኑ አገራቱ ዘግተዋቸው የነበሩ ድንበሮቻቸውን ከፍተዋል፤ አለም አቀፍ አየር መንገዶቹም በረራዎችን ጀምረዋል። የአለም አቀፉ አቪየሽን ድርጅት የአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ እንዲያንሰራራና ተጓዦችም ደህንነታቸቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲጓዙ ለማድረግ እንደ መመሪያነት የሚያገለግል አንድ ሰነድ አውጥቷል። በዚህም መመሪያ ውስጥ ከተካተቱት ጉዳዮች መካከል አውሮፕላኖች በምን መ���ገድ በፀረ- ተህዋሲያን መፀዳት እንዳለባቸውና የፅዳት ድግግሞሽንም ይመለከታል። እንዲሁ ከላይ ከላይ ሲታይ የአየር በረራና አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የሚጣጣሙ አይመስሉም ። ነገር ግን ተቆጣጣሪ አካላት የተለያዩ ፕሮቶኮሎችን በማውጣት አስፈላጊ የሚባሉ የፅዳት መመሪያዎችን ለመተግበር ቀን ተሌት ደፋ ቀና በማለት ላይ ናቸው። ለአየር በረራዎች በዋነኝነት የሚያስፈልገው ፈጣንና፣ በቅልጥፍና የተሞላ ውጤታማ ፀረ- ተህዋሲያን የፅዳት ስርዓት መዘርጋት ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ፍቃድ ያላቸው የፀረ- ተህዋሲያን ፅዳት በሚታዩና፣ ተደራሽ በሆኑ አካላት ላይ ጨርቅን እንዲሁም ተንቀሳቃሽ መርጫን በመጠቀም ማፅዳት ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ። ነገር ግን ሁለቱም የማፅጃ መንገዶች በሰዎች አማካኝነት የሚካዱ ከመሆናቸው አንፃር ውጤታማነታቸውን የሚቀንስ ሲሆን መደረስ የማይችሉ የአውሮፕላኑ አካላትም ላይ ክፍተትን ይፈጥራሉ ተብሏል። ኦክስጅንና ኦዞን በሌላ መልኩ ""አቶሚክ ኦክስጅንን"" እንደ ፀረ-ተህዋሲያነት በመጠቅም አካባቢን ለማፅዳት ተጀምሯል። ከዚህም በተጨማሪ አምቡላንሶችን ለማፅዳት የሚጠቀሙበትን ፀረ ተህዋሲያንንም ለአውሮፕላን የውስጥ ክፍል ለማፅዳት እየታሰበበት ነው። ነገር ግን እነዚህ ማፅጃዎች ባላቸው የንጥረ ነገር በተለይም 'ኦክሳይድ' ባለው ባህርይ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ላይ ጉዳት ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆን በሚለው ስምምነት ላይ አልተደረሰም። መቶ በመቶ ውጤታማ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ በሌለበት ሁኔታ ሌላኛው አማራጭ ""የኦዞን"" ንጥረ ነገሮችን መጠቀም ነው። በአሁኑ ወቅት ኦዞን በአውሮፕላን አካላት ላይ አገልግሎት ላይ ባይውልም በመጠጥ ቤቶችና በተለያዩ የንግድ ተቋማት ላይ በፀረ-ተህዋሲያን ማፅጃነት እያገለገለ ይገኛል። አካባቢውን የኦዞን ንጥረ ነገሮችን በመርጨት ውጤታማ የሆነ ፅዳትን ማግኘት ይቻላል። ነገር ግን ይህ ንጥረ ነገር በከፍተኛ መጠን ሲሆን ለሰዎች ጎጅ በመሆኑ ባለሙያን በመጠቀም መንገደኞች በሌሉበት ሁኔታ ሊረጭ ይገባል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ኦዞን ላይ ያለው ዋነኛ ጥያቄም የኦክሳይድ ንጥረ ነገር መጠኑ ነው፤ 'በአውሮፕላን የውስጥ አካልና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ላይ ያለው ተፅእኖ ላይ መስማማት አልተቻለም። 'አየኖችና የአልትራቫዮሌት ጨረር ' በላብራቶሪ ውስጥ ተሞክሮ ውጤታማ የሆነው ከከባቢ አየር የሚለቀቀውን የውሃ ትነት ውስጥ የኦክስጅንና ሃይድሮጅን ንጥረ ነገሮችን ለይቶ በማውጣት ፀረ ተህዋሲያንን መፍጠር ነው። ይህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ መንገድ በጣም አድካሚና ለሁለት ሰዓታት ያህልም የሚወስድ ጊዜን ይፈጃል። ሆኖም ይሄ መንገድ በከፍተኛ ሁኔታ ውጤታማና መቶ በመቶ የሚተማመኑበት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ፀረ ተህዋሲያኑ ቀላልና ተንቀሳቃሽ በሆነ መልኩ ትልልቅ የአውሮፕላን አካሎችን ማፅዳት ቢቻልም ለማፅዳት ግን ረዘም ያለ ጊዜ መውሰድ ያስፈልጋል። ሌላኛው ደግሞ ሲ የሚባለው የአልትራቫዮሌት ጨረር ሲሆን ይህ ጨረር ሳርስ የተባለውን የኮሮናቫይረስ አይነት ማጥፋት ይችላል። ለዚያም ነው ከፍተኛ ወጪ የሌላቸው ጨረሮች የአውሮፕላን አካላትን ለማፅዳት እየተነደፉ እንዲሁም እየተመረቱ ያሉት። ይህንም ተከትሎ በገበያው ላይ የነዚህ ጨረሮች ፍላጎት በመጨመሩ ምክንያት የአልትራቫዮሌት ጨረሮችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች ምርታቸው በሚቀጥሉት አራት አመታት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምርም ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በርካታ አማራጮች በርካታ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ አማራጮች ከመኖራቸው አንፃር በተለያየ ሂደትም ላይ ናቸው። አሁንም ቢሆን የትኛው የበለጠ ተስማሚ እንደሆነም እስካሁንም አይታወቅም። የትኛው የፀረ ተህዋሲያን ስርአት የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ከተቻለ በኋላ ምን ያህል ጊዜም ይወስዳል የሚለውን ማየት አስፈላጊ እንደሆነም እየተነገረ ነው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አሁንም ስጋት ሆኖ ባለበት ወቅት በርካታ አየር መንገዶች በረራ መጀመራቸው ጋር ተያይዞ ቫይረሱ እንዳይሰራጭ የማድረግ ከፍተኛ ኃላፊነትና ሸክም ተጥሏባቸዋል። የአውሮፕላኑ ሰራተኞች፣ መንገደኞችን ደህንነት በሚያስጠብቅ መልኩ አውሮፕላኖቹ በፀረ ተህዋሲያን መፀዳትም ግዴታ ነው። እነዚህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ ዘዴዎች ቫይረሱን መግታት ብቻ ሳይሆን የአየር መንገድ ኃላፊዎችም ሆነ ተቆጣጣሪዎች የሚያስወጣቸውን ዋጋና እንዲሁም ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መንገድ መፅዳት የሚችሉበትን ሁኔታ መገምገም ይጠበቅባቸዋል። በአንድ መልኩ የአየር ትራንስፖርቱ ወደቀደመ ሁኔታ እንዲመለሱ ግፊት እያደረጉ ሲሆን በሌላ መልኩ በዚህ ወረርሽኝ መካከል የተጓዦች ደህንነት በተጠበቀ መልኩ አገልግሎታቸውን መመለስና በወረርሽኙ ምክንያት ያጡትን ገቢ ለማግኘትም አጣጥመው መሄድ ይጠበቅባቸዋል። በተለይም አውሮፕላኖቹ የሚፀዱበትን ደረጃና ያለውን የስጋት መጠንን መቀነስና፤ የሚፀዳበትን ጊዜ አጣጥመው መሄድም ይጠበቅባቸዋል። የመንገደኞችን ጤንትና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠትም አየር መንገዶቹ እነዚህን ተግባራት እንዲያከናውኑም አለም አቀፉ አቪየሽንም መመሪያ ሰጥቷል። ከአለም አቀፉ አቪየሽን ቡድንና፣ የትራንስፖርት ዘርፍ ተመራማሪዎች የተውጣጡ ግለሰቦችም ውጤታማ የሆኑትን የፀረ ተህዋሲያን የማፅጃ ዘዴዎችንም ለመቀየስ ከፍተኛ ምርምሮችን እያደረጉም ነው፤ የተለያዩ መመሪያዎችንም በማውጣትም ላይ ይገኛሉ።" https://www.bbc.com/amharic/53627279 +sports ሜሲ ወይስ ሞድሪች? ፈረንሳይ አሊያ ሞሮኮ? አዲስ ታሪክ የሚፃፍበት የዓለም ዋንጫ ወደየት ያመራ ይሆን? እንግሊዝ ቅዳሜ ምሽት በፈረንሳይ ተረትታ በበነጋው አውሮፕላን ተሳፍራ ከዶሃ ወጥታለች። አሁን አራት ብሔራዊ ቡድኖች ቀርተዋል - ፈረንሳይ፣ ሞሮኮ፣ ክሮሺያ እና አርጀንቲና። ከአራቱ አንዱ በሚቀጥለው እሑድ ወርቃማውን ዋንጫ ያነሳል። እኚህ አራት ቡድኖች ለግማሽ ፍፃሜ ይደርሳሉ ብሎ የገመተ ጥቂት ነው። አራቱም ብሔራዊ ቡድኖች አዲስ ታሪክ ሊፅፉ ከጫፍ ደርሰዋል። አርጀንቲናዊው ኮከብ በእግር ኳስ ሕይወቱ የመጀመሪያው እና የመጨረሻውን የዓለም ዋንጫ ሊያነሳ ይችላል። ሜሲ ለዋንጫ ብርቅ አይደለም። 10 የስፔን ላሊ ጋ ዋንጫ፣ አራት ጊዜ ቻምፒዮንስ ሊግ፣ አንድ ጊዜ የፈረንሳይ ሊግ እንዲሁም ከአገሩ አርጀንቲና ጋር ኮፓ አሜሪካን አንስቷል። ሜሲ የእግር ኳስ ከዋክብት ጉምቱው ሽልማት የሚባለውን ባሎን ዶር ሰባት ጊዜ በማንሳት ክብረ-ወሰን ጨብጧል። ነገር ግን የ35 ዓመቱን የእግር ኳስ ተዓምረኛ ከማራዶና እና ከፔሌ የሚለየው የዓለም ዋንጫን አለማንሳቱ ነው። አርጀንቲና በዲዬጎ ማራዶና እየተመራች የዓለም ዋንጫ ካነሳች 36 ዓመታት ተቆጥረዋል። ሜሲ ይህን ይደግመው ይሆን? የዓለም ዋንጫ ማንሳቱስ የዘመናችን ድንቁ ተጫዋች የተሰኘውን ስያሜ ያሰጠው ይሆን? ሞሮኮ ከወዲሁ ታሪክ ሰርታ፤ እንዲሁም ጨምራ ሌላ ታሪክ እየፃፈች እዚህ ደርሳለች። ሞሮኮ ከአህጉረ አፍሪካ፣ አልፎም ከአረቡ ዓለም ለግማሽ ፍፃሜው የደረሰች የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። ምንም እንኳ ሞሮኮ እንደ አሽራፍ ሐኪሚ እና ሐኪም ዚዬች ያሉ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ቢኖሯትም እዚህ ትደርሳለች ብለው የገመቱ ጥቂት ናቸው። ክሮሺያ እና ቤልጂዬም የነበሩበትን ምድብ አልፋ፣ ኃያሏ ስፔንን አስወግዳ፣ ፖርቹጋልን አሰናብታ ነው እዚህ የደረሰችው። የአትላስ አናብስት ��ጎል መስመራቸውን ሲከላከሉ ያለ እረፍት ነው። በኳታር የዓለም ዋንጫ ማንም የሞሮኮን መረብ አልደፈረም። ከአንድ ጎል በቀር። እሱም በራስ ላይ የተቆጠረ ነው። ሞሮኮ የዓለም ዋንጫ ድምቀት ሆናለች። ደጋፊዎች ስታደየሙን ከጫፍ ጫፍ ሞልተው ያለማቋረጥ ቡድናቸውን ይደግፋሉ። ሞሮኮ ረቡዕ ዕለት አዲስ ታሪክ ትፅፍ ይሆን? ፈረንሳይ የዓለም ዋንጫ በተከታታይ ሁለት ጊዜ ታነሳ ይሆን? አውሮፓዊቷ አገር የዓለም ዋንጫውን በተከታታይ ሁለት ጊዜ እንዳታነሳ ታሪክ ሠሪዋ ሞሮኮ ልታግዳት ትችላለች። 'ሌ ብሉ' በሚለው ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት ፈረንሳዮች፣ ከስድሳ ዓመታት በኋላ አዲስ ታሪክ ለመፃፍ ይሞክራሉ። ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ በተከታታይ የዓለም ዋንጫ ያነሳችው ብራዚል ስትሆን፣ ይህ ከሆነ 60 ዓመታት ተቆጥረዋል። ጣልያን፣ ስፔን፣ ጀመርን ባለፉት 12 ዓመታት ዋንጫ አንስተው በሚቀጥለው የዓለም ዋንጫ ውድድሩን በጊዜ የተሳነበቱ አገራት ናቸው። ባለፈው ቅዳሜ እንግሊዝን የረታችው ፈረንሳይ ከብራዚል ቀጥላ ዋንጫ ባነሳች ተከታ የዓለም ዋንጫ ውድድር ለግማሽ ፍፃሜ የበቃች አገር ሆናለች። አሠልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ አሁን ትኩረታቸው ሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ ሆናለች። የ2018 ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታን ደግመን ልናየው እንችል ይሆናል። ፈረንሳይ ሞሮኮን፤ ክሮሺያ ደግሞ አርጀንቲናን ካሰናበቱ በሩሲያ ያሳዩንን የፍፃሜ ጨዋታ በኳታር ምድር ይደግሙታል። ክሮሺያ በዙር 16 ጃፓንን፤ በሩብ ፍፃሜው ደግሞ ብራዚልን በመርታት ነው ከመጨረሻዎቹ አራት ቡድኖች ተርታ መሰለፍ የቻለችው። ክሮሺያ ለመጨረሻ ጊዜ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ በ90 ደቂቃ ተጫውታ ያለፈችው ከ24 ዓመታት በፊት ጀርመንን በረታች ወቅት ነው። የክሮሺያ አምበል እና የመሃል መስመሩ ሞተር፤ ሉካ ሞድሪች ዕድሜው 37 ደርሷል። ነገር ግን 120 ደቂቃ ተጫውቶ አገሩን ለዚህ አብቅቷል። ባለፈው የዓለም ዋንጫ በምድብ ጨዋታ በክሮሺያ 3 ለምንም የተረታችው አርጀንቲና ለሞድሪች ቡድን ንቀት እንደማታሳይ ይጠበቃል። አርጀንቲና ከክሮሺያ ማክሰኞ ምሽት 4 ሰዓት ይገናኛሉ፤ ፈረንሳይ ከሞሮኮ ደግሞ ረቡዕ በተመሳሳይ ሰዓት ይፋለማሉ። አዲስ ታሪክ ይመዘገብ ይሆን? https://www.bbc.com/amharic/articles/czq327npyvpo +sports ቶኪዮ ኦሎምፒክ፡ የአትሌቲክስ ቡድን አባላት ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ ነን አሉ "ከነገ ወዲያ በሚጀመረው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድር ላይ ከዚህ ቀደም ከተመዘገበው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸውን አትሌቶች እና አሰልጣኞች ለቢቢሲ ተናገሩ። በጃፓን መዲና የሚካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የፊታችን ዓርብ ሐምሌ 16 ጀምሮ ነሐሴ 8 ይጠናቀቃል። ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ከአትሌቲክሱ በተጨማሪ በውሃ ዋና፣ በብስክሌት ውድድር እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በቴኳንዶ ውድድር ትወከላለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 35 አትሌቶችን ይዞ ወደ ቶኪዮ የሚያመራ ሲሆን አትሌቶች በ7 የተለያዩ ርቀቶች ተወዳዳሪ ሆነው ይቀርባሉ። በኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ቡድን ውስጥ የወቅቱ የ5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ይዛ የምትገኘው ለተሰንበት ግደይ ትገኝበታለች። በኮቪድ-19 ስርጭት ምክንያት በአንድ ዓመት ዘግይቶ ለሚከናወነው የኦሎምፒክ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ያለፉትን 8 ወራት በሆቴል ቆይተው ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል። የአትሌቲክስ ቡድኑ ዝግጅት ምን ይመስል ነበር? ሕዝቡ ምን አይነት ውጤት ይጠብቅ? ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት በዝግጅት ላይ የነበሩ አትሌቶችን ጠይቀናል። ሰለሞን ባረጋ አገሩን ወክሎ በ10ሺህ ሜትር ተወዳዳሪ ሆኖ ይቀርባል። ''ጥሩ ነጥብ እናመጣለን ብዬ አስባለሁ። እስካሁን 5ሺህ ሜትር ስወዳደር ነበር። በ10ሺ�� ከእኔ ጋር ከሚወዳደሩት ጋር ተወዳድሬ ባላውቅም አሯሯጣቸውን ግን አውቃለሁ። ባለ ሪከርድ ከሆኑ የኬንያ እና ኡጋንዳ አትሌቶች ጋር ነው የምወዳደረው"" በማለት አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለቢቢሲ ተናግሯል። የ10ሺህ ሜትር ውድድር ዓርብ ሐምሌ 23 ይካሄዳል። በዚህ ውድድር ከሰለሞን ባረጋ በተጨማሪ ዮሚፍ ቀጄልቻ እና በሪሁ አረጋዊ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ። ባለፉት ሁለት የኦሎምፒክ ውድድሮች ማለትም በሪዮ እና ለንደን ኦሎምፒክ በ5ሺህ እና በ10ሺህ ኦሎምፒክ የወርቅ ተሸላሚው መሐመድ ፋራህ መስፈርት ማሟላት ባለመቻሉ ከመድረኩ ቀርቷል። አትሌት ሹራ ቂጣታ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሎምፒክ ይወዳደራል። አትሌት ሹራ ኢትዮጵያን በማራቶችን የሚወክል ሲሆን፤ ""በዚህ ውድድር ለአገርም ለግልም ወርቅ ማምጣት አለብን በሚል ነው እየተዘጋጀን ያለነው"" በማለት ይናገራል። ከአንድ ዓመት በፊት በለንደን ማራቶን የኬንያውን ኢሊዩድ ኪፕቼጌን ያሸነፈው ሹራ፤ በቶኪዮ ኦሎምፒክም የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ኪፕቼጌ ጋር ይወዳደራል። ከአትሌት ሹራ ጋር አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ እና ሲሳይ ለማ አገራቸውን ወክለው በማራቶን ይሳተፋሉ። የረዥም ርቀት ዋና አሰልጣኝ ኮማንደር ሁሴን ሺቦ በኦሎምፒክ ውድድር ላይ ተሳታፊ ሲሆኑ የቶኪዮ ኦሎምፒክ 6ኛው ሆኖ ይመዘገባል። ""ለአገራችን ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ አትሌቶቻችንም፤ እኛም በአካልም በአእምሮም ዝግጁ ሆነናል"" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። አሰልጣኝ ሁሴን በ5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ውድድሮች የሚሳተፉ አትሌቶችን ይመራሉ። ""አራት ቡድን እመራለሁ። የሴቶች እና የወንዶች 5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ውድድሮችን። 1ኛ እና 2ኛ ደረጃን ለመያዝ አቅደን እየሰራን እንገኛለን"" የሚሉት አሰልጣኙ፤ ከዚህ ቀደም ከተመዘገበ ውጤት በቶኪዮ ኦሎምፒክ ውጤት ይመዘገባል ብዬ እገምታለሁ ብለዋል። አሰልጣኝ ሁሴን በዘንድሮ የቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚሳተፉት አብዛኛዎቹ አትሌቶች በኦሎምፒክ ውድድር ሲሳተፉ የመጀመሪያቸው እንደሆነ ያስረዳሉ። ""ከአጠቃላይ አትሌቶች 98 በመቶ የሚሆኑት ከዚህ ቀደም በኦሎምፒክ ውድድር ተሳትፈው የሚያውቁ ስላልሆኑ በከፍተኛ ተነሳሽነት በውድድሩ ተሳትፈው አመርቂ ውጤት ያስመዘግባሉ የሚል እምነት አለኝ"" ብለዋል። አትሌት ደራርቱ ከሰሃራ በረሃ በታች ከሚገኙ አገራት የኦሎምፒክ ወርቅ ያገኘች የመጀመሪያዋ ጥቁር አትሌት ነች። ዘንድሮ ደግሞ ደራርቱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንን እየመራች ወደ ቶኪዮ ታቀናለች። ""አንዳንድ ችግሮች አይታጡም ግን ዝግጅታችን በጣም ጥሩ ነው። ዓለም ለማሸነፍ ይዘጋጃል። እኛም እንደ አንድ ትልቅ አገር ለማሸነፍ ተዘጋጅተናል"" በማለት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን ፕሬዝደንት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፉት ስምንት ወራት ፌዴሬሽኑ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ሦስት ውድድሮችን አከናውኖ አትሌቶችን ለመመልመል እድል አግኝቷል። ""ፈጣሪ ከረዳን ጥሩ ውጤት እናመጣለን ብለን እናስባለን። እንደ ልባችን እንዳንሰራ የረበሸን ነገር ኮቪድ-19 ወረርሸኝ ነው"" ብላለች አትሌት ደራርቱ።" https://www.bbc.com/amharic/news-57904032 +health ዜና ማየት ቢቀርብንስ? ሌላው ቢቀር ለአእምሯችን ጤና ስንል! "እኛ ራሳችን ዜና አቅራቢ ሆነን ይህን ማለታችን ወለፈንዲ ሊሆን ይችላል። ትዝብት ላይ ሊጥለንም ይችላል። ያም ሆኖ ግን ነገሩ አሳሳቢ ነው። ቀኑን ሙሉ የዜና ቆሎ መቆርጠም ቢቀርብንስ? ሌላው ቢቀር ለአእምሯችን ጤና ስንል። መረጃ ትንፋሽ አሳጣን እኮ፡፡ የመረጃ ሱናሚ ጠራርጎ ወሰደን እኮ… በኮቪድ ዘመን ደግሞ ቤት ተዘግቶ መዋል የዜና ሸመታችንን ሰማይ አድርሶታል፡፡ በብዙ ዓለም ይህ ነገር እውነት ነው፡፡ እስኪ አስቡት… እጃችሁ ���ይ የቲቪ ትዕይንት መዘርዝር መዘወርያ አለ እንበል፡፡ ሪሞት! ሌላኛው እጃችሁ ላይ ደግሞ ስልካችሁ ይኖራል፤ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ በዚህ ዘመን ከስልካችን ከራቅን ጭንቅ ነው የሚሆንብን፡፡ ምናልባትም ይህን ጽሑፍ በስልካችሁ እያነበባችሁት ይሆናል፡፡ ከንባብ የሚያናጥቡ ተከታታይ መልእክቶች እየደረሷችሁም ይሆናል፡፡ በፌስቡክ…በቴሌግራም…በዋትስአፕ…በትዊተር… በዚያ ላይ ‹ይቺን አንብባትማ በሞቴ!› የሚለው ሰው ብዛቱ… ""ጉርሻ ይመስል!"" ለምን እንደሆነ ባይታወቅም ሁሉም ሰው የያዘውን ንባብ እንኳ ሳይጨርስ የማጋራት ሱስ አለበት፡፡ አንዳንዱ አጭሬ የቧልት ቪዲዮ ዓይቶ፣ ስቆ እንኳ ሳይጨርስ አጋርቶ ይጨርሳል፡፡ ጊዜ የለም፡፡ የመረጃ ግሽበት አለ፡፡ ስለዚህ ወደሚቀጥለው፡፡ ሳቅን ለማጣጣም ቀርቶ ፈገግታን ለመጨረስ የሚሆን ጊዜ የለም፡፡ እጃችሁ ላይ የቲቪ 'ሪሞት' አለ ብለናል፡፡ ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ፣ ቢቢሲ ሰበር ዜና እየላኩ የአእምሮ ጫና ይፈጥራሉ፡፡ ፈነዳ፣ አፈነዳ፣ ፈነዱ….ገደለ፣ ገደሉ…ተገደለ፣ አስገደለ፣ ሞቱ፣ ቆሰሉ…አቆሰለ…ቆሰለ፡፡ ጂኒ ጃንካ ቅብርጥሶ… ሪሞቱን ይዛችሁታል ብለናል….፡፡ እንዳትለቁት፡፡ ዓለምን በቲቪ መስኮት እየሾፈራችኋት ነው፡፡ በቲቪ የትእይንቶች መዘርዝር ውስጥ 300 ቻናሎች አሉ፡፡ 300 ምርጫዎች አሏችሁ ማለት ነው፡፡ የትኛውን ማየት ይሻላል? ይህ የምርጫ መብዛት ራሱ ለአእምሮ ጤና መልካም አይደለም፡፡ ከቲቪ መዘርዝሩ ጎን የራዲዮ መዘርዝር አለ፡፡ ከሱ ጎን ላፕቶፕ አለ፡፡ ላፕቶፑ ውስጥ እልፍ ፊልሞች አሉበት፡፡ በዚህ ላይ ከጎረቤት የሆነ ራዲዮ ጣቢያው ላንቃው እስኪሰነጠቅ ይጮኻል፡፡ ከወዲያ በኩል ሼልፍ ላይ ያላነበቧችኋቸው መጻሕፍት እያዛጉ ነው፡፡ ዓለም ትጨንቃለች፡፡ መረጃ ይንዠቀዠቃል፡፡ ሰቆቃ…ዜና…ሰቆቃ…መረጃ…ገደሉ፣ ተገደለ፣ ቆሰሉ አቆሰለ፡፡ ጂኒ ጃንካ ቁልቋል…. በዚሁ ሁሉ መሀል ሌላ መልእክት ይመጣል፡፡ ከወዳጅ፣ ከቴሌ፣ ከቴሌግራም ጉጅሌ፣ ከፌስቡክ ክበብ… መረጃውን እንቀበላለን፤ እንጎርሳለን፡፡ ደግሞ መረጃውን አላምጠን አይደለም የምንጎርሰው፡፡ ምኑ ይላመጥና፡፡ ማስቲካ…ይላመጣል? ይዋጣል? መረጃ ማስቲካ ላንቲካ ሆኗል፡፡ ማመንዠግ ነው እንጂ ሌላ አማራጭ የለም፡፡ ዝምብሎ ማቀበል ነው፣ የሰማው ላልሰማው፡፡ የሰማው ለሰማው፡፡ ወዘተ፡፡ ወዘተ ራሱ ድሮ አጭር ቃል ነበር፡፡ አሁን ወዘተ ረዥም ቃል ሆኗል፡፡ መረጃ ያታክታል፡፡ የዚህ ጽሑፍ እንደ አንጀት መርዘም ራሱ አታካች ነው፡፡ ለምን እዚህ ጋ አናቆመውም፡፡ ምክንያቱም ጸሐፊው ተስፋ ያደርጋላ…ጠቃሚ መረጃ እያቀበለ እንደሆነ ይሰማዋላ፡፡ ስለዚህ አያቆምም ይቀጥላል፡፡ ማንም ደንታው ባይሆንም ይቀጥላል፡፡ ለመረጃ ግሽበት የራሱን አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት፡፡ በዓይንና ጆሮ የምንሸምተው ዜና ካሎሪ ቢሆን እኮ አለመጠን ወፍረን ፈንድተናል፣ ይሄኔ፡፡ ስኳር፣ ጨጓራ፣ ደም ብዛት፣ ደም ግፊት ነበረብን እኮ ይሄኔ፡፡ ሽንታችን ቀለሙ ቢጫ፣ ሽታው ዜና ዜና የሚል ይሆን ነበር ይሄኔ፡፡ ደግነቱ ዜና ካሎሪ የለውም፡፡ ካሎሪ የለውም ማለት ግን ጭንቅላታችን ላይ አይወጣም ማለት ነው እንዴ? አይደለም፡፡ ልክ እንደ ቢጫ ወባ ዘሎ ጭንቅላታችን ላይ ይወጣል፡፡ ይህን የምንረዳው ግን ዘግይተን ነው፡፡ ፓሮል ጎሽ የ32 ዓመት ወጣት ናት፡፡ በዜና ጎርፍ ተወሰደች፡፡ እንደ ቀልድ ሪሞቱን ታነሳዋለች፡፡ አንዱ ዜና ለሌላው ሲያቀብላት፣ ሌላው ለሌላ ሲያሻግራት እንዲሁ እንደ ቅሪላ እየተለጋች ቀኑ መሽቶ ይነጋል፣ ነግቶ ይመሻል፡፡ ‹‹ወንድ ልጅ ቆረጠ፣ ሴት ልጅ ወሰነች›› አልኩ በሆዴ ትላለች ፓሮል፣ የሆነ ቀን፡፡ ፓሮል ቤተሰቦ�� ሕንድ ናቸው፡፡ እሷ ስዊድን ነው የምትኖረው፡፡ ስዊድን ነው የምኖረው ትበል እንጂ እውነተኛ ሕይወቷ ቲቪ ውስጥ ነው፤ ኢንተርኔት ውስጥ ነው፡፡ ስለ ሕንድ አንዱን ዜና ጀምራ ሌላውን ስትገልጥ በሕንድ የወጣች ፀሐይ በስዊድን ትጠልቃለች፡፡ ይህ ሁልጊዜ የሚሆን ነው፡፡ በቀን በቀን፡፡ በመጨረሻ ካሮል ጭንቅላቷ መደንዘዝ ጀመረ፡፡ ‹‹ሕንድ እየሆነ ያለው ነገር ቤተሰቤን የሚጨርስ ስለሚመስለኝ ለተደጋጋሚ ጭንቀት ተዳረኩ›› ብላለች ካሮል፣ ለቢቢሲ፡፡ ክሪስ ክላንሲ ደግሞ አለ፡፡ 33 ዓመቱ ነው፡፡ በአውስትራሊያ፣ ቪክቶሪያ ነው የሚኖረው፡፡ የርሱ ሱስ ጫት አይደለም፡፡ ዜና ነው፡፡ ዜና-ሱስ የሚባል ነገር ታሟል፡፡ ዜና ማየት ብቻ አይደለም ችግሩ፡፡ የዓለም ጋዜጠኞችን ልቅም አድርጎ ይከተላል፡፡ በትዊተር፣ በፌስቡክ እግር በእግር ይከተላቸዋል፡፡ አንዲት ቅንጣት ዜና አታልፈውም፡፡ ከዜና በፊት ዜና ያገኛል፡፡ በቀኑ መጨረሻ ግን ይደነዝዛል፡፡ ይታክታል፡፡ ለካንስ ሳያስበው ዓለም ላይ የተፈጠረ ክፉ ነገሮችን በሙሉ በዐይኑ በኩል ሲጠጣቸው ነው የዋለው፡፡ ልክ ማታ ላይ ጭንቅላቱን ሲወቅረው ነው ይህን የሚረዳው፡፡ ቲቪውንና ስልኩን ሲዘጋ ነው የሚታወቀው፡፡ ወደ መኝታው ሲሄድ ሕልሙ ዜና በዜና፡፡ ሽብር በሽብር፡፡ ደግሞ አያስችለውም፣ ጠዋት መልሶ ይከፍተዋል፡፡ ዜናው ደግሞ አይቀየርም፡፡ መልሶ መላልሶ ያው ጉዳይ ይታኘካል፣ ይመነዠጋል፡፡ ማስቲካ ላንቲካ፡፡ ‹‹ለጤናዬ ሰጋሁ፤ እየታመምኩ መጣሁ፤ እርምጃ ወሰድኩ፡፡ ዜና በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ ማየት ጀመርኩ፡፡›› ይላል ክሪስ ጤናው እንዴት እንደተመለሰለት ሲናገር፡፡ ጎሽ እና ክሪስ ብቻቸውን አይደሉም ይላል ስታትስቲክስ፡፡ ሚሊዮኖች እንደነሱ እየተሰቃዩ ነው፡፡ ምናልባትም ቢሊዮኖች፡፡ ምንም እንኳ በዚህ ክፉ የወረርሽኝ ዘመን ቤት ተዘግቶ መዋል የቲቪ ተጠቃሚዎችን ቁጥር እንዲያሻቅብ ቢያደርግም፤ በብዙ አገራት ግን የዜና ግሽበት ተከስቷል፡፡ ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በከፍተኛ ሁኔታ የተመልካቾቻቸው ቁጥር ቀንሷል፡፡ በአውስራሊያ ደግሞ ከዜና ቻናሎች ይልቅ መዝናኛዎች የተሻለ ተመልካች ቁጥር አስመዝግበዋል፡፡ ፒው የሪሰርች ሴንተር በሰራው አንድ ጥናት ደግሞ በርካታ ሰዎች ስለ ኮሮና ዜና በጭራሽ መስማት አይፈልጉም፡፡ ለምን? አታክቷቸዋላ፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካ ከ10 ሰዎች ሰባቱ ስለ ኮሮና ምንም ዓይነት ዜና መስማት ጠላን ብለዋል፡፡ የአእምሮ ጤና አዋቂዎች ሁለት ነገር ያነሳሉ፡፡ አንዱ የበዛ መረጃ ወደ ታዳሚዎች እየተወነጨፈ የሰዎችን አእምሮ ቀስ በቀስ እየበጠበጠ መሆኑን፡፡ ሁለተኛው ዜና ምን ያህል እንደሚጎዳን አለመገንዘባችን፡፡ ለምሳሌ ስለ ኮሮና ቢጠራቀም አንድ ሜጋ ባይት የሚወጣው ዜና በቀን በቀን ሰምተን ይሆናል፡፡ ግንዛቢያችን ግን በአንድ ኪሎ ባይት እንኳ ጨምሯል? አልጨመረም፡፡ እንደ መረጃው ብዛቱ የመረጃ ጥራት አለን ማለት አይደለም፡፡ የሚመስለን ግን ብዙ በሰማን፣ ባየን፣ ባነበብን ቁጥር ብዙ ማወቃችን ነው፡፡ ለምሳሌ የኮሮና ዜና ዕለታዊ ቢሆንም የሰዎች በበሽታው ላይ ያላቸው ግንዛቤ ግን ተቀራራቢ ነው፡፡ ብዙ ዜና በመስማታቸው ከበሽታው የተፈወሱ የሉም፡፡ ብዙ የዜና እንጀራ በመመገባቸው የተህዋሲውን ክትባት ያገኙ የሉም፡፡ ዛሬ በዚህ አገር እንዲህ ያህል ሰዎች ተያዙ፣ ተመረዙ የሚል ዜና እየወቀረን ስንውል ግን አእምሯችን ላይ ጉዳት እያደረስን ነው፤ እንወቀውም አንወቀውም፡፡ ለምሳሌ ሰዎች ጭምብል ማጥለቅ አለባቸው ተብሏል፣ 2 ሜትር መራራቅ አለባቸው ተብሏል፤ እጃቸውን መታጠብ አለባቸው ተብሏል፡፡ ይህንኑ መረጃ በተለያየ መንገድ ለመቶ ሺ ጊዜ መስማት ትርፉ ምንድነው? ጆን ፖል ዴቪስ ሳይኮቴራፒስት ናቸው፡፡ ደንበኞቻቸው በመረጃ ሱናሚ ምክንያት ብቻ ለድብታ እና ለጭንቀት እንደተዳረጉ ደርሰውበታል፡፡ ጆን ፖል እንደሚሉት ከሆነ በሌላ የዓለም ጥግ የደረሰ አደጋ በዜና መልክ አእምሯችን ከቀሰመው በኋላ የዘነጋነው ይመስለናል፡፡ አእምሮ ግን ውስብስብ ነው፡፡ ባይታወቀንም የሰማነው መጥፎ ዜና ቀናችንን ያገረጣዋል፡፡ በፌስቡክ ሸርተቴ ሲንሸራተቱ፣ በመረጃ ሲንከላወሱ የሚውሉ ሰዎች አሉታዊነት እንደሚያጠቃቸው ብዙ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ እነሱ የድብታ መጫወቻዎች ነው የሚሆኑት፡፡ ዱካክ ከነ ሠራዊቱ እላያቸው ላይ ይሰፍራል፡፡ ሰዎች ነን፤ የመረጃ ዘመን ላይ ነን፡፡ ያለ መረጃ መኖር አንችል ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መረጃ የአእምሮ ጤናን ያውካል እየተባልን ነው፡፡ ስለዚህ ምን ተሻለ? ፕሮፌሰር ዴቪስ የአእምሮ ጤና ተመራማሪ ናቸው፡፡ በቀን አንድ ጊዜ ዋና ዋና ዜናዎችን አለፍ አለፍ እያሉ ማየት በቂ ነው ይላሉ፡፡ በዜና ሱስ ለሚሰቃዩ ሰዎች ግን ሚዲያ ቅኝት በሳምንት አንድ ጊዜ በቂ ነው ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰር ዴቪስ ሌላው ምክራቸው ዜናን ብቻ ሳይሆን ዜና ጣቢያን ማጋበስ አደገኛ እንደሆነ ነው፡፡ የዜና ምንጫችን ከሚታመኑ አንድ ወይም ሁለት ሚዲያዎች ብቻ ብናደርግ ለአእምሯችን ውለታ ዋልንለት ማለት ነው፡፡ ሚዲያዎች ሁሉ መጥፎ አይደሉም፤ ሁሉም ደግሞ ለጤናዎ በጎ አይደሉም፡፡ በረብ የለሽ የመረጃ ጥይት የማያቆስልዎትን ሚዲያዎች መምረጥ የርስዎ ፋንታ ነው፡፡ አሰስ ገሰሱን የሚያቀርብልዎት ማኅበራዊ ሚዲያ ለአእምሮ መቃወስ ሊዳርግ ይችላል፡፡ ፕሮፌሰር ጆን ፖል ዴቪስ ለሁሉም ነገር ድንበር ማበጀት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ያሰምሩበታል፡፡ ለምሳሌ በቀን ውስጥ ጠዋት ወይም ምሳ ሰዓት ላይ አንድ ጊዜ ብቻ ለ15 ደቂቃዎች መረጃ ቃርመን ከዚያ ግን በምንም መልኩ አለመመለስ፡፡ ይህ ግን ይቻላል? እንደሚባለው ቀላል ነው? በዲጂታል ዓለም ችግሩ የሚጀምረው የመጀመርያዋን ዜና ከማየቱ ላይ ነው፡፡ ከዚያማ እያሳሳቀ ይወስደናል፡፡ በመጨረሻ የጥፋተኝነት ስሜቱ አእምሯችን ይቀውራል፡፡ ምናልባት ራስን በጊዜ የሽቦ አጥር ማጠር አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡ ስልክን አንድ ጊዜ አይቼ እዘጋዋለሁ ብለው የሚከፍቱ የዋሆች ናቸው፡፡ በመረጃ ሱናሚ ተጥረግርገው የማይወሰዱት ስንቶቹ ናቸው? ፓራል ጎሽ ሰዎችን በሰዓት ገድቦ መረጃን መቆጣጠር እንደሚችሉ መንገር ቀልድ ነው ትላለች፡፡ እሷ ሞክራው አልተሳካላትም፡፡ ለእሷ መፍትሄ የሆነላት መረጃን ከሰዎች አፍ መቀበልን ነው፡፡ ለሻይ ከሰዎች ጋ ስትገናኝ ሰዎች ያወሩላታል፡፡ መረጃ ከአፍ አፋቸው ትቀልባለች፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው መንገድ አልሰራላትም፡፡ አንድ ጊዜ ወደ ስልኬ ከገባሁማ መውጫ የለኝም ትላለች፡፡ የሷ ታሪክ የሚሊዮኖች ታሪክ ነው፡፡ ‹‹አሁን ነጻ ወጥቻለሁ፤ በዕለታዊ ቅራቅንቦ ዜና አልታለልም፤ ልቦለድ ማንበብ ነው የምወደው፤ ለሱ ጊዜ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ ትላለች፡፡›› ይስመርላት!" https://www.bbc.com/amharic/news-54179474 +politics በሙስሊም አሜሪካውያን የምትመራው የአሜሪካ ከተማ "በአሜሪካዋ ሚቺጋን ግዛት በምትገኘው ሐምትራምክ ዋና ጎዳና መረማመድ በዓለም ያሉ ከተሞችን እንደጎበኙ የሚያደርግ ስሜትን ይፈጥራል። ከተማዋን ያደመቁት የፖላንድ የቋሊማ መሸጫ መደብር፣ የምሥራቅ አውሮፓ ዳቦ ቤት፣ የየመን መገበያያ መደብር እና የቤንጋሊ ልብስ ቤት ከተማዋን የበርካታ ሕዝቦችና ባህሎች መናኸሪያ አድርገዋታል። የቤተ ክርስቲያን ደወልና የሙስሊሞች የፀሎት ጥሪ (አዛን) በተመሳሳይ ወቅት ይሰሙባታል። ""ዓለምን በሁለት ስኩዌር ማይል"" በሚል መፈክሯ የምትታወቀው ሐምትራምክ በአምስት ስኩዌር ኪሎሜትር የቆዳ ስፋቷ ውስጥ ወደ 30 የሚጠጉ ቋንቋዎች የሚነገሩባት በመሆን እውነትም ""ትንሿ ዓለም"" የሚል ስያሜ አሰጥቷታል። በመካከለኛውም ምዕራብ የምትገኘውና የ28ሺህ ሕዝብ መኖሪያ የሆነችው ይህች ከተማ በዚህ ወር ደግሞ በታሪኳ ለየት ጉዳይ ተሰምቶባታል። በሐምትራምክ ሁሉም አባላት የእስልምና ተከታይ የሆኑበት የከተማ ምክር ቤትና የሙስሊም ከንቲባ መርጣለች። በአሜሪካ ውስጥ የሙስሊሞች አስተዳደር ሲመሰረት ይህ የመጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን ታሪካዊ ክስተት ነው ተብሏል። በአንድ ወቅት በከተማይቱ የሚደርስባቸውን መድሎና መገለል ሲታገሉ የነበሩት ሙስሊም ነዋሪዎች የዚህች የብዙ ባህሎች መናኸሪያ ከተማ ዋና አካል ሆነዋል፤ ከሕዝቡም ከግማሽ በላይ የሚሆነውንም ቁጥር ይዘዋል። ምንም እንኳን ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች እና ከፍተኛ የባህል ክርክሮች ቢኖሩም፣ ሐምትራምክ ከተለያዩ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ መሰረቶች የመጡ ነዋሪዎች ተስማምተው አብረው የሚኖሩባት ሆናለች። ይህም በአሜሪካ ውስጥ እየጨመረ ለመጣው ብዝኃነት የወደፊት ዕጣ ፈንታ ትርጉም ያለው የጥናት መነሻም ልትሆን እንደምትችል ተነግሯል። ሆኖም በሐምትራምክ ያለው ታሪካዊ ክስተት በሌሎች የሚደገም ወይስ የተለየ ሆኖ የሚቀር የሚል ጥያቄም እያጫረ ነው። በበርካታ የጀርመን ሰፋሪዎች ጥንታዊ ታሪኳ የሚጀምረው የሐምትራምክ ከተማ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በርካታ ሙስሊሞች የሚኖሩባት ስትሆን ይህ ከጥንት እስካሁን ያለው ገፅታዋም በጎዳናዎቿ ባሉ ኪነ ጥበቦች በግልፅ ይንጸባረቃል። መደብሮቿ በአረብኛና በቤንጋሊ ቋንቋዎች በተጻፉ ስሞች ያጌጡ ሲሆን፣ የባንግላዴሽ ባለ ጥልፍ አልባሳት፣ ከየመን የመጣው አጭር ጥምዝ ቢላ (ጃምቢያስ) በበርካታ መደብሮቿ መስኮቶች ውስጥ ይታያሉ። የከተማዋ ሙስሊም ነዋሪዎች ፓክዝኪ የሚባለውን የፖላንድ ዶናት ለመግዛት ወረፋ ይዘውና ተሰልፈው ይታያሉ። ""አጫጭር ቀሚስ የለበሱና ሰውነታቸው በንቅሳት ያጌጠ እንዲሁም ሙሉ ፊታቸውንና ሰውነታቸውን የሚሸፍን ልብስ ለብሰው በተመሳሳይ መንገድ ሲሄዱ ማየት የተለመደ ነው። ይህ ሁሉ የኛ አካል ነው"" በማለት በከተማዋ መሃል የካፌ ባለቤት የሆነው የቦስኒያ ስደተኛ ዝላታን ሳዲኮቪች ይናገራል። በዲትሮይት በአብዛኛው የተከበበችው ሐምትራምክ በአንድ ወቅት የአሜሪካ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ማዕከል ነበረች። የመኪና አምራቹ ጄኔራል ሞተርስ ፋብሪካ የሚገኘውም በከተማዋና 'ሞተር ሲቲ' ተብላ በምትጠራው ዲትሮይት ድንበር ላይ ነው። የመጀመሪያው ካዲላክ ኤልዶራዶም መገጣጠሚያውን በሐምትራምክ በ1980ዎቹ ከፈተ። በ20ዎቹ ክፍለ ዘመን የፓላንድ ስደተኞች በገፍ መግባታቸውን ተከትሎም ከተማዋ ""ትንሿ ዋርሶ"" የሚል ስያሜ አገኘች። የፖላንድ ተወላጁ የቀድሞው የሮም ሊቃነ ጳጳስ ጆን ፖል በአውሮፓውያኑ 1987 በአሜሪካ ጉብኝት ካደረጉባቸው ከተሞች መካከል አንዷ ናት። በአውሮፓውያኑ 1970 አካባቢም የከተማዋ 90 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የፖላንድ ዝርያ ነበረው። በእነዚያ አስርት ዓመታት ውስጥም የአሜሪካ የመኪና ምርት ኢንዱስትሪ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ ወጣትና ሃብታም ፖላንድ አሜሪካውያን ኑሯቸውን ወደ ሌሎች ከተሞች ማድረግ ጀመሩ። ይህ ለውጥም ሐምትራምክን በሚቺጋን ካሉ ግዛቶች በጣም ድሃ ከተሞች ውስጥ አንዷ አድርጓታል። ሆኖም በከተማው የነበረው የተመጣጠነ የመግዛት አቅም ስደተኞችን መሳብ ጀመረ። ባለፉት 30 ዓመታት ሐምትራምክ በከፍተኛ ለውጥ ያለፈች ሲሆን ለአረብ እና ለእስያ ስደተኞች በተለይም ከየመን እና ከባንግላዴሽ ለመጡት ዋነኛ ተመራጭ ማረፊያ ሆናለች። በአሁኑ ጊዜ ካሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ውስጥ 42 በመቶ የውጭ አገራት ተወላጆች ናቸው። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንደሆኑ ይታመናል። አዲስ የተመረጡትን የምክር ቤት አባላት አወቃቀርም በሐምትራምክ ያለውን ተለዋዋጭ የሥነ ሕዝብ ሁኔታ የሚያንጸባርቅ ነው። የከተማው ምክር ቤት አባላት ሁለት ቤንጋሊ አሜሪካውያን፣ ሦስት የመን አሜሪካውያን እና እምነቷን ወደ እስልምና የቀየረች ፖላንዳዊ-አሜሪካዊ ናቸው። 68 በመቶ ድምጽ በማሸነፍ ኡመር ጋሊብ በአሜሪካ የመጀመሪያው የመን አሜሪካዊ ከንቲባ ሆነዋል። ""ክብር እና ኩራት ይሰማኛል፣ ነገር ግን ትልቅ ኃላፊነት እንደሆነ አውቃለሁ"" በማለት የ41 አመቱ ከንቲባ ተናግረዋል። በየመን አንዲት መንደር ውስጥ የተወለዱት የአሁኑ ከንቲባ ወደ አሜሪካ የመጡት በ17 ዓመታቸው ነው። በወቅቱም ሐምትራምክ አቅራቢያ በሚገኝ ፋብሪካ ውስጥ የፕላስቲክ መኪና መለዋወጫም እንዲሰሩ ተቀጠሩ። በኋላም እንግሊዝኛ ተምረው በህክምና ባለሙያነት የተመረቁ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በጤና ባለሙያነት እያገለገሉ ይገኛሉ። ""የሐምትራምክ ሕዝቦች በመጡበት በራሳቸው ባህል ይኮራሉ። እንዋሃድ ካልን ልዩነታችንን እናጣለን። የእያንዳንዳንችንን ልዩነት እናከብራለን"" ሲሉ በአሁኑ ወቅት ለከተማዋ ምክር ቤት አባል የተመረጡት የ29 ዓመቷ አማንዳ ጃክዝኮውስኪ ተናግረዋል። አክለውም ""እርስ በርሳችን ተቀራርበን ስንኖር በልዩነታችን ላይ ላለማተኮር እንገደዳለን"" ብለዋል። ሆኖም ሁሉ ነገር አልጋ ባልጋ እንዳልሆነ ለ15 ዓመታት ያህል በከንቲባነት ያገለገሉትና በቅርቡ የተተኩት ካረን ማጄውስኪ ይናገራሉ። ""ትንሽ ቦታ ነው፤ ግጭቶችም አሉ"" ይላሉ። በተለይም በአውሮፓውያኑ 2004 የእስላማዊ የፀሎት ጥሪ (አዛን) በድምፅ ማጉያ በአደባባይ እንዲሰማ ድምጽ መሰጠቱን ተከትሎ ውጥረቶች ነግሰው ነበር። አንዳንድ ነዋሪዎች በመስጊድ አቅራቢያ ያሉ ቡና ቤቶችን መከልከል የአካባቢውን ኢኮኖሚ ይጎዳል ሲሉ ተከራክረዋል። ከስድስት ዓመት በፊትም በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ሙስሊም አብላጫውን የያዘበት ምክር ቤት ስታቋቁምም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ሚዲያዎች ሁኔታውን ለመታዘብ ወደ ሐምትራምክ ጎረፉ። አንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን ባወጧቸው ዘገባዎችም በርካታ ሙስሊሞች በመኖራቸው ""ውጥረት የበዛባት"" የሚል ምስልም ለመስጠት ሞክረዋል። የብሔራዊ ቴሌቪዥን አቅራቢም የወቅቱን ከንቲባ ማጄውስኪን ከንቲባ መሆን ያስፈራቸው እንደሆነ ሁሉ ጠይቋል። ይባስ ብሎ ሙስሊሞች በሚቆጣጠሩት ምክር ቤት ውስጥ የሸሪዓ ሕጎች በሕዝቡ ላይ ሊጫኑ ይችላሉ የሚሉ አስተያየቶች ከአንዳንዶች ተነስቷል። ""በሐምትራምክ ነዋሪዎች ለእንደዚህ አይነት ንግግሮች ጆሯቸውን አይሰጡም"" ይላሉ ማጄውስኪ። የሐምትራምክ ሕዝብ እንግዳ ተቀባይ በመሆኑ በጣም የሚያስደስታቸው ጉዳይ ነው እናም አዲስ ነዋሪዎች ባህላቸውንና ቋንቋቸውን ለሚረዱ ተወካዮች ድምፃቸውን ቢሰጡ ""ተፈጥሯዊ"" ነው በማለት ያስረዳሉ። የአሜሪካ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ ስለ ሃይማኖት መረጃ ባይሰበስብም፣ ነገር ግን ፒው የተሰኘ የምርምር ማዕከል በአውሮፓውያኑ 2020 በአሜሪካ ውስጥ ወደ 3.85 ሚሊዮን የሚጠጉ ሙስሊሞች እንዳሉ ግምቱን አስቀምጧል። ይህም አሃዝ ከጠቅላላይ ሕዝቡ 1.1 በመቶ ያህል ነው። በአውሮፓውያኑ 2040 እስልምና በአሜሪካ ውስጥ ከክርስትና በመቀጠል ሁለተኛ ተከታይ ያለው እምነት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ምንም እንኳን የሃይማኖቱ ተከታዮች ቁጥር እያደገ ቢሄድም ሙስሊሞች በአሜሪካ ውስጥ አሁንም ቢሆን ጥላቻ ይደርስባቸዋል። በአሜሪካ ከደረሰው 9/11 ጥቃት ከሁለት አስርት ዓመታትም በኋላ በአ��ሪቱ ያሉ ሙስሊሞች እንዲሁም ሌሎች አረብ አሜሪካውያን ከፍተኛ ጥላቻን እያስተናገዱ ይገኛሉ። የያኔው ዕጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በርካታ ሕዝባቸው ሙስሊም ከሆኑ አገሮች የሚመጡ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ሃሳብ ባቀረቡበት ወቅት ግማሹ ሙስሊም አሜሪካውያን መድልዎና መገለል እንደደረሰባቸው በአውሮፓውያኑ 2016 ለፒው ተናግረዋል። በተጨማሪም ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሁሉም የሃይማኖት ቡድኖች መካከል ሙስሊሞች አሁንም ቢሆን በአሜሪካ ሕዝብ ዘንድ በአሉታዊ ሁኔታ ነው የሚታዩት። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አሜሪካውያን በግላቸው የእስልምና ተከታይ የሆኑ ሰዎችን ባያውቁም፣ እናውቃለን የሚሉ አሜሪካውያን በበኩላቸው እስልምና ከሌሎች ሃይማኖቶች በበለጠ ሁከትን ያበረታታል ብለው እንደማያስቡ ተናግረዋል። ስለ እስልምናም ሆነ ሙስሊሞችን ማወቅ ከእስልምና ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥላቻዎች ትርጉም እንደሌላቸው የሐምትራምክ ከተማ ዋና ማሳያ ናት። ሻሃብ አህመድ የ9/11 ጥቃትን ተከትሎ ለከተማው ምክር ቤት አባልነት ሲወዳደሩ ትልቅ ፈተና ነበር የገጠማቸው። ""ወደ አውሮፕላኑ ያልደረስክ 20ኛው ጠላፊ ነህ የሚሉ በራሪ ወረቀቶች በከተማዋ ሁሉ ተበትነው ነበር"" ሲሉ ቤንጋሊ አሜሪካዊው ሻሃብ ተናግረዋል። በአውሮፓውያኑ 2001 በተካሄደው ምርጫም ተሸነፉ። ሆኖም ተስፋ አልቆረጡም ከሁለት ዓመታት በኋላ በነበረው የምረጡኝ ዘመቻ እንቅስቃሴ የጎረቤቶቻቸውን በር እያንኳኩ ድምፅ ስጡኝ አሉ። የከተማዋም ነዋሪ ሰማቸው፣ ድምፅም ሰጣቸው በዚህም የሐምትራምክ የመጀመሪያው ሙስሊም ከንቲባም ሆነው ተመረጡ። በአውሮፓውያኑ 2017 የትራምፕ አስተዳደር በሙስሊም አገራት ላይ እገዳውን ሲጥል ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ተሰብስበው በከተማዋ ወጥተዋል። ""በሐምትራምክ ውስጥ ለመኖር የሌሎች ሰዎችን ዕምነትና ባህልን ማክበር እንዳለብን በማሳወቅ አንድነታችን እንዲያጠናክር ረድቶናል"" በማለት ""ሐምትራምክ፣ ዩኤስኤ"" የተሰኘ ፊልም በተባባሪ ዳይሬክተርነት የሰራው ራዚ ጃፍሪ ይናገራል። በአገር አቀፍ ደረጃም ቢሆን ሙስሊም አሜሪካውያን በፖለቲካው ዘንድ ጎልተው የሚታዩ ሆነዋል። በአውሮፓውያኑ 2007 የሚኒሶታ ዲሞክራት ኪት ኤሊሰን የመጀመሪያው ሙስሊም የምክር ቤት አባል ሆኑ። በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ምክር ቤት አራት ሙስሊም አባላት አሉት ። ባለፈው ወር በነበረው የሐምትራምክ ምርጫ በርካታ ነዋሪዎች በምርጫ ጣቢያዎች ፊት ለፊት ተሰብስበው ሰላምታ ሲለዋወጡ ብዙዎችም ""መርጫለሁ"" የሚል ወረቀት ሲያሳዩም ነበር። ""ሰዎችን አንድ ላይ ማሰባሰብ የአሜሪካዊነት መገለጫ ነው። አንደኛውም እሴታችን ነው"" በማለት የሚናገሩት ጃክኮቭስኪ ስደተኞች በዲሞክራሲ ሂደት ውስጥ በመሳተፋቸው የነበራቸውንም ደስታ ገልጸዋል። ነገር ግን እንደሌላው የአገሪቱ ክፍል በከተማው ውስጥ ከፍተኛ የባህል ክርክሮች መካሄዳቸው አልቀረም። በሰኔ ወር የከተማው አስተዳደር የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች መለያ የሆነው ሰንደቅ አላማ በከተማው አዳራሽ ፊት ለፊት እንዲውለበለብ ሲፈቅድ አንዳንድ ነዋሪዎችን አስቆጥቷል። በተጨማሪም በግል የንግድ ተቋማትና ቤቶች ውጭ የተሰቀሉ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ሰንደቅ አላማዎች ተቀዳደዋል። ከነዚህም መካከል ከማጄውስኪ ልብስ መደብር ውጪ የተሰቀለው ሰንደቅ አላማም ተቀዶ ተጥሏል። ይህንንም ተከትሎም ""ይህ ለሰዎች በጣም አስደንጋጭ መልዕክት ያስተላልፋል"" ብለዋል። ዕፀ ፋርስም (ማሪዋና) የውዝግብ መንስኤ ሆኗል። በሐምትራምክ የተከፈቱ ሦስት የዕጸ ፋርስ ማከፋፈያዎች በአንዳንድ የሙስሊም እና የፖላንድ-ካቶሊክ ማኅበረሰቦች ቁጣን ቀስቅሰዋል። ሌሎች ነዋሪዎች በበኩላቸው በወግ አጥባቂ ሙስሊም ማኅበረሰቦች ውስጥ ያለው የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ማነስ እንዳሳሰባቸው ሲናገሩ ይሰማሉ። በምርጫው ምሽት ተመራጩ ከንቲባ ጋሊብ ከድምፅ መስጫው በኋላ በደስታ በፈነጠዙና ባቅላቫና 'ክባብ' በሚያከፋፍሉ የመን አሜሪካውያን ተከበው ነበር። የከበቧቸው ከ100 በላይ ደጋፊዎች ሁሉም ወንዶች ናቸው። በምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸው ውስጥ ሴቶች እንደተሳተፉ የሚናገሩት ከንቲባው ሆኖም በባህሉ መሰረት ፆታዎች አንዳይቀላቀሉ ተደርጓል። ምንም እንኳን ራሳቸውን እንደ አሜሪካዊ በሚያዩት ወጣቶች ዘንድ ይህንን ሃሳብ ቢገዳደሩትም ከንቲባው ባህሉ መቀጠል አለበት ይላሉ። ሐምትራምክ ከዚህ ባለፈ ደግሞ በተበላሹ መሰረተ ልማቶችና ውስን በሆኑ የምጣኔ ሃብት ዕድሎች በርካታ ችግሮች ተደቅኖባታል። በበጋው የጣለው ከባድ ዝናብ የከተማውን የፍሳሽ ማስወገጃዎች ሞልቶ በርካታ ቤቶችን አጥለቅልቋል። ለመጠጥ የሚውለው ውሃ በኬሚካል መበከሉ ሁኔታውን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል። የከተማዋ ግማሽ የሚጠጋው ሕዝብ የሚኖረው ከድህነት ወለል በታች ነው። እነዚህ ችግሮች ለአዲሱ የከተማ አስተዳደርም ለዓመታት ሲንከባለሉ የቆዩ አንገብጋቢ የቤት ሥራዎች ናቸው። ""በአብዛኛው ሙስሊም በሚበዛበት ከተማ ዲሞክራሲ ምን ዓይነት መልክ አለው? እንደሌላው ቦታ ሁሉ የተዘበራረቀ እና የተወሳሰበ ነው"" ሲል ዘጋቢ ፊልም ሰሪው ጃፍሪ የተናገረ ሲሆን አክሎም ""አሁን ያለው የደስታ ስሜት ሲቀዘቅዝ ሥራው መሰራት አለበት"" በማለትም ያስረዳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59868775 +sports እግር ኳስ፡ የአውሮፓ ዋንጫ እሑድ ምሽት ፍጻሜውን ያገኛል፤ ማን ያሸንፋል? "የበርካታ እግር ኳስ አፍቃሪያንን ልብ ሰቅዞ ይዞ የከረመው የአውሮፓ ዋንጫ ነገ እሑድ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ፍጻሜውን ያገኛል። በፍጻሜ ጨዋታው ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ዋንጫ ለፍጻሜ የደረሰችው እንግሊዝ እና ምንም ሳትጠበቅ እዚህ የደረሰችው ጣልያን ይፋለማሉ። ጣልያኖች ገና ከምድብ ጨዋታዎች ጀምሮ በርካታ ጎሎችን እያስቆጠሩና እስካሁንም ድረስ ምንም አይነት ሽንፈትም ሆነ አቻ ውጤት ሳያስተናግዱ ነው ለፍጻሜው ጨዋታ የደረሱት። እንግሊዝ ደግሞ በምድብ ጨዋታዎች ግብ ማስቆጠር ተስኗት ነበር። ቀስ በቀስ ግን እነ ሀሪ ኬንን የያዘው ቡድን ወደ ግብ ማግባት መመለስ ችሏል። በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታ ጣልያን ስፔንን በፍጹም ቅጣት ምት በማሸነፍ ለፍጻሜ መድረሷን አረጋግጣለች። በእንግሊዙ ዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዘጠና ደቂቃው እና ተጨማሪ ደቂቃ አንድ አቻ በመጠናቀቁ ሁለቱ ቡድኖች በፍጽም ቅጣት ምት እንዲለያዩ ሆኗል። የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በፈጣን እንቅስቃሴና በስፔን የተበላይነት የተሞላ ቢሆንም ግብ ግን ሳይቆጠር ነበር የተጠናቀቀው። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ የጣልያኑ ፌደሪኮ ኪዬዛ አስገራሚ ግብ አስቆጥሮ ጣልያንን መሪ ማድረግ ችሏል። ነገር ግን ጨዋታው ሊጠናቀቅ እየተቃረበ በነረበት ሰዓት የስፔን ተጫዋቾች በጥሩ ጨዋታ ጣልያን የግብ ክልል ውስጥ የተቀባበሏትን ኳስ ተቀይሮ የገባው አልቫሮ ሞራታ በግሩም ሁኔታ ወደ ግብነት በመቀየር አገሩን አቻ ማድረግ ችሎ ነበር። የጣልያኑ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ያዋቀሩት ቡድን እስካሁን ድረስ ብዙም ሳይቸገር ነበር ለግማሽ ፍጻሜው መድረስ የቻለው። ነገር ግን ከስፔን ጋር የተደረገው ጨዋታ ጣልያኖችን የፈተነ ነበር። ጣልያን ከምድብ ድልድል ጀምሮ ባልተለመደ መልኩ ማጥቃት ላይ መሠረት ያደረገና ብዙ ግቦችን ማስቆጠር የሚያስችል አጨዋወት ነበር ይዛ የመጣችው። አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ብሔራዊ ቡድኑን ከተረከ��� ወዲህ ለ2018ቱ የዓለም ዋንጫ እንኳን ጣልያንን ማሳለፍ አቅቷቸው የነበረ ቢሆንም በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ግን በደንብ የተደራጀና ውጤታማ ቡድን ሠርተው ለፍጻሜ መድረስ ችለዋል። እንግሊዝ ደግሞ በግማሽ ፍጻሜው ዴንማርክን በመርታት ከ55 ዓመት በኋላ ለአንድ ትልቅ የእግር ኳስ ውድድር ፍጻሜ ደርሳለች። በርካታ ተመልካች በሚይዘው የለንደኑ ዌምብሊ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ ፈጣንና በግብ ሙከራዎች የታጀበ ነበር። እንግሊዝ በፈረንጆቹ 1966 ምዕራብ ጀርመንን በመርታት ካነሳችው የዓለም ዋንጫ ውጭ ሌላ ውድድር አሸንፋም ይሁን ለፍጻሜ ደርሳ አታውቅም። ረቡዕ ምሽት ዴንማርክን የገጠመችው እንግሊዝ አንድ ለባዶ ስትመራ ብትቆይም ከ120 ደቂቃዎች ፍልሚያ በኋላ 2-1 መርታት ችላለች። ምንም እንኳ ዴንማርክ በወጣቱ ዳምስጋርድ ግሩም ቅጣት ምት አማካይነት ጨዋታውን ስትመራ ብትቆይም የኋላ ኋላ እጇን ሰጥታለች። የመጀመሪያው አጋማሽ ከመጠናቀቁ በፊት የእንግሊዙ ቡካዮ ሳካ ወደ ጎል የላካትን ኳስ የዴንማርኩ ሳይመን ኬር በራሱ መረብ ላይ በማሳረፉ ጨዋታው አቻ ሆነ። የዴንማርኩ ግብ ጠባቂ ካስፐር ሽማይክል ከሃገሪ ማጓየርና ሃሪ ኬን የተቃጡበትን የጎል ሙከራዎች ማዳን ቢችልም 103ኛው ደቂቃ ላይ ራሂም ስተርሊንግ ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ተጠልፎ ዳኛው ቅጣት ሰጥተዋል። የእንግሊዙ ግብ አዳኝ ሃሪ ኬን ፍጹም ቅጣት ምቱን ሲመታ በረኛው ተወርውሮ ቢያድነውም ሃሪ ኬን ግን ተመልሶ ኳሷን ወደ መረብ በመጠለዝ እንግሊዝ ሁለት ለአንድ እንድታሸንፍ አስችሏል። የጣልያኑ ተከላካይ ሊዮናርዶ ቦኑቺ የፍጻሜ ጨዋታው በእንግሊዙ ዌምብሌይ ስታዲየም መካሄዱ ምንም አይነት ፍርሀት እንደማይፈጥርባቸው ተናግሯል። ""ምንም እንኳን በስታዲየሙ ከሚገኙት ደጋፊዎች መካከል አብዛኛዎቹ እንግሊዛውያን እንደሚሆኑ ብናውቅም ምንም አይነት ስጋት ግን አይገባንም። እንደውም ይሄ ተጨማሪ መነሳሳትን ነው የሚፈጥርልን"" ብሏል። በለንደኑ ዌምብሌይ ስታዲየም የሚካሄደውን የፍጻሜ ጨዋታ እስከ 1 ሺህ የሚደርሱ ጣልያናውያን ደጋፊዎች ገብተው እንደሚከታተሉት ይጠበቃከል። የዩቬንቱስ የመሀል ተካለካይ ቦኑቺ ከ36 ዓመቱ ጆርጂዮ ኪዬሊኒ ጋር በመጣመር እንግሊዝ ግብ እንዳታስቆጥር ከፍተኛ ሥራ ይጠበቅባቸዋል። ነገር ግን አማካይ እድሜው 25 የሆነው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አንጋፋዎቹን ተከላካዮች ሥራ እንዳያበዛባቸው ተሰግቷል። ''በጣም ፈጣን የፊት መስመር ተጫዋቾች አሏቸው። ሙሉ ቡድናቸውንና በተለይ አጥቂዎቹን በትልቅ ትኩረት ነው የምንጠብቃቸው። ምን አይነች ችግር ሊፈጥሩብን እንደሚችሉ እናውቃለን። ፍጥነታቸውን ከግምት ውስጥ አስገብተን ተጠንቅቀን እንጫወታለን'' ብሏል ቦኑቺ። የእንግሊዙ አምበል ሃሪ ኬን በበኩሉ ''ይሄ በእግር ኳስ ሕይወቴ ትልቁ አጋጣሚ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ። ምናልባት ይህ ለሁሉም የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች የሚሠራ ይመስለኛል''ብሏል። ''ልጅ ሆነን እንዲህ አይነት ህልሞችን እናልማለን። አገርን ወክሎ ተጫውቶ ዋንጫ ማሸነፍ። አሁን ይህንን ህልም የመኖር እድል አግኝተናል። ይሄን የመሰለ እድል በቀላሉ አሳልፈን አንሰጥም።'' እንግሊዞች የግማሽ ፍፃሜ እርግማን አለባቸው ይባል ነበር። በወጣት ተጫዋቾች የተሞላችው እንግሊዝ በ2018ቱ የዓለም ዋንጫ ለግማሽ ፍጻሜ ደርሳ በክሮሺያ መሸነፏ ይታወሳል። ጣልያን በተካሄደው የ1990 ዓለም ዋንጫ ላይ እንዲሁ ለግማሽ ፍጻሜ ደርሰው ተሸንፈዋል። በድጋሚ ጣልያን ባስተናገደችው የ1996 አውሮፓ ዋንጫ ላይ ለግማሽ ፍጻሜ የደረሰችው እንግሊዝ ሽንፈት አስተናግዳ ነበር። አሁን ግን ይህንን መጥፎ ጠባሳ ሽራ ለፍጻሜ ማለፍ ችላለች። አሁን ጥ���ቄው እንግሊዝ ከነዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ በዓለም መድረክ ትልቅ ዋንጫ ማንሳት ትችላለች ወይ የሚለው ነው። እሑድ ምሽት 4 ሰዓት በለንደኑ ዌምብሊ ስታድየም በአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ እንግሊዝ ከጣልያን የውድድሩን የመጨረሻ ጨዋታ ያደርጋሉ። ሁለቱም ቡድኖች ባሳዩት አቋም ምክንያት ይሄኛው ቡድን የተሻለ እድል አለው ለማለት እንኳን ከባድ አድርጎታል። ለማንኛውም ግን አሸናፊው ነገ ምሽት የሚታወቅ ይሆናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57787750 +business ኢትዮጵውያንን እየፈተነ ያለው የኑሮ ውድነት መፍትሄው ምን ይሆን? "አቶ አብዲሳ ገቢሳ ከባለቤታቸው እና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር በአዲስ አበባ ከተማ መኖሪያ ቤት ተከራይተው ይኖራሉ። የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑት አቶ አብዲ፤ ወርሃዊ ደመወዛቸው 5ሺህ ብር ሲሆን የባለቤታቸው ገቢ ሲጨመር የቤተሰቡ ወርሃዊ ገቢ 8 ሺህ ብር ይደርሳል። ይሁን እንጂ ይህን ቤተሰብ በ8ሺህ ብር ወርሃዊ ገቢ ማስተዳደር እጅጉን ለአቶ አብዲ ከብዷቸዋል። ""5ሺህ ብር ወር ጠብቄ ነው የማገኘው ነው። ወጪ እና የማገኘው ገንዘብ አይመጣጠንም። የቤት ኪራይ አለ፣ ቀለብ አለ፣ ለልጆች ትምህር ቤት ወጪ አለ። ልጆች ትምህር ቤት ሲሄዱ ምሳ ይዘው ነው የሚሄዱት። ትራንስፖርት፣ ልብስ እንዲሁም ለሠራተኛ የሚከፈል አለ። ሕይወት በጣም እየጎዳን ነው"" ይላሉ። በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የዋጋ ግሽበት በተከታታይ ጭማሪ ሲያሳይ ቆይቷል። በተለይም ኀብረተሰቡ በዕለት ተዕለት በሚጠቀምባቸው መሰረታዊ ፍጆታዎች፣ በግንባታ እቃዎችና በሌሎች ላይ እየታየ ያለው የዋጋ ንረት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዜጎችን ህይወት እጅግ እየተፈታተነው ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ መንግሥት የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በኑሮ ውድነቱ ላይ ከፍተኛ ጫና ሊያሳርፍ እንደሚችል ነዋሪዎች እና የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የሚናገሩት ነው። የበርካታ አገራት ፈተና የሆነው የኑሮ ውድነት በያዝነው አውሮፓውያኑ 2022 በርካታ የዓለማችን አገራት ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አጋጥሟቸዋል። በዩናትድ ኪንግደም ባለፈው ወር በ30 ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የኑሮ ውድነት በ7 በመቶ ተመዝግቧል። ኬንያውያንም በምግብ ዘይት፣ በእህል እና በአትክልት እና ፍራፍሬ ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ አስቆጥቷቸዋል። ከቀናት በፊት የብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፤ ""አሁንም በኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ፈተና እየገጠመን ያለው ከዋጋ ግሽበት ጋር በተገናኘ ሲሆን፥ከአምናው የሚያዚያ ወር ጋር ሲነጻጸር የዋጋ ግሽበቱ 36.6 በመቶ ደርሷል። ነገሩን ይበልጥ ከባድ የሚያደርገው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እየተመዘገበ ያለው የምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ መሆኑ ነው፡፡"" በማለት አትቷል። አቶ አብዲ ገቢያ የምርቶች ዋጋ 'በየቀኑ እና በየሰዓቱ' በሚባል ደረጃ እየጨመረ ነው ይላሉ። ""በየቀኑ፤ በየሰዓቱ ይጨምራል። ለምሳሌ ባለፈው እሁድ ለልጅ ታሽጋ የምትሸጥ ወተት በ20 ብር ነበር የገዛሁት። ማታ ለልጅ ገዝቼ ልግባ ስል ዋጋው 30 ብር ሆኗል። 10 ብር ጨመረ ማለት ነው ! "" በማለት ይናገራሉ። ይህ የመዲናዋ ከተማ ነዋሪ የኑሮ ውድነቱ መቋቋም ከምንችለው በላይ ሆኖብናል ይላሉ። ""የኑሮ ሁኔታ ይህ ነው ማለት የሚቻል አይደለም። በጣም እየከበደ ነው። ከኔ በታች ሆኖ የሚኖር ደግሞ አለ። ከኔ በታች ያለ ሰው በምን ተዓር እንደሚኖር አላውቅም"" በማለት የተጫናቸውን የኑሮ ክብደት ይናገራሉ። የአገሪቱ መንግሥት ለዋጋ ግሽበቱና ላስከተለው የኑሮ ውድነት እንደምክንያት አድርጎ የሚያቀርበው አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን ነው። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የጥሬ ግብዓት ውድነት፣ በተለያዩ የአገሪ��� ክፍሎች እያጋጠሙ ያሉ አለመረጋጋቶች እንዲሁም የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት ለዋጋ ግሽበቱና ለኑሮ ውድነት እንደ ምክንያት የሚጠቀሱ ናቸው። ከጎረቤት ጋር እየተረዳዳን አብረን እንኖራለን አቶ አብዲ ገቢሳ 8 ሺህ ብር ገቢያቸውን በብልሃት ወጪ ያደርጋሉ። በባለቤታቸው ገቢ የቤት ኪራይ ከከፈሉ በኋላ በቀሪው ገንዘብ ቀሪ ወጪዎች እንደሚሸፈኑ ይናገራሉ። ""እሷ ቤት ኪራይ ከቻለች እኔ ደግሞ እንደ ቀለብ፣ ትራንስፖርት፣ የትምህር ቤት ክፍያ፣ ለቤት ሠራተኛ ደመወዝ እክፍላለሁ። ከእነዚህ ወጪዎች የተረፈ ካለ ሌሎች ነገሮች አደርግበታለሁ"" ይላሉ። ""ካልበቃን ደግሞ ከሰው እንበደራለን። ደመወዝ እስኪደርስ ከሰው እንበደራለን። ከጎረቤት ጋር እየተረዳዳን አብረን እንኖራለን"" ይላሉ የኑሮ ውድነቱን ለመቆጣጠር ምን እርምጃ መወሰድ አለበት? መንግሥት የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ አልያም ለመቆጣጠር እየወሰዳቸው ያሉት እርምጃዎች አጥጋቢ አደሉም በሚል ተደጋጋሚ ትችቶች ይቀርቡበታል። ምርት በማከማቸት ዋጋ እንዲንር ምክንያት በሚሆኑ ነጋዴዎች ላይ፣ በሸማች እና አምራች መካከል በመግባት የኑሮ ውድነት የሚያስከትሉ ነጋዴዎች ላይ በቂ እርምጃ አልተወሰደም የሚለው አንዱ መንግሥት ላይ የሚነሳ ቅሬታ ነው። በጅማ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ለታ ሴራ (ዶ/ር) የአንድ ምርት ዋጋ ከፍ የሚለው ፍላጎት ከአቅርቦት ሲያንስ እንደሆነ አስታውሰው፤ መሠረታዊ አቅርቦቶች በገበያ እንዲኖሩ መንግሥት አምራቾችን መደገፍ አለበት ይላሉ። መምህሩ ምጣኔ ሃብታዊ ምክንያት በሌላው ሳይኖር በአንድ ለሊት የምርቶች ዋጋ የሚጨምርበት አጋጣሚ እንዳለ ይናገራሉ። ""አንዳንድ ጊዜ በአገራችን በአንድ ለሊት 'ከገበያ ጠፍቷል' ሲሉ ይሰማል። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ትናንት የነበረ ዕቃ በአንድ ለሊት ጠፍቶ አደራ ሲባል ምርቱን ደበቀው ዋጋውን ከፍ አድርገው መሸጥ የሚፈልጉ ሰዎች መኖራቸውን ያሳያል"" ይላሉ። ይህን የመቆጣጠር ኃላፊነት የመንግሥት መሆኑን የምጣኔ ሃብት መምህሩ ይናገራሉ። አቶ አብዲ ገቢሳ በተመሳሳይ ""መንግሥት ታች ወርዶ ዋጋቸውን እየጨመሩ ያሉ ነገሮችን አይቶ መፍትሄ መስጠት ይችላል"" ይላሉ የብር የውጭ ምንዛሬ የመግዛት አቅም መዳከም የተፈለገውን ያህል ውጤት በምጣኔ ሀብቱ ላይ እንዳላመጣ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በሌላ በኩል በምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች የሚነሳው የአገሪቱ የወጪና የገቢ ንግድን ማመጣጠን አልመቻሉ ነው። የባለፈውን ዓመት ስንመለከት አገሪቱ ከወጪ ንግድ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ስታገኝ በገቢ ንግድ ደግሞ 15 ቢሊዮን ዶላር ወጪ አድርጋለች፤ ይህንንም ከፍተኛ ልዩነት ማመጣጠን አለመቻሉ ከፍተኛ ማነቆ መፍጠሩን ባለሙያዎች የሚያስረዱት ነው። በተጨማሪም ከወጪ ንግዷ በላይ በከፍተኛ ሁኔታ ምርቶች ከውጭ አገር የምታስገባው ኢትዮጵያ የብር ምንዛሬ ማሽቆልቆል ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ማስከተሉና ይህም በዜጎች ላይ እያሳረፈ ያለው ኢኮኖሚያዊ ጫና ከፍተኛ ሆኗል። ከዋጋ ግሸበትም ጋር ተያይዞ መሰረታዊ የሚባሉ ሸቀጦች ዋጋ መናርም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። እነዚህ የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች በዋነኝነት የሚጠቅሱት መፍትሄ አገሪቷ የገቢና ወጪ ንግዷን አመጣጥና የንግድ ሚዛን ጉድለቷን ማስተካከል ነው። ይህንንም ለማድረግ ከግብርና ግብዓቶችና ቁሳቁሶች በመውጣት ወደ ማኑፋክቼሪንግ ዘርፉ መገባት መንግሥት በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራው የሚገባው ጉዳይ ነው ይላሉ። በተጨማሪም መንግሥት የወጪ ንግዱን ለማጠናከር በባለሙያ፣ የፋይናንስ ተቋማቱን እንዲሁም ሌሎች ማሻሻያዎችን በመስራት ችግሩን ሊቀርፍ እንደሚገባም የዘርፉ ባለሙያዎች የ���ሰጡት አስተያየት ነው። ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት በበኩሉ በአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ ጫና የሚፈጥሩ ጉዳዮችን ለመቅረፍ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን እና እርምጃው ቀጣይነት እንደሚኖረው ይገልጻል። ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል ግለቦች እንደ ስንዴ፣ ዘይት፣ የሕጻናት ወተት እና ስኳር ያሉ ምርቶች በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ ወደ አገር እንዲያስገቡ መፍቀድ አንዱ ነው። የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤቱ፤ ""በቀጣይ ጊዜያት በኢኮኖሚያችን ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ጫናዎችን ለመቀነስ የተለያዩ አንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ። የመድኃኒት፣ ነዳጅ፣ ማዳበርያ፣ ዘይት፣ እና ሌሎችም መሠረታዊ ሸቀጦች ግዥን በተገቢው ሁኔታ እንዲካሄድ፣ በእነዚህ ሸቀጦች አቅርቦት ላይ መንዛዛት እንዳይኖር በግዥ ሥርዓቱ ላይ አስፈላጊው ማስተካከያ ይወሰዳል"" ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61418643 +health ኮሮናቫይረስ ፡ ሲሼልስ የኮቪድ -19 ክትባት መስጠት ጀመረች "በርካቶች ለመዝናናት የሚመርጧት አፍሪካዊቷ ደሴታማ አገር፣ ሲሼልስ የኮሮናቫይረስ ክትባት መስጠት መጀመሯን አስታወቀች። ይህንን በማድረግም ከጊኒ ቀጥላ ሁለተኛዋ አፍሪካዊት አገር ሆናለች። ጊኒ የሩሲያውን ስፑትኒክ ቪ ክትባት አነስተኛ ዶዝ ያገኘችው ባለፈው ወር ነበር። የሲሼልስ ፕሬዚደንት ዋቨል ራምካላዋን ዕሁድ እለት የመጀመሪያውን ክትባት በቀጥታ ቴሌቪዥን ሥርጭት እየታዩ ተከትበዋል። ፕሬዚደንቱ ""የተሰማኝ ልክ እንደማንኛውም ክትባት ነው"" በማለት ሌሎች ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ አበረታተዋል። ደሴታማዋ አገር ሲሼልስ ቻይና ያበለፀገችውን ክትባት ከተባበሩት አርብ ኤምሬትስ 50 ሺህ ዶዝ [መጠን] በእርዳታ አግኝታለች። ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ዛሬ የጤና ባለሙያዎች መከተብ እንደሚጀምሩ እና ከዚያ በኋላ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ክትባቱን እንደሚወስዱ ተናግረዋል። ይህ ሲጠናቀቅም ክትባቱ ለሌሎች ሕዝቦቿ ይዳረሳል ተብሏል። አገሪቷ ከሁለት ወር እስከ ሦስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ካሏት 98 ሺህ ሕዝብ 70 በመቶውን ለመከተብ አቅዳለች። ይህንን ለማሳካትም በአንድ ቀን 1 ሺህ ሰዎችን መከተብ ይጠይቃል። ሲሼልስ እስካሁን 508 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመዘገበች ሲሆን ያስተናገደችው አንድ ሞት ብቻ ነው። ይሁን እንጂ ባለሥልጣናት በቅርቡ የታየው የቫይረሱ ሥርጭት አስግቷቸዋል። ቅዳሜ ዕለት ብቻ በአገሪቷ 57 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55614499 +politics በሚየንማር ተቃዋሚዎች ላይ እንደተተኮሰ ተመድ ገለጸ "የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑክ የሚየንማር የጸጥታ ኃይሎች ተቃዋሚዎች ላይ እንደተኮሱ ገለጹ። ይህም ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነው። በጄኔቫ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ልዑኩ ቶማስ አንድሪውስ የመፈንቅለ መንግሥቱን ጠንሳሾች ወቅሰዋል። በአገሪቱ ያልተገቡ ድርጊቶች እየተፈጸሙ እንደሚገኙ የፎቶ ማስረጃ እንዳለም ጠቅሰዋል። ልዑኩ ሚየንማር ላይ የመሣሪያ ማዕቀብ እንዲጣልም ጠይቀዋል። የወታደራዊ ኃይሉ ኃላፊ ተቃውሞ እንዲቆም ቢጠይቁም ለተከታታይ ቀናት ሰልፉ እንደቀጠለ ነው። በሚየንማር የአንድነት ቀን ሲከበር ኃላፊው ጀነራል ሚን አውግ ህላግ ""አገራዊ አንድነት ያስፈልገናል"" ቢሉም ሕዝቡ አን ሳን ሱ ቺን ጨምሮ ሌሎችም አመራሮች ከቁም እስር እንዲለቀቁ እየጠየቀ ነው። በሚየንማር የአንድነት ቀን ሲከበር ወታደራዊ ኃይሉ 55 የውጪ ዜጎችን ጨምሮ 23,000 ታራሚዎችን ከእስር ለቋል። የአንድነት ቀን የሚከበረው እአአ በ1947 በአን ሳን ሱ ቺ አባት አማካይነት የተፈረመውን ስምምነት በማስታወስ ነው። ስዛኣር ሳን የተባለ ተማሪና የመብት ተሟጋች ለ��ቢሲ እንደተናገረው ታራሚዎች የተፈቱት ተቃዋሚዎች ላይ ጥቃት ሊያደርሱ ነው ብሎ ይሰጋል። የተመድ ልዑክ እንዳሉት የድርጅቱ የሰብዓዊ መብት መርማሪዎች ሚየንማር ለመግባት ፍቃድ አላገኙም። ሆኖም ግን ተቃዋሚዎች ላይ ጥይት እንደተተኮሰ ማስረጃ ተገኝቷል። ተመድ የቃል መግለጫ ከማውጣት በዘለለ የመሣሪያ ሽያጭ ላይ ማዕቀብ እንዲጥልና ወታደራዊ ኃላፊዎች የጉዞ ክልከላ እንዲወጣባቸውም ጠይቀዋል። የሳምንቱ መባቻ ላይ ሚያ ትዌ ተዌ ካሂግ የተባለች የ19 ዓመት ወጣት በጥይት ጭንቅላቷን መመታቷ አይዘነጋም። ለሕይወቷ አስጊ ሁኔታ ውስጥም ትገኛለች። ፓሊሶች ተቃዋሚዎችን ለመበተን ውሃ፣ የፕላስቲክ ጥይትና መሣሪያ ተጠቅመዋል። አንድ የቀይ መስቀል ኃላፊ ለሮይተርስ እንደገለጹት ሦስት ሰዎች በፕላስቲክ ጥይት ጉዳት ደርሶባቸዋል። አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች ሚየንማር ውስጥ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ መሪዎች እንዲለቀቁ እየጠየቁ ነው። ወታደራዊ ኃይሉ የብሔራዊ ምርጫ ውጤት ተጭበርብሯል ብሎ መፈንቅለ መንግሥት ካካሄደ 12 ቀናት ተቆጥረዋል። ወታደራዊ ኃይሉ ተቃዋሚዎችን የሚደግፍ ሲሆን፤ አዲስ ፓርላማ መመሥረት ጀምሯል። አን ሳን ሱ ቺ እና ሌሎች መሪዎች በቁም እስር ላይ ሲሆኑ፤ በሕግ ወጥ መንገድ አገር ውስጥ የገባ የራድዮ መገናኛ (ዋኪ-ቶኪ) በመያዝ ክስ ተመሥርቶባቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56041930 +sports ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ ከዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነ ሴኔጋላዊው አጥቂ ሳዲዮ ማኔ ለክለቡ ባየር ሙኒክ ሲጫወት በደረሰበት ጉዳት ምንክያት የጉልበት ቀዶ ህክምና በማከናወኑ ከዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነ። ማክሰኞ ዕለት የሴኔጋል እግር ኳስ ፌደሬሽን ማኔ ከዓለም ዋንጫው “መጀመሪያ ጨዋታችን” ውጭ ይሆናል ብሎ ነበር። ሐሙስ በተደረገለት ተጨማሪ ምርመራም ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈለገው ተረጋግጧል። ባየር ሙኒክ ወርደር ብሬመንን ባሸነፈበት ጨዋታ ነበር ሴኔጋላዊው ጉዳት ደርሶበት ከሜዳ የወጣው። ባየር ሙኒክ ተጫዋቹ ስኬታማ ቀዶ ጥገና ማከናወኑን አስታውቋል። “ተጫዋቹ በጥቂት ቀናት ማገገም ይጀምራል” ብሏል ክለቡ። ሴኔጋል በዓለም ዋንጫው የመጀመሪያ ጨዋታዋን ሰኞ ዕለት ከኔዘላንናድስ ጋር ትጀምራለች። በቀጣይም ከአስተናጋጇ ኳታር ቀጥሎ ደግሞ ኤኳዶር ጋር ትገናኛለች። ለሁለት ጊዜ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ለመሆን የበቃው ማኔ የብሔራዊ ቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች ነው። ባለፈው የካቲት ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያውን የአፍሪካ ዋንጫ እንዲያነሳ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በፍጻሜው ጨዋታ ግብጽን ሲያሸንፉ ወሳኟን የመለያ ምት አስቆጥሮ ነበር። ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ በድጋሚ ከግብጽ ጋር ሲገናኙም ማኔ ለቡድኑ ባለውለታ መሆኑን አረጋግጧል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c28371j103wo +health "ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ ""የከፋ ፈተና"" ሊገጥማት እንደሚችል ከፍተኛ የጤና ባለሙያ አስጠነቀቁ" "በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ እና ታምመው ወደ ሆስፒታል የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ አገሪቱ ""የከፋ ፈተና"" ሊገጥማት እንደሚችል አንድ ከፍተኛ ሳይንቲስት አስጠነቀቁ። ሰኞ ዕለት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተለያዩ ግዛት ፖለቲከኞችን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግን መልሰው እንደ ግዴታ እንዲያስቀምጡ ጥሪ አቅርበው ነበር። በሚያዚያ ወር አጋማሽ ላይም 90 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን አዋቂዎችም የወረርሽኙን መከላከያ እንደሚከተቡም ቃል ገብተዋል። አሜሪካ ባለፈው ሳምንት ብቻ 60,000 ያህል ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን በምርመራ አረጋግጣለች። የአሜሪካ ሕብረተሰብ ጤና ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼሌ ዋሌኒስኪ በዋይት ሐውስ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ""የከፋ ችግር ሊገጥመ��� እንደሚችል እየተሰማኝ ስላለው ስሜት አስተያየት መስጠት እፈልጋለሁ"" ያሉ ሲሆን አክለውም ""ተስፋ ለማድረግ በርካታ ምክንያቶች አሉን ነገር ግን አሁን በጣም ፈርቻለሁ"" ብለዋል። ባለፉት ሳምንታት በቫይረሱ የተያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር በቀን 60 ሺህ ደርሷል። ዶ/ር ዋሌንስኪ አሜሪካ ዳግም ሌላ የኮቪድ-19 ስርጭት እንድታስመዘግብ አልያም በበርካታ አውሮፓ አገራት እንደሆነው ከፍተኛ ሞትን እንድታይ እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። በሚቺጋን እና ኒውዮርክ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል። በቴሌቪዥን ቀርበው ንግግር ያደረጉት ባይደን የግዛት አስተዳዳሪዎች ነዋሪዎቻቸው የአፍ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉ በድጋሚ እንዲያስገድዱ ጠይቀዋል። በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ መከላከያ መመሪያዎች ከግዘት ግዛት ይለያያል። ባይደን ""አሁን መመሪያዎቻችንን ካላላን ቫይረሱ ከመቀነስ ይልቅ ወደ ከፋ ደረጃ ሲሸጋገር እናየዋለን"" ብለዋል። ባይደን አሜሪካ ክትባቱን በማዳረስ ረገድ ያሳያችውን ውጤት በመጥቀስ ከእቅዷ ቀድማለች ብለዋል። በሚያዚያ ወር ክትባት ለመውሰድ ከሚችሉ አዋቂዎች መካከል 90 በመቶዎቹ ከቤታቸው በቅርብ ርቀት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ባይደን አክለውም በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ ሁሉም አዋቂ አሜሪካውያን አንዱን ክትባት ለመውሰድ ይመዘገባሉ ሲሉ እቅዳቸውን ይፋ አድርገዋል። የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣተሪያ ማዕከል እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ከሆነው መካከል ከአምስት አዋቂ አሜሪካውያን መካከል አንዱ ሙሉ ሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ተከትበዋል ሲል አስታውቋል። ክትባቱን ለማግኘት የሚችለው ማን ነው? የሚለው ከግዛት ግዛት ይለያያል። ነገር ግን በሁሉም ግዛቶች በቅድሚያ የጤና ባለሙያዎች፣ ከዚያ በመቀጠል አድሜያቸው ከ65 በላይ ከሆኑት ግለሰቦች ክትባቱን ያገኛሉ። በጆርጂያ እና አሪዞና ደግሞ እድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆነ ክትባቱን ማግኘት ይችላሉ። ባይደን አሜሪካውያን አካላዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56563215 +sports እግር ኳስ፡ 'ከዘረኝነት መልዕክት' እስካልተጠበቁ ውጤቶች ያስመዘገበው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ትናንት ምሽት ፒኤስጂ እና ኢስታንቡል ባሻክሺር በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሊያደርጉት የነበረው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ በዕለቱ አራተኛ ዳኛ የዘረኝነት መልዕክት ተላልፏል በሚል ተጫዋቾች ሜዳውን ለቅቀው በመውጣታቸው ጨዋታው በድጋሚ ዛሬ ሊካሄድ እንደሆነ ተገልጿል። ኢስታንቡል ባሻክሺር እግር ኳስ ክለብ እንዳስታወቀው አራተኛ ዳኛው ሴባስቺያን ኮልትስኩ ስለምክትል አሰልጣኙ ፒዬር ዌብ ሲናገሩ ዘረኛ የሆነ መልዕክት አስተላልፈዋል ብሏል። የቀድሞ የካሜሩን ተጫዋቹ ዌቦ ከሜዳ ውጪ የቀይ ካርድ ሰለባ ሆኖም ነበር። ይህንን ተከትሎ የኢስታንቡል ባሻክሺር ተጫዋቾች ሜዳውን ለቅቀው የወጡ ሲሆን የፒኤስጂ ተጫዋቾችም ተከትለዋቸው ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል። ክስተቱ የተፈጠረው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታው ተጀምሮ 14 ደቂቃዎች ያክል ከተጫወቱ በኋላ ሲሆን ተጫዋቾቹ ሜዳውን ለቅቀው እስከሚወጡ ድረስ ደግሞ ምንም አይነት ግብ አልተቆጠረም ነበር። ጨዋታው ዛሬ ምሽት በድጋሚ እንደሚካሄድ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ያስታወቀ ሲሆን ትናንት ምሽት ማንቸስተር ዩናይትድ በአርቢ ላይፕሲዥ መሸነፉን ተከትሎ ደግሞ ፒኤስጂዎች ከጨዋታው በፊት ወደ ጥሎ ማለፍ ድልድል ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ባወጣው መግለጫ '' ከሁለቱም ቡድኖች ጋር ከተነጋገርን በኋላ ጨዋታው በድጋሚ ከቆ��በት እንዲጀምርና ሌሎች ዳኛዎች ጨዋታውን እንዲመሩት ወስነናል'' ብሏል። አክሎም ''በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እጅግ ፈጣንና ጥልቅ ምርመራ ይካሄዳል፤ የተጣሰ ህግ ካለም ተገቢው እርምጃ ይወሰዳል'' ሲል አስታውቋል። ተቀያሪ ወንበር ላይ የነበረው የኢስታንቡል ባሻክሺር አጥቂው ዴምባ ባ ከአራተኛው ዳኛ ጋር ''ለምን ያኛው ጥቁር ሰው'' ብለህ መጥቀስ አስፈለገህ እያለ ሲከራከር ተስተውሏል። በሌላ ምስል ደግሞ የፒኤስጂው ተከላካይ ''ይህ ሰው የምሩን ነው? በቃ እንሂድ'' ሲል ታይቷል። ምንም እንኳን የፒኤስጂ ተጫዋቾች ለረጅም ሰአት መልበሻ ክፍሉ አካባቢ ሰውነታቸውን እያሟሟቁ ቢጠብቁም የኢስታንቡል ባሻክሺር ተጫዋቾች ባለመመለሳቸው ምክንያት ጨዋታው ለመቋረጥ ግድ ሆኗል። የፒኤስጂው አጥቂ ኪሊያን ምባፔም በበኩሉ በትዊተር ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት ''ዘረኝነት ይብቃ። ዌብ አብረንህ ነን'' ሲል ጽፏል። በሌሎች ጨዋታዎች በጉጉት ሲጠበቅ የማንቸስተር ዩናይትድና አር ቢ ላይፕሲዥ ጨዋታ በአርቢ ላእፕሲዥ 3 ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል። ምንም እንኳን ማንቸስተር ዩናይትዶት ከምድቡ ለማለፍ አቻ ብቻ የሚቃቸው የነበረ ቢሆንም በመጀመሪያዎች 20 ደቂቃዎች አርቢ ላይፕሲዦችን መቋቋም አቅቷቸው ተስተውሏል። ጨዋታው በተጀመረ 13 ደቂቃዎች ውስጥም ሁለት ግቦችን አስተናግደው የመጀመሪያው አጋማሽ 2 ለባዶ የተጠናቀቀ ቢሆንም በሁለተኛው አጋማሽ ሌላ ሶስተኛ ግብ አስተናግደዋል። በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ ማንቸስተር ዩናይትዶች ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ቢችሉም አቻ ማድረግ ግን ሳይችሉ ቀርተዋል። በዚህም ከምድቡ አለማለፋቸውን አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል በሌላኛው የተጠበቀ ጨዋታ ጁቬንቱስ ባርሴሎናን 3 ለባዶ ማሸነፍ ችሏል። ሁለቱን ግቦች ክርስቲያኖ ሮናልድ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረ ሲሆን ሶስተኛዋ ግብ ደግሞ ማክኬኒ በጨዋታ ማስቆጠር ችሏል። ይህን ውጤት ተከትሎ ሁለቱም ቡድኖች ከምድባቸው አንደኛና ሁለተኛ ሆነው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ዛሬም የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ቀጥለው የሚካሄዱ ሲሆን አትሌቲኮ ማድሪድ ከሬድ ቡል ሳልዝበርግ እንዲሁም ሪያል ማድሪድ ከቦርሺያ ሞንቼግላድባክ የሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል። እስካሁን በተደረጉ ጨዋታዎች የጁቬንቱሱ አልቫሮ ሞራታ፣ የቦርሺያ ዶርትሞንዱ ኢርሊንግ ሃላንድ እና የማንቸስተር ዩናይትዱ ማርከስ ራሽፎርድ በ6 ግቦች ኮኮብ ጎል አግቢነቱን እየመሩት ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-55242915 +sports የወደፊቱ የአርሰናል አምበል ይሆናል የተባለለት ቡካዮ ሳካ ለምን የተለየ ሆነ? "ቡካዮ ሳካ በተማረበት ግሪንፊልድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእሱ ሥራዎች የኩራት ምንጭ ናቸው። በትምህርት ቤቱ የእንግዳ መቀበያ አካባቢ በሚገኘው ግድግዳ ላይ ቡካዮ ሳካ የፈረመበት አርሰናል እግር ኳስ ክለብ መለያ ተሰቅሏል። ከስሩ ደግሞ የ19 ዓመቱ እግር ኳሰኛ ""አመሰግናለሁ"" የሚል ጽሁፍ አስፍሯል። በትምህርት ቤቱ የሚገኙ ተማሪዎችም ሆነ አስተማሪዎች ስለ ቡካዮ ሳካ ሲያወሩ በኩራት ሲሆን አሁንም ድረስ የወሬ ርዕስ ሆኖ እንደቀጠለ ነው። ""ሳካ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ሲመረጥ ሁሉም ሰው በጣም ተገርሞ ነበር'' ይላል የሳካ የቀድሞ የሰውነት ማጎልመሻ መምህርና ምክትል አሰልጣኝ ማርክ ሃርቪ። ""በእድሜ ከፍ የሚሉት ተማሪዎች የእሱን ህይወት በሚገባ ይከታተላሉ። ሁሌም ቢሆን እሱ የሆነ ነገር ሲያደርግ፣ ግብ ሲያስቆጥር አልያም ለጎል አመቻችቶ ሲያቀብል በትምህርት ቤቱ የዋትስአፕ ቡድን ላይ ሁሉም ሰው የሚያጋረው እሱን ነው። እንደውም ትንንሾቹ ተማሪዎች እሱ በትምህርት ቤታችን ይማር እንደነበር አያምኑም"" የሚለው ደግሞ የሳካ የቀድሞ አሰልጣኝ የነበረው ዲፔሽ ፓቴል ነው። አርሰናል ሳካን ፍለጋ ወደ ትምህርት ቤቱ የመጣው የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ከመውሰዱ በፊት ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2018 ላይ ትምህርት ቤቱን ሲለቅ በፈተናው አራት ትምህርቶች ላይ ኤ አምጥቷል። ገና በልጅነቱም በእግር ኳን ትምህርት ቤቱን ወክሎ በክልላዊና አገራዊ ውድድሮች ላይ ተሳትፏል። በእሱ ምክንያትም ቡድኑ በርካታ ስኬቶችን አግኝቷል። ""በዚህ ትምህርት ቤት ለበርካታ ዓመታት ቆይቻለሁ፤ ነገር ግን ገና ከመጀመሪያው ነበር ሳካ የተለየ ችሎታ እንዳለው ያስተዋልኩት"" ይላል ዲፔሽ ፓቴል። አክሎም ""ሜዳ ላይ የሚያደርገው እንቅስቃሴ፣ ጨዋታውን የሚመለከትበት መንገድ፣ እንዲሁም የሚወስናቸው ውሳኔዎች በጣም የተለዩ ነበሩ። በጣም የሚያስገርም የቡድን ተጫዋች ነበር።'' ""በትምህርት ቤታችን ቆይታው ሰባተኛው ዓመት ላይ በአንድ ውድድር ላይ ለዋንጫ አልፈን 4 ለ 3 የተሸነፍንተበትን ጨዋታ አስታውሳለሁ። በጨዋታው በርካታ የጎል እድሎችን አግኝቶ አልተጠቀመባቸውም ነበር። ከሜዳ ሲወጣ አስታውሳለው በጣም ተበሳጭቶ ነበር። ለመሸነፋችን ምክንያት እሱ እንደሆነ ነበር ያሰበው። 'ከዚህ በኋላ እግር ኳስ ደግሜ አልጫወትም' አለኝ።"" ""ወደ መጨረሻው ጨዋታ ያለፈነው በቀላሉ ነበር። በአብዛኛዎቹ ጨዋታዎች አስገራሚ ብቃቱን ሲያሳይ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ለሌሎቹ ተጫዋቾች እድል ለመስጠት ስል የጨዋታው ግማሽ ላይ አቀይረው ነበር። ስምንተኛው ዓመት ላይ ግን ሁሉንም ውድድር ማሸነፍ ችለናል። በርካታ ዋንጫዎችን አንስተን ነበር። ሁሌም ቢሆን ስለቡድኑ ነበር የሚያስበው።"" የክንፍ መስመር አጥቂው ሳካ ከሰባት ዓመቱ ጀምሮ ከመድፈኞቹ ጋር የነበረ ሲሆን ለዋናው ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ የተጫወተው በአውሮፓውያኑ 2018 ላይ በአውሮፓ ሊግ ውድድር ነበር። በመቀጠል ደግሞ ጥር ወር ላይ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ለመጀመሪያ ጊዜ መጫወት ችሏል። ነገር ግን ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ከአርሰናል ጋር የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል። በኤምሬትስ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራትም ፈርሟል። ከሁለት ወራት በኋላ ደግሞ ከ16 ዓመት በታች ሲጫወት ከነበረበት ተነስቶ በዋናው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫወተ። በጨዋታው እንግሊዝ ዌልስን አሸንፋለች። ምንም እንኳን ሳካ በአርሰናል ቤት የቋሚነት ቦታውን ለመረከብ እና በብሔራዊ ቡድኑ ሰአልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት ቡድን ውስጥ ሰብሮ ለመግባት ብዙ ኢዜ ባይፈጅበትም የመጣበትን ግን አልረሳም። ""ለብዙ ዓመታት የትምህርት ቤቱ ኃላፊ ከነበሩት ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት አለው። የቼልሲ ደጋፊ ከሆኑት የክፍል ኃላፊውም ጋር ቢሆን በጣም የጠበቀ ወዳጅነት አላቸው'' ይላል ሃርቪ። ""በጣም ቅርብ የሆኑ ጥቂት ጓደኞች ነበሩት። ምናልባት ከአምስት እስከ ስምነት የሚሆኑ ልጆች ነበሩ። ሁሉም በጣም ጥሩ ተማሪዎች ነበሩ። ስፖርቱ ላይ ብቻ ሳይሆን ትምህርት ላይም ቢሆን ጎበዞች ነበሩ።"" የሳካ የቀድሞ ክፍል ኃላፊ ከሁለት ዓመታት በፊት በጡረታ ሲገለሉ የሽኝት ዝግጅቱ ላይ ያለውን ክብር በአካል ተገኝቶ አሳይቷል። ""በሽኝት ዝግጅቱ ላይ ከአባቱ ጋር በመገኘት ለሰዓታት ያክል ቆይቶ ነው ተመለሰው። ከቀድሞ ጓደኞቹንና ከአስተማሪዎቹ ጋር ሲጫወትም ነበር"" ይላል ሃርቪ። ""ሁሉም ሰው ያውቀዋል። ከእንግዳ ተቀባዮቹ እስከ ጥበቃ ድረስ ሁሉም ጋር ጥሩ ግንኙነት አለው።"" ቡካዮ ሳካ ከልጅነቱ ጀምሮ ያልተለየው ነገር ቢኖር ለስኬት ያለው ከፍተኛ ፍላጎት ነው። በአርሰናልና በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ተቀናቃኞቹን የሚሸውድበትና የማይገመቱ ውሳኔዎቹ ሁሌም ልዩ ያደርጉታል። ""በጣም ዝም���ኛ ልጅ ነበር። ሁሉንም ሰው የሚያከብርና በጣም ጥሩ አድማጭ ነው። ሰዎችን ለማስደሰት የሚጥርና በሁሉም ነገር ምርጥ መሆን የሚፈልግ አይነት ሰው ነው"" ይላል ከ18 ዓመት በታች የቀድሞ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኙ ኒል ዴውስኒፕ። ""4-4-3 አሰላለፍ ተጠቅመን ስንጫወት ሁሌም በግራ ተከላካይ መስመር በኩል እንዲጫወት እንዳርገዋለን። ከሜሰን ግሪንዉድ ጋር ተመሳሳይ ቦታ ነው። ሳካ እንደ አንደ መስመር አጥቂም መጫወት ይችላል። በተጨማሪም በቀኝ በኩልም ይጫወታል። በጣም አስገራሚ ተጫዋች ነው።'' ""ከኳሷ ጋርም ሆነ ያለኳስ ሩጫው በጣም ያምራል። ተጫዋቾችንም በቀላሉ ማለፍ ይችላል። ከተከላካዮች ጋር ለአንድ ሲገናኝም ኳሷን ሚገፋበት መንገድ ይለያል፤ ግብ ማስቆጠርም አይከብደውም።'' ""በሁለቱም እግሮቹ መጫወት ይችላል። አጨዋወቱ ማጥቃት ላይ የተመሰረተ ነው'' ይላል የአርሰናል የቀድሞ ተጫዋች መልማይ የነበረው ማርቲን ታይለር። ""ተጫዋቾችን በቀላሉ የማለፍ፣ ግብ የማስቆጠርና ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ላይ በጣም ጥሩ የሆነ ችሎታ አለው። የሚያስገርመው ደግሞ እነዚህን ነገሮች የሚያደርገው ብዙም ሳይጨነቅ ነው። እንደ ቀልድ ነው የሚያደርጋቸው'' ""ገና የ7 እና የ8 ዓመት ህጻን እያለ እንኳን የእግር ኳስ ችሎታውን አለማስተዋል አይቻልም። ይህን አይነት ችሎታ በትምህርት የሚገኝ አይደለም'' ይላል ሀርቪ። ''አንድ ቀን የአርሰናል አምበል ይሆናል'' የሥነልቦና ጥንካሬ እና አካላዊ ብቃት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሁሉ ተጫዋቾች የሚጠበቅ ነገር እየሆነ የመጣ ሲሆን እነዚህን ነገሮች ካሟሉ እድገታቸው ፈጣን እንደሚሆን ማርቲን ያምናል። ""ትምህርት ዋናውና ወሳኙ ነገር ነው። በተለይ ደግሞ ታዳጊ ተጫዋቾች። እነዚህ ወጣት ተጫዋቾች በርካታ የማኅበራዊ ኃላፊነት የሚጠይቁ ዝግጅቶች ላይ ይሳተፋሉ። ቡካዩ ሳካ እና ጓደኞቹ በእነዚህ ቦታዎች ላይ ንግግር ሲያደርጉ በከፍተኛ ብስለትና ማስተዋል ነው።'' ""ከቤተሰቦቹ እና ከአርሰናል ጋር በመሆን እድገቱን ስንከታተል ነበር። ወደ ትምህርት ቤቱ ሄጄም የቀድሞ መዝገቡን ተመልክቻለሁ። በጣም የሚያስገርም ታዳጊ ነው።'' ""ሁሌም ቢሆን ሰው አክባሪ ነው። እንደ ሳካ አይነት የእግር ኳስ ብቃት ኖሮህ የቡድን አጋሮችህ እና ተቀናቃኞችህ ተመጣጣኝ ያልሆነ ብቃት ሲኖራቸው አንዳንዴም ቢሆን ከእነሱ ጋር መመሳሰል ያስፈልጋል፤ በተለይ ታዳጊ እያሉ። ይህ ወጣት ሁሉም አይነት በጎ ምግባር የሚታይበት ነው። ወደፊት የአርሰናል አምበል እንደሚሆን አስባለሁ።'' ታይለር እንደሚለው የሳካ ጠንካራ ሥነልቦናው ነው ለዚህ ሁሉ ስኬት ያበቃው። ""እንደ ኦባምያንግ እና ላካዜት ካሉ ኮከብ ተጫዋቾች ጋር ነው የሚጫወተው። በእድሜም በልምድም ከሚበልጡት ተጫዋቾች ጋር ነው የሚጫወተው፤ በዚህ ታዳጊ እድሜው።"" ""ሁሌም የመጀመሪያ ሀሳቡ ወደፊት መሄድ ነው። በርካታ ተጫዋቾች ይህ ችሎታ የላቸውም። እንደ ቡካዮ ሳካ አይነት በራስ መተማመን ያለው ተጨዋች ማንም ሊያስቆመው አይችልም። በእግሩ ብቻ ሳይሆን በጭንቅላቱም ነው የሚጫወተው። እንዲህ አይነት ችሎታ አብሮህ ይወለዳል እንጂ በልምድ ወይም በትምህርት አይመጣም። ምናልባት በትምህርትና በልምድ ችሎታው ሊዳብር ይችል ይሆናል እንጂ ውስጡ ያለው ብቃት ግን አብሮት የተወለደ ነው።'' በያዝነው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዓመት በጣም ምርጥ በነበረው ጨዋታው ላይ ሳውዝሃምፕተንን 3 ለ 1 ሲያሸንፉ አንድ ግብ አስቆጥሮ ሌላ ደግሞ አመቻችቶ ሰጥቷል። ""አሁንም ቢሆን ገና የእግር ኳስ ሕይወቱ ጅማሮ ላይ ነው ያለው። ምንም እንኳን በክለብም ሆነ በበብሔራዊ ቡድን አስገራሚ ጉዞ እያደረገ ቢሆንም ���ዙ የሚቀሩት ነገሮች አሉ። በጣም ወጣት ታዳጊ ነው'' ይላል ዴውስኒፕ። ""በብሔራዊ ቡድን ደረጃ የሚጫወት ተጫዋች ማሰልጠን ለክለብ አሰልጣኞች የማይገኝ እድል ነው። የመጫወት ፍላጎት፣ ብቃት፣ ድፍረትና ተስፋ ያለው ተጫዋች ነው።''" https://www.bbc.com/amharic/news-56755322 +health ኮሮናቫይረስ፡ክትባት ለመከተብ አጭበርብረዋል የተባሉ ኃላፊ ከስራቸው ለቀቁ "ከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የካዚኖ ቁማር ኩባንያ የሚመሩት ዋና ስራ አስፈፃሚ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት አጭብርብረዋል መባሉን ተከትሎ ከስራቸው ለቀቁ። ኃላፈውና ባለቤታቸው ባለስልጣናቱን አታለዋል በሚል ተከሰዋል። ግሬት ካናዲያን ጌሚንግ የተባለ የካዚኖ ቁማር ድርጅት የሚመሩት ሮድ ቤከርና ባለቤታቸው ኢካትሪና ገጠራማ ወደሆነው ዩኮን ግዛት ክትባት ለመከተብ አቅንተው ነበር። ግዛቱ የቀደምት ካናዳውያን መኖሪያ ሲሆን ከሌሎች የካናዳ ክፍሎች በበለጠ ፈጣን የሆነ የክትባት አሰጣጥ ስርአት እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ። ባለትዳሮቹ ወደ ቦታው ሲያመሩም የሆቴል ሰራተኞች ነን በሚል ሽፋን ነው። በባለፈው ሳምንት በግዛቲቱ ውስጥ በምትገኝ ቢቨር ክሪክ በምትባል መንደር ውስጥ ተከትበው ከጨረሱ በኋላ ወደ አየር ማረፊያ ውሰዱን ማለታቸውን ተከትሎ ነው የተጋለጡት። "" በዚህ ራስ ወዳድ በሆነ ባህርያቸው በጣም ተበሳጭቻለሁ"" በማለት የዩኮን ማህበረሰብ አገልግሎት ሚኒስትር ጆን ስትሬይከር ተናግረዋል። ""በዚህ መንገድ ሰው አጭበርብሮ እንዲህ አይነት ተግባር ይፈፅማል የሚል ነገር በጭራሽ አላሰብንም"" ብለዋል አክለውም። ከዚሁ ጋር ተያያይዞ የዋይት ሪቨር ፈርስት ኔሽን፣ የአካባቢው የቀደምት ህዝቦች ኃላፊ አንጄላ ዴሚት በበኩላቸው ""የእድሜ ባለፀጎቻችንና ተጋላጭ ማህበረሰቦቻችንን ስጋት ውስጥ የሚከቱ የአንዳንድ ግለሰቦች ድርጊት በጣም አሳስቦናል። ተራን ባለመጠበቅ እንዲህ አይነት አስነዋሪ ስራ መፈፀም ራስ ወዳድነት ነው"" ብለዋል። ሮድ ቤከርና ባለቤታቸው ከቫንኮቨር ግዛት ወደ ዩኮን በሄዱበት ወቅት አስገዳጅ የሆነውን የ14 ቀናት ለይቶ ማቆያ ባለማክበር ተቀጥተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55807191 +politics የእስራኤል ተቃዋሚዎች አዲስ የአንድነት መንግሥት ለማቋቋም ተስማሙ "የእስራኤል ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቤንጃሚን ኔታንያሁን የ 12 ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚያከትም አዲስ መንግሥት ለማቋቋም ከስምምነት ደረሱ፡፡ የየሽ አቲድ ፓርቲ መሪው ያይር ላፒድ በስምንት ቡድኖች የተቋቋመ ጥምረት መመስረቱን አስታውቀዋል፡፡ ሥልጣን በዙር በሚከፋልበት በዚሁ ስምምነት መሠረት የያሚና ፓርቲው አለቃ ናፍታሊ ቤኔት በቀዳሚነት ጠቅላይ ሚንስትር ይሆናሉ። በቀጣይ ላፒድ ሥልጣኑን ይረከቧቸዋል። መንግሥት ለመመስረት ቃለ መሐላ ከመፈጸሙ በፊት የፓርላማዉ ይሁንታ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል፡፡ ላፒድ በሰጡት መግለጫ ስለስምምነቱ ለፕሬዚዳንት ሬውቨን ሪቭሊን ማሳወቃቸውን ገልጸዋል። ""ይህ መንግስት ሁሉንም የእስራኤል ዜጎች፣ የመረጡትንም ሆነ ያልመረጡትን ለማገልገል እንደሚሠራ ቃል እገባለሁ"" ብለዋል፡፡ ""ተቃዋሚዎቻቸውን የሚያከብር ሲሆን ሁሉንም የእስራኤልን የህብረተሰብ ክፍሎች አንድ ለማድረግ እና ለማገናኘት የቻለውን ሁሉ ያደርጋል"" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በእስራኤል የመገናኛ ብዙሃን በተሰራጨ ምስል ላፒድ፣ ቤኔት እና የአረብ ኢስላሚስት ራም ፓርቲ ሊቀመንበር ማንሱር አባስ ስምምነቱን ሲፈርሙ ቢታዩም ብዙዎች የማይቻል መስሏቸው ነበር፡፡ አባስ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ""ውሳኔው ከባድ እና በርካታ ክርክሮች ነበሩት። ስምምነቶቹ ላይ መድረስ ግን አስፈላጊ ነበር፡፡ በዚህ ስምምነት ለአረብ የህ��ረተሰብ ክፍሎችን የሚጠቅም ብዙ ነገሮች አሉት"" ብለዋል ፡፡ ላፒድ ለፕሬዚዳንቱ በላኩት ማስታወሻ እአአ ነሐሴ 27/2023 ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እስከሚሾሙ ድረስ ከቤኔት ጋር በመሆን መንግስትን እመራለሁ ብለዋል፡፡ ሪቭሊን በጉዳዩ ላይ የመተማመኛ ድምጽን በተመለከተ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ፓርላማው በተቻለ ፍጥነት እንዲሰበሰብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ህብረቱ በ 120 መቀመጫዎች ባሉት ክኔሴት (የእስራኤል ፓርላማ) የአብላጫውን ድጋፍ ማግኘት ካልቻለ ሃገሪቱ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለአምስተኛ ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ ትገደዳለች፡፡ ጥምረት የፈጠሩት ፓርቲዎች የእስራኤልን ፖለቲካ ሙሉ ገጽታ ያሳያሉ ተብሏል፡፡ ፓርቲዎቹ ኔታንያሁን ለመተካት ከማቀድ ውጭ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ብዙም የሚያመሳስላቸው ነገር የለም፡፡ ረቡዕ ዕለት ረዥም ሰዓታትን የወሰደው ውይይት በቴሌ አቪቭ አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን ዕፀ ፋርስን ህጋዊ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ጉዳዮች አጀንዳ ሆነው ተነስተዋል። የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ሁሉም ሃሳቦች ተነስተው ከስምምነት አልተደረሰም ያሉ ሲሆን ይህም ጥምረቱ የመተማመኛ ድምጹን ያሸንፋል በሚለው ላይ ጥርጣሬ ጭሯል፡፡ የኔታንያሁ ሊኩድ ፓርቲ ከወራት በፊት በተደረገው ምርጫ ብዙ ወንበር ቢያገኝም ስልጣን የሚያስገኝለትን ጥምረት መመስረት አልቻለም። ኔታንያሁ የታቀደው አዲስ መንግስት ""የክፍለ ዘመኑ ማጭበርበር"" ሲሉ ገልጸው የእስራኤልን መንግሥት እና ህዝቡን አደጋ ላይ የሚጥል ብለውታል፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-57333188 +business ከአሜሪካና ከቻይና ቢሊየነሮች በሀብት ማን ይበልጣል? "የዓለም ሕዝብ መከራውን እየበላ ነው። የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ሚሊዮኖች ሳይሆኑ ቢሊዮኖች ናቸው። ቢሊየነሮች ግን ሀብታቸው ሰማይ እየነካ በተድላ 'እየተሰቃዩ' ነው። በሀብት የሚያዋኙት የዓለም ቢሊየነሮች በቁጥር ከዓለም ሕዝብ ጋር ሲነጻጸሩ ጥቂቶች ናቸው። በጣም ጥቂቶች። ኧረ በጣም በጣም ጥቂቶች። ተዝቆ የማያልቅ አዱኛን ካካበቱት መካከል የአማዞን ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ይገኝበታል። ኮሮናቫይረስ ከተከሰተ ወዲህ የቢሊየነሮች ሀብት በአማካይ በ27.5 ከመቶ ተመንድጓል። ወይም ደግሞ የ10.2 ትሪሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል፤ ይህም ከመጋቢት ወር ወዲህ ብቻ መሆኑ ነው። መረጃውን ያወጣው የስዊዘርላንዱ ዩቢኤስ ባንክ ነው። የቢሊየኖች ብዛት ከኮሮናቫይረስ በፊት ቀድሞም ቢሆን ከዓመት ዓመት ጭማሪ እያሳየ ነው የመጣው። በ2017 ዓ.ም በዓለም ያሉ ቢሊየነሮች በድምሩ ቁጥራቸው 2 ሺህ 158 ነበር። አሁን ስንት ደረሱ? በድምሩ 2 ሺህ 189 ደርሰዋል። በሦስት ዓመት ውስጥ የቢሊየነሮቹ ቁጥር በ31 ከፍ ብሏል። በጣም ብዙ ነው። ባንኩ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ በዚህ ዓመት የሃብት በረከት ከዘነበላቸው ቢሊየነሮች ዋንኞቹ ኢንደስትሪያሊስቶች ናቸው። በሦስት ወር ብቻ ሀብታቸው በ44 ከመቶ አድጓል። ቀጥለው የሚገኙት የቴክኖሎጂ ቢሊየነሮች ናቸው። የተሰማሩበት መስክ የኮቪድ-19 ክስተትን ለመጠቀም የተስማማ በመሆኑ ሀብታቸው 41 ከመቶ ጨምሯል። ይህ ዘርፍ የሚያቀርበው የአብዛኛው አገልግሎት ፍላጎት ኮቪድ-19 አመጣሽ ነው። ሰዎች በአካል መገናኘት አደጋ እንደሆነ ሲረዱ ወደ በይነ መረብ ዞረዋል። ይህም ለቴክኖሎጂ ቢሊየነሮች ተጨማሪ ቢሊየኖችን ይዞላቸው መጥቷል። ከጤና ጋር በተያያዙ ምርቶች ላይ የተመሰረቱት ቢሊየነሮችም ኮቪድ-19ን ወደውታል። የሕክምና ቁሳቁስ እንዲሁም የመድኃኒት አምራች ቢሊየነሮች ንግድ ጦፎልናል ብለዋል። ቁጥር አንድ የፕላኔቷ ቢሊየነር የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ እና የቴስላ ኩባንያ መሥራች ኤሎን መስክ የኩባንያዎቻቸው የአክሲዮን ዋጋ ሰማይ በመንካቱ ሀብታቸ�� ላይ በላይ እየተከመረ ነው ብሏል ባንኩ። የቻይና ቢሊየነሮች ባለፉት 11 ዓመታት የቻይና ቢሊየነሮች ቁጥር እያሻቀበ ነው። ሀብታቸው የሚጨምርበት ፍጥነትም አስደንጋጭ ነው። በድምሩ የቻይና ቢሊየነሮች ሀብት በ1 ሺ 146 በመቶ ጨምሯል። ይህም በፈረንጆች ከ2009 ጀምሮ ሲታይ ነው፤ እንደ ባንኩ መረጃ። ለምሳሌ የታላቋ ብሪታኒያ ቢሊየነሮችን ከቻይና ቢሊየነሮች ጋር ብናነጻጽር የእንግሊዞቹ ቢሊየነሮች ሀብታቸው የጨመረው 168 በመቶ ብቻ ነው። ያም ሆኖ በቢሊየነሮች ክምችት አሜሪካንን የሚያህል የለም። ቻይናና አሜሪካንን ብናነጻጽር ለምሳሌ አሜሪካዊ ቢሊየነሮች በድምሩ 3.5 ትሪሊዮን ዶላር ሲያካብቱ ቻይናዎች ግን በድምሩ 1.7 ትሪሊዮን ዶላር ሀብት ነው ያፈሩት። ሆኖም የቻይና ቢሊየነሮች አመጣጥ ለአሜሪካ አስፈሪ ይመስላል። በአጭር ጊዜ እየተቃረቡ ነው። የታላቋ ብሪታኒያ ቢሊየነሮች ሀብት ተለቅ ያለ ካልኩሌተር ፈልገን ብንደምረው 205 ቢሊየን ዶላር ቢሆን ነው። የጀርመኖች 595 ቢሊየን ዶላር ደርሷል። የፈረንሳይ ቢሊየነሮች ድምር ሀብት ደግሞ 443 ቢሊየን ዶላር ብቻ ነው። ስለዚህ ቻይናና አሜሪካ ከአውሮፓዊያኑ ቢሊየነሮች ጋር ሲነጻጸሩ 'ምን ብልተው ነው የሚያድሩት?' ያስብላል። ማን ለጋስ ነው? ዩቢኤስ ባንክ እንደሚለው ብዙ ቢሊየነሮች ከኮቪድ-19 በኋላ ደግ፣ ቸር፣ እና ለጋስ ሆነዋል። ""በእኛ ጥናት መሰረት 209 የዓለም ቢሊየነሮች በይፋ ተናግረው የለገሱት ብር ድምር 7.2 ቢሊየነር ዶላር ነው"" ይላል ባንኩ። ይህ አሐዝ ከመጋቢት እስከ ሰኔ 2020 ብቻ ቃል ተገብቶ የተለገሰ ነው። የዚህ ልግስና ባህሪ ከስከዛሬው የሚለየው በፍጥነት መሆኑና ተለጋሽ ተቋማትም ገንዘቡን ለፈለጉት አገልግሎት በፈለጉት መንገድ እንዲያውሉት መደረጉ ነው ይላል ባንኩ። ጥናቱ የታላቋ ብሪታኒያ ቢሊየነሮች ከብዙ አገሮች አንጻር ትንሹን ልግስና ማሳየታቸው አስገርሞል። በአሜሪካ ለምሳሌ 98 ቢሊየነሮች 4.5 ቢሊዮን ዶላር ለግሰዋል። በቻይና 12 ቢሊየነሮች 679 ሚሊዮን ዶላር ልግሰዋል። በታላቋ ብሪታኒያ ግን 9 ቢሊየነሮች ብቻ ናቸው መለገስ የቻሉት። ድምሩም 300 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ብቻ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-54456858 +politics በሱዳን ዳርፉር ግዛት በተነሳ ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች ተገደሉ በምዕራብ ሱዳን ዳርፉር ግዛት ለቀናት በዘለቀ የብሄር ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች ተገደሉ። በአረብ ጎሳዎች እና በቀድሞ አማፂያን የሚደገፉት የአፍሪካ ማሳሊት ማህበረሰብ ተዋጊዎች መካከል ውጊያ ለቀናት ሲደረግ ቆይቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገለጸው በክሪኒክ ግዛት አካባቢ ባለው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። የተወሰኑትም ድንበር አቋርጠው ወደ ጎረቤት አገር ቻድ መግባታቸው ተገልጿል። ከግጭቱ የተረፉ ግለሰቦች እንደተናገሩት ታጣቂዎች ከክሬኒክ በስተምዕራብ በሚገኝ መንደር ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል፤ እንዲሁም ቤቶችን ከማቃጠላቸው በፊት ተኩስ ከፍተዋል። በዋናው መንገድ ላይም አድፍጠው ህዝቡ ወደሌሎች ቦታዎች እንዳይሻገር ዘግተው ነበር ተብሏል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ማግኘት አልቻሉም። በባለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ እለት በተለያዩ ማህበረሰቦች መካከል በተቀሰቀሰ አዲስ ግጭት በትንሹ 55 ሰዎች ተገድለዋል። ማክሰኞ እለት በአካባቢው በሚገኝ ቁጥቋጦ ውስጥ ተጨማሪ አስከሬኖች የተገኙ ሲሆን የሟቾችንም ቁጥር ከ100 በላይ አድርሶታል። ከዚህም በተጨማሪ በደርዘን የሚቆጠሩ ደብዛቸው የደረሰበት አልታወቀም። ባለፈው ወር በምእራብ ዳርፉር በተለያዩ አካባቢዎች 43 ሰዎች ተገድለዋል። በግጭት በምትናጠው ዳርፉር ደቡባዊ ግዛትም ���ሄር ተኮር ግጭቶች መከሰታቸውም ታውቋል። መንግስት ብጥብጡን ለመቆጣጠር የመከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይልና፣ የፖሊስ ጥምር ሃይል ወደ ምዕራብ እና ደቡብ ዳርፉር አሰማርቷል። https://www.bbc.com/amharic/news-59580108 +sports የሱቶን ግምት፡ አርሰናል ሊቨርፑልን 4 ለ 1 ሊያሸንፍ ይችላል? የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የማንቸስተር ደርቢ ሲቲ በበላይነት ያጠናቅቃል ማለቱ ተሳክቶለታል። በዚህ ሳምንትም በአርሰናል እና በሊቨርፑል ጨዋታ ትልቅ ግምት አስቀምጧል። “ላውሮ ቀድሞ ግምቱን ያስቀምጥ ነበረው የስፖርት ተንታኝ) ሊቨርፑል ይሸነፋል ብሎ አይገምትም። እኔ ግን ይሸነፋሉ ሳይሆን ይቀጠቀጣሉ ነው የምለው” ይላል ሱቶን። የሊጉ የዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ እሑድ እና ሰኞ ይከናወናሉ። ሱቶን እንደተለመደው በዚህ ሳምንትም እንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ጨዋታዎችን ግምት አስቀምጧል። በርንማውዝ ከ ሌስተር በየሳምንቱ በርንማውዝ ይሸነፋል እያልኩ ያለፉትን አራት ጨዋታዎች አልተሸነፉም። ጎልም አላስተናገዱም። ከቆመ ኳስ ሌስተር ላይ ስጋት ቢፈጥሩም ቀበሮዎቹ ምን መስራት እንደሚችሉ ከፎረስተ ጋር አሳይተዋል። ፉክክር ያለበት ጨዋታ ይሆናል። በዚህ ጨዋታም በርንማውዝ ግምቴን የሚያፈርስ ውጤት ያስመዘግባል? ግምት፡ 1 – 2 ዎልቭሶች አሰልጣኝ በሩኖ ላዥን በጊዜ ማሰናበቱ ትንሽ ጭካኔ የሞላው ነው። ጎል ማስቆጠር አለመቻላቸው የአሰልጣኙ ጥፋት ሳይሆን የአጥቂዎቹ መጎዳት ነው። ዎልቭስ አሰልጣኝ ያልተሾመላቸው ሲሆን ይህንን ጨዋታም አያሸንፉም። ቼልሲም ከግርሃም ፖተር ጋር ህይወት የጀመረበት ወቅት ነው። ፒዬር-ኤምሪክ ኦባመያንግ ጎል ማስቆጠር ጀምሯል። ስለዚህ በቀላሉ ሦስት ነጥብ ያሳካሉ። ግምት፡ 2 – 0 የሳውዝሃምፕተኑ አለቃ ራልፍ ሃሰንሃትል ይባረራሉ የሚል ወሬ አለ። ከሲቲ ጋር መጫወት ደግሞ ትልቅ ዕድል ነው። ቡድኑ ባለፈው ዓመት በሁለቱም ጨዋታ አቻ ቢለያዩም ዘንድሮ ግን ኢትሃድ ላይ አያሳኩትም። የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን የጎሎቹን መጠን የቅርጫት ኳስ ሊያስመስለው ይችላል። ካለው የጨዋታ መደራረብ ግን በቂ ጎሎች ላይ ሲደርስ ቡድኑ ይቀዘቅዛል። በዚህ ምክንያት ብዙ ጎል አልገምትም። ሲቲ በፍጥነት አራት ጎሎችን አስቆጥሮ ጨዋታውን መቆጣጠር የሚጀመር ይመስለኛል። ግምት፡ 4 – 0 ባለፈው ሳምንት ኒውካስል ፉልሃምን ሲያሸንፍ ወደ ፊት የሚሄዱበት መንገድ አስገራሚ ነበር። ካለም ዊልሰን ከጉዳት ተመልሶ ምርጥ ብቃት ላይ ሲገኝ ሚጌዌል አልሚሮን ደግሞ ካለፈው ዓመት ተሻሽሏል። ኒውካስል ጨዋታውን በመቆጣጠር እና ዕድሎችን በመፍጠር ያሸንፋል። የብሬንትፎርዱ አጥቂ ኢቫን ቶኒ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ ሲመለስ ማረጋገጥ የሚፈለገው ነጥብ ይኖራል። ግምት፡ 2 – 1 ብራይትን ድንቅ አቋም ላይ ስለሚገኝ ይህን ጨዋታ ለመገመት ከባድ ነው። ሊያንድሮ ትሮሳድ አንፊልድ ላይ አስደናቂ ሆኖ ሲያመሽ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ደ ዜብሪም ማጥቃት የሚወዱ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ቶተንሃም ዘንድሮ ማጥቃት ላይ የተመሠረተ አጨዋወት የሚመርጥ አይመስልም። የብራይተን አጨዋወት ግን ይመቻቸዋል። ግምት፡ 1 – 1 ክሪስታል ፓላስ ከ ሊድስ ይህን ጨዋታ ባለፈው ዓመት ዘግቤዋለሁ። ጨዋታው ሳቢ ካለመሆኑም በላይ 0 ለ 0 ነበር የተጠናቀቀው። ይህም ድንቅ ጨዋታ አይሆንም። ውጤቱን በጣም የሚፈልጉት ፓላሶች ያሸነፋሉ ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 1 – 0 ዌስት ሃም ከ ፉልሃም ዌስተሃም ባለፈው ሳምንት አስፈላጊ ነጥቦችን ከዎልቭስ ላይ ሰብስቧል። መዶሻዎቹ በጥሩ አቋም ላይ ስለመሆናቸው ይህ ጨዋታ የሚፈተሹበት ይሆናል። የፉልሃም ነገር የሚወሰነው በተጎዳው አጥቂያቸው አሌክ��ንደር ሚትሮቪች ጤንነት ላይ ነው። ግምት፡ 2 – 1 አርሰናል ባለፈው ሳምንት ከቶተንሃም ጋር ነበረው ጨዋታ ላይ ሳቢ ነበር። በዚህ ጨዋታም በተመሳሳይ ይደግመዋል። መድፈኞቹ በጥሩ አጨዋወት እና ልበ ሙሉነት ላይ ሲገኙ ቀያዮቹ ግን ነገሮች ገና አልተሰካኩላቸውም። የርገን ክሎፕ ቡድን በቻምፒዮንስ ሊጉ ከሬንጀርስ ጋር ጥሩ ቢሆንም የተከላካይ መስመሩ አልተፈተነም። ማርቲኔሊ፣ ሳካ እና ጂሰስ ግን ፋታ የሚሰጧቸው አይመስልም። ሊቨርፑል ጎል ማስቆጠር ቢችልም አርሰናል ባለው የማጥቃት መስመር ጥንካሬ የበላይ ሆኖ ያጠናቅቃል። ግምት፡ 4 – 1 ኤቨርተን ባለፈው ሳምንት ጥሩ ብቃት ላይ ሳይሆንም ሳውዝሃምፕተንን ማሸነፍ ችሏል። ብዙ ጎል ስለማይቆጠርባቸው ዕድሎችን ባይፈጥሩም በጨዋተ መቆየት ይችላሉ። ማንቸስተር ዩናይትድ ባለፈው ሳምንት በሲቲ የደረሰበት ሽንፈት ሁሉንም የሚያጋጥም ነው። ቡድኑ በኤሪክ ቴን ሃግ ስር የተወሰነ መሻሻል አሳይቷል። ከአራት ድሎቻቸው በኋላ ይሰናከላሉ ብዬ አልጠብቅም። ሲቲን በመሰለ ቡድን በመሸነፋቸውም ችግር ውስጥ ናቸው አልልም። ኤቨርተን በሜዳው የሚያጠቃ ቢመስለኝም ሁለቱም ቡድኖች ነጥብ ይጋራሉ። ግምት፡ 1 – 1 ኖቲንግሃም ፎረስት ከ አስቶን ቪላ የፎረስቱ አለቃ ስቲቭ ኩፐር በኃላፊነታቸው ቢቀጥሉም ነገሮች ጥሩ እየሄዱላቸው አይደለም። በሌላ በኩል በአስር ተጫዋች ለ45 ደቂቃ ያህል የተጫወተውን ሊድስን ማሸነፍ ባለመቻሉ አስቶን ቪላ የሚገኝበትን ለማወቅ ያዳግታል። ቡድኑ በሚጠበቀው ደረጃ አለመሻሻሉን የሚገልጹ ደጋፊዎች አሉ። ፊሊፔ ኮቲንሆም ዘንድሮ ጥሩ አቋም ላይ አይገኝም። የፎረስት በራስ መተማመን ዝቀትኛ በመሆኑ ቪላ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። ግምት፡ 0 – 1 https://www.bbc.com/amharic/articles/cqe742z20d1o +politics አውሮፓዊቷ አገር ቤላሩስ የፈረንሳይ አምባሳደርን አባረርች "በቤላሩስ የፈረንሳይ አምባሳደር አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ በታዘዙት መሠረት ወደ መጡበት መመለሳቸውን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። የኤምባሲው ቃል አቀባይ ለፈረንሳይ ዜና ወኪል እንደተናገሩት አምባሳደር ኒኮላስ ደ ላስት ቤላሩስን ለቀው የወጡት እሑድ ዕለት ነው። የቤላሩስ መንግሥት አምባሳደሩ ዋና ከተማዋ ሚኒስክን ለቀው እንዲወጡ እስከ ሰኞ ድረስ ቀነ ገደብ ሰጥቶ ነበር። የ57 ዓመቱ አምባሳደር ኒኮላስ ባለፈው ዓመት ነበር በቤላሩስ የፈረንሳይ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት። የቤላሩስ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት አምባሳደሩ የሥራ ፈቃዳቸውን ለፕሬዝደንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ አላቀረቡም። ፈረንሳይ ልክ እንደሌሎቹ የአውሮፓ አገራት የቤላሩሱ መሪ ሉካሼንኮ ባለፈው ዓመት ነሐሴ የተደረገውን ምርጫ አሸንፍኩ ብለው ለስድስተኛ ጊዜ ፕሬዝደንት ሆነው መመረጣቸው አልተዋጠላትም። አምባሳደሩ ባለፈው ታኅሣሥ ፕሬዝደንቱን በማግኘት ፈንታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቭላድሚር ማኬይን ነው ያገኙት። ለኤኤፍፒ በተላከ መግለጫ የፈረንሳይ ኤምባሲ ቃል አቀባይ ""የቤላሩስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደሩ ከሰኞ በፊት ለቀው እንዲወጡ ነው ያዘዘው"" ብለዋል። ""ሁሉንም የኤምባሲውን ሠራተኞች ተሰናብተው ነው የሄዱት። ለቤላሩስ ሕዝብ በተንቀሳቃሽ ምስል ቀድተው ያስቀመጡት መልዕክት በኤምባሲው ድረ-ገፅ ይለቀቃል።"" የአውሮፓ ሕብረት በተደጋጋሚ ባለፈው ነሐሴ የተካሄደው ምርጫ ""ነፃና ፍትሐዊ"" ነው ብሎ እንደማያምን አሳውቋል። ሕብረቱ አልፎም በፕሬዝደንት ሉካሼንኮ አገዛዝ ላይ ማዕቀብ መጣሉ የሚዘነጋ አይደለም። ፕሬዝደንቱ ከምርጫው በኋላ ለዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተቃውሞ እያሰሙ ያሉ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የኃይል እርምጃ ወስደዋል። ምንም እንኳ የምዕራቡ ዓ��ም ማዕቀብ ቢጥልባቸውም ሉካሼንኮ ሥልጣናቸውን ተቆናጠው እንደያዙ ናቸው። የ67 ዓመቱ የቤላሩስ መሪ አገራቸውን በፈረንጆቹ ከ1994 ጀምሮ ገዝተዋል። ዘንድሮ ከአውሮፓ አገራት በደረሰባቸው ጫና ምክንያት ከአብዛኛዎቹ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አቋርጠዋል። የፕሬዝደንቱ ዋነኛ ደጋፊ የሚባሉት የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ባለፈው መጋቢት የቤላሩስ መንግሥት የላትቪያ አምባሳደርን ጨምሮ ሁሉንም የኤምባሲ ሠራተኞች ማባረሩ ይታወሳል። ይህ የሆነው በላትቪያ በተካሄደ የበረዶ መንሸራተት ጨዋታ ላይ የቤላሩስ ተቃውሞን የሚያንፀባርቅ ባንዲራ በመታየቱ ነው። የቀድሞ የሶቪዬት ግዛት የነበረችው አገር ባለፈው ነሐሴ ደግሞ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ወደ ቤላሩስ ሊጓዙ ለነበሩት ጁሊ ፊሸር የሥራ ፈቃድ እንደማትሰጥ አሳውቃ ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-58951085 +health እስራኤል የማትሪክ ፈተና ለሚቀመጡ ተማሪዎቿ ክትባት መስጠት ጀመረች እስራኤል ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 18 የሚሆኑ ወጣቶችን ኮቪድ ክትባት መስጠት ጀመረች። ለነዚህ ወጣቶች ክትባቱ እንዲሰጠት የሆነው የማትሪክ ፈተና ሊቀመጡ ስለሆነ ነው። እስራኤል 9 ሚሊዮን ከሚሆነው ሕዝቧ ውስጥ ሩብ ያህሉ የመጀመርያውን የክትባት ጠብታ ወስዷል። የክትባቱ አይነትም ፋይዘር ሰራሹ መሆኑ ታውቋል። እስራኤል ለዜጎቿ ክትባት መስጠት የጀመረችው ባለፈው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ አካባቢ ከዲሴምበር 19 ጀምሮ ነው። ክትባቱ ሲጀመር ቅድሚያ የተሰጣቸው እድሜያቸው ለገፉ አዛውንቶች ሲሆን ከዚያም ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ነበር። አሁን ዕድሜያቸው ከ40 በላይ የሆኑ ዜጎች ክትባቱን በመወሰድ ላይ ናቸው። እስራኤል ኢኮኖሚዋን በየካቲት ወር ሙሉ በሙሉ ለመክፈት እየታተረች ነው። የእስራኤል የትምህርት ሚኒስትር እንዳሉት አሁን ወጣት ተማሪዎችን መከተብ የተጀመረው ወደ ትምህርት እንዲመለሱና ፈተና እንዲቀመጡ ለማስቻል ነው። ወጣት ተማሪዎቹ ክትባቱን የሚወስዱት በወላጆቻቸው ፈቃድ ነው። እስራኤል ያሉ ተማሪዎች የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ሲጨርሱ የሚወስዱት የማትሪክ ፈተና ወደ ዩኒቨርስቲ ለመግባት አለመግባት የሚለዩበት ነው። የሚያመጡት ውጤትም በውትድርና ተሳትፏቸው ላይ ወሳኝ ሚና አለው። በእስራኤል ዜጎች ለተወሰነ ጊዜ የግዴታ የውትድርና አገልግሎትን ይሰጣሉ። የአገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ክትባቱ መሰጠቱን እየቀጠለ ቢሆንም በሚቀጥለው ወር ትምህርት ስለመጀመር አለመጀመሩ ለመናገር ጊዜው ገና ነው። እስራኤል ክትባት በመስጠት ከአለም ፈጣኗ አገር ሆና ነው በዲሴምበር 19 የጀመረችው። በፈረንጆቹ 2020 መገባደጃ የሕዝቧን 10 እጅ ከትባ ጨርሳለች። እስራኤል 600ሺህ በተህዋሲው የተያዙ ዜጎች ያሏት ሲሆን 4ሺ የሚሆኑት ሞተውባታል። ትናንት የእሰራኤል መንግሥት ባወጣው አዲስ መመርያ የመንገደኞች በረራን ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ የጥር ወርን ሙሉ ማገዱን አስታውቋል። ይህም ተህዋሲውን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት አንድ አካል ነው። ቤንያሚን ኔትንያሁ እንደተናገሩት ይህ የበረራ እገድ አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ወደ እስራኤል እንዳይገባ ለማድረግ የሚወሰድ ጥብቅ እርምጃ ነው ብለዋል። በአሁኑ ጊዜ የውጭ ዜጎች ወደ እስራኤል እንዲገቡ እየተፈቀደላቸው አይደለም። እስራኤል በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ 9 ሚሊዮን ዜጎቿን ጸረ ኮቪድ ክትባት በመከተብ የዓለም የመጀመርያዋ አገር ለመሆን ቀን ተሌት እየሰራች ትገኛለች። https://www.bbc.com/amharic/55792458 +politics መርማሪ ቡድኑ በትራምፕ ላይ መጥሪያ እንዲቆረጥባቸው ወሰነ ባለፈው ዓመት የአሜሪካ ምርጫን ተከትሎ የተነሳውን ነውጥ ለመመርመር በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባ���ት የተዋቀረውና 9 አባላት ያሉት መርማሪ ኮሚሽን ትናንት ምሽት ምርመራውን አጠናቋል። በዚህ የመጨረሻ ነው በተባለ የምርመራ ውጤት የመርማሪ ኮሚሽኑ አባላት በትራምፕ ላይ መጥሪያ እንዲቆረጥና ስለሆነው ነገር ሁሉ ቃል እንዲሰጡ በሙሉ ድምጽ ወስነዋል። ‘ለፈጸመው ተግባር ምላሽ እንዲሰጥ ግድ ይላል’ ብለዋል የሚሲሲፒው ዲሞክራት ወኪልና የመርማሪ ሸንጎው ሊቀ መንበር የሆኑት ቤኒ ቶምሰን። ትራምፕ መጥሪያውን ቸል ካሉ ክስና እስር ይጠብቃቸዋል። ይህ መርማሪ ሸንጎ የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ካፒቶል ሒልን ሰብረው ያደረሱትን ጥፋት ሲመረምር ድፍን ዓመት አልፎታል። በዚህ ሸንጎ ከ 9 አባላት ሁለቱ ሪፐብሊካን፣ 7ቱ ደግሞ ዲሞክራቶች ናቸው። የመርማሪ ኮሚሽኑ አባላት ትራምፕ መጥሪያ ተቆርጦላቸው ቃላቸውን እንዲሰጡ የወሰኑት ያለምንም ተቃውሞና ድምጸ ተአቅቦ በሙሉ ድምጽ ነው። ለትራምፕ መጥሪያ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ተቆርጦ ይሰጣቸዋል። የዋዮሚንግ ግዛትና የሪፐብሊካን ተወካይ እንዲሁም የመርማሪው ሸንጎ ምክትል የሆኑት ሊዝ ቼኒ እንዳሉት አሜሪካዊያን ለዚሁ ሁሉ ጥፋት መሠረት ነው ከሚባለው ሰው ሐቁን የመስማት መብት አላቸው። ትናንት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ማታ 2፡00 ሰዓት የጀመረው የመርማሪ ቡድኑ 9ኛ ሸንጎ የመጨረሻ ምርመራ ሰነዶችና የቪዲዮ ማስረጃዎች የቀረቡበት ነበር። በርካታ አስደንጋጭ የተባሉ መረጃዎችም ለሕዝብ በቀጥታ ቴሌቪዥን እንዲታዩ ሆነዋል። በዚህ የቪዲዮ ማስረጃ በተለይካፒቶል ሒል ውስጥ የነበሩ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት፣ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፒሎሲን ጨምሮ ከቢሮ ቢሮ ሲሯሯጡ፣ ለዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ሰዎች ስልክ ሲደውሉና በከፍተኛ ጭንቅ ከነውጠኞቹ ለማምለጥ ሲሞክሩ የሚያሳዩ አዳዲስ ቪዲዮዎች ለሕዝብይፋ ተደርገዋል። እንደራሴዎቹ በተለይ የጋዝ መከላከያ ጭንብል ሲለብሱና በነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ሁኔታ ሆነው ሲንቀሳቀሱ የቪዲዮ ማስረጃዎች የቀረቡበት ነበር የትናንቱምስክርነት። ዶናልድ ትራምፕ ይህን የመርማሪ ኮሚሽኑን ውሳኔ ፖለቲካዊ ብለውታል። ‘አሜሪካዊያን በዲሞክራቶች ቀሽም አመራር በተማረሩበት ወቅት የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር የተቀናበረ ነው፤ የእኔን ምስክርነትከፈለጉ ለምን በምርመራው መጀመርያ አልጠየቁኝም?’ ብለዋል ትራምፕ። ዶናልድ ትራምፕ በ2024 በድጋሚ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጭ ሰጥተዋል። አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ይህ የምርመራ ቡድኑ ውሳኔ ከወር በኋላ ከሳምንታት በኋላ  የሚደረገው ‘ሚድተርም’ ምርጫ ላይ ዲሞክራቶች ሊደርስባቸው የሚችለውን ሽንፈት በመስጋት መራጮችን ለማማለል ሆን ተብሎ የተደረገ ነው ይላሉ። ይህ በሕዝብ እንደራሴዎች የተቋቋመው መርማሪ ቡድን ሙሉ የምርመራ ውጤቱን ከሁለት ወራት በኋላ ይፋ ያደርጋል። ለዓመት ያህል በዘለቀው ምርመራ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን፣ የደህንነት ሰዎችን፣ ሚኒስትሮችን፣ የዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ ረዳቶችን፣ የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ከአንድ ሺህ አሜሪካዊያን በላይ ምስክርነት ሰምቶ መርምሯል። በዚህ መርማሪ ቡድን ሁለቱ ብቸኛ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የሆኑት ሊዝ ቼኒ እና አዳም ኪዚንግር ትናንት ትራምፕ የምስክርነት ማዘዣ ተቆርጦባቸው ቃላቸውን እንዲሰጡ ድምጽ በመስጠታቸው በፓርቲያቸው ዘንድ ከፍተኛ ውግዘት ደርሶባቸዋል። በባለፈው ዓመት የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች የካፒቶል ሒል አመጽ 850 አሜሪካዊያን ክስ ተመስርቶባቸዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c998p5kdkn1o +politics ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በአፍሪካ ህብረት ንግግር ለማድረግ በድጋሚ ጠየቁ "የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በአፍሪካ ህብረት መሪዎችን ለማነጋገር በድጋሚ ጥያቄ እንዳቀረቡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ አስታውቀዋል። ሊቀ መንበሩ በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ጥያቄው የመጣው ከዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ነው። በዚህ ውይይት ላይ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ""ከአፍሪካ ኅብረት ጋር የጠበቀ ግንኙነት የመፍጠር ፍላጎት"" እንዳላቸውም መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸው ተገልጿል። ፋኪ የፕሬዚዳንቱ ጥያቄ ተቀባይነት ይኖረው እንደሆነ ያልገለጹ ሲሆን ነገር ግን ""ከሩሲያ ጋር ላለው ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ አጥብቀው መናገራቸውን"" በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ለሴኔጋሉ አቻቸውና ለወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ማኪ ሳል የአፍሪካ መሪዎችን ለማነጋገር ጥያቄ አቅርበው ነበር። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሩሲያ ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት እንድትታገድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምጽ ያልሰጡ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ የአፍሪካ ሀገራት የበላይነቱን መያዛቸው ይታወሳል። ውሳኔው በ93 ድጋፍ፣ በ24 ተቃውሞ እና በ58 ድምጸ ተአቅቦ ጸድቋል። በአህጉሪቱ ከሚገኙት 54 ሀገራት አንጎላ፣ ግብፅ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ 24ቱ ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል። ከሩሲያ ጋር በታሪክ ጥሩ ግንኙነት የነበራቸው አልጄሪያ እና ኢትዮጵያን ጨምሮ ዘጠኙ እርምጃውን ተቃውመዋል። ሌሎች 11 አገራት ድምፃቸውን ሳይሰጡ ቀርተዋል። 10 ሃገራት ብቻ የሩሲያን ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት መታገድ ደግፈዋል። እነዚህም ቻድ፣ ኮሞሮስ፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ሊቢያ፣ ማላዊ እና ሲሼልስ ነበሩ። አፍሪካ ሩሲያን ለመደገፍ ዝንባሌ የምታሳየው ለምንድነው? በተባበሩት ጠቅላላ ጉባኤው ሩስያን በመቃወም ሁለት ጊዜ ድምጽ ከመስጠት የተቆጠበችው የአህጉሪቱ ትልቁ ኢኮኖሚ ደቡብ አፍሪካ በኩል የተሰጡት አስተያየቶች በተወሰነ መልኩ ያለውን ሁኔታ ያስረዳሉ። ""ግጭቱ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት የአለም አቀፉን ሰላምና ደህንነትን የማስጠበቅ ተልዕኮውን መወጣት አለመቻሉን አጋልጧል"" ሲል የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳን ጠቅሶ ኤኤፍፒ ዘግቧል። ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ሩሲያ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካን ያካተተውና አምስት ቋሚ አባላት ያሉት የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አባልነት ""ጊዜ ያለፈበት እና የማይወክል ነው"" ብለዋል። የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶርም የአገራቸውን ገለልተኝነት አቋም አስመልክቶ በመደገፍ የተከራከሩ ሲሆን ግጭቱ ""የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ኢ-ፍትሃዊነት"" አሳይቷል ሲሉም ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61272797 +health ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ የተከተቡ ዜጎቿ ጭምብል ሳያደርጉ መሰባሰብ ይችላሉ አለች "የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) የኮሮናቫይረስ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ወደቀደመ ህይወታቸው መመለስ ይችላሉ የሚል መመሪያ አውጥቷል። በዚህም መሰረት ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ጭምብል (ማስክ) ሳያደርጉ በቤት ውስጥ መሰብሰብ ይችላሉ ተብሏል። ሲዲሲ እንዳስታወቀው የመጨረሻውን ክትባት ከተከተቡ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከኮሮናቫይረስ ስጋት ነፃ ናቸው ብሏል። እስካሁን ድረስ አሜሪካ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿን ከትባለች። የአገሪቱ የጤና ባለስልጣናት አዲሱን የደህንነት መመሪያ ይፋ ያደረጉት በትናንንትናው እለት ዋይት ሃውስ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ግብረ- ኃይል መግለጫ ላይ ነው። መመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ማድረግ ይ��ላሉ ብሎ ካስቀመጣቸው መካከል፦ ""ከኮቪድ-19 በኋላ ሊኖር የሚችለውን አለም ማየት ጀምረናል። የበለጠ ዜጎቻችን በተከተቡ ቁጥር ማከናወን የምንችላቸውን ተግባራትም ይጨምራሉ"" በማለት የዋይት ሃውስ ከፍተኛ አማካሪ አንዲ ስላቪት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ህዝባዊ በሆነ ቦታ ላይ ጭምብል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ እንዲሁም አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማስወገድና የተጣሉ የጉዞ ገደቦችን መከተል ይኖርባቸዋል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ መመሪያው ያልተከተቡና ለኮሮናቫይረስ በበለጠ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦችም በተለይ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስቀምጧል። አሜሪካ በቅርቡ የምትከትባቸውን ዜጎቿን ቁጥር በከፍተኛ እየጨመረ መሆኑን ያስታወቀች ሲሆን እስካሁን ድረስ 90 ሚሊዮን ሰዎች ተከትበዋል። በተለይም የጆንሰን ጆንሰን የአንድ ጊዜ ክትባት እውቅና ማግኘቱ አቅርቦቱን ጨምሮታል ተብሏል። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ ኮቪድ-19 የማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ መሆኑ ቀጥሏል። አገሪቱ እስካሁን ድረስ 29 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን 525 ሺህ ዜጎቿንም አጥታለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-56330257 +health በኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ ከ22 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ታወቀ "በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፈው ሳምንት ውስጥ በተደረገ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ሰዎች ላይ ወረርሽኙ መገኘቱን የተደረጉ የምርመራ ውጤቶች አመለከቱ። ካለፈው ሰኞ አስከ ትናንት እሁት ድረስ ባለፉት ሰባት ቀናት በ77,083 ናሙናዎች ላይ በተደረጉ ምርመራዎች በ22,321ዱ ላይ ቫይሱ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር በየዕለቱ የሚያወጣቸው የወረርሽኙ ሪፖርቶች ያመለክታሉ። ይህም አስካሁን በአንድ ሳምንት ከተመዘገቡ ከፍተኛ ቁጥር ካላቸው በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ውስጥ የሚመደብ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ሚኒስቴሩ እንዳለው እየተመዘገበ ያለው የበሽታው የመስፋፋት መጠን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ቀደም ሲል በነበሩ ሳምንታት ምርመራ ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል በየዕለቱ ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ከአምስት መቶ በላይ፣ ነገር ግን አንድ ሺህ እንኳን የማይደርስ ነበር። ባለፈው ሳምንት ግን ሰኞ ዕለት ከተመዘገበው 681 ውጪ በሌሎቹ ቀናት አሃዙ ከፍተኛ ነበር። በዚህም መሠረት በየዕለቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር በ2300 እና 5000 መካከል ይገኛል። ዝቅተኛው ማክሰኞ ዕለት የተመዘገበው 2,323 ሲሆን፣ ከፍተኛ ደግሞ ቅዳሜ ዕለት 5,013 የተመዘገበው ሲሆን፣ በሳምንቱ ውስጥ በአጠቃላይ በ22,321 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። የወረርሽኙ ቫይረስ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር ከሚመረመሩት ሰዎች ብዛት አንጻር ከፍና ዝቅ የሚል ቢሆንም ያለፈው ሳምንት አሃዝ ግን ከፍተኛ እንደሆነ ቀደም ካሉት ሳምንታት ጋር የተደረገው ንጽጽር ያመለክታል። ቀደም ሲል በነበረው ሳምንት ውስጥ ከተመረመሩ 53 ሺህ ሰዎች መካከል 8500 ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት የተመዘገበው ቁጥር ግን በእጅጉ ከፍተኛ ነው። በቀደሙት ሳምንታት ምርመራ ካደረጉ ሰዎች መካከል ሦስት በመቶ ያህሉ ላይ ብቻ የኮሮናቫይረስ ይገኝባቸው የነበረ ሲሆን፤ ከአንድ ሳምንት በፊት ግን ቁጥሩ ወደ 28 በመቶ ከፍ ብሎ ነበር። ባለፈው ሳምንት ደግሞ በእጀጉ አሻቅቧል። የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ""እስካሁን የነበረው አካሄድ ጥሩ ነበር። ነገር ግን ከታኅሣሥ 07/2014 ዓ. ም. ወዲህ ባሉት ቀናት በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ��ው"" ብለዋል። ጨምረውም በአሁኑ ወቅት የኮቪድ-19 ምርመራ ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል ""አንድ ሦስተኛው ቫይረሱ እየተገኘባቸው ስለሆነ የጥንቃቄ እርምጃ መወሰድ አለበት። ለዚህም ማስክ በአግባቡ ማድረግና የመከላከያ ክትባት መውሰድ ይገባል"" ሲሉ መክረዋል። በበርካታ የዓለም አገራት መገኘቱ የተረጋገጠውና ከሰው ወደ ሰው የመዛመት አቅሙ ከፍተኛ የሆነው አዲሱ የኦሚክሮን ቫይረስ ዝርያ በኢትዮጵያ ውስጥ መኖር አለመኖሩ ገና ያልተረጋገጠ ሲሆን ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ሚኒስትሩ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ""በሌሎች አገሮች የሚታየው የኦሚክሮን ዝርያ በኢትዮጵያም ምልክቶቹ ታይተዋል። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአስጊ ሁኔታ ጨምሯል። አሁን ናሙና እየመረመርን ነው። እስክናረጋግጥ ድረስ ኦሚክሮን መግባቱን ለመናገር አስቸጋሪ ነው"" ብለዋል ዶ/ር ደረጄ። የኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ መኖሩ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ አስከ ትናንት ድረስ 4 ሚሊዮን 52ሺህ 568 ሰዎች ተመርምረው 400 ሺህ በሚጠጉት ላይ ቫይረሱ የተገኘ ሲሆን፣ 6 ሺህ 898 ደግሞ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሽታውን ለመከላከል የሚረዳው ክትባት በአገሪቱ መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የተከተቡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ካላት አጠቃላይ ሕዝብ አንጻር ይህ አሃዝ ዝቅተኛ እንደሆነ ይነገራል። የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር የተለመዱትን የመከላከያ ዘዴዎች በአግባቡ ዘወትር ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የሚመክሩት የጤና ሚኒትር ዲኤታው ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ክትባት መውሰድም አስፈላጊ መሆኑን መክረዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የጤና ሚኒስቴር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የጤና ባለሙያዎች በአስገዳጅ ሁኔታ ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ እና ያልተከተቡ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የመንግሥት የነጻ ሕክምና ተጠቃሚ እንይሆኑ እንደሚደረግ ጨምረው ገልጸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59796707 +politics """ፖለቲከኞች የሶማሌን ሕዝብ እንደ ኢትዮጵያዊ አያስቡትም"" የኦብነግ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አህመድ መሐመድ" "ከሦስት ዓመታት በፊት ለውጡን ተከትሎ ለሰላማዊ ትግል ወደ አገር ውስጥ ከገቡ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው። ቢቢሲ ስለ ምርጫና ስለ ፓርቲው እንቅስቃሴ ከኦብነግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የፌደራል መንግሥት ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ መሐመድ ጋር ቆይታ አድርጓል። ስለኦብነግ እምብዛምም ከማይታወቁ ነገሮች እንጀምር። አፈጣጠሩ ከዚያድባሬ ወረራ ጋር የሚያያዝ ታሪክ አለው። በሽግግሩ ጊዜ ተሳትፋችኋል። ከምዕራብ ሶማሊያ ነጻነት ግንባር ወጣት ሊግ ነው ኦብነግ የተፈጠረው ይባላል። ክልሉን ለሁለት ዓመት ያህል አስተዳድራኋል። ልክ ነኝ? የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) የተመሰረተው (እአአ) ነሐሴ 15 ቀን 1984 ነው። በወቅቱ የነበረው የምዕራብ ሶማሌ ነጻ አውጭ ግንባር (WSLF) በኢትዮጵያ ውስጥ በነበረችው ሶማሌዎች በሚኖሩበት አገር ከተዳከመ በኋላ የግንባሩ ወጣቶች ዘርፍ የነበሩ አባሎች ተሰባስበው የመሠረቱት ግንባር ነው። የምዕራብ ሶማሌ ነጻ አውጭ ግንባር በኢትዮጵያ ሶማሌዎች የተቋቋመው ነው። ሆኖም በሶማሊያ መንግሥት ይደገፍ የነበረ ድርጅት ነበር። ወጣቶቹ ተሰባስበው፣ ተጠያይቀው ትግላችን እየተዳከመ ስለሆነ ምን እናድርግ በማለት የመሠረቱት ድርጅት ነው- ኦብነግ። እነዚህ ወጣቶች ትግላቸው ከሶማሊያ መንግሥት ነጻ አለመሆኑንና ጣልቃ ገብነት እንዳለው ተረድተው የመሠረቱት ነው። ኦብነግ በሶማሊያም በኢትዮጵያም ክልክል ስለነበርና ተቀባይነት ስላልነበራቸው በድብቅ ለዓመታት ሲሠሩ ቆይተዋል። ድርጅቱ ሲመሠረት አቶ አብዱረህማን መህዲ ነበሩ ሊቀመንበር። ከዚያም መሐመድ አብዲ መገኒ ለሁለት ወር ያህል ሊቀመንበር ሆነዋል። ከዚያም አቶ ሼህ ኢብራሂም አብደላህ ቋሚ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠው ድርጅቱን ለረዥም ጊዜ መርተዋል። እርሳቸው አሁን በሕይወት የሉም። የኦብነግ ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሶማሌዎች ኦጋዴን ተብሎ የሚጠራውን አገር ነጻ ማውጣት ነበር። የደርግ መንግሥት ከወደቀ በኋላ የኦብነግ መሪዎች እና ኃላፊዎች አገር ውስጥ ገብተው በመጎብ ዞን፣ ገርቦ በምትባል ወረዳ ሕዝብ ሰብስበው፤ ብሔራዊ ውይይት አድርገው ሸህ ኢብራሂም አብደላ እንደገና ተመርጠው በሽግግር መንግሥቱ ተሳትፏል። በመጀመሪያው ምርጫም ተሳትፎ በ84 በመቶ ድምፅ አብላጫ ድምጽ አግኝተው በክልሉ መንግሥት መሥርተዋል። ኢህአዴግ/ሕወሓት ምን ዓይነት የሕዝብ ድጋፍ፣ ዓለማና አቋም እንዳለን ካየ በኋላ ግን ወረረን። በዚህ ምክንያት ለትጥቅ ትግል ጫካ ተገባ፡፡ ፍላጎታችን በዲሞክራሲ መሳተፍ ነበር፤ ተገደን፣ ተገፍተን ጫካ ገባን። ለምን ያህል ጊዜ ነው ክልሉን? ለተወሰነ ጊዜ ነበር። አንድ ዓመት ከአሥር ወር ገደማ አስተዳድረናል። አሁን ያለው የክልሉ ሰንደቅ ዓላማ እንዲሁም እስካሁን ያለው በሶማሊኛ የተጻፈ መርሐ ሥርዓተ ትምህርት [ካሪኩለም] በኦብነግ በተመራው ክልላዊ መንግሥት ነበር የተጀመረው። መሠረታዊ የሆኑ ሥራዎችን ከጀመርን በኋላ የሕዝብ ድጋፋችን በጣም ከፍተኛ ስለነበር ጦርነት ተከፈተብን። ኃላፊዎችን መግደል ጀመሩ በዚህ ምክንያት ወደ ጫካ ገባን። ላለፉት 36 ዓመታት የቆየ አንጋፋ ድርጅት ነው። በዋናነት ለራስ ገዝ [self determination] ሲዋጋ የኖረ የፖለቲካ ድርጅት ነው። ለውጡን ተከትሎ በተደረሰ ስምምነት ወደ አገር ቤት መጥታችኋል። ነገር ግን አሁንም ስማችሁ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ነው። እንዴት ይህን ስም ይዛችሁ ትቀጥላላችሁ? በአሁኒቷ ኢትዮጵያ ስሜት ይሰጣል? ጥሩ ጥያቄ ነው። በለውጥ ስማችን አይለወጥም። በሕዝብ ፍላጎት ነው ይህ ስም የተሰየመው። አቋም የያዘውም በሕዝብ ፍላጎት ነው። ዝም ብሎ በመሪዎች፣ በሁለት. . . በሦስት. . . በሃምሳ በመቶ ሰዎች የሚወሰን አይደለም። የመገንጠልም ሆነ ወደ ኢትዮጵያ ለመሳተፍ የሚወሰነው በሕዝብ ድምፅ ነው። ይህ ሕዝብ ምን ዓይነት ድርጅት እንደሚፈልግና ምን ዓይነት አቋም እንደሚይዝ ድርጅቱ የሚወሰነው በሕዝብ ድምፅ ነው። እኛ ከለውጡ ሰዎች ጋራ ስለተግባባን የድርጅቱን ስም፣ አቋምና ዓላማ መለወጥ አንችልም። እንደዚህ ዓይነት ባህርይም የለንም። በሕዝብ የተቋቋመ ድርጅት፣ ለሕዝብ የተቋቋመ ዓላማ ስለሆነ፤ አንቀይርም። መቀየርም አንችልም። ሕዝብ ተጠይቆ፣ ተሰብስቦ፣ ብሔራዊ ስብሰባ ተካሂዶ ነው ዓላማችን የሚቀየረው። የኢትዮጵያ መሪዎች ደግሞ ሕዝብን የመሳብ ጠባይ ካላሳዩ ዝም ብሎ በቀላል የሚቀየር ነገር አይደለም። ታዲያ ኮንፈረንሱን የማታደርጉት ለምንድን ነው? የመቀየር ጊዜው አሁን አይደለም ብላችሁ ስለምታምኑ ነው? ነጻ አውጭ ግንባር ብሎ ራሱን ከማዕከላዊ መንግሥት ለመገንጠል የሚያስብን ድርጅት ስም ይዞ ከሌሎች ፓርቲዎችስ ጋር እንዴት ነው የምትሠሩት? እኔ ግራ የገባኝ፣ እኔ ግራ የሚገባኝ ይሄ ጥያቄያችሁ ነው። ብዙ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ይሄን ጥያቄ ሲጠይቁኝ ቆይተዋል። የመገንጠል [self determination] ጉዳይ ብዙ ጋዜጠኞች …፤ ምንድነው ችግራችሁ? ከዚህ ነጥብ ማለፍ ያቃታችሁስ ለምንድነው? እንዴ! የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ራሱ እስከ መገንጠል ይፈቅዳል። ለምን ይሄ ነገር ለጋዜጠኞች ራስ ምታት (stress) ሆነባችሁ? ለምን የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይዋጥላችሁ ቻለ? ለምን ይሄ ነገር ጉሮሯችሁ ውስጥ ተቀርቅሮ እንደቀረ እኔ ግራ ገባኝ። ሕጋዊ የሆነ ነገር ነው፤ ሕዝብ ይሆንልኛል ባለው መሄድ አለበት። ኢትዮጵያ ከሆነችላቸው በኢትዮጵያዊነት መቆየት ይችላሉ፤ ካልሆነችላቸው ደግሞ የራሳቸውን መንግሥት መፍጠር ይችላሉ። ይህ በዓለም ሕግጋትም ያለ ነው። በኢትዮጵያም ሕገ መንግሥት ያለ ነው። ለምን ደግማችሁ ደጋግማችሁ የእኛን ድርጅት ይሄን ጥያቄ እንደምትጠይቁ ግራ ይሆንብኛል። ጋዜጠኞች ግን ከዚህ ጥያቄ ማለፍ ለምን አቃታችሁ? ከዓመታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ዋና ፀሐፊያችሁ አቶ አብዱራህማን መህዲ በአንድ ቃለ ምልልሳቸው ላይ ""ሶማሌ በማዕከላዊ መንግሥቱ የተናቀና የተረሳ ክልል ነው። እኛ ኢትዮጵያዊነት አይሰማንም፤ በቅኝ ነው ማዕከላዊ መንግሥቱ የያዘን"" ሲሉ ተደምጠዋል። ይህ ቀደም ሲል ያለ ስሜት ነው። ከለውጡ በኋላ ይህ ስሜታችሁ በምን ያህል መጠን ተፈውሷል? በእርግጥ ይህ የመሪዎች ስሜት ሳይሆን የሕዝብ ስሜት ነው። እውነቱን ንገረኝ ካልከኝ የእኛ ሕዝብ፣ የሶማሌው ሕዝብ፣ የኦጋዴኑ ሕዝብ የእኔ መንግሥት የሚል ስሜት አሁንም ያለው አይመስለኝም። ምክንያቱም መንግሥት የራስ የሚሆነው ስለ ራስህ ሲያስብ ነው። ከአጤ ቴዎድሮስ፣ ከአጤ ምንሊክ፣ ከአጤ ኃይለ ሥላሴ፣ ከኮሎኔል መንግሥቱ እና አቶ መለስ ዜናዊ እስከ ዛሬ ድረስ የሶማሌ ሕዝብ ምን ተደረገለት? ምንስ ይደረግ ነበር? የሶማሌ ሕዝብ በፌደራል መንግሥት ምን ያህል ተሳትፎ ተሰጣቸው? ወይም ምን ያህል ጥቅም አገኙ? እንዴትስ ነው የሚታዩት? ዛሬ እኮ የኢትዮጵያን ብር እና የኢትዮጵያን መንግሥት የማያውቁ ሰዎች በክልላችን ውስጥ አሉ። ይሄ ምን ይነግርሃል? ለምን? በምንድን ነው የሚገበያዩት ታዲያ? ለምን? መንግሥት ስላልደረሳቸው ነዋ። የሶማሌ ሕዝብ ወታደር ተልኮ፣ ወታደር ሲጨፈጭፋቸውና ሲገድላቸው ነው የሚያውቁት። ይህን ነገር መቀየር ያለብን እኛ ሳንሆን የኢትዮጵያ መንግሥትና መሪዎች ናቸው። እኔ ልንገርህ ለምሳሌ…በቅርቡ በፌደራል የተዘጋጀ ውይይት ላይ በቢሾፍቱ ተሳትፌ አንድ ሰው ምን ብሎ ጠራኝ መሰለህ። በውይይት ላይ ነው የምልህ…አንድ ሰው ""ወንድሜ ሶማሌው እንደገለፀው"" ይለኛል። ተመልከት እንግዲህ! ምንድነው ችግሩ ታዲያ፣ አልገባኝም? እኔ በማንነቴ እኮራለሁ ችግር የለብኝም። ግን ለምሳሌ ሌላው ተሳታፊ የኦሮሞው ወንድሜ፣ የሃዲያው፣ የጉራጌው እየተባለ በብሔሩ ተሰይሞ ስሙን ከብሔሩ ጋር አያይዞ አልተነሳም። ወንድሜ ኦሮሞው፣ ወንድሜ ሃዲያው አልተባለም። እኔ ለምን ልዩ ሆንኩ? ይህ ምን ያሳይኻል? ይህንን መቀየር ያለብን ደግሞ ፖለቲከኞች፣ ምሁራንና መሪዎች ናቸው። ይህ ልዩነት ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ ያለ ነው። እንደ ሁለተኛ ዜጋ ነው የሚያዩን። ፖለቲከኞች የሶማሌን ሕዝብ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አያስቡትም። ይህንን አለ የምትሉትን የተንሸዋረረ አመለካከት ለማቃናት እናንተስ እንደ አንድ ፓርቲ ምን ያህል ጥረት አድርጋችኋል ብዬ ለጥይቅዎ? ከጥንት እስከ ዛሬ ኢትዮጵያዊ መሆናችን አልቀረም። በድርጅት ብቻ ሳይሆን በሶማሌ ባለሥልጣናት እንደ ሶማሌ ብሔረሰብ ተወያይተው በመሆኑም ድርሻችን ምን ያህል መሆን እንዳለበት መወያየት አለብን። ትልቁ ሚና መጫወት የነበረባቸው በሥልጣን ላይ ያሉ የሶማሌ ባለሥልጣናት ነበሩ። ምን እንዳጡ፣ ምን እንደሚያንሳቸው መጠየቅ ነበረባቸው። እኛ እንደዚህ ብለን ስንጠይቃቸው እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ ነው የሚያዩን። በመሆኑም ለዚህ ከፍ ያለ ሚና መጫወት ያለባቸው በሶማሌ ክልል ያሉ ባለሥልጣናት ነበሩ። እኛ ተወያይተን ምን ማድረግ እንዳለብን ለመወሰን እንደ የቤት ሥራ እናስብበታለን። ድርጅታችንም ያስብበታል። በዚች አገር ኢትዮጵያ ውስጥ እስካለን ድረስ የ���ርሻችንን ማግኘት አለብን። የድርሻችንን መጫዎች እና የድርሻችንን መካፈል አለብን የሚል እምነት ነው ያለን። በአሁኗ ኢትዮጵያ ውስጥ አፋሩም፣ ሐረሪውም ፣ ሶማሌውም፣ ደቡቡም . . . እኔ ተገፍቻለሁ፤ እኔ እንደ ኢትዮጵያ አልቆጠርም እኔ ሁለተኛ ዜጋ ነኝ እያለ ነው። ይህ የስሜት መጎዳት ሁሉም ሕዝብ ላይ እንደሆነ ይታወቃል። ሁሉም አኩራፊ ከሆነ እንዴት ነው ኢትዮጵያን መጠበቅና ወደፊት ማራመድ የሚቻለው? እኔ ተጎድቻለሁ የሚለው ሕዝብስ ወደ መሀል መምጣትና የድርሻውን መወጣት የለበትም ወይ? ይህ ስሜት የማይሰማውስ ብሔር አለ ወይ ኦሮሞው፣ ወላይታው፣ አማራው፣ ሲዳማው . . . በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ያነሳኸው። በዓለም ላይ እኔ ነኝ ጎጂው፣ እኔ ነኝ በዳዩ፣ እኔ ነኝ አጥፊው የሚል ሰው የለም። ጎጂውም ተጎጂውም እንደዛ ነው የሚቀጥሉት። ባለፉት ሥርዓቶች ምን ዓይነት ችግሮች ነበሩ ብለን እንደ አንድ አገር ዜጋ ተወያይተን፣ ስህተታችንን ተጠያይቀን፤ እርቅ ተቀብለን፤ ወደፊት ምን ይሻለናል? ማለት አለብን ብዬ አንስቻለሁ። ነገሩ የአዞ እንባ እንዳይሆን፤ ማን ነው ይህን የሚያመጣው? ሥርዓቶቹ ናቸው። በመለስ ዜናዊ አስተዳደር የህወሓት፣ የትግራይ ጊዜ ይባላል። በደርግም ጊዜ የአማራው ጊዜ ይባላል። እነርሱም ግን ተበድለናል እያሉ ነው። ስለዚህ ቆሻሻችንን ከመቆፈር አሁን ምን ማድረግ አለብን? የሚለው ላይ መምጣት ያስፈልጋል። መጀመሪያ ይቅርታ መጠያየቅ፣ ሕዝብን ማስተማር፣ መቻቻልና፥ አንድ ሰው ተበድያለሁ ካለ ይቅርታ ማለት ያስፈልጋል። አሁን ባለችው ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትና ሥነ ሥርዓት ተከባብረን እየተጓዝን፤ ጥያቄዎች ካሉ በሕጋዊ መሠረት እንዲፈቱ፣ ማንኛውም የወደፊት ዕጣ በሕጋዊ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ነው የማስበው። እኛም እንደዛ ዓይነት አቋም ነው ያለን። ይቅርታ መጠያየቅ ላይ ብዙዎች ጥያቄ የላቸውም። ጥያቄው ይቅርታ የሚጠይቀው ማን ነው? የሚጠየቀውስ ማን ነው? አጥፊው ማነው? ተጎጂው ማነው? የሚለው ነው። የደርግ መንግሥት ብለዋል ደርግ የትኛውን ብሔር ነው የሚወክለው? ከዚያ በፊት ያሉ አስተዳደርና መንግሥታትን ስንቆጥር የትኛውን ብሔር ነው የምናነሳው? የመሪውን ብሔር ነው የምናነሳው? የወከሉት ሕዝብስ ራሱ ሲበደል አልነበር ወይ? እውነት ብለሃል። በተወሰነ መልኩ ካነሳኸው ነጥብ ጋር እስማማለሁ። ምክንያቱም በሥልጣን ላይ የነበረ ሰው ወይም ሰዎች ናቸው ሥርዓቱን ያጠፉት ይባላል። እውነት ነው የአማራ ሕዝብ ተሰብስቦ የሶማሌን ሕዝብ እንበድል አላለም። የትግራይም ሕዝብ እንደዚያው ተነስቶ የሶማሌ ሕዝብ ወይም ሌላውን እንበድል ብሎ አልተነሳም። ግን በመለስ ዜናዊ ጊዜ አራት ድርጅቶች ነበሩ። በኢህአዴግ ሥር የተሰበሰቡ ድርጅቶች። ነገረ ግን ብዙ ጊዜ ሰው ሲናገር በህወሓት የተመራው መንግሥት ነው የሚለው? በህወሓት እነማን ነበሩ ሲባል ትግራዮች ነበሩ እንላለን። በደርግ ጊዜም እነማን ነበሩ ሲባል የአማራው ነበሩ ይባላል። ያው በተወሰነ ደረጃ ካንተ ጋር እስማማለሁ ምክንያቱም ሥርዓቱ ነበር አጥፊው። በተወሰነ ደረጃ ደግሞ ከሥርዓቱ በስተጀርባ የትኛው ብሔር ነበረ? አፍሪካዊያን እኮ ብሔርተኞች ነን ሁላችንም። ይህንን መካድ አንችልም። ኬንያ ብትሄድ ተመሳሳይ ነገር ነው ያለው። ኬንያ ብታነሳ የኪኩዩ መንግሥት ነው የምትለው። እዚህም እንደዛ ዓይነት ነገር አለ። እና መካድ የለብንም፡፡ ይህን መቀበል አለብን ብዬ አስባለሁ። ከአራት ዓመታት በፊት ሊቀመንበራች አቶ አብዱራህማን መኽዲ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ""በመቶ ዓመት ውስጥ ኦጋዴን ውስጥ አንድ ሃይስኩልና አንድ ሆስፒታል ነው ያለን። ሴቶቻችን ሊወልዱ ሲሉ ወ��ም ሲታመሙ ሞቃዲሹ ነበር የሚሄዱት"" ብለዋል። በአንጻሩ ሶማሌ በተለይም ሰፊ ድጋፍ ባላችሁ ኦጋዴን በጋዝ ሃብት ትልቅ ተስፋ የተጣለበትና ትልቅ ሃብት ያለው አካባቢ ነው። አሁን ሕዝባችሁ በልማት እየተጠቀመ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? በዚያ አካባቢ ባለው እንቅስቃሴ ተስፋ ይታያችኋል? ተስፋ አለን። እንደ እንድ ሙስሊም በቁርዓን ላይ (ላ ታቅናጡ ቢራሕማቲላህ) ""በፈጣሪ ፀጋና ሲሳይ ተስፋ አትቁረጡ"" የሚል አንቀጽ አለ። ሁልጊዜም ተስፋ አለን። ምንም እንኳ ብንተችም አሁን ያለው የሶማሌ አስተዳደር በመጠኑ እያደረገ ነው። ጥሩ ነው። ትምህርት ቤቶች በቁጥር አነስተኛ ቢሆኑም በመጠኑ እየተሠሩ ነው፤ ከዚህ በላይ መሆን ነበረበት ማለታችን ባይቀርም ማለቴ ነው። ይህ ማለት ግን እንዳትሳሳት። አሁንም በእሳት ብርሃን (በኩራዝ ብርሃን) የሚወልዱ የሶማሌ እናቶች አሉ። ከ60 በመቶ በላይ የሶማሌ ሴቶች አሁንም እንደዚያው እየወለዱ ነው ያሉት። ጥራታቸው ዝቅተኛ ቢሆንም ትምህርት ቤቶች አሉ። ጥራታቸው በጣም ዝቅተኛ ቢሆኑም ሆስፒታሎችም ክሊኒኮችም በመጠኑ አሉ። እየተሠሩም ነው። ወደፊትም እንዲሠራ፣ እኛም ካሸነፍን ቅድሚያ ሰጥተን የምንሠራው ይህንን ነው። ሌላም ቢያሸንፍ መሠረታዊ የሆኑት እነዚህ ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለበት እናምናለን። የጋዝ ሃብቱ ላይ የምታነሱት የተለየ ጥያቄ አለ? አንድ የሶማሌ ተረት አለ። ""Dhariba ninkii u dhow baa dhuunigiisa leh"" ጭብጡ ምንድነው? ""ምግብ ሲበስል ለቀረበው ሰው ነው ቅድሚያ መሰጠት ያለበት"" የሚል አባባል ነው። የሶማሌው ሕዝብ ከጋዝና ነዳጅ ንብረቱ እንደዚህ ሩቅ መሆን የለበትም። የተሰጠው ድርሻም በቂ አይደለም ብለን እናምናለን። ከዚያ በላይ ነው ማግኘት ያለባቸው ብለን እናምናለን። በፌደራል መንግሥት ያላቸው ድርሻም በቂ አይደለም እንላለን። የፌደራል ሃብትም የሚደርሳቸው ከዚያ በላይ ማግኘት አለባቸው ብለን እናምናለን። አቶ አብዱራሕማን እንዳሉት ሕዝባችን ድሮም በጫካ ያለ ሐኪምና መድኃኒት ሲሞት እንደነበረው አሁንም እየሞተ ነው ያለው። ይህ ግን በእኛም ይሁን በሌላ እንደዚህ ሆኖ መቀጠል የለበትም ብለን እናምናለን። እናንተ ጫካ በነበራችሁበት ዘመን የሶማሌ ሕዝብ በቀድሞ የሶማሌ አስተዳዳሪ አቶ አብዲ ኢሌ ቁም ስቅሉን ሲያይ እንደነበረው እናንተም ፍዳውን ስታበሉት ነበር። አሁን አቶ ሙስጠፌ ከመጡ ወዲህ ግን ክልሉ ከሌሎች ክልሎች አንጻር ብዙም ኮሽታ የሌለበት፣ ሰላም ያለበት እንደሆነ ነው የምናየው፤ ፕሬዝዳንት ሙስጠፌም በዚህ የሚሞካሹ ናቸው። እናንተ እንዴት ነው የምትገመግሙት? አቶ ሙስጠፌ ከመጣ ሰላም መጣ ከማለት እናንተ ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ከፈረማችሁ በኋላ ሰላም መጣ ብትሉ ይመረጣል ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም አቶ ሙስጠፌ እኛ አዲስ አበባ እያለን፤ እኛ የሰላም አቅጣጫ ከመንግሥት ጋር ከተስማማን በኋላ ነው የተሾሙት። ሰላም በአቶ ሙስጠፌ አሊያም በብልጽግና ፓርቲ ሳይሆን፤ በእኛና በኢህአዴግ ነው የተፈፀመው። ሰላም በኦብነግ ነው የመጣው፤ ሰላም በእኛ ውሳኔ ነው የመጣው ብለን እናምናለን። ምክንያቱም ከመንግሥት ጋር ስንፋለም ነበር። እኛ እስከተፋለምን ድረስ 'እነሱን ሕዝብ ይደግፋቸዋል' በሚል ሕዝብ ሲጨፈጭፉ ከእኛም ጋር ሲዋጉ ነበር። አቶ ሙስጠፌ በመሀል ገብቶ ነው እንጂ በእርሱ ሰላም አልመጣም። በእኛ ነው ሰላም የመጣው። አሁንም በእኛ ካልሆነ በሰላም አይቆይም ነበር። ምክንያቱም ድርጊታቸው፣ ጸባያቸው፣ አነጋገራቸው እና ሁሉ ነገራቸው ወደ ሰላማዊ የሚወስደን አይደለም ብዬ አምናለሁ። ሰላም በእኛ ነው የመጣው፤ በእኛ ነው የተመሠረተው። አሁንም በእኛ ነው ያለው። ነገር ግን ሰላ��� ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነጻጸር ጥሩ ነው። የሕዝባችን ውሳኔ ነው። ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁለተኛ ዜጋ ሆነው በያሉበት ቦታ እየተገደሉ ነው። ሶማሌው የሰላምንም የጦርነትንም ዋጋ ስለሚያውቅ፤ እኛ ስለወሰንን ነው ዛሬ ሰላም የሆነው። ዛሬ የሰላም ቀን ነው። የፈለግነውን በሰላም እንፈልግ ከሌሎች ጋር በሰላም እንወያይ፣ በሰላም እንሂድ ብለን የኦብነግ ውሳኔ ስለሆነ ነው በዚያ እየሄድን ያለው። አሁንም እንቀጥላለን። ሰላም ለሕዝባችን ለአፍሪካ ቀንድም እንዲወርድ አላህን እንጠይቃለን። እናንተ ጫካ በነበራችሁ ጊዜ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ፤ አንዳንድ የፈጸማችኋቸው ጥቃቶች አሉ። ግንቦት 2007 እአአ 65 ኢትዮጵያያዊ የጉልበት ሠራተኞች እና ዘጠኝ ቻይናዊያን በማዕድን ቁፋሮ ላይ ሳሉ አቦሌ ላይ ጥቃት አድርሳችሁ ገድላችኋቸዋል። ንጹሃን ሞተዋል። ጅግጅጋም ላይ እንደዚሁ የሰዎች ሕይወት አልፏል። ይህም በእናንተ የሆነ ነው። አሁን ለሰላም ትግል ከመጣችሁ በኋላ ይቅርታ መጠየቅ ያለባችሁ አይመስላችሁም? ሁለት ዝሆኖች ሲጣሉ ብዙ ሳር ይወድማል ይባላል። የትኛውም አገር ጦርነት ሲከሰት የሰላማዊ ሰው ሕይወት ያልፋል። ያለ ነገር ነው። እኛ ዓላማችን ሰላማዊ ሰዎችን እናጥቃ ብለን አልነበረም። ቻይናውያን በማን ጥቃት ነው የሞቱት? ማንን ጠይቀው ነው የኦጋዴን ግዛት የገቡት? ከመግባታቸው በፊትና ከገቡም በኋላ አስጠንቅቀናቸው ሰላም አለመሆኑን እየነገርናቸው 'እምቢ' ብለው ስለገቡ እኛ የመንግሥት ሠራዊትን ዒላማ ስናደርግ ቻይናውያኑ ስለሞቱ መንግሥት ነው ይቅርታ መጠየቅ ያለበት። አምጪው ነው ይቅርታ መጠየቅ ያለበት። ግን ገዳዮቹ እናንተ ናችሁ እኮ? የተገደሉት በእናንንተ አይደለም እንዴ? በሁለቱም በኩል ጥይት ተተኩሷል። በማን ጥይት እንደሞቱ አይታወቅም። በማን ጥይት እንደተገደሉ ማን ይናገራል? በእኛ ብቻ የሚላከክ አይደለም። የእኛ እጅ የለበትም ብለን አንክድም። ነገር ግን ማን ነው ያመጣቸው? ሁለተኛ ደግሞ በማን ኃላፊነት ነው የመጡት? በእኛ ኃላፊነት አልመጡም። እኛ እንደውም ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ነበር 'እምቢ' አሉ። በመሆኑም እኛ ይቅርታ የምንጠይቅበት ሰበብ የለም። በእኛ ፍቃድና ኃላፊነት አልመጡም፡፡ ጽፈንላቸው ይቅርባችሁ ብለን ነው እምቢ ያሉት። አገራችንና ሃብታችንን ሊወስዱ ነበር የገቡት። ስለቻይናውያኑን ይህን ካሉ ኢትዮጵያውያን የጉልበት ሠራተኞች ደም ፈሶ ይቅርታ ለመጠየቅ ለምን ጉልበት ያንሳችኋል? በዚህ ጦርነት ስንት ኢትዮጵያዊያን ሞተዋል? በዚህ ጦርነት ኃላፊው ማን ነበር? እኛ በሰላም ሕዝባችንን እየመራን በነበረበት ሰዓት አመጹን ቀስቅሶ ሕዝብ የጨረሰ ማን ነው? ጦርነቱን ያነሳሳ አካል ነው ለሁሉም ይቅርታ መጠየቅ ያለበት። ከእኛ ጦር ለሞቱት፣ ከመንግሥት ጦር ለሞቱት፣ ለንፁሃን ዜጎች ሁሉ ኃላፊነቱን መወሰድ ያለበት የኢትዮጵያ መንግሥት፤ የኢትዮጵያ መሪዎች ናቸው። ምክንያቱም በሰላም እንዲያወያየንና ችግራችን በሰላም እንዲፈታ ያልሄድንበት የለም። ኢትዮጵያውያንን ከዚህም ከዚያም የሚያዋጉት ኃላፊነት የሚወስዱት አነሱ ናቸው ብለን እናምናለን። ፓርቲያችሁ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ለብቻው ተገናኝቶ ያውቃል? ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኛችሁት መቼ ነበር? ምን ተወያያችሁ? ይህን ቀን ነው ብዬ ልነግርህ አልችልም። ግን ከስድስት ወር በፊት አንዴ በቤተ መንግሥት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ከአቶ አብዱራህማን ጋር ነበር የተወያዩት፤ እስከማውቀው ድረስ። ስለ አገራዊ ሁኔታ፣ ስለመጪው ምርጫ፣ ስለሠላም፣ ስለ ዲሞክራሲ እና ስለተለያዩ ጉዳዮች ነበር ያነሱት። በጥሩ ሁኔታ ነበር የተወያዩት። ይህን ያህል ነ��� የማውቀው። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ግንቦት ወር ላይ ይካሄዳል። እናንተም ትሳተፋላችሁ። በቅርቡ ጥቃት እየፈፀመብን ነው።አባላት ታስረውብኛል። ዶሎ፣ ቸረረ፣ ሸበሌና ቆራሄ ዞኖች ሰብዓዊ ጥሰት አለ። እየተንገላቱብኝ ነው ብላችኋል። አሁንም ችግር አለ ማለት ነው? ይህ ችግርስ ከምርጫ እንድትወጡ ሊያደርጋችሁ ይችላል? በዚህ ላይ ትኩረት ማድረግ እፈልጋለሁ። ዛሬ ከሚደርሱን መረጃዎችና ከምናያቸው ነገሮች በምርጫው እንደምንሳተፍ ሙሉ ቃል መስጠት አልችልም። ጫፍ ላይ የደረስን ይመስለኛል። ነገሮች እየተደማመሩ ነው። ለምሳሌ አሁን ላይ የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ነው። የመራጮች ምዝገባ ጊዜው ተራዝሟል። በቴክኒካል ችግር ሊሆን ይችላል። ሆነ ተብሎም ሊሆን ይችላል። ዛሬ ከሚደርሱን መረጃዎች ነገሮች እየተባባሱ ነው። ለምሳሌ ለመራጮች የሚሰጠው ካርድ ለሶማሌ ክልል ምን ያህል ካርድ እንደሚላክ የምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎቹ ማሳወቅ አለበት። ወደ ምርጫ ጣቢያዎቹ የሚላከውን ካርድ ተወዳዳሪዎች ማወቅ አለባቸው። በምርጫው ምዝገባ ጊዜም ፓርቲዎቹ ወይም ተወዳዳሪዎቹ ታዛቢ ወይም ወኪል መስጠት አለባቸው፤ ነገር ግን ዝም ብለው በተለያዩ ቦታዎች ሳጥኖችን አራገፉ። ሳጥኑ ደግሞ ክፍት ነው። እስካሁን ለእኛ የተሰጠን ካርድ ቁጥር የለም። እና የተያያዘ ነገር እየመጣ ነው። ብዙ ምልክቶች እየታዩ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት ድርጅቱ ተሰብስቦ ይወያይበታል። ሠራተኞቹም መጀመሪያ ሲቀጠሩ ከዘመድ፣ ከመንግሥት ሠራተኛ ሲሆኑ መቶ በመቶ በሶማሌ ክልል ሠራተኞች የብልጽግና ተከፋይ ናቸው። 99 በመቶ የመንግሥት ተከፋይ ናቸው። በመሆኑም በቀላሉ ለመንግሥት ሊገዙ ይችላሉ። በመሆኑም ምንም በሌለን መረጃ መቀጠል የምንችል አይመስለኝም። ሆን ተብሎ የተደረገ ነገርም ይመስላል። በተጨማሪም ብልጽግና በመንግሥት ሃብትና ንብረት እየተጠቀመ ነው ያለው። ሥልጣኑንም እየተጠቀመ ነው። ተወዳዳሪ ልናስመዘግብ አልቻልንም። እዚህ አዲስ አበባ ነው እያስመዘገብናቸው ያለው። ይህንን ስናመለክት እናስተካክላለን ሲሉን ነበር። ምንም የተስተካከለ ነገር የለም። የእኛ ተወዳዳሪዎች ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው። በመንግሥት መኪና ዘመቻ እያደረጉ ነው። ለምን ስንላቸው ደግሞ ታርጋ መፍታት ጀምረዋል። ስለዚህ ሁኔታው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ በምርጫው የምንሳተፍ አይመስለኝም። ምን ያህል ዕጩዎችን የት አስመዝግባችኋል? በሶማሌ ክልልም በሌላ የሶማሌ ማኅበረሰብ ባለባቸው አጎራባች ክልሎች እና አዲስ አበባ ለመወዳደር አስበን ነበር። ግን በተሳሳተ በዕጩዎቻችን የተሳሳተ አረዳድ እና ቴክኒካል ችግር ምክንያት አዲስ አበባ መመዝገብ አልቻሉም። ድሬዳዋ እንዳናስመዘግብ ደግሞ በብልፅግና ተከልክለናል። ተከልክለናል ሲሉ ምንድን ነው ማስረጃዎት? የእኛ ዕጩዎች እንዳይመዘገቡ ተከልክለዋል። በምርጫ ቢሮ ኃላፊዎች አትመዘገቡም ተብለዋል። በገርባ ኢሴ፣ በፊቲ፣ ሃደጋላ ያሉ ዕጩዎችም እንደዚሁ ተብለው አስፈርመዋቸው ከሦስት ቀን እስራት በኋላ ተባረዋል። በሞያሌ፣ በካሱርቱ፣ በዞላአጦ ምርጫ ኮሚሽን ተገናኝተን ለምን አታስመዘግቡም ሲሉ፤ ኦብነግን እንዳናስመዘገብ በመንግሥት ታዘናል የሚል ምላሽ የሰጡ ነበሩ። ብዙ የተከለከልንባቸው ቦታዎች አሉ። እስካሁን 237 የክልል እና 15 ድሬዳዋ ላይ ከዚህ ላይ አምስቱ ዛቻና ማስፈራሪያ ስለደረሰባቸው ወጥተዋል። ከምርጫ ቦርድ ጋር በክልል ሆነ በፌደራል ደረጃ ይህን ያህል ለማስተጋባት ምን ያህል ርቀት ሄዳችኋል? የምርጫ ቦርድ አቅማቸው እስከሚፈቅድ ችግሩን ለመፍታት ሞክረው ነበር። መፍታት ያልቻሉትን ደግሞ አዲስ አበባ መጥተን እንድና���መዘገብ አድርገዋል። ለዚህም እናመሰግናቸዋለን። ይህንን ችግር እንዲፈታ ወ/ሪት ብርቱካን ከክልል መንግሥት ጋር እናገናኛችኋለን ጂግጅጋ እመጣለሁ ብላን ነበር እስካሁን እየጠበቅናት ነው። ችግሩ ይፈታል ብለን እናምናለን። አሁንም ከምርጫ እንቀራለን ማለት አይደለም። ችግሩ ከተፈታ ምርጫ እንካፈላለን፤ ካልተፈታ ግን ውጤቱ መጥፎ ነው። ምርጫ ትሳተፋላችሁ ብለን ተስፋ እናድርግና እናንተ በክልላችሁ አብላጫ ድምፅ የማግኘት ዕድላችሁ ምን ያህል ነው? የሕዝብ ድጋፋችሁን ስትገመግሙት? ከፍተኛ ድጋፍ ያላችሁ በኦጋዴን ጎሳ ነው። የምትወክሉትም ኦጋዴን ጎሳን ብቻ ነው ይሏችኋል። ከኦጋዴን ጎሳ ውጭ ያሉትንስ ትወክላላችሁ? ይቀበሏችኋል? [ሳቅ] እኛ እንደ ጎሳ አይደለንም። እንደዚያ ዓይነት ቃላት የሚናገሩ አስተሳሰባቸው ጠባብ ነው ብለን ነው የምናምነው። እኛ የታገልነው፤ አሁንም የምንታገልለት ለሶማሌው ሕዝብ ነው። በሞያሌ፣ ነገሌ፣ ፊልቱ፣ በጎዱ ኡኩር፣ በጂግጅጋ፣ በድሬዳዋ ባለው የሶማሌ ሕዝበ ተወዳድረናል፤ ደግሞም እንወዳደራለን። ከፍተኛ የማሸነፍ ተስፋ ነው ያለን፤ ነገሩ የምርም በሕዝብ ድምፅ የሚወሰን ከሆነ። እንደዚያ ግን አይመስልም። ለምን በለኝ። ነገሩ በሕዝብ ድምጽ የሚወሰን ከሆነ ለምንድነው ዕጩ እንዳናመዘግብ የሚከለክሉን። ነገሩ በሕዝብ ድምጽ የሚወሰን ከሆነ ለምንድነው አባሎቻችን የሚታሰሩት? እኛ በሕዝብ ልብ ውስጥ ያለን ፓርቲ ነን ብለን እናምናለን። አንድ ሰውም አላሰርንም፤ አንድም ሰውም አላባረርንም በሕዝብ ምርጫ ስለምናምን። ስለዚህ ምርጫው ካልተጭበረበረ 89 በመቶ በላይ ድምፅ እናገኛለን ብለን እናስባለን። ከተጭበረበረ ግን መቶ በመቶ አሸንፈናል ሲል ነበር አቶ መለስ፤ አሁንም እንደዚያ ሊሉን ይችላሉ። እንደው በምርጫው ብትሸነፉ የምርጫውን ውጤት ተቀብሎ ወደፊት ደግሞ ለተሻለ ውጤት ለመሄድ ያላችሁ ዝግጁነት ምን ያህል ነው? መቶ በመቶ ዝግጁ ነን! ምክንያቱም እኛ ከጫካ ትግል መጥተን እንደ ጋዜጠኛ ምን ያህል ሕዝብ አቀባባል እንዳደረገልን ብታይ ጥሩ ነበር፤ አሁንም በቀብሪደሃር፣ በዋርዴር፣ በነገሌ ያለው እንቅስቃሴ ብታይ ጥሩ ነበር። ሕዝባችን እንደሚመርጠን እናምናለን። እንደ ፓርቲ ከተሸነፍንም እንቀበላለን። ከአሸናፊው ጋር አብረን እንሠራለን። ለሕዝብ ልማት ትግላችንን እንቀጥላለን። ለመጪው ምርጫ እንዘጋጃለን። ይህ የሚሆነው ግን ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ሲካሄድ ብቻ ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ግን ""አሸንፈናል ኑ ፈርሙልን"" ቢሉ ግን ""አጭበርብራችኋል እንጂ አላሸነፋችሁም"" ነው የምንላቸው። ዘ ጋርዲያን በሶማሌ ክልል ጋዝ በማውጣት ላይ የተሰማሩ እንደ ፖሊ እና ሲጂኤል ያሉ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ሳቢያ የተፈጠረ አካባቢያዊ ብክለትን ተከትሎ በርካቶች እየሞቱ እንደሆነ ዘግቧል። እአአ በ2014 እስከ 2ሺህ 400 ሰዎች ሞተዋል ብሏል። ይህንን የሚመለከተው የፌደራል መንግሥትን ቢሆንም ስለዚህ ጉዳይ ፓርቲያችሁ ያውቃል? ፌደራል መንግሥቱ ትኩረት እንዲሰጥ ያደረጋችሁት እንቅስቃሴ አለ? ድርጅታችን ይህንን ያውቃል። ችግር እንዳለ እናውቃለን። እኔ ከቆራሂ ዞን ነኝ። ዞኔ ስለሆነ ነገሩን በጥልቀት አውቃለሁ። ዶዶይን፣ ሽላቦ እና ሌሎች ቦታዎች ሄጃለሁ። ሰው በማይታወቅ በሽታ እየሞተ ነው። ሆዳቸው አብጦ በአፍንጫቸው ደም ፈሶ ይሞታሉ። ሐኪም ቤት ሲሄዱም 'ምንም ያገኘነው ነገር የለም ነው' የሚሉት ሐኪሞቹ። እንስሳትም እየሞቱ ነው። የፌደራል መንግሥት መፍትሔ ማድረግ አለበት። ኩባንያዎቹ ምን ዓይነት እንቅስቀሴ እያደረጉ እንደሆነ ማወቅ አለበት። ምን ተበላሽቶ እንደሄደ ማወቅ አለበት። በዓለም ነዳጅ ይወጣል፣ ናፍ��� ይወጣል፣ ቤንዚል ይወጣል። ነገር ግን አካባቢን እንዳይበከል የሚያስችሉ መደረግ ያለባቸው ቅድመ ዝግጅቶች አሟልቷል ወይ የሚለውን ፌደራል መንግሥት የራሱን ኃላፊነት መወጣት አለበት። በተጨማሪም የሶማሌ ክልል መንግሥት ኃላፊነት መወጣት አለበት ብለን እናምናለን። ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይተናል፤ ግን ምንም ግብረ መልስ አላገኘንም። አሁንም እንጽፋለን። ሕዝብ ምንም ማድረግ አይችልም። አንድ ግመል እየጠበቀ ያለ እረኛ ግመሉ ስትሞት ቤተሰቡ ሲሞት ምን ማድረግ ይችላል? ይህ ኃላፊነት የፌደራል መንግሥትና የክልሉ መንግሥት ነው። አሁንም ጥያቄያችንን እንቀጥላል። በቀድሞው አስተዳደር አብዲ ኢሌ ብዙ ጥፋቶች ተፈፅመዋል ከእናንተ ጋር በተያያዘ። የአቶ አብዲ ኢሌን የፍርድ ሂደት ተከታትላችሁ ታውቃለችሁ? ለደረሰባችሁ ጥቃት፣ በደልና ሕዝባችሁ ላይ ለደረሰ ጥፋት ራሳችሁን ችላችሁ ክስ የመመስረት ሐሳብስ አላችሁ? እኛ በአብዲ ኢሌም ሆነ ከእሱ በፊት በነበሩት፣ ከእርሱ ጋር የነበሩትን ጠቅላይ ሚኒስትሮችና የኢህአዴግ መሪዎች በአፍሪካም በዓለም ፍርድ ቤትም ከሰናል። በሶማሌም በሌሎችም ሕዝቦች ላይ ባደረሱት በደል ተጠያቂ እንዲሆኑ ከሰናል። አሁንም እንከታተላለን። ነገር ግን ከሚያሳዝኑን እና ከሚያናድዱን ነገሮች አብዱ ኢሌ እና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በፍርድ ቤት የሚጠየቁት በሶማሌ ሕዝብ ላይ ባደረሱት በደል እና ግፍ ሳይሆን እአአ በነሐሴ 4 በጂግጅጋ የሶማሌ ተወላጅ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ባደረሱት በደል እና በቤተክርስቲያን መቃጠል ብቻ ነው። ይህ ትክክል አይደለም ማለቴ ሳይሆን ከዚያ በፊት ሲያደርግ በነበረውም ጭምር ሊጠየቅ ይገባል። አሁንም የታሰሩትና ያሉት የህወሓት አመራሮች በሶማሌ ሕዝብ ላይ ባደረሱት ግፍና በደል መጠየቅ አለባቸው ብለን እናምናለን። እንከታተላለን። ፍትሕ እስከምናገኝ ድረስ አይደክመንም፤ አይሰለቸንም። የመጨረሻው ጥያቄ የሚሆነው፣ አሁኗን ኢትዮጵያን ድርጅታችሁ እንዴት ነው የሚገመግማት? አገሪቷ ለመፍረስ ቋፍ ላይ ነው ያላችው ከሚለው ጀምሮ አገሪቷ የተሻለ የአንድነት ተስፋ የሚጣልበት ጊዜ ነው የሚሉም አሉ። በብዙ ክልሎች የሚሰማው ዜና ደግሞ የሚረብሽ ነው። እናንተ ደግሞ ድምጻችሁም አይሰማም። ሌላ ቦታ በሚታዩት ነገሮች አይመለከተንም ብላችሁ ነው? በአገር ጉዳይ ለምን ዳር ያዛችሁ? ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው ያለችው። በዚህ ወቅት ገዥው ፓርቲ የሚጫወተው ሚና እጅግ ወሳኝ ነው ብዬ አምናለሁ። እናምናለን። የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ደግሞ እንዲሁ ከፍተኛ ሚና አለው። ይህች አገር እኛ እንደሚመስለን ለምርጫ ከመሮጥ ብሔራዊ መግባባት ያስፈልጋታል ብለን እናምናለን። ለምን? ትላልቅ ፓርቲዎች በዚህ ምርጫ አይሳተፉም ማለት ይቻላል። ለምን? አሁን አዲስ አበባ ነው ያለሁት። ለምርጫው ጥቂት ጊዜ ነው የሚቀረው። ግን ይህን አታይም። ዛሬ እንደከዚህ ቀደሙ የምርጫ ፖስተሮችና ምልክቶች አይታዩም። ሕዝብ ደንታ አይሰጥም ለምርጫ ማለት ነው። ለምን? ብለን መጠየቅ አለብን። በሶማሌና በአፋር ጦርነት አለ። በአማራና በኦሮሞ ሽኩቻ አለ። በትግራይም ያለው ይኸው ነው። ይህ ሁሉ ነገር እያለ፤ ብሔራዊ ውይይት ተደርጎ ሳንስማማ ወደ ምርጫ መሮጣችን ወደ ከፋ ሁኔታ ይወስደናል ብለን እናምናለን። በሁሉም ነገር ባንስማማ በአንድ ነገር ቢያንስ በምርጫ ሂደትና ተሳታፊነት እንኳን ብንስማማ ይመረጣል ብዬ አምናለሁ። እኔ በግሌ አገሪቷ በከፋ፣ በከፋ ሁኔታ ላይ ነው ያለችው ብዬ አምናለሁ። ስለ ነገ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ እርግጠኛ አይደሉም? አይደለሁም። እኔንጃ ወደየት እየሄድን እንደሆነ?" https://www.bbc.com/amharic/news-56795580 +sports ቦክሰኛው ማይክ ታይሰን አውሮፕላን ውስጥ ተሳፋሪን በቦክስ ዘረረ የቀድሞው ባለ ከባድ ሚዛን ሻምፒዮና ማይክ ታይሰን አውሮፕላን ውስጥ አንድን ተሳፋሪ በቦክስ ደብድቧል፡፡ የታይሰን ቃል አቀባይ እንዳለው ታይሰን ግለሰቡን በቦክስ ለመምታት የተገደደው የውሃ ላስቲክ ስለወረወረበት ነው፡፡ ከአውሮፕላኑ ውስጥ የተቀረጸ ተንቀሳቃሽ ምሥል ማይክ ታይሰን ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ ግለሰቡ በመሄድ ይህ ማንነቱ ለጊዜው ያልተለየን ግለሰብ በጡጫ ሲነርተው በከፊል ይታያል፡፡ ቃል አቀባዩ እንዳለው ታይሰን ለዚህ መጥፎ አጋጣሚ የተጋበዘው ተሳፋሪው በተደጋጋሚ ሳለስቸገረው ነው፡፡ ፖሊስ ከዚሁ ክስተት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ አንዱ ግለሰብ በሳንፍራንሲስኮ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ሕክምና እየተደረገለት ሲሆን ጉዳቱ ለሕይወቱ አስጊ አይደለም ተብሏል፡፡ ፖሊስ በትክክል ምን ተከስቶ እንደነበረ ከተጎጂዎች በቂ መረጃን እንዳላገኘ የሳንፍራንሲስኮ ፖሊስ ቃል አቀባይና ባልደረባ ተናግራለች፡፡ በዚህም የተነሳ ምርመራው እንደሚቀጥል፣ ነገር ግን ለጊዜው የተያዙት ሁለት ሰዎችም ከእስር እንደተለቀቁ ገልጻለች፡፡ ፖሊስ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በዚህ ክስተት ውስጥ ይኑሩበት አይኑሩበት ገና እርግጠኛ መሆን አልቻለም፡፡ ይህ የማይክ ታይሰን የአውሮፕላን የቡጢ ክስተት የተፈጠረው ረቡዕ ዕለት ሲሆን አውሮፕላኑ ከሳንፍራንሲስኮ ወደ ፍሎሪዳ ለመጓዝ ገና ደንበኞችን በማሳፈር ላይ ሳለ ነበር፡፡ ክስተቱን ያሳያል የተባለው ተንቀሳቃሽ ምሥል የተቆራረጠና ታሪኩን ለመረዳት በቂ መረጃን የማይሰጥ ሲሆን ሆኖም ግን ግለሰቡ የውሃ ላስቲክ በማይክ ታይሰን ላይ ሲወረውርበት አያሳይም፡፡ ቲኤምዜድ፣የዕውቅ ሰዎችን ጉዳይ በመዘገብ የሚታወቅ ሚዲያ፣ እንዳለው ታይሰን በቅድሚያ ከዚህ ጸብ ውስጥ ከገባው ግለሰብ ጋር ፎቶ ለመነሳት ፈቅዶ ነበር፡፡ ነገር ግን ግለሰቡ ታይሰንን ያልተገባ ነገር እየተናገረ ትዕግስቱን ተፈታትኖታል፡፡ ማይክ ታይሰንም ግለሰቡን ‹ተረጋጋ› ሲል አስቀድሞ መልካም ምክርን ሰጥቶት ነበር፡፡ ማይክ ታይሰን ግለሰቡን በቡጢ ከደበደበው በኋላ ሰዎችን ለመገላገል ሲሞክሩ በተንቀሳቃሽ ምሥሉ ይታያል፡፡ በመጨረሻ ምሥሉ የተደብዳቢው ግንባር ደም በደም ሆኖ ያሳያል፡፡ ማይክ ታይሰን ለእንደዚህ ዓይነት ክስተቶች ሲጋለጥ የመጀመርያው አይደለም፡፡ እንደ አውሮጳዊያኑ በ1992 ዓ/ም ሴት በመድፈር ተወንጅሎ 3 ዓመት ተፈርዶበት ነበር፡፡ በ1997 ዓ/ም ደግሞ የተጋጣሚውን ሆሊፊልድን ጆሮ በመዘንጠሉ ከቦክስ ለጊዜው ገለል እንዲል መደረጉ ይታወሳል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-61195175 +politics 'ለኤርትራ ነጻነት 30 ዓመት ተዋደቅን፤ ለ30 ዓመት ዲሞክራሲን ጠበቅን፤ አልመጣም' የቀድሞው የቢቢሲ ትግርኛ አርታኢ "ኤርትራ ነጻነቷን ካገኘች 30 ዓመት ደፈነች። የቀድሞው የቢቢሲ ትግርኛ አርታኢ የነበረው ሳሙኤል ገብረሕይወት ለነጻነቱ ነፍጥ አንግበው ከተዋደቁ ኤትራዊያን አንዱ ነበረ። ስለ ትግሉ እና እንደ ጉም ስለተነነው ኤርትራዊያን የነጻነትና ዲሞክራሲ ተስፋ እንዲሁም አገሪቱ እንዴት በአምባገነን እጅ ስር እንደወደቀች እንዲህ ይተርካሉ። ለሰላሳ ዓመታት ነፍጥ አንስተን ለነጻነት ተዋጋን፣ እያንዳንዱ ቀንና ሰዓት በጦርነት የሚያልፍ ነበር። ስቃይንና መስዋዕት መሆንን ለመድነው። አብዛኞቻችን ሁለት ወይም ለሦስት ጊዜ ቆስለናል። ይህ ብርቅ አይደለም። እንደነገሩ ታክመን ወደ ሌላ ጦርነት እንዘምት ነበር። በሰሜን ኤርትራ ቃሮራ ግንባርን እንዴት እንደታደግን ይገርመኛል። በደቡብ ኤርትራ ዱሜራን እንዴት እንደተከላከልን ይደንቀኛል። ምሽግ ለምሽግ እየተሳብን፣ እዚያው እያደርን፣ ተራራ እየቧጠጥን፣ ከሸለቆ ሸለቆ እየዘለልን…። ብቻ እኔ ከዕድለኞቹ እመደባለሁ። 65 ሺህ ጓዶቻችን በጦርነቱ ሞተዋል። የነጻነት ግንባሩን የተቀላቀልኩት በፈረንጆች 1982 ላይ ገና በ16 ዓመቴ ነበር። ስለነጻነት ተዋጊ ኤርትራዊያን ብዙ እሰማ ነበር። ቁምጣቸው፣ ረዥም ጸጉራቸው፣ የሚይዙት ኤኬ 47 ጠመንጃ …፣ ይህ ሁሉ ታሪካቸው ያጓጓኝ ነበር። በአራግ ሸለቆ ለጥቂት ወራት ስልጠና ተሰጠኝ። እንዴት ጥቃት መሰንዘር እንደምንችልና እንዴት ማፈግፈግ እንደሚቻል ተማርን። እንዴት ራሳችንን ከአካባቢው ጋር ማመሳሰል እንደምንችል፣ እንዴት መደበቅ እንደምንችል፣ እንዴት ቦምብ ፈቶ መግጠም፣ ነቅሎ መጣል እንደሚቻል፣ አርፒጂ መሣሪያ አጠቃቀምን ሁሉ ሰለጠንን። ስልጠናችን መጥፎ የሚባል አልነበረም። ጎን ለጎን ደግሞ የፖለቲካ ትምህርት እንደወስድ ነበር። ከዚህ መሀል እንዴት ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ማቋቋም እንደምንችል ጭምር ተምረናል። ከዚህ ስልጠና በኋላ በበርካታ ጦርነቶች ውስጥ ተሳትፊያለሁ። መደምደሚያው የነበረው በ1990 (እአአ) በምጽዋ ወደብ ላይ የተደረገው 'የፈንቅል ዘመቻ' ነበር። ያ ድል እጅግ ወሳኝ ነበር። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ከኤርትራ እንዲወጣም ያስገደደ ቁልፍ ወታደራዊ ድል ነበር። ያን ጊዜ ያለማቋረጥ ለ72 ሰዓታት ተዋግተናል። እጅግ ወሳኝ የነበረችውን ምጽዋን ለመያዝ ያልሆነው የለም ማለት ይቻላል። ከዚያ በኋላ ደግሞ ለመከላከል 100 ኪሎ ሜትር ምሽግ ቆፍረን ከአንድ ዓመት በላይ ቆይተናል። በዚህ ውጊያ ጭንቅላቴ ላይ እንዲሁም እጄ ላይ ቆስያለሁ። ከዚያ ሆስፒታል ታክሜ ዳንኩ። ታዲያ ወዲያውኑ ወደ ውጊያ ነበር የተመለስኩት። በ1980ዎቹ መጨረሻ ወደ ኪነትና ባሕል ክፍል ተዛወርኩ። የዚህ ክፍል ዋና ዓላማ ወታደሩን በሙዚቃና ድራማ ሞራሉን ከፍ ማድረግ፣ ማነሳሳት ነበር። በ1991 (እአአ) ከምጽዋ ቅርብ ርቀት በዳሕላክ ደሴት ላይ ነበርን። ዳሕላክ ሳለን ነበር በሕይወታችን እጅግ ጣፋጩን ዜና የሰማነው። ኤርትራ ነጻነቷን እንደተቀዳጀች ተነገረን። የፈንጠዚያ ቀናት በደስታ ሰክረን በጀልባ ወደ ምጽዋ ተጓዝን። እዚያ ስንደርስ ከባድ ተሸከርካሪ ላይ ተጭነን ወደ ዋና ከተማ አሥመራ ጉዞ ጀመርን። ጉዞው ሦስት ሰዓታትን የፈጀ ነበር። የኢትዮጵያ ሠራዊት ደቡባዊ ቀጠናን አለፍነው። ሰው የሚባል አልነበረም። የኢትዮጵያ ወታደሮች ጥለውት ሄደዋል። በአሥመራ ውስጥ ሕልም የሚመስል አውድ ነበር። ነዋሪዎች እኛን የነጻነት ታጋዮችን ለመቀበል ጨርቄን ማቄን ሳይሉ አደባባይ ወጥተው ነበር። በጓይላ ጭፈራ ራሳቸውን ስተው ነበር። ጎዳናው በሙሉ ሕዝብ ፈሶበት አስታውሳለሁ። ይህ በአሥመራ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ከተሞችና መንደሮችም የታየ ኩነት ነበር። ይህ ቀን ከመምጣቱ በፊት አሥመራ ሙሉ በሙሉ ጭንቅ ውስጥ ነበረች። አየር ማረፊያው በተከታታይ በተኩስ ሲናጥ ነበር የሰነበተው። ጥብቅ ሰዓት እላፊም ታውጆ ነበር። ልክ በግንቦት 24 (እአአ) ሁሉ ነገር ተለወጠ። እናቶች የጣዱትን ጀበና ትተው፣ የለኮሱትን ሞጎጎ እንጀራ መጋገሪያቸውን ጥለው፣ የቡና ሥነ ሥርዓታቸውን ጣጥለው ግልብጥ ብለው አደባባይ ወጥተው ነበር። ይህም እኛን ታጋዮችን ለመቀበል ነበር። ብዙ ኤርትራውያን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ይታዩ ነበር። ወጣቶች እየዘለሉ ታንክ ላይ ይወጡ እንደነበረና የዘንባባ ዝንጣፊ እያውለበለቡ ሲቀበሉንም አስታውሳለሁ። ይህ ፈንጠዝያ ለቀናት ቀጠለ። ምሽቶቹም ደማቅ ነበሩ። በእርግጥ በዚህ ደማቅ ስሜት መሀል ጭንቅም ነበረ። ወላጆች የልጆቻቸውን ፎቶ ይዘው በመውጣት በሕይወት ይኖሩ እንደ�� ይጠይቁ ነበር። ""ልጄ ተርፎልኝ ይሆን? ልጄ ሞታ ይሆን?"" የሚል የማያባራ ጥያቄ። በኛ ምድብ ገድለና አባየይ የሚባሉ ጓዶች ነበሩ። ሁለቱ ጓዶች ፊት ለፊት በመኪና ላይ ተጭነው ቤተሰባቸውን ባዩ ጊዜ የሆኑት ትዝ ይለኛል፤ ሲጮኹ፣ ሲስቁ፣ የደስታ እንባ ሲያነቡ። የገድለ አባት ""ልጄን አገኘሁት! ልጄን አገኘሁት!"" እያለ ወደኛ መኪና ሲሮጥ ትዝ ይለኛል። አባየይ ደግሞ ሴት ታጋይ ነበረች። ጋቢና ነበር የተቀመጠችው። የባለቤቷን እናት ስታይ ጊዜ ድንገት እየሄደ ከነበረ መኪና ዘላ ልትወርድና ራሷን ለከፍተኛ አደጋ ልታጋልጥ ስትል ነበር በተአምር የዳነችው። በኋላ ላይ በአዛዦቻችን ፈቃድ ተሰጠን፤ ፈቃዱ ወጥተን ቤተሰባችንን እንድናገኝ ነበር። በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ቤተሰብን ማግኘት ቀልድ አልነበረም። ለእነዚያ ሁሉ ዓመታት የተለዩትን ማግኘት እንዲህ የዋዛ አልነበረም። ሆኖም ብዙዎቻችን ዘመድ አላጣንም። በዚያ ቅጽበት ሁላችንም እናስብ የነበረው ከዚህ ሁሉ በኋላ ኤርትራ በልጽጋ፣ ችግር ከኤርትራ ምድር ጠፍቶ እያንዳንዱ ኤርትራዊ በደስታና በፍሰሐ መኖር ይጀምራል የሚል ነበር። ነገር ግን ይህ ተስፋችን እንደ ጉም ሊተን ብዙ ጊዜ አልወሰደበትም። የነበረንን ሁሉ ሰጠን፣ ለነጻነት ስንል። ወጣትነታችንን፣ ሕይወታችንን…። ብዙዎቻችን ከነጻነት በኋላ ከውትድርና ተሰናብተን ቤተሰባችንን ተቀላቅለን፣ ትምህርታችንን ቀጥለን፣ ወደ ግል ሥራና ኑሮ ለመመለስ ነበር ዕቅዳችን። ሆኖም ሠራዊቱን እንኳ ለመልቀቅ እንደማንችል ስናውቅ ተደነቅን። ወታደራዊ አዛዦቻችን የፖለቲካ መሪዎች ሆኑ። አዲሲቷ አገር በእጇ ምንም ቤሳቤስቲ እንደሌላት ነገሩን። ኤርትራ ያላት ብቸኛ ሀብት የያዝናቸው የጦር መሣሪያዎች እንደሆኑ ተነገረን። ከዚያ ሁሉ የጦርነት ፍዳና መከራ በኋላ የቀድሞ ተዋጊዎች ቀበቷችንን ይበልጥ እንድናጠብቅ በድጋሚ አረዱን። ማንኛውንም ሥራ ያለ ክፍያ እንድንምንሰራ ነገሩን። ምግብ ብቻ ይሰጡናል። በነጻ እናገለግላለን። ይህ ሁኔታ ለሁለት ዓመት ቀጠለ። ከዚያ በኋላ ነው ትንሽ ገንዘብ ማግኘት የጀመርነው። በትግሉ ጊዜ ልክ እንደ አንድ ቤተሰብ ይተሳሰቡ የነበሩ ታጋዮች የመሪዎቹን እውነተኛ ባሕሪ ሲረዱ ተከፉ። ብዙዎቹ ወታደራዊ መሪዎች አገሪቱ ልክ ነጻ ከመውጣቷ አስረሽ ምቺው ውስጥ ገብተው ነበር። በርካታ ታላላቅ አመራሮች በየመሸታ ቤቱ ይታዩ ነበር። ራሳቸውን እስኪስቱ ይጠጡም ነበር። በዚህ ወቅት ታጋዩ ኑሮው አለት ሆኖበት ነበር። የዕዝ ሰንሰለቱ እየላላ፣ መደበኛ ስብሰባዎች እየተረሱ መጡ። መደበኛ ታጋዮች ነገሮች ከዛሬ ነገ ይስተካከላሉ ሲሉ ተስፋ አደረጉ፤ ገፋ ብለው ጠበቁ፣ ጠየቁ። አዲስ ነገር አልነበረም። ከጎረቤት ጋር አዲስ ጦርነት እንደ አውሮፓውያኑ በ1993፣ የኤርትራ ነጻነት 2ኛ ዓመት ሊከበር ዋዜማ፣ የቀድሞ ተዋጊዎች አመጹ። መሪዎቻቸው ብሶታቸውን እንዲያዳምጡም ተማጸኑ። መሪዎቻቸው ታላቅ ስብሰባ በአሥመራ ስታዲየም እንዲጠሩ አስገደዷቸው። የተሰጠው ምላሽ ግን፣ ""ችግራችሁ ይገባናል፣ የተለደመ ችግር ነው፤ ሁሉንም በቅርብ እንፈታዋለን"" የሚል ነበር። ልክ ይህ ስብሰባ እንዳበቃ ታዲያ መሪዎቹ የአመጹን አስተባባሪዎች አፍነው ወሰዱ። አንድ በአንድ። በጥቂት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ዓመት እስከ 15 ዓመት እንደተፈረደባቸው ሰማን። የታጋዩን ችግር በይፋ በመናገራቸው ትልቅ ዋጋ ከፈሉ። ብዙ ""ሰዎች በቃ መሪዎቻችን ወደ አምባገነንነት ሊለወጡ ነው"" ማለት ጀመሩ። ሌሎች ግን ትንሽ መታገስና ማየት እንደሚገባ መከሩ። ኤርትራ እያረቀቀችው ያለው ሕገ መንግሥት ሲጠናቀቅ አገራችን ወደ ዲሞክራሲ እንደምታመራ ተነገረን። ይህ ሁሉ ግን መና ቀረ። ኤ��ትራ በአንድ ፓርቲ የምትመራ፣ ምርጫ አካሄዳ የማታውቅ አገር ሆና ቀረች። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን ኤርትራ ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር ጦርነት ውስጥ ገባች። ከየመን በ1995፣ ከሱዳን በ1996፣ ከኢትዮጵያ በ1998 እና ከጂቡቲ ጋር በ2008። አዲሷ አገራችን ኤርትራ ሌሎች ተጨማሪ 10ሺህ ወጣቶቿን ሕይወት አስቀጠፈች። አሁን የኤርትራ ወታደሮች ከነጻነት በኋላ በ5ኛው ዙር ጦርነት ውስጥ ይገኛሉ። አሁን የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ነው። ከህወሓት ጋር ጦርነት ላይ ናቸው። ህወሓት ኤርትራ ነጻነቷን ባወጀች ጊዜ ሥልጣን ላይ የነበረ ነው። ከ1998 እስከ 2000 ከኢትዮጵያ ጋር በተደረገው ጦርነት ወቅትም የነበረ ነው። ከነጻነት በኋላ በነበረው ጊዜ ከገዢው ፓርቲ የባሕል ክፍል ውስጥ ገባሁ። ለታጋዮች የሚገባቸውን ሞገስ ለማሰጠት ብሎም አገሪቱን ለመገንባት ብዙ ሥራ እሠራለሁ በሚል ነበር። በርካታ ተውኔቶችን፣ ሙዚቃዎችን ደረስኩኝ። ተሳትፌባቸዋለሁም። ተወዳጇ ሔለን መለስ 'ምጽዋ' የሚለውን የኔን ሙዚቃ ተጫወተችው። ሙዚቃው 'ምጽዋ ወድ ልጆችሽ የት ገቡ?' የሚል ነበር። ለውጥ አይቀሬ ነው ትንሽም ቢሆን ጭል ጭል ትል የነበረችው የፖለቲካ ምህዳር ተስፋ የኢትዮጵያ-ኤርትራ ጦርነት ማግስት ከሰመች። መንግሥት ልወረር ነው የሚል ሥነልቦና በሕዝቡ ዘንድ ገዢ ሐሳብ እንዲሆን አደረገ። ይህ ጦርነት በጠረጴዛ ዙርያ ንግግር ብቻ እንዲቀር ማድረግ ይቻል እንደነበር ብዙዎች ያምናሉ። በመስከረም 2001 (እአአ) ደግሞ መንግሥት ያልተጠበቀ እርምጃ እንዲወሰድ አዘዘ። አሥራ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና መካከለኛ ካድሬዎች ድንገት ዘብጥያ ወረዱ። ለዚህ የተዳረጉት ታዲያ አንዳንድ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ስለጠየቁ ብቻ ነው። ከዚያች ዕለት ጀምሮ ሰዎቹ የት እንዳሉ ምንም አልተሰማም። እነዚህን መሻሻል እንዲደረግ የጠየቁ ባለሥልጣናትን ያናገሩ፣ ስለነሱ የጻፉ 11 ጋዜጠኞችም ታስረዋል። ከነዚህ መሐል ወዳጄና ጓደኛዬ ስዩም ይገኝበታል። ስዩም ያኔ በድል ስንገባ ፎቶ ሲያነሳ የነበረ ልጅ ነው። እነዚህ ሁሉ እስረኞች አንዳቸውም ፍርድ ቤት አልቀረቡም። አንዳቸውም ያሉበት አይታወቅም። ኤርትራ አሁንም የአንድ ፓርቲ አገር ናት። ከነጻነት ወዲህ ለ30 ዓመት ምርጫ የሚባል ነገር አድርጋ አታውቅም። ነጻ ፕሬስ የለም። ነጻ አደረጃጀት የለም። ሁሉም ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ሆኑ የአገር ውስጥ ሲቪክ ድርጅቶች ታግደዋል። ይፋ የሚደረጉ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከነጻነት ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ የጤናና የትምህርት አገልግሎት እንደተሻሻሉ ያሳያሉ። ይህን ማመን ግን ከባድ ነው። ካለው ጥቂት የሥራ ዕድል እና አስገዳጅ እንዲሁም ክፍያ አልባ የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ጋር ተያይዞ በርካታ ወጣቶች አገሪቱን እየለቀቁ ነው። በርካታ ወጣቶች በሌሎች የአፍሪካ አገሮችና በአውሮፓ ተጠልለው ይኖራሉ። ይህ ሁሉ ሆኖ ግን አሁንም ብዙዎቻችን ተስፋ አልቆረጥንም። ለውጥ አይቀሬ እንደሆነ በጽኑ እናምናለን። ኤርትራ አንድ ቀን በሰማዕታት ቃል የተገባላትን የዲሞክራሲ ሕልም ትኖረዋለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-57222401 +business ኤርትራ፡ የአሰብና ምጽዋ ወደቦች ምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ? "ስድሳ ከመቶ በላይ የዓለም ነዳጅ በሚመላለስበት የንግድ መስመር ቀይ ባሕር በኤርትራ ውስጥ ከሰሜን ወደ ደቡብ 1 ሺህ ኪሎ ሜትር ይሸፍናል። ኤርትራ ከ300 በላይ ትላልቅና አነስተኛ ደሴቶች አሏት። በዚህ ምጽዋና አሰብ ተብለው የሚጠሩ ሁለት የወደብ ከተሞች አሉ። ወደቦቹ ከ60 ዓመታት በፊት ብዙ የወጪና የገቢ ንግድ የሚመላለስባቸው ነበሩ። በኤርትራ ትጥቅ ትግል ወቅት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ወደቦች ጥገ�� ተደርጎላቸው ከ1983 እስከ 1990 ድረስ አገልግሎት ይሰጡ ነበር። የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ግን ኢትዮጵያ የጅቡቲ ወደብን መጠቀም ጀመረች። በዚህ ምክንያት ተዳክመው የቆዩት ወደቦች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ዳግም መነቃቃት ያሳያሉ ተብሎ ተስፋ ተጥሎባቸዋል። በአሁኑ ወቅት በንግድ መርከብ የሚሰራው የኤርትራ ባሕረኞች ማኅበር አባል የሆነው ካፒቴን መሪሕ ሃብተ የኤርትራ ወደቦችን ከባሕር ትራንስፖርት፣ ከአሳ፣ ከቱሪዝምና ከማዕድን አንጻር ከፋፍሎ ማየት ይቻላል ይላል። የአሰብና የምጽዋ ወደቦች እቃዎችን የመጫንና የማራገፍ፣ የመጋዝን እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚሰጡ ሲሆን በአሰብ እስከ 94 በመቶ የሚገባውና የሚወጣው ንብረት የኢትዮጵያ ንግድ እንደነበረ ቺፍ ኢንጅነር ፓውሎ አንቶንዮ ይጠቅሳል። ከ1983 እስከ 1988 ዓ.ም 3.06 ቶን የሚደርስ ጭነት በወደቦቹ እንደተጓጓዘና እስከ 802 መርከቦች ማስተናገዱንም ይናገራል። ከ1986 እስከ 1989 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ደግሞ ወደቦቹ እስከ 1150 መርከቦች አስተናግደዋል፤ 3.287 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ ጭነትም አራግፈዋል። በ1989 ብቻ 2695 መርከቦች ሲያስተናግዱ 3̋95 ሚሊየን ቶን እቃ እንደተጫነና እንደተራገፈ ቺፍ ኢንጅነር ፓውሎ ይናገራል። የወደቦቹ አቅም የወደቦቹ አቅም ከጎረቤት አገሮች ጋር ሲነጻጸር የኤርትራ ወደቦች ከጂቡቲ ወደቦች ጋር ሲነጻጸሩ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ይህ አገራቱ ከሚከተሉት ፖሊሲ ጋር የሚያያዝ ሲሆን ጂቡቲ የብዙ አገሮች የወደብ ማዕከል በመሆንዋ፣ በተለይ ከ1990 በኋላ ለኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት ስትጀምር አገልግሎት የመስጠት አቅሟ በእጥፍ እንዳደገ የኤርትራ ባሕረኛ የነበረው ካፒቴን ተስፋይ ኢትባረኽ ይናገራል። ማሪታይም ሲልክ ሮድ በመባል የሚታወቀው የቻይና ፕሮጀክት አካል የሆነው ፖርት ሱዳንም ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በኋላ እያደገ መሆኑ ይነገራል። የኤርትራ ወደቦች በተለይ ባለፉት ዓመታት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከየመን ጋር ለምታደርገው ጦርነት ብትጠቀምበትም ምንም አይነት ማሻሻያ አለማሳየታቸው የባሕር እንቅስቃሴ የሚከታተለው አህመድ አብዱ ይገልጻል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአንድ ወቅት ለአገሪቷ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃለ መጠይቅ ""የባሕር እንቁ የሚትባለው ምጽዋ ግን አለች? የባሕር እንቁም አይደለችም፤ ምንም አይደለችም"" በማለት የምጽዋ ወደብ አቅም እንደወረደ ገልጸው ነበር። በአሁን ወቅት በስዊድን አገር በአንድ መርከብ ላይ እየሰራ የሚገኘው ኦፊሰር ቢንያም ታደሰ ""የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች በድንበር ጦርነት ምክንያት በወደብ አገልግሎት ብቻ በቢሊየን ዶላር ከስረዋል"" ይላል። ኦፊሰር ቢንያም ""የኤርትራ ባሕር ግን የወደብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ብቻ የሚውል አይደለም"" በማለት የተለያዩ የአሳ አይነቶች፣ የባህር እንቁ፣ የጨው ማዕድንና ሌሎች የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት የሚችሉ ሃብቶች እንዳሉት ያስረዳል። ኤርትራ ስንት መርከቦች አሏት? በ2002 በተደረገው ጥናት መሰረት በኤርትራ 8 የሚደርሱ ትልልቅ መርከቦች ተመዝግበው ነበር። መርከቦቹም ዮሃና፣ በይሉል፣ ሰላም፣ አንጀሎስ፣ ደንደን፣ መረብ ጋሽ፣ ሳሊናና ኤስሮምና የሚል መጠሪያ አላቸው። መርከቦቹ በአጠቃላይ 31245 ቶን እንደሚመዘኑ የኤርትራ ባሕረኞች ይናገራሉ። ኤስሮም ትላቋ የጭነት መርከብ ስትሆን 12333 ቶን ትመዘናለች። ዲኤምቲ የተባለው ኩባኒያም የመርከቧ ባለቤት ነው። በይሉል የቦት መርከብ ስትሆን መረብ ጋሽ ደግሞ በከረን ሺፒን ላይን የምትተዳደረው የነዳጅ ጫኝ መርከብ ናት። ሳሊና መርከብ የጭነት አገልግሎት የምትሰጥ በግል የምትተዳደር መርከብ ስትሆን ዛፈ ሺፒንግ ሊይን ባለቤትዋ ነው። ""ይሁን እንጂ"" ይላል ኦፊሰር ቢንያም ""በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ አገልግሎት የሚሰጡ በመንግሥትና በተለያዩ ማኅበራት የሚተዳደሩ መርከቦች ሙሉ ለሙሉ ቆመው፤ ሠራተኞቻቸው በስደት በተለያዩ አገራት መርከቦች እየሰሩ ይገኛሉ።"" ከዚህ ቀደም ብዙ ወደ ሆላንድ፣ ሕንድና ፓኪስታን ተልከው የሰለጠኑ በርካታ ባሕረኞች እንደነበሩ የሚገልጸው ካፒቴን ተስፋይ በበኩሉ ""ከነጻነት በኋላ በርካታ ወደ ታንዛኒያ፣ ዱባይና ኤምሬትስ ተልከው ሰልጥነው ነበር"" ሲል ያስታውሳል። ሆኖም ይህ ቀጣይነት ማጣቱን የሚናገረው ካፒቴን ተስፋይ ""የኤርትራ ባሕረኞች አቅም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ነው ያለው"" ሲል ያስረዳል። የመጀመሪያው የኤርትራ ባሕረኞች ማኅበር በ1975 በምጽዋ ተመስርቶ ነበር። ይህ በተለያዩ ምክንያቶች መቀጠል ስላልቻለ በ2015 በስደት የተቋቋመው የኤርትራ ባሕረኞች ማኅበር እስከ 1500 የሚደርሱ አባላት አሉት።" https://www.bbc.com/amharic/news-57193973 +health ኮቪድ-19፡ በስህተት የ16 ሺህ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ውጤት ሳይገለጽ ቀረ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በገጠመ የቴክኒክ ስህተት ወደ 16 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሳይገለጽ ቀረ። ይህም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት የሚደረገውን ጥረት አጓቷል። የአገሪቱ የሕብረተሰብ ጤና ተቋም እንዳለው ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 2 ድረስ 15,841 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በእለታዊ ሪፖርት ሳይካተት ቀርቷል። ሪፖርት ያልተደረጉት ሰዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ በወጡት እለታዊ ሪፖርቶች ተካተዋል። • የኮቪድ-19 ፀር ሳሙና ወይስ ፀረ-ቫይረስ ፈሳሽ? • ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን ለማየት ሆስፒታል ጥለው ወጡ • ልብስ ሳያረጥብ በፀረ ተህዋስ የሚያፀዳው የኢትዮጵያዊው ፈጠራ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ውጤታቸው ቢነገራቸውም ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች መረጃው እንዳልደረሳቸው ተቋሙ አስታውቋል። በገጠመው የቴክኒክ ስህተት ምክንያት ባለፈው ሳምንት የወጡ ሪፖርቶች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን አሳንሰዋል። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በቫይረሱ እንደተያዙ የተገለጸው 7,000 ሰዎች ቢሆንም፤ ትክክለኛው ቁጥር ወደ 11,000 ይጠጋል። ሪፖርት ካልተደረጉት ሰዎች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የሰሜን ምዕራብ ኢንግላንድ ነዋሪዎች ናቸው። በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የሚኖሩት በሊቨርፑል እና በማንችስተር ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች በአጠቃላይ እንደተነገራቸው ገልጸዋል። የክትባት ምርምር ግብረ ኃይል ኃላፊ ኬት ቢንግሀም ለፋይናንሽያል ታይምስ እንደተናገሩት፤ ከዩኬ ዜጎች ከፊሉ ይከተባሉ። “ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ሰዎች ክትባት አይሰጥም። ክትባቱ ከ50 ዓመት በላይ ለሆኑና በዋናነትም ለጤና ባለሙያዎችና አረጋውያንን ለሚንከባከቡ ሰዎች ይሰጣል” ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወረርሽኙን የማሸነፍ ተስፋ እንዳለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ማኅበረሰቡ “ጥንቃቄ ማድረግ እንጂ መፍራት የለበትም” ሲሉም አክለዋል። በአገሪቱ የምርመራ ውጤት መዘግየቱ መንግሥትን እያስተቸ ባለበት ወቅት፤ በስህተት ውጤታቸው ያልተገለጸ ሰዎች የመኖራቸው ዜና ነገሮችን አባብሷል። በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች መረጃውን አለማግኘታቸው ሌላው አሳሳቢ ነገር ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦች በ48 ሰዓታት ውስጥ ሊነገራቸው ይገባል። ስህተቱ የኮምፒውተር እንደሆነና አሁን መስተካከሉ ተገልጿል። መንግሥት ትላንት ባወጣው ሪፖርት ተጨማሪ 22,961 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘ��ቸውና አጠቃላይ በበሽታው የተያዙ ቁጥር 502,978 መድረሱን ገልጿል። የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ኃላፊው ማይክል ብሮይድ እንዳሉት፤ አብዛኞቹ ሪፖርት ያልተደረጉ ቁጥሮች የቅርብ ጊዜ የምርመራ ውጤት ናቸው። “ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍና የምርመራ ውጤቶቹን ለመግለጽ ሞክረናል። ስህተቱ ሊፈጥር የሚችለውን ስጋት እንረዳለን። በቀጣይ ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጠር ጥብቅ እርምጃ ወስደናል” ብለዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54423275 +health ዩናይትድ ኪንግደም ጤነኛ ሰዎችን በኮቪድ ተህዋሲ 'ልትለክፋቸው' ነው የኮቪድ ክትባትን በማግኘት ጥረት ውስጥ ከፊት ከሆኑ አገራት አንዷ የሆነችው ዩናይትድ ኪንግደም የተለየ አይነት የክትባት ሙከራ ለማድረግ ቀዳሚዋ አገር ልትሆን ነው። በጥር ወር ላይ 90 ጤነኛ ሰዎች ሆን ተብለው ለኮቪድ ተህዋሲ እንዲጋለጡ በማድረግ ነው አዲሱ ሙከራ የሚደረገው። ይህም ቶሎ ክትባት ለማግኘት ይረዳል ተብሏል። መንግሥት ከወዲሁ 33.6 ሚሊዮን ፓውንድ ለዚሁ ሙከራ መድቧል። ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግበታል የተባለው ይህ አዲስ የሙከራ ዘዴ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ከአገሪቱ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ይሁንታን ማግኘት ይኖርበታል። በመድኃኒት ቅመማ ሂደት ‹ሂዩማን ቻሌንጅ› በሚል የሚታወቀው ይህ ጤነኞች ላይ በሽታ አምጪ ተህዋስን ሆን ብሎ በማጋባት ሙከራ ማድረግ ብዙም የተለመደ አይደለም። ነገር ግን ከዚህ ቀደም በወባና በኢንፍሉዌዛ የመድኃኒት ግኝቶች ሂደት ውስጥ ተሞክሮ ውጤት ማስገኘቱን ኔቸር መጽሔት ዘግቧል። ሳይንቲስቶች በጥር ወር መጀመርያ ተግባራዊ ያደርጉታል በተባለው በዚህ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉት ሰዎች ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 30 የሚሆን ፍጹም ጤነኛ የሆኑ በጎ ፈቃደኞች ብቻ ናቸው። ሙከራው አንድን ሰው ምን ያህል የተህዋሲው መጠን ነው ለበሽታ የሚያጋልጠው የሚለውንም ለማወቅ ይረዳል ተብሏል። ለበጎ ፈቃደኞቹ በቅድሚያ ተህዋሲው በትንሽ መጠን ይሰጣቸዋል። ፍጹም ጤነኛ ሰዎችን እንደ አይጥ መሞከርያ ማድረግ ቶሎ ውጤት ለማግኘት አስፈላጊ ነው የሚሉ በርካታ ቢሆንም መድኃኒት በሌለው በሽታ ሰዎችን ሆን ብሎ መበከል ከሕክምና ሥነ ምግባር አንጻር ተገቢ አይደለም ሲሉ ነገሩን የሚተቹትም በርካታ ናቸው። ተህዋሲው ለበጎ ፈቃደኞቹ የሚሰጣቸው በአፍንጫቸው በኩል ይሆናል ተብሏል። ለ24 ሰዓታትም ጥብቅ ክትትል ይደረግላቸዋል። በጎ ፈቃደኞቹ ለከፋ አደጋ የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ ነው፤ ምክንያቱም ጤነኞችና ወጣቶች በመሆናቸውና በጥንቃቄ ስለሚመረጡ ነው ይላሉ ተመራማሪዎች። ቅድመ ጥንቃቄው አስተማማኝ በሚባል ደረጃ ላይ ሲደርስ በበጎ ፈቃደኞቹ በአንዳንዶቹ ላይ ሙከራ ላይ የሚገኙ ክትባቶች ይሰጧቸዋል። ለኮቪድ ተህዋሲው ከመገላጣቸው በፊትም ክትባት እንዲወስዱ የሚደረጉ ይኖራሉ። ክትባቱን የወሰዱት ለተህዋሲው ተጋልጠው ተህዋሲው ይይዛቸዋል ወይስ አይዛቸውም የሚለውም ምላሽ ያገኛል። የዚህ ምርምር መሪ የኢምፔሪያል ኮሌጁ ዶ/ር ክሪስ ቺዩ ሰዎች ያን ያህልም ሐሳብ ሊገባቸው አይገባም ይላሉ። ‹‹እኔና ባልደረቦቼ በዚህ መንገድ ላለፉት 10 ዓመታት በርካታ ጤነኛ ሰዎች ላይ ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ ቫይረሶችን በመስጠት ስንሰራ ቆይተናል። እርግጥ ነው የትኛውም ጥናት ቢሆን የራሱ አደጋ የለውም አይባልም። ነገር ግን አደጋውን ለመቀነስ እንታገላለን›› ብለዋል። ረዳታቸው ፕሮፌሰር ፒተር ኦፔን ሻው በበኩላቸው ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲ ሆን ብሎ በመበከል ምርምር ማካሄድ በቀላሉ የሚታይ ነገር ባይሆንም ውጤት ለማግኘት ግን ወሳኝ ነው፤ ያግዛል ብለዋል። በአሁን ሰዓት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኮቪድ ክትባቶች በመጨረሻ ምዕራፍ ሙከራ ላ�� ሲሆኑ ውጤት ያስገኛሉ ተብለው በጉጉት እየተጠበቁ ካሉት መካከል የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው ተጠቃሽ ነው። በጥር ወር ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲው በመበከል የሚደረገው ምርምር ሌላ ፍቱን መድኃኒት ቀድሞ ቢገኝም የሚቋረጥ አይሆንም። ክትባቶች ከተገኙ በኋላ የትኛው ክትባት እጅግ ውጤታማ ነው የሚለው ጥናት ይቀጥላል። ተህዋሲውን በገዛ ፈቃዳቸው ለመውሰድ የፈቀዱ የታላቋ ብሪታኒያ ዜጎች ለጊዜያቸውና ለደፋር ውሳኔያቸው የሚመጥን ነው የሚባል ገንዘብ ይከፈላቸዋል። ሙከራው ከተደረገባቸው በኋላም ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያለማቋረጥ የቅርብ ክትትል ይደረግባቸዋል። https://www.bbc.com/amharic/54617479 +business የናይጄሪያው ሼል ላደረሰው ብክለት ለአርሶ አደሮች ካሳ እንዲከፍል ተወሰነበት "የኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት በኒጀር ዴልታ ተፋሰስ የነዳጅ ብክለት አስከትሏል በሚል በናይጄሪያ የሚገኘውን የሼል ኩባንያ ቅርንጫፍ ጥፋተኛ አድርጎታል፤ ካሳም እንዲከፍል አዞታል። ፍርድ ቤቱ የናይጄሪያው ሼል ጉዳት ለደረሰባቸው ናይጄሪያዊ አርሶ አደሮች ካሳ እንዲከፍል እንዲሁም ተቋራጩ የሆነው የእንግሊዙ-ደች ኩባንያ ለወደፊቱ የሚፈጠርን ጉዳት ለመከላከል አስፈላጊ የሚባለውን ቁሳቁስ እንዲገጥም ትዕዛዝ ተላልፎለታል። በአውሮፓውያኑ 2008 ሼል አካባቢያችንን በክሎታል በሚል አርሶ አደሮቹ ክስ መመስረታቸው ይታወሳል። ሼል በበኩሉ ""ሆን ብሎ የተጠነሰሰብኝ ሴራ ነው"" ይላል። በዛሬው እለት የደች ሼል ባወጣው መግለጫ በውሳኔው ""አዝነናል""ብሏል። ኩባንያው ይግባኝ የመጠየቅ መብት አለው ተብሏል። ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ""ጎይና ኦሩማ በሚባሉ መንደሮች ላይ ነዳጁ ፈስሶ ለደረሰው ጉዳት ኩባንያው ሴረኞች የፈፀሙት ነው ቢልም ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም። ኩባንያው ከነበረው ደካማ አሰራር ጋር የተያያዘ ነው"" ብሏል ችሎቱ። ""በነዚህ አካባቢዎች ተንጠባጥቦና ፈስሶ ለደረሰው ብክለትና ጉዳት ሼል ናይጄሪያ ተጠያቂ ነው"" በማለት ፍርድ ቤቱ አስምሯል። የካሳው መጠንም ከዚህ በኋላ የሚወሰን ይሆናል። ኢኮት አዳ ኡዶ በተባለው መንደር ኩባንያው እንዳለው ሆን ተብሎ የተፈፀመ ለመሆኑ አንዳንድ ፍንጮች በመኖራቸው የበለጠ እመረምረዋለሁ በማለት ፍርድ ቤቱ ለጊዜው ይዞታል። ከሳሾቹ አራት አርሶ አደሮች ከመሬት ስር የተቀበረው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፈስሶ ውሃቸው እንዲሁም መሬታቸው እንደተበከለና መላ ህይወታቸውን ግልብጥብጡን እንዳወጣው ገልፀዋል። ከከሳሾቹ ውስጥ ሁለቱ መሞታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል። አርሶ አደሮቹን ፍሬንድስ ኦፍ ዘ ኧርዝ የተባለ የከባቢ ጥበቃ ቡድን ደግፏቸዋል። ""የደስታ እንባ ነው የማነባው፤ ከአስራ ሶስት አመታት በኋላ አሸነፍን"" በማለት የቡድኑ ኔዘርላንድስ ቅርንጫፍ ተወካይ በውሳኔው የተሰማቸውን ደስታ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በዛሬው እለት የተላለፈው ውሳኔ ከናይጄሪያ አልፎ የኩባንያዎች ኃላፊነት እስከምን ድረስ ሊሆን ይገባል በሚለው ጉዳይ ላይ ሌሎች አገራት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል ተብሏል። በዚህ ክስ ላይ የነዳጁ ፍሰት የተፈጠረው ከ2004-2007 ቢሆንም በአሁኑም ወቅት በኒጀር ደልታ ከነዳጅ መተላለፊያ ቧንቧዎች የሚወጣው ብክለት ትልቅ ችግር ነው ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55859771 +sports ኢሊዩድ ኪፕቾጌ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች አጠናቀቀ "ኢሊዩድ ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በመሮጥ የመጀመሪያው አትሌት ሆነ። ኪፕቾጌ ሩጫውን ለመጨረስ አንድ ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ ፈጅቶበታል። የ34 ዓመቱ ኬኒያዊ አትሌት 42.2 ኪሎ ሜትር ለመሮጥ የፈጀበት ሰዓት እንደ ዓለም ክብረ ወሰን እንደማይመዘገብለት የተገለጠ ሲሆን፣ ለዚህም ምክንያት ነው የተባለው የተጠቀማቸው አሯሯጮች፤ እየተፈራረቁ የሚያሯሩጡት አትሌቶች መሆናቸውና ለሁሉም ክፍት የሆነ ውድድር ባለመሆኑ ነው። ኪፕቾጌ ውጤቱን አስመልክቶ ሲናገር ""ይህ የሚያሳየው ማንም ሰው ሊያሳካው እንደሚችል ነው"" ብሏል። ""አሁን እኔ አሳክቸዋለሁ፤ ከአሁን በኋላ ሌሎችም እንዲያሳኩት እፈልጋለሁ"" ብሏል። • ኪፕቾጌን በሩጫ ይገዳደሩታል? • ከባህር ዳር - አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ዛሬም አልተከፈተም • ነገ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም-የአዲስ አበባ ፖሊስ ይሀ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና የአለም አቀፉን የማራቶን ክብረወሰን በአውሮፓዊያኑ 2018 ጀርመን በርሊን ላይ በሁለት ሰዓት ከ01 ደቂቃ 39 ሰከንድ በእጁ አስገብቶ ነበር። የለንደን ማራቶንን አራት ጊዜ በማሸነፍ ስሙን የተከለው ኪፕቾጌ፤ ከድሉ በኋላ ባለቤቱ ግሬስን ተጠምጥሞ በመሳም የሀገሩን ባንዲራ ለብሶ በአሯሯጮቹ ተከብቦ ደስታውን ገልጧል። ኪፕቾጌ በሚሮጥበት ወቅት ከፊት ከፊቱ በመሆን ሰዓቱን የሚጠቁመው መኪና የነበረ ሲሆን 100 ሜትሩን 17 ደቂቃ ከ08 ሰከንድ በመሮጥ ለስኬት በቅቷል። ኪፕቾጌን 42 አሯሯጮች ያሯሯጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የ1500 ሜትር ሻምፒዮናው ማቲው ቹንትሮ ዊትዝ፣ የ5000 ሜትር የመዳብ ባለቤቱ ፓል ቼሊሞና ኖርዌጂያን ወንድማማቾቹ ጃኮብ፣ ፍሊፕና ሄንሪክ ይገኙበታል። እነዚህ አሯሯጮች እያረፉ ያሯሯጡት ሲሆን የ1500 እና የ5000 ዓለም ሻምፒዮና የሆነው በርናንርድ ላጋት የመጨረሻዎቹን ርቀቶች አሯሩጦታል። ኪፕቾጌም ""እነዚህ በዓለም አሉ የሚባሉ ዝነኛ አትሌቶች ናቸው፤ አመሰግናለሁ"" በማለት፤ አክሎም ""ይህንን ሥራ ስለተቀበሉ አመሰግናለሁ። ያሳካነው በጋራ ነው"" ብሏል። • ""የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም"" ዱቤ ጂሎ • 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፡ የእኛ ሠው በዶሃ የኪፕቾጌ አሰልጣኝ አትሌቱ ልክ እንደ ሌላ ጊዜው የሚጠጣው ውሃ ከጠረጴዛ ላይ አንስቶ ከሚጠቀም ይልቅ በብስክሌት በመሆን ውሃና ኃይል ሰጪ ጄል ሲያቀብሉት ነበር። እንዲህ ዓይነት እገዛ ግን በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕግ መሰረት አይፈቀድም። ኪፕቾጌ የሮጠበት ሥፍራ የተመረጠው የአየር ጠባዩ ምቹ ስለሆነ መሆኑ ተነግሯል። ይህንን ሰዓት ለማሻሻል የተደረገውን ጥረት በገንዘብ የደገፉት እንግሊዛዊው ባለሀብት ሰር ጂም ራትክሊፍ በኩባንያቸው ፔትሮ ኬሚካልስ ስም ነው። ናይክም አምስት የዓለማችን ፈጣን የማራቶን ሯጮች ብቻ ያደረጉት አዲስ ሞዴል ጫማ አበርክቶለታል። የመጨረሻዎቹን ኪሎ ሜትሮች ያጠናቀቀበት ፍጥነት ""አስደማሚ ነበር"" ያሉት ራትክሊፍ ሲሆኑ የኪፕቾጌ አሰልጣኝ በበኩላቸው "" በዚህ ሙከራችን ሁሉም ነገር እንዳሰብነው ሄዷል"" ብለዋል። ""ሁላችንንም ነው ያነቃቃው፤ በሕይወታችን አቅማችንን በመለጠጥ መፈተሽ እንደምንችል አሳይቶናል"" ካሉም በኋላ ""በስፖርቱ ዓለም ለሌሎች አትሌቶች ከሚያስቡት በተሻለ መሮጥ እንደሚችሉ ያሳየ፤ በሌላ ሕይወት መስክ ደግሞ ሌላ ከፍታ መውጣት እንደሚችል ያስተማረ ነው"" በማለት ድሉን አሞካሽተውታል። ""በአጠቃላይ ታሪክ ተሠርቷል፤ የማይታመን ነገር ነው"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-50027271 +sports የሉሲዎቹና የአዳማ ክለብ ጎል አዳኝ ሴናፍ ዋቁማ "የሉሲዎቹና የአዳማ ክለብ ጎል አዳኝ የፊት መስመር ተጫዋች ነች፤ ሴናፍ ዋቁማ። ትውልድና እድገቷ በነቀምት ነው። ለእግር ኳስ ያላትን ፍቅር ስትገልጽ ""ትምህርት ቤት እያለሁ ለኳስ ካለኝ ፍቅር የተነሳ እጫወት የነበረው ከወንዶቹ ጋር ነበር"" ትላለች። ትኩረቷን ሙሉ በሙሉ ለኳስ ከሰጠች በኋላ ነቀምት በሚገኙ የእግር ኳስ ፕሮጀክቶች ውስጥ ታቅፋ ስልጠናዎችን ወስዳለች። ከዚያም በነበራት አቋም ተመርጣ ወደ አሰላ በመሄድ ለአራት ዓመታት ስልጠና ወስዳለች። • ""በሀገራችን ከሶስት ሴቶች አንዷ ላይ ጾታዊ ጥቃት ይደርሳል"" • በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን አቃቤ ሕግ አስታወቀ • የሕዝብ እንደራሴዎችን ጎራ አስለይቶ ያሟገተው ሕግ ""የሰዎች አመለካከት ጥሩ አልነበረም"" የምትለው ሴናፍ፤ በእግር ኳስ ህይወቷ ማህበረሰቡ ሴቶች እግር ኳስ መጫወታቸውን በበጎ አለመመልከቱ የእግር ኳስ ህይወቷን ፈታኝ አድርጎባት እንደነበረ ታስረዳለች። ""ሴቶች ከቤት መውጣት የለባቸውም የሚል አመለካከት ነበር። እግር ኳስ መጫወት ደግሞ እንደ ሃፍረት ነበር የሚቆጠረው"" የምትለው ሴናፍ፤ የማህብረሰቡ አመለካከት በወላጆቿ ላይ ጭምር ጫና በማሳደሩ ወላጆቿ እግር ኳስ መጫወት ማቆም እንዳለባት ሲነግሯት እንደነበረ ታስታውሳለች። ""እኔ ግን ይህ ሁሉ አመለካከት ወደ ኋላ አላስቀረኝም። ዓላማዬ አድርጌ ይዤው ስለነበረ ማንም ሊያስቆመኝ አልቻለም። ቤተሰቦቼም ይህን ሲረዱ እኔን መደገፍ ጀመሩ"" ትላለች። ሴናፍ ተማሪ እያለች ፍቅሯ ለእግር ኳስ እንጂ ለትምህርት አልነበረም። በዚህም ብዙ ጊዜዋን የምታሳለፍው ኳስ በመጫወት ነበር። ""አገርን ወክሎ እንደመሳተፍ የሚያስደስት ነገር የለም"" የምትለው ሴናፍ፤ በ2011 በሁለት ዘርፎች የውድድር አሸናፊ ነበረች። በኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 21 ጎሎችን በማሰቆጠር ኮከብ ግብ አግቢ እና የውድድር ዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ተብላ ተሸልማለች። ክለቧ አዳማም፣ የውድድሩ ሻምፒዮን ሆኖ እንዲጨርስ የራሷን አስተዋጽኦ አበርክታለች። የ25 ዓመቷ እግር ኳሰኛ ሴናፍ፤ ወደፊት በእግር ኳሱ ዓለም ፕሮፌሽናል ተጫዋች ሆና መቀጠል ምኞቷ ነው። ""አንድ ሰው ከቆረጠ እና በያዘው ላይ ካተኮረ ያሰበበትን ማሳካት አይሳነውም"" በማለት ከራሷ የህይወት ተሞክሮ በመነሳት የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋችነት ህልሟን እንደምታሳካ በልበ ሙሉነት ትናገራለች። አንድነት ነገር ማሳካት እንደማይቻል የምናስብ ከሆነ ከስኬት መድረስ እንችልም ስለዚህ ያሰብነው እንዲሳካ በቁርጠኝነት መስራት ይኖርብናል ትላለች። ሴናፍ የኔይማር ጁኒየር አድናቂ መሆኗን ትናገራለች።" https://www.bbc.com/amharic/51505693 +health ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለዓለም ያስገኛቸው አስር ትሩፋቶች በአንድ ዓመት ውስጥ ከ115 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የያዘውና ከ2.5 በላይ ሰዎችን ደግሞ ለሞት ዳረገውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመጣል ሳይንስ፣ ዕውቀትና ትብብር ተጣምረው ብዙ ታግለዋል፤ እየታገሉም ይገኛሉ። ቫይረሱ አዲስ ዝርያ ማፍራቱን ተከትሎ በሚቀጥሉት ሳምንታትና ወራት ምን ሊከሰት እንደሚችል መገመት ቢያዳግትም አንድ ዓመት የሞላው ወረርሽኝ ብዙ አስተምሮናል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ብዙዎችን ቢቀጥፍም ከዚህ በፊት በአዕምሯችን ውል ያላሉ በጎ ትሩፋቶችን አስገኝቷል ይላሉ ባለሙያዎች። ከእዚህ ውስጥም እስቲ አስሩን ከኮቪድ-19 ትሩፋቶች እንመልከት። 1 - ኮቪድ-19 የወባን ማዕረግ መረከቡ ከአንድ ዓመት በፊት ማለትም ስለወረርሽኙ መዘገብ ከጀመረ ከአንድ ወር በኋላ በሕክምና መጽሔቶች ላይ ከ164 በላይ ፅሑፎች ስለኮቪድ-19 ታትሞ ወጥቷል። ከአንድ ዓመት በኋላ ዛሬ ስለወረርሽኙ የተፃፉ የጥናትና የምርምር ዘገባዎች ቁጥር በ600 እጥፍ ጨምሮ ከ100 ሺህ በላይ ሆኗል። ይህን ማዕረግ ቀድሞ ይዞ ነበር ወባ ነበር። ዘንድሮ ለወትሮው አብዝተን ከምንሰማቸው የበሽታ ዘገባዎች በላይ ስለ ኮቪድ-19 በብዛት ይነገራል። በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ ከወባ በላይ ስለኮቪድ-19 የበለጠ ዕውቀት አለ። 2 - ከ200 በላይ ክትባቶች ከአንድ ዓመት በፊት ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ይረዳሉ ተብለው ጥናት ሲደረግባቸው የነበሩ ክትባቶች ቁጥር ስምንት ነበር። ባዮሬንደር የተሰኘው ድርጅት እንደሚለው አሁን ከ195 በላይ ክትባቶች በተለያዩ የሂደት ደረጃ ላይ ሲሆኑ 71 ያህሉ ደግሞ በሙከራ ደረጃ ላይ ናቸው። ፀረ-ኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለማምረት የወጣውን ወጪ፣ ትብብርና ጥናት ያክል ለሌሎች በሽታዎች ይህን የመሰለ ርብርብ አልተደረገም ይላሉ ባለሙያዎች። በዚህ ጥናት ላይ ሕዝቡ፣ የግል ድርጅቶች፣ አጥኚዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ መድኃኒት አምራቾች፣ እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተሳትፈዋል። እርግጥ ነው አንዳንድ የጥናት ሂደቶች በእንጭጭ ቀርተዋል። ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅተ ያፀደቃቸው ደግሞ በርካታ ናቸው። ፋይዘር/ባዮንቴክ፣ ሞደርና፣ አስታራዜኔካ/ኦክስፎርድ፣ ስፑትኒክ 5 እንዲሁም የቻይናው ሲኖፋርምና ጎል ተብለው የሚጠቀሱ ክትባቶች ናቸው። ቢያንስ 20 ሌሎች ክትባቶች ደግሞ የሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ምናልባትም በሚቀጥሉት ሳምንታት አሊያም ወራት ውጤታቸው ተለይቶ ወደ ሥራ ሊገቡ ይችላሉ። 3 - የክትባቶች የጎንዮሽ ጉዳት አነስተኛ መሆን የክትባቶች ትልቁ ደንቃራ በሳይንስ ቋንቋ አናፊላክሲስ ይባላል። ይህም የክትባቶቹ ጎንዮሽ ጉዳት ሲሆን ክትባት ከተወሰደ በኋላ ወዲያው የሚከሰት ሲሆን እስከሞት ሊያደርስ ይችላል። አሜሪካ ውስጥ ክትባቱ በተሰጠበት የመጀመሪያው ወር ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚጠቁመው 17.5 ሚሊየን ክትባቶች ተሰጥዋል። ከእነዚህ የፋይዘርና የሞደርና ክትባቶችን ከወሰዱ ሰዎች መካከል 66ቱ ብቻ ናቸው ይህ የጎንዮሽ ጉዳት የገጠማቸው። ይህ በሚሊዮንኛ ሲሰላ ከአንድ ሚሊዮን ሰው 4 ብቻ ነው ማለት ነው። በመቶኛ ሲሰላ ደግሞ 0.0003 ይሆናል። ከ66ቱ ሰዎች መካከል 21 ሰዎች ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ችግር ገጥሟቸው ያውቃል። በዚህ የጎንዮሽ ጉዳት ምክንያት እስከዛሬ ድረስ የሞተ ሰው የለም። የዚህ ጥናት ውጤት ለጊዜውም ቢሆን የሚጠቁመው ክትባቶች ከጉዳታቸው ጥቅማቸው በእጅጉ እንደሚያመዝን መሆኑ ነው። በተለይ ደግሞ የሞደርና ክትባት ከሌሎቹ በላቀ ደኅንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ ተነግሯል። 4 - ክትባቶች ውጤታማ ናቸው እስራኤል በርካታውን ዜጎቿን በመከተብ ከዓለም ቀዳሚ ናት። እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከ3.67 በላይ እስራኤላዊያን የፋይዘርን የመጀመሪያ ዙር ክትባት ወስደዋል። ይህ ከአገሪቱ ሕዝብ 40 በመቶውን የሚይዝ ነው። ከ28 በመቶ በላዩ ደግሞ ሁለተኛውን ዙር ክትባት ወስደዋል። ከ60 ዓመት በላይ ከሆናቸው ዜጎቿ መካከል ደግሞ 80 በመቶው ተከትበዋል። የክትባቶቹ የመጀመሪያ ዙር ውጤት እንደሚያሳየው ክትባቶች እስካሁን ድረስ ባለው ጥናት መሠረት ውጤታማ መሆናቸውን ነው። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም ከጊዜ ጊዜ እየቀነሰ መጥቷል፤ በለተይ ደግሞ ዕድሜያቸውን 60ና ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ። ሁለቱንም ዙር ክትባት ከወሰዱ 523 ሺህ እስራኤላዊያን መካከል 544 ሰዎች ላይ ብቻ ነው ኮቪድ-19 የተገኘው። እስካሁን ድረስ የተመዘገበ ሞት ግን የለም። ነገር ግን የክትባቱን ውጤታማነት ለማየት የግድ ወደ እስራኤል መሻገር አይጠበቅብንም። የክትባቶችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በአዛውንቶች ማቆያ ማዕከላት የሚኖሩና አሁን ክትባቱ የደረሳቸውን ሰዎች ቁጥር ማየት ይቻላል። በአብዛኞቹ የአውሮፓ አገራት ያሉ በዕድሜ የገፉ ሰዎች አሁን ክትባቱን ካገኙ በኋላ የመያዝ ዕድላቸውና የሞት ቁጥር በእጅጉ እየቀነሰ ነው። 5 - በክትባት ላይ መተማመን መጨመር በዓለም ዙሪያ እስካሁን ድረስ ከ160 ሚሊዮን በላይ ብልቃጦች ጥቅም ላይ ውለዋል። የዚያኑ ያህል ሰዎች በክትባት ላይ ያላቸው መተማንም ከዕለት ዕለት እየጨመረ ነው። ለምሳሌ በአውሮፓ፣ እስያና አውስትራሊያ አገራት የሚኖሩ 13 ሺህ 500 ሰዎችን መሠረት አድርጎ አንድ ጥናት ተሠርቷል። ጥናቱ ከኅዳር እስከ ጥር ባለው ጊዜ የተሠራ ነው። ኅዳር ላይ አገራት ክትባት መስጠት ከመጀመራቸው በፊት 40 በመቶ ሰዎች ብቻ ነበሩ በክትባቱ ሙሉ እምነት የነበራቸው። ነገር ግን ጥር ላይ ከ50 በመቶ በላይ ሰዎች በክትባቶች ላይ ያላቸው እምነት ሲጨምር ክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳት አለው ብለው የሚያምኑ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ቀንሷል። በዩናይት ኪንግደም ካሉ ሰዎች በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ከ78 በመቶ በላይ ሰዎች ክትባቱን ለመውሰድ ዝግጁ ናቸው። 6 - በሽታን የመከላከል አቅም ከ8 ወራት በላይ አይዘልቅም አንድ ሰው በኮቪድ-19 ተይዞ ከተሻለው በኋላ የሚኖረው የመከላከል አቅም ምን ያህል ነው? የሚለውን ለመለየት የተሠሩ ጥናቶች ሙሉ ገፅታውን አያሳዩም። የበሽታ የመከላከል አቅም ምን ያህል ይቆያል የሚለውን መለየት እጅግ ጠቃሚ ነው። ይህ የክትባት የመከላከል አቅምን ለመለየትም ያስችላል። ምንም እንኳ የእያንዳንዱ ሰው በሽታን የመከላከል አቅም ቢለያይም በበርካታ አገራት የተሠሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቆይታው ከ6 አስከ 8 ወራት መሆኑን ነው። ይህ የመከላከል አቅም ቆይታ ሰዎች በበሽታው እጅጉን ተጠቁም አልተጠቁም ተመሳሳይ ነው። 7 - በጣም ለተጎዱ ሰዎች መድኃኒት ፍለጋ ኮቪድ-19 ከሳንባ ምች [ኒሞኒያ] በላይ የከፋ መሆኑን መረዳት ተችሏል። ምንም እንኳ ኮሮናቫይረስን ነጥሎ የሚያጠቃ መድኃኒት ባይኖርም በጣም ለተጎዱ ሰዎች ከሞት የሚታደጉ መድኃኒቶችን ደባልቆ መስጠት ተችሏል። እኒህን መድኃኒቶች ደባልቆ መስጠት ያለውን ሚና የሚለዩ ከ400 በላይ ጥናቶች የሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። በየቀኑ የኮሮናቫይረስ በሽታ ለጠናባቸው ሰዎች የሚሆኑ መድኃኒቶች ቅመማ ከጊዜ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል። 8 - ጉንፋን መጥፋት ኮሮናቫይረስ ዓለምን ማዳረስ በጀመረበት ወቅት የነበረው አንዱ ፍራቻ በክረምት ወራት ከሚነሱ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ጋር እንዴት ያደርገናል የሚለው ነበር። እንደ ጉንፋን፣ ኢንፍሉዌንዛና አስም የመሳሰሉ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ በሽታዎች ወደ ሳንባ ምችና ብሮንካይትስ ሊያመሩ ይችላሉ። እነዚህ በሽታዎች በበርካታ የዓለማችን ክፍሎች በተለይ ደግሞ ተጋላጭ በሚባሉቱ አገራት እስከ ሞት የሚያደርሱ ናቸው። በኢንፍሉዌንዛና በኮሮናቫይረስ በአንድ ጊዜ የተጠቁ ሰዎች የመሞት ዕድል በኮቪድ-19 ብቻ ከተያዙት ላቅ ያለ ነው። በተለይ ደግሞ ዕድሜያቸው ከ70 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ አደጋው ይጨምራል። ነገር ግን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችን መጠቀም እንደ ጉንፋን ያሉ በሽታዎች እንዲቀንሱ ትልቅ ምክንያት ሆኗል። መልካሙ ዜና በክረምት ወራት የሚከሰቱ በሽታዎች ጉዳት እንደሌላው ጊዜ አለመሆን ነው። ነገር ግን ይህ ጉዳይ በቀጣዩ ዓመት ክረምት ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል ይገመታል። ኢንፍሉዌንዛ ኮሮናቫይረስ በባሕሪ በጣም የተለያዩ በሽታዎች መሆናቸውን ልብ ማለት ያሻል። 9 - የበሽታውን ዕድገት በየደቂቃው መከታተል እንችላለን አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ጥቅም ላይ እየዋሉ ባሉ ክትባቶች ላይ ያለው ኃያልነት እስካሁን በውል አልተረጋገጠም። ቢሆንም አንድ መልካም ዜና አለ። አሁን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ላይ እያንዳንዱን ለውጥ በቅርበት መከታተል ይቻላል። ሳይንቲስቶች የበሽታውን ዕድገት የሚያጠኑበትን መንገድ አዳብረዋል። ጥናቶቹ ካለፈው ዓመት የካቲት እስካሁድ ድረስ ያለውን የበሽታውን ዕድገት ከሥር ከሥሩ የሚከታተሉ ናቸው። እኒህ ጥናቶች የበሽታውን አካሄድ አጥንቶ መፍትሄ ለማበጀት ይረዳሉ። የአንድን ወረርሽኝ እያንዳንዱ ዕድገትና ���ውጥ በየደቂቃው ማጥናት የተቻለው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። 10 - የወረርሽኙ መቀዛቀዝ ተደጋግሞ እንደተጠቀሰው የኮሮናቫይረስ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል የሚለው አሁንም እርግጠኛ መልስ አልተገኘለትም። ነገር ግን እስካሁን የነበረውን አካሄድ በማየት በየጊዜ የወረርሽኙ ማዕበሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም። ቢሆንም ተፅዕኗቸው ከዚህ በፊት ከነበረው ዝቅ እያለ የሚመጣ ነው። አሁን እንደ መልካም ዜና እየተቆጠረ ያለው ወረርሽኙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከዚህ በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር መቀዛቀዝ ማሳየቱ ነው። ለዚህ እንደምክንያት ከሚጠቀሱ ነገሮች መካከል አንደኛው በሽታውን የመከላከል አቅም መዳበር ነው። ለመከላከል አቅም አንዱ አጋዥ መሣሪያ ደግሞ ክትባት ነው። ይህም የሽታውን መስፋፋት ለመግታት ትልቅ ተስፋን ሰጥቷል። https://www.bbc.com/amharic/news-56201441 +politics የሰላም ጥረቱ እና የተስተጓጎለው የአፍሪካ ኅብረት ንግግር ፈተናዎች ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. በትግራይ ውስጥ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የተለያዩ ወገኖች ሰላም እንዲወርድ ጥሪ ሲያቀርቡ እና ጥረት ሲያደርጉ እነሆ ሁለት ዓመት ሊሞላ ነው። በተለይ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መቀላጠፍ በሚል መጋቢት 15/2014 ዓ.ም. ላልተወሰነ ጊዜ የሚጸና የተኩስ አቁም ሲያውጅና የትግራይ ኃይሎችም በዚሁ ውሳኔ ሲስማሙ ለድርድር በር ይከፍታል የሚል ተስፋን ፈጥሮ ነበር። ይህንን አጋጣሚ በመጠቀምም የአፍሪካ ኅብረት፣ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና የቀድሞው የኬንያ መሪ ድርድር እንዲጀመርና ጦርነቱ ማብቂያ እንዲያገኝ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። በተለይ የአፍሪካ ኅብረት እና አሜሪካ በተደጋጋሚ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እንዲሁም ከትግራይ ኃይሎች መሪዎች ጋር በአዲስ አበባ እና በመቀለ ንግግር ቢያደርጉም ይህ ነው የተባለ ጦርነቱን የሚያስቆም ውጤት ሳያገኙ ቆይተዋል። የአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ተወካይ እና የአሜሪካ መንግሥት ልዩ ልዑክ ያደረጓቸው ጥረቶች፣ ወደ ትግራይ የሚደርሰውን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲሻሻል ያደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲጸና በማድረግ በዘላቂነት ጦርነቱን ለማስቆም ሳያስችል ቆይቷል። በተባበሩት መንግሥታት፣ በተለያዩ አገራት ያጋጠሙ ግጭቶችን ለማስቆም በተደረጉ ጥረቶች ውስጥ የሰሩት የሕግ ባለሙያ እና ዲፕሎማቱ አቶ ባይሳ ዋቅወያ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማብቃት ፈታኝ እና ውስብስብ ሁኔታዎች እንዳሉ ይናገራሉ። ነገር ግን የትኛውም ዓይነት ጦርነት በተለይም የእርስ በርስ ጦርነቶች የሚያበቁት በተፋላሚ ወገኖች መካከል በሚደረጉ ድርድሮች በመሆኑ “የቱንም ያህል ፈታኝ ሁኔታዎች ቢኖሩም ብቸኛው መፍትሔ ድርድር ነው” ይላሉ። ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱ በድርድር እንዲያበቃ ፍላጎት እንዳላቸው በተደጋጋሚ የገለጹ ሲሆን፣ ንግግሩን ማን ይምራው በሚለው ላይ ግን ልዩነት ነበራቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት የአፍሪካ ኅብረትን ብቸኛ ምርጫው ሲያደርግ፣ የትግራይ ኃይሎች ደግሞ የቀድሞውን የኬንያ ፕሬዝዳንት በአደራዳሪነት መርጠው ነበር። ይህም ከመነሻው ለንግግር የነበረውን ዕድል እንዲጓተት በማድረግ፣ ለመነጋገር የነበረውን ተስፋ እንዲደናቀፍ እና ጊዜ እንዲባክን አድርጎ ነበር። ነገር ግን የትግራይ ኃይሎች ሐሳባቸውን ቀይረው ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት በኩል እንዲካሄድ በመስማማታቸው የሰላም ተስፋው መልሶ አንሰራራ። ከዚህ በፊት ግን ሁለቱ ወገኖች ይፋዊ ባልሆነ መንገድ በአሸማጋዮች አማካኝነት መገናኘታቸው ሲነገር ነበረ። የትግራይ ኃይሎች በአንድ ደብዳቤያቸው ላይ ይህንኑ የገለጹ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ መ��ግሥት ግን ይህንን በሚመለከት ያለው ነገር የለም። የአውሮፓ ኅብረት ልዩ ተወካይ የሆኑት አኔት ቬበር በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ለኅብረቱ አባል አገራት ባሰራጩት አንድ ሰነድ ላይ፣ ሁለቱ ወገኖች በአሜሪካ አመቻችነት በተለያዩ ጊዜያት ይፋዊ ባልሆነ ሁኔታ በጂቡቲ እና በሲሸልስ መገናኘታቸውን ጠቅሰዋል። ይህም ቢሆን ግን ለጦርነቱ ማብቃት የሚያግዝ መደበኛ ድርድር ለማድረግ የሚያስችል ውጤትን ለማምጣት ሳይችል ቀርቷል። የእርስ በርስ ጦርነት መቋጫው ድርድር ነው የሚሉት በድርድር እና በዲፕሎማሲ ዓለም አቀፍ ልምድ ያላቸው አቶ ባይሳ ዋቅወያ፣ ሁለቱም ወገኖች ንግግር ለመጀመር ፍላጎታቸውን እንዲያሳዩ የተለያዩ ወገኖች ጫና እንዳለ ሆኖ፣ አምነውበት የሚገቡበት ነው የሚል አዎንታዊ አመለካከት አላቸው። ቢሆንም ግን በጦርነቱ ጅማሬ ወቅት በዓለም ላይ የነበረው ተጨባጭ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት የለም። በተለይ ምዕራባውያን ትኩረታቸው በዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት መያዙ፣ እንዲሁም በዓለም ዙሪያ የተከሰተው ምጣኔ ሀብታዊ ጫና ነገሮችን ለውጧል። አቶ ባይሳም ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች እና በአገር ውስጥ ያሉ ክስተቶች ተፋላሚ ወገኖች ፊታቸውን ወደ ድርድር እንዲያዞሩ አድርጓቸዋል ይላሉ። “በጦርነቱ ጅማሬ ወቅት የነበረው የምዕራባውያን ወደ አንድ ወገን ያዘነበለ ድጋፍ መመናመን፣ በትግራይ ላይ የቆየው ከበባ፣ በአገሪቱ እየተባባሰ የመጣው የምጣኔ ሀብት ቀውስ እና የኑሮ ውድነት ሁለቱንም ወገን ንግግርን እንዲመርጡ አስገድዷቸዋል።” ባለፉት ሁለት ዓመታት ጦርነቱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ነገር ግን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞት ዳርጓል ተብሎ ይታመናል። የተከሰተው ሰብአዊ ቀውስ ከትግራይ ባሻገር በአማራና በአፋር ክልሎች ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እርዳታ ጠባቂ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። አቶ ባይሳ ሁለቱም ወገኖች የጦርነቱን ከባድ ዋጋ ከማንም በላይ ይገነዘቡታል የሚሉት አቶ ባይሳ፤ ከተጠቀሱት ገፊ ምክንያቶች በተጨማሪ ይህ ደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ጦርነት “ማንም አሸናፊ ሆኖ የሚወጣበት ባለመሆኑ ሁለቱም ወገኖች በንግግር ችግራቸውን ይፈታሉ” የሚል ተስፋ አላቸው። ሁለቱም ወገኖች ንግግሩን እንዲመራ የተስማሙበት አህጉራዊው ድርጀት የሰላም ሂደቱን ለመጀመር ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለመገናኘት ማቀዱን በመግለጽ የግብዣ ጥሪውን መስከረም 21/2015 ዓ.ም. ማቅረቡ ሲነገር ለበርካቶች ድንገተኛ ነበር። በኅብረቱ የተጻፈ የጥሪ ደብዳቤ እንደሚለው በሁለቱ ወገኖች መካከል ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ንግግር ለቀጣይ ድርድር አስፈላጊ የሆኑ ዝርዝር ጉዳዮች ትኩረት እንደሚደረግባቸው አመልክቷል። ንግግሩንም ለአንድ ዓመት የኅብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ሆነው ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ እንደሚመሩትና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የቀድሞዋ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት እንደሚሳተፉ ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥትም የአፍሪካ ኅብረት ግብዣ ከዚህ በፊት ካንጸባረቃቸው አቋሞቹ ጋር የሚጣጣሙ በመሆናቸው በንግግሩ ውስጥ እንዲሳተፍ የቀረበለትን ግብዣ እንደሚቀበለው አሳወቀ። ከትግራይ ኃይሎች በኩልም የቀረበላቸውን የሰላም ንግግር ግብዣን እንደተቀበሉት ገልጸው፣ ነገር ግን ይህ ጥሪ ከመቅረቡ በፊት ከኅብረቱ ጋር ምክክር ባለመደረጉ የሰላም ውይይቱ ተሳታፊዎች፣ ታዛቢዎች እና ዋስትና ሰጪዎች፣ የጉዞ  እና የደኅንነት ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ጠይቀው ነበር። ለሁለቱም ወገኖች የንግግር ጥሪ ከቀረበ ከሳምንት በኋላ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ውስጥ ይካሄዳል የተባለው ንግግር፣ ሁለት ዓመት ሊሞላ��� በተቃረበው ጦርነት ውስጥ ከታዩት ሁሉ ጉልህ እመርታ ሊሆን እንደሚችልና ለቀጣይ ሰላም መሠረት ይጥላል የሚል ተስፋን በብዙዎች ዘንድ ፈጥሮ ነበር። የአፍሪካ ኅብረትም “በሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች መካከል የሚካሄደው ይህ የሰላም ውይይት ጦርነቱን በሰላም ለመቋጨት መሠረት የሚሆኑ መርሆች፣ የአጀንዳ ጉዳዮች፣ አሰራሮች እና የጊዜ ሰሌዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል” ብሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች በንግግሩ ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆናቸውን መግለጻቸውን ተከትሎ፣ አፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ሁለቱም ወገኖች ለግብዣው አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸውን አድንቀው፣ ለሰላም ዕድል እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበው ነበር። ጨምረውም ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ እና የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞዋ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ-ናግኩካ የሚመራ መሆኑን ይፋ አድርጓል። ውይይቱ የሚጀመርበት ዕለት አንድ ቀን ሲቀረው አርብ ከሰዓት በኋላ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ፣ ባጋጠመ የሎጂስቲክስ እክል ምክንያት ንግግሩ ወደ ሌላ ጊዜ መተላላፉን ዘገበ። ነገር ግን ምክንያት ሆነው የሎጂስቲክስ ችግር ምን እንደሆነ ዲፕሎማቶቹ በግልጽ ያሉት ነገር አልነበረም። ይህንን ተከትሎ ደግሞ ከአሸማጋዮቹ አንዱ የሆኑት የቀድሞው የኬንያው ፕሬዝዳንት ድርድሩ የሚጀመርበት ጊዜ ካላቸው ከሌላ ዕቅድ ጋር የሚደራረብ መሆኑን ጠቅሰው መገኘት እንደማይችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መጻፋቸው ይፋ ሆነ። ነገር ግን የኡሁሩ ጥያቄ የጊዜ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ያነሷቸው ጉዳዮች እንዳሉ ደብዳቤያቸው ላይ ጠቅሰዋል። ኡሁሩ በሌላ ጊዜ በሂደቱ ለመሳተፍ እንደሚችሉ፣ ነገር ግን ንግግሩ ስለሚካሄድበት ሂደት አወቃቀር እና አፈጻጸም፣ የተጋበዙ አሸማጋዮች መመሪያ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። እንዲሁም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ማድረግ ከንግግሩ ከአጀንዳዎች ሁሉ ቀዳሚው መሆን እንዳለበት እና ይህም ለንግግሩ ትክክለኛውን ሁኔታ ይፈጥራል በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። ዲፕሎማቱ አቶ ባይሳ እንደሚሉት፣ በዚህ ንግግር ጦርነቱን የሚቋጭ ስምምነት ላይ አይደርሱም። ሁለቱ ወገኖች ንግግር መጀመራቸው ዋነኛው ጉዳይ ነው። በዚህም ለቀጣይ ድርድር የሚያስፈልገውን ተኩስ አቁም ላይ መስማማት እንዲሁም ለጦርነቱ መቋጫ ለሚያስፈልጉ ጉዳዮች ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት እና መስማማት ቀዳሚ እንደሚሆን ያምናሉ። ነገር ግን ይህንን ጦርነት ለማብቃት የሚደረገው ድርድር ቀላል እንደማይሆን የሚጠቅሱት አቶ ባይሳ “እንዲህ አይነት ውስብስብ ፖለቲካዊ ሁኔታ ያለበት ግጭት አይቼ አላውቅም” በማለት ጦርነቱ በቶሎ እንዲያበቃ ይመኛሉ። ባለፈው ነሐሴ የተቀሰቀሰው ጦርነት እየተካሄደ ባለበት፣ ከዚህ በፊት ከታየው በተለየ ሁለቱም ወገኖች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ንግግር ለመጀመር ፍላጎታቸውን ባሳዩበት ሁኔታ በአደራዳሪዎች በኩል ገጠሙ በተባሉ እንቅፋቶች ተስተጓጉሏል። የአፍሪካ ኅብረትም በመጨረሻው ሰዓት ላይ ገጠሙት የተባሉት የሎጂስቲክስ ችግሮችን በተመለከ እንዲሁም በኡሁሩ ኬንያታ በኩል የቀረቡ ጥያቄዎችን በተመለከተ እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። እንዲሁም የገጠሙ ችግሮች ተቀርፈው በቀጣይ ንግግሩ መቼ ሊደረግ እንደሚችል የሚለው እየተጠበቀ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c0w5l1rrxz2o +politics በቡርኪናፋሶ በደረሰ ጥቃት ከ130 በላይ የአንዲት መንደር ነዋሪዎች ተገደሉ "በቡርኪናፋሶ በደረሰ ጥቃት ከ130 በላይ የአንዲት ነዋሪዎች መገደላቸው ተገልጿል። በሰሜን የአገሪቷ ግዛት የደረሰው ይህ ጥቃት በታጣቂዎች የተፈፀመ ሲሆን መንግሥትም እስካሁን ከደረሱት ከፍተኛው ነው ብሏል። ሶልሃን የተባለችውን መንደር ታጣቂዎች ከበው በርካታ ቤቶችንና የአካባቢውንም ገበያ በአንድ ምሽት አቃጥለዋል። ለዚህ ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም በድንበር አካባቢ ፅንፈኛ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃት ያደርሳሉ ይባላል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ኃላፊ ጥቃቱን ""አሰቃቂ"" ሲሉ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳዘናቸውም አስታውቀዋል። ኃላፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ ""ይህንን አሰቃቂና አፀያፊ ጥቃት እናወግዛለን። ጥቃቱም ፍንትው አድርጎ ያሳየን አገራት የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ ያለውን ፅንፈኝነት ለመዋጋት በሚያደርጉት ጥረት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ርብርብና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ነው"" በማለት በቃለ አቀባያቸው በኩል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የቡርኪናፋሶ ፕሬዚዳንት ሮች ካባሬ በዚህ ጥቃት ህይወታቸውን ላጡት የሶስት ቀን ኃዘን ያወጁ ሲሆን በትዊተር ገፃቸውም ባስተላለፉት መልዕክት ""አነዚህ የጥፋት ኢላማዎችን ለመቋቋም በአንድነት መቆም አለብን"" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ አክለውም የነዚህን ንፁኃን ህይወት የቀጠፉትን ታጣቂዎቸም በቁጥጥር ስር ለማዋል የፀጥታ ኃይሎች መሰማራታቸውን ነው። በያዝነው ሳምንት አርብ እንዲሁ በደረሰ ሌላ ጥቃት 14 ሰዎች በአንዲት መንደር ውስጥ ተገድለዋል። ጥቃቱ የደረሰው ታዳርያት በምትባል መንደር ሲሆን አሁን ጥቃቱ ከተፈፀመባት ሶልሃን በ150 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። በባለፈው ወር እንዲሁ በምስራቅ ቡርኪናፋሶ 30 ሰዎች ተገድለዋል። አገሪቷ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታና ደህንንነት ችግር የገጠማት ሲሆን ልክ እንደ ሌሎች ጎረቤቶቿ አገራትም የታጠቁ ቡድኖች መንደሮችን ከበው የንፁኃንን ዜጎች ይቀጥፋሉ እንዲሁም ሰዎችን ይጠልፋሉ። ይህንንም ለመግታት በሚል መንግሥት ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ዘመቻ በግንቦት ወር ቢጀምርም የንፁኃንን ዜጎች ህይወት ከመቀጠፍ አልታደጉትም። በባለፉት ሁለት አመታት በደረሱ ጥቃቶች ከሚሊዮን በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57360811 +health ኮሮናቫይረስ፡ ሁለት ጊዜ ከቡራዩ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ያመለጡት እስረኞች እየተፈለጉ ነው "የምስራቅ ሸዋ ቦራ ወረዳ የሕግ ታራሚዎችና በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሁለት ወጣቶች ቡራዩ ወደሚገኘው የኮቪድ-19 የህክምና ማዕከል ከተወሰዱ በኋላ፤ ከህክምና ማዕከሉ ለሁለተኛ ጊዜ ማምለጣቸው እና ፖሊስ እየፈለጋቸው እንደሆነ ተነገረ። ሻሎ ፊታላ እና ኢሳቾ አበበ የተባሉት ሁለት ወጣቶች እና ሌሎች 3 ታራሚዎች በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦረ ወረዳ ባለ በእስር ቤት ሳሉ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ለህክምና ወደ ቡራዩ ከተማ መወሰዳቸውን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሚሊዮን ታፈሰ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከላይ ስማቸው የተጠቀሰው ሁለቱ ወጣቶች፤ ወደ ቡራዩ በተወሰዱ በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ከለይቶ ህክምና ማዕከሉ ማምለጣቸውን ኢንስፔክተር ሚሊዮን ተናግረዋል። ሁለቱ ወጣቶች ከለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከሉ ካመለጡ በኋላ ወደ ቤተሰቦቻቸው መኖሪያ ቀዬ መመለሳቸውን ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል። ""ወጣቶቹ ከህክምና መስጫው አምልጠው ወደ ወረዳችን ነው የመጡት። በደረሰን ጥቆማ መሠረት ህዝቡን አስተባብረን አንድ የገጠር መንደር ውስጥ ከያዝናቸው በኋላ ወደ ቡራዩ መልሰናችዋል"" ብለዋል። ወጣቶቹ ወደ ለይቶ ማቆያ ማዕከሉ እንዲመለሱ ከተደረጉ ከአራት ቀናት በኋላ ማለትም ቅዳሜ ���ሐሴ 2 ለሁለተኛ ጊዜ ከማዕከሉ ማምለጣቸውን የፖሊስ አዛዡ ተናግረዋል። ""ለሁለተኛ ጊዜ ማምለጣቸውን ከሰማን በኋላ ፍለጋችንን አጠናክረን እየሰራን ነው። ቤተሰቦቻቸው ጋር የሉም። ገጠር ድረስ የህብረሰብ ክፍል መረጃ አድርሰናል። እስካሁን ግን አለገኘናቸውም። ምናልባት ወደ ሌላ ወረዳዎች ውስጥ ተደብቀው ሳይቀሩ አይቀርም"" ብለዋል። የቦራ ወረዳ ምክትል የጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፍጹም ወርቅነህ፤ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ""ከለይቶ ማከሚያ ማዕከል ያመለጡት ወጣቶች ጉዳይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮብናል"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53761489 +health እስካሁን በኮሮናቫይረስ ያልተያዙ ሰዎች ለምን ሳይያዙ ቆዩ? የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተከስቶ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በሁሉም አገራት የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህመም፣ ከተወሳሰበ የጤና ችግር እና ለሞት ዳርጓል። ይህ በሽታ ከተከሰተ ሁለት ዓመት ያለፈው ሲሆን ከመተላለፊያ መንገዶቹ አመቺነት የተነሳ በአጭር ጊዜ መላውን ዓለም አዳርሷል። አንዳንዶች እንዲያውም አብዛኛው የዓለም ሕዝብ በበሽታው የመያዝ ዕድል አለው ይላሉ። ከወረርሽኙ የስርጭት ፍጥነት እና ስፋት አንጻር በርካቶች ለቫይረሱ የተጋለጡ ቢሆንም፣ ተጋላጭ ቢሆኑም በርካቶች አስካሁን በሽታው አልያዛቸውም ይባላል። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው? https://www.bbc.com/amharic/articles/ce9ne2g26qeo +health ረዥም ሰዓት መሥራት በዓመት የ 745 ሺህ ሰዎችን ህይወት እየነጠቀ ነው-ጥናት "ረዥም ሰዓት መሥራት በዓመት በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት እየነጠቀ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡ በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው ዓለም አቀፍ ጥናት መሠረት እአአ በ 2016 ከረዥም ሰዓታት ሥራ በሚከሰት ስትሮክ እና የልብ ህመም ምክንያት 745,000 ሰዎች መሞታቸውን ይፋ አደርጓል፡፡ ሪፖርቱ እንዳመለከተው በደቡብ ምስራቅ እስያ እና በምዕራብ ፓስፊክ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በችግሩ በጣም የተጠቁ ናቸው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ከሆነ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ችግሩ ሊባባስ ይችላል፡፡ ጥናቱ እንዳመለከተው በሳምንት ለ 55 ሰዓታት እና ከዚያ በላይ መሥራት በሳምንት 35 እስከ 40 ሰዓታት በሳምንት ከሚሠሩት ጋር ሲነፃፀር 35 በመቶ በስትሮክ እና 17 በመቶ ደግሞ በልብ ህመም የመሞት ዕድላቸው የጨመረ ነው፡፡ ከዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት (አይኤልኦ) ጋር የተደረገው ጥናቱ እንደሚያሳየው ረዘም ላለ ሰዓት በመሥራታቸው ከሞቱት መካከል ሶስት አራተኛ የሚሆኑት በመካከለኛ ዕድሜ ወይም ዕድሜያቸው የገፋ ወንዶች ናቸው፡፡ ብዙውን ጊዜ በዚህ ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡት ከብዙ አሥርት ዓመታት በኋላ ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት የተከሰተውን ወረርሽኝ ጊዜ አላካተተም። የድርጅቱ ባለሥልጣናት በቅርቡ ከቤት መሥራት እና የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ከረዥም የሥራ ሰዓታት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን ሳይጨምረው አይቀሩም ብለዋል ፡፡ ""ሃገራት ወደ ብሄራዊ እንቅስቃሴ ገደብ ሲገቡ የሥራ ሰዓት በ 10 በመቶ ገደማ እንደሚጨምር የሚያሳዩ ጥቂት ማስረጃዎች አሉን"" ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት የቴክኒክ ባለሙያው ፍራንክ ፔጋ ናቸው። ሪፖርቱ እንደሚለው ከሥራ ጋር ተያያዥነት ካላቸው ህመሞች አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ከረዥም ሰዓት መሥራት ጋር እንደሚገናኙ ይገመታል፡፡ ተመራማሪዎቹ እንዳሉት ረዥም የሥራ ሰዓታት ለጤንነት መጥፎ ውጤት የሚያስከትሉባቸው ሁለት መንገዶች አሉ። አንደኛው ለጭንቀት የሚሰጠው ቀጥተኛ የፊዚዮሎጂ ምላሾች ናቸው። ሁለተኛው ደግሞ ረዥም ሰዓት የሚሠሩ ሠራተኞች እንደ ትምባሆ እና አልኮል መጠጣትን፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካለማድረግ፣ ጤናማ ካልሆ�� አመጋገብ እና የመሳሰሉ ጤናን የሚጎዱ ባህሪያትን የመልመድ ዕድላቸው ከፍተኛ በመሆኑ ነው። የሊድስ ነዋሪ የሆነው የ 32 ዓመቱ መሐንዲስ አንድሪው ፋልስ በቀድሞ ድርጅቱ ያሳለፈው ረዥም የሥራ ሰዓት በአዕምሮው እና በአካላዊ ጤንነቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ይናገራል፡፡ ""ከሃምሳ እስከ 55 ሰዓት በሳምንት መሥራት የተለመደ ነበር፡፡ ለሳምንታትም ከቤቴ እርቅ ነበር"" ብሏል፡፡ ""ጭንቀት እና ድብርት ይመላለሱብኝ ነበር"" ብሏል፡፡ ""ወደታች በሚወርድበት የማያቋርጥ ሁኔታ ውስጥ ነበርኩ"" ሲል ይገልጻል፡፡ ከአምስት ዓመታት በኋላ የሶፍትዌር መሐንዲስ ሆኖ ለመሥራት ሥራውን ለቀቀ፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሠረት ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት ለረጅም ሰዓታት የሚሠሩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን ከጠቅላላው የዓለም ህዝብም ወደ 9 በመቶ ገደማ ናቸው፡፡ የዩኬ በብሔራዊ ስታትስቲክስ ቢሮ እንደሚለው በወረርሽኙ ወቅት ከቤት የሚሠሩ ሰዎች በሳምንት በአማካይ ስድስት ሰዓት ያለክፍያ የትርፍ ሰዓት ሥራዎችን ያከናውኑ ነበር ብሏል፡፡ ከቤታቸው የማይሠሩ ሰዎች በሳምንት በአማካይ በ 3.6 ሰዓታት የትርፍ ሰዓት ሥራ ብቻ ይሠራሉ ሲል ቢሮው አስታውቋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት አሠሪዎች የሠራተኞቻቸውን የሥራ ጤና አደጋዎች ሲገመግሙ ይህንንም ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው ይላል፡፡ የቁርጥ ሰዓት ሥራ ምርታማነትን እንደሚያሳድግ በመታየቱ ለአሠሪዎች ጠቃሚ ይሆናል ሲሉ ፒጋ ገልጸዋል፡፡ ""በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ረዥም የሥራ ሰዓቶችን አለመጨመር የብልህ ምርጫ ነው"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57159219 +health በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ ሦስት ሰዎች ሞቱ "በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ 3 ሰዎች ሞቱ። ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ ተቅማጥ፣ ማስመለስና የመድማት ምልክቶችን እያሳዩ እንደሆነ ተነግሯል። አራቱ ሰዎች እነዚህን ምልክቶች ማሳየት የጀመሩት የአንድ በኢቦላ የሞተችን ነርስ ቀብር ከታደሙ በኋላ ነበር። ባለሥልጣናት አዲስ የተሰራ ክትባት በዓለም ጤና ድርጅት በኩል እንደሚገኝ እየተናገሩ ነው። በፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2016 ብቻ በምዕራፍ አፍሪካ ኢቦላ ወረርሽኝ የ11ሺ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። ወረርሽኙ ጊኒን ጨምሮ ጎረቤቶቿን ላይቤሪያንና ሴራሊዮንን በከፍተኛ ሁኔታ አጥቅቶ ነበር። ይህን ተከትሎም በርካታ ክትባቶች ተሞክረዋል። ክትባቶቹ ወረርሽኞቹን ለማቆም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ አገልግሎት ላይ ሲውሉ ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት የጊኒ ተወካይ አልፍሬድ ጆርጅ ኪ ዜርቦ ""አስፈላጊውን ክትባት ለማቅረብ የዓለም ጤና ድርጅት ከመድኃኒት አምራቾች ጋር እየተነጋገረ ነው ብለዋል። የኢቦላ ክትባት ለመጀመርያ ጊዜ በ2015 በጊኒ ሙከራ ተደርጎ ውጤት ማስገኘቱ ይታወሳል። ከክትባቱ ሌላ ታማሚው የመዳን እድሉን የሚጨምሩ መድኃኒቶች መፈብረካቸውም ይታወቃል። አሁን በጊኒ የተቀሰቀሰው ኢቦላ በአንድ ጤና ጣቢያ ትሰራ የነበረች ነርስ ታማ ከሞተች በኋላ በቀብሯ ላይ የተገኙ ሰዎች በተህዋሲው መጠቃታቸው ነው የተነገረው። ነርሷ ከሞተች ከ4 ቀናት በኋላ ነበር የተቀበረችው። ምናልባት አስክሬን በማጠብ ላይ የነበሩ ሰዎች ተህዋሲውን እንዳዛመቱ ይገመታል። ብዙውን ጊዜ በኢቦላ የሞቱ ሰዎች አስክሬን አደገኛና መርዛማ የኢቦላ ተህዋሲን የመሸከም አቅም አለው። የተህዋሲው እድሜም ከ2 ቀን እስከ 3 ሳምንት ይቆያል። ኢቦላ ቺምፓዚን ከመሰሉ እንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ተህዋሲ ነው። ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውም በደም፣ በሰውነት ፈሳሽ ወይም ተህዋሲው ከነካው አካባቢ ሊሆን ይችላል። አሁን ሁሉም በተህዋሲው የተለከፉት እድሜያቸው ከ25 ዓመት በላይ የሆኑና የነርሷን ቀብር ���ታደሙት ናቸው። የወረርሽኙን መቀስቀስ ተከትሎ ሴራሊዯንና ላይቤሪያ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ። የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ለጤና ሚኒስትሮቻቸው ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተሉ አዘዋል። የቢቢሲ ዘጋቢ ከሴራሊዯን እንደጻፈችው በአገሪቱ ከኮቪድ ተህዋሲ በላይ ሕዝቡ ስጋት ያለበት ለኢቦላ ወረርሽኝ ነው። ኢቦላ ተህዋሲ ድንገቴ ትኩሳት በመፍጠር በአጭር ሰዓት ታማሚውን በማዳከም የጡንቻ ከባድ ሕመም ፈጥሮ ጉሮሮን አቁሱሎ የሚገድል በሽታ ነው። ከዚህም ባሻገር ማስመለስ፣ ማስቀመጥ እና የውስጥና የውጭ መድማትን ያስከትላል። ታማሚዎች የሚሞቱት ብዙውን ጊዜ ፈሳሽ ከሰውነታቸው ተሟጦ ስለሚያልቅ ነው። ይህም የአንዳች ሰውነት አካል ሥራ ማቆምን ያስከትልና ለሞት ይዳርጋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56066789 +sports የጣልያኑ እግር ኳስ ኮከብ ቀብር ወቅት ቤቱ ተዘረፈ "በፈረንጆቹ 1982 የዓለም ዋንጫን ያነሳው የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አባል የነበረው ፓውሎ ሮሲ ቀብር እየተፈፀመ ባለበት ወቅት ሌቦች ቤቱ ገብተው ዘረፉት። የጣልያን መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ትላንት [ቅዳሜ] የእግር ኳስ ኮከቡ ቀብር እየተፈፀመ መሆኑን አጥንተው የመጡ ሌባዎች ናቸው ቤቱን የመዘበሩት። ባፈለው ሐሙስ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ጣልያናዊው ፓውሎ ሮሲ ቀብር በሰሜን ምስራቋ ቪሴንዛ ከተማ ተፈፅሟል። አንሳ የተባለው የጣልያን ዜና ወኪል እንደዘገበው የሮሲ ባለቤት ፌዴሪካ ካፔሌቲ ከቀብር ስትመለስ ቤቷ ተበርብሮ ነው ያገኘችው። ሌቦቹ ከዘረፉት ንብረት መካከል የፓውሎ ሮሲ እጅ ሰዓትና ጥሬ ገንዘብ ይገኝበታል። ፖሊስ ጉዳዩን ምርምሬ ዘራፊዎች ማን እንደሆኑ እደርስበታለሁ ብሏል። ሮሲና ቤተሰቡ ፖጊዮ ሲዜና በተባለች የፍሎረንስ ገጠር አውራጃ ውስጥ ነው የሚኖሩት። ሮሲ በመኖሪያ አካባቢው አንድ የግብርና ኩባንያ አለው። ሮሲ በጣልያን እንደ ጀግና ነው የሚቆጠረው። ለዚህም ነው ሞቱ ብዙዎችን ያስደነገጠው። የጣልያን እግር ኳስ ወርቃማ ዘመን አባል የነበረው ሮሲ ሃገሪቱ ካፈራቻቸው ምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ ተደርጎ ይቆጠራል። ለጣልያን ብሔራዊ ቡድን 48 ጊዜ ተሰልፎ 20 ኳሶችን ከመረብ አሳርፏል። በ1982ቱ የዓለም ዋንጫ ፓውሎ ሮሲ 6 ጎሎችን በማስቆጠር ሃገሩ ጣልያን ዋንጫ እንድታነሳ አግዟል። በክለብ ደረጃ ደግሞ ለቪሴንዛ እና ጁቬንቱስ ተጫውቷል። ሁለት ጊዜ የሴሪ አ ዋንጫ ማንሳትም ችሏል። ቅዳሜ ዕለት የነበረውን ቀብር በርካቶች ታድመውበታል። በተለይ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ የቪሴንዛ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ቀብሩን ታድመዋል። በ1982 ከሮሲ ጋር የዓለም ዋንጫን ያነሱ የቡድን አጋሮቹ የሮሲን አስከሬን ተሸክመው ወደ ሳንታ ማሪያ አኑሲያታ ካቴድራል ወስደዋል። ከቡድን አጋሮቹ መካከል ማርኮ ታርዴሊ፣ ጂያንካሪዬ አንቶጎኖኒ፣ አንቶኒዮ ካብሪኒ እንዲሁም ፉልቪዬ ኮሎቫቲ ይገኙበታል። ""የቡድን አጋሬን ብቻ ሳይሆን ወንድሜን ነው ያጣሁት"" ብሏል አንቶኒዮ ካብሪኒ። ከቀብሩ በፊት የሮሲ አስከሬን ቪሴንዛ ውስጥ ስታዲዮ ሮሜዬ ሜንቲ በተሰኘው ስታድየም እንዲቀመጥ ተደርጎ ነበር። የተጨዋቾቹ ደጋፊዎችና አድናቂዎች ወደ ስታደየሙ በማቅናት አበባ ሲያስቀምጡ ታይተዋል። ቅዳሜ ዕለት በተካሄዱ የሴሪ አ ጨዋታዎች ላይ ተጫዋቾች ለሟቹ ሮሲ ክብር ጥቁር አርማ ክንዳቸው ላይ አስረው ታይተዋል። ጨዋታዎቹ ከመጀመራቸው በፊትም የአንድ ደቂቃ የሕሊና ፀሎት ተካሂዶ ነበር። የሮሲ ፎቶ በስታድየሞቹ ግዙፍ ስክሪን ላይ ተሰቅሎም ታይቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55292306 +sports የዓለም ዋንጫ በየሁለት ዓመቱ እንዲካሄድ የቀረበው ሃሳብ ተቃውሞ ገጠመው "የዓለም ዋንጫ በየሁለት ዓመቱ መከናወኑ በሌሎች ስፖርቶች እና በሥርዓተ ፆታ እኩልነት ላይ ችግር ያስከትላል ይጥላል ሲል ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ተቃውሞውን ገለጸ። ፊፋ በየሁለት ዓመቱ የወንዶችን የዓለም ዋንጫ ለማካሄድ የያዘው ዕቅድ ለሌሎች ስፖርቶችና የሥርዓተ ፆታ እኩልነት ላይ ሥጋት ሊሆን ይችላል ብሎ እንደሚያምን የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (ኢይኦሲ) ገለጸ። በየሁለት ዓመቱ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ እና በታላቁ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች መካከል በተመሳሳይ ጊዜ የመደረግ እና መደራረብ ሊፈጥር ይችላል። የኦሊምፒክ የሴቶች የእግር ኳስ ውድድርም ትልቅ ቦታ ያለው ነው። የአይኦሲ በመግለጫው ከሌሎች ውድድሮች ጋር የሚያጋጥም መደራረብ ""የስፖርትን ብዝሃነት እና ልማት"" ያዳክማል ብሏል። አክሎም ተጨማሪ የወንዶች ስፖርት መኖሩ ለሴቶች እግር ኳስ ""ተግዳሮቶችን"" ይፈጥራል ብሏል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር እና 10 የአውሮፓ ሴቶች ሊጎች በሰጡት የጋራ መግለጫ ዕቅዶቹ ""በጣም ጎጂ"" ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል። የሴቶች የዓለም ዋንጫ ከትልቅ የወንዶች ውድድር ጋር በተመሳሳይ ወቅት ይካሄዳል በማለት በመስከረም ወር ደግሞ የወንዶች ሊጎች የዓለም የእግር ኳስ የበላይ አካል ሃሳብን መቃወማቸውን አረጋግጠዋል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተጫዋቾችን ደኅንነት ጨምሮ በሌሎች የስፖርት አካላት የተነሱትን ስጋቶችን እንደሚጋራ ገልጾ፣ የዓለም ዋንጫን ድግግሞሽ በእጥፍ ማሳየቱ ""በተጫዋቾች አካላዊ እና አእምሯዊ ጤና ላይ የበለጠ ከባድ ጫና ይፈጥራል"" ብሏል። የኦሊምፒክ የበላይ አካል ከስፖርተኛ ተወካዮች ጋር ሰፊ ምክክር እንዲደረግ የሚደረገውን ጥሪ እንደሚደግፍ ገልጾ ይህ ""በግልጽ እንዳልተደረገ"" አስታውቋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58919819 +health ኮሮናቫይረስ ፡ በቫይረሱ የተያዙ በመጀመሪያዎቹ ቀናት የማስተላለፍ እድላቸው ሰፊ መሆኑ ተጠቆመ "በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ምልክቶች በማያሳዩባቸው የመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ውስጥ ቫይረሱን የማስተላለፍ ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን አንድ ጥናት ጠቆመ፡፡ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ሳይንቲስቶች ከሆነ ቫይረሱ ያለባቸውን ቀደም ብሎ በለይቶ ማቆያ ማስገባት ስርጭቱን ለማስቆም ወሳኝ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ የጥናት ውጤቱ በላንሴት ማይክሮብ ላይ ታትሟል። ግለሰቦች የማስተላለፍ ዕድላቸው በብዙ ነገሮች ላይ የተመረኮዘ ሲሆን ራሱን የሚያባዛ ቫይረስ እና በሰውነታቸው ውስጥ ያለው የቫይረስ መጠን ስርጭቱን ከሚወስኑት መካከል ናቸው። አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሰዎች የበሽታ ምልክቶች ከማሳየታቸው በፊት እና በቫይረሱ በተያዙ የመጀመሪያው ሳምንት በጣም አስተላላፊ ናቸው፡፡ በሆስፒታል ውስጥ የበሽታው ምልክት ያለባቸውንና ቫይረሱ የተገኘባቸውን ጨምሮ ሳይንቲስቶች በኮቪድ-19 ላይ 79 ዓለም አቀፍ ጥናቶችን መርምረዋል። ተመራማሪዎች ኢንፌክሽኑ ከጀመረ እስከ ዘጠኝ ቀናት ድረስ ከተወሰዱ የጉሮሮ ናሙናዎች ውስጥ ዋነኛ ቫይረሶችን መለየት እና ማባዛት ችለዋል፡፡ ምልክቶቹ በጀመሩበት ጊዜ ወይም በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍተኛ የቫይረስ ስርጭት እንደሚኖር ከሰዎች የጉሮሮ ናሙና ማወቅ ችለዋል። ምልክቶቹ ከጀመሩ በአማካይ እስከ 17 ቀናት በአፍንጫ እና በጉሮሮ ናሙናዎች ንቁ ያልሆኑ የቫይረስ ቁርጥራጮች ተገኝተዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ እነዚህ ቁርጥራጮቻቸው ከዘጠኝ ቀናት በላይ ቢቀጥሉም አብዛኛዎቹ ሰዎች የማስተላለፍ ዕድላቸው አነስተኛ ነው ብለዋል፡፡ የሴንት አንድሪውስ ዩኒቨርስቲ ባልደረባው ዶ/ር ሙጌ ሴቪክ ለቢቢሲ እንደገለጹት ግኝቶቹ ሰዎች ገና በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት በጣም አስተላላፊ እንደሆኑ አሳይተዋል፡፡ ""ሰዎች የሕመም ምልክቶችን እን���ሳዩ እንዲለዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ምርመራ ውጤቶችን በሚያገኙበት ጊዜ በጣም አስተላላፊ የሚሆኑበትን ደረጃቸውን ያልፉ ይሆናል።"" ""ስለዚህ አንዳንድ ሰዎች ወዲያውኑ ራሳቸውን ያለዩበትን ምክንያት በመመልከት ይህንን እንዲያደርጉ ልንረዳቸው ይገባል"" ብለዋል፡፡ ጥናቱ ምልክት የማያሳዩ ሰዎችን አላካተትም። ሆኖም ሌሎች ጥናቶችን እንደሚያስጠነቅቁት ሰዎች የበሽታ ምልክቶች ከማሳየታቸው በፊትም አስተላላፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ እና ምንም ዓይነት የበሽታ ምልክት ሳይኖር ቫይረሱ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ የእንግሊዝ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ካላቸው ወዲያውኑ ራሳቸውን ቢያንስ ለ 10 ቀናት ማግለል አለባቸው፡፡" https://www.bbc.com/amharic/55026691 +sports እንግሊዝ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰች እንግሊዝ በዩሮ 2020 ፍልሚያ ዴንማርክን በመርታት ከ55 ዓመት በኋላ ለአንድ ትልቅ የእግር ኳስ ውድድር ፍፃሜ ደርሳለች። በርካታ ተመልካች በተሰበሰበበት በለንደኑ ዌምብሊ የተካሄደው ጨዋታው ልብን ሰቅዞ የሚይዝ ነበር። እንግሊዝ በፈረንጆቹ 1966 ምዕራብ ጀርመንን በመርታት ካነሳችው የዓለም ዋንጫ ውጭ ውድድር አሸንፋም ይሁን ለፍፃሜ በቅታ አታውቅም። ረቡዕ ምሽት ዴናማርክን የገጠመችው እንግሊዝ አንድ ለምንም ስትመራ ብትቆይም ከ120 ደቂቃዎች ፍልሚያ በኋላ 2-1 መርታት ችላለች። 66 ሺህ ሰዎች በታጩቀበት የተፋለሙት ሶስቱ አናብስት የተሰኘ ቅጥያ ያላቸው እንግሊዞች ይህን ጨዋታ በማሸነፋቸው በፍፃሜው ከጣልያን ጋር ይገናኛሉ። እንግሊዝ እሁድ ምሽት ጣልያን የምትገጥመው በገዛ ሜዳዋና ሕዝቧ ፊት ነው። ምንም እንኳ ዴንማርክ በወጣቱ ዳምስጋርድ ግሩም ቅጣት ምት አማካይነት ጨዋታውን ስትመራ ብትቆይም የኋላ ኋላ እጇን ሰጥታለች። ነገር ግን የመጀመሪያ አጋማሽ ከመጠናቀቁ በፊት የእንግሊዙ ቡካዮ ሳካ ወደ ጎል የላካትን ኳስ ሳይመን ኬር በራሱ መረብ ላይ በማሳረፉ ጨዋታው አቻ ሆነ። የዴንማርኩ ግብ ጠባቂ ካስፐር ሽማይክል የዳኒሾች ጎል ደጀን ሆኖ ቢያመሽም ከሽንፈት አልታደጋቸውም። ሽማይክል ከሃገሪ ማክጓዬርና ሃሪ ኬን የተቃጡበትን የጎል ሙከራዎች እያዳነ ቢያመሽም ጨዋታው ተጨማሪ 30 ደቂቃዎች ከታከሉበት በኋላ የተሰጥውት ፍፁም ቅጣት ምት ግን ማዳን አልቻለም። 103ኛው ደቂቃ ላይ ራሂም ስተርሊን ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ተጠልፎ ወድቋል ሲሉ ዳኛው ቅጣት ምት ይሰጣሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ የስታድየሙ ታዳሚያን በሁለት ተከፍለው ቅጣት ምቱን በጉጉት ይጠባበቃሉ። ሃሪ ኬን ኳሷን ወደ መረቡ ሲሰዳት ሽማይክል ያገኛታል። ነገር ግን ሲተፋት ተመልሳ የሃሪ ኬን እግር ላይ ታርፋለች። ይህን ወርቃማ ዕድል ያገኘው ኬን ኳሷን ከመረብ ያዋህዳል። ዴንማርክ የዳኛው ውሳኔ ትክክል አይደለም ብለው አቤቱታ ቢያቀርቡም ሰሚ አላገኙም። እንግሊዞች የግማሽ ፍፃሜ እርግማን አለባቸው ይባላል። ምክንያቱ ወዲህ ነው። በወጣት ተጫዋቾች የተሞላችው እንግሊዝ ባለፈው የዓለም ዋንጫ [2018] ለግማሽ ፍፃሜ ደርሳ መሸነፏ ይታወሳል። ጣልያን በተካሄደው የ1990 ዓለም ዋንጫ ላይ እንዲሁ ለግማሽ ፍፃሜ ደርሰው ተሸንፈዋል። በድጋሚ ጣልያን ባስተናገደችው የ1996 አውሮፓ ዋንጫ ላይ ለግማሽ ፍፃሜ የደረሰችው እንግሊዝ ሽንፈት ተከናንባ ነበር። ዘንድሮ ግን ይህንን ሽራ ለፍፃሜ ማለፍ ችላለች። የፍፃሜው ጨዋታ እሁድ ምሽት ይከናወናል። እንግሊዝ ከጣልያን እሁድ ምሽት 4 ሰዓት በለንደኑ ዌምብሊ ስታድዬም የአውሮፓ ዋንጫን ለማንሳት የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል። https://www.bbc.com/amharic/news-57760136 +health የዩናይትድ ኪንግደም ጤና ሚኒስትር የኮቪድ-19ን ደንብ በመተላለፋቸው ከሥራ ለቀቁ "የዩናይትድ ኪንግደም ጤና ሚኒስትር ማት ሃንኮክ የኮቪድ-19 መመሪያ መጣሳቸውን ተከትሎ ከሥራቸው ለቀቁ። ሚኒስትሩ የአካላዊ ርቀትን ደንብ በመተላለፍ የሥራ ባልደረባቸውን መሳማቸውን ተከትሎ ነው ከሥራ የለቀቀቁት። ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሪስ ጆንሰን በፃፉት ደብዳቤ መንግሥት ""በዚህ ወረርሽኝ ላይ መስዋዕትነት ለከፈሉ የማኅበረሰቡ ክፍሎች እኛም ስናጠፋ ተጠያቂ መሆናችንን ማሳየት አለብን"" በማለት አስፍረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የሚኒስትሩን መልቀቂያ መቀበላቸው እንዳሳዘናቸው ገልፀዋል። ተሰናባቹን የጤና ሚኒስትርን በመተካት የቀድሞ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ሳጂድ ጃቪድ የተሾሙ ሲሆን ለዚህ የሚኒስትርነት ቦታ በመመረጣቸው የተሰማቸውን ክብር ገልፀዋል። ማት ሃንኮክ ከረዳታቸው ጋር እየተሳሳሙ የሚያሳይ ቪዲዮ ሰን በተባለው ጋዜጣ ላይ መውጣቱን ተከትሎ ነው በርካቶች ኃላፊነታቸውን እንዲለቁ ግፊት ሲያደርጉባቸው የነበረው። ሁለቱም ያገቡና የሦስት ልጆች ወላጆች ናቸው። ጋዜጣው አክሎ እንደዘገበው ሁለቱንም ግለሰቦች ፎቶግራፉ የተነሳው ባለፈው የግንቦት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ እዚያው የጤና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ውስጥ ነው። ይህንንም ተከትሎ ሚኒስትሩ ለ15 ዓመታት በጋብቻ ከቆዩት ባለቤታቸው ጋር ተፋትተዋል። የሳሟት የሥራ ባልደረባቸው ጋር ያላቸው የፍቅር ግንኙነትም የጠነከረ እንደሆነ ተገልጿል። በርካታ የፓርላማ አባላት፣ የሠራተኛ፣ ማኅበራዊ ጉዳይና በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች የተቋቋመው የፍትህ ቡድን ሚኒስትሩ ከሥራ እንዲባረሩ ሲጠይቁ ነበር። እንዲሁም የፓርላማ አባላቱ ሚኒስትሩ ከሥራቸው እንዲለቁም መምከራቸውን ቢቢሲ ከአንዳንድ የፓርላማ አባላት ሰምቷል። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥራቸው እንዲለቁ ባይፈልጉም ሚኒስትሩ በራሳቸው ፈቃድ መልቀቃቸውን የቢቢሲ የፖለቲካ ዘጋቢ ላውራ ኩንስበርግ ዘግባለች። ከዚህም በተጨማሪ የሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ጂና ኮላዳንጌሎም እንዲሁ ከሥራቸው መልቀቃቸው ተዘግቧል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57631461 +politics ስለ የውጭ ጣልቃ ገብነት፣ ሰብአዊ እርዳታ፣ ውይይት. . . አቶ ደመቀ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ "የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአገራቸው የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረጉ ሙከራዎችን ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ተናገሩ። በኒው ዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው በ76ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥታቸው የሰብአዊ እርዳታን በተመለከተ ያልተቆጠበ ቁርጠኝነት እንዳለው አመልክተው አገራቸው የትኛውንም ጣልቃ ገብነት አትቀበልም ብለዋል። ለነጻ፣ ለገለልተኝነትና ለሰብአዊነት ምርሆች ተገዢ ለሆኑ የእርዳታ አቅርቢ አጋሮች ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ መንግሥታቸው አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ የገለጹት አቶ ደመቀ፤ ""ከዚህ ውጪ ግን የትኛውም ምክንያት በውስጥ ጉዳያችን ውስጥ ጣልቃ ለመግባት የሚደረግ ሙከራን ተቀባይ አያደርገውም"" ብለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን በመግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር በተለያዩ ኢትዮጵያ በሚመለከቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የመንግሥታቸውን አቋም አብራርተዋል። የሰብኢዊ እርዳታ አቅርቦት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሠሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ ስላለው ጦርነት ዝርዝር ያስረዱ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተደጋጋሚ የሚነሳውን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን በተመለከተ በንግግራቸው አንስተዋል። መንግሥታቸው የሚያስፈልገውን ���ሰብአዊ እርዳታ ለማሟላት ጥረት እያደረገ ባለበት ጊዜ ""የጥፋት ቡድኑ ሰብዓዊ ቀውስ የመፍጠር እቅዱን ተግባራዊ ከማድረጉ ባሻገር ክፋት የተሞላበት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ተከፍቶብናል"" ሲሉ ከሰዋል። ጨምረውም ""አሁን በደረስንበት ምዕራፍ የሰብአዊ ድጋፍ የፖለቲካ ዓላማን ማስፈፀሚያ መሳሪያ እንደሆነ እየተገነዘብን ነው"" ያሉት አቶ ደመቀ፤ የሐሰት መረጃን በማቀነባበር የተዛባ ግንዛቤ እንዲፈጠርና ሐሰተኛ ውንጀላ መቅረባቸውን ተናግረዋል። ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦት ግዴታውን መወጣቱ፣ የተናጠል ሰብአዊ የተኩስ አቁም ማወጁ እንዲሁም ጥሰቶችን በተመለከተ ምርመራ እንዲደረግና ተጠያቂነት ለማስፈን እርምጃዎችን መውሰዱን ጠቅሰው ""ቢሆንም ግን የሐሰት ውንጀላዎቹን መቀልበስ አልተቻለም"" ብለዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት ተቋማትና ሌሎች መንግሥታት የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል ሰብአዊ እርዳታ እንዳይቀርብ እንቅፋት ሆኗል በማለት በተደጋጋሚ ሲከሱ ቆይተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በመንግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ላይ ይህን በተመለከተ ምላሽ ሰጥዋል። የውጭ ጫና ኢትዮጵያ ማዕቀቦች በሌሎች ላይ ሲጣሉ መቃወሟን አቶ ደመቀ አስታውሰው ""በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ፍትህና ፍትሕ የሚጎድለው አካሄድ ተግባራዊ እንዳይሆን እንመክራለን"" ብለዋል። ጨምረውም ""ምንም አይነት አላስፈላጊ ጫናዎች ቢኖሩብንም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትና የፖለቲካ ነፃነትን የማስጠበቅ ግዴታችንን እንወጣለን"" ብለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገራቸው ከወዳጆቿ የሚቀርቡ ትብብር እና ቅን ሐሳብን እንደምትቀበል በመጥቀስ ነገር ግን ገንቢ፣ መተማመንን የሚያሰፍንና መግባባትን የሚፈጥር ሊሆን ይገባል ብለዋል። ""በአንድ መንግሥት ውስጣዊ ጉዳይ ላይ ድጋፍን ወይም ሐሳብ ለመሰንዘር የሚደረግ ሙከራ ስለችግሩ ውስብስብነት ሙሉ ግንዛቤን ይጠይቃል"" ሲሉ አሳስበዋል። በትግራይ ክልል ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ምዕራባውያን አገራት በተለይ አሜሪካ በጦርነቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ወገኖች ላይ የተለያዩ ጫናዎችን ለማሳደር እየሞከሩ መሆኑ ይታወቃል። በቅርቡም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ዕቀባዎችን ለመጣል የሚያስችል ትዕዛዝ ላይ ፊርማቸውን ማኖራቸው ይታወሳል። ችግሮችን በውይይት ስለመፍታት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ከተለያዩ ወገኖች የሚሰነዘሩ የውይይት ሐሳቦችን በተመለከተ በንግግራቸው ላይ እንዳነሱት፤ ሁልጊዜም ውይይት የመንግሥታቸው ተመራጭ መፍትሔ እንደሆነ ገልጸዋል። ""ኢትዮጵያ ለሐቀኛ የሰላም ጥረቶች በሯ ክፍት ነው"" በማለት ከአፍሪካ ሕብረትና ከሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ጋር ኢትዮጵያ መር ለሆነ ብሔራዊ ውይይት ለማካሄድ መንግሥታቸው እንደሚሰራ አመልክተዋል። ጨምረውም ኢትዮጵያ ለማንም የደኅንነት ስጋት ሆና እንደማታወቅተ በመጥቀስ ""ኢትዮጵያ ሁሌም ሰላም ወዳድ አገር ሆና የምትኖርና ለቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ሰላም የበኩሏን አስተዋፅኦ ታበረክታለች"" ብለዋል። ከሱዳን ጋር ስላለው ድንበር ጉዳይ በሠሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያውያን እጅ የነበረና ይገባኛል የሚለውን የድንበር አካባቢን መቆጣጡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ተበላሽቶ ቆይቷል። ኢትዮጵያ ሱዳን ከተቆጣጠረችው አካባቢ ሠራዊቷን አስወጥታ ውይይት እንዲጀመር ብትጠይቅም ከሱዳን በኩል ተቀባይነት አላገኘችም። አቶ ደመቀ ���ኮንንም ይህንን ጉዳይ በመንግሥታቱ ድርጅት ስብሰባ ላይ አንስተው የአገሪቱ ግዛት በወረራ ስር መሆኑንና አሁንም ለሰላማዊ መፍትሔ በሯ ክፍት መሆኑን ገልጸዋል። ""ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ በነበረችበት ወቅት ጎረቤት አገር ዓለም አቀፍ ሕግን በመጣስ ግዛታችንን የወረረ ሲሆን ይህ ወረራ እስከዛሬ ድረስ ቀጥሏል። ኢትዮጵያ ይህንን ችግር ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ የመፍትሔ ሐሳቦችን ለመቀበል ዝግጁ ናት።"" ብለዋል። የሕዳሴው ግድብ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል ለዓመታት ያለመግባባት መንጭ ሆኖ የቆየው የታላቁ ሕዳሴን ግድብ በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት፤ ግድቡን ኢትዮጵያ በራሷ ሀብት የገነባችው መሆኑ ሌሎችም አገራት በራስ አቅም ለሚገነባ ለሚከናወኑ ተመሳሳይ ተግባራት ይፈጥራል ብለዋል። ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን በተመለከተ የገጠማትን ፈተና በተመለከተ አቶ ደመቀ መኮንን ለምክር ቤቱ ባስረዱበት ጊዜ እንዳሉት ""የሚያሳዝነው ነገር ከራሳችን ውሃ እንዳንጠጣ መከልከላችን ነው"" ብለዋል። አክለውም አገሪቱ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት ለመጠቀም ያለውን የትውልዶች ፍላጎት ""በቅኝ ገዢዎች ውርስና በብቸኝነት ለመጠቀም ያለ ፍላጎት ምክንያት የሚገደብ አይሆንም"" በማለት ጉዳዩ ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግና በአፍሪካ ሕብረት በሚመራ ሂደት ከመቋጫ ለማድረስ ዝግጁ ይሆናሉ ብላ አገራቸው ተስፋ እንደምታደርግ ገልጸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58680780 +politics ሩሲያ 10 የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን በማባረር አፀፋ መለሰች "ሩሲያ 10 የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከአገሯ እንዲወጡ ትዕዛዝ የሰጠች ሲሆን ሌሎች ስምንት ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ደግሞ ወደ አገሯ እንዳይገቡ ጥቁር መዝገብ ውስጥ ማስገባቷ ተገለፀ። ሩሲያ ይህን ያደረገችው ማክሰኞ ዕለት አሜሪካ ለጣለችባት ማዕቀብ አፀፋዊ ምላሽ ነው። ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ከታገዱት መካከል የአሜሪካ ፌደራል ፖሊስ (ኤፍቢአይ) አባላትና የአሜሪካ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባለሥልጣናት ይገኙበታል። ዋይት ሐውስ ሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ባለፈው ዓመት በነበረው 'የሶላር ዊንድ' የሳይበር ጠለፋ እና ሌሎች ""ጠብ አጫሪ"" ድርጊቶች እንዲሁም በ2020 ምርጫ ጣልቃ ገብነቷ ምላሽ እንደሆነ አስታውቋል። ይህንን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ቅራኔ ውስጥ የገቡት ሁለቱ አገራት፤ አሁን ደግሞ ወደ ባሰበት ውጥረት ውስጥ እየገቡ ነው። ሩሲያ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ያስጠጋች ሲሆን፤ የአሜሪካ የጦር መርከቦችም ወደ ጥቁር ባሕር እያመሩ መሆኑን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስጠንቅቋል። ባለፈው ወር መንግሥትን በሚተቸው አሌክሲ ናቫንሊይ መመረዝ ምክንያት አሜሪካ ሰባት የሩሲያ ባለሥልጣናትን እና በርካታ የመንግሥት ተቋማትን ኢላማ አድርጋለች። ሩሲያ ግን በአሌክሲ መመረዝ እጇ እንደሌለበት ገልጻለች። ሆኖም በዚህ ሳምንት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ለሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ሁለቱ አገራት አብረው ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸው ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ጥሪ አቅርበዋል። ሩሲያም ይህንን በበጎ እንደምትመለከተውና እያሰበችበት እንደሆነ ገልጻለች። ማዕቀቡ የተጣለበት ማነው? ሩሲያ 10 የአሜሪካ ዲፕሎማቶች አገሪቷን ለቀው እንዲወጡ ጠይቃለች። ከዚህ በተጨማሪም ስምንት የአሜሪካ ባለሥልጣናት ወደ አገሯ እንዳይገቡ አግዳለች። ከእነዚህም መካከል፡ • የአሜሪካ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጀነራል ሜሪክ ጋርላንድ፣ • የአሜሪካ ፌደራል ፖሊስ ዳሬክተር ክርስቶፈር ውሬይ እና • የአሜሪካ የውስጥ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሱሳን ራይስ ይገኙበታል። ከዚህም ባሻገር ፖላንድ አምስት የሩሲያ ���ለሥልጣናትን ማባረሯን ተከትሎ አምስት ፖላንዳዊ ዲፕሎማቶች አገሯን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። ሩሲያ በ2020 የአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ላይ ጫና ለማሳደር በመሞከሯ እና ሌሎች የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት አሜሪካ 10 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ማባረርን ጨምሮ 32 ተቋማትና እና ባለሥልጣናትን ኢላማ አድርጋለች። የአሜሪካ የገንዘብ ተቋማትም ከሰኔ ወር ጀምሮ በውጭ ምንዛሪ ላይ መሰረት ያደረገ የውጭ ቦንድ ከሩሲያ ከመግዛት ታግደዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56737751 +health ከኮሮናቫይረስ በእጅጉ እያተረፉ ያሉት ትልልቅ ድርጅቶች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የበርካታ አገራት ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጫና እያደረሰ ቢሆንም ትልልቅ የሚባሉት የዓለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ግን ጥሩ የሚባል ትርፍ እየሰበሰቡ ነው። በበይነ መረብ አማካይነት የተለያዩ አይት መገልገያዎችን የሚሸጠው አማዞን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማግስት ባሉት ሶስት ወራት ብቻ ሽያጩ 40 በመቶ ከፍ እንዳለለት ያስታወቀ ሲሆን ታዋቂው የስልክና የላፕቶፕ አምራች አፕል ደግሞ የአይፎንና ሌሎች መቀየሪያ መሳሪያዎች በደንብ እንደተቸበቸቡለት ገልጿል። ፌስቡክ ደግሞ በስሬ በማስተዳድራቸው እንደ ዋትስአፕና ኢንስታግራም ባሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተጠቃሚዎች ቁጥር 15 በመቶ ከፍ ብሎልኛል ብሏል። • በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትርፉ መጨመሩን ሳምሰንግ አስታወቀ • ኮሮናቫይረስ የቀሰቀሳቸው የአና የሚበሉ ሥዕሎች • ከኮሮናቫይረስ የትኞቹ ድርጅቶች አተረፉ? እነማንስ ከሰሩ? የአማዞን የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ድርጅቱ ከተቋቋመበት ከአውሮፓውያኑ 1994 ጀምሮ ይህ ከፍተኛው ነው ተብሏል። ድርጅቱ እንደውም ከኮሮናቫይረስ መከሰት በኋላ ለሰራተⶉቹ መከላከያ መሳሪያዎችን ለመግዛትና የመከላከያ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱ ትርፉን ዝቅ ያደርገዋል ተብሎ ተፈርቶ ነበር። በአጠቃላይ በበይነ መረብ የሚካሄዱ ንግዶች የሽያጭ መጠኑ 40 በመቶ ከፍ ብሏል። እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ባሉት ሶስት ወራት ደግሞ በአጠቃላይ 88.9 ቢሊየን ዶላር አንቀሳቅሷል። ትርፍም ቢሆን በአስገራሚ ሁኔታ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 2.6 ቢሊየን ዶላር ወደ 5.2 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜያቸውን ማሳለፋቸውን ተከትሎ የበይነ መረብ ሽያጭ በእጅጉ ተጧጡፏል። አማዞንም ቢሆን የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት በሩብ ዓመቱ ብቻ ተጨማሪ 175 ሺ ሰራተኞችን ቀጥሯል። ፍላጎቱ በዚሁ መቀጠሉ ስለማይቀር በርካታ መጋዘኖችንና ሰራተኞችን ለመጨመርም እያሰበ ነው። የአፕል የሩብ ዓመት ትርፍ ደግሞ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 11 በመቶ በመጨመር 59.7 ቢሊየን ደርሷል። ሰዎች ስራቸውን ከቤታቸው ሆነው መስራታቸው የተለያዩ መገልገያዎችን እንዲጠቀሙ አድርጓቸዋል። በዚህም ምክንያት የማክ ላፕቶፖችና አይፓዶች በእጅጉ ተፈላጊ ነበሩ። ሁለቱም የአፕል ምርቶች ከወረርሽኙ መከሰት በኋላ ገበያቸው እንደደራ ድርጅቱ አስታውቋል። በዚህም ምክንያት ባለፈው ከነበረው 10 ቢሊየን ዶላር ትርፍ ወደ 11.25 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። ፌስቡክ ደግሞ ከኮሮናቫይረስ በኋላ ትርፉ በእጅጉ እንደሚቀንስ ቢጠበቅም እንደውም የ 11 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። አነስተኛ ድርጅቶች ያሏቸው ሰዎች ለማስታወቂያ ወደ ፌስቡክ ላይሄዱ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ተንብየው ነበር። ነገር ግን ወረርሽኙን ተከትሎ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በእጅጉ በመጨመሩ ምክንያት ለማስታወቂያ የሚመጡ ድርጅቶችም ቁጥር አብሮ ከፍ ብሏል። በዚህም ምክንያት የድርጅቱ የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር እንዲደርስ ሆኗል። ፌስቡክ እንደሚለው ባለፈው ሰኔ ወር ብቻ በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያዎቸ ላይ 2.4 ቢሊየን ተጠቃሚዎች የነበሩ ሲሆን ይህም የ15 በመቶ ጭማሪ አለው። ከአራቱ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው አልፋቤትም ቢሆን እንደ ሌሎቹ ባይሆንም ትርፋማ ሆኗል። ድርጅቱ በስሩ ጉግልና ዩቲዩብን የያዘ ሲሆን እስካሁን ያገኘሁት ትርፍ 38.3 ቢሊየን ዶላር ነው ብሏል። ይህ ደግሞ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የሁለት በመቶ ቅናሽ ያሳያል። https://www.bbc.com/amharic/news-53605349 +health """ኮሮናቫይረስ በአዲሱ ዓመት ይረታል የሚል ተስፋ አለኝ"" ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም" "የዓለም የጤና ድርጀት ዋና ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም የዓለም አገራት በጋራ የሚሠሩ ከሆነ ኮሮናቫይረስ በአዲሱ የአውሮፓዊያኑ አዲስ ዓመት 2022 ይረታል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገለጹ። የዓለም የጤና ድርጅት በቻይና የተቀሰቀሰውን ቫይረስ በተመለከተ ሪፖርት ከደረሰው ሁለተኛ ዓመቱ በተቆጠረበት በዚህ ወቅት አዲሱን ዓመት በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ""ጠባብ ብሔርተኝነት እና ክትባትን ማከማቸት"" አደጋ ናቸው ሲሉም አስጠንቅቀዋል። እስካሁን በመላው ዓለም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ287 ሚሊዮን የተሻገረ ሲሆን ከ5.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ዶ/ር ቴድሮስ አሁን ላይ ኮሮናቫይረስን ለማከም የተሻሉ መንገዶች መኖራቸውን ገልጸው፣ ፍትሐዊ የሆነ የክትባት ክፍፍል ባለመኖሩ ቫይረሱ ቅርጹን እየቀያየረ እንዲከሰት ዕድል ፈጥሯል ብለዋል። ""በአንዳንድ አገሮች ጠባብ ብሔርተኝነት እና የክትባት ክምችት ፍትሐዊነትን አጓድሏል። እናም ለኦሚክሮን ዝርያ መፈጠር ተስማሚ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። ቫይረሱ እየተለዋወጠ በመጣ ቁጥር የመቆጣጠር እና የመተንበይ አቅማችን እየቀነሰ ይሄዳል"" ያሉት ዶ/ር ቴድሮስ ""ኢ-ፍትሐዊነትን ከገታን ወረርሽኙን እንገታዋለን"" ሲሉም አክለዋል። በአውሮፓ እና በአሜሪካ ሰዎች ቢያንስ አንድ ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት የወሰዱ ሲሆን የዓለም የጤና ድርጅት የአውሮፓዊያኑ 2021 ከመጠናቀቁ በፊት በመላው ዓለም ቢያንስ 40 በመቶ ሕዝብ ክትባት እንዲያገኝ ያቀደው ዕቅድ በተለይም በአብዛኛው የአፍሪካ አገራት ሳይሳካ ቀርቷል። ዶ/ር ቴድሮስ ከዚህ ቀደም የበለፀጉ አገራት የዓለም አቀፍ የክትባት አቅርቦትን ""በማግበስበስ"" አብዛኛው ሕዝባቸውን ሁለት ዙር ሲከትቡ ሌሎች የመጀመሪያውን ዙር ክትባት እየተጠባበቁ ይገኛሉ በማለት ወቅሰዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ለመጪው አዲስ ዓመት 2022 ባስቀመጠው አዲስ ግብ፣ ወረርሽኙን ለማጥፋት በሁሉም አገራት ቢያንስ እስከመጪው ነሐሴ ድረስ 70 በመቶ ክትባቱን ለማዳረስ አቅዷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59845457 +health ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ አለፈ "በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ ማለፉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ህዳር 2/2013 ዓ.ም አስታወቀ። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በፌስቡክ ገፁ ላይ ይፋ እንዳደረገው በኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስ መከሰቱ ከታወቀበት መጋቢት 4 /2012 ዓ.ም ጀምሮ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ አልፏል። የኮቪድ-19 ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በቫይረሱ የተያዘ ሰው የተገኘው መጋቢት 4/ 2012 ዓ.ም ሲሆን እስካሁን ድረስ ለ1,534,470 ምርመራ ተደርጎ 100 ሺህ 327 በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 1ሺህ 537 መሆናቸውን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መግለጫ ያትታል። አክሎም 61 ሺህ 516 ህሙማንም ከበሽታው አገግመዋል ሲል ገልጿል። የጤና ሚኒስቴሩ አክሎም ""ኮሮና የለም"" ከሚል የተሳሳተ አመለካከት በመውጣት ሁሉም የኅ��ረተሰብ ክፍል በመከላከሉ ላይ ጠንክሮ እንዲሰራ ጥሪ አቅርቧል። የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ""ማስክ ካልተደረገ አገልግሎት የለም"" የሚለውን መርህ እንዲከተሉ አሳስቧል። በበርካታ አገራት በኮቪድ-19 የሚያዙ ከፍተኛ ቁጥር መመዝገቡን ተከለትሎ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አልፏል። እንደጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ ከ1.25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። በብዙ አገራት በቂ ምርመራ ባለመደረጉ እንጂ ይህን አሃዝ ከፍ ያለ ነው ተብሎ ይገመታል። በመላው አለም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁትር 51,554,166 መድረሱን የዩኒቨርስቲው መረጃ ያሳያል። በቫይረሱ በከፍተኛ ቁጥር ከተያዙት አገራት መካከል አሜሪካ፣ ሕንድ እና ብራዚል ከቀዳሚዎቹ ተርታ ይገኙበታል። እንደ አፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር መረጃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በአፍሪካ 1,904,820 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 45,954 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን ከዚሁ ጋር በተያያዘ አጥተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54874864 +sports ኢትዮጵያ ባለፉት 20 ዓመታት በኦሊምፒክ ዝቅተኛውን ውጤት ያስመዘገበችው መቼ ነበር? በኮሮናቫይረስ ምክንያት በአንድ ዓመት ተራዝሞ አምና ታቅዶ ዘንድሮ የተካሄደው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ውድድር ተጠናቋል። ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የዘንድሮውን ውድድር በ113 ሜዳሊያዎች በቁንጮነት ስታጠናቅቅ፣ ቻይና ሁለተኛ፣ አዘጋጇ ጃፓን ሦስተኛ፣ ጎረቤት አገር ኬንያ 19ኛ፤ ኢትዮጵያ ደግሞ 56ኛ ሆነው አጠናቀዋል። በዘንድሮው የኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ ያመጣችው ውጤት ዝቅተኛ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ኢትዮጵያ ጎልታ ከምትታይባቸው ዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮች መካከል ቀዳሚው በሆነው በኦሊምፒክ ውድድር ላይ የአገሪቱ አትሌቶች አኩሪ ውጤት እንዲያመጣ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በጉጉት ይጠብቃል። በኦሊምፒክ መድረክ ላይ በባዶ እግሩ ጭምር ሮጦ በተከታታይ በማራቶን ወርቅ በማግኘት ታሪክ የሰራው አበበ ቢቂላ በተወዳደረባት ቶኪዮ በተካሄደው ኦሊምፒክ ላይ ኢትዮጵያ ከፍያለ ድል ታገኛለች ብለው ጠብቀው ነበር። ነገር ግን የታሰበው ሳይሆን ልዑኩ ከመነሻው ባለመግባባት ውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያ በዘንድሮው የኦሊምፒክ ጨዋታ 1 የወርቅ፣ አንድ የብር እና ሁለት የነሐስ በአጠቃላይ 4 ሜዳሊያዎች አግኝታ ባለፉት 20 ዓመታት ከተመዘገበው ዝቅተኛው ውጤት ሆኗል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ብቸኛውን ወርቅ ማግኘት የቻለው በ10 ሺህ ሜትር በአትሌት ሰለሞን ባረጋ አማካይነት ነው። በሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል በአትሌት ግርማ ለሜቻ ብቸኛው ብር ሲገኝ ለተሰንበት ግደይና ጉዳፍ ፀጋይ እያንዳንዳቸው የነሐስ ሜዳሊያ አምጥተዋል። የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ቡድን በአትሌቲክስ 34 አትሌቶችን፣ በብስክሌት እሽቅድምድም አንዲት ሴት ተወዳዳሪ፣ በውሃ ዋና አንድ ተወዳዳሪ እንዲሁም በቴኳዋንዶ አንድ በድምሩ 37 ስፖርተኞችን ይዞ ነበር ወደ ቶኪዮ ያቀናው። ኢትዮጵያ ባለፈው ብራዚል የሪዮ ላይ በተካሄደው የ2016 ኦሊምፒክ 1 የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘች ቢሆንም በሦስት የብርና 4 የነሐስ በድምሩ 8 ሜዳሊዎች ማግኘት ችላ ነበር። ኢትዮጵያ ባለፉት 20 ዓመታት የዘንድሮው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ውጤት ባለፉት 20 ዓመታት ኢትዮጵያ ካስመዘገበቻቸው ውጤቶች ዝቅተኛው የሚባል ነው። የዛሬ 20 ዓመት በተደረገው የሲድኒ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴና በሻለቃ ደራርቱ ቱሉ በ10 ሺህ ሜትር በሁለቱም ፆታዎች እንዲሁም በሚሊዮን ወልዴና በገዛኸኝ አበራ 4 ወርቅ ማምጣቷ ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ በጌጤ ዋሚ፣ በአሰፋ መዝገቡና በተስፋዬ ቶላ አራት ሜዳሊያዎችን በማከል ውድድሩን በ8 ሜዳሊያዎች ነበር ያጠናቀቀችው። ከሲድኒ ቀጥሎ የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን ባዘጋጀችው የግሪኳ አቴንስም ኢትዮጵያ በአትሌቶቿ በሜዳሊያ ተንቆጥቁጣ ነበር። ኢትዮጵያን ወክሎ ወደ ግሪክ መዲና አቴንስ ያቀናው የኦሊምፒክ ቡድን በቀነኒሳ በቀለና በመሠረት ደፋር ሁለት ወርቆችና በሌሎች አትሌቶች ደግሞ ተጨማሪ 5 ሜዳሊያዎች በድምሩ 7 ሜዳሊያዎች ይዞ ተመልሷል። የውድድሩን አዘጋጅነት ከአቴንስ የተረከበችው የቻይናዋ ቤይጂንግም የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍ ብሎ መውለብለቡ ከአእምሮ የሚጠፋ አይደለም። በወቅቱ የቤይጂንግ ኦሊምፒክ ፈርጦች የተባሉት ቀነኒሳ በቀለና ጥሩነሽ ዲባባ እያንዳንዳቸው በ10 ሺህና 5 ሺህ ሜትር ውድድሮች ሁለት ሁለት ወርቅ በማምጣት ደምቀው ነበር። ከጥሩነሽና ቀነኒሳ በተጨማሪ በመሠረት ደፋር፣ በስለሺ ስህንና በፀጋዬ ከበደ ሜዳሊያዎች ታጅቦ ነው ቡድኑ አዲስ አበባ የገባው። በፈረንጆቹ 2012 በተካሄደው የለንደን ኦሊምፒክ ላይም ኢትዮጵያ ሜዳሊያ ብርቋ አልነበረም። በዚህ ውድድር ሦስቱ እንስት አትሌቶች ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሠረት ደፋርና ቲኪ ገላና ወርቅ ማጥለቃቸው ይታወሳል። በለንደን ኦሊምፒክ ከሦስቱ አትሌቶች በተጨማሪ ሁለት ብርና ሦስት የነሐስ ሜዳሊያዎችን በአትሌቶቿ ያገኘችው ኢትዮጵያ ከእንግሊዝ የተመለሰችው በደመቀ ድል ነበር። በሪዮው ኦሊምፒክ ደግሞ አንድ ወርቅ፣ ሁለት ብርና 5 ነሐስ በማምጣት 8 ሜዳሊያዎችን ለማግኘት ችላ ነበር። የዘንድሮው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ውጤት ባለፉት 20 ዓመታት ኢትዮጵያ ከተመዘገበው የሜዳሊያ ብዛት ዝቅተኛው ነው። ቅድመ - 2000 ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ ውድድሮች መሳተፍ የጀመረችው ከፈረንጆቹ 1956 ጀምሮ ነው። እንደ አውሮፓውያኑ በ1956ቱ አውስትራሊያ ውስጥ በተካሄደው የሜልበርን ኦሊምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በውድድሩ ሜዳሊያ ማግኘት ሳይችል ተመልሷል። ነገር ግን በተከታይነት በተካሄደውና ኢትየጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በተሳተፈችበት የሮም ኦሊምፒክ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ በአበበ ቢቂላ አማካይነት ለማግኘት ችላለች። ኢትዮጵያ በ1976 በካናዳው የሞንትሪያል ኦሊምፒክ ጨዋታዎች እንዲሁም በተከታታይ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስና በደቡብ ኮሪያዋ ሴኡል በተካሄዱት ኦሊምፒኮች አልተሳተፈችም። ነገር ግን በፈረንጆቹ 1980 ሞስኮ ላይ በተካሄደው ኦሊምፒክ ተሳትፋ በሁለት የወርቅና በሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች ከዓለም 17ኛ መውጣት ችላለች። ኢትዮጵያ ከመጀመሪያው የኦሊምፒክ ተሳትፎዋ አንስቶ እስከዛሬ ድረስ በተሳተፈችባቸው የኦሊምፒክ ውድድሮች በአትሌቲክስ 55 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። ይህ ውጤት ኢትዮጵያን ከኬንያና ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል በአፍሪካ በርካታ የኦሊምፒክ ሜዳሊያ ያላት ሦስተኛዋ አገር ያደርጋታል። በዘንድሮው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ደግሞ በሜዳሊያ ብዛት ከአፍሪካ አምስተኛ መሆን ችላለች። https://www.bbc.com/amharic/news-58162024 +business በማልኮም ኤክስ ግድያ በስህተት ለ20 ዓመታት የታሰረው ግለሰብ 40 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ጠየቀ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹን ማልኮም ኤክስን ገድለሃል ተብሎ በስህተት ጥፋተኛ ተብሎ 20 ዓመታትን በእስር ያሳለፈው ሙሃመድ አዚዝ ኒው ዮርክ ከተማ 40 ሚሊዮን ዶላር እንዲክሰው ጠየቀ። ሙሃመድ አዚዝ የማልኮም ኤክስን ግድያ ተከትሎ ከታሰረ ከ20 ዓመታት በኋላ ከእስር የተለቀቀው በ1985 ነበር። በ2021 ዐቃቤ ሕግ አዲስ ማስረጃ አግኝቻለሁ በሚል ሙሃመድ አዚዝ ወንጀሉን አልፈጸመም ብሏል። የቀድሞ የባሕር ኃይል አባሉ ሙሃመድ አዚዝ በ1965 ሲታሰሩ የ6 ልጆች አባት እና የ26 ዓመት ወጣት ነበሩ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ማልኮም ኤክስ የአደባባይ ንግግር ለማድረግ ዝግጅት ላይ እያለ በታጠቁ ሦ��ት ሰዎች በጥይት ተደብድቦ ነበር የተገደለው። በወቅቱ በግድያው ተጠርጥሮ ሙሃመድ አዚዝ ከካህሊል ኢስላም ጋር ነበር የታሰረው። 22 ዓመታትን በእስራት ያሳለፈው ኢስላም በ2009 ሕይወቱ አልፏል። ዐቃቤ ሕግ ተጨባጭ ማስረጃ ሳያቀርብ፤ የሚጣረስ ሃሳብ የሰጡ ምስክሮችን አሰምቶ በሁለቱ ግለሰቦች ላይ ብይን ያሰጠው። ግድያው በተፈጸመበት ቦታ በቁጥጥር ሥር የዋለው እና ማልኮም ኤክስን መግደሉን ያመነው ታለማደግ ሃዬር፤ በሁለቱ ግለሰቦች የፍርድ ሂደት ላይ ቀርቦ በወንጀሉ እጃቸው የለበትም ሲል ምስክርነቱን ሰጥቶ ነበር። በ1970ዎቹ ደግሞ በግድያው ሌሎች አራት ሰዎች መሳተፋቸውን ሃየር የጽሑፍ ቃለ መሃላ ፈጽሟል። በ2020 የእነ ሙሃመድ ጉዳይ ተጣርቶ ንጽህናቸው እንዲረጋገጥ ክሱን እንደገና ማየት ተጀምሮ ነበር።  የሁለቱን ተጠርጣሪዎች ጥብቅና የያዘው ዴቪድ ሻኒስ፣ በመንግሥት ግዴለሽ አሰራር ምክንያት ሁለቱ ሰዎች በስሕተት 42 ዓመታትን እስር ቤት እንዲያሳልፉ ተደርገዋል ብሏል። “የዘገየ ፍርድ እንደተነፈገ ይቆጠራል። ሙሃመድ አዚዝ 84 ዓመታቸው ነው። ኢስላም ደግሞ እንዳለመታደል ሆኖ ንጽህናቸው ሳይረጋገጥ ሕይወታቸው አልፏል” ብሏል ጠበቃው ዴቪድ። ባለፈው ዓመት የማልኮም ኤክስ ልጅ የአባቴ ጉዳይ እንደገና ይታይልኝ በማለት አመልክታ ነበር። የማልከም ኤክስ ሴት ልጅ በግድያው ወቅት ፖሊስ የነበረ ሰው ጽፎ አስቀምጦታል ያለችውን ደብዳቤ በመጥቀስ ግድያውን ያቀነባበሩት ኤፍቢአይ እና የኒው ዮርክ ፖሊስ ናቸው ብላለች። እነዚህ ማስረጃዎች ተደማምረው 20 ዓመታትን በእስር ያሳላፉት የ84 ዓመቱ ሙሃመድ አዚዝን በኒው ዮርክ ከተማ ላይ ክስ እንዲመሰርቱ አድርጓቸዋል። ያላአግባብ እና በመንግሥት ግዴለሽ አሰራር ምክንያት ለታሰሩበት ለሁለት አስርት ዓመታትም 40 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cnl8ldxewvvo +business የናይጄሪያ ታጣቂዎች በባቡር ላይ ባደረሱት ጥቃት መንገደኞች ተገደሉ "በናይጄሪያ ርዕሰ መዲና አቡጃ እና ካዱና ከተማ በሚመላለስ ባቡር ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሰባት ተሳፋሪዎች መሞታቸውን የሆስፒታሉ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግሩ። ታጣቂዎቹ ሰኞ ምሽት ሃዲዱ ላይ ፍንዳታ በማድረስ 970 ተሳፋሪዎችን አሳፍሮ የነበረውን ባቡር አስገድደው አስቁመውታል። በመቀጠልም ታጣቂዎች ባቡሩን ከበው ተኩስ መክፈታቸውን አንድ ተሳፋሪ ለቢቢሲ ተናግሯል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ መንገደኞች ታፍነው ተወስደዋል። ባቡሩ በሁለቱ ከተሞች መካከል አስተማማኝ ነው ተብሎ በሚታሰበው የትራንስፖርት ዘዴ ነው። ለገንዘብ ሲሉ እገታ መፈጸም በመላ ናይጄሪያ የተለመደ ሆኗል። ታጣቂዎች በተለያየ ቦታ በመጠበቅ ተሽከርካሪዎችን ዒላማ ስለሚያደርጉ የአቡጃ-ካዱና አውራ ጎዳና በሃገሪቱ ካሉ አደገኛ መንገዶች አንዱ ሆኗል። ይህም መንገደኞች 150 ኪሜ የሚረዝመውን መንገድ በመተው ብዙዎች ፊታቸውን እአአ በ2016 ሥራ ወደ ጀመረው የባቡር መስመር እንዲያዞሩ ገፋፍቷቸዋል። ባለፉት ስድስት ወራት በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለው የባቡር መስመር ዒላማ ሲደረግ ያሁኑ ለለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን እጅግ አሳሳቢውም አሳሳቢውም ነው ተብሏል። ሰኞ ማምሻውን ጥቃቱ የደረሰባቸው 22 ሰዎች ካዱና በሚገኘው ወታደራዊ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ። በካዱና በሆስፒታል በጎ ፈቃደኝነት ሆና የምትሠራ አንዲት ሴት ለቢቢሲ እንደተናገረች በቦታው ከነበሩ ሰዎች እንደሰማችው ጥቃቱ ""አስፈሪ"" እና ""አሰቃቂ"" ነው። አንድ የባቡር መስመሩ ሠራተኛ እራሱን ጨምሮ ""25 ሰዎችን ወደ ጫካ"" ሲወስዱ ከአጋቾቹ ሮጦ ማምለጥ እንደቻለ ተናግሯል። ሌላኛዋ ደግሞ የተተኮሰባት ""ጥይት በጉልበቷ አለፎ"" በኋላም ወታደሮች እንደረሱላት ተናግራለች። አንድ ከፍተኛ የደህንነት ምንጭ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደገለፁት ወታደሮች በፍጥነት ወደ ስፍራው ደርሰዋል። ""በፍጥነት በቦታው የደረሱት ወታደሮች ጥቃቱን መክተዋል። ወታደሮቹ ሲደርሱ ነው አሸባሪዎቹ የሸሹት። ባቡሩ ጥይት የማይበሳው በመሆኑ ወለሉ ላይ ተኝተው የነበሩትን ተሳፋሪዎች ከጉዳት ተከላክሏል"" ብለዋል። የናይጄሪያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን (ኤንአርሲ) በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለውን ሥራ አቁሟል። የካዱና ግዛት አስተዳዳሪ ጥቃቱን ""የሽብር"" ድርጊት ሲሉ አውግዘው ለተጎጂዎች ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝተዋል። የባቡር መስመሩ ከሰሜን ምዕራብ ግዛቶች ወደ አቡጃ እና ወደ ደቡብ አቅጣጫ ለመጓዝ ለሚፈልጉ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች አገልግሎት ይሰጣል። የካዱና ግዛት ባለስልጣናት ሁሉም ተሳፋሪዎች የት እንዳሉ እና ማን በትክክል እንደጠፋ ለማወቅ ከኤንአርሲ ጋር ግንኙነት እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል ። ለገንዘብ ሲሉ ግድያና አፈና የሚፈጽሙ የታጠቁ ቡድኖች በሚገኙበት በሰሜን ናይጄሪያ ወታደሩ በአውሮፕላን ጭምር ጥቃት ቢፈጸምም ጥቃት ከማድረስ አላገዳቸውም። ባለፈው ቅዳሜ የካዱና ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60923871 +sports ሊዮኔል ሜሲ ለፓሪስ ሴንት ዠርሜን ለመጫወት ተስማማ "ሊዮኔል ሜሲ ከባርሴሎና በድንገት መውጣቱን ተከትሎ የፈረንሳዩ ክለብ ለመቀላቀል በሁለት ዓመት ኮንትራት መስማማቱን የቢቢሲ ስፖርት አምድ ጸሐፊው ጊለም ባላግ ተናገረ። ስምምነቱን ለማጠናቀቅ ሕክምና ማጠናቀቅ ብቻ ይቀረዋል። የ34 ዓመቱ የአርጀንቲና አምበል በላሊጋ የፋይናንስ ፍትሃዊ ጨዋታ ህግ መሰረት አዲስ ውል ለመፈረም ባለመቻሉ በብቸኝነት የተጫወተብትን ባርሳን ለመልቀቅ ተገዷል። የማውሪሲዮ ፖቸቲኖው ፒኤስጂ ባለፈው የውድድር ዘመን በሊግ 1 ከሊል በመቀጠል ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ባላግ በቢቢሲ ሬዲዮ 5 ቀጥታ ስርጭት ላይ ""ሁሉም ነገር ተረጋግጧል። ሊዮኔል ሜሲ የፒኤስጂ ተጫዋች ይሆናል። ይህ ነው። ባለፉት ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የተከሰተ ነው"" ብሏል። ""ሃሳቡ የእግር ኳስ ህይወቱን በባርሴሎና ማድረግ ነበር። . . . ከዚያ በኳታር የዓለም ዋንጫ ጥሩ ነገር ማድረግ ነው።"" ከዘመኑ ታላላቅ ተጫዋቾች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ሜሲ በ 13 ዓመቱ ለተቀላቀለበት ባርሳ 778 ጨዋታዎችን አከናውኖ 672 ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል። የባላንዶርን ሽልማት ስድስት ጊዜ በማሸነፍ ባለክብረወሰን ሲሆን ከካታላኑ ክለብ ጋር 35 ዋንጫዎችን አንስቷል። ሜሲ በፒኤስጂ ከቀድሞው የክለቡ አጋሩ ኔይማር ጋር ይገናኛል። ሜሲ፤ ጆርጂንዮ ዋይናልደም፣ ሰርጂዮ ራሞስ እና ግብ ጠባቂው ጂያንሉጂ ዶናሩማ ተከትሎ የፒኤስጂ አራተኛው የነፃ ዝውውር ፈራሚ ይሆናል። ከፍተኛ ግምት የተሰጠው የቀኝ መስመር ተከላካዩ አክራክ ሃኪሚም ከኢንተር ሚላን የፓሪሱን ክለብ ተቀላቅሏል። ስምምነቱ በፍጥነት ከተጠናቀቀ ቅዳሜ የመጀመሪያውን የፒኤስጂ ጨዋታውን ከስትራስቡርግ ጋር ማድረግ ይችላል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58161236 +sports የኮቢ ብራያንት ባለቤት ኮቢ መሞቱን መጀመሪያ የሰማችው ከማኅበራዊ ሚዲያ እንደነበር ገለጸች "የኮቢ ብራያንት ባለቤት ቨኔሳ ብራያንት ባለቤቷ መሞቱን መጀመሪያ የሰማችው በማኅበራዊ ሚዲያ እንደነበር ገለጸች። ""RIP Kobe"" (ኮቢ ነፍስህ በሠላም ትረፍ) የሚል የስልክ የማኅበራዊ ሚዲያ መረጃዎች መልዕክት ጠቋሚ (ኖቲፊኬሽን) ሲደርሳት ነበር ባለቤቷ መሞቱን የተረዳችው። የቅርጫት ኳስ ኮከኩ ኮቢ እአአ ጥር 2020 በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ ከ13 ዓመቷ ሴት ልጁ ጂያና እና ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር ሕይወቱ አልፏል። ቨኔሳ ብራያንት በቸልተኝነት እና ግላዊነትን ባለመጠበቅ ምክንያት የሎስ አንጀለስ ፖሊስ መምሪያን ከሳለች። ኃላፊዎቹ የኮቢ እና የጂያናን አስከሬን ጨምሮ የአደጋውን አስከፊ ፎቶዎች አጋርተዋል ስትል ትከሳለች። ቨኔሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ አደጋው እንዴት እንዳወቀች ተጠይቃ ባለቤቷ እና ሴት ልጃቸው የሄሊኮፕተር አደጋ እንደደረሰባቸው ከቤተሰቡ ረዳት እንደተነገራት አስታውቃለች። ነገር ግን አምስት ሰዎች በሕይወት መትረፋቸው ስለተነገራት በሕይወት ከተረፉት መካከል ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሰቧን ተናግራለች። ከዚያ በኋላ መልዕክቶች በስልኳ ይደርሷት ጀመር። ቨኔሳ ""ስልኬን ይዤው ነበር። ምክንያቱም ለባለቤቴ ለመደወል እየሞከርኩ ነበር። RIP Kobe የሚሉ ማሳወቂያዎች ስልኬ ላይ ይጎርፉ ጀመር"" ስትል ታስታውሳለች። አክላም ""ያለ ባለቤቴ እና ልጄ ሕይወቴ መቼም እንደ ቀድሞው አይሆንም"" ብላለች። በመጋቢት ወር ቨኔሳ የአደጋውን አስከፊ ፎቶዎችን አጋርተዋል ያለቻቸውን የሎስ አንጀለስ የፖሊስ መኮንኖችን ስም ይፋ አድርጋለች። ከፖሊስ መኮንኖች መካከል አንዱ የኮቢ ብራያንት አስከሬን ፎቶ ለመጠጥ ቤት አሳላፊ ሲያጋራ ሌሎቹ ደግሞ ሕይወታቸው ያለፈ ልጆችን፣ የወላጆችን እና የአሰልጣኞችን ፎቶዎች አሰራጭተዋል። የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ ባለፈው ዓመት የካቲት ወር እንደዘገበው፤ የፖሊስ የውስጥ ምርመራ እንደሚያሳየው ባለሥልጣናት የተጎጂዎችን ፎቶዎች አጋርተዋል። ቨኔሳ ""ዛሬ እዚህ መጥቼ ለተጠያቂነት መታገሌ ተገቢ አይመስለኝም። ምክንያቱም ማንም ሰው እንደዚህ ዓይነቱን ስቃይ እና የቤተሰቡን ፍርሃት መታገስ የለበትም። ፎቶዎቹ መጋራታቸው ተገቢ አይደለም"" ብላለች። ቨኔሳ ባለቤቷ እና ሴት ልጃቸው አደጋው ሲደርስ የለበሱትን ልብስ እንዳስቀመጠችው ተናግራለች። ""አንድ ሰው እንዴት በጣም ጨካኝ ሊሆን እንደሚችል እና ለእነሱ ወይም ለጓደኞቻችን ምንም ደንታ እንደሌለው መገመት ይከብዳል። የመንገድ እንስሳት የሆኑ ይመስል ፎቶዎቻቸውን አጋርተዋል"" ብላለች። ቨኔሳ በአደጋ ቦታው ማንም ፎቶ አለማንሳቱ እንዲረጋገጥ መጠየቋን የፖሊስ መኮንን አሌክስ ቪላኑዌቫን ተናግረዋል። የፖሊስ መምሪያው ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ባለው ክስ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59033821 +business ዚምባብዌውያን በሃገሪቷ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ በመቃወም ሰልፍ አካሄዱ "በሺዎች የሚቆጠሩ ዚምባብዌውያን የአሜሪካና የአውሮፓ ህብረትን ማዕቀብ በመቃወም ሰልፍ አድርገዋል። መንግሥት ባዘጋጀው በዚህ ሰልፍ ማዕቀቡ ምን ያህል የዚምባብዌን ኢኮኖሚ እንዳሽመደመደው ተናግረዋል። በሌላ በኩል አሜሪካና የአውሮፓ ሕብረት የተጣለው ማዕቀብ በግለሰቦችና በኩባንያዎች ላይ በመሆኑ የሃገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ ያመጣው ተፅእኖ እንደሌለ እየተናገሩ ነው። •የ ""ጥርስ አልባው"" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? •የዋግ ኽምራ አርሶ አደሮች ለከፋ ችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው ሰልፉን ምክንያት በማድረግም ዚምባብዌ ቀኑን ሕዝባዊ በዓል ስትል ያወጀች ሲሆን ለሰልፈኞቹም የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡም አውቶብሶች ተዘጋጅተው ነበር። በሰልፉ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋም ለተሰበሰበው ሕዝብ ንግግር አድርገዋል። ""ማዕቀቡ በያንዳንዱ ዚምባብዌውያን ላይ ያደረሰው ተፅእኖ የከፋ ነው፤ ማዕቀቡ ስህተት ነው የምንልበትም ምክንያት የሁሉንም ቤት ያንኳኳ በመሆኑ ነው"" ማለታቸውን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ንግግራቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። •ኬንያዊው የፀረ ቅኝ ግዛት ነፃነት ታጋይ መካነ መቃብር ከ62 ዓመታት በኋላ ተገኘ •ማንዴላ�� ውትድርና ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚዎች ""ማዕቀቡ መነሳት አለበት"" የሚል ፅሁፍ ያለባቸውን ቲሸርቶች እንዲሁም ""ማዕቀቡ በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል ነው"" የሚል መፈክር ይዘው ነበር። የተለያዩ ቢዝነስ ባለቤቶችም ለቢቢሲ እንደተናገሩት ማዕቀቡ ""ጠባሳን የተወ"" ነው ብለውታል፤ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚያነሱት ባንኮች ተመጣጣኝ በሆነ ወለድ ማበደር በማቆማቸው ሥራቸውን ቀጥ እንዳደረገው ይናገራሉ። በሰልፉ ላይ የነበሩ ተናጋሪዎችም ዚምባብዌ እያጋጠማት ያለው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቆራረጥና የውሃ እጥረትም በማዕቀቡ ነው ብለዋል። ተችዎች በበኩላቸው ሃገሪቱ የገባችበትን የኢኮኖሚ አዘቅት እንዲሁም ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ያለውን ግሽበት በነዋሪው ላይ የፈጠረውን ንዴት አቅጣጫ ማስቀየሪያ ነው ይላሉ። የቢቢሲ ዘጋቢዎች እንደታዘቡትም የተጠበቀውን ያህል ሰልፈኞች አልመጡም ብለዋል፤ ስታዲየሙ 60ሺህ ሰዎችን የመያዝ አቅም ቢኖረውም የተገኘው ከ15ሺህ እስከ 20ሺህ የሚገመት ነው ተብሏል። •""ሌቱም አይነጋልኝ"" የተባለላት የውቤ በረሃ ትዝታዎች የተቃዋሚ መሪ ኔልሰን ቻሚሳ በበኩላቸው ሰልፉ በሃገሪቱ ላይ የመሪዎችን ውድቀት ለመሸፈን የተደረገ ፕሮፓጋንዳ ነው ብለውታል። በዚምባብዌ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በበኩሉ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ መሽመድመድ ""ደካማ ከሆኑ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች"" ጋር የተያያዘ ነው በሚል በትዊተር ገፁ አስፍሯል። አሜሪካ ከገንዘብ ዝውውርና አለም አቀፍ ጉዞዎች ጋር በተገናኘ 85 ኃላፊዎች ላይ እንዲሁም 56 ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጥላለች። የሃገሪቱ ፕሬዚዳንትም ማዕቀብ ከተጣለባቸው መካከል ናቸው። •አቶ ታደሰ ካሳ፡ ""…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው"" ከዚህም በተጨማሪ የአሜሪካ ማዕቀብ ዚምባብዌ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ግዥ እንዳታደርግ የሚገድብም ነው። የአውሮፓ ህብረት ማዕቀብም በዚምባብዌ የመንግሥት ኃላፊዎችን እንቅስቃሴ መገደብ፣ የገንዘብ እንዲሁም የጦር መሳሪያ ዝውውርና ማገድን ያካትታል። ማዕቀቡ የተጣለው ከሃያ አመታት በፊት ሲሆን በዚህ አመትም የአሜሪካ መንግሥት ባለፈው አመት ከነበረው ተቃውሞ ጋር ተያይዞ በሞቱ ሰዎች ላይ እጃቸው አለበት ያላቸውንም ሰዎች በማዕቀብ ዝርዝሩ አካቷቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-50192157 +health በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱ ተገለጸ "በኢትዮጵያ በየዓመቱ በኤችአይቪ ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱ ተገለጸ። በፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግነኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዳንኤል በስረ በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱን ጥናቶች ያመላክታሉ ብለዋል። በአገር አቀፍ ደረጃ አጠቃላይ የቫይረሱ የስርጭት ምጣኔ 0.86 በመቶ መሆኑን አቶ ዳንኤል ያስረዳሉ። ""ይሄ ማለት በመላው አገሪቱ፤ በሁሉም ማሕበረሰብ ክፍል ተመሳሳይ ነው ማለት አይደለም። በገጠር እና በከተማ የስርጭት ምጣኔው የተለያየ ነው"" የሚሉት ዳንኤል፤ በጋምቤላ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስርጭት ምጣኔው ከፍተኛ መሆኑን ይናገራሉ። ዳንኤል የቫይረሱ ስርጭት በጋምቤላ 4.1 በመቶ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከ3 በመቶ በላይ መሆኑን ያስረዳሉ። 3 በመቶ ምጣኔ ምን ማለት እንደሆን ሲያስረዱ፤ በቀላል ቋንቋ ከመቶ ሰዎች ሦስት ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው አለ ማለት ነው ይላሉ። በሶማሌ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በታች መሆኑን ይናገራሉ። የሶማሌ ክልል 0.01 በመቶ አነስተኛ የቫይረሱ ስርጭት የሚገኘበት ክልል መሆኑ�� ይናገራሉ። በአገሪቱ ክልሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የቫይረሱ ስርጭት ልዩነት እንዴት ሊፈጠረ ቻለ? ተብለው የተጠየቁት አቶ ዳንኤል፤ ለዚህ ጥያቄ ቁርጥ ያለ ምላሽ ለመስጠት በዝርዝር ጥናት ላይ መመርኮዝ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የተሰራ ሥራ ልዩነት ፈጥሮ ሳይሆን ዋናው ምክንያት ከባህል እና ሃይማኖታዊ ጉዳይ ጋር ሊያያዝ ይችላል ይላሉ። አቶ ዳንኤል ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ አጠቃላይ የቫይረሱ ስርጭት ምጣኔ ከ6 በመቶ በላይ ደርሶ የሚያውቅበት አጋጣሚ እንዳለ ይናገራሉ። በከተሞች አካባቢ ደግሞ የስርጭት ምጣኔው እስከ 10 በመቶ ስለመድረሱ ተመዝግቦ ነበር ይላሉ። ""በአንድ አገር አጠቃላይ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫይረሱ ስርጭት ወረርሽኝ ነው የሚባለው"" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ምንም እንኳ በአገር ደረጃ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በታች ቢሆንም የስርጭት መጠኑ ከ1 በመቶ በላይ የሆነባቸው ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች መኖራቸውን ይናገራሉ። የቫይረሱ ስርጭት በጾታ ተከፍሎ ሲታይ ደግሞ፤ ሴቶች ከወንዶች በላይ ተጋላጭ መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሽታውን በመከላከል ረገድ የሚሰሩ ሥራዎች መቀነሳቸውን ዳንኤል አስረድተዋል። መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ቀደም ሲል ሲሰሩ በነበሩበት ልክ ቫይረሱን የመከላከል ሥራ እየሰሩ አይደለም ይላሉ። ለዚህም ምክንያቱ የስርጭቱ መጠን በየዓመቱ መቀነስ በማሳየቱ እና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከመከላከሉ ይልቅ ሕክምናው ላይ ትኩረት በመሰጠቱ ነው ይላሉ። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በአሁኑ ወቅት ከ622 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ይገኛል። ከእነዚህ መካከል ወደ 500 ሺህ የሚሆኑ ጸረ-ኤችአይቪ መድሃኒት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጥናቶች ያሳያሉ ብለዋል ዳንኤል። በየዓመቱ ከ11 ሺህ በላይ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች አሉ። ""ይህን የከፋ የሚያደርገው ከእነዚህ ውስጥ 67 በመቶ ድርሻ የሚይዙት እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች መሆናቸው ነው"" ይላሉ ዳንኤል። የቫይረሱን ስርጭት መከላከል አስፈላጊነትን ከሚያረጋግጡት መካከል አንዱ በበሽታው የሚያዙት አብዛኛዎቹ ወጣቶች መሆናቸው ነው ይላሉ። ""አምራች ኃይል ነው። እንደ ሀገር ተስፋ የሚጣልበት ነው። በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ላይ የስርጭት ምጣኔው ከፍ ብሎ መታየቱ እንደ አገር አደጋ ውስጥ እንዳለን የሚያሳይ ነው"" ብለዋል። ዳንኤል፤ ሴተኛ አዳሪዎች፣ ባሎቻቸውን በሞት ያጡ እና ትዳራቸውን የፈቱ ሴቶች ዘንድ የቫይረሱ ስርጭት መጠን ከፍተኛ ነው ይላሉ። ""በሴተኛ አዳሪዎች የስርጭት ምጣኔው 18 በመቶ ነው። ባሎቻቸውን በሞት ያጡ እና ትዳራቸውን የፈቱ ሴቶች አካባቢ የስርጭት ምጣኔው ወደ 20 በመቶ ሆኖ እናያለን"" ይላሉ። ሕይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ከ12 ሺህ ባለይ ሰዎች ደግሞ በየዓመቱ በኤድስ እና ተያያዥ በሽታዎች ሕይወታቸው እያለፈ ነው። በአገሪቱ ቫይረሱ በደማቸው ይገኘባቸዋል ከተባለው ከ622 ሺህ ባለይ ሰዎች 61 በመቶውን የሚይዙት ሴቶች ናቸው ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት የስርጭት ምጣኔው ከ1 በታች መሆኑ የስርጭት መጠኑ አነስተኛ እንደሆነ ነው የሚያሳየን የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ የስርጭት መጠኑ ግን ሊያዘናጋን አይገባም ይላሉ። ""መዘናጋቱ እና ቸልተኝነቱ በዚህ መንግድ የሚቀጥል ከሆነ፤ እንደ አገር ያልተገባ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል"" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ የልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የድርሻቸውን መ���ጣት አለባቸው ይላሉ። ኮቪድ እና ኤችአይቪ የኮሮናቫይረስ መከሰት ኤችአይቪ በደማቸው በሚገኝባቸው እና መድሃኒት በሚወስዱ ሰዎች ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል ይላሉ። ""ትልቁ ችግር የነበረው ስነ-ልቦናዊ ተጽእኖ ነው"" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ኮቪድ-19 ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸውን ሰዎችን ይጎዳል በሚል በስጋት ወደ ጤና ተቋም ያለመምጣት ሁኔታዎች እንደነበሩ ይናገራሉ። ከዚህ በተጨማሪም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በማሰብ በመንግሥት የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን ተከትሎ ከሚኖሩበት ርቀው መድሃኒት ይወስዱ የነበሩ ሰዎች የትራንስፖርት አማራጭ ባለማግኘት መድሃኒታቸውን መውሰድ የማይችሉት ሁኔታ ነበር። ""ለምሳሌ አዲስ አበባ ላይ ያለ ሰው አዳማ ሄዶ የሚወስድ ከሆነ . . . መንቀሳቀሱ ሲቆም መድሃኒቱን በትክክል ለመወሰድ መቸገር ነበር"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59515396 +business የዶናልድ ትራምፕ ሀብት በአያሌው አሽቆለቆለ "የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀብታቸው በ700 ሚሊዮን ዶላር ቀንሶባቸዋል ሲል ብሉምበርግ ዘገበ። አስገራሚው ነገር ሀብታቸው ያሽቆለቆለው ፕሬዝዳንት በሆኑባቸው ዘመናት መሆኑ ነው። አሁን የሰውየው ድምር ሀብት 2.3 ቢሊዮን ብቻ ነው። ለትራምፕ ሀብት መቀነስ ዋና ምክንያት ተደርጎ የተወሰደው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሲሆን የትራምፕ እውቅ ሆቴሎች፣ ጎልፍ ክለቦችና መዝናኛ ማዕከላቱ በደንበኞች ድርቅ መመታታቸው 700 ሚሊዮን ዶላር አሳጥቷቸዋል። ዶናልድ ትራምፕ አሁን ከቤተሰብ ቢዝነስና ከግብር ክፍያ ጋር በተያያዘ የወንጀል ምርመራ ፋይል ተከፍቶባቸዋል። ብሉምበርግ የሰውየውን ወጪና ገቢ ከግንቦት 2016 ጀምሮ እስከ ጥር 2021 ድረስ ሲያሰላው ቆይቷል። ፕሬዝዳንቱ ነጩ ቤተ መንግሥት ከመግባታቸው በፊትና በኋላ የሀብታቸውን ከፍና ዝቅ አስልቶታል። ትራምፕ የሀብታቸው ሦስት እጅ የሚይዘው የሪልስቴት ልማት ነው። ለቢሮ የሚውሉት የትራምፕ ፎቆች ገቢያቸው በከፍተኛ ሁኔታ ያሽቆለቆለ ሲሆን ይህም በወረርሽኙ ምክንያት ሰዎች ከቤታቸው መሥራት በመጀመራቸው የቢሮ አስፈላጊነት እየቀነሰ በመምጣቱ ነው። የገንዘብና ሀብት ሰነዶችን በማውጣት የሚታወቀው ብሉምበርግ እንደሚለው የዶናልድ ትራምፕን ስምና የንግድ ምልክታቸውን በመሸጥ የሚተዳደሩና በቀጥታ በራሳቸው ሥር የተቋቋሙ 19 ጎልፍ መጫወጫ ሜዳዎች አሏቸው። ከዚህ ሌላ 12 የሚሆኑ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ይገኛሉ። ምንም እንኳ ጎልፍ ተራርቆ በመቆም የሚጫወቱት ስፖርት በመሆኑ በወረርሽኑ ጊዜ ተመራጭ ስፖርት ሆኖ ቢቀጥልም የዶናልድ ትራምፕ በስኮትላንድ የነበሯቸው ሁለት ዕውቅ የጎልፍ ሜዳዎች ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባቸዋል። በተለይም ነውጠኛ ደጋፊዎቻቸው ባለፈው ጥር ካፒቶል ሒልን መውረራቸውን ተከትሎ የአሜሪካ ፕሮፌሽናል ጎልፍ ተጫዋቾች ማኅበር በ2022 በኒው ጀርሲ በትራምፕ የጎልፍ ሜዳ ሊያዘጋጀው የነበረውን የጎልፍ ውድድር በመሰረዙ ትራምፕ ዳጎስ ያለ ትርፍ አምልጧቸዋል። ትራምፕ በ1990ዎቹ የቢዝነስ ክስረት በገጠማቸው ጊዜ ሊያበድራቸው ፈቅዶ የነበረው አጋራቸው ዶቼ ባንክም ከዚህ የካፒቶል ሒል ክስተት በኋላ ""ከእርስዎ ጋር ለመሥራት ይከብደኛል"" በሚል ጥሏቸው ሄዷል። ትራምፕ ከጎልፍ ሜዳዎችና ሆቴሎች እንዲሁም ሰማይ ጠቀስ የቢሮ ፎቆች በተጨማሪ በርከት ያሉ መለስተኛ አውሮፕላኖች አሏቸው። ከእነዚህ መካከል ቦይንግ 757 አውሮፕላኖች ይገኙበታል። ብሉምበርግ እንደሚለው አብዛኞቹ የትራምፕ አውሮፕላኖች አሁን እያረጁ በመሆናቸው ገበያቸው ተቀዛቅዟል። ከትራምፕ አውሮፕላኖች ውስጥ 7 የሚሆኑት በ2015 ግምታቸው 60 ሚሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን በ2020 ደግሞ 5 ሌሎች አውሮፕላኖች ግምታቸው 6 ሚሊዮን ብቻ ሆኗል። ይህም ከአውሮፕላኖቹ ዕድሜ ጋር የተያያዘ ነው። ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ሁሉ ሀብት ውስጥ የፋይናንስ ሰነዶቻቸው ጥርጣሬን የሚጭሩ በመሆናቸው ለምርመራ ተጋልጠዋል። ትራምፕ ምን ያህል ግብር እንደሚከፍሉ ለመግለጽ ሲተናነቃቸው ቆይቷል። ባለፈው ወር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዶናልድ ትራምፕን የግብር ሰነዶቻቸውን ለዐቃቢ ሕግ ይፋ እንዲያደርጉ አዟቸዋል። ይህ ምርመራ የተጀመረው በ2018 ቢሆነም እስከዛሬም አልተቋጨም። ብዙ የሚዲያ መረጃዎች ትራምፕ የግብር ማጭበርበርና የግብር ስወራ እንደፈጸሙ የሚጠቁሙ ናቸው። ትራምፕ ፕሬዝዳንት ሳሉ ያመለጣቸውን ትርፍ አሁን ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ከቲቪና ከመጽሐፍ ስምምነቶች በሚያገኙት ገንዘብ ያካክሱታል ተብሎ ይገመታል፡። ባራክ ኦባማን ሚሼል ኦባማ ከአሳታሚዎች ጋር ባደረጉት ስምምነት በድምሩ 65 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሏቸዋል። ቢል ክሊንተን በ2014 ለሚጽፉት መጽሐፍ 15 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ተከፍሏቸው ነበር። ትራምፕ የሚጽፉት መጽሐፍ አንባቢዎችን ይማርካል ተብሎ አይጠበቅም። የሰውየው ግንዛቤም ጥልቀት ይጎድለዋል ስለሚባል ትራምፕ ከመጽሐፍ የባራክ ኦባማን ያህል ትርፍ ያገኛሉ አይባልም። ሆኖም 74 ሚሊዮን የሚገመቱ ተከታዮቻቸውን ሊማርክ የሚችል ትዕይነት በቴሌቪዥንና በማኅበራዊ የትስስር መድረክ በማቅረብ ዳጎስ ያለ ትርፍ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56441600 +politics የአሜሪካ ምክር ቤት፡ ደጋፊዎቻቸው የአገሪቱ ምክር ቤትን ከወረሩ በኋላ ትራምፕ ከትዊተርና ከፌስቡክ ታገዱ ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዋነኛዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጾች እንዲታገዱ ሆነዋል። ይህ እርምጃ የተወሰደባቸው ደጋፊዎቻቸው የካፒቶል ሂል ግቢን መውረራቸውና አደጋ ማድረሳቸውን ተከትሎ ነው። ዓለምን ባስገረመውና በአሜሪካ ምድር ይሆናል ተብሎ ባልተጠበቀ ነውጥ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የታችኛውና የላይኛው ምክር ቤት መሰብሰቢያ የሚገኝበትንና የመንግሥት መቀመጫ የሆነውን ካፒቶል ሒልን ጥሰው በመግባት አደጋ ያደረሱት ከሰዓታት በፊት ነው። ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጠንካራ መልእክት ያስተላልፋሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ሰዓት 'እወዳችኋለሁ' የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን የተለመደውን ምርጫው ተጭበርብሯል የሚለውን ያልተጨበጠ ክስም በማኅበራዊ ገጻቸው አስተላልፈዋል። ትዊተር ሦስት የትራምፕ መልእክቶችን ከገጹ እንዲወገዱ እንደጠየቀ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከፖሊሲያችን ጋር የሚጻረሩ መልእክቶች ስለሆኑ ነው መወገድ ያለባቸው ብሏል። ካልተወገዱ ግን ትራምፕን እስከመጨረሻው ከትዊተር አሰናብታቸዋለሁ ብሏል። ይህም ትዊተር ዶናልድ ትራምፕን እስከመጨረሻው ለማሰናበት በርካታ ቀናትን ላይጠብቅ ይችላል ማለት ነው። የትዊተር ውሳኔ በእንዲህ ሳለ ፌስቡክ በበኩሉ ትራምፕን ለ24 ሰዓታት እግድ ጥሎባቸዋል። ዩትዩብ በበኩሉ የትራምፕን ቪዲዯዎች ከገጹ እንዲወርዱ አድርጓል። ፌስቡክ ለምን ትራምፕን ለ24 ሰዓታት ከገጹ እንዳገደ በገለጸበት መግለጫው ምክንያቱም እየታየ ላለው ነውጥ ትራምፕ ማባባስ እንጂ ማብረድ ባለመቻላቸው ነው ብሏል። የትራምፕ ደጋፊዎች የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ የሆነውን ካፒቶል ሒልን ሰብረው በመግባት ከፖሊስ ጋር የተጋጩ ሲሆን በዚህ ዓለምን ጉድ ባሰኘው ነውጥ የአንዲት ሴት ሕይወት ማለፉም ተነግሯል። የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሒልን ጥሰው ጥቃት ሲፈጽሙ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት በጆ ባይደን ጉዳይና ድል እየተከራከረ ነበር። በሁለቱ ምክር ቤቶች ሪፐብሊካኖችና ዲሞክራቶች የኖቬምበሩን የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉትን ጆ ባይደንን ውጤት ማጽደቅና አለማጽደቅ ላይ እየተነጋገሩ በነበረበት ሰዓት ነው የትራምፕ ደጋፊዎች ያልተጠበቀ እርምጃ የወሰዱት። ይህ ነውጥ ከመከሰቱ በፊት ትራምፕ በዋሺንግተን ናሸናል ሞል ለደጋፊዎቻቸው ምርጫው ተዘርፏል ሲሉ ነበር። ይህ ከሆነ ከሰዓታት በኋላ ደጋፊዎቹ ካፒቶል ሒልን ጥሰው ገብተው ጉዳት ማድረስ ጀመሩ። ትራምፕ ድርጊቱን ያወግዛሉ ሲባል በቪዲዯ ቀርበው ምርጫው ተጨበርብሯል የሚለውን ንግግር ደገሙት። ይህ አልበቃ ብሎም ነውጠኞቹን እወዳችኋለሁ። ጀግኖች ናችሁ ያልዋቸው። ዩ ትዩብ ይህንን የፕሬዝዳንቱን ንግግር የኔን ፖሊሲ የማይከተል ስለሆነ አስወግጄዋለሁ ብሏል። ትዊተር በበኩሉ ይህንን ቪዲዮ ከማስወገድ ይልቅ ሰዎች እንዳያጋሩት እና መውደዳቸውን የሚያሳየውን ምልክት (ላይክ እንዳያደርጉት)፣ ከቪዲዯው ሥር አስተያየት እንዳይሰጡ በማድረግ የቪዲዯ መልእክቱ እንዳይዛመት አድርጎ ነበር። በኋላ ላይ ግን ቪዲዯውን ሙሉ በሙሉ አስወግዶ ፕሬዝዳንቱም ለጊዜው ከትዊተር እንዲሰናበቱ አድርጓቸዋል። ካፒቶል ሒልን የመውረሩ የነውጥ እንቅስቃሴ ሲስተባበር የነበረው በዋናነት እነዚህኑ ማኅበራዊ የትስስር መድረኮችን በመጠቀም ነበር። https://www.bbc.com/amharic/news-55561320 +politics "የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ""አሜሪካ ጥቁሮች ላይ የምታደርሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰት"" እንድታቆም ጠየቁ" ጆ ባይደን ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በተደረገ የቻይና-አሜሪካ የንግድ ምክክር መድረክ በሁለቱ ኃያል አገሮች ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል ውይይት እየተደረገ ሲሆን ጠጣር የሐሳብ ልውውጦች መደረጋቸው ተሰማ፡፡ በዚህ የሁለትዮሽ ስብሰባ አንዱ ሌላውን አገር ያለ ርሕራሔ እየወቀሰ ይገኛል፡፡ የቻይና ከፍተኛ ባለሥልጣናት አሜሪካን ሌሎች አገሮች ቻይና ላይ ጦር እንዲሰብቁ ታበረታታለች ሲሉ ከሰዋል፡፡ አሜሪካ በበኩሏ ቻይና በዓለም አቀፍ ደረጃ አላስፈላጊ ትኩረትን ለመሳብ ትጥራለች ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ በሁለቱ አገሮች መካከል አሁን ያለው ግንኙነት የሻከረ የሚባል እንደሆነ ዲፕሎማቶች ያወሳሉ፡፡ አሜሪካ በዚህ ስብሰባ ላይ አጨቃጫቂ የሚባሉ ጉዳዮችን እንደምታነሳ ይጠበቃል፡፡ ከነዚህ አንዱ ቤጂንግ የኡህጉሩ ሙስሊሞችን በዢንዣንግ ካምፕ ውስጥ የምታደርስባቸውን ስቃይ እንድታቆም ይጠይቃሉ ተብሏል፡፡ ይህ በቃላት ጦርነት የታጀበ የከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብሰባ እየተካሄደ ያለው በአላስካ ሲሆን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እና የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጄክ ሰሊቫን ተገኝተውበታል፡፡ በቻይና በኩል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ እና የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ባለሥልጣን ያንግ ጂቺ ተሳትፈዋል፡፡ በሁለትዮሹ ስብሰባ በጠንካራ ንግግር ውይይቱን ያስጀመሩት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን አሜሪካ በዚህ ስብሰባ የሚያሳስቧትን የዢንዣንግ ሙስሊሞች አፈና፣ የሆንግ ኮንግን እና የታይዋንን ጉዳይ እንዲሁም ከቻይና የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶችን ጉዳይ ታነሳለች ብለዋል፡፡ ለዚህ ምላሽ የሰጡት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያንግ ዋሺንግተን ባላት የፋይናንስና የወታደራዊ ኃያልነት የተነሳ ሌሎችን ትደፈጥጣለች ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ አክለውም አሜሪካ በብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ስም በርካታ የንግድ ወንጀሎን ትፈጽማለች ብለዋል፡፡ ሌሎች አገራትም ቻይና ጋር ወዳጅ እንዳይሆኑ ታስፈራራለች ሲሉም ወቅሰዋል፡፡ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአሜሪካ የሰብአዊ መብት ጥሰት መባባሱን ጠቅሰው ጥቁሮች በጠራራ ፀሐይ እየተገደሉ ነው ሲሉ አስገራሚ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ይህ በከፍተኛ ባለሥል��ናት ደረጃ የሚደረገው መተቻቸት የዓለም ሚዲያዎች በተገኙበት እየሆነ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡ ይህ አንድ ሁለት መባባል እየተካረረ ከሄደ በኋላ አሜሪካ ቻይናን ‹የተስማማነው 2 ደቂቃ የመክፈቻ ንግግር ለማድረግ ቢሆንም በዚህ ስብሰባ ቻይና መስመር አልፋ ወቅሳኛለች ስትል ከሳታለች፡፡ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን እንደተናገሩት ቻይና በዚህ ስብሰባ ሆን ብላ የዓለም ሚዲያውን ትኩረት ለመሳብ ተዘጋጅታ ነው የመጣችው ብለዋል፡፡ ቻይና በበኩሏ ስብሰባው መክፈቻ ላይ ለ2 ደቂቃዎች ብቻ እንወቃቀስ ብንባባልም ይህን ፕሮቶኮል የጣሰችው አሜሪካ ራሷ እንጂ እኛ ቻይናዊያን አይደለንም ብለዋል፡፡ ጨምረውም አሜሪካ የቻይናን የውጭና የአገር ውስጥ ፖሊሲ በዓለም ሚዲያ ፊት ለማብጠልጠል መሞከራቸው አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡ ሁለቱ አገሮች በዚህ ስብሰባ በትራምፕ ዘመን አፈር ልሶ የነበረውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሻሻል እንደሚጥሩ ይጠበቃል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-56453316 +sports የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት፡ ሁለት አፍሪካዊያን ለዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌቶች ሽልማት ታጩ የዓለም አትሌቲክስ በየዓመቱ በሚያዘጋጀው ምርጥ ሴት አትሌቶች ሽልማት ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ እና ኬንያዊቷ ፔረስ ጀፕቺርቺር ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው ተገለፀ። የዓለም አትሌቲክስ ማክሰኞ እለት በአስሩ ዝርዝር ውስጥ ገብተው ከነበሩ አትሌቶች አምስት ለመጨረሻው ዙር መመረጣቸውን አስታውቋል። ሌሎች ሦስት አፍሪካዊያን አትሌቶች አስሩ ዝርዝር ውስጥ ተካተው የነበረ ቢሆንም 5ቱ ዝርዝር ውስጥ ግን መግባት ሳይችሉ ቀርተዋል። እነዚህ አትሌቶች ኢትዮጵያዊቷ አባበል የሻነህ፣ ኬንያዊያኖቹ ዶ ፌዝ ኪፕየጎን እና ሔለን ኦቢሪ ናቸው። ለ ሌሎቹ በአምስቱ ዝርዝር ውስጥ መካተት ያልቻሉት አትሌቶች ደግሞ የኔዘርላንዷ ፌምኬ ቦል እና እንግሊዟ ላውራ ሙር ናቸው። የዘንድሮው ዓመት የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት ሥነ ሥርዓት በቨርቹዋል [ኢንተርኔት] በአውሮፓዊያኑ ታህሳስ 5 የሚካሄድ ሲሆን በማኅበራዊ ሚዲያም በቀጥታ ይሰራጫል ተብሏል።የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት 5ቱ እጩዎች ለተሰንበት ግደይ በ5000 ሜትር በ14፡06፡62 በመግባት የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብራለች። ቫሌንሺያ በተደረገው በዚህ ውድድር በጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት ዓመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሽላለች ተብሏል። የ22 ዓመቷ ሯጭ የገባችበት ሰዓትም 14 ደቂቃ ከ6.62 ሰኮንዶች ሲሆን የጥሩነሸ ደግሞ 14 ደቂቃ ከ11.15 ሰከንዶች ነበር። በሞናኮ በተካሄደው በዋንዳ ዲያመንድ ሊግም 5000 ሜትር ሩጫ በሁለተኛ ደረጃነት አጠናቃለች። ሲፋን ሐሰን 18,930 ሜትር በአንድ ሰዓት ጊዜ በመሮጥ የዓለም ክብረ ወሰን ይዛለች። በ10 ሺህ ሜትር በ29፡36፡67 በማጠናቀቅም የአውሮፓ ክብረወሰን ያስመዘገበች ሲሆን በታሪክ አራተኛዋ ፈጣኗ ሯጭ ተብላለች። የዓለም ግማሽ ማራቶን አሸናፊ ናት። በሴቶች ውድድር 1፡ 05፡34 እና 1፡ 05፡ 16 ሰዓት በመግባት የግማሽ ማራቶን ክብረወሰንን ሁለት ጊዜ ሰብራለች። በቤት ውስጥና ከቤት ውጭ በተደረጉ አራት የርዝመት ዝላይ ውድድሮች አሸንፋለች። በቤት ውስጥ በተካሄደ የርዝመት ዝላይ ውድድር 15.43 ሜትር በመዝለል የዓለም ክብረ ወሰን ሰብራለች። በሰባት የ100 ሜትር ውድድሮች አሸንፋለች። በዓለም መሪነት 100 ሜትር በ10.85 ሰከንድ ሮጣለች። ከእነዚህ እጩዎች አሸናፊውን ለመለየት ሦስት የድምፅ አሰጣጥ መንገዶች አሉ። የዓለም አትሌቲክስ ምክር ቤት እና የዓለም አትሌቲክስ ቤተሰቦች ድምፃቸውን በኢሜይል የሚሰጡ ሲሆን አድናቂዎቻቸው ደግሞ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ድምፅ ይሰጣሉ። ከአጠቃላይ ድምፁ የምክር ቤቱ ድምፅ 50 ���መቶ ይይዛል። የአትሌቲክስ ቤተሰቦችና የሕዝብ ድምፅ ደግሞ እያንዳንዳቸው 25 በመቶ ይይዛሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-55036276 +sports የቶኪዮ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ በመነከሱ ምክንያት በአዲስ ሊተካ ነው "የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዋ በትውልድ ከተማዋ ከንቲባ ሜዳሊያዋ በመነከሱ ምክንያት አዲስ ሊሰጣት ነው። የጃፓኗ ናጎያ ከተማ ከንቲባ ታካሺ ካዋሙራ በአንድ ዝግጅት ላይ ጭምብላቸውን ዝቅ በማድረግ የሶፍትቦል ተወዳዳሪዋን ሚኡ ጎቶን ሜዳሊያ በመንከሳቸው በማኅበራዊ ድር አምባ ቁጣን ቀስቅሷል። ከንቲባው የኮቪድ -19 ገደቦችን ችላ በማለት እና ""አክብሮት የጎደለው"" በሚል ተከሰዋል። ይሁን እንጅ ከንቲባው ይቅርታ ከጠየቁ እና ለምትኩ ክፍያ እንደሚፈጽሙ ከተናገሩ በኋላ የኦሊምፒክ ባለሥልጣናት የጎቶ ሜዳልያ በአዲስ እንደሚለወጥ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት በሴቶች የሶፍትቦል የፍጻሜ ውድድር ጃፓን በአሜሪካን ላይ ድል አግኝታለች። ከንቲባውም ይህን ድል ለማክበር ነበር ሜዳሊያውን በጥርሳቸው የያዙት፤ በኋላ ላይ ግን በድርጊታቸው ከመብጠልጠል አልዳኑም። የማኅበራዊ ድር አምባ ተጠቃሚዎች ድርጊቱ ንጽሕና የጎደለው እና ለአትሌቷ ያሳዩት ጨዋነት የጎደለው ተግባር ነው ብለዋል። ""ለአትሌቶች የአክብሮት እጦት ከማሳየት ባሻገርም፤ አትሌቶች በሜዳልያ ሥነ ሥርዓቶች ወቅት ቫይረሱን ለመከላከል ሲባል ሜዳልያዎችን ራሳቸው ሲያጠልቁ ወይም ለሌሎች የቡድን አባላቶቻቸው ሲያጠልቁ ቢታዩም እሳቸው ግን ነክሰውታል። ይቅርታ፣ አልገባኝም!"" ሲል የጃፓኑ የብር ሜዳልያ ተሸላሚ ዩኪ ኦታ በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል። በጃፓን በማኅበራዊ ድር አምባዎች ላይ ""የጀርም ሜዳሊያ"" የሚል ሃሳብ በስፋት እየተንሸራሸረ እየታየ ነበር። ጎቶ የምትጫወትበት ቡድን ባለቤት የሆነው ቶዮታም ድርጊቱን ""ተገቢ ያልሆነ"" እና ""እጅግ የሚያሳዝን"" ብሎታል። የ72 ዓመቱ ከንቲባ ለድርጊቱ በኋላ ላይ ይቅርታ ጠይቀዋል። የከንቲባው ድርጊት ከ7,000 በላይ ቅሬታዎች ለከተማው ባለሥልጣናት እንዲደርስ ምክንያት ሆኗል ተብሏል። ""እንደ ናጎያ አስተዳዳሪ ያለኝን ቦታ ረስቼ እጅግ ተገቢ ባልሆነ መንገድ እርምጃ ወስጄ ነበር' ሲሉ ለሚተካው ሜዳሊያ እንደሚከፍሉ ከንቲባው አስታውቀዋል። የቶኪዮ 2020 አዘጋጆች ሐሙስ ዕለት በሰጡት መግለጫ በአዲስ ሜዳሊያ በመተካቱ ዙሪያ በዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እና በጎቶ መካከል ከስምምነት ተደርሷል። ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ወጪዎቹን ይሸፍናልም ብሏል። ሜዳሊያዎችን መንከስ በውድድሮች ውስጥ የተለመደ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ግን ይህን የሚያደርጉት አሸናፊዎቹ ብቻ ናቸው። የቶኪዮ 2020 አዘጋጆች ባለፈው ሳምንት በትዊተር ገጻቸው ላይ ""የ#ቶኪዮ2020 ሜዳሊያዎች የማይበሉ መሆናቸውን በይፋ ለመግለጽ እንፈልጋለን!"" ሲሉ ጉዳዩን ወደ ቀልድ ወስደውት ነበር። ካዋሙራም ሆኑ ጎቶ ግን በጉዳዩ ላይ ወዲያው አስተያየት አልሰጡም።" https://www.bbc.com/amharic/news-58168874 +health ’ኮሮናቫይረስ፡ ካልተከተቡ አይቀጠሩም’ የሚል ህግ ለአዳዲስ ሠራተኞች ተግባራዊ ሊሆን ይችላል "ኩባንያዎች አዳዲስ ሠራተኞቻቸው፣ ከመቀጠራቸው በፊት እንዲከተቡ ቢጠይቁ ህጋዊ ሊሆን ይችላል ሲሉ የእንግሊዝ የፍትህ ሚንስትር አስታወቁ። እንደሮበርት ባክላንድ ከሆነ ነባር ሠራተኞች ባላቸው ውል መሠረት ክትባቶችን እንዲወስዱ የመጠየቅ ነገር ላይኖር ይችላል። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ሰዎች በሥራቸው እንዲቀጥሉ ክትባት እንዲወስዱ ማዘዙ ""አድሎአዊ"" ነው ብሏል። ነገር ግን አንዳንድ ድርጅቶች ክትባቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆኑ አዳዲስ ሠራተኞችን እንደማይቀጥሩ ይናገራሉ፡፡ ባክላንድ ረቡ��� ዕለት ከአይቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አዳዲስ በሥራ ውል ላይ በጽሑፍ እስከቀረበ ድረስ ሠራተኞችን እንዲከተቡ ማስገደድ ይቻል ይሆናል ብለዋል፡፡ ሆኖም አሠሪዎች ምናልባት ነባር ሠራተኞች እንዲህ ዓይነቱን ትዕዛዝ እምቢ ካሉ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ሊያስፈልጋቸው ይችላል ተብሏል። አክለውም ""ያለ ክትባት ሥራ የለም"" የሚሉት መስፈርት ሕጋዊነት ""በቅጥርና በልዩ ውል ላይ የተንጠለጠለ ነው"" ብለዋል፡፡ ""በአጠቃላይ አካሄዱን ሕጋዊ ያደረጉት አሁን ያሉት የሥራ ኮንትራቶች ቢኖሩ እደነቃለሁ፡፡ እውነቱን ለመናገር ጉዳዩ መፈተሽ ያለበት ይመስለኛል"" ብለዋል፡፡ መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የፒምሊኮ ፕለምበርስ ከህክምና ጋር በተያያዘ ካልሆነ በስተቀር ክትባቱን አልፈልግም የሚሉ አዳዲስ ሠራተኞችን አልቀጥርም ካሉት ኩባንያዎች አንዱ ነው፡፡ ከቅጥር ጋር በተያያዘ የሚሠሩ የህግ ባለሙያዎች በመጀመሪያ እርምጃው ላይ ጥያቄ ቢያነሱም መስራቹ ቻርሊ ሙሊንስ ህጋዊ እንደሆነ ምክር እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ ""እኛ በግልጽ ከጠበቆች ጋር የተነጋገርን ሲሆን ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ከወጣ በኋላ ከእኛ ጋር ለሚጀምሩ ማናቸውም አዳዲስ ሠራተኞች የክትባቱ ጉዳይ በውሉ ውስጥ በመካተቱ ባለሙያዎቹ በጣም ደስተኞች ናቸው"" ብለዋል ለቢቢሲ፡፡ ""አዲሶቹን ኮንትራቶች ከሁለት እስከ ሶስት ወራቶች ውስጥ እንጠቀማቸዋለን፡፡ ሰዎች ከእኛ ጋር ሥራ ለመሥራት ሲመጡ ያንን በመፈረም ደስተኛ ካልሆኑ የእነሱ ምርጫ ነው። በእርግጠኝነትም ሥራው ከፒምሊኮ ፕላምበርስ አይሰጣቸውም"" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የቤት እንክብካቤ ላይ የተሠማራው ባርቸስተር ሄልዝኬርም ሁሉም አዲስ ቅጥር ሠራተኞችየመከተብ ግዴታ አለባቸው ብሏል፡፡ ""ከሠራተኞቻችን ጋር በተያያዘ ፍላጎት ያላቸውን ክትባቱን እንዲያገኙ ለማበረታታት የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው። በተጨማሪም ሁሉም አዲስ ሠራተኞች ክትባቱን መውሰዳቸውን ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ማረጋገጥ አለብን"" ያለው ድርጅቱ ደንበኞቹን እና ሠራተኞቹን ጤንነት መጠበቅን ደግሞ በምክንያትነት አስቀምጧል። 'የህግ ክፍተት' ሌዊስ ሲልኪን በሚባለው የሕግ ኩባንያ የሕግ ዳይሬክተር የሆኑት ዴቪድ ሳሙኤል እንዳሉት ድርጅቶች በአዳዲስ ቅጥር ሠራተኞቻቸው ኮንትራቶች ውስጥ ""ያለ ክትባት ሥራ የለም"" የሚል አንቀጽን ከማስገባት የሚያግዳቸው ሕጋዊ ማዕቀፍ የለም፡፡ አሠሪዎች እያንዳንዱን የሥራ ሚና መተንተን እና እንዲህ ዓይነቱን ሐረግ ከማስተዋወቅ በፊት የጤና እና የደህንነትን አደጋዎችን መገምገም አለባቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ይህ ባለማድረጉና አንድ ሠራተኛ ያልተከተበት ምክንያት ቢኖረው ውሉ ኢ-ፍትሃዊ ወይም አድሎአዊ ነው ብሎ ለመከራከር ያስችለዋል፡፡ ሌሎች ስጋቶችም አሉ። ለምሳሌ ፣ ""ካልተከተቡ ሥራ የለም"" የሚለው ፖሊሲ ክትባቱን ለመውሰድ የመጨረሻ መስመር ላይ ባሉ ወጣቶች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ የሚል ስጋት አለ፡፡ ""ይህን ለማጽደቅ ከባድ ይሆናል። በተለይም በዚያ ሂደት ውስጥ ካልገቡ እና ካልሰነዱት በሕጋዊ ጥያቄ የመፈታተናቸው ዕድላቸው ሰፊ ነው"" ሲሉ ሳሙኤል ለቢቢሲ ገልጸዋል፡፡ የአንዳንድ ሠራተኞች የሥራ ሁኔታ በቢሮ ወይም በፋብሪካ እንዲሠሩ የሚያስገድድ ከሆነ ድርጅታቸው እንደዚህ ዓይነት አንቀፅ ሊቀመጥ ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ እንደደረሳቸው አክለው ገልጸዋል፡፡ ""ክትባት መውሰድ ግዴታ አይደለም፤ እናም አንድ ሰው እንዲወስድ ማስገደድ አድልአዊ ነው"" ብለዋል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ፡" https://www.bbc.com/amharic/news-56121979 +health በዓለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከሦስት ሚሊዮን አለፈ "በዓለም ዙሪያ በ���ቪድ-19 ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሦስት ሚሊዮን ማለፉን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ገለጸ። ይህ የተገለጸው የዓለም ጤና ድርጅት ""ዓለም ወደ ከፍተኛው የኢንፌክሽን መጠን እየተቃረበ ነው"" መሆኑን ባስጠነቀቀ ማግስት ነው። ብዙ ሰዎች በቫይረሱ በመያዝ ሁለተኛ የሆነችው ሕንድ ዛሬ ቅዳሜ ብቻ ከ230,000 በላይ አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አስመዝግባለች። ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ ወደ 140 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አርብ ዕለት ""በበሽታው የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአሳሳቢ ደረጃዎች እየጨመረ ነው"" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አክለውም ""ባለፉት ሁለት ወራት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሳምንት በቫይረሱ የሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ሊጨምር ችሏል"" ብለዋል። ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ እንደገለጸው አሜሪካ፣ ሕንድ እና ብራዚል ከፍተኛ ቁጥር ያስመዘገቡ አገራት ሲሆኑ በሦስቱ አገራት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሞተዋል። ባለፈው ሳምንት በዓለም ዙሪያ በየቀኑ በአማካይ 12,000 ሰዎች መሞታቸውን የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ዘግቧል። ይህ ስለወረርሽኙ የሚወጣው አሃዝ በዓለም ዙሪያ በብዙ አገሮች ውስጥ ስላለው የበሽታው ሁኔታ ትክክለኛውን መረጃ ላያንፀባርቅ ይችላል ተብሏል። በሕንድ ምን እየተከሰተ ነው? እስከ ጥቂት ሳምንታት በፊት ድረስ ሕንድ በአንጻራዊ ሁኔታ ወረርሽኙን በቁጥጥር ስር ያዋለች ይመስል ነበር። በጥር እና በየካቲት ወራት በአብዛኛው በቀን ከ20 ሺህ በታች አዳዲስ ታማሚዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ ይህም ከ1.3 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ ላላት አገር ዝቅተኛ ቁጥር ነው። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ሄዶ ቅዳሜ ብቻ ለሦስተኛ ተከታታይ ቀን ክብረ ወሰን የሆነ 234,000 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል። ሆስፒታሎች የአልጋና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠማቸው ነው። የታመሙ ሰዎች ወደ ቤት እየተመለሱ ሲሆን አንዳንድ ቤተሰቦች የሚፈልጉትን መድኃኒት ለማግኘት ወደ ጥቁር ገበያ ፊታቸውን አዙረዋል። በቢቢሲ የምርመራ ዘገባ መሠረት በሕንድ ውስጥ መድኃኒት ከመደበኛው ዋጋ በአምስት እጥፍ ለገበያ እየቀረበ ነው። ባለሥልጣናት ወረርሽኙን ለመግታት በዋና ከተማዋ ደልሂ እና በሌሎች አካባቢዎች በሳምንቱ መጨረሻ ላይ የእንቅስቃሴ እገዳዎች ተጥለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56778230 +business በአርጀንቲና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተቃዋሚው አሸነፉ በኢኮኖሚ ቀውስ እየተናጠች ባለችው አርጀንቲና የግራ ዘመም ተቃዋሚ ፓርቲ መሪው አልቤርቶ ፈርናንዴዝ አሸናፊ ሆነዋል። ፈርናንዴዝ ምርጫውን ያሸነፉት ለድል የሚያበቃውን ከ45 በመቶ የሚበልጥ ድምፅ በማግኘት እንደሆነ ተገልጿል። ምርጫው ሲሶው የአርጀንቲና ህዝብ በድህነት አረንቋ ውስጥ በወደቀበት ጊዜ የተካሄደ እንደመሆኑ የድምፅ ባለቤት የሆነው ህዝብ ድምፁን የሰጠው ሙሉ በሙሉ የእጩዎችን የኢኮኖሚ አማራጭ ሃሳብ በመመዘን ነው ተብሏል። • ሊዮኔል ሜሲ እየሩሳሌም አይሄድም ፈርናንዴዝ ያሸፏቸው የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት ሙርሲዮ ማርሲ በቅድመ ምርጫ ትንበያዎችም ሽንፈታቸውን ሰምተውት ነበር። ትናንትናም መሸነፋቸውን በማመን ተቀናቃኛቸው ፈርናንዴዝን 'እንኳን ደስ ያለዎት ሰኞ ቤተ መንግሥት ይምጡና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ስለማድረግ እንነጋገር' ብለዋቸዋል። አዲሱ ፕሬዘዳንት ፈርናንዴዝም ነገሮችን ሰላማዊ ለማድረግ ከተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ጋር በማንኛውም መንገድ እንደሚተባበሩ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ከ90 በመቶ በላይ የሚሆን ድምፅ ተቆጥሮ ፈርናንዴዝ 47.79 በመቶ ድምፅ ሲያገኙ ማርሲ ደግሞ ያገኙ�� 40.71 በመቶ መሆኑ ተገልጿል። https://www.bbc.com/amharic/50204931 +health ኮሮናቫይረስ፡ ሙሉ ሕዝቧን እየከተበች ያለችው እስራኤል በክትባቱ ፍቱንነት ጥርጣሬ የገባት ለምንድነው? "ሕዝቧን በብዙ ቁጥር እየከተበች ያለችው እስራኤል የክትባቱን ፈዋሽነት የሚጠራጠሩ ዜጎቿ አሳስበዋታል። ተራ ዜጎች ብቻም ሳይሆኑ የጤና ባለሙያዎቿም ስለ ክትባቱ ፈዋሽነት መጠነኛ ጥርጣሬ የገባቸው ይመስላል። እስራኤል የኮቪድ ክትባትን በብዛት በመግዛት አገሯ አከማችታለች። በርካታ ሕዝቧን ክትባቱን ለመክተብ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ትገኛለች። ዝጅግት ላይ ብቻም ሳይሆን ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧን ክትባት እንዲደርሰው አድርጋለች። የእስራኤል ግብ ሙሉ በሙሉ ሕዝቧን መከተብና ተህዋሲውን ታሪክ ማድረግ ነው። እንዲያው አንዳንዶች ይቺ አገር እስራኤል ሕዝቧን ""የቤተሙከራ አይጥ"" ልታደርገው ነው ወይ? እስከማለት ደርሰዋል። ይህን ስታደርግ ታዲያ ብዙ የጤና አዋቂ ሳይንቲስቶች ዐይናቸውን በዚያች አገር ላይ ጥለዋል። ለምን? ዋናው ምክንያት በእስራኤል የሚታየው የክትባት ውጤት ለተቀረው ዓለም ብዙ ተስፋ ስለሚኖረው ነው። ሳይንቲስቶች እስራኤል ላይ ዓይናቸውን የጣሉበት አንዱ ምክንያትም ይኸው ነው። አንድ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ክትባት ሲከተብ በዚያች አገር ተህዋሲው ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አጓጉቷቸዋል። ይህንን የክትባቱን ዘመቻ እያስተባበሩ ከሚገኙት ዋናው ሰው የፋይዘር ክትባት እንደተባለው ፍቱን ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም በሚል ጥርጣሬ እንደገባቸው በይፋ ተናግረዋል። ይህን እንዲሉ ያደረጋቸው ታዲያ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የፋይዘር ክትባትን ከወሰዱ በኋላም ተህዋሲው ስለተገኘባቸው ነው። ጥርጣሬው መፈጠር የጀመረውም አንድም በዚህ የተነሳ ነው። ሌሎች ሳይንቲስቶች ግን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ጊዜው ገና ነው ይላሉ። እኚህ በክትባቱ ላይ ጥርጣሬን ያነሱት ፕሮፌሰር ናችማን አሽ በጤና ጥበቃ ሚኒስትር ጥርጣሪያቸው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። ""የፕሮፌሰሩ አስተያየት ከአውድ ውጭ የተነገረና ትክክል ያልሆነ ነው"" ብሏል የእስራኤል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ። ""በጽኑ የሚታመሙ ዜጎቻችን ቁጥር መቀነስ አለበት ብለዋል ፕሮፌሰሩ፣ ገና 2ኛው ዙር ብልቃጥ በመሰጠት ላይ ያለው አሁን ስለሆነ ይህ ውጤቱ በቀጣይነት የሚታይ እንጂ አሁን ምንም ማለት የሚቻልበት ደረጃ ላይ አይደለንም"" ብሏል ይኸው መግለጫው። እርግጥ ነው ክትባቱ የራሱ ባህሪ አለው። አንድ ሰው ክትባት ከወሰደ በኋላ ሰውነቱ የተህዋሲውን ጄኔቲክ አውቆ ወራሪ ኃይል እንደመጣ ተገንዝቦ ለዚህ የሚሆን መከላከያ ለማዘጋጀት ጊዜ ይፈልጋል። አንቲቦዲና ቲ'ሴል አምርቶ ተህዋሲውን ለመጋፈጥ ጊዜ ይፈልጋል። ይህ እስኪሆን የተከተበ ሰውም ቢሆን ሊታመም ይችላል። ቢመረመር ተህዋሲው ሊገኝበት ይችላል። ይህ ሂደት ታዲያ እስከ 2 ሳምንት ሊወስድ እንደሚችል ፕሮፌሰር ዳኔ አልትማን፣ የኢምፔሪያል ኮሌጅ ለንደን ኢሚኑሎጂስት ይናገራሉ። ክላት በእስራኤል ትልቁ የጤና ሽፋን ሰጪ ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት ከተከተቡ 200 ሺህ፣ እድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑት ውስጥ በዚሁ እድሜ ላይ ያሉ ክትባቱን ግን ካልወሰዱ ሰዎች ጋር በማወዳደር በሰራው ጥናት በሁለት ሳምንት ውስጥ የተከተቡትም ያልተከተቡትም ላይ ተመጣጣኝ ቁጥር ያለው ሰው በተህዋሲው መያዙን ይፋ አድርጓል። ይህ ነው በፋይዘር ክትባት ላይ ጥርጣሬ እንዲነግስ ምክንያት የሆነው። ከዚያ በኋላ ቆይቶ ግን የተከተቡት ካልተከተቡት በ33 ከመቶ ባነሰ በተህዋሲው መያዛቸው እየተስተዋለ መምጣቱ ተነግሯል። ""ይህ ገና ጅምር ላይ ያለ የጥናት ውጤት ነው፤ በ���ህ ደረጃ ራሱ በ33 በመቶ የተህዋሲው መዛመት ቀንሷል። ስለዚህ የሚያሳስብ ነገር የለም"" ብለዋል የክላት ድርጅት የጤና መኮንን ራን ባሊቸር። በፋይዘር የክሊኒክ የሙከራ ጊዜም ቢሆን ተመሳሳይ ነገር ታይቷል። ክትባቱን በወሰዱና ባልወሰዱት መሀል በተደረገ ጥናት ግልጽ ልዩነት ለማየትና የመዛመት ፍጥነት ሲቀንስ ለመታዘብ 100 ቀናት ያስፈልጋሉ ነው የሚለው መድኃኒት አምራቹ ፋይዘር። እስራኤል ዜጎቿን መከተብ የጀመረችው በታህሣሥ 19 ነበር። አሁን የሕዝቧን 10 ከመቶ ከከተበች 2 ሳምንት አልፏታል። ዛሬ ላይ ደግሞ ከ9 ሚሊዮን ሕዝቧ ውስጥ ግማሽ ሚሊዮኑ ክትባት ደርሶታል። ነገር ግን በአገሪቱ ውስጥ በተህዋሲው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ በጉልህ አልታየም። ለምን? ክትባት የወሰደ ሰው የመከላከል አቅም ለማዳበር ከሚወስድበት ጊዜ አንጻር ቢያንስ ለአንድ ወራት ያህል ክትባቱ ያመጣውን ለውጥ ለማወቅ ከባድ ይሆናል ተብሏል። ፕሮፌሰር ባሊቸር ግን በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ወደ ጽኑ ሕሙማን የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣት አለበት ይላሉ። ፋይዘር መድኃኒት አምራች ሁለት ጠብታ ክትባቱን የወሰደ ሰው 95% በተህዋሲው ያለመያዝ እድሉ የሰፋ ነው ይላል። ነገር ግን በብዙ ክትባቶች እንደታየው ከዚህ ያነሰ መቶኛ እንኳ የፈውስ እድል ብዙ ለውጥ ያመጣል። አመታዊው የፍሉ ክትባት ለምሳሌ ፈዋሽነቱ ከ40-60% ብቻ ነው። ሆኖም በየዓመቱ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን ከሞት ይታደጋል። አንዱ አሁን እያነጋገረ ያለው አንድ ጠብታ የወሰዱ ዜጎችን ሁለተኛውን ጠብታ እየሰጡ ቀስ በቀስ ሕዝቡን ማዳረስ ነው ወይስ አንዱን ጠብታ ለሰፊው ሕዝብ ካዳረሱ በኋላ ለ2ኛው ዙር እንደገና መጀመር ይሻላል የሚለው ነው። ታላቋ ብሪታኒያ እንዳመነችው ብዙ ሰዎችን የመጀመርያውን ጠብታ ካዳረሱ በኋላ ለ2ኛው መመለስ ይሻላል የሚል ነው። በዚህ ዘዴ በተህዋሲው የሚጋለጡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ይቻላል ብላ አምናለች። ትንሽ ቁጥር ያለውን ሕዝብ 2 ጠብታ ሰጥቶ ትንሽ ቁጥር ያለውን ሕዝብ ከተህዋሲው በደንብ መከላከል የተሻለ ነው የሚሉም አሉ። ጠብታው መሰጠት ያለበት በ2 ሳምንት ልዩነት መሆኑም ሌላው ፈተና ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው አንድ ጠብታ ከወሰደ በኋላ ሌላ ሁለት ሳምንት መጠበቅ ተህዋሲው ከጋረጠው ፈተና አንጻር ትእግስትን የሚፈታተን በመሆኑ ነው። ፕሮፌሰር ኢቫንስ ማጠቃለያ ሐሳብ ሲሰጡ ይህን ይላሉ፡ ""ከእስራኤል አሁን የሚመጡ ሪፖርቶች ያልተሟሉ ብቻ ሳይሆን መረጃን የሚሰጡ፥ እንዲሁም አጥጋቢ ሆነው አላገኘናቸውም። በታላቋ ብሪታኒያ ሁለተኛውን ጠብታ አዘግይቶ የመጀመርያውን ጠብታ ማዳረስ የሚለውን አሰራር ሊያስቀይር የሚችል ነገርም አላገኘንባቸውም"" ዞሮ ዞሮ በቀጣይ ወራት በእስራኤል ተህዋሲው ድራሹ እየጠፋ ካልመጣ ዓለም መደንገጡ አይቀርም።" https://www.bbc.com/amharic/news-55745103 +sports ኡጋንዳ ውስጥ በማንችስተር 'ደርቢ' ምክንያት አንድ ታዳጊ ተገደለ "ኡጋንዳ ውስጥ የማንችስተር ከተማ ክለቦች እግር ኳስ ጨዋታ ይተላለፍ አይተላለፍ በሚል የተነሳውን ግርግር ለማብረድ የመጣ ፖሊስ አንድ ታዳጊ ገደለ። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በማንችስተር ሲቲና በማንችስተር ዩናይትድ መካከል የነበረውን ፍልሚያ ትምህርት ቤታቸው አላሳይም በማለቱ ወደ ቅጥር ግቢው ድንጋይ ወርውረዋል። የ19 ዓመቱ ታዳጊ ከግርግሩ ለመሸሽ በሚል አንድ ዛፍ ላይ ሳለ ነበር በጥይት ተመቶ የወደቀው ሲሉ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ለቢቢሲ ተናግረዋል። 1 ሺህ ገደማ ተማሪዎች ያሉት ትምህርት ቤቱ በግድያው ምክንያት ለሁለት ሳምንት በመዘጋቱ ወደ ቤታቸው ተሸኝተዋል። የጉሉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አዋኒ ጂሚ በሁኔታው እጅግ ��ንደተበሳጩ ለቢቢሲ ገልጠዋል። ዳይሬክተሩ እንዳሉት በፖሊስ ጥይት የተገደለው ታዳጊ ከሌላ ትምህርት ቤት ተዘዋውሮ ከመጣ ስድስት ሳምንት ቢሆነው ነው። ዳይሬክተሩ ታዳጊውን ""ጨዋ፣ ትሁትና ጠንካራ ተማሪ"" ሲሉ ገልፀውታል። አዋኒ ክስተቱን ሲያስረዱ እሑድ ዕለት የነበረው የማንችስተር 'ደርቢ' ከተማሪዎች የጥናት ክፍለ ጊዜ ጋር በመጋጨቱ ነው ጨዋታው እንዳይታይ የተከለከለው። ዳይሬክተሩ አክለው ትምህርት ቤቱ ለወትሮው ቀደም ብለው የሚጀምሩ ጨዋታዎች በተለይ ደግሞ በሃገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት ከ8-10 ሰዓት ያሉ ጨዋታዎችን ለተማሪዎች ያሳያል። ይህ የሚሆነው ተማሪዎች ምሽት 1፡30 የጥናት ፕሮግራም ስላላቸው ነው። ነገር ግን እሑድ ዕለት የማንችስተር ደርቢ ከሚያመልጠን ጥናት ይቅርብን ያሉ ተማሪዎች ግርግር በማስነሳታቸው የትምህርት ቤቱ ጥበቃዎች ሁኔታውን ለማረጋጋት ጣልቃ ይገባሉ። ሁኔታዎች እየጋለ የመጣው አንድ የአካባቢው ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ ከተኮሰ በኋላ ስልክ ደውል ከወታደራዊው ኃይል እርዳታ ከጠየቀ በኋላ ነው። ""የፀጥታ ኃይሎች የወሰዱት እርምጃ ከተገቢው በላይ ነው ብዬ ነው የማስበው"" ይላሉ ዳይሬክተሩ። አዋኒ ጂሚ እንደሚሉት ትምህርት ቤቱ ከተመሠረተ ጀምሮ ባሉት 30 ዓመታት እንዲህ ዓይነት ነገር አጋጥሞት አያውቅም። የጉሉ ከተማ አስተዳደር ከትምህርት ቤቱ ጋር ከመከረ በኋላ ለሁለት ሳምንት እንዲዘጋና ተማሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ወስኗል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60657877 +politics የቻይናው ፕሬዚዳንት አገራቸው በወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲ እንድትከተል ጥሪ አቀረቡ "የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ አገራቸው ወዳጆቿን ማብዛት እንደምትፈልግ አስታውቀዋል። ለዚህም አገራቸው የገፅታ ግንባታ ያስፈልጋታል ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ከኮሙኒስት ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ቆይታ አገራቸው ""ታማኝ፣ ተወዳጅና ክብር ያላትን የቻይናን ገፅታ መፍጠር አስፈላጊ ነው ማለታቸውን የአገሪቱ የዜና ወኪል ሺኑዋ ዘግቧል። ቻይና ከምዕራባውያኑ ጋር ያላት ግንኙነት ከአመት አመት ወደ ባላንጣነት እንደተሸጋገረ የሚናገሩት ተንታኞች ቻይና ይህንን ማለቷ መሰረታዊ በሆነ መልኩ ዲፕሎማሲያዋን ልትቀይር መሆኑ አመላካች ነው። ቻይና በተለይም እንደ አሜሪካ ጋር ካሉ ታላላቅ ኃያላን አገራት ጋር የሻከረ ግንኙነት ነው ያላት። በአገሪቷ ባሉ ሙስሊም ህዝቦች ላይ በምታደርሰው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና በሆንግ ኮንግ የዲሞክራሲ ደጋፊዎች በምታደርሰው እስሮችና እንግልቶች እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ቻይና ከፍተኛ ውግዘቶችን አስተናግዳለች። በቅርቡም አሜሪካ የኮቪድ-19 መነሻ የቻይና ቤተ ሙከራዎች ነው በሚለው ጉዳይ ላይ ምርመራ አደርጋለሁ ማለቷን ተከትሎ ቻይና በበኩሏ ""የራሳቸውን ጥፋት ለመደበቅና ፖለቲካዊ ማጭበርበር"" ነው በሚል አፀፋዊ ምላሽ ሰጥታለች። ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ ሰኞ እለት ከባለስልጣኖቻቸው ጋር በመከሩበት ወቅት ቻይና ታሪኳን በአዎንታዊ መልኩ ልትናገር ይገባል ብለዋል። ""አጋሮችና ወዳኞች ማፍራት አስፈላጊ ነው።በአለም አቀፉ ዘንድ ያለውን ዋነኛ የህዝብ አስተያየትን ለማስቀየር የወዳጆቻችንን ቁጥር መጨመር አስፈላጊ ነው"" ማለታቸውንም ሺኑዋ ዘግቧል። አክለውም አገራቸው ከአለም ጋር በምታደርገው ግንኙነት ""ግልፅና በራሷ የምትተማመን እንዲሁም ራሷን ከፍ የማታደርግ"" ሆና መታየት እንዳለባት አስረድተዋል። ፖርቲው በሚሰራቸው የፕሮፖጋንዳ ስራዎችም መንግሥታቸው ""ለቻይና ህዝብ ደስታና ብልፅግና የሚሰራ ነው"" የሚለውን አፅንኦት መስጠት ይገባቸዋል ብለዋል። የፕሬዚዳንቱን ንግግር ያጤኑ ተን���ኞች መሪው ለመጀመሪያ ጊዜ የቻይናን መገለልና ብቸኝነት ያመኑበት ነው ብለዋል። ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ የቻይና ፕሬዚዳንትነትን ስልጣን የጨበጡት በአውሮፓውያኑ 2012 ሲሆን በቁርጠኝነትና በጨቋኝነት ይተቻሉ። በአገሪቱ ላይ ለሚሰነዘሩ ማንኛውም አይነት ተቃውሞዎች የአገሪቱ ዲፕሎማቶች ምላሽ ማጣጣል ወይም ደግሞ በጠብ አጫሪነት ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-57333182 +business ኢኮኖሚ ፡ የኢትዮጵያ የብር ኖት መቀየር የሚኖረው አንድምታ "ኢትዮጵያ ከሁለት አስር ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50፣ እናየ100 የገንዘብ ዓይነቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመተካት አዲስ የገንዘብ ኖቶች ይፋ አድርጋለች። ከአዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች ውስጥም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜም የባለ ሁለት መቶ ብር ኖትም አሳትማለች። አገሪቷ ነባሮቹን የብር ኖቶቹን ለመቀየር ሌላ ወጪ ሳይጨምር ለህትመት ብቻ 3.7 ቢሊዮን ብር ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስታውቀዋል። አገሪቱ የገንዘብ ኖቶችን ለመቀየር በኢ-መደበኛ መልኩ ገንዘብ ከባንክ ውጭ በከፍተኛ ሁኔታ መንቀሳቀሱ፣ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚሉ ምክንያቶችን አስቀምጣለች። ከዚህ ቀደም አገሪቷ ከፋይናንስ ዘርፍ (ከባንክ) ውጭ ያለው ገንዘብ ከመደበኛው ባልተናነሰ መልኩ ከፍተኛ በመሆኑም እንዴት ይሰብሰብ የሚሉ ጥያቄዎች የባንኮች ዋና ማዕከል ሆነውም ነበር። በኢ-መደበኛ ሁኔታ ያለውን የገንዘብ ፍሰት ወደ መደበኛ ለማምጣትም ጥረቶች የተደረጉ ሲሆን በተለያየ ጊዜም የወጡ መመሪያዎችም ለዚህ ማመላከቻዎች ናቸው። በኢትዮጵያ ከባንክ ውጭ ያለው ገንዘብ በቢሊዮኖች እንደሚቆጠር ከዚህ ቀደም በፋይናንስ ዘርፉ የተሰራ ጥናት የሚያሳይ ሲሆን በባለፈው ዓመትም አገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት (ሊኩዊዲቲ) አጋጥሟት ነበር። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክም ይህንንም ችግር ለመፍታት አንዳንድ ጊዜያዊ መፍትሄዎችን መውሰዱ የሚታወስ ነው። የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የዋጋ ግሽበት የለውጡ ዋነኛ መሰናክል ሆነው ቆይተዋል በማለትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምጣኔ ሀብቱ መዳከም ምክንያት ያሉትን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት የገንዘብ ኖት ለውጥ ማድረጓም በከፍተኛ ሁኔታ ከዘርፉ ውጭ ያለውን ገንዘብ ወደ መደበኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ ሂደት ለማምጣትም ይረዳታል በማለት የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የብሔራዊ ባንክ ገዢው ዶ/ር ይናገር ደሴ በበኩላቸው መንግሥት የገንዘብ ለውጥ ማድረግ ካስፈለገው ምክንያቶች መካከል ዋነኛው ከገንዘብ ጋር የተገናኙ ሕገ-ወጥ ዝውውሮችን ለመግታት እንደሆነ በብሔራዊው ቴሌቪዥን ቀርበው አስረድተዋል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ በብዛት በጥሬ ገንዘብ ግብይት የሚካሄድበት መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ይናገር ከባንኮች ውጭ ያለው ጥሬ ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። ""አብዛኛው ኅብረተሰባችን ከባንክ ውጭ ነው ግብይት የሚያደርገው በዚህ ምክንያት ብዙ ጥሬ ገንዘብ ከባንክ ውጭ ይገኛል ማለት ነው። በዚህም የጥሬ ገንዘብ እጥረት ባንኮች ላይ ማጋጠም እድሉ ሰፊ ነው።ለ ገቢ አሰባሰብ አመቺ ሁኔታ ይፈጥራል የሚል እምነት ነው ያለን፤ ለአጠቃቀም የተሻለ አገልግሎት ይሰጣል፤ የህትመት ወጪንም በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል"" ብለዋል። ከባንክ ውጭ ያለው ጥሬ ገንዘብ በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት አገራት ጭምር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ""ከባንክ ውጭ የሚገኝ ገንዘብ ደግሞ ለሕገ-ወጥ ተግባራት ሲውል ነው የሚታየው፤ በተለይ በኮንትሮባንድ [ሕገ-ወጥ ንግድ] የተሰማሩ ግለሰቦች ይጠቀሙበታል"" ብለዋል። ዶ/ር ይናገር ከዚህ በተጨማሪ ግለሰቦች ግብር ላለመክፈል ሲሉ ገንዘባቸውን ከባንክ ውጭ የማስቀመጥ ልማድም እየሰፋ መምጣቱን ጠቁመው አሁን ያለውን የገንዘብ ኖት መቀየር አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት አስረድተዋል። ከባንክ ውጭ የተጠራቀመ ገንዘብ ጥቅም የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በኋላም በአውሮፕላን ጣቢያዎችና ድንበሮች እንዲሁም በባንኮች አካባቢ ከፍተኛ ቁጥጥርም ይደረጋል ተብሏል። የፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ ገንዝብ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ከማድረግ በተጨማሪ በሕገ ወጥ መንገድ የሚሰበሰብ ገንዘብ ካገኙ እንደሚወርሱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ከባንኮች ውጭ ያለው ገንዘብ ወደ ባንኮች ሲመለስም የሂሳብ ደብተር ተከፍቶ ባንኮች ውስጥ እንዲቀመጥ ይደረጋል። ለመሆኑ የብር ኖትን መቀየር እንደ ኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እንዴት ሊያስቆም ይችላል? የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከባንክ ሥርዓት ውጭ የሚንቀሳቀስ ከ113 ቢሊየን ብር በላይ መኖሩን ይናገራሉ። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች ያሉት ሲሆን የዋጋ ንረት ከፍተኛ በመሆኑና ባንክ ቤቶች ብር ለሚያስቀምጥ የሚሰጡት ወለድ ዝቅተኛ በመሆኑ ሰዎች ገንዘቤን በእጄ እይዛለሁ የሚል አስተሳሰብ መኖሩን እንደ አንድ ምክንያት ያነሳሉ። በሌላ በኩል በሙስናና በሌሎች ምክንያቶች ""ተቋማትም ግለሰቦችም ሲዘርፉ ስለነበር ነው"" ይላሉ። ለዚህ ንግግራቸውም ከለውጡ በኋላ የተከማቹ በርካታ ገንዘቦች በጆንያ እየታጨቁ እና በመኪና እየተጫኑ ሲዘዋወሩ መያዛቸውን እንደ ምሳሌም ይጠቅሳሉ። የገንዘብ ኖቶቹ ላይ ለውጥ መደረጉም ሰዎች ገንዘባቸውን ለመቀየር ባንክ በሚሄዱበት ጊዜ፤ በጤናማ የግብይት ሥርዓት ገንዘቡን ማግኘት አለማግኘታቸውን ለማረጋገጥ እድል ይሰጣል ብለዋል ባለሙያው። በመሆኑም እስካሁን የተሰሩ የሙስና ምንጮችን ለማወቅም ሆነ ከአሁን በኋላ የሚሰሩ ሙስናዎች ላይ ፍራቻ እንዲፈጥር ሊያደርግ እንደሚችልም ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆኑት ረዳት ፐሮፌሰር ጉቱ ለገስ ደግሞ ከገንዘብ ጋር ተያይዞ ያሉ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የብር ኖቶች መቀየር አንዱ እንጂ፤ ብቸኛው መፍትሔ አለመሆኑን ያሰምሩበታል። ረዳት ፕሮፌሰር ጉቱ ""አንድ ነገር ሲተዋወቅ ውጤታማ ለመሆን አለመሆኑ አንዱ ወሳኙ ነገር፤ ተቋማዊ አደረጃጃትና የመተግበር አቅም ነው። ይህ ካልሆነ ግን አዙሪት ነው የሚሆነው"" ብለዋል። መንግሥት ገንዘቡን ከቀየረ በኋላ ሕገ-ወጥ ገንዘብ ይዘዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች የየራሳቸውን እርምጃ መውሰዳቸው እንደማይቀር የጠቆሙት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ መንግሥት ተቋማዊ አደረጃጀቱ ጠንካራ ሆኖ ይሄን ነገር ልብ ብሎ መከታተል እንዳለበት መክረዋል። አሁን የተወሰደው እርምጃ ቀደም ብለው የተሰሩ ሥራዎች ስላሉ ውጤታማ ይሆናል ተብሎ ይገመታልም ብለዋል። ነገር ግን ""ቀድሞ የነበረው የውጭ ምንዛሬ ጋር ተያይዞ ያለው ሙስናና ደካማ አስተዳደር ካልተስተካከለ ተመልሶ ያው ነው የሚሆነው"" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አዲስ የ200 ብር ኖት ማስገባት ለምን ተፈለገ? በኢትዮጵያ በቅርብ አመታት ውስጥ የገንዘብ የመግዛት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ያሽቆለቆለ ሲሆን ከዚህም አንፃር ባለ ሁለት መቶ ኖቶች ወደ ገበያው ውስጥ መግባት አስፈላጊ እንደሆነም የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይናገራሉ። ረዳት ፕሮፌሰር ጉቱ የዋጋ ንረቱ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በተለያየ ግብይት ሂደት ውስጥ የሚሳተፈው ኅብረተሰብ ብዙ ብር ለመያዝ እየተገደደ መሆኑን በመጥቀስ ያንን ሊያስቀርላቸው እንደሚችል ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ወደ ኤሌክትሮኒክስ የግብይት ሥርዓት እንዲገቡም እየተሰራ ያለው ሥራ ተጠ��ክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። ኢኮኖሚው ሲያድግ ወደዚያ መግባቱ እንደማይቀር በመግለፅ። አቶ ዋሲሁን በበኩላቸው የገንዘብ ኖት ከፍ እያለ ሲመጣ ገንዘቦች መግዛት አቅማቸው መዳከሙን የሚያመላክት መሆኑን ይናገራሉ። በምሳሌ ሲያስረዱም ""አሁን 5 ብር ዝቅተኛው ገንዘብ እየሆነ ነው። አንድ ብርና ሁለት ብር የሚገዛቸው ነገሮች እየጠፉ ነው። ሰዎች መቶ ብርም ይዘው በፊት የሚገዙትን ያህል እቃ መግዛት አይችሉም፤ በመሆኑም ሰዎች ብዙ የወረቀት ገንዘብ ይዘው ከሚሄድ ያድናቸዋል"" ይላሉ። ነገር ግን ከ20 በመቶ በላይ የዋጋ ንረት በሚመዘገብበት ሁኔታና የ100 ብርና የ200 ብር ልዩነት ብዙም ባለመሆኑ መሆን የነበረት የ500 ወይም የ1000 ብር ኖት ወደገበያው መግባት እንደነበር አቶ ዋሲሁን ሙያዊ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የገንዘብ መቀየሩን ተከትሎ ምን ሊፈጠር ይችላል? መንግሥት አሮጌ የብር ኖቶቹን ለመቀየር የሦስት ወር የጊዜ ገደብ አስቀምጧል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው እንደሚሉት ከሆነ አዲሱ መገበያያ ገንዘብ ይፋ መደረጉን ተከትሎ በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ ባልተለመደ መልኩ የገንዘብ ዝውውር ሊስተዋል ይችላል። ""ሰዎች አዳዲስ የሒሳብ ቁጥር እየከፈቱም ሊያስቀምጡ ይችላሉ። ጥሬ ገንዘቡን ወደ ባንክ ላለማስገባትም የንብረት ግዥ ሊጧጧፍ ይችላል። መኪና፣ ቤት መግዛት ሊኖር ይችላል"" ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በሌላ በኩል በሙስና የተከማቸ አሊያም ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ገንዘብ በእጃቸው የያዙ ግለሰቦች፤ የሚመጣባቸውን ጥያቄን በመፍራት በዘመድ አዝማዶቻቸው ስም በርካታ የሒሳብ ቁጥሮችን ሊከፍቱ እንደሚችሉም አመላክተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/54159837 +sports የአፍሪካ ዋንጫ በየአራት ዓመቱ እንዲካሄድ ሀሳብ ቀረበ የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የአፍሪካ ዋንጫ በየሁለቱ ዓመቱ መካሄዱ ቀርቶ በአራት አመት አንዴ ብቻ አንዲካሄድ ለአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር (ካፍ)ሃሳባቸውን አቅርበዋል። ኢንፋንቲኖ በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው የካፍ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር '' በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው አፍሪካ ዋንጫ አውሮፓውያኑ ከሚያስገኙት ሲነጻጸር ገቢው በሃያ እጥፍ ያነሰ ነው። በዚህ አካሄድ በየሁለት ዓመቱ ማካሄዱ አዋጪ ነው? እስቲ በየአራት ዓመቱ ማካሄድን ከግምት ውስጥ እናስገባው'' ብለዋል። • የ2021 አፍሪካ ዋንጫ ጥር ላይ እንዲካሄድ ተወሰነ • አፍሪካ የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት አዲስ አሰራር እንዲኖር ትፈልጋለች ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ በጎርጎሳውያኑ 2021 በካሜሩን አዘጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን ልክ እንደ ቀድሞው ጥርና የካቲት ላይ ሀገራት ውድድር ያደርጋሉ። ባለፈው ዓመት የአፍሪካ ዋንጫ ቀድሞ ከሚካሄድበት ወቅት በተለየ መልኩ ሰኔ እና ሐምሌ ላይ ግብጽ ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በዚሁ ውድድር ተሳታፊ ሀገራት ቁጥርም ወደ 24 ከፍ እንዲል ተደርጓል። የፊፋው ፕሬዝዳንት በንግግራቸው አክለውም ''ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። በእኛ በኩል ሶስት መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ነጥቦችን ለይተናል፤ እነሱም ዳኝነት፣ መሰረተ ልማት እና ውድድሮች ናቸው'' ብለዋል። አክለውም'' አሁን ስለአፍሪካ እግር ኳስ እድገት ብቻ የምናወራበት ሰአት ሳይሆን እርምጃ የምንወስድበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። የትኛውም የአፍሪካ ሀገር ዓለም ዋንጫን አሸንፎ አያውቅም፤ ለምን ብለን መጠየቅም ይገባናል።'' • የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት ከዳኝነት ጋር በተያያዘ ፊፋ የተመረጡ 20 ዳኞችን በገንዘብና በስልጠና በመገደፍ ለአህጉሪቱ እግር ኳስ እድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማድረግ እንዳሰበም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም የአፍሪካ እግር ኳስ አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ በማድረግ በዓለማቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ለማድረግ ፊፋ 1 ቢሊየን ዶላር ፈሰስ ለማድረግና በእያንዳንዱ አባል ሀገር አንድ ዘመናዊ ስታዲየም ለመገንባት እቅድ መያዙም በስብሰባው ላይ ተገልጿል። https://www.bbc.com/amharic/news-51346280 +sports የሊቨርፑል ተጫዋቾች የአሜሪካውን ግድያ ተቃወሙ "የሊቨርፑል ተጫዋቾች በአፍሪካ አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ላይ በፖሊስ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም በልምምድ ሜዳቸው ማሃል ላይ ክብ ሰርተው በጉልበታቸው ተንበርክከው አጋርነታቸውን አሳዩ። 29 የሊቨርፑል ተጫዋቾችን ተንበርክከው የሚያሳየው ፎቶግራፍ የወጣው ""አንድነት ኃይል ነው"" ከሚል የፎቶ መግለጫ ጋር ነው። ተጫዋቾቹ ፎቶውን የተነሱት ዛሬ ሰኞ በነበራቸው ልምምድ ላይ ሲሆን፤ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾቹ ማርከስ ራሽፎርድ እና ጃደን ሳንቾም በዓለም ዙሪያ እየተስተጋባ ባለው ጸረ ዘረኝነት ተቃውሞ ላይ ድምጻቸውን በማሰማት ተሳትፈዋል። የማንችስተር ዩናይትድ እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቹ ማርከስ ራሽፎርድ በበኩሉ ክስተቱ ለመቀበል እንደተቸገረ እንዲህ ሲል ተናግሯል ""በምድራችን ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለመረዳት እየሞከርኩ ነው።"" ጨምሮም ""ሰዎች አንድ ላይ እንዲሆኑ፣ አብረው በመስራት ህብረት እንዲፈጥሩ በሚጠየቅበት ጊዜ፤ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ተከፋፍለን እንገኛለን። ""በዚህም ሰዎች እየተጎዱ ነው ምላሽን ይሻሉ። ስለጥቁሮች ሕይወት ግድ ይለናል። ስለጥቁሮች ባሕል ያገባናል። ስለጥቁሮች ማኅበረሰብ ግድ ይለናል። እኛም ድርሻ አለን። [ብላክ ላይቭስ ማተርስ]"" ብሏል። ከሳምንት በፊት ጆርጅ ፍሎይድ ሚኒያፖሊስ ውስጥ ዴሪክ ቾቪን የተባለ ፖሊስ መሬት ላይ በደረቱ እንዲተኛ አድርጎት በጉልበቱ አንገቱ ላይ ለደቂቃዎች በመጫን ትንፋሽ እንዲያጥረው በማድረግ ካሰቃየው በኋላ ህይወቱ በማለፉ አሁን ድረስ መላዋን አሜሪካ ያናወጠ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው። የፖሊስ መኮንኑ በዚህ ድርጊቱ ከሥራው የተባረረ ሲሆን በግድያ ወንጀልም ክስ ተመስርቶበታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-52883363 +politics ግብፅ የመስኖ እና የውሃ ሚኒስትርን ጨምሮ 13 አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመች የፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ ጥያቄን ተከትሎ የግብፅ ፓርላማ በአገሪቱ የካቢኔ ሚኒስትሮች ላይ ዋነኛ ለውጥ በማድረግ አዳዲስ ሹመቶችን አፀደቀ። ፕሬዝዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመመካከር በአገሪቱ የካቢኔ አባላት ላይ ከፍተኛ የተባለውን ለውጥ ለማድረግ በእረፍት ላይ የነበረው ፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያደረግ የጠየቁት ባለፈው አርብ ነበር። በዚህም መሠረት አብዛኞቹ ሚኒስትሮች በአዲስ የተተኩበት የአገሪቱ የካቢኔ ሚኒስትሮች ስብስብ 13 አዳዲስ ሚኒስትሮች ተካተውበት ለምክር ቤቱ ቀርቦ ዕሁድ ዕለት መጽደቁ ተዘግቧል። በአዲሱ የግብፅ ካቢኔ ውስጥ ዋነኛ የሚባሉት የመስኖ እና የውሃ ሚኒስትርን ጨምሮ 13 ሚኒስትሮች በአዲስ ሲተኩ፣ የገንዘብ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቦታቸው ቀጥለዋል። የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ በሚኒስተሮቻቸው ላይ ለውጥ ያስፈለገበትን ምክንያት በማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረኮች ላይ እንደገለጹት “በአገር ውስጥና በውጪ የአገሪቱን ጥቅም በማስጠበቅና ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት የበለጠ በማጎልበት የመንግሥትን የአፈጻጸም ብቃት ለማጠናከር ነው” ብለዋል። ለዚህም በመስከረም ወር መጨረሻ ላይ ሥራውን ለመጀመር ለሦስት ወራት ዕረፍት ተዘግቶ የነበረው የግብፅ ፓርላማ አባላትም “ለአስቸኳይ ጉዳይ” በሚል ለቅዳሜ እንዲሰበሰቡ ተጠርተው አዲስ የቀረቡትን ሚኒስትሮች ሹመት አጽድቀውታል። ዕሁድ ዕለትም ተሿሚዎቹ ���ኒስትሮች ሥራ ለመጀመር በፕሬዝዳንቱ ፊት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። ግብፅ ከፍተኛ ትኩረት ከምትሰጣቸው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶቿ መከከል አንዱ የሆነውን እና ኢትዮጵያ ልታጠናቅቀው የተቃረበችውን የታላቁ የኢትየጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይን ለዓመታት በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩት የመስኖ እና የውሃ ሚኒስትሩ ሞሐመድ አብደል አቲ በአዲስ ተተክተዋል። ባለፈው ሳምንት በሁለተኛ ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረውና ሦስተኛው ዙር የውሃ ሙሌቱን ያከናወነው በአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ የኢትዮጵያ ግድብ ላይ ግብፅ ለዓመታት ተቃውሞዋን ስታሰማ መቆየቷ ይታወቃል። የግብፅን የመስኖ እና ውሃ ሚኒስትርነት ቦታን የተረከቡት አዲሱ ተሿሚ ሃኒ ሴዊላም ሲሆኑ፣ አዲሱ ሚኒስትር በዘርፉ ሦስት አስርት ዓመታት የሚጠጋ ዕውቀትና ልምድ ያካበቱ መሆናቸው ተነግሯል። ሃኒ ሴዊላም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በአውሮፓውያኑ 1991 እዚያው ግብፅ ውስጥ ከሚገኘው ዛግዚግ ዩኒቨርስቲ የምህንድስና ፋክልቲ በውሃ እና በአካባቢ መህንድስና አግኝተዋል። ሴዊላም ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካ ዩኒቨርስቲ በዘላቂ ልማት እና በውሃ ሃብት አስተዳደር ዘርፍ ቋሚ ፕሮፌሰር ሆነው አገለግለዋል። በዩኒቨርስቲው ውስጥም ሁለት ዘርፎችን በመመስረት እና በዳይሬክተርነት በመምራት አገልግለዋል። በተጨማሪም በጀርመን ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሃይድሮሎጂ ምህንድስና አካዳሚክ ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል እንዲሁም የዩኔስኮ የውሃ እና የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ዋና ዳይሬክተርም ነበሩ። ሃኒ ሴዊላም በዘላቂ ልማት፣ በውሃ ሀብት፣ በውሃ - በኃይል - በምግብ ተያያዥ ጉዳዮች እንዲሁም በደለል እና በሌሎችም የውሃ አስተዳደር ዘርፎች ከ25 ዓመታት በላይ የዘለቀ የማስተማርና የተግባር ልምድ እንዳላቸው ይነገራል። መንግሥታዊው አል አህራም እንዳለው አዲሱ የግብፅ የመስኖ እና የውሃ ሚኒስትር የሚጠብቃቸው ቀዳሚ ሥራ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው የሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ይሆናል። ኢትዮጵያ ግብፅ እና ሱዳን በሕዳሴው ግድብ የውሃ አሞላልና አጠቃላይ አስተዳደር ዙሪያ ለዓመታት ሲያደርጉት የነበረው ድርድር ምንም አይነት ስምምነትን ሳያስገኝ ግድቡ ወደ መጠናቀቁ እየተቃረበ ነው። ምንም እንኳን ግብፅና ሱዳን አስገዳጅ ሕጋዊ ስምምነት ላይ ሳይደረስ ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ የመሙላት ሥራ እንዳትጀመር ግፊት ቢያደርጉም፣ ይህንን ዓመት ጨምሮ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ግድቡ በውሃ መሞላቱን ኢትዮጵያ አስታውቃለች። ባለፈው ሳምንትም ኢትዮጵያ ግድቡ ከሚኖሩት 13 የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች መካከል ሁለተኛውን ሥራ በማስጀመር፣ ቀደም ሲል በየካቲት ወር ኃይል ማመንጨት ከጀመረው ጋር በመሆን ከ500 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ከሕዳሴው ግድብ መመንጨት መጀመሩ ታውቋል። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በግድቡ ዙሪያ ሲያደርጉት የነበረው ድርድር ከተቋረጠ የቆየ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ድርድሩ እንዲቀጥል በተደጋጋሚ ስትጠይቅ ቆይታለች። ባለፈው ሳምንትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሁለተኛውን የኃይል ማመንጫ ተርባይንን ሥራ ባስጀመሩት ወቅት በግድቡ የውሃ ሙሌትና አጠቃላይ ሥራ ላይ ተቃውሞ እያሰሙ ካሉት ከግብፅ እና ከሱዳን ጋር ኢትዮጵያ ድርድር ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ኢትዮጵያ የታችኛው የአባይ ተፋሰስ አገራትን የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት በመጥቀስ “ከድርድር ውጪ ያሉ አማራጮች የግድቡን ግንባታ አያስቆሙትም” በማለት በአገራቱ መካከል ሲካሄድ የነበረውና የተቋረጠው ንግግር እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። ከሳምንት በፊት ኢትዮጵያ የሕዳሴው ግድብ ሦስተኛው ዙር የውሃ ሙሌትን እንደምታከናውን እንደተገለጸላት በመጥቀስ ግብፅ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አቤቱታ አቅርባ ነበር። ግብፅ ለመንግሥታቱ ድርጅት በጻፈችው ደብዳቤ ላይ ኢትዮጵያ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ በተናጠል የግድቡን የውሃ ሙሌት ማከናወን የለባትም በሚል ተቃውሞዋን አስመዝግባለች። ኢትዮጵያ ግን የግድቡ ግንባታም ሆነ የውሃው ሙሌት በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ የሚያስከትለው የጎላ ጉዳት የለም በማለት ግንባታውን እና የውሃ ሙሌቱን ወደ ማጠናቀቅ እየተቃረበች ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cz9krey24dko +business ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዙ የነበሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን 27 ሺህ ዶላር ተወረሰባቸው የአሜሪካ የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዙ ከነበሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቤተሰብ አባላት 27 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መውረሱን አስታወቀ። የአገሪቱ ጉምሩክና ድንበር ጥበቃ ተቋም እንዳስታወቀው እሁድ ሐምሌ 03/2014 ዓ.ም. ከቤተሰብ አባላቱ 27 ሺህ 330 ዶላር የወረሰው የቤተሰብ አባላቱ የያዙትን የገንዘብ መጠን ይፋ ባለማድረጋቸው ነው ብሏል። የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ እንደገለጸው፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አዲስ አበባ በረራ ለማድረግ አምስቱ የቤተሰብ አባላት ዋሽንግተን ደለስ ዓለም አቀፍ አውሮእፓለን ማረፊያ ተገኝተው ነበር። የቤተሰብ አባላቱ አውሮፕላን መሳፈሪያ በር ላይ እንደደረሱ ምን ያክል ገንዘብ እንደያዙ በጉምሩክ እና ድንበረ ጥበቃ መኮንኖች እንዲያሳውቁ ተጠይቀው ነበር። ትውልደ ኢትዮጵያዊ እና የአሜሪካ ዜግነት ያለው አባት 8 ሺህ ዶላር ገደማ እንደያዙ በቃል ምላሽ ሰጥቷል። በመቀጠል የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ ባለሥልጣናት ተጓዞቹ በጉዞ ወቅት የያዙት ገንዘብ በተመለከተ ሪፖርት ስለማድረግ የአገሪቱን ሕግ ለተጓዦች አስታውሰዋል። በአሜሪካ ሕግ መሠረት ተጓዦች ወደ አገር ውስጥ ይዘው በሚገቡትም ሆነ በሚወጡት የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ የለም። ይሁን እንጂ አንድ ተጓዥ ከ10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም ተመጣጣኝ የሌላ አገር ገንዘብ በላይ ከያዘ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ቅጽ ላይ አሳውቆ ለአሜሪካ ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኛ ማሳወቅ ይኖርበታል። የጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፤ 8 ሺህ ዶላር ገደማ ብቻ መያዙን የተናገረው አባት፤ የተጠየቀውን ቅጽ እየሞላ ሳለ፤ በእድሜ ትልቁ የሆነው ልጅ ሌላ 8 ሺህ ዶላር መያዙን ለባለሥልጣናቱ ተናግሯል። በመቀጠል የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ መኮንኖቹ የቤተሰብ አባላቱ ሻንጣዎች ላይ ፍተሻ ካደረጉ በኋላ ያገኙትን 27 ሺህ 330 የአሜሪካ ዶላር ወርሰዋል። “ይህን በተደጋጋሚ ተናግረናል። ተጓዦች የፈለጉትን ያክል ገንዘብ ከአሜሪካ ይዘው መውጣት እና መግባት ይችላሉ፤ ይሁን እንጂ የአሜሪካ ፌደራል ሕግ ተጓዦች ከ10ሺህ ዶላር በላይ ከያዙ ማሳወቅ እንዳለባቸው ያስገድዳል። ይህ በጣም ቀላል ነው” ሲሉ የአካባቢው የጉምሩክ እና ድንበር ባለሥልጣን ዳንኤል ኤስኮቤዶ ተናግረዋል። የጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ ባለሙያዎች ለቤተሰብ አባላቱ 830 ዶላር ከመለሱ በኋላ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ አሰናብቷቸዋል። ይሁን እንጂ በረራው አምልጧቸው የነበሩት የቤተሰብ አባላት፤ ሌላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቲኬት ተቆርጦ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል። የጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ ገንዘብ የተወረሰባቸው ሰዎች በወንጀል ስላልተከሰሱ የማናቸውንም ስም ይፋ እንደማያደርግ ጨምሮ ገልጿል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c51wd1793nyo +sports የዓለም ዋንጫ አሸናፊን ቀድሞ ለመገመት ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ መንገዶች ኳታር እያስተናገደችው ያለውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን የትኛው አገር ይወስዳል? የበርካቶች ጥያቄ ነው። አንዳንዶች ስፖርታዊ ትንታኔን ተከትለው ለመገመት ይሞክራሉ። ሌሎች ደግሞ ‘ጠቋሚ ምልክት’ ይፈልጋሉ። ተስፋቸውን ‘አስማት’ ላይ የጣሉ፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኤአይ) የሚታገዙም አሉ። የኳስ ውጤት መገመት በእርግጥ ቀላል አይደለም። ምክንያታዊ ግምት ቢከተሉም በቁማር ገንዘብ የሚበሉ የበዙትም ለዚያ ይሆናል። የፋይናንስ ተቋማት የወደፊቱን የሚገምት ሞዴል ቢያዘጋጁም፣ የኳስ ውጤት ባልተጠበቀ ሁኔታ መለዋወጡ ለኪሳራ ሲዳርጋቸው ታይቷል። ‘አስማታዊ ኃይል’ ተጠቅመው የወደፊቱን መተበይ እንደሚችሉ የሚያምኑ፣ የኳስ ውጤትን ለመገመት ሲሞክሩ ይስተዋላል። ለምሳሌ ብራዚላዊው አቶስ ሳሎሜን እንውሰድ። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንደሚነሳና፣ ሩሲያ ዩክሬንን እንደምትወር ቀድሞ እንዳወቀ ይናገራል። ምናልባት የዓለም ዋንጫ አሸናፊውንም ይተነብያል። ኳስ ተጫዋቾች፣ አሠልጣኞች እና ጋዜጠኞች ተሰባስበው በመወያየት አሸናፊውን ይገምታሉ። ብዙውን ጊዜ ግምታቸው ስህተት ይሆናል። የዓለም ዋንጫ እጅግ በጉጉት ከሚጠበቁ ሁነቶች አንዱ ነው። የዘንድሮው የኳታር የዓለም ዋንጫ አምስት ቢሊዮን ተመልካቾች እንዳሉት ፊፋ አስታውቋል። በዩናይትድ ኪንግደም የምጣኔ ሀብት ተንታኙ ፕሮፌሰር ሮበርት ሳይመንስ “ሰዎች በተለይም ገንዘብ የሚያገኙ ከሆነ በቁማር ይደሰታሉ” ይላል። የዓለም ዋንጫ ለመገመት አዳጋች ቢሆንም፣ ተመልካቾች ከመቆመር ወደኋላ አላሉም። ለምሳሌ ሳዑዲ አረቢያ አርጀንቲናን፣ ጃፓን ጀርመንን ያሸንፋሉ ብሎ ለመገመት ከባድ ነበር። የዓለም ዋንጫ አሸናፊን ለመገመት ተመልካቾች የሚጠቀሙባቸውን አስደናቂ መንገዶች እንዲህ ቃኝተናል። የኮምፒውተር ቀመር እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት ቀመር በመጠቀም የዓለም ዋንጫ አሸናፊን ለመገመት እየተሞከረ ነው። የዩናይትድ ኪንግደሙ (ዩኬ) አለን ተሪንግ ተቋም ምርምር ከሚያደርጉት መካከል ይገኝበታል። ሳይንቲስቶች 64 የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን በመጠቀም 100,000 የኮምፒውተር ስሌቶች ሠርተዋል። ለዚህ የተጠቀሙት የቀደሚ ውጤቶችን ነው። አንደኛ ደረጃ ግምት የተሰጠው ለአምስት ጊዜ ባለ ድሏ ብራዚል ነው። በመቀጠልም ቤልጄየም እና ሁለት ጊዜ ያሸነፉት አርጀንቲ እና እና ፈረንሳይ ለዋንጫ ይጠበቃሉ ብሎ ነበር፤ ነገር ግን ቤልጂየም ከምድብ ውድድሩ ባሻገር ማለፍ አልቻለችም። ተቋሙ በኮምፒውተር ስሌት የታገዘ ግምቱን ቢያስቀምጥም “የእኛን ግምት ተከትሎ ማንም ሰው እንዳይቆምር። ምክንያቱን ኳስ ለመገመት አዳጋች ነው” ሲል አስጠንቅቋል። ከዚህ በፊት ጎልድማን ሳችስ፣ ዩቢኤስ፣ አይኤንጂ የተባሉ ተቋማት በሁለት የዓለም ዋንጫዎች ግምታቸው ሳይሳካ ቀርቷል። ለንደን የሚገኘው ሊብሪየም ካፒታል የ2014 እና የ2018 አሸናፊዎችን በትክክል መገመት ችሏል። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ግምት መስጠት እንደማይቻል ያምናል። ክሌመንት የተባለው ተቋም እንዳለው፣ አንድ ቡድን የማሸነፍ ዕድሉን 45 በመቶ መገመት ቢችልም የተቀረው 55 በመቶ የቡድኑ ዕድል ላይ የተመሠረተ ይሆናል። የዓለም ዋንጫ አሸናፊን መገመት እንደሚችሉ የሚነገርላቸው ‘አስማተኛ’ እንስሳት አሉ። ፓንዳዎች፣ ግመሎች እና ኦክቶፐስ የተባለው የዓሣ ዝርያ ይጠቀሳሉ። ‘ፖል ዘ ኦክትፑስ’ የተባለው ዓሣ የ2010 የዓለም ዋንጫ አሸናፊን በትክክል ከገመተ ወዲህ ሌሎች የዓለም ዋንጫ አሸናፊዎችንም በትክክል ይገምታል ተብሎ ይታሰባል። ዓሣው ሁለት የአገራት ሰንደቅ አላማ ያለው ሳጥን ይቀርብለታል። ሁለቱም ሳጥን ውስጥ ምግብ ይቀመጣል። ያሸን���ል የሚለው አገር ሰንደቅ አላማ ከተቀባው ሳጥን ይመገባል። 14 ጊዜ ሙከራ ተደርጎ 12ቱ የዓሣው ግምቶች ትክክል ሆነዋል። ይህ ዓሣ አሁን ሕይወቱ አልፏል። ሳይንቲስቶች እንደሚሉት፣ ዓሣው እግር ኳስ ማን እንደሚያሸንፍ የሚያውቅበት ‘አስማታዊ’ ኃይል የለውም። ዓሣ በተፈጥሮው ከአግድም መስመር ቀጥተኛ መስመር ያለበትን ምሥል ይመርጣል። ከቀረቡለት የሰንደቅ አላማ ምርጫዎች ቀጥተኞቹን የመረጠውም ለዚያ ይሆናል። ሳይንቲስቶች ቁማርን አያበረታቱም። ፕሮፌሰር ሳይመንስ እንደሚሉት፣ ምክንያታዊ ግምት በማስቀመጥ ቁማርን የሚያሳልጡ ባለሙያዎች (ቡክሜከርስ) የተሻለ አማራጭ ናቸው። እነዚህ ባለሙያዎች ግምታቸው ትክክል ካልሆነ ገንዘብ ስለሚከፍሉ፣ ትክክለኛ ግምት ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። በእርግጥ ግምት የተሰጣቸው ቡድኖች ሊያሸኝፉም ሊሸነፉም ይችላሉ። ነገር ግን ምክንያታዊ ግምት የማሸነፍ ዕድልን ከፍ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል። የዓለም ዋንጫ በ1930 በኡራጓይ ከተጀመረ ወዲህ ብዙ ተለውጧል። ባለፉት ዓመታት በውድድሩ ከቀረቡ 79 አገራት መካከል ያሸነፉት ስምንት ብቻ ናቸው። ብራዚል (አምስት ጊዜ)፣ ጣልያን እና ጀርመን (አራት ጊዜ)፣ ፈረንሳይ፣ ኡራጓይ እና አርጀንቲና (ሁለት ጊዜ) እንዲሁም ስፔን (አንድ ጊዜ)። ከ1978 ወዲህ ዋንጫውን ያልወሰዱና የጨዋታቸውን የመጨረሻ ዙር የተቀላቀሉ አገራት ሦስት ናቸው። ከአህጉራቸው ውጭ ዋንጫውን የወሰዱ አገራት ብራዚል፣ ጀርመን እና ስፔን ናቸው። እስከ መጨረሻው ዙር የተጓዘ አፍሪካዊ አገር የለም። ከእስያ ለግማሽ ፍጻሜ የደረሰችው ደቡብ ኮርያ ብቻ ናት። ከ1982 ወዲህ ከጀርመን ወይም ከጣልያን አንድ ተጫዋች ያልተሳተፈበት የዓለም ዋንጫ የለም። ለዚህ ነው በዓለም ዋንጫ የባየር ሙኒክ እና ኢንተር ሚላን ስም በተደጋጋሚ የሚነሳው። በኳታር የዓለም ዋንጫ ባየር ሙኒክ 17 ተጫዋዎች አሰልፏል። ኢንተር ሚላን ደግሞ ስድስት ተጫዋቾች አሉት። ታዲያ የኳታሩን የዓለም ዋንጫ ማን ይወስድ ይሆን? https://www.bbc.com/amharic/articles/cekv1p424jro +sports በርካታ ተጫዋቾች በኮቪድና በጉዳት ያላሰለፉት ሌስተሮች ሊቨርፑልን አሸነፉ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ትናንት ማክሰኞ ምሽት በሊቨርፑልና ሌስተር ሲቲ መካከል የተደረገው ተጠባቂ ጨዋታ አዴማላ ሉክማን ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ በሌስተር አሸናፊነት ተጠናቋል። በዚህም ሊቨርፑሎች በደረጃ ሰንጠረዡ ከማንቸስተር ሲቲ በስድስት ነጥብ ርቀው ሁለተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል። ሊቨርፑሎች በመጀመሪያው አጋማሽ 15ኛው ደቂቃ ላይ የፍጹም ቅጣት ምት አግኝተው የነበረ ቢሆንም ግብፃዊው ሞሐመድ ሳላህ ወደ ግብነት መቀየር ሳይችል ቀርቷል። የጨዋታው ኮከብ ተጨዋች ተብሎ የተመረጠው የሌስተሩ ግብ ጠባቂ ካስፐር ሹማይክል ኳሷን ከመረብ እንዳትገናኝ አድርጓል። ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔም ቢሆን በርካታ የግብ ዕድሎችን ቢያገኝም ግብ ማስቆጠር ግን አልቻለም። አብዛኛውን የጨዋታ ጊዜ ወደ ግብ ክልላቸው ተስበው ለመከላከል ተገድደው የነበሩት ሌስተሮች 59ኛው ደቂቃ ላይ ያገኙትን ዕድል በአግባቡ ተጠቅመዋል። የቀድሞው የኤቨርተን የፊት መስመር ተጫዋች አዴማላ ሉክማን ተቀይሮ በገባ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ኪረን ደውስብሪ ያሻማለትን ኳስ ወደ ግብነት መቀየር ችሏል። በርካታ የመጀመሪያ ቡድን ተጫዋቾችን በጉዳትና በኮቪድ ምክንያት ያጡት ሌስተሮች በተደጋጋሚ ሊቨርፑሎች ሲያደርጉት የነበረው የማጥቃት ጨዋታ ተቋቁመው አምሽተዋል። ከስድስት ቀናት በፊት በካራባዎ ዋንጫ ሁለቱ ቡድኖች ተገናኝተው የነበረ ሲሆን ሌስተር ሲቲ ቀድሞ 3 ለ 0 መምራት ችሎ ነበር። ነገር ግን በተከታታይ ባስተናገዱት ሦስት ግብ ምክንያት ጨዋታው አቻ ተጠናቆ በፍጹም ቅጣት ምት ሊቨርፑል ማሸነፍ ችሏል። ፕሪምየር ሊጉ ከተጀመረ ሁለተኛ ሽንፈታቸውን ያስተናገዱት ሊቨርፑሎች ከሊጉ መሪ ማንቸስተር ሲቲ በስድስት ነጥብ ርቀው በ41 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በሌላ በኩል ከሰባት ጨዋታዎች ሁለቱን ብቻ ማሸነፍ የቻሉት ሌስተሮች ትናንት ምሽት ሦስት ሙሉ ነጥብ ማግኘታቸውን ተከትሎ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል። በጉዳት ምከንያት ተከላካዮቻቸውን ያጡት ሌስተሮች የመሀል ክፍል ተጫዋቹ ዊልፍሬድ ንዲዲን በተከላካይ መስመር ለማሰለፍ ተገድደው ነበር። ንዲዲም ሞሐመድ ሳላህ ላይ በፈጸመው ጥፋት ቡድኑ ላይ የፍጹም ቅጣት ምት አስሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂው ግን ኳሷ ግብ እንዳትሆን አድርጓል። የሌስተሩ አጥቂ ጄሚ ቫርዲ ምሽቱን ሙሉ ያገኘውን ኳስ ወደ ሊቨርፑል ግብ ክልል ይዞ በመግባት ትልቅ ፈተና ሆኖ አምሽቷል። በመጀመሪያው አጋማሽም ያገኘውን ኳስ ወደ ግብ ቢመታም ተከላካዩ ጆዌል ማቲፕ ተደርቦ ግብ ከመሆን አድኖበታል። ሊቨርፑሎች ከሜዳቸው ውጪ ካደረጓቸው 29 ጨዋታዎች በትናንቱ ጨዋታ ላይ ብቻ ነው ግብ ማስቆጠር ያልቻሉት። የፊታችን እሁድ ከቼልሲ ጋር የሚፋለሙት ሊቨርፑሎች በደረጃ ሰንጠረዡ ከማንቸስተር ሲቲ ያላቸውን ልዩነት ለማጥበብ የሞት የሽረት ትግል እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉት የሊቨርፑሎቹ ሞሐመድ ሳላህ፣ ሳዲዮ ማኔ እና ናቢ ኬታ ወደ ውድድሩ ከመሄዳቸው በፊት የቼልሲው ጨዋታ የመጨረሻቸው ይሆናል። ትናንት በተካሄዱ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በጥሩ አቋም ላይ የሚገኙት ቶተንሀሞች ከሳውዝሀምፕተን ጋር አንድ አቻ ሲለያዩ ዌስት ሀም ደግሞ ዋትፎርድን 4 ለ1 በማሸነፍ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል መመለስ ችለዋል። በቀድሞው አርሰናል ተጫዋች ፓትሪክ ቪዬራ የሚመሩት ክሪስታል ፓላሶች ደግሞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት ኖርዊቾችን ሶስት ለባዶ አሸንፈዋል። ሰኞ ምሽት የተደረገው የማንቸስተር ዩናይርድና የኒውካስል ጨዋታ አንድ አቻ መጠናቀቁ የሚታወስ ነው። ዛሬ ምሽት ደግሞ ቼልሲ ከብራይተን እንዲሁም የሊጉ መሪ ማንቸስተር ሲቲተ ከብሬንትፎር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። https://www.bbc.com/amharic/news-59802875 +business ዚምባብዌ የመገበያያ ገንዘቧ መዳከምን ለመቋቋም የወርቅ ሳንቲሞችን ልታስተዋውቅ ነው "ዚምባብዌ የመገበያያ ገንዘቧ ከውጭ ምንዛሬ አንፃር ማሽቆልቆልንና በአገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ግሽበት ለመግታት የወርቅ ሳንቲሞችን ለመገበያያነት እንዲውል ልታደርግ ነው። በተጨማሪም የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የአሜሪካ ዶላርን ለሚቀጥሉት አምስት አመታት ህጋዊ መገበያያ ለማድረግም ማቀዱን አስታውቋል። አመታዊው የአገሪቱ የዋጋ ግሽበት 190 በመቶ በላይ ከፍ ማለቱን ተከትሎ የማዕከላዊ ባንክ ዋና የወለድ ምጣኔ በዚህ ወር ከእጥፍ በላይ ወደ 200 በመቶ አድጓል። የዚምባብዌ የመገበያያ ገንዘብ ዶላር በዚህ አመት ከሌሎች ከውጭ አገር መገበያያ ገንዘቦች አንፃር በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆል አሳይቷል። አንድ ትሮይ አውንስ ብዛት ያላቸው 22 ካራት ወርቅ የሆኑ የወርቅ ሳንቲሞች በያዝነው ወር መጨረሻ በገበያ ላይ እንደሚውሉ የዚምባብዌ ሪዘርቭ ባንክ ገዥ የሆኑት ጆን ፒ ማንጉዲያ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ትሮይ አውንስ የከበረ ማዕድናትን እንደ ወርቅ፣ ብር እና ፕላቲኒየም የመሳሰሉትን ለመመዘን የሚያገለግል የመለኪያ አሃድ ነው። መለኪያው ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ የነበረ ሲሆን አንድ ትሮይ አውንስ ከ31.10 ግራም ጋር እኩል ነው። “የወርቅ ሳንቲሞቹ በአለም አቀፍ የወርቅ ዋጋ እና በተመረተበት ዋጋም በበመስረት ለህዝቡ በአገር ውስጥ ምንዛሬ፣ በዶላር እና በሌሎች አገራት የውጭ ምንዛሬዎች ለሽያጭ ይቀርባሉ"" ብለዋል ማንጉዲያ መግለጫው በተጨማሪም ለእያንዳንዱ የወርቅ ሳንቲም መለያ ቁጥር የሚሰጣቸው ሲሆንም ሳንቲሞቹንም  በቀላሉ ወደ ጥሬ ገንዘብ በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ እንደሚለወጥም ገልጿል። በዚምባብዌ እና ዛምቢያ አዋሳኝ ላይ የሚገኘውን የቪክቶሪያ ፏፏቴንም ስያሜ በመውሰድ ""ሞሲ-ኦአ-ቱኒያ” የወርቅ ሳንቲም"" የሚል ስም ተሰጥቶታል። የወርቅ ሳንቲሞቹ ወደ ገበያ መምጣት የዚምባብዌ መንግስት የሀገሪቱን የመገበያያ ገንዘብ ቀውስ ለመቅረፍ የወሰደው እርምጃ አካል ነው።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cw83xygz5x6o +health ከፍተኛው እራስን የማጥፋት ቁጥር በአፍሪካ እንደተመዘገበ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ በመላው ዓለም ከሚመዘገበው እራስን የማጥፋት ክስተት ከፍተኛ ቁጥር ያለው አፍሪካ አህጉር ውስጥ እንደሚፈጸም የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ። እንደ ድርጅቱ መግለጫ ከሆነ በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ከተመዘገበባቸው አስር አገራት ስድስቱ የሚገኙት በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ነው። በአህጉሪቱ የሥነ አእምሮ ህክም እና ድጋፍ የሚሰጡ ባለሙያዎች ቁጥርም እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ገልጿል። በዚህም በአፍሪካ ውስጥ አንድ ሳይኪያትሪስት ሐኪም ለግማሽ ሚሊዮን ያህል ሰዎች አገልግሎት ይሰጣል። ይህ ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅት ከሚያስቀምጠው የባለሙያና የተጠቃሚዎች ምጥጥን አሃዝ በአንድ መቶ እጥፍ ያነሰ ነው። በአፍሪካ ከሚኖሩ 100,000 ሰዎች ውስጥ 11 ሰዎች እራሳቸውን ያጠፋሉ ተብሎ የተመዘገበ ሲሆን፣ ይህ ቁጥር በዓለም ላይ አማካይ ነው ተብሎ ከተቀመጠው ከ100,000 ሺህ ዘጠኝ ሰዎች እራሳቸውን የማጥፋት ክስተት አኳያ ከፍተኛው እንደሆነ የመንግሥታቱ ድርጅት የጤና ተቋም ገልጿል። ለሰዎች እራስን የማጥፋት ድርጊት እንደምክንያት በቀዳሚነት የተቀመጠው የአእምሮ ጤና ችግር ሲሆን፣ ይህም አስከ 11 በመቶ ለሚሆኑት ሰበብ እንደሆነ ተነግሯል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች በአብዛኛው የሚገኙት በከተሞች አካባቢ ስለሚሆን፣ በገጠሩ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች አገለግሎቱን የማግኘት ዕድላቸውን ያጠበዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ክልል ዳይሬክተር የሆኑት ማስሂዲሶ ሞኤቲ እንደሚሉት፣ በአገራት የጤና ፕሮግራሞች ውስጥ የአእምሮ ጤና ችግሮችን የመከላከሉ አማራጭ ቅድሚያ ስለማይሰጠው እራስን የማጥፋት ሁኔታ ዋነኛ የኅብረተሰብ ጤና እክል ሆኗል። እራስን የማጥፋትን ክስተቶች ለመከላከል ግንዛቤን ለመፍጠርና እርምጃዎች እንዲወሰዱ ለማበረታታት የዓለም የጤና ድርጅት በአሁኑ ወቅት በአህጉሪቱ ውስጥ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እኣካሄደ ነው። ይህ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የተጀመረው በመጪው መስከረም 30 ከሚከበረው የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን ቀደም ብሎ ነው። በዚህም ዘመቻው የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ አህጉር ውስጥ 10 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ጋር መልዕክቱን ለማድረስ አቅዶ እየሰራ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cerdy21nxvgo +business በአፍሪካ የነዳጅ ዋጋ ሊጨምር እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ "የዓለም ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ተከትሎ በቀጣይ ሳምንታት በአፍሪካ የነዳጃ ዋጋ በተመሳሳይ ሊጨምር እንደሚችል ባለሙያዎች አመለከቱ። ትናንት ማክሰኞ የአንድ ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል 80 የአሜሪካ ዶላር ደርሶ ነበር። ይህም ከሦስት ዓመት ወዲህ የተመዘገበ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ነው ተብሏል። ዓለም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጫናዎች መላቀቅ ስትጀምር የምጣኔ ሐብት እንቅስቃሴዎች እየተነቃቁ ነው። ይህን ተከት��ም የነዳጅ ፍላጎት ጣራ እየነካ ነው። የዘርፉ ባለሙያዎች አሁን ላይ ለታየው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አንዱ ምክንያት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ የምጣኔ ሐብት እንቅስቃሴዎች መጨመሩ ነው ይላሉ። የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ፓትሪክ ኦባታ፤ የነዳጅ ፍላጎቱ በተለየ በአሜሪካ እና አውሮፓ እየጨመረ ስለሚቀጥል የዋጋ ጭማሪው ለወራት ሊዘልቅ እንደሚችል ያስረዳሉ። በዚህም ምክንያት ነዳጅ አምራች ያልሆኑ አገራት የኃይል ምንጫቸውን ፍላጎት ለማስተካከል በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ሊያደርጉ ይችላሉ ይላሉ። ሌላኛው የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ኬን ጊቺንጋ፤ በምጣኔ ሐብት እድገት ውስጥ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ሚና ስላለው የነዳጅ ዋጋ ሲጨመር የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋም አብሮ ይጨምራል በማለት ያስረዳሉ። የነዳጅ አምራች እና ላኪ አገራት ጥምረት የሆነው ኦፔክ በቀጣይ ሳምንት ይመክራል ተብሏል። የኦፔክ አባላት በቀጣይ ሳምንት ውይይታቸው የነዳጅ አቅርቦትን መጠን ከፍ ለማድረግ ከውሳኔ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ማይክል ፋሞሮቲ በቀጣይ ለዓለም ገበያ የሚቀርበው የነዳጅ መጠን በኦፔክ አባላት የሚወሰን ይሆናል ይላሉ። ነዳጅ አምራች እና ላኪ አገራት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ተከትሎ ተቀዛቅዞ የነበረውን የነዳጅ አቅርቦት መጠን፤ አምራች አገራት የምርት መጠናቸውን ከፍ እንዲያደርጉ በመፍቀድ የነዳጅ ዋጋ እንዲረጋጋ ሊያደርጉ ይችላሉ ሲሉ ይተነብያሉ። ""ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ኦፔክ ጠንከር ያለ እርምጃ ይወስዳል ብዬ እጠብቃለሁ"" ብለዋል የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ማይክል ፋሞሮቲ።" https://www.bbc.com/amharic/news-58723014 +health ቦሪስ ጆንሰን ክትባቱ በመላው ዓለም እንዲዳረስ ኃያላን አገራት ላይ ጫና ሊያደርጉ ነው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እስከ ቀጣዩ የአውሮፓዊያን ዓመት መጨረሻ ድረስ በመላው ዓለም የኮሮናቫይረስ ክትባት እንዲዳረስ ጫና ለማድረግ መዘጋጀታቸው ተሰማ። በመጪው አርብ በአገራቸው በሚደረገው የቡድን ሰባት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ይህንን እቅዳቸውን ያቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል። አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን እና ጃፓን ለዓለም አቀፉ የፍትሃዊ የክትባት ማከፋፈያ ፕሮግራም ኮቫክስ ምን ያህል ክትባት እንደሚያጋሩ ይፋ አድርገዋል። እንግሊዝ እና ካናዳ ግን ምን ያህል አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ እስካሁን ይፋ አላደረጉም። ከኮሮናቫይረስ ጋር እየተደረገ ያለውን ፍልሚያ በስኬት ለማጠናቀቅ እስከሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ በመላው ዓለም ክትባቱን ለማዳረስ ቦሪስ ለመሪዎቹ በኮርንዌሉ ጉባኤ ላይ ጥሪ ያቀርባሉ። እንዲህ ዓይነቱ ስኬት ‹‹በሕክምና ታሪክ ውስጥ ብቸኛና ታላቁ›› ይሆናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ። አገራቸው ዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱን የማምረት ምጣኔን እንዴት ከፍ ማድረግ እንደሚቻል የሚደረጉ ውይይቶችን እንደምታበረታታም ተገልጿል። የቡድን ሰባት የመሪዎች ጉባኤ ከወረርሺኙ መከሰት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ገፅ ለገፅ የሚደረግ ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ከተረከቡ በኋላ ወደ እንግሊዝ የሚያደርጉት የመጀመሪያ ጉብኝት ይሆናል ። እንግሊዝ ምን ያህል ክትባት ለኮቫክስ እንደምታበረክት በጉባኤው ላይ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው ሳምንት የፓርላማ አባላት ብሎም የአገራት መሪዎች እንግሊዝ የተያዘው የፈረንጆች አመት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ቢያንስ 100 ሚሊዮን ክትባት እንድታበረክት ደብዳቤዎችን እንደፃፉላቸው ይታወሳል። የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር በበኩላቸው ‹‹እውነታው›› መንግስታት ‹‹የራሳቸውን ሰዎች የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው››፤ ሁል ጊዜም ለራሳቸው ዜጎች ክትባት ቅድሚያ ይሰጣሉ ሲሉ መናገራቸውም ይታወሳል። አክለውም በዚህ ጉዳይ ፍፁም መሆን አይቻልም፤ ከመዳረሱ በፊትም የተወሰነ ክትባት መለግስ ይቻላልም ብለዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-57381197 +sports የቺሊ ብሔራዊ ቡድን ሊሰልለኝ ነበር ያለውን ድሮን ቢጥልም ስህተት መሥራቱ ታወቀ "በሩጫው የስፖርት መስክ ኢትዮጵያና ኬንያ ተቀናቃኞች እንደሆኑት ሁሉ የደቡብ አሜሪካ አገራት የሆኑት ቺሊና አርጀንቲና ደግሞ ለዘመናት በእግር ኳስ ውድድር ተቀናቃኝነታቸው ይታወቃሉ። ለዚህም ነው ሁለቱ አገራት ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ ሐሙስ ከሚያደርጉት ግጥሚያ ቀደም ብሎ የቺሊ ብሔራዊ ቡድን ልምምድ በሚያደርግበት ሜዳ ላይ አንዲት ድሮን ስታንጃብብ ጥርጣሬ የተፈጠረው። በዚህ ጊዜ የቺሉ ቡድን የገመተው አርጀንቲናውያኑ ተቀናቃኞቻቸው ድሮን አሰማርተው እየሰለሏቸው እንደሆነ ነበር። በምላሹም የእራሳቸውን ድሮን ልከው ""ሊሰልለን መጥቷል"" ያሉትን ድሮን በቁጥጥር ስር አዋሉት። ነገር ግን ድሮኑ እነሱ እንደጠረጠሩት የአርጀንቲናውያን ሳይሆን የአንድ የአገራቸው የኃይል አቅራቢ ኩባንያ ንብረት ሆኖ አግኝተውታል። ይህ የተከሰተው ቺሊና አርጀንቲና ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ሐሙስ ዕለት ከሚያደርጉት ጨዋታ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ነበር። የቺሊ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ለዛሬው ውድድር ለመዘጋጀት በዋና ከተማዋ ሳንቲያጎ ውስጥ በሚገኝ ስታዲየም ልምምድ እያደረጉ ሳለ ነበር ""የስለላ"" ነው ያሉት ድሮንን የተመለከቱት። የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት የቡድኑ አሰልጣኝ ማርቲን ላዛርቴ ናቸው የአጠራጣሪውን ድሮን ምንነት ለማወቅ የራሳቸውን ድሮን በማብረር እርምጃ የወሰዱት። በዚህም ሁለቱ ድሮኖች አየር ላይ ተጋጩ በስፍራው የነበሩ ጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሆን ተብሎ የተፈጠረ ግጭት ነበር። በዚህም ሰላይ የተባለው ድሮን ወደ መሬት ወደቀ። ሲጣራም ድሮኑ አርጀንቲናውያን የቺሊን ብሔራዊ ቡድን ለመሰለል ያሰማሩት ሳይሆን 'ኤኔል' የተባለው ኩባንያ በአካባቢው ለሥራ ያሰማራው እንደሆነ ተደረሰበት። በድሮን አማካይነት በእግር ኳስ ቡድኖች ላይ የሚደረግ ስለላን በተመለከተ ሲነገር ይህ የመጀመሪያው አይደለም። አሰልጣኞችም በዚህ ዙሪያ ቀደም ሲል ቅሬታ አሰምተዋል። ከእነዚህም መካከል ከስድስት ዓመታት በፊት የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ዲዲየ ዴሾ ብራዚል ውስጥ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ወቅት ቡድኑ ከሆንዱራስ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት በልምምድ ስፍራ ላይ ሲንዣብብ የነበረን ድሮን በተመለከተ ፊፋ ምርመራ እንዲያደርግ ጠይቆ ነበር። በተመሳሳይ እአአ 2017 ላይ ሆንዱራስ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በምትዘጋጅበት ጊዜ አውስትራሊያ ድሮን አሰማርታ ቡድኔን እየሰለለች ነው በማለት ክስ አቅርባ ነበር። በተጨማሪም ቡድኑ ክስተቱን የሚያሳይ ቪዲዮ በትዊተር ላይ አሰራጭቶ ነበር። ከአገራት ብሔራዊ ቡድኖች በተጨማሪም ታላላቅ ክለቦች ተመሳሳይ ነገር እንዳጋጠማቸው ተነግሯል። የጀርመኑ ወርደ ብሬመን ክለብ ከሦስት ዓመት በፊት በተቀናቃኙ ሆፈንሃይም ቡድን የልምምድ ሜዳ ላይ ድሮን እንዲያንዣብብ ማድረጉን አምኖ ለድርጊቱ ይቅርታ ጠይቆ ነበር። አሁን አሁን በድሮን አማካይነት በቡድኖች ላይ የሚደረግ ስለላን በተመለከተ የሚቀርቡ ክሶች እየተለመዱ የመጡ ሲሆን፤ አንዳንድ የቡድን አሰልጣኞች ግን አሁንም የቆየውን ተቀናቃኞቻቸውን የመሰለል መንገድን እየተጠቀሙ እንደሆነ ይነገራል። ከሁለት ዓመት በፊት በአውሮፓውያኑ 2019 የእንግሊዙ ሊድስ ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ማርሴሎ ቢየልሳ ተቀናቃኛቸው የሆነውን ደርቢ ካውንቲ እንዲሰ���ልላቸው አንድ የቡድኑን አባል ወደ ልምምድ ሜዳ መላካቸውን ተከትሎ ቡድኑ ይቅርታ መጠየቁ ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57306934 +health ሲዲሲ የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰራጭበት መንገድ ላይ የአሜሪካ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ አሳሰበ የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) የአሜሪካ ግዛቶች የጤና ኃላፊዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት የበለጠ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ቀድሞ የሚታደልበት አማራጭ ላይ ቀድመው እንዲዘጋጁ ማሳሰቡ ተነገረ። ሲዲሲ ትናንት በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው ጽሑፍ ላይ ክትባቱ ለበሽታው የበለጠ ተጋለጭ ለሆኑ ሰዎች እስከ ጥቅምት አጋማሽ ሊሰራጭ እንደሚችል ጠቁሟል። “ሲዲሲ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ በማሰብ ዝግጁ ሊሆን የሚችል የክትባት መጠን እና ጊዜን ለግዛቶች አሳውቋል። ከጥቅምት አጋማሽ እስከ ሕዳር መጨረሻ ድረስ መጠናቸው አነስተኛ ቢሆንም የክትባት ስርጭት ሊኖር ይችላል” ሲሉ የሲዲሲ ቃል አቀባይ ለሬውተርስ ተናግረዋል። ኒው ዮርክ ታይመስ ደግሞ ቀደም ሲል ሲዲሲ ከሁሉም 50 የአሜሪካ ግዛቶች እና አምስት ግዙፍ ከተሞች ከስርጭት ጋር ተያይዞ ያሉ የእቅድ መረጃዎችን ጠይቋል። በኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ላይ ሲዲሲ ጥቅምት አጋማሽ ላይ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ አንድ ወይም ሁለት የኮቪድ-19 ክትባቶች ለስርጭት ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል። ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ ናቸው ለተባሉ እንደ የጤና ባለሙያዎች፣ ለደህንነት ሰራተኞች እና እድሜያቸው የገፉ ሰዎችን የሚንከባከቡ ነርሶች እና ባልደረቦች ክትባቱ ያለ ክፍያ ይሰጣቸዋል ይላል የሲዲሲው ዶክመንት። የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒዮ ፋውቺ ለኤምኤስኤንቢሲ ቴሌቪዥን ትናንት ሲናገሩ፤ ለኮቪድ-19 ክትባት ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥርን ከግምት በማስገባት እስከ ሕዳር ወር ድረስ የትኛው የኮቪድ-19 ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ይቻላል ብለዋል። ሞደርና፣ አስትራዜኔካ እና ፐፊዘር የተሰኙ መድሃኒት አምራቾች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ የሆነ የኮቪድ-19 ክትባት ለማዘጋጀት ጥረት ላይ ይገኛሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-54012503 +politics ባይደን በመሪዎች ስብሰባ ላይ አሜሪካ ለአፍሪካ የቢሊዮን ዶላሮችን ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቁ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ለአህጉሪቱ በድጋፍ እና በኢንቨስትመንት መልክ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አገራቸው ፈሰስ እንደምታደርግ አስታውቁ። ባይደን አሜሪካ ለአፍሪካ የወደፊት ተስፋ ሙሉ ትኩረቷን እንደምትሰጥ በመሪዎች ውይይት ላይ ለመሳተፍ ዋሽንግተን ለተገኙ የ49 አገራት መሪዎች ተናግረዋል። አሜሪካ መሰል የመሪዎች ውይይትን ስታካሂድ ይህ በስምንት ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያው ነው። አሜሪካ ይህን ስብሰባ የጠራችው በአፍሪካ እያደገ ለመጣው የቻይና ተጽእኖ መልስ ለመስጠት ያለመ ተደርጎ ተወስዷል። ከዚህ በተጨማሪ ዶናልድ ትራምፕ በአራት ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው አፍሪካውያን መሪዎችን ገሸሽ ከማድረግ አልፈው፣ አፍሪካውያን አገራትን በማንቋሸሽ በመጥራት የአሜሪካ እና አፍሪካ ግንኙነት አሻክረዋል። ጆ ባይደን ግን ከዚህ በተለየ መልኩ አገራቸው ከአፍሪካ አህጉር ጋር የበለጠ ቅርብ እንድትሆን ፍላጎታቸው መሆኑን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ለተሰበሰቡት የአፍሪካ መሪዎች “አፍሪካ ስኬታማ ስትሆን፤ ዩናይትድ ስቴትስም ስኬታማ ትሆናለች። እውነት ለመናገር፤ መላው ዓለም ጭምር ስኬታማ ይሆናል” ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ዓለም በአሁኑ ወቅት ከገባችበት ቀውስ ለመውጣት የአፍሪካ መሪዎች የመሪነት ጥበብ እና ሃሳብን ትፈልጋለች ብለዋል። የፕሬዝዳንቱ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሰሊቫን አሜሪካ በቀጣይ ሦስት ዓመታት በድጋፍ እና በኢንቨስትመንት 55 ቢሊዮን ዶላር በአፍሪካ ፈሰስ እንደምታደርግ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት ባይደን ረቡዕ ዕለት ሲናገሩ በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ቤኒን የትራንስፖርት ወጪን ለመቀነስ 500 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ታደርጋለች ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በአህጉሪቱ የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማሳደግ 350 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚደረግ ጠቅሰዋል። አሜሪካ ከአፍሪካ አገራት ጋር በዓለም ትልቅ የሆነውን የአፍሪካ አህጉር ነጻ የንግድ ቀጠና ለመፍጠር የመግባቢያ ሰነድ እንደምትፈራረም ጨምረው ተናግራል። ከዚህ ስብሰባ ጎን ለጎን ባይደን በእአአ 2023 ምርጫ ከሚያካሂዱ ስድስት የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። ፕሬዝዳንቱ ከመሪዎቹ ጋር ውይይት ያደረጉት የሚካሄዱት ምርጫዎች ነጻ እና ፍትሐዊ እንዲሆኑ ጫና ለመፍጠር ነው ተብሏል። ባይደን በእአአ 2023 ላይ ወደ አፍሪካ ለሥራ ጉብኝት ሊጓዙ እንደሚችሉ ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ ለሦስተ ቀናት ተካሂዶ ዛሬ ሐሙስ ታኅሣሥ 06/2015 ዓ.ም. ይጠናቀቃል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cekv71zl2gpo +sports የማንችስተር ሲቲና የአርሰናል ግጥሚያ በኮሮናቫይረስ ስጋት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ "ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር ዛሬ እሮብ፤ ሊያደርግ የነበረው የፕሮሪሚየር ሊግ ጨዋታ ""ቅድመ ጥንቃቄ"" በሚልና በርካታ የአርሰናል ተጫዋቾች ራሳቸውን ለይተው በመቀመጣቸው የተነሳ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ። የመድፈኞቹ ተጫዋቾች ራሳቸውን አግልለው በር ዘግተው የተቀመጡት የኦሎምፒያኮስ ባለቤት የሆኑት ኢቫንጀሎስ ማሪናኪስ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ነው። አርሰናል እንዳለው ከሆነ ማሪናኪስ ከሁለት ሳምንት በፊት በነበረው አውሮፓ ሊግ ጨዋታ ወቅት በርካታ ተጫዋቾችን አግኝተው ነበር። የ52 ዓመቱ ማሪናኪስ በኮቪድ 19 [ኮሮናቫይረስ] መያዛቸውን የተናገሩት ማክሰኞ ዕለት ነበር። ኦሎምፒያኮስ በአውሮፓ ሊግ ዎልቭስን ሐሙስ ዕለት የሚያስተናግድ ሲሆን፤ ዎልቭስ ግን አስቀድሞ ጨዋታው እንዲራዘምለት ጠይቆ የነበረ ቢሆንም ተከልክሏል። የፕሪሚየር ሊግ የበላይ ኃላፊዎች ግን ከእንግዲህ ወዲህ ምንም ዓይነት ጨዋታ የማራዘም ሃሳብ እንደሌላቸው ገልፀው ""አስፈላጊው ጥንቃቄ ሁሉ ተወስዷል"" ሲሉ ተናግረዋል። ብራይተን በበኩሉ ከአርሰናል ጋር ያላቸው ግጥሚያ ቅዳሜ እለት በተያዘለት ሰዓት እንደሚካሄድ አስታውቋል። ""ተጫዋቾቹ ራሳቸውን ነጥለው የሚያቆዩበት ጊዜ የሚያበቃው ሐሙስ በመሆኑ አደጋው እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው"" ብለዋል። በዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን ድረስ 382 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ስድስት ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። የኮሮናቫይረስ የስፖርት ውድድሮችን በከፍተኛ ሁኔታ የጎዳ ሲሆን የጣሊያን ሴሪ አ ሲቋረጥ የፈረንሳይና የስፔን ጨዋታዎች በዝግ ስታዲየም እንዲካሄዱ ተወስኗል። ማንችስተር ዩናይትድን፣ ሬንጀርስንና ቼልሲን የሚያሳትፈው የአውሮፓ ዋንጫም በሚቀጥሉት ቀናት በኦስትሪያ እና በጀርመን በዝግ ስታዲየሞች ይካሄዳሉ። በዩናይትድ ኪንግደም ግን ስፖርት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሲስተጓጎል ይህ የመጀመሪያው ጨዋታ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-51830172 +sports የቻይና ቴሌቪዢን በኦዚል ምክንያት የአርሰናልን የቀጥታ ጨዋታ አቋረጠ የቻይናው የዜና ተቋም ሲሲቲቪ እሁድ የተካሄደውን የአርሰናልና የማንቸስተር ሲቲ ጨዋታን እንዳይተላለፍ አግዶታል። ምክንያቱ ደግሞ የአርሰናሉ ሜሱት አዚል በቻይና ስለሚገኙ ሙስሊሞች በማህበራዊ ሚዲያ አስተያየቱን በመስጠቱ ነው። ኦዚል በቻይና ስለ��ገኙ ኡጉር ሙስሊሞች የሰጠው አስተያየት መነጋገሪያ ከመሆን አልፎ ቡድኑ አርሰናል ጉዳዩ እኔን አይመለከተኝም የሚል መግለጫ እንዲያወጣም አስገድዶት ነበር። የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ''አርሰናል እንደ ድርጅት ከፖለቲካ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም'' ብሏል። • የአርሰናሉ ሜሱት ኦዚል ስለ ቻይና ሙስሊሞች የሰጠው አስተያየት ክርክር አስነሳ • ለወሲብ ባርነት ወደ ቻይና የሚወሰዱት ሴቶች አክሎም '' ሜሱት ኦዚል በማህበራዊ ሚዲያ ያስተላለፈውን መልእክት ተከትሎ የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ጉዳዩ እንደማይመለከተውና የኦዚል የግል ሃሳብ መሆኑን መግለጽ እንፈልጋለን'' ብሏል። የቻይና እግር ኳስ ማህበር በበኩሉ የአርሰናሉ ተጫዋች የሰጠው አስተያየት ተቀባይነት የሌለውና የበርካታ ቻይናውያን ኳስ አፍቃሪዎችን ስሜት የጎዳ ነው ብሏል። ሲሲቲቪ ጣቢያም እሁድ የተካሄደውና የባለፈው ዓመት ሻምፒዮኖቹ ማንቸስተር ሲቲዎች አርሰናልን 3 ለባዶ ያሸነፉበትን ጨዋታ በመተው ቶተንሃምና ዎልቭስ ያደረጉትን ጨዋታ አስተላልፏል። ሜሱት ኦዚል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈረው መልእክት የኡጉር ሙስሊሞችን ''እስራትና ስቃይን መቋቋም የሚችሉ ተዋጊዎች'' ብሎ በማድነቅ፤ ቻይና እና ዝምታን መርጠዋል ያላቸው ሌሎች ሙስሊሞችን ተችቷል። • የቻይና ሙስሊሞች ምድራዊ 'ጀሐነም' ሲጋለጥ • ቻይና ሙስሊም ዜጎቿን እየሰለለች ነው ተባለ ቻይና በሚሊየን የሚቆጠሩ የኡጉር ሙስሊም ማህበረሰቦችን ያለፍርድቤት ትእዛዝ አስራለች፤ በማጎሪያ ካምፖችም ታሳቃያቸዋለች በማለት አንዳንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይከሳሉ። ቻይና ማዕከላቱ ሀይማኖታዊ አክራሪነትን ለመዋጋት የሚረዱ የቴክኒክና ስልጠና ማስተማሪያዎች እንጂ ማጎሪያ ካምፖች አይደሉም በማለት በተደጋጋሚ ገልጻለች። https://www.bbc.com/amharic/news-50805305 +politics ምርጫ፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ መደበኛ ሥራቸዉ ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ተባለ "ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ መደበኛ ሥራቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን ሐኪሞቻቸው ተናገሩ። በኮሮናቫይረስ የተያዙት የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮቪድ-19 ሕክምናቸውን መጨረሳቸውን በመግለጽ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ወደ ሥራቸው መመለስ እንደሚችሉ ሐኪማቸው ተናግረዋል። ዶ/ር ሼን ኮንሌይ፤ ፕሬዝዳንቱ ለወሰዷቸው መድሃኒቶች ጥሩ ምላሽ መስጠታቸውንና የጤና ሁኔታቸው አስተማማኝ መሆኑን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕም ይህንን የሐኪማቸውን አስተያየት ተከትሎ ዛሬ ሌላ የኮቪድ-19 ምርመራ ካደረጉ በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። በመሆኑም ለመጨረሻ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ ከነገ ጀምሮ ወደ መደበኛ ሥራቸዉ መመለስና ህዝባዊ ክንውኖች ላይ መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል። ፕሬዝዳንቱ በሚቀጥለው ሳምንት ሐሙስ ከተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን ጋር በቀጥታ በቴሌቪዥን ከሚካሄደው የምርጫ ክርክር ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል። የክርክሩ አዘጋጆች የትራምፕን በኮቪድ-19 መያዝ ካወቁ በኋላ በቴሌቪዥን የሚካሄደው የምረጡኝ ክርክሩ 'ቨርቹዋል' በሆነ መንገድ በርቀት ይከናወናል ማለታቸውን ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ "" በቨርቹዋል ለሚደረግ ክርክር ጊዜዬን አላባክንም"" ብለዋል። የግል ሀኪማቸዉ ዶ/ር ሼን ኮንሌይ፤ አሁን ላይ ፕሬዝዳንቱ ከኮቪድ-19 ጋር ተያይዞ የሚሰጣቸዉን ህክምና ማጠናቀቃቸዉንና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ገበታቸው ተመልሰው መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል። ፕሬዚደንቱ ለ24 ሰዓታት ያህል የኮቪድ-19 ምልክት ያልታየባቸው ሲሆን ለተከታታይ አራት ቀናትም ትኩሳት እንዳልነበራቸው የግል ሐኪማቸው ሼን ኮንሊይ ተናግረዋል። ትራምፕ ረቡዕ ዕለት ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ደህንነት ይሰማቸው እንደነበር ገልፀው፤ ""ይህ በፈጣሪ መባረክ ነው"" ብለዋል። በንግግራቸውም ሁሉም አሜሪካዊያን ለእርሳቸው የተሰጠውን መድሃኒት እንዲያገኙ እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር። በመሆኑም በወቅቱ በመድሃኒት አምራቹ ሬጀኔሮን የተመረተውን መድሃኒት በነፃ ለመስጠት ፕሬዚደንቱ ቃል ገብተዋል። ፕሬዚደንቱ አክለውም ባለፈው ሳምንት የተሰጣቸው በሙከራ ላይ ያለው የሰውነት በሽታ መከላከል አቅምን የሚጨምረው አንቲቦዲ ማገገሚያ ብቻ ሳይሆን ፈዋሽ ነው በማለትም በመቶ ሺዎች የሚቆጠር መጠን [ዶዝ] ያለው መድሃኒት እየተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል። ይሁን እንጅ ድርጅቱ የሚያመርተው መድሃኒት በፌደራል የመድሃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን የተረጋገጠ አይደለም።" https://www.bbc.com/amharic/54475144 +sports ሳዲዮ ማኔ ሴኔጋልን ለአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አደረሳት "በትናንትናው ዕለት ሴኔጋል ቡርኪናፋሶን 3 ለ1 በመርታት ለሶስተኛዋ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ፍጻሜ አልፋለች፤ በዚህም ስኬት ከፍተኛ ሚናን የተጫወተው ሳዲዮ ማኔ ነው። የሚገርሙ ክስተቶች ተስተናግደውበታል በተባለው ጨዋታ ሁለት ፍፁም ቅጣት ምቶች በቪዲዮ ድጋፍ አማካኝነት ሴኔጋል የተከለከለች ሲሆን በመጀመሪያውም ክስተት የቡርኪናፋሶው ግብ ጠባቂ ሄርቬ ኮፊ ተጎድቶ በፋሪድ ኦድራጎ እንዲተካ ሆኗል። የሴኔጋሎቹ አብዱ ዲያሎ እና ኢድሪሳ ጉዬ ሴኔጋል እንድትመራ ያስቻላትን ሁለት ጎሎች ያስቆጠሩ ሲሆን የቡርኪናፋሶው ብላቲ ቱሬ አንድ ጎል በማስቆጠር ልዩነቱን ማጥበብ ችሎ ነበር። ነገር ግን አገሩ የውድድሩ አሸናፊ የሆነችበት ጎል በሳዲዮ ማኔ ተቆጠረች። ለማኔ ለአገሩ ያስቆጠራት 29ኛ ጎል ስትሆን ከሄንሪ ካማራም ጋር የምንግዜም ጎል አስቆጣሪዎች በሚል በአንደኛ ደረጃነት እንዲቀመጥ አድርጎታል። እሁድ በሚጠናቀቀው በአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል፣ ግብፅን ወይም ካሜሩንን ትገጥማለች። ቡርኪናፋሶ ለሶስተኛነት ወይም ለአራተኛነት በሚደረገው ፍልሚያ በመጪው ቅዳሜ ጨዋታዋን ታደርጋለች። ""ይህ የደረስንበትን ወቅት ያሳያል። በሁለት ተከታታይ የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ መድረስ ቀላል እንደማይሆን እናውቅ ነበር፤ ነገር ግን አድርገነዋል። በአሁኑ ወቅት ለኛ መሰረታዊው ጉዳይ ማንም ይሁን ማን ይግጠመን ተፋልመን ማሸነፍ ነው"" ብሏል ማኔ። ማኔ የቡርኪናፋሶ ቡድን በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደነበርና በጣም ከብዷቸውም እንደነበር አልደበቀም። ""በጣም ከባድ ጨዋታ ጠብቀን ነበር። አዎ ፈታኝ ነበር፤ ነገር ግን ተረጋግተን ብዙ እድሎችን ፈጥረናል። ማሸነፍ ይገባናል ብዬም አስባለሁ"" በማለት ተናግሯል። ""ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩኝ ፊቴ ላይ የምታዩት ይመስለኛል፣ ይህ ለኔ የተለመደ ነው። በግሌ እኮራለሁ፣ እናም ለራሴ፣ ለቡድን ጓደኞቼ እና ለአገሬ በጣም ደስተኛ ነኝ።"" ብሏል ማኔ" https://www.bbc.com/amharic/news-60239919 +sports የቻምፒዮንስ ሊጉ ዋንጫ ወደ ማንችስተር ሲቲ ወይስ ቼልሲ? "ዛሬ በእንግሊዝ ቡድኖች መካከል የሚደረግ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ነው። የዛሬ ምሽቱን የአውሮፓ ቻምፒዮንነት ዘውድ የሚጭነው ማንችስተር ሲቲ ወይስ ቼልሲ? የፕሪሚየር ሊጉ ቻምፒዮን ማንችስተር ሲቲ ባለ ትልቁን ጆሮ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማንሳት ይፎካከራል፡፡ የ2012 የአውሮፓ ቻምፒዮኑ ቼልሲ የፔፕ ጋርዲዮላን ቡድን ዘንድሮ በሊጉ እና በኤፍኤ ካፕ ሁለት ጊዜ ማሸነፍ ችሏል። በፖርቶ ስታዲዮ ዶ ድራጋዎ የሚደረገውን ጨዋታ ለመመልከት እስከ 16,500 ታዳሚዎች እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ምን�� እንኳን አርብ በተደረገው ልምምድ ላይ የሲቲው አማካይ ኢካይ ጉንዶጋን ከፈርናንድኒሆ ጋር ተጋጭቶ ትንሽ ጉዳት ያስተናገደ ቢመስልም የሁለቱም ቡድኖች ተጫዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ። አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ""መጫወት የምንፈልገውን መንገድ እና ከማን ጋር እንደምንጫወት ስለምናውቅ ብዙ እንደማላስቸግራቸው አውቃለሁ"" ብሏል፡፡ ""እዚህ መገኘት አስገራሚ ተሞክሮ ነው፡፡ ምን እንደምነግራቸው በትክክልም አውቃለሁ፡፡ የተጨነቁ እና የተደናገጡ ካሉ የተለመደ ነገር እንደሆነ እነግራቸዋለሁ"" ሲል ሐሳቡን ሰጥቷል። በተጨማሪም ""የፍፃሜ ጨዋታውን ለማሸነፍ እንደምንሰቃይ እርግጠኛ ነኝ፡፡ [በጨዋታው] ተዝናኑበት ማለት ጥሩ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ አይቻልም፡፡ ጽናት እና ማስተካከያ ማድረግ ያስፈልጋል"" ብሏል፡፡ የሲቲው አማካይ ኬቪን ደ ብሩይን በበኩሉ ""ካሸነፍክ ጀግና ነህ፣ ከተሸነፍክ ደግሞ ወድቀሀል ማለት ነው። ወደዚህ ደረጃ መምጣት ለቡድኑ አስደናቂ ቢሆንም ዋንጫውን አለማሸነፍ ግን ልምድ አይደለም"" ሲል ገልጿል፡፡ ""ከክለቡ እና ከተጫዋቾች ግቦች አንዱ ነው፡፡ እዚህ መድረስ መቻል እና በዓለም ላይ ከፍተኛ በሆነው መድረክ ላይ መጫወት መቻል ትልቅ ዕድል ነው፡፡"" የሲቲው ስፔናዊ አለቃ ጋርዲዮላ በ2009 እና 2011 ከባርሴሎና ጋር ድሉን ከተቀዳጀ በኋላ ሻምፒዮንስ ሊጉን ለሦስተኛ ጊዜ ለማሸነፍ ይጫወታል፡፡ የቼልሲው አለቃ ቶማስ ቱቼል የመጀመሪያውን የቻምፒየንስ ሊግ ስኬት ለማስመዝገብ ይጫወታል፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን ጀርመናዊው ፓሪስ ሴንት ዠርሜንን ይዞ በባየር ሙኒክ 1-0 ተሸንፎ ዋንጫውን አጥቷል፡፡ ""ሁሉም እንደሚፈልገው ሙሉ እምነት አለኝ፡፡ የድል ረሀብ አለ። እናም ሁልጊዜ በስፖርቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ምን ያህል ፍላጎት አለ የሚለው ነው ዋናው ነገር። በዚህ ሳምንት በጣም የተጠናከርን፣ ትኩረት እና ሥነምግባር ያለን ሆኖ ተሰምቶኛል"" ብሏል ቱቼል፡፡ ""ፔፕ የያዘውን ሲቲ፣ ባየርን ወይም ባርሴሎናን መግጠም ሁልጊዜም ከባድ ነው፡፡ እሱ ትልቅ እምነት እና ስኬት ከመፍጠር ባለፈ ትልቅ የማሸነፍ አስተሳሰብ አለው"" ሲል ገልጿል፡፡ ""ምናልባትም በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ ብሎም በዓለም በጣም ጠንካራው ቡድን ነው። በሊጉ በመካከላችን ትልቅ ክፍተት ቢኖርም በዌምብሌይ እና በማንችስተር ክፍተቱን ዘግተናል"" ብሏል፡፡ የዋንጫው ጨዋታ በ90 ደቂቃ የሚወሰን ሲሆን ካልሆነ 30 ደቂቃዎች ተጨማሪ ጊዜ እና አስፈላጊ ከሆነም ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ያመራል፡፡ በመደበኛው ክፍለ ጊዜ ቡድኖቹ አምስት ተጫዋቾችን የሚቀይሩ ሲሆን ወደተጨማሪ ሰዓት ካመሩ ደግሞ ተጨማሪ አንድ ተጫዋች የመምረጥ መብት አላቸው፡፡ ቱቼል ""በፍጹም ቅጣት ምት በኩል [የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ] ከመቺዎች ጥራት አንፃር ድንቅ ነበር፡፡ 20 ፍጹም ቅጣት ምት ሳይሳት ሲቆጠር የመሰለን ነገር ያየሁ አይመስለኝም"" ብሏል። ""ቅጣት ምቱን የሚመቱትን ለይተናል። ነገር ግን በመጨረሻው ሜዳ ላይ ማን እንደሚቆይ አላውቅም። ስለዚህ በደንብ ማወቅ አለብን። ወደ ቅጣት ምት ከሄድን አብረን እንሄዳለን እና አብረን እንወጣለን፡፡"" የቪድዮ ረዳት ዳኛ (ቫር) ጥቅም ላይ ይውላል። ሲቲ ደግሞ 'በሜዳው የሚጫወተው' ቡድን ተብሎ የተሰየመ ሲሆን፤ በዚህም በተለመደው ሰማያዊ እና ነጭ መለያው ይጫወታል፡፡ የዘንድሮው ፍጻሜ በዓለም ዙሪያ ባሉ ከ200 በላይ አገራት ይተላለፋል። የአውሮፓ ክለቦች ትልቁ ጨዋታ ከመጀመሩ 10 ደቂቃ በፊት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ይደረጋል፡፡" https://www.bbc.com/amharic/57291566 +health አፍሪካ በኤድስ የሚከሰት ሞትን ለመግታት ወደ ኋላ ቀርታለች ተባለ የአፍሪካ አገራት በ2030 በኤችአይቪ ኤድስ አማካኝነት የሚከሰት ሞ���ን ለማስቀረት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ወደ ኋላ መቅረታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት አመለከተ። ነገ ሐሙስ ተከብሮ የሚውለውን የዓለም የኤድስ ቀንን በማስመልከት በድርጅቱ ይፋ የሆነው ሪፖርት እንዳመላከተው በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጭቆና ብሎም አግላይ ሕጎች ለዕቅዱ መጓተት እንደምክንያት ተጠቅሷል። ተመድ 90 በመቶ የሚሆኑ ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ተመርምረው ውጤታቸውን እንዲያውቁ፣ ብሎም ከዚህ ውስጥ 90 በመቶው የፀረኤችአይቪ መድኃኒት እንዲጀምሩ እና ከዚህ ውስጥ ደግሞ 90 በመቶው በደማቸው ውስጥ የሚገኘውን የቫይረስ መጠን ከ200 በታች የማድረግ ዕቅድ አለው። ከሰሃራ በታች በሉ የአፍሪካ አገራት ውስጥ የሚኖሩ እድሜያቸው ከ15 እስከ 24 የሆኑ ሴቶች እና ልጃገረዶች ከወንዶች ጋር ሲነጻጸር፣ በሦስት እጥፍ ለኤችአይቪ የመጋለጥ ዕድል ሲኖራቸው በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 5000 አዳዲስ ሴቶች በቫይረሱ ይያዛሉ። “የአፍሪካ አገራት የሥነ ተዋልዶ ትምህርትን፣ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች የሚሰጥ አገልግሎት፣ ብሎም የኤችአይቪ አገልግሎቶችን በጋራ በማጣመር መስጠት ይኖርባቸዋል። ይህም በጋራ ተጣምረው የሴቶችን ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ሊሰጡ ይገባል” ሲሉ የተመድ የኤችአይቪ ኤድስ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዊኒ ባያኒማ ተናግረዋል። ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም መንግሥታት የቫይረሱን ሥርጭት ለመቀነስ እንደ እንቅፋት የተጠቀሱ ሕጎቻቸውን እንዲያነሱም ጠይቀዋል። “አግላይ ሕጎች ሰዎች ኤችአይቪን የሚመለከቱ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ ብሎም የኤችአይቪ ተጋላጭነትን በመጨመር ከፍተኛ ሚና አላቸው። እነዚህ ሕጎች የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን ግንኙነትን፣ የወሲብ ንግድን፣ የፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት መጠቀምን ወንጀል የሚያደርጉ ሕጎች ይጠቀሳሉ” ሲሉም አክለዋል። ለኤችአይቪ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸውን ሰዎች በወንጀል የሚጠይቁ አገራት በምርመራ እና በህክምናው ሂደት ላይ ዝቅተኛ ውጤት የሚያሳዩ ሲሆን፣ በርካታ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ተመርምረው ውጤታቸውን ሳያውቁ ይኖራሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/ckknl16ln2yo +politics ኔታኒያሁ ጥምር መንግሥት መመሠረት ለእስራኤል አደጋ ነው አሉ "የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይዋቀራል ተብሎ የሚጠበቀው አዲስ የጥምር መንግሥት ለአገሪቱ ""የደህንነት አደጋ"" እንደሚሆን አስጠነቀቁ። የአክራሪ-ብሔርተኝነት መሪ የሆኑት ናፍታሊ ቤኔት መሃል ሰፋሪ ከሚባሉት ያየር ላፒድ ጋር ድርድሩን እንደሚቀላቀሉ ከተናገሩ በኋላ ነው ኔታኒያሁ ለቀኝ ክንፍ ፖለቲከኞች ስምምነቱን እንዳይደግፉ ጥሪ ያቀረቡት። ላፒድ አዲስ የጥምር መንግሥት ለማቋቋም እስከ ረቡዕ ድረስ ቀን ያላቸው ሲሆን ከተሳካላቸው በአገሪቱ ታሪክ ለረጅም ግዜ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት የቆዩት የኔታኒያሁ የስልጣን ዘመን ያበቃል። በማጭበርበር ክስ ፍርድ ቤት የቀረቡት ኔታንያሁ እ.ኤ.አ. በመጋቢት ወር በተካሄደው አጠቃላይ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ማግኘት አልቻሉም ነበር። በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራት ግዜ አጠቃላይ ምርጫ ቢካሄድም ኔታኒያሁ አብላጫ ድምፅ ማግኘትም ሆነ የጥምር መንግሥት ለመመስረት የሚሆን ስምምነት ማድረግ ሳይችሉ ቆይተዋል። ""የግራ ዘመም የጥምር መንግሥት አትመስርቱ፣ ይህ ለእስራኤል ደህንነት አደገኛ ነው"" ሲሉ የ 71 ዓመቱ ኔታኒያሁ ተናግረዋል። ኔታኒያሁ ለ12 ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩ መሪ ሲሆኑ፤ የአንድ ትውልድ እድሜ ላለው ግዜ የእስራኤል ፖለቲከ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይዘው ቆይተዋል። የ49 ዓመቱ ቤኔት በበኩላቸው ፓርቲያቸው የጥምር መንግሥት ለመመስረት የሚደረገውን ድርድር እንደሚቀላቀል በቴሌቪዢን በተላለፈ መልክታቸው ላይ አስታውቀዋል። ""ኔታንያሁ ከዚህ በኋላ ቀኝ ዘመም መንግሥት ለማቋቋም አይሞክርም፣ ምክንያቱም እንደሌለ ስለሚያውቀው ነው"" ያሉት ቤኔት፤ ""የእስራኤል ብሔረተኛ ቡድንን እንዲሁም መላው አገሪቱን ከግሉ አቋም ጎን ለማሰለፍ እየሞከረ ነው"" ሲሉ ተናግረዋል። ቤኔት መግለጫውን ከመስጠታቸው በፊት የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን በተዘረዘሩት የስምምነት ነጥቦች መሠረት ቤኔት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁን እንደሚተኩ እና በኋላም ለ57 ዓመቱ ለማ ላፒድ በቀጣይ ዙር ስልጣኑን እንደሚሰጧቸው ተዘግቧል። ስለ ስምምነቱ በይፋ የተባለ ነገር የለም። ለስምምነት የቀረበው ጥመረት ከቀኝ ፣ ግራ እና ማሃል ሰፋሪ የሆኑ ፖለቲከኞችን ይሰበስባል። ፓርቲዎቹ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ብዙም የሚያመሳስላቸው ነገር ባይኖርም፣ ቤኒያሚን ኔታንያሁ የስልጣን ዘመናቸው እንዲጠናቀቅ ባላቸው ፍላጎት ላይ ግን ይስማማሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-57305762 +politics የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ሸኔ የፈጸማቸው ጥቃቶች ምን ያመለክታሉ? መንግሥት ሸኔ የሚለው እና በሽብርተኝነት የፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ጦር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባ ሦስት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል። የፌደራሉ እና የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ከታጣቂ ቡድኑ ጋር ሰላም እንዲያወርዱ የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም ባለመሳካታቸው ወደ ጦርነት ገብተዋል። በመንግሥት በኩል የተለያዩ ወታደራዊ ዘመቻዎች ተደርገው፣ ታጣቂ ቡድኑ የአገሪቱ የደኅንነት ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሷል ቢባልም፣ ሰሞኑን የፈፀማቸው ጥቃቶች ግን የመንግሥትን እርምጃ ስኬታማነትን ጥያቄ ላይ ጥሎታል። ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር በመሆን በጋምቤላ ከተማ ጥቃት ከፍቶ ከ40 በላይ የሰው ሕይወት መጥፋቱ ይታወሳል። በተመሳሳይ ዕለትም በቄለም እና ምሥራቅ ወለጋ፤ ደምቢዶሎ እና ጊምቢ ከተሞችም ጥቃት በመክፈት “የተሳካ ኦፕሬሽን” ማካሄዱን ገልጾ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ሰኔ 11/2014 ዓ.ም ቅዳሜ፣ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ ጥቃት ፈጽሞ ሴቶችና ህጻናት የሚገኙባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸው ተገልጿል። ነገር ግን ቡድኑ ጥቃቱን የፈፀመው የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ያደራጀው፣ ለየት ያለ የሚሊሻ ቡድን መሆኑን በመግለጽ ጥቃቱ ሲፈፀም ሠራዊቱ በአካባቢው እንዳልነበር ገልጿል። አክሎም ገለልተኛ በሆነ ወገን ምርመራ እንዲካሄድም ጥያቄ አቅርቧል። የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ፣ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ከሳምንታት በፊት የክልሉ እና የፌደራል መንግሥት ጀምረውት የነበረውን ወታደራዊ ዘመቻ አስመልክቶ መግለጫ ሲሰጡ፣ የታጣቂው ቡድን የአገሪቱ ደኅንነት ስጋት ከማይሆንበት ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀው ነበር። ብሔራዊ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ምክር ቤት በበኩሉ የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ወቅታዊ ሁኔታን በገመገመበት ጊዜ በሕግ ማስከበር ዘመቻው ከሺህ በላይ ታጣቂዎች መገደላቸውን እና ዘመቻውም የተሳካ እንደነበር ገልጿል። የጋምቤላው፣ ደምቢዶሎ እና የጊምቢ ጥቃትም ከእነዚህ መግለጫዎች በኋላ የተከሰተ ነው። ከቶሌ ቀበሌ ጥቃት በፊት ያነጋገርናቸው የመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ “በስፍራው የሚገኙ የመንግሥት አካላት [ለተከፈተው ጥቃት] እርምጃ መውሰዳቸውን ነው የማውቀው” በማለት ስለሰሞኑ ጥቃት ለቢቢሲ ተናግረዋል። “በጊምቢ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ቀበሌዎች ተኩስ ተከፍቷል። ልክ እንደ ደምቢዶሎ እና ጋምቤላ ሁሉ ተኩስ መክፈት ነበር። ግን እርምጃ ተወስዶባቸው ከተሞቹ ወደ ሰላማቸው ተመልሰዋል” ብለው ነበር። ታጣቂ ቡድኑ ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሷል ከተባለ በኋላ የዞን እና የክልል መቀመጫ የሆኑ ከተሞችን ገብቶ ጥቃት መፈፀሙ እንዴት ይታያል ተብለው ለተጠየቁት አቶ ከበደ ሲመልሱ “እኔ መንግሥት ታጣቂዎችን አጥፍቷቸዋል የሚል መረጃ የለኝም” ብለዋል። “. . .እርምጃ እየወሰድን ነው፤ ለአገር ደኅንነት ስጋት ሆነዋል። ለዚህም ነው በአዲስ መልክ እርምጃ እየወሰድን የምንገኘው።” የኦሮሞ ነጻነት ጦር ቃል አቀባይ የሆኑት ኦዳ ተርቢ፣ ዘመቻዎቹን አስመልክቶ መንግሥት እያቀረበው ያለው ሪፖርት “የተለመደው ፕሮፓጋንዳ ነው” ሲሉ አጣጥለው አካባቢዎቹን “በስትራቴጂ” መልቀቃቸውን ተናግረው ነበር። የኦሮሞ ነጻነት ጦር አዛዥ ኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተገደሉበት የቶሌ ወረዳ ጥቃት በፊት ለቢቢሲ እንደተናገረው “አሁን፣ በረሃዎችን እና ገጠሮችን ብቻ ሳይሆን ጥበቃ ያላቸው ከተሞችም እየገባን ነው፤ የፖለቲካ ሰዎችን አስታጥቀው ቢያዘምቱም ጥበቃቸውን እያለፍን ነው” ሲል ተናግሯል። ከአንድ ሳምንት በፊት ታጣቂ ቡድኑ የጋምቤላ፣ የደምቢዶሎ እና የጊምቢ ከተሞችን የማጥቃታቸውን አስፈላጊነት ሲገልፁ፣ “አጥፍተናቸዋል የሚለውን የመንግሥትን ሐሰተኛ መረጃ እና ከፖሊስ በነጠቁት ያረጀ መሳርያ ነው የሚዋጉት ለሚለው [ፕሮፓጋንዳ] መልስ እንዲሆን ነው” ይላል መሮ። የኦሮሞ ነጻነት ጦር ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር በመሆን በጋምቤላ ከተማ ላይ ከከፈቱት ጥቃት ጋር በተያያዘ 40 የሚሆኑ ግለሰቦች መገደላቸውን ቢቢሲ ከምንጮቹ ማረጋገጥ ችሎ ነበር። ኩምሳ ድሪባ ይህንን አስመልክቶ ሲናገር፣ በጦርነት በኩል መቁሰል እና መሞት ቢኖርም የደረሰው ጉዳት “የተባለውን አይደለም” ሲል ያስተባብላል። “እኛ ከተማይቱን ተቆጣጥረን በፈለግነው ሰዓት የፈለግነውን ፈጽመን ወጥተናል። ምን ፈጽማችሁ የሚለውን መግለጽ አያስፈልግም” ሲልም አክሏል። በተመሳሳይ ዕለት በተለይ በደምቢዶሎ ከተማ የመንግሥትን ኃይሎች ከሦስት ካምፖች ማባረር መቻላቸውን ኩምሳ ድሪባ ይናገራል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች፣ ታጣቂዎቹ ደምቢዶሎ ከተማ ማለዳ ከገቡ በኋላ ወደ ሆስፒታል አምርተው መድኃኒቶችን ጭነው መውጣታቸውን ተናግረዋል። ሚኒስቴር ዴታው አቶ ከበደም፣ ከተማ ውስጥ ገብተው ተኩስ መክፈታቸውን አረጋግጠዋል። የመንግሥት ታጣቂዎችም እርምጃ እንደወሰዱ ተናግረዋል። የታጣቂው ቡድን ዝርፊያ እና ግድያ እየፈፀመ ሕዝቡ እንዳያርስ እያደረገ ስለሆነ፣ መንግሥት እርምጃ እየወሰደ ነው ብለዋል። ጃል መሮ ለዚህ ምላሽ ሲሰጥ “ሆስፒታል ገብተን ቁስለኞቻችንን አክመን ወጣን እንጂ ጭነን የወሰድነው መድኃኒት የለም” ይላል። የመከላከያ ሠራዊትን በሁሉም ስፍራ ማሰማራት ስለማይቻል፣ ሕዝቡ በዚህ በኩል የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ከበደ ጠይቀዋል። የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተጋጋለበት ጊዜ ይህ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በምሥራቅ ወለጋ፣ ቤጊ እና ጊዳሚ ከተሞችን ተቆጣጥሮ ነበር። ታጣቂዎች ከተሞች ገብተው መውጣታቸው፣ ለሕዝቡ ሰላም ስጋት አይሆንም ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ የመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ምላሽ ሲሰጡም “አሁን ሕዝቡን ይዘናል፤ መሬቱንም ሕዝቡንም የምንይዝበት ጊዜ አለ” ብለዋል። “ያለነው በጦርነት ውስጥ እንጂ ጭፈራ ቦታ ወይንም የእምነት ቤት አይደለም፤ በአንድ ሌሊት አገር መያዝ አይቻልም። እርምጃችንም በዚሁ ሂደት ውስጥ ያልፋል፤ ጦርነት ሞ��� እና መፈናቀልን ያዘ መሆኑ ይታወቃል” ብለዋል። ባለፉት ሦስት ዓመታት ታጣቂዎቹ በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች በሁለት ጦር መካከል ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ለቢበሲ ሲገልፁ ነበር። መንግሥትም፣ ሲከሰቱ ለነበሩት ግድያዎች እና መፈናቀሎች፣ በሽብርተኝነት የፈረጀውን ይህንን ታጣቂ ቡድን ሲከስ ቆይቷል። የኦሮሞ ነጻነት ጦር እና ግንባር በጋራ በ1976 (እኤአ) በወቅቱ የነበረውን ሥርዓት በመቃወም ነጻ አገር ለመመስረት በሚል ነበር የተቋቋሙት። የኦሮሞ ነጻነት ጦር፣ የግንባሩ የጦር ክንፍ ሆኖ ላለፉት 50 ዓመታት “ለኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት” ከተለያዩ ሥርዓቶች ጋር በትጥቅ ሲፋለም ቆይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ አመራሩን በዋነኛነት ኤርትራ አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ክንፍ፣ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወደ አገር ቤት ተመልሷል። በአገር ውስጥ ታጥቆ የነበረው ኃይል ግን የትጥቅ ትግልን የሙጥኝ በማለቱ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በይፋ ከጦሩ ራሱን መነጠሉን እንዲያሳውቅ አድርጓል። የኦሮሞ ነጻነት ጦር መሪ፣ ኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) “ዓላማችን የፖለቲካም የጦርም ግፊት የማይደርስበት የኦሮሞን ሕዝብ ነጻነትን ማረጋገጥ ነው፤ ነጻ እና ራሱን የቻለ ኦሮሞ እና ኦሮሚያን ለመመስረት እና የራስን እድል በራስ ለመወሰን ነው” ይላል። እንዲሁም “ኢትዮጵያ ውስጥ መጨቆን ቀርቶ፣ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በእኩልነት መኖር እፈልጋለሁ ካለም [የኦሮሞ ሕዝብ] እርሱን ለማስከበር እንታገላለን።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ሲወያዩ፣ ህወሓትን ጨምሮ በትጥቅ ትግል ከሚታገሉ የትኛውም አካላት ጋር በውይይት ችግሮችን ለመፍታት ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልፀው ነበር። የመንግሥት ኮሙኑኬሸን ጉዳዮች ቢሮ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ከበደም፣ የኦሮሞ ነጻነት ጦር ወደ ሰላማዊ ትግል እንዲመለስ እንፈለጋለን ብለዋል። “የኦሮሞ ሕዘብ ጥያቄ ምላሽ አግኝቶ አልቋል የሚል እምነት ባይኖረኝም ጥያቄዎቹን በሰላማዊ መንገድ ማንሳት ይቻላል” ይላሉ። “ወደ ምሥራቅ ኦሮሚያ ያሉ ሕዝቦች፣ በአብዛኛው እያረሱ አይደለም። ቡናም እየሰበሰቡ አይደለም። ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስም አስቸጋሪ ነው። ዝርፊያ እና ንብረት ማቃጠል በዝቷል። ስለዚህ መንግሥት ሰላም ለማውረድ ትልቅ ፍላጎት አለው” ብለዋል። ጦሩ ወደ ሠላማዊ መንገድ ለመምጣት ዝግጁነት እንዳለው የተጠየቀው ጃል መሮ፣  “እንደ ሕጻን ልጅ በትንሽ ነገር ተደልሎ የሚገባ ኃይል የለም። የምንፈልገው ነገር አለ። እርሱን ትተን እጅ የምንሰጥበት ምክንያት የለም” ሲል መልሷል። አክሎም “እኛ በመረጥነው ስፍራ መንግሥትም እኛም ይሆንልናል በምንለው ሰው፣ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተገኙበት ጥሪ የሚቀርብልን ከሆነ፣ ለድርድር ዝግጁ ነን” ብሏል። ከዚህ ውጪ “እንደ ልጅ በከረሜላ ደልሎ የሚጠሩን ከሆነ የሚሞኝ የለም።” መንግሥት ሸኔ የሚለው ይህ ታጣቂ ቡድኑ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ በፈጸማቸው ተከታታይ ጥቃቶች ምክንያት ባለፈው ዓመት ከህወሓት ጋር ሽብርተኛ ቡድን መባሉ ይታወሳል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከህወሓት ጋር ግንኙነት አለው በሚል መንግሥት በተደጋጋሚ ሲከሰው የቆየ ሲሆን፣ ትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰው ጦርነት ተስፋፍቶ የህወሓት ኃይሎች ወደ አማራና አፋር ክልሎች ሲገቡ ሁለቱ ቡድኖች በጋራ መንግሥትን ለመውጋት እንደሚተባበሩ በይፋ አሳውቀዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c1rqpll30z7o +politics የደብረ ብርሃን መታወቂያ የሌላቸው ግለሰቦች በከተማዋ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ተገለጸ "በአማራ ክልል በደ���ረ ብርሃን የከተማዋ መታወቂያ የሌላቸው ግለሰቦች ከህዳር 16/2014 ዓ.ም ጀምሮ በቀን እንቅስቃሴ ከማድረግ መታገዳቸውን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚኒኬሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ የከተማዋ ነዋሪዎችና የደብረ ብርሃን ከተማ መታወቂያ ያላቸው ግለሰቦች ብቻ በቀን እንቅስቃሴ ማድረግ ይችላሉ ብሏል። ለዚህም የከተማው አስተዳደር የሰጠው ምክንያት ""በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ሰርጎ ገቦች በመግባት አካባቢን የማጥናትና መረጃ የመስጠት ሥራ እየሰሩ እንደሆነ ስለተደረሰበት ነው"" ብሏል። ""ሰርጎ ገቦችን መለየትና አካባቢውን ከሰርጎ ገቦች ነጻ ለማድረግ፣ ለከተማውና ለነዋሪዎች ደኅንነት ሲባል በከተማው በየትኛውም አካባቢ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪና መታወቂያ ካላቸው ሰዎች ውጪ በቀን እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም"" ብሏል። በጦርነቱ ምክንያት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ የተጠለሉ ነዋሪዎችም በተዘጋጀላቸው መጠለያ እንዲገቡም ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል። የትግራይ ኃይሎች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 225 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ሸዋ ሮቢት ከተማን መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል። ይህንን በተመለከተ ምንም ገለልተኛ ማረጋገጫ የለም። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጦርነቱን ለመምራት ከወሰኑ በኋላ ጦሩ ብዙ ስኬቶችን ማስመዝገቡን እና ድሉም ""በጣም ቅርብ"" ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አማፂያኑን ለመዋጋት ወደ ጦር ግንባር በመሄድ ሠራዊቱን እመራለሁ ያሉ ሲሆን የትግራይ ተዋጊዎችም ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እያመሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ አጎራባቾቹ አማራና አፋር ክልል የተዛመተው ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሰብዓዊ ቀውሶችን ማስከተሉን ቀጥሏል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በረሃብ አፋፍ ላይ ሲሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታትና የእርዳታ ድርጅቶች አመልክተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59412878 +politics ታይዋን ለቻይና እንደማትንበረከክ መሪዋ ተናገሩ "በታይዋን ላይ ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት በአሁኑ ወቅት ፕሬዚዳንት ፃይ ኢንግ ዊን አገራቸው ለቻይና ጫና እንደማንትንበረከክና ባላት ዴሞክራሲያዊ የፅንሰ ሃሳብ መርሆች እየተዳደረች ትቀጥላለች በማለት ተናግረዋል። መሪዋ አክለውም ""ስኬታችን በጨመረ ቁጥር ከቻይና የሚደርስብን ጫናም የከፋ ይሆናል"" ብለዋል። በታይዋን ብሄራዊ ክብረ በዓል ንግግር ያደረጉት የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በበኩላቸው ""ውህደቱን ለማጠናቀቅ"" ቃል ገብተዋል። ታይዋን ራሷን እንደ ሉዓላዊ ግዛት ብትቆጥርም በቻይና በኩል ተመሳሳይ አረዳድ የለም በተፃራሪው ከቻይና እንደተገነጠለች ግዛት ነው የምትመለከተው። ቻይና የምትለውንም ውህደት ለማሳካት ኃይል ልትጠቀም ትችላለች። ለዚህም እንደ ማሳያ የሚሆነው ቻይና ከቅርብ ወናት ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጦር ጄት ወደ ታይዋን የአየር መከላከያ ቀጠና መላኳ ነው።አንዳንድ ተንታኞች በረራዎቹ ለታይዋን ፕሬዝዳንት እንደ ማስጠንቀቂያ ሊታዩ ይችላሉ ብለዋል። ፕሬዚዳንቷ በበኩላቸው ""ታይዋን ለዴሞክራሲ በመወገን ቆማለች"" በማለት ተናግረዋል። ደሴቲቷ ነፃነት፣ ዴሞክራሲ ወይም ሉዓላዊነትን በነፈገ መልኩ ""ቻይና የዘረጋችልንን መስመር"" እንድትወስድ ማስገደድ እንደማይቻል አስረድተዋል። የቻይና ወታደራዊ በረራዎች ወደ ታይዋን የአየር መከላከያ ቀጠና መስመር አልፈው መግባታቸው በብሔራዊ እና በአቪዬሽን ደህንነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቷ "" ሁኔታው በባለፉት 72 ዓመታት በነበረው ወቅት የበለጠ የተወሳሰበ እና የማይገመት ነበር"" ብለዋል። ታይዋን ""በችኮላ እርምጃ አትወስድም"" ቢሉም ነገር ግን መከላከያዋን ታጠናክራለች ብለዋል። መሪዋ ከቻይና አመራሮች ጋር በእኩል ደረጃ ለመወያየት ያቀረቡትን ሃሳብ በድጋሜ ቢያነሱም ""ተገንጣይ"" የሚል ስያሜ የሰጧቸው የቻይና አመራሮች ውድቅ አድርገውታል። ፕሬዚዳንቷ እንደገና በባለፈው ዓመት ሲመረጡ በከፍተኛ ድምፅ ሲሆን ቻይናን ለመገደደር ቃል ገብተዋል። ፕሬዚዳንቷ ንግግር ካደረጉ በኋላም የታይዋን ተዋጊ አውሮፕላኖች ሲያንዣብቡ ታይተዋል። ስለ ቻይና እና ታይዋን ጥቂት መሰረታዊ ነገሮች • ቻይና እና ታይዋን ለምን ደካማ ግንኙነት ኖራቸው? በአውሮፓውያኑ 1940 ዎቹ ቻይና እና ታይዋን በእርስ በእርስ ጦርነት ተከፋፈሉ። ነገር ግን ቻይና አሁንም ቢሆን ደሴቲቷ አስፈላጊ ከሆነ በኃይልም ቢሆን ትመለሳለች የሚል እምነት አላት። • ታይዋን የምትተዳደረው እንዴት ነው? ደሴቲቱ የራሷ ሕገ መንግሥት ፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ መሪዎች ፣ እና በጦሩ 300 ሺህ ገደማ የሚሆኑ የሰራዊት አባላት አሏት። •እንደ ሃገር ለታይዋን ማን እውቅና ሰጣት? ለታይዋን ዕውቅና የሰጧት ጥቂት አገሮች ብቻ ናቸው። በርካታዎቹ ቤጂንግን መቀመጫ ላደረገው የቻይና መንግሥት እውቅና ይሰጣሉ። አሜሪካ ከታይዋን ጋር ኦፊሴላዊ ግንኙነት የላትም ነገር ግን ደሴቲቱ እራሷን ለመከላከል የሚያስችል ድጋፍ እንድትሰጥ የሚጠይቅ ሕግ አላት።" https://www.bbc.com/amharic/news-58860861 +health ተመራማሪዎች የ53 ዓመቷን ሴት ቆዳ የ23 ዓመት የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ሠሩ "የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች የ53 ዓመቷን ሴት ቆዳ የ23 ዓመት እንዲመስል አድርገው መሥራት ችለዋል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ይህንን ፀረ ዕድሜ ግኝት ለሌሎችም የሰውነት ክፍሎች ማድረግ ይቻላል። የዚህ ጥናት ዓላማ ከዕድሜ መግፋት ጋር ለሚመጡ እንደ የስኳር በሽታ፣ የልብ በሽታና የነርቭ ችግሮች መፍትሔ ማፈላለግ ነው። ከ25 ዓመታት በፊት ዶሊ የተባለችውን በግ የፈጠረው ቴክኖሎጂ ነው ያረጀ ቆዳን የወጣት ያስመሰለው። የካምብሪጁ ባብራሃም ተቋም የጥናት ቡድን መሪ ፕሮፌሰር ዎልፍ ሪክ ናቸው። ይህ ግኝት ሰዎች ቢያረጁ በሽታ ሳያገኛቸው ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ ድጋፍ ያደርጋል ብለው እንደሚያምኑ ለቢቢሲ ይገልጣሉ። ""ስለዚህ ጉዳይ ስናልም ነው የኖርነው። በርካታ በሽታዎች ከዕድሜ መግፋት ጋር እየባሱ ይሄዳሉ፤ ታድወያ ሰዎችን ከዚህ ሰቀቀን መገላለግ ያስደስታል"" ይላሉ። ነገር ግን ይላሉ ፕሮፌሰሩ፤ ጥናቱ ገና ጅምር እና ብዙ ሥራ የሚጠይቅ ነው ይላሉ። ይህ ግኝት ከቤተ-ሙከራ ወጥቶ ወደ ክሊኒክ ከመሄዱ በፊት ብዙ ውጣ ውረዶችን ማለፍ ይጠበቅበታል። ቢሆንም የቆዳ ዕድሜን ቀንሶ ማየት ትልቅ ድል እንደሆነ ፕሮፌሰሩ አይክዱም። የዚህ የተሸበሸበ ቆዳን መልሶ ወጣት የማድረግ ግኝት መላ ከ1990ዎቹ አንድ ጥናት የተመዘዘው ነው። በወቅቱ የኤደንብራ አጥኚዎች የቆዳ ሴል ወስደው ወደ ሽል ቀይረውት ዶሊ ብለው የጠሯትን በግ ፈጥረው ነበር። አጥኚዎቹ በጊዜው ዓላማቸው የቤተ-ሙከራ በግ አሊያም ሰው መፍጠር አልነበረም፤ ለሰው ልጅ የሚሆን ኢምብሮይክ ስቴም የተባለ ሴል መፍጠር እንጂ። ይህን ሴል ለውጥ ለሚያስፈልጋቸው የሰውነታችን ክፍሎች መቀየሪያ ማዋል ይችላሉ። ዶሊ የተፈጠረችበት መንገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል። የፕሮፌሰር ሪክ ቡድን የመጨረሻውን ቴክኖሎጂ ተጠቅ��ው ነው የ53 ዓመት ዕድሜ ያለውን ቆዳ የ23 ማስመሰል የቻሉት። ""ለመጀመሪያ ጊዜ ጥናት ስናደርግበት የነበረው ቆዳ በ30 ዓመታት ወጣት መሆኑን ስሰማ የተሰማኝን ደስታ መቆጣጠር አቅቶኝ ነበር"" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ጥናቱ አሁኑኑ ወደ ሥራ የማይገባው አሁን ባለበት ደረጃ ተግባራዊ ቢደረግ በካንሰር የመያዝ ዕድልን ስለሚጨምር ነው። ነገር ግን ቆዳን እንዲህ አሳምሮ ወጣት ማድረግ እንደሚቻል ከታወቀ የጎንዮሽ ጉዳቱ ዝቅ ያለ መላ መፈለግ አያዳግትም። ""ዓላማችን ሰዎች ዕድሜያቸው እንዲጨምር ማድረግ አይደለም፤ ቀሪ ዘመናቸውን ጤናማ ሆነው እንዲኖሩ ማድረግ እንጂ። ሰዎች ጤናማ ሆነው ማርጀት ይችላሉ"" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። አልፎም ሰዎች በአደጋ ምክንያት ቆዳቸው ጉዳት ሲደርስበት አዲሱ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል አጥኚው ይጠቁማሉ። ቀጣዩ እርምጃ ይህ ቴክኖሎጂ ልክ እነጡንቻ፣ ጉበትና የደም ሴል ላይ ሊሠራ ይችላል ወይ የሚለውን ማጥናት ነው። የዘርፉ ሰዎች የዚህ ቴክኖሎጂ ውጤት ገበያ ላይ ወጥቶ የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ይላሉ። ይህ አዲስ ግኝት ሙሉ የሰውነት ክፍልን እንዳያረጅ ማድረግ አሊያም የማያስረጅ ክኒና ወደ መፍጠር ይወስደን ይሆን የሚለው ጥያቄ አሁን ምላሽ ሊያገኝ ይችላል ይላሉ ፕሮፌሰሩ።" https://www.bbc.com/amharic/news-61034943 +politics በጦር መሳሪያ ግዢ ምክንያት ፍጥጫ ውስጥ የገቡት ቱርክና አሜሪካ "የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቱርክ አቻቸው ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን ዛሬ ሩሲያ ውስጥ ተገናኝተው ይነጋገራሉ። ሁለቱ መሪዎች ከሚመክሩባቸው ጉዳዮች መካከል የጦር መሳሪያ ግዢ እና የሶሪያ ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳዎች ይሆናሉ ተብሏል። ቱርክ ከሩሲያ የጦር መሳሪያዎችን መግዛቷ ከአሜሪካ ጋር ውዝግብ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። ""አሜሪካ ክለከላ ማድረግ አትችልም"" ቱርክ ከሩሲያ ለመግዛት ያሰብኩትን ጦር መሳሪያ በተመለከተ አሜሪካ ምንም አይነት ክልከላ ልታደርግ አትችልም ስትል የአሜሪካንን አቋም ተቃውማለች። የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን ቱርክ በርካታ ቁጥር ያላቸው ስልታዊ የሚሳኤል ሥርዓቶችን ከሩሲያ ለመግዛት እቅድ እንዳላት አስታውቀዋል። ፕሬዝደንት ኤርዶሃን አገራቸው ለሁለትኛ ዙር ኤስ-400 ከምድር ወደ ሰማይ የሚወነጨፉ ሩሲያ ሠራሽ ሚሳኤሎችን ለመግዛት በዝግጅት ላይ መሆኗ በታወቀበት ጊዜ አሜሪካ ተቃውሞ አሰምታለች። በዚህም ሳቢያ ቱርክ ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ አጋሯ አሜሪካ ጋር ውዝግብ ውስጥ የከተታት ሲሆን ተጨማሪ ማዕቀብ ሊያስጥልባት ይችላል ተብሏል። አሜሪካ ሩሲያ ሰራሾቹ ኤስ-400 ሚሳኤሎች ለኤፍ-35 ተዋጊ ጄቶቼ ስጋት ናቸው ትላለች። ከዚህ በተጨማሪም ዋሽንግተን ሚሳኤሎቹ ለኔቶ የድንበር መከላከያ ሥርዓት አደጋ ናቸው ትላለች። ቱርክ በበኩሏ የአየር መከላከያ ሥርዓቶችን አጥጋቢ በሆነ መልኩ ከኔቶ አባል አገራት መግዛት እንዳልቻለች በማመልከት ከሩሲያ ጋር ስምምነት ላይ እንደደረሰች ገልጻለች። ""ሊኖረን ስለሚችለው የጦር መሳሪያ ዓይነት ከየትኛውም አገር በየትኛውም ደረጃ ማንም ጣልቃ መግባት አይችልም"" ሲሉ ፕሬዝደንት ኤርዶሃን በአሜሪካው ሲቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ በቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል። ""በዚህ ላይ ማንም ጣልቃ መግባት አይችልም። እንዲህ አይነት ውሳኔ የምንሰጠው እኛ ብቻ ነን"" በማለት ኤርዶሃን የአሜሪካንን አቋም ተችተዋል። ከወራት በፊት ቱርክ የመጀመሪያወን ዙር ኤስ-400 ሚሳኤሎችን ከሩሲያ መግዛቷን ተከትሎ አሜሪካ የቱርክ መከላከያ ኢንደስትሪ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ እሰማኢል ዴሚር እና ሦስት የተቋሙ ሠራተኞች ላይ ማዕቀብ ጥላለች። ከዚህ በተጨማሪም ቱርክ ተመሳሳይ የጦር ���ሳሪያ ግዢ የምትፈጽም ከሆነ ሌላ ማዕቀብ እንደሚጣልባት አሜሪካ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች። ""በየትኛውም ደረጃ ቱርክ ኤስ-400 የሚሳኤል ሥርዓቶችን እንዳትይዝ ወይም የትኛውንም አይነት ሩሲያ ሰራሽ ጦር መሳሪያዎችን ከመግዛት እንድትቆጠብ እናሳስባለን"" ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አሳስበዋል። ቃል አቀባዩ ጨምረውም አሜሪካ ቱርክን እንደ ወዳጅ አገር ነው የምትመለከታት ካሉ በኋላ፤ አለመግባባት ውስጥ ሆነን እንኳ ግንኙነታችንን ማጠናክር ነው የምንፈልገው ብለዋል። ይሁን እንጂ ቱርክ ሁለተኛውን ዙር ኤስ-400 ሚሳኤሎችን የምትረከብበትን መንገድ በተመለከተ ከሩሲያ ጋር ንግግር እያደረገች ትገኛለች። ኤርዶሃን ዛሬ በሩሲያ ተገኝተው ከፕሬዝደንት ቭላድረሚር ፑቲን ጋር በሚያደርጉት ውይይት ዋነኛ ጉዳያቸው ኤስ-400 ሚሳኤሎች እና በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ያለው ግጭት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የቱርክ እና ሩሲያ የውጭ ፖሊሲ አቋም ቱርክ እና ሩሲያ የወዳጅነታቸውን ያህል ፍላጎታቸውን ለየቅል እንደሆነ በሚያሳዩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ይመራሉ። ቱርክ እና ሩሲያ በሶሪያ ጉዳይ የተለያየ ፍላጎት ነው ያላቸው። ሁለቱ አገራት በሶሪያ በተቃራኒ ጎራ የቆሙ ኃይሎችን ይደግፋሉ። ቱርክ የሶሪያውን ፕሬዝደንት ባሻር አል-አሳድን ከሥልጣን ለመግልበጥ የሚታገሉትን ኃይሎች ትደግፋለች። ሩሲያ በበኩሏ አሳድ በስልጣን እንዲቆዩ ድጋፍ ታደርጋለች። ቱርክ እና ሩሲያ ከዚህ ቀደም በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በሚገኘው ኢድሊብ ግዛት የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሷል እያሉ አንዳቸው ሌላኛው ላይ ጣት ሲቀስሩ ነበር። ሞስኮ ሶሪያ የገባሁት በአሳድ መንግሥት ይፋዊ ጥሪ ነው በማለት በጦርነት የምትታመሰውን አገር መልሶ ለመገንባታ የቱርክ ጣልቃ ገብነት እንቅፋት መሆኑን ስትጠቅስ ነበር። ቱርክ በበኩሏ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች ከጎረቤት አገር ወደ ቱርክ እየተሻገሩ ስለሆነ፤ የቀጠናውን ደኅንነት ለማስጠበቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን በሰሜን ሶሪያ አሰማርታ በአሳድ መንግሥት ላይ የተነሱ ወታደሮችን ትደግፋለች። ቱርክ በአሁን ወቅት ወደ 3.6 ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያዊያን ስደተኞችን አስጠልላ ትገኛለች። ቱርክ እና ሩሲያ በሊቢያ ያላቸው አቋምም የተለያየ ነው። ቱርክ በተባበሩት መንግሥታት እውቅና የተሰጠውን መንግሥት ስትደግፍ፤ ዋግነር የተሰኘው ቅጠረኛው የሩሲያ ቡድን ደግሞ ለተቃዋሚው ጀነራል ኻሊፋ ሃፍጣር ጦር ይዋጋል። በአንድ ወቅት የኻፍጣር ጦር ትሪፖሊን ለመቆጣጠር ከጫፍ በደረሰ ወቅት ቱርክ ባሰማራቻቸው ወታደሮች ተገፍቶ እንዲሸሽ ሆኗል። ከሶሪያ በተጨማሪም ቱርክ እና ሩሲያ በሦስተኛ አገር ጉዳይ ጣልቃ ገብተው አቋማቸው ለየቅል የሆነበት አጋማጣሚም አልጠፋም። ከወራት በፊት በተካሄደው የአዘርባጅን እና የአርሜኒያ ጦርነት ቱርክ እና ሩሲያ የተለያየ ጎራን ደግፈው ቆመው ነበር። ቱርክ በዚህ ጦርነት አዘርባጃን በድል እንድትወጣ ቱርክ ሰራሹን ባይራክታር ቲቢ2 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖች) ጥቅም ላይ አውላ ነበር። ቱርክ ከወራት በፊት ለዩክሬን ድሮኖችን መሸጧ ሩሲያን ያበሳጨ ጉዳይም ነበር። ቱርክ እና ሩሲያ ወዳጅነት ምንም እንኳ ቱርክ እና ሩሲያ በሶሪያ፣ ሊቢያ፣ በአርሜኒያ-አዘርባጀን ጦርነት እንዲሁም በዩክሬን ጉዳይ ያላቸው አቋም ይለያይ እንጂ በጦር መሳሪያ ግዢ፣ ኢነርጂ እና ቱሪዝም መስኮች ጠንካራ ግንኙነት መመስረት ችለዋል። ቱርክ ከሩሲያ ከፍተኛ መጠን ያለውን ጋዝ የምታስገባ ሲሆን በተቃራዊው ቱርክ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሩሲያ ጎብኚዎችን በየዓመቱ በማስተናገድ ጠቀም ያለ ገንዘብ ታገኛለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-58723013 +health በአሁኑ ዘመን ስለኤችአይቪ ከሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች በጥቂቱ "ፖል ቶርን ቤተሰቦቹን ለመጨረሻ ጊዜ ያያቸው ከአስርት ዓመታት በፊት ነው። የተለያዩት ልብ በሚሰብር ሁኔታ ነበር፤ የበላበትን ሰሃን ኤችአይቪ ይተላለፍብናል በሚል ፍራቻ ወረወሩት። ግንኙነታቸውም በዚያው አከተመ። ፖል ኤችአይቪ በደሙ መኖሩ የታወቀው በአውሮፓውያኑ 1988 ነበር። ይህንንም ተከትሎ የነርሲንግ ስልጠና ትምህርቱን ማቆም ነበረበት። ""የ20ዎቹን ዕድሜዬን ያሳለፍኩት በፍርሃት ነው"" ይላል። በአሁኑ ወቅት መኖሪያውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው ፖል ስለ ቫይረሱ ብዙም አያሳስበውም። በቀን አንድ ክኒን መውሰድ እና በዓመት ሁለት ጊዜ ዶክተሩን ከማየት ውጪ ይህን ያህል ህይወቱን የሚያሰጋው ጉዳይ አይደለም። ህክምና የሚከታተሉና ጤንነታቸውን የሚጠብቁ በደማቸው ውስጥ የኤች አይ ቪ ቫይረስ የሚገኝባቸው ሰዎች እንደ ሌላው ሁሉ ህይወታቸውን በደስታ መኖር እንደሚችሉ ብዙዎች በዓመታት ተረድተዋል። እንዲሁም ምግብ በመጋራትና አብሮ ጊዜ በማሳለፍ በሽታው ይተላላፋል የሚሉ ያረጁና የተሳሳቱ አመለካከቶች በአብዛኛው ቢጠፋም አሁንም ቢሆን ጎጂ እና የተሳሳቱ መረጃዎች መሰራጨታቸው አልቀረም። 'መድኃኒት አለው' ኬንያዊቷ ዶሪን ሞራ ሞራቻ በደሟ ውስጥ በኤችአይቪ ቫይረስ ኖሮ የተወለደች ቢሆንም ሁኔታዋን ያወቀችው በ13 ዓመቷ በአውሮፓውያኑ 2005 በተደረገላት ምርመራ ነው። በአንድ ወቅት በታንዛኒያ ወደ የሚገኝ የባህል መድኃኒት አዋቂ ነኝ የሚል ግለሰብ ዘንድ የሄደችው ዶሪን እሷንም ሆነ እናቷን ከኤችአይቪ እንደሚፈውሳቸው ነገራቸው። ""እሱ የሚሸጠውን ከዕፅዋት የሚቀመሙ መድኃኒቶችን ጠጥተን ከኤችአይቪ ነፃ መሆናችንን አምነን ተመልሰናል"" ትላለች። በመቀጠልም ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ እንዳይባዛ የሚከለክለውን ፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት (አንታይሪትሮቫይራል) መድኃኒት መውሰድ አቆመች። ነገር ግን ትንሽ ቆይታ በሽታን የመከላከል አቅሟ በመዳከሟ የሳንባ ምች ታመመች። በደሟ ውስጥ ያለው የኤችአይቪ ቫይረስ መጠን መጨመሩንና በዚህም የተነሳ ሌላ ኢንፌክሽን ካጋጠማት እንደምትሞትም ዶክተሯ ነገራት። የኤችአይቪ ቫይረስ ካልታከመ ሰውነት ቀላል ህመሞችን መቋቋም ወደማይችልበት የኤድስ በሽታ ሊያመራ ይችላል። የባህል መድኃኒት አዋቂ የተባለው ሰውዬም ""አጭበርባሪ"" እንደሆነ ግልፅ ሆነላት። ለኤችአይቪ ምንም አይነት ክትባት ወይም መድኃኒት የለውም ነገር ግን ፈውስ አለው ብሎ ማመን የተለመደ ነው ሲሉ የዓለም አቀፍ ኤድስ ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶክተር አዲባ ካማሩልዛማን ተናግረዋል። በቅርቡ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችም ሁኔታ ተስፋን ፈንጥቋል። በቅርቡ በአርጀንቲና የምትኖር አንዲት ሴት በራሷ በሽታ የመከላከል አቅም ከኤችአይቪ ነፃ የሆነች ሁለተኛዋ ሰው ሆናለች። ግን እንዴት እና ለምን እንደሆነ እስካሁን ምክንያቱ አልተገለጸም። 'ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች ሁልጊዜ በሽታውን ያስተላልፋሉ የሚል እምነት' ጋናዊቷ ጆይስ ሜንሳህ ከደረሰባት መገለል ነፃ ለመውጣት ነበር ወደ ጀርመን ያቀናችው። ስለ ሁኔታዋ እንደምትናገረው በተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሳ ከቅርብ ሰዎች ጋር ካላት ግንኙነት ባሻገር ሥራዋን እንዳጣች ትናገራለች። በተለይም መገለሉ የሚመጣው ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች ሁልጊዜም ቢሆን ለትዳር አጋራቸው ወይም ለልጃቸው የማስተላለፍ ስጋት ደቅነዋል ከሚለው የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው ትላለች። ""ግለሰቦች የኤችአይቪ ሁኔታቻውን ለቤተሰቦቻቸው ሲያሳውቁ ... ሰዎች መቶ በመቶ ደኅንነታቸው የተጠበቀ አይደለም የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው። ኤችአይቪ በደማቸው አለ ማለት ሁሌም በሽታውን ያስተላልፋሉ የሚል እምነት አለ"" በማለት ጆይስ ትናገራለች። እንዲያውም በተጻራሪው ፀረ-ኤችአይቪ መድኃኒቶችን ለረጅም ጊዜ ከወሰዱ በኋላ፣ ሰዎች ቫይረሱን በወሲብም ሆነ በሌላ መንገድ የማያስተላልፉበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ። ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ግለሰቦች የዕድሜ ልክ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም ቫይረሱን ከሰው ወደ ሰው ማስተላለፍ ያቆማሉ። ህክምናዋን በየጊዜው የምትከታተለው ጆይስ አራት ልጆች ያሏት ሲሆን አንዱም ቫይረሱ በደሙ ውስጥ የለም። ህክምናው በስፋት እየተስፋፋ በመምጣቱም ከአውሮፓውያኑ 2010 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ሁኔታው በግማሽ ቀንሷል። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ኑሯዋን በጋና ያደረገችው የጆይስ ሴት ልጅ ቫይረሱ በደሟ ውስጥ አለባት፣ እንዲሁም ሌሎችንም ልታሲዝ ትችላለች በሚል በቅርቡ ትምህርት ቤቷ ወደ ቤቷ እንድትመለስ አድርጓታል። ኤችአይቪ በደማቸው ያለ ሰዎች የዩናይትድ ኪንግደም የበጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢያን ግሪን ""ኤችአይቪ ያለብን ሰዎቸቭ ብዙውን ጊዜ እራሳችንን እንደ በሽታ አምጪ አድርገን እንመለከታለን"" ይላሉ። ""ለብዙ ዓመታት ቫይረሱን ለሌላ ሰው አስተላልፋለሁ የሚል ከፍተኛ ስጋት ነበረብኝ።"" ህክምናው ከደረሰበት ደረጃ አንፃር ""ቫይረሱን በአሁኑ ወቅት እኔ በጭራሽ ወደሌላ ሰው ማስተላለፍ እንደማልችል ማወቄ ነፃነት ሰጥቶኛል"" ይላሉ። 'ኤችአይቪ የለም' ኤችአይቪ ከዚህ ቀደም እንደሚታሰበው የሞት ፍርድ ባይሆንም፣ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች መደበኛና ጤናማ ህይወት መኖር ቢችሉም፣ አንዳንድ ዘመቻ አድራጊዎች ግን ቫይረሱ የሚናገሩት እንደሌለ መሆኑ ችግርን እየፈጠረ ነው። ""በኤችአይቪ ህክምናና መከላከያው ላይ በዘመናት ውስጥ አስደናቂ ልኅቀቶች ታይተዋል። ነገር ግን ይህ ኤድስ አብቅቷል የሚለው ሁኔታ በመከላከል ሥራው ላይ ችግር እየፈጠረ ነው። በተለይም የኤችአይቪ ፈውስ ፍለጋም ላይ እንዲሁ ጥረቶችን ከማድረግ አንፃር እክል ሆኗል"" በማለት ዶክተር ካማልዛማን ይናገራሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአውሮፓውያኑ 2020 መረጃ እንደሚያመለክተው በዓለም ዙሪያ ወደ 38 ሚሊዮን የሚጠጉ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ ያለ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 700 ሺዎቹ ከኤድስ ጋር በተያያዙ በሽታዎች ሞተዋል። ይህም ቫይረሱ በጊዜ ባለመታከሙ ሊሆን እንደሚችል መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ፖል እንደሚለው ታዳጊና ወጣቶች ሰዎች በሽታውን እንደ አዛውንት በሽታ ይመለከቱታል እናም በርካቶች ""በአጠቃላይ ዝቅተኛ ግንዛቤ አላቸው"" ብሏል ። ""ኤችአይቪ ያለፈ ነገር ነው ብለው ያስባሉ"" ሲል አክሏል። 'እኔ ኤችአይቪ የሚይዘኝ ሰው አይደለሁም' ልክ ወጣቶች እንደ አዛውንት ህመም እንደሚያዩት ብዙዎች ቫይረሱ ወንድ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎችን ብቻ የሚያጠቃ ነገር አድርገው ይመለከቱታል። በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ ካለባቸው ሰዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። ክሪስቲን ስቴግሊንግ የተባሉት የፍሮንትላይን ኤድስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሠራተኛ ታዳጊና ወጣት ሴቶችን ከሚገድሉ በሽታዎች ዋነኛው ኤድስ እንደሆነ ይናገራሉ። ነገር ግን ካናገሯቸው ሴቶች ውስጥ በጣም ጥቂቶች ናቸው አደጋውን የተረዱት። ""ሴቶች የወሲብ ግንኙነትን በተመለከተ ጥንቃቄ ማድረግና አለማድረግን በተመለከተ አስቸጋሪ ውይይቶች ማድረግ አለባቸው"" ሲሉ ክሪስቲን ስቴግሊንግ ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት በርካታ መሻሻሎች ቢኖሩም አሁንም እየተሰራጩ ያሉ የተሳሳቱ መረጃዎች ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ሰዎችን ግንኙነቶቻቸው ���ንዲቋረጥ፣ ሥራ እንዳይኖራቸው እንዲሁም አልፎ ተርፎም ትክክለኛ ህክምናና ምርመራ እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59493430 +health ኮሮናቫይረስ፡ በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን በአካላዊ ርቀት ምክንያት ለማፅናናት ያልቻለው ግለሰብ "በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን ለማፅናናት አቅፏት የነበረው እንግሊዛዊ አካላዊ ርቀትህን ጠብቅ መባሉ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳበሳጨው ገልጿል። ክሬይግ ቢክኔል ይህ የተነገረው ክራውንሂል በተባለው የቀብር ስነ ስርአት አስፈፃሚ ሰራተኛ ነው። ክሬይግም ሆነ ወንድሙ ወንበራቸውን ራቅ አድርገው እንዲቀመጡ ከመንገር በተጨማሪም የኃዘን ስነ ስርአቱም እንዲቋረጥ ተደርጓል። በኃዘን ልቧ ተሰብራ ከነበረው እናቱ ጎን ተቀምጦም በማፅናናትም ላይ እንደነበረ ተናግሯል። የሚልተን ኬይንስ ምክር ቤት በበኩሉ በተፈጠረው ሁኔታ ማዘኑንና ለወደፊቱም የተሻለ አማራጭ እንጠቀማለንም በማለት ምላሽ ሰጥቷል። የ43 አመቱ ክሬይግ በበኩሉ ""እናቴን ማፅናናት እንደምፈልግ ለሁሉም ተናግሬ ነበር። በከፍተኛ ሁኔታ ሃዘኗም ጨምሮ ስብርብር ስትል አቀፍኳት"" ብሏል። በአባቱ የኃዘን ስርአት ላይ ወንበሮቹ አካላዊ ርቀትን በሚያስጠብቅ መልኩ ተራርቀው የነበረ ሲሆን የናቱንም የበረታ ኃዘንም ተመልክቶ ወደናቱ የተጠጋ ሲሆን ወንድሙም ተከትሎት እናታቸውን ማፅናናት ጀመሩ። የቀብር አስፈፃሚ ሰራተኞቹም ወንበሮቹን በየቦታቸው እንዲመልሱና ማንቀሳቀስ አትችሉም ተብለዋል። በዚህ ሃዘን ላይ እያሉ እንዲህ መባላቸው ከፍተኛ ንዴትና ሃዘን እንደፈጠረበትም ገልጿል። ""በከፍተኛ ሁኔታ የባዶነት ስሜት እንዲሰማኝ አድርጓል"" ያለው ክሬይግ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልና በሰላም እንዲጠናቀቅም ከራሱ ጋር ትግል ማድረግ ነበረበት። ""ፈታኝ ነበር። የአባቴ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልም ውሳኔ ላይ መድረስ ነበረብኝ"" ያለው ክሬይግ አክሎም ""በጣም ያዘንኩበትና የፈራሁበትም ወቅት ነው፤ እንዲህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም"" ብሏል። የሚልተን ኬይነስ ምክር ቤት በበኩሉ ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ሁኔታ ተፈፅሞ እንደማያውቅና ቤተሰቡንም በማሳዘናቸው ይቅርታ ጠይቀዋል። የኃዘንም ሆነ የቀብር አስፈፃሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት ሰብሰብ ብለው ቢቀመጡም ችግር እንደሌለው ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በኃዘንም ሆነ በቀብር ስርአት ላይ መገኘት ያለባቸው 30 ሰዎች መሆናቸው በመመሪያው ላይ የተቀመጠ ሲሆን እነሱም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆኑንም አስፍሯል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54460664 +politics በመቀለ ከተማ ከአንድ ዓመት በኋላ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመለሰ የትግራይ ክልል መዲና መቀለ ከአንድ ዓመት በኋላ የኤሌከትሪክ አገልግሎት አገኘች። የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደገለጹት ከትናንት ማክሰኞች ኅዳር 26/2015 ዓ.ም. ጀምሮ በከተማዋ የኤሌክትሪክ አግልግሎት ተመልሷል። የእርስ በእርስ ጦርነቱን ተከትሎ መዲናዋን ጨምሮ አብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች መብራት፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት እና ባንክን የመሳሰሉ መሠረታዊ አገልግሎቶች ተቋርጦባቸው ቆይቷል። ይሁን እንጂ የፌደራል መንግሥቱ እና ህወሓት ጦርነቱን በማስቆም የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በክልሉ የመሠረተ ልማቶች መልሶ ግንባታ እንቅስቃሴዎች እንደተጀመሩ ተገልጿል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ደም አፋሳሽ ጦርነት ያካሄዱት ሁለቱ ተዋጊ ኃይሎች በደረሱት ስምምነት መሠረት ህወሓት ትጥቅ ሊፈታ የተስማማ ሲሆን የፌደራሉ መንግሥት ደግሞ መሠረተ ልማቶችን የመመለስ እና ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ የበኩሉን ለመወጣት ኃላፊነት ወስዷል። ከኤሌክትሪክ ���ገልግሎት በተጨማሪ፣ የኢትዮ-ቴሌኮም የስልክ አገልግሎት በሽረ እንዳሥላሴ እና በአከባቢው የሙከራ ሥራ ጀምሯል። “በከተማዋ ሁሉም ቦታ ከትናንት (ማክሰኞ) ጀምሮ በሁሉም ቦታ መብራት አለ” ሲል አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግሯል። የኢትዮ-ቴሌኮም ቺፍ ኮምንኬሽን ኦፊሰር የሆኑት አቶ መሳይ ውብሸት ከሳምንት በፊት ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ በሽረ እንዳሥላሴ እና አካባቢው የሙከራ ሥራ እየተካሄደ ነው። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመቀለ ኤሌክትሪክ መስመር ከብሔራዊ መቆጣጠሪያ ማዕከል ግሪድ ጋር መገናኘቱን ትናንት አስታውቆ ነበር። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ፤ የባለሙያዎች ቡድን ለጥገና ሥራ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ይዞ ወደ ክልሉ በቅርቡ ተሰማርቶ፣ የጥገና ሥራውን በአጭር ግዜ በማጠናቀቅ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲመለስ እንደሚሠራ አስታውቋል። ከነገ ጀምሮ ለጥገና ሥራው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በማሟላት፣ ሠራተኞቹ ከሰሞኑ ወደ ክልሉ እንደሚሰማሩና በአጭር ጊዜ የጥገና ሥራውን በማጠናቀቅ የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ኅብረተሰቡ መልሶ እንደሚያገኝ አክሏል። በቅርቡ በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ በረራዎችን መልሶ ለመጀመር ሙሉ ዝግጀቱን እንዳጠናቀቀ የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያደቻ ከሳምንት በፊት ለቢቢሲ ገልጸዋል። ለሁለት ዓመታት የተካሄደው የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ካስከተለው ሰብአዊ ጥፋት ባሻገር ከፍተኛ የንብረት ውድመት አስከትሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cv25xw89qw1o +politics ብሔረ ተኮር ጥቃት ወደ ተፈጸመባቸው የወለጋ ዞኖች የፌደራሉ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለጸ ባለፉት ቀናት ብሔር ተኮር ግጭት ወደ ተቀሰቀሰባቸው የወለጋ ዞኖች የአገር መከላከያ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለጸ። ባለፉት ቀናት በምሥራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በሚገኙ አካባቢዎች በተፈጸሙ ብሔር ተኮር ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸው እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መፈናቀላቸው ሲገለጽ ቆይቷል። ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ለተፈጠረው ግጭት እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው ቡድን እና የአማራ ታጣቂዎችን ተጠያቂ ይደረጋሉ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም በሰሞኑ ግጭት ዋነኛ ተሳታፊዎች መንግሥት ‘ሸኔ’ ብሎ የሚጠራው ቡድን እና የአማራ ታጣቂዎች መሆናቸው ለቢቢሲ አስታውቋል። “የፌደራል ኃይል አባላት አንገር ጉተን ከተማ ከገቡ በኋላ በአካባቢው የጸጥታ መሻሻል አለ” ሲሉ ግጭት ካጋጠመባቸው አንዷ በሆነችው የምሥራቅ ወለጋ ዞን የጊዳ አያና ወረዳ አንድ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአገር መከላከያ ሠራዊት ወደ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ባለፉት ጥቂት ቀናት የተሰማራ ሲሆን በሆሮ ጉዱሩ ዞን ደግሞ ከአንድ ሳምንት በፊት ተሰማርቷል። በምዕራብ ኦሮሚያ እየተፈጠረ ስላለው ግድያ፣ መፈናቀል እና ንብረት መወደም ዝምታን የመረጠው የፌደራሉ መንግሥት ጦሩን ወደ ግጭት ቀጠናው ያሰማራው በርካቶች የዜጎች ደኅንነት እንዲረጋገጥ በስፋት እየጠየቁ ባሉበት ወቅት ነው። ፖለቲከኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ማኅበራት መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት እንዲጠብቅ ሲጠይቁ ነበር። የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በወለጋ ዞኖች በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ሞት፣ መፈናቀል እና ሰቆቃ በእጅጉ ያሳስበኛል ያለ ሲሆን፣ መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማረጋገጥ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ትናንት ማክሰኞ ኅዳር 27/2015 ዓ.ም. ጥሪ አቅ���ቧል። ፖለቲከኛው ጃዋር መሐመድ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ላለው ቀውስ መፍትሄ ናቸው ያላቸውን ምክረ ሃሳቦች የለገሰ ሲሆን፤ መንግሥት ተኩስ በማቆም ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ንግግር መጀመር አለበት ብሏል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና ሌሎችም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳዩን አስመልክተው ባወጧቸው መግለጫዎች፣ ወለጋ ውስጥ በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ እንዳሳሰባቸውና መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል። የፌደራል መንግሥት ጦር በአካባቢዎች መሰማራቱ ይገለጽ እንጂ ግጭት ሸሽተው ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያሻቸው እየተገለጸ ይገኛል። ባለፉት ቀናት በወለጋ ዞኖች በተቀሰቀሱት ግጭቶች በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት እስካሁን በውል ባይታወቅም፣ የምሥራቅ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች ግን ከ60 ያላነሱ ሰዎች በአንድ ጀምበር መገደላቸውን ተናግረዋል። ሰዎች በማንነታቸው ምክንያት የጥቃቶች ዒላማ መሆናቸውን የገለጸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጥቃቶቹ የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ምርመራ ላይ መሆኑን ለቢቢሲ አስታውቋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/czq3yv3n2zwo +health የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ የዓለም ጤና ስጋት ነው ተብሎ ታወጀ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ ወረርሽኝ አንገብጋቢ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አወጀ። በድርጅቱ ምደባ መሠረት ይህ ውሳኔ ከወረርሽኞች አሳሳቢነት አንጻር ከፍተኛው ደረጃ ሲሆን፣ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በዓለም ዙሪያ እየጨመረ በመሄዱ ነው የሕዝብ ጤና ስጋት ተብሎ እንዲፈረጅ የተወሰነው። ውሳኔው የተላላፈው የዓለም ጤና ድርጅት ከቀናት በፊት በቫይረሱ ዙሪያ ለሁለተኛ ጊዜ ማካሄድ በጀመረው የበሽታው የአስቸኳይ ጊዜ ኮሚቴ ስብሰባ ማብቂያ ላይ ነው። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ በ75 አገራት ውስጥ ከ16,000 በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል። አስካሁን በበሽታው ምክንያት አምስት ሰዎች መሞታቸውንም ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የዓለም ሕዝብ የጤና ስጋት ተብለው የተለዩ ሁለት በሽታዎች ያሉ ሲሆን፣ እነሱም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና ለማጥፋት ትግል እየተደረገበት ያለው ፖሊዮ ናቸው። በተካሄደው ስብሰባ ላይ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽን ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው ተብሎ ይወሰን በሚለው ላይ ከውሳኔ ላይ ለመድረስ የጋራ ስምምነት እንዳልነበረ ዶክትር ቴድሮስ ተናግረዋል። ነገር ግን ወረርሽኙ በፍጥነት በዓለም ዙሪያ እየተዛመተ በመሆኑ፣ በእርግጥም ቫይረሱ የዓለም ሕዝብ ጤና ስጋት ነው የሚለውን ውሳኔ ማሳለፋቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። “በዓለም ጤና ድርጅት ግምገማ የበሽታው ስጋት ከፍተኛ ስጋት ከሆነበት ከአውሮፓ በስተቀር በቀረው የዓለም ክፍል መካከለኛ ነው።” በዓለም ዙሪያ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በሽታው የበለጠ መስፋፋት ዕድሉ በአሁኑ ጊዜ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ ወረርሽኙ በስፋት የበለጠ በዓለም ላይ የመስፋፋት ስጋት እንዳለ ግን ግልጽ ነው ሲሉ ባለሥልጣኑ አክለዋል። ይህን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ የዓለም የጤና ስጋት ነው ብሎ ድርጅቱ ማወጁ የመከላከያ ክትባት በፍጥነት እንዲዘጋጅና ቫይረሱ የበለጠ እንዳይዛመት ለማድረግ የሚያስፈልጉ የመከላከያ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲደረግ ያግዛል ብለዋል ዶክተር ቴድሮስ። በተጨማሪም ድርጅቱ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑትን ሰዎች ለመጠበቅና የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት አገራት እርምጃ እንዲወስዱ የሚያደርግ መመሪያን ���ያዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል። “ይህ ወረርሽኝ በትክክለኛ ዕቅዶችና በትክክለኛ ቡድኖች አማካይነት ለማስቆም የሚቻል ነው” ብለዋል ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም። የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ በመጀመሪያ የተገኘው በማዕከላዊ አፍሪካ ውስጥ እንደ አውሮፓውያኑ በ1950ዎቹ ነበር። https://www.bbc.com/amharic/articles/cjj40w44xy9o +politics ሩሲያ እና የክሬን፡ የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቅርብ ታማኝ ሰዎች እነማን ናቸው? የሩሲያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እንደመሆናቸው በዩክሬን ላይ ለተፈጸመው ወረራ ዋነኛው ውሳኔ የሚተላለፈው በፕሬዝዳንት ፑቲን ነው። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ለሚሰጡት ውሳኔያቸው ከአስርት ዓመታት በፊት አንስቶ አብረዋቸው የሰሩ የቅርብ ታማኝ ሰዎቻቸው በሚሰጧቸው ምክር ላይም ይተማመናሉ። እየተካሄደ ካለው ጦርነት አንጻር የፑቲን የቅርብ ታማኝ ሰዎች እነማን ናቸው? ሰርጌይ ሹይጉ የፑቲን የረጅም ጊዜ ታማኝ የቅርብ ሰው የሆኑት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሰርጌይ ሹይጉ ዩክሬንን በተመለከተ ከፕሬዝዳንቱ ጋር ተመሳሳይ አቋምን ያንጸባርቃሉ። በዚህም ዩክሬንን ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ በማድረግ ሩሲያን ከምዕራባውያን ወታደራዊ ስጋት መጠበቅ የሚል አቋም አላቸው። ከቅርበታቸው የተነሳ ሚኒስትሩ ቀደም ሲል የፑቲን ተተኪ ይሆናሉ ተብሎ ይታሰብ ነበር። ነገር ግን አሁንም ድረስ በሩሲያ መንግሥት ውስጥ ከፍ ያለ ተደማጭነት ያላቸው የፕሬዝዳንቱ የቅርብ ሰው ናቸው። ሰርጌይ ሹይጉ ከስምንት ዓመት በፊት ሩሲያ ከዩክሬን የተጠቀቻትን ክሪሚያን ስትይዝ ወታደራዊ ዘመቻውን በመምራት ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም የፑቲን ተቃዋሚዎችን ከሩሲያ ውጪ እያደነ በመርዝ ያጠፋል የሚባለውን የወታደራዊ መረጃ ቡድንን የሚመሩት እኚሁ ግለሰብ ናቸው። የሩሲያ የደኅንት ተንታኝና ፀሐፊ የሆኑት አንድሬ ሶልዳቶቭ እንደሚሉት ሰርጌይ ሹይጉ፣ የጦር ሚኒስትር ብቻ ሳይሆኑ በአብዛኛው በታሪክ ላይ የተመሰረተው የሩሲያ መንግሥት ርዕዮተ ዓለምንም በከፊል የሚቃኙት ናቸው። ቫሌሪ ጌራሲሞቭ የአገሪቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የሆኑት ቫሌሪ ጌራሲሞቭ የዩክሬን ወረራ እና ወታደራዊ እርምጃውን በፍጥነት ማጣናቀቅ ኃላፊነታቸው የነበረ ቢሆንም፣ የተፈለገውን ያህል የተሳካላቸው አይመስሉም። ፑቲን ከ20 ዓመት በፊት በቼቺኒያ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ቫሌሪ ጌራሲሞቭ ሠራዊቱን ሲመሩ የቆዩ ሲሆን፣ በክሪሚያ ወረራ፣ ከዩክሬን ወረራ በፊት ቤላሩስ ውስጥ የተደረገውን ወታደራዊ ልምምድን እንዲሁም ወረራውን በመማራት ከፊት ተሰልፈዋል። በተደነቃቀፈው የዩክሬን ወረራ ጅማሬ እና በሩሲያ ወታደሮች ዘንድ አለ በሚባል ዝቅተኛ ሞራል ምክንያት ወደ ጎን ተገፍተዋል የሚሉ አንዳንድ ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው። ነገር ግን አንድሬ ሶልዳቶ እንደሚያምኑት ይህ ከእውነት የራቀ ምኞት ነው። ምክንያቱም ፑቲን በጦር ሜዳ የሚካሄዱ ነገሮችን በራሳቸው ሊከውኑና ሊቆጣጠሩ አይችሉም። ስለዚህም የቫሌሪ ጌራሲሞቭ ሚና እንዲሁ በቀላሉ የሚተካ እንዳልሆነ ያመለክታሉ። ኒኮላይ ፓትሩሼቭ ፓትሩሼቭ ምዕራባውያን ለሩሲያ መልካም አመለካከት የላቸውም ብለው በጽኑ የሚያምኑ ሲሆን ከአስርታት በፊት አንስቶ ከፑቲን ጋር የጠበቀ ቅርበት አላቸው። ከፓትሩሼቭ በተጨማሪ የአገር ውስጥና የውጭ ደኅንት ኃላፊዎቹ ቦርትኒኮቭ እና ናሪይሽኪን ሌሊን ግራድ ውስጥ ከ1970ዎቹ ጀምሮ ከፑቲን ጋር አብረው የሰሩ ሲሆን፤ አሁን ድረስ የፕሬዝዳንቱ ቁልፍ ሰው ሆነው እንዳሉ ናቸው። ነገር ግን የፓትሩሼቭን ያህል በፑቲን ዘንድ ተደማጭነት ያላቸው ሰዎች በታም ጥቂት እንደሆኑ ይነገራል። ሁለቱ በሶቪየት ዘመን ኬጂቢ ውስጥ የሰሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ሁለቱም የሩሲያን የስለላ ድርጅት አንዳቸው ከአንዳቸው በመረከብ መርተዋል። ከዩክሬን ወረራ ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የደኅንት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ አሜሪካ ዋነኛ ግብ አድርጋ የያዘችው ሩሲያን እንድተርበታተን መድረግ ነው ሲሉ ጠንካራ ክስ አቅርበዋል። አሌክሳንደር ቦርትኒኮቭ የክሬምሊንን እርምጃ በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች እንደሚሉት ቦርትኒኮቭ ከሚመሯቸው የደኅንነት ተቋማት የሚቀርቡ መረጃዎችን ቭላድሚር ፑቲን ከየትኛውም ምንጭ በላይ ያምናሉ። በዚህም ቦርትኒኮቭ የፕሬዝዳንቱ የቅርብ ታማኝ ከሆኑት መካከል ይጠቀሳል። የሩሲያ የፌደራል ደኅንት መሥሪያ ቤትን (ኤፍኤስቢ) የመሪነት ቦታ የያዙት ቦርትኒኮቭ፣ ቦታውን ከሌላኛው የፑቲን የቅርብ ሰው ኒኮላይ ፓትሩሼቭ ነበር የተረከቡት። ይህ የሩሲያ የደኅንት መሥሪያ ቤት በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ሌሎች የደኅንት ተቋማት ላይ ከፍ ያለ ተጽዕኖ ማሳረፍ የሚችል ሲሆን የራሱ ልዩ ኃይልም አለው። አንድሬ ሶልዳቶቭ እንደሚያምኑት ቦርትኒኮቭ በሩሲያ የሥልጣን ማዕከል ውስጥ እጅጉን አስፋለጊ ሰው ቢሆኑም፣ ሌሎች እንደሚያደርጉት የመሪውን ሐሳብ የሚገዳደሩና ምክር የሚሰጡ ሰው አይደሉም ይላሉ። ሰርጌይ ናሪይሽኪን ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ለረጅም ጊዜ አብረው በቅርበት በመስራት ከሚጠቀሱት ባለሥልጣንት መካከል ሰርጌይ ናሪይሽኪን አንዱ ናቸው። ነገር ግን ከዩክሬን ወረራ በፊት በተካሄደውና በቴሌቪዥን በቀረበው የአገሪቱ የደኅንት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲን ለናሪይሽኪን ያሳዩት ምላሽ፣ በብዙዎች ዘንድ በሁለቱ መካከል የነበረው ቅርበት መላላቱን የሚያመላክት ነው ይላሉ። ስለ ክስተቱ አስደንጋጭነት ቤን ኖብል ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን፣ የፑቲን በሚገርም ሁኔታ መረጋጋት በበርካቶች ዘንድ ጥያቄን አጭሯል። አጠቃላይ የስብሰባው ድባብም ግራ አጋቢና መልካማ ያልሆነ ምስል የተንጸባረቀበት ነበር። ሰርጌይ ናሪይሽኪን በ1990ዎቹ ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ፣ በ2004 ፕሬዝዳንትንት ከሆኑ በኋላ፣ ቀጥሎም የአገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ሆነው ከፑቲን ጋር አብረው ሰርተዋል። በተጨማሪም የሩሲያ ታሪክ ማኅበር መሪ ሆነው ሰርተዋል። ሶልዳቶቭ እንደሚሉት ይህ የናሪይሽኪን የታሪክ ዕውቀት ፕሬዝዳንቱ ለሚወስዷቸው እርምጃዎች ርዕዮተ ዓለማዊ መሰረቶችን በመስጠት ያላቸውን ተፈላጊነት አጉልቶታል። ሰርጌይ ላቭሮቭ ምንም እንኳን በሩሲያ ውስጥ በሚሰጡ ቁልፍ ውሳኔዎች ላይ ጉልህ ሚና የላቸውም ተብሎ ቢታሰብም ሰርጌይ ላቭሮቭ ለ18 ዓመታት ቁንጮ ዲፕሎማት በመሆን የአገራቸውን ጉዳይ ለዓለም ሲያቀርቡ ቆይተዋል። የ71 ዓመቱ ላቭሮቭ የረጅም ዘመን አገልግሎት ፕሬዝዳንት ፑቲን አመራራቸው በዋናነት ለዘመናት የካበተ ልምድ ባላቸው ሩሲያውያን ላይ መሠረት ያደረገ መሆኑን ያሳያል። ነገር ግን ለረጅም ጊዜ ዩክሬንን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ተገልለው እንደቆዩ የሚነገርላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ምንም እንኳን ግልፍተኛና ኃይለኛ ናቸው ቢባሉም ዩክሬንን በተመለከተ የፑቲን ጆሮ ባያገኙም ዲፕሎማሲያዊ ንግግርን በመፍትሔነት ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ቫለንቲና ማትቪዬንኮ በፑቲን የቅርብ ክበብ ውስጥ ብቸኛዋ ሴት የሆኑት ቫለንቲና ማትቪዬንኮ፣ የአገሪቱ የላይኛው ምክር ቤት የሩሲያ ኃይሎች ወደ ሌላ አገር ገብተው እንዲሰማሩ ያደረገውን ውሳኔ ሲያጸድቅ የበላይ ሆነው የመሩ ናቸው። ይህም ለዩክሬኑ ወረራ መንገድ ጠርጓል። ቫለንቲና ማትቪዬንኮ ፑቲን ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ ሥልጣን ላይ እያሉ ጀምሮ አብረዋቸው ከመጡ ታማኝ ሰዎች መካከል አንዷ ሲሆኑ፣ ሩሲያ ክሪሚያን ወራ ስትይዝ በውሳኔው ውስጥ ተሳትፎ ነበራቸው። ቢሆንም ግን በቀዳሚ የውሳኔ ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የሚካተቱ ግለሰብ አይደሉም። እንደሁሉም የሩሲያ የደኅንነት ምክር ቤት አባል የቫለንቲና ማትቪዬንኮ ሚና ፕሬዝዳንት ፑቲን አብላልተውና ከውሳኔ ላይ ደርሰው የሚያመጧቸው ሐሳቦች የጋራ ውይይት ተደርጎባቸው የተሰጡ የሚመስል ገጽታ እንዲይዙ ማድረግ ነው። ቪክቶር ዞሎቶቭ የቀድሞው የፕሬዝዳንቱ የግል ጠባቂ ቪክቶር ዞሎቶቭ፣ ከስድስት ዓመት በፊት እንደ ኦእሬዝዳንቱ የግል ሠራዊት በራሳቸው በፑቲን የተቋቋመውን 'ሮስግቫርዲያ' የተባለውን የሩሲያን ብሔራዊ ዘብ ይመራሉ። ፑቲን የግል ጠባቂያቸው ብሔራዊ ዘቡን እንዲመሩ ማድረጋቸው የበለጠ ታማኝነትን ለማረጋገጥ የታለመ ነው። ቪክቶር ዞሎቶቭም ይሚመሩትን ዘብ ቁጥር አሁን 400,000 እንዳደረሱት ይነገራል። የዩክሬን ወረራ ሲታቀድ የአገሪቱ ሠራዊት በቀናት ውስጥ እንዲያጠናቅቀው ታቅዶ ነበር፤ ነገር ግን የታሰበው ሳይሆን ሲቀር የሩሲያ ብሔራዊ ዘብ የመሪነቱን ሚና ተረክቦ ጦርነቱን እያካሄደ ነው። የብሔራዊ ዘቡ ችግር የሚባለው መሪው ቪክቶር ዞሎቶቭ ወታደራዊ ስልጣናና ልምድ የሌላቸው መሆኑና ሠራዊታቸውም ታንክ የታጠቀ አለመሆኑ ለጥቃት ተጋላጭ እንዳደረገው ይነገራል። https://www.bbc.com/amharic/news-60605493 +sports የ105 ዓመቷ እማማ ራምባይ በሩጫ ክብረ ወሰን ሰበሩ ወ/ሮ ራምባይ 105 ዓመታቸው ነው። 100 ሜትርን በ45.40 ሰከንድ በመጨረስ በአዛውንቶች የተያዘውን የሕንድን ክብረ ወሰን ሰብረዋል። ይህንን ውድድር የሚያዘጋጀው አካል እስካሁን ትልቁ የውድድር ተሳታፊ የ85 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cglrkjmrvngo +politics ኢዜማ በሥልጣን ላይ ካሉ ሚኒስትሮች ትይዩ 22 የራሱን ሚኒስትሮች መሰየሙን አስታወቀ "የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ፣ ኢዜማ የመንግሥት ሥራዎችን የሚከታተሉ 22 ትይዩ የካቢኔ ሚኒስትሮችን አዋቅሮ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ። ኢዜማ የራሱን ትይዩ ካቢኔ ማቋቋሙን ባሳወቀበት መግለጫው እንዳመለከተው፣ ይህ ትይዩ ካቢኔ የዕለት ከዕለት የመንግሥት ተግባራትን መከታተል፣ የሚወጡ ረቂቅ ሕጎችን መተቸት፣ የፖሊሲ ንድፈ ሐሳቦችን ማውጣትና መሰል ሥራዎችን ያከናውናል። የፓርቲው ትይዩ ካቢኔ ፀሐፊ አቶ ይመስገን መሳፍንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ካቢኔውን ማቋቋም ያስፈለገበትን ምክንያት ለዲሞክራሲ፣ ለአገራዊ ለውጥ እንዲሁም አገሪቱ እንድትሄድበት በሚፈልገው የልማት መስክ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል በሚል መሆኑን ይናገራሉ። አክለውም አገራዊ ለውጡን ተቋማዊ ለማድረግ ወይንም ደግሞ በትክክል እየተመራ ስለመሆኑ የሚከታተል እና ድጋፍ የሚያደርግ የሰላ ትችቶችንም ለማቅረብ ይረዳል በሚል መቋቋሙን አመልክተዋል። ጨምረውም በኢዜማ የተዋቀረው ትይዩ ካቢኔ መንግሥት በአዋጅ ያቋቋማቸው 22 ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን የሚመሩ ሚኒስትሮችን እንደሾመው ሁሉ፣ ፓርቲው 22 ትይዩ ሚኒስትሮችን መሰየሙን ጠቅሰዋል። ኢዜማ የሰየማቸው ትይዩ ሚኒስትሮች ማንነትና ኃላፊነትን በሚመለከት ከቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ይመስገን ይህንን ለጊዜው ይፋ ከማድረግ ተቆጥበዋል። የፓርቲው ሕገ ደንብ በሚለው መሠረት የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህንን ትይዩ ካቢኔ አዋቅረው ሥራ መጀመራቸውን ያሳወቀው ኢዜማ፣ ይህ መንግሥታዊውን አስተዳደር ከሚያከናውነው መዋቅር በትይዩ የተቋቋመው ካቢኔ ""በምንም መልኩ የተጠባባቂ መንግሥትነትና የባለአደራነት ስብስብ እንዳልሆነ"" አመልክቷል። በካቢኔው በየተለያዩ ዘርፎችን የሚከታተሉ ትይዩ የካቢኔ ሚኒስትሮች የተሰየሙ ሲሆን እሱም ቡድኖችን በማዋቀር ኃላፊነትን በማከፋፈል ፓርቲውን ተፎካ���ሪ ማድረግ ዋነኛ የሥራ ድርሻቸው እንደሚሆን ገልጿል። አቶ ይመስገን አክለውም ፓርቲያቸው ትይዩ ካቢኔውን አዲስ መንግሥት እንደተመሰረተ ይፋ ማድረግ ያልቻለው አገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር መሆኑን ጠቅሰው፣ ፓርቲያቸው የትይዩ ካቢኔውን ምሥረታ ያካሄደው ጥቅምት 08/2021 ዓ.ም እንደነበር አስታወሰዋል። ነገር ግን በዚያ ወቅት በአገሪቱ የሰሜናዊ ክፍል ጦርነት እየተካሄደ ይህንን ይፋ ማድረግ ከፓርቲያቸው እንደማይጠበቅ መሆኑ ስለታመነበት መዘግየቱን ጠቅሰዋል። ኢዜማ ይህንን ትይዩ ካቢኔ ሲያቋቁም በሥልጣን ላይ ያሉ ሕግ አውጪዎች ተፎካካሪዎቻቸው ምን እንደሚሉ እንዲያውቁ የሚያደርግና ለመራጩ ሕዝብ ደግሞ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ሌላም አማራጭ መፍትሔ እንዳለ ያሳያል ብሏል። ይህ ትይዩ ካቢኔ ""ተጠባባቂ መንግሥት ወይም የባለአደራ ስብስብ"" አለመሆኑን በአጽንኦት አመልክቶ፣ በሕግ አውጪ ወይም በሕግ አስፈጻሚ ውስጥ ቀጥተኛ ሚና ተጫዋች በማድረግ የዴሞክራሲ መሣሪያ፣ የሰላምና የልማት መገልገያ አድርጎ ለውጥ አምጪ ማድረግ ይጠበቃል ብሏል ኢዜማ። አዲሱ መንግሥት ሲዋቀር የኢዜማ አመራሮች እና አባላት ሥልጣን ማግኘታቸውን በማንሳት አይጋጭም ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ ይመስገን፣ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፀደቀው የፓርቲው ሕገ ደንብ ላይ የትይዩ ካቢኔ ምሥረታ መስፈሩን አንስተው ሕጋዊ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም የፓርቲያቸው አባላትም ከመንግሥት የቀረበላቸውን የአብረን እንስራ ጥያቄ ተቀብለው በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ መገኘታቸው እንደማይጋጭ በመጥቀስ፣ እንዲያውም የመንግሥት ሥራን ለመከታተል እና እግር በእግር ለመተቸት ጥሩ መደላደል ይፈጥራል ሲሉ አብራርተዋል። በኢዜማ ሕገ ደንብ የመሪው መዋቅር የትይዩ ካቢኔ እንደሚያዋቅር ይደነግጋል። የሕገ ደንቡ አንቀጽ 7.1.9 ፓርቲው ስልጣን ላይ ካልወጣ መሪው፣ ዋና ወይም ዋና ያልሆነ የፓርላማ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ እንደሚሆን ይደነግጋል። ትይዩ ካቢኔ ምንድን ነው? በምርጫ መንግሥት የመመስረት ድምጽ ያላገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትይዩ ካቢኔ/ሚኒስትር የመሰየም ልምድ በተለይ በእንግሊዝ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ሲተገበር የቆየ ነው። በምርጫ የበላይነትን ያገኘው ፓርቲ መደበኛውን የመንግሥት የሥራ አስፈጻሚ ተቋማትን ይዞ ሚኒስትሮችን በመሾም በተግባር የዕለት ከዕለት ኃላፊነቱን ለመወጣት ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚዎች ይህ ሥልጣን ስለማይኖራቸው በፓርቲያቸው መሪ አማካኝነት መንግሥትን ከሚመራው ካቢኔ ትይዩ ተመሳሳይ የሆነ ካቢኔን ሊያዋቅሩ ይችላሉ። በዚህም ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለያዩ የመንግሥት አስተዳደር ዘርፎች ሥልጣን ላይ ካለው መንግሥት በተለየ ያላቸውን አማራጭ እንዲሁም ብቁ ባለሙያዎችን ለሕዝቡ ለማቅረብና ለማስተዋወቅ ይጠቀሙበታል። ትይዩ ካቢኔ/ሚኒስትር ሲዋቀር በኃላፊነት ላይ ካለው መዋቅር ጋር ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ግልባጭ ሲሆን በመንግሥት የሥልጣን መዋቅር ውስጥ ላሉ የሚኒስትርነት ቦታዎች በተመሳሳይ ተቃዋሚዎች የራሳቸውን ሰው ይሰይማሉ። እነዚህም ግለሰቦች የተመደቡባቸውን ቦታዎችን የሚመለከቱ ሕጎች፣ ክስተቶችና ሌሎችም ነገሮች በመያጋጥሙ ጊዜ የፓርቲያቸውን አቋምና አማራጭ ያንጸባርቃሉ። የትይዩ ካቢኔ አባላት በሥልጣን ላይ ካሉት ሚኒስትሮች በተመሳሳይ በፓርቲያቸው የሚሰየሙ በመሆናቸው ትይዩ ሚኒስትር ተብለው በበርካታ አገራት የሚጠሩ ቢሆንም በመንግሥት ውስጥ ተግባራዊ የሚሆን የአስፈጻሚነት ሥልጣን ግን የላቸውም። ' እንዲህ አይነቱ የተቃዋሚ ትይዩ የካቢኔ ሚኒስትሮች ካሏቸው መካከል ዩናይትድ ኪንግደም፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን�� ጃፓን የሚጠቀሱ ሲሆን በርካታ አገራት ውስጥም ይገኛሉ። ከአፍሪካም በደቡብ አፍሪካና ሱዳን ውስጥ የተቃዋሚዎች ትይዩ ካቢኔ አላቸው።" https://www.bbc.com/amharic/news-59854356 +sports ኬንያዊቷ ነርስ በዓለም አቀፍ ውድድር አሸንፋ 250 ሺህ ዶላር ተሸለመች "ኬንያዊቷ ነርስ የዓለም አቀፉን የነርሶች ሽልማት ውድድርን በማሸነፍ 250 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተበረከተላት። በሰሜን ኬንያ መርሳቢት በሚገኘው ሆስፒታል የምትሰራው ነርስ ቀበሌ (Qabale) ዱባ ይህን ሽልማት ያሸነፈችው በምትኖርበት ማኅብረሰብ የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም ባደረገችው ጥረት ነው። በዚህ ውድድር ላይ ከ184 አገራት ከ24 ሺህ በላይ ነርሶች ተሳታፊ ሆነው ነበር። ነርስ ቀበሌ 'ቀበሌ ዱባ ፋውንዴሽን' በሚል መጠሪያ ያቋቋመችው ድርጅት ታዳጊ ሴቶችን ማብቃት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል። ""በድርጅቴ አማካኝነት ልዩ የሆነ ትምህርት ቤት ከፍቻለሁ። ይህ ትምህር ቤት ልጆች እና ወላጆቻቸውን ያስተምራል። እኔ ለተሻለ ነገ ትምህር ቁልፍ ነው ብዬ አምናለሁ"" ብላለች በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ዱባይ ውስጥ በተካሄደው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ። ቀበሌ ያሸነፈችው 'ግሎባል ነርሲንግ አዋርድ' የተካሄደው ሐሙስ ግንቦት 04/2014 ዓ.ም. በዓለም የነርሶች ቀን ላይ ነው። ቀበሌ እአአ 2013 የነርስ ሙያ ትምህርቷን እየተከታተለች ሳለ በኬንያ በተካሄደ የቁንጅና ውድድር ላይ ተሳትፍ፤ 'ሚስ ቱሪዝም ኬንያ 2013' አሸናፊ ሆና ነበር። በዚህ ውድድር አሸናፊ መሆኗን ተከትሎ ባገኘችው ተሰሚነት የሴቶች እኩልነት እና የትምህርት እድል ላይ ብዙ ሰርታለች። በቀበሌ ፋውንዴሽን የተመሰረተው ትምህርት ቤት ቀን ላይ ሴት ልጆችን ከሰዓት በኋላ ደግሞ ወላጆቻቸውን ያስተምራል። ወደ ትምህርት ቤቷ የሚመጡት ጎልማሶች የሚቀስሙት፣ የመጻፍ እና ማንበብ ክህሎትን ብቻ ሳይሆን፤ ሴቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ መሠረታዊ የጤና ትምህርት ይሰጣቸዋል። ከወሊድ በኋላ ለሴቶች መደረግ ስላለበት እንክብካቤ፣ የሥነ-ተዋልዶ ጤና እና ስለሴቶች እኩልነት ስልጠና ይሰጣቸዋል። ይህ የቀበሌ ሥራ በአገሯ እና በተቀረው ዓለም እውቅናን አስገኝቶላታል። እአአ 2019 ላይም ሌላ ዓለም አቀፍ ሽልማትን በማግኘት አሸናፊ ነበረች።" https://www.bbc.com/amharic/61433343 +health ''ኮሮናቫይረስ በሁለት ዓመታት ውስጥ ሊጠፋ ይችላል'' ደ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ገለጹ። ትላንት በሲዊዘርላንድ ጄኔቫ ባደረጉት ንግግር ዳይሬክተሩ ስፓኒሽ ፍሉ በጎርጎሮሳውያኑ 1918 በተከሰተበት ወቅት ለመጥፋት የወሰደበት ጊዜ ሁለት ዓመት ነበር ብለዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም ዓለም አሁን ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ መራቀቅና ከፍተኛ ምርምሮች አንጻር የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ገልጸዋል። ''በሌላ በኩል ደግሞ አሁን ባለው ከፍተኛ የሰዎች ማህበራዊ ትስስር ምክንያት የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ሊሆንም ይችላል'' ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። ''ነገር ግን የሰው ልጅ የደረሰበት የቴክኖሎጂ ርቀት ቫይረሱን ለማስቆም የሚረዳ እውቀት በቶሎ እንዲያዳብር ይረዳዋል'' ካሉ በኋላ አሁንም ቢሆንም ግን ብሄራዊ አንድነትና ዓለማቀፍ ትብብር ላይ ከፍተኛ አጽንኦት ሰጥተው አልፈዋል። የ1918ቱ ስፓኒሽ ፍሉ ቢያንስ 50 ሚሊየን ሰዎችን የገደለ ሲሆን ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን ቁጥር 800 ሺህ ነው። በአጠቃላይ ደግሞ 22.7 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ዶክተር ቴዎድሮስ በመግለጫቸው ላይ የግል መከላከያ መሳሪያዎች ወይም 'ፒፒኢ' ስርጭት በተመለከተ ሙስና እየ���ስተዋለ እንደሆነ ለቀረበላቸውም ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ጉዳዩን ''ወንጀል'' ነው በማለት ገልጸውታል። ''ማንኛውም አይነት ሙስና ተቀባይነት የለውም'' ብለዋል። ''ነገር ግን ከፒፒኢ ጋር የተያያዘ ሙስና ለእኔ በግሌ እንደ ነብስ ማጥፋት ነው የምቆጥረው። ምክንያቱም የጤና ባለሙያዎች ፒፒኢ የማያገኙ ከሆነ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ እየጣልን ነው። በተጨማሪም የሚያገለግሏቸው ሰዎችን ሕይወትም ነው ስጋት ውስጥ የምንከተው'' ብለዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-53872753 +business ለነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት የሆነው የግብጹ መተላለፊያ መዘጋት "በሱዊዝ የመተላለፊያ መስመር ላይ ቆማ የባሕር ላይ ጉዞን ባስተጓጎለችው መርከብ ተነሳ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ታይቷል። በመተላለፊያ መስመሩ መዘጋት ሰበብ የድፍድፍ ነዳጅ አቅርቦት ሊስተጓጎል ይችላል በሚል ስጋት ነው ረቡዕ ዕለት የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የታየበት። በግብጹ የሱዊዝ የባሕር መተላለፊያ ቦይ ዳርቻ ላይ መንቀሳቀስ አቅቷት የዓለማችንን ወሳኝ የባሕር መስመርን የዘጋችውን የጭነት መርከብ ለማንቀሳቀስ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። የግብጽ ባለሥልጣናት እንዳሉት ኤቨር ጊቭን የተባለችው የጭነት መርከብ በመተላለፊያው መስመር ላይ መንቀሳቀስ አቅቷት የቆመችው ማክሰኞ ጠዋት በአካባቢው አሸዋ ያዘለ ከባድ አውሎ ነፋስ በተከሰተበት ጊዜ ነው። በዚህም ሳቢያ ከእስያ ወደ አውሮፓ አስፈላጊ ቁሶችን ጭነው በመተላለፊያው በኩል ለማቋረጥ የመጡ ከቦዩ ሰሜንና ደቡብ በኩል እጅግ በርካታ መርከቦች ማለፊያ አጥተው እንዲቆሙ ተገደዋል። በሰሜናዊ ምሥራቅ አፍሪካ የሚገኘውን ወሳኝ የባሕር ላይ መተላለፊያን ዘግታ የምትገኘው የጭነት መርከብ ባለቤት የሆነው ጃፓናዊ በመርከቧ ምክንያት በዓለም የንግድ ልውውጥ ላይ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ መጠየቁ ተነግሯል። በከባድ ንፋስ ምክንያት መስመሯን ስታ መተላለፊያውን የዘጋችውን መርከብ ለማንቀሳቀስ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ የገለጸው የመርከቧ ባለቤት ""ነገር ግን የተቻላቸውን ጥረት በማድረግ"" ላይ መሆናቸውን ገልጿል። አስካሁን ቢያንስ በመተላለፊያው በኩል ለማቋረጥ እየጠበቁ ያሉ ከ150 በላይ የጭነት መርከቦች ተሰልፈው እየተጠባበቁ መሆኑ ተነግሯል። ሜዲትራኒያንና ቀይ ባሕርን በሚያገናኘው በሱዊዝ መተላላፊያ ቦይ አውሮፓንና አስያን ለማገናኘት አጭሩ መስመር ሲሆን የዓለማችን 12 በመቶ የሚሆነው የንግድ ጭነት የሚያልፈው በዚሁ በኩል ነው። በአሁኑ ወቅት መርከቧን መንገድ እንድትለቅ ለማድረግ ስምንት ጎታች ጀልባዎች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ይህንን ሥራ እያከናወነ የሚገኘው ኩባንያ መተላለፊያውን ለማስከፈት ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ያስጠነቀቀ ሲሆን የመርከቧን ክብደት ለመቀነስ የጫነቻቸውን ኮንቴይነሮች መቀነስ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56506560 +business ኢኮኖሚ፡ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የ200 ብር ኖት ይፋ አደረገች ኢትዮጵያ በገበያ ላይ ባሉት የወረቀት ገንዘቦቿ ላይ ለውጥ ስታደርግ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በወረቀት ገንዘቧ ውስጥ ባለ 200 ብር ኖቶችን መጠቀም ጀመረች። ይህ ይፋ የሆነው ዛሬ [ሰኞ መስከረም 04/2013] ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትዊተር ገጻቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክትና የብር ኖቶቹ ምሰል ነው። በዚህም መሠረተው ከዛሬ ጀምሮ አገሪቱ የ10፣ 50 እና 100 ብር ኖቶቿን ስትቀይር ከዚህ በፊት ያልነበረው የ200 ብር ኖትን ደግሞ መጠቀም ጀምራለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አዲሶቹን የገንዘብ ኖቶች ይፋ መድረግ ያስፈለገው ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናንና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቆጣጠር ያግዛ���።በተጨማሪም አዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች እንዲኖራቸው የተደረጉት የደኅንነት ገጽታዎች አመሳስሎ ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት እንደሚግዙ ተጠቁሟል። በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙት የብር ኖቶች ወደ ዝውውር እንዲገቡ የተደረጉት ከ23 ዓመት በፊት በ1990 ዓ.ም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ እንደነበረ ይታወሳል። ከአጼ ኃይለ ሥላሴ አስተዳደር ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ሥራ ላይ በነበሩ የገንዘብ የወረቀት ገንዘቦች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ለውጥ የተደረገ ሲሆን፤ ወደ አምሳ ዓመታት በሚጠጋው የንጉሡ የሥልጣን ዘመን አራት ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ተደርጓል። ወታደራዊው መንግሥት ዘውዳዊውን ሥርዓት አስወግዶ አገሪቱን መምራት ከጀመረ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በ1969 ዓ.ም የንጉሡ ምስልን የያዙትን የመገበያያ ገንዘቦች ለውጦት ቆይቷል። በተመሳሳይም ኢህአዴግ ደርግን አስወግዶ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላም ለሰባት ዓመታት ያህል ቀድሞ የነበረውን ገንዘብ ሲጠቀም ቆይቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብር ኖቶቹ እንዲቀየሩ አድርጓል። በኢትዮጵያ ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ አገልግሎት ላይ የነበሩት የገንዘብ ኖቶች 1፣ 5፣ 10፣ 50 እና 100 ብር የነበሩ ሲሆን፤ ለረጀም ጊዜ ከፍተኛ ዋጋ ያለው የገንዘብ ኖት 100 ብር ሆኖ ቆይቷል። ቢሆንም ግን በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ ከዋሉት የብር ኖቶች መካከል የ2 ብር እና የ500 ብር ኖቶች ነበሩበት። ስለዚህም በአገሪቱ የወረቀት ገንዘብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የነበረው የብር ኖት ባለ 500 ብር ኖት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ከግብይት እንዲወጣ መደረጉን የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል። ስለዚህም አሁን ከወረቀት የብር ኖቶች መካከል እንዲገባ የተደረገው የባለ 200 ብር ኖት በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሲሆን ወደገበያ ሲገባም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የብር ኖት ለውጥ እንደሚደረግ በተለያዩ መንገዶች ሲነገር የቆየ ሲሆን፤ ከብር ዋጋ መቀነስ ጋር ተያይዞ 500 ዋጋ ያለው የብር ኖት ወደ ገበያ እንደሚገባ አንዳንድ ሰዎች ሲገልጹ ቆይተው ነበር። በአገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች መደረግ ከጀመሩባቸው ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንደሚካሄድ በጉምሩክና በፖሊስ በኩል በተደጋጋሚ የሚወጡ ሪፖርቶች የሚያመለክቱ ሲሆን፤ ይህም ለውጥ ያስፈለገው ይህንኑ ለመከላከል መሆኑ ተነግሯል። https://www.bbc.com/amharic/54144151 +business የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ለምን በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ አያገኝም? ኢትዮጵያውያንን እየፈተነ የሚገኘው የዋጋ ግሽበት በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ እንደማያገኝ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይናገራሉ። ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በመጋቢት ወር የኑሮ ውድነትን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት የዋጋ ግሽበቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር በ34.7 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጾ ነበር። የዋጋ ንረቱ ለምግብነት በሚውሉ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ እና እህሎች፣ ቅመማ ቅመም እና ዘይት፣ ቅቤ እና ቡና እንደሚጨምር ገልጾ ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ከኑሮ ውድነቱ የተነሳ በሚያገኙት ደመወዝ ኑሮን መምራት አዳጋች እንዳደረባቸው ይናገራሉ። ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በአገሪቱ ውስጥ ለሚታየው የኑሮ ውድነት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ቁልፍ መፍትሔ ነው ቢሉም፣ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ግን ከፍተኛ አምራች በሆኑ አካባቢዎች በሰላም እጦት መታመሳቸው አስተዋጽኦ እያደረገ ነው ይላሉ። ���ሁን ያጋጠመው የዋጋ ንረት በቅርብ ጊዜ በተፈጠሩ ምክንያቶች የተከሰተ እንዳልሆነ የሚታመን ሲሆን ለዚህም ለሁለት ዓመታት ያህል የመላውን ዓለም ምጣኔ ሀብት ያቀዛቀዘውን የኮሮናቫይረስወረርሽኝን ተከትሎ  መሆኑን ጫናውን አጉልቶታል። ከዚህ ባሻገር ግን በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል የተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነት፣ በተለያዩ ስፍራዎች ያጋጠሙ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች እንዲሁም የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በነዳጅ፣ በስንዴ እና በምግብ ዘይት ላይ ያስከተኩት ከፍተኛ ጭማሪ ችግሩን አባብሰውታል። ይህ በተደራራቢ ምክንያቶች እየጨመረ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚስተካከል እንዳልሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ሽመልስ አብዲሳም እንዲሁ በአንድ ውይይት ላይ የዋጋ ንረቱ እንዲሁ በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ የሚያገኝ ችግር እንዳልሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ልክ እንደ አቶ ሽመልስ ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዋጋ ግሽበት በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ ያገኛል ማለት “ማታለል ይሆናል” ይላሉ። ሌሎች ደግሞ መንግሥት ወሳኝ የሆኑ አፋጣኝ እርምጃዎችን ከወሰደ በፍጥነት መፍትሔ ሊመጣ ይችላል የሚል ተስፋ አላቸው። ይህ የሃሳብ ልዩነት የሚመነጨው የዋጋ ንረቱ ዋነኛ ምክንያቶች ምንድን ናቸው ከሚለው ነው። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) የግብርና ምርት የሆኑት ፍራፍሬ እና ጥራጥሬ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ አንዳንዶቹ እስከ 100 ፐርሰንት ጭማሪ አሳይተዋል ይላሉ። እናም “በዚህ አገር ውስጥ ኑሮ ያልከበደው ከ5 በመቶ አይበልጥም” በማለት ተናግረዋል። እነርሱም ይላሉ ምሁሩ “በሙስና የከበሩ እና በንግድ ውስጥ በአቋራጭ የበለፀጉ ናቸው” በማለት የችግሩን አስከፊነት ያብራራሉ። ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጀምሮ በኑሮ ዝቅተኛው ወለል ላይ ከሚገኘው ላብ አደሩ ድረስ ለመኖር ከብዶታል ሲሉ የሚያስረዱት ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር)፣ የዋጋ ግሽበቱ ዋነኛ ምክንያት ምርታማ የሆኑ አካባቢዎች ሰላም ማጣታቸው መሆኑን ይገልጻሉ። አክለውም የኢትዮጵያ የውጪ ግንኙነት ፈተና ውስጥ መግባቱ ለኑሮ ውድነቱ አስተዋጽኦ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል እንደሆነ ይጠቅሳሉ። ዶ/ር ጉቱ፣ ልክ እንደ አቶ ሽመልስ ምርት እና ምርታማነት ቀንሷል የሚል አቋም አላቸው። ለዚህም ምክንያት ያሉትን ሲያስቀምጡ፣ በአምራች አካባቢዎች የጦርነት እንቅስቃሴ መኖሩ ነው። ሁለተኛው የኢትዮጵያ የውጪ ግንኙነት በተለይ የኢኮኖሚ ደጋፊ የሚባሉ ምዕራባውያን አገራት ጋር ያለው ግንኙነት ጥሩ አለመሆን፣ አገሪቱን የምታገኛውን የኢኮኖሚ ድጋፍ እንዲሁም ከንግድ ጋር የተያያዘ የውጪ ምንዛሬ አሳጥቷታል ይላሉ። በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ በመጻፍ እና ትንታኔ በመስጠት የሚታወቁት አብዱልመናን መሐመድ በበኩላቸው “መንግሥት በተደጋጋሚ የዋጋ ግሽበቱ ብሎ የሚጠቅሰው ዋናውን ምክንያት ወደ ኋላ ሸሽጎ ነው” ይላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ምርት ደብቆ ዋጋ ጨምሮ ለመክበር የሚደረግ የነጋዴዎች እንቅስቃሴ መንግሥት የሚያነሳው ምክንያት ሲሆን፣ ይህ ግን ዋነኛው ምክንያት ግን አይደለም ይላሉ። “አሁን ላለው የዋጋ ግሽበት ዋነኛ ተጠያቂ መንግሥት ራሱ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ገንዘብ ማተም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ባንኮች ደግሞ ይህንን ገንዘብ ሲያበድሩ በኢኮኖሚ ውስጥ የሚዘዋወረው የብር መጠን ጨምሯል።” ይህ በጦርነት እና በፖለቲካ አለመረጋጋት ምጣኔ ሀብቷ የደከመባት አገር ውስጥ ገንዘብ በገበያ ውስጥ መብዛቱ ኑሮ ያስወድዳል ይላሉ። አብዱልመናን እንደሚሉት አ���ን ያለው የዋጋ ግሽበት መነሻ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የተለቀቀው ገንዘብ ከአገሪቱ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ሁኔታ ጋር ያልተመጣጠ መሆኑ ነው። “መንግሥት ይህንን ማመን አይፈልግም። መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ብዙ ተበድሯል” የሚሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አብዱልመናን ይህ በአፋጣኝ መስተካከል እንዳለበት ይመክራሉ። አብዱልመናን ምርታማ የሆኑ አካባቢዎች ሰላም ማጣታቸው ለምርት መቀነስ ምክንያት መሆኑን ቢስማሙም፣ ኢኮኖሚው ሲቀዛቀዝ በገበያው ውስጥ ያለውን የገንዘብ ፍሰት መቀነስ ሲገባ መንግሥት ተቃራኒውን በማድረግ እንዳባባሰው ያምናሉ። ዶ/ር ጉቱ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የዋጋ ግሽበት “አሁን ባለው ሁኔታ መፍትሔ የለውም። ይህ ተሰምሮበት በግልጽ ልንነጋገርበት ይገባል” ይላሉ። አክለውም “አሁን ባለው ፖለቲካ፣ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ሁኔታ በስድስትም ሆነ በዘጠኝ ወር ውስጥ ለሕዝቡ እፎይታ የሚሰጥ ነገር ማድረግ ይቻላል ብሎ ማሰብ ከባድ ነው።” አገሪቱን ላጋጠማት የዋጋ ግሽበት በአጭር ጊዜ መፍትሔ የሚሆን ተስፋ የለም እንዲሉ ያደረጋቸውም “ችግሩ በጣም ውስብስብ” በመሆኑ የተነሳ እንደሆነ ይናገራሉ። ዶ/ር ጉቱ “የምርታማነት እጥረት ምክንያቱ ፖለቲካ ነው” ብለው “ነገሩ አሁን በተያዘበት መንገድ ደግሞ በአንድ እና በሁለት ዓመት ውስጥ እንኳን ወደ ቦታው የሚመለስ አይደለም” ይላሉ። ምርቶቻቸውን የሚሸጡልን እና የእኛን ከሚገዙ የውጪ አገራት ጋር ያለን ጥሩ ግንኙነት ሻክሯል፤ ይህንንም ወደ ቦታው መመለስ በሁለት እና ሦስት ወር የሚሆን አይደለም ይላሉ። አብዱልመናን በበኩላቸው መንግሥት ይህንን ችግር በሚገባ ተረድቶ በስድስት ወር እና በአንድ ዓመት ውስጥ የከሰተውን የዋጋ ግሽበት ወደ አንድ አሃዝ ለማውረድ ቁርጠኝነት ሊኖረው ይገባል ብለዋል። “የዚህ ችግር መንስዔ ከአቅርቦት ጋር ብቻ የተያያዘ እንደሆነ የሚያስቡ ከሆነ ችግሩ መፍትሔ አያገኝም” የሚሉት አብዱልመናን መንግሥት በራሱ በኩል ጠንከር ያሉ ቁርጠኛ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚያስፈለገው ይመክራሉ። ለዚህም መንግሥት በአፋጣኝ ማድረግ ያለበት “ከብሔራዊ ባንክ የሚበደረውን ገንዘብ መቀነስ ነው፤ ይህ ደግሞ ወገብን ማሰር ይጠይቃል። በተጨማሪ መንግሥት አስፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶችን ማስቆም፣ አስፈላጊ የሚባሉ ፕሮጀክቶችንም ቢሆን ለጊዜው መፍትሔ እስኪገኝ ማዘግየት አለበት” ሲሉ ይመክራሉ። እንዲሁም “የኢትዮጵያን ብር የመግዛት አቅም ከውጪ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ የማውረድ እንቅስቃሴ ወደ አገር ቤት የሚገቡ እቃዎችን ስለሚያንር በአስቸኳይ መቆም አለበት፤ መንግሥት እነዚህን እርምጃዎች የሚወስድ ከሆነ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ውጤት ማየት ይቻላል” ይላሉ አብዱልመናን። https://www.bbc.com/amharic/articles/crgzlx4jqglo +sports ስፖርት፡ እንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጥቁር ስፖርተኛ ሐውልት ያቆመችው መቼ እንደሆነ ያውቃሉ? ጃክ ሌዝሊ፤ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን ማልያ አጥልቆ ታሪክ ከሠራ 100 ዓመታት ሊሞላው ቢሆን እንኳ በቅጡ የሚያስታውሰው ሰው አልነበረም። ይህ የሆነው በቆዳው ቀለም ብቻ ነው። ጊዜው 1925 ነበር። እንግሊዝ ከአየርላንድ ጋር ለነበራት የወዳጅነት ጨዋታ መልማዮች ተጫወቾችን እየመለመሉ ነበር። በወቅቱ ሌዝሊ የፕላይማውዝ ተጫዋች ነበር። መልማዮቹ የሚጫወትበት ሜዳ መጥተው ሲመለከቱ ሌዝሊን ጥቁር ሆኖ ያገኙታል። በዚህም ምክንያት ሌዝሊ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የተሰለፈ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን ታሪክ የሚሠራበትን አጋጣሚ መና ያደርጉበታል። ይኸው ሌዝሊ አሁን ገንዘብ ተዋጥቶለት ሃውልት ሊሰራለት እየታቀደ ነው። እስካሁን ቢያንስ 135 ሺህ ፓ���ንድ ተዋጥቶለታል። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 240 ስፖርተኞችን የሚዘክሩ ሃውልቶች አሉ። ከእነዚህ መካከል 10 ብቻ ናቸው ለጥቁርና አናሳ ቁጥር ላላቸው እንግሊዛውያን ክብር የቆሙት። ከአስሩ መካከል አምስት ለእግርኳስ ተጫዋቾች የቆሙ ሲሆን ጎልፍና ክሪኬት የመሳሰሉ ስፖርታዊ ጨዋታዎች ምንም ዓይነት የጥቁር ግለሰብ ሐውልት የላቸውም። ለምን? ሼፊልድ ዩኒቨርሲቲ የሠራው አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው የጥቁር ስፖርተኞች ሐውልቶች ብቅ ብቅ ማለት የጀመሩት ባለፉት 10 ዓመታት ነው። አብዛኛዎቹ ሐውልቶች በተለይ ደግሞ የእግር ኳስ ተጫዎቾች መታሰቢያዎች ተጫዎቾቹ ጫማ ከሰቀሉ ከ20ና 30 ዓመታት በኋላ ነው የሚሠሩት። አብዛኛዎቹ የጥቁር እግር ኳስ ተጫዋቾች ሐውልቶች ለምን ባለፉት 10 ዓመታት ተሰሩ የሚለውን ጥያቄ የሚመልሱት ዶ/ር ክሪስ ስትራይድ፤ በእንግሊዝ እግር ኳስ መድረክ ከ1980ዎቹ [በአውሮፓውያኑ] በፊት በጣም ጥቂት ተጫዋቾች ነበሩ ይላሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ካላት 240 ሐውልት መካከል 10 ሃውልቶች ለጥቁሮች መድባለች። ከእነዚህ መካከል ዘጠኙ የተገነቡት ባለፉት 10 ዓመታት ነው። ይህ ደግሞ የ1980ዎቹ ተጫዎቾች መታሰብ የጀመሩት አሁን መሆኑን ማሳያ ነው ይላሉ ምሁሩ። እንግሊዝ ውስጥ ከቆሙ የጥቁር ተጫዋቾች ሐውልቶች መካከል ጎልቶ የሚወጣው በአውሮፓውያኑ 2019 የተገነባው የሶስቱ የዌስት ብሮሚች አልቢዮን ተጫዎቾች ሃውልት ነው። ሎሪ ካኒንግሃም፣ ሲሪል ሬጂስና ብንዶን ባስቶን ዌስትብሮም በ1970ዎቹ በእንግሊዝ እግር ኳስ ታዋቂው ቡድን እንዲሆን የጎላ ሚና ተጫውተዋል። እንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጥቁር ስፖርተኛ ሃውልት ያቆመችው በአውሮፓውያኑ 2001 ነው። ይሄም የታዋቂው ቦክሰኛ ራንዲ ቱርፒን ነው። ከዚያ በመቀጠል ሐውልት የቆመለት ጥቁር ተጫዋች የአርሰናሉ ፈረንሳዊ አጥቂ ቲየሪ ሄንሪ ነው። ሴቶች? ዩናይትድ ኪንግደም በዓለማችን በርካታ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ሃውልቶች ያሏት ሃገር ናት። በጠቅላላው በዓለማችን 700 የእግር ኳስ ተጫዋቾች ሐውልት እንደቆመላቸው አንድ ጥናት ይጠቁማል። ነገር ግን ከእነዚህ ሐውልቶች መካከል ለሴት ስፖርተኞች መታሰቢያ የሆኑ ዘንድ የቆሙ ሐውልቶች በጣም ጥቂት ናቸው። ሊሊ ፓር እንግሊዝ ውስጥ ሐውልት የተሰራላት የመጀመሪያዋ ሴት ስፖርተኛ ናት። በ1920ዎቹና 30ዎቹ ዲክ ለተሰኘው የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የተጫወተችው ሊሊ ሃማንቸስተር ውስጥ ሐውልት የተሰራላት ባለፈው ዓመት [2019] ነው። ከሊሊ በተጨማሪ ሃውልት የቆመላቸው እንግሊዛውያን ስፖርተኞች 3 ናቸው። እነዚህም ቴኒስ ተጫዋቿ ዶሮቲ ራውንድ፣ የኦሊምፒክ ሻምፒዮናዎቹ ሜሪ ፒተርስና ኬሊ ሆልምስ ናቸው። ከ1980ዎቹ በኋላ ያለው የእንግሊዝ እግር ኳስ በጥቁር ተጫዎቾች የደመቀ ነው። ያለፈው አስር ዓመትም ጥቁር የእግር ኳስ ፈርጦችን አፍርቷል። የእነዚህን ተጫዎቾች ሐውልት መች እናይ ይሆን? የበርካቶች ጥያዌ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-53763226 +politics ስልጣን በውርስ? ልጆቻቸውን ለስልጣን ያጩት የአፍሪካ መሪዎች የኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሱ ንጌሶ ልጃቸውን ዴኒስ ክሪስቴልን ሚኒስትር አድርገው ሾሙ። ይህንን ሹመት ሚዲያዎች እንዲሁ በቀላሉ አላዩትም። ፕሬዚዳንቱ ልጃቸውን ሊተኩ በዝግጅት ላይ ናቸው በማለትም ነው ሪፖርት ያደረጉት። ስልጣን ዘላለማዊ እንዳለመሆኑ መጠን እንዲህ አይነት መተካካት ሊከሰት ይችላል። ለአርባ አንድ ዓመታት አገሪቷን የገዙት የ77 ዓመቱ ፕሬዚዳንት በቀጣዮቹ ዓመታትም እንዲያስተዳድሩ በመጋቢት ወር ምርጫ አሸንፌያለሁ ብለዋል። በቀጣዮቹ ዓመታትም ስልጣናቸውን አሳልፈው ለመስጠት ምንም አይነት ፍንጭ ባያሳዩም የአሁኑ የስልጣናቸው ወቅት ሲያል�� ልጃቸውን ለመተካት እንደሚያስቡ አንዳንድ ፍንጮች እየተሰሙ ነው። የልጃቸው ዴኒስ ክሪስቴል በኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዚዳንት መሆን አዲስ ነገር አይሆንም፤ በተለይም በማዕከላዊ አፍሪካ አካባቢ እንደሚታየው የልጆች ስልጣን መውረስ ተመሳሳይ እንጂ። በጎረቤት አገር ጋቦን የወቅቱ ፕሬዚዳንት ኦማር ቦንጎ ኦንዲምባ አገሪቷን ከአውሮፓውያኑ 1967 አስከ 2009 የመሯት የኦማር ቦንጎ ልጅ ናቸው። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደግሞ በአውሮፓውያኑ 2001 የተገደሉት የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር የነበሩትን ላውረንት ዴዜሪ ካቢላን በመተካት ልጃቸው ጆሴፍ ካቢላ ለ17 ዓመታት በስልጣን ቆይተዋል። የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ቲዎዲሮ ኦቢያንግ ወደ ስልጣን የመጡት ጨቋኙ አጎታቸውን ፍራንሲስኮ ማሺያስ ንጉዌማን ከስልጣን በማስወገድ ነበር። አጎትየውም በ1979 ወደ ስልጣን የመጡ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ነበሩ። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ፕሬዚዳንቱ ልጃቸው እሳቸውን እንዲተካቸው ምክትል ፕሬዚዳንት አድርገው ሾመውታል። ከአማፂያን ጋር ሲዋጉ ቆስለው ባለፈው ወር ህይወታቸው ያለፈው የቻዱን ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢን በመተካት ልጃቸው ማህማት የሽግግሩ ወታደራዊ ምክር ቤት መሪ ሆኗል። ልጃቸው የጦር ጄኔራል ነው። በካሜሮንም እንዲሁ የስልጣን ሽግግር እንዲመጣ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። እንቅስቃሴው በማን እንደተጀመረ ግልፅ ባይሆንም የ88 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ፓውል ቢያ ልጃቸውን ፍራንክ ቢያን እንዲተኩት ዘመቻም ተጀምሯል። ፕሬዚዳንቱ ለሰባት ዓመት በስልጣን ላይ እንዲቆዩ የተመረጡ ቢሆንም ግማሹንም ጊዜ ገና አላጠነቀቁም። ከፖለቲካ ራሱን አግልሎ በግል ቢዝነስ ላይ ተሰማርቶ የሚገኘው ፍራንክ ከዚህ ዘመቻ ጀርባ እጁ በፍፁም እንደሌለበት የቅርብ ሰዎቹ ይናገራሉ። ነገር ግን ዘመቻውን የመቃወም፣ የማስተባበልም ሆነ አባቱን በስልጣን የመተካት ፍላጎትንም በጭራሽ አላሳየም። ስልጣን መወራረስ አዲስ ነገር አይደለም። በማዕከላዊ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በአሜሪካም የቡሽና የኬኔዲ ቤተሰቦችን እንመልከት። በቅርቡም በኡጋንዳ የወቅቱን ፕሬዚዳንት ዩዌሩ ሙሴቪኒ ልጃቸው ሙሆዚ ካይኔሩግባ በመጪው 2026 በፕሬዚዳንታዊው ምርጫ ተወዳዳሪ እንዲሆን በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች ተከፍተዋል። ነገር ግን ስልጣን የመወራረስ ጉዳይ በምዕራብ አፍሪካ በተለይ የተንሰራፋ ይመስላል። እነዚህ አካባቢዎች በነዳጅ የታደሉ ከመሆናቸው አንፃር የፖለቲካው ትስስር፣ የፔትሮሊየም ምጣኔ ሀብትና የኢምፓየር ግንባታ የተቆራኙ ናቸው። አመራሮቹ የነዳጁንም ምንጭ መቆጣጠር ስለሚያስችላቸው በውስጣቸውም መቆራቆዝ በርካታ ጊዜ ይፈጠራል። ለምሳሉ ያህል በኦቢያንግ ቤተሰቦች መካከል ግጭቶች አንዳሉ ይሰማል። አንዳንድ የቤተሰብ አባላት የፕሬዚዳንቱ ልጅና የነዳጅ ሚኒስትሩ ገብርኤል ምቤጋ ኦቢያንግ ሊማ አማራጭ ፕሬዚዳንት እንዲሆን ይፈልጋሉ። ጋቦን፡ የቤተሰብ ቁርሾ በአውሮፓውያኑ 2016 በጋቦን ምርጫ በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የቀድሞው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ጂን ፒንግ ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎን ያፋጠጠ ነበር። እነዚህ ፖለቲከኞች የጋብቻ ዝምድና አላቸው። የፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ እህት ፓስካሊን የጂን ፒንግ የቀድሞ ባለቤት ናት፤ ይህም ማለት ፕሬዚዳንት አሉ የጂን ፒንግ ሁለት ልጆች አጎት ናቸው። ነገር ግን ጂን ፒንግ በዋነኝነት የፖለቲካ አጀንዳቸውን ወደፊት በማምጣት በአገሪቱ የለውጥና እውነተኛ ዲሞክራሲ መሪ ነኝ በማለት ነበር በተቃዋሚ መሪነት በምርጫ የተወዳደሩት። በዚያን ወቅት በነበረው ምርጫ የተሸነፉት ጂን ፒንግ ከአምስት ዓመታት በኋላም መሸነፋቸውን አይቀበሉትም። በወቅቱ በርካቶች መራራ ያሉት የምርጫ ውድድርና የተአማኒነት ጥያቄ ያነሱበት ይህ ምርጫ በመጨረሻም ፕሬዚዳንት አሊን አሸናፊ አድርጓቸዋል። ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ ወደኋላ እየተመለከቱ አይደለም። በአሁኑ ወቅት ልጃቸውን ኑረዲን ቦንጎ ቫለንቲንን የፕሬዚዳንት ጉዳዮች ዋነኛ አስተባባሪ አድርገው በአውሮፓውያኑ 2019 ሾመውታል። ልጃቸውን ከመሾማቸው ከዓመት በፊት ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ ስትሮክ ታመው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለህክምና አቅንተው ነበር። በዚያን ወቅት የአገሪቱ ኤታማዦር ሹም ብሪስ ላክሩቼ አሊሃንጋ ፕሬዚዳንቱን ተክተው ሥራቸውን ሲያከናውኑ ነበር። ፕሬዚዳንቱም ከህመማቸው አገግመው ተመለሱ ኤታማዦር ሹሙን ከስልጣናቸው አነሷቸው፤ በኋላም ከሥራ ተባረሩ በሙስና ወንጀልም በቁጥጥር ስር ዋሉ። ኤታማዦር ሹሙ ግን ይህንን ይክዳሉ። በአሁኑ ወቅት ልጃቸው ኑረዲን በዚህ ቁልፍ በሚባል ቦታ ላይ ተቀምጧል። አባቱንም በየቀኑ ያገኛል። የፕሬዚዳንቱንም ፍላጎቶች ለማስፈፀምና በጉዳዮች ላይ ለመወሰን ስልጣን አለው። በተለይም የፕሬዚዳንት አሊ የጤና ሁኔታ እያሽቆለቆለ ነው በሚባልበት በአሁኑ ወቅት ኑረዲን በስልጣን ሊተካቸው ይችላል የሚሉ ጉዳዮች ጎልተው እየወጡ ነው። ኑረዲን በዩናይትድ ኪንግደም ስመ ጥር በሆነው ኤተን ኮሌጅ ነው የተማረው፤ ወጣትነቱ እንዲሁም ያለው የዘመናዊነት ሁኔታው የብዙዎችን ቀልብ ስቧል። የፈረንሳይ የሙስና ምርመራ ወደ ቻድ ስንመለስ ደግሞ ለሦስት አስርት ዓመታት አገሪቱን የመሯት ኢድሪስ ዴቢ የሞቱት ከአንድ ወር በፊት ነው። በእሳቸው ቦታ የተተካውን ልጃቸውን ማሃማት ከፍተኛ ተግዳሮቶች ተጋርጠውበታል። በሽግግሩ ምክር ቤት ውስጥ ያሉትን ወታደራዊ አጋሮቹ ጋር በመሆን በአገሪቱ የቆየን ወታደራዊ ልማድ ለማስቀጠል የጎሳዎች ድጋፍ ማግኘት አለበት። በሌላ በኩልም በአገር ውስጥና በዓለም አቀፉም ማኅበረሰብ በኩል ለፖለቲካ ውይይቶችና ትርጉም ያለው ዲሞክራሲ እንዲመጣ ጥረት እንዲያደርግ ከፍተኛ ጫና እየደረሰበት ነው። በኢኳቶሪያል ጊኒ ደግሞ ሌላኛው ስጋትና ሁኔታዎችን የተወሳሰበ ያደረገው ፈረንሳይ በአመራሮቹ ላይ በማነጣጠሯ ነው። የአገሪቷ መሪዎች ከሙስና በተገኘ ገንዘብ ንብረቶች በፈረንሳይ ገዝተዋል በሚልም የሙስና ምርመራ ጀምሬያለሁ ብላለች። የቦንጎም ሆነ የንጌሶ ቤተሰቦች በዚህ ኢላማ ሆነዋል። 13 የሚሆኑ የነዚህ ቤተሰብ አባላት እንዲሁም በቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር ቦንጎ ቤት ጠበቃ ሆኖ ይሰራ የነበረና በርካታ የፈረንሳይ ዜጎች የወንጀል ምርመራ ተከፍቶባቸዋል። በአውሮፓውያኑ 2015 የፈረንሳይ ዳኛ በፓሪስ የሚገኙ ሁለት ንብረቶች በመንግሥት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። የነዚህ ንብረት ትክክለኛ ባለቤቶችም የሳሱ ንጌሶ የወንድም ልጅ ዊልፍሪድ ንጌሶ ናቸው በሚል ነው። ከዚህም በተጨማሪ ቅንጡ የሚባሉ 15 መኪኖችም እንዲሁ እንዲያዙ ተወስኗል። ዊልፍሪድም ይፋዊ የሆነ ምርመራ ተከፍቶበት ነበር። በአውሮፓውያኑ 2016 ሳሱ ንጌሶ የተከፈተባቸው ምርመራ ውድቅ እንዲሆን የሞከሩ ሲሆን ይህንን ጉዳይም ቃል አቀባያቸው ፕሬዚዳንቱን ለማሳጣት የሚደረግ ትልቅ ማጭበርበር ነው በማለት ወርፈዋቸዋል። የፈረንሳይ ዳኞች ግን በዚህ ፍንክች አላሉም። በአውሮፓውያኑ 2017 የፕሬዚዳንቱ ልጅ ጁሊየንና ባለቤቷ ጋይ ጆንሰን፣ ሌላ የወንድም ልጅ ኤድጋር፣ የባለቤታቸው እህት ካትሪን ኢግናንጋ ምርመራ ተጀምሮባቸዋል ተብሏል። በአውሮፓውያኑ 2008-09 አጠራጣሪ በተባለው 22.4 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ዝውውርም መሪዎቹ ተወንጅለዋል። ኢኳቶሪያል ጊኒና ቅንጡ መኪኖቿ የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንቱ ልጅ ���ላኛው ቲዎዶሮ በፓሪስ የሚገኘው ቅንጡ ቤቱ በአውሮፓውያኑ 2012 በፖሊስ ተከበበ። ሁለት ቡጋቲ ቬይሮንስና ሮልስ ሮይስ ፓንቶም የተባሉት መኪኖቹም ተያዙ። መኪኖቹን በመያዝ ብቻ አልበቃም ቲዎዶሮ ራሱ 30 ሚሊዮን ዩሮ ቅጣት እንዲከፍሉ ታዘዘ። በዚህ የተበሳጨው መንግሥት ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ወሰደው። መከራከሪያውም ፎች ማንሽን የተባለው በፈረንሳይ የሚገኘው ቤት 107 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚያወጣና የአገሪቱም ኤምባሲ እንደሆነና ከምንም ነገር የሚጠብቃቸው የዲፕሎማሲያዊ ጥበቃ አለ በሚልም ነው። ነገር ግን ባለፈው ታኅሣሥ ፍርድ ቤቱ ይህንን መከራከሪያ ውድቅ አድርጎታል። የፈረንሳይ ፓርላማ በበኩሉ እነዚህ የተያዙ ንብረቶች በአገሪቱ ለሚገኙ መሰረተ ልማቶች ሊውሉ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ እያረቀቀ ነው። እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ግን በደንብ ሊታሰብባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው። በስዊዘርላንድ፣ ጁኔቫ የሚገኙ ባለስልጣናትም እንዲሁ በቴዎዶርና በሁለት ግለሰቦች ላይ ገንዘብ በማዘዋወር፣ የሕዝብ ሃብትን ያላግባቡ በመጠቀም በሚል ክስ ከፍተው ከሁለት ዓመት በፊትም ነው ጉዳዩ የተቋጨው። በዚህም መሰረት 25 ቅንጡ መኪናዎች አንዲሸጡ ታዘዘ ገንዘቡም ለእርዳታና ለልማት ድርጅቶች እንዲውል ተወሰነ። ከተሸጡት መኪኖችም መካከል ላምቦርጊኒ ቬኖኖ ሮድስታል በ9.1 ሚሊዮን ዶላር፣ ጥቁር ካርበን ኮይኒግሴግ 5.2 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠዋል። ሰባት ፌራሪዎች፣ ሁለት ላምቦርጊኒ፣ አምስት ቤንትሊ፣ ማዘራቲ፣ አስተን ማርቲን፣ ማክላረን የተባሉት መኪኖች በ26 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ተሸጡ። ግማሹ የተገዙት ስማቸው ያልተጠቀሰ ግለሰብ ሲሆን እሳቸውንም ወክሎ አንድ ጀርመናዊ ነው የተጫረተው። ነገር ግን ከአምስት ወራት በኋላ በኢኳቶሪያል ጊኒ መዲና ማላቦ ቲዎዶሮ በጨረታ ከተሸጡት አንደኛዋ መኪና ሲነዳ ታየ፤ ፎቶውንም በኢንስታግራም ቢለጠፍም በኋላ ግን አጥፍቶታል። ምንም እንኳን በነዚህ አገራት ስልጣን በውርስ የማስተላለፍ ሁኔታዎች ቢታይም እየተቀየረች ባለችው አፍሪና ለውጥን በሚሻ ወጣት መካከል የዘለቄታዊነቱን ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል። *የዚሀ ፅሁፍ አዘጋጅ በለንደን የሚገኘው ቻታም ሃውስ የአፍሪካ ፕሮግራም አማካሪው ፓውል ሜሊ ናቸው https://www.bbc.com/amharic/news-57359923 +business በሊባኖስ የወደቀ ኢኮኖሚ የተመሰሉት የፋሲካ ብስኩቶች "የሰዎች የምግብ አዘገጃጀትና አለባበስ በአብዛኛው ያላቸውን የኢኮኖሚ ደረጃ ያመላክታል። የግለሰብን ብቻም ሳይሆን የአገር ኢኮኖሚንም ማንፀባረቂያ መስታወት ነው። ሰው ኑሮውን ይመስላል እንደሚባለው ማለት ነው። ታዲያ ሊባኖሳውያን በአገራቸው ኢኮኖሚ የተመሰሉ የፋሲካ ብስኩቶችን አዘጋጅተዋል። በሊባኖስ የፋሲካ በዓልን ለሚያከብሩ የግሪክ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ባህላዊ ‘ማሞል’ ብስኩት መስራት ወይም መግዛት የተለመደ ነው። ማሞል የተሰኘው ይህ ብስኩት በውስጡ ቅቤ፣ ለውዝ፣ ፍራፍሬ፣ ሥጋ እየተሞላ የሚዘጋጅ ነው። ሊባኖሳውያን በዚህ ጣፋጭ ምግብ ይኮራሉ። በፋሲካ በዓል፣ በኢድ አልፈጥር እንዲሁም በኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ከማዕዳቸው የማይታጣ ምግብ ነው። በሊባኖስ ማሞል ብስኩትን አለማዘጋጀት ማለት በፋሲካ ዶሮ ወጥ፤ በኢድ አልፈጥር ገንፎን እንዳለመስራት ማለት ነው። ይህ ብስኩት በዓውድ ዓመት ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል። በዘንድሮው የፋሲካ በዓል ግን ነገሮች ከወትሮው የተለየ ሆነዋል። ሪታ ስታምቦሊ የግሪክ ኦርቶዶክስ አማኝ ስትሆን ነዋሪነቷ ከቤሩት አንድ ሰዓት ያህል በመኪና በምታስጉዘው ዛህል ነው። ዘንድሮ እያዘጋጀች ያለችው ሞሞል ከወትሮው ለየት ይላል። ብስኩቱን ለመስራት ያድቦለ��ለችው ሊጥ ውስጥ የቴምር ፍሬ እያስገባች ነው ያዘጋጀቸው። ለወትሮው ሥጋ ነበር የምትጨምርበት። “አሁን ኢኮኖሚው ወድቋል። ድህነት ውስጥ ነው ያለነው። ጉዟችን ወደ ኋላ ሆኗል። በፊት እንደምንኖረው እየኖርን አይደለም፤ ስጋ የምናገኘው በወር አንድ ጊዜ ነው” ትላለች። ሪታ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ ፀሐፊ ሆና ነው የምትሰራው። የአገሪቷ ኢኮኖሚ መላሸቅ ልክ እንደ ሌሎቹ ሊባኖሳዊያን የደመዋዟን የመግዛት አቅም አሳንሶታል። “ሁለት ልጆች አሉን። በኪራይ ቤት ነው የምንኖረው። እኔ እና ባለቤቴ እንሰራለን ግን ይህም ሆኖ ገቢያችን በቂ አይደለም” ትላለች። ምንም እንኳን ብስኩቷ ውስጥ መጨመር የምትወደው ፒስታሽዎ የተባለ ፍሬ ቢሆንም አሁን ግን ይህን ማድረግ አልቻለችም። ፒስታሽዎ እንደ ለውዝ ያለ ጠንካራ ሽፋን ያለው ውድ ፍሬ ነው። በዚህ ዓመት ግን ይህንን አትሰራም። የምትሰራው የማሞል ብስኩት ቁጥርም ከዚህ ቀደም ከምታደርገው አነስተኛ ነው። አሁን ብስኩቱ ውስጥ የምትጨምረውን የፒታሽዎ ፍሬ በቅቤ ተክታዋለች። ይህም ቢሆን ግን ዋጋው ቀላል አይደለም። ""ቅቤው የደመወዜን አንድ ሦስተኛ ይወስዳል"" ትላለች። በርካታ ሊባኖሳዊያን የምግብ ባንክ ጠባቂ ሆነዋል። የሶሪያ ስደተኞችን እና ለአደጋ የተጋለጡ ሊባኖሳውያንን የሚደግፈው የልማትና የእርዳታ ድርጅት የሚቀርብለት የእርዳታ ጥያቄ ጨምሯል። ሁኔታውም በጣማ የተባባሰ ሆኗል። በአገሪቷ ውስጥ ባለው ፖለቲካ እና አለመስማማት እርዳታዎችም ባክነዋል። እአአ በ2020 መጨረሻ ከኢራቅ የተገኘ የእርዳታ ስንዴ ለተረጂዎች መሰራጨት ሲገባው ስታዲየም ውስጥ አላግባብ መቀመጡ ተነግሯል። በዚያው ዓመት ነሃሴ ወር ላይ በቤሩት ወደብ ላይ የተከሰተውን ፍንዳታ ተከትሎ ከሲሪላንካ የተገኘ የሻይ ቅጠል ድጋፍም ለፕሬዚደንቱ ጠባቂዎች ቤተሰቦች ተሰጥቷል። በአገቷ ያለውን አለመረጋጋት ተከትሎ የፖለቲካ ፓርቲዎች የራሳቸውን እርምጃ እየወሰዱ ነው። ሂዝቦላህ እና የጦር ድርጅቶች የራሳቸውን የገበያ ማዕከል ከፍተዋል። ነገር ግን በርካሽ የሚሸጡት ለራሳቸው አባላትና ደጋፊዎቻቸው ነው። ታዲያ በቤሩት ዝነኛው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና 'ሊባነን ፎር ቱሞሮው' በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት አምባሳደር የሆነው ጆሴፍ ታውክ ላለፉት ሦስት ቀናት ከቡድኑ ጋር ሆኖ 9 ሺህ የሚሆኑ ማሞል ብስኩቶችን አዘጋጅቷል። ብስኩቶቹን በማዘጋጀት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ይሰጣሉ። የመድሃኒትም ድጋፍ ያደርጋሉ። አገሪቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የአራት ቀናት ቤት ውስጥ የመቀመት ገደብ ጥላለች። በመሆኑም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የፋሲካ በዓልን ፤ ሙስሊሞችም የኢፍጣር ሥነ ሥርዓትን የሚያከብሩት ቤታቸው ሆነው ያላቸውን ነገር እየተቃመሱ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-56962261 +health ኮሮናቫይረስ ፡ በቫይረሱ የተያዙ በመጀመሪያዎቹ ቀናት የማስተላለፍ እድላቸው ሰፊ መሆኑ ተጠቆመ "በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ምልክቶች በማያሳዩባቸው የመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ውስጥ ቫይረሱን የማስተላለፍ ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን አንድ ጥናት ጠቆመ፡፡ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ሳይንቲስቶች ከሆነ ቫይረሱ ያለባቸውን ቀደም ብሎ በለይቶ ማቆያ ማስገባት ስርጭቱን ለማስቆም ወሳኝ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ የጥናት ውጤቱ በላንሴት ማይክሮብ ላይ ታትሟል። ግለሰቦች የማስተላለፍ ዕድላቸው በብዙ ነገሮች ላይ የተመረኮዘ ሲሆን ራሱን የሚያባዛ ቫይረስ እና በሰውነታቸው ውስጥ ያለው የቫይረስ መጠን ስርጭቱን ከሚወስኑት መካከል ናቸው። አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሰዎች የበሽታ ምልክቶች ከማሳየታቸው በፊት እና በቫይረሱ በተ���ዙ የመጀመሪያው ሳምንት በጣም አስተላላፊ ናቸው፡፡ በሆስፒታል ውስጥ የበሽታው ምልክት ያለባቸውንና ቫይረሱ የተገኘባቸውን ጨምሮ ሳይንቲስቶች በኮቪድ-19 ላይ 79 ዓለም አቀፍ ጥናቶችን መርምረዋል። ተመራማሪዎች ኢንፌክሽኑ ከጀመረ እስከ ዘጠኝ ቀናት ድረስ ከተወሰዱ የጉሮሮ ናሙናዎች ውስጥ ዋነኛ ቫይረሶችን መለየት እና ማባዛት ችለዋል፡፡ ምልክቶቹ በጀመሩበት ጊዜ ወይም በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍተኛ የቫይረስ ስርጭት እንደሚኖር ከሰዎች የጉሮሮ ናሙና ማወቅ ችለዋል። ምልክቶቹ ከጀመሩ በአማካይ እስከ 17 ቀናት በአፍንጫ እና በጉሮሮ ናሙናዎች ንቁ ያልሆኑ የቫይረስ ቁርጥራጮች ተገኝተዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ እነዚህ ቁርጥራጮቻቸው ከዘጠኝ ቀናት በላይ ቢቀጥሉም አብዛኛዎቹ ሰዎች የማስተላለፍ ዕድላቸው አነስተኛ ነው ብለዋል፡፡ የሴንት አንድሪውስ ዩኒቨርስቲ ባልደረባው ዶ/ር ሙጌ ሴቪክ ለቢቢሲ እንደገለጹት ግኝቶቹ ሰዎች ገና በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት በጣም አስተላላፊ እንደሆኑ አሳይተዋል፡፡ ""ሰዎች የሕመም ምልክቶችን እንዳሳዩ እንዲለዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ምርመራ ውጤቶችን በሚያገኙበት ጊዜ በጣም አስተላላፊ የሚሆኑበትን ደረጃቸውን ያልፉ ይሆናል።"" ""ስለዚህ አንዳንድ ሰዎች ወዲያውኑ ራሳቸውን ያለዩበትን ምክንያት በመመልከት ይህንን እንዲያደርጉ ልንረዳቸው ይገባል"" ብለዋል፡፡ ጥናቱ ምልክት የማያሳዩ ሰዎችን አላካተትም። ሆኖም ሌሎች ጥናቶችን እንደሚያስጠነቅቁት ሰዎች የበሽታ ምልክቶች ከማሳየታቸው በፊትም አስተላላፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ እና ምንም ዓይነት የበሽታ ምልክት ሳይኖር ቫይረሱ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ የእንግሊዝ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ካላቸው ወዲያውኑ ራሳቸውን ቢያንስ ለ 10 ቀናት ማግለል አለባቸው፡፡" https://www.bbc.com/amharic/55026691 +sports ሞሮኮ በስፔን ላይ ድል ስትቀዳጅ፣ ሮናልዶን ተክቶ የገባው 3 ጎሎችን አስቆጠረ ትናንት በተደረጉ የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ግጥሚያዎች ያልተጠበቀ ውጤት ተመዝግቧል። አፍሪካዊቷ ሞሮኮ የእግር ኳስ ኃያሏ ስፔንን በማሸነፍ የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀላቅላለች። እአአ 1990 ላይ ካሜሮን፣ እአአ 2002 ላይ ሴኔጋል እንዲሁም እአአ 2010 ላይ ጋና ሩብ ፍጻሜን የተቀላቀሉ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ሲሆኑ ሞሮኮም ይህን ታሪክ መጋራት ችላለች። ሁለቱ ቡድኖች ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ውድድር ያለ ጎል በመጠናቀቁ ወደ ተጨማሪ ሰዓት አምርተው ነበር። ቡድኖቹ በተጨማሪ ሰዓትም ጎል ማስቆጠር ባለመቻላቸው በፍጹም ቅጣት ምት መለየት ግድ ሆኗል። ስፔኖች የመጀመሪያዎቹን ሦስት ፍጹም ቅጣት ምቶች ስተዋል። ድንቅ ሆኖ ያመሸው የሞሮኮ ግብ ጠባቂ ያሲን ቦኖ ሁለት ፍጹም ቅጣት ምቶችን ማዳን ችሏል። ማድሪድ ተወልዶ ስፔን ያደገው ሞሮኳዊው አሽራፍ ሃኪሚ ወሳኟን ፍጹም ቅጣት ምት ወደ ጎል በመቀየር ስፔንን ከኳታር አሰናብቷታል። ለዋንጫ ከተገመቱ አገራት መካከል አንዷ የነበረችውን ስፔን ያሸነፉት ሞሮኮዎች ከድላቸው በኋላ ብዙ አድናቆት እየደረሳቸው ይገኛል። የሞሮኮ ንጉስ መሐመድ አምስተኛ ሳይቀሩ ስልክ አንስተው መላው ቡድኑን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። ትናንት ምሽት በተካሄደው ሌላኛው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ፖርቹጋል ስዊዘርላንድን በሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ችላለች። ፖርቹጋል 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ተጋጣሚዋን ብትረታም ትልቁ መነጋገሪያ ሆኖ ያመሸው የክርስቲያኖ ሮናልዶ በተቀያሪ ወንበር ላይ መቀመጥ ነው። የፖርቹጋል አሠልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ ቡድናቸው ከስዊዘርላንድ ጋር በነበረው ጨዋታ ሮናልዶን በተቀያሪ ወንበር ላይ አድርገው ጨዋታቸውን ጀምረዋል። በምድብ ድልድሉ ፖርቹጋል የመጨረሻውን ጨዋታ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ስታደርግ ሮናልዶ ተቀይሮ ሲወጣ ባሳየው ምልክት ደስተኛ እንዳልነበሩ አሠልጣኙ አልሸሸጉም። ሮናልዶ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ትልቅ ግጥሚያዎችን ሲያደርግ በተቀያሪ ወንበር ላይ ሆኖ ጨዋታ የተጀመረው እአአ 2008 ላይ ነበር። በሮናልዶ ተተክቶ ሜዳ የገባው ጎንሳሎ ራሞስ ሦስት ጎሎችን አስቆጥሮ “ሃትሪክ” ሰርቷል። የ21 ዓመቱ የቤነፊካ አጥቂ ራሞስ ሦስት ጎሎችን ያስቆጠረው በዚህ የዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሰለፍ ዕድል ካገኘ በኋላ ነው። ሮናልዶ በ74ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ወደ ሜዳ ሲገባ በደጋፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ሮናልዶ ተቀይሮ ከገባ በኋላ በጨዋታ እንቅስቃሴ ጎል ቢያስቆጥርም ግቧ ከጨዋታ ውጪ ተብላ ተሽራለች። https://www.bbc.com/amharic/articles/c88k1mxdkvro +politics ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች ፑቲን ላይ ማዕቀብ እንደሚጣል ባይደን አስጠነቀቁ "ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ ማዕቀብ እንደሚጣል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስጠነቀቁ። ሩስያ በደቡብ ምዕራብ ድንበሯ ያለችውን ዩክሬንን ከወረረች ""ትልቅ ቅጣት"" እንደሚከተል ባይደን አሳስበዋል። ሌሎች የምዕራቡ ዓለም አገራትም ሩስያን እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። ሩስያ ዩክሬንን የመውረር ዕቅድ የለኝም ብላ አሜሪካ እና ሌሎችም አገራት ""ነገሩን እያጋጋሉ"" ነው ስትል ትወቅሳለች። ሩስያ ይህን ብትልም ድንበሯ ላይ ወደ 100,000 ወታደሮች አሰማርታለች። ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች በቀጥታ ፑቲን ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ እንደሚጣል ነው ባይደን ያስጠነቀቁት። ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች ""ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ትልቁ ወረራ"" ይሆናል ብለዋል። የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) በምሥራቅ አውሮፓ ጠንካራ ክትትል እንደሚያደርግ ጠቅሰው ""የትኛውም የኔቶ አባል ጥቃት ሲሰነዘርበት ኔቶ ይከላከለዋል"" ሲሉ ተደምጠዋል። አሜሪካ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን የመላክ ዕቅድ እንደሌላት ባይደን በተደጋጋሚ ተናግረዋል። ሩስያ በበኩሏ አሜሪካ እና ኔቶ ዩክሬንን በምዕራባውያን አማካሪዎች እና በጦር መሣሪያ ""አጥለቅልቀዋታል"" ስትል ከሳለች። በተባበሩት መንግሥታት የሩስያ ቋሚ መልዕክተኛ ""ሩስያ ድንበር አካባቢ አሜሪካውያኑ ምን እያረጉ እንደሆነ ግልጽ አይደለም"" ሲል መግለጫ አውጥቷል። ሩስያ የነዳጅ መስመር የምትቆርጥ ከሆነ ዝግጁ ሆኖ ለመጠበቅ የመላው ዓለም ነዳጅ አቅራቢዎች ወደ አውሮፓ የሚልኩትን ነዳጅ እንዲጨምሩ ባይደን ጠይቀዋል። የአውሮፓ ሕብረት ከሚያስገባው ድፍድፍ ነዳጅ አንስ ሦስተኛውን የምትልከው ሩስያ ናት። የዩናይት ኪንግደሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፤ የምዕራቡ ዓለም አገራት ሩስያ ላይ ""ከባድ"" የምጣኔ ሀብት ማዕቀብ እንደሚጥሉና አገራቸውም የኔቶ አባላትን ለመደገፍ ወታደሮች እንደምትልክ ተናግረዋል። ሩስያ ከዓለም አቀፉ የክፍያ ሥርዓት ስዊፍት እንደምትታገድ ቢናገሩም፤ በምላሹ የሩስያ ባለሥልጣናት አውሮፓ የሩስያን ምርቶች ገዝታ የምትከፍልበት ሥርዓት አይኖራትም ሲሉ አስፈራርተዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከሩስያ ጋር ውይይት በማድረግ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። አሜሪካ 8,500 ወታደሮቿ በተጠንቀቅ እንዲጠብቁ ማዘዟን ሩስያ ""እጅግ አስጊ"" ብላዋለች። አሜሪካ ከሩስያ በተጨማሪ የሩስያ አጋር የሆነችውን ቤላሩስም አስጠንቅቃለች። ሩስያ በበኩሏ ኔቶ ወደ ምሥራቅ የሚያደርገው መስፋፋት ያሰጋኛል ትላለች። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲማይር ዘለንስኪ በቴሌቭዥን ቀርበው ሕዝባቸውን ለማረጋጋት ሞክረዋል። ""ሁሉም ነገር ቀላል ��ይሆንም ተስፋ አለ። አካላችሁን ከቫይረስ፣ አእምሯችሁን ከውሸች፣ ልባችሁን ከፍርሃት ተከላከሉ"" ብለዋል። ሩስያ እአአ በ2014 ክሬሚያን በግድ የግዛቷ አካል አድርጋለች። ክሬሚያ በሩስያ ግዛት ውስጥ ለመቆየት በሕዝበ ውሳኔ ስትወስን ዩክሬን ግን ሕገ ወጥ ስትል ሐሳቡን ውድቅ አድርጋለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-60136557 +health ኮሮናቫይረስ፡ ስለ አዲሱ የኮቪድ ዝርያ እስከ አሁን የምናውቃቸው 10 ነጥቦች ኮቪድ-19 ክትባት ተገኘለት እፎይ መባል በጀመረ ገና በሳምንቱ ከወደ ብሪታኒያ መጥፎ ዜና ተሰምቷል፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ አዲስ ዝርያ ያለባቸው ሰዎች መገኘት ነው ዜናው፡፡ በፈረንጆች ገና ይህ ያልተጠበቀ ዜና መሰማቱ ለጊዜው አውሮጳን እያመሳት ነው፡፡ ከብሪታኒያ የሚመጡ አውሮፕላኖች ላይ እግድ እያወጡ ያሉት የአውሮጳ አገራት ድንበራቸውን ጠርቅመው እየዘጉት ነው፡፡ 1ኛ፡- በብሪታኒያ በተለይም በሎንደንና አካባቢው እስከዛሬ ታይቶ የማይታወቅ የተህዋሲው ናሙና ተገኝቷል፡፡ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን በታመሙ ሰዎች ላይ በብዛት የሚታየው የቫይረስ ዓይነትም ይኸው ዝርያ መሆኑ ድንጋጤን ፈጥሯል፡፡ 2ኛ፡- ይህ የቫይረስ ዝርያ ሌሎች የተህዋሲ ዝርያዎችን በፍጥነት እየተካ ቦታውን እየያዘ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ 3ኛ፡- ራሱን የሚያባዛበት መንገድ ለየቅል መሆኑ ምናልባት ለቁጥጥር ያስቸግር ይሆን የሚል ስጋትን ጨምሯል፡፡ ከመተንፈሻ አካል ውጭ ያሉ ሴሎችንም ራሱን እየለወጠ የማጥቃት አቅም ሊኖረው ይችል ይhoን የሚል ስጋትም አለ፡፡ 4ኛ፡- ለመጀመርያ ጊዜ ይህ የተህዋሲ ዝርያ የተገኘው በመስከረም ወር ነበር፡፡ በጥቅምት ወር ሎንዶን አካባቢ በኮቪድ ከተያዙት ሲሶዎቹ የዚህ ተህዋሲ መልክ ተገኘባቸው፡፡ በታኅሣሥ ወር ደግሞ 75 ከመቶዎቹ ታማሚዎችን የለከፈው ይህ ልዩ ተህዋሲ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ 5ኛ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ቅዳሜ ዕለት በሰጡት መግለጫ ይህ ተህዋሲ እስከዛሬ ከነበረው ቫይረስ ጋር ሲወዳደር የመዛመት ዕደሉ በ70 ከመቶ የፈጠነ ነው ብለዋል፡፡ 6ኛ፡- አዲሱ የተህዋሲ ዝርያ በጊዜ ሂደት ራሱን ቀይሮ ይሁን ወይም ከሌላ ቦታ መጥቶ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። 7ኛ፡- አዲሱ የተህዋሲ ዝርያ በመላው ብሪታኒያ የተሰራጨ ቢሆንም አሁን ክምችቱ በብዛት የሚኘው በለንደንና አካባቢው ነው፡፡ ከለንደን በተጨማሪ በደቡብ ምሥራቅና በምሥራቅ ኢንግላንድም እንዲሁ በስፋት ተመዝግቧል፡፡ 8ኛ፡- ኔክስትስትሬይን የተሀዋሲ ዝርያዎችን የዘረ መል ኮድ የሚመዘግብ ድርጅት ሲሆን፣ ይህ ልዩ የተህዋሲ ዝርያ ከብሪታኒያ ወደ ዴንማርክና አውስትራሊያ መዛመቱን ተናግሯል፡፡ ኔዘርላንድና ጣሊያንም ይህ አዲሱ የተህዋሲው ዝርያ አገራቸው መግባቱን አረጋግጠዋል፡፡ 9ኛ፡- ይህ ልዩ የተህዋሲ ዝርያ ቅንጣት በደቡብ አፍሪካም ተገኝቷል የተባለ ሲሆን በኋላ ላይ የወጡ መረጃዎች ግን ከዚህ ብሪታኒያ ተገኘ ከተባለው ተህዋሲ ጋር የዝርያ ተመሳሳይነት የላቸውም ብለዋል፡፡ 10ኛ፡- ተህዋሲው ራሱን ቆርጦ እየቀጠለና እያባዛ ሊያመልጥ ቢችልም አሁን ወደ ገበያ እየገቡ ያሉ ክትባቶች ግን ማንነቱን ያጠፉታል፣ ፈውስም ይሆናል ተብሎ በስፋት ታምኗል፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ እስከዛሬ ሌሎች ዝርያዎች ኖረውት ያውቃሉ? አዎ! ዛሬ በተለያየ ዓለም የምናገኘው የቫይረስ ዝርያ ቅንጣት ቻይና ዉሃን ከተማ ከተገኘው ዝርያ ጋር አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ አሁን በብዙ የአውሮጳ አገሮች የሚገኘው D614G የሚባል የተህዋሲ ዝርያ ዓይነት ነው። ተህዋሲው ራሱን እየቀየረ ሊመጣ ይችላል፡፡ ምናልባት መነሻው ሊሆን የሚችለው ደካማ የመከላከል አቅም ካለው በሽተኛ ራሱን ቀይሮ የተነሳ ተህዋሲ ነው የሚሆነው፡፡ አንድ ታማሚ ተህዋሲውን ማሸነፍ ሲሳነው ሰውነቱ የተህዋሲው መራቢያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡ እስከአሁን በዚህ ረገድ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ገና በደንብ መጠናት ይኖርበታል፡፡ ለጊዜው የሚታወቀው በከፍተኛ ፍጥነት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ ብቻ ነው፡፡ ያም ሆኖ ብዙ ሰዎችን ማዳረስ ከቻለ ብዙ ሰዎች አልጋ ይይዛሉ፡፡ ይህ ደግሞ በተዘዋዋሪ ሞትን ሊጨምር ይችላል፡፡ መቶ በመቶ ባይሆንም አሁን የሚገመተው ክትባቶቹ ለዚህ ተህዋሲም ፈውስ እንደሆኑ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው አሁን ተሳኩ የተባሉት ክትባቶች የተህዋሲውን መላ አካሉንና ባህሪውን ሁሉ እንዲያጠቁ የተዘጋጁ ስለሆኑ ተህዋሲው ራሱን እያባዛ ራሱን ሊቀያይር ቢሞክርም እንኳ ከክትባቶቹ ያመልጣል ማለት ዘበት ነው ይላሉ ተመራማሪዎች፡፡ https://www.bbc.com/amharic/55391884 +sports ያልተከተቡ ስፖርተኞች በአውስትራሊያ የሜዳ ቴኒስ መወዳደር አይችሉም ተባለ "የኮሮናቫይረስ ክትባት ያልወሰዱ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾች በ2022ቱ የአውስትራሊያ ኦፕን ላይ እንዲወዳደሩ አይፈቀድላቸውም ሲሉ የውድድሩ ዳይሬክተር ክሬግ ቲሊ ተናግሩ። ከቅርብ ወራት ወዲህ የአውስትራሊያ ፖለቲከኞች የሚሰጡት ተቃራኒ አስተያየት ጉዳዩን ግራ አጋቢ አድርጎት ነበር። በ2021 በወንዶች ዘርፍ አሸናፊ የሆነው ኖቫክ ጆኮቪች ስለ ክትባቱ ሁኔታ በይፋ መግለጽ እንደማይፈልግ ተናግሯል። ""ኖቫክ ለመጫወት መከተብ እንዳለበት ያውቃል።መጥቶ ቢጫወት ደስ ይለናል"" ብለዋል ቲሊ። ""በሚቀጥለው የፈንጆቹ ዓመት በሜልበርን ከጥር 17 አስከ 30 የሚካሄደው ውድድር ሙሉ ተመልካች ባለበት እንደሚካሄድ ቲሊ አረጋግጠዋል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የቴኒስ ተጫዋቾች አልተከተቡም። እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ በዓለም አቀፉ የቴኒስ ማኅበር ዘርፍ ከተወዳደሩ ወንዶች 35 በመቶ ያህሉ ያልተከተቡ ነበሩ። የሴቶች ቴኒስ ማኅበር በተጫዋቾቹ ዘንድ ያለውን የክትባት መጠን ለቢቢሲ ስፖርት ይፋ አላደረገም። የሴቶች ቴኒስ ማኅበር ሁሉም ተወዳዳሪዎች ወደ ሜልቦርን መጓዝ እንደሚችሉ ማወቁን የሚገልጽ ደብዳቤ ለተጫዋቾች በጥቅምት ወር ልኳል። በደብዳቤው አክሎም ሁሉም ተጫዋቾች (ተከተቡም አልተከተቡም) በጉዟቸው 72 ሰዓታት ውስጥ ቫይረሱ እንደሌለባቸው የሚያሳይ ማስረጃ ማሳየት አለባቸው ብሏል። ሆኖም የቪክቶሪያ ግዛት አስተዳዳሪ ዳንኤል አንድሪውዝ በጥቅምት ወር ያልተከተበ የቴኒስ ተጫዋች ወደ አውስትራሊያ ለመግባት ቪዛ ይሰጠዋል ብለው እንደማያስቡ ገልጸዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ አውስትራሊያ በጉዞ እና በእንቅስቃሴ ላይ አንዳንድ ጥብቅ ገደቦች አሳልፋለች። ለ2021 ውድድር የተጓዙ ተጫዋቾች፣ ባለስልጣናት እና ደጋፊ ሠራተኞች አውስትራሊያ ሲደርሱ ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ ተገደዋል። አንዳንዶች አብረዋቸው በተጓዙት ላይ የኮሮናቫይረስ ከተገኙኘ በኋላ ክፍላቸውን ለቀው እንዲወጡ አልተፈቀደላቸውም ነበር። በዚህም በክፍላቸው ውስጥ ጊዜያዊ ልምምዶችን እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59357889 +sports ሲቲ ለአራት ተከታታይ ዓመታት የሊግ ዋንጫን በማንሳት ታሪክ ሠራ "ማንቸስተር ሲቲ ለአራት ተከታታይ ዓመታት የሊግ ዋንጫን በማንሳት ታሪክ ሲሰራ ቶተንሃም አሁንም ዋንጫ አልባው ቡድን ሆኗል። ሁለቱ ቡድኖች በግዙፉ ዌምብሊ ስታድየም ተገናኝተው ሲቲ በአያሜሪክ ላፖርት ጎል አንድ ለባዶ በመርታት ዋንጫ አንስቷል። ላፖርት ጨዋታው ሊገባደድ 8 ደቂቃ ሲቀረው ከኬቪን ደ ብራይን የተሻማለትን ኳስ በጭንቅላቱ ከመረብ በማዋሃድ የቶተንሃምን የዋንጫ ተስፋ አጨልሟል። ባለፈው ሳምንት ሰኞ ጆዜ ሞውሪንሆን ያባረሩት ቶተንሃሞች በጨዋታው ተበልጠው ታይተዋል። ጨዋታው ሁለት ሺ�� ከእያንዳንዱ ቡድን እንዲሁም አራት ሺህ ተጨማሪ ተመልካቾች በአጠቃላይ 8 ሺህ ደጋፊዎች በተገኙበት ነበር የተካሄደው። ሲቲ ይህን ዋንጫ አራት ጊዜ በተከታታይ በማሸነፍ የሊቨርፑልን የ1980ዎቹን ክብረ ወሰን ተጋርቷል። አልፎም ዋንጫውን በአጠቃላይ 8 ጊዜ ዋንጫ በማንሳት ከሊቨርፑል ጋር እኩል ታሪክ መሥራት ችሏል። ""ተጨዋቾቼ እያደረጉ ያሉት ይህን ነው። ለመጪው ዘመን የሲቲ ተጫዋቾች ታሪክ እየሠሩ ነው የሚሄዱት"" ሲሉ የሲቲው አሠልጣኝ ፔፕ ጉዋርዲዮላ አስተያየት ሰጥተዋል። ""ወደ ፍፃሜው ለመድረስ ማንቸስተር ዩናይትድንና አርሰናል ረትተን ነው የመጣነው። ስለዚህ ዋንጫውን ማንሳት ይገባናል ማለት እንችላለን።"" ጉዋርዲዮላ ዋንጫውን ሲያነሱ ፊታቸው በደስታና በሻምፓኝ ረስርሶ ታይቷል። ሲቲ ዘንድሮ አራት ዋንጫ ለመብላት የነበራቸው ተስፋ ባለፈው ሳምንት ከቼልሲ ጋር የኤፍ ዋንጫ ፍልሚያን በመሸነፋቸው ከሽፏል። ነገር ግን ቶተንሃም የካራባዎ ዋንጫን ከመብላት የሚያግዳቸው ቡድን ሆኖ አልተገኘም። ፔፕ ጉዋርዲዮላ ይህ በአሠልጣኝነት ዘመናቸው 30ኛ ዋንጫቸው ነው። የፕሪሚዬር ሊጉን ዋንጫ አንደኛውን እጀታ የጨበጡ ይመስላል። ቻምፒዮንስ ሊግ ለመብላትም የማይወጡት ተራራ ያለ አይመስልም። ነገሮች እየተሳኩለት የማይመስለው ቶተንሃም በሦስት ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ፍፃሜ ደርሶ ዋንጫው ለተቀናቃኝ ቡድን አስረክቦ ተመልሷል። የዋንጫ ጨዋታ እያላቸው ፖርቹጋላዊውን አሠልጣኝ ሆዜ ሞውሪንሆን ያባረሩት የቶተንሃሙ ሊቀ-መንበር ዳንኤል ሌቪ ቡድናቸው የፈረሰው ሱፐር ሊግን መቀላቀሉ አስተችቷቸው ነበር። ሌቪ፤ ቡድናቸው ለዋንጫ ደርሶ ልምድ ያላቸውን አሠልጣኝ አባረው ወጣት መተካታቸው ከደጋፊዎች ተቃውሞ እንዲደርሳቸው ምክንያት ሆኗል። ከቶተንሃም ጋር ዋንጫ አንስቶ የማያውቀው የእንግሊዙ አምበል ሃሪ ኬን ከጉዳት ተመልሶ በፍፃሜው ቢጫወትም ጫና መፍጠር አልቻለም። ደቡብ ኮሪያው ሄውንግ-ሚን ሰን ከፍፃሜው በኋላ ሲያነባ ታይቷል። ቶተንሃም አምስት ጊዜ ለፍፃሜ ደርሰው ሳያሸንፉ ቀርተዋል። ባለፉት አራት የፍፃሜ ጨዋታዎች ጎል ማስቆጠር እንኳን አልቻሉም።" https://www.bbc.com/amharic/news-56884301 +sports አትሌት ቀነኒሳ 'ከዚህ ቀደም በበርሊን ማራቶን የፈጸምኩትን ስህተት አልደግምም' አለ "አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የፊታችን እሁድ በሚካሄደው የበርሊን ማራቶን ውድድር ላይ ከዚህ ቀደም በበርሊን ማራቶን የፈጸምኩትን ሰህተት አልደግምም አለ። አትሌት ቀነኒሳ ከሁለት ዓመት በፊት እአአ 2019 ላይ በጀርመን መዲና በተካሄደው የማራቶን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰንን ለመሻሻል ሁለት ሰኮንዶች ብቻ ቀርተዉት ውድድሩን ማሸነፉ ይታወሳል። ""ከውድድሩ በፊት ክብረ ወሰን ለማሻሻል አእምሮዬን አላዘጋጀሁም ነበር። ክብረ ወሰኑን ለመሻሻል አእምሮዬን ባዘጋጅ ኖሮ፤ ክብረ ወሰኑ የዚያን ዕለት ይሰበር ነበር"" ሲል ቀነኒሳ ኢንስታግራም ገጹ ላይ ባጋራው ቪዲዮ ተናግሯል። ቀነኒሳ በ2019ኙ የበርሊን ማራቶን ሁለት ሰከንዶች ብቻ ቀርተውት ክብረ ወሰን ሳያሻሽል መቅረቱ ""ብዙ ጊዜ ያስደነግጠኛል"" ያለ ሲሆን፤ እሁድ በሚደረገው ውድድር በኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌ የተያዘውን ሪኮርድ ለማሻሻል እቅድ እንዳለው ገልጿል። ቀነኒሳ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ በማራቶን ይሳተፋል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም ኢትዮጵያን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ በተደረገው ማጣሪያ ላይ ባለመሳተፉ ከቡድኑ ውጪ መሆኑ ይታወቃል። ከቀነኒሳ ስኬቶች መካከል አትሌት ቀነኒሳ ተመራጭ ከሚያደርጋቸው ውድድሮች መካከል የበርሊን ማራቶን አንዱ መሆኑን ይናገራል። ""ብዙ ሰው የሚሳተፍበት ነው። ጥሩ የአየር ጸባይ ነው። ከተማውን እወደዋለሁ፤ ንፁህ ከተማ፤ ንፁህ አየር ነው ያለው"" ብሏል። ቀነኒሳ በአሁኑ ወቅት ለውድድሩ የመጨረሻ ዝግጅቱን ከአገር ውጪ እያደረገ እንደሆነም ተናግሯል። ክብረ ወሰን የሚሻሻልበት የበርሊን ማራቶን በርሊን፣ ለንዶን፣ ቦስተን እና ኒው ዮርክ ከተሞች ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸውን የማራቶን ውድድሮችን ያዘጋጃሉ። የበርሊን ማራቶን ደግሞ በተለየ መልኩ ብዙ ጊዜ ክብረ ወሰኖች የሚሻሻሉበት የውድድር መድረክ ሆኖ ቆይቷል። በዘንድሮ ውድድር የማይሳተፈው ኢሉዩድ ኪፕቼጌ እአአ 2018 ላይ ተካሂዶ በነበረው የበርሊን ማራቶን 2፡01፡39 በሆነ ሰዓት የዓለም ክብረ ወሰንን ይዟል። ቀነኒሳ ደግሞ ከአንድ ዓመት በኋላ፤ ማለትም እአአ 2019 ላይ 2፡01፡41 በሆነ ሰዓት መጨረስ ችሏል። በበርሊን ማራቶን የተሻሻሉ ክብረ ወሰኖች በእሁዱ የበርሊን ማራቶን ሌሎች ተጠባቂ አትሌቶች ከአትሌት ቀነኒሳ በቀለ በተጨማሪ፤ አስደናቂ ውጤት ማስመዝገብ የሚችሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተሳታፊ ይሆናሉ። እአአ 2017 ላይ ኪፕቼጌን ተከትሎ ኢትዮጵያዊው ጉዬ አዶላ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። የ22 ዓመት ወጣት የሆነው ኦሊቃ አዱኛም በበርሊን ማራቶን ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል አንዱ ነው። ኦሊቃ እአአ 2020 ላይ የዱባይ ማራቶንን አሸንፏል። እአአ 2021 ላይ በጃፓን የሚካሄደውን ሌክ ቢዋ ማራቶን ውድድርን ያሸነፈው ጃፓናዊው ሂዴካዙ ሂጂካታ ሌላኛው ተጠባቂ አትሌት ነው። የበርሊን ማራቶን የወንዶች ውድድር እሁድ ጠዋት ይካሄዳል። የሴቶች የማራቶን ውድድር በሴቶች የበርሊን ማራቶን ውድድር የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶች የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷቸዋል። ሕይወት ገ/ኪዳን ሚላን ማራቶን ላይ ያስመዘገበችውን 2፡19፡25 ፈጣን ሰዓት ይዛ ውድድሩን ትጀምራለች። የ2015 የኮፐንሃገን እና ሊዝበን ማራቶን ሻምፒዮኗ ኬንያዊቷ ፒዩሪቲ ሪኦኖሪፖ ሌላኛዋ ተጠባቂ አትሌት ነች።" https://www.bbc.com/amharic/58671329 +business አዲሱ ‘የማኅበራዊ ልማት ግብር’ ኑሮን ሊያስወድድብን ይሆን? ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግሥት በዜጎቹ እየጨከነ ይመስላል፡፡ የሚያስጨክነው የኪሱ መመናመን ይሆናል፡፡ በቀደም ለምሳሌ የነዳጅ ድጎማን አነሳ፡፡ አሁን ደግሞ አዲስ ቀረጥ ልጥልባችሁ ነው እያለ ነው፡፡ ይህ እየሆነ ያለው ግሽበቱ 33 ከመቶ በደረሰበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ አዲስ ቀረጥ አስመጪዎች ላይ ብቻ የሚጣል ቢሆንም ቁንጥጫው እነርሱ ዘንድ ይቀራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ አስመጪዎች ምንም ነገር ሲጫንባቸው እንደ ትኩስ ድንች ወደ ሸማች ሲወረውሩት ነው የኖሩት፡፡ መንግሥት ‘ትኩሱ ድንች’ በነጋዴዎች አፍ እንዲቀር ለማድረግ ደግሞ መንገዱም፣ ስልቱም፣ መላውም የለውም፡፡ ከባድም ነው፤ ለቁጥጥር፡፡ ታዲያ ምን ተሻለ? የምጣኔ ሃብት አዋቂዎች መንግሥት እንደ ዘንድሮ የተፈተነበት ዓመት የለም ይላሉ፤ በብዙ ምክንያቶች። የሰሜኑ ጦርነት ዋነኛው ነው። የኮቪድ ወረርሽኝ እና የዩክሬኑ ጦርነትን ተከታትሎ መምጣት ሌላው ነው። የነዳጅ ዋጋ መናር ደግሞ ሦስተኛው ምክንያት ነው፡፡ የሁሉም ሉላዊ ምስቅልቅ ጦሶች ዳፋቸው ለሁሉም ተርፏል። እነዚህ ነገሮች ደግሞ ከማንም ቁጥጥር ውጪ መሆናቸው ነው ጉዳቱ፡፡ መፈናቀል እና የሰላም እጦት ምርት ያሳጣሉ። ምርት ማነስ ደግሞ ገቢን ይጎዳል። በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ መንግሥት እጅ አጥሮታል፡፡ ከበጀት ጋር በተያያዘ ጠንከር ያለ ፈተና ገጥሞታል። የዘንድሮ ዓመታዊ በጀት ከቀደመው በ100 ቢሊዮን ብር ገደማ ይልቃል። ጥቅሉ 800 ቢሊዮን ብር ተጠግቶ ነበር። ምን ዋጋ አለው፤ የበጀት ጉድለቱም ያን ያህል ሰፊ ሆነ። መንግሥት ባመነው ከ200 እስከ 300 ቢሊዮን ብር የበጀት ክፍተት ይጠበቃ��። እርግጥ ነው የኢትዮጵያ በጀት ራሱን ችሎ አያውቅም፡፡ ሁሌም እርጥባን ይሻል፡፡ በድጎማ እና በእርዳታ ነው ሰኔን የሚዘልቀው። ነገር ግን አጋሮች ጀርባቸውን ሰጥተዋል፡፡ በራሳቸው ጉዳይ ተይዘዋል። ዩክሬን ላይ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ቀዳሚ አጀንዳቸው አይደለችም። ቀሪዎቹ ለጋሾች ደግሞ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከመንግሥት ጋር ተኳርፈዋል። ምን ይሻላል? ምስጥ እንጨትን እንደሚበላው ጦርነትም ምጣኔ ሃብትን ቦርቡሮ፣ ቀረጣጥፎ ይበላል፡፡ “ይህ ጦርነት፣ በቀጥታም በተዘዋዋሪም በሕዝብ መዋጮ የተደረገ ጦርነት ነው” ይላሉ፣ ለዚህ ጽሑፍ ማዳበሪያ ያነጋገርናቸው የፋይናንስ ጉዳዮች ባለሙያ አቶ አብነት በላይ፡፡ ‘በቀጥታ’ የሚሉት የቀጥታ መዋጮውን ነው፡፡ ‘በተዘዋዋሪ’ የሚሉት ደግሞ ለጦርነት የዋለው ገንዘብ ምንጭ ዞሮ ዞሮ ከሕዝብ በግብር መልክ ለመሠረተ ልማት የተሰበሰበ ገንዘብ መሆኑን ከመረዳት ነው፡፡ “ያው ሕዝብ በታክስም በምንም ወደ መንግሥት ቋት ያስገባው ገንዘብ ነው ለጦርነት የዋለው።” መንግሥትን ይበልጥ ያሽመደመደውም ለዚሁ ነው፡፡ ዘንድሮ እጅ ያጠረው በጦርነቱ ብዙ ተቋማት በመውደማቸው ብቻ አይደለም፡፡ ኮቪድ የጎዳውን ኢኮኖሚ ነው ወዲያውኑ ጦርነት የተቀበለው፡፡ ቀድሞውኑም ኮቪድ በሁሉም ሆስፒታሎች ላይ ጫና አሳድሯል። መንግሥት ለመድኃኒት የሚያወጣው ወጪ በብዙ እጥፍ ንሯል። እያንዳንዱ ሆስፒታል የበጀት ጨምሩልኝ ጥያቄን እያነሳ ያለውም ለዚሁ ነው። ምን ይሻላል? በጤናው ዘርፍ ብቻ አይደለም ፈተናው፤ በትምህርት ግንባርም ነገሩ ተመሳሳይ ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፤ እሱም ከበቃን ነው ያሉት በቅርብ ነው። እንዲህ ዓይነት ወፍራም ገንዘብ መንግሥት የለውም። በቀድሞ ጊዜ ቢሆን ከዚያም ከዚህም ብሎ ማምጣት ይቻል ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን በልመናም በብድርም የሚሞላ አልሆነም። የዓለም ባንክ ራሱ 300 ሚሊዮን ዶላር ነው የሰጠው፡፡ “አሁን አሁን ረጂዎች ለመስጠት ቃል የሚገቡት ገንዘብ አንድ ወረዳንም መልሶ የሚያለማ አይደለም” ይላሉ የፋይናንስ አዋቂ አቶ አብነት በላይ። ታዲያ ምን ተሻለ? ግብር መጨመር? መንግሥት የበጀት ጉድለትን ዜጎችን አስጨንቆ መሙላት ይችል ይሆናል። ለምሳሌ ግብርን በመጨመር፡፡ ነገር ግን አደጋ አለው። የዋጋ ንረት ያስከትላል። እንደ ሰደድ እሳት የሚቀጣጠል ንረት ሊያመጣብን ይችላል። ዜጎች ላይ የሚጣል ግብር ቤንዚን የማርከፍከፍ ያህል ነው። ለምን ገንዘብ አይታተምም ታዲያ? እሱም አደጋ አለው፡፡ ከፍተኛ አደጋ፡፡ ብር የሚያትም መንግሥትና የአልኮል ሱሰኛ አንድ ናቸው፡፡ አንድ መለኪያና አንድ ረብጣ በጨመሩ ቁጥር ሁለቱም ይሰክራሉ፡፡ በተለይ ገንዘብ ደጋግሞ የሚያትም መንግሥት በግሽበት ራሱን እስኪጥል ይሰክራል፡፡ ስለዚህ ካልተገደደ አያደርገውም፡፡ መንግሥት አሁን ያለውን የግሽበት ራስ ምታቱን  ማብረድ ይፈልጋል። ቀላል ግን አይደለም። ለምን? ምክንያቱም የወጪ-ገቢ ሚዛኑ ለተዛባ አገር የዋጋ ንረትን ማቆም፣ በወንፊት ውስጥ ውሃ ለማቆር የመሞከር ያህል ፈታኝ ስለሆነ ነው። በሌላኛው ግንባር ሌላም ራስ ምታት አለ። በዚህ አገር የራስ ምታቶቹ ብዛት ራሱ ሌላ ራስ ምታት ነው፡፡ በጦርነቱ አከርካሪው የተመታው ኢኮኖሚ ለማገገም ዓመታትን ይፈልጋል። እሱም ሌላ ጦርነት ካልተቀሰቀሰ ነው። የሰሜኑ ጦርነት ከሰብአዊ ጥፋቱ ባሻገር ብዙ መሠረተ ልማትን አውድሟል። ውድመቱን ለመጠገን ቢሊዮኖች ያስፈልጋሉ። አቶ አብነት ድምሩን ወደ 500 ቢሊዮን ብር ያደርሱታል፡፡ አፋር፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል፣ ኦ��ሚያ…፡፡ ጦርነቱ ግማሽ አገር ነው ያወደመው ማለት ያስደፍራል። ይህን ሁሉ መልሶ ለመገንባት የአቶ አብነትን ግምት በግማሽ እንኳ ብንቀንሰው ሩብ ትሪሊዮን ብር ከየት ይታጨዳል፡፡ ወይ ግብር ካልተጨመረ፣ ወይ ደግሞ ገንዘብ ካልታተመ ከየት ይምጣ? ከማን ይሰብሰብ? አንድ መላ መፈጠር ነበረበት። ‘የማኅበራዊ ልማት ግብር’ (Social Welfare levy) የመጣው ታዲያ ከዚህ ሁሉ “የ9 ወር” ምጥ በኋላ ነው። ብዙውን ጊዜ መንግሥት ቁልፍ የሆኑ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለሕዝብ ለማቅረብ ሲፈተን የሚጣል የቀረጥ ዓይነት ነው። መንግሥት በቀረጥና ግብር የሰበሰበው ጠቅላላ ገንዘብ አንሶ ምኑን ከምኑ ላድርገው ብሎ ሲጨነቅ አዲስ ገቢ ማግኛ መንገድ ያስባል። ቀደም ሲል እንዳወሳነው የትኛውም አዲስ ገቢ መሰብሰቢያ መንገድ ግን ጦስ አለው። የዋጋ ንረት እና የገንዘብ ግሽበት የሚባሉ ሁለት ጣጠኞች አሉ። እነርሱን ነካክቶ ኢኮኖሚውን የሚያበግን ነገር ሁሉ በገንዘብ አስተዳደር ላይ የባሰ ቀውስ ይፈጥራል፡፡ የተሻለው ዘዴ እንዲህ ዓይነት ወጣ ያለ አዲስ ቀረጥን ማስተዋወቅ ነው ይላሉ ባለሙያዎች። ኢትዮጵያ ብቻም ሳትሆን በርካታ አገራት መሠረታዊ አቅርቦት ለሕዝባቸው ለማድረስ ብር ሲያጥራቸው ይህን ያደርጋሉ። ‘መሠረታዊ’ የሚባለው ነገር ከአገር አገር ቢለያይም፡፡ የፋይናንስ ባለሙያው አቶ አብነት ይህን ሊያስረዱ በቅርቡ የጎበኟትን ሩሜኒያን እንደ ምሳሌ ያነሳሉ። “ኢኮኖሚያቸው ዲጂታል እየሆነ ስለመጣ ‘የዲጂታል ሊትሬሲ’ መሠረታዊ ነገር እየሆነባቸው ሄደ። መንግሥት በየአካባቢው ኢንተርኔት ማቅረብ ግዴታ ሆነበት። አለበለዚያ ማኅበራዊ አገልግሎታቸን ማቅረብ ከባድ ሊሆንበት ሆነ። በሩሜኒያ ኢንተርኔት ወደ መሠረታዊ ነገር እየተጠጋ የመጣውም ለዚያ ነው” ይላሉ። አቶ አብነት የታክስ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት አማካሪ ናቸው። እንደ እርሳቸው ምልከታ ከሆነ እንዲህ በተተበተበ ችግር ውስጥ ላለ መንግሥት፣ ለ114 ሚሊዮን ሕዝብ መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት ቢከብደው የሚደንቅ አይሆንም። አንደኛ ከበጀቱ ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚይዘው ማኅበራዊ አገልግሎት ነው፡፡ ሁለተኛ ብዙዎቹ ማኅበራዊ አገልግሎቶች በኢትዮጵያ በመንግሥት ቀጥተኛ ወጪ የሚሸፈኑ ናቸው፡፡ አቶ አብነት “ለኔ ኢትዮጵያ የዌልፌር ስቴት ሆና ነው የምትታየኝ፤ በአቅሟ” የሚሉትን ይህን ተመርኩዘው ነው፡፡ ለዚህም ይሆናል ይህ መንግሥት ወደ አዳዲስ የቀረጥ ዓይነቶች ማማተር የጀመረው። ያማተረው ግን ወደ ዌልፌር ታክስ ብቻ አይደለም፡፡ በሌላ ጊዜ የምንመለስባቸው የ‘ፕሮፐርቲ’ [የንብረት] ታክስ እና የነዳጅ ምርቶች ላይ ያለው ኤክሳይዝ ታክስም በመደርደርያችን ላይ ናቸው፡፡ ሌላም አለ፤ በሂደት ላይ ያለ፡፡  የኢትዮጵያ 2 ሺህ ከተሞች ራሳቸውን እንዲችሉ የመንገድ ክፍያን ለማስተዋወቅ በሙከራ ደረጃ ታስቧል፡፡ መንግሥት ራሱን ከበጀት ጭንቅ ለማውጣት ገና ወደ ብዙ አቅጣጫ እንደሚያማትር እነዚህ አመላካቾች ናቸው፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በነሐሴ ወር መባቻ ላይ ባካሄደው ስብሰባ ይህን አዲስ ረቂቅ መክሮና ዘክሮ አጽድቆታል። ይህ ግብር በሁሉም ወደ አገር ቤት በሚገቡ ቁሳቁሶች ላይ የተጣለ ነው። ይሁንና ነዳጅ እና ማዳበሪያ ከዝርዝሩ ወጥተዋል። ይህ ለፋይናንስ አዋቂው አቶ አብነት ብልሃት የታከለበት አካሄድ ሆኖ ይታያቸዋል። ምክንያቱም ነዳጅ እና ማዳበሪያን የሚነኩ ቀረጦች ጦሳቸው ለሰፊው ሕዝብ ስለሚደርስ፡፡ ዲፕሎማቶች የሚያስገቧቸው ዕቃዎችም ከዚህ የዌልፌር ቀረጥ ነጻ ናቸው። ይህ የሆነው ኢትዮጵያ የቪየና ኮንቬንሽን ፈራሚ በመሆኗ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ ውጪ የሱር ታክስ ግዴታ ከሆነባቸው የገቢ ዕቃ���ች ውጪ ባሉት ገቢ ዕቃዎች ሁሉ አዲሱ ቀረጥ ተጭኗል። መንግሥት እንደሚለው ከሆነ በአማካይ በየዓመቱ እስከ 22 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ያስችለዋል። እዚህ ቁጥር ላይ የተደረሰው በየዓመቱ የገቢ ዕቃዎች መጠንን ከግምት በማስገባት ነው። በየዓመቱ ወደ አገር ቤት እስከ 114 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሸቀጥ ይገባል። በእያንዳንዱ ገቢ ዕቃ 3 ከመቶ ግብር ሲሰላ ወደዚህ አሐዝ ይደረሳል። የማኅበራዊ ልማት (ሶሻል ዌልፌር) ቀረጥ የግብር ምጣኔው ሦስት በመቶ ነው። መንግሥት እንደሚለው ይህ ትንሹ የግብር መጠን ሲሆን ተጽእኖ እንዳይኖረው በሚል ነው ሰፊ መሠረት እንዲኖረው ተደርጎ የተበጀ ነው። አቶ አብነት ይህ የግብር ተመን ውድ ነው ወይስ አይደለም ብለው ለመበየን ይቸገራሉ። “በገቢ ዕቃዎች ላይ ከሚጣሉ የታክስ ዓይነቶች አንጻር ከታየ በጣም ዝቅተኛው የቀረጥ ምጣኔ ሊባል ይችላል። ከወደሙ መሠረተ ልማቶች ብዛትና ከሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን  ስፋት አንጻር ሲታይ ደግሞ በተቃራኒው ሊታሰብ ይችላል።” ይህ ግብር በሦስት መንገድ በሕዝብ ላይ ቀጥተኛ ጫና እንዳያደርስ የተሞከረ ይመስላል፤ የናረውን ኑሮ የበለጠ እንዳያንር። አንደኛው ግብሩ የተጣለው በአስመጪዎች ላይ ብቻ መሆኑ። ሁለተኛው የግበሩ ምጣኔ አነስተኛ ተደርጎ መሰላቱ። ሦስተኛ ይህ ግብር እንደ ነዳጅ እና ማዳበሪያ ባሉት ቁልፍ ነገሮች ላይ አለመጣሉ። ይሁንና አቶ አብነት “ዞሮ ዞሮ ገንዘቡን የምናዋጣው እኛ እንጂ መንግሥት እንደሚያስበው አስመጪ ነጋዴዎች አይደሉም” ይላሉ። ይህን የሚሉት ያለ ምክንያት አይደለም። በነጋዴ ላይ የተጣለ ግብር ሄዶ ሄዶ ለሸማቹ መከፋፈሉ እሙን ስለሆነ ነው። ይህ ሲጠቃለል አዲሱ ግብር በኑሯችን ላይ መጠነኛ ቁንጥጫ ላይኖረው አይችልም፡፡ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የገንዘብ ግሽበት፣ የዋጋ ንረት እና ምጣኔ ሃብታዊ ምስቅልቅ አጋጥሟል። ነዳጅ በዓለም ገበያ ሰማይ ነክቶ ነው አሁን ቀስ በቀስ ለማረፍ እያኮበኮበ ያለው። መንግሥት ግን ከነዳጅ ድጎማው ቀስ በቀስ እየወጣ ነው። በዚያ ላይ በጦርነት የደቀቀና ገና እያገገመ ያለን ኢኮኖሚ ይዞ ነው ያለው። ታዲያ በዚህ ሁኔታ ይህ አዲስ ግብር ነገሩን ከድጡ ወደ ማጡ አያደርገውም? ለንግድና ኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ አብነት፣ መንግሥት ይህን ቀረጥ ማስተዋወቁ መጥፎ እርምጃ የሚባል አይደለም። እንዲያውም ከሚያመጣው ጣጣ ይልቅ በጎ ጎኑ ይታያቸዋል፡፡ በዚህ ወቅት የሕዝብ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ይላሉ፡፡ ይህን የሚሉት በምክንያት ነው። ዋናው ምክንያታቸው በመንግሥት ላይ ጫናው መበርታቱን ከመገንዘብ ይመነጫል፡፡ አንደኛ ረጂዎች በዩክሬን ጉዳይ ተጠምደዋል። የረጂዎች መታከት (donors fatigue) እየታየ ነው። ሁለተኛ በጦርነት የወደመው መሠረተ ልማት ቁጥር ሥፍር የለውም። መንግሥት ይህን ክፍተት በሌላ በየትኛውም መንገድ ሊሸፍነው አይቻለውም ባይ ናቸው። መንግሥት ይህን ገንዘብ በዌልፌር መልክ ከመሰብሰብ ሌላ አማራጭ አልነበረውም ወይ ተብለው ሲጠየቁም፣ “ይህን ሐሳብ ያመጡ ሰዎች መቼስ ብዙ አማራጮችን እንዳዩ እገምታለሁ” ይላሉ፡፡ ምናልባት ሌላው አማራጭ በሕዝብ ፈቃደኝነት ላይ በተመሠረተ ተሳትፎ ገንዘቡን መሰብሰብ ሊሆን ይችል ነበር ብለውም ይገምታሉ፡፡ ይሁንና ይህም ፈተናው ቀላል እንዳልሆነ ይረዳሉ፡፡ “ሕዝቡ ለግደቡ፣ ብሎም ለተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች፣ ለመፈናቀሎች በየጊዜው ገንዘብ አዋጣ እየተባለ ተዳክሟል” ይላሉ፡፡ ሌላው መንገድ ለአቶ አብነት ከነጋዴዎች በቀጥታና በፈቃድ ገንዘብ ማሰባሰብ ነው፡፡ ይሁንና “ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር፤ መንግሥት የነጋዴውን ፊት ለማየት የፈራ ይመስለኛል” ይላሉ፡�� ከሕዝብም ከነጋዴም ዐይን እየሸሸ ያለው መንግሥት ታድያ ይህን ገንዘብ በእጅ አዙር ለመሰብሰብ የመረጠ ይመስላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ከግምት ሲገቡ መንግሥት ለመልሶ ማልማት ገንዘብ ለማምጣት ያሰበበት መንገድ ተገቢነቱ ይጎላባቸዋል፤ ለአቶ አብነት በላይ፡፡ ይልቅ እርሳቸውን የሚያሰጋቸው የ3 በመቶ ቀረጥ መጣል አይደለም። ከዚያ ይልቅ የሚያሳስባቸው ሁለት ነገር ነው፡፡ ይህ ገንዘብ ከተሰበሰበ በኋላ ለታለመለት ዓላማ ይውላል ወይ? የሚለው አንዱ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ፣ “በመልሶ ማልማት የገነባነውን መልሰን እንዳናወድመው ነው፡፡” ከፍርሃቶቻቸው የሚልቀው ግን ይህ ነው፡፡ “ከፊት ለፊታችንስ ሌላ አውዳሚ ጦርነት እንደሌለ በምን እርግጠኛ እንሆናለን?” https://www.bbc.com/amharic/articles/cw97er27x2qo +business ኮሮናቫይረስ ያቀጣጠለው የቻይናና የአሜሪካ ፉክክር በአፍሪካ "ዘግየት ብሎ የኮሮናቫይረስ በተከሰተባት አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ አሜሪካና ቻይናም ለአህጉሪቱ ከፍተኛ ድጋፍ በመስጠት እኔ እበልጣለሁ በሚል እሰጣገባና እሽቅድምድሞሽ ተጠምደዋል። ሁለቱ አገራት እያደረጉት ያለው ፉክክር በአፍሪካ የቫይረሱን ስርጭት ከመቆጣጠር በዘለለ ኃያልነታቸውን የማስፈን ተግባር እንደሆነ የቢቢሲ አፍሪካ ዘጋቢው አንድሪው ሃርዲንግ ያትታል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ ከሰሞኑ ""በአፍሪካ ውስጥ ኮቪድ-19ን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ትግል የሚደግፍ ከአሜሪካ በላይ አገር ከየትም አይመጣም"" ያሉ ሲሆን አክለውም ""ለዓለም አቀፉ የጤና ሥርዓት አሜሪካ እንደምታደርገው ድጋፍ የትኛውም አገር አድርጎ አያውቅም፤ መቼም አይደረግም"" ብለዋል። ማይክ ፖምፔዮ ይሄንን ያሉት በአፍሪካ ውስጥ ካሉ ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ነው። የቢቢሲው አንድሪው ሃርዲንግም 'አንዱ እኔ ነበርኩ"" ይላል። ባለፈው ወርም እንዲሁ በትራምፕ አስተዳደደር የተለመደውን ""ማንኛውም አገር ከእኛ በበለጠ አይሰራም"" የሚለውን ንግግር ከአሜሪካ ባለስልጣናት የተሰማ ሲሆን፤ እንዲህ አይነት ተደጋጋሚ ንግግርም የሚሰማው አገሪቱ ለዓለም ጤና ድርጅት የምታደርገውን ድጋፍ ከማቋረጧ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ትችቶችን ፀጥ ለማሰኘት ነው። በተለይም አሜሪካ ለድርጅቱ ታደርገው የነበረውን ድጋፍ ይህ ዓለም አቀፍ ቀውስ ጣራ በነካበት ወቅት ከማቋረጧ ጋር ተያይዞ ብዙዎች ወቀሳቸውን አሰምተዋል። አሜሪካም ከዚህ ለማምለጥ ጥረት እያደረገች ነው። ማይክ ፖምፔዮ አሜሪካ ለአፍሪካ አድርጋዋለች ብለው ከሚኮሩበት የገንዘብ እርዳታ መጠን በቅርቡ የተለገሰው 170 ሚሊዮን ዶላር ነው። ነገር ግን ይህ የገንዘብ መጠን ከቻይና እንደ አገር ከተሰጠው ቀርቶ ቻይናዊው ቢሊየነር ጃክማ ከሰጠው ጋር ሲወዳደር ያንሳል። ከሰሞኑ የአሜሪካና የቻይና ባለስልጣናት አህጉሪቷ ጋር በተያያዘ የሚያደርጓቸውን ንግግሮችን ለታዘበ አፍሪካ ለሁለቱ ኃያላት አገራት አዲሱ የቀዝቃዛ ጦርነት ሜዳ መሆኗን ለመረዳት አይቸገግርም። ከዚህ ቀደምም ሁለቱ አገራት የነበራቸው የቃላት ጦርነት በኮቪድ-19 ቀውስ የተባባሰ ሲሆን አህጉሪቷንም ማዕከል በማድረግ ወደ ውክልና ጦርነት እያመሩ ይመስላሉ። ""የከሸፈው መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲ"" በቅርቡ በቻይና መንግሥት ቁጥጥር ስር ያለው ግሎባል ታይምስ ይዞት በወጣው ፅሁፍ አገሪቱ እያራመደች ያለችው የፖለቲካ ሥርዓት የኮቪድ-19ን ስርጭት ለመግታት እንዴት እንደጠቀማት ያትታል። በመቀጠልም የከሸፈው የምዕራባውያን መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲ በአፍሪካ አገራት ላይ ኢ-ፍትሃዊነት፣ ተበላላጭነት፣ የብሔርና የሐይማኖት መከፋፈል፣ ግጭት እንዲሁም የህይ��ት መጥፋትና የንብረት መውድም ማስከተሉን አስፍሯል። እናም አፍሪካውያን ከዚህ ከከሸፈ ሙከራ ራሳቸውን ገሸሽ በማድረግ የቻይናን የአንድ ፓርቲ መንገድ ሊከተሉ እንደሚገባም ምክር ለግሷል። በቻይና መንግሥት ቁጥጥር ስር ያለ ዕለታዊ የቻይና ጋዜጣም እንዲሁ ቻይና በአህጉሪቷ መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ እያፈሰሰችው ያለችውን መዋዕለ ንዋይና ኢንቨስትመንት አፍሪካን ከታሪካዊ ጭቆና እንዲሁም አሁን ካለችበት መበዝበዝ ያድናታል ብሏል። ""አፍሪካ ለምዕተ ዓመታት በባርነት ቀንበር፣ ቅኝ ግዛት፣ እጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ አሁን ደግሞ በኮሮናቫይረስ ቀውስ ውስጥ ገብታለች። የቻይና የመዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ አላማም አህጉሪቱ ከዚህ አዙሪት እንድትወጣና እንድታገግም ነው"" በሚልም አስፍሯል። የቻይና መንግሥት ለአፍሪካ እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት ማንቆለጳጰስ ለማይክ ፖምፔዮ አልተዋጠላቸውም። የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ በአፍሪካውያን ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍና ለረዥም ዘመናት የሚቆይ የእዳ ጫና እየከመረባቸው ነው ሲሉ ወርፈዋል። በቅርብ ቀናትም የቻይናና አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ አንድ ውይይትም ተደርጎ ነበር። የውይይቱ አስተናባሪ ሁለቱ አገራት በአህጉሪቱ ላይ የሚያደርጉትን እሽቅድምድም ""መርዛማ"" ብለውታል። በወቅቱም አንድ የቻይና ፐሮፌሰር ኮሮናቫይረስ ለአፍሪካውያን ጋዜጠኞች የቻይናን የሚዲያ እሴቶችና ጥሩ ተሞክሮ እንዲያደንቁ አድርጓቸዋል ብለዋል። ""የምዕራባውያን ሚዲያ በጨለምተኛ ዜና የተሞላ ነው፤ ሁሌም አሉታዊ ነው"" ያሉት ፕሮፌሰር ዛንግ ያንኪዩ በእንደዚህ አይነት ቀውስ ወቅት ግን ተስፋን የሚፈነጥቁ ታሪኮችን ሰዎች ማንበብ ይፈልጋሉ ብለዋል። በሌላ መንገድ አፍሪካውያን የቻይና የሚዲያ ሞዴል የሆነውን 'ገንቢ ጋዜጠኝነት'ን (constructive journalism) ይፈልጋሉ ብለዋል። በቅርቡም ፕሮፌሰሯ በኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ዘንድ ለገንቢ ጋዜጠኝነት ያላቸውን ጉጉትና ፍላጎት መታዘባቸውን አስረድተዋል። ነገር ግን ጥያቄው የአፍሪካ ጋዜጠኝነት እንዲህ በቀላሉ ተፅእኖ ውስጥ የሚወድቅ ነው? በንግግራቸው አወዛጋቢ የሚባሉት ትራምፕ ለኮሮናቫይረስ መድኃኒቱ ፀረ-ተህዋሲ (ዲስኢንፌክታንት መጠቀም) እንዲሁም የፀሐይ ጨረር ፈውስ ነው ማለታቸው በአፍሪካውያን ዘንድ ያላቸውን ስም የበለጠ አላጠለሸውም ወይ ተብለው የተጠየቁት ማይክ ፖምፔዮ በቀጥታ አልመለሱም። ነገር ግን ትራምፕ የሚያደርጓቸው ንግግሮችን ብዙ ሰው እንደማይረዳው እንዲሁም በመንግሥት ቁጥጥር ስር ባሉ ሚዲያዎች ሆን ተብሎ ሌላ ትርጉም ይሰጣቸዋል ብለዋል። ከማይክ ፖምፔዮ ጋር የነበረው ቆይታ ለበርካታ ጋዜጠኞች እንግዳ የሆነ ክስተት የተስተናገደበት ነበር። ለአስርት ዓመታት አሜሪካ በአፍሪካ የምትከተለው ዲፕሎማሲ በተወሰነ ደረጃ አምባገነን መንግሥታትን የሚቃወም፣ ከሳንሱር ነፃና ገለልተኛ ጋዜጠኝነትን መሰረት ያደረገ ነበር። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የሚተቿቸውን የአገራቸውን ጋዜጠኞች ""ሐሰተኛ"" ""የሕዝብ ጠላት"" በማለት መወንጀልና ማዋረድ የየዕለት ሥራቸው ሆኗል። ምናልባትም የአሜሪካና የቻይና ገንቢ የጋዜጠኝነት ሃሳብ መንግሥትን አለመተቸት ከሆነ እሳቤያቸው ተቀራርቧል ማለት ይቻላል። በቀድሞው የጆርጅ ቡሽ አስተዳደር ወቅት አሜሪካ ፔፕፋር በተባለው ፕሮግራም ለኤድስ የሚውል እርዳታን ለአፍሪካ የጤና ሥርዓት ተለግሷል። አሜሪካ ካላት የውስጥ ትግልና መከፋፈል ጋር ተያይዞ በአሁኑ ሰዓት ቻይና የኮሮናቫይረስን ሽፋን በማድረግ በአፍሪካ ላይ ፖለቲካዊ አጀንዳዋን ለማስረፅና አሻራም ለማሳረፍ ጥረት እያደረ��ች ትገኛለች። የአፍሪካ አገራትም ሆነ ጋዜጠኞች ባለው የልዕለ ኃያላን ጉልበት ተጽእኖ ተንበርክከው የሚያሸረግዱ ላይሆኑ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን በርካታ አገራትም ባለባቸው ከፍተኛ የቻይና የብድር ጫና እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ባስከተለው የኢኮኖሚ ድቀት የተነሳ ""የከሸፈ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትን"" ገሸሽ በማድረግ የቻይናን የፖለቲካ ሥርአት ይቀበሉ ይሆን? የምናየው ይሆናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-52975241 +politics ህወሓት በክልሉ ያሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን አስጠነቀቀ የትግራይ ክልልን በበላይነት እየመራ የሚገኘው ህወሓት በትግራይ ክልል ያሉ ተቃዋሚ ድርጅቶችን የትግራይ ሕዝብን ትግል “እንዳያደናቅፉ” አስጠነቀቀ። ህወሓት ያወጣውን መግለጫ ጠቅሶ የክልሉ ቴሌቪዥን እንደዘገበው፣ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች “ሕዝባዊ ትግላችንን የሚያደናቅፉ እንቅስቃሴዎች አድርገዋል” ብሏል። በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት)፣ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ (ውናት) እንዲሁም ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) የተባሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጦርነቱን በተመለከተ እና በክልሉ አስተዳደር ላይ በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ በክልሉ ሁሉን አቀፍ የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋም መጠየቃቸው ይታወሳል። ፓርቲዎቹ ክልሉን በማስተዳደር በኩል በህወሓት ሕጋዊነት ላይ ጥያቄ በማንሳት፣ ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበውን ጦርነት ለማብቃት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ይካሄዳል በተባለው ድርድር ላይ ህወሓት ትግራይን ወክሎ የመደራደርም ሆነ ክልሉን በብቸኝነት ማስተዳደር የለበትም ብለዋል። በትግራይ ሕዝብ የኮሙኒኬሽን ቢሮ እና መንግሥት አማካይነት ወጣ በተባለው መግለጫ፣ “ቀደምት ታጋዮች ለሕዝቡ ህልውና በተደጋጋሚ መስዋዕትንት እየከፈሉ” መሆኑን ጠቅሶ፣ ነገር ግን ተቃዋሚዎቹ “የሚከፈለውን መስዋዕትነት በሚያሳንስ ሁኔታ በትግራይ መንግሥት ላይ ክሶችን እያቀረቡ ነው” ብሏል። ጨምሮም ተቃዋሚዎቹ “በትግራይ ሕዝብ እየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ ጦርነት ለማደናቀፍ ጥረት እያደረጉ ነው” ሲል ከሷቸዋል። ተቃዋሚዎቹ ህወሓት ከዚህ በፊት በፌደራል መንግሥቱ ተቀባይነት ያላገኘ ክልላዊ ምርጫዎች በማካሄድ ‘የሕዝብ ተቀባይነት’ አግኝቻለሁ በማለት ሥልጣኑን አጠናክሯል በማለት፣ ከጦርነቱ መቀስቀስ በኋላ ከሥልጣኑ መወገዱን ጠቅሰው ሕጋዊ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል። ህወሓት በመግለጫው ላይ ተቃዋሚዎቹ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ከዚህ በኋላ እንደማይታገሰው አመልክቷል። “ምንም እንኳን የትግራይ መንግሥት እራሳቸውን ያርማሉ ብሎ ቢታገሳቸውም፣ ትግላችንን ከማደናቀፍ አልታቀቡም” ብሏል። ይህንንም በማንሳት በመግለጫው ላይ ተቃዋሚዎቹ በትግራይ ያለው ሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ፈርሷል ስለዚህም የሽግግር መንግሥት ወይም የአንድነት መንግሥት እንዲቋቋም ጠይቀዋል ይህም “ትግሉን በሚያደናቅፍ ሁኔታ የትግራይ መንግሥት ሕጋዊ አይደለም አስከ ማለት ደርሰዋል” ብሏል። ጨምሮም ተቃዋሚ ቡድኖቹ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል የተቀሰቀሰውን የእርስ በእርስ ጦርነት ለማስቆም ህወሓት ከፌደራሉ መንግሥት ጋር ለመደራደር ሥልጣን የለውም ብለዋል። “በአሁኑ ወቅት ትግላችንን የሚያደናቅፍ ተግባራት ላይ አተኩረዋል፤ የትግራይ ክልል መንግሥት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የሰላም ንግግር ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን የለውም” ማለታቸውንም ጠቅሷል። ስለዚህም ተቃዋሚዎቹ “በቃችሁ ሊባሉ ይገባቸዋል። የትግራይ ሕዝብም ሥርዓት ሊያሲዛቸው ይገባል” ብሏል የህወሓት መግለጫ። ለ20 ወራት የዘለቀውን የኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት ለመቋጨት ��ዋጊ ኃይሎች ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ ከተለያዩ ወገኖች ጥያቄ ሲቀርብ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር የሚደራደሩ ሰባት አባላት ያሉት የኮሚቴ ይፋ ካደረገ በኋላ፤ ህወሓትም ከቀናት በፊት ከመንግሥት ጋር ድርድር የሚያደርግ ቡድን ማቋቋሙን ገልጿል። https://www.bbc.com/amharic/articles/ce5yv034lx6o +sports የኮቢ ብራያንት ባለቤት የተከሰከሰው ሄሊኮፕተር ባለቤትን ከሰሰች ባለፈው ወር በሄሊኮፕተር አደጋ ባለቤቷ እውቁ ኮቢ ብራያንትን እና የ13 ዓመት ሴት ልጇን ያጣችው ቫኔሳ ብራያንት፣ በሄሊኮፕተሩ ባለቤት ላይ የመሰረተችው ክስ ጭብጥ በመጥፎ የአየር ሁኔታ ለመብረር መወሰኑ የአብራሪውን ግድየለሽነት ያሳያል የሚል ነው። የሄሊኮፕተሩ ባለቤት አይላንድ ኤክስፕረስ ሄሊኮፕተሮችና አብራሪዎች የተሰኘ ድርጅት ሲሆን፣ ፓይለቱ አራ ጆርጅ ዞባያን ማንኛውም ጠንቃቃ አብራሪ ሊያደርግ የሚገባውን ጥንቃቄ መውሰድ ነበረበት ይላል የቀረበው ክስ። ክሱ እንደሚለው በሄሊኮፕተሩ አደጋ ከኮቢ ብራያንት እና ልጁ ጋር የሞተው የሄሊኮፕተሩ አብራሪ ዞባያን ለበረራ ሲዘጋጅ የአየር ሁኔታ ትንታኔን ከግምት አላስገባም። አብራሪው ሁኔታዎች ከባድ ሆነው እያለም በራራውን ለማቋረጥ አልወሰነም፤ ለበረራው የይለፍ ፍቃድ የሰጠው አይላንድ ኤክስፕረስም ሄሊኮፕተሩ አስቻጋሪ በሆነ የአየር ሁኔታ እንደሚበር እያወቀ ፍቃድ ሰጥቷል ሲል ክሱ ያትታል። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ለጊዜው የተቀመጠ የገንዘብ መጠን ባይኖርም ቫኔሳ ብራያንት ከኩባንያው ካሳና ኩባንያው በወንጀል እንዲቀጣም ትፈልጋለች። • ታዋቂው አሜሪካዊ ስፖርተኛ ከነልጁ በሄሊኮፕተር አደጋ ሞተ • 2019 የአውሮፕላን አደጋ ተጎጂዎች ቁጥር የቀነሰበት ነው ተባለ • ከ33 ዓመት በፊት የተዘረፈው ዘውድ ለጨለቆት ሥላሴ ቤተክርስቲያን እንደሚመለስ ተገለጸ ኮቢ እና ልጁን ይዞ የነበረው ሄሊኮፕተር ካላባሳስ ከተሰኘች ከተማ ከከፍታማ ቦታ ቁልቁል ወርዶ መከስከሱ ቀደም ሲል ተገልጿል። ሄሊኮፕተሩ በተነሳበት ወቅት የአየሩ ሁኔታ ጭጋጋማ ነበር። ምንም እንኳ የአየር ሁኔታው ከባድ የነበረ ቢሆንም ፓይለቱ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን ልዩ ፍቃድ በመጠየቅ እና ፍቃዱን በማግኘት መብረሩም ተገልጿል። አይላንድ ሄሊኮፕተርስ በአሁኑ ወቅት በረራ አቋርጧል። ትናንት በርካታ ሥመ ጥር ሰዎች በተገኙበት ኮቢ እና ልጁ ጊያና ተዘክረዋል። መርሃግብሩን ቢዮንሴ ብያንት ይወደው ነበር ባለችው ዜማዋ ጀምራለች። እንደ ማይክል ጆርዳን፣ ማጅክ ጆንሰን እና የብራያንት የቀድሞ ክለብ ጓደኛ የሆነው ሻኪል ኦኒል ያሉ የቅርጫት ኳስ ኮከቦች በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል። https://www.bbc.com/amharic/51625454 +politics በሕንድ የሚቀናበሩ ፀረ-ሙስሊም ሙዚቃዎች ቁጥር ለምን አሻቀበ? ሳንዲፕ ቻቱርቬዲ 29 ዓመቱ ነው። አዲስ ሙዚቃ ከአድማጮቹ ጆሮ ለማድረስ ተፍ ተፍ እያለ ነው። በሰሜን ሕንድ በምትገኘው ኡታር ፕራዴሽ ግዛት አዮዲያህ ከተማ ከምትገኘው ሱቱዲዮ ተገኝቷል። ዘፈኑ ስለ አንድ መስጂድ ያወራል። የሒንዱ እምነት ተከታዮች በመስጂዱ የመጠቀም መብት እንዳላቸው ይገልጻሉ። ዘፈኑ በሙስሊሞች ላይ በሚሰነዝሩ ጥቃቶች የተሞላ ነው። ቻቱርቬዲ ሙዚቃው ወደ ዘርፉ ገበያ እንደሚያስገባውም ተማምኗል። የቻቱርቬዲ ሙዚቃ ዩቲዩብ እና ሌሎች ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት እየተሰራጩ ከሚገኙ ቀኝ ዘመም የሒንዱ ትርክቶች መካከል ናቸው። ትኩረታቸውም በሙስሊሞች ዙሪያ አደገኛ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ነው። ግጥሞቹ ስድብ አዘል ወይም ማስፈራሪያ የያዙ ናቸው። መሠረታቸው የሒንዱ እምነት ተከታዮች ለዘመናት ተበድለዋል የሚል ነው። አሁን ደግሞ የደረሰውን ኪሳራ መመለሻ ጊዜ ነው ይላሉ። እነዚህ ሙዚቃዎች የገቢ ምንጭ ከመሆናቸውም በላይ ዘፋኞችንም ወደ ታዋቂነት ማማ ያደርሳሉ የሚሉት ፀሐፊ እና የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ኒላንጃን ሙክሆፓድያይ ናቸው። ለእርሳቸው እነዚህ ሙዚቃዎች አይደሉም። “እነዚህ ጦርነት ካልተጀመረ ባዮች ናቸው። ሙዚቃ ጦርነት የሚያሸንፍ ይመስላቸዋል። ይህ ሙዚቃን ያለ ዓላማው መጠቀም ነው። ለዓመታትም ተግባራዊ ተደርጓል” ይላሉ። ቻቱርቬዲ የዩቲዩብ ቻናሉ ከመታገዱ በፊት ሙዚቃው በሚሊዮኖች ታይቷል። እገዳው የመጣው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቅሬታ ማስገባታቸውን ተከትሎ ነው። ሙስሊሞች ናቸው ሙዚቃው አግባብ አይደለም እያሉ ቅሬታ ያስገቡት ይላል። ቻቱርቬዲ “በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮችን በማጣቱ” ቢቆጭም ከዩቲዩብ እያገኘ ያለውን ገንዘብ ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆነም። የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ለመስራት ግን 253 ዶላር ይፈጅበታል። “ከዩቲዩብ ብዙ ገንዘብ እያገኘሁ አልነበረም። ከዚህ ይልቅ እንደ ብሔረተኛ-አብዮታዊ ዘፋኝ ያገኘሁት እውቅና ነው” ሲል በልበ ሙሉነት ተናግሯል። ቻቱርቬዲ አሁን ዩቲዩብ ላይ አዲስ ቻናል ከፍቷል። የለቀቃቸው አንዳንድ ቪዲዮዎች ያላቸው ዕይታ እምብዛም ነው። ይህንን በአዲሱ ዘፈኑ ለመለወጥ ተስፋ አድርጓል። ቻቱርቬዲ በሙዚቃው ብዙ ጊዜ ሙስሊሞችን ዒላማ አድርጓል ተብሎ ቢከሰስም ይቅርታ አይጠይቅም። “የራሴ ለማግኘት እጆቼን አጣጥፌ ብለምን ትስማማለህ? አትቀበልም። ስለዚህ ቀስቃሽ መሆን አለብን፣ አይደል?” ይላል። አፔንድራ ራና መቀመጫው ዴልሂ አቅራቢያ በምትገኘው ዳድሪ ነው። እሱም ተመሳሳይ ሙዚቃ ያዘጋጃል። ተልዕኮዬ ታሪክን “ማረም ነው” ይላል።  ዘፈኖቹ የሂንዱ ተዋጊዎች ላይ ያነጣጠረ ነው። የሙስሊም ገዥዎችንም ተራ አድርጎ ይስላል። “ብዙ እውነት የሆኑ ነገሮች ተደብቀው ውሸት ተጭኖብናል” ሲል በትምህርት ቤቶች ስለሚሰጠው የታሪክ ትምህርት ተናግሯል። ራና ከዩቲዩብ ቪዲዮዎቹ ጥሩ ገቢ እያገኘ መሆኑን ያስረዳል። “ለሕንድ የውጭ ምንዛሪ እያስገኘን ነው። ዩቲዩብ የሚከፍለው በዶላር ነው” ብሎ ዓይኑን ግድግዳው ላይ ዩቲዩብ ከፍተኛ ተከታይ ላላቸው ቻናሎች ወደሚሰጠው ሽልማት እና ወደ ሒንዱ ተዋጊ ምስሎች ወረወረ። ራና የአምልኮ እና የፍቅር ዘፈኖችን ከማቀናበር ወደ “ታሪካዊ” ሥራዎች ከተሸጋገረበት ጊዜ ጀምሮ በዳድሪ ኮከብ ለመሆን በቃ። በዩቲዩብ ላይ ወደ 400,000 የሚጠጉ ተከታዮች አሉት። ብዙዎቹ ዘፈኖቹም በሚሊዮን ለሚቆጠር ጊዜ ታይተዋል። የሙዚቃ ቪዲዮ ለመስራት 100 ዶላር እንደሚያስወጣው ራና ይናገራል። ቪዲዮዎችን መቅረጽን ጨምሮ ካሜራ እና ሌሎች የሙያ ባለቤቶችን ያካተተ ቡድን አለው። ሙክሆፓድያይ እንደሚሉት ከሆነ ሙዚቃን በቁጥር አናሳ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ለማስጠቃት ማዋል ከበፊትም ጀምሮ የመጣ ነው። እአአ በ1989 በቀኝ ዘመሙ ቪሽዋ ሒንዱ ፓሪሻድ (ቪኤችፒ) ባዘጋጀው አወዛጋቢው የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ፕሮግራም ምክንያት በ1992 ባብሪ የተባለ መስጂድ መፍረሱን ያስታውሳሉ። “ከዚያ በፊት የኦዲዮ ካሴቶች ኢንዱስትሪ ብቅ አለ። ሃይማኖታዊ እና ሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ይካተቱባቸው ነበር። ሰዎችን ለማነሳሳትም ሲባል እነዚህ ካሴቶች በተከታታይ ይጫወቱ ነበር” ብለዋል። ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላም ድምፁ እየጨመረ መጥቷል። “ሕንድ ውስጥ መኖር ከፈለክ ቫንዴ ማታራም (“እናቴ አመሰግንሽላሁ”) ማለትን ተማር…በአቅምህ መኖርንም ተማር” ወይም “ሒንዱዎችን ደካማ አድርጎ ማሰብ የጠላት ስህተት ነው” የሚሉ ሥራዎች ማን ላይ እንዳነጣጠሩ መገመት ከባድ አይደለም። እነዚህ ዘፈኖች ቀኝ ዘመም ድርጅቶች የ���ድሬዎቻቸውን “ቀልብ እንዲገዙ” ረድተዋቸዋል። የቀኝ ክንፍ ሒንዱ ራክሻ ዳል ቡድንን የሚመራው ፒንኪ ቻውድሪ “ወጣቶች ጉጉታቸውን እና ሞራላቸውን ከፍ ስለሚያደርጉ እነዚህን ዘፈኖች ይወዳሉ” ሲሉ እንዲህ ዓይነት ዘፈኖች ለወጣቶች ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሚያግዙ ይከራከራሉ። “እነዚህን ዘፈኖች ሳዳምጥ ድንገቴ የሆነ ከፍተኛ ኃይል በፍጥነት ይሰማኛል። በአንድ ወቅት የተደረጉብንን ነገሮች እና አሁን የት እንደደረስን ያስታውሰኛል” ይላል ቪጃይ ያዳቭ። እንደዚህ አይነት ሙዚቃዎችን ማዳመጥ እንደሚወድ የሚናገረው የ23 ዓመቱ ያዳቭ ትምህርቱን እየተከታተለ የሚገኝ ሰዓሊ ነው። ያዳቭ “ድንገቴ የሆነ ከፍተኛ ኃይል” ሲል የተናገረው በሚያዝያ ወር በሚከበሩት የሒንዱ በዓላት ወቅት በበርካታ ግዛቶች ከፍተኛ ግጭቶች የተከሰቱበት ሁኔታን ያሳያል ተብሎ ይታመናል። በበዓላቱ ወቅት ሒንዱዎች ለሃይማኖታዊ ሰልፎች ወጥተው ሙስሊሞች ወደሚበዙባቸው አካባቢዎች ሲቃረቡ ቀስቃሽ ሙዚቃዎች በድምጽ ማጉያዎች ይስተጋባሉ። ከእነዚህ ግጭቶች ውስጥ የቻቱርቬዲ የ2016 ሙዚቃን ጨምሮ ጸያፍ እና ቀስቃሽ ዘፈኖች ሁከትን ለመቀስቀስ አስተዋጽኦ አድርገዋል ተብሏል። ቻቱርቬዲ እነዚህን ክሶች ውድቅ ያደርጋል። “በሙዚቃዬ ግንዛቤን ለመፍጠር እየሞከርኩ ነው። ምንም ነገር በፍቅር አይመጣም። መታገል እና የእኛ የሆነውን መንጠቅ አለብን” ይላል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1d830zekro +sports አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ጥበበኛ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና አረፈ "ከምድራችን የእግር ኳስ ኮከብ ተጫዋቾች መካከል ከቀዳሚዎቹ ውስጥ የሚጠቀሰው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና በ60 ዓመት ዕድሜው አረፈ። የቀድሞው የአርጀንቲና ኮከብ ተጫዋች እና በኋላም የአገሩ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ያረፈው ቤቱ ውስጥ ሳለ በልብ ችግር እንደሆነ ተገልጿል። ማራዶና በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ በአንጎሉ ውስጥ ላጋጠመው የደም መርጋት የተሳካ ቀዶ ሕክምና ተደርጎለት የነበረ ሲሆን በተከታይነትም ከአልኮል ሱስ ለመላቀቅ ሕክምና ይደረግለታል ተብሎ ነበር። የዓለማችን የምንጊዜም ታላላቅ ተጫዋቾች ከሚባሉት አንዱ የሆነው ማራዶና አርጀንቲና እአአ በ1986 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ስትሆን የቡድኑ አምበል የነበረ ሲሆን ድንቅ ችሎታውንና የታወቀባቸውን የኳስ ጥበቡን በማሳየት ዓለምን አስደምሞ ነበር። በተለይ በወቅቱ አርጀንቲና ከእንግሊዝ ጋር ባደረገችው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ እሱ ""የእግዜር እጅ"" ያላትና ዳኞች ሳያዩ በእጁ ያስቆጠራት ግብ ዘወትር ትታወሳለች። በተጨማሪም ለስፔኑ ባርሴሎናና ለጣሊያኑ ናፖሊ ቡድኖች በአውሮፓ ውስጥ የተጫወተ ሲሆን፤ በጣሊያን ሴሪ አ ውስጥም ሁለት ጊዜ ዋንጫ ለማንሳት በቅቶ ነበር። የአርጀንቲና እግር ኳስ ማኅበር የማራዶና ሞት በተሰማ ጊዜ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ ""በጀግናችን ሞት በጣሙን አዝነናል"" በማለት ""ሁልጊዜም በልባችን ውስጥ ትኖራለህ"" ብሏል። ማራዶና ለአገሩ አርጀንቲና በአራት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ በተደረጉ 91 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 34 ግቦችን አስቆጥሯል። ማራዶና የተከለከሉ አበረታች መድኃኒቶችንና ዕጽ በመጠቀም ስሙ በተደጋጋሚ ሲነሳ የቆየ ሲሆን ከስፖርትም እገዳ ተጥሎበት ነበር። ማራዶና ፕሮፌሽናል እግር ኳስን ከዛሬ 23 ዓመት በፊት በ37 ዓመት ዕድሜው ያቆመ ሲሆን፤ በአርጀንቲና ውስጥ ያሉ ቡድኖችን በአሰልጣኝነት ከመራ በኋላ የአገሩን ብሔራዊ ቡድንንም በማሰልጠን ለዓለም ዋንጫ አብቅቷል። ከዚያም በኋላ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና በሜክሲኮ ውስጥ የሚገኙ ቡድኖችን በተለያዩ ጊዜያት አሰልጥኖ ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ደግሞ የአገሩን አንድ ቡድን በማሰልጠን ላይ ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-55074075 +politics በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ምክትል ልዩ መልዕክተኛ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ምክትል ልዩ መልዕክተኛ የነበሩት ፔይተን ክኖፍ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ታማኝ ምንጮች ለቢቢሲ ተናገሩ። ፔይተን አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ መሰየም ከጀመረችበት ካለፈው ዓመት ጀምሮ ምክትል በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተው ነው በዚህ ሳምንት ኃላፊነታቸውን የለቀቁት። ይህም በሰባት ወራት ውስጥ ብቻ ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ቡድኑ ሥራቸውን የለቀቁ ሦስተኛው የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት ያደርጋቸዋል። ፔይተን ከምክትል ልዩ መልዕክተኝነታቸው ባሻገር ከሦስት ወራት በፊት ዴቪድ ሳተርፊልድ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ በጊዜያዊነት የዋና ወኪልነት ቦታውን ሸፍነው ሲሰሩ ቆይተዋል። “እነዚህ ሦስት በርካታ ልምድ እና ብቃት ያላቸው ዲፕሎማቶች ይህንን ወሳኝ ኃላፊነት ወስደው በማገልገላቸው ደስተኞች ነን” ሲሉ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “በአፍሪካ ቀንድ ያለው ያለመረጋጋት እንዲሁም በቀጠናው ያሉት የፖለቲካ፣ የፀጥታ እንዲሁም የሰብአዊ ጉዳዮች ፈተናዎች የአሜሪካን ያልተቋረጠ ትኩረት ይፈልጋሉ” ሲሉም ፕራይስ ለቢቢሲ ገልጸዋል። አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ፔይተን ክኖፍ ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑኩ እንዲሁም ከመንግሥት ሥራ መልቀቃቸውን አረጋግጠዋል። ነገር ግን ለፔይተን ከኃላፊነታቸው መልቀቅ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከእራሳቸውም ሆነ ከሌሎች ምንጮች የተባለ ነገር የለም። በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ነበር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮችን በቅርበት የሚከታተሉ ልምድ ያላቸው ዲፕሎማቶችን የሰየሙት። በጥር 2013 ዓ.ም. የመጀመሪያው የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት ጄፍሪ ፌልትማን በቦታው ላይ ለአንድ ዓመት ገደማ ከቆዩ በኋላ ነበር ከኃላፊነታቸው የለቀቁት። በዚህ ዓመት ጥር ወር ተሹመው ወደ ኃላፊነቱ መጥተው የነበሩት ዴቪድ ሳተርፊልድም ከአራት ወራት በኋላ በተመሳሳይ ራሳቸውን ከኃላፊነቱ አግልለዋል። ከዋና መልዕክተኞቹ በተጨማሪ ለልዑኩ ምክትል በመሆን ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት ክኖፍ ፔይተንም አሁን የቀደሙ አለቆቻቸውን መንገድ ተከትለው ሥራቸውን ለቀዋል። በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚከሰቱ ቀውሶችን በሚከታተለው በዓለም አቀፉ ክራይስስ ግሩፕ ውስጥ ከፍተኛ ተንታኝ የሆኑት ዊሊያም ዳቪሰን፣ ፔይተን “በቀጠናው በርካታ ልምድ እና ጥሩ ግንኙነት ያላቸው ዲፕሎማት” ነበሩ ሲል ይገልጿቸዋል። “እንደ እርሳቸው ያለ አቅም፣ ዕውቀት እና ልምድ ያለው ሰው አዲሱን ልዩ መልዕክተኛ ለመደገፍ መሾም አለበት ብዬ አምናለሁ” ሲል ዳቪሰን ይናገራል። በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን፣ ማይክ ሐመርን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አድርገው መሾማቸውን ገልጸው ነበር። “ይህ ሹመት በቀጠናው ላለን የዲፕሎማሲ ጥረቶች ቁርጠኝነት ማሳያ ነው። በተለይም አንገብጋቢ በሆነው የጋራ ሰላምን እና ብልጽግናን ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለማምጣት የሚደረገውን ሁሉን አካታች ሂደት ለመደገፍ ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል” ሲሉም ስለ አዲሱ መልዕክተኛ የትኩረት አቅጣጫዎች መናገራቸው ይታወሳል። ክኖፍ ፔይተን እጅግ ተቀያያሪ እና ፈታኝ በሆነው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ መልክተኛ ሆነው ለተሾሙት ለሦስቱም መልዕክተኞች ምክትል ሆነው ያገለገ��� ሲሆን አብረዋቸውም በቀጠናው አገራት በርካታ ጉዞዎችን አድርገዋል። ፔይተን ከዚህ ከቀደም በተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ኃላፊነቶቸን በመውሰድ በደቡብ ሱዳን እና በየመን አገልግለዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cy7q55j4lqlo +health ኖቤል ሽልማት፡ 'ሄፒታይተስ ሲ'ን ያገኙት ተመራማሪዎች ኖቤል ተሸለሙ "የሄፒታይተስ ሲ ቫይረስን ያገኙት ሦስት ሳይንቲስቶች በሕክምና ዘርፍ የኖቤል ተሸላሚ ሆኑ። ሳይንቲስቶቹ እንግሊዛዊው ማይክል ሆግተን እና አሜሪካዊያኑ ሀርቪ አልተርና ቻርልስ ራይስ ናቸው። የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ እንዳለው፤ የሳይንቲስቶቹ ግኝት “በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ታድጓል”። ቫይረሱ የኩላሊት ካንሰር ያስከትላል። ህሙማን የኩላሊት ንቅለ ተከላም ያስፈልጋቸዋል። • ሕንድ የሰራችው አዲሱ ፈጣን የኮቪድ-19 መመርመሪያ • ከክትባቱ በኋላ ወደ ቀድሞ ሕይወት ለመመለስ ምን ያህል ጊዜ ያስፈልጋል? እአአ በ1960ዎቹ ደም የተለገሳቸው ሰዎች ባልታወቀ ህመም ሳቢያ ለሄፒታይተስ ይጋለጣሉ የሚል ስጋት ነበር። የኖቤል ሽልማት ኮሚቴው ደም ልገሳ አደገኛ የነበረበት ወቅት እንደነበረ ጠቁሟል። አሁን ግን ለአደጋ የሚያጋልጥ የደም ልገሳን መቅረፍ መቻሉም ተጠቁሟል። በተጨማሪም ፀረ-ቫይረስ መድኃኒቶች ማምረት ተችሏል። ኮሚቴው ""በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ህመሙን መፈወስ ተችሏል። ይህም ሄፒታይተስ ሲን ከዓለም ማስወገድ እንደሚቻል ተስፋ አጭሯል“” ብሏል። ሆኖም ግን በየዓመቱ 70 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ። ከነዚህም 400,000 ይሞታሉ። ገዳዩ ቫይረስ ሄፒታይተስ ኤ እና ቢ የተገኙት በ1960ዎቹ ነበር። በ1972 አሜሪካ ውስጥ ምርምር እያደረጉ የነበሩት ፕ/ር ሀርቪ አልተር ከሁለቱ ቫይረሶች በተጨማሪ ሌላም ገዳይ ቫይረስ መኖሩን ደረሱበት። ብዙዎች ደም ከተለገሳቸው በኋላም ከህመማቸው አልተፈወሱም ነበር። ተመራማሪው፤ ህመም ካለባቸው ሰዎች ለቺምፓንዚዎች ደም መሰጠቱ ለበሽታው ስርጭት ምክንያት መሆኑን ደርሰውበታል። በወቅቱ ምንነቱ ያልታወቀው ህመም ‘ነን ኤ- ነን ቢ’ ወይም ኤም ቢም ያልሆነ ሄፒታይተስ ተብሎ ይጠራ ነበር። ፕ/ር ማይክል ሆግተን በ1989 የቫይረሱን ዘረ መለ መለየት ችለዋል። ከዛም ቫይረሱ ሄፒታይተስ ሲ ተብሏል። • ሩሲያና ቻይና በአሜሪካ ምርጫ ማን እንዲያሸንፍ ነው የሚፈልጉት? በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ይሠሩ የነበሩት ፕ/ር ቻርልስ ራይስ ደግሞ በ1997 ለጥናቱ መደምደሚያ ሰጥተዋል። ሄፒታይተስ ሲ ቫይረስ ላይ ዘረ መል አክለው በቺምፓንዚ ኩላሊት ውስጥ ከጨመሩ በኋላ በሽታው እንዴት እንደሚከሰት ደርሰውበታል። የኖቤል ኮሚቴ ዋና ጸሀፊ ፕ/ር ቶማስ ፐርልማን፤ ከሦስቱ ሳይንቲስቶች መካከል ለሁለቱ ደውለው ኖቤል ማሸነፋቸውን እንደነገሯቸው ገልጸዋል። “ሳነጋግራቸው ደስ ብሎኝ ነበር። ማሸነፋቸውን ሲሰሙ ተገርመዋል። ተደስተዋልም” ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54421300 +health ኢኳዶር ለሁሉም ዜጎቿ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ግዴታ አደረገች ኢኳዶር እየተባበሰ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመግታትና እንደ ኦሚክሮን ያሉ ዝርያዎችን ጉዳት ለመቀነስ በሚል አብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል የኮቪድ-19 ክትባት እንዲወድ የሚያስገድድ መመሪያ አወጣች። የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እንዳለው አጠቃላይ ሕዝቡን ለመከተብ የሚያስችል የክትባት ክምችት ያለ ሲሆን፣ የሕክምና ማስረጃ ያላቸው ሰዎች ብቻ ያለመከተብ መብት ይኖራቸዋል። ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ውስጥም ማንኛውም ዕድሜው ከአምስት ዓመት በላይ የሆነ ሰው በሙሉ ክትባቱን ይወስዳል ተብሏል። እስካሁን ድረስ ዕድሜያቸው ለክትባት ከደረሱ ሰዎች ውስጥ 77.2 በመቶ ያህሉ ሁለት ዙር ክትባት ሲወስዱ ከ900 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሰዎች ሦስተኛ ዙር ክትባታቸውን ወስደዋል። የጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ ክትባቱ ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችል አቅም የፈጠረና ይህም በቫይረሱ ተይዘው ወደ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎችን ቁጥር እና ሞትን ለመቀነስ ያገዘ ነው። በአገሪቱ ሕገ መንግሥት የተቀመጠው የዜጎችን ጤንነት የማስጠበቅ ግዴታ በመንግሥት ጫንቃ ላይ የወደቀ መሆኑንና እርሱን ለማስፈጸም ሕጉን መሠረት ተደርጎ የተሰጠ ውሳኔ መሆኑን የኢኳዶር ጤና ሚኒስቴሩ ገልጿል። አውስትራሊያ እና ጀርመን ተመሳሳይ ውሳኔ የመስጠት ዕቅድ ያላቸው አገራት ናቸው። ኢኳዶር ሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ጥቅም ላይ የሚውል የክትባት የምስክር ወረቀት ለዜጎቿ አዘጋጅታለች። ወደ ሲኒማና ቴአትር ቤቶች ወይም የገበያ ማዕከላት ለመግባት ይህንን ወረቀት ማሳየት ግዴታ ይሆናልም ተብሏል። ኢኳዶር የኮቪድ-19 ወረርሺኝ ከተከሰተ ጀምሮ 33 ሺህ 600 ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዘ ሞት መዝግባለች። https://www.bbc.com/amharic/news-59778546 +politics የኢትዮጵያና የቱርክ መሪዎች ውይይት በአንካራ "በትናንትናው ዕለት በቱርኳ መዲና አንካራ የተገናኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ፕሬዚዳንት ረጂብ ጣይብ ኤርዶጋን የትግራይ ግጭት፣ የሱዳንና የኢትዮጵያ የድንበር ውዝግብን በተመለከተ መክረዋል፤ እንዲሁም ወታደራዊ ስምምነቶችም ላይ መድረሳቸውም ተገልጿል። ሁለቱ አገራት ወታደራዊ የገንዘብ ስምምነትን ላይ መፈራረማቸው ቢገለፅም የስምምነቱ ዝርዝር አስካሁን ይፋ አልሆኑም። ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን የትግራይን ጦርነት በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጠይቀው ግጭቱንም ለመፍታት አገራቸውም የምትችለውን ሁሉ ታደርጋለች ብለዋል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአስቸጋሪ ወቅት እያለፈች መሆኑንም አስታውሰው ለትግራይ ግጭት ለዘብተኛ መፍትሄ ሊፈለግለት እንደሚገባ ሃሳብ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አገራት ውስጥ ቁልፍ ሚና የምትጫወት ናት ያሉት ፕሬዚዳንቱ ""የግዛት አንድነቷ መጠበቅም ሆነ ሰላም ለእኛ ጠቃሚ ነው"" በማለት አገሪቷ ያላትን ስፍራ አፅንኦት ሰጥተዋል። ግጭቱ በሰላም እንዲፈታም ከፍተኛ ትኩረት መንግሥታቸው መስጠቱን ጠቅሰው ""ካለበለዚያ ግጭቱ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የቀጠናው አጎራባቾች አገራትም መጎዳታቸው አይቀርም"" ብለዋል። ፕሬዚዳንት ኤርዶጋንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ረቡዕ ዕለት ነሐሴ 12/2013 ዓ.ም በአንካራ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን የተናገሩት። የሁለቱ አገራት መሪዎች በተገናኙበት ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል በአልፋሽቃ ያለውን የድንበር ውዝግብና ፍጥጫም አንስተዋል። ግጭቱ በውይይት እንደሚቋጭ ተስፋ አድርገው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትናንትናው ዕለት እንዲሁም ከሱዳኑ ሽግግር ምክር ቤቱ ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አልቡህራን ጋር ከሳምንት በፊት ውይይት ማድረጋቸውን ለጋዜጠኞች አስረድተዋል። ""በሰላማዊ ሁኔታ እንዲቋጭም ማንኛውንም አይነት ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ነን። አደራዳሪነትንም ጨምሮ"" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። የሁለቱ አገራት መሪዎች ለዘመናት የዘለቀውን ግንኙነታቸውን በተመለከተ እንዲሁም በምጣኔ ሀብት፣ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት ያለው ትስስር በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። ቱርክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የኢንቨስትመንት ግንኙነት 2.5 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም በመሰረተ-ልማት፣ በትራንስፖርት፣ በጨርቃ ጨርቅና በሌሎችም ዘርፎች ላይ እንደሆነ በወቅቱ ተገልጿል። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ዓመታዊ የንግድ ግንኙነትም 650 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን ፕሬዚዳንቱም አ��ድ ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የሁለትዮሽ ንግድን እውን ለማድረግ መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች መገምገማቸውን ተናግረዋል። በርካታ የቱርክ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰው ከዚህም በተጨማሪ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንንም እኚሁ ኩባንያዎች መቅጠር መቻላቸውንም አስታውሰዋል። ""በኢትዮጵያ ውስጥ የምናደርገው ይህ ኢንቨስትመንትም እንደሚጨምር ተስፋ አለን። በዚህ ረገድም አስፈላጊውን ድጋፍና እውቅና እንሰጣለን፤ ከዚህም ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግሥት ኩባንያዎቻችንን እንደሚደግፍ እርግጠኞች ነን"" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነትም እንዲጠናከር አገራቸው አጥብቃ እንደምትሰራ የመንግሥታቸውን አቋም ገልፀዋል። ለቱርክ ኢንቨስተሮችም ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን በማለትም ለፕሬዚዳንቱ መልሰዋል። ሁለቱ አገራት በተለያዩ ዘርፎች ላይ ጠቃሚ ያሉትን ስምምነቶችን መፈራረማቸውን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህም ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊና፣ ማኅበራዊ ትብብሮችን ስምምነቶችንም ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል። የሁለቱ አገራት ግንኙነት የተመሰረተው ""በመከባበር፣ በመተማመን እና በትብብር ላይ ነው"" በማለት በዚህ አስፈላጊ ወቅትም ቱርክ አጋርነቷንና ወዳጅነቷን ማሳየቷን አድንቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንንም በተመለከተ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ""የቱርክ መንግሥት እና ሕዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር አገራችን ኢትዮጵያ መቼም አትረሳውም"" በማለት አስፍረዋል። ኢትዮጵያ የቱርክን አጋርነትና ወዳጅነት ዋጋ እንደምትሰጥ ገልፀው በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የቱርክ 'ኮኦፐሬሽንና ኮኦርዲኔሽን ኤጀንሲ' በአዲስ አበባ ምስረታንም በመጥቀስ ምስጋናቸውን ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሁለቱን አገራት ጥንታዊ ስልጣኔ ተመሳሳይነት አስታውሰው 16ኛው ክፍለ ዘመንም ወደኋላ ያስቆጠረ ነው ብለዋል። ቱርክ ለብዙዎች አርዓያ የሆነ የአገር ግንባታ እንዳካሄደች በዚሁ አጋጣሚ ጠቅሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በተለይም አገሪቱ በለውጥ ጎዳና እየሄደች ባለችበት በአሁኑ ወቅት ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸውንም ለማጠናከር እየሰሩ እንደሆነ ጠቅሰዋል። የሁለቱም አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የቀጠለ ነው እንዲሁም የቱርክ ፊልም ኢንዱስትሪ ለዚህም ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በአውሮፓውያኑ 2015 ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰው ""ኢትዮጵያ ምንጊዜም ቢሆን የመቻቻልና ልዩነቶች የሚከበሩባት ምድር ናት። ይህም የኢትዮጵያን የአገር ውስጥ እና የውጭ ግንኙነት መሰረት መንፈስን ያጠቃለለ ነው"" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር በቱርክ ያደረጉትን የአንድ ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ረቡዕ ምሽት ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው ተገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58265923 +health ኮሮናቫይረስ፡ ፈተና ውስጥ የገባው የግብርና ዘርፍ ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ በርካታ ነገሮች ተቀያይረዋል። ሰው የማይንቀሳቀስባቸው ዋና ጎዳናዎች ታይተዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚታደሟቸው የእግር ኳስ ውድድሮች ያለ ድጋፍ ተካሂደዋል፣ የዓለም መሪዎች ሳይቀር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርገው ታይተዋል። ምናልባት ለብዙዎችም ኮሮረናቫይረስ ሲባል በጭንቅላታቸው የሚመጡት ምስሎች እነዚህ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን ወረርሽኙ በአይናችን ከምናያቸውና በቅርቡ ከምናስተውላቸው ነገሮች በተጨማሪ የበርካቶችን ሕይወት ከስረ መሰረቱ ቀይሯል፤ እንዳልነበር አድርጎ አበላሽቷል። ነገር ግን ወረርሽኙ ያስከተለው ጉዳት በሁሉም አገራትና አህጉራት ተመሳሳይ አይደለም። እንዳውም ንጽጽሩ በበርካቶች ዘንድ ግርምትን የፈጠረ ነው። አፍሪካ ውስጥ ብቻ በ36 አገራት የሚገኙ 73 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ከባድ የምግብ እጥረት የጋጠማቸው ሲሆን በአውሮፓ ግን ግማሽ ሚሊየን የሚሆኑት ብቻ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል። ከዚህ በፊት በኢቦላ ወረርሽኝ ስትሰቃይ የነበረችው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በእርስ በርስ ጦርነት የምትታመሰው ደቡብ ሱዳን ደግሞ በወረርሽኙ ምክንያት ከፍተኛ የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው አገራት ናቸው። በአፍሪካ የሚገኙ ገበሬዎች በክረምት ወር የሚዘሩትን ዘር ማግኘት ያልቻሉ ሲሆን በአሜሪካ ደግሞ የእርድ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች በመዘጋታቸው ከብቶቻቸውን ሳይፈልጉ ለማቆየት ተገድደዋል፣ ወተት ገዢ አጥተው ምርታቸውን ለመድፋት ተገድደዋል። የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝም በዓለማችን ላይ ያለውን የምግብ ስርጭት ስርአት ቁልጭ አድርጎ አሳይቷል። ባደጉት አገራት ከግብርና ስራ ጋር የተከሰቱት ችግሮች ቀላል የሚባሉ ባይሆኑም ድሀ በሚባሉትና በማደግ ላሉት አገራት ግን ጉዳቱ ከፍተኛ ነው። በድሆቹ አገራት ግብርና በብዛት የጉልበት ስራ ላይ የተንጠለጠለ ሲሆን ዘር ከመዝራት አንስቶ እስከ መሰብሰብ ድረስ ባህላዊ በሆነና በርካታ ሰዎች በሚያሳትፍ መልኩ ነው የሚካሄደው። በአውሮፓ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ጋር ተያይዞ ተግባራዊ በተደረጉት የእንቅስቃሴ ገደብና ሌሎች እርምጃዎች ምክንያት በግብርናው ዘርፍ ላይ በጊዜያዊነት ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ በርካታ ሰዎች ሕይወት የተመሰቃቀለ ሲሆን ምርቱን የሚሸጡትም ሰዎች ቢሆኑ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ይህንን ተከትሎም የምግብ ስርጭቱ ላይ ከፍተኛ አለመረጋጋትና እጥረት ተከስቷል። ለምሳሌ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 75 ሺ ሰዎች በጊዜያዊነት በግብርና ስራ ላይ ተቀጥረው ይሰሩ ነበር። አብዛኛዎቹ ደግሞ ከሌሎች የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት የመጡ ናቸው። ወረርሽኙን ተከትሎ በተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦችና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎች ምክንያት ታዲያ እነዚህ ሰራተኞች በስራ ቦታቸው ላይ መገኘት ባለመቻላቸው አብዛኛዎቹ ወደመጡባቸው አገራት ተመልሰዋል። ገበሬዎችን የጉልበት ስራውን የሚሰራላቸው ሰው በማጣታቸው ተቸግረዋል። በአጠቃላይ በአውሮፓ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ጊዜያዊ ሰራተኞች ከስራ ውጪ መሆናቸውን ተከትሎ የግብርናው ዘርፍ ከፍተኛውን ጉዳት አስተናግዷል። በተመሳሳይ በአውስትራሊያም ቢሆን በአትክልት ምርት ላይ ተሰማርተው ከሚገኙ ሰዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በጊዜያዊነት ተቀጥረው የሚሰሩ ሲሆኑ በአሜሪካ ደግሞ 10 በመቶ የሚሆነውን ቁጥር ይይዛሉ። በካናዳ ያሉ ትልልቅ ማሳዎች ደግሞ ከ60 ሺ በላይ የሚሆኑ ከሌሎች አገራት የመጡ ሰራተኞችን ቀጥረው ያሰራሉ። በብራዚል ደግሞ ቡና አምራች ገበሬዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በጊዜያዊነት ቀጥረው ያሰሩ ነበር። ነገር ግን በእንቅስቃሴ ገደቡ ምክንያት እነዚህ ሰዎች በስራ ገበታቸው ላይ መገኘት አለመቻላቸው ዘርፉ ላይ ከሚያስከትለው ጉዳት በተጨማሪ ሕይወታቸውን በዚሁ ስራ ላይ ላደረጉ ሰዎች ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል። ከግብርናው ዘርፍ ሳንወጣ የከብት አርቢዎች ሕይወትም ቢሆን በዚሁ ወረርሽኝ ምክንያት ተጎድቷል። ምንም እንኳን ይሄ ዘርፍ በተለይም እርድ ላይ ያለው ሂደት ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በፊትም ከፍተኛ ንጽህና የሚፈልግ ቢሆንም ከኮቪድ-19 በኋላ ግን ነገሮች ከባድ ሆነዋል። በአውሮፓ 90 በመቶ የሚሆነው የስጋ ምርት እዛው የተመረተበት አገር ውስጥ አልያም አውሮፓ ውስጥ ነው ጥቅም ላይ የሚውለው። ነገር ግን ይህ ማለት ከእንቅስቃሴ ገደቡ ጋር በተያያዘ ችግር አያጋጥመውም ማለት አይደለም። ምርቱ ተቀናባብሮ ወደ ተጠቃሚዎች እስከሚደርስበት ባሉት የሂደት ስርአቶች ውስጥ የሚሰሩ በርካታ ሰዎች ከስራ ውጪ ሆነዋል አልያም ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ ሆነዋል። እዚህም ጋር ተጠያቂው ኮሮረናቫይረስ ነው። በአፍሪካ ደግሞ በግብርና፣ ማዕድን እና ግንባታ ዘርፎች ላይ የኮሮናቫይረስ ጉዳትን ለመቀነስ አገራት ቀጣይነት ያለውና ውጤታማ እርምጃ በፍጥነት መውሰድ ግድ ይላቸዋል። ግብርና የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ በእጅጉ የሚደግፍ ዘርፍ እንደመሆኑ ደግሞ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ባለሙያዎች ከወዲሁ እያሳሰቡ ነው። በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት የዝናብ ወቅት ሲቃረብ የገበሬዎች ማሳ በተቻለ መጠን በሰብል እንዲሞላ ማድረግ አለባቸው። የአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ መር ሽሽግር በሚያደርጉበት በዚህ ወቅት የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ትልቅ ስጋት ነው። ከዚህ በተጨማሪ መንግሥታት የከተማ ግብርና ላይ ያላቸውን መቀየር ግድ ይላቸዋል። ምክንያቱም ለብዙ ዓመታት ሲሰራበት የነበረውን የግብርና ስርአት ይዞ መቀጠል ስለማይቻል ዜጎች በቀላሉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በከተሞች አካባቢ እንዲ|ያመርቱ ማድረግ ከኮሮረናቫይረስ በኋላም አዋጭ አካሄድ ይሆናል። https://www.bbc.com/amharic/news-54577100 +health “ከኮሮናቫይረስ ባገግምም አሁንም በሽታው ይገድለኛል ብዬ እፈራለሁ” የ42 ዓመቱ ራጀሽ ቲዋሪ ከስልኩ የሰፋ መጠን ያለው ስክሪን ይፈራል። ቴሌቭዥን ወይም ኮምፒውተር አንዳች ጥቃት የሚያደርሱበት ፍጥረቶች ይመስሉታል። ራጀሽ ቅዠት የጀመረው በጽኑ ህሙማን ክፍል ዘለግ ላለ ጊዜ ከቆየ በኋላ ነበር። ሰኔ ላይ ኮሮናቫይረስ ይዞት ስለተዳከመ በቬንትሌተር እየታገዘ እንዲተነፍስ ተደርጓል። ራጀሽ ከሦስት ሳምንት በኋላ ተሽሎት ከሆስፒታል ቢወጣም ሙሉ በሙሉ እንዳላገገመ ተገነዘበ። “ሕክምናው ቢያሽለኝም ከሆስፒታል ከወጣሁ በኋላ የነበሩት የመጀመሪያ ሳምንታት በጣም ከባድ ነበሩ” ይላል። ወደ ቤት ሲመለስ ቤተሰቦቹ እጅግ ተደስተው ነበር። ቆየት ሲል ግን ራጀሽ እንደ ቀድሞው እንዳልሆነ አስተዋሉ። አንድ ቀን ቴሌቭዥን እያየ በጣም ጮኸ። ቲቪውን ለመስበርም ሞከረ። ከዛ በኋላ ቤተሰቡ ቲቪ መመልከትና ላፕቶፕ መጠቀም አቆመ። ራጀሽ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ሳለ የተመለከታቸው የሕክምና መሣሪያዎችን ለመርሳት እየታገለ ነው። የ49 ዓመቱ አሚት ሻርማም ተመሳሳይ ተሞክሮ አለው። ለ18 ቀናት በለይቶ ማቆያ ሳለ በየቀኑ ሰዎች ሲሞቱ አይቷል። ወጣት፣ አዛውንት፣ ሴት፣ ወንድ. . . በርካታ የኮቪድ-19 ታማሚዎች በሞት ሲለዩ አሚት ተመልክቷል። “ሁለት ሰዎች አጠገቤ ሞተው አስክሬናቸው ለረዥም ሰዓት አልተነሳም ነበር። ይህንን ከአዕምሮዬ ማውጣት አልቻልኩም። አሁንም ኮሮናቫይረስ ሊገለኝ ይችላል ብዬ እፈራለሁ” ይላል። አሚት አሰቃቂ ቆይታውን ለመርሳት እየታገለ ነው። ከኮሮናቫይረስ ካገገመ በኋላ ጭምት ሆኗል። ካወራም በበሽታው ሳቢያ ስለሞቱ ሰዎች እንደሚያወራ አጎቱ ይናገራሉ። ኮቪድ-19 የሚያስከትለው የአዕምሮ ጤና ቀውስ በሕንድ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች የአዕምሮ ጤና ቀውስ እየገጠማቸው ይገኛል። የሥነ ልቦና ሀኪሙ ዶ/ር ቫሰንት ሙንድራ “ገና ሆስፒታል ሳይደርሱ አዕምሯቸው ይዳከማል። ከዛ ኮቪድ-19 ደግሞ የስሜት ህዋሳትን የበለጠ ያዝላል” ይላሉ። ህሙማኑ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ አይፈቀድም። ሀኪሞ���ቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ስለሚያደርጉም ፊታቸውን ማየት አይችሉም። ይህም ዶክተሮቻቸውን እንዳያምኑ ያደርጋቸዋል። የኮሮናቫይረስ ህሙማን ሲያገግሙ ብቸኝነት ሊሰማቸው ይችላል። አስጨናቂ ክስተትን ተከትሎ የሚከሰት ድብት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉም ዶ/ር ቫንሰት ያስረዳሉ። ከኮሮናቫይረስ ህሙማን ጋር የተያያዘ የአዕምሮ ህመም ተገቢውን ትኩረት አላገኘም። “በወረርሽኙ ወቅት እየታየ ያለው ሕንድ ለአዕምሮ ጤና ብዙም ቦታ እንደማትሰጥ ነው” የሚሉት ዶ/ር ሶሚትራ ፓትሬ ናቸው። የአዕምሮ ህሙማንን ለማከም በቂ ሆስፒታል እንዲሁም ባለሙያዎች የሉም። በትንንሽ ከተሞች ደግሞ ችግሩ ይከፋል። በከተማና በገጠር የሚኖሩ ሰዎች ለአዕምሮ ጤና ያላቸው ተደራሽነት እኩል አለመሆኑን ወረርሽኙ እንዳሳየ ዶክተሩ ይገልጻሉ። “የሕንድ መንግሥት ችግሩን በአፋጣኝ ካልፈታ የአዕምሮ ህመም ወረርሽኝ ይገጥመናል” ሲሉም ያክላሉ። ባለሙያው እንደሚሉት፤ የመጀመሪያው እርምጃ ሰዎች ስለ አዕምሮ ህመም ምልክቶች እንዲያውቁ ማድረግ ነው። በተለይም ለአነስተኛ ከተማ ነዋሪዎች ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። በደልሂው ፎርቲስ ሆስፒታል የአዕምሮ ጤና ክፍል ኃላፊ ካምና ቺቤር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በርካታ ሰዎች የአዕምሮ ህመም እንደገጠማቸው ይናገራሉ። የእንቅስቃሴ ገደቡና ወደፊት ምን እንደሚከሰት አለማወቅ ብዙዎችን ጭንቀትና ድብርት ውስጥ ከቷል። “ችግሩ ከእለት ወደ እለት እየተባባሰ ነው” ብለዋል ኃላፊዋ። በድህረ ኮቪድ-19 ማገገሚያ እቅድ የአዕምሮ ጤና ጉዳይ እንዲገባ በርካታ ሀኪሞች እየጠየቁ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-54174457 +sports የዓለም ዋንጫ፡ ሴኔጋል ስትሸነፍ የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ልጅ ለአሜሪካ ጎል አስቆጥሯል ባለቀ ሰዓት በተቆጠረባት ጎሎች ሴኔጋል የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታዋን በኔዘርላንድስ 2 ለ 0 ተሸንፋ ጀምራለች። የመጀመሪያውን ጎል የፒኤስቪ አጥቂ ኮዲ ጋክፖ አስቆጥሯል። ተቀይሮ የገባው ዳቪ ክላሰን ሁለተኛዋን ጎል ለብርቱካናማዎቹ ማስቆጠር ችሏል። የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ውጤታማ ባለመሆናቸው ጨዋታው ለረዥም ደቂቃዎች ጎል ሳይቆጠርበት ቀጥሏል። ሴኔጋሎች በጉዳት ያጡት አጥቂያቸው ሳዲዮ ማኔ ምን ያህል እንዳጎደላቸው የታየበት ጨዋታም ሆኗል። የሴኔጋል ደጋፊዎች ስታዲሙን አድምቀውት አምሽተዋል። የሴኔጋሉ ኢስማይላ ሳር በመጀመሪያው አጋማሽ የኔዘርላንድ ተከላካዮችን አስጨንቋል። የኔዘርላንዱ አማካይ ዲ ዮንግ ደግሞ ጨዋታውን በመቆጣጠር ብቃቱን ያሳየበት ምሽት ነበር። ድሉን ተከትሎ ብርቱካናማዎቹ በመክፈቻው ጨዋታ ኳታርን 2 ለ 0 ካሸነፈችው ኢኳዶር ጋር ምድቡን መምራት ችላል። ምሽት ላይ በተካሄደ ሌላ ጨዋታ የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ልጅ ለአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ ኳስ እና መረብ ለማገናኘት በቅቷል። የፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ልጅ የሆነው ቲሞቲ ዊሃ አሜሪካ እና ዌልስ አንድ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ነው ለአሜሪካ ጎል ማስቆጠር የቻለው። ከክርስቲያን ፑሊሲች የተሻገረለትን ኳስ ቲም ዊሃ ድንቅ በሆነ ሁኔታ ከመረብ ጋር አገናኝቷል። በጨዋታው መገባደጃ ላይ ዌልስ አቻ ማድረግ የቻለችውን ጎል ጋሬት ቤል ከፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሏል። ፕሬዝዳንት ዊሃ በአሜሪካ የተወለደው ልጁ የዓለም ዋንጫ ላይ ሲሳተፍ ለመመልከት ዘጠኝ ቀናትን በኳታር አሳልፏል። የፕሬዝዳንቱ ጉዞ በሃገር ቤት ውዝግብ አስነስቷል። የሃገሪቱ የፋይናንስ ሚንስትር ፕሬዝዳንቱ 2ሺህ ዶላር ቀን አበል አለው ማለቱ ነው የውዝግቡ መነሻ። ተቺዎችም ፕሬዝዳንቱ ቃል የገባለትን “ደሃን የሚያቅፍ አጀንዳውን” የሚቃረን ነው ሲሉ ገልጸዋል። የዓለም ዋንጫው ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች እንግሊዝ ከኢራን ባደረጉት ጨዋታ ነው የተጀመረው። ጨዋታውን እንግሊዝ 6 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። እንግሊዝ የጎል ካዝናዋን የከፈተችው በጁድ ቤሊንግሃም የጭንቅላት ጎል ነው። ቡካዮ ሳካ እና ራሂም ስተርሊንግ ከእረፍት በፊት ባስቆጠሯቸው ጎሎች እንግሊዝ 3 ለ 0 መምራት ችላለች። ከእረፍት መልስ ሳካ ለራሱ ሁለተኛዋን ለቡድኑ ደግሞ አራተኛው ጎል አስቆጥሯል። መህዲ ታሬሚ ለኢራን የመጀመሪያዋን ጎል በ65ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል። ማርከስ ራሽፎርድ እና ጃክ ግሪሊሽ ቀሪዎቹን ጎሎች ተቀይረው ገብተው አስቆጥረዋል። ታሬሚ ሁለተኛዋን የኢራን ጎል ከፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሏል። የኳታር የዓለም ዋንጫ ሦስተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ይካሄዳሉ። ሊዮኔል ሜሲን የያያዘችው አርጀንቲና ቀን ሰባት ሰዓት ላይ በሉሳይል ስታዲየም ሳዑዲ አረቢያን ይገጥማሉ። በሜድቡ ሌላኛ ጨዋታ ሜክሲኮ እና ፖላንድ ስታዲየም 974 ላይ ይገናኛሉ። ኤጁኬሽን ሲቲ ስታዲየም ላይ ቱኒዝያ እና ዴንማርክ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። ፈረንሳይ ደግሞ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ከአውስትራሊያ ጋር ትጫወታለች። https://www.bbc.com/amharic/articles/cjr28r4g5yko +health የዝንጀሮ ፈንጣጣን መቆጣጠር እንደሚቻል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ "የዝንጀሮ ፈንጣጣ(ሞንኪፖክስ) ባልተለመደባቸው ከአፍሪካ ውጭ ባሉ አገራት የቫይረሱን ሥርጭት መቆጣጠር እንደሚቻል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። እስካሁን ድረስ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እና አውስትራሊያ ትኩሳትና በሰውነት ላይ ሽፍታ የታየባቸው ከ100 በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይሁን አንጂ ቁጥሩ ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ይጠበቃል፤ ነገር ግን ባለሙያዎች ሰፊ ሕዝብ ለዚህ አደጋ የመጋለጥ እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነው ብለዋል። ቫይረሱ በመካከለኛው እና ምዕራብ አፍሪካ ገጠራማ አካባቢዎች የተለመደ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት የሚከሰቱ አዳዲስ በሽታዎች መሪ ማሪያ ቫን ኬርክሆቭ ቫይረሱን መቆጣጠር የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። "" ከሰው ወደ ሰው እንዳይተላለፍ ማቆም እንፈልጋለን"" ያሉት መሪዋ፣ በቅርቡ በሽታው የተገኘባቸው አውሮፓንና ሰሜን አሜሪካን ጠቅሰው ""በሽታው ወረርሽኝ ባልሆነባቸው አገራት ይህንን ማድረግ እንችላለን"" ብለዋል። ቫይረሱ እስካሁን ከአፍሪካ ውጭ በ16 አገራት ተገኝቷል። ምንም እንኳን ይህ በ50 ዓመታት ውስጥ ከአፍሪካ ውጭ በስፋት የተከሰተ በሽታ ቢሆንም የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ እንደማይተላለፍ እንዲሁም ህክምናውም ቢሆን ከኮሮናቫይረስ ጋር እንደማይወዳደር ባለሙያዎች ተናግረዋል። ""ቫይረሱ የሚተላለፈው በሽታው ካለበት ሰው ጋር በሚኖር የቆዳ ንክኪ ነው። አብዛኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም ቀለል ያለ ህመም ነው ያጋጠማቸው"" ብለዋል ቫን ካርክሆቭ። ሌላ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣንም አሁን የተከሰተውን ወረርሽኝ መንስዔ በተመለከተ ቀደም ብለው ሲሰራጩ የነበሩ መላምቶችን ተከትሎ በሰጡት ምላሽ፣ ሞንኪፖክስ ልውጥ ቫይረስ መሆኑን የሚያሳይ ምንም መረጃ አለመኖሩን ገልጸዋል። በዓለም ጤና ድርጅት የስሞልፖክስ ኃላፊ ሮሳመንድ "" የቫይረሱ ዝርያ ራሱን የመለወጥ ባሕርይ የለውም። ይልቁንስ ዝርያዎቹ ባሉበት የመቆየት ባህርይ ነው ያላቸው"" ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ ባለሥልጣን የተወሰኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከሌሎቹ በበለጠ ለአደጋው ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። የአውሮፓ በሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዳሬክተር ዶክተር አንድሪያ አሞን እንዳሉት በሰፊው ሕዝብ ዘንድ በ���ታው የመተላለፍ እድሉ አነስተኛ ነው፤ ይሁን እንጂ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ሰዎች ለምሳሌ ከተለያዩ ሰዎች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈፅሙ ሰዎች ለበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው። የዝንጀሮ ፈንጣጣ (ሞንኪፖክስ) ቀደም ብሎ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ አለመሆኑ የተገለጸ ቢሆንም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት በሚኖር ቀጥተኛ ንክኪ ሊተላለፍ ይችላል። ዶክተር አሞን አክለውም የዝንጀሮ ፈንጣጣን ለመከላከልም ውጤታማ ነው የተባለውን ስሞልፖክስ ክትባት እንዳላቸው አገራት ማረጋገጥ እንዳለባቸው መክረዋል። 55 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በተገኙባት ዩናይትድ ኪንግደም፣ ባለሥልጣናት በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን ለ21 ቀናት እንዲያገሉ መክረዋል። አንድ ሰው በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈፅሞ ከሆነ ፣ አንሶላ እና ሌሎች አልባሳትን ተጋርቶ ከሆነ አሊያም የበሽታው መከላከያ የህክምና ቁሳቁሶችን በጋራ ተጠቅሞ ከሆነ ለበሽታው ተጋልጦ ሊሆን እንደሚችል ይታሰባል። ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት፣ ማሳከክ፣ በኋላ ላይ ውሃ የሚቋጥር እብጠት የሚያስከትል ሽፍታ የበሽታው ምልክቶች ሲሆኑ እነዚህ ብዙውን ጊዜ ቀለል ያሉ ናቸው። አብዛኛው ሰውም ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት ባሉት ጊዜ ውስጥ ከበሽታው ያገግማሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-61561522 +politics ቦልሶናሮ ተሸንፈው ኢናሲዮ ሉላ የብራዚል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ በብራዚል በተከናወነው ፕሬዝዳናታዊ ምርጫ ግራ ዘመሙ የቀድሞ ፕሬዝዳት ሊውዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የቀኝ አክራሪውን እና የወቅቱ ፕሬዝዳናት ጄር ቦልሶናሮን አሸንፈዋል። እጅግ መከፋፈል ከታየበት የሁለቱ ተቀናቃኞች የምርጫ ዘማቻ በኃላ ሉላ 50.9 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸናፊ ሆነዋል። ይህ ውጤት እንደሚያሸንፉ እምነት ለነበራቸው የቦልሶናሮ ደጋፊዎች አስደንጋጭ ሆኗል። ሆኖም ይህ ምርጫ በአገሪቱ የፈጠረው መከፋፈል በቀላሉ የመጥፋት ዕድሉ ዝቅተኛ ነው። የዚህ ምርጫ ውጤት እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 በተካሄደው ምርጫ ላይ እስር ቤት በመሆናቸው እና እንዳይወዳደሩ ተግደው የነበሩትን ሉላ ወደ ፖለቲካው የመለሰ ነው። ፖለቲከኛው በዛ ወቅት የብራዚል መንግሥት የነዳጃ ኩባንያ የሆነው ፔትሮ ብራስ የውል ስምምነት ለማሰር ጉቦ ተቀብለዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤት ጥፋተኛ እንደሆኑ ወስኖባቸው ነበር። የተላለፈባቸው ብይን ተሰረዞ ወደ ፖለቲካ ህይወታቸው ከመመለሳቸው በፊት 580 ቀናትን በእስር ቤት አሳልፈዋል። ዳ ሲልቫ አሸናፊ መሆናቸውን ከረጋገጡ በኃላ ባደረጉት ንግግር “ከነ ሕይወቴ ሊቀብሩኝ ሞክረው ነበር። እኔ ግን እዚህ ደርሻለሁ” ብለዋል። የቅድመ ምርጫ ግምቶች ሉላ እንደሚያሸንፉ አመለክተው የነበረ ቢሆንም በመጀሪያው ዙር የውጤት ልዩነቱ ከተጠበቀው በታች ሆኗል። በዚህም በርካታ ብራዚላውያን የውጤቱን ትክክለኛነት ተጠራጥረው ነበር። የግራ ዘመሙን ፖለቲከኛ አሸናፊነት አንቀበልም የሚሉት የቦልሶናሮ ደጋፊዎች ዳ ሲልቫን “ሌባ” እያሉ የሚጠሯቸው ሲሆን ክሳቸው መሰረዙ ነጽህናቸውን የሳያል ማለት አይደለም ይላሉ። ጄር ቦልሶናሮ ቢሸነፉም ለሳቸው ቅርበት ያላቸው ህግ አውጪዎች የምክር ቤቱን አብላጫ መቀመጫ አግኝተዋል። ይህ ማለት ሉላ በፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው የሚያወጧቸው ፖሊሲዎች በምክር ቤቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ይገጥመዋል ማለት ነው። ሆኖም እንደ አውሮፓውያኑ ከ2003 እስከ 2010 ለሁለት የምርጫ ዘመን በስልጣን የነበሩት ሉላ ፖለቲካዊ ጥምረት ለመመሰረት አዲስ አይደሉም። በዘንድሮ ምርጫ መክትላቸው ሆነው የተወዳደሩት እና ከዚህ ቀደም ተ���ዋሚያቸው የነበሩትን አልኪም ከጎናቸው ማሰለፍ ችለዋል። ዳ ሲልቫ አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኃላ ባደረጉት ንግግር በተለሳለሰ ሁኔታ የመረጧቸውን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ብራዚላውያንን እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል። “ይህ አገር ሰላም እና አንድነት ይፈልጋል። ይህ ሕዝብ ከዚህ በኃላ ጸብ አይፈልግም” ብለዋል። የ77 ዓመቱ ሉላ ፖለቲካን ከመቀላቀላቸው በፊት የብረታ ብረት ባለሙያ ነበሩ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c3g83xdpdzxo +sports ቻምፒየንስ ሊግ፡ ኔይማር ያነባበት፤ ሌዋንዶውስኪ የፈነደቀበት ምሽት የጀርመኑ ባየርን ሚዩኒክ የፈረንሳዩን ፒኤስጂ በመርታት የኮሮናቫይረስ ዘመን የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ባለድል ሆኗል። የቀድሞው የፒኤስጂ ተጫዋች ኪንግስሊ ኮማን በ59ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ነው የጀርመኑ ክለብ በአውሮፓ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠውን ዋንጫ ለስድስተኛ ጊዜ ያነሳው። ባለፈው ኅዳር ወር ባየርን ሚዩኒክን በጊዜያዊነት የተረከቡት አሠልጣኝ ሃንስ ፍሊክ የጀርመን ቡንደስሊጋን ማንሳታቸው አይዘነጋም። አሁን ደግሞ የሥራ ማመልከቻቸው ላይ ቻምፒየንስ ሊግ ጨምረዋል። የፒኤስጂ የፈት መስመር አሸከርካሪዎች ብራዚላዊው ኔይማርና ፈረንሳዊው ወጣት ምባፔ በሃዘን አንገታቸውን ደፍተው ታይተዋል። የጨዋታው ኮከብ የነበረው የባየርን ግብ ጠባቂ ማኑዌል ኑዌር ኔይማርና ምባፔን አላነቃንቅ ብሎ አምሽቷል። ሁለቱ ቡድኖች ተፈራርተው የገቡበት ጨዋታው የታሰበውን ያክል አዝናኝና ጎል የተመረተበት ባይሆንም ባየርን ሚዩኒክ የተሻለ ቡድን ሆኖ አምሽቷል። የፒኤስጂው ምባፔ በባየርን የጎል ሳጥን ውስጥ በጆሽዋ ኪሚክ ተጠልፎ የወደቀ ቢመስልም የዕለቱ ዳኛ ጥፋቱ ፍፁም ቅጣት ምት የሚያሰጥ አይደለም ብለዋል። ጎል በማምረት የሚታወቁት ባየርኖች የተከላካይ መስመራቸው የሳሳ በመሆኑ በፒኤስጂ ከዋክብት ጉድ ይሆናሉ ተብሎ ቢገመትም ኔይማርና ምባፔ እንዲሁም ዲ ማሪያ ልዩነት መፍጠር አልቻሉም። በኢቫን ፔሪሲች ምትክ ኮማንን ያሰለፉት ሃንስ ፍሊክ ከስፖርት አዋቂዎች ምስጋና ተችሯቸዋል። ባየርን ሚዩኒክ ሁሉንም ጨዋታዎች በማሸነፍ ዋንጫው በማንሳት ታሪክ ከመሥራታቸው አልፎ የስፔንና አውሮፓ ኃያሉን ባርሴሎና በሩብ ፍፃሜው 8-2 በመርታት ብዙዎችን አጀብ አሰኝተዋል። ረብጣ ሚሊዮን ዶላሮች ተጫዋቾች ላይ ያፈሰሰው ፒኤስጂ ለሚቋምጥለት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ፍፃሜ ለመጀመሪያ ጊዜ ቢደርስም ውጤታማ አልሆነም። ባየርን የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ስድስት ጊዜ በማንሳት ከሊቨርፑል ጋር እኩል ተቀምጧል። ዋንጫውን ሪያል ማድሪድ 17 ጊዜ በማንሳት አንደኛ ሲሆን ኤሲ ሚላን 7 ጊዜ በማንሳት ሁለተኛ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-53885866 +business በኢትዮጵያ ተግባራዊ የሆነው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ከባለፈው ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል ጭማሪ አሳየ? "የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መናሩን በምክንያትነት በመጥቀስ ከአራት ወራት በፊት ባወጣው የዋጋ ተመን ላይ ከሚያዝያ 30/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ መንግሥት ባለፉት አራት ወራት የነዳጅ ዋጋን ለመደጎም ባወጣው ወጪ ከፍተኛ ጫና ላይ መውደቁን ያተተ ሲሆን ""በነዳጅ ማረጋጊያ ፈንድ ላይ በወር በአማካይ ወደ ተጠቃሚው መተላለፍ የነበረበት 10 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንዲመዘገብ"" አድርጓል ሲል አክሏል። በዚህም ምክንያት ከእሁድ ሚያዝያ 30 ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ለውጥ ተደርጓል። ቤንዚን በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣ ኬሮሲን በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣ ቀላል ጥቁር ���ፍጣ በሊትር 52 ብር ከ45 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 51 ብር ከ78 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 78 ብር ከ87 ሳንቲም ሆኖ እንደሚሸጥ መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። ተግባራዊ ከተደረገው የተመን ማሻሻያ በፊት ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት ታኀሣሥ ወር ላይ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ላይ ጭማሪ አድርጋ ነበር። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በእነዚህ አራት ወራቶች ውስጥ የነዳጅ ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ ""በከፍተኛ ሁኔታ"" መጨመሩን ገልጿል። በዚህም በታኅሣሥ ወር ቤንዚን በሜትሪክ ቶን 870 የአሜሪካን ዶላር ይሸጥ እንደነበር ጠቅሶ ከአራት ወራት በኋላ ዋጋው በ27 በመቶ በመጨመር 1028 የአሜሪካ ዶላር መግባቱን አስታውሷል። በተመሳሳይ ናፍጣ በሜትሪክ ቶን 730 የአሜሪካን ዶላር ይሸጥ ከነበረበት በ55 በመቶ ወይም በ408 ዶላር ጭማሪ በማሳየት ወደ 1138 የአሜሪካን ዶላር ማሻቀቡን አውስቷል። ሚኒስቴሩ በመግለጫው መንግሥት ለነዳጅ የሚያደርገውን ድጎማ ቢያቆም በአዲስ አበባ አንድ ሊትር ናፍጣ 73 ብር እንዲሁም የአንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋ 66 ብር ከ78 ሳንቲም ይሆን ነበር ብሏል። ""ሆኖም አገሪቱ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ከዓለም መሸጫ ዋጋ ልዩነትን 85 በመቶ የሚሆነውን ጫና መንግሥት በመሸከም፣ ቀሪውን 15 በመቶ ለተጠቃሚው እንዲተላለፍ በመወሰን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ ክለሳ"" ማድረጉን አሳውቋል። የነዳጅ ዋጋ በታኅሣሥ እና ሚያዚያ ምን ያህል ልዩነት አለው? መንግሥት በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መጨመሩን በመግለጽ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቆ ነበር። ለመሆኑ ከታኅሣሥ እስከ ሚያዚያ መገባደጃ በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ በምን ያህል ጫማሪ አሳየ? በዋጋ ጭማሪው እንደ ጥቁር ናፋጣ ያሉ ምርቶች በሊትር እስከ 121 በመቶ ጭማሪ ወይም እስከ 28 ብር ያሻቀቡ ሲሆን ዝቅተኛው የዋጋ ማሻሻያ ጣሪያ ቤንዝን ላይ የተደረገው ሲሆን የ15 በመቶ ጭማሪ የታየበት ነበር። በታኅሣሥ ወር ቤንዚን ላይ በተደረገ የዋጋ ማስተካከያ በሊትር 31 ብር ከ74 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኖ የነበረ ሲሆን በአዲሱ ተመን መሰረት በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ይሸጣል። በዚህ መሰረት የቤንዚን ዋጋ በ15 በመቶ ወይም በ4 ብር ከ87 ሳንቲም ጫማሪ አሳይቷል። በሌላ በኩል ከአራት ወራት በፊት ነጭ ናፍጣ በሊትር 28 ብር ከ94 ሳንቲም እንዲሸጥ ነበር የተወሰነው። አሁን ላይ ነጭ ናፍጣ በ22 በመቶ ወይም በ6 ብር ከ49 ሳንቲም በመጨመር በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም ይሸጣል። ነጭ ጋዝ ወይም ኬሮሲን 28 ብር ከ94 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን፣ በአዲሱ ተመን በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም ይሸጣል። ይህም የ22 በመቶ ወይም 6 ብር ከ49 ሳንቲም ጭማሪ የታየበት ነው። ቀላል ጥቁር ናፍጣ በታኅሣሥ ወር የወጣለት ተመን 23 ብር ከ73 ሳንቲም የነበረ ሲሆን በአዲሱ የመሸጫ ዋጋ በ121 በመቶ ወይም 28 ብር 72 ጨምሮ በሊትር 52 ብር ከ45 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል። ይህ በተመሳሳይ የከባድ ጥቁር ናፍጣም ዋጋ በ121 በመቶ ወይም 28 ብር 49 በማሻቀብ በሊትር ሲሸጥበት ከነበረው 23 ብር ከ29 ሳንቲም ወደ 51 ብር ከ78 ከፍ ብሏል። የከባድ እና ቀላል ናፍጣ ዋጋ ማሻሻያ ከሌሎቹ የነዳጅ አይነቶች እጅግ ከፍተኛው ሆኖ የሚታይ ነው። የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ በሊትር ከ58 ብር ከ77 ሳንቲም ወደ 78 ብር ከ87 ሳንቲም ያሻቀበ ሲሆን የ33 በመቶ ወይም 20 ብር ጭማሪ አሳይቷል። የነዳጅ ምርቶች የዋጋ ጭማሪ በአራት ወራት ውስጥ - በሊትር ከወራት በፊት ሩሲያ እና ዩክሬን የገቡበት ጦርነት በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ እንዲያሻቅብ ሰበብ ሆኗል። ሩሲያ የዓለምን 10 በመቶ ገደማ የሚሆን የነዳጅ ምርት ታቀርባለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-61369467 +business የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የአገሪቱን ሽግግር ለማደናቀፍ ይሞክራሉ ያሏቸውን አስጠነቀቁ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የአገሪቱን የሽግግር ሂደት ለማደናቀፍ ሙከራ የሚያደርጉ ያሏቸውን አካላት አስጠነቀቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት የአገሪቱን የሽግግር አስተዳደር በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት ውስጥ ባሉ ወታደራዊና ሲቪል መሪዎች መካከል ያለው አለመግባባት እየተባባሰ ባለበት ጊዜ ነው። የሱዳን የሽግግር አስተዳደር የተቋቋመው ሰላሳ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ሲያስተዳድሩ የነበሩት ኦማር ሐሰን አልባሽር ከሁለት ዓመት በፊት በሕዝባዊ አመጽ ከሥልጣናቸው ከተወገዱ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አደገኛ ያሉትን በአገሪቱ የተከሰተውን ፖለቲካዊ ቀውስ ለማርገብ ብቸኛው መንገድ በውይይት ብቻ ሊሆን ይገባል ብለዋል። ነገር ግን አገሪቱን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት ውስጥ ሱዳን በታቀደው መሰረት ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረት ለመቀልበስ ከፍተኛ ጥረት የሚያደርጉ የጎላ ተጽእኖና ተሰሚነት ያላቸው የሠራዊቱ አባላት መኖራቸው ይነገራል። ባለፈው መስከረም ወር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ ተሞክሮ ከከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ የሽግግር አስተዳደሩን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። የሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት በሱዳን የሽግግር አስተዳደር ላይና በአገሪቱ ቀጣይ ዕጣ ፋንታ ላይ ወሳኝ ሁኔታዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይገመታል። የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ደጋፊዎች አሁን ያለው የሱዳን መንግሥት በሌላ እንዲተካ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ ቅዳሜ ለማድረግ ጥሪ አቅርበዋል። በሚቀጥለው ሐሙስ ደግሞ ሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትሸጋገር የሚጠይቅ ሌላ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቷል። በአሁኑ ጊዜ ሱዳን ከፖለቲካዊ ቀውሱ ባሻገር ከባድ ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ገጥሟታል። የአገሪቱ ዋነኛ ወደብ በተቃውሞ ሳቢያ በመዘጋቱ ከውጪ የሚገቡ ቁሳቁሶች ዋና ከተማዋን ካርቱምን ጨምሮ ወደ የትኛውም የአገሪቱ ክፍል መንቀሳቀስ ካቆመ ቀናት ተቆጥረዋል። በዚህም ምክንያት በአገሪቱ ውስጥ የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦት ችግር ተከስቷል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ቡድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል። በዚህም ሲቪሉን በመወከል የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን አብደላ ሐምዶክ የያዙ ሲሆን ከሠራዊቱ በኩል ደግሞ የአገሪቱ ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆን አብዱል ፋታህ አልቡርሐን ከፍተኛውን ቦታ ይዘዋል። ነገር ግን የሱዳንን የሽግግር አስተዳደር በሚመሩት ወታደራዊና የሲቪል ባለሥልጣናት መካከል ያለው ግንኙነት የሰከነ ሳይሆን ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የደኅንነት ሁኔታ እየተዳከመ የመጣ ሲሆን፣ ምክንያቱም ወታደራዊ መሪዎቹ ሥልጣን የሚያስረክቡበት ወቅትን ለማስተጓጎል ነው ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። በሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የሚመራው ኃያሉ የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ለሲቪሎች ሥልጣኑን በመጪው ኅዳር እንዲያስተላልፍ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለታል። https://www.bbc.com/amharic/news-58919817 +health የደም ግፊት ታካሚዎች ፓራሲታሞል አዘውትረው ከዋጡ ለልብ ድካም ሊዳርጋቸው ይችላል ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች በሐኪም ትዕዛዝ አዘውትረው ፓራሲታሞል መጠቀማቸው ለልብ ድካም ሊያጋልጣቸው እንደሚችል አንድ ጥናት ጠቆመ። የኤደንብራ ዩኒቨርሲቲ ��ጥኚዎች እንዳሉት ዶክተሮች ለታካሚዎቻቸው ለብዙ ወራት የሚወጣ ክኒና ሲያዙ ጥቅምና ጉዳቱን ከግምት ማስገባት አለባቸው። ሕመም ማስታገሻውን መድኃኒት ለራስ ምታትና ለትኩሳት መውሰድ ችግር እንደሌለው አጥኚዎቹ ይናገራሉ። አንዳንድ ሙያተኞች ደግሞ በርከት ባሉ ሰዎች ላይ ጥናት ተሰርቶ ውጤቱን ማረጋገጥ ተገቢ ነው ይላሉ። ፓራሲታሞል በመላው ዓለም የሚታወቅ ሕመም ለማስታገስ የሚዋጥ ሲሆን አንዳንዴ ጥልቅ ሕመም ለሚያስከትሉ በሽታዎችም ይመከራል። ነገር ግን ክኒናው ለረዥም ጊዜ መፍትሔ አይሰጥም። በፈረንጆቹ 2018 ግማሽ ሚሊዮን ስኮትላንዳዊያን ይህንን ማስታገሻ እንዲውጡ በሐኪም ታዘው ነበር። ይህም ከ10 ስኮትላንዳዊ አንዱ ፓራሲታሞል ይውጥ ነበር ማለት ነው። በዩናይት ኪንግደም ከፍተኛ የደም ግፊት ከሶስት ሰው አንድ ሰውን ያጠቃል። ጥናቱ 110 ፈቃደኛ ሰዎችን አካቶ የተሰራ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ሁለት ሶስተኛው የደም ግፊት መድኃኒቶች ይውጡ የነበሩ ናቸው። የጥናቱ ተሳታፊዎች አንድ ግራም ፓራሲታሞል በቀን አራት ጊዜ ለሁለት ሳምንታት እንዲወስዱ ሆነ። ቀጥሎ ደግሞ ለሁለት ሳምንታት ክኒና የሚመስል ጥቅምም ጉዳትም የሌለው ቁስ እንዲውጡ ተደረጉ። ሙከራው እንዳሳየው ፓራሲታሞል የወሰዱት የደም ግፊታቸው ጨመረ። ይህም ማለት ለልብ ድካምና ስትሮክ የመጋለጣቸው ዕድል ከፍ አለ ማለት ነው ይላሉ የኤደንብራ ፕሮፌሰር ጄምስ ዲር። ዶክተሮች እንደ ደም ግፊት ዓይነት በሽታ ላለባቸው ታካሚዎች መጠኑ ያነሰ ፓራሲታሞል እንዲሰጧቸው አጥኚዎቹ ይመክራሉ። የጥናቱ መሪ የሆኑት ዶክተር ኢያን ማካንታዬር ይህ ጥናት ለአጭር ጊዜ ሕመምን ለማስታገስ የሚወሰድ ፓራሲታሞልን አይመለከትም ይላሉ። የለንደን ዩኒቨርሲቲው ዶክተር ዲፔንደር ጊል፤ አሁን በሰሩት ጥናት መሠረት ክኒናው በነጭ ስከትላንዳዊያን ላይ ለደም ግፊት መባባስ ምክንያት ሆኖ ቢታይም ብዙ የማይታወቁ ጉዳዮች እንዳሉ ያስረዳሉ። አንድ ከዚህ በፊት አሜሪካ ውስጥ የተሠራ ጥናት ለረዥም ጊዜ ፓራሲታሞል መጠቀም ለልብ ድካም ሊያጋልጥ እንደሚችል ጠቁሞ ነበር። ሌሎች አነስ ያሉ ጥናቶች ደግሞ በክኒናውና በልብ ድካም መካከል ያለውን ግንኙነት መለየት አልቻሉም። የኤንድብራ አጥኚዎች በፓራሲታሞልና ልብ ድካም መካከል ያለውን ግንኙነት ይህ ነው ብለው ባያስረዱም የጥናታቸው ውጤት ለሌላ ሰፋ ላለ ጥናት እንደሚጠቀም ተገልጧል። ነገር ግን የብሪታኒያው ኸርት ፋውንዴሽን ዶክተሮችና ታካሚዎቻቸው የትኛው መድኃኒት አስፈላጊ ካልሆነ መዋጡ ያለውን ጥቅምና ጉዳት እንዲያገናዝቡ አደራ ብሏል። ወደፊት የደም ግፊት ባለባቸው ሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በሌለባቸው ሰዎች ላይም ፓራሲታሞል አዘውትሮ መጠቀም ያለውን ጉዳት መቃኘት አስፈላጊ እንደሆነ የዘርፉ ሙያተኞች እየተናገሩ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-60298844 +sports ስፖርት፡ በቻን የወንዶች እግር ኳስ ውድድር ላይ በዋና ዳኝነት የምትሳተፈው ሊዲያ ታፈሰ "ዛሬ ቅዳሜ ጥር 08/2013 ዓ.ም ካሜሩን ውስጥ የሚጀመረው 'ቻን' በመባል የሚታወቀው የአፍሪካ አገራት የእግር ኳስ ሻምፒዮና ውድድር ጨዋታዎችን እንዲዳኙ በአህጉሪቱ የእግር ኳስ የበላይ አካል ካፍ ከ31 አገራት 47 ዋና ዳኞችና ረዳት ዳኞችን ሰይሟል። ይህን የወንዶች የእግር ኳስ ውድድር ከሚዳኙት ዳኞች መካከል አራት ሴቶች ከወንዶች አቻዎቻቸው ጋር በአካላዊና ስፖርታዊ እንዲሁም የእግር ኳስ ጨዋታን በመረዳት ባላቸው ብቃት ተመዝነው እንደተመረጡ ተገልጿል። ለውድድሩ ዳኝነት ከተመረጡት 47 ዳኞች መካከል፣ 19ኙ በዋና ዳኝነት ጨዋታዎችን የሚመሩ ሲሆን ቀሪዎቹ በመስመር ዳኝነትና በቪዲዮ ዳኝነት የመሃል ዳኞችን የሚያግዙ ናቸው። ���ዲያ ከ19ኙ ዋና ዳኞች መካከል ብቸኛዋ የመሃል ዳኛ ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ ናት። ሊዲያ በአገር ውስጥና በተለያዩ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድሮችን በመዳኘት ብቃቷን ያስመሰከረች ስትሆን የአፍሪካ የእግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ውስጥ አንዱ በሆነው 'የቻን' የወንዶች የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ በዋና ዳኝነት ጨዋታ የምትመራ ቀዳሚዋ ሴት ሆናለች። ካፍ የሚያዘጋጃቸው የወንዶች የእግር ኳስ ውድድሮችን በመዳኘት በኩል ሴቶች እንዲሳተፉ ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ፣ በውድድሮቹ ሂደት ውስጥ ሴቶች የተለያዩ ኃላፊነቶችን በመያዝ እንዲሳተፉ እያደረገ ነው። በዚህም መሠረት ከሊዲያ ታፈሰ በተጨማሪ በቻን ውድድር ላይ በረዳት ዳኝነት ከማላዊ፣ ከናይጄሪያና ከካሜሩን የተመረጡ ሴቶች ይሳተፋሉ። የአንድ ልጅ እናት የሆነችው ሊዲያ ታፈሰ ወደ ስፖርት የገባቸው ጅማ ውስጥ ባዳበረችው የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ፍቅር ምክንያት ነው። ሊዲያ በታዳጊነቷ እግር ኳስ ትጫወት የነበረ ሲሆን ዋነኛው ስፖርቷ ግን ቅርጫት ነበር። አሁን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የወንዶች እግር ኳስ ሊግ ውስጥ በብቃታቸው ከሚጠቀሱ ዳኞች መካከል አንዷ የሆነችው ሊዲያ፣ መጀመሪያ ላይ ባገኘችው ስልጠና ተስባ ነበር ወደ ዳኝነቱ የገባችው። በዳኝነቱ ዘርፍ ከሴቶች አንጻር ከቀዳሚዎቹ ውስጥ የምትጠቀሰው ሊዲያ፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን መዳኘት በጀመረች ጊዜ፣ ጥያቄና ፈተናዎች ገጥመዋት እንደነበር ካፍ ድረ ገጽ ላይ በወጣው ታሪኳ ላይ ሰፍሯል። ""በጣም አስቸጋሪ ነበር። አንዳንዶች ሌላ ሴት በሌለችበት ዘርፍ ላይ በእግር ኳስ ዳኝነት ለመሰማራት ለምን እንደወሰንኩ ሁሉ የሚጠይቁኝ ሰዎች ነበሩ"" ትላለች። ሴት ዳኞችን ለማፍራት በታቀደ ፕሮጀክት ውስጥ ስልጠና አግኝታ፣ ከ15 ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ ልጆች የእግር ኳስ ጨዋታዎችን በዳኝነት በመምራት የጀመረችው ሊዲያ፤ በአገሪቱ ፐሪሚየር ሊግ ውስጥ ጨዋታዎችን በዳኝነት መምራት ችላለች። በዳኝነቱ ላይ ያሳደረችው ፍቅር ቢጠነክርም፣ ሴት ሆና የወንዶችን ጨዋታዎች ስትዳኝ እንደ እንግዳ ነገር የሚመለከቷት ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን ከወንዶች ጋር እግር ኳስ በምትጫወትበት ጊዜ ያዳበረችው በራስ መተማመን የወንዶችን ውድድሮች ያለችግር እንደትመራ እንደረዳት የምትናገረው ሊዲያ፤ የቤተሰቧ ድጋፍ ደግሞ ወሳኙ እንደነበር ታነሳለች። በአገር ውስጥ ውድድሮች ላይ ባሳየችው የዳኝነት ብቃት ለዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎች የታጨችው ሊዲያ፤ በመጀመሪያ ከ15 ዓመት በፊት ናይጄሪያና ላይቤሪያ አቡጃ ውስጥ ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ውድድር ለዋንጫ ለማለፍ ያደረጉትን ግጥሚያ ዳኝታለች። ""ያንን ጨዋታ አልረሳውም ምክንያቱም በጣም አስቸጋሪ ነበረ። ስታዲየሙ ኢትዮጵያ ውስጥ ከምናውቀው በጣም ይተልቃል፣ ተመልካቹም የተለየ ነበር"" ትላለች። በመቀጠልም የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ግጥሚያዎችን ያጫወተች ሲሆን በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደውን የአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫ ውድድርን በተከታታይ ለአራት ጊዜ በመዳኘት ለቀጣዩ እየተዘጋጀች ነው። ከዚህ በተጨማሪም ከአራት ዓመት በፊትና ከአንድ ዓመት በፊት የተካሄዱትን የፊፋ የሴቶች እግር ኳስ የዓለም ዋንጫን፣ እንዲሁም የፊፋ ከ17 ዓመት በታች የታዳጊዎች የዓለም ዋንጫንና ከ20 ዓመት በታች ውድድሮች ላይ በዳኝነት ተሳትፋለች። ሊዲያ ልጇን በጸነሰችበትና ከወለደች በኋላም ወደምትወደው የዳኝነት ሙያዎ ለመመለስ ፈተናዎች ገጥመዋት ነበር። ""ከእርግዝና በኋላ አካላዊ ለውጥ ያጋጥማል። ክብደቴ በጣም ጨምሮ ስለነበር ወደ ቀድሞ አቋሜ ለመመለስ በጣም መስራት ነበረብኝ። በርትቼ በመስራት መጨረሻ ላይ ተሳክቶልኝ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ እድሉን አገኘሁ"" ብላለች። ለዚያ ውድድር በምትዘጋጅበት ጊዜ ጉዳት አጋጥሟት እንደነበር የምትናገረው ሊዲያ፣ ወደ አገሯ እንደምትመለስና በዚህ ምክንያት ከስፖርቱ ልትወጣ እንደሆነ ስጋት ፈጥሮባት ነበር። ነገር ግን በኋላ ላይ አገግማ ዛሬ ላይ ደርሳለች። ከጉዳቷ በኋላ ወደ ተጨማሪ ሰዓት የተሸጋገረውን የካሜሩንና የኮትዲቯርን የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ መርታ ነበር። ""ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰዓት ሲሸጋገር ሜዳ ውስጥ ከእግር ኳስ ተጫዋቾቹ በላይ ጠንካራ ነበርኩ። በጣም ደስ ብሎኝ ነበረ"" ስትል ሊዲያ ታስታውሳለች። ሊዲያ በበርካታ ታላላቅ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ወሳኝ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ በዳኝነት ተሳትፋለች። ወደፊትም በታላቁ የአፍሪካ የወንዶች ዋንጫ ላይ በዳኝነት እንደምትሳተፍ ተስፋ አላት። ሊዲያ ከዳኝነቱ በተጨማሪ የፋርማሲ ባለሙያ ስትሆን፣ በዚህ የኮሮናቫይረስ ዘመን የእግር ኳስ ውድድሮች ለወራት ተቋርጠው በነበረበት ጊዜ በሙያዋ ወገኖቿን ለማገልግል ሰርታለች። በዚህም ሰዎች ራሳቸውንና ሌሎችን ከወረርሽኙ እንዲከላከሉ የህክምና መረጃዎችን በተለያዩ መንዶች ስትሰጥ ቆይታለች። በየትኛውም ጊዜ ከልምምድ ርቃ የማታውቀው ሊዲያ፣ እንደ ሴት በቤተሰቧና በእግር ኳስ ዳኝነት ሙያዋ መካከል ያለውን ሚዛን በመጠበቅ እንደተሳካላት ትናገራለች። ለዚህ ደግሞ ከባሏና ከልጇ የምታገኘው ድጋፍና ማበረታታት በሙያዋ በስኬት እንደትቀጥል እንዳደረጋት ገልጻለች። በአፍሪካ አህጉር አሉ ከሚባሉ ኮከብ ሴት የእግር ኳስ ዳኞች መካከል ከፊት የምትጠቀሰው ሊዲያ ታፈሰ፣ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ውስጥ ወደፊት ለሚመጡ ሴት ዳኞች መልካም አርአያ እንደምትሆን ታምናለች። ወደፊትም ከሙሉ ጊዜ የእግር ኳስ ዳኝነት አረፍ ስትል በፋርማሲ ሙያዋ ከመቀጠል በተጨማሪ፣ በዳኝነቱ የእሷን እግር ተከትለው መሥራት የሚፈልጉትን የማሰልጠን ፍላጎት አላት።" https://www.bbc.com/amharic/news-55681377 +health ኮሮናቫይረስ፡ በኤርትራ ቢራ በኩፖን መሸጥ ተጀመረ "የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት ምግብ ቤቶች፣ ካፌዎችና መጠጥ ቤቶቿን በዘጋችው ኤርትራ ቢራ በኩፖን (መሸመቻ ካርድ) መሸጥ መጀመሯ ተገልጿል። ብቸኛው ሜሎቲ ቢራ በሱቆች በመሸመቻ ካርድ አማካኝነት እየተሸጠ እንደሚገኝም ቢቢሲ ትግርኛ ከምንጮች ያገኘው መረጃ አመላክቷል። ደንበኞች ቢራውን ማግኘት የሚችሉት በሱቆች ብቻ ሲሆን አንድ ቢራም በአስር ናቅፋ (ወደ 25 ብር በሚጠጋ) ዋጋ እንደሚሸጥ ተገልጿል። ኩፖኑን (የመሸመቻ ካርዱን) የያዙ ሰዎችም በአንድ ሳምንት መግዛት የሚፈቀድላቸው የቢራ ብዛት ስምንት ጠርሙስ ብቻ ነው። በኤርትራ ዳቦ፣ ዘይት፣ ስኳርና ማሽላ የመሳሰሉትን መሰረታዊ ሸቀጦች በስርጭት (በመሸመቻ) ካርድ በቀበሌዎች ሲሆን መግዛት የሚቻለው፤ መጠኑም በቤተሰብ ቁጥሩ ይወሰናል። በተለይም ዳቦ ለመግዛት በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዳቦ ቤቶች ተመዝግበውም በየእለቱ ጧት የቤተሰባቸውን ቁጥር መሰረት ባደረገ መልኩም እንዲገዙ ይፈቅድላቸዋል። ሜሎቲ ቢራም በተመሳሳይ መልኩ እንደ ዳቦና ስኳር በሱቆች በመሸመቻ ካርድ መሸጡ አንዳንድ የመጠጥ ቤት ባለቤቶችን ቅር አሰኝቷል። በአስመራ የሚገኝ ስሜ አይጠቀስ ያለ አንድ የመጠጥ ቤት ባለቤት ነጋዴ ""የንግድ ፍቃድ ያለን ሰዎች ንግድ ቤታችሁን ዝጉ ተብለን፤ ለሰራተኞች ደሞዝ ክፈሉ ተብለን ስናበቃ እኛ ልንሸጠው የሚገባ ቢራ በሱቆች እየተሸጠ ይገኛል"" በማለት ለቢቢሲ ተናግሯል። ነጋዴው እንደሚለው መጠጥ ቤቶቹ የተዘጉት የሰዎችን መሰባሰብ ለመቀነስ መሆኑን ቢረዳም ቢራው በሱቆች መሸጥ ለመጀመሩ ምክንያቱ ግልፅ አልሆነለትም። መጠጥ ቤቶቹ ሱቆች አሁን እያደረጉት እንዳለው ቢራ መሸጥ ይችሉም እንደነበር ይናገራል። ""ሰባት ወር ሙሉ ከስራ ውጪ ሆነናል። ለሰራተኞቻችን ደግሞ ምንም ሳንሰራ ደመወዝ እንድንከፍል እየተገደድን ነው። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ደንበኞች ቢራ በሱቆች ገዝተው እየሄዱ ነው፤ ገበያችንንም እያሳጡን ነው"" ይላል። በአሁኑ ወቅት ቢራ በሱቆች መሸጥ ከመጀመሩም ጋር ተያይዞ ወጣቶች በሱቆች ገዝተው ተሰባስበው እየጠጡ እንደሚያመሹም ምንጫችን ትዝብቱን ይገልጻል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሳልፋ የነበረችው ኤርትራ አዋጇን ቀስ በቀስ እያላላች ትገኛለች። ሰዎችም ከቦታ ወደ ቦታ እንደልባቸው እየተንቀሳቀሱም ይገኛሉ። በተለይም በአገሪቷ ከጥቂት ከጎረቤት አገራት የመጡ ሰዎች በስተቀር ይህ ነው በማይባል ሁኔታ ወረረሽኙ አለመኖሩ እንዲሁም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ባለመኖራቸው አዋጁ ለምን በይፋ እንደማይነሳ በርካቶች ይጠይቃሉ። በኤርትራ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ጊዜ ጀምሮ የንግድ እንቅስቃሴ የቆመ ሲሆን በተለይ ኑሮው ከእጅ ወደ አፍ የሆነውን ህዝብ ከመንግሥት ምንም ዓይነት ድጋፍ ስለማይደረግለት ኑሮ ከድጡ ወደ ማጡ በሆነና በፈታኝ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ይናገራሉ። በኤርትራ አንድ ብቻ የሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ። አንድ አይነት ቢራ፣ አንድ አውሮፕላን፣ አንድ ሥርዓት ያለው የባንክ አገልግሎት፣ እንድ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ፣ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ፣ አንድ የቴሌቪዝን ጣቢያ . . . ከ1939 ጀምሮ በኤርትራ ሲጠመቅ ቆይቷል። ይህ ለኤርትራ ብቸኛ የሆነው ቢራ በበርካቶች ዘንድ ትዝታ እና ተወዳጅነትን ያተረፈ ነው። የቢራ ፈላጊውን እና የአቅርቦት መጠኑ ተመጣጣኝ ስላልነበረ ከቅርብ ዓመታት በፊት አንድ ሰው ሁለት ቢራ ብቻ ገዝቶ እንዲጠጣ ነበር የሚፈቀድለት። ከሁለት በላይ ደጋግሞ መጠጣት የፈለገ፤ ቢራ የማይጠጣ ሰው ወደ መጠጥ ቤት ይዞ በመሄድ የዚያን ሰው ኮታ ይጠጣ እንደነበር ሰምተናል። አሁን ላይ በቢራ ፋብሪካው በተካሄደ ለውጥ የቢራ አቅርቦቱን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስኑ የድንበር በሮች በተከፈቱ ጊዜ የኢትዮጵያ ቢራ ምርቶች አሥመራን አጥለቅልቀዋት እንደነበረ በዚህም የአንድ ሜሎቲ ቢራ ዋጋ ከ25 ናቅፋ ከ11-15 እንደወረደ ነዋሪዎች ነግረውናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54703886 +sports በሩዋንዳ ለነፍሰጡር እናቶች የሚሆን የስፖርት እንቅስቃሴ ተጀመረ "ሩዋንዳ ለነፍሰጡር እናቶች የሚጠቅምና በጋራ የሚደረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደጀመረች ተገለጸ። ለመጀመሪያ ጊዜ በአገሪቱ በተካሄደው በዚህ የነፍሰጡር እናቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ ለቢቢሲ እንደተናገሩት መደሰታቸውንና ባለስልጣናትም ስፖርታዊ እንቅስቃሴው እንዲቀጥል እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። በዋና ከተማዋ ኪጋሊ ውስጥ በተካሄደው የመጀመሪያው የስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ ከ100 በላይ ነፍሰጡር እናቶች የተሳተፉ ሲሆን አላማውም የነፍሰጡር ሴቶችን አካላዊ ሁኔታን በተመለተ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ለመለወጥ መሆኑን አዘጋጆቹ ተናግረዋል። • ፊደል ያልቆጠሩት ኢትዮጵያዊት የቀዶ ህክምና ባለሙያ • በጀርባቸው የሚተኙ ነፍሰጡሮች ህይወት የሌለው ልጅ እየወለዱ ነው አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅትና ስፖርታዊ እንቅስቃሴውን ያስተባበረው መሪ ኔልሰን ሙካሳ እንደገለጹት፤ በርካታ ሩዋንዳውያን አንዲት ሴት ስታረግዝ ከሁሉም አይነት አካላዊ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ አለባት ብለው ያምናሉ። ""ነፍሰጡር እናት እንቅስቃሴ የማታደርግ ከሆነ ለራሷና ለተሸከመችው ልጇ ደህንነት በጣም አደገኛ ነው"" ብለዋል ሙ��ሳ። በስፖርታዊ እንቅስቃሴው ላይ ተሳታፊ ከነበሩት ነፍሰጡር እናቶች መካከል አንዷ ሊብሬ ኡዊዜይማና ለቢቢሲ እንደገለጸችው በእርግዝናዋ ጊዜ ፈጽሞ አካላዊ እንቅስቃሴ አድርጋ አታውቅም። ""ስላልለመድኩት በጣም ደክሞኝ ነበር፤ ነገር ግን ከሌሎች ነፍሰጡር ሴቶች ጋር አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረጌ በጣም ደስተኛ ነኝ"" ብላለች። የሰባት ወር እርጉዝ የሆነችው ሩትም ሌሎች ተመሳሳይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍ እንደምትፈልግ ተናግራለች። • የሴቶች የቆዳ ክሬሞች የደቀኑት አደጋ ""በጣም ጥሩ ነገር ነው፤ ልምምድ አድርጌያለሁ። ዘና የማለት ስሜት ፈጥሮብኛል፤ በተጨማሪም የጽንሱ እንቅስቃሴም ደስ የሚል ስሜትን ፈጥሮብኛል"" ስትል የተሰማትን ገልጻለች። በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ውስጥ የማህጸንና ጽንስ ሃኪም የሆኑት ዶክተር ጂያን ኒይሪንክዋያ ወደ ግል ክሊኒካቸው የሚመጡትን ሁሉም ነፍሰጡር እናቶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። ""የእግር ጉዞ፣ ዋናና ሰዎነትን ማፍታታት ምንም አይነት አሉታዊ ተጽዕኖ በእርጉዝ ሴቶች ላይ የለውም"" ይላሉ ዶክተር ጂያን። የስፖርታዊ እንቅስቃሴው አስተባባሪዎች በዝግጅታቸው ላይ ለታደሙ እርጉዝ ሴቶች የሚሆኑና ምንም አይነት የጎንዮሽ ውጤት የሌላቸውን የእንቅስቃሴ አይነቶችን መምረጣቸውን ገልጸዋል። ጨምረውም ወንዶች በዚሁ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-50167137 +politics በእነ አቶ ጃዋር የሕክምና ጉዳይ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ይግባኝን ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ "የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ሰዎች የሕክምና ጉዳይን በማስመልከት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት እነ አቶ ጃዋር መሐመድ በመረጡት የግል ሃኪም እና የግል ሕክምና ጣቢያ እንዲታከሙ መፍቀዱን በመቃወም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ነበር። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቤቱታን ውድቅ ያደረገ ሲሆን፤ ተከሳሾች ግን በመረጡት ሃኪም የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ያለባቸው በግል ሆስፒታል ሳይሆን ተከሳሾች ታስረው በሚገኙበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲሆን ትዕዛዝ መስጠቱን ከእነ አቶ ጃዋር ጠበቆች መካከል አቶ ሚኪያስ ቡልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አዳነን ጨምሮ ሌሎች በእነ አቶ ጃዋር የክስ መዝገብ ውስጥ የሚገኙ ተከሳሾች ከ25 ቀናት በላይ በረሃ አድማ ላይ እንደሚገኙ ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። ተከሳሾቹ እያደረጉት ባለው የረሃብ አድማ ምክንያት የቅርብ የጤና ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው የተከሳሾች የግል ሃኪም ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ከዚህ ቀደም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ተከሳሾች 'ለደህንነታችን እንሰጋለን' በማለት በመንግሥት የሕክምና አገልግሎት መስጫ ስፍራ ለመታከም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የተከሳሽ ጠበቆች እንደሚሉት ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ በግል የጤና ተቋም እንዳይታከሙ የተከራከረው የተከሳሾችን ደህንነት በግል ሆስፒታል ማረጋገጥ አይቻልም በሚል ነው። የዛሬው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ""የላንድ ማርክ ሃኪሞች ተደራጅተው ተከሳሾች ባሉበት በመምጣት ሕክምና እንዲሰጣቸው ነው"" በማለት ጠበቃው አቶ ሚኪያስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""ፍርድ ቤቱ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቤቱታ የሕግ መሠረት የለውም ብሎ ውድቅ ካደረገ በኋላ ተከሳሾች ማረሚያ ቤት ሆነው ይታከሙ መባሉ እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነው"" በማለት የተከሳሽ ጠበቆች በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ደስተኛ አለመሆናቸውን ተ���ግረዋል። ጠቃው እንደሚሉት ደንበኞቻቸው ሆስፒታል ተኝተው መታከም የሚያስፈልጋቸው ከሆነ፣ የሆስቲታል ማሸኖች ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ እንዲሁም በጤና ባለሙያ የቅርብ ክትትል ቢያስፈልጋቸው በማረሚያ ቤት ሆነው መታከማቸው ይህን ስለማያሟላ፤ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤቱ መልሰው እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም እነ አቶ ጃዋር የረሃብ አድማውን እንዲያቆሙ በሃይማኖት አባቶች እና ፖለቲከኞች ቢጠየቁም ፍቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ይታወሳል። ከእነ አቶ ጃዋር ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ከድር ቡሎ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ጠበቆች እና የቤተሰብ አባላት ምግብ እንዲበሉ ሲጠይቋቸው ቢቆዩም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ መሆኑን ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የረሃብ አድማው ተከሳሾችን የከፋ አደጋ ላይ እንዳይጥል የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ አስነብቧል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56170346 +health 'በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ህሙማን መጨመርን ተክትሎ ኦሚክሮን መግባቱን ለማረጋገጥ የናሙና ምርመራ እየተደረገ ነው' ጤና ሚኒስቴር "በኢትዮጵያ በያዝነው ሳምንት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ አዲሱ የቫይረሱ ዝርያ ኦሚክሮን ገብቶ ከሆነ ለማረጋገጥ የናሙና ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ለቢቢሲ ገለጹ። ባለፈው ሳምንት ከተመረመሩ 53 ሺህ ሰዎች መካከል 8500 በቫይረሱ ሲያዙ፣ 34 ሰዎች ሞተዋል። በተጨማሪም 440 ሰዎች የጽኑ ሕሙማን ክፍል ገብተዋል። ካለፉት ሳምንታት በተለየ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ ኦሚክሮን ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ መሆኑን ለማወቅ የናሙና ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝና ውጤቱ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይፋ እንደሚደረግ ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል። ""እስካሁን የነበረው አካሄድ ጥሩ ነበር። ነገር ግን ከታኅሳስ 7/2014 ዓ. ም. ወዲህ ባሉት ቀናት በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው"" ብለዋል። የዛሬ ሳምንት ገደማ ከሚመረመሩ ሰዎች 3% ብቻ ቫይረሱ ይገኝባቸው የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት ግን ቁጥሩ ወደ 28% እንዳደገ ገልጸዋል። ""በሌሎች አገሮች የሚታየው ኦሚክሮን ዝርያ በኢትዮጵያም ምልክቶቹ ታይተዋል። በአስጊ ሁኔታ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል። አሁን ናሙና እየመረመርን ነው። በናሙና እስክናረጋግጥ ድረስ ኦሚክሮን መግባቱን በይፋ ለመናገር ያስቸግራል"" ሲሉ ዶ/ር ደረጄ አብራርተዋል። በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመርምረው 382 ሺህ ቫይረሱ ሲገኝባቸው፤ 6880 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ሕዝቧ ወደ 10 ሚሊዮን ገደማ ዜጎችን ከትባለች። ዶ/ር ደረጄ እንዳሉት፤ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት ዜጎች ክትባት እንዲወስዱ ከማበረታታት ባሻገር ከዚህ ቀደም የተከተቡ ሰዎች ማጎልበቻ (ቡስተር) እንዲወስዱ እንደሚደረግም ጠቁመዋል። ከ100 በላይ አገሮች ውስጥ የተገኘው የኦሚክሮን ዝርያ በፍጥነት በመሰራጨት ላይ ነው። ���ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ ትናንት ከተመረመሩ 13147 ሰዎች መካከል 3793 ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ጤና ሚኒስትር ገልጿል። ""በቫይረሱ በድጋሚ የመያዝ ዕድል አለ። ማኅበረሰቡ ወረርሽኙ 'ውሸት ነው' ወይም 'ለፖለቲካ ነው' ሳይል ክትባት ይውሰድ። ስለ ክትባት ሐሰተኛ ወሬ ማሰራጨት ያቁም። ከዚህ ቀደም እንደነበረው ለሕሙማን አልጋ የጠፋበት ደረጃ እንዳንደርስ ተጠንቀቁ"" ሲሉ አሳስበዋል። የጤና ሚኒስቴር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ከሚወስዳቸው እርምጃዎች መካከል፤ የጤና ባለሙያዎች በአስገዳጅ ሁኔታ ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ እንዲሁም ያልተከተቡ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የመንግሥት የነጻ ሕክምና ተጠቃሚ እንይሆኑ ማድረግ መሆኑን ዶ/ር ደረጄ ጠቅሰዋል። ""አሁን ላይ ከሚመረመሩት ሰዎች አንድ ሦስተኛው ቫይረሱ እየተገኘባቸው ስለሆነ የጥንቃቄ እርምጃ መወሰድ አለበት። ማኅበረሰቡ ማስክ ማድረግ፣ ክትባት መከተብም ይገባዋል"" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የጤና ሚኒስቴር የወረርሽኙን ስረጭት ለመከላከል የሚያወጣቸውን ሕጎች በማስተግበር ረገድ ሕግ አስፈጻሚው አካል ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል። በተጨማሪም የጥንቃቄ እርምጃዎችን ማኅበረሰቡ እንዲተገብር ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እስከ ቀበሌ የሚወርድ ንቅናቄ እንደሚደረግ ጠቁመዋል። ለገና በዓል ከሚመጡ ዳያስፖራዎች ጋር በተያያዘ የምርመራ ውጤት እና የክትባት ሰርተፍኬት ከማረጋገጥ አንስቶ ክትባቱን አገር ውስጥ እስከማቅረብ ድረስ እንደሚዘጋጁ ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59778547 +sports የማራዶና ሬሳን የማቃጠሉ ሥነ ሥርዓት እንዲዘገይ ፍርድ ቤት ወሰነ የእግር ኳሱ ንጉሥ አርጀንቲናዊው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና አባታችን ነው የሚሉ ልጆች የማራዶና ሬሳ በሰላም እንዳያርፍ እያደረጉት ነው። ትናንት የአርጀንቲና አንድ ፍርድ ቤት የማራዶና ሬሳ ለዘረ መል (DNA)ምርመራ ስለሚፈለግ ‹ባለበት ይጠበቅ› የሚል ውሳኔን አሳልፏል፡፡ አሁን ሬሳው ለጊዜው ቦነስ አይረስ ውስጥ በሚገኝ በአንድ የግል መካነ መቃብር ላይ ያረፈ ሲሆን የዳኛው ውሳኔ ሬሳውን ወደ አመድነት የመቀየር ሥነ ሥርዓቱን ያዘገየዋል ተብሏል፡፡ ማራዶና ባለፈው ወር በተወለደ በ60 ዓመቱ ከልብ ጋር በተያያዘ በሽታ ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል፡፡ ዳኛው ሬሳው ‹ በመልካም ሁኔታ እንዲቆይ ይደረግ› የሚለውን ውሳኔ ሊያስተላልፉ የቻሉት አንዲት ሴት ማራዶና አባቴ ሳይሆን አይቀርም በሚል ለፍርድ ቤቱ ማመልከቷን ተከትሎ ነው፡፡ ማራዶና አባቷ እንደሆነ ለማረጋገጥ የግድ የዘረመል ናሙና ስለሚያስፈልግ ነው ሬሳውን የማስወገዱ ሥነ ሥርዓት እንዲዘገይ የሆነው፡፡ ማራዶና በጋብቻ ያፈራቸው ሁለት ሴት ልጆች ብቻ ነው ያሉት፡፡ ከነዚህ ሴት ልጆች እናት ጋር ከተፋታ በኋላ ግን በትንሹ 6 ልጆችን ‹ልጆቼ ናቸው› ብሎ ተቀብሏቸዋል፡፡ ሆኖም እርሱ ከጋብቻ ውጪ የወለዳቸው ልጆች ቁጥር ከዚህ በብዙ እጥፍ ሊኖሩ እንደሚችሉ የአኗኗር ዘይቤውን የሚያውቁ ይገምታሉ፡፡ የሱን ሞት ተከትሎ ልጆቹ ነን ያሉ በርካታዎች ሲሆኑ አሁን ለጊዜው ለፍርድ ቤት ያመለከተችው የ25 ዓመቷ ማጋሊ ጊል ናት፡፡ ማጋሊ ጊል ማራዶና በሕይወት እያለ ልጄ ናት ብሎ እውቅና ሰጥቷት አያውቅም፡፡ ማጋሊ በጉዲፈቻ ያደገች ሲሆን እናቷን ከ2 ዓመት በፊት ባገኘቻት ጊዜ አባቴ ማን ነው ብላ ስትጠይቃት፣ አርማንዶ ማራዶና ሊሆን ይችላል እንዳለቻት አስታውሳለች፡፡ ማጋሊ ጊል በኢንስታግራም በለቀቀችው ቪዲዮ ሰዎች ገንዘብ በመሻት ያደረገችው አድርገው እንደሚያስቡ ጠቅሳ ነገር ግን አባቷን የማወቅ ሂደት ዓለም አቀፍ መብት ነው ብላለች፡፡ ማራዶና በኖቬምበ��� 25 መሞቱን ተከትሎ ቦነስ አይረስ በአንድ መካነ መቃብር ውስጥ ነው የተቀበረው፡፡ ፍርድ ቤት የማራዶና ሬሳ ወደ አመድነት የመቀየሩ ተግባር እንዲዘገይ መጀመርያ የወሰነው በአሟሟቱ ላይ የሬሳ ምርመራ እንዲደረግ በማስፈለጉ ነበር፡፡ ማራዶና በሕክምና ስህተት ነው እንጂ አይሞትም ነበር ብለው የሚገምቱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በግል ሐኪሙ ላይ ፖሊስ መርመራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ የትናንቱ የፍርድ ቤት ውሳኔ ግን የማራዶና ልጅ ነን የሚሉትን ለማስተናገድ በሚል የተራዘመ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ሮይተርስ የዜና ወኪል የማራዶናን ጠበቃ አናግሮ ባገኘው መረጃ መሰረት የማራዶና ዘረ መል ቅንጣት ማራዶና ከመሞቱ በፊት የተወሰደና የተቀመጠ ስለሆነ ሬሳውን የማቃጠሉ ሥነ ሥርዓት ማዘግየት አያስፈልግም ብሏል፡፡ ማራዶና የፋይናንስ አያያዙ የተዝረከረከ ስለነበረ በህጋዊ ልጆቹና ከጋብቻ ውጭ የተወለዱት ልጆቹ እንዲሁም የማራዶና ልጆች ነን እያሉ በመጡ ልጆች መሀል ዘለግ ያለ የፍርድ ሒደት ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-55359562 +sports """19 ዓመታትን በእስር፣ አሁንም እየቆጠርን ነው"" የፔን ተሸላሚው አማኑኤል ወንድም" """አስራ ዘጠኝ አመታት በእስር ፣ አሁንም እየቆጠርን ነው። በጣም ከፍተኛ ህመም አለው"" ይህንን የተናገረው በቅርቡ አለም አቀፉን የፔን ሽልማት የተጎናፀፈውና በእስር ላይ የሚገኘው ኤርትራዊው ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት ወንድም ዳንኤል ነው። በሰላ ትችቱ የሚታወቀውን ኤርትራዊ ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት ለበርካቶች ደፋር ፀሃፊ ነው። ለዚህም ነው ፔን በሚፅፉት ወይም በሚናገሩት ነገር የሚደርስባቸውን ጫናና ጣልቃ ገብነት ተቋቁመው የበለጠ ወኔ ላሳዩ ፀሃፊዎች እውቅናን የሚሰጥበትን ""አለም አቀፉ ደፋር ፀሃፊ"" በሚል ስያሜም ሽልማቱን ያቀናጀው። ወንድሙን ለሁለት አስርት አመታት ያህል ላላየው ዳንኤል ምንም እንኳን በደንብ ሽልማቱ ይገባዋል ብሎ ቢያምንም ለሱም ቢሆን ለቤተሰቡ ከፍተኛ አድናቆትን እንደፈጠረባቸው አልደበቀም። ከሽልማቱ ጀርባም አማኑኤል አብሯቸው አለመሆንንም ለቤተሰቡ ማስታወስ የየቀኑ መራር እውነታ ነው። ""በጣም በጣም ከፍተኛ ህመም አለው"" በማለትም መሃል ላይ ኃዘኑን በሚያሳብቅ ድምፅ የሚተነፍሰው ዳንኤል ""በነዚህ አመታት ውስጥ ሊያገባ ይችል ነበር፤ ልጆች ያፈራ ነበር። ትምህርቱን መቀጠል ይችል ነበር። ለአገሪቷም በርካታ ትልልቅ ነገሮችን ማድረግ ይችል ነበር። ከዚህ በላይ ህመም የሆነው ደግሞ መቼ እንደሚፈታ አለማወቃችን ነው። በህይወት ይኑርም፣ አይኑርም አናውቅም""ብሏል ኃዘን በተሞላ ድምፁ አማኑኤል በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት በኤርትራ የጋዜጠኝነት ታሪክ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የዘመን ጋዜጣም ዋና አዘጋጅ ነበር። በሰላ ትችቱም የሚታወቀው ጋዜጠኛ በወቅቱም በኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት መካከል የተፈጠረውን ቅራኔም ይፋ በማውጣት ይፅፍ ነበር። በተለይም ከመቶ ሺዎች ህይወት በላይ የቀጠፈውን የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን አጥብቀው ከሚቃወሙት መካከልም ነው። ይህንኑም በፅሁፉ ላይ ያንፀባርቅ ነበር። ለፔን ሽልማትም ያበቃው ስለ ጦርነት አስከፊነት የሚያወሳበት ግጥሙ ነው። በዚህ ግጥሙም ምን ያህል ጦርነቱ የሁለት ወንድማማቾችና ቤተሰቦች ጦርነት እንደሆነም በተመረጡ ቃላቶች ያስታውሳል። በርካታ ቤተሰቦችን ልጅ አልባ፣ ወንድም አልባ፣ ባለቤት አልባ አድርጓል፤ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን ቀጥፏል። የጦርነቱን አስከፊነትና አስቀያሚነት አማኑኤል ሲያወሳም በሰላማዊ መንገድ ተደራድረው መፍታት የሚችሉትንና ፣ ጦር���ት የመረጡትን ሁለቱንም መንግሥታት ይተቻል። ይህ የሰላ ትችቱ ግን ዋጋ ያስከፈለው ሲሆን ኤርትራም የግል ጋዜጦችን ዘጋች እንዲሁም የሚቀርቡበትን ትችት ዝም ለማሰኘት በጀመረው ዘመቻም የኤርትራ መንግሥት ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችንና ተማሪዎችን ለእስር ዳርጓል። አማኑኤልን ጨምሮ በርካታ የግል ጋዜጣ አዘጋጆችም በጎሮጎሳውያኑ 2001 ለእስር ተዳረጉ። አማኑኤልም ሆነ ሌሎች ፀሃፊዎች ያሉበት ሁኔታ የማይታወቅ ሲሆን እስካሁንም ያናገራቸው አካል የለም። ቤተሰቦች ድምፁን ሰምተው አያውቁም፤ ያለበትንም አያውቁም። ""የኤርትራ መንግሥት አምባገነን ነው። መንግሥቱ ከሌሎች ለየት ያለ ነው። እንደ መንግሥት ደንብና አወቃቀር የለውም። ኤርትራ የምትመራው በአንድ ሰው ነው።በአገሪቱም ያለው በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያለ አንድ ሚዲያ ነው "" የሚለው ዳንኡል ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናትም ቢሆኑ አማኑኤልን ሆነ ሌሎች እስረኞች ያሉበትን ቦታ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተው ስለማያውቁም ""ቤተሰቦቼ፣ ዘመዶቼ የት ነው የታሰሩት ተብሎ መጠየቅ አይቻልም፤ የሚጠየቅ አካልም የለም፤ ፖለቲከኛም ሆኑ ጋዜጠኛ"" በማለት ዳንኤል ያስረዳል። አማኑኤል ሁለገብ ነው፤ ከጋዜጠኝነትም በላይ ገጣሚ፣ የሙዚቃ ግጥም ፀሃፊ፣ ሂሰኛና የሌሎችም ድርብርብ ባለሙያ ነው። ለሁለት አስርት አመታት የሚጠጋ በእስር ላይ የሚገኘው አማኑኤልን ጨምሮ ጥቂት ፀሃፊዎች በህይወት እንዳሉና በእስርም ላይ እንደሚገኙ ይታመናል።ታሳሪዎቹ ምንም ክስ እንዳልቀረበባቸውና መንግስትም መረጃ እንደማይሰጥ የሰብአዊ መብት ተሟጓቾች ይገልጻሉ። ከዚህም በተጨማሪ የህክምና አቅርቦት ማጣት እንዲሁም ሌሎች እንግልቶችና ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሆነ ይታመናል። ገጣሚ አማኑኤል ለዚህ ሽልማት ያጨው ጃማይካዊ- ኢንግሊዛዊ ገጣሚ ሊንቶን ክዌሲ ጆንሰን ""አንድ ዜጋ ፍጹም በማይታወቅ እስር ቤት ለ20 አመታት ማጎር የአምባገነን ስርአት ማሳያ ነው። በአፍሪካዊ ዲያስፖራነቴ ትብብርና ወገንተኝነቴን ለማሳየት ደግሞ ይሄን ሽልማት ለገጣሚ አማኑኤል አስራት እንዲሸለም መርጫለሁ"" ማለቱን ፔን ኤርትራ ገልጿል። በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፈው የአማኑኤል ወንድም ከጋዜጠኛው ስራዎች አንዱ የሆነውን ግጥምም አቅርቧል። አማኑኤል አስራት በ2016 ከሌሎች ግብጻዊና ቱርካዊ ጸሃፍያን በመሆን በፔን ኦክስፋም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ሽልማት ተሰጥቶታል።" https://www.bbc.com/amharic/54544011 +health ኮሮናቫይረስ፡ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ የኮቪድ ክትባትን የሚቃወሙ ሰልፈኞች ከፖሊስ ተጋጩ በአሜሪካ፣ ካሊፎርኒያ ግዛት፣ ሎስ አንጀለስ ከተማ የኮቪድ ክትባት ውሸት ነው የሚሉ ቀኝ አክራሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፡፡ ከፖሊስ ጋር የተጋጩት ክትባት እየተሰጠበት የሚገኘውን የዶገር ስታዲየም በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሰልፈኞቹ ይህን የክትባት መስጠቱ ሂደት ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል እንዲስተጓጎል አድርገዋል፡፡ ቁጥራቸው 50 የሚሆኑ የጸረ ክትባት አቀንቃኞች ስታዲየሙን ለማዘጋት የቻሉት መግቢያውን በመዝጋት ጭምር ነው፡፡ ክትባት ለማግኘት ሰልፍ ላይ የነበሩ በርካታ መኪኖች በነዚህ የክትባት ተቃዋሚዎች ምክንያት አገልግሎት ሳያገኙ ተመልሰዋል፡፡ ሰልፈኞቹ የኮቪድ ክትባት የተጭበረበረ ስለመሆኑ የሚያወሱ መፈክሮችን የያዙ ሲሆን ኅብረተሰቡን ‹አትከተቡ፤ እናንተ የቤተ ሙከራ አይጥ አይደላችሁም› እያሉ ሲቀሰቅሱ ታይተዋል፡፡ የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ቀኝ አክራሪ ሰልፈኞቹ ለክትባት የተሰለፉ ሰዎችን ‹ ነፍሳችሁን አድኑ፣ የውሸት ሳይንስ መጫወቻ አትሁኑ እያሉ እየጮኹ ሲቀሰቅሱ ነበር፡፡ የ��ትባት መስጫውን ሰልፈኞቹ የተቆጣጠሩትም በአገሬው አቆጣጠር ከቀኑ 8 ሰዓመት ጀምሮ ነው፡፡ የሎስ አንጀለስ ፖሊስ በትዊተር እንዳስታወቀው ስታዲየሙ አልተዘጋም፤ ክትባቱ ቀጥሏል ብሏል፡፡ የካሊፎርኒያ ገዥ ጋቪን ኒውሰን በስታዲየሙ እየተሰጠ የነበረው የክትባት ዘመቻ በሰልፈኞች ለጊዜው ቢስተጓጎልም ወደ ሥራ ተመልሷል ብለዋል፡፡ ጀርማን ጃኩዝ የተባለና ክትባት ለማግኘት ሰልፍ ሲጠባበቅ የነበረ ዜጋ ለሎስ አንጀለስ ታይምስ ቁጣውን የገለጸ ሲሆን ‹‹ይህ የቀኝ አክራሪዎች ድርጊት ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው› ብሏል፡፡ ‹‹ለሳምንታት ክትባት ለማግኘት ስጠባበቅ ነበር፡፡ እኔ የጥርስ ሐኪም ነኝ፡፡ በሽተኞቼን ሳክም በጣም ተጠግቻቸው ነው፡፡ ከኮቪድ መጠበቅ እሻለሁ፡፡ ክትባቱ ያስፈልገኛል፡፡ ተህዋሲውን ለመከላከል ብቸኛው መንገድ ክትባት ነው›› ሲል ሐሳቡን አጋርቷል፡፡ በአመዛኙ የትራምፕ ደጋፊ የነበሩ እንደሆኑ የሚገመቱና ቀኝ አክራሪ የሆኑት ሰልፈኞች ከያዟቸው መፈክሮች አንዱ ‹‹ሲኤንኤን እያታለላችሁ ነው›› ይላል፡፡ ሌሎች መፈክሮች፣ ‹‹ጭምብላችሁን ቀዳዳችሁ ጣሉት››፣ ‹‹የሰው አይጥ አትሁኑ›› የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ከአሜሪካ ግዛቶች ካሊፎርኒያ በተህዋሲው ክፉኛ ከተጠቁት ተርታ ትመደባለች፡፡ 40ሺ የግዛቲቱ ነዋሪዎች በኮቪድ ሞተዋል፡፡ 3 ሚሊዮኑ ተህዋሲው አለባቸው፡፡ በመላው አሜሪካ በኮቪድ ተህዋሲ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች በሚቀጥለው ወር ግማሽ ሚሊዮን እንደሚያልፍ ይጠበቃል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-55876977 +health ሰሜን ኮሪያ፡ ታመዋል ሲባሉ የነበሩት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ድንገት ተከሰቱ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ታመዋል ከሚለው ጀምሮ፣ አብቅቶላቸዋል፣ ሞተዋል እየተባለም ብዙ ይወራባቸው ነበር፡፡ ድንገት በፓርቲ ስብሰባ ተከስተው መመርያ ሰጥተዋል፣ ትናንት፡፡ ሰሜን ኮሪያ ትልቅ አደጋ ከፊቷ ተደቅኗል ያሉት ኪም ሕዝቡ በተጠንቀቅ እንዲሆን አዘዋል፡፡ ትልቅ አደጋ እየመጣ ነው ያሉት ኪም አደጋዎቹ በዋናነት ሁለት መሆናቸውን አውስተዋል፡፡ አንዱ ኮሮና ቫይረስ ሲሆን ሌላው ደግሞ አውሎ ንፋስ ነው፡፡ ኪም ከሰሞኑ ጠፍተው ስለነበር የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ስለነበረ ምናልባት ሞተው ይሆን? ሲባል ነበር፡፡ ሰሜን ኮሪያ እስካሁን አንድም ሰው በኮቪድ-19 አልተያዘብኝም ስትል ታስተባብላለች፡፡ አይበለውና ወረርሽኙ ወደዚያች አገር ቢገባ ባላት ደካማ የጤና መሰረተ ልማት ከፍተኛ አደጋ ሊያጋጥማት ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡ ይህ በእንዲህ ሳለ ባቪ የሚሰኝ አደገኛ አውሎ ነፋስ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሰሜን ኮሪያን ሊመታት ይችላል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ የፖሊትቢሮ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ኪም በስብሰባው ላይ ንግግር እያደረጉ ሲያጨሱ ይታዩ ነበር፡፡ በዚህ ንግግራቸው ኮቪድን በተመለከተ አንዳንድ ችግሮች ተስተውለዋል ብለዋል፡፡ ምን ማለታቸው እንደሆነ ግን የሚያውቅ አልተገኘም፡፡ ፒዮንግያንግ ለረዥም ጊዜ ወረርሽኙ እኔ ጋ ድርሽ አላለም ስትል እያስተባበለች ቆይታለች፡፡ ነገር ግን ይህን የሰሜን ኮሪያን አስተያየት ብዙዎች በጥርጣሬ ነው የሚመለከቱት፡፡ አንድም በቫይረሱ የተጠቃ ሰው የለም ስትል የነበረው ሰሜን ኮሪያ በቫይረሱ አጠባበቅ ዙርያ ችግሮች ታይተዋል ማለቷ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል፡፡ ሰሜን ኮሪያ ከጥርጣሬ የተነሳ አንዲት የድንበር ከተማ ሰዎች ተገለው እንዲቀመጡ ያደረገች ሲሆን ነገር ግን ከዚህ የዘለለ ስለተያዘ አንድም ሰው ተጠቅሶ አያውቅም፡፡ ኪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክብደት እየጨመሩ ስለሆነ በወጣትነታቸው ሊቀጠፉ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች በስፋት ይሰነዘሩ ነበር፡፡ በቅርቡም ለእህታቸው ኪም ዮ ጆንግ በርከት ያሉ ሥልጣኖችን ሰጥተዋት ነበር፡፡ ይህንን ሁኔታ እንደ ኑዛዜ የወሰዱት ሚዲያዎችም ነበሩ፡፡ ሰሜን ኮሪያ 25 ሚሊዮን ዜጎች አሏት፡፡ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቿ የረሀብ አደጋ ገጥሟቸዋል ይላል የተባበሩት መንግሥታት፡፡ የረባ የንግድ ግንኙነት ከአገራት ጋር ያልመሰረተችው ሰሜን ኮሪያ ከቻይና ጋር የምታደርገው ንግድ ወሳኝ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ይህም በኮሮና ምክንያት እክል ገጥሞታል፡፡ በፒዮንግያንግ መቀመጫቸውን ያደረጉ በርካታ ግብረሰናይ ድርጅቶችና የኤምባሲ ሰራተኞች አገሪቱን ለቀው እንደወጡ ተዘግቧል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/53915684 +business "#8 እሷ ማናት፡ ""አፍሪካዊያንን ሚሊየነር ለማድረግ አስባለሁ""- ሐና ተክሌ" "ሐና ተክሌ እባላለሁ። አዲስ አበባ አብነት፣ ቀበሌ 28 አካበቢ ነው ተወልጄ ያደግሁት። እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ግን ወደ ደቡብ አፍሪካ ሄጄ ኑሮዬን በዚያ አድርጌያለሁ። ባለትዳርና የሦስት ልጆች እናት ነኝ። በ2004* ሂልኮ የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ነበርኩ። ሁሌም የራሴን ሥራ መስራት እፈልግ ስለነበር በርካታ መጽሐፍትን ሳነብ የሕይወቴን መስመር ቀየርኩ። የሕይወት መስመሬ በትምህርት ብቻ አለመሆኑን ስረዳ የተለያዩ ነገሮችን በአማራጭነት መመልከት ጀመርኩ። ያኔ እጄ ላይ ከወደቀው እድል አንዱ ኔትወርክ ማርኬቲንግ ነው። በተለይ እናቴ ያሳደገችኝ ብቻዋን መሆኑ ወደዚህ ሥራ እንድገባ ምክንያት ሆኖኛል። • ""የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ላይ የሚለወጡ ነገሮች ይኖራሉ"" የጠ/ሚ የኢኮኖሚ አማካሪ እናቴ ስድስት ልጆች ነበሯት እኔ ከሦስቱ ጋር ነው ያደግሁት። አምስተኛ ልጇ ነኝ። ልጆቿን ለማኖር ለረዥም ጊዜ በሥራ የኖረችው ዱባይ ነበር። ሁሌም የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ከትምህርት መልስ እናቶቻቸው ምሳ አዘጋጅተው፣ ቡና አጫጭሰው ሲጠብቋቸው እናታችን አጠገባችን ስለሌለችና ይህንን ማየት ባለመቻሌ አዝን ነበር። እንደ ሌሎች ልጆች እናቶች ቤት ቡና ቀራርቦ እናቴ እንድትጠብቀን የማድረግ የልጅነት ሕልሜ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ኔትወርክ ማርኬቲንግ ስሰማ ልቤ ውስጥ የነበረው ሰርቼ ውጤታማ ብሆን እናቴን ከዱባይ አምጥቼ ቤት ስገባ ዘወትር ባገኛት የሚለው ሀሳብ ነው ያነሳሳኝ። ከዚያም በዚሁ ሥራ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጓዝኩ፤ ደቡብ አፍሪካ የሄድኩት በአጋጣሚ ነው። ለሁለት ሳምንት ለሥራ በሄድኩበት ነው እዚያው የቀረሁት። የመጀመሪያውን አንድ ዓመት ወጣ ገባ እያልኩ ቆየሁ። ከዚያ በኋላ ግን ጠቅልዬ እዚያው መኖር ጀመርኩ። ወደ ደቡብ አፍሪካም የተጓዝኩት እዚያ ደንበኞችን ለማፈፍራት ነበር። በመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ጉዞዬ ቢዝነሱ ስኬታማ ሆኖ ሰፍቶ ነበር። እስከ 2009 ድረስም ስሰራ ቆይቻለሁ። በኔትወርክ ማርኬቲንግ ውስጥ ከገንዘብ በተጨማሪም የአመራር፣ የተግባቦት፣ የሽያጭና አስተዳደር ክህሎቶችን አግኝቼበታለሁ። ኔትወርክ ማርኬቲንግ ብዙ አስተምሮኛል። ማግኘትና ማጣት ብዙ አስተምሮኛል። • ቀኝ እጇን ለገበሬዎች የሰጠችው ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት በራስ መተማመኔን የጨመረውም እርሱን እየሰራሁ ነው። ይህ የሥራ ሕይወት የተለያዩ በሮች እንዳሉትና በየትኛውም መንገድ ብጓዝ ስኬታማ እንደምሆን ያየሁበትም ነው። 2009 ላይ ግን ይህንን ሥራ አቁሜ ሌሎች ሥራዎችን ጀመርኩ። ከሕንድ እቃዎችን እያስመጣሁ ለቸርቻሪዎች መስጠት ጀመርኩ። በእርግጥ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሥራዎችንም ሰርቻለሁ። ትርፍና ኪሳራውን አይቼ በ2015 ላይ አቆምኩት። በእርግጥ ሥራውን ያቆምኩት ስለከሰርኩ ነው ብል ይሻላል። 2013 ላይ ትዳር መስርቼ ወዲያው የመጀመሪያ ልጄን ወለድኩ። ልጆች ስወልድ ለልጆቼ የተሻለ ጥሪት የመቋ��ር ፍላጎት በብርቱ ፈተነኝ። ባለቤቴ ጋቦናዊ ሲሆን የህይወት እቅዱ በሙሉ ተምሮ ስኬታማ መሆን ነው። የሒሳብ ትምህርት ያጠና ሲሆን ያን ጊዜ ሦስተኛ ዲግሪውን እየሰራ ነበር። ስንጋባ 35 ዓመቱ ነበር። እሱም 40 ዓመት ሳይሞላው ፕሮፌሰር ለመሆን በማለም እየጣረ ነበር። የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ክፍያ ደሞዙን ሳሰላው ባሌ በሚያገኘው ገንዘብ ልኖረው የምፈልገው ህይወት ሩቅ መሆኑ ተሰማኝ። ስለዚህ ከ2013 ጀምሮ የልቤን ፍላጎት ይዤ በየቀኑ አዳዲስ የንግድ ሀሳቦችን እመለከት ጀመር። ከዚያ እርሱ ከሥራ ወደቤት ሲመለስ ያገኘኋቸውን የንግድ ሀሳቦች እንመካከርባቸዋለን። ሁለተኛ ልጄን ከወለድኩ በኋላ ቢትኮይንን ተዋወቅሁ። 2015 ነሐሴ ወር ላይ ስለቢትኮይን ሰምቼ ለባለቤቴ ብነግረውም ሊቀበለኝ አልቻለም። • ስድስት መሠረታዊ ጥያቄዎች በጣና እምቦጭ ዙሪያ ስለቢትኮይን ለመጀመሪያ ጊዜ ልታስረዳኝ የሞከረችውን ልጅ ለስድስት ዓመት ልጅ እንደምታስረጂ አድርገሽ አስረጂኝ ብያት ብታስረዳኝም አልገባኝም ነበር። ጎግል ላይ በቀላሉ መረዳት የሚቻልበት መንገድን ጠይቄ ያገኘሁት መረጃ ግን ረዳኝ። ባለቤቴ የዘወትር ውትወታዬ ሲበረታበት አንድ ለሊት ቁጭ ብሎ ማንበብ ጀመረ። ባነበባቸው ጥናቶች ውስጥ የተሳተፉ ዩኒቨርስቲዎች፣ የተደረጉ ጥናቶች ቢዝነሱ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ አሳዩት። በኋላ ትኩረት ልሰጠው እንደሚገባ ነገረኝ። ከዚህ በኋላ ነው ቀላል የምለውንና አቅሜ የሚችለው ላይ የተሳተፍኩት። ከሁለት ወር በኋላ ደግሞ 'ማይኒንግ' [በቢትኮይን ውስጥ ያለ ሥራ] ላይ መስራት ጀመርኩ። በዚህ ሥራ ላይ ተሰማርቼ ገና መስመር ሳይዝ ባለቤቴ በካናዳ ኦንታሪዮ ሪሰርች ኢንስቲትዩት የተመራማሪነት እድል አግኝቶ እኔና ልጆቼ ደቡብ አፍሪካ ቀርተን እርሱ ብቻውን እንዲሄድ ተስማማን። በዚህ ተስማምተን እርሱ ካናዳ ሄዶ ቤተሰቡን ለማስተዳደር ከሚያገኘው ገቢ ላይ ወደ ደቡብ አፍሪካ መላክ ነበረበት። ነገር ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቢትኮይን ገንዘብ ማግኘት ጀመርኩ። በስድስት ወር ውስጥ የእርሱን የዓመት ደሞዝ ያህል ማግኘት ጀመርኩ። ከዚያ በኋላ ወደ ካናዳ የመሄድ ሀሳቤን ተውኩት። ከስድስት ወር በኋላ ሊጠይቀን ሲመጣ ያለውን ለውጥ ተመለከተና ከሦስት ወር ቆይታ በኋላ የካናዳ ሥራውን ጥሎ እኔን ለመደገፍ መጣ። • ዓለም ሁሉ የሚያወራለት ክሪይፕቶከረንሲ ምንድነው? በዚህ ሥራ ውስጥ ከተሰማራሁ በኋላ በአንድ ዓመት ከግማሽ ውስጥ አንድ ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ችያለሁ። ከዚያ በኋላም ቢዝነሱ እየሰፋ እና እየተጠቀምኩ ነው። ሚሊየነር መሆን ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው መንገዱ ክፍት ነው። ልጅ ወልደው ተደራራቢ ኃላፊነት ላለባቸው በቀላሉ ሊሰሩት የሚችሉት ሥራ ነው። እኔ በሰው አገር እየኖርኩ፣ ሦስት ልጆች እያሉኝ፤ ሁሉም ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ፤ መስራት ከቻልኩ ሌሎችም መስራት ይችላሉ። ለዚህ ሥራ ኢንተርኔትና ሀብታም የመሆን ፍላጎት እስካለ ድረስ መስራት ይቻላል። አትችይም የሚሉኝ ሰዎች ሁሌም ለሌላ ተጋድሎ ያነሳሱኛል። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሀገሩን ቋንቋ አትናገሪም ያሉኝ፣ ሴት መሆኔን ያስታወሱኝ ሰዎች በአጠቃላይ ዛሬ ለደረስኩበት አነሳስተውኛል። ባለቤቴ ቤት ውስጥ ከማርገዝና ከማጥባት ውጪ ሁሉንም ነገር ያግዘኛል፤ ይደግፈኛል። በዚህም እድለኛ ነኝ። ገንዘብ ለሁሉም ነገር መፍትሔ አይደለም። ነገር ግን ገንዘብ ሁሉንም ነገር ያቀላል። ስለዚህ ገንዘብ ሁሌም ለማግኘት ጠንክሬ እሰራለሁ። እንደ አፍሪካዊ የእኔ ሕይወት ሲቀየር የሌሎችም ሕይወት ስለሚቀየር የአንድን ሰው ሕይወት ለመለወጥ ጠንክሬ ነው የምሰራው። ብዙ አፍሪካዊያንን ሚሊየነር ለማድረግ አስባለሁ�� ቢትኮይን ልክ እንደ ዶላር እንደ ዩሮ ሁሉ ገንዘብ ነው። ሌላው ቢትኮይንን ከአንድ ሰው ወደ ሌላው በቀላሉ ዋጋው ሳይሸራረፍ ማስተላለፍ ይቻላል። ቢትኮይን ለመላክ የሦስተኛ አካል ጣልቃ ገብነትን አስወግዷል። እኔ ቢትኮይን ማይኒንግ ላይ ከተሰማራሁ በኋላ ሁሌም ለሌሎች የምነግረው ቢትኮይንን ገዝተው ማስቀመጥ እንደሚችሉ፣ ቢትኮይን ንግድ ላይ የመሰማራት እድል መኖሩን አልያም ንግዳቸውን በቢትኮይን መገበያየት እንደሚችሉ ነው። ይህ ለሁሉም ሰው ያለ እድል ነው። ግን በጥንቃቄ መስራት ያስፈልጋል። በዓለም ላይ በርካታ አጭበርባሪዎች ስላሉ በሚገባ አጥንቶ መግባት ያስፈልጋል። ሚሊየነር መሆን ይቻላል ስል በአንድ ጀምበር መሆን ይቻላል እያልኩ አይደለም። ጠንክሮ መስራትን ይጠይቃል። እኔ የተሰማራሁበት ቢትኮይን ማይኒንግ ይባላል። ቢትኮይን ማይኒንግ ገንዘብ ማተም እንደማለት ነው፤ ቢትኮይን ማተም ነው። ለዚህ ሁሉ ግን ጠንከር ያለ ገንዘብ እንዲሁም ታማኝ አጋር ማግኘት ያስፈልጋል። • የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ 'ሊብራ' ጥያቄን አስነሳ • አዲሱ የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ አፍሪካን ያጥለቀልቅ ይሆን? እኔና ባለቤቴ 2015 ላይ 'አቺቨርስ ክለብ አካዳሚ' የተሰኘ ተቋም አቋቁመን ክሪፕቶከረንሲ አካዳሚ እና ኔትወርክ ማስተማር ጀመርን። ይህንንም ከፕሪቶሪያ ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር ነው የምንሰራው። በአካዳሚያችን ፋንዳሜንታል ኦፍ ብሎክ ቼይን፣ ክሪፕቶከረንሲ ኤንድ ክሪፕቶ ፋይናንስ፣ ብሎክ ቼይን ፎር ቢዝነስን የተሰኙ ኮርሶች እናስተምራለን። እኔ ደግሞ በአቺቨርስ ኔትወርክ በኩል ወደ ተለያዩ አገራት እየሄድኩ ልምዴን አካፍላለሁ። ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር እንሰራለን። የምንሰራው በአፍሪካ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለማችን 33 አገራት ውስጥ ነው። እስካሁን 30 የሚሆኑ ሰዎች በሥራቸው ሚሊየን ዶላር እንዲያገኙ አድርገናል። ከእነዚህ ሰዎች መካከልም በሥራ ገበታቸው ላይ ሆነው የሚሰሩ አንዳንዶቹም የለቀቁ ይገኙበታል። በአፍሪካ ውስጥ በዚህ ትምህርት ሰፊውን ሥራ እየሰራን ነው። አሁን መቀመጫውን ፖላንድ ካደረገ ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራርመን እየሰራን ነው። እኔ ሰዎችን አስተምራለሁ፤ አፍሪካ ውስጥ ላለ ሰው ትልቅ እድል ነው። ማንም ሰው ቢሰማራበት ውጤታማ ሊሆን ይችላል። *ሁሉም የዘመን አቆጣጠሮች በአውሮፓዊያን ነው እሷ ማናት? የሚለው ጥንቅራችን ያሰቡበትን ዓላማ ለማሳካት ብዙ ውጣውረዶችን ያሳለፉ ሴቶችን ታሪክ የምናስቃኝበት ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-50909604 +health "ኮሮናቫይረስ ፡ በአውሮፓ ከተሞች ""ኮቪድ-19 ውሸት ነው"" የሚሉ ተቃውሞዎች እየተካሄዱ ነው" "ከአርብ ጀምሮ እየተካሄዱ ያሉ ሰልፎች መልከ ብዙ ቢሆኑም 'ጭራሽ ኮሮና የሚባል ቫይረስ ብሎ ነገር የለም፣ እየተጭበረበርን ነው' ብለው የሚያምኑ ሰልፈኞችም የተገኙበት ሆኗል፡፡ የብዙዎቹ ሰልፈኞች ጥያቄ ግን በኮሮና ምክንያት የተጣሉ ገደቦች ይነሱ የሚሉ ናቸው፡፡ በጀርመን በርሊን ሰፊ ተቃውሞ የተካሄደ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ 300 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ የጀርመን ሰልፈኞች ያነሱት ተቃውሞ በዋናነት 'በኮሮናቫይረስ ምክንያት ጥብቅ የተደረጉ መመሪያዎች ይነሱልን መረረን' የሚል ነው፡፡ በጀርመን ለተቃውሞው 40ሺ የሚጠጉ ሰዎች አደባባይ ወጥተዋል፡፡ በአመዛኙ ሰላማዊ ሆኖ የቆየው ተቃውሞ በነጭ አክራሪዎች ነውጥ ምክንያት መልኩን እየቀየረ መጥቷል፡፡ ድንጋይና ጠርሙስ መወራወርም ተጀምሯል፡፡ በበርሊን ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የአውሮፓ ከተሞች ተመሳሳይ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡ በለንደን በዝነኛው ትራፋልጋር አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች ብዙዎቹ ""ኮሮናቫይረስ ብሎ ነገር የለም፤ እየተ���በረበርን ነው"" የሚል ይዘት ያላቸው መፈክሮችን ይዘው ታይተዋል፡፡ በፓሪስ፣ በቪየና እንዲሁም በዙሪክ ይኸው ተቃውሞ በተመሳሳይ መንፈስ ቀጥሏል፡፡ በጀርመን የተካሄደው ተቃውሞ ፍትጊያ የበዛበትና ማኅበራዊ ርቀትን ለማስጠበቅ አስቸጋሪ እንደነበር ፖሊስ አምኗል፡፡ ""ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ የሚቻለውን ለማድረግ ሙክረናል፡፡ በሰልፈኞች መሀል የኮሮናቫይረስ ደንቦችን ማስጠበቅ ግን አልቻልንም"" ብሏል ፖሊስ በትዊተር ገጹ፡፡ ፖሊስ በቁጥጥር ካዋላቸው ሰዎች መሀል አንዱ ""ኮሮናቫይረስ ብሎ ነገር የለም፣ ዉሸት ነው የሚለውን መላምት በማራገብ የሚታወቀው አቲላ ሂልድማን"" ይገኝበታል፡፡ ሂልድማን ለሰልፈኞች ድምጽ ማጉያ ይዞ ተከታታይ ንግግር ሲያደርግ ነበር፡፡ ሂልድማን በጀርመን እውቅ የምግብ አብሳይ ባለሙያ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የነጭ አክራሪዎችን አስተሳሰብ በመጋራት ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ ሆኗል፡፡ ""ኮሮናቫይረስ የሚባል ነገር የለም፤ ጀርመን ከቢልጌትስ መወገኗን ታቁም"" የሚሉ አስተሳሰቦችን ማራመድ በመጀመሩ ብዙ ተከታዮችን አፍርቷል፡፡ ብዙዎቹ ሰልፈኞቹ ጭምብል ማጥለቅና ሌሎች ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚወሰዱ መመርያዎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ስለሆኑ እንዳሻን እንሁን የሚል ጥያቄ ነው ያነሱት፡፡ ከሰልፈኞቹ መሀል እውቅ ሰዎችም ተገኝተውበታል፡፡ ለምሳሌ ሮበርት የጆን ኤፍ ኬኔዲ ልጅ ለሰልፉ ድጋፍ ከሰጡት መሀል ይገኝበታል፡፡ ሮበርት ኬኔዲ ጁንየር በሰው እጅ የተገደሉት የዝነኛው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ የወንድም ልጅ ሲሆን ክትባትን በመቃወም ከፍተኛ ተከታይ ያፈራ ሰው ነው፡፡ ሮበርት ኬኔዲ በርሊን ድረስ በመምጣት ሰልፉን ተቀላቅሏል፡፡ ጀርመን እስካሁን 242,000 ሰዎች በኮቪድ-19 እንደተጠቁባት እና ከ10ሺ ሰዎች በታች እንደሞቱባት ይታወቃል፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-53963766 +health ኮሮናቫይረስ፡ በድሬዳዋ ከሃያ በላይ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኮቪድ-19 ተያዙ "በድሬዳዋ 21 የሕክምና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የከተማዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለቢቢሲ አረጋገጠ። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ስንታየሁ ደበሳ እንደተናገሩት በሕክምና ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው እተደረገ ያለውን ወረርሽኙን የመከላከል ሥራን ያዳክመዋል የሚል ስጋት አለ ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። ወይዘሮ ስንታየሁ ለጤና ባለሙያዎቹ በሽታውን ለመከላከል አስፈጊ የሆኑ አቅርቦቶችን በተመለከተም አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ ማቅቡንና ገልጸው ""እስካሁን ድረስ እጥረት የለብንም"" ብለዋል። ነገር ግን በሕክምና ተቋማቱ የሚኖሩ ንክኪዎች ባለሙያዎቹን ለቫይረሱ ማጋለጡን የሚናገሩት አስተባባሪዋ፤ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገ ውይይት ለቫይረሱ የተጋለጡት በየትኛው ጊዜ እንደሆነ ለማለየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። በህክምና ተቋማቱ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ግን ይላሉ ባለሙያዋ ""በሕክምና ሥራ ላይ እያሉ ተጋላጭ መሆናቸውን ነው"" በማለት ባለሙያዎቹ እየወሰዱ ያሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""የጤና ባለሙያዎቻችን በቫይረሱ እየተያዙ መምጣት ወረርሽኙን ለመከላከል የምናደርገውን ጥረት ያዳክማል"" ሲሉም በአስተዳደሩ በኩል ያለውን ስጋት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በቫይረሱ ከተያዙት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል በድንገተኛ እና በጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚሰሩ ነርሶችና ዶክተሮች እንደሚገኙበት በመጥቀስ፤ በዚህ ክፍል የሚሰሩት ባለሙያዎች በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት ተጋላጭ መሆናቸውን አብራርተዋል። በድሬዳዋ እስካሁን ድረስ ስምንት ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ናሙናዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሲደረገላቸው፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ ከ500 በላይ ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸውንና 17 ሰዎች ደግሞ በዚሁ ምክንያት መሞታቸው ታውቋል። በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ400 በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ማገገማቸውን የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ስንታየሁ ደበሳ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በተያያዘ ዜና በምሥራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ 66 ታራሚዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን የዞኑ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ተካ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጊኒር ከተማ እና በወረዳው በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ በተደረገው የኮቪድ-19 ምርመራ እነዚህ ታራሚዎች ኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ኃላፊው ተናግረዋል። እነዚህ ቫይረሱ የተገኘባቸው ታራሚዎች ለህክምና ወደ ሮቤ ሆስፒታል መላካቸውንም ቢቢሲ ከኃላፊው መረዳት ችሏል። ኃላፊው በእነዚህ ፖሊስ ጣቢያዎች ታራሚዎች አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ በማያስችላቸው እና ያለ ምንም ጥንቃቄ መልኩ መታሰራቸው በሽታው እንዲስፋፋ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች የፀረ ተህዋሲ ርጭት ተደርጓል። በቀላል ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችም የዋስ መብታቸው ተጠብቆ እንዲወጡ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆኑንም ተናግረዋል። ታራሚዎቹን ለመጠየቅ የሚመጡ ቤተሰቦችም በሽታውን ወደ ኅብረተሰቡ ይዘው በመሄድ ስርጭቱ ይስፋፋል የሚል ስጋት ቢኖርም እስካሁን ድረስ ከተጠረጠሩት ሰዎች ላይ በተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ ምርመራ የተያዘ ሰው አለመገኘቱን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን 470 ሺህ የሚጠጋ ምርመራ ተደርጎ ወደ 21 ሺህ 452 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ከእነዚህም መካከል በወረርሽኙ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 380 ደርሷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53696685 +politics አሜሪካና ሩሲያ በተመድ ስብሰባ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ተፋጠጡ "ሩሲያ በዩክሬን ድንበር ላይ ከፍተኛ ሰራዊት ማስፈሯን ተከትሎ በተጠራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ላይ በአሜሪካና በሩሲያ ልዑካን መካከል ቁጣና ንዴት የተሞላበት ፍጥጫ እንደነበር ተገልጿል። ይህንን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ የጠራችው አሜሪካ ናት። በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ሩሲያ በድንበር ላይ እያደረገችው ያለው የጦር ስምሪት በአውሮፓ በአስርት አመታት ውስጥ ከታየው ትልቁ ነው ብለዋል። የሩሲያ አቻቸው በበኩላቸው አሜሪካ የማያስፈልግ ውዥንብር እየፈጠረች ነው በሩሲያ ጉዳዮች ላይ ተቀባይነት የሌለው ጣልቃ ገብነት እያደረገች ነው ሲሉ ከሰዋታል። ሩሲያ ዩክሬንን የምትወር ከሆነ ተጨማሪ ማዕቀብ እንጥላለን ሲሉ አሜሪካና ዩናይትድ ኪንግድም ቃል ገብተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ ለክሬምሊን ቅርብ ከሆኑ ግለሰቦች እና ንግዶች ባለፈ መልኩ ሰፋ ያሉ ጉዳዮች ላይ የሚያነጣጥር ህግ እየተዘጋጀ ነው። የአሜሪካ ባለስልጣን በበኩላቸው ለክሬምሬሊን ቅርብ የሆኑ ግለሰቦች ከአለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት እንዲቆራረጡ የሚያደርግ ማዕቀብ ይጣላል ብለዋል። ሩሲያ 100 ሺህ የሚገመቱ ወታደሮች፣ ታንኮች፣ መድፍ እና ሚሳኤሎችን በዩክሬን ድንበር አካባቢ አስፍራለች። ሰኞ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታ�� ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የሩሲያ አምባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዛ እንዳሉት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እቅድ ለማውጣቷ ምንም አይነት ማረጋገጫ እንደሌለ እና በድንበሩ ላይ ያለው የሰራዊት ግንባታዋ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተረጋገጠ አይደለም ብለዋል። ሩሲያ አብዛኛውን ጊዜ ጦሯን በፈለገችው ግዛቷ እንደምታሰማራ እና ይህ የዋሽንግተን ጉዳይ እንዳልሆነም አምባሳደር ቫሲሊ ተናግረዋል። ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ክፍት ስብሰባ እንዳይደረግ ብትከላከልም 10 ለሁለት በሆነ ድምፅ ተሸንፋ ጉባዔው ተደርጓል። የባይደን አስተዳደር “ውጥረቶችን በማነሳሳትና ትርክቶችን በመፍጠር ግጭቶች እንዲቀሰቀስ እየሰሩ ነው” ሲሉ አምባሳደሩ ወቅሰዋቸዋል። ""ይህ በአገራችን የውስጥ ጉዳይ ላይ ተቀባይነት የሌለው ጣልቃ ገብነት ብቻ ሳይሆን አለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለአካባቢው ትክክለኛ ሁኔታ የተሳሳተ መረጃ እንዲኖረው እና በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ ውጥረት ምክንያቶች መነሻ ነው በሚል ለማሳየት የሚደረግ ሙከራ ነው"" ብለዋል። አምባሳደር ቶማስ ግሪንፊልድ በበኩላቸው አሜሪካ አሁንም ቢሆን ለዩክሬን ጉዳይ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዳለ እንደምታምን ቢያስረዱም፤ ነገር ግን ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች አገራቸው ቆራጥ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች። የዚህ ውጤትም “አሰቃቂ” ነው ብለዋል። ""ይህ በአውሮፓ በአስርት አመታት ውስጥ ያላየነው ትልቁ የወታደር ማስፈር ነው"" ሲሉ ተናግረዋል። “በአሁኑ ወቅት ይህንን እየተናገርን ባለንበት ወቅት ሩሲያ ተጨማሪ ኃይሎችን እና የጦር መሳሪያዎችን ወደ ድንበር እየላከች ነው” ብለዋል። ሞስኮ በአጎራባቿ ቤላሩስና በዩክሬን ሰሜናዊ ድንበር ላይ የምታሰማራውን ጦር ወደ 30 ሺህ ለማሳደግ አቅዳ ነበር ሲሉ አስረድተዋል። ሰኞ ምሽት ላይ የአሜሪካ መንግሥት ሰራተኞች ቤተሰብ አባላት ከቤላሩስ እንዲወጡ አሜሪካ አዛለች። ለዚህም “ያልተለመደው የሩሲያ ጦር ማስፈርን” ጠቅሳለች። ባለፈው ወር አሜሪካ በዩክሬን መዲና ኪየቭ የሚገኘውን ኤምባሲ ሰራተኞችና ቤተሰቦች እንዲወጡ አዛለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-60211915 +politics በምዕራብ ጉጂ ዞን የጸጥታ ኃላፊን ጨምሮ 7 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ "በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት አንድ የአካባቢው ባለሥልጣንን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። በምዕራብ ጉጂ ዞን ውስጥ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት በዞኑ የሚገኘው ገላና ወረዳ የጸጥታና የደኅንነት ኃላፊ የሆኑትን አቶ ጃርሶ በካሎን ጨምሮ ሰባት ሰዎች በታጣቂዎቹ መገደላቸውን የወረዳው የኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ገበየሁ ያደቴ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ገበየሁ እንዳሉት ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 14/2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 11 ሰዓት አካባቢ ሲሆን በአጠቃላይ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። ከደቡብ ክልል የአማሮ ወረዳ ጋር በሚዋሰነው በዚህ አካባቢ እንዲህ ያለው ጥቃት ሲፈጸም የመጀመሪያ አይደለም። ከዚህ በፊትም በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ግድያዎች መፈጸማቸው ይታወሳል። ባለፈው መጋቢት ወር ሁለቱ ወረዳዎች በሚያዋሰኑበት ሥፍራ ስብሰባ ላይ በነበሩ አመራሮችና ነዋሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሰባት ሰዎች ሲገደሉ ስድስት ደግሞ ቆስለው ነበር። በወቅቱ ጥቃቱን የፈጸሙት መንግሥት 'ሸኔ' ብሎ የሚጠራውና እራሳቸውን 'የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት' የሚሉት ታጣቂዎች እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፤ አሁንም ለሰባት ሰዎች ህልፈት ምክንያት ለሆነው ጥቃት ይኸው ታጣቂ ቡድን በተጠያቂነት ይከሰሳል። በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ውስጥ በሰዎች ላይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶችና የንብረት ውድመቶች ጋር በተያያዘ ከሳምንታት በፊት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቡድኑን ሽብርተኛ ቡድን ብሎ መሰየሙ ይታወሳል። ከሳምንት በፊት የቀድሞ የምዕራብ ወለጋ ዞን ጸጥታ ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ አምስት የመንግሥት ሠራተኞች በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ በታጣቂ ቡድኑ መገደላቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀው ነበር። የምዕራብ ጉጂው ጥቃት በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ የኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ገበየሁ ያደቴ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጥቃቱ በታጣቂዎቹ የተፈጸመው ኃላፊውና ሌሎች የጸጥታ አካላት ለሥራ እየተጓዙ በነበረበት ጊዜ ነው። ""በዚህም በወረዳው የጸጥታና የደኅንነት ኃላፊ አቶ ጃርሶ በካሎ የተመራ ቡድን የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ቦሬ ቀበሌ እየተጓዘ ሳላ ጨልቤሳ ሾሮ በተባለ ሥፍራ ላይ ነው ጥቃቱ የተፈጸመባቸው"" ብለዋል። በጥቃቱም ከወረዳው አስተዳደር ወገን የነበሩ ሰባት ሰዎች ሲገደሉ ከታጣቂዎቹ በኩል ደግሞ ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል። በጥቃቱ ሁለት የሚሊሻ አባላት፣ ሦስት የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት፣ የወረዳው ጸጥታና ደኅንነት ኃላፊና እና የጽህፈት ቤቱ የደኅንነት ባለሙያ በአጠቃላይ 7 ሰዎች ተገድለዋል። በታጣቂዎቹ ከተገደሉት ባሻገር ሌሎች 7 ሰዎች ደግሞ በተለያየ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ዲላ ሆስፒታል ተወስደው የህክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑን አቶ ገበየሁ ገልጸዋል። በጥቃቱ ሰባት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ሰባት ሰዎች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ በጥቃቱ ወቅት ከታጣቂዎቹ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሁለት የታጣቂው አባላት መሞታቸው ተነግሯል። በአካባቢው የአመራር አባላትና የጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለመያዝ ጥቃቱ በተፈጸመበት ሥፍራ የተጠናከረ አሰሳና እርምጃ እየተወሰደ መሆኑም ኃላፊው ገልጸዋል። ጥቃቱ በተፈጸመበት የምዕራብ ጉጂ ዞን የገላና ወረዳ ታጣቂዎች ድንበር ላይ ባሉ የወረዳው ቀበሌዎች ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱና በተለያዩ ጊዜያትም በጸጥታና በሚሊሻ አባላት ላይ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ጨምረው አመልክተዋል። ቅዳሜ ዕለት በታጣቂዎቹ ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ሥርዓተ ቀብር እሁድ ዕለት መፈጸሙንም የኮምዩኒኬሽን ኃላፊው ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባወጣው መረጃ በዚህ ዓመት ብቻ በኦሮሚያ ክልል 'ሸኔ' በተባለው ታጣቂ ቡድን በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ18 በላይ በመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ 112 የፖሊስ አባላት እንዲሁም 57 በሚሊሻ አባላት በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ ውስጥ ተገድለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57222409 +business የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሲብ ንግድን ማገድ ለምን አስፈለገው? ከሰሞኑ የአዲስ አበባ አስተዳደር የጎዳና ልመናና የወሲብ ንግድን ለማገድ ረቂቅ ሕግ ማዘጋጀቱን ተከትሎ በብዙዎች ዘንድ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ከእግዱ አላማ አንስቶ እስከተደረጉ ዝግጅቶች፣ እንዲሁም የአስተዳደሩ ሥልጣን ባሉና በተያያዙ ጉዳዮች ውይይቶች ቀጥለዋል። ረቂቅ ሕጉ በአሁኑ ወቅት ለካቢኔ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ብቻውን መወሰንም ስለማይችል ባለድርሻ አካላት በተለይም የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተያየት እንዲሰጡበትም እየተደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ፌቨን ተሾመ አስረድተዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-49444559 +sports በመድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለው እግር ኳስ ተጫዋች ሮቢንሆ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ሆነ "ብራዚላዊው የእግር ኳስ ተጫዋች ሮቢንሆ እ.ኤ.አ. በ 2013 በሚላን ከተማ በቡድን በተፈጸመ የመድፈር ወንጀል የቀረበበትን ፍርድ ለመጨረሻ ግዜ ይገባኝ ቢልም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የታችኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ውድቅ አደረገ። ትላንት ረቡዕ የተሰየመው የሮም ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ 37 ዓመቱን ኳስ ተጨዋች ተፈርዶበት የነበረውን የዘጠኝ ዓመት እስራት አጽንቷል። እ.ኤ.አ. በ 2017 ሮቢንሆ እና ሌሎች አምስት ብራዚላውያን የ22 ዓመቷን አልባኒያዊ ሴት በምሽት ክበብ ውስጥ የጾታዊ ጥቃት በማድረስ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት። ከዚህ ቀደም በታህሳስ 2020 ይግባኝ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ቢቀርብበትም ይግባኙ ውድቅ ተደርጎ ነበር። ሮቢንሆ የሚኖርበት ብራዚል በሕገ መንግስት ደረጃ መንግስት ዜጎቹን ለሌላ አገር አሳልፎ እንዳይሰጥ የሚከለክል መሆኑን ተከትሎ ቅጣቱን ይፈጽማል የሚል ግምት ባይኖርም ጣሊያን ደቡብ አሜሪካዊቷን አገር ቅጣቱን በአገሩ ውስጥ እንዲፈጽም መጠየቅ ትችላለች። ለብራዚል 100 ጊዜ የተጫወተው ሮቢንሆ በ2005 ኑሮውን ወደ ሪያል ማድሪድ ከማዛዋሩ የእግር ኳስ ህይወቱን በሳንቶስ ነበር የጀመረው። በአራት የውድድር ዘመናት ሁለት የላሊጋ ዋንጫዎችን አንስቷል። እ.ኤ.አ. በ 2008 ማንቸስተር ሲቲን ሲቀላቀል በወቅቱ የእግሊዝ ከፍተኛው ክፍያ 32.5m ፓውንድ ተከፍሎት ነበር። ነገር ግን በእንግሊዝ ቆይታው ውጤታማ ለመሆን ባለመቻሉ በጥር 2010 ለሳንቶስ በውሰት ተሰጥቷል። በኤስ ሚላን ቆይታው ሴሪአን አሸንፏል። በቻይና እና በቱርክ ላሉ ክለቦች ከተጫወተ በኋላ 2020 በአምስት ወር ኮንትራት ወደ ሳንቶስ ቢመለስም ፊርማው ከፍተኛ ትችት ማጋጠሙን ተከትሎ የብራዚሉ ክለብ ኮንትራቱን አቋርጦ ""ተጫዋቹ በጣሊያን እየተካሄደ ባለው ጉዳይ በመከላከሉ ላይ ብቻ እንዲያተኩር"" ስል ውሉን አቋርጫለሁ ሲል አስታወቆ ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-60034979 +business ከመንግሥት 550 ሚሊዮን ብር መዝብራ የተሰወረችው ዴንማርካዊት ተፈረደባት "ከመንግሥት አምስት መቶ አምሳ ሚሊዮን ብር መዝብራ የተሰወረችው ዴንማርካዊት ከሰሞኑ ክስ ተመስርቶባታል። በመንግሥት ማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ድርጅት ውስጥ ለአርባ ዓመታት የሠራችው ብሪታ ኔልሰን አቅማቸው ለደከሙ ግለሰቦች የገንዘብ እርዳታን የሚለግስን ተቋም ገንዘብ ትቆጣጠር እንደነበር ተገልጿል። ከሁለት ዓመታት በፊት በተደረገ ምርመራ ግን ገንዘቡን ኪሷን ለማደለብ ተጠቅማበታለች ተብሏል። የዴንማርክ ፍርድ ቤትም የስድስት ዓመት ተኩል እስር ከሰሞኑ ፈርዶባታል። • ከማዕከላዊ ስልጣን የተገፋው ህወሓት ከዬት ወደዬት? • ኢትዮጵያዊቷ ከ20 ዓመት በኋላ የኤርትራዊቷን ቤት ሊያስረክቡ ነው በዝቅተኛ ሙስናና መንግሥት ሁሉን ነገር ግልፅ በሆነ አሠራር በዓለም አቀፉ መድረክ ተምሳሌት በሆነችው ዴንማርክ ይህ የተለመደ ነገር አይደለም። ብሪታ ኔልሰን ውንጀላዎቹ በቀረቡባት ወቅት ደቡብ አፍሪካ ተሰውራ ነበር። ወደ ዴንማርክ ለመመለስ የወሰነችው ዓለም አቀፉ የወንጀል አጣሪና አዳኝ ኢንተርፖል የእስር ትዕዛዝ ካወጣባት በኋላ ነው። ለሃያ አምስት ዓመታትም ድርጅቱን በመመዝበርም ተወንጅላለች። • ውጤት ለማሻሻል ወሲብን ተጠቅመዋል የተባሉት የዩኒቨርሲቲ መምህራን ታገዱ • ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮ በሹመታቸው ዙሪያ ምን ይላሉ? ብሪታ ኔልሰን 'ሶሻልስትይሬልሰን' በሚባለው ብሄራዊ የጤናና ደህንነት ላይ የሚሠራው መንግሥታዊ ድርጅት ውስጥ ነው የሰራችው። የዴንማርክ መስማት የተሳናቸው ማኅበርን ጨምሮ ሌሎች የአካል ጉዳተኞችም በጀት የሚመደብላቸው ከዚህ ድርጅት ነበር፤ ገንዘብ መመደብም የሷ ኃላፊነት ነበር ተብሏል። ከሦስት ዓመታት በፊት በድርጅቱ ውስጥ ላደረገችው አስተዋፅኦ የብር ሜዳልያ ሽልማትም ተሸልማለች። ኖርዲክ ሌበር ጆርናል፤ ብሪታ ኔልሰን ለመመዝበር ያመቻት ምንም አይነት የተጠያቂነት መዋቅር ስላልነበረው ነው በማለት ፍርድ ቤቱ ላይ መከራከሪያ ሃሳብ አቅርቧል። የ65 አመቷ ብሪታ ኔልሰን በበኩሏ ""ብሩን አካውንቴ ውስጥ መጨመር ቀላል ነበር፤ ከዚያም ወደ ባሃማስ ለመዝናናት መሄድ"" ብላለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-51557291 +politics የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዓመት በኋላ ከቤታቸው ውጪ ታዩ "የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዓመት በኋላ ከቤታቸው ውጪ መታየታቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ገለጹ። ቢቢሲ አቶ ዳውድ ዛሬ ረፋድ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ስብሰባ ለመቀመጥ ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አምርተው እንደነበር ከታማኝ ምንጮች ተረድቷል። የሊቀ መንበሩን ከእቁም እስር መለቀቅን ፓርቲያቸውም አረጋግጧል። የኦነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ሽጉት ገለታ፤ ""ታጉረው ከነበሩበት ቤታቸው መውጣት ችለዋል። መቶ በመቶ ተፈተዋል ማለት ባይቻለም ትልቅ ለውጥ ግን አለ። . . . ሰው አያነጋግራቸውም ነበር፣ ከቤት እንዲወጡ አይፈቀድላቸውም ነበር። ምርጫ ቦርድ ካነጋገራቸው በኋላ ግን ከቁም እስር ተለቀዋል"" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ምርጫ ቦርድ ከቀናት በፊት የኦነግ የረጅም ጊዜ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለው በቁም እስር ላይ እንደቆዩ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ገልጾ ነበር። ይህም ድርጊት ከሕግ ውጪ መሆኑን በመጥቀስ በሊቀ መንበሩ ላይ የተጣለው የመንቀሳቀስ ገደብ በአፋጣኝ እንዲነሳ ቦርዱ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን እና ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን በደብዳቤ መጠየቁ ይታወሳል። ከአቶ ዳውድ የቁም እስር በተጨማሪ በርካታ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በእስር ላይ ይገኛሉ። የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑትን ሚካኤል ቦረን እና አብዲ ረጋሳን ጨምሮ ኬነሳ አያና፣ ኮሎኔል ገመቹ አያና፣ ዳዊት አብደታ እና ለሚ ቤኛ በእስር ላይ ይገኛሉ። የኦነግ ቃል አቀባይ በቴ ኡርጌሳ ደግሞ ከጥቂት ቀናት በፊት ከእስር ቢለቀቁም፤ በእስር ላይ ሳሉ ያጋጠማቸውን የጤና መታወክ ተከትሎ በጤና ተቋም ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ። የፖለቲከኞቹ ጠበቆች ደንበኞቻችን በፍርድ ቤት በነጻ ቢለቀቁም ፖሊስ ነጻ ለማሰናበት ፍቃደኛ አይደለም ሲሉ ከዚህ በፊት ለቢቢሲ ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60761359 +business ሰሜን ኮርያ፡ ፕሬዝዳንት ኪም የአገራቸው ምጣኔ ሀብት እቅድ አለመሳካቱን ተናገሩ "የሰሜን ኮርያ ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን የአገራቸው የአምስት ዓመት የምጣኔ ሀብት እቅድ ""በሁሉም ዘርፎች ሊባል በሚችለ ሁኔታ"" የተቀመጠለትን ግብ አለማሳካቱን ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን የያሉት በፓርቲያቸው ጉባኤ መክፈቻ ላይ ነው። የሰሜን ኮርያ የሠራተኞች ፓርቲ ስብሰባ ሲያደርግ ይህ ስምንተኛው ብቻ ነው ተብሏል። ሰሜን ኮርያ ካለፈው ዓመት ታኅሣስ ወር ጀምሮ ምንም እንኳ አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው የለም ብትልም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚል ድንበሯን ዘግታለች። ይህም ከጎረቤቷና አጋሯ ቻይና ጋር ተቆራርጣ እንድትቀር አድርጓታል። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 80 በመቶ መውደቁ ተገልጿል። በሰሜን ኮርያ አውሎ ንፋስ እና ጎርፍ ቤቶችን ያወደመ ሲሆን በኒውክለር ፕሮግራሟ የተነሳም ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥብቅ የሆነ ማዕቀብ ተጥሎባታል። ፕሬዝዳንት ኪም የሚሰሯቸውን ስህተቶች ሲያምኑ የመጀመሪያቸው አይደለም። በቴሌቪዥን በተላለፈው የፓርቲው ጉባኤ ላይ አዳራሹ በተሰብሳቢዎች ሞልቶ የታየ ሲሆን አንዳቸውም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አላደረጉም። ፕሬዝዳንቱ ወደ ስብሰባ አዳራሽ ሲገቡ ሁሉም ከመቀመጫቸው ተነስተው በ��ብጨባ ተቀብለዋቸዋል። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው በ2016 ያስተዋወቁት የአምስት ዓመት የምጣኔ ሀብት ስትራቴጂ ""በሁሉም ዘርፍ ሊባል በሚችል ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ዝቅተኛ አፈጻጸም አስመዝግቧል ""ስህተቶችን ደግሞ በይፋ መቀበል ያስፈልጋል"" ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ የፓርቲያቸው አባላትን የኮሮናቫይረስን በመከላከል ረገድ ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል። ሰሜን ኮርያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መጠርጠራቸውን ለዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ሪፖርት ብታደርግም አንድም ሰው በቫይረሱ ተይዟል ብላ ሪፖርት አላደረገችም። ፕሬዝዳንት ኪም ለምክር ቤቱ አባላት አዲስ የአምስት ዓመት የምጣኔ ሀብት እቅድ ያስተዋውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55561319 +business በአንድ ቀን 1 ቢሊዮን ዶላር ያተረፈው ጆርጅ ሶሮስ ማን ነው? "አንድ የደበተው ሰኞ ከሰዓት፤ በ2019 ኅዳር ወር ላይ መሆኑ ነው፣ ምንነቱ ያልታወቀ የፖስታ ጥቅል በኒውዮርክ የባለጸጎች መንደር በሚገኝ አንድ ግዙፍ ቤት ተቀመጠ፤ ደጅ የፖስታ ሰንዱቅ ውስጥ። ጥቅሉ አጠራጣሪ ነገሮች ነበሩት። አንደኛ የተመላሽ ስም በትክክል አልተጻበትም። ሁለተኛ በተላከበት ቀን ነው የደረሰው። ፖሊስ ተጠራጠረ፤ ኤፍቢአይ ተጠራ። የጆርጅ ሶሮስ ቪላ ተወረረ። • የዓለማችን ቁጥር አንድ ሃቀኛዋ ሃገር በዚያ ጥቅል ውስጥ የሶሮስ ፎቶ ነበር፤ ከፊት ለፊት የይገደል ምልክት ተጽፎበታል። 6 ኢንች የሚረዝም የፕላስቲክ ጎማ፣ ቁልቁል የሚቆጥር ሰዓት፣ ባትሪና የኤሌክትሪክ ሽቦዎች ነበሩበት፤ በጥቅሉ ፖስታ። ተመሳሳይ ጥቅል ወደ ኦባማና ሂላሪ ቤት ተልኳል። ደግነቱ አንዱም አልፈነዳም፤ ፖሊስ አክሽፎታል። ቀኝ ዘመም የአሜሪካ ሚዲያ ቶሎ ጣቱን የቀሰረው ወደ ሶሮስ ነበር። ራሱ ሶሮስ የሸረበው ሸር ነው በሚል። ሶሮስ እንዴት አድርጎ ወደ ራሱ ቦምብ ይልካል? ጥሩ ጥያቄ ነው። ነገር ግን የትራምፕ አክራሪ ደጋፊዎች በአመዛኙ ለርትዕ ፊት አይሰጡም ይባላል፤ ለፖለቲካ ተዋስኦ ክፍት አይደሉም፤ አመክንዮ ይቀፋቸዋል። የትራምፕ ደጋፊዎች የሚቀናቸው ሴራ ነው። የአሻጥር ፖለቲካ የነጭ አክራሪዎች ኦፒየም ነው። ስለዚህም አደባባይ ወጡ። ጆርጅ ሶሮስን ሊያወግዙ። ""ትራምፓችን ሆይ! ሶሮስን እሰር! ሶሮስን ዘብጥያ አውርድልን"" የሚል ድምጽ በዋይት ሃውስ ደጅ ላይ አስተጋባ። ደግነቱ ፖሊስ ቦምቦቹን በጥቅል የላከውን ሰው ደረሰበት። የ56 ዓመቱ የፍሎሪዳ ነዋሪ ሲዛር ሳዮክ ነበር። ሰውየው እንዲያውም ብዙዎች እንደገመቱት ሪፐብሊካን አልነበረም። ቤት ለቤት ፒዛ አዳይ እንጂ። • በትራምፕ የድጋፍ ደብዳቤ ወደ አሜሪካ ያቀናችው የአሲድ ጥቃት የደረሰባት ኢትዮጵያዊት ሆኖም አእምሮው በሴራ ፖለቲካ ናውዞ ነበር። እንደ ብዙዎቹ ቀኝ አክራሪዎች። ከሁሉም ፖለቲካ ጀርባ ጆርጅ ሶሮስ የሚባል ሰው አለ ብሎ ያምን ነበር፤ ሶሮስ የነጭ የበላይነትን ሊያጠፋ የተነሳ ጠላት ነው ብሎ ያስብ ነበር፤ የትራምፕ ጠላት ነው ብሎ ያምን ነበር፤ ስለዚህ መገደል አለበት በሚል ነው ቦምቡን በፖስታ የላከው። የዚህ ወንጀለኛ ፌስቡክ ሲበረበር ደግሞ ሌላ ጉድ ተገኘ። ""ዓለም ከእንቅልፉ ሲነቃ የሶሮስን አሳዛኝ ዜና ይሰማል!"" ይህ ግለሰብ ለጊዜው 20 ዓመት እስር ተከናንቧል። ጆርጅ ሶሮስ ግን አሁንም የሴራ ፖለቲካ ገፈት ቀማሽ እንደሆነ አለ። ከሁሉም የዓለም ፖለቲካ ለውጥ ጀርባ የሶሮስ እጅ አለ የሚል አስተሳሰብ ናኝቷል። ለመሆኑ ሶሮስ እንደሚገመተው የዓለም የአሻጥር ፖለቲካ ሾፌር ነው? ጆርጅ ሶሮስ ከፖለቲከኞች አፍ የሚጠፋ ስም አይደለም። አምባገነኖች በተለይ ይፈሩታል። የእነዚህ አምባገነኖች መቀመጫ እሲያም ይሁን አፍሪካ፣ ምሥራቅ አውሮፓም ይሁን ደቡብ አሜሪካ ወይም መካከለኛው ምሥራቅ... ብቻ መንግሥታቱ ከሚነሳባቸው ተቃውሞ ጀርባ የቢሊየነሩ ጆርጅ ሶሮስ እጅ እንዳለበት ይገምታሉ። እውነት አላቸው? ለመሆኑ ይሄ ለግራ ዘመም ፖለቲከኞች ብር ይረጫል የሚባለውና በልግስናው ስመ ገናናው ጆርጅ ሶሮስ ማን ነው? ትውልደ ሀንጋሪያዊ-አሜሪካዊው ሶሮስ የተወለደው በቡዳፔስት በ1930 ዎቹ መጀመርያ ከአይሁድ ቤተሰብ ነበር። እንዲያውም ""ጆርጂዮ ሽዋትዝ"" ነበር የቀድሞ ስሙ። በጊዜው በአውሮፓ በአይሁዳዊያን ላይ በነበረው ሥር የሰደደ ጥላቻ ምክንያት አባቱ ከግድያ ለማምለጥ፣ ቤተሰባቸውንም ለመታደተግ እንዲረዳቸው ሲሉ ነው የቤተሰባቸውን ስም ከሽዋትዝ ወደ ""ሶሮስ"" የቀየሩት። ስሙን መቀየር ብቻም ሳይሆን በተለይ ለጆርጅ አዲስ ማንነትና መታወቂያ ተዘጋጅቶለት ልክ አይሁድ ያልሆነ ሌላ አንድ ተራ የቤተሰብ አባል ተደርጎ እንዲኖር ተደረገ። በዚህም ያንን አስቸጋሪ ዘመን መሻገር ቻለ። • ""ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው"" አቨቫ ደሴ ሶሮስ በ14 ዓመቱ የአንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ልጅ እንደሆነ ተደርጎ መታወቂያ ወጥቶለት ለጥቂት ሳይገደል ቀርቷል። ሶሮስ ከግድያዎች ያምልጥ እንጂ በዚህ ወቅት የአይሁዶች ንብረት ሲዘረፍ፣ ክብራቸው ሲገፈፍ ዓይኑ በብረቱ ተመልክቷል። በዚያ ዘመን፣ በተለይም በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ግማሽ ሚሊዮን የሀንጋሪ አይሁዶች እንዲገደሉ የሆነው 8 ሳምንታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር። እንዲያውም በመላው ዓለም ካሉ አገራት እንደ ሀንጋሪ አይሁዶች በአጭር ጊዜ በስፋት የተረሸኑበት አገር የለም ይባላል፤ ወላ በጀርመንም ቢሆን። ሶሮስ ከናዚዎች ግድያ ተርፎ እፎይ ብሎ መኖር ሲጀምር ሀንጋሪ ወደ ኮምኒስት አገርነት ተለወጠች፤ ሌላ ፈተና። በዚህ ጊዜ ነበር ገና በ17 ዓመቱ ከቡዳፔስት ወደ ለንደን የሸሸው። ጎረምሳው ሶሮስ እንግሊዝ እንደገባ የሻይ ቤት አስተናጋጅ ሆነ። ከዚያም የባቡር አውራጅና ጫኝ ሆነ። ቀጥሎ ዩኒቨርስቲ ገባና ከዝነኛው የለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ በምጣኔ ሀብት ዘርፍ ዲግሪ ያዘ። እዚያ ዩኒቨርስቲ ሳለ ነበር አስተሳሰቡን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የለወጠለትን ሰው ያገኘው። ይህ ሰው ፈላስፋው ሰር ካርል ሬይመንድ ፖፐር ነበር። ፈላስፋው ፖፐር ልክ እንደ ሶሮስ ሁሉ አይሁድ ስደተኛ ነው። ኦስትሪያዊ አይሁድ። ጆርጅ ሶሮስ አስተሳሰቡ የተጠረበው በዚህ መምህሩ እንደሆነ ይታመናል። • ሐኪሞች ለቀዶ ህክምና የሚጠቀሙበት የናዚ መፅሐፍ የዚህ መምህሩ በፖለቲካ ፍልስፍና ዓለም የናጠ ሥራው ""The open society and its enemies"" ይሰኛል። ከዚህ ከመምህሩ የጥናት ሥራ በተወሰደ ስም ነው ኋላ ጆርጅ ሶሮስ ዓለም ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ ድርጅቱን የመሠረተው፤ ስሙም ""ኦፕንሶሳይቲ ፋውንዴሽን"" ይባላል። ብቻ ከዚህ በኋላ ጆርጅ ሶሮስ በ1970 የሶሮስ ፈንድን አቋቋመ። እሱን ዓለም የሚያውቀው ግን በሁለት ነገር ነው፤ አንዱ እሱ አምጦ በወለደውና ቀደም ሲል በጠቀስነው ""ኦፕን ሶሳይቲ"" በሚባለው ድርጅቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የእንግሊዝን ባንክ በእንብርክክ በማስኬዱ ነው። ከሁለተኛው እንጀምር... በ1992 እንግሊዞች ""ጥቁሩ ረቡዕ"" (ብላክ ወይንስዴይ) ብለው የሚያውቁት ታሪክ አለ። ብሪታኒያ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ የገባችበት አስገራሚ ቀን ነው። ይህ ቀን ለብሪታኒያ ጥቁር ነበር ካልን ለጆርጅ ሶሮስ ግን ነጭ ነበር፤ የእርሱ የብልጽግና በር የተከፈተው በዚች ቀን ነበር ማለት ይቻላል። ነገሩን በአጭሩ ለማስረዳት፡ ብዙዎቹ የአውሮፓ አገራት ዩሮን ወይም እሱን የሚመስል የጋራ ገንዘብ ለመፍጠር እያለሙ ነበር።ይህን መንገድ የሚጠርግ The European Exchange Rate Mechanism (ERM) የሚባል ህብረት ነበራቸው። ይህንን ለማ��ካት ደግሞ አባል አገራት የገንዘባቸው ጥንካሬ ከተወሰነ መጠን ዝቅ እንዳይል ይጠበቅባቸው ነበር። የብሪታኒያ መንግሥት የሚገበያይበት ፖውንድ ስተርሊንግ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል የወለድ ምጣኔን ከፍ በማድረግ ጭምር ሞከረ። ሆኖም አልተሳካም። በዚህ ታሪካዊ ቀን እንግሊዝ ገንዘቧን ፓውንድን ከመውደቅ ማዳን አቃታት፤ ስላቃታትም ከአውሮፓ አገራት የውጭ ምንዛሬ መወሰኛ ኅብረት (ERM) ለመውጣት ተገደደች። ይህ ""ጥቁሩ ረቡዕ"" ብሪታኒያ ብሔራዊ ኪሳራን በአገር ደረጃ ያወጀችበት ዕለት ነበር። ጆርጅ ሶሮስ ከዚህ ቀን ቀደም ብሎ የፓውንድ መውደቅ አይቀሬ እንደሆነ በመተንበይ ፓውንድ አብዝቶ ከባንኮች ይበደር ነበር። በርካታ ፓውንድ እየተበደረ መልሶ ከባንክ ውጭ በርካሽ ይሸጠዋል። በተከታታይ ፓውንድ ዝቅ ባለ ዋጋ በመሸጥ ሌላ የገንዘብ ኖት በማከማቸቱ (በተለይም የጀርመን ማርክን) ብቻ በትንሹ በአንድ ቀን 1 ቢሊየን ዶላር ማትረፍ ችሏል። በዚህም የተነሳ ጆርጅ ሶሮስ ""የእንግሊዝን ባንክ የያንበረከከው ሰው"" በመባል ይታወቃል። ጆርጅ ሶሮስ በዚያ ዓመት እንግሊዝን 3.3 ቢሊዮን ፓውንድ አክስሯታል፤ በሌላ አነጋገር እያንዳንዱ እንግሊዛዊ በተናጥል 15 ፓውንድ ለሶሮስ ከፍሏል ማለት ነው። በእንዲህ ዓይነት አስቀድሞ የገንዘብ ጥንካሬን በመተንበይ በዓመታት ውስጥ በበርካታ አገራት ውስጥ ቢሊዮን ዶላር ማጋበስ እንደቻለ ይነገርለታል፤ ሶሮስ። እንደ ፈረንጆቹ በ1979 የተመሠረተው ኦፕን ሶሳይቲ በአሁኑ ጊዜ በ120 አገራት እየሠራ ነው። በኢትዮጵያም ቢሮ ለመክፈት በሂደት ላይ እንደነበር አንድ ሰሞን መዘገቡ ይታወሳል። የአገር ቤቱ ሪፖርተር ጋዜጣ የእንግሊዝኛው ቅጂ በፈረንጆች ኅዳር 30 እትሙ እንደዘገበው ደግሞ ኦፕን ሶሳይቲ እገዛ ሊያደርግላቸው ካሰባቸው ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች መሀል አዲስ ስታንዳርድ የድረገጽ ጋዜጣና አዲስ ፎርቹን የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ይገኙበታል። ሁለቱ ሚዲያዎች ከ160 እስከ 200ሺህ ዶላር እንደሚለገሳቸውም ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። ሪፖርተር በዚሁ ዘገባው የድርጅቱን ኃላፊ ሩት ኦሜንዲን ጠቅሶ እንዳለው ከሆነ ኦፕንሶሳይቲ በቅርብ ጊዜ ቢሮውን አዲስ አበባ ይከፍታል። እስከዛሬ እውን አልሆነም። • የወንድ የዘር ፍሬን ልክ እንደ ዓይን፣ ኩላሊት መለገስ ይቻላልን? ሊበራል ዲሞክራሲን በማስፋፋት የተጠመደው ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን የብዙ አገሮች ራስ ምታት መሆኑ አልቀረም። በተለይ አገራት ወደ ዲሞክራሲ እንዲሸጋገሩ ""አመጾችን ለማቀጣጠል የሚውል ገንዘብ ይረጫል"" የሚባለው ኦፕን ሶሳይቲ በሰብአዊ መብትና በትምህርት ላይ ያሳደረው የላቀ አስተዋጽኦ የሚካድ አይደለም። ሚስተር ጆርጅ ሶሮስ ለሴራ ፖለቲካ ለመጀርመያ ጊዜ የተጋለጠው በ1990ዎቹ መጀመርያ ቢሆንም በተለይ በ2003 የኢራቅ ጦርነትን መቃወሙ በሪፐብሊካኖች ዘንድ ጥርስ እንዲነከስበት ሆኗል። ""ያለኝን ሀብት በሙሉ ጆርጅ ቡሽን ለማስወገድ ብጠቀምበት አይቆጨኝም"" ማለቱ ብዙ ሲያነጋግር ነበር፤ በዚያ ዘመን። ሶሮስ በ2018ቱ የአሜሪካ ምርጫም በተመሳሳይ ገንዘቡን ረጭቷል ተብሎ ይነገራል። ከባራክ ኦባማ መመረጥ ጀርባ ትልቁ ገንዘብ የሶሮስ ነው ተብሎም ይታመናል። እንግሊዝ ከአውሮፓ ኅብረት ፍቺ እንዳትፈጽም ለሚተጋ ቡድን ወደ 800 ሚሊዮን ዶላር ለግሷል። የጆርጅ ሶሮስ ስምን ገናና ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ የቅርቡ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የነበረው ፍጥጫ ነው። ዶናልድ ትራምፕን የሚያወግዙ ማናቸውም ሰልፎችን በከፍተኛ ገንዘብ ይደግፋል የሚባለው ሶሮስ፤ ከሆንዱራስ ተነስተው በሜክሲኮ አድርገው ወደ አሜሪካ በእግር የዘመቱ ሥራ አጦችን ያዘመተብን እሱ ነው የሚል ክስ ይቀርብበታል። ውግን���ው ለትራምፕ እንደሆነ የሚነገርለት ፎክስ ኒውስ በተከታታይ በሰራቸው ዘገባዎች ጆርጅ ሶሮስ ሁሉም የአገራት ድንበሮች እንዲከፈቱና በሕዝቦች መካከል ያልተገደበ ዝውውር እንዲኖር ይሻል ሲል ከሶታል። ዶናልድ ትራምፕም በትዊተር ሰሌዳቸው ገንዘብ ለስደተኞች ሲታደል የሚያሳይ ቪዲዮ በመለጠፍ የገንዘቡ ምንጭ ሶሮስ እንደሆነ ለማመላከት ሞክረዋል። ""ዱርዬዎች የአሜሪካንን ድንበር እንዲሰብሩ እየተከፈላቸው ነው"" በሚል። በኋላ ጋዜጠኞች እንዳጣሩት ከሆነ ግን ትራምፕ ያጋሩት ቪዲዮ በጭራሽ በሆንዱራስ እንዳልተቀረጸና የቪዲዮው ምንጭም ጓቲማላ እንደሆነች ማረጋገጥ ችለዋል። ትራምፕ ግን ይህ ግድ አልሰጣቸውም። ከዚህ ትራምፕ ካራገቡት የሴራ ፖለቲካ በኋላም በአይሁዳዊያን ላይ የደረሰውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ የሶሮስ ስም በድጋሚ አንሰራራ። በዚህ ጥቃት አንድ ነጭ የአይሁዶች ምኩራብ ውስጥ ገብቶ 11ዱን ከፈጀ በኋላ ግለሰቡ ጆርጅ ሶሮስ የላከው ተደርጎ ሲዘገብ ነበር። ኋላ ላይ ሲጣራ ግን እንዲያውም ወንጀለኛው የጆርጅ ሶሮስ ቀንደኛ ጠላት እንደሆነ ተደርሶበታል። • በኢትዮጵያ ካምፕ ውስጥ ባለ2 ፎቅ መኖሪያ የገነባው ስደተኛ ይህ አክራሪ ነጭ ሽብርተኛ ጽፎታል በተባለ ምሥጢራዊ ሰነድ ማወቅ እንደተቻለው ""ጆርጅ ሶሮስ ቀስ በቀስ የነጮችን የበላይነት በአሜሪካና በአውሮፓ ለማጥፋት የሚሰራ ጠላት ነው"" ብሎ ያምን ነበር። ይህ አክራሪ ነጭ ሽብርተኛ የታወረበት የሴራ ፖለቲካ እንደሚያትተው ዓለም ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ነጮችን የማዳከምና የነጮችን አገር በጥቁር ስደተኞች ቀስ በቀስ የመሙላት ሐሳብ አለ፤ ይህን ሐሳብ በገንዘብ የሚደግፈው ሰው ደግሞ ጆርጅ ሶሮስ ይባላል። ያንን ጥቃት እንዲያደርስ የተገፋፋውም ይህንን የጆርጅ ሶሮን እንቅስቃሴ ለመግታት ነው። የዶናልድ ትራምፕ ሰዎች እጅግ ከማይወዷቸው ቢሊየነሮች ግንባር ቀደሙ ጆርጅ ሶሮስ ነው። በትራምፕ ወዳጆች ዘንድም ሶሮስ ላይ ከባድ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶበት ነበር። ""ሶሮስ ናዚ ነው""፤ ""ኦባማና ሂላሪ የሶሮስ አሻንጉሊቶች ናቸው""፤ ""አሜሪካን ለማፍረስ የሚተጋው አይሁድ ጠሉ ጆርጅ ሶሮስ ነው"" የሚሉ ወሬዎች ኢንተርኔቱን ሞልተውት ነበር አንድ ሰሞን። • የወንድ የዘር ፍሬን ልክ እንደ ዓይን፣ ኩላሊት መለገስ ይቻላልን? የጦር መሣሪያ ቁጥጥር እንዲጠብቅ፤ ጸረ ትራምፕ ሰልፎች እንዲፋፋሙ እንዲሁም የፍሎሪዳ ጥቃትን ተከትሎ የተደረገው ""ማርች ፎር አወር ላይቭስ ሙቭመንት"" በሶሮስ ገንዘብ የተቀነባበሩ እንደሆነ ይታመናል። የትራምፕ ተቺዎችን ለመግደል ያለመ የጥቅል ፖስታ ቦምብ እደላ በተደረገበት ወቅትም በቁጥር አንድ የትራምፕ ጠላትነት የተፈረጀው ሶሮስ ነበር። ከመካከለኛው አሜሪካ ኑሮ መረረን ያሉ ስደተኞች ወደ አሜሪካ የእግር ጉዞ ሲጀምሩ ትራምፕ የግምብ አጥሩን ቶሎ እንገንባው በሚሉበት ወቅት ይህንን የሕዝቦች ስደትን የሚደግፈው ጆርጅ ሶሮስ ነው የሚሉ ወሬዎች መነዛት ጀምሩ። ትራምፕም ይህንኑ እንደሚጠረጥሩ ተናግረዋል። ""እሱ ነው ቢሉኝ አልደነቅም፤ እሱ ስለመሆኑ አላውቅም፤ እሱ እንደሚሆን ግን እገምታለሁ፤ አያስደንቀኝም"" ብለው ነበር ዶናልድ ትራምፕ ለጋዜጠኞች። የትራምፕ ልጅ በተዋናይት ሮሰን ባር የትዊተር ሰሌዳ ስለ ሶሮስ የተጻፈውን መራር ጥላቻ ማጋራቱም ምን ያህል ሶሮስ በነ ትራምፕ ቤተሰብ የማይወደድ ቢሊየነር እንደሆነ መገመት አስችሏል። ተዋናይት ባር የጻፈችውና የትራምፕ ልጅ ያጋራው ጽሑፍ እንዲህ ይላል። • ወደ ለንደን የሚሄደው አስደናቂው የትራምፕ ጓዝ ""በነገራችሁ ላይ ጆርጅ ሶሮስ ናዚ ነው። የገዛ አይሁድ ጓደኛውን በጀርመን ማጎርያ ካምፕ ውስጥ አስገድሎ ገንዘቡን የዘረፈ ናዚ"" ይህን ተከትሎ የሶሮስ ቃል አቀባይ ""እንዲህ ዓይነት መሠረተ ቢስ ክሶች በሶሮስ ሳይሆን በመላው አይሁድ ሕዝብ ላይ የተቃጡ ስድቦች ናቸው፤ በተለይም በጅምላ ፍጅቱ ተጠቂዎች ላይ..."" ብሏል። እርግጥ ነው ሶሮስ አገሮች ነጻ እንዲሆኑ፤ የሕዝቦች ነጻ እንቅስቃሴ እንዲኖር ይተጋል። ይህ ግን አገሮች ድንበር አይኑራቸው ከሚል ጽንሰ ሐሳብ የሚመነጭ አይደለም። የጆርጅ ሶሮስ ተቺዎች ሶሮስ በአገራት የውስጥ ፖለቲካ ጣልቃ ይገባል፤ እጁም ረዥም ነው ይሉታል። እርግጥ ነው ለሂላሪና ለኦባማ የምርጫ ዘመቻ ትልቁን ገንዘብ ስለመስጠቱ የሚካድ አይደለም። ይህ ተግባሩ ግን በአሜሪካ ብቻ የሚወሰን አልሆነም። ሶሮስ በ1980ዎቹ የሀንጋሪ ኮምኒስቶችን ለማዳከም ገንዘቡን አውሎታል። ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን ለዲሞክራሲ እሴቶች የሚተጋ ነው። በዓመታት ውስጥ ወደ 30 ቢሊዮን ዶላር ለዚህ ድርጅቱ ፈሰስ አድርጓል ሶሮስ። ይህ ገንዘብ በምንም መለኪያ ትንሽ አይደለም። • ትራምፕ ስለስደተኞች በተናገሩት ወቀሳ ደረሰባቸው ""ይህን ድርጅት ያቆምኩት አስተማማኝ ዲሞክራሲን በመላው ዓለም ለመዘርጋት ነው"" ይላል፤ እሱም ቢሆን። ሶሮስ በትውልድ አገሩ ሀንጋሪ ቢሊዮን ዶላሮችን በማፍሰስ የሰብአዊ መብት ፕሮጀክቶችንና በትምህርት ቤቶች ነጻ የምግብ እደላዎች እንዲኖሩ አስችሏል። ከሁሉም በላይ በኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ጭምር ዝነኛ የሆነውና የውጭ የትምህርት ዕድል በመስጠት የሚታወቀው የሴንትራል ዩሮፒያን ዩኒቨርስቲን (CEU) የመሠረተው ጆርጅ ሶሮስ ነው። ""አንዳንድ ጊዜ ትልቅ ለማይመስሉ ነገር ግን ለምናምንባቸው ነገሮች መቆም አለብን"" ይላል ሶሮስ። ከእነዚህ መሀል አንዱ በስደተኞች ላይ ያለው አቋሙ ነው። በአውሮፓ የሚገኙ ስደተኞችን ለማገዝ የሚተጋው ሶሮስ ከበርካታ አገራት መንግሥታት ጥላቻን አትርፏል። ""የነጮች አህጉር የሆነችውን አውሮፓን በስደተኛ ልታጥለቀልቃት ነው ሀሳብህ"" የሚል ክስ ይነሳበታል። እሱም ""በስደተኛ ላይ ያለኝ አቋም ብዙ ጠላት አፍርቶልኛል"" ይላል። • ማሽተት አለመቻል ምን ይመስላል? ለምሳሌ የገዛ ትውልድ አገሩ ሀንጋሪ ለሶሮስ ያላትን ጥላቻ በጎዳና ላይ ቢልቦርድ ጭምር ሰቅላዋለች። አሁን ያለው የሀንጋሪያዊያን መንግሥት በአመዛኙ ጥቁር ጠል የሚባል ነው። በሀንጋሪ ለስደተኞቸ ድጋፍ የሰጠ ዜጋ በእስር ይቀጣል። የሚደንቀው ታዲያ የዚህን የቅጣት ሕግ ስም ሳይቀር የሃንጋሪ መንግሥት ""ስቶፕ ሶሮስ"" ብሎ ነው የሚጠራው። ያው ስደተኞችን እያጋዘ የሚያመጣብን ጆርጅ ሶሮስ ነው በሚል። የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የሶሮስ ቀንደኛ ጠላት ናቸው። በስሎቫኪያ የጋዜጠኛ መገደልን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ የተደናገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንድ ወቅት ባደረጉት ንግግር፡ ""ይሄ የጆርጅ ሶሮስ እጅ ነው። በስሎቫኪያ የተነሳው ነውጥ የሶሮስ ሥራ ነው። እሱ ስደተኛ እንዳይመጣባቸው ለሚፈልጉ አገራት አይራራም። የጎዳና ላይ ነውጥ እያስነሳ ይገለብጣቸዋል"" ብለው ነበር። ጆርጅ ሶሮስ ከአፍሪካ እስከ ምሥራቅ አውሮፓ፣ ከትራምፕ እስከ ሞዲ ስለሱ የሚባለውን ሲሰማ ምን ይላል? በእርግጥ የዓለም ፖለቲካን የሚዘውረው ሰው ጆርጅ ሳሮስ ነው? ""የእኔ እጅ ረዥም እንደሆነ የሚነገረው የተጋነነ ነው። እንደሚባለው የእንግሊዝ ባንክን አላንኮታኮትኩትም። ገበያው ነው ያንኮታኮተው። እንደሚባለው ስደተኛን እያጋዝኩ ወደ አውሮፓና አሜሪካ አላስኮበልልም። ኦፕን ሶሳይቲን የመሠረትኩት ዲሞክራሲንና የዲሞክራሲ ተቋማትን ለማጎልበት ነው"" ይላል። ጆርጅ ሳሮስ እንደ ትራምፕ የሚንቀው ሰው ያለ አይመስልም። ""ትራምፕ አታላይና በራሱ ፍቅር የናወ�� ሰው ነው"" ይላል። ትራምፕን ብሔራዊ ጥቅምን ሳይቀር ለግል ስምና ዝናው አሳልፎ ለመስጠት የማይሳሳ ነው ይለዋል። የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ዠን ፒንግን ደግሞ በቴክኖሎጂ መላ ሕዝቡን ለመቆጣጠር የሚሞክር አምባገነን ይለዋል። ዓለማችን ሁለቱን መሪዎች ብታስወግድ የተሻለ እንኖር ነበር ይላል ሶሮስ። ሶሮስ በስዊዘርላንድ ዳቮስ በቅርቡ ባደረገው ንግግር ዘረኝነት በአገራት እየተስፋፋ መምጣቱ እንደሚያሳስበው ተናግሯል። ጥላቻ እንዳይነግስ ለሚሰሩ፣ የመቻቻል ፕሮጀክቶችን ለማጎልበት ደግሞ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 1 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ቃል ገብቷል። በዘረኞችና በሀሰት ወሬ አራጋቢዎች የምትሾረው ዓለም ለሶሮስ ታሳስበዋለች። ክሪቲካል ቲንኪንግ ወይም ምክንያታዊነትን ቶሎ ካላስፋፋን መጪው ጊዜ አስፈሪ ነው ይላል ሶሮስ። ከመሞቴ በፊት ማድረግ ይመፍልገውም ይህንን ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-51276518 +sports ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዓለም ዋንጫው ላይ አዲስ ታሪክ ጻፈ ፖርቹጋል በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ ጋናን 3 ለ 2 ስታሰንፍ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ጎል በማስቆጠር የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል። አጥቂው ከማንቸስተር ዩናይትድ በስምምነት እንዲለቅ ካደረገው አነጋጋሪ ቃለ መጠይቅ በኋላ ሲጫወት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የ37 ዓመቱ ተጫዋች ጎሏን ያስቆጠረው በፍጹም ቅጣት ምት ነው። የፖርቹጋሉ አጥቂ ቀደም ብሎ ያገኛቸውን ሁለት ዕድሎች ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል። ጋና ጎሉ ከተቆጠረባት በኋላ ባሳየችው መነሳሳት በአንድሬ አዬው ማካይነት አቻ ለመሆን በቅታለች። ጆአኦ ፌሊክስ እና ራፋኤል ሊአኦ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ፖርቹጋል 3 ለ 1 ለመምራት ችላለች። ኦስማን ቡካሪ ለጋና ሁለተኛ ጎል ማስቆጠር ቻለ። አፍሪካዊቷ ሃገር ባለቀ ሰዓት አቻ ለመሆን ያደረገችው ከፍተኛ ጥረት አልተሳካም። በምድቡ የሚገኙት ኡራጓይ እና ደቡብ ኮሪያ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይተዋል። በኤጁኬሽን ስታዲም በተደረገው ጨዋታ ደቡብ ኮሪያዎች የተሻለ ቢንቀሳቀሱም የጎል ዕድል መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። ትላንት የተደረጉት ጨዋታዎች የተጀመሩት ስዊዘርላንድ እና ካሜሩን ባደረጉት የምድብ ሰባት ፍልሚያ ነው። ስዊዘርላንድ ጨዋታውን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች። ብሪል ኤምቦሎ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ያሳረፈ ተጫዋች ሆኗል። ካሜሩን ተወልዶ ለስዊዘርላንድ የሚጫወተው አጥቂ ጎሉን ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን ከመግለጽ ተቆጥቧል። የማይበገሩት አንበሶች ካሳዩት እንቅስቃሴ አንጻር ተሸንፈው መውጣት አልነበረባቸውም ተብሏል። በሌላ የምድብ ሰባት ጨዋታ ለዋንጫው ትልቅ ግምት የተሰጣት ብራዚል ሰርቢያን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች። ጥንቃቄ የተሞላበትን የሰርቢያን አጨዋወት ሰብሮ ለመግባት ብራዚሎች 62 ደቂቃ ለመጠበቅ ተገደዋል። ሪቻርልሰን ደግሞ ጎሏን ያስቆጠረው ተጫዋች ነው። ከደቂቃዎች በኋላ ቄንጠኛ ጎል ከመረብ አሳርፎ ቡድኑን ለአሸናፊነት አብቅቷል። አሌክስ ሳንድሮ እና ካሰሚሮ በጎሉ ብረት የተመለሰባቸውን ጨምሮ ብራዚሎች በርካታ ዕድሎችን አምክነዋል። ኔይማር ተግድቶ የወጣ ሲሆን ብራዚሎች የህክምና ውጤቱን በተስፋ እየጠበቁ ነው። የዓለም ዋንጫው ቀጣይ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ። በምድብ ሁለት የሚገኙት ዌልስ እና ኢራን ቀን ሰባት ሰዓት በአህመድ ቢን አኪ ስታዲየም ይገናኛሉ። ኢራን በእንግሊዝ ተሸንፋ ዌልስ ደግሞ ከአሜሪካ አቻ ተለያይታ ነው የሚገናኙት። አዘጋጇን ኳታርን እና ሴኔጋልን የሚያገናኘው ጨዋታ ቀን 10 ሰዓጥ ይከናወናል። ሁለቱም ቡድኖች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በመሸነፋቸው ዛሬ የሚሸነፈው ቡድን ከምድቡ እንደማያልፍ ያረጋግጣል። ኔዘርላንድ እና ኢኳዶር ደግሞ ምሽት አንድ ሰዓት ይገናኛሉ። ሦስት ሦስት ነጥብ ስላላቸው የሁለቱ አሸናፊ በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ መግባቱን ያረጋግጣል። በዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ እንግሊዝ እና አሜሪካ ይጫወታሉ፥ እንግሊዝ ሦስት አሜሪካ ደግሞ አንድ ነጥብ ይዘው ነው ሁለተኛ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑት። https://www.bbc.com/amharic/articles/c723dk17lwro +politics የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦማር ጊሌ ለ5ኛ ጊዜ ምርጫ አሸነፉ የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለ5ኛ ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድረው ከመራጩ ሕዝብ 98 ከመቶ ድምጽ በማግኘት አሸነፉ። ብቸኛው ተፎካካሪያቸው የነበሩት ዛካሪያ ኢስማኢል ፋራህ 1.59 በመቶ ብቻ የመራጮችን ድምጽ ሊያገኙ መቻላቸው ተነግሯል። የዋነኛው ተቃዋሚ መሪው ዕጩ ባለፈው አርብ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድኔ በምርጫ ጣቢያዎች አካባቢ እንግልት ደርሶበታል በሚል ድምጽ ሳይሰጡ ራሳቸው ከውድድሩ አግልለው ነበር። ምርጫውን በበላይነት የመሩት የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሙሚን አሕመድ ሼክ አርብ ዕለት 177 ሺህ መራጮች ድምጽ መስጠታቸውን ተናግረዋል። በመጀመሪያ ላይ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ላይ ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡት ሰዎች ድምር 200 ሺህ እንደነበር ተዘግቧል። ኤስማኤል ጊሌ አሁን የ73 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ እንደ አውሮፓውያን ከ1999 ጀምሮ በጂቡቲ የፕሬዝዳንተንት የሥልጣን መንበር ላይ ቆይተዋል። የዘንድሮውን ምርጫም በከፍተኛ የበላይነት በማሸነፋቸው ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት ጂቡቲን እንዲመሩ ያስችላቸዋል ተብሏል። በቆዳ ስፋት አነስተኛ ሆና ነገር ግን በአፍሪካ ቀንድ ቁልፍ አካባቢያዊና ወታደራዊ ቦታ የያዘችው ጂቡቲ ጠቅላላ የሕዝብ ብዛቷ ከአንድ ሚሊዮን ያነሰ ነው። አሜሪካ፣ ቻይናና ፈረንሳይ በጂቡቲ ወታደራዊ ጦር ሰፈር ገንብተዋል። የዓለም ባንክ በቅርብ ያወጣው አንድ መረጃ ከ14 ከመቶ በላይ የሚሆኑ ጂቡቲያዊያን በከፍተኛ የድህነት ውስጥ ነው የሚኖሩት ይላል። https://www.bbc.com/amharic/news-56702735 +health የካናዳዋ ግዛት ባልተከተቡት ላይ የጤና ግብር ልትጥል ነው "የካናዳዋ ኪዩቤክ ግዛት የኮቪድ-19 ክትባት ባልወሰዱ ነዋሪዎቿን የጤና ግብር ልታስከፍል ነው። ከዚህ ቀደም በካናዳ ካሉ ግዛቶች በወረርሽኙ መስፋፋት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ኩዩቤክ በአሁኑ ወቅትም የቫይረሱ ስርጭት አይሎባታል። ትናንት የክልሉ ገዢ ኪዩቤክ በካናዳ ክትባት ያልወሰዱትን በገንዘብ ስትቀጣ የመጀመሪያዋ ትሆናለች ብለዋል። እስካሁን ከግዛቷ ነዋሪዎች 12.8 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ነዋሪዎች ናቸው ክትባቱን ያልወሰዱት። ይሁን እንጂ በኮቪድ ተይዘው ሆስፒታል ከሚገቡት ወደ ግማሽ የሚጠጉት ያልተከተቡ ሰዎች ናቸው። የግዛቷ አስተዳዳሪ ፍራንኮኢስ ሌጋኡለተ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ያልወሰዱ ሰዎች ""መዋጮ"" መክፈል ይኖርባቸዋል ብለዋል። የክፍያ መጠኑ ባይገለጽም፤ ክፍያው ""ቀላል"" እንዳልሆነ ተናግረዋል። ግዛቷ የኮቪድ ስርጭቱን ለመግታት የሰዓት እላፊ ገደብ አስተዋውቃለች እንዲሁም ሰዎች አገልግሎት ፍለጋ ተቋማትን ከመጎብኘታቸው በፊት የክትባት ማስረጃ እንዲያሳዩ ትጠይቃለች። ይህ የግዛቱ አስተዳዳሪዎች ውሳኔ የተሰማው ባለፉት 24 ሰዓታት በኪዩቤክ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የ62 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ከተገለጸ በኋላ ነው። 8ሺህ 710 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በአሁኑ ወቅት ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ 2ሺህ 742 ሰዎች ሆስፒታል የገቡ ሲሆን 244 የሚሆኑት በጽኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ። ኪዩቤክ ክትባት ባልወሰዱት ላይ የገንዘብ መቀጮ ያስተዋወቀች ብቸኛዋ አይደለችም። አውሮፓዊቷ ግሪክ ከሳምንታት በኋላ ክትባት ያልወሰዱ እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆነቸው ሰዎችን በየወሩ 100 ዩሮ ክትባት እስኪወስዱ ድረስ እንዲከፍሉ ውሳኔ አስተላልፋለች። ሲንጋፖር ደግሞ የኮቪድ ክትባት ያልወሰዱ ሰዎች የጤና ክፍያዎችን ከኪሳቸው እንዲሸፍኑ አዛለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-59954381 +health በትግራይ በሕጻናት ላይ የሚከሰቱ በሽታዎች እየጨመሩ መሆናቸው ተነገረ በትግራይ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት የክትባት መጠን በመቀነሱ በክትባት መከላከል የሚቻሉ በሕጻናት ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ ዓይነት በሽታዎች እየጨመሩ መሆኑ ተነገረ። የክልሉ የጤና ባለሥልጣናት እንዳሉት ክትባት የሚያገኙ ሕጻናት ቁጥር በመቀነሱ ልጆችን የሚያጠቁ ኩፍኝን፣ ፖሊዮን እና ቲታነስን የመሳሰሉ በሽታዎች እየጨመሩ ነው። ከትግራይ ጤና ቢሮ የወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት ውስጥ በክልሉ መደበኛ የበሽታዎች መከላከያ ክትባቶችን የሚያገኙ ልጆች መጠን ከ10 በመቶ በታች አሽቆልቁሏል። የጤና ቢሮው ‘ጋቪ’ በመባል ለሚታወቀው በዓለም ዙሪያ ክትባቶችን የሚያቀርበው ዓለም አቀፍ ትብብር በጻፈው ደብዳቤ ላይ፤ “የጨቅላ ሕጻናት እና የልጆች ክትባትን ጨምሮ ሕይወት አድን የሆኑ መድኃኒቶች እና የሕክምና አቅርቦቶች እንዳያገኙ በመደረጋቸው” ለተለያዩ በሽታዎች ተዳርገዋል ብሏል። በዚህም ሳቢያ የኩፍኝ፣ የተቅማጥ፣ የማጅራት ገትር፣ የልጅነት ልምሻ [ፖሊዮ] እና የመሳሰሉ ወረርሽኞች በክልሉ ውስጥ መከሰታቸውን የጤና ቢሮው በጻፈው ደብዳቤ ላይ አመልክቷል። ለዚህም በምክንያትነት የተጠቀሰው በክልሉ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት የክትባት አቅርቦት በመቀነሱ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ባለመኖሩ ከትባቶችን በተገቢው መጠን አቀዝቅዞ ለማስቀመጥ ባለመቻሉ እና በገጠር አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ወደ ጤና ተቋማት ለክትባት መምጣት ባለመቻላቸው እንደሆነ የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል። የኩፍኝ ወረርሽኝ በክልሉ ውስጥ ካሉ 35 ዞኖች በ10 ዞኖች ውስጥ መከሰቱን ሪፖርት መደረጉን የገለጸው ቢሮው፣ እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 ዜሮ የነበረው በጨቅላ ሕጻናት ላይ የሚከሰት ቲታነስ አሁን 25 መድረሱን አመልክቷል። በመጪው ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ሁለተኛ ዓመቱን በሚይዘው በትግራይ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት በርካታ የጤና ተቋማት ላይ ውድመት ማጋጠሙንና ከሥራ ውጪ መሆናቸውን ከዚህ በፊት የወጡ ሪፖርቶች አመለክተዋል። ጋብ ብሎ የነበረው ጦርነት በቅርቡ መቀስቀሱ ደግሞ በክልሉ ውስጥ ያለውን የጤና አገልግሎት የአቅርቦት ችግር የበለጠ ሊያባብሰው ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cmjdp7xy23no +politics አል ቡርሐን እራሳቸውን የሱዳን ጊዜያዊ መሪ አድርገው ሾሙ "በሱዳን የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት በመምራት ወታደሩ ሥልጣን እንዲይዝ ያደረጉት ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሐን አዲስ ምክር ቤት ሲመሠርቱ እራሳቸውን ደግሞ መሪ አድርገው ሰይመዋል። ሐሙስ ዕለትም ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። ጄነራል ቡርሐን፤ ምክትላቸው መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎችን ከጥቅምት 25ቱ መፈንቅለ መንግሥት በፊት በነበራቸው ሥልጣን እንዲቆዩ አድርገዋል። 14 አባላት ያሉት የሽግግር ምክር ቤት ሲቪል ዜጎችን ቢያካትትም ከመፈንቅለ መንግሥቱ በፊት ሥልጣን ላይ ከነበረው የፖለቲካ ጥምረት አንድም ወኪል አልተካተተም። ከሥልጣን የተባረሩት የሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ሐምዛ ባሎል አዲሱን የአል ቡርሐን እርምጃ የመፈንቅለ መንግሥቱ ቅጥያ አድርገው ገልጸዋል። ሕዝቡ ""አሸንፎ ሽግግሩን ያስቀጥላል"" ብለዋል። ምክር ቤቱ የተቋቋመው መፈንቅለ መንግሥቱን ለመቀልበስ ከአገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ አካላትም ጫናው በጨመረበት ወቅት ነው። በ���ዳን የተባበሩት መንግሥታት ተወካይ ቮልከር ፔርዝስ፤ የጦሩ ዋና አዛዥ ጄነራል አል ቡርሐን የሰጡት የአንድ ወገን የምክር ቤት ሹመት፤ አገሪቱ ወደ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለመመለስ እንድትቸገር ያደርጋታል ብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት መልዕክተኛው የሱዳንን ፖለቲካ እና ምጣኔ ሀብት ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ በአስቸኳይ ድርድር እንዲካሄድ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ጦሩ የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን ሙሉ ነጻነት መመለስን ጨምሮ ሌሎች ""የመተማመኛ እርምጃዎችን"" እንዲወስድም አሳስበዋል።" https://www.bbc.com/amharic/59258061 +sports ዩናይትድን ከቶተነሃም ያፋጠጠው የ11ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት የቢቢሲው  የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን አንድንድ ጊዜ የሚሰጠው ግምት አስደንጋጭ የሚባል ነው። ባለፈው ሳምንት ሊቨርፑል በሜዳው በማንቸስተር ሲቲ 4 ለ 1 እንደሚሸነፍ ግምቱን አስቀምጦ ነበር። በሊቨርፑል ዙሪያ ስሀተት ሲሰራ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በርንማውዞች ምን ይበሉ? ያለፉትን 10 ሳምንታት ጨዋታዎች በሙሉ እንደሚሸነፉ ግምቱን አስቀምጧል። የ11ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ትላንት ምሽት ተጀምረዋል። ሱቶን በብራይተን የበላይነት ይጠናቀቃል ያለው የብራይተን እና ኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታ ያለጎል አቻ ተጠናቋል። ክሪስታል ፓላስ እና ዎልቭስ ደግሞ አንድ አቻ ይለያያሉ ሲል ግምቱን አስቀምጦ ነበር። ፓላስ ግን ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የሌሎች ጨዋታዎችን ግምት እንደሚከተለው እንቃኛለን። አርሰናል ከማንቸስተር ሲቲ ማድረግ የነበረባቸው ይህ ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። በርንማውዝ ከ ሳውዝሃምፕተን የትኛውም የበርንማውዝ ደጋፊ በማይጠብቀው መልኩ ቡድኑ ያሸንፋል ብዬ ግምቴን ላስቀምጥ። በርንማውዝ ይህን ጨዋታ ማሸነፍ ይኖርበታል። ሳውዝሃምፕተኖች ከዌስትሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ አንድ ነጥብ ማግኘታቸው ዕድለኛ ያደርጋቸዋል። በርንማውዞች ከፉልሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ ያስቆጠሩት የመጀመሪያ ጎል ድንቅ ነበር። ግምት፡ 2 – 1 ቼልሲዎች ባለፈው እሁድ አስቶን ቪላን ማሸነፍ ችለዋል። ከብሬንትፎርድ ምን መጠበቅ እንዳለብኝ አላውቅም። ከብራይተን ጋር በነበራቸው ጨዋታ አጥቂ ክፍላቸው ወደ አቋሙ የተመለሰ መስሏል። ቼልስ በጥሩ አቋም ላይ ካልተገኘ እና ብሬንትፎርዶች በተመሳሳይ መልኩ ከተጫወቱ አንድ ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 1 – 1 ሊቨርፑል ከ ዌስት ሃም ከሰሞኑ ከሊቨርፑል ደጋፊዎች ብዙ ትችት አስተናግጃለሁ። ሊቨርፑል ከሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ በተለይም የኋላ መስመሩ አስደናቂ ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ ደጋፊው ከጎናቸው የቆመበት እና አንፊልድ ወደ ቀድሞ አቋሙ የተመለሰበት አጋጣሚ ነበር። ወደ አቋማቸው ለመመለስ በተገቢው መንገድ ላይ ያሉ ይመስለኛል። የዌስትሃም የኋላ መስመር መሳሳት የሚረዳቸው ሲሆን ጂያንሉካ ሳማካ ደግሞ ጎል ያስቆጥራል። ግምት፡ 3 – 1 ኒውካስል ኦልትራፎድ ላይ አለማሸነፉ ትንሽ ዕድለ ቢስ ያደርገዋል። ቡድኑ ሚዛኑን ያገኘ ይመስላል። በመከላከል በኩል ጥሩ ሲሆኑ የተወሰኑ ዕድሎችንም ማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ለመፍጠር ችለዋል። እስከ ስድስት ባለው ደረጃ ውስጥ ለምን እንደተቀመጡ መረዳት የሚቻል ሲሆን አሁን ካላቸው ነጠብ የተሻለም ማግኘት ነበረባቸው። ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች የተሸነፉት ኤቨርተኖች በዚህ ጨዋታም ይቸገራሉ ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 – 0 ማንቸስተር ዩናይትዶች ከኒውካስል ጋር ዕድል ያመለጣቸው ይመስለኛል። የስፐርስ ጨዋታ ሌላ ጉዳይ ነው። ሃሪ ኬን ዕድል ካገኘ ጎል የማስቆጠር ብቃቱ ላይ ይገኛል። ዩናይትድ ደግሞ ጥርስ አልባ መሆኑን ባለፈው ሳምንት አሳይቷል። ቡድኑ ክርስቲያን ኤሪክሰንን በህምም ምክንያት ማጣቱ የጎዳው ሲሆን ለዚህ ለቀድሞ ክለቡ ጨዋታም ላይደርስ ይችላል። ኤሪክሰን ቢሰለፍም አንቶኒዮ ኮንቴ በመልሶ ማጥቃት የሚያሸንፍ ይመስለኛል። ግምት፡ 1 – 3 ፉልሃም ከ አስቶን ቪላ አስቶን ቪላዎች ባለፈው ሳምንት ከቼልሲ ጋር በነበራቸው ጨዋታ በመጀመሪያ አጋማሽ ጥሩ ቢሆኑም በዚያው አልቀጠሉበትም። አሰልጣኝ ስቴቨን ዤራርድ ጫና ውስጥ የወደቀ ሲሆን ደጋፊዎችም ፊታቸውን ያዞሩበት ይመስላል። ስለዚህ በዚህ ጨዋታ ጥሩ ውጤት ይጠብቃል። ፉልሃም እና ብርንማውዝ ባለፈው ሳምንት ባደረጉት ጨዋታ ፉልሃሞች አደገኛ እንደሆኑ ተመልክቻለሁ። ይህ ጨዋታ አቻ ይጠናቀቃል ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 1 – 1 ሌስተር ከ ሊድስ ሌስተሮች ተጽዕኖ ፈጠሪ የሆነውን ተጫዋቻቸውን ጀምስ ማዲሰንን በቅጣት አያገኙም። በአርሰናል የተሸነፉበትን ጨምሮ ሊድሶች በዘንድሮው ዓመት እንደአጨዋወታቸው የሚገባቸውን ውጤት ያላገኙባቸው ጨዋታዎች አሉ። በዚህ ጨዋታ ግን ይህንን የሚቀይሩበት እንደሚሆን እገምታለሁ። አጨዋወታቸውንም የምወደው ሲሆን ተገቢውንም ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 1 – 4 https://www.bbc.com/amharic/articles/c80p4lnr1p0o +sports ፖሊስ የኮቢ ብሪያንት አሟሟት አሰቃቂ ምስሎችን አሳይቷል ስትል ባለቤቱ ከሰሰች "በባለፈው አመት በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወቱን ያጣው ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብሪያንት ባለቤት የአሟሟቱን ሁኔታ የሚመለከቱ አሰቃቂ ምስሎችን አውጥቷል ስትል ፖሊስን ከሳለች። አሰቃቂ ምስሎች አውጥተዋል ያለቻቸውን የሎስ አንጀለስ ግዛት ፖሊሶች ስምም ጠቅሳለች። ፖሊሶች በቸልተኝነትና የግል ኑሯቸውን በጣሰ መልኩ እነዚህን ፎቶዎች አውጥተዋል በማለት የግዛቱን የፖሊስ ኃላፊዎች የከሰሰችው። ""በሚዲያ የፍርድ ሂደቱ እንዲካሄድ ስለማንፈልግ ምንም ነገር ከማለት ተቆጥበናል"" በማለት የፖሊስ ኃላፊው ምላሽ ሰጥተዋል። ስመ ጥሩው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢና ልጁን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች በባለፈው አመት በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ መሞታቸው የሚታወስ ነው። በያዝነው ሳምንት ረቡዕ ቫኔሳ አሰቃቂ ፎቶን አውጥተዋል ያለቻቸውን አራት የፖሊሶች ስም በኢንስታግራም ገጿ አስፍራለች። ቫኔሳ እንደምትለው ፖሊሶቹ የዘጠኙን ሰዎች አስከሬን ፎቶዎች ካነሱ በኋላ አንደኛው ፖሊስ በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ የኮቢን ፎቶ እያሳየ ነበር ብላለች። ሌሎቹ ደግሞ ህፃናት ያሉበት፣ ወላጆቻቸውንና አሰልጣኞቻቸውን አሰቃቂ ፎቶዎች ለበርካቶች ሲያሳዩ ነበር ብላለች። የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ በየካቲት ወር ላይ ውስጣዊ የፖሊስ የምርመራ መዝገብን ጠቅሶ ፖሊሶች የሟቾችን አሰቃቂ ፎቶዎች አጋርተዋል ብሏል። ቫኔሳ እንደምትለው የ13 አመት ልጇ ጂያና የአስከሬን ፎቶ ሳይቀር ""ለአሉባልታ ብቻ"" ለዕይታ ውሏል ብላለች። የፖሊሶቹ ስም ይፋ እንዳይወጣ ባለፈው ሳምንት ለፍርድ ቤት ጥያቁ ቢቀርብም ዳኛው በበኩላቸው ስማቸው ይፋ እንዲሆን አዟል። የሎስ አንጀለስ ግዛት ፖሊስ ኃላፊ አሌክስ ቪላኑቫ የቫኔሳን ትዊተር አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ የፍርድ ቤቱን ምላሸ እንጠብቃለን ብለዋል። ቫኔሳ ስምንት ፖሊሶች ለራሳቸው ጥቅም እንዲውል በሚል በርካታ ፎቶዎች ያነሱ ሲሆን አንደኛው ግለሰብም ከ25-100 ፎቶዎችን አንስቷል ብላለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-56453317 +politics ተቃውሞ ተጠናክሮ በቀጠለባት አውሮፓ፤ ኦስትሪያ የእንቅስቃሴ ገደብ ጣለች "የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አዲስ የወጡ የእንቅስቃሴ ገደቦች አውሮፓ ተቃውሞ እየገጠማቸው ባለበት ወቅት አውሮፓዊቷ ኦስትሪያ አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥላለች። ከት��ንት ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ ኦስትሪያውያን ከቤት እንዲሠሩ የታዘዙ ሲሆን መሠረታዊ አገለግሎት የማይሰጡ የንግድ ተቋማትም ተዘግተዋል። የተለያዩ የአውሮፓ አገራት እንደ አዲስ የእንቅስቃሴ እገዳዎችን የጣሉ ሲሆን ይህም ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ነው። የእንቅስቃሴ ገደቡን በመቀወም በኔዘርላንድስ፣ ቤልጂየም፣ ክሮሺያ እና ዴንማርክ ሰዎች ድምጻቸው አሰምተዋል። በኔዘርላንድስ እና ቤልጂየም ደግሞ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል። በአህጉሪቱ በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። ቅዳሜ ዕለት በአውሮፓ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ሃንስ ክሉጅ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በመላው አውሮፓ እንደ ክትባት መውሰድን እና የፊት እና አፍ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግን የመሰሉ እርምጃዎች በጥብቅ ካልተተገበሩ፤ በሚቀጥለው የፀደይ ወራት በቫይረሱ ምክንያት ግማሽ ሚሊዮን ተጨማሪ ሞት ሊመዘገብ ይችላል። ባለፈው ሳምንት ኦስትሪያ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ሕጋዊ ግዴታ ያደረገች የመጀመሪያዋ አውሮፓ አገር ሆናለች። ሕጉ በየካቲት ወር ተግባራዊ ይሆናል። በአጎራባቿ ጀርመን ያሉ ፖለቲከኞች ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ እየመከሩ ነው ተብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ኦስትሪያ ለአራተኛው ጊዜ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥላለች። የአገሪቱ ባለስልጣናት ምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ፀጉር ቤቶች፣ ቲያትር ቤቶች እና መሠረታዊ አገልግሎት የማይሰጡ የንግድ ተቋማት እንዲዘጉ አዘዋል። የአገሪቱ ጤና ሚንስትር ዎልፍጋንድ ሙቸክስታይን፤ ""ከባድ የሆነውን የእንቅስቃሴ ገደብ መጣል ብቸኛው አማራጭ ነው"" ሲሉ ተናግረዋል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በኦስትሪያ መዲና ቪዬና የእንቅስቃሴ ገደብ ከመተግበሩ በፊት አደባባይ ወጥተው የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። በተለያዩ የአውሮፓ አገራት በሳምንቱ መጨረሻ ኮቪድ-19 ለመከላከል የወጡ እና ጠንከር ያሉ ገደቦችን በመቃወም በርካቶች አደባይ የወጡ ሲሆን አንድ አንድ አገራት ላይ ተቃውሞው ወደ ሁከት ተቀይሮ ታይቷል።" https://www.bbc.com/amharic/59370725 +politics ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የተዘጋጀው ብሔራዊ ቀብር ‘ውድ ነው’ ያለው ጃፓናዊ ራሱን አቃጠለ ለቀድሞው የጃፓን ፕሬዝዳንት የተዘጋጀውን ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመቃወም አንድ ጃፓናዊ ራሱን በእሳት አቃጠለ። ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ በሰው እጅ ለተገደሉት ሺንዞ አቤ ቀብር በመቶዎች የሚቆጠሩ የውጭ አገራት መሪዎች ተጠርተዋል። የጃፓን መንግሥት ያዘጋጀችው ይህ ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት በሚቀጥለው ሳምንት መስከረም 17/2015 ዓ.ም. ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህንን ሥነ ሥርዓት በመቃወም ትላንት ማክሰኞ አንድ ጃፓናዊ ራሱን በእሳት ማቃጠሉ ተዘግቧል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አቅራቢያ ግለሰቡ ራሱን ሲያቃጥል የተመለከቱ የዐይን እማኞች ለፖሊስ ደውለው አሳውቀዋል ። ፖሊሶቹ በቦታው ደርሰው እሳቱን ካጠፉ በኋላ ግለሰቡን ወደ ሆስፒታል ወስደዋል። ግለሰቡ ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ ነፍሱን ያውቅ ነበር ተብሏል። ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰበትና አሁን በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ገና አልታወቀም። ግለሰቡ በ70ዎቹ ዕድሜ ክልል እንደሚገኝ የጃፓን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። መንግሥት ስለ ግለሰቡ ተቃውሞ እስካሁን አስተያየቱን አልሰጠም። ሆኖም የሺንዞ አቤን ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት የሚቃወሙ ጃፓናውያን ቁጥር ባለፉት ወራት እየጨመረ መጥቷል። አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች ለቀብሩ ከፍተኛ ወጪ እየወጣ ነው ብለው ያምናሉ። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ለፓርቲ���ቸው ቅስቀሳ ሲያደርጉ በአንድ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ጥይት በ67 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል። ግለሰቡ ራሱን ከማቃጠሉ አስቀድሞ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አካባቢ ቀብሩን ሲቃወም እንደነበረ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ይገኛሉ። ፖሊስ ግን ገና አላረጋገጠም። ግለሰቡ ራሱን ያቃጠለበት አካባቢ ቀብሩን የሚቃወም መልዕክት ያዘሉ ወረቀቶች እደተገኙም ተዘግቧል። ጃፓንን ለረዥም ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ሺንዞ አቤ ግድያ ጃፓንን ሲያስደነግጥ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አውግዞታል። ጃፓን ውስጥ እንዲህ ያለ በአደባባይ ላይ የሚከሰት ፖለቲካዊ ቀውስ ወይም የተኩስ ጥቃት የተለመደ አይደለም። በበተጨማሪም በአገሪቱ ውስጥ ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓትም አልተለመደም። የሺንዞ አቤን ብሔራዊ ቀብር እየተቃወሙ የሚገኙ ጃፓናውያን፣ ወደ 11.4 ሚሊዮን ዶላር የሕዝብ ገንዘብ የሚጠይቀውን ሥነ ሥርዓት ኮንነዋል። ኮንስቲትዩሽናል ዴሞክራቲክ ፓርቲ የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ በቀጣዩ ሳምንት በሚካሄደው ብሔራዊ ቀብር እንደማይሳተፍ አስታውቋል። ሺንዞ አቤን ተኩሶ የገደላቸው ግለሰብ እንዳለው፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ዩኒፊኬሽን ከሚባል እምነት ጋር ትስስር ስላላቸው ነው የገደላቸው። ይህ እምነት የቤተሰቦቹን ሃብት አሟጦ እንደወሰደም ተናግሯል። የጃፓን የሕዝብ ተወካዮች ከዚህ እምነት ጋር ትስስር አላቸው በሚል ሌሎችም ጃፓናውያን ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cl432pp7py8o +sports ሴኔጋላዊው የፒኤስጂ ተጫዋች ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ድጋፍ አልሰጠም መባሉ አነጋጋሪ ሆነ የፒኤስጂው ኢድሪሳ ጋና ጌዬ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪን ድጋፍ ለመግለጽ የቀረበውን መለያ ለመልበስ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል መባሉ አነጋጋሪ ሆነ። ሴኔጋላዊው የፓሪስ ሴንት ዠርሜይን አማካይ ኢድሪሳ ጌዬ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪን ድጋፍ ለመግለጽ የቀረበውን መለያ አለብስም ብሏል ሲል አንድ ጋዜጣ ዘግቧል። የፈረንሳይ ሊግ፤ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን ለሚያደርጉት እንቅስቃሴን ድጋፉን ለመግለጽ ተጫዋቾች መለያቸው ላይ የሚሰፍረውን ቁጥር በቀስተ ደመና ቀለም እንዲሆን አድርጓል። ባሳለፍነው ሳምንት በነበሩት የሊግ ፍልሚያዎች ተጫዋቾች ይህን መለያ ለብሰው ሜዳ ገብተዋል። አማካዩ ኢድሪሰ ጌዬ ግን ይህን መለያ ለብሶ ወደ ሜዳ ለመግባት ፍቃደኛ ሳይሆን መቅረቱ በስፋት ተዘግቧል። የፒኤስጂው አሰልጣኝ ሞሪሲዮ ፖቸቲኖ አማካዩ ሳይሰለፍ የቀረው “በግላዊ ምክንያቶች” ነው ከማለት ውጪ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። አጥባቂ የእልምና እምነት ተከታይ የሆነው ኢድሪሳ ይህን መለያ ለብሼ ወደ ሜዳ አልገባም ብሏል የሚሉ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ድጋፍ እና ነቀፌታ እያስተናገደ ይገኛል። ለኢድሪሳ ድጋፋቸውን ከሰጡት መካከል የሴኔጋሉ ፕሬዝደንት ማኪ ሳል ይገኙበታል። ፕሬዝደንቱ የኢድሪሳ “ኃይማኖታዊ መርሆች መከበር አለባቸው” ብለዋል። በተቃራኒው በቅርቡ በተካሄደው የፈረንሳይ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እጩ የነበሩት ቫለሪ ፔክሬስ ተጫዋቹ ላይ እገዳ መጣል አለበት ብለዋል። ፕሬዝደንታዊ እጩዋ “የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪን ጥላቻ ለመግታት ለሚደረገው ጥረት ኢድሪሳ ጋና ፍቃደኛ አለመሆን ያለ ቅጣት መታለፍ የለበትም” ሲሉ ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል። ሃይማኖተኛ ሕዝብ ባላት ሴኔጋል የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በብዙዎች ዘንድ ጸያፍ ድርጊት ተደርጎ ይቆጠራል። በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በአምስት ዓመት እስር እና በ2500 ዶላር ያስቀጣል። በዚህ ምክንያት በአገሪቱ የሚገኙ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን ማንነታቸውን በመደ���ቅ ለመኖር ይገደዳሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-61492225 +health በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ ሰዎች መጨመሩን ተከትሎ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መመሪያዋን አሻሻለች "በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ፣ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዝ የተሻሻለ መመሪያ መውጣቱ ተገልጿል። በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ከስድስት አመት በላይ የሆኑ ህፃናት ማስክ እንዲያደርጉ፣ በሰርግ፣ በቀብር እንዲሁም በስብሰባዎች ላይ የሚገኙ ሰዎች ብዛት ከአምሳ እንዳይበልጥ፣ በካፌዎችና በሬስቶራንቶች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዳይቀመጡ የሚሉና ሌሎች ዝርዝሮች ተካትተውበታል። የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያወጡት ይህ መመሪያ ከነሐሴ 13 ፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ማንኛውም ሰው ማስክ ሳያደርግ እንዳይንቀሳቀስ የሚያግድ ሲሆን ይህም ከስድስት አመት በላይ የሆኑ ህፃናትን እንደሚጨምር የጤና ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አስገዳጅ የማይሆነው ከስድስት አመት በታች ለሆኑ ህፃናት እንዲሁም በማስረጃ የተረጋገጠ የመተንፈሻ አካላት ወይም መሰል ችግር ካለባቸው በስተቀር ሁሉም ዜጎች ሲንቀሳቀሱ ማስክ ማድረግ አለባቸው። የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎች በክፍት ገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች ከመደረግ በተጨማሪ ሁለት የአዋቂ እርምጃ (አካላዊ ርቀት) መጠበቅ አስገዳጅ ነው ተብሏል። በማንኛውም መንግስታዊ እና የግል ተቋም አገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ላይ ሰራተኞችና ደንበኞች ከሁለት የአዋቂ እርምጃ ወይም አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲገለገሉና ማስክ እንዲያደርጉ ያስገድዳል። በእነዚህ የአገልግሎት ስፍራዎች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዲቀመጡ ማድረግም ተከልክሏል። ማንኛውም የመንግሥታዊ እና የግል ተቋማት በመግቢያና መውጫ በሮች የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን ማቅረብና አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው ብሏል። በአስከሬን ማስተካከል፣ ግነዛና ማጓጓዝ ወቅትም ሊደረጉ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎችም መመሪያው አስቀምጧል። ከቀብር በኋላ ሀዘን ለማስተዛዘን በድንኳን፣ በቤት ውስጥ ወይም ለዚሁ በተዘጋጀው ቦታ ላይ ለቅሶ የሚደርሰው ሰው ከ50 እንዳይበልጥ ያዛል። አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አለባቸው ይላል። በስብሰባም ወቅት በተመሳሳይ የኮቪድ-19 ጥንቃቄዎችን በተከተለ መልኩ እስከ 50 ሰው መሰብሰብ ይቻላል። ከ50 ሰዎች በላይ መሰብሰብ ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ስብሰባው ሊደረግበት የታሰበበት ስፍራ ጠቅላላ ስፋት ከግምት ውስጥ ሊገባ እንደሚገባ ጠቁሞ በዚህም መሰረት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛ በማይበልጥ መሆን አለበት። እንዲሁም ልዩ ፈቃድ ከሰላም ሚኒስቴር እንዲሁም ከክልሉ፣ ዞን እና ወረዳ የሰላም እና ፀጥታ መዋቅሮች መገኘት አለበት። ስብሰባውንም የጠራው አካል የመከላከያ ዘዴዎቹ መተግበራቸውን ማረጋገጥ ይገባዋል ይላል። የሃይማኖት ስነ ስርዓትን በተመለከተ ሃይማኖታዊ አገልግልቶች አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ ሊፈፀሙ እንደሚገባ መመሪያው አስቀምጧል። የሃይማኖት ስርዓት የሚከናወንባቸው ስፍራዎችም እንዲሁ መያዝ ከሚችሉት አንድ አራተኛ በማይበልጥ ስርዓቱን እንዲያካሂዱ ተቀምጧል። በእነዚህ ��እምነት ተቋማት ቅጥር ግቢ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ ነው። የቤት ውስጥ ማህበራዊ ዝግጅቶችን በተመለከተም ለልደት፣ ምረቃ፣ ማህበር እና ቀብር እና ከቀብር መልስ ያሉ ስነ ስርዓቶች ውጭ እና መሰል በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ማህበራዊ በዓላት ከቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጭ ተጠራርቶ ማክበር የተከለከለም ነው። ሰርግን በተመለከተም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እና ተገቢውን የኮቪድ-19 መከላከያ የንፅህና እርምጃዎች በተገበረ መልኩ ከ50 በማይበልጡ ሰዎች ማካሄድ እንደሚቻል ተቀምጧል። የአደባባይ በዓላትን አከባበር ጋር ተያይዞ ህዝብን በብዛት የሚያሳትፉ የአደባባይ ላይ በዓላት የወረርሽኙ ስርጭት እስኪረጋጋ ድረስ ባይደረጉ በማለትም ምክረ-ኃሳብ አስቀምጧል። በዓላቱ የሚደረጉ ከሆነ ግን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መደረጉን እንዲሁም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ብሏል። ስፍራዎቹም ከሚይዙት ቦታ ከአንድ አራተኛ ቦታ በማይበልጥ ሰው ስርዓቱ ሊካሄድ እንደሚገባም ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብሏል። ስፖርታዊ ውድድሮችም በተመለከተ በተመሳሳይ ስፍራው ከሚይዘው የታዳሚ ብዛት ከአንድ አራተኛ በማይበልጥ እንዲሆን ተቀምጧል። አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ካፌዎች፣ ባር፣ ሬስቶራንቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ የመዝናኛ እና መጫዎቻ አገልግሎቶች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ሰው በላይ ማስተናገድ አይችሉም። በእያንዳንዱ ጠረጴዛ የሁለት ሜትር ርቀት መጠበቅ አለበት። አገልግሎትን የሚሰጡም ሆነ ደንበኞች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ከዚህም በተጨማሪ የወረርሽኙ ስርጭት ያለበት ሁኔታ በየጊዜው እየታየ በሌላ መመሪያ እስኪወሰን ድረስ የአረጋዊያን መጦሪያዎች ስፍራዎች እና የማገገሚያ ማዕከላት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በአካል መጠየቅ የተከለከለ መሆኑን አስፍሮ ነገር ግን እርዳታ ማቅረብ የሚፈልጉ ከተቋሙ አስተዳደር ድረስ በመቅረብ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉም ጠቁሟል። በማረሚያ ቤቶች ላይ ታራሚን ለመጠየቅ አካላዊ ርቀትን ጨምሮ ሌሎች አስገዳጅ የኮቪድ- 19 መከላከያን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ተብሏል። በቤት ውስጥ ማቆያ እና እንክብካቤን በተመለከተ ቀለል ባለ በኮቪድ-19 የተያዘ ታማሚ በቤት ውስጥ የኮቪድ-19 ህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ይደረጋል። ህመምተኞቹ ከሌላው የቤተሰብ አባላት ራሳቸውን መለየት፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ ቢያንስ ለ10 ተከታታይ ቀናት መለየትና ከቤት አለመውጣት ይጠበቅባቸዋል። ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ቫይረሱ እንዳለበት እያወቀ ወደ ሃገር ውስጥ መግባት፣ ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀል ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር መገናኘት የተከለከለ ነው። ከትራንዚት መንገደኛ በስተቀር በአገሪቱ አለም አቀፍ ማረፊያ በኩል የሚገባ ከአስር አመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ተጓዥ ከ120 ሰዓት ወይም አምስት ቀን በላይ ያልሆነው የተረጋጋጠ ምርመራ ኔጌቲቭ ውጤት ይዞ መምጣትና ለሰባት ቀናት መንገደኞች ራሳቸውን ለይተው ማቆየት አለባቸው። ነገር ሰባት ቀናት ራሳቸውን ለመለየት የማይገደዱት በ90 ቀናት ውስጥ ኮቪድ-19 ታመው ያገገሙ፣ ዲፕሎማቶች፣ የኮቪድ-19 ክትባትን በተሟላ ሁኔታ ወስደው ያጠናቀቁ ከሆነ ለተለያዩ ስብሰባዎች የሚመጡ ቱሪስቶች ወይም ለድንገተኛ ጉዳይ የሚመጡ መንገደኞች ናቸው። ለተለያዩ ጉባዔ የሚመጡ ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግና ውጤታቸው ኔጌቲቭ መሆን አለበት። ማንኛውም ፖዘቲቭ ሰው ወደ ሃገር ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው።. በአገሪቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል የሚያልፉ የትራንዚት መንገደኞችን በተመለከተም በረራቸው እስኪደርስ ድረስ አየር መንገዱን ለቆ መሄድ ወይም አየር መንገዱ ከለያቸው ሆቴሎች ውጪ ወደ ከተማ መግባት አይችሉም። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሳምንታት በፊት ሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እየጀመረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ እንደሆነ አስታውቋል። በተለያዩ የዓለም ሀገራት መረጃዎች እና ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሦስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱ ታውቋል። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው የኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ሲሆን በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 የዴልታ ቫይረስ መኖሩ ባይረጋገጥም የሶስተኛ ዙር ወረርሽኝ መከሰቱን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየት መጀመራቸውም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ሁለተኛው ዙር ካበቃ በኋላ በተወሰነ መልኩ በማህበረሰቡ መዘናጋቶች እንዲሁም የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በአግባቡ ባለመተግበራቸው ሶስተኛው ዙር ሊከሰት የሚችልበት ምልክቶች እየታዩ ነው። ተቋሙ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎቹ እንዲከበሩና ማስክ ማድረግ፣የእጅን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ እና ርቀትን በመጠበቅ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የኮቪድ-19 መከላከከልና መቆጣጠር እንደሚቻልም አሳሳስቧል። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተርር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ""ከፊታችን የተጋረጠብንን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እንዲያልፍ፣ የጥንቃቄ መንገዶችን፣ ክልከላዎችና ግዴታዎች እያንዳንዱ ዜጋ፣ ተቋም፣ አመራር፣ የህግ አስከባሪ አካላት በከፍተኛ የሃላፊነት መንፈስ በመተግበርና በማስፈፀም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ"" ማለታቸውም በመግለጫው ላይ ሰፍሯል። በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ 295 ሺህ 19 ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 268 ሺህ 252 ግለሰቦች ከኮቪድ-19 ቫይረስ አገግመዋል እንዲሁም 4ሺህ 553 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። አጠቃላይ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁጥርም 2,335 ሺህ 71 ሲሆን አገሪቷ በአጠቃላይ 3,134 ሺህ 967 ምርመራዎችን አካሂዳለች።" https://www.bbc.com/amharic/58297000 +sports ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከወራት በፊት ለፈጸመው ጥቃት የሁለት ጨዋታ ቅጣት ተጣለበት የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች የነበረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከአንድ የኤቨርተን ደጋፊ እጅ ላይ ሞባይል ስልክ መትቶ በማስጣሉ ከሁለት የአገር ውስጥ ጨዋታዎች እገዳ ተጥሎበታል። የ37 ዓመቱ ሮናልዶ ይህንን ድርጊት የፈጸመው ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ላይ በጉዲሰን ፓርክ ስታዲየም ሽንፈት ከገጠማቸው በኋላ በስታዲየሙ መተላላፊ በኩል ሲወርድ መሆኑ ተገልጿል። ከቡድኑ ማንችስተር ዩናይትድ እና ከአሰልጣኑ ኤሪክ ቴን ሃግ ጋር በተፈጠረው የግንኙነት መሻከር ምክንያት፣ ባለፈው ማክሰኞ ሮናልዶ እና ቡድኑ በጋራ በደረሱት ስምምነት ተጫዋቹ ተሰናብቷል። ሮናልዶ ከወራት በፊት በአንድ ተመልካች ላይ ፈጽሞታል ከተባለው ጥቃት ጋር ተያይዞ ከሁለት ጨዋታ ከመታገዱ በተጨማሪም፣ የእግር ኳስ ማኅበሩ የ50,000 ፓወንድ ቅጣትም ጥሎበታል። ይህ የጨዋታ ዕገዳ ግን ዛሬ ከአፍሪካዋ ተወካይ ጋር በዓለም ዋንጫ የመጀመሪያዋን ግጥሚያ ለምታደርገው ለአገሩ ፖርቱጋል ከመሰለፍ አያግደውም ተብሏል። በኳታሩ የዓለም ዋንጫ በምድብ 'ሸ' ከጋና፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከኡራጓይ ጋር የተደለደለችውን የፖርቱጋልን ብሔራዊ ቡድን በአምበልነት የሚመራው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትልቅ ኃላፊነት ይጠብቀዋል። ከማንችስተር ዩናይትድ ከተሰናበተ በኋላ በአሁኑ ወቅት የሚጫወትበት ቡድን የሌለው ሮናልዶ፣ የተጣለበት የክለብ ጨዋታ ዕገዳ በአንግሊዝም ሆነ በሌላ አገር በቀጣይ በሚቀላቀው ቡድን ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል። ነገር ግን ይህ ቅጣት ቡድኑ በሚያደ��ገው የአገር ውስጥ የሊግ ጨዋታ ላይ እንጂ ሻምፒዮን ሊግን በመሳሰሉ አህጉራዊ የክለቡ ተሳትፎዎች ላይ ተፈጻሚ አይደረግም ተብሏል። ሮናልዶን ለሁለት ጨዋታ ዕገዳ የዳረገውን ድርጊት በተመለከተ በእንግሊዝ የእግር ኳስ ማኅበር በኩል ገለልተኛ ማጣራት ከተካሄደ በኋላ ነው ተገቢ ያልሆነ እና ጎጂ ጥፋት ፈጽሟል ተብሎ ጥፋተኛ የተባለው። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ሮናልዶ ከፖሊስ ማስጠንቀቂያ የደረሰው ሲሆን፣ ጥቃት አድርሶበታል የተባለው ወጣት የእግር ኳስ ተመልካችን ከክስተቱ በኋላ ይቅርታ መጠየቁም ተነግሯል። የእንግሊዝ እግር ኳስ ማኅበር ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተገቢ ያልሆነ ባህሪይ ማሳየቱን እንዳመነ፣ ነገር ግን ጎጂ ፀባይ የተባለውን እንዳልተቀበለው ገልጸወል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ቀድሞ ክለቡ ማንችስተር ዩናይትድ ከተመለሰ በኋላ የነበረው ቆይታውን እንዲያበቃ ያደረገው አወዛጋቢ ቃለ ምልልስ ከሰጠ በኋላ ነበር። በቃለ ምልልሱ ሮናልዶ ቡድኑን ክፉኛ ያብጠለጠለ ሲሆን፣ ለአሰልጣኙ ኤሪክ ቴን ሃግም “አክብሮት እንደሌለው” ከገለጸ በኋላ መነጋገሪያ ሆኖ ትችትና ድጋፍ ከተለያዩ ወገኖች ደርሶታል። ይህ ሁኔታ የፈጠረው መቃቃርም ተጫዋቹ በቡድኑ ውስጥ የመቀጠሉን ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ አስገብቶ ከቆየ ከሳምንት በኋላ በስምምነት ከኦልትራፎርድ ተሰናብቷል። ነገር ግን ሮናልዶ በቀጣይ ወደ የትኛው አገር እና ቡድን ሊያመራ እንደሚችል አስካሁን የታወቀ ነገር የለም። https://www.bbc.com/amharic/articles/c5180mk7p53o +sports አርሰናል፣ ዩናይትድ፣ ሊቨርፑል. . .ከዓለም ዋንጫ በፊት የመጨረሻውን ጨዋታ እነማን ያሸነፋሉ? የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለሳምንታት ከዓይን ሊርቅ የአንድ ሳምንት ዕድሜ ይቀረዋል። ሊጉ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ምክንያት ይቋረጣል። የአስራ ስድስተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜና እሑድ ይከናወናሉ። የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታን ክሪስ ሱቶን የሊጉን አስር ጨዋታ ግምት አስቀምጧል። ተጫዋቾች ድካም ላይ በመሆናቸው ከዓለም ዋንጫው በፊት አሰልጣኞች ከአቋም ጋር በተያያዘ እረፍት ለመስጠት ትልቅ ውሳኔ የሚሰጡበት ሳምንት ነው። ፔፕ ጋርዲዮላ ኃላፊነቱ ለክለቡ ስለሆነ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሲቲ ነው። ሲቲ ባለፈው ሳምንት በ10 ተጫዋቾች ከብዙ ልፋት በኋላ ከፍጹም ቅጣት ምት በተገኘች ጎል ቢያሸንፍም በዚህ ሳምንት ነገሮች ይቀሉታል። ብሬንትፎርዶች ከሜዳቸው ውጭ ጥሩ አይደሉም። ዘንድሮ ከሜዳቸው ውጭ ማሸነፍም አልቻሉም። ግምት፡ 4 - 0 ሁለቱ ቡድኖች በሳምንቱ አጋማሽ በካራባኦ ዋንጫ ሲገናኙ ተጨዋቾቻቸውን ቀይረዋል። በርንዝማውዝ ማሸነፉን ተከትሎም አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ላይ ጫናዎች በርትተዋል። ይህ ጨዋታ ከሳምንቱ አጋማሽ እንደሚለይ እሙን ነው። ኤቨርተን የፊት መስመሩ ክፍተት አለበት በርንማውዝ ደግሞ በሁለት ጎል ከመምራት ነጥብ መጣል ቀጥለዋል። ግምት፡ 1- 1 ናታን ጆንስ ሳውዝሃምፕተንን ይዘው ወደ አንፊልድ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀናሉ። ዘንድሮ ለሊቨርፑል የምሰጠው ግምት በብዛት ባይሳካም ከቶተንሃም ጋር የነበራቸውን ጨዋታ በትክክል ገምቼ ነበር። በአቋም መዋዠቅ ምክንያት ቀዮቹ ስለማሸነፋቸው እርግጠኛ አይደለሁም። ክሎፕ ከዓለም ዋንጫው በፊት ድል ለማስመዝገብ እንደሚትሩ እገምታለሁ። ግምት፡ 3- 0 ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ክሪስታል ፓላስ ማንም የሰንጠረዡ ግርጌ ላይ በመሆን ወደ ዓለም ዋንጫው እረፈት ማቅናት ስለማይፈልግ ፎረስት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደርጋል። ፎረስት ባለፈው ሳምንት ከብሬንትፎርድ ጋር በነበረው ጨዋታ የመጀመሪያ አጋማሽ ጥሩ ነበር። በኋላ ግን ተፍረከረኩ። በጨዋታው አንድ ነጥብ ከማግኘት ባለፈ በሳምንቱ አጋማሽ በተካሄድ የካራባኦ ዋንጫ ጨዋታ ቶተንሃምን አሸንፈዋል። ፓላስ ደግሞ ጥሩ ከመጫወት ባለፈ የፊት መስመሩ ድንቅ ነው። ብዙ ጨዋታን መግደል የሚችሉ ተጫዋቾች አሏቸው። ግምት፡ 1- 2 የስፐርሱ አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴ ተጫዋቾቻቸው መዳከማቸውን ገልጸዋል። የሊድሱ ጄሴ ማርሽ ደግሞ ከሊቨርፑል ድል በኋላ ከበርንማውዝም ሦስት ነጥብ ነጥቀዋል። የቶተንሃምን ተከላካይ መስመር ማመን ቢከብድም ለመጥፎው የሳምንቱ አጋማሽ ሽንፈት ምላሽ ይሰጣሉ። ይህ ሁለቱም ቡድኖች ሊያሸንፉት የሚችሉት ዓይነት ጨዋታ ቢሆንም ግምት የምሰጠው ለቶተንሃም ነው። ግምት፡ 3 - 1 ሌስተር እያንሰራራ ሲሆን በዚህ ወቅት ውድድሩ እንዲቋረጥም አይፈልገም። የቡድኑ ተከላካይ መስመር ድንቅ ሲሆን ሃርቪ ባርነስ እና ጀምስ ማዲሰንም በጥሩ ብቃት ላይ ናቸው። ይህ ፉክክር ያለበት ጨዋታ ሲሆን ዌስት ሃም ወደ ብቃቱ ጥግ ባይደርስም የሚሸነፍ አይመስለኝም። ግምት፡ 1- 1 ቼልሲዎች ባለፈው ሳምንት ከአርሰናል ጋር ጥሩ አልነበሩም። አርሰናሎች የራሳቸው አጨዋወት ሲኖራቸው ሰማያዊዎቹ ግን ወደ ፊት ሲሄዱ ምን መሥራት እንዳሰቡ የሚያውቁ አይመስልም ነበር። ኒውካስሎች የትኛውም ውጤት ቢመዘገብ እስከ አራት ባለው ደረጃ ውስጥ የሚቆዩ ሲሆን በደረጃቸውም ሆነ በአጨዋወታቸው ደስተኞች ናቸው። ብዙ ጎሎች የሚቆጠሩበት ጨዋታ ባይሆንም ኒውካስሎች የሚያሽነፉ ይመስለኛል። ግምት፡ 1  0 ዎልቭሶች በዚህ ጨዋታ በስቲቭ ዴቪስ ቢመሩም አዲስ አሰልጣኝ በመሾማቸው ለአርሰናል ከባድ ይሆናል። የአርሰናል ደጋፊዎች ትኩረታቸው ሊጉ ላይ በመሆኑ በሳምንቱ አጋማሽ ከካራባኦ ዋንጫ መውጣታቸው አያሳስባቸውም። ቡድኑ ቼልሲን ሲያሸንፍ በራስ መተማመን የነበረው ሲሆን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታም ለዋንጫ እንደሚፎካከሩ ጠቁመዋል። ካላቸው የአጥቂ እና የተከላካይ መስመር ጥንካሬ አንጻር ጨዋታውን ያሸንፋሉ። ግምት፡ 0 - 2 ብራይትን ከ አስቶን ቪላ አዲስ አሰልጣኝ በመሾም ባለፈው ሳምንት ማንቸስተር ዩናይትድን ያሸነፉት ቪላዎች ድላቸውን ማስቀጥ ይፈልጋሉ። ከተከታታይ ድል በኋላ ብራይተኖች ጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። አሁን ባላቸው አቋም እስከ ስድስት ባለው ደረጃ ቢያጠናቅቁ ይገባቸዋል። ግምት፡ 2 - 1 አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ በመጀመሪያዎቹ ወራት የዩናይትድ ቆይታቸው ደስተኛ ቢሆኑም ችግሮችን በሙሉ እንዳልፈቱ ባለፈው ሳምንት ተመልክተናል። ቡድኑም የዓለም ዋንጫውን እረፈት በመጠቀም መደራጀት ያለበት ይመስለኛል። አሰልጣኙ ሃሪ ማጓየርን አጥቂ በማድረግ እና ሮናልዶን አምበል በማድረግ ግራ አጋቢ ውሳኔ አሳልፈዋል። ከሜዳ ውጭ ሦስት ጊዜ የተሸነፈው ቡድናቸው ተመሳሳይ ዕጣ ይጠብቀዋል። ፉልሃም ባለፈው ሳምንት በ10 ተጫዋች ካሸነፋቸው ሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ መጥፎ ባይሆኑም የማሸነፍ መተማመን አልነበራቸውም። በሜዳቸው ድንቅ ድል በማስመዝገብ ወደ ዓለም ዋንጫው ይጓዛሉ ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 2 - 1 https://www.bbc.com/amharic/articles/c2595g1ew0ro +sports ቻይና ከክረምት ኦሊምፒክ እራሳቸውን የሚያገሉ አገራት 'የእጃቸውን ያገኛሉ' ስትል አስጠነቀቀች "ቻይና ከምታስተናግደው የቤይጂንግ የክረምት የኦሊምፒክ ጨዋታዎች እራሳቸውን የሚያገሉ አገራት ""ለሚፈጽሙት ስህተት ዋጋ ይከፍሏታል"" ስትል አስጠንቅቃለች። ቻይና ሰብአዊ መብት እየጣሰች ነው በማለት አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ አውስትራሊያና ካናዳ የመንግሥት ተወካዮቻቸውን እንደማይልኩ ይፋ አድርገዋል። ቻይና ዊጋ ሙስሊሞች ላይ ሰብአዊ ጥሰት ትፈፅማለች የሚል ወቀሳ ይሰነዝርባታል። ቀጣዩን የክረምት ኦሊምፒክ የምታዘጋጀው ፈረንሳይ ግን ከአጋሮቿ በተለየ እስካሁን ተወካዮቿን እንደማትልክ አላሳወቀ���ም። የዘንድሮው የክረምት ኦሊምፒክ በሚቀጥለው የካቲት ቤይጂንግ ላይ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለታል። ""አሜሪካ፣ ብሪታኒያ እና አውስትራሊያ የኦሊምፒክ ጨዋታውን እንደ ፖለቲካ መድረክ ተጠቅመውበታል"" ሲሉ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ተናግረዋል። የቻይና ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ረቡዕ ዕለት ቤይጂንግ ""ወትሮውንም ቢሆን 'በአንሳተፍም ፖለቲካ' የናወዙ የአሜሪካና የምዕራቡ ዓለም ፖለቲከኞችን የመጋበዝ ዕቅድ የላትም"" ብሏል። በዲፕሎማሲ ምክንያት አልሳተፍም ስትል መጀመሪያ ድምጿን ያሰማችው አሜሪካ ስትሆን፤ አውስትራሊያ፣ ካናዳና ዩናይትድ ኪንግደም ተከታትለው ተመሳሳይ ሐሳባቸውን አሰምተዋል። ይህ የአገራቱ አቋም ግን አትሌቶችን በጨዋታው ከመሳተፍ አያግዳቸውም። ይህን እርምጃ ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የሚደገፍ ብሎታል። ""የመንግሥት ተወካዮችን መላክ የፖለቲካ ውሳኔ ነው። ኮሚቴው በዚህ ውሳኔ እጁን አያስገባም"" ብለዋል የኮሚቴው ፕሬዝደንት ቶማስ ባህ። ከክረምት ጨዋታዎች እራሳቸውን የሚያገሉ አገራትና በቻይና መካከል ያለው ግንኙነት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየሻከረ መጥቷል። አሜሪካ፤ ቻይና በዢያንዢያንግ ግዛት ያሉ የዊጋና ሌሎች አናሳ ሙስሊም ማኅበረሰቦች ላይ የዘር ማጥፋት ፈጽማለት ስትል ትከሳለች። ቻይና የሚቀርቡባትን ሁሉንም የሰብአዊ መብት ጥሰት ክሶች የምታጣጥል ሲሆን፤ በዢያንዢያንግ ግዛት ያሉት የማቆያ ካምፖች የዊጋ ሙስሊሞችንና ሌሎችን ""መልሶ ለማስተማር"" የሚውሉ ናቸው ትላለች። ሌላው ቻይና የምትወቀስበት ጉዳይ በሆንግ ኮንግ ባለው ሁኔታና በቅርቡ የቻይና ባለሥልጣንን በወሲባዊ ጥቃት ምክንያት ከተናገረች በኋላ ለሳምንታት ሳትታይ በቆየችው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቿ ፔንግ ሹዋይ ነው። የሴቶች ቴኒስ ማኅበር ባለፈው ሳምንት ቻይና የሚደረጉ ሁሉም የቴኒስ ውድድሮች የፔንግ ሁኔታ እስኪታወቅ ድረስ እንዲቋረጡ አዟል። ቻይና ከካናዳ ጋር ያላት ግንኙነት የቆረቆዘው የቻይናው ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሁዋዌ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በመታሠሩ ምክንያትና በምትኩ ቻይና ሁሉት ካናዳዊያንን በማገቷ ምክንያት ነው። ሦስቱም ግለሰቦች በያዝነው ዓመት መባቻ ተለቀዋል። ሌላኛው የመንግሥት ተወካዮቼን አልክም ያለችው አገር ኒው ዚላንድ ስትሆን፤ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ቢያሳስባትም ተወካዮቿን ከመላክ የተቆጠበችው በኮቪድ ምክንያት ነው። እንደ ጃፓን ያሉ ጎረቤት አገራትም ከጨዋታዎቹ እራሳቸውን ያርቃሉ የሚል ግምት አለ። ጣልያን እሳተፋለሁ ስትል ፑቲን የቻይናን ግብዣ ተቀብለው በሥፍራው እንደሚገኙ አሳውቀዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59599811 +sports በናይጄሪያውያን ልብ ዘንድ የነገሰው የቦክስ ሻምፒዮኑ አንቶኒ ጆሹዋ "ቅዳሜ ምሽት እንግሊዛዊው አንቶኒ ጆሹዋ ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የቦክስ ግጥሚያውን ከቡልጋሪያው ኩብራት ፑሌቭ ጋር ያደርጋል። በርካታ ነገሮችን ከስረ መሰረቱ በቀየረው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ይህንን ፍልሚያ በቅርብ ሆነው ማየት የሚችሉት አንድ ሺህ ሰዎች ብቻ ናቸው። ፍልሚያው ዝም ብሎ አይደለም አንቶኒ የሶስት ጊዜ ከባድ ሚዛን ሻምፒዮንነቱን የሚያስጠበቅበትም ነው። ኤስኤስኤ በተባለው ትልቅ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን ሚሊዮኖች አድናቂዎቹም በቴሌቪዥን፣ ሬድዮ ይከታተሉታልም ተብሎ ይጠበቃል። በተለይም በናይጄሪያ የሚኖረው ድጋፍ ይህ ነው የሚባል አይሆንም። የ31 አመቱ ቦክሰና ለእንግሊዝ በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ቢያስገኝላትም በናይጄሪያ ያለው የጀግነነት ቦታ ለየት ያለ ነው። በተለይም የቤተሰቡ የትውልድ ስፍራ ነው በሚባለው የደቡብ ምዕራብ ግዛት ሳጋሙ ከአምልኮት ባልተናነሰ መልኩ ነው የሚታየው። ጅማሮው የአንቶኒ ወላጆች ብቻ ሳይሆን ቅድመ አያቶቹም በሳጋሙ ስመ ጥር ናቸው። ቅድመ አያቱ ዳንኤል አደባነምቦ ጆሹዋ የመሬት ከበርቴና ኃብታም ነጋዴ ነበሩ። እምነታቸውን ወደ ክርስትና ከቀየሩም በኋላ የመጨረሻ ስማቸውን እንደቀየሩ ይታመናል። ዳንኤል አንደኛውን ልጃቸው አይዛክ ኦላሴኑ ጆሹዋን ለትምህርት ወደ እንግሊዝ ላኩት። እሱም ትምህርቱን ጨርሶ አየርላንዳዊ ሴት አግብቶ ወደ ናይጄሪያ ተመለሰ። ሰባት ልጆችም ወለዱ። የነሱም አንደኛው ልጅ ሮበርት እዛው የሳጋሙ ተወላጅ የሆነችውን የታ ኦዱሳንያን አግብቶ ቦክሰኛውን አንቶኒና እህቱን ጃኔትን ወለዱ። አንቶኒ ትውልዱም ሆነ እድገቱ እንግሊዝ ነው ለአያቱ ትልቅ ክብር ያለው አንቶኒ አጠቃላይ ትውልዱም በግዛቲቷም ሆነ በናይጄሪያ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸው ናቸው። ናይጄሪያ በልቡ ያለችው ቦክሰኛ አንቶኒ ጆሹዋ በናይጄሪያዊ ቤተሰቦቹ ትልቅ ክብርና ኩራት አለው። በቀኝ ጀርባው በኩል የአፍሪካ ካርታ ያለበትና ናይጄሪያ ደምቃ የምትታይበት ንቅሳት አለው። በፍልሚያዎቹም ላይ የናይጄሪያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደርጋል። ወደ ፍልሚያ ሜዳውም ሲገባ በናይጄሪያ ሙዚቃ ታጅቦ ነው። በቅርቡ ከአንዲ ሩይዝ ጁኒየር ጋር በነበረው ግጥሚያም የታዋቂዎቹን በበርና ቦይና ፌሚ ኩቲን ሙዚቃ ታጅቦ ነበር የገባው። ፌሚ ኩቲ የአፍሮ ቢት ፈጣሪው ፌላ ኩቲ ልጅ ነው። ለናይጄሪያ ሙዚቃ ጥልቅ ፍቅር ያለው አንቶኒ በማህበራዊ ሚዲያዎችም ላይ አብሮ እየዘፈነ ያሉ ቪዲዮዎች ማሳያ ናቸው። የናይጄሪያ ምግብ እያበሰለም በርካታ ቪዲዮዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቹ ላይ ለቋል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለተጠቁ ቤተሰቦቹም በርካታ ምግብና ሌሎች ቁሳቁሶችም ወደ ናይጄሪያ ልኳል። በቅርቡም ናይጄሪያውያን የፖሊስ የጭካኔ በትርን በቃን ብለው በመቃወም ሲነሱ አንቶኒም ድጋፉን በማሳየት ከአገሪቷም ሆነ ከህዝቡ ጋር ያለውን ፅኑ ቁርኝት አሳይቷል። የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪም አድናቂው ናቸው። ከፕሬዚዳንቱ ጋር በባለፈው አመት የተገናኙ ሲሆን አንቶኒም የሻምፒዮንነት ቀበቶዎቹን አሳይቷቸዋል። ታዋቂው የናይጄሪያ ቦክሰኛ ሰውነቱ በጡንቻ የተሞላው፣ ስርአት የተላበሰ፣ ቀስ ብሎ መናገር የሚወደው አንቶኒ የብዙዎችን ቀልብ የሚስብ ፈገግታም አለው። በቦክሱ ዘርፍ ዘንድ ያስመዘገበው ድል በአገሪቱ የስፖርት ታሪክ ትልቅ ስም የተከለ አድርጎታል። በአሜሪካው ቅርጫት ኳስ ዘንድ የኤንቢኤ ጨዋታ ታዋቂነትን ካተረፈው ሐኪም ኦላጁዎን ቀጥሎ ናይጄሪያዊ ዝርያ ያለው ትልቁ ስፖርተኛ ነው። ከአንቶኒ በፊትም ቢሆን ናይጄሪያዊ ዝርያ ያላቸው የከባድ ሚዛን ቦክስ ሻምፒዮኖች ቢኖሩም የአንቶኒን ያህል ተወዳጅነት ያገኘ የለም። ሄንሪ አክንዋንዴና ሳሙኤል ፒተር ሁለቱም የከባድ ሚዛን ቦክሽ የሻምፒዮንነት ስፍራ ቢቆናጠጡም ዝናቸውም ሆነ ተወዳጅነታቸው ከአንቶኒ ጋር አይወዳደርም። አንቶኒ በናይጄሪያውያን ልብ ዘንድ ነግሷል። በሳጋሙ የአንቶኒ አድናቂዎች ክለብ ከሶስት አመት በፊትም ተመስርቷል። ""አንቶኒ ሳጋሙን በአለም ላይ አሳውቋታል"" በማለት የአንቶኒ ጆሹዋ ደጋፊዎች ክለብ መስራች አዚዝ አደኩንሌ ኦኩኖረን ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ተናግረዋል። ""መጨረሻ ላይ ከአንዲ ሩይዝ ጋር ያደረገውን ግጥሚያ ህዝቡ ሁሉ እንዲከታተለው ለማድረግ በትልልቅ ስክሪኖችና በፕሮጀክተር አሳይተናል"" ""በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቹም ፍልሚያውን ሊያዩ ወጥተው ነበር። አንዳንዶችም ፍልሚያውን ለመታደም ከአዋሳኝ ግዛቶች ተጉዘዋል"" ይላል አዚዝ ""የመጪውንም ውድድር ታሳያላችሁ ወይ የሚል በ���ካታ ጥያቄዎችም እየጎረፉልን ነው"" በማለትም አዚዝ ያስረዳል። የሚዲያን ቀልብ የተቆጣጠረው ቦክሰኛ በናይጄሪያ የሚገኙት ቴሌቪዥን፣ ድረ-ገፅ፣ ጋዜጣ፣ መፅሄት በአጠቃላይ የትኛውም አይነት ሚዲያ ስለ አንቶኒ አውርተው አይጠግቡም። በወላጆቹ ትውልድ ቦታም ግጥሚያው በበለጠ ድምቀት ይኖረዋል በሚል ነዋሪው ብቻ ሳይሆን ሚዲያዎቹም ወደ አካባቢው አቅንተዋል። ውድድሮቹን በቴሌቪዥን መከታተል ለማይችሉም ማህበራዊ ሚዲያዎችን አማራጭ አድርገዋል፤ ደማቅም ነው፤ በውይይትና አስተያየት የተሞላ ምልከታም ነው። በባለፈው አመት ወደ ሳጋሙ መጥቶ የነበረው አንቶኒ የአካባቢውን ባህላዊ መሪና ኃላፊዎች ቢያገኝም የአድናቂዎቹን ክለብ ግን አላገኛቸውም። ሆኖም ለነ አዚዝ ይኼ ምንም ማለት አይደለም፤ መውደዳቸውም ትንሽም ቢሆን አይቀንስም። ""ምንም ማለት አይደለም። አሁንም ቢሆን ልጃችንና ተወካያችን ነው"" ይላል አዚዝ ""አባቱ፣ አያቱ፣ ቅድመ አያቱና ዘሩ ከዚህ መሆኑን እናውቃለን። እናም መቼም ቢሆን እንደግፈዋለን። አንድ ቀንም እሱም እኛን ተመልክቶ ይደግፈን ይሆናል"" ይላል አዚዝ አክሎም ""ለስኬቱ መፀለያችንን አናቆምም። ግን አሻራውን የሚያስታውስ እንደ ጂም፣መዝናኛ ማዕከል ወይም ሆስፒታል ቢገነባ እንወዳለን። በርካቶች ተመልክተው ሊያስታውሱት የሚችሉት ነገር ቢሆን ጥሩ ነው"" በማለትም ያስረዳል። የወጣቱ አርዓያ አንቶኒ አሻራውን በወጣቶች ላይ እያሳረፈ ይገኛል፤ በተለይም በንግድ መዲናዋ ከተማ ሌጎስ። ወጣት ናይጄሪያውያን አንቶኒ አስደናቂውንና ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ ጉዞውን ያውቁታል። በእንግሊዝ ከበጥባጭነትና ረባሽ ወጣት መንገዱን ፈልጎ ወደ ሙያዊ እንዲሁም የሃብት ስኬት መድረሱ በርካቶችን የሚያነቃቃ ነው። የሱን ፈለግም በመከተል በርካታ የአማተር ቦክስ ሜዳዎች እንደ አሸን እየፈሉ ነው። የመንግሥትና የህዝብ ትምህርት ቤቶችም ከትምህርት በኋላና ቅዳሜና እሁድ የቦክስ ሜዳዎችም ሆነው እያገለገሉ ነው። ምንም እንኳን የተሟላ ቁሳቁስም ሆነ ብቁ አሰልጣኝ ባይኖርም በርካቶች የሱን ፈለግ በመከተል ላይ ናቸው። ሌካን ሙይቢ ወይም በቅፅል ስሙ 'ሞተሩ' በተስፋ ከተሞሉ አማተር ቦክሰኞች አንዱ ነው። የ21 አመቱ የመኪና መካኒክ ቅፅል ስሙንም ያገኘው በጥንካሬው፣ በስራው፣ በሚሰነዝነረው ጡጫም ነው። ከሳጋሙ በ35 ኪሎሜትር ርቀት ሞዌ በምትባል አካባቢ ነዋሪ የሆነው ሌካን አንቶኒን እንደ ጀግናው ነው የሚያየው። ""ወደ ቦከስ ስፖርት ያስገባኝ ማይክ ታይሰን ነው። ነገር ግን ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚቻል ደግሞ ያሳየኝ አንቶኒ ነው ምክንያቱም እሱም እንደ እኔ ናይጄሪያዊ ነው"" በማለትም ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ተናግሯል። የፌስቡክ ገፁንም በማየት የአንቶኒ ምን ያህል አድናቂም እንደሆነና ያለውንም ፅናት መረዳት ይቻላል። የአንቶኒ ጆሹዋ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች እንዲሁም የሌሎች ስፖርተኞች የፌስቡክ ገፁን ሞልተውታል። ሌካንም ቦክስ ሲለማመድ፣ እንዲሁም እዚህ ግባ በማይባሉ የመለማመጃ መሳሪያዎች የሚያደርገው ዬየቀን ትግልም ቪዲዮ ለስፖርቱ ያለውን ፍቅር ያሳያል። የአንቶኒንም ቪዲዮ ለሰዓታት በዩቲዩብ በመከታተተል ችሎታውንም ለማሻሻል ጥረት ያደርጋል። ""ከሱ ብዙ እማራለሁ። ከፍተኛ የሆነ ጉልበት ቢኖረውም ኃይሉን ለመቆጠብ የሚጠቀመው ቴክኒክ አለው"" ይላል። አክሎም "" ጡጫ በሚሰነዝርበት ወቅት በተጠና መልኩ ነው። ተፋላሚውንም በደንብ ባወቀ መልኩም ነው የሚሰነዝረው። ቀድሞም በደንብ ይረዳቸዋል"" ይላል። ""ህልሜ ከሱ ጋር አንድ ቀን መሰልጠን እንዲሁም መፋለም እፈልጋለሁ። ከሱ ብዙ የምማረው አለ"" በማለትም ይናገራል። ሌ��ን ከአንቶኒ ጋር መሰልጠንም ሆነ መፋለም ህልሙ ቢሆንም ለአብዛኛው ናይጄሪያዊ አድናቂዎቹ አንቶኒ ፍልሚያውን ናይጄሪያ ቢያደርግ ትልቅ ነገር ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-55292093 +health ባለሙያዎች በኮቪድ ምክንያት የጠፋን የማሽተት ስሜት ለመመለስ 'የማሽተት ሥልጠና' ውሰዱ አሉ "በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተከትሎ የማሽተት ስሜታቸውን በፍጥነት መመለስ ያልቻሉ ሰዎች የማሽተት ሥልጠና እንዲወስዱ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ ሰጡ። ባለሙያዎቹ የማሽተት ስሜትን ለመመለስ የስትሮይድስ ህክምና ከመከታተል ይልቅ 'የማሽተት ስልጠና' መውሰዱ የተሻለ እንደሆነ ገልጸዋል። ይህ የማሽተት ስልጠና ለወራት የተለያዩ ሽታዎችን በማሽተት አእምሮን እንደገና በማሰልጠን የተለያዩ ሽታዎችን እንዲለይ የማድረግ ሂደት ነው። የዓለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን እንደሚለው የማሽተት ስልጠና ዋጋው ርካሽ እና ሂደቱም ቀላል ነው። ከስቴሮይድስ ሕክምና ጋር ሲነጻጸርም፤ የማሽተት ስልጠናው የጎንዮሽ ጉዳቶች የሉትም። ከትኩሳት እና ከማያቋርጥ ሳል በተጨማሪ የመሽተት እና የጠዓም ስሜት ማጣት ከኮሮናቫይረስ ዋና ዋና ምልክቶች መካከል ተጠቃሾች ናቸው። ማሽተት አለመቻል ብዙውን ጊዜ ሕመሙ ካለፈ በኋላ በፍጥነት ይመለሳል። ሆኖም ከአምስት ሰዎች መካከል አንዱ ከህመሙ ከስምንት ሳምንት በኋላም የማሽተት ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ሪፖርት አድርገዋል። የኢስት አንግሊያ ዩኒቨርሲቲ ኖርዊች የሕክምና ትምህርት ቤት ባልደረባው ፕሮፌሰር ካርል ፊልፖት እንደሚሉት ኮርቲኮስትሮይድስ ማሽተትን የመመለስ አቅሙ በጣም ጥቂት ነው። ""የታወቁ የጎንዮሽ ጉዳቶች ስላሉት ከቫይረሱ በኋላ በሚመጣ የማሽተት ስሜት ማጣትን ለማከም መታዘዝ የለባቸውም ብለን እንመክራለን"" ብለዋል። ""እንደ ዕድል ሆኖ በኮቪድ-19 የተነሳ ሽታ ማጣት የሚገጥማቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች በፍጥነት የማሽተት ስሜታቸውን መልሰው ያገኛሉ"" ብለዋል። ከስቴሮይድ የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል የደም ግፊት እና የስሜት መለዋወጥ ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው። ዓለም አቀፍ የአለርጂ እና ሪህኖሎጂ ኦረም መጽሔት ላይ በወጣው ጽሑፍ መሠረት ተመራማሪዎቹ ""የማሽተት ሥልጠና""ን በአማራጭነት አቅርበዋል። ይህም ተለይተው የሚታወቁ እና በቀላሉ የሚለዩ ሽታ ያላቸውን አራት ነገሮችን ማሽተትን ያካትታል። ለምሳሌ ብርቱካን፣ አዝሙድ፣ ነጭ ሽንኩርት እና ቡናን በቀን ሁለት ጊዜ ማሽተት። ፕሮፌሰር ፊልፖት እንዳሉት ጥናቶች 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ከስድስት ወር በኋላ የማሽተት ስሜታቸውን ሙሉ በሙሉ መልሰው ያገኛሉ። በዚህ ጊዜ ካልተመለሰ ግን አእምሮ ሽታ እንዲለይ እና የተለያዩ ሽታዎችን እንደገና እንዲያውቅ ""የማሸተት ስልጠና"" ይረዳል።" https://www.bbc.com/amharic/56870718 +politics የሱዳን ፖሊስ መንፈንቅለ መንግሥቱን ለመቀወም አደባባይ በወጡት ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኮሰ "የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች በመዲናዋ ካርቱም ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ይቋቋም በሚል የተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ዜጎች ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸው ተሰምቷል። በተቃውሞ ሰልፉ እየተሳተፉ የሚገኙ በርካታ መምህራንም በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሌሊቱን ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ተቃዋሚዎች ለሁለት ቀናት የሚቆየውን ጫና የማሳደር እንቅስቃሴ ለማጠናከር ጎማዎችን በማቃጠል እና ድንጋይ በመጠቀም የተለያዩ መንገዶችን ዘግተዋል። ጥያቄያቸውም በመፈንቅለ መንግሥት ስልጣን የያዘው ወታደራዊ መንግሥት በሰላማዊ መንገድ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም መንገዱን ይክፈት የሚል ነው። የአረብ ሊግ አገራት መሪዎች መፈንቅል መንግሥቱን ካደረጉት ወታደሮች ጋር ድርድር ለማድረግ ወደ መዲናዋ ካርቱም መግባታቸ���ን ተከትሎ ነው ሰልፈኞች በድጋሚ ወደ አደባባይ መውጣት የጀመሩት። ከመጀመሪያው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ በጠቅላይ ሚንስትርነት የተመረጡት አብደላ ሀምዶክ በአሁኑ ሰዓት በቤታቸው የቁም እስረኛ ሆነው የሚገኙ ሲሆን ወታደሮቹም አብረዋቸው እንዲሰሩ ጫና እያሳረፉባቸው ስለመሆኑ ተዘግቧል። ባለፈው ወር የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ጀነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሀን መንግሥት ከሲቪሎች ጋር ስልጣን ለመጋራት ያደረገውን ስምምነት ያፈረሱ ሲሆን በርካታ የሲቪል መሪዎችንም በቁጥጥር ስር አውለዋል። አስከትለውም በአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። ምንም እንኳን በአገሪቱ ባለው የኢንተርኔ መቆራረጥ ምክንያት በርካታ ሰዎች የሁለት ቀን የተቃውሞ ሰልፍ መጠራቱን ያልሰሙ ቢሆንም ጥቂት የማይባሉ መምህራን ግን በትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በር ላይ በመሰባሰብ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ""ጀነራሉ የወሰዱትን እርምጃ ለመቃወም በዝምታ የታጀበ ሰልፍ በሚኒስቴሩ በር ላይ አካሂደናል"" ሲል ሞሀመድ አል አሚን የተባለው መምህር ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ተናግሯል። ""ትንሽ ቆይቶ ግን ፖሊስ መጥቶ አስለቃሽ ጭስ መተኮስ ጀመረ። እኛ ምንም አላደረግንም ነበር። በዝምታ መንገድ ላይ በመቆም የጽሁፍ መልእክቶችን ነበር ያስተላለፍነው። ለምን አስለቃሽ ጭስ እንደተተኮሰብን አላውቅም"" ብሏል። በሰሜናዊ የካርቱም ክፍል የጸጥታ ኃይሎች ዋና ዋና መንገዶችን በጥብቅ እየተቆጣጠሩ ሲሆን አስለቃሽ ጭስ፣ ፈንጂዎችና ዱላዎችን ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ ሮይተርስ ዘግቧል። አብዛኛው የካርቱም ነዋሪ በአሁኑ ሰዓት ቁጣ ላይ መሆኑን ቢቢሲ ተዘዋውሮ ማስተዋል ችሏል። በርካቶችም ወደ መንደራቸው የሚወስዱ መንገዶችን በመዝጋት ተቃውሟቸውን እየገለጹ ነው። ምንም እንኳን ከሁሉም አቅጣጫ የተቃውሞ ድምጾች እየተሰሙ ቢሆንም ወታደራዊው መንግሥት ግን ምንም ስህተት እንዳልሰራ እየገለጸ ነው። ""ይህ መፈንቅለ መንግሥት እንዳልነበረ በጊዜ ብዛት የሚታይ ይሆናል። የሲቪል መንግሥት መስርተን ምርጫም እንዲካሄድ አናደርጋለን"" ብለዋል አድሚራል ፋታህ አል ራህማን።" https://www.bbc.com/amharic/news-59174010 +sports የአፍሪካ ዋንጫ ወደ ሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ተወሰነ "በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የአፍሪካ ዋንጫ እንዲገፋ መወሰኑን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ አስታወቁ። ውድድሩ በሚቀጥለው ዓመት ከሰኔ አስከ ሐምሌ ባለው ጊዜ አይቮሪኮስት ውስጥ እንዲካሄድ መርሃ-ግብር ወጥቶለት የነበረ ቢሆንም፣ ወቅቱ በአገሪቱ ከባድ ዝናብ የሚጥልበት በመሆኑ ነው ለቀጣይ ዓመት የተሸጋገረው። ደቡብ አፍሪካዊው የካፍ ፕሬዝዳንት የአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር እየተካሄደባት ካለችው ሞሮኮ ዋና ከተማ ራባት ባስተላለፉት መልዕክት ""በሚኖረው የአየር ሁኔታ ምክንያት ምንም ማድረግ አንደፍርም” ብለዋል። የዓለም ዋንጫ ከሌላው ጊዜ በተለየ በሚቀጥለው ዓመት ኅዳርና ታኅሣሥ ወር ላይ የሚካሄድ በመሆኑ፣ የአፍሪካ ዋንጫን ወደፊት ከማምጣት ይልቅ ወደ ቀጣይ ዓመት ማሸጋገሩ የግድ ሆኗል። በዚህም ምክንያት የአፍሪካ ዋንጫ በዚህ ዓመት ካሜሩን ውስጥ እንደተካሄደው ሁሉ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ በጥርና የካቲት ይከናወናል። የአውሮፓ ክለቦች በውድድር ላይ ሳሉ ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ተጫዋቾችን እንዲለቁ በመጠየቅ የሚነሳውን ውዝግብ ለማስቀረት ሲባል ካፍ በ2017 (እአአ) የአፍሪካ ዋንጫ በተለመደው ሁኔታ ሲካሄድባቸው ከነበሩት ጥርና የካቲት ወራት ወደ ሰኔ እና ሐምሌ ለማዘዋወር ወስኗል። ""በአውሮፓ ክለቦች ምክንያት ጥር ለውድድሩ አመቺ ወቅት አይደለም��� ነገር ግን ለአሁን ያለን ብቸኛው አመራጭ እሱ ነው” ሲሉ የካፍ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል። በቀድሞው የካፍ ፕሬዝዳንት ኢሳ ሃያቱ የአመራር ዘመን የአህጉሪቱ መለያ የሆነውን የእግር ኳስ ውድድር ማካሄጃ ወቅት ወደ ሌላ ወቅት የማሸጋገሩ ጉዳይ ተቀባይነት ሳያገኝ ቆይቷል። ሃያቱን የተኩት ማዳጋስካራዊው አህመድ አህመድ የአፍሪካ እግር ኳስን ለመምራት ወደ ሥልጣን በመጡ በአራት ወራት ውስጥ ከአባል አገራት ባለሥልጣናት ጋር በመነጋገር ለውጥ አድርገዋል። የካፍ ዋና ፀሐፊ ቬሮን ሞሴንጎ ኦምባ እንዳሉት ምንም እንኳን በአህጉሪቱ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ያለው የአየር ሁኔታ ልዩነት ቢኖረውም ውድድሩን ቀድሞ ወደ ነበረበት ጥርና የካቲት የመመለስ ፍላጎት የለም። ሰኔ እና ነሐሴ የዝናብ ወቅት መሆኑ እየታወቀ የውድድር ጊዜውን ወደ ሌላ ጊዜ የማሸጋገሩ ውሳኔ ለምን ዘገየ የሚለውን ጥያቄ ካፍ “ለአስተናጋጇ አገር አመቺነት” ሲባል መሆኑን ከመግለጽ ባለፈ ከባለሥልጣንት የተሰጠ ማብራሪያ የለም። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና ዋና ፀሐፊ የእግር ኳስ ውድድሩ የሚካሄድበት ወቅት በአንድ ዓመት መገፋቱን ያሳወቁት የአፍሪካ የሴቶች አግር ኳስ ዋንጫ ውድድር እየተካሄደ ከሚገኝበት ከሞሮኮ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cxr6ll129pro +business የሊባኖስ ዋነኛ ኃይል ማመንጫዎች ሥራ በማቆማቸው መብራት ተቋረጠ በሊባኖስ ሁለት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ሥራ በማቆማቸው ሳቢያ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል መብራት ጠፍቷል። ሁለቱ ማመንጫዎች ነዳጅ በመጨረሳቸው ነው አገልግሎት መስጠት ያቆሙት። በሊባኖስ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስላለ ከአገር ውጭ ለሚገኙ የኃይል አቅራቢ ድርጅቶች ገንዘብ መክፈል አልተቻለም። የመድኃኒት መደብሮች የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ስለገጠማቸው የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል። ዴር አማር እና ዛህራኒ የተባሉት ኃይል ማመንጫዎች የሊባኖስን 40 በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ይሸፍናሉ። እነዚህ ኃይል ማመንጫዎች መሥራት ያቆሙት አርብ ዕለት እንደሆነ ተገልጿል። ሁለቱን የኃይል ማመንጫዎች የሚያስተዳድረው ኤሌክትሪሲት ዱ ሊባን (ኢዲኤል) የተባለ ድርጅት ነው። ኃይል ማመንጫዎቹን የሚያንቀሳቅስ ነዳጅ ጭነው የነበሩ መርከቦች በዶላር ካልተከፈላቸው ነዳጁን እንደማያወርዱ ተናግረዋል። ዛህል በተባለት የሊባኖስ ከተማ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን እንዲቀንሱ ተጠይቀዋል። በአገሪቱ ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቋረጥ በተጨማሪ ውሃም በፈረቃ መከፋፈል ጀምሯል። ባለፉት 18 ወራት ሊባኖስ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ገጥሟታል። መገበያያቸው የሊባኖስ ፓውንድም ዋጋ አጥቷል። የካንሰር እና የልብ ሕክምና የሚሰጡ አንዳንድ ሆስፒታሎች የመድኃኒት እጥረት ገጥሟቸዋል። የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉት መድኃኒት መደብሮች ማኅበር እንደሚለው በመዲናዋ ቤይሩት 80 በመቶ የመድኃኒት መደብሮች ተዘግተዋል። ከዕለት ወደ ዕለት በአገሪቱ የኑሮ ሁኔታ እያሽቆለቆለ በመጣባት ሊባኖስ፤ ግማሽ ያህሉ ዜጎች በድህነት ውስጥ እንዲኖሩ ምክንያት ሆኗል። በአገሪቱ በሙስና የተወነጀሉ ፖለቲከኞች ከሥልጣን እንዲወርዱ በሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎችም ትናጣለች። ላለፉት አስር ዓመታት በሊባኖስ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ሲቆራረጥ ነበር። መብራት በፈረቃ ስለሚለቀቅ ነዋሪዎች ጄነሬተር ለመጠቀም ይገደዳሉ። አሁን ግን አብዛኛው የአገሪቱ ክፍል በጨለማ ተውጧል። ጄነሬተሮችን የሚያንቀሳቅስ ነዳጅ በቀላሉ ስለማይገኝ ጄነሬተርን እንደ አማራጭ መጠቀመም አይቻልም። https://www.bbc.com/amharic/news-57787745 +politics ኢንጂኒየር ስለሺ በአሜሪካ፣ ጄነራል ���ጫ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ ባለፉት ዓመታት የውሃ፣ ኢነርጂ እና መስኖ ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ዶ/ር ኢ/ነ ስለሺ በቀለ በአሜሪካ እንዲሁም ጄነራል ባጫ ደበሌ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ። ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአምባሳደርነት ሹመት የተሰጣቸው ዲፕሎማቶች የተመደቡባቸውን አገራት ይፋ አድርገዋል። በዚህ መሠረት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሲነሳ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱ ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዶክተር ኢንጂኒየር ስለሺ በቀለ መቀመጫቸውን ዋሸንግተን ዲሲ በማድረግ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንዲሆኑ ተመድበዋል። ቀደም ሲል በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሲሰሩ የቆዩት ፍጹም አረጋ የነበሩ ሲሆን አሁን ይፋ በተደረገው የምደባ ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም። ዶክተር ኢንጂኒየር ስለሺ በቀለ የውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ከዚያም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የድንበር ተሻጋሪ ወሃዎችን አማካሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ብልጽግና ፓርቲን ወክለው አዲስ አበባ ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መመረጣቸው ይታወሳል። እንዲሁም ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ስማቸው ጎልቶ የወጡት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች አምባሳደር ባጫ ደበሌ እና አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም ኬንያ እና ግብፅ ተመድበዋል። ጄነራል ባጫ ከትግራዩ ጦርነት መቀስቀስ በኋላ በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ከጥቂት ወራት በፊት ነበር የሙሉ ጄነራልነት ሹመትን ያገኙት። አምባሳደር ተፈራ ደርበው ጃፓን የተመደቡ ሲሆን፣ አምባሳደር ደሴ ዳልኬ-ደቡብ ኮሪያ፣ አምባሳደር ዳባ ደበሌ-ሩዋንዳ፣ አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው-አውስትራሊያ፣ አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታ-ስዊዲን፣ አምባሳደር ፍቃዱ በየነ-ኤርትራ ተመድበዋል። ከዚህ በተጨማሪም ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ ሆኖ በተለያዩ አገራት የሚሰሩ እና ምክትል የሚሲዮን መሪ አምባሳደሮች መሾማቸውን ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-60776787 +health ኮቪድ -19፡ ልጆች ኮሮናቫይረስን ያስተላልፋሉ? ደቡብ ኮርያ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ልጆች ኮሮናቫይረስን አፍንጫቸው ላይ ይዘው እስከ ሦስት ሳምንታት መቆየት ይችላሉ። ከዚህ ቀደም የተሠሩ ጥናቶች፤ በርካታ ልጆች መጠነኛ የበሽታውን ምልክት እንደሚያሳዩ ወይም እስከነጭራሹ ምልክት እንደማይታይባቸው ይጠቁማሉ። እነዚህ ግኝቶች ልጆች ምን ያህል በሽታውን ያሰራጫሉ? ለሚለውና እስካሁን ግልጽ ምላሽ ላልተገኘለት ጉዳይ ፍንጭ ይሰጣሉ። ለወራት እንቅስቃሴ አቁመው በነበሩ አገሮች ትምህርት ቤቶች እየተከፈቱ ነው። አካላዊ ርቀትና ንጽህናን መጠበቅ መዘንጋት እንደሌለበትም ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ኮቪድ-19 እና ልጆችን በተመለከተ ሦስት ዋና ጥያቄዎች እንዳሉ የሚናገሩት የሮያል ኮሌጅ ፕሮፌሰር ራሰል ቪነር ናቸው። የሚከተሉት ጥያቄዎቻቸው ናቸው፦ ልጆች በቫይረሱ እንደሚያዙ በጥናቱ ተረጋግጧል። ፕ/ር ራሰል እንደሚሉት፤ ከፀረ እንግዳ አካላት (አንቲቦዲ) ምርመራ በተገኘ መረጃ መሠረት በተለይም ከ12 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ከአዋቂዎች ባነሰ ለቫይረሱ ይጋለጣሉ። • የ2013 የትምህርት ዘመንን ለማስጀመር ምን እየተሰራ ነው? • ኮሮናቫይረስ በማገርሸቱ ደቡብ ኮሪያ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው እንዲዘጉ አዘዘች ልጆች በቫይረሱ ከተያዙ የአዋቂዎች ያህል እንደማይታመሙም ሳይንቲስቶች እርግጠኛ ናቸው። እንዲያውም በርካታ ልጆች የበሽታውን ምልክት አያሳዩም። እምብዛም መልስ ያልተገኘለት ጥያቄ ልጆች በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ያስተላልፋሉ የሚለው ነው። የደቡብ ኮርያው ጥናትም እዚህ ላይ ያተኮረ ነው። የደቡብ ኮርያው ጥናት ምን ይላል? ጥናቱ የተሠራው 91 ልጆች ላይ ነው። መጠነኛ ወይም ምንም ምልክት የማያሳዩ ልጆች እስከ ሦስት ሳምንት ድረስ ቫይረሱ እንደሚቆይ ከናሙና መረዳት ተችሏል። አፍንጫቸው ላይ የቫይረሱ ምልክት መገኘቱ፤ ልጆች በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ማስተላልፍ እንደሚችሉ እንደሚጠቁም የጥናቱ ጸሐፊዎች አስረድተዋል። ደቡብ ኮርያ በምታካሂደው ምርመራና በሽታው ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች በምትለይበት ሂደት አማካይነት፤ የበሽታውን ምልክት የማያሳዩ ሰዎች ሳይቀሩ ይገኛሉ። ህሙማን ከተለዩ በኋላ ከቫይረሱ ነፃ እስኪሆኑ በተደጋጋሚ ተመርምረዋል። ጥናቱ ልጆች ቫይረሱን እንደሚሸከሙ፣ ወደ ሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፉ እንደሚችሉም ጠቁሟል። ሆኖም ግን ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ አልሰጠም። ልጆች አፍንጫ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል ማለት የአዋቂዎች ያህል ቫይረሱን ያስተላልፋሉ ማለት አይደለም። በሕፃናት ሕክምና ክፍል የሚሠሩት ዶ/ር ሮበርታ ዲባሲ ልጆች ቫይረሱን ሊያስተላልፉ አይችሉም ማለት እንደማይቻል ያስረዳሉ። የቫይረሱ ዘረ መል ከመተንፈሻ አካላት በሚወሰድ ናሙና ላይ መገኘቱ በሽታውን ከማስተላለፍ ጋር የግድ እንደማይተሳሰር የሚናገሩት ደግሞ የሊቨርፑል ዩኒቨርስቲ ፕ/ር ካሉም ሰምፕል ናቸው። የጥናቱ ድምዳሜ ምንድን ነው? ልጆችም ይሁን አዋቂዎች መጠነኛ ወይም ምንም አይነት ምልክት ካላሳዩ በሽታውን የማስተላለፍ እድላቸው አናሳ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ። የማያስሉ ወይም የማያስነጥሱ ሰዎች ቫይረሱን ወደ አየር እምብዛም አይለቁም። ሆኖም ግን ምልክት የማያሳዩ ሰዎች በሽታውን አያሰራጩም ማለት አይደለም። ዶክተሩ እንደሚሉት፤ አብዛኞቹ ልጆች በተወሰነ ደረጃ ወይም ሊታይ በማይችል ሁኔታ ነው በቫይረሱ ሊያዙ የሚችሉት። በማኅበረሰቡ ውስጥ ቫይረሱን ሊያሰራጩ ግን ይችላሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-53957592 +business ቢትኮይን ፡ በኤል ሳልቫዶር የቢትኮይንን ሕጋዊ መገበያያነት በመቃወም ሰልፍ ተደረገ በላቲን አሜሪካዋ አገር ኤል ሳልቫዶር በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች መንግሥት ቢትኮይንን እንደ ሕጋዊ የመገበያያ ገንዘብ በመቀበሉ ቁጣቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጡ። የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ናይብ ቡኬሌ ክሪፕቶከረንሲ በውጭ አገር የሚሰሩ ሳልቫዶራውያን ገንዘባቸውን በቀላሉ ወደ አገራቸው እንዲልኩ ይረዳቸዋል ብለዋል። ሰልፈኞቹ ግን በከፋ ድህነት ውስጥ የምትገኘውን ኤል ሳልቫዶር ወደ በለጠ የዋጋ ግሽበት ብሎም ያለመረጋጋት ይወስዳታል ብለው ይሰጋሉ። ከሰልፈኞቹ መካከል የተወሰኑት አንድ አዲስ የቢትኮይን ማሽን በእሳት ሲያቃጥሉ ሌሎች «ቡኬሌ አምባገነን» የሚል መፈክር ይዘው ታይተዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ኤል ሳልቫዶር ከአሜሪካ ዶላር በተጨማሪ ክርፒቶከረንሲን እንደ ሕጋዊ የመገበያያ ዘዴዋ በመጠቀም የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። በዋና ከተማዋ ሳን ሳልቫዶር የተሰበሰቡት ሰልፈኞቹ ይህንን ሰልፍ ያካሄዱት አገራቸው 200ኛውን የነፃነት በዓሏን በምታከብርበት ቀን ነው። « እምቢ ለቢትኮይን» እና «ሕገ -መንግሥቱ ይከበር» የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ላይ ከታዩት መካከል ናቸው። ሰልፈኞቹ ፕሬዚዳንቱ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ቆይታቸውን ለማራዘም አቅደው ተንቀሳቅሰዋል ሲሉም ይከሳሉ። ምንም እንኳን ሕገ-መንግሥታዊ ገደብ ቢቀመጥም ቡኬሌ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ለፕሬዝደንትነት እንዲወዳደሩ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፈቅዶላቸዋል። «ዛሬ ማለዳ ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር- በቃ! ማለት ነው። መንግሥት እያደረገ ያለው እብሪተኛ እና አምባገነናዊ ተግባር ነው» ሲሉ አንድ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ ግለሰብ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ነገር ግን ፕሬዝደንት ቡኬሌ አሁንም በኤል ሳልቫዶር ጠንካራ ድጋፍ አላቸው። በቅርቡ አንድ የአገር ውስጥ ጋዜጣ ባደረገው የሕዝብ አስተያየት ጥሪ 85.7% የሚሆኑ ድምጽ ሰጪዎች ለፕሬዝደንቱ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-58554994 +sports ሴኔጋል ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮን ሆነች "ሴኔጋል ግብጽን 4 ለ 2 በመለያ ምት በመርታት የመጀመሪያዋን የአፍሪካ ዋንጫ ለማንሳት በቃች። ጨዋታው በሁለቱ የሊቨርፑል አጥቂ ሳዲዮ ማኔ እና መሐመድ ሳላህ መካከል የተደረገ ፍልሚያ ተብሎ በብዙዎች በከፍተኛ ጉጉት የተጠበቀ ነበር። ጨዋታው ያለምንም ጎል በመጠናቀቁ ነበር ወደ መለያ ምት የተሸጋገረው። ማኔ በሰባተኛው ደቂቃ ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል። የቼልሲው የግብ ዘብ ኤዱዋርድ ሜንዲ በበኩሉ በመለያ ምቱ ወቅት ሞኢሃናደድ ላሺን ኳስ አድኖ ለቡድኑን አሸናፊነት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የፈርንኦቹ ግብ ጠባቂ ጋባስኪም ድንቅ ሆኖ አምሽቷል። ሴኔጋል ከዚህ ቀደም በሁለት የፍጻሜ ጨዋታዎች ከተሸነፈች በኋላ በመጨረሻም የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ለመሆን በቅታለች። ግብጽ ውድድሩን በማሸነፍ ክብረወሰኗን ወደ ስምንት የምታሳድግበትን ዕድል ሳትጠቀም ቀርታለች። የሴኔጋሉ አሰልጣኝ አሊዩ ሲሴ ""ጠንክረህና ጸንተህ ከሠራህ የምትፈልገውን እንደምታገኝ ያሳያል"" ሲሉ ድሉን ገልጸውታል። ""በጣም ስሜታዊ ሆኛለሁ ምክንያቱም የሴኔጋል ህዝብ ይህን ዋንጫ ለ60 ዓመታት ናፍቋል"" ብለዋል አሰልጣኙ። በውድድሩ ላይ አራቱም የግብጽ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ወደ ተጨማሪ ሰዓት ተሸጋግረዋል። ፈርኦኖቹ አይቮሪኮስትን እና አስተናጋጇ ካሜሩንን በመለያ ምት አሸንፈው ነበር ለፍጻሜው የደረሱት። ጨዋታው ወደ መለያ ምት ከመሸጋገሩ በፊት ጋባስኪ ቀደም ሲል በውድድሩ ላይ አራት መለያ ምቶችን አድኖ ነበር። ግብጻዊው ተከላካይ መሀመድ አብደልሞኔ መለያ ሳይጠቀምበት የቀረ ሲሆን በፍጥነት ጋባስኪ የቡና ሳርን ኳስ ለመዳን ችሎ ነበር። የላሺን መለያ ምት በሜንዲ ሲድን የመጨረሻዋን ኳስ ማኔ አስቆጥሮ ለዋንጫ ሴኔጋሎች ዋንጫውን አንስተዋል። የሊቨርፑል የቡድን አጋሩ ሳላህ አምስተኛ መቺ በመደረጉ የመለያ ምቱን እንኳን ለመምታት ዕድል አላገኘም። ሴኔጋል በፈረንጆቹ 2002 እና 2019 ለፍጻሜ ቀርባ ተሽንፋለች። ሳላህ በሴኔጋል ተከላካዮች ቁጥጥር ስር ባመሸበት ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት ሙከራዎችን አድርጓል። በሁለተኛው አጋማሽ ፈርኦኖቹ ጎል ለማስቆጠር ያደረጉት ሙከራ ፍሬ ሳያፈራ ቀርቷል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በጭማሪው ሰዓት ሞቅ ብሎ ተከናውኗል። በመጨረሻም ድሉ ላለፉት ሦስት ዓመታት የአፍሪካን የሃገራት ደረጃ ለመራችው ሴኔጋል ሆኗል። አሰልጣኝ አልዩ ሲሴም በተጫዋችነት በ2002 ወሳኟን የመለያ ምት ከሳቱ እና ከሦስት ዓመት በፊት በፍጻሜው ከተሸነፉ በኋላ ያገኙት ድል ሆኖ ተመዝግቧል። ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ከአንድ ዓመት በኋላ በአይቮሪ ኮስት ይከናወናል። ሁለቱ ቡድኖች በሚቀጥለው ወር ለኳታር የዓለም ዋንጫ ለማነፍ በድጋሚ ተገናኝተው በደርሶ መልስ ስለሚጫወቱ ግብጽ በቅርቡ የመበቀል ዕድል ይኖራታል።" https://www.bbc.com/amharic/60253411 +health በቀን ሦስት ጊዜ ባንመገብስ? ቁርስ፣ ምሳና እራት ልማድ ወይስ አስፈላጊ የምግብ ጊዜ? "ምግብ ከእጅ ወደ አፍ፣ ከአፍ ደግሞ ወደ ሆድ የሚላክ ነገር ብቻ አይደለም። ምግብ የባህል አካል ነው። ያለ ምግብ ውሎን፣ አዳርን፣ በዓልን ማሰብ ከባድ ነው። በየዓይነቱ አዘጋጅቶ ገበታውን ሙሉ አድርጎ ወዳጅ ዘመድን መጋበዝ የፍቅርና የወዳጅነት መግለጫ ነው። እዚህ ላይ ትንሽ ኢትዮጵያዊነት እንጨምርበት ካልን 'በሞቴ' እያሉ መጎራረስ ይቻላል። ይህም ምግብ በሰው ልጆች አካላዊ እና አዕምሮአዊ ዕድገት ውስጥ ካለው ቁልፍ ተግባር አልፎ ማኅበራዊ ትስስርን የሚገነባ ተጨማሪ መንገድ መሆኑን ያመላክት ይሆናል። የሆነው ሆኖ የምግብ ዋነኛ ዓላማዎች ሁለት ናቸው - ለሰውነት ጉልበት እና ኃይልን መስጠት እንዲሁም በሽታ የመከላከልን ሥርዓትን ማዳበር። የምግብ ተግባር ይህ ከሆነ በቀን ስንት ጊዜ፣ ምን እና እንዴት እንመገብ? ስንት ጊዜ የሚለውን እናቆየው! 'ሰው የሚመገበውን ይመስላል' የዕለት ተግባራችንን በበቂ ጉልበት ለመከወን፤ የበሽታ መከላከል አቅማችንንም ለማደርጀት ምን እንመገብ የሚል ጥያቄ ሲነሳ የምግብ ስብጥር [food diversity] የሚል ሃሳብ ይነሳል። ምን ማለት ነው? ለምሳሌ አቮካዶ እና እንቁላል [በተለይ አስኳሉ] በበርካታ ንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ምን አልባትም አቻ የሌላቸው ምግቦች ናቸው። ነገር ግን እነርሱን ብቻ መመገብ ይጎዳል ባይባል እንኳን ለሰውነት ከሚያስፈልጉ እና ጠቃሚ ከሆኑ ሌሎች ንጥረ ነገሮች ውጪ ያደርጋል። እናም በቀን ውስጥ የተለያዩ የምግብ አይነቶችን መመገብ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን በአንድ ጊዜ ለመግኘት ያግዛል። ይህ የምግብ ስብጥር ይባላል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ሳይንስ እና ሥነ ምግብ ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ቃለአብ ባዬ በሥነ ምግብ ጉዳይ ላይ በዓለም ዙሪያ የሚሰሩ ተመራማሪዎች ያዘጋጇቸው የአመጋገብ መመሪያዎች በሌሎች ጉዳዮች የተለያዩ ሃሳቦችን ሊያንጸባርቁ ቢችሉም ምግብን ማሰባጠር በተመለከተ ""ሁሉም ማለት ይቻላል"" ተመሳሳይ አቋም አላቸው ይላሉ። እንደ እርሳቸው ገለጻ የምንመገባቸው ምግቦች አይነት ""በተቻለ መጠን"" በበዛ ቁጥር ""የሚያስፈልገንን ኃይል እና ንጥረ ነገር የሟሟላት ዕድላችን ከፍ ይላል።"" ""እኛ ሰዎች ማለት የበላነው ምግብ ነን"" የሚሉት በዲላ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ሳይንስ እና የሥነ ምግብ መምህሩ ዶ/ር ይኹኔ አየለ ደግሞ ""ሰውነታችን በአጠቃላይ በትክክለኛ የተፈጥሮ ሂደቱ ሥራውን ይከውን ዘንድ ቢያንስ 53 ዓይነት ሚኒራሎች/ማዕድናት እና ቫይታሚኖች ያስፈልጉታል"" ሲሉ ያብራራሉ። ""በምድር ላይ እነዚህን ሁሉ ሚኒራሎችና አስፈላጊ ነገሮችን አሟልቶ የያዘ አንድ ምግብ ልናገኝ አንችልም"" ስለዚህ ""በተቻለ መጠን ባለን አቅም"" ምግቦችን የማሰባጠርን አስፈላጊነት ይመክራሉ። ጎመን በሥጋ ዶ/ር ይኹኔ ለምግብ ስብጥር ከሚሰጧቸው ምሳሌዎች አንዱ አትክልት እና የእንስሳት ተዋፅኦን በጋራ መመገብን ነው። በኢትዮጵያ የተለመደውን ጎመን በሥጋ ስብጥርን በተመለከተ ለዓለም ትምህርት የሚሆን ሲሉ ይገልጹታል። እንደ እርሳቸው ገለጻ አይረን/የብረት ማዕድንን ከሥጋ 70 በመቶ፣ ከአትክልቶች ደግሞ እስከ 17 በመቶ ይገኛል። ይህ ሁኔታ ሥጋን 'ቸር' አትክልትን ደግሞ 'ንፉግ' ያሰኘዋል ይላሉ። ታዲያ ጎመን በሥጋ ጋር ይህ አይሰራም፤ ሁለቱ በጋራ ሲዘጋጁ ጎመን አትክልታዊ ባህሪው ተቀይሮ 'ቸር' ይሆናል። ለየብቻ ሲዘጋጁ ከሚገኘው ንጥረ ነገር የላቀ ጠቀሜታን ያቀርባል። አትክልት፣ የእንስሳት ተዋፅኦ፣ የእህል ዘር፣ ፍራፍሬና የቅባት እህል በሰፊው የምግብ አይነቶች/ዘርፎች ውስጥ የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የምግብ አይነቶች በዓለም ጤና ድርጅት እና የምግብ እና እርሻ ድርጅት በተዘጋጁ የሥነ ምግብ መመሪያዎች ውስጥ ከተካተቱ 10 የምግብ አይነቶች/ዘርፍ ውስጥ የተጠቀሱ ናቸው። ታዲያ በቀን ውስጥ እነዚህ የምግብ አይነቶችን አሰባጥሮ መመገብ ነው ባለሙያዎቹ የሚመክሩት ነው። ነገሩ እነዚህን ሁሉ ለሟሟላት ያውም በየቀኑ አቅም ከየት ይመጣል? የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም። ዶ/ር ይኹኔ ግን መልስ አላቸው - መቼም ውድ የሚሆነው የእንስሳት ተዋፅኦ ነው። ስለዚህ የእንስሳቱን ተዋፅኦ ዝቅ አድርጎ ከሌሎች ምግቦች ጋር መጠቀም። ""ሽሮ ላይ እንቁላል ወይም ቋንጣ ጣል ማድረግ"" ሲሉ ያስቀምጣሉ። ይህስ ባይቻል? ንፍሮ እና ቆሎ ከእጽዋት የሚገኙትን ምግቦች ማሰባጠር። ዶ/ር ይኹኔ እዚህ ጋርም በኢትዮጵያ የሚዘወተር እና ሊበረታታ የሚገባው የሚሉት ምሳሌ አላቸው - ከተለያዩ ጥራጥሬዎች የሚዘጋጅ ንፍሮ። እያንዳንዱ ጥራጥሬ የራሱ ጥቅም ያለው እና አንዱ የሌለው በሌላኛው ስለሚተካ የሥነ ምግብ ጠቀሜታውን ከፍ ያደርገዋል። ከዚህም ባሻገር የገብስ ቆሎ ሲዘጋጅ ለውዝ፣ ኑግ እና መሰል ጥራጥሬዎችን ያካትታል። ይህ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሊበለጽግ የሚገባው እና በሳይንስ እጅግ የሚደገፈው ምግብን የማሰባጠር ልማድ እንዳለ የሚያረጋግጥ ነው ይላሉ። ስለዚህ ሥጋው ጋር ማን አድርሶን ቢባል እንኳን ተፈጥሮ በአይነት በአይነት ያቀረበቻችውን አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎችና ጥራጥሬዎች ማሰባጠር የተለያዩ ጠቀሜታዎችን ያስገኛል። ዶ/ር ቃለአብ የምግብ አይነቶች/ዘርፎች በውስጣቸው በተለያዩ ቀለማት የሚቀመጡ ምግብን ስለያዙ ""ምግባችን ምን ያህል ቀለም አለው?"" ብሎ መጠየቅ የምግቡን ስብጥር ሊያመላክት ይችላል። በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የምግብ ሥርዓት እና ሥነ ምግብ ምርምር ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ ""ጥግብ!"" ብዬ በላሁ ማለት በቀን ውስጥ ለሰውነት የሚያስፈልገንን ንጥረ ነገር ስለማግኘታችን ያረጋግጣል ማለት አይደለም ሲሉ ያስረዳሉ። ስለዚህም በ24 ሰዓት ውስጥ በዓለም ጤና ድርጅት እና የምግብ እና እርሻ ድርጅት በተዘጋጁ የሥነ ምግብ መመሪያዎች ውስጥ ከተካተቱ 10 የምግብ አይነቶች/ዘርፍ ውስጥ ቢያንስ አምስቱን ለማካተት መሞከር ተገቢ ነው ይላሉ። ኃላፊው ይህንን መመሪያ ኢትዮጵያ እንደምትቀበለው እና በጤና ሚኒስቴርም የሚመከር መሆኑን ይጠቅሳሉ። የምግብ ሰሃናችን ምን ምን ይዟል? በአሜሪካ በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ላስቬጋስ በምግብ ዝግጅት እና ሥነ ምግብ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ሼፍ አዲስዓለም ብዙአየሁ ""በቀን ውስጥ ሰውነት የሚያስፈልገውን ምግብ ተመግቤያለሁ ወይ?"" ብሎ መጠየቅ ይገባል ሲሉ ይገልጻሉ። ይህንን ጥያቄ በቀላሉ የምግብ ሰሃኑ ሊመልሰው እንደሚችል ጠቅሰዋል። ""የምግብ ሰሃናችን ግማሹ አትክልት መሆን ነው ያለበት። ጥቅል ጎመን ሊሆን ይችላል፤ ካሮት፣ ቀይስር፣ የሀበሻ ጎመን፣ ቲማቲም፣ ዝኩኒ አይነት ነገር"" ሊሸፈን ይችላል። የሰሃኑ አንድ አራተኛ ወይም ሩብ ደግሞ ፕሮቲን አዘል በሆነ ምግብ መሸፈን ይገባል። ""ለምሳሌ ቦሎቄ፣ እንቁላል፣ ዓሳ፣ የዶሮ ሥጋ ወይም የከብት ሥጋን የመሰሉ ምግቦች መያዝ ይኖርበታል"" የተቀረው ደግሞ ካርቦ ሃይድሬትን እንደ ሩዝ፣ ፓስታ ወይም ዳቦ አይነት ምግቦችን ቢያካትት ይመከራል ሲሉ ገልጸዋል። ሰሃኑ ላይ እንደ እንጀራ ያለ ማባያ ሲከተት ደግሞ በርከት ያለ ንጥረ ነገር የመገኘት እድሉን ከፍ ያደርገዋል። የሰሃኑ ግማሹ ክፍል አቮካዶን በመሰሉ ፍራፍሬዎች ሊተካ እንደሚችልም ጠቁመዋል። ከዚህ ባሻገር ደግሞ ከመደበኛ የምግብ ሰዓት ባሻገር የተለያዩ አይነት ፍራፍሬዎችን መመገብ እጅግ የሚያበረታታ ነው። እንደ ሼፍ አዲስዓለም ገለጻ ምግቦችን ማሰባጠር የተለያዩ የሰውነት ክሎች የሚፈልጓቸውን ንጥረ ነገሮች በተመጣጠነ ሁኔታ እንዲያገኝ ያስችላል። በዚህ ምክረ ሃሳብ መሰረት ምሳ ፓስታ በዳቦ የበላን ሰው አስቡት! እንዴት እንመገብ? ከምግቦች ስብጥር ባሻገር የአመጋገብ ሁኔታ በጤና ሥርዓተ ምግብ ውስጥ ወሳኝ ቦ��� አለው። በኢትዮጵያ ያለው ለምግብ የተለየ ሰዓት የመስጠት ልማድ ሊበረታታ ይገባል ይላሉ የሥነ ምግብ ባለሙያዎቹ። ከዚህ ልማድ በተቃራኒ እየመጡ ያሉ ልማዶች ከጅምሩ መቅረፍ ቢቻል ተገቢ ነው የሚሉት ዶ/ር ቃለአብ ናቸው። ዶ/ር ቃለአብ መኪና እያሽከረከሩ፣ ሥራ እየሰሩ፣ ስልክ እየተጠቀሙ ወይም ሌላ ትኩረትን ሊስብ የሚችል ነገር ላይ ተጠምዶ ምግብ መመገብ ከሚያስፈልገው መጠን በላይ ምግብ ለመውሰድ ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ። ""ተጽዕኖ ከሚፈጥሩ ነገሮች በጸዳ መልኩ ቁጭ ብሎ ጊዜ ወስዶ ረጋ ብሎ መመገብ ያለውን ጥቅም በሳይንሱ በሂደት እየተረዳነው ነው"" የሚሉት ዶ/ር ቃለአብ ""በጋራ ምግብን የፍቅር እና የጥሩ ጊዜ ማሳለፊያ አድርጎ ቁጭ ብሎ መመገብ ከንጥረ ነገር ባለፈ አመጋገባችን ላይ ወሳኝነት ስላለው እና የምግብ መጠን ቁጥጥርን"" ስለሚያግዝ እጅግ የሚበረታታ ነው ይላሉ። የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ምግብ መምህሩ ዶ/ር ይኹኔ በበኩላቸው የቅርብ ጊዜ ጥናቶች የጋራ ገበታ ያላቸውን ፋይዳ እያረጋገጡ እንደሆነ ይገልጻሉ። በጋራ እየተጨዋወቱ መመገብ የተመጠነ ምግብ በተሻለ ሁኔታ ለማግኘት እና በተረጋጋ ሁኔታ ሥርዓተ ምግብን ለመከወን ይረዳል። በሌላ በኩል ዶ/ር ቃለአብ ""ያለማቋረጥ ቶሎ ቶሎ መብላት አይመከርም"" ሲሉ ያስረዳሉ። ያለማቋረጥ ቶሎ ቶሎ መመገብ [binge eating] ለሆድ መነፋት ከማጋለጥ ጀመሮ በአጠቃላይ የአመጋገብ ሥርዓት ላይ ጫና እስከማድረስ የዘለቀ ጉዳት አለው። በቀን ስንት ጊዜ እንመገብ? ነገሩ አከራካሪ ነው። ቢቢሲ እንዳነጋገራቸው ባለሙያዎች ገለጻ ግን በቀን ስንት ጊዜ እንመገብ የሚለው ጥያቄ እምብዛም አያሳስብም። ዋናው ጉዳይ በቀን ውስጥ ሰውነት የሚፈልገውን ንጥረ ነገሮችን የያዙ ምግቦችን አሰባጥሮ መመገብ ላይ ነው። ይህ ሲሆን በተለያየ መጠንና በተለያየ ሰዓት ሊሆን ይችላል። ይህ ሃሳብ የሚመለከተው ግን በጥቅሉ የጎላ የጤና ችግር የሌለባቸውን ወይም በሌላ የተለየ ሁኔታ ውስጥ የሌሉ አዋቂ ሰዎችን ነው። ህጻናት በተለየ ሁኔታ በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ መመገብ ሊኖርባቸው ይችላል። ስለዚህ ለአዋቂ ሰዎች ቁርስ፣ ምሳና እራት አስፈላጊና መዘለል የማይገባው ነው፤ የሚለው ጉዳይ ወደ ልማድና ባህል ያዘነበለ ነው። ሳይንሱ እንደ መመሪያ አንድ ሰው በቀን ውስጥ ማግኘት ያለበትን የንጥረ ነገር፣ የኃይል መጠን ይገልጻል። ስለዚህ ከሳይንስ አንጻር ከታየ የምናወዳድረው በቀን ውስጥ የተመገበው የቀን ፍላጎቱን አሟልቷል ወይስ አላሟላም የሚለውን እንደሆነ ዶ/ር ቃለአብ ያብራራሉ። ጨምረውም ""ስለዚህ አንድ ሰው በቀን ውስጥ ሁለቴ በልቶ ሊሆን ይችላል፤ ሦስት ጊዜ በልቶ ሊሆን ይችላል፤ ከሳይንስ አንጻር የሚገመገመው ግን ሰውነቱ በቀን ከሚያስፈልገው የኃይል እና የንጥረ ነገር ፍላጎቱ አንጻር ነው"" በማለት የረሃብ ስሜትን ግን ቸል ማለት እንደማይገባና ተገቢውን ምላሽ መሰጠት ይገባል ብለዋል። ሆኖም በቀን ውስጥ ሦስት ጊዜ መመገብ ለተመጋቢውና ለሥርዓተ ምግብ የተመቸ ነው። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የሥነ ምግብ ምርምር ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማስረሻ ወሳኙ ነገር በቀን የምናገኘው የንጥረ ነገር መጠን መሆኑን ጠቅሰው፣ በቀን ከሦስት ጊዜ በላይ መመገብ የሰውነት ክብደትን እንዲጨምር ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይጠቅሳሉ። በእድሜና በጤና ሁኔታ የተለያየ ቢሆንም ምግብ በጨጓራ ውስጥ በአማካይ እስከ አራት ስዓት እንደሚቆይ የሚያስረዱት ዶ/ር ይሁኔ ደግሞ ""ጨጓራ መጨናነቅ ስለሌለበት የበላነው ምግብ በአራት ሰዓት ውስጥ ተፈጭቶ ወደ ሰውነት ከተሰራጨ በኋላ"" ቀጣዩን ምግብ መመገብ እንደሚመከርና ""ሆድ እስኪሞላና ጨጓራ እስኪጨናነቅ"" መ���ገብ እንደማይገባ ይመክራሉ። ታዲያ በዚህ ስሌት መሰረት ከ24 ሰዓቱ 8ቱ ለእንቅልፍ ቢተውና የቀረው ቢከፋፈል ወደ ተለመደው የምግብ ሰዓት እንደሚያደላ አስረድተዋል። ባለሙያዎቹ ያተኮሩበት ሌላኛው ነጥብ በቀን ስንት ጊዜ እንመገብ የሚለው ጥያቄ ሰዎች ያላቸው የሥራና አካላዊ እንቅስቃሴ ሁኔታ ላይ የተመረኮዘ ነው። ብዙ የሚንቀሳቀስ፣ ጉልበት የሚያወጣና ቢሮ ውስጥ የሚሰራ ሰው ተመሳሳይ የምግብ ጊዜና መጠን ሊኖራቸው አይችልም። 'ላቡ ጠብ' እስኪል የሚደክም ሰው ያን የሚተካ ምግብ ማግኝት ይኖርበታል። ምግቡ ስንት ቀለማት አሉት የሚለው ጉዳይ ሳይዘነጋ።" https://www.bbc.com/amharic/news-60150890 +business በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ቻይና አሜሪካንን በልጣ ከዓለም 1ኛ ሆነች ቻይና በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት (FDI) ለመጀመርያ ጊዜ አሜሪካንን በመብለጥ የምድራችን ቁጥር አንድ አገር ለመሆን በቃች። ትናንት እሑድ ይፋ በተደረገ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥናት መሠረት ቻይና አዳዲስ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በመሳብ ይሆናል ተብሎ ከተገመተው በአጭር የጊዜ ሂደት አሜሪካንን ለመብለጥ ችላለች። ይህ የተባበሩት መንግሥታት ያወጣው መረጃ እንደሚያትተው ወደ ቻይና ድርጅቶች አዳዲስ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ4 ከመቶ ተመንድጓል። በሌላ አነጋገር በፈረንጆቹ 2020 ወደ ቻይና የተመሙ አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች ወደ አሜሪካ ከተመሙት አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች በእጅጉ ያላቁ ናቸው። ይህ የሚያሳየው ቻይና በዓለም ዙርያ ያላት ተጽእኖ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ነው ብሏል ሪፖርቱ። ከውጭ አገራት ወደ አሜሪካ የሚገቡ አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች ባለፈው ዓመት (2020) በግማሽ መቀነሳቸውን ዘገባው አትቷል። ሆኖም ወደ ቻይና የሚተሙ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንቶች ከዕለት ዕለት እየጨመሩ ነው የመጡት። በዚህም ምክንያት ነው ቻይና ከአሜሪካ ልቃ እንድትገኝ ያስቻላት። ቻይና ባለፈው ዓመት ብቻ 163 ቢሊዮን ዶላር ወደ አገሯ አዲስ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፈሶላታል። አሜሪካ ግን 134 ቢሊዮን ብቻ ነው ወደ አገሯ የቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ የቻለችው። ይህን አሐዛዊ ዘገባ ያወጣው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በንግድና በልማት ኮንፈረንስ (UNCTAD) ላይ ነው። በ እአአ 2019 አሜሪካ የ251 ቢሊዮን ዶላር አዲስ የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ ችላ ነበር። በዚህ ጊዜ ቻይና የ140 ቢሊዮን የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ነበር ማግኘት የቻለችው። ምንም እንኳ ቻይና በተገባደደው የፈረንጆች ዓመት አዲስ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ አሜሪካንን ቀድማ አንደኛ ብትሆንም በጠቅላላ የውጭ ኢንቨስትመንት ክምችት ግን አሁንም ዓለምን የምትመራው አሜሪካ ናት። ይህም የሚያሳየው ለዓመታት አሜሪካ የአዳዲስ የውጭ ኢንቨስትመንቶች መዳረሻ ተመራጭ አገር እንደነበረችና የውጭ ኢንቨስትምነት ምን ያህል የተከማቸባት አገር መሆኗን ነው ይላል ሪፖርቱ። የምጣኔ ሀብት አዋቂዎች ግን በአዳዲስ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የታየው የአሰላለፍ ልዩነት አሁን ቻይና በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ወሳኝ የሆነ ተጽእኖ ማሳረፍ መጀመሯን አመላካች ነው ይላሉ። በአሜሪካ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ2016 የትራምፕን መምጣት ተከትሎ ነበር ወደ 472 ቢሊዮን ዶላር የተመነደገው። ያን ጊዜ ቻይና 134 ቢሊዮን ዶላር ላይ ነበረች። ያን ጊዜ የትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ ኩባንያዎች ቶሎ ቻይናን እየለቀቁ ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ ከፍተኛ ማበረታቻ እየሰጠ ነበር። በተመሳሳይ የትራምፕ አስተዳደር የቻይና ኩባንያዎች ለደኅንነት ስጋት ስለሚሆኑ በየጊዜው ይመረመራሉ በሚል በአሜሪካ የነበራቸው ሚና ለማንኳሰስ ሞክሯል�� ይህ የትራምፕ አስተዳደር በዚህ መንገድ ተጽእኖ ለመፍጠር በመቻሉ ሊሆን ይችላል ባለፉት ዓመታት የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት የበላይነት በአሜሪካ ተይዞ የቆየው። ሆኖም ባለፈው ዓመት (2020) የአሜሪካ ኢኮኖሚ በኮቪድ ወረርሸኝ የተነሳ ሲቀዛቀዝ የቻይና ኢኮኖሚ ግን ቶሎ ማንሰራራት ችሏል። በ2020 የቻይና የአገር ውስጥ ጥቅል ምርት መጠን (GDP) በ2.3% ማደጉን መረጃዎች ይጠቁማሉ።. ይህም ቻይናን በኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ የኢኮኖሚ ድቀት ብዙም ያልተሰማት ብቸኛዋ የዓለም አገር አድርጓታል። ብዙ ኢኮኖሚስቶች በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የቻይና ኢኮኖሚ በፍጥነት ማንሰራራቱ አስገርሟቸዋል። በ2020 በዓለም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በጠቅላላው በ42% ወድቋል። ብዙውን ጊዜ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት የሚባለው አንድ የውጭ ኩባንያ በሌላ አገር ውስጥ ያሉ ኩባንያዎችን በመግዛት ወይም ከራሱ ኩባንያ ጋር እንዲጣመሩ በማድረግ ወይም በአዲስ ኩባንያ አዲስ ሥራ ለመጀመር መዋእለ ነዋዩን ማፍሰስ ሲጀምር ነው። https://www.bbc.com/amharic/55792460 +business ናይጄሪያ ምግብ ከውጪ ለማስገባት ገንዘብ የለኝም አለች "የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሐመዱ ቡሐሪ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፈጠረው ችግር የተነሳ አገራቸው ምግብ ከውጪ ለማስገባት ""ገንዘብ የላትም"" አሉ። በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ከኢትዮጵያ ቀድማ የመጀመሪያውን የሆነችው ናይጄሪያ የውጪ ምንዛሪ ችግር ስላጋጠማት የአገሪቱ አርሶ አደሮች ሕዝቡን መቀልብ የሚችል መጠን ያለው ምግብ እንዲያመርቱ ፕሬዝዳንቱ ጠይቀዋል። ቡሐሪ ይህንን የተናገሩት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሚከሰትን የምግብ ዋስትና ችግር በተመለከተ ስጋቶች በመፈጠራቸውና በአገሪቱም በምግብ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ተከትሎ ነው። እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት የአገሪቱ አርሶ አደሮች እንኳን በዚህ በወረርሽኙ ወቅት ይቅርና ከዚያ በፊትም 200 ሚሊዮን የሚደርሰውን ሕዝብ የምግብ ፍላጎት ማሟላት አይችሉም ነበር። ምንም እንኳን የናይጄሪያ የግብርና ዘርፍ በርካታ ሰዎች የተሰማሩበት ዋነኛ መስክ ቢሆንም፤ ከነዳጅ ዘይት በሚገኝ ገቢ ላይ በከፍተኛ ደረጃ ጥገኛ በሆነው የአገሪቱ መዕተዓኘየ ሐዓዕጠዕ ተነሳ ትኩረት ተነፍጎት ቆይቷል። ናይጄሪያ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በድንበሮቿ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ከታይላንድ በሕገ ወጥ መንገድ የሚገባውን የሩዝ ምርት በመግታት በአገር ውስጥ ለሚመረተውን ሩዝ ገበያ ለማመቻቸት ጥረት ስታደርግ ነበር። ናይጄሪያ ከውጪ የሚመጣ የሩዝ ምርት ላይ ክልከላ ከመጣሏ ቀደም ብሎ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊየን ቶን በላይ ሩዝ ከታይላንድ ታስገባ ነበር። አገሪቱን በሚያዋስኗት አገራት ድንበር በኩል የሚገባው ሩዝ የተከለከለ በመሆኑ በወደብ በኩል ብቻ ነው ሩዝ ወደ ናይጄሪያ እየገባ ያለው። በዚህም ላይ ከፍተኛ ግብር በመጣሉ ዋጋውን አስወድዶታል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ በኋላ ናይጄሪያ ውስጥ የምግብ ዋጋ ላይ ጭማሪ የተከሰተ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዘይት ዋዳ በመውደቁ ምክንያት ደግሞ መንግሥት ያገኘው የነበረው በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እንደተነበየው በአፍሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላት ናይጄሪያ በዚህ ዓመት ኢኮኖሚዋ በ1.5 በመቶ ያሽቆለቁላል።" https://www.bbc.com/amharic/news-52796481 +health ንግሥት ኤልዛቤት ሆስፒታል ገብተው እንደነበር ተገለጸ "የዩናይትድ ኪንግደሟ ንግሥት ኤልዛቤት ቀዳሚ የህክምና ምርመራ ለማድረግ ረቡዕ ምሽት ሆስፒታል ገብተው እንደነበር የባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት አስታወቀ። የ95 ዓመቷ ንግሥት ኤልዛቤት ማእከላዊ ለንደን በሚገኝ አንድ የግል ሆስፒታል ውስጥ ህክምናቸውን ተከታትለው ዊንድሰር ወደ ሚገኘው መኖሪያቸው መመለሳቸውን ተገልጿል። አሁን በመልካም ሁኔታ ላይ ናቸው የተባሉት ንግሥቲቱ ወደ ሰሜን አየርላንድ ለመጓዝ የነበራቸውን እቅድ ሰርዘዋል። የህክምና ባለሙያዎች ንግሥቲቷ ወደተለመደው ሥራቸው ከመመለሳቸው በፊት ለጥቂት ቀናት እረፍት ማድረግ እንደሚገባቸው መክረዋል ተብሏል። ሐሙስ ምሽት ስለንግሥቲቱ መግለጫ የሰጠው የባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት እንዳለው ""ንግሥቲቱ ረቡዕ ዕለት ወደ ሆስፒታል ያቀኑት የተለመደ ክትትል ለማድረግ ሲሆን ሐሙስ ምሳ ሰዓት አካባቢ ተመልሰዋል፤ መንፈሳቸውም ተነቃቅቷል"" ብሏል። ንግሥቲቱ ወደ ንጉሥ ኤድዋርድ ሰባተኛ ሆስፒታል የተወሰዱት ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ምክንያት እንዳልሆነም ተገልጿል። ንግሥት ኤልዛቤት ሁለተኛ ሆስፒታል ውስጥ ለህክምና ሲኣሳልፉ ከፈረንጆቹ ከ2013 በኋላ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ማዕከላዊ ለንደን የሚገኘው ንጉሥ ኤድዋርድ ሰባተኛ የግል ሆስፒታል በንጉሣውያን ቤተሰቦች ይዘወተራል። በቅርቡ በሞት የተለዩት የንግሥቲቱ ባለቤትን ጨምሮ ንጉሣዊያን ቤተሰቦች የሚታከሙት በዚሁ ሆስፒታል ነው። ንግሥቲቷ ወደ ሰሜን አየርላንድ መሄዳቸውን ትተው ወደ ሆስፒታል ያቀናሉ የሚለው ዜና ጭንቀት እንዳይፈጥር ተሰግቶ ነበር። ምንም እንኳ ኤልዛቤት ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በተሳተፉባቸው ዝግጅቶች ላይ ነቃ ብለው ቢታዩም ዕድሜያቸው ለጤናቸው ስጋት ሊሆን እንደሚችል አያጠርጥርም። ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት ስለ ንግሥቲቱ የጤንነት ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠበው ግላዊ ሕይወታቸውን ለመጠበቅ ነው ተብሏል። ምንም እንኳ ቤተ-መንግሥቱ ምንም መረጃ ላለመስጠት አስቦ የነበረ ቢሆንም ዘ ሰን የተሰኘው ጋዜጣ ያወጣው ፅሑፍ ነው የቤተ-መንግሥቱን ሰዎች መረጃ እንዲያወጡ ያስገደዳቸው። ንግሥቲቱ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በርካታ ቦታዎችን እየተዘዋወሩ ሲጎበኙ፤ የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲታደሙ ነበር የከረሙት። የንግሥት ኤልዛቤት የዕለተ ከዕለት ተግባር መመዝገቢያ እንደሚያሳየው በፈረንጆቹ የጥቅምት ወር ብቻ 16 ዝግጅቶችን ታድመዋል። ይህ ወደ ሰሜን አየርላንድ ሊያደርጉ ያሰቡትን ጉብኝት ሳይጨምር ነው። ቤተ-መንግሥቱ እንዳለው ንግሥቲቱ ወደ ሰሜን አየርላንድ ለማድረግ ያሰቡት ጉብኝት አለመሳካቱ ቢያበሳጫቸውም የዶክተር ምክርን ሰምተው ዕረፍት እያደረጉ ይገኛሉ። ንግሥቲቱ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚካሄደው የግላስጎው የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-58991734 +health ኮሮናቫይረስ ፡ በእንግሊዝ ለበርካታ ሕዝብ የኮቢድ-19 ክትባት የሚሰጡ ማዕከላት ሊከፈቱ ነው "እንግሊዝ በመላው አገሪቱ በሰባት ቦታዎች ላይ በሚቋቋሙ የኮሮናቫይረስ የክትባት መስጫ ማዕከላት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን ልትከትብ መሆኑን አስታወቀች። የእንግሊዝ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት በዚህ ሳምንት ተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትንም ይከፈታል ተብሏል። መንግሥት በየካቲት ወር አጋማሽ ላይ እድሜያቸው ከ70 ዓመት በላይ የሆኑ፣ የጤና ሠራተኞች እንዲሁም ተያያዥ የጤና ችግር ያለባቸውን በመላዋ ዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ 15 ሚሊዮን ሰዎችን ያህል ሰዎች ለመከተብ እቅድ ይዟል። የጤና ሚኒስትሩ ማት ሐንኮክ የመንግሥትን የክትባት አሰጣጥ እቅድ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ሚኒስትሩ ""ይህ ምክረ ሃሳብ ከወረርሽኙ ለመውጣት የመሰረት ድንጋይ የምንጥልበት ነው"" ብለዋል። መንግሥት በየቀኑ ለምን ያህል ሰዎች ክትባቱን እንደሰጠ የሚያሳይ አሃዛዊ መረጃም ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ሃንኮክ እሁድ እለት እንዳሉት በዩናይትድ ኪንግደም 2 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ተከትበዋል። በእንግሊዝ በየቀኑ ወደ 200 ሺህ ያህል ክትባቶች መስጠት ተችሏል። ዩናይትድ ኪንግደም ወረርሽኙ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ 80 ሺህ ያህል ሰዎችን በተህዋሲው ምክንያት አጥታለች። በአገሪቱ ከፍተኛ በተህዋሲው የተያዙ ሰዎች የሚገኙባት ከተማ ሱሬይ ስትሆን፣ በከተማዋ ጊዜያዊ የቀብር ማስፈፀሚያ ቢሮ በሆስፒታል ውስጥ እንዲከፈት ተደርጓል። ይህ የሆነው የቀብር አስፈጻሚዎች ከአቅማቸው በላይ የሆነ አስከሬኖችን መቀበላቸው ከተሰማ በኋላ ነው። ቢያንስ 200 አስከሬኖች ከዚህ ቀደም የጦር ኃይሉ ሆስፒታል በነበረበት ስፍራ በጊዜያዊነት የተቀመጡ ሲሆን፣ ተመሳሳይ ጊዜያዊ ማቆያ በቅርቡ እንደሚከፈት የአካባቢው አስተዳደር ለቢቢሲ ገልጿል። ቅዳሜ እለት ሳይንቲስቶች እጅግ ጥብቅ የሆነ የእንቅስቃሴ ገደብ በእንግሊዝ ያስፈልጋል ሲሉ ምክራቸውን ሰጥተዋል። የጤና ሚኒስትሩም የአገሪቷን ሕዝቦች የተቀመጠውን የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲያከብሩ ተማጽነዋል። ሃንኮክ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ""ሁልጊዜ ገደቡን ባላላን ቁጥር ውጤቱ የከፋ ነው የሚሆነው"" ሲሉ ተደምጠዋል። አክለውም ""እንደ ማኅበረሰብ በጋራ ልናደርግ የምንችለው በየቤታችን መቆየት ነው"" ብለዋል። በእንግሊዝ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዲወጡ የሚፈቀደው ምግብ ለመግዛት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ወይንም ከቤታቸው ሆነው መስራት ለማይችሉ ወደ ሥራቸው ለመሄድ ብቻ ነው። ተመሳሳይ ሕግ በስኮትላንድ፣ በዌልስ እንዲሁም በሰሜን አየር ላንድም ተጥሏል። የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ ጤና አገልግሎት የሚሰጠው ይህ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት በታሪኩ ትልቁ ነው ተብሏል። ክትባቱ በቤት ውስጥ እንክብካቤ ለሚያገኙ አዛውንቶች፣ እስከ ጥር ወር አጋማሽ ድረስ ተሰጥቶ ያበቃል የተባለ ሲሆን፤ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰቡ ክፍሎች ደግሞ እስከ የካቲት ወር አጋማሽ ድረስ የሚሰጥ ይሆናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55614498 +sports 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፡ የእኛ ሠው በዶሃ "ቀድሞኝ ዶሃ የከተመው የሥራ ባልደረባዬ አንድ መልዕክት ስልኬ ላይ አኖረልኝ። 'ልብስ ይዘህ እንዳትመጣ' የሚል። መጀመሪያ መልዕክቱ ፈገግ አሰኘኝ። የወዳጄ መልዕክት ቀጭን ትዕዛዝ መሆኑ የገባኝ የዶሃን አየር ፀባይ በተመለከተ መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ድረ ገፆች ጎራ ባልኩበት ጊዜ ነው። ሃማድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንኳን እኔ 'ሦስተኛ ዓለም' ከሚሉት ቀጠና የመጣ ይቅርና አሜሪካውያንና እንግሊዛዊያንን በአግራሞት አፍ ያስከፍታል። እንዴት ያን የሚያክል ህንፃ እንደ ቤተ-መቅደስ በመልካም መዓዛ ይታወዳል? ሀሉም ነገር ተብለጨለጨብኝ። • በቤተ መንግሥት ግቢ የተገነባው አንድነት ፓርክ በውስጡ ምን ይዟል? • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ ዶሃ የገባሁት ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ ነበር። ቪዛና ሌሎቹ ኮተቶቼን አጠናቅቄ ከአየር መንገድ ስወጣ 2 ሰዓት ገደማ ሆኗል። ልክ ከአየር መንገዱ ስወጣ የተቀበለኝ ጥፊ ነው። አዎ ጥፊ! ወበቁ ይጋረፋል። ያስደነግጣል። ""ለዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነው የመጣኸው?"" አንድ በደንቡ የለበሰ ሰው ጠየቀኝ። ""አዎ!""። ""በል ተከተለኝ"" . . . ምን አማራጭ አለኝ. . . በፈገግታ የተሞላው ቃጣሪ [የኳታር ዜጋ] ለአንድ ሕንዳዊ አቀበለኝ። ""ጌታዬ፤ ወደ ሆቴል ነው ወደ ስታድዬም?""። ኧረግ 'ጌታዬ'፤ ኧረ ልጅ ዓለም በለኝ ልለው አሰብኩና ከአፌ መለስኩት። የሆቴሌን ስም የነገርኩት ሕንዳዊ ሹፌር ሻንጣዎቼን የመ��ናው ሳንዱቅ ውስጥ ጨምሮ ጉዞ ጀመርን። • በበዴሳ ከተማ ታዳጊውን ለመታደግ የሞከሩ 4 ሰዎች የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ ልክ ወደ መኪናዋ ስዘልቅ የተሰማኝ ቅዝቃዜ. . . የሆነ ነገር አንቆኝ ስታገል ቆይቼ በስተመጨረሻ የተገላገልኩ ያክል ተሰማኝ። የዶሃ መለያዋ ምንድነው? ቢሉ ሰው ሰራሽ ማጤዣዋ [ኤሲ] እልዎታለሁ። ከኤርፖርት ወደ ሆቴል የነበረውን ጉዞ በሕንፃዎች መካከል እየተሹለኮለክን አለፍነው። የሕንፃ ጫካ አይቶ፤ 'ቬጋስ ተንቆጥቁጣ' ሲል ያቀነቀነው ዘፋኝ ዶሃን አላያትም ማለት ነው? እያልኩ ወደ ማረፊያዬ ደረስኩ። ኤሲ፣ ኤሲ፣ ኤሲ. . . ኑሮ በዶሃ በኤሲ የተቃኘ ነው። ወደ መኪና ሲገቡ ኤሲ፤ ወደ መገበያያ ሥፍራ ሲገቡ ኤሲ. . . ሌላው ቀርቶ 50 ሺህ ውጦ አላየሁም የሚለው ኻሊፋ ዓለም አቀፍ ስታድዬም ኤሲ ተገጥሞለታል። ለ50 ሺህ ሰው አየር ማቀዝቀዣ! የምዕራብ እስያዊቷ ሃገር ኳታር የሕዝብ ቁጥር 2.8 ሚሊዮን ይገመታል። ከዚህ ውስጥ አረብ ወይም ቃጣሪ ተብለው የሚጡት የአገሪቱ ዜጎች 15 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ሲነገር፤ የተቀሩቱ ከሌሎች አገራት የመጡ ዜጎች ናቸው። የሕንድ፣ ኔፓል፣ እና ፊሊፒንስ ዜጎች ኳታርን ሞልተዋታል። በንጉሳዊ አገዛዝ የምትተዳደረው ኳታር በዓለም ሦስተኛዋ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት ያለባት አገር ነች። የዜጎቿ የነብስ ወከፍ ገቢም በዓለም አሉ ከሚባሉት የሚመደብ ነው። ዶሃ ውስጥ ያለ ፓስፖርት ወይም ሕጋዊ ማስረጃ መንቀሳቀስ ቀላል አይደለም። ይህንን ስል በየመንገዱ ፖሊስ እያስቆመ 'ፓስፖርት ወዲህ በል' ይላል ማለቴ አይደለም። ዶሃ የመጀመሪያ ተግባሬ የነበረው ሲም ካርድ ማውጣት ነበር። ወደ አንዱ የቴሌኮም ድርጅት ሄጄ ሲም ካርድ ፈልጌ ነው አመጣጤ ማለት፤ 'ፓስፖርት እባክዎን ጌታዬ'፤ ኧረ ልጅ ዓለም ይበቃል. . .አሁንም በውስጤ። ሰውዬው ፓስፖርቴን ከተቀበለ በኋላ ወደ አነስተኛ ማሽን ሲያስጠጋት ሚስጥሬ ሁሉ ስክሪኑ ላይ ተዘረገፈ። የትውልድ ቀንና ቦታ፤ ለምን ያህል ጊዜ ዶሃ እንደመጣሁ. . . • ስቶርምዚ በካምብሪጅ የጥቁር ተማሪዎች ቁጥር እንዲጨምር አስተዋፅኦ አድርጓል ተባለ ቀጣይ ተግባሬ ደግሞ ዶላር ወደ ኳታሪ ሪያል መመንዘር። እዚህም ያስተናገደኝ ሰው ፓስፖርቴን ለአንድ ማሽን ቢያቀብል ሙሉ መረጃዬ ተዘረገፈ። አንድ ዶላር በ3 ሪያል ሂሳብ መንዝሬ ሳበቃ የዶሃ መንግሥት እንዴት የዜጎቹን ሚስጥር እንደሚቆጣጠር እየገረመኝ ሹልክ አልኩ። ዶሃ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎች ጥያቄ ይወዳሉ። በተለይ ሕንዶችና እና ኔፓሎች። ጋዜጠኛ እኔ ሳልሆን እነሱ ነበር የሚመስሉት። ታዲያ ጨዋታቸው ደስ ይላል። 'ከየት ነው የመጣኸው?' የሁሉም ጥያቄ ነች። ከዚህ ነው የመጣሁት፣ አመጣጤ ደግሞ ለዚህ ነው. . . እኔም መልሴን አዘጋጅቼ መጠባበቅ ያዝኩ። ከሆቴል ወደ ስታድዬም መሄድ ነበረብኝና 'ኡበሬን' መዥረጥ አድርጌ ታክሲ ብጠራ ፀጋይ ከች። የአገር ሰው መቼም የሃገር ነው ብዬ ተንገብግቤ ነበር ፀጋይ 'ሰላም ነህ ወንድሜ?' ስል እጄን የሰጡት። ፀጋይ አማርኛ ሁለተኛ ቋንቋው እንደሆነ ቢያሳብቅም አቀላጥፎ ይናገራል። ፀጋይ ኤርትራዊ ነው። ዶሃ ከከተመ በርካታ ዓመታት ሆነውታል። ባለቤቱና ልጆቹ ኑሯቸው አስመራ ነው። በዓመትም ይሁን በሁለት እየተመላለሰ እንደሚጎበኛቸው አጫወተኝ። ታድያ ኑሮ በዶሃ እንዴት ነው?፤ ""ይገርምሃል እኔ ዶሃን በደንብ ነው የማውቃት። መቼም ቃጣሪዎች በቁጥር ትንሽ እንደሆኑ ታውቃለህ። ግን ገንዘቡ ያለው በእነርሱ እጅ ነው። እዚህ አገር የማታገኘው ዓይነት የውጭ ዜጋ የለም። ከአፍሪቃ እና እስያ ሃገራት የሚመጡት ተውና ከአሜሪካ እና ከአውሮጳ ሳይቀር እዚህ መጥተው የሚሠሩ ብዙ ናቸው።"" • የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተዘረፈው ዘውድ ይመለስልኝ እያለች ነው ፀጋይ የማይጠገብ ጨዋታውን እየመገበኝ ስታድየም ደረስን። ስልክ ተለዋውጠን ተለያየን። ከዚያ ቀን በኋላ ወደ ምፈልገበት ቦታ ሲያደርሰኝ የነበረው ፀጋይ ነበር። ጨዋታው የሚጠገብ አይደለም። ስለ ዶሃ ብዙ አጫወተኝ። አንገቴን እስኪያመኝ ቀና ብዬ የማያቸው መጨረሻ የሌላቸው ሕንፃዎችን ከነስማቸው እየዘረዘረልኝ ጉዞዬን አሰመረው። ""እዚያ ጋር ይታይሃል? ፎቶ እና ቪድዬ ማንሳት ክልክል ነው የሚል የተለጠፈበት አጥር?""። ወደ ጠቆመኝ ቦታ እየተመለከትኩ ጭንቅላቴን በአዎንታ ወዘወዝኩ። ""የአልጃዚራ ዋና መሥሪያ ቤት ነው። ገና ምኑን አይተህ፤ መጨረሻ የለውም።"" እውነትም መጨረሻ የለውም። በዶሃ ቆይታዬ ፖሊስ ያየሁት ስታድየም ዙሪያ ብቻ ነው። ዶሃ ተፈልጎ የማይገኘው ሌላው የትራፊክ አደባባይ ነው፤ አዎ! አደባባይ። ብዙዎቹ መንገዶቹ ማሳለጫቸው መስቀለኛ ነው። በአቅጣጫ ጠቋሚ የትራፊክ መብራቶች ተሞልተዋል። ታዲያ፤ መሽቷል፣ አልያም ትራፊክ የለም በሚል ተልካሻ ምክንያት መብራት መጣስ ጣትን ወደ እሳት እንደመስደድ ነው። አንድ ጋናዊ ሹፌር እንደነገረኝ የትራፊክ መብራት መጣስ እስከ 6000 የቃጣር ሪያል ያስቀጣል። ወደ 59 ሺህ ብር ገደማ ማለት ነው። ተሽከርካሪዎች ጥፋት መፈፀም አለመፈፀማቸውን መርምረው የሚያሳብቁ ካሜራዎች በየቦታው ተተክለዋል። ""እያየህ ግባበት ነው"" ያለው ፀጋይ ወዶ አይደለም። • ግብጽ በአባይ ላይ ያለኝን መብት ለመከላከል ኃይሉም ቁርጠኝነቱም አለኝ አለች ፀጋይም ሆነ ሌሎች ያጋጠሙኝ አሽከርካሪዎች እንዲሁም የዶሃ ነዋሪዎች በአንድ ጉዳይ ይስማማሉ። ዶሃ ለኑሮና ሥራ ምቹ ናት። ዋናው ነገር ሕጉን ማክበር ነው። ሕግ ጥሰው የተገኙ እንደሆነ የፀጥታ ሰዎች ካሉበት መጥተው ነው የሚለቅምዎት ሲሉ ብዙዎች ያስረዱኝ። ዶሃ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን እንዳሉ ፀጋይ አጫውቶኛል። እኔም ወዲያ ወዲህ ስቅበዘበዝ ያገኘኋቸው እና ለሰላምታ የተጠመጠምኩባቸው የዶሃ ምድር ይቁጠራቸው። ኳታር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 25 ሺህ ይገመታል። ይህም የጠቅላላው ሕዝብ ቁጥሩን 0.8 በመቶ ድርሻ ይይዛል። በቤት ሠራተኝነት የተሰማሩ፣ አሽከርካሪዎች፣ የጥበቃ ሠራተኞች. . . እንዲሁም ሌሎች የሥራ መስኮች ኢትዮጵያውያን ተሠማርተው ኑሯቸውን የሚገፉባቸው መስኮች ናቸው። ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን 'ፕሮፌሽናል' ተብለው የሚጠሩ የሥራ መስኮችም ውስጥ ተሰማርተው ይገኛሉ። እርግጥ ነው የአትሌቲክስ ቡድናቸውን ለመደገፍ ኻሊፋ ስታድየም የተገኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በርካታ ነበር። በባንዲራ ጉዳይ ጎራ ከፍለው ቢቀመጡም። ምን ያህል ኤርትራውያን ኳታርን መጠለያቸው እንዳደረጉ ግን ውል ያለው መረጃ የለም። ፀጋይ፤ ቢበዛ 5 ሺህ ገደማ ብንሆን ነው ሲል አጫውቶኛል። • ""ምን ተይዞ ምርጫ?"" እና ""ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ"" ተቃዋሚዎች እንደው አንድ ቀን የቡና ጥም ከዶሃ ሙቀት ጋር ተቀላቅሎ ቢያንገላታኝ ስታርባክስ የተሰኘ ቡና መሸጫ ሱቅ ገባሁ። ታዲያ ከፊት ለፊት የተቀበለኝ ኢትዮጵያ የሚል ስም ደረቱ ላይ የለጠፈ የታሸገ ቡና ነው። ጀበናችንም ከረጢቱ ላይ ተስላ ትታየኛለች። ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ኮለምቢያ አለች። በገዛ ቡናችን እንደባይተዋር ተሰልፌ ተራዬ ሲደርስ ሸምቼ ወንበሬን ስቤ ተቀመጥኩ። አንድ 'ሱፐርማርኬት' ገብቼ ቡናዎች ከተደረደሩበት ሥፋራ ባቀናም የኢትዮጵያ ስም የተለጠፈበት አንድ እሽግ አይቻለሁ። የሚደንቀው ነገር የኢትዮጵያን ስም እንደ ታርጋ የሚጠቀሙት እኒህ እሽግ ቡናዎች ዋጋቸው ከሌሎቹ ወደድ ያለ መሆኑ ነው። ምናልባት እኔ ነገሮች ተመቻችተውልኝ ��ለጎበኘኋት ይሆን? ብቻ ዶሃ አትጠገብም። ጊዜ ቢያጥረኝ እንጂ ከእግር እስከ ራሷ ብጎበኛት ደስታዬ ወደር አልነበረውም። በቻልኩት መጠን ግን በርካታ ሥፍራዎችን ሲቻል ወደ ውስጥ ዘልቄ ሳይሆን ሲቀር ከቅርብ ርቀት ማየት ችያለሁ። የዶሃ ቅርሶች አብዛኛዎች ሰው ሰራሽ ናቸው። ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች፣ የሕንድ ውቅያኖስ ላይ የተንሳፈፉ ሆቴሎች፣ ሌላው ቀርቶ ሰው ሰራሽ ደሴቶችና ጫካዎች የከበቧት ናት፤ ዶሃ። • በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ ቃጣሪዎች ዶሃ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ ማሳያዎች ብዙዎች ናቸው። ከብዙ ሃገራት ተቃውሞ ቢገጥመውም የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበራት ፌዴሬሽን የዘንድሮውን ውድድር ከማምጣት አልተቆጠበም። በገንዘብ ገዙት እንጂ እንዴት በዚህ በረሃ ላይ የሩጫ ውድድር ይካሄዳል እያሉ ሃሜት እና ምሬት ሲያሰሙ ያደመጥኳቸው አሉ። ነገር ግን ኳታር ዝግጅቱን በድል ጀምራ በድል አጠናቃዋለች። የመጀመሪያዎቹ ቀናት የተመልካች ድርቅ መቶት የነበረው ግዙፉ ስታድየማቸው እያደር ደምቆላቸዋል። አሁን ሁሉም 2022ን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ናቸው። የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን። 'ገንዘብ ካለ. . . 'የሚለውን አባባል እውን ያደረጉት ቃጣሪዎች የሚሳናቸው ያለ አይመስልም።" https://www.bbc.com/amharic/news-50020788 +politics በኬንያ ፖለቲከኞች ለድምጽ ሰጪዎች ጉቦ እየሰጡ የገንዘብ እጥረት አጋጠመ በኬንያ ምርጫ ዕጩዎች የመራጮችን ድምጽ ለማግኘት ጉቦ እየሰጡ በመሆናቸው የ100 እና የ200 ሽልንግ የገንዘብ ኖቶች እጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ። በኬንያ ባንኮች የ100 እና 200 ሽልንግ [የኬንያ ገንዘብ] ኖት እጥረት ያጋጠመው ፖለቲከኞች ለመራጮች ጉቦ እየከፈሉት መሆኑን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፍሬድ ማቲያንጊ ተናግረዋል። ኬንያ ነሐሴ 03/2014 ዓ.ም. ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ በአገሪቱ በሚካሄዱ ምርጫዎች ዕጩዎች የመራጮችን ድምጽ በገንዘብ የመግዛት ሪፖርት አዲስ አይደለም። ፍሬድ ማቲያንጊ “ገንዘብ በቦርሳ የያዙ ሰዎች መንገድ ላይ ተሰልፈው ለሚገኙ ዜጎች 200 ሽልንግ ሲሰጧቸው ሳትመለከቱ አይቀርም” ማለታቸውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል፣ ኤኤፍፒ ዘግቧል። ሚኒስትሩ ቀጣዩ የአገሪቱ ፓርላማ በሕገ-ወጥ መንገድ በተገኘ ገንዘብ የመራጮችን ድምጽ ገዝተው ወንበር በያዙ ፖለቲከኞች ሊሞላ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የኬንያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን መደጋፍ በሚመለከት መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ባደረጉበት ወቅት፤ መሰል የፖለቲከኞች ተግባር አገሪቱ በሙስና ላይ እያካሄደች ያለውን ጦርነት አደጋ ውስጥ የሚጥል ነው ብለዋል። ፍሬድ ማቲያንጊ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦች ሥልጣን ቢጨብጡ እራሳቸውን ለመከላከል ሲሉ የአገሪቱን ሕግ እና መመሪያዎችን ሊቀይሩ ይችላሉም ብለዋል። በኬንያ ከዚህ ቀደም በነበሩ ምርጫዎች ዕጩዎች ለመመረጥ ከሚያስተዋውቋቸው ርዕዮተ ዓለሞች ይልቅ ዝናቸው እና ለምርጫ ወጪ የሚደርጉት የገንዘብ መጠን በውጤት ላይ ለውጥ ያመጣል። ከ22 ሚሊዮን በላይ መራጮች ለተመዘገቡበት ምርጫ ማስፈጸሚያ ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር 400 ሚሊዮን ዶላር በጀት መድባለች። ይህ ገንዘብ ከሌሎች አገራት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው ተብሏል። ኬንያውያን ከሳምንት በኋላ ለሁለት የሥልጣን ዘመናት አገሪቱን ያስተዳደሩትን ኡሁሩ ኬንያታን የሚተካ አዲስ ፕሬዝዳንት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን እና የግዛት አስተዳዳሪዎችን ይመርጣሉ። ኬን���ን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት በምክትል ፕሬዝዳንቱ ዊሊያም ሩቶና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ መካከል ጠንካራ ፉክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cq5vdxky4qyo +health በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ6 ሺህ በላይ ሆነ በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ስድስት ሺህ ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ባለፉት ጥቂት ወራት በአገሪቱ ውስጥ በወረርሽኙ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአሳሳቢ ሁኔታ መጨመሩን በየዕለቱ የሚወጣው መረጃ የመለክታል። የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ እንደተናገሩት በኮሮናቫይረስ ተይዘው ለሞት ከተዳረጉት ሰዎች መካከል ሁሉም በሚባል ደረጃ ያልተከተቡ ናቸው። በአገሪቱ ውስጥ ከሰኔ ወር አጋማሽ ጀምሮ እሰከ ነሐሴ ወር አጋማሽ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በወረርሽኙ ከሞቱ ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ ብቻ የመጀመሪያውን የኮቪድ መከላከያ ክትባት የወሰደ ሲሆን ሌሎቹ በሙሉ ያልተከተቡ መሆናቸው ተገልጿል። በኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ወደ ሦስት ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች መከላከያ ክትባቱን ማግኘታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል። በሽታው በአገሪቱ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ ጊዜ ጀምሮ ለሞት የተዳረጉ ሰዎች አሃዝ አስከ ትላንት ድረስ ከስድስት ሺህ በታች የነበረ ሲሆን ሰኞ ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም 36 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 6026 ደርሷል። የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበሽታው የሚያዙ፣ በጽኑ የሚታመሙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ለመጨመሩ በአገሪቱ ውስጥ አደገኛው የዴልታ ዝርያ መኖሩ፣ በአንድ ስፍራ በብዛት የሚደረጉ መሰባሰቦችና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን ጨምሮ የበሽታውን የመከላከያ መመሪያዎች በአግባቡ ተግባራዊ አለማድረግ ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ጨምረውም በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑንና ባለፈው ሳምንት ብቻ 308 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ይህም ወረርሽኙ ከበኢትዮጵያ ከተከሰተ በኋላ ከፍተኛው የሞት አሃዝ ሆኖ እንደተመዘገበ ሚኒስትሯ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በየዕለቱ በአማካይ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ የሚረጋገጥ ሲሆን፤ ባለፈው ሳምንት በየቀኑ በአማካይ 44 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል። በአገሪቱ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ምረመራ መደረግ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ አስከ ትናንት ድረስ 3,557,710 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው በ355,001ዱ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ከእነዚህ ውስጥም 324,450ው ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን 6,026ቱ ደግሞ ህይወታቸው ማለፉንም የጤና ሚኒስቴር አመልክቷል። https://www.bbc.com/amharic/news-58858520 +politics ጆ ባይደን የካፒቶል ሒል ነውጠኞችን እና ትራምፕን አወገዙ "ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የካፒቶል ሒል ነውጠኞችን እና አውራቸውን ዶናልድ ትራምፕን አወገዙ። ፕሬዝዳንቱ በካፒቶል ሒል ቅጥር ባደረጉት ንግግር ነውጠኞቹ ‹የአሜሪካን ዲሞክራሲ ጉሮሮ ላይ ቢላ የሰነቀሩ› ሲሉ በጠንካራ ቃላት አውግዘዋቸዋል። የባይደን ንግግር በቀጥታ ለሰፊው የአሜሪካ ሕዝብ ተላልፏል። ጆ ባይደን የጥር 6 የካፒቶል ሒል አመጽን አንደኛ ዓመት መታሰቢያን በማስመልከት ነው ይህን ንግግር ያደረጉት። የዶናልድ ትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ልክ የትናንትና አንድ ዓመት ነበር የአስተዳደር ሕንጻና የሕዝብ እንደራሴዎች መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚገኝበትን፣ የአሜሪካ የዲሞክራሲ ምልክት ተደርጎ የሚታየውን ካፒቶል ሒልን በኃይል በመውረር ያልታሰበ ጥቃት የፈጸሙት። በወቅቱ የአሜሪካ የሕዝብ እንደራሴዎች የጆ ባይደንን ምርጫ ለማጽደቅ ሸንጎ ላይ ነበሩ። ይህ ዓይነቱ ክስተት በአሜሪካ ምድር ይሆናል ተብሎ ያልተጠበቀ ስለነበረ ድርጊቱ ዓለምን አስደንግጦ ነበር። ትናንት ሐሙስ ጆ ባይደን ንግግራቸውን ካደረጉ ከሰዓታት በኋላ ተቀዳሚያቸው የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ ቁጣ የተቀላቀለበት የመልስ መግለጫ አውጥተዋል። የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ይህን ትራምፕና ነውጠኛ ደጋፊዎቻቸው ፈጸሙት በሚባለው ያልተገባ ድርጊት ለማውገዝ፣ ዕለቱንም ለማሰብ የተለያዩ የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓቶችን አዘጋጅተዋል። በርካታ የሕዝብ እንደራሴዎችም ዕለቱን ለማሰብ በሚዘጋጁ መሰናዶዎች በዕለቱ ያዩትን እና የታዘቡትን ለሕዝብ ያጋራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተዋቀረው ሀቅ አፈላላጊ ቡድን በዚህ ዕለት የዛሬ ዓመት በትክክል ምን እንደተፈጠረና ማንስ ተጠያቂ መደረግ እንዳለበት አሁንም እየመረመረ ይገኛል። እስከ አሁን 700 የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። በዚህ በጠንካራ ቃላት በታጀበው የትናንቱ የመታሰቢያ ንግግራቸው ጆ ባይደን ትራምፕን ‹በአፍቅሮተ- ራሰ የተሞላ ሰውዬ› ሲሉ አብጠልጥለዋቸዋል። ""እሱ ከአሜሪካ ዲሞክራሲ ይልቅ ግድ የሚለው የራሱ አለልክ የተወጠረ ምሥለ-ራስ ነበር፤ ይህ ምሥለ ራስ ደግሞ በሽንፈቱ የተነሳ ቆስሎ ነበር"" ሲሉ ዶናልድ ትራም ያን አመጽ የቀሰቀሱት በራስ ወዳድነትና አልሸነፍ ባይነት የተነሳ እንደሆነ አመላክተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/59905057 +sports የዓለም ዋንጫ፡ አርጀንቲና ወደ ቀጣዩ ዙርፍ ስታልፍ ያሸነፈቻት ሳዑዲ በጊዜ ተሰናብታለች አርጀንቲና በኳታር የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታ የደረሰባትን ሽንፈት በመቀልበስ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ችላለች። የሊዮኔል ሜሲ ሃገር ምድቡን በአንደኝነት በመምራት ጭምር ነው ለማለፍ የቻለችው። አርንጀንቲና ትላንት ምሽት ፖላንድን 2 ለ 0 በማሸነፍ ነው ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፈችው። አርጀንቲና አወዛጋቢ በሆነ ሁኔታ ያገኘችውን ፍጹም ቅጣት ምት አምበሉ ሊዮኔል ሜሲ ሳይጠቀምብት ቀርቷል። ማክ አሊስተር አርጀንቲናን ቀዳሚ የምታድርገውን ጎል በ46ኛው ደቂቃ አስቆጠረ። አልቫሬዝ ደግሞ ሁለተኛዋን ኳስ ከመረብ አሳርፏል። በሌላ የምድቡ ጨዋታ አርጀንቲናን በማሸነፍ ድንቅ አጀማመር ያደረገችው ሳዑዲ አረቢያ ፍጻሜዋ አላማረላትም። በሜክሲኮ 2 ለ 1 ተሰንፋለች። ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ተጭና የተጫወተችው ሜክሲኮ የበላይ ለመሆን ችላለች። ሄነሪ ማርቲን የመጀሪያዋን ጎል በ47ኛው ደቂቃ አስቆጠረ። ሊዊስ ቻቬዝ ደግሞ ሌላኛዋን ጎል ለሜክሲኮ አስቆጥሯል። ጨዋታው በዚሁ ውጤት ተጠናቀቀ ሲባል ሳዑዲ ባለቀ ሰዓት በሳሌም አል ዳውሳሪ አንድ ጎል አስቆጥራለች። አርጀንቲና ምድቡን በስድስት ነጥብ አንደኛ በመሆን አጠናቃለች። ፖላንድ እና ሜክሲኮ አራት አራት ነጥብ ቢይዙም በጎል ክፍያ ፖላንድ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። ሳዑዲ አርጀንቲናን በማሸነፍ ባገኘችው ሦስት ነጥብ ምድቡን በአራተኝነት አጠናቃለች። በምድብ አራት ደግሞ ቱኒዝያ ፈረንሳይን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች። በርካታ የመጀመሪያ ተሰላፊ ተጫዋቾቿን ቀይራ ወደ ሜዳ የገባችው ፈረንሳይ በቱኒዝያ ተሸንፋለች። ዋህቢ ካዚ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ያሳረፈ ተጫዋች ሆኗል። ፈረንሳይ ቋሚ ተጫዋቾቿን ቀይራ ውጤቱን ለመቀልበስ ብትሞክርም አልተሳካላትም። አንቶኒ ግሪዝማን ባለቀ ሰዓት ያስቆጠራት ጎል ከጨዋታ ውጭ በመሆኑ ተሽራለች። ድሉ በርካታ በፈረንሳይ የተወለዱ ተጫዋቾችን ላሰለፈችው ቱኒዝያ ጣፋጭ ሆኖ አምሽቷል። በሌላ የምድቡ ጨዋታ አውስትራሊያ እና ዴንማርክ ተገናኝተዋል። አውስትራሊያ በ60ኛው ደቂቃ በማቲው ሌኪ ብቸኛ ጎል ለማሸነፍ ችላለች። ከምድ��� ቀድማ ማለፏን ያረጋገጠቸው ፈረንሳይ በስድስት ነጥብ አንደኛ ለመሆን በቅታለች። ትላንት ያሸነፈችው አውስትራሊያ በተመሳሳይ ስድስት ነጥብ ሁለተኛ ሆና ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋግጣለች። ቱኒዝያ በአራት ነጥብ ሦስተኛ ስትሆን ዴንማርክ በአንድ ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ሆነው ጨርሰዋል። በጥሎ ማለፉ የምድብ ሦስት እና አራት ቡድኖች የሚገናኙ ይሆናል። አርጀንቲና ከአውስትራሊያ ቅዳሜ ምሽት ትጫወታለች። ፈረንሳይ ደግሞ ፖላንድን እሑድ ታስተናግዳለች። የምድብ አምስት እና ስድስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይከናወናሉ። 12፡00 ሰዓት ላይ ክሮሽያ እና ቤልጂየም እንዲሁም ካናዳ እና ሞሮኮ ይገናኛሉ። ምድብ ስድስትን ክሮሺያ በአራት ነጥብ ትመራለች። ሞሮኮ በተመሳሳይ አራት ነጥብ ሁለተኛ ናት። ቤልጂየም ሦስት ነጥብ ሲኖራት ካናዳ ያለምንም ነጥብ በምድቡ ግርጌ ላይ ትገኛለች። ክሮሺያ፣ ሞሮኮ እና ቤልጂየም ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋ አላቸው። ምሽት 4፡00 ሰዓት ደግሞ ጃፓን ከስፔን እንዲሁም ኮስታሪካ ከጀርመን ይጫወታሉ። ምድብ አምስትን ስፔን በአራት ነጥብ ትመራለች። ጃፓን እና ኮስታሪካ አራት አራት ነጥብ አላቸው። ጀርመን በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛለች። የዚህ ምድብ አራቱም ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋ አላቸው። https://www.bbc.com/amharic/articles/clkzl9zjrzno +business የውጭ ባንኮች መግባት አገር በቀል ባንኮችን ያከስማቸዋል? ለተጠቃሚውስ ምን ይዞ ይመጣል? የኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ለውጭ አገር ባንኮች አዲስ አይደለም። ባንኮ ዲ ሮማ እና አቢሲኒያ ባንክን መጥቀስ ይቻላል። ቢሆንም ላለፈው ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የኢትዮጵያ ገበያ እንደ ባንክ እና ቴሌኮም ያሉ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ለውጭ አገር ኢንቨስተሮችና ለግል ባለሀብቶች ዝግ አድርጎ ቆይቷል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በፈረንጆቹ 2012 በዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ቀርበው ኢትዮጵያ ባንክ እና ቴሌኮምን “ክፍት የምታደርግበት አቅም የላትም” ሲሉ ጠንከር ያለ ንግግድ አድርገው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ “አይደለም እኛ ልንቆጣጠራቸው፤ ልንረዳቸው የማንችላቸው መሳሪያዎች ነው የሚጠቀሙት። እንዴት ብለን ነው ታዲያ የምንቆጣጠራቸው? አይቻልም፤ አሁን አቅሙ የለንም” የሚል ንግግር አሰምተው ነበር። ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን አቋም የሚደግፉት የመኖራቸውን ያህል ከዓለም ገበያ ተነጥለን መቆየት አንችልም ብለው የሚከራከሩም አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ በመንግሥት እጅ ያሉ ተቋማት ቤቶች ለሽያጭ ሊቀርቡ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተው ነበር። መንግሥት ይህን ለማድረግ የወሰነው ተጨማሪ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እና በግብርና ላይ የተመሰረተው የአገሪቱ ምጣኔ ሐብትን ለማዘመን በሚል እንደሆነ ይነገራል። በተጨማሪም ይህ እርምጃ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በማቀላጠፍ፣ በሥራ ፈጠራ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በማጎልበት ለምጣኔ ሐብት ዕድገት አስፈላጊ ነው ተብሎ ታምኗል። እነሆ የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ አገር ኢንቨስተሮች ክፍት መሆኑን ተከትሎ የባንኩ ኢንዱስትሪ ለውጭ አገር ባንኮች ክፍት እንዲሆን ተወስኗል። ባለፈው የካቲት ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር “ባንኮች በዘመናዊ መንገዶችና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ከዓለም ዕድገት ጋር የሚጓዝ እንዲሁም ከሌሎች አገራት ባንኮች ጋር ለመወዳደር የሚያበቃ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል” ብለው ነበር። ብሔራዊ ባንክ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲያስችለው የባንክ ፖሊሲ፣ ሕግጋት እና ደንቦችን ሲያሻሽል ቆይቷል። ማሻሻያው የውጭ ባንኮች በቅድሚያ በሽርክና ሥራ እንዲጀምሩ የሚያስችል ዝቅተኛ ካፒታል ማዘጋጀትን ያካትታል። ለመሆኑ የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ለአገር በቀል ባንኮች ስጋት ይሆን? ለተጠቃሚውስ ምን ይዘው ይመጣሉ? በርካታ የአፍሪካ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመዝለቅ ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነ የማዕከላዊ ባንክ አስተዳዳሪ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ከወራት በፊት ተናግረው ነበር። ባለፉት ዓመታት የተለያዩ የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ከፍተው የአገሪቷን ገበያ እያጤኑ እንደሆነ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ። ‘ፋርዘር አፍሪካ’ የተባለ ድረገጽ በ2020 ባወጣው መረጃ እ.ኤ.አ ከ2015 ጀምሮ በኢትዮጵያ ዘጠኝ የውጭ ባንኮች ወኪል ጽህፈት ቤት ከፍተዋል። የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ግሎባል ሊቀመንበር ዘመዴነህ ንጋቱ “አዋጁ ትልቅ እርምጃ ነው” ይላሉ። ዘርፉን ክፍት ያደረጉ የሌሎች አገራትን ተሞክሮ ልምድ የሚወጠቅሱት የፋይናንስ ባለሙያው፤ በአጠቃላይ አገራዊ ምርት [ጂዲፒ] ከሰሃራ በታች ከናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጥላ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ ዘርፉ መክፈቷ “ለቢዝነስ ዝግጁ መሆኗን የሚያሳይ ነው” ይላሉ። “የውጭ ባንኮች ሲመጡ ዓለም አቀፍ ልምዳቸውን ይዘው ነው የሚመጡት። የማኔጅመንት [አስተዳደር] ልምዳቸውን፣ ቴክኖሎጂያቸውን፣ እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ይዘው ይመጣሉ። ከውጭ የሚመጣን ኢንቨስተር የማስተናገድ አቅም አላቸው።” ዘመዴነህ ባንኮቹ ለደንበኞቻቸው የሚያቀርቡት አገልግሎትንም እንደ አንድ ጥቅም ያወሳሉ። “ለምሳሌ በአሜሪካ ባንኮች ደንበኞቻቸውን በጣም ይንከባከባሉ። እኛ አገር ተጠቃሚው ባንኩን ለምኖ ነው የሚጠቀመው። የተገላቢጦሽ ነው። የሚያበድሩትም ለተወሰነ ሰው ነው።” የዩናይትድ ኪንግደም የተመሰከረላቸው የሒሳብ አዋቂዎች ማኅበር አባል የሆኑት የማማከር እና ኦዲቲንግ ባለሙያው ጥላሁን ግርማ፣ በተመሳሳይ የውጭ አገር ባንኮች ወደ አገር ቤት መምጣታቸው አንደኛው ጥቅሙ የውጭ ኢንቨስተሮችን መሳባቸው ነው ይላሉ። “በሩ ለውጭ አገር ባንኮች መከፈቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል፤ አዳዲስ የባንክ አገልግሎቶች ለደንበኞች እንዲዳረሱ መንገድ ይፈጥራል፤ የአገር ውስጥ ባንኮች በቂ ፋይናንስ ይሰጡኛል ብለው የማይተማመኑ የውጭ አገር ኢንቨስተሮችን ሊጋብዝ ይችላል።” አማካሪው “ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲቲባንክ አሊያም ስታንዳርድ ቻርደተርድ ቢገባ የውጭ አገር ኢንቨስተሮች ጥናት ሲሰሩ አንደ አንድ መልካም ጎን ያዩታል” ሲሉ ያክላሉ። ነገር ግን አቶ ጥላሁን እንደሚሉት ኢትዮጵያ የባንኩን ኢንዱስትሪ ለውጭ ባንኮች የከፈትችው ከዓለም አቀፍ ተቋማት በደረሰባት ጫና ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ። “የዓለም ንግድ ድርጅት አንደኛው መመዘኛው አገራት የንግድና አገልግሎት መሣለጥን ማገድ የለባቸውም የሚል ነው። ስለዚህ ጫናው በዋናነትነ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማትና ከዓለም ንግድ ድርጅት የመጣ ነው” ሲሉ ይከራከራሉ። ዘመዴነህ፤ ዓለም አቀፍ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ከአገር በቀል ባንኮች ጋር የመሥራት ዕድል ስላላቸው ቴክኖሎጂው ይሸጋገራል ይላሉ። ቢሆንም የሒሳብ አማካሪው ጥላሁን የአገር ውስጥ ባንኮች ከቀድሞው በተሻለ የካፒታልና የቴክኖሎጂ ደረጃ ላይ ቢሆኑም ገና በጣም ብዙ እንደሚቀራቸው ይናገራሉ። ታድያ የኢትዮጵያ የግል ባንኮች ይህንን ፉክክር እንዴት መግጠም ይችላሉ? የውጭ ባንኮች እንዲገቡ መፈቀዱ ለአገር በቀል ባንኮች “መልካም አጋጣሚ” ነው የሚሉት ዘመዴነህ ንጋቱ፣ “የአገር ውስጥ ባንኮች አትራፊ ቢሆኑም በዓለም አቀፍ ደረጃ የመወዳደር ልምድ የላቸውም። እነዚህ የውጭ ባንኮች በሚመጡበት ጊዜ አብረው የመሥራት ዕድል ይኖራቸዋል” የሚል መከራከሪያ ያስቀምጣሉ። መንግሥት አገር በቀል ባንኮች አዲሱን ፖሊሲ ተከትሎ ተፎካካሪ ሆነው መቀጠል የሚሹ ከሆነ መዋሃድ አለባቸው የሚል ሐሳብ ይሰጣል። ዘመዴነህ በዚህ ሐሳብ ይስማማሉ። ለበርካታ ዓመታት ኧርንስት ኤንድ ያንግ ከተሰኘው ኩባንያ ጋር የሠሩት ዘመዴነህ፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ትልቁ የግል ባንክ የሆነው አዋሽ ባንክ በአፍሪካ ደረጃ እንኳ 83ተኛ ደረጃ ላይ ነው የተቀመጠው” በማለት ባንኮች መጣመር እንዳለባቸው ያሰምራሉ። “በዘርፉ ባንኮች የሚኖራቸው አቅም ትልቅ ዋጋ አለው። 18 ባንኮች አሉን፤ በቅርቡ ሦስት፣ አራት ሊጨመሩ ይችላሉ። 10 ገደማ ደግሞ ፈቃድ እየጠበቁ ነው። ይህ ጨርሶ አስፈላጊ አይደለም። በእኔ ግምት የዛሬ አንድ ዓመት ተኩል 5 ትላልቅ አቅም ያላቸው የግል ባንኮች ይኖራሉ።” ባንኮች ቢዋሃዱ የማበደር አቅማቸው ከፍ ይላል፣ ቴክኖሎጂያቸው ያድጋል፣ አልፎም ውጭ ባንኮች ቢመጡም የመቋቋም አቅም ይኖራቸዋል ይላሉ። ናይጄሪያን በምሳሌነት የሚጠቅሱት አማካሪ እና ኦዲተሩ ጥላሁን “መጀመሪያ በውዴታ እንዲዋሃዱ ሊደረግ ይችላል፤ አሊያም አቅም ያለው አቅም የሌለውን ሊጠቀልል ይችላል” የሚል ትንበያ አላቸው። የውጭ ባንኮች ሲገቡ አገር በቀል ባንኮች ሊከስሙ ይችላሉ የሚለውን ስጋት በተመለከተም “የኢትዮጵያ ባንኮች ይጠፋሉ የሚል ግምት የለኝም። ‘ኮርፖሬት’ ደንበኞቻቸውን ይነጠቃሉ? አዎ!” ይላሉ አቶ ጥላሁን። “መሳሳት የሌለብን እነዚህ የውጭ ባንኮች ገጠር ድረስ ዘልቀው በዝቅተኛ ደረጃ [ሪቴይል ባንኪንግ] ይሠራሉ ተብሎ አይታሰብም።” ዘመዴነህ ከባንኮች መዋሃድ በተጨማሪ ‘ጆይንት ቬንቸር’ የተሰኘው የኢኮኖሚ ሥርዓት መተግበር ቢችል አዋጭ ነው ባይ ናቸው። “ለምሳሌ ቻይና መጀመሪያ ባንኮች ሲገቡ ‘በጆይንት ቬንቸር’ እንዲገቡ ነው የፈቀደችው። ይህ ማለት የውጭ ባንኮች የተወሰነ ድርሻ ገዝተው እንዲገቡ ማድረግ ማለት ነው።” ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ባንኮች ድርሻ ገዝተው አብረው መሥራት ቢችሉ የማደግ ጥሩ ዕድል ይኖራቸዋል የሚል ሐሳብ አላቸው። አገር በቀል ባንኮች አይጠፉም ሲሉ የሚከራከሩት ጥላሁን የውጭ ባንኮች ትኩረታቸውን በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች ላይ ስለሚያደርጉ፣ አገር በቀል ባንኮች የተቀረውን ማኅበረሰብ ማገልገል ይችላሉ ይላሉ። “በፖሊሲ ካላስገደድናቸው በቀር ሥራቸውን የሚሠሩት በአንድ ዋና መሥሪያ ቤት፤ የተቀረውን ደግሞ በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር እንጂ፣ እንደኛ ባንኮች በየመንደሩ ቅርንጫፍ ይከፍታሉ ተብሎ አይታሰብም።” አማካሪው ‘ኮርፖሬት ደንበኛ’ የተሰኘውን ሐሳብ ደጋግመው ያነሳሉ። ለመሆኑ ኮርፖሬት ደንበኛ ምን ማለት ነው? “በባንክ ኢንዱስትሪ 20/80 የሚባል ነገር አለ። 20 በመቶው ለባንኮች ትልቅ የውጭ ምንዛሬ የሚያመጡ ናቸው። የውጭ ባንኮች እነዚህን ደንበኞች ለመንጠቅ አሰፍስፈው እንደሚመጡ ምንም ጥርጥር የለኝም። ዒላማቸው ‘ኮርፖሬት’ ደንበኛ ናቸው እንጂ ታች ወርደው ብድር ይሰጣሉ ብሎ ማሰብ ስህተት ነው።” ጥላሁን፤ “ለዚህ ነው ለውድድር እንዲመቻቸው መዋሃድ ይኖርባቸዋል የምለው፤ ብሔራዊ ባንኩም ሰላሳ አርባ ባንክ መቆጣጠር አይጠበቅበትም” ይላሉ። ባለሙያው፤ የብሔራዊ ባንክ የባንኮችን ‘ካፒታል’ አሁን ካለበት በቅርቡ ከፍ ሊያደርገው የሚችል ሲሆን፣ “ይህንን ለማሟላት ደግሞ አገር በቀል ባንኮች ያላቸው አማራጭ መዋሃድ ብቻ ነው።” በምጣኔ ሃብት ጉዳዮች የተለያዩ ጽሑፎችን በማቅረብ የሚታወቁት የኩዌት ኢንስቲትዩት ፎር ሳይንቲፊክ ሪሰርች ተመራማሪው አየለ ገላን (ዶ/ር) የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መፈቀዱን አጥብቀው ከሚቃወሙ መካከል ናቸው። “ይህ ውሳኔ የራስ ምታት ላለበት ሰው የሆድ ቁርጠት መድኃኒት እንደመስጠት ነው” የሚሉት የምጣኔ ሃብት ምሁሩ፣ የባንክ ኢንዱስትሪውን ለውጭ ባንኮች ክፍት ማድረግ “አገር ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘብ አይደለም” ይላሉ። እንደ አየለ ገለፃ የኢትዮጵያ የባንክ እና የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ሁለት ቀንደኛ ችግሮች አሉበት። አንደኛው ‘ስትራክቸራል ኢንባላንስ’ ማለትም ትላልቅ የመንግሥት ባንኮች የሚወዳደሩት ‘ትናንሽ’ ከሚባሉት ጋር መሆኑ ነው ሲሉ ይተነትናሉ። ይህንን ለመፍታት እኒህ ትላልቅ ባንኮች ተከፋፍለው አነስተኛ ባንኮች እንዲሆኑ አሊያም የግል እንዲሆኑ ማድረግ [ፕራይቬታይዝ] ነው እንጂ የውጭ ባንኮችን ማምጣት መፍትሔ አይሆንም ይላሉ። እንደምጣኔ ሃብት ባለሙያው ገለፃ ሁለተኛው የፋይናንስ ዘርፍ ችግር ቁጥጥር (ሬጉሌሽን) ነው። የባንኮችን የብድር የወለድ መጠንን እንደምሳሌ ይጠቅሳሉ። “ከዓለም አገራት በ15 አሊያም በ18 በመቶ የወለድ መጠን ተበድሮ፣ ነግዶ፣ አትርፎ ብድሩን በመመለስ አገር ይለውጣል ማለት ዘበት ነው።» ይህ ችግር የመነጨው የመንግሥት አስተዳደር ውስጥ ያሉ አካላትና የባንክ ባለቤቶች በመስማማት በመወሰናቸው ነው ይላሉ። ነገር ግን ዘመዴነህም ሆኑ ጥላሁን የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የወለድ መጠኑ እንዲቀንስ ያስችላል ሲሉ ይከራከራሉ። “የእነዚህ የውጭ ባንኮች መግባት ሌሎቹን የግል ባንኮች ያነቃል። ለምሳሌ የወለድ ቅናሽ ሊኖር ይችላል” ይላሉ ጥላሁን። እንደ ሌሎች አገራት የብድር ወለድ መጠን ወደ ሰባት እና ስድስት በመቶ መውረድ አለበት ብለው የሚከራከሩት አየለ ገላን (ዶ/ር) ባንኮች ትርፋቸው ሊቀንስ ቢችልም፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከዚህ በፊት መበደር ያልቻሉ ሰዎች የብድር አቅርቦት ያገኛሉ ሲሉ ያስረዳሉ። ባለሙያው መንግሥት የውጭ ባንኮች እንዲገቡ መፍቀዱ ከላይ ከተነሱት ሁለት አበይት ችግሮች ጋር “በፍፁም አይገናኝም” ይላሉ። ተመራማሪው የውጭ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ይዘው ይመጣሉ የሚለውን ሐሳብ አጥብቀው ይተቻሉ። ይህንን ሲያብራሩም “ለዘላቂ ችግር ጊዜያዊ መፍትሔት ማበጀት ፋይዳ የለውም” የሚለውን የፈረንጅ አባባል በማውሳት ነው። “ወደ ሃገር ቤት የሚመጣው ኩባንያ ሲገባ መጀመሪያ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ይዞ ሊመጣ ይችላል። ነገር ግን ሥራ ከጀመረ በኋላ በየወሩ ዶላር ወደ ውጭ ይልካል። ዶላር ወደ ሃገር ቤት የሚመጣ ምርት ወደ ውጭ ስንልክ ነው እንጂ፣ እነዚህ ባንኮች ዶላሩን ወደ አገር ቤት አምጥተው የሚለግሱበት ምንም ምክንያት የላቸውም።” አየለ፤ የውጭ ባንኮች አዳዲስ ቴክኖሎጂ ያስተዋውቃሉ የሚለውን መከራከሪያም “ፎልስ ኢኮኖሚክስ” ነው በማለት ውድቅ ያደርጉታል። “እነዚህ ባንኮች የሚያመጡት ቴክኖሎጂ የሮኬት ሳይንስ አይደለም። ቴክኖሎጂ በሰው አአምሮ ውስጥ እንጂ በባንኮች እጅ አይደለም ያለው። የመኪና መገጣጠሚያ አሊያም የማዳበሪያ ፋብሪካ እናስገባለን ቢሉ ያስማማል” በማለት። የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሲገቡ ምን ዓይነት ቁጥጥር ሊደርግባቸው ይገባል? የሚለው ጥያቄ ሌላኛው መከራከሪያ ነው። “ባፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ አንድም ባንክ አልከሰመም ሲሉ የሚናገሩት ዘመዴነህ ብሔራዊ ባንክ እስካሁን በቁጥጥር ረገድ መልካም ሥራ ሠርቷል ብለው ያምናሉ። “ነገር ግን አሁን የውጭ ባንኮች እየመጡ ስለሆነ ብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር አቅሙን ከፍ ማድረግ አለበት። ምክንያቱም ሃገር በቀል ባንኮችን መቆጣጠር እና በጣም ውስብስብ የሆኑ ዓለም አቀፍ ባንኮችን መቆጣጠር በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው።” ጥላሁንም ‘ኮርፖሬት’ ደንበኛ ላይ አተኩረው ለሚሠሩ ባንኮች የሚሆን አዲስ ቁጥጥር በቅርቡ ሊወጣ እንደሚችል ይገምታሉ። ብሔራዊ ባንክ፤ የውጭ ሃገራት ወደ ሃገር ቤት ሲገቡ “የጤናማ ብድር መጠን ሕጉን ያስተካክላል” ብለው ያምናሉ። ነገር ግን ይላሉ፤ “አሁን እንዲገቡ እንደተፈቀደላቸው ሁሉ ሲወጡ እንዴት ነው የሚለው ሊታሰብበት ይገባል።” “ብሔራዊ ባንክ የሚያወጣቸውን መመሪያዎች መከታተል ይኖርብናል። በየዓመቱ ምን ያክል ገንዘብ ማስወጣት ይችላሉ የሚለው ነገር መመጠን ያለበት ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊያን ድርሻ የሚገዙበትም አግባብ ሊኖር ይገባል።” https://www.bbc.com/amharic/articles/ckv82ekpjk5o +health የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ-19 ለተጨማሪ አንድ ዓመት አብሮን ሊቆይ ይችላል አለ "በመላው ዓለም የሚገኙ ድሃ አገራት የኮቪድ-19 ክትባትን በተገቢው ጊዜና መጠን እያገኙ ባለመሆናቸው ወረርሽኙ መቆየት ከሚገባው በላይ አንድ ተጨማሪ ዓመት አብሮን ይኖራል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በድርጅቱ ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ብሩስ አሊዋርድ በዚሁ ችግር ምክንያት የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ እስከ አውሮፓውያኑ 2022 ድረስ ይቆያል ብለዋል። እስካሁን 5 በመቶ ብቻ የሚሆነው የአፍሪካ ሕዝብ ክትባቱን ማግኘት የቻለ ሲሆን በሌሎች አህጉራት ደግሞ እስከ 40 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ክትባቱን አግኝቷል። ዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን 10 ሚሊዮን ክትባቶችን ለድሃ አገራት ያደረሰች ሲሆን አጠቃላይ እቅዷ 100 ሚሊዮን ክትባቶችን ማድረስ ነው። ሀብታሞቹ አገራት ክትባቱን ለማግኘት የሚያደርጉትን እሽቅድድም ገታ አድርገው ትልልቅ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራት ላይ ትኩረታቸውን እንዲያደርጉ እንዲፈቅዱላቸው ዶክተር ብሩስ ጠይቀዋል። አክለውም ""ሀብታም አገራት በያዝነው ዓመት የቡድን 7 ስብሰባ ላይ እርዳታ ለማድረግ የገቡትን ቃል መልሰው ሊቃኙት ይገባል"" ብለዋል። ""እውነታውን ልንገራችሁ፤ ከእቅዳችን በጣም ወደኋላ ቀርተናል። ቃል የተገባውን ገንዘብ በፍጥነት ልንጠቀምበት ይገባል። አለበለዚያ ግን ይህ ወረርሽኝ ለተጨማሪ ዓመት አብሮን እንዲቆይ ይሆናል።'' የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጥምረት የሆነው 'ፒፕልስ ቫክሲን' ባወጣው መረጃ መሰረት የበለጸጉት አገራትና ትልልቅ የመድኃኒት አምራች ድርጅቶች ለመስጠት ቃል ከገቡት የክትባት መጠን ቢያንስ ከእያንዳንዱ 7 ክትባት አንዱ ብቻ ነው ወደ ድሃ አገራት እየደረሰ የሚገኘው። በተቃራኒው ክትባቶቹ ከፍተኛ ገቢ ላላቸውና በበለጸጉት አገራት ለሚኖሩ ዜጎች ነው በስፋት እየተዳረሱ የሚገኙት። አፍሪካም ቢሆን እስካሁን ከመላው ዓለም ካለው ፍላጎት 2.6 በመቶ የሚሆነው ብቻ ነው የቀረበላት። በተጨማሪም እንደ ኦክስፋም እና ዩኤንኤይድ የመሳሰሉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን የያዘው ጥምረት ዩናይትድ ኪንግደም እና ካናዳ በኮቫክስ በኩል የሚመጡ ክትባቶን ለዜጎቻቸው አከፋፍለዋል በማለት ተችቷል። ይፋዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዩናይትድ ኪንግደም በኮቫክስ በኩል 536 ሺህ 370 የፋይዘር ክትባቶችን የተረከበች ሲሆን ካናዳ ደግሞ ለአንድ ሚሊዮን የቀረቡ የአስትራ ዜኔካ ክትባቶችን ወስዳለች። ኮቫክስ የኮቪድ-19 ክትባት ለደሃ አገራት እንዲደርስ የተመሰረተ ዓለም አቀፍ ጥምረት ነው። የበለጸጉት አገራት ለኮቫክስ ኢኒሺዬቲቭ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። በተለይ ደግሞ 92 ደሃ የሚባሉ አገራት ከሌሎች 98 አቅም ካላቸው አገራት እኩል ክትባቱን እንዲቀበሉ ይደረጋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራት የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ናቸው። ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ደግሞ በኮ���ክስ በኩል የተገኙ 2.2 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶች ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን ክትባቱም አስትራዜኔካ ሠራሽ ነው። ኮቫክስ መጀመሪያ ላይ በመላው ዓለም 2 ቢሊየን የክትባት ብልቃጦችን ለማድረስ እቅድ ይዞ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ግን ማሳካት የቻለው 371 ሚሊየን ክትባቶችን ብቻ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-58991727 +politics አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት ቁልፍ አጀንዳዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? "የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ መስከረም 24/2014 ዓ.ም አዲሱ የፌደራል መንግሥት እንደሚመሰረት ገልጸዋል። ክልሎችም በበኩላቸው አዳዲስ መስተዳደሮቻቸውን ለማዋቀር እየተዘጋጁ ሲሆን የኦሮሚያ ምክር ቤት ቅዳሜ መስከረም 15/2014 ዓ.ም ባካሄደው ጉባኤ አዲሱን የክልሉን መንግሥት መስርቷል። በተመሳሳይ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መስከረም 19፣ የጋምቤላ፣ የአማራ እና የሲዳማ ክልሎች ደግሞ መስከረም 20 እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 21/2014 ዓ.ም መስተዳደሮቻቸውን ያዋቅራሉ። ለመሆኑ መስከረም 24/2014 ዓ.ም የሚመሰረተው የፌደራል መንግሥት ቁልፍ አጀንዳዎቹ ምን ሊሆኑ ይችላሉ? 'ያልተሰበረው የጦርነት አዙሪት' በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር የሆኑት ውሂበእግዜር ፈረደ (ዶ/ር) አዲሱ መንግሥት የሚያስቀምጣቸውን አጀንዳዎች የመፈፀም አቅም የሚያገኘው ከሚመሰርተው መንግሥት ባህርይ ነው ይላሉ። የሚመሰረተው መንግሥት የሚኖረው ባህርይ እና አካታችነቱ ሊሰሩ ይችላሉ ተብለው የሚቀመጡ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ የራሱ አስተዋጽኦ ሊኖረው ይችላል ሲሉ ያስረዳሉ። የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሚመሰረተው መንግሥት ከዚህ በፊት ከነበረው ""ትልቅ ሊባል የሚችል የምጣኔ ሀብት ተግዳሮት ነው ሊገጥመው ይችላል"" ሲሉ ሙያዊ ግምገማቸውን ይሰጣሉ። አዲሱ መንግሥት ሲመሰረት ከዚህ በፊት በይደር የተቀመጡ፣ በተለያየ ምክንያት ሳይፈፀሙ ቀርተው ወደ ዛሬ የተንከባለሉ ጉዳዮችን እንደሚረከብ የሚጠቅሱት ውሂበእግዜር (ዶ/ር)፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ የኢትዮጵያውያን የዘመናት ጥያቄ የሆነው የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጉዳይ አንዱ መሆኑን ያነሳሉ። አዲሱ መንግሥት ለዚህ የዘመናት ሕዝብ ጥያቄ ቢያንስ ቁልፍ የሆነ መሠረታዊ ጅማሮ ያሳያል ብለው እንደሚጠብቁ በማንሳትም፣ ለዚህ ደግሞ አካታች የሆነ መንግሥት መመስረት ቀዳሚውና ወሳኙ እርምጃ ነው ይላሉ። አክለውም አሁን ላይ ያጋጠሙ የሰላም መደፍረሶችን ለመፍታትና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት መሥራት እንዳለበት፣ ይህም የአዲሱ መንግሥት ቁልፍ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባ ይናገራሉ። ዘላቂ መፍትሔ ተብሎ የሚቀመጠው ጉዳይ ምንድን ነው? የሚለውን ለመወሰን በወታደራዊ መንገድ ነው ወይስ በብሔራዊ መግባባት ማዕቀፍ ሊታይ ይችላል የሚለውን የሚወስነው የሚመሰረተው አዲሱ መንግሥት ይሆናል። መንግሥት የሕዝብን ጥያቄ በጠመንጃ አፈሙዝ ከመፍታት ይልቅ በተሻለ መንገድ ማስተናገድ የሚችልበት ጠንካራ ማዕቀፍ ይዞ ይመጣል የሚል ተስፋ ያላቸው ውሂበእግዜር (ደ/ር)፤ እነዚህን ጉዳዮች ለመፍታት የፖለቲካ ሪፎርሙ ሂደት እንዲሁም የብሔራዊ መግባባት ውይይቱ እነማንን ያካትታል የሚለው ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በአገሪቱ ያሉ የፖለቲካ ተቃርኖዎች በሃሳብ የበላይነት፣ በውይይት ይፈታሉ የሚል ተስፋ ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ኢትዮጵያ ዳግም የጦርነት አዙሪት ውስጥ መግባቷን ያነሳሉ። የጦርነት አዙሪትን ለመሰብርና ኢትየጵያውያንን ወደ አንድ የፖለቲካ ስበት ማዕከል ለማምጣት በአገሪቱ የሚካሄደው የለውጥ እርምጃ አካ���ች ሊሆን ይገባል ሲሉ ሃሳባቸዋውን ይሰነዝራሉ። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዚህ ጦርት በርካታ ቁጥር ያላቸው ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ እንዲሆን የግብርና ምርት ሰንሰለቶች፣ ብዙ የኢንደስትሪ ተቋማት ብዙ ባለሀብቶች እና ትልልቅ የንግድ ተቋማት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መጎዳታቸውን ያነሳሉ። በሠሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት፣ በምዕራብ እና ደቡብ ያለው አለመረጋጋት ብዙ የምጣኔ ሀብት አውታሮች እና መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመትን አድርሷል። በዚህ በደከመ፣ በተጠቃና በተጎዳ የምጣኔ ሀብት መሠረተ ልማት አዲስ የሚመሠረተው መንግሥት ምን ያህል የሕዝቡን ፍላጎት ሊያዳርስ ይችላል የሚለው ሲታሰብ ትልቅ ፈተና ሆኖ እንደሚታይ ያስረዳሉ። የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ውሂበእግዜር ፈረደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የተጀመረውን ሪፎርም ተቋማዊ ማድረግ እንደሚገባ አስረግጠው፤ ይህም ከንግግር በዘለለ ""ኢትዮጵያ ከየት ተነስታ የት እንደምትደርስ በግልጽ የሪፎርም አጀንዳው መቀመጥ አለበት"" በማለት ይመክራሉ። ከዚህ ጋር አብሮ ተያይዞ ሪፎርሙን ተቋማዊ በማድረግ ሂደት ውስጥ አብሮ ሊታይ የሚገባው፣ ""ሕገመንግሥቱን ማሻሻል አልያም አዲስ ሕገመንግሥት ማርቀቅ፤ የፌዴሬሽኑን ቅርጽ እና የወደፊት እጣ ፈንታ፣ የአገሪቱን የአስተዳደራዊ መዋቅር ቅርጽ እንዴት መሆን አለበት"" የሚለው ሊሆን እንደሚችል ይጠቅሳሉ። ከእነዚህ ጉዳዮች በላይ ግን የብሔራዊ ውይይት (ናሽናል ዲያሎግ) እንደሚቀድም ያነሳሉ። በርካታ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ ይህንን ጉዳይ አጀንዳ አድርገው ሲወተውቱ እንደነበር ያስታወሱት ውሂበእግዜር (ዶ/ር)፣ መንግሥት በአዲሱ ዓመት ከሚመሰረተው መንግሥት ብሔራዊ መግባባትን ያመጣሉ ብሎ ያሰባቸውን ውይይቶች እንደሚጀምር ሲያነሳ መደመጡን ሳይጠቅሱ አላለፉም። ቀጠናዊ ለውጦች እና አዲሱ መንግሥት የአዲሱ መንግሥት ቁልፍ አጀንዳዎች ሲነሱ የሚታዩ ቀጠናዊ ለውጦች መኖራቸውን ያነሳሉ። ከሱዳን ጋር ያለን ግንኙነት ወደ አዲስ ትብብር የማሳደግ እና በሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ እንድ በጎ እድል የመጠቀም እንቅስቃሴ ይኖራል ሲሉ ተስፋቸውን ውሂበእግዜር (ዶ/ር) በይናገራሉ። ሱዳን ኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ስትራቴጂካዊ ማድረግ ይቻላል የሚሉት ዶክተሩ ፣ ነገር ግን ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከሱዳን ጋር የነበራትን የሁለትዮሽ አጋርነት ዳግም የማስቀጠል ሥራ መሰራት እንደሚኖርበት አንስተዋል። በሱዳን ውስጥ የሚካሄደውን የለውጥ እንቅስቃሴዎች በበጎ መልኩ በመጠቀም ወደ ቀድሞው መልካም ግንኙትን መመለስ እንደሚያስፈልግም ይመክራሉ። ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በሱዳን ጥቅም ላይ ይህ ነው የሚባል ጉዳት እንደማያደርስ ምሁራኖቻቸውም ሆኑ ፖለቲከኞቻቸውም ያውቁታል ያሉት ውሂበእግዜር (ዶ/ር)፣ የድንበር ውዝግቡም ቢሆን ለመፍታት ""በጣም ቀላል ይመስለኛል"" ሲሉ ተስፋቸውን ይናገራሉ። ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ሲያስረዱም ""ድንበሩን በጋራ የማልማት ስትራቴጂ መከተል አንዱ መንገድ"" መሆኑን ያነሳሉ። ዋናው ከሱዳን ጋር የነበረው የድንበር ውዝግብ ችግር ውስጥ እንዲወድቅ ያደረገው በኢትዮጵያ በኩል የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ድክመት መሆኑን ምሁሩ አንስተዋል። በኤርትራ በኩል የተጀመረው አዲስ የወንድማማችነት ሕብረት በውስጡ ይዞት የሚመጣው እድል በዘላቂነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ያድጋል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም አክለው ተናግረዋል። ""በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያሳድጉ ሥራዎች ይሰራሉ ብዬ እጠብቃለሁ።"" ኬንያ��� አዲሲቱ የምሥራቅ አፍሪካ ኃይል አንቀሳቃሽ ሆና ለመውጣት እየተንቀሳቀሰች መሆኑን በማንሳትም ስትራቴጂካዊ ትብብርን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል። በቀጣይ ዓመታት ""ኢትዮጵያ ከቀጠናው አገራት ጋር የሚኖራትን ግንኙነት ከታክቲካል ወደ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የማሳደግ ሂደት ውስጥ የምትገባ ይመስለኛል።"" ከአገሮች ጋር ከምታደርገው ግንኙነት በተጨማሪ አዳዲስ ተቋማትን የመመስረት፣ የመገንባት፣ ኢጋድን ከማጠናከር በተጨማሪ፤ የቀይ ባሕር ጉዳይን የሚመለከት አዲስ ተቋም የመገንባት፣ በአባይ ሸለቆ ላይ ደግሞ ከዚህ በፊት ከነበረው የ'ናይል ቤዚን ኢንሼቲቭ' በመውጣት የላይኛው ተፋሰስ አገራት ጥምረትን በተመለከተ አዲስ ተቋም የምታዋቅርበት ሊኖር እንደሚችል ያስረዳሉ። ዓለም አቀፉ ግንኙነት እና አዲሱ መንግሥት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) አሜሪካ እና አውሮፓ ከዚህ በፊት በቃል ሲዝቱበት የነበረውን የምጣኔ ሀብት ማዕቀብ አሁን በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ፈርማ ወደ ተግባር እየገቡበት መሆኑን ያነሳሉ። ""በተለይ ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ጋር ተጋጨን ማለት ኢትዮጵያን ከሰማይ ወደ ምድር እንደመወርወር ነው"" የሚሉት ምሁሩ፣ አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት እስከ ዛሬ ከነበሩት መንግሥታት በተለየ ትልቅ ተግዳሮቶችና ፈተናዎች ስለሚገጥሙት ""ወገቡን አስሮ መጠነ ሰፊ ርብርብ ማድረግ"" እንደሚጠበቅበት ይመክራሉ። ኢትዮጵያ የበጀት ድጋፍ በቀዳሚነት ከአሜሪካ፣ በመቀጠል ከእንግሊዝ፣ በሦስተኝነት ደግሞ ከተለያዩ የአውሮፓ አገራት እንደምታገኝ ዶ/ር ጉቱ ያነሳሉ። ""እነዚህ ሁሉ ጀርባቸውን የሚሰጡን ከሆነ፣ አሁን የጀመሩትን ማዕቀብ የሚያስቀጥከትሉ ከሆነ፣ ኢትዮጵያ ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ውስጥ ሁሉ ልትገባ ትችላለች"" ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ። የፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩም በበኩላቸው የኃያላን አገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚፈጥሩት ተጽዕኖ፣ በተለይ በአሜሪካና ኢትዮጵያ ግንኙት ላይ ዲፕሎማሲውን ማጠናከር እንደሚያስፍልግ ያስረዳሉ። የአውሮፓ እና የአሜሪካ መንግሥታት በትግራይ ጦርነት ምክንያት እያሳደሩ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመቋቋም የአዲሱ መንግሥት የትኩረት አቅጣጫ ይሆናልም ይላሉ። አዲስ የውጭ ግንኙነት መርህ እና እንቅስቃሴ ከእነማን ጋር ቢሆን የተሻለ ዘላቂ እና ስትራቴጂክ የሆነ ጥቅም ይኖረናል የሚለው ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫ ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ። ""ይህንን በሚመለከት ከቀዝቃዛው ጦርነት ኢትዮጵያ ትምህርት የምትወስድ ይመስለኛል"" የሚሉት ውሂበእግዜር (ዶ/ር)፣ በአሜሪካ በኩል ያለውንም ግንኙነት ""ተበላሽቷል፤ የማይታከም ነው፤ የሚል ድምዳሜ ላይ ይደርሳል ብዬ አላስብም"" ብለዋል። ""የተጠና ዲፕሎማሲ በመጠቀም ከምዕራብም ከምሥራቅም ኃይል የማሰባሰብ ትኩረት የሚሰጠው ይመስለኛል"" በማለት አሁን ያለው የዓለም አሰላለፍን በጥልቀት የመገንዘብና የመተንተን ሥራ እንደሚሰራም ያላቸውን ግምት ተናግረዋል። ""ከምዕራባውያን ጋር ስንጋጭ ከውጭ ባለሃብቶች ጋር ነው የምንጋጨው። እዚህ ያለው ጠቅልሎ ይሄዳል። ሌላውም አይመጣም"" ያሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) ቀዳሚው ነገር ከአሜሪካ ጋር መስማማት፣ መደራደር ነው ሊሆን እነደሚገባ ያሰምሩበታል። ""የሚቻል ከሆነ በዲፕሎማሲ ጥበብ ለማሸነፍ መሞከር ነው።"" "". . .አገር ውስጥም ይሁን በውጭ አገራት የሚገኙ ዲፕሎማቶች ከየትኛውም ጊዜ ይልጥ ሽንጣቸውን ገትረው ትልቅ የዲፕሎማሲ ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ መስራት የሚጠበቅባቸው ጊዜ ነው"" ሲሉም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። እንደ ጉቱ (ዶ/ር) አዲሱ መንግሥት ���ያንስ ቢያንስ ማዕቀቦቹ ተግባራዊ እንዳይሆኑ ለኢትዮጵያ የእፎይታ ጊዜ በሚሰጥ ሁኔታ ላይ ሊሰራ ይገባል። ጦርነት እና አለመረጋጋት እያለ የትኛውም የምጣኔ ሀብት እርምጃ መፍትሄ አያመጣም የሚሉት ጉቱ፣ ""መጠነ ሰፊ የሆነ የኢኮኖሚ መረጋጋት ለማምጣት በአገሪቱ ውስጥ ያለው ጦርነት እና አለመረጋጋት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም አለበት"" ይላሉ። በማጠቃላያቸውም ላይ ""የሆኖ ሆኖ አሁን ከገባንበት ቀውስ ወጥተን ዘላቂ እና ፈጣን እድገት ወደ ምናስመዘግብበት ጎዳና ላይ ለመሰለፍ ከአምስት እስከ አስር ዓመት ይወስድብናል"" ሲሉ ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58703272 +business የኤርትራ ምጣኔ ሃብት ባለፉት 30 ዓመታት "ኤርትራ በ1992 ዓ.ም 52ኛ አፍሪካዊት አገር ስትሆን ዜጎቿና የነጻነት ጉዞዋን ሲከታተሉ የነበሩ ተንታኞች 'ኤርትራ በአጭር ጊዜ ኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝገብ የአካባቢዋ ሞዴል ትሆናለች' የሚል ተስፋ ነበራቸው። ከነጻነት በኋላ የነበሩ የጊዝያዊ አስተዳደሩ ስራ አስፈጻሚዎችም ""ኤርትራን ሲንጋፑር እናደርጋታለን"" ሲሉ ተናግረው ነበር። አገሪቷ በ1994 ያጸደቀችው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ በግብርና ኢንዳስትሪ፣ አሳና ጨው፣ የመሰረተ ልማቶች ግንባታ፣ ኤሌክትሪክና ውሃ ማስፋፋት፣ ትምህርት፣ ጤናና ሌሎች የማስፈጸም ተልእኮ ተሰጥቶት ስራ ተጀመረ። ሰነዱ መግቢያ ላይ ""ኤርትራ ከጦርነትና ግጭት፣ ከጭቆና አገዛዝ nጻ ወጥታ ወደ አዲስ ብልጽግናና ሰላም እየገባች ነው። ይህ በመስዋእትነት የተገኘው ሰላምና መረጋጋት ፈጣን ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እያሳየ ነው። በጦርነት የወደመው ምጣኔ ሃብትን ለመገንባትም ጥረት እየተደረገ ይገኛል"" ይላል። የአፍሪካ ፖለቲካል ሳይንስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር መንግስትአብ ኪዳነ የኤርትራ መንግሥት በግል ባለሃብቶች የሚመራ የኢንቨስትመንትና ወደ ውጪ የሚላክ ምርት ትኩረት ያደረገ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ እንደነደፈ ያስታውሳሉ። ""መንግሥት የህግደፍ ኢኮኖሚ፣ የመንግሥት ኢኮኖሚ፣ የግል ኢንቨስትመንት ኢኮኖሚ በሚል ሦስት መንገድ የተገበረውን ፖሊሲ ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለበት መንገድ እጁ ማስገባት ስለጀመረ ብዙ ርቀት ሳይጓዝ ነው የተደናቀፈው"" ይላል። በተዘበራረቀ አሰራር ምክንያት ህዝብ የመንግሥት የሆነው ንብረት ከፓርቲ ሃብት ለይቶ ማየት እንዳልቻለ የሚናገረው ፕሮፌሰር መንግስትአብ፤ ""ለምሳሌ ህዝብ ማዕድን በመንግሥት ነው ወይስ በፓርቲ የሚተዳደረው የሚያውቀው ነገር አልነበረም"" በማለት የአገሪቷ የምጣኔ ሃብት ስርአት የተዘበራረቀ መሆኑ ይናገራል። በሳውዝ ባንክ ዩኒቨርሲቲ ለንደን ፕሮፌሰር የሆነው ጋይም ክብረአብ በበኩሉ፤ ህዝቡ፣ በመንግስት በኩል የነበረበትን አስተዳደራዊ ችግር ""ልምድ እስኪያገኙ ድረስ ነው"" እያለ ጊዜ ቢሰጠውም በጊዜ ማስተካከል ባለመቻሉ የአገሪቷ ምጣኔ ሃብትና ፖለቲካ ወደ ኋላ ቀርቷል ይላል። በዚህ ምክንያት ብዙ በኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ፍላጎት የነበራቸው ዜጎች እውቀታቸውና ገንዘባቸው ይዘው ከስደት ወደ አገራቸው ቢመለሱም፤ የግል ኢኮኖሚው ህጋዊ ግብር የማይከፍለው የፓርቲ ኢኮኖሚ ጋር መወዳደር ባለመቻሉ ቀስ በቀስ እንደከሰረ ያስረዳል። ይህ አሰራር ማን ምን እንደሚያስተዳድር ስለማይታወቅ ለሙስና የተጋለጠ እንደሆነ የሚያነሳው ፕሮፌሰር መንግስትአብ፣ በፓርቲ የሚመራው የኢኮኖሚ ተቋም በኢንዳስትሪ፣ ግንባታ፣ ትራንስፖርት፣ መሰረታዊ ሸቀጦች ሳይቀር ስለሚሳተፍ የኢኮኖሚው መተላለፊያ በመቆጣጠር ነጋዴዎች እድል ስለነፈጋቸው ኢኮኖሚው በአግባቡ መራመድ አልቻለም ይላል። ""መንግሥትና ፓርቲ የውጭ ምንዛሪና ብድር ተቆጣጥረው የግል ኢንቨስትመንቱን አዳከሙት። በዚህ ላይ ወጣቱ በአገራዊ ግዳጅ ስለተጠመደ በግብርና እና የቀን ስራ የሚተዳደሩ ቤተሰቦች ሰራተኛ አጥተው ኢኮኖሚው እንዲወድቅ ሆኗል"" በማለት ያስረዳል። እንዲህም ሆኖ ዜጎች በንግድና ኢንቨስትመንት ተሳትፎ ያደርጉ ስለለነበረ በ1996 የአገሪቷ ኢኮኖሚ እስከ 6.7 በመቶ እድገት እንዳስመዘገበ ፕሮፌሰር ጋይም ይናገራል። በፋይናንስ ሚኒስትር የኢኮኖሚ ኃላፊ የነበረው አቶ ክብሮም ዳፍላ በወቅቱ ከኤርትራ መገናኛ ብዙሃን ባደረገው ቆይታ እሱ ኃላፊነት ላይ በነበረበት ወቅት ያስተዳድረው የነበረው ተቋም 'ሂምቦል የውጭ ምንዛሪና ሃዋላ' ብቻ በአመት እስከ 80 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ ይመነዘር ነበር ብሏል። በተጨማሪም በተመሳሳይ ንግድ ተሰማርተው የነበሩ ሌሎች የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለመስጠት ፍቃድ የተሰጣቸው 29 ተቋማት እንደነበሩ ገልጿል። የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትና ለ20 ዓመታት የዘለቀው ውዝግብ በአስተዳደራዊ ችግርና ጫና ለህግደፍ የንግድት ተቋማት ይሰጥ በነበረው ኢፍትሃዊ የግብርና ቀረጥ እፎይታ ሲያዘግም የነበረው ብቸኛ ኢኮኖሚ፣ ለሁለት አመታት በዘለቀው የኢትዮ ኤርትራ ግጭት ምክንያት ተንኮታኮተ። ጦርነቱ ተከትሎ ላለፉት 18 አመታት በቀጠለው ውዝግብም አብዛኛው ዜጋ በብሄራዊ አገልግሎት እንዲጠመድ ስለሆነ እንደምንም ሲንቀሳቀስ የነበረው ኢኮኖሚ በጦርነት ታግቶ እንደቆመ ፕሮፌሰር ጋይም ይናገራል። ""የኤርትራ ብሄራዊ በጀት የሚመለከት ሆነ አገራዊ ኢኮኖሚያዊ ሪፖርት ስለሌለ በጦርነቱ ምክንያት ምን ያክል ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እንደደረሰ ባይገለጽም የነበረውን መባከኑን ግን ግልጽ ነው"" ይላል። የኤርትራ መንግሥት ባለስልጣናት ግን ""በቅድሚያ የአገር ሉአላዊነት መረጋገጥ ስላለበት አገር ሳናስጠብቅ የውስጥ ጉዳዮቻችን ላይ መነጋገር ጊዜው አይደለም"" ሲሉ ቆይተዋል። የመንግሥት ኢኮኖሚያዊ ቅርጽ ሁሉንም የኢኮኖሚ አማራጮች በመቆጣጠሩ ዲሞክራሲያዊ አሰራር እንዳይኖር አድርጓል የሚለው ፕሮፌሰር መንግስተአብ በበኩሉ፤ ""ፓርቲው የራሱ ኢኮኖሚ ስለገነባ ከህዝብ ጋር የሚያስተሳስረው መንገድ አይኖረውም። ለዚህም እስከ ዛሬ ለህዝብ ጥያቄ ጆሮ አልሰጠም። ህዝቡም ድምጹን የሚሰጥበት እድል ስለሌለ በድምጹ ተቃውሞ ማሰማት አልቻለም"" ይላል። በዲሞክራሲያዊ አገር ፓርቲ ከአባላቶቹ በሚሰበስበው መዋጮ ነው የሚተዳደረው። በኤርትራ ግን ህገ መንግሥታዊ ስርአት ስሌለለ አገሪቷን የሚያስተዳድር ፓርቲም አንድና አንድ ብቻ ስለሆነ፤ ህግደፍ የአገሪቷን ንብረት በሙሉ እያስተዳደረ ይገኛል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ ያላደገበት አንድ ምክንያትም ዴሞክራሲያዊ የሆነ አሰራር አለመኖሩ ነው ሲል ፕሮፌሰር ጋይም ያስረዳል። ማዕቀብ ኤርትራ እኤአ በ2009 ከሶማልያ ጋር በተያያዘ፣ በ2011 ከጅቡቲ ጋር በነበራት አለመግባባት የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክርቤት የመሳሪያ ግዢና የተወሰኑ ሰዎች ባንክ እንዳይንቀሳቀስ በማለት ማዕቀብ ጥሎባት ነበር። መንግሥት 'መሬት ላይ የሌለ ነገር በመጠቀም ኤርትራን ለማዳከም የተወሰደ ተከታታይ የአሜሪካ መንግሥታት ሴራ ነው፤ ከኢትዮጵያ ጋር በነበረው ግጭት ምክንያት በማድረግ የአፍሪካን ቀንድ ለመቆጣጠር ያሴሩት ነው' ሲል ቅሬታው ይገልጽ ነበር። በመጨረሻም ኤርትራና ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ሲፈርሙ ህዳር 14 2019 ላይ ማእቀቡ ተነሳ። ሁለቱም አገራት ስምምነት ከፈረሙ በኋላ የተዘጉ ድንበሮች ሲከፈቱ የአገሪቷ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አሳይቶ ነበር። ይሁን እንጂ ድንበሮቹ ምክንያቱ በውል ባይታወቅም ተመልሰው በመዘጋታቸው የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ዳግም ማሻቀቡን የኤርትራ ምንጮች ይገልጻሉ። ፕሮፌሰር ጋይም ግን ከዚህ በፊት ኤርትራ ��ይ የተደነገጉ ማዕቀቦች በአገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ ጫና አሳድሯል የሚለው እምነት እንዳለው ተናግሯል። በሌላ በኩል መንግሥት በ2015 ህገ ወጥ የውጭ ምንዛሬ ጭማሪ ለመቆጣጠር፤ የአገሪቷን ገንዘብ በመቀየር ሁሉንም በህዝብና ነጋዴዎች እጅ የነበረው ገንዘብ ባንክ እንዲገባ ካደረገ በኋላ ታላላቅ የንግድ ልውውጥ በባንክ እንዲከናወን ትእዛዝ አስተላለፈ። ዜጎችም ከ5 ሺ ናቅፋ በላይ ከባንክ ማውጣት እንደማይችሉ የሚቆጣጠር ህግ ተግባራዊ ሆኖ እየተሰራበት ይገኛል። ይህም ምታኔ ሃብቱ እንዲዳከም ማድረጉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳል። የኤርትራ ህዝብ ለነጻነት ሲታገሉ የነበሩ ድርጅቶች በቻለው ሁሉ እርዳታ በማድረጉ ለድል በቅቷል የሚለው ፕሮፌሰር መንግስትአብ በጣልያን እና ሌሎች አገሮች በስደት የነበሩ እናቶች ከፍተኛ የሞራልና የኢኮኖሚ ድጋፍ አድርገዋል ይላል። ከ1998 እስከ 2000 በነበረው የድንበር ግጭት ብዙ ህዝብ የአገሩን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ቦንድ በመግዛትና በጥሬ ገንዘብ በመለገስ ማገዙን የሚያነሳው ፕሮፌሰር መንግስትአብ 'አገሬ ሽልማቴ' በማለት እናቶች ሽልማታቸውን አበርክተዋል ሲል ያስታውሳል። በተጨማሪም ከጦርነቱ በኋላም ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ሳይመጣ በአንጻሩ ለውጥ ሲጠይቁ የነበሩት ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችና ጋዜጠኞች ያለ አግባብ ታስረው ይገኛሉ፤ እነዚህ እና ሌሎች ተያየዓዥ ምክንያቶች ተደማምረው የአገሪቱ ምጣኔ ሃብት እንዲጎዳ አድርጓል ይላል። በመሆኑም ""ፖለቲካዊ ለውጥ ካልመጣ ኢኮኖሚያዊ እድገት የማይታሰብ ነው"" ሲል ፕሮፌሰር ጋይም መሰረታዊ ማሻሻያ ለማድረግ የማክሮ ኢኮኖሚ መርሆዎችን ተመልሶ ማየት አስፈላጊ ነው ሲል ይመክራል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57140215 +politics በሱዳን የዴሞክራሲ ደጋፊ ሰልፈኞች በአደባባይ ተቃውሟቸውን ማሰማት ቀጥለዋል የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች በመዲናዋ ካርቱም ዴሞክራሲን እንደግፋለን የሚሉ ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተኩሰዋል። ተቃዋሚዎቹ በሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት ቢሰበሰቡም ከፍተኛ የጸጥታ ኃይሎች አላፈናፍን ብለዋቸዋል። ወታደራዊው መንግሥት ለሰልፈኞቹ የአደባባይ ተቃውሞ አጸፋዊ ምላሽ በከተማዋ የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶችን ገድቦ እንደነበር ዘገባዎች አመልክተዋል። ፖርት ሱዳንን ጨምሮ በሌሎች ከተሞችም የአደባባይ ተቃውሞች ታይተዋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በሱዳን የተፈጠረውን መፈንቅለ መንግሥት በመቃወምና የሲቪል አገዛዙ ይመለስ የሚል ጥያቄም አንግበው ወደ አደባባይ ወጥተዋል። ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ተቃውሞ ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የጸጥታ ሃይሎችም ከ12 በላይ ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የመድፈር ወንጀሎችን ፈጽመዋል የሚል ክሶች ቀርቦባቸዋል። በሱዳን ጦሩ ስልጣንን በሃይል የተቆጣጠረበትን ሁለተኛ ወር በማስመልከት፣ ኢንተርኔት ከመቋረጡ በፊት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በትናንትናው ዕለት ተከታታይ የአደባባይ ላይ የተቃውሞ ሰልፎች አቅደው ነበር። አንድ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደገለጹት የኢንተርኔት መቋረጥ የተፈጠረው ዘርፉን የሚቆጣጠረው የሱዳን ብሄራዊ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን (ኤንቲሲ) ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ነው። በመዲናዋ ተጨማሪ የጸጥታ ሃይሎች መሰማራታቸውንና ካርቱምን ከሌሎች ከተሞች ጋር የሚያገናኙት የናይል ወንዝ ድልድዮች መዘጋታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የአደባባይ ተቃውሞው ደጋፊ የሆነው የዶክተሮች ማህበር እንዳሳወቀው የጸጥታ ሃይሎች ጉዳት የደረሰባቸ���ን ተቃዋሚችን እያሳደዱ እንደነበረና በሆስፒታል ውስጥ አስለቃሽ ጭስ እና ፈንጂ መተኮሳቸውን ነው። የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን በጥቅምት ወር ጦሩ ስልጣንን በኃይል የተቆጣጠረው የፖለቲካ ቡድኖች ሰላማዊ ዜጎች በጸጥታ ኃይሎች ላይ እንዲነሱ ከመቀስቀሳቸው ጋር ተያይዞ ሊፈጠር የሚችለውን የእርስ በርስ ጦርነት ለመከላከል ነው ሲሉ ተሰምተዋል። ከአመት በኋላ ሊታቀድ ለተደረገው ምርጫና ወደ ሲቪል አገዛዝ ለመሸጋገር ቁርጠኛ እንደሆኑም ተናግረዋል። ነገር ግን አዲሱ ሲቪል መንግሥት በወታደራዊው ጫና ስር ስለሚውል ምን ያህል ስልጣን ይኖረዋል የሚለው ጥያቄን አጭሯል። ጄኔራሉ አሁን እየተካሄዱ ያሉ ተቃውሞዎች ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊ ሽግግርን ሊያደናቅፍ እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል። የዲሞክራሲ ደጋፊ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ለረዥም ዘመን ሱዳንን የገዙትን ኦማር አልበሽር ከስልጣን እንዲወገዱ ምክንያት የሆነውን አብዮት ጦሩ ጠልፏል በማለት ይከሷቸዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-59793345 +sports 'ከምንግዜም ምርጡ' የፍጻሜ ጨዋታ በኋላ ማን ምን አለ? "“እንደዚህ ዓይነት ነገር በፍጹም ደግም አናይም” ያለው የእንግሊዝ የቀድሞ ተከላካይ ሪዮ ፈርዲናንድ ነው። ፈርዲናንድ ብዙዎች ያሰቡትን ነው ቅልብጭ አድርጎ የገለጸው። ሁሉም ሙሉ የነበረበት ነው። ከዋክብቱ ሊዮኔል ሜሲ እና ክሊያን ምባፔ የተፋጠጡበት። ጨዋታው አበቃ ሲባል ድጋሚ ነፍስ የሚዘራበት አስገራሚ ምሽት። ስሜትን ሰቅዞ የሚይዝ የመለያ ምት ያለበት ጨዋታ። ማህበራዊ ሚዲያው የተጥለቀለቀበት። የስፖርት ከዋክብት የፈዘዙበት፤ በሉሳይል ስታዲም የተገኙ ደግሞ ታሪክ በዓይናቸው ያዩበት ምሽት። “ይህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም። ሁለት ግዙፍ ቡድኖች እግር በእግር የተያያዙበት ነው” ሲል ፈርዲናንድ ለቢቢሲ ዋን ገልጿል። ""በሁለቱም ቡድኖች ያሉት ሁለቱ ኮከቦች ጎል በጎል ላይ ያስቆጠሩበት . . . ግሩም"" ብሎታል። የቀድሞ እንግሊዝ አጥቂ አለን ሺረር ደግሞ ""ትንፋሽ አጥሮናል፤ ለማመን የሚከብድ ፍጻሜ ነበር። እንደዚህ ያለ ነገር አይቼ አላውቅም። እንደገናም አያለሁ ብዬ አላስብም። በጣም አስገራሚ ነበር"" ሲል ተናግሯል። የአርጀንቲናው አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ከጨዋታው በኋላ ""ተረጋግቻለሁ"" ቢልም ስሜቱን ግን መደበቅ አልቻለም። ""ጨዋታው ሙሉ በሙሉ እብደት ነበር። ጥሩ እንደተጫወትን አውቃለሁ። በ90 ደቂቃው ማሸነፍ እንችል ነበር"" ብሏል። “ከመቼውም ጊዜ የተሻለ ጥሩ ስሜት ተፈጥሮብኛል። በጣም አስፈላጊው ነገር ይህንን ያሳካንበት መንገድ ነው"" ሲል አክሏል። ከጨዋታው በፊት አብዛኛው ትኩረት አርጀንቲናዊው ሜሲ እና ፈረንሳዊው ምባፔ ላይ ነበር። ለኮከብ ጎል አግቢነት ከሚደረገው ግብግብ ሌላ ቡድናቸው ለዋንጫ የሚያበቁ መሆኑ ሲነገርላቸው ነበር። ምባፔ በመጀመርያው አጋማሽ ሜዳ ላይ መኖሩም ተረስቶ ነበር። አርጀንቲና በአሌክሲስ ማክ አሊስተር አማካኝነት የመጀመሪያውን ሙከራ ለማድረግ አራት ደቂቃ ብቻ ወሰደባት። ከዚያ በኋላም ጨዋታውን በበላይነት ተቆጣጠረች። የሜሲ ተሳትፎ የጀመረው በ23ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ፍጹም ቅጣት ምት አርጀንቲናን ቀዳሚ ሲያድርገ ነው። አንጄል ዲ ማሪያ ከ13 ደቂቃ በኋላ ሁለተኛዋን አስቆጠረ። ፈረንሳዮች ግራ ተጋብተው ነበር። ምባፔ ተሳትፎው በጣም ተገድቦ ነበር። በቃኝ ያሉት አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ 41ኛው ደቂቃ ሁለት ተጫዋቾችን ቀየሩ። ኦሊቪዬ ዥሩ እና ኦስማን ዴምቤሌ ወጥተው ራንዳል ኮሎ ሙዋኒ እና ማርከስ ቱራምን ተኳቸው። ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል ሁለቱ ቡድኖች ሲያመሩ ፈረንሳይ ወደ ጎል ምንም ሙከራ አላደረገችም። አርጀንቲና 2 ለ 0 እየመራች ነው። ጨዋታው ተጠናቋል በሚል ጋዜጠኞች የጨዋታ ሪፖርታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ነበሩ። ድራማው ግን ገና አልተጀመረም። የአርጀንቲናውን ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን በ67ኛው ደቂቃ ስትፈትን እንኳን ፈረንሳይ ገና ወደ ጨዋታው አልተመለሰችም። ወዲው ግን ነገሮች በፍጥነት መቀያየር ያዙ. . . ሙአኒ በፍጹም ቅጣት ክልል ውስጥ በኒኮላስ ኦታሜንዲ ተጠልፎ ወደቀ።  ምባፔ ፍጹም ቅጣት ምት ሊመታ ማርቲኔዝ ጎሉን ላለማስደፈር ተፋጠጡ። አሁን ጨዋታ ደራ። አርጀንቲና 2 ፈረንሳይ 1። አርጀንቲናዎች ትንፋሽ እንኳን ሳይሰበስቡ ምባፔ በአስደናቂው ሁኔታ ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው 2-2 ሆነ። ተጨማሪ 30 ደቂቃ ተጀመረ። የሜሲ ምሽት ነበር በ 108 ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ዋንጫዋ ወደ አርጀንቲና አዘነበለች። ምባፔ ግን ሥራውን አላጠናቀቅም። ሃትሪክ ያስቆተረበትን ጎል በ118ኛው አሳካ። ይህም ከእንግሊዙ ሰር ጂኦፍ ሁረስት (1966) በመቀጠል 3 ጎሎችን በዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ያስቆጠረ ሁለተኛው ተጫዋች አድርጎታል። አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት ማምራት ግድ ሆነ። በጨዋታው ሁለት ጊዜ መምራት ችላ የነበረችው አርጀንቲና ከ1986 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ አነሳች። ማርቲኔዝ የኪንግስሌይ ኮማንን ኳስ ሲኣድን እና አውሬሊ ቹአሜኒ ደግሞ ኳሷን ወደ ው ሰዷታል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c4nk1d65gvzo +health ኮሮናቫይረስ ፡ በየደቂቃው በዓለም ዙሪያ ኮቪድ-19 የሚይዛቸውና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርን የሚያሳይ ካርታ ከቻይናዋ ሁቤይ ግዛት ተነስቶ ሰው ከማይኖርበት አንታርክቲክ ውጪ ሁሉንም የዓለማችንን አህጉራትን ያዳረሰው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአሁኑ ወቅት የምድራችን ዋነኛ የጤና ስጋት ሆኗል። ኮቪድ-19 በመባል የሚታወቀው ይህ ወረርሽኝ የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃ ሲሆን፤ መጀመሪያ ትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ከሳምንት በኋላ ደግሞ የትንፋሽ ማጠርን ያስከትላል። እስካሁን በቫይረሱ ከ186 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል። በበሽታው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተያዙና ከሞቱ ከአንድ ዓመት በኋላ የተለያዩ አይነት ክትባቶች ተገኝተው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ለሰዎች እየተሰጡ ይገኛሉ። ነገር ግን አሁንም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ የእጅን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በሽታውን ለመከላከል ዋነኞቹ መንገዶች መሆናቸውን ባለሙያዎች አጥብቀው ይመክራሉ። በየደቂቃው በዓለም ዙሪያ ባሉ አገራት ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ፣ ከበሽታው የሚያገግሙና በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎችን አሃዝ ቀጥሎ ከተቀመጠው ዝርዝር ላይ ይመልከቱ። የኮሮናቫይረስ ሁለት ዋነኛ ምልክቶች ከፍተኛ ትኩሳትና ደረቅ ሳል ናቸው። በአንዳንድ ታማሚዎች ላይ እነዚህ ምልክቶች ወደ ትንፋሽ ማጠር ይወስዳሉ። ደረቅ ሳል ሲባል በጣም ጠንካራ የሆነ አንዳንድ ጊዜ ለአንድ ሰዓት የሚቆይ ነው። ከዚህ በፊት ደረቅ ሳል ካለብዎ የኮሮናቫይረስ ሳል በጣም ለየት ያለና ከባድ መሆኑን ማስተዋል ይችላሉ። ከፍተኛ ትኩሳት የሚባለው ደግሞ የሰውነት ሙቀት መጠን ከ37.8 ዲግሪ ሴልሲየስ ሲልቅ ነው። ይህ ትኩሳት ሰውነት እንዲግል ወይም ደግሞ ከፍተኛ ብርድና መንቀጥቀጥ እንዲሰማን ያደርጋል። ከእነዚህ ሁለቱ ዋነኛ ስሜቶች ባለፈ ራስ ምታትና ተቅማጥ አንዳንድ የበሽታው ታማሚዎች ያሳይዋቸው ምልክቶች ናቸው። የማሽተትና የመቅመስ አቅም ማጣትም ምልክቶች ሆነው ተመዝግበዋል። ምልክቶቹ ቫይረስ ሰውነት ውስጥ በገባ በአምስት ቀናት ሊታዩ ይችላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ዘገባ ምልክቶቹ እስከ 14 ቀናት ድረስ ሳይታዩ ሊቆዩ እንደሚችሉ ያስረዳል። https://www.bbc.com/amharic/news-51868474 +sports በኳታር የዓለም ዋንጫ ከጨዋታው ቀድመው ሌሎች ጉዳዮች ለምን አነጋጋሪ ሆኑ? የኳታሩ የዓለም ዋንጫ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። ነገር ግን አገሪቱ ባላት የመብት አያያዝ ዙሪያ በርካታ ወቀሳ እና ተቃውሞ እየቀረበባት ነው። ይህም በውድድሩ ላይ ጥላውን ሊያጠላበት ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል። የውጭ አገር የጉልበት ሠራተኞች አያያዝ ጉዳይ፣ የመናገር መብትን እና አገሪቱ ከተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን አንጻር ያላት አቋም ኳታርን እያስወቀሱ ከሚገኙ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cg6vlpg310eo +politics ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በፓርላማ ንግግራቸው ምን ምን ቁልፍ ነጥቦች አነሱ? "ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች መንግሥት በዚህ ዓመት ትኩረት በሚያደርግባቸው ጉዳዮችን በተመለከተ ንግግር አድርገዋል። ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የሥራ ዘመኑን ሲጀምር፣ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ በንግግራቸውም ቀጣይ የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫዎችን አመልክተዋል። ""ጠንከራ ፓርላማ ለመልካም አስተዳደር"" ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ በፓርላማው የተለያዩ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩበት፤ ተከራክረው የሚያሸንፉበት ቦታ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል። ፕሬዝዳንቷ ሲወሰዱ የነበሩ የምጣኔ ሀብት ማሻሻያዎች፤ ኢኮኖሚው ከነበረበት የቁልቁለት ጉዞ በመታደግ እና በማነቃቃት ከፍተኛ ውጤት አምጥተዋል ሲሉ ተናግረዋል። በ2014 በጀት ዓመት የመንግስት ገቢን 600 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማድረስ መታቀዱንና፤ ከዚህም ውስጥ 83 በመቶው የሚሆነው ገቢ በታክስ እንደሚሰበሰብ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ገለፀዋል። ጠቅላላ የሸቀጦች ንግድ ገቢም 5 ነጥብ 25 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እንደሚሰራም ተናግረዋል። ሆኖም ግን የኑሮ ውድነት እና ሥራ አጥነት የምጣኔ ሀብቱ ዋነኛ ፈተናዎች ሆነው መቀጠላቸውን እና የመንግሥት ዋነኛ የምጣኔ ሀብት ትኩረት እንደሚሆኑ ገልጸዋል። ""ማይክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ይቀጥላሉ፣ የሥራ እድል ፈጠራን ማስፋፋት፣ የዋጋ ግሽበት በመቀነስ የኑሮ ውድነት እንዲስተካከል፣ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ተግዳሮቶች የገጠሙ ጉድለቶችን በማረም ሁለንተናዊ እድገት እንዲረጋገጥ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።"" እየጨመረ ለመጣው የዋጋ ግሽበት መንስኤ የሆኑ የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመመጣጠን፣ ዝናብን መሰረት ያደረገ የግብርና ሥርዓት፣ የተዛባ ንግድ ሥርዓት ለማስተካከል በትኩረት ይሰራል ሲሉም አክለዋል። የገንዘብ እና ፊስካል ፖሊስ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚሆንም ገልፀዋል። የአረንጓዴ አሻራ መንግሥት በቀጣይ ዓመት የደን ሀብት ቁጥርን ለመጨመር ስለማቀዱ ፕሬዝዳንቷ አመላክተዋል። በአራት ዓመት 20 ቢሊዮን ዛፎች ለመትከል የተያዘውን እቅድ በማሳካት የሕዝቡን የምግብ ዋስትና ማረጋጋጥ ይገባል ብለዋል። አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ የሥራ እድል እንዲፈጠር በትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል። ከፍተኛ ማዕድን በሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች እንዲቀረፉ በልዩ ትኩረት ይሰራል ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ ለባህላዊ እና አነስተኛ ማዕድን አምራቾችም ልዩ ትኩረት ይሰጣል ሲሉ ተናግረዋል። ኮንስትራክሽን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን አቅም በመገንባት አብዛኛው የአገር ውስጥ ፍላጎት በአገር በቀል ኩባንያዎች እንዲሸፈን እንደሚደረግ የተናገሩት ፕሬዝዳንቷ፣ ""ኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ከፍተኛ የሥራ እድል ይፈጥራል ""ብለዋል። ነባር የቱሪስት መዳረሻዎችን እና አዳዲ��� መዳረሻዎች እንዲለሙ ይደረጋል። በገበታ ለአገር የተጀመሩ ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ የቱሪስት መዳረሻዎች በእቅዳቸው መሰረት ይከናወናሉ ሲሉም ገልፀዋል። የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት በተጠናቀቀው ዓመት ተከናውኖ እንደነበረ ያስታወሱት ፕሬዝዳንቷ፤ የውሃው ሙሌት እንዳይከናወን ዓለም አቀፍ ጫናዎች እንደነበሩ ጠቁመዋል። ሕዳሴ ግድብ በተያዘው ዓመት ""ብርሃን ይሆናል"" ብለዋል ፕሬዝደንቷ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ስድስተኛ ዙር የሥልጣን ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት የሁለቱን ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎቻቸውን የመረጡ ሲሆን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በተመሰረተው ምክር ቤት አማካይነት ለቀጣይ አምስት ዓመታት አገሪቱን እንዲመሩ ተመርጠው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58785329 +health ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ-19 ሞት መዘገበች "የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በምታደርገው ጥረት የምትመሰገነው እስያዊቷ አገር ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ -19 ሞት መዘገበች። ይህም እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ሞት ላልመዘገበችው ቬትናም አሳዛኝ ክስተት ሆኗል። በበሽታው የሞቱት የ70 ዓመቱ ግለሰብ ከሆይ አን ከምትባል ግዛት መሆናቸውንም የአገሪቷ ሚዲያ ዘግቧል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ ሪዞርት አቅራቢያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከመመዝገባቸው በፊት ከሦስት ወራት ለሚበልጥ ጊዜ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። 95 ሚሊየን ሕዝብ ያላት ቬትናም፤ ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ እስካሁን 509 በቫይረሱ ተይዘውባታል። ይህም ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ ቁጥር ነው። በእርግጥ አገሪቷ ከሌሎች አገራት በተለየ ቫይረሱን ለመከላከል እርምጃ መውሰድ የጀመረችው አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሳይኖር ነበር። ድንበሮቿንም ወደ አገራቸው ከሚገቡ ዜጎቿ በስተቀር ለተጓዦች ዝግ ያደረገችው ቀድማ ነበር። ከዚህም ባሻገር ወደ አገሪቷ የሚገባ ማንኛውም ግለሰብ መንግሥት ባዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ለ14 ቀናት መቆየትና መመርመር ግድ ነው። እነዚህ የጥንቃቄ እርምጃዎችም ውጤት አሳይተው ከሚያዚያ ወር አጋማሽ ጀምሮ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። በዚህ በወቅት በሽታውን ለመቆጣጠር ባደረገችው ጥረት እንዲሁም በቫይረሱ ተይዞ ሁለት ወራትን በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ላሳለፈው ስኮትላንዳዊ አብራሪ ላደረገችው እንክብካቤም አድናቆት ተችሯታል። ይሁን እንጂ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በታዋቂው ዳ ናንግ ሪዞርት አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የመገኘታቸው አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል። በዚህ ወቅትም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአገሪቷ ጎብኝዎች በከተማዋ ውስጥ ነበሩ ተብሏል። መንግሥት ረቡዕ ዕለት በከተማዋ ሙሉ ለሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣሉ በፊትም ከተማዋን ለጎብኝዎች ዝግ አድርጎ ነበር። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ የተከሰተውን ወረርሽኝ ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስተር ጉየን ዡዋን ፑክ ""ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በፍጥነትና በትጋት እርምጃ መውሰድ አለብን"" በማለት በአገሪቷ ያሉ ግዛቶችና ከተሞችን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቃቸውን የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል።" https://www.bbc.com/amharic/53610860 +health የዝንጀሮ ፈንጣጣ ለኢትዮጵያ ምን ያህል ስጋት ነው? "በአሁኑ ጊዜ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ ቢያንስ በ13 አገራት ከ90 በላይ ሰዎች ላይ መከሰቱ የዓለም ጤና ድርጅት አረጋግጧል። በሽታው በስፋት የታየው በአሜሪካ እና በአውሮፓ አገራት ውስጥ ነው። በንክኪ የሚተላለፈው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከኮቪድ-19 ጋር ሲነጻ���ር የመዛመት ፍጥነቱ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ እንደ ዩናይትድ ኪንግድም ያሉ አገራት ""ችላ የምንለው አይደለም"" ብለው በልዩ ትኩረት እየሰሩ ነው። ለመሆኑ ይህ በሽታ ኢትዮጵያን ያሳስባታል? በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲቲዩት የበሽታዎች ቅኝት እና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ወሰን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በኢትዮጵያ የመከሰት ""ከፍተኛ ዕድል አለው ብለን እናስባለን"" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ዳይሬክተሩ የወርርሽኞች አቅም እና የመተላለፊያ መንገዶቻቸው የበሽታውን አሳሳቢነቱን እንደሚወስኑ ያብራራሉ። ""ብዙ አገራትን የሚያዳርሱ በሽታዎች ብዙ ጊዜ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚዛመቱት በትንፋሽ የሚተላለፉት በሽታዎች ናቸው"" የሚሉት አቶ መስፍን ቀጥሎ ያለውን ደረጃ የሚይዙት ደግሞ በንክኪ የሚተላለፉት መሆኑናቸውን ጠቁመዋል። በንክኪ የሚተላለፉ በሽታዎች በፍጥነት የመዛመት ዕድላቸው ዝቅ ያለ ነው። ""ያ ማለት ግን ከአገር ወደ አገር አይተላለፍም ማለት አይደለም።"" እዚህ ጋር የዝንጀሮ ፈንጣጣ በንክኪ እንደሚተላለፍ ልብ በሉ። ዳይሬክተሩ በሽታው እስካሁን በኢትዮጵያ እንዳልተከሰተ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ በታሪክም በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው ተመዝግቦ አያወቅም። ሆኖም በሽታው ከተከሰተባቸው አገራት የሚነሳ ማንኛውም ሰው የዝንጀሮ ፈንጣጣን ""በቀላሉ"" ወደ ኢትዮጵያ ይዞት ሊመጣ እንደሚችል ነው አቶ መስፍን የሚናገሩት። ""የኢትዮጵያ ሁኔታ ከአፍሪካ አገሮች ወደ አውሮፓ እና ከአውሮፓ ወደ አፍሪካ አገራት ብዙ ትራንዚት እና ከፍተኛ የሰዎች ዝውውር ስላለ ከፍተኛ የመከሰት ዕድል አለው... ለሌሎችም አገራት ስጋት እስከሆነ ድረስ ለእኛም ስጋት መሆኑ አይቀርም፤ እኛም እየተንቀሳቀስን ያለነው ለአገራችንም ስጋት ነው ብለን ነው"" ብለዋል። አቶ መስፍን ይህ በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓ አገራት በስፋት እየታየ ያለው በሽታ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ""በተቻለ መጠን"" አስፈላጊውን ተግባር እያከናወኑ መሆናቸውን አመልክተዋል። ራስ ምታት እና ከ35.5 በላይ የሆነ የሰውነት ሙቀት [ትኩሳት] ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ምልክቶች ውስጥ መካከል ይካተታሉ። በዚህም መነሻ በአገሪቱ በሁሉም ዓለምአቀፍ የየብስ እና የአየር በሮች ላይ የሙቀት ልኬት እየተከናወነ ነው። ከሚጠበቀው በላይ የሆነ የሰውነት ሙቀት ያላቸው ሰዎች ለዚሁ ዓላማ ወደተዘጋጁ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት ተወስደው ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚደረግላቸው ያነሱት ኃላፊው፣ ለባለሙያዎች ሥልጣና እየተሰጠ እና በሽታው ቢያጋጥም የሚወሰዱ እርማጃዎችን በሚመለከት ""የምላሽ መመሪያ"" እየተዘጋጀ ነው ብለዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢከሰትስ? አቶ መስፍን እንደሚሉት በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢከሰት በሚል መነሻ አስፈላጊ ግብአቶችን የሟሟላት እና አቅም የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። በሁሉም ክልሎች ይህንን በሽታ የሚቆጣጠሩ ግብረ ኃይሎችን ማቋቋም፣ የተያዙ ሰዎችን ጉዳይ ለመከታተል የሚስችሉ ሥርዓቶችን ማጎልበት፣ የፈጣን ምላሽ ቡድን ማዋቀር እና የአቅም ግንባታ ተግባራትን በክልሎች ለማከናወን ""የዓለም ጤና ድርጀትን ጨምሮ ከሌሎች አጋሮች ጋር እየሰራን ነው"" ሲሉም አክለዋል። ወደ አገሪቱ መግቢያ እና መውጫ በሆኑ በሮች በሚደረጉ ምርመራዎች እስካሁን ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር የተያያዘ አሳሳቢ ሁኔታ አለመከሰቱን ኃላፊው አመላክተዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድን ነው? የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በተሰኘ ቫይረስ የሚከሰተው በሽታው 'ስሞልፎክስ' ተብሎ የሚጠራው የፈንጣጣ ዝርያ ውስጥ የሚካተት ነው። ከሰው ብቻ ሳይሆን ከእንስሳት እና ቫይረሱ ካለባቸው ቁሶች ጋር በሚኖር ንክኪ የሚተላለፈው በሽታው ለምጀመሪያ ጊዜ እንደ አውሮፓውያኑ በ1958 በዝንጀሮ ላይ የተገኘ ነው። በ1978 ደግሞ በዲሞክራቲክ ኮንንጎ በሰው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘቱ ተረጋግጧል። በገጠራማ የማዕከላዊ እና ምዕራባዊ አፍሪካ አገራት በፋት የሚያጠቃው የዝንጀሮ ፈንጣጣ እጅግ አሳሳቢ የሚባል አይደለም። በሽታውን 85 በመቶ መከላከል እንደሚችል የተረጋገጠ ክትባትም አለው። አንዳንድ ጊዜ ያለምንም ህክምና በራሱ ጊዜ ሊጠፋ የሚችል ነው ። ሆኖም በምዕራብ አፍሪካ በበሽታው ምክንያት ህይወት አልፏል። የበሽታው የሞት ምጣኔ ከ3 እስከ 6 በመቶ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጀት ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል። ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የሰውነት እብጠት፣ የጀርባ እና የጡንቻ ህመም ደግሞ የበሽታው ምልክቶች ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/news-61564071 +politics ቻርለስ የዩናይትድ ኪንግደም ንጉሥ መሆናቸው በይፋ ታወጀ በሴንት ጄምስ ቤተ መንግሥት በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ቻርለስ ሳልሳዊ የዩናይትድ ኪንግደም ንጉሥ መሆናቸው ታወጀ። ቻርለስ የእናታቸው ንግሥት ኤልዛቤጥ ዳግማዊት ሞትን ተከትሎ ወዲያውኑ ንጉሥ ቢሆኑም፣ታሪካዊ በተባለለት ጉባኤ በይፋ ንጉሥነታቸው ዛሬ ቅዳሜ ተረጋግጧል። ንግሥናውን ባወጀው ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ምንም እንኳን እስካሁን የንግሥቲቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት የሚፈጸምበት ዕለት ባይታወቅም፣ ንጉሡ የቀብሩ ዕለት ሥራ ዝግ የሚሆንበት ዕለት እንዲሆን አጽድቀዋል። ይህ ንግሥናው የጸደቀበት ጉባኤ ሥነ ሥርዓት በቴሌቪዥን ተላልፏል። ይህም በታሪክ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። በጉባኤው መጀመሪያ ላይ ንጉሡ ያልተገኙ ሲሆን፣ ነገር ግን በሁለተኛው ክፍል ላይ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ የምክር ቤቱ አባላት እና የተለያዩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ታድመው ነበር። የምክርቤቱ ፀሐፊ የሆኑት ሪቻርድ ቲልብሩክ “እግዚአብሔር ንጉሡን ይጠብቅ” ከማለታቸው በፊት ቻርለስን “ንጉሥ፣ የኮመንዌልዝ የበላይ፣ የእምነት ጠባቂ” በማለት አውጀዋል። በለንደንቤተ መንግሥትውስጥ ባለው አዳራሽ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ታድመው የነበሩት ከፍተኛ ፖለቲከኞች፣ ዳኞች እና ባለሥልጣናት “እግዚአብሔር ንጉሡን ይጠብቅ” ሲሉ በጋራ ተሰምተዋል። ንጉሡምበበኩላቸው “በጣም አሳዛኝ ኃላፊነት” ያሉትን የእናታቸውን ሞት አውጀዋል። ንጉሥቻርለስ “እናንተ፣ አጠቃላይ አገሩ እንዲሁም አጠቃላይ ዓለም ለደረሰብን የማይጠገን ሐዘን ያሳየንን ጥልቅ ርህራሔ አውቃለሁ። ይህም ለእህቴ እና ለወንድሞቼ ታላቅ መጽናኛ ነው” ብለዋል። ንግሥናውየታወጀበት ሥነ ሥርዓት ላይ የቀድሞዎቹን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ቦሪስ ጆንሰንን፣ ቴሬሳ ሜይን፣ ዴቪድ ካሜሩንን፣ ጎርደን ብራውንን እና ጆን ሜጀርን ጨምሮ 200 የምክር ቤቱ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል። በኋላምከሴንት ጄምስ ቤተ መንግሥትውጪ ተሰብስቦ የነበረው ሕዝብ በጋራ “እግዚአብሔር ንጉሡን ይጠብቅ” ካሉ በኋላ የአገሪቱ ብሔራዊ መዝሙር ተዘምሯል። ይህ ሥነ ሥርዓት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዥን ለሕዝብ የተላለፈ ሲሆን፣ይህንንም የወሰኑት ንጉሡ ቻርለስ ሳልሳዊ ናቸው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cqvz3j9w786o +sports ኮሮናቫይረስ፡ የበርሊን ማራቶን መቼ እንደሚካሄድ አልታወቀም "በአለማችን ከሚካሄዱ ስድስት ታላላቅ የስፖርት ውድድሮች መካከል የሆኑት የበርሊንና የለንደን ማራቶን በተያዘላቸው ጊዜ እንደማይካሄዱ ታወቀ። የበርሊን ማራቶን በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ሴፕቴምበር 27 ቀን 2020 ይካሄዳል ተብሎ የታቀደ ቢሆንም ጀርመን የእንቅስቃሴ ገደቧን እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ በማራዘሟ የተነሳ እንደማይካሄድ ታውቋል። የውድድሩ አዘጋጆች በመግለጫቸው በታቀደለት ጊዜ ""አይካሄድም"" ከማለት ውጭ ለሌላ ጊዜ ይተላለፍ አይተላለፍ የገለፁት ነገር የለም። ቀጣዩን እርምጃ እንደሚያስተባብሩም ጨምረው ገልፀዋል። • ኢትዮጵያን ጨምሮ አስር የዓለም አገራት ከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተደቅኖባቸዋል-የዓለም ምግብ ድርጅት • በሴቶች የሚመሩ አገራት ወረርሽኙን በተሳካ ሁኔታ እንዴት ተቆጣጠሩት? • አሜሪካ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ መስጠት ልታቆም ነው የበርሊኑ ውድድር ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ከለንደኑ ማራቶን በፊት አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ሲሆን በኋላ ላይ ግን የለንደኑ ማራቶን እኤአ ወደ ኦክቶበር 4 ተገፍቷል። የለንደኑ ማራቶን በመጀመሪያ እቅዱ መሰረት በዚህ ሳምንት መጨረሻ ለመካሄድ እቅድ ተይዞ የነበረ ሲሆን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ነው ወደ ሌላ ጊዜ የተላለፈው። የበርሊን ማራቶን አዘጋጆች በቅርብ ጊዜ እንዲካሄድ የሚወስኑ ከሆነ በሕዳር ወር አጋማሽ ሊሆን ይችላል የተባለ ሲሆን በዚያ ወቅትም ግን የኒው ዮርኩ ማራቶን እንደሚካሄድ የወጣው የጊዜ ሰሌዳ ያሳያል። የበርሊን ማራቶን ፈጣን ውድድር ሲሆን ባለፉት አመታት በወንዶች ማራቶን ውድድር ሰባት ጊዜ ክብረ ወሰን ተሻሽሎበታል። እአአ በ2018 ኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ ሁለት ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከ39 ሰከንድ በመግባት ክብረወሰኑን በእጁ አስገብቷል። ባለፈው አመት ቀነኒሳ በቀለ ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ የተመዘገበውን 2:01:41 በመግባት ያሸነፈ ሲሆን በዚህ ዓመት ከኪፕቾጌ ጋር በለንደን ማራቶን ለመፎካከር ቀጠሮ ነበራቸው። ጀርመን ከዩናይትድ ኪንግደም አንጻር አነስተኛ ሰዎች ብቻ ነው የሞቱባት። ጆንስ ሆፕኪንስ ባጠናቀረው መረጃ መሰረት በጀርመን 4,948 ሲሞቱ በዩናይትድ ኪንግደም 17,337 ሞት ተመዝግቧል። በዚህም የተነሳ ጀርመን በከፊል የእንቅስቃሴ ገደቧን አንስታለች።" https://www.bbc.com/amharic/52378021 +politics የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ በቁም እስር ላይ መሆናቸው እንዳሳሰበው አምነስቲ ገለጸ "የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በቁም እስር ላይ ከአንድ ወር በላይ መቆየታቸው እንዳሳሰበው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገልጸ። ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው አቶ ዳውድ ኢብሳ ምንም አይነት ክስ ሳይቀርብባቸው በቁም አስር ላይ የሚገኙት ከሚያዝያ 25/2013 ዓ.ም ጀምሮ ነው። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አንጋፋ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅት ሲሆን አቶ ዳውድ ኢንብሳም በሊቀመንበርነት ግንባሩን በስደት ለበርካታ ዓመታት ሲመሩ ቆይተው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ወደ አገር ቤት የተመለሱት። በአምንስቲ ኢንተርናሽናል በአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብት አጥኚ የሆኑት አቶ ፍሰሃ ለቢቢሲ እንደገለፁት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ነው በቁም እስር ላይ የሚገኙት። ሊቀመንበሩ ከቤት መውጣት የተከለከሉት ፖሊስ ካለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መኖሪያቸውን ፈትሾ ኮምፒውተሮችናን የሞባይል ስልኮችን ጨምሮ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል። ከዚያ ቀን በኋላ ፖሊስ ማንም ሰው ከቤቱ እንዳይወጣና ወደ ቤቱም እንዳይገባ የከለከለ ሲሆን አሁን በቤቱ ውስጥ ምግብና ሌሎች መሠረታዊ ነገሮች አልቀው ወይም እያለቁ ሊሆኑ ስለሚችሉ አቶ ዳውድ ያሉበት ሁኔታና ደኅንነታቸው አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ አመልክቷል። እንደ አቶ ፍሰሃ ከሆነ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ይህንን መግለጫ ሲያወጣ፣ አቶ ዳውድ ከቤታቸው እንዳይወጡ ሲደረግ በስፍራው የነበሩ ሰዎችን እንዲሁም የፓርቲያቸው አመራሮችን በማናገር መሆኑን ገልፀው፣ በአሁኑ ወቅት በአቶ ዳውድ ዙሪያ የቤት ሠራተኛቸው ብቻ እንደምትገኝ ማጣራታቸውን ገልጸዋል። አስካሁን ባለሥልጣናት በኦነግ ሊቀመንበር ላይ ምንም አይነት ክስ ያላቀረቡ በመሆናቸው በአስቸኳይ ከቁም አስሩ ነጻ እንዲወጡ ጨምሮ ጠይቋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጉዳዩን በማስመልከት ለሠላማ ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ደብዳቤ የጻፈ ሲሆን፤ በዚህም የአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሕግ ውጪ በቁም አስር ላይ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸው እንዳሳሰበው አመልክቷል። የኦነግ ቃል አቀባይን ጠቅሶ አምነስቲ እንዳሰፈረው የአቶ ዳውድ እስር እንዲሁ የተከሰተ ሳይሆን ሌሎች የግንባሩ አባላትና መሪዎች ከሕግ ውጪ በመታሰራቸውእንዲሁም በአዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎች የሚገኙ ጽህፈት ቤቶቻቸው በመዘጋታቸው በሚቀጥለው ሳምንት ከሚካሄደው ምርጫ መውጣቱን ጠቅሷል። አምነስቲ እንዳለው ባለሥልጣናት ለአቶ ዳውድ ኢብሳ የቁም እስር የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካለማቅረባቸው በተጨማሪ ምክንያቱም ምን እንደሆነ አልተገለጸላቸውም። የአቶ ዳውድ ከሕግ ውጪ በተራዘመ የቁም እስር ላይ መሆናቸው በመንቀሳቀስና በመሰባሰብ ነጻነታቸው ላይ እቀባ እንደተጣለ ተገልጿል። አምነስቲ ጉዳዩን በማስመለከት ለሠላም ሚኒስተሯ ለወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በጻፈው ደብዳቤ ላይ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ በተቀበለችው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ግዴታ መሠረት ሃሳብን የመግለጽና የመደራጀት መብትን እንዲያከብሩና እንዲጠብቁና ጠይቋል። አምነስቲ መንግሥትን አቶ ዳውድ ኢብሳን በአስቸኳይ ከቁም አስሩ እንዲለቅ ወይም የፈጸሙት ጥፋት ካለና በቂ ማስረጃ ካለውም በተገቢው ሁኔታ ክስ እንዲመሰርት ጠይቋል። አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዚህ ቀደምም ለተወሰኑ ቀናት ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ በጸጥታ ኃይሎች ተከልክለው እንደነበረ መዘገቡ ይታወሳል። በጉዳዩ ላይ የመንግሥት አካላትን ምላሽ ለማግኘት አምንስቲ መሞከሩን የሚናገሩት አቶ ፍሰሃ፣ ምላሽ ማግኘት መቸገራቸውን አብራርተዋል። አቶ ፍሰሃ አክለውም በርካታ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አባላት በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ እንደሚገኙ፣ ፍርድ ቤት ነጻ ያላቸውም ቢሆኑ እስካሁን ድረስ ታስረው እንዳሉ ገልጸዋል። ጨምረውም በአሁኑ ጊዜ የባልደራስ አመራር የሆኑት አቶ እስክንድር እንዲሁም በፖለቲካ ንቁ ታሳታፊ የሆኑ በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን እንደሚያውቁ በመጥቀስ ""የፖለቲካ አመራሮች በበርካታ ችግሮች ውስጥ እያለፉ እንደሚገኙ"" ተናግረዋል። አምንስቲ በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮችን የፍርድ ሂደቱ በቅርበት እየተከታተለ እና ማስረጃዎችን በሚገባ እየተመለከተ መሆኑን አክለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57473850 +business """ከ80 ሚሊዮን ሕዝቦቼ በድህነት የሚኖሩት 17ቱ ብቻ ናቸው"" የቻይናዋ ግዛት" የቻይናዋ ጂአንግሱ ግዛት ከ80 ሚሊዮን ነዋሪዎቼ በደህነት የሚኖሩት 17 ሰዎች ብቻ ናቸው አለች። የግዛቷ አስተዳዳሪዎች በግዛቷ ውስጥ በዓመት ከ863 ዶላር በታች (26ሺህ ብር ገደማ) የሚያገኙት ሰዎች ቁጥር 17 ብቻ ናቸው ብለዋል። ይህን ማሳካት የተቻለው መንግሥት ሁሉንም ተደራሽ የሚያደርጉ ውጤታማ ሥራዎችን ማከናወን በመቻሉ ነው ተብሏል። በፈረንጆቹ 2019 ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙ አሃዞች እንደሚጠቁሙት፤ ባለፉት አራት ዓመታት 2.54 ሚሊዮን የጂአንግሱ ግዛት ነዋሪዎችን ከድህነት አረንቋ ማውጣት ተችሏል። ግዛቷ በፈረንጆቹ 2020 ድህነትን ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ አቅዳ ስትንቀሳቀስ ነበር። አሁንም በድህነት ውስጥ ነው የሚኖሩት የተባሉት 17ቱ ሰዎች፤ ተቀጥሮ ለመስራት የሚያስችል አቅም እንዳላቸው የግዛቷ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ምንም እንኳን ቻይና ባለፉት ጥቂት አስርተ ዓመታት ኢኮኖሚዋ በፍጥነት ቢያድግም የተፈለገውን ያህል ድህነትን ከመላው ቻይና ማስወገድ አልተቻለም። ይልቁንም በድሆች እና በባለጠጎች መካከል ያለው ልዩነት እጅጉን ሰፍቶ ቆይቷል። በዚህም የቻይና መንግሥት ድህነትን ከቻይና ማራቅ የሚለው ዓላማው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ሆኗል። በቻይና 'ድህነት' ለሚለው ቃል በትክክል የሚያግባባ ትርጓሜ ማግኘት አስቸጋሪ ነው። የቻይና ግዛቶች ለድህነት የሚሰጡት ትርጓሜ እንደየደረጃቸው ይለያያል። በሃገር አቀፍ ደረጃ በዓመት ከ331 ዶላር በታች የሚያገኝ ዜጋ ድሃ ተብሎ ይፈረጃል። እንደ ጂአንግሱ ግዛት ያሉ ደግሞ ነዋሪያቸውን ድሃ የሚሉት በዓመት ከ863 ዶላር በታች የሚያገኝ ከሆነ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-51076677 +business ሩሲያ በምዕራባውያኑ ፋብሪካ የሶቪየት ኅብረት ዘመን መኪናን መልሳ ማምረት ጀመረች በዩክሬን ላይ ከተፈጸመው ወረራ በኋላ ተዘግቶ ቆይቶ በኋላ ላይ መንግሥት ቁጥጥር ስር በገባው የቀድሞው የሬኖ መኪና ፋብሪካ የሶቪየት ዘመን ተሽከርካሪን ሩሲያ ማምረት ጀመረች። ምርት የጀመረው የጭነት ተሽከርካሪ አምራቹ “ካማዝ” እንዳስታወቀው የመጀመሪያዎቹ ምርቶቹ በቀጣይ ታኅሣሥ ወር ለሽያጭ ይቀርባሉ። ፋብሪካው ዲዛይናቸው የተሻሻሉ በሶቪት ኅብረት ዘመን በስፋት ይታወቁ የነበሩት “ሞስኮቪች” የተሽከርካሪ አይነትን መልሶ በገበያው ላይ እንዲያንሰራራ እንደሚያደርግ ተነግሯል። የፈረንሳዩ መኪና አምራች ሬኖ ሩሲያን ለቆ የወጣው የዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ምዕራባውያን ኩባንያዎች በገፍ አገሪቱን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ነው። ወረራውን ተከትሎ ከሩሲያ ለቀው ከወጡት ታላላቅ ስም ካላቸው የምዕራቡ ዓለም ተቋማት መካከል ማክዶናልድስ እና ስታርባክስ ይጠቀሳሉ። ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ ያጣሏቸው ማዕቀቦች አገሪቱ በዩክሬን ላይ ለከፈተችው ወረራ ምላሽ ሲሆን፣ ከቀሪው ዓለም እንድትነጠል በማድረግ ከውጪ የሚገቡ ግብአቶችን እንዳታገኝ ለማድረግ የታለመ ነው። የመኪና አምራቹ ፋብሪካ የቴክኖሎጂ አጋር ለመሆን ባለፈው ዓመት ሐምሌ ከካማዝ ጋር ስምምነት የፈረመ ሲሆን፣ በተጨማሪም የሩሲያ መንግሥት ከቻይናው የመኪና አምራች ጄኤሲ ጋር እየሰራ መሆኑን ሮይተርስ በስም ካልጠቀሳቸው ምንጮች መረጃ መግኘቱን አመልክቷል። ካማዝ ባወጣው መግለጫ እንዳለው በሂደት ለተሽከርካሪ ምርቱ የሚያስፈልጉትን ግብአቶች ለማግኘት የአገር ውስጥ አቅራቢዎችን በሂደት ለማጠናከር እንደሚያስብ ገልጾ፣ ለጊዜው ምርቱ ውስን ሊሆን እንደሚችል ጠቅሷል። ካማዝ በቀጣይ አንድ ወር ውስጥ 600 የሚደርሱ መኪኖችን አመርታለሁ ብሎ እንደሚጠብቅ ገልጿል። በቀጣይ የፈረንጆች ዓመት ውስጥ ደግሞ የምርቱን መጠን ወደ 100,000 ተሽከርካሪዎች እንዲደርስ የሚያደርግ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል የተወሰኑት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ይሆናሉ ብሏል። በዩክሬን የሚካሄደው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በሩሲያ የሚመረተው የተሽከርካሪዎች አጠቃላይ ቁጥር ቀንሷል። በዚህም ሳቢያ የተሽከርካሪዎች ሽያጭ መጠን ከአንድ ሚሊዮን በታች ሊያሽቆለቁል የሚችል ሲሆን፣ ይህም በዘመናዊው የሩሲያ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያጋጥም ዝቅተኛው ሽያጭ እንደሚሆን ሮይተርስ ዘግቧል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0y2dl4vq5o +health ኮሮናቫይረስ፡ ታንዛኒያ 'ክትባቱ ይቅርብኝ ባህላዊ መድሃኒት ይሻለኛል' አለች "ታንዛኒያ ለኮቪድ-19 የተሰሩ ክትባቶችን መጠቀም እንደማትፈልግና በምትኩ አገር በቀል መድሃኒቶች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደምትፈልግ ማስታወቋ ተገለጸ። ከኢስት አፍሪካ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት የታንዛኒያ የጤና ሚኒስትር ጄራልድ ቻሚ ከውጪ የ���ገቡ ክትባቶች ላይ ከድህንነትና ከውጤታማነት አንጻር ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል። ሚንስትሩ ክትባቶቹ የተሰሩበት ፍጥነት እንደሚያሳስባቸውም ተናግረዋል። ምንም እንኳን አሁን የተሰሩትና ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት ክትባቶች ሁሉንም የደህንነትና ውጤታማነት ዓለማ አቀፍ መመዘኛዎች ቢያልፉም ሚንስትሩ ግን እምብዛም አላሳመነኝም ብለዋል። በሌላ በኩል የታንዛንያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የኮሮረናቫይረስን በተመለከተ በሚሰጧቸው አስተያየቶችና በሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች የዓለምን ትኩረት መሳብ የቻሉ መሪ ናቸው። ኮቪድ-19 ታንዛኒያ ሲደርስ ፕሬዚዳንቱ ሰዎች በቤታቸው መቆየት የለባቸውም ብለው አጥብቀው ይከራከሩ ነበር። እንዳውም ቫይረሱ እንዲጠፋ ቤተክርስቲያን እና መስጂድ ሄደው እንዲጸልዩ አበረታትተዋል። ''ኮሮናቫይረስ እርኩስ መንፈስ ነው፤ በክርስቶስ ሰውነት ውስጥ ሊቆይ አይችልም. . . . . ወዲያውኑ ይቃጠላል'' ሲሉም ተደምጠዋል ወግ አጥባቂው ክርስቲያን መሪ ጆን ማጉፉሊ። ፕሬዝዳንቱ ከዚህ በተጨማሪ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ስለማድረግ በተመለከተ ሲናገሩ ተግባራቱ ምንም ፋይዳ የላቸውም ሲሉም ተደምጠው ነበር። ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ጎረቤት አገራት የእንቅስቃሴ ገደብ መጣላቸውን በመተቸትም እሳቸው ግን በዚህ መልኩ ኢኮኖሚውን መጉዳት እንደማይፈልጉ በተደጋጋሚ ገልጸዋል። እንደውም ወርሃ ሰኔ ላይ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ አገራቸው ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ነጻ መሆኗን አውጀው ነበር። አነጋጋሪው ፕሬዝዳንት እንዳሉት ታንዛኒያ ከወረርሽኙ ነጻ የወጣችው በሕዝቧ ጸሎት መሆኑን ነው እንደ ምክንያት የጠቀሱት። ""እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን የኮሮናቫይረስ በሽታ ተጣራርጎ ተወግዷል"" ሲሉ ዶዶማ በተባለችው ከተማ ውስጥ በአንድ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው ለነበሩ ምዕመናን ተናግረዋል። ''በአገራችን በርካታ በቫይረስ የሚተላለፉ በሽታዎች አሉ፤ እንደ ኤችአይቪ ኤድስ ያሉትን መጥቀስ ይቻላል። ሁሌም ቢሆን ኢኮኖሚያችን መቅደም አለበት። ኢኮኖሚው እንዲተኛ መፍቀድ የለብንም፤ ሕይወትም መቀጠል አለባት'' ብለው ነበር ፕሬዝዳንቱ። በተጨማሪም ''ሌሎች የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚያቸውን ቸኩለው በመዝጋታቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ ስለሚገቡ በቅርብ ዓመታት ምግብ ከእኛ ለመግዛት መምጣታቸው አይቀርም'' ሲሉም ተደምጠው ነበር። ግንቦት ወር ላይ ደግሞ ታንዛኒያ ከማደጋስካር ያዘዘችውን የኮቪድ-19 'መድሃኒት' ተቀብላ ነበር። በወቅቱ የታንዛኒያው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር መድሃኒቱን ሲቀበሉ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን በኢንስታግራም ገጻቸው ላይ የለጠፉ ሲሆን በአንዱ ፎቶ ላይ የማደጋስካሩ ሚንስትር ለታንዛኒያው አቻቸው በኮቪድ-19 'መድሃኒት' የተሞላ ካርቶን ሲሰጡ ይታያል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55346940 +business ክሪፕቶከረንሲ፡ ኢራን ከመብራት መጥፋት ጋር በተያያዘ ቢትኮይንን ለአራት ወራት አገደች በከተሞቿ ተደጋጋሚ የመብራት መጥፋት ያጋጠማት ኢራን እንደ ቢትኮይን ያሉ እና ከፍተኛ ኃይል የሚፈልጉ የክሪፕቶከረንሲ ሥርዓቶች ላይ ለአራት ወራት እገዳ መጣሏን አስታውቃለች፡፡ ክሪፕቶከረንሲን ዲጂታል ገንዘብ ወይም መገበያያ ብለን በግርድፉ ልንተረጉመው እንችላለን። ቢትኮይን ከእነዚህ ገንዘቦች መካከል አንዱ ሲሆን አዲስ ቢትኮይን ወደ ገበያ የሚገባበት ሥርዓት ደግሞ ማይኒንግ ይባላል። ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሃኒ በካቢኔያቸው ስብሰባ እንደተናገሩት የመብራቱ መጥፋት ዋነኛ መንስኤ በድርቅ ምክንያት በሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ላይ ተጽዕኖ በመፈጠሩ ነው፡፡ የክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግ (85 በመቶው ያልፈቃድ የሚሠራ ነው) በየቀኑ ከ2 ጌጋዋት በላይ ኃይል እየተጠቀመ መሆኑንም ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል፡፡ ከቢትኮይን ማይኒንግ ውስጥ 4.5 በመቶ የሚሆነው በኢራን እንደሚካሄድ ይገመታል። ኢሊፕቲክ እንደተባለው የትንታኔ ኩባንያ ከሆነ ውሳኔው አገሪቱ ማዕቀቦችን እንድታልፍ እና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመግዛት የሚያስችል በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር የክሪፕቶ-ሃብት እንድታገኝ ያስችላታል፡፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኑክሌር ስምምነት በመተዉ እአአ በ2018 በጣሉት ማዕቀቦች ምክንያት የኢራን ባንኮች ከዓለም የገንዘብ ሥርዓት ውጭ ሲሆኑ የነዳጅ ሽያጯም እየቀነሰ በመሄዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እና ገቢ እንዳታገኝ አድርጓታል፡፡ ቢትኮይን እጅግ ከፍተኛ የኮምፒተር ኃይል ስለሚጠይቅ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ይጠቀማል። ኢሊፕቲክ እንደሚለው የኢራን ባለሥልጣናት እ.ኤ.አ. በ2019 ነበር የክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግን በይፋ እውቅና የሰጡት። በኋላም በሥራው የሚሳትፉ እንዲለዩ፣ ለኤሌክትሪክ ከፍተኛ ታሪፍ እንዲከፍሉ እና ቢትኮይናቸውን ለኢራን ማዕከላዊ ባንክ እንዲሸጡ የሚያስገድድ የፈቃድ ሥርዓት ይፋ አደረጉ፡፡ ብሔራዊው የኤሌክትሪክ ኩባንያ ቅዳሜ ዕለት እንደገለጸው ፈቃድ የተሰጣቸው የክሪፕቶከረንሲ ማይንኒግ ተቋማት የኃይል መቆራረጥ ችግሩን ለማቃለል ሥራቸውን ቀድሞውኑ በፈቃደኝነት አቁመዋል፡፡ ሩሃኒ ረቡዕ ዕለት እንደተናገሩት ፈቃድ ያልተሰጣቸው ተቋማት ከስድስት እስከ ሰባት እጥፍ የሚበልጥ ኃይል እየተጠቀሙ በመሆኑ እስከ መስከረም 22 ቀን ድረስ ሁሉንም የክሪፕቶከረንሲ እንቅስቃሴዎች ለማገድ ተገደዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም የኢነርጂ ሚንስትሩ ባለፈው ሳምንት በቴህራን እና በሌሎች በርካታ ከተሞች ባልታሰበ ሁኔታ መብራት በመጥፋቱ ኢራናውያንን ይቅርታ መጠየቃቸው ትክክል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-57230085 +business የአፍሪካ-ፈረንሳይ ስብሰባ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሦስት አገራት የብድር እፎይታ ሃሳብ በማቅረብ ተጠናቀቀ "ላለፉት ጥቂት ቀናት በፓሪስ ሲካሄድ የቆየው የፈረንሳይ-አፍሪካ ስብሰባ ብድር መክፈል ለተሳናቸው የአፍሪካ አገራት የብድር እፎይታ ሃሳብ በማቅረብ ተጠናቀቀ። የቀረበው ምክረ ሃሳብ ለኢትዮጵያ፣ ቻድ እና ዛምቢያ የብድር እፎይታ እንዲደረገ የሚጠይቅ ሲሆን ይህም ምክረ ሃሳብ በቀጣይ ወር ለጂ7 አገራት ይቀርባል ተብሏል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ባለጸጋ አገራት ደሃ አገራት የሚጠበቅባቸውን ብድር የሚከፍሉበትን ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ ለማራዘም ተስማምተው ነበር። የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ስምምነት ከተደረሰላቸው አገራት መካከል 40 ያክሉ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ናቸው። በስብሰባው ላይ ከ20 በላይ የአፍሪካ አገራት መሪዎች፣ የአውሮፓ አገራት መንግሥታት፣ የአውሮፓ ሕብረት ልዑካን እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ (አይኤምኤፍ) ዳይሬክተር ተሳታፊ ሆነዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በስብሰባው መጠናቀቂያ ላይ የስብሰባው ተሳታፊዎች በኮቪድ-19 የተጎዳውን የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚ መልሶ እንዲያንሰራራ ተጨማሪ 100 ቢሊዮን ዶላር ለማፈላለግ ተስማምተዋል ስለማለታቸው ኤፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ከዚህ መካከል አይኤምኤፍ የአፍሪካ አገራት ምርት ወደ አገራቸው እንዲያስገቡ እንዲረዳቸው 33 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል። ይህ ድጋፍ አገራቱ ባላቸው ሃብት ላይ ትኩረት በማድረግ በኮሮናቫይረስ ስርጭት ምክንያት የተጎዳ ምጣኔ ሃብታቸው እንዲያንሰራራ ትኩረት እንዲያደርጉ ያስችላል ተብሏል። ይህ የፈረንሳይ-አፍሪካ ውይይት የአፍሪካ አገራት የኮቪድ-19 ክትባት ስለሚያገኙበት አማራጭ ላይም መወያየቱን ሬውተርስ ዘግቧል። እንደ ኤፒ ዘገባ ከሆነ የውይይቱ ተሳታፊዎች የአፍሪካ አገራት ለዜጎቻቸው የኮቪድ-19 ክትባቶችን በራሳቸው በስፋት ማምረት እንዲቻላቸው ከአእምሮ መብት ጥበቃ ጋር የተያያዙ ክልከላዎች መላላት አለባቸው በሚል ተስማምተዋል ብለዋል ማክሮን። ""የአፍሪካ አዲስ ስምምነት"" የሚል መጠሪያ የሰጡት የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ የአፍሪካ አገራትን ለመደገፍ 100 ቢሊዮን ዶላር በቂ አለመሆኑን ገልጸው፤ ""በቀጣይ ዋነኛ ሥራችን የሚሆነው ሌሎች አገራት እንደ ፈረንሳይ ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ማግባባት ነው፤ ይህም ከዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ይጀምራል"" ብለዋል። የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጂኦርጂቫ አይኤምኤፍ ተጨማሪ 33 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያቀርብ ይፋ አድርገው፤ ከኮሮናቫይረስ ስርጭት በኋላ የአፍሪካ አገራት እንደተቀረው ዓለም በፍጥነት ከገቡበት የምጣኔ ሃብት አጣብቂኝ ፈጥነው መውጣት አለመቻላቸው አሳሳቢ ነው ብለዋል። የተቀረው ዓለም በአማካይ የምጣኔ ሃብት እድገታቸው 6 በመቶ ሲሆን በአፍሪካ አገራት ግን የምጣኔ ሃብት እድገቱ 3.2 በመቶ ብቻ መሆኑን ዳይሬከተሯ ገልጸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/57173549 +politics በኦሮሚያ ክልል ወረ ጃርሶ ወረዳ በርካታ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው ተነገረ "በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በርካታ ሰዎችን መግደላቸውን እና ቤተሰቦች አስክሬን ተከልክለው ቀብር መፈጸም አለመቻላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሟች ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች ማክሰኞ ሚያዚያ 25/2014 ዓ.ም. 18 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል። የወረዳው አስተዳዳሪ በበኩላቸው የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ18 ያነሰ እና ""ከጠላት ጋር የነበሩ ናቸው"" ብለዋል። የክልሉ አስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ስለ ክስተቱ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የክልሉ መንግሥት 'ኦነግ ሸኔን የማጽዳት ዘመቻ ጀምሪያለሁ' ካለ በኋላ ባለፉት ሳምንታት ሰላማዊ ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች መገደላቸው በስፋት እየተነገረ ነው። የሆነው ምንድነው? ነዋሪዎች እንደሚሉት ማክሰኞ ሚያዚያ 25/2014 ዓ.ም. በወረ ጃርሶ ወረዳ አዋሮ ጎልጄ ቀበሌ በዳዳ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራ ስፍራ 18 ሰዎች ተገድለዋል። ሰዎቹ ከመገደላቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማለትም ሰኞ ሚያዚያ 24/2014 ዓ.ም. ጠዋት ላይ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ወደ ወረዳዋ መምጣታቸውን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ልጃቸው በፀጥታ ኃይሎች እንደተገደለባቸው የሚናገሩት ስማቸውን የማንጠቅሰው አባት፤ ""[ሰኞ] ጠዋት በግምት 12፡15 ላይ ከብቶች አውጥተን ቆመን ነበር። 'ኑ' ብለው ጠሩን [የፀጥታ ኃይሎች] ከዚያ 'ትክክለኛ ሸኔ አሁን አገኘን' ብለው ልጄን ያዙት። ወዲያው ኮቱን አስወልቀው እጁን ወደ ኋላ አሰሩት"" ይላሉ። በቀጣይ ቀን ማክሰኞች ሚያዚያ 25 በመንግሥት ኃይሎች የተያዘባቸውን ልጃቸውን ለመጠየቅ ልብስ እና ምግብ ይዘው የመንግሥት ኃይሎች ወዳሉበት ካምፕ መሄዳቸውን እኚህ አባት ይናገራሉ። "". . . ሕግ ነው ያሰረው ብዬ ማክሰኞ ምግብ እና ልብስ ይዤ ልጄን ልጠይቀው ወደ ካምፕ ሄድኩ"" ይላሉ። ይሁን እንጂ ልጃቸውን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ማክሰኞ ንጋት 11 ሰዓት ላይ መገደላቸውን ዋሻ ሚካኤል ጸበል ለመጠመቅ ከሚሄዱ ሰዎች መስማታቸውን ይናገራሉ። ""መንግሥት የማያውቃቸውን ልጆቻችንን ጨረሰብን"" በማለት ልጃቸው ከሕግ ፊት ሳይቀርብ መገደሉን ይናገራሉ። ልጃቸው የታጣቂ ቡድኑ አባል ወይም ከታጣቂ ቡድኑ ጋር አንዳች ግንኙነት እ���ዳለው የተጠየቁት አባት፤ ""በጭረሽ"" ሲሉ መልሰዋል። ""ከእነሱ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ከአጠገቤ ተለይቶ አያውቅም። ከሰው ጋር ተጣልቼ እጄ ተሰብሮ ከ10ኛ ክፍል አቋርጦ እኔ ለመርዳት ወደ እርሻ ተመልሶ ነበር"" በማለት ይናገራሉ። 'ሦስት ዘመዶቼ ናቸው የተገሉብኝ' ሌላኛው ቢቢሲ ያነጋገረው ነዋሪ ደግሞ ወንድሙ እና ሁለት የአጎቱ ልጆች በዕለቱ መገደላቸውን ይናገራል። ሁለቱ በ20ዎቹ የእድሜ ክልሎች ውስጥ ሲገኙ ሦስተኛው ደግሞ ዕድሜው 20 መሆኑን ያስረዳል። ይህ ነዋሪ ከተገደሉት ሦስቱ መካከል ሁለቱ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ዲያቆኖች መሆናቸውን አንዱ ደግሞ ለፋሲካ በዓል ከአዲስ አበባ ወደ ከተማ የሄደ መሆኑን በመናገር ከታጣቂ ቡድኑ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የላቸውም ይላል። ሦስቱ ወጣቶች ሰኞ ተይዘው ማክሰኞ መገዳላቸውንም ይናገራል። ቢቢሲ ያነጋገረው ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ በዕለቱ ከተገደሉት 18 ሰዎች መካከል 14ቱ ከእነርሱ ጎጥ መሆናቸውን ጠቅሰው ""ከእኛው አካባቢ ነው ይዘዋቸው የሄዱት። እስር ቤት ያስገቧቸዋል ብለን ስንጠብቅ ገደሏቸው። እስካሁን አልተቀበሩም"" ይላሉ ነዋሪው። ይህ ነዋሪ ከሟቾች መካከል የቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ ዲያቆኖች፣ በጉልበት ሥራ የሚተዳደሩ እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሚገኙበት ይናገራሉ። ቢቢሲ ያነጋገራቸውን የሟች ቤተሰቦችና ዘመዶች ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸውን አይጠቅስም። ከላይ ያለው ምስልን ያጋረው 'የወረ ጃርሶ ወረዳ ብልጽግና' የፌስቡክ ገጽ ሲሆን፣ ከተለየ አቅጣጫ የተነሳ ተመሳሳይ ምስልም በወረዳው ኮሚኒኬሽን አማካይነት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተጋርቷል። ቢቢሲ ከሟች ቤተሰቦች እንደተረዳው በዚህ ምስል ላይ ከሚታዩት ሰዎች መካከል ቢያንስ ሁለቱ በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደባቸው እርምጃ ከተገደሉት ውስጥ ናቸው። ቢቢሲ ዛሬ አርብ ሚያዚያ 28/2014 ዓ.ም. ረፋድ ላይ የቤተሰብ አባላትን መልሶ ያነጋገረ ሲሆን፤ ማክሰኞ ሚያዚያ 25/2014 ዓ.ም. ንጋት ላይ የተገደሉት ሰዎች አስክሬን እስካሁን አልተነሳም። ""አስክሬን ስጡን ስንላቸው 'እናተም መጨመር ፈላጋችሁ' አሉን። . . . አውሬ እና አእዋፍ እየበላው ነው (አስክሬኑን)። ምን እናደርግ? አስክሬን ሰጥተውን ከመቅበር ውጪ ሌላ ምን እንፈልጋለን?"" ሲሉ ልጃቸው የተገደለባቸው አባት ይናገራሉ። የመንግሥት ምላሽ ከግድያው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሰኞ ሚያዚያ 24/2014 ዓ.ም. የወረ ጃርሶ ወረዳ ኮሚኒኬሽን በፌስቡክ ገጹ ""የኦነግ-ሸኔ አባላት"" ናቸው ያላቸው 18 ሰዎች መያዛቸውን ገልጾ ከዚህ በላይ ያለውን ምስል አጋርቷል። የወረ ጃርሶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አየለ መንግሥቱ ትናንት ሐሙስ እንደተናገሩት የተገደሉት ""ከጠላት ጋር የነበሩ ናቸው"" ብለዋል። ""አብዛኛዎቹ የተያዙት ከጠላት ጋር የነበሩት ናቸው። ከዚያ ውጭ ደግሞ ማን አለበት የሚለውን እያጣራን ነው። ከአገር መከላከያ ጋር እያጣራን ነው"" ሲሉ መልሰዋል። የሕዝብ ጥያቄን ተከትሎ የመንግሥት ፀጥታ ኃይል በወረዳው ተሰማርቶ ""የማጽዳት ሥራ እየሰራ ነውም"" ብለዋል። ""የፀጥታ ችግር ባለበት አካባቢ ንጹሃን ሰዎች ሊጎዱ ስለሚችሉ"" ከተገደሉት ሰዎች መካከል ንጹሃን ሰዎች ስለመኖራቸው እየተመረመረ ነው ብለዋል። አቶ አየለ፤ ""18 አይደርሱም [የተገደሉት ሰዎች ቁጥር] ግን የተገደሉ ሰዎች አሉ"" በማለት ተናግረዋል። ቢቢሲ ተጨማሪም ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ክልሉ የአስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ስልክ ደውሎ ነበር። ኮሎኔል አበበ ስለጉዳዩ ""አላውቀም"" ሲሉ አጭር ምላሸ ሰጥተዋል። መሰል ድርጊት ከእርሳቸው እውቅና ውጪ ሊፈጸም እንደሚችል ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ፤ ""እኔ እንደዚህ አይነት ትዕዛዝ አልሰጠሁም፤ አላውቀም"" ሲሉ መልሰዋል። ""ሸኔን የማጽዳት ዘመቻ"" ከሰሞኑ መንግሥት 'ሸኔ' ብሎ የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን ""የማጽዳት ዘመቻ"" ጀምሬያለሁ ካለ በኋላ በሁለቱ አካላት መካከል የሚደረገው ግጭት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ይህን ተከትሎ ባለፉት ሳምንታት በተለይ በምዕራብ ሸዋ ዞን በሚገኙ አካባቢዎች በርካታ ሰዎች ስለመገደላቸው በስፋት ተዘግቧል። ከእነዚህ መካከል አርብ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም. ምዕራብ ሸዋ ዞን አደአ በርጋ ወረዳ የተገደሉት ሰዎች ይገኙበታል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በዕለቱ ከ20 የማያንሱ ነዋሪዎች በወረዳው ጂማታ ተብላ በምትጠራ ቦታ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት መገደላቸውን ተናግረው ነበር። ይህ ግድያ የተከሰተው በክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ላይ በአካባቢው የነበሩ ታጠቂዎች ጥቃት ሰንዝረው ግድያ ከፈጸሙ በኋላ መሆኑንም ነዋሪዎች ገልጸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61343985 +business ቻይና በ2060 ከካርበን ልቀት ነጻ እሆናለሁ አለች ቻይና በ2060 ከካርበን ልቀት ነጻ እንደምትሆን ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ ይፋ አደረጉ። ፕሬዝደንቱ አገራቸው የካርበን ልቀት ምጠንን ዜሮ የምታስገባበት ጠንከር ያሉ ቅድመ ተከተሎች እንደሚኖሩ በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። ይህ የቻይና ውሳኔ በካርበን ልቀጥ መጠን እየጨመረ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥን ወደተሻለ ደረጃ ይወስዳል ተብሎ ታምኖበታል። ቻይና ከጠቅላላ የካርበን ልቀት የ28 በመቶ ድርሻን በመያዝ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲከሰት ዋነኛዋ አገር ናት። በዓለም አቀፍ ደረጃ የካርበን ልቀት መጠንን ለመቀነስ የሚደረጉ ስምምነቶች አዎንታዊ ለውጥ ሳያሳዩ በመቅረታቸው ቻይና ከዚህ መሰል ውሳኔ የመድረሷ ዜና ያልተጠበቀ ነበር። ፕሬዝደንት ዢ አገራቸው የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ቆርጣ መነሳቷን ለተባበሩት መንግስታት አባል አገራት ካረጋገጡ በኋላ ሌሎች አገራት የቻይናን ተምሳሌት እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል። ሺ ዢንፒንግ እንዳሉት ቻይና ከ2030 በኋላ የካርበን ልቀቷ በተከታታይ መቀነስ ከጀመረ በኋላ ነው በ2060 የካርበን ልቀት መጠኑ ዜሮ የሚሆነው። ምንም እንኳ ቻይና እአአ 2018 እና 2019 ላይ የካርበን ልቀት መጠኗ መጨመርን ቢያሳይም በኮቪድ-19 ምክንያት በ2020 የካርበን ልቀቷ መቀነስን አሳይቶ ነበር። አሁን ላይ ዳግም ቻይና የድንጋይ ከሰል አጠቃቀሟ ላይ ማሻሻያ ባለማድረጓ የካርበን ልቀት መጨመር ምልክት እየታየ ነው። የቻይናው ፕሬዝደንት ይህን የአገራቸውን ውሳኔ ይፋ ያደረጉት አሜሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ ግዴለሽነት እያሳየች ባለችበት ወቅት ነው። እአአ 2015 ላይ ፕሬዝደንት ዢ እና የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ፓሪስ ላይ የካርበን ልቀት መጠንን ለመቀነስ ተስማምተው እንደነበረ ይታወሳል። ሺ ዢንፒንግ ይፋ ባደረጉት የቻይና ውሳኔ ዙሪያ አሁንም ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች አሉ። ለምሳሌ ቻይና የካርበን ልቀቷን ዜሮ ለማድረስ የምትወስዳቸው እርምጃዎች ምንድናቸው የሚለው አልተመለሰም። https://www.bbc.com/amharic/news-54262908 +sports ታዳጊዋ የአሜሪካ 'ስፔሊንግ ቢ' በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ጥቁር አሜሪካዊት ሆነች ድንቅ የቅርጫት ኳስ ችሎታ ያላት ታዳጊ የአሜሪካን ብሔራዊ 'ስፔሊንግ ቢ' ያሸነፈነች የመጀመሪያው አፍሪካ-አሜሪካዊ ሆናለች። ስፔሊንግ ቢ ተወዳዳሪዎች የሚነገራቸውን ቃላት ትክክለኛ ፊደላት እየተናገሩ የሚፎካከሩበት መድረክ ነው። የሉዊዚያና ኒው ኦርሊያንስ ነዋሪ የሆነችው የ14 ዓመቷ ዛይላ አቫንት-ጋርድ “ሙራያ” (murraya) የሚለው ቃል ትክለኛ ፊደላት ተናግራ ነው ያሸነፈችው። ሙራያ በሞቃታማ አካባቢ የሚገኝ የዛፍ ዓይነት ነው። ወደዚህ ደረጃ ለመድረስ “querimonious” እና “solidungulate” የተሰኙትን ቃላት ፊደላት በትክክል መናገር ነበረባት። ምንም እንኳን በቀን እስከ ሰባት ሰዓታት ያህል ብትለማመድም የቃለት ፊደልን መናገርን የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ አድርጋ ነው የምትመለከተው። ዛይላ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ለመሆን ነው ፍላጎቷ። በአንድ ጊዜ በርካታ ኳሶችን በማንጠር ሦስት የዓለም ክብረወሰኖችን ስትይዝ ከናሽናል ባስኬትቦል አሶስዬሽን (ኤንቢኤ) ኮከቡ ስቴፈን ከሪ ጋር ማስታወቂያ የመሥራት እድልም አግኝታለች። ዛይላ ሐሙስ ዕለት ከአስራ አንድ የመጨረሻ ተወዳዳሪዎች ጋር ተፎካክራ አሸናፊ ሆናለች። በፍሎሪዳ ኦርላንዶ የተካሄደውን ዝግጅት በማሸነፏም 50,000 ዶላር አግኝታለች። በመጨረሻው ዙር የፍሪስኮ ቴክሳስዋን ነዋሪ እና የ 12 ዓመቷን ቻይትራ ቱማላን አሸንፋለች። እአአ ከ 2008 ወዲህ የእስያ ዝርያ የሌለው/የሌላት አሸናፊ ወይም ከአሸናፊዎቹ መካከል አንዱ/ዷ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለድል ሳይሆኑ የቀሩበት መድረክ መሆኑን አሶሺዬትድ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡ ዛይላ በፍጻሜው ቀን ‘ኔፓታ’ (የሚንት ዝርያ ነው) በሚለው ቃል ላይ ያመነታች ቢሆንም በትክክል ፊደሉን መጥራት ችላለች፡፡ በቤት ውስጥ የምትማረው ታዳጊ ለኒው ኦርሊያንስ ጋዜጣ ታይምስ-ፒካዩን “አብዛኛውን ጊዜ ወደ 13,000 ቃላት [በየቀኑ] ለማጥናት እሞክራለሁ። ይህ ደግሞ እስከ ሰባት ሰዓት ወይም ተቀራራቢ ጊዜ ይወስዳል” ብላለች። “በእርግጥ ከመጠን በላይ በሆነ መንገድ እንዲሄድ አንፈቅድም። ትምህርት እና ቅርጫት ኳስም አለብኝ።“ ዛይላ ውድድሩን ያሸነፈች ሁለተኛዋ ጥቁር ታዳጊ ሆናለች። የጃማይካዋ ተወላጅ ጆዲ አን ማክስዌል እአአ በ1998 በ12 ዓመቷ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡ በ2019 ስምንት ሕጻናት በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋራ አሸናፊ ለመሆን በቅተዋል። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ውድድሩ ባለፈው ዓመት ተቋርጦ ነበር። https://www.bbc.com/amharic/news-57773978 +business ፈረንሳይ ምርቶቿ ላይ ማዕቀብ እንዳይጣል የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን ጠየቀች "ፈረንሳይ የተለያዩ ቁሳቁሶቿ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚደረጉ ቅስቀሳዎችን የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት እንዲያስቆሙ ጠየቀች። ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ ነብዩ መሐመድን የሚያሳዩ ካርቱኖችን መሣል ይቻላል የሚል አቋም ማንጸባረቃቸውን ተከትሎ የፈረንሳይ እቃዎች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጥሪ እየተደረገ ነው። በኩዌት፣ ጆርዳን እና ካታር የሚገኙ አንዳንድ መደብሮች የፈረንሳይ ምርቶችን ማስወገድ ጀምረዋል። በሊቢያ፣ ሶርያ እና የጋዛ ሰርጥ ተቃውሞ ተካሂዷል። ፈረንሳያዊ መምህር ሳሙኤል ፓቲ፤ የነብዩ መሐመድን የካርቱን ሥዕል ለተማሪዎቹ ካሳየ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉ ይታወሳል። ክስተቱን ተከትሎ ፕሬዘዳንት ማክሮን ""ኢስላሚስቶች ነጋችንን መቆጣጠር ይፈልጋሉ። ፈረንሳይ ግን ካርቱን መሥራት አታቆምም"" ብለው ነበር። የነብዩ መሐመድን እንዲሁም የአላህን ምስል ማሳየት በእስልምና የተከለከለ ነው። የማክሮን ንግግርም ቁጣ ቀስቅስሷል። . በፈረንሳይ አንገቱን ለተቀላው መምህር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፋቸውን አሳዩ . ቻርሊ ሄብዶ መፅሄት አወዛጋቢውን የነብዩ መሐመድ ካርቱንን እንደገና አተመ ፈረንሳይ ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ነጻ የሆነች አገር እንደሆነች ትገልጻለች። የአንድ ማኅበረሰብን ስሜት ላለመጉዳት በመጠንቀቅ ውስጥ የንግግር ነጻነት መገደብ የለበትም የሚል አቋም ታንጸባርቃለች። ማክሮን ""መቼም ቢሆን እጅ አንሰጥም"" ሲሉ ትዊት አድርገዋል። በቱርክ እና በፓኪስታን ያሉ የፖለቲካ መሪዎች ማክሮንን ተችተዋል። የሃይማኖት ነጻነትን እየተጋፉ እንዲሁም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፈረንሳይ የሚኖ��� ሙስሊሞችን እያገለሉ እንደሆነም ገልጸዋል። የቱርኩ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ማክሮን ስለ እስልምና ያላቸውን አቋም በተመለከተ ""አእምሯቸውን ይመርመሩ"" ብለዋል። ፈረንሳይ ቱርክ ከሚገኙ አምባሳደሯ ጋር ለመምከር ወደ ፈረንሳይ ጠርታቸዋለች። የፓኪስታኑ መሪ ኢምራን ከሀን ""እስልምናን ሳይገነዘቡ ሃይማኖቱን እያጥላሉ ነው"" ብለዋል። በወሩ በባቻ ላይ ማክሮን ""እስላማዊ ገንጣይ"" ያሏቸው ቡድኖች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረው ነበር። የምዕራብ አውሮፓ ትልቁ የሙስሊም ማኅበረሰብ ማክሮን፤ ሃይማኖታዊ ጫና እያደረጉባቸው እንደሆነና እንቅስቃሴያቸው ሙስሊም ጠል እንደሆነ ተናግረዋል። እአአ 2015 ላይ የፈረንሳዩ ሽሙጥ አዘል መጽሔት ቻርሊ ሄድቦ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸው አይዘነጋም። መጽሔቱ የነብዩ መሐመድን ካርቱን አትሞ ነበር። ባሳለፍነው እሑድ በጆርዳን፣ ካታር እና ኩዌት ያሉ አንዳንድ መደብሮች የፈረንሳይ ምርቶችን አስወግደዋል። የፈረንሳይ ውበት መጠበቂያ ምርቶች ከመደርደሪያ ተነስተዋል። ክዌት ውስጥ ትልቁ የአከፋፋዮች ማኅበር የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል አዟል። የሸማቾች ማኅበርም በተደጋጋሚ ነብዩ መሐመድን የሚያጥላሉ አስተያየቶች በመሰንዘራቸው ተመሳሳይ ትዕዛዝ አስተላልፏል። የፈረንሳይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ባወጣው መግለጫ ""ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የተደረገው ጥሪ መሠረተ ቢስ ነው። ይህ ጥሪና በጥቂት አክራሪዎች የሚጫሩ አገሪቱ ላይ የሚቃጡ ጥቃቶች መገታት አለባቸው"" ብሏል። በሳኡዲ አረቢያ እንዲሁም በሌሎች የአረብ አገራትም የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚጠይቁ የበይነ መረብ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። የፈረንሳዩ መደብር ካርፉር እንዲዘጋ የሚጠይቀው ሀሽታግ፤ በሳኡዲ የትዊተር ተጠቃሚዎች ዘንድ ከነበሩ አነጋጋሪ ጉዳዮች ሁለተኛውን ደረጃ ይዟል። በሊቢያ፣ ጋዛ እና ሶርያ ፈረንሳይን የሚያወግዙ ተቃውሞዎች ተካሂደዋል።" https://www.bbc.com/amharic/54689433 +business በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ግሽበት ወዴት እያመራ ነው? መፍትሔውስ ምንድነው? ሰናይት ‘ሱዙኪ ዲዛዬር’ የተሰኘች 1200 ‘ሲሲ’ ያላትን መኪና ባለፈው ግንቦት የገዛችው 1.38 ሚሊዮን ብር ነበር። ከአምስት ወር በኋላ ተሽከርካሪዋ 2.2 ሚሊዮን ብር እየተሸጠች እንደሆነ ቢቢሲ አዲስ አበባ ከሚገኙ መኪና ሻጮች መረዳት ችሏል። በአገረ ሕንድ የምትመረተው ዲዛዬር ሦስተኛ ምርት (ሰርድ ጄነሬሽን) መኪና ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ ለገበያ ውላለች። የመኪናዋ ዋጋ በአሜሪካ ዶላር ሲሰላ 10 ሺህ ዶላር ገደማ ነው። ይህ አሁን ባለው የባንክ ምንዛሪ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል። ይህ ዋጋ በጎረቤት አገር ኬንያ ከ1.3 እስከ 1.4 ሚሊዮን ሽልንግ ይገመታል። ይህ ወደ ዶላር ሲመታ 11 ሺህ ዶላር ይጠጋል። በኡጋንዳ ደግሞ መኪናዋ በካምፓላ ገበያ በ43 ሚሊዮን የኡጋንዳ ሽልንግ ትሸጣለች። ይህም በዶላር ወደ 11 ሺህ ገደማ ይመነዘራል። ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ባለፈው ዓመት መጋቢት ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር በ34.7 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጦ ነበር። የዋጋ ንረቱ ለምግብነት በሚውሉ አትክልት እና ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ እና እህሎች፣ ቅመማ ቅመም እና ዘይት፣ ቅቤ እና ቡና ላይ ይጠነክራል። ሄኖክ የልጁን አንደኛ ዓመት ልደት “አነስ ባለ ድግስ” ለማክበር 40 ሺህ ብር ገደማ እንዳወጣ ለቢቢሲ ገልጿል። “ከባለቤቴ ጋር ብዙ ሰው አንጠራም ብለን ተስማማተን ቤተሰብ ብቻ ነው ልደቱን የታደመው” ይላል። “ዲኮር ብቻ 6 ሺህ ብር የፈጀው። ዲኮር ስልህ ፊኛና ‘ዲም ላይት’ እንጂ ሌላ ምንም ���ልነበረውም። ለባለቤቴ ባሕላዊ ቀሚስ፤ ለእኔና ለሁለት ልጆቼ ደግሞ ከላይ የሚለበስ ልብስ 10 ሺህ ብር፤ ስጋና ሽንኩርት እንዲሁም ዘይትና አትክልት 11 ሺህ ብር ገደማ፤ ኬክ 3 ሺህ አውጥቻለሁ።” ሄኖክ ከልጁ ልደት በኋላ ትራንስፖርትን ጨምሮ ለሌሎች ጥቃቅን ወጪዎች ያወጣውን ሲያሰላ 40 ሺህ እንደደረሰ ሲረዳ ግራ እንደተጋባ ይናገራል። ይህ ብቻ አይደለም ለትልቁ ልጁ ደብተር ሊገዛ ወጥቶ ከብዙ አሰሳ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ስሙ የገነነ ደብተር አንዱን ደርዘን 880 ብር አውጥቶ ሸምቶ ተመልሷል። የዋጋ ግሽበት ጉዳይ በማኅበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ዘንድም ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። በአዲስ አበባ ከተማ የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ተብሎ በሚታወቀው ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በንግድ ሥራ ላይ የተሠማራ አንድ ወጣት፣ ከቅርብ ወራት ወዲህ በተለይ የቲማቲም እና የነጭ ሽንኩርት ዋጋ እጅግ መናሩን ለቢቢሲ ይናገራል። “አንድ ኪሎ ቲማቲም በችርቻሮ ዋጋ እንደ ጥራቱ ከ55 አስከ 70 ብር፤ ነጭ ሽንኩርት ደግሞ እስከ 250 ብር በኪሎ ይሸጣል።” የዋጋ ግሽበት የአንድ ሸቀጥ አሊያም አገልግሎት ዋጋ መናር ነው። ቬኒዝዌላ በዓለም ትልቁ የዋጋ ግሽበት ያለባት አገር ናት። በዚህ ዓመት መጀመሪያ (2022) በአገሪቷ የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት 1198.0 በመቶ ነበር። በዚህ ምክንያት በገበያ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ በፍጥነት የሚቀያየር በመሆኑ የንግድ ተቋማት የሚያቀርቧቸውን ምርቶች ዋጋ መተመን ትተው ደንበኞች በየቀኑ የሚኖረውን ዋጋ እንዲጠይቁ ብለው ነበር። እንዲህ ዓይነት የዋጋ ንረት፤ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አሊያም ‘ሃይፐር ኢንፍሌሽን’ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የመንግሥት ወጪ ከልክ በላይ ሲሆን እና መንግሥት ወጪዎቹን ለመሸፈን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በብዛት ሲያትም የሚከሰት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ነው። ‘ሃይፐር ኢንፍሌሽን’ ብዙውን ጊዜ በጦርነት፣ በሥርዓት ለውጥ ወይም ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተከትሎ የሚመጣ ነው። ቬኒዝዌላ፤ ከደቡብ አሜሪካ አገራት ከፍተኛ የነፍስ ወከፍ ገቢ የነበራት ነበረች። አብዛኛው የአገሪቱ ገቢ ከነዳጅ ንግድ የሚገኝ ስለነበረ በ80 እና 90ዎቹ የነዳጅ ዋጋ ሲዋዥቅ ኢኮኖሚዋን ለአደጋ አጋለጠው። የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ በ2014 ከነበረው 100 ዶላር በ2016 ከ30 ዶላር በታች ሲወርድ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ትልቅ ኪሳራ ደረሰበት። ከአፍሪካ አገራት ሱዳን፤ በባለፈው ዓመት አጋማሽ ላይ 340.0 በመቶ የዋጋ ንረት ተመዝግቦባታል። በዚህ ምክንያት በዓለም ሁለተኛ ትልቁ የዋጋ ንረት ያለባት አገር ሆናለች። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሱዳን የምግብና መጠጥ ዋጋ መናሩ እንዲሁም ዶላር በጥቁር ገበያ ያለው ምንዛሪ መናሩ የዋጋ ግሽብቱ  ከፍተኛ ደረጃ ጭማሪ እያሳየ ነው። ይህ የዋጋ ንረት የወለደው የሱዳን ተቃውሞ የቀድሞው ፕሬዝደንት ኦማር አል-ባሽር በ2019 ከስልጣናቸው እንዲነሱ ምክንያት ሆኗል። በአጠቃላይ ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ወደ 12.2 በመቶ ያደገ ሲሆን አብዛኛዎቹ አገራት ጠንካራ የማዕከዊ ባንክ ሥርዓት ስለሌላቸው ነው ይላል ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ። የዋጋ ግሽበት፤ በስሪ ላንካ የነበረው ፖለቲከዊ አለመረጋጋት እንዲጋጋል ከማድረጉም በላይ ሕዝባዊ ተቃውሞውን ተከትሎ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ከሥልጣናቸው ወርደዋል። የዋጋ ግሽበት በአሁኑ ወቅት በርካታ የዓለም አገራትን እየፈተነ ሲሆን የኤነርጂ (ኃይል አቅርቦት) ዋጋ መጨመር፣ የምግብ እና የሌሎች ግብዓቶች አቅርቦት እጥረት እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለዚህ መባባስ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ይነገራል። በኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት 37.2 በመቶ ነበር። ይህ ��ፈረንጆቹ 2011 በኋላ ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ነው። የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ነሐሴ 2014 ዓ.ም. የተመዘገበው ዓመታዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 32.5 በመቶ ደርሷል። ኤጀንሲው በዚህ ወር የዋጋ ግሽበቱ መጠን ዝቅ ያለበት ምክንያት የምግብ ዋጋ ግሽበት አንጻራዊ መረጋጋት ስላሳየ ነው ይላል። ሆኖም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ካላቸው አገራት ተርታ ትገኛለች። በአፍሪካ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት የተመዘገበባት አገር ዚምባብዌ ስትሆን ይህም 285 በመቶ ነው። በተከታይነት ደግሞ በፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ የምትገኘው ሱዳን በ125 በመቶ የሸቀጦች የዋጋ ሁለተኛ ናት። የፋይናንስ አማካሪው እና የኦዲት ባለሙያው ጥላሁን ግርማ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዋጋ ግሽበት “በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተከሰተው ጋር የሚያያዝ ነው” ይላሉ። ባለሙያው “ዓለም እንዲህ ያለ የዋጋ ግሽበት አይታ አታውቅም” ሲሉ የዓለም አገራት ችግር ላይ እንደወደቁ ያስገነዝባሉ። በሩሲያና በዩክሬን መካከል እየተካሄድ ያለው ጦርነት እንደ ነዳጅ፣ ስንዴ፣ ዘይትና ሌሎች መሠረታዊ ፍጆታዎች ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ይላሉ። የነዳጅ ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጨመረበት ወቅት “የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ነዳጅ ላይ ያደርግ የነበረውን ድጎማ ማንሳቱ ችግሩ የበለጠ እንዲባባስ አድርጓል” ይላሉ። “በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ የነዳጅ ዋጋ በሚጨምርበት ወቅት የሁሉም ምርቶች ዋጋ ከፍ ይላል። ከነዳጅ ጋር በቀጥታ ጋር የሚገናኙ ዘርፎች ብቻ ሳይሆን የማይመለከታቸውም መጨመራቸው አይቀርም።” አቶ ጥላሁን አክለው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተሄድ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት “ለኑሮ ውድነት መባባስ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል” በማለት ግጭቱ በጊዜ ካልተቋጨ ሁኔታው እንደሚባባስ ያሳስባሉ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በፍጥነት እየጨመረ የሄደውን የተሽከርካሪዎች ዋጋ መናር እንደምሳሌ የሚጠቅሱት ባለሙያው የዶላር እጥረት ትልቅ ድርሻ አለው ይላሉ። “ወደ አገር ቤት መኪና የሚያስገቡ አስመጪዎች እንደሚፈልጉት ዶላር እየተፈቀደላቸው አይደለም። ተፈቅዶላቸው ዶላር አግኝተው ሲያስገቡ ደግሞ ትልቅ ትርፍ በማግኘት ነው የሚሸጡት።” የተሽከርካሪዎች ብቻ ሳይሆን የሌሎች ቁሳቁሶች ዋጋ መናር ዶላር በጥቁር ገበያ ካለው ዋጋ ጋር እንደሚገናኝ አቶ ጥላሁን ያስረዳሉ። “አንድ የአሜሪካን ዶላር ጥቁር ገበያው ላይ እስከ 90 ብር እየተመነዘረ ነው። መንግሥት ደግሞ በ53 ብር ተምኖታል። መኪና የሚያስገቡ አስመጪዎች ዶላር ከባንክ የሚጠይቁት ለይምሰል ነው እንጂ ዶላር ከጥቁር ገበያው እየገዙ ነው መኪና የሚያስገቡት። ታዲያ ይህንን የጥቁር ገበያ ዋጋ ነው ለገዢዎች የሚያስተላልፉት።” የቢዝነስ ድረ-ገፁ ብሉምበርግ ረቡዕ ዕለት ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ ጥቁር ገበያ አንድ የአሜሪካን ዶላር እስከ 92 ብር እየተመነዘረ ነው ሲል ስማቸውን ያልተጠቀሱ ምንጮችን በመጥቀስ አስነብቧል። በተቃራኒው ባንኮች አንድ ዶላር በ52.5 ብር እየመነዘሩ እንደሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ብሉምበርግ፤ ዶላር በጥቁር ገበያውና በባንክ መካከል ላለው ልዩነት ትልቁ ምክንያት የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በርስ ጦርነት ነው ሲል የማዕከላዊ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ዋና የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ፍቃዱ ድጋፌን ዋቢ በማድረግ ፅፏል። ኢትዮጵያ በዋጋ ንረት ከአፍሪካ አገራት በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሸቀጦች ዋጋ ግሽበት የተመዘገበው በምግብ እና በምግብ ነክ ቁሳቁሶች እንዲሁም በግንባታ ግብአቶች ላይ ነው። መንግሥት በተለያዩ ወቅቶ�� ለሸቀጦች እና ለቁሳቁሶች የዋጋ ተመን ቢያወጣም መሰል ፖሊሲዎች ከጥቂት ሳምንት በላይ ተግባራዊ አይሆኑም። ለምሳሌ በቅርቡ የሲሚንቶ ዋጋ መናርን ተከትሎ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አዲስ የዋጋ ተመን ማውጣቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ሲሚንቶ ከፋብሪካ የሚወጣበት አዲሱ የዋጋ ተመን ዝቅተኛው 510 ብር ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 683 ብር ከ44 ሳንቲም እንዲሆን ሚኒስቴሩ ወስኗል። ነገር ግን ይህ አዲስ ተመን ከወጣ በኋላ ሲሚንቶ እስከ 1050 ብር እየተሸጠ እንዳለ አንድ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ ደላላ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውጭ አገር ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲሠሩ መንግሥት መፍቀዱን ተከትሎ ያናገርናቸው የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ሊቀ-መንበር ዘመዴነህ ንጋቱ ባንኮቹ ዶላር ይዘው መምጣታቸው ችግሩን ሊያቃልል እንደሚችል ያምናሉ። “እንደ አጭር ጊዜ መፍትሔ መንግሥት፤ ሕዝቡ በየቀኑ መሠረታዊ ፍጆታዎች ላይ ድጎማ ማድረግ አለበት” የሚሉት የፋይናንስ አማካሪው አቶ ጥላሁን ደግሞ “ነገር ግን ለዋጋ ግሽበት ዋናው መፍትሔ የግብር አሰባሰብ።” “ለምሳሌ እኔ ለተሽከርካሪዬ የመድን ፈንድ ለመክፈል በቅርቡ ሄጄ ነበር። ለአንድ ዓመት 125 ብር ብቻ ነው ያስከፈሉኝ። ይህ ምን ያደርግላቸዋል?” በማለት በግብር አሰባሰብ ሂደቱ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ። “የግብር አሰባሰብ ሂደቱ በደንብ መታየት አለበት። ግብር ማለት ካለው ላይ ሰብስበህ ለሌለው እንደመስጠት ነው። በዚህ ላይ መንግሥት ጠንክሮ መሥራት አለበት።” ከዚህ ቀደም የዋጋ ግሽበትን አስመልክቶ ያናገርናቸው የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) “ችግሩ እጅግ ውስብስብ ስለሆነ” የአጭር ጊዜ መፍትሔ አለው ብለው እንደማያምኑ ገልጠዋል። ለንዶን የሚኖሩት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አብዱልመናን መሐመድ ደግሞ “መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ የሚበደረውን ገንዘብ መቀነስና አስፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶችን ማቆም፣ አስፈላጊ የሚባሉ ፕሮጀክቶችንም ቢሆን ለጊዜው መፍትሔ እስኪገኝ ማዘግየት አለበት” ሲሉ መክረዋል። “የኢትዮጵያን ብር የመግዛት አቅም ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ የማውረድ እንቅስቃሴ ወደ አገር ቤት የሚገቡ እቃዎችን ስለሚያንር በአስቸኳይ መቆም አለበት፤ መንግሥት እነዚህን እርምጃዎች የሚወስድ ከሆነ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ውጤት ማየት ይቻላል” ይላሉ አብዱልመናን። የዓለም ባንክ፤ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያስመዘገቡ አገራት የሕዝባቸውን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ላይ መትጋት አለባቸው ሲል ይመክራል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cw9dvwvnrv0o +politics በምሥራቅ ዩክሬን ዶንባስ የሚደረገው ጦርነት ደም አፋሳሽ እንዳይሆን ተፈርቷል የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ወደ 2ኛ ወሩ እየተጠጋ ነው፡፡ ሩሲያ በሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮችን አጥታለች፡፡ በርካታ ጄኔራሎችም ተገድለውባታል፡፡ ዋና ከተማ ኪየቭን በአጭር ቀናት የመቆጣጠሩ ነገር አልሆነላትም፡፡ አሁን ኪየቭን የከበበው የሩሲያ ጦር ሙሉ በሙሉ ለቋል፡፡ ቭላድሚር ፑቲን፣ ከዚህ በኋላ ትኩረታችን በምሥራቅ ዩክሬን ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አዲስ ጄኔራልም ሾመዋል፡፡ ይህን ተከትሎም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊታቸው ወደ ምሥራቅ ዩክሬን እየገሰገሰ ነው፡፡ የዶንባስ ክልል አካል የሆነችው ቁልፏ የወደብ ከተማ ማሪዮፖል አልህ አስጨራሽ ጦርነት እየተደረገባት ይገኛል፡፡ በቀጣይ ቀናት በሩሲያ እጅ ልትወድቅ ትችላለች የሚሉ በርካታ ናቸው፡፡ በዚያ የሚገኙ የዩክሬን ተዋጊዎች ወደ 4ሺህ የሚጠጉ ሲሆን የሩሲያ ጦር ግን የዚህን ሦስት እጥፍ ይሆናል፡፡ የማሪዮፖል ከንቲባ በዚያች ከተማ በሩሲያ ወታደሮች የተገደሉ ሰላማዊ ሰዎች ቁጥር 21ሺህ ይጠጋል ሲሉ ትናንት ተናግረዋል፡፡ በዘግናኝና ኢሰብአዊ ሁኔታ የተገደሉ ዩክሬናዊያንም ሬሳዎቻቸው በድበቅ ቦታ በጅምላ እየተቀበረ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ማሪዮፖል እንደተፈራው በቀጣይ ቀናት በሩሲያ እጅ ከወደቀች ዶንባስ ክልል ዙርያውን ከበባ ውስጥ ይገባል የሚል ፍርሃት አለ፡፡ ዞሮ ዞሮ በቀጣይ ቀናት እና ሳምንታት በምሥራቃዊ ዩክሬን የሚኖረው ጦርነት ከእስከዛሬው ሁሉ የከፋና እልህ አስጨራሽ እንዲሁም ደም አፋሳሽ እንደሚሆን ከወዲሁ እየተነገረ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ዩክሬናዊያን ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ከዶንባስ ክልል ለመሸሽ እየተሸቀዳደሙ ያሉት፡፡ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ዉሾች እንኳ የሚሆነውን የተረዱ ይመስላሉ፡፡ ከርቀት የተኩስ ድምጽ በሰሙ ቁጥር ጩኸታቸው ያሰማሉ፤ ያላዝናሉ፡፡ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩት ዩክሬናዊያን ምሥራቁን ክፍል ጥለው እየሸሹ ያሉት በብዛት ወደ ምዕራብ ዩክሬን ነው፡፡ እስከአሁን ወደ 4.6 ሚሊዮን የሚጠጉ ዩክሬናዊያን ውድ አገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡ በዚህ ወቅት የሳተላይት ምሥሎች እንዳረጋገጡት የሩሲያ ሰራዊት በረዥም ሰልፍ ወደ ምሥራቅ እየተመመ ነው፡፡ የዩክሬን ሰራዊትም ሳይቀደም ለመቅደም ብረት ለበስ ተሸከርካሪዎችን፣ አየር መቃወሚያዎችን እና ሌሎች ከምዕራብ አገራት የተገኙ ውስብስብ የጦር መሣሪያዎችን ወደ ምሥራቅ በማጓጓዝ ተጠምዷል፡፡ ነገር ግን ከሩሲያ ሰራዊት ጋር ሲወዳደር ቁጥሩ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በርካታ የጦር አዋቂዎች እንደሚሉት የምሥራቁ ጦርነት ወሳኝና አሸናፊ የሚኖር ከሆነም ያንኑ የሚለይ ይሆናል፡፡ ሁሉንም ተንታኞች ያስማማው ነጥብ ግን ይህ ጦርነት የዋዛ ጦርነት እንደማይሆን ነው፡፡ እጅግ ዘግናኝና ደማ አፋሳሹ ጦርነት ይኸው የምሥራቁ ጦርነት ነው ተብሎ ተፈርቷል፡፡ ቢቢሲ በዩክሬን ወታደሮች ፈቃድ የመከላከያ ምሽጎችን መመልከት የቻለ ሲሆን ወደ ስፍራው መድረስ የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ ብረት ለበስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ነው፡፡ ቢቢሲ በስፍራው እንዳይቀርጽ የተከለከላቸው በርካታ የአየር መቃወሚያዎችን፣ ራዳርና ሮኬቶችንም ተመልክቷል፡፡ ሩሲያ ጄት ወይም ድሮኖችን ከላከች በሚል እነሱን ለመምታት የተፈበረኩና ከምዕራብ አገራት ለዩክሬን የተለገሱ ውስብስብ መሣሪያዎችንም ቢቢሲ ለመመልከት ችሏል፡፡ ሩሲያ እስከዛሬ በነበረው ጦርነት በአየር ኃይል የበላይነት ብትይዝም ይህ ግን ከዚህ በኋላ ዘላቂ ላይሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ ምክንያቱም አሁን ያገኘቻቸው መሣሪያዎች ዓይነትና ብዛት ነው፡፡ ሩሲያና ዩክሬን አሁን በስፍራው እያንዳንዳቸው ከ30 እስከ 40 ሺህ ሰራዊት እንደሚያሰልፉ ይጠበቃል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ተንታኞች ሩሲያ በቅርብ ጊዜ ይህን የሰራዊት ቁጥር በሦስት እጥፍ እንደምታሳድግ ይናገራሉ፡፡ ሩሲያ ባለፉት ሳምንታት በተደረጉ ጦርነቶች የሰራዊቷን 20 ከመቶ አጥታለች የሚሉ ተንታኞች አሉ፡፡ በዚህም የተነሳ የሩሲያ ወታደሮች ላይ ብርታትና መነቃቃት አይታይም፤ እንደ ዩክሬናዊያን ለመዋጋት ሞራል የላቸውም ይላሉ የምዕራቡ ዓለም የጦር አዋቂዎች፡፡ የዩክሬናዊያን ወታደሮች ሞራልና የመዋጋት ፍላጎት በአንጻሩ ከፍ ያለ ነው፡፡ በጦርነቱ መሀል የምዕራብ አገራት አሜሪካን ጨምሮ ከፍተኛ የስለላና ደኅንነት ቁልፍ መረጃዎችን ወዲያውኑ ከዩክሬን ያቀብላሉ፡፡ ቢቢሲ ይህ እውነት ስለመሆኑ ከዩክሬንም ሆነ ከምዕራብ አገራቱ ማረጋገጫ አግኝቷል፡፡ ይህም ማለት የሩሲያ ሰራዊት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል ለዩክሬን ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርሷት አውሮጳና አሜሪካ ተግተው ይሠራሉ፡፡ ይልቅ ለዩክሬናዊያን ራስ ምታት የሆኑት ሩሲያ ያሰማራቻቸው ሰላዮች��� አሻጥረኞች ናቸው፡፡ ቢቢሲ በክራማቶር ከተማ አንድ ፖሊስ ጣቢያ በርካታ የሩሲያ አሻጥረኞች ናቸው የተባሉ እስረኞችን ለመመልከት ችሏል፡፡ በዩክሬን ለሩሲያ ስስ ልብ ያላቸው በርካታ ዩክሬናዊያን በብዛት የሚገኙት በዚህ ዶንባስ ክልል ነው፡፡ ለዚህም ነው ፖሊስ በየመንገዱ ነዋሪዎችን እያስቆመ ተደጋጋሚ ፍተሻን የሚያደርገው፡፡ ፑቲን ትናንት ከቤላሩሱ አጋራቸው አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር ተገናኝተው መክረዋል፡፡ አገራቸው በዚህ ጦርነት ድል እንደምታስመዘግብም ተናግረዋል፡፡ የሰላም ተስፋ እንደሌለም ጠቁመዋል፡፡ ሉካሼንኮ በበኩላቸው ቤላሩስ ምንጊዜም ከሩሲያ ጎን ትቆማለች ብለዋል፡፡ በቀጣዮቹ ሳምንታት ምናልባትም በአውሮጳ ታሪክ ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ፈጽሞ ያልታየ እልቂት ሊኖር ይችላል እየተባለ ነው፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-61090526 +health አውሮጳ፡ የፖርቹጋሉ ፕሬዚደንት በባህር ማዕበል ሲናወጡ የነበሩ ሁለት ሴቶችን ታደጉ የፖርቹጋሉ ፕሬዚደንት ማርሴሎ ሬቤሎ ደ ሶውሳ በአልጋርቭ የባህር ዳርቻ የሽርሽር ጀልባቸው ተገልብጣባቸው ነፍሳቸውን ለማትረፍ ሲታገሉ የነበሩ ሁለት ሴቶችን ሕይወት መታደጋቸው ተገለፀ። የ71 ዓመቱ ፕሬዚደንት ቅዳሜ እለት በማዕበል እየተናወጡ የነበሩ ሴቶችን ለመታደግ ወደ ጀልባዋ ሲዋኙ የሚያሳይ ምስሎች ወጥተዋል። ፕሬዚደንት ሬቤሎ ዲ ሶውሳ በእረፍት ላይ የነበሩ ሲሆን፣ ጊዜያቸውን ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ የተለያዩ ቦታዎችን በመጎብኘት እያሳለፉ እንደሆነ ተገልጿል። በወቅቱም በአልጋርቭ የባህር ዳርቻ ነበሩ። ሴቶቹ ከውሃው ለመውጣት ሲታገሉ የተመለከቱትም ከጋዜጠኞች ጋር እየተነጋገሩ ባለበት ጊዜ እንደነበር የጠቀሱት ፕሬዚደንቱ፤ በአቅራቢያ ካለ የባህር ዳርቻ በማዕበል ተገፍተው እንደመጡም በኋላ ላይ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በመገናኛ ብዙኀን ይፋ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችም ፕሬዚደንቱ ሴቶቹን ለመርዳት እየዋኙ ሲሄዱ አሳይተዋል። ሲደርሱ ግን ሌላ ሰው ቀድሟቸው እነርሱን ለመርዳት እየሞከረ ነበር ያገኙት። ከዚያም ሌላ ግለሰብ የሞተር ጀልባ ይዞ እርዳታ ለመስጠት በሥፍራው ደርሷል። የሞተር ጀልባ ይዞ የደረሰው ግለሰብም ጀልባዋን ወደ ባህር ዳርቻው ማውጣት ችሏል። እርሳቸውም ጀልባዋን ወደ ነበረችበት ለመመለስ ፈታኝ እንደነበር ገልፀው፤ የሞተር ጀልባ የያዘው ግለሰብ እርዳታ እንዳደረገላቸው ተናግረዋል። ለወደፊቱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሴቶቹን አሳስበዋቸዋል። ፖርቹጋል በርካታ እንግሊዛዊያን ጎብኝዎች ያሏት ሲሆን በዓመት ከ3 ሚሊየን በላይ ጎብኝዎች የሚጎርፉትም ከዩናይትድ ኪንግደም ነው። ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ጎብኝዎችም በአብዛኛው የሚሄዱት ወደ አልጋርቭ ባህር ዳርቻዎች ነው። ፖርቹጋል በዋናነት ኢኮኖሚዋ የተመሰረተው በቱሪዝም ኢንዱስትሪ ላይ ቢሆንም በዘንድሮው ዓመት ግን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ዘርፉ ከፍተኛ ተፅዕኖ ደርሶባታል። https://www.bbc.com/amharic/53803506 +business በአፍሪካ አየር ላይ ‘የአንበሳውን ድርሻ’ እየያዘ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 75 ዓመታት በሙሉ ስመ ገናና ሆኖ ዘልቋል-የኢትዮጵያ አየር መንገድ። ለስመ ገናናነቱም መገለጫ ከሆነው አንዱ ከበርካታ አየር መንገዶች ልቆ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደጋጋሚ ሽልማቶችን መቀዳጀቱ ነው። የአውሮፕላን ጭነት ዘርፍ የደንበኞች መስተንግዶ ሽልማትን በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜም ያሸነፈው በቅርቡ ነው። አየር መንገዱ የዘንድሮውን፣ የ2022 የአፔክስ ክልላዊ የመንገደኞች ምርጫ ሽልማት ላይ በአፍሪካ ምርጥ አገልግሎትን በመስጠት 'Best Entertainment ' እና 'Best cabin service ' በሚል ዘርፎች አሸናፊም ሆኗል። ለተወዳዳሪነቱ በርካቶች የሚመሰክሩለት አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የዘርፈ ብዙ ሽልማቶች ተሸላሚና በአፍሪካ ትልቁ የአየር ዕቃ ጭነት አገልግሎት ሰጪም ነው። በርካታ ሽልማቶችን በማሸነፍ በዓለም ላይ ስመ ጥርና በአቪየሽን ኢንዱስትሩው ዘርፍም ከሚጠቀሱት አንዱ አድርጎታል። ከሰባት አስርት ዓመታት በላይ ወደ ኋላ ታሪክን ስንዳስስ አየር መንገዱ ሲ-47 በተባሉ ቀደምት አውሮፕላኖች በአውሮፓውያኑ 1946 ሥራውን መጀመሩን ከድረ ገጹ ላይ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። በወቅቱም ካይሮ፣ ጅቡቲ እና ኤደን ከመጀመሪያ መዳረሻዎቹ መካከል መሆናቸው ተጠቅሷል። ጅማ ደግሞ ቀዳሚዋ የአገር ውስጥ መዳረሻ ነበረች። ሥራውን ሲጀምር የነበሩት ሲ-47 አውሮፕላኖች ቁጥር በዚያው ዓመት ዘጠኝ ደረሱ። እነዚህ አውሮፕላኖች ቀደም ሲል ለአሜሪካ ጦር ግልጋሎት የሰጡ ሲሆን ተጣጣፊ መቀመጫዎችም የተገጠሙላቸው ነበሩ። ከሸራ ከተሰሩት መቀመጫዎች በተጨማሪ የተሳፋሪዎችን ዕቃ ለመጫን መተላለፊያዎቹ ጥቅም ላይ ይውሉ ነበር። ፊት ለፊት ‘ተፋጠው’ የሚሄዱባቸው መቀመጫዎች የተገጠሙላቸው አውሮፕላኖችም ነበሩት። በመቀጠልም መዳረሻዎቹን በማሳደግ አየር መንገዱ ወደ ናይሮቢ፣ ፖርት ሱዳን እና ቦምቤይ በረራዎችን ማድረግ ጀመረ። በዚህ መንገድ ወደ ስኬት መንደርደር የጀመረው አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ከ22 በላይ የአገር ውስጥ መዳረሻዎች አሉት። ከ130 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችንም ያካልላል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑት አየር መንገዶች አንዱ ነው። በአህጉሩ ያለውን ተቀባይነት ለማስፋትም ደፋ ቀና እያለ ሲሆን በዋነኝነትም በአህጉሪቱ ውስጥ በሚገኙ የአየር መንገዶች ድርሻ መግዛትን ተያይዟል። አየር መንገዱ በዘርፉ የአህጉሩን ‘የአንበሳ ድርሻ’ ለመያዝ እንደቻለም አስታውቋል ። በተለያዩ የአህጉሪቱ አየር መንገዶች ድርሻ በመያዝም ስድስት የሚበልጡ የአፍሪካ አገራትን ደርሷል። በአውሮፓውያኑ 2025 ቀዳሚው የአፍሪካ አየር መንገድ ለመሆን ዕቅድ አውጥቶ እየተገበረም ነው። ይህንን እቅድ ለማሳካት ደግሞ ከአንዳንድ የአፍሪካ አየር መንገዶች ጋር በሽርክና በመሥራት ላይ ይገኛል። በአስተዳደራዊ እና በስትራቴጂክ አጋርነት ከእነዚህ አገራት አየር መንገዶች ጋር ይሠራል። በተጨማሪም በአንዳንድ አገራት ያሉ አየር መንገዶችን ድርሻ እስከ መግዛትም ደርሷል። በአንዳንድ በረራዎች ወቅት የተለያዩ አየር መንገዶች ስም እና አርማ ባረፉባቸው አውሮፕላኖች በረው ይሆናል። እነዚህ አውሮፕላኖች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በሽርክና የሚሠሩ አየር መንገዶች ሊሆኑም ይችላሉ። ለመሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ያለው ተሳትፎ ምን ይመስላል? የተወሰኑትን እንመልከት። 'ኤይር ኮንጎ' የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አየር መንገድ ሲሆን ከፍተኛ ባለቤትነቱን የአገሪቱ መንግሥት ነው የተቆጣጠረው። የአገሪቱ መንግሥት ከአየር መንገዱ ድርሻ 51 በመቶውን ይይዛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ ቀሪውን 49 በመቶ በመያዝ ሥራቸውን በጋራ ያከናውናሉ።\n'ኤይር ኮንጎ' ከአስር የሚበልጡ አውሮፕላኖች ባለቤት ነው። ከእነዚህም ውስጥ ዳሽ 8-400፣ ቦይንግ 737 እና ቦይንግ 787 ተጠቃሽ ናቸው። ለአየር መንገዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ያቀርባል። የዛምቢያ አየር መንገድ የዛምቢያ ሪፐብሊክ አየር መንገድ መሆኑን ከድረ ገጹ የተገኘው መረጃ የሚያስረዳ ሲሆን መቀመጫውም ሉሳካ ነው። በቅርቡ ሥራ ከጀመረው አየር መንገድ 45 በመቶ ድርሻው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። ቀሪው ድርሻ የአገሪቱ ነው። ሥራቸውንም በቦምባርዲየር ኪው-400 ጀምረዋል። አየር መንገዱ ቀደምት ከሚባሉት አንዱ የነበረ ሲሆን የኋላ ኋላ ግን በደረሰበት ኪሳራ ከሥራ ውጭ ሆኖ ነበር። በሞዛምቢክ የሚገኘው አየር መንገድ- የኢትዮጵያ ሞዛምቢክ አየር መንገድ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ይህ ጥምረት የተጀመረው በአውሮፓውያኑ 2018 ነበር። ሥራው ሲጀመር በዋናነት የአገር ውስጥ በረራ ላይ ትኩረት አድርጎ ነው። በአገር ውስጥ ከዘጠኝ በላይ መዳረሻዎች ነበሩት። ለእነዚህ በረራዎች ኪው 400 የሚባሉ አውሮፕላኖችን ይጠቀማል። የኮቪድ ወረርሽኝ ከፍተኛ ደረጃ በደረሰበት ወቅት ሥራቸው ተቋርጦ ቢቆይም በኋላም ወደ በረራ ገብተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 99 በመቶ የሚደርስ ድርሻ እንዳለው ታውቋል። መቀመጫውን ማፑቶ ሞዛምቢክ አድርጓል። የዓለም አቀፍ በረራዎቹን በቅብብሎሽ በአዲስ አበባ በኩል ነው የሚያደርግ ይሆናል። 'ኤስካይ' ዋና መቀመጫውን ቶጎ ሎሜ ያደረገ አየር መንገድ ነው። ኤስካይ በዋናነት ትኩረቱን በምዕራብ እና በመካከለኛው አፍሪካ አገራት ላይ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በምዕራብ አፍሪካ ለሚሰጠው አገልግሎት ድጋፍ ያደርጋል። ሁለቱ አየር መንገዶች በጋራ ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል። ይህ ስምምነት የቴክኒክ እና የስተራቴጂያዊ አጋርነት መሆኑ ተጠቅሷል። አየር መንገዶቹ መንገደኞችን በመለዋወጥም አብረው ይሠራሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ አቅንቶም አገልግሎቱን አስፋፍቶ በመስራት ላይ ይገኛል። ማላዊ አየር መንገድ የሃገሪቱ ንብረት ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዚህን አየር መንገድ 49 በመቶ ድርሻ ይዟል። የአየር መንገዱን አስተዳደር ሥራዎችንም ያከናውናል። ስምምነቱ በኢትዮጵያ እና በማላዊ አየር መንገድ መካከል በአውሮፓውያኑ ሐምሌ 11/2007 ተፈረመ። በዚህ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አዲስ የተቋቋመው የማላዊ አየር መንገድ የበረራ መርሃ ግብራቸውን በማጣጣም ለመንገደኞች ምርጥ አማራጮችን ያቀርባሉ ተብሏል። አየር መንገዱ በኪው 400 እና ቦይንግ ቢ737-700 በተሰኙ አውሮፕላኖች የበረራ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አየር መንገድ ለመመስረት ከቻድ መንግሥት ጋር የተስማማው በአውሮፓውያኑ ነሐሴ 2018 ነበር። 'ቻዲያ' አየር መንገድ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። 49 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲሆን መቀመጫውንም በቻድ ዋና ከተማ አድርጓል። ሥራው የተጀመረው ስምምነቱ በተፈረመበት ዓመት በአገር ውስጥ በረራ ነው። በአዲስ አበባ በኩል ደግሞ ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከተቀረው ዓለም ጋር ይገናኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢኳቶሪያል ጊኒው ሲ2-ሲዬባ ኢንተርኮንቲኔንታል ጋርም ውል አለው። አየር መንገዱ መቀመጫውን ኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ አድርጓል። ሁለቱ አየር መንገዶች አስተዳደራዊ ስምምነት የደረሱት በአውሮፓውያኑ የካቲት 2018 ነው። ለዓለም አቀፍ በረራዎች አዲስ አበባ ማዕከል ሆና ታገለግላለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጨማሪ ከሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶች ጋር ውል በመፈጸም በጋራ ይሰራል። በዚህም በአህጉሪቱ ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ አልሟል። ባወጣው የ15 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ በአውሮፓውያኑ 2025 የአህጉሪቱ ተቀዳሚ አየር መንገድ ለመሆን በመሥራት ላይ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዳዲስ አውሮፕላኖችን በማስገባትም ይታወቃል። ከአንድ ወር በፊት አምስት ቦይንግ ቢ777 የጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት አዟል። አየር መንገዱ ከ80 በላይ የቦይንግ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ላይ ይገኛል። በአፍሪካ ትርፋማ ከሆኑ አየር መንገዶችም ቀዳሚው በመሆን ይታወቃል። የኢትዮጵያ አየር መንገ�� ከኮሮና ወረርሽኝ በፊት በነበሩት ሰባት ተከታታይ ዓመታትም 25 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cd15revlryqo +politics ምርጫ ቦርድ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ላይ የተጣለው የመንቀሳቀስ ገደብ በአስቸኳይ እንዲነሳ ጠየቀ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የረጅም ጊዜ ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለው በቁም እስር ላይ እንደቆዩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ገለጸ። ይህም ድርጊት ከሕግ ውጪ በመሆኑ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ላይ የተጣለው የመንቀሳቀስ ገደብ በአፋጣኝ እንዲነሳ ቦርዱ ለፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን እና ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በደብዳቤ ጠይቋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ለሁለቱ የፀጥታ ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንዳመለከተው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር ለረጅም ጊዜ ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ የቀረበውን አቤቱታ አጣሪዎችን በማሰማራት ማረጋገጡን ገልጿል። በዚህም መሠረት ከቦርዱ የተላኩት አጣሪዎች የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ወደ ሚገኘው የአቶ ዳውድ ኢብሳ መኖሪያ በሄዱበት ጊዜ ሲቪል የለበሱ የፀጥታ ሠራተኞች በር እንደከፈቱላቸውና ማንም ሰው መግባት እንደማይችል መረዳታቸውን ደብዳቤው አመልክቷል። ወደ መኖሪያ ቤቱ በመግባት ሊቀመንበሩን ለማግኘትም ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው፣ በዚህም መሠረት አጣሪዎቹ ከየት እንደመጡና ማንነታቸውን ተጠይቀው አቶ ዳውድን እንዲጎበኙ እንደተፈቀደላቸው ገልጸዋል። የኦነግ ሊቀመንበርን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ከማግኘታቸው በፊትም በፀጥታ ሠራተኞቹ ቦርሳቸው መፈተሹ እንዲሁም ስልክ ይዘው መግባት እንደማይችሉ እንደተነገራቸውና ይህንኑ በማድረግ በመጨረሻ አቶ ዳውድን እንዳገኙ ቦርዱ በደዳቤው ላይ ጠቅሷል። አጣሪዎቹ ከኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ባደረጉት ውይይት ከመጋቢት 24፣ 2013 ዓ.ም በቤታቸው እንዲገደቡና እንዳይወጡ መከልከላቸውን አስረድተዋል። የታጠቁ ሰዎች በመኖሪያ ቤታቸው ግቢ ተመድበውም እንደከለክሏቸውም ምርጫ ቦርድ በመግለጫው አስፍሯል። ከዚህም በመነሳት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ የመንቀሳቀስ መብት ተገድቦ በቁም እስር በቤታቸው ውስጥ እንዳይወጡ መደረጋቸውን መገንዘቡን በደብዳቤው ላይ አመልክቷል። በመሆኑም ቦርዱ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ላይ የተፈጸመው ይህ የመንቀሳቀስ ገደብ በየትኛውም ሕግ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በመግለጽ ያሉበት የቁም አስር በአፋጣኝ እንዲነሳ ጠይቋል። ቦርዱ ፌደራል ፖሊስ እና ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በጻፈው ደብዳቤ በሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ቤት የተመደቡት ጥበቃዎች በአስቸኳይ እንዲነሱና የግለሰቡ የመንቀሳቀስ መብታቸው እንዲከበር አድርገው ለቦርዱ በአስቸኳይ እንዲያሳውቁ ጠይቋል። ከዚህ ቀደም የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በቁም እስር ላይ መሆናቸው እንዳሳሰበው የመብት ተቆርቋሪው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ማስታወቁ ይታወሳል። ሊቀ መንበሩ ምንም አይነት ክስ ሳይቀርብባቸው በቁም አስር ላይ የሚገኙት ከሚያዝያ 25/2013 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑንም ገልጾ ነበር። አቶ ዳውድ ከቤት መውጣት የተከለከሉት ፖሊስ ካለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መኖሪያቸውን ፈትሾ ኮምፒውተሮችናን የሞባይል ስልኮችን ጨምሮ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል። ከዚያ ቀን በኋላ ፖሊስ ማንም ሰው ከቤቱ እንዳይወጣና ወደ ቤቱም እንዳይገባ የከለከለ ሲሆን አሁን በቤቱ ውስጥ ምግብና ሌሎች መሠረታዊ ነገሮች አልቀው ወይም እያለቁ ሊሆኑ ስለሚችሉ አቶ ዳውድ ያሉበት ሁኔታና ደኅንነታቸው አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ አመልክቷል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጉዳዩን በማስመልከት በወቅቱ የሰላም ሚኒስትር ለነበሩት ሙፈሪያት ካሚል ደብዳቤ የጻፈ ሲሆን፤ በዚህም የአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሕግ ውጪ በቁም አስር ላይ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸው እንዳሳሰበው አመልክቷል። አምነስቲ በዚሁ ደብዳቤ ላይ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ በተቀበለችው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ግዴታ መሠረት ሃሳብን የመግለጽና የመደራጀት መብትን እንዲያከብሩና እንዲጠብቁና ጠይቋል። አምነስቲ መንግሥትን አቶ ዳውድ ኢብሳን በአስቸኳይ ከቁም አስሩ እንዲለቅ ወይም የፈጸሙት ጥፋት ካለና በቂ ማስረጃ ካለውም በተገቢው ሁኔታ ክስ እንዲመሰርት ጠይቆ ነበር። አቶ ዳውድ ኢብሳ ለረጅም ዓመታት የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን በሊቀመንበርነት ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ግንባሩ በሽብርተኛ ቡድንነት በተፈረጀበት ጊዜ መቀመጫቸውን ኤርትራ ውስጥ በማድረግ የትጥቅ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ ወደ ሥልጣን መጥተው ፖለቲካዊ ለውጥ በአገሪቱ ሲደረግ በኦነግ ላይ ተጥሎ የነበረው የሽብርተኛ ድርጅትነት ፍረጃ ተነስቶለት በአገሪቱ ፖለቲካዊ መድረክ ውስጥ ለመሳተፍ መሪዎቹ ወደ አገር ቤት ሲመለሱ የተወሰነው የቡድኑ ተዋጊም ወደ ተሃድሶ መግባቱ ይታወሳል። በግንባሩ ውስጥ በተደጋጋሚ መከፋፈል ያጋጠመ ሲሆን አቶ ዳውድ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ የተወሰኑ የቡድኑ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ሳይፈቱ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል። በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ በስፋት የሚንቀሰቀሰው መንግሥት ሸኔ የሚለውና እራሱን የአሮሞ ነጻነት ጦር የሚለው ቡድን በሚፈጽማቸው ጥቃቶች ምክንያት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ቡድን ተብሎ ተሰይሟል። ከቡድኑ ታጣቂ ኃይል በተጨማሪ አዲስ አበባ በገቡት የፖለቲካ አመራሮች መካከል ልዩነት ተፈጥሮ በግንባሩ የመሪነት ሚና ላይ መከፋፈል መፈጠሩ ይታወቃል። ከአቶ ዳውድ ኢብሳ የተለየውን ቡድን የሚመሩት አካላት ትክክለኛው የኦነግ መሪዎች መሆናቸውን በመግለጽ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ለመሳተፍ ሙከራ አድርገው ነበር። ይህ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን ኦነግ እውቅና የነፈገውና የግንባሩ ትክክለኛ አመራር መሆኑን የሚገልጸው አካል ባለፈው ዓመት ከተካሄደው ምርጫ በኋላ መንግሥት ተቃዋሚዎችን በሚመሰርተው መንግሥት ውስጥ ለማሳተፍ በገባው ቃል መሠረት የተወሰኑት በኦሮሚያና በፌደራል መንግሥቱ ውስጥ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-60622088 +business ጫንጮ አቅራቢያ ገንዘብ በጠየቁ አጋቾች እጅ የቆዩት የሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች ተለቀቁ "ከአዲስ አበባ በስተሰሜን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለበርካታ ሳምንታት በታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የኢትዮ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች መለቀቃቸውን የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ ገለጹ። ከአዲስ አበባ በ47 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ጫንጮ ከተማ አቅራቢያ ከሚገኘው የሲሚንቶ ፋብሪካ የምርት ግብዓት ማውጫ ስፍራ በታጣቂዎች ተይዘው የቆዩ ዘጠኝ ግለሰቦች ነበሩ ተብሏል። የሱሉልታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ግርማ ወዬሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በታጣቂዎቹ ታግተው የማስለቀቂያ ገንዘብ ተጠይቆባቸው የቆዩት ዘጠኙ ግለሰቦች ተለቅቀዋል። ለሳምንታት በዘለቀው በዚህ እገታ በቅድሚያ 27 ሰዎች የሲሚንቶ ፋብሪካው ሠራተኞች ተይዘው የነበረ ሲሆን፣ 18ቱ ከሁለት ሳምንታት በፊት መለቀቃቸውን ተዘግቧል። በታጣቂዎቹ ተለይተው ከቀሩት መካከል ስድስቱ የሕንድ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ፣ ሦስቱ አስተርጓ��ዎቻቸው እንደነበሩም በወቅቱ ተዘግቦ ነበር። አቶ ግርማ ታጋቾቹ ተለቅቀው ቀጣሪያቸው ኢትዮ-ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደሚገኝበት የጫንጮ ከተማ መመለሳቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የግለሰቦቹ እገታ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ለመሰብሰብ አላማ ያደረገ እንደነበረ የተነገረ ሲሆን፣ አሁን ታጋቾቹ በምን ሁኔታ እንደተለቀቁ ቢቢሲ ከአካባቢው አስተዳዳሪ ማብራሪያ ቢጠይቅም ስለተለቀቁበት ሁኔታ መረጃው እንደሌላቸው ተናግረዋል። ቢቢሲ በታጠቂዎች እገታ ስር የቆዩት ግለሰቦች ቀጣሪ የሆነውን ኢትዮ-ሲሚንቶን በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር በተደጋጋሚ ስልክ ቢደውልም ምለሽ ሳያገኝ ቀርቷል። ""ሕብረተሰቡን በማወያየት እና የፀጥታ ኃይሉን በማጠናከር እንዲህ አይነት ተግባራትን ለማስቆም ጠንካራ ሥራ እየሰራን ነው"" ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል። የሲሚንቶ ፋብሪካው ሠራተኞች በታጣቂዎች ከተያዙ በኋላ ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር በመሆን ጥበቃ ሲደርግ ብሎም ታጋቾቹን ለማግኘት መንግሥት የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል። አክለውም ተመሳሳይ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ የፀጥታ ኃይሉ በአካባቢው ተጠናከረ ክትትልና ጥበቃ እያደረገ መሆኑንም አስተዳዳሪው አቶ ግርማ ወዬሳ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ተመሳሳይ እገታና ጥቃቶች ማንነታቸው ባልተገለጸ ታጣቂዎች እንደሚፈጸም ሲዘገብ ቆይቷል። እንዲህ አይነት ድርጊቶች እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራውና መንግሥት 'ሸኔ' የሚለው በሽብርተኝነት የተፈረጀ ድርጅት የሚፈጽመው መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣንት ቢናገሩም፣ ቡድኑ ግን በእንዲህ ያለው ድርጊት ውስጥ እጁ እንደሌለ ያስተባብላል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60906446 +politics የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር የኮሮናቫይረስ መመሪያን በመተላለፋቸው ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተጠየቁ የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ኮሮናቫይረስን ተከትሎ የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ በመተላለፍ አንድ የመጠጥ ድግስ ላይ መታደማቸውን ካመኑ በኋላ በርካቶች ከኃላፊነታቸውን እንዲነሱ እየወተወቱ ነው። ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአውሮፓውያኑ 2020 ላይ ላደረጉት ነገር ይቅርታ ቢጠይቁም ሰሚ አላገኙም። ''በዚህ ምክንያት በርካቶች ቢቆጡ አልፈርድባቸውም'' ብለዋል ጠቅላዩ። የካቢኔ አባል የሆኑት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን ቆመዋል። ነገር ግን የስኮትላንድ ካቢኔ መሪው ዳግላስ ሮስ እና ሌሎቹ የእንደራሴ ምክር ቤት አባላት ዊሊያም ራግ፣ ካሮሊን ኖክስ እና ሮጀር ጌል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠይቀዋል። ትናንት ረቡዕ ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ይቅርታ ከጠይቁ በኋላ የስኮትላንድ ካቢኔ መሪው ዳግላስ ሮስ ''አስቸጋሪ ውይይት'' ነበር ብለዋል። መሪው አክለውም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያላቸው እምነት መሸርሸሩን የሚገልጽ ደብዳቤ መሰል ጉዳዮችን ወደሚከታተለው ምክር ቤት እንደሚጽፉ አስታውቀዋል። ''እሱኮ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው፤ የእሱ መንግስት ነው እነኚህን መመሪያዎች ያስቀመጠው፤ ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሰራው ስህተት ተጠያቂ መሆን አለበት'' ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ወግ አጥባቂዎቹ 54 የህዝብ እንደራሴዎች በአውሮፓውያኑ 1922 ለተቋቋመው ኮሚቴ ግልጽ ደብዳቤ የሚጽፉ ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልቅ ፈተና ሊገጥማቸው ይችላል። በርካታ የዩኬ ሚኒስትሮች በበኩላቸው የህዝብ እንደራሴዎቹ በሲቪል አገልጋይ ሱ ግሬይ የሚመራው መርማሪ ቡድን መረጃ እስነከሚያጠናቅር ድረስ ትንሽ እንዲታገሱ የጠየቁ ሲሆን ግኝቱ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል። ነገ�� ግን የእንደራሴ ምክር ቤት አባሉ ዊሊያም ራግ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እራሳቸውን መከላከል የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ነው የሚገኙት ብለዋል። '' የጠቅላይ ሚኒስትሩ እጣ ፈንታ በመርማሪው ኮሚቴ ግኝት ላይ ብቻ የተንጠለጠለ መሆን የለበትም'' በማለት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ሌላኛዋ የህዝብ እንደራሴ ቶሪ ካሮላይን በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መላውን ወግ አጥባቂ ቡድን እየጎዱ ስለሆነ በፍጥነት ከስልጣናቸው መልቀቅ አለባቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ከዚህ በፊትም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የሰላ ትችት ይሰነዝሩ የነበሩት የህዝብ እንደራሴዋ በአይቲቪ ላይ በቀረቡበት ወቅት ''በትክክል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደካማ ጎናችን ናቸው'' ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋ ይቅርታ መጠየቃቸው ከምህረት ይልቅ ትልቅ ቀውስ ነው ይዞባቸው የመጣው። ሌላው ቀርቶ ጥቂት የማይባሉ የእርሳቸው ደጋፊ የህዝብ እንደራሴዎች ጭምር ቦሪስ ጆንሰን ከኃላፊነታቸው ይነሱ እያሉ ይገኛሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-59976252 +health በአሜሪካ የኮቪድ ክትባት ያልተከተበው ግለሰብ የልብ ንቅለ ተከላ ተሰረዘ "በአሜሪካ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ታካሚው የኮቪድ-19 ክትባት ባለመውሰዱ የልብ ንቅለ ተከላውን ሰረዘ። ዲጄ ፈርጉሰን የተሰኘው የ31 ዓመት ታካሚ አንገብጋቢ የሆነ የልብ ንቅለ ተከላ የሚያስፈልገው ቢሆንም በቦስተን የሚገኘው ሆስፒታል ግን ግለሰቡን ከታካሚዎች ዝርዝር ውስጥ አስወጥቶታል። የብሪንግሃም እና የሴቶች ሆስፒታል የልብ ንቅለ ተከላውን የሰረዘው ታካሚው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ባለመውሰዱ ነው። የታካሚው ወላጅ አባት ዴቪክ፤ የኮቪድ ክትባት ከልጃቸው መሠረታዊ መርሆች ጋር የሚቃረን መሆኑን በመግለጽ ልጃቸው በክትባት እንደማያምን ገልጸዋል። ሆስፒታሉ በበኩሉ ንቅለ ተከላውን የሰረዝኩት መመሪያ በመከተል ነው ብሏል። ""በውስጥ አካላት ጉዳት ምክንያት በንቅለ ተከላ አዲስ የውስጥ አካል የተቀበለ ታካሚ በሕይወት የመትረፍ እድሉ ከፍተኛ እንዲሆን የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን"" ሲል የብሪግሃም እና የሴቶች ሆስፒታል ለቢቢሲ ገልጿል። የሆስፒታሉ ቃል አቀባይ ሆስፒታላቸው የታካሚዎችን በሽታ የመከላከል አቅም ከግምት በማስገባት ንቅለ ተከላው የመሳካት እድሉን እና ታካሚዎች ከቀዶ ጥገናው በኋላ የመትረፍ እድላቸው ከፍ ለማድረግ ከንቅለ ተከላ በፊት የኮቪድ-19 ክትባት እና የአኗኗር ዘይቤዎችን እንደሚመለከቱ ገልጸዋል። በሆስፒታሉ የአካል ክፍሎችን ለመተካት በተጠባባቂ መዝገብ ውስጥ ከሚገኙት 100,000 ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በአምስት ዓአመት ጊዜ ውስጥ የውስጥ አካል እንደማያገኙ እና የአካል ክፍሎች እጥረት ከፍተኛ መሆኑንም ገልጿል። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ፈርጉሰን ባጋጠመው የልብ ሕመም ምክንያት ላለፉት አራት ወራት ሆስፒታል ተኝቶ በመታከም ላይ ይገኛል። ለግለሰቡ ገንዘብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው የጎ ፈንድ ሚ አካውንት ላይ አዘጋጆቹ እንደገለጹት ፈርጉሰን ክትባቱን ከወሰደ በልቡ ላይ ተጨማሪ ሕመሞች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ሰግተዋል። የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ኤጄንሲ ሲዲሲ በበኩሉ የንቅለ ተከላ ተቀባዮች እና በአቅራቢያቸው ያሉ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንዲከተቡ እንዲሁም ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባት እንዲወስዱ ያበረታታል። ዶ/ር አርተር ካፕላን በኒዩ ግሮስማን የሕክምና ትምህርት ቤት የሕክምና ሥነ ምግባር ኃላፊ ናቸው። ለሲቢኤስ ኒውስ እንደተናገሩት፤ ማንኛውም የሰውነት አካል ከተቀየረ በኋላ የታካሚው በሽታ የመከላከል ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ይዘጋል። በተጨማሪም በተራ ጉንፋን እንኳን ለሞት ሊዳርግ ይችላል። ""የውስጥ አካል ክፍሎቹ በጣም አነስተኛ ቁጥር ስላላቸው አናሳ ���መዳን እድል ላለው ሰው ላለመስጠት እንሞክራለን። ሌሎች ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች ከንቅለ ተከላው በኋላ የመዳን እድላቸው ከፍተኛ ነው"" ሲሉ ተናግረዋል። ወላጅ አባቱም ልጃቸው በራሱ ሰውነት ላይ የመወሰን መብት እንዳለው እና ሕመሙንም በጀግንነት እየታገለ እንደሆነ ተናግረዋል። በዚህ አስቸጋሪ ግዜ ውስጥ ባሳየው ቁርጠኝነትም ለልጃቸው ያላቸው ክብር መጨመሩን ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60136750 +politics አንቶኒ ብሊንከን፡ አዲሱ ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት ማን ናቸው? "በአሜሪካ ጆ ባይደን አዲስ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ አዳዲስ ተሿሚዎችም የኃላፊነት ቦታቸውን ተቀብለዋል፤ ከነዚህም ውስጥ አንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ናቸው። አዲሱ ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት ማን ናቸው? የቢቢሲ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዩ ዘጋቢ ባርባራ ፕሌት አሸር በአንደበቷ ትነግረናለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ተሿሚዎችን ሹመት ስታደም ለሶስተኛ ጊዜዬ ነው። አስታውሳለሁ የዶናልድ ትራምፕ ልዑካን ሬክስ ቲለርሰንና ማይክ ፖምፒዮ ሹመት ወቅት መረማመጃውም ሆነ አዳራሹ በሰው ተሞልቶ ነበር። በርካቶችም ደስታቸውን፣ ተስፋቸውን እንዲሁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቶች የተዥጎደጎዱበት ወቅት ነበር። ለአዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሹመት ግን ሁሉ ፀጥ ረጭ ብሏል። ለዚህም ዋነኛው የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት በወጣው መመሪያ ምክንያት ነው። ነገር ግን በርካቶች በዓለ ሲመታቸውን ባይታደሙም፤ ፊት ለፊት ተገኝተው እንኳን ደስ አለዎት ባይሉም በዲፕሎማቱ ማህበረሰብ ውስጥ የእፎይታ ስሜት ተፈጥሯል። ""ብዙዎች በብሊንከን መምጣት ከመጠን በላይ በፈንጠዝያ ላይ ናቸው፤ በሱ መምጣት ብቻ ሳይሆን የቀድሞው ቡድን ቢሮውን ለቆ በመውጣቱ"" በማለት አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን በቤታቸው በዓለ ሲመቱን እየተመለከቱ ባሉበት ነግረውኛል። ብሊንከን አንጋፋ የሚባሉ ዲፕሎማት ናቸው። ለበርካታ አመታት በዘርፉ ላቅ ያለ ልምድን አካብተዋል። ነገር ግን በርካታ ሁኔታዎች ተቀይረዋል፤ ""እምነትንና ሞራልና ለመመለስ የሚገጥማቸው ፈተና ቀላል ላይሆን ይችላል"" ይላሉ እኚሁ ባለስልጣን። በትራምፕ አስተዳደር ወቅት ሁኔታውን መቀበል ያቃታቸው 1 ሺህ ሰራተኞች ለቅቀዋል። በሃሳብ ብንለያይም ከአስተዳደሩ ጋር እንቀጥላለን ያሉ ደግሞ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዲፕሎማሲያዊ ያልሆነ አካሄድ ወደ ጎን በመገፋት፣ በሬክስ ቲለርሰን አጉል አሰራር በመሰላቸት እንዲሁ የትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊ በሆኑት ማይክ ፖምፒዮ ፖለቲካ ገሸሽ እንዲደረጉ ሆኗል። ""ሁላችንም ቢሆን በአለም ላይ ያለን ገፅታ መቀየሩ ከፍተኛ ደስታ ይሰጠናል"" ይላሉ ባለስልጣኑ። ""በአራት አመቱ የትራምፕ አስተዳደር ገሽሽ ተደርጎ የነበረው ሁሉ ወደ ስራ ለመግባትና ነገሮችን ለመቀየር እየሞከረ ነው"" በማለት ያክላሉ። የፕሬስ ፅህፈት ቤቱ መተላለፊያ የነበረው የማይክ ፖምፒዮ ፎቶ ተነስቶ በምትኩ የተለያዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፎቶ እንዲሰቀል ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ የሥራ አስፈላጊነትና ባለሙያነት ጋር የተያያዘ በማይክ ፖምፒዮ የተፃፈ ትልቅ ቢልቦርድ የጆ ባይደን በዓለ ሲመትን ተከትሎ እንዲወርድ ተደርጓል። አዲሱ የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ላይ የረዥም አመት ልምድን አካብተዋል፤ ለዘመናትም የባይደን ቅርብ አማካሪ በመሆን ጠንከር ያለ ግንኙነትን መስርተዋል። በሹመታቸው ወቅት ለዘብ ባለ ንግግግራቸው የትራምፕን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በመቀልበስ እንደገና እንደሚፅፉት ያስገነዘቡ ሲሆን ከፍተኛ ድጋፍም ተችሯቸዋል። የአሜሪካ እንደራሴዎች��� ቢሆን ይህንን ከሌሎች አገሮች ጋር መጋተሩንና ""አሜሪካ ትቅደም"" የሚለውን አካሄድ ወደኋላ መተው ይፈልጋሉ። ብሊንከን መጀመሪያ አከናውናቸዋለሁ ብለው ቃል የገቧቸው ጉዳዮች ቢኖሩ የሩሲያ ሳይበር ጥቃትና የምርጫ ጣልቃ መግባት ምላሽ፣ ሳዑዲ በየመን የምታደርገውን የአየር ጥቃት ማስቆም፣ በትራምፕ አስተዳደር አሸባሪ ተብለው የተፈረጁትን የሁቲ አማፅያን ሁኔታ እንደገና መገምገም የሚሉ ናቸው። የሁቲ አማፅያን በአሸባሪነት መፈረጅ በየመን ያለውን የሰብዓዊ እርዳታዎች ላይ እክል ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ይታመናል። ኢራንን በተመለከተ ብሊንከን ባይደን ቃል የገቡትን የደገሙ ሲሆን ይኸም የ2015ቱን የኢራን የኒውክሊየር ስምምነትን መመለስ ነው። ባራክ ኦባማ በስልጣን ዘመናቸው ወቅት አሳክተዋቸዋል ከሚባሉት ጉዳዮች ውስጥ (JCPOA) ተብሎ የሚጠራው የኢራን የኒውክሊየር ፕሮግራም ሲሆን ፕሬዚዳንት ትራምፕ በ2018 ስምምነቱን አፍርሰዋል። ወደ ስምምነቱ እንዲመለሱ ግን ኢራን የገባችውን ቃል ስታከብር እንደሆነና ይህ የማይሆን ከሆነ በጥንቃቄ ሊታይ ይገባል ይላሉ። ቻይናን በተመለከተ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጠንከር ያለ አስተያየትና አካሄድ ጋር ይስማማሉ። ቻይናን ለማዳከም ትራምፕ ውድቅ ካደረጓቸው የዲሞክራሲ ደጋፊዎችና አለም አቀፍ ተቋማት ጋር መተባበር ያስፈልጋል በማለት አፅንኦት ይሰጣሉ። የአዲሱ ከፍተኛ ዲፕሎማት ዋነኛ አላማና ተልዕኮ የአሜሪካን መሪነት ቦታ እንደገና በዚያ መንገድ መመለስ ነው። ነገር ግን በተሾሙበት ቀን ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ውይይት በመጥፎ ይታይ ከነበረው የአሜሪካ አስተዳደር ጋር ተያይዞ እንዴት የቀድሞ አጋሮቿ ያምኗታል የሚል ነበር ። ነገር ግን ብሊንከን አሜሪካ ወደቀደመ ስፍራዋ ለመመለስ ያለው ፍላጎት ከአጋሮቿም በኩል የመጣ ነው ይላሉ። በመጀመሪያ ቀናቸው ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ውይይት ከሚዲያውና ከጋዜጠኞች ጋር ለመስራት ያላቸውን ቀናነት በግልፅ አሳይተዋል። ይህ አካሄድ ደግሞ ከቀድሞው አስተዳደደር ተቃራኒ ነው። ማይክ ፖምፒዮ እንደ አለቃቸው ሚዲያን አይወዱም አያዳምጡም፤ አንዳንድ ጊዜም ሲያወግዙ ይሰማሉ። ለጥያቄዎቻችን ኢሜይል መልስ ለማግኘት በጣም ፈታኝ ነበር። ደፈር ያሉ የኮሚዪኒኬሽን ቡድኑ አባላት ምንም የምንለው የለም የሚል መልስ ይሰጡን ነበር። የብሊንከን አካሄድ ልታይ ልታይ ይሉ ከነበሩት የማይክ ፖምፒዮ ሁኔታ ተቃራኒ ነው። ሆኖም በአሁኑ ወቅት በአዲሱ አስተዳደር የፕሬዚዳንቱ የአየር ንብረት ለውጥ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑትና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸው ከፍተኛ ስፍራ የተጎናፀፉት የቀድሞ አለቃቸው ጆን ኬሪ ጋር ይወዳደራሉ። ነገር ግን ብሊንከንም ቢሆኑ ለየት ያለ ባለታሪካቸው የተጎናፀፉት ማንነት አለ። አያታቸው በሩሲያ የነበረውን የፀረ- ይሁዲዎች ነውጥ ፈርተው ወደ አሜሪካ በስደት መጡ፤ ፖላንዳዊ እንጀራ አባታቸው እንዲሁ በናዚዎች ከተቃጣባቸው ግድያ በአሜሪካውያን ወታደሮች የዳኑ ናቸው። ""ማንነታችን ይኼ ነው። በአለም ላይ የምንወክለውም ይህንኑ ነው። እንደ ሰው ጉድለቶች ቢኖሩንብንም ምርጥ ለመሆን እንሞክራለን"" ብለዋል። በአሁኑ ወቅት አሜሪካ አሁንም ቢሆን ጠቃሚነቷን ማረጋገጥ የስራቸው ማዕከል እንደሆነ ያስባሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-55829616 +politics የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ሶስተኛ የስልጣን ዘመናቸውን አወጁ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ለሶስተኛ ጊዜ አገሪቷን ሊመሩ ነው። ዢ ዢንፒንግ የቻይናው ገዥ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ባደረገው ጉበኤ ዋና ጸሓፊ አድርጎ መምረጡን ተከትሎም ነው ለሶስተኛ ጊዜ ስልጣናቸው የተራዘመው። የፓርቲው ዋና ጸሃፊ በሃ���ሪቱ የመሪነት ቦታ የሚያስገኝ ሲሆን መጋቢት በሚደረገውም የብሄራዊ ህዝቦች ጉባኤ በይፋ ስልጣናቸው ይጸድቃል። ፓርቲው በተጨማሪም 25 አባላት ያሉትን የፖሊት ቢሮ እንዲሁም ሰባት አባላት ያሉትን ቋሚ የፖሊት ቢሮን መርጧል። ፕሬዚዳንቱ ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸውንም ያስተዋወቁ ሲሆን ከነዚህም መካከል የቀድሞው የሻንጋይ ፓርቲ መሪ ይገኙበታል። ሊ ኪያንግ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ይሆናሉ። ዢ ጂንፒንግ በዛሬው ዕለት አዲሱን የፖሊት ቢሮ ቋሚ ኮሚቴንም እየመሩ ወደ መድረክ መጥተዋል። ፕሬዚዳንቱ ለመገናኛ ብዙኃንም ፓርቲያቸው በትናንትናው ዕለት ያደረገውን ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዳጠናቀቀና ገልጸው “ጥንካሬያችንን በማሰባሰብ በአንድነት ወደፊት እንቀጥላለን” ብለዋል። አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጉባኤውን በከፍተኛ ፍላጎት ሲከታተል መቆየቱን ጠቅሰው የሀገር መሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክትና ደብዳቤ መላካቸውን በመግለጽ ለሁሉም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከዚያም አዲሱን የፖሊት ቢሮ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በማስተዋወቅ “ሁሉንም በደንብ ታውቋቸዋላችሁ” በማለት ተናግረዋል። ዢ ሶስተኛ የስልጣን ዘመናቸውን አውጀው አዲሱ የአመራር ቡድናቸውን ካስተዋወቁ በኋላም ንግግር አድርገዋል። በዚህ ንግግራቸው ቻይናን የምትመራበት አቅጣጫ በተመለከተ ፍንጭ ሰጥተዋል። ሃገሪቱ ለአለም ኢኮኖሚ በሯን እየዘጋጀች ነው የሚል ስጋት በጨመረበት ወቅት ፕሬዚዳንቱ “ ቻይና ያለተቀረው አለም ማደግ አትችልም እናም አለምም ቻይናን ይፈልጋል” ብለዋል። አክለውም “ከአርባ ዓመታት በላይ ባደረግነው የለውጥ እንቅስቃሴ ሁለት ተአምራትን መፍጠር ችለናል። ፈጣን የኢኮኖሚ ልማት እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ማህበራዊ መረጋጋት ነው” ብለዋል https://www.bbc.com/amharic/articles/cx8w5pxrz4vo +sports የኢትዮጵያ ታሪክ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያና ሜዳሊያ የተገናኙት ገና ከጅምሩ ፊንላንድ ሄልሲንኪ በተደረገው የመጀመሪያው ውድድር ነበር። በዚህ የመጀመሪያው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ለኢትዮጵያ እንዲሁም ለአፍሪካ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ከበደ ባልቻ ነው። ከበደ በማራቶን ውድድር ሁለተኛ ወጥቶ የብር ሜዳሊያ በማጥለቅ ችቦውን አቀጣጠለ። ነገር ግን ቀጥሎ በጣሊያኗ ከተማ ሮም በተካሄደው ሁለተኛው ውድድር ኢትዮጵያ አልተሳተፈችም ነበር። በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በርካታ ሜዳሊያ በመሰብሰብ አሜሪካንን የሚደርስባት የለም። ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ደግሞ ጎረቤት አገር ኬንያ ናት። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር እስካሁን ባከማቻቸው ሜዳሊያዎች ከዓለም ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ተሾመ ቀዲዳ የ2022 የኦሬገን ሻምፒዮናን ሳይጨምር ኢትዮጵያ 85 ሜዳሊያዎች አሏት ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። “ኢትዮጵያ በዓለም ቻምፒዮና ታሪክ 29 ወርቅ፣ 30 ብር እንዲሁም 26 የነሐስ ሜዳሊያዎች፤ በአጠቃላይ 85 ሜዳሊያ አላት።” በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የተለየ ታሪክ አላት የሚለው ጋዜጠኛው፣ አትሌት ከበደ ባልቻም በማራቶን መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ የብር ሜዳሊያ ያስገኘ አፍሪካዊ መሆኑን ያወሳል። በፈር ቀዳጁ ውድድር ኢትዮጵያ በከበደ ባልቻ ነሐስ ሜዳሊያ ከዓለም 15ኛ ሆና አጠናቃለች። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት የቻለች ብቸኛዋ አፍሪካዊት አገር ናት። በወቅቱ ምሥራቅ ጀመርን [ጀርመን አንድ ከመሆኗ በፊት] 19 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ፣ የውድድሩ ኃያል አገር አሜሪካ ደግሞ ሁለተኛ ሆና ነበር። በጣልያኗ ሮም በተካሄደው ��ለተኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና “የአትሌቲክስ ቡድን እየመራ የሚጓዝ አሠልጣኝ ባለመገኘቱ ነው ኢትዮጵያ ያልተሳተፈችው” ይላል ጋዜጠኛ ተሾመ። ኢትዮጵያ በዚህ ታላቅ የአትሌቲክስ መድረክ የመጀመሪያውን ወርቅ ያገኘችው በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ አማካይነት ነው። ኃይሌ የጀርመኗ ስቱትጋርት ባዘጋጀችው አራተኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ ማምጣት ችሏል። አትሌቱ በዚህ ሳይገታ በ5 ሺህ ውድድር ደግሞ የነሐስ ሜዳሊያ ለአገሩ አስገኝቷል። አትሌት ፊጣ ባይሳ ደግሞ ሌላ ነሐስ አክሎ ኢትዮጵያ በሦስት ሜዳሊያ አሸብርቃ ተመለሰች። ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መድረክ በስዊድኗ ጉተምበርግ ከተማ እስከተሰናዳው ውድድር ድረስ ከአፍሪካ አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ ቆየች። ነገር ግን በጉተምበርግ በተካሄደው ውድድር ኬንያ ወደ ኃይልነት መጣች። በዚህ ውድድር ኬንያ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጨምሮ ስድስት ሜዳሊያ በመሰብሰብ ስሟን ከፍ አደረገች። በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያና ኬንያ ከጉተምበርጉ ፍልሚያ በኋላ ፉክክራቸው እየበረታ መጣ። በፈረንጆቹ 2003 በተካሄደው የፓሪሱ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 3 ወርቅ፣ 2 ብርና 2 ነሐስ በማምጣት ከዓለም አራተኛ ሆና ያጠናቀቀችበት መድረክ የሚረሳ አይደለም ይላል ጋዜጠኛ ተሾመ። በሄልሲንኪ የተካሄደው 10ኛው ሻምፒዮና ግን ልዩ ነበር ሲል ያክላል። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ከአሜሪካና ከሩሲያ በመቀጠል በ3 ወርቅ፣ በ4 ብርና በ2 ነሐስ ከዓለም ሦስተኛ ሆና አጠናቀቀች። ይህ የሄልሲንኪው ውድድር “አረንጓዴው ጎርፍ” ተብሎ ይጠራል። አረንጓዴው ጎርፍ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት ዓለምን አጀብ ያሰኙበት ዘመን ነው። አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 2 ወርቅ ባጠለቅችበት በዚህ ውድድር የአረንጓዴው ጎርፍ አርማዎቹ መሠረት ደፋር፣ ብርሃኔ አደሬ እና እጅጋየሁ ዲባባ የነበራቸው ተሳትፎ የሚዘነጋ አይደለም። በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ደግሞ ቀነኒሳ በቀለና ስለሺ ስህን ተከታትለው በመግባት ሄልሲንኪን የማይረሳ አድረጓት። ከሁለት ዓመታት በኋላ ግን ጃፓን ኦሳካ ባሰናዳችው ውድድር ድል ወደ ኬንያ ዞረ። ኬንያ በዚህ ሻምፒዮና 5 ወርቅን ጨምሮ 15 ሜዳሊያዎች አሸነፈች። ከዚያ በኋላ በነበሩት የበርሊን፣ ዴጎ፣ ሞስኮ፣ ቤይጂንግ፣ ለንዶን፣ ዶሃ ላይ ኬንያ በሜዳሊያ ብዛት ኢትዮጵያን እየመራች ቆይታለች። ደራርቱ ቱሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና የተሳተፈችው በፈረንጆቹ 1991 ቶኪዮ በተዘጋጀው ውድድር ነበር። ምንም እንኳ ደራርቱ በተሳተፈተችበት የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ሜዳሊያ ባታመጣም በቀጣዩ ዓመት ባርሴሎና በተዘጋጀው ኦሊምፒክ ላይ ወርቅ ማጥለቅ ችላለች። የአገሯን ስም በተለያዩ መድረኮች ያስጠራችው ደራርቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆና ከተመረጠች በኋላ ለውጥ ማምጣት ችላለች ቢባል ማጋነን አይሆንም። ነገር ግን ለደራርቱ ሁኔታዎች ሁሉ የተመቻቹ ነበሩ ማለት ከባድ ነው። ደራርቱ ፌዴሬሽኑን መምራት ከጀመረች ወዲህ ሁለት ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና፤ አንድ ጊዜ በኦሊምፒክ መድረክ፤ አንድ ጊዜ ደግሞ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ተሳትፋለች። በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ በተሰናደው የ2019 የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብርና አንድ ነሐስ ይዛ ተመልሳለች። በዚህ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በሚታወቁበት የመካከለኛና ረዥም ርቀት ውድድር የተለመደውን ወርቅ ማስመዝገብ ባይችሉም ተስፋ ያላቸው አትሌቶች ታይተዋል። ኢትዮጵያ በመድረኩ በስምንት ሜዳሊያ አምስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች። ከዚህ በኋላ በደራርቱ የተመራው የኢትዮጵያ ���ትሌቲክስ ቡድን ታላቅ ወደ ሚባለው የኦሊምፒክ መድረክ ነው ያቀናው። በ2022 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ያገኘችው ሜዳሊያ ብዛት አራት ነው። ይህ ውጤት ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ ካመጣቻቸው ዝቅተኛ ከተባሉት የሚመደብ ነው። ቀጥሎ ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ዓለም አቀፍ መድረክ ባለፈው መጋቢት የተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ፍልሚያ ነው። ይህ መድረክ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ነበር። ኢትዮጵያ፤ በአራት ወርቅ፣ በሦስት ብርና በሁለት የነሐስ አሜሪካን አስከትላ ከዓለም ቁንጮ ሆና አጠናቃለች። በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት እየተካሄደ ባለው የዘንድሮው የዓለም ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ውጤት ከጅምሩ አመርቂ መሆን ችሏል። በተለይ በመድረኩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የምንጊዜም ተቀናቃኝ የሆነችው ኬንያ በምትታወቅባቸው ሩጫዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ብቅ ብቅ ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ኬንያና ኢትዮጵያ ድንበር ብቻ አይደለም የሚጋሩት። ሜዳሊያ የሚታደልበት የአትሌቲክስ መድረክንም ጭምር እንጂ። በተለይ በረዥም ርቀት የሩጫ ውድድር ሁለቱ አገራት በየመድረኩ አንገት ለአንገት ሲተናነቁ ማየት አዲስ አይደለም። ኃይሌና ፖልቴርጋን በሚሊ ሜትር ተቀዳድመው ሲገቡ የነበረውን ትዕይንት ማን ይዘነጋል። ቀነኒሳና ኪፕቾጌ በሁለት ሰከንድ ልዩነት የጨበጡት የማራቶን ክብረ ወሰንም እንዲሁም ተመዝገቦ የሚኖር ነው። ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በመካከለኛ ርቀት ማለትም በ5 ሺህና በ10 ሺህ ሜትር፤ ኬንያ ደግሞ በአጭርና በመካከለኛ የ800፣ የ1500 እና የ3000 ሜትር ርቀቶች ሲነግሱ ማየት የተለመደ ነው። ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኬንያዊያን በመካከለኛ ርቀት ኢትዮጵያን ሲፋለሙ ተመልክተናል። ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደግሞ በ1500 እና 3000 ሜትር መሰናክል ውድድሮች ኬንያዊያንን መፈተን ይዘዋል። ለምሳሌ በ2019 የዶሃ ዓለም ሻምፒዮና በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ኬንያዊው ኪፕሩቶ ታዳጊው ኢትዮጵያዊ ሌሜቻ ግርማን በሚሊ ሜትር ቀድሞ ወርቅ ያጠለቀበት ውድድር የሚዘነጋ አይደለም። ለሜቻ ግርማ በ3000 መሰናክል ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ያስገኘ የመጀመሪያው ወንድ አትሌት ነው። አትሌት ሶፊያ አሰፋ በ2013 ሞስኮ ላይ ያገኘችው ነሐስ በርቀቱ ብቸኛው የኢትዮጵያ ሜዳሊያ ነበር። በዘንድሮው የኦሪገን ዓለም ሻምፒዮና የታየውም ይህ ነው። ለሜቻ ግርማ በርቀቱ ሁለተኛ ብሩን በተከታታይ አጥልቋል። ጉዳፍ ፀጋይ ደግሞ በ1500 ሜትር ለአገሯ ብር አስገኝታለች። ኬንያዊቷ ፌይዝ ኪፕየጎን ለአገሯ ብቸኛውን ወርቅ አስገኝታለች። የኬንያ መገናኛ ብዙኃን በዘንድሮው የኦሪገን ውጤት ደስተኛ አለመሆናቸውን እየገለጡ ነው። ኬንያ ባለፈው የዓለም ሻምፒዮናም ሆነ በኦሊምፒክ መድረክ ከኢትዮጵያ ልቃ ብታጠናቅቅም በዓለም የቤት ውስጥ ውድድርና በአሜሪካው የዓለም ሻምፒዮና የተመዘገበው ውጤት አመርቂ ሆኖ አልተገኘም። በአሜሪካዋ ኦሪገን ግዛት እየተካሄደ የሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መጪው እሁድ ይጠናቀቃል። በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ  በወንዶች እና ሴቶች ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉ የውድድር ዘርፎች እየተሳተፈች ትገኛለች። በዚህ ውድድር እስከ አሁን ሦስት የወርቅ ሜዳሊያ፣ አራት ብር እና አንድ የነሃስ ሜዳልያ በማምጣት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ እሑድ እለት የሚካሄዱት የ800 እና 5000 ሜትር ውድድሮች በጉጉት ይጠበቃሉ። ኢትዮጵያ እስከ አሁን በዚህ ውድድር ካገኘቻቸው ስምንት ሜዳሊያዎች አምስቱ በሴት አትሌቶች የተገኙ ናቸው። የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በፈረንጆቹ ከ1983 ጀምሮ በየሁለት ዓመት ልዩነት መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ5000 እና በ10000 ሜትር ውድድሮች ስመ ጥር ሆነውበታል። ቀደም ሲል በ10 ሺህ ሜትር፣ በ5 ሺህ ሜትር እና በግማሽ ማራቶን፤ ሦስት የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ በዚህ ታላቅ መድረክ አሸናፊነቷን አስጠብቃለች። ለተሰንበት ከውድድሩ በኋላ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠችው አስተያየት “ህልሜ እውን ሆኗል። ይህ ድል ከዓለም ክብረወሰን በበለጠ ለእኔ ትልቅ ነው። በውጤቱ በጣም ደስተኛ ነኝ” ብላለች። አትሌት ጎተይቶም ገብረሥላሴም በሴቶች ማራቶች የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን በመስበር አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል። በኦሪገን መድረክ ደግሞ በማራቶን ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ከዚህ በፊት ማሬ ዲባባ በ2015 ቤይጂንግ በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆና ነበር። ኢትዮጵያ፤ በተለይ በፈረንጆቹ ከ1999 እስከ 2007 ባሉት ዓመታት በ10 ሺህ እና በ5 ሺህ ሜትር ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ውድድሩን በማሸነፍ በርካታ ሜዳሊያ አካብታለች። ጌጤ ዋሚ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ወርቅነሽ ኪዳኔ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ አልማዝ አያና እና ሌሎች በአትሌቲክሱ ዓለም አገራቸውና ያስጠሩ ሴት አትሌቶች ናቸው። አሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ያለውን ውድድርን ሳይጨምር ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው የአትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች 85 ሜዳሊያዎችን ስታስመዘገብ፣ ከዚህ ውስጥ ደግሞ ወደ ግማሽ የሚጠጋው የተገኘው በሴቶች ነው። በዚህም 38ቱ ሜዳሊያዎች በ1500፣ በ3000፣ 5000 እና በ10000 ሜትር እንዲሁም 2 ሜዳሊያዎች በማራቶን ውድድሮች ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ያሰነፉት ሲሆን በአጠቃላይም 40 ሜዳሊያዎችን አስገኝተዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c51dx3qnynpo +health ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መጨመር እንዳሳሰባት ገለፀች "በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ደቡብ ሱዳን እንዳሳሰባት ገልፃለች። መጋቢት ወር ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጀምሮ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመጣባት ኢትዮጵያ በባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳኗ መዲና ጁባ በየቀኑ ከአዲስ አበባ በረራ የሚያደርግ ሲሆን ይሄም ሁኔታ አስጊ ነው በማለት የጤና ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። ""በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር በእርግጥ ሊያሳስበን ይገባል፤ ስለዚህ የመከላከያ መንገዶቻችንንም ልናጠናክር ይገባል"" በማለት የጤና ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ዶክተር ቶው ሎይ ሲንጎት በጁባ ለሚገኙ ሪፖርተሮች ተናግረዋል። ሆኖም ከአዲስ አበባ ወደ ጁባ በየቀኑ የሚደረጉት በረራዎችም እንደሚቀጥሉ የተናገሩት ቃለ አቀባይ ሁሉም አገራት ለዜጎቹ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት እንደሚደረገው ከፍተኛ ጥንቃቄን ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል። ""ከአዲስ አበባ የሚደረጉ የየቀኑ በረራዎች የሚቀጥሉ ይሆናል። አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ካልሆነ አይቆምም"" ብለዋል ዶክተር ቶው ሎይ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 59 ሺህ 648 ደርሷል፤ ከነዚህም ውስጥ 21 ሺህ 789 ያገገሙ ሲሆን 933 ህይወታቸው እንዳለፈ በትናንትናው ዕለት የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጋራ መግለጫ አስፍሯል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54068173 +health ከአምስት ወራት በኋላ የሕክምና መገልገያዎች ዛሬ ትግራይ መድረሳቸውን ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል አስታወቀ "በጦርነት ክፉኛ ለተጎዳችው ትግራይ ከአምስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው ዕለት ጥር 18/2014 ዓ.ም ህይወት አድን የህክምና መገልገያዎችን ማድረሱን ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ገለጸ��� ከ15 ወራት በላይ በዘለቀው ጦርነት መድኃኒትና ምግብን ጨምሮ በመሰረታዊ ቁሳቁሶች እጥረት እየተሰቃየችው ላለችውም ትግራይ ይህ ዜና የተስፋ ጭላንጭል ነው ተብሏል። በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የጤና አስተባባሪ አፖሎ ባራሳ ""የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ ወደ ትግራይ ሆስፒታሎች መድረሱ ትልቅ እፎይታ ነው። ድጋፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ማስቀጠል የሚያስችል ነው"" ብለዋል። በዛሬው ዕለት ጥር 18/2014 ዓ.ም አስፈላጊ መድኃኒቶችን የያዘ አውሮፕላን ወደ ትግራይ መዲና መቀለ እንደደረሱም ተገልጿል። በመጪዎቹ ቀናትም ተጨማሪ በረራዎች እንዲሁም እርዳታ የጫኑ መኪኖችንም እንደሚልክ ድርጅቱ አስታውቋል። ይህም ተፈጻሚ የሆነው መንግሥት በህወሓት ቁጥጥር ስር ለምትገኘው የትግራይ ክልል አስፈላጊ የሆኑ የምግብ እና የሕክምና አቅርቦቶችን በአየር ለማጓጓዝ ለማመቻቸት የገባውን ቃል ተከትሎ ነው። ሆኖም በትግራይ እና አፋር ክልሎች አዋሳኝ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እርዳታውን በጭነት መኪኖች ለማድረስ የበለጠ ሊያወሳስበው እንደሚችልም እየተገለጸ ነው። ድርጅቱ ቀደም ሲል በትግራይ ያለው የመድኃኒት እና ሌሎች የህይወት አድን ቁሳቁሶች እጥረት የህክምና ባለሙያዎች ጓንቶችን እንደገና አጥበው እንዲጠቀሙ አስገድዷቸዋልም ብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት በትግራይ ክልል ካለፈው ዓመት ሐምሌ አጋማሽ የሕክምና ቁሳቁሶች ለማቅረብ በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ሊፈቀድለት እንዳልቻለ ገልጾ ነበር። ሆኖም በጦርነቱ ለተጎዱት አማራና አፋር ክልሎች የሕክምና ቁሳቁሶች ማድረስ መቻሉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ በቅርቡ በትግራይ አንዳንድ የጤና አገልግሎቶች በአስፈላጊ መድኃኒት እጥረት ሳቢያ ሥራ አቁመዋል ብሏል። በትግራይ ክልል የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች ህፃናትን ጨምሮ ህሙማን በከፍተኛ መድኃኒት እጥረት ምክንት እየሞቱ መሆናቸውን ከሰሞኑ ባወጡት መግለጫ እንዲሁ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ከተጣለው እገዳ ጋር ተያይዞ መድኃኒት እና ሌሎች የህይወት አድን ቁሳቁሶች ወደ ሆስፒታሎች ባለመድረሳቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ መንግሥት ምንም አይነት እገዳ በትግራይ ላይ እንዳልጣለና በአሁኑ ወቅት ለተፈጠረው ችግር ህወሓትን ተጠያቂ አድርገዋል። በክልሉ መዲና መቀለ በሚገኘው ትልቁ የጤና ተቋም የሚገኙ ዶክተሮች እንደተናገሩት በቀዶ ህክምና ወቅት የሚያስፈልጉ በደም ስር የሚሰጡ እና የሰመመን መስጫ መድኃኒቶች ባለመኖራቸው ቀዶ ህክምና ማድረግ አለመቻላቸውን ነው። የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሠራተኞች ባወጡት መግለጫ በተደጋጋሚ የሚከሰተው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና ያልተሟላ የኦክስጂን አቅርቦት ለታካሚዎች ሞት ምክንያት ነው ብለዋል። ጓንቶች፣ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ አንቲባዮቲክ መድኃኒቶች፣ የህመም ማስታገሻዎች፣ በምጥ ላይ ላሉ ሴቶች ወሳኝ መድኃኒቶች እንዲሁም ለተለያዩ የአዕምሮ ህመም የሚውሉ መድኃኒቶችና መሰረታዊ የላብራቶሪ ምርመራዎች በሌሉበት ሁኔታ በሆስፒታሉ ውስጥ እንዲሰሩ መገደዳቸውን ጠቅሰዋል። የህክምና ባለሙያዎቹ የመገልገያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶች እንደሚጠቀሙና ያለውም ብቸኛ አማራጭ እሱ በመሆኑ አሁንም አስቸኳይ እንክብካቤ ለሚያስፈልጋቸው ህሙማንም በቻሉት መጠን እየተንከባከቡ እንደሆነ አስፍረዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና የህወሓት ባለሥልጣናት የህክምና ቁሳቁሶችን ጨምሮ የእርዳታ አቅርቦትን በማደናቀፍ እርስ በእርሳቸው ሲወቃቀሱ ይሰማል። ከጦርነቱ ጋር ተያ��ዞ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶች መብራት፣ ውሃ፣ ስልክ፣ ትራንስፖርትና የባንክ አገልግሎቶች አሁንም እንደተቋረጡ ናቸው። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። ከአስራ አራት ወራት በላይ ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ የአፍሪካ ሕብረት እንዲሁም የሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ እና ሌሎች አጋሮች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥታቸው ከትግራይ ኃይሎች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን መናገራቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ወኪል (ኤፒ) ዘግቧል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60144165 +politics ፖለቲከኞች በአዲሱ ዓመት ሰላም እንዲያሰፍኑ 24 የሲቪል ማኅበራት ጠየቁ "በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች ምክንያት እየደረሰ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ አሳስቦናል ያሉ 24 አገር በቀል የሲቪል ማኅበራት በግጭቶቹ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው አካላት በአዲሱ ዓመት ሰላም እንዲያወርዱ ጠየቁ። አስር ነጥቦች ባለው በዚሁ ጥሪያቸው፤ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ቀውሶቹ በውይይት እንዲፈቱ የተደረጉ ጥረቶች እስካሁን ድረስ መፍትሔ አለማምጣታቸውን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ ሚዲያ ሴቶች ማኅበር፣ ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ፣ ሴታዊት ንቅናቄ፣ ሴንተር ፎር ጀስቲስ፣ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር፣ ኢኒሺዬቲቭ አፍሪካ፣ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት እና የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል ከተቋማቱ ውስጥ ይገኙበታል። ""ጦርነት እና ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ደኅንነት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ በተለይም ሕፃናት፣ ሴቶች እና አረጋውያን ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸው አሳስቦናል"" ሲሉ ተቋማቱ ገልጸዋል። እንዲሁም ለጦርነት መንስኤ የሆኑ የተለያዩ የፖለቲካ ችግሮች በጦርነት በዘላቂነት ሊፈቱ አይችሉም የሚል እምነት አለን ያሉት የሲቪል ተቋማቱ፤ በጦርነት ለመፍታት የሚደረግ ጥረት ዋናው ዋጋ ከፋይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ብለዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩትን ከቀያቸው አፈናቅሎ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብን ለረሃብ አደጋ አጋልጧል። ይህ ጦርነት በተለይም በወጣቱ የማኅበረሰብ ክፍል ላይ እያስከተለ ያለው እልቂት፣ የምጣኔ ሀብት ውድመት እንዲሁም የከፋ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በዓለም አቀፍ ሕጎች የተወገዘ ብሎም በአገሪቷ መጻኢ እድል ላይ መጠነ ሰፊ ጫና የሚያስከትል ሆኖ እንዳገኙት ማኅበራቱ ገልጸዋል። የዚህ ጦርነት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራዎች ከአገር አቀፍ ጉዳት አልፎ ወደ ቀጠናዊ ቀውስ ሊያመራ የሚችልበት እድል በመኖሩ እንዲሁም ጦርነቱ በመሠረተ ልማቶች ውድመት በማስከተል ኢትዮጵያን ወደ ከፋ ድህነት የሚጎትት ሆኖ በማግኘታቸው የሰላም ጥሪ እንዳደረጉ አስታውቀዋል። ከምጣኔ ሀብታዊ ብሎም ከፖለቲካዊ ኪሳራዎች ባሻገር ይህ ጦርነት በማኅበራዊ ግንኙነት ላይ እያስከተለ የመጣው ጫና አሳሰቢ ነው ያሉት ተቋማቱ፤ በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ፣ በሶማሊ፣ በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በደቡብ ክልሎች የሚካሄዱ ግጭቶችም እንዳሳሰቧቸው ተናግረዋል። ""ሕፃናት ልጆቻችን፣ በዕድሜ የገፉ ወገኖቻችን እና ሴቶቻችን በተለየ ሁኔታ ለመከራ ተጋላጭ እየሆኑ፣ ጾታዊ ጥቃትንና ግድያን ጨምሮ የተለያዩ የሰብዓዊ ጥሰቶች ሰለባ በመሆን ላይ ናቸው"" ሲል ጥሪው ያስነብባል። ""ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት የም���ጠቀምባቸው የሽምግልና እና የዕርቅ ባህላዊና ማኅበራዊ አቅሞቻችንን ለመጠቀም እያደረግን ያለነው ሁለገብ ጥረት እስካሁን ሰላምን ሊያረጋጋጥልን አልቻለም። በመሆኑም ሕዝባችንን ለዘመናት ደግፈው ያቆዩ ማኅበራዊ እሴቶቻችን ሳይቀሩ አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ"" ሲሉም ማኅበራቱ ስጋታቸውን ገልጸዋል። በእነዚህ ግጭቶች ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ የፖለቲካ ብሎም የጦር ኃይሎች በመጪው ዓመት ቆም ብሎ በማሰብ የሰላም አማራጭን እንዲመርጡ ጠይቀዋል።" https://www.bbc.com/amharic/58511480 +sports ሩሲያ ከሁሉም ስፖርታዊ ውድድሮች ልትታገድ ትችላለች "የዓለማ አቀፉ የጸረ አበረታች መድሃኒቶች ኤጀንሲ (ዋዳ) ከሩሲያ ላቦራቶሪዎች የተገኙት መረጃዎች ወጥ ስላልሆኑ ሃገሪቱ ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ልትታገድ ትችለች ብሏል። ሩሲያ ጉዳዩን በአግባቡ ለማስረዳት ሶስት ሳምንታት የተሰጣት ሲሆን አጥጋቢ ምላሽ የማትሰጥ ከሆነ ግን ከኦሎምፒክና የዓለም ሻምፒየንሺፕ ውድድሮች መታገዷ እንደማይቀር ኤጀንሲው አስታውቋል። በተጨማሪም ማንኛውም አይነት ውድድሮች ከማዘጋጀትም ልትታደግ እንደምትችል አስጠንቅቋል። • አባታቸውን የገደሉት እህትማማቾች እንዲለቀቁ ፊርማ እየተሰበሰበ ነው • ሩሲያዊው ቄስ በባለቤታቸው ""ሀጥያት"" ለስደት ተዳረጉ ''ከላቦራቶሪ ውጤቶቹ መካከል ብዙዎቹ መጥፋታቸውን አረጋግጠናል'' ሲሉ ጆናታን ታይለር የተባሉ የዓለማ አቀፉ የጸረ አበረታች መድሃኒቶች ኤጀንሲ ከፍተኛ ሃላፊ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ሩሲያ ተመሳሳይ ክስ ቀርቦባት ለሶስት ዓመታት የተጣለባትን እገዳ ከጨረሰች በኋላ ነበር ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ የላቦራቶሪ ውጤቶቹን ለዋዳ ያስረከበችው። የዋዳ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሰኞ ዕለት እንዳስታወቁት መረጃዎቹ ወጥነት ስለሚጎድላቸውን ሆን ተብሎ የጠፉም ስላሉ ይፋዊ የሆነ ምርመራ ተጀምሯል። ሩሲያ ጥፋተኛ ሆና ከተገኘች ከሁሉም ስፖርታዊ ውድድሮች ልትታገድ የምትችል ሲሆን ቅሬታ ካላት ደግሞ ለዓለማ አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለት እንደምትችል ኮሚቴው ገልጿል። የዓለማ አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በዋዳ ቀርቦለት የነበረውን ሩሲያን ከ2016ቱ የሪዮ ኦሎምፒክ የማገድ ሃሳብ ወደጎን ብሎት የነበረ ሲሆን በ2018 በፒዮንግያንግ በተካሄደው የክረምት ኦሎምፒክ ግን ሩሲያ እንዳትሳተፍ ማድረጉ ይታወሳል። የዓለማ አቀፉ አትሌቲክስ ሻምፒየንሺፕ ከአራት ቀናት በኋላ በኳታር ዶሃ የሚጀመር ሲሆን የሩሲያ ተሳታፊዎች ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል አልታወቀም። ''ወጣም ወረደ ሩሲያ ለመደበቅ የሞከረቸው መረጃ ካለ በቀጣዩ ዓመት በቶክዮ ከሚዘጋጀው የቶክዮ ኦሎምፒክና ከ2022 ዓለም ዋንጫ መታገዷ አይቀርም'' ብለዋል ጆናታን ታይለር። • የ56 ዓመቷ ሩሲያዊት በአሳሞች ተበላች የሩሲያው ስፖርት ሚኒስትር ፓቬል ኮሎብኮቭ ''ምን አይነት የመረጃ መለያየት እንደተፈጠረ ሊነግሩን ይገባል፤ ልዩነቶቹ ከምን ጋር የተያያዙ መሆናቸውም ግልጽ መደረግ አለበት'' ማለታቸውን 'ታስ' የተባለው የዜና ወኪል ዘግቧል። ''የዲጂታል ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ከሁለቱም በኩል በትብብር እየሰሩ ነው። በእኛ በኩል ማንኛውም አይነት ትብብርና እርዳታ ለማድረግ ዝግጁ ነን'' ብለዋል። ሩሲያ ባለፈው ዓመት የላቦራቶሪ ውጤቶቹን ለዋዳ ስታስረክብ የተቀመጠላትን ቀነ ገደብ አሳልፋ ነበር። ይህ ደግሞ ብዙ ጥርጣሬዎች እንዲፈጠሩ አድርጎ ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-49806815 +politics የዩክሬን ጦርነት ክራይሚያ ነጻ ወጥታ መጠናቀቅ አለበት ሲሉ ዜለንስኪ ተናገሩ "የዩክሬን ጦርነት በክራይሚያ የተጀመረ በመሆኑ ጦርነቱ ሲጠናቀቅም ክራይሚያን ነፃን በማውጣት መሆን አለበት ሲሉ የዩክሬን ፕሬዝ��ንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት የሩሲያ አየር ኃይል መሰረት በሆነ ቦታ ላይ ፍንዳታዎች ከተከሰቱ እና የአንድ ሰው ሕይወት ካለፈ ከሰዓታት በኋላ ነበር። ዜለንስኪ በንግግራቸው ስለ ፍንዳታዎቹ ምንም ባይሉም የምሽት መግለጫቸውን ክራይሚያ ላይ ያተኮረ ነበር። “ክሪሚያ የዩክሬን ስለሆነ እኛም በፍጹም አሳልፈን አንሰጥም’’ ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። ሩሲያ ፍንዳታውን አቅልላ የተመለከተች ሲሆን አንድ ከፍተኛ የዩክሬን አማካሪ ዩክሬን ለፍንዳታው ኃላፊነቱን እንደማትወስድ ተናግረዋል። ክሬይሚያ የዩክሬን አካል የነበረች ሲሆን ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ሕገ-ወጥ ባለው ሕዝበ ውሳኔ ከ2014 ጀምሮ ሩሲያ አካል ነች በማለት ጠቅልላ ይዛለች። ብዙ ዩክሬናውያን ይህንን የክራይሚያን ጉዳይ ሩሲያ ከአገራቸው ጋር ለጀመረችው ጦርነት የመጀመሪያ እርምጃ አድርገው ይመለከቱታል። ትላንት ማክሰኞ ከክራሚያ በስተ ምዕራብ በሚገኘው በኖቮፌዶሪቭካ አቅራቢያ በሚገኘው ሳኪ በተሰኘው የሩሲያ የጦር ሰፈር በሩሲያ ቱሪስቶች ተወዳጅ በሆኑ የባህር ዳርቻዎች አቅራቢያ በርካታ ፍንዳታዎች ተከስተዋል። በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተዘዋወሩ ምስሎች በባሕር ዳርቻው ላይ የሚዝናኑ ሰዎች ፍንዳታዎቹን ተከትሎ ሲሯሯጡ አሳይተዋል። የዓይን እማኞች ቢያንስ 12 ፍንዳታዎችን እንደሰሙ ተናግረዋል። በክራይሚያ የሚገኝ የሩሲያ የጤና ባለስጣን አንድ ሲቪል ሰው ሲገደል ሌሎች ስምንት ሰዎች ቆስለዋል ብሏል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ፍንዳታዎቹ በአንድ የጦር መሳሪያዎች ማቆያ ውስጥ የተቀመጡ ጥይቶች ፈንድተው የተከሰተ ነው ሲል ቢናገርም እስካሁን ድረስ የተረጋገጠ ነገር የለም። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ረዳት የሆኑት ማይካሂሎ ፖዶሊያክ ዩክሬን ከፍንዳታው ጀርባ የለችም ሲሉ ያጣጣሉ ሲሆን ለዶዝድ ኦንላይን የቴሌቪዥን ጣቢያ ""በፍጹም፣ እኛ ከዚህ ጋር ምን አገናኘን?’’ ሲሉም ተደምጠዋል። ፕሬዘዳንት ዜለንስኪም ማክሰኞ ዕለት ባደረጉት ንግግር ፍንዳታውን በቀጥታ ባይጠቅሱም ስለ ክራይሚያ ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል። “የሩሲያ ጦርነት በዩክሬን ላይ የተጀመረው ክራይሚያን በመውረር መሆኑን አንዘነጋም። ይህ የሩሲያ ጦርነት... ክሪሚያ ጋር ተጀምሮ በክራይሚያን ነፃ በማውጣት ማብቃት አለበት"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c0jw41zwn25o +business የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት አውሮፕላናቸውን ሸጠው ሕገ-ወጥ ስደትን ሊቀንሱ አስበዋል "የሜክሲኮው ፕሬዝዳንት አንድሬ ማኑዌል ሎፔዝ ኦብራዶር አውሮፕላናቸውን ሸጠው የሚያገኙትን ትርፍ ሕገ-ወጥ ስደትን ሊከላከሉበት እንደሆነ አሳውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ሃሳቡን ያመጡት ሃገራቸው ሜክሲኮ ከአሜሪካ ጋር በደረሱት ስምምነት መሠረት ሲሆን ስምምነቱ ሜክሲኮ ከማዕከላዊ ወደ አሜሪካ የሚደረገውን ጉዞ መግታት የምትችል ከሆነ የዶናልድ ትራምፕ መንግሥት ሜክሲኮ ላይ የጫነውን ቀረጥ እንደሚቀንስ ያትታል። ፕሬዝዳንቱ በምረጡኝ ቅስቀሳቸው ወቅት የፕሬዝዳንቱን አውሮፕላን ሸጬ ደሃ ሜክሲኳዊያንን ሕዝብ እረዳለሁ ሲሉ ቃል ገብተው ነበር። • ከፍተኛ መጠን ያለው ዕፅ በአሜሪካና ሜክሲኮ ድንበር ተያዘ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር የተሰኘው የፕሬዝዳንቱ አውሮፕላን 150 ሚሊዮን ዶላር [ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ገደማ] ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ስማቸው የረዘመባቸው የሃገሪቱ ሰዎች 'አምሎ' ብለው የሚጠሯቸው ፕሬዝዳንት ሎፔዝ አውሮፕላኑን ሸጨ እኔ ከሕዝብ ጋር ተጋፍቼ እሄዳለሁ ሲሉ ነበር ቃል የገቡት። አውሮፕላኑ ላለፉት ጥቂት ወራት ካሊፎርኒያ የሚገኝ አንድ መጋዘን ውስጥ ለሻጮች ክፍት ሆኖ ቆይቷል። ሜክሲኮ የፕሬዝዳንቱን አውሮፕላን አ���ሎ ሌሎች 60 የመንግሥት አውሮፕላኖችንና 70 ሄሊኮፕተሮችን ለመሸጥ ቆርጣ ተነስታለች። • ""አቶ ጌታቸው አሰፋን ሜክሲኮ አግኝቻቸው ነበር"" ነጋ ዘርዑ ሜክሲኮ ሶስተኛዋ ሃያል የአሜሪካ የንግድ አጋር ስትሆን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በነበራት እሰጥ-አገባ ምክንያት ከሜክሲኮ የሚመጡ ምርቶች ላይ ቀረጥ ተጭኖ ነበር። ሜክሲኮ አውሮፕላኗን ከመሸጥ አልፋ 6 ሺህ ገደማ ፖሊሶችን ወደ ጓቲማላ ልካ ሕገ-ወጥ ስድትን ለመግታት ቃል ገብታለች። የፕሬዝዳንቱ አውሮፕላን መሸጥ ለበርካታ ሜክሲኳውያን የተዋጠ አይመስልም፤ በሕዝብ ገንዘብ የተገዛ ንብረትን እንዴት ተደርጎ? እያሉም ይገኛሉ። • አሜሪካና ሜክሲኮን የሚለየው ግንብ መገንባት ተጀመረ" https://www.bbc.com/amharic/news-48619205 +business የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌና ላልይበላ በረራዎችን ሰረዘ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ መቀሌና ላልይበላ ጨምሮ በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍሎች ዛሬ ሊያደርጋቸው የነበሩ በረራዎችን ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት መሰረዙን አስታወቀ። አየር መንገዱ ጨምሮም በተመሳሳይ ወደ ጎንደር፣ አክሱምና ሽሬ ሊያደርጋቸው የነበሩ በረራዎችም ዛሬ ጠዋት በነበረው አመቺ ያልሆነ የአየር ሁኔታ ሳቢያ መስተጓጎሉን አመልክቷል። በዛሬው ዕለት የተሰረዙትን በረራዎች ያለው የአየር ሁኔታ መሻሻሉን በተመለከተ ከብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት የሚገኝን መረጃ መሰረት በማድረግ እንዲቀጥል የሚደረግ መሆኑን ገልጿል። ነገር ግን አሁን ከብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በረራዎችን ያስተጓጎለው የአየር ሁኔታ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ውስጥም ሊቀጥል እንደሚችል አመልክቷል። በተያያዘ ዜና ከአርብ ከሰዓት ጀምሮ ቅዳሜ ዕለትም የባህር ዳር ከተማ ሰማይ በአቧራ ጭጋግ ተሸፍኖ እንደነበር ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ይህንን ክስተት በተመለከተ የምዕራብ አማራ የሜቲዮሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል የትንተናና ትንበያ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ቡድን አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጥላሁን ውቡ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ""ጠንካራ የአቧራ ጭጋግ ተከስቷል።"" ይህ የአቧራ ጭጋግ የሚከሰተው በደረቅ አካባቢዎች የሚከሰትን አውሎ ነፋስ ተከትሎ ነው የሚሉት ባለሙያው፤ በባህር ዳር ላይ የታየው የአቧራ አውሎ ነፋስ ሱዳን ላይ በተከሰተ ዝቅተኛ የአየር ግፊት ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። ይህ የአቧራ ጭጋግ የተከሰተው በባህር ዳር ከተማ ብቻ አለመሆኑን የሚናገሩት ባለሙያው ጎንደር ላይም መታየቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ክስተቱ ብዙ ጊዜ ለረዥም ሰዓት አይቆይም የሚሉት አቶ ጥላሁን ቶሎ ሊጠፋ እንደሚችል ያስረዳሉ። ነገር ግን በእንዲህ ዓይነት የአየር ሁኔታ አውሮፕላኖች ለመነሳትም ሆነ ለማረፍ እይታን ስለሚጋርድ ለበረራ አስቸጋሪ እንደሚሆን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ ግን በረራዎች ከተስተጓጎሉባቸው ከተሞች ውስጥ የአቧራ ጭጋጉ የተከሰተባት የባህር ዳር ከተማ የለችበትም። ባለሙያው ጨምረውም እንዲህ አይነት አቧራ ጭጋግ የመተንፈሻ አካል ችግር በተለይ አስም ላለባቸው ሰዎች አስቸጋሪ እንደሚሆን አስታውሰው፤ እንዲሁም ክስተቱ የማጅራት ገትር በሽታ መንስዔም ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ባህር ዳር የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳረጋገጠው የአቧራ ጭጋጉ ዛሬ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ቢሆንም የተወሰኑ ምልክቶች ግን እንዳሉ አመልክቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-51894638 +health ኮሮናቫይረስ ፡ የካናዳው ሚኒስትር በኮቪድ-19 ወቅት ሽርሽር በመሄዳቸው ምክንያት ሥልጣናቸውን ለቀቁ "የካናዳዋ ኦንታሪዮ ግዛት የገንዘብ ሚኒስትር የሆኑት ግለሰብ በኮቪድ-19 ወቅት ለመዝናና��� ወደ ካሪቢያን በመጓዛቸው ምክንያት ሥራ ለቀዋል። የግዛቲቱ ገዥ ዶግ ፎርድ የገንዘብ ሚኒስትራቸው ሥልጣን እንዲለቁ ያደረጉት ኦንታሪዮ የእንቅስቃሴ ገደብ ላይ እያለች ሽርሽር ብለው በመጓዛቸው ነው። ሚኒስትር ሮድ ፊሊፕስ ይቅርታ ጠይቀዋል። ጉዟቸውንም ""የሞኝ ሥራ"" ብለውታል። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ እንዳሉት ""የፋይናንስ ሚኒስትሩ ሥልጣን መልቀቃቸው መንግሥታቸው ኃላፊነትን በአግባቡ የማይወጡ ሰዎችን እንደማይምር ማሳያ ነው"" ብለዋል። በካናዳ ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት የኦንታሪዬ ግዛት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ጠበቅ ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሏ ይታወቃል። የፕሮግረሲቭ ኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ አባል የሆኑት ሚኒስትር ሴይንት ባርትስ ወደ ተሰኘችው የካሬቢያን ደሴት ለሽርሽር የሄዱት በዚህ በታኅሣስ ወር ነው። በወቅቱ የኦንታሪዮ የጤና ባለሥልጣናት በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁትሩ በመጨመሩ ምክንያት ነዋሪዎች ከቤታቸው ንቅንቅ እንዳይሉ አዘው ነበር። ኦንታሪዮ ከቀናት በፊት እንደ አዲስ ጠበቅ ያለ የኮቪድ-19 ሕግ አውጥታለች። ባለፈው ሐሙስ ብቻ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከገባ በበሽታው የተያዙ ከፍተኛው የተባለው ቁጥር [3328] ተመዝግቧል። 56 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ በካናዳ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ582 ሺህ በላይ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 15 ሺህ 600 ደርሷል። ሚኒስትሩ ከሽርሽር ሲመለሱ ሥራቸውን ለመቀጠል አስበው የነበረ ቢሆንም የግዛቲቱ አስተዳደር ሥልጣናቸውን ቢለቁ የተሻለ እንደሆነ ነግረዋቸዋል። ""እንምታዩት በጣም ከባድ ስህተት ፈፅሜያለሁ። ተጠያቂ መሆን ደግሞ አለብኝ። መሄድ በሌለብኝ ወቅት ነው የተጓዝኩት። ምንም ምክንያት መደርደር አይጠበቅብኝም"" ብለዋል ስልጣናቸውን የለቀቁት ሚኒስትር። የኦንታሪዮ አስተዳዳሪ ሥልጣን በለቀቁት ሚኒስትር ምትክ ሌላ ሰው በጊዜያዊነት ሾመዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55505118 +business የዓለማችን ግዙፉ ባለሁለት ሞተር ቦይንግ አውሮፕላን የሙከራ በረራውን አደረገ "ቦይንግ 777ኤክስ የተሰኘው የዓለማችን ግዙፉ ባለሁለት ሞተር አውሮፕላን የሙከራ በራራውን በድል አጠናቋል። ቦይንግ የተሰኘው አውሮፕላን ፈብራኪ ድርጅት 737 ማክስ በተሰኙ አውሮፕላኖቹ ላይ በደረሰ እክል ምክንያት የሰው ሕይወት ከጠፋ በኋላ ገበያ ለማግኘት ሲዳክር ከርሟል። የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢንዶኔዢያ አቻው ንብረት የሆኑ ሁለት አውሮፕላኖች በወራት ልዩነት ተከስክሰው በድምሩ 346 ሰዎች ሞተዋል። ከአደጋዎቹ በኋላ የተቀሩትን 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከበረራ ያገደው ቦይንግ እነሆ ግዙፍ አውሮፕላን ይዞ ብቅ ብሏል። ለአራት ሰዓትታ የዘለቀው የሙከራ በረራ ሲያትል የተሰኘችው የአሜሪካ ከተማ አቅራቢያ ነው የተከወነው። የተሳካው በረራ ከመካሄዱ በፊት ሁለት ጊዜ በአየር ፀባይ ምክንያት በረራዎች እንዲቋረጡ ተደርገዋል። 252 ጫማ [76 ሜትር] የሚረዝመው አውሮፕላን የዓለማችን ግዙፉ ባለሁለት ሞተር የንግድ አውሮፕላን ነው ተብሎለታል። ቦይንግ እስካሁን 309 777ኤክስ አውሮፕላኖች ሸጫለሁ የአንዱ ዋጋ ደግሞ 442 ሚሊዮን ዶላር ነው ብሏል። የድርጅቱ ግብይት ባለሙያ ዌንዲ ሶወርስ ""ድርጅታችን ትልቅ ነገር ማድረግ እንደሚችል ያሳየ ነው"" ሲሉ ተደምጠዋል። አውሮፕላኑ 360 ሰዎች የመጫን አቅም ካለው ኤርባስ ኤ350-1000 ጋር ተመሳሳይ ባሕሪ አለው ተብሏል። ቦይንግ አደጋ የጠናባቸውን 737 ማክስ አውሮፕላኖች ሲያመርት ለደህንነት የሰጠው ዋጋ ዝቅ ያለ ነው ተብሎ ብዙ ወቀሳ ደርሶባታል። እንዳይበሩ የታገዱት አውሮፕላኖች እንደገና ተፈትሸው ወደ ሰማይ ይወጣሉ ሲል ድርጅቱ ማሳወቁ አይዘነጋም። ማክስ 737 የቦይንግ እጅግ በብዛት የተሸጡ አውሮፕላኖች ሲሆን አውሮፕላኖቹ እንዳይበሩ በመተጋዳቸው ምክንያት ቦይንግ 9 ቢሊዮን ዶላር እንደከሰረ ይገመታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-51253933 +business "ቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቼን አሜሪካ ""በማን አለብኝነት እያስፈራራቸው"" ነው አለች" "የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ቲክቶክ፣ ዊቻት በአሜሪካ መታገዳቸውን ተከትሎ ቻይና ኩባንያዎቿ ግልፅ የሆነ ""የማስፈራሪያ ጥቃት"" በአሜሪካ እየደረሰባቸው ነው ብላለች። የቻይና መንግሥትም ""በአሜሪካ የበላይነትና ማን አለብኝነት"" ብሎ በጠራው የተፈጠረውን ጫና ለማስተካካልም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የሚገዛ አለም አቀፍ መመሪያዎችን አውጥታለች። በአዲሱ ጅማሮ መሰረት የዜጎችን የግል መረጃ በህገወጥ መንገድ መሰብሰም ሆነ በዜጎች ላይ የሚደረግ ከፍተኛ ስለላና ክትትል ህጋዊ አይደለም በማለት አስምሯል። በባለፈው ወርም እንዲሁ መረጃዎችን ከመጠበቅና ደህንነት ጋር ተያይዞም አሜሪካ ""ክሊን ኔትወርክ"" (ከማንም ነፃ የሆነ ኔትወርክ) የሚል እሳቤን አስተዋውቃለች። የመረጃን ደህንንነት በተመለከተ እሰጣገባ የገቡት አሜሪካና ቻይና ፤ ቲክቶክ፣ ሁዋዌና ዊ ቻትም መወዛገቢያ ሆነዋል። በቅርብ ወራትም የትራምፕ አስተዳደር የቻይና የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭና ተንቀሳቃሽ ስልኮች አምራች ሁዋዌን ጨምሮ የማህበራዊ ሚዲያዎቹን ቲክቶክና ዊቻት ብሄራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ ይጥላሉ በሚል አግዷል። ""አንዳንድ ሃገራት በማን አለብኝነትና በትምክህተኝነት አገራትን ሲያዋርዱ ይታያሉ። መረጃን በመጠበቅና ደህነነት በሚል ሽፋንም በአለም እየመሩ ያሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ለማጥቃት አነጣጥረዋል"" በማለት የቻይና መንግሥት አማካሪ ዋንግ ይ ተናግረዋል። ""ይሄ ግልፅ ያለ ማስፈራራትና ጉልቤነት ነው። ልንቃወመው ይገባል"" ብለዋል። ዋንግ በዛሬው እለት እንደተናገሩት ቻይና ያወጣቻቸው አዳዲስ መመሪያዎች ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የግል መረጃዎቻቸውንና አገልግሎታቸውን ለተለያዩ ኩባንያዎች አስተላልፈው እንዳይሰጡም ጥሪ አድርጓል። አሜሪካ በበኩሏ የቻይናው ቴሌኮም አገልግሎት ሰጭና ተንቀሳቃሽ ስልኮች አምራች ኩባንያ ሁዋዌ በስልኮቹ ላይ መረጃዎችን አሳልፎ የሚሰጥ የተገጠመ ማሽን አለው በማለት ትወነጅላለች። ""የአለም አቀፉ መረጃ ደህንነት ሁሉም አገራት በመከባበር፣ በመተሳሰብና አለም አቀፍ ተሳትፎን መሰረት ያደረገ ነው"" በማለት ዋንግ አስረድተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54068170 +health ኮሮናቫይረስ፡ ሳይታወቅ ለዓመታት በሌሊት ወፎች ውስጥ ነበር የሰው ልጆች ላይ ጉዳት እያስከተለ ያለው ኮሮናቫይረስ ለበርካታ ዓመታት ሳይታወቅ በሌሊት ወፎች ሰውነት ውስጥ እንደነበር ጥናቶች ያሳያሉ። ኮቪድ-19ን የሚያስከትለው ቫይረስ በሌሊት ወፎች ላይ ከታየ ከ40 እስከ 70 ዓመታት አልፈዋል። ወደ ሰው ልጆች ከተሻረገ ጥቂት ጊዜው መሆኑን ሳይንቲስቶች ይናገራሉ። መረጃው፤ ኮቪድ-19 በሰው የተሠራና ከቤተ ሙከራ አምልጦ የወጣ ነው የሚለው የሴራ ትንተና ላይ እውነትን የተመረኮዘ ስለመሆኑ ጥያቄ ያጭራል። ፕ/ር ዴቪድ ሮበርትሰን በግላስጎው ዩኒቨርስቲ ነው የሚሠሩት። የሳቸው ጥናት ‘ኔቸር ማይክሮባዮሎጂ’ በተባለ መጽሔት ላይ ታትሟል። ፕ/ር ዴቪድ እንደሚናገሩት፤ ሳርስ-ኮቭ-2 ከሌሊት ወፎች ቫይረስ ጋር የዘረ መል ተመሳሳይነት ቢኖረውም፤ አንዳቸው ከሌላቸው የበርካታ ዓሠርታት ልዩነት አላቸው። “እነዚህ ሰውን ሊይዙ የሚችሉ ቫይረሶች ዘለግ ላለ ጊዜ እንደኖሩ ጥናቱ ያሳያል” ይላሉ። ቫይረሱ መቼ እና እንዴት ወደ ሰው ልጆች እንደተሸጋገረ መታወቅ እንዳለበት ተመራማሪው ያስረዳሉ። “በሌሊት ወፎች ላይ ቫይረሱ እንዳለ ካወቅን ለመቆጣጠር መሞከር አለብን።” ለወደፊቱ ወረርሽኞች እንዳይቀሰቀሱ፤ ሰዎች የሚገጥሟቸው ህመሞች የቅርብ ክትትል እንደሚያሻቸው ጥናቱ ያሳያል። ከዱር የሌሊት ወፎች ላይ ናሙና ተወስዶ ምርመራ መካሄድም አለበት። ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት፤ “እነዚህ ቫይረሶች ዓመታት አስቆጥረዋል ማለት ሰዎችን ጨምሮ ሌላም መኖሪያቸው የሚያደርጉት አካል አግኝተዋል ማለት ነው።” በጥናቱ፤ የሳርስ-ኮቭ-2 ዘረ መል ተቀራራቢው ከሆኑ የሌሊት ወፍ ላይ ያሉ ቫይረሶች ማለትም አርኤቲጂ13 እንዲሁም ከሌሎች ጋር ንጽጽር ተደርጓል። ሁለቱ አይነቶች በምን ወቅት ላይ ተመሳሳይ የዘር ግንድ እንደነበራቸውም ተጠንቷል። በዚህ መሠረትም ሁሉቱ ዓይነቶች ከአስርታት በፊት በተለያየ የእድገት ሁኔታ ማለፋቸው ተደርሶበታል። በሪዲንግ ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ፕ/ር ማርክ ፓጌል በጥናቱ ባይሳተፉም፤ ሰዎችን ሊጎዱ የሚችሉ ኮሮናቫይረሶች ሳይታወቁ በሌሊት ወፎች ላይ ከ40 እስከ 70 ዓመታት መኖራቸውን ምርምሩ እንደሚያሳይ ይስማማሉ። “ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ በሽታዎች ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ ጥናቱ ያሳያል። እንስሳት ውስጥ በጥገኝነት የሚኖሩና ለሰው ልጅ ጎጂ የሆኑ፤ እስካሁን ድረስ ግን ያልታወቁ ሌሎች ቫይረሶችም ሊኖሩ ይችላሉ።” ቫይረሶቹ ወደ ሌሎች የዱር እንስሳት ተላልፈው ሊሆን ይችላል። በተለይም በሕገ ወጥ የእንስሳት ዝውውር ሳቢያ እርስ በእርስ የተቀራረቡ እንስሳት የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። እስካሁን ድረስ ያለው መረጃ እንደሚያሳየው ግን የቫይረስ ዋነኛ ተሸካሚ የሆኑት የሌሊት ወፎች ናቸው። ከዚህ ቀደም የሰሠሩ ጥናቶች ፓንጎሎኖች ለሳርስ-ኮቭ-2 ዝግመተ ለውጥ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ያሳያል። አሁን ግን ይህ ትክክል እንዳልሆነ ተደርሶበታል። ቻይናን መዳረሻው ባደረገ ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ ወቅት ፓንጎሊኖች ከሌሎች እንስሳት ጋር ንክኪ ነበራቸው። ስለዚህም ፓንጎሊኖች ለቫይረሱ የተጋለጡት በቅርቡ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-53600806 +health ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት ገበያ እንዲወጣ የተባለው የአፕል ጭማቂ "በደቡብ አፍሪካ የሚመረተው ሲረስ የተባለው ታሸገ ጭማቂ ከፍተኛ መጠን ያለው ለጤና ጎጂ የሆነ ንጥረ ነገር በውስጡ በመገኘቱ ከሰባት የአፍሪካ አገራት ገበያ እንዲሰበሰብ መደረጉ ተዘግቧል። የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በበኩሉ ሲረስ አፕል ጁስ የተሰኘው ጭማቂ ""በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት"" ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ አውጥቷል። ባለስልጣኑ ስለተገኘው መርዛማ ንጥረ ነገር በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በኩል በሰጠው ማብራሪያ በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰት ማይኮቶክሲን ከሚባል ከሻጋታ የሚመነጭ መሆኑን አመልክቶ ኅብተሰቡ የተጠቀሰውን ምርት እንዳይጠቀም መክሯል። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተመርቶ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚሰራጨው ሲረስ የአፕል ጭማቂ በመበስበስና በመሻገት የሚከሰተው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር ስለተገኘበት ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ ነው። በጭማቂው ላይ በተደረገ ቤተ ሙከራ ፍተሻ እንደተረጋገጠው ሲረስ በተባለው የአፕል ምርት ላይ በአንድ ሊትር ውስጥ እንዲኖረው ከተፈቀደው 50 ማይክሮ ግራም ከፍ ያለ መጠን መገኘቱ ተገልጿል። ይህ የማይኮቶክሲን ውጤት የሆነው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር በአፕል እና በአፕል ምርቶች ውስጥ በሚከሰቱ በተለያዩ ሻጋታዎች አማካይነት የሚፈጠረው። በጭማቂው ውስጥ የተገኘው ንጥረ ነገር ፓቱሊን በተጠቃሚዎች ላይ ማቅለሽለሽና ማስታወክን በማስከተል ጤናን ሊያው�� ይችላል ተብሏል። ይህ ሲረስ የተባለው የአፕል ጭማቂ በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አመልክቶ ኅብረተሰቡ እንዳይ ጠቀመውና በገበያ ላይ ከተገኘም ጥቆማ እንዲሰጠው ጥሪ አቅርቧል። ምርቱ በተጨማሪም በኬንያ፣ በዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ በዛምቢያ፣ ዚምብብዌ፣ ኡጋንዳ፣ ሲሸልስ እና ሞሪሺየስ ገበያዎች ውስጥ ተሰራጭቶ እንደሚገን ተነግሯል። የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ የንግድ ቀጠና (ኮሜሳ) የንግድ ውድድር ኮሚሽን በአገራቱ ውስጥ ያሉ የምርቱ ተጠቃሚዎች ባለፈው ሰኔ ወር ተመርተው የተሰራጩ የሲረስአፕል ጭማቂ ምርቶችን ከገበያ አስወጥተው ለአምራቹ እንዲመልሱ ጥሪ አቅርቧል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58919812 +health ኮሮናቫይረስ፡ክትባት ለመከተብ አጭበርብረዋል የተባሉ ኃላፊ ከስራቸው ለቀቁ "ከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የካዚኖ ቁማር ኩባንያ የሚመሩት ዋና ስራ አስፈፃሚ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት አጭብርብረዋል መባሉን ተከትሎ ከስራቸው ለቀቁ። ኃላፈውና ባለቤታቸው ባለስልጣናቱን አታለዋል በሚል ተከሰዋል። ግሬት ካናዲያን ጌሚንግ የተባለ የካዚኖ ቁማር ድርጅት የሚመሩት ሮድ ቤከርና ባለቤታቸው ኢካትሪና ገጠራማ ወደሆነው ዩኮን ግዛት ክትባት ለመከተብ አቅንተው ነበር። ግዛቱ የቀደምት ካናዳውያን መኖሪያ ሲሆን ከሌሎች የካናዳ ክፍሎች በበለጠ ፈጣን የሆነ የክትባት አሰጣጥ ስርአት እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ። ባለትዳሮቹ ወደ ቦታው ሲያመሩም የሆቴል ሰራተኞች ነን በሚል ሽፋን ነው። በባለፈው ሳምንት በግዛቲቱ ውስጥ በምትገኝ ቢቨር ክሪክ በምትባል መንደር ውስጥ ተከትበው ከጨረሱ በኋላ ወደ አየር ማረፊያ ውሰዱን ማለታቸውን ተከትሎ ነው የተጋለጡት። "" በዚህ ራስ ወዳድ በሆነ ባህርያቸው በጣም ተበሳጭቻለሁ"" በማለት የዩኮን ማህበረሰብ አገልግሎት ሚኒስትር ጆን ስትሬይከር ተናግረዋል። ""በዚህ መንገድ ሰው አጭበርብሮ እንዲህ አይነት ተግባር ይፈፅማል የሚል ነገር በጭራሽ አላሰብንም"" ብለዋል አክለውም። ከዚሁ ጋር ተያያይዞ የዋይት ሪቨር ፈርስት ኔሽን፣ የአካባቢው የቀደምት ህዝቦች ኃላፊ አንጄላ ዴሚት በበኩላቸው ""የእድሜ ባለፀጎቻችንና ተጋላጭ ማህበረሰቦቻችንን ስጋት ውስጥ የሚከቱ የአንዳንድ ግለሰቦች ድርጊት በጣም አሳስቦናል። ተራን ባለመጠበቅ እንዲህ አይነት አስነዋሪ ስራ መፈፀም ራስ ወዳድነት ነው"" ብለዋል። ሮድ ቤከርና ባለቤታቸው ከቫንኮቨር ግዛት ወደ ዩኮን በሄዱበት ወቅት አስገዳጅ የሆነውን የ14 ቀናት ለይቶ ማቆያ ባለማክበር ተቀጥተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55807191 +health እህል በአፏ የማይዞረው ታዋቂዋ ምግብ አብሳይ "ሎሬታ ሃርሜስ ለስድስት ዓመታት ምግብ የሚባል ነገር ወደ አፏ አላስጠጋችም። ምግብ ከማብሰል የሚያግዳት ግን አልሆነም። ሎሬታ የምትሠራው ምግብ ጨው ይብዛው ይነሰው መቅመስ ባትችልም በኢንስታግራም መድረክ በርካታ ወዳጆች አፍርታለች። ሎሬታ ቀቅላ የጠበሰችውን ድንች በሹካ እየፈረካከሰች እንፋሎቱን ትምጋለች። ሎሬታና እናቷ ጁሊ ይህን ማዕድ በጥንቃቄ ያበሰሉት ምናልባትም ይህ የመጨረሻዋ ይሆናል ብለው አስበው ነው። በደቂቃዎች ውስጥ አንድ ከበድ ያለ ስቃይ ሆዷን እየቦረቦረ እንደሚገባ ታውቀዋለች። ይህን ለምዳዋለች። እህልና ፈሳሽ ወደ አፏ ሄዱ ማለት ስቃይ ነው ትርፉ። ነገር ግን የመጣው ይምጣ ብላ ስቃይዋን ተቀብላ በቤተሰቦቿ ኩችና ወንበር ላይ ትውላለች። ኩችናው ማብሰል የተማረችበት አስኳላ ነው። ""ከእናቴና እህቴ ጋር አንድ አፍታ ቁጭ ብሎ መመገብ የሚሰጠው ደስታ ለየት ያለ ነው።"" ጊዜው በፈረንጆቹ 2015 ነበር። የ23 ዓመቷ ሎሬታ ለዓመታት በፈ���ሽ መልክ በሚሰጣት ምግብ ነው የምትንቀሳቀሰው። ቤተሰቦቿ ለእራት ጠረጴዛ ሲከቡ እሷ ተለይታ ክፍሏ ውስጥ ከመቀመጥ ያለፈ ዕጣ አልነበራትም። በነጭ ሽንኩርትና ሎሚ ያበደውን የዶሮ ሥጋ አንስቶ መግመጥ ይቅርና ቢላና ሹካ ማንሳት ራሱ ብርቅ ነው የሚሆንባት። ነገር ግን ይኸው ዛሬ አንድ ጊዜ እንኳ ከቀረበላት ማዕድ ላይ ምግብ አንስታ እንድትበላ ሆነች። ይህን ያደረገው አንድ ባለሙያ ነው። ባለሙያው ሎሬታ ለምን ምግብ ስትበላ እንደሚያማት፣ ለምንስ ሽንት ቤት መጎብኘት እንደማትችል ለመመርመር ነው ዕቅዱ። ሎሬታ የዚያን ቀን ጠዋት ለንደን ወደ ሚገኘው ቅዱስ ማርቆስ ሆስፒታል አቅንታ በአፍንጫዋ ወደታች በተላከ አንድ ቀጭን ቱቦ የትንሹ አንጀቷን ጤንነት ተመርምራ መጥታለች። ሎሬታ ጨቅላ ሳለች በቴሌቪዥን መስኮት የሚታዩ የምግብ ዝግጅት ቅንብሮችን አስመስላ ለቤተሰቦቿ ታቀርብ ነበር። ምግብ ማብሰል መክሊቷ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም። የ11 ዓመት ታዳጊ ሳለች ዘወትር ማክሰኞ እናቷ ከሥራ አምሽታ እንደምትመጣ ስለምታውቅ እራት አሰናድታ ትጠብቃት ነበር። እናቷ ጁሊ እንደምትለው ሎሬታ ማብሰል የጀመረችው በቲማቲም ስልስ የተቀመመ ፓስታ በመሥራት ነው። ነገር ግን ትንሽ ቆይታ ከበድ ያሉ ምግቦችን ማሰናዳት ተያያዘችው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን እየተከታተለች ሳለ የምግብ ማብሰል ውድድር ላይ ተሳትፋ አሸንፋለች። ከትምህርት ቤት አልፋ በሌሎች ውድድሮች ላይ ታላላቆቹን ሳይቀር ረትታ ዋንጫ ይዛ መጥታለች። ""የሎሬታ ትልቁ ብቃቷ ኩችና ውስጥ ባለው ነገር የሆነ ምግብ መሥራት መቻሏ ነው"" ትላለች እናቷ ጁሊ። 15 ዓመት ሲሞላት የምግብ መብላት መመሰቃቀል የሚያስከትለው 'ኢቲንግ ዲስኦርደር' የተሰኘው በሽታ አገኛት። ነገር ግን እሷ እንደምትለው በሽታው ከአንድ ዓመት በላይ አልቆየም። ቢሆንም በታዳጊነት ዘመኗ የምግብ አለመፈጨት በጣም ያስቸግራት እንደነበር ታስውሳለች። ይህ ምግብ በበላች ቁጥር የሚጎረብጣት ስሜት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ መጣ። የሆነ ሆኖ ይህን ስሜት እየታገለች ምግብ ማብሰሏንና መመገቧን ቀጠለች። ሎሬታ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን እንደጨረሰች ለንደን ውስጥ ያለ አንድ ትልቅ የምግብ ዝግጅት ጥበብ ኮሌጅን ተቀላቀለች። ነገር ግን የሦስቱን ዓመት ኮርስ መማር የቻለችው ለአንድ ዓመት ብቻ ነው። ለዚህ ተጠያቂው ደግሞ የጤናዋ ሁኔታ ነበር። በ19 ዓመቷ ትምህርቷን አቋርጣ፣ ከምትወደው ኩችና ተነጥላ አልጋዋ ላይ ስቃይዋን እያስታመመች መኖር ሆነ ሥራዋ። በሽታው ሥጋዋን መጦ ከሰውነት ተራ እንድትወጣ አደረጋት። አልፎም የአእምሮ ጤናዋ ተቃወሰ። ሎሬታ በአንድ ወቅት ክብደቷ ሲለካ መመዘኛው ላይ የሚታየውን ብዙዎች ማመን አልቻሉም። 25 ኪሎ ይላል። ይህ ደግሞ ለሕይወቷ ጭምር አስጊ እንደሆነ ዶክተሯ በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል። ምንም እንኳ ስቃዩ ለጠላቷ የማትመኘው ቢሆንም እየቻለችውን መመገብና ክብደቷን ማስተካከል እንዳለባት አመነች። ሎሬታ የአመጋገብ መመሰቃቀል ያመጣባትን ጫና ተከትሎ የአእምሮ ጤናዋም ይዳከም ጀመር። በርካታ ጊዜ ራሷን ለማጥፋት ሙከራ እንዳደረገች ትናገራለች። እርዳታ እንድታገኝ የተላከችበት ካምፕ ውስጥ ስድስት ጊዜ መመገብ ግዴታ ነው። ሦስት ጊዜ ዳጎስ ያለ ምግብ፤ ሦስቱን ደግሞ ብስኩት የመሳሰሉ ቀለል ያሉ ምግቦችን መብላት ግድ ነበር። ታማሚዎች የቀረበላቸውን ምግብ በተመደበላቸው ደቂቃ የመጨረስ ግዴታ አለባቸው። ሎሬታ ግን ብዙ ጊዜ ራሷን የምታገኘው ምግቡ ላይ ስታፈጥ ምግቡም ሲያፈጥባት ነው። እሷ ማዕዷን ሳታገባድ ማንም ሰው ከጠረጴዛው ላይ እንዲነሳ አይፈቀድለትም። በዚህ ምክንያት ብዙዎቹ ታማሚዎች ቂም ይቋጥሩባታል። ሁሉም ታካሚዎች ምግብ ከበሉ በኋላ ለአንድ ሰዓት ያክል ቁጥጥር ይደርግላቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ ዞር ብለው ጣታቸውን ከተው እንዳያወጡት በሚል ነው። ከዓመታት ምርምርና ጥናት በኋላ የሎሬታ ሆድ ዕቃ በግማሽ ከጥቅም ውጭ እንደሆነ ተደረሰበት። በሽታው በዘር የሚመጣ እንደሆነም ሐኪሞች አወቁበት። ሎሬታ እንድትበላ ማስገደድ ምንም ዋጋ እንደሌለው የተደረሰበት ይሄኔ ነው። ሎሬታ ከምግብ አለመብላት ጋር ከባድ የራስ ምታት፣ ድካምና የልብ በፍጥነት መምታት ያጋጥሟት ነበር። ይህ በሽታ እስኪደረስበት ድረስ ከ10 እስከ 14 ዓመት ድረስ ሊወስድበት እንደሚችል ዶክተር አላን ሐኪም ይናገራሉ። ሎሬታ ምግብ በአፏ ከዞረ ስድስት ዓመታት አልፈዋል። ከዚህ በኋላ ድጋሚ እህልም ሆነ ፈሳሽ ወደ አፏ እንደማታስገባ ታውቀዋለች። አሁን ምግብ የምታገኘው በቀን ለ18 ሰዓታት አንጠልጥላ በምትዞረው ቱቦ አማካይነት ነው። ቱቦው በደረቷ በኩል ገብቶ ወደ ደም ዝውውሯ በፈሳሽ መልክ ምግብ ያሰራጫል። ሎሬታ ይህን ሁሉ አልፋ፤ አሁን ምግብ ለማብሰል ያላትን ፍቅር የማትበላውን ኧረ እንደውም የማትቀምሰውን ማዕድ በማሰናዳት እየተወጣች ነው። የምትሠራውን ምግብ የማትቀምስ አብሳይ መሆኗ በኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ዘንድ ታዋቂነትን አትርፎላታል። ሁሌም ከጎኗ የሆኑት እናቷና እህቷ እንዲሁም አብራት የምትኖረው ባልንጀራዋ የሎሬታን ጣት የሚያስቆረጥሙ ምግቦች በፍቅር ይጎርሳሉ። ሎሬታ ግን ሕይወቷን በቱቦ በሚተላለፍ ምግብ ትገፋለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-56795578 +business በዘይት እጦት እየተንገፈገፉ ያሉት አልጄሪያውያን "በሰሜናዊቷ አፍሪካ አገር አልጄሪያ የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ሲሆን ለዚህም የአንበሳ ድርሻውን የያዘው በአገሪቱ የተከሰተው የዘይት እጥረት ነው። በገበያ ውስጥ ያለው ዘይትና እና ወተት ምርቶች በጣም አናሳ በመሆኑ ምክንያት ሸማቾች በመደብሮች ውስጥ በሚገበዩበት ወቅት ነጋዴዎችን መለማመጥ እንዲሁም ማሞካሸት ይጠበቅባቸዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ተጥለው የነበሩ መመሪያዎች እንዲሁም በቅርቡ የተከሰተው የዩክሬን ጦርነት ተደማምሮ እጥረቱን ያባባሰው ሲሆን ለሸማቾችም ህይወትን ፈታኝ አድርጓታል። ""መድኃኒት የመግዛት አይነት ስሜት አለው"" ትላለች የ31 አመቷ ሳሚሃ ሳመር በንዴትና በምጸት በተቀላቀለው ድምጸት። ለቤተሰቦቿና ጓደኞቿ ኬክ መስራት ትወድ የነበረችው ሳሚሃ በዚህም ገቢም ታገኝ ነበር በአሁኑ ወቅት ግን ለኬክ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ማግኘት አልቻለችም። ""ከየትኛውም መደብር ዘይት ለመግዛት የሱቁ ባለቤት ጋር ወዳጅነት ወይም ትውውቅ መኖር አለበት"" በማለት ሁኔታውን ታስረዳለች። የግብይይት ሁኔታውም የሚከናወነው ሚስጥራዊ በሆነ ሁኔታ ነው። ዘይት እንደማንኛውም እቃ መደብሩ መደርደሪያ ፊት ለፊት ላይ አይታይም፤ ሻጮች መደብሮች ውስጥ ደብቀው ነው የሚያስቀምጡት። እንደ በርካታ አልጄሪያውያን የኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ከፍተኛ ጫና ሲያደርሱና በርካታ ነገሮችን ሲቀይሩ የተመለከተችው ባለፈው ዓመት ነበር። የሙስሊሞች ረመዳን ፆም ሊጀምር በተቃረበበት በአሁኑ ወቅትና ቅዱስ ወር ተብሎ በሚጠራው በዚህ ወር ለሚሰሩ የተለያዩ ዓይነት ምግቦች ግብዓት የሚሆነውን ዘይት ለመሸመት ነዋሪዎች ፍለጋቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። ሳሚሃ አንዳንድ ጊዜ ፍራፍሬ እና አትክልቶችን ለመግዛትም ከምትኖርበት ከተማ ቢልዳ ረከስ ወዳለባትና ወደ አቅራቢያዋ ወደምትገኘው ኮሊያ ሄዳ መሸመት ይኖርባታል። ሌሎች የምግብ ሸቀጦችም እንዲሁ ዋጋቸው ንሯል። ለምሳሌ ድንችን ብንወስድ ከጥቂት ወራት በፊት ከነበረው ከ30 በመ�� በበለጠ አሻቅቧል። ወተት ለመግዛት ነዋሪዎች ጸሃይ ከመውጣቷ በፊት ወደ መደብሮች በማቅናት ረጅም ወረፋ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። ""ወተት ለማግኘት የተሰለፉ ሰዎችን መግፋት አንዳንዴም መጣላት ስለሚያጋጥም አሁን አቁሜያለሁ"" በማለት የአስተዳደሩ ጸሃፊ ይናገራሉ። ""በጣም የሚያዋርድ ተግባር ነው "" የሚሉት ጸሃፊዋ እነዚህን ሰልፎች መራቅ ግን ዋጋ አስከፍሏቸዋል። ከህዝብ ጋር እየተገፋፉና ረጅም ወረፋ መጠበቅንም በመተው ከውጭ አገር ለሚገባ አንድ ኪሎ የዱቄት ወተት 2.90 ዶላር አካባቢ መክፈል ይጠበቅባቸዋል። በመንግሥት ድጎማ የሚደረግለት ወተት ዋጋ 17 ሳንቲም ዶላር ነው። አልጄሪያ ወተት ብታመርትም ነገር ግን መጠኑ በጣም አናሳ ነው። ለዓመታትም ከፈረንሳይ፣ ከሌሎች የአውሮፓ ህብረት ሃገራት እንዲሁም በቅርብ ጊዜ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሚመጣ ወተት ጥገኛ ናት። የሚገባው ወተት በዱቄት መልክ ሲሆን ለሸማቾች ከመድረሱ በፊት ፋብሪካዎች ወደ ፈሳሽነት ይቀይሩታል። ወተት እጥረት ቢኖርም በርካታ አልጄሪያውያንን እያስጨነቀ ያለው የዘይት ዋጋ መናር ነው። እንደ ወተት ዘይትም ቢሆን በመንግሥት ድጎማ ቢደረግለትም በቅርቡ ከተከሰተው ቀውስ በፊትም ቢሆን ውድ ነበር። በዚያን ጊዜም የአምስት ሊትር ዘይት ዋጋ 4.20 ዶላር ወይም 216 ብር ነበር። የአልጄሪያውያን ወርሃዊ ደመወዝ በአማካይ በግሉ ዘርፍ 240 ዶላር እንዲሁም የመንግሥት ሰራተኞች ደግሞ 410 ዶላር ሲሆን ባለስልጣናቱም በናረው የሸቀጥ ዋጋ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ጫና ቢፈጠርባቸው ብዙም አያስገርምም። በአገሪቷ ኢኮኖሚ ሳቢያ ምግብ ማከማቸት እንዲሁም ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ማንሰራራቱን የፓርላማው ኮሚቴ በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል። በፓርላማው የተመረጠው ኮሚቴ አባል የሆኑት ሂሻም ሳፋር ለቢቢሲ እንደተናገሩት የዘይት ነጋዴዎች ከመንግሥት ተጨማሪ ገንዘብን ለመጠየቅ በሚል ድጎማ የተደረገለት ዘይት ላይ ሰው ሰራሽ የሆነ የዋጋ ንረት እየፈጠሩ ይገኛሉ። ባለፈው ዓመት ወደ 150 ሺህ የሚጠጉ ጥሰቶች ለባለስልጣናቱ ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን አብዛኞች ፍርድ ቤት ቀርበዋል እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ የንግድ ፈቃዶች ተነጥቀዋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ በአገሪቷ ድጎማ የተደረገላቸው ሸቀጦች በደቡባዊ ድንበር አቋርጦ በጎረቤት ሃገራት በህገወጥ መንገዶች እየተሸጡ ይገኛሉ። ይህም መጠነ ሰፊ እንደሆነ የፓርላማ ኮሚሽኑ መጠነ ሰፊ እንደሆነም አመልክቷል። ምንም እንኳን ይፋ የሆነ አሃዝ ባይኖርም ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት 12 የሚሆን የጭነት መኪና ዘይት ወደ ማሊና ኒጀር በድብቅ ይወሰዳል። ህገወጥ ነጋዴዎቹ በመንግሥት ድጎማ የተደረገለትን ዘይት በመቸብቸብ በአንድ ጭነት መኪና እስከ 17 ሺህ 800 ዶላር ትርፍ እንደሚያገኙም ምንጮቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔ ከውጭ የመጡ ምርቶች ወይም ግብዓታቸው ከውጭ የመጣ እንደ ዘይት፣ ስኳር፣ ፓስታ፣ ሰሞሊና እና የስንዴ ምርቶች ወደ ውጭ እንዳይላኩ አግደዋል። ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ፕሬዚዳንቱ መሰል ድርጊቶች ሆን ብሎ የአገሪቱ ምጣኔን ሆን ብሎ ለማደናቀፍ የተሸረበ ሴራ ስለሆነ ከፍተኛ ቅጣት እንዲጣልባቸው ይፈልጋሉ። ነገር ግን በአልጄሪያ ለተነሳው ቀውስ ጥልቅ መንስኤዎችን ለማወቅ ወደ ኋላ መለስ ብሎ መመልከት እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ""አገሪቷ በማፍያ ተዘርፋለች"" የአገሪቷ ምጣኔ ኃብት መሰረቱ ጋዝ እና ድፍድፍ ነዳጅ መሆኑ እንዲሁም የመንግሥት ገቢ ምንጭም በነዚህ ምርቶች ላይ ጥገኛ መሆኑ በርካታ ችግሮችን ፈጥሯል ይላሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አብዳል ራህማን ሀዴፍ። በዘርፉ ላይ የሚ��ረጉ ስምምነቶች መልካም አስተዳደር ጉድለት የሚታዩበትና ከፍተኛ ገንዘብ የሚወጣባቸው መሆናቸውንም አብዳል ይናገራሉ። የኢኮኖሚው ችግር ወደ ከፋ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋትም ፈጥሯል። የዋጋ ንረቱ ""በህዝቡ እና በአስተደዳሩ መካከከል መካከል ያለው ደካማ ግንኙነት ሊፈርስ የሚችልበት ደረጃ ላይ ሊያደርሰው ይችላል፣ ይህም በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ቅሬታን ይፈጥራል"" ሲሉ የሶሺዮሎጂ ባለሙያ ፕሮፌሰር ራቺድ ሃማዶቼ ያስጠነቅቃሉ። የቀድሞው ፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቡተፍሊካ በአውሮፓውያኑ 2019 የተነሳውን ሰፊ ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል። ተተኪው ፕሬዚዳንት በአንድ ወቅት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቅርብ አጋር የነበሩ ሲሆን በቡተፍሊካ መሪነት ""የሀገሪቱን ካዝና የዘረፈውን ማፍያ"" ደጋግመው ሲያወግዙም ተዘሰምቷል። የፕሬዝዳንቱ ለውጥ ቢኖርም በርካታ ወጣቶች ለውጥ ባለመኖሩ ቅር እንደተሰኙ ነው ከዚህም ጋር ተያይዞ የኮሮናቫይረስ ወረረርሽኝ እስከተከሰተበት ድረስ በርካታ የአደባባይ ተቃውሞዎች አድርገዋል። የአገሪቱ ሶስት አራተኛ ህዝብ ከ37 አመት በታች ነው፣ ስራ አጥነት 11 በመቶ ደርሷል፤ ይባስ ብሎ በርካታ ስራ አጦች የዩኒቨርስቲ ምሩቃን ናቸው። መንግሥት የህዝቡን እሮሮ በጊዜያዊነት ለማስታገስ በሚመስል መልኩ በንቃት ስራ እየፈለጉ መሆናቸውን ማረጋገጥ የሚችሉ ስራ አጥ ዜጎች 90 ዶላር የሚጠጋ ወርሃዊ አበል እንደሚሰጣቸው ተናግሯል። በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው የነዳጅ ዋጋ መጨመር ሁኔታውን ቀለል የሚያደርግላቸው ሲሆን ለባለሥልጣናቱ ይህንን ገንዘብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመክፈል ያስችላቸዋል ተብሏል። ነገር ግን አልጄሪያ በዚህ አጋጣሚ የተገኘው የነዳጅ ገቢን ማባከን እንደማትችል የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች አጥብቀው ይከራከራሉ ። አሁን ግን እንደ ሳመር ያሉ ሸማቾች በአሁኑ ወቅት ወዳጅ የሚሆናቸውም ባለመደብርና የተደበቀ ዘይት ላይ ተስፋቸውን ጥለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60904242 +business በርካታ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች በአነስተኛ ዋጋ በበይነ መረብ ላይ ለሽያጭ ቀረቡ "በርካታ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች እንደ ኢቤይ እና አማዞን ባሉ የኢንተርኔት መገበያያ ገጾች ላይ በአነስተኛ ዋጋ ለሽያጭ ቀረቡ። እነዚህ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ እንደሆኑ የተገመቱ ቅርሶች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በብዛት በበይነ መረብ የግብይት መድረኮች ርካሽ በሚባል ዋጋ እየተሸጡ እንደሆነ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ይገኛሉ። ከእነዚህ ቅርሶች ውስጥ በርከት የሚሉት ""ኢቤይ"" በተሰኘው የበይነመረብ ገበያ ላይ እንደቀረቡ መመልከት ይቻላል። ይህ በድንገት በርካታ የኢትዮጵያ ቅርሶች ወደ ገበያ መውጣት ምናልባት በጦርነቱ ወቅት ከትግራይ የተዘረፉ ናቸው የሚለውን ጥርጣሬ አጭሯል። በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀውስን ጦርነት ተከትሎ በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በክርስትና እና እስልምና የሃይማኖት ተቋማት ላይ ጥቃት ስለማድረሳቸው ከዚህ ቀደም ተዘግቧል። በሃይማኖት ተቋማት ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ ጥንታዊ ቅርሶች ስለመዘረፋቸው ተገልጿል። በጉዳዩ ላይ የፌደራል ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣንን ምላሽና ማብራሪያን ለማግኘት ቢቢሲ በተደጋጋሚ ያደረገው የስልክ ጥሪ ባለመነሳቱ ለጊዜው ሳይሳካ ቀርቷል። የቢቢሲ ኒውስዴይ ፕሮግራም በጉዳዩ ዙርያ ያነጋገራቸው የቋንቋ ታሪክ ተመራማሪ እና በሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ የድኅረ ዶክትሬት ተማሪ የሆኑት ሐጎስ አብረሃ (ዶ/ር) በጦርነቱ ወቅት ""ከበርካታ የትግራይ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናትን ቅርሶች መዘረፋቸውን አረጋግጫ��ሁ"" ይላሉ። ሐጎስ (ዶ/ር) በወቅቱ ከተዘረፉት ቅርሶች አንዳንዶቹ ጥንታዊና እጅግ ብርቅዬ የነበሩ ናቸው ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ተመራማሪው ከኢትዮጵያ የተዘረፉት ቅርሶች በብዛት እየተሸጡ ያሉበት ዋጋ እጅግ ርካሽ የሚባል እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጠዋል። በዚህ ወቅት እንዴት ተዘርፈው ከአገር ሊወጡ እንደቻሉ ማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ በሱዳንና ኬንያ በኩል ሊሆን እንደሚችል ግን ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በኢቤይ የበየነመረብ የግብይት መድረክ ላይ ባለፉት ጥቂት ወራት በርካታ ከኢትዮጵያ የሆኑ ጥንታዊ ሃይማኖታዊ ቅርሶችን ለሽያጭ ካቀረቡት ሻጮች መካከል አንዱ ዎርሌይ ኢንተርፕራይስ ኢንተርናሽናል ኤልኤልሲ (Worley Enterprises International LLC) የተሰኘው ሻጭ ይገኝበታል። ይህ ነጋዴ ለሽያጭ ካቀረባቸው የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርጾች መካከል አንዱ ከ15ኛው አስከ 17ኛ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ በእጅ የተጻፈ ሃይማኖታዊ መጽሐፍ ይገኝበታል። ይህ በእንስሳት ቆዳ ላይ በግዕዝ ቋንቋ የተጻፈ ጽሑፍ ጥር 12/2014 ዓ.ም. በ240 የአሜሪካ ዶላር ለገበያ ቀርቧል። ሌላኛው ከ15ኛው አስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን ባሉት ዓመታት በግዕዝ ቋንቋ ሳይጻፍ አይቀርም የተባለለት መጽሐፍ በ1250 የአሜሪካ ዶላር በዚሁ ገጽ አማካይነት ለገበያ ቀርቧል። እንደ ኢቤይ ባሉ የኢንተርኔት ገበያዎች ላይ ግለሰቦች ምዝገባ አድርገው መግለጫ እና ፎቶ በማያያዝ እቃዎችን ለገበያ ያቀርባሉ። ዎርሌይ ኢንተርፕራይስ ኢንተርናሽናል ኤልኤልሲ ያስተዋወቃቸው መነሻቸው ከኢትዮጵያ የሆኑ ቅርሶች ""መቶ በመቶ ትክክለኛ"" ስለመሆናቸው በመግለጽ፤ ገዢዎች ""ይህ መልካም እድል እንዳያመልጣችሁ"" በማለት ሰዎች ቅርሶቹን እንዲገዙ ያበረታታል። ይህ ሻጭ ለሽያጭ በሚያቀርባቸው እቃዎች መግለጫ ላይ፤ መሰል ጥንታዊ እቃዎችን ለሽያጭ የሚያቀርበው ሰዎች እቃዎቹን እንዲሸጡለት ከሰጡት በኋላ እንደሆነ ይገልጻል። ከዚህ በተጨማሪም እራሱ በተለያዩ ወቅቶች ከሰበሰባቸው ክምችቶቹ አልያም ከሌሎች ስፍራዎች ገዝቶ ኢቤይ ላይ መልሶ ለሽያጭ እንደሚያቀርብ ያትታል። ለ15 ወራት ያክል የዘለቀው የኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት በእምነት ስፍራዎች ላይ ካደረሰው ጉዳት ባሻገር፣ ከባድ የሚባል ውድመትን እንዲሁም ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስን አስከትሏል። በጦርነቱ ሳቢያ ቁጥራቸው አስካሁን በውል ባይታወቅም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለሞት የተዳረጉ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩት ደግሞ ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል። በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ውስጥ ተቀስቅሶ ወደ አጎራባቾቹ የአማራና የአፋር ክልሎች የተስፋፋው ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ለከፋ ረሀብ ያጋለጠ ሲሆን፣ ወደ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን ሰብዓዊ እርዳታን እንዲጠብቁ መገደዳቸውን ድርጅቱ አመልክቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60335006 +politics መንግሥትና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጦርነቱን አቁመው ልዩነታቸውን በድርድር እንዲፈቱ ኦፌኮ ጠየቀ "በኢትዮጵያ መንግሥትና በአሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንዲቆምና ልዩነታቸውን በድርድር እንዲፈቱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ጥሪ አቀረበ። በሁለቱ አካላት መካከል ያለው ግጭት መንስዔው ""ፖለቲካዊ ነው ያለው"" ኦፌኮ መፍትሄውም ""ፖለቲካዊ"" መሆን እንዳለበትም በትናንትናው ዕለት ሚያዝያ 3፣ 2014 ዓ.ም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኦሮሚያ ክልል ከቀናት በፊት ""አሸባሪ"" ብሎ የጠራውን የ""ሸኔን ኃይል"" ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ የሚያስችል ጠንካራ ዘመቻ ተጀምሯል ብሏል። በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኑ መካከል ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ�� የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ቃለ አቀባይ ኦዳ ተርቢ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። በአሁኑ ወቅት ጦርነቱ ከመፋፋሙና እንደ አዲስ ዘመቻ ከመጀመሩ ጋርም ተያይዞ ኦፌኮ ይህ ሁኔታ የኦሮሚያን ክልልን እንዲሁም አገሪቱን ለተጨማሪ አደጋ የሚዳርግ መሆኑንም አፅንኦት ሰጥቷል። ""መንግሥት ሰሞኑን በአዲስ መልኩ ያወጀው ዘመቻ በጥቂቱ ፈንጥቆ የነበረውን የሰላም ጭላንጭል መልሶ የሚያደበዝዝ፤ኦሮሚያና አገሪቱን ለተጨማሪ አደጋ የሚያጋልጥ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ እንደማያስገኝ ደጋግመን ማሳሰብ እንፈልጋለን። "" ብሏል ከሰሞኑ የኦሮሚያ ክልል የፌደራል ኃይሎች እና የክልል ኃይሎች በቅንጅት በወለጋ፣ በጉጂ፣ በምዕራብ እና ሰሜን ሸዋ በሚንቀሳቀሱ የታጣቂዎቹ አባላት ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውን ገልጿል። መግለጫው መንግሥት ""ሸኔን"" እደመስሳለሁ የሚለውን ሁኔታውን አቁሞ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እንደተጀመረው የሰላም አካሄድ እንዲከተልም ጥሪ አቅርቧል። ""መንግስት 'ሸኔን ማጥፋት' ከሚለው ውጤት አልባ የዘመቻ አዙሪት ወጥቶ በሰሜኑ ያገራችን ክፍል እንደጀመረው ሁሉ በኦሮሚያ ክልል ያለውን አለመግባባትም ተመሳሳይ በሆነ ሰላማዊ አካሄድ እንዲፈታ በድጋሜ ጥሪ እናደርጋለን፡፡"" በማለት አስፍሯል። ስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ሚያዝያ 1፣ 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በተጨማሪ ያነሳው ሃሳብ ከአማራ ክልል የመጡ ያላቸው ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል እየፈጠሩት ያለውን የጸጥታ ችግር አስመልክቶ ነው። እነዚህ ታጣቂዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል በመግባት "" የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት እየፈጸሙ እንዲሁም ሰላማዊ ሰዎችን እየገደሉ፣ አርሷአደሮችን ከመሬታቸው በማፈናቀል የኦሮሚያ ክልልን ወደማያባራ የግጭት ቀጠና እየለወጡት ነው"" ብሏል። ""የጦር ዘመቻና የመሬት ወራራ"" እየተፈጸመ እንደሆነ ያሰፈረው ይህ መግለጫ ይህም ሁኔታ በምስራቅ ወለጋ፤ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፤ሰሜን ሸዋ፤ ምዕራብ ሸዋና በምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ በተቀናጀ አኳኋን እየተካሔደ እንደሆነ መረዳቱንም ጠቅሷል። ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በተጨማሪ አገሪቱ የተፈጠረው የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነትን አንስቶ በመወያየት መንስዔውም የርስ በርስ ጦርነቱ እንደሆነና መፍትሄው ""ሀገሪቱን በሁሉም አቅጣጫ እያመሰ ያለውን የርስ በርስ ጦርነት ወደሚያስቆም ውይይትና ድርድር ፊትን ማዞር ብቻ ነው"" ብሏል። ጦርነቱ የውስጥና የውጪ ንግድ እንዲቀዛቀዝ፣ የግብርናና ፋብሪካዎች ምርታማነት እንዲቀንስ፣ የውጪ ኢንቨስትመንት እንዲዳከም እንዲሁም በማዕቀቡ ምክንያት በእርዳታና በብድር ወደ አገር ይገባ የነበረ ገንዘብ እንዲቀንስ ወይም እንዲቋረጥ በማድረጉ የአገሪቱ ምጣኔ ኃብት ላይ ከፍተኛ ጫና አሳርፏል ይላል የኦፌኮ መግለጫ በአጠቃላይ በአገሪቱ እየተከሰቱ ያሉ የጸጥታ ችግሮችም ሆነ የኑሮ ውድነቱን ችግር ለመፍታት በተለያዩ ስፍራዎች ያሉ ግጭቶችን ማስቆምና የፖለቲካ ልዩነቶችን በምክክር መፍታት አስፈላጊ ነው ሲል አሳስቧል። ""መንግሥትም ሆነ ማንኛውም ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል ወደምክክር መድረክ በመመለስ፤ የኢኮኖሚ ውድቀት፤ በህዝብ ላይ የተጫነውን መከራ፤ እንዲሁም አገሪቱን ከብተና እንዲያድኑ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡"" በማለት መግለጫው አስፍሯል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61077377 +politics የኢትዮጵያ ምርጫ 2013፡ የትኞቹ ፓርቲዎች ጠንካራ ተፎካካሪ ሊሆኑ ይችላሉ? "በግንቦት ወር መጨረሻና በሰኔ ወር መጀመሪያ ከትግራይ ክልል ውጪ በመላው ኢትዮጵያ ለማካሄድ በታቀደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ 52 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። ቢቢሲ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የኋላ ታሪክ፣ የመሪዎቻቸውን ተጽዕኖ ፈጣሪነ��� እና አሁናዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን መነሻ በማድረግ በፌዴራሉና በክልሎች እንዲሁም በከተማ መስተዳድሮች ምክር ቤቶች ድምጽ የማግኘት እድል ሊኖራቸው እንደሚችል የሚገመቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንደሚከተለው ዘርዝሯል። ፓርቲዎቹ የተዘረዘሩት በእንግሊዘኛ መጠሪያቸው ሆሄያት ቅደም ተከተል መሠረት ነው። አብን ረዥም የፖለቲካ የትግል ታሪክ ባይኖረውም በወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ ውስጥ ተጽዕኖው ቀላል የሚባል አይደለም። በብሔር ተኮር የፓለቲካ እንቅስቃሴ የአማራ ብሔርተኝነትን በመወከል የሚንቀሳቀሰው አብን የተመሠረተው በ2010 ዓ.ም ነው። ንቅናቄው ዋነኛ ዓላማዬ ""የአማራ ህዝብን ጥቅምና መብት ማስከበር ነው"" የሚል ሲሆን ከምስረታው በኋላ ባሉት ሦስት ዓመታት ጎልቶ መምጣት ችሏል። ፓርቲው በአማራ ክልል በወጣቱ ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው ይታመናል። በክልሉ በርካታ ስፍራዎችም ቢሮዎችን ከፍቶ ይንቀሳቀሳል። ከአምስት ወራት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ከሚቀርቡ ፓርቲዎች መካከል አብን አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል። በቅርቡ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ቆይታ የነበራቸው የንቅናቄው ሊቀ መንበር አቶ በለጠ ሞላ፤ ለምርጫው ሰፊ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናውን ገልጸዋል። ""በሕዝብ ለመዳኘትና ውጤቱን በጸጋ ለመቀበል"" ዝግጁ ስለመሆናቸውም ተናገረዋል። አብን ከአማራ ክልል ውጪም የአማራ ተወላጆች በብዛት በሚኖሩባቸው በተለያዩ የኢትዮጰያ ክፍሎች ጽህፈት ቤቶችን እያደራጀ ሲሆን ይህም በምርጫው ጠንካራ ተፎካካሪ ሊያደርገው እንደሚችል ይታመናል። ባልደራስ በቀድሞው ጉምቱ ጋዜጠኛ እና የመብት ተሟጋች በዛሬው ፖለቲከኛ አቶ እስክንድር ነገ የሚመራ ፓርቲ ነው። አቶ እስክንድር በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስና ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ተሳትፎ አለው። ባልደራስ ""የአዲስ አበባን ጥቅም ለማስከበር"" ያስጀመረው እንቅስቃሴ ሲሆን፤ እንቅስቃሴው አድጎ አዲስ አበባን መሠረት በማድረግ ወደ ፓለቲካ ፓርቲነት አድጓል። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ መሪው አቶ እስክንድር የታሰርበት ባልደራስ፤ በከተማ አስተዳደሩ ይሰራሉ ያላቸውን 'ሕገ ወጥ' ተግባራት እንደሚታገል ሲገልጽ ቆይቷል። ባልደራስ በተለያዩ ወቅቶች የሚጠራቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎችና ሰልፎች ግልጽ ባልሆኑ ምክንያቶች ሲሰረዙ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። ፓርቲው በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ በፈጠረው ተጽዕኖ እና አቶ እስክንድር በፖለቲካው ውስጥ ባለው 'የገዘፈ' ስም ምክንያት፤ ባልደራስ በመጪው ምርጫ አዲስ አበባ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ኢዜማ በምርጫ 97 ተሳትፏቸው የታወቁ እውቅ ፖለቲከኞችን ያቀፈ ነው። በመላው አገሪቱ ሊባል በሚያስችል መልኩ ከ400 በላይ የምርጫ ወረዳ ጽህፈት ቤቶችን ከፍቷል። ከብሔር ፖለቲካ በተለየ ""ዜግነትን መሰረት ያደረገ"" ፖለቲካን እንደሚያራምድ የሚገልጸው ፓርቲው፤ በኢትዮጵያ ማህበራዊ ፍትህን ማረጋገጥ ቀዳሚ ግቤ ነው ይላል። ፓርቲው ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለየ መልኩ፤ በአገሪቱ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊና የውጪ ግንኙነት ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ 40 የፖሊሲ ሰነዶችን እንዳዘጋጀም ገልጿል። ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ሕገ ወጥ ነው ያለውን የመሬትና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ወረራ በተመለከተ ያወጣው የጥናት ሪፖርት የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በ97ቱ ምርጫ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከነበሩ ፖለቲከኞች መካከል ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የፓርቲው መሪ፤ አቶ አንዱአለም አራጌ ደግሞ የፓርቲው ምክት መሪ ናቸው። ከጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን መምጣት ቀደም ብሎ የጎላ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የነበረውን ሰማያዊ ፓርቲ ሲመሩ የነበሩት አቶ የሺዋስ አሰፋን ሊቀ መንበር ያደረገው ኢዜማ፤ 6 ፓርቲዎች ከስመው የመሰረቱት ነው። ከእነዚህ ውስጥ ነፍጥ አንግቦ ሲታገል የነበረው አርበኞች ግንቦት 7 ተጠቃሽ ነው። ይህ ድርጅት በውጪና በአገር ውስጥ ቀላል የማይባል ደጋፊዎች እንዳሉት ይገለጻል። ታዲያ የዚህ ሁሉ ድምር ኢዜማን በምርጫ 2013 ለውጤት ከሚጠበቁ ፓርቲዎች አንዱ አድርጎታል። ኦብነግ በፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ረዥም እድሜ ያስቆጠረ ድርጅት ነው። ከ37 ዓመታት በፊት የተመሠረተው ኦብነግ መሰረቱን በሶማሌ ክልል ያደረገ ነው። ከ1986 እሰከ 2010 ዓ. ም በትጥቅ ትግል የቆየው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር፤ ከ1983-87 የነበረው የሽግግር መንግሥት አካል ነበር። በ1984 በተከናወነው የአካባቢ ምርጫ 87 በመቶ የሚሆነውን ድምጽ በማሸነፍ የሶማሌ ክልልን ለሁለት ዓመታት አስተዳድሯል። ሆኖም በኦብነግና ማዕከላዊ መንግሥቱ መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ግንባሩ ወደ ትጥቅ ትግል እንዲገባ አድርጎታል። በዚህም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 'አሸባሪ' ተብሎ ተፈርጆ ነበር። በ2010 የጠቅላይ ሚኒሰትር ዐብይን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከተሎ ከሽብር መዝገብ ተሰርዞ በሕጋዊ ፓርቲነት ተመዝግቧል። የሶማሌ ክልል ሕዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ማረጋገጥ ዋነኛ ዓላማዬ ነው የሚለው ፓርቲው፤ በቀጣዩ ምርጫ በሶማሌ ክልል ብርቱ ተፎካካሪ እንደሚሆን ይጠበቃል። የፓርቲው አመራሮች በ2011 ወደ አገር ቤት በገቡበት ወቅት የተደረገላቸው 'ሞቅ' ያለ አቀባበል ግንባሩ አሁንም ያለውን ተቀባይነት ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ምርጫ ያለውንም ተስፋ የሚያመላክት ይመስላል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የረዥም ዘመን ተሳትፎ ያላቸው መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር) የሚመሩት ኦፌኮ፤ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ተሳታፊ ነበር። ሊቀ መንበሩ መረራ (ፕሮፌሰር) በፌዴራሉ የፓርላማ አባል ሆነው በቆዩባቸው ዓመታት በፓርላማ ውስጥ በሚሰጧቸው አስተያየቶች በበርካቶች ዘንድ ይታወሳሉ። በተደጋጋሚ የታሰሩ ሲሆን ለመጫረሻ ጊዜ ከእስር ሲፈቱ በርካታ ደጋፊዎቻቸው አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን ገልጸዋል። በተመሳሳይ አሁን እስር ቤት የሚገኙት ምክትል ሊቀ መንበሩ አቶ በቀለ ገርባ የዳበረ የፖለቲካ ልምድ ያላቸው ናቸው። በኦሮሚያ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ተቀባይነት ያለው አቶ ጀዋር መሐመድ ፓርቲውን መቀላቀሉ የኦፌኮን ተጽዕኖ ከፍ እንዳደረገው ይታመናል። መረራ (ፕሮፌሰር)፣ አቶ በቀለ እና አቶ ጀዋር ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት በኦሮሚያ የተለያዩ አከባቢዎች በተጓዙበት ወቅት የተደረገላቸው አቀባል ኦፌኮ በምርጫ 2013 ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንደሚቀርብ ያመላከተ ነበር። በኢትዮጵያ የምርጫ ስርዓት ልምድ ያካበቱ ጉምቱ ፖለቲከኞችን መያዙ [ምንም እንኳን በእስር ላይ የሚገኙ ቢኖሩም] ኦፌኮን በቀጣዩ ምርጫ ለውጤት የሚጠበቅ ፓርቲ አድርጎታል። ከተመሠረቱ ብዙ ዓመታት ካስቆጠሩት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል አንዱ ኦነግ ነው። በበርካታ የኦሮሚያ አከባቢዎች የነጻነት አርማ ተደርጎ የሚቆጠረው ኦነግ በ1965 ዓ. ም ነበር የተመሠረተው። ግንባሩ የ1983ቱ የሽግግር መንግሥት አካል የነበረ ሲሆን ብዙም ሳይቆይ ግን አማጺ ቡድን ሆኖ ጫካ ገባ። እናም ለዓመታት በትጥቅ ትግል ቆይቶ ከ3 ዓመታት በፊት የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ ወደ አገር ቤት ተመልሷል። ከበርካታ ዓመታት የትጥቅ ትግል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ለመወዳደር የተዘጋጀው ፓርቲው፤ በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከፍተኛ ግምት ከሚሰጣቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ ነው። ፓርቲው በውስጣዊ ችግሮቹ እና በፓርቲ አመራሮች እስር ታጅቦ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ያለውን የገዘፈ ስምና የትጥቅ ትግል ታሪክ ይዞ ምርጫው እየተጠባበቀ ነው። ፓርቲው በመንግሥት ይደርስብኛል በሚለው ጫናና በአመራሮቹ መካከል የተፈጠረው ቅራኔ በምርጫ ተሳትፎው ላይ ተጽዕኖ ካላደረገበት በስተቀር በኦሮሚያ ክልል ብርቱ ተፎካካሪ መሆኑ የሚቀር አይመስልም። ብልጽግና፤ ያለፉትን 5 አገራዊ ምርጫዎች 'አሸንፊያለሁ' ያለውና አገሪቱን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሲያስተዳድር የቆየው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ውጤት ነው። ብልጽግና ከኢሕአዴግ መክሰም በኋላ አንዳንድ ለውጦችን እንዳደረገ ቢነገርም፤ ህወሓት ብቻ የተቀነሰበት የቀድሞው ኢሕአዴግ ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከህወሓት ውጪ ግንባሩን ከ 'አጋሮቹ' ጋር በመዋሃድ ብልጽግና የተሰኘ አዲስ ፓርቲ ፈጥረዋል። የቀድሞውን ኢሕአዴግ ሀብት እና ንብረቶች ጠቅልሏል። አብዮታዊ ዲሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብን ሽሮ መደመር በተሰኘ የፓርቲው ፕሬዝዳንትና በአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እሳቤ ተክቷል። ፓርቲው በመላው ሀገሪቱ አለኝ ከሚለው በሚሊዮን የሚቆጠር አባላት እንዲሆም ረጅም አመታት ያሰቆጠር ጠንካራ መዋቅር በቀጣዩ ምርጫ ተጠባቂ እንዲሆን አርጎታል። የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐቢይ (ዶ/ር) አምጥተውታል የሚባለው ለውጥና በአገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ያላቸው ድጋፍ እንዲሁም ፓርቲው በክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች ተጽዕኖ ፈጣሪ አመራሮችን መያዙ በምርጫው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንዲገመት አድርጎታል። ከላይ የተጠቀሱት አንዳንድ ፓርቲዎች በተለያዩ ምክንያቶች በቀጣዩ ምርጫ ላይሳተፉ እንደሚችሉ እየገለጹ ቢሆንም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ይኖራቸዋል ተብሎ የሚጠበቀው ፍክክር ምርጫ 2013 ከባለፉት በተሻለ ዓይን የሚጣልበት እንዲሆን አድርጎታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56027522 +business ምጣኔ ኃብት፡ ከመቶ ሺህ ብር በላይ ያላቸው በአንድ ወር መቀየር እንዳለባቸው ተገለፀ አዲሱ የብር ኖት ቅየራ በዛሬው ዕለት፣ መስከረም 6/2012 ዓ.ም ከሰዓት መጀመሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ አቶ አልሰን አሰፋ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በዝግጅቱ ላይም የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ የተገኙ ሲሆን፤ ዛሬ ከቀኑ 9፡30 ጀምሮም በአዲስ አበባ አካባቢ ባሉ ባንኮች ብር መቀየር ተጀምሯል ብለዋል ሥራ አስኪያጁ። በመሆኑም የብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው መመሪያ መሠረት፤ 100 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ገንዘብ በእጃቸው ላይ ያለ ግለሰቦችና አካላት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ወደ ባንክ በመሄድ ገንዘቡን መቀየር እንደሚችሉም አቶ አልሰን ገልፀዋል። አገልግሎቱ በማንኛውም የባንክ ቅርንጫፍ እንደሚሰጥ የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ፤ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች እጃቸው ላይ ያለውን ብር ወደ አዲሱ መቀየር አሊያም ከሒሳብ ቁጥራቸው አዲሱን የብር ኖት ማውጣት እንደሚችሉ ተናግረዋል። እጃቸው ላይ ከ100 ሺህ ብር በታች ያላቸው ግለሰቦችም እስከ 2 ወር ከግማሽ ድረስ ገንዘባቸው እንዲቀይሩ ቀነ ገደብ ተቀምጧል ብለዋል። ከ100 ሺህ ብር በላይ ያላቸው ግን በዚህ አንድ ወር ብቻ ቅየራውን ማጠናቀቅ ያለባቸው ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ የሚመጣ በየትኛውም ባንክ እንደማይስተናገድ ሥራ አስኪያጁ አስጠንቅቀዋል። በመሆኑም በዚህ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ራሳቸውን ከኮሮና በመጠበቅ እጃቸው ላይ ገንዘባቸው በአዲሱ የብር ኖት እንዲለውጡ አሳስበዋል። ከዚያ በታች የገንዘብ መጠን ያላቸው ሰዎች የተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ እስከ ሁለት ወር ከግማሽ ቢሆንም በዚህ ወር ውስጥም ግን መቀየ��� እንደሚችሉ አቶ አልሰን ጠቁመዋል። 10 ሺህ እና ከዚያ በላይ እጃቸው ላይ ያለ ሰዎች ደግሞ ገንዘባቸው አካውንታቸው ላይ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን የሒሳብ ቁጥር ከሌላቸውም መታወቂያ እና ጉርድ ፎቶግራፍ በመያዝ የሒሳብ ቁጥር ከፍተው ገንዘባቸው እዚያ ማስቀመጥ ይችላሉም ተብሏል። በተቀመጠው ጊዜም ከባንክ ውጪ የሚገኙ ገንዘቦች የሚሰበሰቡበት ሁኔታዎች መመቻቸታቸውንም ሥራ አስኪያጁ አክለዋል። አቶ አልሰን እንዳሉት ገንዘቡን ለመሰብሰብ የተሰጠው አጠቃላይ ጊዜ ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሦስት ወራት ውስጥ ነው። በዚህ ጊዜም ከባንክ ውጭ አለ ተብሎ የሚገመተው ወደ 113 ቢሊየን ብር ወደ ባንክ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅም ኃላፊው ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ኢትዮጵያ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50 እና የ100 የገንዘብ ኖቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመተካት አዲስ የገንዘብ ኖቶችን ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። ከአዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች ውስጥም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የባለ ሁለት መቶ ብር ኖትም አሳትማለች። አገሪቷ ነባሮቹን የብር ኖቶች ለመቀየር ሌላ ወጪን ሳይጨምር ለህትመት ብቻ 3.7 ቢሊየን ብር ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስታውቀዋል። https://www.bbc.com/amharic/54183500 +politics የጋዳፊ ልጅ ከፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ታገዱ "የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ ጋዳፊ ከሳምንታት በኋላ በሀገሪቱ ከሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውድድር ውጪ ሆነዋል። የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ሰይፍ አል ኢስላም ጋዳፊን ጨምሮ በርካታ እጩዎችን ""በህጋዊ ምክንያቶች"" በምርጫው እንዳይሳተፉ እንዳገደ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። አል ኢስላም ጋዳፊን አባቱ የሰሜናዊቷን አፍሪካዊ ሀገር ሊቢያን በሚያስተዳደሩበት ወቅት በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጦር ወንጀል እና በነፍስ ግድያ የሚፈለግ ሰው ነበር። በዚህም ሳቢያ የጋዳፊ ልጅ ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ ከተሰማ በኋላ ውዝግብ አስነስቷል። በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች የወንጀል ክስ የቀረበባቸው ዝነኛው ካሊፍ ሃፍታር ለምርጫ ለመወዳደር መዘጋጃታቸው በሀገሪቱ ውስጥ ውዥንብር ፈጥሯል። ነገር ግን ምርጫ ኮሚሽኑ ከፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ያድርጋቸው አይድርጋቸው የታወቀ ነገር የለም። የሊቢያ ወታደራዊ አቃብያነ ህግ የጋዳፊ ልጅ እና የሃፍታር በቀረበባቸው ክስ ላይ ተገቢ መልስ እስኪያቀርቡ ድረስ የምርጫ ኮሚሽኑን በእጩነት ለማሳተፍ የሚያደርገውን ሂደት እንዲያቆም ጠይቀው ነበር። ሰኞ በተጠናቀቀው የእጩዎች ምዝገባ ስልሳ ሰዎች ሊቢያን በፕሬዝዳንት ለመምራት የተመዘገቡ ሲሆን የ46 ዓመቷ የሴቶች መብት ተሟጋች ሊላ ቤን ካሊፋ ብቸኛዋ ሴት ተወዳዳሪ ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/59406242 +politics አሜሪካ ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ልዩ መልዕክተኛ ሾመች "አሜሪካ በኢትዮጵያና በአካባቢዋ ባሉ አገራት ውስጥ ስላሉ ጉዳዮች በቅርበት የሚከታተሉላትን ልዩ መልዕክተኛ መሾሟን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስታወቀ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ይፋ እንዳደረጉት በተለይ ኢትዮጵያ ለምትገኝበት የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ጄፍሪ ፌልትማንን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አድርገው መሾማቸውን ገልጸዋል። አሜሪካ አዲስ የሾመቻቸው የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በተለይ በኢትዮጵያና በዙሪያዋ ስላሉ ሁኔታዎች የተለየ ትኩረት እንደሚሰጡ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አመልክቷል። በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን ግጭት ጨምሮ በአገሪቱ ያለው ተለዋወጭ ሁኔታ፣ ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር አለመግባባት እንዲሁም በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለው ውዝግብ የልዩ ልዑኩ ቀዳሚ ሥራ እንደሚሆን ተገልጿል። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ በመግለጫው ላይ እናዳለው ቁልፍ በሆነው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ""በአሁኑ ጊዜ መሠረታዊ ለውጥ እየተካሄደበት ነው"" ብሏል። የአዲሱን ልዩ መልዕክተኛ አስፈላጊነት በተመለከተም በአካባቢው ""በትውልዶች ውስጥ አንድ ጊዜ ለሚያጋጥም የለውጥ ዕድል አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የግጭት ስጋትን ለማስቀረት በከፍተኛ የሥልጣን ደረጃ የአሜሪካ ተሳትፎ አስፈላጊ"" በመሆኑ ነው ብሏል። ይህ የልዩ መልዕክተኛ ሹመት የባይደን አስተዳደር በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለውን ተያያዥ የሆኑትን ፖለቲካዊ፣ የደኅንነትና የሰብአዊ ጉዳዮች ምፍትሔ እንዲያገኙ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ጥረቶችን ለመምራት ያለውን ቁርጠኝነት ያመለክታል ተብሏል። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥና በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ የሰሩት ጄፍሪ ፌልትማን በአፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ላይ ለረጅም ዘመን ልምድ እንዳላቸው ተገልጿል። በተጨማሪም ፌልትማን በርካታ አገራትን ባካተቱ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሚደረጉ ድርድሮችና ሽምግልናዎች ውስጥ የአሜሪካንን ተያያዥ ስትራቴጂን በማስፈጸም ልምድ አላቸው ብሏል ሹመታቸውን ያሳወቀው መግለጫ። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትና በተባበሩት መንግሥት ውስጥ በተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ በመሥራት ሠፊ ልምድ እንዳላቸው የሚነገርላቸው የ62 ዓመቱ ጄፍሪ ፌልትማን በዓለም አቀፍ ፖለቲካ የጥናት ተቋማት ውስጥ እጉልህ ሚና አላቸው። ፌልትማን በድርድርና የሽምግልና ጉዳዮች ላይ ጥናትን በማካሄድና በአደራዳሪነትም ከፍ ያለ ልምድ እንዳላቸው ይነገራል። ፌልትማን በፖለቲካዊና በውጭ ጉዳዳ ፖሊሲዎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞውንና የአሁኑን ሊቃነ መናብርት ባን ኪሙን እና አንቶኒዮ ጉቱሬዝን ያማከሩ ሲሆን፤ ለጸጥታው ምክር ቤት በሠላምና በደኅንነት ጉዳዮች ማብራሪያዎችን በመስጠት ይታወቃሉ። በተባበሩት መንግሥታት ቆይታቸው ወቅትም በልዩ መልዕክተኝነት አገልግለዋል፤ በተጨማሪም በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥ ለ26 ዓመታት ያገለገሉት ፌልትማን በሌባኖስ፣ በኢራቅ፣ በእስራኤል፣ በቱኒዚያ፣ በሃንጋሪና በሄይቲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው አገልግለዋል። አሜሪካ በትግራይ ክልል ውስጥ ወታደራዊ ግጭት ከመከሰቱ በፊት በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ውስጥ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማካይነት ጭምር ስትሳተፍ መቆየቷ ይታወሳል። በተለይ በትግራይ ክልል ውስጥ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ ከፍተኛ የአገሪቱ ባለስልጣንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጨምሮ ከሌሎች የኢትዮጵያው ባለሥልጣናት ጋር በተደጋጋሚ መወያየታቸው ሲነገር ቆይቷል። ባለፈው መጋቢት ወርም የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ሴናተር ክሪስ ኩንስ ለቀናት የቆየ ጉብኝት በአዲስ አበባ አድርገው ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያይተው ነበር። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ትግራይ ውስጥ ስላለው ግጭትና የሰብአዊ ጉዳዮች ሁኔታ በተደጋጋሚ ጠንከር ያሉ መግለጫዎችና ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞ ማሰማቱ ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56867423 +health ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መጨመር እንዳሳሰባት ገለፀች "በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመ�� ደቡብ ሱዳን እንዳሳሰባት ገልፃለች። መጋቢት ወር ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጀምሮ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመጣባት ኢትዮጵያ በባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳኗ መዲና ጁባ በየቀኑ ከአዲስ አበባ በረራ የሚያደርግ ሲሆን ይሄም ሁኔታ አስጊ ነው በማለት የጤና ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። ""በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር በእርግጥ ሊያሳስበን ይገባል፤ ስለዚህ የመከላከያ መንገዶቻችንንም ልናጠናክር ይገባል"" በማለት የጤና ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ዶክተር ቶው ሎይ ሲንጎት በጁባ ለሚገኙ ሪፖርተሮች ተናግረዋል። ሆኖም ከአዲስ አበባ ወደ ጁባ በየቀኑ የሚደረጉት በረራዎችም እንደሚቀጥሉ የተናገሩት ቃለ አቀባይ ሁሉም አገራት ለዜጎቹ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት እንደሚደረገው ከፍተኛ ጥንቃቄን ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል። ""ከአዲስ አበባ የሚደረጉ የየቀኑ በረራዎች የሚቀጥሉ ይሆናል። አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ካልሆነ አይቆምም"" ብለዋል ዶክተር ቶው ሎይ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 59 ሺህ 648 ደርሷል፤ ከነዚህም ውስጥ 21 ሺህ 789 ያገገሙ ሲሆን 933 ህይወታቸው እንዳለፈ በትናንትናው ዕለት የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጋራ መግለጫ አስፍሯል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54068173 +sports በአሜሪካ ታዋቂ አትሌቶች የወሲብ ጥቃቶችን ችላ በማለት ኤፍቢአይን ሊከሱ ነው በአሜሪካ የብሔራዊ የጂምናስቲክ ቡድን ዶክተር የወሲብ ጥቃት ደርሶብናል ያሉ አትሌቶች ኤፍቢአይን በ1 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ሊከሱ ነው። ቅሬታ አቅራቢዎቹ የአሜሪካ ፌደራል የምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) በሕክምና ባለሙያው ላሪ ናሳር የተፈጸሙ የወሲብ ጥቃቶች ላይ ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎች ቢቀርቡም በአግባቡ አላስተናገደም ብለዋል። ከከሳሾቹም መካከል የኦሎምሊክ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎቹ ሲሞን ባይልስ፣ አሊ ሬይስማን እና ማኬይላ ማሮኒ ይገኙበታል። ዶክተር ላሪ ናስር የጂምናስቲክ ስፖርተኞቹ ላይ ትንኮሳ እንዲሁም ወሲባዊ ጥቃቶችን በማድረስ ወንጀል የ175 ዓመት እስራት ተፈርዶበት በእስር ላይ ይገኛል። የኤፍቢአይ የበላይ ጠባቂ በበኩሉ ኤፍቢአይ ስለ ዶክተሩ የቀረበውን ክስ ችላ ማለቱንና የምርመራው ጅማሮ ላይም ስህተቶችን መሥራቱን አጋልጧል። ባለፈው ዓመት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአሜሪካ የፍትሕ ዲፓርትመንት የዋና ኢንስፔክተር ጽሕፈት ቤት ሪፖርት ኤፍቢአይ በዶክተሩ ላይ ስላከናወነው ምርመራ ግምገማ ሰጥቷል። በሪፖርቱ መሠረት በአውሮፓውያኑ 2015 ዶክተሩ ፈፅሟቸዋል በተባሉ ጥቃቶች ላይ ምርመራ ቢጀመርም ምንም ነገር ሳይደረግ ከአንድ ዓመት በላይ እንዲቀጥል ተደርጓል ይላል። ለዚህም የኤፍቢአይ ወኪሎች ስህተቶችን በመፈጸም እንዲሁም ሆን ብለው ለመሸፋፈን እንደሞከሩ ሪፖርቱ አመልክቷል። ለኤፍቢአይ ሪፖርት ከተደረገ በኋላም ዶክተሩ ወሲባዊ ጥቃት እንዳደረሰባቸው ተከሳሾቹ አጋልጠዋል። አብዘኞቹ የአሜሪካ ብሔራዊ የጂምናስቲክ ፕሮግራም አካል እንዲሁም በሚቺጋን ዩኒቨርስቲ በሚገኘው የዶክተሩ ክሊኒክ ሕክምና ይከታተሉ የነበሩ አትሌቶች ናቸው። ሪፖርት የተደረገላቸው የኤፍቢአይ መርማሪዎች እዚህ ግባ የማይባል እርምጃ እንደወሰዱ እና ምርመራ በማከናወን ዘርፉ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም እንዲሁም ሌሎች ባለሥልጣናትን አላስጠነቀቁም ተብሏል። “የነዚህ ወሲባዊ ጥቃቶች ሰለባ የሆንን አትሌቶች እኛን ሊጠብቁን በሚገቡ ሁሉም ተቋማት ማለትም በአሜሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ በአሜሪካ ጂምናስቲክስ፣ በ��ፍቢአይ እንዲሁም በፍትሕ ዲፓርትመንቱ ተክደናል” በማለት  የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነችው ኬይላ ማሮኒ በሰጠችው መግለጫ ተናግራለች። ከሁለት ሳምንት በፊት የአሜሪካ የፍትሕ ዲፓርትመንት ኤፍቢአይ ምርመራውን በተሳሳተ መንገድ ይዘውታል የተባሉ ሁለት የኤፍቢአይ ወኪሎች ላይ ክስ ላለመመሥረት ወስኗል። ከሳሾቹ አትሌቶች ተቋሙ ላደረሰው ጉዳት ካሳ የጠየቁ ሲሆን ይህም ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚሆን ይጠበቃል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c4nwddg511go +sports በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. "በጋ ፈረንጆቹን ያፈካቸዋል። ኮምጫጫ አውሮፓዊ ለማያውቀው መንገደኛ ሳይቀር ፈገግታ የሚመጸውትበት ጊዜ ነው። ለሀበሾችስ ቢሆን? በጋው የፌሽታ ነው። በረዶ ያቆፈነው በጓንት የተጀቦነ እጅ እንጀራ ለመጠቅለል የሚፍታታበት ወቅት ነው። ካፖርታና ጋቢ ወዲያ የሚሽቀነጠርበት ወቅት ነው። በከፊል ዕርቃን መዘነጥ የሚያስችል በቂ ንዳድ አለ። ከሁሉ በላይ ዓመታዊው የባህልና ስፖርት አውደፌሽታ አለ። ቁርጥ አለ፤ በቂቤ ያበደ ሽሮ አለ፤ ጎረድ ጎረድ አለ። ቡናው ይንከሸከሻል…እጣኑ ይንቦለቦላል…፤ የአገር ሰው ከዚህ በላይ ምን ይሻል? ይህ አገር ቤት እየኖረ እንግሊዝኛ ለሚቀናው ሰው ‹‹ሶ ዋት?›› የሚያስብል ሊሆን ይችላል። ከአገር ለራቀ ሰው ግን ትርጉሙ ራስ ዳሽን ነው። ለዚህም ነው ለዓመታዊው የሐበሾች ‹‹መካ›› በየዓመቱ በሺዎች የሚተሙት፡፡ ዘንድሮ ተረኛዋ ዙሪክ ነበረች። እጅግ አምሮባት ተኩላ ነበር እንግዶቿን የጠበቀችው። እርግጥ ነው በነዚህ መድረኮች ላይ ሀበሾቹ የሚገናኙት ለሳቅ ለጨዋታ ነው። የሚጠራሩት ለእስክስታና ፌሽታ ነው። ሆኖም ክትፎና ቁርጥ ቀማምሰው ሲጨርሱ ቡጢ ይቀማመሳሉ። መነሻው ምንም ሊሆን ይችላል። በሐበሾች መንደር ግን ጸብ ጠፍቶ አያውቅም። በዙሪክ ይህ ባይሰተዋልም በስቱትጋርት ሆኗል። •""እናቴ ካልመጣች አልመረቅም"" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ እንዴት እጅግ የተነፋፈቀ የአገር ልጅ ለያውም በሰው አገር፣ ለያውም ለሳቅ ለጨዋታ ተጠራርቶ ቡጢ እንደሚሰነዛዘር መተንተን የቻለ ሊቅ ለጊዜው አልተገኘም። ብቻ የአገር ልጆች በየዓመቱ ተሰባስበው የ‹‹ፍቅር ቡጢ››ን እንካ ቅመስ-እንቺ ቅመሽ ሲባባሉ ዓመታት አስቆጥረዋል። ለምሳሌ የዛሬ ዓመት የፌሽታው አስተናጅ ስቱትጋርት ነበረች። ቴዲ አፍሮ መጥቶ አፍሮ ተመልሷል፤ ሳይዘፍን። ንብረት ወድሟል። የአዳራሽ መስታወት እንዳልነበር ሆኗል። የጀመርን ፖሊስ ‹‹ኤሎሄ! ዘንድሮ ምን ጉድ ላ'ክብን›› ብሏል። ጸቡ ከእኛም አልፎ ወንድም ኤርትራዊያንን ያሳተፈ ነበር። የቢራ ጠርሙስ ከአንድ ኢትዮጵያዊ እጅ ተምዘግዝጎ ሌላ ኢትዮጵያ የራስ ቅል ላይ አርፏል። ሀበሾች ሲገናኙ ‹‹አብሿቸው›› ይነሳል መሰለኝ ፍቅራቸው በጸብ ካልደመቀ…። ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ዙሪክ የከተሙት ይህንኑ የጸብ ትዝታ ይዘው ነበር። ዙሪክ አላሳፈረቻቸውም። ለሰላሙ ቅድሚያ ሰጥታ አጫውታ፣ አዝናንታ አፋቅራ ሸኝታቸዋለች። በአሉታዊነቱ ስቱትጋርት እንደ ምሳሌ ተነሳ እንጂ፣ ሮም በ2012 ‹‹የፌዴሬሽኑን ገንዘብ ይዘው ተሰውረዋል›› በሚሉና ‹‹እንዲያውም አዘጋጅተን ከሰርን›› በሚሉት መሀል መራር ጸብ ነበር። ደግነቱ የሮም ጸበኞች ዘንድሮ በዙሪክ ይቅር ለእግዛብሔር ተባብለዋል። በ2014 ሙኒክ ላይም ምክንያቱ መናኛ የሆነ ዱላ መማዘዝ ነበር። ‹‹ሐበሻ ድሮም አብሮ መብላት እንጂ…አብሮ መሥራት…›› የሚል ተረት የሚያስተርቱ አጋጣሚዎች በርካታ ነበሩ። ሆኖም ይህን ሁሉ ዓመት ከጸብና መወነጃጀል መራቅ ለምን አልተቻለም? የሚለው ጥያቄ ዛሬም ሙሉ በሙሉ ምላሽ አላገኘ��። አንድ ሁለት ምክንያቶችን መዘርዘር ግን ይቻላል። አንዱ በየዝግጅቶቹ ውስጥ የአገር ቤቱ ፖለቲካ የሚያጠላው ጥላ ሰፊ መሆኑ ነው። ሌላው በጎ ፈቃድ እንጂ የአመራር ክህሎት በሌላቸው ሰዎች ትልቅ ድግስ መሰናዳቱ የሚፈጥረው ትርምስ ነው። ሦስተኛው ለጥቅም መንሰፍሰፍ ነው። •የጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ 'መራር' ትዝታ ‹‹እንዲህ ዓይነቱን ሺህዎች የሚታደሙበት አውደ ፌሽታ ለማሰናዳት ከመቶ እስከ ሁለት መቶ ሺህ ዩሮ ፈሰስ መደረጉ አይቀርም›› ይላሉ ወጪውን የሚያውቁት። ይህንን ወጪ ለመመለስ፣ ብሎም በትርፍ ለመንበሽበሽ አድብቶ የሚጠብቀው ብዙ ነው፤ በዚህ መሀል ትርምስ ይፈጠራል። ከፍተኛ የጥቅም ግጭት ይነሳል። ‹‹ስልጡን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሰለጠነ መንገድ መነጋገር ይሳናቸዋል። በሰለጠነ መንገድ ሂሳብ ኦዲት አያስደርጉም። በሰለጠነ መንገድ ወጪና ገቢ አያሰሉም። መጨረሻው የማያምረው ለዚህ ይመስለኛል›› ይላል በዓመታት ውስጥ ባየው ነገር ተስፋ ቆርጦ ራሱን ከአዘጋጅነት ተሳትፎ ያገለለ ወጣት ለቢቢሲ። የዙሪኩ መሰናዶ ግን በሁሉም መለኪያ የተሻለና የተዋጣለት መሆኑ ለብዙዎች መልካም ስሜትን ፈጥሯል። ለሌሎች ቀጣይ አዘጋጅ ቡድኖችና ከተሞችም ምሳሌ መሆን የሚችል ነበር። ከደርግ ጀምሮ ከዚያም ቀደም ብሎ ከአገር የወጡ ኢትዮጵያዊያን አሉ። በአውሮፓ የሚኖሩ የድሮ የብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ብዛታቸው ለጉድ ነው። ይህ ዓመታዊ አውደ ፌሽታ ታዲያ ለአንዳንዶች የፌሽታ ያህል ፌዝ አይደለም። የምር ጉዳይ ነው። የአገር ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያን ናፍቀው ኢትዮጵያ መግባት የማይችሉ በርካታ ዜጎች ነበሩ። በፖለቲካም ይሁን በያዙት የስደተኛ ወረቀት ምክንያት። ስለዚህ ኢትዮጵያዊን ባይረግጡም ‹‹የኢትዮጵያን ኮፒ›› መርገጥ ይፈልጋሉ። በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኮፒ ደግሞ ይህ ዓመታዊ አውደ ፌሽታ ብቻ ነው። በዚህ ምክንያት ዝግጅቱን እንደዋዛ አያዩትም። በማንከሽከሻ የሚቆላ ቡና…እጅ የሚያስቆረጥም ቁርጥ…ምራቅ የሚያስውጥ ክትፎ፣ ከሸክላ የሚንቆረቆር አገርኛ ሙዚቃ…ከኢትዮጵያ ብዙ ሚሊየን ማይሎች ርቆ ለሚኖር ሰው ቀልድ አይደለም፡፡ መዝናኛ ብቻ አይደለም። አገር የመግባት ያህል ነው። ለነዚህ ኢትዮጵያዊያ የአገርን፣ የአገር ልጅን ናፍቆትም ለመወጣት ሁነኛ ሥፍራ ይኸው መድረክ የሆነውም ለዚሁ ነው። ጎረቤታሞች ቡና ሊጠራሩ ቀርቶ በማይተያዩበት፣ በሁለት ሦስት ሥራ ደፋ ቀና ካላሉ ሕይወት በማይገፋበት፣ ጥሬ ሥጋ መጉረስ ዜና በሚሆንበት አውሮፓ ኢትዮጵያዊያንን የሚያገናኘው ፌስቲቫል ከተጀመረ ዘንድሮ 17ኛ ዓመቱን ይዟል። አውሮፓ ውስጥ ኢትዮጵያውያን የሚገናኙበት ምናልባትም ብቸኛው ፌስቲቫል ነው። ለዚህም ነው ጁላይ 31 እስከ ኦገስት 2! ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን በቀን መቁጠሪያቸው ላይ በደማቅ ቀለም ያከበቡት። ቀኑ ሲደርስ ራቅ ካሉቱ እንደ ኖርዌይ እና ስዊዲን በጢያራ በረሩ። ቀረብ ካሉቱ ከጀርመን፣ ከፈረንሳይ፣ ከእንግሊዝ…በአውቶቡስ ተሳፈሩ፣ የባቡር ትኬት ቆረጡ፣ የመኪናቸውን ሞተር ቀሰቀሱ። ሆኖም ድንበር ሲደርሱ ስዊዘርላንድ ‹‹የማይደረገውን!?›› አለች። ስዊዘርላንድ ከተቀሩት የአውሮፓ አገሮች የድንበሯን ነገር በዋዛ ባለመመልከት ትታወቃለች። በቂ የጉዞ ሰነድ የላቸውም ያለቻቸውን ኢትዮጵያዊያንን ወደመጡበት መልሳቸዋለች። ከእነዚህ መካከል በዙሪክ ለመጫወት የተንቀሳቀሱት የፈረንሳዩ ኢትዮ-ማርሴይ የእግር ኳስ ቡድን እና ከኢትዮ-ፍራንክፈርት ሁለት ቡድኖች አንዱ፣ እንዲሁም የጀመርኑ ዳርምሽታት የእግር ኳስ ቡድን አባላት በከፊል ይገኙበታል። አብዛኞቹ በሚኖሩበት አገር ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ ተሰጥቷቸው የዜ���ነት ማረጋገጫ ወረቀት የሚጠብቁ ወይም የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ወይም ጭርሱኑ ያላገኙ ናቸው። የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ አሳየኸኝ ጥላሁን ለቢቢሲ እንደተናገሩት እንግሊዝ ከ40ሺ የሚልቁ ኢትዮጵያዊያን የሚገኙባት አገር ሆኖ ነገር ግን ይህ ፌስቲቫል እንግሊዝ የማይዘጋጅበት አንዱ ምክንያት እንዲህ ዓይነቱ ችግር እንዳያጋጥምና ኢትዮጵያዊያኑ እንዳይንገላቱ በመስጋት እንደነበር ያስረዳሉ። ‹‹ይህ ዝግጅት ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ዓመታዊ የሥነ ልቦና ቴራፒ የሚያገኙበት ነው። በጉጉት የሚጠብቁት ነው፤ ከድንበር መመለሳቸው ያሳዘነን ጉዳይ ነው›› ይላሉ አቶ አሳየኸኝ። ፌስቲቫሉ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2001 ላይ ሲጀመር ከአንድ ቀን የእግር ኳስ ግጥሚያ የዘለለ አልነበረም። 2003 ላይ ግን የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማለትም ግርማ ሳህሌ፣ ዩሀንስ መሰለ፣ ከበደ ኃይሌና ሌሎችም፤ በተዋቀረ ሁኔታ የሚንቀሳቀስ ፌደሬሽን መመሥረታቸውን በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የባህልና የስፓርት ፌደሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ብስራት ይናገራል። ፌስቲቫሉ በተጀመረበት ወቅት አውሮፓ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንደዛሬው አልተበራከቱም ነበር። የእግር ኳስ ቡድኖቹ በቂ ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ስለማያገኙ አውሮፓውያንን ያካትታሉ። ያኔ ፌስቲቫሉ እንደዛሬው ብዙ ኢትዮጵያውያን ታዳሚዎችም አልነበሩትም። ""ከ2007 ወዲህ የሊቢያ መንገድ ሲከፈት ወጣቱ ግልብጥ ብሎ ወደ አውሮፓ መጣ። እዚያ የሚኖሩ ህጻናትም እያደጉ የእግር ኳስ ቡድኖችን መቀላቀል ጀመሩ። በጣም ጠንካራ ኳስ መጫወት የተጀመረው ከዚያ ወዲህ ነው"" ይላል ዳንኤል። ባለፈው ዓመት ፌስቲቫሉ የተካሄደው በጀርመኗ ስቱትጋርት ነበር። ከዚያ በፊት ሮም፣ ጄኔቭ፣ ስቶኮልም፣ አምስተርዳምና ሌሎችም የአውሮፓ ከተሞች ፌስቲቫሉን አስተናግደዋል። አውሮፓ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ባቋቋሟቸው ቡድኖች መካከል የሚካሄድ የእግር ኳስ ግጥሚያ ፌስቲቫሉን ደማቅ ያደርገዋል። ዘንድሮ አበበ ቢቂላ፣ ሻላ እና ቡና የተባሉ የጤና ቡድኖች መቀመጫቸውን አውሮፓ ካደረጉት ቡድኖች ጋር ለመፋለም ከኢትዮጵያ ወደ ዙሪክ አቅንተዋል። በስም ከሚታወቁት የቀድሞ ተጨዋቾች መካከል ሳሙኤል ደምሴ (ኩኩሻ)፣ ስንታየሁ ጌታቸው (ቆጬ)፣ ተክሌ ብርሃኔ፣ ቴዎድሮስ ቦካንዴ፣ ሃብቶም ብርሃኔ፣ ሰይፈ ውብሸት፣ ጌታቸው ካሳ (ቡቡ)፣ ኃይሉ አድማሱ (ቻይና)፣ግርማ ሳህሌ ይጠቀሳሉ። በነዚህ ጨዋታዎች በየዓመቱ ይገኛሉ። በዘንድሮው የሦስት ቀን ፌስቲቫል ከአምስት ሺህ እስከ አስር ሺህ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የፌስቲቫሉ አዘጋጅ የሆነው ኢትዮ-ዙሪክ ቡድን ፕሬዘዳንት ሙሉጌታ በየነ በመክፈቻው ዕለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በፌስቲቫሉ ላይ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያን ባህል የሚወዱ የሌሎች አገሮች ዜጎችም ይገኛሉ። ኢትዮጵያዊያንን ያገቡ ዜጎች ይህ ዝግጅት ነፍሳቸው ነው። ከሰሜን አሜሪካው ፌስቲቫል ቀጥሎ ኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ ውጪ የሚገናኙበት ፌስቲቫል እንደመሆኑ ፍቅርና አንድነትን የሚያስተጋቡ ሙዚቀኞች መጋበዛቸውን ሙሉጌታ ይገልጻል። ዘንድሮ ጋሽ ማሕሙድና ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላን) ጨምሮ በርካታ ስመ ገናና ድምጻዊያን ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ራስ ምታት ከኢትዮጵያ ውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵዊያን ትኩሳት ይለቅባቸዋል።አሰላለፋቸው ያሸብራል። ልዩነታቸው የሀበሻ ሬስቶራንት ድረስ ይዘልቃል። የእንቶኔ ብሔር በቀነጠሰው በርበሬ የተሰራ ዶሮ ወጥ በአፌም አይዞር እስከማለት… በፖለቲካ አሰላለፍ ጎራ ተለይቶ መራ���ት ዕለታዊ በሆነበት አውሮፓ 'አንዲት ኢትዮጵያ' በሚል ፌስቲቫል ማዘጋጀት ምን ይመስል ይሆን? የየወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታስ ፌስቲቫሉ ላይ ጥላውን አላጠላም? ብለን አቶ ዳንኤልን ጠይቀነው ነበር። ""…ፖለቲካው ፌስቲቫሉን ሊያፈርስ የደረሰበት ወቅትም ነበር"" ሲል መልሷል። የእግር ኳስ ቡድኖች የመንግሥት ተቃዋሚና ደጋፊ በሚል እንደሚከፋፈሉ ካስታወሰ በኋላ በተለይ በምርጫ 97 ሰሞን የተካሄደውን የእግር ኳስ ግጥሚያ ያሸነፈው ቡድን አባላት በፖለቲካ አቋም ልዩነት ምክንያት አኩርፈው ዋንጫ ሳይቀበሉ ወደ መጡበት አገር መመለሳቸውን እንደ አብነት ያነሳል። ""ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት ያላቸው መገናኛ ብዙኃን ሲመጡ እንደ ፌደሬሽን የማስተናገድ ግዴታ አለብን ስንል የሚቃወሙ አካላት አሉ። ሜዳ ላይ ያለውን መንፈስ ይረብሻል። እነ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ ታማኝ በየነ፣ ተስፋዬ ገብረአብ ይመጡ ነበር። ያ አንዳንዶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊፈጥር ይችላል። ግን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የመምጣት መብት አለው። አትምጡ ልንላቸው አንችልም›› ይላል፤ ያም ሆኖ መድረኩ ከፖለቲካ የጸዳ የባህልና የስፖርት ፌስቲቫል ብቻ እንዲሆን አዘጋጆቹ ይተጋሉ። ፌስቲቫሉን በየዓመቱ ማን ያዘጋጀው በሚለው ላይ ሁለት ተሞክሮዎች እንዳሉ አቶ ዳንኤል ያብራራል። እንደ ሰሜን አሜሪካው ውድድር ፌዴሬሽኑ ያሰናዳው ወይስ አዘጋጅ አገር? 2017 ላይ የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ፌደሬሽኑ እንዲሆን ተወስኖ ጣልያን ውስጥ ፌስቲቫሉን ለማካሄድ መሰናዶ ተጀምሮ ነበር። ሆኖም የፌደሬሽኑ አመራሮች ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ እሰጣ ገባ መፈጠሩን ይናገራል። ከዚህ የሮሙ ክስተት በኋላ ፌስቲቫሉ በየዓመቱ በተለያዩ የእግር ኳስ ቡድኖች እንዲዘጋጅ ውሳኔ ተላለፈ። በዚህም መሠረት የዘንድሮውን ፌስቲቫል ያዘጋጀው ኢትዮ-ዙሪክ ቡድን ነው። የኢትዮ ዙሪክ ቡድኑ ፕሬዝዳንት ሙሉጌታ፤ ፖለቲካው ለጊዜው እንዲቆይ ይማጸናል። ወደ ፌስቲቫሉ የሚሄዱ ሰዎች ""ፖለቲካን ማሰብ የለባቸውም። እንዲያውም እዚያ ሜዳ ላይ ፌስቡክን አጥፍቶ፤ ሰላም ተባብሎ መጫወት፣ መብላት፣ መጠጣት፣ መሳቅን ነው ማየት የምንፈልገው"" ሲል በበዓሉ መክፈቻ ዕለት ለቢቢሲ ምኞቹን አጋርቷል። የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል አውሮፓ ውስጥ የተወለዱ የኢትዮጵያ ልጆች እነሱን ከሚመስሉ ልጆች ጋር የሚገናኙበትም መድረክ ነው። ብዙዎቹ ታዲያ በግማሽ ኢትዮጵያዊ ካልሆኑ ወላጆች የተገኙ ናቸው። በተለይ ኢትዮጵያን ረግጠው የማያውቁ የኢትዮጵያዊያን ልጆች በእናት በአባታቸው ቋንቋ እየተኮላተፉ ሲያወሩ መስማት አንዳች ልዩ ስሜት ያጭራል። በየዓመቱ የሚጋበዙት ኢትዮጵያዊያን ሙዚቀኞች ታዳጊዎቹን ከአገሪቱ ባህል ጋር በመጠኑም ቢሆን ያስተዋውቋቸዋል። ‹‹ፌስቲቫሉ የአዋቂዎች ብቻ መሆን የለበትም፤ ለነዚህ ሕጻናት በቂ ትኩረት መሰጠት አለበት›› ይላል ለዚሁ መሰናዶ ዙሪክ የሚገኘው ጋሽ አበራ ሞላ። የእግር ኳስ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊዎች ዕድለኛ ከሆኑ ለተለያዩ አገራት ብሔራዊ ቡድኖችና ክለቦች ሊታጩ የሚችሉትም በዚሁ ፌስቲቫል ላይ ነው። በደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫ ብሔራዊ ቡድናችን ላይ የተሰለፈው ዩሱፍ ሳሊህ ከዚሁ መድረክ የተገኘ ነው። ፌስቲቫሉን ለመታደም በዙሪክ፣ ክሎተን ስቴድየም ከተገኙ ኢትዮጵያዊያን አንዷ የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ቅድስት በላይ ናት። በልጆች ክፍለ ጊዜ መርሀ ግብር የምትታወቀው ቅድስት የምትኖረው ስዊዘርላንድ ሲሆን፤ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል ላይ ስትሳተፍ የዘንድሮው የመጀመሪያዋ ነው። ፌስቲቫሉ፤ አውሮፓ ውስጥ ተወልደው በምዕራባውያን ባህል የሚያድጉ ልጆች ስለ ኢትዮጵያ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ትናገራለች። ""ስብስቡ ማኅበራዊ ትስስሩን ያጠነክራል። ልጆችም በጣም ደስተኛ ይሆናሉ። ለምሳሌ የጓደኛዬ ቤተሰቦች ከኖርዌይ መጥተው ከሌሎች ልጆች ጋር ስለ ስዊዝና ኖርዌይ ባህል ሲያወሩ ነበር።"" ኢትዮጵያዊያን በብዛት በሌሉበት አካባቢ ለሚኖሩ ልጆች፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በሚውለበለብበት፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በሚነገሩበት፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች በሚበሉበት ቦታ መገኘትን የሚተካ ነገር እንደሌለም ቅድስት ታስረዳለች። አውሮፓ በሮቿን ለስደተኞች ባትዘጋም ከጊዜ ወደ ጊዜ ሽንቁሩ እየጠበበ ይመስላል። ምናልባትም ለወደፊት ወደ አውሮፓ የሚሄዱ ኢትዮጵዊያን ቁጥር ያሽቆለቁል ይሆናል። ይህ መላ ምት፤ አሁን በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የጀመሩትን ፌስቲቫል ለወደፊት የሚረከባቸው ይኖራልን? የሚል ጥያቄ ማጫሩ አይቀርም። ከኢትዮጵያዊያን እና ከሌሎች አገሮች ዜጎች የሚወለዱ ህጻናት እየተበራከቱ መጥተዋል። እነዚህ በከፊል ብቻ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ልጆች ከኢትዮጵያዊ ማንነታቸው ጋር የሚያስተሳስራቸው ፌስቲቫል አስፈላጊነት የሚታያቸው እስከ መቼ ነው? ሌላው ጥያቄ ነው። ዳንኤል የፌስቲቫሉ ቀጣይነት አያጠራጥርም ይላል። አንድም ""በቀጣይ ለሚመጣው ትውልድ ብቸኛ መገናኛው ይህ ፌስቲቫል ነው"" ሲል ያስረዳል። በልጅነታቸው ወደ አውሮፓ ቢሄዱም የእግር ኳስ ፌደሬሽኑን ለዓመታት ያገለገሉ ወጣቶች መኖራቸውም ተስፋ ይሰጠዋል። ዳንኤል፤ አውሮፓ ተወልደው ያደጉ ልጆች በፌስቲቫሉ ድምቀት በመማረክ ከዓመት ዓመት ቀጠሮ ሲይዙ አስተውሏል። ለነጭ ጓደኞቻቸው 'የኢትዮጵያ ፌስቲቫል ሄጄ ነበር' ብለው በኩራት እንደሚያወሩም ሰምቷል። እነዚህ ልጆች አሁን ያለውን ሥርዓት እንዲረከቡ ከተደረገ የፌስቲቫሉ ዕድሜ እንደሚረዝም ያምናል።የቡናው መዓዛ ሳይጠፋ…እስክስታው ሳይለዝዝ፣ ቁርጡ ሳይወደር፣ ሙዚቃው ሳይጎትት የዛሬ ዐሥር፣ ሀያ፣ ሠላሳ ዓመት ኢትዮጵያዊያኑ ይገናኙ ይሆን? ከብዙ ፍቅርና ከትንሽ ቡጢ ጋ'ም ቢሆን…" https://www.bbc.com/amharic/49220661 +politics ምርጫ 2013 ፡ የስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ተስፋ እና ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው? "ኢትዮጵያ ስድስተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ ለግንቦት 28 እና ሰኔ 5 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ይዛለች። ለዚህም ፓርቲያቸውን ወክለው የሚወዳደሩ የተለያዩ ዕጩዎች ምዝገባም በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በቤኒሻንጉል፣ በሃረሪ፣ በጋምቤላ እና ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልሎች ከየካቲት 08 ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል። በእነዚህ አካባቢዎች የእጩዎች ምዝገባ የሚጠናቀቀው የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑንም በምርጫ ቦርድ ተገልጿል። በአፋር፣ አማራ፣ ሲዳማ ፣ ደቡብ ሕዝቦች እና ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥቶች ደግሞ ከየካቲት 15 እስከ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. የዕጩዎች ምዝገባ የሚከናወንበት ጊዜ እንደሚሆን ቦርዱ አሳውቋል። በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ የሚካሄደው ከዛሬ ሰኞ የካቲት 22/2013 ዓ.ም ጀምሮ ይሆናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አመራሮች አባላቶቻቸውና መሪዎቻቸው መታሰራቸውን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ቢሮዎቻቸው መዘጋታቸውን በመግለጽ ይህም በምርጫ ተሳትፏቸው ላይ ጥላ ማጥላቱን ገልፀዋል። አባላቶቻቸው ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸውን አክብሮላቸው እንኳ አለመፈታታቸውን በመግለጽም ተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለሚመለከታቸው አካላት አቅርበዋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ወደ ምርጫ መግባት ያሳስበናል ሲሉ ተናግረዋል። ከቀደሙት ምርጫዎች የተለየ ምርጫ ሊሆን ይችላል? በማክስ ፕላንክ ተቋም የፖስት ዶክቶራል ፌሎ የሆኑት ዶ/ር በሪሁን አዱኛ በሕገመንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ በርካታ ጥናቶችን ሰርተዋል። ስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ ኢትዮጵያ ካካሄደቻቸው ካለፉት አምስት ምርጫዎች ልዩ የሚያደርገው አገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ መሆኑን በመግለጽ ይጀምራሉ። በርካቶች ይህንን ምርጫ እንደ ከዚህ ቀደሙ የዲሞክራሲ፣ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱ ያለችበትን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቅራኔዎች ይፈታል ብለው መጠበቃቸው፤ አገራዊ መሠረታዊ ለውጥ ያስፈልጋል የሚለው ላይ የጋራ መግባባት መኖሩም ለየት እንደሚያደርገው ይናገራሉ። ዶ/ር በሪሁን ይህ ምርጫ መሠረታዊ ምርጫ መሆኑን መንግሥት ማሰብ ይኖርበታል ሲሉም ይመክራሉ። ይህ ምርጫ እንደከዚህ ቀደሞቹ ዓይነት ምርጫ ካልሆነ እና መሠረታዊ ምርጫ ከሆነ ደግሞ ""ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር አብሮ መሥራት አለበት፤ ብቻውን ሊያደርገው የሚችለው ነገር አይደለም"" ሲሉ አክለዋል። የባለፉት አምስት ምርጫዎች ኢህአዴግ በሚባል ፓርቲ ማዕቀፍ ውስጥ የተደረገ ነው በማለት ይሄኛው ስድስተኛ አገራዊ ምርጫ ግን በአዲስ ብልጽግና በሚባል ፓርቲ መዋቅር ስር የሚደረግ መሆኑን በራሱ ልዩ እንደሚያደርገው ያስረዳሉ። ሌላው ለዶ/ር በሪሁን ይህ ምርጫ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ምርጫዎች በመላው አገሪቱ የሚካሄድ አለመሆኑም ለየት ያደርገዋል። በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ መደፍረስ ይህንን ምርጫ ስጋትና ተስፋ ይዞ እንዲካሄድ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንዱ መሆኑንም ይናገራሉ። የፖለቲካ ለውጥ እና የፖለቲካ ሽግግር ወሬ በሚሰማበት ወቅት የሚደረግ ምርጫ መሆኑ ደግሞ ይህንን ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ለየት እንደሚያደርገው ይስታውሳሉ። ሆኖም ግን ይላሉ ዶ/ር በሪሁን ይህንን ምርጫ ከዚህ በፊት ከነበሩት ምርጫዎች የተለየ ነው ወይንም አይደለም የሚለውን የሚወስነው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያቀርቡት ሃሳብ ነው ይላሉ። ከዘንድሮው ምርጫ ምን ይጠበቃል? እንደከዚህ ቀደሙ የዲሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን ብቻ ይዞ እነርሱን ለመፍታት የሚደረግ የምርጫ ውድድር ከሆነ ካለፉት በብዙ ላይለይ ይችላል ሲሉ ይገልጻሉ። ነገር ግን አሁን አገሪቱ ላይ ያሉትን የማኅበራዊ እና የፖለቲካዊ ችግሮችን በመሰረታዊ መልኩ ለመፍታት የሚደረግ እና በዚያ እሳቤ ለመፍታት የሚካሄድ ምርጫ ከሆነ ደግሞ ካለፉት ምርጫዎች የተለየ ሊሆን ይችላል ብለዋል። በተደጋጋሚ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የመንግሥትን እርምጃዎች በመተቸት የሚታወቁት አቶ እያስፔድ ተስፋዬ በበኩላቸው ይህ አገራዊ ምርጫ ከዚህ በፊት ሲካሄዱ ከነበሩ አምስት ተከታታይ ምርጫዎች የተለየ ይሆናል ብለው አያስቡም። ይህንን ሃሳቡን ሲያብራሩም ኢህአዴግ ከዚህ በፊት በአውራ ፓርቲነት ከመራቸውና ከተሳተፈባቸው አምስት ተከታታይ ምርጫዎች የተለየ የፖለቲካ ባህል በዚህኛው ምርጫ አለማስተዋላቸውን ይጠቅሳሉ። ከዚህ ቀደም የተካሄዱት ምርጫዎች ከምርጫ በፊት፣ በኋላ እና በምርጫ ወቅት የተለያዩ ጉድለቶች እንደሚስተዋልባቸው የሚጠቅሱት አቶ እያስፔድ፤ ለዚህም ማሳያዎች ፓርቲዎች እንዳይንቀሰቅሱ ማድረግ፣ አባላቶቻቸውን ማሰር፣ ቢሯቸውን መዝጋት መሆናቸውን ይገልጻሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን በመጡበት ወቅት ቀጣዩ ምርጫ ከዚህ በፊት ከተደረጉት አምስት ምርጫዎች ሁሉ የተለየ ይሆናል የሚል ተስፋ እንደነበራቸው የገለፁት አቶ እያስፔድ፤ ይህ ግን በሂደት መጥፋቱን ይናገራል። በወቅቱ ተስፋ አድርገው የነበሩበትንም ምክንያት ሲያስረዱ፣ የፖለቲካ ምሕዳሩ ከዚህ በፊት ከነበረው ጊዜ ሁሉ የተሻለ መስፋቱን እና በእስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች መፈታታቸው መሆኑን ያስታውሳሉ። ከዚህ በተጨማሪም ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን እንደ ልባቸው ተንቀሳቅሰው ያሻቸውን ያለ ተጽዕኖ የሚሰሩበት እድል ተመቻችቶ እንደነበርም አልዘነጉም። ከምርጫ እና ዲሞክራሲ ጋር ተያይዞ ያሉ ተቋማትን የሚመሩ ሰዎችንም በሚመለከት በሕዝቡም ሆነ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ዘንድ ከሞላ ጎደል እምነት የሚጣልባቸውን ግለሰቦች ወደ አመራርነት ማምጣት መቻሉን በማንሳት ቀጣዩ ምርጫ ተስፋ አለው ብለው እንደነበር ለቢቢሲ ገልፀዋል። ""ግን እነዚህ ነገሮች እንዳለ ተቀልብሰው ወደ ነበርንበት ተመልሰናል"" የሚሉት አቶ እያስፔድ የፖለቲካ ምሕዳሩ መጥበብ ብቻ ሳይሆን በርካቶች እስር ቤት እንደሚገኙም ይጠቅሳሉ። ዛሬም ፍርድ ቤት ንፁህ መሆናቸውን ገልጾ የታሰሩ መኖራቸውን በተለያዩ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርቶች ላይ መገለፁን የሚያነሱት አቶ እያስፔድ፤ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸውን አክብሮላቸው ነገር ግን ፖሊስ ከመልቀቅ ይልቅ አሁንም ከተማ እና ፍርድ ቤት እየቀያየረ የተለያየ ክስ የሚመሰርትባቸው መኖራቸውን ይገልጻሉ። የባልደራስ አባላት እንዲሁም የተለያዩ የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መታሰር ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም የቤንሻንጉል ጉሙዝ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የምርጫ ቦርድ ግቢ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ መታገታቸውን ራሱ የምርጫ ቦርድ የገለፀው መሆኑን በማንሳት በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የፖለቲካ ምሕዳሩ ጠብቦ ""ፍትሃዊና የተለየ ምርጫ ይደረጋል ብሎ ማሰብ የማይታሰብ ነው"" ይላሉ። ጋዜጠኞችን በሚመለከትም ሲናገሩ ሲፒጄ ዶ/ር አብይ ወደ ሥልጣን በመጡበት ወቅት አንድም ጋዜጠኛ ያልታሰረባት አገር ያላት ኢትዮጵያ፣ በአሁኑ ሰዓት ግን ከቤላሩስ በመቀጠል በፍጥነት ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛዋ አገር በሚል እንደፈረጃት ይጠቅሳሉ። ዶ/ር በሪሁን በበኩላቸው ፖለቲከኞች እስር ቤት ውስጥ ሆነው የሚካሄድ ምርጫ የቅርብ እና የሩቅ ጊዜ ተጽዕኖ እንዳለው ይናገራሉ። በቅርብ ምርጫውን በሰላማዊ መንገድ ለማካሄድ አለመቻል ሲሆን፣ አርቆ ሲመለከቱት ደግሞ ከምርጫ በኋላ ለሚመጣው የፖለቲካ ሥርዓት አሉታዊ ተጽዕኖ አለው ሲሉም ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። ፓርቲዎች ይደርስብናል ያሏቸው ችግሮች ከአሁኑ መፍታት አለመቻል በኋላ ላይ ምርጫውን ለማከናወን የሰላም እና የደኅንነት ችግር ሊፈጥር ይችላል ሲሉም አክለዋል። ምርጫውም ካለፈ በኋላ ምርጫውን ያሸነፈው ፓርቲ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ሕጎችን ቢያወጣ፣ የሕገመንግሥት ማሻሻያ ማድረግ ቢፈልግ የሚወሰነው ፓርላማ ባሉ ፓርቲዎች እና ሰዎች በመሆኑ፣ ከዚህ ውጪ የሆኑ የአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎችን በአጠቃላይ ትርጉም ባለው መልኩ የማያሳትፍ ይሆናል ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። የምርጫው ነጻና ፍትሃዊነት ዶ/ር በሪሁን በምርጫ ቦርድ አካባቢ የማይካዱ የአስተዳደር እና የሕግ ለውጦች መካሄዳቸውን ይገልጻሉ። የምርጫ ቦርድ አመራሮች ቀጣዩን ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ ለማድረግ ቁርጠኝነቱ እንዳላቸው ""እንደ ግለሰብ ግምት አለኝ"" የሚሉት ዶ/ር በሪሁን አጠቃላይ ሁኔታው ሲታይ ግን ያለው ችግር ከእነርሱ በላይ ነው ይላሉ። ምርጫ ቦርድ በራሱ ብቻ ማስፈፀም የሚችለው ነገር የለም በማለትም መንግሥት፣ ፍርድ ቤቶች፣ የፀጥታና ደኅንነት አካላት ሁሉም የየራሳቸው ድርሻ አላቸው ብለዋል። አሁን ያለው ጉዳዩ ከምርጫ ቦርድ በላይ ነው የሚሉት ዶ/ር በሪሁን፣ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ነጻና ��ትሃዊ ለማድረግ ""ዝም ብሎ በምርጫ ቦርድ ላይ ብቻ የምንንጠለጠል አይሆንም"" ይላሉ። መንግሥት፣ ተቃዋሚዎች፣ ሕዝቡ፣ የፍትህ አካላት ሁሉም በትብብር ካልሰሩ አንዱ ተቋም ብቻ ይህንን ምርጫ በሥነ ሥርዓት ማድረግ ይችላል ማለት ከባድ ነው ሲሉ ያክላሉ። ዶ/ር በሪሁን ይህንን ሁሉ ከግንዛቤ አስገብተው ምርጫ ቦርድ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ ይችላል ለሚለው ጥያቄ ""መልሴ አይችሉም ነው"" ይላሉ። አቶ እያስፔድ የምርጫ ቦርድ ፍትሃዊነት ላይ ያላቸው እምነት እየተሸረሸረ መምጣቱን ገልፀው የኦነግ እና ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ቢሮዎች በተለያዩ አካባቢዎች ተዘግተው፣ ፓርቲዎቹ ምርጫ ላይ እንዴት መሳተፍ ይችላሉ በማለት፣ ምርጫ ቦርድ ይህንን የፓርቲዎቹን ችግር እንኳ ለመፍታት ቁርጠኝነት እንዳልታየበት ያስረዳሉ። እርሳቸው እና ሌሎች ግለሰቦች በጋራ በመሆን ባካሄዱት የማኅበራዊ ድረ ገጽ ዘመቻ የኦነግና ኦፌኮ ቢሮዎች የት የት ቦታ እንደተዘጉ አቅማቸው በፈቀደ በአካል በመሄድ፣ ሌሎቹን ደግሞ ከፓርቲው መረጃ በመሰብሰብ በፌስቡክና ትዊተር ላይ ማስፈራቸውን ያስታውሳሉ። ፓርቲዎቹም ቢሆኑ ይህንኑ ጉዳይ ለቦርዱ በደብዳቤ በተደጋጋሚ ማሳወቃቸውን አቶ እያስፔድ አክለዋል። ምርጫ ቦርድ ግን ""ኦነግም ሆነ ኦፌኮ ቢሮዎቻቸው የት የት ቦታ እንደተዘጉባቸው በትክክል ስላላቀረቡላቸው መቸገራቸውን"" ሲናገር መስማታቸውን ይጠቅሳሉ። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ከፓርቲዎች የሚቀርቡለትን ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን በመቀበል ምላሽና መፍትሔ እንዲያገኙ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ጥረት እንደሚያደርግ በተለያዩ ጊዜያት መግለጹ ይታወሳል። ምርጫውን የሚያሸንፍ ፓርቲ መሠረታዊ የፖለቲካ ለውጥ ማምጣት የሚፈልግ ከሆነ አሁን ከምርጫ በፊት ቁጭ ብሎ ""በተለይ ኦሮሚያ ውስጥ ካሉ እና ሌሎችም ፓርቲዎች ጋር መነጋገር፤ በተለይ መንግሥትን ለሚያስተዳድረው፣ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በይበልጥ ፓርቲ ለብልጽግና ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ"" ይላሉ። ስጋቶች እና ተስፋዎች ኢትዮጵያ ይህንን ምርጫ የምታካሄደው በተለያዩ የደኅንነት እና የፀጥታ ስጋቶች ውስጥ ሆና ነው። የሕዳሴ ግድብ ድርድር ጉዳይ፣ ከሱዳን ጋር ያለው የድንበር ይገባኛል ውዝግብ፣ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የፀጥታ ችግሮች ቢኖሩም አገሪቱ ያለችባቸውን የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት ""ቢዘገይም ምርጫ ማካሄድ አማራጭ የሌለው ነገር ነው"" ዶ/ር በሪሁን ይላሉ። መንግሥት የሕዝቡን ይሁንታ ማግኘት እንዲችል የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎች እና ሕጎች ተቀባይነትና ተፈጻሚነት እንዲያገኙ ምርጫ ማድረጉ አማራጭ የለውም ሲሉም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ከዶ/ር በሪሁን ጋር ተመሳሳይ አስተያየት ያላቸው አቶ እያስፔድ ይህንን ቀጣይ አገራዊ ምርጫ እስር ቤት ካሉ የፖለቲካ አመራሮች ጋር እውነተኛ የሆነ ድርድር ሳያካሄዱ ማከናወን ከዚህ ቀደም ""አገሪቱ የሄደችበትን መንገድ መድገም"" ይሆናል ሲሉ ይናገራሉ። አምስተኛው አገራዊ ምርጫ ኢህአዴግ መቶ በመቶ ማሸነፉን ያስታወሱት አቶ እያስፔድ፣ አሁን የተወሰኑ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በሰላማዊ ሁኔታ እንዳይንቀሳቀሱ እድሎችን መዝጋት ወደሌላ አማራጭ ሊያመራ እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ። ውይይትና ድርድር እንደሚያስፈልግ የሚናገሩት አቶ እያስፔድ የመራጮች ምዝገባ እየተጠናቀቀ መሆኑ ግን ይህንን ተስፋቸውን እያመነመነው መሆኑን ተናግረዋል። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል የሚሉት አቶ እያስፔድ፣ ሕዝቦች በተለያየ ምክንያት ተወካዮቻቸው ባልተሳተፉበት እና በሌሉበት ምክር ቤት ለሚወጡ ሕጎች ተገዢ ይሆናሉ ብሎ ማሰብ ከባድ መሆኑን ከዚህ ቀደም ���ተደረጉ ተቃውሞዎችን በማስረጃነት በመጥቀስ ይናገራሉ። ዶ/ር በሪሁን ምርጫ ማለት አገሪቱን ለቀጣይ አምስት ዓመት ማን ያስተዳድራት በሚል የሚከናወን መሆኑን በማንሳት አሁን ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ፣ የሕግ እና ሌሎች በርካታ ልዩነቶች ያሉበት መሆኑን ጠቅሰው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ለየት እንደሚል ተናግረዋል። አሁን ኢትዮጵያን እያስተዳደረ ያለው ፓርቲም ሆነ የሚመረጠው ፓርቲ አገሪቱ ያለችበትን ችግሮች ሁሉ ብቻውን የሚፈታቸው አይደሉም የሚሉት ዶ/ር በሪሁን፣ ከምርጫውም በፊት ሆነ በኋላ መነጋገር አስፈላጊ መሆኑን ያሰምሩበታል። ስለምርጫውና ከምርጫው በኋላ ምን ማድረግ እንችላለን፣ የቆዩ መሠረታዊ ጥያቄዎችንና ልዩነቶችን እንዴት መፍታት እንደሚቻል ማሰብ፣ አገሪቱ የምትፈልገውን መሠረታዊ ለውጥ ታሳቢ ያደረገ ውይይት ያስፈልጋል ሲሉም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ዶ/ር በሪሁን ላለፉት ሁለት ዓመታት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የእንነጋገር ጥያቄ ሲያቀርቡ እንደነበር ገልፀው አሁንም ግን ጊዜ መኖሩን ይናገራሉ። ለዚህም ረዥም ርቀት መሄድ ያለበት መንግሥት መሆኑን ይናገራሉ። ምርጫው በተለያዩ ልዩነት መንፈሶች ውስጥ የሚካሄድ መሆኑንም በማንሳት፣ ውይይቶች እና ንግግሮች ከምርጫው በፊትም ሆነ በኋላ መደረግ እንዳለባቸው ያሰረዳሉ። አለበለዚያ ግን ከሰኔው ምርጫ በኋላ መንግሥት ችግሮችን ካልፈታ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከምርጫ በኋላ ቀውስ ላለመከተሉ ማረጋገጫ የለም ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-56224264 +health ኮሮናቫይረስ፡ ስንት የኮቪድ-19 ክትባቶች አሉ? ለኢትዮጵያስ የትኛው ይደርሳታል? "ኮሮናቫይረስ ተከስቶ የዓለምን አጠቃላይ ገጽታ መቀየር ከጀመረ እንሆ አንድ ዓመት ሊሞላው ተቃርቧል። በዚህ ጊዜም ከ71 ሚሊዮን በላይ የምድራችን ነዋሪ በበሽታው መያዙ የተረጋገጠ ሲሆን ከ1.6 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሽታው ያላዳረሰው የዓለም ክፍል የሌለ ሲሆን እንደተሰጋው የከፋ ጉዳትን ባያደርስም በአፍሪካ አገራት ውስጥም ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ከ56 ሺህ በላይ ድግሞ ለሞት ተዳርገዋል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ በኢትዮጵያ ከ116 ሺህ ሰዎች በላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ከ1 ሺህ 880 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ከበሽታው ያገገሙ ቢሆንም አስካሁን ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ መድኃኒት ለቫይረሱ አልተገኘም። በሽታው ቻይና ውስጥ መከሰቱ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ አገራት ለበሽታው መከላከያ የሚሆን ክትባት እንዲሁም የተያዙ ሰዎችን ለማከም የሚያገለግል መድኃኒት ለማግኘት ሊቃውንት ቀን ከሌት እየጣሩ ይገኛሉ። እስካሁን በተደረጉ ምርምሮችና ሙከራዎች በርካታ ተስፋ ሰጪ የክትባት ውጤቶች መገኘታቸው ከመነገሩ ባሻገር፤ በሽታውን ለመከላከል ያስችላሉ የተባሉ ጥቂት ክትባቶችም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው ለተባሉ ሰዎች መሰጠት ተጀምሯል። በዚህ ረገድ ቀዳሚውን የተጠቃሚነት ዕድል ያገኙት ባለጸጋ አገራት ሲሆኑ የዓለም ጤና ድርጅት ደግሞ ክትባቶቹ ለሁሉም እንዲዳረስ ጥረት እያደረገ መሆኑን አመልክቷል። አገራትም ለዜጎቻቸው ክትባቱን ለማቅረብ ባላቸው አማራጮች ሁሉ እየሞከሩ ነው። ኢትዮጵያም እንዲሁ ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት ድጋፍ ሰጪና እቅራቢ በኩል ለአገልግሎት ከሚቀርቡት የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ጥያቄ እንዳቀረበች የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ባለፈው ሳምንት ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ጨምረውም ለአገልግሎት ብቁ ከሆኑ የክትባት አይነቶች መካከል ኢትዮጵያም እንድታገኝ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረው፤ በኮቫክስ በኩል ክትባቱን በፍጥነት ለማግኘትና በቅድሚያ መከተብ ለሚገባቸው ወገኖች እንዲደርስ እንደሚደረግ ገልጸዋል። ለመሆኑ የትኞቹ ክትባቶች ጥቅም ላይ ውለዋል? በአሁኑ ጊዜ በርካታ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎችና አገራት ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚሆን ክትባት በማበልጸግ ላይ ሲሆኑ ጥቂቶቹም በስራ ላይ መዋል ጀምረዋል። ፋይዘር/ባዮንቴክ ኮሮናቫይረስን በመከላከል 90 በመቶ ውጤታማ ነው የተባለው ይህ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ይፋ የሆነው በፈረንጆቹ ሕዳር 9/2020 ላይ ነበር። በወቅቱ ክትባቱን ይፋ ያደረጉት ፋይዘር እና ባዮኤንቴክ ኩባንያዎች ግኝቱ ለሳይንስና ለሰው ልጅ ትልቅ እድል ነው ብለዋል። የአሜሪካ እና የጀርመን ኩባንያ የሆኑት ፋይዘር እና ባዮንቴክ በስድስት የተለያዩ ሃገራት 43 ሺህ 500 ሰዎች ላይ መሞከራቸውን የገለፁ ሲሆን አንድም ጊዜ አሳሳቢ የጤና ችግር አልታየም ብለዋል። ፋይዘርና ባዮንቴክ ክትባቱን በፈረንጆቹ የህዳር ወር መጨረሻ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎም ዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱ ጥቅም ላይ እንዲውል በመፍቀድ ከዓለማችን ቀዳሚዋ አገር ሆናለች። ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ማክሰኞ ዕለት ለዜጎቿ መስጠት የጀመረች ሲሆን የዘጠና ዓመቷ አዛውንት የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባትን በመውሰድ በዓለም የመጀመሪያዋ ሰው ሆነዋል። በመላው ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የሚገኙ ከ70 በላይ የሚሆኑ ሆስፒታሎች እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ ለሆኑ አዛውንቶች እና ለጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ለመስጠት መዘጋጀታቸው ተገልጿል። የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር መስሪያ ቤትን (ኤፍዲኤ) የሚያማክሩ ባለሙያዎች በፋይዘር/ባዮንቴክ የበለጸገው የኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ሀሳብ ማቅረባቸውም ተገልጿል። ባለሙያዎቹ ይህን ምክረ ሃሳብ የሰጡት 23 አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ክትባቱ ሊፈጥረው የሚችለው ስጋት ከሚሰጠው ጥቅም አንጻር ምን ሊመስል እንደሚችል ምክክር ካደረጉ በኋላ ነው ተብሏል። የአሜሪካ የጤና ሚንስትር አሌክስ ረቡዕ ዕለት ''በሚቀጥሉት ቀናት ክትባቱ በእጃችን ሊገባ ይችላል፤ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን ዜጎች መከተብ ልንጀምር እንችላል'' ብለዋል። የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባት እስካሁን በዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ፣ ባህሬን እና ሳኡዲ አረቢያ ጥቅም ላይ ለመዋል ፍቃድ አግኝቷል። ሞደርና የዩናይትድ ስቴትስ መድኃኒት አምራች ኩባንያ የሆነው 'ሞደርና' ከኮሮናቫይረስ 95 በመቶ የሚከላከል አዲስ ክትባት ማግኘቱን ይፋ ካደረገ ሰነባብቷል። በአሁኑ ሰአትም ከአውሮፓና አሜሪካ ፈቃድ ሰጪዎች ክትባቱን ለመጠቀም የሚያስችል ፈቃድ ጠይቆ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ሞደርና የምርምር ውጤቱን ይፋ ያደረገበትን ዕለት 'ታላቅ ቀን' በማለት ሐሴቱን የገለፀ ሲሆን፤ በቅርብ ሳምንታትም ክትባቱን ለመጠቀም ፈቃድ እንደሚያገኝ አስታውቋል። የቤተ ሙከራ ሂደቶች እንደሚያሳዩት ኤምአርኤንኤ የተሰኘው ክትባት 94 በመቶ ውጤታማና ሰዎችን ከኮሮናቫይረስ የሚያድን ነው። የክትባቱ ሙከራ አሜሪካ ውስጥ ያሉ 30 ሺህ ሰዎችን ያሳተፈ ሲሆን፤ ግማሾቹ በየአራት ሳምንቱ ክትባቱ ሲሰጣቸው ግማሾቹ ደግሞ ጥቅምና ጉዳት የሌለው መርፌ ተወግተው ውጤቱን ለመለየት ተሞክሯል። ከዚህ ሙከራ በተገኘ ውጤት መሠረት 94.5 በመቶ ሰዎች በክትባቱ ምክንያት ለኮሮናቫይረስ ሳይጋለጡ ቀርተዋል ተብሏል። ስለ ክትባቱ ውጤቱ የቀረበው ዘገባ ጨምሮም፤ ሙከራ ከተደረገባቸው መካከል 11 በኮቪድ-19 ክፉኛ የታመሙ ሰዎች የመከላከል አቅም አዳብረዋል ይላል። ስፑትኒክ 5 ይህ ሩሲያ ሰራሽ ክትባት ይፋ በተደረገ ጊዜ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአገር ውስጥ በተደረገ ምርምር አገር በቀል ክትባት አግኝተናል፤ ለሰዎች አገልግሎት እንዲውልም ይፋዊና ብሔራዊ ፍቃድ ሰጥተናል ብለው ነበር። በዓለም የመጀመርያው የተባለው ይህ ስፑትኒክ-5 ክትባት ሞስኮ የሚገኘው ጋማሊያ ኢንስቲትዩት ነው ያመረተው። ክትባቱ ይፋ የተደረገውም ነሀሴ ወር ላይ ነበር። ኢንስቲትዩቱ እንደሚለው ክትባቱ አስተማማኝ የመከላከል አቅም ይሰጣል። ፑቲን በበኩላቸው ገና ቀደም ብሎ ""ይህ ክትባት አስተማማኝ እንደነበር አውቅ ነበር"" ብለዋል። ""ሁሉንም ሳይንሳዊ ሂደቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ማለፍ ችሏል"" ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል። ፑቲን ከልጆቻቸው ለአንዷ ክትባቱ ተሰጥቷት ትንሽ አተኮሳት እንጂ ምንም አልሆነችም ብለዋል። ፑቲን የትኛዋ ልጃቸው ክትባቱን ወስዳ እንዳተኮሳት ግን በስም አልገለጹም። የሩሲያ ሳይንቲስቶች የመጀመሪያ ዙር ሙከራዎች ተደርገው ሁሉም ድንቅ ውጤት አስመዝግበዋል ብለዋል። ሳንቲስቶቹ ሰዎች ላይ ጉንፋንን የሚያመጣው አዲኖቫይረስ የተሰኘውን የተላመደ የተህዋስ ቅንጣት ተጠቅመው ነው ክትባት ሰራን ያሉት። ይህን ለማዳ ተህዋሲ አዳክመው ወደ ሰውነት በማስገባት ሕዋስ በማቀበል ክትባቱ ሰውነት ኮቪድ-19 ተህዋሲ ሲገባ ነቅቶ እንዲዋጋ ያደርገዋል ብለዋል። በአውሮፓውያኑ ታሕሳስ 5/2020 ላይ ደግሞ ይሄው ክትባት በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ መሰጠት ተጀምሯል። በመጀመሪያው ዙር ክትባቱን ለመውሰድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተመዝግበዋል። ሩሲያ ምን ያህል ክትባት ማምረት እንደምትችል ግልጽ ባይሆንም፤ አምራቾች እስከ ዓመቱ መገባደጃ ሁለት ሚሊዮን ጠብታ እንዲያዘጋጁ ይጠበቃል። 13 ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩባት የሞስኮ ከተማ ከንቲባ ሰርጌ ሶቢያን እንዳሉት፤ ክትባቱ ለማኅበረሰብ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ለጤና ባለሙያዎች እና ለትምህርት ቤት ሠራተኞች ይሰጣል። ተጨማሪ ክትባቶች ሲመረቱ ለተቀረው ማኅበረሰብ እንደሚዳረስ ከንቲባው ጠቁመዋል። ከላይ በተዘረዘሩት የሙያ መስኮች የተሰማሩና እድሜያቸው ከ18 እስከ 60 የሆኑ ዜጎች በድረ ገጽ ተመዝግበዋል። በሞስኮ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የክትባቱን አገልግሎት የሚሠጡ 70 ማዕከሎች ተከፍተዋል። ክትባቱ የተሰጣቸው ባለፉት 30 ቀናት የመተንፈሻ አካል ህመም የገጠማቸው፣ የከፋ የጤና እክል ያለባቸው፣ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እንደሚለዩ ተገልጿል። ሲኖቫክ መላው ዓለም ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ደፋ ቀና ሲል ቻይናም እጇን አጣጥፋ አልተቀመጠችም። ሲኖቫክ የተባለ ክትባት መስራት ከጀመረች ሰነባብታለች። እንደውም በጎ ፈቃደⶉችን መከተብ ከጀመረች ቆየት ብላለች። በቻይና በሙከራ ላይ የሚገኘው የኮቪድ-19 ክትባት አመርቂ የሚባል ውጤት እያስገኘ ነውም ተብሏል። ሆኖም ክትባቱ አመርቂ ውጤት ያስገኘው በረዥም የሙከራ ሂደት ውስጥ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ሳይሆን፣ መካከለኛ ምዕራፍ በሚባለው ክፍል ነው። ተመራማሪዎች እንዳረጋገጡት ከቻይና ሰራሽ ክትባቶች አንዱና ታዋቂ እየሆነ የመጣው በሲኖቫክ ባዮቴክ የተመረተው ሲኖቫክ ክትባት በ700 ሰዎች ላይ ተሞክሮ ይበል የሚያሰኝ ውጤት አስገኝቷል። ክትባቱ የተሞከረባቸው ሰዎች በሽታን የመከላከያ ህዋሳቸውን አንቅቶ ቫይረሱን መመከት እንደቻለ ተደርሶበታል። ላንሴት በሚባለው ሥመ ጥር የሳይንስ ጆርናል ላይ ይህንን ክትባት በተመለከተ የተዘገበው፤ ክትባቱ ለጊዜው በምዕራፍ አንድና ሁለት ያስመዘገበው ውጤት እንጂ አሁን ያለ���ትን ደረጃ አይገልጽም። በተጨማሪም የስኬት ምጣኔው ምን ያህል እንደሆነ ይፋ አልተደረገም። በዚህ ጆርናል ላይ ስለዚህ ቻይና ሰራሹ ክትባት ከጻፉት ተመራማሪዎች አንዱ የሆኑት ዙ ፋንቻይ እንደሚሉት፤ በምዕራፍ አንድ እና በምዕራፍ 2 ሙከራዎች 600 ሰዎች ላይ ጥናት ተደርጎ ክትባቱ ለአስቸኳይ ሕክምና አገልግሎት ላይ መዋል ይችላል የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል። ነገር ግን ወሳኝ በሚባው በምዕራፍ ሦስት ሙከራ ላይ ይህ የቻይና ክትባት ስላስገኘው ውጤት በተጨባጭ ተአማኒ ሳይንሳዊ ጆርናል ላይ የተጻፈ ዘገባ የለም። በቻይና በአሁን ሰዓት ሙሉ በሙሉ ሊባል በተቃረበ ደረጃ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በቁጥጥር ሥር የዋለበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ሆኖም ቻይና ለዜጎቿ ይህንን ክትባት መስጠቷን ቀጥላበታለች። በአሁኑ ሰአት ደግሞ መቀመጫውን ቤዢንግ ያደረገው የክትባት አምራቹ ኩባንያ ያዘዛቸው በርካታ የህክምና ቁሳቁሶች ከኢንዶኔዢያ መግባት ጀምረዋል። ይህ ደግሞ አገሪቱ በቅርቡ ዜጎቿን በይፋ መከተብ ልትጀምር እንደሆነ ማሳያ ነው ተብሏል። በዓለም ላይ ኮቪድ-19 ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰባቸው አገራት ተርታ የምትመደው የደቡብ አሜሪካዋ ትልቅ አገር ብራዚል በበኩሏ ቻይና ሰራሽ ክትባት ለሕዝቤ አድላለሁ ማለቷ የሚታወስ ነው። የሳኦ ፖሎ ገዥ ጃዎ ዶሪያ እንዳሉት የፌዴራል መንግሥት 46 ሚሊዮን ጠብታዎችን ለመግዛት ስምምነት ላይ ደርሷል። የክትባት ዘመቻው መቼ ይጀመራል በሚል የተጠየቁት የሳኦ ፖሎ ገዥ በፈረንጆች አዲሱ ዓመት የመጀመርያ ወር ላይ ሊሆን ይችላል ብለዋል። አስትራዜኒካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ አስትራዜኒካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እያበለፀጉ ያሉት ክትባት ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው ክትባቶች መካከል ነው። ይሄው ክትባት በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሙከራ መልክ ተሰጥቷል። ደቡብ አፍሪካ ለዚህ የክትባት ሙከራ የተመረጠችው በዘርፉ ባሏት ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ በርካታ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ያሉባትና ወረርሽኙም በፍጥነት እየተስፋፋባት በመሆኑ ነው። ይህ የክትባት ሙከራ ኦኤክስ1ኮቪድ-19 ክትባት የሚባል ሲሆን፤ ኮሮናቫይረስን የሚያስከትለው ሳርስ-ኮቪ-2 በተባለው ቫይረስ ሰዎች እንዳይያዙ ለመከላከል የታለመ ነው። በደቡብ አፍሪካ የሚደረገው የክትባት ሙከራ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ጥልቅ ፍተሻ ተደርጎበት በደቡብ አፍሪካ መንግሥት የጤና ምርቶች ተቆጣጣሪ ተቋምና በዊትስ ዩኒቨርስቲ ፈቃድ ተሰጥቶታል ተብሏል። ይህ ክትባት ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ከአራት ሺህ ሰዎች በላይ የተሳተፉበት ክሊኒካል ሙከራ የተደረገበት ሲሆን፤ በደቡብ አፍሪካ ከሚደረገው ሙከራ ጋር ተመሳሳይና ተዛማጅ የሆነ ሙከራ ብራዚል ውስጥ ሊጀመር እንደሆነ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም ከሁሉም የላቀ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የሚሳተፉበት የዚህ ክትባት ሙከራ አሜሪካ ውስጥ በ30 ሺህ ሰዎች ላይ ለማካሄድ ዕቅድ ተይዟል። በሌሎች ድርጅቶች የሚሠሩ እና በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ክትባቶች ሙከራ ተጨማሪ ውጤቶች በሚቀጥሉት ሳምንታት እና ወራቶች ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በአሁኑ ሰአትም የመጨረሻው የሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኙ በርካታ ተጨማሪ ክትባቶች አሉ። ከነዚህም መካከል ከታች የተዘረዘሩት የሚጠቀሱ ናቸው። የክትባቶቹ ደኅንነትስ? ክትባቱ እስካሁን በደኅንነት ጉዳይ ይህ ነው የሚባል ነገር አልተነሳበትም። ነገር ግን የትኛውም መድኃኒት መቶ በመቶ እንከን አልባ ሊሆን አይችልም። አንዳንድ ተሳታፊዎች ክትባቱን የወሰዱ ሰሞን መጠነኛ ድካም፣ ራስ ምታትና ሕመም እንደተሰማቸው አስታውቀዋል። የሞደርና እና የፋይዘር ክትባት ከ90 በመቶ በላይ ውጤታማ መሆና���ው ተነግሯል። ነገር ግን የሁለቱም ድርጅቶች ውጤት የመጨረሻ ደረጃ ላይ አልደረሰም። ውጤታማነቱም ሊቀየር ይችላል ተብሏል። ቢሆንም የሞደርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ ለማስቀመጥ ከሌሎቹ ክትባቶች በተለየ ቀላል እንደሆነ ተነግሯል። የሞደርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ እስከ አንድ ወር መቆየት ሲችል የፋይዘር ግን ለአምስት ቀናት ብቻ ነው የሚቆየው። ሩስያ የለቀቀችው ስፑትኒክ 5 የተሰኘው ክትባትም 92 በመቶ የመከላከል አቅም እንዳለው ተነግሯል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55273576 +business የመንግሥት ድርጅቶችን 'ፕራይቬታይዝ' ጉዳይ እጅግ አከራካሪ ሆኗል "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን የመጡ ሰሞን ነበር ከኤርትራ ጋር ሰላም እንደሚያሰፍኑ፤ በመንግሥት ስር ያሉ ግዙፍ የኢኮኖሚ ተቋማት ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ወደ ግል እንዲሸጋጋሩ ለማድረግ እንደሚሰሩ ይፋ አደረጉ። በወቅቱ ሁለቱም አበይት ጉዳዮች አነጋጋሪ ነበሩ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀዳሚ ሥራ የነበረው ግን የኤርትራ ጉዳይ ነበር። 'የፕራይቬታይዜሽኑ' ጉዳይ በይደር ተቀምጦ ቆይቷል። ጉዳዩ ለሕዝብ ጆሮ ከደረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ አሁን እንደ አዲስ ተነስቶ መናጋገሪያ ሆኗል። ሐሙስ እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዉጭ ኩባንያዎች በቴሌኮሙኑኬሽን ዘርፍ መዋዕለ ነዋይ እንዲያፈሱ የሚፈቅድ ረቂቅ ሕግ አፅድቋል። ምክር ቤቱ ገለልተኛ የኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን መስሪያ ቤትን ለማቋቋም የሚያስችል አዋጅም እንዳጸደቀ የተከበሩ ዶ/ር ሙሉጌታ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ባለስልጣኑ የቴሌኮም ዋጋ ትመናን፣ የኮምኒኬሽን ፖሊሲዎችን ማስፈጸምና የኮምኒኬሽን ድርጅቶችን፣ ኢንተርኔትንና የሬዲዮ ሞገዶችን ይቆጣጠራል ሲሉም ያብራራሉ። • «አማካሪ አያስፈልገኝም ብሎ የሚያስብ መሪ አልገባውም ማለት ነው» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ 'ፕራይቬታይዜሽን' ወይንም የመንግሥት ድርጅቶችን ለግል ይዞታነት የማዞር ጉዳይ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችንና ፖለቲከኞችን በሦስት ጎራ ከፋፍሏል። አንደኛው ጎራ 'አዎ መሸጥ አለባቸው፤ እኒህ ድርጅቶች ገበያውን በሞኖፖል ይዘውት እስከመቼ?' የሚል ሃሳብ የሚያነሱ ግለሰቦች ስብስብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ 'ይህ ሃገር ከመሸጥ አይተናነስም፤ የመወዳደር አቅም ሳይኖረን እንዴት ሃብታሞች ሃገራችን እንዲገቡ እንፈቅዳለን?' ሲሉ ይሞግታሉ። ሦስተኛው 'መሸጥ ያለባቸው እና የለሌባቸው አሉ' ሲሉ የሚመክሩ ናቸው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ከሁለቱ ፅንፍ ሃሳቦች መሃል ላይ ናቸው። «ይህንን ፖሊሲ የሚያስፈፅሙ ሰዎች ሁሉም ነገር ፕራይቬታይዝ ይደረጋል ብለው ማሰብ የለባቸውም። መደረግ ያለባቸው አሉ፤ መደረግ የሌለባቸው አሉ። ለምሳሌ በምንም መሥፈርት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደረግ የለበትም። በፖለቲካም በኢኮኖሚም መሥፈርት መደረግ የለበትም። ከሃገር ጥቅምም አንፃር መደረግ የሌለበት ነው"" በማለት አጥብቀው ይከራከራሉ። ነገር ግን ይላሉ ፕሮፌሰር አለማየሁ «ሌሎቹን ለምሳሌ ስኳር ፋብሪካን ፕራቬታይዝ ብታደርገው፤ ብትሸጠው አዋጭ ነው። ኢትዮ-ቴሌኮም ላይ ስትመጣ ደግሞ አብዛኛውን ድርሻ እኛ ይዘነው ለምሳሌ 70 በመቶውን ከያዝነው በኋላ ሌላውን መሸጥ አዋጭ ነው። ቀሪውን ድርሻ የሚይዘው ደግሞ አፍሪካዊ ድርጅት ቢሆን ይመረጣል፤ በዚያውም የቀጠናውን ጥምረት ለማጠናከር።» • ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? መሸጡ የግድ ቢሆን እንኳ 'ሬጉላቶሪ ቦዲ' [ተቆጣጣሪ አካል] ማቋቋም ሊውል ሊያድር የሚገባው ጉዳይ እንዳልሆነ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። «ለምሳሌ መንግሥት 60 በመቶ ገቢ ያገኘው ከቴሌ ነው። ሌላው 30 በመቶ ከንግድ ባንክ ነው። ስለዚህ ንግድ ባንክን፤ ቴሌን ሸጥክ ማለት ባዶ እጅህን ነው አራት ኪሎ ቁጭ የምትለው። ስለዚህ ምጣኔ ሃብታዊ ውሳኔ ለመወሰን ምንም ዓይነት 'ኢንቨስትመንት' የለህም ማለት ነው። አሁን መንግሥት ማድረግ ያለበት፤ በተለይ እንደ ቴሌ ላሉት የተወሰነውን ሽጦ ሲያበቃ የመቆጣጠር አቅሙ ሲጎለብት ለሌሎች ክፍት ማድረግ ነው።» የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የነበሩት ፖለቲከኛው ዮናታን ተስፋዬ የመንግሥትን 'ፕራቬታይዜሽን' ዕቅድ ከሚደግፉት መካከል አንዱ ናቸው። «ፕራቬታይዝ የማድረጉ አንደኛ ጥቅም 'ሞኖፖሊ' እንዳይኖር ማድረጉ ነው። ሁለተኛ የፉክክር ገበያ ይኖራል፤ ይህ ደግሞ ሕብረተሰቡ የተሻለ ምርትና አገልግሎት እንዲያገኝ ያደርጋል።» ምጣኔ ሃብታዊውን ትንታኔ ለባለሙያዎች ልትወው፤ የሚሉት አቶ ዮናታን «የመንግሥት ድርጅቶች በመንግሥት ቁጥጥር ሥር መሆን አምባገነንነትን ያበረታታል» ባይ ናቸው። «'እኔ ነኝ አሳቢ፤ እኔ የተሻለ ለማሕበረሰቡ እጨነቃለሁ' የሚል ሥነ-ልቡናን እያሳደረ ነው የሚሄደው። ይህ አስተሳሰብ ደግሞ ሥር በሰደደ ቁጥር ሌሎች ተፎካካሪ ኃይሎችን እንደ ሥልጣን ተቀናቃኝ ነው የሚያየው፤ ምክንያቱም ራሱ ነጋዴው መንግሥት እየሆነ ስለሚመጣ። ስለዚህ ፖለቲካዊ ብልሽትን ይፈጥራል፤ ነፃ ገበያ እና ፉክክር የሌለበት፤ አንድ ወገን ብቻ እሴት የሚጨምርበት በጣም ደካማ የገበያ ሥርዓት እንዲኖር ነው የሚያደርገው።» • ኢትዮጵያ ኢንትርኔትን ስታቋርጥ በየቀኑ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ታጣለች የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች 'ዘ ቢግ ፋይቭ' ይሏቸዋል፤ አየር መንገድ፣ ቴሌኮም፣ ባንክ፣ ባቡር እና ስኳር ፋብሪካዎች። መንግሥት እነዚህን ድርጅቶች ለግል ባለሃብቶች ሲሸጥ ሕዝብን ማማከር አለበት የሚሉ ሃሳቦች በአለፍ ገደም እያሉ ይደመጣሉ። አቶ ዮናታን «ይሄ እኮ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው. . .» ይላሉ። «ይሄ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው። የኢኮኖሚ ጉዳይ ደግሞ በባለሙያዎች ጥናት ተደርጎ፤ በዚያ ጥናት ላይ ተመርኩዞ፤ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ይሄ ያዋጣል ብለን የምንወስነው ነገር ነው እንጂ ልክ እንደባንዲራ ጉዳይ ወይም የክልል እንሁን ጥያቄ ሕዝበ-ውሳኔ የሚደረግበት አይደለም። በየትኛውም ዓለም ላይ ሕዝብ በእንደዚህ ዓይነት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ቀጥተኛ የሆነ ውሳኔ ማሳለፍ አይችልም።» መሰል የፖሊሲ ለውጦች የሕዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ባይኖራቸው እንኳ ምርጫ እስኪመጣ መጠበቅ አይቻልም ወይ? በርካቶች የሚያነሱት ጥያቄ ነው። እርግጥ ነው አቶ ዮናታን በዚህ ጉዳይ ይስማማል። ግን እሱ አልሆነም፤ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ለሃገሪቱ ይጠቅማል የሚለውን ፖሊሲ የማፅደቅ መብት አለው ይላል። «አሁን ባለንበት ወቅት ኢኮኖሚው እየወደቀ ነው። ለዚህ ደግሞ አንድ ትልቅ ድርሻ የሚወስዱት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ናቸው። እነዚህ የልማት ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ ስላልሆኑ አሁን ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ምንም ሊቋቋመው የሚችለው አይደለም። የውጭ ባለሃብቶችን መሳብ የሚቻለው ደግሞ የኢኮኖሚ ፖሊሲውን መቀየር ሲቻል ነው።» ነዋሪነቱን እንግሊዝ ያደረገው የምጣኔ ሃብት ምሁሩ እዮብ ባልቻ፤ አዲሱ የፕራቬታይዜሽን አጀንዳ በግለሰቦች የሚመራ ነው ሲል ይሞግታል። እንደ እዮብ ትንተና አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩን በምጣኔ ሃብት ጉዳይ የሚያማክሩ ግለሰቦች ከዓለም ባንክና እና ዓለም አቀፉ ገንዘብ ድርጅት ጋር በቀጥታም ሆነ ተዘዋዋሪ ቁርኝት ያላቸው ናቸው። ምንም እንኳ የእዮብ ትንታኔ ግለሰቦቹ ላሳኩት ግብ ምስጋና ቢሰጥም በፕራቬታይዜሽን ጉዳይ ላይ ያላቸው አቋም አያስተማምንም ይላል። ፕሮፌሰር አለማየሁም ቢሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሥር ጫና እንዳ��ና ያንን ጫና ለመቋቋም የሚያስችል የምጣኔ ሃብት አቅም የላቸውም ባይ ናቸው። ለፕሮፌሰሩ የመንግሥት ድርጅቶችን ለገበያ የማቅረብ ጊዜው አሁን አይደለም። ትርፉ ከመንግሥት ሞኖፖሊ ወደ ግለሰብ ሞኖፖሊ መሸጋገር ነው ይላሉ። • ወሳኝ ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃዎች በ100 ቀናት «ለምሳሌ ቴሌን በ5 ወይም 10 ቢሊዮን ዶላር ሸጥነው እንበል። ነገ ያ ድርጅት የሚያተርፈውን አትርፎ የቀረውን ይዞ ሹልክ ይላል። በኢትዮጵያ ሕግ ደግሞ ያተረፍከውን ገንዘብ 'እክስፓትረየት' [ይዘህ መውጣት] ማድረግ ትችላለህ፤ የፈለግከውን። መሰል ስትራቴጂክ ነገሮችን ስታስብ መንግሥት ለፕራቬታይዜሽን መጣደፍ የለበትም። መንግሥትም ስለጨነቀውና ዶላር ስላጠረው እንጂ ፈልጎት አይመስለኝም» ይላሉ። ለአቶ ዮናታን ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው። መከራከሪያው ደግሞ ኢኮኖሚያችን እየደቀቀ ነው የሚል። ፕሮፌሰር አለማየሁ ደግሞ ጉዳዩን በሁለት ከፍለው ያዩታል። «አንደኛው ፖለቲካዊ ነው፤ ማለት አንድ መንግሥት ይህንን ፖሊሲ አስተዋውቆ የሕዝቡን ይሁንታ ካገኘ ሊያስፈፅመው ይችላል። ምክንያቱም እነዚህ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ የሚቆጣጠሩ ተቋማት ናቸው» ይላሉ። • የስኳር ፋብሪካዎችን ለግል ባለሃብቶች የመስጠት ፋይዳና ፈተናዎቹ ስለዚህ ትክክለኛው ጊዜ መንግሥት የሕዝቡን ፖለቲካዊ ውክልና ባገኘበት ጊዜ መሆን እንዳለበት የሚጠቅሱት ፕሮፌሰር አለማየሁ «በኢኮኖሚ መነፅር ስናየው ግን አሁን ባለው ሁኔታ በእኔ ግምት ትክክል አይደለም። ምክንያቱም መንግሥትም አልተረጋጋም፤ ሃገሩም አልተረጋጋም። ግን ደግሞ መንግሥት ብር የለውም። ከጀርባቸው ጠንካራ ኃይሎች ካልሸጣችሁ እይሏቸው ይሆናል። ስለዚህ ያለው አማራጭ ቅድም ያነሳሁት ሃሳብ ነው። የተወሰነውን ፕራይቬታይዝ ማድረግ።»" https://www.bbc.com/amharic/news-48619211 +business አሜሪካ በጦር መሳሪያ ንግድ ቀዳሚነቷን ስታስጠብቅ ሽያጯም ከፍ ብሏል "ባለፉት አምስት ዓመታት አሜሪካ ለሌሎች አገራት የምታቀርበው የጦር መሳሪያ መጠን በ37 በመቶ መጨመሩን አንድ በስዊዲን የሚገኝ የምርምር ተቋም አስታወቀ። ከአሜሪካ በተጨማሪ ፈረንሳይና ጀርመን ለሌሎች አገራት በሽያጭ የሚያቀርቡት የጦር መሳሪያ መጠን መጨመር በሩሲያና በቻይና አቅርቦት ምክንያት የተፈጠረውን ክፈተት የሚሞላ ነው ተብሏል። በአሁኑ ጊዜ የአገራት የጦር መሳሪያ ግዢና ሽያጭ መጠን ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ ከፍተኛ ከሚባለው ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም፤ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሰበብ ለውጥ ሊኖር ይችላል ተብሎ ይገመታል። በዓለም ላይ ከታየው የጦር መሳሪያ ግዢ ውስጥ ከፍተኛው የተመዘገበው በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ነው ተብሏል። የጦር መሳሪያዎች ግዢና ሽያጭን በተመለከተ ምርምሩን የሰራው የስቶክሆልም የሠላም ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ፒተር ዊዝማን ""ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የታየው ፈጣን የጦር መሳሪያ ግብይት አብቅቷል ለማለት ጊዜው ገና ነው"" ብለዋል። ባለሙያው ጨምረውም የኮሮናቫይረስ የሚያስከትለው የምጣኔ ሀብት ተጽዕኖ አገራት በቀጣይ ዓመታት ውስጥ የሚገዙትን የጦር መሳሪያ መጠን መለስ ብለው እንዲቃኙ ሳያደርጋቸው አይቀርም። ""ወረርሽኙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ባለፈው ዓመት እንኳን፣ በርካታ አገራት ወሳኝ የሚባሉ ጦር መሳሪያዎችን ለመግዛት ከፍተኛ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።"" የጥናት ተቋሙ እንዳመለከተው ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ቀደም ሲል ከነበረው ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ጋር ሲነጻጸር በነበረበት የመርጋት ሁኔታ አሳይቶ ነበር። አሜሪካ ወደ ውጭ ከምትልከው የጦር መሳሪያ ወደ ግማሽ የሚጠጋው፣ ማለትም 47 በመቶው፣ ለመካከለኛው ምሥራቅ አገራት የቀረበ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥም ሳዑዲ አረቢያ ብቻዋን ከአጠቃላዩ የአሜሪካ የመሳሪያ ሽያጭ 24 በመቶውን ትወስዳለች። ባለፉት አምስት ዓመታት የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ድርሻ በጨመረበት ጊዜ 96 አገራት ደንበኞቿ ሆነዋል። ከአሜሪካ በመከተል የፈረንሳይ የጦር መሳሪያ ሽያጭ በ44 በመቶ ሲጨምር የጀርመን ደግሞ በ21 በመቶ ከፍ ብሏል። ከእነዚህ በተጨማሪም እስራኤልና ደቡብ ኮሪያ ምንም እንኳን ከዋነኞቹ ጋር ሲነጻጸር የሚያቀርቡት የጦር መሳሪያ መጠን ዝቅተኛ ቢሆንም በዚህ ወቅት ሽያጫቸው በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። ግጭትና ውጥረት በማይለየው መካከለኛው ምሥራቅ የጦር መሳሪያ ግዢ ፍላጎት በፍጥነት እያደገ ይገኛል። በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት ወደዚህ አካባቢ የተሸጠው የጦር መሳሪያ መጠን ቀደም ሲል ከነበሩት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር በ25 በመቶ ከፍ ብሏል። ከፍተኛው የጦር መሳሪያ ግዢ የተከናወነውም በሳዑዲ አረቢያ ሲሆን በዚህም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ከተላከው 61 በመቶውን ገዝታለች። በተከታይነት ግብጽና ኳታር ይጠቀሳሉ። የእስያና የኢዢያ አገራት ቀደም ሲል 42 በመቶ የሚሆነውን ከፍተኛ መጠን ያለውን ዋነኛ የጦር መሳሪያዎችን በመሸመት ቀዳሚ ነበሩ። በአካባቢው ሕንድ፣ አውስትራሊያ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያና ፓኪስታን ዋነኞቹ የጦር መሳሪያ ሸማች አገራት ነበሩ። ምንም እንኳን አሁንም ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገራት ዋነኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢዎች ቢሆኑም፤ ቀደም ሲል ከዋነኞቹ የጦር መሳሪያ ላኪዎች መካከል የነበሩት ሩሲያና ቻይና ሽያጫቸው ቀንሷል። በዚህም ሳቢያ ሩሲያ ወደ ውጭ አገራት የምትልከው መሳሪያ በ22 በመቶ የቀነሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ ሕንድ የምትልከው 53 በመቶ የሚሆነው ነበር። የዓለም ትልቋ አምስተኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢ የሆነችው ቻይና ሽያጯ በ7.8 በመቶ ቀንሷል። ፓኪስታን፣ ባንግላዲሽና አልጄሪያ ዋነኞቹ የቻይና ጦር መሳሪያ ገዢዎች ነበሩ።" https://www.bbc.com/amharic/news-56398435 +sports የእንግሊዝ እግር ኳስ ክለቦች ማሕበራዊ ሚድያን ጥለው ሊወጡ ነው "የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ፣ እንግሊሽ ፉትቦል ሊግ እና የሴቶች ሱፐር ሊግ ክለቦች ለአራት ቀናት ከማሕበራዊ ድር አምባዎች ራሳቸውን ሊያገሉ ነው። ክለቦች ከዚህ ውሳኔ የደረሱት ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ የሚታዩ ብዘበዛዎችና ማግለሎችን በመቃወም ነው። አድማው የሚጀምረው ከአምስት ቀናት በኋላ ሚያዚያ 22 ነው። የእግር ኳስ ማሕበር፣ እንዲሁም ሌሎች ይመለከተናል የሚሉ መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ ኪክ ኢት ኦፍ የተባለው ፀረ-ማግለል ድርጅት በዚህ አድማ ላይ ይሳተፋሉ። የኪክ ኢት ኦፍ ሊቀመንበር ሳንጃይ ባንዳሪ ""ይህ አድማ ምን ያክል እንደመረረን የሚያሳይ ነው"" ይላሉ። ""ማሕበራዊ ድር አምባ አሁን አሁን በጣም መርዛማ ለሆኑ ብዝበዛዎች የተጋለጠ ሆኗል ።"" እኛ አንድ ላይ ሆነን ይህን አድማ የምንመታው ሥልጣኑ ላላቸው መልዕክት ለማስተላለፍ ነው። እርምጃ እንድትወስዱ እንፈልጋለን። ለውጥ እንድታመጡ እንሻለን።"" ሊቀ መንበሩ ማሕበራዊ ድር አምባዎች ፊታቸውን ደብቀው ለሚበዘብዙ ሳይሆን ለእግር ኳሱ ቤተሰቡ ነው የተመቸ ሊሆን የሚገባው ሲሉ ይሞግታሉ። ባለፈው ዓመት የቆዳ ቀለሙን አስመልክቶ ብዝበዛ የደረሰበት የሼፊልድ ዩናይትዱ ዴቪድ ማክጎልድሪክ ""ጊዜው አሁን ነው"" ይላል። ""በእኔ ላይ የደረሰው በሌሎች በርካታ ተጫዋቾች ላይ ደርሷል። የሆነ ነገር ሊፈጠር ይገባዋል። የቆዳ ቀለምን መሠረት አድርጎ ጥቃት ማድረስ ለብዙዎች ቀላል ነው።"" ጎልድሪክ ትላንት [ቅዳሜ] ምሽት ከብራይተን ጋር በነበረው ጨዋታ አንድ ጎል አስቆጥሮ ቡድኑ እንዲያሸንፍ አስችሏል። ተጫዋቹ ከግጥ���ያው በኋላ በሰጠው አስተያየት ""ሱፐር ሊግን በ48 ሰዓታት አስወገድን። ዘረኝነት መርታት ያቃተን ለምንድነው?"" ሲል ጠይቋል። የብራይተኑ ፈረንሳዊ አጥቂ ኒል ሞፔም በተመሳሳይ ማሕበራዊ ድር አምባው ላይ ጥቃት ደርሶበታል። ተጫዋቹ ለስካይ ስፖርት በሰጠው ድምፅ ""አድማው ትክክለኛ ነው"" ሲል ተደምጧል። ""ተጫዋቾች በይነ መረብ ላይ ብዙ ጥቃት ይደርስባቸዋል። ይህን መዋጋት አለብን። አሁን አንድ ላይ መሆናችን መልካም ነገር ነው።"" ክለቦችን ጨምሮ አስተዳዳሪ አካላት እንዲሁም የእግር ኳስ ዳኞች ማሕበር ከትዊተር፣ ፌስቡክና ኢንስታግራም ራሳቸውን ለአምስት ቀናት ለማግለል ተስማምተዋል። ከሳምንታት በፊት ስዋንሲ ሲቲ የተሰኘው ቡድን ተጫዋቾቹ ላይ በደረሰው ጥቃት ምክንያት የአንድ ሳምንት አድማ አድርጎ ነበር። ሌላኛው የቻምፒዮንሺፕ ቡድን በርሚንግሃም ሲቲና የስኮትላንዱ ሬንጀርስም ማሕበራ ድር አምባው ላይ አድማ መትተው ነበር። የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች ፈረንሳዊው ቲዬሪ ሄንሪ በዘረኝነትና በሌሎች ጥቃቶች ሳቢያ ከማሕበራዊ ድር አምባዎች ራሱን ሙለ በሙሉ ማግለሉን ማስታወቁ አይዘነጋም። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ የነበረው የ43 ዓመቱ ሄንሪ ""በቃ ማለት በቃ ነው"" ሲል ተቃውሞውን ገልጿል። ሊቨርፑል ሶስቱ ጥቁር ተጫዋቾቹ አሌክሳንደር-አርኖልድ፣ ናቢ ኬታና ሳዲዮ ማኔ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ ቁጣውን መግለፁ ይታወሳል። አድማ መቺዎች ዓላማቸው ማሕበራዊ ድር-አምባዎች ጥላቻን እንዲያስወግዱና ትምህርትም እንዲሰጡ መሆኑን በመግለጫቸው አትተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ትላልቅ የማሕበራዊ ድር አምባ ኩባንያዎች ችግሩን መቅረፍ ካልቻሉ ቅጣት እንደሚጥል ዝቶ ነበር። ፌስቡክ የካቲት ላይ ከበድ ያሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ እንዳሰበ አስታውቆ ነበር። በፌስቡክ የሚተዳደረው ኢንስታግራም ደግሞ ባለፈው ሳምንት ተጠቃሚዎች ጓደኞቻቸው ያልሆኑ ሰዎች መልዕክት እንዳይልኩላቸው የሚያስችል መንገድ አምጥቻለሁ ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56877326 +business በስህተት የጣለውን ቢትኮይን በ13 ሚሊዮን ዶላር እያፈላለገ ያለው ግለሰብ ከ10 ዓመታት በፊት ነው። ጄምስ ሃዌልስ ያስቀመጠውን ቢትኮይን ረስቶ የኮምፒውተሩን የመረጃ ቋት (ሃርድ ድራይቭ) አውጥቶ ጣለው። ጄምስ ተዝናግቶ የወረወረው ቢትኮይን ዘንድሮ ባለው ገበያ 184 ሚሊዮን ዶላር ሊያወጣ ይችላል። ይህ የከነከነው ጄምስ ከዓመታት በፊት የጣለውን ቢትኮይን ሚሊዮን ዶላር ከፍሎ ሊያስቆፍረው አስቧል። የሰውዬው ‘ሃርድ ድራይቭ’ ኒውፖርት በተሰኘችው የዩናይትድ ኪንግደም ከተማ ቆሻሻ መጣያ ሥፍራ ይኖራል ተብሎ ተገምቷል። ጄምስ ይህ ውድ ቁስ ከተገኘለት ከቢትኮይኑ 10 በመቶውን ቆንጥሮ ከተማዋን የክሪፕቶከረንሲ ማዕከል ለማድረግ ቃል ገብቷል። ነገር ግን የከተማዋ ምክር ቤት የቆሻሻ መጣያውን መቆፈር ሥነ-ምኅዳራዊ (ኢኮሎጂካል) ቀውስ ያስከትላል እያለ ነው። የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (አይቲ) ባለሙያው ጄምስ ከዘጠኝ ዓመት በፊት በፈረንጆቹ 2013 ነበር፤ 8 ሺህ ቢትኮይን ያቀፈውን ሃርድ ድራይቭ ጠርጎ የጣለው። ወቅቱም ቢትኮይን የተሰኘው ዲጂታል የመገበያያ ገንዘብ ብቅ ብቅ ማለት የጀመረበት ነበር። ቢትኮይን ገበያው ላይ የሚታወቀው በሚዋዥው ዋጋው ነው። ለምሳሌ የጄምስ ቢትኮይን ዋጋ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት [2021] 256 ሚሊዮን ዶላር ደርሶለት ነበር። ነገር ግን ከዘንድሮው ዓመት መባቻ ጀምሮ ዋጋው አሽቆልቁሏል። ጄምስ በተደጋጋሚ ለኒውፖርት ከተማ ምክር ቤት ቆሻሻ ማከማቻው ይቆፈርልኝ ብሎ ቢያመልክትም ጥያቄው ሰሚ አጥቷል። ይህ ያታከተው ግለሰብ አሁን ሃርድ ድራይቩ ከተገኘ 10 በመቶ ገቢውን ለከተማዋ የክሪፕቶ���ረንሲ ማስፋፊያ ለመስጠት ወስኗል። ነገር ግን የጄምስን መዳፍ የምታክል ቁስ ለማግኘት ሲል ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ወጪ አውጥቶ ለዓመታት የተከማቸውን ቆሻሻ ይቆፍር እንደሁ አልታወቀም። ከተማ አስተዳደሩ የቆሻሻ ማከማቻውን ማመስ አካባቢውን ሊበክለው ይችላል የሚል ስጋት አለው። ጄምስ ደግሞ “እኔ ማከማቻውን የማስቆፈር አቅም እንዲሁም አደጋ ሳያደርስ የሚያስስ ባለሙያ አለኝ” ይላል። “እርግጥ ነው ቆሻሻ ማከማቻ መቆፈር ራሱን የቻለ ትልቅ ሥራ ነው” ይላል ጄምስ። “ነገር ግን ማስቆፈሪያ ወጪውን እችላለሁ። የሰው-ሠራሽ ልኅቀት [አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ] ባለሙያ አስመጥተናል። ሃርድ ድራይቩን ነቅሎ የሚያወጣ ቴክኖሎጂ አለ።” ግለሰቡ ይህ ብቻ ሳይሆን ከበቢያዊ አደጋን የሚመረምር ቡድን ማዘጋጀቱን ይገልጣል። “በሁሉም ዘርፍ የተካኑ ልምድ ያላቸው ሙያተኞች ይዣለሁ። ከተፈቀደላቸው ይህንን ሥራ በብቃት መከውን የሚችሉ ናቸው።” ነገር ግን ሃርድ ድራቩን ማግኘት ብቸኛው ሥራ አይደለም። ይህ የመረጃ ማከማቻ ቁስ ቢገኝ እንኳ ለመሥራቱ ማስተማመኛ የለም። ይህ በርካታ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ቢትኮይን ያቀፈው ቁስ ቢገኝ ጄምስ ሚሊየነር ይሆናል። ነገር ግን የቢትኮይንን የገበያ ዋጋ መገመት ከባድ ነው። ቢሆንም የ37 ዓመቱ ግለሰብ የበርካታ ሚሊዮን ዶላሮች ባለቤት ሊሆን ይችላል። ጄምስ ገንዘቡ ተቆፍሮ ይውጣለት እንጂ፣ ያደገባትን ከተማ የክሪፕቶከረንሲ ማዕከል ለማድረግ ቆርጦ ተነስቷል። “ሕብረተሰቡን የሚጠቅም ሥራ ለመሥራት የሚያስችል ዕቅድ አስቀምጫለሁ” ይላል። “አንደኛው ሥራ የቆሻሻ ማከማቻውን ማዘመን ነው። ከተቻለ በአካባቢው በነፋስ ኃይል የሚሠራ የኤሌክትሪክ ማመንጫ እንገነባለን።” የኒውፖርት ማኅበረሰብ የሚጠቀምበት የክሪፕቶከረንሲ ገበያ ለመዘርጋት ነው የጄምስ ዓላማ። ለእያንዳንዱ የኒውፖርት ነዋሪ 61 ዶላር ዋጋ ያለው ቢትኮይን ለመስጠትም ቃል ገብቷል። በተከማዋ ዋና ዋና ቦታዎች ደግሞ ክሪፕቶ ላይ የተመሠረቱ ፌርማታዎች ለመግንባትም አስቧል። የኒውፖርት ከተማ ምክር ቤት ግን በተደጋጋሚ የሰውዬውን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል። የከተማዋ ቃል አቀባይ “ቆሻሻ ማከማቻን በተለመከተ የተቀመጠ ሕግ አለን። ይህን ሕግ መከተል አለብን” ብለዋል። “አንደኛው ጉዳይ ይህ የቆሻሻ ማከማቻ ከተቆፈረ በአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ የሚያደርሰው ሥነ ምኅዳራዊ አደጋ ነው። የጄምስ ዕቅድ ደግሞ ይህን አደጋ የሚያስከትል ነው። ይህን ልንቀበለው አንችልም። በሕጉ መሠረት እንዲያውም ከግምት ውስጥ ልናስገባው የምንችለው ሐሳብ አይደለም።” https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n347241vro +sports ሳሙኤል ኤቶ እግር ኳስ ሊያቆም ነው "አራት ጊዜ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ መመረጥ የቻለው ካሜሩናዊው ሳሙኤል ኤቶ ከ22 ዓመታት የእግር ኳስ ህይወት በኋላ ጫማውን ሊሰቅል ስለመሆኑ ጠቁሟል። የ38 ዓመቱ የቀድሞው የካሜሩን ብሄራዊ ቡድንና የባርሴሎናው አጥቂ በኢንስታግራም ገጹ ላይ ባሰፈረው መልእክት ''ተፈጸመ፤ ወደ ሌላ የፈተና ጉዞ ተጀመረ'' ሲል ጽፏል። • “በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነኝ” አትሌት ገብረእግዚአብሔር • በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ኤቶ ለሃገሩ ካሜሩን በ118 ጨዋታዎች 56 ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በኤልሲና በኤቨርተን ተጫውቷል። ባለፈው ዓመት ደግሞ ለቱርኩ ኮንያስፖር ለአጭር ጊዜ ከተጫወተ በኋላ የኳታሩን ስፖርት ክለብ ተቀላቅሏል። እ.አ.አ. ገና የ16 ዓመት ታዳጊ እያለ የስፔኑን ሪያል ማድሪድ በ1996 ቢቀላቀልም መጫወት የቻለው ሶስት ጨዋታዎችን ብቻ ነበር። ከዛም በውሰት ለሌጋኔዝ፣ ኤስፓኞል እና ማሎርካ ተጫውቷል። በ2000 ለማሎርካ በ133 ጨዋታዎች 54 ግቦችን በማስቆጠር የቡድኑ የምን ጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ታሪክ ሰርቷል። በ2004 ደግሞ ባርሴሎናን ከተቀላቀለ በኋላ ሶስት ጊዜ የስፔን ላሊጋን ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በ2006 እና በ2009 ቡድኑ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ እንዲሆን አስችሏል። በሁለቱም የፍጻሜ ጨዋታዎችም ግብ አስቆጥሮ ነበር። በ2006 የውድድር ዘመን ለባርሴሎና በ34 ጨዋታዎች 26 ግቦችን ካስቆጠረ በኋላ በሊጉ የወርቅ ጫማ ማሸነፍ የቻለ ብቸኛው አፍሪካዊ ተጫዋች መሆን ችሏል። በአጠቃላይ በ144 ጨዋታዎች 108 ግቦችን ለባርሴሎና ያስቆጠረው ኤቶ በ2009 ወደ ኢንተር ሚላን በመሄድ ለሶስተኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማንሳት ችሏል። የጣሊያን ሴሪ አ እና የፊፋ ክለቦች የዓለም ዋንጫዎችን ከቡድኑ ጋር አንስቷል። በመቀጠል ኤቶ ያመራው ወደ ራሺያ ነበር። አንዚ ማካቻካላ ከሚባለው ቡድን ጋርም ለሁለት ዓመታት ከቆየ በኋላ በ2013 ቼልሲን ተቀላቀለ። ኤቨርተን፣ ሳምፕዶሪያ እና አንታሊያስፖር ደግሞ የተጫወተባቸው ሌሎች ቡድኖች ናቸው። ለካሜሩን ብሄራዊ ብድን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጫወት ሳሙኤል ኤቶ ገና የ17 ዓመት ታዳጊ ነበር። በ1998 በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ሃገሩ ከኮስታሪካ ስትጫወት በመሰለፍ የጀመረው ኤቶ በውድድሩ ትንሹ ተጫዋች ተብሎ ነበር። • ""አንድ አትሌት በህይወቱ የሚያስደስተው የአለም ሪከርድን መስበር ነው"" ዮሚፍ ቀጀልቻ ከብሄራዊ ቡድን እራሱን እስካገለለበት ጊዜ ድረስ ሃገሩን ወክሎ በአራት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ ተሳትፏል። በ2000 እና በ2002 የተካሄዱትን ተከታታይ የአፍሪካ ዋንጫዎችንም ከሃገሩ ጋር አንስቷል። በውድድሮቹም 18 ጎሎችን በማስቆጠር ኮኮብ ግብ አግቢ ሆኖ መጨረስ ችሎ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በ2000 በተካሄደው ኦሎምፒክ ከቡድን አጋሮቹ ጋር በመሆን ለሃግሩ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-49625124 +sports ወልቂጤ ከነማ 'የጨዋታ መጭበርበር ነበር' በሚል ቅሬታ አቀረበ "እየተገባደደ በሚገኘው በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ በድሬዳዋ ከነማ እና ፋሲል ከነማ መካከል የተደረገው ጨዋታ ተጭበርብሯል ሲል ወልቂጤ ከነማ ቅሬታውን ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን አቀረበ። ከትላንት በስቲያ ግንቦት 9፣ 2013 ዓ.ም በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9 ሰዓት ላይ በነበረው ጨዋታ የዘንድሮው የዋንጫ ባለድል ፋሲል ከነማ በድሬ ዳዋ ከነማ 3 ለ 1 ተረትቷል። ከዚህ ጨዋታ በኋላ ወራጅ ቀጠና የሚገኘው ወልቂጤ ከነማ ጨዋታው ተጭበርብሯል ሲል ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅሬታውን አቅርቧል። የደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳዩን እንዲያጣሩለት ለሊግ አወዳዳሪው ኩባንያ እና ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ደብዳቤ መጻፉን ምክትል ፕሬዝዳንት ሸረፋ ደልቾ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በሊጉ አዳማ ከነማ እና ጅማ አባጅፋር መውረዳቸው ሲታወቅ በሦስተኛነት ላለመውረድ ከሚጫወቱ ክለቦች መካከል ድሬዳዋ ከነማ፣ ወልቂጤ ከነማ እና ሲዳማ ቡና ይገኙባቸዋል። ጨዋታው በመጭበርበሩ ""ድሬ ዳዋ ከነማን ይጠቅማል፣ ወልቂጤ ከነማ ላይ ጉዳት ያደርሳል"" ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሩ። ""በ24ኛው ሳምንት ትላንት በነበረው የ9 ሰዓት ጨዋታ ላይ ድሬዳዋ ከነማ ከፋሲል ከነማ ጋር ጨዋታ ነበራቸው። በጨዋታው ፋሲል ከነማ ከአቅም በታች ተጫውቷል። የጨዋታ የማጭበርበር ሥራ ተሰርቶብኛል ብሎ ነው ወልቂጤ ከነማ ቅሬታ ያቀረበው። ይህ ደግሞ በክልሉ እግር ኳስ ፌደሬሽንም በኩል በበቂ ሁኔታ ታምኖበት የክልሉ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ይህንን ቅሬታ ለሚመለከታቸው አካላት አቅርቧል"" ብለዋል። የክልሉ እግርኳስ ፌደሬሽን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፈው ደብዳቤ በጨዋታው ከፍተኛ የጨዋታ ማጭበርበር እንደተፈጸመ እና ይህንንም ፌደሬሽኑ ባደራጀው የቴክኒክ ኮሚቴ አካላት ሪፖርት እንደቀረበለት አስታውቋል። ""የወልቂጤ እግር ኳስ ክለብ ላይ የተፈጸመው በደል እና የጨዋታ ማጭበርበር ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ዕድገት ጸር ነው"" ያለው ደብዳቤው የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል። ከበፊት ጀምሮ ጨዋታዎች 'ሊጭበረበሩ ይችላሉ' የሚሉ የተወሰኑ መረጃዎች ስለነበሩ ፌደሬሽኑ የተወሰኑ ባለሙያዎችንም አሰማርቶ ሁኔታውን ይከታተለው ነበር ብለዋል። ""ቅሬታው ዛሬ ነው የቀረበው አወዳዳሪው አካልም ሆነ እግር ኳስ ፌደሬሽኑ መልስ እኛም ክለቡም ይጠብቃል"" ሲሉ ገልጸዋል። ጥያቄያቸው በዋነኝነት የጨዋታው ሂደት በገለልተኛ አካል ይገምገም የሚል መሆኑን ጠቅሰው ""የጨዋታውን ሂደት የሚገመገምበት ብዙ ፓራሜትሮች ስላሉ ብዙ የሚያስቸግር አይደልም"" ሲሉ አክለዋል። ፋሲል ከነማ ቀደም ሲል የነበረው እንቅስቃሴ [ፐርፎርማንስ]፣ ያሰለፋቸው ተጫዋቾች እና አጠቃላይ የነበረውን ሂደት በገለልተኛ አካል እንዲታይ ተጠይቋል ብለዋል። ፋሲል ዋንጫ በማንሳቱ ተጫዋቾች መቀየሩ አንዱ ግምት ሊሆን ይችላል። ""በዚህ ጨዋታ ብቻ ሳይሆን በጥቅሉ ይህ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ከፍተኛ ጥንቃቀቄ ለማድርግ ጥረት ሲደረግ እንደነበር እናውቃልን"" ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ""ለሁሉም በሚገባ ጥብቅ መመሪያ እና ትዕዛዝ እንደተላለፈ መረጃዎች አሉ"" ብለዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ ባህሩ ጥላሁን በበኩላቸው ደብዳቤው እንደደረሳቸውና ቅሬታውን የመመልከት ሥልጣን ያለው ሊግ አወዳዳሪው ኩባንያ እንደሆነ ነገር ግን ከኩባንያው አቅም በላይ ከሆነ ፌዴሬሽኑ እንደሚመለከተው ገልጸዋል። ፋሲል ከነማ 22 ጨዋታ ተጫውቶ በ52 ነጥብ ሻምፒዮን መሆኑን ባረጋገጠበት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዲያ ሆሳዕና ይከተላሉ። የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር በ27 ጎሎች የሊጉን የምንግዜም ከፍተኛ አግቢነት ክብረወሰን በመስበር ጭመር ሲመራ ሙጂብ ቃሲም በ20 እንዲሁም ጌታነህ ከበደ በ12 ጎሎች ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57164707 +health ኮሮናቫይረስ፡ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ መምህር በቫይረሱ ሕይወታቸው አለፈ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሕብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ በኮሮናቫይረስ ተይዘው የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው ዛሬ ሕይወታቸው ማለፉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ለቢቢሲ ገለፁ። ሕክምና እየተከታተሉ በሚገኙበት የመቀለ የኮሮና ታማሚዎች ማገገሚያ ማዕከል ሕይወታቸው ማለፉንም የገለፁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት፤ ከእርሳቸው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላት አንድ ግለሰብም በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጦ ሕክምና እየተደረገላት እንደሚገኝ አክለዋል። በዩኒቨርስቲው የተለያዩ ግቢዎች በሚገኙ ለይቶ ማቆያዎች የሚሰሩ 1 ሹፌር፣ 2 የፀረ ተህዋስ ኬሚካል ርጭት ባለሙያዎች፣ 23 የፅዳት ሰራተኞች እና 10 የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸውን በዩኒቨርሲቲው ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ዘ ሚካኤል ገልፀውልናል። ዶ/ር ፍሰሃየ ከመምህርነት ባሻገር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮሮናቫይረስ ፈጣን ግብረ መልስ ቡድን መሪ በመሆን እንዲሁም በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ በኮሮናቫይረስ መረጃ ትንተና እና ትንበያ ክፍል እየሰሩ እንደነበር ዶ/ር ኪሮስ ገልፀውልናል። ዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመምህርነት፣ በተመራማሪነትና በሙያ አማካሪነት ለ17 ዓመታት አገልግለዋል። ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በመዛወር በዩኒቨርሲቲው የሕብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ፍሰሃየ በእናቶችና ህፃናት ህክምና፣ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች፣ በስነ-ምግብ፣ በወባ፣ በኤች አይቪ ኤድስና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ጨምሮ በሌሎች የሕብረተሰብ ጤና ዘርፎች ከ50 በላይ ችግር ፈቺ ጥናቶችን በታዋቂ ጆርናሎች ማሳተማቸውን አክለዋል። የቀብር ሥነ ስርዓታቸውም ነገ በመቀለ ከተማ እንደሚፈፀም ዶ/ር ኪሮስ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በትግራይ ክልል እስካሁን በተደረገ 25 ሺህ 579 ናሙናዎች ተመርምረው 1016 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን የ5 ሰዎች ሕይወት አልፏል። https://www.bbc.com/amharic/news-53699944 +sports ኢትዮጵያ የቶኪዮ ኦሎምፒክስ የአትሌቲክስ ተወዳዳሪዎቿን ይፋ አደረገች በቅርቡ በኔዘርላንድስ ሄንግሎ በተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የአትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድሮች ከአንድ እስከ ሶስተኛ የወጡ አሸናፊዎች በቶኪዮ ኦሎምፒክስ አገራቸውን ወክለው እንደሚወዳደሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በዚህም መሰረት ከ800-10 ሺህ ሜትር ባሉ ውድድሮች እንዲሁም 3000 ሜትር መሰናክልን ጨምሮ በአምስት ውድድሮች በሁለቱም ፆታ አገራቸውን የሚወክሉ አትሌቶች በውጤታቸው መሰረት ተሰላፊዎቹና ተጠባባቂዎቹ ተለይተዋል። ከቀናት በፊት በነበረው የ10 ሺህ የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ለተሰንበት ግደይከሁለት ቀናት በፊት በሲፋን ሀሰን ተሰብሮ የነበረውን የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር አሸናፊ መሆን ችላለች። በዚህ በ29 ደቂቃ ከ1.03 አሸናፊ በሆነችበት ውድድር ፅጌ ገብረ ሰላማ በሁለተኝነት፣ ፀሃይ ገመቹ በሶስተኝነት አሸናፊ ሆነዋል። በቀጣዩ የቶኪዮ ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩት ለተሰንበት ግደይ፣ ፅጌ ገብረሰላማ፣ ፀኀይ ገመቹና በተጠባባቂነት ያለም ዘርፍ የኋላው ናቸው። በቶኪዮ ኦሎምፒክስ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች ዝርዝር በ800 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በ1500 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በ5000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በ1000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በ3000 ሜትር መሰናክል የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሴት ተወዳዳሪዎች በወንዶች 10ሺህ ሜትር ማጣሪያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ አራተኛ ደረጃ የያዙ ሲሆን አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ26 ደቂቃ 49 ሰከንድ ከ51 ማይክሮሰከንድ በሆነ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል። እሱን በመከተል ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ሀጎስ ገብረህይወት ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። በ1500 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች በ5000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች በ10000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች በ3000 ሜትር መሰናክል የቶኪዮ ኦሎምፒክ ወንድ ተወዳዳሪዎች የቶክዮ ኦሎምፒክ 2020/2021 ከሐምሌ 16- ነሐሴ 2 ድረስ ይካሄዳል። https://www.bbc.com/amharic/57444933 +health ሕንድ ውስጥ በርካቶች ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ታመው ሆስፒታል ገቡ በሕንድ ውስጥ በሚገኝ አንድ ግዛት ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ታመው ሆስፒታል መግባተቸው ተነገረ። የአገሪቱ ባለስልጣናት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ 140 ሰዎችን ሆስፒታል እንዲገቡ ያደረገው በሽታን ምንነት ለማወቅ ምርምራ እያካሄዱ ነው። የህክምና ተመራማሪዎችም የዚህን በሽታ ምንነት ለመለየት እና የሕመሙን መንስኤ ለማወቅ ጥረት መጀመራቸው አስታውቀዋል። አንድራ ፕራዴሽ ከሚባለው ግዛት የመጡት ታማሚዎች በርካታ የተለያዩ የሕመም ምልክቶች ሲያሳዩ የነበረ ሲሆን፤ ከምልክቶቹ ውስጥም ማቅለሽለሽ እና እራስን ስቶ ተዝለፍልፎ መውደቅ ደግሞ አብዛኛዎቹ ላይ የተስተዋለ እንደሆነ ዶክተሮች ገልጸዋል። ኢሉሩ የተባለው የመንግሥት ሆስፒታል ደግሞ ምናልባት ተጨማሪ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች ከመጡ በሚል በርካታ አልጋዎች ነጻ ሆነው እንዲጠባበቁም ተደርጓል ተብሏል። ሕንድ የኮሮናቫይረስ ተጽእኖን ለመቀነስ እና ስርጭቱን ለመቆጣጠር ደፋ ቀና በምትልበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ምንነቱ ያልታወቀ ሕመም መከሰቱ በርካቶችን አሳስቧል። የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ደግሞ ሁሉም ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ታማሚዎች የኮሮናቫይረስ ምርምራ የተደረገላቸው ሲሆን ማናቸውም ግን በቫይረሱ አልተያዙም። በኢሉሩ የመንግሥት ሆስፒታል የሚሰራ አንድ የጤና ባለሙያ ለኢንዲያን ኤክስፕረስ ሲናገር '''አይናችን አካባቢ ማቃጠል ይሰማናል' ብለው ወደ ሆስፒታላችን ከመጡት መካከል በተለይ ደግሞ ሕጻናቱ ወዲያው ማስመለስ ጀመሩ። አንዳንዶቹ እራሳቸውን የሳቱ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ቅዝቃዜ ተሰምቷቸው ይንቀጠቀጡ ነበር'' ብሏል። ወደ ሆስፒታል ከተወሰዱት ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን አንዳንዶቹም ተሽሏቸው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል። የአንድራ ፕራዳሽ የጤና ሚኒስትር አላ ካሊ ካሊ ክሪሽና እንዳሉት ደግሞ ከሁሉም ታማሚዎች ላይ የደም ናሙና የተወሰደ ቢሆንም ምንም አይነት የቫይረስ ኢንፌክሽን ምልክት ግን አልታየባቸውም። ''ባለሙያዎቻችን የሰዎቹን መኖሪያ አካባቢ ከጎበኙ በኋላ በምርመራችን የአየር እና የውሃ ብክለት አለመሆኑን ደርሰንበታል። ምስጢራዊ የሆነ ሕመም ይመስላል፤ የትኛውም የላብራቶሪ ምርመራ ምክንያቱን ሊያውቀው አልቻለም'' ብለዋል የጤና ሚንስትሩ። https://www.bbc.com/amharic/news-55211959 +business ሊባኖስ፡ ለመሠረታዊ ሸቀጦች የሚደረገው ድጎማ እንዳይነሳ ቤይሩት ውስጥ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ በአንዳንድ መሠረታዊ ሸቀጦች ላይ መንግሥት ያደርገው የነበረው ድጎማ ሊቀነስ መሆኑን በመቃወም በሊባኖሷ መዲና ቤይሩት ውስጥ ተቃዋሚዎች መንገዶችን መዝጋታቸው ተነገረ። የድጎማውን መቀነስ በተመለከተ የወጡ መረጃዎችን ተከትሎ እርምጃውን የተቃወሙ ሰልፈኞች በማዕከላዊ ቤይሩት መንገዶች ላይ ጎማዎችን ያቃጠሉ ሲሆን አንዳንዶቹም ቁጣቸውን ለመግለጽ ወደ አገሪቱ ፓርላማ ህንጻ አምርተዋል ተብሏል። የአገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ ኃላፊ መንግሥት በዱቄት፣ በነዳጅና በመድኃኒቶች ላይ ያደርግ የነበረው ድጎማ ከቀጣዮቹ ሁለት ወራት በኋላ ሊቀጥሉ እንደማይችሉ ተናግረው ነበር። በአገሪቱ ውስጥ በተከሰተው የኢኮኖሚ ድቀት ሳቢያ በተለይ ድሃ ቤተሰቦች ላይ ከባድ ማኅበራዊ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት አስጠንቅቀዋል። ከሰኞ ጀምሮ የሌባኖስ ዜጎች በመሠረታዊ ሸቀጦች ላይ መንግሥት ያደርግ የነበረው ድጎማ ለማንሳት ማሰቡን በተመለከተ በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ከሰኞ ጀምሮ ከፍተኛ ዘመቻ እያካሄዱ ነው። ሊባኖስ ለተራዘመ ጊዜ እያሰቃያት ባለው የምጣኔ ሐብት ቀውስ ምክንያት የአገሪቱ ገንዘብ የመግዛት አቅም በከፍተኛ ደረጃ በመዳከሙ ማዕከላዊው ባንክ ዱቄትና ነዳጅን የመሳሰሉ ምርቶች ከውጭ ለሚያስገቡ አስመጪዎች የውጭ ምንዛሪ በቅናሽ እያቀረበ ቆይቷል። የምጣኔ ሐብት ቀውሱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሊባኖሳዊያንን ወደ ድህነት የከተተ ሲሆን፤ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ደግሞ ቀውሱን የበለጠ አባብሶታል። ��ለፈው ዓመት ነሐሴ ላይ በቤይሩት ወደብ ላይ ተከስቶ ከ200 በላይ ሰዎችን የገደለውና በሺዎች ያቆሰለውን ከባድ ፍንዳታ ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች በዋና ከተማዋ ያሉትን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጥሰው ገብተው እንደነበር ይታወሳል። ለፍንዳታው ምክንያት የሆነውን ወደቡ ውስጥ በሚገኝ አንድ መጋዘን ውስጥ ለረጅም ጊዜ ተከማችቶ የነበረውን ሁለት ሺህ ቶን የሚደርስ የአሙኒየም ናይትሬት አደገኛ ንጥረ ነገር እንዳይፈነዳና ጉዳት እንዳያደርስ ባለስልጣናት ለማድረግ አልቻሉም በሚል በወቅቱ በርካታ የሊባኖስ ዜጎች ቁጣቸውን ገልጸው ነበር። በደረሰው ከባድ ጉዳትና በተቀሰቀሰው ከባድ ተቃውሞ ምክንያት አገሪቱን ያስተዳድር የነበረው የሊባኖስ መንግሥት ስልጣኑን እንዲለቅ ተገዶ ነበር። https://www.bbc.com/amharic/news-55226709 +business የቻይናን የለውጥ ሂደት ለ40 ዓመታት በካሜራው የሰነደው ግለሰብ በሐምሌ ወር የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ 100ኛ የምስረታ ዓመቱን ያከብራል። በማኦ ዜዱንግ የተቀረጸው ፖሊሲ በ1950ዎቹ እና 60ዎቹ ረሃብ እና ቀውስ አስከትሎ ነበር። የእርሳቸውን ሞት ተከትሎ በቻይና ሰፊ የሚባል ለውጥ መጥቷል። ያን ዢጋንግ የተባለ ቻይናዊ ታዲያ ለ40 ዓመታት የቻይና ጎዳናዎችን በካሜራ እየቀረጸ ለውጡን ሰንዷል። https://www.bbc.com/amharic/news-57677744 +health ኮሮናቫይረስ፡ የለንደን ፖሊስ ክልከላዎችን በመተላለፍ ሰልፍ የወጡ ሰዎችን አሰረ በለንደን ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ለመቃወም ከወጡ ሰዎች መካካል 18 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ውሳኔውን የተቃወሙ በርካታ ሰዎች ከዩናይትድ ኪንግደም ንጉሳውያን መኖሪያ በሆነው ባኪንግሃም ቤተ-መንግስት ፊትለፊት ተሰባስበው ነበር። በመቀጠል ተቃዋሚ ሰልፈኞች ወደ ትራፋልጋር አደባባይ አምርተዋል። ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች በኮቪድ ምክንያት የተነጠቅነው ነጻነት ይመለስልን ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል። የሜትሮፖሊታን ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ እንዲበተኑ የተደረገ ቢሆንም ዜጎች ግን አሁንም ቢሆን አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል። በዌስትሚኒስተር ድልድይ ላይ ደግሞ ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ለመበተን ጥረት በሚያደርግበት ወቅት አንዳንድ ችግሮች ተፈጥረው ነበር ተብሏል። የፖሊስ አባላት ቀላል የሚባል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፖሊስ ሰልፈኞቹ በቁጥጥር ሥር ያዋልኩት የተለያዩ ሕግጋቶችን በመተላለፍ ነው ብሏል። ከጥፋቶቹ መካከልም የኮሮረናቫይረስ ሕጎችን በመጣስ፣ የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ ላይ ጉዳት ማድረስና ነውጠኝነት በዋነኛነት ተጠቃሽ ናቸው። ለንደን በያዝነው ሳምንት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ጠበቅ ያሉ ገደቦች ተጥለውባታል። ''ሰዎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ሲገኙ አካላዊ ርቀታቸውን አለመጠበቃቸውና የተቀመጡ ሕግና ደንቦችን አለማክበራቸው በእጅጉ አሳስቦናል'' ብለዋል የሜርሮፖሊታን ፖሊስ አዛዡ ኮማንደር አዴ አዴሌካን። አክለውም ''የተቃውሞ ሰልፉ አዘጋጆች የሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በቂ ዝግጅት አላደረጉም። በዚህ ሰአት ነው የህብረተሰቡን ደህንነት ለማረጋገጥ በማሰብ ፖሊሶች የተሰበሰቡትን ሰዎች ለመበተን የተንቀሳቀሱት'' ብለዋል። ''አብዛኛዎቹ የተሰበሰቡት ሰዎች የፖሊስ አባላቱ የነገሯቸውን በመስማታቸውና አካባቢውን ቶሎ በመልቀቃቸው ደስተኞች ነን። ነገር ግን ጥቂቶች ተባባሪ ለመሆን ፈቃደኛ አልነበሩም። ሆነ ብለው ፖሊሶች የሚነግሯቸው ነገር ችላ ሲሉ ነበር። ዌስትሚኒስተር ድልድይንም ዘግተው ነበር'' ብለዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54681599 +politics ከስድስት ዓመታት በላይ በአማፂያን ታግተው የነበሩት ኮሎምቢያዊት ለፕሬዚዳን���ነት ሊወዳደሩ ነው "የቀድሞዋ የኮሎምቢያ ሴናተርና ከ20 አመታት በፊት በግራ ክንፍ አማፂያን ታግተው የነበሩት ኢንግሪድ ቤንታኮርት ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ አስታወቁ። ኢንግሪድ በአውሮፓውያኑ 2002 በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበረበት ወቅት በፋርክ አማፂያን ተወስደው ከስድስት ዓመታት በላይ ታግተው ቆይተዋል። ፖለቲከኛዋ በመጪው ግንቦት ወር የሚደረገውን ምርጫ ካሸነፉ ሙስናን እና ድህነትን ለመቅረፍ ቃል ገብተዋል። ""በአሁኑ ወቅት ልወዳደር የመጣሁት የጀመርኩትን ለመጨረስ ነው"" ሲሉ በሃገሪቱ መዲና ቦጎታ ላሉ ደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል። ""እኔ ፊታችሁ የተገኘሁት ፍትህ የማያገኙ 51 ሚሊዮን ኮሎምቢያውያንን መብት ለመጠየቅ ነው፤ ምክንያቱም የምንኖረው ወንጀለኞችን ለመሸለም በተዘጋጀ ስርአት ውስጥ ነው"" ሲሉም ተደምጠዋል። የፋርክ አማፅያን ከ50 ዓመታት በላይ ከኮሎምቢያ መንግሥት ጋር ደም አፋሳሽ ጦርነት ያካሄዱ የማርክሲስት ቡድን ነበሩ። በመጨረሻም በአውሮፓውያኑ 2016 የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ተደረሰ። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ መጪው ሰኔ ለሚደረገው ምርጫ ከ20 በላይ እጩዎች እንደሚወዳደሩ ታውቋል። የቦጎታ የቀድሞ ከንቲባ እና ኤም- 19 የተባለው የአብዮታዊ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን አባል የነበሩት ጉስታቮ ፔትሮ በአሁኑ ጊዜ በህዝብ የምርጫ አስተያየት መስረት በግንባር ቀደምትነት እየመሩ ነው። በርካታ ኮሎምቢያውያን በአሁኑ ጊዜ አገሪቱን እየመሩ ካሉትና ተወዳጅነታቸው እያሽቆለቆለ ከመጣው የቀኝ ክንፍ ፖለቲከኛው ፕሬዚዳንት ኢቫን ዱክ የተሻለ አማራጭ አድርገው ያዩዋቸዋል ጉስታቮ ፔትሮን። ፕሬዚዳንት ኢቫን ዱክ በጊዜ ገደብ ምክንያት በዘንድሮው ምርጫ መወዳደር አይችሉም። ኢንግሪድ ቤንታኮርት በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነት ቢኖራቸውም በአውሮፓውያኑ 2008 በኮሎምቢያ ወታደራዊ ሃይሎች አማካኝነት ከተለቀቁ በኋላ ድምፃቸው አይሰማም። በአሁኑ ወቅትም ፓርቲያቸውን ኦክስጅንን ጨምሮ በተዋቀረው ሴንትሪስት በተባለው ጥምረት እጩነትን ለማሸነፍ ከባድ ፈተና ይገጥማቸዋል። የመጀመሪያ ደረጃ ምርጫ ሁለት ወራት ብቻ በቀረውና ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በግጭት ሰለባ ሆነው በመንግሥት በተመዘገቡባት ሀገር ራሳቸውን እንደ አስታራቂ እጩ አድርገው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ኢንግሪድ ቤንታኮርት በፋርክ አማፂያን የታገቱት ሳን ቪሰንቴ ዴል ካጉዋን በምትባል ከተማ የነበራቸውን የምርጫ ቅስቀሳ አጠናቀው ሲመለሱ መንገድ ላይ ነው። በኮሎምቢያ ጫካ ውስጥ በቆዩባቸው ስድስት ዓመታት ውስጥ በአጋቾቻቸው ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል። በፋርክ አማፂያን ውስጥ የነበሩ ሰርጎ ገብ የኮሎምቢያ ጦር አባላትም ተቀናጅተው ነው በአውሮፓውያኑ 2008 ያስለቀቋቸው። ከተለቀቁም በኋላ በርካታ አመታትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በፈረንሳይ ነው የኖሩት። የፋርክ አማጽያን ከ50 ዓመታት በላይ ከመንግሥት ጋር ባደረጉት የእርስ በርስ ጦርነት ከ200 ሺህ ሰዎች በላይ ተገድለዋል። ቡድኑ በአውሮፓውያኑ 2016 የሰላም ስምምነት ከማዕከላዊው መንግሥት ጋር ተፈራርመው የተወሰኑት ወደ ፓርላማ ሲገቡ የቀሩት ደግሞ በጦርነቱ ቀጥለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60034973 +health ኮሮናቫይረስ፡ 33 ሚሊዮን ፓውንድ ያሰባሰቡት የ100 አመቱ ሽማግሌ በኮቪድ-19 ሞቱ "በእንግሊዝ ለጤና ባለሙያዎች ያላቸውን ክብር ለመቸር 33 ሚሊዮን ፓውንድ በማሰባሰብ ከፍተኛ ስም ያተረፉት ካፕቴን ቶም ሙር በመቶ አመታቸው በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አልፏል። 33 ሚሊዮን ፓውንድ ለአገሪቱ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት ወይም ኤንኤችኤስ ማሰባሰብ የቻሉት የ100 አመቱ የዕድሜ ባለፀጋ ���ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ከመተንፈሻ እክል ጋር በተያያዘ ቤድፎርድ ወደተባለ ሆስፒታል ተወስደው ነበር። ልጃቸው፣ ሃና ኢንግራም ሙር በባለፉት ሳምንታት በሳንባ ምች ህመም ሲሰቃዩ እንደነበርና በዚህ ሳምንት በኮሮናቫይረስ እንደተያዙ ተናግራለች። ግለሰቡ የ2ኛው የዓለም ጦርነት ተዋጊ ሲሆኑ ከቤታቸው ጓሮ በሚገኘው ሜዳ 100 ዙር በመሮጥም ነው የእርዳታ ገንዘብ ያሰባሰቡት። ይህንንም ያደረጉት ከመቶኛ አመት ልደታቸው በፊት ነው። ልጆቻቸው ሃና ኢንግራም ሙርና ሉሲ ቲየክሴራ እንዳሉት ""ውድ አባታችን ካፕቴን ሰር ቶም ሙር መሞታቸውን በታላቅ ሃዘን ነው የምንናገረው"" ብለዋል። በመጨረሻው ሰዓትም ከአባታቸው ጎን በመሆናቸው ትልቅ ክብር እንደነበር ገልፀዋል። ""ለሰዓታት ያልህ ስለ ልጅነታችን፣ ስለ ውዷ እናታችን ስናወራ ነበር። ረዥም ሰዓት ሳቅን፣ አለቀስን። አባታችን በባለፈው አመት አስቦትና አልሞት የማያውቀው ነገር ተሳክቶለታል። ""ብለዋል አክለውም ""ምንም እንኳን ለአጭር ወቅት ቢሆን በብዙዎች ልቦና ዘንድ የማይረሳ ነገርን ጥሏል። ለኛ አስደናቂ አባት፣ አያት ነው፤ ሁልጊዜም ቢሆን በልባችን ይኖራል"" በማለት ኃዘናቸውን አጋርተዋል። የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ለአባታቸው ያደረጉላቸውን እንክብካቤ አድንቀዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55909539 +health ኮሮናቫይረስ : አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በመላው ዓለም ሊሰራጭ ይችላል ተባለ "አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በመላው ዓለም ሊሰራጭ ይችላል ተባለ። ኬንት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ በዓለም ላይ በስርጭቱ ቀዳሚው ሊሆን ይችላል ሲሉ የዩናይትድ ኪንግደም የዘረ መል ክትትል መርሃ ግብር ኃላፊ ገልጸዋል። ኃላፊው ፕሮፌሰር ሻሮን ፒኮክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አዲሱ ዝርያ ""በአገሪቱ የተሰራጨ"" ሲሆን ""በመላው ዓለም የመሰራጭ ዕድሎችም"" አሉት ብለዋል፡፡ በኬንት የተገኘው ዝርያ ከ50 በላይ በሆኑ አገራት ውስጥ ተሰራጭቶ ይገኛል። የኮሮናቫይረስ ዝርያ በደቡብ ምስራቅ እንግሊዝ በጎርጎሮሳዊያኑ መስከረም 2020 ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ ሲሆን፤ በቀጣይ ወራት በፍጥነት ተስፋፍቶ በጥር ወር በመላው ዩናይትድ ኪንግደም አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ምክንያት ሆኗል። ፕሮፌሰር ፒኮክ ""በእውነቱ ከሆነ እኛን በመጉዳት ላይ የሚገኘው በከፍተኛ ፍጥነት መተላለፉ ነው"" ብለዋል። ለኮሮናቫይረስ የተሠሩ ክትባቶች ቀደም ሲል ለነበረው የቫይረሱ ዙሪያ የተመረቱ ቢሆንም ሳይንቲስቶች አሁንም ቢሆን በአዲሱም ዝርያ ላይ ይሠራሉ ብለው ያምናሉ። ውጤታማነታቸውን ግን ጥሩ ላይሆን ይችላል። በዩናይትድ ኪንግደም ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀደላቸው ክትባቶች በአገሪቱ ውስጥ ባሉ የቫይረስ ዓይነቶች ላይ በጥሩ ሁኔታ የሚሠሩ ይመስላሉ ብለዋል ፕሮፌሰር ፒኮክ።" https://www.bbc.com/amharic/news-56027521 +business የአሜሪካ ኢኮኖሚ በኮሮናቫይረስ ሰበብ በ30 በመቶ ያሽቆለቁላል ተባለ "የአሜሪካ ኢኮኖሚ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከ20 እስከ 30 በመቶ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል የፌደራል መንግሥቱ ግምጃ ቤት ሊቀ መንበር ተናገሩ። ጄሮም ፓውል ለሲቢሲ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ እንዳመለከቱት የኢኮኖሚ መቀዛቀዙ በወራት ውስጥ የሚያበቃ ብቻ ሳይሆን እስከ ቀጣዩ የፈረንጆች ዓመትም ሊዘልቅ እንደሚችል ገልጸዋል። ምናልባትም የአገሪቱ ኢኮኖሚ ከወደቀበት ተነስቶ ወደነበረበት ለመመለስ ለወረርሽኙ ክትባት እስኪገኝ ድረስ መቆየት ሊያስፈልገው እንደሚችልም ጠቁመዋል። በዚህም ምክንያት የግምጃ ቤት ሊቀመንበሩ ፓውል ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ተጨማሪ የኢኮኖሚ ማነቃቂያና እርዳታ እንዲያጸድቁ ጥሪ አቅርበው ነበር። የኮሮናቫይረስ ባስከተለው ጫና ምክንያት ከመጋቢት ወር አጋማሽ ወዲህ ከ36 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን ሥራቸውን በማጣታቸው ምክንያት የመንግሥትን ድጋፍ ለማግኘት አመልክተዋል። ጄሮም ፓውል ጨምረውም ""የአሁኑ ወቅት ከባድ ችግር ያጋጠመን ጊዜ ነው። ዜጎች ያሉበትን ስቃይ በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል። ቢሆንም ግን ጊዜ ሊወስድ ይችላል እንጂ ኢኮኖሚው ማገገሙ አይቀርም"" በማለት እስከ ቀጣይ ዓመት ድረስ ችግሩ ሊቀጥል እንደሚችል አመልክተዋል። እስካሁን ያለው የሥራ አጦች ቁጥር እስከ 25 በመቶ ሊድረስ እንደሚችልና ተጎጂዎቹም ""ዝቅተኛ ክፍያ የሚያገኙ ሰዎች"" እንደሚሆኑና በተለይ ደግሞ ሴቶች በኢኮኖሚ ቀውሱ ክፉኛ ተጎድተዋል ብለዋል። ነገር ግን የአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ጤናማ በመሆኑና ወረርሽኙም ከኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውጪ ያጋጠመ ""ውጫዊ ክስተት"" በመሆኑ አሜሪካ የኢኮኖሚ ድቀት እንደማይገጥማት ተናግረዋል። ሊቀ መንበሩ አክለውም ባለፉት ሦስት ወራት ኢኮኖሚው እስከ 30 በመቶ ቢያሽቆቁልም፤ ወረርሽኙ ለሁለተኛ ዙር ተመልሶ ጉዳት ካላስከተለ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ ""በፍጥነት የማገገም ዕድል አለ"" ብለዋል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ የተመታችው አሜሪካ ከዓለም አገራት ሁሉ የላቀ ቁጥር ያለቸው ሰዎች በሽታው ከመያዛቸው በተጨማሪ ከፍተኛውን የሟቾች ቁጥር መዝግባለች። በአንዳንድ ግዛቶቿ በእንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ዕገደ ከመላላቱ ጋር ተያይዞ በሸታው ተመልሶ ለሁለተኛ ጊዜ ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል።" https://www.bbc.com/amharic/news-52703735 +health ኮሮናቫይረስ፡ ኩባ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማምረት የምታደርገው ጥረት ይሳካ ይሆን? "በኩባዋ ዋና ከተማ ሃቫና የሚገኘው ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት ምናልባት ከሌሎች የዓለማችን ማዕከላት አንጻር ሲታይ ያረጀና ጊዜ ያለፈበት ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በዚህ ማዕከል የሚሰራው የምርምር ሥራ እጅግ ዘመናዊ ነው። የአገሪቱ ከፍተኛ ተመራማሪዎች እረፍት አልባ ረጅም ፈረቃዎችን ጭምር በመስራት ለኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ መፍትሄ ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ነው። የክትባቱ ስም 'ሶቤሬና 2' የሚባል ሲሆን በኩባ ተመራማሪዎች ኩባ ውስጥ የተሰራ ነው። ይህ ክትባት በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፈቃደኞች ላይ ይሞከራል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ባለፉት ሳምንታት በተደረጉ ክሊኒካዊ ሙከራዎች በጣም አመርቂ የሚባል ውጤት የተመዘገበ ሲሆን ይህ አገሪቱ ክትባቱን ለማግኘት በምታደርገው ጥረት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የኢንስቲትይቱ ዳይሬክተር ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ ቤንኮሞ ገልጸዋል። በኩባ መንግሥት እቅድ መሰረት ክትባቱ ክሊኒካዊ ሙከራውን ከጨረሰ በኋላ በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ አካባቢ ለሁሉም ዜጎች መሰጠት ይጀመራል። ""የእኛ እቅድ በመጀመሪያ ሕዝባችንን መከተብ ነው'' ይላሉ ዶክተር ቪሴንቴ። ""ከሕዝባችን በኋላ ምናልባት ለሌሎች አገራት መላክ ልንጀምር እንችላለን። ከ2021 መጨረሻ በኋላ ምናልባት 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን አምርተን ሕዝባችን ሙሉ በሙሉ ለመከተብ እቅድ ይዘናል።"" ይህ ክትባት የአሜሪካም ሆነ የየትኛውም አገር እርዳታ አልተደረገለትም። ኩባ በባዮቴክኖሎጂ ከ30 ዓመታት በላይ ልምድ ያላት አገር እንደመሆኗ ይህ ምንም የሚገርም ነገር አይደለም። በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ የኩባ ሳይንቲስቶች ለማጅራት ገትር ቢ (ሚኒንጃይተስ) ክትባት ካመረቱ የመጀመሪያዎቹ ሲሆኑ የወቅቱ የአገሪቱ መሪ ፊደል ካስትሮ መሰል ሥራዎችን ለማበረታታት ነበር ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት እንዲቋቋም ያደረጉት። በአሜሪካ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የሚሰሩ መድኃኒቶች ወደ ኩባ እንዳይገቡ ሲደረግ አገሪቱ በራሷ መንገድ መድኃኒቶቹን ማምረት ትችላለች በማለት ፊደል ካስትሮ ይከራከሩ ነበር። ነገር ግን አሁን ባለው ቴክኖሎጂ እና ዘመናዊ አሰራር እንኳን ያለ ሌሎች አገራት ድጋፍና እርዳታ 100 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦችን አምርቶ ሕዝቡን መከተብ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ""ክትባቱን በማምረት ሂደቱ ላይ ግንኙነት የፈጠርነው ከአውሮፓ አገራትና እና ካናዳ ጋር ነው። ከጣልያን እና ፈረንሳይ የመጡ ተመራማሪዎችም በሂደቱ ላይ ይሳተፋሉ"" ብለዋል ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ። አክለውም ""በሚያሳዝን ሁኔታ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የአሜሪካ ተሳትፎ የለም። ምናልባት ወደፊት በመሰል ሂደቶች ላይ ትብብር ሊኖረን እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን"" ብለዋል። እንደ ፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን መሰል ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኩባ ለኮሮረናቫይረስ የሚሆነውን ክትባት በማግኘት የመጀመሪያዋ የላቲን አሜሪካ አገር እንደምትሆን ተስፋ ያደርጋሉ። ""ኩባ ክትባቱን እንደምታገኝ ተስፋ እናደርጋለን'' ይላሉ በኩባ የድርጅቱ ተወካይ ዶክተር ሆዜ ሞቫ። ''የሶብሬና 2 ክትባት ሁለተኛ ደረጃ ሙከራ ውጤትን ከሰማን በኋላ ሂደቱን በቅርበት ስንከታተለው ነበር። ካለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ ኩባ የክትባቱን ውጤታማነትና ደኅንነት ስትመረምር እንደነበርም እናውቃለን።'' በአሁኑ ጊዜ በክትባቱ ዙሪያ ያለው ጉጉት ትልቅ ነው። በመጀመሪያ አገሪቱ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው። ወረርሽኙ በጀመረበት የመጀመሪያዎቹ ወራት ውስጥ በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ የነበረ ሲሆን ከብራዚልና ሜክሲኮ ጋር ሲነጻጸር ግን ቁጥሩ ብዙም አስፈሪ አይደለም። ነገር ግን የአገሪቱን የጤና ሥርዓት በእጅጉ ፈትኖታል። ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ ዓመት አጋማሽ ላይ ኩባ የወረርሽኙን ስርጭት መግታት ችላ ነበር። በዋነኛነት አየር ማረፊያዎችን በመዝጋትና የማኅበረሰቡን እንቅስቃሴ በመገደብ ነበር ይህንን ማሳካት የቻለችው። ሐምሌ እና ነሐሴ ላይ በጣም ዝቅተኛ የሚባል ስርጭትና ሞት ነበር የተመዘገበው። የፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን ተወካዩ በአሁኑ ጊዜ ያለው የቫይረሱ ስርጭት መቆጣጠር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ አልደረሰም ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ኩባ ውስጥ በወረርሽኙ ምክንያት በርካታ እንቅስቃሴዎች በመገደባቸው በጣም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ መላሸቅ አጋጥሟታል። እንደውም ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ ከፍተኛው የኢኮኖሚ መድቀቅ ነው እየተባለ ነው። ክትባቱ በአገር ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ደግሞ ሕዝቡን ከመክተብ ባለፈ ከሽያጭ ሊገኝ የሚችለው ገቢ ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ሁኔታ ሊረዳው ይችላል ተብሎ ይታመናል። በተጨማሪም ከትባቱን ከሌሎች አገራት ማስመጣት ሊያስከትለው የሚችለውን ወጪ ይቀንሳል። ኮሮረናቫይረስን ተከትሎ በኩባ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ባለፈው ዓመት ብቻ ኢኮኖሚው 11 በመቶ ኪሳራ አጋጥሞታል። በተጨማሪም የምግብ ሱቆችና ሱፐር ማርኬቶች አካባቢ ከፍተኛ ሰልፍና ግፊያም ታይቷል። በዚህ ወቅት ሁሉም ህጻናት ከትምህርት ቤት ቀርተዋል፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች በእጅጉ ተቀዛቅዘዋል፣ የእንቅስቃሴ ገደቦችም ቢሆን የዜጎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ አስቸጋሪ አድርጎታል። ስለዚህ የክትባቱ ዜና በርካቶች በጉጉት እንዲጠብቁት አድርጓቸዋል። የዚህ ክትባት ውጤታማ መሆን የዜጎችን ጤንነት ከመጠበቅ ባለፈ ለጎረቤት አገራት ከሚደረገው ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ኢኮኖሚውን እንደሚያነቃቃው ይታመናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56088539 +politics ከ‘ትግራይን እከላከላለሁ’ እስከ ‘ናይሮቢን እቆጣጠራለሁ’ የሚሉት አወዛጋቢው ጄኔራል የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ እና የኡጋንዳ ጦር ከፍተኛ መኮንን የሆኑት ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ አነጋጋሪ የሆኑ አስተያየቶችን መስጠታቸውን ቀጥለዋል። የኡጋንዳ የምድር ጦር አዛዥ የሆኑት ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ አገራትንና መሪዎችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በመጻፍ ቅሬታን ሲፈጥሩ ቆይተዋል። በተለይ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነትን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሯቸው መልዕክቶች ምክንያት በኢትዮጵያውያን ዘንድ መነጋገሪያ ለመሆን በቅተዋል። ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ ከሁለት ቀናት በፊት በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ላይ፣ “. . . ትግራይን እከላከላለሁ” ብለው ካሰፈሩ ከሰዓታት በኋላ “ዳግማዊ ሚኒሊክ አያታችን ናቸው” በማለት ኢትዮጵያን የተመለከተ ሌላ ትዊት ለጥፈው ነበር። በአፍሪካ በሥልጣን ላይ ለረጅም ዓመታት በመቆየት ከሚጠቀሱት አንዱ የሆኑትን አባታቸውን ዩዌሪ ሙሴቬኒን በመተካት ቀጣይ የኡጋንዳ መሪ ሊሆኑ ይችላሉ የሚባሉት የጦር መሪ ሰኞ ዕለት በኬንያውያን ዘንድ መነጋገሪያ ሆነዋል። ጄኔራሉ ምንም ባልተፈጠረበት ድንገት ብድግ ብለው “እኔ እና ሠራዊቴ የኬንያን መዲና ናይሮቢ ለመያዝ ሁለት ሳምንታት ይበቃናል” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። ሌ/ጄኔራል ካይኒሩጋባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ስለ ኢትዮጵያ እና ኬንያ እያነሱ መጻፋቸው ከአገራቸው መንግሥት አቋም ጋር የሚያያዝ ስለመሆኑ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አነጋጋሪ በመሆን ትኩረትን ስበዋል። ይህንንም ተከትሎ የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማክሰኞ መስከረም 24/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ የጄኔራሉን የትዊተር መልዕክት በቀጥታ ሳይጠቅስ፣ ከጎረቤት ኬንያ ጋር ለሚኖር ሰላም እና ትብብር ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል። እሁድ መስከረም 22/2015 ዓ.ም. በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሳፈሩት ጽሑፍ፤ “ትግራይ ሁሌም በልቤ አለች! ትግራይን እንድወድ እና እንድከላከል ከፈጣሪዬ ከእየሱስ ክርስቶስ የመጣ ትዕዛዝ ነው” ብለዋል። በተመሳሳይ ዕለት ከሰዓታት በኋላ ደግሞ ጄኔራሉ ኢትዮጵያን በተመለከተ ባሰፈሩት ሌላኛው ጽሑፍ፤ “ዳግማዊ ሚኒሊክ አያታችን ናቸው። ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ አካል ናት። እንድትወድም አንፈቅድም። ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንወዳለን!” ሲሉ ጽፈዋል። የ48 ዓመቱ ጎልማሳ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያን የተመለከተ በተለይ ደግሞ ከትግራይ ጋር የተያያዙ አስተያየቶችን ሲሰጡ ነበር። ጄኔራሉ የኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት አንድ ዓመት በደፈነበት ጥቅምት 2014 ዓ.ም. ላይ የትግራይ ኃይሎችን ደግፈው ትዊት አድርገው ነበር። “የትግራይ መከላከያ ኃይሎች . . . የቆማችሁበትን ዓላማ እደግፋለሁ። የትግራይ እህቶቻችንን የደፈሩ እና ወንድሞቻችንን የገደሉ መቀጣት አለባቸው” ሲሉ ጽፈው ነበር። ይህን የሌ/ጀነራል ሙሆዚ ትዊት ተከትሎ የኡጋንዳ መንግሥት አስተያየቱ የጄኔራሉ እንጂ የጦሩን አቋም አይወክልም የሚል ማስተባበያን ሰጥቶ ነበር። በተጨማሪም ጄኔራሉ ከአገራቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ከጥቂት ወራት በፊት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋርም ተገናኝተው ነበር። የኡጋንዳ የምድር ጦር አዛዥ የሆኑት ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ የጎረቤት አገር ኬንያ መዲና ናይሮቢን በተመለከተ በትዊተር ገጻቸው ላይ የለጠፉት ሐሳብ ስላቅ ይሁን ጽኑ ፍላጎት ኬንያውያን ያስደሰተ አልነበረም። ጄኔራሉ “እኔ እና ሠራዊቴ ናይሮቢን ለመያዝ ሁለት ሳምንት ቢወስድ���ን ነው” ብለዋል። ቀጠል አድርገውም “ጦራችን ናይሮቢን ከቆጣጠረ በኋላ የት መኖር መጀመር አለብኝ? ዌስትላንድስ ወይስ ሪቨርሳይድ?” ሲሉ የናይሮቢ አካባቢዎችን በመጥቀስ ትዊት አድርገዋል። ይህ የጄኔራሉ ትዊት ግን ኬንያውያንን ያስቆጣ ሆኗል። አንዳንዶች ሙሴቪኒ የሰፋቸውን ሙሉ ልብስ ለብሰው የሚያሳይ ምስል በማያያዝ “ቅደሚያ የአባትህን ልብ ሰፊ ተቆጣጠር” በሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከሰኞ ጀምሮ ኬንያውያን በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የጄኔራሉን ጉዳይ በማንሳት ትችት እየሰነዘሩ ሲሆን፣ አንዳንዶችም ጄኔራሉ እንደሚባለው የአባታቸውን ሥልጣን የሚረከቡ ከሆነ ለአገራቸው ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ጽፈዋል። ሌሎች ደግሞ በኬንያ እና ኡጋንዳ መካከል ያለውን ዴሞክራሲ በማነጻጸር የሙሴቪኒ ቤተሰብ ኡጋንዳውያንን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ነፍገዋል ሲሉ ተችተዋል። ይህን የጄኔራሉን አስተያየት ተከትሎ የኬንያ መንግሥትም ሆነ የኡጋንዳ ባለሥልጣንት በይፋ ያሉት ነገር የለም። ሌ/ጄኔራል ካይኒሩጋባ ኬንያን በተመለከተ ሌላ ጸሁፋቸው ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ያለኝ ብቸኛው ችግር ለሦስተኛ ዙር አለመወዳደራቸው ነው ብሏል። በኬንያ ሕገ-መንግሥት መሠረት አንድ ፕሬዝዳንት አገር መምራት የሚችለው ለሁለት የሥልጣን ዘመን ብቻ ነው። በዚህ መሠረት ኡሁሩ ከሁለት ወራት በፊት በተካሄደው ምርጫ ሳይሳተፉ ሥልጣን አስረክበው መንበራቸውን ለቀዋል። ሌ/ጄኔራል ካይኒሩጋባ ግን “ከተወዳጁ ትልቁ ወንድሜ ጋር ያለኝ ብቸኛ ችግር ለሦስተኛ ዙር አለመወዳደሩ ነው። በቀላሉ ማሸነፍ እንችል ነበር” ሲሉ ጽፈዋል። የምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የምድር ጦር አዛዡ በሌላኛው አነጋገሪ ጽሑፋቸው ደግሞ ቀጣይዋን የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር የተመለከተ ነው። ባለፈው ሳምንት በተደረገ ምርጫ ፓርቲያቸው በማሸነፉ የጣሊያን መሪ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ሰፊ ግምት ለተሰጣቸው ሴት ፖለቲከኛ ጂዮርጂ ሜሎኒ ጥሎሽ የመስጠት ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል። “ለቀጣይዋ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ስንት ከብቶችን ልትሰጡ ትችላለችሁ?” ሲሉ ትዊተር ላይ የጠየቁት ጄኔራሉ፤ “አውሮፓውያን ለሚወዷቸው ሴቶች አበባ ይሰጣሉ፤ በአገሬ ባህል ግን ለምንወዳቸው ሴቶች የምንሰጠው ከብቶችን ነው” በማለት ባለ ግዙፍ ቀንድ ከብቶችን ምስል አያይዘው ትዊተር ላይ ለጥፈዋል። ቀደም ብሎ ደግሞ በኡጋንዳ የጣሊያን አምባሳደር የጥሎሽ ዋጋ እንዲደራደሩ ሽማግሌ አድርጌ መርጫለሁ ሲሉ ጽፈው ነበር። አነጋጋሪው ጄኔራል በኡጋንዳ ጦር ሠራዊት ውስጥ ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው ሲሆን፣ የሚሰጧቸው አስተያየቶችም መነጋገሪያ ከመሆን አልፈው ቁጣን እያስከተሉ ነው። ሌ/ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ በተለይ በትዊተር ላይ የሚያሰፍሯቸው አነጋጋሪ እና አወዛጋቢ ፖለቲካዊ አስተያየቶች፣ በርካታ ተከታዮችን እያፈራለቸው ነው። ከዚህ አንጻር ግባቸው መነጋገሪያ በመሆን በርካታ ተከታዮችን ማግኘት ነው የሚሉ ሰዎች አሉ። የኡጋንዳ መንግሥት ጄኔራሉ ትዊተር ላይ በሚያሰፍሯቸው መልዕክቶች ዙሪያ ብዙ ጊዜ ዝምታን የሚመርጥ ሲሆን፣ አንዳንድ ጊዜ ግን የጄኔራሉ ሐሳብ የአገሪቱ መንግሥት አቋም ሳይሆን የግለሰቡ አስተያየት ነው በማለት ያስተባብላል። አሁንም ኬንያውያን ከጄኔራሉ ሳይሆን የኡጋንዳ መንግሥት በይፋ የጄኔራሉን ጽሁፍ የሚያስተባብል ምላሽ እንዲሰጥ እንደሚፈልጉ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየጠየቁ የነበሩ ሲሆን ይፋዊ መግለጫም ወጥቷል። የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጄኔራሉን የትዊተር መልዕክት ሳይጠቅስ በተዘዋዋሪ የተሰነዘረው ሐሳብ የመንግሥት እንዳልሆነ ገልጿል። በዚህም የኡጋንዳ መንግሥት ከየትኛውም አገር ጋር የሚኖረው ግንኙነትን በተመለከተ ከማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚገኙ እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያዎች በኩል በሚተላለፉ መልዕክቶች አማካይነት አይሆኑም ብሏል። ጨምሮም ኡጋንዳ ከኬንያ መንግሥት እና ሕዝብ ጋር ላለው ግንኙነትን ከፍተኛ ዋጋ እንደምትሰጥና ይህም የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደምትፈልግ ገልጿል። ጄኔራሉ ግን በትዊተር ላይ ያሰፈሩት መልዕክት የቀሰቀሰውን ቁጣ ተከትሎ ማስተባበያ፣ ምላሽ ወይም ማብራሪያ ሳይሰጡ ሌሎች ጉዳዮችን በማንሳት ትዊት ማድረግ መቀጠላቸው በርካቶችን ግራ አጋብቷል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cz7derezj88o +politics ለፈረንሳይ ፕሬዝደንትነት ማክሮን እና ማሪን ሌ ፔን ለፍጻሜ ቀረቡ በፈረንሳይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተደረገ ነው፡፡ 12 ተፎካካሪዎች በቀረቡበት የመጀመርያ ድምጽ አሰጣጥ ሁለቱ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙት ዕጩዎች ተለይተዋል፡፡ ለ2ኛ ጊዜ ፈረንሳይን ለመምራት የሚወዳደሩት ኢማኑኤል ማክሮን ሁነኛ ተፎካካሪያቸውን ለይተዋል፡፡ የቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ማሪን ሌ ፔን የኢማኑኤል ማክሮን ቀንደኛ ተቀናቃኝ ሆነው ቀርበዋል፡፡ ሁለቱ እጩዎች ለፕሬዝዳንትነት እጩ ሆነው ሲቀርቡ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ቀኝ አክራሪዋ ማሪን ሌ ፔን ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ይህ ለ3ኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ በኋላ ከተሸነፉ ምናልባትም የፖለቲካ ሕይወታቸው መጨረሻ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ የትናንቱን የድምጽ አሰጣጥ ተከትሎ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙት ማክሮን፣ ‹‹በፍጹም እንዳትሳሳቱ፣ ምንም እርግጠኛ የሆነ ነገር የለም፡፡›› ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው በስሜት የተሞላ ንግግር አድርገዋል፡፡ በፈረንሳይ ትናንት በተደረገ የመጀመርያ ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማክሮን ከፍተኛውን ድምጽ ያገኙ ሲሆን ሌ ፔን 2ኛውን ከፍተኛ ድምጽ በማግኘታቸው ነው ወደ 2ኛ ዙር ምርጫ እየተኬደ ያለው፡፡ ትናንት በተደረገው ድምጽ አሰጣጥ 97 ከመቶ ድምጽ ቆጠራ ተጠናቋል፡፡ በዚህም መሠረት ከጠቅላላ ድምጽ ሰጪዎች 27.35% ለማክሮን ድምጻቸውን ሰጥተዋል፡፡ ስደተኛ-ጠል ናቸው የሚባሉት ቀኝ አክራሪ ፓርቲን የሚመሩት ማሪን ሌ ፔን 23.97% ድምጽ በማግኘት 2ኛ ሆነዋል፡፡ ግራ ዘመም ፓርቲን የሚመሩትና ስሜት የሚኮረኩር ንግግር በማድረግ የተዋጣላቸው ዣን ሉክ ሚሌቾን 21.7% ከመቶ ድምጽ በማግኘት 3ኛ ሆነዋል፡፡ ዣን ሉክ ፈረንሳዊያን በፍጹም ድምጻቸውን ለቀኝ አክራሪዋ ሌ ፔን እንዳይሰጡ አሳስበዋል፡፡ ትናንትና ለፕሬዝዳንትነት እጩ ሆነው የቀረቡት ማክሮንን ጨምሮ 12 ፖለቲከኞች ነበሩ፡፡ ሆኖም የድምጽ ሰጪውን 10 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ድምጽ ማግኘት የቻሉት ሦስቱ ፓርቲዎች ብቻ ናቸው፡፡ አሸናፊውን ለመለየት ማክሮን እና ማሪን ሌ ፔን ለፍጻሜ ቀርበዋል፡፡ ሌ ፔን እና ማክሮን ከወዲሁ ከፍተኛ የምረጡኝ ቅስቀሳ ውስጥ ገብተዋል፡፡ የቀኝ አክራሪዋ ላ ፔን ከማክሮን ደጋፊዎች ውጭ ያሉ ፈረንሳዊያን በሙሉ ድምጻቸውን ለሳቸው እንዲሰጡ ተማጽነዋል፡፡ ትንንሽ ድምጽ ያገኙ ፓርቲዎችና ደጋፊዎቻቸው ድጋፋቸውን ለማሪን ሌ ፔን ከሰጡ ማክሮን የማሸነፍ ዕድላቸው አጣብቂኝ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በፈረንሳይ ታሪክ በወጣትነት ዕድሜ ፕሬዝዳንትነትን የተቆናጠጡ መሪ ናቸው፡፡ ሥልጣን ሲረከቡ 39 ዓመታቸው ነበር፡፡ ለዚህኛው ምርጫ በቂ ቅስቀሳ እንዳላደረጉ የተነገረ ሲሆን ለምርጫው 8 ቀናት ሲቀሩት ብቻ ነው ሞቅ ወዳለ ቅስቀሳ የገቡት ተብሏል፡፡ ይህም የሆነው በዋናነት በዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ጉዳይ በመጠመዳቸው ነው ተብሏል፡፡ የሁለተኛ ዙር ድምጽ አሰጣጡ የሚደረገው ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚያዚያ 24 ነው፡፡ ማዳም ማሪን ሌ ፔን በፈረንሳይ ቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪነት ዘለግ ላለ ጊዜ የቆዩ ናቸው፡፡ ለመጤዎች በጎ አመለካከት የሌላቸው ሲሆን በአደባባይ ኢስላማዊ ሒጃብ እንዳይለበስ ሕግ እደነግጋለሁ ብለዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ፈረንሳይ ከአውሮጳ ኅብረት እንድትወጣ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ይፈልጋሉ፡፡ ወደ ፈረንሳይ የሚገቡ ስደተኞችን ቁጥር በእጅጉ ለመቀነስና ድንበርን ለመዝጋትም ፍላጎት አላቸው፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-61064285 +politics ፑቲን በዩክሬን ጦርነት ጣልቃ የሚገባ አገር ላይ መብረቃዊ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ዛቱ የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ጦርነት እጁን የሚያስገባ ማንኛውም አገር ላይ መብረቃዊ ጥቃት እንደሚፈጸምበት አስጠነቀቁ፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ አገራቸው ሩሲያ አቅምም ብቃትም አላት ብለዋል፡፡ ‹‹ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን›› ሲሉ ብዙዎችን ያሳሰበ ንግግር አድርገዋል፡፡ አንዳንድ ተንታኞች ፑቲን በዚህ ንግግራቸው ለመጠቆም የሞከሩት ባለስቲክ ሚሳኤልና የኑክሊየር መሣሪያን ነው በማለት ግምት ወስደዋል፡፡ ፑቲን ወረራውን በጀመሩ ማግስት ለጦር ሹማምንቶቻቸው የኑክሊየር መሣሪያ በተጠንቀቅ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡ ይህ የፑቲን መራር ንግግር የተሰማው ደግሞ ምዕራባዊያን ለዩክሬን እጅግ ውስብስብና ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመስጠት በተጠመዱበት ማግስት ነው፡፡ በተለይም ባለፉት ቀናት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ኦስቲን በኪየቭ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ጉብኝታቸውም ለዩክሬን ወደ 700 ሚሊዮን ዶላር የተጠጋ እርዳታን ይፋ አድርገዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ ደግሞ የምዕራብ አገራት በጀርመን ተሰብስበው ለዩክሬን የሚደረገውን የጦር መሣሪያ እርዳታ እንዴት ከዚህም በላቀ መልኩ ማሳደግ ይቻላል በሚል ተወያይተው ነበር፡፡ በጦርነት ጣልቃ ያለመግባት ጥብቅ ፖሊሲን ትከተል የነበረችው ጀርመን ሳይቀር ያልተጠበቀ የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ ለዩክሬን 50 የአየር መቃወሚያ ታንኮችን እሰጣለሁ ብላለች፡፡ በአሁን ጊዜ ጦርነቱ ተፋፍሞ የቀጠለ ቢሆንም የምዕራብ አገር ተንታኞች ሩሲያ በምሥራቅ ዩክሬን ልታደርገው ያሰበችው መጠነ ሰፊ ጥቃት እንደተስተጓጎለባት እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ ሩሲያ ከዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ከበባ ወደ ኋላ እንድታፈገፍግ ከተደረገች በኋላ ትኩረቷን ወደ ደቡብ ምሥራቅ ዩክሬን በተለይም ዶንባስ በሚባለው ክልል ለማድረግ ወስና ነበር፡፡ ይሁንና በምሥራቅ ግንባር ሩሲያ ያሰበችውን ግስጋሴ አላሳካችም፡፡ ከዩክሬናዊያን ያልጠበቀችው መከላከል ገጥሟታል፡፡በርካታ ወታደሮችም ተገድለውባታል፡፡ ይህ በአንዲህ እያለ የአውሮጳ ኅብረት ሩሲያ ለፖላንድና ቡልጋሪያ ጋዝ አልሸጥም ማለቷን አውግዟል፡፡ የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሊየን እንዳሉት ይህ የሚያሳየው ሩሲያ የማታስተማምን የንግድ አቅራቢ መሆኗን ነው፡፡ ሩሲያ በበኩሏ ይህን እርምጃ የወሰድኩት ወዳጅ ያልሆኑ አገራት ለማቀርብላቸው ጋዝ ክፍያቸውን በሩብል እንዲያደርጉ ያሳለፍኩትን ውሳኔ ፖላንድና ቡልጋሪያ ስላላከበሩት ነው ብላለች፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-61245799 +sports እግር ኳስ፡ የአፍሪካ ዋንጫ ካይሮ ውስጥ ጠፋ የአፍሪካ ዋንጫን ጨምሮ በርካታ ዋንጫዎች ካይሮ ከሚገኘው ከግብጽ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና መስሪያ ቤት መጥፋታቸው ተነገረ። የግብጽ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም በጉዳዩ ላይ ይፋዊ ምርመራ ጀምሪያለሁ ብሏል። ግብጽ እአአ 2010 ተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ መሆኗን ተከትሎ ነበር ዋንጫው ግብጽ እንድትወስደው ���ተደረገው። ግብጽ የአፍሪካ ዋንጫን ለተከታታይ ሶስት ጊዜ ያሸነፈችው በ2006፣ 2008 እና 2010 በተደረጉት ውድድሮች ነበር። አርብ ዕለት የግብጽ እግር ኳን ፌደሬሽን በርካታ ዋንጫዎች መጥፋታቸውን ተከትሎ ይፋዊ ምረመራ መጀመሩን አስታውቋል። ''ፌደሬሽኑ ዋና መስሪይ ቤቱን በማደስና ወደ ሙዚየምነት ለመቀየር እየተሯሯጠ ባለበት ወቅት የዋንጫዎቹ መጥፋት አመራሩን በጣም አስደንግጦታል'' ብሏል ፌደሬሽኑ ባወጣው መግለጫ። የቀድሞው የግብጽ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አህመድ ሾቢር በበኩላቸው ከጠፉት ዋንጫዎች መካከል የ2010ሩ ዋንጫም እንደሚገኝበት ተናግረዋል። በአውሮፓውያኑ 2013 የግብጽ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ጥቃት ከተፈጸመበት በኋላ ዋንጫዎቹ ወደ ሌላ ማቆያ ስፍራ እንዲወሰዱ ተደርጎ ነበር። ነገር ግን የፌደሬሽኑ ባለስልጣናት የመስሪያ ቤቱን መግቢያና መውጫ በሮች በማስተካከል ጎብኚዎች ዋንጫዎቹን እንዲጎበኙ ለማድረግ እድሳት በሚሰሩበት ወቅት ነው ዋንጫዎቹ መጥፋታቸውን ይተነገረው። በአፍሪካ አግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ወይንም ካፍ ሕግ መሰረት አንዲት አገር ዋንጫውን ለሶስት ተከታታይ ጊዜ ካሸነፈች ዋንጫውን ማስቀረት ትችላለች። በዚህም ሕግ መሰረት ነው ግብጽ ዋንጫውን በአገሯ ያስቀረችው። በአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ለሶስት ተከታታይ ጊዜ ማሸነፍ የቻለችው ሌላኛዋ አገር ጋና ስትሆን ሶስተኛውን ዋንጫ ያነሳችው በአውሮፓውያኑ 1978 ላይ ነበር። https://www.bbc.com/amharic/news-54039405 +sports አርጀንቲና፣ ቺሊ፣ ኡራጓይና ፓራጓይ የዓለም ዋንጫን በጥምረት ለማዘጋጀት ጠየቁ "አርጀንቲና፣ ቺሊ፣ ኡራጓይ እና ፓራጓይ በአውሮፓውያኑ 2030 ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫን በጋራ ለማዘጋጀት ጥያቄ አቀረቡ። የአለም ዋንጫ የመጀመሪያውን ውድድር በአውሮፓውያኑ 1930 ያስተናገደችው ኡራጓይ የአለም ዋንጫ መቶኛ አመቱን ሲያከብር ወደተጀመረባት አገር ማምጣት እንደምትፈልግ አስታውቃለች። የደቡብ አሜሪካዎቹ አገራት የአለም ዋንጫን በጋራ ለማዘጋጅት መጠየቃቸውንም አስመልክቶ “ ይህ የአንድ አህጉር ህልም ነው” በማለት የደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ኮንሜቦል) ፕሬዝዳንት አሌሃንድሮ ዶሚኒጌዝ ተናግረዋል። ከደቡብ አሜሪካዎቹ አገራት በተጨማሪ የአውሮፓ ሃገራቱ ስፔን እና ፖርቹጋል በጋራ ለማዘጋጀት ውድድሩ ላይ ቀርበዋል። ሞንቴቪዲዮ ሴንቴናሪዮ ስታዲየም በተደረገው የመጀመሪያው የአለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ኡራጓይ አርጀንቲናን ያሸነፈች ሲሆን ፕሬዚዳንት አሌሃንድሮ ዶሚኒጌዝ በዚህ ስታዲየም ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። “ተጨማሪ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ይኖራሉ ፣ ነገር ግን የዓለም ዋንጫ ጨዋታ 100 አመቱን የሚያከብረው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ስለዚህ ወደተጀመረበት ወደ ቤቱ መምጣት አለበት” ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል። ቺሊ የዓለም ዋንጫን በአውሮፖውያኑ 1962 ስታስተናግድ፣ አርጀንቲና ደግሞ በአውሮፓውያኑ 1978 አዘጋጅታለች። ""የአለም ዋንጫ ውድድር ከ100 አመት በኋላ በተጀመረበት ቦታ መካሄዱ ትክክለኛ ነው"" በማለት የኡራጓይ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ኢግናሲዮ አሎንሶ ተናግረዋል። የ2022 የአለም ዋንጫ በኳታር የሚካሄድ ሲሆን ካናዳ፣ሜክሲኮ እና አሜሪካ የ2026 የጋራ አስተናጋጅ ይሆናሉ። ፊፋ የ2030 አስተናጋጅን ከሁለት አመት በኋላ፣ በ2024 ለመምረጥ እቅድ ይዟል። የዩናይትድ ኪንግደም እና የአየርላንድ ሪፐብሊክ የእግር ኳስ ማህበራት ለ2030ው የአለም ዋንጫ አስተናጋጅነት ላለመወዳደር እና በምትኩ ዩሮ 2028ን በጋራ ለማዘጋጀት በሚደረገው ጥረት ላይ ለማተኮር ተስማምተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cw9753j3191o +politics ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ሆኑ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን የቀረቡ አስራ አንድ ዕጩዎችን ሲሾም፣ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው ተሰየሙ። ምክር ቤቱ ዛሬ ሰኞ የካቲት 14/2014 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው በአፈ ጉባኤው ታገሰ ጫፎ በቀረቧቸው 11 ዕጩ ተሿሚዎች ላይ ድምጽ ተሰጥቶ ሹመታቸው ጸድቋል። ከአስራ አንዱ የኮሚሽነሮች መካከል በሰብሳቢነት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ሲሾሙ፣ ወይዘሮ ሂሩት ገብረሥላሴ ደግሞ የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ ሆነዋል። ከምክር ቤቱ አባላት 335 አባላት በተገኙበት በተሰጠው ድምጽ፣ አምስቱ ድምጸ ታዕቅቦ ያደረጉ ሲሆን ቀሪዎቹ እንደራሴዎች ሹመቱን ደግፈው አጽድቀውታል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል ሂደትን የሚመራና የሚያስተባብር አካል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካይነት ለማቋቋም ጥቆማ መካሄዱ ይታወሳል። ከጥቂት ወራት በፊት ለሕዝብ በቀረበ ጥሪ መሠረት 632 ዕጩዎች ለኮሚሽኑ አባልነት በተለያዩ ወገኖች ተጠቁመው ከእነዚህ መካከልም ኮሚሽኑን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ መስፈርቶች መሠረት 42ቱ ተለይተው ኅብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ዝርዝራቸው ይፋ መድረጉ ይታወሳል። ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኮሚሽነርነት ከቀረቡት ከ42ቱ ዕጩ ተጠቋሚዎች መካከል መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ አሟልተዋል የተባሉት ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ተሹመዋል። በዚህ መሠረትም፦ 1. ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ 2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረሥላሴ 3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ 4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሐመድ 5. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ 6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ 7. አምባሳደር መሐሙድ ድሪር 8. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድኅን 9. አቶ ዘገየ አስፋው 10. አቶ መላኩ ወልደማሪያም 11. አቶ ሙሉጌታ አጎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስራ አንዱን ኮሚሽነሮች ከመሰየሙ በፊት ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የተጠቆሙትን የ42ቱን ግለሰቦች ዝርዝር ከአጭር የትምህርትና የሥራ መግለጫ ጋር በድረ ገጹ ላይ ይፋ አድርጎ ሕዝቡም አስተያየት እንዲሰጥባቸው ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ከዚህ ሂደት በኋላም በተጠቋሚ ዕጩዎቹ ላይ በተዘጋጀው መስፈርት መሠረት ከሕዝብ የሚቀርበው አስተያየት ተገምግሞ የመጨረሻዎቹ 11 ዕጩ ኮሚሽነሮች ተለይተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ እንዲሾሙ አድርጓል። ኮሚሽኑ በአገሪቱ ለዘመናት የቆዩ ናቸው በተባሉ የተለያዩ አወዛጋቢና ጉዳዮች ላይ የሚመለከታቸው ወገኖችንና ኃይሎችን በማቀራረብ ውይይት ተደርጓ መግባባት ላይ እንዲደረስ ለማድረግ የሚያስችሉ ምክክሮችን ይመራል ተብሎ ይጠበቃል። https://www.bbc.com/amharic/news-60461921 +sports ከወሳኝ የምድብ ጨዋታቸው በፊት ኢራን በአሜሪካ ላይ ለፊፋ ክስ አቀረበች የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአሜሪካን ቡድን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ ካወጣው የኢራን ሰንደቅ ዓላማ ጋር በተያያዘ ለፊፋ ክስ አቀረበ። የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ለዓለም አቀፉ የእግር ኳስ የበላይ አካል አቤቱታ ያረበው የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የኢራን ብሎ ያወጣው ሰንደቅ ዓላማ እስላማዊ ሪፐብሊኳን የሚወክለውን አርማ አንስቶታል የሚል ነው። ኢራን እና አሜሪካ ነገ ማክሰኞ ከሚኖራቸው የዓለም ዋንጫ የምድብ ግጥሚያ በፊት፣ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን በትዊተር፣ በፌስቡክ እና በኢንስታ ግራም ላይ ከለጠፈው የኢራን ባንዲራ ላይ የአገሪቱ መለያ አርማ አልተካተተም። አሜሪካ ለዚህ ክስ በሰጠችው ምላሽ በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄዱ ካሉት ፀረ መንግሥት ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ “በኢራን መሠረታዊ መብቶች እንዲከበሩ እየታገሉ ላሉት ሴቶች ድጋፈችንን ለመግለጽ” የአገሪቱን ይፋዊ ሰንደቅ ዓላማ ላለመጠቀም መወሰኑን ገልጻለች። በኢራን ውስጥ ማህሳ አሚኒ የተባለች የ22 ዓመት ወጣት ሂጃብ በአግባቡ አልለበሰችም በሚል በአገሪቱ የሥነ ምግባር ፖሊሶች ተይዛ ከታሰረች በኋላ መሞቷን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። “ሙያዊነት በጎደለው ተግባር፣ የአሜሪካ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢንስታግራም ገጽ በሰንደቅ ዓላማው ላይ ያለውን የአላህ ምልክትን አስወግዶታል” ሲል የኢራን መንግሥት ዜና ወኪል ኢርና ገልጸወል። ይህንንም ተከትሎ “የኢራን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የእግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪው አካል ፊፋ ለአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ኢሜይል ልኳል።” በኋላ ላይ ግን አንድ የአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ እንዳሉት፣ ቅሬታ የቀረበበት የሰንደቅ ዓላማ ምስል ከማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ እንዲነሱ መደረጋቸውንና በምትካቸውም ትክክለኛው የኢራን ሰንደቅ ዓላማ እንዲወጣ መደረጉን ገልጸዋል። ነገር ግን “አሁንም የኢራን ሴቶችን እንደግፋለን” ብለዋል። ኢራን አሜሪካንን እና ሌሎች ባላንጣዎቿን በአገሯ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ በማባባስ የምትከስ ሲሆን፣ የኢራን መንግሥት በተቃዋሚዎች ላይ እየወሰደ ካለው እርምጃ ጋር ተያይዞ አሜሪካ በአገሪቱ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው። በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ላይ በምድብ ለ ከእንግሊዝ፣ ከአሜሪካ እና ከዌልስ ጋር የተደለደለችው ኢራን ሦስት ነጥብ ይዛ ከእንግሊዝ በመከተል በምድቡ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በእግሊዝ 6 ለ 2 ተሸንፋ ዌልስን 2 ለ 0 ያሸነፈችው ኢራን የምድቡ ወሳኝ ጨዋታዋን ነገ ማክሰኞ ኅዳር 20/2015 ዓ.ም. ከአሜሪካ ጋር ታደርጋለች። ኢራን ታካሂደዋለች በሚባለው የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ግንባታ ፕሮጀክት የተነሳ ለዓመታት እየተወዛገበቻት ከምትገኘው ከአሜሪካ ጋር በአንድ ምድብ ተደልድለው ከጨዋታቸው ቀደም ብሎ ከሰንደቅ ዓላማዋ ጋር በተያያዘ ቅሬታዋን አቅርባለች። አሜሪካ እና ኢራን በአይነ ቁራኛ የሚጠባበቁ ባላንጣዎች ሲሆኑ፣ የዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን ካቋረጡ ከአርባ ዓመታት በላይ ሆኗቸዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n6exxx0e9o +health ኮሮናቫይረስ፡ የአስትራዜንካን ክትባት ተጠቀሙ- የዓለም ጤና ድርጅት "በርካታ የአውሮፓ ሃገራት የኮሮናቫይረስ መከላከያ የሆነውን አስትራዜንካ ክትባት ማገዳቸውን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል። ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያንና ስፔይንን ጨምሮ ሌሎች አገራት የኦክስፎርዱ አስትራዜንካ ክትባት ደም መርጋት በተያያዘ ችግር አለበት በሚል ክትባቱ እንዳይሰጥ አግደውታል። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ደም መርጋት ስለማስከተሉ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ይላል። የድርጅቱ የክትባት ደህንነት ልሂቃንም በዛሬው ዕለት ተሰብስበው ስለ ክትባቱ ይመክራሉ ተብሏል። የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲም እንዲሁ ስለ ክትባቱ በዛሬው ዕለት የሚወያዩ ሲሆን በያዝነው ሃሙስም የደረሱበትን ማጠቃለያ ለህዝብ ያሳውቃሉ ተብሏል። ሆኖም ኤጀንሲው ክትባቱን ተጠቀሙ ብሏል። በአውሮፓ ክትባቱን ከተከተቡ በኋላ የደም መርጋት ችግር ያጋጠማቸው ሰዎች አሉ ብሏል። ነገር ግን ባለሙያዎቹ እንደሚሉት በአጠቃላይ ከህዝብ ብዛቱ ጋር ሲነፃፀር የደም መርጋት ያጋጠማቸው ሰዎች ድንገተኛ መጨመር አላሳየም ይላሉ ። በአውሮፓ ህብረት አባላት አገራትና ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 17 ሚሊዮን ሰዎች የአስትራዜንካ ክትባትን መከተባቸውና ከባለፈው ���ምንት ጀምሮ 40ዎቹ የደም መርጋት ችግር እንዳጋጠማቸው አስትራዜንካ አስታውቋል። እየተወሰዱ ያሉ ጥንቃቄዎች ይህንንም ተከትሎ የጀርመን ጤና ሚኒስቴር በያዝነው ሳምንት ሰኞ ዕለት አስትራዜንካ ክትባት መስጠት በአስቸኳይ እንዲቆም ትዕዛዝ አስተላልፏል። ክትባቱ የአዕምሮ ደም መርጋት ወይም ሴሬብራል ቬይን ቶርምቦሲስ ችግር ጋር መገናኘቱን አይተናል ብለዋል። የጤና ሚኒስትሩ ጄንስ ስፋን እንዳሉት ውሳኔ ""ፖለቲካዊ"" እንዳልሆነ ነው። ""ሁላችንም ቢሆን ይህ ውሳኔ ሊያስከትለው የሚችለውን ጉዳት እንረዳለን። በቀላሉም የደረስንበት አይደለም"" ብለዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እንዲሁ የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ ውሳኔውን እስኪያሳውቅ ድረስ አገራቸው ክትባቱን ታግዳለች ብለዋል። ""ቀለል ያለ መመሪያ ነው ያለን፤ ሳይንስንና በዘርፉ ላይ ዕውቀት ያላቸውን የጤና ባለስልጣናት ምክር ነው የምንከተለው፤ ይህም የአውሮፓ ስትራቴጂ ምን መምሰል አለበት የሚለውን የሚጠቁም ይሆናል"" ብለዋል። የጣልያን መድኃኒት ኤጀንሲም እንዲሁ የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ የሚደርስበትን ማጠቃለያ እጠብቃለሁ በማለት አግዳዋለች። የስፔን ጤና ሚኒስትር ካሮሊና ዳሪያስ በበኩላቸው ክትባቱ ለመጪው ሁለት ሳምንት ይታገዳል ብለዋል። አየርላንድ፣ ፖርቹጋል፣ዴንማርክ፣ ኖርዌይ፣ ቡልጋሪያ፣ አይስላንድ፣ ስሎቬኒያ ክትባቱን በጊዜያዊነት ያገዱ ሲሆን ዲሞክራቲክ ኮንጎና ኢንዶኔዥያ የክትባት መስጪያ ጊዜያቸውን አራዝመውታል። ኦስትሪያን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ አገራት ለጥንቃቄ ሲሊ ቢያግዱትም ቤልጂየም፣ ፖላንድና ቼክ ሪፐብሊክ ክትባቱን እየሰጡ ነው። የቤልጂየም ጤና ሚኒስትር ፍራንክ ቫንደንብራውኬ እንዳስታወቁት ቤልጂየም ካላት ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ቁጥርን በማየት ክትባቱን አለመስጠት አትችልም ብለዋል። የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በበኩላቸው አስትራዜንካን ጨምሮ በአገሪቱ እየተሰጡ ያሉ ክትባቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን የጤና ባለስልጣናቱ ነግረውኛል ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56411232 +sports ቅርጫት ኳስ ፡ የኦባማ እና የጆርዳን የቅርጫት ኳስ መለያዎች በከፍተኛ ገንዘብ በጨረታ ተሸጡ በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማና በታዋቂው የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ኮከብ ማይክል ጆርዳን የተለበሱ ሁለት የቅርጫት ኳስ መለያዎች አርብ ዕለት ሎስ አንጀለስ ከተማ ውስጥ በተካሄደ ጨረታ ክብረ ወሰን ነው በተባለ ከፍተኛ ገንዘብ ተሸጡ። ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ማይክል ጆርዳን በ1984 (እአአ) ለቺካጎ ቡልስ ቡድን ለመጫወት በፈረመበት ጊዜ የለበሰው ባለ 23 ቁጥር መለያ ለጨረታ ቀርቦ 320 ሺህ ዶላር ተሽጧል። ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ለትምህርት ቤታቸው ፑናሁ ቡድን በተጫወቱበት ጊዜ ለብሰውት የነበረው መለያ ደግሞ በ192 ሺህ ዶላር ሲሸጥ፤ ይህም በጨረታ ከተሸጡ የተማሪዎች መለያ ከፍተኛውን ዋጋ አውጥቷል። ባለፈው ዓመት በተካሄደ ጨረታ ኦባማ ተማሪ ሳሉ ለብሰውት የነበረ ሌላ የቅርጫት ኳስ መለያ በ120 ሺህ ዶላር ተሽጦ ነበር። በከፍተኛ ዋጋ የተሸጠው የኦባማ መለያ የትምህርት ቤታቸው ቡድን በ1979 (እአአ) የሃዋይ የቅርጫት ኳስ ውድድርን ባሸነፈበት ጊዜ ለብሰውት የነበረው ባለ 23 ቁጥር መለያ ነው። የቀድሞው ፕሬዝደንት ለቅርጫት ኳስ ስፖርት ከፍተኛ ፍቅር ያላቸው ሲሆን፤ በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፋቸው ላይ የተፎካካሪ ቡድን አባላት ወላጆች ተገቢ ያልሆነ የበላይነትን እንዲያገኙ አድርገዋል በሚል ቅሬታ በማሰማታቸው ልጃቸው ሳሻ የምትጫወትበትን የቅርጫት ኳስ ቡድን ማሰልጠን እንደተዉ ጽፈዋል። የመጀመሪያው ቢሊየነር ስፖርተኛ የሆ��ው ኮከቡ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ጆርዳን ቡድኑ ቺካጎ ቡልስ በአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ውድድር የበላይ ሆኖ ስድስት ጊዜ አሸናፊ ለመሆን አስችሎታል። የጆርዳን መለያዎች በተለያዩ ጊዜያት በጨረታ የተሸጡ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት ከተሸጡ 23 ቁጥር መለያዎች ከፍተኛው 288,000 ዶላር ነበር። https://www.bbc.com/amharic/news-55156386 +health ኮሮናቫይረስ፡ በፈረንሳይ ከተሞች የሰዓት እላፊ ታወጀ የፈረንሳይ መዲና ፓሪስን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የሰዓት እላፊ ታወጀ። የሰዓት እላፊ የታወጀው እየጨመረ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ነው። ፈረንሳይ ከአውሮፓ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ከሆኑባቸው አገራት መካከል አንዷ ናት። የሰዓት እላፊ በታወጀባቸው ከተሞች የሚኖሩ ዜጎች ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ከቤት መውጣት አይችሉም። የሰዓት እላፊው ከታወጀባቸው ከተሞች መካከል ፓሪስ፣ ማርሴል፣ ሊዮን እና ሊል ይገኙበታል። 20 ሚሊዮን ፈረንሳውያን የሰዓት እላፊው አዋጅ ይተገበርባቸዋል። የፈረንሳይ መንግሥት የሰዓት እላፊ አዋጁ መተግበሩን የሚያረጋግጡ 12ሺህ የፖሊስ አባላት እንደሚያሰማራ አስታውቋል። ከምሽቱ 3 ሰዓት በፊት ምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ካፊቴሪያዎች እና ሲኒማ ቤቶች መዘጋት ይኖርባቸዋል። የሰዓት እላፊውን ተላልፎ የሚገኝ ሰው 135 ዩሮ የሚቀጣ ሲሆን፤ ዳግም ተላልፎ የተገኘ ደግሞ የስድስት ወራት እስር እና የ3ሺህ 700 ዩሮ ቅጣት ይጠብቀዋል። እንደ ሰርግ ያሉ ማህበራዊ ሰብስቦች ክልክል ናቸው። በፈረንሳይ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ከ32ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ኮሮናቫይረስ በሌሎች የአውሮፓ አገራት የስፔን መንግሥት በማድሪድ እና አካባቢዋ ለ15 ቀናት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። 7ሺህ ፖሊስ አባላት አዋጁን ያስፈጽማሉ። መሠረታዊ ላልሆኑ ጉዳዮች ከማድሪድ መውጣትም ሆነ መግባት ክልክል ነው። ሆቴሎች እና ምግብ ቤቶች መያዝ ከሚችሉት አቅማቸው ግማሹን ብቻ ነው ማስተናገድ የሚችሉት። በኔዘርላንድስ የቫይረሱ ስርጭት ዳግም እያገረሸ ይገኛል። በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍልም በከፊል የእንቅስቃሴ ገደቦች እየተጣሉ ይገኛሉ። በአምስተርዳም መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች እየተዘጉ ነው። በጀርመንም በተመሳሳይ የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ ይገኛል። በቀን ከ7ሺህ በላይ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እየተመዘገቡ ይገኛል። ጀርመን አንዳንድ ጎረቤት አገራትን የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶባቸዋል ስትል አውጃለች። ከእነዚህም መካከል ፈረንሳይ እና ኔዘርላንድስ ተጠቃሽ ናቸው። ከእነዚህ አገራት ወደ ጀርመን የሚገባ ተጓዥ ራሱን ለይቶ የማቆየት ግዴታ ይኖርበታል። አየርላንድ በበኩሏ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የተለያዩ ገደቦችን ከጣለች አራት ሳምንታት አልፈዋታል። በመኖሪያ ቤት ሄዶ ወዳጅ ዘመድ መጠየቅ ከተከለከለ ሰነባብቷል። https://www.bbc.com/amharic/news-54581080 +business የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ከፍተኛ መጠን ያለው የስንዴና ዘይት ግዢ መፈጸሙ ተገለጸ በኢትዮጵያ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴና 12.5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። ግዢው የተፈጸመው በጥቅምትና ኅዳር ወራት ሲሆን ከተገዛው 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኩንታል ስንዴ ወደ አገር ውስጥ መግባቱም ተገልጿል። የተቀረውም ስንዴ በተቻለ ፍጥነት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ የስንዴ ዋጋንም ከፍ እንዳይል የራሱ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብሏል ገንዘብ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ዛሬ ታኅሣሥ 26/2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ። ግዢ የተፈጸመበት 12.5 ሚሊ��ን ሊትር ዘይት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆኑንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል። ከፍተኛ መጠን ያለው ስንዴና ዘይት ግዢ መፈጸሙ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠርና የገበያ ዋጋን በማረጋጋት ረገድ ፋይዳ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን የተረጋጋ ማክሮ ምጣኔ ሀብት ከማስፈን አንፃርም ሚና ይጫወታል ተብሏል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት የመቶ ቀን እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በተካሄደበት ወቅት ነውም ይህንን የገለጸው። በተጨማሪም ዘይትና ዱቄት አስመጪዎች በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ እንዲያስገቡ በመደረጉ የሸቀጦች ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል አስችሏልም ተብሏል። በሰሜኑ ጦርነትና በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት የዋጋ ግሽበት አስከትሎባታል በተባለችው ኢትዮጵያ በተወሰነ መልኩ መቀነስም አሳይቷል ተብሏል። በያዝነው ዓመት ጥቅምት ወር 34.2 በመቶ የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በኅዳር ወር ወደ 33.0 በመቶ ዝቅ ብሏል። በተጨማሪም በ2014 በኅዳር ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት ከጥቅምት ወር ጋር ሲነጻጸር በ1.8 በመቶ የቀነሰ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት 1.0 ከመቶ የጨመረ መሆኑን መረጃው ጠቁሟል። https://www.bbc.com/amharic/news-59868390 +politics የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብታዊ እመርታ ስጋት ላይ የጣለው ጦርነት "ባለፉት አስር ወራት የተደረገው ጦርነት ኢትዮጵያን ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ ውስጥ ከቷታል። በሺዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋል፤ ሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል እንዲሁም ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው በርካቶች ናቸው። ጦርነቱ በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ በሆነችው ኢትዮጵያ እያደረሰው ያለው ጉዳት ይህ ብቻ አይደለም። ከፍተኛ የሆነ ምጣኔ ሀብታዊ ወጪን አስከትሏል፤ ይህንንም ለመጠገን ዓመታት ሊወስድ ይችላል። በመዲናዋ አዲስ አበባ ነዋሪ የሆነችውና ሙሉ ስሟ እንዳይጠቀስ የጠየቀችው የ26 ዓመቷ ትዕግስት ወርሃዊ ወጪዋ በሁለት ምክንያቶች በእጥፍ ጨምሯል ትላለች። እነዚህም በጥቅምት ወር ወር በሠሜናዊ ትግራይ ክልል የተቀሰቀሰው ጦርነት እና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ናቸው። ""ከኮቪድ-19 እና ከግጭቱ በፊት መሠረታዊ ሸቀጦችን ለመሸመት በየወሩ አንድ ሺህ ብር አወጣ ነበር። በአሁኑ ወቅት ግን ይህ ወጪ ተመንድጎ ሁለት ሺህ ብር ሆኗል"" ትላለች። አክላም ""አሁን በርካታ ነገሮች ዋጋቸው የማይቀመስ ሆኗል ለምሳሌ - ስልኮች፣ ምግብ እና አልባሳት።"" ይፋዊ የሆነውን ስታቲስቲክስ በምንመለከትበትም ወቅት የመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ዋጋ በእርግጥም በኢትዮጵያ ጨምሯል። በዚህም ከአንድ ዓመት በፊት በሐምሌ ወር የነበረውና የዘንድሮው ዋጋ ሲነፃፀር በአማካይ ሩብ ያህል ውድ ሆኗል። ትግስት ቤተሰቦቿን ለመደገፍ በትልቅ የገበያ መደብር (ሱፐርማርኬት) ውስጥ በገንዘብ ተቀባይነት ተቀጥራ ትሰራለች። ወንድሟ የቤት ኪራዩን የሚሸፍን ሲሆን የምግቡ ወጪ ደግሞ የእሷ ኃላፊነት ነው። ""የዶላር ምንዛሪ ጥሩ አይደለም ለምሳሌ ባለፈው ዓመት 1 ዶላር በ35 ብር ሲመነዘር የነበረ ሲሆን በአሁ ወቅት ግን የአንድ ዶላር ምንዛሬ ወደ 45 ብር አሻቅቧል"" ትላለች። የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ ተንታኝ የሆኑትና መቀመጫቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ፋይሰል ሮብሌ አገሪቷ በጦርነት ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰሷ ""በእውነቱ ኢትዮጵያ ዶላር የማግኘት አቅሟ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል"" እና የምንዛሪው ተመንም እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል ይላሉ። ጦርነቱ አገሪቱን ምን ያህል እንዳስወጣ እስካሁን ግልፅ አይደለም ነገር ግን በትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ትንበያ መሰረት ወታደራዊ ወጪዋ በመጪው ታኅሣሥ ወር መጨረሻ ላይ ወደ 502 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ብሏል። በባለፈው ዓመት 460 ሚሊዮን ዶላር ነበር። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባለፈው ሳምንት ጦርነቱ ""ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ከአገሪቱ ካዝና አስወጥቷል"" ብለዋል። ከዓለም አቀፉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እና ከጦርነቱ በፊት የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት በቀጠናው በፍጥነት በማደግ ላይ ከነበሩ አንዱ ነበር። ከዓለም ባንክ የተገኘውም መረጃም አገሪቱ ከሁለት ዓመት በፊት በነበረው አስር ዓመታት ውስጥ እድገቷ በዓመት በአማካይ 10 በመቶ ነበር። ትዕግስት የጠቀሰቸው በባንኮች የሚመነዘረውን የውጭ ምንዛሪ ሲሆን መደበኛ ባልሆነው ገበያ ውስጥ ግን የብር ዋጋ በእጅጉ አሽቆልቁሎ ወደ አንድ ዶላር 65 ብር እንደሚመነዘር ፋይሰል ተናግሯል። ጨምሮም በአገሪቱ ያሉ የነጋዴዎች ጦርነቱ ከትግራይ ተሻግሮ ወደ አጎራባቾቹ የአፋርና የአማራ ክልሎች በመስፋፋቱ እያሽቆቆለ ያለው የደኅንነት ሁኔታ በእጅጉ ያሳስባቸዋል። በርካቶቹም ከአካውንታቸው ገንዘባቸውን እያወጡ እራሷን ነጻ አገር አድርጋ ወዳወጀችው ሶማሌላንድ በማሻገር በመቀየር የብር የመግዛት አቅምን የበለጠ እንዲዳከም እያደረገው መሆኑን ፋይሳል ይገልጻል። በትግራይ የባንኮች መዘጋት የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ መክሰምና የምርጫ መራዘምን ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሚመራው አስተዳርና በህወሓት መካከል የነበረው አለመግባባት ተካሮ በነበረበት ጊዜ በፌደራሉ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ላይ ትግራይ ውስጥ ጥቃት ሲሰነዘር ነበር ጦርነቱ የተቀሰቀሰው። ከጥቅምት ወር ማብቂያ ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኤርታራ ወታደሮች፣ የክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሻዎች ከትግራይ ኃይሎች ጋር ደም አፋሳሽ ጦርነት አካሂደዋል። በዚህም ጊዜ አስገድዶ መድፈርና የሰላማዊ ሰዎች የጅምላ ግድያን ጨምሮ ጭፍጨፋዎችን በመፈጸም ሁሉም ወገኖች ሲከሰሱ ቆይተዋል። ባለፈው ሰኔ ወር አማጺያኑ የክልሉን ዋና ከተማ መልሰው ከያዙ በኋላ በትግራይ ውስጥ የፌደራል መንግሥቱ የቴሌኮሚዩኒኬሽንና ባንኮችን አገልግሎቶችን ጨምሮ መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ አድርጓል። ትግራይ ሙሉ በሙሉ ተዘግታለች። በትግራይ ከ 400 ሺህ በላይ ሰዎች በረሃብ አፋፍ ላይ ናቸው። የእርዳታ ስርጭቱ በከፍተኛ ሁኔታ ተመናምኖ የኤሌክትሪክ እና የነዳጅ አቅርቦቶች ባለመኖሩም የሸቀጦች ዋጋ እንዲንር አድርጎታል። የመቀለ ነዋሪ የሆነው ፊልሞን ብርሃኔ ለቢቢሲ ትግርኛ እንደተናገረው ምግብና ኪራይ ሰሞኑን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግሯል። ""ሁሉም ባንኮች ተዘግተው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ደመወዝ ስለማይከፍሉ ገንዘብ የለም"" ይላል። የቴሌኮም ጨረታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጦርነቱ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ባላት ስም ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ነው ሲሉ የኤን.ኬ.ሲ የአፍሪካ ኢኮኖሚ አማካሪ ቡድን የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ኢርማጋርድ ኢራስመስ ይናገራሉ። ""ሸማቾ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ጫና ካጋጠማቸው በአሜሪካ ወይም በዩሮ ዞን እንደምናየው በሸማቾች የሚመራ ዕድገት አያዩም"" ይላሉ። ""ይህም ማለት በአጠቃላይ የምጣኔ ሀብት እድገቱ የሚመራው በውጭ ኢንቨስትመንት ይሆናል፤ ነገር ግን ይህ ሁኔታም ባለው የኢትዮጵያ አሉታዊ ስም እየተጎዳ ነው"" በማለት ይጠቅሳሉ። ኢርማጋርድ በቅርቡ የደቡብ አፍሪካው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ኤምቲኤንን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት አቅራቢዎችን ፍላጎት የሳበውን የኢትዮጵያን የቴሌኮም ዘርፍ ፈቃድ ይጠቅሳሉ። ምንም እንኳን በመጀመሪያ ዙር በርካታ ዓለም አቀፍና ስመ ጥር ኩባንያዎች ፍላጎት ቢያሳዩም በመጨረሻ ግን ለሁለት የቴሌኮም ፈቃድ የወጣው ጨረታ አንዱ ብቻ ነው የተሳካው። በዚህም በኬንያው ሳፋሪኮም የሚ��ራው ጥምረት 850 ሚሊዮን ዶላር በማቅረብ ማሸነፍ ችሏል። የሞባይል ገንዘብ ሥርዓትን እንዳይሠሩ የሚገድቡ ሕጎች ከፈቃዱ ጋር በተያያዘ አሉታዊ ጫና ነበረባቸው ቢባልም የኩባንያዎቹ ፍላጎት የቀነሰው ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ እንደሆነ የኢንዱስትሪው ምንጮች ያስረዳሉ። ጦርነቱ እንዲቆም እየተደረገ ያለ ጫና የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለፈው ዓመት በ2020 ከነበረበት 6 በመቶ በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት በ2021 ሁለት በመቶ ብቻ እንደሚያድግ ተገምቷል። ይህም በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከታየው በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ የአይኤምኤፍ መረጃ ያሳያል። አገሪቱ በዓመት ወደ 14 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እቃዎችን ከውጭ የምታስገባ ሲሆን 3.4 ቢሊዮን ዶላር ብቻ የሚያወጣ ምርቶችን ወደ ውጪ ትልካለች። ከዚህም በተጨማሪ የአገሪቱ ብሔራዊ ዕዳ በዚህ ዓመት 60 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) 70 በመቶ ይደርሳል ከመባሉ ጋር ተያይዞ በርካታ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚያሳስብ ነው ይላሉ። ""ይህ ዝቅ ተደርጎ በተደረገ ግምገማ የቀረበ ግምት ነው"" ያሉት ባለለሙያዋ ""የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ ከተገመተው በላይ ሊሆን ይችላል እና ቀደም ሲል ሪፖርት ያልተደረገ ዕዳም አለበት"" ይላሉ። አሜሪካ በጦርነቱ ተሳታፊ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለስልጣናት ላይ አንዳንድ የቪዛ ገደቦችን ስትጥል እና የተወሰነ ድጋፍን ብትከለክልም፣ እስካሁን ድረስ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በመንግሥት ላይ ከፍተኛውን የኢኮኖሚ ጫና ለማሳረፍ ወይም ከፍተኛ የእርዳታ ፕሮግራሞችን ለመቋረጥ ፈቃደኛ አይደለም። በአገሪቱ ሩብ ገደማ የሚሆነው ሕዝብ ከብሔራዊ የድህነት ወለል በታች የሚኖር ሲሆን አማካይ ዓመታዊ ገቢ በአንድ ሰው 850 ዶላር ብቻ ነው። ""ከሁለት ዓመታት በፊት የኖቤል የሰላም ሽልማትን ያሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ግጭቱን ማስቆም ካልቻሉ ማዕቀቡን የማስፋት ሁኔታ እንዳለም"" በዋሽንግተን የቲንክ ታንክ ፌሎው ዊትኒ ሽኔይድማን ይናገራሉ። የባይደን አስተዳደር አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ የገባው ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ከዓለም ሳትገለል ጦርነቱ እንዲቆም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ላይ በቂ ጫና ማሳደር ነው ይላሉ። ""ሁሉም አማራጮች ጠረጴዛው ላይ ናቸው። ነገርን በአገሪቷ ከ110 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አለ። ከዚያም በተጨማሪ አገሪቷ ጠቃሚ፣ አስፈላጊ እንዲሁም በጣሙን ስትራቴጂካዊ ናት"" ይላሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-58374340 +politics የብሪታኒያ መንግሥት በኢትዮጵያ ያሉ ዜጎቹ በአስቸኳይ እንዲወጡ ጠየቀ "የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር በኩል ረቡዕ ምሽት ባወጣው ማሳሰቢያ ዜጎቹ የንግድ በረራዎችን በመጠቀም ""አሁን"" ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ጠየቀ። ሚኒስትሯ ቪኪ ፎርድ እንዳሉት ግጭቱ እየተባባሰ በመሄዱ ""ጦርነቱ ወደ አዲስ አበባ እየቀረበ ሊመጣ ከቻለ ከኢትዮጵያ ለመውጣት ያሉ አማራጮች ውስን ሊሆኑ ይችላሉ"" ብለዋል። ስለዚህም ሁሉም የብሪታኒያ ዜጎች በረራዎች ባሉበትና የቦሌ አየር ማረፊያ ክፍት ሆኖ እየሰራበት ባለበት ጊዜ በአስቸኳይ እንዲወጡ፣ ገንዘብ ለሌላቸውም የአየር ትኬት ብድር መመቻቸቱንም ገልጸዋል። ጨምረውም ""ከኢትዮጵያ ለመውጣት የማይፈልጉ ከሆነም በሚቀጥሉት ሳምንታት ለደኅንነታቸው አስተማማኝ በሆነ ስፍራ እንዲቆዩ"" መክረዋል። ቀደም ሲልም ጀርመን እና ፈረንሳይ ዜጎቻቸው አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የመከሩ ሲሆን ሌሎች አገራትም በተመሳሳይ ዜጎቻቸው ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ የመከሩ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም አንዳንድ ሠራተኞቹን በጊዜያዊነት ማዛወሩን ገልጿል። አገራቱ ይህንን ጥሪ እያቀረቡ ያሉት የትግራይ ተዋጊዎች ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እያመሩ መሆናቸውን ባስታወቁበትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አማፂያኑን ለመዋጋት ወደ ጦር ግንባር በመሄድ ሠራዊቱን እመራለሁ ባሉበት ወቅት ነው። በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ አጎራባቾቹ አማራና አፋር ክልል የተዛመተው ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሰብዓዊ ቀውሶችን ማስከተሉን ቀጥሏል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በረሃብ አፋፍ ላይ ሲሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታትና የእርዳታ ድርጅቶች አመልክተዋል። የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎች ላይ መሻሻሎች ቢታዩም መሬት ላይ ያለው ጦርነት መባባስ ሁኔታውን ስጋት ላይ ጥሎታል ብለዋል። ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች በወታደራዊ ድል አፋፍ ላይ መሆናቸውን ያመኑ ይመስላሉ ብለዋል ልዩ መልዕክተኛው። ፌልትማን አማጽያኑ ወደ አዲስ አበባ የሚጠጉ ከሆነ ተቀባይነት የሌለው እና አስከፊ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል። ከጦር ግንባሩ የሚወጡ ዘገባዎች ለማጣራት ቢከብዱም ህወሓት ተዋጊዎቹ ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማን መቆጣጠራቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት ቀደም ሲል የአማጺያኑን ድል ዘገባን አስተባብሏል። ""ግንባር ላይ እንገናኝ"" የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቿ አማራጭ የንግድ በረራዎችን በመጠቀም መውጣት አለባቸው ሲል ፈረንሣይ በበኩሏ ዜጎቿ ""ሳይዘዩ"" አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳስባለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጣዊ የደኅንነት ሰነድ ""ብቁ የሆኑ የዓለም አቀፍ ሠራተኞች ቤተሰብ አባላት"" እስከ ኅዳር 16/2014 ዓ.ም ድረስ አገሪቱን ለቀው መውጣት አለባቸው ብሏል። ቀደም ሲል አሜሪካና ዩናይትድ ኪንግደም አስፈላጊ ያልሆኑ የዲፕሎማቲክ ሠራተኞች እያስወጡ መሆኑን አስታውቀው ሌሎች በአገሪቱ የሚገኙ ዜጎቻቸውም አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ከጥቂት ዓመታት በፊት የኖቤል የሰላም ሽልማት ያገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ሰኞ ማምሻውን ባስተላለፉት መልዕክት የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምራት ወደ ጦር ግንባር እንደሚሄዱ ገልጸዋል። ""ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ"" በማለት ሌሎችም የእሳቸውን አርአያ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ድላቸውን ያገኙት የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ተከትሎ ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀው ውጥረት ማክተሚያ መፍትሄ በመሆናቸው ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ ግንባር በመሄድ ጦሩን እመራለሁ ማለታቸውን የህወሓት ቃለ አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ አጣጥለውታል። ""የእኛ ኃይሎች በሕዝባችን ላይ ያለውን (የዐብይን) ማነቆ ለማብቃት እያደረጉት ካለው ግስጋሴ አይመለሱም"" ብለዋል አቶ ጌታቸው። ጦርነቱ በድርድር እንዲቋጭ የአፍሪካ ሕብረት ጥረቶችን እያደረገ ቢሆንም ሁለቱም ወገኖች ለውይይት ቁርጠኛ አይደሉም። ለጦርነቱ ዋነኛ መነሻ የሆነው በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እና ትግራይን ብቻ ሳይሆን መላ አገሪቷን በበላይነት ይመራ በነበረው ህወሓት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ የፖለቲካ ምህዳሩን ከማስፋት በተጨማሪ ለረጅም ጊዜ በጠላትነት ሲተያዩ ከነበሩት ኤርትራ ጋር እርቅ መፍጠርና ሌሎች ማሻሻያዎችን አካሂደዋል። በዚህ ወቅት ህወሓት ወደ ጎን ገሸሽ ተደርጓል። በህወሓትና በጠቅላይ ሚኒስትሩ መካከል የከረመው መሻከርም ወደ ጦርነት አምርቷል። ከዓመት በፊት የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል እንዲሁም መሳሪያ ዘርፈዋል በሚልም የፌደራል መንግሥቱ ወታደራዊ ምላሽ ሰጥቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59384118 +health “የጥርሴ ቢጫ መሆን ሕልሜን አመከነው” በልጅነት ፍሎራይድ የበዛበትን ውሃ መጠቀም የጥርስ ቀለምን ወደ ቢጫ እንዲቀየር እና እንዲበልዝ ያደርጋል። ይህ ሁኔታም ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ያጋጥማል። ፍሎራይድ የጥርስን የላይኛውን ክፍል በመጉዳት ቀለሙ እንዲቀየር እና እንዲሸራረፍ ምክንያት ይሆናል። በዚህም ሳቢያ በርካታ ሰዎች በጥርሳቸው ቀለም እፍረት እና መገለል ይገጥማቸዋል። የወደፊት ዕቅዳቸው ተሰናክሎብናል የሚሉም አሉ። የታንዛኒያዋ አሩሻ በውሃ ውስጥ ከፍተኛ የፍሎራይድ መጠን ካለባቸው ስፍራዎች መካከል አንዷ ስትሆን፣ እዚያ የአሩሻ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ወጣት ሴቶች ስለገጠማቸው ችግር ይናገራሉ። ሁለቱ ወጣቶች በጥርሳቸው ቀለም መቀየር ምክንያት መድሎ እንደሚደርስባቸው ገልጸዋል። መፍትሔ ይኖረው ይሆን የጥርስን ቀለም የሚቀይረውን ከፍተኛ የፍሎራይድ መጠን ያለውን ውሃ ማጣራት እጅግ ከባድና ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ነው። አሁን ግን ቀላል የውሃ ጣሪያ ዘዴ ተፈጥሯል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n023lnxdqo +sports ፔንግ ሹዋይ፡ በጾታዊ ጥቃት ሳቢያ በቻይና የሚደረጉ የቴኒስ ውድድሮች ታገዱ "የቻይናዊቷ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ፔንግ ሹዋይ ጉዳይ ያሳሰበው የሴቶች ቴኒስ ማኅበር (ደብሊውቲኤ) በቻይና የሚደረጉ ሁሉንም ውድድሮች በአስቸኳይ ማገዱን አስታውቋል። የ35 ዓመቷ ፔንግ የቻይናን ከፍተኛ ባለሥልጣን በጾታዊ ጥቃት ከከሰሰች በኋላ ለሦስት ሳምንታት ከሕዝብ ዕይታ ጠፍታለች። የማኅበሩ ዋና ኃላፊ ስቲቭ ሳይመን እንዳሉት ፔንግ ""ነጻ፣ ደህንነቷ የተጠበቀ እና ለማስፈራሪያ ያልታጋለጠች ስለመሆኑ ከባድ ጥርጣሬዎች አሉን"" ብለዋል። ""በጥሩ ህሊና ስፖርተኞቻችን እዚያ እንዲወዳደሩ እንዴት እንደምጠይቅ አይታየኝም"" ብለዋል ኃላፊው። ማኅበሩ በፔንግ ክሶች ዙሪያ ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ ደጋግሞ ጠይቋል። የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዣንግ ጋዎሊን በጾታዊ ጥቃት ከከሰሰች በኋላ በፔንግ ጉዳይ ስጋት ተፈጥሯል። በኅዳር ወር ከዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ቶማስ ባህ ጋር ባደረችው የቪዲዮ ጥሪ ""ደህና"" መሆኗን ተናግራለች። ማኅበሩ ግን ቪዲዮው ስለፔንግ ""ደህንነት በቂ ማስረጃ አይደለም"" ብሏል። ሳይመን በ2022 በቻይና ውድድሮች ቢደረጉ ተጫዋቾቹ እና ባልደረቦቻቸው ሊያጋጥሟቸው ስለሚችለው አደጋ ""በጣም አሳስቦኛል"" ብሏል። ""በቻይና ያለው አመራር በዚህ አሳሳቢ ጉዳይ ላይ በምንም መልኩ ሊታመን አይችልም"" ብለዋል። ""ታላላቅ ሰዎች የሴቶችን ድምጽ ማፈን እና የጾታዊ ጥቃትን ውንጀላን ማጥፋት ካልቻሉ ማኅበሩ ከተመሠረተበት የሴቶች እኩልነት ዓላማ ትልቅ እንቅፋት ይገጥመዋል።"" ሲሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል። ""ይህ በማኅበሩ እና በተጫዋቾቹ ላይ እንዲደርስም እንዲሆንም አልፈቅድም"" ብለዋል። እገዳው በሆንግ ኮንግ የሚካሄዱ ውድድሮችንም ያካትታል። የቀድሞዋ የዓለም ቁጥር አንድ ቴኒስ ተጫዋች እና የማህኅበሩ መስራች ቢሊ ዣን ኪንግ ድርጅቱ ጠንካራ አቋም መያዙን አድንቃለች። ኪንግ በትዊተር ላይ ""ይህ የሴቶች ቴኒስ በሴቶች ስፖርት ውስጥ መሪ የሚሆንበት ሌላው ምክንያት ነው።"" ብላለች። ""ደብሊውቲኤ ተጫዋቾቻችንን በመደገፍ በታሪክ ጎን ቆሟል።"" ስትልም አክላለች። የሁለት ጊዜ የዊምብልደን ሻምፒዮናዋ ፔትራ ክቪቶቫ እና የዩኤስ ኦፕን የሩብ ፍጻሜ ተወዳዳሪ የነበረችው ሼልቢ ሮጀርስን ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾች ለውሳኔው ድጋፋቸውን በትዊተር ገልጸዋል። የፔንግ ጉዳይ 'ከሥራ ይበልጣል' - ሳይመን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ላለፉት ሁለት ዓመታት በቻይና ምንም አይነት የማኅበሩ ውድድሮች አልተካሄዱም። ይሁን እንጂ የበላይ አካሉ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ባደረጋቸው ውድድሮች በቻይና ኢንቨስትመንቶች ላይ በእጅጉ ከመንጠላጠሉም በላይ በአገሪቱ በርካታ ውድድሮች እንዲካሄዱ አድርጓል። ቻይና እአአ በ2019 የውድድር ዓመት ዘመን ውድድሮችን አስተናግዳለች። የውድድር ዘመኑ ማብቂያ ለሆነው የማኅበሩን የፍጻሜ ውድድርን ጨምሮ በድምሩ 30.4 ሚሊዮን ዶላር በሽልማት ሰጥታለች። ሳይመን በቻይና ያለመጫወት የሚያስከትለው የፋይናንስ ችግር እንዳሳሰበው ለቢቢሲ ስፖርት ገልጸው የፔንግ ጉዳይ ግን ""ከሥራም የበለጠ ነው"" ብለዋል። ""ይህ በቀላሉ ልንወጣው የማንችለው ነገር ነው"" ሲሉ ገልጸዋል። ""ከጠየቅነው ነገር ርቀን ከሄድን ለዓለም እየነገርነው ያለው ወሲባዊ ጥቃትን እና አሳሳቢነት አለመመልከት በመሆኑ አይሆንም።"" ብለዋል። ""እኛ እንዲሆን መፍቀድ የማንችለው እና ከዚያ መሸሽ የማንችለው ነገር ነው"" ሲሉም አክለዋል። በድርብ ውድድር የቀድሞዋ የዓለም ቁጥር አንድ የነበረችው ፔንግ በቻይና ማኅበራዊ ድር አምባ ዌይቦ ላይ ከዣንግ ጋር ጾታዊ ግንኙነት እንድትፈጽም መገደዷን ገልጻለች። ጽሁፉ ከደቂቃዎች በኋላ የተነሳ ሲሆን ፔንግ ለተወሰነ ጊዜ በአደባባይ አልታየችም። በርካታ የቴኒስ ተጫዋቾች በትዊተር ላይ #WhereisPengShuai (ፔንግ ሹዋን የታለች) የሚለውን ሃሽታግ ተጠቅመው ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ አድርገዋል። ሳይመን በወንዶች ውድድር ላይ የወንድ ቴኒስ ተጫዋቾች ማኅበር ተመሳሳይ አቋም እንዲይዝ እንደማይጠይቁ ለቢቢሲ ስፖርት ተናግረዋል። የማኅበሩ የበላይ አካል ግን አቋማቸውን እንደሚደግፍ ተናግሯል። ""[የወንዶቹ ማኅበር ውድድሮችን አለማቋረጡ] አቋማችንን የሚጎዳው አይመስለኝም"" ብለዋል። ""የእኛ አቋም ለደብሊውቲኤ እና ለሴቶች ስፖርተኞች የተሻለው ነገር ነው እና እኛ በዚያ አቋም እንቀጥላለን።"" ሲሉም አቋማቸውን ገልጸዋል። ""ሌሎች ለእነሱ ተስማሚ ናቸው ብለው ያሰቡትን ውሳኔ ያሳልፋሉ።"" ብለዋል ሳይመን። የቻይና ባለሥልጣናት የፔንግን ጥያቄዎች ""በሕጋዊ መንገድ ለመፍታት"" እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ተስፋ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። 'ምርጫ የለም' ሳይመን አክለውም ""እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ በጣም አዝኛለሁ። የቻይና መሪዎች ግን ማኅበሩ ምንም አማራጭ እንዳይኖረው አድርገዋል።"" ይላሉ። ""ቻይና የጠየቅናቸውን እርምጃዎች እስካልወሰደች ድረስ በቻይና ውድድሮችን በማድረግ ተጫዋቾቻችንን እና ሠራተኞቻችንን አደጋ ላይ መጣል አንችልም።"" ብለዋል። ቻይና በጥቅምት ወር ባወጣችው መግለጫ ""ሰዎች ሆን ብለው ይህንን ጉዳይ ፖለቲካዊ ማድረግ ይቅርና [ጉዳዩንም] ማበረታታቸውን ማቆም አለባቸው"" ብላለች። እአአ በ2018 ከመንግሥት ሥራቸው ጡረታ የወጡት ዣንግ ጋዎሊ ስለቀረበባቸው ክስ እስካሁን ምላሽ አልሰጡም። የ2022 የክረምት ኦሎምፒክ እና ፓራሊምፒክ በቤጂንግ በየካቲት እና በመጋቢት ወር ሊካሄድ ታቅዷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59501635 +sports ግሌዘሮች ለክለቡ 'ደንታ የላቸውም’፤ ኔቪል እና ሩኒ ጓደኞቼ አይደሉም- ሮናልዶ "የማንቸስተር ዩናይትዱ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የክለቡ ባለቤቶች የሆኑት የግሌዘር ቤተሰቦች ከስፖርት አኳያ ከታየ “ስለክለቡ ምንም ደንታ የላቸውም” ሲል ገለጸ። ሮናልዶ ክለቤ “ከዳኝ” ብሎ ለቶክ ቲቪ የሰጠው ቃለ መጠይቅ መነጋገሪያ ሆኗል። የቃለ ምልልሱ ሌላኛው ክፍል ሰኞ ምሽት ተለቋል። ""ማንችስተር ንግድ ክለብ ነው፤ ከገ��ያ ገንዘብ ያገኛሉ"" ሲል ተናግሯል። ""በሚቀጥሉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት ማንቸስተር ሜዳ ላይ የበላይ ለመሆን ከባድ ይሆንበታል"" ብሏል። በዘንድሮው የውድድር ዘመን አንድ ግብ ብቻ ያስቆጠረው የ37 ዓመቱ ፖርቱጋላዊ የፊት መስመር ተጫዋች ""የክለቡ ባለቤቶች የሆኑት ግሌዘሮች ስለ ክለቡ ደንታ የላቸውም"" ብሏል። ሮናልዶ አክሎም በ2005 ክለቡን ከተረከቡት የግሌዘር ቤተሰብ አባለት ጋር ተገናኝቶ እንደማያውቅም ተናግሯል። ዩናይትድ ለሮናልዶ ቃለ መጠይቅ ሰኞ ዕለት ምላሽ ሰጧል። ክለቡ ""ማንቸስተር ዩናይትድ የክርስቲያኖ ሮናልዶን ቃለ መጠይቅ አስመልክቶ የሚዲያ ዘገባዎችን ተከታትሏል። ክለቡ ሙሉ መረጃዎች ከወጡ በኋላ የሚሰጠውን ምላሽ ግምት ውስጥ ያስገባል” ብሏል። ""ትኩረታችን ለሁለተኛው የውድድር አጋማሽ መዘጋጀት እና በተጫዋቾች፣ በአሰልጣኞች፣ በሠራተኞች እና በደጋፊዎች መካከል እየተገነባ ያለውን መነሳሳት፣ እምነት እና አንድነት ማስቀጠል ላይ ነው"" ሲልም ክለቡ አክሏል። እአአ በ2017 ለመጨረሻ ጊዜ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ያነሳውን ክለብ ባለቤቶች በመቃወም ደጋፊዎች በርካታ ተቃውሞዎችን አካሂደዋል። የፖርቹጋሉ አምበል ሮናልዶ አክሎም ""ደጋፊዎቹ ሁሌም ትክክል ናቸው። እውነታውን ማወቅ አለባቸው። ተጫዋቾቹ ለክለቡ ጥሩ ነገር ይፈልጋሉ። እኔም ለክለቡ ጥሩ ነገር እመኛለሁ። ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ የመጣሁትም ለዚህ ነው። ለዚህም ነው ይህንን ክለብ የምወደው” ብሏል። “ማንቸስተር እንደ ሲቲ፣ ሊቨርፑል እና አሁን ደግሞ እንደ አርሴናል ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዳይደርስ የሚያደርጉ አንዳንድ ነገሮች በክለቡ ውስጥ አሉ።“ ""ውስብስብ ነው። ከባድ ነው። በጣም ከባድ ነው።"" ""ኔቪልና ሩኒ ጓደኞቼ አይደሉም"" በእሑዱ ቃለ ምልልስ ወቅት ሮናልዶ የቀድሞው የዩናይትድ የቡድን አጋሩ ዋይኒ ሩኒ ስለተቸው ተበሳጭቶ እንደሆን ተጠይቆ ነበር። ሮናልዶ ""ምናልባት በሠላሳዎቹ ዕድሜው ጫማውን ስለሰቀለ ይሆናል። እኔ አሁንም በትልቅ ደረጃ እየተጫወትኩ ነው። ከሱ የተሻልኩ ነኝ አልልም። ምክንያቱም እውነት ነው. . .።"" አሁን ደግሞ ትኩረቱን ወደ ሌላ የቀድሞ የዩናይትድ አጋሩ ጋሪ ኔቪል አዙሯል። የቀድሞ የእንግሊዝ የቀኝ መስመር ተከላካይ በቅርቡ ለስካይ ስፖርት ተንታኝ ሆኖ ሲሠራ ሮናልዶ ሠላም ሳይለው ቀርቷል። ""ከአንተ ጋር ከተጫወቱ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱን ትችት እና አሉታዊነት ማዳመጥ በጣም ከባድ ነው። ለምሳሌ ጋሪ ኔቪል። ሁለቱም ጓደኞቼ አይደሉም"" ሲል ሮናልዶ ተናግሯል። ""መተቸት ቀላል ነው። በቴሌቪዥን ሠርቶ የበለጠ ታዋቂ ለመሆን መተቸት ግዴታ ይሁንባቸው አላውቅም። በእርግጥም አልገባኝም።“ ""ሞኞች ስላልሆኑ  (የእኔን ስም) የሚያነሱት ሊጠቀሙበት ይመስለኛል። ከአንተ ጋር በአንድ መልበሻ ክፍል የነበሩ ሰዎች በዚያ መንገድ ሲተቹ ማየት በጣም ከባድ ነው"" ብሏል። ከዚህ በፊት ምን ተፈጠረ? ቀደም ሲል በተለቀቀው የቃለ ምልልሱ ክፍል በሳምንት 500 ሺህ ፓውንድ የሚከፈለው ሮናልዶ ክለቡ አስገድዶ ሊያስወጣው እየሞከረ መሆኑን እና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግን እንደማያከብር ተናግሯል። ሮናልዶ ከአውሮፓውያኑ 2003 እና 2009 ለዩናይትድ 118 ጎሎችን አስቆጥሯል። በ2021 ክረምት ወደ ክለቡ በድጋሚ የተመለሰው በክለቡ ደጋፊዎች ዘንድ በአክብሮት ነበር። በዚህ ሳምንት የሚተላለፈው ሙሉው ቃለ መጠይቅ ብዙ ደጋፊዎችን ከእሱ እንደሚያርቅ ይጠበቃል። ሮናልዶ አሁን በኳታር ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c980grz0n04o +business ዩክሬን ውስጥ እዳቸውን መክፈል ያልቻሉ ሰዎች የውስጥ ልብስ ለጨረታ ቀረበ ���ክሬን ወስጥ እዳቸውን መክፈል ያልቻሉ ሰዎች የውስጥ ልብስ ጭምር ለጨረታ መቅረቡ በርካቶችን አስገርሟል። በዩክሬን ማዕከላዊ ከተማ ክሪይቪ ሪህ የተለያዩ አልባሳት እና ጫማዎች በአገሪቱ የፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ይፋዊ ድረ ገጽ ላይ ለሽያጭ ቀርበዋል። የአልባሳቱ መነሻ የመሸጫ ዋጋ ደግሞ 70 ሳንቲም ዶላር እንደሆነ ተገልጿል። መስሪያ ቤቱ ከአልባሳት በተጨማሪ ላሞችና በጎችንም ጭምር ለሽያጭ አቅርቧል። የ ኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ እስከ 2 ሚሊየን የሚደርሱ ዩክሬናውያን ከመንግሰት አበዳሪ ተቋማት የተለያዩ የብድር አይነቶችን ወስደዋል። ቢቢሲ ከአንድ ዩክሬን መስሪያ ቤት ባገኘው መረጃ መሰረት ባለፈው ዓመት ብቻ የተበዳሪዎች ቁጥር በ300 ሺ ጨምሯል። ባለፈው ዓመት በአንድ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ መልዕክት ሁለት የቤት እንስሳ የሆኑ ውሻዎች ለሽያጭ ቀርበው በርካቶች ተቃውሟቸው ን ሲገልጹ ነበር። አንድ የሕዝብ እንደራሴ ደግሞ እዳዋን መክፈል ያልቻለች አንዲት ጡረተኛ ውሻዎቿን ሸጣም ቢሆን እዳዋን መክፈል አለባት ብለው ነበር። በወቅቱም በርካቶች ተቃውሟቸውን ገልጸው ነበር። የፍትህ ሚኒስትሩ ዴኒስ ማሊዩስካ ወደኋላ ላይ ግን የቤት እንሳስቱን መሸጥ እምብዛም አዋጪ ነገር እንዳልሆነና ቢቻል በጥሩ ገንዘብ ሊሸጡ የሚችሉ ንብረቶች ላይ ትኩረት ቢደረግ ይሻላል ብለዋል። ኦኢሲዲ የተባለው አንድ ተቋም ባለፈው ወር ባወጣው ሪፖርት መሰረት የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ዩክሬን ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሊያጋጥማት የሚችል ሲሆን ይህም ባለፉት 10 ኣመታት ከታየው በጣም ትልቁ ነው። ወረርሽኙን ተከትሎም አገሪቱ ካላት 41 ሚሊዮን ዜጎች ውስጥ 9 ሚሊዮን የሚሆኑት እጅግ በከፋ ድህነት ውስጥ ይኖራሉ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰራው ጥናት መሰረት ደግሞ ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ከአጠቃላይ ህዝቡ 40 በመቶ የሚሆኑ ቤተሰቦች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የቤተሰብ አባላቸው ስራ አጥቷል። ዩክሬን ውስጥ እዳቸውን መክፈል ያልቻሉ ሰዎችን ንብረት ለሽያጭ የሚያቀርበው ድረ ገጽ የተቋቋመው በአውሮፓውያኑ 2015 ነበር። የፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደሚለው እስካሁን 506 ሚሊየን ዶላር ከሽያጩ ተገኝቷል። ከዘህ በተጨማሪም መስሪያ ቤቱ እዳቸውን መክፈል ካልቻሉ ሰዎች የተወሰዱ ንብረቶችን ለወላጅ አልባ ህጻናት፣ ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች በነጻ እንዲሰጡ እንደሚደረግ ተገልጿል። https://www.bbc.com/amharic/news-56090926 +sports ሁለት ሜትር ከሃያ አምስት ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ሴኔጋላዊ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች "ሴኔጋላዊው ታኮ ፎል ወደ ቅርጫት ኳሱ ዓለም የተቀላቀለው ገና ከሰባት ዓመታት በፊት ቢሆንም የ2.25 ሜትር ርዝማኔ ያለው ይህ ተጫዋች በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ (ኤንቢኤ) ከፍተኛ ስፍራ እያገኘ ነው። ከዓለም ረዥሙ የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች ሮማኒያዊው ጆርጅ ሙሬሳን በ6.3 ሴንቲ ሜትር የሚያጥረው የ23 አመቱ ታኮ፤ የታዋቂው የቦስተን ሴልቲክስ ከቋሚዎቹ አስራ አምስት ተጫዋቾች አንዱ ለመሆንም ጥረት ላይ ነው። • የደቡብ አፍሪካ ባሕር ጠላቂዎች በኬንያ አስክሬን ፍለጋ ላይ ሊሰማሩ ነው • የካቶሊክ ቄሶች ማግባት ይፈቀድላቸው ይሆን? • በአሜሪካዊቷ ፖሊስ የፍርድ ሂደት ምስክርነት የሰጠው የዐይን እማኝ ተገደለ ሴልቲክስ ታኮ ፎልን የመረጠበት ምክንያትም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ እንደሆነም ተገልጿል። በሴኔጋሏ መዲና ዳካር የተወለደው ታኮ፤ ወደ አሜሪካ የሄደው በ16 ዓመቱ ሲሆን፤ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ቅርጫት ኳስ ይጫወት ነበር። ታኮ ለቢቢሲ እንደተናገረው፤ ዩኒቨርስቲው ውስጥ ብዙዎች ሙያውን እንዲያሳድግ ድጋፍ አድርገውለታል። ታዳጊ ሳለ ብዙም ስለ ቅርጫት ኳስ እንደማያውቅ ይናገራል። ጊዜውን ያሳልፍ የነበረው ካርቱን ፊልሞች በማየት ነበር። የአያቱ ቅርጫት ኳስ መውደድ ስፖርቱ ላይ ፍቅር እንዲያሳድር አድርጎታል። ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ሙሉ ትኩረቱን ወደ ቅርጫት ኳስ አድርጓል። ጉዞው ግን አልጋ በአልጋ አልነበረም። ""ቅርጫት ኳስ መጫወት አልችልም ነበር። ብዙ ነገር መማር ይጠበቅብኝ ነበር። እድለኛ ሆኜ ብዙ ሰዎች ራሴን እንዳሻሽል ረድተውኛል"" ይላል። ሂውስተን አንድ ዓመት ከቆየ በኋላ ወደ ቴኒሲ፣ ጂዎርጂያ እና ፍሎሪዳ አቅንቷል። በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ሁለት ዓመት ቆይቷል። ""አንድ ሴኔጋላዊ ታዳጊ ነበርኩ። ቅርጫት ኳስ መጫወት የጀመርኩትም ከስድስት ዓመት በፊት ነበር። ኤንቢኤ ውስጥ ለመጫወት ብዙ ለፍቻለሁ። በጣም እድለኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል። ቅርጫት ኳስ ሕይወቴ ነው። አንድ ቀን እንኳን ሳልጫወት ባልፍ አዝናለሁ"" ሲል ይናገራል።" https://www.bbc.com/amharic/news-49960041 +politics ቦርዱ የኦነግን ጠቅላላ ጉባኤና በምርጫ የመሳተፍ ጥያቄን ውድቅ አደረገ "በቅርቡ አዲስ የአመራር አባላትን መርጫለሁ ያለው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ክንፍ ያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤና በምርጫ ለመሳተፍ ያቀረበው ጥያቄ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ውድቅ ተደረገበት። በኦነግ ከፍተኛ የአመራር አባላት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሳቢያ ግንባሩ በሁለት ወገኖች መካከል ተከፍሎ በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ የዕጩዎች ምዝገባ ሳያከናውን የጊዜ ገደቡ ጊዜ እንዳለፈው ይታወሳል። ቦርዱ ውሳኔውን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው በግንባሩ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ክፍፍልና ውዝግብን ተከትሎ ከሁለቱም ወገን አቤቱታዎችና የማሳወቂያ ደብዳቤዎችን ሲቀበል መቆየቱ በመግለጽ ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የበኩሉን ጥረት ማድረጉን ገልጿል። ግንባሩ በቀደምት ሊቀመንበሩ በአቶ ዳውድ ኢብሳና ምክትላቸው በነበሩት በአቶ አራርሶ ቢቂላ መካከል ለሁለት ተከፍሎ የተለያየ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ውሳኔዎችን እየሰጠ ነው። በአቶ ዳውድ የሚመራው ቡድን በግንባሩ ላይ የተለያዩ ጫናዎች እየደረሱ ነው በሚል በምርጫው ላይ እንደማይሳተፍ ቢገልጽም የአቶ አራርሶ ቡድን ግን ተገቢውን ማስተካከያ እንዳደረገ በመግለጽ በምርጫው የመሳተፍ ፍላጎቱን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቅርቦ ነበር። በግንባሩ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትም ሁለቱ ወገኖችን በተናጠል እንዲሁም የፓርቲውን የሥነ ሥርዓት እና የቁጥጥር ኮሚቴን በማነጋገር ያሉ አስተዳደራዊና ሕጋዊ መንገዶች ሁሉ በመጠቀም መፍትሔ ለመስጠት ጥረት ማድረጉን ቦርዱ ገልጿል። በመጨረሻም የግንባሩን ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት ፓርቲው ለገጠመው ችግር ብቸኛ መፍትሔ መሆኑን በማስረዳት በውዝግብ ውስጥ ያሉ አመራሮችም ይህንኑ ሃሳብ በመቀበል የተፈጠረውን ችግር በጠቅላላ ጉባኤ እንዲፈታ መወሰኑ የምርጫ ቦርድ መግለጫ አስታውሷል። በዚህም የግንባሩ አንደኛ ወገን ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ አዲስ የአመራር አባላት መምረጡን በመግለጽ፣ ""በውስጥ ችግሩ ምክንያት የጠቅላላ ጉባኤ ሳያካሂድ በመቆየቱ የነበረበትን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት የምልክት መረጣና የዕጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዲያደርግ እንዲፈቅድለት ጠቅላላ ጉባኤውንም እንዲጸድቅለት"" መጠየቁን ምርጫ ቦርድ አመልክቷል። ቦርዱም የቀረቡለትን ሰነዶች መርምሮ በጠቅላላ ጉባኤው አካሄድና ተሳታፊዎች በኩል የግንባሩን ሕገ ደንብ ባከበረ መንገድ አለመካሄዱን የሚያመለክቱ አምስት ነጥቦችን በማስቀመት የቀረበለትን የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔና በምርጫ የ��ሳተፍ ጥያቄን እንዳልተቀበለው ገልጿል። ስለዚህም በመጪው ግንቦት ወር ማብቂያ ላይ በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎቱን ገልጾ የነበረው በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የኦነግ አንድ ክፍል ያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ባለፈው ሳምንት በአገሪቱ ምክር ቤት ቀርበው ለተነሱ ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት ያለው ፓርቲን አሁንም ቦርዱ ቢቀበለው እንደሚደግፉ ገልጸው ነበር። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ኦነግ በምርጫው የመሳተፉ ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ የቆየ ቢሆንም አሁን በገጠመው ችግር ምክንያት ከምርጫው ውድድር ውጪ ሆኗል። ከዚህ ቀደምም የኦሮሞ ፌደራሊስte ኮንግረስ በአባላቱ መታሰርና በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ጽህፈት ቤቶቹ መዘጋትን እንደምክንያት በማቅረብ በምርጫው ላይ ለመሳተፍ እንደሚቸገር መግለጹ ይታወሳል። የብልጽግና ፓርቲ ሕዝብ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ፓርቲዎቹ መንግሥት ጫና ያደርስብናል፣ አባላቶቻችንን ያስራል፣ ጽህፈት ቤታችንን ዘግቷል ሲሉ የሚያቀርቡትን ውንጀላ ""መሰረት የሌለው"" ሲሉ ከዚህ በፊት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በመጪው ግንቦት ወር መጨረሻና በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ከትግራይ ክልል በስተቀር በቀሪው የአገሪቱ አካባቢዎች በሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ የሚወዳደሩ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም 125 የግል ዕጩዎች ለመወዳደር ተመዝግበዋል። ባለፈው ሳምንት ደግሞ ሁለት ወር ያህል በቀረው ምርጫ ላይ ድምጽ የሚሰጡ የመራጮች ዝገባ መጀመሩን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56555595 +business የተትረፈረፈ ቢመስልም የአሸዋ እጥረት ዓለም ላይ ተፈጥሯል "በተለይም በበረሃና በባህር ዳርቻዎች የሚገኘው አሸዋ የትም የሚገኝ ቢመስልም በዓለም ላይ ሰዎች እጅጉን እየተጠቀሟቸው ካሉ ነገሮች ሁለተኛው ነው። ባለፈው መስከረም ወር ብቻ ደቡብ አፍሪካዊ ሥራ ፈጣሪ፣ ሁለት ህንዳዊያን እንዲሁም ሜክሲኳዊ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ብዙ ዋጋ ባልተሰጠው ነገር ግን በጣም አስፈላጊ በሆነው አሸዋ ምክንያት ተገድለዋል። • እየጨመረ የመጣው የአሸዋ ፍላጎት ወንዞችን እያጠፋ ነው • አሸዋ የሰረቁ ፈረንሳያውያን ጥንዶች ለእስር ተዳረጉ ብዙም ባይመስልም አሸዋ እጅጉን አስፈላጊ ነገር ነው። በጥቅሉ ለከተሞች ግንባታ ወሳኝ ግብአት ነው- አሸዋ። የገበያ ማዕከሎች፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ የአስፓልት መንገዶች ግንባታ ያለ አሸዋ የሚታሰብ አደለም። በየቦታው የሚታዩት የመስታወት መስኮቶች፤ የስማርት ስልኮች ስክሪን ጭምር ከቀለጠ አሸዋ የሚሰሩ ናቸው። በስልኮቻችን እንዲሁም በኮምፒውተሮቻችን ውስጥ ያሉ ሲልከን ቺፖችም ከቀለጠ አሸዋ የተሰሩ ናቸው። ይህም ብቻ አይደለም በመኖሪያ ቤቶቻችን ለሚገኙ የኤሌክትሪክ መገልገያ እቃዎች ስሪትም አሸዋ ግብአት ነው። ምንም እኳ ከሰሃራ እስከ አሪዞና ባሉ ሰፋፊ በርሃዎችና በባህር ዳርቻዎች ቢገኝም፤ በአቅራቢያ ከሚገኝ መደብር በቀላሉ ልንገዛው የምንችለው ነገር ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ዓለም ላይ የአሸዋ እጥረት አጋጥሟል። • ሳናውቀው እያለቁብን ያሉ ስድስት ነገሮች ለመሆኑ በዓለም ላይ የትም ቦታ የሚገኝ ነገር እንዴት እጥረት ሊፈጠርበት ይችላል? በዓመት 50 ቢሊዮን ቶን አሸዋ በሰዎች ጥቅም ላይ ይውላል። ይህ የአሸዋ መጠን መላዋን እንግሊዝ ሊያለብስ የሚችል ነው። አጥኚዎቹ እንደሚሉት ችግሩ ያለው ጥቅም ላይ እየዋለ ባለው አሸዋ አይነት ምክንያት እንደሆነ እየተናገሩ ነው። ከላይ ለተጠቀሱት አገልግሎቶች ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ለስላሳውና በቀላሉ በንፋስ የሚበነው የበረሃ አሸዋ አይደለም። ይህ በጣም ደቃቅ የበረሃ አሸዋ ለኮንክሪት የሚሆን አይደለም። ይልቁንም ለሰዎች አስፈላጊ የሆነው ባለ ማእዘኑ እና በወንዞች እና በሃይቆች የሚገኘው ነው። ስለዚህም ይህኛውን አሸዋ ለማግኘት በወንዞች መድረሻ፣ በእርሻ ማሳዎ እንዲሁም በጫካዎች ውስጥ ሕገ ወጥ ፍለጋ ይካሄዳል። ጥቂት በማይባሉ አገራትም የወንጀለኛ ቡድኖች በዚህ የአሸዋ ንግድ ላይ ተሰማርተዋል፤ በዚህ ሳቢያ ደግሞ የአሸዋ ጥቁር ገበያም ተስፋፍቷል። • ኢትዮጵያ አርባ በመቶ ዕፀዋቶቿን ልታጣ እንደምትችል ተነገረ ""የአሸዋ እጥረት ጉዳይ ብዙዎች እያስገረመ ነው ግን ሊያስገርም አይገባም። ያለ ምንም አካባቢያዊ ተፅዕኖ የአንድን ተፈጥሯዊ ሃብት 50 ቢሊዮን ቶን የሚያክል ነገር ማውጣት የሚቻል ነገር አይደለም"" ይላሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ተመራማሪው ፓስካል ፔዱዚ።" https://www.bbc.com/amharic/news-50555337 +business የኢትዮጵያ ከአግዋ መታገድ በሥራ ዕድል እና በውጭ ምንዛሪ ምን ያጎድልባታል? "የአሜሪካ መንግሥት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገራት የዘረጋው ከቀረጥ ነጻ ዕድል ተጠቃሚ የነበረችው ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ ከዚህ ዕድል መታገዷ ተሰምቷል። በ2005 ዓ.ም የአግዋ ፎረምን ያስተናገደችው ኢትዮጵያ በአግዋ በኩል ለሁለት አስርት ዓመታት የተለያዩ ምርቶችን [በስፋት ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት] ለአሜሪካ ገበያ በማቅረብ ለመቶ ሺዎች የሥራ ዕድል በመፍጠር በሚሊዮኖች የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ ስታገኝ ቆይታለች። እንደ አውሮፓውያኑ በ2000 ይፋ በተደረገው በዚህ የቀረጥ ነጻ ዕድል ተጠቃሚ ከሆኑ 38 አገራት አንዷ የነበረችው ኢትዮጵያ የተለያዩ ምርቶችን ለአሜሪካ ገበያ ስታቀርብ ቆይታ ከዚህ ተጠቃሚነት መታገዷ የውጭ ምንዛሪ ማጣትንና የሥራ ዕድል ማጥበብን ጨምሮ በርካታ ጉዳቶችን እንደሚያስከትልባት ይታመናል። ኢትዮጵያ ከጆ ባይደን አስተዳደር ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች በኋላ የአግዋ ዕድልን የተነጠቀች ሲሆን በኢትዮጵያ ያለው ችግር አሳሳቢ ነው የምትለው አሜሪካ አገሪቱ በሚቀጥሉት 60 ቀናት ውስጥ የሚጠበቅባትን የምታከናውን ከሆነ ወደ አግዋ ዳግም ልትመለስ እንደምትችል አስታውቃለች። አግዋ ምንድን ነው? The African Growth and Opportunity Act [በግርድፍ ትርጉሙ የአፍሪካ ዕድገት እና ዕድል ድንጋጌ] ወይም አግዋ በአሜሪካ የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉና ከሰሃራ በታች ለሚገኙ አገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነጻ ለአሜሪካ ገበያ እንዲያቀርቡ የሚያስችል ዕድል ወይም ችሮታ ነው። በአግዋ የተካተተ ማንኛውም አገር የሕግ የበላይነትን ለማስፈን መስራት፣ የሰብአዊ እና የሠራተኛ መብቶችን ማክበር፣ ፖለቲካዊ ብዝሃነትን ማስተናገድ፣ ገበያ መር ኢኮኖሚን መከተል ወይም ለመከተል መስራትን ጨምሮ የተለያዩ መስፈርቶች የተቀመጡ ሲሆን መስፈርቶቹ የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን እና በዕድሉ ለመቆየት የሚያስችሉ እንደሆነ በአዋጁ ተቀምጧል። አግዋ እንደ አውሮፓውያኑ በግንቦት 18/2000 በአሜሪካ ኮንግረንስ የጸደቀ ሲሆን በ2025 ክለሳ ይደረግበታል። ይህ የንግድ ዕድል ሥርዓት እንደ አውሮፓውያኑ ከ2000 እስከ 2008 እንዲተገበር ታስቦ የተጀመረ ቢሆንም፣ በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳት የነበሩት ጆርጅ ቡሽ እስከ 2015 እንዲራዘም ፈርመዋል። በ2015 ላይ ደግሞ ይህ ዕድል እስከ 2025 እንዲራዘም የያኔው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በፊርማቸው አጽደቀዋል። በአሜሪካ መንግሥት ችሮታ የቀረበውና አፍሪካን በሚመለከት የአገሪቱ የንግድ ፖሊስ አካል የሆነው አግዋ ከሰሃራ ��ታች ባሉ አገራት እና በአሜሪካ መካከል የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስርን ማበረታታት፤ በአገራቱ ያሉ ንግዶችን ለአሜሪካ ኢንቬስተሮች ክፍት ማድረግ እንዲሁም ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያን እና ዕድገትን መደገፍ ቀዳሚ ግቦቹ ናቸው። ኢትዮጵያ ከአግዋ ምን ተጠቀመች? እንድ አውሮፓውያኑ በ2019 በአግዋ ሥርዓት አማካኝነት አሜሪካ 8.4 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ማስገባቷን የአሜሪካ ፌዴራል መንግሥት የንግድ ጉዳዮች አማካሪ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ይህ ተቋም ባወጣው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ በዚያው ዓመት 246 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን በአግዋ አማካኝነት ወደ አሜሪካ ልካለች። ከተላኩት ምርቶች አብዛኛውን የሚሸፍኑት አልባሳት፣ አበባ እና ጫማን የመሳሰሉ ናቸው። ናይጄሪያ በአግዋ ዕድል 3.1 ቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ ምርቶችን [በብዛት ድፍድፍ ነዳጅ] በመላክ የዚያ ዓመት የዕድሉ ቀዳሚ ተጠቃሚ ነበረች። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢኮኖሚ አማካሪ ማሞ ምህረቱ (ዶ/ር) ፎሬይን ፖሊስ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ኢትዮጵያ በአግዋ ሥርዓት በኩል እንደ ለአሜሪካ ገበያ ያቀረበችው ምርት ወደ 150 ሚሊዮን ዶላር ማደጉን አስፍረዋል። ይህም ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ከላከችው አጠቃላይ ምርት ግማሹን የሚሸፍን ነው። አግዋ ይፋ በሆነበት ዓመት ከኢትዮጵያ የተላከው ምርት 28 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሲሆን ከ20 ዓመታት በኋላ የተላከው ምርት ከአምስት እጥፍ የላቀ ነው። ሂደቱም ለኢትዮጵያ ዘላቂ የሆነ የውጭ ምንዛሪ ግኝት እና የዜጎች የሥራ ዕድል ምንጭ ሆኖ ቆይቷል። ማሞ ምህረቱ በጽሁፋቸው በአግዋ ዕድል አማካኝነት ኢትዮጵያ ከምትልካቸው ምርቶች አልባሳትና የቆዳ ምርቶች ኢንዱስትሪ ብቻቸውን ለ200 ሺህ ዜጎች ቀጥተኛ የሥራ ዕድል መፍጠሩን ገልጸው ከተጠቃሚዎቹ 80 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። አማካሪው 30 ሺህ ሠራተኞች ያሉትን የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ለአብነት በማንሳት 95 በመቶ የሚሆኑት ሠራተኞች ሴት መሆናቸው እና የሥራ ልምድ ለሌላቸው ወጣቶች ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል። አጠቃላይ የኢንዱስትሪ ማዕቀፉ ደግሞ እንደ ትራንስፖርትና ሆቴል ካሉ አነስተኛ ቢዝነሶች እስከ ጥሬ ዕቃ አቅራቢ ባለው ትስስር ከአንድ ሚሊዮን ለሚልቅ ዜጋ የገቢ ምንጭ መሆኑን አስረድተዋል። በሌላ በኩል የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ ሌሊሴ ነሜ ለአሜሪካ መንግሥት በጻፉትና በኮሚሽኑ ማኅበራዊ ገጾች በተሰራጨ ግልጽ ደብዳቤ፣ አግዋ አሜሪካን ጨምሮ ታላላቅ የዓለም ኩባንያዎች ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ዕድል መስጠቱን አስታውሰዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚመረቱ ጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት 80 በመቶ በአግዋ በኩል የገበያ መዳረሻቸው አሜሪካ እንደሆነ ያነሱት ኮሚሽነሯ፣ አግዋ በከተሞች ዙሪያ ለሚኖሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች የገቢ ምንጭ ሆኖ ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ እያገዘ እንደሆነ ገልጸዋል። በተጨማሪም ከገጠር ወደ ከተማ ሥራ ፍለጋ ለሚፈልሱና በርካታ ሴቶች የእንጀራ ገመድ መሆኑንም በደብዳቤያቸው አስፍረዋል። ኢትዮጵያ ከአግዋ ዕድል መታገዷ ከመገለጹ ከሳምንታት በፊት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው ስለ አግዋ አስተያየት የሰጡት ማሞ ምህረቱ አግዋ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪን እንድታስፋፋ አስተዋፅኦ እንደነበረው ጠቁመዋል። ""ከጥቂት ዓመታት በፊት የነበረን የኢንዱስትሪ ፓርክ አንድ ብቻ ነበር። አሁን ግን በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የኢንዱስትሪ ፓርኮችን መገንባት ችለናል። ያንንም ተከትሎ ብዙ ሠራተኞች ቀጥረናል ያንንም ተከትሎ የወጪ ንግዳችንን ማስፋት ችለናል በግብርና ላይ መሰረት ያደረገው ኢኮኖሚ ሌሎች የኢኮኖሚ ሴክተሮችንም ለማበረታታት አግዋ የራሱ የሆነ አስተዎፅኦ አበርክቷል"" ብለዋል። የኢትዮጵያ ከአግዋ መታግድ ምን ጉዳት ያስከትላል? ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ከኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ ተማጽኖ በተቃራኒ የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያን ከአግዋ አግዷል። ይህም አገሪቱን ከአግዋ የምታገኘውን ጥቅም በሙሉ እንድታጣ ያደርጋታል። የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ በደብዳቤያቸው ኢትዮጵያ ከአግዋ የምትታገድ ከሆነ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ ኢንቨስተሮችም ተጎጂ እንደሚሆኑ አንስተዋል። ማሞ ምህረቱ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ሲናገሩ በኢትዮጵያ ያለው አስተዳደር የተሻለ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑን ገልጸው ኢትዮጵያ በአግዋ ለመቆየት የሚስያችሏት መስፈርቶችን ""ከመቼውም ጊዜ በላይ"" ያሟላችበት ወቅት ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በስፋት እንዲገነቡና ሰፊ የሥራ እድል እንዲፈጠር ምክንያት ከሆኑ ጉዳዮች አግዋ አንዱ እንደሆነ ያነሱት ማሞ ""የአግዋ እድል በሚቀርበት ጊዜ ይሄ ሁሉ ነገር ይቀራል ማለት አይደለም። ግን አሉታዊ ውጤት ይኖረዋል ማለት ነው። .... አግዋ ቢሄድም እንኳን እነዚህ ኢንቨስተሮች ነቅለው ይሄዳሉ ማለት አይደለም"" ሲሉ ገልጸዋል። ሆኖም የኢትዮጵያ ከአግዋ ዕድል መታገድ ዋነኛ ተጠቂ የሚያደርገው ከማንም በላይ የፋብሪካዎች ሠራተኞችን ቢሆንም ከእነሱ ጋር ተያይዘው የሚጎዱ ተጠቃሚዎች መኖራቸውን አመልክተዋል። ""በተለይ ሴት ሠራተኞች ይጎዳሉ። በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ፓርኮች አካባቢ ሌሎች በተዘዋዋሪ መልኩ የሥራ እድል የፈጠሩ ሰዎችንም ይጎዳል"" በማለት የምግብ፣ የትራንስፖርት፣ የትምህርት፣ የቤት ኪራይ እና መሰል አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ ሰዎች ተጎጂ እንደሚሆኑ አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት የተነጠቀችው የአግዋ ዕድል በቀጥታና በተዘዋዋሪ የሥራ ዕድል ያገኙ ዜጎች ላይ ጫና ከማሳረፍ እና የውጭ ምንዛሪ ግኝቷን ከመቀነስ ባሻገር በጦርነት፣ በኮቪድ 19 ወርርሽኝና በሌሎች ምክንያቶች ለተፈተነው ምጣኔ ሀብቷ ሌላ መስናክል መሆኑ አይቀርም።" https://www.bbc.com/amharic/news-59151040 +politics በምዕራብ ወለጋ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 28 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ "በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት 28 ሰዎች መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ገለጸ። ማክሰኞ መጋቢት 21/2013 ዓ.ም በዞኑ ውስጥ በሚገኘው ባቦ ገንቤል ወረዳ በቦኔ ቀበሌ የተፈጸመውን ጥቃት ኦነግ-ሸኔ የተባለው ቡድን እንደፈጸመው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ አመልክተዋል። ቡድኑ በጥቃቱ ዕለት ከምሽቱ ሦሰት ሰዓት ላይ ከ50 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችን ሰብስቦ ""ጭፍጨፋ ፈፅሟል"" ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። በጥቃቱ ከተገደሉት 28 ሰዎች መካከል 16ቱ ወንዶች ሲሆኑ 12ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን የተናገሩት በተጨማሪ 12 ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል። ጥቃቱን በተመለከተ መግለጫ ያወጣው የኦሮሚያ ክልል መንግሥትም ""አሰቃቂና ዘግናኝ"" ያለውን ጥቃት የፈጸመው ኦነግ-ሸኔ እንደሆነ አመልክቷል። የፖሊስ ኮሚሽነሩ አራርሳ መርዳሳም ከጥቃቱ በኋላ የክልሉ ፖሊስ በአካባቢው በወሰደው እርምጃ የታጣቂው ቡድን አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት መግለጫ በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉና የጸጥታ አካላት በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ በጥቃት ፈጻሚዎቹ ላይ ስለደረሰ ጉዳት ያለው ነገር የለም። ጨምሮም ቡድኑን የህወሓት ተላላኪ በመሆን በአካባቢው የመንግሥት መዋቅርን በማፍረስ በገጠርና በከተማ በመንግሥት አመራሮችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከዚህ በፊት ""ዘግናኝ የሽብር ጥቃቶችን ሲፈፅም ቆይቷል"" ብሏል። ቡድኑ በሚፈጽመው ጥቃት የቀበሌና የክልል አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን ያመለከተው የክልሉ መንግሥት መግለጫ፤ በጥቃቶቹ የግልና የመንግሥት ንብረቶች መውደማቸውንም ገልጿል። መንግሥት ""የኦነግ ሸኔ እኩይ ተግባር ለማስወገድ በወሰደው የሕግ የበላይነትን የማስከበር እርምጃ"" ቡድኑ እየተዳከመ መሆኑን በመጥቀስ ነገር ግን ""በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ የጥፋት ሴራውንና እርምጃውን ቀጥሏል"" ብሏል። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተለይቶ የወጣውና መንግሥት ኦነግ-ሸኔ የሚለው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል። በዚህ አካባቢ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሠላማዊ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ሲዘገብ ቆይቷል። በተጨማሪም በአካባቢው ባሉ የመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችና፣ የጸጥታ አካላትና አመራሮች በተለያዩ ጊዜያት በተፈጸሙ ጥቃቶች ሰለባ ሆነዋል። ለእነዚህ ጥቃቶችም መንግሥት በኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) ይመራል የሚባለው ኦነግ-ሸኔን ተጠያቂ ሲያደርግ ቡድኑ ግን ግድያዎቹን አለመፈጸሙን ሲያስተባብል ቆይቷል። መንግሥት ታጣቂ ቡድኑን ከአካባቢው ለማስወገድ በተለያዩ ጊዜያት በወሰዳቸው እርምጃዎች በርካታ አባላቱን መግደሉንና መማረኩን ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሉት ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የጸጥታ አካላት በኦነግ-ሸኔ ላይ በተወሰዱት እርምጃ 1947 አባላቱ ሲገደሉ 489ቱ ደግሞ መማረካቸውን ተናግረዋል። በዚህም ከጥቂት ወራት በፊትም የቡድኑ መሪ የሆነው ኩምሳ ድሪባ በጸጥታ ኃይሎች መገደሉ የተነገረ ቢሆንም ከቀናት በፊት በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ላይ መታየቱ አነጋጋሪ ሆኗል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56569258 +business በቻይና ተጠቃሚዎች የሚያዙት የምግብ መጠን ላይ ገደብ ሊበጅ ነው "ቻይና የምግብ ብክነትን ለማስቀረት ቆርጣ እንደተነሳችና በርካታ እርምጃዎችን ለመውሰድ መዘጋጀቷን አስታውቃለች። ፕሬዝዳንት ሺ ዢን ፒንግ በአገሪቱ የሚስተዋለውን የምግብ ብክነት '' አስደንጋጭና አሳዛኝ'' ሲሉ ገልጸውታል። 'ክሊን ፕሌት ካምፔይን' ወይም በአማርኛ ንፁህ የምግብ ሰሀን እንቅስቃሴ የተጀመረው ፐሬዝዳንቱ ከኮቪድ-19 በኋላ የምግብ ብክነት ቁልጭ ብሎ ታይቷል ማለታቸውን ተከትሎ ነው። ፕሬዝዳንቱ አክለውም '' የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ ይህንን ጉዳይ ልንከታተለው ይገባል'' ብለዋል። በተጨማሪም በቻይና ለሳምንታት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በርካታ የደቡባዊ የአገሪቱ ክፍሎች በጎርፍ መመታታቸውን ተከትሎ በቶኖች የሚቆጠር የገበሬዎች ምርት እንዳልንበር ሆኗል። ነገር ግን የቻይናው ብሄራዊ የዜና ተቋም 'ግሎባል ታይምስ' እነዚህ ምክንያቶች የምግብ እጥረት የሚያስከትሉ አይደሉም ካለ በኋላ የምግብ ብክነት በራሱ ግን እንደ ትልቅ ጉዳይ ሊታይ እንደሚገባው ገልጿል። የቴሌቪዥን ጣቢያው በበይነ መረብ አማካይነት በርካታ ምግቦችን ሲመገቡ በቀጥታ የሚያስተላልፉ ሰዎች ላይም ወቀሳ መሰል አስተያየት ሰጥቷል። የሺ ዢን ፒንግን ንግግር ተከትሎም የዉሃን የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሩ ማህበር ምግብ ቤቶች ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቡት የምግብ ቁጥር ላይ ገደብ እንዲያስቀምጡ እየወተወተ ነው። በዚህም መሰረት በቡድን የሚመጡ ሰዎች ካላቸው ቁጥር በአንድ ያነሰ የምግብ አይነት ብቻ ነው ማዘዝ የሚችሉት። አራት ሰዎች ወደ አንድ ምግብ ቤት ጎራ ብለው አራት ምግብ ማዘዝ አይችሉም ማለት ነው። ስለዚህ አዝዘው መመገብ የሚችሉት ሶስት ምግብ ብቻ ይሆናል። ነገር ግን ይህ አሰራር ወደ ማህበረሰቡ ዘልቆ እስከሚገባ ብዙ ጊዜ ሊፈጅ እንደሚችል ተገምቷል። በቻይናውያን ባህል መሰረት ደግሞ ከሚመገቡት ምግብ በላይ ማዘዝ እንደ ጥሩ ነገር የሚቆጠር ነው። ሰዎች በቡድን ሆነው ሲመገቡ ሰሀኖችና ትሪዎች ባዶ ሆነው ከታዩ አስተናጋጁ ግለሰብ ወይም ድርጅት እንደ መጥፎ እንግዳ ተቀባይ ነው የሚቆጠረው። 'ኤን-1' የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ሀሳብ በበርካቶች ትችትን አስተናግዷል። ""በጣም አስጨናቂ ነገር ነው"" ብለው የተከራከሩም አልጠፉም። '' አንድ ሰው ብቻውን ወደ ምግብ ቤት ቢሄድስ? ምን ያክል ምግብ ነው ማዘዝ የሚችለው? ምንም?'' ሲል አንድ ግለሰብ በአንድ የቻይና ማህበራዊ ሚዲያ በኩል ሀሳቡን አስፍሯል። ሌሎች ደግሞ አብዛኛዎቹ ምግብ ቤቶች ምግብ እንዲባክን አያደርጉም፤ እንደውም በርካታ የመንግስት ባለስልጣናት ናቸው በየአጋጣሚው ምግብ እንዲባክን የሚያደርጉት ብለዋል። የቻይናው የዜና ወኪል ሲሲቲቪ በበኩሉ በቀጥታ ስርጭት በአንድ ጊዜ ብዙ ምግብ በአፍ የመጉረስ ትእይንት የሚያሳዩ ግለሰቦችም ለዚህ ብክነት አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደሆነ ገልጿል። ''ሙክባንግ' በመባል የሚታወቁት እነዚህ የቀጥታ ስርጭቶች በብዙ የቻይና አካባቢዎችና እስያ አገራት ተወዳጅ ናቸው። ቻይና ይህን መሰል የምግብ ብክንትን የመከላከል እንቅስቃሴ ስትጀምር ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። በአውሮፓውያኑ 2013 እጅግ የተጋነኑ የምግብ ድግሶችን እና የባለስልጣናት ግብዣዎችን ለማስቀረት ስራዎችን አከናውና ነበር። አንድ ቻይና ውስጥ የሚንቀሳቀስና አካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰራ ድርጅት እንዳስታወቀው በአውሮፓውያኑ 2015 በአገሪቱ ከ17 እስከ 18 ሚሊዮን ቶን ምግብ ተርፎ ተደፍቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53762650 +politics ትራምፕን ያስቆጣውና አጋጥሞ አያውቅም የተባለው የኤፍቢአይ እርምጃ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፍሎሪዳው መኖሪያ ቤታቸው ላይ የኤፍቢአይ አባላት ያደረጉት ብርበራ እሳቸውን ብቻ ሳይሆን ደጋፊዎቻቸውን አስቆጥቷል። ድርጊቱን “የፖለቲካ ሴራ ነው” የሚሉት ትራምፕ፣ ባወጡት መግለጫ ፖሊስ ፍተሻውን ያካሄደው ለዋይት ሐውስ ዳግም እንዳልወዳደር እንቅፋት ለመፍጠር ነው ብለዋል። ፍተሻው ከቀድሞ ፕሬዝዳንት የመንግሥታዊ ሰነዶች አያያዝ ጋር በተገናኘ ነው የተባለ ሲሆን፤ ፍተሻው ከዚህ በፊት በየትኛውም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ላይ ያላጋጠመ ነው ተብሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cz9k3nyypvwo +health ኮሮናቫይረስ፡ በእንግሊዝ በየቀኑ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ "በእንግሊዝ ውስጥ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በየቀኑ በኮሮናቫይረስ እንደሚያዙ አንድ ጥናት ጠቆመ፡፡ እንደለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ ጥናት ከሆነ ወረርሽኙ በፍጥነት እየጨመረ ሲሆን በየዘጠኝ ቀናትም በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ይጨምራል፡፡ አጥኚዎቹ ""ወሳኝ ደረጃ ላይ በመሆናችን አንድ ነገር መደረግ አለበት"" እያሉ ነው፡፡ ፈረንሳይ እና ጀርመን ቫይረሱን ለመቆጣጠር የተለያየ ደረጃ ያለው ገደብ ጥለዋል፡፡ በፀደይ ወራት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ወደ ነበረበት ደረጃ በፍጥነት እየተቃረብን ነው በማለት ባለሙያዎቹ ያስጠነቅቃሉ፡፡ ጥናቱ ወቅታዊ የሆነው የኮቪድ -19 ጥናት በመሆኑ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው ተብሎለታል፤ 86 ሺህ የሚጠጉ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉበት እና የመጨረሻዎቹ ምርመራዎች እሁድ የተካሄደበት ጥናት መሆኑን በመጠቆም፡፡ ጥናቱ እንዳሳየው ቫይረሱ በሁሉም የእድሜ ክልል እና በእያንዳንዱ የእንግሊዝ ግዛት እየጨመረ መሆኑን ያሳያል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ስርጭቱ ከፍተኛ ቢሆንም በደቡብ በኩል ቢሆን በፍጥነት እያደገ ነው፡፡ ከአጥኚዎቹ አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ስቲቨን ሪሌይ መረጃው መገኘት ሲጀምር እንዳዘኑ ገልፀው ""አሁን ያሉት እርምጃዎች በቂ አይደሉም"" ብለዋል ፡፡ ""ለውጥ መኖር አለበት። ፍጥነት በእውነቱ በጣም ፈጣን በመሆኑ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከገና በፊት ለውጥ ሊኖር ይገባል"" ብለዋል ፡፡ ህዝቡ በደንብ ህጎችን ማክበር አለበት ወይም መንግሥት ከባድ ገደቦችን መጣል አለበት ሲሉም ተከራክረዋል ፡፡ ""መረጃዎቹ በፍጥነት መወሰንን የሚሹ ናቸው"" ብለው ገልጸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54726762 +health "ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ ኮቪድ-19 በጽኑ የሚታመሙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ""በአስደንጋጭ ሁኔታ"" ጨመረ" "በኢትዮጵያ ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚያዙ፣ ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡና በበሽታው ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር ""በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ"" መሆኑን የሕብረተሰብ ጤና ኢነስቲቲዩት አስታወቀ። ቀደም ሲል በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ህክምና እያገኙ የነበሩ ሰዎች ቁጥር በአራት መቶዎች ውስጥ የቆየ ሲሆን ይህ አሃዝ ባለፉት ቀናት ውስጥ አምስት መቶን ተሻግሮ ወደ ስድስት መቶ መጠጋቱን በየዕለቱ የሚወጣው የበሽታው የዕለት ሁኔታ ሪፖርት ያመለክታል። ሰኞ ዕለት በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኙ የነበሩት ሰዎች ቁጥር 531 የነበረ ሲሆን ትናንት ማክሰኞ ቁጥሩ በ60 ጨምሮ 591 በመድረሱ በህክምና ተቋማቱ ላይ ጫና መፈጠሩ ተነግሯል። በዚህም ሳቢያ የጽኑ ህሙማን ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በሚውሉት የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን አቅርቦት ላይ እጥረት አጋጥሟል የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ትናንት እናደለው የሰውሰራሽ መተንፈሻ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች መካከል ስምነቱ በመጠባበቅ ላይ ነበሩ። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በነበሩ ቀናት የተደረጉ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤቶች እንደሚያመለክቱት በየዕለቱ በአማካይ ከ1300 በላይ ሰዎች ላይ በወረርሽኙ መያዛቸውን ያመለክታል። አጠቃላይ የምርመራው ውጤት በመቶኛ ሲሰላ ከተመረመሩት 100 ሰዎች ውስጥ በአማካኝ 19 ሰዎች ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በዚህም በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ32 በመቶ በላይ ጨምሯል። በበሽታው ሰበብ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎችን ቁጥር ስንመለከትም ከዕለት ዕለት ዕየጨመረ በአማካይ ከ15 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት እያለፈ ነው። ይህም ቀደም ካሉት ሳምንታት ጋር ሲነጻጸር በ89 በመቶ መጨመሩን ባለሙያዎቹ ተናግረዋል። ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን ተሰግቷል የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ማክሰኞ ዕለት፣ በሰጡት መግለጫ ""ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጭ ከመሆኑ በፊት ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት አለበት"" ሲሉ አሳስበዋል። የበሽታው ስርጭት ባለፉት ወራት በተለይም ባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ጠቅሰው፤ ቀደም ሲል በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ከ10 በመቶ በታች የነበረው ከፍ ብሎ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ 17 በመቶ ማሻቀቡን ተናግረዋል። በዚህም እስካሳለፍነው ቅዳሜ ድረስ በነበሩት 10 ቀናት ውስጥ ""ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ የ149 ሰዎች ህይወትም በወረርሽኙ ሳቢያ አልፏል"" ብለዋል። የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን እንዲሁም የጽኑ ህሙማን ህክምና የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥርም በባለፉት ቀናት ለመጀመሪያ ጊዜ ከ450 መብለጡን ተናግረዋል። በዚህም ሳቢያ የጽኑ ህሙማን ክፍሎች መሙላታቸውን፣ ያሉ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) በህሙማን ሙሉ ለሙሉ መያዛቸውን እንዲሁም የኦክስጅን እጥረት ማጋጠሙን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ እስከ መጋቢት 06/2013 ዓ.ም ድረስ በተደረገ የኮሮናቫይረስ ምርመራ 176,618 ሰ��ች በወረርሽኙ መያዛቸው የተረጋጠ ሲሆን 2,555 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በተጨማሪም 531 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ ይህ ቁጥርም በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኘ በኋላ ከፍተኛው ነው። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ተቋም እንዳለው ከእነዚህም ውስጥ 66ቱ ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ተቋም ዛሬ ባወጣው መረጃ መሰረት ያሉት የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች በመያዛቸው በጽኑ የታመሙ 8 ያህል ግለሰቦች የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። ""ክትባት መሰጠቱ ይቀጥላል"" የጤና ሚኒስትሯ በአገሪቷ እየተሰጠ ያለውን የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት አስመልክቶ የአስትራዜኒካ ክትባትን መስጠት እንደሚቀጥል ተናግረዋል። አንዳንድ አገራት ከአስትራዜኒካ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ባሉት ችግር ምክንያት ክትባቱን መስጠት ቢያቆሙም በኢትዮጵያ ክትባቱ መሰጠት እንደሚቀጥል የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌይ እና ስፔንን ጨምሮ ስምንት የአውሮፓ አገራት ክትባቱ ከደም መርጋት ጋር የተያያዘ ችግር ሊኖረው ይችላል በሚል የአስትራዜኔካ ክትባት ለጊዜው እንዲቆም አድርገዋል። የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ ማክሰኞ፣ በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እየተሰጠ ያለው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ጋር በተያያዘ እስካሁን ያጋጠመ ችግር እንደሌለ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መሰጠት የተጀመረው ወረርሽኙ በአገሪቱ ውስጥ መገኘቱ ይፋ በተደረገ በዓመቱ ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 04/2013 ዓ.ም ነበር። በአገሪቱ እየተሰጠ የሚገኘው የአስትራዜኔካ ምርት የሆነው 2.2 ሚሊየን ብልቃጥ ክትባት ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት አቅርቦት ጥምረት የቀረበ ነው። ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ እስካሁን ባለው መረጃ ተከሰተ የተባለው ችግር ""ከአስትራዜኒካ ክትባት ጋር ግንኙነት እንደሌለውና ክትባቱ መቀጠል እንዳለበት የዓለም የጤና ድርጅት፣ የአውሮፓና የእንግሊዝ የመድኃኒት ጥናትና ቁጥጥር ባለስልጣን በይፋ አስታውቀዋል"" ብለዋል። በአውሮፓ ሕብረት አባላት አገራትና በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ እስካሁን 17 ሚሊዮን ሰዎች የአስትራዜንካ ክትባትን መከተባቸውና ከእነዚህ ውስጥም 40ዎቹ የደም መርጋት ችግር እንዳጋጠማቸው የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት በርካታ የአውሮፓ አገራት የአስትራዜኒካ ክትባት እንዳይሰጥ ማገዳቸውን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ክትባቱ የደም መርጋት ስለማስከተሉ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ብሏል። ዶ/ር ሊያ ታደሰም ክትባቱ በበርካታ አገራት ውስጥ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች መዳረሱንና በኢትዮጵያም መሰጠቱ እንደሚቀጥል ተናግረው ጉዳዩ ""በሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኩል ጥብቅ ክትትል ይደረግበታል"" ብለዋል። በዚህም መሠረት ክትባቱን በተመለከተ አዲስ ነገር የሚኖር ከሆነ ሕብረተሰቡ እንዲያውቀው እንደሚደረግ ገልጸው ""ከክትባቱ ጋር ተያይዞ እስካሁን የገጠመ ችግር ባለመኖሩ ክትባቱን መስጠታችንን እንቀጥላለን"" ብለዋል። በዚህም መሠረት ክትባቱ ለጤና ባለሙያዎች፣ ተጓዳኝ በሽታ ላለባቸው ሰዎችና ለአረጋዊያን በተከታታይ የሚሰጥ መሆኑን በመግለጽ እስከሚቀጥለው ዓመት ታኅሣስ ድረስ ከአገሪቱ ሕዝብ 20 በመቶውን እንዲከተብ ይደረጋል ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56398440 +sports የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ዓይናቸውን ለምን እስያ ላይ ጣሉ? "“ሃይማኖተኛ አደለሁም። የማምነው ���ገር የለኝም። ሊቨርፑል እምነቴ ነው። ለእኔ የሕይወቴ መስመር ነው።” ይህን ያለው ቪጃይ ነው። ቪጃይ ውልደቱ ሲንጋፖር ነው። ከሊቨርፑሉ አንፊልድ ስታዲየም 11 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቆ ይገኛል። የሚወደው ቡድን ትውልድ ከተማውን እንዲጎበኝ እአአ ከ2011 ጀምሮ ሲጠብቅ ቆይቷል። ይህ ግን የእሱ ብቻ ታሪክ አይደለም። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በሊቨርፑል እና በክሪስታል ፓላስ መካከል የወዳጅነት ጨዋታ ተደርጓል። ከ50,000 በላይ ደጋፊዎች የሲንጋፖርን ብሔራዊ ስታዲየም ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልተውታል። ለሦስት ዓመታት የተጣለው የኮቪድ የጉዞ እገዳ ተነሳ። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቡድኖችም ለቅድመ-ውድድር ዝግጅት አድማስን እያቋረጡ ነው። ጉዞዎቹ በገንዘብ ረገድ ያላቸው ጠቀሜታ ለመገመት አስቸጋሪ ነው። ማንቸስተር ዩናይትድ እአአ በ2021 ወደ 56 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ እንዳጣ ክለቡ ይፋ አድርጎ ነበር። “ዋነኛው” ምክንያት ኮቪድ መስተጓጎል መሆኑ ተጠቅሷል። ከዚህ መካከል አንዱ በሕንድ ሊደረግ የነበረው የቅድመ ውድድር ዘመን ጉብኝት መሰረዙ ነው። አሁን እገዳው ቀንሷል። ክለቦችም ቁጥር አንድ ወደሚሉት የገበያ ስፍራ እየጎረፉ ነው። የሊቨርፑል ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ቢሊ ሆጋን “እስያ በደጋፊዎች ብዛት ቀዳሚዋ መዳረሻችን ናት” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “የትኛውንም አውሮፕላን ተሳፍረህ ወደ ኤስያ ብትሄድ የሊቨርፑል ደጋፊዎችን ማግኘት ትችላለህ፣ ሲል አንድ ሰው የነገረኝን ማስታወስ እፈልጋለሁ። አንድ ሦስተኛው ዓለም አቀፍ ደጋፊያችን መገኛው እዚህ ነው። በእስያ ውስጥ ትልቅ ዕድል እንዳለ ይሰማናል።” በዚህ ክረምት ማንቸስተር ዩናይትድ ፊቱን ወደ ታይላንድን እና አውስትራሊያን አዙሯል። ከሊቨርፑል እና ከክሪስታል ፓላስ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አከከናውኗል። ቶተንሃም ሆትስፐር ወደ ደቡብ ኮሪያ አቅንቷል። ደቡብ ኮሪያ የክለቡ ከፍተኛ ኮከብ ግብ አግቢው ሶን ሄንግ ሚን አገር ነች። ከስፖርት አንጻር እነዚህ ጉዞዎች ትርጉማቸው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በተለያዩ የሰዓት ዞኖች የሚደረጉ ረዥም በረራዎች፣ በከፍተኛ ሙቀት እና እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ልምምድ ማድረግን ያካትታል። ይህ ግን እንግሊዝ ለሚኖራቸው የአዲሱ የውድድር ዘመን ዝግጅት ጥሩ  አይደለም። የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “የምመርጠው ነገር አይደለም” ብለዋል። “ሲጀምር እኔ አሰልጣኝ ነኝ። ለሁለት ሳምንት ኦስትሪያ ቆይተን በቀን ሁለት ጊዜ ብናሰልጥን ጥሩ ነበር። “የደጋፊዎቻችን ቁጥር እስያ ውስጥ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ እናውቃለን። ወደ እነርሱ ቀረብ ማለት ጥሩ ነገር ነው።” እንደ እውነቱ ከሆነ በእግር ኳስ ውስጥ ለረዥም ጊዜ የከረመ ክርክር ነበር። ክርክሩ ከረጅም ጊዜ በፊት ውሳኔ ያገኘ ይመስላል። ከፋይናንስ ጋር ያለው ወገን የበላይነት ይዟል። በዚህ ዓመት የወጡ አዳዲስ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ፕሪሚየር ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዓለም አቀፍ ጨዋታ አስተላላፊዎች ከፍተኛ ገቢ ያገኛል። ይህም ለመጀመሪያ ጊዜ ከእንግሊዝ ገበያ ከሚገኘው የበለጠ ገቢ ይሆናል። በሚቀጥለው የውድድር ዓመት እስከ 2025 ባለው ጊዜ ከእስያ ገበያ 1.4 ቢሊዮን ዶላር ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል። ስፐርስ በደቡብ ኮሪያ የወደጅነት ጨዋታ አድርጓል። ይህም ከሃገሪቱ ክለቦች ከተወጣጡ የኮከቦች ቡድን ጋር ተደረገ ሲሆን፣ የጨዋታው ትኬት በ25 ደቂቃ ውስጥ ተሸጦ ተጠናቋል። በአገሪቱ ታሪክ ከፍተኛ ስርጭት ያገኘ የስፖርት ዝግጅት ሆኗል። ባንኮክ የሚገኙ የውድድሩ አዘጋጆች በማንቸስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል መካከል ለሚደረገው ���ወዳጅነት ጨዋታ የትኬት መነሻ ዋጋው 136 ዶላር አድርገዋል። በሲንጋፖር ርካሽ የተባለለት ቲኬት 107 ዶላር ተቸብችቧል። እነዚህ ዋጋዎች ከእንግሊዝ የነጥብ ጨዋታዎች አንጻር እንኳን ውድ የሚባሉ ናቸው። ሆኖም የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ ክለቦችን የመሳብ ጠንካራ አቅም አላቸው። የሊቨርፑል ቃል አቀባይ “የእነዚህን የቲኬቶች ዋጋ እኛ አልወሰንም። እኛ የተወሰነልንን ክፍያ እንቀበላለን። እኛ ከትኬት ገቢ ምንም አይነት ድርሻ አንቀበልም"" ብለው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የእስያ ገቢ ክለቦቹ ከእነዚህ የወዳጅነት ግጥሚያዎች ምን ያህል እንደሚያገኙ አይታወቅም። ምክንያቱም መረጃው በጥብቅ ስለሚያዝ። ተንታኞች እንደሚሉት ግን ክፍያውን ለጉዞዎቹ ብቸኛ ምክንያት አድርጎ አያስቀምጥም።  ለዚህ እንደምክንያት የሚቀመጠው የጉዞ እና የሠራተኞች ወጪዎች መኖራቸው ነው። “በእውነቱ ከሆነ ቡድኖቹ ከቅድመ-ውድድር ጨዋታዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በቀጥታ አያገኙም። ምናልባትም በአንድ ግጥሚያ ጥቂት ሚሊዮን ዶላር ቢገኝ ነው” ሲል የስፖርት ቢዝነሱ የእስያ-ፓስፊክ አርታኢ ኬቨን ማኩላግ ይገልጻል። “ነገር ግን አንድ ትልቅ ዓላማ አለ። ይህም የስም ግንባታ እና በቀጣይ የቴሌቭዥን ሥርጭት ገበያውን በሚመራውና የስፖንሰርሺፕ ስምምነቶችን በሚያስገኘው ገበያ ውስጥ መሳተፍ ነው። ትክክለኛው ገንዘብ ይህ ነው።” ሊቨርፑል በሲንጋፖር በከተመበት ወቅት ከ240 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው አዲስ የማሊያ ስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ ስታንዳርድር ቻርተርድ ከተባለውና ትኩረቱን እስያ ላይ ካደረገው ባንክ ጋር ተደርሷል። የእግር ኳስ ክለቦች የስፖንሰርን አቅማቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከማሳደግ ባለፈ የደጋፊዎችን መረጃ ሊያቀርቡላቸው ይችላሉ። ለምሳሌ ማንቸስተር ዩናይትድ የደጋፊ ግንኙነት አስተዳደር (ሲአርኤም) ዳታቤዝ 50 ሚሊዮን መዝገቦችን እንደያዘ ይገምታል። ባለፈው ዓመት በማኅበራዊ ሚዲያው 176 ሚሊዮን አስፍሯል። ይህም ለስፖንሰርሺፕ ገንዘብ፣ ስያሜ እና ለግብይት ክፍል የሚረዱ ከክለቡ ጋር የተመዘገቡ ወይም የተሳተፉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደጋፊዎችን ጠቃሚ መረጃ ያስገኛል። “የመጀመሪያው ትልልቅ ስፖንሰሮች የሚጠይቁት በደጋፊዎች ዙሪያ ያለውን መረጃ ነው” ሲል ማኩላግ ተናግሯል። “ገንዘባቸውን ፈሰስ ከማድረጋቸው በፊት አንድ ክለብ ምን ያህል ደጋፊ እንዳለው፣ ዕድሜ፣ ወንድ፣ ሴት፣ የገቢ መጠን እና የመሳሰሉትን ነገሮች ማወቅ ይፈልጋሉ።” የእንግሊዝ እግር ኳስን በገንዘብ በስፋት እንዲሰበሰብ ያስቻለው ግን የቴሌቭዥን ገቢ ነው። ለዓመታት ሌሎች የስፖርት ሊጎች (የአውሮፓ እግር ኳስ ሊጎችን ጨምሮ) ፕሪሚየር ሊጉን በቅናት ሲመለከቱ ኖረዋል። ወደ እስያ በማቅናት እነዚህ ሊጎች ቀዳሚ ናቸው። የፕሪሚየር ሊጉ ፉክክር፣ ልዩ የሆነው የደጋፊዎች ባህል እና ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ጋር ያለው ትስስር ሊጉ በዓለም አቀፍ ደረጃ 3.2 ቢሊየን ተመልካቾችን በመሳብ በብዛት የታየ የስፖርት ሊግ እንዲሆን አስተዋጽኦ አድርጓል። ፕሪሚየር ሊግ እንደሚለው ግማሹ የዓለም ደጋፊ እና አንድ አራተኛው የቴሌቭዥን ተመልካቾች በእስያ ፓስፊክ ይገኛል። ይህ ሁሉ የሆነው ብዙ ጨዋታዎች በእኩለ ሌሊት እየተጠናቀቁም ነው። እነዚህን ሁሉ ደጋፊዎች ይዞ ማቆየት ፈታኝ እንደሚሆን ባለሙያዎች ይናገራሉ። በተለይም ለወጣቱ ትውልድ በጣም ሰፊ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች እና የአኗኗር ዘይቤዎች አማራጮች መኖራቸው ዋነኛው ስጋት ነው። የስፔኑ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንት የሆኑት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ባለፈው ዓመት “ወጣቶች በእግር ኳስ ላይ ፍላጎት የላቸውም። ራሳቸ���ን የሚያዘናጉባቸው ሌሎች መድረኮች አሏቸው” ማለታቸውን ማስታወስ ተገቢ ነው። ይህ አመለካከት የቴሌቭዥን ገቢ ውሎ አድሮ እየቀነሰ እንደሚሄድ ከተገመተው ትንበያ ጋር ተደማምሮ በአውሮፓ ከፍተኛ የእግር ኳስ ክለቦች ውስጥ ያሉ አንዳንድ ኃላፊዎችን ደጋፊዎቻቸውን ለማሳተፍ አዲስ ውድድር መፈጠር እንዳለበት አሳምኗቸዋል። አንደኛው ሃሳብ የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ነበር። አምስት የእንግሊዝ ክለቦችን ጨምሮ ሁሌም ተሳታፊ በሚሆኑ ክለቦች የሚደረግ ውድድር ለማድረግ ያቀደ ነበር። ይህም በዓለም ዙሪያ በተለይም በእስያ ውስጥ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አድናቂዎችን ታላሚ ያደረገ ነበር። እነዚህ ሁሌም ኃያል ቡድኖች እርስ በእርስ ሲፎካከሩ ማየት የሚፈልጉ ናቸው፤ ግን በጅምር ቀረ። በዩናይትድ ኪንግደም እና በዓለምአቀፍ ደጋፊዎች ዘንድ ያስነሳው ቁጣ እንዲሰረዝ ምክንያት ሆነ። “የአውሮፓ እግር ኳስ ክለቦች ስለእስያ ግምት መያዝ የለባቸውም። ስለሚያገኙት እያንዳንዱ ዶላር መታገል ግን አለባቸው” ሲሉ በፈረንሳይ በኤምሊዮን ቢዝነስ ትምህርት ቤት የስፖርት ፕሮፌሰር የሆኑት ሲሞን ቻድዊክ ተናግረዋል። “የእስያ ሸማቾች ብልህ፣ የተራቀቁ እና አስተዋይ ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአውሮፓ እግር ኳስ በእስያ ደጋፊዎች መካከል መጠነኛ መለያየት እንዳለ ሊከራከሩ ይችላሉ። ስለዚህ ክለቦች እስያን በቀላሉ እንደሚቆጣጠሩት በማሰብ እብሪተኛ ወይም የዋህ እንዳይሆኑ ይመከራሉ።"" ቻድዊክ አክለውም የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች በውጭ አገራት ሊደረጉ ይችላሉ ተብሎ በ 2008 ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበው ሃሳብ ከአጭር እስከ መካከለኛ ባለው ጊዜ የማይሳካ ነው። ጉዳዩ ግን በድጋሚ ሊታይ ይችላል። ወደ ሲንጋፖር እንመለስ፤ ቪጃይ ሸሚዙን አውልቆ ጀርባውን ያሳያል። በንቅሳት ተዥጎርጉሯል። የሊቨርፑል ስም እና ክለቡ በታሪኩ ዋንጫ ያገኘባቸው ዓመታትን ተነቅሷል። ስለ ወደፊቱም ቢሆን ብሩህ ተስፋ ሰንቋል። “አባቴ የሊቨርፑል ደጋፊ ነበር። ከሴት ልጆቼ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረግኩት ነገር የሊቨርፑል ማሊያን ለእነሱ ማልበስ ነበር። እመኑኝ ይህ በትውልዶችን ቅብብል ይቀጥላል” ሲል ያጠናቅቃል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/crg7j1m7792o +politics ታጣቂዎች የጋምቤላ ከተማን በከፊል ተቆጣጥረው እንደነበረ ክልሉ ገለጸ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ ላይ ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ ላይ ጥቃት ከፍተው የከተማዋን የተወሰነ ክፍል ተቆጣጥረው እንደነበረ የክልሉ መንግሥት ገለጸ። የክልሉ መስተዳደር ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በጋምቤላ ከተማ “የሸኔ እና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር” በጋራ ጥቃት ከፍተው እንደነበረና ከረፋድ አራት ሰዓት በኋላ መጠነኛ መረጋጋት እንዳለ አመልክቷል። በታጣቂዎች እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል ዛሬ ማክሰኞ ከማለዳ ጀምሮ በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ በክልሉ የፀጥታ አባላት እና በታጣቂዎቹ ላይ ጉዳት መድረሱንም የቢቢሲ ምንጮች ገልጸዋል። የጋምቤላ ክልል ርዕሰ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ መስተዳደር ስለተከሰተው ሁኔታ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ በሰጡት መግለጫ እናዳሉት፣ በጋምቤላ ከተማ ያጋጠመው የፀጥታ ችግር የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል። ከተማዋም በአሁኑ ጊዜ በክልሉ የፀጥታ ኃይል ቀጥጥር ስር ሙሉ ለሙሉ መግባቷን አቶ ኡሞድ ገልጸው፣ ታጣቂዎቹ የከፈቱትን ጥቃት ተከትሎ የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ “በታጣቂዎቹ ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን” አመልክተው በፀጥታ ኃይሉ ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል። በጋምቤላ ከተማ ማክሰኞ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም. ከንጋት 11 ሰዓት ተኩል ገደማ ጀምሮ ለሰዓታት ���ቆየ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ እንደነበርና ከፊል የከተማዋ ክፍልም በታጣቂዎቹ ቁጥጥር ስር መግባቱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። አንድ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ክስተቱ በጋምቤላ ከተማ ውስጥ ማጋጠሙን አረጋግጠው፣ በዚህም የሰው ህይወት መጥፋቱንና የተጎዱ መኖራቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የክልሉ ባለሥልጣን ከዕኩለ ቀን በፊት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቢያንስ ሁለት የፀጥታ ኃይሎች እንዲሁም ከታጣቂዎቹ የሦስቱ ህይወት ማለፉን ከሆስፒታል ምንጮቻቸው መረዳታቸውን ተናግረዋል። ክልሉ ማክሰኞ ረፋድ ላይ ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ መካከል የደረሰው ጉዳት በውል እንደማይታወቅ አመልክቶ በታጣቂዎችና በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጾ ነበር። ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የተኩስ ልውውጥ “ያለማቋረጥ እስከ ረፋዱ 4 ሰዓት ከ20 ድረስ ሲካሄድ ቆይቶ” አሁን በከተማዋ ውስጥ መረጋጋት እንደሚታይና “የመንግሥት የፀጥታ ኃይል ባካሄደው ብርቱ ትግል ከተማውን በከፊል ነፃ ማውጣት እንደተቻለ” ክልሉ ገልጿል። ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች እንዳሉት በዚሁ ክስተት ሳቢያ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የንግድ ሥራዎች ብሎም ሌሎች መደበኛ እንቅስቃሴዎች የተስተጓጎሉ ሲሆን ነዋሪዎችም በቤታቸው ዘግተው መቀመጣቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት ክስተቱን በሚመለከት ረፋድ ላይ ባወጣው መግለጫ ላይ የከተማው ነዋሪ ኅብረተሰብ ከቤት ባለመውጣት የፀጥታ ኃይሉ እያደረገ ላለው የሕግ ማስከበር ተግባር የበኩሉን እንዲወጣ ተጠይቋል። በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ አካባቢም ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ላለፉት አስከ ረፋድ አራት ሰዓት ድረስ ሲሰማ እንደነበረ አንድ በአቅራቢያው የነበሩ ነዋሪ ጠዋት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በከተማዋ ስለተከሰተው የተኩስ ልውውጥና አሁን ስላለው ሁኔታ “ምንም የምንሰጠው መረጃ የለም’’ ሲሉ ረፋድ ላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቢቢሲ ተጨማሪ መረጃ ከርዕሰ መስተዳደሩ ለማግኘት ቢጠይቅም ለጊዜው ከዚህ ያለፈ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። በዚህም የከተማዋን የተወሰነ ክፍል ታጣቂዎቹ መቆጣጠራቸውን ብሎም የጥቃቱ ኢላማ የርዕሰ መስተዳደሩን ጽህፈት ቤት ለመቆጣጠር ያለመ ሳይሆን እንደማይቀር የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። በተኩስ ልውውጡ በርካቶች መቁሰላቸውን ብሎም ታጣቂዎቹ ከርዕሰ መስተዳደሩ ጽህፈት ቤት በተጨማሪ በተለምዶ ቤተ መንግሥት የሚባለውን የርዕሰ መስተዳደሩን መኖሪያ ቤት እንዲሁም የነዳጅ መከማቻ ዴፖ ለመቆጣጠር ጥቃት ከፍተው እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል። የክልሉ ባለሥልጣንም ጥቃቱን በሚመለከት “ለፌደራል መንግሥት አሳውቀናል። ከአቅራቢያ ወደ ከተማው ኃይል ለማሰማራት እየሞከሩ እንደሆነ ነግረውናል። እዚህ ያለው ኃይላቸው ግን ትንሽ ነው’’ ሲሉ ማክሰኞ ጠዋት ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት አንድ የከተማው ነዋሪ ከባሮ ወንዝ ተሻግሮ ያለው የከተማው ክፍል በታጣቂዎች ቁጥጥር ስለሆነ ጠዋት ከባሮ ማዶ ተሻግረው እንደሚገኙ ተናግረዋል። “ከአራት ቀን በፊትም ተመሳሳይ ሙከራ ተደርጎ ነበር። ከዚህ በፊት በዚህ መጠን የታጣቂዎች እንቅስቃሴ አይተን አናውቅም ነበር’’ ሲሉም ነዋሪው አክለዋል። መንግሥት በሽብርተኝነት የሰየመውና ኦነግ-ሸኔ የሚለው፣ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሲል የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የሕዝብ ግንኙነት ኦዳ ተርቢ የተሰኘው ግለሰብ በትዊተር ገጹ ሠራዊቱ ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር በመሆን በጋምቤላ ከተማ ወታደራዊ ዘመ�� እያካሄደ ነው ብሏል። ይኸው ገጽ አክሎም ከጋምቤላ በተጨማሪም በምዕራብ ኦሮሚያ በደምቢ ዶሎ ተመሳሳይ ወታደራዊ ዘመቻ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። የጋምቤላ ክልል በምዕራብ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የሚዋሰን ሲሆን፣ ታጣቂዎች ይንቀሳቀሱባቸዋል ከሚባሉት ከምዕራብ ኦሮሚያ እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ጋር ይዋሰናል። በተለያዩ ጊዜያት ከጎረቤት አገር ሱዳን ዘልቀው የሚገቡ ታጣቂዎች በነዋሪዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጽሙ እንደነበረም አይዘነጋም። https://www.bbc.com/amharic/articles/cmje02png3mo +politics ስደተኛው የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት ሚሊዮን ዶላሮችን አሽሽተዋል መባሉን አስተባበሉ "በቅርቡ ከአገራቸው የሸሹት የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት የነበሩት አሽረፍ ጋኒ ሚሊዮን ዶላሮችን ከካቡል ይዘው ወጥተዋል የሚለው ወሬ ‹መሰረተ ቢስና ሐሰተኛ› ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡ አሽረፍ ጋኒ ትናንት በቪዲዮ ከተጠለሉበት የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በሰጡት መግለጫ ከአገሪቱ በርካታ ገንዘብ መውሰዳቸው በስፋት እንደሚወራ ጠቅሰው ይህ ግን ፍጹም ሐሰት ነው ብለዋል፡፡ የታሊባንን ወደ ካቡል መገስገስ ተከትሎ ከአገራቸው የሸሹት የአፍጋኒሰታን የቀድሞ ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ የት አገር እንደሄዱ እስከ ትናንት ድረስ ሲያነጋግር ነበር፡፡ በመጨረሻ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ አሽረፍ ጋኒ ከእኔ ዘንድ ናቸው ብላለች፡፡ አሽረፍ ጋኒ ካቡልን የለቀቁት ታሊባኖች ካቡል መግባታቸው እስደተሰማ በሰዓታት ውስጥ ባለፈው እሑድ ነበር፡፡ የኢምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሽረፍ ጋኒን እና ቤተሰባቸውን በእንግድነት የተቀበለው በሰብአዊነት ምክንያት ነው ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡ አገራቸውን በክፉ ጊዜ በዚያ ፍጥነት ጥለው መሄዳቸው አሽረፍ ጋኒን ለከፍተኛ ትችት ዳርጓቸው ቆይቷል፡፡ ትናንት ረቡዕ የቪዲዮ መግለጫ የሰጡት አሽረፍ ጋኒ ግን ‹እኔ ቶሎ አገሪቱን ጥዬ ባልሄድ ኖሮ በካቡል ደም ይፈስ ነበር› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ""ለጊዜው ኢምሬትስ ነው ያለሁት፡፡ ደም መፋሰስ እንዲቆም በሚል ነው ወደዚህ የመጣሁት፡፡ አሁን ንግግር ጀምረናል፤ ወደ አፍጋኒስታን የምመለስበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እየተነጋገርኩ ነው"" ብለዋል በመግለጫቸው፡፡ የ72 ዓመቱ ስደተኛው ፕሬዝዳንት አሽረፍ ጋኒ አገሪቱን ለታሊባን አስረክበው በዚያ ፍጥነት መሸሻቸው አፍጋኒስታናዊያንን ብቻ ሳይሆን ጆ ባይደንንም ያስገረመ ይመስላል፡፡ ባይደን ባለፈው ሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አፍጋኒሰታናዊያን ለመዋጋትና ለመሞት የማይፈቅዱለትን ጦርነት የአሜሪካን ወታደሮች የሚሞቱት ምን በወጣቸው ሲሉ አስተያየት ሰጥተው ነበር፡፡ በፌስቡክ በቀጥታ ለሕዝብ በተላለፈው የአሽረፍ ጋኒ የትናንቱ መግለጫ ላይ ከካቡል የወጡበትን ሁኔታ የገለጹት ስደተኛው ፕሬዝዳንት እንዳብራሩት ከቤተ መንግሥት እንዲለቁ የተደረጉበትን ፍጥነት ‹ጠባቂዎቼ ጫማዬን እስካጠልቅ ድረስ እንኳ አልታገሱኝም›› ብለዋል፡፡ ‹ፋታ አልነበረም፡፡ ከታሊባን ጋር የጥምረት መንግሥት እንዲኖር ለመደራደር ፈልጌ ነበር፡፡ ሆኖም ፋታ አልነበረም› ብለዋል አሽረፍ ጋኒ፡፡ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከአገራቸው ለሚሸሹ መሪዎች ከለላ ስትሰጥ ይህ የመጀመርያዋ አይደለም፡፡ ኢምሬቶች ከዚህ ቀደም የፓኪስታኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ለነበሩት ቤናዘር ቡቶ በ1990ዎቹ በተመሳሳይ ሁኔታ ዱባይ የክፉ ጊዜ ቤታቸው እንድትሆን ፈቅደው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የተባቡሩት አረብ ኢምሬትስ የሌሎች አገሮች ፖለቲካ በፍጹም ወደ አፈሯ እንዲመጣ አትሻም ብሏል የቢቢሲ የደኅንነት ጉዳዮች ዘጋቢ ፍራንክ ጋርድነር፡፡ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በርካታ ፓኪስታናዊያንና አፍጋኒስታናዊ��ን በሠራተኝነት ይኖራሉ፡፡ አሽረፍ ጋኒ ወደ ሥልጣን የመጡት በ2014 ሲሆን በየካቲት 2020 ደግሞ በድጋሚ ምርጫን አሸንፈው ነበር፡፡ ከዓመት በፊት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው አንድ ቃለ ምልልስ ታሊባን ወታደራዊ ድሎችን እያገኘ መሆኑ ያሳስባቸው እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ ‹ይህ ቬትናም አይደለም፡፡ መንግሥት ሊወድቅ አይችልም› ሲሉ ምላሽ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-58243666 +business የኢትዮጵያ አበባ ላኪዎችን ገቢ ክፉኛ የጎዳው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ በሆነው ኮሮናቫይረስ ምክንያት በጥቂት ቀናት ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ማጣታቸውን የአበባ አምራቾች ገለጹ። ኢትዮ አግሪሴፍት በሆለታ እና በባህርዳር ካሉት ሁለት የአበባ እርሻዎች በዓመት እስከ 40 ሚሊዮን አበባ ዘንግ ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ያቀርብ እንደነበር ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ኢሳያስ ከበደ ለቢቢሲ ገልጸዋል። እንደ አቶ ኢሳያስ ገለጻ በቀጥታ እና በጨረታ ለዓለም ገበያ በሽያጭ ይቀርብ የነበረው አበባ ባለፉት ሶስት ሳምንታት ዋጋው በከፍተኛ ደረጃ ወርዷል። በየቀኑ እስከ 45ሺህ ዘንግ የሚጠጋ አበባ ለዓለም ገበያ ያቀርብ የነበረው አግሪ ሴፍት ከማርች 15 በኋላ በመቋረጡ በየቀኑ 21200 የአሜሪካ ዶላር ወይም 678400 ብር እያጣ መሆኑን ገልፀዋል። • በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሦስት ሰዎች ተገኙ • የአሜሪካ እስር ቤቶች በኮሮናቫይረስ ምክንያት እስረኛ መልቀቅ ጀመሩ ድርጅቱ ሠራተኞቹን እረፍት እንዲወጡ እያደረገ ከመሆኑም በላይ በየቀኑ ወደ አንድ መቶ ሺህ የሚጠጋ የአበባ ዘንግ ወደ ኮምፖስተነት ለመቀየር ተገዷል። ከባህርዳር ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኘው ጣና ፍሎራም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተመሳሳይ ችግር ገጥሞታል።ድርጅቱ ባለፉት ስምንት ቀናት ብቻ አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዘንግ ገበያ በማጣት ምክንያት ለመጣል መገደዱን የጣና ፍሎራ ሽያጭ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብነት በላይነህ ገልጸዋል። ባለፉት ስምንት ቀናት በገጠመው የገበያ ችግር ምክንያት ወደ 10 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ማጣቱን አስታውቀዋል። አክለውም ከ700 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞቹም ያለሥራ መቀመጣቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አበባና አትክልት አምራች ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ዘውዴ በተለይ ለቢቢሲ እንደገለጹት ማህበሩ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ጀምሮ በሥራቸው ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ተጽዕኖ እና በእርሻዎቹ እንዳይሰራጭ ለማድረግ እየተሠራ ቆይቷል። ከየካቲት እስከ ግንቦት ያሉት ወራት በአበባ ሥራ ትልቅ የንግድ እንቅስቃሴ ያለበት መሆኑን ጠቅሰው አሁን ያለው የአበባ ዋጋ ካለፈው አመት አማካይ ጋር ሲነጻጸር በ85 በመቶ መቀነሱን አስታውቀዋል። በቶሎ የሚበላሽ እና የማይከማች ምርት ከመሆኑም በላይ የወጪ ንግዱ 80 በመቶ ቅናሽ በማሳየቱ አምራቾችን በገንዘብ ረገድ እንዲፈተኑ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። እንደ አቶ ኢሳያስ ገለጻ ከሆነ በአሁኑ ወቅት አበቦች እንዳይጎዱ በመንከባከብ እና ቀሪ ሠራተኞችን ደግሞ እረፍት እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ከስምንት መቶ በላይ ሠራተኞች ያሉት ድርጅቱ ችግሩ በዚሁ ከቀጠለ ደሞዝ ለመክፈል እንደሚቸገር ተናግረዋል። በዚህ ሃሳብ የሚስማሙት አቶ አብነት በበኩላቸው መንግስት በዘርፉ ለተሰማሩ አካላት ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። • ሁለት ኢትዮጵያዊያን ጣሊያን ውስጥ በኮሮናቫይረስ መሞታቸው ተረጋገጠ ችግሩ ከመባባሱ በፊት መንግስት ድርጅቶች ብድር የሚከፈሉበትን ጊዜ በማስረዘም፤ ተጨማሪ ብድር የሚያገኙበትና የአበባ ፍላጎት ወዳሉባቸው አገራት ካርጎ እንዲጀመር የኢትዮጵያ አበ��ና አትክልት አምራች ላኪዎች ማህበር ጠይቋል። መንግስት ችግሩን መገንዘቡንና በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ምላሽ ይሰጣል ብለው እንደሚጠብቁ አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል። የኮሮና ወረርሽኝ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተጨባጭ ጉዳት ፈጥኖ በመለየት የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ መንግሥት እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መግለፃቸው ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/news-51986046 +business ኢንዶኔዥያ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ጥላ የነበረውን እገዳ አነሳች "ኢንዶኔዥያ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ጥላ የነበረውን እገዳ አነሳች። የላየን ኤር አየር መንገድ ከሦስት ዓመታት በፊት 189 ሰዎች የሞቱበት የአውሮፕላን መከስከስ ከገጠመው በኋላ የቦይንግ ማክስ 737 አውሮፕላኖች እንዳይበሩ ተከልክሎ ነበር። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ከአንድ ወር በኋላ ወደ በረራ ለመመለስ በመጨረሻው የዝግጅት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መግለጹ ይታወሳል። በመጋቢት 2011 ዓ. ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሶ 149 መሞታቸውን ተከትሎ ቦይንግ 737 ማክስ ከበረራ ታግዶ ቆይቷል። አሜሪካ እና የአውሮፓ አገራት 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ በረራ እንዲመለስ ከፈቀዱ ወራት ተቆጥረዋል። ዘንድሮ አውስትራሊያ፣ ጃፓን፣ ሕንድ፣ ማሌዥያ እና ሲንጋፖር 737 ማክስ ላይ የጣሉትን እገዳ ያነሱ ሲሆን፤ እስካሁን ባጠቃላይ 180 አገራት ለ737 ማክስ ፈቃድ ሰጥተዋል። የኢንዶኔዥያ የትራንስፖርት ሚኒስቴር እንዳለው፤ በ737 ማክስ የደኅንነት መቆጣጠሪያ ላይ ፍተሻ መካሄዱን ተከትሎ አውሮፕላኑ በቅርቡ ወደ በረራ እንዲመለስ ተወስኗል። አየር መንገዶች 737 ማክስ አውሮፕላኖቻቸውን ከማብረራቸው በፊት መከተል ያለባቸውን የፍተሻ መመሪያ ተደንግጓል። መንግሥትም ፍተሻ የሚያካሂድ ይሆናል። ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኑ የተከሰከሰበት ላየን ኤር 10 ማክስ አውሮፕላኖች ያሉት ሲሆን፤ አውሮፕላኖቹ ወደ በረራ እንዲመለሱ ከተወሰነ በኋላ ከቢቢሲ አስተያየት ቢጠየቅም እስካሁን ምላሽ አልተኘም። በኢንዶኔዥያ መንግሥት የሚተዳደረው ጋሩዳ አየር መንግድ በበኩሉ አሁን ላይ ዋነኛ ትኩረቱ ያለበትን ዕዳ ማቃለል እንደሆነና 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ በረራ የመመለስ ዕቅድ እንደሌለው ገልጿል። እገዳው ከመጣሉ በፊት አየር መንገዱ አንድ 737 ማክስ አውሮፕላኑ ብቻ ነበር እየተንቀሳቀሰ የነበረው። አየር መንገዱ ወጭ ለመቀነስ ሲል የሚያበራቸውን አውሮፕላኖች ከ144 ወደ 66 መቀነሱንም አስታውቋል። እአአ በ2018 የላየን ኤር አየር መንገድ የበበራ ቁጥር 610 አውሮፕላን ከጃካርታ ተነስቶ ጉዞ ማድረግ በጀመረ በ13 ደቂቃ ውስጥ ነበር ወድቆ የተከሰከሰው። ከአምስት ወር በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ለመብረር ከተነሳ ከደቂቃዎች በኋላ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ መከስከሱ ይታወሳል። በሁለቱ አደጋዎች በአውሮፕላኖቹ ውስጥ የነበሩ ሁሉም 346 ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ቦይንግ ለሟቾቹ ቤተሰቦች በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ካሳ እንዲከፍል ተጠይቋል። አደጋዎቹን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ላየን ኤር ብቻ ሳይሆኑ በዓለም ዙሪያ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ካለባቸው የደኅንነት መቆጣጠሪያ ችግር ጋር በተያያዘ በረራ እንዲያቆሙ ተደርገው ቆይተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረማሪያምን ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ፤ አየር መንገዱ ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የሚሰጠው ለደኅንነት መሆኑን በመግለጽ አውሮፕላኖቹ ወደ አገልግሎት ሊመለሱ መሆኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ ወደ በረራ ለመመለስ የወሰነው በዓለም ዙሪያ ያሉ የበረራ ደኅንነት ተቆጣጠሪ አካላት ቦይንግ 737 ማክስ ለበረራ ብቁ ነው ብለው አስፈላጊውን ፈቃድ ከመስጠታቸው በተጨማሪ ""በዓለም ዙሪያ ያሉ ሌሎች 34 አየር መንገዶች አውሮፕላኑን ወደ በረራ መመለሳቸውን ተከትሎ ነው"" ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59815429 +sports በካሜሩን እየተካሄደ ያለው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ የግጥሚያ ፕሮግራምና ውጤቶች በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለአንድ ዓመት የተራዘመው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከእሑድ ጥር 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ ካሜሩን ውስጥ እየተካሄደ ነው። እተካሄደ ያለውን የአፍሪካ ዋንጫ የግጥሚያ ፕሮግራሞችንና ውጤቶችን ቀጥሎ ከተቀመጠው ዝርዝር ላይ ይመልከቱ። የውድድሩ አዘጋጅ ካሜሩን በአፍሪካ ዋንጫ በመሳተፍ ከምድቡ ሃገራት የሚያክላት የለም። ቡርኪና ፋሶ ለ12ኛ ጊዜ፤ ኢትዮጵያ ደግሞ በአንድ ዝቅ ብላ ለ11ኛ ጊዜ ትሳተፋለች። ለውድድሩ እንግዳ ያልሆነችው ኬፕ ቨርዴ የዘንድሮ ተሳትፎዋ ለሶስተኛ ጊዜ ነው። ከኢትዮጵያ በቀር ሁሉም የምድቡ ሃገራት በአውሮፓ ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋቾቻቸውን ይዘው ነው ወደ ካሜሩን ያቀኑት። ነገር ግን ከሽመልስ በቀለና ሙጂብ ቃሲም በቀር ሁሉንም ተጫዋቾቿን ከሃገር ውስጥ ክለቦች የመረጠችው ኢትዮጵያ የውድድሩ ክስተት ልትሆን እንደምትችል ብዙዎች ይገምታሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-59928971 +business የአውሮፓ አቪየሽን ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ዳግም መብረር እንዲችል ፈቀደ የአውሮፓ የአቪየሽን ደኅንነት ኤጀንሲ (EASA ) የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከዚህ በኋላ ወደ ሰማይ ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ሲል አረጋገጠ። የኤጀንሰው ኃላፊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አውሮፕላኖቹ ከዚህ በኋላ ለመብረር አንዳችም ስጋት እንደሌለባቸው እርግጠኛ ሆነን መናገር እንችላለን ብለዋል። የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓትሪክ፣ ድርጅታቸው ከአውሮፕላኖቹ አምራች ጋር በመሆን ጥብቅ ፍተሻና ምርመራ እንዳደረገና ለበረራ ዝግጁ እንደሆኑም እንዳረጋገጠ ለቢቢሲ አብራርተዋል። አውሮፕላኖቹ ከበረራ የተገለሉት በአወሮፓውያኑ 2019 እንደነበር ይታወሳል። አውሮፕላኖቹ ከበረራ የታገዱት በኢትዯጵያና በኢንዶኔዢያ ሰማይ ላይ ተከስክሰው 346 መንገደኞች ማለቃቸውን ተከትሎ ነበር። አሁን የቦይንግ ማክስ አውሮፕላኖች በአሜሪካ እና በብራዚል፣ ከጥር አጋማሽ ጀምሮ ደግሞ በመላው አውሮፓ በረራ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል። የማክስ አውሮፕላኖች የመጀመርያው አደጋ የተመዘገበው በላየን አየር መንገድ ሲሆን ይህም በጥቅምት 2018 በኢንዶኒዢያ ሰማይ ላይ ነበር። ሁለተኛው አደጋ ደግሞ ወደ ናይሮቢ በማቅናት ላይ በነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ እንደነበር ይታወሳል። የሁለቱም አደጋዎች ምንጭ ከአውሮፕላኑ የአደጋ ጊዜ ሶፍት ዌር እንከን ጋር የተያያዘ እንደነበር አይዘነጋም። ሶፍትዌሩ ራሱን በራሱ የሚያዝና፣ በተሳሳተ ጊዜ ራሱን የሚያነቃ ሆኖ የተሰራ ሲሆን፣ አውሮፕላኑን ከአብራሪው ቁጥጥር ውጭ እንዲሆን የሚያደርግ ሆኖ በመነደፉ እክል እንደነበረበረበት በኋላ ላይ ተረጋግጧል። የአውሮፓ አቪየሽን ቁጥጥር ባለሥልጣን ኃላፊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት እነዚህ እክል የነበረባቸው አውሮፕላኖች ወደ ሰማይ እንዲመለሱ ለመወሰን የነበረባቸው እክል ብቻ መመርመር በቂ አልነበረም። ስለዚህ መላ ስሪታቸውን እንደ አዲስ ፈትሸን ነው እንዲመለሱ የወሰነው ብለዋል። ለማክስ አውሮፕላን የተገጠመለት አዲስ ሶፍትዌርን በተመለከተ አብራሪዎች አዲስ ስልጠና እንዲወስዱ ይገደዳሉ ተብሏል። https://www.bbc.com/amharic/55391882 +health 'መድኃኒት' አግኝቻለሁ ስትል የነበረችው ማደጋ���ካር ክትባት ለማግኘት ጠየቀች ፕሬዝዳንቷ ከተለያዩ እጽዋት በተዘጋጀ ውህድ የኮሮናቫይረስን ማከም ይቻላል ሲሉ የነበረችው ማደጋስካር፣ የበሽታውን መከለከያ ክትባት ለማግኘት ከሚያስችላት ዓለም አቀፍ ጥምረት ውስጥ ገባች። የኮሮናቫይረስ ከተከሰተ ከጥቂት ወራት በኋላ በሽታውን ለማከም ያስችላል ያለችውን ባሕላዊ መድኃኒት ያስተዋወቀችው ማደጋስካር ክትባት እንደማያስፈልጋት ገልጻ ነበር። ኮቫክስ የተባለውና ለበርካታ አገራት የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለማቅረብ ከሚሰራው ጥምረት የአገራት ዝርዝር ውስጥ ባለመግባቷ ክትባቱን ሳታገኝ ቆይታለች። ማዳጋስካር ኮቪድ-ኦርጋኒክስ የተባለውን ባሕላዊ መድኃኒት በፕሬዝዳንቷ አማካይነት ስታስተዋውቅ የቆየች ሲሆን መድኃኒቱ ወደ ሌሎች አገራትም እንደተላከ ተዘግቦ ነበር። ነገር ግን የመድኃኒቱ ምንነትና ያስገኘውን ውጤት በሚመለከት በጤና ባለሙያዎች የተባለ ነገር የለም። ማዳጋስካር የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ተቀብለው ሕዝባቸውን እየከተቡት ያለውን የወረርሽኙን መከላከያ ክትባት በኮቫክስ በኩል ለማግኘት ጥያቄ አቅርባለች። የአገሪቱ የጤና ሚኒስትር ፕሮፌሰር ጃን ልዊስ ራኮቶቮ እንዳሉት ክትባቱን ለማግኘት የተለያዩ ደረጃዎችን ማለፍ አለበት ለዚህ ደግሞ ምዝገባን መፈጸም ዋነኛው እርምጃ ነው ሲሉ የክትባት አቅርቦት ጥምረት ከሆነው ኮቫክስ ውስጥ ለመግባት ማዳጋስካር እያደረገች ያለውን ገልጸዋል። የማደጋስካሩ ፕሬዝደንት አንድሬ ራጆሊን ኮቪድ-19ን ይፈውሳል በማለት ሲያስተዋውቁት የነበረው 'መድኃኒት' በስፋት መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። እስካሁን ባለው የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሠረት ኮሮናቫይረስን የሚፈውስ ምንም አይነት መድኃኒት የለም። በማዳጋስካር እስካሁን ከ24 ሺህ 400 በላይ ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸው የታወቀ ሲሆን 418 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሰበብ ለሞት ተዳርገዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-56599700 +politics የትራምፕ ቤት እንዲበረበር ያዘዙት ዳኛ ዝርዝር መረጃዎች ይፋ እንዲሆኑ አዘዙ "የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት እንዲፈተሽ ትዕዛዝ የሰጡት ዳኛ ብርበራውን እንዲያጸድቁ ያደረጓቸው ሰነዶች ይፋ እንዲሆኑ አዘዙ። በዐቃብያነ-ሕግ የተሰበሰቡትን ማስረጃዎች ብሎም ለችሎቹ ያቀረቡት ቃለ መሃላ ሰነድ ቅጂ ይፋ የሚሆን ከሆነ ስለምርመራው ተጨማሪ መረጃዎችን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። የአገሪቱ የፍትህ ሚኒስቴርም መረጃው ይፋ የሚወጣ ከሆነ በሂደት ላይ ያለውን ምርመራ ይጎዳል ሲል ወቅሷል። የብርበራ ማዘዣው እንደሚገልጸው ትራምፕ የፕሬዝዳንትነት ግዜያቸው ካበቃ በኋላ ከኋይት ሀውስ ወደ ቤታቸው የመንግሥትን መዛግብት አላግባብ ወስደዋል በሚል ወንጀል በመጠርጠራቸው ነው ኤፍቢአይ ምርመራውን የጀመረው። የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ከሥልጣናቸው ሲለቁ ሰነዶችን እና ኢሜሎችን ወደ ብሔራዊ ቤተ መዛግብት የማስተላለፍ ግዴታ አለባቸው። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የቀረበባቸውን ውንጀላ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን መርማሪዎች በፍሎሪዳ በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ አግኝተነዋል ያሏቸውን ሚስጥራዊ ሰነዶች እርሳቸው ቀድመው ያሳወቁ መሆናቸውን አስረድተዋል። ጉዳዩ ላይ የተሰየሙት ዳኛ ብሩስ ራይንሃርት ትላንት በሰጡት ትዕዛዝ ዛሬ ዓርብ ከምሽትቱ አንድ ሰዓት ላይ ዝርዝር መረጃዎችን የያዘው የቃለመሃላ ሰነዱ እንዲለቅ አዘዋል። ዳኛው ዐቃቤ ሕግ የምስክሮችን፣ የሕግ አስከባሪ አካላትን፣ ያልተከሰሱ አካላትን ማንነትእ ንዲሁም የምርመራውን ስልት፣ አቅጣጫ፣ ወሰን፣ ምንጭ እና ዘዴ የሚገልጹ የሰነዱን ክፍሎች ይፋ እንዳይሆኑ አሳማኝ ምክንያት በማቅረቡ እነዚህ ዝርዝሮች ��ፋ በሚሆነው ሰነድ ውስጥ እንደማይካተቱ ተናግረዋል። የፍትህ ሚኒስቴር በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሠረት የቅጣት ውሳኔዎችን የያዘ የቃለ መሃላ ቅጂ ለችሎቱ ማስገባቱን አስታውቋል። የተሻሻለው ሰነድ ትራምፕ ምስጢራዊ ሰነዶችን በፕሬዝዳንትነታቸው የመጨረሻ ቀናት ለምን እንደወሰዱ እና በፓልም ቢች ውስጥ ተከማችተው በነበሩበት ጊዜ ምን እንደፈጸሙ ፍንጭ ሊሰጥ ይችላል ተበሎ ይጠበቃል። የተለያዩ የዜና አውታሮች ጉዳዩ ላይ የሕዝብ ጥቅም ስላለው ብሎም የፍተሻውን ታሪካዊነት ከግምት ውስጥ በመክተት ሰነዱን ለሕዝብ ለማውጣት ችሎቱን ጠይቀዋል። የፍትህ መሥሪያ ቤቱ በበኩሉ ይህ የሚሆን ከሆነ በሂደት ላይ ያለውን ምርመራ ሊጠገን የማይችል ጉዳት ሊያደርስበት ይችላል ሲል እርምጃውን ተቃውሟል። ከውስጡ የሚወጡት መረጃዎች ሲቀነሱም ሰነዱን “ትርጉም የለሽ” ያደርጉታል ብሏል። ትራምፕ እና ጠበቃቸው ፍተሻው ፖለቲካዊ ይዘት ያለው እና ሕገ ወጥ ነው ያሉ ሲሆን ምንም መረጃ ያልተቀነሰበት ሰነድ እንዲለቀቅ ጠይቀዋል። የትራምፕ ቃል አቀባይ ቴይለር ቡዶዊች ይዘቱን ""ለመደበቅ"" የሚደረገው ጥረት ""አስቂኝ"" እና ""የመንግሥት ሙስናን ለመደበቅ ያለመ ሊሆን ይችላል"" ብለዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የዶናልድ ትራምፕ የጠበቆች ቡድን ምርመራው እንዲታገድ ብሎም ገለልተኛ የሦስተኛ ወገን ጠበቃ እንዲመጣላቸው እና ኤፍቢአይ በፍተሻው ወቅት የወሰዳቸውን ሰነዶች እንዲከታተል ጠይቋል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c72r7klmz8xo +politics ኢትዯጵያ፡ አገራዊ ምርጫው በዚህ ዓመት መካሄድ እንደሚችል ተገለጸ "የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ስድስተኛው ዙር አገራዊ መርጫ ሊካሄድ እንደሚችል የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ አስታወቁ። በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት አስከ አንድ ዓመት ለሚደርስ ጊዜ እንዲሸጋገር የተወሰነው ምርጫ እንዲካሄድ የወረርሽኙ ሁኔታን በተመለከተ ከጤና ባለስልጣናት የሚሰጡ ምክሮችን መሰረት እንደሚያደርግ ተገልጾ ነበር። በዚህም መሰረት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በአገሪቱ ያለውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሁኔታን በተመለከተ የመስሪያ ቤታቸውን ግምገማ ለሕዝብ ተወካዮች ምከክር ቤት ባቀረቡበት ጊዜ ነው አገራዊ ምርጫን ለማካሄድ እንደሚቻል አመልክተዋል። ካለው የወረርሽኝ ስጋት አንጻር የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመከላከል የሚያስችሉ እርምጃዎችን ከግምት ውስጥ የሚያስገባ የምርጫ ሥነምግባር፣ ደንብና ማስፈፀሚያ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ስድስተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ማካሄድ እንደሚቻል ሚኒስትሯ ገልጸዋል። አክለውም ምርጫውን ለማካሄድ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ካጋጠመ ""ይህ በተለየ ሁኔታ መታየት ሊያስፈልገው እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት ያስፈልጋል"" ሲሉ ሚኒስትሯ በሪፖርታቸው ላይ ጠቅሰዋል። ሚኒስትሯ እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ወረርሽኙ በሁሉም ክልሎች የተሰራጨ ሲሆን፤ በዚህም የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 95 በመቶ የሚሆኑት የታወቀ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። እስካሁንም በተደረገው ምርመራ ከ66 ሺህ 200 ሰዎች በላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን 1 ሺህ 45 ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት መሞታቸውን ገልጸዋል። ነገር ግን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነሰ ባይሆንም የቅድመ መከላከልና ስርጭቱን በመግታት ሂደት ውስጥ በሁሉም ደረጃ አቅም ማሳደግ መቻሉን አመልክተዋል። በዚህም የአገሪቱ የመመርመርም ሆነ የክትትል አቅም በማደጉ በከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ጋር መድረስ እንደተ��ለ ተናግረዋል። ከዚህም ባሻገር ከበሽታው መከላከልና ሕክምና አንጻር የተሰሩ ሥራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለምክር ቤቱ ዝርዝር የሆነ ሪፖርት አቅርበዋል። በአገሪቱ ካለው የወረርሽኝ መስፋፋት ሁኔታ አኳያ አገራዊ ምርጫን ከማካሄድ አንጻር የበርካታ አገራት ተሞክሮዎች ላይ ምልከታ የተደረገባቸው ሲሆን፣ በአንዳንዶቹ በወረርሽኝ ወቅት ምርጫ ተካሂዷል፤ በአብዛኞቹ ደግሞ እንዲተላለፍ ተደርጓል። በኢትዮጵያም በሽታውን የመከላከልም ሆነ የመቆጣጠር ዝግጅነቱ ዝቅተኛ በነበረበት ወቅት ምርጫን ማከናወን ስጋቱ የበለጠ የሚያሳድገው በመሆኑ በተላለፈው ውሳኔ እንዲራዘም መደረጉ ይታወሳል። ስለዚህም ወረርሽኙ የጤና ስጋት መሆኑ እንዳለ ቢሆንም ቀደም ሲል ከነበረው ልምድ እንፃር ከፍተኛ አለመሆኑ፣ በሽታው ከዚህም በኋላ ረዘም ላለ ጊዜ ስጋት ሆኖ ሊቆይ ሰለሚችል፤ ምርጫው ሲራዘም ከነበርንበት ሁኔታ አንጻር ስለስርጭቱ የተሻለ መረጃ መኖሩ ተገልጿል። እንዲሁም አስፈላጊውን የበሽታው ምርመራ፣ ክትትል፣ ሕክምናና ጥንቃቄን በተመለከተ የተሻለ አቅምና ግንዛቤ በመኖሩ፤ በተጨማሪም የተለያዩ አገራትን የምርጫ ተሞክሮን በማየት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ እንዳለ ተገልጿል። ይህንንም ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀጣዩን አገራዊ ምርጫን በተመለከተ በቀረበውን የጤና ሚኒስቴር ሪፖር ላይ በመወያየት ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ስጋት ሳቢያ እንዲራዘምና በክልሎችና በፌደራል ደረጃ ያሉት ምክር ቤቶች ቀጣዩ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ በሥራቸው ላይ እንዲቀጥሉ መወሰኑ ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54198845 +health “ከስኳር ሕመምተኞች አንድ አራተኛው ስለበሽታው ምንም መረጃ አያገኙም” ጥናት ከስኳር ታማሚዎች አንድ አራተኛው ምንም ዓይነት እርዳታ እንደማያገኙ አንድ ጥናት አረጋገጠ። የዓለም የስኳር ሕመም ፌዴሬሽን እንዳለው ከታማሚዎች 26 ከመቶ የሚሆኑት ስለበሽታው ምንም ዓይነት መረጃ አያገኙም። በዚህ የተነሳ ሕይወታቸው ትልቅ ፈተና ውስጥ ይወድቃል። በቂ መረጃ እና ትምህርት ስለማያገኙ ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስትሮክ፣ የኩላሊት ሕመም፣ መታወር፣ የእግር እብጠት እና የአእምሮ ጤና መቃወስ ይገጥማቸዋል። ይህ ጥናት እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው በበይነ መረብ አማካኝነት 3 ሺህ 208 የሚሆኑ የስኳር ታማሚዎችን እና የጤና ባለሙያዎችን መጠይቅ ካደረገላቸው በኋላ ነው። ተጠያቂዎቹ ከብራዚል፣ ሕንድ እና ናይጄሪያ ናቸው። ይህ የጥናት ውጤት ለሌላው አስደናቂ ቢመስልም በችግሩ ላለፉት ግን ምንም ነው። በሰባት ዓመቴ ‘ዓይነት-1’ የስኳር በሽታ እንዳለብኝ የተነገረኝ ኮስታሪካ እያለሁ ነበር። ያደኩት ስለበሽታው ምንም መረጃ ሳይኖረኝ ነው። ልጅነቴ በብዙ ጭንቅ የተሞላ ነበር። ለአጥንት ሕመም የተሰጠኝ መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳት አድርሶብህ ነው ለስኳር የተዳረከው ተባልኩ። በልጅነቴ የስኳር መጠን (ጉሉኮስ) መለኪያ አልነበረኝም። ድንገተኛ እና ከባድ ድንጋጤ [ፓኒክ አታክ] በየቀኑ ያጋጥመኝ ነበር። ኢንሱሊን መውሰድ አለመውሰዴን እስክዘነጋ ድረስ እሰቃይ ነበር። ምናልባት ሳልወስድ የወሰድኩ መስሎኝ ነው እያልኩ ኢንሱሊን ሁለት ጊዜ ወስጄ አውቃለሁ። 25 ዓመት ሲሆነኝ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ሄድኩ። ያን ጊዜ ነው ስለ በሽታዬ በደንብ ማወቅ የቻልኩት። ዛሬ ግን ከዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ ጤና አገልግሎት በቂ መረጃ በማግኘቴና ክትትል በማድረጌ በተሻለ የስኳር ሕመሜን መቆጣጠር ��ያለሁ። እንደኔው ብዙ መረጃ ሳያገኝ የሚሰቃይ ሰው ይኖር ይሆን ወይ? ብዬ ስጠይቅ አና ሉሺያን አገኘሁ። አና ከሜክሲኮ ናት። እሷ እንደነገረችኝ ከሆነ የስኳር ሕመምተኛ እንደሆነች ባወቀች ጊዜ የእርሷ ብቻ ሳይሆን የቤተሰቧ ሕይወትም ነው አብሮ የተቃወሰው። አና ሉሺያ የዓይነት 1 የስኳር በሽታ ታማሚ ናት። ይህ የሆነው ገና 8 ዓመት ሳይሞላት ነበር። ይህን ያወቀችው ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል ከተወሰደች በኋላ ነበር። “ገና ልጅ ነበርኩ፤ ጣፋጭ ነገር አትበይም አሉኝ፤ ይህን ተመገቢ፣ ያን አትመገቢ ሲሉኝ ጊዜ ተስፋ ቆረጥኩ” ትላለች። እናቷ ክሌመንቲና ስለልጃቸው አና ሲናገሩ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ፈታኝ እንደነበሩ ያሰታውሳሉ። “ሐኪሞቹ መርፌ አወጋግ እንድለማመድ እና እሷን እንድወጋት ነገሩኝ። ቀስ በቀስ አብረን ተማርን” ይላሉ ክሌመንቲና። ነገር ግን አናና እናቷ ስለ ስኳር ሕመም መረጃ ባላገኙባቸው የመጀመርያ ጊዜያት ብዙ ምስቅልቅል እንዳጋጠማቸው አይዘነጉትም። “ትምህርት ቤት ራሱ የተለየ እንክብካቤ ሊኖር ይገባል፤ ስኳር ሕመምተኛ ተማሪዎችን ሲያገኙ ከዚህ በኋላ ሕይወትሽን በዚህ ሁኔታ መምራት ይኖርብሻል ማለት አለባቸው።’’ ስኳር የማይድኑት በሽታ ነው። አንድ ታማሚ ስኳር አለው የሚባለው ሰውነቱ የስኳር መጠንን ማመጣጠን ወይም መቆጣጠር ሲያቅተው ነው። ይህም የሚሆነው ኢንሱሊን በሚባለው ሆርሞን የተነሳ ነው። በአጠቃላይ ሁለት ዓይነት የስኳር ሕመም አለ። ዓይነት-1 እና ዓይነት-2 የሚባል። አሁን አና ሉሺያ ዕድሜዋ 17 ደርሷል። አሁን ሁሉን ነገር በራሷ ነው የምትወጣው። ነገር ግን በስኳር በሽታ መያዝ ቀላል እንዳልሆነ ትናገራለች። “ትንሽ ሰዓት ነው የምተኛው። ምክንያቱም የስኳር መጠኔን መለካት አለብኝ። መርፌ ራሴን ከወጋሁ በኋላ ደግሞ ትንሽ ሰዓት መቆየት አለብኝ።” አሁን ዘመናዊ የሚባል የስኳር መጠን መለኪያ [ጉሉኮስ ሴንሰር] አላት። ‘ፍሪስታይል ሊብሬ’ ይባላል። እጇን በመርፌ ሳትወጋ በቀላሉ የጉሉኮስ መጠኗን ማወቅ ያስችላታል። አሁን አሁን ስታስበው “ምናለ ቀደም ብሎ ይህ መሣሪያ በነበረኝ” ትላለች። ምንም እንኳ አና ሉሺያ የቤተሰብ ድጋፍ ባይለያትም ከትምህርት ቤት፣ የቤት ሥራ እና ፈተና ጋር ስኳርን ማስታመም ቀላል እንዳልሆነ ደጋግማ ትናገራለች። ፕሮፌሰር አንድሩ ቦልተን እንደሚሉት የስኳር በሽተኞች ተገቢው መረጃ ካልተሰጣቸው ለጭንቀት እና ድብታ እንዲሁም በኋላ ላይ ነገሩ ከከፋ ራስን እስከማጥፋት የሚያደርስ ነው። ጥናቱ እንደሚለው ከሆነ ታማሚዎች ብቻም ሳይሆኑ የጤና ድጋፍ ሠራተኞችም በስኳር በሽታ ዙርያ በቂ ሥልጠና ማግኘት አለባቸው። ብዙዎቹ ለምሳሌ ስኳር ሕመም ለከፋ ድብታ እንደሚዳርግ መረጃው የላቸውም። “ብዙ የስኳር ታማሚዎች ከፍተኛ ድብታ ውስጥ ሲገቡ ለራሳቸው አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ ያስጠላቸዋል። የስኳር መጠናቸውን መቆጣጠር ይተዋሉ” ይላሉ ፕሮፌሰር ቦልተን። ፕሮፌሰሩ የሚመክሩት የስኳር ታማሚዎች ማንኛውንም መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ያን መረጃ ከጤና ባለሙያ ብቻ እንዲቀበሉ ነው። ብዙ ሰዎች ከማኅበራዊ ሚዲያ መረጃ ቃርመው ችግር ውስጥ እየገቡ ነው። ሌላው ችግር ታማሚዎች ሐኪም ለማየት መስጋታቸው ነው። ጥናቱ እንዳሳየው ከሆነ ስኳር ሕመምተኞች 99 ከመቶ የሚሆኑት በዓመት በድምሩ ከሦስት ሰዓት የበለጠ ሐኪም ዘንድ ቀርበው አያወሩም። ይህ ደግሞ አደጋውን የከፋ ያደርገዋል። ስኳር ከሐኪም ጋር በመመካከር የሚገፋ ደዌ ነው። ለብቻ አይወጡትም። https://www.bbc.com/amharic/articles/cyxr563deqyo +sports ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ዓለም አቀፍ የግብ ክብረ ወሰንን ሰበረ የ36 ዓመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አሁንም በዓለም እግር ኳ��� መድረክ ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል። ሮናልዶ ትናንት ምሽት አገሩ ፖርቹጋል በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከአየርላንድ ባደረገችው ጨዋታ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር በወንዶች ዓለም አቀፍ ውድድር ከፍተኛውን ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች መሆን ችሏል። ፖርቹጋል አየርላንድን 2 ለ1 ባሸነፈችበት ጨዋታ ሮናልዶ መጀመሪያ ላይ የተገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት ወደ ግብ መቀየር አለመቻሉ በርካቶችን ያስቆጨ ቢሆንም በጨዋታው መገባደጃ አካባቢ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች በዓለማችን ለብሄራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ሆኗል። በዚህም መሰረት ሮናልዶ ለአገሩ 111 ግቦችን በስሙ ያስቆጠረ ሲሆን ከዚህ በፊት ሪከርዱን ይዞት የቆየው ኢራናዊው አሊ ዳኢ ነበር። እሱም ከአውሮፓውያኑ 1993 እስከ 2006 ባሉት ዓመታት ባደረጋቸው ጨዋታዎች 109 ግቦችን አስቆጥሮ ነበር። ሮናልዶ በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ፈረንሳይ ላይ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች አማካይነት የአሊን ክብረ ወሰን መጋራት ችሎ የነበረ ሲሆን በርካቶችም ይህ ዓመት ሳይጠናቀቅ ተጨማሪ ጎሎችን እንደሚያስቆጥርና ክብረ ወሰኑን የግሉ እንደሚያደርገው ሲገልጹ ነበር። ከዚህ ክብረ ወሰን በተጨማሪ ደግሞ፤ ባሳለፍነው ሳምንት ለማንቸስተር ዩናይትድ በድጋሚ የፈረመው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ለብሄራዊ ቡድን 180 ጊዜ ጨዋታዎችን በማድረግ በአውሮፓ ለብሄራዊ ቡድን በመጫወት አሁንም ክብረ ወሰኑን ከስፔኑ ሰርጂዮ ራሞስ ጋር መጋራት ችሏል። በዓለማችን እግር ኳስ ታሪክ ለብሄራዊ ቡድን ከፍተኛውን ጨዋታ በማድረግ ክብረ ወሰኑን የያዘው ደግሞ ማሌዢያዊው ሶህ ቺን አን ሲሆን ለአገሩም ከአውሮፓውያኑ 1969 እስከ 1984 ባሉት ዓመታት 195 ጊዜ ተጫውቷል። ከጁቬንቱስ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ዝውውሩን የጨረሰው ሮናልዶ ለብሄራዊ ቡድን ከ90 በላይ ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሁለተኛው ተጫዋች ሲሆን አንደኛው ደግሞ ኢራናዊው አሊ ነው። ''በጣም ደስተኛ ነኝ። ክብረ ወሰኑን በመስበሬ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን በጨዋታው መጨረሻ አካባቢ የተለየ እንቅስቃሴ አድርገናል። ባለቀ ሰአት ለአገሬ ሁለት ግብ ማስቆጠሬም ጥሩ ነው። የብድን አጋሮቼም በጣም የሚደነቁ ነበሩ። እስከመጨረሻው ድረስ ተስፋ አልቆረጥንም ነበር። በጣም ደስ ብሎኛል'' ሲል ደስታውን ገልጿል ሮናልዶ። በበርካታ የእግር ኳስ አፍቃሪያን የዓለማችን የምን ጊዜም ምርጥ ተጫዋች እየተባለ የሚሞካሸው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ይህን ታሪክ መስራቱ ይበልጥ ይህ ክብር ይገባዋል ለሚሉት ትልቅ ማሳያ ሆኗል። ሮናልዶ ለበርካታ ዓመታት ከፖርቹጋል እስከ እንግሊዝ እንዲሁም ከስፔን እስከ ጣልያን በዘለቀው አስገራሚ የእግር ኳስ ህይወቱ በቻምፒየንስ ሊግ ከፍተኛውን ግብ ማስቆጠር የቻለ ተጫዋች ሲሆን እስካሁንም 5 ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ ነው። በጣም በሚያስገርም ሁኔታ ደግሞ ሮናልዶ ካስቆጠራቸው ግቦች መካከል ግማሽ የሚሆኑትን ያስቆጠረው በጨዋታዎች የመጨረሻ 30 ደቂቃዎች ውስጥ ነው። 33 ግቦችን ደግሞ በመጨረሻዎቹ 15 ደቂቃዎች አስቆጥሯል። ሮናልዶ እስካሁን ባደረጋቸው 180 ጨዋታዎች ለአገሩ 11 ግቦችን ሲያስቆጥር በርካቶች ከሮናልዶ በላይ ነው እያሉ የሚያሞካሹት አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ደግሞ በ151 ጨዋታዎች 76 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። ከዚህ በኋላ ደግሞ የ34 ዓመቱ ሜሲ ይህንን የሮናልዶ ክብረ ወሰን የማሻሻል እድሉ ያለው አይመስልም። https://www.bbc.com/amharic/news-58418103 +sports ሰንበሬ ክብረ ወሰን ስታሻሽል ማራቶን ያሸነፈው ኢትዮጵያዊ ውጤቱ ተሰረዘበት "እሁድ ዕለት ጀርመን ውስጥ በተካሄደ ውድድር አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ የ5 ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰንን ስታሻሽል ኦስትሪያ ቬይና በተደረገው ማራቶን ያሸነፈው ደራራ ሁሪሳ ���ልተፈቀደ ጫማ አድርጎ በመሮጡ ውጤቱ ተሰረዘበት። አትሌት ሰንበሬ የ5 ኪሎ ሜትር ውድድሯን ከዚህ ቀደም በኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቼፕኮኤች በ14፡44 ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን 14፡30 በሆነ ሰዓት ማሻሻል ችላለች። በቶኪዮ ኦሊምፒክ 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃ የነበረችው አትሌት ሰንበሬ ከውጤቱ በኋላ ""በጣም ደስታ ተሰምቶኛል"" ያለች ሲሆን፤ ""ከኦሊምፒክ በኋላ ይህን የዓለም ክብረ ወሰን ማሻሻል እንደምችል ገብቶኛል"" ማለቷን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪ ትናንት ኬንያዊቷ አትሌት አግነስ ቲሮፕ ጀርመን ውስጥ በተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር የዓለም ክብረ ወሰንን ማሻሻል ችላለች። አትሌት አግነስ በሞሮኮ አትሌት አሰማኤ ሌግህዛኦዩ ከ19 ዓመት በፊት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በ28 ሰከንዶች በማሻሻል 30፡17 በሆነ ሰዓት ውድድሯን አጠናቃለች። ያልተፈቀደ ጫማ እሁድ መስከረም 02/2014 ዓ.ም ኦስትሪያ ዋና ከተማ ቬይና በተካሄደው የወንዶች ማራቶንን አሸንፎ የነበረው ኢትዮጵያዊው አትሌት ደራራ ሁሪሳ ተጫምቶት የነበረው የጫማ ሶል (መርገጫው) ከሚፈቀደው በላይ አንድ ሴንቲ ሜትር ወፍሮ በመገኘቱ ውጤቱ ውድቅ ተደርጎበታል። አትሌት ደራራ ውድድሩን 2፡09፡22 በሆነ ሰዓት ቢያጠናቅቅም ከ45 ደቂቃዎች በኋላ የውድድር ደንብን በመጣሱ ውጤቱ እንደተሰረዘበት ተነግሮታል። የውድድሩ አዘጋጆች አትሌቶች መጫማት የሚችሉት የጫማ ሶል ውፍረት 4 ሳንቲ ሜትር መሆን አለበት ይላሉ። አትሌቱ ግን ተጫምቶት ነበረ የተባለው የጫማ ሶል 5 ሳንቲ ሜትር የሚወፍር መሆኑን ሮይተር የዜና ወኪል የውድድሩን አዘጋጆች ጠቅሶ ዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪም አትሌት ደራራ ከውድድሩ መጀመር በፊት በሞላው ቅጽ ላይ የተለየ ጫማ አድርጎ ወደ ውድድሩ ስለመግባቱ ተመልክቷል። ""በቴክኒክ ስብሰባ ላይ በጫማ ዙሪያ ያለውን መመሪያ ትኩረት ሰጥተን ተናግረናል። አለመታደል ሆኖ የአትሌቱን ውጤት ከመሰረዝ ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረንም"" በማለት የውድድሩ አስተባባሪ ሃነስ ላንገር ተናግረዋል። ""እንደዚህ አይነት ነገር ሲከሰት ይህ የመጀመሪው ነው። በውድድሮች ላይ እንደዚህ አይነት ነገር እንዳይከሰት ቀድሞ ማጣራት የሚቻልበት አሰራራ ከአሁን በኋላ ይኖራል ብዬ አስባለሁ"" ሲሉ የውድድሩ አዘጋጅ ተናግረዋል። ከአትሌት ደራራ ቀጥሎ በሁለተኛነት ያጠናቀቀው ኬንያዊው ሊኦናርድ ላንጋት የአንደኝነት ደረጃውን በመያዝ የውድድሩ አሸናፊ ተብሏል። ""የአትሌቱ ውጤት እንደተሰረዘ አልሰማሁም ነበር። ውድድሩን ለማሸነፍ አቅጄ ነበር። በመጨረሻ በማሸነፌ ፈጣሪን አመሰግናለሁ"" ብሏል ኬንያዊው አትሌት ላንጋት። ይህ ውድድር በየዓመቱ ሚያዝያ ወር ላይ ይካሄደ የነበረ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት መካሄዱ በበርካታ አትሌቶች ተቃውሞን አስተናግዶ ነበር። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ከፍተኛ ሙቀት ነው። በተያያዘ ዜና እዚያው ኦስትሪያ ውስጥ በግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረ አትሌት ሕይወቱ ስለማለፉም ተሰምቷል። የውድድሩ አዘጋጆች እንዳሉት ከሆነ፤ የ40 ዓመቱ የኦስትሪያ አትሌት ውድድሩን ከጨረሰ በኋላ ራሱ ስቶ ሆስፒታል ከገባ በኋላ ነው ሕይወቱ ያለፈው። የውድድሩ አዘጋጆች በክስተቱ እጅጉን ማዘናቸውን ከመግለጽ ውጪ ስለ አትሌቱ አሟሟት ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።" https://www.bbc.com/amharic/news-58541869 +health ኮቪድ-19 በእንፋሎት ይጠፋል ያሉት ጆን ማጉፉሊ በሽታው ይዟቸው ይሆን? "ለአስራ አንድ ቀናት ያልታዩት የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ ጉዳይ ጥያቄ እያስነሳ ነው። ቀንደኛ ተቃዋሚው ቱንዱ ሊሱ 'ምንጮቼ እንደነገሩኝ ከሆነ ፕሬዝደንቱ ኮሮናቫይረስ ይዟቸው ሕክምና ለማግኘት ወደ ኬንያ አምርተዋል' ��ሉ ለቢቢሲ ሹክ ብለዋል። ነገር ግን ቢቢሲ ይህንን ጉዳዩ ማጣራት አልቻለም። የማጉፉሊ አስተዳደር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን የመከተበት መንገድ ብዙ ትችት አስተከትሏል። ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሃገር የኮቪድ-19 ክትባት ላለመግዛት መወሰኗም አነጋጋሪ ነበር። የ61 ዓመቱ ማጉፉሊ ኮቪድ-19ን ሲያናንቁት ነው የከረሙት። ለዚህ በሽታ ፀሎትና እንፋሎት መታጠን በቂ ነው ሲሉም ተደምጠዋል። ባለፈው ወር መገባደጃ ገደማ አንድ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ቀብር ላይ የተገኙት ማጉፉሊ ታንዛኒያ ኮቪድን ባለፈው ዓመት አሸንፋለች፤ ዘንድሮም ትደግማለች ብለው ነበር። ባለሥልጣኑ የሞቱት በከፊል ራስ ገዝ የሆነችው የዛንዚባር ደሴት ምክትል ፕሬዝደንት በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን ካጡ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነው። ተቃዋሚው ሊሱ እንደሚሉት ፕሬዝደንቱ ሰኞ ምሽት ሕክምና ለማግኘት ወደ ናይሮቢ ሆስፒታል አቅንተዋል። ሊሱ አክለው ፕሬዝደንቱ የልብ ሕመም እንዳጋጠማቸውና አደገኛ ሁኔታ ላእ እንደሚገኙ ይናገራሉ። የታንዛኒያ መንግሥት ጆን ማጉፉሊ ከአደባባይ ስለመጥፋታቸው እስካሁን ትንፍሽ ያለው ነገር የለም። ነገር ግን ለመጨረሻ ጊዜ ከ11 ቀናት በፊት ዳሬ ሳላም ውስጥ ስለታዩት የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ያልተረጋገጡ መረጃዎች እንዳይወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። የናይሮቢ ሆስፒታል በበኩሉ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት አልችልም ብሏል። አቶ ሊሱ መንግሥት ስለ ፕሬዝደንቱ ደህንነት መረጃ አለመስጠቱ ከተማውን ሃሜት እንዲሞላው እያደረገው ነው ይላል። አክለው የፕሬዝደንቱ ጤና ጉዳይ ግላዊ ምስጢር ሊሆን አይገባም ሲሉ መንግሥትን ይተቻሉ። የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ኮቪድ-19 ቢይዛቸው የሚገርም አይደለም፤ ምክንያቱም ጥንቃቄ ሲያደርጉ አልነበረም ይላሉ ሊሱ። ""የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርገው አያውቁም፤ ደግሞ ሕዝብ ወደተሰበሰበበት ያለምንም ጥንቃቄ ይሄዳሉ"" ይላሉ በስደት ቤልጂየም የሚገኙት ተቃዋሚው ሊሱ። ""እሳቸው እኮ ለወራት የበሽታውን መድኃኒት ሲያጣጥሉ የከረሙ ናቸው። ፀሎትና ቅጥል ነው የሚያድነው ሲሉ ነበር።"" የ53 ዓመቱ ተቃዋሚ አክለው የፋይንናስ ሚኒስትሩ ፊሊፕ ምፓንጎም በኬንያዋ መዲና ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እያገኙ ነው ይላሉ። ማጉፉሊ እንደተባለው ኮሮናቫይረስ ይዟቸው ከሆነ አንድም በሽታውን ሲክዱ መኖራቸው ያስተቻቸዋል፤ ሁለት ደግሞ ጎረቤት ሃገር ሄደው መታከማቸው የተደራጀ የጤና ሥርዓት እንደሌለ ማሳያ መሆኑ ያስወርፋቸዋል ትላለች የቢቢሲ አፍሪካ ባልደረባ ለይላ ናቱ። የታንዛኒያ መንግሥት ኮሮናቫይረስን በተመለከተ መረጃ ስለማይሰጥ የበሽታውን መስፋፋት መጠን መለየት ከባድ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-56356719 +sports ኢትዮጵያ፡ አካል ጉዳተኛው የቴኳንዶ ስፖርት አሰልጣኝ "ከማል ቃሲም የተወለደው ጎንደር ከተማ ነው። በህጻንነቱ ከቤተሰቦቹ ጋር በመሆን ወደ ወረታ አመሩ። ""ተጫዋችና ደስተኛ"" ነበርኩ የሚለው ከማል በአምስት ዓመቱ የገጠመው አደጋ ህይወቱን እስከወዲያኛው ቀይሮታል። ""ጉዳት የደረሰብኝ በ1985 ዓ.ም ነበር። ወረታ ውስጥ ከእኩዮቼ ጋር ስጫወት በመንግሥት ሽግግር ወቅት ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ በተተወ ታንክ ነው ጉዳት የደረሰብኝ።"" በወቅቱ የአምስት ዓመት ታዳጊ የነበረው ከማል ታንኩ ላይ እየተጫወተ ሳለ ""አፈሙዙን በሚያሽከረክረው ክፍተት መሐል አንድ እግሬ ሆኖ ለመሻገር ስሞክር አንደኛው እግሬ አፈሙዝ ስር ገባ። በዚያው ቅጽበት አፈሙዙ በሚዞርበት ጊዜ እግሬ ላይ አደጋው ደረሰ"" ሲል ያስታውሳል። ከወረታ ወደ ባሕር ዳር ለህክምና ተወስዶ ለወራት እዚያው ከቆየ በኋላ ወደቀየው ተመለሰ። በድንገተኛው አደጋ ጉዳት የደረሰበ��� ታዳጊው ከማል ከህክምናው ሲመለስ ቀኝ እግሩ ጉልበቱ ላይ ተቆርጦ በሁለት ምርኩዞች ተደግፎ ነበር። ""ህይወት እንደ አዲስ ተጀመረ። ያኛው ሌላ አሁን ደግሞ ሌላ ህይወት"" የሚለው ከማል ""በአካባቢያችን ሌላ አካል ጉዳተኛ አልነበረም። እንኳን በዚያ ወቅት አሁን እንኳን ማኅረሰቡ ውስጥ ስለአካል ጉዳተኝነት ያለው አመለካከት ፈታኝ ነበር። መውጣት መግባት መጫወት አልችልም ነበር"" ይላል። በታዳጊነቱ በደረሰበት አደጋ አካል ጉዳተኛ የሆነው ከማል ተደራራቢ ችግሮችን መጋፈጥ ጀመረ። ሌላ ችግር ቤተሰቡ ውስጥ ተከሰተ፤ አባት እና እናቱ ተለያይተው በተለያየ ቦታ በየፊናቸው ህይወታቸውን ለመምራት ሲወስኑ፤ እሱም ከእናቱ ተለይቶ ከአባቱ ጋር መኖር ጀመረ። አደጋው ከደረሰበት በኋላ ከማል ሰባት ዓመት ሲሆነው ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ጀመረ። ነገር ግን ""ሙሉ ለሙሉ ህይወቴ ስለተቀየረ ትምህርት ቤት እረብሽ፣ እነጫነጭ ነበር"" ሲል በጸባዩ ላይ ለውጥ መከሰቱን ያስታውሳል። ለአካል ጉዳተኞች የሚመች መሠረት ልማት አለመኖር እና ህብረተሰቡ ስለ አካል ጉዳተኝነት ያለው አስተሳሰብም ህይወቱን ከባድ አድርጎት ነበር። ""ከባድ ነው። ትምህርት ቤት ነጻ ሆኜ መጫወት አልችልም። ትልልቆቹም ባለፍኩ ባገደምኩ ቁጥር ከንፈር መምጠጥ፤ በዚህ እድሜው እንደዚህ ሆኖ እያሉ ሲናገሩ መስማት ተስፋ ያስቆርጣሉ"" ይላል። በሁለት ክራንች መንቀሳቀስም መጫወትም አልመችህ ሲለው አንዱን ክራንች በመተው እንደልቡ ለመሆን ሞከረ። በዚህም ለመንቀሳቀስ በሚያደርገው ሙከራ በተደጋጋሚ በመውደቅ እግሩ መጎዳት እና መድማት ይገጥመው ጀመር። በዚህ መልኩ እስከ ስድስተኛ ክፍል ወረታ ውስጥ ተማረ። በወቅቱ ""ጸባዬ አስቸጋሪ እረባሽና አልቃሻ ሆኜ። ከባድ ጊዜ ነበር ያሳለፍኩት። ከልጆች ጋር ጋር መግባባት እየተቸገርኩ እጣላ ነበር። አንዳንድ ጊዜም በክራንች እስከመማታት እደርስ ነበር"" የሚለው ከማል 6ኛ ክፍል ሲደርስ ወደ እናቱ ተመልሶ ጎንደር መኖር ጀመረ። ጎንደር ሌሎች የአካል ጉዳተኞችን ተዋወቀ ስለዚህም ከወረታ ብቸኝነቱ በተወሰነ ደረጃ ተላቀቀ። ነገር ግን እናቱ ሥራ ስላልነበራቸው የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ የሚያገኙት አንድ አካል ጉዳተኞችን ከሚረዳ ድርጅት ነበር። ""ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጠውን ስንዴ እና ዘይት በችግር ላይ ለነበረችው እናቴ አመጣላት ነበር። እዚያ ሌሎች አካል ጉዳተኞችን ባገኝም ጥሩ ስሜት አይሰማኝም ነበር። የዝቅትኝነት ስሜት ይሰማኝ ጀመር"" የሚለው ከማል 'ረጂ እንጂ ተረጂ አልሆንም' ብሎ እርዳታውን መቀበል አቆመ። ስምንተኛ ክፍል ደርሶ ለማለፍ የሚያስችለውን ውጤት ባለማምጣቱ ለመድገም ተገደደ። በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ሠው ሠራሽ እግር ለማሠራት ወደ ደሴ አምርቶ ለወራት እዚያው በመቆየቱ ስምንተኛ ክፍልን በማታው ክፍለ ጊዜ መማር ጀመረ። የማታ ተማሪ መሆኑ እንዲሁም ቀን ላይ የሚሰራው ነገር ስላልነበረው አጋጣሚው ከቴኳንዶ ስፖርት ጋር እንዲተዋወቅ ዕድል ፈጠረለት። ከጓደኛው ጋር ቴኳንዶ የሚሰራበት ቦታ በመሄድ ስፖርቱን የተመለከተው ከማል፤ ለሰዓታት ከተመለከተ በኋላ አንዳች ነገር ውስጡ ተፈጠረ። ከማልን የተመለከተው የቴኳንዶ አሰልጣኙ ስሜቱን ጠይቆት ፍላጎት ካለው በነጻ እንዲማር ስለፈቀደለት በቴኳንዶ ፍቅር ወደቀ። ""እየወደቅኩ እየተነሳሁ ከምንም በላይ በአስተማሪዬ ድጋፍ እና በጓደኞቼ አይዞህ ባይነት ቴኳንዶውን መለማመድ ቀጠልኩ"" ነገር ግን በዙሪያው ካሉ ሰዎችና ከቤተሰቡ ጭምር 'ምን ያደረግልሃል?' ይሉት ነበር። ሆኖም እንዳሰበው ቀላል አልነበረም። ከወላጆቹ በስተቀር ሁሉም 'ምን ሊያደርግልህ?' የሚል ጥያቄ እያቀረቡ ተስፋ አስቆራጭ አስተያት ሰጥተውታል። ""በአንድ እግር ቴኳንዶ ከባድ ነው። ወድቄ እሰበራለሁ። እጄን ተሰብሬያለሁ። የቀረችውን አንድ እግሬን ተሰብሬ 2 ወር በተኛሁበት ጊዜ የነቀፉኝ ሰዎች ደስ አላቸው። እኔ ግን እስከ ህይወቴ ፍጻሜ ስፖርቱን ከመሥራት ማንም እንደማያግደኝ አወቅኩኝ።"" ከማል ቴኳንዶ መጀመሩ ብዙ ነገሮችን እንዲለውጥ ምክንያት ሆኖታል። አንደኛው ደግሞ ክራንቹን የሚጠቀምበትን ዘዴ መቀየሩ እና በሚመቸው መንገድ እንዲያስተካክለው ማድረጉ ነው። ""ክራንቹ መጀመሪያ ላይ ብረት ብቻ ነው። ቴኳንዶ ይህንን ምቹ እንዳደርግ ረድቶኛል። ይኸውም እንደጫማ ምቹ አድርጌ እንድሠራ አድርጎኛል። እንደጀመርኩ እግሬን ሳነሳ ክራንቹ ተሰብሮ ወድቄያለሁ። ሳስተምርም ወደቄ አውቃለሁ። የውሃ ቱቦ ነው በየጊዜው ቼክ አደርገዋለሁ። በየጊዜው እቀይረዋለሁ አሁን በምቾት እሠራለሁ።"" ቴኳንዶ በተለያዩ የቀበቶ ቀለሞች የሚሰጡ ደጃዎች አሉት። ጀማሪዎች በነጭ ቀበቶ ይጀምራሉ። ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ቀይ እና ጥቁር። እነዚህን ቀበቶዎች አንድ ሰልጣኝ የተለያዩ የስልጠናዎችን ካጠናቀቀ በኋላ ከአሰልጣኙ የሚያገኘው ይሆናል። ከዚያ በኋላ ደግሞ በዲግሪ የሚገለጹና ዳን የሚባሉ ዘጠኝ ደረጃዎች አሉ። ዳን የሚሰጠው በአሰልጣኝ ሳይሆን በቴኳንዶ ማኅበራት የተግባርና የጽሁፍ ፈተና ሲታለፍ ከኮሪያ የሚሰጥ ነው። ""ወደ ሦስተኛ ዳን ዲግሪ ደርሻለሁ። የሚሻሻሉ ዲግሪዎች ናቸው። አሁን 3ኛ ዳን አለኝ። በዚህ ዓመት አራተኛውን ላገኝ እችላለሁ። ጊዜው ደርሷል"" ይላል ከማል በቴኳንዶ የደረሰበትን ደረጃ ሲገልጽ። ""ለእኔ ሲባል ምንም የተለየ የሚደረግልኝ ነገር የለም"" የሚለው ከማል በዚህ ሂደት ውስጥ ሁሉ የተለያዩ ጉዳቶች ቢገጥሙትም ወደኋላ አላለም። ሦስተኛ ዳን የፈተኑት የውጭ አገር ሰዎች እንደነበሩ የሚኣስታውሰው ከማል፤ የሚተበቅበትን ካከናወነ በኋላ ፈታኞቹ ቆመው እንዳጨበጨቡለት ይናገራል። ""የተፈተንነው 15 ነበርን፤ ስድስቱ ወደቁ። ዘጠኛችን አለፍን። የእኔ ውቴት ጥሩ ነበር። ቴኳንዶ የሚጠይቀውን የሥራ የፓተርን ሙሉ ሠርቼ ነው ያገኘሁት"" ነው በማለት ተወዳድሮ ፈተና በማለፍ አሁን ላለበት መብቃቱን ይጠቅሳል። ከማል ቴኳንዶን ለሌሎች ማስተማር በሚያስብበት ጊዜ አካል ጉዳተኛ የቴኳንዶ አስተማሪ ስለሌለ 'ይሳካልኝ ይሆን?' እያለ ጥርጣሬ ቢገባውም የጓደኞቹና የአስተማሪው ማበረታቻ ድጋፍ ሆኖት በ2002 ዓ.ም ወረታ ውስጥ የማስተማሪያ ማዕከል ከፍቶ ማስተማር ጀመረ። ሆኖም እንዳሰበው ቀላል አልነበበረም። ለማስተማር የሚረዳውን ፈቃድ አላገኘም። መንቀሳቀሻ የሚሆን በቂ ገንዘብ እጁ ላይ አልነበረውም። ለመንቀሳቀሻ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘትም ፎቶውን አስር አስር ብር ሸጦ ወደ ሁለት ሺህ ብር ገደማ ሲያገኝ ሥራውን ጀመረ። ""ማስታወቂያ ስለጥፍ ግራ ገባቸው። 'ማነው የሚያስተመረው አሉኝ?' ሰዉ ለመማር ፈቃደኛ አልሆነም። የማውቃቸውን ጠርቼ በነጻ ማሠራት ጀመርኩኝ። አዳራሽም ዘመድ ፈቀደልኝ። አራት ወይም አምስት ሰው ይዤ ስሠራ ሌላው ሰው አዳራሽ ሞልቶ ያይ ነበር"" ይላል። ከዚያም ሰልጣኞች መምጣት ሲጀምሩ ፈቃድ ማውጣት ስለነበረበት ወደ አዲስ አበባ ሄዶ በመፈተን በተግባርና በጽሑፍም አንደኛ በመውጣት ፈቃድ ማግኘቱን ይናገራል። ከስድስት ወር የቴኳንዶ ስልጠና በኋላ 40 ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ አስመረቀ። የተለያዩ ፈተናዎችና ውጣ ውረዶች የገጠሙት ከማል ቃሲም ከወራታ ፓዌ ከዚያም ወደ ባሕር ዳር በመሄድ ስልጠና ሰጥቷል። በ2007 ዓ.ም ላይ አዲስ አበባ በተዋወቀው አንድ የውጭ አገር ዜጋ አማካይነት ባገኘው ድጋፍ ወደ ጀርመን በመሄድ ሰው ሠራሽ እግር ሲሰራለት በዚያውም የአንድ ወር ስል��ና አግኝቷል። ከማል ለዓመታት በዘለቀው የቴኳንዶ ስፖርት ህይወቱ የተለየ ደስታ የፈጠረለትን አጋጣሚ ""የመጀመሪያዋውን ጥቁር ቀበቶ ስቀበል ነው"" ሲል ያስረዳል። ባለትዳር እና የልጅ አባት የሆነው ከማል በቀጣይ ለቤተሰቡ ""ጥሩ ነገር መስጠት"" እንዲሁም የቴኳንዶ ስልጠና ሥራውን የበለጠ የማጠናከር አላማ አለው። ከዚህ በተጨማሪም በግል ህይወቱ ዙሪያ መጽሐፍና ዘጋቢ ፊልም ማዘጋጀት ይፈልጋል። አሁንም ብዙዎች ቴኳንዶ መሥራቱን እንደሚጠራጠሩ የሚናገረው ከማል ""ለሰዎች ፎቶዬን ሳሳያቸው በፎቶ ጥበብ የተዘጋጀ ነው ይሉኛል። እኔም ወስጄ በተግባር እሰራሁ አሳያቸዋልሁ።"" በቴኳንዶ ስፖርት ከ15 ዓመት በላይ የቆየው ከማል በወረታ፣ በፓዌ እና በባሕር ዳር በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን አሰልጥኗል። በተጨማሪም በዘርፉ ውድድር ባይኖርም የተለያዩ መድረኮች ላይ ትዕንቶችን በማቅረብ ሽልማቶችን አግኝቷል። በመላው ኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች በሚሳተፉበት የፓራሎምፒክ ውድድር ላይ ደግሞ የአማራ ክልልን በመወከል በጦርና አሎሎ ውርወራ፤ በተሽከርካሪ ወንበር እንዲሁም ክብደት ማንሳት ተሳትፎ ከሃያ በላይ ሜዳሊያዎችን አጥልቋል። በቅርቡ በተመሠረተው የተሸከርካሪ ወንበር የቅርጫት ኳስ ውድድርም ተሳታፊ በመሆን ላይ ይገኛል። ከስፖርቱ ጎን ለጎን ከማል ቃሲም የተሽከርካሪ ወንበር ተጠቃሚዎችና የእግር አካል ጉዳተኞች ማኅበር ሊቀ መንበር በመሆን ያለውን ልምድ በማካፈል ላይ ይገኛል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54507780 +sports የለንደን ደርቢ፡ ሁለቱ አሰልጣኞች ለምን ቀይ ካርድ ተመዘዘባቸው? ስታምፎርድ ብሪጅ ለአሰልጣኞች ፍጥጫ እና የደስታ መፈንጫ ቦታ መሆንን ቀጥሎበታል። የቼልሲው አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል እና የቶተንሃሙ አቻቸው አንቶኒዮ ኮንቴ ቡጢ ቀረሽ ግብግብ ውስጥ በመግባታቸው ሁለቱም ከጨዋታው ፍጻሜ በኋላ ቀይ ካርድ ተመዞባቸዋል። “አየሩም፣ ሜዳውም፣ ጨዋታውና ተቀያሪ ቦታውም ሁሉም ሞቅ ያለ ነበር፥ እንዲህ ዓይነት ጨዋታ በውድድሩ ጅማሬ ላይ መሆኑ ያስደስታል” ሲሉ ቱሄል ከጨዋታ በኋላ ፈገግ ብለው አስተያየት ሰጥተዋል። በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ፍትጊያ የበዛበት ጨዋታ እሰከ 68ኛው ደቂቃ ድረስ የተረጋጋ ይመስል ነበር። ካሊዱ ኩሊባሊ ክለቡ ቼልሲን መሪ ማድረግ ችሎ ነበር። ፒዬር-ኤሚል ሆቢዬር ቶተንሃምን አቻ ያደረገች ጎል ማስቆጠሩ የጨዋታውን መልክ ቀየረች። ከጎሉ ህጋዊነት ጋር ተያይዞ ሁለቱ አሰልጣኞች ተፋጠው በአራተኛው ዳኛ ገላጋይነት ተለያዩ። ሁለቱም የማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ ተመዘዘባቸው። ጎሉ ከመቆጠሩ በፊት ካይ ሃቨርትዝ ጥፋት ተፈጽሞበታል የሚል ነው የቼልሲ ክስ። የቶተንሃሙ ሪቻርለሰን ጎሉ ሲቆጠር ከጨዋታ ክልል ውጭ ከመሆን ባለፈ የግብ ጠባቂውን እይታ ከልሎታል የሚልም ቅሬታ በቼልሲ ቀርቦ ነበር። ከዘጠኝ ደቂቃ በኋላ ሪስ ጀምስ በድጋሚ ቼልሲን ቀዳሚ አደረገ። ቱሄል በደስታ እየቦረቁ ሲሮጡ ታዩ። በተጨማሪ ስድስት ደቂቃዎች ሃሪ ኬን በጨዋታም በጎልም ተበልጦ የቆየውን ቡድኑን አቻ ለማድረግ በቃ። የመሐል ዳኛው ጨዋታው መጠናቀቁን የሚያበስረውን ፊሽካ አሰሙ። እንደተለመደው አሰልጣኞቹ ተጨባብጠው ሊለያዩ ነው ሲባል ተጨባብጠው የእጃቸውን ጥንካሬ ይፈትሹ ገቡ። ይህ ደግሞ ወደ ግብግብ አምርቶ ሁለቱም ቀይ ካር ለማየት በቁ። ኬን ከማስቆጠሩ በፊት ክርስቲያን ሮሜሮ የቼልሲውን አዲስ ፈራሚ ማርክ ኩኩሬላን ጸጉር ስቧል የሚል ሌላ ቅሬታ በቼልሲ ቀረቧል። “ሁለቱም ጎሎች በቫር ዘመን መጽደቅ አልበረባቸውም። ዳኛው ትልቅ ሚና መጫወት ነበረባቸው” ሲሉ ቱሄል ለቢቢሲ ገልጸዋል። “የመጀመሪያው ጎል እንዴት ከጨዋታ ውጭ እንዳልሆነ እና ሁለተኛው ደግሞ ቀይ ካርድ አለመሆኑ አልገባኝም” ብለዋል። የመሐል ዳኛው ቴይለር ወደፊት የቼልሲን ጨዋታ መምራት የለባቸውም ሲሉም ቅሬታ አሰምተዋል። ሲጨባበጡም የመከባበር ነገር ከኮንቴ በኩል እንዳላዩ የቼልሲው አሰልጣኝ ገልጸዋል። “ሰው ሲጨባበጥ ዓይን ለዓይን መተያየት ያለብን ይመስለኛል። ብቻ ብዙ ነገሮች ትክክል አልነበሩም” ብለዋል። ኮንቴ ግን በጉዳዩ ላይ ብዙም ማውራት የፈለጉ አይመስሉም። “ችግር ካለ በእኔ እና በእሱ መካከል ነው” ብለዋል። “በተፈጠረው ክስተት ተዝናንተናል። በሚቀጥለው ጊዜ ስንጨባበጥ ችግሩን እንፈታዋለን። እኔም በቦታዬ እሱም በቦታው እንቀመጣለን” ሲሉ አክለዋል። ቱሄል ሁለተኛው ጎል ሲቆጠር እየዘለሉ ደስታቸውን በመግለጻቸው ግማሽ ይቅርታ ጠይቀዋል። “መሐል ላይ ማድረግ እንደሌለብኝ ተሰምቶን ነበር። ግን አንዳንድ ጨዋታዎች እንደዚህ ያደርጋሉ” ብለዋል። ፕሪሚየር ሊጉ ከተጀመረ በኋላ ቶተንሃም ስታምፎርድ ብሪጅ አይቀናውም። ወደ ሰማያዊዎቹ ሜዳ አቅንቶ 22 ጊዜ ተሸንፏል። አንድ ጊዜ ብቻ ሲያሸንፍ 12 ጊዜ አቻ ተለያይቷል። “ብዙ ጊዜ በስታፎርድ ብሪጅ አይቀናንም። ስለዚህ ባለቀ ሰዓት ጎል አስቆጥረን አንድ ነጥብ ማግኘታችን አስደስቶናል” ያለው የቶተንሃሙ አምበል ሃሪ ኬን ነው። “ቀይ ካርዶቹን መመልከት ያሳዝናል። በስሜት የተሞላ የለንደን ደርቢ ነበር። ሁለቱም ቡድኖች ለማሸነፍ ተጫውተዋል። አንዳንዴ ተመሳሳይ ነገር ያጋጥማል” ብሏል። ሌላ ውድድር ካላገናኛቸው በስተቀር የትናንቱ ጨዋታ በየካቲት የሚደረገው የሁለቱ ቡድኖች ግጥሚያ ከወዲሁ በጉጉት እንዲጠበቅ በር ከፍቷል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cjj4pl2840go +politics ለመጀመሪያ ጊዜ ለዋይት ሀውስ ጥቁር ሴት ቃል አቀባይ ተሾመች "ካሪን ጄን-ፒይር የመጀመሪያዋ ጥቁር፣ ሴት፣ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ቃል አቀባይ ሆና በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተሰይማለች። የ44 ዓመቷ ካሪን ቦታውን የምትረከበው ከጄን ሳኪ ነው። ከቀጣዩ ሳምንት በኋላ ከዋይት ሀውስ ዘገባ ለሚሠሩ ጋዜጠኞች መረጃ መስጠት ትጀምራለች። ጄን ሳኪ ግራ ዘመሙ ኤምኤስኤንቢሲ ውስጥ በቅርቡ ሥራ እንደምትጀምር ተገልጿል። ቦታዋን የምትረከበውን ቃል አቀባይ ""በሥነ ምግባር የታነጸች ድንቅ ሴት"" ስትል ገልጻለች። ""የራሷ የአሠራር ስልት አላት። ድንቅና የላቀ ችሎታዋን እንደምታሳይ አልጠራጠርም"" ስትለም አክላለች። የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ የአሜሪካ መንግሥት ፊት ሆኖ ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ለመላው ዓለምም ይታያል። ማንኛውም ፖለቲካዊ ቀውስ ወይም ብሔራዊ አደጋ ሲከሰት ቀድመው የሚታዮት እነዚህ ቃል አቀባዮች ናቸው። ቃል አቀባዮች ፖሊሲ ባያረቁም አንድ የአሜሪካ አስተዳደር በሕዝቡ ዘንድ በምን መንገድ እንደሚታይ ይቀርጻሉ። የባይደን አስተዳደር እስከ ዛሬ ድረስ በፖለቲካው መድረክ ገሸሽ የተደረጉ ጥቁር ሴቶችን በማሳተፍ ቀጥሏል። ምክትል ፕሬዝዳንቷ ካሚላ ሐሪስ፣ የአገር ውስጥ ፖሊሲ ካውንስል ቃል አቀባይ ሱዛን ራይስ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ኬታንጂ ብራውን ጃክሰን፣ በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ካሪን ጄን-ፒይር ከዚህ ቀደም በኤምኤስኤንቢሲ ተንታኝ ነበረች። በፖለቲካው የሁለት አሥርታት ተሞክሮ አዳብራለች። በፍሬንች ካረቢያኗ ማርቲኒኪው ደሴት ተወልዳ ኒው ዮርክ አድጋለች። በኦባማ አስተዳደር ቁልፍ ቦታ ከነበራቸው አንዷ ናት። እአአ በ2016 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሲካሄድ ሙቭኦን የተባለው ብሔራዊ ንቅናቄ ቃል አቀባይ ነበረች። ባይደን ካሚላ ሐሪስን ምክትላቸው አድርገው ከመረጡ በኋላ በቃል አቀባይነት ሠርታለች። የፊታችን ጥቅምት በአሜሪካ የአስተዳደር አጋማሽ ምርጫ ይካሄዳል። ይህም ባይደን ፕሬዝዳንት ሆነው የሚቀጥሉበት ዓመታት በምን አቅጣጫ እንደሚጓዙ ይወስናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61343905 +business ቀጣዩ 8.5 በመቶ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እድገት በባለሙያዎች ዕይታ "የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እንደሚያደርገው በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፅህፈት ቤት አዳራሽ ሐሙስ ሰኔ አራት ቀን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዶ 476.1 ቢሊዮን ብር ገደማ ይሆናል በተባለው በቀጣዩ የበጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቷል። ከዚሁ ውስጥ በመንግሥት ረቂቅ በጀት መሰረት 176 ቢሊዮን ብር ገደማ የሚሆነው ለክልሎች የሚሰጥ ሲሆን፤ የፌዴራል መንግሥት ደግሞ ለመደበኛ ወጪዎቹ 133 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎቹ 160 ቢሊዮን ብር ይደርሰዋል መባሉን የአገር ውስጥ የብዙሃን መገናኛ አውታሮች ዘግበዋል። ረቂቅ በጀቱን በሚመለከት ማብራሪያ የሰጡት የፌዴራል መንግሥቱ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ቀጣዩ የበጀት ዓመት በኢትዮጵያ 8.5 በመቶ ዕድገት እንደሚመዘገብ ለሕዝብ እንደራሴዎቹ ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ኢትዮጵያ 9 በመቶ የምጣኔ ሃብት ዕድገትን እጠብቃለሁ ብላ ነበር። ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አገራት ምጣኔ ሃብት ላይ ከባድ የሚባል ጫናን እየፈጠረ ባለበትና የዚህ በሽታ ተጽዕኖ ለዓመታት ባይሆን ለቀጣይ ረዥም ወራት እንሚቀጥል እየተነገረ ባለበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዚህ መጠን ሊያድግ የሚችልበት ዕድል መኖሩ እያነጋገረ ነው። የቀጣዩን የበጀት ዓመት የአገሪቱን በጀትና ተጠባቂ ዕድገትን በተመለከተ ቢቢሲ የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎቹን አለማየሁ ገዳን (ዶ/ር) እና አቶ ዋሲሁን በላይ ያላቸውን ዕይታ ጠይቋል። የምጣኔ ሃብት ተንታኙ አቶ ዋሲሁን በላይ ባለፈው የበጀት ዓመት ቀርቦ ከነበረው 386.9 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር ዘንድሮ የቀረበው በጀት ከፍ ያለ ብልጫ ያለው ቢመስልም፤ በመገባደድ ላይ ያለው የበጀት ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት መንግሥት 28 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ተጨማሪ በጀት ማስፀደቁን ጨምረው በማስታወስ አሁንም ጭማሪው የሚታይ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ነገር ግን የቀጣይ ዓመት የአገሪቱ በጀት ከመጨመሩ ጎን ለጎን ይመዘገባል ተብሎ በገንዘብ ሚኒስትሩ የቀረበው የተጠባቂ ዕድገት ቁጥር ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ላይ ባለሞያዎቹ ጥያቄዎችን ያነሳሉ። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለም ዙርያ ምጣኔ ሃብቶችን በሚገዳደርበት እና ""በርካታ አገራት ዕድገታቸው የቁልቁል እንደሚሆን በተነበዩበት ወቅት፤ ከስምንት በመቶ የሚሻገር ዕድገትን መጠበቅ አስቸጋሪ ነው"" ይላሉ አለማየሁ (ዶ/ር)። ""ምናልባት በገንዘብ ሚኒስትሩ የቀረበው የተጠባቂ ዕድገት መጠን በወረርሽኙ የሚደርሰውን ምጣኔ ሃብታዊ ጡጫ ያላካተተ ይሆን?"" ሲሉም ይጠይቃሉ። ወረርሽኙ በ2013 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት (ከቀጣዩ ሐምሌ እስከ መስከረም) ድረስ የኢትዮጵያን ምጣኔ ሃብት ክፉኛ ይደቁሳል፤ ከዚያ ወዲያ ግን ተግ ይላል ብለን ብናስብ እንኳ ይላሉ ባለሞያው አለማየሁ ""በእኔ ግምት ምጣኔ ሃብቱ በ5.6 በመቶ ይቀነሳል"" ሲሉ የእራሳቸውን እይታ ያስቀምጣሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ግምታቸውን ባደረጉት ጥናት ላይ መሠረት እንዳደረጉ ይገልፁና ""ይህ ማለት የ8.5 በመቶ ዕድገት ላይ ለመድረስ ወረርሽኑ ከሚያደርሰው ጉዳት ጋር የሚደመር አጠቃላይ የ14 በመቶ ገደማ ይጠበቃል እንደማለት ነው"" ይላሉ። ይህን መሰል ዕድገት ማስመዝገብ ደግሞ የመሆን ዕድሉ የጠበበ ነው ባይ ናቸው። የገንዘብ ሚኒስትሩ የተጠባቂ ዕድገት መግለጫ የወረርሽኙን ጉዳት ያላካተተ ከሆነ ግን ከጉዳቱ ጋር ተወራርዶ የሚኖረው ዕድገት 3 በመቶን የሚጠጋ ይሆናል እንደማለት ነው እንደእርሳቸው ግምት። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን እንደሚሉት ምንም እንኳ የወረርሽኙ ዳፋ ለኢትዮጵያ ባይቀርላትም፤ ቢያንስ እስካሁን እጅጉን የተጋነነ ስርጭትን ባለማስተዋሏ ወደሌሎች አገራት የምትልካቸው ቡናን የመሳሰሉ ምርቶች ፍላጎትም ሲቀንስ ባለመታየቱ መልካም ነገር ነው ይላሉ። የኮሮናቫይረስ ጣጣ ለረጅም ጊዜ ሊዘልቅ እንደሚችል የሚሰጉት አለማየሁ (ዶ/ር) እንደሚሉት የወረርሽኙ ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት ላይ ብቻ ይቀጥላል ማለት ""ይህ ጥሩ የሚባለው፥ ከቀናን (ቤስት ኬዝ ሲናርዮ) የሚባለው ግምት ነው"" ይላሉ። ወደ እውነታ የሚጠጋው ግምት ግን የወረርሽኙ ምጣኔ ሃብታዊ ጫና ""አነሰ ቢባል ለስድስት ወራት ያህል፤ ያ ማለት እስከ ታኅሳስ ወር ድረስ"" ይዘልቃል የሚለው ነው እንደ አለማየሁ (ዶ/ር)። ለሁለት ሩብ የበጀት ዓመታት ያ ማለት እስከወርሃ ታህሳስ ድረስ የኮቪድ-19 መዘዝንና ቡጢውን ምጣኔ ሃብቱ ላይ ማሳረፉን ከቀጠለ ደግሞ ባለሙያው እንደሚገምቱት ምጣኔ ሃብቱ በአስራ አንድ በመቶ እንደሚቀንስ ነው። ""በታዳጊ አገራት ከፍ ያለ ዕድገትን ማስመዝገብ አስገራሚ ነገር አይደለም"" የሚሉት አቶ ዋሲሁን፤ ከዚሁም አንፃር በአዲሱ የበጀት ዓመት 8.5 በመቶ ዕድገት ይመዘገባል መባሉ የሚደንቅ ሊሆን አይገባም ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""ከፍተኛ በጀት በጅተህ መሠረተ ልማት ላይ ማፍሰስ ብቻውን እኮ የአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርትን (ጂዲፒውን) እንዲያድግ ያደርገዋል"" ሲሉ የእድገት ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉት ነገሮች መካከል ይጠቅሳሉ፤ አቶ ዋሲሁን። አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ድረስ ምጣኔ ሃብቱን ለማረጋጋት ብሎም ለማነቃቃት የወሰዳቸውን እርምጃዎች ያደንቃሉ፤ የበለጠ እንዲያደርግም ይመክራሉ። በአንድ በኩል መንግሥት እንደሌሎች በርካታ አገራት ምጣኔ ሃብቱን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት በኢትዮጵያ አውድ እንደማያዋጣ አውቆ እርሱን ያለማድረጉ እና ከዚያ ይልቅ ሥራዎች ከሞላ ጎደል እየተሰሩ ጥንቃቄዎች እንዲወሰዱ ማድረግን ዓይነተኛ አቅጣጫ አድርጎ መንቀሳቀሱ ተገቢ ነበር ይላሉ። ""ሰዎች የጤናቸው ሁኔታ ባሉበት መስሪያ ቤት አካባቢ እየተጠበቀ፤ ምጣኔ ሃብቱ እንዲንቀሳቀስ ማድረጉ ቆንጆ ነገር ነው።"" በሌላ ወገን ወረርሽኙ ለሚጎዱ ዘርፎች የማነቃቂያ ድጋፍ ማዘጋጀቱና ይህንን ለማቅረብ መስራቱም መልካም ነው ባይ ናቸው። ሆኖም ""የግል ክፍለ-ኢኮኖሚውን በተለይ ኢንደስትሪው አገልግሎት ላይ ያሉትን ሰዎች እንዴት እንደሚደግፍ ኮስተር ያለ ዕቅድ አውጥቶ መከታተል ያለበት ይመስለኛል። [የእስካሁኑን እንቅስቃሴ] ሳየው ወጥ የሆነ አሰራር አይመስልም"" ይላሉ። ""በደንብ ታስቦበት፣ በአጭር ጊዜ እንደዚህ [ይሆናል] በረጅም ጊዜ እንደዚህ [ይሆናል] ተብሎ እየተሄደበት አይመስለኝም።"" ከዚህም በዘለለ ቁጥራቸው ከሦስት ሚሊዮን ይሻገራል ያሏቸውን ራሳቸውን በራሳቸው (አንዳንዶቹ) ቤተሰባቸውን ጨምሮ የሚያስተዳድሩ ሰዎች ""የመንግሥታዊ ድጋፍ ጠበል አልደረሳቸውም"" ይላሉ። የእነዚህ ሰዎች ዋነኛ ወጪ የመስሪያ ቦታ ኪራይ ክፍያ በመሆኑ እርሱን በተመለከተ በአከራዮች በጎ ፈቃድ ላይ የማይመሰረት የክፍያ ቅነሳ እርምጃ ያስፈልጋል ባይ ናቸው። መንግሥት የኪራይ ወጪያቸውን በተወሰነ ድርሻ እንዲከፍል ማድረግም ሌላ የማነቃቂያ እርምጃ ሊሆን ይችላል ሲሉ አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። በቀጣይ ዓመት ኢትዮጵያ ሊኖራት የሚችለውን ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ትንበያን በተመለከተ አቶ ዋሲሁን ግምታቸውን ሲያስቀምጡ ""የተለጠጠ ታቅድና በጥረት የምትደርስበት ያህል ነው የምትሰራው። መንግሥት ይሄን ሲያስቀምጥ የጥረቱን ያስቀመጠ ይመስለኛል።"" ""ምክንያቱም ምን ያህል በሽተኛ ይዘህ ነው 8.5 በመቶ አድጋለሁ የምትለው? ሰላሳ አርባ ሺህ ነው ወይንስ አሁን እየሆነ እንዳለው በየቀኑ መቶ መቶ እየጨመርን? የሚለውም መታየት አለበት"" ሲሉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በቀጣይ ወራት ሊፈጥር የሚችለው እንቅፋት ከግምት ውስጥ መግባት እንዳለበት ይጠቅሳሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-53021260 +health በደቡብ ኮርያ የሀሎዊን በዓል በአደባባይ ሲከበር በደረሰ አደጋ ቢያንስ 151 ሰዎች ሞቱ በደቡብ ኮርያ የሀሎዊን በዓል ለማክበር የወጡ ሰዎች በገጠማቸው አደጋ ቢያንስ 151 የሚደርሱት ሕይወታቸው አልፏል። 82 ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል። በመዲናዋ ሴዑል በሚገኝ ጠባብ አደባባይ ላይ በዓሉን ለማክበር የወጡ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነበር። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወዲህ ያለ አፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የተካሄደ የመጀመሪያው የአደባባይ ክብረ በዓል ነበር። የሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ስለነበር መገፋፋትና መረጋገጥ መከሰቱ ተዘግቧል። ከሞቱት መካከል አብዛኞቹ በ20ዎቹ ዕድሜ ክልል የሚገኙ ሲሆን፤ 19ኙ የውጭ አገር ዜጋ ናቸው። አደጋው በምን ምክንያት እንደተከሰተ ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል። አስቸኳይ ስብሰባ ከተካሄደ በኋላ የደቡብ ኮርያ ፕሬዝዳንት ዮን ሱን-ዮል የተጎዱትን የሚያክም ግብረ ኃይል አቋቁመዋል። እአአ ከ2014 ወዲህ በአገሪቱ የተከሰተ የከፋ አደጋ ነው ተብሏል። ያኔ ስዑል የተባለ መርከብ ሰጥማ 300 ሰዎች ሞተዋል። ሀሎዊን የተከበረበት ኢታዎን የተባለው ሰፈር በምሽት ሕይወት ዝነኛ ነው። በተለይ ቅዳሜና እሑድ አገሬውና ጎብኚዎች ያዘወትሩታል። ሀሎዊን በደቡብ ኮርያ ብዙ ሰው ወደ አደባባይ ከሚወጣባቸው ቀኖች መካከል ነው። ትላንትም በዓሉን ለማክበር 100,000 በቦታው ተገኝተው እንደነበር ተገልጿል። በአንድ የተጨናነቀ መንገድ ላይ መገፋፋቱ እንደተጀመረ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የወጡ ቪድዮዎች አሳይተዋል። መንገዱ እጅግ ጠባብ ሲሆን፣ በቦታው የነበሩ ሰዎች በርካታ ነበሩ። አንድ ቪድዮ ሰዎች መተንፈስ ተቸግረው ያሳያል። ሰዎች በሰዎች ላይ ተደራርበውም ይታያል። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አስክሬኖች ሲያወጡ የሰዎች ለቅሶና ሲቃም ይሰማ ነበር። የተወሰኑ ሰዎች አስክሬን ወደ አምቡላንስ ሲወሰድ፣ የተቀሩት አስክሬን በፕላስቲክ ተሸፍኖ መንገድ ዳር ተቀምጦ ታይቷል። ራሳቸውን የሳቱ ሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ ትንፋሽ በመስጠት ሲሞክሩ የነበሩም አሉ። ከመላው አገሪቱ በመቶች የሚቆጠሩ የአደጋ ሠራተኞች ናቸው በቦታው የተገኙት። የሞቱትን ሰዎች አስክሬን ቤተሰቦቻቸው እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን፤ የሟቾች ቁጥር በርካታ በመሆኑ ሂደቱ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተገልጿል። አደጋው ሲከሰት የ30 ዓመቷ ጂዎን ጋውል ከጓደኞቿ ጋር እየጠጣች እንደነበር ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ነግራለች። “ሰዎች መጎዳታቸውን ጓደኛዬ ስትነግረኝ ደንግጬ ከመጠጥ ቤቱ ወጣሁ። መንገድ ላይ ራሳቸውን ለሳቱ ሰዎች ትንፋሽ የሚሰጡ ሰዎች አየሁ” ብላለች። በቦታው የነበረ ዶክተር እንዳለው፣ መጀመሪያ ላይ ለተወሰኑ ሰዎች ትንፋሽ በመስጠት ሕይወታቸውን ለማዳን ሲሞክር ነበር። ቆይቶ ግን ራሳቸውን የሳቱ ሰዎች ቁጥር እየናረ ሄዷል። አካባቢው መጨናነቁን ያዩ ሰዎች አደጋ ሊገጥም እንደሚችል የሚጠቁሙ ጽሑፎች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲጽፉ ነበር። ፓርክ የንግ-ሁን የተባለ የዓይን እማኝ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንዳለው፣ ለገና እና ሌሎች በዓሎች ከሚሰበሰቡ ሰዎች የበለጠ ነበር የወጣው። የአደባባይ በዓሎች እና የሰዎች ደኅንነትን የተመለከቱ ፖሊሲዎች እንዲከለሱ ውሳኔ ተላልፏል። የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ፣ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የአውሮፓ ኅብረት ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል እና የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጄክ ሱልቪን የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cg3lzn6v10wo +politics መንግሥት እርዳታ ከማቅረብ ውጪ በሌሎች ተግባራት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን ከአገር ላስወጣ እችላለሁ አለ "በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ከማቅረብ ይልቅ በሌሎች ተግባራት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን ከአገር እስከማስወጣት የሚደርስ ውሳኔ ሊውስድ እንደሚችል መንግሥት አስታወቀ። የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ድኤታ አምባሳደር ሬድዋን ዛሬ በሰጡት መግለጫ እርዳታ ለመስጠት ወይም ለማስተባበር ከሚፈልጉ አካላት መካከል ""ከእርዳታ ይልቅ ፕሮፓጋንዳ የማስተባበር፣ የኢትዮጵያን መንግሥት የማዋከብ፣ የማጠልሸት ዘመቻ ላይ ያሉ"" እንዳሉ ጠቅሰዋል። መንግሥት እነዚህ አካሎች እንዳስጠነቀቀ ተናግረው፤ ""ጉዳዩ በዚህ ከቀጠለ መንግሥት አገር የማዳን ኃላፊነት ስለሚወጣ ከአንዳንዶቹ ጋር አብሮ የመሥራት ሁኔታውን እንደገና እንደሚቃኝ፣ አንዳንዶቹንም ከአገር ለማስወጣት እንደሚገደድ"" ገልጸዋል። ይህንን ማሳሰቢያ የሰጡት ለተባበሩት መንግሥታት እንዲሁም ለሌሎች እርዳታ አቅራቢ እና አስተባባሪ አካሎች ነው። መንግሥት የተኩስ አቁም አውጆ ሳለ፤ ""በሌላኛው ወገን የሚደረገው ትንኮሳ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ መንግሥት ያሳለፈውን ውሳኔ እንደገና ለማጤን ይገደዳል። በዚህም ምክንያት ሁሉን አቀፍ እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል"" ሲሉም አስጠንቅቀዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ""በሌላኛው ወገን የሚደረገውን ትንኮሳ አንዲያጋልጥ፣ እንደዲኮንን"" የፌደራል መንግሥቱ ይጠይቃል ሲሉም በመግለጫው አስታውቀዋል። 'ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔውን አልደገፈም' የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ መንግሥት በትግራይ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ሲል የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ ቢወስድም፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግን ""አፍራሽ ዝንባሌ አሳይቷል"" ብለዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበተሰብ ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ መንግሥት ተኩስ እንዲያቆም ሲጠይቅ ቢቆይም፤ የፌደራል መንግሥት የተኩስ አቁም ከወሰነ በኋላ ግን ውሳኔውን በአዎንታዊ መንገድ እንዳላየው ወቅሰዋል። አምባሳደር ሬድዋን፤ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሲጠይቁ የነበሩ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወገኖች ""አዎንታዊ ውሳኔውን ተከትሎ አዎንታዊ ድጋፍ ለማድረግ ሳይሆን፤ ብዙዎች ሲንቀሳቀሱለት የነበረወን ውሳኔ መንግሥት ወስኖም እያለ ይህንን ከማደነቅ፣ የጎደለውን ከመሙላትና ከማሳሰብ ይልቅ ለዚህ አፍራሽና አሉታዊ ምክንያት በመደርደር የውሳኔውን አነስተኛነት ለማሳየት ተንቀሳቅሰዋል"" ሲሉ ወቅሰዋል። መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔው፤ ""ተጨማሪ እልቂትን ለማስቀረት ያለመ፣ የምጣኔ ሀብትና ፖለቲካዊ አመክንዮም ያለው"" እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጿል። የትግራይ ሀይሎች በበኩላቸው የመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ድል እንደተቀዳጁ ገልጸው፤ የፌደራል መንግሥት የተኩስ አቁም ለመቀበል ባለ ሰባት ነጥብ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል። የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ጉዳይ የተለያዩ የረድኤት ድርጅቶች የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል እርዳታ እንዲዳረስ ተገቢውን ድጋፍ እያደረገ እንዳልሆነ ወቅሰዋል። አምባሳደር ሬድዋን ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ""የሰብዓዊ እርዳታ እናቀርባለን ወይም እናስተባብራለን ያሉ አካላት ሲጠይቋቸው የነበሩ ነገሮች በአጠ���ላይ ተመልሰው እያለም አሁንም መንግሥት በአካባቢው በነበረበትና ግጭት ይካሄድ በነበረበት ወቅት ያሰሟቸው የነበሩ ወቀሳዎችና ስሞታዎች እያሰሙ ነው"" ሲሉ ገልጸዋል። ከሳምንታት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ወደ ትግራይ ክልል የምግብ እርዳታ ጭኖ ሲሄድ መሰናክል ገጥሞት እንደነበረ ከቀናት በኋላ ግን እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎቹን ወደ ክልሉ ማስገባት መቻሉን ገልጿል። በአውሮፓ ሕብረት አቅራቢነት የጸደቀውን የውሳኔ ሐሳብ በተመለከተ በ47ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ሕብረት ከትግራዩ ግጭት ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንደሚያሳስበውና የኤርትራ ሠራዊት አባላት ከትግራይ በአስቸኳይ እንዲውጡ በመጠየቅ ያቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ይህ የሕብረቱ የውሳኔ ሐሳብ ""ጊዜውያን ያልጠበቀ እና በፖለቲካ ፍላጎት የተላለፈ"" ነው ሲል ተቃውሟል። አምባሳደር ሬድዋን ይህንኑ ጉዳይ አንስተው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ""ስሞታ ሳያሰማ፣ መንግሥት አልተባበረንም ሳይል፤ አንዳንድ አገራትን በማስፈራራት፣ አንዳንዶቹን በማባበል የውሳኔ ሐሳብ ቀርቦ ኢትዮጵያ ላያ አቋም እንዲወጣ መደረጉ"" የመንግሥትን አዎንታዊ እርምጃ ከግምት ያላስገባ እንደሆነ ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57853275 +politics “መንግሥት ውስጥ የተሸሸገ ሸኔ አለ” የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ታዬ ደንደአ የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ የግድያ ማስፈራሪያዎች እንደሚደርሷቸው ለቢቢሲ ተናገሩ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማኅበራዊ ሚዲያዎች እና በተለያዩ መድረኮች በሚያነሷቸው ሃሳቦች አነጋገሪ የሆኑት ሚኒስትር ዲኤታው፤ በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ አለ ስለሚሉት ‘የማፊያ ቡድን’ እና በግል ስለሚደርሱባቸው ጫናዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ታዬ በቅርብ በተካሄደው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ስብሰባ ላይ አስተያየት “እንዳልሰጥ ድምጼ ታፍኗል” ብለው የፌስቡክ ገጻቸው ላይ ካሰፈሩ በኋላ ጉዳዩ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። አቶ ታዬ በጨፌው [በኦሮሚያ ምክር ቤት] የሆነው ሲያስረዱ፤ አፈ ጉባኤዋ የዕለቱን አጀንዳ ካቀረቡ በኋላ ምክር ቤቱ በሁለት ተጨማሪ ጉዳዮች ላይ እንዲነጋገር አጀንዳ ለማስያዝ ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱን ይናገራሉ። የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት አቶ ታዬ፤ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ከመቼውም ጊዜ በላይ “እየተበላሸ መጥቷል” ስላሉት የክልሉ የደኅንነት ሁኔታ አጀንዳ አድርጎ እንዲወያይበት ማቅረብ ፈልገው እንደነበረ ይገልጻሉ። ሁለተኛው ማንሳት የፈለጉት ጉዳይ ደግሞ “ከሌብነት ጋር በተያያዘ በክልላችን አስተዳደሩ ተዳክሟል” የሚል መሆኑን ጠቅሰዋል። “እጄን ሳወጣ ይዩኝ አይዩኝ [አፈ ጉባኤዋ] አላውቅም ዝም ብለው አጀንዳ ወደማጸደቅ ሄዱ። ከዚያ ‘ክብርት አፈ ጉባኤ የማነሳው ሃሳብ አለኝ’ አልኩ” ይላሉ አቶ ታዬ። “ከዚያ ዕድል እንደመስጠት አሉና እንዳልናገር ደግሞ ማይክሮፎኑን ዘጉብኝ። ትንሽ ቆይተው ‘ዕድሉን መጠቀም አልቻሉም’ አሉ። ‘ዝጉበት፣ ዝጉበት’ የሚል ድምጽ ይሰማ ነበር” በማለት አቶ ታዬ በጨፌው አጋጥሟል ያሉትን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ታዬ አስተያየቴን እንዳልሰጥ የተከለልኩት፤ ምክር ቤቱ በአጀንዳነት የያዛቸው ሪፖርቶች ችግር እንዳሉባቸው ስለሚታወቅ ነው ይላሉ። ከአንድ ዓመት በፊት የኦሮሚያ የፀጥታ ስጋት በአጭር ወራት ውስጥ ይወገዳል ተብሎ፣ ከአንድ ዓመት በኋላ ስንገናኝ የክልሉ የፀጥታ ችግር ተባብሷል የሚሉት አቶ ታዬ፤ ለዚህ የፀጥታ መደፍረስ ምክንያቱ ምንድን ነው? ተጠያቂውስ ማን ነው? በሚሉ ጉዳዮች ላይ ምክር ቤቱ እንዲወያይ ቢፈልጉም ዕድሉ እንደተነፈጉ ያስረዳሉ። የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ታዬ፤ በፓርቲው ውስጥ “ሌብነት ላይ የተሰማራ የተደራጀ ማፊያ አለ” ሲሉ ይከስሳሉ። አክለውም “ለዜጎች ክብር የለውም” ያሉት ቡድን በአካል እንጂ በሃሳብ ብልጽግና አይደለም ሲሉ ተናግረዋል። “ወረቀት ይዞ ብልጽግና ነኝ ሊል ይችላል እንጂ፣ ይህ ሰው አስፈራርቶ አፍኖ የሚወስድ ቡድን ብልጽግና አይደለም። . . . የታገልንለት ወደ ኋላ እንዲመለስ፤ ማፊያ እጅ እንዲገባ እኛ እንፈልግም” ብለዋል። አቶ ታዬ በንግግራቸው በኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ውስጥ አለ ያሉት የማፊያ ቡድን፣ አባላቱ እነማን እንደሆኑ እንዲሁም “ማፊያ” ያሉት ቡድን ፈጽሟል ስላሉት አሉታዊ ተግባር ያቀረቡት ማስረጃ የለም። “እዚህ ቡድን ውስጥ ያሉት እነ እከሌ ናቸው ብሎ ለመዘርዘር ጊዜው አሁን አይደለም። ጊዜው ሲደርስ ስማቸውን እንዘረዝራለን” ሲሉ በደፈናው ማለፍን መርጠዋል። አቶ ታዬ በቅርቡ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ የደኅንነት ስጋት እንዳለባቸው ገልጸው ነበር። “ ‘እንረሽንሃለን...ግንባርህን እንልሃለን’ እያሉ በግልጽ የሚያስፈራሩ አሉ።...ሁሉንም አስፈራርቶ አይሆንም። ሰው መጉዳት፣ ሰው መግደል ይቻላል። ይህ ብዙ ቦታ ሆኗል። ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይም ተፈጽሟል” በማለት ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል። የግል ጠባቂዎቻቸው እንዲነሱ መደረጋቸውን የሚናገሩት ሚኒስትር ዲኤታው፣ ምንም እንኳ የግድያ ዛቻን ጨምሮ ማስፈራሪያ ቢደርስባቸውም፤ “በትግላቸው” እንደሚቀጥሉ ይናገራሉ። ቢቢሲ የሚኒስትር ዲኤታ ጠባቂዎች ስለመነሳታቸው ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ማረጋገጥ አልቻለም። “... እኛ ከቤት የወጣነው ለነጻነት ነው። ለሕዝብ ነጻነት ታግዬ ብታፈን በተቃራኒ ጎራ ስለታገልኩ ነው። ዋስትናችን ትግላችን ነው” ሲሉም አክለዋል። አቶ ታዬ በኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ውስጥ አሉ የሚሏቸው ብልሹ አሰራሮችን በንግግር ለመፍታት መንገዶች ዝግ መሆናቸውን ይናገራሉ። “በውይይት ውስጣችንን ማየት አለብን። በኦሮሚያ ሥልጣን ላይ ያለው ቡድን ግን ይህ እንዲደረግ አይፈልግም። ለውይይት በሩ ዝግ ነው። እኔ በጣም ብዙ ጊዜ ሞክሪያለሁ። ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ እችላለሁ። የሚሰማኝ ግን አጣሁ” ብለዋል። የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታው አሁን በኦሮሚያ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ “...ወንድ ልጅ የሚደፈርበት፣ አባ ገዳዎች የሚገደሉበት፣ ሰው ወጥቶ መግባት የማይችልበት፣ እጅግ በጣም አስቀያሚ ነገሮች ያሉበት” ሲሉ ይገልጹታል። አቶ ታዬ የዜጎች ደኅንነትን ማረጋገጥ ሳይቻል ሰው ወጥቶ መግባት ስጋት ሆኖበት ሳለ፤ “በክልሉ አጠቃላይ ስኬት ማስመዝገብ ተችሏል ሲባል፤ ቀድሞ ምን ታቅዶ ነበር” ያስብላል ይላሉ። “በክልሉ ከተገነቡት ትምህርት ቤቶች ይልቅ የተቃጠሉት ይበልጣሉ። ሕዝባችን መኖሪያ ቤቱ ተቃጥሎ መሄጃ አጥቷል። በሬው ታርዶበት የሚያርስበት የለውም። ያለው ችግር ተቆጥሮ አያልቅም።” አቶ ታዬ ለጠቀሷቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች እርሳቸው አባል የሆኑበትን አስተዳደርን ተጠያቂው ያደርጋሉ። “ከሁሉም በላይ የሕዝብ ደኅንነት የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት መንግሥት ነው። ...ስለዚህ በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያ ለተከሰተው ችግር ትልቁን ኃላፊነት መውሰድ ያለበት መንግሥት ነው” ብለዋል። አቶ ታዬ “ክልሉ ገብቶበታል” ላሉት ችግር ከመንግሥት በተጨማሪ ሌሎች ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው አካላት እንዳሉ ይናገራሉ። “በሰላማዊ መንገድ ከተማ ተገብቶ ከዚያ በኋላ ወደ ጫካ መሄድ አግባብ አይደለም” በማለት በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድንም “የሰላም ፀር” መሆኑን አንስተዋል። አቶ ታዬ ከዚህ ቀደም በአሮሚያ ክልል ሁለት ሸኔ ነው ያለው ሲሉ ተደምጠው ነበር። ሚኒስትር ዲኤታው መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጀው እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ቡድን አንዱ መሆኑን ገልጸው፤ “ሌላኛው ሸኔ መንግሥት ውስጥ የተሸሸገው ነው” ሲሉ ጠንከር ያለ አስተያየት ይሰጣሉ። “ጫካ ያለው አለ። ሌላኛው ደግሞ መንግሥት ውስጥ የተሸሸገው አለ። ወንጀል ደግሞ በዚህም በዚያም ይፈጽማሉ። ስለዚህ እኛ ውስጥ ያለ አለ፤ ከውጪም አለ” ብለዋል። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ካሉ የፀጥታ ችግሮች አንጻር የመስተዳደሩ መዋቅር ላይ ትችቶች ሲሰነዘሩበት የቆየ ሲሆን፣ ባለሥልጣናትም መዋቅራቸውን ለማስተካከል እርምጃ እንደሚወስዱ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲናገሩ ቆይተዋል። አቶ ታዬ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው እና በተለያዩ መድረኮች አባል የሆኑበትን አስተዳደር አጥብቀው የሚተቹት ‘ሥልጣን ስለሚፈልጉ ነው’ የሚሉ ትችቶች ሲነሱባቸው ይታያል። አቶ ታዬ ግን ይህ “ቀልድ ነው” ይላሉ። “ሥልጣን ብንፈልግ ኖሮ በወያኔ ዘመንም አገኘው ነበር። ወያኔ አይደለም ለእኛ አይነት ሰው በአግባቡ መጻፍ ለማይችሉት ሁሉ ሥልጣን ሲሰጥ ነበር። ሥልጣን ፍለጋ እድሜያችንን አልገበርንም።” አቶ ታዬ አሁን ያሉበት የሚኒስትር ዲኤታ ሥልጣን ከዚህ ቀደም ከነበሩበት ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረው፤ “ሰው በየዕለቱ እየተገደለ፣ ኢኮኖሚ እየደቀቀ፣ ወጥቶ መግባት እና በሕይወት መኖር አሳሳቢ በሆነበት ጊዜ ምን አይነት ሥልጣን ያምራል? የማይመስል ነገር ከማስመስል ቢቀር ይሻላል” ብለዋል። **** ማስታወሻ፡ አቶ ታዬ ደንደአ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ ለሰነዘሯቸው ሃሳቦች ከሚመለከታቸው የኦሮሚያ ክልል አካላት ምላሽ ለማግኘት ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ነገር ግን ከዚህ በኋላም ምላሽ ለመስጠት የሚፈልግ ወገን ካለ ለማስተናገድ ዝግጁ ነን። https://www.bbc.com/amharic/articles/cqlk0392qlko +business የቴስላ የገበያ ደርሻ መዳከሙን ተከትሎ ኤለን መስክ ቁጥር አንድ ባለጠጋ መሆኑ ቀረ ኤለን መስክ የሐብቱ ዋና ምንጭ የሆነው የቴስላ የኤሌክትሪክ መኪና አክሲዮን ዋጋ በመቀነሱ በዓለም የሐብታሞች ደረጃ የቀዳሚነቱን ቦታ አጥቷል። በጥር ወር መጀመሪያ ላይ ከ 880 ዶላር በላይ የደረሰው የቴስላ አክሲዮኖች ዋጋ አሁን ላይ 20 በመቶ በላይ አሽቆልቁሏል። ኩባንያው በቅርቡ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር ቢትኮይን ላይ ኢንቨስት በማድረጉ ምከንያት የቴስላ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል። ይህን ተከትሎም የአማዞኑ አለቃ ጄፍ ቤዞስን በሐብታሞች ዝርዝር ውስጥ ወደ ነበረበት ቀዳሚ ቦታ ተመልሷል። ምንም እንኳን ኩባንያው የገበያ ደርሻው መቀነሱ ችግር ውስጥ ባይከተውም፤ ኩባንያው ከቢትኮይን ጋር መያያዙ አንዳንድ የቴስላ ባለአክሲዮኖች የአክሲዮን ድርሻቸውን እንዲሸጡ አነሳስቷቸዋል ሲሉ የዌድቡሽ ሴኩሪቲሱ ተንታኝ ዳን ኢቭስ ተናግረዋል። ቴስላ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር ቢትኮይን መግዛቱ እና ቢትኮይንን እንደ ክፍያም ለመቀበል ማቀዱን ተከትሎ የቢትኮይን ዋጋ በቅርብ ሳምንታት በ50 በመቶ አድጓል። እንደ ማስተርካርድ እና የኒው ዮርክ ባንክ ያሉ ዋና ዋና ኩባንያዎች ቴስላን ተከትለው የዲጂታል ገንዘብን ለመቀበል ማቀዳቸውን አስታውቀዋል። መስክ ለቢትኮይን ትኩረት በሰጠበት ወቅት ቴስላ ሌሎች ተግዳሮቶችም እየገጠሙት ነው ፡፡ ኩባንያው ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸውን መኪኖች ለማሻሻል በማሰብ የመኪኖቹን ሽያጭ በቅርቡ አቁሟል። ከዚህ በተጨማሪም፤ በዚህ ወር መጀመሪያ የቻይና ተቆጣጣሪዎች የባትሪ ቃጠሎ እና ያልተለመደ የፍጥነት ሪ��ርት ከተደረገ በኋላ በደህንነት እና በጥራት ጉዳዮች ላይ ድርጅቱን አነጋግረዋል። እነዚህም ምክንያቶች የቴስላን ገቢ ከቀነሱ ጉዳይ መካከል ተጠቅሰዋል። እንደ ጄኔራል ሞተርስ እና ቮልስዋገን ያሉ ተፎካካሪ መኪና አምራቾችም በቅርብ ወራት በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ትኩረታቸውን አጠናክረዋል። እነዚህ ተግዳሮቶች የመጡት የቴስላ የአክሲዮን ዋጋዎች ከ 90 ዶላር ወደ 700 ዶላር በላይ በመመንደግ አስገራሚ ጭማሪን ካስከተሉ በኋላ የመጡ ናቸው። ጭማሪዎች መስክ በጥር ወር ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም የሐብታሞች ዘውርዝር የአማዞኑን ባለቤት ጄፍ ቤዞስን እንዲበልጥ አስችለውት ነበር። https://www.bbc.com/amharic/56179063 +business በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ዋጋን አላስቀምስ ያሉት አራት ማነቆዎች "በኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄዱ በርካታ የግንባታ ሥራዎች አማካይነት እውን ከሚሆኑ ጠቃሚ ግንባታዎች በተጨማሪ ዘርፉ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የሥር ዕድልን እንደፈጠረ ይነገራል። ይሁን እንጂ ዋነኞቹ የግንባታ ግብዓቶች በሆኑት በሲሚንቶ እና በብረት ላይ የሚታየው የዋጋ ንረት፤ በአገሪቱ እየተከናወኑ ላሉ የግንባታ ሥራዎች ዋነኛ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል። በአገሪቱ የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች፤ በስርጭት ችግር፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ በደኅንነት እጦት እና በጥሬ ዕቃ አቅርቦት መስተጓጎል ምርታቸው እየተፈተነ ነው። እነዚህም ዋጋቸው በከፍተኛ ደረጃ እንዲንር ምክንያት ሆነዋል። ይህም የአገሪቱን የግንባታ ዘርፍ ከፍኛ እየጎዳው እንደሆነ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችና ተቋማት ይናገራሉ። ስርጭት በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ዋጋ ጣራ እንዲነካ ከፍተኛ ድርሻውን ከሚይዙት ምክንያቶች መካከል አንዱ በስርጭት ሥርዓቱ ውስጥ ያለ እንከን ነው። ምርቱ ያለቀለት ሲሚንቶ ከፋብሪካ ወጥቶ የመጨረሻው ተጠቃሚ ጋር እስኪደርስ ድረስ ብዙ ሰንሰለቶችን ያልፋል። ፍቃድ ያላቸው ወኪሎች የሲሚንቶ ምርት ከፋብሪካ ተረክበው ለጅምላ አካፋፋዮች ያስረክባሉ። ጅምላ አከፋፋዮች ደግሞ ለቸርቻሪዎች ያቀርባሉ። የቢቢሲ ሪፖርተር በአዳማ ከተማ ተዘዋውሮ የሲሚንቶ ዋጋ ሁኔታን ተመልክቷል። በዚህም ባለፉት ጥቂት ወራት የሲሚንቶ ዋጋ ከነበረበት 500 ብር ገደማ ጨምሮ ከ1ሺህ ብር በላይ እየተሸጠ መሆኑን ተረድቷል። የኦሮሚያ ክልል ከሲሚንቶ ሰርጭት ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ሲሚንቶ የማከፋፈሉን ሥራ ከወኪሎች እጅ በማውጣት ኃላፊነቱን በማኅበር ተደራጅተው ለሚገኙ ወጣቶች ለመስጠት ስለማቀዱ ገልጿል። አቶ ደረጄ ብርሃኑ ሲሚንቶ አከፋፋይ ወይም ወኪል ናቸው። አቶ ደረጄ ሲሚንቶ ከፋብሪካ ተረክበው 'በተመጣጣኝ ዋጋ' ለጅምላ ሻጮች እንደሚያከፋፍሉ ይናገራሉ የሚናገሩት አቶ ደረጄ፤ ለሲሚንቶ ዋጋ መናር ችግሩ ያለው ወኪሎች ጋር አይደለም ይላሉ። ""ፋብሪካዎች ጥሬ ዕቃ በማጣታቸው ዋጋ ጨምረዋል። እንጂ ወኪሎች አይደሉም የጨመሩት። . . .ሌላው ዋጋ እየጨመሩ ያሉት ባለ ሱቆች ናቸው (ቸርቻሪዎች)። ብዙ ፈላጊ ስላለ ባለ ሱቆች ናቸው ዋጋ ጨምረው እየሸጡ ያሉት"" ይላሉ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሲሚንቶ ሸማቶች እንደሚሉት ከሆነ አከፋፋዮች (ወኪሎች) ከፋብሪካ የሚረከቡትን ሲሚንቶ ለነጋዴዎች ከመሸጥ ይልቅ አየር በአየር ለደላሎች የሚሸጡበት አጋጣሚ እንዳለ ያስረዳሉ። ""እንደዚህ አይነቱ ለደላሎች አየር በአየር የመሸጥ ሥራ የሚሰሩ ሊኖሩ ይችላሉ"" የሚሉት አቶ ብርሃኑ ሁሉም ግን በዚህ ድርጊት ውስጥ አሉበት ማለት እንደማይቻል ይገልጻሉ። ሲሚንቶ በችርቻሮ የሚሸጡበት ሱቅ ያላቸው አቶ ሙሴ እምሩ ደግሞ በሲሚንቶ ስርጭት ውስጥ ፈተና የሆኑት ደላሎች መሆናቸውን በማንሳት፣ ""እኛ የምንረከበው ከደላሎች ነው"" ይላሉ። ሲሚንቶ የሚያስረክቧቸው ደላሎች ሲሚንቶውን ከሌሎች ደላሎች በመግዛት የሚሸጡበት ሱቅ ሳይኖራቸው የምርት ዝውውሩን በስልክ ብቻ የሚያከናውኑ መሆናቸውን ይጠቅሳሉ። እንደ አቶ ሙሴ ገለጻ ከሆነ ወኪሎች የሲሚንቶ ምርት ከፋብሪካ ከተረከቡ በኋላ ሲሚቶው የመጨረሻው ተጠቃሚ ጋር ከመድረሱ በፊት በአካፋፋዮች እና ከአንድ በላይ በሆኑ ደላሎች በኩል ያልፋል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት እና የሲሚንቶ ችግርን ለመቅረፍ የተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አወሉ አብዲ ከሲሚንቶ ስርጭት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመቅፍ የክልሉ መንግሥት ወኪሎችን ከንግድ ሰንሰለቱ ሙሉ በሙሉ አስወጥቶ ስርጭቱ በተደራጁ ወጣቶች እንዲከናወን መወሰኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""ወጣቶች አደራጅተን ማከማቻ እና የሽያጭ ቦታዎችን በየከተሞቹ እናዘጋጃለን። በፋይናንስ በኩልም ሁኔታዎች ይመቻቻሉ። ከሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎች ጋር አብረው እንዲሰሩ ይደረጋል"" ብለዋል። የባለሥልጣናት ቤተሰቦች በስርጭቱ ውስጥ መሳተፍ ከሲሚንቶ ስርጭት ጋር ተያይዞ ከሚነሱት ወቀሳዎች መካከል የመንግሥት ባለሥልጣናት የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ በጥቅም የተሳሰሩ የአከፋፋዮች ሰንሰለት አንዱ ሊሆን እንደሚችል በዘርፉ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ይናገራሉ። በሲሚንቶ አከፋፋይነት ተሰማርተው ከሚገኙት መካከል ቢቢሲ ያናገራቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰቦች እንደሚሉት ይህ የተወሰኑ ባለሥልጣናት ቤተሰቦች እና ከእነሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች በስርጭቱ ውስጥ እንዳሉበት እንደሚወራ በመግለጽ በተጨባጭ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ አመልክተዋል። ሌሎች ደግሞ በግላጭ ማንነታቸው ወጥቶ አይታወቅ እንጂ በተዘዋዋሪ ብዙም ባይሆኑ የተወሰኑ ግለሰቦች በስርጭቱ ውስጥ እጃቸውን እንዳስገቡ እንደሚያምኑ ገልጸዋል። በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ አባላት በሲሚንቶ ንግድ ውስጥ የባለሥልጣናት ቤተሰብ አባላት ተሳትፎ አላቸው በሚል እርስ በእርስ ሲካሰሱ እንደነበር ይታወሳል። አቶ አወሉ አብዲ ግን በሲሚንቶ ንግድ ውስጥ የባለሥልጣናት የቤተሰብ አባላት ተሳታፊ ናቸው የሚባለውን እውነት አይደለም ይላሉ። ""የክልሉ ባለሥልጣናት የቤተሰብ አባላት በሲሚንቶ ንግድ ውስጥ ገብተዋል የሚላው በተደረገው ምርመራ ሐሰት መሆኑ ተደርሶበታል። ዘመድ ሳይሆን የዘመድ ዘመድ በሲሚንቶ ንግድ የተሳተፈ አልተገኘም"" ይላሉ አቶ አወሉ። ""በአገር ደረጃ ዘጠና አካባቢ ወኪሎች ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል አንድም የባለሥልጣን ዘመድ የለም። በባለቤቶቻቸው ስም ሲሚንቶ እየነገዱ ነው የሚለው የሐሰት ወሬ ነው"" ብለዋል። የደኅንነት ችግር በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሲሚንቶ የገበያ ድርሻውን ይዘው የሚገኙት በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ናቸው። ዳንጎቴ፣ ደርባ፣ ሙገር፣ ኢትዮ ሴሜነን- በአንድ አካባቢ ይገኛሉ። በምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ። በእነዚህ ስፍራዎች ደግሞ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው እና መንግሥት ሸኔ ብሎ አሸባሪ ሲል የፈረጀው ታጣቂ ቡድን ይንቀሳቀሳል። ይህንን በታጣቂዎች የሚፈጠር የደኅንነት ስጋትን ለማስወገድ መንግሥት በግዙፍ ተቋማት አካባቢ ደኅንነትን ለማረጋገጥ የረዥም እና የአጭር ጊዜ እቅድ አውጥቶ እየሰራ እንደሆነ አቶ አወሉ ይናገራሉ። ""ወደፊት 'ኢንደስትሪያል ፎርስ' የተባለ ኃይል ተደራጅቶ ይህን የኢንዱስትሪ ደኅንነት እንዲያረጋግጥ አቅጣጫ ተቀምጧል። እስከዚያው ድረስ ደግሞ በቂ ፀጥታ ኃይል በአካባቢዎቹ እንዲሰማራ ከውሳኔ ተደርሷል"" ይላሉ። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የውጭ አገር ዜጎችን ጨምሮ የሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች በታጣቂዎ��� ታግተው ማስለቀቂያ ገንዘብ ተጠይቆባቸው ነበር። የአካባቢው ባለሥልጣናት ለዚህ እገታ ታጣቂውን ቡድን 'ሸኔ'ን ተጠያቂ አድርገው ነበር። በቅርቡ ከሲሚንቶ ምርት እና ስርጭት ጋር ተያይዞ ላሉ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የማዕድን ሚንስትሩ ታከለ ኡማ እና ሲሚንቶ አምራቾች ውይይት አካሂደው ነበር። በዚህ ውይይት ላይ የማዕድን ሚንስትሩ ከደኅንነት እጦት ጋር ተያይዞ ላሉ ቸግሮችን ለመፍታት የአካባቢው ወጣቶች በዘርፉ ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አንዱ መፍትሄ መሆኑን መግባባት ላይ እንደተደረሰበት ገልጸዋል። ኢንጅነር ታከለ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ""የአካባቢው ወጣቶች በዘርፉ ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ማስከበር በአንድ በኩል የወጣቶችን ህይወት የሚያሻሽል ሲሆን በሌላ በኩል ማኅበረሰበቡ በአካባቢው ለሚገኙ ተቋማት የሚኖሮውን የኔነት ስሜት የሚያሳድግ ነው። ይህም ለአካባቢው ሰላም እና ፋብሪካዎቹ የሚገጥማቸውን የፀጥታ ችግር ለማስቀረት የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተግባብተናል"" ብለዋል። የውጭ ምንዛሬ እጥረት ኢትዮጵያ ባለፉት በርካታ ዓመታት በተለይም የሰሜኑ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት ውስጥ እንደምተገኝ የተለያዩ አስመጪዎችና ሪፖርቶች ያመለክታሉ። የውጭ ምንዛሬው እጥረት በኮንትራክሽን ዘረፉ ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ ትልቁን ፈተና እንደደቀነ ከውጪ በሚመጡ ምርቶች ላይ የሚታየው የዋጋ መናር ቀላሉ ማሳያ ነው። አምራቾች ከውጪ ለሚያስገቧቸው ግብዓቶቻቸው በውጭ ምንዛሬ መክፈል ይጠብቅባቸዋል። ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ደግሞ ለምርታቸው የሚያስፈልጓቸውን የድንጋይ ከሰል እና መለዋወጫዎችን ከውጭ ያስገባሉ። አቶ አወሉም በኢትዮጵያ ከየሲሚንቶ ምርት ጋር ተያይዞ ያለው ዋነኛው ችግሩ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ነው ይላሉ። በተደጋጋሚ እንደተጠቀሰው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ለውጭ ምንዛሬ እጥረት ዘላቂው መፍትሄ አገሪቱ ለውጭ ገበያ የምታቀርበውን ምርት (ወጪ ንግድ) ላይ በርትቶ መስራት ሁነኛ አማራጭ ነው ይላሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-61438921 +politics የኦሮሚያው ግጭት እርዳታ የሚጠብቁ ሰዎችን ቁጥር እንደጨመረው ተመድ ገለጸ በኦሮሚያ ክልል እየተባባሰ የመጣው ግጭት የሰብአዊ እርዳታ የሚጠባበቁ ነዋሪዎችን ቁጥር እንደጨመረው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ዩኤን ኦቻ) አስታወቀ። በክልሉ የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ ባሻገር የመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ላይም ጫና እንደተፈጠረ ኦቻ ባወጣው ሪፖርት ገልጿል። በተባባሰው ግጭት ምክንያት በቅርቡ ምን ያህል ሰዎች እንደተፈናቀሉ ለማወቅ አዳጋች ቢሆንም፣ የክልሉ ባለሥልጣናት እስካሁን ባወጧቸው አሐዞች መሠረት በምዕራብ ወለጋ ዞን 106,000 ነዋሪዎች እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ 116,000 ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል። “በክልሉ ተደራራቢ ቀውሶች መፈጠራቸው የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል። ግጭቶችን ተከትሎ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉም ነው” ሲል ኦቻ ኅዳር 28 ቀን 2015 ዓ. ም. ባወጣው ሪፖርት ገልጿል። ባለፉት ቀናት በምዕራብ ኦሮሚያ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ብሔር ተኮር በሆኑ ጥቃቶች ሰላማዊ ሰዎች ሰለባ መሆናቸው ሲገለጽ ቆይቷል። በተለይም በምሥራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ በሚገኙት ጊዳ አያና እና ኪራሙ ወረዳዎች ባለፉት ቀናት በነበሩ ጥቃቶች በርካቶች ሲገደሉ በመቶ ሺዎች መፈናቀላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች እና ጥቃቶች ሳቢያ እየደረሱ ያሉ ግድያዎች፣ የአ���ል ጉዳቶች እና መፈናቀሎች እጅግ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደሆኑ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኅዳር 28/2015 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። የሰሞነኛው ግጭት ዋነኛ ተሳታፊዎች “ሸኔ እና የአማራ ታጣቂዎች” ናቸው ያለው ኢሰመኮ፤ በክልሉ ዞኖች በታጣቂ ቡድኖቹ በተፈጸሙ ጥቃቶች በመቶዎች የሚገመቱ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን እና ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ገልጿል። ኦቻ በበኩሉ፣ ከሰሞኑ በተነሳው ግጭት ምን ያህል ሰዎች እንደተፈናቀሉ ገና ባይታወቅም፣ እስካሁን በእነዚህ አካባቢዎች የተፈናቀሉና እርዳታ የሚጠባበቁ ሰዎችን ቁጥር ከፍ እንደሚያደርገው ጠቅሷል። ክልሉ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ሰዎች ተጨማሪ መጠለያዎችን እያዘጋጀ እንደሆነ በሪፖርቱ ተገልጿል። የእርዳታ አቅርቦት እና እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር እንደማይመጣጠን የገለጸው ኦቻ፣ በምዕራብ ወለጋ ዞን እርዳታ ከሚፈልጉ 19,000 አባወራዎች መካከል 1,100 ብቻ ድጋፍ እንዳገኙና በምሥራቅ ወለጋ ዞን እርዳታ ከሚፈልጉ 30,000 አባወራዎች 9,337 ብቻ ድጋፍ እንዳገኙ አስታውቋል። በበጀት እጥረት እና እርዳታ ማሳለጫ መንገዶች በማጣት፤ ኦቻ ኦሮሚያን ጨምሮ ሰብአዊ እርዳታ በሚያደርስባቸው አካባቢዎች ድጋፍ ከሚፈልጉ ሰዎች ግማሽ ያህሉን እንኳን ማዳረስ እንዳልቻለ በሪፖርቱ አካቷል። በክልሉ በተለይም በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች የሕጻናት መቀንጨር መከሰቱንም የኦቻ ሪፖርት ያመለክታል።እስካሁን 563,000 ሕጻናት ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን፣ 1.96 በመቶው በከፋ ሁኔታ እንዲሁም 18 በመቶው በተወሰነ መጠን መቀንጨር ገጥሟቸዋል። የኮሌራ እና ኩፍኝ ወረርሽኝ ያለውን ችግር እንዳባባሱት እንዲሁም የተመጣጠ ምግብ እጥረት ላይ የቤተሰቦች አለመኖር ክፉኛ በድርቅ የተጎዱ ወረዳዎች ያሉ ሕጻናትን ለአደጋ ማጋለጡን ኦቻ አክሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c72n3zyy0gmo +business አሳሳቢ የሆነው በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ ዝርፊያ እና የባንኮች ኃላፊነት አቶ እንዳለ ገ/መድኅን ከሚሰሩበት የመንግሥት መሥሪያ ቤት የቁጠባ አገልግሎት በብድር ያገኙትን 200 ሺህ ብር ለጋራ መኖሪያ ቤት ቅድሚያ ክፍያ ለመክፈል በማሰብ በባንክ አስቀምጠው በመጠባበቅ ላይ ነበሩ። ነገር ግን ምንም አይነካብኝም ብለው ያሰቡት ሁለት መቶ ሺህ ሊሞላ 5 ሺህ ብር የጎደለው ገንዘባቸው፣ ባልጠበቁት መንገድ በዘራፊዎች ከአካውንታቸው ተመንትፎ ለዘርፈ ብዙ ቀውስ መዳረጋቸውን ይናገራሉ። አንድ ዕለት “ከባንክ ነው የምንደውለው” ያሉት ግለሰቦች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚያካሂደው “ይቆጥቡ ይሸለሙ” መርሃ ግብር የሞተር ሳይክል ሽልማት እንደደረሳቸው ተነገራቸው። ቀጥሎም በወቅቱ ሞተር ሳይክሉን ሊሰጧቸው እንደማይችሉ ነገር ግን ገንዘቡን ሊያስገቡ እንደፈለጉ በመናገር የተለያዩ መረጃዎችን ጠየቋቸው። ይህንንም ተከትሎ አቶ እንዳለ የተጠየቁን ቁጥር ሁሉ ተናግረው በመጨረሻም በአቢሲኒያ እና በንግድ ባንክ አካውንቶቻቸው ውስጥ የነበረው 195 ሺህ ብር ተወስዶባቸዋል። ይህ የአቶ እንዳለ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በርካታ ሰዎች የገጠማቸው የማጭበርበር ድርጊት ነው። ዝርፊያው በተለይም የሞባይል ባንኪንግ አገልገሎት የሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፣ በርካቶች በተለያየ ማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ላይ እሮሮ ሲያሰሙ የከረሙበትም ጉዳይ ነው። የፌደራሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዚህ የማጭበርበር ድርጊት ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲሁም ክስ የተጀመረባቸው መዝገቦችን በተመለከተ ባደረገው ጥናት በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ ምዝበራዎች መበራከታቸውን አመልክቷል። የሞባይል ባንኪንግን ጨምሮ በመዝገብ የተያዙት ወንጀሎች በአምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ 1.9 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ማድረሳቸውን ጥናቱ አትቷል። በዝርዝሩም ከፍተኛ ዝርፊያ ያጋጠመው በንግድ ባንክ ሲሆን አቢሲኒያ ባንክ እና ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ይከተላሉ። በቼክ የሚፈጸሙ፣ በቁጠባ ሂሳብ ላይ፣ በሃዋላ በሚላክ ገንዘብ ላይ፣ የይለፍ ቃል ምንተፋ ብሎም በሌሎች መንገዶች ስርቆቱ እንደሚፈጸም ጥናቱ ያሳያል። በሞባይል ባንኪንግ የሚፈጸመው ስርቆት በርካታ ስልቶች ያሉት ሲሆን ከተዋናዮቹ መካከል የባንክ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች እና ሌሎች የባንክ ሠራተኞች ጭምር እንደሚሳተፉበት ይገልጻል። ሠራተኞቹ ከደንበኞች አካውንት ጋር የራሳቸውን ወይም የዘመዶቻቸውን ብሎም የጓደኞቻቸውን ቁጥር በማያያዝ እና ሐሰተኛ ቅጽ በመሙላት ስርቆቱን እንደሚፈጽሙ ጥናቱ አመልክቷል። በማሳያነት የተጠቀሰው መዝገብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፒኮክ መናፈሻ ቅርንጫፍ ሠራተኛ የሆነ አንድ ግለሰብ በባንኩ ደንበኛ ለረጅም ጊዜ ሳይንቀሳቀስ የቆየውን አካውንት በማንቀሳቀስ ስርቆት መፈጸሙን ያሳያል። ለዚህም ግለሰቡ ካስገቡት የሞባይል ባንኪንግ ቁጥር ውጪ ሌላ በማስገባት በአጠቃላይ 2.5 ሚሊዮን ብር ገደማ ከግለሰቡ ሂሳብ ወስዷል ሲል ጥናቱ ያሳያል። አክሎም የስርቆቱ ዋና ተዋናዮች የባንክ ኃላፊዎች መሆናቸውን ጠቅሶ፣ ነገር ግን መደበኛ የባንኩ ሠራተኞች አይሳተፉበትም ብሎ ለመደምደም ግን አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጿል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ለዓመታት በባንክ ሥራ ላይ የቆዩ አንድ ግለሰብ እንደሚሉት በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ የባንክ ሠራተኞች ለእስር እየተዳረጉ ነው። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ በባንኮች ውስጥ ሆነው ወንጀሉን የሚፈጽሙ ሰዎች እንደማይያዙ ያክላሉ። በባንኮች መካከል የቅልጥፍና ውድድር በመኖሩ ምክንያት የባንክ ሠራተኞች ሁልጊዜ የባንኩን የአሰራር ሥነ ሥርዓት እንደማይከተሉ የሚናገሩት እኚሁ ግለሰብ፤ በምሳሌነትም በሥርዓቱ መሰረት ያለ ባንክ ደብተር ገንዘብ መክፈል ባይቻልም በአብዛኛው የባንክ ደንበኞችን ለመያዝ በሚደረገው ፉክክር ያለ ደብተር ክፍያ መፈጸም እጅግ የተለመደ ነው ይላሉ። በዚህም ሳቢያ አንድ ሰው ያለደብተር በመቅረብ አጭበርብሮ ገንዘብ ቢዘርፍ ከፋዩ ባለሙያ በኋላ ላይ ሲጣራ ተጠያቂ ሲሆን ባንኩም “ባስከመጥኩለት ሥርዓት መሰረት አልሰራም” በሚል አሳልፎ ይሰጠዋል ሲሉ ያስረዳል። ይህ ሁኔታ ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ የሚካሄድበትን የቼክ ማጭበርበር ወንጀልንም ይመለከታል። ዝርፊያው ከተፈጸመ በኋላ ከፋዩ ወይም የቅርብ አለቃው ለእስር ይዳረጉ እንጂ፣ ዋነኛዎቹ አጥፊዎች ሌሎች እንደሚሆኑ ይናገራሉ። “ባንኮች ትልልቅ ደንበኞቻቸውን ለመያዝ ከፍተኛ ፉክክር ያደርጋሉ” የሚሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱት የባንክ ባለሙያ፣ ቼክ ለመክፈል የሚያስፈልጉ ሂደቶችን በሙሉ ማሟላት ካስፈለገ አንድ ቀን ሙሉ ሊወስድ እንደሚችል በመጥቀስ “ይህ ደግሞ ትልልቅ ደንበኞችን ያርቃል” ይላሉ። ታዲያ አንድ ግለሰብ ቼክ ፈርሞ ለተከፋይ ሲልክ ለባንኩ ቀድሞ ደውሎ ገንዘቡ እንዲዘጋጅ ካዘዘ በኋላ ገንዘብ የሚወስደው ግለሰብ ገንዘቡን ተቀብሎ ይሄዳል። ቼኩ ማለፍ ያለበት ሂደትን ግለሰቡ ገንዘቡን ይዞ ከሄደ በኋላ የሚከናወን ይሆናል። በአሰራሩ መሰረት ግን ቼኩን የተቀበለው የመጀመሪያው ሠራተኛ ወደ ደንበኛው በመደወል ካረገገጠ በኋላ በመፈረም ለቀጣይ አለቃው ያስፈርማል። ቀጥሎም መስኮት ላይ ያለው ከፋይ በድጋሚ ፊርማዎቹን አረጋግጦ ይከፍላል። ነገር ግን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ባለው ፉክክር፣ በቅርብ አለቆቻቸው ዝርዝር ሂደትን እንዳይከተሉ የሚበረታቱት ��ፋዮች መጨረሻ ወንጀል መፈጸሙ ሲታወቅ ግን ሂደቱን አልተከተሉም ተብለው ለእስር እንደሚዳረጉ እኚሁ በባንክ ሥራ የበርካታ ዓመታት ልምድ ያላቸው ግለሰብ ይናገራሉ። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣው የሞባይል ባንኪንግን መሰረት ያደረገ ዘረፋ ግን በርግጥም በባንኮች የአሰራር ግድፈት ጭምር የታገዘ መሆኑን ይናገራሉ። “የስማርት ስልክ የሌለው፣ እንኳን ስልኩን አንብቦ አገልግሎቱን መፈጸም ቀርቶ ፊርማ እንኳን በአሻራ የሚፈርሙ ሰዎች የሞባይል ባንኪንግ አግልገሎት እንዲጠቀሙ እና እንዲመዘገቡ መደረጉ ለከፍተኛ ዝርፊያ ይዳርጋል” ሲሉም ይናገራሉ። ቀጥሎም ገንዘብ ያለው እና የሌለው ሰውን እንዲሁም የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቱን የሚጠቀመውን እና የማየጠቀመውን በመለየት ለሦስተኛ ሰው አሳልፈው የሚሰጡት ራሳቸው በባንኮች ውስጥ የሚሰሩ አንዳንድ ሰዎች እንደሆኑም ያስረዳሉ። አሁን አሁን ከአካውንት ወደ ቴሌ ብር በማስላክ ዝርፊያውን ቀላል እንዳደረገውም ግለሰቡ ተናግረዋል። በዚህ ሂደት ሐሰተኛ መታወቂያ ከሚያወጡ የቀበሌ ሠራተኞች እስከ የባንክ ኃላፊዎች ተሳታፊ መሆናቸውም አልቀረም። የባንክ ግልጋሎቶች በዘመኑባቸው አገራት እንዲህ አይነት በባንክ አካውንት ላይ ብሎም የሞባይል ክፍያ አገልግሎቶች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ባንኮች ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን ይሰራሉ። ከእነዚህም መካከል ከአንድ በላይ የሆነ የደንበኛውን ማንነት የማረጋጥ ሂደት ይጠቀሳል። ከዚያ በመለስ ባንኮች ለደንበኞቻቸው በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አጭር የጽሁፍ መልዕክት በመላክ ሳይታክቱ ያስተምራሉ። የኢትዮጵያ ባንኮች ምን ማድረግ አለባቸው የሚለውን ኋላ ላይ የምንመለስበት ቢሆንም ለምን ይህንን ማደረግ አይፈልጉም ስንል ግን የባንክ ሠራተኛ የሆኑ ምንጫችንን ጠይቀናቸዋል። “ገበያ ያርቅብናል ብለው ስለሚያስቡ ነው” ይላሉ። ይህም በተለይም እንደ ሞባይል ባንኪንግ ያሉ አገልግሎቶች ገና እየተለመዱ ያሉ ሲሆኑ ደንበኞች እንደዚህ አይነት ችግር ካለው ይቅርብን ብለው እንዳይተዉት በመስጋት መሆኑን ይናገራሉ። ይህ ዘላቂ እና አዋጭ መንገድ ነው ወይ ስንል የባንክ እና የኢኮኖሚ ባለሞያውን አብዱልመናን መሐመድን ጠይቀናቸዋል። ባንኮች ደንበኞቻቸውን ማስተማር እንደሚገባቸው እንዲሁም ይህ የማስተማር ሂደት በተገቢው የመገናኛ ዘዴ ሊሰጥ እንደሚገባ ተናግረዋል። በተለይም በዲጂታል ባንኪንግ ሥርዓት ወቅት ደንበኞችን ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ማጭበርበሮች ማስተማር ከፍተኛ ትርጉም አለው ይላሉ። የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ያጠናው ጥናት በራሱ የባንኮችን ኃላፊነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። “እነዚህ በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የሚያመሳስላቸው ነገር በአብዛኛው ከባንክ አሰራር ጋር ግንኙነት ያላቸው “የውስጥ ሠራተኞች’’ ሳይሳተፉባቸው የማይፈጸሙ ናቸው። የትኛውም ወንጀል ከመፈጸሙ በፊት አካውንቱ ላይ ገንዘብ ያለውን ከሌለው መለየት ያስፈልጋል” ሲል በግልጽ የባንኮች ተሳትፎን ያሳያል። እንዲሁም እነዚህን መረጃዎች በዚህ ጥልቀት እና ስፋት ከአንዳንድ የባንክ ሠራተኞች ትብብር ውጪ ማግኘት የማይቻል መሆኑንም ጥናቱ ያትታል። አብዱልመናን እንደሚሉት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የግል መረጃዎች የመጠበቅ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባቸው ሲሆን፣ በአብዛኛውም ይህንን እንደሚፈጽሙ ይናገራሉ። ነገር ግን ይህ እምነት የማይጣስበት አጋጣሚ የለም ማለት እንዳልሆነ ያክላሉ። ጨምረውም ይህንን ለመፍታትም ባንኮች በሚጠቀሙባቸው ሥርዓቶች ውስጥ ሠራተኞቻቸው ለመጥፎ አላማ ሊያውሏቸው የሚችሉ ክፍተቶችን የመሙላት አስፈላጊነትን አጽንኦት ይሰጣሉ። እንዲሁም መንግሥት ሕጎቹን በመከለስ በባንኮች ውስጥ ሥልጣን ያላቸው ሰዎች ያለ አግባብ እንዳይመዘብሩ ማድረግ ይገባዋል፤ እንደ ባለሙያው ገለጻ። ይህ ካልሆነ ግን ከደንበኞች ባሻገር እንዲህ ያሉ ተግባራት ባንኮች ላይ የሚጣለውን አመኔታ በመሸርሸር ለበለጠ ችግር ሊዳርጋቸው እንደሚችልም ይናገራሉ። ይህ በጥቅሉ ኢኮኖሚውን በመጉዳት ጉዳቱን የከፋ ያደርገዋል ሲሉም ያስጠነቅቃሉ። ነገር ግን እነዚህ ችግሮች እስከሚፈቱ ድረስ ደንበኞች በአጭበርባሪዎች መበደላቸው ብሎም ክስ ከመመስረት ውጪ ገንዘባቸውን ለማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል። በምሳሌነትም አቶ እንዳለ ለፖሊስ ያላቸውን ማስረጃዎች በሙሉ ይዘው ቢያመለክቱም፣ እስካሁን የተያዘ ተጠርጣሪ ያለመኖሩ ያሳስባቸዋል። ነገር ግን አሁንም በብድር ያገኙትን ገንዘባቸውን የሚያስመልስላቸው ፍትህ እየተጠባበቁ ነው። ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተደራርቦ ይህን ያህል ገንዘብ ማጣታቸው ከባድ ቀውስጥ ውስጥ እንደከተታቸው የሚገልጹት አቶ እንዳለ፣ ባዶ እጃቸውን ቢቀሩም “ያው እዳ ስለሆነ ከደመወዜ እየተቆረጠ መክፈል መች ይቀርልኛል?” ሲሉ በተስፋ መቁረጥ ይናገራሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c4nxpn797wgo +business ከኮሮናቫይረስ በእጅጉ እያተረፉ ያሉት ትልልቅ ድርጅቶች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የበርካታ አገራት ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጫና እያደረሰ ቢሆንም ትልልቅ የሚባሉት የዓለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ግን ጥሩ የሚባል ትርፍ እየሰበሰቡ ነው። በበይነ መረብ አማካይነት የተለያዩ አይት መገልገያዎችን የሚሸጠው አማዞን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማግስት ባሉት ሶስት ወራት ብቻ ሽያጩ 40 በመቶ ከፍ እንዳለለት ያስታወቀ ሲሆን ታዋቂው የስልክና የላፕቶፕ አምራች አፕል ደግሞ የአይፎንና ሌሎች መቀየሪያ መሳሪያዎች በደንብ እንደተቸበቸቡለት ገልጿል። ፌስቡክ ደግሞ በስሬ በማስተዳድራቸው እንደ ዋትስአፕና ኢንስታግራም ባሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተጠቃሚዎች ቁጥር 15 በመቶ ከፍ ብሎልኛል ብሏል። • በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትርፉ መጨመሩን ሳምሰንግ አስታወቀ • ኮሮናቫይረስ የቀሰቀሳቸው የአና የሚበሉ ሥዕሎች • ከኮሮናቫይረስ የትኞቹ ድርጅቶች አተረፉ? እነማንስ ከሰሩ? የአማዞን የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ድርጅቱ ከተቋቋመበት ከአውሮፓውያኑ 1994 ጀምሮ ይህ ከፍተኛው ነው ተብሏል። ድርጅቱ እንደውም ከኮሮናቫይረስ መከሰት በኋላ ለሰራተⶉቹ መከላከያ መሳሪያዎችን ለመግዛትና የመከላከያ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱ ትርፉን ዝቅ ያደርገዋል ተብሎ ተፈርቶ ነበር። በአጠቃላይ በበይነ መረብ የሚካሄዱ ንግዶች የሽያጭ መጠኑ 40 በመቶ ከፍ ብሏል። እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ባሉት ሶስት ወራት ደግሞ በአጠቃላይ 88.9 ቢሊየን ዶላር አንቀሳቅሷል። ትርፍም ቢሆን በአስገራሚ ሁኔታ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 2.6 ቢሊየን ዶላር ወደ 5.2 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜያቸውን ማሳለፋቸውን ተከትሎ የበይነ መረብ ሽያጭ በእጅጉ ተጧጡፏል። አማዞንም ቢሆን የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት በሩብ ዓመቱ ብቻ ተጨማሪ 175 ሺ ሰራተኞችን ቀጥሯል። ፍላጎቱ በዚሁ መቀጠሉ ስለማይቀር በርካታ መጋዘኖችንና ሰራተኞችን ለመጨመርም እያሰበ ነው። የአፕል የሩብ ዓመት ትርፍ ደግሞ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 11 በመቶ በመጨመር 59.7 ቢሊየን ደርሷል። ሰዎች ስራቸውን ከቤታቸው ሆነው መስራታቸው የተለያዩ መገልገያዎችን እንዲጠቀሙ አድርጓቸዋል። በዚህም ምክንያት የማክ ላፕቶፖችና አይፓዶች በእጅጉ ተፈላጊ ነበሩ። ሁለቱም የአፕል ምርቶች ከወረርሽኙ መከ���ት በኋላ ገበያቸው እንደደራ ድርጅቱ አስታውቋል። በዚህም ምክንያት ባለፈው ከነበረው 10 ቢሊየን ዶላር ትርፍ ወደ 11.25 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። ፌስቡክ ደግሞ ከኮሮናቫይረስ በኋላ ትርፉ በእጅጉ እንደሚቀንስ ቢጠበቅም እንደውም የ 11 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። አነስተኛ ድርጅቶች ያሏቸው ሰዎች ለማስታወቂያ ወደ ፌስቡክ ላይሄዱ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ተንብየው ነበር። ነገር ግን ወረርሽኙን ተከትሎ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በእጅጉ በመጨመሩ ምክንያት ለማስታወቂያ የሚመጡ ድርጅቶችም ቁጥር አብሮ ከፍ ብሏል። በዚህም ምክንያት የድርጅቱ የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር እንዲደርስ ሆኗል። ፌስቡክ እንደሚለው ባለፈው ሰኔ ወር ብቻ በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያዎቸ ላይ 2.4 ቢሊየን ተጠቃሚዎች የነበሩ ሲሆን ይህም የ15 በመቶ ጭማሪ አለው። ከአራቱ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው አልፋቤትም ቢሆን እንደ ሌሎቹ ባይሆንም ትርፋማ ሆኗል። ድርጅቱ በስሩ ጉግልና ዩቲዩብን የያዘ ሲሆን እስካሁን ያገኘሁት ትርፍ 38.3 ቢሊየን ዶላር ነው ብሏል። ይህ ደግሞ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የሁለት በመቶ ቅናሽ ያሳያል። https://www.bbc.com/amharic/news-53605349 +business ስፔን፡ በሙስና እየተወነጀሉ ያሉት ንጉስ ጁዋን ካርሎስ አገር ጥለው አቡዳቢ ገቡ ተባለ የቀድሞው የስፔን ንጉስ ጁዋን ካርሎስ ከተከፈተባቸው የሙስና ምርመራ ጋር ተያይዞ አገራቸውን ለቀው ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አቅንተዋል ተብሏል። ኤንአይዩኤስ የተባለው የስፔን ሚዲያ ቡድን የቀድሞው ንጉስ አቡዳቢ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሚያሳይ ፎቶም ይዞ ወጥቷል። ንጉስ ጁዋን ካርሎስ አገራቸው ስፔንን ለቅቄ እሄዳለሁ የማለታቸው ዜና በርካቶችን ከሰሞኑ አስደንግጧል። ንጉሱ ምንም ስህተት እንዳልፈፀሙና አቃቤ ህግም ለጥያቄ ከፈለጋቸው ለመተባበርም ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቀው ነበር። ስፔንን ለቀው መሄዳቸው በዘውዳዊው ስርአት ላይ ከፍተኛ ክርክርና ውዝግብም አስከትሏል፤ ንጉስ ካርሎስም የት ናቸው የሚለው ላይም በርካቶች የተለያየ አስተያየት እየሰጡ ነው። የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ወደ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ፣ ካሪቢያን ደሴቶችና የስፔን ጎረቤት ወደሆነችው ፖርቹጋል ሄደዋል የሚሉ ዘገባዎችንም አስነብበዋል። ነገር ግን አዲስ የወጡት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ንጉስ ጁዋን ካርሎስ በአቡዳቢ ባለ አምስት ኮከቡ ኤምሬትስ ፓላስ ሆቴል ውስጥ እንዳሉ ነው። አንድ ሙሉውን ፎቅ ተቆጣጥረዋልም ተብሏል። ንጉስ ካርሎስ ከአቡዳቢው አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላቸው። ነገር ግን አሁንም ቢሆን በርግጠኝነት ያሉበት ቦታ አልታወቀም። የስፔን የልዑላውያን ቤተሰብም ሆነ መንግሥት ንጉስ ካርሎስ ያሉበትን ቦታ አስመልክቶ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ንጉሥ ካርሎስ ከጎርጎሳውያኑ 1975 ጀምሮ ለአርባ ዓመታት ስፔንን በንግሥና ከመሩ በኋላ በ2014 ነበር ስልጣነ መንበሩን ለልጃቸው ያስተላለፉት፡፡ ስልጣኑን ለልጃቸው የሰጡት የሴት ልጃቸው ባለቤት ጋር ተያይዞ በተነሳ የሙስና ውንጀላ ነው። ስፔን የምጣኔ ኃብት ቀውስ በነበረችበት ወቅት የዝሆን አደን በማካሄድ ቅንጦታዊ ድርጊት ፈፅመዋል የሚል ውዝግብም ተከትሎ ነው። እነዚህ ውዝግቦች በዚሁ አላቆሙም። ከወራት በፊትም የስፔን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ንጉሱ ከሳዑዲ አረቢያ የፈጣን ባቡር ግንባታ ጋርም ተያይዞ በሙስና ምርመራ ከፍቶባቸዋል። ይህንንም ተከትሎ የቀድሞው ንጉስ ያለመከሰስ መብታቸውን አጥተዋል። ከቀናት በፊትም የ82 አመቱ ንጉስ ካርሎስ ለልጃቸው ፍሊፕ ካርሎስ ስድስተኛ በፃፉትም ደብዳቤ ነው አገር ጥለው እንደሚሄዱ ውሳኔያቸውን ያሳወቁት። የስፔንን ህዝብንም ሆነ ተቋማቱን በበለጠ ለማገልገል አገር ጥለው እንደሄዱ የጠቆመው ደብዳቤው እሳቸው በሌሉበትም መንገድ ልጃቸው በተረጋጋ መንገድ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበውታል። https://www.bbc.com/amharic/news-53711892 +sports አልቀመስ ያለው የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ብሔራዊ ቡድኖች የማሊያ ዋጋ "ኳታር እያስተናገደች ያለው የ2022 የፊፋ የዓለም ዋንጫ እጅግ ውድ የሆነው የዓለም ዋንጫ ብቻ አይደለም። በዓለም ዙሪያ ያሉ ደጋፊዎች የሚወዷቸውን የብሔራዊ ቡድኖቻቸውን ማሊያ ለመግዛት ከፍተኛ  ገንዘብ ማውጣት አለባቸው። በአንዳንድ አገሮች አንድ ሰው በወር ከሚያገኘው ዝቅተኛ ደመወዝ ከአንድ ሦስተኛ በላይ ማውጣት ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው። ጃኒን ጋርሺያ የጎዳና ንግድ በሚደራበት የሪዮ ዴ ጄኔሮ ሰሜናዊ ክፍል ሳንስ ፔና አደባባይ ላይ ያለውን ድንኳን ስታይ ሁለት ጊዜ አላሰበችም። ከየአቅጣጫው በተንጠለጠሉ በመቶዎች በሚቆጠሩ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ማሊያዎች ያጌጠ ቢጫ እና ሰማያዊ መብራት ነበር። የ42 ዓመቷ መምህርት እየሳቀች “ሰማያዊ ወሰድኩ (የብራዚል ሁለተኛ ማሊያ)። በጣም የሚያምር ስለነበር ብዙ የሥራ ባልደረቦቼ እና ጓደኞቼ እንድገዛላቸው ጠይቀውኛል” ብላለች። ጋርሺያ ለማሊያው 14 ዶላር ነው ያወጣችው። ይህም በአሜሪካው ግዙፍ የስፖርት ትጥቅ አምራች ናይኪ ከሚሸጥበት ዋጋ አንድ አምስተኛ (65 ዶላር) ያህል ነው። በ2022 የዓለም ዋንጫ ላይ የብራዚል ተጫዋቾች ከለበሱት ማሊያ  ጋር ተመሳሳይ የሆነ ፕሪሚየም ጥራት ያለው አለ፤ ይህ ግን 130 ዶላር ያስከፍላል። በብራዚል ዝቅተኛው ደመወዝ 225 ዶላር አካባቢ ነው። የርካሹ ማሊያ የዚህን ደሞዝ 30 በመቶ የሚጠጋ ሲሆን ውድ የሆነው ማሊያ ደግሞ 58 በመቶ አካባቢ ነው። “የእግር ኳስ ማሊያዎች ለእኛ የቅንጦት ዕቃ ሆነዋል” ትላለች ጋርሺያ። በመስከረም ወር ላይ የብራዚል የቢዝነስ መጽሔት “ኤግዛሜ” ባወጣው መጣጥፍ፣ ከዓለም ዋንጫው በፊት ይፋ የሆነው አዲሱ የብራዚል ማሊያ ከአራት ዓመታት በፊት ከወጣው ዋጋው 40 በመቶ ጨምሯል ሲል ዘግቧል። ነገር ግን የማሊያ ዋጋ መናር ግርምትን የፈጠረባት፣ ቅሬታ ያስነሳባት አገር ብራዚል ብቻ አይደለችም። ትልቅ የኢኮኖሚ ቀውስ በተጋፈጠችው እንግሊዝም ለ2022 የዓለም ዋንጫ የተዘጋጀው ማሊያ እስካሁን ከተሸጡት ሁሉ እጅግ ውድ የሚባል ነው (መደበኛ የሚባለው ማሊያ 85 ዶላር ይሸጣል)። ቀደም ሲል የነበረው የዋጋ ጭማሪ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮንን ጨምሮ ከበርካታ ፖለቲከኞች ወቀሳ ደርሶበታል። ካሜሮን እአአ በ2014 ለቢቢሲ “በጣም ውድ ነው። ወላጆች አዲሱን ማሊያ ለመግዛት ከፍተኛ ጫና ውስጥ ይገባሉ። እኛ መጠቀሚያ ልንሆን አይገባም” ሲሉ ገልጸው ነበር። ያለፈው ውድድር አሸናፊ ፈረንሳይ ደጋፊዎች ለማሊያ 93 ዶላርአካባቢ ያወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ለሁለቱም ቡድኖች ትጥቅ የሚያቀርበው ናይኪ ነው። ዋጋው በእነዚህ አገራት በደጋፊዎች ኪስ ላይ ያለው ተጽእኖ ከአንዳንድ ቡድኖች ጋር ሲወዳደር አነስተኛ ነው። በእንግሊዝ ዝቅተኛው የአንድ ሰዓት ሥራ ክፍያ 11.50 ዶላር ገደማ ሲሆን፣ ይህም በወር 1,750 ዶላር አካባቢ ይደርሳል። በፈረንሳይ ዝቅተኛው የወር ደሞዝ ወደ 1,400 ዶላር ገደማ ነው። በጋና ያለው የመግዛት አቅም እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ለዚህም ነው በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ ያሉ ደጋፊዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቅሬታቸውን የገለጹት። ምክንያት ሲባሉ በጀርመኑ ፑማ ኩባንያ የተሰራው የ“ጥቋቁር ከዋክብቱ” የዓለም ዋንጫ ትጥቅ ዋጋ 94 ዶላር ገደማ መሆኑ ነው። “ፎርጂዱ ማልያ እስካሁን ገበያ ላይ አልዋለም?"" ሲል አንድ ደጋፊ ጠይቋል። እንደ የሥራ እና የሠ���ተኛ ግንኙነት ሚኒስቴር ከሆነ በጋና ያለው ሕጋዊ ዝቅተኛ የደመወዝ ጣሪያ በሰዓት 0.95 ዶላር ነው። በወር 145 ዶላር አካባቢ ማለት ነው። የወቅቱ የአፍሪካ ሻምፒዮና በሆነችው ሴኔጋል ሐሰተኛ ማልያዎች የዋና ከተማዋ ዳካርን ጎዳናዎች አጥለቅልቀዋል። የአገሪቱ እግር ኳስ አስተዳዳሪ “ብሔራዊ ቡድኑን ለመደገፍ” ሲባል ደጋፊዎች በፑማ የተሠራውን ዋናውን ማሊያ እንዲገዙ ጠይቋል። እስከ ቅርብ ቀን ድረስ ዋናው ማሊያ በ71 ዶላር እየተሸጠ ነበር። ይህም ከ75 በመቶ በላይ ከሚሆኑ የሴኔጋል ወርሃዊ ዝቅተኛ ደሞዝ ጋር ተመሳሳይ ነው። “ዋናው ማሊያ በጣም ውድ ነው። ጥሩ ማሊያ ነው፣ እዚህ ያሉ ሰዎች ግን ምንም ገንዘብ የላቸውም” ሲል ሴኔጋላዊው የጎዳና ላይ ነጋዴ ማሊክ ለሬዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል ተናግሯል። “ብዙ ደንበኞች እያገኘሁ ነው” ካለ በኋላ ሴኔጋል ለጥሎ ማለፍ ብትበቃ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ እሸጣለሁ ሲል ተስፋ ሰንቋል። የእግር ኳስ ቡድኖችን ማሊያ ለማምረት የሚወጣው ወጪ ውድ አይደለም። በባርሴሎና ዮሃን ክራይፍ የስፖርት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት መምህር የሆኑት ሪቻርድ ዴንተን እንደሚገምቱት አንድ ማሊያ ለማምረት የሚያስፈልገው ወጪ ከ10 ዶላር በታች ነው። “በእርግጠኝነት የገበያ ዋጋውን ተመጣጣኝ እንዳይሆን ከማድርግ ባለፈ ለዚህ ምንም ማረጋገጫ የለም ብሎ ለመከራከርም በር ሊከፍት ይችላል” ሲሉ ዴንተን ይናገራሉ። “ለአንድ ሰው ምክንያታዊ ያልሆነው ዋጋ ለሌላው ምክንያታዊ ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም ሌሎች ወጪዎች እና ኢንቨስትመንቶች በመጨረሻው ዋጋ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉና” ብለዋል። በእግር ኳስ ቢዝነስ ላይ የተካኑት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ሴሳር ግራፊቲ በበኩላቸው የእግር ኳስ ማሊያ ዋጋ በዋናነት በምርቱ ዋጋ ብቻ የሚገለጽ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ታክስ፣ የሎጂስቲክስ ወጪዎች እና ትራንስፖርትን ጨምሮ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወዲህ ባለው የምርቶች ግብአት የአቅርቦት ችግር የእቃ ዋጋ ጨምሯል። በዩክሬን ያለው ጦርነትም ዓለም አቀፍ የነዳጅ ወጪ እንዲንር አድርጓል። ግራፊቲ አክለውም “ለክለቦች እና ለብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ከፍተኛ ገንዘብ መክፈል ስላለባቸው ትጥቅ አምራች ኩባንያዎች ከማልያ ሽያጭ ብዙ ገንዘብ አያገኙም” ይላሉ። እንደ ናይኪ እና የጀርመን ተቀናቃኙ አዲዳስ ያሉ ግዙፍ አምራቾች ስም ያላቸው ቡድኖች ትጥቆቻቸውን እንዲለብሱ ለማድረግ ብዙ ወጪ ያፈሳሉ። በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ናይኪ ከ32ቱ ተሳታፊ ቡድኖች ለ13ቱ ትጥቅ አቅራቢ ነው። አዲዳስ የአራት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮናዋን ጀርመንን፣ የሁለት ጊዜ ሻምፒዮን የሆነችውን አርጀንቲናንና ለውድድሩ ትልቅ ግምት የተሰጣትን ስፔንን ጨምሮ ለሰባቱ ትጥቅ ያቀርባል። ሁለቱ አምራቾች በጋራ በመሆን እንደ አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን እና ስፔን ላሉ ቡድኖች ትጥቅ ያቀርባሉ። ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖቻቸውም በአጠቃላይ በዓመት 275 ሚሊዮን ዶላር እንደሚከፍሉ የስፖርት ቢዝነስ ላይ የሚሰራው ስፖርትስፕሮ ዘግቧል። “አዲዳስ ወይም ናይኪ ከእግር ኳስ ቡድኖቹ ጋር በሚደረጉ ስምምነቶች ውስጥ ያንን ኢንቨስትመንት ካላስመለሱ የማይደሰቱ ባለአክሲዮኖች አሏቸው” ሲሉ ዴንተን ይገልጻሉ። “ነገር ግን ማሊያው ውድ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን በራሳችን መወሰን አለብን። ለዚህም ነው አንዳንድ ሰዎች ርካሽ ወይን ሲጠጡ ሌሎች ደግሞ ውድ ወይን የሚጠጡት።” ቢቢሲ አስተያየት እንዲሰጡት አዲዳስ፣ ፑማ እና ናይኪን ጠይቋል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ምላሽ የሰጠው አዲዳስ ብቻ ነው። ኩባንያው በሰጠው ም���ሽም ዋጋው ማሊያዎቹን ለመሥራት ጥቅም ላይ ከሚውለው የጨርቅ ጥራት እና ከዘላቂነቱ ጋር የሚያያዝ መሆኑን ገልጿል። “የእኛ ማሊያዎች በሜዳ ላይ ከሚለበሱት ጋር ተመሳሳይ በሆነ ጨርቅ ያዘጋጃሉ። ደጋፊዎች ለዓመታት በኩራት እንዲለብሷቸውም ነው የተዘጋጁት። ዋጋው ወደ ማሊያነት የሚያመጣውን ዘላቂነት እና የፈጠራ ደረጃን የሚያንፀባርቅ ነው” ብሏል። ጃኒን ጋርሺያ እና ጓደኞቿ ከዋናው ማሊያ እየወጡ ነው። ሁሉም ሰው በዋጋው መወደድ የራቀ አይመስልም። የናይኪ ተወካዮች እንዳሉት ለዘንድሮው የኳታር ውድድር የተዘጋጀው ማሊያ በ26 ዓመታት ውስጥ በኩባንያው እና በብራዚል እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ሲቢኤፍ) መካከል በነበረው ሽርክና በመሸጥ ቀዳሚው ነው። ጋርሺያ ግን በዚህ ሃሳብ አትስማማም። “ማን እንደሚገዛቸው ማወቅ እፈልጋለሁ” ትላለች። “ሁሌም እንደሚለበሱት እንደ ዲዛይነር ቦርሳ ወይም ልብስ አይደሉም።”" https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1567j3kmko +health ኮሮናቫይረስ፡ በሕንድ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5 ሚሊየን አለፈ በሕንድ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አምስት ሚሊየን ማለፉ ተገለፀ። ይህም አገሪቱን በአሜሪካ በመቀጠል በቫይረሱ ክፉኛ የተጎዳች እንድትሆን አድርጓታል። በሕንድ በአንድ ቀን ብቻ እስከ 90 000 ሰዎች በኮቪድ-19 እየተያዙ ሲሆን ቫይረሱም በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው ተብሏል። እስካሁን ድረስ በአገሪቱ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ በቫይረሱ ምክንያት በጽኑ ለታመሙ አልጋ እንዲሁም የኦክስጅን አቅርቦት እጥረት ተከስቷል። በሕንድ የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ የመጣው በመጋቢት ወር ተጥሎ የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ የምጣኔ ሃብቱን ለማነቃቃት በሚል ከተነሳ ወዲህ ነው። ቫይረሱ ወደትንንሽ ከተሞች ከመሰራጨቱ በፊት እንደ ሙምባይና ደልሂ ያሉ ግዙፍ ከተሞችን ክፉኛ አጥቅቶ ነበር። ሕንድ ምጣኔ ሃብቷን ክፍት ማድረግ በጀመረችበትና ሰዎች ወደ ስራ በተመለሱበት ወቅት የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ መምጣቱ ተስተውሏል። ባለፉት ሳምንት ብቻ 600,000 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል። በሕንድ አሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5,020,359 የደረሰ ሲሆን፣ ባለፈው 24 ሰዓታት ብቻ 90,123 መያዛቸው መታወቁ ተገልጿል። በአገሪቱ የኦክስጅን ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ኦክስጅን አምራች ኢንደስትሪዎች ገልፀዋል። በዚህ ወር ብቻ ሆስፒታሎችና የእንክብካቤ ማዕከላት 2,700 ቶን ኦክስጅን የተጠቀሙ ሲሆን፣ በሚያዚያ ወር ግን 750 ቶን ብቻ ነበር ፍጆታቸው ተብሏል። የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረባቸው ከሚገኙ የህንድ ከተሞች መካከል ማሃራሽትራ፣ ማድያ ፕራዴሽ፣ ጉጅራት፣ ራጃስታን፣ ቴሌንጋና፣ አንድሃራ ፕራዴሽ ናቸው። https://www.bbc.com/amharic/news-54165435 +business በሃርጌሳ የገበያ ሥፍራ በደረሰው የእሳት አደጋ በቢሊየን ዶላር የሚገመት ውድመት ደርሷል ተባለ "ባለፈው አርብ ራስ ገዝ አስተዳደር በሆነችው ሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሃርጌሳ በገበያ ስፍራ በተከሰተ የእሳት አደጋ በቢሊየን ዶላር የሚገመት ንብረት ሳይወድም እንዳልቀረ ተገለጸ። በአደጋው ለተጎዱት ከአጎራባች አገራት ዕርዳታ መግባት መጀመሩን ተከትሎ በአካባቢው አስተዳደር የተቋቋመው ኮሚሽን፣ የእሳት አደጋው ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመቱ ንብረቶችን ሳያወድም እንዳልቀረ አስታውቋል። በእሳት አደጋው ምክንያት ከደረሰው ከፍተኛ ውድመት በኋላ የተቀረፁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተጋርተዋል። አርብ አመሻሽ ላይ የተነሳው እሳት በአጠቃላይ የገበያውን ሥፍራ አውድሞታል። በሃርጌሳ የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ቤተሰቦችን ሜዳ ላይ ያስቀረውን ይህንን እሳት ለማጥፋትም ሰዓታት ፈጅቷል። በሶማሊላንድ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ የተዋቀረውና በአደጋው የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራው ኮሚሽን በአደጋው ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ ውድመት ሳይደርስ እንዳልቀረ አመልክቷል። ""እንደ የመጀመሪያ ደረጃው ሪፖርት ከሆነ በእሳት አደጋው የደረሰው የጉዳት መጠን ከ1.5 እስከ 2 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይገመታል"" ሲሉ የሃርጌሳ ከተማ ከንቲባ አብዲካሪን አሕመድ ሞጌ ተናግረዋል። የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮብሌ እሁድ ዕለት ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ከተወያዩ በኋላ ባደረጉት ንግግር መንግሥታቸው በሃርጌሳ የንግድ ገበያ ዋሂን ለደረሰው ከባድ የእሳት አደጋ ለአደጋ ጊዜ ምላሽ የሚውል 11.7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። በሌላ በኩል የእንግሊዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን እና የአሜሪካ የኮንግረንስ አባል ኢልሃን ኦማርን ጨምሮ የዓለም መሪዎች በሃርጌሳ ሕዝቦች ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን የገለፁ ሲሆን በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጎናቸው እንደሚቆሙ ገልጸዋል። የገበያው ሥፍራ በመቶዎች በሚቆጠሩ ትናንሽ ሱቆች እና ነጋዴዎች የተጨናነቀ ነበር። በዚህ በሃርጌሳ ከተማ የንግድ ማዕከል በሆነውና በሺዎች የሚቆጠሩ ሹቆችና ሸዶች መገኛ ዋሂን የገበያ ሥፍራ ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤ እስካሁን አልታወቀም። የገበያ ሥፍራው ለኢትዮጵያ፣ ለጂቡቲ እና ለተወሰኑ የሶማሊያ አካባቢዎች አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን በአፍሪካ ቀንድ ሦስተኛው ትልቁ የገበያ ሥፍራ ነበር። በአደጋው ለተጎዱት ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ ሲሆን ጎረቤት አገራትም የልዑካን ቡድን ወደ ሶማሊላንድ በመላክ ከሃርጌሳ ሕዝብ ጋር የደረሰውን ጉዳት መጋራት ችለዋል። ሶማሊላንድ እአአ በ1991 የሲያድ ባሬ መንግሥት መውደቅን ተከትሎ ከሶማሊያ ነጻ መውጣቷን ያወጀችው ከ30 ዓመታት በፊት ሲሆን እስካሁን ግን ይፋዊ እውቅና አላገኘችም።" https://www.bbc.com/amharic/news-60985421 +sports ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በኬፕ ቨርዴ ተረታች ብርኪና ፋሶ እና አዘጋጇ ካሜሩን ከዳረጉት የመክፈቻ ጨዋታ በኋላ በኦሌምቤ ስታዲየም በተደረገው ሁለተኛ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ኢትዮጵያን 1 ለ 0 አሸንፋለች። አሰልጣኝ ቡቢስታ ጭምሮ የኬፕ ቨርዴ ዘጠኝ ተጫዋቾች በኮቪድ ምክንያት በስታዲየሙ ያልተገኙ ሲሆን ብሉ ሻርኮች ከዋልያዎቹ ጋር ባደረጉት ጨዋታ 6 ተጨዋቾችን ብቻ በተጠባባዊ ወንበር ላይ ለማስቀመጥ ተገደው ነበር። ይሁን እንጂ የኬፕ ቨርዴ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹን በመርታት 3 ነጥብ ይዘው ወጥተዋል። በጨዋታው ጅማሬ ላይ የዋልያዎቹ ያሬድ ባዬህ በተጋጣሚው ጁሊዮ ታቫሬስ ላይ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ያሬድ መጀመሪያ ላይ በአንጎላዊው ዳኛ ሄልደር ማርቲንስ ዴ ካርቫልሆ ቢጫ ተስጥቶት የነበረው ቢሆንም በረዳት ዳኛው ጥያቄ የማሃል ዳኛው ክስተቱን በቪ ኤ አር ከተመከቱ በኋላ ተጨዋቹ በቀይ ወጥቷል። ተቀይሮ የገባው ምኞት ደበበ በራሱ ላይ ጎል ለማስቆጠር ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም የዋልያዎቹ ግብ ጠባቂው ተክለማርያም ሻንቆ ግብ ከመሆን ታድጎታል። በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ በተጀመረው የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ካሜሮን ቡርኪና ፋሶን 2-1 አሸንፋለች። በያውንዴ በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ቡርኪና ፋሶ የመጀመሪያ አጋማሽ ጎል አስቆጥረው መምራት ችለው ነበር። ሆኖም የአስተናጋጇ ካሜሮን አምበል አቡባካር ቡድኑ ያገኘውን የቅጣት ምቶች ዕድል ወደ ጎል በመቀየር ከእረፍት በፊት የውጤትን ብልጫ ወደ አስተ��ጋጆቹ ዞሯል። ምድብ ሀ በድል የጀመሩት የማይበገሩት አናብስት ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በሁለተኛው አጋማሽ ሁለት ወሳኝ ሙከራዎችን ግብ እንዳይሆኑ አክሽፏል። ዛሬ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አራት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን የባለፈው የውድድር ዘመን ሁለተኛ የነበረችው ሴኔጋል እና የአራት ጊዜ ሻምፒዮኗ ምሽት ላይ ይጫወታሉ። https://www.bbc.com/amharic/59933436 +business ሩሲያ ወደ አሜሪካ እና አውሮፓ በምትልካቸው ምርቶች ላይ ማዕቀብ ጣለች "ሞስኮ በምዕራባውያን አገራት ለተጣለባት ማዕቀብ አጸፋ ከ200 በላይ የተለያዩ አይነት ምርቶች ከሩሲያ ወደ ውጭ እንዳይላኩ እገዳ ጣለች። በዚህ የሩሲያ የማዕቀብ እርምጃ የቴሌኮም፣ የህክምና፣ የግብርና፣ የኤሌክትሪክ እና የቴክኖሎጆ መሳሪያዎች ማዕቀብ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በተጨማሪም ""ሩሲያን የሚጎዳ እርምጃ የወሰዱ"" ባለቻቸው አገራት ላይ የእንጨት ምርቶች ሽያጭን አግዳለች። ይህ የሩሲያ እርምጃ የአውሮፓ ሕብረትን እና አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች 48 አገራትን የሚመለከት ነው። የሩሲያ የማዕቀብ ውሳኔ ከአገሪቱ የሚላኩ ምርቶች ላይ አስካለንበት የፈረንጆች ዓመት ማብቂያ ድረስ እገዳ እንዲጣልባቸው አድርጓል። በሩሲያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሚኻይል ሚሹስቲን በተፈረመው በዚህ ትዕዛዝ ላይ እንደተጠቀሰው ከሩሲያ ወደ ውጭ አገራት የሚላኩ ምርቶችን ማቀብ ""በሩሲያ ገበያ ውስጥ መረጋጋት ለመፍጠር አስፈላጊ ነው"" ተብሏል። ይህ የሩሲያ የአጸፋ እርምጃ በዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን ተከትሎ ምዕራባውያን በሩሲያ የገንዘብ እና የኃይል አቅርቦት ላይ ከባድ የሚባሉ ተከታታይ ማዕቀቦችን በመጣላቸው የመጣ ነው። ከዚህ በተጨማሪም በምዕራቡ ዓለም ከፍተኛ ሀብት ካላቸው ሩሲያውያን ከበርቴዎች መካከል ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ቅርበት አላቸው በተባሉት ላይም ንብረታቸውን እንዳያንቀሳቅሱና ጉዞ እንዳያደርጉ ዕቀባ ተጥሎባቸዋል። ሩሲያ ወደ ውጭ እንዳይላኩ ካገደቻቸው ምርቶቿ መካከል መኪኖች፣ የባቡር ፉርጎዎች፣ የእቃ ማጓጓዣ ኮንቴይነሮች እና የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች እንደሚገኙበት ታውቋል። በቅርብ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመልክቱት ዩናይትድ ኪንግደም ከሩሲያ ጋር ከፍተኛ የንግድ ልውውጥ ከሚያደርጉ አገራት መካከል ስትሆን በዚህም በሁለቱ አገራት መካከል በአጠቃላይ 15.9 ቢሊዮን ፓወንድ የሚያወጣ የንግድ ልውውጥ ይካሄዳል። ሩሲያ ለአውሮፓ አገራት ነዳጅ እና ጋር በማቅረብ ከፍተኛ ድርሻ ያላት ሲሆን፣ ከጦርነቱ በኋላ አገራት እነዚህን ምርቶች መግዛታቸውን ለማቆም ውይይት እያደረጉ ነው። አሜሪካ ከሩሲያ ትገዛ የነበረው የነዳጅ እና የጋዝ አቅርቦት እንዲቋረጥ በዚህ ሳምንት ወስናለች። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ወረራ ሳቢያ ምዕራባውያን በአገሪቱ ላይ ከባድ ምጣኔ ሀብታዊ እቀባን እየጣሉ ሲሆን፣ ግዙፎቹ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎቻቸውም ሥራቸውን እያቋረጡ ከሩሲያ እየወጡ ነው። በዚህም ምክንያት ሩሲያ በአጸፋው ለእነዚህ አገራት የምታቀርባቸውን ተለያዩ አይነት ምርቶችን ላለመሸጥ የወሰነችው።" https://www.bbc.com/amharic/news-60696158 +sports ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ምስጢር ምን ይሆን? እርግጥ ነው በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ቀድሞ ኢትዮጵያን የወከለው አትሌት ከበደ ባልቻ ነው። ከበደ የፊንላንዷ ሄልሲንኪ በፈረንጆቹ 1983 ባዘጋጀችው ሻምፒዮና ለአገሩ እንዲሁም ለአፍሪካ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አመጣ። ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ወደ ሜዳሊያ የተመለሰችው በኃይሌ ገብረ ሥላሴ አማካይነት ጀርመን ባዘጋጀችው የ1993 ዓለም ሻምፒዮና ነበር። ነገር ግን በ1995 ላይ አዲስ ታሪክ ተፃፈ። አትሌት ደራርቱ ቱሉ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የወከለች የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት ሆና ወደ ስዊዲን አቀናች። ደራርቱ በ10 ሺህ ሜትር ውድድር ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ይዛ ተመለሰች። ደራርቱ የከፈተችውን መንገድ ተከትለው ጌጤ ዋሚ ወርቅ፣ ቁጥሬ ዱለቻ እና አየለች ወርቁ በ1999 ስፔን ሲቪያ ላይ በተደረገው ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ ይዘው ተመለሱ። ወደ ካናዳ እናቅና። ኤድመንተን 8ኛውን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና አሰናዳች። ደራርቱ ቱሉ ወርቅ፣ ብርሃኔ አደሬ ብር፣ ጌጤ ዋሚ እና አየለች ወርቁ ደግሞ ነሐስ ሰበሰቡ። በአውሮፓውያን አቆጣጠር 2003 ዓ.ም. በፈረንሳይ ፓሪስ በተዘጋጀው ዘጠነኛው ሻምፒዮና፣ የ18 ዓመቷ ጥሩነሽ ዲባባ በ5 ሺህ ሜትር ታዋቂዎቹን ስፔናዊቷ ማርታ ዶሚንጌዝን፣ ብርሃኔ አደሬን እንዲሁም ኬንያዊቷ አዲት ማሳይን በአስደናቂ ብቃት በመቅደም ወርቅ አጠለቀች። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ከዓለም አራተኛ ሆና አጠናቀቀች። 2005 በፊንላንድ ሄልሲንኪ የተካሄደው ሻምፒዮና ግን ልዩ ነበር። በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ውድድሮች ሴት አትሌቶች ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት “አረንጓዴው ጎርፍን” ለዓለም አስተዋወቁ። ጥሩነሽ ዲባባ በሁለቱም ርቀቶች ወርቅ ደራርባ በማጥለቅ ኢትዮጵያ አሜሪካና ሩሲያን ተከትላ ከዓለም ሦስተኛ እንድትሆን አደረገች። ሴት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ያስመገቡት ድል ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። ሶፊያ አሰፋ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያመጣች አትሌት ናት። ሴቶች አትሌቶቻችን በቻምፒዮናው መድረክ በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ሜትር ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት የሚደርሳቸው የለም። ጥሩነሽ ዲባባ በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና 5 ጊዜ ወርቅ በማምጣት የአገሯን ሰንድቅ ዓላማ ከፍ ማድረግ ችላለች። ዘንድሮ በአሜሪካዋ ኦሪገን ግዛት በተካሄደው ውድድርም ሴት አትሌቶች ደምቀው ታይተዋል። ኢትዮጵያ ካገኘቻቸው አራት የወርቅ ሜዳሊያዎች ሦስቱ የተገኙት በሴት አትሌቶች ነው። ለመሆኑ ሴት አትሌቶች በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከጊዜ ጊዜ እየደመቁ የሄዱበት ምስጢር ምን ይሆን? “ዘንድሮ ያስመዘግበነው ውጤት ያስፈልገን ነበር” ትላለች የስፖርት ጋዜጠኛዋ ሃና ገብረሥላሴ። “ሕዝቡ ለአትሌቶቹ ያደረገውን አቀባበል ስንመለከት፣ የተገኘው ውጤት ትርጉሙ ምን ያህል እንደሆነ የሚያሳይ ነው።” ከአትሌቶች ምርጫና ከዝግጅት ጋር በተያያዘ እንደሌላው ጊዜ ባይሆንም የተወሰነ ስጋት እንደነበረ የምታወሳው ሃና፣ ሌሎች አገራት ካደረጉት ዝግጅት አንፃር ሲታይ ከተጠበቀው በላይ የሆነ ውጤት መጥቷል ትላለች። ጋዜጠኛዋ አክላ ከዚህ በፊት ከነበሩት የቅርብ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች ጋር ሲነፃፀር የዘንድሮው ውጤት ልዩ ነው የሚል ምልከታ አላት። “ሄልሲንኪና ፓሪስ ጥሩ ውጤት ያመጣንባቸው መድረኮች ናቸው። ከቅርብ ጊዜ ትዝታችን ዴጉ ነው አነስ ያለ ውጤት ያመጣንበት። ከዚህ አንፃር የዘንድሮው ውጤት በልዩነት የሚታይ ነው።” ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስከ ዛሬ 33 የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጨምሮ በጠቅላላው 95 ሜዳሊያዎችን መሰብሰብ ችላለች። በዚህ ውጤት መሠረት ኢትዮጵያ ከዓለም ስድስተኛ፤ ከአፍሪካ ደግሞ ከኬንያ በመቀጠል ሁለተኛ ናት። የዘንድውን የኦሪገን ውጤትን ጨምሮ ሴት አትሌቶች 47 ሜዳሊያ አስገኝተዋል። ወንድ አትሌቶች ደግሞ 48። ሃና “የዚህ ምስጢሩ ፅናት ነው” ትላለች። አትሌቲክስ ፅናት የጠይቃል የምትለው ሃና “ለሴቶች አዳላሽ እንዳልባል እንጂ፣ ሴት አትሌቶቻችን የሚያሳይት ዓይነት ወጥ አቋም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በወንዶች ላይ አታ���ም። “አትሌቲክስ በጣም ተግቶ የመዘጋጀት፤ በተደጋጋሚ የሚመጡ የውድድሮችን ተጠቅሞ ብቃትን ማሳየት ይጠይቃል።” ሃና፤ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ብቻ ሳይሆን ባለፉት ጥቂት የኦሊምፒክ ውድድሮች ሴት አትሌቶቻችን ደምቀው እንደታዩ ታወሳለች። “በሁለቱም መድረኮች ሴት አትሌቶቻችን በብዛትም፣ በተፎካካሪነትም የበለጠውን ድርሻ ሲወስዱ እየተመለከትን ነው።” ቢሆንም በትክክል ይሄ ነው ምክንያቱ ለማለት ጥናት ማድረግ እንደሚገባ ሃና ትናገራለች። “ሴት አትሌቶች ምክር ይሰማሉ። ታዛዥ ናቸው። የሚሰጣቸውን ሥልጠና በትክክል ይተገብራሉ የሚባሉ ሐሳቦች ሲነገሩ እሰማለሁ” ስትል የስኬታቸውን ምስጢር ታስቀምጣለች። የአገሯን ስም በተለያዩ መድረኮች ያስጠራችው ደራርቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆና ከተመረጠች በኋላ ለውጥ ማምጣት ችላለች የሚል አስተያየት በተደጋጋሚ ይሰማል። ነገር ግን ለደራርቱ ሁኔታዎች ሁሉ የተመቻቹ ነበሩ ማለት ከባድ ነው። ደራርቱ ፌዴሬሽኑን መምራት ከጀመረች ወዲህ ሁለት ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና፤ አንድ ጊዜ በኦሊምፒክ መድረክ፤ አንድ ጊዜ ደግሞ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ተሳትፋለች። በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ በተሰናደው የ2019 የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብርና አንድ ነሐስ ይዛ ተመልሳለች። በዚህ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በሚታወቁበት የመካከለኛና ረዥም ርቀት ውድድር የተለመደውን ወርቅ ማስመዝገብ ባይችሉም ተስፋ ያላቸው አትሌቶች ታይተዋል። ኢትዮጵያ በመድረኩ በስምንት ሜዳሊያ አምስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። ከዚህ በኋላ በደራርቱ የተመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ታላቅ ወደ ሚባለው የኦሊምፒክ መድረክ ነው ያቀናው። በ2022 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ያገኘችው ሜዳሊያ ብዛት አራት ነበር። ይህ ውጤት ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ ካመጣቻቸው ዝቅተኛ ከተባሉት የሚመደብ ነው። ቀጥሎ ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ዓለም አቀፍ መድረክ ባለፈው መጋቢት የተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ፍልሚያ ነው። ይህ መድረክ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ነበር። ኢትዮጵያ፤ በአራት ወርቅ፣ በሦስት ብርና በሁለት የነሐስ አሜሪካንን አስከትላ ከዓለም ቁንጮ ሆና አጠናቃለች። በደራርቱ አመራር ወደ ኦሪገን የተጓዘው የአትሌቲክስ ቡድን አራት ወርቅ፣ አራት ብርና ሁለት ነሐስ በመሰብሰብ ከዓለም ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ሃና፤ ደራርቱ ቱሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየመጣ ላለው ውጤት ብቸኛዋ ምክንያት ባትሆንም ትልቅ ሥፍራ እንዳላት ትናገራለች። “በውድድር ዝግጅት ወቅት እየመጣች የምታበረታታ ናት። ከልጅነትህ ጀምሮ የምታደንቃትን ሴት በቅርበት ማግኘት በራሱ ትልቅ ሚና አለው። እንደሷ ጀግና የመሆን ፍላጎት እንዲያድር፤ እንደሷ ከተወዳዳሪነት አልፎ ወደፊት ለሌሎች ምሳሌ የመሆን ምኞት እንዲያድር ያደርጋል። “እንኳን ለአትሌቶች ቀርቶ ለእኛ ራሱ፤ ደራርቱን ማግኘት የሚሰጠው መነቃቃት የተለየ ነው።” ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚታየው የዘንድሮውም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና አገር ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ የተንፀባረቀበት ነው። ጉዳፍ ፀጋይ የ5 ሺህ ሜትር ውድድርን ባሸነፈችበት ወቅት አንድ ተመልካች የትግራይ ክልል ባንዲራን ይዞ ወደ መሮጫ ትራክ ሲገባ በቀጥታ ቴሌቪዥን ሥርጭት ታይቷል። ከዚህ በፊትም አትሌቶች ፖለቲካዊ መልዕክት ያዘለ ምልክት በሩጫ መደረኮች ላይ ማሳየታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ከአራት የወርቅ ሜዳሊያዎች ሦስቱን ያስገኙት ሴት አትሌቶች ከትግራይ ክልል የመጡ ናቸው። አሁን ባለው የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት አትሌቶቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገ��ኘት አለመቻላቸውም ይታወቃል። አትሌቶቹ ይህን ጫና ተቋቁመው ድል መንሳታቸው የሚደነቅ ነው ሲሉ በርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ሃናም ይህ የሚደነቅ ነው ትላለች። “ባለው ፖለቲካ ምክንያት በቤተሰብ፣ በበማኅረሰብ ያለው ጫና፤ በተለይ መጀመሪያ አካባቢ ከአትሌቶች ጋር የጋራ ልምምድ ማድረግ እስኪከብድ ድረስ መድረሱ፤ በተመሳሳይ መጀመሪያ አካባቢ የውድድር ዕድል አለማግኘትን የመሳሰሉ ጫናዎች ተቋቁመው ነው ውጤት ያመጡት።” ሃና አትሌቶች የተሸከሙት ጫና ከምናነገርውም፤ ከምናስበውም በላይ ነው ትላለች። “ጫናው የበለጠ ጠንካራ እንዲሆኑ፤ ለፅናት እንዲቆሙ አድርጓቸዋል ብዬ አስባለሁ። ለዚያም ነው ሦስቱም አትሌቶች ላይ ስሜታዊነት የተመለክተነው። ውድድሩን እንዳገባደዱ የሚታይባቸው ስሜት ደስታና ሃዘን የተደበላለቀበት እንደሆነ ይታያል። ከቤተሰቦቻቸው የተሰሙትን አስተያየቶች ስትመለከት ደስታህን ጎዶሎ ሊያደርገው እንደሚችል እውን ነው።” አትሌቶቹ አገር ቤት ሲገቡ ሞቅ ያለ አቀባበል ጠብቋቸዋል። ሐሙስ ዕለት በቤተ-መንግሥት በተካሄደው የዕውቅና እና ሽልማት መርሃ ግብር ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተለይ ደግሞ ሴት አትሌቶች ያመጡትን ውጤት በማድነቅ ምስጋናቸውን ገልጠዋል። ፕሬዝዳንቷ “ለተጨነቀው፣ ላዘነው፣ ለተከዘው፣ ኑሮ ለከበደው፣ እንደ አገር የት ነን ለሚለው ፈገግታን ያስገኘ ነው። . . . እኔ ላሸነፍ፣ እኔ ልቀደም ብቻ ሳይሆን በመተባበር በቡድን በመስራት ለሌሎች በር የከፈቱ አይተናል፤ ለተሰንበት የሰጠሽን ትልቅ ትምህርት ነው” ብለዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አትሌት ደራርቱ ቱሉ በበኩሏ በትግራይ ያለው ሁኔታ ከክልሉ የመጡ አትሌቶች ቤተሰቦቻቸው ማግኘት አስቸጋሪ እንዳደረገው ተናግራለች። “በትግራይ አትሌቶች አሉን፤ አልመጡም። ስለዚህ ባሉበት ልምምድ እንዲጀምሩ፤ አስፈላጊ አትሌቶች ደግሞ እዚህ እንዲመጡ መንግሥትም ለእነዚህ አትሌቶች መንገድ ከፍቶ ቤተሰቦቻቸው እንዲያገኙ ትብብር እንዲያደርግልን እጠይቃለሁ” ብላለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ድል የቀናት በማሬ ዲባባ አማካይነት በ2015 የቤይጂንግ ውድድር ላይ ነበር። በዘንድሮው ሻምፒዮና የርቀቱን ክብረ ወሰንን በመስበር ወርቅ ያጠለቀችው አትሌት ጎተይቶም ገብረሥላሴ ከውድድሩ በኋላ በተደበላለቀ ስሜት ውስጥ ሆና ታይታ ነበር። “የቤሰተብ ናፍቆት እንጂ ሌላ የደረሰብኝ ጫና የለም። ምግብ ስበላ ቤተሰቦቼ ትዝ ይሉኛል። ይሄ ተፅዕኖ ይፈጥራል። ሰው ሲደሰት አይቻለሁ። ቤተሰቦቻችን ያሉበት ቦታ ብንሄድ ደግሞ የእኛም ደስታ ሙሉ ይሆን ነበር። የእግር እንጂ የአዕምሮ እረፍት አልነበረንም” ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። ጎተይቶም ከመንግሥት ዕውቅና እና ሽልማት ከተበረከተላት በኋላ ለቢቢሲ በሰጠችው አስተያየት፤ “ሁሉም አሸንፋለሁ ብሎ እንደሚገባው እኔም አሸንፋለሁ በሚል ተስፋ ነው የገባሁት” ብላለች። “ከተፎካካሪዬ ጋር ስንሄድበት የነበረው ፍጥነት የአስር ሺህ እንጂ የማራቶን አይመስልም ነበር፤ ይህም ውድድሩን ፈታኝ አድርጎታል።” “ከውጤት አንፃር አብዛኛው በሴቶች የመጣ መሆኑን ሳይ ደስተኛ አድርጎኛል፤ ግን ወንዶቹም ጠንክረው ሠርተዋል። ማራቶን ላይ ወንዶች ማሸነፋቸው ደግሞ እኛም እንድናሸንፍ ሞራል ሆኖናል።” https://www.bbc.com/amharic/articles/cjj4v9vp8pzo +business ታንዛኒያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ተመደበች ታንዛኒያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ዝርዝር ውስጥ መግባቷ ተገለፀ ። ይህ የሆነው የዓለም ባንክ የዓለም አገራትን ምጣኔ ሐብት ከተመለከተ በኋላ ���ው። ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ታንዛኒያ ከዚህ ዝርዝር ውስጥ የገባችው፤ በአገሪቷ ያለው የአንድ ሰው ዓመታዊ አማካይ የነፍስ ወከፍ ገቢ በ1006 እና 3955 ዶላር መካከል በመሆኑ ነው። የአንድ ሰው ዓመታዊ አማካይ ነፍስ ወከፍ ገቢ አገሪቷ የምታገኘው ዓመታዊ ገቢ የዶላር ዋጋ ለሕዝብ ብዛቷ በማካፈል የሚገኝ ስሌት ነው። ባለፈው ዓመት የታንዛኒያ ኢኮኖሚ በ6.8 በመቶ ያደገ ሲሆን፤ ከሁለት ዓመታት በፊትም 7 በመቶ እድገት አሳይቶ ነበር። ይህም በዓለማችን ፈጣኑ የኢኮኖሚ እድገት ከሚባሉት ውስጥ የሚመደብ ነው። እንደ አጥኚዎቹ ከሆነ ይህ የምጣኔ ሐብት እድገት ለአስር ዓመታት የቀጠለ ሲሆን ፕሬዚደንት ጆን ማጉፉሊም ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላም እንደቀጠ ይገኛል። አገሪቷ በቀጠናው ከፍተኛ ምጣኔ ሐብት ያላት ሁለተኛዋ አገር ሆናለች። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወደ አፍሪካ መዛመቱን ተከትሎ ሚያዚያ ወር ላይ የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 ምክንያት የኢኮኖሚ ድቀት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ተንብዮ ነበር። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በዚህ ዓመት ብቻ በ2.1 በመቶ የሚጎዳ ሲሆን ይህ ጉዳት እስከ 5.1 ድረስ ሊደርስ ይችላል ብሏል። የዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አበዳሪ አገራት ለአፍሪካ እዳቸውን ለተወሰነ ጊዜ እንዲያራዝሙ እና አገራት ያላቸውን ገንዘብ ወደ ሕይወት ማዳንና ኑሮን ማሻሻል ላይ ማዋል እንዲችሉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። በአፍሪካ በምጣኔ ሃብታቸው ግዙፍ የሆኑት ናይጄሪያና አንጎላ በወረርሽኙ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መውረድ ምጣኔ ሃብታቸው ክፉኛ ከተጎዳ አገራት መካከል ይገኙበታል። ደቡብ አፍሪካም ብትሆን የማዕድን ገቢዋ አሽቆልቁሎባታል። https://www.bbc.com/amharic/news-53282427 +health ኮሮናቫይረስ፡ የደልሂ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተከሰተውን የኦክስጂን እጥረት 'አሳፋሪ' ሲል ተቸ "በሕንድ ደልሂ የሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማዕከላዊው መንግሥት በከተማው ያለውን የኦክስጂን እጥረት የያዘበትን መንገድ በይፋ ተችቷል፡፡ አገሪቱ ረቡዕ 2 ሺህ 23 ሰዎች መሞታቸውን በኮቪድ ምክንያት ሪፖርት ሲሆን ይህም በቀን የተመዘገበው ከፍተኛው ቁጥር ሆኗል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከ 200 በላይ የሚሆኑት የኦክስጂን እጥረት በገጠማቸው በደልሂ ሆስፒታሎች የተመዘገቡ ናቸው፡፡ ፍርድ ቤቱ በስድስት የግል ሆስፒታሎች ባለቤቶች የቀረበለትን አቤቱታ እየሰማ ይገኛል። መንግስት የኦክስጂን አቅርቦት ከፋብሪካዎች ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ወደ ሆስፒታሎች እንዲደርስ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ ""ይህ አሳፋሪ ነው። መንግሥት በመላ ህንድ የኦክስጂን አቅርቦትን አስመልክቶ ምን እየሰራ እንደሆነ ማወቅ እንፈልጋለን። የኦክስጂን አቅርቦቶችን ለማረጋገጥ መለመን፣ መበደር ... መስረቅ ካለበት ይህ የመንግስት ሃላፊነት ነው"" ብለዋል ዳኞቹ፡፡ ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ባይቻልም በመላ አገሪቱ በርካታ ሰዎች ኦክስጅን ሲጠብቁ ህይወታቸው አልፏል፡፡ የህንድ ማህበራዊ ድር አምባዎችም እንዲሁ በኦክስጂን ያስፈልገናል ጥሪ ተሞልተዋል፡፡ በዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ እና በሞሉ ሆስፒታሎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ይሰባሰባሉ፡፡ የጤና አገልግሎቶች ችግሩን ለመቋቋም በመታገል ላይ ናቸው፡፡ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አንዱ የሆነው የምዕራባዊው የማሃራሽትራ ግዛት ባለሥልጣናት የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ ከሐሙስ ምሽት ጀምሮ ተጨማሪ ገደቦችን ጥለዋል፡፡ ግዛቲቱ ቀድሞውኑም በከፊል እገዳ ስር ነበረች። ማሃራሽትራ በሕንድ የበለፀገች ግዛት ስትሆን የፋይናንስ ማዕከልዋ ሙምባይ የምትገኝበት ነው፡፡ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶም የኮቪድ ስርጭት ማዕከል ሆናለች፡፡ በህንድ በቫይረሱ ከተያዙ ከ 15 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መካከል ሩብ ያህሉ በግዛቲቱ የተመዘገቡ ናቸው፡፡ ማሃራሽትራ ከሌሎች ግዛቶች በበለጠ 67 ሲህ 468 በቫይረሱ የሞቱ ሰዎችን ሪፖርት አድርጋለች። በህንድ ከ 180 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መሞታቸውን አረጋግጣለች፡፡ የሟቾች ቁጥር ቢጨምርም የሞት ምጣኔው በአንፃራዊነት ዝቅተኛ ነው፡፡ ህንድ ባለፈው ወር ጥብቅ ባልነበረው የደህንነት ፕሮቶኮሎች፣ በአዲሱ የቫይረሱ ዓይነት እና ሚሊዮኖች በተሳተፉበት የሂንዱዎች ፌስቲቫል ምክንያት ቁጥሩ በከፍተኛ ፍጥነት መጨመሩ ተገልጿል፡፡ በብሄራዊ የቫይሮሎጂ ተቋም እንዳስታወቀው በማሃራሽትራ ከተመረመሩት መካከል 61 በመቶ የሚሆኑት ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። በየደረጃው ምርጫ በሚደረግበት በምዕራብ ቤንጋል ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ጨምሮ ግዙፍ የምርጫ ስብሰባዎች መካሄዳቸው አልተቋረጠም፡፡ መራጮች ሐሙስ ለ 6ኛ ዙር ምርጫ ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መንግስት ምርጫው እንዲካሄድ ያሳለፈውን ውሳኔውን ተከላክሏል፡፡ ብዙዎች በሀገሪቱ እየዘገየ የመጣው የክትባት እንቅስቃሴ ስርጭቱን ለመግታት ሲባል በፍጥነት መካሄድ አለበት ብለዋል፡፡ በህንድ ከ 130 ሚሊዮን በላይ ክትባቶችን ብትሰጥ የደረሳቸው የጤና ሠራተኞች፣ ተጋላጭ ሠራተኞች እና ከ 45 አመት በላይ የሆኑ እና ማንኛውም በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ከግንቦት 1 ጀምሮ ደግሞ ከ 18 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ለክትባቱ ብቁ ይሆናሉ፡፡ የአቅርቦት መዘግየት ሂደቱን የበለጠ ሊያዘገየው ይችላል ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56841524 +business የኢትዮጵያን ገበያ ያንኳኳው 'የቻይና በርበሬ' የት ገባ? "ያሳለፍነው የኅዳር ወር ክረምቱን ተሰቅሎ የሚቆየው የበርበሬ ዋጋ የሚረጋጋበት፤ አዲስ ምርት የሚገባበት እና በርካታ ኢትዮጵያዊያን ረዘም ላለ ጊዜ የሚያቆያቸውን የበርበሬ ምርት የሚሸምቱበት ነው። ወቅቱ ገበሬው፣ ሸማቹ፣ ነጋዴው እና ደላላው በጋራ የሚረባረቡበት ነው። ታዲያ አዲስ አበባ በርበሬ አብቅላ ኢትዮጵያን ባትመግብም በመላው አገሪቱ የሚመረተው ሁሉ ተሰብስቦ ወደ የክልሉ ይከፋፈልባታል። በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚዘዋወርበት ተክለሐይማኖት ደግሞ ዋነኛው የበርበሬ ግብይት ማዕከል ይባላል። ታዲያ ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ በእነዚህ አከፋፋዮች ዘንድ ያልተለመደ ምርት ""የቻይና በርበሬ"" በሚል ስያሜ ብቅ ብሎ መስከረም አጋማሽ ላይ መጥፋቱን ነጋዴዎች ይናገራሉ። ""በርበሬውን ከተክለ-ሐይማኖት ስናመጣው የታሸገበት ማዳበሪያ 'ሜድ ኢን ቻይና' [ቻይና የተሰራ] ይላል"" ሲል ብርሌው አየሁ የተባለ ነጋዴ ይናገራል። መሪ አካባቢ በሚገኘው የበርበሬ ገበያ 30 ገደማ የበርበሬ ነጋዴዎች ቢገኙበትም በጥቅምት ወር አጋማሽ ለዚህ ዘገባ ሲባል ""የቻይና በርበሬ ያለህ"" ተብሎ ቢፈለግም አለኝ ያለ አልተገኘም። ብርሌው እንደሚለው ከሆነ ነጋዴዎቹ በርበሬውን ይሸጡ እንደነበር እንኳን እንዲታወቅባቸው አይፈልጉም፤ ደንበኛ ላለማጣት። በርግጥ ተክለሐይማኖት አካባቢ የሚገኙት ዋነኛ የበርበሬ አከፋፋዮች ለዚህ ምስክር ናቸው። ቢቢሲ ተዘዋውሮ ያነጋጋራቸው ሦስት አከፋፋዮች ""ይዘነውም አይተነውም አናውቅም"" ይላሉ። ነገር ግን በተቃራኒው አብዲ የተሰኘ አንድ አከፋፋይ አብዛኛው አከፋፋይ ይይዘው እንደነበር እና በኅዳር ወር አዲስ የበርበሬ ምርት በመድረሱ እና ዋጋውም በመረጋጋቱ 'የቻይና በርበሬ' ከገበያ መውጣቱን ይናገራል። ቢቢሲ ይህንን 'የቻይና በርበሬ' የተባለውን የበርበሬ ምርት ምንጭ በተ���ለከተ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም። በአሁኑ ጊዜ የበርበሬ ዋጋ ቢያንስ እስከ መቶ ብር ድረስ ቅናሽ አሳይቷል። የሐረር በርበሬ 220 ብር በመሸጥ ዝቅተኛ ዋጋውን ይዟል። ከፍተኛ ጥራት አለው የሚባለው የማረቆ በርበሬ ደግሞ በኪሎ ቢበዛ 300 ብር ቢሸጥ ነው ሲል አብዲ ይናገራል። እስካለፈው ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ ዝቅተኛው የበርበሬ ዋጋ 340 ብር ደርሶ እንደነበር ሸማቾች ይናገራሉ። በርበሬ ወይም 'ሬድ ፔፐር' በዓለም ላይ ከቲማቲም ቀጥሎ በከፍተኛ ደረጃ የሰው ልጆች የሚመገበው የምግብ ምርት ነው። በአውሮፓውያኑ 2018 በተደረገ ጥናት ቬትናማውያን በዓለም ከፍተኛው የበርበሬ ወይም 'ሬድ ፔፐር' ተጠቃሚ ተብለዋል። ቀጥሎም ሕንድ እና አሜሪካ የሚከተሉ ሲሆን ሦስቱ አገራት በዓለም ላይ በዓመት ጥቅም ላይ ከሚውለው በርበሬ ውስጥ 41 በመቶውን ያህል ይመገባሉ። ኢትዮጵያዊያን አጥብቀው የሚወዱት በርበሬ ዋጋ ለምን ይዋዥቃል? ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ከሚያመርቱት በርበሬ ውስጥ 92.4 በመቶ የሚሆነውን ለገበያ እንደሚያቀርቡና ይህም በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ከፍተኛ የገበያ ሰብሎች ውስጥ እንደሚያስመድበው ከሁለት ዓመት በፊት አራት ምሁራን ባሳተሙት ጥናት ላይ ተጠቅሷል። አምራች ገበሬዎቹ ከ60 በመቶ በላይ ምርታቸውን በአካባቢያቸው ለሚገኙ ጅምላ ነጋዴዎች ይሸጣሉ ሲል በአበበ ቢራ፣ ጥጋቡ ዳኘው፣ አበበ ዳኘው እና አስማማው አለሙ የተጠናው ጥናት ያሳያል። መነሻው ከደቡብ አሜሪካ እንደሆነ የሚነገርለት በርበሬ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች በከፍተኛ መጠን ይመረታል። ታዲያ ባለሞያዎቹ ባጠኑት ጥናት መሰረት ከፍተኛው የበርበሬ ምርት ተግዳሮት የግብአት እጥረት ነው። የበርበሬ ምርት ከፍተኛ የሆነ ለበሽታ ተጋላጭነት ደግሞ ሌላኛው ማነቆ ነው። በተጨማሪም በርበሬ ሲተከል፣ ሲታረም እና ደርሶ ሲሰበሰብ ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል ይፈልጋል። ስለዚህም በርበሬን ለማምረት የሚያስፈልገው ከፍተኛ የሰው ኃይል በምርቱ ላይ እና በዋጋው ላይ የእራሱ ተጽእኖ እንዳለው አጥኚዎቹ አመልክተዋል። ሌላው ዋነኛ የበርበሬ ገበያ ላይ ያለው ማነቆ በግብይት ወቅት ያሉ ችግሮች ሲሆኑ፣ አጥኚዎቹ ያነጋገሯቸው አምራቾች እንደሚሉት ከመንግሥት ድጋፍ ማጣት ዋነኛው የገበያው ችግር አባባሽ ነው። በመቀጠልም በቂ የመጋዘን ስፍራ አለመኖር፣ የብድር አገልግሎት እጥረት፣ በገዢ እና በሻጭ መካከል ያለ የትክክለኛ መረጃ ክፍተት እንዲሁም ከጥራት ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች የበርበሬን ገበያ በመፈተን ይጠቀሳሉ። በኢትዮጵያ የኢኮኖሚስቶች ማኅበር ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት እና የመንግሥት የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ያገለገሉት ተባባሪ ፕሮፌሰር ሰዒድ ኑሩ (ዶ/ር) አራት ዋና ዋና ማነቆዎች በርበሬን ጨምሮ ሌሎች ወቅትን ጠብቀው የሚመረቱ ምርቶች ላይ ለሚታዩ የዋጋ መናር ምክንያት ናቸው ይላሉ። የመጀመሪያው ምርቱን በበቂ ሁኔታ ያለማምረት ነው። አንድ ምርት በበቂ ሁኔታ በአገር ውስጥ ማምረት ካልተቻለ የቱንም አይነት እርምጃ ቢወሰድ ውጤት ማየት አይታሰብም ይላሉ ሰዒድ (ዶ/ር)። እንደ የተባበሩት አረብ ኤምሬት ያሉ በቂ የውጪ ምንዛሬ ያላቸው አገራት ""ከበለገው ይግጣሉ"" በማለት፣ በቂ ገንዘብ ያለው አገር በልግ ከሆነበት አገር የፈለገውን ምርት ገዝቶ ከዓመት ዓመት ሕዝቡን በተረጋጋ ገበያ ሊመግብ እንደሚችል ያብራራሉ። ሁለተኛው እንደ በርበሬ ያሉ ምርቶችን ተገቢ የሆነ የማቆያ ዘዴዎችን በመጠቀም ከዓመት ዓመት እንዲቆይ ማድረግ ሌላው እርምጃ ነው። እንደ ቲማቲም ያሉ ከበርበሬ ይልቅ በአጭር ጊዜ የሚበላሹ ��ርቶችን እንኳን ከገበያ እንዳይጠፉ የሚያደርግ ዘዴ መኖሩን የሚያስታውሱት ሰዒድ (ዶ/ር) ይህንን በበርበሬ ላይ መተግበር ቀላል ነው ይላሉ። ሌላው መፍትሄ ነጋዴዎች ምርቱ በረከሰ ጊዜ እንዲያከማቹ ማስቻል ነው። ""ኢትዮጵያ ውስጥ ነጋዴዎች ምርትን ያከማቻሉ የሚለው በአሉታዊ መልኩ ብቻ መወሰዱ አግባብ አይደለም"" ይላሉ የኢኮኖሚ ባለሞያው። ""በውጪው አገር ኢንቨርተሪ የሚባል ኢንቨስትመንት አለ። አንድ ምርት ሲረክስ ነጋዴዎች ሰብስበው የሚያቆዩበት እና ምርቱ ገንዘባቸውን ይዞ ለቆየበት እንደ ሽልማት የተወሰነ ጭማሪ አድርገው፣ ምርቱ ሲጠፋ ለገበያ የሚያቀርቡበት ሥርዓት ማለት ነው። ይህ መጥፎ ጊዜ ጠብቀው ምርት የሚያከማቹትን አያጠቃልልም። በሪል ስቴት ወይም መሰል ምርቶች ላይ እንደሚደረግ ኢንቨስትመንት ማለት ነው"" ሲሉ ሰዒድ (ዶ/ር) ያብራራሉ። ሌላኛው ማነቆ እንደ በርበሬ ያሉ ምርቶች ላይ እሴት የሚጨምር ኢንዱስትሪ ቁጥር ትንሽ ከመሆኑ ጋር ይያያዛል። በርበሬ ተመጥኖ እና ተዘጋጅቶ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ምርት እንደመሆኑ፣ ዋጋው በረከሰ ወቅት በርበሬው ቢዘጋጅ ምርቱ በማይኖርበት ጊዜ የተወሰነ ገንዘብ ጨምሮ መሸጥ ዋነኛ አማራጭ መሆን ይቻላል ሲሉም ሦስተኛውን ችግር እና መፍትሄውን ያመላክታሉ። የምርት እጥረት ባለበት ወቅት ከውጪ ማስገባቱ መፍትሄ ይሆናል? የምርቱ እጥረት ባለበት ወቅት ከውጪ ማስገባት በእርግጥም በቂ የውጪ ምንዛሬ ላለው አገር መፍትሄ ነው የሚሉት ሰዒድ (ዶ/ር)፣ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች ግን በርካታ ችግሮችን የሚያስከትል እርምጃ ነው ይላሉ። ነገር ግን አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ማስገባት በጥንቃቄ የሚወሰድ እርምጃ ከሆነ በርካታ ጥቅሞች እንዳሉት አጽንኦት ይሰጡታል። ባለሙያው ስለ ጥቅሞቹ ከማብራራታቸው በፊት እጥረትን እንደ ችግር መመልከት ማቆም እንደሚያስፈልግ እና ለአንድ አልሚ እጥረት የገበያ እድል ሆኖ መታየት እንደሚገባው ያብራራሉ። ይህም የማምረት ችግር ለሌለበት አገር በተለይም ለእጥረት መፍትሄ መስጠት ለአምራቾች የገበያ እድል ነው ይላሉ። ለዚህ ምሳሌ ሲጠቅሱ፡ ""ከዓመታት በፊት የአገር ባህል ልብስ ከአውሮፓ ከሚመጡ ልብሶች በላይ ውድ መሆኑን ያዩ ቻይናውያን ወስደው በርካሽ ቴክኖሎጂ ሰርተው መልሰው አመጡት። ይህ እንግዲህ በየዕለቱ የማንለብሰው የክት ልብስ ነው። ታዲያ በየዕለቱ የምንጠቀማቸው ምርቶች እጥረት ሲፈጠር ይሄንን ለመሙላት መንቀሳቀስ ነበር የሚገባን"" ሲሉ ሰዒድ (ዶ/ር) ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ የበርበሬ እጥረትን ለመፍታት ከውጪ አገር ማስገባቷ ዘላቂ እስካልሆነ ድረስ ለጥቅም ማዋል እንደሚያግዝ ያስረዳሉ። አንዱ ቴክኖሎጂውን መቅሰም ነው። የምግብ ምርት እንደመሆኑ አመራረቱን ማየት ቢያስፈልግም አንድን ምርት አንድ ጊዜ ወይም ሁለቴ አስገብቶ ምርቱን መሞከር ችግር እንደሌለውም ይናገራሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች በግብርና ሥራ ለዘመናት የቆዩበት ሙያ ሆኖ ሳለ ልክ እንደ ኢንዱስትሪ ምርቶች የግብርና ምርት ማስገባት ግን አስመጪውን እና ሸማቹን ለስንፍና መንግሥትን ደግሞ ለከባድ የውጪ ምንዛሬ እጥረት ይዳርጋል ይላሉ። ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውን እንደ ማሽኖች ያሉ ግብአቶችን ለማስገባት እንጂ አንድም ኪሎ የግብርና ምርት በቋሚነት ኢትዮጵያ ማስገባቷ አግባብ አይደለም ሲሉም ያክላሉ። ""አስመጪዎች በተሻለ ጥራት በቅናሽ የተመረት የግብርና ምርት ማምጣት ከጭቃው ከአፈሩ ጋር መታገልን ያስቀርላቸዋል። ይህ አንዴ ከተለመደ ከባድ ነው። ስንፍናን ያመጣል። ሱፐር ማርኬት ውስጥ ከግብፅ የሚመጣ አራት ፍሬ ብርቱካን በ280 ብር ይሸጣል። የተገነጠለ ዶሮ፣ እንቁላል እንዲሁም ሽንኩርት ከውጪ ይገባል። የአየር ንብረታችን እጅግ የተመቸ ሆኖ ሳለ ይህ እንዴት ሆነ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል"" ይላሉ ሰኢድ ኑሩ (ዶ/ር)። እንደ መውጫ ከመስከረም አስከ ኅዳር ድረስ በግዴታ ነጋዴው ይዞ ሲሸጠው የቆየው 'የቻይና በርበሬን' በተመለከተ ነጋዴዎቹ በእርግጥም ቅሬታ ነበራቸው። በርበሬው ገና ከማዳበሪያው ሲፈታ ጀምሮ ""የኬሚካል ሽታ"" እንዳለው እና በርበሬውን የገዙ ደንበኞችም ደስተኛ እንዳልሆኑ ብርሌው ተናግሯል። ""የቻይናው በርበሬ በ250 ሲመጣ የአገር ውስጥ በርበሬ 350 ነበር የሚሸጠው። ይሄ ከፍተኛ የዋጋ ልዩነት ነበር። የገዙኝ ደንበኞችም ሲፈጭም ዱቄቱ እንደሚያምር ነግረውኝ ነበር። ምግብ ውስጥ ሲገባ ነው ችግሩ"" ሲል ብርሌው ለቢቢሲ ተናግሯል። ደንበኞቹ ቅር መሰኘታቸውን እንደነገሩት አልሸሸገም። የኢኮኖሚ ባለሞያው ሰዒድ (ዶ/ር) ከውጪ አገር እንዲህ ያሉ የግብርና ምርቶች ሲገቡ በሽታ ይዘው እንዳይመጡ ጥንቃቄ ተደርጎ መሞከር ይገባዋል ሲሉም ያስጠነቅቅቃሉ። ገበሬዎች የቅንጬ አረም የሚሉት ከፍተኛ ጉዳት ያለው አረም ብሎም በአንድ ወቅት ከሕንድ የገባ ማንጎን ተከትሎ የመጣ የሰብል በሽታን በምሳሌነት ያነሳሉ። ""ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የነጋዴ ቁጥር ለቁጥጥር የማይመች ነው"" የሚሉት ባለሙያው በሌላው አገር አነስተኛ ቁጥር ያለው ትልልቅ ነጋዴ ስላለ ከመንግሥት ጋር ለመደራደር ቀላል ያደርገዋል። ይህ ለአምራች ገበሬውም እንደሚሰራ ይናገራሉ። ትርፍ የሚገኘው አንድም ብዙ ምርት በአነስተኛ ዋጋ በመሸጥ ወይም አነስተኛ ምርት በከፍተኛ ዋጋ በመሸጥ እንደሆነ የሚናገሩት ባለሙያው፣ አነስተኛ ነጋዴም ሆነ ገበሬ ያለበት አገር የዋጋ መናሩ የሚገመት ነው ይላሉ። ""ባደጉ አገራት መንግሥት የሚደራደረው አራት አምስት ከሚሆኑ ሱፐርማርኬቶች ጋር ነው። እኛ ጋር 20 ሺህ ሱቆችን ዘጋን የሚል ዜና እንሰማለን። ይህ የበለጠ እጥረት ይፈጥራል። አንድ አዲስ አበባ በቅርቡ የተከፈተ ሱፐር ማርኬት አለ። ከራሱ ማሳ ብርቱካን 30 ብር በኪሎ አምጥቶ ይሸጣል። ከእርሱ ሱፐርማርኬት ምርቱን የገዙ አጠገቡ ያሉ ትንንሽ ሱቆች ራሱን ብርቱካን በእጥፍ 60 ብር ይሸጣሉ"" ሲሉ ሰዒድ (ዶ/ር) በትልልቅ አቅራቢዎች እና አነስተኛ ቸርቻሪዎች መካከል ያለውን ልዩነት ያስረዳሉ። እንዲሁም የኢትዮጵያ የገበያ መዋቅር ደላላ የተጫነው እና ሰዎች በምርት ሥራ ላይ ከመሳተፍ ይልቅ በመሃል በመደለል እያተረፉ መኖርን መምረጣቸው ሌላው ከፍተኛ ችግር ነው ይላሉ ሰኢድ (ዶ/ር)። ልክ እንደ አበባ ሁሉ የምግብ የሚያመርቱ ትልልቅ ኩባንያዎችን በማገዝ ወደ አገር ውስጥ በመጋበዝ ከእነሱ መማር እንደሚያስፈልግም ይናገራሉ። ""በአንድ ጊዜ 100 ሻማ ማብራት አይቻልም"" የሚሉት ሰኢድ ""ከአንድ ሻማ መጀመር ግን ይቻላል"" ይላሉ። የአበባ አምራቾች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ከ10 ዓመት በፊት ኬንያ ውስጥ ምርጫን ተከትሎ የመጣ ቀውስን ሸሽተው ነበር። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የአበባ ምርት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ምንጭ እንደሆነ እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአገር ውስጥ ባለሃብቶች የገቡበት ብሎም የቴክኖሎጂ ሽግግሩም በተሳካ ሁኔታ የተሳለጠበት ዘርፍ መሆኑን ያነሳሉ። ይህ በሌላው ዘርፍ መደገም አለበት እንደ ሰኢድ ኑሩ (ዶ/ር) ትንታኔ። ""የመጀመሪያውም፣ ሁለተኛውም ሦስተኛውም መፍትሄ አንድ ነው። በግብርና ራሳችንን መቻል ነው"" ሲሉ ዘመናዊ ግብርናን ማስፋፋት ብቸኛው መፍትሄ መሆኑን ባለሙያው ለቢቢሲ ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59807834 +health ኮቪድ-19፡ የዓለማችን ትልቁ የፕላስቲክ ጓንት አምራች ድርጅት ፋብሪካዎቹን ሊዘጋ ነው "የዓለማችን ትልቁ የፕላስቲክ ጓንት አምራቹ 'ቶፕ ግላቭ' ከግማሽ በላይ የሚሆ���ትን ፋብሪካዎቹን እንደሚዘጋ አስታወቀ። ድርጅቱ ይህን ያለው 2500 የሚሆኑ ሠራተኞቹ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ነው። ንብረትነቱ የማሌዥያ የሆነው 'ቶፕ ግላቭ' ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ሲባል 28 ማምረቻዎቹን ተራ በተራ ይዘጋል ተብሏል። ፋብሪካዎቹ መቼ መዘጋት እንደሚጀምሩ የታወቀ ነገር ባይኖርም ደረጃ በደረጃ ለመዝጋት መታቀዱ ተገልጿል። ድርጅቱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ የበሽታው መከላከያ ግብዓት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮለት ነበር። ይሁን እንጅ በሚተማመንባቸው ዝቅተኛ ተከፋይ ስደተኛ ሰራተኞቹ የሥራ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ስጋቶች ነበሩ። ሰኞ ዕለት የማሌዥያ የጤና ሚኒስተር የቶፕ ግላቭ ፋብሪካዎች እና የሰራተኞች መኖሪያ በሚገኙበት አካባቢው የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ስርጭት መጨመሩን አስታውቋል። ይህንን ተከትሎ 5 ሺህ 800 ሰራተኞች እስካሁን የተመረመሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 2 ሺህ 453ቱ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ብሏል። ቶፕ ግላቭ በማሌዥያ 41 ፋብሪካዎች ያሉት ሲሆን አብዛኞቹ ሰራተኞቹ ከኔፓል የመጡና በተጨናነቁ የመኖሪያ ህንፃዎች የሚኖሩ ናቸው። ""በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ሆስፒታል ገብተዋል። የቅርብ ንክኪ ያላቸውም ራሳቸውን ለይተዋል"" ሲሉ የጤና ሚኒስቴር ዳሬክተር ጀነራል ኑር ሂሻም አብዱላህ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ቶፕ ግላቭ በዚህ ዓመት በዓለማችን ከፍተኛ ትርፍ በማስመዝገብ በዓለም ትኩረት ውስጥ ቆይቷል፤ በዚህ ብቻም ሳይሆን በሰራተኞች የጉልበት ብዝበዛ ክሶችም የዓለም ዋነኛ ትኩረትም ሆኗል። ሐምሌ ወር ላይ አሜሪካ የሰራተኞች የጉልበት ብዝበዛን ምከንያት በማድረግ ከሁለት የድርጅቱ ቅርንጫፎች ጓንቶች እንዳይገቡ አግዳለች። የአሜሪካ የሰራተኛ መሥሪያ ቤት በቅርቡ ባወጣው ሪፖርትም ተመሳሳይ ሃሳብ አንስቷል። መስከረም ወር ላይም ስደተኛ ሰራተኞች ለሎስ አንጀለስ ታይምስ በቶፕ ግላቭ ፋብሪካዎች ያለውን የሥራ ሁኔታ አስቸጋሪነት ተናግረዋል። ስደተኞቹ በሳምንት 72 ሰዓታት እንደሚሰሩና ዝቅተኛ ክፍያ እንደሚከፈላቸውና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩ ነበር ለሎስ አንጀልስ ታይምስ ያስረዱት። ከጥቂት ሳምንታት በኋላም ድርጅቱ ከገለልተኛ አማካሪው በተሰጠው ምክረ ሃሳብ መሰረት ለሰራተኞቹ የቅጥር የማካካሻ ክፍያ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቆ ነበር። የማሌዥያ የፕላስቲክ ጓንት አምራቹ ቶፕ ግላቭ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ፣ ኮንዶም፣ የፕላስቲክ ድድ እንዲሁም ሌሎችን ምርቶችን በማምረት ይታወቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55036274 +health ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 ምን እንደሆነ አናውቅም የሚሉት 10 አገራት ኮቪድ ዓለምን አምሷል፡፡ እኛ ግን አናውቀውም የሚሉ 10 አገሮች አሉ ብንላችሁስ፡፡ ለመሆኑ እነዚህ አገሮች እነማን ናቸው? የማያውቁት ኮቪድ እንዴት እያደረጋቸው ይሆን? 1.ፕላው (Palau) ይቺ አገር የት ያለች ትመስልዎታለች? ሩቅ ምዕራብ ፓስፊክ ነው የምትገኘው፡፡ ማይክሮኒዢያ ሪጂን በሚባለው አካባቢ ከነ ፊሊፒንስ እና ኢንዶኒዢያ ነጠል ብላ በባትሪ ተፈልጋ የምትገኝ ጢኒጥ ደሴት ናት፡፡ እዚያ ፕላው የሚባል ሆቴል አለ፡፡ ድሮ በ1982 ነበር የተከፈተው፡፡ ያኔ የአገሩን ስም የያዘው ይኸው እስከዛሬ አለ፡፡ በአገሩ ሌላ ሆቴል የሌለ ይመስል፡፡ በፓስፊክ ውቅያኖስ ሰማያዊ ቀለም ውሀ ውስጥ ጠብ ያለች ነጥብ የምትመስለው ይቺ አገር የቱሪስት አገር ናት፡፡ ያለፈውን ዓመት ብቻ አሐዝ ብንወስድ፣ ወደ ፕላው ደሴት 90ሺህ ቱሪስት ገብቷል፡፡ ይህ አሐዝ ከፕላው ጠቅላላ ሕዝብ አምስት እጥፍ ይበልጣል ብንላችሁስ? 40 ከመቶ የአገሪቱ ጥቅል አገራዊ ምርት ገቢ በቱሪዝም የሚታለብ ነው፡፡ ይ��� ግን ከኮቪድ በፊት ያለ ታሪክ ነው፡፡ ኮቪድ ድንበሯን ሲያዘጋት ፕላው ደሴት ጉሮሮዋ ተዘጋ፡፡ እንኳን ሌላው መዝናኛ ይቅርና የአገሪቱን ስም የያዘው ሆቴል ሳይቀር ተዘጋ፡፡ ‹‹ለውድ ደንበኞቻችን፡- ኮቪድ የሚባል በሽታ በተቀረው ዓለም ስለተከሰተ ፕላው ሆቴል ለጊዜው ዝግ መሆናችንን ለውድ እንገልጻለን›› ብለው በር ላይ ሳይለጥፉ አልቀሩም፡፡ ፕላው አገር አንድም ዜጋ በቫይረሱ ባይያዝባትም ቫይረሱ ግን ቱሪዝማዊ ኢኮኖሚዋን ደም እያስተፋው ነው፡፡ 2. የማርሻል ደሴቶች 4ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀው በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ መሀል፣ ከምድር ወገብ ሰሜን፣ ብጥስጥስ ብለው ከሚገኙት የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ውስጥ የማርሻል ደሴቶች ይገኙበታል፡፡ በሀዋይ እና በፊሊፒንስ መሀል ነው የሚገኙት፡፡ በውስጣቸው 1200 ጥቃቅን ደሴቶችና የጎመራ ፍንጥቅጣቂ የሆኑ የሰመጡ ደቂቀ ደሴቶች (ኮራል አቶልስ) ይገኛሉ፡፡ ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ የአሜሪካ የሩቅ ግዛት ሆነው የቆዩ ቢሆንም ከ1986 ወዲህ ራሳቸውን ችለዋል። ደህንነቱና መከላከያን እንዲሁም ጠቀም ያለ ድጎማን ግን አሁንም ከአሜሪካ ነው የሚያገኙት። የሕዝብ ብዛት 55ሺህ ሲሆን ዋና ከተማቸው ማጁራ ትባላለች፡፡ እነዚህ ደቂቀ ደሴቶችና የቱሪስት መዳረሻ የሆኑ ስብስቦች ማርሻል ደሴቶች ተብለው ይጠራሉ፡፡ ኮቪድ ምን እንደሆነ ባያውቁም ምጣኔ ሀብታዊ ቁንጥጫው ግን ፓሲፊክን አቋርጦ ተሰምቷቸዋል። ታዲያ አንድ ፕላው በቱሪዝም በኩል አይደለም ቁንጥጫው፡፡ በዓሣ ማጥመድና መላክ ጥሩ ገንዘብ ያገኙ ነበር፡፡ ኮቪድ ይህንን አስተጓጎለባቸው፡፡ በኮቪድ ምክንያት 700 ሰዎች ሥራ አጥተዋል፡፡ ይህ ትንሽ ሕዝብ ላላት ማርሻል አይላንድስ ብዙ ቁጥር ነው፡፡ የሕዝብ ብዛቷ 300ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ዋና ከተማዋ ፖርትቪላ ይባላል፡፡ በ1ሺህ 300 ኪሎ ሜትር ላይ የተሰፉ የሚመስሉ 80 ደሴቶች የፈጠሯት አገር ናት፡፡ ከፈረንሳይና እንግሊዝ ቅኝ ነጻ የወጣችው ገና በ1980 ነበር፡፡ አብዛኛው ሕዝቧ ገጠር የሚኖር ገበሬ ነው፡፡ የብዙ አገር ህዝቦች ድንበር ክፈቱልን ሥራ እንስራበት እያሉ ነው የሚያስቸግሩት፡፡ ቫኑዋቱ ብትሄዱ ግን በተቃራኒው ነው የምትሰሙት፡፡ ዶ/ር ሌን ታሪቮንዳ የኅብረተሰብ ጤና ዳይሬክተር ናቸው፣ የቫኑዋቱ ደሴት፡፡ ዶ/ር ሌን የመጡባት ደሴት አምባኡ ደሴት ትባላለች፡፡ 10ሺ ሰዎች ይኖሩባታል፡፡ ‹‹እኔ የመጣሁበት ደሴት ሄዳችሁ ድንበሩ ይከፈት ወይ ብትሏቸው አረ እንዳታስጨርሱን ነው የሚሏችሁ›› ይላሉ ለቢቢሲ፡፡ መታመም አንፈልግም ነው የሚሉት፡፡ 80 ከመቶ የታሪቮንዳ አገር ሕዝብ ገጠር ነው የሚኖር፡፡ የኮቪድ ሕመም ብዙም አልተሰማቸውም፡፡ እርሻ እንጂ ቱሪዝም ላይ ስላልተንጠላጠሉ ሊሆን ይችላል፡፡ ዶር ሌን ድንበር ለመክፈት አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ጎረቤት ፓፓዎ ጊኒ ለወራት ከቫይረሱ ነጻ ሆና ቆይታ ሐምሌ ላይ እንዴት ጉድ እንደሆነች ሰምተዋል፡፡ ስለዚህ ድንበር መክፈቱ ይቆየን ብለዋል፡፡ 4. ቶንጋ ቶንጋን የፈጠሩት ደግሞ 170 ደቂቀ ደሴቶች ናቸው፡፡ እዚያው ደቡባዊ ፓስፊክ ነው የሚገኙት፡፡ ቶንጋ ደሴቶቿን ብትሰበስብ በስፋት ከጃፓን አታንስም፡፡ ለ165 አመታት ንጉሣዊ የፊውዳል አስተዳደር ነበራት፡፡ ከዚህ ፊውዳላዊ ሥርዓት የወጣችው በ2010 ዓ. ም ነበር፡፡ ጥብቅ ክርስቲያን አማኞች ያሏት ቶንጋ ከእንግሊዝ ነጻ የሆነችው በ1970 ዓ.ም ነበር፡፡ ቶንጋ ምን አይነት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ የሌላት አገር ተደርጋ ትታያለች፡፡ ማዕድን አልባም ናት ይባላል፡፡ ይህ ነው የሚባል የተፈጥሮ ማዕድን ሀብት ባይኖራትም በዓሣ ሀብት ራሷን ትደጉማለች፡፡ ሌላው የገቢ ምንጭ እርሻ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ቶንጋዊያውን ከውጭ አገር የሚልኩት ገንዘብ ነው፡፡ ብዙዎቹ ቶንጋዊያን ያሉት በኒዊዚላንድ ነው፡፡ በአገሪቱ የሥራ አጥ ቁጥር ከፍ ያለ ነው፡፡ ያም ሆኖ የውጭ ምንዛሬዋን የምታገኝበት አንዱ ቀዳዳ ቱሪዝም ስለነበር ኮቪድ ባይደርስባትም ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት አድርሶባታል፡፡ 5. ሰሙዋ በፓስፊክ ውቅያኖስ የምትገኘው ሰሙዋ እስከ 1961 ዓ. ም ድረስ በኒውዚላንድ ሥር ነበር የምትተዳደረው፡፡ 9 የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ነው የፈጠሯት ይቺን አገር፡፡ ሆኖም 99 ከመቶ ሕዝቧ የሚኖረው በኡፖሉና ሳቫይ ደሴቶች ነው፡፡ ዋና ከተማዋ አፒያ ይባላል፡፡ ምጣኔ ሀብቷ በእርሻና በዓሣ ሀብት የተንጠለጠለ ነው፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቱሪዝም ሞቅ ደመቅ ብሎላት ነበር፡፡ በተለይ ያማሩ የባሕር ዳርቻዎቿ ተወዳጅ ሆነውላታል፡፡ ከቱሪዝም ጋር የባሕር ማዶ ዓለም አቀፍ ኦፍሾር የባንክ አገልግሎት በማሳለጧ ሀብታሞች ሸሸግ ማድረግ የፈለጉትን ገንዘብ ይዘው እዚያ ይሄዳሉ፡፡ አንድም ለመዝናናት፣ አንድም ለባንክ አገልግሎት፡፡ 200ሺህ የማይሞላው ሕዝቧ የወግ አጥባቂ ባህልና የጥብቅ ክርስትና ተከታይ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ዜጎቿ ወደ ኒውዚላንድና ሌሎች አገሮች እየተሰደዱ ገንዘብ ወደ ቤተሰብ ይልካሉ፡፡ ኮሮና በሌሎች አገሮች ያደረሰው ጉዳት ሕመሙ ተሰምቷል፣ ሩቅ በምትገኘው በሰሙዋ ደሴት፡፡ 6.ቱቫሉ ቱቫሉን የፈጠሩት 9 ደሴቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ 5ቱ እሳተ ገሞራ ወልዶ፣ አሳብጦ፣ በድጋሚ አስምጦ ዳግም የወለዳቸው (ኮራል አቶልስ) ናቸው፡፡ የተቀሩት አራቱ ደግሞ ሕዝብ በደንብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቱቫሉ በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ ነው የምትገኘው፡፡ ፉናፉቲ ይባላል ዋና ከተማዋ፡፡ በቱቫሉ ተራራ አይታሰብም፡፡ ከባሕር ጠለል በላይ ከ4.5 ሜትር ከፍ ያለ ቦታ የለም፡፡ የአየር ንብረት በቱቫሉ ትልቁ ጉዳይ ቢሆን የማይገርመውም ለዚሁ ነው፡፡ የባሕር ጠለል ከፍታ ከምድረ ገጽ ከሚያጠፋቸው አገሮች አንዷ ቱቫሉ ነው የምትሆነው፡፡ በቱቫሉ ወንዝም ምንጭም ስለሌለ ኑሮ የዝናብ ጥገኛ ነው፡፡ የኮኮናት ተክል የአገሪቱ ገቢ ምንጭ ነው፡፡ ይህ ገቢ እንዲታወክ ምክንያት በመሆኑ ኮቪድ ቱቫሉ ባይገባም ገብቷል፡፡ 7. ናውሩ በዓለም ትንሽዋ አገር ናውሩ ናት፡፡ ይቺ ደሴት ስሟ በቅርብ ጊዜ ይነሳ የነበረው አውስትራሊያ አገሪቱን እንደ ጓሮ እየተጠቀመቻት ነው በሚል ነው፡፡ ናውሩ ስደተኞች ማጎርያ አለ፤ ንብረትነቱ የአውስትራሊያ የሆነ፡፡ ይሄ ማጎርያ ታዲያ ለናውሩ አንድ የገቢ ምንጭ መሆኑ ይገርማል፡፡ ናውሩዎች አንዱ ሥራ ቀጣሪ ኢንደስትሪያችሁ ምንድነው ቢባሉ የአውስታራሊያ የስደተኛ ካምፕ ብለው ሊመልሱ ይችላሉ፡፡ ከ2013 ጀምሮ አውስትራሊያ በጀልባ ወደ አገሯ ሊገቡ የሚሞክሩ ስደተኞችን በሙሉ ወደ ናውሩ ነው የምትወስዳቸው፡፡ ካልሆነም ፓፓው ኒው ጊኒ፡፡ ከአውስትራሊያ 3ሺህ ኪሎ ሜትር ርቃ በሰሜን ምሥራቅ ፓስፊክ አቅጣጫ የምትገኘው ናውሩ የዜጎቿ ብዛት 10 ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ናውሩን የሚያኖራት እርዳታ ነው፡፡ ሌላው ብቸኛ ሀብቷ ፎስፌት ማዕድን ነው፡፡ በናውሩ የውጭ ጋዜጠኛ ሄዶ መዘገብ አይችልም፡፡ ምክንያቱም በካምፖቹ ውስጥ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ያጋልጣል፡፡ ይህ ደግሞ ናውሩ የገቢ ምንጬን ሊጎዳብኝ ይችላል ትላለች፡፡ ናውሩን በዓመት የሚጎበኛት ሰው ከ200 አይበልጥም ይባላል፡፡ ቴሌግራፍ በአንድ ዘገባው በናውሩ እስከዛሬ የገባው ቱሪስት ቢደመር ከ15ሺህ አይበልጥም ሲል ጽፏል፡፡ በስፋት ቫቲካን ሲቲና ሞናኮ ብቻ ናቸው የሚበልጧት፤ ለዚህም ነው የዓለም ትንሽዋ ሪፐብሊክ ደሴት የምትባለው፡፡ ቱሪስት የአገሪቱ ገቢ ምንጭ አለመሆኑ በኮቪድ-19 አልተጎዳችም ማለት ግን አይደለም፡፡ ለጊዜው ከ10ሺህ ዜጎቼ አንድም ሰ�� ኮቪድ-19 አልያዘውም ብትልም ሕመሙ ግን ናውሩም ደርሷል፡፡ 8. ኪሪባቲ ኪሪባቲ የብጥስጣሽ ደሴቶች አገር በመሆኗ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ 4ሺህ ኪሎ ሜትር፣ ከሰሜን ደቡብ ደግሞ 2ሺህ ኪሎ ሜትር ታስኬዳች፡፡ ይህ ማለት ግን ይህ ሁሉ ርቀት ሰው የሚኖርበት ደረቅ መሬት ነው ማለት አይደለም፡፡ ነጻነቷን ያገኘችው ከእንግሊዝ በ1979 ዓ.ም ነው፡፡ በ1960ዎቹ ይቺ አገር አንዳንድ ደሴቶቿ ለእንግሊዝ የኑክሌር መሞከሪያ ሆነው አገልግለዋል፡፡ እንደ ብዙዎቹ የፓስፊክ ደቂቀ ደሴቶች ሁሉ ኪሪባቲም የዓለም ሙቀት መጨመር ከምድረ ገጽ ሊያጠፋት እንደሚችል ይገመታል፡፡ ኪሪባቲ ከፊጂ ደሴት መሬት ተከራይታ ምግብ ታመርታለች፡፡ ኢኮኖሚዋ ደካማ ሲሆን ኮኮናትና ኮፕራ በመላክ ነው የምትታወቀው፡፡ የዓሣ ማጥመድ ፍቃድ ለውጭ ኩባንያዎች እየቸበቸበች ኢኮኖሚዋን በከፊል ትደጉማለች፡፡ 9ኛ የሰለሞን ደሴቶች፤ 10ኛ ማይክሮኒዢያ በዝርዝሩ 9ኛ እና 10ኛ ላይ ያሉት የሰለሞን ደሴቶች እና ማይክሮኒዢያ ናቸው፡፡ ሁለቱም አገራት በዓሣ ምርትና በቱሪዝም ይታወቃሉ፡፡ ሁሉም በኮቪድ-19 የተጠቃ ዜጋ የለባቸውም፡፡ ይህ ዝርዝር ታዲያ ሰሜን ኮሪያና ቱርከሜኒስታን አላካተተም፡፡ ሆኖም እነዚህ ሁለት አገራት በይፋ ከኮቪድ-19 የያዘው ዜጋ አለም የለምም ብለው አያውቁም፡፡ ወይም አይታመኑ ይሆናል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-53864759 +sports ‹‹ባል›› የብዙዎችን ሕይወት ይቀይራል የተባለለት የአፍሪካ አዲሱ የቅርጫት ኳስ ሊግ ‹‹አፍሪካ፤ መጥተናል፤ ጨዋታው ይጀመር›› በሚሉት ቃላት ነበር ለአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የቅርጫት ኳስ ሊግ ወይም ባል ሴኔጋላዊ ፕሬዘዳንቱ አማዱ ጋሎ ፋል ያስጀመሩት፡፡ የመጀመሪያው የሊጉ ጨዋታ እሁድ በናይጄሪያ እና በሩዋንዳ መካከል ተካሂዶ ናይጄሪያ የመጀመሪያውን ጎል በማስቆጠር ታሪካዊ ብትሆንም ሩዋንዳ ጨዋታውን 83 ለ 60 ረትታለች፡፡ በሜዳዋ እና በደጋፊዎቿ ፊት የተጫወተችው ሩዋንዳ ክፍተኛ ድጋፍ እንደነበራትም ተዘግቧል፡፡ ‹‹ይሄ የብዙዎችን ህይወት ይቀይራል፡፡ በመላው አህጉሩ ላሉ ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን ለመመገብ የሚያስችል እና ሌሎች በርካታ እድሎችን የሚፈጥር ነው›› ሲል የቀድሞው የኤን.ቢ.ኤ ተጫዋች እና አሁን ለናይጄሪያ ተሰልፎ የሚጫወተው ቤን ኡዞ ለቢቢሲ ስፖርት ተናግሯል፡፡ ‹‹ይህ የአፍሪካ ኤን ቢኤ ነው፣ እናም በዚህ አህጉር ለሚያድጉ ልጆች ይህ የራሴ ብለው የሚጠሩት እና የመጪውን ግዜ ተጫዋቾች የምናፈራበት ነው›› ሲልም አክሏል፡፡ የሊጉ ጨዋታዎች ከአንድ አመት በፊት እንዲጀመሩ እቅድ ተይዞላቸው የነበረ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለ14 ወራት ዘግይቶ ተጀምሯል፡፡ በዚህ የመጀመሪያው የውድድር አመት ከ12 አገራት የሚወጣጡ ቡድኖች የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡ አንጎላ፣ ግብጽ፣ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል እና ቱኒዚያ እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡ ቀሪ ስድስት ቡድኖች የማጣሪያ ጨዋታዎችን አድርገው ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የዚህ አመት የሊጉ ጫዋታዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በሩዋንዳዋ ዋና ከተማ በሚገኛው እና 10 ሺህ ሰው በሚይዘው የኪጋሊ አሬና ይካሄዳል፡፡ በእያንዳንዱ ጨዋታም 1ሺህ500 አካባቢ ታዳሚዎች እና ተጋባዥ እንግዳዎች ይከታተሉታል፡፡ በሊጉ 26 ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን እስከ ፍፃሜው ጨዋታ ድረስ ሁለት ሳምንታትን የሚፈጅ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-57127671 +sports በፕሪሚየር ሊጉ የጥር ወር የዝውውር መስኮት ማን ማንን አስፈረመ? የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጥር ወር የዝውውር መስኮት በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ትናንት እኩለ ለሊት ላይ ተጠናቋል። ከዚህ በታች የትኞቹ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ማንን አስፈረሙ የሚለውን እንመለከታለን። ኒውካስትል ዩናይትድ ለጥቂት ሳምንታት በቆየው የዝውውር መስኮት በርካታ ተጫዋቾችን ካስፈረሙ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቀዳሚ ስፍራን የሚይዘው ኒውካስትል ነው። ኒውካስትል ብሩኖ ጉዊማሬዝን ጨምሮ ስመ ጥር እግር ኳሰኞችን በዚህ የጥር ወር የዝውውር መስኮት መያዝ ችሏል። ብሩኖ ጉዊማሬዝን ከፈረንሳዩ ሊዮን በ35 ሚሊዮን ፓዎንድ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ አምርቷል። ኒው ካስትል የግራ መስመር ተመላላሹን ማት ታርጌት ከአስተን ቪላ በውሰት ወስዷል። የ26 ዓመቱ ታርጌት እስከ የውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ በሴንት ጀምስ ፓርክ የሚቆይ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም ኒውካስትል ዳን በርን ከብራይተን በ13 ሚሊዮን ፓውንድ በማስፈረም የተከላካይ መስመሩን አጠናክሯል። ክሪስ ውድ ከበርንሊ ወደ ኒውካስትል በ25 ሚሊዮን ፓውንድ ተዘዋውሯል። በጥሩ የዝውውር መስኮት ኒውካስትልን ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች መካከል ብዙ ልምድ ያለው የ31 ዓመቱ ተከላካይ ኪረን ትሪፒየር ይገኝበታል። ቲሪፒየር እስከ ቀጣይ ዓመት የውድድር ዘመን ማብቂያ ድረስ በ12 ሚሊዮን ፓውንድ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ኒውካስትልን ተቀላቅሏል። ኤቨርተን ፍራንክ ላምፓርድን አሰልጣኙ አድርጎ የቀጠረው የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን በዚህ የዝውውር መስኮት ብዙ ተጫዋቾችን ካስፈረሙ ክለቦች መካከል አንዱ ነው። የኤቨርተን የጥር ወር ትልቁ ፈራሚ የቶተንሃም ተጫዋች የነበረው ዴሊ አሊ ነው። ዴሊ አሊ እስከ 40 ሚሊዮን ፓውንድ ሊደርስ በሚችል ወጪ ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ወደ ሊቨርፑል ከተማ መጥቷል። ኤቨርተን ቢሊ ክሬሊን ከፍሊትዉድ ታውን ይፋ ባልተደረገ መጠን አዘዋውሯል። ሌላው የኤቨርተን የጥር ወር ትልቁ ፈራሚ የማንችስተር ዩናይትዱ ዶኒ ቫን ደ ቢክ ነው። በኦልትራፎርድ በቂ የጨዋታ ጊዜን እያሳለፈ ያልነበረው አማካዩ ቫን ደ ቢክ በውሰት ወደ ኤቨርተን አቅንቷል። ኤቨርተን የአስተን ቪላውን አንዋር ኤል ጋዚን በውሰት ሲወስድ ከሬንጀርስ ደግሞ የቀኝ ተመላላሹ ናታን ፒተርሰንን በ12 ሚሊዮን ፓውንድ ለአምስት ዓመታት አስፈርሟል። ሊቨርፑል ሌላኛው የመርሲሳይድ ክለብ ሊቨርፑል ሉዊዝ ዲያዝን ከፖርቶ አስመጥቷል። ክሎፕ ለኮሎምቢያዊው የክንፍ ተጫዋች 37 ሚሊዮን ፓውንድ በመክፈል ለቀጣይ አምስት ዓመታት አስፈርመውታል። ቶተንሃም የሰሜን ለንደኑ ክለብ ንዶምብሌን አሰናብቶ ሁለት የጁቬንቱስ ተጫዋቾችን ወደ ሰሜን ለንደን አምጥቷል። የኡራጋዩ አማካይ ሮድሪጎ ቤንታንኩር ለቀጣይ 4 ዓመታት በሰሜን ለንደኑ ክለብ ለመቆየት ውል ያኖረ ሲሆን፤ የስዊድኑ የክንፍ ተጫዋች ዴጃን ኩሉሴቪስኪ ለ18 ወራት በውሰት ቶተንሃምን ተቀላቅሏል። በሌላ በኩል ቶተንሃም ክብረ ወሰን በሆነ ዋጋ ያስፈረመውን ንዶምብሌን በውሰት ለሊዮን ሰጥቷል። አርጀንቲናዊው ጂኦቫኒ ሎ ሴልሶ ቪላሪያን እንዲሁም የ20 ዓመቱ ታዳጊ ብራያን ጊል ቫሌንሺያን እስከ ውድድሩ ዘመኑ መጠናቀቂያ በውሰት ተቀላቅለዋል። አስተን ቪላ ሉካስ ዲኘ ከኤቨርተን ወደ ቪላ በ25 ሚሊዮን ፓዎንድ ተዘዋውሯል። የፈረንሳዩ የግራ መስመር ተጫዋች በኤቨርተን ቆይታው ተመራጭ ሳይሆን በመቅረቱ ክለቡ እንዲለቀው ጥያቄ አቅርቦ ነበር ተብሏል። የበርካቶችን ቀልብ ስቦ የነበረው የስቲቨን ጄራርድ ፈራሚ ብራዚላዊው ፊሊፔ ኩቲኒዮ ነው። ኩቲንሆ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ከባርሴሎና በውሰት ወደ ቪላ መጥቷል። ቪላዎች የአርሰናሉን ተከላካይ ካለም ቻምበርስን በነጻ ወስደዋል። ስዊዲናዊው ግብ ጠባቂ ሮቢን ኦሴን ከጣሊያኑ ሮማ አስንተን ቪላን በውሰት ተቀላቅሏል። ማንችስተር ሲቲ የፕሪሚየር ሊጉን ሰንጠረዥ በሰፊ የነጥብ ልዩነት እየመሩ የሚገኙት ሲቲዎች አርጀንቲናዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ለአምስት ዓመታት አስፈርመዋል። ከሪቨር ፕሌት ሲቲን የተቀላቀለው ጁሊያን አልቫሬዝ እስከ ሐምሌ ድረስ በክለቡ ይቆያል። ብሬንትፎርድ የክርስቲያን ኤሪክሰን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለስ የበርካቶችን ልብ በደስታ ያሞቀ ይመስላል። የቀድሞ የቶተንሃም ተጫዋች በ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር አገሩን ዴንማርክን ወክሎ እየተጫወተ ሳለ በልብ ሕመም ተዝለፍልፎ ሜዳ ላይ ወድቆ እንደነበረ ይታወሳል። የ29 ዓመቱ ኤሪክሰን በአውሮፓ ዋንጫ ላይ ካጋጠመው ክስተት በኋላ እግር ኳስ ባይጫወትም፤ ብሬንትፎርድ ለስድስት ወራት አስፈርመውታል በተመሳሳይ አርሰናል በርካታ ተጫዋቾቹን ከኤሜሬትስ አሰናብቶ፤ ለአሁናዊ ችግሩ መፍትሄ ሊሰጥ የሚችል አዲስ ተጫዋች ወደ ኤሜሬትስ ማምጣት ተስኖታል። የሚኬል አርቴታው አርሰናል፤ ጎል አዳኙን ፒዬር ኦባሚያንግ በነጻ ለባርሴሎና አሳልፎ ሰጥቶ ተተኪውን አጥቂ ማስፈረም ሳይችል የውድድር መስኮቱ ተዘግቷል። https://www.bbc.com/amharic/news-60218464 +health ኮሮናቫይረስ ፡ አውስትራሊያ 85 ሚሊዮን ክትባቶች ለዜጎቿ ልታቀርብ ነው "የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚንስትር አሁን እየበለጸጉ የሚገኙት ሁለቱ ክትባቶች ስኬታማ የሚሆኑ ከሆነ 85 ሚሊዮን ክትባቶችን መንግሥት ለሕዝቡ እንደሚያቀርብ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት ሞሪሰን አገራቸው የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቿ በነጻ ለማቅረብ ሁለት የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለመግዛት ስምምነቶችን ፈርማለች ብለዋል። እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሆነ አውስትራሊያ ክትባቶቹን ለመግዛት 1.24 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ታደርጋለች። ""25 ሚሊዮን አውስትራሊያውያን ከየካቲት 2013 ጀምሮ ክትባቱን ማግኘት ይችላሉ ለዚህ ግን ማረጋገጫ የለም"" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት የካቲት ላይ ለዜጎች ክትባቱን በነጻ ማቅረቡ መቶ በመቶ እርግጠኛ ባይሆንም የአገሪቱ የጤና ባለሙያዎች ክትባቶቹ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይሁንታቸውን የሚሰጡ ከሆነ፤ አውስትራሊያ ክትባቶቹን ቀድማ እንደምታገኝ ጠቁመዋል። አንደኛው ክትባት በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና በመድኃኒት አምራቹ ኩባንያ አስትራዜኔካ ጥምረት እየበለጸገ የሚገኝ ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ በአውስትራሊያው ኩዊንስላንድ ዩኒቨርሲቲ እና ሲኤስኤል የሚመረት ነው። አውስትራሊያ ለመግዛት ውል ከያዘችው መካከል 33.8 ሚሊዮን ክትባት ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን 51 ሚሊዮን የሚሆነው ደግሞ በኩዊንስላንድ ዩኒቨርሲቲ የሚመረተውን ነው። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየተዘጋጀ የሚገኘው ክትባት በሦስተኛ ደረጃ ክሊኒካዊ ሙከራ ላይ የደረሰ ሲሆን በ30ሺህ ሰዎች ላይ ክትባቱ ተሞክሯል። በመላው ዓለም የሚገኙ አገራት የኮሮናቫይረስ ክትባት እንዲደርሳቸው የተለያዩ አይነት ጥረቶችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ሐምሌ ወር ላይ የዓለም ጤና ድርጅት 165 የዓለም አገራት፤ ድሃ አገራት ክትባቱን ለዜጎቻቸው እንዲያደርሱ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት ማሳየታቸውን አስታውቆ ነበር። በዓለም ዙሪያ በአሁኑ ወቅት 140 የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለማበልጸግ ምርምሮች እየተከናወኑ ይገኛሉ። አውስትራሊያ እስካሁን ድረስ ከ26ሺህ በላይ ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን 769 ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54053426 +health የኮቪድ ወረርሽኝ ትልቅ አደጋ ነው - ኪም ጆንግ ኡን "በሰሜን ኮሪያ በፍጥነት እየተዛመተ ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለሀገሪቱ ""ትልቅ አደጋ"" ነው ሲሉ መሪዋ ኪም ጆንግ ኡን መናገራቸውን የመንግሥት ሚዲያዎች ዘግበዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ ሞት መመዝገቡን ያስታወቀችው ሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም በያዝነው ሳምንት ቅዳሜ ዕለት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሁለንተናዊ ትግል እንዲደረግ ጠይቀዋል። ባለስልጣናቱ በያዝነው ሳምንት ሃሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው መረጋገጡን አስታውቀዋል። ባለሙያዎች በበኩላቸው አሁን ተያዙ የተባሉት የመጀመሪያ እንዳልሆኑና ለተወሰነ ጊዜ እየተዛመተ ነበር ይላሉ። በሰሜን ኮሪያ ወረርሽኙ ከፍኛ ሊሆን እንደሚችልና አስከፊ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋትም ጭሯል። 25 ሚሊዮን ነዋሪዎቿ በክትባት መርሃ ግብር እጥረት እና በደካማ የጤና አጠባበቅ ስርአት ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ መሆናቸውም ተገልጿል። ባለፉት ሳምንታት ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በማይታወቅ ትኩሳት እንደተጠቁ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ቅዳሜ እለት ዘግበዋል። የሃገሪቱ የመመርመር አቅምም የተገደበ በመሆኑ በኮቪድ-19 ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም። ይህ አኃዝ አርብ እና ሐሙስ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህም ሁኔታ በሰሜን ኮሪያ እየተከሰተ ስላለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አንዳንድ ፍንጮችን ይሰጣል ተብሏል። ""የከፋው ወረርሽኝ በአገራችን ላይ የወደቀ ትልቅ አደጋ ነው"" በማለት መሪው መናገራቸውን የኬ ሲ ኤንኤ የዜና ወኪል ዘግቧል። ኪም ለዚህ ችግር መንስኤ ያሉትን የቢሮክራሲ ቀውስ እና የህክምና ብቃት ማነስ እንደሆነ ጠቁመው እንደ ጎረቤት ቻይና ካሉ ሀገራት ምላሽ መማር እንደሚቻልም ጠቁመዋል። ከሚያዝያ ወር ጀምሮ 27 ሰዎች ትኩሳት ካጋጠማቸው በኋላ መሞታቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል። በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ በኦሚክሮን ልውጥ ከሞተው አንድ ሰው በስተቀር እነዚህ ግለሰቦች ኮቪድ- 19 ተይዘው ነበር ወይ ስለሚለው ጉዳይ ሪፖርቶቹ ያሉት ነገር የለም።" https://www.bbc.com/amharic/news-61454622 +sports እየተካሄደ ስላለው የአፍሪካ ዋንጫ ሊያውቋቸው የሚገቡ አንኳር ነጥቦች "የፈረንጆቹ 2022 የመጀመሪያውና ትልቁ የእግር ኳስ ድግስ በሚቀጥለው እሑድ በካሜሩን መዲና ያውንዴ ይጀመራል። የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግን ጨምሮ በሌሎች ሊጎች የምናውቃቸው ኮከቦች መናኸሪያቸውን ካሜሩን አድርገዋል። በመክፈቻው ጨዋታ አዘጋጇ ካሜሩን ቡርኪና ፋሶን ታስተናግዳለች። ለጥቆ ደግሞ ኢትዮጵያ ከኬፕ ቨርድ ትገናኘለች። የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ሊካሄድ የነበረው ባለፈው ዓመት ጥር ነበር። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ዓመት ተራዝሞ ወደ ዘንድሮ ተሸጋግሯል። የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪ ካፍ ባለፈው ወር ውድድሩን በኦሚክሮን ዝርያ መስፋፋት ምክንያት ያራዝመዋል ተብሎ የተናፈሰው ወሬ ሃሰት ነው ማለቱ ይታወሳል። የቀድሞው የአርሰናልና የእንግሊዝ አጥቂ የነበረው ኢያን ራይት መገናኛ ብዙሃን ስለአፍሪካ ዋንጫ ሲዘግቡ ""በንቀትና የዘረኝነት መንፈስ ተላብሰው ነው"" ሲል ወቅሶ ነበር። የጨዋታው ሰንጠረዥ ምን ይመስላል? የአፍሪካ ዋንጫ 24 ብሔራዊ ቡድኖችን ያሳትፋል። ይህ በውደድሩ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ይህ ማለት እያንዳንዳቸው አራት ቡድኖችን ያቀፉ ስድስት ምድቦች አሉት ማለት ነው። ከእነዚህ መካከል አንደኛና ሁለተኛ የሚወጡት ወደ ቀጣዩ ዙር በቀጥታ ሲያልፉ፤ አራት ምርጥ ሶስተኛ ቡድኖችም ወደ ዙር 16ን ይቀላቀላሉ። የምድብ ጨዋታዎች ቀን 10 ሰዓት እንዲሁም ምሽት 1 ሰዓትና ማታ 4 ሰዓት ይከናወናሉ። በቀጣዩ የጥሎ ማለፍ ውድድር ጊዜ ደግሞ `ጨዋታዎቹ ማታ 1 እና 4 ሰዓት ይታያሉ። ለዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጥቅም ላይ የሚውለው ኳስ ቶጉ የሚባል ካሜሩን ውስጥ ታዋቂ ከሆነ ጨርቅ ስሙን ያገኘ ኳስ ነው። ለዋንጫ እነማን ይፎካከራሉ? በማንችስተር ሲቲው የክንፍ ተጫዋች የምትመራው ያለፈው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ አልጄሪያን ለዋንጫው አለማጨት ከባድ ነው። የሳድዮ ማኔ ሃገር ሴኔጋል በአፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች ሰንጠረዥ አናት ላይ የምትገኝ ሲሆን ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ በአልጄሪያ ተረታ ሁለተኛ መሆኗ አይዘነጋም። ያለፉትን 34 ጨዋታዎች ሽንፈት ካላስተናገደችው አልጄሪያና ከሴኔጋል ቀጥሎ በወቅቱ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ኮከብ ሞሐመድ ሳላህ የምትመራው ግብፅም ስሟ ለዋንጫ ከሚቀናቀኑ መካከል ይነሳል። ግብፅ የአፍሪካ ዋንጫ ለሰባት ጊዜ በማንሳት የሚገዳደራት የለም። ጋና እና ናይረጄሪያ በአፍሪካ በጣም ውጤታማ ከሚባሉ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ቢሆኑም ለ2022 የዓለም ዋንጫ ያደረጉት ጉዞ ግን ብዙም አሳማኝ አልነበረም። ለስድስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ለማንሳት የምትፋለመው ካሜሩን ደግሞ በሕዝቧ ፊት ዋንጫውን ለማስቀረት ትጥራለች። የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ጨዋታዎችን ያለምንም ሽንፈት ያከናወነችው ማሊ የውድድሩ ክስተት ልትሆን ትችላለች። አይቮሪ ኮስት፣ ሞሮኮና ቱኒዚያም ከዚህ በፊት ውድድሩን ያነሱ ቡድኖች ሲሆኑ ኮሞሮስና ጋምቢያ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሳተፉ ይሆናል። ውድድሩ የሚካሄድበት ወቅት አንዳንድ የአውሮፓ ሊግ ክለቦች ተጫዋቾችን በዚህ ወቅት አንለቅም በማለት ብዙ ግርግር አስነስተው ነበር። ዋትፈርድ የተሰኘው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ክለብ ለምሳሌ የናይጄሪያውን ኢማኔኤል ዴኒስ አልለቅም በማለት ክርክር አስነስቶ ነበር። ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ በሚቀጥለው ዓመት ሰኔና ሐምሌ በአይቮሪ ኮስት አዘጋጅነት ይካሄዳል። የፊፋው አለቃ ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የብሔራዊ ቡድን ውድድሮች በመስከረምና ኅዳር መካከል ይከናወኑ የሚል ሐሳብ አቅርበዋል። የኮሮናቫይረስ ጉዳይ? ወረርሽኙ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ጥላውን ማንዣበቡ አልቀረም። ካፍም የታዳሚዎችን ቁጥር 60 በመቶ ቀንሷል። አዘጋጇ ካሜሩን የምታደርጋቸው ፍልሚያዎች 80 በመቶ ታዳሚ እንዲኖራቸውና ሁለት ጊዜ የተከተቡና የኮቪድ ውጤታቸው ኔጌቲቭ የሆኑ ሰዎች ናቸው ወደ ስታድዬም መግባት የሚችሉት። እስካሁን 2 በመቶ ሕዝቧ ብቻ የተከተበው ካሜሩን በሚቀጥሉት 30 ቀናት ሕዝቧ ለጨዋታው በማለት ወደ ክትባት ጣቢያዎች ያመራ ይሆን የሚለው አጓጊ ሆኗል። በኢትዮጵያ ምድብ የምትገኘው ኬፕ ቨርደን ጨምሮ የተወሰኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫቾች እንዲሁም ጋምቢያ ልምምድ እያደረጉ በሚገኙበት ካምፕ ወረርሽኙ አግኝቷቸው ነበር። የ2019 የአፍሪካ ዋንጫን እንድታስተናግድ ተመርጣ የነበረችው ካሜሩን በቂ መሠረተ ልማት የላትም ተብሎ ውድድሩ ወደ ግብፅ መዛወሩ ይታወሳል። ካሜሩን የደህንነት ጉዳይም ያሳስባታል። በደቡብ ምዕራብ የምትገኘው የሊምቤ ከተማ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በታጣቂዎች ጥቃት እየታመሰች ትገኛለች። ውድድሩን እንዴት መከታተል እችላለሁ? ቢቢሲ፤ ሁለት የሩብ ፍፃሜ ፍልሚያዎች፣ ሁለት የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያችና ፍፃሜውን ጨምሮ 10 የተመረጡ ጨዋታዎችን ያስተላልፋል። ስካይ ስፖርት የተሰኘው ጣቢያ ሁሉንም ጨዋታዎች በቴሌቪዥን ሲያስተላልፍ፤ ሱፐርስፖርት፣ ቤይንስፖርትና ካናልፕላስ ካሜሩን ተገኝተው ውድድሩን በቴሌቪዥን መስኮት ከሚያቀርቡ መካከል ናቸው። የቢቢሲ ስፖርት ድረ-ገፅ ደግሞ ከስር ከስር ሁሉንም ክስተቶች እየተከታተለ ይዘግብላችኋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59904953 +business 3.7 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የብር ኖቶች ምን ይዘዋል? "የወረቀት የብር ኖቶች በኢትዮጵያ የግብይት ሥርዓት ውስጥ ጥቅም ላይ መዋል ከጀመሩ በኋላ አገሪቱ ለ7ኛ ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ማድረጓን መስከረም 04/2013 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል። በብዙዎች ዘንድ የባንክ ኖቶች ለውጥ ሊኖር ይችላል የሚለው ግምት መነገር ከጀመረ ጥቂት ዓመታ�� ተቆጥረዋል። አሁን ግን አዲሱ ዓመት በገባ በአራተኛው ቀን ምንም ነገር ሳይሰማ ይፋ የተደረገው የብር ለውጥ አገሪቱ እያካሄደችው ካለው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብር በዘመናት ሂደት ውስጥ በርካታ ለውጦችን ያስተናገደ ሲሆን፤ ከዋጋ አንጻርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ አሁን ካለበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና የሐሰተኛ የብር ኖት በገበያው ውስጥ በተደጋጋሚ መከሰታቸው በተለያዩ ጊዜያት ሲዘገብ ቆይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የብር ለውጡ ለሕገ ወጥ ተግባራት የሚውለውን ገንዘብ ለማስቀረት፣ ሙስናንና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር ይረዳል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በአገሪቱ ያጋጠመውን የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መዛባትን ለማስተካከል ባለፉት ሁለት ዓመታት የተለያዩ ጥረቶች በመደረጋቸው ምጣኔ ሀብቱ ከነበረበት ችግር በመውጣት በማንሰራራት ላይ መሆኑን አመልክተዋል። ጨምረውም በአገሪቱ ያለውን የዋጋ ንረት የመቆጣጠሩ ተግባር በሚፈለገው መጠን ማከናወን እንዳልተቻለ ጠቅሰው፤ ለዚህ ደግሞ ከባንክ ውጪ የሚንቀሳቀስ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ መኖሩ ደግሞ ችግሩን በማባባሱ የብር ኖት መቀየር አንድ መፍትሄ መሆኑን ተናግረዋል። ምን ተለወጠ? አዲሶቹ የብር ኖቶች ቀደም ሲል ከነበሩት በተሻለ ለአጠቃቀም ምቹና ረዥም ጊዜ እንዲያገለግሉ ተደርገው መሰራታቸ የተገለጸ ሲሆን፤ ኖቶቹን በመቀየሩ ሥራ ለህትመት ብቻ በአጠቃላይ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገ ተነግሯል። ከቀለም አንጻር አዲሱ ባለ 200 ብር ኖት ሐምራዊ፣ ባለ100 ብር ኖት ውሃ ሰማያዊ፣ ባለ50 ብር ኖት ቀይ ብርቱካናማ፣ ባለ10 ብር ኖት ደግሞ አረንጓዴ ቀለም አላቸው። ቀደም ሲል በዝውውር ውስጥ የቆየው የባለ5 ብር ኖት ለውጥ ሳይደረግበት በሥራ ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ ነገር ግን የወረቀት ገንዘቡ ቀስ በቀስ በሳንቲም እንደሚተካ ተገልጿል። በአዳዲሶቹ የብር ኖቶች ላይ ቀደም ሲል በነበሩት ላይ ያልነበሩ የአገሪቱን ገጽታ የሚያሳዩ ምስሎች የተካተቱበት ሲሆን፤ በዚህም በባለ አስር ብር ኖት ላይ ግመል፣ በባለ መቶ ብር ኖት ላይ ደግሞ የሶፍ ኡመር ዋሻና የሐረር ግንብ እንዲካተቱባቸው ተደርጓል። ከባንክ ውጪ ያለ ብር የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ እንዳመለከቱት ""ከኢትዮጵያ ውጪ በጎረቤት አገራት ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያ ብር ተከማችቶ ይገኛል።"" ከብር ለውጡ ጋር ተያይዞም በውጪ አገራት ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብር ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት ብሔራዊ ባንክ ያወጣው ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ በቤት ውስጥ ማስቀመጥ የሚከለክለው ሕግም ተግባራዊ መሆኑ የሚቀጥል ሲሆን፤ ይህንን ደንብ በመተላለፍ የሚንቀሳቀስ ገንዘብ በቁጥጥር ስር ውሎ ለመንግሥት አገልግሎት ይውላል። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በየጊዜው ድንገተኛ ፍተሻ እንደሚኖርም ተገልጿል። የብር ለውጥ ሂደት ላለፉት 23 ዓመታት በዝውውር ላይ የነበሩትን የብር ኖቶች ከገበያ በማስወጣት በአዲሶቹ የመተካቱ ሂደት በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚከናወን የጊዜ ሰሌዳ ተቀምጧል። ነገር ግን አሮጌዎቹን የብር ኖቶች በአዲስ በመተካቱ ሂደት ውስጥ 100 ሺህ እና ከዚያ በላይ ብር ያላቸው ሰዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መቀየር እንዳለባቸው ተገልጿል። በዚህ ሂደት ውስጥ እስከ 10 ሺህ ብር ድረስ ለሚደረግ የብር ለውጥ ቀጥታ ገንዘቡን በመስጠት የሚከናወን ሲሆን፤ ከአስር ሺህ ብር በላይ የሚቀየር ከሆነ ደግሞ ብሩን ለመለወጥ ባመጣው ግለሰብ ስም የባንክ ደብተር ተከፍቶ እንዲቀመጥ ይደረጋል ተብሏል። የደኅንነት ገጽታዎች ይፋ የተደረጉት አዳዲሶቹ የብር ኖቶች አስመስለው የሚሰሩ ሐሰተኛ የብር ኖቶችን ለመከላከልና ለመለየት በሚያስችል ሁኔታ የተለያዩ የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታዎች እንዲኖሯቸው ተደርጓል። በተጨማሪም ለዓይነ ስውራን አጠቃቀም እንዲያመች የመለያ ምልክት ያለው ሲሆን፤ በዚህም ዓይነ ስውራን የብሩን ዋጋ በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት ምልክትና የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታ አላቸው። ከዚህ ባሻገርም የብር ኖቱ ወደ ላይ ወይም ወደታች በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታ ያለው ሲሆን፤ የብር ኖቶቱ በእጅ ሲዳሰሱ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም የብሩ ዋጋ ይታያል። አዲሶቹ ኖቶች ተጨማሪ ባለቀለም ኮከብ የደኅንነት ገጽታን ከማካተታቸው ባሻገር አብረቅራቂ የደኅንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስያሜ በምህጻረ ቃላት በአማርኛና በእንግሊዝኛ እንዲሁም የብሩ መጠን ሰፍሮ ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ አዲሶቹ የብር ኖቶችን ወደ ብርሃን አቅጣጫ በማዞር ሲታዩ ከፊት ከሚታየው ምስል ትይዩ ተመሳሳይ ደብዛዛ መልክ የያዘ ምልክት ይታያል። እንዲሁም የብር ኖቶቹ በብርሃን አቅጣጫ ሲታዮ ኳስ የሚመስሉ ምልክቶች ከኖቶቹ በስተጀርባ ካለው ተመሳሳይ ምልክት ጋር በፍፁም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ። የብር ለውጥ ታሪክ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙት የብር ኖቶች ወደ ዝውውር እንዲገቡ የተደረጉት ከ23 ዓመት በፊት በ1990 ዓ.ም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ እንደነበረ ይታወሳል። ከአጼ ኃይለ ሥላሴ አስተዳደር ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ሥራ ላይ በነበሩ የገንዘብ የወረቀት ገንዘቦች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ለውጥ የተደረገ ሲሆን፤ ወደ አምሳ ዓመታት በሚጠጋው የንጉሡ የሥልጣን ዘመን አራት ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ተደርጓል። ወታደራዊው መንግሥት ዘውዳዊውን ሥርዓት አስወግዶ አገሪቱን መምራት ከጀመረ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በ1969 ዓ.ም የንጉሡ ምስልን የያዙትን የመገበያያ ገንዘቦች ለውጦት ቆይቷል። በተመሳሳይም ኢህአዴግ ደርግን አስወግዶ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላም ለሰባት ዓመታት ያህል ቀድሞ የነበረውን ገንዘብ ሲጠቀም ቆይቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብር ኖቶቹ እንዲቀየሩ አድርጓል። በኢትዮጵያ ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ አገልግሎት ላይ የነበሩት የገንዘብ ኖቶች 1፣ 5፣ 10፣ 50 እና 100 ብር የነበሩ ሲሆን፤ ለረጀም ጊዜ ከፍተኛ ዋጋ ያለው የገንዘብ ኖት 100 ብር ሆኖ ቆይቷል። ቢሆንም ግን በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ ከዋሉት የብር ኖቶች መካከል የ2 ብር እና የ500 ብር ኖቶች ነበሩበት። ስለዚህም በአገሪቱ የወረቀት ገንዘብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የነበረው የብር ኖት ባለ 500 ብር ኖት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ከግብይት እንዲወጣ መደረጉን የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል። ስለዚህም አሁን ከወረቀት የብር ኖቶች መካከል እንዲገባ የተደረገው የባለ 200 ብር ኖት በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሲሆን ወደገበያ ሲገባም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የብር ኖት ለውጥ እንደሚደረግ በተለያዩ መንገዶች ሲነገር የቆየ ሲሆን፤ ከብር ዋጋ መቀነስ ጋር ተያይዞ 500 ዋጋ ያለው የብር ኖት ወደ ገበያ እንደሚገባ አንዳንድ ሰዎች ሲገልጹ ቆይተው ነበር። በአገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች መደረግ ከጀመሩባቸው ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንደሚካሄድ በጉምሩክና በፖሊስ በኩ��� በተደጋጋሚ የሚወጡ ሪፖርቶች የሚያመለክቱ ሲሆን፤ ይህም ለውጥ ያስፈለገው ይህንኑ ለመከላከል መሆኑ ተነግሯል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54145137 +health ሐኪሞች የንግሥት ኤልዛቤት የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ነው አሉ "የዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት የሆኑት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት ሐኪሞች የንግሥቲቱ ጤና አሳሳቢ ነው አሉ። የንግሥቲቱ ይፋዊ መኖሪያ ቤት ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት እንዳስታወቀው ንግሥት ኤልዛቤት ሁለተኛ በጤና ክትትል ስር እንደሚገኙ ይፋ አድርጓል። የንግሥት ኤልዛቤት ልጅ ልዑል ቻርልስ ንግሥቲቱ ወደሚገኙበት ባልሞራል ቤተ-መንግሥት አቅንተዋል። የ96 ዓመቷ የዩኬ እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት በ70 ዓመት የንግሥና ዘመናቸው በርካታ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦችን ተመልክተዋል። ከቀናት በፊት የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ሊዝ ትረስ በንግሥት ኤልዛቤት የንግሥና ዘመን 15ኛዋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል። የንግሥቲቱን የጤና መቃወስ ዜና መሰማቱን ተከትሎ አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ ""መላው አገር"" በዜናው ""እጅጉን ተረብሿል"" ብለዋል። የንግሥቲቱ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ተከትሎ በርካርታ የንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት ወደ ስኮትላንድ እያቀኑ ነው። ለባልሞር ቤተ-መንግሥት ቅርበት ባለው አበርዲን አየር መንገድ ከወትሮ በተለየ እንቅስቃሴ እየታየ ነው። ንግሥቲቱ ወዳሉበት ስኮትላንድ ከተጓዙት መካከል ልዑል ቻርልስ ይገኙበታል። የሰሴክስ መስፍን እና ሶፋኒት ሄሪ እና ሜጋን ወደ ስኮትላንድ እንደሚሄዱ የጥንዶቹ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። የዮርክ መስፍን ልዑል አንድሩ ወደ ስኮትላንድ እያቀኑ ሲሆን፣ ልዕልት አን ቀደም ሲል ስኮትላንድ ደርሰዋል። አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ የእኔ እና የዩናይትድ ኪንግደም ሕዝብ መልካም ምኞት ከንግሥት ኤልዛቤት እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ነው ብለዋል። የንግሥት ኤልዛቤት የጤና ሁኔታ ማሽቆልቆሉ መገለጹን ተከትሎ በርካታ በአገሪቱ ያሉ ተዋቂ ግለሰቦች እና ፖለቲከኞች መልካም ምኞታቸውን እየገለጹ ነው። የካንትበሪ ሊቀጳጳስ ጀስቲን ዌብሊ፤ እኔ፣ የእንግሊዝ ቤተ-ክርስቲያ እና መላዋ አገሪቱ ንግሥቲቷን በጸሎታቸው እያሰቡ ነው ብለዋል። የስኮትላንድ ተቀዳሚ ሚንስትር ኒኮላ ስተርጅን የንግሥቲቱ ጤና እጅጉን አሳስቦኛል ብለዋል። ተቀዳሚ ሚኒስትሯ ለንግሥት ኤልዛቤት እና ለመላው ንጉሣውያን ቤተሰቦች መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c51088xn194o +sports ዋሊያዎቹ ከማላዊና ከግብፅ በሚያደርጉት ጨዋታ ምን ውጤት ይጠበቃል? ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ በፈረንጆቹ 2023 በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ሊካሄድ ዕቅድ ተይዞለታል። የአህጉሪቱ እግር ኳስ አስተዳዳሪ ከፍተኛ አካል ካፍ ዕጣ ደልድሎ አገራት የማጣሪያ ጨዋታቸውን ማድረግ ጀምረዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አራት ከግብፅ፣ ከጊኒ እና ከማላዊ ጋር ተደልድላለች። ካፍ የኢትዮጵያ ሜዳዎች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ለማድረግ ብቁ አይደሉም በማለቱ ዋሊያዎቹ በገለልተኛ ሜዳ ይጫወታሉ። ዋሊያዎቹ በሜዳቸው ለመጫወት “ባለመታደላቸው” ከግብፅ የሚያደርጉትን የመጀመሪያ ዙር ፍልሚያ በባዳ ስታዲየም ሊያደርጉ ወስነዋል። ነገር ግን በመጀመሪያ ጨዋታቸው ማላዊን የሚገጥሙ ይሆናል። አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ዋሊያዎቹን እየመሩ ወደ ማላዊ ዋና ከተማ ሊሎንጉዌ ከማቅናቸው በፊት መግለጫ ሰጥተዋል። አሠልጣኙ “ፈርዖኖቹን በገዛ ሜዳችን ብንገጥም ደስ ይለን ነበር” የሚል የቁጭት አስተያየት ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግንቦት 16 ��ምሮ ለማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል። አሠልጣኝ ውበቱ መጀመሪያ 28 ተጫዋቾችን መልምለው ከሌሶቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር አዲስ አበባ ላይ የወዳጅነት ፍልሚያ አድርገው የመጨረሻ 23 ተጫዋቾችን ለይተዋል። እነማን ወደ ማላዊ ይጓዛሉ? አሠልጣኝ ውበቱ የባሕር ዳሩ ፋሲል ገብረሚካዔልን፣ የኢትዮጵያ ቡናው ታዳጊ በረኛ በረከት አማረንና የሐዋሳ ከተማውን ዳግም ተፈራ በግብ ጠባቂነት ይዘው ወደ ማላዊ ይሄዳሉ። አስራት ቱንጆ፣ ረመዳን የሱፍ፣ ሄኖክ አዱኛ፣ ሱሌይማን ሃሚድ፣ ምኞት ደበበ፣ ያሬድ ባዬ፣ ጊት ጋትኩትና ሚሊዮን ሶሎሞን የተከላካይ መስመሩን እንዲቆጣጠሩ የተመረጡ ናቸው። የአማካይ መስመሩን የሚመራው ጉምቱው ሽመልስ በቀለ ነው። በተጨማሪ አማኑዔል ዮሐንስ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ በዛብህ መለዮና መስዑድ ሞሐመድ ተመርጠዋል። የኢትዮጵያ ቡናው ፈርጥ አቡበከር ናስር የአጥቂውን መስመር እየመራ ወደ ሊሎንጉዌ ያቀናል። አማኑዔል ገብረመድህን፣ ቸርነት ጉግሳ፣ ዳዋ ሆጤሳ፣ በረከት ደስታና ይገዙ ቦጋለ ሌሎች በአጥቂ መስመር ላይ የሚሰለፉ ናቸው። ውበቱ እንደተለመደው በ4-4-3 አሰላለፍ ተጋጣሚዎቻቸውን እንደሚገጥሙ ይጠበቃል። የፕሪሚዬር ሊጉን ኮከብ ጎል አግቢ ሰንጠረዥ በጥምር የሚመራው ነባሩ አጥቂ ጌታነህ ከበደ ከአሠልጣኙ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ሳይመረጥ እንደቀረ ውበቱ ጠቁመዋል። ጌታነህ በዘጠኝ ቁጥር ቦታ አለመኖሩ አቡበከር ናስር ስኬታማ በሚሆንበት መስመር በደንብ እንዲጫወት ዕድል ሊፈጥር ይችላል። የጌታነህ ከበደን አለመኖር ተከትሎ ሽመልስ በቀለ ቡድኑን በአምበልነት እየመራ ወደ ማላዊ ያቀናል። ሽመልስ በቀለ ሶከር ኢትዯጵያ ከተሰኘው የአገር ውስጥ የስፖርት አውታር ባደረገው ቃለ-ምልልስ ከሁለቱ ጨዋታዎች ቢያንስ አራት ነጥብ ለማግኘት እንደሚጫወቱ ተናግሯል። 'ዘ ፍሌምስ' በተሰኘ ቅጽል ስሙ የሚታወቀው የማላዊ ብሔራዊ ቡድን ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ ከምድቡ ማለፍ ችሎ ነበር። ዘ ፍሌምስ በዙር 16 ጨዋታ በሞሮኮ ተርትተው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። ኢትዮጵያና ማላዊ ከፈረንጆቹ 2003 ጀምሮ በተለያዩ ውድድሮችና በወዳጅነት ስድስት ጊዜ ተገናኝተዋል። ማላዊ ሁለት ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ስትይዝ ኢትዮጵያ አንድ ጊዜ ረትታለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥተዋል። የማላዊ ብሔራዊ ቡድን ዘ ፍሌምስ መጋቢት በወጣው የፊፋ የዓለም የብሔራዊ ቡድኖች ሠንጠረዥ 120ኛ ላይ ተቀምጠዋል። ዋሊያዎቹ ደግሞ ከዓለም 140ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 44ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። የማላዊ ብሔራዊ ቡድን በአብዛኛው አገር ውስጥ በሚጫወቱ ተጫዋቾች፣ መቀመጫቸውን አውሮፓና በሌሎች የአፍሪካ አገራት ባደረጉ እግር ኳሰኞች የተዋቀረ ነው። አውሮፓ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች መካከል ለሞልዶቫው ሽሪፍ የሚጫወተው ቻርልስ ፔትሮ ይጠቀሳል። ኢትዮጵያና ማላዊ እሁድ ግንቦት 26/2014 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በቢንጉ ብሔራዊ ስታድዬም ይጫወታሉ። ሞሐመድ ሳላህ ፈርዖኖቹን ለመቀላቀል ወደ ግብፅ አቅንቷል። ግብፅ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ፍልሚያዋ በሜዳዋ እሁድ ምሽት 4፡00 ሰዓት ጊኒን ታስተናግዳለች። ፈርዖኖቹ ከምድብ በቀላሉ የማለፍ ግምት ተሰጥቷዋል። በፕሮፌሽናል እግር ኳሰኞች ማኅበር (ፒኤፍኤ) የዓመቱ ምርጥ ዕጩ ሆኖ የተመረጠው ሳላህ ቡድን እየመራ ወደሜዳ እንደሚገባ ይጠበቃል። ግብ ጠባቂው ሞሐመድ ኤል-ሼናዊን ጨምሮ ሰባት የአል አህሊ ተጫዋች በብሔራዊ ቡድኑ ተካተዋል። የአርሰናሉ ሞሐመድ ኤልኔኒ እንዲሁም የኢስታንቡል ባሼክሽር አማካይ ሞሐመድ ትሬዚጌ ለፈርዖኖቹ ተመርጠዋል። ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሚደረገውን ፍልሚያ መርታት የተሳናት ግብፅ አዲስ አሠልጣኝ ቀጥራለች። ተሰናባቹን ፖርቹጋላዊ አሠልጣኝ ካርሎስ ኬሮዥን የተኩት የ54 ዓመቱ ኢሃብ ጋላል ለቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ቀዳሚው ዕቅዳቸው እንደሆነ ገልጠዋል። ግብፅ ከጊኒ ጨዋታዋ ቀጥሎ ኢትዮጵያን በገልለተኛ ሜዳ ለመግጠም ወደ ማላዊ ታቀናለች። ዋሊያዎቹ ከፈርዖኖቹ ሐሙስ ሰኔ 02/2014 በማላዊ ስታድዬም ምሽት 1፡00 ሰዓት ይፋለማሉ። ከአሠልጣኝ ውበቱ አባተ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ ባሕሩ ጥላሁን መግለጫ ሰጥተዋል። “ፌዴርሽኑ ዋሊያዎቹን ለመደገፍ የታቸለውን ሁሉ እያደረገ ነው” ብለዋል ዋና ፀሐፊው። ዋሊያዎቹ ከሌሶቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርጉ ፌዴሬሽኑ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን አቶ ባሕሩ ጠቅሰዋል። እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋሊያዎቹ ግብፅ የሚያደርጉትን ጨዋታ ማላዊ ላይ እንዲያከናውኑ የወሰነው “ከወጪ አንፃር” መሆኑን ፀሐፊው ጠቅሰዋል። አልፎም ተጫዋቾቹ ከማላዊ ጨዋታ መልስ እዚያው ሆነው እንዲያገግሙ በማሰብ እንደሆነም አስረድተዋል። አቶ ባሕሩ “በማላዊ ስታድዬም ከግብፅ ጋር ለመፋለም ቢያንስ 50 ሺህ ዶላር ያስፈልገናል” ብለዋል። ዋና ፀሐፊው አክለው “የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወጪያችሁን እንቻልና ጨዋታው ካይሮ ይሁን” ብሎ እንደጠየቃቸው ይፋ አድርገዋል። “ነገር ግን...” ይላሉ ዋና ፀሐፊው “... ነገር ግን ይህ ክብረ ነክ ነው ብለን አንቀበልም ብለናል።” የመጀመሪያው ዙር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በሚቀጥለው ሳምንት ከተጠናቀቀ በኋላ ሁለተኛው ዙር ጨዋታ በመጪው መስከረም ይካሄዳል። መስከረም ላይ በሚደረጉት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ከጊኒ ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ ታደርጋለች። ተንታኞ ከምድቡ ለኢትዮጵያ ዝቅተኛ ግምት ቢሰጡም አሠልጣኝ ውበቱና ተጫዋቻቸውን ግን ይህን ለመሻር አቅደዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/crgn6184knno +health ኮሮናቫይረስ፡ የፖላንዱ ፕሬዝዳንት በኮቪድ-19 ተያዙ "የፖላንድ ፕሬዝዳንት አንድሬ ዱዳ በኮቪድ-19 መያዛቸው ተገለፀ። የፕሬዝዳንቱ ጤና ሁኔታ ""መልካም"" መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ራሳቸውን ለይተው ውሸባ ገብተዋል ተብሏል። የ48 ዓመቱ ጉልማሳ ፕሬዝዳንት ዱዳ፣ አርብ እለት የኮሮናቫይረስ ማድረጋቸውንና መያዛቸው መታወቁ ዛሬ፣ ቅዳሜ ይፋ ተደርጓል። ፕሬዝዳንቱ በኮሮናቫይረስ የተያዙ የተለያዩ ርዕሰ ብሄሮችን ያገኙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ይገኙበታል። 38 ሚሊዮን ዜጎች ያላት ፓላንድ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት እያገረሸ ሲሆን አርብ ዕለት ብቻ ከ13 ሺህ 600 በላይ ሰዎች እንደሚያዙ የሚወጣው ሪፖርት ያሳያል። አገሪቱ በአጠቃላይ "" አደገኛ ቀጠና"" ውስጥ መግባቷ የተገለፀ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ሆቴሎች በከፊል ተዘግተዋል። ፕሬዝዳንት ዱዳ በቫይረሱ እንዴት እንደተያዙ የተገለፀ ነገር ባይኖርም፣ ሰኞ ዕለት የቡልጋርያ ፕሬዝዳንት ሩመን ራዴቭ በተገኙበት በታሊን በተዘጋጀ በዓል ላይ ተገኝተው ነበር ተብሏል። የቡልጋርያው ፕሬዝዳንት ከዚህ በዓል በኋላ ራሳቸውን ለይተው መቀመጣቸውን ተሰምቷል። ""ፕሬዝዳንቱ ትናንት ተመርምረው በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል"" ሲሉ የፕሬዝዳንታዊ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው የትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። አክለውም የፕሬዝዳንቱን ጤንነት ለመከታተል ከአስፈላጊ ሕክምና ባለሙያዎች ጋር ግንኙነት እያደረጉ መሆኑን ይናገራሉ። አውሮፓ እስካሁን ድረስ 7.8 ሚሊዮን በቫይረሱ ሲያዙ፣ በዚሁ ምክንያት ደግሞ 247 000 ሰዎች ሞተዋል። በአውሮፓ ጣልያን፣ ኦስትርያ፣ ክሮሺያ፣ ስሎቫንያ እና ቦሲኒያ በቫይረሱ ክፉኛ ከተጎዱ አገራት መካከል ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/54672465 +business በምዕራቡ ዓለም የሥራ አስፈጻሚዎች ደመወዝ ለምን በሚሊዮን ዶላሮች ሆነ? "በአውሮፓና አሜሪካ ለምን ለሥራ አስፈጻሚዎች በሚሊዮን ዶላር ይከፈላል? ካፒታሊዝም ነው፡፡ ድሆች ይበልጥ ድሀ፣ ሀብታሞች ይበልጥ ሀብታም እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ ካፒታሊዝም ነው፡፡ ሀብታሞች በጣም ሀብታም፣ ወዝ አደሮች ደግሞ ከድህነት አረንቋ ይወጣሉ፡፡ ቀስ በቀስ፡፡ ሁለቱ አተያዮች ሊያከራክሩ ይችላሉ፡፡ ሁለቱም ግን እውነትነት አላቸው፡፡ የዓለም አዱኛ ከዓለም ሕዝብ 1 እጅ እንኳ በማይሞሉ ጥቂት ሰዎች መያዙ ግን አያከራክርም፡፡ የዚህ ጽሑፍ ማጠንጠኛ ደመወዝ ነው፡፡ የወዝ ደም፤ የላብ ክፍያ፡፡ የሚያልባቸው ሁሉ ለምን ተቀራራቢ ደምወዝ አይከፈላቸውም? የነጭ ባለኮሌታዎች ዋጋ ለምን ይንራል? ዋናዎቹ ባለጉዳዮቻችን የኩባንያ ባለቤቶች ሳይሆኑ ሥራ አስፈጻሚዎቻቸው ናቸው፡፡ እርግጥ ነው አንዳንድ ኩባንያዎች ፈጣሪዎቻቸው ሥራ አስፈጻሚዎቻቸውም ጭምር ናቸው፡፡ እነሱንም እንመለከታለን፡፡ ይቺ ዓለም ፍትሐዊ ናት? ይህ ጥያቄ እንደመላሹ ነው፡፡ በሚሊዮን ዶላር የሚከፈለው አለቃ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ አዎንታዊ ነው፡፡ ለላብ አደሩ አሉታዊ ነው፡፡ በ2020 ብዙ ኩባንያዎች የገንዘብ ቀውስ ገጥሟቸዋል፡፡ ብዙዎች ሠራተኞቻቸውን በትነዋል፡፡ ያም ሆኖ ለሥራ አስፈጻሚዎቻቸው በሚሊዮን ዶላሮች ከፍለዋል፤ ይከፍላሉ፡፡ ለምሳሌ የአሜሪካኑን ጎልድማን ሳክስ ባንክ ሥራ አስፈጻሚ ዴቪድ ሰሎሞንን ደመወዝ እንውሰድ፡፡ በዓመት 30 ሚሊዮን ዶላር በአማካይ ወደ ባንክ ደብተሩ ሸርተት ብሎ ይገባለታል፡፡ ዘንድሮ ብቻ ነው 10 ሚሊዮን የተቀነሰበት፡፡ እሱም ከማሌዢያ መንግሥት ጋር በተፈጠረ ምዝበራ የተነሳ ነው፡፡ ድሮ ደመወዝ እንደዚህ አልበረም፡፡ በላብ አደሩና በአሰሪ አለቆች መካከል እንዲህ የሰማይና የምድር ያህል የሚራራቅ ክፍያ ልዩነት አልነበረም፡፡ የሎንዶኑ ‹ሃይ ፔይ ሴንተር› የሠራው አንድ ጥናት የፋይናንሻል ታይምስ ስቶክ ኤክሰቼንጅ (ኤፍቲኤስኢ) ኃላፊዎች በአማካይ 5 ሚሊዮን ዶላር ነው ደመወዛቸው ይላል፡፡ ይህ ማለት ሁሉም ቋሚ ሰራተኞች ከሚያገኙት ድምር መቶ እጥፍ ማለት ነው፡፡ ኢካዶ የድረገጽ ሱፐርማርኬትን እንውሰድ፡፡ ሥራ አስፈጻሚው ቲም ስቴይነር በ2019 ዓ/ም ደመወዙ ስንት ነበር? ማመን ይከብዳል፡፡ 59 ሚሊዮን ዶላር፡፡ አዎ አልተሳሳቱም፡፡ 59 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡ ይህ ክፍያ ማለት አማካይ የሱፐርማርኬቱ ሰራተኞች በጠቅላላ ተደምሮ 2ሺ 605 ጊዜ እጥፍ ክፍያ ማለት ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ቲም በቀን የሚከፈለው የሌሎቹ የዓመት ደመወዛቸው ተደምሮ በ7 ቢባዛ የሚያገኙት ነው፡፡ እና ይቺ ዓለም ፍትሐዊ ናት? ለቲም ትሆን ይሆናል፡፡ ካች አፕና የጨው ብልቃጥ ለሚደረድር የኢካዶ ሠራተኛ ግን በፍጹም፡፡ አትላንቲክን እንሻገር፡፡ ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢኮኖሚክ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት በሠራው ጥናት 350 የአሜሪካ ግዙፍ ኩባንያዎች ሥራ አስፈጻሚዎች የሚያገኙት አማካይ ደመወዝ 21 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ ይህ ጥናት ይፋ የሆነበት ጊዜ ራሱ አስገራሚ ነው፡፡ በሽታ ሰው አይመርጥም ይባላል፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ ግን ደሃና ጥቁሩ ላይ ነው የበረታው፡፡ ለምን? ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ አንዱ ላብ አደሩ የጤና መድኅን የለውም፡፡ ሌላው ላብ አደሩ የሚሠራበት ሁኔታ ለተህዋሲው የሚያጋልጥ ነው፡፡ ሌላው ላብ አደሩ ጥሮ ግሮ ሲሠራ ፋታ የለውም፡፡ ራሱን ለመጠበቅ አይችልም፡፡ ሌላው ላብ አደሩ የሚያድረው ባልተመቻቸ ሁኔታና በተጨናነቀ ጭርንቁስ ሰፈር ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ምንጭ የክፍያ ማነስ ነው፡፡ ለምሳሌ ‹ወሳኝ ሠራተኞች› እያለ ሚዲያው የሚጠራቸው ለፍቶ አዳሪዎች የሰውን ነፍስ ለማዳን ራሳቸውን የሚያጋልጡ ናቸው፡፡ የጤና ረዳቶችን ይጨምራል፡፡ ሆኖም ሕዝብ እየወጣ ሻማ አበራላቸው እንጂ ክፍያ አልጨመረላቸውም፡፡ ብዙ ሚስኪን ላብ አደሮች ለፍተው ሲያድሩ በዚያው ፍግም ብለው ያልፋሉ፡፡ አኗኗራቸውም አሟሟታቸውም አላማረም፡፡ የካታሊስት ሥርዓት ግን ሊያደርግ የቻለው ደማቅ የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ማሰናዳት ነው፡፡ ሌላም ያደረገው ነገር አለ፡፡ ሚሊዮን ዶላር የሚያገኘው/የምታገኘው ሥራ አስፈጻሚ በሻማ ማብራቱ ሥነ ሥርዓት ላይ የሐዘን ቃል ያሰማሉ፡፡ ይህ ለሥራ አስፈጻሚዎች ቁልል ደመወዝ የመክፈሉ ሐሳብና ፖሊሲው በሬገን መንግሥት ጊዜ ነው ይበልጥ እየተዋወቀ የመጣው ይባላል፡፡ በታላቋ ብሪታኒያ ደግሞ ማርጋሬት ታቸር ናቸው የጀመሩት ይላሉ፡፡ ምናልባት የፖለቲካ ፍልስፍናቸው የነጭ ካፒታሊዝም ስለነበር ይሆናል፡፡ ያን ጊዜ ሁሉም ነገር ወደ ግል ዘርፉ እየሄደ ነበር፡፡ ሁሉም ነገር ለነጻ ገበያ ተላልፎ እየተሰጠ ነበር፡፡ ሬገንም ሆኑ ታቼር የሠራተኛ ማኅበራትን በበጎ አይመለከቱም ነበር፡፡ ለዚህም ይመስላል ሠራተኞች ለክፍያ መሻሻል ሳይታገሉ፣ ቢታገሉም ፍሬ ሳያፈራላቸው እንዲሁ ላብ አደር ሆነው ጉልበታቸው ሲበዘበዝ የኖረው፡፡ ""ያንን ዘመን ልብ ብለን ካስተዋልን ክፍያ ሲሻሻል የሁሉም በአንድ ላይ ነበር እንጂ የሥራ አስፈጻሚው ለብቻ ተነጥሎ አይታይም ነበር"" ይላሉ ሳንዲ ፔፐር፡፡ ሳንዲ በሎንዶን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የክፍያ ጉዳዮች ተመራማሪ ናቸው፡፡ ሳንዲ ለምን በየዘመኑ የተራ ሠራተኞችና የሥራ አስፈጻሚዎች ክፍያ እየተንቦረቀቀ መጣ በሚለው ላይ ጥናት አድርገዋል፡፡ ቀድሞ አለቃና ተራው ሠራተኛ በክፍያ ጭማሪ ወቅት በእኩል ይታይ የነበረው አሠራር እየፈረሰ የመጣው የሥራ አስፈጻሚዎች ክፍያ ከሽርክና ዋጋ እና ውጤት ተኮር አበሎች ጋር እየተሳሰረ መምጣቱን ተከትሎ ነው፡ ይላሉ ሚስተር ሳንዲ፡፡ ትርፍን ብቻ የሚያሳድደው ኒዎ ሊበራሊዝም ይህን አሠራር እያበረታታው መጣ፡፡ ከ2000 ዓ/ም ጀምሮ የተወሰደ የኤፍቲኤስኢ100 ዳታ እንደሚያሳያው የሠራተኞች ደመወዝ ጭማሪ በየዓመቱ በአማካይ 3 ከመቶ ሲሆን የሥራ አስፈጻሚዎች ግን በ10 ከመቶ ይመነደጋል፤ በየዓመቱ፡፡ አሁን ባለው አሰራር የሥራ አስፈጻሚዎችን ክፍያ የሚወስነው የኩባንያዎች ዓመታዊ የትርፍ አፈጻጸም እየሆነ መጥቷል፡፡ ምክንያቱም ሥራ አስፈጻሚዎች ለኩባንያዎች ማበብና መክሰም ወሳኞች እየሆኑ መምጣታቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ከመደበኛ የደመወዝ ምጣኔ በተጨማሪ ሥራ አስፈጻሚዎች ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንዲንበሸበሹ አድርጓቸዋል፡፡ ከነዚህም መካከል በኩባንያው ውስጥ ድርሻ እንዲኖራቸው በማድረግ የባለቤትነት ስሜት እንዲያድርባቸው ማስቻል፤ ኩባንያው ትርፋማ ሲሆን ደግሞ በተገኘው ትርፍ ልክ አበል መስጠትን ያካትታል፡፡ ለአብነት ቅድም ባነሳነው የኢካዶ የድረ ገጽ ሱፐርማርኬት ምሳሌ ሥራ አስፈጻሚው ስቴይነር በ2019 ከተከፈላቸው ዓመታዊ ደመወዝ ውስጥ 54 ሚሊዮን ፓውንድ ጉርሻ ይገኝበታል፡፡ ይህም የኩባንያውን የ5 ዓመት የእድገትና ትርፍ እቅድ በማሳካታቸው ያገኙት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ኩባንያዎች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም የሚወስንላቸው በዓመት አንድ ጊዜ በሚሰበሰብ ቦርድ ነው፡፡ የቦርድ አባላት ደግሞ ከሌሎች ኩባንያዎች የተውጣጡ ሥራ አስፈጻሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህ በእንዲህ ሳለ ብዙዎቹ የብሪታኒያ ቢዝነሶች በግለሰቦች ባለቤትነት መሆናቸው በአያሌው ቀንሷል፡፡ የትልልቅ ሼር ባለቤቶች ጡንቻ እየፈረጠመ ነው የመጣው፡፡ እነሱ ደግሞ የስቶክ ዋጋ በፍጥነት እንዲጨምርላቸው ይፈል��ሉ፡፡ ስለዚህ ለሥራ አስፈጻሚዎች ወፍራም ደመወዝ ይከፍላሉ፡፡ የቦርድ አባላት ደግሞ የሼር ባለቤቶችን ለማስደሰት የሥራ አስፈጻሚን ደመወዝ ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ጥቅማ ጥቅም የሚሰላው ከተመሳሳይ ኩባንያዎች ጋር በማወዳደር ነው፡፡ እነሱ በሌላ ኩባንያዎች ሥራ አስፈጻሚ ስለሆኑ የሌላውን ሲያሻሽሉ የነሱም እንደሚሻሳል ይረዳሉ፡፡ ስለዚህ ወፍራሙን ደመወዝና ቁልሉን አበል ያጸድቁታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የቦርድ አባላት ከሠራተኞችም ይወከላል፡፡ ሠራተኞች ትልቁን አለቃ ማስቀየም አይፈልጉም፡፡ ነገ ሊያባርራቸው ይችላል፡፡ ወይም በትርፍ ላይ ያለን ኩባንያ ጥሎ ሄዶ ኮርፖሬሽኑን ለሌላ ኪሳራ ሊያጋልጠው ይችላል፡፡ ኩባንያው ከሰረ ማለት የሥራ ዋስትና ታጣ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የክፍያ ጭማሪን በምንም መልኩ ለመቃወም አይደፍሩም፡፡ ምንም እንኳ ለሥራ አስፈጻሚዎች የሚከፈለው ረብጣ ዶላር ልክ ነው አይደለም በሚለው ላይ ሰፊ ክርክር ቢኖርም የነጻ ገበያ አቀንቃኝ የሆኑ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ግን አስፈጻሚዎች ለኩባንያ የሚያመጡት ገቢ አጥጋቢ እስከሆነ ድረስ የሚያጠግብ ደመወዝ መከፈሉ ምንድነው ችግሩ? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ ነገሩ ሁሉ ገበያ መር ነው፡፡ አንድ ኩባንያ በኪሳራ እየሰመጠ ለአለቆች ያን ያህል ሊከፍል አይችልም፡፡ ገበያ መር ስንል የቁስ ዋጋን ብቻ ሳይሆን የወዝአደር ዋጋም ማለታችን ነው ይላሉ፡፡ ""ሥራ አስፈጻሚዎች ቁልፍ የስኬት ሞተሮች ናቸው፡፡"" ይላሉ በአዳም ስሚዝ ኢንስቲትዩት የኒዮሊበራል ባለሙያዎች ስብስብ (ቲንክታንክ) ፕሮግራም ኃላፊ ዳኒኤል ፕራዮር፡፡ ""ግልጽ ነው እኮ፤ አንድን ኩባንያ አትራፊ ማድረግ የሚያስችል የአስተዳደር ጥበብ፣ የዕውቀት ስንቅና ብልሀት ያላቸው ሰዎች ጥቂት ናቸው፡፡ በገበያው እንዲህ ዓይነት ላቅ ያለ የአመራር ክህሎት ሁሉም ሰው የለውም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ጥቂት ሰዎች ላይ ገበያው ይራኮታል፡፡ ክፍያቸው ጣሪያ የሚነካውም ለዚሁ ነው"" ይላሉ፡፡ ዴቪድ ቦልቾፈር ግን በዚህ አይስማሙም፡፡ ""ማነው የአመራር ክህሎት ያላቸው ሰዎች ጥቂት ናቸው ያለው ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ይሄ ማጭበርበር ነው፡፡"" ሚስተር ዳንኤል ክፍያው ተገቢ ነው የሚሉት የአፕሉን ስቲቭ ጆብስ፣ የአማዞኑን ጄፍ ቤዞስ፣ የተስላና የስፔስኤክስ ፈጣሪን ኤሎን መስክንና የመሳሰሉትን እጅግ የነጠረ ክህሎት በማንሳት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች አዲስ ነገር ፈጥረው የገበያና የቴክኖሎጂ አብዮት ያመጡ ሰዎች ናቸው፡፡ ""መደበኛ ሥራ አስፈጻሚዎች ግን እንደነ ኤሎን መስክ ያሉት አይደሉም"" ይላሉ ዴቪድ ቦልቾፈር፡፡ እነዚህ መደበኛ ሥራ አስፈጻሚዎች ሚናቸውም ክፍያቸውም የተጋነነ ነው ብለው የሚከራከሩትም ለዚሁ ነው፡፡ አንድ ኩባንያ በሥራ አስፈጻሚው ብርታትና ምጥቀት ብቻ አይደለም ትርፋማ የሚሆነው የሚሉት ሚስተር ዴቪድ ፔይ ቼክ በሚለው መጽሐፋቸው ላይ ይህን ጉዳይ በዝርዝር ጽፈውታል፡፡ አንዳንድ ዘርፎች በተለያዩ ምክንያቶች አትራፊነታቸው ይቀጥላል፤ የትኛውም ተመሳሳይ አቅም ያለው ሰው ቢመራቸው፡፡ የቴሌኮም ዘርፎችን ምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡ ወይም ቀድሞውኑም ጥሩ መሠረት ላይ የተገነቡ ቢዝነሶች፡፡ በዚህ ረገድ ሥራ አስፈጻሚዎች ምንም ቦታ ላይኖራቸው ይችላል፡፡ ምናልባት የሠራተኞች ትጋት ይሆናል የትርፍማነቱ ምንጭ፡፡ ሆኖም አለቆች የሚበሉት ደመወዝ የትየሌሌ ነው፡፡ ""በኮርፖሬሽኖች የሥራ አስፈጻሚዎች ሚና ብዙውን ጊዜ ይጋነናል፡፡ ይህ ሆን ተብሎ የሚደረግ ማጭበርበሪያ ነው፡፡"" ይላሉ ዴቪድ ቦልቸር፡፡ ቦልቸር ሌላም ማስረጃ ያቀርባሉ፡፡ ለምሳሌ የ2008 የፋይናንስ ቀውስ ጊዜ ባንኮች በኪሳራ ሲንኮታኮቱ ሥራ አስፈጻሚዎቻቸው ግን ሚሊዮን ዶላሮችን ታቅፈው ነው የሄዱት፡፡ ይህ ነገር በጊዜው ብዙዎችን አቁስሎ ነገሩ ላይ ጥያቄም መነሳት ጀምሮ ነበር፡፡ ""ክፍያ አስፈጻሚዎች ባስገኙት የስኬት መጠን ነው ከተባለ የነዚህ ባንኮች ሥራ አስፈጻሚዎች ለምን ከኪሳ በኋላም ወፍራም ደመወዝ እየተከፈላቸው ቆዩ?"" ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡ መልሱን ራሳቸው ሲመልሱም የጥቅም ትስስር ስላለ ነው ይላሉ፡፡ የጥቅም ትስስሩ በቦርድ አባላት፣ በሥራ አስፈጻሚዎችና በሽርክና ባለቤቶች መካከል ነው፡፡ ተራው ሠራተኛ ደመወዙ ለምን ያሽቆለቁላል? የሥራ አስፈጻሚዎች ደመወዝ ሲመነደግ የተራ ሠራተኛው ደመወዝ ቁልቁለቱን ተያይዞታል፡፡ ለምሳሌ በዚህ ወረርሽኝ የወሳኝ ሰራተኞች ደመወዝ ማነሱ ብቻ ሳይሆን እሱንም ለማግኘት ሕይወታቸው ላይ ለመቆመር ይገደዳሉ፡፡ ይህ የተራ ሠራተኞች ደመወዝ ማሽቆልቆል ብዙዎችን ደም እያፈላ ነው፡፡ ለምሳሌ በሺህ የሚቆጠሩ የብሪቲሽ ጋስ ኩባንያ ሰራተኞች የ5 ቀን የሥራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የሠራተኛ ቅነሳ መደረጉ ነው፡፡ ብዙ ሠራተኞች በጥቂት መብቶች ብቻ ተወስነው በአስቸጋሪ ሁኔታ እንዲሰሩ መገደዳቸው ነው፡፡ ውጥረቱ ይበልጥ የተካረረው ደግሞ ከ2018 ጀምሮ ብሪቲሽ ጋስን በባለቤትነት የያዘው ሴንትሪካ ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚ የ44 ከመቶ ጭማሪ ማግኘታቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ዓመታዊ ደመወዛቸው 2 ሚሊዮን ተኩል ፓውንድ ያልፋል፡፡ ""ይህ ስግብግብነት ነው"" ይላል የ32 ዓመቱ የብሪቲሽ ጋስ ሰራተኛ ጆን፡፡ ይህ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንኳ የማይከፈላቸው ደመወዝ መጠን ነው፡፡ እንዴት ነው ሰራተኛን እየቀነሰ ያለ ኩባንያ ለሥራ አስፈጻሚው ይህን ያህል ፓውንድ የሚከፍለው? በጭራሽ ስሜት አይሰጥም፡፡ አንዳንድ መልካም ሥራ አስፈጻሚዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ የቦይንግ፣ የማሪዮት ኢንተርናሽናል የፒደብሊውሲ ሥራ አስፈጻሚዎች ሰራተኛ እንዳይቀነስ ሲሉ ደመወዛቸውን ጭማሪ ይቅርብን ያሉ ናቸው፡፡ አንዳንዶች ይህን ድርጊታቸውን ለታይታ የተደረገ እንጂ መሰረታዊ ለውጥ የማያመጣ ነው ሲሉ ይተቹታል፡፡ መጪው ጊዜ አስፈሪ ነው፡፡ ለተራ ሰራተኛ፣ ለላብ አደሩ፣ ድምጹ ለማይሰማው፣ ላቡ ለሚንቆረቆረው ብዙኃን በተለይ መጪው ዘመን ቀበቶ ጠበቅ የሚደረግበት ነው፡፡ ምክንያቱም ኩባንያዎች ገቢ ቀንሷል፡፡ ከቴክ ኩባንያዎች ውጭ ያለው ዘርፍ በወረርሽኙ ድባቅ ተመቷል፡፡ የአርተፊሻል ልህቀትና ሌሎች ማሽኖች የጉልበት ሥራን ዋጋ እያሳጡት ነው፡፡ ኢንተርኔት ንግድ የሰራተኛን አስፈላጊነት እምብዛምም አድርጎታል፡፡ ፋይናንስ ኢንዱስትሪዎች በእንብርክክ እየሄዱ ነው፡፡ የሰራተኛ ማኅበራት እየተዳከሙ ሄደዋል፡፡ ስለዚህ መጪው ጊዜ ሚሊየነሮች ቢሊየነሮች የሚሆኑበት፣ ላብ አደሮች ይበልጥ ላባቸው በከንቱ የሚፈስበት እንደሆነ የዓለም ምጣኔ ሀብትን በቅርብ የሚከታተሉ አዋቂዎች ትንቢት ነው፡፡ የዓለም ሀብት በጥቂቶች እጅ ይቀፈደዳል፡፡ ቢሊዮኖች ግን በቃ ቁጥር ናቸው፡፡ ተወልደው፣ ኖረው፣ ጥረው ግረው፣ የሚሞቱ፡፡" https://www.bbc.com/amharic/55854396 +sports ማርቲን ሉተር ኪንግ ማነው? ለምንስ እስከ ዛሬ ይታወሳል? "'ሕልም አለኝ' የሚለው የማርቲን ሉተር ኪንግ ንግግር አሜሪካ ውስጥ ያለውን የዘር ጭቆና እና የእኩልነት መብት አለመከበር የሚቃወም ነበር። በርካቶችን ለተሻለ አስተሳሰብ አነሳስቷል፤ ታዋቂና ቀንደኛ ሰዎችን አከራክሯል፤ ዘንድሮም ድረስ የሚነገርለት ሐሳብ ሆኗል። ነገር ግን ዛሬም ላይ እነዚህ ጉዳዮች አልባት አላገኙም። ጥቁርና ድሀ ማኅበረሰቦችን ለማግለል ተብለው የሚወጡ የምርጫ እገዳዎችና ሌሎችም ተግባራት ማርቲ�� ሉተር ኪንግ ሲታገልለት የነበረው ጭቆና አሁንም ድረስ ስለመኖሩ ማሳያ ነው። ማርቲን ሉተር ኪንግ ማነው? ነሐሴ ወር 1963 ላይ እስከ 250 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ዋሽንግተን ዲሲ ወደሚገኘው ታዋቂው ሊንከን ሜሞሪያል ተምመው ነበር። ይሄ ሁሉ ሰው ታዲያ አንድ ሰው ንግግር ሲያደርግ ለማዳመጥ ነበር። ስሙም ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ይባላል። ንግግሮቹ ዛሬም ድረስ በመላው ዓለም እንደ ነጻነት ማብሰሪያ ይታያሉ። ማርቲን ሉተር ኪንግ በደቡባዊ ጆርጂያ ግዛት ከአንድ የሃይማኖት አባት ነው የተወለደው። አባቱ እሳቸው ካለፉበት የሕይወት ዓይነት በተለየ መልኩ ልጆቻቸው እንዲሄዱ ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው። ዘርና ቀለምን መሠረት ያደረገ መድልዎ በመላው ደቡባዊ አሜሪካ ተንሰራፍቶ ነበር። በርካታ ይህንን የሚደግፉ ሕጎችም ተግባራዊ ይደረጉ ነበር። ጥቁር ሰዎች እና ነጭ ሰዎች በተለያየ አካባቢ ነበር የሚኖሩት። እንዲገናኙ አይፈለግም። ጥቁሮች ለጥቁሮች ብቻ ተብለው በተሰሩ ምግብ ቤቶች እና መጠጥ ቤቶች ብቻ ነበር የሚዝናኑት። ሌላው ቀርቶ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ እንኳን ጥቁሮች ለብቻው እጅግ ባረጁ መኪናዎች እንዲጠቀሙ ተደርጓል። በአጠቃላይ ጥቁሮች ምንም ያህል ጥሩ ሥራ ቢሠሩም ከነጮች ያነሰ ክፍያ እንዲሰጣቸው ሕጎች ነበሩ። የጥቁሮች ትምህርት ቤት፣ የጥቁሮች የጤና ተቋማት እና የጥቁሮች መንደር እየተባለ መከፋፈል በጊዜው የተለመደና ተቀባይነት ያለው ተግባር ነበር። በፖለቲካው ዘርፍ ደግሞ ጥቁሮች እነሱ የፈለጓቸውን መሪዎች እንዳይመርጡ በተጠና እንዲሁም በተዘዋዋሪ መልኩ ሲሠራ ነበር። ነገር ግን አሁን ላይ የማርቲን ሉተር ኪንግ ሕልሞች በሙሉ ተሳክተዋል ብላችሁ ካሰባችሁ ተሳስታችኋል። የእርሱ ቤተሰቦች እንደሚሉት በተለይ በቅርብ ወራት እየተስተዋሉ ያሉ ነገሮች ከማርቲን ሕልም በእጅጉ የራቁና የተቃረኑ ናቸው። በእነማርቲን ሉተር ኪንግ ዘመን ጥቁሮችን በግልጽ ያገልሉ የነበሩ ሕጎች አሁንም መልካቸውን ቀይረው እንዳሉ ናቸው። የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊ ፖለቲከኞች አሁንም ድረስ የአናሳ ቡድኖች በተለይም የጥቁር ማኅበረሰቦችን ስም የማጠልሸትና ከሌላው ማኅበረሰብ በመለየት በምርጫ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ መቀነስን ተግባራዊ ያደርጋሉ። ለዚህ እንደ ማሳያ የሚጠቀሰው ጥቁሮች ብሔራዊ መታወቂያ የሚያገኙበትን መንገድ ማጥበቃቸው ነው። በተጨማሪ ደግሞ ሰዎች ለምርጫ በሚሰለፉበት ወቅት የሚቀርቡ ምግብና መጠጦችን መከልከልም ይጠቀሳል። ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በምርጫ አሸንፈው ዋይት ሀውስን ከተቆጣጠሩ በኋላ መሰል ሕጎች እንደ ፍሎሪዳ፣ ቴክሳስ እና አሪዞና ባሉ ግዛቶች በስፋት ተግባራዊ ተደርገዋል። አሜሪካ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግን በምታስታውስበት የፈረንጆቹ ጥር 17/2022 የታዋቂው ነጻነት ታጋይ ልጆች፤ ሰዎች ዝም ብለው በደፈናው ስሙን ብቻ አስበው እንዳይውሉ ጠይቀዋል። ቀኑን ማክበር ብቻ ሳይሆን የእሱን ፈለግ በመከተል የጥቁር ሕዝቦችን ነጻነትና እኩልነት የሚያረጋግጡ ሕጎች እንዲወጡ ለማስገደድ የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። ሴት ልጁ በርኒስ ኪንግ ""እኛ የማርቲን ሉተር ኪንግን በዓል እያከበርን ሲሆን እናንተም በተመሳሳይ እንድታከብሩት እጠይቃለው። ነገር ግን የምርጫ መብታችን አደጋ ላይ ከወደቀ ሁላችንም ይህንን ቀን ምክንያት አድርገን እሱ ያደርገው የነበረውን ማስቀጠል አለብን"" ብላለች። ""አባቴ የሚወዳት አገሩ በፍጹም ዴሞክራሲ እንድትመራ ይናገርና ያደርግ የነበረውን እንቅስቃሴ የአሜሪካ ሴኔት ላይ ጫና በማሳረፍ እንድናስቀጥለው እጠይቃለው።"" የጥቁሮች የምርጫ መብት ጥያቄ ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ በአሜሪካ ታሪክ ው��ጥ ትልቅ ውዝግብን ያስነሳ ጉዳይ ነው። ታዋቂው የሃይማኖት መሪ ሬቭረንድ አል ሻርፕተን 'የአሜሪካን ዴሞክራሲ የሚፈታተን ወሳኝ ጊዜ' ነው ብለዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በበኩላቸው የምርጫ መብት ጉዳይ የአሜሪካ የልብ ትርታ ነው ብለዋል የማርቲን ሉተር ኪንግ መነሻ በሆነችው አትላንታ ንግግር ሲያደርጉ። ""ከማርቲን ሉተር ኪንግ ጎን መሆን ነው የምትፈልጉት ወይስ ከጆርጅ ዋላስ?"" ሲሉም ጥያቄ ሰንዝረዋል። ጆርጅ ዋላስ የቀድሞ የአለባማ ገዢ የነበሩና የጥቁሮችን የበታችነት የሚሰብኩ ሰው ናቸው። ማርቲን ሉተር ኪንግ ምንድነው የሠራው? ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ያንን ንግግር ሲያደርግ ክፍፍልን አምርሮ ይተች ነበር። ነገር ግን ከነጭ ወግ አጥባቂዎች በኩል ያገኘው ምላሽ ከበድ ያለ ነበር። ቤተሰቦቹ በየዕለቱ የእንገድላችኋለን ማስፈራሪያዎች ይደርሷቸው የነበረ ሲሆን ቤታቸውም በቦምብ ጋይቷል። ኪንግ ምንም አይነት አመጽ ባልተቀላቀለበት የትግል መንገድ የሚያምን ሲሆን ሁሌም ቢሆን ሰዎች በንግግርና በኅብረት ብቻ ማሸነፍ እንደሚችሉ ያምናል። ፕሮፌሰር ቤንቶ እንደሚሉት በርካቶች የእሱን መንገድ ደካማነትና ሽንፈትን እሺ ብሎ መቀበል ሊመስላቸው ይችላል። ነገር ግን ይህ ትልቅ ስህተት ነው ይላሉ። ""ኪንግ ከአመጽ የጸዳችና በመግባባት ላይ የተመሠረተች አሜሪካን ያስብ ነበር። ዘረኝነት የተወገደበት፣ እኩልና ነጻ ማኅበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ትልቁ ሕልሙ ነበር።"" በአውሮፓውያኑ 1963 ማርቲን ሉተር ኪንግ በዋሺንግተን ያደረገውም ንግግር በነጻነት መብት ትግል ውስጥ ወሳኝ ሚና አለው። በወቅቱ ኪንግ ከአመጽ ነጻ በሆነ መልኩ እንዴት ለውጥን ማምጣት እንደሚቻልና የዘር አኩልነትን ማስፈን እንደሚገባ መርሑን በግልጽ አስቀምጧል። በቀጣዩ ዓመት በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ላይ ጥቁሮች እንዲሄዱ አልያም በሁሉም ቦታ ተንቀሳቅሰው ሥራ እንዲሠሩ የሚፈቅደው ሕግ ጸደቀ። ነገር ግን ፍልሚያው ገና በጅምር በሚባል ደረጃ ላይ ነበር። የእኩልነት ጠላቶች በወቅቱ ዘረኛ ፖሊሲዎች እንዲወጡ ከፍተኛ ጫና ያሳድሩ ነበር። በደቡባዊ ግዛቶችም ጥቁሮች በተለይ ምርጫ ላይ ያላቸውን ተሳተፎ በእጅጉ የሚቀንሱ ፖሊሲዎች ይጡ ነበር። ኪንግም 1965 ላይ መሰል ሕጎች እንዳይወጡ የሚቃወመውን በአለባማ ሰልማ የተካሄደውን ሞንቶጎመሪ ሰልፍ አካሂዷል። በወቅቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቹ ተቃውሟቸውን ቢያሰሙም ከፖሊስም ሆነ ከነጮች የጠበቃቸው ጭካኔ የተሞላበት ምላሽ ነበር። ነገር ግን ኪንግ አሁንም ከአመጽ የጸዳ በሚለው መርሑ በመመራት ጥያቄውን ሲያሰማ ነበር። ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዴት ነው የሞተው? ኪንግ በተለያዩ ጊዜያት 29 ጊዜ ታስሯል። ሚያዝያ 4/1968 አሪዞና ሜምፊስ በሚገኘው የሆቴል ክፍል በረንዳ ላይ ነው አንድ ነጭ ግለሰብ በጠመንጃ ተኩሶ የገደለው። የኪንግ ግድያ ግን የእሱን ሥራዎች በአሜሪካ አላንኳሰሰውም። የኪንግ ትግልና የትግል መንገድ እንዲሁም ተጽዕኖው አሁንም ድረስ ቀጥሏል። የኪንግን ግድያ ተከትሎ በርካታ የመብት ተሟጋቾች ፈርተዋል። ""የእሱ ሥራዎች ሁሌም ሕያው ሆነው ይቆያሉ። ማኅበራዊ ፍትሕን ለማስፈን ምን አይነት ተቃውሞና ኅብረት መታየት እንዳለበት አሳይቶናል"" ይላሉ ፕሮፌሰር ቤንቶ። የማርቲን ሉተር ኪንግ ንግግሮች በሰው ልጆች ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ በርካቶችን ካበረታቱ እና ለተሻለ ለውጥ ካነሳሱ ንግግሮች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው። ለሰዎች አኩልነት ድምጹን ማሰማት አቁሞ የማያውቀው ማርቲን ሉተር ኪንግ ሁሌም የግል ደኅንነቱን ትልቅ አደጋ ላይ ጥሎ ነው ለዴሞክራሲ የታገለው።" https://www.bbc.com/amharic/news-60028025 +politics የታገ��� የካማሺ ዞን የማረሚያ ቤት ኃላፊዎችን ለማስለቀቅ እየተሞከረ እንደሆነ ተገለጸ "በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሺ ዞን የማረሚያ ቤት አዛዥ ተወካይን ጨምሮ ሦስት የጸጥታ አካላት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች መታገታቸውን የክልሉ ኮሚሽን ለቢቢሲ ገለጸ። ታጋቾቹን ለማስለቀቅም የኦሮሚያና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ጥረት መጀመራቸውን አስታውቀዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ምስጋናው እንጅፋታ ለቢቢሲ እንደገለጹት በማረሚያ ቤት ኃላፊዎቹ ላይ እገታው የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ መጋቢት 22፣ 2014 ዓ.ም ከአሶሳ ከተማ ወደ ካማሺ ዞን እየሄዱ ባሉበት ወቅት መንገድ ላይ ነው። ሦስቱ ታጋቾች የት እንዳሉና በምን ምክንያት እንደታገቱ ሙሉ መረጃ ባይኖርም እስከ ትላንት በስቲያ ድረስ በሕይወት እንዳሉ መረጃ እንዳላቸው ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። ""በሌላ ስልክ አስደውለው በሕይወት እንዳሉና ""አታስቡ"" የሚል መልዕክትም ለቤተሰብ ማስተላለፋቸውን'"" ምክትል ኮሚሽነሩ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ከኦሮሚያ ክልል ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነና የክልሉም አባ ገዳዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ግለሰቦቹን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረጉ ነው ብለዋል። በካማሺ ዞን በኩልም የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ወደ ስፍራው አምርተው ቀጥታ ግንኙነት በማድረግ በውይይት ሰዎቹ እንዲለቀቁ ለማድረግም እቅድ እንዳለ አስታውቀዋል። ከካማሺ ዞን በኩል የሚወከሉት እኚሁ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስፍራው እንደሚያመሩም አስታውቀዋል። አጋቾቹ እነማን እንደሆኑ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምክትል ኮሚሽነር ምስጋናው ሲመልሱ "" እስካሁን በግልፅ የደረስንበት ነገር የለም፤ ነገር ግን በመረጃ ደረጃ በአካባቢው ታጣቂው የኦነግ ሸኔ ኃይል በስፋት ይንቀሳቀሳል። የተለያዩ ግድያዎችንም እዛው መንገድ ላይ በተደጋጋሚ ይፈፅሙ ነበር። ጥርጣሬያችንም ኦነግ ሸኔ ነው የሚል ነው"" ብለዋል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺና መተከል ዞኖችን ጨምሮ በተለያዩ ዞኖች ከዚህ ቀደም በታጣቂዎች በተደጋጋሚ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ምክንያት በርካታ ሰዎች ለሞትና ለመፈናቀል ሲዳረጉ መቆየታቸው ይታወሳል። የክልሉ መንግሥት እነዚህንም ጥቃቶች በመፈጸም ታጣቂውን የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን ተጠያቂ ሲያደርግ ቆይቷል። ከዚህ ቀደም የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥትና ታጣቂው የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞከራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) ቡድን በክልሉ በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስቆም የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60992723 +politics ትራምፕ እና ኦባማ ስለመጪው የግማሽ አመት ምርጫ ምን አሉ? ሁለቱ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች ባራክ ኦባማ እና ዶናልድ ትራምፕ በፔንሲልቫኒያ ባደረጉት የግማሽ አመት የምርጫ የድጋፍ ቅስቀሳ ምሽት ላይ ሁለቱም ስለ አገራቸው ያላቸውን የተለያየ ስጋት ገልጸዋል። ኦባማ ይህ የግማሽ አመት ምርጫ የአሜሪካን የዴሞክራሲ ጉዞ የሚወስን ነው ሲሉ፤ ትራምፕ ደግሞ የአገሪቷን የደህንነት ጉዳይ ቁርጡን የምናውቅበት ነው ሲሉ ቀስቅሰዋል። የፔንሲልቫኒያ ግዛት ዴሞክራቶችም ሆኑ ሪፐብሊካን የበላይነት የሌላቸው ሲሆን በተለያየ ግዜ ለተለያየ ፓርቲ የሚመረጥበት በተለምዶ ‘’ስዊንግ ስቴት’’ ተብለው ከሚጠሩ ግዛቶች አንዱ ነው። በግዛቲቱ ሪፐብሊካኑም ሆኑ ዴሞክራቱ በሚያሸንፉበት ወቅት የሚኖረው የድምጽ ልዩነት እጅግ ጠባብ ነው። በቅርቡ ለሚካሄደው የግማሽ አመት ምርጫ የግዛቲቱ ድምጽ አጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ነው ሁለቱ የቀድሞ ፕሬዘዳንቶች ፓርቲያቸውን ለማገዝ እና ለመቀስቀስ የተገኙት። እ.ኤ.አ. በ 2016 ትራምፕ ዋይት ሃውስን ለማግኘት የዚሁ ግዛት ድል ረድቷቸዋል። በመቀጠልም በ 2020 የጆ ባይደን የትውልድ ግዛት የሆነችውን ፔንሲልቫኒያን ዴሞክራቶች 2 በመቶ በሚሆን የድምጽ ብልጫ አሸንፈው ተረክበዋታል። ጆ ባይደን በፊላደልፊያ ቅዳሜ ዕለት ተገኝተው ቅስቀሳቸውን ባደረጉበት ወቅትም ‘’ወደ ቤቴ በመመለሴ ደስ ብሎኛል’’ ብለዋል። ፓርቲያቸው ላቀረባቸው ዕጩም ድጋፋቸውን ለግሰዋል። ዲሞክራቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ ድምጽ የማያገኙ ከሆነ የጤና መድህን ብሎም የጽንስ ማቋረጥ መብቶች ላይ ተጨማሪ እገዳ እንዲጣል ማስቻል እንደሆነም ተናግረዋል። የምርጫው ውጤት ትንበያዎች እንደሚያሳዩት ዴሞክራቶች በኮንግረስ የበላይነትን አያገኙም። ይህንንም ተከትሎ ቢያንስ በሴኔት የበላይነትን ለማግኘት ከፍተኛ ትንቅንቅ እያደረጉ ናቸው። ‘’በዚች የአሜሪካ የልብ ምት በሆነችው ግዛት ውስጥ መስቀለኛ መንገድ ላይ እንገኛለን’’ ሲሉ ጆ ባይደን ተናግረዋል። አክለውም ለዲሞክራቶች ድምጽ መስጠት ማለት ለሴቶች ጤና፣ በጦር መሳሪያ ቁጥጥር ብሎም ለጤና አገልግሎት ድምጽ መስጠት ነው ሲሉም አክለዋል። አንድ የግዛቲቱ ነዋሪ የትኛውንም ፓርቲ ይደግፉ የፕሬዘዳንቶቹ መገኘት ነዋሪው ወጥቶ እንዲመርጥ ያስችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነገር ግን ፕሬዘዳንቶቹን ለመመልከት ከወጡት ነዋሪዎች መካከል የተወሰኑ ኦባማን ለማየት መምጣታቸውን እና ባይደን ለብቻቸው ቢሆኑ ኖሮ ግን እንደማይመጡ ተናግረዋል። በምርጫ ዘመን አጋማሽ ላይ የሚደረገው ይህ ‘የሚድ ተርም’ ምርጫ በስልጣን ላይ ያለው ፕሬዘዳንት ላይ የሚደረግ ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ ይታያል። የጆ ባይደን ተቀባይነት 40 በመቶ ላይ እንዳለ በሚነገርበት በዚህ ወቅት ሪፐብሊካኑ የኑሮ ውድነት እና ስደትን የመሳሰሉ ምክንያቶችን በማንሳት ፕሬዘዳንቱ ላይ ቅስቀሳቸውን እንዲያጧጡፉም ረድቷቸዋል። ትራምፕ በበኩላቸው ዲሞክራቶች በዋሽንግተን የሚቆዩ ከሆነ ለተጨማሪ ወንጀሎች እንዲሁም ላልተገደበ የስደተኞች ፍሰት ያጋልጣሉ ሲሉ ቀስቅሰዋል። ‘’ለቤተሰባችሁ ደህንነት እና ጥበቃ የምትፈልጉ ከሆነ እያንዳንዱን ዴሞክራት በድምጻችሁ ከወንበሩ ማስነሳት አለባችሁ’’ ብለዋል። ‘’ያለው ምርጫ አንድ ብቻ ነው። የአሜሪካን መውደቅ የምትፈልጉ ከሆነ ድምጻችሁን ለአክራሪ ዴሞክራቶች ስጡ። የአገራችንን መውደም የማትፈልጉ ከሆነ ግን ሪፐብሊካንን ምረጡ’’ ሲሉ ትራምፕ ቀስቅሰዋል። እንዲሁም በ 2024 ለሚደረገው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሊወዳደሩ እንደሚችሉም ጠቁመዋል። እንዲሁም በድጋሚ የአሜሪካ የምርጫ ስርአት የተጭበረበረ ነው የሚለውን የሃሰት ክሳቸውን ማቅረባቸውን ቀጥለዋል። አንድ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ‘’ህይወትን ያለ ጭቆና እና ምን ማድረግ እንዳለብን ሳይነገረን እንድንኖር ረድተውናል’’ በሚል ለድጋፍ መውጣቱን ተናግሯል። በርካታ መራጮች በፍርሃት እና በሃሰት ቅስቀሳዎች ታጅበው ከሁለት ቀናት በኋላ በሚካሄደው የግማሽ አመት ምርጫ ይሳተፋሉ። ይህም የአሜሪካን የምርጫ ስርአት ታማኝነት የሚፈተሽበት ነውም ብለው ያምናሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c28wl49vp3eo +politics ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን ለሩሲያ ታማኝ የሆነ መሪ ለማስቀመጥ እያሴሩ ነው ተባለ "ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን ለሩሲያ ታማኝ የሆነ መሪ ለማስቀመጥ እያሴሩ እንደሆነ ብሪታኒያ ደርሼበታለሁ አለች። ዩናይትድ ኪንግደም ፕሬዝዳንት ፑቲን የሩሲያ ደጋፊ የሆነ ፖለቲከኛ የዩክሬንን መንግስት እንዲመራ ለማድረግ አሲረ��ል ስትል ከሳለች። የቀድሞ የዩክሬን ፓርላማ አባል የነበሩት ፖለቲከኛ ኢቭሄን ሙሬዬቭን የሩሲያ ምርጫ እንደሆኑ የዩኬ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ስም ጠቅሶ ገልጿል። ሩሲያ 100 ሺህ ወታደሮቿን ዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ያሰፈረች ቢሆንም ወረራ የማድረግ እቅድ የለኝም ስትል በተደጋጋሚ ገልጻለች። የዩናይትድ ኪንግደም ሚኒስትሮች የሩስያ መንግስት ዩክሬን ላይ ወረራ የሚፈጽም ከሆነ ከባድ መዘዝ ይጠብቀዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሊዝ ትረስ በጽሁፍ በሰጡት መግለጫ ""በዛሬው የወጣው መረጃ ዩክሬንን ለመናድ ሩስያ እያደረገች ያለችውን እንቅስቃሴ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ሲሆን የሩሲያ መንግስትንም እሳቤ የሚያንጸባርቅ ነው"" ብለዋል። ሩሲያ ጉዳዩን እንድታረግብ፣ የወረራ ዘመቻዋን እንድታቆም ሀሰተኛ መረጃ ከማሰራጨት እንድትቆጠብ እና የዲፕሎማሲ መንገድን እንድትከተል ሲሉም አሳስበዋል። ""ዩኬ እና አጋሮቻችን ደጋግመው እንደተናገሩት በዩክሬን ላይ የሚፈጸም ማንኛውም የሩሲያ ወታደራዊ ወረራ ከባድ ኪሳራን የሚያስከትል ትልቅ ስትራቴጂካዊ ስህተት ነው"" ሲሉም አክለዋል። እንደ አውሮፓውያኑ በ2014 ሩሲያ የዩክሬንን ግዛት ከመያዟ ቀደም ብሎ በሀገሪቱ ለሩስያ የታመኑ ፕሬዝዳንቷን ከስልጣን ተወግደው ነበር። የምዕራባውያን እና የዩክሬን የስለላ አገልግሎቶች በተያዘው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ በድንበር ላይ የሰፈረው የሩሲያ ጦር ሌላ ወረራ ሊፈጽም እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ምንም አይነት ጥቃት ዩክሬን ላይ ለማድረስ እቅድ የለኝም የምትለው ሩሲያ ደግሞ ዩክሬን ወደ ኔቶ ወታደራዊ ጥምረት መግባት የለባትም የሚል አቋም ግን አላት። ፕሬዝዳንት ፑቲን በአከባቢው ኔቶ እያደረገ ያለው ወታደራዊ ልምምድን የሚልከው የጦር መሳሪያ መላኩን ለሩሲያ ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት እንደሆነ ጠቅሰው ይህ እንዲቆም ጠይቀዋል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው የብሪታኒያ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሀሰት መረጃዎችን እያሰራጨ ነው ያለሲሆን ""ይህን መሰል ቀስቃሽ ተግባር እንዲያቆም"" እና ""እርባና ቢስ ወሬውን እንዲተው"" አሳስቧል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60101331 +sports የቱርካዊው የእግር ኳስ ኮከብ ጉዞ ከታዋቂ ፖለቲከኛነት እስከ ታክሲ ሹፌርነት ሃካን ሱኩር በቱርክ እግር ኳስ ታሪክ በርካታ ጎሎችን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። እስካሁንም የሚድርስበት አልተገኘም። በአንድ ወቅት በአውሮጳ እግር ኳስ አሉ ከሚባሉ ተጫዋቾችም አንዱ ነበር። አሁን ግን አሜሪካ ውስጥ የታክሲ ሹፌር ሆኗል፤ መፃሕፍትም ይሸጣል። እንዴት? ከአንድ የጀርመን ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረገው የ48 ዓመቱ ሳኩር ሕይወቱ ባልተጠቀ መንገድ እንዴት እንዲህ ሊሆን እንደቻለ ያስረዳል። ሱኩር፤ ከቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ጋር ያለኝ ቅራኔ ነው ለዚህ ያበቃኝ ይላል። ከእንገድልሃለን ማስፈራሪያ ጀምሮ እስከ ገንዘብ ክልከላ ድረስ የዘለቀ እርምጃ እንደተወሰደበት ይዘክራል። «ምንም ነገር የለኝም። ኤርዶዋን ሁሉን ነገር ወስዶብኛል። ነፃነቴን ገፎኛል። ሃሳቤን ነፃ ሆኜ መግለፅ ተሳነኝ፤ ሠርቼ መብላት አልቻልኩም።» በፈረንጆቹ ከ92-2007 ባለው ጊዜ ሳኩር ለቱርክ 112 ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን 51 ጎሎችን አስቆጥሯል። ቱርክ በ2002 የዓለም ዋንጫ ሶስተኛ ስትወጣ የቡድኑ አባል ነበር። ለእንግሊዙ የእግር ኳስ ክለብ ብላክበርን ይጫወት የነበረው ሱኩር፤ የእግር ኳስ ሕይወቱን አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፈው ጋላታሳራይ ለተሰኘው የቱርክ ክለብ በመጫወት ነበር። ሱፐር ሊግ በመባል በሚታወቀው የቱርክ እግር ኳስ ሊግ እንደ ሱኩር ብዙ ጎል ያገባ እ���ካሁን አልተገኘም። ሱኩር ጫማ ሲሰቅል ወደ ፖለቲካ ገባ። በግሪጎሪያን አቆጣጠር 2011 ላይ ምርጫ የኤርዶዋንን ፓርቲ ወክሎ ተዋዳድሮ በማሸነፉ በላይኛው ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴ ለመሆን በቃ። ነገር ግን ፌቱላህ ጉሌን ከተሰኘው የኤርዶዋን ዋነኛ ተቀናቃኝ ድርጅት ጋር ተያይዞ ስሙ ይነሳ ነበር። የቱርክ መንግሥት ደግሞ 2016 ላይ ለተከሰተውና በርካታ ሰዎችን ለቀጠፈው የቱርክ የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ ድርጅቱን ተጠያቂ ያደርጋል። ሱኩር በወቅቱ አሜሪካ ነበር። የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራውንም አጣጥሏል። ነገር ግን የቱርክ መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ ተጨዋቹ የፌቱላህ አባል ነው፤ አሁን በጥገኝነት አሜሪካ ይገኛል ሲል ዘገበ። ዘገባው ሱኩር፤ ሳን ፍራንሲስኮ በተሰኘችው የአሜሪካ የሃብታሞች ከተማ 3 ሚሊዮን ዶላር በሚያወጣ ቤት ውስጥ ይኖራል፤ የራሱ ካፌም አለው ሲል አተተ። «እርግጥ ነው ካሊፎርኒያ ውስጥ ካፌ ነበረኝ። ነገር ግን የማላውቃቸው ሰዎች ካፌዬን መጎብኘት ጀመሩ። አሁን የኡበር ሹፌር ነኝ።» ቱርክ ውስጥ ያሉ ቤቶቹ፣ ቢዝነሶቹም ሆኑ የባንክ አካውንቶቹ በኤርዶዋን መንግሥት እግድ እንደተጣለባቸው ይናገራል። የመንግሥትን ወቀሳም ያጣጥላል። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ኒው ዮርክ ታይምስ ከተሰኘው ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረገው ሱኩር «ሃገሬን እወዳለሁ፣ ሕዝቡን እንዲሁ። ምንም እንኳ ስለኔ ያላቸው አተያይ የተጣመመ ቢሆንም» ብሏል። በወቅቱ ዘገባው የኤርዶዋን መንግሥትን ጨቋኝነት ያሳያል በሚሉ ሰዎች ዘንድ ትኩረት አግኝቷል። 2018 ላይ የአርሴናሉ አማካይ ሜሱት ኦዚል ከፕሬዝደንት ኤርዶዋን ጋር ፎቶ በመነሳቱ ነቀፌታ አስተናግዶ ነበር። ኤርዶዋን፤ ኦዚል ሲሞሸር ሚዜው ሆነው መታየታቸውም አይዘነጋም። https://www.bbc.com/amharic/51116646 +business በኪራይ አህያ ንግድ ጀምረው ቢሊየነር የሆኑት ኢትዮጵያዊ ቶኩማ ፊጤ እባላለሁ፣ ተወልጄ ያደግኩት በምዕራብ ሸዋ ዞን በባኮ ትቤ ወረዳ፣ ቦኖ በሚባል ገጠር ውስጥ ነው። እዚያም ለቤተሰቦቼ ከብት ስጠብቅ ቆይቼ እድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ ወደ ትምህርት ቤት ተላኩኝ። ነፍስ ካወቅኩ ጀምሮ በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሰው ነገር ቢኖር የንግድ ሥራ ነው። የንግድ ሥራን በደንብ የጀመርኩትም የሰባተኛ እና የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ነው። በዚያን ጊዜ አህያ ተከራይቼ፣ ከገጠር ወደ ከተማ እህል በማመላለስ እሸጥ ነበር። ከከተማ ስመለስ ደግሞ እንደ ጋዝ፣ ዘይት፣ ጨው፣ ቡና የመሳሰሉትን ነገሮች በመግዛት አምጥቼ እሸጥ ነበር። በውስጤ ትልቅ ራዕይ ነበረኝ። ጠንክሬ ከሠራሁ አንደምለወጥ አምን ነበር። ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወደ ወረዳ ከተማ በመጣሁበት ጊዜ የበለጠውኑ እየተጠናከርኩ ራሴን መቻል ጀመርኩ። የሚያስፈልጉኝን ወጪዎች ከመሸፈን አልፌ ቤተሰቦቼን መደጎም የቻልኩት በዚህ ጊዜ ነው። ከዚህ በፊት ከአንድ ገበያ ወደ ሌላ ገበያ በመሄድ ያገኘሁትን ነገር ሁሉ እሸጥ ነበር። በኋላ ላይ ገን አንድ አዲስ ሃሳብ በአእምሮዬ ሽው አለ። እርሱም የንግድ ፈቃድ አውጥቶ መስራት የሚል ነበር። በዚህም መሰረት ወደ አምቦ ሄጄ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸውን መጻሕፍት ለመግዛት የሚያስችለኝን የንግድ ፈቃድ አወጣሁ። በዚህም መሠረት ያገለገሉትን ወረቀቶችን ሰብስቦ ለፋብሪካ ማቅረብ የሚያስችለኝን ንግድ የጀመርኩት በዚሁ ነበር። ያገለገሉ መጽሐፍትን በየትምህርት ቤቱ እየዞርኩ መግዛት ጀመርኩ። ይህንን ፈቃድ በማወጣበት ሰዓት በባንክ የቁጠባ ሂሳብ ደብተሬ ላይ የነበረኝ 72 ብር ብቻ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜም እነዚያን መጽሐፍት ገዝቼ የጫንኩት ኖኖ ቁንባ ከሚባል ወረዳ ነበር። የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው መጽሐፍት ከ���ጣሉበት እና ከተከማቹበት በማሰባሰብ በመኪና ጭኜ ወሰድኩኝ። በዚያን ቀን ለረዱኝ ሰዎች፣ ለጨረታ ኮሚቴዎች፣ ለመኪና ማስጫኛ የሚሆን የክፍያ ገንዘብ አልነበረኝም። እሁን እንጂ ሸጬ እከፍላችኋለሁ ብዬ ለምኜ አሳመንኳቸው። ከዚያ በኋላ መጽሐፍ የተባለ፣ አልያም ያገለገለ ወረቀት ከያለበት ዞሬ ያላሰባሰብኩበት የኦሮሚያ ዞን የለም ማለት ይቻላል። ይህንን የማሰባስበውን ወረቀት ደግሞ ለወረቀት ፋብሪካዎች አስረክባለሁ። ለእኔ ትልቅ ሥራ ነው ብዬ የጀመርኩት እንግዲህ እርሱን ነበር። ያገለገሉ መጽሐፍትን ሰብስቦ መሸጡ ጥሩ ገቢ ባገኝበትም ቀጣይነት ያለው ሥራ ስላልነበረ ሌላ ንግድ ሃሳብ ማሰላሰል ጀመርኩ። በዚህም መሰረት ቀጥሎ የከጀመርኩት ሥራ ያገለገሉ ብረታ ብረቶችን መሰብሰብ ነው። በገጠር አካባቢዎች በመዞር ከገበሬዎች ላይ አሮጌ በርሜሎችን፣ የተሰባበሩ መጥረብያዎችን እና የመሳሰሉትን ማሰባሰብ ጀመርኩ። እነዚህን የማሰባስባቸውን ብረታ ብረቶች የማቀርበው ደግሞ ለአቢሲኒያ ብረታ ብረት ፋብሪካ ነበር። ይህ የወዳደቁ ብረታ ብረቶችን የማሰባሰብ ሥራ ከሌሎች የተሻለ ስለነበር ጥሩ ገቢ ማግኘት ጀመርኩ። ይሁን እንጂ አንደ እርሱን እየሰራሁ፣ እንደለመደብኝ ቀጥሎ ምን መሥራት እንዳለብኝ ወደ ማሰላሰል ገባሁ። ሦስተኛውን የንግድ ፈቃድ ያወጣሁበት ሥራ የኤጀንሲ ፈቃድ ነበር። ይህንንም ያሰብኩት ሥራ ለሌላቸው ወጣቶች ሥራ ይፈጥራል በሚል አስተሳሰብ ነበር። በመጀመሪያ ስለ ኤጀንሲ ብዙ እውቀት አልነበረኝም። ስለሆነም በደንብ አጥንቼ አንዴት እንደሚሰራ ለማወቅ እና ፈቀድ ለማውጣት ሦስት ዓመታት ወስዶብኛል። እንዲህ ዓይነቱን የኤጀንሲ ሥራ የማውቃቸው ሰዎች እየሰሩ ስላልነበረ ለመልመድ ትንሽ ተቸግሬ ነበር። በመጨረሻ ግን ተሳክቶልኝ በአዲስ አበባ ውስጥ በዚህ የኤጀንሲ ሥራ ፈቃድ አገኘሁ። በዚህን ሰዓት ነበር በሁለት ነገሮች ስኬታማ መሆን እንደምችል የተረዳሁት። አንደኛው የቢዝነስ ሥራዬን ማሳደግ እንደምችል ሁለተኛው ደግሞ ለሌላቸው ዜጎች ሥራ መፍጠር እንደምችል አመንኩ። ይህ የኤጀንሲ ሥራ በወኪልነት ለድርጅቶች ሠራተኛ መቅጠር ነበር። ለምሳሌ እንደ ጥበቃ፣ የጽዳት ሥራ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል። በዚህም መሠረት እኛም ከተለያዩ ቦታዎች ሰዎችን ለሥራ እንመለምል ነበር። እነዚህንም ሰዎች አውቶብስ ተራ ድረስ ሄዶ በመቀበል፣ ወዳዘጋጀንላቸው መጠለያ በመውሰድ፣ ሥልጠና በመስጠት ወደ ተቀጠሩበት ስፍራ እናደርሳለን። በመሆኑም ይህ ሥራ ውስብስብ እና ከባድ ነበር። በተለይም ከገጠር ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ሰዎች አንዳንዶቹ ቋንቋ ስለማይችሉ ይቸገራሉ። ከተማም ለመልመድ የሚቸገሩም ሰዎች ነበሩ። ይሁን እንጂ ባለፉት 12 ዓመታት ውስጥ ከተለያዩ ቦታ ለመጡ ለ32000 ሰዎች የሥራ እድል እንዲያገኙ አድርገናል። ከእነዚህም መካከል 8500 የሚሆኑት በራሴ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው ደመወዝ የምንከደፍላቸው ሠራተኞች ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ ሥራቸውን እየሰሩ ትምህርታቸውን በመከታተል የመንግሥት ሥራ ሲቀጠሩ፣ ለትምህርት ወደ ውጪ አገር የሄዱ ጭምር ይገኙበታል። በአሁኑ ጊዜ ድርጅታችን 29 ፈቃዶች አሉት። ከእነዚህ መካከል 18 ፈቃዶች ከውጪ አገር እቃዎችን የምናስገባበት ሲሆን፣ 11 ፈቃዶች ደግሞ በአገር ውስጥ የተለያዩ ሥራዎች የምንሰራበት ነው። በአገራችን ውስጥ በክልሎችም ሆነ በፌደራል ደረጃ እንደ ቴሌ፣ መብራት ኃይል እና ውሃና ፍሳሽ ያሉ ተቋማት የሚያወጧቸው ጨረታዎች የከፍተኛ ብር ነው ጨረታ የሚያወጡት። በእንደዚህ ዓይነት ትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ስንጫረት ደግሞ ከብዙ ባለሀብቶች እና ከታዋቂ ሰዎች ጋር ነው የምንወዳደረው። እንደዚህ አይነት ትላልቅ ጨረታዎች ላይ ደግሞ እንደኛ ዓይነት ብዙ ሰው አይሳተፍም። ይህ ደግሞ ተጽዕኖም አለ። ይሁን እንጂ እኔ ደግሞ እንዲህ ዓይነት ነገሮችን መሞከር እወዳለሁ። አንዳንዴ ሰባት ጊዜ ወድቀን በስምንተኛው ይሳካልናል። ሌሎቹ ደግሞ አትችሉም ይሉናል። እኛም ሰምተን እንደምንችል አሳይተናቸዋል። እንደ እነዚህ ያሉ ጨረታዎች ደግሞ በቢሊዮኖች በሚተመን ብር የሚካሄድ ጨረታ ነው። በአብዛኛውም ጊዜ ደጋግመን በመሞከር በመጨረሻም ይሳካልናል። በዓመትም እንደዚህ ዓይነት ያሉ እስከ 50 ጨረታዎች ላይ እንሳተፋለን። በአሁኑ ሰዓት ሁለት ትልልቅ ድርጅቶች አሉን። እነርሱም ቲኤፍጂ ጄነራል ትሬዲንግ እና ቶኩማ ጄኔራል ትሬዲንግ ይባላሉ። እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተለያዩ የሕንጻ ግንባታ በማካሄድ ላይ እንገኛለን። ይህንን ስናደርግ ግን አንዲት ካሬ ሜትር እንኳ ከመንግሥት አልተሰጠንም። ሁሉንም በራሳችን ገንዘብ ገዝተን ነው የምናለማው። በአሁኑ ሰዓት ያለኝ ሀብት ግንባታዎችን እና በባንክ ያለኝ ገንዘብ ተደማምሮ ቢያንስ 5 ቢሊየን 500 ሚሊየን ይጠጋል። በቋሚነት ድርጅቴ ውስጥ የሚሰሩ 8500 ሠራተኞችም ደሞዝ እንከፍላለን። ልዩ የሚያደርገን አንዱ ነገር ከባንክ ተበድሬ አለማወቄ ነው። የምሠራቸውን ማንኛቸውንም ሥራዎች በራሴ አቅጄ ነው የምሰራው። ሰባራ ሳንቲም የባንክ ዕዳ የለብኝም። ይህ ያለኝን ሀብት ደግሞ የራሴ ብቻ አይደለም። የሠራተኞቼ እና የሕዝቡም ነው ብዬ አምናለሁ። በዚህም የተነሳ በዓመት በሚሊየን ብር የሚቆጠር ለተለያዩ ወገኖች ድጋፍ እንዳርጋለን። ለምሳሌ ባለፈው ዓመት በባኮ ወረዳ 26 ኪሎ ሜትር መንገድ በራሳችን ወጪ አሰርተናል። በአሁኑ ጊዜ በባኮ ገጠር የጀመርኩት ሥራ ተስፋፍቶ ዱባይና አሜሪካ ደርሷል። እቅዴም ይህንኑ ሀብት በትሪሊየን እንዲደርስ ማድረግ ነው። በማደግ ላይ ላሉ ወጣቶች የማስተላልፈው ምክር ቢኖር “ሥራ መናቅ የለባችሁም” የሚል ነው። ሥራን ከትንሽ ነገር መጀመር አለባቸው። ሀብት ማፍራት በሂደት የሚመጣ ስለሆነ “በአንዴ ለምን ሀብታም አልሆንኩም” ብሎ ተስፋ መቁረጥ የለባቸውም። በትንሽ በመጀመር እርሱኑ በማሻሻል ወደ ተሻለ ነገር በማሳደግ የሀብት ባለቤት ወደ መሆን ይደረሳል። እኔ ንግድ በጀመርኩበት ሰዓት ከአንቦም ሆነ ከአዲስ አበባ ምንም ዘመድ አልነበረኝም። አዲስ አበባ መጥቼ ለአልጋ ከፍዬ የማድርበት በማጣት መንገድ ላይ አድሬ አውቃለሁ። ይሁን እንጂ ተቸግርያለሁ፣ ከስሬያለሁ ብዬ ተስፋ ቆርጬ አላውቅም። ይኸው እኔ የገጠር ልጅ ዛሬ በአንቦ እና በአዲስ አበባ ብቻም ሳይሆን፣ በተለያዩ የዓለም ከተሞች በመዘዋወር እቃዎችን ገዝቼ ወደ አገሬ አስገባለሁ። ለዚህ ደግሞ ያበቃኝ ትዕግስትና ተስፋ አለመቁረጤ ነው ብዬ አስባለሁ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cz5negrvzp1o +politics """እስካሁን ደቂቃ ድረስ ድርድር አልተደረገም"" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ" """እስካሁን ደቂቃ ድረስ ከህወሓት ጋር ድርድር አልተደረገም። ድርድር አላደረግንም ማለት ግን እስከናካቴው ድርድር አይኖርም ማለት አይደለም"" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምላሽ ሰጡ። በዛሬው ዕለት የካቲት 15፣ 2014 ዓ. ም. በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም የመንግሥታቸው የስድስት ወራት አፈጻጸም በተመለከተ ማብራሪያ ሲስጡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የፌደራል መንግሥቱ ከህወሓት ጋር ድርድር እያደረገ ነው? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ነው ይህንን ምላሽ የሰጡት። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ፤ በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል እየተካሄደ ነው ስለሚባለው ድርድር ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። በተለይም ህወሓት በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ ከመፈረጁ አንጻር ድርድሩ፣ ከሞራል፣ ከሕጋዊነት እና ቅቡልነት አንፃር እንዴት ይታያል? የሚልም ጥያቄ በማቅረብ ማብራሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይስጡኝ ብለዋል። በተጨማሪም በቅርቡ መንግሥት የእነ አቶ ስብሃት ነጋን ክስ ማቋረጡ ከሕግ አግባብ ውጭና ሕገ መንግሥቱን የሚጣረስ ነው በሚል ውሳኔው እንዲቀለበስና ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በሦስተኛው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባሎች የቀረቡላቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሁለት ከፍለው ምላሽ ሰጥተዋል። ከሰሜኑ ጦርነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች፣ በአፋር ክልል እንደ አዲስ ያገረሸው ጦርነት፣ የእስረኞች መፈታት፣ ከህወሓት ጋር እየተደረገ ያለው ድርድር፣ የሻከረው ዲፕሎማሲ፣ የልዩ ኃይሎች መዋቅር እንዲሁም በአምባሳደሮች ሹመት ላይ ምላሽ ሰጥተዋል። ስለ እስረኞች መፈታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም ስለእነ አቶ ስብሃት ነጋ ክስ መቋረጥና እስረኞች የተፈቱበትን ምክንያት እንዲያብራሩ ከብዙ የምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ እስረኞች የተፈቱት ""እኛ የሞራል ልዕልና ስላለን ነው"" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ""እኛ የሞራል ልዕልና አለን። እናፈርሳቸዋልን፣ እንገድላቸዋለን ላልናቸው ምሕረት መስጠታችን የሞራል ልዕልና ይሰጠናል። ጉዳት የለውም"" ሲሉ ውሳኔውን አስረድተዋል። አያይዘውም ""ጠላቶቻን በቀየሱልን መንገድ መጓዝ አሸናፊ አያደርገንም። እኛ ለድል የሚያበቃንን መንገድ መቀየስ አለብን"" ብለዋል። እስረኞችን ለመፈታት የወሰኑት በሦስት ምክንያቶች እንደሆነ ጠቅሰው ""አንደኛው ዘላቂ ሰላም ለማምጣትና የጋራ ቤት ለመሥራት ነው"" ብለዋል። ጨምረውም ""ሁለተኛውም ምክንያት የታሳሪዎችን ሁለንተናዊ ሁኔታ ያገናዘበ ነው። ሁሉም እስረኛ አይደለም የተፈታው። ሦስተኛው ምክንያታችን ያገኘውን ድል ለማጽናት ነው"" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። እስረኞችን ክስ አቋርጦ መፍታት ሕጋዊ ተቃርኖ የሌለው ውሳኔ እንደሆነ ጠቅሰው ""በእርስ በእርስ ጦርነት ፍፁም ድል የለም። እኛ የምንመርጠው በቂ ድል ነው። አገርን ለመታደግ ነው"" ሲሉ እስረኞች የተፈቱበት ምክያት አስረድተዋል። አያይዘውም ""እነዚህ ሰዎች በመፈታታቸው ኢትዮጵያ ተጠቃሚ ናት። የፈታናቸው በጉቦ፣ በዝምድና አይደለም። የመፈታታቸውን ጥቅም አይተነዋል"" ብለዋል። ድርድር እየተደረገ ነው? የፌደራል መንግሥቱ ከህወሓት ጋር ድርድር እያደረገ ነው? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ""እስካሁን ደቂቃ ድረስ ድርድር አልተደረገም። ድርድር አላደረግንም ማለት ግን እስከናካቴው ድርድር አይኖርም ማለት አይደለም"" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ለሰላም አማራጮች የሆኑ መንገዶች እንደሚወሰዱ ጠቁመው ""የሰላም አማራጭ ካለ፣ ህወሓት ቀልብ ከገዛ በደስታ እናየዋለን"" ሲሉ ተናግረዋል። ትላንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገር ምክክር ኮሚሽነሮች መመረጣቸውን አጣቅሰው ""እኔ ድርድር ብዬ የማስበው አገር አቀፍ ውይይቱን ነው"" ብለዋል። በምክር ቤቱ የጸደቁት 11 ኮሚሽነሮች ሚናቸው ""ሁሉንም ማኅበረሰብ ማወያየት ነው እንጂ በሕዝበ ውሳኔ የሚወስነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው"" ሲሉም አክለዋል። ብሔራዊ ውይይት ይህ ብሔራዊ ውይይት በቀላሉ መታየት እንደሌለበትና የተቃዋሚ ፖርቲዎችም ዕድሉን መጠቀም እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል። ""ለህወሓትም ሆነ ለየትኛውም ኃይሎች"" ትናንት የጸደቁት ኮሚሽነሮች ዋነኛ ተግባራቸው መድረኮችን ማመቻቸትና አጀንዳዎችን መፍጠር ነው ብለዋል። በአፍሪካ ውስጥ በአብዛኛው የሚደረገው የልሂቃን ውይይት እንደተደረገና ይህ ደግሞ አገራዊ አጀንዳ ሳይሆን ሥልጣን ክፍፍል መሆኑን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት አገሪቷ የምትዘጋጅበት ውይይትም ሆነ ድርድር የሥልጣን ክፍፍል አለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል ብለዋል። የሥልጣን ክፍፍሉ በምርጫ የተጠናቀቀ ጉዳይ ነው ብለው፤ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ኢትዮጵያን የሚገዛት ብልፅግና ፓርቲ መሆኑን አስታውሰዋል። ብሔራዊ ውይይቱና ምክክሩ የሚደረገው በቆሰሉ ታሪኮችና ነገ በምንገነባት ኢትዮጵያ ላይ ፟እንደሆነ ""የምንገነባው አገር ከሥልጣናችን በላይ ስለሆነ ነው፤ ለወደፊቱ ትውልድ ስለሆነ ነው"" ሲሉም አስረድተዋል። የውይይቱ ሂደት በዋነኝት ሊያካትታቸው የሚገባ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህም ግልፅ፣ የሚገለል ማኅበረሰብ የሌለበትና ሁሉንም ሕዝብ አሳታፊ ሊሆን እንደሚገባም አንስተዋል። እንደ ምሳሌ የጠቀሱት በሕገ መንግሥቱ ላይ ያለውን አንቀፅ 39፣ በርካታ ጥያቄ የሚያነሱ ፓርቲዎችን ጉዳይ እንዲሁም የሰንደቅ አላማ ጉዳይን ሲሆን በአሁኑ ወቅት አገሪቱን የሚያከራክሩና የሚያጣሉ ጉዳዮች መቋጫ ሊያገኙ የሚችሉበት ነው ብለዋል። ውይይት የሚያስፈልገው ሽኩቻ፣ ጦርነትና የፖለቲካ ሽግግር ሲኖር መሆኑን ጠቅሰው አገሪቷ እያተዘጋጀችበት ያለችውም ምክክር አራት ምዕራፎች እንዳሉት ጠቅሰዋል። እስካሁን የተካሄደው ቅድመ ዝግጅት ሲሆን እስካሁን ያለው ብሔርና ፆታን ባሳተፈ መልኩ የተዋቀረ በመሆኑ ጥሩ ጅማሮ ነው ብለዋል። ""በውይይትና በድርድር የሚፈታ ችግር ካለ መንግሥት ለማንም በሩ ክፍት ነው። እኛ የምንጠላው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚነካ ሲሆን ነው"" ብለዋል። በጦርነቱ ለተጎዱት አማራና አፋር ክልሎች በጀት በጦርነቱ የተጎዱትን የአማራና የአፋር ክልሎች መልሶ ለማቋቋም የተመደበው በጀት አነስተኛ ነው በሚል ከምክር ቤት አባላት ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። የሁለቱን ክልሎች ብቻ ሳይሆን የሌሎችም ሕዝቦች ችግር መጠቀስ አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ""የትግራይ ሕዝብ መብራት የለውም፣ ምግብ እየተቸገረ ነው፣ መድኃኒት እጥረት ላይ ነው"" ብለዋል። አክለውም ""ትግራይ እንድትገነጠል አንፈልግም፤ ትግራይ ትገንጠል ብትባል 100 ፐርሰንት አይሆንም ትላላችሁ። እንዲገነጠሉ የማንፈልግ ከሆነ እንዳይጎዱም ስለ ሕዝቡ የሚገባውን መብት ማሰብ አለብን። ያንን ማድረግ ከቻልን ነው አብረን ነው መኖር የምንችለው"" ብለዋል። በተጨማሪ በሰሞኑ እንደ አዲስ ካገረሸው ጦርነት ጋር ተያይዞ የአፋር ክልል በፌደራሉ ወይም በመከላከያ ተዘንግቷል በሚል ከምክር ቤት አባል ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በምላሹ የፌደራል መንግሥት ከአፋር ክልል ጋር በከፍተኛ ቅርበት እንደሚሠራ ተናግረዋል። ""ማንኛውም የአፋር ጥቃት፣ የአማራ ጥቃት የኢትዮጵያ ጥቃት ነው"" በማለትም የሰሞኑ ጥቃት አላማ አፋር አይደለም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በትግራይና በአፋር ክልል የተነሳውን ጦርነት ህወሓት ""የእርዳታ እህል እንዳይገባ በሚል ነው ጥቃት የከፈተው"" ብለውታል። የአማራና የአፋር ክልሎች ወደ ትግራይ እርዳታ እንዳይገባ ዘግተዋል የሚባለውም ከእውነት የራቀ እንደሆነም አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ዘንድ መንግሥታቸው የትግራይን ሕዝብ ሆን ብሎ እንደሚያስርብና እርዳታ እንደሚከለክል እንደሚታሰብም ገልጸዋል። ""ስማችን በዓለም ላይ ጠልሽቷል፤ እኛ ሕዝብ እንዲራብ አንፈልግም"" ብለዋል። በዚህ ጦርነት እንደ ትግራይ ክልል የተጎዳ የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራና የአፋር ሌላውም ኢትዮጵያ ትግራይን መገንባት እንዳለበትም አስረድተዋል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር የሚለውና መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለውን ቡድን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ ""ኃይሉ አላማ የሌለው፣ ዘረፋና ግድያና የሚፈፅም"" መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ኃይልም ለመግታት መንግሥትና የኦሮሚያ ክልል ለወራት ያህል ከፍተኛ መስዋዕትነት እንደከፈሉ ተናግረዋል። በኦሮሚያ ላይ ከፍተኛ መሠረተ ልማቶችን ቢያወድምና መንግሥትም ኃይሉን ለመግታት ከፍተኛ ሥራ ቢሠራም ""በወታደራዊ ሥራዎች ብቻ የሚፈታ አይደለም። ሕዝቡስ ለምን ተሸከመው? ለምን ቀለበው? የሚለው ጥያቄ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ መፈታት አለበት"" በማለት አስረድተዋል። ሆኖም የትኛውም ታጣቂ ኃይል ""ኢትዮጵያን አያሸንፍም"" ብለዋል። ልዩ ኃይል የልዩ ኃይል አወቃቀር ላይ የተነሳውን ጥያቄ በተመለከተ በየክልሉ ያለውን ችግር ለመፍታት ልዩ ኃይል አስፈላጊ እንደሆነና የልዩ ኃይል አባላት እንዴት ይሥሩ? የሚለው ላይ ግን ንግግር በማድረግ ለወደፊት አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚቻል ተናግረዋል። የተቃዋሚዎች ተሳትፎ የምክር ቤቱ አባላት ካነሱት ጥያቄ መካከል መንግሥት ምን ያህል ከተቃዋሚዎች ጋር ይሠራል? የሚለው ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በምላሻቸው የአገር ምክክር ኮሚሽን በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚኖረውን መናበብ የተሻለ ያደርጋል ብለው እንደሚያምኑ ጠቁመዋል። እስካሁን ድረስ በነበረው ሂደት ""የልሂቃን አክራሪነት እጅግ አደገኛ ነው። ዋልታ ረገጥነት አገርን ይጎዳል"" ሲሉ አጠቃላይ የፖለቲካ ልሂቃል ግምገማቸውን አስቀምጠዋል። ድርቅ በሶማሌ፣ ኦሮሚያና ሌሎችም በአገሪቱ በተለያዩ ክልሎች የተስፋፋውን አሳሳቢ ድርቅ በተመለከተ ምላሽ ሲሰጡ ""እስካሁን ሰው አልሞተብንም"" ብለው እስካሁን 750 ሺህ ኩንታል ምግብን ጨምሮ የልጆች ምግብ፣ የከብት መኖ እና ክትባት እንደተላከ ጠቅሰዋል። ግድቡ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨትና ከሱዳን እንዲሁም ከግብፅ ጋር ያለውን ውጥረት በተመለከተ ""ውሃው ተርባይኑን መትቶ ሄዷል። ከዚህ በኋላም በድርድርና በውይይት አብረን እንሠራለን"" በማለት ኢትዮጵያ ሦስቱንም አገራት ያማከለ አካሄድ እንደምታራምድ ተናግረዋል። የዲፕሎማቶች ሹመት በአገሪቱ ውስጥ አነጋጋሪ የተባሉት የሁለቱ ጄኔራሎች ባጫ ደበሌና ሃሰን ኢብራሂም እንዲሁም የኢንጂነር ስለሺ በቀለ በአምባሳደርነት የተሾሙበት መስፈርት ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል። በተለይም በቅርቡ የተሰጡ የአምባሳደር ሹመቶችን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ""ብቃት ያላቸው ሰዎች ናቸው የተሾሙት"" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ""በኢትዮጵያም በዓለምም ብዙ ወታደር አምባሳደር አለ። ውጊያ መምራት እና ዲፕሎማሲ ተመጋጋቢ ነው"" በማለት ሹመቶቹ በምን ምክንያት እንደተሰጡም ጠቁመዋል። ሳዑዲ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ በተለይም በእስር ቤቶች የሚንገላቱ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ፤ ሁሉም ሳዑዲ ያሉት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለሱ ያደረገው ምክንያት ከመካከላቸው ""የሠለጠኑ ገዳዮች"" እንዲሁም በሌላ መንገድም የደኅንነት ስጋት የሆኑ ስላሉበት እንደሆነ አስረድተዋል። ""ከሳዑዲ ጋር በቅርበት እየሠራን ው። ስንመልሳቸው ጥፋት የሚያስከትሉ እንደሚኖሩ ስጋት ስላለብን ነው። አብረው የሚጎዱ ንጹሀንም ስላሉ ጥናት እያደረግን ነው"" ሲሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/60479375 +sports ዋሊያዎቹ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ደቡብ አፍሪካን ዛሬ ይገጥማሉ በኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ከዚምባብዌ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሶስተኛ የምድብ ጨዋታውን ቅዳሜ መስከረም 28/2014 ዓ.ም በባህር ዳር ስቴዲየም ከባፋና ባፋናዎች ጋር ያደርጋል። በምድቡ የመጀመ��ያ ጨዋታው ወደ ጋና ያቀኑት ዋሊያዎቹ በጨዋታው አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት መሸነፋቸው የሚታወስ ነው። ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ኳስ ይዞ ለመጫወትና የበላይነት ለመውሰድ ቢሞክርም በጨዋታው ግን ግብ ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል። ጨዋታው በተጀመረ 35ኛው ደቂቃ ላይ የጋናው ሚባራክ ዋክሶ ከርቀት የሞከራት ኳስ ወደ ግብነት ተቀይራ ጨዋታው በጋና አንድ ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል። በመቀጠል በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በባህር ዳር ስቴዲየም ዚምባቡዌን የገጠመ ሲሆን ጨዋታውን አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። ከባድ የተባለው ምድብ ውስጥ የተደለደሉት ዋሊያዎቹ ለድል ያበቃቻቸውን ግብ ማስቆጠር የቻሉት በጨዋታው መጠናቀቂያ ሰዓት ላይ የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ተከላካዩ አስቻለው ታመነ ወደ ግብነት በመቀየሩ ነው። ጨዋታውን አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት በማሸነፍ ዋሊያዎቹ የመጀመሪያውን ሦስት ነጥብ በባህር ዳር ስታዲየም ማግኘት ችለዋል። እስካሁን በምድቡ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ደቡብ አፍሪካ ዚምባብዌን ካሸነፈች በኋላ ከጋና ደግሞ አቻ ተለያይታለች። ዚምባብዌ ደግሞ ከደቡብ አፍሪካ አቻ ተለያይታ በኢትዮጵያ አንድ ለባዶ ተሸንፋለች። በዚህም ምድቡን ደቡብ አፍሪካ በአራት ነጥብ ስትመራ፣ ጋናና ኢትዮጵያ በተመሳሳይ በሦስት ነጥብ በመያዝ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃቸውን አስጠብቀዋል። ዚምባቡዌ ደግሞ በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኳታር በምታስተናግደው የ2022 የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ እድላችን አሁንም ከፍተኛ ነው የሚሉት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ፤ ከደቡብ አፍሪካ አቻቸው ጋር ላለባቸው የምድብ ማጣሪያ በባህር ዳር በመከተም ዝግጅት ጀምረዋል። ለዚህ ጨዋታ ዝግጅት ለማድረግ ደግሞ ለ25 ተጨዋቾች ጥሪ አድርገዋል። በዚህም ግብ ጠባቂዎች ጀማል ጣሰው፣ ተክለማርያም ሻንቆና ፋሲል ገብረሚካኤል ሲሆኑ፤ ተከላካዮች አስቻለው ታመነ፣ አስራት ቱጂ፣ ሱሌማን ሀሚድ፣ ረመዳን የሱፍ፣ ያሬድ ባዬ፣ ደስታ ዮሐንስ፣ ምኞት ደበበና መናፍ አወል ተካተዋል። አማካዮች ደግሞ ሽመልስ በቀለ ፣ ይሁኔ በላይ፣ ጋቶች ፓኖም፣ መሱድ መሐመድ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ ታፈሰ ሠለሞን፣ ሽመክት ጉግሳና አማኑኤል ዮሐንስ ናቸው። የፊት መስመር ተጫዋቾች ደግሞ አማኑኤል ገብረሚካኤል፣ ጌታነህ ከበደ፣ አቤል ያለው፣ ቸርነት ጉግሳ፣ መስፍን ታፈሰና አቡበክር ናስር መሆናቸው ይፋ ተደርጓል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት በአለም ዋንጫ ማጣሪያ የፊታችን ቅዳሜ የደቡብ አፍሪካ አቻውን የሚገጥሙት ዋልያዎቹ መደበኛ ልምምዳቸውን ሐሙስ ዕለት መስራታቸውን ገልጿል። ለግብጹ ጎና ኤፍሲ የሚጫወተው የመሀል ክፍል አንቀሳቃሹ ሽምስ በቀለ ከቀናት በፊት ባህር ዳር የሚገኘውን ቡድን የተቀላቀለ ሲሆን ከቡድን አጋሮቹ ጋርም ልምምድ መስራቱን ፌደሬሽኑ አስታውቋል። https://www.bbc.com/amharic/news-58839830 +health የኮቪድ -19 ዝርያዎች በክትባቱ ላይ ‘ስጋት’ ፈጥረዋል ተባለ "በከፍተኛ ተላላፊ የሆኑት የኮሮናቫይረስ ዓይነቶች መስፋፋት በአሜሪካ ""ለአራተኛ ጊዜ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ሊያንረው ይችላል"" የሚል ስጋት መኖሩን አንድ ከፍተኛ የጤና ባለሥልጣን አስጠንቅቀዋል፡፡ የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል (ሲ ዲ ሲ) ኃላፊ በቅርቡ የሚወጡት የኮቪድ -19 መረጃዎች እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት በቀን ወደ 70 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መያዛቸው መመዝገቡን ""በጣም ከፍተኛ ቁጥር"" ነው ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ በየቀኑ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች እንደሚሞቱ ተናግረዋል፡፡ ""እባካችሁ በግል��� አድምጡኝ በዚህ ዝርያ ስርጭት ያገኘነውን ስኬት ልናጣው እንችላለን፡፡ አዳዲሶቹ ዝርያዎች ለህዝባችንም ሆነ ለዕድገታችን እውነተኛ ስጋት ናቸው"" ሲሉ የሲዲሲዋ ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼል ዋለንስኪ ሰኞ ዕለት ገልጸዋል። በርካታ የኮቪድ -19 ዝርያዎች ስርጭት ቢኖርም የጤና ባለሙያዎች ለጥቂቶቹ ብቻ ትኩረት ሰጥተዋል፡፡ በዚህም መጀመሪያ በእንግሊዝ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በብራዚል ይበልጥ ተላላፊ የሚመስሉ ዓይነቶችን ያካትታሉ፡፡ ሲዲሲ በእንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በጣም ተላላፊው B.1.1.7 የተሰኘው ዝርያ በዚህ ወር በአሜሪካ ዋነኛው ስጋት እንደሚሆን ተንብይዋል፡፡ ክትባቶች መሰጠት ከጀመሩበት ጥር ወር ጀምሮ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ዕለታዊ የሰዎች በቫይረሱ የመያዝ እና የሞት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል፡፡ ሲዲሲ ይህን ለብዙዎች ክትባት እስከሚሰጥ ድረስ አዲሶቹ ዝርያዎች ቀድሞውኑ በችግር ላይ ያሉ የጤና ስርዓቶችን አደጋ ላይ እስከሚጥሉ ድረስ በፍጥነት ሊዛመቱ ይችላሉ ብሏል፡፡ እንደሲዲሲ መረጃ ከሆነ አሳሳቢ የሆኑ ዝርያዎችን የሚያካትቱ ከ 2 ሺህ 463 በላይ ኢንፌክሽኖች ሪፖርት ተደርገዋል፡፡ ቢያንስ 2 ሺህ400 የሚሆኑት በእንግሊዝ የተገኘው ዝርያ ዓይነት ናቸው፡፡ በአሜሪካ ውስጥ በአዳዲሶቹ ዝርያዎች የተያዙ ሰዎች እውነተኛ ቁጥር ከዚህ የበለጠ ነው ተብሎ ይገመታል፡፡ በአዳዲሶቹ ዝርያዎች የሚጠቁ ሰዎች ላይ በጣም ከባድ በሽታ ስለማምጣቱ ምንም ማስረጃ የለም፡፡ የሳይንስ ሊቃውንት በሥራ ላይ የዋሉት ክትባቶች አዳዲሶቹንም ዝርያዎች ጭምር ይከላከላሉ ብለው ያምናሉ፡፡ እስከሰኞ ድረስ አሜሪካ ከ 76 ሚሊዮን በላይ ክትባቶችን እንደሰጠች የሲዲሲ መረጃዎች ያመለክታሉ። አሜሪካ ከዓለም ሀገሮች ከፍተኛውን የክትባት መጠን ሰጥታለች፡፡ ሆኖም ቁጥሮቹ ከሕዝብ ቁጥር ለ100 ሰዎች ከተሰጠው አንጻር ሲወዳደር አሜሪካ ከእንግሊዝ፣ ከአረብ ኤሚሬቶች እና ከእስራኤል ቀጥሎ በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በአሜሪካ ክትባት ከተሰጣቸው መካከል የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ እንደሚገኙበት ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡ ሁለቱም በጥር ወር ኋዋይት ሃውስ ክትባቱ እንደወሰዱ አንድ አማካሪ ለኒው ዮርክ ታይምስ እና ለሌሎች የአሜሪካ የመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል፡፡ የትኛው ክትባት እንደወሰዱ ግልፅ ባይሆንም በጥር ወር በተቆጣጣሪዎች ፈቃድ ያገኙት የፋይዘር እና ሞደርና ክትባት ብቻ ነበር፡፡ በጆንሰን እና ጆንሰን የተሠራው እና አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠው ክትባት በአሜሪካ ጥቅም ላይ እንዲውል ቅዳሜ ፈቃድ አግኝቷል፡፡ ዶ/ር ዋለንስኪ በአሜሪካ ግዛቶች ሪፖርቶች ""በእውነት ተጨንቄያለሁ። ሰዎችን ከኮቪድ-19 ለመከላከል ወደምንመክረው ትክክለኛ የህዝብ ጤና አጠባበቅ እርምጃዎችን ወደ ኋላ ትመልሳለች"" ብለዋል፡፡ ""አራተኛ ዙር ከፍተኛ ቫይረሱ ስርጭር በዚህ እንዳይከሰት የማስቆም አቅም አለን፡፡ እባካችሁ በእምነታችን ጠንካራ እንሁን"" ብለዋል፡፡ አሜሪካ ከ 28 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙባት እና ከኮቪድ -19 ጋር በተያያዘ 500,000 ሰዎችን ሞት አስመዝግባለች ይላል የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-56249154 +health ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮና ክትባትን በዓለም ለማሰራጨት 8ሺህ ግዙፍ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ ይበለውና የኮሮና ክትባት ቢሳካ በነገታው እንወጋዋለን ማለት አይደለም፡፡ በመላው ዓለም ማሰራጨቱ በራሱ ሌላ ትልቅ ፈተና ነው ሲል የአቪየሽን ኢንደስትሪ ማኅበር ተናግሯል፡፡ ምናልባትም በአውሮፕላን የካርጎ ታሪክ እጅግ ከባዱ ፈተና፣ እጅግ ከባዱ ኃላፊነት ይሆናል ተብሏል፡፡ የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር (IATA) እንደሚለው ምናልባት ክትባቱ ቢሳካ እያንዳንዳቸው የቦይንግ 747 አውሮፕላኖች አይነት ግዝፈትና ፍጥነት ያላቸው 8ሺህ ግዙፍ የካርጎ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ ብሏል፤ ክትባቱን ለማዳረስ፡፡ ምንም እንኳ ለጊዜው ክትባት ባይፈበረክም፣ መሳካቱ አይቀርም በሚል የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ነገሮችን ለማቀናጀት ከወዲሁ ተፍ ተፍ እያለ ነው፡፡ ማኅበሩ በጤና ዙርያ ከሚሰሩት በርካታ ድርጅቶች፣ ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከመድኃኒት አምራቾች፣ ከመድኃኒት አቀባባዮች፣ አከፋፋዮች፣ ከአውሮፕላን ካርጎ ሥራ ተሳታፊዎች ጋር በጥምረት መስራት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይህ 8ሺህ ቦይንግ ያስፈልጋል የተባለው ታዲያ አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ብቻ፣ አንድ ጠብታ ክትባት ብቻ ነው የሚያስፈልገው በሚል የተሰላ ሲሆን ይህ ግምት ለምሳሌ በእጥፍ ቢጨምር እጥፍ ካርጎ አውሮፕላን ያሻል ማለት ነው፡፡ የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ አሌክሳንደር ዴ ጁኒያክ እንዲህ ተናግረዋል፣ ‹‹የኮቪድ 19 ክትባትን በጥንቃቄ ማጓጓዝ የዚህ ክፍለ ዘመን ትልቁ የካርጎ ኢንዱስትሪ ግብ ነው፡፡ ነገር ግን እንዲሁ በዘፈቀደ የሚጓጓዝ አይደለም፤ ከፍተኛ ዝግጅት ይፈልጋል፡፡ ለዝግጅቱ ትክክለኛው ጊዜ ደግሞ አሁን ነው›› በርካታ አየር መንገዶች በወረርሽኙ ጊዜ የሰዎች ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ በመታቀቡ ወደ ካርጎ ሥራ ገብተው ቆይተዋል፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይጠቀሳል፡፡ ነገር ግን ማንም እቃ የሚያጓጉዝ አየር መንገድ ክትባትን ማጓጓዝ ይችላል ማለት አይደለም፡፡ ክትባት ለማጓጓዝ ካርጎው ከ2 እስከ 8 ሴንትግሬድ የሙቀት መጠን ሊኖረው ይገባል፡፡ አንዳንድ ክትባቶች ደግሞ እጅግ ቀዝቃዛ (ከዜሮ በታች) የሆነ የሙቀት መጠንን ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ ይህን ማሟላት ለብዙ አየር መንገዶች ፈተና ሊሆን ይችላል፡፡ ዝግጅት ከወዲሁ የተጀመረውም ለዚሁ ነው፡፡ ይህንን ክትባት የማጓጓዙን ፈተና ለመቀነስ አንዱ መንገድ አገራት በየራሳቸው ክትባቱን እንዲያመርቱት ማድረግ ቢሆንም ይህ ለብዙ የዓለም አገራት የሚቻል አይሆንም፡፡ በተለይ በርካታ የካርጎ በረራዎች ወደ ደቡብ ምሥራቅ ኢሲያ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ሕዝብ ስለሚገኝና ክትባት የማምረት አቅም ያለው አገርም ባለመኖሩ ነው፡፡ ክትባቱን በቀላሉ ወደ አፍሪካ ለማጓጓዝም የሚቻል አይደለም ብሏል ማኅበሩ፡፡ ይህም በቂ የካርጎ አቅም ስለሌለ፣ አፍሪካ ሰፊ አህጉር በመሆኗና የድንበር ውስብስብነት መኖሩ ነው፡፡ የካርጎ ሥራው ልክ ወታደራዊ ጥንቃቄን የሚፈልግ ነው፤ ከተጓጓዘ በኋላም ቢሆን የሚቀመጥበት ቦታ መድኃኒቱን ለማስቀመጥ የሚሆን መሆን አለበት፡፡ ይህ ደግሞ ለበርካታ የአፍሪካ አገሮች ፈተና ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዓለም ደረጃ 140 ቤተ ሙከራዎች ክትባት ለመሥራት ተፍ ተፍ ማለት ጀምረው ነበር፡፡ አሁን 24 የሚሆኑት በሰዎች ላይ ሙከራ ጀምረዋል፡፡ ከነዚህ ሁሉ ትልቅ ተስፋ የተሰጠው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው የክትባት ሙከራ ነው፡፡. ሩሲያ ክትባቱ በእጄ ገብቷል ብትልም ዓለም በአገሪቱ ላይ እምነት በማጣቱ ይመስላል እምብዛምም የራሺያ ክትባት አይወራም፡፡ የጤና ባለሙያዎች የሩሲያ ክትባት ሳይንሳዊ ሂደትን የተከተለ አይደለም፣ ብሔራዊ ኩራተን ከጤና አስበልጧል ሲሉ ይተቹታል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-54093179 +politics ትግራይ ፡ የቀድሞው ርዕሰ መስተዳደርና ምክትል ሚኒስትር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ "የቀድሞው የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር፣ የገንዘብ ምክትል ሚኒስትርና ምክትል ርዕሰ መስተዳደርን ጨምሮ በርካታ የህወ��ት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው እንዲሁም መገደላቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሠራዊቱ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንደገለጹት በጸጥታ አካላት ከተያዙት ውስጥ ሰባት የህወሓት ፖለቲካዊ አመራሮች እንዲሁም ""ከአገር መከላከያ ሠራዊት ከድተው ቡድኑን የተቀላቀሉ"" ወታደራዊ መኮንኖች እንደሚገኙበት አመልክተዋል። የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት አቶ አባይ ወልዱ እና ቀደም ሲል የፌደራል የገንዘብ ምክትል ሚኒስትር በኋላ ደግሞ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ከተያዙት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ይገኙበታል። በተጨማሪም ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ከአገር መከላከያ ሠራዊት ከድተው ከህወሓት ጋር ተሰልፈው ነበር ያሏቸው ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖች እንዲሁም የግል ጥበቃዎቻቸው ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል። መገደላቸው ከተነገረው ከፍተኛ መኮንኖች መካከል የቀደሞው የአገር መከላከያ የሎጂስቲክስ ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል እና የመከላከያ ሠራዊት የኢንዶክትሪኔሽን የቀድሞ ኃላፊ የነበሩት ብርጋዲየር ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም እንደሚገኙበት ተጠቅሷል። በክልሉ የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ከነበሩ ውስጥም የትግራይ ኦዲተር ቢሮ ኃላፊ ረዳኢ በርሄ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ኃላፊ ሙሉጌታ ይርጋ (ዶ/ር)፣የኃይማኖት ጉዳይ ክትትል ኃላፊ አቶ ዕቁባይ በርሄ፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤትና የሠላምና ደኅንነት ኃሃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈሪ እንዲሁም የክልሉ ማኅበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ ኪሮስ ሐጎስ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተገልጿል። የመከላከያ ሠራዊቱ የስምሪት መምሪያ ኃላፊው ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ጨምረው እንደተናገሩት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ከተገለጹት ሁለት ጄነራል መኮንኖች በተጨማሪ ከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖችና የግል ጥበቃዎቻቸው እንዲሁም አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበረና ከፖሊስ የከዳ ግለሰብ መገደላቸውን አመልክተዋል። በተጨማሪም ከመከላከያ ሠራዊት ከድተው ከህወሓት ጋር ተቀላቅለው ነበር ያሏቸው ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር አምባዬና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ የተባሉ ሁለት ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። እየተፈለጉ ያሉትን የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮችን ለመያዝ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት በጥምረት አሰሳና ፍተሻ እያደረጉ መሆናቸውን ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው አመልክተዋል። ቀደም ሲል የተያዙ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ወደ አዲስ አበባ መወሰዳቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከእነዚህም መካከል በሰማኒያዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙትና የህወሓት መስራች የሆኑት አቶ ስብሐት ነጋ የሚገኙበት ሲሆን አብረዋቸውም ሌሎች በክልሉና በቡድኑ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የነበሩ ግለሰቦች ይገኙበታል። ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ የጸጥታ ኃይሉ ባደረገው አሰሳ የተገደሉና በቁጥጥር ስር የዋሉ የህወሓት ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል አመራሮች የስም ዝርዝር ይፋ መደረጉ ይታወሳል። የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ታኅሳስ 23 ቀን 2013 ዓ. ም. በሰጠው መግለጫ፤ የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ሙሉ ገብረእግዚአብሔርና በርካታ ወታደራዊ መኮንኖች መማረካቸውን እንዲሁም በርካቶች መደምሰሳቸውን አስታወቆ ነበር። እስካሁን መገደላቸው እንዲሁም መያዛቸው ከተገለፁ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ሌላ የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አዲስዓለም ባሌማንና የቀድሞዋን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ ኬርያ ኢብራሂም ጨምሮ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የቀድሞ ባለሥልጣናት ይገኛሉ። እየተፈለጉ ያሉ አመራሮች እስካሁን ድረስ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤልም ሆኑ ሌሎች ከፍተኛ ሹማምንቶች ያሉበት ሁኔታ በዚህ መግለጫ ላይ አልተጠቀሰም። ከጥቂት ሳምንት በፊት የመከላከያ ሠራዊቱ ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ያሉበትን ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ማዘጋጀቱን መግለጹ ይታወሳል። መንግሥት በቁጥጥር ስር ውለዋል ወይም ተገድለዋል ያላቸውን የህወሓት ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል አመራሮችን በተመለከተ ከቡድኑም ሆነ ከሌላ ገለልተኛ ወገን የተሰማ ነገር የለም። የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ስትገባ የህወሓት አመራሮች ውጊያውን እንደሚቀጥሉ ከገለጹ በኋላ ስላሉበት ሁኔታና ወቅታዊ ጉዳዮች በይፋ የሰጡት መግለጫ የለም። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ምሽት የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት ተቀስቅሶ ክልሉን ይመራ የነበረው ህወሓት ከሥልጣን መወገዱ ይታወሳል። በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይፋ አድርገው ነበር። ለእስር ማዘዣውም ዋነኛ ምክንያቶቹ ህወሓትን በበላይነት በመምራት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል ፈጽመዋል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ነው። በተጨማሪም የቀድሞው የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አመራሮችም በአገር ክደትና በሠራዊት አባላት ላይ በተፈጸመ ወንጀል ተጠርጥረው የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55610109 +sports ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ማስተናገድ የሚያስችል የተሟላ ስታዲየም የላትም ተባለ የአፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር (ካፍ) የባሕር ዳር ስታዲየም ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዳያስተናግድ ማገዱን ተከትሎ አገሪቱ መሰል ውድድሮችን ማስተናገድ እንደማትችል ተረጋግጧል። የብሔራዊ ቡድን ውድድሮችን ላለፉት ዓመታት ሲያስተናግድ የቆየው የባሕር ዳር ስታዲየም የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ እና የአፍሪካ የክለብ ሻምፒዮና ውድድሮች እንዳይካሄድበት ማገዱን ካፍ አስታውቋ። ካፍ ይህን ውሳኔውን ያስታወቀው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ ነው። የባሕር ዳር ስታዲየም የካፍ የስታዲየሞች መመዘኛ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ባለማሟላቱ በገደብ ውድድሮችን ሲያስተናግድ መቆየቱ ይታወሳል። ካፍ ከሳምንታት በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በየትኛው አገር እና ስታዲየም ለመጫወት እንደምትመርጥ ኢትዮጵያ ከጥቅምት 10 በፊት በአስቸኳይ እንድታሳውቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህ ማድረግ ካልተቻለ ካፍ ጨዋታውን ወደ ተጋጣሚዋ አገር ጋና እንደሚወስድ አሳውቋል። የባሕር ዳር ስታዲየም የጨዋታ ሜዳው እና ለጨዋታ ሜዳው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ባለሟሟላቱ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የቡድኖች እና የጨዋታ አመራሮች ማረፊያ ክፍሎች ስለሌሉ እንዲሁም የህክምና ክፍሉ የተሟላ ባለመሆኑ ውድድር እንዳይካሄድበት የታዘዘው። በተጨማሪም የተመልካቾች መሠረተ ልማት ባለመሟላታቸው፣ የክብር እንግዶች መቀመጫ እና የመስተንግዶ አካባቢ በበቂ ደረጃ ባለመዘጋጀቱ፣ በስታዲየሙ ደረጃውን የጠበቀ የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል አለመኖር እና የልምምድ ሜዳው ዝቅተኛ ደረጃ በመያዙ ለመታገድ በቅቷል። የካፍ የክለብ ላይሰንሲንግ ኃላፊ መሐመድ ሲዳት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ አቅንተው የተለያዩ ስታዲየሞችን ገምግመዋል ተብሏል። ኃላፊው በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከባሕር ዳር ስታዲየም በተጨማሪ የአበበ ቢቂላ እና የጅማ ዩንቨርሲቲ ስታዲየሞችን ተመልክተዋል። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በርካታ ማሟላት ያለባቸው ነገሮች እንዳሉት ገልጸው ስታዲየሙ የተጓደሉትን ነገሮች ካሟላ ወደፊት የገምጋሚ ቡድን እንደሚልኩ አስታውቀዋል። ስታዲየሙ አሁን ባለው ሁኔታ ምንም አይነት ዓለም አቀፍ ውድድር ማስተናገድ እንደማይችል አሳውቀዋል። የአበበ ቢቂላ ስታዲየም በታዳጊ ደረጃ የሚዘጋጁ ውድድሮችን እና የሴት የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎችን በጊዜያዊነት ማስተናገድ እንደሚችል ገልጸዋል። የሐዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየምን በተመለከተ መጫወቻ ሳሩ ደረጃውን ያልጠበቀ፣ ሜዳው አጠገብ ያለው መሮጫም መስተካከል እንዳለበት የገለጹ ሲሆን መልበሻ ክፍሎቹ በአዲስ መልክ ሊሻሻሉ እንደሚገባቸው አስታውቀዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-58964342 +politics በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩባት የቨርጂኒያ ምርጫ የሪፐብሊካን ዕጩ እየመሩ ነው "በርካታ ትቅልደ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባት የአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት እየተካሄደ ባለው የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ምርጫ የሪፐብሊካኑ ዕጩ ግሌን ዮንከን ተቀናቃኛቸውን እየመሩ መሆኑ ተነገረ። አንዳንድ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ከአሁኑ ግሌን ዮንከን ማሸነፋቸውን ይፋ ማድረግ ጀምረዋል። ከጥቂት ሰዓታት በፊት በነበረ ውጤት ግሌን ዮንከን በ2.7 ነጥብ የዲሞክራቱን ዕጩ ቴሪ መካሌፍ ቀድመዋቸዋል። እስከ አሁን 95 ከመቶ የሚሆው ድምጽ ተቆጥሯል። የዲሞክራቱ ዕጩ ሚስተር መካሌፍ በፈረንጆች 2014 እስከ 2018 ድረስ ለአራት ዓመታት የግዛቷ ገዢ ሆነው ያገለገሉ ናቸው። ይህ ምርጫ ጆ ባይደን ፕሬዝዳንትነት ከተመረጡ በኋላ ዲሞክራቶች በሕዝብ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት መለኪያ ተደርጎ ተወስዷል። በዚህ ግዛት ዲሞክራቶች ከተሸነፉ የጆ ባይደን ቅቡልነት ማጣት አንድ ማሳያ እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ጆ ባይደን ቨርጂኒያን በ10 ነጥብ የበላይነት ማሸነፋቸው አይዘነጋም። አሁን የገዥነት ምርጫውን እየመሩ የሚገኙት ግሌን ዮንከን ባደረጉት የድል ንግግር ""ይህ ወሳኝ ድል ነው"" ብለዋል። የዲሞክራቱ ዕጩ ቴሪ በበኩላቸው ሽንፈቱን ገና ያልተቀበሉ ሲሆን ለደጋፊዎቻቸው ""ጊዜው ገና ነው"" እያሉ ነው። ከቨርጂኒያ ሌላ በኒው ጀርሲም በዲሞክቶችና በሪፐብሊካን መካከል ጥብቅ ፉክክር እየተደረገ ነው። ጆ ባይደን ወደ ዋይት ሐውስ ከገቡ ወዲህ የዋጋ ግሽበት መባባስ፣ የተቀዛቀዘው የምጣኔ ሀብት ቶሎ አለማንሰራራት እና ዝርክርክ የተባለው የአሜሪካ ከአፍጋኒስታን የወጣችበት መንገድ በሕዝብ ዘንድ ለዲሞክራቶች የነበረው ተስፋና እምነትን ሸርሽሯል እየተባለ ነው። በርካታ ትውልድ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን በሚገኙባት ቨርጂኒያ አሸናፊው ማን እንደሆነ በይፋ ማምሻውን ይለይለታል ቢባልም ፎክስ ኒውስን ጨምሮ በርካታ የአሜሪካ ሚዲያዎች አሸናፈው የሪፐብሊካኑ ግሌን ዮንከን መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59145177 +business አሜሪካ ከቻይና የተወሰኑ ምርቶች እንዳይገቡ ልታግድ ነው "አሜሪካ ከቻይና ግዛት ዢንጂያንግ የሚገቡ የተወሰኑ ምርቶች ወደ አገሯ እንዳይገቡ ልታግድ መሆኑ ተገለፀ። ለአሜሪካ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈችው ምርቶቹ ሰዎች ያለፈቃዳቸው ጉልበታቸውን በመጠቀም የተመረቱ ናቸው የሚል ነው። ምርቶቹን እንዳይገቡ የማድረግ እቅዱ የጥጥ እና ቲማቲም ምርቶችን የሚያካትት ሲሆን፤ እነዚህ ምርቶች ቻይና ወደ አሜሪካ የምትልካቸው ሁለት ዋነኛ ምርቶች ናቸው። የትራምፕ አስተዳደር የዢንጂያንግ የኡገር ሙስሊሞችን አያያዝ ተከትሎ በቻይና ላይ ጫና እያሳደረ ነው። በቅርብ ዓመታትም ቻይና ገንጣዮችና ሽብርትኝነትን እንደ ችግር በመጥቀስም በዢንጂያንግ ያላትን የፀጥታ አካላት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምራለች። በአንዳንዶች ግምት እስከ ሚሊየን የሚደርሱ ግለሰቦች በቀላል ጥፋቶች ያለ ምንም ክስ በካምፖች ውስጥ ታጉረው ይገኛሉ። ቻይና በበኩሏ ትምህርት የሚሰጥባቸው ካምፖች ናቸው እንጂ እስር ቤቶች አይደሉም ብላለች። የአሜሪካ ጉምሩክና የድንበር ጥበቃ አሁን ላይ በግዳጅ የጉልበት ሥራ የሚመረቱ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ምርቶች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ለማገድ የሚያስችል ሕግ እያዘጋጀ ነው። ሕጉ ሕገ-ወጥ የሰዎችን ዝውውርን፣ የህፃናት የጉልበት ብዝበዛን እና የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለመከላከል ያለመ ነው ተብሏል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች በዢንጂያንግ በግዳጅ የጉልበት ሥራ የሚመረቱ ሁሉንም ምርቶች ከግምት በማስገባት፤ በተገቢው መልኩ የተመረቱ መሆናቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ መጠየቅ የሚያስችል ሕግ አርቅቀው ነበር። የጉምሩክና የድንበር ጥበቃ ኮሚሽነር ብሬንዳ ስሚዝ ""ከዢንጂያንግ ከሚመጡ የጥጥ እና ቲማቲም ጋር በተያያዘ በምርት አቅርቦት ሂደት የግዳጅ ጉልበት የመጠቀም አጋጣሚዎች እንደሚኖሩ ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ ማስረጃ ባይኖረንም፤ ምክንያት ግን አለን "" ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል። እነዚህን ክፍተቶች ለመሙላትም ምርመራችንን እንቀጥላለን ብለዋል ኮሚሽነሯ። ረቂቅ ሕጉ በአሜሪካ ነጋዴዎች፣ ልብስ አምራቾች እና የምግብ አቅራቢዎች ላይ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል ተብሏል። ቻይና የዓለማችንን 20 በመቶ ጥጥ ፍላጎት አቅራቢ ስትሆን አብዛኛው የሚመጣው ከዢንጂያንግ ግዛት ነው። ግዛቷ የቻይና ፋብሪካዎች ግብዓት የሆኑ የፔትሮሊየም ኬሚካል እና ሌሎች ጥሬ እቃዎች ምንጭም ናት።" https://www.bbc.com/amharic/54078493 +sports ከፍተኛ ገንዘብ የተከፈለባቸው አፍሪካዊያን ተጫዋቾች እነማን ናቸው? "በከፍተኛ የዝውውር ክፍያ ለአርሰናል የፈረመው የፊት መስመር ተጫዋቹ ኒኮላስ ፔፔ ውድ ዋጋ የወጣበት አፍሪካዊ የእግር ኳስ ተጫዋች ሆኗል። በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ውድድር ቀዳሚ ተጠቃሽ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የለንደኑ አርሰናል ኮትዲቯራዊውን ኒኮላስ ፔፔን በ89 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ካዘዋወረ በኋላ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል። በዚህም ነሐሴ 3 2011ዓ.ም በሚጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ ቡድናቸው የተጠማውን ዋንጫ ያስገኝልናል በሚል የአርሰናል ደጋፊዎች የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ እየገለጹ ነው። • አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ • ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ? • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ' የተለያዩ አፍሪካዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች በተለያየ የገንዘብ መጠን ከአንድ ቡድን ወደ ሌላ ቡድን ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። እስከ ዛሬ ከፍተኛ ክፍያ የተፈጸመባቸው አፍሪካዊያን ተጫዋቾች እነማን ናቸው። • ኒኮላስ ፔፔ - 89 ሚሊዮን ��ላር (72ሚሊዮን ፓወንድ) • ሴድሪክ ባካምቡ - 79 ሚሊዮን ዶላር (65 ሚሊዮን ፓወንድ) • ሪያድ ማህሬዝ - 72 ሚሊዮን ዶላር (60 ሚሊዮን ፓወንድ) • ፒየር ኤምሪክ ኦባሚያንግ - 68 ሚሊዮን ዶላር (56.1 ሚሊዮን ፓወንድ) • ናቢ ኬዬታ - 64 ሚሊዮን ዶላር (52.75 ሚሊዮን ፓወንድ) በከፍተኛ ወጪ በመዘዋወር ክብረ ወሰኑን የጨበጠው ኒኮላስ ፔፔ በፈረንሳይ ሊግ አንድ፣ ውስጥ ለሚገኘው ሊል ለተባለው ቡድን ሲጫወት በ74 ጨዋታዎች 35 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በፊት ደግሞ እዚያው ፈረንሳይ ውስጥ አንገርስ ለተሰኘ ቡድን ይጫወት ነበር። ፔፔ ለአርሰናል በፈረመበት ወቅት እንደተናገረው ""እዚህ በመምጣቴ የተለየ ስሜት ተሰምቶኛል"" ብሏል። ጨምሮም ""ከከፍተኛ ትግልና ከረጀም ጉዞ በኋላ ለዚህ ታላቅ ቡድን ስፈርም ለእኔ ትልቅ ሽልማት ነው"" በማለት ለአርሰናል በመፈረሙ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-49204222 +health ‘ሲጨንቀን ከሐኪም የማይጠበቅ ምክር እንሰጣለን' - በዓይደር ሆስፒታል የካንሰር ሕክምና ባለሙያ "ተክለመድኅን ተክለሃይማኖት የ14 ዓመት ልጅ ነው፤ ከስድስት ወር በፊት ሆዱ አብጦ፣ ከባድ ሙቀት፣ የክብደት መቀነስ እና የአፍንጫ መድማት ምልክቶች ሲያሳይ ወላጆቹ ከተንቤን ወደ መቀለ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ይዘውት ሄዱ። የሕክምና ባለሙያዎቹ ምርመራቸውን አደረጉ፤ የደም ካንሰር (lukimea) እንዳለበትም ለቤተሰብ አሳወቁ። በወቅቱ የመጀመርያው ደረጃ የኬሞቴራፒ (የጨረር) ህክምና ተደርጎለት መጠነኛ የጤና መሻሻል ማሳየቱን የጤና ባለሞያዎቹ ይናገራሉ። ሁለተኛው የኬሞቴራፒ ህክምና እንዲደረግለትም ከሁለት ሳምንታት በኋላ እንዲመለስ ተነግሮት ከሆስፒታሉ ቢወጡም፣ ወላጆቹ ግን ለስድስት ወራት በዚያው ጠፉ። በዚህ ሁኔታ መቆየት ከሚገባበት በላይ ዘግይቶ እንደገና ወደ ሆስፒታሉ ሲመለስ ግን ከዚህ ቀደም የታዩት ምልክቶች ተባባሱ። ""ለደም ምርመራ እና መድኃኒት መግዣ የሚሆን ገንዘብ ስለሌለን ነው የጠፋነው"" ይላሉ ወላጆቹ። በዚህ ምክንያት፣ ልጁ የሚያሳያቸው ምልክቶች ከቀን ወደ ቀን መሻሻል ያሳዩ ይሆናል በሚል ተስፋ ቤት ይዘውት መቀመጣቸውን ይናገራሉ። ሆኖም ግን በዚህ ወቅት በሽታው በመባባሱ ሆስፒታል ተኝቶ ህክምና ማግኘት እንዳለበት ተነገራቸው። የዓይደር ሆስፒታል ሠራተኞች ግን፣ ሆስፒታሉ ባጋጠመው የመድኃኒት እና ሌሎች ቁሳቁሶች እጥረት ምክንያት፣ ህጻናት እና አዋቂዎች የካንሰር ህሙማን የሚያክሙበት አቅም እየተሟጠጠ መምጣቱን ይናገራሉ። አክለውም 'ተስፋ መቁረጥ ደረጃ ላይ ነን' ብለዋል። አብዛኛው በክልሉ ህጻናት ላይ የሚታየው ካንሰር የደም ካንሰር መሆኑን የሚገልጸው የካንሰር ሐኪም እና ጥናት [ኦንኮሎጂ] ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዶክተር ክብሮም ሕሉፍ፣ ህጻናት ላይ የሚታዩ የካንሰር አይነቶች በቀላሉ መታከም የሚችሉ ናቸው ይላል። ሆኖም ""አሁን ህክምና የለም፤ በህይወት እንዲቆዩ ብቻ የመጠቀሚያ ቀን ያለፈባቸው መድኃኒቶች እየሰጠናቸው ነው። ምናልባት እድለኞች ከሆኑ፤ ከጊዜ በኋላ ምን ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ግን ማወቅ አንችልም"" ሲል ለቢቢሲ ገልጿል። በክልሉ የካንሰር ህሙማን ልጆች ያሉዋቸው ቤተሰቦች ገንዘብ የሚያገኙበት አማራጭ በመቋረጡ ምክንያት ልጆቻቸውን ከክልሉ ውጪም ቢሆን ለማሳከም ለትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎች ገንዘብ ለማግኘት መቸገራቸው ይናገራሉ። የካንሰር ህክምና ከባድ ወጪ እና ረጅም ጊዜ የሚፈልግ ነው። በዚህ ምክንያት፣ እንደ ኬሞቴራፒ ያሉ ለካንሰር ህሙማን የሚሰጡ የህክምና አይነቶች ባለማግኘታቸው በርካታ ህጻናት ቤት ውስጥ እየሞቱ ነው የሚል ስጋት ከሕክምና ባለሙያዎቹ ይሰማል። ከአምስት ዓመት በፊት በ1999 ዓ.ም በዓይደር ሆስፒታል የህጻናት የካንሰር ህክምና ክፍል ሲከፍት መሰል ችግሮችን ለማቃለል እና ሰዎች በአቅራቢያቸው አገልግሎት እንዲያገኙ ለማገዝ በሚል መንግሥት የኬሞቴራፒ ወጪውን ግማሽ ክፍያ ሲሸፍን፣ ቀሪውን ክፍያ ደግሞ ቤተሰቦች በብድር መልክ እንዲከፍሉ በማድረግ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ባለፉት ሦስት ዓመታትም ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች፣ የተወሰኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች፣ ከአፋር እንዲሁም ከኤርትራ የሚመጡ የካንሰር ሕሙማን በሆስፒታሉ አገልግሎት ሲያገኙ እንደነበረ እና የአዲስ ተካሚዎች ቁጥር ከ72 ወደ 110 ከፍ ብሎ እንደነበር ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በጦርነቱ ምክንያት እና ከዚያ በኋላ በቀጠለው የማኅበራዊ አገልግሎቶች መቋረጥ ምክንያት ግን ይሄንን ቁጥር በግማሽ መቀነሱ ይጠቀሳል። ለ17 ወራት በቀጠለው ጦርነት ምክንያት በክልሉ የሚገኙ የካንሰር ህሙማን በከባድ ችግር ላይ ወድቀው ከሚገኙ ታካሚዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ባሉ ጊዜያት 1643 አዋቂዎች እና 126 ህጻናት የካንሰር ታካሚዎች ወደ ሆስፒታሉ መምጣታቸው የሚያሳየው የሆስፒታሉ ሪፖርት፣ አብዛኛዎቹ ግን በትራንስፖርት ችግር፣ በገንዘብ ማጣት እና የስልክ አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት መጥተው ህክምና ማግኘት አልቻሉም ሲል የሆስፒታሉ አስተዳደር ያስረዳል። ""70 በመቶ የካንሰር ታካሚዎቻችን ሴቶች ናቸው። ከእነዚህ 30 በመቶ የጡት ካንሰር አለባቸው። የማህጸን በር ካንሰር ያለባቸው 126 ሴቶች ሲኖሩ ከእነዚህ 15 ብቻ ናቸው የመጀመሪያው ደረጃ ቀዶ ጥገና የተደረገላቸው። ቀሪዎቹ 111 ግን የኬሞቴራፒ ህክምና ባለመኖሩ ምንም አማራጭ ስለሌለ ወደ ቤታቸው ልከናቸዋል"" ይላል ሆስፒታሉ። ባለፈው ወር የሆስፒታሉ ባለሙያዎች፣ ከላባራቶሪ እስከ የኬሞቴራፒ መድኃኒት ድረስ እጥረት በማጋጠሙ ምክንያት ከ1700 በላይ የካንሰር ህሙማን ለሞት አደጋ ተጋልጠዋል ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። ከጦርነቱ በፊት፣ ሆስፒታሉ ከ60 እስከ 70 በመቶ የኬሞቴራፒ አገልግሎት በመስጠት ከ45 በላይ የካንሰር መድኃኒቶች በሆስፒታሉ እንደነበሩት ይገለጻል። በአሁኑ ወቅት ያለው የኬሞቴራፒ አገልግሎት ከ10 በመቶ በታች ሲሆን፣ ሦስት የመድኃኒት አይነቶች ብቻ እንዳሉትም የካንሰር ሕክምና ክፍል መጋቢት ወር ላይ ያወጣው ሪፖርት ያመለክታል። በዚህ ምክንያት የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶችም እያለቁ ናቸው ሲል ዶክተር ክብሮም ያስረዳል። ""አሁን ላይ ኬሞቴራፒ ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል። የካንሰር መድኃኒቶች እጅግ ከባድ ናቸው። ለምሳሌ ኬሞቴራፒ የሚወስድ ታካሚ ወደ ላይ የማለት ችግር ሊኖረው ስለሚችል ለዚህ የሚሰጥ መድኃኒት ነበር፤ አሁን እሱም ነው የሌለን። በግሉኮስ መልክ የሚሰጡ መድኃኒቶች የሉም። አብዛኛዎቹ ታካሚዎች ህክምና የለም እያልን ነው የምንመልሳቸው፤ የማጽናናት ሥራ እንጂ የህክምና ሥራም እየሰራን አይደለም"" ይላል። የአንጀት ካንሰር ታካሚዎች ህክምናቸው ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል የሚለው ኃላፊው፣ ሁሉም የካንሰር ታካሚዎች ከባድ ችግር ላይ ናቸው ሲል ይናገራል። ""የተለያዩ መድኃኒቶችን ነበር የሚወስዱት፤ ካጋጠመን እጥረት አንጻር አራት ለሚወስዱት አንድ ስንሰጣቸው ነበር፤ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ጭምር። አሁን ግን እሱም ተቋረጠ"" ሲል ለቢቢሲ ገልጿል። 'ሲጨንቀን ከሐኪም የማይጠበቀውን እንላለን' የካቲት ወር አጋማሽ ላይ የዓለም የጤና ድርጅት በስድስት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አንቲባዮቲክስ፣ የወባ እና የስኳር እንዲሁም የከባድ የምግብ እጥረት መድኃኒቶች የያዙ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ እንዲያስገባ ፈቃድ አግኝቶ ነበር። ሆኖም ክልሉ ውስጥ ባለው የነዳጅ እጥረት ምክንያት ወደ ሚፈለገው ቦታ ማድረስ አልተቻለም ሲል የገጠመውን ተግዳሮት ገልጾ ነበር። ባለፈው መጋቢት ወር፣ የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች ለሰብዓዊነት በሚል ግጭት ለማቆም ከወሰኑ በኋላ፣ በተለያዩ ጊዜያት ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና የቀይ መስቀል መኪኖች መቀለ መድረሳቸው ተነግሯል። አብዛኛው ወደ ክልሉ የገባው መድኃኒት አጣዳፊ ለሆኑ ወይም በኢንፌክሽን ለሚመጡ በሽታዎች መከላከያ የሚሆን እንጂ፣ እንደ ካንሰር ያሉ በሽታዎችን ከግምት ውስጥ ያስገቡ አይደሉም የሚለው ዶክተር ክብሮም፣ ""በዚህ ሳቢያ በቅርቡ በርካታ ታካሚዎቻችን አጥተናል፤ ልናጣቸው ጫፍ የደረሱም አሉ"" በማለት ስጋቱን ይገልጻል። ""500 ተከታታይ ኬሞቴራፒ ማግኘት ያለባቸው፣ 300 የሚጠጉ ደግሞ ፈጣን የጨረር ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች አሉ። ችግሩ በዚህ ከቀጠለ እነዚህንም እናጣቸዋለን ማለት ነው። ስልክም ስለሌለ መድኃኒት የለም ብለን ወደ ቤታቸው የመለስናቸው ታካሚዎች ምን እንደገጠማቸው አናውቅም"" ብሏል። በተለይ ከመቀለ ውጪ የሚኖሩ የካንሰር ህሙማን በገንዘብ እጥረት እና በትራንስፖርት ችግር ምክንያት ወደ ሆስፒታሉ መምጣት ማቆማቸውን ባለሙያው ይናገራል። ""ካንሰር ከባድ በሽታ ነው፤ ሞት ደረጃ የሚያደርስ እና ህክምናውም ከባድ የሆነ በሽታ ነው። ከአሁን በፊት ህክምና እየሰጠን ተስፋ አላችሁ እንላቸው ነበር። አሁን ግን 'በሽታህ ይህ ነው፣ መድኃኒት ግን የለም፤ ምንም ማድረግ አልችልም' ማለት ለእኔ የሞት ፍርድ መንገር ነው። ሲጨንቀን ከሐኪም የማይጠበቀውን እንላለን፤ እስቲ ፀበል ሞክሩ ብለን ነው የምንሸኛቸው"" ሲል ያስረዳል። ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል አሁን ያጋጠሙት ችግሮች መፍትሄ ካላገኙ ሆስፒታሉ ለህጻናት እና ለአዋቂዎች የካንሰር ህሙማን ህክምና መስጠት የማይችልበት ደረጃ ደርሶ ""መፍረስ"" ላይ ነው የሚገኘው በማለት የጤና ሚኒቴር እና ሌሎች ተቋማት ትኩረት እንዲሰጡት የሆስፒታሉ ሠራተኞች ይማጸናሉ። ""ማስታገሻ ሳይቀር እኮ ነው ያጣነው፤ አንድ ሰው እባክህ ወደ ላይ እያለኝ ነው ብሎን መድኃኒት መስጠት አልቻልንም። ሆስፒታሉ የሚዘጋበት ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ይህ ማለት ህክምና በማጣት ምክንያት ትውልድ ማጣት ነው። የእኔ ትልቅ ስጋት ይህ ነው"" ይላል ዶክተር ክብሮም።" https://www.bbc.com/amharic/news-61369295 +politics በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣናቸውን ያጡት የኖቤል ሎውሬት አን ሳን ሱ ቺ ማን ናቸው? በአንድ ወቅት የሰብአዊ መብትና የዲሞክራሲ ባንዲራ ሆነው ይታዩ ነበር፡፡ አሁን ግን በብዙ ተቋማት ዓይንዎትን ላፈር ተብለዋል፤ አን ሳን ሱ ቺ፡፡ ከሳምንት በፊት በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣናቸውን አጥተዋል፡፡ አሁን በቁም እስር ላይ ናቸው፡፡ ከስማቸው አወዛጋቢነት እስከ አገሪቱ ትክክለኛ የስም አጠራር ድረስ የቀድሞዋ በርማ የአሁኗ ሚየንማር፣ የቀድሞዋ የሰብአዊ መብት እመቤት፣ የአሁኗ እስረኛ የሰሞኑ የሚዲያ ዐቢይ ጉዳይ ሆነዋል፡፡ በእርግጥ የሴትዮዋ ‹ሌጋሲ› በትክክል ምንድነው? በሚለው ጉዳይ ሚዲያዎችና ተቋማት ተስማምተው አያውቁም፡፡ ለመሆኑ ኦን ሳን ሱ ቺ ማን ናቸው? አን ሳን ሱ ቺ አባታቸው የበርማ የነጻነት አባት የሚባሉት የጄኔራል ኦን ሳን ሴት ልጅ ናቸው፡፡ ታላቋ ብሪታኒያ በርማን (በአዲሱ ስሟ ሚየንማር) ለአንድ ክፍለ ዘመን ያህል ጊዜ በቅኝ ገዝታታለች፡፡ ጄኔራል ኦን ሰን ለበርማ ነጻነት ተዋድቀዋል፡፡ የተገደሉትም በ1947 በተቀናቃኞቻቸው ነበር፡፡ ያን ጊዜ ሳን ሱ ቺ ገና 2 ዓመቷ ነበር፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በሰኔ 19፣ 1945 ነበር የተወለዱት፡፡ ኦን ሳን ሱ ቺ በ1960ዎቹ መጀመርያ ከእናታቸው ���ው ኪን ኬዪ ጋር ወደ ሕንድ ሄዱ፡፡ እናታቸው በደልሂ የበርማ አምባሳደር ተደርገው በመሾማቸው ነበር ወደዚያ ያቀኑት፡፡ ሕንድ አራት ዓመት ከኖሩ በኋላ ወደ ታላቋ ብሪታኒያ በማቅናት በሥመጥሩ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ፍልስፍናን፣ ፖለቲካንና ምጣኔ ሀብትን አጥንተዋል፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ሳሉ የወደፊት ባለቤታቸው ጋር ተገናኙ፡፡ እንግሊዛዊው ባለቤታቸው ማይክል አሪስ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ነበሩ፡፡ አሁን በሕይወት የሉም፡፡ ኦን ሳን ሱ ቺ ከትምህርት በኋላ በቡታን እና በጃፓን በተለያዩ ሥራዎች ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ታላቋ ብሪታኒያ በመሄድ ጎጆ መሥርተው አሌክሳንደርና ኪም የሚባሉ ልጆችን አፍርተዋል፡፡ በ1988 ከታላቋ ብሪታኒያ ወደ ሚየንማር ዋና ከተማ ያንጎን ሲመለሱ በጠና ታመው የነበሩትን እናታቸውን ለማስታመም ነበር፡፡ የአጋጣሚ ነገር ሆኖ በበዚያ ወቅት በሚየንማር በርካታ የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን ያነሱ ወጣቶች አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ያስነሱበት ጊዜ ነበር፡፡ ተቃዋሚዎቹ ወጣቶች ብቻ ሳይሆኑ የቡድሀ መነኮሳት፣ የቢሮ ሰራተኞችና ተማሪዎችም ይገኙበት ነበር፡፡ ይህን ተቃውሞ ተከትሎ አን ሳን ሱ ቺ ጠቅልለው በሚየንማር መኖር ጀመሩ፡፡ ከ2 ዓመት በኋላ በ1990 አዲስ በተመሠረተው የናሽናል ሊግ ፓርቲ ውስጥ ገብተው ተቃውሞ ውስጥ በቀጥታ መሳተፍ ጀመሩ፡፡ በአካባቢ ምርጫ ተወዳድረውም አሸነፉ፡፡ በከፍተኛ ድምጽ የኦን ሳን ሱ ቺ በምርጫ ማሸነፍ ያስቆጣው ወታደራዊው መንግሥት ሴትዮዋን ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት በቁም እስር አስቀመጣቸው፡፡ በ1991 ኦን ሳን ሱ ቺ በቁም እስር ላይ ሳሉ የኖቤል ሽልማትን አሸነፉ፡፡ ይህም ወታደራዊውን መንግሥት በይበልጥ አስቆጣ፡፡ በ2010 ኦን ሳን ሱ ቺ ከቁም እስር ነጻ ተባሉ፡፡ በ2012 አን ሳን ሱ ቺና ፓርቲያቸው በአካባቢ ምርጫ እንዲሳተፉ ወታደራዊው መንግሥት ፈቀደ፡፡ በ2015 የብሔራዊ ሊግ ለዲሞክራሲ (NLD) ፓርቲያቸው ለመጀመርያ ጊዜ በተደረገ ከፍተኛ ፉክክር በታየበት ምርጫ አሸነፈ፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በሚየንማር የሮሒንጋ ሙስሊሞች ላይ ወታደሩ ያደረሰውን ግፍና ጭፍጨፋ ለማውገዝ አለመፍቀዳቸው በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ፡፡ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የሮሒንጋ ሙስሊሞች ከሚየንማር ሞትን ሽሽት ወደ ባንግላዴሽ ተሰደዋል፡፡ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ክብራቸው ዝቅ ይበል እንጂ አን ሳን ሱ ቺ በአገራቸው ቡድሀዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ናቸው፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በ2015 የተደረገውን ምርጫ አሸንፈው መንግሥት ቢመሠርቱም የአገሪቱ ፕሬዝዳንት መሆን ግን አልተፈቀደላቸውም፡፡ ይፋዊ ሥልጣናቸው ‹የመንግሥት የበላይ ጠባቂ› ወይም ስቴት ካውንስለርነት ነው፡፡ ይህም የሆነው ያፈሯቸው ልጆች የውጭ ዜግነት ስላላቸው ነው፡፡ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሚስተር ዊ ቢሆኑም አን ሳን ሱ ቺ ግን በውስጥ ታዋቂነት (de facto) የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሆነው ይወሰዳሉ፡፡ ስቴት ካውንስል የሚባለው ሹመት የተፈጠረው አን ሳን ሱ ቺ ሕጋዊ ፕሬዝዳንት መሆን ስለማይችሉ ነው፡፡ ሆኖም በፖለቲካ ሥልጣን ረገድ የጠቅላይ ሚኒስትር ያህል ቁልፍ ቦታ ነው፡፡ አን ሳን ሱ ቺ ይህን ሥልጣን ከመቆናጠጣቸው በፊት ለአጫጭር ጊዜም ቢሆን የኢነርጂ ሚኒስትር፣ የትምህርት ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ማለትም 2020 አን ሳን ሱ ቺ እና ፓርቲያቸው ምርጫ ማሸነፍ ችሎ ነበር፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉትም አዲሱን መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና በሚሉበት ሰዓት ነው፡፡ በ2021 የዛሬ ሳምንት አካባቢ የተወካዮች ምክር ቤት ሸንጎ አዲ��� የሥራ ዘመን ስብሰባ በሚጀምርበት ቀን አን ሳን ሱ ቺ በድጋሚ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ አን ሳን ሱ ቺ አሁን የ76 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ናቸው፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-55975691 +sports "ኦሊምፒክ ፡ ""ኮሮናቫይረስ ጠፋም አልጠፋ"" በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ ይካሄዳል" "በኮሮናቫይረስ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ የነበረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በሚቀጥለው ዓመት በማንኛውም ሁኔታ እንደሚካሄድ ተገለጸ። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንት ""ኮቪድ-19 ጠፋም አልጠፋ በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ ይካሄዳል"" ብለዋል። ጆን ኮትስ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንዳረጋገጡት በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ የሚጀምረው በሐምሌ 23 ይሆናል። ኦሊምፒክ መካሄድ የነበረበት ዘንድሮ በሐምሌ ወር ነበር። ሆኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ተከትሎ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ ነበር። ሆኖም ውድድሩን ከፈረንጆቹ 2021 ወዲያ መግፋት ስሜት የሚሰጥ ነገር አይደለም ብለዋል። በሐምሌ ወር የቶክዮ 2020 ኦሊምፒክ ሊቀመንበር ቶሺሮ ሙቶ ""ውድድሮቹን በዝግ ስታዲየም ማካሄድ ይቻል ነበር። ያንን ስላልፈለግን ነው ያዘገየነው"" ብለው ነበር። ምናልባት ከየአገሩ የሚመጡ ወኪሎችን ቁጥር በመቀነስ፣ በየውድድሩ የሚታደሙ ተመልካቾችን በማሳነስ፣ እንዲሁም የመክፈቻና መዝጊያ ሥነ ሥርዓቱን ቀለል በማድረግ የሚካሄድበት መንገድ ሊቀየስ ይችላል። ከመላው ዓለም 11 ሺህ አትሌቶች ከ200 አገራት እንደሚገኙ ይጠበቅ ነበር። በሚቀጥለው ዓመት ሐምሌ ላይ ውድድሩ ሲታሰብ የጉዞ ገደቦችን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም። ሚስተር ሙቶ የኦሊምፒክ ውድድሩን ለማድረግ የኮቪድ-19 ክትባትን መጠበቅ አይኖርብንም ብለዋል። የጤና ባለሙያዎች በበኩላቸው በወረርሽኝ መሀል ክትባት ሳይኖር እንዲህ ዓይነት ውድድር ሊካሄድ አይችልም ይላሉ። ""ክትባት ከተገኘ መልካም፤ ካልተገኘ ግን እሱ እስኪገኝ ኦሊምፒክ አይቆምም"" ብለዋል ሊቀመንበሩ። የውድድሩ አስተባባሪ ዮሺሮ ሞሪ በሚያዝያ ወር ኦሊምፒክ በ2021 ካልተደረገ እስከናካቴው መሰረዝ ነው ያለበት ብለው ነበር። ከዚህ ቀደም የኦሎምፒክ ውድድር በጦርነት ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቶ ያውቃል እንጂ የሚካሄድበት ጊዜ ሲገፋ ይህ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/54053429 +sports አሜሪካ ከኦሊምፒክ መቅረቷ ዋጋ ያስከፍላታል ስትል ቻይና አስጠነቀቀች "አሜሪካ በአውሮፓውያኑ 2022 ቤጂንግ በሚካሄደው የክረምት ኦሎምፒክ ዲፕሎማቶቿ እንደማትልክ ማስታወቋን ተከትሎ ይህ ውሳኔዋ ዋጋ ያስከፍላታል ስትል ቻይና ዛተች። የቻይና የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ዛሆ ሊጂያን ዝርዝር መረጃ ሳይሰጡ ቻይና ለአሜሪካ ውሳኔ የአጸፋ ምላሽ ትሰጣለች ሲሉ ተናግረዋል። ትናንት ሰኞ አሜሪካ ከቻይና የሰብአዊ መብት አያያዝ ጋር በተያያዘ ነው ዲፕሎማቶቿን ለኦሊምፒክ ውድድሩ እንደማትልክ ያስታወቀችው። ይህንንም ስጋቷን ለመግለፅ ምንም ዓይነት ኦፊሴላዊ ልዑካን ወደ ውድድሩ እንደማትልክ ኋይት ሃውስ አስታውቋል። ሆኖም የአሜሪካ ስፖርተኞች መወዳደር እንደሚችሉ እና የመንግሥትን ሙሉ ድጋፍ እንደሚያገኙ ተነግሯል። ከዚህ ቀደም አሜሪካ ያለመሳተፍ ውሳኔ ካስተላለፈች፣ ቻይና ""ተመሳሳይ እርምጃዎችን"" እንደምትወስድ ተናግራለች። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ወር የዲፕሎማቶች ልዑካን ላለመላክ እያሰቡ መሆኑን ተናግረዋል። የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ሰኞ ክልከላውን መደረጉን አረጋግጠው አስተዳደሩ የዚህ አካል አይሆንም ብለዋል። ""የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ውድድሩ በዢንጂያንግ አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ጭካኔ እየተካሄደ ባለበት ወቅት መሆኑ የተለመደው የቻይና መደበኛ እንቅስቃ��� አድርገው ይመለከቱታል። እኛ ያንን ማድረግ አንችልም"" ሲሉ ገልጸዋል። ሳኪ አክለውም የአሜሪካ መንግሥት እንዳሉት ""ለውድድሩ ሲዘጋጁ የነበሩ ስፖርተኞች መቅጣት ትክክለኛው እርምጃ ነው"" ብሎ አያስብም። ሆኖም በውድድሩ ላይ የአሜሪካ ልዑካንን አለመላክ ""ግልጽ መልዕክት ሊያስተላልፍ ይችላል"" ብለዋል። ""የፖለቲካ መድረክ"" በዋሽንግተን ቻይና ኤምባሲ በበኩሉ የአሜሪካን ውሳኔ አስመልክቶ በሰጠው ምላሽ ድርጊቱ ""የኦሊምፒክ መንፈስን በእጅጉ የሚጻረር ነው"" ብሏል። ""እነዚህ ሰዎች መጡ ቀሩ አይመጡ ማንንም አያሳስብም። በቤጂንግ 2022 የክረምት ኦሊምፒክ ላይም ምንም ዓይነት ተጽእኖ የለውም"" ሲሉ ቃል አቀባዩ ሊዩ ፔንግዩ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ሊዩ አክለውም ለአሜሪካ ፖለቲከኞች ምንም ግብዣ እንዳልቀረበላቸው ገልጸው ""ስለዚህ ይህ 'የዲፕሎማቶች አለመሳተፍ' ከየት እንደመጣ አይታወቅም"" ብለዋል። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን ከውሳኔው ቀደም ብሎ እንደተናገሩት ""አሜሪካ የራሷን መንገድ ለመያዝ ካሰበች ቻይናም ተመሳሳይ እርምጃዎችን ትወስዳለች"" ብለዋል ። ""የክረምት ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የፖለቲካዊ ፍላጎት መጠቀሚያ መድረክ አለመሆኑን አፅንኦት መስጠት እፈልጋለሁ"" ሲሉ ዣኦ በመደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል ። በቻይና ማህበራዊ ድር አምባ ዌይቦ ላይ ""የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በቤጂንግ የክረምት ኦሊምፒክ ያለመሳተፍ ውሳኔ"" የሚለው የፍለጋ ርዕስ ከማክሰኞ ማለዳ ጀምሮ ሳንሱር ተደርጓል። ግሎባል ታይምስ በተባለው የመንግሥት ሚዲያ ላይ ከወጣው ጽሁፍ በታች ያሉት አብዛኛዎቹ አስተያየቶች ተሰርዘዋል። ከ1 ሺህ 500 የሚጠጉ አስተያየቶች ውስጥ ስምንቱ ብቻ ናቸው ያልተነኩት። ""ኦሊምፒክ የስፖርተኞች ነው። ከፖለቲከኞች ጋር ምን አገናኘው? ላለመሳተፍ ብትወስኑ የሚጎዱት የራሳችሁ ሃገር ሰዎች (ስፖርተኞችን ጨምሮ) ነው"" ይላል አንዱ አስተያየት። ከአሜሪካ እና ከሌሎች ሀገራት የተወከሉ ከፍተኛ የመንግሥት ተወካዮች ብዙውን ጊዜ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ይገኛሉ። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን በቶኪዮ በተካሄደው የበጋ ኦሎምፒክ የአሜሪካን ልዑካን መርተው ተገኝተዋል። አሜሪካ ውስጥ የዲፕሎማቶች አለመሳተፍ ውሳኔው በዲሞክራቲክ እና ሪፐብሊካን ህግ አውጭዎች ድጋፍ አግኝቷል። የሪፐብሊካኑ የዩታ ሴናተር ሚት ሮምኒ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት የባይደን አስተዳደር በኦሊምፒክ የዲፕሎማቶች ተሳትፎን እንዳይኖር ""መከልከሉ ማለቱ ትክክል ነው"" ብለዋል። ዲሞክራቷ የምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲም ውሳኔውን አድንቀዋል። ""ስፖርተኞቻችንን መደገፍ እና ማክበር ቢኖርብንም አሜሪካ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለእነዚህ ጨዋታዎች የእኛን ይፋዊ ድጋፍ መስጠት አንችልም። ወይም ኦሊምፒክ የዘር ማጥፋት እና ጅምላ የሰብአዊ መብት ረገጣ በሚፈጽምባት ሃገር ውስጥ መካሄዱ ምንም ችግር እንደሌለው አድርገን መቀጠል አንችልም"" በማለት ፔሎሲ ተናግረዋል። አንዳንድ የዩናይትድ ስቴትስ ፖለቲከኞች ግን የዲፕሎማቶች አለመሳተፍ በቂ አይደለም ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ሴናተር ቶም ኮተን ውሳኔውን ""ግማሽ እርምጃ"" ሲሉ የገለጹ ሲሆን አስተዳደሩ በውድድሩ ላይ ""ሙሉ በሙሉ አለመሳተፍ ነበረበት"" ብለዋል። ቻይና በዚንጂያንግ ራስ ገዝ አስተዳደር ውስጥ በኡይግሮች እና ሌሎች አናሳ የሙስሊም ዜጎች ላይ ጭቆና እየፈጸመች ነው ስትል አሜሪካ ትከሳለች። ዩናይትድ ኪንግደም እና አውስትራሊያን ጨምሮ ሌሎች ሃገራት ተመሳሳይ እርመጃ ለመውሰድ እያሰቡ ነው ተብሏል። አሜሪካ ከዚህ ቀደም ሶቪየ��� አፍጋኒስታንን በመውረሯ ምክያት በአውሮፓውያኑ 1980 ውድድር ስፖርተኞቿ እንዳይሳተፉ አድርጋለች። ሶቪየት ህብረት እና አጋሮቿ በበኩላቸው በሎስ አንጀለስ የተካሄደውን ቀጣዩን የ1984ቱን የበጋ ኦሊምፒክን ሳይሳተፉ ቀሩ። አሜሪካ በአውሮፓውያኑ 2028 ኦሊምፒክን በሎስ አንጀለስ ልታዘጋጅ ሽር ጉድ እያለች ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-59559003 +health ኮሮናቫይረስ፡ እስራኤል 5ሺ የኮቪድ ክትባት ጠብታዎችን ፍልስጤማዊያን ልትሰጥ ነው 9 ሚሊዮን ሕዝቧን በሙሉ ለመከተብ በከፍተኛ ዘመቻ ላይ የሆነችው እስራኤል 5ሺ ጠብታ ክትባቶችን ለፍልስጤማዊያን አበረክታለሁ ብላለች። ሆኖም እነዚህ ክትባቶች የሚሰጡት በፍልስጤም የጤና መኮንን ለሆኑ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ነው። እስራኤል በአሁን ሰዓት በጣም የተቀላጠፈ የክትባት ዘመቻ በማካሄድ ላይ ካሉ የዓለም አገራት ቁንጮዋ ናት። ሆኖም በዌስት ባንክና ጋዛ የሚገኙ ፍልስጤማዊያን ይህ ወግ አልደረሳቸውም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እስራኤል በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖሩ ፍልስጤሞችን የመከተብ ግዴታ አለባት ሲል አሳስቧል። ሆኖም እስራኤል በመጀመርያ ይህ ግዴታ የለብኝም፤ በሁለተኛ ደረጃ ከፍልስጤም አስተዳደርም ቢሆን ጥያቄው አልቀረበልኝም ብላለች። እስራኤል 640ሺህ ዜጎች በተህዋሲው ተይዘውባት 5ሺ የሚጠጉት ሞተውባታል። ይበልጥ የተጠቁት ደግሞ በዌስት ባንክና በጋዛ 160ሺ ፍልስጤማዊያን በተህዋሲው እንደተያዙና ወደ 2ሺ የሚጠጉት እንደሞቱ ጥናቶች ያሳያሉ። እስራኤል ክትባት እያቀረበላት ካለው ፋይዘር ጋር ያላት አንዱ ስምምነት በዜጎች ጤና ላይ መረጃን ለመድኃኒት አምራቹ በየጊዜው ማቅረብ ነው። እስራኤል እስከአሁን የሕዝቧን 20 እጅ የኮቪድ ክትባት ከትባለች። ይህም በድምሩ ወደ 2 ሚሊዮን እየተጠጋ ያለ ቁጥር ነው። እነዚህ ሕዝቦቿ ታዲያ የፋይዘርን በሳምንታት ልዩነት የሚሰጠውን 2 ጠብታ ክትባት ሙሉ በሙሉ ያገኙ ዜጎች ናቸው። ከነዚህ ሌላ ደግሞ 3 ሚሊዮን ዜጎቿ የመጀመርያውን ዙር ጠብታ ማግኘት ችለዋል። አገሪቱ በክትባት ደረጃ ብዙ ርቀት ብትሄድም የእንቅስቃሴ ገደቦች አሁንም እንዳሉ ነው ያሉት። የእሰራኤል መከላከያ ሚኒስትር የሆኑት ቤኒ ጋንዝ ቢሮ እንዳረጋገጠው እስራኤል የተወሰኑ ጠብታዎቹን ወደ ፍልሥጤም አስተዳደር ታስተላልፋለች። ጠብታዎቹን ግን ፍልስጤሞች እሺ ብለው ስለመቀበል አለመቀበላቸው ያሉት ነገር የለም። በፍልስጤም ከፊል አስተዳደር ሥር የሚገኘው ዌስት ባንክም ሆነ በሐማስ አስተዳደር ሥር ያለው ጋዛ ምንም ዓይነት የክትባት ዘመቻን አልጀመሩም። የፍልስጤም ባለሥልጣናት ከመድኃኒት አቅራቢዎች ጋር ንግግር መጀመራቸው ይግለጹ እንጂ መቼ ክትባት እንደሚደርስና ለሕዝባቸው በምን መንገድ እንደሚያቀርቡ እስከአሁን ያሉት ነገር የለም። የፍልስጤም ባለሥልጣናት ተስፋ ያደረጉት የዓለም ጤና ድርጅት የሚደግፈውን ኮቫክስ የተሰኘ ፕሮጀክት ጥላ ሥር መታቀፍና ድጋፍ ማግኘትን ነው። ይህ ፕሮጀክት ድህ አገራት ክትባት እንዲያገኙ የሚያግዝ ነው። እስከአሁን ጥቂት ሩሲያ ሰራሹ ክትባት ፍልስጤም መድረሱ ቢነገርም ለማን እንደታደለ ግን የሚታወቅ ነገር የለም። በዌስት ባንክ ወደ 3 ሚሊዮን፣ በጋዛ ደግሞ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጠማዊያን ይኖራሉ። ለፍልስጤሞች ክትባት የመስጠቱ ኃላፊነት የማን ነው የሚለው ጉዳይ ግን አሁንም እያነጋገረ ነው። እስራኤል በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ ለመስጠት የኦስሎ ስምምነትን ትጠቅሳለች። የኦስሎ ስምምነት ዌስት ባንክና ጋዛ የፍልሥጤም አስተዳደር ሙሉ ዘላቂ ሰላም ስምምነት እስኪፈረም በጊዜያዊነት እንዲያስተዳድሩ ስለሚል የጤና ጉዳዮችንም የሚመለ��ተው ይህን አስተዳደር ነው ስትል ትከራከራለች። ፍልስጤሞች በበኩላቸው ይህ የኦስሎ ስምምነት አንዳች ወረርሽኝ በመጣ ጊዜ እስራኤል ለጋዛና ዌስት ባንክ ትብብር ትሰጣለች የሚል አንቀጽ እንዳለውም ይጠቅሳሉ። የተባበሩት መንግሥታት ባልደረባ ግን በግድ በተያዙ ግዛቶች ሁሉ የጄኔቫ ስምምነት ተግባራዊ እንደሚሆንና ፍልስጤሞችን የመከተቡ ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ የእስራኤል እንደሆነ ያሰምሩበታል። የአለም አቀፍ ጉዳዮች አዋቂ የሆኑ ሰዎች በዚህ ረገድ የተለያየ አቋምን ያንጸባርቃሉ። እስራኤል አሁን የጀመረችው ሰፊ የክትባት ዘመቻ የአረብ እስራኤል ዜጎችን እንዲሁም እስራኤል በጉልበት በያዘቻቸው የምሥራቅ ኢየሩሳሌም አካባቢዎች የሚገኙ ፍልስጠማዊያንን የሚያካትት ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-55883434 +sports የኳስ ሃሜት፡ 'ምባፔ ከፈረንሳይ ለመውጣት የቤተሰብ ፈቃድ ያስፈልገዋል' እሁድ እንደመሆኑ የእግር ኳስ ዓለም ምን እያለ ነው የሚለውን እናስቃኛችሁ። የፈረንሳዩ የ21 ዓመት እግር ኳሰኛ ኪሊያን ምባፔ በአንጋፋ የአውሮፓ ክለቦች እየተፈለገ ነው። ለፓሪስ ሰይንት ዠርሜይን የሚጫወተው ወጣቱ ምባፔ ግን ክለቡን ሊለቅ የሚችለው ከቤተሰብ ፈቃድ ካገኘ ነው ሲል ሰን የተሰኘው ጋዜጣ በእሁድ ዕትሙ አስነብቧል። ዩቬንቱስ፡ ወደ ጣልያን ስናቀና አሮጊቶቹ ዩቬንቱሶች የማንቸስተር ዩናይትዱን አማካይ ፖል ፖግባ በሚቀጥለው ጥር በውል ለማስፈረም አቅደዋል ያለው ሚረር ነው። ዩናይትድ ፖግባን ለዩቬንቱስ ሰጥቶ በምትኩ ብራዚላዊው የክንፍ ተጫዋች ዳግላስ ኮስታና ከባርሴሎና በውሰት ዩቬንቱስ የሚገኘው ሚራለም ፒያንቺን እንዲወሰድ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል ብሎ ያተመው ደግሞ ካልቺዮ መርካቶ ነው። ዶርትመንድ፡ የቦሩሲያ ዶርትመንድ ቀንደኛ አጥቂ የሆነው የ20 ዓመቱ ኧርሊንግ አላንድ አባት አልፍ-ኢንግ ልጃቸው አሁን በዶርትመንድ ደስተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ነገር ግን ወደፊት ክለብ ሊቀይር ይችላል ይላሉ። አልፍ-ኢንግ ለእንግሊዙ ሊድስ ተከላካይ ሆነው ተጫውተዋል። ይህ ወሬ የተገኘው ከጣልያኑ ቱቶስፖርት ጋዜጣ ነው። አርሴናል፡ የአርሴናሉ አሠልጣኝ ማይክል አርቴታ የ32 ዓመቱ ጀርመናዊ አማካይ ሜሱት ኦዚል የኮንትራት ውሉ ከመገባደዱ በፊት ለክለቡ ሊጫወት ይችላል ብሏል ያለው ስታር ነው። ኦዚል ከአርቴታ ጋር ባለመጣጣሙ ምክንያት ከቡድኑ መቀነሱ ይታወሳል። ኮንትራቱ ሳይጠናቀቅ ወደ ሌላ ክለብ ሊዘዋወር ይችላል የሚሉ ወሬዎች እየተሰሙ ነው። ዎልቭስ፡ ዎልቨርሃምፕተን ዎንደረርስ የ23 ዓመቱን የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋች ኦልክሳንደር በ19 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም የነበራቸው ተስፋ ጨልሟል። ነገር ግን በሚቀጥለው ጥር ሌላ ጥያቄ ያቀርባሉ ሲል ስታር ጋዜጣ በእሁድ ዕትሙ አስነብቧል። ቶተንሃም፡ የቶተንሃም ሆትስፐርስ ሊቀ መንበር ዳኒኤል ሌቪ እንግሊዛዊው ዴሊ አሊ ክለቡን ለቆ እንዳይወጣ የ18 ወራት ገደብ ሊጥሉበት ነው ብሏል 90ሚን የተሰኘው የስፖርት ጋዜጣ። አሊ ከቶተንሃም ጋር ያለው ኮንትራት ከመጠናቀቁ በፊት ወደ ፓሪስ ሴይንት ዠርሜይን ሊያመራ ይችላል የሚሉ ወሬዎች አሉ። ዩናይትድ፡ የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ሉዊስ ቫን ሃል የኔዘርላንዱ አማካይ ቫን ደ ቢክ ዩናይትድን መቀላቀሉ ትክክለኛ ውሳኔ አልነበረም ብለዋል ያለው ደግሞ በደች ቋንቋ የሚታተመው ዚጎ ስፖርት ነው። ቼልሲ፡ ሰማያዊዎቹ ግብ ጠባቂያቸው ኬፓ አሪዛባላጋን የሚገዛ አጥተዋል እየተባለ ነው። ወሬው የሰንደይ ኤክስፕረስ ነው። ቼልሲ ኬፓን ለመሸጥ ቢያቅዱም ገዥ አልተገኘም። ከኬፓ ሌላ የ29 ዓመቱ ስፔናዊ ማርኮስ አሎንሶን የሚፈልገው ክለብ ጠፍቷል ተብሏል። ኬፓ በእንግሊ��� ፕሪሚዬር ሊግ ታሪክ ውዱ በረኛ ቢሆንም ከቼልሲዎች ልብ ወጥቷል። በሌሎች ወሬዎች ዌስትብሮም የኒውካስትሉን ድዋይት ጌይል ለመግዛት ዕቅድ ላይ መሆናቸው፤ አርሴናል ደግሞ ዊሊያም ሳሊባን ከገዛ ዓመት ሳይሆን ለሽያጭ ሊያቀርብ መሆኑ ተሰምቷል። ሊቨርፑል ደግሞ ለገና በዓል ለወትሮው የሚደረገውን የምሳ ግብዣ ዘንድሮ በኮቪድ-19 ምክንያት እንደማይኖር ዩርገን ክሎፕ አሳውቀዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-55292812 +politics በጋምቤላ በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 40 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆሰሉ በጋምቤላ ከተማ ታጣቂ ቡድኖች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን በክልሉ የተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሚገኙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለቢቢሲ ተናገሩ። የክልሉ መስተዳደር የኦነግ-ሸኔ እና የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች ናቸው ያላቸው ኃይሎች ማክሰኞ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም. ማለዳ ላይ በዋና ከተማዋ ውስጥ ጥቃት ከፍተው ለሰዓታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር መካሄዱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ አንድ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ጥቃቱን ተከትሎ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገልጸው፤ ከዚህ ውስጥ 10ሩ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የታጣቂው ኃይሉ አባላት ናቸው ብለዋል። ሌላ ባለሥልጣን በተመሳሳይ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከአርባ እንደሚልቅ ገልጸው ከመካከላቸውም ሁለት ሰላማዊ ሰዎች እንዲሁም 11 የፀጥታ ኃይል አባላት መሞታቸውንና ቀሪዎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት ታጠቂዎች ናቸው ብለዋል። ጨምረውም የፀጥታ ኃይሉ በጫካ ውስጥና በተለያዩ ስፍራዎች አሰሳ እያካሄደ በመሆኑ፣ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ስለሚችል ትክክለኛውን አሃዝ አሁን ማወቅ አስቸጋሪ ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በጥቃቱ ሕይወታቸው ከጠፋው ሰዎች በተጨማሪ 36 ሰዎች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ባለሥልጣኑ አመልከተዋል። ትናንት በከተማዋ ላይ የተከፈተው ጥቃት በተለይ በክልሉ ምክር ቤት እና በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት አካባቢ ላይ አትኩሮ የነበረ በመሆኑ፣ ቁልፍ የክልሉን ተቋማት ለመቆጣጠር ያለመ ይመስል እንደነበር ቢቢሲ ያነጋገራቸው የክልሉ ባለሥልጣንና ነዋሪ ተናግረው ነበር። ታጣቂዎቹ የጋምቤላ ከተማን ከፊል ተቆጣጥረው እንደነበረና እስከ እኩለ ቀን ድረስ በዘለቀው የተኩስ ልውውጥ በርካታ የታጣቂው ቡድን አባላት መገደላቸው ተነግሯል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ላይም የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ በታጣቂዎቹ ላይ “ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን፣ በወገን ጦር ላይም መጠነኛ ጉዳት መድረሱን” ተናግረዋል። የከተማው ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩትና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጩ ምስሎች እንዳሳዩት በርካታ የታጠቂው ቡድን አባላት ናቸው የተባሉ አስከሬኖች በጋምቤላ ከተማ መንገዶች ላይ ታይተዋል። ዛሬ ረቡዕ ረፋድ ላይ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪ እንደሚሉትም፣ ከተማዋ ሰላም መሆኗንና ከጠዋት ጀምሮ በመንገዶች ላይ ወድቀው የነበሩ አሰከሬኖች እየተሰበሰቡ ናቸው። ነገር ግን ከጥቃቱ ጋር ተያይዞ ማክሰኞ ዕለት ተዘግተው የዋሉት የመንግሥት ተቋማት እና የግል የሥራ እንቅስቃሴዎች መልሰው እንዳልተጀመሩ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከማክሰኞ ዕኩለ ቀን በኋላ በከተማዋ ውስጥ የተኩስ ድምጾች መቆሙን፣ ነገር ግን ከከተማው ወጣ ባሉ አካባቢዎች አሁንም የተኩስ ድምጽ አልፎ አልፎ እንደሚሰማ ተናግረዋል። ማለዳ ላይ በድንገት ጥቃት ከፍተው የነበሩት ታጣቂዎቹ በርከት ያለውን የጋምቤላ ከተማን ክፍሎች ለመ���ጣጠር ችለው የነበረ ሲሆን፣ የክልሉ የፀጥታ ኃይል በወሰደው እርምጃ ረፋድ ላይ ታጣቂዎቹን ከአብዛኛው የከተማዋ ክፍሎች ለማስወጣት መቻሉን ነዋሪዎች ለቢበሲ ተናግረው ነበር። የክልሉ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ “የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ባካሄዱት ቅንጅታዊ ማጥቃት ከተማዋን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር እንደቻሉ” ገልጸዋል። መንግሥት በሽብርተኛ ቡድንነት የፈረጀው እና ሸኔ በሚል የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ዓለም አቀፍ የሕዝብ ግንኙነት እንደሆነ የሚነገረው ኦዳ ተርቢ፣ በትዊተር ገጹ ላይ የቡድኑ ታጣቂዎች ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር ተቀናጅተው ጥቃት መፈጸማቸውን አረጋግጧል። ማክሰኞ ዕለት በጋምቤላ ከተማ ውስጥ የተከሰተውን ጥቃት በተመለከተ የፌደራል መንግሥት አስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚዋሰነው የምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሆነው የጋምቤላ ክልል ታጣቂዎች ከሚንቀሳቀሱባቸው የምዕራብ ኦሮሚያ እና የከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ጋር ይዋሰናል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cpe11842gy7o +politics ትራምፕ 'ትሩዝ ሶሻል' የተባለ አዲስ ማኅበራዊ ሚዲያ ሊመሠርቱ ነው "የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 'ትሩዝ ሶሻል' የተባለ አዲስ ማኅበራዊ ሚዲያ ሊመሠርቱ መሆኑን አስታወቁ። ትራምፕ ማኅበራዊ ሚዲያው በአሜሪካ የተቃዋሚ ድምጾችን ዝም በማሰኘት የሚታወቁ ""ታላላቅ የቴክኖሎጂ ጭቆና ያስቆማል"" ብለዋል። ትራምፕ የሚመሩት ትራምፕ ሚዲያ እና ቴክኖሎጂ ቡድን (ቲኤምቲጂ) በደንበኝነት ምዝገባ ቪዲዮ-በፍላጎት የሚሰጥ አገልግሎት ለማስጀመር አስቧል። በጥር ወር ደጋፊዎቻቸው የአሜሪካን ምክር ቤት ህንጻን ካፒቶል ሂልን በመውረራቸው ምክንያት ትራምፕ እንደ ትዊተር እና ፌስቡክ ካሉ ታዋቂ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር መድረኮች በጊዜያዊነት ወይም በቋሚነት ታግደዋል። እሳቸው እና አማካሪዎቻቸው ከዚያ በኋላ ተፎካካሪ የማኅበራዊ ሚዲያ ለመፍጠር ስለማቀዳቸው ፍንጭ ሰጥተዋል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ 'ከዶናልድ ጄ ትራምፕ ዴስክ' የሚባል ድረ-ገጽ ጀምረው ነበር። ድረ-ገጹ ከተጀመረ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ እስከወዲያኛው ተዘግቷል። በቲኤምቲጂ መግለጫ መሠረት 'ትሩዝ ሶሻል' በሚቀጥለው ወር ለተመረጡ ሰዎች ብቻ ክፍት ሆኖ በአውሮፓውያኑ 2022 የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ይለቀቃል ተብሏል። ትራምፕ ""ታሊባን በትዊተር ላይ ትልቅ ቦታ ኖሮት ተወዳጁ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዝም እንዲል በተደረገበት ዓለም ውስጥ እየኖርን ነው"" ሲሉ ጽፈዋል። ""ሁሉም ሰው ለምን ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን አትገዳደሩም ብሎ ይጠይቀኛል? ደህና፣ በቅርቡ ይሆናለን!"" በማለት አክለዋል። አዲሱ ኩባንያ የሚሠራ ገጽ እንዳለው የሚጠቁም ነገር የለም። ትራምፕ ትዊተር ወይም ፌስቡክን የሚገዳደር መድረክ መፍጠር ቢፈልጉም ያ ግን በቀላሉ የሚሳካ አይመስልም። ቲኤምቲጂ በፍላጎት መሠረት የሚሠራው የቪዲዮ አገልግሎት የመዝናኛ ፕሮግራምን፣ ዜናዎችን፣ ፖድካስቶችን እና ሌሎችንም ያሳያል ተብሏል። ኩባንያው በናስዳክ የአክሲዮን ላይ ከተዘረዘረው ከስፔክ ጋር ለመዋሃድ አስቧል። ትራምፕ አዲስ ማኅበራዊ ሚዲያ ይፋ የተደረገው የቀድሞው ረዳታቸው ጄሰን ሚለር 'ጌትር' የተባለ ሌላ የማኅበራዊ ሚዲያ ከጀመረ ከወራት በኋላ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-58964348 +sports ሴሬና ዊሊያምስ ከሜዳ ቴኒስ ከመገለሏ በፊት የምታደርገውን ውድድር በድል ጀመረች "ሴሬና ዊልያምስ በኒውዮርክ በተስፋ እና በፈንጠዝያ በተሞላው አዝናኝ ምሽት መሰናበቻዋ የሆነውን የየዩኤስ ኦፕን ውድድርን በድል ጀመረች። ከውድድሩ በኋላ ከሜዳ ቴኒስ የምትርቀው ዊሊያምስ የሞንቴኔግሮዋን ዳንካ ኮቪኒችብ 6-3 እና 6-3 አሸንፋለች። በአርተር አሼ ስታዲየም የተገኙት 25 ሺህ ተመልካቾች ለኮከቧ ያላቸውን ከብር የገለጹ ሲሆን እና እሷም በተለመደው መንገድ ምላሽ ሰጥታለች። የ40 ዓመቷ ዊሊያምስ ረቡዕ ዕለት በሚደረገው የሁለተኛው ዙር ጨዋታ ከኢስቶኒያዋ አኔት ኮንታቬይት ጋር ትጫወታለች። የ23 ጊዜ የግራንድ ስላም አሸናፊዋ ሴሬና በአውስትራሊያዋ ማርጋሬት ኮርት የተያዘውን ክብረወሰን ለመጋራት አንድ ድል ብቻ ይቀራታል። ከታላቅ እህቷ ቬኑስ ጋር በጥንዶች ውድድር እየተሳተፈች ትገኛለች። በዚህም ስንብት ውድድሯን ለማራዘም ያለመች ይመስላል። ጉዞዋንም 80ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችውን ኮቪኒችን በማሸነፍ ጀምራለች። ከተመልካቾች ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘችው ሴሬና የደጋፊዎች ሁኔታ ውሳኔዋ ላይ ተጽዕኖ እንዳለቸው “አሁንም በጣም ከባድ ነው ምክንያቱም እዚያ መገኘትን በጣም እወደዋለሁ” ስትል ትገልጻለች። ""ብዙ ውድድሮችን በተጫወትኩ ቁጥር ብዙ መሳተፍ እንደምችል ይሰማኛል።  የበለጠ በተጫወትኩት ቁጥር የበለጠ ማንጸባረቅ እንደምችል ማሰብ በጣም ከባድ ነው።“ ""ነገር ግን ወደ ቀጣዩ ነገር ለመሸጋገር ጊዜው አሁን ነው። ማድረግ የምፈልጋቸው ሌሎች ብዙ ነገሮች ስላሉ አስፈላጊ ይመስለኛል"" ብላለች። ዊሊያምስ ከቴኒስ ተጫዋችነት በላይ ሆና ቆይታለች። አሜሪካዊት ተምሳሌት እና በዓለም ላይ በጣም ታዋቂ ከሆኑ የስፖርት ኮከቦች አንዷ ለመሆን በቅታለች። ከስፖርቱ እንደምትለይ ታዋቂ በሆነው የፋሽን መጽሔት ቮግ ላይ ማስታወቋ ይታወሳል። የቀድሞዋ የዓለም ቁጥር አንድ ከስፖርቱ መገለል የሚለውን ቃል ባትጠቀምም ከስፖርቱ “ጋር መለወጥ ፈልጌ ነው” ማለትን መርጣለች። ዓላማዋ አንጸባራቂ የስፖርት ህይወቷን በሀገሯ ውድድር ለማጠናቀቅ ነው። የሚስማማው፣ የመጨረሻ ግጥሚያዋ ሊሆን ለሚችለው፣ የታዋቂነት እና የአድናቆት ምሽት ነበር። ዊልያምስ ወደ ሜዳ ስትግባ ከፍተተኛ አቀባበል ተደርጎላታል። “ሜዳ ስገባ አቀባበሉ በጣም አስደናቂ ነበር:: በጣም ጥሩ ስሜት ነበር"" ብላለች። ""የማልረሳው ስሜት ነው። ለእኔ ትልቅ ትርጉም ነበረው።"" ዊልያምስን ""ታናሽ እህቴ” ብሎ የጠራው የፊልም ዳይሬክተሩኡ ስፓይክ ሊ በሜዳ ተገኝቷል። ሌላዋ ቅርብ ጓደኛዋ የቮግ መጽሔት አርታኢ አና ዊንቱር ከተጫዋቹቿ ቤተሰብ ጀርባ ባለው ሳጥን ውስጥ ተቀምጣ ነበር። በስታዲየም ከተገኙ እና ምስላቸው ከታዩት ታዋቂ ሰዎች መካከል የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን፣ ሙዚቀኛዋ ግላዲስ ናይት፣ ቦክሰኛው ማይክ ታይሰን እና ሞዴል ቤላ ሃዲድ ይገኙበታል። ልጇ ኦሎምፒያ ከአባቷ አሌክሲስ እና ከአያቷ ጋር በሜዳ ተገኝታለች። ደጋፊዎችም ለእሷ አድናቆታቸውን በተለያዩ መንገዶች ገልጸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/czvngj5rdkko +health ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስፎርዱ የክትባት ሙከራ ላይ አንድ ሰው ቢሞትም የደህንነት ስጋት የለበትም ተባለ በአስትራዜኔካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በጥምረት እየበለጸገ የሚገኘው የኮሮናቫይረስ ክትባት ላይ ሙከራ በሚደረግባት ብራዚል የአንድ በጎ ፈቃደኛ ሕይወቱ ማለፏን ተከትሎ ክትባቱ ምንም አይነት የድህንነት ስጋት እንደሌለበት ተገለጸ። የብራዚል ጤና ባለስልጣን ከሙከራው ጋር በተያያዘ ሕይወቱ ስላለፈው በጎ ፈቃደኛ ምንም አይነት መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ቡድን በበኩሉ በጉዳዩ ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ እንደሚደረግና ክትባቱ ግን ምንም አይነት የደህንነት ስጋት እንደሌለበት አስታውቋል። ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ደግሞ በጎ ፈቃደኘው ክትባቱን አልወሰደም። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየተሰራ የሚገኘው ክትባት ላይ ከሚሳተፉት በጎ ፈቃደኞች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ብቻ ሲሆን ክትባቱን እንዲወስዱ የተደረገው ቀሪዎቹ ደግሞ ማረጋገጫ የተሰጠው የማጅራት ገትር ክትባት ነው የተሰጣቸው። የሙከራው ተሳታፊ በጎ ፈቃደኞችም እራሳቸው የሚሰጣቸው የኮሮረናቫይረስ ክትባት ይሁን የማጅራት ገትር የሚያውቁት ነገር የለም። ይህ የሚደረገውም በገዛ ፈቃዳቸው ነው ተብሏል። ግዙፉ የመድሀኒት አምራች አስትራዜኔካ በበኩሉ በእያንዳንዱ የግለሰብ የሙከራ ሂደት ላይ አስተያየት እንደማይሰጥና ሙከራው ሲካሄድ ግን አስፈላጊው ጥንቃቄና የደህንነት እርምጃዎች መወሰዳቸውን አስታውቋል። ''ሁሉም ወሳኝ የጤና ሁኔታዎች በጥንቃቄ ተመርምረዋል፤ ከግምት ውስጥም ገብተዋል። ሙከራውም ሆነ የምርምር ሂደቱ ምንም አይነት አሳሳቢ ነገር አልተገኘባቸውም፤ የሚመለከታቸው ኃላፊዎችም ሂደቱን እንዲከታተሉት አድርገናል'' ብሏል። በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው የክትባት ሙከራዎች መካከል ይሄኛው በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በቅርቡ ለገበያ እንደሚበቃም ይጠበቃል። እስካሁን ደረጃ አንድና ደረጃ ሁለት የሙከራ ሂደቶችን በስኬታማነት ያጠናቀቀው ይኸው ክትባት ደረጃ ሶስትን ለማጠናቀቅ ደግሞ በዩኬ፣ ብራዚልና ሕንድ በበጎ ፈቃደኞች ላይ ሙከራውን እያካሄደ ይገኛል። ባሳለፍነው ወር በዩኬ ይካሄድ የነበረው ሙከራ የጎንዮሽ ጉዳት ሊኖረው ይችላል በሚል ተቋርጦ የነበረ ሲሆን ከቀናት በኋላ ግን ሙከራውን ለማከናወን ምንም ስጋት እንደሌለ በመገለጹ ሂደቱ በድጋሚ እንዲጀመር ሆኗል። የብራዚል ጤና ባለስልጣን በጎ ፈቃደኛው ሕይወቱ ስለማለፉ ከትናንት በስትያ መስማቱን አስታውቋል። የብራዚል መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው ሕይወቱ ያላፈችው ግለሰብ የ28 ዓመት የህክምና ባለሙያ እንደሆነና ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ሕይወቱ እንዳለፈች ዘግበዋል። ይህ ክትባት ሙሉ ፈቃድ የሚያገኝ ከሆነ ብራዚል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብልቃጦችን ለመግዛት ወስናለች። በአገሪቱ እስካሁን 5.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከአሜሪካና ሕንድ በመቀጠል በዓለማችን ሶስተኛው ከፍተኛ ቁጥር ነው። የሟቾች ቁጥር ደግሞ እስካሁን 155 ሺ መድረሱ ተረጋግጧል። https://www.bbc.com/amharic/news-54641714 +health ቀይ መስቀል በሰሜን ኢትዮጵያ የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ እጥረት አሳስቦኛል አለ "በሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ተከትሎ በአካባቢው የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች አቅርቦት አለመኖር በእጅጉ እንዳሳሰበው ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ። አንድ ዓመት ካለፈው ጦርነት ጋር ተያይዞ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የሚገኙ የሕክምና ተቋማት ውድመት የገጠማቸው ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአሁኑ ወቅት የአስፈላጊ አቅርቦቶችን ችግር እንደገጠማቸው ተነግሯል። ""የሕክምና አገልግሎት አቅራቢዎች መሠረታዊ ግብዓቶችን እያገኙ አይደለም፤ እንዲሁም በአንዳንድ መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል"" ብሏል ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) ጥር 09/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ። ቀይ መስቀል የመድኃኒት እና ሕክምና መስጫ መሳሪዎች እጥረት ከጤና መሠረተ ልማት ውድመቶች ጋር ተደማምሮ የጤና አገልግሎት አቅርቦትን እጅግ አስቸጋሪ አድርጎታል ይላል። ቀይ መስቀል በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ፤ ""ሰዎች ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን መሠረታዊ ነገር ከመከልከል"" ጋር የሚስተካከል ነው ብሏል። አይሲአርሲ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን የበለጠ ተጎጂ በሆኑት ላይ ትኩረት እያደረኩ ነው በሏል። ""የሕክምና አቅርቦቶች በመቀነሳቸው ምላሽ የመስጠት አቅማችንን ተገድቧል"" ያለው ቀይ መስቀል፤ ጦርነት፣ የደኅንነት እጦት እና ገደቦች የሰብዓዊ እርዳታውን ፈተና ውስጥ ከከተቱት ምክንያቶች መካከል ቀዳሚ መሆናቸውን በትናንቱ መግለጫው አስታውቋል። ""በአማራ ክልል አንዳንድ ሆስፒታሎች በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ተዘግተዋል"" ሲሉ በአማራ እና አፋር ክልሎች የቀይ መስቀል ተወካይ ሚቻ ዌዲኪንደ ተናግረዋል። ""ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያለባቸው ሰዎች በየዕለቱ እየሞቱ ነው። የጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው፤ ውሃ ወይም መብራት ስለማይኖራቸው እናቶች በቤት ውስጥ እየወለዱ ነው"" ብለዋል የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የአማራ እና አፋር ክልል ተወካይ። ከአማራ እና አፋር በተጨማሪ በትግራይ ክልልም ከፍተኛ የሆነ መድኃኒት እና የሕክምና ቁሳቁሶች እጥረት መኖሩ ቀይ መስቀል በመግለጫ ተመልክቷል። ""በትግራይ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ እንደ ጓንት፣ የቀዶ ሕክምና ቁሳቁሶች እና ሰውነት ውስጥ የሚገቡ የሕክምና ቱቦዎች ሳይቀሩ እየታጠቡ ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ ነው"" ሲሉ በኢትዮጵያ የቀይ መስቀል የጤና አስተባባሪ አፖሎ ባራሳ። ከላይ የተጠቀሱት አይነት ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸውን የጤና መሳሪያዎችን ዳግም መጠቀም፤ ለኢንፌክሽን የመጋለጥ እድልን ያሰፋል ይላሉ ተወካይዋ። በአንዳንድ አካባቢዎች ታካሚዎች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ከመውሰዳቸውም በተጨማሪ ሐኪሞች የሰዎችን ቁስል ለማጽዳት ጨው ለመጠቀም መገደዳቸውን ጭምር አፖሎ ባራሳ ይገልጻሉ። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት በፍጥነት የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ የበኩላቸውን እንዲወጡ በመግለጫው ጠይቋል። ኮሚቴው ከኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመሆን እአአ 2021 ላይ በአማራ፣ በአፋር፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች ለሚገኙ 130 የጤና ተቋማት ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። በዚህም ወደ 120 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ድጋፉን ማግኘታቸውን በመግለጫው አመልክቷል። የቀይ መስቀል ኮሚቴ እያደረገ ካለው የሕክምና ድጋፍ በተጨማሪ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ አካባቢዎች ያለው የምግብ እና የኑሮ ሁኔታ ያሳስበኛልም ብሏል። ኮሚቴው በስድስት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማራ ክልል ላልይበላ ከተማ እንዲሁም በመቀለ ከተማ ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። በመጨረሻም ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጨምሮም በቅርቡ ንጹሃን ዜጎችን ለጉዳት የዳረገ ግጭት መኖሩ አሳስቦኛል ብሏል። ኮሚቴው የግጭቱ ተሳታፊዎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ሕግጋቶችን እንዲያከብሩ ጠይቋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የሕዝብ መገልገያ መሠረተ ልማቶች ላይ በተለይም የሕክምና ተቋማት ላይ ዘረፋና ውድመት መፈጸሙ የተለያዩ መንግሥታዊና የተራድኦ ድርጅቶች ያወጧቸው ሪፖርቶች አመልክተዋል። የጤና ተቋማት በገጠማቸው ችግርና በመድኃኒትና በሕክምና መገልገያዎች አለመኖር ምክንያት በአካባቢዎቹ ያሉ ነዋሪዎች ከባድ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ለአደጋ መጋለጣቸው እተነገረ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-60041869 +sports "እግር ኳስ: ካፍ የኢትዮጵያ ስታድየሞች ""ይታረሱ"" ያለው ለምን ይሆን?" "ዋሊያዎቹ በሜዳቸው ማድረግ ያለባቸውን ጨዋታ 'በባዕድ ሜዳ' ማድረግ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የካፍን መመዘኛ የሚያሟሉ ስታድየሞች የላችሁም መባሉ ነው። ኢትዮጵያ የሜዳ እጥረት የለባትም ቢባል ማጋነን አይሆንም። በየክልሉ ቢያንስ አንድ 50 ሺህ ሰው የሚያስተናግድ ስታድየም ተገንብቷል። እና ካፍ ኢትዮጵያ ""ደህና"" ስታድየም የላትም የሚለው ለምንድነው? ከቅርብ ጊዜ ክስተት እንነሳ። ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ማጣሪያዋን ለማድረግ እየተሰናዳች ነው። ግብፅ፣ ማላዊና ጊኒ ኢትዮጵያ ባለችበት ምድብ ይገኛሉ። ዋሊያዎቹ በሕጉ መሠረት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ ከማላዊ ጋር ያደርጋሉ። ነገር ግን ቀጣዩ ጨዋታቸው ከግብፅ ጋር በገዛ ሜዳቸው እንደሆነ የካፍ የጨዋታ መረሃ ግብር ያሳያል። ቢሆንም ይህ ጨዋታ እዚያው ማላዊ እንዲደረግ የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪው አካል ካፍ ወስኗል። የማላዊ እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዝደንት ዋልተር ኒያሚላንዱ ""በአገሬ ያላችሁ የሊቨርፑል ደጋፊዎች ሞ ሳላህ ሊመጣላችሁ ነው፤ እንኳን ደስ አላችሁ"" የሚል መልዕክት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። ብዙዎች ይህ ""የግብፅ ሤራ ነው"" ይላሉ። ለዚህም የሞሐመድ ሳላህ አገር የኢትዮጵያ ሜዳ አይመጥነኝም ብላ ቅሬታ በማቅረቧ ነው ይህ የሆነው የሚል አመክንዮ ያስደምጣሉ። ነገሩ ግን ወዲህ ነው ይላል የኢትዮጵያን እግር ኳስ በቅርበት የሚከታተለው ፍሬው አሥራት። ""የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንና ስፖርት ኮሚሽኑ ካፍ 'ሜዳዬን አሻሽያለሁ፤ ምርመራ ይደረገልኝ' ብለው በጠየቁት መሠረት ነው ምርመራ የተደረገው"" ይላል ፍሬው። በዚህ ጥያቄ መሠረት የካፍ መርማሪ የሆኑት ግለሰብ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ ባሕር ዳር ስታድየም አቅንተው የሜዳውን ጥራት ተመልክተው ተመልሰዋል። ""ይህ ማለት ግብፅ ሜዳው ይመርመርልኝ አላለችም ማለት አይደለም"" ይላል ፍሬው። ""በተመሳሳይ ሰዓት የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ ደብዳቤ አስገብቶ ነበር። ነገር ግን ካፍ መልዕክተኛ የላከው በኢትዮጵያ ጥያቄ መሠረት ነው።"" ፍሬው የግብፅ ደብዳቤ አዲስ አበባ ያለችበትን ከፍታ ወይም ""አልቲቲዩድ"" በመፍራት የተፃፈ እንጂ የሜዳ ጉዳይን በዋነኛነት የሚዳስስ አይደለም ይላል። ""ሜዳው ይታረስ"" የካፍ መልዕክተኛ የባሕር ዳር ስታድየምን ከእግር እስከ ራሱ ከመረመሩ በኋላ ውጤቱን በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩት ባለሥልጣናት የሰጡት ምላሽ አዎንታዊ አልነበረም። መርማሪው ""ምን አጎደልን?"" በሚል ስሜት ውስጥ ለነበሩት የፌዴራልና የክልል ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች ይህን ትዕዛዝ አስተላለፉ፡ ""ሜዳው ይታረስ።"" መርማሪው የባሕር ስታድየም የካፍን ዝቅተኛ መመዘኛዎች እንኳ አያሟላም የሚል መርዶ ተናገሩ። ""እርግጥ ስታድየም የመገንባት ችግር የለብንም"" ይላል ፍሬው። ነገር ግን. . . ሲል ያክላል ""ነገር ግን ስታድየሞቹ ካፍ የሚጠይቀውን ደረጃ ይዘው አይጠናቀቁም። ውጫዊ ቁመናቸው ያምርና አጨራረሳቸው ግን የሚያስከፋ ይሆናል።"" ካፍ ""ሚኒመም ስታንዳርድ"" ይላቸዋል። አማርኛው ቢያንስ ይህን እንኳን አሟሉልኝ መሆኑ ነው። ፍሬው ካፍ ከሚጠይቃቸው በርካታ መመዘኛዎች ጥቂቱን እንዲህ ይጠቅሳል። ""አንደኛው የመጫወቻ ሜዳ ነው። አብዛኛዎቹ ስታድየሞች የመጫወቻ ሜዳቸው ዝናብ ሲዘንብ ውሃ ያቁራሉ። ብዙዎቹ ስታድየሞቻችን ይህን ለማስወግድ የሚያስችል የፍሳሽ ሥርዓት (ድሬይኔጅ ሲስተም) የላቸውም።"" ""ከዚያ ውጪ ደግሞ መልበሻ ክፍሎቻችን መቀመጫ አልባ ናቸው። ይህ ደግሞ የካፍን መመዘኛ እንድንወድቅ ከሚያደርገን መካከል ነው።"" ፍሬው ይቀጥላል. . . ""አብዛኞቹን ሜዳዎች ተመልክተህ ከሆነ ለደጋፊዎች የተሠራ መቀመጫ የላቸውም። ይህ ደግሞ ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው። ካፍ ውድድሮቹ በመሰል ስታድየሞች እንዲደረጉ በፍፁም አይፈልግም።"" ፍሬው ጨምሮም አብዛኞቹ ሜዳዎቻችን በምሽት ጨዋታ እንዲደረግ የ��ያስችል መብራት እንደሌላቸው ያወሳል። ""በተጨማሪ ካፍ ስታደየሞቹ ቢቻል ጣራ እንዲኖራቸው ይጠይቃል። የእኛ ስታድየሞች ደግሞ ጣራ አልባ ናቸው። ሌላው ደግሞ የተሟላ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ""ሚድያ ሩም"" [የመገናኛ ብዙኃን ክፍል] ጉዳይ ነው። ይህንንም አላሟላንም።"" ""አልፎም ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና ክፍል እንዲኖረን ካፍ ያስገድዳል።"" ፍሬው እንደሚለው ከላይ ከተጠቀሱት መመዘኛዎቹ የተወሰኑት እንኳ ቢሟሉ ጨዋታዎች እየተደረገ ማሻሻያ እንዲከናወን ይፈልጋል፤ ነገር ግን ባሕር ዳርን ጨምሮ ሁሉም ስታድየሞች ዝቅተኛውን መመዘኛ አላሟሉም። ""ካፍ ባሕር ዳር ስታድየምን ከተመለከተ በኋላ ሜዳው ድጋሚ ታርሶ ሣር ይተከልበት ነው ያለው። የፈሳሽ ውሃ ማሳለጫው [ድሬይኔጅ ሲስተም] እንዲስተካከልም ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ጥራት አለው ብለን የምንለው የባሕር ዳር ስታድየም መልበሻ ክፍልም ፈርሶ እንደ አዲስ መሠራት አለበት የሚል ግብረ መልስ ሰጥቷል።"" በቅርብ ጊዜ ከተሠሩና የተሻለ የምንለው የባሕር ዳር ስታድየም ይህን ካላሟላ ሌሎቹስ የሚል ጥያቄ ያነሳል ፍሬው። የኢትዮጵያ ስታድየሞች የማን ናቸው? የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስታድየሞችን የመገንባትም ሆነ የማስተዳደር ኃላፊነት የለብኝም ይላል። የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሐፊ ባሕሩ ጥላሁን በየትኛውም አገር የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ስታድየም የመገንባትም ሆነ የማስተዳደር ሥልጣን የለውም ይላሉ። ""የእኛ ሥልጣን እግር ኳስን ማስፋፋት እንጂ መሠረተ ልማት መገንባት አይደለም። ይህ ጉዳይ የሚመለከታቸው የፌዴራል መንግሥቱና የክልል መንግሥታት ናቸው።"" ዋና ፀሐፊው ""ይህ ማለት ግን ፌዴሬሽኑ 'ቴክኒካል' ድጋፍ አይሰጥም ማለት አይደለም"" ይላሉ። ""በዚህ ሥራ የተካኑ ባለሙያዎችን ከመንግሥት ጋር ማገናኘት፤ ኤክስፐርቶችን የማቅረብ ሥራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሊሆን ይችላል።"" አቶ ባሕሩ ""እንደውም በፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት ጥረት ነው ለበርካታ ጊዜያት ስታድየሞቻችን ሳይታገዱ የሰነበቱት"" ይላሉ። ""ለበርካታ ጊዜያት ጨዋታዎችን በባሕር ዳር ስናደርግ የነበረው በገደብ ነበር። ይህ የእግር ኳስ ዲፕሎማሲው ውጤት ነው። አቶ ኢሳያሳ ጅራ [የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት] ያለንበትን ሁኔታ ለካፍ እያስረዱ ነው ይህ ሲሆን የቆየው፤ እንጂ ሙሉ በሙሉ ስታድየሞቻችንን ለማገድ ያሰቡት የዛሬ ሁለት ዓመት ነበር።"" ዋና ፀሐፊው ካፍ በየጊዜው የሚልክላቸውን ደብዳቤዎች ለአማራ ክልልና ለስፖርት ኮሚሽን በማቅረብ መፍትሔ ለማበጀት ይሠሩ እንደነበር ያወሳሉ። ""ምንም እንኳ የተወሰነ መሻሻል ብናሳይም ካፍ በሚፈልገው መልኩ ግን አልነበረም። ካፍም መሻሻል እንዳለ አምኗል፣ ነገር ግን በዚህ ደረጃ ጨዋታን ማካሄድ እንደማይችል ነው የነገረን።"" አቶ ባሕሩ ጨምረውም በሂደቱ ውስጥ መሻሻሎችን ማሳወቅና ባለሙያ ማቅረብ ነው ሲሉ የፌዴሬሽኑን ኃላፊነት ያብራራሉ። ""ለምሳሌ ግሪጎሪ ኢንተርናሽናል የተባለ አፍሪካ ውስጥ ከ20 በላይ ስታድየሞችን የገነባ ድርጅት አምጥተን ከባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር አገናኝተን፤ የአዲስ አበባ ስታድየም እድሳትን ተመልክቶ፤ የሚሠራበትን ዋጋ አቅርቦ ነው የሄደው።"" አቶ ባሕሩ ኢትዮጵያ ከሜዳዋ ውጪ በመጫወቷ ዋጋ እየከፈለ ያለው ፌዴሬሽኑ ነው ይላሉ። ""ፌዴሬሽኑ ፊፋና ካፍ በሚመድቡለትና ከስፖንሰር በሚያገኘው ገቢ ነው የሚተዳደረው። ለብሔራዊ ቡድኑ ተብሎ ከመንግሥት የሚመደብለት ገንዘብ የለም።"" ዋና ፀሐፊው ብሐራዊ ቡድኑ ከማላዊ ቀጥሎ ከግብፅ ጋር ያለውን ጨዋታ በማላዊ ስታድዬም ለማድረግ የወሰነው ከወጪ አኳያ እንደሆነ ይገልጣሉ። ""ባለፈው በጋና ጨዋታ ተመልክተናል። አሁንም ደግሞ ማላዊ ላይ ግብፅን ለመግጠም አስበናል። ማላዊን የመረጥነው ወጪ ለመቀነስ በማሰብ ነው። ሁለተኛ ደግሞ ተጫዋቾቻችን ከአገር አገር በመመላለስ እንዳይዳከሙ በማሰብ ነው። ታድያ ይህ የሚያሳፍር እንጂ ደረት የሚያስነፋ አይለም።"" ""አሁን የምንቀሳቀስበት ገንዘብ ስላገኘን እየተሳተፍን ሊሆን ይችላል። ነገሩ እየከበደን ሲሄድ ግን ውድድር እስከማቋረጥ ልንደርስ እንችላለን። ይህ ደግሞ እንደአገር ብዙ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። ነገር ግን ይህን ለማስወገድ ከባሕልና ስፖርት ጋር እየሠራን ነው።"" ያለው ተስፋ ምንድነው? ፍሬውም ከዋና ፀሐፊው ሐሳብ ጋር ይስማማል። ስታድየም ገንብቶ ማጠናቀቅና ማስተዳደር ያለበት የፌዴራል መንግሥት አሊያም የክልል የስፖርት ቢሮዎች እንጂ የፌዴሬሽኑ አይደለም ይላል። ለምሳሌ የአዲስ አበባ ስታድየም የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ንብረት ነው። የሚቆጣጠረውም ኮሚሽኑ ነው ይላል። ""ቢሆንም ግን የሚጠቀምበት ስታድዬም እስከሆነ ድረስ ስታድየሞቻችን ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ ጫና የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት አምናለሁ።"" ምንም እንኳን ስታዲየሞቻችን ከካፍ ዝቅተኛው መመዘኛ በታች ቢሆኑም አሁን እድሳት ላይ ያለው የአዲስ አበባ ስታድየምና የአደይ አበባ ስታድየም ግንባት የተስፋ ስንቅ እንደሚሆኑ ፍሬው ይናገራል። የድሬዳዋና የባሕር ዳር ስታድየሞችም የካፍ መመዘኛን ባሟላ መልኩ ቢያንስ በዚህ ዓመት ሊጠናቀቁ እንደሚችሉ ፍሬው ይጠቁማል። ""ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ሆ ብሎ ስታድየሞችን በአንድ ጊዜ መጨረስ የሚከብድ ይመስለኛል"" የሚለው ፍሬው አሁን የስፖርት ሚኒስቴር እያደረገ ያለው የተጀመሩ ስታድየሞችን በደረጃ የማጠናቀቅ እርምጃ አዋጭ እንደሆነ ያብራራል። ""እንደውም ቢርቅ በሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ ዋሊያዎቹ በሜዳቸው ሲጫወቱ ልናይ እንችል ይሆናል።""" https://www.bbc.com/amharic/news-61507185 +business በዓለም ግዙፉ የፀሐይ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ሊገነባ ነው "በዓለም ከፀሐይ ብርሃን ከሚመነጩ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጮች አንዱ ይሆናል የተባለለትን ፕሮጀክት ዩናይትድ ኪንግደም ልትገነባ ነው። 880 ሺህ ፓናል የፀሐይ ብርሃን ተቀባይ ሰሌዳዎች የሚዘረጉበት ሜዳ የተዘጋጀ ሲሆን ይህም 890 ሄክታር ስፋት ይኖረዋል። የፀሐይ ብርሃን ሰሌዳዎች ይዘረጉበታል የተባለው ቦታ በሰሜን ኬንት ጠረፍ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የገጠሩን ውበት ያጠፋል በሚል ፕሮጀክቱን ክፉኛ ተቃውመውታል። ፕሮጀክቱ ከ2017 ጀምሮ ሲያጨቃጭቅ ቆይቶ ከሦስት ዓመታት ክርክርና ንትርክ በኋላ መጽደቁ ተዘግቧል። ይህ የፀሐይ ብርሃን ኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ለ91 ሺህ መኖርያ ቤቶች ኤሌክትሪክ ማቅረብ ይችላል። ከ350 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ያመነጫል። የፕሮጀክቱ ወጪ 450 ሚሊዮን ፓውንድ ሲሆን እንደ ፈረንጆቹ በ2022 ሥራ ይጀምራል ተብሏል። ፕሮጀክቱ በዓለም ካሉ ግዙፍ የኃይል ማጠራቀሚያ ቋቶች አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል። የኃይል ማጠራቀሚያ ቋቱ 20 የእግር ኳስ ሜዳዎች ቢዘረጉ የሚኖራቸው ስፋት ይኖረዋል። ግንባታውን በጥምረት የሚያካሄዱት ሃይቭ ኢነርጂና ዊርሶል ኢንርጂ የተባሉ የሶላር ኃይል ተቋራጭ ኩባንያዎች ናቸው። የአረንጓዴ መብት ተቆርቋሪዎች በዚህ ፕሮጀክት ላይ የተለያየ አቋም የወሰዱ ሲሆን የዱር አራዊቶችን ሕይወትና ብዝሃነት ያዛባል የሚሉ አልጠፉም። ውብ የገጠር ሕይወትን ወደ ተራ ኢንዱስትሪ አውራጃ ገጽታ ይቀይረዋል ብለው የተቃወሙትም በርካታ ናቸው። ፍሬንድስ ኦፍ ኧርዝ የተባለ የአረንጓዴና ልምላሜ ተቆርቋሪ ድርጅት ግን ፕሮጀክቱን ደግፎታል። ምክንያቱ ደግሞ የፀሐይ ብርሃን ተቀባይ ሰሌዳዎች የሚዘረጉበት ቦታ ለዘመናት የታረሰና ���አረንጓዴ ቢሸፈንም ለሰደድ እሳት የሚጋለጥ በመሆኑ ነው። ""ይህን ለዘመናት የታረሰ መሬት ለምርት ለማብቃት በርካታ ማዳበሪያ ያስፈልጋል፤ ይህ ራሱን የቻለ ጉዳት ነው። ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ መጠቀም ብልህነት ነው"" ብሏል ድርጅቱ። ፕሮጀክቱ ዩናይትድ ኪንግደም ታዳሽ ኃይልን ለመገንባትና ከበካይ የኃይል አቅርቦት ለመታቀብ የገባችው ቃል አንድ አካል ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-52845065 +politics ከቤተሰቦቻቸው ጋር መሣሪያ ደግነው ፎቶ የተነሱት የአሜሪካ ምክር ቤት አባል እየተተቹ ነው "የአሜሪካ ኮንግረስ አባል የሆኑት ግለሰብ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መሣሪያ ደግነው ለገና የተነሱት ፎቶ ከሁሉም አቅጣጫ ትችት እንዲያስተናግዱ አድርጓቸዋል። የኬንታኪ የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይ የሆኑት ቶማስ ማሲ በትዊተር ገፃቸው የለጠፉት ይህ ፎቶ ""መልካም ገና። ሳንታ እባክህ አሞን ይዘህ ና"" የሚል ፅሑፍ የታከለበት ነው። ይህ የኮንግረስ አባሉ ፎቶ ሰውዬው ከሁለቱም የአሜሪካ አውራ ፓርቲዎች ትችት እንዲዘንብባቸው አድርጓቸዋል። ቢቢሲ የኮንግረስ አባሉን አስተያየት ለማካተት ጥረት እያደረገ ይገኛል። ሰውዬው ፎቶውን ትዊተር ላይ ከሰቀሉ በኋላ ድጋፍ የሰጧቸውን ሰዎች 'ሪትዊት' በማድረግ ድምፃቸውን ሲያስተጋቡ የተቃወሟቸው ሰዎች ደግሞ ምላሽ ሲሲጡ ተስተውለዋል። ቶማስ ፎቶውን የለጠፉት ሚሺጋን ውስጥ አንድ የ15 ዓመት ተማሪ የአባቱን ሽጉጥ ተጠቅሞ ትምህርት ቤት ውስጥ በከፈተው ተኩስ አራት ሕፃናት ሞተው ሰባት መቁሰላቸው ከተሰማ ከቀናት በኋላ ነው። የተጠርጣሪው ወላጆች በሰው ልጅ ሞት እጃቸው አለበት፤ አደጋው ከመድረሱ በፊት ማስጠንቀቂያ አልሰጡም በሚል ቢከሰሱም ጥፋተኛ አይደለንም ብለዋል። በጦር መሣሪያ ጉዳይ ለሁለት በተከፈለችው አሜሪካ መሰል አደጋዎች በየጊዜው ይከሰታሉ። ከዚህ በፊት በነበሩ የትምህርት ቤት ተኩሶች ምክንያት ልጆቻቸውን ያጡ ወላጆች የኮንግረስ አባሉን ድርጊት በፅኑ ተቃውመውታል። የፍሬድ ጋተንበርግ ሴት ልጅ ሃይሜ ከሶስት ዓመት በፊት ፓርክላንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ውስጥ በተከፈተ ተኩስ ነው ሕይወቷን ያጣችው። ፍሬድ ከኮንግረስ አባሉ ፎቶ ሥር የልጁን ጉርድ ፎቶ እና የመቃብሯን ፎቶ ለጥፎ፤ ""የቤተሰቦቻችንን ፎቶ እየለጠፍንም አይደል፤ ይሄ የኔ ቤተሰብ ፎቶ ነው። አንደኛው የልጄ ፎቶ ነው፤ ሌላኛው ደግሞ የመቃብሯ። ልጄን ያጣሁት በመሣሪያ ምክንያት ነው። በቅርቡ ተማሪዎችን የገደለው ተማሪም እንዲሁም እንዳንተ ቤተሰብ ከወላጆቹ ጋር መሣሪያ ይዞ ፎቶ ይነሳ ነበር"" ሲል ፅፏል። ሌላኛው ዮዋኪን የተሰኘው ልጁን በፓርክላንድ ትምህርት ቤት ተኩስ ሳቢያ ያጣው ማኔኤል ኦሊቨር የሰውየው ደርጊ ፍፁም ተቀባይነት የለውም ሲል ለሲኤንኤን ተናግሯል። የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላትም ይህን የቶማስ ድርጊት በፅኑ አውግዘውታል። የኢሊኖይ ግዛት የኮንግረሱ ሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አዳም ኪንዚንገር የፓርቲ አጋራቸውን ወቅሰዋል። ይሁን እንጂ ሌሎች ትላልቅ ስም ያላቸው ወግ አጥባቂ የአሜሪካ ፖለቲከኞች ደግሞ ለሰውዬው ድጋፋቸውን አሳይተዋል። የኮሎራዶ ተወካይ የሆኑትና የጦር መሣሪያ መብት ባለቤትነት መብት ተሟጋች የሆኑት ሎረን ቦበርት እንዲሁም ሌላኛው ሪፐብሊካን ሆዜ ካስቲሎ ለቶማስ ድጋፋቸውን ችረዋል። ቶማስ ማሴ የኬንታኪ ተወካይ ሆነው ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡት በፈረንጆቹ 2012 ነበር። ሰውዬው 'ሰከንድ አሜንድመንት' በመባል የሚታወቀው የጦር መሣሪያ የመታጠቅ መብት ሕግ ቀንደኛ አቀንቃኝ ናቸው። የጦር መሣሪያ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ በትምህርት ቤቶች የሚከሰተውን ግድያ አያቆመውም ብለውም ተከራክረዋል። ባለፈው ሚ���ዚያ የጦር መሣሪያ የሚገዙ ሰዎች ዕድሜ ከ21 ወደ 18 ዝቅ ሊል ይገባል ብለውም ሞግተዋል። በአሜሪካው ባለፈው ዓመት ብቻ 20 ሺህ ሰዎች በጦር መሣሪያ አመፅ ምክንያት ሞተዋል። ይህም ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ከታየው የላቀ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-59545032 +business የኢትዮጵያ የምግብ ዘይት እጥረት አዙሪት እና ምክንያቱ "ከሰሞኑ የምግብ ዘይት ዋጋ መናር የኢትዮጵያውያን ዋነኛ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል። ትልቁን የገበያ ድርሻ በሚይዘው የፓልም ዘይትም ሆነ በሱፍ (ሰንፍላወር) ዘይት ላይ ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል። ይህም በተጠቃሚው ላይ ከፍተኛ ጫናን ፈጥሯል። በ6500 ወርሃዊ ደሞዝ 7 የቤተሰብ አባላት የሚያስተዳድሩት አንድ የመንግሥት ሠራተኛ፤ 5 ሊትር የፓልም ዘይት ከ1000 አስከ 1200 ብር እየገዙ መሆኑን በመናገር፤ "" . . . አንድ ፍሬ ሳሙና ከ26-30 ብር እየተገዛ፤ ለተለያዩ ጉዳዮች ከደሞዝ እየተቆረጠ መኖር በጣም ከባድ ነዉ"" በማለት ምሬታቸውን ይገልጻሉ። አቶ ነጌሳ ቱካና ደግሞ በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ የአንድ አነስተኛ ምግብ ቤት ባለቤት ናቸው። በቀን ከ80 እስከ 100 ለሚሆኑ ተጠቃሚዎችም ምግብ ይሸጣሉ። ""ሦስት ሊትር ዘይት 550 ብር ገብቷል። እሱ ራሱ አይገኝም። ለምግብ ቤቶች ሥራ በጣም አስቸጋሪ ሆኗል"" ይላሉ። በዘይት የችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩት የመንዲ ከተማ ነጋዴው በምርት እጥረት እና ዋጋ ንረት የንግድ ሥራቸው መቀዛቀዙን ይናገራሉ። የዘይት ዋጋ በኢትዮጵያ በድንገት ከፍተኛ ጭማሪ ሲያሳይ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። እንደው በድንገት የዘይት ዋጋ ለምን ጣራ ይነካል? ስንል አምራቾችን፣ ጅምላ አካፋፋዮችን፣ ቸርቻሪዎችን እና የሚመለከተውን የመንግሥት አካል ጠይቀናል። የኢትዮጵያ የዘይት ምርት እና ፍጆታ ከጥቂት ዓመታት በፊት ፉድ፣ ቤቨሬጅ ኤንድ ፋርማሱቲካል ዲቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ኦፍ ኢትዮጵያ እና ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢምፕሩቭድ ኒዩትሪሸን የሰሩት ጥናት በአገሪቱ የዘይት ገበያ ላይ የፓልም፣ የሱፍ፣ የአትክልት፣ የወይራ (ኦሊቭ ኦይል) እና የሶያ ዘይት አይነቶች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ አሳይቷል። ይህ ጥናት እንደሚያመለክተው ከሆነ ኢትዮጵያ እስከ 90 በመቶ የሚሆነውን የዘይት ፍላጎቷን በፓልም ዘይት የምታሟላበት ዓመታት አሉ። ኢትዮጵያ በፓልም ዘይት ምርታቸው ከሚታወቁት ኢንዶኔዢያ እና ማሌዢያ ከፍተኛ መጠን ያለው የፓልም ዘይት ታስገባለች። ታዲያ የፓልም ዘይትን ወደ አገር ውስጥ እንዲያስገቡ ተፈቅዶላቸው የነበሩት መንግሥታዊዎቹ አለ በጅምላ እና ጅንአድ ናቸው። በእነዚህ የመንግሥት ተቋማት በኩል የሚገባው ፓልም ዘይት ለተጠቃሚዎች የሚደርሰው በሸማቾች ማኅበራት በኩል ነው። እንደ ፌቤላ እና ሸሙ ያሉት የግል የዘይት ፋብሪካዎችም የፓልም ደፍድፍ ወደ አገር ውስጥ በማስገባት በአገር ውስጥ የፓልም ዘይት ያመርታሉ። የተቀሩትን የዘይት አይነቶች ደግሞ የግል ተቋማት በኢትዮጵያ እንዲያመርቱ እና ከውጪ እንዲያስገቡ ይፈቀድላቸዋል። የሰሞኑ የዘይት ዋጋ ጭማሪ በቅርቡ ላገጠመው የዘይት ዋጋ ጭማሪ፤ ከሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እስከ 'የተጋነነ ትርፍ ፈላጊ ነጋዴዎች' በምክንያትነት ቀርበዋል። ዘይት አምራቾች ምን ይላሉ? የዛሬ አንድ ዓመት ፌቤላ የተባለው ግዙፉ የዘይት ፋብሪካ ተመርቆ ወደ ሥራ ሲገባ፤ የኢትዮጵያን የዘይት እጥረት ይቀርፋል ተብሎ ተስፋ ተደርጎ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቡሬ ከተማ ተገኝተው ፋብሪካውን መርቀው ከፍተዋል። በወቅቱም 60 በመቶ የኢትዮጵያን የዘይት ፍላጎትን ያሟላልም ተብሎለት ነበር - ፌቤላ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ። ነገር ግን ዛሬም የዘይት ዋጋ መናር ብዙዎ���ን እንዳማረረ ቀጥሏል። ፋብሪካው በበኩሉ ከጥሬ ዕቃ አቅርቦት ጋር የተያያዙ ብዙ ፈተኛ ሁኔታዎች ቢገጥሙኝም የተቻለኝን ሁሉ እያደረኩ ነው ይላል። ፌቤላ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ አካል ሲሆን የኩባንያው ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰጠኝ እንግዳው፣ ፋብሪካው ባለፈው አንድ ዓመት 166 ሚሊዮን ሊትር የፓልም ዘይት አምርቶ ማከፋፈሉን ይናገራሉ። አቶ ሰጠኝ ፋብሪካቸው በአምስት ዙሮች 105 ሺህ ሜትሪክ ቶን የፓልም ድፍድፍ ዘይት ከውጪ ማስመጣቱንም አመልክተዋል። በሊትር ከ40 ወደ 82 ብር ከአንድ ዓመት በፊት ፋብሪካው 1 ሊትር ዘይት በ40 ብር ለገበያ ሲያቀርብ እንደነበረ የሚያስታውሱት አቶ ሰጠኝ፤ ዛሬ ላይ ግን የ1 ሊትር የፓልም ዘይት ዋጋ 82 ብር መሆኑን ይናገራሉ። ፋብሪካው ዋጋውን በእጥፍ እንዲጨምር ያስገደዱት በርካታ ምክንያቶች ናቸው በማለት፣ የመጀመሪያው የፓልም ድፍድፍ ዘይት ዋጋ መጨመርን ይጠቅሳሉ። ""አንድ ሜትሪክ ቶን የፓልም ድፍድፍ ዘይት 762 ዶላር ነበር የምንገዛው። 4ኛው ዙር ላይ ለአንድ ሜትሪ ቶን 1361 ዶላር ከፍለናል። አሁን እያሰራጨን ያለነው ዘይት ደግሞ በ5ኛው ዙር በ1407 ዶላር ተገዝቶ በገባ ድፍድፍ ፓልም የተመረተ ነው"" በማለት የዋጋውን ጭማሪውን ያስረዳሉ። ከፓልም ድፍድፍ ዘይት መወደድ በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የደኅንነት ስጋት፣ የአገር ውስጥ ግብዓት ዋጋ ጭማሪ እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሌሎች ለፋብሪካው ፈተኛ ሁኔታዎችን የፈጠሩ ናቸው ይላሉ። አቶ ሰጠኝ ፌቤላ ባሉት ግዙፍ 5 ማሽኖች አማካይነት በቀን እስከ 1.5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት የማምረት አቅም ቢኖረውም አሁን ላይ የምርት አቅማቸው በግማሽ መገደቡን ይጠቅሳሉ። ""በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት በቀን 750 ሺህ ሊትር ብቻ ነው የምናመርተው። ይህን ችግር ለመቅረፍ ከፍተኛ የነዳጅ መጠን የሚጠቀሙ ጀነሬተሮችን ገዝተን እየተጠቀምን ነው።"" በአሁኑ ወቅት ፋብሪካው ከቅባት እህሎች ዘይት ለማምረት የሚያስፈልገውን ግብዓት ማቅረብ የሚችል የአገር ውስጥ አቅራቢ ባለመኖሩ፣ ለዘይት ምርቱ የሚያስፈልገውን ግብዓት ለማግኘት የራሱ እርሻ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ አለው። ይሁን እንጂ በክልሉ ያለው የፀጥታ ችግር የእርሻ ሥራቸው ውጤታማ እንዳይሆን እንዳደረገው አቶ ሰጠኝ ይገልጻሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፌቤላ ፋብሪካ አንድ ሊትር በ82 ብር ለአካፋፋዮች ያቅርብ እንጂ ቢቢሲ ባደረገው ቅኝት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ባለ 1 ሊትር ፓልም ዘይት እስከ 150 ብር፣ ባለ 3 ሊትር 550 ብር እና ባለ5 ሊትር ደግሞ በትንሹ 900 ብር ይጠየቅበታል። ለባለ 1 ሊትሩ ሰንፍላወር ዘይት ደግሞ ከ180 አስከ 190 ብር ይጠየቃል። አቶ ሰጠኝ ግን ""አከፋፋዮች አሁን (ማክሰኞ የካቲት 29) ፋብሪካ በር ላይ 1 ሊትር ፓልም ዘይት በ82 ብር ነው እየጫኑ ያሉት"" ይላሉ። ይህ ሰፊ የዋጋ ልዩነት ከየት መጣ? ""ጭማሪው እኛን አይመለከትም"" ይላሉ አቶ ሰጠኝ፤ ፋብሪካው ከመንግሥት በተሰጠው ኮታ መሠረት ለ7 ክልሎች እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከላይ በተጠቀሰው የፋብሪካ ዋጋ የፓልም ዘይት እያከፋፈለ እንደሆነ በመጥቀስ። ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈገ ለጉዳዩ ቅርበት ያለው የሽያጭ ባለሙያ፤ ከፍተኛ ፍላጎት ባለባቸው የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ የሚተመነው በግለሰቦች ፍላጎት እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግሯል። ይህ ዘይትን ጨምሮ መሠረታዊ ሸቀጦችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት እና በማከፋፈል ሂደት ውስጥ የበርካታ ዓመታት ልምድ ያለው የሽያጭ ባለሙያ እንደሚለው፤ በመሠረታዊ ሸቀጦች አስመጪዎች ከ30 በመቶ ያላነሰ ትርፍ መያዛቸው የተለመደ ነው። የሽያጭ ባለሙያው እንደሚለው ከሆነ የዘይትም ሆነ የሌሎች መሠረታዊ ፍጆታዎች የሽያጭ ዋጋ የሚተመነው ምክንያታዊ በሆኑ ምጣኔ ሃብታዊ ስሌት ላይ ተመስርቶ ሳይሆን በግለሰቦች ፍላጎት ነው። አስመጪዎች ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ ከባንኮች ማግኘት ስለማይችሉ ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም ይገደዳሉ። እናም በተለያየ መንገድ ያገኙትም የውጭ ምንዛሪ የሚያካክሱት በሚያስገቡት ምርት ላይ ዋጋ ያስፈልገናል የሚሉትን በመጨመር ነው ይላል የሽያጭ ባለሙያው። 'የውጭ ምንዛሬ ታጣ ይሉናል' ዘይት ከአስመጪዎች በመግዛት በጅምላ እና በችርቻሮ ለተጠቃሚዎች የሚያደርሱት የመንዲ ከተማ ነጋዴ በአካባቢያቸው የምርት እጥረት መኖሩን ይናገራሉ። ""ዘይት ከእዲስ አበባና ከአዳማ ነበር የምናመጣዉ። አሁን ግን አጥተናል፤ ማምጣት ልቻልንም"" ይላሉ። ""አስመጪዎችን ስንጠይቅ 'የውጭ ምንዛሬ ታጣ' ይሉናል"" በማለት የሚሰጣቸውን ምላሽ ይናገራሉ። የንግድ ሰንሰለት ርዝመት የሽያጭ ባለሙያ ዘይትን ጨምሮ በሌሎች መሠረታዊ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዲከሰት የሚያደርገው ሌላኛው ትልቁ ምክንያት የንግድ ሰንሰለቱ መርዘም ነው ይላል። ""የንግድ ሰንሰለቱ በጣም ረዥም ነው። አስመጪዎች ምርቱን ከሞጆ ደረቅ ወደብ አንስተው መርካቶ ያስገባሉ። አስመጪዎች ዋጋ ተምነው ለጅምላ አካፋፋዮች ያደርሳሉ"" በማለት የገበያ ሰንሰለቱን ሂደት ያብራራል። ""ከዚያም ጅምላ አፋፋዮች ደግሞ የራሳቸውን ትርፍ ይዘው ክፍለ አገር ላለ ሌላ ጀምላ አከፋፋይ ያደርሳሉ። እነዚህ ጀምላ አካፋፋዮች ደግሞ ለቸርቻሪ ይሸጣሉ። ቸርቻሪ በነጠላ እቃ ላይ ብዙ ትርፍ ይይዛል። በመጨረሻ ዘይቱ ተጠቃሚው ጋር ሲደርስ ዋጋው ይከመራል።"" ከዚህ በተጨማሪም አቅም ያለው ተጠቃሚ ደግሞ ""ገና ለገና 'ዘይት ጠፋ ሲባል' ከሚያስፈልገው በላይ ካርቶን ሙሉ ገዝቶ ስለሚያስቀምጥም ፍላጎት እንዲጨመር ያደርጋል"" በማለት ተጨማሪ ምክንያት ያስቀምጣል። የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በንግድ እና የቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ አበባ ታመነ ከሰሞኑ ለተከሰተው የዘይት ዋጋ ጭማሪ ዋነኛ ምክንያቱ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ነው ይላሉ። ወ/ሮ አበባ እንደሚሉት በአዲስ አበባ ከተማ ያጋጠመው የሰንፍላወር (የሱፍ) ዘይት እጥረት እንጂ የፓልም ዘይት አይደለም። ዩክሬን ከፍተኛ የሱፍ ዘይት አምራች አገር መሆኗን በማስታወስ፤ በጦርነቱ ምክንያት አስመጪዎች ምርት ማግኘት ባለመቻላቸው እጥረት አጋጥሟል ይላሉ። ""በራሳቸው ዶላር ምርት ያገኙት እንኳ 'ዋጋ እየጨመረ ስለሚሄድ ነገ እና ከነገ ወዲያ የተሻለ ትርፍ አገኛለሁ' በሚል አስተሳሳብ ጂቡቲ ወደብ ላይ ምርት የሚያቆዩ ነጋዴዎች ስላሉ እጥረቱ ሊያጋጥም ችሏል"" ይላሉ። የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሯ ሰኞ የካቲት 28/2014 ዓ.ም ለቢቢሲ በተናገሩበት ቀን፤ መንግሥት ገበያውን ለማረጋጋት 40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ከሳዑዲ አረቢያ ለማስገባት ስምምነት መጨረሱን ተናግረው ነበር። ""በአካል ተገናኝተው ከስምምነት ተደርሷል። 20 ሚሊዮን ሊትሩ የሰን ፍላወር ነው ቀሪው ፓልም ነው። ይህ ዘይት በቅርብ ቀን ይገባል ገበያውንም ያረጋጋል"" ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። ወ/ሮ አበባ ይህን ይበሉ እንጂ የገንዘብ ሚኒስቴር 40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ለመግዛት ከስምምነት አለመድረሱን እና ጉዳዩ ገና በጥናት ላይ እንደሚገኝ ስለመናገሩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60658208 +sports በ2020 በስፖርት ሜዳዎች ላይ የተስተዋሉ የተቃውሞ ምልክቶች "በፈረንጆቹ 2000 የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ኔልሰን ማንዴላ ""ስፖርት ዓለምን የመቀየር ኃይል አለው"" ሲሉ ተናግረው ነበር። ከሁለት አሥርት ዓመታት በኋላ በ2020 ይህ እውን ሆኖ ታይቷል። ያለፈው የፈረንጆቹ ዓመት [2020] በሁሉም የስፖርት ዘርፎች ያሉ የዓለማችን ስፖርተኛ ዓለምን ለመቀየር ቆርጠው የተነሱበት ነበር። ዘረኝነት ይብቃ ሲሉ ጮኸዋል። ለውጥ ይምጣ ሲሉም ጠይቀዋል። ሴራሊዮናዊው አጥቂ ኬይ ካማራ በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ነው የሚጫወተው። የቀድሞ ክለቡ ከኮሎራዶ ራፒድስ ሚኒሶታ ዩናይትድን ተቀላቅሏል። ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ እጅ በግፍ መገደሉን ተከትሎ ተቃውሟቸውን ካሰሙ ተጫዋቾች መካከል ነው ካማራ። ""የልጆቼ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ነው አቋሜን በይፋ እንድገልፅ ያደረገኝ"" ይላል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ። ከአሜሪካ አልፎ በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ የሚጫወቱ እግር ኳሰኞች ዘረኝነትን በመቃወም መንበርከክ የጀመሩት በ2020 ነው። አሜሪካዊቷ የዝላይ ውድድር ክብረ-ወሰን ባለቤት ቶሪ ፍራንክሊን እንደምትለው ስፖርት በሰዎች አስተሳሰብ ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ይችላል። አልፎም ዘረኝነት ለመዋጋት በሚደረገው ፍልሚያ የስፖርት ሚና የሚናቅ አይደለም ትላለች። ""እኔ ስፖርት ትልቅ ተፅዕኖ ማምጣት እንደሚችል ነው የማስበው"" ትላለች ፍራንክሊን። ""በአሜሪካ ባህል ስፖርት ትልቅ ቦታ አለው። በቴሌቪዥን ሰፊ ሽፋን ይሰጠዋል። መገናኛ ብዙሃን ይዘግቡታል። ለዚህ ነው ዘረኝነትን በመቃወም እጃችንን ስናነሳ ለውጥ ልናመጣ እንችላለን የምለው።"" ባለፈው ነሐሴ የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ክለብ ሚልዋውኪ ባክስ ተጫዋቾች ከኦርላንዶ ማጂክ ጋር የነበራቸውን ጨዋታ ጃኮብ ብሌክ የተሰኘው ጥቁር አሜሪካዊ በፖሊስ ጥይት መመታቱን ተከትሎ አንጫወትም ብለው ነበር። ብሌክ በፖሊስ ጥይት በተደጋጋሚ የተመታው በቅርጫት ኳስ ክለቡ ስታድየም አቅራቢያ ነበር። ይህንን ተከትሎ ኤንቢኤ የተባለው የቅርጫት ኳስ አስተዳደር ሌሎችም ጨዋታዎች እንዲሰረዙ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር። በወቅቱ በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮች እንዲሰረዙ ተደርጎ ነበር። የሚያነሳሳ ለውጥ በአትሌቲክስ ዓለም ትልቁ ውድድር የኦሊምፒክ ጨዋታ ነው። ይህ ውድድር በ2020 ሊካሄድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ይህ ሳይሆን ቀርቷል። ከዚህ ቀደም በነበሩ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በርካታ አትሌቶች ለውጥ ለማምጣት እጃቸውን ወደላይ አንስተው ነበር። አትሌቶቹ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ለውጦችን የሚጠይቁ ርዕሶችን አንስተዋል። ነገር ግን ባፈለው ዓመት ጥር የኦሊምፒክ ኮሚቴ አዲስ ሕግጋትን አውጥቷል። ሕጉ አትሌቶቹ በኦሊምፒክ መድረክ ላይ ፖለቲካዊ፣ ሐይማኖታዊ፣ አሊያም ከዘር ጋር የተገናኘ መልዕክት ማስተላለፍ አይችሉም ይላል። ኮሚቴው በተለይ ደግሞ በእጅ ምልክት ማሳየትና መንበርከክ ክልክል ነው ብሏል። የኦሊምፒክ ሕጎችን አልቀበልም ማለት እንደማይቻልም ኮሚቴው አዲስ ባወጣው መመሪያ ላይ አስቀምጧል። በ2019 በተካሄደው የፓን አሜሪካን ጨዋታዎች ላይ ተቃውሟቸውን እጃቸውን ከፍ በማድረግ ያሳዩ ሁለት አትሌቶች የ12 ወራት ቅጣት ተላልፎባቸው ነበር። በኦሊምፒክ ሜዳ ከታዩ ታሪካዊ ተቃውሞዎች መካከል አንዱ አሜሪካዊያኒ ቶኒ ስሚዝና ጆን ካርሎስ በ1968 የሜክሲኮ ኦሊምፒክ ያለ ጫማ፣ በጥቁር ካልሲና ጥቁር ጓንት ሆነው እጃቸውን በማንሳት ተቃውሟቸውን የገለፁበት መንገድ ነው። አትሌቶቹ በዚህ ድርጊታቸው ዕግድ ተጥሎባቸው ነበር። ሌላኛው ክስተት የታየው በ2016ቱ የሪዮ ኦሊምፒክ ነው። በወቅቱ በማራቶን ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት የነበረው ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ሌሊሳ ሁለት እጆቹን ወዳላይ በማንሳት በማጣመር የኦሮሞ ተቃውሞን ያጎላበት መንገድ ነው። ፈይሳ ይህን ምልክት የተቃውሞ ምልክት ያሳየው በውድድሩ መጠናቀቂያ መስመር ላይና በጋዜጣዊ መግለጫ ቦታ ላይ ነበር። ይህ ከሆነ ከሁለት ዓመት በኋላ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን ወርደው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተተኩ። ምንም እንኳ ፈይሳ ብቻውን ለውጥ አምጥቷል ባይቻልም በወቅቱ በአገር ቤት የነበረውን ተቃውሞ ለዓለም ሕዝብ በማንፀባረቅ ሚና እንደተጫወተ የሚካድ አይደለም። ነገር ግን የኮሚቴው መመሪያ መሰል ተቃውሞዎች በምንም ዓይነት መንገድ በኦሊምፒክ መድረክ ላይ እንዲታይ አይፈቅድም። አሁን ሁሉም ስፖርተኞች ጥያቄያቸው አንድ ነው - ቀጣይ ምን ማድረግ እንችላለን? የሚል። አብዛኛዎቹ ገና ብዙ መንገድ ይቀረናል ይላሉ። ለውጥ ለማምጣት ስፖርት የበኩሉን መወጣት ይቻል እንጂ ብቸኛው መንገድ እንዳልሆነ በርካቶች ይስማማሉ። ነገር ግን ታሪክ ስፖርት ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆኑን መዝግቦ አሳይቶናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55505986 +business የዓለማችን 10 ቱጃሮች ከወረርሽኙ በኋላ ሃብታቸው እጥፍ ማደጉ ተሰማ "የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ቱጃሮችን የበለጥ ባለጸጋ፤ በድህነት አረንቋ ውስጥ የነበሩትን ደግሞ የበለጠ ደሃ እንዳደረጋቸው ኦክስፋም የተሰኘው የእርዳታ ድርጅት አስታወቀ። ድርጅቱ እንዳለው የዓለማችን ደሃ ሃገራት የገቢ ምንጫቸው በመድረቁ ምክንያት በቀን 21 ሺህ ሰው እየሞተባቸው ነው። ነገር ግን የምድራችን 10 ባለሃብቶች በፈረንጆቹ ከመጋቢት 2020 ጀምሮ ሃብታቸው እጥፍ ማደጉን ኦክስፋም ገልጧል። ድርጅቱ ለወትሮው ዳቮስ ከሚከናወነው የዓለም ምጣኔ ሃብት ስብሰባ በፊት ነበር የምድራችን የሃብት ክፍፍልን የሚያሳይ መረጃ የሚለቀው። ዳቮስ፤ በየዓመቱ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የመብት ተሟጋቾች፣ የምጣኔ ሃብት ሰዎች እንዲሁም ጋዜጠኞች በስዊዝ ስኪ ሪዞርት ተሰባስበው ውይይት የሚያደርጉበት፣ የሚከራከሩበት እንዲሁም ዘና የሚሉበት ስፍራ ነው። ነገር ግን ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የዳቮስ ምጣኔ ሃብት ጉባዔ በኦሚክሮን ምክንያት በበይነ መረብ የሚከናወን ይሆናል። በዚህ ሳምንት የሚከናወነው ጉባዔ የወረርሽኙ ጉዳይ፣ የክትባት ክፍፍልና ኃይል ማመንጨት ሐሳብ ይነሳበታል ተብሎ ይገመታል። የኦክስፋም የታላቋ ብሪታኒያ ቅርንጫፍ ኃላፊ ዳኒ ስሪስካንዳራጃህ እንዳሉት ድርጅታቸው ሪፖርቱን የስብሰባው ሰሞን የሚለቀው የምጣኔ ሃብት፣ የንግድና ፖለቲካ ሰዎችን ቀልብ ለመግዛት ነው። ""በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ቢያንስ በየቀኑ አንድ ሰው ቢሊየነር ይሆናል። በሌላ በኩል 99 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ሕዝብ በእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ታፍኖ ነበር። የዓለም አቀፍ ንግድና ቱሪዝም ተቀዛቅዞም ነበር። በዚህ ምክንያት 160 ሚሊየን የዓለማችን ሰዎች ወደ ድህነት ዓለም ተገፍትረዋል።"" ""አንዳች ነገር የዓለማችንን ምጣኔ ሃብት ሸንቁሮ ይዞታል"" ሲሉ አክለዋል ኃላፊው። ኦክስፋም የፎርብስ መፅሔት መረጃን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የዓለማችን አስር ሃብታሞች እኚህ ናቸው፤ ኢላን መስክ፣ ጄፍ ቤዞስ፣ በርናርድ አርኖልት፣ ቢል ጌትስ፣ ላሪ ኤሊሰን፣ ላሪ ፔጅ፣ ሰርጌ ብሪን፣ ማርክ ዛከርበርግ፣ ስቲቭ ባልመር እና ዋረን ባፌት። አስሩ ስማቸው የከበደ ቱጃሮች ጠቅላላ ሃብታቸው ከ700 ቢሊየን ወደ 1.5 ትሪሊየን ሲያድግ በግል ደግሞ የኢላን መስክ ገቢ በአንድ ሺህ እጥፍ ሲወንጨፍ ቢል ጌትስ በበኩሉ 30 በመቶ ጭማሪ አምጥቷል። ፎርብስ መፅሔት የዓለማችን ቱጃሮችን የሚለካው ባለቸው ተቀማጭ ሃብት ለምሳሌ መሬትና ሌሎች ሲቀነስ ዕዳ በማድረግ ነው። ኦክስፋም ከዓለም ባንክ ወስዶ በሪፖርቱ ባካተተው መረጃ መሠረት በጤና አገልግሎት እጦት፣ በረሃብ፣ ፆታዊ ጥቃት እንዲሁ�� የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በየአራት ሰከንዱ አንድ ሰው ይሞታል። ድርጅቱ እንዳለው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት 160 ሚሊየን የዓለማችን ሰዎች በቀን ከ5.50 ዶላር በታች ገቢ ነበራቸው። የዓለም ባንክ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት በቀን 5.50 ዶላር የደህነት መለኪያ ነው ይላል። የኦክስፋም ዘገባ አክሎ ደሃ ሃገራት ዕዳቸው እየበዛ ስለመጣ ከማሕበረሰባዊ ወጪያቸው ላይ እየቀነሱ ለሌላ እያዋሉት ነው ብሏል። የፆታ እኩልነትን በተለመከተ ደግሞ በፈንጆቹ 2019 ጋር ሲነፃፀር 13 ሚሊዮን ሴቶች ከሥራ ገበታቸው ተፈናቅለዋል። በተለይ ደግሞ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ባንግላዴሽና ዩናይትድ ስቴትስ ጥቁሮች በኮቪድ ምክንያት እጅግ ተጎድተዋል። ዳኒ ስሪስካንዳራጃህ የዓለም መንግሥታት አሁን እየሄድንበት ያለውን የከፋ መንገድ ለመቀልበስ አንድ መላ መምታት አለባቸው ይላሉ። ይህ ቱጃሮችን መቅረጥን ሊያካትት ይገባል፤ ከፍተኛ ገቢ ካላቸው የሚገኘው ቀረጥ ጥራት ላለው የጤና አገልግሎትና ለማሕበረሰባዊ ግልጋሎቶች ሊውል ይጋል ይላሉ ኃላፊው።" https://www.bbc.com/amharic/news-60020490 +business ሪሃና የፌንቲ የውበት መጠበቂያ ምርቶቿን በአፍሪካ ልታቀርብ ነው ሪሃና ፌንቲ ቢውቲ እና ፌንቲ ስኪን የተባሉ የውበት መጠበቂያ ምርቶቿን ከዚህ ወር መጨረሻ ጀምሮ በስምንት የአፍሪካ ሃገራት ገበያዎች እንደሚቀርቡ አስታውቃለች። ሪሃና በማህበራዊ ድረ-ገጿ ላይ እንዳሰፈረችው ምርቶቿን ወደ አህጉሪቷ የማምጣቱን ሁኔታ በጉጉት እየጠበቀች እንደነበር እና ይህም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ተናግራለች። የውበት ምርቶቹ በቦትስዋና፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ናሚቢያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌ እንደሚገኙም ተጠቅሷል። ሮቢን ሪሃና ፌንቲ ወይም ሪሃና ፌንቲ የተሰኘውን የውበት መጠበቂያ ምርቶቿን ከቅንጦት እቃዎች አምራቹ ሞየት ሄነሲ ሉዊ ቩቶን ጋር በመጣመር በአውሮፓውያኑ 2017 ጀመረች። አርቲስቷ 1.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት ያላት ሲሆን 1.4 ቢሊዮን ዶላር የሚገመተው ከፌንቲ ቢውቲ የተገኘ ነው። ኩባንያው በመጀመሪያዎቹ 40 ቀናት ውስጥ 100 ሚሊዮን ዶላር እንዳገኘ ተዘግቧል። እንደ ፎርብስ ዘገባ ከሆነ እንደ ካይሊ ጄነር የውበት መጠበቂያ አምራች የሆነው ካይሊ ኮስሜቲክስ፣ የኪም ካርዳሺያን ኬኬደብልዩ ቢውቲና የጀሲካ አልባ ኦነስት ካምፓሊ በበለጠ የሪሃና የውበት ማስጠበቂያ ምርቶች ኩባንያ የበለጠ ገንዘብ ያገኛል። https://www.bbc.com/amharic/61392235 +business የዓለም የምግብ ዋጋ ለተከታታይ አምስት ወራት መቀነሱን የፋኦ መረጃ አመለከተ የተባበሩት መንግሥታት በዓለም ዙሪያ ባደረገው ጥናት ለተከታታይ አምስት ወራት የምግብ ዋጋ ቅናሽ መታየቱን አመለከተ። ይህም በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ያለው የኑሮ ውድነት ላይ ጫና ከሚያሳድሩ ችግሮች አንዱ ሊቀንስ እንደሚችል ማሳያ ነው ተብሏል። መረጃው እንዳለው በነሐሴ ወር የዋጋ ጠቋሚው ወደ 138 የቀነሰ ሲሆን፣ አሁን ላይ ደግሞ ሩሲያ ዩክሬንን ከመውረሯ በፊት ከነበረው ጊዜ ዝቅ ማለቱን አሳይቷል። ሩሲያ እና ዩክሬን የሱፍ ዘይት፣ በቆሎ እና ስንዴን ጨምሮ ሌሎች የምግብ ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ ዋነኛ አገራት ናቸው። የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) እንዳለው ሐምሌ ወር ላይ በድርጅቱ የተደገፈውና የዩክሬን ወደቦች እንዲከፈቱ የተደረሰው ስምምነት የጥራጥሬ እና የአትክልት ዘይት ዋጋን ቀንሷል። ይህም ማለት ተጨማሪ ምርቶች ወደ ዓለም አቀፍ ገበያው ገብተዋል ማለት ነው። የፋኦው ኢሪን ኮሌር፣ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የምግብ ዋጋ መቀነስ ምክንያቶች የተለያዩ ናቸው። “የጥራጥሬ ምርት አቅርቦት ችግር በዚህ ዓመት ለተከሰተው የምግብ ዋጋ መናር ዋነኛው መንስዔ ሆኖ ነበር። ነገር ግን አሁን ላይ አቅርቦቶች እየጨመሩ ነው” ብለዋል ኮሌር። ለዚህም ምክንያቱ በተለይ በካናዳ፣ በአሜሪካ እና በሩሲያ ያለው ምርት የተሻለ በመሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል። እነዚህ ሦስት አገራት ዋነኛ የስንዴ ላኪዎች ናቸው። በሌሎች ምግቦች ላይም ምግቦችን ወደ ውጪ ለመላክ የነበረው ገደብ በመቅለሉ የስኳር እና የዘይት ዋጋ እንዲቀንስ የረዳ ሲሆን፣ በሌሎች ምርቶች ላይ ያለው ፍላጎት መቀነስም የሥጋ እና የወተት ተዋፅኦ ውጤቶች ዋጋ እንዲቀንስ አድርጓል ብለዋል። ኢንዶኔዥያ የፓልም ዘይት የውጪ ንግድ ቀረጥን በጊዜያዊነት በመቀነሷም የምግብ አምራቾች በብዛት ለሚጠቀሙት የአትክልት ዘይት ተጨማሪ አማራጭ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል። የምግብ ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚከሰት የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ ነው። በዚህ ሳምንት ዩሮዞን በነሐሴ ወር ዓመታዊ የዋጋ ግሽበቱ 9.1 በመቶ መድረሱን አስታውቋል። ለዚህ የዋጋ ግሽበት ምክንያቱ አንዱ ኢነርጅ (ኃይል) ሲሆን አሃዙም 38.3 በመቶ ነበር። ነገር ግን ያልተቀነባበሩ ምግቦች በ10.9 በመቶ ግሽበት ተመዝግቦባቸው ከኃይል በሁለተኛ ደረጃ ላይ ነበር የተቀመጡት። በቅርቡ በዩናይትድ ኪንግደም እና በአሜሪካ የታየው የዋጋ ግሽበት መረጃ ተመሳሳይነት ታይቶበታል። የፋኦ መረጃ፣ በወተት ተዋፅኦ፣ ሥጋ እና ስኳር ምርቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ መታየቱን አመልክቷል። የከብት እና ሌሎች የእንስሳት ምርቶች ዋጋ በግንባር ቀደምትነት ወደ ውጪ በሚላኩባቸው አገራት ውስጥ ባለው ደካማ ፍላጎት ምክንያት ቀንሷል። ለዚህ ምን አልባት ሸማቾች ወደ ርካሽ አማራጮች ፊታቸውን እያዞሩ መሆኑን እንደሚያመላክት ፋኦ ጠቁሟል። የኢዲ ኤንድ ኤፍ ማን የግብርና ምርቶች ድርጅት የምርምር ኃላፊ ኮና ሃቅ እንዳሉት፣ የምጣኔ ሐብት ውድቀቱ አሳሳቢነት እያደገ በመምጣቱ እንደ በቆሎ፣ የአትክልት ዘይት እና ሌሎች ምርቶች ፍላጎት ይወድቃል የሚል ስጋት ተፈጥሯል። ሆኖም ኮሌር፣ አሁን ባለው የአቅርቦት ሰንሰለት ችግር እና ለውጡ እንዲመጣ በሚወስደው ጊዜ ምክንያት ሁሉም አገራት የዋጋ መቀነሱን ወዲያውኑ ሊመለከቱት አይችሉም ብለዋል። የፋኦ መረጃ እንደሚያሳየው መጋቢት ወር ላይ ከፍተኛ ሆኖ ከተመዘገበው 159.7 በመቶ የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ቢሆንም ባለፈው ዓመት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ግን አሁንም በ10 ነጥብ ከፍ ያለ ነው። በአውሮፓ የተከሰተውን የሙቀት ማዕበል እና በፓኪስታን የተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅን በመጥቀስም የአየር ሁኔታ በምግብ ሰብል ዋጋ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ መጨመሩን ኮሌር አስረድተዋል። በዚህ ሳምንት የዩክሬን የግብርና ሚኒስትር ማይኮላ ሶልስኪ፣ በጦርነቱ ምክንያት በመጪዎቹ ምርቶች ላይ ጉዳት እንደሚደርስ አስጠንቅቀዋል። ለሚቀጥለው ዓመት ምርት ስንዴ እና ገብስ የሚዘራባቸው ቦታዎች በሩሲያ ወረራ ምክንያት 20 በመቶው እንዲቀንስ ሆኗል። የዩክሬን ግብርና ምክር ቤት በበኩሉ ድጋፎች በመጥፋታቸው ምርት እንደሚቀንስ አሳውቋል። ኮሌር በበኩላቸው አሁን ላይ በዓለም አቀፍ የምግብ ዋጋ መቀነስ ከታየ በኋላም ቢሆን በ2011 ከታየው በላይ ሊጨምር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። “ለዚህም በርካታ ምክንያቶች አሉ። አንዱ የኢነርጂ ዋጋ መጨመር ሲሆን ይህም የማዳበሪያ ዋጋ መናርን  እንዲሁም የአቅርቦት አለመረጋጋትን ያስከትላል” ብለዋል። “ምንም እንኳን የተወሰኑት የዩክሬን ወደቦች ቢከፈቱም ጊዜያዊ ነው የሚሆነው፣መጠኑም ቢሆን አነስተኛ ነው ። በመሆኑም የምግብ ዋጋን ይበልጥ ለመቀነስ እንዲረዳ ይህንን መጠን መጨመር ያስፈልጋል��� ሲሉ ተናግረዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c2lg5qzp2dxo +sports ሲም ካርድ ከመቀየር እስከ ጽንስ ማቋረጥ የደረሰው የአውስትራሊያ እግር ኳስ ዘረኝነት "የአውስትራሊያ እግር ኳስ ሊግ በአገሪቱ በጣም ውጤታማ ከሆኑት ክለቦች የአንዱ ከአገሪቱ ቀደምት ነዋሪዎች ከሆነው ማኅበረሰብ የመጡ ተጫዋቾች ላይ ከፍተኛ ጥቃት በአሰልጣኞች ደርሶባቸዋል በሚል ምርመራ ጀመረ። እንደ አውስትራሊያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኤቢሲ) ዘገባ ከሆነ ተጫዋቾቹ ከቤተሰባቸው እንዲገለሉ እና ከፍቅር አጋሮቻቸው ጋር እንዲለያዩ ተነግሯቸዋል። በሌላ አጋጣሚ ደግሞ እርግዝና እንዲያቋርጡ ታዘዋል ሲል አመልክቷል። ሃውቶን የተባለው እግር ኳስ ክለብ ""አሳዛኝ"" ያለውን ጉዳይ ለመመርመር ቃል ገብቷል። ይህ የታወቀው ቡድኑ በነባር የአገሪቱ ተወላጆች [አቦርጂንስ] ዙሪያ ስላለው አያያዝ በተገመገመበት ወቅት ነው። የሪፖርቱን ይዘት ጠንቅቆ የሚያውቀው ኤቢሲ ከ2005 እስከ 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ መቀመጫውን ሜልበርን ባደረገው ክለብ ላሳለፉ ሦስት ተጫዋቾችን ቃለ መጠይቅ አድርጓል። ሃውቶን ሃውክስ በመባልም ይታወቃል። ከስፖርቱና በቤተሰቦቻቸው አንዱን እንዲመርጡ መገደዳቸውን ለመገናኛ ብዙኃኑ ተናግረዋል። ሌላው ደግሞ አንድ አሰልጣኝ ""ያልተወለደ ልጄን እንዳስወርድ እና የትዳር ጓደኛዬን መተው እንዳለብኝ ጠይቆኛል"" ብለዋል። ""ሲም ካርዴን ከስልኬ እንዳወጣ እና በእኔ እና በቤተሰቤ መካከል ምንም ተጨማሪ ግንኙነት እንዳይኖር ተደርጌያለሁ። ከዚያ ምሽት ጀምሮ ከአንዱ አሰልጣኝ ጋር እንደምኖርም ተነገረኝ"" ብሏል። የትዳር ጓደኛው ፅንሱን ያላቋረጠች ሲሆን ጥንዶቹ ከወራት በኋላ ታርቀዋል። የመጀመሪያ ልጃቸውን ከወለዱ በኋላ እንደገና በድጋሚ ያረገዘችው ሚስት ተመሳሳይ መከራ እንዳያጋጥማቸው እርግዝናውን ማቋረጥ እንደሚገባት ተሰምቷት እንደነበር ለኤቢሲ ተናገራለች። ሌላ ተጫዋችም ለኤቢሲ እንዳስታወቀው ሃውቶን ጓደኛው ማርገዟን ሲያውቅ ተመሳሳይ ምላሽ እንደሰጠው ተናግሯል። በኋላም ከእርሷ ጋር ለመለያየት እና ግንኙነቱን ለማቋረጥ ተገደደ። እሷም በኋላ ላይ ፅንስ አቋረጠች። ከሌላ ግዛት የመጣው ሦስተኛው ተጫዋች በበኩሉ ቤተሰቡ ከእሱ ጋር ለመኖር ወደ ሜልበርን እንዳይዛወር ለማድረግ ክለቡ መሞከሩን ተናግሯል። ሦስቱም ጥንዶች ከክስተቶቹ በኋላ የነበራቸውን የአዕምሯዊ ጤንነት ውጣ ውረድን ተናግረዋል። ውንጀላውን የሚገልጸው ዘገባ ከሁለት ሳምንት በፊት በሃውቶን እንደደረሰው ኤቢሲ ዘግቧል። ለአውስትራሊያ እግር ኳስ ሊግ (ኤኤፍኤል) ባለሥልጣናትም ተላልፏል። ዛሬ ረቡዕ ዕለት መገናኛ ብዙኃን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኤኤፍኤል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጊለን ማክላክላን የኤቢሲን ዘገባ ""ፈታኝ እና የሚረብሽ"" ብለውታል። ""ከዚህ በላይ ከባድ ውንጀላዎችን ማግኘት ከባድ ነው"" ብለዋል። በስም ጥር ጠበቃ የሚመራ ገለልተኛ ቡድን ጉዳዩን ለመመርመር እንደሚመደብም ጠቁመዋል። ምርመራው በሚከናወንበት ወቅት አሰልጣኞች ከኃላፊነታቸው ይነሱ አይነሱ በሚለው ላይ ክለቦች ዛሬ ይወሰናሉ። የሃውቶን ቃል አቀባይ ግኝቱ ""አስጨናቂ ታሪካዊ ውንጀላዎችን"" ቢያነሳም በክለቡ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ""ካለው ባህል አኳያ ደኅንነቱ የተጠበቀ"" መሆኑንም አመልክቷል። ""ክለቡ በዚህ ሂደት ለተሳተፉት ሁሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል። ደኅንነታቸውም ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው"" ሲል አክሏል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ የኤኤፍኤል ተጫዋቾች በስታዲየም ከሚገኙ ተመልካቾች የሚደርስባቸውን የዘረኝነት ጥቃት እና የክለብ ባለሥልጣናትን ደካማ ድጋፍ በማንሳት ቅሬታ አቅርበዋል። ቀደምት የአ���ሬው ተወላጅ እና  የኤኤፍኤል ኮከብ የነበረው አዳም ጉደስ እንደተናገረው በተቀናቃኝ ደጋፊዎች ለዓመታት ሲደርስበት የነበረው ግፍ ""ልቡ ተሰበሮ"" በ2015 ጫማውን እንዲሰቅል አስገድዶታል። ሌላው መቀመጫውን ሜልበርን ያደረገው ኮሊንግዉድ የተባለው ክለብ ባለፈው ዓመት በተደረገ ግምገማ ""ከዘረኝነት"" ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c974qrz47nro +politics የዚምባብዌ ምክትል ፕሬዚዳንት ባለቤት በባለቤታቸው ግድያ ሙከራ ተከሰሱ "የዚምባብዌ ምክትል ፕሬዚዳንት ባለቤት ሜሪ ሙባይዋ በባለቤታቸው ግድያ ሙከራ ተከስሰዋል። የሙስና ክስ ያለባቸው ሜሪ ሙባይዋ ሰኞ እለት ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን፤ ክሱንም ውንጀላ ነው በማለት ክደውታል። አቃቤ ህግጋት በበኩላቸው ባለቤታቸውን ጄኔራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋን ደቡብ አፍሪካ ህክምና እያደረጉ በነበረበት ወቅት ሊገድሏቸው ሞክረዋል ብለዋል። •ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ •መንግሥት አደገኛ የሆነውን የትግራይን መገለል መለስ ብሎ ሊያጤነው ይገባል- ክራይስስ ግሩፕ •የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ክፍፍልና ጠብ ጄኔራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ ሮበርት ሙጋቤ ከሁለት አመት በፊት ከስልጣናቸው ሲገረሰሱም ቁልፍ ሚናን ተጫውተዋል። ጄኔራሉም ቢሆኑ ከስድስት ወራት በፊት በደቡብ አፍሪካ ህክምና እንዳያገኙ ""ከፍተኛ ጫና አድርጋብኛለች"" በማለት ወንጅለዋታል። ከዚህም በተጨማሪ በፕሪቶሪያ ሆስፒታል ውስጥ እየታከሙ በነበረበት ወቅትም ግሉኮሱን ነቅላዋለች ብለዋል። ጄኔራሉ ለተጨማሪ ህክምና ቻይና ሄደውም ከአራት ወራት ቆይታ በኋላ ተመልሰዋል። ሜሪ ሙባይዋ በቁጥጥር ስር የዋሉት በባለፈው ሳምንት ቅዳሜ እለት ሲሆን ዋስም ተከልክለዋል። ከግድያ ሙከራ በተጨማሪ 750ሺ ዶላር ገንዘብ ከማጭበርበርና በህገወጥ መንገድ በማዘዋወርም ተከሰዋል። የቢቢሲ አፍሪካ ዘጋቢ አንድሪው ሃርዲንግ እንደሚለው ከበርቴዎቹ በግድያ ሙከራና በመመራረዝ ውንጀላዎች ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ ከመምጣታቸው አንፃር ይህ ሁኔታ አዲስ ነገር አይደለም።" https://www.bbc.com/amharic/50818834 +sports ግዙፉ የአውስትራሊያው የስፖርት ክለብ “ዘረኛ” ነው ተባለ በአውስራሊያ ሊግ ተሳታፊ ከሆኑት ክለቦች መካከል አንዱ እና ግዙፉ ኮሊምግዉድ “ዘረኛ የሆነ ስርዓትን ዘርግቷል” ሲል አንድ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን አጋለጠ። ይህ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳተተው ይህ ግዙፍ የራግቢ ቡድን ዘረኝነትን በተመለከተ ለሚነሱ ቅሬታዎች ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት የለውም ከፍ ሲልም ቅሬታ በሚያነሱት ላይ ቅጣት ያስተላልፋል ብሏል። ሪፖርቱን ተከትሎ ግዙፉ ክለብ “የተሻለ ለመሆን እጥራለሁ” ብሏል። የክለቡ ፕሬዝደንት ክለቡ ጥፋተኛ መሆኑን አምነው ጸረ-ዘረኛ የሆኑ ፖሊሲዎችን በማርቀቅ የተሻለ ስፍራ ለመሆን እሰራለሁ ብሏል። ጥናቱ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ የዘር መድሎ ደርሶብኛል ከሚል ስፖርተኛ ይልቅ ዘረኝነትን በተመለከተ በመገናኛ ብዙሃን ለሚነሱ ጥያቄዎች ክለቡ ምላሽ ይሰጣል፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዘረኝነትን ለመከላከል ክለቡ ምንም አይነት ስትራቴጂ አልነበረውም፤ እንዲሁም ዘረኝነትን በተመለከተ በክለቡ ሲወሰዱ የነበሩ እርምጃዎች ተጎጂውን ሳይሆን የክለቡን ስምእና ዝና ለመጠበቅ ያለመ ነው። ይህ የጥናት ውጤት ይፋ የተደረገው ገለልተኛ ጥንት አድራጊ ቡድኑ ተጫዋቾችን፣ የክለቡ ሰራተኞችን እና ደጋፊዎችን ካነጋገረ በኋላ ነው። በዚህ ጥናት ላይ የቀድሞ የክለቡ ተጫዋች ሄሪቲኤር ሉሙምባ በክላቡ አጋጥሞኛል ስላለው ጉዳይ ተሞክሮውን አጋርቷ��። የዘር ሃረጉ ከብራዚል እና አንጎላ የሚመዘዘው ተጫዋች የቡድን አባላቶቹ ‘ቺምፕ’ (ቺምፓዚ) በሚል ስም ይጠሩት እንደነበረ ተናግሯል። የቀድሞ የክለቡ ተጫዋች ሉሙምባ ክለቡን ኮሊንግውድ እና የአውስትራሊያ ሊግን ለመክሰስ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል። የአውስትራሊያው ራግቢ ሊግ በርካታ ተመልካቾች ያሉት ሊግ ሲሆን በሊጉ ውስጥ ዘረኝነትን ለመከላከል የተለያዩ ጠንካራ እርምጃዎችችን እንደሚወስድ አስታውቋል። https://www.bbc.com/amharic/news-55893665 +politics ለረጅም ዓመታት ጃፓንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ሺንዞ አቤ ሲታወሱ ለጃፓን የላይኛው ምክር ቤት የሚወዳደር ዕጩን ወክለው ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት በተተኮሰባቸው ጥይት ሕይወታቸው ያለፈው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በብዙ መልኩ ይታወሳሉ። “ጠብ አጫሪ” በሆነው የውጭ ፖሊሲያቸው እንዲሁም 'አቤኖሚክስ' ተብሎ በሚጠራው ለየት ያለ የምጣኔ ሀብት ስትራቴጂያቸው በጃፓን ስም አትርፈዋል። ህያው ሥራ ከመቃብር በላይ ነው እንዲሉ፣ በርካቶች ሲገልጿቸው “ወግ አጥባቂ ብሔረተኛ ይሏቸዋል” የ67 ዓመቱን ፖለቲከኛ። አቤ ፓርቲያቸውን ሊበራል ዲሞክራቲክ ፓርቲን (ኤልዲፒ) ሁለት ጊዜ አሸናፊ እንዲሆን አድርገውታል። የመጀመሪያው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቆይታቸው አጭር ነበር። በአውሮፓውያኑ 2006 ወደ ሥልጣን መጥተው አንድ ዓመት አካባቢ አገሪቱን የመሩት አቤ የሥልጣን ቆይታቸውም አወዛጋቢ ነበር። ነገር ግን ከስድስት ዓመታት በኋላ በአውሮፓውያኑ 2012 በአስገራሚ ሁኔታ ተመልሰው በጤና ምክንያት ከሥልጣን እስከለቀቁበት 2020 ድረስ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ። አቤ ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ አገራቸው የምጣኔ ሀብት ድቀት ላይ ነበረች። የገንዘብ ፖሊሲውን በማላላት፣ ማነቃቂያዎች እንዲሁም መዋቅራዊ የሆኑ ማሻሻዎችን በማድረግ እያሽቆለቆለ የነበረውን ምጣኔ ሀብት ወደ ተረጋጋ ሁኔታ እንደሚመጣ አድርገዋል ተብለው ይወደሳሉ። ጃፓን በአውሮፓውያኑ 2011 በቶሁኩ ከደረሰው ከባድ ርዕደ መሬት እንዲሁም ሱናሚ እንድታገግም ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። በዚህ የመሬት መንቀጥቀጥ እና ሱናሚ ወደ 20 ሺህ የሚደርሱ ጃፓናውያን ሕይወት ከመቅጠፍ በተጨማሪ የፉኩሺማ የኒውክሌር ማመንጫዎችን አቅልጦ ከፍተኛ ቀውስ አድርሷል። ከሁለት ዓመት በፊት በአውሮፓውያኑ 2020 አቤ በፈቃዳቸው ከሥልጣናቸው ወረዱ። ለሳምንታት ያህል የጤናቸው ሁኔታ መወያያ ከሆነም በኋላ ነበር ከሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡት። መጀመሪያም ከስድስት ዓመት በፊት ሥልጣን በለቀቁበት ወቅት በአንጀት አልሰር (ቁስለት) ህመም ሲሰቃዩ የነበረ ሲሆን፣ በዚህም ወቅት ይህ ቁስለት ማገርሸቱን አስታውቀው ነበር። እሳቸውንም በመተካት የፓርቲያቸው አባልና የቅርብ አጋር የሆኑት ዮሺሃዴ ሱጋ ወደ ሥልጣን መጡ። ሆኖም አቤ በጃፓን ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ያላቸው ሰው ተደርገው መታየታቸው አላከተመም። አቤ ከፖለቲከኛ ቤተሰብ ነው የመጡት። አባታቸው የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም አያታቸው ደግሞ ጃፓንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ኖቡሱኬ ኪሺ ናቸው ። ለፓርላማ አባልነት የተመረጡት በአውሮፓውያኑ 1993 ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2005 የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁኒቺሮ ኮይዙሚ ከፍተኛ የካቢኔ ፀሐፊ አድርገው ሾሟቸው። ከዚያም በአውሮፓውያኑ 2006 ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ በዕድሜ የጃፓን ትንሹ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ቻሉ። ነገር ግን አስተዳደራቸው በተከታታይ ቅሌቶች የተሞላ ነበር። ወደ 50 ሚሊዮን የሚጠጉ ጉዳዮችን የያዘው የመንግሥት የጡረታ መዝገብ መጥፋት አስደዳደራቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ጎድቶታል። በአውሮፓው��ኑ 2007 ለተደረገው የላይኛው ምክር ቤት ምርጫም ፓርቲያቸው ኤልዲፒ ከባድ ኪሳራን አስተናገደ። በዚያው ዓመትም በአንጀት አልሰር (ቁስለት) ምክንያት አቤ ከሥልጣናቸው ለቀቁ። ከስድስት ዓመት በኋላም በህክምና በሽታውን አሸንፌያለሁ በማለት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት መንበር ተመለሱ። በመቀጠልም በነበሩት ምርጫዎች በአውሮፓውያኑ 2014 እና 2017 በድጋሚ ተመርጠዋል። ይህም ለረጅም ዓመታት ጃፓንን የመሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ያደርጋቸዋል። ተወዳጅነታቸውም በዓመታት ውስጥ ቢለዋወጥም በፖርቲያቸው ኤልዲፒ ውስጥ በነበራቸው ከባድ ተፅእኖ ምክንያት የተገዳደራቸው አልነበረም። የፓርቲያቸውንም ደንብና ሕግ በማሻሻል ለሦስተኛ ጊዜ የፓርቲው መሪ ለመሆን ችለዋል። አቤ በመከላከያ እና በውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው ቁርጠኛና 'ጠብ አጫሪ' የሚባል አቋም ነበራቸው። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃት በኋላ ሰላማዊ የሚባለውንም የጃፓን ሕገ መንግሥት ለማሻሻል ሲጥሩ ቆይተዋል። በአሜሪካ የተረቀቀውን የጃፓን ሕገ መንግሥት ወግ አጥባቂዎች፣ የጃፓን ወታደሮች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የደረሰባቸውን አሳፋሪ ሽንፈት ማስታወሻ ነው ሲሉ ይተቹታል። ጭፍን ብሔረተኛነታቸውም ከቻይና እና ከደቡብ ኮሪያ ጋር ውጥረት ውስጥ እንዲገቡ ምክንያት ሆኗል። በተለይም በሁለተኛው ከዓለም ጦርነት በፊትና በዚያው ወቅት ጃፓን ነበራት ከሚባለው የጦረኝነት አቋም ጋር ተያይዞ አወዛጋቢ የሆነውን በቶኪዮ የሚገኘውን ያሱኩኒ ቤተ መቅደስ በአውሮፓውያኑ 2013 መጎብኘታቸውን ተከትሎ ከሁለቱ አገራት ጋር ነገሮች ተጋግለው ነበር። አቤ ያሱኩኒን በተደጋጋሚ መጎብኘታቸውም በጃፓን የሚገኙ የግራ ዘመም ፖለቲከኞችን ያስቆጣ ነበር። አቤ በጦርነቱ ወቅት ጃፓን ያደረሰችውን የመብት ጥሰቶችና ጭካኔዎች ለማንፃት እየሞከሩ ነው ብለዋቸዋል። የጋራ የራስ መከላከል መብት የሚል ፅንሰ ሃሳብ በማስተዋወቅ ሰነዱ ተቀባይነት እንዲያገኝ በአውሮፓውያኑ 2015 ይከራከሩ ነበር። ይህም ጃፓን እንዲሁም ጥቃት የደረሰባቸውን አጋሮቿን ለመካላከል በውጭ አገራት ወታደሮችን እንድታሰማራ የሚል ነው። ይህ ሰነድ ከጃፓን ጎረቤት አገራት እንዲሁም ከጃፓን ሕዝብ እንኳን ሳይቀር ተቃውሞ ቢገጥም የአገሪቱ ፓርላማ ይህንን አወዛጋቢ ዕቅድ አጸደቀው። ሆኖም የጃፓንን ጦር እንደገና ለማወቀር ሕገ መንግሥቱን የመከለስ ትልቁ አላማቸው አልተሳካም ነበር። እናም በአሁኑ ወቅትም ይህ ዕቅዳቸው በአገሪቱ ውስጥ ከፋፋይ ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል። በተጨማሪም ጃፓን ሰሜናዊ ግዛቶቼ ብላ የምትጠራቸውን ቦታዎችን ማስመለስ አልቻሉም። ይህ ቦታ ጃፓን እና ሩሲያ ይገባኛል ብለው የሚወዛገቡባበቸውና በሰሜናዊ የሆካይዶ ግዛት ውስጥ ያሉ የደሴቶች ሰንሰለትን ይሸፍናል። አቤ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ጥብቅ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን፣ አሜሪካ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ላይ የጣለችውን አስከፊ  የንግድ ታሪፍ በጃፓን ላይ ተግባራዊ እንዳይሆን ተከላክለዋል በሚልም በበጎ ይነሳሉ። 'አቤኖምክስ' በመባል የሚታወቀው የአቤ ለየት ያለ የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ በመጀመሪያ የሥልጣን ዘመናቸው እድገት እንዲታይ እንደረዳቸው ታይቷል። ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነጌቲቭ (አሉታዊ) የወለድ ተመን በማስተዋወቅ ሸማቾች እና ኩባንያዎች ገንዘብ እንዲበደሩና እንዲያወጡ ረድቷቸዋል። የመንግሥት ወጪን በመሰረተ ልማት ላይ ማሳደግ፣ የግብር እፎይታን የመሳሰሉ ማበረታቻዎችንም አመጡ። በተጨማሪም በርካታ ሴቶች ወደ ሥራው ዓለም እንዲመጡና የጉልበት ጫናን ለማቃለል ስደተኞች ወደ ሥራ እንዲገቡ የመሳሳሉ በርካታ ስር ነቀል ማሻሻያዎችን አመ��። ነገር ግን ጥረታቸው ፈተና ገጠመው። በተለይም በአውሮፓውያኑ 2020 ጃፓን እንደገና ምጣኔ ሀብቷ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ ዘላቂነቱና ውጤታማነቱ ላይ ጥያቄ ተነሳባቸው። በምጣኔ ሀብት ፖሊሲያቸው ዘላቂነት ላይ ጥያቄ ሲነሳባቸው የነበረው አቤ፣ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ አያያዛቸው ጋርም ተያይዞ ስጋቶች መነሳት ጀመሩ። ተቺዎቻቸው እንደሚሏቸው የአገር ውስጥ ቱሪዝምን ለማሳደግ በሚል ያደረጓቸው ዘመቻዎች ወረርሽኙ እንዲባባስ አስተዋፅኦ አድርገዋል ብለው ያምናሉ። ሌሎች በአቤኖሚክስ ፖሊሲ የተገቡ ቃሎች ለምሳሌ ተጨማሪ ሴቶችን በሥራ ኃይል ማብቃት፣ ወገንተኝነትን መዋጋት እና ጤናማ ያልሆኑ የሥራ ባህሎችን መለወጥ ሳይፈጸሙ ቀርተዋል ይላሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ በ11 አገራት መካከል የተካሄደውን ግዙፍ የንግድ ስምምነት፣ ትራንስ ፓስፊክ ፓርትነር ሺፕ፣ በተለይም በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገዛዝ ዘመን አሜሪካ በድንገት መውጣቷን ተከትሎ አጋርነቱን በማስጠበቅ ዕውቅና ተችሯቸዋል። አቤ ከሥልጣን የለቀቁት ከሁለት ዓመት በፊት ነሐሴ መጨረሻ ገደማ በአውሮፓውያኑ 2020 ነበር። ተተኪ ባለመምረጣቸውም በፓርቲያቸው ኤልዲፒ ውስጥ ባሉ አንጃዎች መካከል የውስጥ ትግል አስከተለ። በመጨረሻም በአንጋፋው ፖለቲከኛ እና የረዥም ጊዜ የካቢኔ አባል በሆኑት ዮሺሂዴ ሱጋ ተተኩ። ነገር ግን አቤ በጃፓን የውስጥ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ቦታ ነበራቸው። ሱጋ በአሁኑ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ቢተኩም የአቤ በፖለቲካው ላይ የቁንጮነት ቦታ አልተነካም። በዛሬው ዕለት አርብ ሐምሌ 01/2014 ዓ.ም አቤ በደቡባዊ ናራ ከተማ ለጃፓን የላይኛው ምክር ቤት የሚወዳደር ዕጩን ወክለው ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር። ንግግር እያደረጉ ባለበት ወቅት በአንድ ታጣቂ በጥይት ተመቱ። የተኮሰባቸው የ41 ዓመቱ ግለሰብ በጃፓን እንደ ባሕር ኃይል የሚታየው የራስ መከላከያ ኃይል የቀድሞ አባል እንደሆነም ይታመናል። አቤ በጥይት ተመትተው ሲወድቁና ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱም ራሳቸውን ያውቁ ነበር። ነገር ግን ከደረሰባቸው ጉዳት አላገገሙም፤ ላይመለሱ አሸለቡ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cy0ydy4p0m5o +politics በአማኑዔል ወንድሙ ግድያ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምላሽ "በያዝነው ሳምንት ግንቦት 3፣ 2013 ዓ.ም በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ አማኑኤል ወንድሙ የተባለ ወጣት በአደባባይ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መገደሉን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአካባቢው የመንግሥት ኃላፊዎች ወጣቱ ባለስልጣናትን በመግደል የሚታወቀው 'አባ ቶርቤ' የተባለ ህቡዕ አባል ቡድን ነው በማለት መገደሉን ቢያረጋግጡም ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ሲሉ አስተባብለዋል። የደምቢ ዶሎ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት እንዲሁ ሰዎችን ሲገድል በነበረው እና 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በሆነው ግለሰብ ላይ እርምጃ ተወሰደ ሲልም በፌስቡክ ገጹ ላይ ጽፏል። የአማኑኤል ወንድሙን ግድያ በተመለከተ ቢቢሲ የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻን የጠየቀ ሲሆን ኃላፊው በክልሉ ህዝብን እያሸበሩ ነው የሚሏቸው አካላት ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ በአፅንኦት ተናግረዋል። ""በከተሞች ሰውን እየገደሉ ህዝብን ማሸበር የነሱ የእለት ተእለት ተግባር ነው። እነሱ የሚያደርጉት መግደል ነው። ሰላምን ለማስከበር የሚሄደው ኃይል እነዚህ አካላትን አጋልጦ እርምጃ ወስዶ ሊቆጣጠር ይገባል የሚል እምነት አለኝ። ስለዚህ የተወሰደው እርምጃ የትኛውም አይነት ይሁን ህዝብን አሸብሮ፣ አስፈራርቶ እቆጣጠራለሁ የሚለው ኃይል ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት።"" ብለዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ይህንን በተመለከተም አቅጣጫ ሰጥቶ እየሰራበት መሆኑንም በተጨማሪ ገልፀዋል። ""ሰው በቤቱ፣ በቀዬው ነው እየተገደለ ያለው፤ በማያውቀው ነገር ነው እየሞተ ያለው፤ እንዲህ አይነት ተግባር በሚፈፅሙ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ እነሱ በሚፈፅሙት ልክ ተመጣጣኝ መሆን አለበት።"" በማለትም ይናገራሉ። ነገር ግን አማኑኤል በአደባባይ ነው የተገደለው ስለሚባለው ጉዳይ """"ወጣቱ የደምቢ ዶሎ ነዋሪ አደባባይ ላይ ነው የተገደለው ስለሚባለው ነገር ግን መረጃ የለኝም"" ብለዋል። የቄለም ወለጋ ዞን የደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዋሪዮ በበኩላቸው ወጣቱ ቆስሎ ከተያዘ በኋላ ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ይላሉ። ""ተጠርጣሪ አይደለም"" የሚሉት አቶ ተሰማ፤ ይህ ወጣት ሁለት ሰዎች በጥይት መትቶ እያመለጠ ሳለ በፀጥታ ኃይሎች በጥይት ተመትቶ መያዙን ይናገራሉ። የደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑት እና ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁ ግለሰብ ወጣቱ በአደባባይ ሲገደል ማየታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""አማኑኤል ሕዝብ የሚወደው ልጅ ነበር"" ካሉ በኋላ፤ በጥይት ተመትቶ ከተያዘ በኋላ ""ሲገደል በዓይናችን አይተናል"" ብለዋል። እኚህ ነዋሪ እንደሚሉት ከሆነ የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪ አካላት ወጣቱ ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ ወጣቱ ከአንድ ሱቅ እቃ እየገዛ ነበር ይላሉ። የአማኑኤል ወንድሙ ግድያን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያና (extrajudicial killing) በአደባባይ ለህዝብ እንዲታይ የተደረገበት መንገድ እንዳሳሰበው ትናንትና ግንቦት 4/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኮሚሽኑ ማንኛውንም ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎችን የሚያወግዝ መሆኑን አስታውቆ ሁሉም የሕግ አስፈፃሚ አካላት ሕጋዊ መንገዶች ብቻ አንዲተገብሩ መልዕክቱን አስተላልፏል። እናንተ ክልሉን እያስተዳደራችሁ እንዴት የወጣቱን የአደባባይ ግድያ አናውቅም ትላላችሁ? ተብለው ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ የ ክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ወንጅለዋል። ""የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሁልጊዜ የክልሉን ስም ለማጥፋት ስለሚሰራ እነሱ ያላቸው መረጃ እኔ የለኝም። እነሱ ሄደው አይተው ነው ወይስ ከማህበራዊ ሚዲያ ያገኙትን ይዘው ነው ይህንን መግለጫ ያወጡት?"" በማለት የሚጠይቁት አቶ ጌታቸው አክለውም ""ይህ መጣራት አለበት። በማስረጃ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። ማን ምን አደረገ የሚለውን ነገር ሳይቀበሉ እንዲሁ ሆነ ብሎ ከአንድ ወገን ብቻ መረጃ ይዞ ማውራት ተቀባይነት የለውም። ለሰብዓዊ መብት ነው የምሰራው የሚል ተቋም ጉዳዩን መዘገብ ያለበት በአካል ተገኝቶ ነው። የሚጠየቅም አካል ካለ እርምጃ ሊወሰድ የሚችለው መረጃው ሙሉ ሲሆን ነው።"" ይላሉ ኮሚሽኑ በበኩሉ ""ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎች ህዝቦች በሕግ የበላይነት ላይ ዕምነት እንዲያጡ እና በዚህ ረገድ የተገኙ ስኬቶች እንዲቀለበሱ ያደርጋሉ"" ከማለት በተጨማሪ ባለሥልጣናት ጉዳዩን በአፋጣኝ እንዲመረምሩ እና ተገቢ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጠይቋል። ከዚህ ቀደምም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ያለው የእስረኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እንዳሳሰበው መግለፁ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን በሕግ ከመዳኘት ይልቅ የፖለቲካ (የአስተዳደራዊ) ውሳኔዎች ሰለባ እንዲሆኑ ተድርጓል ብሎ ነበር። ከሰሞኑ የወጣው ቪዲዮ ምንን ያሳያል? በዚህ የፌስቡክ ገጽ ላይ ወጣቱ ከመገደሉ በፊት ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጥ ይታያል። ቪዲዮን እየቀረጸ የሚገኘው ሰው የወጣቱን ስም እና የትውልድ ስፍራውን ይ���ይቀዋል። እጁ ወደ ኋላ የታሰረው ወጣት አንገቱ ላይ ሽጉጥ ተንጠልጥሎ ይታያል። በወጣቱ እግር ላይ እና በዙሪያው ደም የሚታይ ሲሆን ልብሱም በጭቃ ተለውሷል። አደባባይ ፊትለፊት የቆመው ወጣት ስሙ አማኑኤል ወንድሙ ከበደ እንደሚባል እና ትውልዱ ደምቢ ዶሎ ከተማ 07 ተብሎ በሚጠራ ስፍራ እንደሆነ ይናገራል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎ ተከቦ ይታያል። ስለ ግድያው የአካባቢው ባለስልጣናት ምን አሉ? የከተማው ኮሚውኒኬሽን ጽ/ቤት እንደሚለው ከሆነ ይህ ወጣት የመንግሥት ባለስልጣናትን በመግደል የሚታወቀው ""አባ ቶርቤ' የተሰኘው ህቡዕ ቡድን አባል ነበር። ወጣቱ ትናንት በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊትም ንጋት ላይ ገመቹ መንገሻ የተባለ ግለሰብ በጥይት መትቶ ለማምለጥ ሲሞክር ""በጸጥታ ኃይሎች ጠንካራ ትስስር እግሩን ተመትቶ ተይዟል"" ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ከቀናት በፊት በደምቢዶሎ ከተማ የኦሮሚያ ብሮድካስቲን ኔትዎርክ ጋዜጠኛ የነበረውን ሲሳይ ፊዳ የገደለው የአባ ቶርቤ ቡድን ነው ሲል አክሏል። አቶ ተሰማ በደምቢዶሎ አካባቢ ከሰሞኑ በኦነግ ሸኔ እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ ተናግረው፤ ወጣቱ አንገት ላይ የተንጠለጠለው ሽጉጥ ንጹሃን ዜጎችን እና የመንግሥት ኃይሎችን ሲገድልበት የነበረ ነው ብለዋል። ቢቢሲ የዞኑ ፖሊስ ባልደረቦችን አነጋግሮ ያገኘው ምላሽ አቶ ተሰማ ከሰጡት አስተያየት ጋር ተመሳሳይ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-57097406 +business ሮናልዶ፣ ኬን፣ ምባፔ፣ ግሪዝማን. . . የተሳኩትና ያልተሳኩት ዝውውሮች የትኞቹ ናቸው? ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ያደረገውን ዝውውር ጨምሮ የፕሪሚየር ሊጉን ክለቦች ከአንድ ቢሊየን ፓውንድ በላይ በዝውውር መስኮቱ አውጥተዋል። አጠቃላይ ወጪው ግን ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት ቀንሷል። ትልቁ ስምምነት ኒኮላ ቭላሲክ ከሲኤስኬኤ ሞስኮ ወደ ዌስትሃም በ26.8 ሚሊዮን ፓውንድ ያደረገው ሆኗል። በአጠቃላይ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በዝውውር መስኮቱ 1.1 ቢሊዮን ፓውንድ ወጪ አድረገዋል። ከቀዳሚው ዓመት የ1.3 ቢሊዮን ፓውንድ ዝውውር በ11 በመቶ ዝቅ ብሏል። እንደ ፋይናንስ ድርጅቱ ዴይሎት ዘገባ ከሆነ ይህ ከ2015 ጀምሮ በፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ዝቅተኛ ጠቅላላ ወጪ ሆኖ ተመዝግቧል። የመጨረሻው ቀን የፕሪሚየር ሊጉ ዝውውሮች የትኞቹ ናቸው? ቶተንሃም ለባርሴሎናው ተከላካይ ኤመርሰን ሮያል 25.8 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጣ ሲሆን የመስመር ተጫዋቹ ዳንኤል ጄምስ ከማንችስተር ዩናይትድ በ25 ሚሊዮን ፓውንድ ሊድስን ተቀላቅሏል። ብራይተን የስፔኑን ተከላካይ ማርክ ኩኩሬላን ከጌታፌ በ15.4 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈርሟል። ሴኔጋላዊው አጥቂ አብደላህ ሲማ ወደ ስቶክ በውሰት ከመዛወሩ በፊት ከሲላቪያ ፕራግ በተመሳሳይ ብራይተንን ተቀላቅሏል። ከቭላሲክ በተጨማሪ ዌስትሃም የአማካዩን አሌክስ ክራልን ከስፓርታክ ሞስኮ በውሰት አምጥቷል። ሌስተር በበኩሉ ከአርቢ ሌፕዢንግ የክንፍ ተጫዋቹን አዴሞላ ሉክማንን በአንድ ዓመት የውሰት ውል አስፈርሟል። በርንሌይ ዌልሳዊውን ኮነር ሮበርትስን ከስዋንሲ በማምጣት በጥቂት ቀናት ውስጥ ሁለተኛውን ተከላካይ አስፈርሟል። ክሪስታል ፓላስ በበኩሉ አጥቂውን አድሰን ኢዶዋርድን ከሴልቲክ በ15 ሚሊዮን ፓውንድ አዘዋውረዋል። አርሴናል የጃፓኑን ተከላካይ ታሂሮ ቶሚያሱን ከቦሎኛ አስፈርሟል። በውሰት ደግሞ አርሰናል ሄክቶር ቤለሪን ወደ ሪያል ቤቲስና ሬይስ ኔልሰን ወደ ፌይኖርድ እንዲዛወሩ ፈቅደዋል። ሰሎሞን ሮንዶን በነጻ ዝውውር ለኤቨርተን ፊርማውን አኑሯል። ሜክሲኳዊው አጥቂ ሳንቲያጎ ሙኖዝ ደግሞ ወደ ኒውካስል አቅንቷ���። የአውሮፓ ዋና ዋና ዝውውሮችስ ምን ይመስላሉ? ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ክለቦች በዝውውሩ መጠናቀቂያ ዕለት ንቁ ተሳትፎ ቢኖራቸውም ሪያል ማድሪድ ምባፔን ለማስፈረም ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። የስፔኑ ግዙፍ ክለብ የፈረንሳዩን አማካይ ኤድዋርዶ ካማቪንጋን ከሬንስ አስፈርሟል። ሮናልዶን በማንችስተር ዩናይትድ የተነጠቁት ጁቬንቱሶች አጥቂው ሞይስ ኬንን ከኤቨርተን በሁለት ዓመት የውሰት ውል እንደገና ማስፈረም ችለዋል። ባርሴሎና ያሉበትን የፋይናንስ ስጋቶችን ለማቃለል ተጫዋቾችን የለቀቀ ሲሆን ኢላይክስ ሞሪባን ለአርቢ ሌፕዢንግ አሳልፎ ሲሰጥ አንቶኒ ግሪዝማን ደግሞ በውሰት ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ተመልሷል። ትልልቆቹ ዝውውሮች የትኞቹ ናቸው? አርሰናል፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ቼልሲ አራቱ ከፍተኛ ገንዘብ ያወጡ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ሆነዋል። ማንቸስተር ሲቲ ትልቁን የዝውውር መስኮቱን ስምምነት የእንግሊዝን የዝውውር ክብረ ወሰንን በመስበር ጃክ ግሪሊሽ ከአስቶን ቪላ በ 100 ሚሊዮን ፓውንድ የግሉ አድርጓል። የአውሮፓ ሻምፒዮኑ ቼልሲ ደግሞ አጥቂውን ሮሜሎ ሉካኩን ከኢንተር ሚላን በ97.5 ሚሊዮን ፓውንድ መልሶ አስፈርሟል። ማንችስተር ዩናይትድ ጄደን ሳንቾን ከዶርትመንድ በ 73 ሚሊዮን ፓውንድ እና ራፋኤል ቫራንን ከሪያል ማድሪድ በ34 ሚሊዮን ፓውንድ ኦልድ ትራፎርድ አድርሷል። አርሰናል በዝውውር መስኮቱ ከፍተኛ ገንዘብ ካወጡ ክለቦች አንዱ ነበር። ቤን ዋይት ከብራይተን (50 ሚሊዮን ፓውንድ)፣ ማርቲን ኦዴጋርድ ከሪያል ማድሪድ (30 ሚሊዮን ፓውንድ) እና አሮን ራምስዴል ከሸፊልድ ዩናይትድ (24 ሚሊዮን ፓውንድ) ጨምሮ ሌሎችንም ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ቀላቅሏል። ሊቨርፑል በአንጻራዊ ሁኔታ የተቀዛቀዘ የዝውውር መስኮት አሳልፏል። ተከላካዩን ኢብራሂማ ኮናቴን ከአርቢ ሌፕዢንግ ለማስፈረም 36 ሚሊዮን ፓውንድ አውጥቷል። በመጨረሻው የዝውውር ቀን የአራት ዓመት ውል የፈረመውን አምበሉን ጆርዳን ሄንደርሰን ጨምሮ ለበርካታ ቁልፍ ተጫዋቾቹን ውል አራዝሟል። በጣም ትኩረት የሳበው ዝውውር ሊዮኔል ሜሲ ለ21 ዓመታት ከቆየበት ባርሴሎና በነጻ ዝውውር ወደ ፓሪስ ሴንት ዠርሜን ያቀናበት ሆኗል። ያልተሳኩት ዝውውሮችስ? የ2021 የክረምት የዝውውር መስኮት ባልተሳኩ ስምምነቶችም ይታወሳል። ማንችስተር ሲቲ አብዛኛውን የዝውውር መስኮት የእንግሊዙን አምበል ሃሪ ኬንን ለማዘዋወር ጥረት ቢያደርግም አጥቂው በስፐርስ ለመቆየት ተስማምቷል። ሪያል ማድሪድ ምባፔን ለማስፈረም ሁለት ጊዜ ሞክሯል። ማድሪዶች ሁለት ጊዜ ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ያቀረቡት ዋጋ በፓሪስ ሴንት ዠርሜን ውድቅ ተደርጓል። ቼልሲ ፈረንሳዊውን ተከላካይ ጁልስ ኩንዴን ለማስፈረም ቢፈልግም ሲቪያ ከመሸጫ ዋጋው 80 ሚሊዮን ዩሮ በታች ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። አይንስሊ ማይትላንድ-ኒልስ ማህበራዊ ድር አምባውን ተጠቅሞ ከአርሰናል ለመልቀቅ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። የጄሴ ሊንጋርድ ወደ ዌስትሃም የታቀደው ዝውውር ባለመሳካቱ በማንችስተር ዩናይትድ ይቆያል። ዎልቭስም የሊሉን አማካይ ሬናቶ ሳንቼዝን ዘግይቶ ለማዘዋወር ያደረገውን ጥረት አቋርጧል። https://www.bbc.com/amharic/news-58386455 +politics ጀርመን ውስጥ መፈንቅለ መንግሥት ለመፈጸም አሲረዋል የተባሉ 25 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ፖሊስ በመላዋ ጀርመን ባካሄደው ዘመቻ መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ እያሴሩ ነበሩ የተባሉ 25 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ። የጀርመን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ ቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች እና የቀድሞ የጦር አባላት ሪችስታግ የተባለውን የአገሪቱን ምክር ቤት ሕንጻ በኃይል በመያዝ የመንግሥትን ሥልጣን ለመቆጣጠር አሲረው ነበር ተብሏል። የዚህ ያልተጠበቀ ሴራን በማቀናበር ሄንሪች 8ኛ የተባለው የ71 ዓመት ግለሰብ ዋነኛ ተዋናይ መሆኑም በስፋት ተዘግቧል። እንደ የጀርመን ዐቃቤ ሕግ ከሆነ ይህ ግለሰብ መፈንቅለ መንግሥት ሲያሴሩ ከነበሩ ሁለት ዋነኛ ግለሰቦች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጿል። 23ቱ ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት ጀርመን ካሏት 16 ግዛቶች በ11ዱ ውስጥ ነው። ሁለት ተጨማሪ ሰዎች ደግሞ በኦስትሪያ እና ጣሊያን ከሴራው ጋር በተገናኘ በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል የጽንፈኛው ሪችስበርገር ንቅናቄ አባላት ይገኙበታል። የዚህ ንቅናቄ አባላት ኃይል በተቀላቀለባቸው ጥቃቶች እና ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ድርጊቶች በጀርምን ፖሊስ ጥብቅ ክትትል ሲደረግባቸው የቆዩ ናቸው። በግምት 50 የሚሆኑ ሰዎች የዚህ ንቅናቄ አካል የነበሩ ሲሆን፤ አሁን ላይ ያለችውን የጀርመን አስተዳደርን አይቀበሉም። ዓላማቸውም ያለውን የጀርመን ሪፐብሊክ ሥርዓትን በማስወገድ እአአ 1871 ላይ የነበረውን የጀርመን አስተዳደርን መመለስን ይፈልጋሉ። “ለዚህ ቡድን እስካሁን መጠሪያ የለንም” ሲሉ የፌደራል መንግሥቱ ዐቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። የጀርመን የፍትሕ ሚኒስትር ማርኮ በሽማን ግዙፍ ፀረ-ሽብር ዘመቻ በመላው አገሪቱ እየተካሄደ እንደሆነ እና “ሕገ-መንግሥታዊ አካላት ላይ ጥቃት” ታቅዶ እንደነበረ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል። የአገሪቱ ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ከሆነ ቡድኑ ከእአአ 2021 ጀምሮ ባለፉት 12 ወራት መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሲያሴር ቆይቷል። በጀርመን ጦር ውስጥ ልዩ የኮማንዶ አባላት የነበሩ ግለሰቦችም የመፈንቅለ መንግሥቱ ቁልፍ አካል መሆናቸው ተመላክቷል። መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሲያሴሩ የነበሩት ግለሰቦች ዕቅዳቸውን ከተገበሩ በኋላ፣ ጀርመንን እንዴት ማስተዳደር እንዳለባቸው ዝርዝር ዕቅድ አውጥተው ጨርሰው እንደነበረ ተገልጿል። የቡድኑ አባላት ዓላማቸውን እውን ማድረግ የሚችሉት “ሰዎችን መግደልን ጨምሮ፣ ኃይል በተቀላቀለበት መንገድ ብቻ ነው” ብሏል የአገሪቱ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c87em2n78gpo +health ኮቪድ-19 ፡ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ የኮቪድ-19 ክትባት ተከተቡ "የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ በቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭት እየታዩ የኮሮናቫይረስ ክትባት ተከተቡ። ምክትል ፕሬዚደንቱ ለተመልካቾችና ለዶክተሮች ""ምንም ነገር አልተሰማኝም"" ብለዋል። ማይክ ፔንስ በቀጥታ ሥርጭት እየታዩ የመከተባቸው ዓላማ የክትባቱን ደህንነትና ውጤታማነት ለማስተዋወቅና በአሜሪካ ሕዝቦች ዘንድ መተማመንን ለመፍጠር እንደሆነ ዋይት ሃውስ አስታውቋል። በዚህ በዋይት ሃውስ በተሰናዳው ዝግጅት የምክትል ፕሬዚደንቱ ባለቤት እና የጤና ጥበቃ ጠቅላይ ኃላፊ [ሰርጅን ጀነራል] ጀሮሜ አዳምስም ክትባቱን ወስደዋል። የ61 ዓመቱ ማይክ ፔንስ ከባለቤታቸው ካረን እና አዳምስ ጋር የመጀመሪያዎቹን ሁለት ዶዝ የፋይዘር/ ባዮንቴክ ክትባት የወሰዱት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ነው። አሜሪካ 95 በመቶ በሽታውን ይከላከላል የተባለውን የፋይዘር/ ባዮንቴክ ክትባት መከተብ የጀመረችው ባሳለፍነው ሰኞ ነበር። የመጀመሪያ ሦስት ሚሊየን ዶዝ [መጠን] ክትባቶችም በ50 የአገሪቷ ግዛቶች ተሰራጭተዋል። ጥቅምት ወር ላይ በኮሮናቫይረስ ተይዘው በሆስፒታል ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ ያገገሙት ማይክ ፔንስ፤ ክትባቱን ለመውሰድ ጊዜ አስቀምጠው እንዳልነበርና በተገቢው ጊዜ ግን ለመከተብ በጉጉት ሲጠባበቁ እንደነበር ተናግረዋል። ዘጋቢዎች እንደሚሉት በርካታ ደጋፊዎቻቸው ስለክትባቱ ደህንነትና ���ጤታማነት ጥርጣሬ አላቸው። ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ከሆኑት የሚመደቡት የ78 ዓመቱ ተመራጩ ፕሬዚደንት ጆ ባይደንም በሚቀጥለው ሳምንት ይከተባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጆ ባይደን በመጭው በፈረንጆቹ ጥር 20 ወር በዋይት ሃውስ ሥራቸውን ሲጀምሩ በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት፤ 100 ሚሊየን የአሜሪካ ሕዝቦችን ለመከተብ ግብ አስቀምጠዋል። ይህ ቁጥር የአሜሪካ ሕዝብ አንድ ሦስተኛ እንደሆነ ይገመታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሞደርና የሚመረተው ሁለተኛው ክትባት በባለሙያዎች ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ለድንገተኛ ጊዜ እንዲውል ፈቃድ ለማግኘት እየተቃረበ ነው። በአሜሪካ ከ310 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በዓለማችን ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዙ እና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከተመዘገበባቸው አገራት ግንባር ቀደሟ ናት።" https://www.bbc.com/amharic/news-55365780 +sports ሊዮኔል ሜሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ ዋንጫ አነሳ ሊዮኔል ሜሲ በኮፓ አሜሪካ የፍፃሜ ፍልሚያ ሃገሩ አርጀንቲና ብራዚልን መርታቷን ተከትሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ ዋንጫ ማንሳት ችሏል። ሁለቱ ሃገራት በግዙፉ ሪዮ ማራካኛ ስታዲዬም የፍፃሜውን ጨዋታ አድርገው አርጀንቲና በዲ ማሪያ ጎል አንድ ለባዳ ረትታለች። የ34 ዓመቱ ሜሲ የጨዋታውን ፍፃሜ የሚያበስረው ፊሽካ ሲነፋ በደስታ መሬታ ላይ ከመውደቁ የቡድን አጋሮቹ እየሮጡ ሲከቡት ይታያል። ሜሲ ሃገሩ አርጀንቲና ዋንጫ እንድታገኝ 10 ጊዜ ትላልቅ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳካለት ዘንድሮ ነው። የስድስት ጊዜ የዓለም ኮከብ ሽልማት ባለቤቱ ሜሲ ሃገሩ አርጀንቲያ ከ28 ዓመታት በኋላ ዋንጫ እንድታነሳም አስችሏል። አንሄል ዲ ማሪያ የማሸነፈያ ጎል በማስቆጠር የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። ሜሲ በፍፃሜው ጨዋታ ጎልና መረብ የሚያገናኝበት አንድ ወርቃማ ዕድል አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል። የውድድሩ አዘጋጅ የሆነችው የባለፈው ኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ባለድል ብራዚል በሜዳዋ ዋንጫ የማንሳት ሕልሟ ሳያሳካላት ቀርቷል። በሜሲ ተቃራኒ 10 ቁጥር ለብሶ የሚጫወተው ኔይማር በጨዋታው ፍፃሜ በሐዘን አንገቱን ሲደፋ ታይቷል። ኔይማር፤ ብራዚል ያለፈውን የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ስታነሳ በጉዳት ምክንያት የቡድኑ አባል መሆን አልቻለም ነበር። ባርሴሎና እያሉ ለአራት ዓመት አብረው የተጫወቱት ኔይማርና ሜሲ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ረዘም ላለ ደቂቃ ተቃቅፈው ታይተዋል። በኮቪድ-19 ምክንያት ጨዋታውን መታደም የቻሉት 7 ሺህ ሰዎች ብቻ ቢሆንም በውድድሩ ለጀመሪያ ጊዜ ነው ተመልካቾች ገብተው መታደም የቻሉት። በወረርሽኙ ምክንያት በአንድ ዓመት የዘገየው የኮፓ አሜሪካ ፍልሚያ አርጀንቲናና ኮሎምቢያ እንዲያዘጋጁት ነበር የታሰበው። ነገር ግን ከሁለት ዓመት በፊት አዘጋጇ ብራዚል ትሁን ተብሎ ቢወሰንም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ውሳኔው ትክክል አይደለም የሚሉ ቅሬታዎች ቀርበውበት ነበር። ሜሲ በአራት ዓለም ዋንጫዎችና በስድስት ኮፓ አሜሪካ ውድድሮች ሃገሩ አርጀንቲናን ወክሎ ተጫውቷል። 10 የላሊ ጋ ዋንጫ፣ 4 ጊዜ የቻምፒየንስ ሊግ ባለድል እና የስድስት ባለንደኦር ባለቤት የሆነው ሜሲ በዓለም አቀፍ መድረክ ምንም ድል አላገኘም የሚል ትችት ይቀርብበት ነበር። ከአርጀንቲና ጋር ድል ማጣጣም ያልቻለው ሜሲ በአንድ ወቅት ራሱን ከቡድኑ ማግለሉን አስታውቆ መልሶ መጫወት መጀመሩ ይታወሳል። ከባርሴሎና ጋር ያለውን ውል ያጠናቀቀው ሜሲ ቀጣይ መዳረሻው የት ነው የሚሆነው የሚለው አሁንም አነጋጋሪ ሆኗል። ኳታር በምታዘጋጀው የ2022 ዓለም ዋንጫ ላይ ይሳተፋል አይሳተፍም የሚለውም ሌላኛው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-57794201 +health ኮቪድ-19፡ የኮሮናቫ���ረስ ክትባቶች ቅይጥ ቫይረሱን በጥሩ መንገድ መከላከል እንደሚችል ጥናት አመለከተ "ለመጀመሪያውም ይሁን ለሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት የተለያዩ ምርቶችን ቀላቅሎ መጠቀም ቫይረሱን በሚገባ መከላከል እንደሚችል በዩናይትድ ኪንግደም የተደረገ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ የፋይዘርና የአስትራዜኒካ ክትባቶችን በተለያየ ቅደም ተከተል በመስጠት የተደረገው ሙከራ ውጤታማ ነው ተብሏል። በሁለቱም ቅደም ተከተል የተደረገው ሙከራ በጥሩ ሁኔታ ሰርቷል የተባለ ሲሆን በሽታ የመከላከል ሥርዓትን ማሻሻላቸውም ተጠቅሷል፡፡ ታዲያ ይህ ግኝት አዳዲስ የክትባት አይነቶች እንዲመረቱ በር የሚከፍት መሆኑን ባለሙያዎች አስረድተዋል። የሙከራ ውጤቱም ቀደም ሲል ሁለት ዙር የአስትራዜኒካ ክትባት በክረምት ወቅት የወሰዱ ሰዎች ተጨማሪ ክትባት ቢወስዱ ጠንካራ የመከላከል አቅማቸውን ሊያዳብሩ እንደሚችሉ ፍንጭ ተሰጥቷል፡፡ በዩናይትድ ኪንግደም የታወቁት የሕክምና ባለሙያ ፕሮፌሰር ጆናታን ቫንታም በዩኬ ውስጥ አሁን እየተሰጠ ያለውንና ውጤታማ የሆነውን ተመሳሳይ [ያልተቀላቀለ] ክትባትን የማዳረስ መርሃ ግብርን ለመለወጥ ምንም ምክንያት የለም ያሉ ሲሆን፤ ክትባቶቹ በጥሩ አቅርቦት ላይ ያሉ እና ሕይወትን የሚያድኑ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል። ሆኖም ለወደፊቱ አንዳች ነገር ለሆን ይችላል የሚሉት ፕሮፌሰሩ ""ክትባቶቹን ቀይጦ መጠቀም መርሃ ግብሩን የበለጠ እንደጊዜው ለማስኬድ እንዲሁም የክትባት ምርት ሂደት ላይ ያሉ አገራትን ለመደገፍ እና የክትባት አቅርቦት ችግር ያጋጠማቸው አገራትን ለመርዳት ይግዛል"" ብለዋል። የተለያዩ አገራት ክትባቶችን ቀላቅለው መጠቀም ጀምረዋል። ስፔን እና ጀርመን የአስትራዜኔካ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ለወሰዱ ታዳጊዎች ፋይዘር ወይም ሞዴርና የተሰኙ ክትባቶችን ለሁለተኛ ዙር እየሰጡ ነው። ይሁን እንጅ ክትባቶችን ቀላቅለው የወሰዱ ሰዎች አልፎ አልፎ የደም መርጋት ችግርን እንዳጋጠማቸው ተገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57648418 +sports የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የቀጣይ ቀናት ጨዋታዎች ግምት በምንም ነገር ላይ እርግጠኛ መሆን አይቻልም ይባላል። ማንቸስተር ዩናይትድስ በሊቨርፑል መሸነፉ እርግጥ ነው? “ከአስሩ የሊጉ ጨዋታዎች ብቸኛው በእርግጠኝነት የምገምተው ጨዋታ ነው” ይላል የቢቢሲው ክሪስ ሱቶን። “ማንቸስትር ስንት ጎል ያስተናግዳል? የሚለው ነው ጥያቄው። ከድጡ ወደ ማጡ እንደሚሆንባቸው እርግጠኛ ነኝ” ይላል። ሱቶን ከሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ውጪም የሌሎችንም ጨዋታዎች ግምት አስቀምጧል። ቶተንሃም ከ ዎልቭስ ባለፈው ሳምንት ቶተንሃም ከቼልሲ ጋር በነበረው ጨዋታ ባሳየው አቋም ተበሳጭቻለሁ። ዎልቭሶች ፖርቹጋላዊውን ጎንካሎ ጉዋዴዝን በማስፈርም የፊት መስመራቸውን አጠናክረዋል። ዎልቭሶች ባለፈው ዓመት የማጥቃት መስመራቸው ስስ መሆኑ ታይቷል። ቶተንሃም ተመሳሳይ ችግር የለበትም። ግምት፡ 3 - 1 ክሪስታል ፓላስ ከ አስቶን ቪላ ክሪስታል ፓላስ ሰኞ ዕለት ከሊቨርፑል ጋር ድንቅ ፉክክር አድርጓል። ከውጤቱም ጥሩ መነሳሳት ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ። ቪላም ከኤቨርተን ጋር ከነበረው ጨዋታ ጥሩ መነቃቃት ያገኛል ብዬ አስባለሁ። ይህ ለመገመት ከባድ የሆነ ጨዋታ ነው። ግምት፡ 1 - 1 ኤቨርተን ከ ኖቲንግሃም ፎረስት ኖቲንግሃም ፎረስት ባለፈው ሳምንት ዌስት ሃምን በማሸነፍ ትልቅ ውጤት አስመዘግቧል። ኤቨርተንም የውድድር ዓመቱን በጥሩ መልኩ ለማስኬድ ተመሳሳይ ድል ይፈልጋል። ቡድኑ ይህ ነው የሚባል ጥሩ አጥቂ የለውም። በዚህ ጨዋታ ግን ውጤቱ ይቀናቸዋል ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 - 0 ፉልሃም ከ ብሬንትፎርድ የብሬንትፎርድ ጉዞ ተመችቶኛ��። ባለፈው ሳምንት 3 ለ 0 ማንቸስተር ዩናይትድን ያሸንፋሉ ብዩ 4 ለ 0 አሸንፈዋል። ፉልሃም ደግሞ ከሊቨርፑል ነጥብ በተጋራበት መንገድ ይጫወታል ብዬ አስባለሁ። ከፍተኛ ፉክክር ያለው ጨዋታ ይሆናል። ፉልሃም ሁለቱንም የመክፈቻ ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። የዚህ ሳምንቱም ተመሳሳይ ይሆናል። ግምት፡ 1 - 1 ሌስተር ከ ሳውዝሃምፕተን የሳውዝሃምፕተኑ አለቃ ራልፍ ሃሰንሃልት ጫና ውስጥ ወደቁ ይመስላል። በቅድመ ውድድር ወቅት በሦስት ተከላካይ ቢጫወቱም ሊጉ ሲጀመር ወደ አራት ተከላካይ ተመልሰዋል። ሌስተሮች በተከላካይ መስመር ላይ ክፍተት ቢኖርባቸውም ወደ ፊት ሲሄዱ ግን ጥሩ ናቸው። በዚህ ጨዋታ ጎል የሚቆጠር ሲሆን የብሬንዳን ሮጀርስ ቡድን እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 - 1 በርንማውዝ ከ አርሴናል አርሴናል ድንቅ አጀማመር ያደረገ ሲሆን፣ ጋብርኤል ጂሰስም ልዩነት ፈጣሪ መሆን ችሏል። ስለዝውውሩ ብዙ የተባለ ሲሆን እሱም ማስመከር ችሏል። በዚህ ጨዋታ ግን ጎል አያስቆጥርም። በመድፈኞቹ አጀማመር ተደንቀን ለዋንጫ ልንገምታቸው ይገባል የሚል ግምት የለኝም። በርንማውዝ ባለፈው ሳምንት በማንቸስትር ሲተቲ ተሸንፏል። ግምት፡ 0 - 2 ሊድስ ከ ቼልሲ ሊድስ ከሳውዛሃምፕተን ጋር በነበረው ጨዋታ ከ2 ለ 0 ከመምራት አቻ መለያየታቸው የሚያስቆጭ ነው። የቼልሲ የፊት መስመር አሁንም ያልተመለሰ ጥያቄ አለበት። ከቶትንሃም ጋር በነበረው ጨዋታ ግን ድንቅ ነበሩ። ኤላንድ ሮድ ላይ በተተመሳሳይ መንገድ ከተጫወቱ ሦስት ነጥቡን ያሳካሉ። ግምት፡ 0 - 3 ዌስት ሃም ከ ብራይተን ዌስት ሃሞች የመጀመሪያዎቹን ሁለት ጨዋታዎች ቢሸነፉም በቅድመ ውድድር ዘመን ከደረሰባቸው የጉዳት መጠን አንጻር ስጋት ሊኖር አይገባም። ውጤቱን በቅርቡ እንደሚያሻሽሉ ጥርጥር የለኝም። ብራይተንን ባለፉት አስር ጨዋታዎች ማሸነፍ አለመቻላቸውን ግን አሁንም አይቀይሩትም። የግረሃም ፖተር ቡድን በደንብ የተቀናጀ ሲሆን ነጥብ እንደሚያገኝም እገምታለሁ። ግምት፡ 1 - 1 ኒውካስል ከ ማንቸስትር ሲቲ በኒውካስል ሜዳ ድንቅ ድባብ እንደሚፈጠር እና አንድ ወይም ሁለት ዕድል እንደሚፈጥሩ አስባለሁ። ጨዋታው በማንቸስተር ሲቲ የበላይነት እንደሚጠናቀቅ እገምታለሁ። ኤርሊንግ ሃላንድ በበርንማውዝ ጨዋታ ተሳትፎው ዝቅ ያለ ነው ቢባልም ለኢካይ ጉዶዋን ጎል ማስቆጠር ዕድል አመቻችቷል። ኒውካስሎች አጥቂውን ላይ በማተኮር ለመቆጣጠር ካሰቡ ለሌሎች ክፍተት ሊፈጥርላቸው ይችላል። ግምት፡ 1 - 3 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል ማንቸስተሮች ይህንን ጨዋታ ካሸነፉ ከሊቨርፑል በላይ ይቀመጣሉ። ግን አይሳካላቸውም። ኤሪክ ቴን ሃግ ያላቸውን ቡድን እንዴት እንደሚቀይሩ አላውቅም። ሊቨርፑል ካደረገው ደካማ አጀማመር ሌላ የዳርዊን ኑኔዝ ቅጣት እና ጉዳቶች እንቅፋት ይሆኑባቸዋል። ምንም ቢሆን ግን የየርገን ክሎፕ ቡድን የበላይነቱን ይይዛል። ግምት፡ 1 - 5 https://www.bbc.com/amharic/articles/c51dr554ny4o +health ሕክምና ፡ ቁመት ለመጨመር ምን አይነት ቀዶ ሕክምና ነው የሚደረገው? "ሳም ቤከር የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ ሳለ የክፍሉ ረዥም ልጅ ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆነው ጓደኞቹ ሁሉ ዘለግ ዘለግ ያሉ ሲሆኑ የእሱ ቁመት ግን አልጨመረም። ""ኮሌጅ ስገባ ከሌሎች ወንዶችና ሴቶች ያጠርኩ መሆኔን አስተዋልኩ። ሴቶች ከእነሱ ከሚያጥር ሰው ጋር ፍቅር አይጀምሩም። እናም ሚስት አላገኝም ብዬ እሰጋ ነበር"" ይላል። የ30 ዓመቱ የኒው ዮርክ ነዋሪ ሳም እረዝማለሁ ብሎ ቢጠብቅም ቁመቱ አልጨምር አለው። ""ቁመትና ስኬትን አስተሳስሬ ነው የማየው"" የሚለው ሳም ቁመት ለመጨመር አማራጮች ያስስ ጀመር። ከፍ ያለ ጫማ ማድረግ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ወዘተ. . . የሚሉት አማራጮች አላሳመኑትም። እግር ስለሚያረዝም ቀዶ ሕክምና ሲያነብ ግን ትኩረቱን ሳበው። ""ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ"" በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቁመታቸውን ለመጨመር ቀዶ ሕክምና ያደርጋሉ። ቀዶ ሕክምናው ብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሳም ስለ ቀዶ ሕክምናው ከእናቱ ጋር ከተወያየ በኋላ የጎንዮሽ ጉዳት ቢኖርም እንኳን ለማካሄድ ወሰነ። ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ሲሆን፤ ይህም ከ162 ሴንቲ ሜትር ወደ 170 ሴንቲ ሜትር ከፍ እንዲል አስችሎታል። ""ሐኪሙ መጀመሪያ ሲያገኘኝ ቀዶ ሕክምናው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ነግሮኛል። ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ።"" ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሆስፒታል ውስጥ የማገገሚያ ሕክምና ተደርጎለታል። ለስድስት ወራት፣ በሳምንት ለአራት ቀን ሕክምና ይሰጠው እንደነበር ያስታውሳል። ""እንደ አዲስ መራመድ መማር ነበረብኝ"" ይላል። ብዙ አገሮች እግር ለማርዘም ቀዶ ሕክምና ይሰጣሉ። እስከ አምስት ኢንች ወይም 13 ሴንቲ ሜትር ድረስ ቁመት መጨመርም ይቻላል። አሜሪካ፣ ጀርመን እና ደቡብ ኮርያ የሚገኙ ሆስፒታሎች በዓመት ከ100 እስከ 200 ቀዶ ሕክምናዎችን ያደርጋሉ። ስፔን፣ ሕንድ፣ ቱርክ እና ጣልያን ውስጥ በዓመት ከ20 እስከ 40 የሚደርሱ ቀዶ ሕክምናዎች ይካሄዳሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ደግሞ በዓመት 15 ጊዜ ቀዶ ሕክምናው ይደረጋል። ቀዶ ሕክምናውን የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ቀዶ ሕክምናው እንዴት ይካሄዳል? ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ቀዶ ሕክምናው እስከ 50 ሺህ ፓውንድ ያስከፍላል። አሜሪካ ውስጥ ደግሞ ከ75 ሺህ እስከ 280 ሺህ ዶላር ያስወጣል። ቀዶ ሕክምናው ውድ ነው። ረዥም ሰዓታት ይወስዳል። ያማልም። በሕክምናው ፈር ቀዳጅ የሆኑት የሶቪየቱ ጋቪል ሊዝሮቭ ናቸው። ሕክምናውን የጀመሩት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተረፉ ወታደሮችን ለማከም ነበር። ቀዶ ሕክምናው ባለፉት 70 ዓመታት ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል። ሕክምናው የሚካሄደው የእግር አጥንትን ቦርቡሮ ለሁለት ከከፈሉ በኋላ አነስተኛ ብረት በክፍተቱ በመክተት ነው። ግለሰቡ የሚፈለገው ርዝመት ላይ እስኪደርስ ብረቱ በየቀኑ አንድ ሚሊ ሜትር ከፍ እንዲል ይደረጋል። ታካሚው ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ለወራት የማገገሚያ ሕክምና ይሰጠዋል። ቀዶ ሕክምናው ነርቭ ሊጎዳ፣ የደም ዝውውር ሊገታም ይችላል። የእግር አጥንትን መልሶ ለመግጠም የሚያስቸግርበትም ጊዜ አለ። ""ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር"" ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከአምስት ዓመት በፊት ጣልያን ሲሆን፤ 3 ኢንች ጨምሯል። የእግር ቀዶ ሕክምና እንዲያደርግ የታዘዘው በሐኪሞች ምክር ነበር። ""ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር። የእግሬ አጥንት መልሶ ሊገጥም አልቻለም። የሦስት ኢንች ክፍተት ተፈጥሮ ነበር"" ይላል። ቀዶ ሕክምናው ምቾት ነስቶት እንደነበር ይናገራል። ""እያንዳንዱ የእግሬ ነርቭ እንደተወጠረ ይሰማኝ ነበር። ህመሙ ቀላል አልነበረም።"" የብሪትሽ የአጥንት ሕክምና [ኦርቶፒዲክ] ማኅበሩ ፕሮፌሰር ሀሚሽ ሲምሰን እንደሚሉት፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሕክምናው እየተሻሻለ መጥቷል። ""ሂደቱ አስተማማኝ እየሆነ ቢመጣም ከአጥንት በተጨማሪ ጡንቻ፣ ነርቭ፣ የደም መዘዋወሪያ እና ቆዳን ማሳደግም ስለሚያስፈልግ ሂደቱ ውስስብ ነው"" ይላሉ። በዩናይትድ ኪንግደም የሚሠሩት ዶ/ር ዴቪድ ጎደር፤ አንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ለማዳን ብለው ደኅንነቱ በማያስተማምን ቦታ ቀዶ ሕክምናውን እንደሚያገኙ ይናገራሉ። ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ካካሄደ ከአምስት ዓመታት በኋላ ነው የመጨረሻውን የሕክምና ደረጃ ያጠናቀቀው። በስተመጨረሻ እግሩ ውስጥ የቀረው ብረት እንዲወጣ ተደርጓል። ""የአንዳንዶች ቀዶ ሕክምና በስኬት ይጠናቀቃል። እኔ ግን ለማገገም ገና ጊዜ ይወስድብኛል። ሆኖም ቀዶ ሕክምናውን ማድረጌ አይጸጽተኝም። አጭር ሰዎች ከሚገጥማቸው መድልዎ ነጻ ሆኜ ሕይወቴን እንድገፋ እድል ሰጥቶኛል"" ይላል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55198053 +politics "መንግሥት ከህወሓት ጋር ""የተደራደሩ"" ጥያቄን በፍጹም እንደማይቀበል በድጋሚ አስታወቀ" "የኢትዮጵያ መንግሥት ከአጋር አገራት እየቀረበለት ያለውን 'ከህወሓት ጋር ተደራደሩ' የሚሉ ምክረ ሐሳቦች በፍጹም እንደማይቀበል በድጋሚ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው የኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ ነው። ሚኒስቴሩ ከአጋር አገራት ጋር በቅርብ መሥራቱን እንደሚቀጥል በመግለጫው አረጋግጦ ሆኖም ግን፤ እጅ ለመጠምዘዝ የሚሞክሩ ያላቸውን መንግሥታትን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የአገሪቱን ሉዓላዊነት እንዲያከብሩ አስጠንቅቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ ጠንከር ያለ መግለጫው በኢትዮጵያ ላይ እጃቸውን የሚያስገቡ የውጭ መንግሥታትን የኮነነው የሚነሱበትን ክሶች በአምስት ፈርጅ በመክፈል አንድ በአንድ ከዳሰሰ በኋላ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በርካታ ጊዜ ከእነዚህ መንግሥታት ጋር በበጎ ስሜት ለመነጋገር መሞከሩን ያስታወሰው መግለጫው፤ ነገር ግን ከአጋር አገራት ተመሳሳይ ስሜት ባለማየቱ አጋር የሚባሉ አገራትን እውነተኛ ፍላጎት ለመጠራጠር እየተገደደ መምጣቱን ያወሳል። አጋር አገራት ኢትዮጵያ በተጨባጭ ያለችበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለመረዳት አለመሞከራቸውን እና ከዚያ ይልቅ ችግሩን የሚያባብሱ ሆነው መገኘታቸውንም ይዘረዝራል። እነዚህ በስም ያልተገለጹት አጋር አገራቱ በሐሰተኛ ሚዲያዎችና ዜናዎች እየተመሩ ወደተሳሳተ አቅጣጫና ድምዳሜ እየሄዱ እንደሆነም ይጠቅሳል። ይህም በመሆኑ መንግሥት በ5 ጉዳዮች ላይ የማያሻማና ግልጽ መልእክት ማስተላለፍ አስፈልጎታል ሲል እነዚህን አንኳር የተባሉ ጉዳዮችን ይዘረዝራል። እነዚህ አንኳር የተባሉት ጉዳዮች በዋናነት በትግራይ ስላለው ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት፣ በአገሪቱ የለተያዩ አካባቢዎች እየተፈፀሙ ነው ስለሚባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ከህወሓት ጋር የተኩስ አቁም ስለማድረግና በጠረጴዛ ዙርያ ንግግር እንዲጀመር የሚቀርቡ ውትወታዎች እና የመብት አራማጆችን ድምጽ ስለማፈን በተነሱ ጉዳዮች ዙርያ ዘርዘር ያሉ ማብራሪያዎች በመግለጫው ተካተውበታል። የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት መንግሥት ሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ላይ ያለውን ዝግጁነት ብቻም ሳይሆን ቆራጥነቱን በሥራ አሳይቷል የሚለው መግለጫው፤ በትግራይ ለሚዳረሱ ሰብአዊ ድጋፎች ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሙሉ አጋርነት መስጠት ብቻም ሳይሆን በመላው ትግራይ ገብተው እንዲሰሩም ፈቅዷል ይላል። መግለጫው እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አሁንም ሰብአዊ ድጋፍ የሚያቀርቡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መድረስ አልቻልንም ብለው መናገራቸው ከእውነት የራቀ ነው ብሏል። በደኅንነት ስጋት የተነሳ አንዳንድ አካባቢዎች ለሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ምቹ እንዳልሆኑና ይህንንም ድርጅቶቹ እንደሚረዱ አብራርቷል። ሀቁ ይህ ሆኖም ዓለም አቀፍ ሰብአዊ ድጋፍ ሰጪዎች ተመሳሳይ ቅሬታ ማቅረባቸው እንዳሳዘነው ገልጧል፡፡ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተም የሚደርሱትን ቅሬታዎች ለማጣራት በፌዴራል ዐቃቤ ሕግ እና በፌዴራል ፖሊስ የሚመራ ቡድን መቋቋሙን፣ ምርመራ ለማድረግም ወደ ትግ���ይ ማቅናቱን አስታውሶ፤ የምርመራ ውጤታቸውን ባለፈው ሳምንት ይፋ ማድረጋቸውን ገልጧል። በዚህም ጥፋተኞች ተጠያቂነት እንደሚኖርባቸው ማረጋገጡን አስምሮበታል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የማይካድራ ጭፍጨፋን ጨምሮ በርካታ ምርመራዎችን አድርጎ መግለጫ ያወጣ መሆኑን አውስቷል። ከዚህም ባሻገርም መግለጫው ኢሰመኮ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጀት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በቅንጅት ምርመራ ለማድረግ መስማማቱንም አስታውሷል። በኢትዮጵያ መንግሥት ግብዣ የአፍሪካ ኅብረት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ራሱን የቻለ ምርመራ እያደረገ እንደሆነም ጠቅሶ፤ ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያን ቸልተኛ እንደሆነች አድርጎ መክሰስ ፖለቲካዊ ጫና ለማሳደር ከመሻት የመነጨ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም ብሏል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ። ግጭት ይቁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ በተለይ ግጭት እንዲቆም ከስምምነት እንዲደረስ እና ብሔራዊ ምክክርን በተመለከተ የውጭ መንግሥታት እየሰነዘሩ ያሉትን ሐሳብ ክፉኛ ተችቷል። ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ከሲቪል ማኅበረሰቡና ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራንና የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተከታታይ ንግግሮችን እያደረገ ያለበት ሁኔታን በዝርዝር ጠቅሶ፤ ነገር ግን አጋር አገራት መንግሥት ከህወሓት ጋር ንግግር እንዲጀምር ግፊት ማድረጋቸው በጭራሽ ተቀባይነት እንደሌለው አትቷል። ፓርላማው ድርጅቱን በአሸባሪነት በፈረጀበት ሁኔታ ከህወሓት ጋር በጠላትነት መተያየቱ እንዲቀርና ድርድር እንዲጀመር የሚጠይቁ አጋር መንግሥታትን ተደጋጋሚ ጥያቄዎቻቸውን በፍጹም እንደማይቀበል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ""ህወሓት ሕገ-ወጥ ቡድን ነው። የአገሪቱን ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ የከተተና ሕገ-መንግሥቱን የጣሰ ቡድን ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ቡድን ተርታ ውስጥ እንዲገባ ወስኗል። ለዚህም ነው የኢትዮጽያ መንግሥት የአጋር አገራትን ግጭት ቆሞ ከህወሓት ጋር የተደራደሩ ጥሪ በፍጹም ሊቀበለው የማይችለው"" ይላል መግለጫው። መግለጫው አንዳንድ አጋር መንግሥታት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባታቸውን እንዲያቆሙም ጠይቋል። በተለይም የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በተመለከተ የሚሰነዘሩ ሐሳቦችን እንደማይቀበል የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጧል። ""ኢትዮጵያ ሉዓላዊት አገር ናት። የራሷን የጸጥታ ኃይልና ሠራዊት በግዛቷ በፈለገችው ሁኔታና መልክ ማሰማራት ትችላለች። የአማራ ልዩ ኃይል በትግራይ መሰማራትም በዚህ አግባብ የተፈጸመ ነው"" ብሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ ጉዳዮች ላይ አሁንም ቢሆን ከአጋር መንግሥታት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ቢሆንም እጅን ለመጠምዘዝ የሚሞከሩ ሁኔታዎች የሚቀጥሉ ከሆነ ግን ይህን ግንኙነት በድጋሚ ለማጤን ይገደዳል ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ።" https://www.bbc.com/amharic/57155325 +health አስትራዜኒካ ከሚያመርተው የኮሮናቫይረስ ክትባት ትርፍ መሰብሰብ ሊጀምር ነው "አስትራዜኒካ የሚያመርተውን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ያለትርፍ ለአገራት የሚሰራጭበትን አሠራር ሊቀይር እንደሆነ ተሰምቷል። ግዙፉ መድኃኒት አምራች ኩባንያ ከቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ ተከታታይ የንግድ ስምምነቶች የተፈራረመ ሲሆን ከክትባቱ ሽያጭ መጠነኛ ገቢ እንደሚያስገባ አስታውቋል። ሆኖም ኩባንያው ለድሃ አገራት ክትባቱን ያለትርፍ ማቅረቡን እንደሚቀጥል ገልጿል። ኩባንያው ከዚህ ቀደም ከክትባቱ ገንዘብ ለማግኘት አቅዶ የነበረው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት መሆኑ ካበቃ በኋላ ነው። የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓስካል ሶሪዮት�� ወረርሽኙ ወደተወሰኑ አከባቢዎች እየጠበበ መምጣቱን ተናግረዋል። ""ቀደም ሲል ያለምንም ትርፍ ክትባቱን ለማቅረብ የወሰነው ዋናው ዓላማችን የዓለምን ጤና መጠበቅ ስለነበር ነው"" ብለዋል። ""ምንም እንኳን በተለያዩ አገራት የፖለቲካ ትችቶችን ብናስተናግድም ከተፎካካሪዎች በተቃራኒ ትርፍ ለማግኘት አለመሥራታችን ምንም አይነት ፀፀት አላስከተለብንም"" ሲሉ ሥራ አስፈጻሚው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተደረገ ትብር የበለጸገው ክትባቱ በዓለም ዙሪያ የአንድ ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት መታደግ መቻሉንም ጠቅሰዋል። ""በፍፁም አልፀፀትምም። እንደ ኩባንያ እኛ በሠራነው ሥራ ኩራት ይሰማናል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን አድነናል። የአስተራዜኒካ ቡድን ጥሩ ሥራ መሥራቱን ቀጥሎበታል"" ሲሉም አክለዋል። ከክትባቱ ሽያጭ ከፍተኛ ገቢ እንደማይጠበቅ የገለጹ ኃላፊው፤ ክትባቱ በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረቡን ለማረጋገጥ ለአገራት በየደረጃው የዋጋ ተመን እንደሚወጣ ተናግረዋል። እስከዚህ የፈረንጆቹ ዓመት መገባደጃ ድረስ አስትራዜኒካ 250 ሚሊዮን ክትባቶችን በኮቫክስ መርሐ ግብር አማካይነት ለታዳጊ አገራት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። ፋይዘር እና ሞደርናን ጨምሮ ሌሎች የክትባት አምራቾች ከምርቶቻቸው ትርፍ እያገኙ ያገኛሉ። በመድኃኒት ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለው መደበኛ የትርፍ ጣሪያ 20 በመቶ መሆኑን የሚገልጹት ሶሪዮት፤ የኮቪድ-19 ክትባት ግን አንድ ብልቃጥ 5 ዶላር የሚሸጥ በመሆኑ አስተራዜኒካ አነስተኛ ትርፍ እንደሚያገኝ ጠቁመዋል። 'ግሎባል ጀስቲስ ናው' የተሰኘ እንቅስቃሴ ዳይሬክተር ኒክ ዴርደን በበኩላቸው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በቀጠለበት በዚህ ወቅት አስትራዜኒካ ከክትባቱ ትርፍ ለማግኘት መወሰኑ ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ ውሳኔውን ተቃውመዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59272481 +health በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ ሰዎች መጨመሩን ተከትሎ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መመሪያዋን አሻሻለች "በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ፣ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዝ የተሻሻለ መመሪያ መውጣቱ ተገልጿል። በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ከስድስት አመት በላይ የሆኑ ህፃናት ማስክ እንዲያደርጉ፣ በሰርግ፣ በቀብር እንዲሁም በስብሰባዎች ላይ የሚገኙ ሰዎች ብዛት ከአምሳ እንዳይበልጥ፣ በካፌዎችና በሬስቶራንቶች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዳይቀመጡ የሚሉና ሌሎች ዝርዝሮች ተካትተውበታል። የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያወጡት ይህ መመሪያ ከነሐሴ 13 ፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ማንኛውም ሰው ማስክ ሳያደርግ እንዳይንቀሳቀስ የሚያግድ ሲሆን ይህም ከስድስት አመት በላይ የሆኑ ህፃናትን እንደሚጨምር የጤና ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አስገዳጅ የማይሆነው ከስድስት አመት በታች ለሆኑ ህፃናት እንዲሁም በማስረጃ የተረጋገጠ የመተንፈሻ አካላት ወይም መሰል ችግር ካለባቸው በስተቀር ሁሉም ዜጎች ሲንቀሳቀሱ ማስክ ማድረግ አለባቸው። የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎች በክፍት ገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች ከመደረግ በተጨማሪ ሁለት የአዋቂ እርምጃ (አካላዊ ርቀት) መጠበቅ አስገዳጅ ነው ተብሏል። በማንኛውም መንግስታዊ እና የግል ተቋም አገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ላይ ሰራተኞችና ደንበኞች ከሁለት የአዋቂ እርምጃ ወይም አካ���ዊ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲገለገሉና ማስክ እንዲያደርጉ ያስገድዳል። በእነዚህ የአገልግሎት ስፍራዎች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዲቀመጡ ማድረግም ተከልክሏል። ማንኛውም የመንግሥታዊ እና የግል ተቋማት በመግቢያና መውጫ በሮች የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን ማቅረብና አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው ብሏል። በአስከሬን ማስተካከል፣ ግነዛና ማጓጓዝ ወቅትም ሊደረጉ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎችም መመሪያው አስቀምጧል። ከቀብር በኋላ ሀዘን ለማስተዛዘን በድንኳን፣ በቤት ውስጥ ወይም ለዚሁ በተዘጋጀው ቦታ ላይ ለቅሶ የሚደርሰው ሰው ከ50 እንዳይበልጥ ያዛል። አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አለባቸው ይላል። በስብሰባም ወቅት በተመሳሳይ የኮቪድ-19 ጥንቃቄዎችን በተከተለ መልኩ እስከ 50 ሰው መሰብሰብ ይቻላል። ከ50 ሰዎች በላይ መሰብሰብ ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ስብሰባው ሊደረግበት የታሰበበት ስፍራ ጠቅላላ ስፋት ከግምት ውስጥ ሊገባ እንደሚገባ ጠቁሞ በዚህም መሰረት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛ በማይበልጥ መሆን አለበት። እንዲሁም ልዩ ፈቃድ ከሰላም ሚኒስቴር እንዲሁም ከክልሉ፣ ዞን እና ወረዳ የሰላም እና ፀጥታ መዋቅሮች መገኘት አለበት። ስብሰባውንም የጠራው አካል የመከላከያ ዘዴዎቹ መተግበራቸውን ማረጋገጥ ይገባዋል ይላል። የሃይማኖት ስነ ስርዓትን በተመለከተ ሃይማኖታዊ አገልግልቶች አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ ሊፈፀሙ እንደሚገባ መመሪያው አስቀምጧል። የሃይማኖት ስርዓት የሚከናወንባቸው ስፍራዎችም እንዲሁ መያዝ ከሚችሉት አንድ አራተኛ በማይበልጥ ስርዓቱን እንዲያካሂዱ ተቀምጧል። በእነዚህ የእምነት ተቋማት ቅጥር ግቢ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ ነው። የቤት ውስጥ ማህበራዊ ዝግጅቶችን በተመለከተም ለልደት፣ ምረቃ፣ ማህበር እና ቀብር እና ከቀብር መልስ ያሉ ስነ ስርዓቶች ውጭ እና መሰል በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ማህበራዊ በዓላት ከቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጭ ተጠራርቶ ማክበር የተከለከለም ነው። ሰርግን በተመለከተም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እና ተገቢውን የኮቪድ-19 መከላከያ የንፅህና እርምጃዎች በተገበረ መልኩ ከ50 በማይበልጡ ሰዎች ማካሄድ እንደሚቻል ተቀምጧል። የአደባባይ በዓላትን አከባበር ጋር ተያይዞ ህዝብን በብዛት የሚያሳትፉ የአደባባይ ላይ በዓላት የወረርሽኙ ስርጭት እስኪረጋጋ ድረስ ባይደረጉ በማለትም ምክረ-ኃሳብ አስቀምጧል። በዓላቱ የሚደረጉ ከሆነ ግን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መደረጉን እንዲሁም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ብሏል። ስፍራዎቹም ከሚይዙት ቦታ ከአንድ አራተኛ ቦታ በማይበልጥ ሰው ስርዓቱ ሊካሄድ እንደሚገባም ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብሏል። ስፖርታዊ ውድድሮችም በተመለከተ በተመሳሳይ ስፍራው ከሚይዘው የታዳሚ ብዛት ከአንድ አራተኛ በማይበልጥ እንዲሆን ተቀምጧል። አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ካፌዎች፣ ባር፣ ሬስቶራንቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ የመዝናኛ እና መጫዎቻ አገልግሎቶች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ሰው በላይ ማስተናገድ አይችሉም። በእያንዳንዱ ጠረጴዛ የሁለት ሜትር ርቀት መጠበቅ አለበት። አገልግሎትን የሚሰጡም ሆነ ደንበኞች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ከዚህም በተጨማሪ የወረርሽኙ ስርጭት ያለበት ሁኔታ በየጊዜው እየታየ በሌላ መመሪያ እስኪወሰን ድረስ የአረጋዊያን መጦሪያዎች ስፍራዎች እና የማገገሚያ ማዕከላት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በአካል መጠየቅ ���ተከለከለ መሆኑን አስፍሮ ነገር ግን እርዳታ ማቅረብ የሚፈልጉ ከተቋሙ አስተዳደር ድረስ በመቅረብ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉም ጠቁሟል። በማረሚያ ቤቶች ላይ ታራሚን ለመጠየቅ አካላዊ ርቀትን ጨምሮ ሌሎች አስገዳጅ የኮቪድ- 19 መከላከያን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ተብሏል። በቤት ውስጥ ማቆያ እና እንክብካቤን በተመለከተ ቀለል ባለ በኮቪድ-19 የተያዘ ታማሚ በቤት ውስጥ የኮቪድ-19 ህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ይደረጋል። ህመምተኞቹ ከሌላው የቤተሰብ አባላት ራሳቸውን መለየት፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ ቢያንስ ለ10 ተከታታይ ቀናት መለየትና ከቤት አለመውጣት ይጠበቅባቸዋል። ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ቫይረሱ እንዳለበት እያወቀ ወደ ሃገር ውስጥ መግባት፣ ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀል ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር መገናኘት የተከለከለ ነው። ከትራንዚት መንገደኛ በስተቀር በአገሪቱ አለም አቀፍ ማረፊያ በኩል የሚገባ ከአስር አመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ተጓዥ ከ120 ሰዓት ወይም አምስት ቀን በላይ ያልሆነው የተረጋጋጠ ምርመራ ኔጌቲቭ ውጤት ይዞ መምጣትና ለሰባት ቀናት መንገደኞች ራሳቸውን ለይተው ማቆየት አለባቸው። ነገር ሰባት ቀናት ራሳቸውን ለመለየት የማይገደዱት በ90 ቀናት ውስጥ ኮቪድ-19 ታመው ያገገሙ፣ ዲፕሎማቶች፣ የኮቪድ-19 ክትባትን በተሟላ ሁኔታ ወስደው ያጠናቀቁ ከሆነ ለተለያዩ ስብሰባዎች የሚመጡ ቱሪስቶች ወይም ለድንገተኛ ጉዳይ የሚመጡ መንገደኞች ናቸው። ለተለያዩ ጉባዔ የሚመጡ ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግና ውጤታቸው ኔጌቲቭ መሆን አለበት። ማንኛውም ፖዘቲቭ ሰው ወደ ሃገር ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው።. በአገሪቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል የሚያልፉ የትራንዚት መንገደኞችን በተመለከተም በረራቸው እስኪደርስ ድረስ አየር መንገዱን ለቆ መሄድ ወይም አየር መንገዱ ከለያቸው ሆቴሎች ውጪ ወደ ከተማ መግባት አይችሉም። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሳምንታት በፊት ሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እየጀመረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ እንደሆነ አስታውቋል። በተለያዩ የዓለም ሀገራት መረጃዎች እና ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሦስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱ ታውቋል። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው የኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ሲሆን በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 የዴልታ ቫይረስ መኖሩ ባይረጋገጥም የሶስተኛ ዙር ወረርሽኝ መከሰቱን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየት መጀመራቸውም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ሁለተኛው ዙር ካበቃ በኋላ በተወሰነ መልኩ በማህበረሰቡ መዘናጋቶች እንዲሁም የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በአግባቡ ባለመተግበራቸው ሶስተኛው ዙር ሊከሰት የሚችልበት ምልክቶች እየታዩ ነው። ተቋሙ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎቹ እንዲከበሩና ማስክ ማድረግ፣የእጅን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ እና ርቀትን በመጠበቅ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የኮቪድ-19 መከላከከልና መቆጣጠር እንደሚቻልም አሳሳስቧል። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተርር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ""ከፊታችን የተጋረጠብንን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እንዲያልፍ፣ የጥንቃቄ መንገዶችን፣ ክልከላዎችና ግዴታዎች እያንዳንዱ ዜጋ፣ ተቋም፣ አመራር፣ የህግ አስከባሪ አካላት በከፍተኛ የሃላፊነት መንፈስ በመተግበርና በማስፈፀም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ"" ማለታቸውም በመግለጫው ላይ ሰፍሯል። በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ 295 ሺህ 19 ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 268 ሺህ 252 ግለሰቦች ከኮቪድ-19 ቫይረስ አገግመዋል እንዲሁም 4ሺህ 553 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። አጠቃላይ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁጥርም 2,335 ሺህ 71 ሲሆን አገሪቷ በአጠቃላይ 3,134 ሺህ 967 ምርመራዎችን አካሂዳለች።" https://www.bbc.com/amharic/58297000 +business በኢትዮጵያ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በምን ያህል ጨመረ? የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ትናንትና መስከረም 18/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በነዳጅ ምርቶች ላይ ከመስከረም 18/2015 ዓ.ም. እኩለ ሌሊት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የዋጋ ማሻሻያ መደረጉን አሳውቋል። በአገሪቱ ለነዳጅ ሲደረግ የነበረውን ድጎማ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለው ተከታታይይ የዋጋ ጭማሪ ምክንያት ማስቀጠል አለመቻሉን የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ ድጎማውን “ደረጃ በደረጃ ለማስቀረት” እየሰራ እንደሆነ ጠቁሟል። ድገማውን የማንሳት ተግባር ከሦስት ወራት በፊት የተጀመረ ሲሆን ይህም በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎችን በማይጎዳ እና “በበቂ ጥናት ዝግጅት” እየተከናወነ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጻል። የነዳጅ ድጎማው በየሦስት ወሩ እየተቀነሰ ከጊዜ በኋላ ሙሉ በሙሉ ተነስቶ በተጠቃሚዎች የሚሸፈን ይሆናል። በዚህ መሠረትም የመጀመሪያው ዙር የድጎማ ቅነሳ ከሐምሌ 2014 እስከ መስከረም 2015 ዓ.ም ተግባራዊ የሆነ ሲሆን “ከውስን ክፍተቶች በስተቀር በአጥጋቢ ሁኔታ ሲከናወን ቆይቷል” ብሏል - ሚኒስቴሩ። በመጀመሪያው ዙር የነዳጅ ድጎማ ቅነሳ ላይ የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣና የኬሮሲን ዋጋ ላይ ሲደረግ የነበረው ድጎማ 75 በመቶ በመንግሥት መከፈሉን ቀጥሎ 25 በመቶው ደግሞ በተጠቃሚዎች ሲከፈል ቆይቷል። ሆኖም የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ የሚደረገው ድጎማ ቀጥሎ ከ65 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተሽከርካሪዎች ከ310 ሚሊዮን ብር በላይ መከፈሉን ሚኒስቴሩ አመላክቷል። ባለፉት ሦስት ወራት በመንግሥት ሲደረግ የቆየው ድጎማ ላይ ለውጥ የተደረገ ሲሆን ይህም የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ላይ ለውጥ አምጥቷል። በዚህ መሰረትም አንድ ሊትር ቤንዚን 57 ብር ከ05 ሳንቲም፣ ነጭ ናፍጣ 59 ብር ከ90 ሳንቲም፣ ኬሮሲን 59 ብር ከ90 ሳንቲም የሚሸጥ ይሆናል። አንድ ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ 76 ብር ከ87፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 43 ብር ከ89 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 43 ብር ከ06 ሳንቲም የሚሸጥ ሲሆን፣ ቀድመው ሲሸጡበት በነበረው ዋጋ ቀጥለዋል። ለመሆኑ አዲሱ የነዳጅ ዋጋ ከባለፈው ጋር ሲነጻጸር  በምን ያህል ጨመረ? እስከ መስከረም 18/2015 ዓ.ም. እኩለ ሌሊት ድረስ ሲተገበር በቆየው የነዳጅ ዋጋ የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣ እና የኬሮሲን ዋጋን መንግሥት 75 በመቶ ሲደጉም የቆየ ሲሆን፣ ለቀጣዮቹ ወራት የሚያደርገውን ድጎማን ለውጥ ተደርጎ የቤንዚን ድጎማ ወደ 50 በመቶ፣ የነጭ ናፍጣ ደጎማ ደግሞ ወደ 66.77 በመቶ ዝቅ ተደርጓል። ከአጠቃላይ ማስተካካያው ዝቀተኛ ጭማሪ የተደረገው ቤንዚን ላይ ሲሆን የ9 ብር ከ22 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጎበታል። በነዳጅ ምርቶቹም ላይ ባለፉት ሦስት ወራት ከነበረበው ዋጋ ከ16 በመቶ እስከ 18 በመቶ ጭማሪ ታይቷል። በዚህ መሠረትም አንድ ሊትር ቤንዚን 47 ብር ከ83 ሳንቲም ሲሸጥ ከነበረበት 16 በመቶ ወይም በ9 ብር ከ22 ሳንቲም ከፍ ብሎ በ57 ብር ከ05 ሳንቲም ይሸጣል። ነጭ ናፍጣ ከሐምሌ 2014 እስከ መስከረም 2015 ዓ.ም 49 ነጥብ 02 በሊትር የሚሸጥበት ዋጋ ወደ 59 ብር ከ90 ሳንቲም አሻቅቧል። ይህም ካለፈው መሸጫ ዋጋ የ10 ብር ከ 88 ሳንቲም ወይም የ18 በመቶ ጭማሪን ያሳየ ነው። እስከ ትላንት አንድ ሊትር ኬሮሲን ወይም ነጭ ጋዝ በ49 ብር ከ02 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን ከነጭ ናፍጣ  ዋጋ ጋር በእኩል በመጨመር  የ10 ብር ከ 88 ሳንቲም ወይም የ18 በመቶ ጭማሪን ተደርጎበት 59 ብር ከ90 ሳንቲም መሸጥ ጀምሯል። ንግድና ቀጠናዊ ሚኒስቴር በአውሮፕላን ነዳጅ፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣ እና በከባድ ጥቁር ናፍጣ ላይ እየተደረገ ስ��ነበረው ድጎማ መጠን ሳይጠቅስ የነዳጅ ምርቶቹ ባሉበት ይቀጥላሉ ብሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c13jdvgv0vvo +health ኮሮናቫይረስ፡ በእንግሊዝ በየቀኑ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ "በእንግሊዝ ውስጥ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በየቀኑ በኮሮናቫይረስ እንደሚያዙ አንድ ጥናት ጠቆመ፡፡ እንደለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ ጥናት ከሆነ ወረርሽኙ በፍጥነት እየጨመረ ሲሆን በየዘጠኝ ቀናትም በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ይጨምራል፡፡ አጥኚዎቹ ""ወሳኝ ደረጃ ላይ በመሆናችን አንድ ነገር መደረግ አለበት"" እያሉ ነው፡፡ ፈረንሳይ እና ጀርመን ቫይረሱን ለመቆጣጠር የተለያየ ደረጃ ያለው ገደብ ጥለዋል፡፡ በፀደይ ወራት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ወደ ነበረበት ደረጃ በፍጥነት እየተቃረብን ነው በማለት ባለሙያዎቹ ያስጠነቅቃሉ፡፡ ጥናቱ ወቅታዊ የሆነው የኮቪድ -19 ጥናት በመሆኑ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው ተብሎለታል፤ 86 ሺህ የሚጠጉ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉበት እና የመጨረሻዎቹ ምርመራዎች እሁድ የተካሄደበት ጥናት መሆኑን በመጠቆም፡፡ ጥናቱ እንዳሳየው ቫይረሱ በሁሉም የእድሜ ክልል እና በእያንዳንዱ የእንግሊዝ ግዛት እየጨመረ መሆኑን ያሳያል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ስርጭቱ ከፍተኛ ቢሆንም በደቡብ በኩል ቢሆን በፍጥነት እያደገ ነው፡፡ ከአጥኚዎቹ አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ስቲቨን ሪሌይ መረጃው መገኘት ሲጀምር እንዳዘኑ ገልፀው ""አሁን ያሉት እርምጃዎች በቂ አይደሉም"" ብለዋል ፡፡ ""ለውጥ መኖር አለበት። ፍጥነት በእውነቱ በጣም ፈጣን በመሆኑ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከገና በፊት ለውጥ ሊኖር ይገባል"" ብለዋል ፡፡ ህዝቡ በደንብ ህጎችን ማክበር አለበት ወይም መንግሥት ከባድ ገደቦችን መጣል አለበት ሲሉም ተከራክረዋል ፡፡ ""መረጃዎቹ በፍጥነት መወሰንን የሚሹ ናቸው"" ብለው ገልጸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54726762 +sports ማንቸስተር ሲቲ ከሊቨርፑል፡ ስለኃያላኑ ፍልሚያ ማወቅ የሚገባዎ "እሑድ አመሻሹን ማንቸስተር ሲቲ ከሊቨርፑል በኤቲሃድ ስታድዬም ተገናኝተው የውድድሩን ዘመኑን ትልቁን ፍልሚያ ያደርጋሉ። ጨዋታው ዋንጫው ወዴት ሊሄድ እንደሚችልም ጠቋሚ ነው። የፔፕ ጉዋርዲዮላ ቡድን በ73 ነጥብ ሊጉን ይመራል። ቀያዮቹ የዩርገን ክሎፕ ልጆች ደግሞ በአንድ ነጥብ ይከተላሉ። የዘንድሮው ፕሪሚዬር ሊግ ሊገባደድ ሰባት ከዛሬው ፍልሚያ በኋላ ሰባት ጨዋታዎች ይቀራሉ። ሊቨርፑል ያለፉትን 10 ጨዋታዎች አሸንፏል። ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ ካለፉት አምስት ጨዋታዎች አምስት ነጥብ ጥሏል። ሊቨርፑል ይህን ጨዋታ ከረታ ከጥቅምት አንድ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊጉን ይመራል። ሁለቱ ቡድኖች ባለፉት ስምንት የፕሪሚዬር ሊግ ዘመናት 10 ጨዋታ እየቀረ ተገናኝተው ሰባት ጊዜ የረታው ሁለተኛ ያለው ቡድን ነው። ካራባዎ ዋንጫን ያነሱት ሊቨርፑሎች አራት ዋንጫ በማንሳት ታሪክ ሊሠሩ ይችላሉ። ሲቲዎች ደግሞ ፕሪሚዬር ሊጉን፣ ቻምፒዮንስ ሊግና ኤፍ ኤ ዋንጫን ለማንሳት ይፋለማሉ። ዩርገን ክሎፕ ይህ ጨዋታ በጣም ወሳኝ እንደሆነ ነጋሪ እንደማያስፈልገው በጋዜጣዊ መግለጫቸው አውስተዋል። ጉዋርዲዮላ ደግሞ ሊቨርፑል በማጥቃት ሊበልጠን ቢችልም በብዙ ነገር ተመሳሳይነት አለን ሲሉ ተደምጠዋል። ሁለቱ ቡድኖች በዚህ የውድድር ዘመን 147 ጎሎች አስቆጥረዋል። ሊቨርፑል በሰባት ጎሎች በልጦ የመጀመሪያውን ሥፍራ ይዟል። የእግር ኳስ መረጃ ሰብሳቢው ኒዬልሰን ግሬስኖት ሲቲ ይህን ጨዋታ ከረታ ዋንጫውን የማንሳት ዕድሉ 86 በመቶ ከፍ ይላል፤ ሊቨርፑል ከረታ ደግሞ 68 በመቶ ተስፋ ይኖረዋል ይላል። ማንቸስተር ሲቲ ካይል ዎከርና ፊል ፎደንን በሙሉ አቋማቸው ሊያሰልፋቸው ይችላል። ወጣቱ ፎደን ሲቲ ከሊቨርፑል ባደረጋቸው ያለፉት ሶስት ጨዋታዎች ጎል ማስቆጠር ችሏል። ዛሬ አንድ ጎል ካከለ ከጄሚ ቫርዲ ቀጥሎ ቀያዮቹ ላይ በተከታታይ ያስቆጠረ ተጫዋች ይሆናል። ክሎፕ በሊቨርፑል በኩል አዲስ የተጎዳ ተጫዋች እንሌለ ገልጠዋል። የ14 ነጥብ ልዩነት የሃሰት ነበር ከፈረንጆቹ 2018/19 የውድድር ዘመን ጀምሮ ሁለቱ ቡድኖች 144 ጨዋታዎች አድርገው ሲቲ 338 ነጥብ ሲሰበስብ ሊቨርፑል ደግሞ 337 ይዟል። ባለፈው ጥር ሲቲ በኬቪን ደ ብራይን ጎል በርንሊ አንድ ለዜሮ ሲረታ ብዙዎች ዋንጫው ወደ ኤቲሃድ አመራ ብለው ነበር። በወቅቱ ማንቸስተር ሲቲዎች ከሊቨርፑል ጋር የነበራቸው የነጥብ ልዩነት 14 ነበር። ሊቨርፑል በዚህ ጊዜ ከቶተንሃም አቻ በመውጣት በሌይስተር በመረታት ቀጥሎ ከቼልሲ ነጥብ በመጋራት የዋንጫ ተስፋቸውን ያጨለሙ መሰሉ። ሲቲ በበኩሉ ከሳውዝሃምፕተንና ፓላስ አቻ ሲወጣ በቶተንሃም ተረታ። የ14 ነጥብ ልዩነት የት ገባ ተብለው የተጠየቁት ጉዋርዲዮላ ""ልዩነቱ የሃሰት ነበር"" ሲሉ መልሰዋል። ሊቨርፑል የትኛውም የእንግሊዝ ቡድን አድርጎት የማያውቀውን በአንድ ዓመት አራት ዋንጫ የመብላት ሕልማቸውን ለማሳካት ይፋለማሉ። በኤፍ ኤ ዋንጫ ድጋሚ ሊቨርፑልና ሲቲ በሚቀጥለው ቅዳሜ ይገናኛሉ። ይህ ማለት ከሁለቱ ቡድኖች አንዱ ኤፍ ኤን የማንሳት ሕልሙ ይከስማል ማለት ነው። ነገር ግን ለፔፕ ጉዋርዲዮላ ከምንም በላይ የቻምፒዬንስ ሊግ ዋንጫን ማንሳት ይቀድማል። ፔፕና ክሎፕ በጀርመን ቡንደስሊጋንና በፕሪሚዬር ሊጉ 22 ጊዜ ተገናኝተዋል። ዘጠኝ ጊዜ ክሎፕ ሲረቱ አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥተዋል። ሲቲ ባለፉት 11 ጨዋታዎች ሊቨርፑልን ገጥሞ ጎል ሳይቆጥር የወጣበት ጨዋታ የለም። ሁለቱ ኃያላን ቡድኖች ዛሬ አመሻሹን ድጋሚ ይገናኛሉ። ማን ይረታ ይሆን? ጊዜ ይፈታዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61056854 +health በሕንድ በኮቪድ-19 ፅኑ ህሙማን ክፍል በተነሳ እሳት ስምንት ሰዎች ሞቱ "በሕንድ ምዕራባዊ ከተማ አህሜዳባድ በሚገኝ የኮቪድ -19 ሆስፒታል ከፅኑ ህሙማን ክፍል በተነሳ እሳት ሳቢያ የስምንት ህሙማን ሕይወት ማለፉ ተገለፀ። የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ራጀሽ ብሃት ለቢቢሲ እንደተናገሩት እሳቱ የተነሳው አንድ የሆስፒታሉ ሰራተኛ የበሽታ መከላከያ መሳሪያ ባጋጠመ የኤሌክትሪክ ችግር ሳቢያ በእሳት በመያያዙ ነው ብለዋል። ሰራተኛዋ በድንጋጤ ወደ ፅኑ ሕሙማን ክፍል የገባች ሲሆን እሳቱም በዚያ መዛመቱን የገለፁት ባለሙያው፤ ይህንንም ተከትሎ አንድ የሆስፒታሉ ዳሬክተር በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ መጀመሩን አስረድተዋል። ባለሙያው አክለውም ምሽት 3፡30 ገደማ የተነሳው የእሳት አደጋው ከአንድ ሰዓት በኋላ በቁጥጥር ሥር መዋሉን እና በዚያው የሚገኙ 40 ህሙማንም ወደ ሌላ ክፍል መዛወራቸውን ገልፀዋል። ይህንን ተከትሎም እርሳቸውና የእሳትና ድንገተኛ ክፍል ቡድን ከህሙማኑ ጋር የቅርብ ንክክኪ ስለነበራቸው ወደ ለይቶ ማቆያ እንደሚገቡ ተናግረዋል። ዋና ከተማዋ አህሜዳባድ የሆነችው ጉጃራት ግዛት ሚኒስተር ሆነው ያገለገሉትና ጠቅላይ ሚኒስተር ናሬዳንድራ፤ በተፈጠረው አደጋ ማዘናቸውን ገልፀው ለተጎጂ ቤተሰቦች የመቋቋሚያ ድጋፍ እንደሚደረግ በትዊትር ገፃቸው አስፍረዋል። አሁን በሥራ ላይ ያሉት የግዛቷ ሚኒስተር ቪጃይ ሩፓኒ በበኩላቸው ሃዘናቸውን ገልፀው በአደጋው ላይ ምርምራ እንደሚደረግ ቃል ገብተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የተወሰኑት ተጎጂዎች ቤተሰቦች ""ሆስፒታሉ እሳት አደጋ ክፍል ለመጥራት ዘግይቶ ነበር"" በማለት አንዳንድ የተጎጂ ቤተሰቦች ስለ አደጋው እንዳልተነገራቸው ይከሳሉ። "" የሆስፒታሉ ሰራተኞች ምንም ዓይነት መረጃ አልሰጡንም። ���ንም እሳቱ እንዴት ሊነሳ እንደቻለ እና ምን እንደተፈጠረ የነገረን የለም"" ሲሉ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ የነበረውን ሁኔታ ተናግረዋል። ፖሊስ ለአደጋው ተጠያቂ የሆነውን አካል ለመለየት ሦስት ቀናት የሰጠ ሲሆን፤ አደጋውን አንደ ድንገተኛ አደጋ በመመዝገብ አንድ የሆስፒታሉን ዳይሬክተር በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53681457 +sports ለአውሮፓ የእግር ኳስ ከዋክብት ቅንጡ ድግስ የሚያዘጋጁት ሦስቱ ጓደኛሞች የጁቬንቱሱ አጥቂ ዱሳን ቭላሆቪች በዋትስአፕ ቁጥርዎ አርብ ደውሎ ለቅዳሜ የግል አውሮፕላን እፈልጋለሁ ብሎ ሲጠይቅ ያስቡት። ይህ የሦስቱ ጓደኛሞች የዕለተለት ኑሮ ነው። ሦስቱ ወጣት ጓደኛሞች ለአውሮፓ ኮከብና ሀብታም እግር ኳሰኞች ድግስ ማሰናዳት ነው ሥራቸው። ለቭላሆቪችና ጓደኞቹ አውሮፕላን አዘጋጅተው የድግስ ዓለም ወደምትባለው የስፔኗ ደሴት ኢቢዛ መሸኘት አለባቸው። የ26 ዓመቱ ኢማኑዔል፣ የ24 ዓመቱ ሚቼልና የ23 ዓመቱ ዋርድ ለእግር ከዋክብት ቅንጡ ድግስ የሚያሰናዳ ድርጅት አላቸው። አምስላክስ አውሮፓ ውስጥ ለታዋቂ እግር ኳሰ ተጫዋቾች ቅንጦት ከሚያመቻቹ ድርጅቶች መካከል ቀንደኛው ነው። ዓላማቸው አንድና አንድ ነው - የእግር ከዋክብቱ የሚጠይቅቱን ነገር ሁሉ ሟሟላት። 125 ሺህ ፓውንድ የሚያወጣ የእጅ ሰዓት? አሊያም 20 ሺህ ፓውንድ የሚጠይቅ ቦርሳ? ወይ ደግሞ 10 ሺህ ፓውንድ የተተመነለት አዲስ የጂም ጫማ? ምንም ችግር የለውም። ይህ ለሦስቱ ጓደኛሞቹ የሚያስጨንቅ ጉዳይ አይደለም። ሥራቸው ነውና። ጓደኛሞቹ ከሦስት ዓመት በፊት ነው መኖሪያቸው በሆነችው አምስተርዳም ሳሉ ነው ይህ ሐሳብ ብልጭ ያለላቸው። በወቅቱ ኢማኑዔል የጥሪ ማዕከል ሠራተኛ ነበር፤ ዋርድና ሚቼል ደግሞ ጂምናስቲክ አሠልጣኝ ነበሩ። ነገር ግን ሦስቱም በእግር ኳስ ፍቅር ያበዱ ናቸው። በዲዛይነር ለሚሰፉ አልባሳት ያላቸውም ፍቅር ለየት ያለ ነው። ጓደኛሞቹ አዲስና ብርቅዬ የሚባሉ የጂም ጫማዎችና አልባሳት የት እንደሚገኙ ጠንቅቀው ያውቃሉ። አንድ ማለዳ በዘመናይ ፋሽን አለባበሱ ለሚታወቀው ቱርካዊው የክንፍ ተጫዋች ቢላል ባሳሺኮግሉ የኢንስታግራም መልዕክት ይልኩለታል። መልዕክቱ እንዲህ ይላል “በኢንስታግራም ገፅህ ማስታወቂያ የምትሠራልን ከሆነ በጣም ውድ የሆነ ጫማ እናቀርብልሃለን።” ቢላል ተስማማ፤ ጓደኛሞቹም ቢዝነሳቸው ተመነደገ። ሌሎች ተጫዋቾች መግተልተል ጀመሩ። ስምምነቱ ተመሳሳይ ነው። እነሱ ጫማና አልባሳት ያቀርባሉ፤ ተጫዋቾቹ ደግሞ በማኅበራዊ ገፆቻቸው ያስተዋውቋቸዋል። ኔዘርላንድ ውስጥ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች አልፎ የጣሊያን ሴሪ አ ከዋክብት የመልዕክት ሳንዱቃቸውን ያንኳኩ ጀመር። አሌሳንድሮ ባስቶኒ፣ ፌዴሪኮ ኪዬዛ፣ ዌስሊ ፎፋና. . . ሌሎችም የአውሮፓ እግር ኳስ ከዋክብት መምጣት ያዙ። ከተጫዋቾቹ አልፎ የከዋክብቱ ሚስቶች አንድ ነገር ሲፈልጉ ለሦስቱ ጓደኛሞች ስልክ መምታት ጀመሩ። ኢማኑዔል፣ ዋርድና ሚቼል አሁን ከ100 በላይ ተጫዋቾችን በደንበኝነት ይዘዋል። ሦስቱ ባልንጀሮች ጫማና ልብስ ከማቅረብ አሊያም የፋሽን ምርቶችን ከማጋዘት ያለፈ ሥራ መሥራት ፈለጉ። “ለተጫዋቾቹ ሦስት ነገር ነው የምናቀርበው - ጊዜ፣ ዕውቀትና እምነት። የሚፈልጉትን የትኛውም ነገር በማቅረብ ጊዜያቸውን እንቆጥባለን” ይላል ኢማኑዔል። “ይህ ብቻ አይደለም፤ ምን ዓይነት ፋሽን ቢከተሉ እንደሚሻል ምክር እንሰጣለን። በእኛ እምነት እንዲኖራቸው እናደርጋለን።ከፋሽን ባለፈ የእረፍት ቀናቸውን የሚያሳይልፉበት ቦታ፣ የእጅ ሰዓት፣ ግል አውሮፕላን፣ ፓርቲ እንድናዘጋጅላቸው ይጠይቁን ጀመር።” በተለ�� በኮቪድ ወረርሽኝ ጊዜ ከቤታቸው መውጣት ስለማይችሉ የፈለጉትን ነገር የሚያርቡላቸው እነሱ ነበሩ። ጓደኛሞቹ ደንበኞቻቸውን ወደ ቅንጡዎቹ የእረፍት ጊዜ ማሳለፊያዎች ኢቢዛና ማያሚ ወስደው ይመልሳሉ። “ደንበኞቻችን [ከዋክብቱ] ትኩረታቸው ሜዳ ላይ ብቻ እንዲሆን ነው የምንፈልገው” ይላል ኢማን። ሦስቱ ሥራ ፈጣሪዎች አሁን የድሮ ሥራቸውን እርግፍ አድርገው ትተው ሰጥ ለጥ ብለው የእግር ኳስ ከዋክብትን ቅንጡ ሕይወት ያስተዳድራሉ። እርግጥ ነው ይህ አዲሱ ሕይወታቸው ብዙ አስገራሚ ነገር እንዲያዩም ምክንያት ሆኗቸዋል። “አንድ ተጫዋች ‘ለቫለንታይን ዴይ’ አበባ እንድናደርስለት ጠየቀን። ‘በእኛ ይሁንብህ’ ብለን አድራሻ እንዲልክልን ስንጠይቀው የአራት የተለያዩ ሴቶችን አድራሻ ላከልን።” አድራሻዎቹ በአራት የተለያዩ አገራት የሚገኙ ሴቶች ነበር። እነሱም ሥራቸውን በአግባቡ ከውነው የታዘዙትን አደረሱ፤ “ትዕዛዙን የሰጠን ተጫዋችም፣ አበባው ተላከላቸው ሴቶችም በጣም ተደስተው ነበር” ይላሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cv29zrr5znzo +politics ኢራቅ የአይ ኤስ የፋይናንስ ኃላፊን መያዟን ገለጸች "ኢራቅ ከድንበሯ ውጭ ባደረገችው ዘመቻ የጂሃዲስቱን እስላማዊ መንግሥት የፋይናንስ ኃላፊ መያዟን ገለጸች። ሳሚ ጃሲም አል-ጃቡሪ በኢራቅ ብሔራዊ የስለላ አገልግሎት ""ከሃገር ውጭ ውስብስብ በሆነ መንገድ"" በቁጥጥር ስር ውሏል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ አል-ካዲሚ ቦታውን ሳይገልጹ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። አክለውም ጃሲም ወይም ሐጂ ሐሚድ በመባል የሚታወቀው ግለሰብ በሟቹ አቡበከር አል-ባግዳዲ ሥር የአይኤስ ምክትል መሪ ሆኖ ያገለግል ነበር። አሜሪካ ግለሰቡ እንዲያዝ መረጃ ለሚሰጥ ሰው 5 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብታ ነበር። የኤፍቢአይ የሪዋርድስ ፎረ ጀስቲስ ድረ ገጽ በበኩሉ ""ለአይኤስ የሽብር ተግባራት ፋይናንስን በማስተዳደር ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል"" ብሏል። ቡድኑ እአአ በ2014 ሰፊ ግዛትን በኢራቅና በሶሪያ በተቆጣጠረበት ወቅት ""በሕገወጥ መንገድ ከነዳጅ፣ ከጋዝ፣ ከጥንታዊ ቅርሶች እና ከማዕድናት ሽያጭ የቡድኑን የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን"" ሲመራ ነበር ሲል ገልጿል። የኢራቃውያን ባለሥልጣናት የሳሚ ጃሲምን መያዝ አይኤስ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶበታል ይላሉ። የኢራቅ የደህንነት ሚዲያ ሴል እንዳለው ግለሰቡ እአአ በ 2019 ሶሪያ ውስጥ በተደበቀበት የአሜሪካ ወታደር የወሰደውን ጥቃት ተከትሎ ራሱን ያጠፋው ባግዳዲን ከተካው ከአዲሱ የአይኤስ መሪ አሚር መሐመድ ሰይድ አብዱል ራህማን አል ማውላ ቅርብ ሰው ነበር። ምንም እንኳን ጃሲም የት እንደተያዘ ካዲሚ ባይገልጹም አንድ ከፍተኛ የኢራቅ ወታደራዊ ምንጭ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ቱርክ መሆኑን ተናግረዋል። ስለጉዳዩ ከቱርክ ባለሥልጣናት የተሰጠ ምላሽ የለም። በፈረንጆቹ 2021 መጀመሪያ የኢራቅ መንግሥት ሌላውን ምክትል የአይኤስ መሪ ጃቢር ሳልማን ሳሌህ አል-ኢሳዊን መግደሉን አስታውቋል። የደቡባዊ ኢራቅ የአይኤስ መሪ ጃባር አሊ ፈያድን መግደሉን በተመሳሳይ ገልጿል። አይኤስ በአንድ ወቅት 88,000 ካሬ ኪ.ሜ ስፋት ያለው እና ከምሥራቅ ኢራቅ እስከ ምዕራብ ሶሪያ የሚደርሰውን ግዛት ተቆጣጥሮ አገዛዙን ወደ ስምንት ሚሊዮን በሚጠጉ ሰዎች ላይ ጥሎ ነበር። ቡድኑ እአአ በ 2017 በኢራቅ በእንዲሁም እአአ በ2018 በሶሪያ ሽንፈት ቢከናነብም በሺህዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች በሁለቱም ሃገሮች ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ይገመታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58880581 +politics በኦሮሞ ነጻነት ጦር ታጣቂዎች የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት በርካቶች ተገደሉ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሽዋ ዞን ተገደው የወጡ ሰላማ�� ዜጎች በተገኙበት የታጣቂዎች የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገደሉ። ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በምዕራብ ሸዋ በዞን በምትገኘው ጮቢ ወረዳ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ቡድን ያሰለጠናቸውን ታጣቂዎች እያስመረቀ ሳለ ነበር የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሙ የተነገረው። ቢቢሲ ከአካባቢው ነዋሪዎች እንደሰማው የአየር ጥቃቱ የተፈጸመው መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ሰላማዊ ዜጎች በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዲገኙ አስገድዶ የምርቃት ስነ-ስርዓቱ እየተካሄደ በሚገኝበት ወቅት ነው። በዚህ ጥቃት ሰላማዊ ዜጎችን እና የታጣቂ ቡድኑ አባላትን ጨምሮ እስከ 70 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ120 ያላነሱ መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ባለፉት ጥቂት ቀናት የፌደራሉ መንግሥት ታጣቂ ቡድኑ ላይ ያነጣጠር የአየር ጥቃቶችን በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ሲፈጽም ቆይቷል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ትናንት በትዊተር ገጻቸው ላይ ከጥቅምት 10/2015 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ ቢያንስ 6 የሰው አልባ አውሮፕለን ጥቃቶች ተፈጽመዋል ብለዋል። ቃል አቀባዩ ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኙ ሜታ ወልቂጤ እና ጮቢ ወረዳዎች የተገደሉ 'ሰላማዊ ሰዎች ከ150 በላይ ናቸው' ይላሉ። ኦዳ ተርቢ በጮቢ ጨምሮ 150 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ይበሉ እንጂ በወረዳው የአየር ጥቃቱ የተፈጸመው የታጣቂ ቡድኑ የምርቃት ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ሳለ ስለመሆኑም ይሁን በእነዚህ የአየር ጥቃቶች የተገደሉ የታጣቂ ቡድኑ አባላት ስለመኖራቸው ያሉት ነገር የለም። የአየር ጥቃቶቹን በተመለከተ ቢቢሲ የጮቢ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ የአካባቢው ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ መረጃ ካለው ተጠይቆ ተፈጽመዋል የተባሉ የአየር ጥቃቶችን በተመለከተ ምርመራ እያደረገ እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጿል። በምዕራብ ሸዋ ጮቢ ወረዳ ከተፈመው የአየር ጥቃት በኋላ የነበረን ሁኔታ የሚያሳይ ነው የተባለ ተንቀሳቃሽ ምስል በስፋት በማሕብራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር ቆይቷል። ቢቢሲ የዚህን ተንቀሳቃሽ ምስል ትክክለኛነት ባያረጋግጥም፤ በምስሉ ላይ ተመሳሳይ የሆነ የደንብ ልብስ የለበሱ በወጣትነት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ይታያሉ። የአከባቢው ነዋሪዎች ባለፉት ቀናት በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች በተፈጸሙት የአየር ጥቃቶች ዒላማ የተደረጉት የታጣቂ ቡድኑ አባላት ይሁን እንጂ ሰላማዊ ሰዎችም ሰለባ ስለመሆናቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ ወረዳ በነበረ ሌላ የአየር ጥቃት ሦስት ወንድሞቹን ያጣው ነዋሪ ለታጣቂዎች የሚሰነዘሩት የአየር ጥቃቶች የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፉ እንደሆነ ይናገራል። ነዋሪው እንደሚለው በአየር ጥቃቱ የተገደሉት ሦስቱ ወንድሞቹ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነበሩ። “ባለፈው ዕሮብ (ጥቅምት 9) ጎሮ ከተማ በተፈጸመው ጥቃት ነው የተገደሉት። . . . ጉዳት የደረሰባቸው ተዋጊዎች ቁጥራቸው ሲበዛ በቤት ውስጥ ተሸሽገው የነበሩ ተማሪዎችን 'ቁስለኞችን ያዙልን' በማለት ከቤት ማስወጣት ጀመሩ። ወንድሞቼ ልክ ከቤት እንደወጡ አየር መጣና ወንድሞቼን ጨረሰ” በማለት የነበረው ሁኔታ ያስረዳል። “ጫካ ያለው ኃይል ሕዝብ ውስጥ በዝቶ ስላለ ከአየር ላይ ሆነው እንዴት ለይተው ይመታሉ? በአንድ ላይ ነው የሚመቱት። ወንድሞቼ ብቻ አይደሉም። በርካታ ሕዝብ ነው ያለቀው።” ከምዕራብ ሸዋ ዞን ወረዳዎችን በተጨማሪ ባለፉት ቀናት የአየር ጥቃት ከተፈጸመባቸው አካባቢዎች መካከ��� ሌላኛው በምስራቅ ወለጋ ዞን ኑኑ ቁምባ ወረዳ አዳሬ ከተማ ነው። በከተማዋ አርብ እና እሁድ የአየር ጥቃቶች መፈጸማቸውን አንድ ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በሁለቱ ቀናት በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች መንግሥት ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን አባላት በተጨማሪ ከብቶች ሲያግዱ የነበሩ ታዳጊዎች መገደላቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። መንግሥት 'ሸኔ' የሚለውን እና እራሱን 'የኦሮሞ ነጻነት ጦር' ብሎ የሚጠራው ቡድን በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ በስፋት በመንቀሳቀስ ለክልሉ እና ለፌደራል መንግሥት ፈተና ሆኖ ቆይቷል። ታጣቂ ቡድኑ የሚንቀሳቀስባቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች የደኅንነት እጦት ያለባቸው ሆነዋል። ይህ ቡድን ለበርካታ ሰላማዊ ሰዎች ሕይወት መጥፋት ጥፋተኛ ሲደረግ ቆይቷል። እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራው ቡድን በጀምላ ግድያ፣ ዘረፋ፣ በንጹሃን እና በመንግሥት ባለሥልጣናት ግድያ፣ መንገድ በመዝጋት፣ የሕዝብ እና የመንግሥት ንብረት በማውደም፣ ሰዎችን አፍኖ በመውሰድ እና በሌሎች ወንጀሎችም ይከሰሳል። ይሁን እንጂ ታጣቂ ቡድኑ የሚቀርብበትን ክስ ሲያስተባብል ቆይቷል። የክልሉ እና የፌደራል መንግሥት ይህን ቡድን ለማጥፋት ቁርጠኛ መሆናቸውን እና በተለያዩ ጊዜ ዘመቻ መጀመራቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1vrl500dpo +politics በደቡብ ክልል ለወራት ታስረው የነበሩ ከአንድ ሺህ በላይ የትግራይ ተወላጆች መፈታታቸው ተነገረ "በደቡብ ክልል ሃድያ ዞን ሾኔ በተሰኘች ከተማ ለወራት ታስረው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች መፈታታቸውን ቢቢሲ ከተፈቱ ግለሰቦች ሰምቷል። ወደ 1 ሺህ 300 የሚሆኑ እስረኞች በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ በአውቶብስ ተጭነው አዲስ አበባ መድረሳቸውን መረሳና አይናለም የተሰኙና በስፍራው ታስረው እንደነበር የገለጹ የትግራይ ተወላጆች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለዘጠኝ ወራት ያህል ክስ ሳይመሰረትባቸውና የተጠረጠሩበት ወንጀል ሳይነገራቸው እንደቆዩ የሚናገሩት መረሳና አይናለም ሲለቀቁም ምንም መረጃ እንዳልተሰጣቸው ለቢቢሲ አስረድተዋል። ከትናንት በስቲያ ከነበሩበት እስር ቤት ውጡ እንደተባሉና በየእያንዳንዱ አውቶብስ ሁለት ፖሊሶች ተመድቦ እንደመጡና በአዲስ አበባ ቃሊቲ እንዳወረዷቸውም መረሳ ተናግሯል። ""የት እንደሚወስዱን፣ ወደ የት እንደምንሄድ አናውቅም። ብንጠይቅም፣ አናውቅም የሚል ምላሽ ተሰጠን"" ሲለ መረሳ ያስረዳል። በእስር ላይ ያሉ የትግራይ ተወላጆችን ቢቢሲ ከሰሞኑ ባናገራቸው ወቅት በብሔራቸው ምክንያት በቂ የምግብ፣ የውሃና የመድኃኒት አቅርቦት በሌለበት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ታስረናል ሲሉ ተናግረው ነበር። የደቡብ ክልል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን 'በብሔራችን ምክንያት ነው የታሰርነው' የሚለውን ክስ ያጣጣሉ ሲሆን በክልሉ ውስጥ በተገለፀው መጠን የታሰሩ ሰዎች መኖራቸውን እንደማያውቁም ተናግረው ነበር። ከእስር የተፈቱት አብዛኞቹ ከአፋር ክልል ተሳፍረው ወደ ሳዑዲ የሄዱና፣ በሳዑዲ እስርን ጨምሮ መጠነ ሰፊ እንግልትና ስቃይ ደርሶባቸው የመጡ ተመላሾች እንደሆኑ የሚናገረው መረሳ እስከ 12 ዓመት በእስር ተንገላትተው የመጡ እንደሚገኙበት ገልጿል። ሌሎቹ ደግሞ ከአዲስ አበባና ከአፋር ክልል እንዲሁም ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡ ይገኙበታል ብሏል። ቃሊቲ በወረዱበት ወቅት መረሳና ቤተሰብ ያላቸው ወደ የዘመዶቻቸው ቢሄዱም በርካቶች ማረፊያ እንዲሁም ብርም ስለሌላቸው መሄጃ ጠፍቶባቸው ነበር ብሏል። በስፍራው ላይ መንግሥት እንዲደጉማቸውና አቅም የለንም የሚሉ ሰዎች እንዲመዘገቡ በስፍራው ከነበሩት ባለድርሻ አካላት ጥያቄ ቢቀርብም ""ነገር ግን ወ��የት እንደሚወስዷቸው እርግጠኛ ስላልሆነ መመዝገብ አልፈለጉም። ወደ እስር ቤት ሊያስገቡን ይችላል"" በሚልም እንዳልተመዘገቡ ተናግሯል። በዚህ በአዲስ አበባም ""ቤተሰብ፣ ስልክ እንዲሁም ለዕለት ጉርስና መጠለያም ስለሌላቸው ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው የማያጠራጥር ነው"" ይላል። ከሳዑዲ ተመላሾች መካከል አንዱ የሆነው አይናለም በያዝነው ማክሰኞ ተፈትቶ ወደ አዲስ አበባ መምጣቱን ለቢቢሲ ገልጿል። ሐምሌ ወር ላይ ከሳዑዲ ተመላሾች አንዱ ሆኖ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ሲሆን ከሳምንት በኋላ ወደ ትውልድ አካባቢው ትግራይ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር በመጓዝ ላይ እያለ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል። ""በአፋር ክልል ሎጊያ እንደገባን ተይዘን እዛም ለአንድ ወር አሰሩን። መስከረም ወር ላይ ደግሞ ወደ ደቡብ ክልል ወስደውናል"" ብሏል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዋች ከሳዑዲ አረቢያ የመጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በዘፈቀደ እንደታሰሩ፣ እንግልት እንደደረሰባቸውና እንደተሰወሩም በያዝነው ዓመት ታህሳስ ወር ባወጣው ሪፖርቱ ማስታወቁ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከሳዑዲ አረቢያ የመጡ የትግራይ ተወላጆችን ወደ ትግራይ በሚወስዱ ኬላዎች እንዲሁም በአፋር ክልል ሰመራ አውሮፕላን ማረፊያ ይዘው ወደ አፋር ወይም ደቡብ ክልል በሚገኙ እስር ቤቶች አዘዋውረዋቸዋል ብሏል ድርጅቱ። በአዲስ አበባ ስራ ላይ የነበረው መረሳም እረፍት ወስዶ ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ትግራይ ሲሄድ በአፋር ክልል ሚሌ ኬላ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን ያስረዳል ። በኬላው ሶስት ሌሊት ካደሩ በኋላ እሱን ጨምሮ በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች በዘጠኝ መኪና ተጭነው ወደ ደቡብ ክልል ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ የእርሻ ምርምር ማዕከል ውስጥ መወሰዳቸውንና በዚያም ለወራት መታሰራቸውን ተናግሯል። በእስር ቤቱ ሴቶችና ህፃናት የነበሩ ሲሆን በአጠቃላይ 130ዎቹ ሴቶች እንደሆኑና በእስር ቤት ቆይታቸውም ሶስት ነፍሰ ጡሮች በእስር ቤት መገላገላቸውን ያስረዳል። ለባለፉት ዘጠኝ ወራት በከፍተኛ ስቃይ እንዳሳለፉ የሚናገረው መረሳ በርካታ ሴቶች መታመማቸውና የአዕምሮ ጤና እክል ያጋጠማቸውም እንዳሉና እጃቸውና እግራቸው ታስሮ የቆዩና የተሰቃዩም እንዳሉ ገልጿል። "" እጅግ በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ነበር። እስካሁን በህይወቴ ካየኋቸው የከፉ ነገሮች እሱን እዚህ ነው ያየሁ። ሰው ያለ ወንጀል ያለ ጥፋት በብሔሩ፣ በስም፣ በመታወቂያ እየተለየ መታሰር፣ መቆየትና መሰቃየቱ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው"" ብሏል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ወራት ላይ የትግራይ ኃይሎች በአማራና አፋር ክልሎች ያሉ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ አስቸኳይ ጊዜ መታወጁ ይታወሳል። የአስቸኳይ አዋጁንም ተከትሎ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ እስሮች መበራከታቸው ስጋት እንዳሳደረባቸው የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጠቅሰዋል። በርካቶች የሰብዓዊ መብቶች ደረጃን ባላሟሉ በተጨናነቁ ፖሊስ ጣቢያዎች መታሰራቸውን፣ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውንና ክስ እንዳልተመሰረተባቸው መግለጻቸው የሚታወስ ነው። ተቋሟቱ በብሔር ላይ ያነጣጠረ ከህግ ውጭ እስር ነው ቢሉም የኢትዮጵያ መንግሥት በወንጀል ተጠርጥረው ሊታሰሩ እንደሚችሉና ማንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ እስር እንደማይከናወን መግለጹ ይታወሳል። ለዘጠኝ ወራት በታሰሩበት ወቅት ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡና ክስም እንዳልተመሰረተባቸው የሚናገሩት እስረኞቹ ምላሽ የሚሰጥ አልነበረም ይላሉ። በአካባቢው የነበሩት ጠባቂዎች ""ከዚህ ዘወር ብለህ እንዳትንቀሳቀስ እኛ ስለ ወንጀላችሁ አናውቅም አትጠይቁን"" ይሏቸው እንደነበርና በተጨማሪም"" የፖለቲካ ስድብ፣ ማስፈራራት እንዲሁም መሳሪያ መደገንና ድብደባ ነበር"" ብሏል መረሳ። ""እንደዚህ እንወጣለን ብለን አልጠበቅንም። ሊያመልጡ ብለው በፖሊስ የተመቱም አሉ፣ የሞቱም አሉ፣ አብዛኛዎቻችን ተርፈናል። ይህንን ችግር አልፎ ለዚህ በቅተናል እግዚአብሔር ይመስገን"" ብሏል። ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ታስረው ስለሚገኙት ሰዎች ጉዳይ እየተከታተለ መሆኑን ቢቢሲ ከተቋሙ መረጃ ቢያገኝም ነገር ግን ዝርዝር መረጃ ማግኘት አልተቻለም። የደቡብ ክልል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ክሱ ሐሰት ነው በማለት ባለፈው ሳምንት ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61104122 +politics ሁለት አንጋፋ ፖለቲከኞች ለፕሬዝዳንትነት የተፋጠጡበት የኬንያ ምርጫ ወዴት ያመራል? ባለፈው ማክሰኞ ለብሔራዊ ምርጫ ድምጻቸውን የሰጡት ኬንያውን ውጤቱን በጉጉት እየተጠባበቁ ነው። የድምጽ ቆጠራው አሁንም እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ለፕሬዝዳንትንት የቀረቡት ዋነኛዎቹ ዕጩዎች በጠባብ የድምጽ ልዩነት እየተፎካከሩ ነው። በአፍሪካ ጠንካራ ምጣኔ ሀብት፣ የፍትሕ እና የምርጫ ሥርዓት እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ካላቸው ጥቂት አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኬንያ የሚካሄደው ምርጫ ውጤት ከአገሪቱ ባሻገር በአህጉሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ትኩረትን የሚያገኝ ነው። 22 ሚሊዮን የሚደርስ ሕዝብ በመራጭነት የተመዘገበበትና 14 ሚሊዮኑ ድምጹን በሰጠበት በዚህ ምርጫ ኬንያውያን ለፕሬዝዳንት፣ ለግዛቶች አስተዳዳሪዎች፣ የብሔራዊ እና የአካባቢያዊ ምክር ቤቶች አባላትን ለመምረጥ ድምጽ ሰጥተዋል። ከዚህ መካከል ከፍተኛ ትኩረትን የሳበው ግን አገሪቱን ለቀጣይ አምስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የሚደረገው ፉክክር ነው። ይህ ፉክክር በዋናነት በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት በሆኑት ዊሊያም ሩቶ እና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መካከል የሚደረገው ፉክክር ከባድ እንደሚሆን ቀድሞም ተጠብቆ ነበር። በሁለቱ ግዙፍ ፖለቲከኞች መካከል ያለው ፉክክር ግጭትን እንዳያስከትል የብዙዎች ስጋት ሲሆን፣ አስካሁን በነበረው ሁኔታ ግን ይህ ነው የሚባል የጎላ የፀጥታ ችግር በተፎካካሪዎቹ ደጋፊዎች መካከል አልተከሰተም። ነገር ግን ድምጽ ተሰጥቶ ቆጠራው ከተጀመረ ሁለተኛው ቀን ቢሆንም እስካሁን ሩቶ እና ራይላ ከመራጮች ባገኙት ድምጽ ግልጽ የበላይነት ማግኘት አልቻሉም። በምርጫው ድምጽ ከሰጡት መራጮች መካከል ወደ ግማሽ የሚሆነው ድምጽ የተቆጠረ ቢሆንም ልዩነታቸው ጠባብ የሚባል በመሆኑ ኬንያውያን ውጤቱን በጉጉት እየጠበቁ ነው። በርካታ ሚሊዮኖች ለቀጣዩ አምስት ዓመታት አገራቸውን የሚመራውን ፕሬዝዳንት መርጠው ውጤቱን እየተጠባበቁ ይገኛሉ። የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀ መንበርም ምርጫ ከተደረገበት ማክሰኞ ነሐሴ 03 እስከ ቀጣዮቹ ሰባት ቀናት ድረስም የምርጫውን ውጤት ማሳወቅ ይኖርባቸዋል። ነገር ግን በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ምን አይነት ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ ብለን እንጠብቅ? የመጀመሪያው በምርጫው ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት ግልጽ አሸናፊ ይኖራል። በዚህም አሸናፊው በቀጥታ ይፋ ይሆናል። ይህም ማለት ከተሰጠው አጠቃላይ ድምጽ ውስጥ ከግማሽ በላይ እና ቢያንስ ከ47ቱ የአገሪቱ ግዛቶች ውስጥ በ24ቱ ከተሰጠው ድምጽ 25 በመቶውን ማግኘቱን ካረጋገጠ ነው። ይህም አከራካሪ የማይሆን ሲሆን ሌሎቹም ዕጩ ተወዳዳሪዎች አምነው መቀበል አለባቸው። አሸናፊው በቀላሉ በቀጥታ የሚለይ ከሆነ፣ ውጤቱ ይፋ ከተደረገ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ባለው የመጀመሪ��ው ማክሰኞ መንበሩን ለመረከብ ቃለ መሃላ እና የሲመት ተግባር ይከናወናል። ሌላኛው ሁኔታ ደግሞ አሸናፊው በምርጫ ኮሚሽኑ ቢነገርም ውጤቱ በፍርድ ቤት አከራካሪ የሚሆኑበት ነው። ውጤቱ አከራካሪ ነው ከተባለ አሸናፊው በኮሚሽኑ ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ ቅሬታ አቅራቢዎች ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብ አለባቸው። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም አቤቱታው በቀረበ በ21 ቀናት ውስጥ ውሳኔ መስጠት ይኖርበታል። ፍርድ ቤቱ በዚህም ብያኔው ድሉን ያጸናል ወይም ውድቅ ያደርገዋል። የምርጫውን ውድቅ የሚያደርገውም ከሆነ በ60 ቀናት ውስጥ አዲስ ምርጫ እንዲደረግ ትዕዛዝ ያስተላልፋል። ሌላኛው ከዚህ የምርጫ ውጤት የሚጠበቀው ኮሚሽኑ አሸናፊውን ፕሬዝዳንትን ያውጃል፣ ነገር ግን ተሸናፊው ዕጩ ፕሬዝዳንት አሸንፌያለሁ ብሎ ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ፈቃደኛ በማይሆንበት ጊዜ ነው። በዚህ ሁኔታ የተመረጠው ፕሬዝዳንት ቃለ መሃላ እንዲፈጽም ይደረጋል። ሆኖም በዚህ ወቅት የተወሳሳሰቡ ነገሮች ሊከተሉ ይችላሉ። በአውሮፓውያኑ በ2007 ከተደረገው ምርጫ በኋላ እንደታየው የፖለቲካ እና የብሔር ውዝግብ ባስነሳው ብጥብጥ ወቅት በርካታ ሕይወትን የፈጠረው አይነት ቀውስም ሊያስከትል ይችላል። ሌላ ሊፈጠር የሚችለው ጉዳይ ደግሞ ግልፅ አሸናፊ አለመኖር ነው። ይህም ማለት ዕጩ ተወዳዳሪዎቹ ከግማሽ በላይ የመራጮችን ድምፅ ባያገኙና ቢያንስ ከ47 ክልሎች ውስጥ በ24ቱ ከተሰጡት ድምጾች 25 በመቶውን ማግኘት ካልቻሉ ነው። ይህ የሚፈጠር ከሆነ በሁለቱ ግንባር ቀደም ዕጩዎች መካከል ሁለተኛ ዙር ምርጫ መደረግ አለበት። ይህም ምርጫ የሚከናነው የመጀመሪያው ምርጫ ከተከናወነ ከ30 ቀናት በኋላ ይሆናል። ከአምስት ዓመት በፊት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የአሁኑ ዕጩ ራይላ ኦዲንጋ እንዲሁ እጅግ ተቀራራቢ በሆነ ድምጽ ሲፎካከሩ ቆይተው በመጨረሻ ላይ ሥልጣን ላይ የነበሩት ኬንያታ ማሸነፋቸው መታወጁ ይታወሳል። ነገር ግን ውጤቱ ላይ ጥያቄዎች ተነስተው በአንዳንድ ቦታዎችም የተቃዋሚው ፖለቲከኞች ደጋፊዎች ወደ ጎዳና በመውጣት ግጭቶች ተከስተው ነበር። አሸናፊው የበላይነቱን ሲገልጽ ተሸናፊው ግን ማጭበርበር ተፈጽሟል በሚል ውጤቱን ባለመቀበል አገሪቱ ውጥረት ውስጥ እንድትገባ ምክንያት ሆኖ ነበር። ፖለቲከኞቹም ተቃውሞውና ውጥረቱ ጋብ እንዲል ደጋፊዎቻቸውን ሲጠይቁ፣ በምርጫው አሸናፊ ነኝ ያሉት ተቃዋሚው ራይላ ደግሞ አቤቱታቸውን ወደ ፍርድ ቤት ይዘው ሄዱ። ኬንያ አሉኝ ብላ ከምትኮራባቸው አገራዊ ተቋሞቿ መካከል አንዱ የሆነው ጠቅላይ ፍርድ ቤቷ የቀረበለትን አቤቱታ የምርጫውን ያህል ጉጉትን በፈጠረ ሁኔታ ሲመለከት ቆይቶ ውሳኔ አሳለፈ። ፍርድ ቤቱ ከሁለቱም ወገኖች የቀረቡለትን አቤቱታዎችና ማስረጃዎችን ከመረመረ በኋላ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ፣ በሥልጣን ላይ ያለው ፕሬዝዳንት ያሸነፈበትን የምርጫ ውጤት ውድቅ በማድረግ ምርጫው እንዲደገም ወሰነ። አፍሪካም ዓለምም ውሳኔውን በአድናቆት ተመለከቱት፣ አሸናፊነታቸው ታወጆ የነበሩት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታም የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተቀብለው ለድጋሚ ምርጫ መዘጋጀታቸውን ጀምረው ነበር። በአጭር ጊዜ ውስጥ በድጋሚ በተደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሁን ሁለተኛ አምስት ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው አጠናቀው የሚሰናበቱት ኡሁሩ ኬንያታ በድጋሚ ማሸነፋቸው ተረጋገጠ። ነገር ግን ራይላ የሁለተኛው ዙር ሽንፈታቸውንም በፀጋ ባለመቀበል ሕጋዊው ፕሬዝዳንት ነኝ በማለት በይፋ ቃለ መሐላ አስከመፈጸም ደርሰው ነበር። ኋላ ላይ ግን ፕሬዝዳንቱ እና ተቃዋሚው ፖለቲከኛ ተቀራርበው ሰላም አውርደው አሁን አጋር አስከመሆን ደርሰዋል። በዚህ በአሁኑ ምርጫም ፕሬዝዳንት ኬንያታ ከምክትላቸው ሩቶ ይልቅ ለተቃዋሚው ራይላ ድጋፋቸውን በተደጋጋሚ ገልጸዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cgx0ew0ekz4o +business 2011፡ በፖለቲካና ምጣኔ ኃብት "የ2011 ዓ.ምን ስንብት አስታክከን የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ መልክዐ ምድር የኋሊት ስንገመግም ዓመቱ የስክነትም የውዥንብርም ነበር ማለት እንችላለን። የቀዳሚውን 2010 ዓ.ም ገሚስ ስልጣን ላይ ያሳለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና መንግሥታቸው ወራቱን ትንፋሽ ለመሰብሰብ እንኳን ፋታ ይሰጥ በማይመስል እንቅስቃሴ፤ በርካታ ስር ነቀል እርምጃዎችን አከታትለው ሲከውኑ ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ተችሯቸው ነበር። ሞቅታው ሊረግብ ግን ጊዜ አልፈጀበትም። • የንግድ ሽርክና ከኤርትራ ጋር? • ወሳኝ ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃዎች በ100 ቀናት • ""ለዋጋ ግሽበት የውጪ ምንዛሪ ማሻሻያው ምክንያት ነው"" ተከትሎ የመጣው እና አሁን ሊጠናቀቅ ጫፍ ላይ የደረሰው ዓመት ግን ገና በማለዳው ፈንጠዝያው ሰከን ብሎ መረር ያለ እውነታ የተተካበት ሆኗል። በአዲስ አበባ ዳርቻዎች እና በአጎራባች ቡራዩ አካባቢዎች በዓመቱ መባቻ የተከሰቱት የብሔር መልክ ያላቸው ግጭቶች እና ጥቃቶች፣ የዜጎች መፈናቀል፤ ወራት እየተተካኩ ሲሄዱ በበርካታ የአገሪቱ ስፍራዎች ተደጋግመው የዓመቱ አይነተኛ ምልክት ሆነዋል። በርካቶች ተገድለዋል፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፤ ታዳጊዎች ከትምህርታቸው ተነጥለዋል። መንግሥት ለነዚህ ችግሮች የሰጠው ምላሽ የቁጥር ሙግት ውስጥ ከመግባት አንስቶ፤ በተለይ በሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች እርቅን እስከማከናዎን በኋላም ተፈናቃዮችን ወደ መነሻ ቀየዎቻቸው እስከመመለስ የሚደርስ ነው። በክረምት መባቻ የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ከሚል መንግሥታቸው ሁሉንም ተፈናቃዮች የመመለስ ዕቅድ እንዳላቸው መናገራቸው ይታወሳል። ከዚህም በዘለለ ለሞት እና መፈናቀል ምክንያት ሆነዋል የተባሉ አካላትን ለፍርድ ማቅረብ መንግሥት አድርጌዋለሁ የሚለው ሌላኛው እርምጃ ነው። ፍርድ ቤቶች እንደቀደሙት ዓመታት ሁሉ በዚህም ዓመት የትኩረት ማዕከል ነበሩ። • ጥቁር ገበያውን ማሸግ መፍትሄ ይሆን? • አየር መንገድንና ቴሌን ለሽያጭ ለማቅረብ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው? ከአንድ ዓመት በፊት በመስቀል አደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ለመደገፍ በተጠራው ሰልፍ ላይ በተፈፀመና የሁለት ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈው ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ከተከሰሱ ሰዎች አንስቶ፤ የሃገርን ሐብት በመመዝበርና ያላግባብ በስልጣን በመባለግ ችሎት እስከተገተሩ ሰዎች ድረስ፤ በኋላም በባህር ዳር እና በአዲስ አበባ በተፈፀሙ የከፍተኛ ባለስልጣናት እና ወታደራዊ መኮንኖች ግድያዎች ጋር በተገናኘ የታሰሩ ተጠርጣሪዎች የችሎት ሒደቶች አትኩሮትን ይዘው ነበር። አንዳንድ ክሶችን የተደበቀ ፖለቲካዊ ዓላማ አላቸው ሲሉ ትችት የሚያሰሙ የመኖራቸውን ያህል የችሎት መጓተት እና የቀጠሮዎች መደጋገምን የቅድመ-ዐብይ ጊዜያትን ያስታውሳል ብለው የሚነቅፉም አሉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩን አስተዳደር ክፉኛ ከፈተኑ ጉዳዮች መካከል የአስተዳደራዊ አሃድ ጥያቄዎች ናቸው። ገንነው የተስተዋሉት ክልል የመሆን ጥያቄዎች ሲሆን የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄ የበርካቶችን ሞትና ጉዳት አስከትሏል። በወርሃ መጋቢት አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው 'የአዲስ ወግ' መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዋናው ቁምነገር ዋልታ የረገጡ አመለካከቶችን ወደ መካከል ማምጣት እንደሆነ ተናግረው ነበር። ያለፈው ዓመት ግን ተቃርኖዎች እምብዛም ሲለዝቡ አልተስተዋሉበትም። እርሳቸው በሚመሩት እና አገሪቷን እያስተዳደረ ባለው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ውስጥ ያለ ተቃርኖ ገሃድ የወጣበትም ዓመት ነው። በተለይም በግንባሩ ሁለቱ ቀዳሚ አባል ፓርቲዎች ህወሃት እና አዴፓ መካከል ያለው ግልጽ የሆነ የቃላት ጦርነት እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚያነሱት የፓርቲ ውህደት የሚጣጣሙ አይመስሉም። ፍትጊያው የጎንዮሽ በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ብቻ አልነበረም፤ ኢሕአዴግ ሙሉ በሚያስተዳድረው ፌደራል መንግሥት እና የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች በሚያስተዳድሯቸው የክልል መንግስታት ጭምርም እንጅ። ይህም ፌደራላዊው መንግሥት የአስፈፃሚነት አቅም አንሶታል ለሚሉ ትችቶች ተዳርጓል። 2011 የሰልፍ ዓመትም ጭምር ነበር። ሐኪሞች፣ መምህራን እንዲሁም ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎቻችን አልተመለሱም ያሉ በርካታ ዜጎች አደባባይ ወጥተዋል። በምጣኔ ኃብት ረገድ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት ጋር ተያይዞ ገዥው ፓርቲ ከዚህ ቀደም እከተለዋለሁ ይለው ከነበረው መንግሥታዊ ተሳትፎን የሚያበረታታ ፖሊሲ ማፈንገጥ መጀመሩ በተንታኞች ይወሳል። የተገባደደው ዓመት ይህን የፖሊሲ ለውጥ የሚያመላክቱ እርምጃዎች ሲወስዱ የተስተዋለበት ሆኖ አልፏል። በአንድ በኩል መንግሥት ለወትሮው አይነኬ መሆናቸውን ይናገርላቸው ከነበሩ የልማት ድርጅቶች እና ዘርፎች መካከል አንዳንዶቹን ለግል ባለሃብቶች ክፍት እንደሚያደርግ ካሳወቀ በኋላ በተሰናባቹ ዓመት የክንውን ዕቅዱን በተመለከተ በአንፃራዊነት የተሻለ መረጃ ሰጥቷል። በዚህም መሰረት ለምሳሌ የግል ባለሃብቶች ከግዙፉ ኢትዮቴሌኮም ድርሻ መገብየት እንደሚቻላቸው ይህም ተቋም በከፊልም ቢሆን ወደግል በመዛወር በቅድሚያ ከሚሰጣቸው መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል። ትርፋማው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለግል ባለሃብቶች ክፍት ይሆናል መባሉ ግን ከተለያዩ ተችዎች ነቀፌታን አስተናግዷል። በሌላ በኩል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የንግድ ክንውን ለማሳለጥ ያግዛሉ የተባሉ የሕግ እና የአሰራር ማዕቀፎችን ለመቅረጽ ብሎም ወደስራ ለመግባት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የተደረጉ ውይይቶችን ለሕዝብ ሲያሳውቅ ቆይቷል። ይሁንና እነዚህን መሰል ለግሉ ዘርፍ ይሰጥ የነበረውን አትኩሮት የሚጨምሩ፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ጨምሮ ዘርፉን የሚጋብዙ የፖሊሲ መስመሮች፣ በተለይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ይተገብሩትና ተተኪያቸው ሃይለማርያም ደሳለኝ አስቀጥለውት ነበር ከሚባለው ድሃ ተኮር የምጣኔ ኃብት ፖሊሲ ትሩፋቶች ላይ ውሃ የሚቸልስ ነው ሲሉ የሚተቹት አልታጡም። የመንግሥት የምጣኔ ኃብት ባለሟሎች በበኩላቸው ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት የምጣኔ ሃብት ቁመና የነበረውን ጎዳና ይዞ መቀጠል የማይቻል በመሆኑ ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗል ይላሉ። 2011 ዓ.ም እንደሌሎች የቅርብ ዓመታት ሁሉ የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት ኢትዮጵያን ሰንጎ የሸሸበትም ነበር። የዕጥረቱ ዳፋ በተለይ ከውጭ የሚመጡ ጥሬ ዕቃዎችን ለሚጠቀሙ አምራቾች እንዲሁም ቁሳቁሶችን ከውጭ በማስመጣት ላይ ለተሰማሩ ነጋዴዎችና የንግድ ድርጅቶች ፈተና አብዝቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በውጭ አገራት የሚገኙና ብዛታቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እና የኢትዮጵያ የዘር ግንድ ያላቸው የውጭ አገር ዜጎችን የምጣኔ ኃብቱን በማነቃቃት ረገድ ሚና እንዲጫወቱ ፍላጎት እንዳላቸው መገንዘብ አያዳግትም። ሆኖም ያሳለፍነው ዓመት በዚህ ረገድ ምን ያህል ስኬትን አስጨብጧቸዋል የሚለው ብዙም ግልፅ አይደለም። ለምሳሌ በወርሃ ግንቦት የግብርና ዘርፍ��� ከማዘመን ጋር በተያያዘ በተዘጋጀ አንድ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲናገሩ በውጭ አገራት ካሉ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ የዘር ግንድ ካላቸው የሌሎች አገራት ዜጎች በ'ኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ' በኩል ለመሰብሰብ የታሰበውን ያህል ገንዘብ ማግኘት እንዳልተቻለ አምነዋል። ተሰናባቹ ዓመት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ምርቃት ቢያስተናግድም፣ እንደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ያሉ ግዙፍ መንግሥታዊ ፕሮጀክቶች እምብዛም ከነበሩበት ፈቀቅ ሲሉ አልታዩም። ከዚያ ይልቅ በተለይ መዲናዋን አዲስ አበባን ማዕከል ያደረጉ ሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶች ይፋ ተደርገዋል።" https://www.bbc.com/amharic/49631096 +health ኮሮናቫይረስ፡ የአውሮፓ ሕብረት አገራት በዩኬ ላይ የጣሉትን የጉዞ እገዳ እንዲያነሱ አሳሰበ "የአውሮፓ ሕብረት 27 አባል አገራት ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር በተያያዘ የተጣሉ ገደቦችን በተመለከተ የተባበረ ምላሽ ለመስጠት እንደሚሞክሩ አስታወቁ። ይህን ያሉት በዩናይትድ ኪንግደም ከተገኘው አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ጋር ተያይዞ በርካታ አገራት የጉዞ እገዳ መጣላቸውን ተከትሎ ነው። ዛሬ ማክሰኞ የአውሮፓ ኮሚሽን፤ አገራት የጣሉትን የጉዞ እገዳ እንዲያነሱና ወሳኝ የሆኑ ጉዞዎችን እንዲጀምሩ ምክረ ሃሳብ ሰጥቷል። ይሁን እንጂ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት በድንበር ቁጥጥር ላይ የራሳቸውን ሕግ ለማስቀመጥ ነጻ በመሆናቸው በራሳቸው ፖሊሲዎችም ይህንን ማድረግ ሊቀጥሉ ይችላሉ። አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ከነባሩ በበለጠ ይበልጥ ተስፋፊ ሲሆን፤ የበለጠ ገዳይ ስለመሆኑ ግን የሚያመላክት ማስረጃ የለም። የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት ሁሉም በሚባል ደረጃ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚደረግ የጉዞ እገዳ እየጣሉ ነው። የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን፤ አባል አገራቱ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲያደርጉ ወይም ራሳቸውን እንዲያገሉ በማድረግ ሰዎች ወደ የሚኖሩበት አገራቸው እንዲሄዱ መፍቀድ አለባቸው ብሏል። ነገር ግን አስፈላጊ ያልሆነ ጉዞ ሊበረታታ እንደማይገባ ገልጿል። አክሎም እንደ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ያሉ መጓጓዣ አገልግሎት ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች ከተጣለው የጉዞ እገዳ እና አስገዳጅ ምርመራ ሊካተቱ አይገባም ብሏል። የተሰጡት ምክረ ሃሳቦችም ለሕብረቱ አምባሳደሮች የሚቀርብ ሲሆን አባል አገራቱ የሚጥሏቸውን ገደቦች ከግምት ያስገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ምንም እንኳን ይህ ምክረ ሃሳብ ቢሰጥም፤ አገራት በራሳቸው ፖሊሲዎች እቀባውን የመቀጠል እድላቸው ሰፊ መሆኑን የቢቢሲው ጋቪን ሊ ከብራስልስ ዘግቧል። በሌላ በኩል የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋዎች ኃላፊ ማይክ ርያን ""አዲሱ የቫይረስ ዝርያ የወረርሽኙ ዝግመተ ለውጥ መደበኛ አካል ነው። ከቁጥጥር ውጭም አልሆነም"" ብለዋል። ይህ ንግግራቸው ግን ከዚህ ቀደም የዩኬው የጤና ሚኒስትር ማት ሃንኮክ ከተናገሩት ጋር የሚቃረን ነው ተብሏል። በዩኬ እየተሰጠ ያለውን የፋይዘር ክትባት አምራች የሆነው የባዮንቴክ ተባባሪ መስራች ኡጉር ሳሂን በበኩላቸው ብሩህ ተስፋን ሰንቀዋል። ኡጉር ""በሳይንሳዊ መልኩ ከክትባቱ የሚገኘው የበሽታ መከላከያ ምላሽ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ሊቋቋም ይችላል"" ብለዋል። አክለውም ""ካስፈለገ አዲሱን ዝርያ የሚከላከል ክትባት በስድስት ሳምንታት ውስጥ ሊሰጥ ይችላል"" ሲሉም ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/55416249 +business የዋጋ ንረት ምንድን ነው? እንዴትስ ሊቀረፍ ይችላል? "ይህ ቃል በእንግሊዝኛው (ኢንፍሌሽን) የሚባለው ነው፡፡ አንዳንድ የምጣኔ ሀብት አዋቂዎች የዋጋ ግሽበት ይሉታል። ሌሎች ደግሞ የለም ""የዋጋ ግሽበት"" የሚለው ቃል ይበልጥ የሚወክለው የዋጋ መውረድን (ዲፍሌሽንን) እንጂ የዋጋ ንረትን (ኢንፍሌሽንን) አይደለም ብለው ይከራከራሉ። ለማንኛውም የአማርኛ ቃሉ የቱን በትክክል ይወክላል የሚለውን ክርክር ገታ አድርገን እንቀጥል። በዚህ ሐተታ የዋጋ ንረት ወይም የገንዘብ ግሽበትን (ኢንፍሌሽን) ለሚለው ጽንሰ ሐሳብ መጠቀማችንን ልብ ይሏል። ለመሆኑ የዋጋ ንረት ምንድነው? እንዴትስ ይፈጠራል? ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለተመሳሳይ አገልግሎት ብዙ ገንዘብ ከኪስዎ አውጥተው ለረዥም ሰዓት ይቆጥራሉ? በአንበሳ ድፍረት ገበያ ወጥተው ዋጋ ሲጠራ ግን ነብር እንዳየ ሰው ይበረግጋሉ? በፊት ሳይጨናነቁ ይገዙት የነበረ ነገር ሁሉ አሁን ደርሶ ከበረብዎ? ከቀይ ሽንኩርት እስከ ነጭ ሽንኩርት፣ ከቲማቲም እስከ ቃሪያ አልቀመስ አለ? የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አንድ አካል የሆነው የዓለም ሥራ/ሠራተኞች ድርጅት (ILO) እንደሚለው ከሆነ በዓለም ላይ ዓመታዊ የዋጋ ንረት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ጨምሯል። ባለፈው መጋቢት 3.7 ከመቶ ነበር። በዚህ ዓመት መጋቢት 9.2 በመቶ ተመዘገበ። ይህ ማለት የማንኛውም ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች እንዲሁም አገልግሎቶች ዋጋ በምድር ላይ በሚያስደነግጥ ፍጥነት አሻቅቧል። በቀላሉ እናስቀምጠው ካልን የዋጋ ንረት (ኢንፍሌሽን) የሚባለው ለአንድ ሸቀጥ ወይም አገልግሎት የሚከፈለው ዋጋ በጊዜ ሂደት እየተወደደ ሲመጣ ማለት ነው። በኪስዎ የያዙት ተመሳሳይ ገንዘብ ትናንትና ያገኙትን ተመሳሳይ አገልግሎት ሳይሰጥ ሲቀር ማለት ነው። የዋጋ ንረት ለምን ይከሰታል? ብለው ይጠይቁ ይሆናል። ነገሩ ትንሽ እንቆቅልሽ ነው። ሁለት ቀላል ምክንያቶችን ግን መጥቀስ ይቻላል። አንዱ የፍላጎት መናር የሚፈጥረው የዋጋ ንረት ነው። ይህ ሲባል ምን ማለት መሰላችሁ፤ ለአንድ አገልግሎት ብዙ ሰዎች ከፍተኛ ፍላጎት ሲያሳዩ የዋጋ ንረት ይፈጠራል። ለምሳሌ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው በሬዎች እየታረዱ ነገር ግን በጣም በርካታ ሕዝብ ድንገት በቁርጥ ሥጋ ፍቅር ቢወድቅ የዋጋ ንረት ይፈጠራል። እንዲህ ዓይነቱ ንረት የሚፈጠረው ለብዙ ጊዜ ሲንኮታኮት የቆየ ምጣኔ ሀብት እያገገመ ሲመጣ ነው። ሰዎች ኑሯቸው አስተማማኝ ሲሆን፣ ገቢያቸው ሲደረጅ፣ በመንግሥት ሥርዓቱና መዋቅሩ፣ በገበያ መነቃቃቱ እምነት ሲኖራቸው ገንዘብ ከመቆጠብ ይልቅ ገንዘብ ለማጥፋት ይበረታታሉ። ወደ ገበያ የሚወጣው ሰው ይበረክታል፡፡ ምግብ ቤቶች በበላተኛ ይጥለቀለቃሉ። በዚህ በፍላጎት መናር የሚከሰተው የዋጋ ንረት (ኢንፍሌሽን) ተገልጋዩ ማኅበረሰብ የሚፈጥረው ነው። ነጋዴዎች የፍላጎትን መጨመር በበቂ ለማስተናገድ ሲያቅታቸው ዋጋ ንረት ይኖራል። ነጋዴዎች ዋጋ ቢጨምሩም ተገልጋይ/ሸማች በቀላሉ ስለማይሸሽ አያሳስባቸውም፡፡ ሸማች በፍጹም አልደነግጥ ሲል ደጋግመው ዋጋ ይጨምራሉ። ይህ ዓይነቱ የዋጋ ንረት በሸማቾች ምቾትና መደላደል የሚፈጠር ሲሆን በእንግሊዝኛው (ፕራይስ ኢንፍሌሽን) ተብሎ ይጠራል። አዲስ ፍላጎት የፈጠረው አዲስ ዋጋ እንደማለት ነው። ሁለተኛው የዋጋ ንረት የሚፈጠረው የብዙ ነገሮች ዋጋ መጨመር ነው፡፡ ይህ በእንግዝኛ ኮስት ፑሽ ኢንፍሌሽን (Cost-Push Inflation) ተብሎ ይጠራል። ይህ ደግሞ እንዴት እንደሚፈጠር እንመልከት። አንድን አገልግሎት ወይም ምርት ለማሟላት ግብአቶች በየደረጃው ይወደዳሉ። ይህ በብዙ ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡ ለምሳሌ አንዱና ዋንኛው የነዳጅ ዋጋ መጨመር ነው። ነዳጅ ሲጨምር አብዛኛው አገልግሎትና ሸቀጥ አብሮ ይንራል። በአጭሩ አንድን ምርት ወደ ገበያ አጠናቆ ለማውጣት በሂደቱ ያሉ ሌሎች ግብአቶች ዋጋ በመጨመራቸው ምክንያት ያንን የዋጋ ጭማሪ ሸማቹ/ተገልጋዩ እንዲከፍለው ሲደረግ ማለት ነው። ቀድመን ባነሳነው የቁርጥ ሥጋ ምሳሌ እንቀጥል። በዚህ ሁኔታ የተፈጠረው የዋጋ ንረት የግድ የቁርጥ ሥጋ ተመጋቢው ቁጥር በመጨመሩ ምክንያት ሳይሆን በሂደቱ ላይ የሚከሰት ጭማሪ ያመጣው ነው የሚሆው። በዚህ ሁኔታ ሥጋ ወዳዱ ማኅበረሰብ ቁጥሩ አልጨመረም እንበል። ነገር ግን በሬውን ለመቀለብ የወጣ ወጪ፣ በሬውን ከሐረር አዲስ አበባ ጭኖ ለማምጣት የወጣ የአይሱዙ ዋጋ፣ በሬው ቄራ ሲታረድ የተከፈለው ዋጋ፣ የቁርጥ ቤት አስተናጋጆች ደመወዝ መጨመር፣ የአዋዜ መወደድ፣ ስል ቢላዎችን በብዛት ለመግዛት የዋጋ መጨመር ያስከትላል። በተጨማሪ ደግሞ የሥጋ ቤቱ ባለቤት የተከራየው ቤት መጨመር፣ ለምግብ ቤቱ የሚያወጣው የውሃና መብራት ዋጋ ወጪ ሲጨምር፣ የሥጋ ቤቱ ባለቤት ልጆች የሚማሩበት ውድ ትምህርት ቤት ዋጋ በእጥፍ ሲጨምር ወዘተ. . . የዋጋ ንረቱ እንዲከሰት ምክንያት ይሆናል ማለት ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመላው ዓለም እየተከሰተ ያለው የዋጋ ንረት/የገንዘብ ግሽበት ምክንያት ታዲያ ይህ ሰንሰለታማ ጣጣ ያመጣው ነው። በተለይ የኮቪድ ወረርሽኝ ያቀዛቀዘውን ምጣኔ ሃብት ለማንሰራራት እየደኸ በነበረበት ጊዜ ሩሲያ ዩክሬንን ወረረችና ነገሩ ከድጡ ወደ ማጡ ሆነ። ሩሲያና ዩክሬን ደግሞ በዓለም የገበያ ሰንሰለት እጅግ ቁልፍ የሚባሉ መጋቢ አገሮች ነበሩ። የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት አስደንጋጭ ከሚባሉት አገሮች የሚደመር ነው ብንልም፣ ከኢትዮጵያ የባሱ በርካታ አገራት አሉ። ነገሩ ያልነካው የለም፡፡ በብዙ አገራት የዋጋ ንረቱ በሁለት አሐዝ የሚሰላ መሆኑ ነው ጉድ እያስባለ ያለው። በቱርክ ለምሳሌ የዋጋ ንረቱ 70 ከመቶ ደርሷል፡፡ በአርጀንቲና 51 በመቶ፣ በስሪላንካ 30 በመቶ ነው። የስሪላንካ ሕዝብ ነገሩ አንገሽግሾት አደባባይ ወጥቷል፡፡ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርም በሕዝብ ተቃውሞ ሥልጣናቸውን ለቀዋል። በኢራንም ተመሳሳይ ተቃውሞ ተቀስቅሶ የነበረ ቢሆንም አሁን በረድ ብሏል። የቴህራን መንግሥት ያመነው ንረቱ 40 በመቶ መሆኑን ነው፡፡ ነገር ግን እውነታው ከ50 በመቶ በላይ መድረሱ ነው። ለዋጋ ንረትም ሌላ ንረት አለው። አንዳንድ ጊዜ የዋጋ ንረት በራሱ ሊያብጥ ይችላል፡፡ ይህ የሚሆነው ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ሲሆኑ ነው። ከፍተኛ የዋጋ ንረት የምንለው የአንድ አገር የገንዘብ አቅም ጨርሶ ሲንኮታኮት ነው። ይህ ነገር እዚህ በአህጉራችን ዚምባብዌ ተከስቶ ያውቃል። በመካከለኛው ምሥራቅ ደግሞ በሊባኖስ እንዲሁም በደቡብ አሜሪካ በቬንዝዌላ ውስጥ ተከስቶ ነበር። የአገሬው ገንዘብ ከወረቀት እኩል ወደ መሆን ሲቃረብ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ወይም (ሃይፐር ኢንፍሌሽን) ይባላል። በተጋነነ ምሳሌ ለማስረዳት የአገሬውን ብር በጆንያ ይዞ ሱቅ ሄዶ አንድ ኪሎ ስኳር ገዝቶ የመመለስ ዓይነት። ለምሳሌ ስንዴን እንውሰድ። ዩክሬንና ሩሲያ የዓለም ዋነኛ አምራቾችና ሻጮች ናቸው። ዓለምን ስንዴ የሚያበሉት ሁለቱ አገሮች ነበሩ። ሁለቱ አገሮች ጦርነት ገጠሙ። ከእነርሱ እየገዙ ሕዝባቸውን የሚቀልቡ አገራት በሙሉ ችግር ውስጥ ገቡ። እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ገዝተው ለሌሎች የሚሸጡም ችግር ውስጥ ወደቁ። ዘይትም ተመሳሳይ ችግር ነው የገጠመው። ዋንኛ አምራቾቹ እነ ኢንዶኔዥያና ማሌዥያ ዘይት ቅድሚያ ለሕዝባችን ብለው የወጪ ንግድ ላይ ዕቀባ አስቀመጡ። በዚህ የተነሳ ሸማች አገራት ለከፍተኛ ችግር ተዳረጉ። አሁን የዋጋ ንረቱን ምንድነው የፈጠረው? ዓለም ከምንገምተው በላይ በንግድ ሰንሰለት የተሳሰረ ነው። ለምሳሌ ኮቪድ ወረርሽኝና ምጣኔ ሃብትን ምን አገናኛቸው? ልትሉ ትችሉ ይሆናል። ሁሉ ነገር የተሳሰረ ነው ያልነው ለዚህ ነው። እንዴት? ለምሳሌ ኮቪድ የእንቅስቃሴ ገደብ አስከተለ፤ ላብ አደር ፋብሪካ አልሄደም��፡ ምርት አልተመረተም። ፋብሪካው ገቢ ቀነሰበት፤ ሠራተኛው ሥራውን አጣ፡፡ ሸማች ምርት አልደርስ አለው። በኮቪድ የተነሳ ዕዳቸውን በቱሪዝም ገቢ የሚከፍሉ አገራት ጭንቅ ውስጥ ገቡ። አምራች አገራት በበቂ ማምረት አቆሙ። አንድ ቻይና የምትመረት ብሎን በወቅቱና በጊዜው ተመርታ ወደ አዲስ አበባ አለመድረሷ አንድ ሙሉ ፋብሪካን ልታዘጋ ትችላለች። የዚያ ፋብሪካ መዘጋት፣ ሺህ ሠራተኛን ሊያፈናቅል ይችላል። የዚያች ብሎን ነገር በቻይናና በአዲስ አበባ ብቻ አያበቃም፡፡ ይህን ሐተታ ያረዝመዋል እንጂ ጉዳዩ ቢጻፍ ዓለምን ያዳርሳል። የዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ከምናስበው በላይ የተሳሰረ ነው የምንለው ለዚህ ነው። በአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ በርካታ ቦታዎች በድርቅ ተመተዋል። በጦርነቱ የተነሳ የነዳጅ ዋጋ ንሯል። ነዳጅ ሲንር የሁሉንም ቁሳቁስ ዋጋ አብሮ ያነዳል፡፡ የኮቪድ ጠባሳ ቀላል አይደለም። የሠራተኞች መመናመን በጋዝ፣ በምግብና በመኪና ዋጋ ላይ ከባድ ምት አሳርፏል። በዩክሬን ጦርነት የተነሳ በስንዴ፣ በማዳበሪያ፣ በጋዝ እንዲሁም በነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ቡጢውን አሳርፏል። ጋዝና ነዳጅ በሳንቲም ሲጨምሩ ፋብሪካዎች ሸብ ረብ ይላሉ። ወጪያቸውን ለማካካስ በትንንሽ ምርቶቻቸው ላይ ሁሉ ትንንሽ ዋጋ ይጨምራሉ። ትንንሹ ጭማሪ በየሰንሰለቱ ትንንሽ እየተጨመረበት ይሄዳል። በመጨረሻ ጭማሪው የእያንዳንዱን ሸማች ቤት ያንኳኳል። ደግሞ አንርሳ፤ ነጋዴው ሸማች ነው። ሸማችም ነጋዴ ነው። ከዚህ ሰንሰለት የሚወጣ የለም። ሻይ ስንጠጣ ሸማች ነን። ሻይ ቅጠል ስንተክል ነጋዴ ነን። እሽክርክሪቱ ከምንገምተው በላይ አስገራሚ ነው። በየዘመኑ ይህ የዋጋ ንረት ይከሰታል። የዘንድሮስ የከፋ ነው ሲባል ሌላ የከፋ ይመጣል። አገሮች ይህን የሚቋቋሙበት አንድ ሁነኛ መላ የላቸውም። ነገሩ ከምንገምተው በላይ ውስብስብ ስለሆነ። ለዚህም ነው የምጣኔ ሃብታ አዋቂዎች ቀጥተኛ መልስ መስጠት የሚከብዳቸው። ሆኖም ግን ከችግሩ መውጣት የሚቻለው አንዱ መንገድ ምርትን በመጨመር ነው። እርግጥ ነው ድሃ አገራት መርፌን ሳይቀር ከውጭ ስለሚያስገቡ፣ ከዚህ የዋጋ ንረት ለመውጣት ፍዳቸውን ማየታቸው የሚጠበቅ ነው። ትክክለኛ የማክሮና የማይክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲን በመከተል ህመሙን ማሰታገስ ይችላሉ። ምጣኔ ሃብት ጽንሰ ሐሳቦች ሙልጭልጭ ናቸው። ሽቅብ የተቆለለ መጽሐፍ ማለት ናቸው። አንዱ ሲነካ ሌላው ሊፈርስ ይችላል። የየዋጋ ንረትን ለማስታገስ የሚወሰድ እርምጃ ሥራ አጥነትን ሊፈጥር ይችላል። የወለድ ምጣኔ መጨመር ወይም መቀነስ፣ አንዳች የጎንዮሽ ጉዳትን ያመጣል። የምጣኔ ሃብት ሳይንስ እንደ መድኃኒት ነው። ያለ ጎንዮሽ ጉዳት አይፈውስም፣ አይፈወስም ይላሉ ባለሙያዎች። አንዳንዶቹ ችግሮች የዓለም የገበያ ትስስር የሚፈጥራቸው በመሆናቸው ከአንድ አገር አቅም በላይ ይሆናሉ። አሁን የተፈጠሩት ሁኔታዎችም በብዛት ዓለም አቀፋዊ መልክ ያላቸው ናቸው። ይሁንና የዋጋ ንረት ብሔራዊ ባንክና መንግሥታት በሚወስዷቸው የንዑስ እና ጥቅል ምጣኔ ሃብታዊ እርምቶች (Micro/Macroeconomics) ሊሻሻል ይችላል። ይህም ለምሳሌ በወለድ ምጣኔ ማስተካከያ ሊገለጽ ይችላል። መንግሥት የሚያካሄዳቸውን መጠነ ሰፊና ግዙፍ መሠረተ ልማቶች ጋብ በማድረግም ሊቃለል ይችላል። ይህን ማድረግ በሌላ አንጻር ሥራ አጥነትን ሊያባብስ ይችል ይሆናል። የወለድ ምጣኔ ከፍ መደረግ ደግሞ የገበያ ፍላጎትን ይቀንሳል። ይህም የኢኮኖሚ ዕድገቱን ዘገምተኛ ያደርገዋል፤ ሆኖም የዋጋ ንረትን አደብ ያስገዛዋል ይላሉ አዋቂዎች። በገበያው ውስጥ እየተሸከረከረ ያለው ገንዘብን መሰብሰብ፣ የትርፍ ግብርን መጨመርም ���ንዳንድ ጊዜ የዋጋ ንረትን ሊያረግብ ይችላል የሚሉ አሉ። መፍትሄውን መጠቆም ስለ ጉዳዩ መጣጥፍ እንደመጻፍ ቀላል ስላልሆነ በዚሁ ብንገታውስ?" https://www.bbc.com/amharic/articles/c80pxpr49neo +sports ኪፕቾጌ በቶኪዮ የኦሎምፒክ ማራቶን ሻምፒዮንነቱን አስጠበቀ "ኬንያዊው አትሌት ኢሉይድ ኪፕቾጌ በተከታታይ የማራቶን ኦሎምፒክን በማሸነፍ ሻምፒዮንነቱን አስጠብቋል። በአውሮፓውያኑ 1980 የኦሎምፒክ ሻምፒዮንነቱን ያስጠበቀውን ሌላኛውን የአገሩን አትሌትም ተክቷል ተብሏል። በተከታታይ የኦሎምፒክ ማራቶን ውድድሮችን በማሸነፍ የአለማችን ሶስተኛው አትሌት ኪፕቾጌ ውድድሩን በሁለት ሰዓት ከስምንት ደቂቃዎች ከ38 ሰኮንድ አጠናቋል። በተከታታይ የኦሎምፒክ ማራቶን በማሸነፍ ከታሪክ መዝገብ ስሙ የሰፈረው ኢትዯጵያዊው አበበ ቢቂላ ነው። በአለማችን ላይ ታላቁ የማራቶን ሯጭነትን ስፍራ ያገኘው የ36 አመቱ ኪፕቾጌ ከኔዘርላንዱ አትሌት አብዲ ናጌዬ በአንድ ደቂቃ ከ 20 ሰኮንድ ቀድሞም ነው ውድድሩን ያጠናቀቀው። በዚህ ውድድር ላይ ሶስተኛ ሆኖ ውድድሩን ያጠናቀቀው ቤልጂየማዊው በሽር አብዲ ነው። ኢትዮጵያን ወክለው በርቀቱ የተወዳደሩት አትሌቶቻችን ውድድራቸው ለማቋረጥ ተገደዋል። የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነው ኪፕቾጌ ከውድድሩ በኋላም "" ለሁለተኛ ጊዜ በተከታታይ የማራቶን ውድድር በማሸነፍ ራዕዩን ያስፈፀምኩኝ ይመስለኛል። ቀጣዩን ትውልድ አነሳሳለሁ ብየም ተስፋ አደርጋለሁ"" በማለት ተናግሯል። ""በዚህ ሁሉ ውዥንብር ውስጥ ሆኖ የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሊከናወን ችሏል። ይሄ ትልቅ ነገር ነው። ተስፋ አለ ማለት ነው። ወደ መደበኛ ህይወት ለመመለስ በትክክለኛው ጎዳና ላይ ነን ማለት ነው"" በማለት አትሌቱ ለቢቢሲ ስፖርት ተናግሯል። አክሎም "" ወደተለመደው ህይወታችን ለመመለስ መንገዱን ጀምረናል ይሄም ነው የኦሎምፒክ ትርጉሙ"" ብሏል። ""የሻምፒዮን ማዕረጌን ማስጠበቄና ለቀጣዩም ትውልድ በማሳየቴ ደስተኛ ነኝ። ስፖርቱን አንድ ሰው አክብሮ በስርዓት መቀጠል ከተቻለ ህልማቸውን ዕውን ማድረግ ይቻላል"" በማለትም ምክሩን አስተላልፏል። ከሁለት ሰዓት በታች በመሮጥ አለምን ላስደመመው አትሌት የቶኪዮ አራተኛ የኦሎምፒክ ሜዳልያው ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-58134926 +health ኮሮናቫይረስ፡ በአውስትራሊያ የተከሰተው አዲሱ ዙር ወረርሽኝ ከለይቶ ማቆያ ሆቴሎች ጋር የተገናኘ ነው ተባለ በአውስትራሊያዋ ከተማ ቪክቶሪያ የተከሰተው አዲሱ ዙር ወረርሽኝ ከለይቶ ማቆያ ሆቴሎች ጋር የተያያዘ መሆኑ ተገልጿል። ከሌላ አገራት የተመለሱ መንገደኞች ራሳቸውን ለይተው ባቆዩባቸው ሆቴሎች ወረርሽኙ መነሳቱም በምርመራ ተጣርቷል። በዚህ ምርመራ እንደተገኘው የሆቴሉ አጠቃላይ ሰራተኞችም ያልተገባ ስልጠና ወስደዋል ተብሏል። የአውስትራሊያ ሚዲያ እንደዘገበው የሆቴሉ ጠባቂዎች ጭምብልም ሆነ ሌሎች የመከላከያ ቁሳቁሶችን ማድረግ አስፈላጊ አይደለም፤ አካላዊ ርቀታችሁን እስከጠበቃችሁ ድረስ የሚል ምክር ተሰጥቷቸዋል። ይህንንም ተከትሎ ቪክቶሪያ ላይ አዲስ ዙር ወረርሽኝ ተከስቷል፤ ከተማው እንቅስቃሴዋ እንዲታገድ ትዕዛዝ ተላልፏል። በሌላኛዋ ከተማ ሜልቦርን እንዲሁም ጥብቅ የተባለ የእንቅስቃሴ ገደብ ለስምንት ሳምንታት ተጥሎባታል። በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በቪክቶሪያ 282 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 25ቱ ሞዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮም ከፍተኛ እንደሆነም ተገልጿል። መጋቢት መጨረሻ ላይ የአውስትራሊያ ፌደራል መንግሥት በሌላ አገራት የሚኖሩ ዜጎቹ ሲመለሱ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባት አለባቸው የሚል ውሳኔን አስተላልፏል። ይህንንም ተግባራዊነት የሚያስፈፅሙት የተለያዩ ከ��ማ አስተዳዳሪዎች ናቸው። በሜልቦርን የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ቤን ሃውደን እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት የተከሰተው አዲሱ ዙር ወረርሽኝ ውስጥ 99 በመቶው ከውጭ አገራት ከመጡ መንገደኞች ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል። ስለ መንገደኞቹ ማንነትም ሆነ የትኞቹ ሆቴሎች እንደሆኑ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠም። ምርመራው ሆቴሎች ለይቶ ማቆያዎቻቸውን እንዴት እያስተዳደሩ እንደነበርም በምርመራው በጥልቀት እየታየ ነው ተብሏል፤ ይህም ለወደፊቱ ለይቶ ማቆያዎች በማሻሻያነት ግብአት እንዲሆን ነው። ለይቶ ማቆያዎቹ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን መግታት ሳይሆን የበለጠ ማስፋፊያ ሆነዋልም ተብሏል። https://www.bbc.com/amharic/news-53798545 +politics የቱርኩ ፕሬዘዳንት ኤርዶዋን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይን እንኳን ደስ አለዎት አሉ "የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ማስተላለፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በማኅበራዊ ገጾቹ ያወጣው ጽሑፍ እንደሚለው፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በአገር መሪነት በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ኤርዶዋን አስተላልፈዋል። በተጨማሪም የጠቅላይ ሚንስትሩ የሥልጣን ዘመን ""ለኢትዮጵያ እና ለሕዝቧ ብልፅግና የሚያመጣ"" እንዲሆን መመኘታቸው ተገልጿል። በኢትዮጵያ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ከተሰማሩ እና ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ካፈሰሱ መካከል የቱርክ ዜጎች በዋነኛነት ይጠቀሳሉ። በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም የሰሜኑ ጦርነት ከተነሳ ወዲህ ስማቸው በተደጋጋገሚ ከሚነሳ አገሮች መካከል ቱርክ ትገኝበታለች። ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የአመራር ዘመን የቱርክ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት ይጎለብታል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አትቷል። ""እስካሁን የዘለቀው በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ወዳጅነት እና ትብብር ከዚህ በኋላም እንደሚቀጥል ሙሉ እምነት አለኝ"" ማለታቸውንም አስታውቋል። በ2013 ዓ. ም. ነሐሴ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ወደ ቱርክ አቅንተው ከፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ጋር መገናኘታቸው ይታወሳል። በምጣኔ ሀብት እና በሌሎችም ዘርፎች ሁለቱ አገራት ለመደጋገፍ ስምምነት መፈራረማቸውም አይዘነጋም። በወቅቱ ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ከመጠየቃቸው በተጨማሪ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል አሸማጋይ ለመሆን እንደሚሹም ተናግረው ነበር። ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ወደ ቱርክ ያደረጉትን ጉዞ ""የተሳካ"" ሲሉ ኤርዶዋን እንደገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር መረጃ ይጠቁማል። በተጨማሪም የጠቅላይ ሚንስትሩ ጉብኝት ""በሁለቱ አገሮች መካከል የዘለቀውን ዲፕሎማሲያዊ ትስስር 125ኛ ዓመት ክብረ በዓል ያደመቀ"" ሲሉ ገልጸውታል ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59052196 +business የኬንያ አየር መንገድ በታሪኩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ ደረሰበት "ግዙፍ ከሚባሉት የአፍሪካ አየር መንገዶች መካከል አንዱ የሆነው የኬንያ አየር መንገድ በታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን ኪሳራ እንዳጋጠመው ተነገረ። ምንም እንኳን ለበርካታ ዓመታት በኪሳራ ውስጥ ሆኖ የአገሩን ስም ሲያስጠራ የቆየው የኬንያ አየር መንገድ፤ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ከፍተኛ የተባለለትን 332 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ተመዝግቦበታል። የኬንያ አየር መንገድ ቀደም ባለው ዓመትም የ118 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ የገጠመው ሲሆን የአሁኑ ግን እጅግ ከፍተኛው ነው ተብሏል። ያጋጠመው ኪሳራ ከ2019 የፈረንጆቹ ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ179 በመቶ ሲያሻቅብ፤ ለኪሳራ በምክንያትነት የተጠቀሰው በኮቪድ-19 ምክንያት ዓለም አቀፍ በረራዎች እንዲቆሙ መደረጋቸ��� ነው። የኬንያ አየር መንገድ እንዳለው በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተጓዦች ቁጥር ወትሮ ከነበረው በ65.7 በመቶ ሲቀንስ ይህም የ473 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አሳጥቶታል። የኬንያ አየር መንገድ ሊቀመንበር ማይክል ጆሴፍ ""የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ማንም የገመተው አልነበረም፤ በአየር ትራንስፖርት ዘርፉ ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖም ለመጪዎቹ ሁለትና ሦስት ዓመታት ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል"" ሲሉ ተናግረዋል። ቀደም ሲል በነበሩት ዓመታት ካጋጠመው ኪሳራ ለመውጣት ሲጥር ለነበረው አየር መንገድ ያለፈው ዓመት ኪሳራ ከባድ ጉዳትን አስከትሎበታል ተብሏል። ሊቀመንበሩ ጨምረውም የአየር መንገዱ የወደፊቱ ሁኔታ አሁንም ተስፋ ሰጪ አይደለም ያሉ ሲሆን ስለዚህም ከገጠማቸውን ከባድ ፈተና ለመውጣት የሚያስችል አማራጭ በመፈለግ ጥረት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ አየር መንገዱ ኪሳራውን ለመቀነስ ሲል ባለፈው የፈረንጆች ዓመት 650 ሠራተኞቹን የቀነሰ ሲሆን በተቀሩት ሠራተኞቹ ላይ ደግሞ የደሞዝ ቅነሳ አድርጓል። በተጨማሪም የተወሰኑ ንብረቶቹን የሸጠ ሲሆን ለመንገደኞች አገልግሎት ይውሉ የነበሩ አንዳንድ አውሮፕላኖቹን ደግሞ ወደጭነት ማጓጓዣነት ቀይሯቸዋል። ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር እንደተነበየው በኮሮናቫይረስ ምክንያት በተከሰተው የአየር ትራንስፖርት መስተጓጎል ምክንያት የአፍሪካ አየር መንገዶች አስከ 6 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ኪሳራ ሊገጥማቸው ይችላል። በዚህም ሳቢያ በዘርፉ ተሰማርተው የነበሩ 172 ሺህ ያህል ሰዎች የሥራ ዕድል ችግር ይገጥማቸዋል ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56506558 +sports በክፍያ ምክንያት አኩርፎ የነበረው የካናዳ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ልምምድ ጀመረ "የካናዳ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ከፓናማ አቻው ጋር የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ ሰርዟል። በዚህም ሳያበቃ ""እንደውም ልምምድ አናደርግም"" ሲል አምጿል። ነገሩ ወዲህ ነው። የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ለዓለም ዋንጫ በመድረሳቸው የሚሰጣቸው ገንዘብ እንዴት ነው የሚከፈለን በሚለው ከእግር ኳስ አስተዳዳሪው አካል ጋር ሊስማሙ አልቻሉም። አሁን ግን ""ጥያቄዎቻችን ባይመለሱም"" ወደ ልምምድ እንመለሳለን ብለዋል። ተጫዋቾቹ የካናዳ እግር ኳስ አስተዳዳሪ የሆነው ካናዳ ሶከር ""አራክሶናል"" ይላሉ። ብሔራዊ ቡድኑ ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ ከእግር ኳስ ማኅበሩ ኃላፊዎች ጋር ብንወያይም ""ከስምምነት አልደረስንም"" ብሏል። መግለጫው አክሎ ከስምምነት ለመድረስ ""ተጨማሪ ድርድሮች ይኖራሉ"" ሲል ገልጧል። ካናዳ ሶከር በበኩሉ ""ከስምምነት ለመድረስ ስብሰባ አመቻችተናል"" ሲል በማኅበራዊ የትስስር ገፁ ላይ አሳውቋል። ካናዳ፤ ኳታር በምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችላትን ነጥብ አምጥታለች። ካናዳ በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ስትሳተፍ ይህ በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው ሜክሲኮ ባዘጋጀችው የ1986ቱ ዓለም ዋንጫ ነበር። ካናዳ ሶከር ብሔራዊ ቡድኑ ለዓለም ዋንጫ በማለፉ ስላበረከተው ሽልማት የሚጋጩ ዘገባዎች ሲወጡ ነበር። ቲኤስኤን የተባለው የዜና አውታር እንደዘገበው ካናዳ ሶከር ከፊፋ ከሚያገኘው ገንዘብ 10 በመቶውን ለተጫዋቾች ለመስጠት ቃል ገብቷል። ይህ መቶኛ ወደ ገንዘብ ሲቀየር 10 ሚሊዮን ዶላር መሆኑ ነው። ነገር ግን ቅዳሜ ዕለት ካናዳ ሶከር እኔ ቃል የገባሁት 60 በመቶ ነው ሲል ለቲኤስኤን ተናግሯል። ይህ 60 በመቶ ገንዘብ ለሴቶችና ወንዶች ብሔራዊ ቡድን እኩል የሚከፋፈል ነው። ነገር ግን ተጫዋቾቹ ከ75 አስከ 100 በመቶ የሚሆነው ገንዘብ ይሰጠን ሲሉ ይጠይቃሉ። የካናዳ መገናኛ ብዙኃን እንደሚሉት ሌላኛው ተጫዋቾቹን ያስቆጣው ነገር ለእያንዳንዱ የብሔራዊ ቡድን አባል ሁለት የቤተሰብ አባል ብቻ የዓለም ዋንጫ ቲኬት መሰጠቱ ነው። ተጫዋቾቹ ""ገቢውን እኛ እያመጣነው ተጠቃሚ ግን አልሆንንም"" የሚል ቅሬታ እንዳላቸው ይነሳል። ካናዳ በኮንካፍ ኔሽንስ ሊግ ውድድር ሐሙስ ዕለት ከኩራዎሳ ፍልሚያ ይጠብቃታል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/czdxd9ped4lo +business የሎተሪ አሸናፊዋ የ26 ሚሊዮን ዶላር ቲኬቷን በልብስ አጠባ እንዳጣችው አስታወቀች የካሊፎርኒያ ነዋሪ የሆነች አንዲት ግለሰብ የ26 ሚሊዮን ዶላር አሸናፊ ያደረጋትን የሎተሪ ቲኬት ሱሪዋ ኪስ ውስጥ ረስታው በመታጠቡ ከጥቅም ውጭ መሆኑንን ለአሜሪካ ሚዲያዎች ተናግራለች። ግለሰቡ ይህንን ያህል መጠን አሸናፊ ያደረጋትን ቲኬት የገዛችው ሎስ አንጀለስ በሚገኝ አንድ የገበያ መደብር ውስጥ ህዳር ወር ላይ ነበር። ስሟ ያልተጠቀሰው ግለሰብ ቲኬቱን በወቅቱ ከመደብሩ ስትገዛ በካሜራ የተቀረፀች ሲሆን አሸናፊ የሚያደርጋት ቁጥር መያዟም ታውቋል። የዕጣው አሸናፊ ገንዘብ የሚወስድበት የመጨረሻ ቀን በያዝነው ሳምንት ሃሙስ ነበር። አሸናፊው እንደታወቀ ቲኬቱን በገዙበት በ180 ቀናት ሊወስዱ ይገባል። ኤስፐራንዛ ሄርናንዴዝ የተባለው የገበያ መደብር ሰራተኛ የሆኑ ግለሰብ ካሊፎርኑያ ዊቲየር ደይሊ ኒውስ እንደተናገሩት በያዝነው ሳምንት ረቡዕ ሎተሪ ያሸነፈችው ግለሰብ መጥታ በአጋጣሚ ቲኬቷ ሱሪዋ ውስጥ ተረስቶ እንደታጠበ ተናግራለች። የካሊፎርኒያ ሎተሪ ቃለ አቀባይ ካቲ ጆንሰን በበኩላቸው ለጋዜጣው እንደተናገሩት ግለሰቧ ቲኬቱን ስትገዛ የሚያሳየው የመደብሩ ቪዲዮ ገንዘቡን ለመጠየቅ በቂ እንዳልሆነና ቲኬቱን በእጇ መያዝ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ሆኖም ቪዲዮው ለሎተሪው አዘጋጅ አካል እንደደረሰና ቀጣይ ምርመራም እየተደረገበት እንደሆነ ካቲ ተናግረዋል። የሎተሪው አሸናፊ ከሌለ ገንዘቡ ለካሊፎርኒያ የህዝብ ትምህርት ቤቶች እንደሚከፋፈል አዘጋጆቹ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። መግለጫው አክሎም አሸናፊ የሆነውን ቲኬት የሸጠው መደብር በአሰራሩ መሰረት 130 ሺህ ዶላር እንደተከፈላቸው መግለጫው አክሏል። በካሊፎርኒያ ትልቅ ስፍራ ያለው ይህ ሎተሪ አሸናፊው ብሩን ሳይወስድ ሲቀር የተለመደ እንዳልሆነና አሸናፊም ነኝ ብሎ ቲኬት አለማሳየትም እንዲሁ የመጀመሪያ ነው ተብሏል። በአውሮፖውያኑ 2016ም እንዲሁ አንዲት እንግሊዛዊት ሴት አሸናፊ የሆነችበትን የሎተሪ ቲኬት ቆሻሻ ጅንሷ ውስጥ ረስታው በልብስ ማጠቢያ ማሽን ውስጥ ገብቶ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። https://www.bbc.com/amharic/news-57099027 +politics ምርጫ 2013: 28 ሚሊዮን ተመዝግበዋል ለተባለው ምርጫ ምዝገባው ለተጨማሪ ቀናት ተራዘመ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አዲስ አበባ እና ድሬ ዳዋን ጨምሮ በክልሎች የመራጮች ምዝገባ ለተጨማሪ 7 ቀናት እንዲራዘም ማድረጉን አስታወቀ። ቀደም ብሎ ይፋ በተደረገው ቀነ ገደብ መሠረት የመራጮች ምዝገባ ከአፋር እና ከሶማሌ ክልል በስተቀር የሚጠናቀቀው ዛሬ ነበር። ይሁን እንጂ ባለፉት ቀናት በተደራራቢ ብሔራዊ የበዓል ቀናት ምክንያት በርካታ የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች ዝግ ሆነው መቆየታቸው እና ንኡስ ጣቢያዎችን ለማደራጀት ጊዜ መውሰዱን በመጥቀስ ምዝገባውን ማራዘም ማስፈለጉን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ቦርዱ ተቀዛቅዞ የነበረው የመራጮች ምዝገባ በከፍተኛ ሁኔታ ተሻሽሎ በአሁኑ ወቅት በጊዜያዊነት በተሰበሰበው መረጃ ከ28 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊዮን የሚደርሱ መራጮች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ብሎ ነበር። በአሁኑ ወቅትም በ41,798 ምርጫ ጣቢያዎች ምዝገባ እ��ተከናወነ እንደሚገኝ ቦርዱ አስታውቋል። ቦርዱ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፣ በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ በአማራ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል፣ በጋምቤላ ክልል፣ በሃረሪ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በሲዳማ ክልል የመራጮች ምዝገባ እስከ አርብ ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ለተጨማሪ 7 ቀናት እንዲከናወን ወስኗል። ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ በተከናወኑባቸው ስፍራዎች ነዋሪዎች በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፤ የቦርዱ አስፈጻሚዎች እና አስተባባሪዎች ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የመራጮች ምዝገባን እንዲያከናውኑ አስታውቋል። https://www.bbc.com/amharic/57024494 +health "ኮሮናቫይረስ፡ ""ኮቪድ-19ን አትፍሩት"" ትራምፕ ከሆስፒታል ሲወጡ" "በኮሮናቫይረስ ተይዘው ለሶስት ቀናት ሆስፒታል አልጋ ላይ ውለው የነበሩት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህክምናቸውን በቤተ መንግሥታቸው፣ ዋይት ሃውስ ለመቀጠል ከሆስፒታል ወጥተዋል። ዋይት ሃውስ በረንዳም ላይ ሲደርሱም ጭምብላቸውን አውልቀውታል። ይህም ሁኔታ በርካታ የዋይት ሃውስ ሰራተኞች በቫይረሱ በተያዙበት ሁኔታ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም አስደናቂ አድርጎታል። ""በጣም በጥሩ ስሜት ላይ ነኝ። ኮቪድን አትፍሩት። ህይወታችሁን እንዲቆጣጠረው አትፍቀዱለት"" በማለትም በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። አሜሪካውያን ቫይረሱን እንዳይፈሩት ባስተላለፉበት የትዊተር መልዕክታቸውም "" በአሁኑ ወቅት ከሃያ አመታት በፊት ከነበረው ጥሩ ስሜት ይሰማኛል፤ በቅርቡም ወደ ምረጡኝ የቅስቀሳ ዘመቻዬ እመለሳለሁ"" በማለትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ 7.4 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፣ 210 ሺህ ዜጎቿም ህይወታቸውን አጥተዋል። ከፕሬዚዳንቱ ህመም ጋር በተያያዘ እርስ በርስ የሚጋጩ መግለጫዎች መውጣታቸውን ተከትሎ የትራምፕ ህመም ምን ያህል የጠና ነበር የሚለው ላይ ጥያቄ አስነስቷል። ፕሬዚዳንቱ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ለሁለተኛ ጊዜ ለመመረጥ የሚያደርጉትና፣ ወር የቀረውን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳቸውን አቋርጠው ነበር። ዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው ዋልተር ሪድ የህክምና ማዕከል ሲወጡም "" ሁላችሁንም አመሰግናለሁ"" ያሉ ሲሆን ከሚዲያዎች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አልፈቀዱም። አጠር ካለ የሄሊኮፕተር በረራ በኋላም በዋይት ሃውስ የደረሱ ሲሆን ጭምብላቸውን አውልቀው ብራቮ በሚልም የአውራ ጣታቸውን ምልክት አሳይተዋል እንዲሁም የጦሩን ሰላምታ አይነትም ሰጥተዋል። ፕሬዚዳንቱ አሜሪካውያን ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመልሱ የሚጠይቅም የቪዲዮ መልዕክት አስተላልፈዋል። ""ታሸንፉታላችሁ፤ ምርጥ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶች አሉን። በቅርቡ የተሰራ ምርጥ መድኃኒት አለን"" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ክትባት በቅርብ እንደሚመጣ ቢናገሩም የአሜሪካ የበሽታዎች ቁጥጥርና ክትትል ማዕከል በበኩሉ በአሁኑ ወቅት የሚጠበቅ ክትባት እንደሌለ አስታውቋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54409384 +business """የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ላይ የሚለወጡ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ"" የጠ/ሚ የኢኮኖሚ አማካሪ" በኢትዮጵያ እየተደረጉ ያሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከምዕራቡና ከአረቡ ዓለም የገንዘብ ድጋፍና ብድር እያገኘች ነው። እየተደረገ ካለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ 'አገር በቀል ኢኮኖሚ' የሚል አካሄድን እየተከተለ መሆኑንም መንግሥት እየገለፀ ነው። በቅርቡም የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ለኢትዮጵያ የ2.9 ቢሊዮን ዶላር የብድር ድጋፍ ለማድረግ ተስማምቷል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ነመራ ገበየሁ ማሞን በአገሪቱ እየተደረገ ስላለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሁም ስለ አይኤምኤፍ ብድር ጠይቀናቸዋል። ቢቢሲ፡ አይኤምኤፍ ብዙ ጊዜ የሚያበድረውም ሆነ የእርዳታ ድጋፍ የሚያደርገው ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ ነው። ኢትዮጵያስ የ2.9 ቢሊዮን ዶላሩን ብድር በምን አግባብ አገኘች? ዶ/ር ነመራ፡ እውነት ነው እነ አይኤምኤፍ ከአሁን በፊት ብድር የሚሰጡት ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ነው። ቅድመ ሁኔታው ደግሞ ከማክሮ ኢኮኖሚ እስከ ታች ያሉ ነገሮችን የሚነካ ነው። አሁን የኢትዮጵያን ለየት የሚያደርገው፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ከአንድ ዓመት በላይ ባሉት ጊዜያት ብዙ የፖለቲካ ማሻሻያዎችን እያካሄደች፤ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት ሃገር በቀል የሆነ የለውጥ መንገድ ስትተገብር ነበር። አይኤምኤፍ ደግሞ ለእንደዚህ ያሉ ነገሮች እርዳታ የማድረግ አካሄድ አለው። በዚህ መንገድ መጥተው ነው ኢትዮጵያን እንረዳለን ያሉት። • የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጁ በዋጋ የሚያንራቸው ምርቶች ስለዚህ እነሱ ያስቀመጡት ቅድመ ሁኔታ የለም። ኢትዮጵያ በመንግሥት እጅ ያሉ ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዛወር እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ እጥረት ችግርን ለመፍታት የወሰነቸው አይኤምኤፍ ከመምጣቱ በፊት ነው። አሁን ያለው መንግሥት ማሻሻውን የጀመረው ቀድሞ ነው። ከዚያ እነሱ ይሄንን ሀሳብ እንደግፋለን ብለው ነው ብድሩን ሊሰጡ የቻሉት። ቢቢሲ፡ ለአይኤምኤፍ ተብሎ ባይሆንም ቅድመ ሁኔታዎቹ በኢትዮጵያ በኩል ተሟልተው ነበር ማለት እንችላለን? ዶ/ር ነመራ፡ በትክክል፤ በእርግጥ በአይኤምኤፍም በዓለም ባንክም እነዚያ በ1980 እና 90 ዎቹ የነበሩት የመዋቅር ማስተካከያ ፕሮግራሞች Structural Adjustment Policy) የሉም፤ እየላሉ መጥተዋል። ከነበሩ ልምዶች ተነስተው ነገሮችን ለቀቅ እያደረጉ የመጡበት ሁኔታ ነው ያለው። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ደግሞ ከግብር መሰብሰብ ጀምሮ እስከ የውጭ ምንዛሪ ያሉ የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር ችግር ውስጥ ስለሆነ ያንን መቅረፍ ግዴታ ነበር። እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የተወሰደውን ተነሳሽነት ለመደገፍ ነው እነ አይኤምኤፍ የመጡት። ስለዚህ በሚቀጥሉት ከ3 እስከ 5 ዓመት የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ፍጥነት የሚወስነው የኢትዮጵያ መንግሥት እንጂ ማንም አደለም። ኢትዮጵያ ባላት የሰው ኃይል እና ሌሎች ሁኔታዎች ፍጥነቱን ጠብቃ መሄድ አለባት የሚለው ጠንካራ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠውም በኢትዮጵያ መንግሥት ነው። በሌላ በኩል አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ ደግሞ እርዳታ ሲሰጡ ግልጽነት ይፈልጋሉ፤ እውነት ይሄ ለውጥ በሚፈለገው አቅጣጫ እየሄደ ነው ወይ? የሚለውን ማወቅ ይፈልጋሉ። እዚህ ላይ ከእነሱ ጋር የሚሰራበት ሁኔታ ይኖራል ግን ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ እንደሚባለው እጅ ለመጠምዘዝ ኢትዮጵያ ላይ አቅም የሚኖራቸው አይመስለኝም። ቢቢሲ፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአይኤምኤፍ የሚያገኘውን ብድር በሚፈልገው ሁኔታ ወጪ የማድረግ ነጻነት ይኖረዋል? ዶ/ር ነመራ፡ አዎ፤ ግን እንደፈለገ ሲባል መንግሥት የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት ስላለበት፤ የራሱን ቀዳሚ ሥራዎችን በመለየት ግልጽነት ባለው መንገድ ለሚፈለገው አላማ ገንዘቡን የማዋል ሙሉ ስልጣን አለው። ለምሳሌ ፕራይቬታይዜሽን ላይ የተለያዩ ሥራዎች ይኖራሉ። ድርጅቶቹ ላይ ለውጥ የማድረግ፣ አቅም መገንባት የመሳሰሉ ሥራዎች የፋይናንስ ድጋፍ የሚፈልጉ ናቸው። • ኢትዮጵያ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ትውጣ? ወደ በጀትም ከሄድን፤ ባለፉት 50 ዓመታት ሲያከራክር የነበረው ጉዳይ መንግሥት ወጪዎችን መቀነስ አለበት የሚለው ነው። አሁን ያለው የኢኮኖሚ ለውጥ ትኩረት ያደረገው የመንግሥትን ግብር የመሰብሰብ አቅም ማሳደግ ላይ አንጂ ወጪ መቀነስ ላይ አይደለም። የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ላይ ለውጥ ማድረግ፣ ከመንግሥት ወደ ግል ማዞርም ላይ የሚሰሩ ብዙ ሥራዎች አሉ። ለዚህም የገንዘብ ድጋፍ ስለሚያስፈልግ እዚህ ላይ ይውላል እርዳታው። ሌሎች ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል የተባሉ እንደ ግብርናና ቱሪዝም ያሉ ዘርፎችም አሉ፤ ገንዘቡ እዚህ እዚህ ላይ ነው የሚውለው። መጨረሻ ላይ ግን ይህ ብር የኢትዮጵያ ተወዳዳሪነትን በማጎልበት ወደ ውጭ ሃገር የምትልከውን ምርት በማሳደግ ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት መቅርፍ አለበት፣ ሃገር ውስጥ ያለውን የሥራ ፈጠራና የገቢ እድገት ማረጋገጥ አለበት፤ ምክንያቱም ድህነትን ለመቀነስ ሁለቱም ቀዳሚ ጉዳዮች ናቸውና። ቢቢሲ፡ መንግሥት እየተከተለ ያለው አካሄድ ወጪውን ለመቀነስ የሚያደርጋቸውን ድጎማዎች ማንሳት ሳይሆን የታክስ ገቢውን ማስፋት እንደሆነ ገልፀውልኛል። ሰሞኑን ለፓርላማ የቀረበው ኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ የዚህ ውጤት ነው? ዶ/ር ነመራ፡ አዎ፤ መንግሥት ድህነት ለመቀነስና መሰረት ልማት ለማስፋፋት የሚያርገው የገንዘብ ወጪ ላይ ትልቅ ለውጥ አይኖርም፤ ግን ኢትዮጵያን የሚያስቸግሯት እንደ ሙስናና የሃብት ብክነትን የመሳሰሉ ነገሮች ላይ ትልቅ ለውጥ እየተካሄደ ነው። ኢትዮጵያ ላይ እንደ ትልቅ አጀንዳ ተወስዶ እየተሰራ ያለው ነገር ግን፤ ከተቋም ጀምሮ እስከ ፖሊሲ ግብር መሰብሰብ ላይ ነው፤ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን አቅም ማሳደግ ላይም ብዙ ሥራ እየተሰራ ነው። ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥም ግብር የመሰብሰብ አቅም እያደገ መጥቷል። ታክስን በተመለከተ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚታዩ የፖሊሲ ክፍተቶች አሉ፤ እዚህ ላይም ማሻሻያ እየተደረገ ነው። ወደ ፓርላማ የተላከው የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅም ከዚህ አንፃር የሚታይ ነው። አገር ውስጥ የሚመረቱና ከውጭ የሚገቡ አንዳንድ ምርቶች ላይ የንግድ ምህዳሩን በማይጎዳ መልኩ የመንግሥትን ግብር የመሰብሰብ አቅም ለማሳደግ የሚደረጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች አሉ። • ከ20 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? ኢትዮጵያ የምትታወቀው በአፍሪካ ደረጃ ጭምር ዝቅተኛ ግብር በመሰብሰብ ነው። ስለዚህ እዚህ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ትልቅ ሥራ እየተሰራ ሲሆን እርምጃው ኤይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ ከሚያተኩሩባቸው ነገሮች ጋር አብሮ የሚሄድ ነው። ቢቢሲ፡ እየወጡ ባሉት መረጃዎች መሰረት ረቂቅ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ እንዳለ ከፀደቀ የብዙ ነገሮችን ዋጋ የማናር አዝማሚያ ይኖረዋል የሚል ትልቅ ስጋት አለ። እርሶ እንዴት ነው አዋጁን የሚያዩት? ዶ/ር ነመራ፡ ምን አይነት ጫና ይኖረዋል የሚለውን አሁን መናገር ትንሽ ይከብደኛል። ረቂቅ አዋጁ ገና ብዙ መንገድ ያልፋል፤ ብዙ የሚቀየሩ ነገሮችም ይኖራሉ። ለምን አስፈለገ የሚለው ላይ ግን፤ ከምንልከውና ከምናስገባው ምርት ጋር በተያያዘም መንግሥት በጣም ዝቅተኛ ገቢ እየሰበሰበ ስላለ መሞላት ያለባቸው ክፍተቶች ስላሉ ነው ፖሊሲው የመጣው። ጫናው ግን ደሃው የህብረተሰብ ክፍል ላይ እንዳይሆን ጥንቃቄ ይደረጋል። ቢቢሲ፡ በአጠቃላይ አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ ብድር የሰጠው ፕራይቬታይዜሽንን ለማሳለጥ ነው ብለን መውሰድ እንችላለን? ዶ/ር ነመራ፡ የአይኤምኤፍ ብድር ፕራይቬታይዜሽን ላይ፣ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ እንዲሁም በብሔራዊ ባንክ የሚደረጉ አንዳንድ የፋይናንስ ፖሊሲ ማሻሻያዎች ገንዘብ ስለሚጠይቁ እዚያ ላይ ይውላል። ነገር ግን ይህ ዋነኛው ምክንያት ነው፤ ይሄኛው ሁለተኛ ነው የምልበት መመዘኛ ስለሌለኝ፤ ፕራይቬታይዜሽን ዋነኛው አጀንዳ ነው ማለት ይከብደኛል። ግን ሁለት ነገሮች ላይ ማለትም የመንግሥት የልማት ተቋማትን ማሻሻል እንዲሁም ወደ ግል ይዞታ ማዞር ላይ ትልቅ ሥራ እየተሰራ ነው። ቢቢሲ፡ ኢትዮጵያ ትልቅ የእዳ ጫና ያለባት አገር ናት፤ ከዚህ አንፃር የተጨማሪ ብድር አስፈላጊነት እንዴት ይታያል ? ዶ/ር ነመራ፡ የብድር ጫና የሚባለው መጠኑ አይደለም። ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ምጣኔ አንጻር ሲታይ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ብድሩ 60 በመቶ ጠቅላላይ የሀገር ውስጥ ምርት አይሆንም፤ ስለዚህ ይህ በራሱ ችግር አደለም። አሁን ኢትዮጵያ ላይ ትልቅ ችግር እየፈጠረ ያለው ብዙዎቹ የውጭ ብድሮች፤ በትልቅ የወለድ መጠን በአጭር ጊዜ የሚከፈሉ ሆነው መምጣታቸው ነው። የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ካየን ግን ዶላር የማግኘት አቅሙ በጣም ዝቅተኛ ነው። ችግሩ እዚህ ጋር ነው ያለው። • «አማካሪ አያስፈልገኝም ብሎ የሚያስብ መሪ አልገባውም ማለት ነው» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ከአይኤምኤፍ፣ ከአለም ባንክ፣ ከአውሮፓ ሕብረትና ሌሎች አገራት እየተደረጉ ያሉትን የብድር ድጋፎች በዝቅተኛ ወይም በዜሮ የወለድ መጠን የሚወሰኑ ናቸው። የምንመልስበት ጊዜም በረጅም ጊዜ ነው። የውጭ ምንዛሪ ላይ ጫና ሳይፈጥር ነው የሚከፍለው፤ ስለሆነም ከዚህ በፊት በከፍተኛ ወለድ ከቻይና የወሰድናቸውን ብድሮችም ወደ ዝቅተኛ ወይም ዜሮ ወለድ እንዲቀየሩ እያደረግን ነው። ይህ ኢትዮጵያ ላይ ያለውን ጫና እየቀነሰ ይሄዳል ከዚህ ወዲህም አካሄዱ በዚህ አንፃር ይሆናል። ቢቢሲ፡ መንግሥት እያደረገው ያለውን ማሻሻያ ተከትሎ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ብድርና ድጋፍ እየተገኘ ነው። ብድሩና እርዳታው የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነት እና ሌሎች የኅብረተሰቡን ችግሮች ለመቅረፍ የሚረዱት እንዴት ነው? ዶ/ር ነመራ፡ የዚህ ሁሉ ማሻሻያ ዋና አላማ የግል ዘርፉን ምርታማነት ማሳደግ ነው። የዚህ ዘርፍ ምርታማነት ካላደገ ኢኮኖሚው ውስጥ የሥራ ፈጠራ እድሎችን ማስፋት አይቻልም። ኢትዮጵያን አንቆ የያዛት ትልቅ ነገር የግል ዘርፉ ምርታማነት ዝቅተኛ መሆን ነው። የጠቀስናቸው አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መጨረሻ ግብ የግሉን ዘርፍ ምርታማነት ማሳደግ ነው። በግብርና፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን፣ ማኑፋክቸሪንግ፤ በተለይ ደግሞ በአግሮ ኢንዳስትሪ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል። ለእነዚህ ዘርፎች ቅድሚያ መስጠት ያስፈለገው የሥራ መፍጠር አቅማቸው ታይቶ ነው። ጊዜ ሊወስድ ቢችልም በአጭርና መካከለኛ ጊዜ የሚደረጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ኅብረተሰቡን እንዲያግዙ የተቀመጡ ግቦች አሉ። ቢቢሲ፡ አገር በቀል ኢኮኖሚ ምንድን ነው? ዶ/ር ነመራ፡ የተለየ የኢኮኖሚ እሳቤ አይደለም ይልቁንም አሁን የምንከተለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ በመደመር እሳቤ ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብን በመጠቀም ያለብንን የፖለቲካል-ኢኮኖሚ ችግሮች መፍታት አለብን የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ እሳቤ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፈው ሃያ ወራት እየተደረገ ያለው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ለውጥ መነሳሳት እና እሳቤው የመጣው ከዚሁ አንፃር ከአገር ውስጥ ነው። ለውጡ የውጭ ግፊት የወለደው ሳይሆን ከራስ የመጣ ስለሆነ ነው አጠቃላይ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የተባለው። ቢቢሲ፡ ዋና ዋና ተብለው ሊገለፁ የሚችሉ የአገር በቀል ኢኮኖሚ እሳቤ መገለጫዎች አሉ? ዶ/ር ነመራ፡ ዋናው ነገር እሳቤው፣ ፍቃደኝነትና ተነሳሽነቱ የመንግሥት መሆኑ ነው። የኢኮኖሚ ጎኑን ብቻ ካየን ግን ሦስት ዋና ነገሮችን ይዞ ነው የተነሳው። የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር በጣም በሚያስፈራ ሁኔታ ላይ ነው ያለው። የብድር ጫናው፣ የወጪ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱ፣ የወጪ እና የገቢ ንግድ አለመመጣጠን የፈጠረው መዛባት ትልቅ መሆን፣ በአገሪቱ የገንዘብ ፖሊሲ ምክንያት የገንዘብ ሥርዓቱ በጣም የቀጨጨ እንዲሁም ቁጠባና ኢንቨስትመንት መካከል ያለው ሚዛንም አስፈሪ ነበር፤ የሥራ አጥነትና የዋጋ ግሽበትን ካየን ነገሮች በጣም ከባድ ነበሩ። • ዝነኞቹ ቮልስዋገኖችና ድንቅ ታሪኮቻቸው የግል ዘርፉም በብዙ ማነቆዎች የተያዘ ነው የሚያበረታታው ነገር የለም። ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ከግንዛቤ ገብተው አገር በቀል ኢኮኖሚው ትኩረት ያደረገባቸው ዋንኛ ነገሮች ማክሮ ኢኮኖሚ ማኔጅመንቱ፣ የቢዝነስ ተነሳሽነቶችን ማምጣትና የኃይል እንዲሁም የሎጀስትክ ዘርፍ ላይ ማሻሻያ ማድረግ ናቸው። በዚህ ረገድ የማዕድን እና የቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ ትኩረት የሚደረግባቸው ናቸው። ቢቢሲ፡ ትልልቅ የውጭ ብድሮች በተቋማት የማስፈፀም አቅም ማነስና በሙስና የታለመላቸውን ዓላማ ሳያሳኩ ሲቀሩ ታይቷል። አሁን ኢትዮጵያ እያገኘች ካለችው ብድር ጋር በተያያዘ ይህ እንዳይሆን የሚያስችል ሥርዓት አለ? ዶ/ር ነመራ፡ እውነት ነው ይህ ትልቅ ስጋት ነው። የኢትዮጵያ ተቋማዊ ሥርዓት ጥራትና አቅም ማነስ በሙስናም ይሁን በሌላ ለሕዝብ ሃብት ብክነት ምክንያት ናቸው። አሁን ብዙ እየተባለ ያለው ስለ ፕራይቬታይዜሽን ብቻ ሆነ እንጂ በለውጡ እየተሰራ ያለው ትልቅ ነገር በመንግሥት እጅ ያሉና ትልቅ ሙስና እየተሰራባቸው ያሉ ድርጅቶች አስተዳደር ላይ ማሻሻያ ማድረግ ነው። [የማሻሻውን ውጤት ማየት ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም።] ቢቢሲ፡ በመሰረተ ልማት ግንባታ በብድርም ሆነ በንግድ ኢትዮጵያ ጠንካራ ትስስር የነበራት ከቻይና ጋር ነው። በአሁኑ ወቅት በተለይም ከለውጡ ወዲህ ኢትዮጵያ ፊቷን ወደ ምዕራቡና አረቡ ዓለም አዙራለች። የቻይና አጋርነት እያበቃ ነው? ዶ/ር ነመራ፡ አንድ አገር ያላት የብድር፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ሁለት መልክ አለው። አንዱ በማስፋት፤ ሁለተኛው በጥልቀት መሄድ ነው። ከቻይና ጋር ባለፉት 15 ዓመታት በጣም በጥልቀት ነው የሄድንበት፤ አሁንም ኢትዮጵያ ይህንን ትታ ሌላ መፈለግ ላይ አይደለም ያለችው። ያለው ነገር ላይ መጨመር ማስፋት ነው እየተደረገ ያለው። አዲስ ምንጭ፣ አዲስ የንግድ አጋር የማፈላለግ ሥራ ነው እየተሰራ ያለው። እርግጥ ነው ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲ ከምዕራቡና ከአረቡ ዓለምም ጋር ጥሩ ትስስር እየፈጠረች ነው። ቻይና አሁንም ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት አላት። https://www.bbc.com/amharic/news-50909822 +business ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ "ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በፎርብስ የዓመቱ ኃያል/ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ። ፎርብስ ባወጣው 100 የዓመቱ (2020) ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ፕሬዘዳንቷ በ96ኛ ደረጃ ተቀምጠዋል። የመጀመሪያዋ ሴት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሳህለወርቅ፤ በዝርዝሩ የተካተቱ ብቸኛዋ አፍሪካዊ ናቸው። ፎርብስ በድረ ገጹ ""ለምክር ቤት ባደረጉት የመጀሪያ ንግግር ለሴቶች ድምጽ ለመሆን ቃል ገብተዋል"" ሲል ገልጿቸዋል። የፕሬዝዳንቷ መመረጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጠኑም ቢሆን የሴቶች ውክልና እየጨመረ መምጣቱን እንደሚያሳይም ፎርብስ አስነብቧል። በዝርዝሩ እነማን ተካተቱ? በዝርዝሩ አንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት የጀርመኗ መራሔተ መንግሥት አንግላ መርከል ናቸው። መርከል በዝርዝሩ ለአስር ተከታታይ አመታት መሪነቱን ይዘዋል። በዝርዝሩ ሲካተቱ ደግሞ ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ ነው። በሦስተኛ ደረጃ ላይ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዘዳንት ሆነው የተመረጡት ከማላ ሃሪስ ይገኛሉ። የኒው ዚላንዷ ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደን ደግሞ 32ኛ ናቸው። ይህ ዓመታዊ ዝርዝር ሲወ��� ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ መሆኑን የፎርብስ ድረ ገጽ ይጠቁማል። በዘንድሮው ዝርዝር ከ30 አገራት የተውጣጡ ሴቶች ተካተዋል። ከእነዚህ መካከል አስሩ የአገር መሪዎች ሲሆኑ፣ 38ቱ ሥራ አስኪያጆች፣ አምስቱ ደግሞ በመዝናኛው ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶች ናቸው። በዝርዝሩ ከተካተቱት ሴት መሪዎች መካከል የኮሮናቫይረስ ስርጭትን መገደብ የቻሉ እንደሚገኙበት ተገልጿል። ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የተመረጡት ጀሲንዳ አርደን፤ በኒው ዚላንድ የመጀመሪያውን እና ሁለተኛውን ዙር ወረርሽን በብቃት መወጣት ችለዋል። በ37ኛ ደረጃ የተቀመጡት የታይዋኗ ፕሬዘዳንት ሳይ ኢንግ ዌን፤ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለማግኘት ውጤታማ አሠራር ዘርግተዋል። 23 ሚሊዮን ሰዎች በሚኖሩባት ታይዋን በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡት ሰባት ሰዎች ብቻ ናቸው። የኖርዌይ ጠቅላይ ሚንስትር ኤርና ሶልበርግ (52ኛ) ""ዴሞክራሲ ሰፍኖ ሰብአዊ መብት የተከበረባቸውና ሴቶች በማኅበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ የደርሱባቸው አገራት ኮቪድ-19ን መዋጋት ችለዋል"" ብለው ነበር። በዝርርዝሩ ከተካተቱ መካከል በአምስተኛ ደረጃ ሜሊንዳ ጌትስ እና በሰባተኛ ደረጃ ናንሲ ፔሎሲ ይጠቀሳሉ። ኦፕራ ዊንፍሪ በ20ኛ ደረጃ ተቀምጣለች። ከመዝናኛው ዘርፍ ድምጻውያኑ ሪሀና (69) እና ቢዮንሴ (72) ይጠቀሳሉ። ጥቂት ስለ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ አዲስ አበባ ተወልደው ያደጉት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ የሁለት ወንድ ልጆች እናት ናቸው። ለዓመታት በዲፕሎማሲው ዘርፍ ሠርተዋል። በወርሃ የካቲት 1942 የተወለዱ ሲሆን ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዘኛና አማርኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ። ከፈረንሳዩ ሞንተፔለ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ምሩቅ ሲሆኑ፤ እአአ ከ1989-1993 ተቀማጭነታቸውን ሴነጋል በማድረግ የማሊ፣ የኬፕ ቨርዴ፣ የጊኒ ቢሳዎ፣ የጋምቢያና የጊኒ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል። እአአ ከ1993-2002 ደግሞ በጅቡቲ አምባሳደር ሆነው የሠሩ ሲሆን፤ በወቅቱ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ቋሚ ተወካይም ነበሩ። ከዚያም በመቀጠል ከ2002-2006 በፈረንሳይ አምባሳደር እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም ተወካይ ሆነው ሠርተዋል። በኋላም በተባበሩት መንግሥታት ልዩ መልዕክተኛ ውስጥ የተቀናጀው የሰላም አስከባሪ ኃይል ተወካይ በመሆን በሴንትራል አፍሪካ (BINUCA) ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። በአፍሪካ ሕብረት ውስጥና በተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ውስጥም የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሆነው አገልግለዋል። በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥም የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው ሰርተዋል። እአአ በ2011 የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ የነበሩት ባን ኪሙን፤ በኬንያ የተባበሩት መንግሥታት ዳይሬክተር ጄነራል አድርገው ሾመዋቸው አገልግለዋል። በተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ በአፍሪካ ሕብረት ልዩ ተወካይ እንዲሁም በአፍሪካ ሕብረት የተባበሩት መንግሥታት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል። ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው እያገለገሉ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-55246627 +business ምጣኔ ሃብት፡ በቱርክ የኑሮ ውድነት 70 በመቶ ገደማ መጨመሩ ተገለጸ "በቱርክ የኑሮ ውድነት በአንድ ዓመት ውስጥ 70 በመቶ ገደማ መጨመሩ ተገለጸ። ይህም በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው ተብሏል። የመጓጓዣ፣ የምግብ፣ እና የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች ዋጋ በዓመቱ ከፍተኛ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። በመላው ዓለም ያሉ አገራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የዋጋ ንረት ምክንያት እየተፈተኑ ነው። በቱርክ የተከሰተው የዋጋ ንረት ግን ���ሬዚደንቱ የዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት የሚረዳውን 'የወለድ ምጣኔን መጨመር' ባለመፈለጋቸው የተከሰተ መሆኑን የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ተናግረዋል። በአገሪቱ የምግብ እና አልኮል የሌላቸው መጠጦች ዋጋ 89.1 በመቶ ዓመታዊ የዋጋ ጭማሪ የታየባቸው ሲሆን የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች እና ቁሳቁሶች ዋጋ እስከ 77.64 በመቶ ጨምሯል። ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር በሚያዝያ ወር የዋጋ ንረቱ በ7.25 በመቶ ማሻቀቡን ከቱርክ ስታቲስቲክስ ኢንስቲቲዩት የተገኘው መረጃ አመላክቷል። ፕሬዚደንት ሬሲብ ጣይብ ኤርዶዋን የውጭ ምንዛሬን ከማረጋጋት ይልቅ ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች ላይ ትኩረት በማድረጋቸው የቱርክ መገበያያ ገንዘብ ሊራ ዋጋም ወድቋል። ፕሬዚደንት ኦርዶዋን የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የወለድ ምጣኔን ማስተካካል የሚለው አሠራር አይዋጥላቸውም። ""የወለድ ምጣኔ የሁሉም መጥፎ ነገሮች እናት እና አባት"" ሲሉ ነው የሚገልጹት። በመሆኑም ፕሬዚደንቱ በውጭ ምንዛሬ ገበያዎች ውስጥ ጣልቃ መግባትን ጨምሮ የዋጋን ንረትን ለማረጋጋት ያልተለመደ ፖሊስ ተጠቅመዋል ሲሉ ባለሙያዎች ይተቻሉ። የቱርክ ፕሬዚደንት ባለፈው ዓመት የአገሪቱን ማዕከላዊ ባንክ አመራር ያሻሻሉ ሲሆን ባንኩ ከመስከረም ወር ጀምሮ 19 በመቶ የነበረውን የወለድ ምጣኔ ወደ 14 በመቶ ዝቅ አድርጓል። በሚያዝያ ወር በተከታታይ ለአራተኛ ወር የዋጋ ግሽበቱ እየተባባሰ ቢመጣም የወለድ ምጣኔው ባለበት ነው። በብሉቤይ ንብረት አስተዳዳር የገበያ ባለሙያ የሆኑት ቲሞቲ አሽ ""በቱርክ ውስጥ ያለው አስገራሚ የገንዘብ ፖሊስ ውድቀት ነው"" ብለዋል። ""ዝቅተኛ የወለድ ምጣኔ የዋጋ ግሽበትን ያስከትላል"" የሚሉት ባለሙያው የምጣኔ ሐብት ፖሊሲን እንደገና ለመጻፍ መሞከር መሬትን ጠፍጣፋ ለማድረግ ከመሞከር ጋር ተመሳሳይ ነው"" በማለት ለተከሰተው የዋጋ ንረት ፕሬዚደንቱን ከሰዋል። በካፒታል ኢኮኖሚክስ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ጃሰን ቱቪይ በበኩላቸው ፖሊሲ አውጭዎች እርምጃ እንደሚወስዱ እና የወለድ ምጣኔዎችን ሊጨምሩ እንደሚችሉ የሚያሳዩ ምንም ምልክቶች የሉም ብለዋል። በመሆኑም የዋጋ ግሽበቱ በዚህ ዓመትም ባለበት እንደሚቀጥል ተንብየዋል። በዓለም ዙሪያ ከኮቪድ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በተፈጠሩ የአቅርቦት ችግሮች እና በዩክሬን ባለው ጦርነት ምክንያት የመሠረታዊ ፍጆታዎች ዋጋ በመላው ዓለም በፍጥነት እየጨመረ ነው። በርካታ አገራት የወለድ ምጣኔን በመጨመር ግለሰቦችና ድርጅቶች ገንዘብ ተበድረው ጥቂት እንዲያጠፉ በማበረታታት ለተከሰተው ችግር ምላሽ ሰጥተዋል። ረቡዕ ዕለት የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ከፍተኛ የሆነ የወለድ ምጣኔ መጨመሩን አስታውቋል። ሕንድ እና አውስትራሊያን ጨምሮ ሌሎች አገራትም የወለድ ምጣኔን ጨምረዋል። ባንክ ኦፍ ኢንግላንድም የወለድ ምጣኔውን እንደሚጨምር አሊያም ባለበት እንደሚቀጥል ዛሬ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61306676 +health መስፈርት ሳያሟሉ የኮቪድ-19 ምርመራ ለሚያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተገቢውን መስፈርት ሳያሟሉ የኮቪድ-19 ምርመራ የሚያደርጉ ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ ሰጠ። ኢንስቲትዩቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ተገቢውን መስፈርት ሳያሟሉ የኮቪድ-19 ምርመራ የሚያደርጉ ተቋማት መኖራቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል። “በቅርቡ ‘የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እናደርጋለን እስከ 6 ሰዓትም ውጤት እናሳውቃለን’ እያሉ ማስታወቂያ የሚያሰራጩ ተቋማት መኖራቸውን ደርሰንበታል” ብሏል የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ባወጣው መግለጫ። ኢንስቲትዩቱ የኮቪድ-19 ወረር��ኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሶ፤ የላብራቶሪ ማስፋፊያ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል። በምርምር ተቋማት፣ በክልል ላብራቶሪዎች፣ በዩኒቪርቲዎች እንዲሁም ከግል ተቋማት ጋር በመተባበር የኮቪድ-19 ምርመራ ተቋማት ተስፋፍተዋል ብሏል። ኢንስቲቲዩቱ እስካሁን ተገቢውን መስፈርት ያሟሉ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ፍቃድ የተሰጣቸው የግል ተቋማት ብዛት 15 ናቸው ያለ ሲሆን የተቋማቱን ዝርዝር በፌስቡክ ገጹ ላይ አውጥቷል። ኢትዮጵያ እስካሁን ከ2 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርምራ አድርጋ 158ሺህ 053 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጣለች። ከጤና ሚንስቴር በሚሰጠው ዕለታዊ የኮቪድ-19 ወቅት መግለጫ መሠረት ቫይረሱ በኢትዮጵያ ሪፖርት ከተደረገ ወዲህ 134ሺህ 736 ሰዎች ከበሽታው ሲያገግሙ፤ 2ሺህ 354 ሰዎች ከበሽታው ጋር በተያያዙ ሕመሞች ህይወታቸው አልፏል። https://www.bbc.com/amharic/news-56229305 +politics የአሜሪካ ቀዳማዊ እመቤት ዩክሬንን እየጎበኙ በለበት ወቅት አሜሪካ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ሩሲያ ላይ ጣለች "የአሜሪካ ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን ከዩክሬን አቻቸው ኦላንዝ ዜሌንስኪ ጋር በዩክሬኗ ኡዙሁኡድ ከተማ ተገናኙ። ሁለቱ ቀዳማዊ እምቤቶች ዩክሬን ውስጥ በተገናኙበት ወቅት ዋሽንግተን ሞስኮ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ጥላለች። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ባለቤት ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ በይፋ ሲታዩ ይህ የመጀመሪያቸው ነው ተብሏል። አሜሪካ የሩሲያ እና ቤላሩስ ዜግነት ያላቸው 2 ሺህ 600 ስዎች ላይ የቪዛ ዕቀባ ጥላለች። በተጨማሪም ሦስት የሩሲያ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን እና አመራሮቻቸውም በአሜሪካ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል። በሌላ በኩል የቡድን ሰባት (ጂ7) አገራት መሪዎች ከሩሲያ ነዳጅ በጊዜ ሂደት ውስጥ አናስገባም ወይም እናግዳልን ብለዋል። ሁለቱ ቀዳማዊ እመቤቶች የተገናኙት በድንበር አቅራቢያ ተፈናቃዮች ተጠልለውበት በሚገኙበት ትምህርት ቤት ነው። የአሜሪካ ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን የአሜሪካ ሕዝብ ከዩክሬናያውን ጎን እንደቆመ ለማስየት በስፍራው መገኛታቸውን ገልጸው፤ ሦስት ወራት ያስቆጠረው ጦርነት ""በጭካኔ የተሞላ"" እና መቆም የሚገባው ነው ብለዋል። የዩክሬኗ ቀደማዊት እመቤት በበኩላቸው በጦርነት ውስጥ የምትገኘዋን ዩክሬንን መጎብኘት ""ድፈረትን የሚጠይቅ"" ነው ብለዋል። በእናቶች ቀን የተደረገው ይህ ጉብኝት ለዩክሬን እና ለአሜሪካ ተምሳሌታዊ ነው ሲሉም አክለዋል። ""በዚህ ወሳኝ ጊዜ የእናንተን ፍቅር እና ድጋፍ አይተናልም"" ብለዋል። ሁለቱ ቀዳማዊ እመቤቶች እንደመጠለያነት እያገለገለ ባለው ትምህርት ቤት ውስጥ ህጻናቱን ሲያጫውቱም ታይተዋል። በዩክሬን ይህ በሚሆንብት ሰዓት የቡድን ሰባት ወይም ጂ7 አገራት መሪዎች በቪዲዮ ካደረጉት ስብሰባ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ንግግር እያደረጉ ነበር። የአሜሪካ አዳዲስ ማዕቀቦችም የተጣሉት ከዚህ በኋላ ነበር። አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን አዲሱ ማዕቀብ በሩሲያ ትልቅ ከሆኑት ባንኮች መካከል አንዱ የሆነውን የጋዛፕሮም ባንክ 27 አመራሮችን እንደሚመለከት ተናግረዋል። ሆኖም ማዕቀቡ የባንኩን ንብረቶች ማገድ አሊያም ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውሩን መግታትን አይመለከትም። አሜሪካ 2 ሺህ 600 የሩሲያ እና ቤላሩስ ዜግነት ያላቸው ስዎች ላይ ማዕቀብ እንደጣለች ከመግለጽ ውጪ የዕቀባው ሰለባ የሚሆኑ ሰዎች ዝርዝር አልተገለጸም። ይህ የአሜሪካ ማዕቀብ የተሰማው ዩክሬን ውስጥ ታላላቅ የሚባሉ ዲፕሎማሲያዊ ሁነቶች ከተከወኑ በኋላ ነው። ይህም የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጅስቲን ትሩዶ፣ የጀርመን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና የአሜሪ�� ቀዳማዊት እመቤት በዩክሬን በተለያዩ አካባቢዎችን ከጎበኙ በኋላ ነው። የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ አገራቸው ለዩክሬን ተጨማሪ ጦር መሳሪያ እና ቁሳቁስ እንደምትልክ እና ጉዳዩ በሚመለከታቸው የሩሲያ ዜጎች እና ኩባንያዎች ማዕቀብ እንደምትጥል አሳውቀዋል። የአውሮፓ ሕብረት ሩሲያ ላይ 6ኛ ዙር ማዕቀብ ለመጣል እየተዘጋጀ ሲሆን ከሩሲያ ነዳጅ ማስገባት ማቆምን ጨምሮ በአንዳንድ እርምጃዎች ላይ ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ነው የተዘገበው።" https://www.bbc.com/amharic/news-61375827 +health በኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዶሮዎችን የገደለው በሽታና የተጣለው የገበያ እግድ "ከሰሞኑ የዶሮ እርባታ ማዕከል በሆነችው በቢሾፍቱ፣ በአዲስ አበባና በአንዳንድ አጎራባች አካባቢዎች በተከሰተ ያልታወቀ የዶሮ በሽታ በበርካታ ሺህ የሚቆጠሩ ዶሮዎች መሞታቸውን ተከትሎ የግብርና ሚኒስቴር ዶሮና የዶሮ ውጤቶች ለገበያ እንዳይቀርቡ ሰኔ 03/2014 ዓ.ም እግድ ጥሏል። በአንዳንድ የዶሮ እርባታ ጣቢያዎች ውስጥ መቶ በመቶ በሚባል ሁኔታ ዶሮዎችን ገድሏል የተባለው ያልታወቀ የዶሮ በሽታ፣ ምንነትና መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ ዶሮ፣ ጫጩቶችና እንቁላሎች ከተለያዩ ክልሎች ማጓጓዝ አይቻልም። በተጨማሪም ዶሮ አርቢዎች ዶሮና የዶሮ ውጤቶችን ለገበያ ማቅረብ እንደማይችሉ የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና የእንስሳት ሃብት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በተለይ በሽታው በዋነኝነት በተከሰተባቸው በቢሾፍቱ፣ በአዲስ አበባና በአጎራባች አካባቢዎች ዶሮና የዶሮ ውጤቶችን ማጓጓዝ እንዲሁም ከውጭም ማስገባትም ሆነ ወደ ውጭ መላክ አይቻልም። በሽታው በተከሰተባቸው ስፍራዎች ብቻ ተወስኖ እንዲቀርና ወደሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት የእንቅስቃሴው ገደብ እንደተጣለ የሚናገሩት ዶክተር ፍቅሩ፣ ለተለያዩ ክልሎችም የየራሳቸውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። በአሁኑ ጊዜ መጀመሪያ ላይ እንደነበረው የዶሮዎች ሞት እየተከሰተ እንዳልሆነና የመቀነስ አዝማሚያ እንዳሳየ የሚናገሩት ሚኒስትር ዲኤታው ሆኖም ሙሉ በሙሉ አለመገታቱን አመልክተዋል። ይህንንም ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የተፈለፈሉ ጫጩቶች፣ እንዲሁም የደረሱ እንቁላሎች ለገበያ እንዳይውሉ እግድ በመጣሉ በርካታ ዶሮ አርቢዎች ለችግር ተጋልጠናል ብለዋል። የዶሮ በሽታው የተከሰተው ከሳምንት በፊት ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ የተሻሻለ የዶሮ እርባታ ያላቸው በሚባሉት ስፍራዎች በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱና በአጎራባች አካባቢዎች መሆኑን ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያስረዳል። የበሽታው መዛመትም ከቢሾፍቱ እስከ አዳማ ባለው ኮሪደር በስፋት ተከስቶ የነበረ መሆኑንም ብርሃኑ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ምንም እንኳን የዶሮ በሽታዎች በተደጋጋሚ ቢከሰቱም በሽታው በፍጥነት የመተላለፍና የመዛመት ባህርይ በማሳየቱ እንዲሁም በገባባቸው የዶሮ እርባታ ማዕከላት በብዛት እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ዶሮዎችን መግደሉን ዶክተር ፍቅሩ ይናገራሉ። በተለይም ያጠቃው አነስተኛ እና መካከለኛ የዶሮ እርባታ ማዕከላትን ሲሆን ሁሉም ዶሮዎች ያለቁባቸው ማርቢያዎችም ታይተዋል። እስካሁን ባለው መቶ ሺህ ወይም ከዚያ በላይ ዶሮዎች ሞተዋል ተብሎ የሚገመት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተጣራ መረጃ ላይ እንዳልደረሰና ገና ስለሁኔታ ግምገማም እያደረገ ነው። “በዚህ አይነት ፍጥነት መዛመቱና ዶሮዎችን በከፍተኛ ሁኔታ መግደሉ ስጋት ፈጥሯል። ዝም ከተባለም ከአንድ እርባታ ማዕከል ወደ ሌላ እርባታ ማዕከል የመዛመት ሁኔታ ሲያ���ይ ወደ እንቅስቃሴ ገደብ ገብተናል” ይላሉ ዶክተር ፍቅሩ። ከሰሞኑ የተከሰተው ያልታወቀ የዶሮ በሽታ ትልልቅ የዶሮ ማርቢያዎችን ያላጠቃ ቢሆንም፣ እነዚህ ማዕከላትም ቢሆን ዶሮና የዶሮ ግብዓቶች ማጓጓዝም ሆነ መሸጥ አይችሉም። የእንስሳት ህክምና ባለሞያ የሆኑት ዶክተር ደመቀ ወንድማገኝ መንግሥቴ፣ በሽታው በአነስተኛና በመካከለኛ ዶሮ እርባታ ማዕከል ያስከተለውን ከፍተኛ ሞት በማየት ክስተቱ ከበድ ያለ ሊሆን እንደሚችል ይጠቅሳሉ። በሽታው ሁሉንም አይነት ዶሮዎች፣ ጫጩቶችን ጨምሮ መጠነ ሰፊ ሞት በማድረሱና ሰፊ ቦታ በመሸፈኑ የዶሮ በሸታ ወረርሽኝ ሊባል እንደሚችል ዶክተር ደመቀ ያስረዳሉ። አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው በሽታው እያጠቃ ያለው በበለጠ የእንቁላል ዶሮዎችን እንደሆነና ጫጩቶችን ወይም የሥጋ ዶሮዎችን እየገደለ እንዳልሆነ ይገልጻሉ። እስካሁን ስለበሽታው የታወቀ ነገር ስለሌለ ምንነቱን ለመለየት የግብርና ሚኒስቴር የምርምር ሥራዎችን በዋነኝነት እያከናወነ ይገኛል። ሆኖም በተደረገው ዳሰሳና ከበሽታው ባህርይ በመነሳት በንክኪ ስለሚተላለፍ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱና በኦሮሚያ ክልል የዶሮና የዶሮ ውጤቶች ገቢም ሆነ ወጪ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ውሳኔ ተላልፏል። ለዚህ ውሳኔ ምክንያቱም አንዳንድ አርቢዎች ዶሮዎች ሲታመሙባቸው ከማስወገድ ይልቅ የመሸጥ ሁኔታ በመታየቱና በሌሎች ስፍራዎች ተዛምቶ በአጠቃላይ በአገሪቱ የዶሮ እርባታ ዘርፍን እንዳይጎዳ በሚል የተወሰደ እርምጃ እንደሆነ ሚኒስትር ዲኤታው ይጠቅሳሉ። አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው ጠበቅ ያለና ሙሉ እገዳ ነው የተጣለው ያሉ ሲሆን፣ እሳቸውም ሲጠቅሱ በኢትዮጵያ ደረጃ ከክልል ወደ ክልል ዶሮና የዶሮ ግብዓቶችን እንቁላልና ጫጩቶችን ማጓጓዝ አይቻልም። ከዶሮና የዶሮ ውጤቶች በተጨማሪ ከዶሮ ጋር ንክኪ የሚኖራቸውን መገልገያዎችን መኖን ጨምሮ ማጓጓዝ እንደተገደበ ያስረዳሉ። ከዚህ ባለፈ ዶሮ፣ ጫጩቶች፣ ቄቦች፣ የዳበረ (የለማ) እንቁላል ከውጭ አገራትም እንዳይገቡ እንዲሁም ወደ ውጭ እንዳይላኩ እገዳው ይከለክላል። ለገበያ ማቅረቡም ሆነ የእንቅስቃሴ ገደቡ በሽታው ተለይቶ በቁጥጥር ስር እስኪውል ድረስም የሚቀጥል እንደሚሆን በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተገልጿል። ባለፈው ሳምንት የሞት መጠኑ ከፍተኛ የነበረ ቢሆንም፣ ባለፉት ቀናት ግን ጋብ የማለት ምልክት እንዳሳየም ሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ፍቅሩ፣ አቶ ብርሃኑ እንዲሁም ዶክተር ደመቀ ያስረዳሉ። “ሞት ቆሟል ማለት በሽታው አይዛመትም ማለት ስለማይቻል፣ ምን አይነት ተፅእኖ እንደሚያመጣ ስለማይታወቅ፤ የኅብረተሰብ ጤና ጉዳይም ስለሚኖረው ያንን ማጣራት ያስፈልጋል” ይላሉ ዶክተር ደመቀ። ሆኖም በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱና አጎራባች አካባቢዎች ያሉ ዶሮ አርቢዎች ምርቶቻቸውን ማጓጓዝ እና ለገበያ ማቅረብ ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርገናል ይላሉ። በተለይም አቶ ብርሃኑ እንደሚናገሩት አብዛኞቹ አነስተኛ የዶሮ አርቢዎች በመሆናቸው ከዶሮ ምርታቸው በሚያገኙት ገቢ ላይ ጥገኛ በመሆናቸው ከፍተኛ ጉዳት አስከትሎባቸዋል። በዶሮዎች ላይ ከተከሰተው በሽታ ጋር በተያያዘ በተጣለው ገደቡ ምክንያት ባለፈው ሳምንት ውስጥ ብቻ 40 ሺህ የሚሆኑ ጫጩቶች በአንድ የእርባታ ስፍራ ተቀብረዋል ይላሉ። አቶ ብርሃኑ እንደሚሉት አንዳንድ ማዕከላት ዋነኛ ተግባራቸው ጫጩት እያስፈለፈሉ መሸጥ ስለሆነ ይህም በሺዎች የሚቆጠሩ ጫጩቶች ያስፈለፈለው ማዕከል ማጓጓዝ ባለመቻሉ ለማስወገድ ተገዷል። ሌላኛው አቶ ብርሃኑ የሚጠቅሱት የዶሮ እርባታና ማቀናበሪያ ማዕከል መፈልፈል የነበረባቸው 50 ሺህ እንቁላሎች እንደያዘ በመቆየቱ ከጥቅም ውጪ ��ንደሚሆን ነው። በተጨማሪም ከውጭ አገራት በዶላር ከፍተኛ ክምችት አስገብተው እንቁላል መፈልፈልና መሸጥ ቢኖርባቸውም እነዚህ ማዕከላት ይህንን ማድረግ ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጋቸውንም ያስረዳሉ። በርካታ የዘር እንቁላሎችም ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ይህ ሁኔታ አርቢዎችን በተለይም አነስተኛ አርቢዎችን ከሥራ እያስወጣ መሆኑንም ይገልጻሉ። ሌላኛው የሚያነሱት ችግር እነዚህ አርቢዎች ከሚያገኙት ገቢ መኖ መግዛት ባለመቻላቸው፣ እገዳው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ዶሮዎቹ በረሃብ ያልቃሉ የሚል ስጋትም ተጋርጦባቸዋል። “ዶሮዎቹ ከበሽታው በበለጠ በረሃብ ሊያልቁ ይችላሉ” ይላሉ አቶ ብርሃኑ። የአገሪቱን ከሃምሳ በመቶ በላይ የሆነ የእንቁላል አቅርቦት የሚይዙት አነስተኛ አርቢዎች ናቸው የሚሉት አቶ ብርሃኑ፣ ከሞቱ በላይ ምርት አለመሸጥ ከፍተኛ ጉዳት ስላላው ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ያስረዳሉ። “ነገ ከነገ ወዲያ የእነዚህ የዶሮ እርባታ ማዕከላት ዕጣ ፈንታ ምንድን ነው?” ሲሉም ይጠይቃሉ። ቅሬታቸውንም ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን በአጭር ጊዜም መፍትሄ ያገኛል የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። በርካታ አባሎቻቸውም ከፍተኛ ቅሬታ እያነሱ ሲሆን አፋጣኝ ጥናት ተደርጎ በሽታው ከተለየና ሌላ ችግር የማያስከትል ከሆነ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ ወደ ሥራ የሚመለሱበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንደሚፈልጉ አመልክተዋል። ለአቶ ብርሃኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጣላቸው የእንቅስቃሴ ገደቦች ከባድ የሚባሉ መሆናቸውን ነው። በተጨማሪም በሽታው የከፋ ስጋት እንደማይደቅን ከሚጠቅሷቸው ምክንያቶች ዋነኛው ወደ ሰው አለመተላለፉን ነው። የበሽታው ምንነት በአሁኑ ወቅት እየተመረመረ ቢሆንም ሚኒስትሩም ሆነ አቶ ብርሃኑ በሽተኛ ዶሮዎችን ሲንከባከቡ ከነበሩ ግለሰቦች እንዲሁም በማዕከላቱ ከተደረገው አሰሳ ወደ ሰው እንደማይተላለፍ ነው። በሽተኛ ዶሮዎችን ሲንከባከቡ የነበሩ ግለሰቦች ምንም አይነት የህመም ምልክት አላሳዩም። ሌላኛው አቶ ብርሃኑ የሚጠቅሱት ምክንያት በአንዳንድ የእርባታ ማዕከላት አቅራቢያቸው ያለው ማዕከል በበሽታ ቢጠቃም ወደሌሎች አለመዛመቱ ሌላው የሚጠቅሱት ምክንያት ነው። በተጨማሪም በባለፉት ሦስት እና አራት ቀናት ሞት እንዳልተከሰተ፣ በሽታውም የለም በሚባልበት ደረጃ ላይ እንዳለ እንዲሁም በትልልቅ የማራቢያ ማዕከላት ባለመከሰቱ መሆኑ ሌላኛው በጎ ምልክት ነው ይላሉ። በአነስተኛና መካከለኛ ደረጃ ላይ ባሉ ጣቢያዎች መከሰቱ የጥንቃቄ መላላት (ባዮ ሴኩሪቲ ደካማ) መሆን ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ሲሉም ይጠቁማሉ። “በሽታ አለ። ዶሮ ሁልጊዜም ከበሽታ ጋር ነው የሚኖረው። ለሰው ጤና ጉዳት የማያመጣ ከሆነ ሌላውን በክትባትም እየተቋቋምን መኖር እንችላለን። ለምሳሌ ኒውካስትል የሚባለው የዶሮ በሽታ 70 አስከ 80 በመቶ ገዳይ ነው። ይህም ተመሳሳይ በሽታ ከሆነ ማዕከላቱ ጥንቃቄ እያደረጉ ወደ ሥራ መመለስ ይኖርባቸዋል። አሁን በርካታ ጉዳቶች እየደረሱ ናቸው” ይላሉ። ሚኒስትሩ የተጣሉት ገደቦች ከባድ ነው በሚለው አይስማሙም “ከባዱ ነገር ዶሮዎቹ ማለቃቸው ነው” ይላሉ። ምንነቱ ያልታወቀው በሸታ በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ የማርቢያ ማዕከላት ተዛምቶ ዶሮዎችን ቢጨርስስ? ብለው የሚጠይቁት ሚኒስትር ዲኤታው በአጠቃላይ የዶሮ እርባታና ማቀናበር ሥርዓቱን ሊገድል ይችላል ይላሉ። ሆኖም በዶሮ አርቢዎች ላይ ያለውን ተፅእኖና ኪሳራ እንደሚረዱ ገልጸዋል። “ወደን ሳይሆን ከመጥፎው የተሻለ መጥፎን መምረጥ ነው። ለጊዜው እንቁላሉንም ሽያጩንም ያዝ አድርገው እኛ ደግሞ የተከሰተባቸው ቦታዎች ላይ እርምጃ ወስደን ከተቆ���ጠርን በኋላ የተሻለ ነገር ይኖራል” ይላሉ። እንዲህ አይነት እርምጃዎች በበርካታ አገራት የሚወሰዱ የተለመዱ አሰራሮችም መሆናቸውንም አፅንኦት ይሰጣሉ። ለዶክተር ደመቀም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጣለው እገዳ ሳይንሱን ተከትለው ነው ይላሉ። የትኛውም አገር ላይ ወረርሽኝ ሲያጋጥም እንቅስቃሴ መገደብ የተለመደ መሆኑን የሚጠቅሱት ዶክተር ደመቀ፣ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ይጠቅሳሉ። መሥሪያ ቤቱ በንክኪ መዛመትን ለመግታት እንቅስቃሴን መገደብን በዚህም ሕዝቡንም ሆነ የዶሮ እርባታ ማዕከላትን ለመጠበቅ፣ እንዲህ አይነት እርምጃ በበርካታ አገራት ተግባራዊ ይደረጋል ይላሉ። ሆኖም ሳይንሱ ይህንን ቢልም በኢትዮጵያ አንድምታ አብዛኛው ዶሮ አርቢ መኖና የተለያዩ መገልገያዎች የሚገዛው ከቢሾፍቱ ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ በሽታ ያልገባባቸው አካባቢዎች በመኖና በሌሎች መገልገያዎች ጥገኛ ስለሚሆኑ በሎጂስቲክ መቋረጥ ምክንያት ችግር ውስጥ እንደሚገቡም ያስረዳሉ። ሆኖም ይላሉ ዶክተር ደመቀ “እንዲህ አይነት ውሳኔዎች ሲወሰኑ በጣም መጥፎ ከሚባለው፣ የተሻለውን መጥፎ መምረጥ የሚለውን አሰራር ተከትሎ ነው።"" ዶክተር ደመቀ እንደሚያስረዱት የዶሮ በሽታ ወረርሽኝ አለ የሚባለው ከሁለት በላይ የሆኑ የዶሮ እርባታ ማዕከላትን ሲያጠቃ ነው። በዚህም ወቅት የተከሰተው በሽታ በርካታ ማዕከላትን ማጥቃቱ ወደ አጎራባች አካባቢዎች መዛመቱ የዶሮ ወረርሽኝ ሊባል ይችላል ይላሉ። ከዚህ በፊት አጋጥሞ ቢያውቅም በዚህ ደረጃ እንዳልነበርና መለስ ያሉ የዶሮ መሞት መጠን እንደነበረና የተወሰነውንም መርጦ እንዳጋጠመ ያወሳሉ። ዶክተር ፍቅሩም በአንዳንድ የዶሮ እርባታ ማዕከላት መቶ በመቶ ዶሮዎቹን በመጨረሱ ወረርሽኝ ነው ለማለት እንደሚያስችል ያስረዳሉ። ወረርሽኝ በሚያጋጥምበት ወቅት እንቅስቃሴዎችን መገደብን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎች እንደሚወሰዱ የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ፣ ወረርሽኝ ነው ተብሎ የሚታሰብ ከሆነ በፍጥነት መለየት እንዳለበት ያስረዳሉ። “የዶሮ እርባታ ዘርፉ በቋፍ ላይ ነው” የሚሉት አቶ ብርሃኑ በርካታ ችግሮች ያሉበትና እድገት የማያሳይ ነው የሚሉትን ዘርፍ ሊያቀጭጨው እንደሚችልም ያስጠነቅቃሉ። አሁን ባለው ሁኔታም ላይነሳ ከሚወድቅበት ደረጃ ላይ በመሆኑ እግዱ ላላ ሊል ይገባል ይላሉ። ወረርሽኝ ተከስቶ እንደማያውቅ የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ በ1997ም ‘በርድ ፍሉ’ ነው በሚል እሳቤ በርካታ ዶሮዎች መገደላቸውን አስታውሰው። የላብራቶሪ ውጤቱ ግን ወረርሽኝ እንዳልሆነ በማሳየቱ የተወሰደው ትክክለኛ እርምጃ እንዳልነበር ያወሳሉ። በዚህም ወቅት ተመሳሳይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ የሚናገሩት ሥራ አስኪያጁ በሽታው ታውቆ ለዚያ የሚሆን ትክክለኛ እርምጃ ቢወሰድ ችግር እንደሌለውም ያስረዳሉ። ነገር ግን “በአሁኑ ወቅት ውጤቱ ባልታወቀበትና አመላካች ሁኔታዎች ብዙ ወረርሽኝ በማይመስሉበት ሁኔታ” ወደ እገዳ እርምጃ መገባቱ ትክክል እንዳልሆነም አፅንኦት ይሰጣሉ። የዶሮ እርባታ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣ ዘርፍ ነው የሚሉት ዶክተር ፍቅሩ፣ ይህም እንዳይጎዳ ስለ በሽታው ምንነት በማያሻማ መልኩ ውጤቱ አስኪታወቅ ድረስ ገደቡ የሚቀጥል ሲሆን፣ አሁን በተያዘው ሁኔታ ረጅም ጊዜ ሊቆይ እንደማይችልም ያስረዳሉ። የዶሮ አርቢዎች ማኅበር በተጨማሪ የሚያነሱት ቅሬታ በግብርና ሚኒስቴር እየተላለፉ ያሉ ውሳኔዎች ማኅበሩን ያገለሉ መሆናቸውን ነው። ማኅበሩ እንደ ዋና ባለ ድርሻ አካል በምርምሮቹና በመፍትሄዎቹ ላይ ተሳታፊ ቢሆን ለመከላከያ እርምጃውም የተሻለ ግብዓት እንዲሁም በተቀላጠፈ ጊዜ ቶሎ ��ጤት ላይ ለመድረስ ይቻላል ብለው ያምናሉ። ከተከሰተው የዶሮ በሽታ ጋር በተያያዘ ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጣ ግብረ ኃይል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አቋቁሟል። ግንዛቤ የማስጨበጥ እንዲሁም በሸታው በተከሰተባቸው ስፍራዎች የክትትል ሥራ፣ ምርምሮች፣ ምላሽ የመስጠት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በርካታ ዶሮዎች በየጢሻው ተጥለው በመገኘታቸው በሽታው እንዳይስፋፋና በድጋሚ እንዳይከሰት እነዚህን የሞቱ ዶሮዎችን አሰባስቦ የማስቀበርና የማቃጠል ሥራዎች እየተሰሩ ነው። በሽታው በተከሰተባቸው ስፍራዎች ሌላ በሽታ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ኬሚካል የመርጨት ተግባር እየተከናወነ ነው። ትልልቆቹ የዶሮ እርባታ ማዕከላትም የደኅንነት አጠባበቃቸውን በማሳደግ በዚያው ምርቶቻቸውን እንዲይዙ ተደርጓል። የዶሮ እርባታ ማዕከላት ላይ በሽታዎች የመከሰት ነገር የተለመደ መሆኑን የሚናገሩት ዶክተር ፍቅሩና ዶክተር ደመቀ፣ በሽታዎች ሲከሰቱ ሊያደርሷቸው የሚችሉ ጉዳቶችን በተመለከተ አስቀድመው መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች (የባዮ ሴኩሪቲ ደኅንነት) ቢኖርም አንዳንዶች በትክክል ተግባራዊ እንደማያደርጉ ይናገራሉ። በተጨማሪም ኬሚካሎችና የጽዳት ግብዓቶች (ዲስኢንፌክታንት) የማይጠቀሙ፣ ክትባትም ጊዜውን ጠብቀው በአግባቡ የማይሰጡ የእርባታ ማዕከላት ሲኖሩ በሽታዎች እንደሚከሰቱ ጠቅሰው፣ በአሁኑ ወቅት ጥንቃቄዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ዶክተር ፍቅሩ ለአርቢዎች የሚመክሩት በአካባቢያቸው የሞቱና የተጣሉ ዶሮዎች ካሉ በአግባቡ ማስወገድ፣ የኬሚካል ርጭትም ካለ ያንን ማከናወን ከተሰማራው ግብረ ኃይል ጋር በከላከል ሥራው ላይ እንዲሳተፉ መክረዋል። ኅብረተሰቡም ቢሆን ጥቆማ እንዲያደርግ የሚመክሩት ዶክተር ፍቅሩ፣ በተባባረ መንገድም በፍጥነት ለመቆጣጠርና ለማጥፋት ይረዳል ይላሉ። በተለያዩ መንገዶች እየወጡ ያሉ መረጃዎች ኅብረተሰቡን ዶሮና እንቁላል ከመመገብ ፍርሃት ውስጥ የሚከቱ ናቸው የሚሉት አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው፣ ለሰው ጤና አስጊ ባልሆነበት ሁኔታ ለመረጃዎች ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ይላሉ። “ይሄንን ያህል የሚያስፈራ ነገር የለም። ነገር ግን በደንብ ያልታወቀ ጉዳይ ደግሞ እንዲህ አድርጉ ማለት አይቻልም። ምንም አይነት የገጠመ ወይም ሪፖርት የተደረገ የለም። ነገሮችን እስከምናውቅ ብሉ አትብሉ ልንል አንችልም” ይላሉ ዶክተር ፍቅሩ በበኩላቸው። ዶክተር ደመቀ ሕዝቡ ዶሮንም ሆነ የዶሮ ተዋፅኦ የሚጠበቅበት መንድ አብስሎ ስለሆነ፣ በደንብ ማብሰልና ንፅህናውን የመጠበቅ ሁኔታ ካለ ተጠቃሚውን የሚያሰጋ ነገር ሊኖር ይችላል ብለው እንደማያስቡ ያስረዳሉ። ሆኖም በአጠቃላይ ባለሙያው የሚያስተላልፉት መልዕክት የዶሮ እርባታ ወደ ኢንዱስትሪ ሊያድግ እንደሚችል ጠቅሰው፣ ይህም የራሱ ችግር ስለሚያመጣ ተገቢ የሆነ የዶሮ በሽታ መከላከልና መቋቋም ሥራ በተገቢው መንገድ መሰራት እንዳለበት ነው። ይህንንም የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትም ሆነ የግል ሴክተሩ አንድ ላይ ሆነው ፕሮግራም ቢቀርጹ ጥሩ ነው በማለት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c4nlzg7pry9o +sports አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለት መኪና እና መሬት እስካሁን ለምን አልተሰጠውም? "አትሌት ሰለሞን ባረጋ ከወራት በፊት ታላቁ ቤተ-መንግሥት በተካሄደ ስነ-ስርዓት መኪና በሽልማት መልክ እንደተበረከተለት ቢገለጽም መኪናው እስካሁን ድረስ እጁ አልደረሰም። በ32ኛ የቶኪዮ ኦሎምፒክ በ10ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ሰለሞን 3 ሚሊዮን ብር ያወጣል የተባለው መኪና ከፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ እጅ እንደተበረከተለት ቢ��ለጽም ከ7 ወራት በኋላ ሽልማቱ ከአትሌቱ እጅ አልደረሰም። አትሌት ሰለሞን ባረጋ የቀድሞ የፌደራል ስፖርት ፌዴሬሽን የአሁኑ የስፖርት እና ባህል ሚኒስቴር ትብብር ባይነፈገውም በውጭ ምንዛሬ ችግር ምክንያት መኪናው እስካሁን እጁ እንዳልገባ ለቢቢሲ ተናግሯል። ""ሚኒስትሮች ተቀያይረዋል። አዲስ የመጡ ሰዎች ናቸው። እኔም 'የት ደረሰ' እያልኩ አልጠየቅኩም። ሞኤንኮ ያስገባል ተብሎ ነበር። ይመስለኛል ኩባንያው መኪናውን ለማስገባት የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሬ ማግኘት አልቻለም። እንዳደውም በጣም እየተባበሩኝ እኔ በምፈልግበት ሁኔታ እየሄዱ ነው ያሉት"" በማለት አትሌት ሰለሞን ሁኔታውን አብራርቷል። በባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት አምባሳደር መስፍን ቸርነት፤ ለአትሌቱ ቃል የተገባለት ስጦታ በውጭ ምንዛሬ እጥረት እስካሁን እንዳልተሰጠው ተናግረዋል። አትሌቱ ላስገኘው ድል የሚመጥን ስጦት ለመስጠት ከውሳኔ ከተደረሰ በኋላ፤ ""የተመረጠው መኪና አገር ውስጥ ስለሌለ በጀቱ ተይዞ እንደሚቀርብ ተወስኖ ነው ፕሮግራሙ የተካሄደው"" ብለዋል አምባሳደር መስፍን። ልጁ አሸንፎ ይገባል የሚል ዝግጅት አልነበረም። ግን አሸንፎ አገር ቤት እንደገባ የአገርን ክብር የሚመጥን ሽልማት ሊደረግለት ይገባ ነበር። ስለዚህ የተፈለገውን መኪና ሞዴል ተመርጦ ዝግጅቱ ተካሄደ። ሞኤንኮ 'አሁን እጄ ላይ መኪና የለም ከውጭ አስመጣለሁ' አለን። በሸልማት ስነ-ስርዓቱ በፎቶ የታየው መኪና ቃል የተገባው እንጂ የተሰጠው አይደለም"" ሲሉ ሚኒስትር ዲኤታው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነሐሴ 27/2013 ዓ.ም. በታላቁ ቤተመንግሥት የተዘጋጀውን የሽልማት ስነ-ስርዓቱን ያሰናዳው የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን ስለመሆኑ መንግሥታዊ የሆኑ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በወቅቱ ዘግበው ነበር። በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የብር ሜዳሊያ ላመጣው አትሌት 1.5 ሚሊዮን ብር እንዲሁም የነሐስ ሜዳሊያ ላስገኙት አትሌቶች ደግሞ የ1 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት ለመስጠት ቃል ተገብቶ ነበር። በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ3ሺህ ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ለሜቻ ግርማ ቃል የተገባለት የገንዘብ ሽልማት እንደተፈጸመ ለቢቢሲ ተናግሯል። በተጨማሪም በ10ሺህ እና 5ሺህ ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ ያስገኙት አትሌት ለተሰንበት ግደይ እና ጉዳፍ ጸጋይ እያንዳንዳቸው ቃል የተገባላቸውን የ1 ሚሊዮን ብር ሽልማት መቀበላቸውን ቢቢሲ ለአትሌቶቹ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች ማረጋገጥ ችሏል። አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለት የመኪና ሽልማት እስካሁን እጁ ባይደርስም በሁኔታው ቅር አለመሰኘቱን ለቢቢሲ ተናግሯል። ""አገሪቱ ካለችበት ሁኔታ ጋር ተያይዞ የውጭ ምንዛሬ ስለሌለ እንጂ ሌላ ነገር ተፈጥሮ አይደለም። ይሄ ትንሽ ዘገየ እንጂ ከእኔ በፊት የነበሩ አትሌቶች እንደዚሁ ነው። ይዘገያል። ቆይቶ ነው የተሰጣቸው"" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ""በጣም ነው እየተባበሩኝ ያሉት። እየተከታተሉ ነው። ዝም ብለው ነው ፌስቡክ ላይ የሚያወሩት። እኔ ያስገባሁት ቅሬታም የለም። ሲጀመር በዚህ ሰዓት አገራዊ ነገሮች ባልተስተካከሉበት ሰዓት መኪና አልተሰጠኝም የምልበት ጊዜ አይደለም"" ብሏል አትሌት ሰለሞን በሽልማት መልክ ሊሰጠው የነበረው መኪና ዋጋ በብር ተሰጥቶት፤ እርሱ በራሱ የውጭ ምንዛሬ የፈቀደውን መኪና ከቀረጥ ነጻ ለማስገባት ከስፖርት እና ባህል ሚኒስቴር ጋር ከተነጋገረ በኋላ ሚኒስቴሩ ትብብር እያደረገለት መሆኑን ለቢቢሲ አስረድቷል። ""ከቀረጥ ነጻ እንዳስገባ ስፖርት ሚኒስቴር የጻፈው ደብዳቤ አሁን ገንዘብ ሚኒስቴር"" ይገኛል ብሏል አትሌት ሰለሞን ባረጋ። በተመሳሳይ ���ምባሳደር መስፍን ቸርነት በአትሌት ሰለሞን ጥያቄ መሠረት የመኪና ግዢ የሚፈጸምበት ገንዘብ ገቢ ተደርጎለት በራሱ የውጭ ምንዛሬ ከቀረጥ ነጻ መኪና እንዲያስገባ ደብዳቤ ለገንዘብ ሚኒስቴር ልኮ ጉዳዩ እንዲፈጸምለት እየተከታተልን ነው ሲሉ ለቢቢሲ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የወልቂጤ 10ሺህ ካሬ ሜትር አትሌት ሰለሞን ከቶኪዮ ኦሎምፒክ ድሉ በኋላ ከመኪናው በተጨማሪ በወልቂጤ ከተማ 10 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት እንደሚሰጠው ሐዋሳ ከተማ ላይ በተደረገ ስነ-ስርዓት ተገልጾለት ነበር። ይኹን እንጂ ይሄም ሽልማት በተመሳሳይ ከአትሌቱ እጅ አልደረሰም። ""ወልቂጤ ዞን ላይ ነው። 10ሺህ ካሬ ሜትር ነው። እነሱም ቦታ በማፈላለግ ላይ ናቸው። በስልክ እየተነጋገርኩ ነው። ጥሩ ቦታ እየመረጡ ነው ያሉት። 'ስናስጨርስ እንደውልልሃለን' ብለውኛል ስልክ እየጠበቀኩ ነው"" በማለት አትሌት ሰለሞን ያለውን ሁኔታ ለቢቢሲ አስረድቷል። በጉዳዩ ላይ የኢትዯጵያ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አስተያየትን ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።" https://www.bbc.com/amharic/61143075 +politics የሄይቲው ጠቅላይ ሚኒስትር ከግድያ ሙከራ አመለጡ "የሄይቲው ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርዬል ሄንሪ ባለፈው ቅዳሜ የሃገራቸውን የነፃነት ቀን እያከበሩ ሳለ በታጣቂዎች የግድያ ሙከራ እንደተረገባቸው ባለሥልጣናት ገለጡ። በሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ጎናይቭስ ከተማ ባለ አንድ ቤተ እምነት ውስጥ ሥነ ሥርዓቱን እየታደሙ ባሉበት ወቅት ነው ሙከራው የተደረገባቸው። ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ የተለጠፉ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደሚያሳዩት ጠቅላይ ሚኒስትሩና አጃቢዎቻቸው ከነበረው የተኩስ እሩምታ በመሸሽ ወደመኪናቸው ሲሮጡ ነበር። ሄይቲ፤ ፕሬዝደንቷ ከተገደሉባት በኋላ የደህንነት መዋቅሯ የተፈረካከሰ መስሏል። ፕሬዝደንት ጆቬኔል ሞይዝ ባለፈው ሐምሌ ነበር የተገደሉት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃገሪቱ ውስጥ የሚታየውን አፈና ለማስቀረት አደገኛ የወንጀለኞች ቡድንን መረብ እበጣጥሳለሁ ብለው ቃል ገብተው እንደነበር ይታወሳል። እኒህ በቡድን የተደራጁ ወንጀለኞች ወደተለያዩ ሥፍራዎች የሚሠራጩ ነዳጆችን በመዝረፍ በሄይቲ የነዳጅ እጥረት አስከተሏል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ እንዳለው ""ባንዳዎችና አሸባሪዎች"" ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ግድያ ጀርባ አሉበት። አልፎም በቁጥጥር ሥር ውለው ለፍርድ እንዲቀርቡ ማዘዣ ወጥቷል። ኦሶሺዬትድ ፕሬስ የተሰኘው የዜና ወኪል እንደዘገባው ታጣቂው ቡድን ጳጰሱን በማስፈራራት የቤተ ክርስትያኒቱን አጥር ከበው የጠቅላይ ሚኒስትር ሄንሪን መኪና ለማጥቃት ሲጠብቁ ነበር። በነበረው የተኩስ ልውውጥ አንድ ሰው ሲገደል ሁለት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ሲሉ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት ባለፈው ሐምሌ ፕሬዝደንቷን ላጣችው ሃገር ከባድ ፈተና ነው ተብሏል። ጠቅላይ ሚንስትር ሄንሪ የፕሬዝደንት ሞይዝን ግድያ ተከትሎ የሃገሪቱ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ። ፕሬዝደንት ሞይዝ የተገደሉት በቀድሞ የአሜሪካ ሠራዊት አባላት ትብብር ነው ተብሎ የተነገረው እስካሁን አልተጣራም። አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመምረጥ እስካሁን ቀን አልተቆረጠም። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሄይቲን ደጋግሞ የጎበኛት የተፈጥሮ አደጋ እንዲሁም እያደገ የመጣው አመፀኝነት ከምጣኔ ሃብት ሁኔታው ጋር ተዳምሮ የሃገሪቱ ዜጎች ስደትን እንደሚርጡ አስገድዷቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59864518 +health ኮሮናቫይረስ፡ ኒውዚላንድ 14 በከሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች አገኘች የኒውዚላንዷ ትልቋ ከተማ ኦክላንድ በድጋሚ የእንቅስቃሴ ገደብ ከተጣለባት በኋላ አዲስ 14 በኮሮረናቫይረስ የ��ያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተገለጸ። በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ አራት አንድ የቤተሰብ አባላት የሆኑ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲሰማ መላው ኒውዚላንድ በድንጋጤ ተውጦ የነበረ ሲሆን የአሁኑ ደግሞ ነገሮችን አባብሷል። ከውጭ አገራት በቫይረሱ ተይዘው ከሚመጡ ሰዎች ውጪ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ አገሪቱ ላለፉት ሶስት ወራት ምንም በቫይረሱ የተያዘ ሰው አላገኘችም ነበር። ዛሬ ከተገኙት ተጨማሪ 14 ሰዎች መካከል 13ቱ ከዚሁ ቤተሰብ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን አንደኛው ግለሰብ ደግሞ ከሌላ አገር ወደ ኒውዚላንድ ገብቶ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ እንደሆነ ተገልጿል። ከትላንት ረቡዕ ጀምሮ ደግሞ በኦክላንድ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። '' ሁኔታው ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ማየት እንችላለን'' ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጃሲንዳ አርደርን። በሰጡት ጋዜታዊ መግለጫ ላይ አክለውም '' ጉዳዩ በተገቢው መንገድ ክትትል እየተደረገበት ነው፤ ፈጣንና ተገቢው እርምጃም ይወሰዳል'' ሲሉ ተደምጠዋል። ሁሉም ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን ኃላፊዎች ያስታወቁ ሲሆን ከነሱ ጋር በማንኛውም መንገድ ንክኪ የነበራቸው ሰዎችም ክትትል እንደሚደረግባቸው ገልጸዋል። ኒውዚላንድ እስካሁን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በወሰደቻቸው ፈጣንና ውጤታማ እርምጃዎች ከመላው ዓለም ምስጋናና ሙገሳ ሲጎርፍላት ነበር። ይህ ዜና ከተሰማ በኋላም በመላው አገሪቱ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ግዴታ የተደረገ ሲሆን ቫይረሱ በተገኘባት ኦክላንድ ደግሞ ጠንከር ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። ከማክሰኞ በፊት በኒው ዚላንድ በአገር ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ሳታገኝ 102 ቀናት መቆየት የቻለች አገር ነበረች። የአገሪቱ የጤና ኃላፊዎችና ሰራተኞች ቫይረሱ ከየት እንደተነሳ ለማወቅ በፍጥነት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ተገልጿል። በኮቪድ-19 የተያዙት ሰዎች ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና የስራ ባልደረቦችም ተለይተው ምርመራ ይደረግላቸዋል ተብሏል። '' ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት ያለእረፍት እየሰራን ነው። ምንጩ ከየት እንደሆነም ለማወቅ የምንችለውን ነገር በሙሉ እያደረግን ነው'' ብለዋል ብሄራዊ የጤና ኃላፊው አሽሊ ብሉምፊልድ። ቫይረሱ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በድጋሚ ሲያገረሽ ይሄ የመጀመሪያው አይደለም። በርካታ የአውሮፓ አገራት ሁኔታዎች መሻሻል ሲያሳዩ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ማንሳታቸውን ተከትሎ ቫይረሱ ሁለተኛ ዙር መስፋፋት ጀምሯል። ቪየትናም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሳታገኝ 99 ቀናት ሳታገኝ ከቆየች በኋላ ዳ ናንግ በተባለችው ከተማ ስርጭቱ በድጋሚ መጀመሩ የሚታወስ ነው። በኒውዚላንድ ወረርሽኙ በድጋሚ መቀስቀሱ ምናልባት በሌሎች ከተሞችም የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ሊያስገድድ እንደሚችል ተፈርቷል። አገሪቱ ደግሞ በሳምንታት ልዩነት ውስጥ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ነበረች። ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ምን አይነት ውሳኔዎች እንሚተላለፉ ነገ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። https://www.bbc.com/amharic/news-53761579 +sports """ማንቸስተር ሲቲን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሼ ነበር"" ክርስቲያኖ ሮናልዶ" "ክርስቲያኖ ሮናልዶ “የልቡን መሻት” ተከትሎ ማንቸስተር ዩናይትድን በድጋሚ ከመቀላቀሉ በፊት ለማንቸስተር ሲቲ ለመፈረም ከጫፍ ደርሶ እንደነበር ተናግሯል። ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጫዋች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ክለቡ “ከድቶኛል” ሲል ለቶክ ቲቪ ከተናገረ በኋላ መነጋገሪያ ሆኗል። የሙሉ ቃለ ምልልሱ የመጀመሪያ ክፍል ረቡዕ ምሽት የተለቀቀ ሲሆን በኦልድ ትራፎርድ ስላለው ጉዳይ በዝርዝር መግለጫ ሰጥቷል። ���ቲን ሊቀላቀል እንደነበር ሲናገር ""እውነት ለመናገር ከጫፍ ደርሶ ነበር"" ብሏል። ሮናልዶ ክለቡን ለቆ ሪያል ማድሪድን ከተቀላቀለ ከ11 ዓመታት በኋላ ነሐሴ 2013 ነበር ከጁቬንቱስ ወደ ኦልድ ትራፎርድ የተመለሰው። በወቅቱ በሲቲው አለቃ ፔፕ ጋርዲዮላ እንደሚፈለግ ተነግሮ  ነበር። ሮናልዶ ፍላጎቱን እንደነበር አረጋግጦ ከቀድሞው አሰልጣኙ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ዩናይትድ ለመመለስ መወሰኑን ተናግሯል። የ37 ዓመቱ ተጫዋች አክሎም “እንደምታውቀው በማንቸስተር ዩናይትድ ያለኝ ታሪክ፣ ልብህ፣ ከዚህ በፊት የሠራኸውን ስታስታውስ [ውሳኔ ላይ] ለውጥ ያመጣል። በዚያ ላይ ደግሞ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን አለ” ብሏል። ""ከሱ ጋር ተነጋገርኩኝ። ‘ወደ ማንቸስተር ሲቲ መምጣት ለአንተ የማይቻል ነገር ነው’ አለኝ። እናም 'እሺ አለቃ' አልኩት” ሲል ገልጿል። በሆድ ሕመም ምክንያት ዛሬ ፖርቹጋል ከናይጄሪያ ጋር የምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ የሚያመልጠው ሮናልዶ በቃለ መጠይቁ ወቅት የወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾችን አመለካከት እና ፕሮፌሽናልነት በመተቸት በዕድሜ የገፉ እና ልምድ ያላቸውን የቡድን አጋሮቻቸውን ""አያከብሩም"" ሲል ወቅሷል። “ረሃባቸው [የተለየ ነው]። ነገሮች ቀለል ያሉላቸው ይመስለኛል። ሁሉም ነገር ቀላል ነው። አይለፉም። እናም ግድ የላቸውም” ሲል አክሏል። ""በማንችስተር ዩናይትድ ያሉ ጥቂቶችን ብቻ ማለቴ አይደለም። ነገርግን በሁሉም የዓለም ሊጎች ውስጥ ያሉ ወጣቶቹ ሁሉ እንደ እኔ ትውልድ አይደሉም። ""ነገር ግን እነሱን መውቀስ አይቻልም። ምክንያቱም የሕይወት እና የአዲሱ ትውልድ አካል ነው። አዳዲስ ቴክኖሎጂ ትኩረታቸውን ይከፋፍለዋል"" ብሏል። የ23 ዓመቱ የዩናይትድ እና የፖርቹጋል የቡድን አጋሩን ዲዮጎ ዳሎ ሊያመሰግናቸው ከሚችላቸው ጥቂት ወጣት ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደሆነ ሮናልዶ ገልጿል። ሮናልዶ አክሎም ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ እና ካሴሚሮ በክለቡ የሚያደንቃቸው ሌሎች ተጫዋቾች መሆናቸውንም ተናግሯል። ""በማንቸስተር ዩናይትድ ዳሎትን መጥቀስ እችላለሁ። ወጣት ነው ነገር ግን በጣም ፕሮፌሽናል ነው። በእግር ኳስ ረዥም ዕድሜ እንደሚኖረው አልጠራጠርም። ""ምክንያቱም እሱ ወጣት፣ ብልህ፣ አስተዋይ እና በጣም ፕሮፌሽናል ነው። ምናልባት ማርቲኔዝ እና ካሰሚሮም (ዕድሜው በ30ዎቹ ውስጥ ቢሆንም) ይካተታሉ።  ዳሎን ግን እጠቅሳለሁ"" ሲል ተናግሯል። ሮናልዶ ወደ ዩናይትድ ከተመለሰ ከሁለት ወራት በኋላ የቀድሞ የቡድን ጓደኛው ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ከአሠልጣኝነት ተሰናበተ። በምትኩ ራልፍ ራይኒክ እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ ጊዜያዊ አሠልጣኝ ሆነው ተሾሙ። ጀርመናዊው አርቢ ሌፕሺግ፣ ሻልክ እና ሌሎች በርካታ ክለቦች አሰልጥነዋል። የእግር ኳስ ፍልስፍናቸው እንደ ዩርገን ክሎፕ እና ቶማስ ቱሄል ባሉ አሠልጣኞች ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ይነገርላቸዋል። ሮናልዶ ግን በሹመቱ እንዳስገረመው ተናግሯል። ""ሰውየው አሠልጣኝ እንኳን አይደለም። እንደ ማንቸስተር ዩናይትድ ያለ ትልቅ ክለብ የስፖርት ዳይሬክተር ሲያመጣ እኔን ብቻ ሳይሆን ዓለምን ሁሉ አስገርሟል"" ብሏል። ስለ ራይኒክ ሰምቶ ያውቅ እንደሆን ሮናልዶ ሲጠየቅ “በጭራሽ ሰምቼ አላውቅም። ካነጋገርኳቸው ሰዎች ማንም አያውቀውም"" ብሏል። ""[እሱን] አከብራለሁ። በሙያዬ ውስጥ ያሉ አሠልጣኞችን ሁሉ ‘አለቃ’ ብዬ ልጠራቸው ይገባ ነበር። እሱን ግን እንደ አሠልጣኝ አላየውም። ምክንያቱም እኔ ያልተስማማሁባቸውን አንዳንድ ነጥቦች ስላየሁ ነው” ሲልም አክሏል። ሮናልዶ የማንቸስተር ዩናይትድ የቀድሞ ተጫዋቾች የሆኑት ዋይኒ ሩኒ እና ጋሪ ኔቪል ባህሪውን በተመለከተ በ��ርቡ ጥያቄ ካስነሱ በኋላ ተችቷቸዋል። ባለፈው ወር ከቶተንሃም ጋር በነበረው ጨዋታ ተቀይሮ ወደ ሜዳ ለመግባት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ሮናልዶ በክለቡ አላስፈላጊ ውዝግብ እየፈጠረ ነው በሚል ሩኒ ተናግሯል። ፖርቹጋላዊው ስለ ሩኒ ሲናገር “ለምን በጣም በክፉ እንደሚተቸኝ አላውቅም። ይቀናብኝ እንደሆነ አላውቅም” ብሏል። ""እንዲህ ያሉ ሰዎች በእውነት አይገቡኝም። የዜና የፊት ገጽ መሆን ወይም አዲስ ሥራ ወይም ሌላ ነገር ይፈልጉ አላውቅም። ""ምናልባት [ቅናት ሊሆን ይችላል]። ምክንያቱም ጫማውን የሰቀለው በ30 ዎቹ ውስጥ ነው። እኔ አሁንም በከፍተኛ ደረጃ እየተጫወትኩ ነው"" ብሏል። ኔቪልን በተመለከተ ሲናገር ደግሞ “ጓደኞቼ አይደሉም። ባልደረቦቼ ናቸው። ለምሳሌ አብረን እራት አንበላም“ ሲል ተናግሯል። ""ነገር ግን ይህ የጉዞዬ አካል ነው። ሁልጊዜም ይተቹኛል። እኔም ጉዞዬን መቀጠል እና ከሚወዱኝ ሰዎች ጋር መገናኘት አለብኝ” ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cpw4vl15n0lo +health ኮሮናቫይረስ፡ የዩኬ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በአሜሪካ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው ተባለ "እንግሊዝን እያስጨነቃት ያለው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በአሜሪካም በፍጥነት እየተስፋፋ እንደሆነ አንድ ጥናት ይፋ አድርጓል። በከፍተኛ መጠን የመተላለፍ ባህርይ አለው የተባለው ይህ ዝርያ በአሜሪካ በባለፉት ቀናት በእጥፍ እየተስፋፋ መሆኑን ይኼው ጥናት አስታውቋል። የዝርያው የመስፋፋት ፍጥነት ቢ1117 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን በአለም አቀፉ የክትባት ሂደቶችም ላይ ከፍተኛ ጫና አሳርፏል ተብሏል። የአሜሪካው የበሽታዎች ቁጥጥርና ክትትል (ሲዲሲ) የዩኬው የኮሮናቫይረስ ዝርያ በመጋቢት ወር ዋነኛው ኮሮና ይሆናል በማለት ተንብይዋል። ጥናቱ የተለያዩ ተመራማሪዎችና ሳይንቲስቶች የተጣመሩበት ሲሆን ሜድርክሲቭ በተባለ ድረገፅም ላይ ወጥቷል። በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በአሜሪካ አሁንም ትንሽ ነው ተብሏል። የአዲሱ ዝርያ ከተመዘገበባቸው ግዛቶች መካከል ፍሎሪዳ የምትመራ ሲሆን ካሊፎርኒያ ትከተላለች። ""ጥናታችን እንደሚያሳየው ሌሎች አገሮች ላይ ቢ117 በከፍተኛ ሁኔታ ተስፋፍቶ ዋነኛው የኮቪድ-1ዝርያ መሆን እንደቻለው እኛም ወደዛ እየገሰገስን ነው። የኮሮናቫይረስን አስከፊነትና ገዳይነት ለመቀነስ አስቸኳይና ወሳኝ እርምጃዎች እንደሚያስፈልጉም ማሳያ ነው"" ብለዋል የሪፖርቱ ፀሃፊዎች። በሪፖርቱ መሰረት አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከቀድሞው በበለጠ 35-45 በመቶ ብልጫ ፍጥነት ይተላለፋል። ሲዲሲ አዲሱ የቫይረስ ዝርያ መኖሩን ባሳወቀበት ባለፈው ወር ከሚመዘገቡት ህሙማን ቁጥር በአዲሱ ዝርያ የተያዙት 0.5 ያነሰ ቢሆን በቅርቡ ግን ከ3.6 በመቶ በላይ በፍጥነት እየገሰገሰ እንደሆነ ጥናቱ አመላክቷል፥ በአሜሪካ በየቀኑ የሚመዘገበው የህሙማን ቁጥር ከባለፈው ወር ጀምሮ መቀነስ ቢያሳይም የሟቾች አማካይ ቁጥር አሁንም እንዳሻቀበ ነው። በአገሪቷ በየቀኑ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ 3 ሺህ ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን ሆስፒታሎችም የህሙማኑን ከፍተኛ ቁጥር ለማስተናገድ ተቸግረዋል ተብሏል። ቢቢ117 የሚል ስያሜ የተሰጠውና በመጀመሪያ ጊዜ በእንግሊዝ የተገኘው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ወደ አምሳ አገራት ተዛምቷል። ልክ እንደ ቀድሞው ቫይረስ ለአዛውንቶችና ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው ሰዎች የበለጠ አደጋ አለው። አዲሱ ዝርያ ከ30 በመቶ በላይ ለሞት ያጋልጣል ቢባልም የተሰጡት ማስረጃዎች ጠንካራ እንዳልሆኑ ተነግሯል። በአሁኑ ሰዓት ያሉ ክትባቶች ቀደም ላሉት የቫይረሱ ዝርያዎችን እሳቤ ውስጥ ከተው ቢሆንም ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፋይዘር፣ ኦክስፎርድ አስትራዜንካና ሞደርና ክትባቶች ከቢቢ117 ዝርያ ይጠብቃሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-55991564 +health “ከኮሮናቫይረስ ባገግምም አሁንም በሽታው ይገድለኛል ብዬ እፈራለሁ” የ42 ዓመቱ ራጀሽ ቲዋሪ ከስልኩ የሰፋ መጠን ያለው ስክሪን ይፈራል። ቴሌቭዥን ወይም ኮምፒውተር አንዳች ጥቃት የሚያደርሱበት ፍጥረቶች ይመስሉታል። ራጀሽ ቅዠት የጀመረው በጽኑ ህሙማን ክፍል ዘለግ ላለ ጊዜ ከቆየ በኋላ ነበር። ሰኔ ላይ ኮሮናቫይረስ ይዞት ስለተዳከመ በቬንትሌተር እየታገዘ እንዲተነፍስ ተደርጓል። ራጀሽ ከሦስት ሳምንት በኋላ ተሽሎት ከሆስፒታል ቢወጣም ሙሉ በሙሉ እንዳላገገመ ተገነዘበ። “ሕክምናው ቢያሽለኝም ከሆስፒታል ከወጣሁ በኋላ የነበሩት የመጀመሪያ ሳምንታት በጣም ከባድ ነበሩ” ይላል። ወደ ቤት ሲመለስ ቤተሰቦቹ እጅግ ተደስተው ነበር። ቆየት ሲል ግን ራጀሽ እንደ ቀድሞው እንዳልሆነ አስተዋሉ። አንድ ቀን ቴሌቭዥን እያየ በጣም ጮኸ። ቲቪውን ለመስበርም ሞከረ። ከዛ በኋላ ቤተሰቡ ቲቪ መመልከትና ላፕቶፕ መጠቀም አቆመ። ራጀሽ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ሳለ የተመለከታቸው የሕክምና መሣሪያዎችን ለመርሳት እየታገለ ነው። የ49 ዓመቱ አሚት ሻርማም ተመሳሳይ ተሞክሮ አለው። ለ18 ቀናት በለይቶ ማቆያ ሳለ በየቀኑ ሰዎች ሲሞቱ አይቷል። ወጣት፣ አዛውንት፣ ሴት፣ ወንድ. . . በርካታ የኮቪድ-19 ታማሚዎች በሞት ሲለዩ አሚት ተመልክቷል። “ሁለት ሰዎች አጠገቤ ሞተው አስክሬናቸው ለረዥም ሰዓት አልተነሳም ነበር። ይህንን ከአዕምሮዬ ማውጣት አልቻልኩም። አሁንም ኮሮናቫይረስ ሊገለኝ ይችላል ብዬ እፈራለሁ” ይላል። አሚት አሰቃቂ ቆይታውን ለመርሳት እየታገለ ነው። ከኮሮናቫይረስ ካገገመ በኋላ ጭምት ሆኗል። ካወራም በበሽታው ሳቢያ ስለሞቱ ሰዎች እንደሚያወራ አጎቱ ይናገራሉ። ኮቪድ-19 የሚያስከትለው የአዕምሮ ጤና ቀውስ በሕንድ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች የአዕምሮ ጤና ቀውስ እየገጠማቸው ይገኛል። የሥነ ልቦና ሀኪሙ ዶ/ር ቫሰንት ሙንድራ “ገና ሆስፒታል ሳይደርሱ አዕምሯቸው ይዳከማል። ከዛ ኮቪድ-19 ደግሞ የስሜት ህዋሳትን የበለጠ ያዝላል” ይላሉ። ህሙማኑ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ አይፈቀድም። ሀኪሞቻቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ስለሚያደርጉም ፊታቸውን ማየት አይችሉም። ይህም ዶክተሮቻቸውን እንዳያምኑ ያደርጋቸዋል። የኮሮናቫይረስ ህሙማን ሲያገግሙ ብቸኝነት ሊሰማቸው ይችላል። አስጨናቂ ክስተትን ተከትሎ የሚከሰት ድብት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉም ዶ/ር ቫንሰት ያስረዳሉ። ከኮሮናቫይረስ ህሙማን ጋር የተያያዘ የአዕምሮ ህመም ተገቢውን ትኩረት አላገኘም። “በወረርሽኙ ወቅት እየታየ ያለው ሕንድ ለአዕምሮ ጤና ብዙም ቦታ እንደማትሰጥ ነው” የሚሉት ዶ/ር ሶሚትራ ፓትሬ ናቸው። የአዕምሮ ህሙማንን ለማከም በቂ ሆስፒታል እንዲሁም ባለሙያዎች የሉም። በትንንሽ ከተሞች ደግሞ ችግሩ ይከፋል። በከተማና በገጠር የሚኖሩ ሰዎች ለአዕምሮ ጤና ያላቸው ተደራሽነት እኩል አለመሆኑን ወረርሽኙ እንዳሳየ ዶክተሩ ይገልጻሉ። “የሕንድ መንግሥት ችግሩን በአፋጣኝ ካልፈታ የአዕምሮ ህመም ወረርሽኝ ይገጥመናል” ሲሉም ያክላሉ። ባለሙያው እንደሚሉት፤ የመጀመሪያው እርምጃ ሰዎች ስለ አዕምሮ ህመም ምልክቶች እንዲያውቁ ማድረግ ነው። በተለይም ለአነስተኛ ከተማ ነዋሪዎች ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። በደልሂው ፎርቲስ ሆስፒታል የአዕምሮ ጤና ክፍል ኃላፊ ካምና ቺቤር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በርካታ ሰዎች የአዕምሮ ህመም እንደገጠማቸው ይናገራሉ። የእንቅስቃሴ ገደቡና ወደፊት ምን እንደሚከሰት አለማወቅ ብዙዎችን ጭንቀትና ድብርት ውስጥ ከቷል። “ችግሩ ከእለት ወደ እለት እየተባባሰ ነው” ብለዋ�� ኃላፊዋ። በድህረ ኮቪድ-19 ማገገሚያ እቅድ የአዕምሮ ጤና ጉዳይ እንዲገባ በርካታ ሀኪሞች እየጠየቁ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-54174457 +sports የአውሮፓ እግር ኳስ፡ 26 ጨዋታዎች በሁለት ሳምንት ተኩል ይደረጋሉ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግን ጨምሮ፣ የጣልያን፣ ስፔንና ጀርመን ሊጎች ተጠናቀዋል። አሁን ጊዜው የአውሮፓ ሊጎች ነው። በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለአምስት ወራት ያክል ተቋርጠው የነበሩት የቻምፒየንስ ሊግና የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ዛሬ [ረቡዕ] ምሽት በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀምራሉ። ማንቸስተር ሲቲና ቼልሲ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ሲፋለሙ፤ ማንቸስተር ዩናይትድና ዎልቭስ በዩሮፓ ሊግ ተሳታፊ ናቸው። በሚቀጥለው ሁለት ሳምንት ተኩል 26 ጨዋታዎች ይከናወናሉ። አምስት ጊዜ ቻምፒየንስ ሊግ ያነሳው የጁቬንቱሱ ክርስቲያኖ ሮናልዶና አራት ጊዜ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ የሳመው የባርሳሌናው ሊዮኔል ሜሲን የምንመለከታቸው ይሆናል። የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ነሐሴ 15 ኮሎኝ ውስጥ እንዲካሄድ እቅድ የተያዘለት ሲሆን፤ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ነሐሴ 17/2012 በፖርቹጋል፤ ሊዝበን ይካሄዳል። ቻምፒየንስ ሊግ ከመቋረጡ በፊት የመጨረሻውን ጨዋታ ያደረጉት ሊቨርፑልና አትሌቲኮ ማድሪድ ናቸው። በሌላ ስታድየም ደግሞ ፒኤስጂ ከዶርትመንድ ተፋልመዋል። በውጤቱም ሊቨርፑልና ዶርትመንድ ከውድድሩ መሰናበታቸው አይዘነጋም። አትሌቲኮና ፒኤስጂ አትላንታና የጀርመኑ አርቢ ሊፕዝግን ተከትለው ወደ መጨረሻዎቹ ስምንት አልፈዋል። ሲቲዎች በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ማድሪድን በቤርናቢዩ ስታድየም 2-1 ረተዋል። ሁለተኛው ዙር ጨዋታ በሲቲ ስታድየም የሚካሄድ ይሆናል። አሮጊቶቹ በተሰኘ ቅፅል ስማቸው የሚታወቁት ጁቬንቱሶች በሊዮን ሜዳ 1-0 ተረተዋል። የሮናልዶ ቡድን ሁለተኛውን ዙር ጨዋታ ለማሸነፍ ዝተዋል። ቼልሲ በባየርን ሙኒክ 3-0 እየተመራ ነው ሁለተኛውን ዙር ጨዋታ በሜዳው ስታንፎርድ ብሪጅ የሚያከናውነው። ሌላኛው ጨዋታ በበርሴሎናና በናፖሊ መካከል የሚካሄደው ነው። የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በናፖሊ ሜዳ 1-1 ነበር የተጠናቀቀው። የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ደግሞ ዛሬ ምሽት ይጀምራሉ። የመጀመሪያውን ዙር ጨዋታ 5-0 ያሸነፈው ማንቸስተር ዩናይትድ በሜዳው የኦስትሪያው ኤልኤኤስኬን ይገጥማል። ሬንጀርስ ከባየር ሊቨርኩሰን ዎልቭስ ከኦሎምፒያኮስ ሌሎች የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ናቸው። ሁሉም የቻምፒየንስ ሊግ እና የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች በዝግ ስታድየም የሚደረጉ ናቸው። https://www.bbc.com/amharic/news-53662247 +health ኮሮናቫይረስ፡ በታንዛኒያ 'የኮቪድ-19 ምልክቶችን ያሳዩ' በርካታ መነኮሳትና ካህናት መሞታቸው ተሰማ "በታንዛኒያ ስድሳ መነኮሳትና 25 ካህናት ባለፉት ሁለት ወራት መሞታቸውን የአገሪቱ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስታወቀች። እነዚህ ካህናትና መነኮሳት የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ታይቶባቸው ነበር ተብሏል። በአገሪቱ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ህሙማን መረጃ ይፋ በማይሆንባት ታንዛኒያ ቤተ ክርስቲያኗ የአገሬው ሰው ከወረርሽኙ እንዲጠነቀቅ ምክሯን ለግሳለች። የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ወረርሽኙን ሲያጣጥሉ የተሰሙ ሲሆን ባለፈው ወር የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ታንዛኒያ ወረርሽኙን ለመከላከል ክትባት የመስጠት ዕቅድ የላትም ብለዋል። በተቃራኒው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ያላትን ስጋት ስትገልፅ ቆይታለች። የታንዛኒያ የካቶሊክ ኤፒስኮፓል ጉባኤ ፀሐፊ ቄስ ቻርለስ ኪቲማ እንዳስታወቁት የኮቪድ-19 ስጋት በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል። ""ራሳችንንም ሆነ ሌሎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑትን ጥንቃቄዎች ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው። በተለይም የእድሜ ባለፀጎችንና ተጓዳኝ ህመም ያለባቸውን ሰዎች ትኩረት ልንሰጣቸው ይገባል"" በማለት በዳሬሰላምከተማ በተደረገ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ቄስ ቻርለስ እንዳሉት መነኮሳቱና ካህናቱ ምርመራ ባለማድረጋቸው በኮሮናቫይረስ ሞተዋል ብላ ለማወጅ ቤተ ክርስቲያኗ ብትቸገርም ሁሉም የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ታይቶባቸዋል ተብሏል። በርካቶችም በከፍተኛ ሁኔታ ለመተንፈስ ተቸግረው እንደነበር ተገልጿል። ""ዜጎች እየተመረመሩ አይደለም። ይሄ ትልቁ ፈተና ነው። ቤተ ክርስቲያኗ በአገሪቱ ውስጥ 500 የጤና ማዕከላት ቢኖሯትም ኮሮናቫይረስ መመርመር አልተፈቀደላትም። እንዲሁም የመመርመሪያ መሳሪያውም የለንም"" ብለዋል። ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን በተመለከተ ከመንግሥታቸው በኩል የሚሰጡ አስተያየቶች በቅርቡ እንደተቀየረ ቢናገርም፤ ነገር ግን ታንዛኒያ ግልፅ የሆኑ መመሪያዎችን ባለማስቀመጧ ብዙዎች እንደማይጠነቀቁ ተናግረዋል። ቤተ ክርስቲያኗ የወረርሽኙን አስከፊነት በተመለከተ በተደጋጋሚ የምትናገር ሲሆን ጥር ወር ላይ የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡን ገልፃለች። ታንዛኒያ ካለፈው ዓመት የግንቦት ወር በኋላ የታማሚዎችን ቁጥር ማሳወቅ አቁማለች። የዓለም ጤና ድርጅት የታማሚዎችን ቁጥር እንድታሳውቅና በክትባቱ ላይ ያላትን አቋም እንድትቀይር ተማፅኗል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56272129 +health የእንግሊዝ ትልልቅ ሬስቶራንቶች ምግቦቻቸው የያዙትን ካሎሪ ይፋ ማድረግ ሊጀምሩ ነው "እንግሊዝ ውስጥ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ምግብ ቤት የሚያቀኑ ሰዎች በሜኑ (የምግብ እና የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ) ላይ እያንዳንዱ ምግብ ያለውን ካሎሪ ማግኘት ይችላሉ። በመሆኑም ከ250 በላይ ሠራተኞች ያሏቸው ምግብ ቤቶችና ካፍቴሪያዎች የሚያዘጋጇቸው ምግቦች ውስጥ ምን ያህል ካሎሪ እንዳለ በሜኑዎቻቸውና በድረ ገጻቸው ላይ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል። አዲሱ ሕግ ሰዎች ጤናማ ምርጫ በማድረግ ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ለመቋቋም መንግሥት ያወጣው ዕቅድ አካል ነው። አንዳንድ ምግብ ቤቶች ሕጉ ወጪያችንን ይጨምራል ብለው ሰግተዋል። በአመጋገብ ችግር ላይ የሚሠራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ደግሞ ሕጉ ለጎጂ አስተሳሰቦች እና ባህሪያት አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብሏል። ሕጉ ምን አዲስ ነገር አለው? በአዲሱ ሕግ መሠረት በእንግሊዝ የሚገኙ 250 እና ከዚያ በላይ ሠራተኞች ያሏቸው የምግብ እና የመጠጥ ቤቶች ቀድመው ካልተዘጋጁ ምግቦች እና ለስላሳ መጠጦች ውጭ የካሎሪ መረጃ ማሳየት አለባቸው። እንደ ዌዘርስፑንስ ፐብስ እና የሪል ግሪክ ሬስቶራንት ያሉት ስለሚያበስሉት ምግብ የካሎሪ ይዘት መረጃ በሜኑዋቸው ላይ ያትማሉ። ማክዶናልድም ይህን ማድረግ ከጀመረ ከአስር ዓመታት በላይ ሆኖታል። የሜክሲኮ ምግብ በማሰናዳት ስም ያተረፈው የዋሃካ መስራች ማርክ ሴልቢ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ድርጅቱ ለደንበኞቹ በሚያቀርበው ምግብ እና መጠጥ መረጃ ላይ ""ግልጽ ለመሆን ዝግጁ ነው"" ብለዋል። ካሎሪንን በመለካት ላይ ያለው ትኩረት ችግር መሆኑንም ጠቁመዋል። ""ይህ የታሪኩን አንድ ክፍል ብቻ ይነግረናል። የበለጠ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ብለን የምናስበውን በምግብ ዙሪያ አንዳንድ በጣም አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ ነገሮችን ግን ይዘነጋል። ይህም በእርግጠኝነት ሊታሰብበት የሚገባ ይመስለኛል።"" ብለዋል። ሰዎች ዋሃካን የሚጎበኙት እንደ ""ግብዣ"" መሆኑን እንደሚያምኑ ሴልቢ ገልጸው ማንም ሜኑውን ከካሎሪ አንጻር እንደማይመለከተው ተናግረዋል። በተጨማሪም ምግብ አብሳዮች በምግብ ቤቶች ውስጥ በየቀኑ የሚጠቀሙባቸውን 250 ግብአቶች በትክክል መጠቀማቸውን የሚያረጋግጥ አሠራር መፍጠር በንግዱ ላይ ""በግልጽ ተጽእኖ በማሳደር ወጪውን ያንራል"" ብለዋል። ኩባንያው ለውጡን በመጠቀም እያንዳንዱ ምግብ የአየር ንብረት ላይ ያለውን ተፅዕኖ ለመለካት ተጠቅሞበታል ብሏል። የማስተርሼፍ ውድድር (የምግብ አብሳዮች ውድድር) አሸናፊው ስቬን-ሃንሰን ብሪት በትዊተር ገፃቸው ለውጡ ""በኢንዱስትሪው ላይ የደረሰ አሰቃቂ ነገር ነው"" ብሏል። ሕጉ ""ፈጠራን፣ ልዩ መሆንን የሚያቆም እና ወደ አሰልቺ ምግብ የማብሰል አሠራር ሊያመራ ይችላል"" ሲልም አስጠንቅቋል። ""ልጆች የሚያድጉት በሬስቶራንቶች፣ በሆቴሎች እና በካፌዎች ውስጥ ከምግቡ ስር ያለውን ትንሽ ቁጥር ብቻ በመመልከት ነው። ምርጫ የሚደረገው በቁጥር ላይ ተመርኩዞ ብቻ ነው። ጣዕም፣ ግብዓት፣ ታሪክ፣ የምግብ አሰራር ወይም የተመጣጠነ ምግብ ተፈላጊነት ይጠፋ እና ይሸፈናል። ትኩረቱም ወደ አዲስ አቅጣጫ ይዞራል"" ብሏል። የዩኬ ሆስፒታሊቲ ኃላፊ ኬት ኒኮልስ አዲሱ ሕግ ""ሥራቸውን ለማስቀጠል ለሚታገሉት በሺህዎች የሚቆጠሩ ድርጅቶች በጣም በመጥፎ ጊዜ የመጣ ነው"" ብለዋል። ""የካሎሪ መጠን ማሳወቂያ አተገባበር እንዲዘገይ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ጠይቀን ነበር። ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ አስገዳጅ እንዳይሆን እና የተወሰነ የማስተንፈሻ ጊዜ ያስፈልጋል"" ሲሉም አክለዋል። ""በኮቪድ ምክንያት ባለፉት 24 ወራት የተንገዳገዱ ድርጅቶች ኪሳራቸውን እንዲመልሱ የሚጠበቁ ንግዶች ውስብስብ እና ውድ የሆኑ አዲስ መረጃ በድንገት እንዲያስተዋውቁ መጠበቅ በጣም አሳሳቢ ነው።"" ብለዋል ኬት ኒኮልስ ተመጋቢዎችስ ምን ይላሉ? ቻርሎት ሮበርትስ ለተባለችው የማክልስፊልድ ነዋሪ ለውጡ በምግብ ምርጫዋ ላይ ምንም ተጽዕኖ አይኖረውም። ""ወደ ሬስቶራንቱ የመጣሁት መብላት የምፈልገውን አውቄ ነው። ጥሩ ምግብ እንደሚሆን እያወቅኩ ወደዚያ እሄዳለሁ። መብላት የምፈልገውን ብቻ ነው የምበላው"" ትላለች የ19 ዓመቷ ወጣት። የለንደን ነዋሪው ጄምስ ሃውለትም ለውጡ በምርጫው ላይ ተጽዕኖ እንደማይኖረው ተናግሯል። ""መረጃዎቹን እንዳለሰፈሩ አላስተዋልኩም ነበር"" ብሏል። ""በየትኛውም ቀን የሚሰማኝ ነው የሚሆነው። ፒዛ ከፈለግኩ ፒዛ እመገባለሁ። በርገር ካማረኝም በርገር አዛለሁ።"" ከሞንማውዝ ለመጡት የ57 ዓመቱ ፓትሪክ ካላጋን ግን እርምጃው በምግብ ምርጫቸው ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ ይናገራሉ። ""ሰዎች ለሚመገቡት ነገር ትኩረት ይሰጣሉ ብዬ አስባለሁ። ከኮሮና ወረርሽኝ በኋላ ሰዎች የበለጠ ንቁ የሆኑ ሲሆን ስለሚወስዱት ካሎሪም የማወቅ ፍላጎት አላቸው"" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የ56 ዓመቷ ኬት ካላጋን ሰዎች ""ለምንበላው ነገር ራሳቸን ኃላፊነት መውሰድ አለብን"" ሲሉ በሕጉ መስማማታቸውን አስታውቀዋል። በዩናይትድ ኪንግደም የአመጋገብ ሥርዓት ችግር ላይ የሚሠራው ቢት የተሰኘው በጎ አድራጎት ድርጅት እንደሚለው በምግብ ዝርዝር ውስጥ ካሎሪ መጥቀስ አስገዳጅ መደረጉ ለጎጂ የአመጋገብ ችግር አስተሳሰቦች እና ባህሪያት መባባስ አስተዋጽኦ ያደርጋል። የበጎ አድራጎት ድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ዳይሬክተር ቶም ኩዊን እንዳሉት የካሎሪ መረጃ በአመጋገብ ችግር የተጎዱ ሰዎች ላይ ጭንቀትና ድብርት እንደሚፈጥር የሚያሳይ ማስረጃ አለ። ""ሕጉ የሰዎችን የአመጋገብ ልማዶችን ስለመቀየሩ የሚያሳዩ ማስረጃዎች በጣም ውስን ናቸው"" ብለዋል። ቢት ለቢቢሲ እንደገለጸው በእንግሊዝ ብቻ 1.25 ሚሊዮን ሰዎች የአመጋገብ ችግር አለባቸው። መንግሥት በአመጋገብ ችግር በተጎዱ ሰዎች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ እንዲያሰላስል እና ""የአመጋገብ ችግር ባለሙያዎችን እንዲያማክር"" ያለማቋረጥ መጠየቁን አስታውቋል። ከመጠን ያለፈ ውፍረት አገሪቱ ካጋጠሟት የጤና ችግሮች አንዱ መሆኑን የጤና እና የማኅበራዊ እንክብ���ቤ ሚኒስቴር አስታውቋል። የምግብ ዝርዝር መገለጹ ሰዎች ጤናማ ምርጫ እንዲያደርጉ በመርዳት ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው ተናግሯል። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አክለውም ሰዎች በሱፐር ማርኬቶች የሚሸጡ ምርቶችን የምግብ መረጃ ማየትን ተለማምደዋል ብለዋል። መንግሥት ፖሊሲው በጥናት የተረጋገጠ መሆኑን አስታውቋል። ከአዕምሮ ጤና በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ባለሙያዎች ጋር ""በሰፊው"" መምከሩንም ገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61020761 +business የኑሮ ውድነትን ለማቅለል መንግሥታት መውሰድ የሚችሏቸው እርምጃዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባለፉት ሁለት ዓመታት በመላው ዓለም ከባድ ምጣኔ ሀብታዊ ተጽእኖን አስከትሏል። እሱን ተከትሎ በተለያዩ ስፍራዎች የተከሰቱት ጦርነቶች እና ፍጥጫዎች ደግሞ ችግሩን አባብሰውታል። እነዚህ ክስተቶች ደግሞ በምርቶች እና በአገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ እጥረትና የዋጋ ጭማሪን አስከትለዋል። በተለይ ነዳጅ እና የምግብ ምርቶች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ በመናሩ በውጤቱ የሌሎችም ዋጋ ጨምሯል። ይህ ሀብታም ከድሃ ሳይል በሁሉም የምድራችን አገራት ላይ ውጤቱ የታየው የኑሮ ውድነት፣ በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ሕዝብ እየጎዳ ነው። ነገር ግን ይህንን ቀውስ ለማስታገስ እና ለማቃለል መንግሥታት ተለያዩ አመራጮችን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይመክራሉ። ምን ማድረግ ይችላሉ? https://www.bbc.com/amharic/articles/cx0qvpwxnq1o +business ክሪፕቶአርት: ዲጂታል ሥዕል በመሸጥ ሚሊየነር እየሆኑ ያሉ የሥነ ጥበብ ባለሙያዎች "ክሪፕቶአርት ይባላል። አሁን አሁን ይህ የዲጂታል ሥዕል ግብይት ዘዴ እጅጉን የገነነ ነው። ለዘመናት በድህነት የጎበጡ የሥነ ጥበብ ሰዎች ክሪፕቶአርት ሠርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል። ይህን አዲስ ጥበብ በዚህ አዲስ ዘመን ላይ በመምጣቱ ሕይወታቸውን እየለወጡ የሚገኙ የምዕራቡ ዓለም አርቲስቶች ቁጥር ቀላል አይደለም። አርቲስት ቢፕል ከሰሞኑ አንድ ዲጂታል ሥዕል 69 ሚሊዮን ዶላር በመሸጥ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል። ሥዕሉ የተሸጠው በብሎክቼይን የዲጂታል ግብይት ዘዴ ነው። በዚህ መንገድ ሥዕሉን የሸጠው አርቲስት እንደሚለው ይህ የክሪፕቶአርት ሽያጭ በዓለም ላይ ትልቅ ተሰሚነት ካላቸው 3 አርቲስቶች መሀል አንዱ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ አላና ኤዲንግተን ሌላዋ አርቲስት ናት። በእዳ ቁልል ኑሮዋን ስትገፋ ነው የኖረችው። ይህ የዲጂታል ሥዕል ገበያ ግን ሚሊየነር አድርጓታል። በምህጻሩ ኤንኤፍቲ (NFT) በሚሉ ቃላት የሚወከለው ይህ አዲስ ዘዴ Non-Refundable Token የሚል ሐረግን የሚወክል ነው። ነገሩ አርቲስቶች ሥራዎቻቸውን በዲጂታል መንገድ የሚሸጡበት አዲስ አሰራር ነው። በሌላ አነጋገር ኤንኤፍቲ የዲጂታል ጉሊት ሲሆን አርቲስቶችና አጫራቾች እንዲሁም ሸማቾች የሚገናኙበት ዲጂታል ሥፍራ አድርገን ልናየው እንችላለን። ገዢው የሚገዛው የአርቲስቱን ቱባ ሥራ ዲጂታል የባለቤትነት ካርታ ነው። እንደ ቢትኮይን ያለ የዲጂታል ገንዘብ አንድ ቅጥያ የሆነው ኤንኤፍቲ ዓለምንና የገንዘብ ልውውጥን ከሥር መሠረቱ ይለውጣል ተብሎ የሚጠበቀው የክሪፕቶከረንሲ አካል ነው። በዚህ ዘዴ የሚሸጠው የዲጂታል ሥዕል በምንም መንገድ እንዳይቀዳ፣ እንዳይባዛ፣ እንዳይጋራ ስለሚደረግ ዘላለሙን ቱባነቱን ይዞ ይቆያል። አንድ ሰው ይህን ዓይነት ሥራ ሲገዛ የሥዕል ሥራው ወደሚገኝበትን ፋይል ለመግባት የሚያስችል ቁልፍ ወይም ዲጂታል ካርታ አገኘ ማለት ነው። ልክ ሰዎች ለመሬታቸው ካርታ እንደሚሰጣቸው ሥዕሉን የሚገዛው ሰው ዲጂታል የባለቤትነት ካርታን ያገኛል። ገንዘቡን በሥዕል ሥራው ላይ የሚከሰክሰውም ይህንኑ ለማግኘት ነው። ይህም ካርታ በምንም መልኩ የማይደመሰስና በሌላ ሰው የማይቀዳ ዘላለማዊ የሥዕል ሥራ በእጅ የማስገባት መብትን ያስገኛል። ይህ ሥዕል በድጋሚ በተሸጠ ቁጥር ፈጣሪው በመቶኛ ትርፍ ስለሚያገኝ ሁልጊዜም ተጠቃሚ እንዲሆን ያደርገዋል። ሰዎች ቢትኮይንን በቢትኮይን ሊቀይሩ ይችሉ ይሆናል። ይህ የዲጂታል ካርታ ግን በምንም መልኩ ሊጋሩት ወይም ሊለዋወጡት የሚችሉት አይደለም። አንድ ቢትኮይን በሌላ ቢትኮይን ቢቀየር በተመሳሳይ ጊዜ ከሆነ አንድ ብርን በአንድ ብር መቀየር እንደማለት ነው። የይህንን ዲጂታል ካርታ ከሌላ ሰው ጋር ለመጋራት መሞከር ግን አንድን የኮንሰርት ትኬት ግማሹን ቆርጦ ለሰው የመስጠት ያህል ትርጉም አልባ ነው። ይህ ቱባነቱ ነው ሰዎች በዲጂታል ገበያ እንዲወዳደሩና ገንዘባቸውን ከስክሰው ዲጂታል የሥዕል ባለቤትነት ካርታን እንዲገዙ የሚያደርጋቸው። ሚሊየነርነት እንደዋዛ አርቲስት አላና ጎበዝ ሠዓሊ ብትሆንም ራሷን ""መሸጥ"" የምትችል ሴት አልነበረችም። ዓይነ አፋር ናት፤ ሥራዎቿን ጋለሪ ለመውሰድ እንኳ ትፈራለች። ስለዚህ በትርፍ ጊዜዋ ሥዕል እየሰራች 3 ልጆቿን በማሳደግ ተጠምዳ ነው የኖረችው። ኑሮዬን ከደጎመልኝ በሚል በዲግሪ የአበባ እርሻ ሳይንስ ስታጠና ቆየች። እንደ ብዙ የዓለም ሕዝብ ሁሉ ሁልጊዜም ሐሳቧ ከዞረ ድምር የዕዳ እሽክርክሪት መቼ እንደምትወጣ ስትጨነቅ ነው የኖረችው። ኑሮ ሞልቶላት አያውቅም። ሸራ ላይ በዘይት ቀለም የሠራችውን ሥዕሏን የሆነ ቀን ድንገት ወደ ድረ-ገጽ ገብታ በ500 ዶላር ስትሸጠው ለራሷ ደነገጠች። በሌላ ቀን ወደ ድረ-ገጽ የሥዕል ጨረታ በገባችበት ጊዜ 16 ሥዕሎቿን በመቶ ሺህ የካናዳ ዶላር የሚገዛ ሰው አገኘች። ይህ ከአእምሮ በላይ ሆነባት። ማመን ተሳናት። የ35 ዓመቷ አርቲስት አላና ""ሰዎች ለእኔ ሥዕል ይህን ያህል ዋጋ ይከፍላሉ ብዬ ለማመን ተቸግሬያለሁ"" ስትል ተናግራለች። ይህ ስኬቷ የአርቲስቷን ሕይወት ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገረው። መጀመርያ የኮሌጅ ትምህርት ክፍያዋን ከፈለች፣ ጣሪያ የነኩ የእዳ ክምሮቿን አቃለለች፣ ቤተሰቧን ወደ ሌላ ከተማ ወስዳ ማኖርም ጀመረች። በአእምሮ እድገት ውስንነት ይሰቃይ የነበረውን አንድ ልጇን ጥሩ ሕክምና እንዲያገኝም አደረገች። ""ይህ የዲጂታል ሥዕል ግብይት በተለይ ለሴት አርቲስቶች አዲስ በር የከፈተ ነው"" ትላለች አርቲስት አላና። ኤንኤፍቲ ምንድን ነው? ኤንኤፍቲ (NFT)ዲጂታል ሰርተፍኬት ወይም የሥዕል ባለቤትነት ካርታ እንደማለት ነው። የአንድን የፈጠራ ሥራ ባለቤትነት የሚመሰክር ዲጂታል ካርታ። በክሪፕቶአርት ዓለም አንድን የፈጠራ ሥራ አንድ ሰው ብቻ በባለቤትነት ይዞት ይቆያል። ቱባውን የሥዕል ሥራ ማባዛትም፣ መቅዳትም፣ መለወጥም አይችልም። ይህ ዲጂታል ሰርተፍኬት በብሎክቼይን ውስጥ ነው የሚገኘው። ብሎክቼይን ቴክኖሎጂ የዲጂታል ገንዘብ ልውውጥና ግብይት የሆነውን ክሪፕቶከረንሲን የሚያስተዳድር ሲሆን ቢትኮይን የመሰሉ ዲጂታል ገንዘቦች በስሩ ይገኛሉ። ይህም ኤንኤፍቲ የዚህ አካል ነው። ስለዚህ አንድ የሥዕል ሥራን ሁሉም ሰው ኦንላይን ገብቶ ቅጂውን ሊያየው ቢችልም ኤንኤፍቲ ግን ባለቤትነቱን ለገዛው ሰው ብቻ ስለሚሰጥ የሥዕሉ ባለቤት ያ ሰው ብቻ ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ ሥዕሉን ሁልጊዜም በአስተማማኝ ጥበቃ ስር እንዲቆይ ያደርገዋል። ልክ የቤት ካርታ እንደመያዝ ሁሉ የኤንኤፍቲ ካርታ መያዝ የባለቤትነት ሰርተፍኬት ያስገኛል። አንድ የመሬት ባለቤት መሬቱን ሲሸጥ ካርታ እንደሚሸጠው ይህ ኤንኤፍቲ የፈጠራ ባለቤትነት መብት ለሌላ ሁለተኛ ሰው ለማስተላለፍም ተመሳሳይ ሂደትን ይከተላል። ሰዎች ሥዕሉን በገዙበት ጊዜ ሁሉ ግን የፈጠራ ባለቤትነቱ ���አርቲስቱ ሆኖ ይቆያል። ከሽያጩም በመቶኛ ክፍያን ያገኛል። ""ሙልጭ ያልኩ ድሀ ነበርኩ፤ድንገት በአንድ ጊዜ የ250ሺህ ዶላር ጌታ ሆንኩ"" የሳይንስ ልቦለድና የ3ዲ አርቲስት ዳሪየስ ፑያ ሕይወቱን የቀየረውን አጋጣሚ ሲያስብ ይገረማል። መጀመርያ ጓደኞቹ በድረ ገጽ ሥራዎቻቸውን መሸጣቸውን ሲነግሩት አላመነም ነበር። እስኪ ልሞክረው ብሎ ፈራ ተባ እያለ ገባበት። ብዙም ተስፋ አድርጌ አልነበረም ዲጂታል ገበያውን የተቀላቀልኩት ይላል። ዳሪየስ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሳንቲሞችን ማግኘት ጀመረ። አክሮፎቢያ የተሰኘው ዲጂታል ሥዕል ሥራው በአንድ ጊዜ 12 ሺህ ዶላር ተሸጠለት። ማመን አልቻለም። ""ፍቅረኛዬን ወዲያውኑ ደውዬ፣ ምን እየሆነ እንደሆነ ልትነግሪኝ ትችያለሽ? ይህ የማየው ነገር እውነት ነውን?"" ስል ጠየቅኳት ይላል። ከዚህ ስኬት በኋላ አርቲስት ዳሪየስን የሚያቆመው ሰው ጠፋ። ""ከ20 ቀናት በፊት ሳንቲም ቸግሮኝ ግራ የገባኝ ሰው ነበርኩ። በ20 ቀን ውስጥ የ250 ሺህ ዶላር ጌታ ሆንኩ፤ ይህም ማን ያምናል?"" ይላል። ዲጂታል ሥዕሎችን የሚገዛው ማን ነው? ራጋቫንዴራ ራዉ በኬምብሪጅ ዩኒቨርስቲ የገንዘብና ተያያዥ ጉዳዮች ፕሮፌሰር ናቸው። ይህ የዲጂታል ግብይት ዘላቂ ይሆናል ብለው እምብዛም አያምኑም። ""ብዙ ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ወደ ውጭ ስለማይወጡ ለዚያ ማካካሻ ገንዘባቸውን በዚህ መንገድ ወጪ እያደረጉት ነው የሚመስለው"" ሲሉ ለቢቢሲ ሐሳባቸውን አጋርተዋል። ፕሮፌሰሩ እንደሚተነብዩት ዲጂታል ግብይቱ ቢቀጥል እንኳ በዚህ ዘዴ ወደፊት ሁሉም አርቲስት ይሸጣል ማለት አይደለም። ምናልባት ገናናዎቹ ብቻ በዚህ የዲጂታል ግብይት ተፈላጊነታቸው ሊቀጥል ይችል ይሆናል። ""ገዢዎች ለጊዜው ብዙ ገንዘብ ሊያገኙ ይችላሉ፤ ብዙ ገንዘብም ሊያጡ ይችላሉ። እንዲህ ዓይነት ነገሮች አስተማማኝ አይደሉም፤ ጊዜያዊ ናቸው"" ይላሉ። በኤንኤፍቲ ገበያ ላይ ተሳታፊው ኔልሰን ሮህርባች በበኩሉ የክሪፕቶ አርት መነቃቃትና መጎልበት የአመጽ ያህል ነው ይላል። ለዓመታት አርቲስቶች ሲበዘበዙና ሥራቸውም ዋጋ እያጣ ቆይቷል። አሁን ያን ለመቀየር የተደረገ ተቃውሞ ነው። እሱ እስካሁን 20 ሺህ ዶላር በማውጣት የተወሰኑ ሥዕሎችን መግዛት ችሏል። ያን ማድረጉ ትልቅ ኢንቨስትመንት እንደሆነ እንጂ ብክነት አድርጎ አያስበውም። ወደፊት ግብይት የሚደረገው በዚህ መንገድ መሆኑ አይቀርም ይላል። ""አርቲስቶችን ማገዝ እፈልጋለሁ። አርቲስቶች ለሥራዎቻቸው ዋጋ ሲያገኙ ማየት ነው ህልሜ። ገንዘቤን በዚህ መንገድ ዲጂታል ሥዕል በመግዛት ማውጣቴ አደጋ አለው፤ ነገር ግን የሚመጣውን ለመቀበል ፍቃደኛ ነኝ"" ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56417944 +health ኮሮናቫይረስ ፡ በእንግሊዝ ለበርካታ ሕዝብ የኮቢድ-19 ክትባት የሚሰጡ ማዕከላት ሊከፈቱ ነው "እንግሊዝ በመላው አገሪቱ በሰባት ቦታዎች ላይ በሚቋቋሙ የኮሮናቫይረስ የክትባት መስጫ ማዕከላት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን ልትከትብ መሆኑን አስታወቀች። የእንግሊዝ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት በዚህ ሳምንት ተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትንም ይከፈታል ተብሏል። መንግሥት በየካቲት ወር አጋማሽ ላይ እድሜያቸው ከ70 ዓመት በላይ የሆኑ፣ የጤና ሠራተኞች እንዲሁም ተያያዥ የጤና ችግር ያለባቸውን በመላዋ ዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ 15 ሚሊዮን ሰዎችን ያህል ሰዎች ለመከተብ እቅድ ይዟል። የጤና ሚኒስትሩ ማት ሐንኮክ የመንግሥትን የክትባት አሰጣጥ እቅድ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ሚኒስትሩ ""ይህ ምክረ ሃሳብ ከወረርሽኙ ለመውጣት የመሰረት ድንጋይ የምንጥልበት ነው"" ብለዋል። መንግሥት በየቀኑ ለምን ያህል ሰዎች ክትባቱን እንደሰጠ የሚያሳይ አሃዛዊ መረጃም ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ሃንኮክ እሁድ እለት እንዳሉት በዩናይትድ ኪንግደም 2 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ተከትበዋል። በእንግሊዝ በየቀኑ ወደ 200 ሺህ ያህል ክትባቶች መስጠት ተችሏል። ዩናይትድ ኪንግደም ወረርሽኙ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ 80 ሺህ ያህል ሰዎችን በተህዋሲው ምክንያት አጥታለች። በአገሪቱ ከፍተኛ በተህዋሲው የተያዙ ሰዎች የሚገኙባት ከተማ ሱሬይ ስትሆን፣ በከተማዋ ጊዜያዊ የቀብር ማስፈፀሚያ ቢሮ በሆስፒታል ውስጥ እንዲከፈት ተደርጓል። ይህ የሆነው የቀብር አስፈጻሚዎች ከአቅማቸው በላይ የሆነ አስከሬኖችን መቀበላቸው ከተሰማ በኋላ ነው። ቢያንስ 200 አስከሬኖች ከዚህ ቀደም የጦር ኃይሉ ሆስፒታል በነበረበት ስፍራ በጊዜያዊነት የተቀመጡ ሲሆን፣ ተመሳሳይ ጊዜያዊ ማቆያ በቅርቡ እንደሚከፈት የአካባቢው አስተዳደር ለቢቢሲ ገልጿል። ቅዳሜ እለት ሳይንቲስቶች እጅግ ጥብቅ የሆነ የእንቅስቃሴ ገደብ በእንግሊዝ ያስፈልጋል ሲሉ ምክራቸውን ሰጥተዋል። የጤና ሚኒስትሩም የአገሪቷን ሕዝቦች የተቀመጠውን የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲያከብሩ ተማጽነዋል። ሃንኮክ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ""ሁልጊዜ ገደቡን ባላላን ቁጥር ውጤቱ የከፋ ነው የሚሆነው"" ሲሉ ተደምጠዋል። አክለውም ""እንደ ማኅበረሰብ በጋራ ልናደርግ የምንችለው በየቤታችን መቆየት ነው"" ብለዋል። በእንግሊዝ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዲወጡ የሚፈቀደው ምግብ ለመግዛት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ወይንም ከቤታቸው ሆነው መስራት ለማይችሉ ወደ ሥራቸው ለመሄድ ብቻ ነው። ተመሳሳይ ሕግ በስኮትላንድ፣ በዌልስ እንዲሁም በሰሜን አየር ላንድም ተጥሏል። የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ ጤና አገልግሎት የሚሰጠው ይህ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት በታሪኩ ትልቁ ነው ተብሏል። ክትባቱ በቤት ውስጥ እንክብካቤ ለሚያገኙ አዛውንቶች፣ እስከ ጥር ወር አጋማሽ ድረስ ተሰጥቶ ያበቃል የተባለ ሲሆን፤ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰቡ ክፍሎች ደግሞ እስከ የካቲት ወር አጋማሽ ድረስ የሚሰጥ ይሆናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55614498 +business ኩባ ኢኮኖሚዋን ለግሉ ዘርፍ ክፍት ልታደርግ ነው ኢንዱስትሪዎች በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ብቻ በሚንቀሳቀሱባት ኩባ አንዳንድ ዘርፎች ከመንግሥት እጅ ወጥተው በግሉ ዘርፍ ለባለሀብቶች ክፍት ሊደረጉ ነው። የሥራና ሠራተኞች ሚኒስትር ማርታ ኤሌና እንዳሉት አሁን የግል ባለሀብት ሊገባባቸው የሚችሉ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ከ127 ወደ 2000 እንዲሆኑ ተደርጓል። ይህም ማለት ጥቂት ዘርፎች ብቻ ናቸው በመንግሥት ይዞታ ሥር የሚቆዩት። የኮሚኒስቷ አገር ኩባ ባለፉት ዓመታት ምጣኔ ሀብቷ ክፉኛ መጎዳቱ ይታወሳል። ይህም የሆነው አንድም በወረርሽኝ ምክንያት ሲሆን ሁለተኛው የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኩባ ላይ ጥሎት በነበረው ማዕቀብ ነው። ባለፈው የአወሮፓውያኑ ዓመት ብቻ የኩባ ኢኮኖሚ 11% ቁልቁል ተንሸራቷል። ይህም በ30 ዓመት ውስጥ የከፋው ነው ተብሏል። ኩባዊያን ለኑሮ መሠረታዊ የሚባሉንት እንኳ ለመሸመት ተችግረዋል። ሚኒስትሯ ማርታ 124 ኢንዱስትሪዎች ብቻ ናቸው ለግል ዘርፍ ክፍት የማይደረጉት ብለዋል። ሆኖም እነዚህ የትኞቹ እንደሆኑ ከመዘርዘር ተቆጥበዋል። አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ምናልባት እነዚህ በመንግሥት እጅ ብቻ ይቆያሉ የተባሉት ሚዲያ፣ ጤናና መከላከያ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ይሆናሉ ሲል ግምቱን አስቀምጧል። በኩባ በሺህ የሚቆጠሩ በግል ከተያዙ አነስተኛና ጥቃቅን እርሻዎች ሌላ በመንግሥት ያልተያዘው ዘርፍ በባለቤትነት የሚይዙት እንደ የነጋዴዎች ማኅበር፣ የእጅ ሙያ ባለቤቶች ማኅበር እንዲሁም የታክሲ አሽከርካሪዎች ማህበርና የመሳሰሉት ናቸው። የአገሪቱ 40 ከመቶ የሚሆነው የግል ቢዝነስ ከቱሪዝም ጋር የተያያዘ በመሆኑ ወረርሽኙን ተከትሎ ከፉኛ ተጎድቷል። ላለፉት 60 ዓመታት በአሜሪካና በኩባ መካከል የነበረው ቅራኔ መሻሻል አሳይቶ የነበረው በአውሮፓውያኑ 2015 ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማና የኩባው ራውል ካስትሮ ግንኙነታቸውን ጤናማ ለማድረግ መስማማታቸውን ተከትሎ ነበር። ይህን ተከትሎ የአሜሪካ ዜጎች ኩባን እንዲጎበኙ፣ አገር በቀል ኢንዱስትሪዎችም እንዲያብቡ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ተፈጥረው ነበር። ሆኖም ይህ የትራምፕ ግንኙነቱን የማሻሻል ጥረት በተተኪያቸው ዶናልድ ትራምፕ ውድቅ ተደርጓል። የትራምፕ ደጋፊ የሆኑ የኩባ አሜሪካዊያን የኦባማን ከራውል ካስትስሮ ጋር መገናኘት የኮሚኒስት አገሯን የመለማመጥ ያህል ነው ብለው ሲቃወሙ ነበር። ትራምፕም የደጋፊዎቻቸውን ቅሬታ ሰምተው ኩባ ላይ ማእቀብ ጥለዋል። አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በምርጫ ቅስቀቸው ወቅት አገራቸው ከኩባ ጋር ያላትን ግንኘኙነት ለማደስ እንደምትፈልግ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን ነገር ግን ይህ አጀንዳ ምን ያህል ቅድሚያ የሚሰጡት ይሆናል የሚለው ግልጽ አይደለም። https://www.bbc.com/amharic/news-55968658 +politics """በደምቢ ዶሎ ከፍርድ ውጭ የተፈጸመው ግድያ አሳሳቢ ነው""- ኢሰመኮ" "በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ በወንጀል የተጠረጠረውን አማኑኤል ወንድሙ ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡ ኮሚሽኑ ይህንን ያሳወቀው በዛሬው ዕለት ግንቦት 4፣ 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ነው። ማክሰኞ ዕለት በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ አማኑኤል ወንድሙ የተባለ ተጠርጣሪ ወጣት በአደባባይ በመንግሥት ኃይል መገደሉን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአካባቢ የመንግሥት ባለስልጣናትም የወጣቱን መገደል አረጋግጠው፤ ወጣቱ ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ ""በአደባባይ አልተገደለም"" ሲሉ አስተባብለዋል። የአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናት ወጣት አማኑዔል 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በመሆኑ 'እርምጃ ተወስዶበታል' በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል። ኮሚሽኑ በመግለጫው ምን አለ? በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ በወንጀል ተጠርጥሯል የተባለው አማኑኤል ወንድሙ ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያና (extrajudicial killing) በአደባባይ ለህዝብ እንዲታይ የተደረገበት መንገድ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገልጿል፡፡ ኮሚሽኑ ማንኛውንም ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎችን የሚያወግዝ መሆኑን አስታውቆ ሁሉም የሕግ አስፈፃሚ አካላት ሕጋዊ መንገዶች ብቻ አንዲተገብሩ መልዕክቱን አስተላለፏል፡፡ ""ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎች ህዝቦች በሕግ የበላይነት ላይ ዕምነት እንዲያጡ እና በዚህ ረገድ የተገኙ ስኬቶች እንዲቀለበሱ ያደርጋሉ ብሏል፡፡ ባለሥልጣናት ጉዳዩን በአፋጣኝ እንዲመረምሩ እና ተገቢ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ኮሚሽኑ ጠይቋል። ኮሚሽኑ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ ስለ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ የአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናት ወጣት አማኑዔል 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በመሆኑ 'እርምጃ ተወስዶበታል' በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል። የደምቢ ዶሎ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት በበኩሉ ሰዎችን ሲገድል በነበረው እና 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በሆነው ግለሰብ ላይ እርምጃ ተወሰደ ሲል በፌስቡክ ገጹ ላይ ጽፏል። የከተማው ጽ/ቤት በፌስቡክ ገጹ ላይም ወጣቱ ከመገደሉ በፊት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል አትሟል። በአካባቢው በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተ��ረጀው የ""ሸኔ"" ቡድን እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል። በምዕራብ ኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች ቡድኑ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት በማድረስ በተደጋጋሚ ይወነጅላል። በቪዲዮው ላይ ምን ይታያል? በዚህ የፌስቡክ ገጽ ላይ ወጣቱ ከመገደሉ በፊት ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጥ ይታያል። ቪዲዮን እየቀረጸ የሚገኘው ሰው የወጣቱን ስም እና የትውልድ ስፍራውን ይጠይቀዋል። እጁ ወደ ኋላ የታሰረው ወጣት አንገቱ ላይ ሽጉጥ ተንጠልጥሎ ይታያል። በወጣቱ እግር ላይ እና በዙሪያው ደም የሚታይ ሲሆን ልብሱም በጭቃ ተለውሷል። አደባባይ ፊትለፊት የቆመው ወጣት ስሙ አማኑኤል ወንድሙ ከበደ እንደሚባል እና ትውልዱ ደምቢ ዶሎ ከተማ 07 ተብሎ በሚጠራ ስፍራ እንደሆነ ይናገራል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎ ተከቦ ይታያል። ወጣቱ ለምን ተገደለ? የከተማው ኮሚውኒኬሽን ጽ/ቤት እንደሚለው ከሆነ ይህ ወጣት የመንግሥት ባለስልጣናት በመግደል የሚታወቀው ""አባ ቶርቤ' የተሰኘው ህቡዕ ቡድን አባል ነበር። ወጣቱ ትናንት በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊትም ንጋት ላይ ገመቹ መንገሻ የተባለ ግለሰብ በጥይት መትቶ ለማምለጥ ሲሞክር ""በጸጥታ ኃይሎች ጠንካራ ትስስር እግሩን ተመትቶ ተይዟል"" ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ከቀናት በፊት በደምቢዶሎ ከተማ የኦሮሚያ ብሮድካስቲን ኔትዎርክ ጋዜጠኛ የነበረውን ሲሳይ ፊዳ የገደለው የአባ ቶርቤ ቡድን ነው ሲል አክሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57088295 +politics "የጋዜጣ አዘጋጁ ስለ ቤንያሚን ኔታንያሁ አሉታዊ ዜናዎች ""እንዳላትም ታዝዣለሁ"" አለ" "በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሙስና ክስ የፍርድ ሂደት ላይ ምስክር ሆኖ የቀረበው አዘጋጅና የቀድሞ ስራ አስፈፃሚ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ አሉታዊ ዜናዎችን እንዳያትም ትእዛዝ እንደተሰጠው ተናግሯል። ኢላን የሹዋ የተባለው የዋላ ድረ-ገፅ የቀድሞ ስራ አስፈፃሚ ችሎት ፊት ቀርቦ እንዳስረዳው አሉታዊ ፅሁፎችን ከመከልከል በተጨማሪ ሻውል ኢሎቪትች የተባሉት የድረገፁ ባለቤት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ተቀናቃኞችን የሚያጥላላ ፅሁፎች እንዲያወጣ ታዝዣለሁ ብሏል። አቃቤ ህግ እንደሚለው ቤንያሚን ኔታንያሁ እርሳቸውን የሚደግፍና የሚያሟካሽ ፅሁፍ እንዲወጣ በማለት በሚሊዮን ዶላሮች የሚያስወጣ ውሳኔን አስተላልፈዋል በማለት ይከሳቸዋል። የድረገፁም ባለቤት ይሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንም አይነት ስህተት አልፈፀምንም ሲሉ ይናገራሉ። በሙስና፣ በማጭበርበርና እምነት በማጉደል በሶስት ተነጣጣይ ወንጀሎች የተከሰሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ክሱን ""ሽፋን"" ነው በማለት በተፃራራው አቃቤ ህግ መንግሥታቸውን ለመጣል የሚያደርገው ሙከራ ነው ብለውታል። የባለፈውን ወር ምርጫ ተከትሎ ቀጣዩን መንግሥት የሚመሰርተውን አካል ለመወሰን የእስራኤሉ ፕሬዚዳንት የምክር ቤቱ እንደራሴዎቹን ሰብስበው ነበር ተብሏል። በዚህም ወቅት በተደረገው የድምፅ መስጫ ስነ ስርዓት አገሪቷ በሁለት አመት ውስጥ አራት ምርጫዎችን እንድታደርግ ያስገደዳትን ፖለቲካዊ አጣብቂኝ መፍታት ሳይቻል ቀርቷል ተብሏል። የቀኝ ክንፍ መሪው ኔታንያሁና በአንድ ጎራ እንዲሁም በሌላ ጎራ ያሉት ተቀናቃኞቻቸው ቀጣዩን መንግሥት ለመመስረት ከፍተኛ ድምፅ ማግኘት አልቻሉም ተብሏል። የእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ሩቨን ሪቭሊን በሚቀጥለው ሳምንት የፓርቲውን አመራሮች ጋሮች ለመምከር ቀጠሮ የያዙ ሲሆን በመቀጠልም ቀጣዩን የጥምር መንግሥት ለመመስረት ትልቅ እድል ያለውን አካል እጩ ያቀርባሉ ተብሏል። ክሶቹ ምንድንናቸው? አንደኛው የተነሳባቸው ጉዳይ አንድ የእስራኤል ጋዜጣ በአዎንታዊ መልክ ስለሳቸው እ��ዲዘግብ አድርገዋል ነው። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ የህትመቱ አዘጋጅም ክስ እንደሚጠብቃቸው ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል። ሁለተኛው ውንጀላም ወደ 300 ሺ ዶላር የሚያወጣ ስጦታ ከታዋቂው ባለሀብትና በሆሊውድ ታዋቂ የፊልም ኩባንያ ባለቤትና አርኖን ሚልቻንና ከሌሎች ደጋፊዎቻቸው ተቀብለዋል የሚል ነው። ጀሩሳሌም ፖስት እንደዘገበው ስጦታዎቹ ሻምፓኝ፣ ሲጋራና ሌሎች ሲሆኑ በምላሹም አርኖን የአሜሪካ ቪዛ እንዲያገኙ አመቻችተዋል የሚል ነው። ፖሊስ ጨምሮ እንደገለፀውም ኔታንያሁ ስጦታውን ከተቀበሉ በኋላ የአርኖን ሚልቻን ህግ እንዲፀድቅ ግፊት አድርገዋል ይላል። ይህም ከአስራኤል ውጭ የሚኖሩ እስራኤላውያን ሀገራቸው በሚመለሱበት ጊዜ ለአስር ዓመታት ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ነው። ይህ ረቂቅም በገንዘብ ሚኒስትሩ ውድቅ ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪ ከአውስትራሊያዊው ቢሊየነር ጄምስ ፓከር ጋር በተያያዘ በማጭበርበር እንዲሁም እምነትን በመጣስ ተከሰዋል። የእስራኤሉ ቻናል 10 የተባለው ሚዲያ እንደዘገበውም ቢሊየነሩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለባለቤታቸው ስጦታ እንደሰጡ ለመርማሪዎች እንደተናገሩ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-56645974 +business የክሪፕቶከረንሲዎች ዋጋ እንዲያሽቆለቁል ያደረገው ምንድን ነው? ባለፈው ወር  ሁለት ብዙም የማይታወቁ ግን በጣም ትልቅ የሆኑ ዲጂታል ገንዘቦች ተንኮታኩተዋል። ይህም በአጠቃላይ በዲጂታል ገበያው ላይ ያለውን አመኔታ አሳጥቷል። ቢትኮይን እና ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎች በእጅጉ ቀንሰዋል። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? ቢቢሲ የተወሰኑ ነጥቦችን ለይቷል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cq5z2l7xpg0o +sports ፊፋ ብዙ ጸያፍ ስድቦችን በማኅበራዊ ሚዲያ ያስተናገዱ ሁለት ተጫዋቾችን ይፋ አደረገ የዓለም እግር ኳስን የሚያስተዳድረው አካል ፊፋ ከፍተኛ ዘለፋን እንዲሁም ጸያፍ ስድብን በማኅበራዊ ሚዲያ ያስተናገዱ ተጫዋቾችን ለየ። ፊፋ ይህን የለየው ከተጨዋቾች ኅብረት ‘ፊፍፕሮ’ ጋር በጥምረት በሠራው አንድ ጥናት ነው፡፡ ጥናቱ ግብ ያደረገው እግር ኳስ ተጨዋቾች ላይ ከፍተኛ ዘለፋን እና መረን የለቀቁ ስድቦችን የሚያደርሱ የማኅበራዊ ትስስር መልዕክቶችን በመከታተል ላይ ነበር። በዚህም ጥናቱ 400 ሺህ በማኅበራዊ ትስስር መድረክ የተለጠፉ መልዕክቶችን በናሙናነት ወስዷል። ናሙናዎቹ የተወሰዱት በ2020 የአውሮፓ ዋንጫ እና የአፍሪካ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ላይ በተሰነዘሩ የማኅበራዊ ሚዲያ መስተጋብሮች ነበር። የጥናቱ ውጤት እንዳመላከተው ከጠቅላላ በውድድሩ ከተሰለፉ ተጫዋቾች 50 ከመቶ የሚሆኑት ይነስም ይብዛ አንዳች ዘለፋና ስድብ ተሰንዝሮባቸዋል። ይህ ጥናት ሌላ ደረስኩበት ያለው ለከፍተኛ ዘለፋ ከሚጋለጡት ሁሉ የከፋ ዘለፋ የሚደርስባቸው ጥቁር ተጫዋቾች እና ፍጹም ቅጣት ምት የሳቱ ተጨዋቾች መሆናቸው ነው። ቢቢሲ ስፖርት ጥናቱን መሠረት አድርጎ በሠራው ትንታኔ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች፣ ማርከስ ራሽፎርድ እና ቡካዮ ሳካ አገራቸው በፈረንጆቹ 2020 በአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ በጣሊያን ስትረታ ፍጹም ቅጣት ምት የሳቱ ተጫዋቾች መሆናቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ከፍተኛውን የማኅበራዊ ሚዲያ ዘለፋ ያስተናገዱ ተጨዋቾች እንደሆኑ ደርሶበታል። የጥናቱን ውጤት ይፋ መሆን ተከትሎ የፊፋው ፕሬዝዳንት ኢንፋንቲኖ “ዓላማችን በእግር ኳስ ትልቅ ፈንጠዚያን የሚያመጡልንን ውድ ተጨዋቾች ከተራ ዘለፋና ከቆሻሻ የማኅበራዊ ሚዲያ ጥቃት መከላከል ነው” ብለዋል። ይህ ጥናት በደረሰበት ድምዳሜ መሠረት በሁለቱ የዋንጫ ውድድሮች ዛቻና ዘለፋን በማኅበራዊ ሚዲያ ያደረሱት በዋናነት ከባለጋራ ቡድን ደጋፊዎች ይልቅ የተጫዋቾቹ የገዛ አገር ዜጎች መሆናቸው ��ው። ከዘለፋዎቹና ጸያፍ ስድቦች ውስጥ 40 ከመቶ ድርሻን የያዙት የተመሳሳይ ጾታ ምርጫ ላይ ያነጣጠሩ ሲሆን፣ 38 ከመቶ ደግሞ ቆዳ ቀለም ላይ ያነጣጠሩ ነበሩ። ይህን ጥናት መሠረት በማድረግ ፊፋ እና ፊፍፕሮ ከዚህ ወዲህ ውድድሮች ሲካሄዱ ግጥሚያዎቹ ላይ ትኩረት ያደረጉ ጸያፍ ስድቦችን የሚለዩ የክትትል ሥራዎችን ለማድረግ አቅደዋል። ይህም ጸያፍ ስድቦች በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች በተጻፉበት ቅጽበት ሌሎች በርካታ ሰዎች ሳይመለከቷቸው ወዲያውኑ ከገጽ እንዲጠፉ የሚያደርግ ሙከራ ይሆናል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cjq9wdye7q3o +politics ሩስያ አፍሪካ የጋራ ፎረም፡ ፑቲን ከአፍሪካ የሚፈልጉት ምንድን ነው? "ትናንት ጥቅምት 11፣ 2012 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በሩሲያ አፍሪካ የጋራ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ሩስያ ሶቺ አቅንተዋል። በሩስያ ሶቺ ከተማ በሚካሄደው በዚህ ጉባዔ ላይ ከ35 የአፍሪካ አገራት መሪዎች በላይ ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ በቆይታቸውም የሩስያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ጨምሮ ከአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሏል። ሶቪየት ሕብረት ከቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት በፊት በአፍሪካ የተለያዩ አገራት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተሰማርታ የነበረች ቢሆንም ከዚያ በኋላ ግን በአፍሪካ ውስጥ በምጣኔ ኃብትና በፖለቲካ ያላት ተጽዕኖ እየቀነሰ መጥቷል። • ""ኢትዮጵያ የኢህአዴግ አባት እንጂ፤ ኢህአዴግ የኢትዮጵያ አባት አይደለም"" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሩሲያ ከአፍሪካ ይልቅ ከአውሮጳና ከኢሲያ ጋር የተሻለ የንግድ ግንኙነት አላት። እኤአ ከ2017 ወዲህም አፍሪካ ጠንካራ የንግድ ግንኙነት ያላት ከሕንድ፣ ቻይናና አሜሪካ እንጂ ከሩሲያ ጋር አይደለም። ለአፍሪካ ሩሲያ ከምታደርገው ሰብዓዊ እርዳታም በላቀ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ጃፓንና አውሮጳ ሕብረት ያደርጋሉ። ""ሩሲያ በአንድ ወቅት የሶቪየት ሕብረት በአፍሪካ ላይ የነበራትን ተጽዕኖ ይኖራታል ማለት ከባድ ነው"" የሚሉት ባለሙያዎች ""የሩሲያ ተጽዕኖ ውስን ከሆኑ የአፍሪካ አገራት ጋር በወሳኝ ጉዳዮች ላይ ብቻ በሚኖር ትብብር ይመሰረታል"" ይላሉ። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ቀዳሚ አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል። ለመሆኑ ሩሲያ ከአፍሪካ የምትፈልገው ምንድን ነው? ሞስኮ በአፍሪካ ያላትን ሥፍራ ለማስፋት እንዲሁም ግንኙነቷን ማጠናከር እንደምትፈልግ ከሶቪየት ሕብረት ወቅት ጀምሮ የታወቀ ነው። ፑቲን ከዚህ ጉባዔ ቀደም ብሎ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ እንዳስታወቁት "" የሩሲያ አፍሪካ ግንኙነት እያደገ ነው"" በማለት ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፎችን፣ የመከላከያና ደህንነት ርዳታዎችን፣ የምጣኔ ኃብት ድጋፍ፣ ሕክምና፣ ሰብዓዊ ርዳታ እንዲሁም የሙያ ትምህርት ስልጠና ላይ ድጋፍ ለማድረግ እንደተዘጋጁ ዘርዝረዋል። • የዋግ ኽምራ አርሶ አደሮች ለከፋ ችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው ሩሲያ ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን ፖለቲካዊ ግንኙነት ከ12 አፍሪካ መሪዎች ጋር እኤአ ከ2015 ጀምሮ የጀመረች ሲሆን ከእነዚህ መካከል ስድስቶቹ በ2018 የተቀላቀሉ ናቸው። ባለፈው ዓመት የቀድሞው የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን አሜሪካ ለአፍሪካ አዲስ አጋርነት ስልት እንዳዘጋጀች ጠቅሰው የዚህ ስልት ከፊሉ የቻይናና ሩሲያን ተጽዕኖ መቀነስ ያለመ ነው ብለው ነበር። ነገር ግን በቅርቡ በዋሺንግተን ፖስት ላይ የወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው ሩሲያ ""በደህንነት ጉዳዮች ላይ ግንኙነቶችን ማጠናከርና ስምምነቶች ላይ መድረስ"" በከፍተኛ ሁኔታ ትፈልጋለች። ሩሲያ ለአ���ሪካ ዋነኛ የመከላከያ አጋር ስትሆን የጦር መሳሪያም አቅራቢ ናት። ነገር ግን የመከላከያ ገበያዋ ዋነኛ መዳረሻ አፍሪካ ሳትሆን ኢሲያ ነው። እንደ ስቶክሆልም ዓለም ዓቀፍ የሰላም ጥናት ተቋም ከሆነ ከ2014 እስከ 2018 በአፍሪካ ግብፅን ሳይጨምር ከሩሲያ 17 በመቶ መሳሪያ ገዝተዋል። ከዚህ 17 በመቶው ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የምትይዘው አልጄሪያ ስትሆን ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ድርሻቸው በጣም ያነሰ ነው። • አዲስ አበባ ውስጥ ሲካሄዱ የነበሩ ስብሰባዎች በወጣቶች መስተጓጎላቸው ተነገሯል ለሩሲያ የመሳሪያ ዋና ገበያ ኢሲያ ስትሆን ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራት ድርሻ በጣም አናሳ ነው። ይህ ቢሆንም ግን ሩሲያ ከ2014 ጀምሮ ከ19 የአፍሪካ አገራት ጋር ወታደራዊ ስምምነት ከፈፀመች ወዲህ እያደገ ነው። እኤአ በ2017/ 18 ሩሲያ ከአንጎላ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን፣ ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ጋር የመሳሪያ አቅርቦት ስምምነት ፈርማለች። ይህ የተዋጊ ጀቶችን፣ የጦርና የመጓጓዣ ሂሊኮፕተሮችን፣ ፀረ ታንክ ሚሳዔል እና ለተዋጊ አውሮፕላኖች የሚሆን ሞተሮችን ማቅረብን ያጠቃልላል። የሩሲያ ወታደራዊና ደህንነት ስምምነት የጦር መሳሪያ ሽያጭ ላይ ያተኮረ ብቻ ሳይሆን፣ አንዳንዴ የግል ጠባቂ ቡድኖችን እስከማቅረብ የደረሰ ስምምነት ያላቸው የአፍሪካ አገራት አሉ። ለምሳሌ ሩሲያ በማዕከላዊ አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈውን መንግሥት ከአማጺያን ጥቃት ለመከላከል ተሰማርታለች። ነገር ግን በዚያ ያለው የሩሲያ ወታደራዊ ኃይል ለመንግሥት እና ወሳኝ ለሆኑ የኢኮኖሚ ሀብቶች ጥበቃ ያደርጋል። የሩሲያ የግል ጠባቂ ወታደራዊ ኃይል፣ ከክሬምሊን ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገረው የግል ጠባቂ ኃይል፣ ዋግነር፣ በሱዳንና በሊቢያ እንዲሁም በሌሎች የአፍሪካ አገራት ጥበቃ እንደሚያደርግ ይታወቃል። የሩሲያ ባለሥልጣናት ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ከማለት ተቆጥበዋል። የምጣኔ ኃብት ፍላጎቶች ሩሲያ በአፍሪካ በግልጽ የምጣኔ ኃብት ፍላጎቶች አሏት። እንደ ማንጋኒዝ፣ ቦክሳይት እና ክሮሚየም ያሉና ለኢንዱስትሪ ወሳኝ ግብዓት የሆኑ ማዕድኖችን ትፈልጋለች። የሩሲያ የመንግሥት ኩባንያዎች በጊኒ ቦክሳይት ማዕድን የሚያወጡ ሲሆን በአንጎላ ደግሞ ዳይመንድ ለማውጣት ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ከሞዛምቢክ ጋርም እንዲሁ ጋዝ በማውጣት ላይ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል። • ""አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ነገ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደሚገባ ግልጽ ነው"" አቦይ ስብሃት ትልቁ የሩሲያ ኢነርጂ ኩባንያ በካሜሮን፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ፕሮጀክቶች ያሉት ሲሆን በኮንጎ ደግሞ ስምምነት ላይ ለመድረስ እየሰራ እንደሆን ለማወቅ ተችሏል። ሩሲያ ለበርካታ የአፍሪካ አገራት የኒውክለር ኃይል ቴክኖሎጂን የምታቀርብ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በሚቀጥለው ዓመት በግብፅ በ25 ቢሊየን ዶላር ብድር የሚገነባው የመጀመሪያው የኒውክለር ኃይል ይገኝበታል።" https://www.bbc.com/amharic/50149249 +business ቻይና የምጣኔ ሀብት እድገቷ ዝግ ስላለ የወለድ መጠን ቀነሰች ቻይና ባልተጠበቀ ሁኔታ የወለድ መጠኗን ቀነሰች። ውሳኔው ከሁለት ዓመታት ወዲህ የመጀመሪያው ነው። ቻይና ውሳኔውን ያሳለፈችው የምጣኔ ሀብት እድገቷ በመቀዛቀዙ ዝግ ስላለ ነው ተብሏል። ካለፈው ዓመት አንጻር ባለፉት 3 ሳምንታት ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት 4 በመቶ መጨመሩን ብሔራዊ ስታትስቲክስ አስታውቋል። እድገቱ ከተገመተው የተሻለ ቢሆንም ካለፈው መንፈቅ አንጻር ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቷል። የምጣኔ ሀብት እድገቱ ዝግ ማለቱን የሚያሳየው ታኅሣሥ ላይ የሸቀጥ ሽያጭ ወደ 1.7 በመቶ ማሽቆልቆሉ ነው። በአጠቃላይ የቻይና እድገት ሲታይ ግን የ8.1 በመቶ እድገት ታይቷል። ቤይጂንግ ከ6 በመቶ በላይ እድገት ይመዘገባል ብላ ገምታ ነበር። ባለፈው አንድ ዓመት የታየው መቀዛቀዝ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር እንደሚያያዝ የምጣኔ ሀብት ተንታኞች ይናገራሉ። የኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒቱ ዩ ሱ እንደሚሉት፤ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርቱ የተሰላው የኦሚክሮን ዝርያ ያደረሰው ተጽዕኖ ሳይሰላ ነው። የቻይና ብሔራዊ ባንክ ምጣኔ ሀብቱን ለማነቃቃት ሲል የወለድ መጠኑን መቀነሱን ገልጿል። ይህ ውሳኔ ቻይናን ከሌሎች አገሮች ብሔራዊ ባንኮች ወደኋላ ያስቀራታል። የአሜሪካ ፌደራል ሪዘርቭ የወለድ መጠኑን በዚህ ዓመት ሦስት ጊዜ የመጨመር ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል። የዩናይትድ ኪንግደም ባንክም የዋጋ ግሽበትን ተከትሎ ባለፈው ወር ወለዱን ጨምሯል። በቤይጂንግ ነጋዴዎች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና የቻይና ምጣኔ ሀብት ላይ ጉዳት ሳያሳድር እንዳልቀረ ይነገራል። በቻይና የእዳ ቀውስ ውስጥ የገቡ ባለሀብቶች በመብዛታቸው ሳቢያ ኢንቨስትመንት ተቀዛቅዟል። ይህ ቤት አልሚዎች ከባንክ መበደር የሚችሉት የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ከተጣለ በኋላ የመጣ ቀውስ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ቻይና ወረርሽኙ በተቀሰቀሰበት ወቅት እንደነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ መጣል መጀመሯም ገበያውን አፍዝዞታል። በዚህ የተነሳም ሸማቾች አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል። ከተፈጠረው ውጥንቅጥ ለመውጣት ሲል ነው የቻይና ብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠንን ለመቀነስ የወሰነው። በእርግጥ ቻይና ትልልቅ ንግዶችን የመደገፍ ዕቅድ የላትም። የወረርሽኙ ስርጭት እጅግ ስለሚያሰጋት የእንቅስቃሴ ገደብ የማንሳት ፍላጎትም አላሳየችም። https://www.bbc.com/amharic/news-60026435 +health የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሚኒስትሮቻቸው በምሽት ክበቦች በመገኘታቸው ይቅርታ ጠየቁ "በጃፓን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት የወጣውን መመሪያ ተላልፈው ወደ ምሽት ክበቦች የሄዱ የአገሪቱ ባለስልጣናት ጉዳይ ከፍተኛ ትችትን አስከትሏል። ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሚኒስትሮቻቸው ስም ለህዝቡ ይቅርታ ለመጠየቅ ተገደዋል። መንግሥት በተደጋጋሚ አላስፈላጊ የሆኑ ስብሰባዎችን ህዝቡ እንዲያስወግድ ሲናገር የነበረ ሲሆን ይህንንም ሁኔታ ሚኒስትሮቹ አለማክበራቸው አወዛጋቢ ሆኗል። ""ዜጎቻችንን ከምሽት ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ሬስቶራንቶች ወጥታችሁ አንዳትበሉ እንዲሁም አላስፈላጊ የሆኑና አስቸኳይ ካልሆነ ከቤታችሁ አትውጡ በምንልበት ወቅት ይህ በመፈጠሩ በጣም አዝኛለሁ"" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺሂዴ ሱጋ በዛሬው እለት ለፓርላማው አስረድተዋል። የጃፓን የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ሪፖርት ባደረጉት መሰረት አንደኛው ሚኒስትር ባለፈው ሳምንት የጣልያን ሬስቶራንት ውስጥ እራት ከበሉ በኋላ ሞቅ ደመቅ ባለው የመዲናዋ ቶክዮ ማዕከል በሆነው ጊንዛ ወደሚገኙ ሁለት የምሽት ክበቦች አምርተው ነበር ብለዋል። እንዲሁ ሌላኛው ሚኒስትር ጊንዛ በሚገኝ ታዋቂ ክለብ በተደጋጋሚ መሄዳቸውን የአገሪቱ ሚዲያ አስነብቧል። የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝ ለሁለተኛ ዙር እያገረሸ ባለባት ቶክዮ ባለስልጣናቱ የአስቸኳይ ጊዜ አውጀዋል። በጃፓን ከ370 ሺህ በላይ ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከ5 ሺህ በላይ ዜጎቿንም አጥታለች።" https://www.bbc.com/amharic/55810201 +sports የኮቢ ብሪያንት ባለቤት በሀዘን ልቧ እንደተሰበረ ገለፀች "የኮቢ ብሪያንት ባለቤት ቫኔሳ ባለቤቷና ልጇ አሰቃቂ በተባለው የሄሊኮፕተር አደጋ መሞት ተከትሎ ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረች ሲሆን ""ልቤ ተሰብሯል፤ የሚሰማኝን ሃዘንና ህመም ሊገልፅልኝ የሚችል ቃል አይገኝም"" ብላለች። በአደጋው ዝነኛው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብሪያንትና ልጁን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል። በኢንስታግራም ገጿ ላይ የቤተሰባቸውን ፎቶ በመለጠፍ ሐዘኗን የገለፀችው ቫኔሳ ""ድንቅ አባትና አፍቃሪ ባሌን እንዲህ ድንገተኛ በሆነ ሁኔታ በማጣቴ ሐዘኔ ጥልቅ ነው። አሳቢ፣ ቆንጆ፣ ትሁትና ግሩም የሆነ ባህርይ የነበራትን ልጄን ማጣቴ ደግሞ ሃዘኔ ድርብ እጥፍ ያደርገዋል"" ብላለች። •""አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ"" የረዳት አብራሪው ጓደኛ •ታዋቂው አሜሪካዊ ስፖርተኛ ከነልጁ በሄሊኮፕተር አደጋ ሞተ አክላም ""ለዘላለም አብረውን ቢኖሩ ምኞቴ ነበር። በአጭሩ ተቀጩ፤ እኔም ምርቃቶቼን ተነጠቅኩኝ። ህይወትን ያለነሱ ማሰብ አዳጋች ነው። የነገውን ሳስብ ይጨልምብኛል፤ ያስፈራኛል።"" ኮቢና ቫኔሳ በአደጋው የሞተችውን የአስራ ሦስት ዓመቷን ጂያናን ጨምሮ አራት ልጆችን አፍርተዋል። ጭጋጋማ በነበረው የአየር ጠባይ በምዕራብ ሎስ አንጀለስ የተከሰተው የሄሊኮፕተር አደጋ ምርመራ እስካሁን አልተቋጨም። በወቅቱም ኮቢ የልጁን ቅርጫት ኳስ ቡድን ለማሰልጠን ወደ ማምባ ስፖርት አካዳሚ እያቀና ነበር ተብሏል። ምንም እንኳን አደጋው የደረሰው እሁድ ቢሆንም የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ዝርዝር ይፋ አልሆነም። አድናቂዎቹ በዚህ ፈታኝ ወቅት ላሳዩት ድጋፍ ያመሰገነችው ቫኔሳ በአደጋው ህይወታቸውን ያጡትን ለመዘከር እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ ማምባ ስፖርት የሚባል ድርጅት እንደሚመሰረት ገልፃለች። •ቦይንግ ""ከእንግዲህ የሚታመን ድርጅት አይደለም"" በአደጋው ኮቢና ልጁን ጨምሮ፣ ፓይለቱ፣ ሁለት የአስራ ሦስት ዓመት እድሜ ያላቸው የቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች፣ ሦስት ወላጆችና አሰልጣኙ ህይወታቸው አልፏል። በቅርጫት ኳሱም ሆነ በስፖርቱ ዓለም ስመ ገናና የነበረው ኮቢ ክለቡን ሎስ አንጀለስ ሌከርስን አምስት ጊዜ የሻምፒዮንነት ስፍራን ያስጨበጠና ሁለት ጊዜም የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያን ማሸነፍ ችሏል። ኮቢ ከሃያ ዓመት የተሳካ የስፖርት ዓለም ቆይታው በኋላ ራሱን ከቡድኑ ያገለለው ከሦስት ዓመታት በፊት ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-51306325 +politics በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር ከ85 ወደ 59 ቀነሰ በኢትዮጵያ ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ ተብለው በቁጥር ከሚታወቁት 85 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል 26ቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመሰረዛቸው ብዛታቸው ወደ 59 ቀነሰ። በቦርድ መሰረዛቸው የተገለጸው በተለያዩ ጊዜያት ተመስርተው በብሔርና በአገር አቀፍ ፓርቲነት በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ከሚገኙት ውስጥ በፓርቲነት ለመቀጠል የሚያስችላቸውን መስፈርቶች ሳያሟሉ የቀሩት 26 የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው። በአገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት ተመዝግበው ከነበሩት ከአንድ መቶ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የተወሰኑት በተለያዩ ምክንያቶች የሚጠቅባቸውን ባለማሟላታቸው በመሰረዛቸው፤ በአሁኑ ወቅት በምርጫ ቦርድ የተመዘገቡና በተለያዩ የምዝገባ ሂደት ላይ የሚገኙት 59 ፓርቲዎች ናቸው። የምርጫ ቦርድ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በምዝገባው ማጣራት ሲደረግባቸው የነበሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር 85 የነበሩ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 26ቱ ተሰርዘዋል። ከተሰረዙት መካከልም የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የመላው ኢትዮጵያዊያን ብሔራዊ ንቅናቄ (መኢብን)፣ የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ)፣ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ይገኙባቸዋል። ከተሰረዙት ባሻገር በተለያዩ ምክንያቶች ማብራሪያ እንዲሰጡ ወይም የሚጠበቅባቸውን አሟልተው እንዲያቀርቡ የተወሰነ እና የማጣራት ሂደታቸው ያልተጠናቀቀ ፓርቲዎች ያሉ ሲሆን የሚሰረዙት ቁጥር ሊጨምር ይችላል�� በዚህም መሰረት በተለያዩ ምክንያቶች ማብራሪያ እንዲሰጡ ወይም የሚጠበቅባቸውን አሟልተው እንዲያቀርቡ የተወሰነና የማጣራት ሂደታቸው ያልተጠናቀቀ 12 ፓርቲዎች እንዳሉ የምርጫ ቦርድ መግለጫ አመልክቷል። ከእነዚህ ውስጥም የመላው ኢትዮጵያዊያን አንድነት ድርጅት ( መኢአድ) እና የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ይገኙበታል። በተጨማሪም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማጣራት ሂደታቸው የተጠናቀቀ ነገር ግን የቴክኒክ መስፈርቶች ማሟላት ይቀራቸዋል ያላቸውን ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ራያ ራዩማ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ፣ አሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲና ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይን ጨምሮ ሰባት ፓርቲዎች መሆናቸውን ገልጿል። ከዚህ በሻገር በምዝገባው ሂደት የሚጠበቅባቸውን በማሟላት የማጣራት ሂደታቸው የተጠናቀቀ ፓርቲዎች 40 ሲሆኑ፤ ከእነዚህ ውስጥም ገዢው ፓርቲ ብልጽግና፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) እና ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉአላዊነት (አረና) ይገኙበታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዳለው በተሻሻለው አዋጅና ፓርቲዎች ማሟላት የሚገባቸውን ግዴታዎች በሚደነግገው መመሪያ መሰረት የተመዘገቡና በሂደት ላይ ያሉ ፓርቲዎች የተቀመጡ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን ሲያጣራ ቆይቷል። በዚህም መሰረት ፓርቲዎቹ ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ነገሮች በማጣራት ከ35 በመቶ በላይ የመስራች አባላት ፊርማ ትክክል የሆኑ ፓርቲዎችን ምዝገባ ያጸደቀ መሆኑን ቦርዱ አመልክቶ ከ35 በመቶ በታች የሆኑትን 26 ፓርቲዎችን እንዲሰረዙ ወስኗል። ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በድጋሚ ለመመዝገብ የሚጠበቅባቸውን መመዘኛዎች አላሟሉም ያላቸውን 27 የፖለቲካ ፓርቲዎች በተመሳሳይ መሰረዙ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከወሰዷቸው የማሻሻያ እርምጃዎች መካከል የምርጫ ቦርድ በገለልተኝነት እንዲመራ ማድረግ አንዱ መሆኑ ይታወሳል። በዚህም መሰረት ቦርዱ እንደ አዲስ ተዋቅሮ የሕግ ማሻሻያዎች ከተደረጉ በኋላ ቀደም ሲል በነበረው አሰራር ተመስርተው በአገሪቱ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአዲሱ ሕግ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ በማድረግ በድጋሚ እንዲመዘገቡ ሲደረግ ቆይቷል። እስካለፈው ዓመት ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚታወቁ ከ106 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የነበሩ ሲሆን በድጋሚ ምዝገባ በማድረግ አውቅናቸውን እንዲያድሱ ባለፈው ዓመት ጥሪ ቀርቦላቸው ነበር። በዚህም መሠረት ቦርዱ ባደረገው ማጣራት የሚጠበቅባቸውን ሳያሟሉ የቀሩ 53 አገራዊና የብሔር የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሰረዙ መወሰኑን ባለፈው ዓመት ግንቦት 07/2012 ዓ.ም እና በዚህ ዓመት ታኅሳስ 13/2013 ዓ.ም ወስኗል። https://www.bbc.com/amharic/news-55421931 +health ንግሥት ኤልዛቤት ሆስፒታል ገብተው እንደነበር ተገለጸ "የዩናይትድ ኪንግደሟ ንግሥት ኤልዛቤት ቀዳሚ የህክምና ምርመራ ለማድረግ ረቡዕ ምሽት ሆስፒታል ገብተው እንደነበር የባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት አስታወቀ። የ95 ዓመቷ ንግሥት ኤልዛቤት ማእከላዊ ለንደን በሚገኝ አንድ የግል ሆስፒታል ውስጥ ህክምናቸውን ተከታትለው ዊንድሰር ወደ ሚገኘው መኖሪያቸው መመለሳቸውን ተገልጿል። አሁን በመልካም ሁኔታ ላይ ናቸው የተባሉት ንግሥቲቱ ወደ ሰሜን አየርላንድ ለመጓዝ የነበራቸውን እቅድ ሰርዘዋል። የህክምና ባለሙያዎች ንግሥቲቷ ወደተለመደው ሥራቸው ከመመለሳቸው በፊት ለጥቂት ቀናት እረፍት ማድረግ እንደሚገ���ቸው መክረዋል ተብሏል። ሐሙስ ምሽት ስለንግሥቲቱ መግለጫ የሰጠው የባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት እንዳለው ""ንግሥቲቱ ረቡዕ ዕለት ወደ ሆስፒታል ያቀኑት የተለመደ ክትትል ለማድረግ ሲሆን ሐሙስ ምሳ ሰዓት አካባቢ ተመልሰዋል፤ መንፈሳቸውም ተነቃቅቷል"" ብሏል። ንግሥቲቱ ወደ ንጉሥ ኤድዋርድ ሰባተኛ ሆስፒታል የተወሰዱት ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ምክንያት እንዳልሆነም ተገልጿል። ንግሥት ኤልዛቤት ሁለተኛ ሆስፒታል ውስጥ ለህክምና ሲኣሳልፉ ከፈረንጆቹ ከ2013 በኋላ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ማዕከላዊ ለንደን የሚገኘው ንጉሥ ኤድዋርድ ሰባተኛ የግል ሆስፒታል በንጉሣውያን ቤተሰቦች ይዘወተራል። በቅርቡ በሞት የተለዩት የንግሥቲቱ ባለቤትን ጨምሮ ንጉሣዊያን ቤተሰቦች የሚታከሙት በዚሁ ሆስፒታል ነው። ንግሥቲቷ ወደ ሰሜን አየርላንድ መሄዳቸውን ትተው ወደ ሆስፒታል ያቀናሉ የሚለው ዜና ጭንቀት እንዳይፈጥር ተሰግቶ ነበር። ምንም እንኳ ኤልዛቤት ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በተሳተፉባቸው ዝግጅቶች ላይ ነቃ ብለው ቢታዩም ዕድሜያቸው ለጤናቸው ስጋት ሊሆን እንደሚችል አያጠርጥርም። ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት ስለ ንግሥቲቱ የጤንነት ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠበው ግላዊ ሕይወታቸውን ለመጠበቅ ነው ተብሏል። ምንም እንኳ ቤተ-መንግሥቱ ምንም መረጃ ላለመስጠት አስቦ የነበረ ቢሆንም ዘ ሰን የተሰኘው ጋዜጣ ያወጣው ፅሑፍ ነው የቤተ-መንግሥቱን ሰዎች መረጃ እንዲያወጡ ያስገደዳቸው። ንግሥቲቱ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በርካታ ቦታዎችን እየተዘዋወሩ ሲጎበኙ፤ የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲታደሙ ነበር የከረሙት። የንግሥት ኤልዛቤት የዕለተ ከዕለት ተግባር መመዝገቢያ እንደሚያሳየው በፈረንጆቹ የጥቅምት ወር ብቻ 16 ዝግጅቶችን ታድመዋል። ይህ ወደ ሰሜን አየርላንድ ሊያደርጉ ያሰቡትን ጉብኝት ሳይጨምር ነው። ቤተ-መንግሥቱ እንዳለው ንግሥቲቱ ወደ ሰሜን አየርላንድ ለማድረግ ያሰቡት ጉብኝት አለመሳካቱ ቢያበሳጫቸውም የዶክተር ምክርን ሰምተው ዕረፍት እያደረጉ ይገኛሉ። ንግሥቲቱ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚካሄደው የግላስጎው የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-58991734 +business ከ770 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አደንዛዥ ዕጽ በአዲስ አበባ አየር ማረፊያ ተያዘ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን 97 ኪሎ ግራም የሚመዝንና ከ773 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ የሚያወጣ የኮኬይን አደንዛዥ ዕጽ ቦሌ አየር ማረፊያ ውስጥ መያዙን አስታወቀ። እንደ ኮሚሽኑ መረጃ ይህ በአዲስ አበባ አየር ማረፊያ ውስጥ የተያዘው አደንዛዥ ዕጽ፣ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተያዙ ከፍተኛ መጠን ካላቸው አደንዛዥ ዕጾች መካከል አንዱ ሊባል የሚችል ነው። 97.48 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ይህ የኮኬይን አደንዛዥ ዕጽ የተያዘው ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ በመጣች ግለሰብ ሻንጣ ውስጥ ነው። ግለሰቧ አንድ መቶ ኪሎ ግራም የሚጠጋው ዕጽ በሁለት ሻንጣዎች ውስጥ እኩል በ49 ኪሎ ግራም ገደማ ይዛ ለማሳለፍ ስትሞክር በጉምሩክ ኮሚሽን ኤርፖርት ቅርንጫፍ አባላት በቁጥጥር ስር መዋሏ ተነግሯል። ተጠርጣሪዋ ቀረጥና ታክስ የሚከፈልበትን እቃ ያልያዙ መንገደኞች በሚያልፉበት ዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ወይም አረንጓዴ የጉምሩክ ማለፊያ መስመር በኩል ልታልፍ ስትል መያዟ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን 97 ኪሎ ግራም የሚመዝነውንና በገንዘብ ቢተመን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ሊያወጣ የሚችለውን አደንዛዥ ዕጽ ስታዘዋውር ተይዛለች ስለ ተባለችው ግለሰብ ዜግነትና ማንነት የሰጠው መረጃ የለም። ጉምሩክ ኮሚሽን እንዳለው ግለሰቧ ዕጹን በእያንዳንዱ ሻን�� 48.62 እና 48.86 ኪሎ ግራም በማድርግ እቃዎች በሚፈተሹበት መሳሪያ እንዳይለዩ ለማድረግ መጽሐፍ በማስመሰል እና በአልሙኒዬም ፎይል በመጥቅለል ለመደበቅ ሞክራለች ተብሏል። በሻንጣዎቹ ላይ በተደረገው ፍተሻ 100 ኪሎ ሊሞላ ከሦስት ኪሎ ያነሰ የጎደለው ኮኬይን የተባለው ዕጽ መያዙንና ይህም በምርመራ መረጋገጡን ኮሚሽኑ አሳውቋል። ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው አደንዛዥ ዕጽ ከጉምሩክ ቁጥጥር አልፎ ቢገባ ወደ 773 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ግምት እንደነበረው የተጠቀሰ ሲሆን፤ ከባድ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ እና የደኅንነት ችግር ሊያስከትል ይችል እንደነበር ተገልጿል። ከዚህ በፊት ከምዕራብ አፍሪካ አገራት እንዲሁም ከእስያ አገራት በሚጓዙ መንገደኞች እጅ ላይ የተለያየ መጠን ያላቸው አደንዛዥ ዕጾች በሕግ አስከባሪዎች ቁጥጥር ስር መዋላቸው የተነገረ ሲሆን፣ ይህ የአሁኑ ግን ከፍተኛ መጠን ካላቸው ውስጥ የሚጠቀስ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cn02n0563dro +sports በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሴሪ አ ውድድሮች ካለተመልካች ሊካሄዱ ነው "በኮሮናቫይረስ በአውሮፓ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በሞተባት በጣሊያን የሴሪ አ እግር ኳስ ግጥሚያዎችን ጨምሮ ሁሉም የስፖርት ውድድሮች ለአንድ ወር ያህል ለተመልካች ዝግ ሆነው እንደሚካሄዱ ተገለጸ። በተጨማሪም መንግሥት በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለውን ይህንን በሽታ ለመግታት ሲል ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለ10 ቀናት እንዲዘጉ አዟል። በአውሮፓዊቷ ጣሊያን ውስጥ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መቀስቀሱ ከታወቀ በኋላ የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ 197 መድረሱ ተነግሯል። የአገሪቱ ባለስልጣናት እንደገለጹት በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 49 ሰዎች በበሽታው ህይወታቸውን አጥተዋል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ4600 በላይ ደርሷል። በኅዳር ወር የበሽታው ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰባት ቻይና ቀጥሎ ጣሊያን ብዙ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የሞተባት አገር ሆና ተመዝግባለች። የዓለም የጤና ድርጅት እንዳለው እስካሁን ድረስ በሽታው በተገኘባቸው አገራት ውስጥ 100 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል። ከዚህ ሁሉ የባሰው ደግሞ በአራት ወር ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ሲሞቱ አብዛኛው ሞት ያጋጠመው ደግሞ ቻይና ውስጥ መሆኑ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክትር ቴድሮስ አድሃኖም የበሽታውን መስፋፋት ""በጣም አሳሳቢ"" በማለት የገለጹት ሲሆን ሁሉም አገራት ወረርሽኙን መግታት ቀዳሚና ዋነኛው ተግባራቸው እንዲሆን ጠይቀዋል። የጣሊያን ባለስልጣናት ከፍተኛውን የሟቾች ቁጥር ይፋ ያደረጉት ትናንት ነው። የጣሊያን ብሔራዊ የጤና ኢንስቲቲዩት እንዳለው የሞቱት ሰዎች አማካይ ዕድሜ 81 ሲሆን አብዛኞቹ ሌላ የጤና ችግር የነበረባቸው ነበሩ። ከሟቾቹ ውስጥም 72 ከመቶ የሚሆኑት ወንዶች ናቸው። ጣሊያን በዓለም ላይ በርካታ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ከሚኖሩባቸው አገራት መካከል አንዷ ናት።" https://www.bbc.com/amharic/news-51780953 +health አንሶላችንን መቀየር ያለብን በምን ያህል ቀናት ልዩነት መሆን አለበት? "ነገሩ በአደባባይ አይወራም የሚሉ ብዙ ናቸው። ግን የአንሶላ ቅያሪ ጉዳይ የሁላችንንም ደጅ ያንኳኳል። ብዙዎች በምን ያህል ቀናት አንሶላ ይቀየር? በሚለው ቁጥር ላይ አይስማሙም። እርስዎ ግን በምን ያክል ጊዜ አንሶላዎ ይቀይራሉ/ ያጥባሉ? አንሶላ በምን ያህል ቀናት ልዩነት መቀየር አለበት የሚለውን ከጤና ጋር የሚያስተሳስሩ አሉ። ስለጉዳዩ ጥናት የሠራችው ዩናይትድ ኪንግደምን እንደ ማሳያ እንውሰድ። አንሶላ በየስንት ቀኑ ይቀየር ለሚለው ጥያቄ የተሰጠው መልስ በጥናቱ በተሳተፉ 2 ሺህ 250 ዜጎች መካከል የአቋም ልዩነት እንዳለ ጠቁሟል። ግማሽ ያህ��� ወንደላጤዎች አንሶላቸውን ለአራት ወር እንዳላጠቡ ተናግረዋል። 12 በመቶው ደግሞ አንሶላ የሚያጥቡት ትዝ ሲላቸው ነው። ይህም ከአራት ወራት ሊበልጥ ይችላል። የሥነ ልቦና ባለሙያ፣ ኒውሮሳይንቲስትና የእንቅልፍ ተመራማሪዋ ዶ/ር ሊንዚ ብሮውኒንግ ""ይሄ ትክክል አይለም"" ትላለች። ከሴተላጤዎች 62 በመቶዎቹ በየሁለት ሳምንቱ አንሶላ እንደሚቀይሩ ይናገራሉ። የተወሰኑት ደግሞ በየሦስት ሳምንቱ። አንሶላ መቀየር ለምን ይጠቅማል? አንሶላ በየሳምንቱ ወይም በየሁለት ሳምንቱ መቀየር አለበት ትላለች ዶ/ር ሊንዚ። ይህ የሚደረገው ለንጽህና ሲባል ነው። ከሰውነታችን የሚወጣውን ላብ የሚሰበስበው አንሶላችን እንደመሆኑ በላብ ተጠቅልሎ መተኛት ያስቸግራል። ""ላብ አንሶላን ያሸታል፣ ይጨመድደዋለም"" ትላለች ዶክተሯ። ስንተኛ ምቾት እንዲሰማን በአካባቢያችን ነፋሻማ አየር ቢኖር ይመረጣል። አንሶላ አለመቀየር የሚያስከትለው በላብ ተዘፍቆ መተኛትን ብቻ አይደለም። ከሰውነታችን ላይ የሚነሱ ሙት ህዋሳት እንቅልፋችንን እንዲያስተጓጉሉትም ያደርጋል። ስንተኛ ከቆዳችን ላይ ሙት ህዋሳት ይወድቃሉ። ይህም አንሶላችን ላይ ይሰበሰባል። አንሶላ በቀናት ልዩነት የማንቀይር ከሆነ እነዚህን ሙት ህዋሳት አናስወግድም ማለት ነው። ""አንሶላችንን ቶሎ ቶሎ የማናጥብ ከሆነ ሙት ህዋሳት አንሶላው ላይ ይከማቻሉ"" ትላለች ዶክተር ሊንዚ። ችግሩ በዚህ ብቻ አያከትምም። ማይት የሚባሉ ጥቃቅን ነፍሳት ህዋሳቱን ለመመገብ አንሶላችን ላይ ይሰበሰባሉ። ይህም ለቆዳ በሽታ ያጋልጣል። በእንቅልፍ ወቅት ምቾትም ይነሳል። አንሶላ በምን ያህል ጊዜ ይቀየር? ዶክተሯ እንደምትለው፣ አንሶላ ከተቻለ መቀየር ያለበት በየሳምንቱ ነው። ግን በቀዝቃዛ ወቅት ከሳምንት ጥቂት አለፍ ሊልም ይችላል። ከሁለት ሳምንት በላይ አንሶላ ሳይቀይሩ መቆየት ግን አስጊ እንደሆነ ታስጠነቅቃለች። ስንተኛ እጃችን በመጠኑም ቆሽሾ እንደመሆኑ አንሶላ ማቆሸሻችን አይቀርም። ከትንፋሻችን የሚመወጣውም አየር ሁሌ ንጹህ አይደለም። አንዳንዶች ከመተኛት በፊት ሰውነት መታጠብ አንሶላ እንዳይቆሽሽ ይረዳል ቢሉም ሁነኛው መፍትሄ አንሶላ መቀየር እንደሆነ ባለሙያዎች ይመክራሉ። ቶሎ አንሶላ የማንቀይረው ለምንድን ነው? መልሱ እንደየሰዉ ይለያያል። መግቢያችን ላይ የጠቀስነው የዩናይትድ ኪንግደም ጥናት እንደሚለው ግን፣ 67 በመቶ የአገሪቱ ዜጎች አንሶላ ቶሎ ቶሎ የማይቀይሩት ስለሚረሱት ነው። 35 በመቶው ግድ አይሰጣቸውም። 22 በመቶው ንጹህ ተለዋጭ አንሶላ አያገኙም። 38 በመቶ ያህሉ ደግሞ አንሶላ በየጊዜው መታጠብ አለበት ብለው አያስቡም። ዶ/ር ሊንዚ፣ መኝታ ቤት እንደተቀደሰ ስፍራ ሊጠበቅ ይገባል ትላለች። ""መኝታ ቤት የምንወደው ቦታ መሆን አለበት። ወደ መኝታ ቤት ስንገባ በደስታ ልንሞላም ይገባል።"" እንቅልፍ የማጣት ችግር ያለባቸው ታካሚዎቿን ከምትመክራቸው ነገሮች መካከል አንሶላችሁን አጽዱ የሚለው አንዱ ነው። ""ንጹህ አንሶላ አንጥፈን ስንተኛ ምቾት ይሰማናል። ደስ ይለናል። እንረጋጋለን።""" https://www.bbc.com/amharic/news-61330283 +politics የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ ካሊፋ በ73 አመታቸው አረፉ በአለም ላይ ካሉት ከናጠጡ ንጉሶች አንዱ የሆኑት የየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን በ73 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ከአውሮፓውያኑ 2004 ጀምሮ የተባባሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት የሆኑት ሼክ ካሊፋ በአውሮፓውያኑ 2014 በስትሮክ ህመም በመጠቃታቸው ከመንግሥት ስራዎች ገለል ብለው ነበር። ወንድማቸው ሞሃመድ ቢን ዘይድ አል-ናህያን በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ጉዳዮች ��ላፊ ናቸው። የአል-ናህያን ቤተሰብ 150 ቢሊዮን ዶላር ሀብት እንዳላቸው ይታመናል። ሼክ ካሊፋ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት ከመሆናቸውም በተጨማሪ የሰባቱ ኤምሬት መዲናና በነዳጅ የበለፀገችው አቡ ዳቢ ገዥ ነበሩ። የሞታቸው ዜና ይፋ የሆነው በደብልዩ ኤም የዜና ወኪል ነው። የፕሬዝዳንት ጉዳዮች ሚኒስቴር ከዛሬ ዓርብ ጀምሮ ለ40 ቀናት የሐዘን ቀናትን ያወጀ ሲሆን በዚህም ወቅት ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ እንዲሁም በመንግሥትም ሆነ በግል ዘርፍ ስራ ለሶስት ቀናት ታግዷል። ሼክ ካሊፋ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሁለተኛ ፕሬዝዳንት ሆነው በአውሮፓውያኑ 2004 ከአባታቸው ስልጣን የተረከቡ ሲሆን የአቡ ዳቢ 16ኛ ገዥ ነበሩ። በስልጣን ዘመናቸው በመጀመሪያዎቹ አስርት አመታት የፌደራል መንግስቱንም ሆነ የአቡዳቢን የመንግሥት መዋቅር በመለዋወጥ ትልቅ ሰራ ሰርተዋል። ነገር ግን በስትሮክ ህመም ከታመሙ በኋላ ውሳኔዎችን ቢያስተላፉም በአደባባይ ብዙም አይታዩም ነበር። https://www.bbc.com/amharic/news-61424047 +politics ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም እስማማለሁ አለ "ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ላለፉት 16 ወራት ግጭት ውስጥ የቆየው ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም እንደሚስማማ ገለጸ። ህወሓት ይህን ያለው ትናንት ሐሙስ መጋቢት 15/2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲደርስ ለማስቻል ግጭት ለማቆም መወሰኑን ካስታወቀ በኋላ ነው። የፌደራሉ መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የተከሰተውን ሰብአዊ ቀውስ ""በእጅጉ ሊያሻሽል"" ስለሚችል እና ""በቀጣይ ያለተጨማሪ ደም መፋሰስ ለግጭቱ መፍትሔ ሊያመጣ እንደሚችል"" ተስፋ በማድረግ መሆኑን ገልጿል። መንግሥት ይህ ውሳኔ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ""በትግራይ ክልል የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም ጥቃት እንዲታቀቡና በኃይል ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ"" ጠይቋል። ይህን ተከትሎ ህወሓት ባወጣው መግለጫ ላይ በበቂ መጠን እና ተቀባይነት ባለው ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ጥሪውን እንደሚቀበል ገልጿል። በትግራይ ካለው የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ እና ተቀባይነት ባለው ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታው የሚደርስ ከሆነ ""የትግራይ መንግሥት ግጭት ለማቆም ቁርጠኛ ነው"" ብሏል። በህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በኩል የተጋራ እና ከትግራይ የውጭ ጉዳይ ጽ/ቤት የተሰጠው ነው በተባለው መግለጫ ላይ፤ ፖለቲካዊ እና የሰብዓዊ ጉዳዮች ማገናኘት ተቀባይነት አይኖራቸውም ካለ በኋላ ""የትግራይ መንግሥት እና ሕዝብ ለሰላም እድል ለመስጠት የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን"" ብሏል። የፌደራሉ መንግሥት ከዚህ ቀደም ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ጋር በክልሉ ለሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን በትናንቱ መግለጫው አስታውሷል። ነገር ግን ይህ አቅርቦት በክልሉ ያለውንችግር ለመፍታት ባለማስቻሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ሰብዓዊ እርዳታ ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየገቡ መሆናቸውን አመልክቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ለሰብአዊነት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔን ይፋ መድረጉን ተከትሎ አውነታዊ ምላሽ ከሰጡት መካከል የዩናይትድ ኪንግደም እና የአሜሪካ መንግሥታት ይገኙበታል። ዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ መንግሥት የወሰደውን ግጭት የማቆም እርምጃ አድንቃ አስፈላጊውን ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኗን ገልጻለች። አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ ���ንግሥት በአስቸኳይ ተግባራዊ የሚሆን ግጭት የማቆም እና ሰብአዊ እርዳታ ያለችግር እንዲደርስ ለማድረግ ከረድኤት ድርጅቶች ጋር ለመሥራት ያሳለፈውን ውሳኔ አድንቃለች። ይህ ውሳኔ ድጋፍ ለሚሹ ኢትዮጵያውያን በፍጥነት ለማቅረብ አስፈላጊ እርምጃ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው ለአገሪቱ ደኅንነትና ብልጽግና ሁሉን አካታች የሆነ ፖለቲካዊ ሂደት ለማስጀመር መሠረት እንደሚሆንም ጠቅሷል። ጨምሮም በሁሉም ወገኖች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እንዲቆሙና ከዚህ በፊት ለተፈጸሙ በደሎችና ጭፍጨፋዎች ተጠያቂነት እንዲኖር ጠይቋል። ይህንን ግጭት የማቆም ውሳኔን በመከተልም ተፋላሚ ወገኖቹ አስፈላጊ የደኅንነት ሁኔታዎችን ማመቻቸትን ጨምሮ በድርድር ላይ ወደተመሠረተ ዘላቂ ተኩስ አቁም እንዲደርሱ መክሯል። ይህ የመንግሥት ውሳኔ ይፋ የሆነው የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ጉብኝት አድርገው ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ከተወያዩ በኋላ ነው። አምባሳደሩ በኢትዮጵያ ከነበራቸው ቆይታ በኋላ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ዋነኛ ትኩረት በጦርነት ብዙ ምስቅልቅል ባጋጠመው ትግራይ ክልል እና በሌሎችም አካባቢዎች የሰብአዊ እርዳታ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ እንደሆነ ገልጸው ነበር። ይህንን በተመለከተም ሳተርፊልድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር የተወያዩ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ያልተቋረጠ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲደርስ ቁርጠኛ ቢሆንም፣ በህወሓት ታጣቂዎች ምክንያት የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱ እክል እየገጠመው መሆኑን ለልዩ መልዕክተኛው መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ካለፈው ታኅሣሥ ወር ወዲህ ወደ ትግራይ ክልል የእርዳታ አቅርቦት በየብስ አለመድረሱ የተነገረ ሲሆን፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ወደ ትግራይ ክልል የእርዳታ ምግብ ለማግኘት ከፌደራል መንግሥቱና ከክልል ባለሥልጣንት ፈቃድ ማግኘቱን ከቀናት በፊት አስታውቋል። በ2013 ዓ. ም. ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተቀስቅሶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች በተስፋፋው ጦርነት ምክንያት ከፍ ያለ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት መድረሱ የተነገረ ሲሆን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለችግር ተዳርገዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልገው ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ገልጿል። ጦርነቱ እስካሁን መቋጫ ስላላገኘ የተፈናቀሉትን ወደ ቀያቸው ለመመለስና እርዳታ ለማቅረብ አስቻጋሪ በመሆኑ በአስቸኳይ እርዳታ ማቅረብ ካልተቻለ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ የእርዳታ ድርጅቶች ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል። ህወሓት የኢትዮጵያ መንግሥት እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይገባ እገዳ ጥሏል በማለት ሲከስ መንግሥት ደግሞ በእርዳታ አቅርቦት መስመሮች ላይ ጥቃት በመክፈት የእርዳታ አቅርቦትን ያስተጓጎለው አማጺው ኃይል ነው ሲል ይወቅሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60870948 +business የትዊተር የድርሻ ባለቤቶች ኤለን መስክ ትዊተርን በ44 ቢሊዮን ዶላር እንዲገዛ ፈቀዱ የትዊተር የድርሻ ባለቤቶች ኤለን መስክ ትዊተርን በ44 ቢሊዮን ዶላር እንዲገዛ መፍቀዳቸው ተገለጸ። ሳን ፍራንሲስኮ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት የትዊተር ኢንቨስተሮች ባካሄዱት የስልክ ውይይት ነው ውሳኔው የተላለፈው። በዚህ ውሳኔ መሠረት ኤለን መስክ ትዊተርን እንዲገዛው የድር�� ባለቤቶቹ በፍርድ ቤት ለማስገደድ ይሞክራሉ ማለት ነው። የቀድሞው የትዊተር የደኅንነት ኃላፊ በአሜሪካ ምክር ቤት አስደንጋጭ ምስክርነት ከሰጠ በኋላ ነው የትዊተር ውሳኔ የተሰማው። ሚያዝያ ላይ ትዊተር ድርጅቱን ለዓለማችን ቁጥር አንድ ሀብታም ኤለን መስክ ለመሸጥ ተስማምቶ እንደነበር ይታወሳል። ትዊተር እንደሚለው፣ በየቀኑ ገጹን ከሚጠቀሙና ማስታወቂያዎችንም ከሚመለከቱ ተጠቃሚዎች መካከል  አምስት በመቶው በሰው ሳይሆን በማሽን እየተመሩ አንዳች አጀንዳን ለማራመድ የሚውሉ ገጾች ናቸው። ኤለን መስክ በበኩሉ ቁጥሩ ከዚህ ከፍ ያለ እንደሆነ ይከራከራል። መጀመሪያ ላይ ትዊተርን ለመግዛት ኤለን መስክ ያቀረበው 44 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ አሁን ላይ የትዊተር የገበያ ዋጋ 32 ቢሊዮን ዶላር ነው። የትዊተር የድርሻ ባለቤቶች ያሳለፉት ውሳኔ ድርጅቱ ኤለን መስክን ወደ ፍርድ ቤት እንዲወስድ የሚያስችል ይሆናል። የፊታችን ጥቅምት በዳላዌር በሚገኝ ፍርድ ቤት ክርክሩ የሚጀምር ሲሆን፣ ኤለን መስክ ትዊተርን መግዛት አለበት ወይስ የለበትም የሚለውን ዳኛ ይወስናል። የቀድሞው የትዊተር ሠራተኛና የአሁኑ መረጃ አጋላጭ ፒይተር ዛትኮ፣ በምክር ቤት ተገኝቶ ትዊተር የደኅንነት ክፍተቶች እንዳሉበት ምስክርነት ሰጥቷል። ትዊተር ገጹ ምን ያህል ደኅንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ “ሕዝቡን እያደናገረ ነው” ብሏል። ደኅንነትን ለመጠበቅ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በመተግበር ረገድ ትዊተር “ኋላ ቀር ነው” ሲልም ምስክርነቱን ሰጥቷል። ትዊተር በበኩሉ የቀድሞው የደኅንነት ሠራተኛው ከሥራው እንደተሰናበተ ገልጾ፣ ስለ ተቋሙ የሰጠው ምስክርነትም የተዛባ እንደሆነ ገልጿል። የቀድሞው የትዊተር ሠራተኛ፣ ትዊተር ላይ ያሉት ሐሰተኛ ገጾች (spam) ወይም በሰው ሳይሆን በማሽን እየተመሩ አንዳች አጀንዳን ለማራመድ የሚውሉ ገጾች (bot accounts) ኤለን መስክ እንዳለው ከፍተኛ ቁጥር እንዳላቸው ከዚህ ቀደም ተናግሯል። የትዊተር የቀድሞ ሠራተኛ በምክር ቤት ተገኝቶ የሰጠውም ምስክርነት የኤለን መስክ ጠበቆች በፍርድ ቤት ሲከራከሩ እንደ ማስረጃነት መጠቀም እንደሚችሉ አንድ ዳኛ ወስነዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cp6lw1xn208o +politics ሪሺ ሱናክ ቀጣዩ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ ነው "በተሾሙ በሰባት ሳምንት ስልጣን በቃኝ ያሉትን የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመተካት በተደረገው ውድድር ሪሺ ሱናክ አሸናፊ ሆኑ። ሪሺ ሱናክ የዩናይትድ ኪንግደም የመጀመሪያው እስያዊ ዝርያ ያላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ። ሪሺ ሱናክ ዩናይትድ ኪንግደም በከፍተኛ የምጣኔ ኃብት ተግዳሮት ባለችበትም ወቅት ነው የመሪነት ቦታውን የሚረከቡት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት ከሰባት ሳምንታት በተደረገው ፉክክር ተወዳድረው የነበሩት ሪሺ ሱናክ በሊዝ ትረስ መሸነፋቸው ይታወሳል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት ከሰባት ሳምንታት በተደረገው ፉክክር ተወዳድረው የነበሩት ሪሺ ሱናክ በሊዝ ትረስ መሸነፋቸው ይታወሳል። ሊዝ ትረስ ግብር እቀንሳለሁ፤ ንግድን አሳልጣለሁ ያሉት አዲስ ፖሊሲ ፍጹም ያልተጠበቀ የገበያ ምስቅልቅልና ብሔራዊ ጦስ ይዞባቸው መጥቶ ነው ሥልጣን እንዲለቁ የሆኑት። ሊዝ ትረስ ሥልጣን እንዲለቁ ጫናው ከበረታባቸው በኋላ እጅ አልሰጥም ብለው ለጥቂት ቀናት ቢፋለሙም አልሆነላቸውም። ትረስ በይፋ በቃኝ ያሉት ባለፈው ሐሙስ ‘ነምበር ቴን’ በሚል ከሚታወቀው የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር መኖርያና ቢሮ ደጅ ላይ ሆነው ነበር። ለ45 ቀናት ስልጣን ላይ የቆዩት ሊዝ ትረስ በዩኬ ታሪክ ለአጭር ጊዜ የቆዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመዝግበዋል። ሱናክ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲወዳደሩ ከሊዝ ትረስ ጋር ባደረጓቸው እልህ አስጨራሽ ክርክሮች የሊዝ ትረስ የታክስ ቅነሳ ከባድ ቀውስ ይዞ እንደሚመጣ ተምብየው ነበር። ያን ጊዜ ሰሚ ቢያጡም ትንቢታቸው በ45 ቀናት እውን ሆኖ ታይቷል። ይህንንም ተከትሎ የዩናይትድ ኪንገግደም ቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን ሪሺ ሱናክን ጨምሮ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ድጋፍ ለማግኘት እየተወዳደሩ ነበር። በፓርቲው አሠራር መሠረት ወደ ሥልጣን የሚመጣው ሰው ቢያንስ መቶ የሕዝብ እንደራሴዎችን ድጋፍ ማግኘት አለበት። ሪሺ ሱናክ የቀድሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አጋሮችን ጨምሮ ከፓርቲያቸው 128 የፓርላማ አባላትን ድጋፍ በመሰብሰብ ውድድሩን እየመሩም ተብሎ ነበር። የወግ አጥባቂው ወይም በሌላ ስሙ የቶሪ ፓርቲ የምክር ቤት አባላት ቁጥር ደግሞ 357 ነው። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በ53 የድምጽ ድጋፍ ሁለተኛ ሆነው እየተከተሉ ስለመሆናቸው ቢቢሲ መረጃ አግኝቷል። ሆኖም ቦሪስ ጆንሰን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት በድጋሚ እንደማይወዳደሩ ማስታወቃቸውን ተከትሎም ሪሺ ሱናክ ሙገሳቸውን አቅርበውላቸዋል “ቦሪስ ጆንሰን ብሬግዚት እና የክትባት ስርጭት ላይ ስኬታማ ነበሩ” ሲሉ ሪሺ ሱናክ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። “ፈታኝ ከሆኑ ጊዜያቶች በአንዱ አገራችንን መርተዋል። ፑቲን በዩክሬን የጀመሩት አረመኔያዊ  ጦርነት ወቅትም ነበሩ። ለዚህም ሁሌም እናመሰግናቸዋለን።"" በማለት ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cxev75kx5d2o +business ዘይት፣ ስኳር፣ ሩዝ እና ወተት ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ከውጭ እንዲገቡ ተወሰነ የገንዘብ ሚኒስቴር ዘይት፣ ስኳር፣ ስንዴ፣ የህጻናት ወተት እና ሩዝ ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፍቃድ ( ፍራንኮ ቫሉታ) በጉምሩክ በኩል በቀጥታ እንዲገቡ መወሰኑን አስታወቀ። ውሳኔው የተላለፈው በአገሪቷ ውስጥ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት የውጭ አገር የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን የፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ በአፋጣኝ እንዲፈቀድላቸው ጥያቄ እያቀረቡ በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል። በመሆኑም መሠረታዊ የሆኑ የምግብ ሸቀጦች የሆኑት ዘይት፣ ስንዴ፣ ስኳር፣ የህጻናት ወተት እና ሩዝ ያለ ውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ለስድስት ወራት በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል በቀጥታ እየተፈቀደ እንዲገባ መወሰኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል። የምንዛሬ ምንጩም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይረጋገጣል ተብሏል። ሚኒስቴሩ የምግብ ዋጋን ለማረጋጋት ምርትን ያለውጭ ምንዛሬ ፈቃድ እንዲገባ ሲፈቅድ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ባለፈው ዓመትም ተመሳሳይ እርምጃዎችን መውሰዱ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ይህ ብቻውን የዋጋ ንረቱን ማረጋጋት እንዳልቻለ የዘርፉ ባለሙያዎች አስተያየት ሲሰጡ ቆይተዋል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚከሰቱ ግጭቶች እና የምጣኔ ሃብት አለመረጋጋቶች ለምግብ ዋጋ ንረት እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ። ይህንን ችግር ለማቃለል የአገር ውስጥ ምርትን መጨመር ወሳኝ መፍትሔ እንደሆነ ባለሙያዎች ይጠቁማሉ። ፍራንኮ ቫሉታ ምንድን ነው? ፍራንኮ ቫሉታ ሕጋዊ ከሆነ ምንጭ የሚገኝ የውጭ ምንዛሬ ሲሆን የባንክ ቤት ፈቃድ ሳያስፈልገው ከውጪ አገር ዕቃ ለማስገባት የሚያስችል ፈቃድ ነው። የፍራንኮ ቫሉታ መብት ያላቸው አስመጪዎች ወደ አገር ውስጥ ለሚያስገቧቸው ምርቶች የውጪ ምንዛሬን በተመለከተ በብሔራዊ ባንክ የወጡ እና በንግድ ባንኮች የሚተገበሩ ጥብቅ መመሪያዎችን የማለፍ ግዴታ የለባቸውም። ይህም ማለት የውጪ ምንዛሬ ለማግኘት የባንክ ቤቶች ፍቃድ ሳያስፈልገው በፍራንኮ ቫሉታ የሚገቡ ምርቶችን ወደ አገር ውስ�� የማስገባት መብት ያገኛል ማለት ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-61020766 +business አዲስ አበባ ለውጭ አገር ሰራተኞች ለኑሮ ርካሽ ከሆኑት መካከል ናት ተባለ አዲስ አበባ መቀመጫቸውን በከተማዋ ላደረጉ የውጭ አገር ሰራተኞች ለኑሮ ርካሽ ከሆኑት መካከል አንዷ መሆኗን አንድ ጥናት ይፋ አድርጓል። የ209 ከተሞችን የቤት ኪራይ፣ ትራንስፖርትና ምግብ ዋጋ የገመገመው ይህ ጥናት አዲስ አበባን በ194ኛ ደረጃ አስቀምጧታል። ጥናቱን ያከናወነው መርሰር የተባለ ድርጅት ሲሆን በባለፈው አመት በነበረው የኑሮ ውድነት ግምገማ አዲስ አበባ በ182ኛ ደረጃ አስቀምጧት ነበር። በዚህ ጥናት መሰረት በአለም ውዷ ከተማ የቱርክሜኒስታን መዲና አሽጋባት ናት። በማዕከላዊ እስያ የምትገኘው የዚህች አገር መዲና ለውጭ አገር ሰራተኞች በውድነት በቁንጮ ስፍራ ተቀምጣለች። በባለፈው አመት በውድነት ተቀምጣ የነበረችው ሆንክ ኮንግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን የሊባኖሷ መዲና ቤይሩትና የጃፓን መዲና ቶክዮ ይከተላሉ። መርሰር የተባለው ድርጅት እንዳስቀመጠው ይህንን ሪፖርት ለማጠናቀር 200 የሚገመቱ እቃዎችን ዋጋ እንዲሁም አገልግሎቶችን ገምግሜያለሁ ብሏል። ይህም ጥናት ኩባንያዎችና መንግሥታት የውጭ አገር ሰራተኞቻቸውን ምን ያህል መክፈል እንዳለባቸው ጠቋሚ እንደሆነም ተገልጿል። በመርሰር ከአንድ እስከ አስር ውድ ተብለው የተቀመጡት ከተሞች የቢዝነስ ማዕከላት የተባሉ ሲሆን ካላቸውም የምጣኔ ኃብት እድገት ጋር ተያይዞ በዕቃዎችና በአገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬ ያሳዩ ናቸው። በተለይም ይህ የዋጋ ግሸበት የታየው በቤት ኪራይና ሌሎች መሰረታዊ በሚባሉ ሸቀጦች ነው። ነገር ግን የአሽጋባት የኑሮ ውድነት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር የተያያዘ ሲሆን ካለው ከፍተኛ ግሽበት ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል። በነዳጅ ሃብቷ የምትታወቀው ቱርክሜኒስታን በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ እየተናጠችም ሲሆን በርካቶችም ለከፋ ድህነትም ተዳርገዋል። በቀድሞው የሶቭየት ህብረት አባል የነበረችው ቱርክሜኒስታን በዋናነት ለሩሲያ ነዳጅን በመላክ ነው ምጣኔ ኃብቷ የተመሰረተው። የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታም በማሽቆልቆሉ ነው ምጣኔ ኃብቷ የተጎዳው። https://www.bbc.com/amharic/news-57583029 +business "የኃያላን አገራት ""አዲሱ የአፍሪካ ቅርምት""" "የዓለም ኃያላን አገራት አፍሪካ ላይ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የበላይነት ለማግኘት ድምፃቸውን አጥፍተው እየተፋለሙ ያሉበት ጊዜ ነው። የአፍሪካ አገራት መሪዎች ያለ እረፍት የአፍሪካ ነክ ጉባኤዎችን ለመታደም ወደ ተለያዩ የዓለም አገራት በመጓዝ ላይም ናቸው። እነዚህ የቻይና አፍሪካ ፣ የዩናትድ ኪንግደም አፍሪካ፣ ጃፓን አፍሪካ ጉባኤ . . . እየተባሉ የሚዘጋጁ መድረኮች በማስታወቂያ ሁለቱንም ወገን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አጋርነቶች ተደርገው ይገለፃሉ። እውነቱ ግን ይህ ነው? የዓለም ኃያላን ዳግም አይናቸውን አፍሪካ ላይ የጣሉት ለምንድን ነው? እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት የአፍሪካ መሪዎች የተገኙባቸው የቻይና፣ የጃፓን እና የሩሲያ የአፍሪካ ጉባኤዎች ተካሂደዋል። በባለፈው ወር የእንግሊዝ አፍሪካ የኢንቨስትመንት ጉባኤም 15 የሚሆኑ የአፍሪካ መሪዎች ተካፍለዋል። በፈረንሳይ፣ በሳውዲ አረብያና በቱርክ በዚህ ዓመት ሊካሄዱ ለታሰቡ ተመሳሳይ የአፍሪካ ጉባኤዎችም ጥሪ ተላልፏል ተብሎ ይገመታል። የአህጉሪቱ ከፍተኛ የማዕድን ክምችት፣ ድንግል የግብርና መሬት እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ አገራት 54 ድምፅ፣ በአህጉሪቱ እየጨመረ ያለው የእስልምና አክራሪነት፣ ስደት አፍሪካን ዳግም የኃያላኑ አይን ውስጥ ያስገቡ ተጠቃሽ ጉዳዮች ናቸው። በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ መፅሃፍትን ለንባብ ያበቃችው እውቋ ዛምቢያዊት ኢኮኖሚስት ዳምቢሳ ሞዮ ""ዓለም በቅርቡ የዓለም ችግር መሆናቸው የማይቀር የአፍሪካ ችግሮችን ለመፍታት የአፍሪካ አገራት እርዳታ ያሻቸዋል"" ትላለች። ሞዮ እንደምትለው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አፍሪካን ለመደገፍ እርምጃ ቢወስድ እርምጃው ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብም ትርፋማ ነው። የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በቅርቡ አሜሪካ ላይ አፍሪካ ለቀሪው ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የደህንነት ስጋት የምትጋርጥ እንዲሁም በስደተኞች ምዕራባውያንን ችግር ውስጥ የምትከት ብቻ ሳትሆን ለቀሪው ዓለም ሰፊ የኢንቨስትመንት እድልን የምትሰጥም እንደሆነች ተናግረው ነበር። ኡሁሩ በንግግራቸው ቻይና፣ አሜሪካ፣ ሩሲያና ሌሎች አገሮች አፍሪካን ለመቆጣጠር የሚያደርጉትን ከፍተኛ ፉክክር እንዲያቆሙም አስጠንቅቀዋል። እአአ በ2013 የአፍሪካ መሪዎች አህጉሪቱ በ2063 ያጋጥማታል ያሉትን ፈተና ለመወጣት ያስችል ዘንድ በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት አጀንዳ 2063 የተሰኘውን እቅድ ነድፈዋል። እቅዱ ከሁሉም በላይ በአህጉሪቱ ላይ የሚቃጡ ጦርነቶች ማስቆም፣ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ የሚያተኩር ሲሆን በአህጉሪቱ ዜጎች ከአገር አገር ነፃ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ራዕይ የሰነቀ ነው። ሌላው ወሳኝ ፕሮጀክት የአፍሪካ ነፃ ገበያ ምህዳርን መክፈት ሲሆን ይህ የነፃ ገበያ ማዕቀፍ በርካታ አገራትን አሳታፊ በማድረግ የዓለም ትልቁ የነፃ ገበያ ማዕቀፍ ስምምነት ነው። ይህ የነፃ ገበያ ስምምነት በአፍሪካ አገራት መካከል የሚደረግ ንግድን ለማስፋፋት የታለመ ነው። ከጥቂት ወራት በኋላ ተግባራዊ እንደሚሆን የሚጠበቀው ይህ የአፍሪካ ነፃ ገበያ ስምምነት አገራት የውስጥ ገበያቸውን ለመጠበቅ ባወጧቸው ቀደምት ህጎችና እንዲሁም የደካማ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ምክንያት ከፍተኛ ችግር እንደሚገጥመው አስተያየት እየተሰጠ ነው። ሁሉንም የአፍሪካ አገራት መዲናዎች እና የንግድ ማዕከሎች በፈጣን ባቡር መስመር ማገናኘት፣ በአፍሪካ አገራት መካከል የሚደረግ ንግድን ማበረታታት እንዲሁም የአፍሪካ አገራት በዓለም አቀፍ የንግድ ገበያ ተሳትፎን ማጎልበት አጀንዳ 2063 ካስቀመጣቸው ግቦች መካከል ናቸው። የአፍሪካውያን በአህጉሪቱ ነፃ የመዘዋወር፣ የመስራት እና የመኖር መብት እንዲኖራቸው ማድረግ እንዲሁም በአህጉሪቱ ያሉ ግጭቶችን ማስቆም እና ሌሎችም በርካታ ግቦች በእቅዱ ላይ ተቀምጠዋል። ነገር ግን የአፍሪካ ሕብረት እነዚህን አጀንዳዎች ለማስፈፀም በእጅጉ እየተፈተነ ሲሆን ችግሩ ሕብረቱ አባል አገራት በገቡት ስምምነት መሰረት ነገሮችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማስገደድ አለመቻሉ ነው። ተንታኞች እንደሚሉት የአፍሪካ አገራት ያለባቸውን ከፍተኛ የእዳ ጫና ለመክፈል የሚያደርጉት ትግል ትልቁን አህጉራዊ አጀንዳ ችላ እንዲሉ ግድ ብሏቸዋል። ቢሆንም ግን የአፍሪካ አገራት በየጊዜው እየናረ ከመጣው የኃያላኑ ፍላጎት አትራፊ ለመሆን ጠንካራ ድርድር ማድረግ የሚያስችላቸውን የፖሊሲ አቅጣጫ በማስቀመጥ የዚህ/የዚያ የሚባሉ የአፍሪካ ጉባኤዎች ላይ የሚቀርቡ የአጭር ጊዜ ስምምነቶችን ከመቀበል ይልቅ ትልቁን አህጉራዊ አጀንዳ ታሳቢ ያደረጉ ስምምነቶችን ማድረግ እንደሆነ ተንታኞቹ ምክረ ሃሳባቸውን ያስቀምጣሉ።" https://www.bbc.com/amharic/51687298 +sports ለዓለም ዋንጫ ወደ ኳታር በእግሩ እየተጓዘ የነበረው ስፔናዊ ኢራን ውስጥ ታሰረ "በኳታር በሚካሄደው የ2022 የዓለም ዋንጫ ለመታደም ከስፔን ማድሪድ ተነስቶ ወደ ኳታር በእግር እየተጓዘ የነበረው ስፔናዊ ኢራን ውስጥ መታሰሩ ተሰማ። የ41 ዓመቱ የእግር ተጓዥ እና የእግር ኳስ ደጋፊ ሳንዲያጎ ሳንቼዝ ጉዞውን የጀመረው ጥር ወር ላይ ሲሆን ለእስር የተዳረገው ኳታር ከመድረሱ የመጨረሻዋ አገር በሆነችው ኢራን ነው። ሳንቼዝ ጉዞውን በተመለከተም በኢንስታግራም ገጹ ላይ በተከታታይ ፎቶዎችን ሲያጋራ ቆይቷል። ለመጨረሻ ጊዜም የኢራን መዳረሻ ወደ ሆነው ሰሜናዊ ኢራቅ የመጨረሻ መንደር መድረሱን ገልጾ ከፎቶ ጋር በኢንስታግራም ገጹ ላይ አጋርቷል። ከዚያ በኋላ ግን ምንም ዓይነት ፎቶግራፎችን በገጹ ላይ ያለጠፈ ሲሆን ከእርሱ ጋር የነበረው ግንኙነት ከ26 ቀናት በፊት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ በሳንቼዝ መጥፋት ለሳምንታት ሲጨነቁ ከቆዩ በኋላ ግለሰቡ በኢራን መዲና ቴህራን እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኝ ተሰምቷል። ከጓደኞቹ መካከል አንዱ የሆነው ፍራንቾ ሳላማንካ፣ ሳንቲያጎ መታሰሩን እና አሁን ላይ በቴህራን እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኝ ለቢቢሲ ተናግሯል። ስለ ጉዳዩ በቢቢሲ የተጠየቀው የስፔን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በቴህራን የሚገኘው ኤምባሲያቸው ከኢራን ባለሥልጣናት ጋር መነጋገሩን ገልጾ፣ተጨማሪ አስተያየት ከመስጠት ግን ተቆጥቧል። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተያየት እንዲሰጥ ቢጠየቅም ምላሽ አልሰጠም። ሳንቼዝ ወደ ኢራን ከገባ በኋላ ምን እንደገጠመው እስካሁን በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። በኢራቅ እና በኩርዲስታን ድንበር ላይ ተቀማጭነቱን ያደረገው ሄንጋው የሰብዓዊ መብት ድርጅት ስማቸውን ያልገለጸቸው ምንጮቹን ጠቅሶ፣ ሳንቼዝ፣ “ሂጃብሽን በአግባቡ አለበሽም” በሚል ታስራ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሳለች የሞተችውን የማሻ አሚኒን የመቃብር ሥፍራ ከጎበኘ በኋላ በኢራን የጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን ገልጿል። የ22 ዓመቷ አሚኒ ባለፈው ወር መጀመሪያ ላይ መሞቷን ተከትሎ በመላ አገሪቷ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሷል። ተቀማጭነቱን በኖርዌይ ያደረገው የኢራን ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን፣ ተቃውሞውን ተከትሎ 29 ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 234 ተቃዋሚዎች በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ገልጿል። የኢራን መሪዎች በበኩላቸው የተፈጠረው አለመረጋጋት ""በጠላት የውጭ ኃይሎች"" የተቀሰቀሰ ነው ብለውታል። ሳላማንካ፣ ሳንቼዝ ከመታሰሩ በፊት በስልክ አውርተዋል። በኢራን በሚያደርገው ጉዞም ከእርሱ ጋር ለመቀላቀል አብሮት ለመሄድ እቅድ ነበረው።ነገር ግን በሥራ ምክንያት ሳይሳካለት ቀርቶ ሳላማንካ እዚያው ስፔን ቀረ። ሳላማንካ እንደሚለው ጓደኛው ሳንቼዝ በአውሮፓውያኑ 2019 ወደ ሳዑዲ አረቢያ ባደረገው ጉዞ በጎበኛት ኢራን በኩል የመሄድ እድል በማግኘቱ ደስተኛ ነበር። “የኢራን ሕዝቦች በሚገባ ተንከባክበውታል። በጣም ጥሩ ሕዝቦች ናቸው። ብዙም ረድተውታል” ብሏል ሳላማንካ። የቀድሞው የአየር ኃይል አባል የነበረውና የሪል ማድሪድ ደጋፊ የሆነው ሳንቼዝ ፣ ወደ ወደ ቴህራን ለመሄድ አቅዶ ነበር። እዚያም አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቃለ መጠይቅ ሊያደርግለት ፈልጎ ነበር። ከዚያም በጀልባ ወደ ኳታር ወደሚያመራበትና በደቡብ ኢራን በሚገኘው ባንዳር አባስ ወደብ ለማምራት እቅድ ነበረው። ሳንቼዝ በኢራን ኢንተርኔት የማግኘት እድሉ አነስተኛ እንደሆነ ለቤተሰቦቹ እና ለጓደኞቹ ተናግሮ ስለነበር መጀመሪያ ላይ ድምጹ ሲጠፋባቸው በኢንተርኔት ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል በሚል ብዙም አልተጨነቁም ነበር። ሆኖም ለአስር ተከታታይ ቀናት ቤተሰቦቹ ጋር ባለመገናኘቱ ስጋታቸው እያየለ መጥቶ ቤተሰቦቹ ልጃቸው መጥፋቱን አሳውቀዋል። “በጣም ተጨንቀናል። እኔ እና ባለቤቴ ለቅሷችንን ማቆም አልቻልንም"" ሲሉ እናቱ ሴሊያ ኮገዶር ለአሶሼትድ ፕረስ የዜና ወኪል በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ተናግረዋል። ሳንቼዝ እስር ቤት እንደሆነ በስፔን መንግሥት የተነገራቸው ሲሆን የእስሩ ምክንያት ምን እንደሆነ ግን በይፋ አልተገለጸም። ሳንቼዝ ኢራቅ ከመግባቱ በፊት በአውሮፓ እና በቱርክ እያቆራረጠ በድንኳን፣ በሆቴል እና በሰዎች ቤት ውስጥ እያደረ ነበር ጉዞውን ያደረገው።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cllqg33mev9o +sports ሰይፉ ቱራ የቺካጎ ማራቶንን አሸነፈ ኢትዮጵያዊው አትሌት ሰይፉ ቱራ የቺካጎ ማራቶንን አሸናፊ ሆነ። ሰይፉ ከፍተኛ ግምት ከሚሰጣቸው የማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነውን የቺካጎ ማራቶን ውድድር ለማጠናቀቅ፣ 2 ሰዓት 06 ደቂቃ 12 ሰከንድ ፈጅቶበታል። አትሌቱ ሦስተኛው የማራቶን ድሉ ሲሆን በአቦት የዓለም የማራቶን ውድድር የመጀመሪያውን ድል መጎናጸፉን መረጃዎች ያመለክታሉ። ከፍተኛ ግምት አግኝቶ የነበረው አሜሪካዊው ጋለን ሩፕ ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል። ከ30ኛው ኪ.ሜ ጀምሮ ከመሪዎቹ ሯጮች ጋር የነበረው ሰይፉ አምስት ኪሎ ሜትሮች ሲቀሩ ብቻውን ተነጥሎ በመምራት ውድድሩን ማሸነፍ ችሏል። ሰይፉን እና ሩፕን ተከትሎ ኬንያዊው ኤሪክ ኪፕታኑ በሦስተኝነት ውድድሩን አጠናቋል። እስከ 25ኛው ኪሎ ሜትር ድረስ ውድድሩን ሲመሩ ከነበሩት መካከል የነበረው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሺፈራ ታምሩ አምስተኛ ሆኖ ጨርሷል። ውድድሩን በቀዳሚነት የጨረሱት አስር አትሌቶች አምስቱ ከአሜሪካ፣ ሁለቱ ከኢትዮጵያ፣ ሁለቱ ከኬንያ ሲሆኑ ቀሪው አትሌት ከጃፓን ነው። በሴቶች የማራቶን ውድድር ኬንያዊቷ ሩት ቼፕጌቲች አሸናፊ ሆናለች። ሩት ውድድሩን 2 ሰዓት 22 ደቂቃ 31 ሰከንድ በሆነ ሰዓት ነው የጨረሰችው። አሜሪካዊያኑ ማ ቤትስ እና ሳራ ሃል ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀዋል። ከቀዳሚዎቹ አስር የአሸናፊነት ቦታ ከያዙ አትሌቶች ውስጥ ሰባት አሜሪካዊያን ይገኙበታል። አሸናፊዋን ሩትን ጨምሮ ሁለቱ ኬንያዊያን ሲሆኑ ኢትዮጵያዊቷ መሠረት በለጠ ዘጠነኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቃለች። https://www.bbc.com/amharic/58867134 +sports "ቶክዮ ፓራሊምፒክ፡ ""ለኢትዮጵያ አገሬ ክብር መስራቴ ደስ ብሎኛል"" አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ" ትዕግስት ገዛኸኝ መንግሥቱ በጃፓን፣ ቶኪዮ እየተካሄደ ባለው የፓራሊምፒክ ውድድር ላይ በአንድ ሺህ አምስት መቶ ሜትር የሩጫ ውድድር ላይ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት ታሪክ አስመዝግባለች። ይህ የወርቅ ሜዳሊያ በኢትዮጵያ የፓራሊምፒክ ተሳትፎ ታሪክ ውስጥ አገሪቱ ያገኘችው የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳልያ ነው። ትዕግስት የቶክዮው ፓራሊምፒክ ሁለተኛ ውድድሯ ነው። ከዚህ ቀደም በቱኒዝያ ሚኒማ ማሟያ ውድድር አድርጋ አሸንፋለች። ቢቢሲ የወርቅ ሜዳሊያ ካስገኘችው አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል። ቢቢሲ፡ እንኳን ደስ ያለሽ! ቶክዮ ላይ ታሪክ ነው የሰራሽው። ምን ተሰማሽ? በጣም ደስ ብሎኛል! ይህ ነው ብዬ መናገር አልችልም። ምክንያቱም ከሚኒማ ውድድሩ ውጪ በፓራሊምፒክ ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ ስሳተፍ የመጀመሪያዬ ነው። ለኢትዮጵያ ማለት. . . ለአገሬ ክብር በመስራቴ በጣም ደስ ብሎኛል። ቢቢሲ ፡ ከኢትዮጵያ ወደ ቶክዮ ስትሄጂ ወርቅ አመጣለሁ ብለሽ አስበሽ ነበር? ወርቅ አመጣለሁ ብዬ ነው በራሴ ያሰብኩት። ምክንያቱም ማን እንዳለ፣ ምን እንደሆነ፣ እንዴት እንደሆነ ብዙም አላውቅም። ብዙ ተወዳዳሪ ይኑር፣ ጥሩ ተፎካካሪ ይኑር አላውቅም ነበር። እናም እፎካከራለሁ ብዬ ነው የሄድኩት። ነገር ግን በትክክል በራሴ ውስጤ አስብ የነበረው ወርቅ ለማምጣት ነው። ውድድሩ ሳይታወቅ ይህን አመጣለሁ ብዬ ለሌሎች አልተናገርኩም። በራሴ ግን ወርቅ አመጣለሁ ብዬ አስቤያለሁ። ወርቅ እንኳን ባላመጣ አሪፍ ውድድር እወዳደራለሁ፤ አሪፍ ውጤት አመጣለሁ ��ለትም ቢያንስ ሁለተኛ እንኳን እሆናለሁ ብዬ አስቤያለሁ። ቢቢሲ፡ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ፓራሊምፒክ ላይ ወርቅ አምጥታ አታውቅም። ይህን ታውቂ ነበር? አውቃለሁ። አሰልጣኞችም ሲነግሩን ነበር፤ ዘንድሮ የመጀመሪያው ወርቅ የሚመጣበት ነው ሲሉም ነበር እና ከዚህ በፊት ወርቅ መጥቶ እንደማያውቅ ነግረውኛል፤ ሰምቻለሁ። ቢቢሲ ፡ ማጣሪያውንም ፍጻሜውንም ስታሸንፊ በብዙ ርቀት ነው ያሸነፍሽው። ሌላ ውድድር ላይ ብሳተፍ ማሸነፍ እችል ነበር ብለሽ ታስቢያለሽ? በነበረኝ አቋም ሌላ ውድድር ላይ ብሳተፍ አሸንፋለሁ ብዬ አስባለሁ። ለዚህ ውድድር ብዬ ስለተዘጋጀሁ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነበርኩ። በዚህ ውድድር ሪከርድ ለማሻሻል ባልችልም ወርቅ አመጣለሁ ብየ አስቤያለሁ። ለሪከርዱም ትንሽ ነበር የቀረኝ። ሪከርዱ ስንት እንደሆነ መጀመሪያ አላወቅኩም ነበር። ስሮጥ እየነገሩኝ ነበር፤ ግን አልሰማኋቸውም። ከ መግባቴ በፊት አስቤበት ስላልገባሁም ይሁን ስላላየሁትም ለሪከርድ አልነበረም የሮጥኩት። ወርቅ እንደማመጣ ግን ወደ ፍጻሜ ውድድሩ ስገባ እርግጠኛ ሆኜ ነበር የገባሁት። ሌላ ውድድር ቢኖርም አሪፍ እሮጣለሁ ብዬ አስባለሁ። ቢቢሲ፡ እንዳትሮጭ ያደረገሽ ሚኒማ ስላላሟላሽ ነው? ሰው አልነበረም። ሌላ ርቀት ላይ ያለው ተወዳዳሪ በእኔ በቲ- 13 ዘርፍ ውስጥ አልነበረም። ሚኒማ ላይም አልተሮጠም ይመስለኛል። ሌላ ቦታም ሰው አልነበረም። በዚያ ምክንያት ሌላ ውድድር አልነበረም። አሁን 5 ሺህ መሮጥ እፈልጋለሁ። ሚኒማ ሲሟላ 5 ሺህ ተሮጦ ቢሆን ኖሮ እዚህም ውድድሩ ይኖር ነበር ሲሉ ነው የሰማሁት፤ እዚያ ላይ ያ አልበረም እና አልተወዳደርንም። በእኔ ፊልድ የለም መሰል . . . የሞከረም ሰው የለም። ግን እርግጠኛ አይደለሁም። ቢቢሲ ፡ በ1500 ሜትር ቲ-13 ነው የተወዳደርሽው። ቲ-13 ማለት ምን ማለት ነው? ቲ-13 ማለት ሙሉ ለሙሉ ዓይነ ሥውር ያልሆነ፤ ግን ትንሽ የዕይታ ችግር ያለበት ማለት ነው። ቢቢሲ፡ እንዴት ነው አትሌቲክስ የጀመርሽው? አርአያሽስ ማነው? እኔ የተወለድኩት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ኢላኒ ቀርሳ የምትባል አካባቢ ነው። ሩጫ በጣም ነበር የምወደው። ልጅ ሆኜ ትምህርት ቤት እያለን እነ ጥሩነሽ ሮጠው ባንዲራ ለብሰው ሳይ በጣም ነበር ደስ የሚለኝ። በዚያ ምክንያት ትምህርት ቤት እያለሁ ነው ሩጫ የጀመርኩት። ቢቢሲ፡ ከዚያ የት ክለብ ገባሽ? እኔ ሩጫ የጀመርኩት 2006 ዓ.ም ላይ ነው̀። ጫጫ የምትባል ትንሽ ከተማ ሄጀ ነው ሩጫ የጀመርኩት። እዚያ ጥቂት ልጆች ተሰባስበው ያሉበት ትንሽ ፕሮጀክት ነበር። መጀመሪያ እዚያ ነበር የገባሁት። እዚያ እየሰራሁ ቆየሁና 2010 ዓ.ም ላይ ከዚያ ወጥቼ ደብረ ብርሃን ገባሁ። እዚያ እየሰራሁ እያለሁ ነው በ2011 ዓ.ም ላይ ፌደራል ፖሊስ የገባሁት። ክለቤ ፌደራል ፖሊስ ነው። ቢቢሲ፡ ቶክዮ በተለያዩ ውድድሮች የሚሳተፉ ብዙ አገራት፣ በርካታ አትሌቶችም አሉ። በተደጋጋሚ ሜዳሊያ ያገኙ አትሌቶችም አሉ። እነርሱን አይተሽ ያስቀናሽ ነገር ምንድን ነው? ሌሎች አገራት በጣም ብዙ ማለትም 20 ወይም 30 ሆነው የመጡ አገራት አሉ። እኛ ከኢትዮጵያ የመጣነው ሦስት ብቻ ነን። እና የተወዳዳሪ ቁጥር ቢጨምር፣ ድጋፍ ቢኖር እና ሚኒማ ማሟያው ሄዶ ለመወዳደር በዓለም አቀፉ ፓራሊምፒክስ ኮሚቴ ተጨማሪ ሰው ቢሰጠው እና ለኢትዮጵያ ፓራ አትሌቲክስ ተጨማሪ ዕድል ቢሰጥ ኢትዮጵያውያን በጣም ብዙ ማሸነፍ የሚችሉት ውድድር አለ። ልጆቹ በጣም ጠንካራ ናቸው። የኢትዮጵያ አትሌቶች መሮጥ የሚችሉ ናቸው። የአሁኑ አልፏል፤ ለወደፊቱ ግን ድጋፍ ተደርጎ የአትሌቶችን ቁጥር መጨመርና ማሻሻል ቢቻል እንዲሁም በአትሌቲክስ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ስፖርት ላይ መሳተፍ ቢቻል አሪፍ ነው። በጣም ጥሩ ውጤት እናመጣለን ብየ አስባለሁ። ከአሁን በኋላ ባለው ላይ እንደዚኣ ቢደረግ መልካም ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-58386636 +business ሄዝቦላህ በዓለም አቀፍ የዕጽ ምርትና ንግድ ውስጥ የለሁበትም አለ "የሌባኖስ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ አምፊታሚን የተባለውን አደንዛዥ ዕጽ ምርት ውስጥ ይሳተፋል መባሉን መሪው አስተባበሉ። የሶሪያ መንግሥት የቅርብ ወዳጅ የሆኑት የሄዝቦላህ መሪ ሼክ ሐሰን ናስላላህ በቡድናቸው ላይ የቀረበውን ክስ ""ምንም ተአማኒነት የሌለው"" ሲሉ አጣጥለውታል። በቡድኑ ላይ ጥርጣሬ የተፈጠረው ባለፈው ዓመት ሠኔ ወር ላይ 14 ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕጽ ጣሊያን ውስጥ ከተያዘ በኋላ ነው። የጣሊያን ባለሥልጣናት እንዳሉት ዕጹ የተጓጓዘው ላታኪያ ከምትባለው የሶሪያ ወደብ ነበረ። ""ዕጹ ከየት እንደመጣ ለማወቅ የጣሊየን ባለሥልጣናትን አግኝተናቸው ነበር"" ብለዋል የሄዝቦላህ መሪው ሐሰን ናስራላህ። ""ክሱ በተግባር ምንም መሠረት አልነበረውም። በተቃራኒው በአይኤስ፣ በጣሊያንና በሩሲያ የማፍያዎችና በሌሎች የወንጀል ቡድኖች ላይ ምርመራ እያደረጉ ነው"" ብለዋል። መሪው ጨምረውም ሄዝቦላህ ""የሐሰተኛ ዜና"" ኢላማ ተደርጓል በማለት የምዕራቡ ዓለም ""ፕሮፓጋንዳ"" ከቀረበባቸው ክስ ጀርባ አለ ብለው እንደሚያምኑ ተናገረዋል። የአሜሪካና የአውሮፓ ተቋማት የሌባኖሱ ታጣቂ ቡድን ከዕጽ ንግድ ትርፍ እያጋበሰ ነው ሲሉ ለረጅም ጊዜ ሲከሱት ቆይተዋል። በቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግራቸው የሄዝቦላው ዋና ጸሐፊ እንዳሉት ""በሁሉም የዕጽ አይነቶች ላይ ያለን አቋም ግልጽ ነው። ማምረት፣ መሸጥ፣ መግዛት፣ ማዘዋወርና መጠቀም በሐይማኖታችን የተከለከለ ነው። አንዳንድ ጊዜ ቅጣቱ እስከ ሞት ሊደርስ ይችላል"" ብለዋል። ጨምረውም ለጠላትም ቢሆን ዕጽን መሸጥ የተከለከለ እንደሆነ ቢጠቅሱም፤ የእስራኤል ፖሊስ ሄዝቦላህ ወደ ግዛቱ ሐሺሽ በድብቅ ያስገባል ሲል ይከሳል። ሌባኖስ በዓለም ዋነኛ የሐሺሽ አምራች ከሆኑ አገራት መካከል የምትገኝ ሲሆን፤ በኢራን በሚደገፈው በሄዝቦላህ ቁጥጥር ስር የሚገኙ አካባቢዎችን ጨምሮ ዕጹ በግልጽ እንዲበቅል ይደረጋል። ጣሊያን ውስጥ ከወራት በፊት የታያዘው ዕጽ በጣም ትልቅ የሚባል መጠን ያለው ነበር። በዚህም 85 ሚሊዮን የዕጽ እንክብሎች በማሽን ክፍሎች ውስጥ ተደብቆ በመርከብ ወደጣሊያን ሊገባ ሲል ነበር የተያዘው። የጣሊያን በገንዘብ ዙሪያ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የሚከታተለው የፖሊስ ቡድን በቁጥጥር ስር የዋለውና ተቃጥሎ እንዲወገድ የተደረገው ዕጽ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ሊያወጣ የሚችል እንደነበር አመልክቶ መጀመሪያ ላይ በአይኤስ ቡድን የተመረተ ነው ብሎ ነበር። ነገር ግን የዕጹ መጠን በአይኤስ አቅም ሊመረት የሚችል አይደለም በማለት ጥርጣሬውን በሶሪያው ፕሬዝዳንት በሻር አል አሳድ ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች በሚገኙ ፋብሪካዎች ሳይመረት እንዳልቀረ ተጠርጥሯል። የዕጹን ምንጭ በትክክል ማወቅ ሳይችሉ ከቀሩ በኋላ የጣሊያን ባለሥልጣናት ከዕጹ ጋር በተያያዘ ተጣያቂው ማን እንደሆነ በይፋ ወጥተው አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። በአንድ የወንጀለኞች ቡድን ላይ ይደረግ በነበረ ክትትል ምክንያት ዕጹ ሊያዝ እንደቻለ የተነገረ ሲሆን፤ ነገር ግን የቡድኑ ተሳትፎ በአሻሻጭነት ነበር። የዕጹ መድረሻ አውሮፓ ውስጥ ሳይሆን በጦርነት ወደምትታመሰው ሊቢያ እንደሆነ ይታመናል። የሶሪያ መንግሥትና አጋሮቹ በዕጽ ምርት ትርፍ እያጋበሱ ነው በሚል ክስ ይቀርብባቸዋል። ለዓመታት በዘለቀው ጦርነት ሳቢያ የተከሰተው ሕግ አልባነትና በምዕራባዊያን አገራት በተጣለባት ማዕቀብ ባጋጠማት የገንዘብ እጥረት ሳቢያ ሶሪያ ወደ ሕገ ወጥ የዕጽ ምርት ፊቷን ሳታዞር አልቀረችም ተብሎ ይታመናል። ከዕጾቹ መካከል ካፕታጎን የሚባለው ዕጽ በግጭት አካባቢ በሚገኙ ተዋጊዎች ዘንድ በስፋት ጥቀም ላይ ይውላል። ካፕታጎን ከመጠን ያለፈ እንቅልፍ የሚያስቸግራቸው ሰዎችን ንቁ እንዲሁኑ የሚያደርግ ነበር። ተዋጊዎቹም በጦርነት ጊዜ ፍርሐታቸውን ለማስወገድ እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል። ዕጹ የአረቡን ዓለም ያጥለቀለቀ ሲሆን ለመዝናኛነት ይጠቀሙታል። ዕጹ በከፍተኛ መጠን በሳዑዲ አረቢያ፣ በኩዌይትና በዮርዳኖስ ውስጥ ተይዟል። ባለፈው ኅዳር ወር ብቻ ግብጽ ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የዕጹ እንክብሎችና በሺዎች ኪሎ የሚገመት ሐሺሽ ከሶሪያ ሲገባ ተይዟል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55601347 +business ቤይሩት ፍንዳታ፡ በአደጋው 15 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ውድመት መድረሱ ተገለፀ "የዓለም መሪዎች ከአምስት ቀናት በፊት በከባድ ፍንዳታ ለተመታችው የሊባኖሷ መዲና ቤይሩት እርዳታ ለማሰባሰብ ዛሬ ጉባኤ እንደሚያካሂዱ ተገለፀ። ይህ በበይነ መረብ (ቨርቹዋል) የሚካሄደው ስብሰባ በፈረንሳይና በተባበሩት መንግሥታት የተዘጋጀ ሲሆን ስምንት ሰዓት ላይ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለአገሪቷ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማሰባሰብ ማስተባበር እንደሚፈልጉ የተናገሩት ሐሙስ ዕለት ቤይሩትን በጎበኙበት ወቅት ነበር። ዛሬ የሚካሄደው ጉባኤ የሊባኖስ ዋና ዋና ዓለም አቀፍ አጋሮችን ለማሰባሰብና ከዓለም አቀፍ ማሕበረሰቡ አስቸኳይ ድጋፍ ለማሰባሰብ ያለመ መሆኑም ከፕሬዚዳንቱ ቢሮ የወጣው መግለጫ አመልክቷል። በጉባኤው ላይ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት ተወካዮች ፣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ግብፅ፣ ጆርዳን እና ዩናይትድ ኪንግደም የሚሳተፉ ሲሆን ሌሎች በርካቶችም ተጋብዘዋል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቤይሩት ስለተከሰተው ድንገተኛ አደጋ ከፕሬዚደንት ኢማኑኤል ጋር ተወያይተው እንደነበር ገልፀው፤ በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ እንዳቀዱ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። በርካታ አገራት ቤይሩትን ለመርዳት በሚሊየን ዶላሮች የሚገመት እርዳታ፣ መርከቦች፣ የጤና ባለሙያዎችንና ቁሳቁሶችን ልከዋል። ይሁን እንጂ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአገሪቷ ከፍተኛ ቀውስ ሊያጋጥም እንደሚችል በማስጠንቀቅ ተጨማሪ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ጥሪ አቅርቧል። በርካታ ቤቶች የውሃና የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸው ሲሆን የምግብ ፍጆታ እጥረት እንደሚያጋጥምም ስጋት አለ። ከዚህም ባሻገር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭት እየጨመረ ሲሆን ይህም በፍንዳታው በተጎዱ ሰዎች በተጨናነቁት ሆስፒታሎች ላይ ተጨማሪ ጫና ፈጥሯል። የዩኒሴፍ ቃል አቀባይ ማሪክሴ ሜርካዶ አርብ ዕለት ጀኔቫ ለሚገኙ ጋዜጠኞች ""አፋጣኝና ከፍተኛ ድጋፍ"" እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የሊባኖስ ባለሥልጣናት 2 ሺህ ቶን የሚመዝን አሞኒየም ናይትሬት ደህንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለስድስት ዓመታት ተከማችቶ በነበረበት መጋዘን በተከሰተው ፍንዳታ፤ 15 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ጉዳት እንደደረሰ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በፍንዳታው ቢያንስ 158 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 5 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት አጋጥሟቸዋል፤ 300 ሺህ የሚሆኑት ቤት አልባ ሆነዋል። ይህንንም ተከትሎ ቅዳሜ ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መንግሥትን ለመቃወም አደባባይ የወጡ ሲሆን፤ ፖሊስም በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ላይ ድንጋይ በመወርወር ተቃውሟቸውን ሲገልፁ በነበሩት ላይ አስለቃሽ ጭስ ረጭቷል። የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን ዲያብም ከዚህ ቀውስ ለመውጣት ቀድሞ ከተያዘው ጊዜ ቀድሞ ምርጫ እንዲካሄድ ሊጠይቁ እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን በጉዳዩ ላይም ካ���ኔው ሰኞ ውይይት ያደርግበታል ተብሏል። ቀደም ሲል በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ የገባችው ሊባኖስ፤ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመዋጋት እየተጣጣረች ባለበት ሰዓት ነው ፍንዳታው ያጋጠማት። በአገሪቷ ያጋጠመውን የኢኮኖሚ ቀውስና የመገበያያ ገንዘቧ ዋጋ መውደቅ ተከትሎ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ተቀስቅሶ ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-53711893 +politics አወዛጋቢው የሙሴቪኒ ልጅ ፕሬዝዳንት እሆናለሁ ሲሉ ቃል ገቡ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ ልጅ የአባታቸውን የስልጣን መንበር ለመረከብ ያላቸውን ፍላጎት ገለፁ። ጄነራል ሙሆዚ ካያኔሩጋባ በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ እናታቸውን ፕሬዝዳንት በመሆን እንደሚክሷት በመግለጽ ጽፈዋል። ኡጋንዳን ለረዥም ዓመታት ያስተዳደሩት ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ልጅ፣ የአባታቸው ሥልጣን ወራሽ ናቸው የሚለውን ጥርጣሬ የሚያረጋግጥ መልዕክት ማስፈራቸው ብዙዎችን አስደንቋል። ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ እኤአ ከ1986 አንስቶ በስልጣን ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ልጃቸው ጄነራል ሙሆዚ የስልጣናቸው ወራሽ ናቸው የሚለው አሉባልታ ለረዥም ጊዜ ሲወራ ቆይቷል። ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ጄነራል ሙሆዚ በትዊተር ገጻቸው ላይ ሰዎች ፕሬዝዳንት መሆን እንዳለባቸው ያስቡ አንደሆን ጠይቀው ነበር። በድጋሚ በዚህ ወር ደግሞ “ለኡጋንዳ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ ከአባቴ በኋላ በማንኛውም ምርጫ በዝረራ አሸንፋችኋለሁ። ኡጋንዳውያን እናንተን ከሚወዱት በላይ እኔን ይወዱኛል” ሲlu ጽፈዋል። የ48 ዓመቱ ጄኔራል በትዊተር ላይ በሚለጥፏቸው መልዕክቶች መነጋገርያ ከመሆን ታቅበው አያውቁም። በጥቅምት ወር መጀመርያ ላይ ኬንያን ለመውረር ዝተው፣ አገራቸው ኡጋንዳ በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ ከአገሪቱ ጋር ያላትን ጠንካራ ትስስር እንድታረጋግጥ አስገድደዋል። ከዚህ በኋላም አወዛጋቢው የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ልጅ ሌፍተናንት ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ ከአገሪቱ የምድር ጦር ኃይል አዛዥነት ሥልጣናቸው ተነስተዋል። ከዚህ በኋላም አባታቸው ፕሬዝዳነት ሙሴቪኒ በመንግሥት ጉዳዮች ዳግም ትዊት እንደማያደርግ የገለፁ ቢሆንም ወድያውኑ “ማንም ምንም ነገር ከማድረግ አያግደኝም” ሲሉ ጄኔራሉ ትዊተር ጽፈዋል። ጄኔራሉ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያን የተመለከተ በተለይ ደግሞ ከትግራይ ጋር የተያያዙ አስተያየቶችን ሲሰጡ ነበር። የኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት አንድ ዓመት በደፈነበት ጥቅምት 2014 ዓ.ም. ላይ የትግራይ ኃይሎችን ደግፈው ትዊት አድርገው ነበር። “የትግራይ መከላከያ ኃይሎች . . . የቆማችሁበትን ዓላማ እደግፋለሁ። የትግራይ እህቶቻችንን የደፈሩ እና ወንድሞቻችንን የገደሉ መቀጣት አለባቸው” ሲሉ ጽፈው ነበር። የጄኔራል ሙሆዚ ትዊት ተከትሎ የኡጋንዳ መንግሥት አስተያየቱ የጄኔራሉ እንጂ የጦሩን አቋም አይወክልም የሚል ማስተባበያን ሰጥቶ ነበር። በተጨማሪም ጄኔራሉ ከአገራቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ከጥቂት ወራት በፊት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋርም ተገናኝተው ነበር። መስከረም 22/2015 ዓ.ም. በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሳፈሩት ጽሑፍ፤ “ትግራይ ሁሌም በልቤ አለች! ትግራይን እንድወድ እና እንድከላከል ከፈጣሪዬ ከእየሱስ ክርስቶስ የመጣ ትዕዛዝ ነው” ብለዋል። በተመሳሳይ ዕለት ከሰዓታት በኋላ ደግሞ ጄኔራሉ ኢትዮጵያን በተመለከተ ባሰፈሩት ሌላኛው ጽሑፍ፤ “ዳግማዊ ሚኒሊክ አያታችን ናቸው። ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ አካል ናት። እንድትወድም አንፈቅድም። ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንወዳለን!” ሲሉ ጽፈዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n9kgv094vo +business የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጁ በዋጋ የሚያንራቸው ምርቶች "የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሳስ 7 2012 ዓ.ም ባካሄደው ስድስተኛ መደበኛ ስበሰባው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል። ከእነዚህ ረቂቅ አዋጆች መካከል ተሻሽሎ የቀረበው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ይገኝበታል። በሥራ ላይ የሚገኘው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ያሉበትን ጉድለቶች መቅረፍ ያስችላል ተብሎ የቀረበው ይህ ረቂቅ አዋጅ፤ በሃገር ውስጥ በሚመረቱና ከውጪ በሚገቡ የተመረጡ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ ጥሏል። •ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት •""ማርታ፣ ለምን ለምን ሞተች?"" ረቂቅ አዋጁ የኤክሳይዝ ታክስ እንዲጣልባቸው የለያቸው የምርቶች አይነት የሚከተሉት አይነት ናቸው። መሠረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ተፈላጊነታቸው አይቀንሱም የተባሉት የምርቶች አይነት፤ እቃዎቹ ኤክሳይዝ ታክስ ስለተጣለባቸው በተጠቃሚዎች ላይ ብዙም የዋጋ ልዩነት የማያመጡ፤ ነገር ግን ለመንግስት ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኙ ስለመሆናቸው ተነግሯል። •'የአልባኒያ ተቃዋሚዎች' በትግራይ በረቂቅ አዋጁ ላይ የኤክሳይዝ ታክስ እንዲጣልባቸው ከተለዩ ምርቶች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው። ኤክሳይዝ ታክስ ለመንግሥት ከፍተኛ ገቢ ከማስገኘቱ በተጨማሪ፤ ከውጪ የሚገቡ እቃዎች ሃገር ውስጥ የተመረቱትን ከገበያ ውጭ እንዳያደርጓቸው ታስቦ ይጣልባቸዋል። ይህም የሃገር ውስጥ አምራቾችን እንደሚያበረታታ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ኤክሳይዝ ታክስ በአምራቹ ወይም አስመጪው ይከፈላል። ምርቶች የተመረቱት በሃገር ውስጥ ከሆነ፤ ከተመረቱበት ወር ቀጥሎ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ እንዲሁም ምርቶቹ ከውጪ የሚገቡ ከሆነ አስመጪው ግለሰብ ወይም ድርጅቱ ከጉምሩክ ክልል በሚያወጣበት ጊዜ ታክሱ ይከፈላል፡፡ ይህ ረቂቅ አዋጅ የሚጸድቅ ከሆነ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ 307/1995 ተሽሮ በዚህ አዋጅ ይተካል። በተጨማሪም ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማንኛውም ሕግ፣ መመሪያ ወይም አሠራር ይህንን አዋጅ በሚመለከት ተፈፃሚነት አይኖረውም።" https://www.bbc.com/amharic/news-50839154 +business ትግራይ ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች የሚፈልጉትን ገንዘብ ለማውጣት ተቸገርን አሉ "ትግራይ ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ገንዘብ ማውጣት አለመቻላቸው ተናገሩ። ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች የሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ደንበኞች ገንዘብ ማውጣት አለመቻላቸውን ለቢቢሲ ገለጸዋል። በአብዛኞቹ የኢዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ከአንድ ሺህና ከሁለት ሺህ ብር በላይ ማውጣት እንደማይችሉ ተነግሮናል ይላሉ። ለምሳሌ በዓድዋ ከተማ ሰሎዳ ዓዲኣቡን በተባለው ቅርንጫፍ ብር ለማውጣት የሄደችው ተጠቃሚ ወጣት፤ ""ከሁለት ሺህ ብር በላይ ማውጣት አትችይም"" መባሏን ለቢቢሲ ትናገራለች። • በስህተት የተሰጣቸውን 1 ሚሊየን ብር የመለሱት መምህር • በሴት ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የባንክ ቅርንጫፍ ተከፈተ በዚህ ከተማ የሚገኙ ሌሎች ቅርንጫፎች ደግሞ ከ2 ሺህ እስከ 5 ሺህ ሲሰጥ እንደዋለ ከዚያ በላይ ግን ብር የለም በማለት አልስጥም መባላቸውን ተገልጋዮች ለቢቢሲ ገልጸዋል። በተመሳሳይ በውቅሮ ክልተውላዕሎ የሚገኘው ቅርንጫፍ ከአንድ ሺህ ብር በላይ አልሰጥም ማለቱን የባንኩ ደንበኞ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። አምስት ሺህ ለማውጣት ወደ ቅርንጫፉ ሂዳ፤ አንድ ሺህ ብር ብቻ የተሰጣት አንድ ነዋሪም በተመሳሳይ የገጠማትን ተናግራለች። • የብር የመግዛት አቅም መቀነስ አንድምታዎች ከዚህ መጠን በላይ ማውጣት አትችሉም ተብለው የተከለከሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ተጨንቀው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏ���። እንዲሁም ደግሞ ደመወዛቸው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚከፈላቸው የክልሉ የመንግሥት ሠራተኛ በተመሳሳይ ""ብር የለም ጠብቁ"" መባላቸውን ምንጮች ይናገራሉ። በመቀለ የሚገኘው የቢቢሲ ሪፖርተር ተዘዋወሮ እንተመለከተው፤ በመቀለ የሚገኙ ቅርንጫፎችም በወረፋ መጨናነቃቸውንና የጠየቁት ብር ሳይሰጣቸው ስለቀረ ሲበሳጩና በቁጣ ሲናገሩ ታዝቧል። • ""ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም"" ፀደቀ ይሁኔ (ኢንጂነር ) ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው አንድ በመቀለ ቅርንጫፍ በኃላፊነት ላይ የሚገኝ የባንኩ ሠራተኛ፤ ባንኩ የገንዘብ እጥረት እንዳጋጠመው ይናገራል። በተለይ በትግራይ የሚገኙ ቅርንጫፎች ምንም ብር እንደሌላቸው ተናግሯል። ለዚህ እንደምክንያት የተጠቀሰውም የተለያዩ ሰዎች ገንዘባቸው ከባንኩ እያወጡ እንደሆነ ነው። ችግሩ በሌሎች አከባቢዎችና በሌሎች የግል ባንኮችም፤ ሊከሰት እንደሚችል አመላክቷል። የባንኩ ሠራተኛ አክሎም በትግራይ ውስጥ፤ ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የተሰጣቸው አራት ዋና ዋና አከፋፈይ ማዕከላት በመቀለ፣ በማይጨው፣ በዓድዋና ሽረ እንዳሥላሰ የሚገኙ ሲሆን፤ በእነዚህ ማዕከላት ውስጥ የብር እጥረት ስለአጋጠመ ነው ወደ ቅርንጫፎች ብር ያልተላከው ይላል። • ""ኢስላማዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል?"" ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀው ይኸው ኃላፊ እንጋለው ብሔራዊ ባንክ ችግሩን በጥቂት ቀናት ለመፍታት እየሰራ እንደሆነ አክሎ ተናግሯል። ቢቢሲ ያናገራቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አልሰን አሰፋ ግን የገንዘብ ዕጥረት እንደሌለ ገልጸዋል። ""የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገንዘብ ዕጥረት አልገጠመውም። ምናልባች የኔትወርክ ችግር ቢኖርበት ነው"" በማለት የተባለው ውሸት እንደሆነ ጠቅሰዋል። ጨምረውም ""ከ2 ሺህ ብር በላይ አታወጡም የሚል ህግም የለም"" የሚሉት አቶ አልሰን፤ ያለው ችግር ከቴሌ ጋር የሚያያዝ እንደሆነም ይናገራሉ። ገንዘብ የማውጣት ገደቡንም በተመለከተ ""ይሄ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም። የባንኩ አሰራርም አይደለም"" ብለዋል። ""ማንኛውም ሰው በባንኩ ያስቀመጠውን ብር በየትኛውም ቅርንጫፍ የማውጣት መብት አለው። ይህንን መብቱ የመከልከል መብት የለንም። የተባለው ችግር በትግራይ ካለ ለምን የእዚያ አከባቢ ቅርንጫፍ ኃላፊዎች አላነሱልንም? እንደሱ የሚባል መረጃ አልደረሰንም"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-51315502 +health ከአደገኛ የወረርሽኝ መቅሰፍት የሰው ልጅን የታደጉት ክትባቶች የትኞቹ ናቸው? በዓለም ላይ በተለያዩ ጊዜያት ወረርሽኞች ተከስተው የሰው ልጅን ሕይወትና ደኅንነት ለአደጋ አጋልጠውት ነበር። ወረርሽኞች ብዙዎችን ገድለዋል፣ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉትን ደግሞ አካል ጉዳተኛ አድርገዋል። ነገር ግን እነዚህን ወረርሽኞች ለመግታት የተቻለው በክትባት ነው። ለመሆኑ በክትባት ምክንያት የሰው ልጅ ከስቃይ እና ከሞት ተረፈባቸው በሽታዎች የትኞቹ ናቸው? https://www.bbc.com/amharic/news-56344363 +politics የሩሲያ የጦር ጀት ከዩኬ አውሮፕላን አጠገብ ሚሳኤል ተኮሰ የሩሲያ የጦር ጀት ከዩናይትድ ኪንግደም አየር ኃይል አውሮፕላን አቅራቢያ ሚሳኤል መተኮሱን ዩኬ አስታወቀች። የዩናይትድ ኪንግደም መከላከያ ሚንስትር ቤን ዋለስ የሞስኮ ጀት ሚሳኤል የለቀቀው ካልታጠቀው እና በጥቁር ባሕር ላይ ቅኝት ሲያደርግ ከነበረ የዩኬ አውሮፕላን አቅራቢያ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሩሲያ መስከረም 19/2015 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ የአየር ክልል ላይ ክስተቱ ያጋጠመው ‘በቴክኒክ ችግር’ ነው ብላለች። ይህን ክስተት ተከትሎ ዩኬ በጥቁር ባሕር ላይ ታደርግ የነበረውን የቅኝት ስራ አቁማ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ቅኝት የሚያ���ርጉ አውሮፕላኖች በጦር ጀት ታጅበው ሥራቸውን ጀምረዋል ተብሏል። ቤን ዋለስ ለዩኬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሲናገሩ፤ አገራቸው ክስተቱን የጠብ አጫሪነት ድርጊት አድርጋ ባትመለከተውም የሩሲያ ተግባር ግን “ነገሮች እንዴት አገደኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሳያ ነው” ብለዋል። ቤን ዋለስ ይህን ለምክር ቤት የተናገሩት ለአስቸኳይ የሥራ ጉዳይ ካቀኑበት አሜሪካ ከተመለሱ በኋላ ነው። መከላከያ ሚንስትሩ ከአሜሪካው አቻቸው ጋር በዩክሬን ስላለው ሁኔታ እና የሩሲያ የኒውክለር ጦር መሳሪያ የመጠቀም ዛቻን በተመለከተ መክረዋል ተብሏል። ባለፈው ወር አጋማሽ ላይ ክስተቱ ሲያጋጥም በአየር ክልሉ ውስጥ ከነበሩት ሁለት የሩሲያ ኤስዩ-27 የጦር ጀቶች መካከል አንዱ ወዳልታጠቀው እና ቅኝት ላይ ወደነበረው የዩኬው አርሲ-135 አውሮፕላን አቅራቢያ ሚሳኤል ለቅቋል። በጥቁር ባሕር ላይ ያጋጠመውን ክስተት ተከትሎ ቤን ዋለስ የተሰማቸውን ቅሬታ ለሩሲያው መከላከያ ሚንስትር ደብዳቤ መላካቸውን ገልጸዋል። ክስተቱን በተመለከተ የሩሲያ መከላከያ ሚንስትር በሰጡት ምላሽ ጦራቸው በጉዳዩ ላይ ምርመራ ማካሄዱን እና የሩሲያው ጀት ባጋጠመው ቴክኒክ ችግር ሚሳኤሉ መተኮሱን ገልጸውልናል ሲሉ ቤን ዋለስ ተናግረዋል። ክስተቱ ያጋጠመው በዓለም አቀፉ የአየር ክልል ውስጥ መሆኑንም የሩሲያ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል ብለዋል መከላከያ ሚንስትሩ። በጥቁር ባሕር ላይ የተከሰተው ነገር የሩሲያ ጦር ስህተት ሊሰራ እንደሚችል ወይም ሕግ እነሱ ላይ ተፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል እንደሚያስቡ ያሳየ ነው ሲሉ ቤን ዋለስ ጨምረው ተናግረዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cw87g80q7e1o +sports ካስተር ሰሜኒያ የደቡብ አፍሪካን የእግር ኳስ ቡድን ተቀላቀለች "የሁለት ጊዜ የ800 ሜትር የኦሎምፒክ አሸናፊዋ ደቡብ አፍሪካዊቷ ሯጭ ካስተር ሰሜኒያ የደቡብ አፍሪካን የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ተቀላቀለች። የ28 ዓመቷ አትሌት ሰሜኒያ ከፍተኛ 'ቴስቶስትሮን' የተሰኘው ሆርሞን ያላቸው ሴት ሯጮችን በተመለከተ የወጣውን ሕግ ተከትሎ በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን በውድድር ላይ እንዳትሳተፍ ተደርጓል። • ደቡብ አፍሪካዊቷ ሯጭ ለፍርድ ቤት ይግባኝ አለች • ሰሜኒያ ሴት ስፖርተኞች ደግፈዋት እንደማያውቁ ተናገረች ሕጉን በመቃወም ያቀረበችውን አቤቱታ የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም (ካስ) ውድቅ ካደረገባት በኋላ ወደ ስዊዘርላንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አምርታ እየተከራከረች ትገኛለች። በ800 ሜትር ለአገሯ ደቡብ አፍሪካ ሦስት ጊዜ ወርቅ ያመጣችው ሰሜኒያ፤ በወርሃ መስከረም ዶሃ ላይ በሚካሄደው ውድድር ላይ እንደማትሳተፍም ታውቋል። ምክንያቱ ደግሞ ""ለሴት አትሌቶች ከሚፈቀደው በላይ የቴስቴስትሮን ሆርሞን በውስጧ አለ"" በመባሉ ነው። በመሆኑም አሁን ላይ ከሩጫው ዓለም ወደ እግር ኳሱ ዘርፍ ጎራ ማለቷ ተሰምቷል። ሰሜኒያ፤ ተቀማጭነቱን ደቡብ አፍሪካ ጓተንግ ያደረገውን JVW የተሰኘ የሴቶች እግር ኳስ ቡድንን በመቀላቀል ሥልጠና እየወሰደች ነው። በቡድኑ ድረ ገፅ ላይም፤ ""በአዲሱ ጉዞዬ እቀጥላለሁ፤ ቡድኑ ያሳየኝን ፍቅርና ያደረገልኝን ድጋፍ አደንቃለሁ"" የሚለው አስተያቷ ሰፍሮ ይገኛል። 'JVW FC' የተሰኘው የእግር ኳስ ቡድን ከስድስት ዓመታት በፊት በደቡብ አፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን አምበል ጃናይን ቫን ውይክ የተቋቋመ ሲሆን፤ ዓላማው ሴት እግር ኳሰኞችን መመልመል፣ ማጎልበት እና ብቃት ያላቸውን ተጨዋቾች ማፍራት ነው። ቡድኑ በጓተንግ ግዛት ታዋቂ ከሆኑ እግር ኳስ ቡድኖች አንዱ ነው። የቡድኑ መስራች ጃናይን ቫን ውይክ፤ ""ሰሜኒያ በሩጫው ፈፅሞ ተስፋ አልቆረጠችም"" ብለዋል። አሁን ላይ እረፍት ላይ መሆኗ��ም በመግለፅ፤ በዚህ የእረፍት ጊዜዋ የተለየ ነገር ማድረግ ስለፈለገች ቡድኑን እንደተቀላቀለች ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንደ ቡድኑ መሪ ከሆነ ሰሜኒያ እስካሁን ሁለት የሥልጠና ዙሮች ላይ ተካፍላለች፤ ነገር ግን የሩጫ ዓለምና የእግር ኳስ ሜዳ ስለሚለያዩ ተጨማሪ ሥልጠናዎች ያስፈልጋታል። • ስለ አቶ ዱቤ ጅሎ ሽልማት ምን እናውቃለን? ""የእሷ ወደ እግር ኳሱ መምጣት ለቡድኑ በጣም ጠቃሚ ነው፤ በደቡብ አፍሪካ ለእግር ኳስ የሚሰጠው ክብር ከፍ እንዲል ያደርገዋል"" ሲሉም ሰሜኒያ እግር ኳስ ስትጫወት ለቡድኑ አባላትና ለሌሎች ወጣት ሴቶች ተነሳሽነትን መፍጠር ትችላለች በማለት በእሷ ላይ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል። ሰሜኒያ የእግር ኳስ ቡድን የተቀላቀለች ብቸኛዋ ሯጭ አይደለችም፤ ከሁለት ዓመታት በፊት የዓለማችን የአጭር ርቀት ሯጭ ዩዜን ቦልት ኮንትራቱን ሳይፈራረም ቢቀርም በኖርዌያዊያን ቡድን ሥልጠና ወስዶ ነበር። የሰሜኒያ የቀድሞ አሰልጣኝ ማሪያ ሙቶላም ወደ እግር ኳሱ ዓለም ተቀላቅለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-49619077 +sports ከውድድር የታገዱ ናይጄርያዊያን አትሌቶች በቶኪዮ ሰልፍ አደረጉ "በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለመወዳደር ብቁ አይደላችሁም የተባሉ ናይጄርያዊያን ስፖርተኞች በጃፓን፣ ቶኪዮ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ። የኦሎምፒክ የአትሌቲክስ የሥነ ምግባር መከታተያ ቡድን 10 ናይጄርያዊያን ስፖርተኞችን ጨምሮ 20 ተወዳዳሪዎች ከውድድር በፊት የአበረታች መድኃኒት መስፈርቶችን ባለማሟላታቸው ከውድድር አግዷቸዋል። አትሌቶቹ ""በሌላ ሰው ቸልተኝነት እኛ ለምን እንሰቃያለን'' የሚለውን ጨምሮ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ባለሥልጣናቱን እና ውሳኔያቸውን ነቅፈዋል። ሰልፍ ካካሄዱት ናይጄርያዊያን ስፖርተኞች በተጨማሪም አርብ እለት በተደረገው 100 ሜትር ማጣሪያ ውድድር ላይ በአንደኝነት ያጠናቀቀችው ስፕሪንተር ብለሲንግ ኦካግባሬ በተመሳሳይ መታገዷ ታውቋል። የ32 ዓመቷ አትሌት ከውድድር በኋላ በተደረገላት ምርመራ ሰው ሠራሽ ሆርሞን እንደተገኘባት ተገልጿል። በቤጂንግ ኦሎምፒክ በረዥም ዝላይ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ የነበረችው አትሌቷ ከውድድሩ በግዜያዊነት መታገዷ ዛሬ ቅዳሜ ተገልጾላታል። ትላንት በተደረገው ማጣሪያ ውድድር 11.5 ሰከንዶች ያስመዘገበች ሲሆን በግማሽ ፍጻሜው ከእንግሊዛዊቷ አሸር-ስሚዝ እና ከጃማይካዊቷ ኢሌን ቶምፕሰን-ሄራት ጋር ትወዳደር ነበር። አትሌቷ ሌሎች 10 ናይጄርያዊያን አትሌቶች በአበረታች መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ውጪ ከሆኑ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው መታገዷ የተሰማው።" https://www.bbc.com/amharic/news-58038499 +health ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ በአስከሬን ላይ የሚደረገው የኮሮናቫይረስ ምርመራ መቆሙ ተገለፀ ኢትዮጵያ ከአስከሬን ላይ ናሙና በመውሰድ ታደርገውን የነበረውን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማቆሟን አስታውቃለች። ይህንን ያስታወቀችውም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በፃፈው ደብዳቤ ነው። የአለም ስጋት ሆኖ የቀጠለውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት አገሪቷ የተለያዩ የመካላከልና የመቆጣጠር ስራዎችን እየሰራች እንደነበር የጠቀሰው ደብዳቤው ከነዚህም መካከል ከአስከሬን የላብራቶሪ ናሙና መውሰድም ነበር። የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ጤና ሚኒስቴር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላትም ጋር በመሆን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ ማስተባበሪያ ማዕከል በሟቋቋም የቫይረሱን ስርጭትና መጠን ለማወቅም ከተሰሩ ስራዎች መካከል ከአስከሬን የሚወሰድ የላብራቶሪ ናሙና መሆኑን አስታውሷል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ የቫይረሱ የማህበረሰብ ስርጭት ከ95 በመቶ በላይ በመሆኑና ከአስከሬን ይደረግ የነበረው የናሙና ምርመራም በህዝቡም ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ሲያስነሳበትም እንደነበር ደብዳቤው ጠቅሶ በነዚህም ምክንያቶች እንዲቆም ተወስኗል። በአሁኑ ወቅትም የብሄራዊ የኮቪድ-19 መከላከልና እና መቆጣጠር ግብረ ኃይል በወቅቱ ያለውን አለም አቀፋዊና ሃገራዊ ስርጭት ከግምት ውስጥ በማስገባትም ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ልዩ ትኩረት በመስጠትም የመከላከሉና የምርመራው ስራ ይቀጥላል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ማንኛውንም ሞት በኮሮናቫይረስ እንደሆነ ተደርጎም በቀብር ስነ ስርአቱ ላይ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባም አሳስቧል። ከሰባት ወራት በፊት የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ የተገኘባት ኢትዮጵያ እስከዛሬዋ እለት፣ መስከረም 19፣ 2013 ዓ.ም ባለው መረጃ በአገሪቷ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች 73 ሺህ 944 የደረሰ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 177 ዜጎቿን በሞት ተነጥቃለች። በበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 30 ሺህ 753 የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 260 ሺህ 929 የላብራቶሪ ምርመራዎችን አከናውናለች። https://www.bbc.com/amharic/54341609 +health አስትራዜኒካ ከሚያመርተው የኮሮናቫይረስ ክትባት ትርፍ መሰብሰብ ሊጀምር ነው "አስትራዜኒካ የሚያመርተውን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ያለትርፍ ለአገራት የሚሰራጭበትን አሠራር ሊቀይር እንደሆነ ተሰምቷል። ግዙፉ መድኃኒት አምራች ኩባንያ ከቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ ተከታታይ የንግድ ስምምነቶች የተፈራረመ ሲሆን ከክትባቱ ሽያጭ መጠነኛ ገቢ እንደሚያስገባ አስታውቋል። ሆኖም ኩባንያው ለድሃ አገራት ክትባቱን ያለትርፍ ማቅረቡን እንደሚቀጥል ገልጿል። ኩባንያው ከዚህ ቀደም ከክትባቱ ገንዘብ ለማግኘት አቅዶ የነበረው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት መሆኑ ካበቃ በኋላ ነው። የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓስካል ሶሪዮት፤ ወረርሽኙ ወደተወሰኑ አከባቢዎች እየጠበበ መምጣቱን ተናግረዋል። ""ቀደም ሲል ያለምንም ትርፍ ክትባቱን ለማቅረብ የወሰነው ዋናው ዓላማችን የዓለምን ጤና መጠበቅ ስለነበር ነው"" ብለዋል። ""ምንም እንኳን በተለያዩ አገራት የፖለቲካ ትችቶችን ብናስተናግድም ከተፎካካሪዎች በተቃራኒ ትርፍ ለማግኘት አለመሥራታችን ምንም አይነት ፀፀት አላስከተለብንም"" ሲሉ ሥራ አስፈጻሚው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተደረገ ትብር የበለጸገው ክትባቱ በዓለም ዙሪያ የአንድ ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት መታደግ መቻሉንም ጠቅሰዋል። ""በፍፁም አልፀፀትምም። እንደ ኩባንያ እኛ በሠራነው ሥራ ኩራት ይሰማናል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን አድነናል። የአስተራዜኒካ ቡድን ጥሩ ሥራ መሥራቱን ቀጥሎበታል"" ሲሉም አክለዋል። ከክትባቱ ሽያጭ ከፍተኛ ገቢ እንደማይጠበቅ የገለጹ ኃላፊው፤ ክትባቱ በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረቡን ለማረጋገጥ ለአገራት በየደረጃው የዋጋ ተመን እንደሚወጣ ተናግረዋል። እስከዚህ የፈረንጆቹ ዓመት መገባደጃ ድረስ አስትራዜኒካ 250 ሚሊዮን ክትባቶችን በኮቫክስ መርሐ ግብር አማካይነት ለታዳጊ አገራት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። ፋይዘር እና ሞደርናን ጨምሮ ሌሎች የክትባት አምራቾች ከምርቶቻቸው ትርፍ እያገኙ ያገኛሉ። በመድኃኒት ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለው መደበኛ የትርፍ ጣሪያ 20 በመቶ መሆኑን የሚገልጹት ሶሪዮት፤ የኮቪድ-19 ክትባት ግን አንድ ብልቃጥ 5 ዶላር የሚሸጥ በመሆኑ አስተራዜኒካ አነስተኛ ትርፍ እንደሚያገኝ ጠቁመዋል። 'ግሎባል ጀስቲስ ናው' የተሰኘ እንቅስቃሴ ዳይሬክተር ኒክ ዴርደን በበኩላቸው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በቀጠለበት በዚ�� ወቅት አስትራዜኒካ ከክትባቱ ትርፍ ለማግኘት መወሰኑ ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ ውሳኔውን ተቃውመዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59272481 +business በትግራይ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለመመለስ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚገባ ተገለጸ በትግራይ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የተቋረጡ የመሠረተ ልማት እና መሠረታዊ አገልግሎቶችን ዳግም ለማስጀመር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ መድረስ እንደሚገባ ተገለጸ። እነዚህን መሠረተ ልማቶችን ለማስመለስ “አስቻይ የሆነ ሁኔታ በፍጥነት ለመፍጠር የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጉ አስፈላጊ” መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት ያቋቋመው ተደራዳሪ ቡድን ገልጿል። ከትግራይ ክልል ጋር ያለውን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት የተቋቋመው የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 11/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ይቻልም ዘንድ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ንግግሩን እንዲያስጀምር ጠይቋል። የሰላም ውይይቱ የሚካሄድበትን ቦታ እና ጊዜ በፍጥነት ተወስኖ ንግግር እንዲጀመር ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑንም መገምገሙን ተገልጿል። ከዚህም ንግግር በኋላ በሚደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት መሠረታዊ አገልግሎቶችን ዳግም ለማስጀመር አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረገም ነው ተብሏል። “ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት ሲገባ በሚፈጠረው አስቻይ ሁኔታ፣ መሠረታዊ አገልግሎቶችን በተቻለ ፍጥነት መልሶ ማቅረብ ይቻል ዘንድ፣ አስፈላጊ ቅደም ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን” ኮሚቴው ገልጿል። በትግራይ ሃይሎች ውስጥ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ የሰላም ኮሚቴውን መግለጫ “ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማታለል የሚደረግ የማደናገሪያ ጨዋታ ነው” በማለት ውድቅ አድርገውታል። አቶ ጌታቸው የፌዴራል መንግሥቱ “በተለያዩ ግንባሮች” ትንኮሳ አድርጓል ሲሉ ከሰዋል። “ሁኔታውን የማዘግየት ስልቶችን ከመከተል በስተቀር ለሰላማዊ ድርድር ምንም ፍላጎት የላቸውም” በማለትም በዛሬው ዕለት በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። ከትግራይ በተጨማሪ በአፋር እና በአማራ ክልል አካባቢዎች ነዋሪዎች እየገጠማቸው ያለውን ችግር መቅረፍ እንደሚገባም በዚሁ መግለጫ የተጠቀሰ ሲሆን፣ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተማማኝ እና ዘላቂ በሆነ መንገድ ለማድረስም ኮሚቴው አስቻይ የሆኑ ሁኔታ ለመፍጠር የተኩስ አቁም ስምምነት መድረስ ይገባል ብሏል። ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት ሊያደርስ የሚችል እንዲሁም ለቀጣይ የፖለቲካ ውይይቶችም የሰላም ምክረ ሃሳብ ላይ ውይይት በማድረግ የምክረ ሃሳብ ሰነድ በማዳበር ማጽደቁንም አስታውቋል። ይህ ምክረ ሃሳብ ለአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ወኪል እንዲቀርብ መወሰኑም ተጠቅሷል። ከትግራይ ኃይሎች ጋር የሚደረገው ምንም አይነት ድርድር ሊመራ የሚችለው በአፍሪካ ኅብረት ብቻ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አቋሙን በተደጋጋሚ ያስታወቀ ሲሆን፣ ከዚህ በፊት በኅብረቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ የገለጹት የትግራይ አመራሮች ድርድሩ በኅብረቱ ጥላ ስር ብቻ እንዲሆን እንደማይፈልጉ ገልጸዋል። ማንኛውም ድርድር በሰላም ጥረት ውስጥ ንቁ ሚና የተጫወቱትን የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ማካተት አለበት ብለዋል። ከዚህ ቀደምም የትግራይ አመራሮች የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ያላቸው ቅርበት እንዳሳሰባቸው መግለፃቸው ይታወሳል። መንግሥት በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ አማራና አፋር የተዛመተውን ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላም ለመቋጨት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጾ፣ ከእ���ዚህም ውስጥ የሰብዓዊነት ተኩስ አቁም ማወጅ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማንሳት፣ እስረኞች መፍታትና የሰብዓዊ ድጋፍ በከፍተኛ ማሳለጥ መሆኑን ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሰላም ውይይት ያለ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታ እና ጊዜ ለመጀመር ዝግጁነት እንዳለው  መግለጹንም ጠቁሟል። ሆኖም ተቋርጠው የሚገኙ መሠረተ ልማቶችን በተመለከተ የመንግሥታቸውን አቋም ያስታወቁት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፤ ቀደም ሲል አገልግሎት ማስጀመር የሚቻልባቸው ሁኔታ መፍጠር እና የሰላም ንግግር መጀመር ቀዳሚ መሆን አለበት ብለው ነበር። መሠረተ ልማቶች መመለስ እንደ ቅድመ ሁኔታ መወሰድ የለበትም ሲሉ የትግራይ አመራሮች በተደጋጋሚ ሲናገሩም ተሰምተዋል። በተጨማሪም በቅርቡ የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ እና የደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይና የአውሮፓ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦሬል መሠረታዊ አገልግሎቶችን መመለስ ሕይወትን የማዳን ጥያቄ ስለሆነ ክርክርም ሆነ ድርድር የሚደረግበት አይደለም ብለዋል። በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ እና የአውሮፓ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኞች በአዲስ አበባ ካሉ ባለሥልጣናት እንዲሁም ከትግራይ አመራሮች ጋር መሠረታዊ አገልግሎቶች የሚመለሱበትን ሁኔታ ተነጋግረዋል። ልዑካኑ ትግራይ ደርሰው ከመጡ በኋላ በነዳጅ፣ በጥሬ ገንዘብ እና በማዳበሪያ ላይ ተጥሎ ያለው ክልከላ መነሳት አለበት ያሉ ሲሆን፤ በክልሉ ተቋርጠው የሚገኙ መሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሰው ለሚጠግኑ ባለሙያዎች ደኅንነት የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ከትግራይ አመራር ለፌደራል መንግሥት ይዘው መመለሳቸውም ተመልክቷል። ይህንን አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግሥት ቅሬታ ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን፣ ልዑካኑ ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ላይ አተኩረዋል ብሏል። ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበውን የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በድርድር ለመቋጨት የአፍሪካ ኅብረት፣ አሜሪካ እና የተለያዩ አገራት ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል። ባለፈው መጋቢት ወርም የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት አመቺነት የተኩስ አቁም ማወጁን አስታውቆ የህወሐት አመራሮችም ተቀብለውት ተቋርጦ የነበረው የረድኤት አቅርቦት ተጀምሯል ቢባልም በነዳጅ እጥረት ምክንያት መዳረስ እንዳልቻለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል። ሁለቱም ወገኖች ለድርድር ዝግጁ መሆናቸውንና ተደራዳሪ ወገኖችም መሰየማቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም። https://www.bbc.com/amharic/articles/c253y8llleqo +politics ሱዳን ከትንኮሳ በዘለለ የያዘችው ተጨማሪ የኢትዮጵያ ግዛት የለም - መንግሥት ሱዳን እና ኢትዮጵያ በሚወዛገቡበት አልፋሽጋ ድንበር ላይ የደረሰ ጥቃትም ሆነ ተጨማሪ የያዙት ቦታ እንደሌለ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሸን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ለቢቢሲ ገለጹ። የሱዳን ጦር በድንበር ግዛቶች ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ በከባድ መሳሪያና በታገዘና የአየር ጥቃት ከትናንት ጀምሮ ማድረሱ ቢዘገብም አቶ ከበደ ሐሰተኛ መረጃ ነው ሲሉ ውድቅ አድርገውታል። “በእርግጥ ትንኮሳዎች አሉ፤ ከቀናት በፊትም የተፈጸመው ትንኮሳ በሱዳን ኃይል ነው የተጀመረው። በዚህም የአካባቢው ሚሊሻ እርምጃ ወስዶባቸዋል” የሚሉት ባለሥልጣኑ ለደረሰውም የሕይወት መጥፋት መንግሥት ማዘኑን መግለጹን አስታውሰዋል። አቶ ከበደ በድንበር አካባቢ ወደሚገኙት መንደሮች ከባድ መሳሪያ መተኮስና አንዳንድ ትንኮሳዎች ከሱዳን በኩል እንዳሉ አመልክተው፣ የጠፋ የሰው ሕይወትም ሆነ የወደመ ንብረት የለም በማለት በተለያዩ መገና�� ብዙኃን በኩል የተሰራጫው ዜና ሐሰት ነው ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል። የሱዳን ጦር በድንበር ስፍራዎች ላይ በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ጥቃት እየፈጸመ እንደሆነም ሮይተርስ አንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። በዚሁ ዘገባው ላይ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያወዛግባት ድንበር አቅራቢያ ይገኛል ያለውን ጃባል ካላ አል ላባን የተሰኘ ቦታን መቆጣጠሯን አሳውቃለች ብሏል። የሱዳን ጦር በከባድ መሳሪያና በአየር በመታገዝ የተጠቀሰውን ቦታ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሮይተርስ የሱዳንን ወታደራዊ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። በአልፋሽጋ ግዛት ውስጥ የሚገኘው ጃባል ካላ አል ላባን በኢትዮጵያ ጦር ቁጥጥር ስር የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በሱዳን ጦር ቁጥጥር ስር መሆኑንንም የዐይን እማኞች እንደነገሩት የዜና ወኪሉ ገልጿል። ሚኒስትር ዲኤታው አቶ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው ይህንን ውድቅ በማድረግ፣ ሱዳኖች ተጨማሪ የተቆጣሩት የኢትዮጵያ መሬት የለም ብለዋል። ከሱዳን በኩል የሚሰነዘረውን ጥቃትን በተመለከተ ቢቢሲ ያናገራቸው የምዕራብ ጎንደር ዞን የምዕራብ አርማጨሆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ አያና እንዳሉት፣ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ከሚተኮሰው ከባድ መሳሪያ ውጪ የሱዳን ጦር ባለፉት ቀናት የያዘው ተጨማሪ ቦታ እንደሌለ ገልጸዋል። ሱዳን ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ቁጥጥር ስር የነበሩትን ሰፊ ለም የእርሻ መሬቶችን የያዘውን የአልፋሽጋ አካባቢን መቆጣጠሯ ይታወሳል። ከአንድ ዓመት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተቀሰቀሰበት ወቅት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ሱዳን ግዛቷን ወርራ ተቆጣጥራለች በማለት አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ ከእነዚህ ግዛቶች ሱዳን ጦሯን እንድታስወጣ በተደጋጋሚ ብትጠይቅም ሱዳን ግን የቀደሙ ግዛቶቼን ነው ያስመለስኩት በሚል እንደማትወጣ አስታውቃለች። ከቀናት በፊት የሱዳን ጦር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጹት ከሱዳን ግዛት የተወሰዱ ወታደሮቻቸው ወደ ኢትዮጵያ ከተወሰዱ በኋላ ተገድለዋል እንዲሁም አስከሬናቸው በአደባባይ እንዲታይ ተደርጓል ሲል ክስ ማቅረባቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሱዳን ምርኮኞችን በአደባባይ ገድሏል በሚል የሱዳን ጦር ያወጣውን መግለጫ መሰረት የሌለው ነው ሲል ውድቅ አድርጎታል። የመከላከያ ሠራዊት ግጭቱ በተነሳበት ስፍራ እንዳልነበርና የኢትዮጵያን ግዛት ዘልቆ ገብቷል ያለው የሱዳን ኃይል ከአካባቢው ሚሊሻዎች ጋር ተጋጭቷል ሲል ጦሩ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። ሚኒስትር ዲኤታው በበኩላቸው ከቀናት በፊት የሱዳን ጦር የህወሓት ታጣቂዎችን ይዞ ለመግባትና በእነሱ ድጋፍም ለመግባት ተሞክሯል ብለዋል። በዚህም የአካባቢው ሚሊሻዎች መከላከላቸውንና ጥቃትም እንደተፈጸመባቸው አክለው ገልጸዋል። ይህን ክስ አስመልክቶ የትግራይ ክልል ባወጣው መግለጫ “አገዛዙ በአገሪቱ ውሰጥ እየሆነ ካለውን አሳፋሪ ሁኔታ ለመሸፋፈን ትግራይን እንደ መጠቀሚያ አድርጓታል። የሱዳን ኃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በገቡበት ወቅት የትግራይ ኃይሎች ተቀላቅለዋል የሚለው የሰሞኑ ውንጀላም የአገዛዙን ቅዠት የሚያሳይ ነው” ብሏል። በሁለቱ አገራት መካከል ከተከሰተው ውጥረት ጋር ተያይዞ የአፍሪካ ኅብረት ፍጥጫው ወደ ወታደራዊ ግጭት እንዳያመራም ጥሪ አቅርቧል። “ኢትዮጵያ አፍሪካ ውስጥ ባሉ ችግሮች ላይ አፍሪካዊ መፍትሔን ቅድሚያ ትሰጣለች። ለአፍሪካ ኅብረትም ትልቅ ክብር እንዲሁም ታሪካዊ ትስስር አላት። ለአፍሪካውያንና ለአፍሪካ ተቋማት ትልቅ ክብር አለን እንደ አገርም የምንከተለውም መርኅ ነው” ብለዋል አቶ ከበደ። አክለውም “ከሱዳን ሕዝብ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረንና በሰላማዊ መንገድ ችግሮቻችንን ለመፍታት ነው ጥረት እያደረግን ያለነው” ሲሉ የሚያስረዱት ሚኒስትር ዲኤታው የመንግሥታቸው አቋም እንዳልተቀየረም ይናገራሉ። ከሱዳን መንግሥት ጋር ለመነጋገር መንግሥት እያደረገው ያለው ጥረት እንዳለ ከቢቢሲ የተጠየቁት ሚኒስትሩ መንግሥት ችግሮችን በመነጋገር ለመፍታት በተደጋጋሚ ፍላጎቱን መግለጹን አስረድተዋል። “የኢትዮጵያ መንግሥት ከሱዳን ሕዝብ ጋር ምንም አይነት ግጭት ውስጥ መግባት አይፈልግም። ሰላም የመጀመሪያ አማራጩ አድርጓል። በተለያዩ መንገዶች ግንኙነቶች ነበሩ” ብለዋል። የድንበር ግጭት ሲነሳ እንዴት መፈታት እንዳለበት ቀደም ብለው ተስማምተውበት የነበረ ጉዳይ መኖሩን አቶ ከበደ ጠቅሰው ከዚያ ያለፈ የተለየ ነገር የለም ብለዋል። በቀጣይም ኢትዮጵያ የሰላም አማራጭን በዋነኝነት ብታስቀምጥም “ሰላም ስለተፈለገ ብቻ አይመጣም። በአንድ ወገን ብቻ አይረጋገጥም። እኛ ከዚያ አልፎ የሚመጣውን ለመመከትና የአገሪቷን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ በቂ ቁመናና ዝግጅት አለን” ብለዋል። አክለውም “ዝም ብሎ ኢትዮጵያን ገብቶ እንደፈለጉ አድርጎ የሚወጣበት አጋጣሚ አይኖርም። የሕዝቦቿን ደኅንነት ለማረጋገጥ ማንኛውንም እርምጃ በመውሰድ ራሳችንን የመከላከል አቅሙ አለን” ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ እና በሱዳን ኃይሎች መካከል ግጭቶች ባለፉት አስርት ዓመታት የተለመደ ቢሆንም ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ግን እየተባባሰ መጥቷል። በአሁኑ ወቅት ሁለቱ አገራት በጋራ ድንበራቸው አቅራቢያ ባለው አል ፋሻጋ ለም የእርሻ ቦታ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ውጥረት ነግሷል። በአውሮፓውያኑ 2008 በሁለቱ አገራት መካከል የተፈረመ ስምምነት ቢኖርም የሁለቱን አገራት ግጭት ማስቆም አልቻለም ። ኢትዮጵያ እና ሱዳን በአባይ ወንዝ ላይ በሚገነባው ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይም ውዝግብ ውስጥ ናቸው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c88w766gjz1o +politics አርሚን ላሼት የአንጌላ መርክል ሲዲዩ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ አርሚን ላሼት የጀርመኗ መራሔተ መንግሥት አንጌላ መርክል ፓርቲ ለሆነው ክርስቲያን ዲሞክራት ሕብረት [ ሲዲዩ] ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ። የሰሜን ርሂን ውስትፓሊያ ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ላስሼት ቨርቹዋል በተካሄደ የፓርቲው ስብሰባ ነው ሁለት ተፎካካሪያቸውን ያሸነፉት። 16 ዓመታት ሥልጣን ይዘው የቆዩት አንጌላ መርክል በመጭው መስከረም ወር ሥልጣናቸውን ሲለቁ ለመተካት ጥሩ አቋም ላይ ይገኛሉም ተብሏል። ይሁን እንጂ የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ተከትሎ በርካታ ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች ይገጥሟቸዋል። የ59 ዓመቱ ላሼት ወግ አጥባቂውን የቢዝነስ ሰው ፍሬድሪክ መርዝ 521 በሆነ ድምፅ ያሸነፉ ሲሆን፤ ሦስተኛው እጩ ኖርበርት ሮትገን ደግሞ በመጀመሪያው ዙር ውድድር ተሰናብተዋል። በዚህም መሠረት ላሼት ከሁለት ዓመታት በፊት የተሾሙትን የፓርቲው መሪ የነበሩትን አኔግሬት ክራምፕ ካሬንቦርን ይተካሉ። ጀርመን መስከረም ላይ ምርጫ የምታካሂድ ሲሆን፤ የሲዲዩ ፓርቲ ሊቀመንበር ለመራሔ መንግሥትነት እጩ ተወዳዳሪ ለመሆን ምንም ዋስትና የለውም። የላሼት ምክትሎች ሆነው ከተመረጡት አንዱ የጤና ሚኒስትር ጀንስ ስፓን እና የሲዲዩ ባቫሪያን እህት ፓርቲ ሲኤስዩ መሪ ማርከስ ሶደርም ኃላፊነቱን ስለመፈለጋቸው ባይገልፁም፤ ወደ ውድድሩ ቀለበት ግን መግባት ችለዋል። የመጨረሻው ውሳኔያቸው በመጪው ፀደይ ወቅት ይታወቃል ተብሏል። ላሼት የአንጌላ መርክል ታማኝ ደጋፊ ናቸው። https://www.bbc.com/amharic/news-55693637 +politics የሙሴቬኒ ልጅ የሆኑት የኡጋንዳ ጦር ከፍተኛ መኮንን አዲስ አበባ ገ�� የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ የሆኑት የአገሪቱ ጦር ከፍተኛ የጦር መኮንን ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ አዲስ አበባ ገቡ። የኡጋንዳ የምድር ጦር አዛዥ የሆኑት ጄኔራል ሙሆዚ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ጄኔራሉ አዲስ አበባ ሲደርሱ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት አቶ ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከጄኔራሉ በተጨማሪ የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኦኬሎ ኦሪየም እና ሌሎች የደኅንነትና ወታደራዊ ከፍተኛ አመራሮች አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ የኡጋንዳ መገናኛ ብዙኃን ጄኔራሉ ወደ አዲስ አበባ የተጓዙት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበላቸውን ግብዣ ተከትሎ ነው ሲሉ ዘግበዋል። ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚገናኙም በስፋት ተዘግቧል። ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው የኢትዮጵያ እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በሚለጥፏቸው ጽሑፎች ብዙ አነጋጋሪ ናቸው። አባታቸውን ሊተኩ ይችላሉ የሚባሉት የ48 ዓመቱ ጎልማሳ፣ በአንድ ወቅት ጡረታ ልወጣ ነው ካሉ በኋላ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆነው ነበር። ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ጥብቅ ግንኙነት ያላቸው አገራት ሲሆኑ በተለይ ከአባይ ወንዝ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፣ ኢትዮጵያ በውሃው የመጠቀም መብቷን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በይፋ ድጋፋቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም። ባለፈው ሳምንትም ታንዛኒያ ውስጥ በተካሄደው የአባይ ተፋሰስ አገራት የውሃ ሚንስትሮች ስብሰባ ላይ ሱዳንና ግብፅ እስካሁን ያልፈረሙትን የተፋሰሱ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በቶሎ እንዲያጸድቅ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ጥሪ ማድጋቸው ተዘግቧል። ጄኔራል ሙሆዚ ከዚህ ቀደም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ጦርነት ውስጥ ያሉትን የትግራይ ኃይሎች በመደገፍ በትዊተር ገጻቸው ላይ መልዕክታቸውን ማስቀመጣቸው ብዙዎችን አነጋግሮ ነበር። ጄኔራሉ የኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት አንድ ዓመት በደፈነበት ጥቅምት 2014 ዓ.ም. ላይ የትግራይ ኃይሎችን ደግፈው ትዊት አድርገው ነበር። “የትግራይ መከላከያ ኃይሎች . . . የቆማችሁበትን ዓላማ እደግፋለሁ። የትግራይ እህቶቻችንን የደፈሩ እና ወንድሞቻችንን የገደሉ መቀጣት አለባቸው” ሲሉ ጽፈው ነበር። ይህን የጀነራል ሙሆዚ ትዊት ተከትሎ የኡጋንዳ መንግሥት አስተያየቱ የጄኔራሉ እንጂ የጦሩን አቋም አይወክልም የሚል ማስተባበያን ሰጥቶ ነበር። የኡጋንዳ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ብሪክ ፌሊክስ ኩላይግዬ የጄኔራሉ ትዊት የኡጋንዳ ሕዝቦች መከላከያ ኃይሎችን አይወክልም ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ቃል አቀባዩ አክለውም፣ አስተያየቱ የተሰጠው ከጄኔራሉ እንጂ ከአገሪቱ ጦር ስላልሆነ የአገሪቱን አቋም አያንጸባርቅም ብለዋል። ምንም እንኳ የኡጋንዳ ጦር ይህ አመለካከት የጄኔራሉ እንጂ ጦሩ አይደለም ይበል እንጂ፣ ጄኔራሉ የትግራይ ኃይሎችን ደግፈው ያኖሩት ልጥፍ ለውጥ ሳይደረግበት አሁን ድረስ በገጻቸው እንዳለ ይገኛል። ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ ለትግራይ ኃይሎች ድጋፋቸውን ሰጥተው ይጻፉ እንጂ በሌላ ወቅት ደግሞ ‘ከወንድሜ’ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ችግር የለብኝም ብለው ጽፈዋል። “ከወንድሜ የተከበሩ ዐቢይ አሕመድ ጋር ችግር ኖሮኝ አያውቅም፤ እንደውም አከብራቸዋለሁ። የምንፈልገው በኢትዮጵያ ሰላም እንዲኖር ነው” በማለት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፎቶግራፍ አያይዘው ትዊት አድርገው ነበር። በቅርቡም አንድ ሪፖርትን ተክትሎ የኡጋንዳ ሠራዊት የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ���ግራይ (ህወሓት) አባላትን በማሰልጠን ኢትዮጵያን ለማናጋት እየሰራ ነው የሚል ክስ ቀርቦበት ነበር። ነገር ግን የኡጋንዳ ጦር ሠራዊት ቃል አቀባይ ብርጋዲየር ፌሌክስ ኩላዬጊዬ ከጥቂት ሳምንት በፊት በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ላይ፣ ኡጋንዳ የኢትዮጵያን ሰላም ለማናጋት ጥረት እያደረገች ነው የሚለው ክስ ፍጽም ፈጠራ ነው ሲሉ አጣጥለውታል። ይህንን ክስ የተመለከተው ዝርዝር ጽሁፉ መቀመጫው ኒውዚላንድ በሆነ የበይነ መረብ ገጽ ላይ የወጣ ሲሆን፣ ጽሁፉ ህወሓትን በተመለከተ የሚካሄደውን ሥራ የሚያስተባብሩ ናቸው የተባሉ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና ሌሎች የደኅንነት ኃይሎች አባላትን ስም ዝርዝር ይዟል። በዘገባው ላይ ስማቸው ከተጠቀሱት የኡጋንዳ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች መካከልም የፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ እና የአገሪቱ የምድር ጦር ጠቅላይ አዛዥ የሆኑት ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ ይገኙበታል። የወጣው ሰነድ ጨምሮ እንደሚያመለክተው ከ4,000 በላይ የህወሓት ተዋጊዎች ኡጋንዳ ውስጥ በሚገኙ በአራት የማሰልጠኛ ጣቢያዎች ውስጥ ለወታደራዊ ሥልጠና መግባታቸውን አመልክቶ ነበር። የኡጋንዳ ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዲየር ፌሌክስ ኩላዬጊዬ፣ በዚህ ጉዳይ ውስጥ ኡጋንዳና ደቡብ ሱዳን በጋራ እየሰሩ ነው የሚለው ክስም ሐሰት ነው ብለዋል። ጄኔራል ሙሆዚ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ለዲፕሎማሲያዊ ሥራዎች ወደ ጎረቤት አገራት በአባታቸው ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ይላካሉ። ኡጋንዳ እና ሩዋንዳ ለሦስት ዓመታት ድንበራቸውን እንዲዘጉ ያስገደዳቸውን አለመግባባት ለመፍታት ወደ ኪጋሊ የተጓዘውን ልዑክ ጄኔራሉ መርተውት ነበር። እንዲሁም ለኬንያው ተሰናባች ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ልዩ መልዕክት ለማድረስ በሙሴቪኒ ወደ ናይሮቢ ተልከው ነበር። በኡጋንዳ ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑት ጄኔራሉ አገሪቷን ወክለው ወደ ጎረቤት አገራት ለዲፕሎማሲያዊ ሥራዎች መጓዛቸውን እና በፍጥነት የሚያገኟቸውን እድገቶች ከግምት በማስገባት፤ ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ልጃቸውን ለመንበረ ሥልጣን እያዘጋጁ መሆኑን ያሳያል የሚሉ በርካቶች ናቸው። የ48 ዓመቱ ጀነራል የተወለዱት ከሙሴቬኒ እና ከእአአ 2016 ዓ.ም. የትምህርት ሚኒስትር ከሆኑት እናታቸው ጃኔት ሙሴቬኒ ነው። እአአ 1974 በታንዛኒያ የተወለዱት ሙሆዚ፤ ፖለቲካ ሳይንስ የናይትድ ኪንግደም ውስጥ የተማሩ ሲሆን እአአ 1999 ላይ የአገሪቱን ጦር ተቀላቅለዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c1ezjqv13d7o +sports ለጭቁኖች ተቆርቋሪው የክፍለ ዘመኑ ታላቅ የእግር ኳስ ጥበበኛ ዲያጎ ማራዶና "አንፀባራቂ ስብዕና፣ ድንቅ ችሎታ፣ የላቀ አእምሮ፣ ተናዳጅ፣ ቁጡ፣ ለተጨቋኞች አዛኝ፣ እብሪተኛ ሌላም ሌላም. . . በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የእግር ኳሱ ሊቅ ዲያጎ ማራዶና በህይወት እያለ ይሰጠው የነበሩ ስሞች ናቸው - የዓለማችን የእግር ኳስ ጀግና። ለእግር ኳስ የተፈጠረ ነው የሚባልለት አርጀንቲናዊው ማራዶና ለየት ያለ ድንቅ ችሎታን፣ ራዕይና ፍጥነትን ቀልብ ከመሳብ ጋር በማጣመር በርካታ አድናቂዎቹን አስደምሟል። ""የአምላክ እጅ"" ተብሎ በሚጠራው አወዛጋቢ ጎል፣ በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ መዘፈቁና ሌሎች ከግል ህይወቱ ጋር በተያያዘም ደጋፊዎቹ የተመሳቀለ እይታ እንዲኖራቸው አድርጓል። በአሁኑ ወቅት ጣልያንን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ያሉ አድናቂዎቹ እየዘከሩት ሲሆን በተለይም በፍልስጥኤማውያን ዘንድ ታላቅ ቦታ አለው። በርካታ ጊዜያትም ""ልቤም ሆነ ውስጤ ፍልስጥኤማዊ ነው"" ሲል የተሰማው ማራዶና ""ጭቆናን እናውቃለን"" በማለትም እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ለፍልስጥኤም ያለውን ድጋፍ አሳይቷል። አጭርና ጣፋጭ ህይወት- የእ���ር ኳሱ ሊቅ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና የተወለደው በአርጀንቲናዋ፣ ቦነስ አይረስ የድሆች መንደር ውስጥ ከዛሬ 60 ዓመት በፊት ነበር። የእግር ኳስ ፍላጎቱም የተጠነሰሰው ገና በታዳጊነቱ ሲሆን፤ በእግር ኳስ ታሪክ ታላቅ ቦታ ላይ መድረስ ችሏል። አንዳንዶችም ከታላቁ የብራዚል እግር ኳስ ተጫዋች ፔሌ ያስበልጡታል። ማራዶና በ491 ጨዋታዎች 259 ጎሎችን በማስቆጠል የደቡብ አሜሪካ ተቀናቃኙን ፔሌን በመብለጥ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ ተጫዋች መሆን ቢችልም፤ ወደ በኋላ እግር ኳስን በበላይነት የሚያስተዳድረው ፊፋ የምርጫ ሕጉን በመቀየሩ ሁለቱም የክፍለ ዘመኑ ምርጥ በመሆን ተሰይመዋል። በእናቱ ማህፀን እግር ኳስን የለመደ ይመስል ማራዶና ገና በህፃንነቱ ነበር የላቀ ችሎታውን ማሳየት የጀመረው። ሎስ ሴቦሊታስ የተባለ የታዳጊዎች ቡድንን በመምራት በ136 ጨዋታዎች ባለመሸነፍ አይበገሬነቱን አሳይቷል። የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ህይወቱንም የጀመረው በ16 ዓመቱ አካባቢ ነው። አጠር ብሎ ደንደን ያለ ሰውነት ያለው ማራዶና ቁመቱም 1.65 ሜትር ነው። ሲታይ የተለመደው አይነት የስፖርተኛ ሰውነት የለውም። ነገር ግን ቀልጣፋነቱ፣ ነገሮችን ቀድሞ የመረዳት ችሎታው፣ የኳስ ቁጥጥሩ፣ ኳስ ማንቀርቀብና ቶሎ ማሳለፍ መቻሉ ላለመረጋጋቱና ብዙ ጊዜ የሚያጋጥመውን የክብደት ችግሩን አካክሶለታል። ምንም እንኳን የተቀናቃኝ ቡድንን ተከላካዮች በቀላሉ ማለፍ ቢችልም ማራዶና በግል ህይወቱ ራሱን በርካታ ጊዜ ችግር ውስጥ ተዘፍቆ አግኘቶታል። የአምላክ እጅና የክፍለ ዘመኑ ጎል ማራዶ ለአገሩ በተሰለፈባቸው 91 ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ላይ 34 ጎል አስቆጥሯል። ነገር ግን ይህ ምናልባት ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ጨዋታ ታሪኩ ውስጥ ከወንዝ ውሃን በማንኪያ እንደ መጨለፍ የሚቆጠር ነው። በጎሮጎሳውያኑ በ1986 ሜክሲኮ ላይ በተደረገው የዓለም ዋንጫ ብሔራዊ ቡድኑን የመራው ማራዶና ከአራት ዓመታት በኋላም አገሩን ለመጨረሻ ዙር አደረሳት። በተለይም በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ የተከሰተው ውዝግብ የማራዶና መታወቂያ ሆነ። በወቅቱ አርጀንቲናና እንግሊዝ ያደርጉት ጨዋታ እግር ኳስ ብቻ አልነበረም፤ ፖለቲካም የተቀላቀለበት ነበር። ከውድድሩ ከዓመታት በፊት ለአስር ሳምንታት ያህል ፎክላንድስ ተብላ በምትጠራው ደሴት ምክንያት አርጀንቲና ከእንግሊዝ ጋር ጦርነት ገጥማ ነበር። በጨዋታው ላይ ሁለቱም የውጊያው መንፈስ ሳይለቃቸው ወደ ሜዳ ገብተው በእግር ኳሱም ላይ ይሄው የፀበኝነት ስሜት ነበር የተንፀባረቀው። ለ51 ደቂቃዎችም ያህል ያለ ምንም ጎል ጨዋታው ሲካሄድ ቆይቶ በድንገት ማራዶና ከግብ ጠባቂው ፒተር ሺልተን ጋር ዘሎ የተሻማትን ኳሷን በተቃራኒው መረብ አስቆጠረ። ማራዶና ከጨዋታው በኋላም ግቧ እንዴት እንደተቆጠችረ በተናገረበት ወቅት በጎሉ ውስጥ ""ማራዶና ትንሽ ነበረበት፤ የአምላክም እጅ በትንሹ ነበረበት"" በማለት ተናገረ። በዚሁ ጨዋታ ላይ ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ብዙዎች 'የክፍለ ዘመኑ ጎል' ብለው የጠሩትን ግብ አስቆጠረ። የተቀናቃኙን ቡድን አባላት እጥፍጥፍ አድርጎ፤ ሜዳው ላይ ብቻውን ያለ ሰው ይመስል፤ ጎሏን አስቆጠረ። ""ድንቅ ጎል ነበረች። የእግር ኳስ እልቅና የታየበት፤ የሚገርም ነው"" በማለት የቢቢሲው ዘጋቢ ቤሪ ዴቪስ ተናግሯል። በጨዋታው እንግሊዝ አንድ ጎል ብታስቆጥርም፤ አርጀንቲና 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። ለማራዶና ማሸነፉ ከጨዋታው፤ ከእግር ኳስም በላይ ነበር ""እንግሊዞችን መዘረር"" ፖለቲካዊ ድልም ነበረው። የናፖሊው ጀግና- በአደንዛዥ እፅ መዘፈቅ የዓለም አቀፍ የዝውውር ክብረ ወሰንን ማራዶና ሁለት ጊዜ መስበር ችሏል። በአገሩ ሲጫወትበት ከነበረው ቦ��� ጁኒየርስ ወደ ስፔኑ ባርሴሎና በጎሮጎሳውያኑ 1982 ሲዛወር በ3 ሚሊዮን ፓውንድ ነበር። ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ ወደ ጣልያኑ ክለብ ናፖሊም በ5 ሚሊዮን ፓውንድ ተዛወረ። በጣልያኗ ሳን ፓውሎ ስታዲየም በሄሊኮፕተር ሲያርፍም 80 ሺህ አድናቂዎቹና ወዳጆቹ ተገኝተው ነበር- አዲሱን ጀግና ለመቀበል። ይህም በእግር ኳስ ታሪኩ ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገበት ወቅት ነው። ክለቡ በ1987 እና በ1990 የሊጉ አሸናፊ እንዲሆን እንዲሁም የአውሮፓ ሊግ ዋንጫን በ1989 እንዲያነሳም ቀዳሚውን ሚና የተጫወተው ማራዶና ነው። የመጀመሪያውን ድል በማስመልከት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች በጎዳናዎች ላይ በመውጣት ለአምስት ቀናት ያህል ደስታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ወቅት ማራዶና የሁሉንም ትኩረት ሳበ የሚጠበቅበትም ኃላፊነት ከፍተኛ ሆነ። ይህ ደግሞ ጫናንና መጨናነቅን አስከተለ። ""ታላቅ ከተማ ናት ግን መተንፈስ እንኳን አልቻልኩም። ነፃ ሆኜ በመንገዶች ላይ መረማመድ እፈልጋለሁ። እኔም እንደ ሌላው ሰው ነኝ"" ብሏል በወቅቱ። ከጣልያኑ የካሞራ ማፊያ ቤተሰብ ጋር ግንኙነት አለው በሚል፣ የኮኬይን አደንዛዥ እፅ ሱስ ውስጥ መዘፈቅና ከልጅ ማደጎ ጋር በተፈጠረ እሰጣገባም ጋር ስሙ በተደጋጋሚ መነሳት ጀመረ። በጎርጎሳውያኑ በ1990 ጣልያን ላይ በተዘጋጀው የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በጀርመን 1 ለ 0 አገሩ አርጀንቲና መሸነፏን ተከትሎ እንዲሁም በቀጣዩ ዓመትም በተደረገለት ምርመራ አደንዛዥ እፅ መጠቀሙ በመታወቁ ለ15 ወራት እንዲታገድ ምክንያት ሆነ ። ከዚህ ሁሉ አገግሞና ራሱን አድሶ በጎሮጎሳውያኑ 1994 አሜሪካ ላይ ወደ ተካሄደው የዓለም ዋንጫ ቢመለስም ጎል አስቆጥሮ ደስታውን የገለፀበት መንገድ ያልተለመደና በርካቶችንም ያስደነገጠ ነበር። ማራዶና የታገደውን ኤፊድሪን የተባለ የተከለከለ አበረታች መድኃኒት ወስዶ በመገኘቱ ከውድድሩ እንዲወጣ ተደረገ። ህይወት ከጡረታ በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ አበረታች እፅ በደሙ ውስጥ ከሦስት ዓመት በኋላ መገኘቱን ተከትሎ በ37 ዓመቱ ከእግር ኳስ ጨዋታዎች ራሱን አገለለ። ነገር ግን ተጫዋቹን ችግሮች አልለቀቁትም። በጋዜጠኞች ላይ ተኩሷል በሚልም ሁለት ዓመት ከአስር ወራት እስር ቢፈረድበትም በማስጠንቀቂያ ታልፏል። የኮኬይንና የአልኮል መጠጡም የጤና እክል አስከትሎበታል ተብሏል። በከፍተኛ ሁኔታም ኪሎው የጨመረ ሲሆን፤ በአንድ ወቅት 128 ኪሎ ግራምም ይመዝን ነበር። በጎሮጎሳውያኑ 2004 በልብ ህመም ምክንያት ፅኑ የህሙማን ክፍል ውስጥ ገብቶም ነበር። ማራዶና ክብደቱን ለመቀነስ ቀዶ ህክምና ያደረገ ሲሆን ከአደንዛዥ ዕፅ ሱስም ለመላቀቅ ኩባ መኖር ጀመረ፤ የቀድሞውን የኩባ መሪና ሶሻሊስትና የነፃነት ታጋይ ፊደል ካስትሮንም አግኝቷቸው ነበር። ከዚህ ሁሉ በኋላ በጎሮጎሳውያኑ 2008 የአርጀንቲና ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣን ሆነ። በዚያው ዓመትም በነበረው የዓለም ዋንጫ አገሩ ለሩብ ፍፃሜ የበቃች ቢሆንም በጀርመን 4 ለ 0 ከተሸነፈ በኋላ ከቡድኑ ጋር የነበረው የሁለት ዓመት ቆይታ ተቋጫ። ውሻው ሻሪ ፔይ ከንፈሩን ነክሳው ቀዶ ህክምና ማድረጉ፣ ከትዳሩ ውጭ ለወለደው ለዲያጎ አርማንዶ ጁኒየር እውቅና መስጠቱም ስሙ ከየመድረኩ እንዳይጠፋ አደረገው። ከሁለት ዓመት በፊት ሩሲያ በተደረገው የዓለም ዋንጫ አርጀንቲናና ናይጄሪያ ባደረጉት ጨዋታ ላይ ተገኝቶ የነበረው ማራዶና የብዙዎች መነጋገሪያነት ሆኖ ነበር። ከናይጄሪያ ደጋፊ ጋር አብሮ መደነሱ፣ ከጨዋታው በፊት ወደ ሰማይ አንጋጦ ያደረገው ፀሎት፣ ሊዮነል ሜሲ ጎል ሲያስቆጥር በከፍተኛ ሁኔታ መደሰቱ፣ መሃል ላይ መተኛቱ እንዲሁም አርጀንቲና ሁለተኛ ጎል ስታስቆጥር የመሃል ጣቱን ሁለት ጊዜ ማ��የቱ ለሚዲያዎች ትኩስ ወሬ ነበር። ማራዶና ባለ ብዙ ስሙ፣ ለተጨቋኞች አዛኝ፣ አዝናኝ፣ ታላቅ፣ ቁጡ፣ የሚያዋርድና ሌሎች የተባለው ታላቁ እግር ኳሰ ተጨዋች ይህችን ዓለም ቢሰናበትም ህይወቱን የኖረበት መንገድ ለወደፊት ትውልድ የሚዘከረው፣ በእግር ኳስ ችሎታው የማይሞት ስምና አሻራ ትቶ አልፏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55089960 +health ኮሮናቫይረስ፡ የላቲን አሜሪካው ቁጥር-1 ቢሊዮነር በኮቪድ ተያዙ በመላው ላቲን አሜሪካ የናጠጡ ሀብታም የሚባሉት ካርሎስ ስሊም በኮቪድ ተህዋሲ መያዛቸው ታወቀ፡፡ የ80 ዓመቱ ቢሊዮነር ካርሎስ ሜክሲኳዊ ሲሆኑ በቴሌኮሚኒኬሽን ቢዝነስ እውቅ ናቸው፡፡ ለጊዜው መጠነኛ የኮቪድ ምልክቶችን ብቻ እያሳዩ ነው ተብሏል፡፡ ልጃቸው በትዊተር ሰሌዳው እንደጻፈው ‹አባቴ ደህና ነው አታስቡ› ብሏል፡፡ የቢሊየነሩ በኮቪድ መያዝ ዜና የተሰማው የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት የ67 ዓመቱ አንድሬስ ማኑል ሎፔዝ ኦብራዶር በኮቪድ መያዛቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሜክሲኮ ከዓለም አገራት ክፉኛ በኮቪድ ከተጎዱ አገራት ተርታ የምትመደብ ናት፡፡ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በተህዋሲው የተያዙ ሲሆን 150ሺህ ዜጎች ደግሞ ሕይወታቸው በዋዛ አልፏል፡፡ ዛሬ ሰኞ የካርሎስ ስሊም ልጅ ዶሚት ካርሎስ ስሊም እንደጻፈው ‹አባቴ ለአንድ ሳምንት መጠነኛ ምልክቶችን ካሳየ በኋላ አሁን ሻል እያለው ነው፤ ለውጥ አለው›› ብሏል፡፡ ቢሊየነሩ ካርሎስ ስሊም ዋንኛውን የሜክሲኮ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሰጪ፣ ሞቪል ኩባንያን በባለቤትነት ያስተዳድራሉ፡፡ ፎርብስ መጽሔት የዚህ ቴሌኮም ኩባንያቸው ግምት 52 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል ሲል ገምቶታል፡፡ ሜክሲኮ አሁን ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ በመስፋፋቱ በዋና ከተማዋ ሜክሲኮ ሲቲ ሆስፒታሎች እየሞሉ ነው ብሏል በሜክሲኮ የቢቢሲ ዘጋቢ ዊል ግራንት፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ ያገኛቸውና አሁን ከቤታቸው ሆነው ሥራ እየሠሩ ያሉት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሎፔዝ ኦብራዶር የሩሲያ ሠራሹን ስፑትኪን ክትባትን ወደ አገራቸው ለማስገባት ከፑቲን ጋር እንደተነጋገሩ ተዘግቧል፡፡ በዚህም መሠረት 24 ሚሊዮን ጠብታዎች በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ሜክሲኮ ይደርሳሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-55807195 +sports የሜዳ ቴኒስ ኮከቡ ኖቫክ ጆኮቪች አውስትራሊያ እንዳይገባ ተከለከለ "የሜዳ ቴኒስ ኮከቡ ኖቫክ ጆኮቪች ወደ አውስትራሊያ ሊገባ ያደረገው መኩራ ሜልቦርን ከደረሰ በኋላ በተፈጠረ ግርግር ምክንያት ከሽፎበታል። የዓለም ቁጥር አንድ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ጆኮቪች በከተማዋ አየር ማረፊያ ለሰዓታት ከተንገላታ በኋላ ወደ አውስትራሊያ ለመግባት የሚስችለውን ቅደመ ሁኔታ አሏማላም ተብሎ ወደመጣበት እንዲመለስ ታዟል። ጆኮቪች በተደጋጋሚ መንግሥት ወዳሰናዳው ማቆያ ሆቴል እየገባ እየወጣ ሂደቱን በመከታተል ላይ ይገኛል። ይህ የኮከቡና የአውስትራሊያ መንግሥት ግርግር ዜና የተሰማው ጆኮቪች አውስትራሊያ ኦፕን በተሰኘው ውድድር ላይ ሊሳተፍ ባቀደበት ወቅት ነው። ጆኮቪች ወደ ሜልቦርን እንዳይገባ የተከለከለው ምናልባት ክትባት ስላልወሰደ ነው የሚሉ መላ ምቶች እየተሰሙ ነው። ምንም እንኳ የሜ ዳቴኒስ ተጫዋቹ ይከተብ አይከተብ ይፋ ባያደርግም የክትባቱ ደጋፊ እንዳልሆነ ባለፈው ዓመት ጠቆም አድርጎ ነበር። ቴኒስ አውስትራሊያ እንዳለው ችግሩ የተፈጠረው ጆኮቪች ረቡዕ ዕለት ከዱባይ በመጣበት ወቅት ነው። የአውስትራሊያ ድንበር ጥበቃ ባወጣው መግለጫ ""ጆኪቪች ወደ አውስትራሊያ ለመግባት የሚያስችለውን ቅደመ ሁኔታ አሏማላም፤ በዚህም ምክንያት ቪዛው ተሰርዞበታል"" ብሏል። ""ትክክለኛ ቪዛ ያልያዙ አሊያም ቪዛቸው የተሰረዘባቸው የአውስትራሊያ ዜጎች ���ልሆኑ ሰዎች በቁጥጥራችን ሥር ውለው ከአውስትራሊያ ይወገዳሉ"" ይላል መግለጫው አክሎ። የቪክቶሪያ ግዛት ጊዜያዊ ስፖርት ሚኒስትር ግዛታቸው በጆኮቪች የቪዛ ሂደት ጣልቃ እንደማትገባ አስታውቀዋል። የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ጆኮቪች ተነጥሎ በደል ደርሶበታል መባሉን አጣጥለው ማንም ከሃገሪቱ ሕግ በላይ አይደለም ብለዋል። ሐሙስ ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ሞሪሰን ለጆኮቪች የተለየ የሕክምና ይለፍ እንዳልተሰጠውና የቀረበው ማስረጃ በቂ እንዳልሆነ ተናግረዋል። የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ጆኪቪች ጉዳዩን በሕግ ይዞት አሊያም ድጋሚ ለቪዛ አመልክቶ ሊገባ እንደሚችል ዘግበዋል። ሮይተርስ የዜና ወኪል ደግሞ ተጫዋቹ ከአየር ማረፊያው ሜልቦርን ወደሚገኝ ከዚህ በፊት የኮቪድ-19 ማገገሚያ ሆኖ ሲያገለግል ወደነበር ማቆያ ተወስዶ ነበር ሲል ፅፏል። የአውስትራሊያ ጤና ሚኒስትር ጆኮቪች ላይ የደረሰው ""ቆራጥ"" ውሳኔ ቢሆንም ""ትክክል"" ነበር ሲሉ ሞግተዋል። የቴኒስ ኮከብ አውስትራሊያ ውስጥ መንገላታት የሃገሩ ሰርቢያ ልጆችን አስቆጥቷል። አባቱ ስርጃን ጆኮቪች ልጃቸው አየር ማረፊያ ውስጥ በፖሊስ ተከቦ እንዳለ ተናግረው ነበር። ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ቩቺች ኮከቡ ""የጥቃት ሰለባ"" ሆኗል ብለው ሁሉም ሰርቢያዊ ከተጫዋቹ ጀርባ እንደሆነ ተናግረዋል። አውስትራሊያ ጥብቅ በሆነው የኮቪድ-19 ደንብ ትታወቃለች። ከሃገሪቱ ሕዝብ 90 በመቶ ከ16 ዓመት በላይ ያሉ ዜጎች ሙሉ በሙሉ ተከትበዋል። እንዲያም ሆኖ አንዳንድ ሰዎች ከግዛት ግዛትም ሆነ ከሃገር ውጭ መብረር አይችሉም። በርካታ አውስትራሊያውያን ከዚህ በፊት መንግሥት ታዋቂና ሃብታም ሰዎች እንደልብ እንዲገቡ እንዲወጡ እየፈቀደ ነው ሲሉ ወቀሳ ያሰሙ ነበር። ጆኮቪች ዘጠኝ ጊዜ ዋንጫውን ያነሳው የአውስትራሊያ ኦፕን የሜዳ ቴኒስ ውድድር በፈረንጆቹ ጥር 17 በሜልቦርን አዘጋጅነት ይጀመራል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59890972 +sports ኢትዮጵያውያን የደመቁበት የቶኪዮ ኦሎምፒክ ማጣሪያ በኔዘርላንድስ ሄንግሎ በተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ማጣሪያ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልኡካን ቡድን እሁድ ምሽት ወደ ውድድር ስፍራው ተጉዞ ውድድሮችን አካሂዷል። በዚህ በሄንግሎ በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር በቶኪዮ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ከ800 ሜትር እስከ 10 ሺህ ሜትር እንዲሁም 3000 ሜትር መሰናክልን ጨምሮ በአምስት ውድድሮች በሁለቱም ፆታ አገራቸውን የሚወክሉ አትሌቶች በውጤታቸው መሰረት ተሰላፊዎቹና ተጠባባቂዎቹ ይለያሉ፡፡ በዚህም መሰረት በ10 ሺ ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ከሁለት ቀናት በፊት በሲፋን ሀሰን ተሰብሮ የነበረውን የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር አሸናፊ መሆን ችላለች። ለተንሰበት ውድድሩን በ29 ዲቂቃ ከ1.03 ሰከንድ በመግባት አጠናቃለች። ለተንሰንበትን ተከትላ ሁለተኛ የወጣችውን ፅጌ ገብረሰላማን ደግሞ ከአንድ ደቂቃ በላይ በሆነ ሰዓት ነው ቀድማ ውድድሯን የጨረሰችው። በአጠቃላይ ከአንድ እስከ አምስት ያለውን ቦታ የያዙት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ጸሀይ ገመቹ ሶስተኛ፣ የዓለምዘርፍ የኋላው አራተኛ እንዲሁም ቦሰና ሙላቴ አምስተኛ ሆነው ማጠናቀቅ ችለዋል። ከስድስተኛና ስምንተኛ ደረጃዎች ውጪ ደግሞ እስከ 14ኛ ደረጃዎችን አሁንም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እንደያዙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያሳያል። በወንዶች 10ሺህ ሜትር ማጣሪያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ አራተኛ ደረጃ የያዙ ሲሆን አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ26 ደቂቃ 49 ሰከንድ ከ51 ማይክሮሰከንድ በሆነ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል። እሱን በመከተል ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ሀጎስ ገብረህይወት ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። በሴቶች 5 ሺ ሜትር ማጣሪያም ቢሆን የኢትዮጵያውያን የበላይነት የታየበት ነበር። ከአንድ እስከ ስምንተኛ ያሉትን ደረጃዎች ኢትዮጵያውን የተቆጣጠሩት ሲሆን አትሌት ጉድፍ ጸጋዬ ውድድሩን በ14 ደቂቃ 13 ሰከንድ 32 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰአት በአንደኝነት ጨርሳለች። እሷን በመከተል አትሌት እጅጋየሁ ታዬ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ ሶስተኛ ሆነው ጨርሰዋል። ፋንቱ ወርቁ፣ መስከረም ማሞ፣ ፋንታዬ በላይነህ፣ ሀዊ ፈይሳ እና ሚዛን ዓለም ደግሞ እስከ ስምነተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። በወንዶች 5 ሺ ሜትር ማጣሪያ አትሌት ጌትነት ዋለ ውድድሩን በ12 ደቂቃ 53 ሰከንድ 28 ማይክሮ ሰከንድ አሸናፊ ሆኗል። ከሁለተኛ እስከ ስድስተኛ ያለውን ደረጃም ቢሆን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተቆጣጥረውታል። በዚህም መሰረት ንብረት መላከ፣ ሚልኬሳ መገሻ፣ ሙክታር ድሪስ፣ ያሲን እና ሰለሞን በሪሁ ከሁለት እስከ ስድስት ያሉትን ቦታዎች ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል። በሴቶች 800 ሜትር በተካሄደው ማጣሪያም ቢሆን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሰባተኛ ያሉትን ቦታዎች ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል። በዚህም አትሌት ወርቅውሃ ጌታቸው ውድድሩን በ2 ደቂቃ ከ20 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰአት ጨርሳለች። ከሁለተኛ ጀምሮ ቀጣዮቹን ደረጃዎች የያዙት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደግሞ ሀብታም ዓለሙ፣ ወርቅነሽ መሰለ፣ ነጻነት ደስታ፣ ማህሌት ሙሉጌታ፣ አያል ዳኛቸው እና ቅሳነት ዓለም ናቸው። በወንዶች 800 ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሁለተኛ እስከ ስድስተኛ ያለውን ቦታ ይዘው ነው ያጠናቀቁት። የሞሮኮው ኤልሀሳኔ ሙጃሂድ አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀ ሲሆን አትሌት ባጫ ዋርካ ደግሞ የሁለተኛ ደራጃውን ይዞ ጨርሷል። ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ተማም ቱራ፣ አዲሱ ግርማ እና ኤፍሬም መኮንን ከሶስት እስከ ስድስት ያለውን ቦታ ይዘዋል። በሴቶች 1500 ሜትር አሁንም የበላይነታቸውን በማሳየት ከአንድ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ውድድሩን በ3 ደቂቃ 57 ሰኮንድ ከ33 ማይክሮ ሰከንድ በማስመዝገብ ያሸነፈች ሲሆን ድርቤ ወልተጂ፣ ለምለም ኃይሉ፣ ትእግስት ከተማ እና ሂሩት መሸሻ ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ ያሉትን ደረጃዎች ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል። በወንዶች 1500 ሜትር ማጣሪያ ከአንድ እስከ አራተኛ ደረጃ ያሉት ቦታዎች ኡንም በኢትዮጵያውያን ተይዘዋል። ውድድሩን አትሌት ታደሰ ለሚ በ3 ደቂቃ 31 ሰከንድ 90 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰአት ያጠናቀቀ ሲሆን የአገሩ ልጆች ሳሜኤል አባቴ፣ ሳሙኤል ተፈራ እና መለሰ ንብረት እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። በሴቶች 3 ሺ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ውድደርም ቢሆን ኢትዮጵያውያን ከአራተኛው ደረጃ በስተቀር ከአንድ እስከ ስምንት ያሉትን ቦታዎች ይዘው ጨርሰዋል። አትሌት መቅደስ አበበ በ9 ደቂቃ 13 ሰከንድ ከ63 ማይክሮ ሰከንድ ውድድሩን ያሸነፈችበት ሰአት ነው። አትሌት ሎሚ ሙለታ ደግሞ ሁለተኛ ስትሆን አትሌት አገሬ በላቸው ሶስተኛ ሆና ጨርሳለች። የኡጋንዳዋ አትሌት ፔሩዝ ቼሙታይ አራተኛ ሆና ያጠናቀቀች ሲሆን ቀሪዎቹን ደረጃዎች ደግሞ ኢትዮጵያውያኑ ብርቱካን አዳሙ፣ ብርሀን ገብረጊዮርጊስ፣ አስማረች ነጋ እንዲሁም ወይንሸት አንሳ ይዘውታል። በወንዶች 3 ሺ ሜትር መሰናክል ማጣሪያም ኢትዮጵያውያን የበላይነት በመውሰድ ከአንድ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይው ማጠናቀቅ ችለዋል። በዚህም መሰረት አትሌት ቢቂላ ታደስ ውድድሩን በ8 ደቂቃ 09 ሰከንድ ከ37 ማይክሮ ሰከንድ ���ሆነ ሰአት ማሸነፍ ችሏል። በመቀጠል ደግሞ አብራሀም ስሜ፣ ኃይለማርያም አማረ፣ ሳሙኤል ፍሬው እና ተገኑ መንግስቱ ከሁለት እስከ አምስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በማጣሪያው ተሳትፈው ጥሩ ሰአት ያስመዘገቡ አትሌቶችን በአምስቱም ውድድሮች ይፋ ያደርጋል። ኮሚቴው አትሌቶቹ ያስመዘገቡትን ሰአት፣ ወቅታዊ ብቃት እንዲሁም አስቸጋሪ ሁኔታዎችን የመቋቋም ብቃታቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከነተጠባባቂ እስከ አራት የሚደርሱ አትሌቶችን በቅርቡ ምናልባትም በዚህ ሳምንት ይፋ ሊያደርግ እንደሚችል ይጠበቃል። https://www.bbc.com/amharic/news-57415608 +health ኮሮናቫይረስ፡ ኦማን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ10 አገራት የሚመጡ መንገደኞችን አልቀበልም አለች ኦማን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአስር አገራት የሚመጡ መንገደኞችን ለቀጣዮቹ 15 ቀናት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት የተነሳ እንደማትቀበል አስታወቀች። ኦማን እገዳ ከጣለችባቸው አስር አገራት መካከል ስምነቱ የአፍሪካ አገራት ሲሆኑ እነሱም ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ፣ ጋና፣ ጊኒ እና ሴራሊዮን ይገኙባታል። ቀሪዎቹ ሁለት አገራት ደግሞ የመካከለኛ ምሥራቅ አገሯ ሌባኖስና የደቡብ አሜሪካዋ ብራዚል ናቸው። እንደ ኦማን የጤና ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ከሆነ የአገሪቱ ዜጎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ቤተሰቦቻቸው ብቻ ከእነዚህ አገራት የሚመጡ ከሆነ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል። ኦማን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከምሥራቅ አፍሪካ ወደ አገሯ ከገቡ መንገደኞች መካከል 18 በመቶ ያህሉ በኮሮናቫይረስ ተይዘው በመገኘታቸው ነው። ከኦማን ጋር የታሪክ እና የባህል ትስስር ላላቸው አገራት ይህ ውሳኔ አስደንጋጭ ነው ተብሏል። ዕገዳው ከተጣለባቸው መካከል የምትገኘው ታንዛኒያ ካለፈው ዓመት ግንቦት ወር ጀምሮ አንድም በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው በአገሯ ስለመኖሩ አላሳወቀችም። ለበርካታ ወራት ከኮቪድ ወረርሽኝ ነጻ መሆኗን ስትናገር የቆየችው ታንዛኒያ በድንገት ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ ሕዝባቸው ከኮቪድ-19 እንዲጠነቀቅ ምክራቸውን ለግሰዋል። እንደ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ናይጄሪያ ያሉ አገራት ደግሞ በየዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በቫይረሱ የተያዘ ሰው እየመዘገቡ ነው። እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ከሆነ ኦማን 140,000 በኮሮና ተሕዋሲ የተያዙ ሰዎች በአገሯ መኖራቸውን በምርመራ ስታረጋግጥ ከእነዚህ መካከል 1,500 ያህሉ ሞተዋል። በኦማን ከባለፈው ወር ጀምሮ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቀስ በቀስ መጨመር እያሳየ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-56156451 +politics ዩኬ፡ ሊዝ ትረስ በ45 ቀናቸው ስልጣን እንደሚለቁ አስታወቁ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ሊዝ ትረስ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታወቁ። ሊዝ ትረስ ዛሬ ሐሙስ ከሰዓት በዳውኒንግ ስትሪት በሰጡት መግለጫ የተመረጥኩበትን ኃላፊነት መወጣት አልቻልኩም ብለዋል። ከበርካታ ጋዜጠኞች ፊት ቀርበው መግለጫ የሰጡት ሊዝ ትረስ ወደ ስልጣን የመጣሁት “ከፍተኛ የምጣሄ ሃብት እና ዓለም አቀፍ አለመረጋጋት ባለበት ወቅት ነው” ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሯ የወግ አጥባቂ ፓርቲ አባላት ለጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታ ሲመርጧቸው፤ የሰጧቸውን ኃላፊነቶች መወጣት ባለመቻላቸው ስልጣን እንደሚለቁ አስታውቀዋል። ተሰናባቿ ጠቅላይ ሚንስትር በአጭሩ ንግግራቸው፤ ወግ አጥባቂ ፓርቲያቸው የመረጣቸው ግብር እንዲቀንሱ እና የምጣሄ ሃብት እድገት እንዲያመጡ እንደሆነ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ትረስ፡ “ወግ አጥባቂ ፓርቲ ለመረጠኝ ኃላፊነት መወጣት እንደማልችል ተረድቻለሁ” ብለዋል። የ��ግ አጥባቂ ፓርቲ ተቀናቃኝ የሆነው የሌበር ፓርቲ መሪ ሰር ኬር ስታርመር እና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች የጠቅላይ ሚንስትሯን መሰናበት ተከትሎ አጠቃላይ ምርጫ እንዲካሄድ ጠይቀዋል። ሊዝ ትራስ እርሳቸውን የሚተካ ፖለቲከኛ እስኪገኝ ድረስ በስልጣን ላይ እንደሚቆዩ ጨምረው የገለጹ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት የአመራር ምርጫ እንዲጀመር ከስምምነት መደረሱን ተናግረዋል። ሊዝ ትረስ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር በሆኑ በ45ኛ ቀናቸው ስልጣን መልቀቃቸው በአገሪቱ ታሪክ ለአጭር ጊዜ የመሩ ሰው ያደርጋቸዋል። ሊዝ ትረስ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት የዩኬ ወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ነበር። ባለፉት ዓመታት የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ሊዝ ትረስ፤ የወግ አጥባቂ መሪ ለመሆን ከቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ብርቱ ፉክክር ገጥሟቸው ነበር። ይሁን እንጂ የኋላ ኋላ ሊዝ ትረስ በሰፊ የድምጽ ብልጫ ሪሺ ሱናክን በመብለጥ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ እንዲሆኑ በፓርቲው አባላት ተመርጠው ነበር። ትረስ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የምጣሄ ሃብት ፖሊሲያቸው እጅጉን ሲያስተቻቸው ነበር። ሜሪ ኤልዛቤት ትረስ በሚለው ሙሉ የመዝገብ ስማቸው የሚታወቁት ፖለቲከኛዋ፣ ከሂሳብ ሊቁ አባታቸው እና ከነርስ እናታቸው እአአ 1975 በኦክስፎርድ፤ ኢንግላንድ ነበር የተወለዱት። ሊዝ ትረስ በወጣትነት እድሜያቸው ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ገብተው፤ ፍልስፍና፣ ፖለቲካ እና ምጣሄ ሃብት አጥንተዋል። በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በተማሪዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁ ተሳትፎን ያደርጉ ነበር። አሁን ላይ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ይሁን እንጂ፤ ሊዝ ትረስ በተማሪነት ዘመናቸው ሊብራል ዴሞክራት ነበሩ። ሊዝ በፀረ ንጉሣዊ አስተዳደር ላይ በሚያንጸባርቁት ጠንካራ አቋም ይታወቁ ነበር። ሊዝ ገና በኦክስፎርድ ሳሉ ነበር የፖለቲካ አቋም ለውጥ በማድረግ ፊታቸውን ወደ ወግ አጥባቂ ፓርቲ ያዞሩት። ሊዝ የፓርላማ አባል በሆኑ በሁለት ዓመታት ውስጥ የትምህርት ሚንስትር ሆነው ተሾሙ። ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ በእድገት የአካባቢ ጥበቃ ሚንስትር በመሆን ሌላ ሹመት አግኝተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ አስተዳደር ውስጥ የፍትሕ ሚኒስትር፣ ከዚያም ደግሞ የግምጃ ቤት ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል። እአአ 2019 ላይ ቦሪስ ጆንሰን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ወደ ሥልጣን ሲመጡ ደግሞ ሊዝ ትረስ የዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር ሆነው ማገልገል ጀምረዋል። ሊዝ የ46 ዓመት ጎልማሳ ሳሉ ነበር ትልቁን የመንግሥት ኃላፊነት የተረከቡት። እአአ 2021 ከዶሚኒክ ራብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሥልጣንን ተረክበዋል። የሊዝ ትረስ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ያደረጉት ጉዞ አልጋ ባልጋ አልነበረም። ከተቀናቃኛቸው ሪሺ ሱናክ ጋር በነበሯቸው ክርክሮች ላይ ባቀረቧቸው መከራከሪያዎች ሲተቹ ነበር። ይሁን እንጂ የምርጫ ውጤቱ ሊዝ ትረስ ከሪሺ ሱናክ ይልቅ በፓርቲ አባላት ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት እንዳላቸው አሳይቷል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cg3lgqwx7ywo +politics እነ አቶ እስክንድር ነጋ እና እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ከእስር ተለቀቁ "የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የተከሰሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት አርብ ታኅሣሥ 29/2014 ዓ.ም ከእስር መፈታታቸው ተገለጸ። የእነ አቶ ጃዋር ጠበቃ የሆኑት አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት እነ አቶ ጃዋር ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ እንደተነገራቸው እና በመምሸቱ አንወጣም ማለታቸውን ገልጸው የነበረ ቢሆንም ምሽት ላይ ከአስር ቤት መውጣታቸው ተነግሯ��። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ደግሞ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ከፍተኛ አመራሮቹ ከእስር እንደተለቀቁ አመልክቷል። ቢቢሲ ከባልደራስ ፓርቲ ምንጮች ያገኘው መረጃ እንዳመለከተው የባልደራስ የእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋና አቶ ስንታየሁ ቸኮልና ሌሎች በእስር ላይ የነበሩ አመራሮች ከአስር ወጥተዋል። አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አርብ ዕለት ስለመፈታታቸው ቀደም ሲል እንዳልተነገራቸውና እንዳልተዘጋጁ ገልጸዋል። በዕለቱ አመሻሽ ላይ እቃቸውን እዘው እንዲወጡ በድንገት ተነግሯቸው ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት መውታጣቸውን እንጂ ስለተፈቱበት ሂደቱ ቀደም ያለ መረጃ እንደሌላቸው ከእስር ቤት ከወጡ ከደቂቃዎች በኋላ ለቢቢሲ በስልክ ተናግረዋል። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ምሽት ላይ እንዳስታወቀው ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ አስር ላይ ቆዩት ከፍተኛ አመራሮቹ አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወ/ሮ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሴ ከእስር ተለቀዋል። በተመሳሳይ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በፊት የታሰሩት አቶ ጃዋር መሐመስ በስማቸው ባለ መዝገብ ላይ የተከሰሱት ከ20 በላይ ግለሰቦች ሲሆኑ፣ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ሁሉም ይለቀቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል። በእነ አቶ ጃዋር የክስ መዝገብ ውስጥ ከተካተቱት እና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከሚገኙት መካከል ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነ፣ ጋዜጠኛ መለሰ ዲሪብሳ እና የአቶ ጃዋር መሐመድ ጥበቃዎች ይገኙበታል። የአቶ ጃዋር ጠበቃ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ስለተፈቱበት ሂደት በዝርዝር እንደማያያውቁ፣ ነገር ግን መፈታታቸውን በተመለከተ እንዲወጡ እንደተነገራቸው እንደሚያውቁ ""ደብዳቤም ሳይሰጧቸው እንደማይቀርም"" አመልክተው፤ በነገው ዕለት (ቅዳሜ) ያለውን ሁኔታ ወደ ስፍራው በመሄድ እንደሚያጣሩ ጠበቃ ቱሊ ገልፀዋል። ይህ የፖለቲከኞቹ የመፈታት ዜና የተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገና ዕለት ከሰዓት በኋላ ይቀርታና ምህረትን በተመለከተ ""ድላችን ዘላቂ ለማድረግ እንድንችል በአሸናፊ ምህረት ግጭቱ የፈጠረውን ውጥረት እናረግባለን"" በማለት መግለጫ ማውጣታቸውን ተከትሎ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም ""ያጠፋ እንዲቀጣ፣ የበደለ እንዲክስ የሚያደርግ ሁሉን አቀፍ ፍትሕ በሽግርር እና በተሃድሶ ፍትህ እይታ፣ አገራዊ ባህሎቻችን እና አሴቶቻችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ፍትህ እናሰፍናለን"" ብለዋል። የእነ አቶ ጃዋር ጠበቃ በምን አይነት ሁኔታ ይፈቱ ተብሎ እንደተወሰነ እንደማያውቁ ተናግረው ""እስካሁን ጥፋተኛ አልተባሉም ስለዚህ የሚሆነው ክስ ማቋረጥ ነው"" ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ቱሊ ይህንን ሲያብራሩም በሕጉ መሰረት አንድ ተከሳሽ ይቅርታ የሚደረግለት ጥፋተኝነቱ ተረጋግጦ የተፈረደበት እንደሆነ ነው ይላሉ። ነገር ግን በክስ ሂደት ላይ ያለን ሰው ደግሞ ክርክሩን ከማስቀጠል ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ክሱን ማቋረጥ እንደሚቻል ሕጉ እንደሚደነግግ ያስረዳሉ። ስለዚህ ከዚህ አንጻር ከታየ የእነ አቶ ጃዋር መለቀቅ ክስ ማቋረጥ እንደሚሆን ጨምረው አብራርተዋል። ነገር ግን አሁን መንግሥት ""የትኛውን እንደተጠቀመ"" እንደማያውቁ ገልፀዋል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ እንዲፈቱ የተወሰነበት ሁኔታ ግልጽ አለመሆኑ የገለፁት አቶ ቱሊ፤ ""መንግሥት ደንብና ሥርዓትን ተከትሎ መልቀቅ አለበት፣ ስለዚህ መለቀቃቸው ቢያስደስተንም ነገር ግን በአግባቡ ሂደቱን ተከትሎ አለመፈተታቸው ያሰጋናል"" ሲሉ አክለዋል። ጨምረውም ""አሁን ዳኞች መዝገቡን እንዴት አድርገው እንደሚዘጉ ግራ የሚያጋባ ነው"" የ��ሉት አቶ ቱሊ ""እንደዚያ ባይሆን ጥሩ ነው ግን ትልቁን ምስል ስናይ ያለ አግባብ ስለታሰሩ በነጻ መለቀቃቸው ያስደስተናል"" በማለት አስረድተዋል። አቶ ቱሊ እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ይፈቱ ተብሎ በመወሰኑ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፣ በተከሰሱበት ወቅት ክሳቸው ዓመታት ሊወስድ እንደሚችል መግለጻቸውን ነገር ግን ""ፍርድ ቤት እና ዳኛ ካለ"" ነጻ እንደሚሆኑ ያውቁ እንደነበር ተናግረዋል። እነ አቶ ጃዋርም ሆኑ ጠበቆቻቸው ከመጀመሪያ ጀምሮ ይህ ጉዳይ በፍርድ ቤት የሚፈታ አለመሆኑን ይናገሩ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ቱሊ፣ ""በድርድር፣ በንግግር እና በፖለቲካዊ ውሳኔ መፈታት እንዳለበት"" ይናገሩ እንደነበር አስታውሰዋል። ""ከፍርድ ቤት ውጪ ማለቁ እኛም ስንከራከርበት እነ ጃዋርም ሲከራከሩበት የነበረ ነው። ፍርድ ቤት አንሄድም ሲሉ የነበረበት ምክንያት ይኸው መጣ"" ሲሉ ተናግረዋል። የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አስክንድር ነጋና ሌሎች የፓርቲው አመራሮች እንዲሁም የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ አባል የሆኑት ታዋቂው ፖለቲከኛ አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ አመራሮችና አባላት ለእስር የተዳረጉት የታዋቂው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መገደልን ተከትሎ ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ነበር። አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ከአንድ ዓመት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ መኪናው ውስጥ ሳለ በጥይት ተመትቶ መገደሉን ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል የበርካታ ሰዎች ህይወት ያለፈበትና ከፍተኛ ንብረት የወደመበት ሁከት መከሰቱ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ ካለመረጋጋቱ ጋር በተያያዘ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን ጨምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል። የፍትህ ሚኒስቴር ከአመሻሹ ባወጣው መግለጫ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የወንጀል ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሕገ-መንግስት እና የሽብር ችሎት እየታየ ከነበሩት ተከሳሾች መካከል በነጃዋር ሲራጅ መሃመድ እና በእነ እስክንድር ነጋ ፈንታ መዝገብ ያሉ ተከሳሾች ክሳቸው በአዋጅ ቁጥር 943/2008 መሰረት እንዲነሳ ተደርጓል ብሏል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መሰረት ክሱ እንዲነሳ የተደረገው"" በቀጣይ የሚደረገውን ሃገራዊ የምክክር መድረክ ሂደት ውጤታማነት እና አካታችነት ከፍ ለማድረግ በማሰብ ነው።"" ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59893883 +health ኮሮናቫይረስ፡አማዞን ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ ሰራተኞቹ በኮሮና እንደተያዙ አስታወቀ አማዞን ኩባንያ 19 ሺህ 816 ሰራተኞቹ በኮሮናቫይረስ እንደተያዙ ገልጿል። ይህ ቁጥር ከመጋቢት ወር ጀምሮ የተመዘገበ ሲሆን በአሜሪካ ያሉት ሰራተኞቹም ናቸው። በአጠቃላይ ኩባንያው 1.37 ሚሊዮን ሰራተኞች ያሉት ሲሆን በኮሮናቫይረስ የተያዙትም ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ ቁጥር ጋር ሲሰላ 1.44 በመቶ ነው ተብሏል። የኩባንያው ሰራተኞች፣ የሰራተኛ ማህበራትና ኃላፊዎችም የሰራተኞችን ደህንነት አደጋ ላይ ጥሏል በሚልም ኩባንያው ከፍተኛ ትችት እየቀረበበት ነው። ሆኖም ኩባንያው በበኩሉ በቫይረሱ የተያዙት ሰራተኞች ቁጥር ከተጠበቀው በታች ነው ብሏል። ኩባንያው ባወጣው መግለጫም በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ከግምት ውሰት በማስገባት 33 ሺህ 952 ሰራተኞቹ በቫይረሱ እንደሚያዙ ጠብቆ እንደነበር አስታውቋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በርካታ ኩባንያዎች ለተወሰነ ጊዜ ስራቸውን ቢያቆሙም አማዞን በበኩሉ የትኞቹንም ቅርንጫፎች አልዘጋም። በዚህ ወረርሽኝ ወቅትም ትርፋማ ከሆኑት ኩባንያዎች አንዱ መሆን ችሏል። አገራት ወረርሽኙን ለመግታት በሚል ያወጧቸውን መመሪያዎች ተከትሎ በርካቶች ቤታቸው በመቀመጣቸው የበይነ መረብ (ኢንተርኔት) ግብይይት ሁነኛ አማራጭ ሆኗል። ይህም ሁኔታ ለግዙፉ ኩባንያ አማዞንና በአለም አንደኛ ለሆነው ባለቤቱ ጄፍ ቤዞ በትርፍ ላይ ትርፍ ሆኖለታል። በባለፉት ሶሰት ወራትም ውስጥ ኩባንያው 40 በመቶ ሽያጩ ጨምሯል። ከመጋቢት እስከ ሰኔ ወራት ባሉትም 88.9 ቢሊዮን ዶላር ሽያጭን ሲያስመዘግብ፣ ከዚህም ውስጥ 5.2 ቢሊዮን ዶላሩ ትርፍ ነው። ኩባንያው ከተመሰረተበት ከጎሮጎሳውያኑ 1994 ጀምሮም እንዲህ አይነት ትርፍ አስመዝግቦ አያውቅምም ተብሏል። https://www.bbc.com/amharic/news-54389476 +business ካናዳ በገፍ የሚደረግ የመድኃኒት ወጪ ንግድን አገደች "ካናዳ በገፍ የሚደረግ የመድኃኒት ወጪ ንግድን ማገዷ ተሰምቷል። በአገሪቷ እጥረት ያጋጥማል በሚልም ፍራቻ ነው በጤና ባለሙያዎች ማዘዣ የሚሸጡ መድኃኒቶች ላይ እገዳ የጣለችው። አሜሪካ በቅርቡ መድኃኒቶችን ከካናዳ በማስመጣት በቅናሽ ዋጋ ለመሸጥ ማቀዷን ተከትሎ ነው ይህ ውሳኔ የተላለፈው። ምንም እንኳን በካናዳ ከሌሎች አገራት ጋር ሲወዳደር በጤና ባለሙያዎች ማዘዣ የሚሸጡ መድኃኒቶች ዋጋ ውድ ቢሆንም፤ በአሜሪካ ካለው ግን የቀነሰ ነው። ዶናልድ ትራምፕ ከካናዳ ለመግዛት ያሰቡት መድኃኒት ክምችትም በአገሪቷ ከፍተኛ እጥረትም እንደሚያስከስትልም የካናዳ መድኃኒት አቅራቢዎችም ሲያስጠነቅቁ ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝን ተከትሎም በአንዳንድ መድኃኒቶች ላይ ያለው የገበያ ፍላጎትም በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ያሳያል። ካናዳ 68 በመቶ የሚሆነውን የመድኃኒት ክምችቷን ከአገር ውጭ የምታስገባ ሲሆን በመድኃኒት አቅርቦትም ላይ ችግር ምንም አይነት እክል እንዳያጋጥም መስራት እንደሚገባ የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል። ""ኩባንያዎች እጥረት ተከስቷል ወይም ይከሰታል የሚል ስጋት ካላቸው ለመንግሥት ማሳወቅ አለባቸው። ከዚህም በተጨማሪ በ24 ሰዓታት ውስጥ ሊያስከትለው የሚችለውን የጤና ስጋት ገምግመው ሪፖርት ማድረግ አለባቸው"" ብሏል የጤና ሚኒስቴሩ መግለጫ። ዶናልድ ትራምፕ ረከስ ያለ መድኃኒት ከካናዳ እንዲገባ የሚያስችል ትዕዛዝ የፈረሙት በሐምሌ ወር ነበር። ይህንንም ተከትሎ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ሌሎች አገራትን የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት ለማቅረብ ያላቸውን ፈቃደኝነት ጠቅሰው ተቀዳሚው ነገር ግን የአገራቸውን ሕዝብ ፍላጎት መጠበቅ ነው ብለው ነበር። በአሜሪካ ያሉ የመድኃኒት አምራች ፋብሪካዎች በአዳዲስ መድኃኒቶች ላይ ያለው ውድ ዋጋን እንዲሁም በቀደሙ መድኃኒቶች ላይ የዋጋ ጭማሪን አስመልክቶ ትችቶችን እያስተናገዱ ነው። እነዚህ ወቀሳዎች በዋነኝነት የመጡት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ከፖለቲከኞች፣ ከኢንሹራንስ ኩባንያዎችና ከህመምተኞች ቡድን በኩል ነው። ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንም የመድኃኒት ዋጋዎችን ለማውረድ ከሌላ አገር ለማስመጣት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55120403 +politics በትግራይ ያሉ ካህናት የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለመመስረት መወሰናቸው ተነገረ "የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የእምነት አባቶች ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ቤተ-ክህነት በመነጠል የትግራይ ጠቅላይ ቤተ-ክህነት ለመመስረት መወሰናቸው ተነገረ። የህወሓት ንብረት በሆነው በድምጺ ወያኔ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የቀረቡት የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች በክልሉ ስላለው ነባራዊ ሁኔታ ውይይት ካካሄዱ በኋላ ከዋናው ጠቅላይ ቤተ-ክህነት የተለየ የትግራይ ጠቅላይ ቤተ-ክህነት ለመመስረት መወሰናቸውን ተናግረዋል። የሃይማኖት አባቶቹ የኢት��ጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን በትግራዩ ጦርነት ለፌደራል መንግሥቱ ወግናለች ሲሉ ከሰዋል። ከዚህ በተጨማሪም 'በትግራይ ሰዎች ሲገደሉ፤ በተቋማት ላይ ውድመት ሲደርስ ቤተ-ክህነቱ ጦርነቱን አላወገዘችም፣ ይቁም አላለችም' ብለዋል። በዚህም ምክንያት ""የፈረሰውን ለመጠገን እና ሕዝብን ለማጽናናት የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነትን መመሠረት አስፈልጓል"" ብለዋል የሃይማኖት አባቶቹ። ይህ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ውሳኔ የተሰማው፤ የሃይማኖት አባቶቹ ከህወሓት ሊቀ መንበር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር መገናኘታቸው ከተዘገበ ከቀናት በኋላ ነው። ድምጺ ወያኔ ከአራት ቀናት በፊት ማለትም ጥር 27/2014 ዓ.ም. በዘገባው የህወሓት ሊቀ መንበር እና የሃይማኖት አባቶች በተገናኙበት ወቅት፤ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)፤ ""የትግራይ ሕዝብ ተጠቃ ማለት የትግራይ ቤተ ክርስትያን ተጠቃች ማለት ነው"" ስለማለታቸው ዘግቧል። ይህ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ቤተ-ክህነት የተለየ ሌላ ቤተ-ክህነት የመመሠረት ጥረት ሲደረግ ይህ የመጀመሪያ አይደለም። ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ለመመስረት ጥረት ሲደረግ ነበር። ከ15 ወራት በፊት በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ ተቀረው የሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተስፋፋው ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳቶችን አስከትሏል። በጦርነቱ ሳቢያ በእምነት ተቋማር ላይ ውድመትና ተዘፈፋ መፈጸሙ በተለያዩ ጊዜያት የተዘገበ ሲሆን፣ በርካታ ሰዎችም በእምነት ተቋማት ውስጥ መገደላቸውን የእምነቱ ተከታዮች ይናገራሉ። የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመመስረት ውሳኔን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የፓትሪያርኩ ጽ/ቤት አስተያየት ለማግኘት ቢቢሲ ያደረግነው ጥረት አልተሳክም። የትግራይ ጦርነትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የፀሎት እና ምህላ በማወጅ ሰላም እንዲወርድ ጥሪ ስታደርግ ቆይታለች። ከዚህ ባሻገር የትግራይ ሀገረ ሰብከት ከዚህ ቀደም ጦርነቱን በማውገዝ በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ የመድኃኒት እና የምግብ እጥረት በመከሰቱ የሰዎች ሕይወት እያለፈ መሆኑን ገልጿል። በሌላ በኩል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ግንቦት 2013 ላይ ተቀርጾ በወጣ ቪዲዮ ላይ ስለትግራይ እንዳልናገር ""ድምጼ ታፍኗል"" በማለት መናገራቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክስርስትያን ፓትርያርክ የሆኑት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በትግራይ ክልል የሚካሄደውን ጦርነት ""የአረመኔነት ሥራ"" በማለት ጠርተው ብዙ ጊዜ በጉዳዩ ላይ የሰጡት አስተያየት ፈቃድ መታገዱን ተናግረው ነበር። ይህ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያ ንግግር በፈረንሳዩ የዜና ወኪል የተቀረጸ ሲሆን ፓትሪያርኩ በቪዲዮው ላይ በትግራይ ክልል ስላለው ግጭት እና ስለሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲናገሩ ተሰምተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60287131 +business ከ‘ሂውማን ሄር እስከ ውስኪ’ እንዳይገቡ የተከለከሉበት ምክንያት ምንድን ነው? "ኢትዮጵያ ‘ቅድሚያ የማይሰጣቸው’ የሚባሉ 38 ዓይነት ዕቃዎች እንዳይገቡ ዕገዳ ጥላለች። አስመጪዎች እነዚህን ምርቶች ወደ አገር ቤት ለማስገባት የሚያስችላቸው ‘ኤልሲ’ እንዳይሰጣቸው መንግሥት ያገደው፣ በአገሪቱ እየተስተዋለ ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመግታት በሚል ነው ። ቅድሚያ የማይሰጣቸው አሊያም የቅንጦት ከሚባሉት ዕቃዎች መካከል ተሽከርካሪዎች፣ የምግብ ምርቶች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች እና የአልኮል መጠጦች ይገኙበታል። የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፃፈው ደብዳቤ፣ እነዚህን ዕቃዎች ወደ አገር ቤት ለሚያስገቡ አስመጪዎች ፈቃድ እንዳይሰ��ቸው አዟል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ባለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት እንደሆነና አስፈላጊ የሚባሉ እንደ መድኃኒት፣ የግብርና ጥሬ ዕቃዎች፣ ለአገር በቀል ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆኑ ዕቃዎችን ለማስመጣት በቂ የውጭ ምንዛሪ እንዲኖር በማለት ነው። እነዚህን ዕቃዎች በብዛት የሚያስገቡ አስመጪዎች መመሪያው እንዲነሳ በኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት አማካኝነት ‘ይግባኝ’ እያሉ እንደሆነም ቢቢሲ ሰምቷል። ይህ ትዕዛዝ ከመውጣቱ በፊት ኤልሲ የተከፈተላቸው ዕቃዎች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ መመሪያው ይፈቅዳል። ለመሆኑ ኤልሲ ማለት ምን ማለት ነው? መንግሥት ይህን መመሪያ በማውጣቱ ምን ያህል የውጭ ምንዛሪ ያተርፋል? የአስመጪዎቹ ይግባኝስ የት ደረሰ? ከውጭ እንዳይገቡ ዕግድ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል አንዱና የማኅበራዊ ሚድያ መነጋገሪያ የነበረው ሰው ሠራሽ ፀጉር ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋጋው እየናረ የኪስ መለካኪያ መሆን እየጀመረ የመጣው ‘ሂውማን ሄር’ ከባንክ በወጣ ኤልሲ አገር ቤት እንዳይዘልቅ መመሪያ ወጥቶበታል። ስሜን አትጥቀሱ ያለን አንድ ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ ሰው ሠራሽ ፀጉር የሚያስመጣ ነጋዴ፣ ይህንን ምርት ከዚህ ቀደም በሕጋዊ መንገድ ያስመጣ እንደነበር ይናገራል። አስመጪው “የሚከፈለው ቀረጥ፣ ገበያው ላይ የሚሸጠው እና የዕቃው ዋጋ ሲወዳደር ስለማይመጣጠን አብዛኛው ነጋዴ ከቀረጥ ውጪ ነው የሚያስገባው” ብሏል። “የሚቀረጠው እጅግ ውድ ስለሆነ ሁሉም ነጋዴ ዕቃውን በመንገደኛ ሻንጣ ይዞ ነበር የሚገባው። ይህ አሁንም አለ፤ ነገር ግን ከዚህ በፊት ከነበረው አንጻር ቀንሷል። በሕጋዊ መንገድ የሚገባ ሂዩማን ሄር የለም።” ምንጫችን፤ አሁን ኢትዮጵያ ገበያ ላይ ያለው በኮንትሮባንድ የሚገባ ‘ሲንቴቲክ’ ፀጉር ስለሆነ ይህንን ለመቆጣጠር ታስቦ የወጣ ሕግ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለው። ነገር ግን አዲሱን መመሪያ ተከትሎ የሰው ሠራሽ ፀጉር ዋጋ በእጥፍ እንዲጨምር፣ የአቅርቦት ችግር እንዲፈጠርና ነጋዴዎች ጫና ላይ እንዲወድቁ ምክንያት መሆኑን ይገልጻል። “አዎ ተፅዕኖ አሳድሮብኛል። ሙሉ በሙሉ ወደ ኢትዮጵያ መላክ አቁሚያለሁ። ቀረጥ ከፍ አድርጎ ማስገባት ፍትሐዊ አይደለም። ከዚህ ቀደም 400 ግራም ፀጉር 120 ዶላር ነበር፤ አሁን ግን አምስት/ስድስት [የታሸገ] ፀጉር ይዞ የሄደ ሰው ሦስት እጥፍ [360 ዶላር] ቀረጥ ይከፍላል። ስለዚህ አያዋጣም።” አዲሱን ዕቀባ ተከትሎ ሂውማን ሄር በአማካይ ዋጋ 15 ሺህ ብር ጭማሪ ማሳየቱን ነጋዴዎች ይናገራሉ። ከዚህ ቀደም 18 ሺህ ብር ይሸጥ የነበረው ፀጉር፣ አሁን ዋጋው ወደ 29 ሺህ ብር ከፍ ብሏል። ሂውማን ሄር ብቻ ሳይሆን ቸኮሌት፣ ትምባሆ፣ የታሸጉ ጭማቂዎች፣ ውሃ እና ለስላሳ መጠጦች፣ የተጠበሰ ድንች፣ የአልኮል መጠጦች፣ እንዲሁም ‘ሜክ አፕ’ የመሳሰሉ የመዋቢያ ዕቃዎች ከተከለከሉት 38 የዕቃ ዝርዝሮች መካከል ይገኛሉ። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍ፤ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2023 የሚኖራት የውጭ ምንዛሪ አቅም አስፈላጊ የሚባሉ እንደ ነዳጅ፣ ማዳበሪያ እና መድኃኒት ለመግዛት የሚሆን ብቻ ነው ሲል ይተነብያል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ አገር ቤት በአስመጪዎች እንዳይገቡ ከተከለከሉት ምርቶች በዓመት 100 ሚሊዮን ዶላር ማትረፍ ይቻላል ይላል። የአሜሪካ የውጭ ግብርና አገልግሎት እንደሚለው ኢትዮጵያ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 18 ቢሊዮን ዶላር አውጥታ ከውጭ ዕቃ አስገብታለች። በዚህም ምክንያት በገቢ እና በወጪ [ኢምፖርት-ኤክስፖርት] መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መጥቷል። ኢንተርናሽናል ግሮውዝ ሴንተር የተሰኘው የምጣኔ ሃብት ተቋም ካንትሪ ኢኮኖሚስት የ��ኑት ቴዎድሮስ መኮንን ይህ ሕግ የወጣበት ምክንያት የውጭ ምንዛሪ ገበያው አደጋ ስለተደቀነበት ነው ይላሉ። “በተለይ ባለፉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት የኢትዮጵያ የክፍያ ሚዛን [ባላንስ ኦፍ ፔይመንት] ተዛብቷል። ኮቪድና የሰሜኑ ጦርነት እንደ ምክንያት የሚጠቀሱ ናቸው። ወደ አገር ቤት የሚመጡ ቱሪስቶች፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች እንዲሁም ከውጭ አገር የሚላክ ገንዘብ [ሬሚታንስ] ቅናሽ አሳይቶ ነበር።” የምጣኔ ሃብት ባለሙያው በጦርነቱ ምክንያት ‘ካፒታል አካውንት’ ተብለው የሚጠሩት እርዳታ፣ ብድር እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት፤ አሉታዊ ተፅዕኖ ደርሶባቸዋል ይላሉ። “በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል።” መመሪያው በዋናነት የዶላር ዋጋ በባንክ እና በጥቁር ገበያው ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ተብሎ የወጣ እንደሆነ ተንታኙ ይናገራሉ። አክለው አስፈላጊ ያልሆኑ ዕቃዎች ላይ የሚውለው ወጪ፤ በተለይ ደግሞ አንዳንድ ዕቃዎች የሚገቡት ከትይዩ ገበያ [ብላክ ማርኬት] ከሚገኝ የውጭ ምንዛሪ ስለሆነ ያንን ፍላጎት ለመቀነስ ታስቦ የተደረገ ነው ይላሉ። ክልከላው በጥናት የተደገፈ ነው የሚለው ብሔራዊ ባንክ፤ በ38ቱ ምርቶች ላይ የተላለፈው የኤልሲ ዕግድ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ መሆኑን አሳውቋል። ምርቶቹ ለሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር መበራከት ምክንያቶች መሆናቸውም ተገልጧል። ኤልሲ ማለት ‘ሌተር ኦፍ ክሬዲት’ ማለት “ዓለም አቀፍ ንግድን በቀላሉ ለማሳለጥ የሚያስችል መንገድ ነው” ይላሉ ቴዎድሮስ መኮንን። አክለው ሲያብራሩ፤ “ከውጭ አገር ዕቃውን የሚሸጠው እና አስመጪው በባንኮች በኩል እርስ በርስ የሚስማሙበት፣ ዕቃው መላኩን እና መድረሱን የሚያረጋግጡበት” እንደሆነ ያስረዳሉ። “አንድ ሰው ዕቃ ማስመጣት ሲፈልግ ባንክ ይሄድና ‘ይህን ዕቃ ለመግዛት የውጭ ምንዛሪ እፈልጋለሁ’ ይልና የሚያስመጣበት ፈቃድ [ኢምፖርት ፐርሚት] ይሰጠውና ከዚያ ኤልሲ ይከፈታል።” ኤልሲ፤ ዕቃ ለማስመጣት [ኢምፖርት] ብቸኛው መንገድ እንዳልሆነና ሌሎችም መንገዶች [ለምሳሌ ቲቲ የተሰኘ ቅፅ] እንዳለ ባሙያው ይናገራሉ። አሁን መንግሥት ያወጣው ሕግ ለእነዚህ ዕቃዎች ኤልሲ እንዳይከፈት ያዛል። ስለዚህ እነዚህን ዕቃዎች በባንክ በኩል ማስመጣት አይቻልም ማለት ነው። በእርግጥ ይህ እርምጃ በአገሪቱ ውስጥ ላለውን የውጭ ምንዛሪ ችግር የሚፈለገውን ውጤት ያስገኛል? “አንድን ትልቅ ሚስማር ለመምታት ለሚስማሩ የሚመጥን መዶሻ መጠቀም ይኖርብሃል” በማለት የአገሪቱ የውጪ ምንዛሪ ችግር ትልቅ ሆኖ ሳለ ከቁጥር የማይገባ እርምጃ መውሰዱ እውነተኛ መፍትሔ አይሆንም ይላሉ የምጣኔ ሀብት ተመራማሪው አየለ ገላን (ዶ/ር)። በኢነርጂ፣ ንግድ፣ ግብርና እና በቱሪዝም ፖሊሲዎች ላይ የጥናት ፅሑፎች ያቀረቡት ምሑሩ በአሁን ወቅት በኩዌት የሳይንስ ምርምር ተቋም ተመራማሪ ኢኮኖሚስት ናቸው። አየለ (ዶ/ር)፤ እነዚህ ምርቶች ከውጭ እንዳይገቡ የውጭ ምንዛሪ መከልከል ወይም ‘ሌተር ኦፍ ክሬዲት’ ላይ ገደብ መጣል የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመቋቋም የሚረዳ እምርጃ ነው ብለው አያምኑም። “መደረግ ያለበትን እና ለአገር የሚጠቅመውን ሳያውቁት ቀርተው አይደለም፤ ነገር ግን ዳር ዳር እያሉ ያልፉታል። ምክንያቱም እዚያው ውስጥ የመንግሥትን እጅ አሥረው እንደፈለጉ የሚያደርጉ ስላሉ ነው።  ስለዚህ መሠረቱ ከተነካ የትላልቆቹ [ጥቅም] ይነካል” ይላሉ ተመራማሪው። የኢንተርናሽናል ግሮውዝ ሴንተር ኢኮኖሚስቱ ቴዎድሮስ በበኩላቸው በዋናው እና ጥቁር ገበያው መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሪ ዋጋ ለማጥበብ ካሉት ሁለት መፍትሔዎች አንደኛው ቁጥጥርን ማጥበቅ እንደሆነ ይ��ገራሉ። የመጀመሪያውና ዋነኛው የሚሉት መፍትሔ ግን “የውጭ ምንዛሪው በትክክለኛ መንገድ እንዲሠራ የሚያደርጉ ፖሊሲዎችን መቅረፅ ነው።” “ቁጥጥርን ማጥበቅ ዘላቂ የሆነ ለውጥ አያመጣም። ለምሳሌ በአዲስ አበባ የሚንቀሳቀሱ የጥቁር ገበያ ምንዛሪ ሱቆችን መንግሥት ሲዘጋ ለተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሪው ይወርድና ከዋና ገበያ ጋር ይቀራረባል። ነገር ግን ትንሽ ቆይቶ ቁጥጥሩ ሲላላ ተመልሶ ከፍ ይላል።” አሁን የተከለከሉት ምርቶች ወደ አገሪቱ ከሚገቡት ምርቶች ዋጋ አንጻር እዚህ ግባ የሚባሉ አይደለም የሚሉት አየለ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ከተፈቀደላቸው የውጭ ምንዛሪ አቅም በላይ የሚያወጡ ምርቶች ሲገቡ መንግሥት እርምጃ ባለመውሰዱ ኢትዮጵያ ማግኘት የነበረባትን የውጭ ምንዛሪ አጥታለች ይላሉ። ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ በአገሪቱ ያለውን ችግር መፍታት የሚቻለው “ችግሩ ከመሠረቱ ሲደርቅ ነው"" የሚሉት ምሑሩ፣ ይህ እንዳይነካ የተፈለገበት ምክንያት “በዚህ ውስጥ ያለው አስመጪው ነጋዴ ብቻ ሳይሆን፣ ዶላር ሰብሰበው ውጭ እንዲቀር የሚሠሩ ነጋዴዎችና ፖለቲከኞች ስላሉ ነው” ሲሉ ይወቅሳሉ። ሁለቱም ያነገራናቸው የምጣኔ ሃብት ሙያተኞች በአዲሱ መመሪያ ዘላቂነት ላይ ጥያቄ ያነሳሉ። አየለ ገላን (ዶ/ር)፤ ሌላ የተሻለ የአጭር ጊዜ አማራጭ አለ ባይ ናቸው። አንደኛው አማራጭ ‘ዱዋል ኤክስቼንጅ ሬት’ [ባለሁለት የምንዛሬ ተመን] ነው ይላሉ። ይህ ምን ማለት ነው? እንደ ምሑሩ ገለጻ ‘ዱዋል ኤክስቼንጅ ሬት’ ማለት መንግሥት በጥቁር ገበያው እንደ ነጋዴው በመሳተፍ የምንዛሪ እጥረትን ለመቀነስ የሚሞክርበት መንገድ ነው። “ነጋዴው በውጭ አገራት በድፍረት በጥቁር ገበያው የሚሳተፈው ስለሚያዋጣው ነው” የሚሉት አየለ (ዶ/ር)፤ “መንግሥትም ነጋዴው የሚያደርገውን ለምን እራሱ አያደርግም?” ሲሉ በጥያቄ መልክ አስፈላጊ እርምጃ መሆኑን በማስረገጥ ይናገራሉ። የጎረቤት አገር ኬንያን ልምድ እንደ ምሳሌ የሚጠቅሱት ተመራማሪው፣ ማንኛውም ሰው ወደ ኬንያ ሲገባ የፈለገውን ያክል ዶላር መጠን መግዛት እንደሚችል ይገልጣሉ። “መንግሥት ከነጋዴው በላይ ብር አለው። ነጋዴው በዓለም አገራት እየዞረ ሰብስቦ ውጭ የሚያስቀረውን ዶላር መንግሥት በጥቁር ገበያ በመሣተፍ ወደ አገር ቤት እንዲገባ ማድረግ ይችላል” የሚል የመፍትሔ ሐሳባቸውን ያቀርባሉ። ቴዎድሮስ መኮንን ደግሞ አዲሱ መመሪያ በሕገ-ወጥ መንገድ ምርቶችን የሚያስገቡ ሰዎች የበለጠ ትርፍ እንዲያጋብሱ ሊያደርጉ ይችላሉ የሚል ስጋት አላቸው። “ምርቶች በኮንትሮባንድ ሊገቡ ይችላሉ። አንድ ቁጥጥር ሲደረግ ሙሉ በሙሉ የማስፈፀም አቅም ስለማይኖር ክፍተቶች ይፈጠራሉ። ጥቂት ሰዎች እነዚህን ክፍተቶች ተጠቅመው ብዙ ያተርፋሉ። ቁጥጥሩን ማስፈፀም ከተቻለ ስኬታማ ይሆናል። ነገር ግን ተቋማዊ ክፍተቶች ስለሚኖሩ የተወሰኑ ግለሰቦች በጣም ተጠቃሚ ይሆናሉ።” እንደ ቴዎድሮስ እምነት ይህንን ችግር በዘላቂነት መቅረፍ ከሚቻልባቸው መንገዶች አንደኛው ትክክለኛ ፖሊሲ መከተል አስፈላጊ ነው መሆኑን በመጥቀስ፣ “የምናስገባውን ገቢና የምናወጣውን ወጪ ማመጣጠን አለብን” ይላሉ። “መንግሥት በራሱ አንድ ትልቅ የውጭ ምንዛሪ ተጠቃሚ ነው። ብዙ ፕሮጀክቶች አሉበት። እነዚህ ፕሮጀክቶች ላይ ብክነት ይታያል። በአገር ውስጥ ከሚመረተው ይልቅ ከውጭ የሚመጣው ይበልጣል። ስለዚህ ይህ ሁኔታ የሚለወጥበት መንገድ መኖር አለበት።”" https://www.bbc.com/amharic/articles/c97gzdn8j27o +health የወባ በሽታን 70 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል አንድ ጥናት አመለከተ "በአንድ ጥናት መሰረት አዲስ አይነት የመከላከል መንገዶችን በመጠቀም አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ህጻና�� በወባ በሽታ የመያዝና የመሞት ዕድላቸውን በ70 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል ተጠቆመ። የወባ በሽታ በተደጋጋሚ የሚከሰትባቸው ወራት ከመድረሳቸው በፊት ክትባቱን እንዲወስዱ ማድረግና በተጨማሪ ደግሞ ሌሎች መከላከያ መድኃኒቶችን እንዲጨምሩበት በማድረግ ሙከራው ከፍተኛ የሆነ ውጤት ማስገኘቱን በለንደን የሚገኙ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል። የዚህ የወባ በሽታን የመከላከል ሙከራው የተደረገው ከቡርኪናፋሶ እና ከማሊ የተወጣጡ ከ17 ወራት በታች የሆኑ 6 ሺህ ህጻናት ላይ ነው ተብሏል። አፍሪካ በየዓመቱ በወባ በሽታ ምክንያት እስከ 400 ሺህ ሞቶችን የምታስመዘግብ ሲሆን አብዛኞቹ ደግሞ እድሜያቸው ከአምስት ወራት በታች ነው። ይህ ጥናት 'በኒው ኢንግላንድ ጆርናል ኦፍ ሜድሲን' የህክምና መጽሔት ላይ የታተመ ሲሆን በሙከራው ላይ ለህጻናቱ አሁን ላይ የሚገኙ የወባ ክትባቶችን ቀድሞ መስጠትና የወባ በሽታ በብዛት በሚከሰትባቸው ወራት ደግሞ (አብዛኛውን ጊዜ የዝናብ ወራት ናቸው) ሌሎች የወባ መከላከያ መድኃኒቶችን በመስጠት ነው ከፍተኛ ውጤት የተገኘው። ""እኛ እናገኘዋለን ብለን ካሰብነው ውጤት በጣም የተሻለ ነገር ነው ያገኘነው"" ብለዋል የምርምር ቡድኑ አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ብራያን ግሪንዉድ። ""በሁለቱም አገራት ሙከራውን ከጀመርን በኋላ በወባ በሽታ ምክንያት ሆስፒታል የሚገቡና ህይወታቸው የሚያልፍ ህጻናት ቁጥር በእጅጉ ቀንሷል።"" ባለፉት ሦስት ዓመታት በተሰራው ሙከራ የዝናብ ወራት ከመድረሳቸው በፊት ሦስት የወባ ክትባቶች ለህጻናቱ የተሰጣቸው ሲሆን የዝናብ ወቅት ሲገባ ደግሞ የተለያዩ አይነት የወባ መከላከያ መድኃኒቶችን እንዲወስዱ ተደርጓል። በዚህም የወባ በሽታ ስርጭትን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ታይቶበታል። የዚህ ሙከራ ውጤትም ከየትኛውም አይነት ክትባትና መድኃኒት በተሻለ መልኩ ውጤት ያስገኘ ሲሆን በአፍሪካ በወባ በሽታ የሚጠቁ ህጻናትን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ይህም ሚሊየኖችን ህይወት እንደሚታደግ ከወዲሁ ተገምቷል። በሙከራው ላይ ክትባቱን ቀደም ብለው ከወሰዱትና በዝናብ ወቅት ደግሞ ሌሎች መከላከያዎችን ከወሰዱት ህጻናት መካከል 624ቱ በወባ በሽታ የተያዙ ሲሆን 11 ህጻናት ደግሞ ሆስፒታል ገብተው ህክምና ወስደዋል። በተጨማሪም የሟቾች ቁጥር በእጅጉ ቀንሶ 3 ብቻ ነበር። በዚህ ሙከራ እንዳይካተቱ ከተደረጉት ተመሳሳይ ቁጥር ካላቸው ህጻናት መካከል ደግሞ 1661 ህጻናት በወባ በሽታ የተያዙ ሲሆን 37 ህጻናት ደግሞ ሆስፒታል ገብተዋል። የሟቾች ቁጥር ደግሞ 11 ነበር። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ይህ አዲስ ሙከራ በጣም ውጤታማ ስለመሆኑ ማሳያ ነው። ከዚህ በፊት በሚደረጉ ሙከራዎች ጉንፋንን ቀድሞ ለመከላከል መሰል ጥረቶች ቢደረጉም በወባ በሽታ ላይ ሲሞከር ግን ይህ የመጀመሪያው ነው። የዓለም ጤና ድርጅት የወባ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ፔድሮ አሎንሶ ደግሞ ""ይህን አዲስ አይነት የወባ በሽታ ክትባትና መከላከል ሥራ በመልካም ጎኑ ነው የምንመለከተው። አፍሪካ ውስጥ በርካታ ሞትን ማስቀረት እንደሚያስችል እንገምታለን"" ብለዋል። የወባ በሽታ ክትባቱ እስካሁን 740 ሺህ ለሚሆኑ ጋና፣ ኬንያ እና ማላዊ ውስጥ ለሚገኙ ህጻናት የተሰራጨ ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅት ይሁንታውን እስኪሰጥ እየተጠበቀ ነው። በዚህ ሙከራ ላይ የትኛውም ህጻን ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንዳላስተናገደ ተመራማሪዎቹ አስታውቀዋል። በዚህም መሰረት ህጻናት ክትባቱን እና መከላከያ መድኃኒቶቹን እስከ 5 ዓመታቸው ድረስ እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን በዚያውም ሌሎች የተሻሉ አማራጮች ከመጡ አብረው እንደሚካተቱ ተገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58345206 +health በሉትዌንያ ከአንድ ኪሎ በላይ ብረታ ብረቶች ከሆዱ ውስጥ የወጣለት ግለሰብ "ከአንድ የሉትዌንያ ዜጋ ሆድ ውስጥ ከአንድ ኪሎ በላይ የሚመዝኑ የተለያዩ አይነት ብረታ ብረቶች መውጣታቸውን የአገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን ዘገቡ። ከግለሰቡ ሆድ ውስጥ በቀዶ ህክምና ብረታ ብረቶቹን ያወጡት ሐኪሞች እንዳሉት ሚስማሮችን፣ ቡሎኖችንና ቢላዎችን ማውጣት ችለዋል። ዶክተሮች እንዳሉት ግለሰቡ የአልኮል መጠጥ ካቆመ በኋላ ለአንድ ወር ያህል የተለያዩ ብረታ ብረቶችን ሲውጥ ቆይቶ እንደነበር ደርሰውበታል። ክላይፔዳ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሚገኘው ሆስፒታል ውስጥ በተደረገው ቀዶ ህክምና ወቅት ከግለሰቡ ሆድ ውስጥ ከተገኙት ብረቶች መካከል 10 ሴንቲ ሜትር ድረስ የሚረዝሙ እንዳሉበት ተዘግቧል። ቀዶ ህክምናውን ያደረጉት ዶክተር ሳሩናስ ዳይሊዴናስ ከአንድ ኪሎ በላይ የሚመዝኑትን ብረታ ብረቶች ከግለሰቡ ሆድ ውስጥ ካወጡ በኋላ እንደተናገሩት ያጋጠማቸውን ""የተለየ ጉዳይ ነው"" ሲሉ ገልጸውታል። ከግለሰቡ ሆድ ውስጥ ብረታ ብረቶቹን ለማውጣት ሦስት ሰዓታትን የፈጀ ቀዶ ህክምና የተደረገ ሲሆን አንድ የቀዶ ህክምና ትሪ ሙሉ ብረት መወገዱን የዩንቨርስቲው ሆስፒታል ይፋ ባደረገው ፎቶ ላይ ታይቷል። ግለሰቡ ወደ ሆስፒታል በአምቡላንስ የመጣው እጅግ ከባድ የሆድ ህመም ካጋጠመው በኋላ ሲሆን፤ ከቀዶ ህክምናው በኋላም ጤንነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። ነገር ግን አሁንም በሆስፒታል ውስጥ ሆኖ አስፈላጊው ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58756170 +politics ኡጋንዳ በአሜሪካ ጥያቄ 2ሺህ የአፍጋኒስታን ስደተኞችን ልትቀበል ነው ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ በአሜሪካ ጥያቄ 2ሺህ የአፍጋኒስታን ስደተኞችን ልትቀበል መሆኑ ተነገረ። ታሊባን አፍጋኒስታንን መቆጣጠሩን ተከትሎ በርካቶች አፍጋኒስታንን ለቀው ለመውጣት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። ትናንት እና ከትናንት በስቲያ አስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከአፍጋኒስታን ለመውጣት በመዲናዋ የሚገኘውን አየር ማረፊያ አጨናንቀው ታይተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ሰዎች አውሮፕላን ለመሳፍር በሚያደርጉት ጥረት ከ8 ያላነሱ የአፍጋን ዜጎች ሕይወታቸው አልፏል። ከእነዚህም መካከል በአውሮፕላን ተገጭተው እንዲሁም አውሮፕላን ላይ ተንጠልጥለው አውሮፕላኑ ከተነሳ በኋላ ወድቀው ሕይወታቸው ያለፉ ስለመኖራቸው በስፋት ተዘግቧል። የኡጋንዳ የስደተኞች ጉዳይ ሚኒስትር ኢስተር አንያኩን ለቢቢሲ እንደገለፁት ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ስደተኞቹን በአሜሪካኖች ጥያቄ ለመቀበል ተስማምተዋል። ይህ የሆነው በሳምንቱ መጨረሻ እጅግ ፈጣን የሆነው ታሊባን መስፋፋት እና የአፍጋኒስታን መንግሥት መውደቅን ተከትሎ ነው። የመጀመሪያቹ 500 የሚጠጉ አፍጋኒስታን ዜጎች በኢንቴቤ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በጥቂት ሰዓታት ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሚንስተሯ አክለውም ስደተኞቹ የኮቪድ ምርመራ እንደሚደረግላቸው እና ለይቶ ማቆያ እንደሚገቡ ተናግረዋል። ሁሉም ሎጂስቲክስ እና ወጪዎች በአሜሪካ መንግሥት ይሸፈናሉ። ኡጋንዳ ከአፍጋኒስታን ወቅታዊ ቀውስ የሚሸሹ ሰዎችን በመቀበል የመጀመሪያዋ የአፍሪካ ሀገር ትሆናለች። ኡጋንዳ ስደተኞችን በማስተናገድ ረጅም ታሪክ አላት። በአሁኑ ጊዜ ከግጭቶች ወይም ከሌሎች አደጋዎች የሸሹ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞች መኖሪያ ነች። በኡጋንዳ የሚገኙ ስደተኞች ከሃገሪቱ ዜጎች ጎን በመንደሮች ወይም በመጠለያዎች ውስጥ ይኖራሉ። አንዳንዶቹ መሬት ተሰጥቷቸው እንዲሠሩም ተፈቅዶላቸዋል። ታሊባን በከፍተኛ ፍጥነት በርካታ የአፍጋኒስታን አካባቢዎችን በመቆጣጠር ከትናንት በስቲያ እሁድ በመዲናዋ ካቡል የሚገኘውን ፕሬዝደንታዊ ቤተ-መንግሥት ወርሷል። ነገሮች በፍጥነት በተቀያየሩባት አፍጋኒስታን፤ የአገሪቱ ፕሬዝደንትም አገር ጥለው ሸሽተዋል። ታሊባን በጎርጎሮሲያዊያኑ 1990ዎቹ መጀመርያ በሰሜን ፓኪስታን ብቅ ያለ መደበኛ ያልነበረ እንቅስቃሴ ነበር። እንደ ጎርጎሮሶዊያኑ 1998 ታሊባን የአፍጋኒስታንን 90 ከመቶ ይቆጣጠር ነበር። በዚያን ጊዜ ሕዝብ ዘንድ ሰፊ ተቀባይነትን ማግኘት ችሎ ነበር። ይሁን እንጂ አፍጋኒስታንን ሲያስስተዳድሩ የነበሩት ታሊባኖች እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ በ2001 በአሜሪካን አማካኝነት ሥልጣናቸውን አጥተው ነበር። አሜሪካ ለ20 ዓመታት ከቆየችበት አፍጋኒስታን ጦሯን ማስወጣቷን ተከትሎ ታሊባን መላ አፍጋኒስታንን መልሶ በመያዝ ሥልጣን በእጁ ማስገባት ችሏል። https://www.bbc.com/amharic/58246649 +business የኬንያ አየር መንገድ ‘ኢትዮጵያ ገንዘቤን ትክፈለኝ’ ሲል ጠየቀ ከፍተኛ ኪሳራ ላይ የሚገኘው የኬንያ አየር መንገድ ለኢትዮጵያ መንግሥት የክፍያ ጥያቄን አቀረበ። ክፍያው የኬንያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ ለሰጣቸው አገልግሎትና ሽያጮች ገንዘብ ከብር ወደ ዶላር ተቀይሮ  መሰጠት የነበረበት ነው። አየር መንገዱ ተመሳሳይ ጥያቄን ለናይጄሪያ መንግሥትም አቅርቧል። በአሠራር ደረጃ አየር መንገዶች አገልግሎታቸውን በውጭ አገራት ሲሸጡ በአገሬው ገንዘብ ከተገበያዩ በኋላ ገንዘባቸው የሚሰጣቸው በዶላር ነው። የኬንያ አየር መንገድ በሁለቱ አገራት የሚገኘውን ገንዘቡን ማግኘት ያልቻለው በውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደሆነ ይታመናል። የኬንያ ባለሥልጣናት ለኬንያ አየር መንገድ የሚገባውን ክፍያ እንዲሰጡ የኢትዯጵያንና የናይጄሪያን ባለሥልጣናት በማነጋገር ላይ እንደሆኑ ተዘግቧል። ገንዘቡ በአየር መንገዶችና በአገሮች መካከል የገቢ ክፍያ ልውውጥ በጊዜ ባለመካሄዱ የተከሰተ ችግር ነው። የኬንያ አየር መንገድ ሁለቱ መንግሥታት ሊከፍሉት ይገባ የነበረ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ሊያገኝ ያልቻለው ግን በዋናነት በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ነው። የኬንያ አየር መንገድ በአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ የተነሳ፣ እንዲሁም በሌጎስና አዲስ አበባ ባጋጠመ የውጭ ምንዛሬ እጦት ገንዘቡ ስላልተከፈለው ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 82 ሚሊዮን ዶላር ከስሬያለሁ ብሏል። ሆኖም የኬንያ ባለሥልጣናት አየር መንገዱ ከሁለቱ አገሮች ምን ያህል ገንዘብ ማስመለስ እንዳልቻለ ትክክለኛ አሐዝ ከመግለጽ ተቆጥበዋል። የአገሪቱ ባለሥልጣናት አሁን ይህን ለኬንያ አየር መንገድ የሚገባውን ገንዘብ ከአዲስ አበባና ከሌጎስ ለማግኘት ዲፕሎማሲን አማራጭ አድርገዋል። በተያያዘ ዜና የዓለም አቀፉ አየር ትራንስፖርት ማኅበር ይፋ እንዳደረገው ለተለያዩ አየር መንገዶች መከፈል የነበረበት ግማሽ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በናይጄሪያ ቀርቷል። የዱባዩ ኢምሬትስ ግሩፕ በተመሳሳይ በናይጄሪያ የሚገኘው ገንዘቤን ማግኘት አልቻልኩም በሚል ወደዚያ የሚያደርጋቸውን በረራዎች ማቋረጡ ይታወሳል። ይህም የዶላር እጥረት በአቪየሽን ኢንዱስትሪው የፈጠረው ሌላ ችግር ሆኖ ተመዝግቧል። የውጭ አየር መንገዶች አገልግሎታቸውን መሸጥ ያለባቸው በአገሬው የመገበያያ ገንዘብ ነው። ይሁንና ገንዘባቸውን የሚወስዱት ግን ወደ አሜሪካን ዶላር ከተቀየረ በኋላ ነው። መደበኛ አሠራሩ ይህ ይሁን እንጂ በርካታ አገሮች በውጭ ምንዛሬ እጥረት በመቸገራቸው ዕዳቸውን በዶላር ለመክፈል እየተንገታጉ ይገኛሉ። በአፍሪካ የሕዝብ ቁጥር ቀዳሚ የሆነችው ናይጄሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ግዙፍ የውጭ ኩባንያዎች ላቀረቡት ምርትና አገልግሎት በሚከፈ���ቸው ዶላር መጠን ላይ ገደብ ለመጣል ተገዳለች። https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2eg5v0gx4o +business 20 ዶላር ለማዳን ወንዝ የገባው ላይቤሪያዊ ሰምጦ ቀረ 20 ዶላር ለማውጣት ወንዝ የገባው ወጣት ሕይወት ተቀጠፈ አሳዛኝ አጋጣሚ ነው፡፡ ይህ ወጣት በላይቤሪያ ዋና ከተማ ሞንሮቪያ ነዋሪ ነው፡፡ ክፉ አጋጣሚ፤ ድልድይ ሲሻገር 20 ዶላር ወደቀበት፡፡ 20 ዶላሯ በንፋስ ተንከላውሳ ወንዝ ውስጥ ስትገባ ተመለከታት፡፡ አላስቻለውም፡፡ ዘሎ ገባ፤ ተከተላት፡፡ ስሙ ታምባ ላሚኔ ይባላል፡፡ ቸርቻሪ ነው፤ የጎዳና ለፍቶ አዳሪ፡፡ የሚደንቀው ታዲያ ሰምጦ አልቀረም፡፡ 20 ዶላሯን ይዟት ወጣ፡፡ ተሰብስበው ሁኔታውን ይመለከቱ ለነበሩ ሰዎችም አሳያቸው፡፡ ከዚያ ግን ድንገት ተመልሶ ሰመጠ፡፡ ላሚኔ 20 ዶላሯትን ተከትሏት ወንዝ ሲገባ ከጓደኛው ጋር በእግር እየተጓዙ ነበር፡፡ ድልድዩ ላይ ሲደርሱ ግን እንዴት ዶላሯ ከእጁ እንዳመለጠች አልታወቀም፡፡ ገንዘቡን ማዳን የፈለገው አብሮት ለሚሰራው ጓደኛው ለመክፈል ነው፡፡ እዳ ነበረበት፡፡ ከ20 ዶላሩ 5ቱ ዶላር የሱ አይደለም፡፡ ለመስጠት ብሎ ነው፡፡ 5ቱን ዶላር የሚመልሰው ሁለቱ ጓደኛሞች አንድ በጋራ የሰሩት ‹ሽቀላ› ነበር፡፡ ትርፉን ሊጋሩ ተስማምተው ነበር፡፡ ላሚኔ በዚህ መንገድ ሕይወቱን ማጣቱ አሳዛኝ ክስተት ሆኗል፡፡ ላይቤሪያ ከአሜሪካና ከካሪቢያን በግፈኛና ዘረኛ ነጮች ነጻ የተደረጉ የቀድሞ ‹ባሪያዎች› የተፈጠረች አገር ናት፡፡ በዚያች አገር የአሜሪካን ዶላር ከላይቤሪያ ገንዘብ ጋር ጎን ለጎን አገልግሎት ይሰጣል፡፡ አሁን አሁን የዶላር ዋጋ ለላይቤሪያ ገንዘብ ጋር ሲነጻጸር በከባድ ሁኔታ እየጠነከረ በመምጣቱ ዶላር ትልቅ ዋጋ እንዲሰጠው አድርጓል፡፡ የላሚኔ ሬሳ እንስከሁን አልተገኘም፡፡ ሰምጦ የቀረው በመሱራዱ ወንዝ ውስጥ ነው፡፡ ወንዙ ከሞንሮቪያ ተነስቶ በሽሮድ ደሴት ይዘልቃል፡፡ የዶላሩንና የወጣቱን ሁኔታ ለማየት የተሰበሰበው ሰው ላሚኔ 20 ዶላሯን ከፍ አድርጎ ለአፍታ ሲያሳያቸው ገንዘቡም እሱም ተርፈዋል ብለው ተደስተው ነበር፡፡ያጨበጨቡም ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከአፍታ ቆይታ በኋላ ላሚኔ በዚያው ሰምጦ ቀርቷል፡፡ 20 ዶላሩን እንደዚያው፡፡ የላሚኔ ሞት በሞንሮቪያ ከፍተኛ ሐዘን መፍጠሩን የቢቢሲ ዘጋቢ ጽፏል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/54453318 +sports የኳታር የዓለም ዋንጫ፡ ኃያላኑን ቤልጂየም እና ጀርመን በጊዜ ተሰናበቱ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቤልጂየም እና ጀርመን በጊዜ ሲሰናበቱ ብዙ ያልተጠበቁት ሞሮኮና ጃፓን ደግሞ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈለዋል። ትላንት ምሽት የምድብ አምስት እና ስድስት የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ተከናውነዋል። በምድብ አምስት የምትገኘው ጃፓን ትላንት አወዛጋቢ በሆነ መንገድ ጎል በማስቆጠር ስፔንን አሸንፋ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። አልቫሮ ሞራታ በ11ኛው ደቂቃ ስፔንን ቀዳሚ ማድርግ ቻለ። ስፔኖች በመጀመሪያው አጋማሽ የነበራቸውን የበላይነት ተጠቅመው ተጨማሪ ጎሎችን ማስቆጠር አልቻሉም። በሁለተኛው አጋማሽ በሦስት ደቂቃ ልዩነት ዶአን እና አኦ ታናካ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ጃፓን አሸናፊ ለመሆን ችላለች። ታናካ ሁለተኛውን ጎል ከማስቆጠሩ በፊት ኳሱ ከሜዳ የወጣ ቢመስልም በቪዲዮ የታገዘ ዳኝነት (ቫር) ኳሱ መስመሩን አለማለፉን በማሳወቁ ጎሉ ጸድቋል። በዚህም ጨዋታው 2 ለ1 ተጠናቋል። በዚህ ምድብ የሚገኙት ጀርምን እና ኮስታ ሪካ ያደረጉት ጨዋታም መልከ ብዙ ነበር። አራቱም ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋ የነበራቸው ሲሆን በጨዋታዎቹ ወቅት አራቱም ቡድኖች የማለፍ ዕድል የፈጠሩበት ጊዜም ተፈጥሯል። ጀርመን በቀድሞ አርሰናል ተጫዋች ግናብሪ አማካይነት ቀዳሚ መሆን ቻለች። በዚህ ወ��ት ስፔን ጃፓንን 1 ለ 0 እየመራች ስለነበር ጀርመን እና ስፔን ተያይዘው ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያወልፉ መስሎ ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ ኮስታ ሪካ በተከታታይ ባስቆጠረቻቸው ጎሎች ቀዳሚ መሆን ቻለች። በዚህ ወቅት ስፔንም 2 ለ1 በመመራቷ ከምድቡ ኮስታሪካ እና ጃፓን ተያይዘው ሊያልፉ መስሎ ነበር። ጀርመን የኋላ ኋላ በሃቨርትዝ ሁለት ጎሎች እና በፉልክግ ተጨማሪ ጎል  ጨዋታውን 4 ለ 2 ማሸነፍ ቻለች። ከዚህ ሁሉ ድራማ በኋላ ጃፓን ምድቡን በስድስት ነጥብ  አንደኛ ሆና አጠናቃለች። ስፔን እና ጀርመን አራት አራት ነጥብ በመያዝ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ምስጋና ኮስታ ሪካ ላይ ላዘነበችው የጎል ናዳ ይሁንና ስፔን ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች። ጀርመን እና ኮስታሪካ ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ ሃገራቸው ይመለሳሉ። የምድብ ስድስት የመጨረሻ ጨዋታዎችም ትላንት ምሽት ተከናውነዋል። በዚህም ሞሮኮ ካናዳን በማሸነፍ ምድቡን በበላይነት ማጠናቀቅ ችላለች። የአትላስ አንበሶቹ በሃኪም ዛይች አማካይነት በአራተኛው ደቂቃ ቀዳሚ ለመሆን ቻሉ። ዩሴፍ ኤን-ነስሪ ሁለተኛ ጎል አስቆጥሮ የሞሮኮን ድል ይበልጥ አስተማማኝ አደረገው። የሞሮኮው ናይፍ አጉርድ በራሱ ላይ በማስቆጠሩ ካናዳ የማስተዛዘኛ ጎል ለማግኘት በቃች። ይህቺ ጎል የኳታሩ ዓለም ዋንጫ 100ኛ ጎል ሆና ተመዝግባለች። ጨዋታውም በሞሮኮ 2 ለ 1 የበላይነት ተጠናቋል። በሌላ የምድቡ ጨዋታ ክሮሽያ እና ቤልጂየም ያለምንም ጎል አቻ  ተለያይተዋል። ጨዋታው በሩሲያው የዓለም ዋንጫ ሁለተኛ በወጣችው ክሮሽያ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ባጠናቀቀችው ቤልጂየም መካከል ነበር። ቤልጂየም ማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ቢያሳልፋትም ውጤታማ መሆን ሳትችል ቀርታለች። ከጉዳት የተመለሰው ሮሜሉ ሉካኩ ተቀይሮ ገብቶ በተደጋጋሚ ያገኛቸውን ዕድሎች ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል። በመጨረሻም ክሮሽያ ለቀጣዩ ዙር የሚያስፈልጋትን አንድ ነጥብ አሳክታለች። በቅርቡ እንኳን የፊፋን የሃገራት ሰንጠረዥ ስትመራ የነበረችው አሁን ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን የያዘችው ቤልጂየም ‘ከወርቃማ ትውልዷ’ ተስፋን እንጂ ውጤት ማሳካት ሳትችል ቀርታለች። የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ከጨዋታው በኋላ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተናግረዋል። ስፔናዊው አሰልጣኝ በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ አንድ ጎል ብቻ ያስቆጠረው ቡድናቸውን የተረከቡት በ2016 ነበር። “የመጨረሻ ጨዋታዬ ስለነበር ስሜታዊ ያደርጋል። ይህ ውሳኔ ከዓለም ዋንጫው በፊት የተወሰነ ነው” ብለዋል ማርቲኔዝ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ። ውጤቶቹን ተከትሎ ሞሮኮ በሰባት ነጥብ ምድቡን እየመራች ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። ክሮሽያ በአምስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ቤልጂም እና ካናዳ ጥሎ ማለፉን ሳይቀላቀሉ መቅረታቸውን አረጋግጠዋል። ሰኞ ጃፓን እና ክሮሽያ በጥሎ ማለፉ ይገናኛሉ። ሞሮኮ ስፔንን ሰኞ ዕለት ትገጥማለች። የዓለም ዋንጫው የመጨረሻዎቹ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ይከናወናሉ። ዛሬ ምሽት 12፡00 ሰዓት ደቡብ ኮሪያ ከፖርቹጋል እና ጋና ከኡራጓይ ይጫወታሉ። ፖርቹጋል ከዚህ ምድብ ማለፏን አረጋግጣለች። ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ጋና ማሸነፍ ከቻለች ጥሎ ማለፉን ትቀላቀላለች። ደቡብ ኮሪያ እና ኡራጓይም ከምድቡ የማለፍ እድል አላቸው። ምሽት አራት ሰዓት ደግሞ ሰርቢያ ከስዊዘርላንድ እና ካሜሮን ከብራዚል የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ። ብራዚል ከዚህ ምድብ ማለፏን ቀድማ አረጋግጣለች። ሦስት ነጥብ ያላት ስዊዘርላንድን ጨምሮ ካሜሮን እና ሰርቢያም የማለፍ ተስፋ አላቸው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1kq7ed54xo +politics ሊባኖስ ከዓመት በኋላ ባለሀብቱን ፖለቲከኛ ��ቅላይ ሚኒስትር አድርጋ ሾመች ሌባኖስ የቀድሞው አስተዳደር ሥልጣን ከለቀቀ በኋላ በአገሪቱ ቁጥር አንድ ባለሀብቱን ናጂብ ሚካቲን በጠቅላይ ሚኒስትርነት በመሰየም አዲስ መንግሥት አቋቋመች። ከአንድ ዓመት በፊት ውድመትን ያስከተለው በቤይሩት ወደብ ላይ ከደረሰው ከባድ ፍንዳታ በኋላ ነበር የቀድሞው የሊባኖስ አስተዳር ሥልጣን የለቀቀው። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሊባኖስ ውስጥ ቀዳሚው ባለሀብት ሲሆኑ ከዚህ ቀደምም ሁለት ጊዜ በዚሁ ኃላፊነት ላይ አገልግለዋል። ናጂብ ሚካቲ በጠቅላይ ሚኒስትር ቦታ ላይ መሰየምና ኢዲስ የካቢኔ ሚኒስትሮች መሾም የአገሪቱን ፖለቲካ እና አስተዳር ለወራት አሽመድምዶት የቆየውን ክፍተት ይሞላዋል ተብሏል። አዲሱ መንግሥት የተቋቋመው ሊባኖስ በታሪኳ ከገጥሟት ቀውሶች የተወሳሰቡ የአገር ውስጥ በርካታ ችግሮችን እየታገለች ባለበት ጊዜ ነው። የአገሪቱ ገንዘብ ዋጋ ወድቋል፣ የሥራ አጥ ቁጥርና የዋጋ ውድነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ የኤሌክትሪክ፣ የነዳጅ እና የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ለሕዝቡን ኑሮ አክብዶታል። በዚህ እየተነሳ መላዋ ሊባኖስ መሠረታዊ የፖለቲካ ለውጥ እንዲደረግ በሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎች ስትናጥ እነሆ ሁለት ዓመታት ተቆጥረዋል። ከአንድ ዓመት በፊት የቤይሩት ወደብን ያወደመውና ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን አሰቃቂ ፍንዳታ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሰን ዲያብ ሥልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ ሊባኖስ በአግባቡ ሥራውን የሚያከናውን መንግሥት ሳይኖራት ቆይታለች። በወደቡ ላይ ፍንዳታ የተከሰተው በአግባቡ ባልተከማቸ አሞኒየም ናይትሬት በተባለ አደገኛ ንጥረ ነገር ሲሆን፤ አደጋው ለ203 ሰዎች ሞት ምክንያት ሲሆን ከ6ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። ፍንዳታው በቢሊዮኖች ዶላር የሚገመት የንበረት ውድመትን በአገሪቱ ላይ አስከትሏል። በኮሮናቫይረስ ምክንያት በተከሰተ የኢኮኖሚ ቀውስ ወቅት የደረሰው ይህ አደጋ በሊባኖስ መንግሥት ላይ ከባድ ቁጣና ተቃውሞን ቀስቅሷል። ተቃዋሚዎች የፍንዳታውን ምክንያት በአገሪቱ መንግሥት ውስጥ ያለው ሙስና፣ የብቃት ማነስና ብልሹ ፖለቲካዊ ሹመት እንደሆነ ከሰዋል። አደጋው አገሪቱ የገጠማትን ምጣኔ ሀብታዊና ፖለቲካዊ ቀውስ የበለጠ ያባባሰው ሲሆን ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ የሊባኖስ ገንዘብ 90 በመቶ የመግዛት አቅሙን አጥቷል። በዚህም ሳቢያ በርካታ የአገሪቱ ዜጎች በድህነት ውስጥ ለመኖር ተገደዋል። በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሾሙ በኋላ ናጂብ ሚካቲ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቀዳሚ ተግባራቸው የአገሪቱን ኢኮኖሚ መታደግ መሆኑን አመልክተው ለዚህም ከዓለም የገንዘብ ድርጅት ጋር ንግግር እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል። ባለጸጋው አዲሱ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምረውም ምንም እንኳን እርሳቸው ሀብታም ቢሆኑም በአገሪቱ ያለው ቀውስ በሕዝቡ ህይወት ላይ ምን ያህል ጫናን እንዳሳረፈ እንደሚረዱ ገልጸል። በሊባኖስ ያለው ሐይማኖትን መሠረት ያደረገ የሥልጣን ክፍፍል ከአንድ ዓመት በፊት ሐሰን ዲኣብ ሥልጣን ሲለቁ አዲስ ለመንግሥት ለመመስረት የተደረገውን ጥረት እንዳይሳካ አድርጎት ቆይቷል። እንደ አውሮፓውያኑ ከ1975 አስከ 1990 በአገሪቱ የተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ማብቃትን ተከትሎ የተዘረጋው ሥርዓት የፖለቲካ ሥልጣን በተለያዩ የሐይማኖት ተከታዮች እንዲያዝ ያደርጋል። በዚህም መሠረት የአገሪቱ ፕሬዝዳንትነት ሥልጣን በክርስቲያኖች የሚያዝ ሲሆን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታው በሱኒ ሙስሊሞች እንዲሁም የምክር ቤት አፈ ጉባኤነት ቦታው ደግሞ በሺዓ ሙስሊሞች እንዲዝ ይደረጋል። አሁን ተከስቶ አገሪቱን በአግባቡ የሚመራ አስተዳደር እንዳ��ኖራት ያደረገው ይህ ሂደት ጊዜን የሚፈለግና ውስብስብ ነው። በዚህ አሰራር የሚሾሙት ሚኒስትሮች በሁሉም ሐይማኖቶችና አንጃዎች ይሁንታን ካላገኙ መንግሥት የመመስረቱ ሂደት ረጅም ጊዜን በሚፈጅ ድርድር ይጓተታል። https://www.bbc.com/amharic/news-58519816 +sports ማንቸስተር ዩናይትድ ሮማን 'ሲረመርም' አርሰናል ተሸንፏል "ብሩኖ ፈርናንዴዝና ኤዲሰን ካቫኒ እያንዳንዳቸው 2 ጎሎችን በማስቆጠር በትናንትው ምሽት የዩናይትድ ድልን አድምቀውት አምሽተዋል። በአውሮፓ ሊግ አሊያም እነሱ እንደሚሉት በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ በታዋቂው ኦልድ ትራሮፍርድ የእንግሊዙ ማንቸስተር ዩናይትድና የጣሊያኑ ሮማ ሐሙስ ምሽት ተፋልመዋል። ማንቸስተር ዩናይትድ 6 ለ 2 ሮማን 'ረምርሟል'። በጨዋታው ዩናይትዶች በብሩኖ ፈርናንዴዝ አማካይነት በጨዋታ መባቻ ቅድሚያ ቢያገኙም ሮማዎች በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት ጎሎችን አከታትለው አስቆጥረዋል። የበረኛው ሳጥን ውስጥ ፖል ፖግባ ኳስ በእጁ በመንካቱ የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት ሎሬንዞ ፔሌግሪኒ ሲያስቆጥር የቀድሞው የማንቸስተር ሲቲው አጥቂ ኤዲን ዤኮ ደግሞ ሁለተኛውን አስቆጥሮ ነው ቡድኖቹ እረፍት የወጡት። ነገር ግን ማንቸስተር ዩናይትድ አፈር ልሶ በመንሳት በሁለተኛው አጋማሽ ውጤቱን ቀልብሶታል። ኡራጋያዊው ጉምቱ አጥቂ ኤዲሰን ካቫኒ ከእረፍት መልስ ባስቆጠራት ጎል ዩናይትድ አቻ ሆነ። በዚህ ያልተመለሰው ካቫኒ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ በረኛው የመለሳትን ኳስ አግኝቶ እንደገና ከመረብ ዶላት። የአሠልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ልጆች እንደ መጀመሪያው አጋማሽ ሮማ ጎል እንዲያስቆጥርባቸው አልፈቀዱም። ምንም እንኳ ዩናይትድ ያገኘው ፍፁም ቅጣት ምት ዕድለኛ የሚያስብለው ቢሆንም ክሪስ ስሞሊንግ የሠራውን ጥፋት ተከትሎ የተገኘችውን 'ሪጎሬ' ፈርናንዴዝ ወደ ጎል ከመቀየር ያገደው አልነበረም። በስተመጨረሻ ታዳጊው ግሪንውድ ከካቫኒ የተሻገረችለትን ኳስ በቀኝ እግሩ ወደ መረብ በመላክ ስድስተኛዋን ጎል አስቆጥሯል። ቀጥሎ ደግሞ ፈረንሳዊው ፖል ፖግባ ከፈረናንዴዝ የተሻመለትን ኳስ በጭንቅላቱ ከመረብ አዋህዷታል። ማንቸስተር ዩናይትድ በአውሮፓ ከፍተኛ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ስድስት ጎል በማስቆጠር ታሪክ ፅፈዋል። ዩናይትድ በአውሮፓ ጨዋታ ሮማ ላይ በርካታ ጎል ሲያዘንብ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በአውሮፓ ቻምፒዬንስ ሊግ በ2007 በተገናኙ ወቅትም ጎል እንደ በረዶ ወርዶ ነበር። የአሁኑ አሠልጣኝ ሶልሻዬር ተቀያሪ በነበረት ጨዋታ ዩናይትድ ሮማን 7ለ 1 ነበር የረታው። ኦሌ ምናልባት ዋንጫ ማንሳት የሚችል ከሆነ 'ልምድ የለውም'፤ 'ዋንጫ መብላት አይችልም' ሲሉ የሚሞግቱ ተቺዎቹን አፍ ሊዘጋ ይችላል። ዩናይትድ ወደ ፍፃሜው የሚያደርገውን ጉዞ ያሳመረ ይመስላል። ተንታኞች ለዩናይት በቀጣዩ ወር የፍፃሜ ጨዋታ አስጊ ሊሆን የሚችለው አንድ ነገር የተከላካይ መስመሩ ነው ይላሉ። ምንም እንኳ የዩናይትድ ተከላካይ መስመር ባለፉት ስድስት የአውሮፓ ሊግ ጨዋታዎች አንድ ጎል ብቻ ቢቆጠርበትም ከሮማ ጋር በነበረው ጨዋታ ግን ሁለት ጎል አስተናግዷል። ከጨዋታው በኋላ አስተያየት የሰጠው ኦሌ ""መልካም ውጤት ነው ግን ሥራችን አልተጠናቀቀም"" ሲል ተደምጧል። በሌላኛው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ አርሰናል በቪያሪያል 2 ለ 1 ተሸንፏል። በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት ጎሎች የተቆጠሩበት አርሰናል በሁለተኛው አጋማሽ በተገኘች ፍፁም ቅጣት ምት ተስፋ የምትሰጥ አንድ ጎል አስቆጥሮ ወደ መቀመጫው ለንደን ተመልሷል። የግማሽ ፍፃሜ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ ይከናወናሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-56939667 +politics ፔሎሲ ወደ ታይዋን ቢያቀኑ መዘዙ ከባድ ይሆናል ስትል ቻ��ና አስጠናቀቀች የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ታይዋን ቢያቀኑ መዘዙ ከባድ ነው ስትል ቻይና አስጠነቀቀች። አፈ ጉባኤዋ ታይዋንን ሊጉበኙ ነው የሚል መረጃ መውጣቱ ቻይናን እጅጉን አበሳጭቷል ተብሏል። ለአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ መንበር ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ፔሎሲ፤ የራስ ገዝ ግዛት ወደሆነችው ታይዋን ጉዞ ቢያደርጉ ከእአአ 1997 ወዲህ ታይዋንን የጎበኙ ከፍተኛ ባለስልጣን ያደርጋቸዋል። ታይዋን ራሷን እንደ ሉዓላዊ ግዛት ብትቆጥርም ቻይና ግን እንደ ተገነጠለች ግዛቷ ነው የምትመለከታት። ቻይና አስፈላጊ ከሆነም በኃይል ታይዋንን መልሳ የግዛቷ አካል ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል ከዚህ ቀደም ገልጻለች። ይህ የፔሎሲ ጉዞ ቤጂንግን ማበሳጨት ብቻ ሳይሆን፤ የባይደን አስተዳደርም የጂኦፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ከትቷል። ዋይት ሃውስ ፔሎሲ ወደ ታይዋን እንዳይጓዙ ጫና እያሳደረ መሆኑም ተገልጿል። ከአንድ ሳምንት በፊት ፕሬዝዳንት ባይደን የፔሎሲን ጉዞ በተመለከተ፤ “ጦሩ ጥሩ ሃሳብ አይደለም ብሎ ያስባል” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረው ነበር። ዋይት ሃውስ ደግሞ የቻይናን ማስጠንቀቂያ “ጠቃሚ ያልሆነ” ሲል ገልጾታል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በበኩሉ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ለመሄድ በይፋ አለማሳወቃቸውን እና አሜሪካ በታይዋን ጉዳይ ያላት አቋምም እንዳልተቀየረ ገልጿል። አሜሪካ ታይዋን ራሷን እንድትከላከል ለመርዳት የሚያስገድድ ሕግ አላት። ይህ ሕግ ግን ሆነ ተብሎ ግልጽ እንዳይሆን ተደርጓል። በዚህም ቻይና ታይዋንን ብታጠቃ የአሜሪካ ምላሽ በትክክል ምን ሊሆን እንደሚችል ግልጽ አይደለም። ይሁን እንጂ አሜሪካ ለታይዋን የጦር መሳሪያዎችን ስትሸጥ ቆይታለች። ታይዋን የምትመራበት የራሷ የሆነ ሕገ-መንግሥት አላት። በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጡ መሪዎችም አሏት። ከ300 ሺህ ያላነሰ የጦር ሠራዊት አባላትም ባለቤት ነች። የአሜሪካ ኮንግረስ ለታይዋን ጠንካራ ድጋፍ ይሰጣል። በምክር ቤት አባልነት ከ35 ዓመት በላይ ልምድ ያላቸው ፔሎሲ ቻይናን አጥብቀው በመተቸት ይታወቃሉ። የቻይናን የሰብዓዊ መብት አያያዝ እና በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ደጋፊዎች ላይ የሚደርሰውን ጫና በማንሳት ቻይናን ይተቻሉ። ፔሎሲ የታይዋን ጉዟቸውን በተመለከተ በዝርዝር ያሉት ነገር ባይኖርም፤ ከአንድ ሳምንት በፊት “ለታይዋን ድጋፍ ማሳየታችን ለእኛ አስፈላጊ ነው” ብለው ነበር። ቻይና እንደ አንድ የራሷ ግዛት አድርጋ የምታየት ታይዋን ከዋሽንግተን ዲሲ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግነኙነት ማጠናከሯ እረፍት ይነሳታል። ሚያዚያ 2014 ዓ.ም. አራት የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ታይዋንን መጎብኘታቸው ቻይናን አበሳጭቶ ነበር። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛሆ ሊጂአን ፔሎሲ ወደ ታይዋን የሚጓዙ ከሆነ፤ አገራቸው “ጠንካራ እርምጃ” ትወስዳለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ደግሞ ቤጂንግ ወታደራዊ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችልም ጠቁመዋል። “የአሜሪካ ወገን በዕቅዱ የሚቀጥል ከሆነ፤ የቻይና ጦር ዝም ብሎ አይመለከትም። የውጪ ጣልቃ ገብነትን ለማስቆም እና ተገንጣይ ኃይሎች ‘ነጻ ታይዋንን’ ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጥረት ለመቀልበስ ጠንካራ እርምጃ ይወስዳል” ሲሉ ኮሎኔል ታን ኬፊ ለቻይና ዴይሊ ተናግረዋል። ቻይና እና ታይዋን የተለያዩት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሲሆን በጊዜው ቻይና ራሷ በአንድነት መንግሥት እና በኮሚዩኒስት ፓርቲ መካከል ለሁለት ተከፍላ ጦርነት ላይ ነበረች። በአውሮፓውያኑ 1949 ኮሚዩኒስት ፓርቲ ድል ሲቀዳጅ የወቅቱ መሪ ማኦ ዜዱንግ ቤይጂንግን መቆጣጠር ቻሉ። ሽንፈትን ያስተናገዱት የብሔራዊ ፓርቲው ደጋፊዎችና መሪዎች ታይዋን ሸሽተው ገቡ። የፓርቲው መሪ ቻንግ ካይ ሼክም ታይዋንን መደበቂያቸው አደረጓት። ትንሽ ቆይተውም ኩሚ ታንግ የተባለውን ፓርቲ እዚያው ታይዋን ውስጥ መሠረቱ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ታዲያ ይህ ፓርቲ ታይዋን ውስጥ ወሳኝ የሚባል የፖለቲካ ክንፍ ሆኖ ቆይቷል። https://www.bbc.com/amharic/articles/czkl34lym4zo +health ኮሮናቫይረስ፡ የኦክስፎርድ ክትባት የአረጋውያንን የበሽታ መከላከያ 'ያነቃቃል' ተባለ "የኦክስፎርድ ኮሮናቫይረስ ክትባት በ60 ዎቹ እና በ70ዎቹ የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን በሽታ የመከላከል አቅም ጠንካራ በሆነ መልክ ማነቃቃቱ ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑና በዕድሜ የገፉ ሰዎቸን ሊጠብቅ ይችላል የሚል ተስፋን ፈንጥቋል። እንደ ተመራማሪዎቹ ከሆነ 560 ጤናማ በጎ ፈቃደኞችን መሠረት ያደረጉት የምዕራፍ ሁለት ግኝቶች ""አበረታች"" ናቸው። በምዕራፍ ሦስት ደግሞ ክትባቱ ኮቪድ -19 የያዛቸው ሰዎችን ይከላከል እንደሆነ ይጥናል፡፡ የዚህ ምዕራፍ ወሳኝ ውጤቶች በሚቀጥሉት ሳምንታት ይጠበቃሉ፡፡ ፋይዘር-ባዮኤንቴክ፣ ስፑትኒክ እና ሞደርና የተሰኑ ሦስት ክትባቶች በሦስተኛ ምዕራፍ ሙከራዎች ጥሩ ውጤት ማስመዝገባቸውን ሪፖርት አድርገዋል። አንዱ ክትባት ደግሞ ከ65 ዓመት በላይ ከሆኑ ሰዎች መካከል 94 በመቶ የሚሆኑት ከኮቪድ -19 ሊጠበቁ እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡ የኦክስፎርድ ሪፖርት የክትባቱን ደህንነት እና የሰውነት ምላሽን በሚፈትሽበት ቀዳሚ ምዕራፍ የተገኘ ነው። ለማከማቸት ማቀዝቀዣ ስለማይፈልግ ክትባቱ በረዥም ጊዜ በቀላሉ ሊዳረስ ይችላል ተብሏል። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የጥናት መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አንድሪው ፖላርድ ለቢቢሲ ከ70 ዓመት በላይ ለሆኑት ጠንካራ የመከላከል አቅም መፍጠሩ ""ፍፁም ደስ ብሎኛል"" ብለዋል፡፡ ክትባቱ ሰዎችን ከኮቪድ -19 መከላከሉን በተመለከተ አለመታወቁን ገልጸው፤ ቀጣይ ሪፖርት ""ከገና በፊት"" ይለቀቃል ብለዋል፡፡ ከሌሎች ክትባቶች ጋር ""ፉክክር የለም"" ያሉት ፕሮፌሰር ፖላርድ፤ በርካታ ክትባቶች ስኬታማ እንዲሆኑ ይፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በዓለም ዙሪያ ያሉትን ሰዎች ለመጠበቅ ሁሉንም እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ የኮሮናቫይረስ ክትባት የማዘጋጀት ተግዳሮት የሚሆነው በየትኛውም ዕድሜ ላይ ያለ ሰው የሰውነቱን በሽታ የመከላከል አቅም አዳብሮ ቫይረሱን እንዲዋጋ ማነቃቃቱ ነው፡፡ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ደካማ የሰውነት በሽታ የመከላከል ሥርዓት ስላላቸው ክትባቶች በወጣቶች ያላቸውን ውጤማነት ያህል አይደሉም ማለት ነው፡፡ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ሙከራዎች ተመሳሳይ ችግር ላይገጥማቸው ይችላል ማለት ነው፡፡ ዕድሜያቸው ከ56-69 እና ከ70 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ከ18-55 ዕድሜ ካላቸው አዋቂዎች ጋር ተመሳሳይ የመከላከል አቅም እንዳላቸው መረጃዎቹ አሳይተዋል፡፡ ""ቀጣዩ እርምጃ [ክትባቱ] ከበሽታው እንደሚከላከል ማየት ነው"" ሲሉ በኦክስፎርድ የክትባት ቡድን መርማሪ የሆኑት ዶ/ር ማሄሺ ራማሳሚ ገልጸዋል፡፡ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ቀለል ያሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችን የማያሳዩ ሲሆን ካሳዩም ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡ ChAdOx1 nCov-2019 የተባለው ክትባት ከባድ የደኅንነት ስጋቶች የሉትም ተብሏል፡፡ የኦክስፎርድ ክትባት ቫይረሱ ተዳክሞ በሰው ልጆች ውስጥ ማደግ እንዳይችል ሆኖ የተሠራ ነው። ክትባቱ ጥር ተጀምሮ ከሦስት ወር በታች በሆነ ጊዜ የተሠራ ሲሆን፤ ሰዎች ላይ ሙከራዎችን በማድረግ በአውሮፓ የመጀመሪያው ነው፡፡ ሰዎችን ከኮቪድ -19 የመከላከል አቅሙ ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ የሚመለከተው የክትባቱ ሦስተኛ ዙር ሙከራ ነሐሴ መጨረሻ ላይ ተጀምሯል፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-55003308 +business የግዙፉ አማዞን ሠራተኞች አሜሪካ ውስጥ የመጀመሪያውን ማሕበር መሠረቱ "የግዙፉ ቴክኖሎጂ ኩባንያ አማዞን ሠራተኞች አሜሪካ ውስጥ እውቅና ያለው ማሕበር በመመሥረት ታሪክ ፅፈዋል። ከግማሽ በላይ ኒውዮርክ የሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች የአማዞን ሠራተኞች ማሕበርን ለማቋቋም ተስማምተው ድምፅ ሰጥተዋል። ይህን አብዮት የመራው የቀድሞ የድርጅቱ ሠራተኛ የሆነውና ግዙፉ አማዞን ለሠራተኞቹ ደኅንነት ደንታ የለውም በማለት ሲሞግት የነበረው ክሪስ ስሞልስ ነው። የክሪስ ስሞልስ ድል ለዘመናት ሠራተኞች ማሕበር እንዳይመሠርቱ ሲታገል ለነበረው አማዞን ሽንፈት ሆኗል። ነገር ግን አላባማ ውስጥ በተመሳሳይ ማሕበር ለመመሥረት ጥረት እያደረጉ የነበሩ የአማዞን ሠራተኞች ሳይሳካላቸው ቀርቷል። አማዞን አሜሪካ ውስጥ በርካታ ሠራተኞች ካሏቸው ድርጅቶች መካከል ሁለተኛው ነው። ክሪስ ስሞልስ ከችሎት ሲወጣ ድካም የተጫጫነው ቢመስልም የድል ብርሃን ፊቱ ላይ ይበራል። ደስታውን የተጋሩ የድርጅቱ ሠራተኞች ቻምፖኝ ከፍተው ተራጭተዋል። ""ማሕበሩ እንዳይቋቋም ለማድረግ የተደረገውን ጥረት ለመርታት ብዙ ጥረት አድርገናል"" ሲል ለተሰበሰበው ሰው ተናግሯል። የማሕበሩን መቋቋም አስመልክቶ መግለጫ ያወጣው አማዞን በኒውዮርክ ሽንፈት እንደተበሳጨ አልካደም። ወደፊት እንዴት እንደምንቀጥል እየገመገምኩ ነው፤ አልፎም ያለአግባብ ድምፅ እንዲመጣ ያደረጉትን እመረምራለሁ ብሏል ድርጅቱ። ""ሠራተኞች ከድርጅቱ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ቢኖራቸው ይጠቀሙ ነበር"" ይላል የግዙፉ ድርጅት መግለጫ። የሩትገርስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ሬቤካ ጊቫን የክሪስ ስሞልስን ድል ""የዳዊትና ጎሊያድ"" ታሪክ ሲሉ ይገልጡታል። ነገር ግን ገና ብዙ ትግል ከዓለማችን ቱጃሩ ግለሰብ ድርጅት እንደሚጠብቀው ፕሮፌሰሯ ይናገራሉ። ""አማዞን ይህንን ድል ለመቀልበስ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ማሕበሩን ለማፈራረስ ብዙ ጉድጓድ ይቆፍራል። ይህ ድል ለሌሎችም መነሳሳት ስለሆነ።"" ክሪስ ስሞልስና የሠራተኞች አደራጅ ቡድኑ አሁን ማሕበር መሥርተዋል። አማዞን መታገል የሚችል ገለልተኛ የሠራተኞች ማሕበር አቋቁመዋል። ሰውዬው የቀድሞ የድርጅቱ ሠራተኛ ነው። አማዞን ክሪስን ""ብልሃት የሌለው፤ ንግግር የማይችል"" ሲል በአንድ ድብቅ ደብዳቤ ወቅሶት ነበር። የ33 ዓመቱ ክሪስ ለአራት ዓመታት ድርጅቱን ካገለገለ በኋላ በፈረንጆቹ 2020 የኮሮናቫይረስ ሕግጋት እየተጣሱ ነው ብሎ በመቃወሙ ነበር የተባረረው። ነገር ግን እንደ ክሪስ ተሰብስበው ለሚጠብቁት ሠራተኞች ""ነገር ግን ይህ ድል ከዚህም በላይ ነው።"" አማዞን አሜሪካ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች አሉት። ድርጅቱ ጥብቅ የሆነ አመራር በሠራተኞች ላይ በማራመድ ይታወቃል። አማዞን ከምሥረታው ጀምሮ ሠራተኞች ማሕበር እንዳይመሠርቱ ሲታገል ቆይቷል። ነገር ግን ይህ ድል ሌሎችም የድርጅቱ ሠራተኞች ማሕበር እንዲመሠርቱ ማነሳሻ ይሆናል ሲሉ ተሟጋቾች ተስፋ ያደርጋሉ። አማዞን የመጋዘን ፍጥነትን ያደናቅፋሉ ያላቸውን ማሕበራት እንዳይቋቋሙ ለማድረግ ብዙ መንገድ ተጉዟል። ሹመኞች ድርጅቱ ጥሩ የሚባል ደሞዝና ጥቅማጥቅም ስላለው ሠራተኞች ቀጥታ ግንኙነታቸው ከኛ ጋር ቢሆን መልካም ነው ሲሉ ይሞግታሉ። የኒውዮርኩን ማሕበር ለመመሥረት በነበረው ስብሰባ ላይ ሹመኞቹ የማሕበሩ መሪ የሥራ ስምምነትን [ኮንትራክት] ለማድረግ አቅም የለውም ሲሉ ተከራክረዋል። አማዞን የኒውዮርክ ማሕበር የተቋቋመው ብሔራዊው የሠራተኞች ግንኙነት ቦርድ ክስ እመሠርታለሁ ባለ ጊዜ ስለሆነ ይግባኝ እጠይቃለሁ ብሏል። ከ4 ሺህ በላይ ሠራተኞች የኒው ዮርኩን ማሕበር ለማቋቋም ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ከነዚህ መካከል 2654 ሰዎች ማሕበሩን ለመመሥረት ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ክሪስ፤ ድርጅቱ የተሻለ ክፍያ ሊከፍል፤ የጤና መድኅን ሊሰጥ፤ ማግለል ሊያቆምና የእረፍት ቀናትን ሊያሻሽል ይገባል ሲል የአማዞን ሠራተኞች ማሕበርን ያቋቋመው ባለፈው ዓመት ነበር። አሜሪካ ውስጥ 6.1 በመቶ ብቻ የግል መሥሪያ ቤት ሠራተኞች የሠራተኛ ማሕበራት አባል ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/news-60971936 +business """የቻይናን ኃያልነት ለመግታት ረፍዷል""" "በቻይና መንግሥት ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታወቀው አርቲስትና የፊልም ባለሙያ አይ ዌይዌይ ቻይና በአለም አቀፉ ያላት ኃያልነት ከፍተኛ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት መግታት አይቻልም ብሏል። ""የምዕራቡ አለም ስለ ቻይና መጨነቅ የነበረበት ከአስርት አመታት በፊት ነበር። በአሁኑ ሰዓትም ግን ረፍዷል። ምክንያቱም ምዕራባውያን ከቻይና ጋር ጠንካራ ስርአት ዘርግተዋል ዝም ብለው ቢያቋርጡትም በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳሉ። ለዚያም ነው ቻይና የእብሪተኛ ባህርይ የምታሳየው"" ብሏል። በ2008ቱ የቤጂንግ ኦሎምፒክስ የወፍ ጎጆ ስታዲየምን ዲዛይን ያደረገው አርቲስቱ የቻይናን መንግሥት መተቸቱንም ተከትሎ ነው ከባለስልጣናቱ ጋር ችግሮች መፈጠር የጀመሩት። በ2015ም ቻይናን ለቆ በበርሊን ኑሮውን አድርጎም ነበር። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ መኖሪያውን ካምብሪጅ አድርጓል። አይ ዌይዌይ እንደሚለው በአሁኑ ወቅት ቻይና ያላትን የምጣኔ ኃብት ኃያልነት ለፖለቲካዋ ተፅእኖም ትጠቀምበታለች። በቅርብ አመታት የቻይና የፖለቲካ ተፅእኖ በጉልህ መታየት ጀምሯል። እየጨመረ የመጣው ተፅእኖ ከአስር አመታት በፊት የነበረችው ቻይና ልታይ ልታይ የማትልና፣ ድምጿም በአለም ጎልቶ አይሰማም ነበር። የመንግሥት ባለስልጣናቷም ይዘውት የነበረው መፈክርም ""ብርሃንን ደብቆ ጊዜን መግዛት"" የሚል ነበር። በርካታ ሚኒስትሮቿም ቻይና አሁንም ቢሆን ታዳጊ አገር ናት ከምዕራቡ አለምም ብዙ መማርን ትሻለች ሲሉም ይሰሙ ነበር። ሆኖም የዢ ሺንፒንግ ወደ ስልጣን መምጣት ቻይና በአለም ታሳየው የነበረውን ባህርይ ሙሉ በሙሉ ቀየረው። በ2012 ዢ ሺንፒንግ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ፀሃፊ ሆኑ፣ በቀጣዩ አመት ፕሬዚዳንት ዢ ሺንፒንግ ቻይና በአለም ላይ ያላትን ቦታም ሆነ ገፅታ በአዲስ መልክ ያዋቀሩ ናቸው ይባልላቸዋል። የአገሪቷም መፈክር ""ለስኬት እንስራ"" በሚል ተተካ። በሆነ መንገድ ቻይና አሁንም ቢሆን ታዳጊ አገር ናት ምክንያቱ 250 ሚሊዮን ህዝቦቿ ከድህነት ወለል በታች ስለሚገኙ። በአለም ላይ ሁለተኛ ታላቅ የምጣኔ ኃብት ባለቤት ናት። በአሁኑም ወቅት አሜሪካን የምትገዳደራትና በቀጣዩ አመታትም ትቀድማታለችም ተብሎ የምትጠበቅም ሃገር ናት፣ ቻይና። ቻይና በአለም ላይ ያላት ተፅእኖ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ እየታየ ነው። በተቃራኒው ኃያሏ አገር አሜሪካም በሚታይ መልኩ ተፅእኖዋ እያሽቆለቆለ ነው። ቻይና በፖለቲካው ላይ ያላት ተፅእኖና ጫና በመላው አለምም እየተንሰራፋ ነው። ከጫፍ ጫፍ በሚባል ሁኔታ ከግሪላንድ፣ ካሪቢያን ደሴቶች፣ ፔሩ፣ አርጀንቲና፣ ፓኪስታን፣ ሞንጎሊያ የቻይና እጅ የሌለበት የለም። በቅርቡም የካሪቢያኗ ባርቤዶስ ደሴት የእንግሊዟን ንግሥት በርዕሰ ብሄርነት አንፈልጋቸውም ማለቷን ተከትሎ የእንግሊዙ የፓርላመንት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ቻይና ናት ሃሳቡን ያመጣችው በማለት ወቅሰዋታል። ቻይና በአለም ላይ ያላት ተፅእኖ በዚህ ተመለስ የሚባል አይደለም፤ በብሄራዊ ፍላጎቷ የሚመጣንም አገር ዝም ብላ አታልፈውም። የቲቤት መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማ በቅርቡ ለንደንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ የእንግሊዝና የቻይና ���ንኙነት በተወሰነ መልኩ ሻክሮ ነበር። በቅርቡም የቼክ ሪፐብሊክ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ታይዋንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ፣ ከፍተኛ ዲፕሎማት አስጠንቅቀዋል። ግልፅ በሆነ መልኩ ቻይናን ለመተንኮስም ሆነ ከጀርባቸው ሆነው የሚያሴሩ የፀረ- ቻይና ኃይሎችን አገራቸው እንደማትታገስና የሚከተለው ነገር ክፉ ይሆናል ብለዋል። የቻይናና የሌሎች አገራት ፍጥጫ ምንም እንኳን አንዳንዶች ቻይና ያላትን ምጣኔ ኃብት በመጠቀም ከፍተኛ ተፅእኖም ታሳርፋለች ቢሉም ተናጋሪውና ተፅእኖ ፈጣሪው የቻይና ግሎባል ታይምስ ጋዜጣ አዘጋጅ ሁ ሺን አይስማማም። ቻይና አገራትን እያብረከረከች ነው የሚለውም ተቀባይነት የለውምም ይላል። ""አንድ መጠየቅ የምፈልገው ነገር ቢኖር ቻይና መቼ ነው አንድን አገር ያለ ፈቃዷ ምንም ነገር ለማድረግ ግፊት ወይም ጫና ያደረገችው?። በአለም ላይ አሁንም ቢሆን አሜሪካ ናት እቀባ በተለይም ኢኮኖሚያዊ እቀባ በመጣል ከፍተኛ ጫና ለማሳረፍ እየሞከረች ያለችው። ቻይና የትኛዋ አገር ላይ ነው ማዕቀብ የጣለችው?"" በማለትም ይጠይቃል። አክሎም ""ማዕቀብ ጥለን እናውቃለን። እንደ ሃገር አንዳንድ የማንስማማባቸው ጉዳዮች ላይ ስሜታችንን እናፀባርቃለን ይህም ብዙ ጊዜ የሚፈጠረው የአገራችን ብሄራዊ ጥቅም ሲነካ ነው"" ይላል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት ቻይና ከታይዋን አውስትራሊያ፣ ጃፓን፣ ካናዳና ህንድ በሆነ መልኩ ተፋጣለች። በተለይም ከህንድ ጋር በድንበር ከተማዋ ስከርሚሽ ጋር በተያያዘ መሳሪያም ተማዘዋል። ከእንግሊዝና ከአሜሪካም ጋር ያለው መፋጠጥም እንደቀጠለ ነው። በግሎባል ታይምስ ላይ ያሉት ርዕሰ አንቀፆች የማኦ ዜዶንግን አገዛዝም ያስታውሳሉ ይባላል። በቅርቡ ርዕሰ አንቀፁ ላይ አውስትራሊያን አስመልክቶም ""ከቻይና ጫማ ስር ያለች ማስቲካ"" በሚልም አንድ ፅሁፍ አውጥቷል። አዘጋጁም አውስትራሊያ በተደጋጋሚ በቻይና ላይ ለምታደርገው ጥቃት ምላሽ ነው ብሏል። ""አሁንም ቢሆን የሚሰማኝ በጫማዬ ላይ የተለጠፈች ማስቲካ ነው እንደሆነች ነው። ላራግፈው የማልችል ነገር ግን መጣበቁ ደስ የማይል ስሜት ነው የሚሰማኝ። ይህንን እንደ አገላለፅ ነው የተጠቀምኩበት፤ ይህንን ደግሞ እንደ አስተያየት መስጠት መብቴ ነው"" ብሏል። ለአዘጋጁ በዋናነት የቻይና ፍጥጫ ከአሜሪካ ጋር ነው። በመጪው ህዳር የሚደረገው የአሜሪካ ምርጫን ለማሸነፍ በሚልም ዶናልድ ትራምፕ በቻይና ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው ይላል። መጪው ምርጫም አሜሪካ ከቻይና ጋር ሊኖራት የሚችለውን ግንኙነት የሚወስን ይሆናል። ሆነም ቀረም በአለም ላይ ኃያሏንና ታላቋን አገር ቻይና አሜሪካም ሆነ ሌሎች አገራት በጠላትነት ሊመለከቷት አይገባም። አይ ዌይዌይ እንዳለው ለምዕራቡ አለምም ሆነ በአለም ላይ ቻይና ያላትን ተፅእኖ ለመግታት ጊዜው ረፍዷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54408180 +sports ዚነዲን ዚዳን ከሪያል ማድሪድ አሰልጣኝነት ለሁለተኛ ጊዜ ለቀቀ "የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ከቡድኑ አሰልጣኝነት ለሁለተኛ ጊዜ መልቀቁ ተነገረ። በዘንድሮው የውድድር ዘመን ያልተሳካለት ሪያል ማድሪድ የዚዳንን ከቡድኑ መልቀቅ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ የአሰልጣኙን ውሳኔ ""አሁን ማክበር አለብን"" ብሏል። ቡድኑ የ48 ዓመቱን አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ለዓመታት በነበረው ቆይታው ለሪያል ማድሪድ ላበረከተው ""የሙያ ብቃትና ከፍተኛ ፍቅር"" ምስጋና አቅርቧል። የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ዚዳን እአአ ከ2001 አስከ 2006 ለሪያል ማድሪድ የተጫወተ ሲሆን፤ በአሰልጣኝነት ቡድኑን በመራባቸው ከ2016 አስከ 2018 ባሉት ዓመታት ውስጥ በተከታታይ ሦስት የቻይምፒየንስ ሊግና የላ ሊጋ ዋንጫዎችን ማስገኘት ችሏል። ቀደም ሲል ቡድኑን ከለቀቀ ከ10 ወራት በኋላ ተመልሶ ኃላፊነቱን በመረከብ ለሁለተኛ ጊዜ የላ ሊጋን ዋንጫ ለማንሳት አስችሏል። ""ዚዳን ከሪያል ማድሪድ ታላላቅ ከዋክብት መካከል አንዱ ሲሆን በቡድኑ ላይ በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት ያሳረፈው አሻራ ለዘመናት አብሮን ይኖራል"" ሲል የቡድኑ መግለጫ ዚዳንን አሞግሶታል። ""እሱም በሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች ልብ ውስጥ ቦታ እንዳለው ያውቃል፤ ቡድኑ ምንጊዜም ቤቱ ነው"" ብሏል። ቀጣይ የዚነዲን ዚዳን መድረሻ የት እንደሚሆን ለወራት የስፔን ጋዜጦች መነጋገሪያ ሆኖ ከርሟል። ዚዳን በሪያል ማድሪድ ውስጥ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ሦስት ጊዜ በማንሳት ብቸኛው አስልጣኝ ሆኗል። በተጨማሪም ሁለት የዓለም ክለቦች ዋንጫን፣ ሁለት ጊዜ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ አሸናፊ እንዲሁም ሁለት የስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫን በማሸነፍ ታሪክ ሰርቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57251124 +sports በቶክዮ ኦሎምፒክስ ታዳሚዎች ሊገኙ ይችላሉ ተባለ "የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክስ ኮሚቴ ኃላፊ ቶማስ ባህ፤ በቶክዮ ኦሎምፒክስ ላይ ታዳሚዎች እንደሚገኙ ""በጣም እርግጠኛ ነኝ"" አሉ። ታዳሚዎች ወደ ቶክዮ ከመሄዳቸው በፊት እንዲከተቡ ለማስቻል ኮሚቴው ጥረት እንደሚያደርግም አስታውቀዋል። አሁን ጃፓን ሄደው ስለ ኦሎምፒክስ ውድድር ውይይት እያደረጉ ነው። ዘንድሮ ሐምሌ ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ኦሎምፒክስ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ተራዝሟል። በጎርጎሮሳውያኑ 2021 ሐምሌ ላይ ከ200 አገሮች የተውጣጡ 11,000 ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ዮሺሂንዴ ሱጋ ጋር የተነጋገሩት የኦሎምፒክስ ኮሚቴ ኃላፊው ለኤኤፍፒ ""በኦሎምፒክስ ስቴድየም ታዳሚዎች እንደምናስተናግድ በጣም እርግጠኛ ነን"" ብለዋል። ከዓለም አቀፉ የኦሎምፒክስ ኮሚቴ ባሻገር ጃፓንም ውድድሩ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጥታለች። የጃፓን ቶክዮ ኦሎምፒክስ 2020 ዋና ኃላፊ ቶሺሮ ሙቶ፤ ዓመቱ መባቻ ላይ አንዳንድ ውድድሮች በአነስተኛ ታዳሚዎች እንደሚካሄዱና አገራት የሚመድቧቸው የቡድን አባላት ሊቀነሱ እንደሚችሉም ተናግረው ነበር። የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክስ ኮሚቴ ኃላፊ ቶማስ ባህ ባለፈው ሳምንት አንዳንድ ተወዳዳሪዎች ውድድሩን ሰርዘው እንደሆነ ተጠይቀው፤ ማንም ውድድሩን እንዳልሰረዘ አስረግጠው ምላሽ ሰጥተዋል። ምክትላቸው ደግሞ ""ኮቪድ-19 ቢኖርም ባይኖርም ውድድሮቹ ይካሄዳሉ"" ብለዋል። የኦሎምፒክስ ሚንስትር ሴኮ ሃሺማቶ ውድድሩ ""በዚህም አለ በዛ ይካሄዳል"" ሲሉ ተናግረዋል። እስከ ቀጣዩ ዓመት ድረስ ለወረርሽኙ ክትባት ሊመረት እንደሚችል የሚጠቁሙ ዜናዎች እየተሰሙ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/54958645 +business የዓለማችን ምርጥ 10 አየር መንገዶች የትኞቹ ናቸው? "ስካይትራክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ በአሁኑ ወቅት የዓለማችን ምርጥ ናቸው ያላቸውን አየር መንገዶች ይፋ አድርጓል። በኢቪዬሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ግምት ከሚሰጣቸው ሽልማቶች መካከል አንዱ የሆነው ስካይትራክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ፤ በ2021 የዓለማችን ምርጡ አየር መንገድ የኳታሩ፤ ኳታር ኤይርዌይስ ነው ብሏል። ስካይትራክስ ባለፉት 23 ወራት ከ13 ሚሊዮን በላይ ተጓዦች ባሰባስብኩት ባለው መረጃ መሠረት ከኳታር ኤየርዌይስ በመቀጠል፤ ትናንት በይፋ በተገለጸው የስካይትራክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ ከላይ ከተጠቀሱት በመቀጠል እንደ ቅድመ ተከተላቸው ምርጥ 10 የዓለማችን አየር መንዶች ውስጥ የተካተቱት አየር መንገዶች፤ ካቲ ፓሲፊክ አየር መንገድ፣ ኢቫ ኤይር፣ ካንታስ አየር መንገድ፣ ሃይናን አየር መንድ እና የፈንሳይ አየር መንድ ናቸው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ዓመት ቀድሞ ከነበረበት ደረጃ 7 ደረጃዎችን በማሻሻል ከዓለም 37ኛ ደረጃን ይዟል። በአፍሪካ ከሚገኙ አየር መንዶች መካከል የኬንያ አየር መንድ 79ኛ፣ የሞሮኮው ሮያል ኤይር ማሮክ 81ኛ እንዲሁም ኤይር ሞሪሺየስ 82 ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ተብሎ በስካይትራክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ ተሸልሟል። ከዚህ በተጨማሪም አየር መንገዱ በተጨማሪ ሦስት ዘርፎች አህጉራዊ ምርጥ አየር መንገድ ተብሏል። አየር መንገዱ በአፍሪካ ምርጡ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚ ክላስ ተብሎ ተሸልሟል። በአፍሪካ ምርጡ ካቢን ክሩ (የበረራ ሠራተኞች) የያዘ አየር መንገድ ተብሎ ስካይትሬክስ ዎርልድ ኤየርላይን ሽልማትን ወስዷል። ሽልማቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ገ/ማርያም፤ ኩባንያቸው የስካይትራክስ ሽልማት ማግኘቱ፤ አየር መንገዱ ለመንገደኞቹ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እያቀረበ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ብለዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው "". . . የስካይትራክስ ሽልማት አየር መንገዱ በትክክለኛው አቅጣጫ እያመራ እንደሆነ ያሳያል በዚህም ጥልቅ በሆነ ኩራት እነዚህን ሽልማቶች እንቀበላለን"" ብለዋል። ሌሎች ምርጥ አህጉራዊ አየር መንገዶች ስካይትራክስ የፈረንሳዩ ኤየር ፍራንስ የአውሮፓ ምርጡ አየር መንገድ ሲል መርጦታል። የእንግሊዙ ብሪቲሽ ኤይርዌየስ እና የጀርመኑ ሉፍታንዛ ደግሞ ከኤይር ፍራንስ ቀጥሎ የአውሮፓ ምርጦቹ አየር መንዶች ተብለው ተመርጠዋል። በሰሜን አሜሪካ ካሉ አየር መንገዶች ደግሞ የአሜሪካው ዴልታ አየር መንገድ ቀዳሚውን ደረጃ ሲይዝ ጄትብሉ አየር መንገድ እና ኤይር ካናዳ ደግሞ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ኳታር አየር መንገድ በመካከለኛው ምሥራቅ ከሚገኙ አየር መንዶች መካከል ምርጡ የተባለ ሲሆን፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፤ ኢሚሬትስ እና ኢትሃድ አየር መንገድ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። የዳሰሳ ጥናቱን እንዴት ተከናወነ? ስካይትሬክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ በተለያዩ ዘርፎች ይሰጣል። ከእነዚህም መካከል የዓለማችን ምርጡ ንጹህ አየር መንገድ፣ ምርጥ ካቢን ክሩ (የበረራ ሠራተኞች) እና ምርጥ ቢዝነስ ክላስ የሚሰኙ ዘርፎች ይገኙበታል። ስካይትሬክስ ከመስከረም 2019 እስከ ሐምሌ 2021 ባሉት 23 ወራት 13.42 ሚሊዮን ተጓዦች ላይ የዳሰሳ ጥናት አድርጎ ባገኘው ውጤት መሠረት ምርጥ የሚላቸውን አየር መንዶች በተለያዩ ዘርፎች ይፋ ያደርጋል። ድርጅቱ እንደሚለው ከ100 በላይ ዜግነት ያላቸው ሰዎች በዳሰሳ ጥናቱ ተሳትፈዋል። ስካይትሬክ በዳሰሳ ጥናቱ ስለታሳተፉ ሰዎች ገንዘብ አይከፍልም። በዚህ የዳሰሳ ጥናት ላይ ከ350 በላይ አየር መንገዶች መሳተፋቸውንም ስካይትሬክ ገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58867140 +sports 2019 የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር . https://www.bbc.com/amharic/news-48640190 +politics ምርጫ ቦርድ ብልፅግናን ጨምሮ በርካታ ፓርቲዎችን አሳሰበ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ገዢው ፓርቲ ብልፅግናን ጨምሮ በርካታ ፓርቲዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዲያደርጉ አሳስቧል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዳር 23/ 2014 ዓ.ም ከፓርቲዎች ጋር ባደረገው ውይይት ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ መጠናቀቅ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱ ገልጦላቸው ነበር። ነገር ግን ፓርቲዎቹ የሚጠበቅባቸውን አጠናቀው ባለማቅረባቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተነሳ በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያከናውኑ እና ለቦርዱ እንዲያስገቡ መወሰኑ ይታወሳል ሲል ቦርዱ ያወጣው መግለጫ ያትታል። አሁን የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋ���ን በማንሳቱ ፓርቲዎቹ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዲያደርጉ እንዲሁም የሰነድ ማሻሻያ እንዲከውኑ አሳስቧል። ካለፈው ሃገራዊ ምርጫ በኋላ ጠቅላላ ጉባዔ አላደረጉም፤ አልፎም የሰነድ ማሻሻያ አላከናወኑም ተብሎ በቦርዱ የተጠቀሱት 26 ፓርቲዎች ናቸው። ገዢው ብልፅግናን ጨምሮ 13 ሃገራዊና 13 ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቦርዱ ባወጣው መግለጫ ላይ ስማቸው ተጠቅሷል። ቦርዱ በማሕበራዊ ድር አምባ ገፆቹ በለጠፈው መግለጫ ስማቸው ከተጠቀሰ ፓርቲዎች መካከል የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ይገኙበታል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው ሃገራዊው ምርጫ ባለፈው ዓመት ተካሂዶ ገዢው ፓርቲ አብዛኛውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ማግኘቱ ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/news-60413352 +health ’ኮሮናቫይረስ፡ ካልተከተቡ አይቀጠሩም’ የሚል ህግ ለአዳዲስ ሠራተኞች ተግባራዊ ሊሆን ይችላል "ኩባንያዎች አዳዲስ ሠራተኞቻቸው፣ ከመቀጠራቸው በፊት እንዲከተቡ ቢጠይቁ ህጋዊ ሊሆን ይችላል ሲሉ የእንግሊዝ የፍትህ ሚንስትር አስታወቁ። እንደሮበርት ባክላንድ ከሆነ ነባር ሠራተኞች ባላቸው ውል መሠረት ክትባቶችን እንዲወስዱ የመጠየቅ ነገር ላይኖር ይችላል። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ሰዎች በሥራቸው እንዲቀጥሉ ክትባት እንዲወስዱ ማዘዙ ""አድሎአዊ"" ነው ብሏል። ነገር ግን አንዳንድ ድርጅቶች ክትባቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆኑ አዳዲስ ሠራተኞችን እንደማይቀጥሩ ይናገራሉ፡፡ ባክላንድ ረቡዕ ዕለት ከአይቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አዳዲስ በሥራ ውል ላይ በጽሑፍ እስከቀረበ ድረስ ሠራተኞችን እንዲከተቡ ማስገደድ ይቻል ይሆናል ብለዋል፡፡ ሆኖም አሠሪዎች ምናልባት ነባር ሠራተኞች እንዲህ ዓይነቱን ትዕዛዝ እምቢ ካሉ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ሊያስፈልጋቸው ይችላል ተብሏል። አክለውም ""ያለ ክትባት ሥራ የለም"" የሚሉት መስፈርት ሕጋዊነት ""በቅጥርና በልዩ ውል ላይ የተንጠለጠለ ነው"" ብለዋል፡፡ ""በአጠቃላይ አካሄዱን ሕጋዊ ያደረጉት አሁን ያሉት የሥራ ኮንትራቶች ቢኖሩ እደነቃለሁ፡፡ እውነቱን ለመናገር ጉዳዩ መፈተሽ ያለበት ይመስለኛል"" ብለዋል፡፡ መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የፒምሊኮ ፕለምበርስ ከህክምና ጋር በተያያዘ ካልሆነ በስተቀር ክትባቱን አልፈልግም የሚሉ አዳዲስ ሠራተኞችን አልቀጥርም ካሉት ኩባንያዎች አንዱ ነው፡፡ ከቅጥር ጋር በተያያዘ የሚሠሩ የህግ ባለሙያዎች በመጀመሪያ እርምጃው ላይ ጥያቄ ቢያነሱም መስራቹ ቻርሊ ሙሊንስ ህጋዊ እንደሆነ ምክር እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ ""እኛ በግልጽ ከጠበቆች ጋር የተነጋገርን ሲሆን ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ከወጣ በኋላ ከእኛ ጋር ለሚጀምሩ ማናቸውም አዳዲስ ሠራተኞች የክትባቱ ጉዳይ በውሉ ውስጥ በመካተቱ ባለሙያዎቹ በጣም ደስተኞች ናቸው"" ብለዋል ለቢቢሲ፡፡ ""አዲሶቹን ኮንትራቶች ከሁለት እስከ ሶስት ወራቶች ውስጥ እንጠቀማቸዋለን፡፡ ሰዎች ከእኛ ጋር ሥራ ለመሥራት ሲመጡ ያንን በመፈረም ደስተኛ ካልሆኑ የእነሱ ምርጫ ነው። በእርግጠኝነትም ሥራው ከፒምሊኮ ፕላምበርስ አይሰጣቸውም"" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የቤት እንክብካቤ ላይ የተሠማራው ባርቸስተር ሄልዝኬርም ሁሉም አዲስ ቅጥር ሠራተኞችየመከተብ ግዴታ አለባቸው ብሏል፡፡ ""ከሠራተኞቻችን ጋር በተያያዘ ፍላጎት ያላቸውን ክትባቱን እንዲያገኙ ለማበረታታት የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው። በተጨማሪም ሁሉም አዲስ ሠራተኞች ክትባቱን መውሰዳቸውን ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ማረጋገጥ አለብን"" ያለው ድርጅቱ ደንበኞቹን እና ሠራተኞቹን ጤንነት መጠበቅን ደግሞ በምክንያትነት አስቀምጧል። 'የህግ ክፍተት' ሌዊስ ሲልኪን በሚባለው የሕግ ኩባንያ የሕግ ዳይሬክተር የሆኑት ዴቪድ ሳሙኤል እንዳሉት ድርጅቶች በአዳዲስ ቅጥር ሠራተኞቻቸው ኮንትራቶች ውስጥ ""ያለ ክትባት ሥራ የለም"" የሚል አንቀጽን ከማስገባት የሚያግዳቸው ሕጋዊ ማዕቀፍ የለም፡፡ አሠሪዎች እያንዳንዱን የሥራ ሚና መተንተን እና እንዲህ ዓይነቱን ሐረግ ከማስተዋወቅ በፊት የጤና እና የደህንነትን አደጋዎችን መገምገም አለባቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ይህ ባለማድረጉና አንድ ሠራተኛ ያልተከተበት ምክንያት ቢኖረው ውሉ ኢ-ፍትሃዊ ወይም አድሎአዊ ነው ብሎ ለመከራከር ያስችለዋል፡፡ ሌሎች ስጋቶችም አሉ። ለምሳሌ ፣ ""ካልተከተቡ ሥራ የለም"" የሚለው ፖሊሲ ክትባቱን ለመውሰድ የመጨረሻ መስመር ላይ ባሉ ወጣቶች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ የሚል ስጋት አለ፡፡ ""ይህን ለማጽደቅ ከባድ ይሆናል። በተለይም በዚያ ሂደት ውስጥ ካልገቡ እና ካልሰነዱት በሕጋዊ ጥያቄ የመፈታተናቸው ዕድላቸው ሰፊ ነው"" ሲሉ ሳሙኤል ለቢቢሲ ገልጸዋል፡፡ የአንዳንድ ሠራተኞች የሥራ ሁኔታ በቢሮ ወይም በፋብሪካ እንዲሠሩ የሚያስገድድ ከሆነ ድርጅታቸው እንደዚህ ዓይነት አንቀፅ ሊቀመጥ ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ እንደደረሳቸው አክለው ገልጸዋል፡፡ ""ክትባት መውሰድ ግዴታ አይደለም፤ እናም አንድ ሰው እንዲወስድ ማስገደድ አድልአዊ ነው"" ብለዋል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ፡" https://www.bbc.com/amharic/news-56121979 +sports እውቁ ተጫዋች እግር ኳሰኞች ዘረኝነትን በመጠየፍ ማሕበራዊ ሚድያን መተው አለባቸው ይላል የእንግሊዝ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝና የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ፊል ኔቪል እግር ኳስ ተጫዋቾች እራሳቸውን ከማሕበራዊ ሚድያ በማግለል ዘረኝነትን እንደሚጠየፉ ማሳየት አለባቸው ሲል አሳስቧል። ሰኞ ምሽት ማንችስተር ዩናይትድ ከዎልቭስ ጋር በነበረው ጨዋታ ፖል ፖግባ ፍፁም ቅጣት መሳቱን ተከትሎ ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ ዘረኝነት የተጠናወታቸው ትችቶች ቀርበውበት ነበር። «እስከመቼ ነው እንዲህ የምንዘልቀው? ተጫዋቾቼ ያጋጥማቸዋል፤ ፕሪሚዬር ሊግ ላይ አለ፤ እንዲሁም ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ። ትዊተርም ሆነ ኢንስታግራም ግድ ከሌላቸው እኛ የሆነ ነገር ማድግ አለብን» ብሏል ኔቪል። በሁኔታው እግጅ የበገነው ኔቪል «እኔ ማሕበራዊ ድር አምባን በሚዘውሩ ሰዎች ተስፋ ቆርጫለሁ» ይላል። «ሁኔታውን እየተከታተልን ነው ብለው ኢሜይል ይልኩልሃ። ነገር ግን ምን ሲፈጠር አታይም።» ለዚያም ነው ማሕበራዊ ሚድያን ማግለል ያዋጣል የሚለው ኔቪል። «ቢያንስ ለ6 ወራት ማቋረጥ። እስቲ ምን እንደሚፈጠር እንይ» ብሏል። ፖል ፖግባ ላይ ዘረኛ አስተያየቶች ከተሰጡ በኋላ ትዊተር ሁኔታውን 'አምርሮ እንደሚቃወም' አሳውቆ 'የተወሰኑ ገፆችን ዘግቻለሁ' ብሏል። ድርጅቱ 'በተለይ እንግሊዝ ውስጥ በሚጫወቱ ተጫዋቾች ላይ የበይነ-መረብ ዘረኝነት ጥቃት እየተሰነዘረ መሆኑን ተረድናል' ሲል አትቷል። • ማንቸስተር ሲቲ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አደጋ? ፌስቡክም እንዲሁ ለዘረኛ አስተያየቶች 'ቦት እንደሌለው' አሳውቆ ኢንስታግራምን ጨምሮ በሌሎች መድረኮች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመመከት እየሠራን ነው ሲል ገልጿል። የፈረንሳዊው እግር ኳሰኞ ፖግባ የሥራ ባልደረቦች በይነ-መረብ ላይ ያስተዋሏቸውን ፀያፍ እና ዘረኛ ጥቃቶች አምርረው አውግዘዋል። ሃሪ ማክጓዬር፣ ማርከስ ራሽፎርድ እና ዴቪድ ዲ ሂያ ጥቂቶቹ ናቸው። የዩናይትድ አመራሮችም ጥቃቱን እንደሚቃወሙ ለማሳወቅ ጊዜ አልወሰደባቸውም። https://www.bbc.com/amharic/news-49417562 +business ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያ የሞባይል ባንኪንግን ዘርፍ ለአገር በቀል ኩባንያዎች ክፍት አደረገች "በባንኮችና በጥቃቅን የገንዘብ ድርጅቶች ተይዞ የነበረውን የሞባይል ባንኪንግ ዘርፍ ለሌሎችም ድርጅቶችም ክፍት እንዲሆን ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዲስ መመሪያ ወሰነ። ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የጥሬ ገንዘብን በመጠቀም የሚፈጠረው ግንኙነት ለመቀነስ ኢትዮጵያ በሞባይል ባንኪንግ ያላትን ህግ በማላላት የአገር ውስጥ ባለኃብቶች እንዲሰማሩበት ክፍት አድርጋለች። ይህም ንክኪን ለመቀነስና ህዝቡ ሙሉ በሙሉ ጥሬ ገንዘብ መጠቀምን ያቆማል ተብሏል። •ኢትዮጵያ፡ ሁለት ሰዎች ከኮቪድ-19 መዳናቸው ተገለፀ •በአማራ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የትምህርት ተቋማት ለመጠለያነት ተዘጋጁ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረትም ፈቃድ ለማውጣት የሚፈልጉ አምሳ ሚሊዮን ብር፣ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆን እንዲሁም 10 ባለድርሻ ያሉት አክሲዮን መሆን እንዳለባቸው አስታውቋል። መመሪያውም ከትናንትና መጋቢት 24፣2012 ዓ.ም ጀምሮ በተግባር ላይ የዋለ ሲሆን በቀን ስምንት ሺ ብር ያህል እንዲሁም በወር 60ሺ ብር ማውጣት ይቻላል። የሞባይል ባንኪንግ ፈቃድ ያላቸው ኩባንያዎችም ገንዘብ የማስቀመጥ፣ ብድር፣ ኢንሹራንስ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት መስጠት ያስችላቸዋል። በመንግሥት ይዞታ ስር ያሉ ተቋማትም የሞባይል ባንኪንግ ፈቃድ መጠየቅ እንደሚችሉም ባንኩ በመመሪያው አስቀምጧል፥ ይህ ውሳኔም እንደ ኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ ሌሎች ድርጅቶች እንዲወዳደሩ በር ይከፍትላቸዋል። •""ከቤት አትውጡ የሚሉን ልጆቼን ምን እንዳበላቸው ነው?"" •በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች በርካታ ኢትዮጵያውያን ግብይይት የሚፈፅሙት በጥሬ ገንዘብ ሲሆን የሞባይል ባንኪንግ እንደ ሌሎች አገራት የተለመደ አይደለም። በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ባለስልጣናት ብዙዎች ቤታቸው እንዲቀመጡና በተጨናነቁ ስፍራዎች መገኘት እንዲቆጠቡ ምክርም ቢለግሱም ብዙዎች ወደ ባንኮች የሚያደርጉትን ጉዞ አልቀነሱም፤ በጥሬ ገንዘብ የሚደረጉ ንክኪዎችም አልቀነሱም። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከትራንስፖርት ጀምሮ የተለያዩ ክፍያዎችን የሚፈፅመው በጥሬ ገንዘብ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/52138509 +politics የሶሪያው ፕሬዝዳንት አሳድ ታሪካዊ የታባለ ጉብኝት በአረብ ኤምሬትስ አደረጉ "የሶሪያው የእርስ በእርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ከ11 ዓመታት በኋላ ፕሬዝዳንት ባሻር አሳድ የመጀመሪያቸውን የአረብ አገር ጉብኝት በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ አድርገዋል። ጉብኝቱ በጦርነቱ ምክንያት አሳድን አግልለው የነበሩ የአረብ አገራት ዳግም ግንኙነታቸውን ሊያድሱ እንደሚችሉ አመላካች ነው ተብሏል። ሆኖም አሜሪካ ጉዞው ""በጣም ቅር አሰኝቶኛል"" ብላለች። ፕሬዝዳንት አሳድ በጉብኝታቸው ኤምሬትስ ውስጥ ካገኟቸው ሰዎች መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ውዝግቦች ስማቸው የሚናሳው የዱባዩ ቢልየነር ሼክ መሐመድ አል ማክቱም አንዱ ናቸው። ባለሐብቱ ካሏቸው 25 ልጆች መካከል አንዷ የሆነችው ላቲፋ እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 ከዱባይ ለማምለጥ ያደረገችው ሙከራ ከከሸፈ በኋላ አሁን ታግታ እንደምትገኝ ተናግራ ነበር። እናም አሳድ ያገኟቸው እኚህ ባለሐብት በዚህ እና በሌሎች ጉዳዮች ስማቸው ይብጠለጣላል። በተጨማሪም አሳድ ወደ ተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ዋና ከተማ አቡዳቢ በመጓዝ ከልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ለመገናኘት ችለዋል። ""ሶሪያ ለአረብ አገራት ደኅንነት ቁልፍ እንደሆነች እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከአገሪቱ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን"" የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። መሪዎቹ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለሶሪያ ፖለቲካዊ እና ሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ በምትችልበት መንገድ እንዲሁም በአገራቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን የኢኮኖሚና ንግድ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸው ተዘግቧል። ፕሬዝዳንት አሳድ ከማንቸስተር ሲቲ እግር ኳስ ክለብ ባለቤት ሼክ መንሱር ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ፎቶ ሲነሱም ታይተዋል። የሶሪያ ፕሬዝደንት በአገራቸው ከአስር ዓመት በፊት በተቀሰቀሰው ደም አፋሳሽ የእርስ በእርስ ጦርነት ሳቢያ 350,000 ሰዎችን መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያመለከተ ሲሆን፣ ባሻር አል አሳድ ከጦርነት መጀመር ወዲህ በጣም ጥቂት ዓለም አቀፍ ጉዞዎችን ብቻ ነው ያደረጉት። ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ በተጨማሪ እስካሁን ድረስ ፕሬዝዳንት አሳድ በጦርነት የምትታመሰውን አገራቸውን ለቀው ወታደራዊ ድጋፍ ወደ ሚያደርጉላቸው ሩሲያ እና ኢራንን ተጉዘዋል። የፕሬዝዳንቱን ጉብኝት ተከትሎም የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አሳድን ለመቀበል መወሰኗ በጣም አሳዛኝ እና ቅር የሚያሰኝ ነው ስትል አሜሪካ ገልጻለች። አሜሪካ በሶሪያ ያለውን የእርስ በርስ ጦርነትን መፍትሄ ለመስጠት መሻሻል እስኪታይ ድረስ ከሶሪያ መሪ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማደስ የሚደረጉ ጥረቶችን እንደምትቃወም ትገልጻለች። እንደ አብዛኞቹ የአረብ አገራት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የበሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ከአገሪቱ ጋር ግንኙነቷን አቋርጣ የነበረ ሲሆን፣ የአማፅያኑ ተዋጊዎች የአሳድን መንግሥት ለመጣል ያደረጉትን ሙከራ የደገፈችበት ወቅትም ነበር። ሆኖም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ቀስ በቀስ እየተሻሻለ ሲሆን ከአሜሪካ ተቃውሞ ቢያጋጥማትም የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ሶሪያን ከአረቡ ዓለም ጋር የነበራትን የቀድሞ ግንኙነት ለማደስ ጥረት እያደረገች ነው። እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ዳግም የከፈተች ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ዲፕሎማቶች ፕሬዚዳንት አሳድን እንዲያገኙ ልካ ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-60804731 +sports የማይክል ጆርዳን ማሊያ በ10.1 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ "የቅርጫት ኳስ ኮከቡ ማይክል ጆርዳን እአአ በ1998 የውድድር ዘመን የለበሰው ማሊያ ክብረ ወሰን በሆነ 10.1 ሚሊዮን ዶላር ተሽጧል። ይህም ከፍተኛ ዋጋ ያወጣ ስፖርት ቁሳቁስ ለመሆን በቅቷል። አጫራች ድርጅቱ ሰዘቢስ እንዳለው ሽያጩ ለስፖርት አድናቂዎች እና ለማስታወሻ ሰብሳቢዎች “ትልቅ ደስታን” የፈጠረ መሆኑን ተናግሯል። ጆርዳን ስድስተኛውን እና የመጨረሻውን የናሽናል ባስኬት ቦል አሶሴሽን (ኤንቢኤ) ዋንጫ ማሸነፉን የሚያስታውስ ማሊያ ነው ተብሏል። በውድድር ዓመቱ ዙሪያ ‘ዘ ላስት ዳንስ’ በሚል ኔትፍሊክስ የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም አለ። ሰዘቢስ አጫራች ድርጅ ሐሙስ ዕለት እንዳስታወቀው ጆርዳን ለቺካጎ ቡልስ ሲጫወት የለበሰው ማሊያ 20 ተጫራቾችን ትኩረት ስቧል። የሰዘቢስ ኃላፊ ብራህም ዋቸር ተጫራቾች ""ብርቅዬውን ታሪካዊ ልብስ ለመውሰድ ጓጉተዋል"" ብለዋል። ""የዛሬው ክብረወሰን የሰበረ ሽያጭ '... ማይክል ጆርዳን በማያሻማ መልኩ የምንግዜም ኮከብ መሆኑን የሚያጠናክር ነው። ዛሬም ስሙ እና ወደር የለሽ ትሩፋቱ ከዛሬ 25 ዓመት በፊት እንደነበረው ነው"" ሲሉ ተናግረዋል። ዋጋው በ1986 የዓለም ዋንጫ ወቅት በእግር ኳስ ኮከቡ ዲዬጎ ማራዶና ለተለበሰውና 9.28 ሚሊዮን ዶላር ከተሸጠው ማሊያ በልጦ ክበረ ወሰኑን ይዟል። ጀርዳን የፊት ገጽ ሽፋን ከያዘበት እና እአአ ሰኔ 1998 ከታተመው ስፖርት ኢላስትሬትድ መጽሔት ጋር ነው ለጨረታ የቀረበው። ጆርዳን በቅርጫት ኳስ ታሪክ ምርጡ ተጫዋች እንደሆነ በብዙዎ��� ዘንድ ይታመናል። አብዛኛውን የጨዋታ ዘመኑን ቺካጎ ቡልስ ጋር አሳልፏል። በዚህም ዓለም አቀፋዊ ተምሳሌት ከመሆን ባለፈ የኤንቢኤን ስም በዓለም ዙሪያ ከፍ ለማድረግ አግዟል። ቺካጎ ቡልስ በኤንቢኤ የፍጻሜ ጨዋታ የመጀመሪያ ጨዋታን በዩታህ ጃዝ ተሸነፈ። የሚቀጥሉትን ሦስት ጨዋታዎች ቡልስ አሸነፈ። አምስተኛውን ጨዋታ ዩታህ ጃዝ በሁለት ነጥብ በልጦ ማሸነፍ ቻለ። በስድስተኛው ጨዋታ አንገት ለአንገት የተናነቁበት ነበር። ጆርዳን ጨዋታው 5.2 ሰከንዶች ሲቀሩት ቡልሶች 87-86 በሆነ ውጤት እንዲያሸንፉ ያስቻላቸውን ነጥቦች አስቆጠረ።  ኮከቡ የመጨረሻውን የኤንቢኤ ዋንጫውን ከፍ ለማድረግ በቃ። ጆርዳን በሰሜን ካሮላይና የአባቱን መገደል ተከትሎ በ1993 ከቅርጫት ኳስ ራሱን አገለለ። ኮከቡ ቺካጎ ቡልስ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ሻምፒዮን እንዲሆን አስችሏል። ጆርዳን ""ሁሌም አፅንዖት መስጠት እፈልጋለሁ... የመነሳሳት እና እንደ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች አንድ ነገር የማረጋገጥ ስሜት ሲጠፋብኝ ለማቆም ጊዜው አሁን ነው እላለሁ"" ብሏል። 59 ዓመቱ ጆርዳን በ2003 ነበር ጫማውን ለመጨረሻ ጊዜ የሰቀለው።" https://www.bbc.com/amharic/articles/clj4g99l113o +politics "ዩክሬን ግጭት፡ ጆ ባይደን ፑቲን ዩክሬንን ለመውረር መወሰናቸው ""እርግጥ ነው"" አሉ" "የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ላይ ወረራ ለመክፈት መወሰናቸው ""እርግጥ መሆኑን"" የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ተናገሩ። ጆ ባይደን ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምትፈፅመው ወረራ ""በሚቀጥሉት ቀናት"" ሊከሰት ይችላል ብለዋል። ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት የአሜሪካ የስለላ ድርጅት የዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ የወረራው ኢላማ እንደምትሆን ባወጣው መረጃ ላይ ተመስርተው እንደሆነ ተናግረዋል። ሩሲያ በበኩሏ ዩክሬንን ለመውረር አቅዳለች መባሏን በተደጋጋሚ አስተባብላለች። ምዕራባውያን አገራት ሩሲያ ጥቃት ለመሰንዘር ምክንያት ለመፍጠር በዩክሬን ተገንጣይ ምሥራቃዊ ክልሎች የሐሰት ቀውስ ለመፍጠር እየሞከረች ነው ሲሉ ይከሳሉ። በዩክሬን ውስጥ እና በድንበር አካባቢ ከ169 ሺህ እስከ 190 ሺህ የሩሲያ ሠራዊት አባላት እንደሚገኙ አሜሪካ ግምቷን አስቀምጣለች። ይህ አሃዝ ራስ ገዝ በሆኑትና በምሥራቅ ዩክሬን በሚገኙት ተገንጣዮቹ ዶኔትስክ እና ሉሃንስክ ሪፐብሊክ የሚገኙትን በሩሲያ የሚደገፉ ተዋጊዎችን የሚያካትት ነው። እነዚህ ክልሎች እአአ በ1922 ወደ ዩክሬን የተጠቃለሉ ሲሆን አብዛኞቹ ነዋሪዎች የመጀመሪያ ቋንቋቸው ሩሲያኛ ነው። ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከዋይት ሐውስ በቴሌቪዥን በተላለፈው መግለጫቸው አሜሪካ የሩሲያ ኃይሎች በሚቀጥለው ሳምንት ዩክሬንን ለማጥቃት እቅድና ፍላጎት እንዳላቸው ለማመን የሚያስችል ""በቂ ምክንያት"" አላት ብለዋል። ባይደን አክለውም ""ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ፑቲን ውሳኔውን መወሰኑን አምኛለሁ"" ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ፐሬዚደንቱ እና ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልትወስድ ስለምትችለው እርምጃ በእርግጠኝነት እንደማያውቁ ተናግረው ነበር። ሆኖም ፕሬዚደንት ባይደን ሩሲያ አሁንም ዲፕሎማሲያዊ መንገድን ልትመርጥ ትችላለች በማለት ውጥረቱን ለማርገብ እና ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለመመለስ አሁንም አለመርፈዱን ገልጸዋል። አርብ ዕለት ውጥረቱ እየጨመረ በመምጣቱ የሁለቱ ተገንጣይ አካባቢ መሪዎች ዩክሬን ድብደባ ለመፈፀምና ጥቃት ለማድረስ አቅዳለች በማለት ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ አስታውቀው ነበር። ይሁን እንጂ ዩክሬን ጥቃት የማድረስ እቅድ እንደሌላት በተደጋጋሚ ገልጻለች። የአገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚይትሮ ኩሌባ ""ይህ የሩሲያ የሐሰት መረጃ ነው"" ሲሉም ክሱን አጣጥለውታል። ��ዶኔትስክ ሕዝቦች ሪፐብሊክ መሪ የሆኑት ዴኒስ ፐሺሊን፣ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ያሳሰቡት አርብ ዕለት በወጣ ተንቀሳቃሽ ምሥል አማካይነት ነው። ይሁን እንጂ ቢቢሲ ባደረገው የመረጃ ማጣራት ተንቀሳቃሽ ምሥሉ የተቀረጸው ከውጥረቱ መባባስ ከሁለት ቀናት በፊት መሆኑን ለማወቅ ችሏል። ዩክሬን፤ ፕሬዚደንት ፑቲን ከተገንጣይ አካባቢዎች ለሚፈልሱ ሰዎች የአደጋ ጊዜ እርዳታ ለማቅረብ በድንበር አቅራቢያ የስደተኞች መጠለያ እንዲቋቋሙ ማዘዛቸውን ገልጻለች። በርካታ የአካባቢዎቹን ነዋሪዎች የጫኑ አውቶብሶችም ወደ ሩሲያ ማምራታቸውን የሩሲያ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መነገሩ ሩሲያ ጥቃቱን ለመሰንዘር ኃይሏን እያጠናከረች ላለው ዝግጅት ዓለምን ለማዘናጋት የተደረገ "" የሞስኮ አሳፋሪ እርምጃ "" ነው ብሎታል። ዋይት ሐውስ ነዋሪዎችን እንዲወጡ ማድረግ ሞስኮ ሐሰተኛ መረጃን ለጦርነት ሰበብ መጠቀሟን የሚያሳይ ምሳሌ ነው ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60427362 +politics ምርጫ 2013፡ በአንድ ዓመት ውስጥ ሁሉን አቀፍ ምርጫ እንዲካሄድ ኦፌኮ ጠየቀ "ከቀናት በፊት ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በተደረገው ስድስተኛ ብሔራዊ ምርጫ ያልተሳተፈው የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ በአንድ ዓመት ውስጥ ሁሉን አቀፍ ምርጫ እንዲደረግ ባወጣው መግለጫ ጠየቀ። ፓርቲው ለአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ የመፍትሔ ሃሳብ ብሎ የሰነዘራቸውን ሦስት ነጥቦችንም ዘርዝሯል። በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉን አካታች የጋራ መንግሥት እንዲቋቋምና ""ያልተሳካ"" ብሎ የጠራውን የመንግሥት ተሃድሶ እንዲቀጥል፣ ""ሁሉን አካታች ብሔራዊ የመግባባት ድርድር እንዲጀመር"" የሚሉ ሃሳቦችን አስፍሯል። በሦስተኛነትም የጋራ መንግሥቱ በጋራ የሚፈጥር ፍኖተ ካርታ እንዲመቻችና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሁሉን አቀፍ ነፃ ፍትሃዊና ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድም የሚሉ ሃሳቦችን አቅርቧል። በብሔራዊ መግባባት ያልታጀበ ምርጫ አገሪቷን ከገባችበት ችግር ውስጥ እንደማያወጣት ደጋግሞ ሲናገር እንደነበር ፓርቲው አስታውሶ ከመንግሥት በኩልም ሰሚ ባለመገኘቱ ""የአገራችን ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ እየተሸጋገረ ነው"" ብሏል። ኦፌኮና ኦነግ አመራሮቻው በመታሰራቸው፣ በርካታ ቢሮዎቻቸው በመዘጋታቸው ምክንያት ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል። በዚህ ምርጫ ኦፌኮ ተገፍቶ መውጣቱንና ""የመላውን ኢትዮጵያ ሕዝቦችን የማይወክል ምርጫ ስጋታቸውንም ከሌሎች ፓርቲዎች ማረጋገጥ"" እንደቻሉም አስፍረዋል። በምርጫ ሂደቱም ውስጥ የታዩ ችግሮችንም ጠቅሶ በተለያዩ ምክንያቶች ""ሕዝቡን ያላካተተ ምርጫ"" እንደሆነም ኦፌኮ በመግለጫው አካቷል። ምርጫው እንደታሰበው ""የገዥውን ፓርቲ ቀልብ መሳብ ባለመቻሉ"" የመራጮች ምዝገባ ሦስት ጊዜ ተራዝሟል ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ቦርዱ የማያውቃቸው ሰባ ዘጠኝ የምርጫ ጣቢያዎች ተቋቁመው መገኘታቸው፣ በመቶዎች በሚቆጠሩ የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ አለመካሄዱ የምርጫውን ጉድለት የሚያሳዩ ናቸው ብሏል። በተጨማሪም ""በኦሮሚያ ክልል በመቶዎች በሚቆጠሩ ወረዳዎች ውስጥ ገዥው ፓርቲ ብልጽግና በብቸኝነት መወዳደሩን"" አስፍሯል። በትግራይ ውስጥ ባለው ጦርነት ምርጫ ባለመካሄዱና ሌሎች ምክንያቶችንም በመጥቀስ ""ሃምሳ በመቶው ሕዝብ ከምርጫ ውጪ ነው"" ብሎታል። ""በምንም ተአምር የአገራችንን ፍላጎቶችን የማያሟላ ምርጫ ማለትም ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋትንና ሁሉንም በእኩልነት የምታስተናግድ ዲሞክራቲክ ኢትዮጵያን የማይፈጥር ከሆነ ለሚሊዮኖች የሚሆን ልማትና ብልጽግናን አያመጣም"" ብሏል። ከ37 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በመራጭነት የተመዘገበበት እና 47 ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውን ያቀረቡበት ብሔራዊ ምርጫ ሰኔ 14/2013 የተካሄደ ሲሆን፤ ምርጫው በፀጥታና በሌሎች ምክንያቶች መካሄድ ባልተቻለባቸውም አካቢዎች ደግሞ ጳጉሜ 1 እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ከነዚህም መካከል በሶማሌ ክልልና ሐረሪ ክልል እንዲሁም በፀጥታ ችግር ምክንያት ምርጫው በተራዘመባቸው ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ምርጫው እንዲራዘም መወሰኑ ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/57596729 +politics ፕሬዝዳንት ፑቲን እና ኤርዶሃን ለንግግር ኢራን ገቡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ጋር ለመነጋገር ኢራን ገቡ። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው የካቲት ወር በዩክሬን ላይ ሠራዊታቸውን ካዘመቱ በኋላ ወደ ኢራን ሲጓዙ ይህ ሁለተኛው የውጭ ጉዟቸው ሆኗል። ፑቲን እና ኤርዶሃን በኢራን ቆይታቸው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚነጋገሩ እና የአገሪቱን የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒን ያገኛሉ ተብሏል። የእህል ምርት ገበያ፣ ሶሪያ እና ዩክሬን ፑቲን በቴህራን በሚያደርጉት ጉብኝት ላይ መነጋገሪያ ጉዳዮች እንደሚሆኑ አንድ የቱርክ ባለሥልጣን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲን ከጦርነቱ በኋላ ከአገር ውጪ የሚያደርጉት ጉብኝት በቀድሞ የሶቪየት ኅብረት አገራት ተወስኖ ቆይቷል። ከአንድ ወር በፊት ፑቲን የቀድሞ የሶቪየት ኅብረት አካል ወደነበሩት እና በአሁኑ ወቅት የሩሲያ አጋር በሆኑት በታጃኪስታን እና በቱርክሜንስታን ጉብኝት አድርገው ነበር። የዛሬው የፑቲን ጉብኝት ልክ እንደ ሩሲያ ሁሉ በምዕራባውያን ማዕቀብ ስር ከምትገኘው ኢራን ጋር ያላቸውን ወዳጅነት የሚያጠናክሩበት ይሆናል ተብሏል። ይህ የፑቲን የኢራን ጉብኝት የተሰማው የአሜሪካ ባለሥልጣናት ቴህራን ለሞስኮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖችን [ድሮኖች] ለማቅረብ በዕቅድ ላይ ናት ማለታቸው ከተሰማ በኋላ ነው። ዛሬ የሩሲያው ግዙፍ የኃይል ተቋም ጋዝፕሮም ከእስራኤል መንግሥት የነዳጅ ኩባንያ ጋር 40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ስምምነት ተፈራርሟል። የፑቲንን የኢራን ጉብኝት በማስመልከት የፕሬዝዳንቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊስ አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ በሰጡት መግለጫ ጉብኝቱ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ብለዋል። ፑቲን ከአያቶላህ አሊ ኻሚኒ ጋር መገናኘታቸው “በጣም ጠቃሚ ነው” ያሉት አማካሪው፤ ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መተማመን ላይ የተመሠረተ ንግግራቸው ዳብሯል ብለዋል። ምንም እንኳ ቱርክ እና ሩሲያ በሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት በተቃራኒ ጎራ የተሰለፉ ቡድኖችን በየፊናቸው እየደገፉ የቆዩ ቢሆንም፤ በቅርብ ወራት ግን በአገሪቱ ሰላም ለማስፈን ጥረት እያደረጉ ነው። የሩሲያን ወረራ ተከትሎ ምዕራባውያን በሞስኮ ላይ መጠነ ሰፊ ማዕቀቦችን ሲጥሉ፤ አንካራ ግን የሩሲያ እና ዩክሬን አሸማጋይ ለመሆን ስትጥር እንጂ ሞስኮ ላይ ማዕቀብ ስትጥል አልታየችም። ይሁን እንጂ ቱርክ በቅርቡ በሰሜን ሶሪያ የሚንቀሳቀሱትን እና በአሜሪካ የሚደገፉትን የኩርድ ታጣቂዎች ላይ አዲስ ጥቃት ለመክፈት ዝታለች። ይህን የቱርክ ዛቻ ሞስኮ እና ቴህራን በበጎ አልተመለከቱትም። ኤርዶሃን ይህን ኦፕሬሽን ለማካሄድ ያቀዱት ከሶሪያ በሚያዋስናቸው የድንበር አካባቢ 30 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ደኅንነቱ የተረጋገጠ አካባቢን የመፍጠር እቅዳቸውን እውን ለማድረግ ነው። ከፑቲን እና ኤርዶሃን ንግግር በኋላ በዩክሬን ወደብ ላይ የሚገኘው 22 ሚሊዮን ቶን እህል ወደ ሌላ አገር እንዲሄድ ጦርነት ውስጥ የገቡት የሩሲያ እና ዩክሬን መሪዎች ከስምምነት እንዲደርሱ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል። ሩሲያ በጥቁር ባሕር ላይ ያሰማራቻቸው መርከቦች ምንም አይነት ጭነቶች ከዩክሬን እንዳይወጡ እና ወደ ዩክሬን እንዳይገቡ እያደረጉ ይገኛሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cnkz929yeklo +health በ20 ቀናት ሁለት ጊዜ ኮሮና የተገኘባት ስፔናዊት በአጭር ጊዜ ዳግም በቫይረሱ የተያዘች ሳትሆን አትቀርም ተባለ "የ31 ዓመቷ የጤና ባለሙያ በ20 ቀናት ውስጥ ሁለት ጊዜ በኮሮና ቫይረስ እንደታያዘች ተገልጿል። ይህንንም ተከትሎ በቫይረሱ ሁለት ጊዜ በመያዝ የታወቀ አጭሩ ጊዜ ነው ሲሉ የስፔን ተመራማሪዎች ገልጸዋል። ባለሙያዋ በሃያ ቀናት ውስጥ ዴልታ እና ኦሚክሮን በተባሉ ሁለት የኮቪድ ዝርያዎች መያዟ ነው የተረጋገጠው። ታዲያ ይህ ሁኔታ አንድ ሰው በቫይረሱ ቀደም ብሎ ቢያዝም ሆነ ሙሉ በሙሉ ክትባቱን ቢወስድ ዳግም በቫይረሱ ሊያዝ እንደሚችል ያመላከተ ነው ሲሉ ተመራማሪዎች ገልጸዋል። በዩኬ ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ዳግም ለመያዝ ቢያንስ 90 ቀን እንደሚፈጅ ታውቋል። በዚህ እሳቤ መሰረት በሀገሪቱ 900 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በዚህ ወር መግቢያ በቫይረሱ ዳግም የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ የጤና ዘርፉ ባለስልጣናት አሳውቀዋል። በላብራቶሪ ባለው ሂደት እና የሚወሰደው ናሙና ጥቂት በመሆኑ በቫይረሱ ዳግም የተያዙ ሰዎችን ትክክለኛ ቁጥር ለመያዝ አዳጋች ነው። በሃያ ቀናት ልዩነት በቫይረሱ የተያዘችው ስፔናዊት በቫይረሱ እንደተያዘች ካረጋገጠች በኋላ ምንም ዓይነት የኮሮና ምልክቶች አልታዩባትም ነበር። ሆኖም ግን ከሶስት ሳምንታት በነሳ ጊዜ ውስጥ የቫይረሱን ምልክቶች በማየቷ ድጋሚ ለመመርመር ምክንያት ሆኗታል። በውጤቱም ቫይረሱ እንደያዛት የተረጋገጠ ሲሆን ከመጀመሪያው የተለየ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ሁለተኛው ምርመራ ላይ ተገኝቷል። በአውሮፓ ውስጥ በሚገኝ አንድ የህክምና ምርምር ተቋም ጉዳዩን አስመልክቶ ገለጻ ያደረጉት ዶክተር ጄማ ሪሶ ይህ ሁኔታ ኦሚክሮን ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ በተፈጥሮ የሚያዳብሩትን ወይም በክትባት የሚያገኙትን በሽታ የመከላከል አቅም እንደሚበግር የሚያሳይ ነው ብለዋል። ""በሌላ አገላለጽ በኮቪድ 19 ተይዘው የነበሩ ሰዎች ክትባቱን ሙሉ በሙሉ ቢወስዱ እንኳን ለቫይረሱ አንጋለጠም ብለው ማስብ አይችሉም"" ሲሉ አስረድተዋል። ሆኖም ግን በቫይረሱ ቀድሞ መያዝ እና ክትባቱን መውስድ ከከፍ ህመም እና ሆስፒታል ከመግባት ሳይታደግ አይቀርም ሲሉ አክለዋል። ተመራማሪዋ ክትባት ሙሉ በሙሉ ወስደው በቫይረሱ ዳግም የሚያዙ ሰዎች ላይ የሚደረገው ምርመራ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው የኮቪድ ዝርያዎች ለክትባት ያላቸውን አይበገሬነት ለማጥናት ይረዳል ብለዋል። በዓለም ዙሪያ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ዳግም እንደተያዙ የሚያመላክቱ ቁጥሮች ከፍ ያሉት ኦሚክሮን የተባለው ዝርያ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ነው። በሌላ በኩል ባለፈው ወር ቢኤ 2 የተባለው የኮሮና ዝርያ መገኘቱን ተከትሎ በቫይረሱ ዳግም የሚያዙ ሰዎች ተበራክተዋል። ይህ ዝርያ ከመገኘቱ በፊት በዩኬ ለሁለተኛ ጊዜ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር 1 በመቶ ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን ወደ 11 በመቶ አሻቅቧል። አብዛኞቹ ሰዎች ቀደም ብሎ አልፋ ወይም ዴልታ በተሰኘው ቫይረስ ተይዘው የነበረ ሲሆን ለሁለለተኛ ጊዜ ሲያዙ የተገኘው ኦሚክሮን ዝርያ ነው። በዚህም መነሻ ማንኛውም ሰው በቫይረሱ ሁለት ጊዜ ሊያዝ እንደሚችል እና በህይወት ዘመን ውስጥ ከሁለት ጊዜም በላይ የመያዝ እድል እንዳል ሳይንቲስቶች ግምታቸውን አስቀምጠዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61172476 +sports የ53 ዓመቱ ጃፓናዊ የእግር ኳስ ኮከብ በተጫዋችነት እንዲቀጥል ኮንትራቱ ተራዘመ "አንጋፋው ጃፓናዊ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋች ካዙዮሺ ሚዩራ እስከ 54 ዓመቱ ድረስ ለመጫወት የሚያስችለውን ውል በመፈራራም በዮኮሃማ ክለብ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለመቆየት ተስማማ። የ2021 የጃፓን ሊግ ውድድር ከመጀመሩ ከአንድ ቀን በፊት ሚዩራ የካቲት 26 ቀን 54 ዓመት ይሆነዋል። የቀድሞው የጃፓን ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ዮኮሃማን ከ15 ዓመት በፊት የተቀላቀለ ሲሆን ለ17ኛ የውድድር ዘመን ለክለቡ ይጫወታል። ""ለእግር ኳስ ያለኝ ፍላጎትና ፍቅር እየጨመረ ነው"" ብሏል። ሚዩራ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው በብራዚሉ ሳንቶስ ክለብ ውስጥ 1986 (እአአ) ነበር። በ2017 ደግሞ በ50 ዓመት ከ14 ቀናት ዕድሜው ቴስፓኩሳትሱ ጉንማ ላይ ግብ በማስቆጠር በጃፓን ፕሮፌሽናል ሊግ ጨዋታ ግብ ያስቆጠረ የአንጋፋው ተጫዋችነት ክብረ ወሰንን ይዟል። በጃፓን 'ኪንግ ካዙ' [ንጉሥ ካዙ] ተብሎ የሚጠራው ሚዩራ በአገሪቱ ውስጥ በጣም ተወዳጅ ከሆኑ ስፖርተኞች መካከል አንዱ ሲሆን፤ በ1993 (እአአ) ጄ ሊግ ሲጀመር የውድድሩ ምልክት ተደርጎ ተወስዷል። ለጃፓን በ89 ጨዋታዎች 55 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን በክሮሽያና በአውስትራሊያ ከመጫወቱ በፊት በጣሊያን ሴሪ አ ለጄኖዋ ተጫውቷል። ሚዩራ ክለቡን በአምበልነት አገለግሏል። ከእግር ኳስ ቤተሰብ የተገኘው ተጫዋቹ ሺዙካ ውስጥ ነው ያደገው። አባታቸው የእግር ኳስ ደጋፊ ሲሆኑ ታላቅ ወንድሙ ያሱቶሺም ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ነበር። ""አባቴ በሜክሲኮው የ1970 የዓለም ዋንጫ ተገኝቶ ከመመልከት ባለፈ እነፔሌ ያሉበት ጨዋታን ቀርጾ ስለነበር እሱን እያየሁ ነው ያደግኩት"" ብሏል በአንድ ወቅት በሰጠው ቃለመጠይቅ። በሦስት ዓመቱ የተቀረጸውን ቪዲዮ መመልከት ብቻ ሳይሆን ""የብራዚል ደጋፊ ሆንኩኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ ፕሮፌሽናል ተጫዋች ለመሆን እፈልግ ነበር"" ብሏል። ወደ ብራዚል በማቅናትም ጁቬንቱስ ለተባለው የአገሪቱ እግር ኳስ ክለብ ፈረመ። ውጣ ውረዶች ቢኖሩበትም በስኬት አለፋቸው። ከእግር ኳስ ሌላ የሚያስበው መስክ ይኖር እንደሆን ሲጠየቅም ""ምንም ሃሳብ አልነበረኝም። ሁሌም የምፈልገው ፕሮፌሽናል ተጫዋች መሆን ነበር። ከባድ ጥያቄ ነው"" ሲል መልሷል። ብራዚል ውስጥ ፔሌ የተጫወተበንትን ሳንቶስን ጨምሮ በተለያዩ የብራዚል ክለቦች በመዘዋወርም መጫወት ችለወል። ከዚያም ወደ ጃፓን ታዋቂ ተጫዋች ሆኖ ተመለሰ። ጄ ሊግ ሲጀመርም እንደ ጋሪ ሊነክር ያሉ ተጫዋቾችን በመቅደም ኮከብ ሆኖ የውድድር ዓመቱን አጠናቀቀ። በ1994 ወደ ጄኖዋ በውሰት ሄዶ የተጫወተ ሲሆን በዚህም በሴሪ አው የተጫወተ የመጀመሪያው ጃፓናዊ ለመሆን በቃ። በ2005 (እአአ) አሁን ለሚጫወትበት ዮኮሃማ የፈረመ ሲሆን ክለቡ በሁለተኛው ዲቪዚዮን ይጫወት ነበር። ቡድኑ በቀጣዩ ዓመት ወደ ዋናው ሊግ ለማደግ ቻለ። ሚዩራ በተደጋጋሚ ካለመጎዳቱም በላይ ባለው አካላዊ ብቃት አጠባበቅ ይታወቃል። ካለው ጠንካራ አካላዊ ብቃት ባሻገር ታዋቂነቱም እየተጫወተ እንዲቀጥል አድርጎታል። እሱ የሚጫወት ከሆነ እስከ 4000 የሚደርሱ ተጨማሪ ተመልካቾች ወደ ሜዳ ይገባሉ ተብሏል። እና የ53 ዓመቱ ካዙ አሁንም እንደ ታዳጊዎች በየዕለቱ በፍቅር ልምምዶችን ያከናወናል? ተብሎ ሲጠየቅ ""አዎ። አሁንም እግር ኳስ መጫወት ያስደስተኛል። ብራዚል ከነበርኩበት ጊዜ በበለጠ እግር ኳስ መጫወት ያስደስተኛል"" ሲል ምላሽ ይሰጣል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55621028 +politics ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት ይፋዊ ያልሆነ ውድድር ተጀመረ የዩይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ ከካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውና ከምክር ቤት አባላት ድጋፍ ሳያገኙ በመቅረታቸው ከወግ አጥባቂው ፓርቲያቸው መሪነት መልቀቃቸውን ተከት��� እርሳቸውን ለመተካት ፉክክር ተጀምሯል። የፓርላማ አባሉ ቶም ቱጌንዳት ይህንን ውድድር ተቀላቅለው፣ የቦሪስን ቦታ ለመተካት ፍላጎት ያሳዩትን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሱዌላ ብሬቨርማን እና ስቴቭ ቤከርን ተቀላቅለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ፣ እርሳቸውን የሚተካ ሰው እስከሚገኝ እስከ መስከረም ድረስ በጠቅላይ ሚንስትርነት በሥልጣናቸው ላይ ለመቆየት አቅደዋል። ሆኖም በርካታ ባልደረቦቻቸው እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አሁኑኑ ሥልጣን እንዲለቁ ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክፍት የነበሩትን የካቢኔ ቦታዎችን በሌሎች ተክተዋል። በርካታ የካቢኔ አባላሎቻቸው አስተዳደራቸውን በመቃወም ሥራ ከለቀቁ በኋላ ቦሪስ ጆንሰን ሥልጣናቸውን ይዘው ለመቆየት ለሁለት ቀናት እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ካደረጉ በኋላ ሐሙስ ዕለት ከፓርቲ መሪነት እንደሚነሱ ገልጸዋል። ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በከፍተኛ እና በዝቅተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ወደ 60 የሚጠጉ የወግ አጥባቂ ፓርቲ የምክር ቤት አባላት ከመንግሥት ኃፊነት መልቀቃቸው መንግሥት ኃላፊነቱን ለመወጣት ያለውን አቅም ጥራጣሬ ውስጥ ከቶታል። ቦሪስ ጆንሰን አዲስ ለተሾሙት ካቢኔ አባሎቻቸው ሐሙስ ዕለት ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ቀሪ ጊዜያቸውን ዋና ዋና የፖሊሲ ለውጦችን ለማድረግ እንደማይጠቀሙበት ቃል ገብተዋል። የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ አመራር ውድድር የጊዜ ሰሌዳ በሚቀጥለው ሳምንት የሚታወቅ ሲሆን፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እስከ መስከረም ወር ማብቂያ ድረስ ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይሁን እንጂ ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ውድድሩ በመካሄድ ላይ ነው። የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቱገንዳት፣ አርብ ዕለት ለዴይሊ ቴሌግራፍ በጻፉት ጽሁፍ የአመራርነት ወድድራቸውን የጀመሩ ሲሆን “የግብር ቅነሳ እና አዲስ ጉልበትና ሃሳብ” ይዘው እንደሚመጡ ቃል ገብተዋል። የቦሪስ ጆንሰን ቀንደኛ ተቺ የነበሩት የቀድሞ ወታደር ቱገንዳት “ከዚህ ቀደም በጦሩ ውስጥ አገልግያለሁ፣ አሁን ደግሞ በፓርላማ ውስጥ እየሰራሁ ነው። አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የቀረበልኝን ጥሪ ለመመለስ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብራቨርማን በበኩላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሚወዳደሩ አረጋግጠዋል። የብሬግዚት ሚኒስትሩ ቤከርም ሰዎች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲወዳደሩ ከጠየቋቸው በኋላ ለመወዳደር እንዳሰቡ ተናግረዋል። የቦሪስ ጆንሰን ተቃዋሚ የነበሩት የቀድሞው የጤና ኃላፊ ሳጂድ ጃቪድ እና የትራንስፖርት ኃላፊ ግራንት ሻፕስም ውድድሩን ለመቀላቀል እንዳሰቡ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሊዝ ትረስ፣ የቀድሞ ቻንስለር ሪሺ ሱናክ እና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጀረሚ ሃንትም በውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይገመታል። በሚቀጥሉት ቀናት በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ገለጻ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። ሆኖም ማይክል ጎቭ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ እና የቀድሞ የጤና ኃላፊ ማት ሃንኩክን ጨምሮ የቀድሞ የፓርቲው አመራር አባላት እንደማይወዳደሩ ተናግረዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c9873qy97g9o +politics አገር ጥለው የሸሹት የቀድሞው የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት ህዝቡን ይቅርታ ጠየቁ "ታሊባን የአፍጋኒስታንን መዲና ካቡልን መክበቡን ተከትሎ አገር ጥለው ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የተሰደዱት የቀድሞው የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋኒ ህዝቡን ይቅርታ ጠየቁ። ""ካቡልን ለቅቆ መውጣት በሕይወቴ ውስጥ በጣም ከባድ ውሳኔ ነበር።"" በማለት የተናገሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከዚህ በተለየ መልኩ ባለማድረጋቸውም ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የታሊባን ታጣቂዎች ነሐሴ መጀመሪያ ላይ መዲናዋን ካቡልን መ��በባቸውን ተከትሎ ነው አሽራፍ ጋኒ በድንገት ሃገር ጥለው የሸሹት። ህዝቡን ለመተው ሃሳባቸው እንዳልነበር የተናገሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ""ብቸኛው መንገድ ነው"" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም 169 ሚሊዮን ዶላር ይዘው ነው ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የተጓዙት የሚለውን ""መሠረተ ቢስ"" ውንጀላ በሚል በድጋሚ አስተባለዋል። ረቡዕ ዕለት በትዊተር ላይ በተጋራ መግለጫ እንደተጠቀሰው የቀድሞው ፕሬዚዳንት በአገሪቱ ሁከት እንዳይፈጠር አገሪቱን ለቅቆ ከመውጣት ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ተናግረዋል። ""በ 1990ዎቹ የእርስ በእርስ ጦርነትና የከተማ ላይ ውጊያ ካቡል ከደረሰባት ተመሳሳይ አደጋ ላይ እንዳትወድቅ በቤተ መንግሥቴ ደህንነት የተሰጠኝን ምክር በመስማት ነው የወጣሁት። ካቡልን እና ስድስት ሚሊዮን ዜጎቿን ለማዳን"" በማለትም አስፍረዋል። አፍጋኒስታንን ""ዲሞክራሲያዊ ፣ የበለፀገች እና ሉዓላዊ መንግሥት"" እንድትሆን ለመርዳት ለ20 ዓመታት መስራታቸውንም ጠቅሰዋል። አክለውም ""የኔ የስልጣን ምዕራፍ ከቀዳሚዎቼ ጋር ተመሳሳይ በሆነ በአሳዛኝ ሁኔታ መቋጨቱ ጥልቅ ጸጸት አሳድሮብኛል"" ብለዋል። አገሪቱን ለቀው በመውጣታቸው ከአፍጋኒስታን ፖለቲከኞች ከፍተኛ ትችትን ያስተናገዱት የ 72 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ""እኔ ከመውጣቴ በፊት የነበሩትን ክስተቶች"" በተመለከተ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በፌስ ቡክ በቀጥታ በተላለፈ መልዕክታቸው አሽራፍ በደህንነት ቡድናቸው ከአገር ለመውጣት እንደተገደዱ ተናግረዋል። ምክንያቱንም ሲያስረዱ ""ተይዤ የመገደሌ ሁኔታ ከፍተኛ ነበር"" ብለዋል። የታሊባን ታጣቂዎች በካቡል ወደሚገኘው የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት ካቀኑ በኋላ ""ከክፍል ወደ ክፍል እየተዟዟሩ እኔን መፈለግ ጀመሩ"" በማለትም አስረድተዋል። አገሪቱን ለቅቀው ሲወጡ ከፍተኛ ገንዘብ ወስደዋል የሚለውን ክስ በተመለከተም ""ሸበጥ ጫማዬን እንኳ አውልቄ ደህና ጫማ እንዳደርግ አልተፈቀደልኝም"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58500497 +business ጋናዊው ባለሀብት ቼልሲን በ3.1 ቢሊዮን ዶላር ሊገዙ እንደሆነ ተዘገበ ጋናዊው የንግድ ሰው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ኃያል ክለብ የሆነውን ቼልሲ የእግር ኳስ ቡድንን በ3.1 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ፍላጎታቸውን መግለጻቸው ተዘገበ። በስፋት ዉንቱሚ በሚለው ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት ጋናዊው ባለሀብት ቤርናርድ አንትዊ ቦሲያኮ የቼልሲ ቡድንን የመግዛት ፍላጎታቸው የሚሳካ ከሆነ የፕሪሚዬር ሊግ ኃያል ቡድን ባለቤት በመሆን የመጀመሪያው አፍሪካዊ ይሆናሉ። ጋናዊው ባለሀብት ቡድኑን በእጃቸው ካስገቡ የማንችስተር ዩናይትዱን ክሪስቲያኖ ሮናልዶን እና የፓሪ ሴንጄርሜኑን ሊዮኔል ሜሲን የመሳሳሉ የእግር ኳስ ከዋክብትን ወደ ቡድኑ የማምጣት ፍላጉት እንዳላቸው ተነግሯል። ጋናዊው ባለሀብት ቤርናርድ በአገሪቱ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ባለቤት እና ፖለቲከኛ ሲሆኑ፣ በስፖርቱ ዘርፍ ብዙም የሚታወቅ ታሪክ ስለሌላቸው ቼልሲን የመግዛት ፍላጎታቸው ይፋ ሲሆን በርካታ ጋናውያንን አስደንቋል። የግለሰቡ የሀብት ምንጭ የወርቅ ማዕድን ሲሆን በተጨማሪም የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አሏቸው። ነገር ግን አስካሁን ያላቸውን የሀብት መጠን በይፋ ገልጸው ስለማያውቁ ምን ያህል እንደሆነ መረጃ የለም። ባለሀብቱ ቤርናርድ ከማዕድን ማውጣቱ በተጨማሪ በጋና ፖለቲካ ውስጥ ተሳታፊ ሲሆኑ፣ በዚህም የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ የአሻንቲ ክልል ሊቀመንበር ናቸው። የወቅቱ የቼልሲ እግር ኳስ ቡድን ባለቤት ሩሲያዊው ሮማን አብራሞቪች ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከተሎ ባጋጠማቸው ጫና ቡድኑን እንደሚሸጡ ከሳምንት በፊት ማሳወቃቸ��� ይታወሳል። አብራሞቪች የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን ጋር የቀረበ ግንኙነት አላቸው ከተባሉ ሩሲያውያን ከበርቴዎች መካከል አንዱ በመሆናቸው ከዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በኩል እቀባዎች ተጥሎባቸዋል። አብራሞቪች ቼልሲን ለመሸጥ ያላቸውን ፍላጎት ይፋ ካደረጉ በኋላ የጋናዊው ባለሀብት ጠበቆች እና የንግድ አማካሪዎች ከቼልሲ ባለቤት ጋር ድርድር ለማድረግ ለንደን እንደነበሩ ተገልጿል። ከበርቴው ንብረታቸው በመታገዱ እና የጉዞ እቀባ ስለተጣለባቸው የእግር ኳስ ቡድናቸውን የመሸጥ ፍላጎታቸው ለጊዜው ተግባራዊ እንዳያደርጉ መገደዳቸው አይቀርም ተብሏል። https://www.bbc.com/amharic/news-60696157 +health ክብደትዎን መቀነስ ይፈልጋሉ? ቁርስ እንዴት መመገብ እንዳለብዎ እንንገርዎ ቁርስዎን በደንብ መመገብ እና ቀለል ያለ እራት መብላት የረሃብ ስሜት እንዳይኖር በማድረግ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል ይላሉ ተመራማሪዎች። ሳይንቲስቶች ከበድ ያለ ቁርስ ወይም ከበድ ያለ እራት በሰዎች ክብደት ላይ የሚያመጣውን ተፅእኖ ለማነፃፀር ሞክረዋል። የቀኑን ዋነኛ ምግብ በየትኛው ሰዓት ቢመገቡ ሰዎች የሚያቃጥሉት ካሎሪ ተመሳሳይ ሆኖ እንደሚሆን የአበርዲን ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ደርሰውበታል። ነገር ግን በደንብ ቁርሳቸውን የተመገቡ ሰዎች በቀን ውስጥ ያላቸው የምግብ ፍላጎት አነስተኛ ሆኖ ታይቷል፤ ይህም ማለት የሚፈልጉትን አመጋገብ ለመከተል ቀላል ያደርገዋል። አጥኚዎቹ በዚህ ምርምራቸው ‘ክሮኖ ኒውትሪሽን’ የተሰኘው ፅንሰ ሃሳብን በጥልቀት ለማየት ሞክረዋል። [ክሮኖ ኒውትሪሽን በየትኛው ሰዓት ምግብ መመገብ የበለጠ ውጤታማ ያደርገናል የሚለውን የሚመረምር ሳይንስ ነው። የሰውነትዎን አካላዊ፣ አዕምሯዊ እና ስሜታዊ ዑደቶችን የሚቆጣጠረው ክፍል ምግብ ጋር ያለውንም ዝምድና ይገመግማል። ] ከመሸ በኋላ መመገብ ለሰውነታችን መጥፎ ጊዜ ነው፣ ምክንያቱም የሰውነታችን ሰዓት ምግብን ወደ ኃይል የሚለውጠውን (ሜታቦሊዝም) ወደ እንቅልፍ ስለሚቀይረው ነው። ተመራማሪዎቹ ያሳተፏቸው 30 በጎ ፈቃደኞች ከሁለት ወራት በላይ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት በቀን በአጠቃላይ እስከ 1 ሺህ 700 ካሎሪ የሚሆን ምግብ ተዘጋጅቶላቸው ነበር። በአንደኛው ወር ለቀን የሚያስፈልገውን የካሎሪ መጠን ግማሹን ለቁርስ እንዲበሉ እና ምሳ እና እራት ደግሞ አነስ ያለ ምግብ እንዲመገቡ ተደርገዋል። በሁለተኛው ወር እነዚህ በጎ ፈቃደኞች ከቁርስ ይልቅ እራት ላይ ከበድ ያለ ምግብ እንዲበሉ ተደረጉ። ሴል ሜታቦሊዝም በተሰኘው ጆርናል ላይ በታተመው ውጤት መሰረት የቀኑን ከባድ ምግብ በየትኛውም ሰዓት መመገብ ሰውነታችን በቀን ምን ያህል ካሎሪ ያቃጥላል የሚለው ላይ ምንም ልዩነት የለውም። ዋነኛው ልዩነት ግን የታየው በምግብ ፍላጎት ወይም የረሃብ ስሜት ላይ ነው። ከፍተኛ ቁርስ የሚመገቡ ሰዎች በቀን ውስጥ አነስተኛ የምግብ ፍላጎት እንዲኖራቸው ማድረግና የረሃብ ስሜትንም እንዲቆጣጠሩ ያደርጋል። ፕሮፌሰር አሌክሳንድራ ጆንስተን እንደሚሉት በርካቶች የሚመገቡትን የምግብ መጠን በማይቆጣጠሩበት ሁኔታ ውስጥ ጥናቱ ወሳኝ ሊሆን ይችላል። “ጥናቶቹ እንደሚጠቁሙት የምግብ ፍላጎትን ለመቆጣጠር በደንብ ቁርስ መመገብ መሠረታዊ ነው” ይላሉ። “ቀንዎን በጤናማ እና በትልቅ ቁርስ መጀመር ከቻሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ እንዲሁም በተቀሩት ሰዓታት ያለውን የምግብ ፋላጎትን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ዕድል ይሰጣል” በማለት ያስረዳሉ። በጥናቱ ውስጥ የተካተቱት የቁርስ ዓይነቶች የፍራፍሬ ጭማቂ፣ እርጎ፣ እንቁላል፣ ቋሊማ (ሶሴጅ) እና እንጉዳይ የያዘ ሲሆን፣ ይህም ሁሉም ሰዎች ጥጋብ እንዲሰማቸው የሚያደር�� ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ያለው ነው። ከፍተኛ ቁርስ መመገብ ለምን የምግብ ፍላጎትን እንደሚቀንስ ግልፅ አይደለም። ነገር ግን ፕሮፌሰር ጆንስተን እንደሚሉት ይህ ሁኔታ ከአዕምሯችን የምግብ ፍላጎት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ሃሳቦች አሉ ይላሉ። “የአዕምሯችን የምግብ ፍላጎት የሌሊቱን ጾም የምንፈታበትና የመጀመሪያ ምግብ ጋር የበለጠ የተጣጠመ ነው” ይላሉ። ነገር ግን ይህ ውጤት ከበርካቶች የአመጋገብ ልምድ ጋር ተቃራኒ ነው። “በርካቶች የሚተኙበትን ሰዓታት ለመጨመር እየሞከሩ ባለበት ወቅት በማለዳ ተነስተው ምግብ ለማዘጋጀትም ሆነ ተቀምጠው በደንብ ለመብላት ጊዜ አይኖራቸውም። ይህ ማለት በርካቶች በደንብ የሚበሉት እራት ነው” ይላሉ ፕሮፌሰር ጆንስተን። በአሁኑ ወቅት ሳይንቲስቶች በፈረቃ የሚሰሩ ሠራተኞች እኩለ ሌሊት ላይ ሲመገቡ ምን እንደሚፈጠር እየመረመሩ ነው። በተጨማሪም ግለሰቦች እንደ ባህርያቸው የጠዋት ሰዎች ከሆኑ ጠዋት፣ ወይም ደግሞ የማታ ሰዎች ከሆኑ ማታ መብላት ይኖርባቸው ይሆን? የሚለውን ለማየት እየሞከሩ ነው። “አመጋገብዎን ለመለወጥ እያሰቡ ከሆነና የሚራቡበትን ወይም ተጨማሪ መክሰስ ሰውነትዎት የሚፈልግበትን ወቅት ያስቡ” በማለት የሚናገሩት የአስተን ዩኒቨርስቲ የአመጋገብ ባለሙያ ዶክተር ዱዋን ሜሎር ናቸው። “ረሃብ የሚሰማዎት ጠዋት ከሆነ በደንብ ቁርስ መመገብ ሊረዳዎት ይችላል። በተመሳሳይም የምሽት ተመጋቢ ከሆኑም በቀን ውስጥ አነስተኛ ምግቦችን ተመግበው እራት ላይ በደንብ መመገብ ሊጠቅምዎ ይችላል” ይላሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n0dgyddg8o +health ኮሮናቫይረስ፡ አውስትራሊያ የኮሮና ክትባት በነጻ እሰጣለሁ አለች አውስትራሊያ ኮቪድ-19 ክትባትን ለአገሬ ሕዝብ ሽራፊ ሳንቲም ሳልቀበል አድላለሁ ብላለች፡፡ አውትራሊያ 25 ሚሊዮን ለሚሆነው ሕዝቧ የምታድለውን ክትባት የምታገኘው ከእንግሊዝ ነው፡፡ አሁን በሙከራ ላይ ካሉ የክትባት ዜናዎች ሁሉ ላቅ ያለ ተስፋ የተጣለበት የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው ክትባት ነው፡፡ ኦክስፎርድ ክትባቱን ከታዋቂው የመድኃኒት አምራች አስትራዜኔካ ጋር በመቀናጀት እያዳበረው ይገኛል፡፡ ይህ ክትባት በቀጣይ የሚደረጉ የመጨረሻ ምዕራፍ የክሊኒካል ሙከራዎች ስኬታማ ሆነው ከተጠናቀቁ አውስራሊያ ክትባቱን ለመግዛት ቀዳሚ አገር ሆና ተሰልፋለች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን፡፡ ሞሪሰን እንደሚሉት ክትባቱን እያንዳንዱ ዜጋ እንዲወስድ ግዴታ ይጣልበታል፡፡ በአውስትራሊያ የሟቾች ቁጥር 450 አልፏል፡፡ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰውም በቪክቶሪያ ግዛት ነው፡፡ በዚህ ወር መጀመርያ አካባቢ ቪክቶሪያ የአስቸኳይ ጊዜ በመደንገግ ሰዎች ቤታቸው እንዲቀመጡ አስገድዳ ነበር፡፡ ይህም በሽታው ሥርጭት ከፍ ብሎ በመታየቱ ነው፡፡ አሁን በአውስራሊያ 7ሺ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ እንደተነኩ ይገመታል፡፡ ሆኖም አሁን በየቀኑ አዳዲስ ታማሚዎቸ ቁጥር እየጨመረ ሳይሆን እየቀነሰ ነው ያለው፡፡ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲና የአስትራዜኔካ ጥምረት እየተሞከረ ያለው ክትባት በዓለም ላይ አሁን ተስፋ ከተጣለባቸው አምስት ሙከራዎች በዋነኛነት የሚጠቀስ ነው፡፡ አገራት ይህን ክትባት ወደ ገበያ ሲወጣ ቅድሚያ አግኝተው ለሕዝባቸው ለማድረስ ከፍተኛ ፉክክር ላይ ናቸው፡፡ የመጨረሻው የሙከራ ምዕራፍ ስኬታማ ሲሆን አውስራሊያ መድኃኒቱን በአገሯ ለማምረት ተዘጋጅታ ከወዲሁ ስምምነት ፈጽማለች፡፡ ሞሪስ እንደሚሉት ‹‹ወዲያው አምርተን ወዲያው 25 ሚሊዮን ሕዝባችንን እንከትባለን፡፡›› አንድ አገር ሙሉ ሕዝቧን ለመክተብ ምን ያህል ወጪ ያስወጣታል የሚለው ገና አልተሰላም፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አውስትራሊያ ���ላ ስምምነት አድርጋለች፡፡ ይህ ስምምነት 25 ሚሊዮን ዶላር አስከፍሏታል፡፡ ስምምነቱ ከአሜሪካ የመድኃኒት ቁሳቁስ አምራች ቤክተን ዲኪንሰን ጋር ሲሆን 100 ሚሊዮን መርፌና ስሪንጆችን ለማቅረብ የተደረገ ስምምነት ነው፡፡ አውስትራሊያ ከአስትራዜኔካ ጋር ያደረገቸው የክትባት ስምምነት በታሪኳ የመጀመርያው ነው፡፡ የአውስትራሊያ ሕዝብ መቼ ይከተባል ለሚለው ሚስተር ሞሪሰን ‹‹ክትባቱ የመጨረሻው ሙከራ ከተሳካ በመጪው ዓመት የመጀመርያዎቹ ወራት አውስትራሊያዊያን ይከተቡታል›› ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሁሉም ዜጋ የመከተብ ግዴታ ይጣልበታል ቢሉም ይህ አከራካሪ ጉዳይ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ሞሪሰን መንግስታቸው በዚህ ረገድ ገና ፖሊሲ እየቀረጸ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ለአንድ የአገሬው ራዲዮ ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሚስተር ሞሪሰን ‹‹በተለየ የጤና ምክንያት መድኃኒቱን ለመከተብ የማይገደዱ›› እንደሚኖሩ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹እያወራን ያለነው የዓለምን ምጣኔ ሀብት ስላንኮታኮተ ወረርሽኝ ነው፡፡ ሺዎችን ሕይወት ስለቀጠፈ ወረርሽኝ ነው፤ ክትባቱ አማራጭ ተደርጎ የሚወሰድ ይሆናል ብዬ አልጠብቅም›› ብለዋል አስገዳጅነቱ አይቀሬ መሆኑን ሲያስገነዝቡ፡፡ ሚስተር ሞሪሰን በትንሹ 95 ከመቶ አውስትራሊያዊያንን ለመከተብ እንደታሰበ አልሸሸጉም፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-53831242 +politics ኢዜማ በ28 ምርጫ ወረዳዎች ምርጫ እንዲደገም ያቀረበው አቤቱታ ላይ ቦርዱ ምላሽ እንዲሰጥ ፍርድ ቤት ወሰነ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ሰኔ 14 በተካሄደው ብሔራዊ ምርጫ በሃያ ስምንት የምርጫ ወረዳዎች ምርጫው እንዲደደገም ያቀረበው አቤቱታ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምላሽ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል። ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ የምርጫ ጉዳይ ችሎት በዛሬው ዕለት መሆኑንም ኢዜማ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል። ፍርድ ቤቱ ፓርቲው በ28 ምርጫ ወረዳዎች ምርጫ እንዲደገም ያቀረበውን አቤቱታ ሲመረምር ቆይቶም ፓርቲው ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ተቀብሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ይዞ እንዲቀርብ ተወስኗል። ምርጫ ቦርድ ለሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ምላሹን ይዞ መቅረብ እንዳለበትም ፍርድ ቤቱ በዛሬው እለት መበየኑ ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ኢዜማ ከዚህ ቀደም ለምርጫ ቦርድ ያስገባቸውን የቅሬታ ማስገቢያ ቅፆች ቅጂም ከሐምሌ 30 በፊት ቦርዱ ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ተላልፏል። ኢዜማ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገባው የይግባኝ አቤቱታ ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል ባላቸው 28 የምርጫ ወረዳዎች ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያስተላልፍለት በመጠየቅ ነው፡፡ ኢዜማ በነዚህ ምርጫ ወረዳዎች የተፈጸሙ ግድፈቶች አሉ በሚል ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዱ የሚታወስ ነው። ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ ያስገባው ኢዜማ፤ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰድኩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀርብኩለትን ቅሬታዎች እንዲሁም ማስረጃዎችን ሳይገመግም ውሳኔ ስላስተላለፈብኝ ነው ብሏል፡፡ ኢዜማ ሰኔ 14 በተደረገው አገራዊ ምርጫ ከድምጽ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ከቀበሌ እስከ ክልል ባሉ የገዢው ፓርቲ አመራሮች፣ ከቀበሌ ሚሊሻ እስከ ክልል ልዩ ኃይል ድረስ ባሉ የጸጥታ አስከባሪዎች፣ ምርጫ አስፈጻሚዎችና ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች አማካኝነት ምርጫው ሲስተጓጎል ነበር ሲል ከሷል፡፡ ይህም በምርጫው ውጤት ላይ ተጽእኖ አሳድሯል ብሏል፡፡ ለዚህም በቂ የሆነ የሰው፣ የሰነድ የቪዲዮና የምሥል ማስረጃዎችን ማጠናቁሩንም ገልፆ ነበር፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-58008367 +politics የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር በመጠጥ ድግስ ተገኝተዋል በሚል ቁጣ በረታባቸው "በመላው ዩናይትድ ኪንግደም የኮቪድ እንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎ በነበረበት ወቅት ቦሪስ ጆንሰን በአንድ የመጠጥ ድግስ ላይ ተገኝተዋል በሚል ክፉኛ እየተብጠለጠሉ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ወቀሳ እያዘነቡ ያሉት የሌበርና በገዛ ፓርቲያቸው በኮንሰርቫቲቭ እንደራሴዎች ጭምር ነው። ቦሪስ ወይ ፈጣን ምላሽ ይስጡ ወይም ሥልጣን በአስቸኳይ ይልቀቁ ሲሉ በርካታ የፓርቲ ተወካዮች ድምጻቸውን አሰምተዋል። ይህ የመጠጥ ድግስ ተደርጓል የተባለው ደግሞ በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ዳውኒንግ ጎዳና በሚገኘው መናፈሻ ነው። ዳውኒንግ ስትሪት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋዊ መኖርያ እና ጽ/ቤት የሚገኝበት መንገድ ነው። ወትሮም የጋለ ክርክርና ሙግት የማይጠፋበት የዩኬ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ድግስና የቦሪስ ጆንሰን በድግሱ ተገኝተዋል በሚለው ነጥብ ዙርያ ለቀናት ሲናጥ ነው ቆይቷል። የሌበር ፓርቲ ምክትል አንጌላ ራይነር፣ 'የቦሪስ ጉድ ለጊዜው ተሸሽጎ ሊሆን ይችላል፣ ተደብቆ ግን አይዘልቅም፣ እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል' ሲሉ ተናግረዋል። ይህ የመጠጥ ፌሽታ ድግስ ተደረገ የሚባለው እንደነርሱ አቆጣጠር በግንቦት፣ 2020 ዓ/ም ሲሆን ይህ ጊዜ ደግሞ ዩኬ በጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ውስጥ የነበረችበት ወቅት ነው። የስኮቲሽ ወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ ዳግላስ ሮስ በበኩላቸው ቦሪስ ጆንሰን እንደሚባለው በወቅቱ የኮቪድ እንቅስቃሴ ገደብ ጥሰው ከነበረ ያለምንም ማወላወል ሥልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እስከአሁን በዚህ ድግስ ስለመገኘት አለመገኘታቸው ትንፍሽ አላሉም። ሆኖም የዚህን ዜና ሾልኮ መውጣት ተከትሎ የተቆጡት እንደራሴዎች ዛሬ ረቡዕ በጥያቄና መልስ ሸንጎ ላይ የሚገኙትን ቦሪስ ጆንሰንን ፊት ለፊት ያፋጠጧቸዋል፣ መፈናፈኛም ያሳጧቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። ሰኞ ዕለት አይቲቪ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና የግል ጸሐፊያቸውን ማርቲን ሬይኖልድስ 100 የሚሆኑ ሰዎችን በቦሪስ መኖርያ በሚገኝ መናፈሻ ለመጠጥ ድግስ ጥሪ ያደረጉበትን ኢሜይል አሾልኮ በማውጣት ለሕዝብ ይፋ አድርጎታል። ይህን ተከትሎ ነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የሥልጣን ይልቀቁ ጥያቄ የበረታው። የዓይን እማኞች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት በወቅቱ በዚህ የመጠጥ ድግስ ላይ ቦሪስ ጆንሰን እና ባለቤታቸው ኬሪ ጆንሰን ተገኝተውም ተዝናንተውም ነበር። የወግ አጥባቂው ፓርቲ የቀድሞ ሚኒስትር ጆኒ ሜርሰር በትዊተር ሰሌዳቸው፤ ""ይህ እጅግ አሳፋሪ ነገር ነው፤ የቦሪስ ድርጊት የፓርቲያችንን አገርንና ሕዝብን ምሳሌ ሆኖ በመምራት ላይ የተመሠረተ ባሕል አይወክልም።"" ሲሉ ጽፈዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ ብቻ ሳይሆን የእርሳቸው ቃል አቀባይም ምላሽ አለመስጠት በዩኬ ነገሩን አነጋጋሪ አድርጎታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59954382 +sports አትሌት ሹራ ቂጣታ የአበበ ቢቂላን የቶኪዮ ኦሊምፒክ ታሪክ ለመድገም እቅድ አለኝ አለ "በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች የማራቶን ውድድር ትልቅ ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው ሹራ ቂጣታ የአበባ ቢቂላን የቶኪዮ ኦሊምፒክ ታሪክ ለመድገም እቅድ አለኝ አለ። ""አበበ ቢቂላ ባስገኘው ድል ለአገር ትቶ ያለፈውን ታሪክ ለማስመለስ ጥረት እያደረግን ነው። ይህን ውድድር አሸንፌ የአበበ ቢቂላን ታሪክ ወደ አገር ቤት ለመመለስ ሐሳብ አለኝ"" ሲል አትሌት ሹራ ቂጣታ ለቢቢሲ ተናግሯል። አበበ ቢቂላ አእአ በ1964 በቶኪዮ ተካሂዶ በነበረው የኦሊምፒክ መድረክ በማራቶን ውድድር ተወዳዳሪዎቹን ከ4 ደቂቃዎች በላይ ጥሎ በመግባት ማሸነፉ ይታወቃል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድንም በዘንድ���ው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በማራቶችን ወርቅ በማምጣት የአበበ ቢቂላ የማራቶን ድል ለመድገም ከፍተኛ መነሳሳት ውስጥ እንዳለ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ደራርቱ ቱሉ ትናገራለች። በኦሊምፒክ መድረክ ወርቅ የወሰደችው የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት ደራርቱ ቱሉ፤ ""አበበ ቢቂላ ያስመዘገበው ድል ዛሬ የሆነ ይመስለኛል"" ትላለች። በዘንድሮው የቶኪዮ ኦሊምፒክ የማራቶን ውድድር ለማሸነፍ ጠንካራ ዝግጅት መደረጉንም ጠቁማለች። ""እኛም አገርም የወርቅ ሜዳሊያ እንጠብቃለን"" ያለው ደግሞ በማራቶን ውድድሩ ተስፋ የተጣለበት አትሌት ሹራ ቂጣታ ነው። ""እኛ የወርቅ ሜዳሊያ እየጠበቅን ነው። አገርም እንዲሁ የወርቅ ሜዳሊያ ያመጠሉ ብሎ ይጠብቀናል"" በማለት አትሌት ሹራ ቂጣታ ለቢቢሲ ተናግሯል። በኦሊምፒክ መድረክ አገሩን ሲወክል የመጀመሪያ ጊዜ የሆነው ሹራ፤ ""በራስ በመተማመን የሚሮጥ ሰው ሊያሸንፍ ይችላል"" በማለት ይናገራል። ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ በወንዶች ማራቶችን አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። በሮም እና በቶኪዮ ኦሊምፒክ አበበ ቢቂላ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለአገሩ አስገኝቷል። እአአ በ1968 በተካሄደው የሜክሲኮ ኦሊምፒክ ደግሞ ማሞ ወልዴ ወርቅ ሲያስገኝ ገዛኸኝ አበራ በሲድኒ ኦሊምፒክ ወርቁን ወስዷል። ኢትዮጵያን በወንዶች ማራቶን የሚወክሉት አትሌቶች ሹራ ቂጣታ፣ ለሊሳ ዴሲሳ እና ሲሳይ ለማ ናቸው። በወንዶች ማራቶን የአሸናፊነት ግምቱ የተሰጠው ኬኒያዊው ኢሊዩዲ ኪፕቼጌ ነው። ኪፕቾጌ የርቀቱ ክብረ ወሰን ባለቤት ከመሆኑም በላይ በሪዮ ኦሊምፒክም የወቅት ሜዳሊያ አሸንፏል። ከአንድ ዓመት በፊት በተደረገው የለንደን ኦሊምፒክ ግን ሹራ ኬንያዊውን ኪፕቾጌን ማሸነፍ ችሎ ነበር። ኪፕቾጌ፤ ""በኦሊምፒክ አሁንም ወርቅ ማግኘት እፈልጋለሁ። ይህን ማድረግ ከቻልኩ ለእኔ ትልቅ ስኬት ነው"" በማለት ለሮይተርስ ተናግሯል። ኪፕቾጌ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ድል ከቀናው በተከታታይ የማራቶን ውድድር በማሸነፍ የአበበ ቢቂላን ታሪክ ይጋራል። ኢትዮጵያ ከኪፕቾጌ ቀጥሎ በማራቶን ፈጣን ሰዓት ያለውን አትሌቷ ቀነኒሳ በቀለን ትታ ነው ወደ ቶኪዮ ያቀናችው። ቀነኒሳ የኦሊምፒክ ማጣሪያ ላይ ለመወዳደር ፍቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ በዚህ ውድድር አይሳተፍም ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ እንደነ ሹራ ባሉት ጠንካራ አትሌቶች ተስፋ ሰንቃለች። ሌላኛው ተጠባቂ አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ ነው። አትሌት ሌሊሳ ከሁለት ዓመት በፊት በኳታር፣ ዶሃ በተደረገው የዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በማራቶን የወርቅ አሸናፊ ነበር። አትሌት ሲሳይ ለማ ደግሞ በ2020 ሎንዶን ማራቶን ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል። በቶኪዮ ከፍተኛ ሙቀት ስላለ የማራቶን ውድድሩ ከቶኪዮ ከተማ በ800 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሳፖራ ከተማ ይከናወናል። ውድድሩ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58079205 +politics የቡድን ሰባት አገራት የቻይናን አለምአቀፋዊ ተፅዕኖ የሚገዳደር እቅድ አቀረቡ "የቡድን ሰባት (ጂ 7) አመራሮች ቻይና በመካከለኛና ዝቅተኛ አገራት የምታደርገውን የመሰረተ ልማት ግንባታ ሊገዳደር የሚችል እቅድ አቅርበዋል። የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይን ከቻይና ፕሮግራም በከፍተኛ ጥራት ደረጃ አማራጭ ነው ያሉትን በአሜሪካ የተደገፈ የተሻለ አለም መገንባት እቅዳቸውንም አስረድተዋል። በአለም ላይ ያለውን የቻይና ተፅእኖን ለመቀልበስ በሚል የቡድን ሰባት አገራት የራሳቸው አማራጭ ያሉትን ሃሳብ አቅርበዋል። የቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሺየቲቭ (ቢአርአይ) በበርካታ አገራት ባቡሮችን፣ መንገዶችንንና ወደቦችን ለመገንባት በቢሊዮኖች ዶላር የሚገመት የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋ��። ነገር ግን አገራት ከማይወጡበት የብድር አዘቅት በመክተትም ከፍተኛ ትችቶች ይቀርቡበታል። በእንግሊዟ ኮርንዌል በነበረው የቡድን ሰባት ጉባኤ የወጣው መግለጫ ""በጥራት ከፍተኛ ደረጃ ያለውን ግልፅነት በተሞላ መልኩ አጋርነትን የሚያሳይ ግንኙነትን"" ከነዚህ አገራት ጋር መመስረት እንደሚፈልጉ አትቷል። ነገር ግን ቡድን ሰባት ያቀረቡት ይህ እቅድ ፈንዱ ከየት እንደሚመጣ አልተነገረም። የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ መርኬል ለዚህ ጅማሮ ገንዘብ ከየትም ሆነ እንዴት እንደሚመደብ ለመወሰን ጊዜው ገና ነው ብለዋል። አሜሪካ ለአመታት ያህል ቻይና በአገራቱ ላይ የምታካሂደው ""የብድር ዲፕሎማሲ"" ነው በማለት በከፍተኛ ሁኔታ ታወግዛታለች። ቡድን ሰባት የተባሉት የአለም ሃብታምና በዲሞክራሲ የዳበሩ አገራት የቻይናን ተፅእኖ ከመቀልበስ በተጨማሪ አለም የሚያጋጥማትን የወደፊቱ ወረርሽኝ ለመከላከልም አዲስ እቅድ ነድፈዋል። አገራቱ ለኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት የሚያስፈልገው ፈቃድ ከመቶ ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ መስጠት የሚያስችል እርምጃ ለመውሰድ መክረዋል። ይህ እቅድ ከጉባኤው ይፋዊ መግለጫ ጋር እሁድ ይወጣል ተብሏል። በካብሪስ ቤይ ሪዞርት የሚደረገውን የሶስት ቀን ጉባኤ በጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-57458940 +health ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያ ነፃ የኮቪድ-19 ምርመራ መስጠት መጀመሯን አስታወቀች የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ነፃ ምርመራ ማድረግ እንደሚችሉ የጤና ሚኒስቴር እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቀዋል። በአዲስ አበባ በሚገኙ በተመረጡ 34 የጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች ከክፍያ ነፃ ናሙና በመስጠትም ምርመራ ማድረግ ይችላሉም ተብሏል። የጤና ማዕከላቱንም ዝርዝር የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው አውጥተዋል። ነፃ የኮቪድ-19 ምርመራ ይሰጥባቸዋል ተብለው ከተጠቀሱትም መካከል ሚኒልክ ሆስፒታል፣ አቤት ሆስፒታል፣እንጦጦ ፋና የጤና ማዕከል፣ ህዳሴ የጤና ማዕከል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ የካቲት 12 ሆስፒታል፣የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ይገኙበታል። ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የጤና ማዕከላት የነፃ ምርመራን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም። በአዲስ አበባ በሚገኙ የጤና ማዕከላት ውስጥ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ለማድረግ 1 ሺህ 250 ብር ክፍያ የሚጠየቅ ሲሆን፤ አንዳንድ የጤና ተቋማትም 1 ሺህ 500 ብር ያስከፍላሉ። አገሪቷ ከዚህ ቀደም የኮሮናቫይረስ ምልክት የሚያሳዩና፣ከህመምተኞች ጋር ንክኪ ያላቸውን ብቻ ነበር በነፃ የምትመረምረው። በአሁኑ ወቅት አገሪቷ አስገዳጅ አድርጋው የነበረው የጭምብል ማጥለቅ መመሪያ ላላ ብሏል። የአፍሪካ በሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል፣ ሲዲሲ ባወጣው መረጃ መሰረት በአፍሪካ ከፍተኛ የህሙማን ቁጥር ከተመዘገባቸው አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ነው። ኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ወደ 1.7 ሚሊዮን የላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን፣ 114 ሺህ 834 ህሙማንንም መዝግባለች። ከነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 769 ዜጎቿንም በኮሮናቫይረስ እንዳጣች የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ በዛሬው ዕለት እንደተናገሩት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ሜዲካል ኮሌጅ ሲኒየር አንስቴቲስት የሆኑት አቶ ገብረሥላሴ አባዲ በኮቪድ-19 መሞታቸውንም ገልፀዋል። https://www.bbc.com/amharic/55260304 +health ኬንያ ያልተከተቡ ሰዎች መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ ልታግድ ነው "ኬንያውያን የኮቪድ-19 ክትባት ካልወሰዱ ከታኅሣሥ 21 ጀምሮ የሕዝብ ማመላለሻን ጨምሮ የመንግሥት አ���ልግሎቶችን አያገኙም ሲሉ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ሙታሂ ካግዌ ተናግሩ። እገዳው አውቶቡሶችን፣ ታክሲዎችን፣ ባቡሮችን እና የአገር ውስጥ በረራዎችን እንደሚያጠቃልል ገልጸዋል። በተጨማሪም እገዳው የሆስፒታል እና የእስር ቤት ጉብኝትን ጨምሮ በትምህርት፣ በኢሚግሬሽን እና በግብር ቢሮዎች ተፈጻሚ ይሆናል ብለዋል። እስካሁን ከአገሪቱ ሕዝብ ከ10 ከመቶ ያነሱ ኬንያውያን ብቻ ናቸው የወረርሽኙን መከላከያ የተከተቡት። ኦፊሴላዊው መረጃ እንደሚያሳየው ኬንያ ከተቀበለችው 10.7 ሚሊዮን ክትባት ውስጥ 6.4 ሚሊዮኑን ብቻ ነው የከተበችው። ሆኖም በአገሪቱ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንጻራዊነት ዝቅተኛ ነው። ሮይተርስ የዜና ወኪል ባጠናቀረው መረጃ መሠረት በየቀኑ በአማካይ 59 አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ። የካግዌ መግለጫ በቅርቡ ከሚከበሩት የአዲስ ዓመት እና የገና በዓላት በፊት የክትባት ዘመቻውን ለማጠናከር ያለመ ይመስላል። በበዓላት ሰሞን ጉዞ እና ማኅበራዊ ግንኙነት ስለሚጨምር ሰዎች በበሽታው የመጠቃት ዕድላቸው ይጨምራል። መንግሥት በታኅሣሥ ወር መጨረሻ ለ10 ሚሊዮን ሰዎች ክትባት ለመስጠት አቅዷል። ይህም ከጠቅላላው ሕዝብ 20 በመቶውን ብቻ ስለሚይዝ አብዛኛው ሕዝብ የመንግሥት አገልግሎቶች ላያገኝ ይችላል። እገዳዎቹ ሁሌም በጥብቅ ተፈጻሚ ላይሆኑ ይችላሉም ሲሉ ካግዌ ጠቅሰዋል። ካግዌ ""ኬንያውያን እስከ ታኅሣሥ 21 ድረስ ክትባቱን እንዲወስዱ ጊዜ ሰጥተናል። እነዚህን እርምጃዎች እስከምንተገብር ድረስ ያለው ተጠያቂነት የግለሰቦች ነው"" ማለታቸውን ጠቅሶ የኬንያው ስታንዳርድ ጋዜጣ ዘግቧል። ከማክሰኞ ጀምሮ ከ15 ዓመት በላይ የሆናቸው ሰዎች የፋይዘር ክትባት ሊያገኙ ይችላሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-59108453 +health ኮሮናቫይረስ፡ ሳኡዲ አረቢያ የኡምራ ጉⶋን በመስከረም ወር መጨረሻ ልትጀምር ነው "በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለሰባት ወራት ያህል ተቋርጦ የነበረው የኡምራ ሃይማኖታዊ ጉዞ በዚህ ወር እንደሚጀመር ሳዑዲ አረቢያ አስታወቀች። ከመስከረም 24፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮም ስድስት ሺህ የሳዑዲ ዜጎች በየቀኑ የኡምራ ጉዞ እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸዋል። ከሌላ አገር የሚመጡ የኡምራ ፀሎተኞችም ከጥቅምት 22፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ መምጣት ይችላሉ ተብሏል። የየቀኑም ተጓዦች ቁጥር ወደ 20 ሺህ ያድጋል እንደሚያድገም ሳዑዲ አስታውቃለች። ከእስልምና እምነት መሰረቶች አንዱ የሆነው የኡምራ ጉዞ በየትኛውም ወቅት ማከናወን ቢቻልም የሃጂ ጉዞ ግን የእስልምና እምነት ተከታዮች በህይወት ዘመናቸው አንዱ ሊያደርጉት የሚገባ የተቀደሰ ተግባር ነው። በመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የሃጅ ጉዞ በዘንድሮው እክል ገጥሞታል። ከዚህ ቀደም ከሁለት ሚሊዮን በላይ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከየአገሩ ተሰባስበው ቢመጡም በዚህ አመት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሳዑዲ አረቢያ የፈቀደችው ጥቂት ሺዎች እንዲታደሙ ነው። ከሃጅ ጉዞ በተለየ መልኩ በየዓመቱ የትኛውም ጊዜ ላይ መደረግ ለሚችለው ለኡምራ ጉዞ ቢያንስ በዓመት ስምንት ሚሊዮን የሚሆኑ ወደ መካ ያቀኑ ነበር። በየቀኑ 20 ሺህ ተጓዦችን ለመቀበል ያቀደችው ሳዑዲ አረቢያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል የሚለው በይፋ እስኪነገር የምትቀበለው ተጓዦች ቁጥር ተወስኖ እንደሚቆይም የሳኡዲ ዜና ወኪል የአገር ውስጥ ሚኒስትሩን ዋቢ አድርገው ዘግበዋል። ""ከሌላ አገራት የሚመጡ የኡምራ ፀሎተኞችና ተጓዦችን የምንቀበለው ቀስ በቀስ ሲሆን፤ ከወረርሽኙ ነፃ የሆኑ አገሮችንም ቅድሚያ እንሰጣለን"" ማለታቸውም ተዘግቧል። ተጓዦች የኮሮናቫይረስ ወርርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎ��� እንደ የፊት ጭምብል፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅን ፅዳትን መጠበቅ እንደሚኖርባቸውም የዜና ወኪሉ አስነብቧል። በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ እስካሁን ባለው 330 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 4 ሺህ 452 ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54276747 +business በኢንተርኔት አማካኝነት እጽ ይሸጡ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተያዙ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ፖሊስ በጥምረት ባካሄዱት ኦፐሬሽን ማንነታቸውን በመደበቅ በኢንተርኔት አማካኝነት አደንዛዥ እጽ ሲሸጡ የነበሩ 179 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው ተገለጸ። ከግለሰቦቹ በተጨማሪ ፖሊስ ከ6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ግምት ያለው ጥሬ ገንዘብ እና ዲጂታል ገንዘብ የያዘ ሲሆን እጽ እና የጦር መሳሪያ ከግለሰቦቹ ጋር መያዙም ተነግሯል። እነዚህ ሰዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከበርካታ የአውሮፓ አገራት እና አሜሪካ ሲሆን የተደራጁ ወንጀሎች ተከላካይ ኃይል ዩሮፖል፤ “ማንነትን በመደበቅ የሚደረገው ሕገ-ወጥ ግብይነት ጊዜው አብቅቷል” ሲል መግለጫ አውጥቷል። የዩሮፖል የኢንተርኔት ወንጀል ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ኤድቫራዳስ ሲሌሪስ “ድብቁ ኢንተርኔት ከአሁን በኋላ ሚስጥር አይሆንብንም” ብለዋል። “ዲስራፕትቶር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ኦፕሬሽንን የአሜሪካው የፍትሕ ቢሮ እና ዩሮፖል በቅንጅት ያስፈጸሙት ሲሆን በኦፕሬሽኑ እንደ ፌንታኒ፣ ሄሮይን፣ ኮኬን እና ኤክስቴሲ የተሰኙ እጾች ተይዘዋል። በቁጥጥር ሥር ከዋሉት 179 ሰዎች መካከል 119 በአሜሪካ፣ 2 በካናዳ፣ 42 በጀርመን፣ 8 በኔዘርላንድ፣ 4 በዩኬ፣ 3 በኦስትሪያ እና 1 ግለሰብ ደግሞ ስዊድን ውስጥ መያዛቸው ተገልጿል። ሰዎች ማንነታቸው እና መገኛቸው ሳይታወቅ ልዩ መተግበሪያዎችን በመጠቀም “ዳርክ ዌብ” ተብሎ በሚጠራው የኢንተርኔት ክፍል ላይ በርካታ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ያከናወናሉ። “በዳርክ ዌብ” ላይ ሰዎች ማንነታቸውን መደበቅ ስለሚችሉ እንደ ኩላሊት ካሉ የሰው ልጆች አካላት እስከ አደንዛዥ እጽ መገበያየት ይቻላል ይላሉ የኢንፎሜሽን መረብ ደህንነት ባለሙያዎች። ፖሊስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሰል ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር እያዋለ ይገኛል። ኤድቫራዳስ ሲሌሪስ ሕግ አስከባሪ አካላት በቅንጅት መስራት ከቻሉ ወንጀለኞችን መቆጣጠር የማይቻልበት ምክንያት የለም ብለዋል። እነዚህ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም “የዳርክ ዌብ ወርቃማ ዓመታት” እያለፉ መምጣታቸውን ያሳያል ተብሏል። https://www.bbc.com/amharic/news-54261909 +sports እግር ኳስ ፡ የልምምድ ቦታ ክስተቶች ማፈትለካቸው አሰልጣኝ ማይክል አርቴታን አስቆጣ "የአርሰናሉ አሰልጣኝ ማይክል አርቴታ በዳኒ ሴባዮስ እና በዴቪድ ሉዊዝ መካከል የተፈጠረውን ችግር ይፋ ያደረጉ አካላት የእጃቸውን ያገኛሉ ሲሉ ገለጹ። በልምምድ ወቅት ሴባዮስ አደገኛ አጨዋወት መምረጡን ተከትሎ ሁለቱ ተጫዋቾች ተጋጭተው ሉዊዝ በሰነዘረው ቡጢ የቡድን አጋሩ መድማቱን ሪፖርቶች ገልጸዋል፡፡ አርቴታ ድርጊቱን ""ምንም አይደለም"" ሲሉ የገለጹ ሲሆን ከዚያ ይልቅ ጉዳዩ ይፋ መሆኑ ይበልጥ እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል፡፡ ""እኔ ክስተቱ መውጣቱን በጭራሽ አልወደድኩትም"" ብለዋል፡፡ ስፔናዊው አሰልጣኝ አክለውም ""ከየት እንደመጣ ማወቅ እፈልጋለሁ። እንደዚያ ከሆነ ደግሞ ከሌላው የምጠብቀውን ግላዊ እና ሚስጥራዊ ነገሮችን መያዝን ሙሉ በሙሉ የሚፃረር ስለሆነ መዘዞች ይኖራሉ"" ብለዋል፡፡ ክስተቱን እንዲያብራሩ የተጠየቁት አርቴታ ፣ ""ልምምዶች በጣም ፉክክር ያለባቸው ናቸው። እነዚህ ጉዳዮች ብዙ ጊዜ የሚከሰቱ ናቸው። ሲከሰቱም በቡድኑ ወዲያውኑ መፍትሄ ያገኛሉ። ስለዚህ ብዙም የምለው ነገር የለም"" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ""በጭራሽ ምንም ችግር የለም "" ሲሉም አክለዋል፡፡ ከሪያል ማድሪድ በውሰት ለአርሴናል በመጫወት ላይ ሚገኘው የስፔኑ አማካይ ሴባዮስ መረጃው ሐሙስ ይፋ ከሆነ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያው ዘገባውን ውድቅ አድርጎታል፡፡ የ 24 አመቱ ተጫዋች ከመድፈኞቹ ተጫዋቾች ጋር በአደባባይ አለመግባባት ሲፈጠር የመጀመሪያው አይደለም፡፡ አርሰናል ፉልሃምን 3-0 ባሸነፈበት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ተቀይረው ለመግባት ሲያሟሙቁ ከኤዲ ንኬቲያ ጋር መጋጨታቸው ይታወሳል፡፡ የ 33 ዓመቱ ብራዚላዊው ሉዊዝ በ2019 ነበር ቼልሲን ለቅቆ አርሰናልን የተቀላቀለው፡፡" https://www.bbc.com/amharic/55026782 +sports በመጪው ጥቅምት ስታዲየሞች ለተመልካቾች ክፍት ሊደረጉ ይችላል ተባለ "የፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ጨዋታዎችንና ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮችን ለመመልከት ከመጪው ጥቅምት ጀምሮ ወደ ስታዲየም መግባት ሊፈቀድላቸው እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ተናገሩ። ከሦስት ወር በኋላ ስታዲየሞችን ለተመልካች ክፍት ለማድረግ በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ሙከራዎች ማድረግ የሚጀመር ሲሆን ነገር ግን የትኛውም ስታዲየም የሚከፈተው የኮሮናቫይረስ መከላከያ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ከቻሉ ብቻ ነው። እግር ኳስን ጨምሮ አንዳንድ የስፖርት ውድድሮች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ለወራት ከተቋረጡ በኋላ በዝግ ስታዲየሞች መካሄድ ጀምረዋል። ""የስፖርት ውድድሮች የሚካሄዱባቸውን ስታዲየሞችን በመሰሳሉ በርካታ ሕዝብ የሚታደምባቸው ስፍራዎችን ለመክፈት የሚያስችል ሙከራዎችን እናደርጋለን"" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆንሰን ዛሬ ተናግረዋል። ከጥቅምት ወር ጀምሮም ስታዲየሞች ውስጥ ተመልካቾች እንዲገቡ ለማድረግ ወረርሽኙ የማይተላለፍባቸው ሁኔታዎችን ለማረጋገጥ አሁን የሚደረገው ፍተሻ የተሳካ መሆን እንዳለበት አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም ""ይህ ለውጥ ሲደረግ ከኮሮናቫይረስ ነጻ በሆነና በአስተማማኝ ሁኔታ መሆን ያለበት ሲሆን ለዚህም ነሐሴ ላይ የሚደረገው ሙከራ ውጤታማ መሆን ይኖርበታል"" ብለዋል። ከመጋቢት በኋላ ተቋርጠው የነበሩት የአገር ውስጥ የውድድር ስፖርቶች በሰኔ ወር የተጀመሩ ሲሆን፤ የፕሪሚየር ሊግና የእንግሊዝ እግር ኳስ ሊግ ጨዋታዎች በሰኔ ወር አጋማሽ ላይ በተከታታይ ተጀምረዋል። ዓለም አቀፍ የክሪኬት፣ የጎልፍ፣ የፈረስ ግልቢያ ውድድሮችና ሌሎችም በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ መካሄድ ጀምረዋል። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ በኋላ በአምስት ወራት ውስጥ 45 ሺህ ሰዎች ከበሽታው ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ292 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በበሽታው መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53447238 +health ኮሮናቫይረስ፡ ድሃ ሃገራት ክትባት እያለቀባቸው ነው- የዓለም ጤና ድርጅት "በዓለም አቀፍ የክትባት የመጋራት መርሃግብር አማካይነት የኮቪድ -19 ክትባቶችን የሚያገኙ ብዙ ድሃ ሃገሮች ለመከተብ የሚያስችል በቂ መጠን የላቸውም ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ አማካሪው ዶ/ር ብሩስ አይልወርድ በኮቫክስ መርሃ ግብር 90 ሚሊዮን ዶዝ ክትባት ለ 131 ሃገራት መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ይህ ግን በዓለም ዙሪያ እየተዛመተ ከሚገኘው ቫይረስ ህዝቦችን ለመከላከል በቂ አለመሆኑን አስታውቀዋል። እጥረቶቹ የተከሰቱት በአንዳንድ የአፍሪካ ሃገሮች ሦስተኛ ዙር ማዕበል መከሰቱን ተከትሎ ነው፡፡ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሃገራቸውን እየጨመረ የመጣውን ቫይረስ ለመከላከል እየሠራች ባለችበት ወቅት ሃብታም ሃገራት ክትባት ማከማቸታቸውን እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በአህጉር ደረጃ አፍሪ�� ውስጥ 40 ሚሊዮን ዶዞች (መጠን) ብቻ መሰጠቱ ከአጠቃላዩ ህዝብ ከ2 በመቶ በታች እንዲደርሰው ምክንያት መሆኑን ራማፎሳ ገልጸዋል፡፡ ይህንን ለመቅረፍ በደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ ክትባቶችን ለማምረት የሚያስችል ማዕከል ለመክፈት መንግስታቸው ከኮቫክስ ጋር እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኮቫክስ ባለፈው ዓመት የኮቪድ-19 ክትባት በዓለም ዙሪያ እንዲቀርብ ለማድረግ የበለጸጉ አገራት ለድሃ አገራት ወጪዎችን ድጎማ በማድረግ የተቋቋመ ነው፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚመራው ኮቫክስ እአአ በ 2021 መጨረሻ በዓለም ዙሪያ ሁለት ቢሊዮን ክትባቶችን ለማቅረብ ግብ አንግቦ ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ለድሃ አገራት በመስጠት ቢያንስ 20 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ ለመከላከል የሚረዳ በቂ ክትባቶችን ለማሰራጨት ተስፋ አቅዶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የክትባቶቹ ስርጭት በምርት መዘግየት እና በአቅርቦት መቆራረጥ ተስተጓጉሏል። በዚህም በኮቫክስ ላይ ሙሉ በሙሉ ተስፋ ባደረጉ ሀገሮች እጥረት አስከትሏል፡፡ በቅርቡ ክትባቶች እንዳለቀባቸው ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት መካከል ኡጋንዳ፣ ዚምባብዌ፣ ባንግላዲሽ እና ትሪኒዳድ እና ቶባጎ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ሰኞ በጄኔቫ የዓለም ጤና ድርጅት መግለጫ ላይ ዶ/ር አይልወርድ መጠነ ሰፊ እጥረቶች መኖራቸውን አምነዋል፡፡ በኮቫክስ ከተሳተፉት 80 ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ውስጥ ""ቢያንስ ግማሾቹ ፕሮግራማቸውን ለማስቀጠል የሚያስችል በቂ ክትባት የላቸውም"" ብለዋል ዶ/ር አይልወርድ፡፡ ""በየቀኑ ከሃገራት የምንሰማውን ከተመለከትን ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሃገሮች እጥረት አለባቸው። ተጨማሪ ክትባት ለማግኘትም ጥሪ እያቀረቡ ነው፡፡ እውነታው ግን ምናልባትም ከዚህ የበለጠ ሊሆን ይችላል፡፡"" . አንዳንድ አገራት እጥረቶችን ለመቋቋም አማራጭ መንገዶችን እንደሞከሩ ገልጸው ለክትባቶች ከገበያ ዋጋ በላይ መክፈላቸውን በምሳሌነት አንስተዋል፡፡ የክትባት አቅርቦቶች ጫና ውስጥ በመግባታቸው ትርፍ ክትባት ያላቸው አንዳንድ ሃብታም ሀገሮች በኮቫክስ እና በሌሎችም መንገዶች ልገሳን ለማሳደግ ጥረቶችን እያደረጉ ናቸው፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ሰኞ ዕለት 55 ሚሊዮን ክትባቶችን ለተቸገሩ ሃገሮች ለመስጠት እንዴት እንዳቀደ አስታወቋል፡፡ 41 ሚሊዮን የሚሆኑትን በኮቫክስ በኩል ሲያሰራጭ 14 ሚሊዮኑ ደግሞ ቅድሚያ ያስፈልጋቸው ተብለው ለሚታመኑ ሃገራት ይከፋፈላል፡፡ እነዚህ ክትባቶች አሜሪካ በኮቫክስ በኩል 500 ሚሊዮን ዶዝ ለመለገስ ያቀደችው ውስጥ አይካተቱም፡፡ ፕሬዝዳንት ባይደን ይህን ቃል የገቡት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በቡድን ሰባት ስብሰባ ላይ ነው፡፡ በስብሰባው የቡድን ሰባት ሃገራት በዚህ የፈረንጆች ዓመት አንድ ቢሊዮን ክትባቶችን ለድሃ አገራት ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡ ህልም የሌለው፣ በጣም ቀርፋፋ እና ምዕራባዊያኑ መሪዎች የምዕተ ዓመቱን የከፋ የህብረተሰብ ጤና ቀውስ ለመቋቋም ቁርጠኛ አይደሉም ሲሉ ተሟጋቾች ዕቅዱን ተችተዋል። አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች በዓለም ዙሪያ ወረርሽኙን ለማስቆም በቂ ሰዎች እስኪከተቡ ወራትን ሊጠይቅ ይችላል ብለው ያምናሉ፡፡ የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ሰኞ ዕለት ስለ ዓለም አቀፍ ክትባት ፍላጎት ተጠይቀው ""ከዓለም ጋር የምንጋራው ብዙ ክትባት አለን። ትልቁ ተግዳሮት ሆኖ ያገኘነው አቅርቦቱ ሳይሆን የሎጂስቲክስ ፈተናው ነው"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57563812 +politics የኡጋንዳ ምርጫ 2021፡ ዩዌሪ ሙሴቪኒና ቦቢ ዋይን ለፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተፋጠዋል "በኡጋንዳ አነጋጋሪ በሆነው ምርጫ የ38 ዓመቱ ኡጋንዳዊው የሙዚቃ ኮከብ ቦቢ ዋ���ን በአፍሪካ ካስተዳደሩ መሪዎች አንዱ የሆኑትን ዩዌሪ ሙሴቬኒ እየተገዳደራቸው ነው። ሮበርት ክያጉላይ በመድረክ ስሙ ደግሞ ቦቢ ዋይን በመባል የሚታወቀው የሙዚቃ ኮከብ የአገሪቷን ወጣት ትውልድ እንደወከለ የተናገረ ሲሆን፤ የ76 ዓመቱ ዩዌሪ ሙሴቪኒ በበኩላቸው ለአገሪቷ መረጋጋት መቆማቸውን ተናግረዋል። በምርጫ ቅሰቀሳ ዘመቻ ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ የነበረ ሲሆን በርካታ ሰዎችም ተገድለዋል። መንግሥት ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲዘጉ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፕሬዚደንት ሙሴቪኒ ይህ የሆነው ፌስቡክ የፓርቲያቸውን በርካታ ደጋፊዎች ገጽ በማገዱ ነው ብለዋል። የኡጋንዳ ፖሊስ በምርጫው ዕለት በዋና መዲናዋ ካምፓላ የሕንጻ ጣሪያዎች ላይ ፖሊስ እንደሚያሰማራ ገልጿል። ሆኖም መሳሪያ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች ግን በጎዳናዎች ላይ ቁጥጥር ማድረጋቸውን ጀምረዋል። ምርጫው አንድ ሰዓት ላይ የተከፈተ ሲሆን የምርጫው ውጤት ከቅዳሜ በፊት ይወጣል ተብሎ አይጠበቅም። ፕሬዚደንት ሙሴቪኒ 35 ዓመታትን በሥልጣን ካሳለፉ በኋላ ለስድስተኛ ጊዜ ለመመረጥ ይወዳደራሉ። በዋና መዲናዋ ካምፓላ እና በሌሎች በርካታ አካባቢዎች ዘመቻዎችን ማካሄድ ተከልክሏል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይህ የተደረገው ዘመቻ ማካሄድ በተከለከለባቸው ቦታዎች በርካታ ደጋፊዎች ስላላቸው እንደሆነ ተናግረዋል። መንግሥት ግን ምክንያቱን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመከላከል ነው ብሏል። ቦቢ ዋይንን ጨምሮ የተቃዋሚ ተወዳዳሪዎች፣ ደጋፊዎችና የዘመቻ ባልደረቦቻቸው በተለያዩ ጊዜያት ታስረዋል። ፖሊስ በገበያ ማዕከላትና ሌሎች ትላልቅ ሕንፃዎች ላይ ኃይሉን ለማሰማራት ያሰበው ባለፈው ሕዳር ወር የተቃዋሚ ፓርቲ አንቂዎች ከሕንጻ ጣሪያዎች ላይ ተቃውሞ መጥራታቸውን ተከትሎ ነው። በዚህ ወቅትም ቦቢ ዋይን ከታሰረ በኋላም ከ50 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። የምርጫ ታዛቢዎች የምርጫ ታዛቢዎች ከአሜሪካ ሳይሆን ከአፍሪካ መሆናቸው ተገልጿል። አሜሪካ ረቡዕ ዕለት አብዛኛው ምርጫውን ለመታዘብ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ታዛቢዎቿን ማስወጣቷን ገልጻለች። በኡጋንዳ የአሜሪካ አምባሳደር ናታሌ ብራውን በመግለጫቸው ""ያለ ታዛቢ ፕሬዚደንታዊውም ሆነ የፓርላማ ምርጫው ተጠያቂነት ፣ ግልፅነትና አመኔታ አይኖረውም"" ብለዋል። አምባሳደሯ በርካታ ኡጋንዳዊያንም ምርጫውን ለመታዘብ ፈቃድ እንዳላገኙ አክለዋል። የአውሮፓ ሕብረት የምርጫ ባለሙያዎችን ለመላክ ያቀረበው ሃሳብም ተቀባይነት አላገኘም። በምላሹ የፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ቃል ቃባይ ዶን ዋንያማ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ከአፍሪካ ሕብረትና ከምስራቅ አፍሪካ ማሕበረሰብ ታዛቢዎች እንዳሉ ገልጸዋል። አክለውም ""ኡጋንዳ ለመጨረሻ ጊዜ የምርጫ ታዛቢዎችን ወደ አሜሪካ መቼ እንደላከች አላስታውስም"" ብለዋል። የአገሪቷ መንግሥት ቀደም ብሎ ምርጫው ነጻና ፍትሐዊ እንደሚሆን ተናግሮ ነበር። በሌላ በኩል ቦቢ ዋይን መራጮች ሐሙስ ዕለት በምርጫ ጣቢያዎቹ እንዲቆዩና የምርጫ ማጭበርበርን ለመከላከል በስልኮቻቸው ካሜራ እያንዳንዱን ሂደት እንዲቀርጹ ጥሪ አቅርቧል። የአገሪቷ የቴሌኮም ድርጅቶች የኡጋንዳ ኮሚዩኒኬሽን ኮሚሽን ትዕዛዝን ተከትሎ ሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ ዎችንና የጽሁፍ መልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎችን መዝጋቱን ለደንበኞቹ ያስታወቀው ረቡዕ ዕለት ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-55657979 +politics በስዊድን የመጀመርያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር በተመረጡ በሰዓታት ውስጥ ሥልጣን ለቀቁ በስዊድን ታሪክ የመጀመርያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን ለቀቁ፡፡ ማግዳሊና አንደርሰን ሥልጣን የለቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በተሾሙ በሰዓታት ውስጥ ነው፡፡ ትናንትና ረቡዕ መሪ ሆነው መመረጣቸው ይፋ ከሆነ ከሰዓት በኋላ ነው አንደርሰን የለቀቁት፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከርሳቸው ፓርቲ ጋር ጥምረት የፈጠረው የፖለቲካ ድርጅት ከጥምረቱ በመልቀቁና የሳቸው ፓርቲ ሶሻል ዲሞክራት ያቀረበው የበጀት ጥያቄ በምክር ቤቱ ሊያልፍ ባለመቻሉ ነው፡፡ ከዚያ ይልቅ ምክር ቤቱ፣ የቀኝ አክራሪ ጸረ- ስደተኛ አቋም ያለው ፓርቲ ያቀረበው በጀት ላይ ድምጽ ሰጥቷል፡፡ ‹‹በዚህ ጊዜ ለአፈጉባኤው ሥልጣን ብለቅ እመኛለሁ ብዬ ነገርኩት›› ብለዋል አንደርሰን ለጋዜጠኞች፡፡ ከርሳቸው ፓርቲ ጋር ጥምረት የፈጠረው ግሪንስ ፓርቲ ‹‹በቀኝ አክራሪዎች የቀረበን በጀት አልቀበልም ሲል ነበር ከጥምረቱ የለቀቀው፡፡ አንደርሰን በዚህ ሁኔታ ለመቀጠል እንደማይፈልጉና የገዛ ፓርቲያቸው በአብላጫ ድምጽ አግኝቶ መንግሥት ሲመሰርት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መመረጥ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ‹‹በሕገ መንግሥቱ አካሄድ የጥምር መንግሥት ከተመሠረተና አንድ ፓርቲ ከጥምረቱ ከወጣ መንግሥት ሥልጣን ይለቃል፤ በእንዲህ ሁኔታ ቅቡልነቱ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ መንግሥትን መምራት ደግሞ አልፈልግም›› ብለዋል አንደርሰን፡፡ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አንደርሰን ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የፓርቲ መሪዎችን እንደሚያነጋግሩ ይጠበቃል፡፡ አንደርሰን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ስዊድንን እንዲመሩ ድምጽ ያገኙት ትናንትና ነበር፡፡ በስዊድን ሕግ አብዛኛዎቹ የተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች በተቃውሞ ድምጽ ካልሰጡ ተመራጭ ጠቅላይ ሚኒስትር ያደርጋል፡፡ ሪክስዳግ የሚባለው የስዊድን ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 349 አባላት አሉት፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንደርሰንን የተቃወሙት 174ቱ ናቸው፡፡ ይሁንና 117ቱ ድምጽ ሰጥተዋቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር እንዴት ተመረጡ ሊያስብል ቢችልም 57ቱ ድምጽ ተአቅቦ ማድረጋቸው በስዊድን ሕገ መንግሥት ከምክር ቤት አባላት በድምሩ ብዙ ተወካይ ባይመርጣቸውም ስላልተቃወማቸው ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡ አንደርሰን በዚህ የተነሳ አንድ ተጨማሪ ድምጽ አግኝተው ነበር ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት፡፡ በስዊድን ሴቶች ድምጽ መስጠት ከጀመሩ ከመቶ ዓመታት በኋላ የ54 ዓመት ሴት አንደርሰን ሶሻል ዲሞክራትን በመምራት ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ሲበሰር የምክር ቤቱ አባላት ቆመው ነበር ያጨበጨቡላቸው፡፡ በዩኒቨርስቲ ሲቲ ኡፕሳላ የአዳጊዎች የውሃ ዋና ሻምፒዮን የነበሩት አንደርሰን ፖለቲካ ውስጥ የገቡት በ1996 የጠቅላይ ሚኒስትር ጎራን ፐርሰን አማካሪ በመሆን ነበር፡፡ ላለፉት ሰባት ዓመታት ደግሞ በገንዘብ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡ ማግደሊና አንደርሰን በሕዝብ እንደራሴዎች ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ድምጽ ከማግኘታቸው በፊት ስዊድን ከኖርዲክ አገሮች ሁሉ ብቸኛዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ኖሯት የማያውቅ አገር ሆና ቆይታለች፡፡ ስዊድን የጾታ እኩልነት ከፍ ባለ ደረጃ የምታከብር ብልጹግ አገር ናት፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-59406243 +health ኮሮናቫይረስ፡ በድሬዳዋ ከሃያ በላይ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኮቪድ-19 ተያዙ "በድሬዳዋ 21 የሕክምና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የከተማዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለቢቢሲ አረጋገጠ። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ስንታየሁ ደበሳ እንደተናገሩት በሕክምና ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው እተደረገ ያለውን ወረርሽኙን የመከላከል ሥራን ያዳክመዋል የሚል ስጋት አለ ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያ��ቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። ወይዘሮ ስንታየሁ ለጤና ባለሙያዎቹ በሽታውን ለመከላከል አስፈጊ የሆኑ አቅርቦቶችን በተመለከተም አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ ማቅቡንና ገልጸው ""እስካሁን ድረስ እጥረት የለብንም"" ብለዋል። ነገር ግን በሕክምና ተቋማቱ የሚኖሩ ንክኪዎች ባለሙያዎቹን ለቫይረሱ ማጋለጡን የሚናገሩት አስተባባሪዋ፤ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገ ውይይት ለቫይረሱ የተጋለጡት በየትኛው ጊዜ እንደሆነ ለማለየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። በህክምና ተቋማቱ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ግን ይላሉ ባለሙያዋ ""በሕክምና ሥራ ላይ እያሉ ተጋላጭ መሆናቸውን ነው"" በማለት ባለሙያዎቹ እየወሰዱ ያሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""የጤና ባለሙያዎቻችን በቫይረሱ እየተያዙ መምጣት ወረርሽኙን ለመከላከል የምናደርገውን ጥረት ያዳክማል"" ሲሉም በአስተዳደሩ በኩል ያለውን ስጋት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በቫይረሱ ከተያዙት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል በድንገተኛ እና በጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚሰሩ ነርሶችና ዶክተሮች እንደሚገኙበት በመጥቀስ፤ በዚህ ክፍል የሚሰሩት ባለሙያዎች በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት ተጋላጭ መሆናቸውን አብራርተዋል። በድሬዳዋ እስካሁን ድረስ ስምንት ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ናሙናዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሲደረገላቸው፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ ከ500 በላይ ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸውንና 17 ሰዎች ደግሞ በዚሁ ምክንያት መሞታቸው ታውቋል። በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ400 በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ማገገማቸውን የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ስንታየሁ ደበሳ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በተያያዘ ዜና በምሥራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ 66 ታራሚዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን የዞኑ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ተካ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጊኒር ከተማ እና በወረዳው በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ በተደረገው የኮቪድ-19 ምርመራ እነዚህ ታራሚዎች ኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ኃላፊው ተናግረዋል። እነዚህ ቫይረሱ የተገኘባቸው ታራሚዎች ለህክምና ወደ ሮቤ ሆስፒታል መላካቸውንም ቢቢሲ ከኃላፊው መረዳት ችሏል። ኃላፊው በእነዚህ ፖሊስ ጣቢያዎች ታራሚዎች አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ በማያስችላቸው እና ያለ ምንም ጥንቃቄ መልኩ መታሰራቸው በሽታው እንዲስፋፋ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች የፀረ ተህዋሲ ርጭት ተደርጓል። በቀላል ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችም የዋስ መብታቸው ተጠብቆ እንዲወጡ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆኑንም ተናግረዋል። ታራሚዎቹን ለመጠየቅ የሚመጡ ቤተሰቦችም በሽታውን ወደ ኅብረተሰቡ ይዘው በመሄድ ስርጭቱ ይስፋፋል የሚል ስጋት ቢኖርም እስካሁን ድረስ ከተጠረጠሩት ሰዎች ላይ በተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ ምርመራ የተያዘ ሰው አለመገኘቱን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን 470 ሺህ የሚጠጋ ምርመራ ተደርጎ ወደ 21 ሺህ 452 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ከእነዚህም መካከል በወረርሽኙ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 380 ደርሷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53696685 +business ኤቨር ጊቭን፡ የሱዩዝ ቦይን ዘግታ ለቀናት የቆየችው መርከብ ከወራት በኋላ ወደ አገሯ ተመለሰች "በመጋቢት ወር የሱዩዝ ቦይን ዘግታ ለቀናት የቆየችው ኤቨር ጊቭን የዕቃ መጫኛ መርከብ ባለፍነው ሳምንት ያለምንም ችግር ዘግታው በቆየችው የሱዩዝ ቦይ በኩል ወደ አገሯ ተመለሰች። መርከቧ ከሜድትራኒያን ወደ ቀይ ባሕር ከሚጓዙ መርከቦች መካከል እንደነበረች እና በአውሮፓ ጭነቷን በማራገፍ አሁን በድጋሚ ወደ እስያ እያመራች መሆኗን የሱዩዝ ካናል ባለሥልጣን አስታውቋል። ኤቨር ጊቭን በቦዩ ውስጥ መንቀሳቀስ አቅቷት በቆየችባቸው ቀናት አንድ ሰው ለሞት የዳረገ ከፍተኛ ርብርብ ከተደረገ በኋላ ነበር ከቦዩ የተላቀቀችው። የግብፅ ባለሥልጣናት ቦዩ በመዘጋቱ የደረሰባቸው ካሳ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ ኤቨር ጊቭን ለተጨማሪ ሦስት ወራት በኢስማሊያ ቦይ አካባቢ ቆይታለች። መርከቧ ለሦስት ተጨማሪ ወራት በኢስማሊያ ቦይ እንድትቆይ የተደረገችው በግብፅ እና ኤቨር ጊቭን ባለቤቶች መካከል የካሳ ስምምነት እስከሚደረግ ነበር። የሱዩዝ ቦይ ባለሥልጣን በትዊተር ገጹ እንዳስታወቀው ኤቨር ጊቭን በሁለት ጀልባዎች እና በተቋሙ ከፍተኛ መሪዎች ታጅባ ቦዩን በማቋረጥ ወደ አገሯ ተመልሳለች። መርከቧ ትናንት አርብ ከሰሜን ወደ ደቡብ ከተጓዙት 26 መርከቦች መካከል አንዷ ስትሆን ሌሎች 36 መርከቦች በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዙ ነበር። የስዊዝ ካናል ባለሥልጣንም ""ምሥራቁን ከምዕራብ ጋር የሚያገናኘው በጣም አጭር እና ፈጣን መንገድ"" በማለት መተላለፊያውን አሞግሰዋል። በዓለማችን ካሉ ግዙፍ የጭነት መርካቦች አንዷ የሆነችው ኤቨር ጊቭን 18,300 ኮንቴይነሮችን በሮተርዳም፣ በፊሊክስቶዌ እና በሀምቡርግ በማራገፍ አሁን ወደ ቻይና እየተጓዘች ትገኛለች። የካሳው መጠን ባይታወቅም በቦዩ ላይ ለደረሰው ጉዳት ብሎም መርከቡን ለማስለቀቅ ለተደረጉ ሥራዎች የግብፅ ባለሥልጣናት የጠየቁት 550 ሚሊዮን ዶላር በሂደት እንደተከፈለ ታውቋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58290762 +health በሙቀት ወቅት እንዴት ጥሩ እንቅልፍ መተኛት እንችላለን? ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን የዝናብ ወቅት ቢሆንም፣ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ሙቀቱ የሚበረታበት ጊዜ ነው። በተጨማሪም ምድራችን በገጠማት የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በየትኛውም ወቅት የሚያጋጥመው ሙቀት በእጅጉ ከፍ ብሏል። በዚህም ሳቢያ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ መዝነብ ትቷል። ሙቀትም እየበረታ ነው። ተመራማሪዎችም የዓለም ሙቀት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እንደሚጨምር ባለፈው ዓመት ተንብየዋል። ይህ ሙቀት የተያዘውን ዓመት ጨምሮ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት እንደሚበረታ ነው ተመራማሪዎቹ የተናገሩት። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት የአየር ንብረት ለውጥ ነው ይላሉ። ሙቀት ጨምሯል። አውሮፓ በሙቀት እየተለበለበች ነው። የሙቀት መጨመርን ተከትሎ የጤና ባለሥልጣናት ሕዝባቸውን እያስጠነቀቁ ነው። ኢትዮጵያም በአንዳንድ አካባቢዎች ከፍተኛ ሙቀትን እያስተናገደች ነው። ከሳምንታት በፊት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የሙቀት መጠን በመጨመሩ ነዋሪዎች የሰውነታቸውን ሙቀት ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ እንዲቆጣጠሩ አሳስቦ ነበር። ሙቀት ቀልድ አይደለም። እንዲህ ዓይነት ሙቀት ሲያጋጥም በርካቶች ከሚቸገሩበት አንዱ ሌሊቱን በጥሩ እንቅልፍ ማሳለፍ ነው። ከቀኑ ይልቅ ሌሊቱ ይረዝማል። እንቅልፍ ይታወካል። ይህ ብቻም ሳይሆን ለእንቅልፍ ጋደም ከማለትዎ በፊት የሰውነትዎን ሙቀት በንቃት ካልተከታተሉ ሰላም ብለው በተኙበት በዚያው ማሸለብን ሊያስከትል ይችላል። ለመሆኑ በሙቀት ወቅት እንዴት ጥሩ እንቅልፍ መተኛት እንችላለን? የተወሰኑ ዘዴዎችን እንጠቁማችሁ። የሙቀት የአየር ጠባይ ቀን ላይ ድካም እንዲሰማን ያደርጋል። ምክንያቱም የሰውነታችንን ሙቀት ለመቆጣጠር ብዙ ኃይል የምንጠቀመው ቀን ላይ ስለሆነ ነው። በመሆኑም ሌሊት ላይ ለመተኛት የሚቸገሩ ከሆነ ቀን ላይ ድካም ቢሰማዎትም ለአፍታም ቢሆን ባያሸልቡ ይመከራል። በሙቀት ወቅት እንቅልፍ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ውድ ነው። በመሆኑም እንቅልፍዎን ለሌሊት መቆጠብ ያስፈልጋል። የሙቀት የአየር ጠባይ የወትሮውን ልምዳችንን ሊለውጠው ይችላል። ግን አትለውጡት። ከቀየራችሁት እንቅልፋችሁን ሊረብሸው ይችላል። ወደ አልጋዎ ከመሄድዎ በፊት የሚያደርጓቸውን የተለመዱ ተግባራትዎን ያከናውኑ። የሚሰሩት ሥራም ካለ እንዲሁ። መኝታ ክፍልዎ ቀዝቃዛ መሆኑን ያረጋግጡ። ቀን ላይ የሞቀው አየር እንዳይገባ በቤትዎ በፀሐይ አቅጣጫ ያሉትን መስኮቶች መዝጋትዎን ያረጋግጡ። ከዚያም ወደ መኝታዎ ከመሄድዎ በፊት ነፋሻ አየር እንዲገባ ሁሉንም መስኮቶች ይክፈቷቸው። በቀዝቃዛ ወቅት የሚደራርቧቸውን አንሶላና ብርድ ልብሶች ይቀንሱ። ነገር ግን ስስ አንሶላ ማንጠፍዎን አይዘንጉ። ስስ እና ከጥጥ የተሰራ አንሶላ ላብን የመምጠጥ ኃይል አለው። ከጥጥ የተሰሩ አልባሳት ምንም እንኳን ሙቀት የሚሰጡ ቢሆንም ሌሊት ላይ የሰውነታችን ሙቀት ስለሚቀንስ ብዙም አያሳስብም። አንዳንዴ ብርድ ተሰምቶን ከእንቅልፋችን የምንነቃው በምሽት የሰውነታችን ሙቀት ስለሚቀንስ ነው። በሞቃታማ የአየር ጠባይ በተለይም ወበቅ በሚኖርበት ጊዜ ትንንሽ የቤት ማቀዝቀሻዎች (ፋን) መጠቀም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ላብ እንዲተን በማድረግ የሰውነት ውስጣዊ የሙቀት መጠንን ለመቆጣጠር ቀላል ያደርገዋል። ማቀዝቀዣ ግን ሁሉም ሰው ጋር ላይኖር ይችላል። ከሌለ በምትኩ የሙቅ ውሃ መያዣ ኮዳ ውስጥ ቀዝቀዛ ፈሳሽ በመሙላት ለመያዝ ይሞክሩ። ከዚህም ሌላ ካልሲዎን አቀዝቅዘው ያድርጉት። እግርዎን ማቀዝቀዝ የቆዳዎንና የሰውነትዎን አጠቃላይ የሙቀት መጠን ለመቀነስ ይረዳል። በሙቀት ወቅት ቀን ላይ በቂ ውሃ መጠጣት የሚመከር ሲሆን ወደ መኝታዎ ከመሄድዎ በፊት ግን ብዙ ውሃ መጠጣትን ያስወግዱ። ምን አልባት ሌሊት የውሃ ጥም እንዲቀሰቅስዎ ላይፈልጉ ይችላሉ። ነገር ግን ከመኝታዎ እየተነሱ ወደ መጸዳጃ ቤት መመላለስ  ደግሞ አይፈልጉም። በመሆኑም እንቅልፍዎ እንዳይረበሽ ይህንን ልማድ ያስወግዱ። እዚህ ላይ ግን ችላ ልንለው የማይገባው ጉዳይ የምንጠጣውን ነገር ነው። ለስላሳ መጠጦች አይጎንጩ። አብዛኞቹ ለስላሳ መጠጦች በውስጣቸው ኅብለ ሰረሰር የተባለውን የነርቭ ሥርዓታችንን የሚያነቃቃ 'ካፌን' የተባለ ንጥረ ነገር ስላላቸው ንቁ እንድንሆን ያደርጉናል። ብዙ የአልኮል መጠጦች መውሰድም አይመከርም። በርካታ ሰዎች የአየር ጠባዩ ሞቃታማ ሲሆን ብዙ የአልኮል መጠጦችን ይወስዳሉ። ምንም እንኳን የአልኮል መጠጦች ለመተኛት ሊረዱ ቢችሉም ቀድመን እንድንነቃና የማያረካ እንቅልፍ እንድንተኛ ያደርጉናል። ሙቀት ሰውነታችን ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው? የመጀመሪያው ድርቀት ወይም በሰውነት ውስጥ ያለ ፈሳሽ ማነስ እንዲፈጠር በማድረግ ነው። ይህ እንዳይሆን በሽንት፣ በላብና በትንፋሽ የሚወጣውን ፈሳሽ ለመተካት በቂ ውሃ መጠጣት ያስፈልጋል። ሌላኛው ተፅዕኖው ከመጠን በላይ የሆነ ሙቀት ማስከተል ነው። ይህ በተለይ የልብ ወይም የአተነፋፈስ ችግር ላለባቸው የተለየ ችግር ሊሆን ይችላል። ምልክቶቹ ራስ ምታት፣ የቆዳ መደንዘዝ እና ማቅለሽለሽ ናቸው። ከፍተኛ የሆነ ድካምም በሙቀት ወቅት የሚያጋጥመን ሌላኛው ችግር ነው። ይህ የሚከሰተው ሰውነታችን በቂ ውሃ ወይም ጨው ማጣት ሲጀምር ነው። ራስን የመሳት ስሜት፣ አቅም ማጣት ወይም የጡንቻ መሸማቀቅ የተወሰኑ ምልክቶቹ ናቸው። የሙቀት ስትሮክ (ሂት ስትሮክ) በሙቀት ወቅት ሰውነታችን የሚያጋጥመው እክል ነው። ሂት ስትሮክ አጋጥሟል የሚባለው የሰውነታችን ሙቀት 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ወይም ከዚያ በላይ ሲሆን ነው። ምልክቶቹ በሙቀት ሳቢያ ከሚከሰ�� ድካም ጋር ይመሳሰላሉ። ነገር ግን ይህ ያጋጠመው ሰው ራሱን ላያውቅ ይችላል፣ ደረቅ ቆዳ ይኖረዋል እና ላብ ከሰውነቱ መውጣትም ይቆማል። ለመተኛት እየታገሉ ከሆነ ይነሱና የሚያረጋጋዎትን ነገር ያድርጉ ። ለማንበብ፣ ለመጻፍ አሊያም ልብስዎን ለማጠፍ ይሞክሩ። ስልክዎን እያዩ አሊያም የቪዲዮ ጌሞችን እየተጫወቱ አለመሆኑን ግን ያረጋግጡ። ምክንያቱም በስልካችን የምናየው ብርሃን የእንቅልፍ ስሜት እንዲቀንስ ያደርጋል። ጨዋታውም ቢሆን ጭራሽኑ እንድንነቃቃ ነው የሚያደርገን። ከዚያም ሥራዎትን ጨርሰው እንቅልፍዎ ሲመጣ ወደ አልጋዎ ይመለሱ። ልጆች ብዙውን ጊዜ ጥሩ እንቅልፍ ይወስዳቸዋል፤ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በቤተሰብ ስሜትና በዕለተ ተዕለት ለውጦች ምክንያት ስሜታቸው ሊቀየር ይችላል። በመሆኑም የተለመደውን የመኝታና የመታጠቢያ ጊዜያቸውን አያሳልፉ። ሙቀት ነው ብለው ይዘዋቸው ለመውጣት አይሞክሩ። ወደ መኝታቸው ከመሄዳቸው በፊትም ለብ ባለ ውሃ ማጠብ ይመከራል። ውሃው ግን ቀዝቃዛ መሆን የለበትም። ምክንያቱም ሰውነት ራሱን የሚያሞቀው የደም ዝውውርን በመጨመር ስለሆነ ቀዝቃዛ ውሃ የደም ዝውውር እንዲጨምር ያደርጋል። ሕጻናት እየታጠቡበት ያለው ውሃ ቀዝቃዛ አሊያም ሙቅ መሆኑን አይነግሯችሁም። በመሆኑም የሙቀት መጠኑን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው። ሕጻናት ጥሩ እንቅልፍ የሚወስዳቸው የክፍላቸው የሙቀት መጠን ከ16 እስከ 20 ዲግሪ ሴልሺየስ ሲሆን በመሆኑ ከተቻለ ሕጻናት የሚተኙበት ቦታ የሙቀት መለኪያ (ቴርሞሜትር) መግጠም መልካም ነው። አብዛኞቻችን ሥራችንን በአግባቡ ለመስራት በእያንዳንዱ ምሽት ለሰባት ወይም ለስምንት ሰዓታት ጥሩ እንቅልፍ መተኛት እንፈልጋለን። ቢሆንም ግን ጥቂት ሰዓት ብቻ ነው የተኛሁት ብለው አይጨነቁ። በርካታ ሰዎች አንድ ሌሊት ሳይተኙ አሊያም የተረበሸ ሌሊት አሳልፈው ሥራቸውን በሚገባ ይከውናሉ። ምንም እንኳን ከወትሮው በተለየ ደጋግሞ ማዛጋት ቢኖርም ካልተደጋገመ ምንም አትሆኑምና አትጨነቁ። እነዚህ የጤና ምክሮች በሎውቦሮው ዩኒቨርሲቲ የክሊኒካል እንቅልፍ ምርምር ክፍል የቀድሞ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ኬቨን ሞርጋን እና የእንቅልፍ የምክር አገልግሎት ባልደረባ ሊዛ አርቲስ በሰጡት ገለጻ የተመሠረቱ ናቸው። ጽሑፉ ለመጀመሪያ የታተመው ሐምሌ 2019 ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2r4pxlk29o +health ስዊድናዊቷ ነርስ ደሴት ለብቻዋ ተለቆላት 60 ፊልሞችን ልትመለከት ነው "ስዊድናዊቷ ነርስ ደሴት ለብቻዋ ተለቆላት 60 ፊልሞችን ልትመለከት ነው፡፡ ነርሷ ይህን ዕድል ያሸነፈችው በስዊድኗ 2ኛ ከተማ በጎተቦሬ (ጉተንበርግ) የሚደረገውን የፊልም ፌስቲቫል በማሸነፏ ነው፡፡ ሊዛ ኤርኖት ይህንን ውድድር ያሸነፈችው ከ12ሺህ የፊልም አፍቃሪዎች መሀል ተወዳድራ ነው፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ይህን ዕድል ያመለከቱት ከስዊድን ብቻ ሳይሆን ከመላው ዓለም አመልክተው ነው፡፡ በፌስቲቫሉ የሚቀርቡት 60 ፊልሞች ናቸው፡፡ ነርሲቱ ፊልሞቹን የምትመለከተው ከስዊድን ጠረፍ በምትገኝ ደሴት ቁጭ ብላ ላይትሐውስ ውስጥ በመቀመጥ ነው፡፡ በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት ነርሷ በሆስፒታል ውስጥ የኮቪድ ታማሚዎችን ስትንከባከብ የነበረች ጀግኒት እንደነበረች ተነግሯል፡፡ ""አሁን ብቻዬን ከሰዎች ገለል ብዬ መዝናናት እፈልጋለሁ፡፡ የተለየ ሁኔታ ውስጥ መሆን ነው የምሻው"" ስትል ተናግራለች፡፡ የፌስቲቫሉ አሰናጆች ወትሮ ብዙ ሺህ ሕዝብ የሚገኝበትን ይህን የፊልም ትእይንት በወረርሽኙ ምክንያት ሊያካሄዱት አልቻሉም፡፡ በሲኒማ ቤቶች የሚታዩ ፊልሞችም አይኖሩም፡፡ ከዚያ ይልቅ ሁሉም የፊልም ፌስቲቫሉ ኩነቶች በቀጥታ በበይነ መረብ ይተላለፋሉ ብለዋል፡፡ የ��ህ ፌስቲቫል አሰናጆች ላለፉት ወራት አንድ እውነተኛ የፊልም ወዳጅ ሰው ሲያፈላልጉ ነበር፡፡ አሸናፊው ሰው ብቻውን አንድ ደሴት ላይ ቁጭ ብሎ 60 ፊልሞችን ለመመልከት በሥነ ልቡና እና በስሜት ዝግጁ የሆነ መሆን ይኖርበታል ብለው ነበር፡፡ ነርስ ሊዛ ኤንሮት የኮቪድ ታማሚዎችን በመንከባከብ ጉልበቷ እንደተሟጠጠና አሁን ግን ለአንድ ሳምንት እፎይ ማለት እንደምትሻ ለቢቢሲ የስቶክሆልም ዘጋቢያችን ማዲ ሳቪጅ ነግራታለች፡፡ ነርሲቱ ፓተር ኖስተር ላይትሐውስ ሐምነስካር በምትባል ደሴት የምትቆየው ያለምንም ቴክኖሎጂያዊ ቁሳቁሶች ነው፡፡ ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ መጻሕፍትንም ሆነ ሌላ ጊዜ ለማሳለፍያ የሚሆን ነገር መያዝ አይፈቀድላትም፡፡ ‹‹ንፋሱ፣ ባሕሩ እና በደሴት ብቻዬን መሆን ይህ ሁሉ እጅግ ልዩ ስሜት ውስጥ የሚከተኝ ነው የሚሆነው›› ብላለች ነርስ ሊዛ፡፡ ሊዛ በብዛት የኖረችው ስኮቭዴ በምትባል የጎተቦርግ ምሥራቅ የምትገኝ ትንሽዬ ከተማ ውስጥ ነው፡፡ በዚች ትንሽ ከተማ ውስጥ የአንድ የፊልም ወዳጆች ማኅበርም አባል ናት፡፡ ትናንት ቅዳሜ ሊዛ ወደ ደሴቲቱ በታንኳ የተወሰደች ሲሆን ይቺ ደሴት በስዊድን ጠረፍ ከማርስትራንድ ቅርብ የምትገኝ ናት፡፡ ሊዛ በደሴቲቱ የምታሳልፈው ጊዜ በቪዲዮ ለዓለም ይተላለፋል፡፡ የዚህ ታላቅ የፊልም ፌስቲቫል ዋና አሰናጅ ሚሪያ ዌስተርን ይህን ልዩ ዕድል ለአንዲት የኮቪድ ጀግና መስጠታችን የሚገባ ብቻም ሳይሆን ለኛም ትልቅ ደስታን ይፈጥርልናል ብለዋል፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-55876982 +health ኮሮናቫይረስ፡ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ያልተገኘባት የሰሜን አሜሪካ ክፍል በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንዳንድ የካናዳ አካባቢዎች እየጨመረ ቢሆንም አንዲት በሰሜናዊ በኩል የምትገኝ አካባቢ ግን ቫይረሱ በማህበረሰቡ ውስጥ እስካሁን አልገባም። ቦታዋም 'ኑናቩት' ትባላች። ባለፈው መጋቢት ወር በርካታ የዓለማችን አገራት ድንበራቸውን እየዘጉ በነበረበት ወቅት የኑናቩት ኃላፊዎችም ቢሆኑ የሚመጣውን አደጋ በማሰብ የጥንቃቄ እርምጃ ለመውሰድ ወስነው ነበር። በዚህም ከካናዳ የሚመጡ ሰዎችን በተመለከተ ጠበቅ ያለ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን ከነዋሪዎች በስተቀር ማንም ሰው ከካናዳ በኩል ወደ ኑናቩት መግባት አይችልም ነበር። ነዋሪዎችም ቢሆኑ ከሌላ ቦታ ሲመጡ ለሁለት ሳምንታት እራሳቸውን ለይተው መቀመጥ ግዴታቸው ሲሆን መንግሥት ባዘጋጃቸው ለይቶ ማቆያዎች አልያም እንደ ዊኒፔግ፣ የሎውናይፍ፣ ኦታዋ እና ኤድመንተን ባሉ ከተሞች ውስጥ በሚገኘኑ ሆቴሎች እንዲቆዩ ይደረጋሉ። የመንግሥት ጥበቃ ኃይሎችም ቢሆኑ በለይቶ ማቆያዎቹ እና ሆቴሎቹ አካባቢ ከፍተኛ ጥበቃ ያደርጋሉ። እስካሁንም 7 ሺ የሚሆኑ የኑናቩት ነዋሪዎች ወደቤታቸው ሲመለሱ በነዚህ ማዕከላት ሁለት ሳምንታትትን አሳልፈዋል። ነገር ግን ይህ ሁሉ ስራ አልጋ በአልጋ አልነበረም። አንዳንድ ሰዎች ሕጉን በመጣሳቸው ምክንያት ለተጨማሪ ቀናት በለይቶ ማቆያ ማዕከላቱ እንዲቆዩ ተደርገዋል። በማዕከላቱ ውስጥ የነበሩ ሰዎችም የምግብ ጥራት ችግር እንዳለ ገልጸዋል። ነገር ግን በመላው ካናዳ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲመጣና በጎረቤት አካባቢዎች ከፍተኛ የጥንቃቄ እርምጃዎች መወሰድ ሲጀምሩ ኑናቩት ግን እንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው አላገኘችም። በኑናቩት ወደ 36 ሺ የሚጠጉ ሰዎች የሚኖሩ ሲሆን 25 ማህበረሰቦች ሁለት ሚሊዮን ስኩዌር ኪሎሜትር የሚሸፍን ቦታ ላይ ተበታትነው ኑሯቸውን ይገፋሉ። በሰዎቹ ተፈጥሮአዊ የአኗኗር ዘይቤ ምክንያት አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በጣም ቀላል ነው። ነዋሪዎቹ ያን ያክል ስፋት ባለው ቦታ ላይ ሲኖሩ ከሰዎች ጋር የመገናኘት ዕድላቸው በጣም ዝቅተኛ ነው። መንግሥትም ቢሆን ነዋሪዎቹን በዓመት አንዴም ይሁን ሁለቴ የሚያገኛቸው በአውሮፕላን በመታገዝ ነው። በመስከረም ወር መጨረሻ አካባቢ ግን ማዕድን ማውጣት ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች ከኑናቩት 160 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ በኮሮረናቫይረስ መያዛቸው ተዘግቦ ነበር። ነገር ግን እነዚህ ሰራተⶉች ወደ ክልሉ ባለመግባታቸው አሁንም ነዋሪዎቹ ከኮሮረናቫይረስ ነጻ ናቸው ተብሏል። ነዋሪዎቹ ወደ ማዕድን አውጪዎቹ አልያም ማዕድን አውጪዎቹ ወደ ነዋሪዎቹ ምንም አይነት ጉዞ ባለማድረጋቸው ቫይረሱ ባለበት ሊቀር ችሏል። ነገር ግን በዚህ አካባቢ እንደ ፈተና የሚቆጠረው በተገቢው መልኩ የኮሮረናቫይረስ ምርመራ ማድረግ አለመቻሉ ነው። መመርመሪያ መሳሪያዎች በአውሮፕላን በመታገዝ ተበታትነው ወደሚኖሩት ማህበረሰቦች መድረስ አለበት። በሆነ አጋጣሚ የሆነ ሰው ቫይረሱ ቢገኝበት ከሌሎች ሰዎች ጋር ንክኪ ከማድረጉ በፊት መረጃውን ለማድረስ አልያም ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት በጣም ከባድ ያደርገዋል። በተጨማሪም የጤና አገልግሎት መስጫዎች በአካባቢው በበቂ ሁኔታ የሉም። 'ኪኪታኒ' በመባል የሚታወቀው ሆስፒታል ለጽኑ ህሙማን የሚሆኑ 35 አልጋዎች ያሉት ሲሆን በኮቪድ-19 የተያዙ 20 ታማሚዎችን ብቻ ነው ማስተናገድ የሚችለው። ምናልባት ወረርሽኙ በዚህ አካባቢ ቢከሰት ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ተገቢውን ክትትል ለማድረግና ለይቶ ማቆያዎችን ለማቋቋም አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ይህ በንዲህ እንዳለ በኑናቩት የሚኖሩት 'ኢኑይት' በመባል የሚታወቁት ቀደምት ማህበረሰቦች ለኮሮረናቫይረስ ተጋላጭ ከሚባሉት መካከል ናቸው። በቂ ያልሆኑና ደህንነታቸው ያልተጠበቁ ቤቶች፣ በአንድ ቦታ ላይ በርካታ ሰዎች ተሰብስበው መኖር እንዲሁም የቲቢ በሽታ ስርጭት ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። 80 በመቶ የሚሆነውን የኑናቩት ነዋሪ የሚሸፍኑት ኢኑይቶች ከሌሎች ነዋሪዎች አንጻር በቲቢ የመያዝ ዕድላቸው 300 በመቶ ከፍ ያለ ነው። ካናዳ በአጠቃላይ እንደ ሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ያሉ የጥንቃቄ እርምጃዎች በመውሰዷ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሞክራለች።ነገር ግን አሁንም ቢሆን ለመቆጣጠር አልቻለችም። እስካሁንም ድረስ 191 ሺ 732 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 9 ሺ 699 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። ነገር ግን እንደ ኪቤክና ኦንታሪዮ ባሉ በርካታ ሰዎች በሚኖሩባቸው ግዛቶች በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መጥቷል። በአሁኑ ሰአት 77 ሺ የሚሆኑ ካናዳውያን በየቀኑ የኮሮረናቫይረስ ምርመራ የሚደረግላቸው ሲሆን የአገሪቱ ግብ ግን በየቀኑ 200 ሺ ሰዎችን ለመመርመር ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-54596957 +sports ማንችስተር ሲቲ ላይ የተጣለው ቅጣት በአሰልጣኙና በተጫዋቾቹ ላይ ምን ውጤት ይኖረዋል? ማንችስተር ሲቲ የአውሮፓ እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ የሆነውን አካል የፈቃድና የገንዘብ አጠቃቀም ደንብን በመጣሱ ለቀጣይ ሁለት የውድድር ዘመኖች በሚደረጉ የአውሮፓ ክለቦች ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጣለበት። ከዕገዳው በተጨማሪ ቡድኑ የሰላሳ ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ቅጣት የተጣለበት ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ካገኘው ነጥብ ላይ ሊቀነስበት እንደሚችልም ተጠቅሷል። ይህ የዕገዳና የቅጣት ውሳኔ የስፖርት ጉዳዮች ግልግል ፍርድ ቤት ላይ ይግባኝ ሊባልበት የሚችል እንደሆነም ተነግሯል። ቡድኑም በቅጣት ውሳኔው መሳዘኑንና ሕግን ያልተከተለ መሆኑን ገልጾ ይግባኝ እንደሚጠይቅ ገልጿል። የቡድኖችን የገንዘብ ሁኔታ የሚቆጣጠረው አካል እንዳለው ማንችስተር ሲቲ ለአራት ዓመታት ከስፖንሰር ያገኘውን ገቢ ደንብ ተላልፎ፣ አንሮ በማሳወቅና ሌ��ች ጥሰቶች፣ በተጨማሪ በምርመራው ሂደት ለመተባበር ፈቃደኛ አልነበረም ብሏል። የቅጣቱ ውሳኔ በይግባኝ እስካልተቀለበሰ ድረስ ቡድኑ ከሁለት የታላቁ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ውጪ የሚሆን ሲሆን ይህም ለቡድኑም ሆነ ለአሰልጣኙ ትልቅ ጉዳትን ያስከትላል። በአውሮፓ የሻምፒዮን ሊግ ውድድር ላይ መታየት ለተጫዋቾችና ለአሰልጣኞች እንደአንድ ስኬት ስለሚቆጠር ቅጣቱ ቡድኑ ውስጥ ያሉትን አሰልጣኞችና ተጫዋቾችን ሊያሸሽ እንዲሁም ሌሎችን ለመቅጠር እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አለ። እኤአ እስከ 2021 በማንችስተር ሲቲ ውስጥ ለመቆየት ኮንትራት የፈረመው ፔፕ ጋርዲዮላና ሌሎች እሱን ተከትለው ክለቡን የተቀላቀሉት ተጫዋቾች፣ ቡድኑ በታላቁ የአውሮፓ ክለቦች የውድድር መድረክ ላይ ለሁለት ተከታታይ ወቅቶች የማይሳተፍ ከሆነ ሲቲ ውስጥ የመቆየታቸው ነገር አጠያያቂ ነው። ይህ ደግሞ በዓመታት ውስጥ አሉ ከተባሉ የእንግሊዝ እግር ኳስ ቡድኖች መካከል ለመሰለፍ ከፍተኛ ገንዘብን በማፍሰስ ስሙን የገነባውን ቡድን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሊጥለው ይችላል። የሲቲ ባለስልጣናት ግን የተባለው አይነት ቅጣት እንዲጣልባቸው የሚያደርግ አንዳችም ጥፋት አለመስራታቸውን ለአሰልጣኙ ጋርዲዮላ ያረጋገጡላቸው ሲሆን፣ ይህ ተጫወቾችንም እንዲረጋጉና ቡድኑ ውስጥ እንዲቆዩ ያግዛል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን የስፖርት ጉዳዮች የግልግል ፍርድ ቤት በማንችስተር ሲቲ ላይ የተጣለውን ቅጣት ተገቢ አይደለም ብሎ ካነሳው ነው። ቡድኑም ጉዳዩን በቀላሉ እንደማይተወው አሳውቋል። https://www.bbc.com/amharic/sport-51513602 +business ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ ለተወሰኑ እቃዎች እና ሸቀጦች የውጭ ምንዛሪ እንዳይሰጥ ተወሰነ የኢትዮጵያ መንግሥት ከተለያዩ አገራት ለሚገቡ በተወሰኑ እቃዎች እና ሸቀጦች ላይ ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ እንደማይፈቅድ አስታወቀ። ከእነዚህም መካከል ከረሜላዎች፣ ብስኩቶች፣ ለስላሳ መጠጦች፣ ዊስኪ፣ ወይን፣ ቢራ፣ የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች እና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች፣ ሰው ሰራሽ ፀጉር፣ የውበት ወይም መኳኳያ እቃዎች ተካትተውበታል። የገንዘብ ሚኒስቴር በቁጥር 38 የሚሆኑ ሸቀጦች እና እቃዎችን ዝርዝር በማውጣት የውጭ ምንዛሬ እንዳይፈቅድላቸው ያሳለፈውን ውሳኔ ብሔራዊ ባንክ ተግባራዊ እንዲያደርግ በደብዳቤ አዟል። በገንዘብ ሚኒስቴር ዲኤታው ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያትተው የዓለም አቀፉ ምጣኔ ሀብት ቀውስ በአገሪቱ ላይ እየፈጠረ ያለው ጫና እንዲሁም የዋጋ ግሽበት በሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለውንም ችግር ለመፍታት የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱንም አስታውሷል። እነዚህንም እርምጃዎች ውጤታማ ለማድረግም የውጭ ምንዛሬ ለመሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች፣ ለመድኃኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎች እንዲውል ተወስኗል። በተጨማሪም ከውጭ ገብተው በአገር ውስጥ እሴት ለሚጨመርባቸው ምርቶች የሚውሉ ግብዓቶችና የካፒታል ዕቃዎችን ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ ጥቅም ላይ እንዲውል ውሳኔ መተላለፉም ተገልጿል። ከሰኞ ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ እንዳይሰጡ ክልከላ የተጣለባቸው ከውጭ ወደ አገሪቱ የሚገቡ ሸቀጦች እና ምርቶች የሚከተሉት ናቸው። ከረሜላዎች፣ ማስቲካዎችና ሌሎች ጣፋጭ ምርቶች፣ ቼኮሌት፣ ብስኩቶች እና ዋፈሮች፣ የፍራፍሬ ጭማቂዎች እና የታሸጉ ፍራፍሬዎች፣ ከፍራፍሬ የተዘጋጁ ጃሞች፣ የድንች ጥብሶች፣ የአሳማ ሥጋ፣ የዶሮ ሥጋ፣ የተለያዩ የአሳ ምርቶች፣ የገበታ ጨው፣ የታሸጉ ውሃዎች፣ ለስላሳ መጠጦች እና አልኮል የሌላቸው መጠጦች ለምግብነት ከሚውሉ ውስጥ ይጠቀሳሉ። እንዲሁም ዊሰኪ፣ ወይን፣ ቢራ ���ና ለሎች አልኮል መጠጦች በሙሉ፣ ሲጋራ፣ ከብርጭቆ የተዘጋጁ የመጠጥ መጠጫዎች፣ የሲጋራ መተርኮሻዎች የተካተቱ ሲሆን፣ ሽቶዎች፣ የውበት ወይም የመኳኳያ ምርቶች፣ የሰው እና አርቴፊሻል ፀጉሮች፣ አርቴፊሻል ጌጣጌጦች፣ የተለያዩ የፀጉር ጌጣጌጦች፣ ባርኔጣዎች እና ኮፍያዎች፣ ሳሙናዎች፣ ርችቶች፣ ቦርሳ እና ዋሌቶች፣ አንዳንድ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች ተካተዋል። ብስክሌቶች፣የተለያዩ መጫወቻ እቃዎች፣ የእጅ፣ የጠረጴዛ እና የግድግዳ ሰዓቶች፣ ዣንጥላዎች፣ ምንጣፎች፣ ከሴራሚክስ እና ፖርስሊን የተዘጋጁ የቤት እቃዎች፣ ጋዝ ላይተር፣ ልብስ ማሳያ አሻንጉሊቶች፣ የአበባ መያዣና ተመሳሳይ እቃዎች፣ የታተመ ስዕላዊ መግለጫ ያላቸው ካርዶች፣ የቀን መቁጠሪያ ካሌንደሮች፣ ሥዕሎች፣ አርቲፊሻል አበባዎች። በተጨማሪም በኤሌክትሪክ ከሚሰሩት ውጪ የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢል እና ባለሦስት እግር ተሸከርካሪዎች እና ሞተር ሳይክሎችን ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ ተከልክሏል። ነገር ግን ይህ ክልከላ በአገር ውስጥ ለሚገጣጠሙ መኪኖች እና ተሽከርካሪዎች እንዲሁም በኤሌክትሪክ የሚሰሩትን አይመለከትም። መንግሥት በአገሪቱ ያለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ ባለፈው ሳምንት ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የውጭ ምንዛሪ ግብይትን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አሳውቆ ነበር። በዚህም በአገሪቱ እየተባባሰ ያለውን የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት በሕገወጥ መንገድ የሚካሄዱ የተለያዩ የገንዘብ ዝውውሮችን ለመቆጣጠር ያስችላሉ ያላቸውን እርምጃዎችን አሳውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ የሚካሄዱ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውሮችን ለመቆጣጠር በጥቆማ ለሚተባበሩ ግለሰቦች የተለያየ መጠን ያለው ወሮታ እንደሚከፍል አስታወቆ ነበር። በዚህም በባንክ ከተፈቀደው በላይ የገንዘብ መጠን ይዘው የሚገኙ ግለሰቦችን ለጠቆሙ ከተያዘው ገንዘብ 15 በመቶ፣ የውጭ አገር ገንዘብ ዝውውር ለሚጠቁሙ 15 በመቶ፣ ሕገወጥ ሐዋላን ለሚጠቁሙ 25 ሺህ ብር ወሮታ ብሔራዊ ባንክ እንደሚከፍል ገዢው አሳውቀዋል። ከዚህ በተጨማሪም የወርቅ ኮንትሮባንድ ለሚጠቁሙ 15 በመቶ የወርቁን ዋጋ፣ የሐሰተኛ የገንዘብ ኖት ህትመትን ለሚጠቁሙ ከ20 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር የሚደርስ ወሮታ እንደሚከፈልም ተገልጿል። በተጨማሪም ከአገር ውስጥ ጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪን በመግዛት ከውጭ እቃ እያስገቡ ያሉትን ለመቆጣጠር፣ በፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ እቃ የሚያስመጡ ግለሰቦችና ተቋማት በውጭ አገር ያላቸውን የዶላር መጠን የሚያሳውቅ የባንክ ስቴትመንት ለብሔራዊ ባንክ የማቅረብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሪ ዋጋ እየጨመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ያለው የምንዛሪ ዋጋ ከዚህ በፊት ከነበሩት ሁሉ ከፍተኛው ነው። በዚህም በይፋዊው የባንኮች ግብይት የዶላር የምንዛሪ ዋጋ የአንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ 52 ብር አካባቢ ሲሆን፣ በጥቁር ገበያ በእጥፍ እንደሚመነዘር ይነገራል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1nq0n7v1zo +sports ከሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛን አቀላጥፎ መናገር የቻለው የማንችስተር ተጫዋች "የሮሪ ከርትስ ጉዳይ ትንግርት ካልተባለ ምን ሊባል ይችላል? ታሪኩን በአንድ አንቀጽ የሚከተለውን ይመስላል። ሮሪ በ22 ዓመቱ ዘግናኝ የመኪና አደጋ ደረሰበት። ከሳምንታት በኋላ ከሰመመን ነቃ። በቅጡ ተናግሮት የማያውቀውን ፈረንሳይኛ እንደ ልሳን ያንበለብለው ጀመር። ሰው የማያውቀውን ቋንቋ እንዴት ሊናገር ይችላል? ሮሪ ለማንችስተር ታዳጊ ቡድን ተጫዋች ነበር። በሕይወቱ ከኳስ ሌላ ሕልም አልነበረውም። በአንድ ክፉ አጋጣሚ መኪናውን በእንግሊዝ አውራ ጎዳና በፍጥነት ሲያሽከረክር ተገለበጠ። ያን ቀትር ዶፍ እየዘነበ ነበር። መንገዱ ያንሸራትት ነበር። እሱ ከከባድ መኪና ጋር ሲጋጭ ከኋላው በፍጥነት እየተነዱ የነበሩ ስድስት ሌሎች የቤት መኪናዎች ተገጫጭተው እላዩ ላይ ወጡበት። የእርሱ መኪና ጭምድድድ. . . አለች፤ እንደ ካርቶን። እንኳን ሰው ዝንብ ከዚያ አደጋ ይተርፋል ያለ ማንም አልነበረም። ሮሪ ግን ሲፈጥረው በቀላሉ አትሙት ተብሏል መሰለኝ. . .፡፡ ራሱን ሳተ እንጂ ነፍሱ አልወጣችም ነበር። አምቡላንስ መጣ፤ ሆስፒታል ተወሰደ። ለሳምንታት አልነቃም። ሐኪሞቹ የዚህ ወጣት ነፍስ የመትረፍ ዕድሏ የተመናመነ እንደሆነ ለቤተሰቦቹ በይፋ ተናገሩ። ኾኖም ግን አንድ በሙከራ ላይ ያለ መድኃኒት እንዳለና ፍቃዳቸው ከሆነ እሱን መድኃኒት ሊወጉት እንደሚችሉ ጠየቁ። ቤተሰቡ ምን አማራጭ ነበረው? እሺ ከማለት ሌላ። የሮሪ ወላጆች ተስማሙ። አዲሱን መድኃኒት ተወጋ። ሆኖም ከሰመመኑ አልተመለሰም። በግማሽ ሞት፣ በግማሽ ሕይወት መሀል ሆኖ ለሳምንታት ራሱን እንደሳተ ቆየ። እውነት ለመናገር ቤተሰቦቹ እርም ለማውጣት በዝግጅት ላይ ነበሩ። ሁሉም ነገር ተስፋ አስቆራጭ በሚመስልበት በዚያ ሰዓት አንድ ማለዳ ሮሪ ዓይኑን ገለጠ። እሱ ሲነቃ አጠገቡ አንዲት ጥቁር ነርስ ነበረች። አንዳች ነገር ማጉረምረም ጀመረ። ቀጥሎ የሆነው ግን ለሳይንስም ግራ ነው የሆነው። ፈረንሳይኛ ቋንቋን ያንበለብለው ነበር። በአጋጣሚ አጠገቡ የነበረችው ጥቁር ነርስ ፈረንሳያዊት ስለነበረች ልጁ የፈረንሳይ ዜጋ እንደሆነ እርግጠኛ ነበረች። ኋላ ላይ አባትየውን ፈረንሳይ የት አካባቢ እንደሚኖሩ የጠየቀቻቸውም ለዚሁ ነበር። እርሳቸው ግን ""ኧረ እኛ ከእግሊዝ ነን፤ የምን ፈረንሳይ አመጣሽብኝ?"" አሉ። ""ታዲያ እንዴት ልጆዎ ፈረንሳያዊ ሊሆን ቻለ? በእናቱ ወገን ይሆን?"" ነርሷ ጠየቀች። በፍጹም ጥርጣሬ አልገባትም ነበር። ሆኖም ሮሪ አይሪሽ እንጂ ፍሬንች አልነበረም። እርግጥ ልጅ እያለ ድሮ በትምህርት ቤት መጠነኛ ፈረንሳይኛ ተምሯል። አለ አይደል? ለመግባባት ያህል የምትሆን ፈረንሳይኛ። ያን ከመማሩ ውጪ በዚህ ደረጃ ቋንቋውን አቀላጥፎ ተናግሮት አያውቅም። አይችልምም። እንዲያውም ልጅ እያለ ከተማረው በኋላ ቋንቋውን ተናግሮ ስለማያውቅ ጭራሽ ፈረንሳይኛን እንደማያስታውሰው ነበር የሚታወቀው። ነገር ግን ከሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛውን አንበለበለው። ይህ ትንግርት ነበር፤ ለሐኪሞቹም፣ ለወላጆቹም፣ ለሳይንስም። ሮሪ ከሳምንታት ሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛ ይናገር እንጂ ማን እንደነበረ በጭራሽ አያውቅም ነበር። ለማንችስተር ታዳጊ ቡድን ይጫወት እንደነበረ ቢነገረው ሊገባው አልቻለም። ኳስ ይወድ እንደነበረ እንኳ ረስቷል። ስላለፈ ሕይወቱ በጭራሽ የሚያስታውሰው ነገር የለም። አንዳችም ነገር! ለምሳሌ ምን ሆኖ ወደ ሆስፒታል እደገባ፣ ጭኑ አካባቢ እንደተሰነጠቀ፣ ክርኑ እንደተሰበረ፣ ጭንቅላቱ እንደተፈለጠ ሁሉ አያውቅም። ፈረንሳይኛ ብቻ ያውቃል። ፈረንሳይኛው እንደ ልሳን. . . እንደ ማር. . . ከአፉ ጠብ ይል ነበር። ሆኖም ብዙ አልዘለቀም። በድንገት ዝም አለ። ፈረንሳይኛው በድንገት እንደ ጉም በነነ። በቃ አቃተው። ተናገር ሲባል ኧረ እኔ ፈረንሳይኛ አልችልም ነበር ያለው። እንዴት ይህ ሊሆን ቻለ? ቅደም አያቶቹ ከፈረንሳይ መሆናቸው ይሆን? ""አባቴ ነገሩ አስገርሞት መመራመር ያዘ። የደረሰበት ነገር ቢኖር የእርሱ ቅድመ አያቶች ከሰሜን ምዕራብ ፈረንሳይ ኖርማንዲ ግዛት የሚመዘዙ መሆናቸው ነበር"" ይላል ሮሪ። ይህ ዘመን ግን በ1800 አካባቢ መሆኑ ነው። ይህ ታዲያ እንዴት ከሮሪ ፈረንሳይኛ መናገር ጋር ሊገናኝ ይችላል? ቋንቋ እንደ ስኳርና ደም ግፊት በደም አይተላለፍ ነገር! ይተላለፍ ይሆን እንዴ? ሮሪ በእርሱ ላይ የደረሰው ትንግርት እንዴት ዓለምን ሲያነጋግር እንደቆየ ለቢቢሲ ሲናገር ""ዩቲዩብ ላይ ስሜን ጉግል ብታደርገው ከእኔ መላምቶች ጋር በተያያዘ ብዙ ቪደዮዎችን ታገኛለህ። አንዳንዱ ቋንቋ በትምህርት ብቻ ሳይሆን በዘር የሚተላለፍና አእምሯችን ጓዳ ሊቀበር እንደሚችል የሚገልጽ ነው"" ይላል። ሮሪ ላይ ይህ አደጋ የደረሰው በ2012 ላይ ነበር። ያን ጊዜ ሮሪ 22 ዓመቱ ነበር። ዛሬ 30 ዓመት ደፍኗል። ሮሪ ያን ጊዜ ለማንችስተር ዩናይትድ ታዳጊ ቡደን እየተጫወተ በትርፍ ሰዓቱ ለአንድ ተቋራጭ ኩባንያ በተላላኪነት ይሰራ ነበር። የሚገርመው ከዚህ ሁሉ ዓመት በኋላ ዛሬም ድረስ ያ አደጋ እንዴት እንደተፈጠረ ምንም ትዝ አይለውም። ያ አሰቃቂ የመኪና አደጋ ከትዝታ ቋቱ የተፋቀ ጉዳይ ነው። ሆኖም የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ሮሪ በዚያ ዝናብ በከፍተኛ ፍጥነት እየነዳ በፍጥነት መስመር ሲቀይር ነበር ከፊት ለፊቱ ከሚገኝ ከባድ ተሸከርካሪ ጋር ሄዶ የተላተመው። ከዚያም ከኋላው የነበሩ መኪናዎች እላዩ ላይ ወጡበት። የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች ሮሪን ከተጫኑት ስድስት መኪናዎች ውስጥ ፈልፍለው ለማውጣት ከግማሽ ሰዓት በላይ ወስዶባቸዋል። ያን ጊዜ ትንፋሽ አልነበረውም። ሆኖም አምቡላንስ ውስጥ የመተንፈሻ መሣሪያዎች ተገጥመውለት በርሚንግሀም ወደሚገኘው ቅድስት ኤልዛቤጥ ሆስፒታል ተወሰደ። ሮሪ የኋላ ታሪኩ ሲጠና 7 ዓመቱ ላይ ሳለ የማጅራት ገትር የመሰለ ሕመም ታሞ እንደነበር ታውቋል። ያን ጊዜም ቢሆን የመትረፍ እድሉ 50 በመቶ ብቻ ነበር። ለ6 ሳምንት በበርሚንግሀም የሕጻናት ሆስፒታል ውስጥ ክትትል ተደረገለት። ከዚያ በኋላ በተወነ ደረጃ ዕይታው ስለተጋረደ መነጽር ማድረግ ጀምሮ ነበር። ""ያን ጊዜ ሆስፒታል ከነበርነው ሕጻናት እኔ ብቻ ነኝ የልጅነት ልምሻ ያልያዘኝ። ያለምንም ጉዳት ድኜ ስወጣ ሰው ሁሉ ገርሞት ነበር"" ይላል። ይኸው ነው ቅድመ ታሪኩ። ሮሪ ከዚህ በኋላ ምንም የጤና እክል አላጋጠመውም። እንዲያውም ንቁና ቀልጣፋ በመሆኑ እግር ኳስ አካዳሚ ተመዘገበ። ቤተሰቡ የለየለት የበርሚንግሀም ቀንደኛ ደጋፊዎች ናቸው። በ11 ዓመቱ ለበርሚንግሀም የታዳጊ ቡድን እንዲጫወት ተፈቅዶለት ነበር። በ13 ዓመቱ ለሴንትራል አያክስ ቡድን አጥቂ ቦታ ሲጫወት የማንችስተር ዩናይትድ መልማዮች አይተውት ወደዱት፤ ወሰዱት። ከዚህ በኋላ ነበር አሰቃቂው አደጋ የደረሰበት። ከሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛ መናገሩ ብቻ አይደለም የሮሪ አስገራሚው ነገር። እድሜውንም ረስቶ ነበር። ያኔ 22 ዓመቱ የነበረ ቢሆንም እርሱ ግን የ10 ዓመት ልጅ እንደሆነ ነበር የሚያውቀው። ""ውሻዬ የት ሄዳ ነው?"" ይላል። ""እማዬ ውሻዬን አምጪልኝ"" ይለኝ ነበር ትላለች እናቱ። ውሻዋ እኮ ድሮ እሱ ልጅ እያለ ነው እኮ የሞተችው። እርሱ ግን ረስቶታል። ሮሪ በበኩሉ ""ቀስ እያልኩ እድሜዬ 10 ሳይሆን 12 እንደነበር ትዝ አለኝ"" ይላል። የሚደንቀው ይህ አይደለም። ከሰመመን ከነቃ ከጊዜ በኋላ ደግሞ ሮሪ ራሱን የሆሊውድ ዝነኛ ተዋናይ ማቲው መካነሄይ እንደሆነ ነበር የሚያስበው። ቅዠት ሳይሆን በእውን እርሱ የሆሊውዱ ማቲው ማካነሄይ እንደሆነ በትክክል ያምን ነበር። መጀመርያ እንዲያ ያስብ የነበረው ሆስፒታል አልጋ ላይ ሳለ ነበር። ያስጨንቀው የነበረውም ቶሎ ተነስቶ ቀጣዩን ዝነኛ ፊልሙን መቅረጽ ነበር። እርሱ የኦስካር አሸናፊ ማቲው መካነሄይ እንደነበረ እቺን ታህል ጥርጣሬ አልበረውም። ""ክንዴና ጭኔ አካባቢ ተሰብሬ ስለነበር እናቴ ነበረች ሽንት ቤት የምታደርሰኝ። የመጀመሪያ ከሰመመን ነቅቼ ሽንት ቤት ሳለሁ በመስታወት የማ���ው ልጅ ማን ነው? ስል ግራ ተጋባሁ። አላውቀውም ነበር። ራሴን አላውቀውም። የራሴን መልክ አላውቀውም። እኔ የማውቀው ማቲው መካነሄይን መሆኔን ነበር"" ይላል ሮሪ። ምናልባት ሮሪ ያን ጊዜ መስታወቱ የዋሸው ያህል ሳይሰማው አልቀረም። እሱ ቆሞ እንዴት የሌላ ሰው ፊት ያሳየዋል? ሮሪ በኅዳር 2012 ከሆስፒታል ሲወጣ አብዛኛውን ነገር ዘንግቶ ነበር። እንኳንስ የድሮውን ይቅርና ከ15 ደቂቃዎች በፊት ያደረገውን ይረሳል። ስለዚህ ማስታወሻ ደብተር ተገዛለት። ምሳ ሲበላ ምሳ በልቻለሁ ብሎ ይጽፋል። ገላውን ታጥቦ እንደወጣ ገላዬን ታጥቢያለሁ ብሎ ይጽፋል። ""በዚህ መንገድ የጨረስኩት የማስታወሻ ደብተር ብዛቱ!"" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ሮሪ በዚህ መንገድ ማንነቱን መልሶ ለማግኘት ብርቱ ጥረት አደረገ። በመጨረሻም አንድ ዓመት ካገገመ በኋላ ራሱ ልብሱን መቀየር ቻለ። ከዚያ ሙሉ በሙሉ ድኖ ወደሚወደው እግር ኳስ ለመመለስ ሞከረ። ከስድስት ዓመት በፊት ለስቶርፖርት ክለብ መጫወት ጀመረ። ሐኪሞች ማመን አቃታቸው። እንዴት በዚያ ደረጃ የተጎዳ ልጅ ድኖ ኳስ ሊጫወት እንደሚችል ትንግርት ሆነባቸው። ""በእርግጥ መገረም ብቻ ሳይሆን እንዳልጫወት መክረውኛል። ምክንያቱም በጭንቅላቴ ኳስ መግጨት ስለማይኖርብኝ ነው። ጭንቅላቴ በአደጋው ተጎድቶ ነበር"" ይላል። ምናልባት ሮሪ ቋንቋ ማስታወስ የቻለው የጭንቅላቱ የቋንቋ ቋት በድንገት በሩ ተከፍቶ ይሆን? አንዳንዶች ጭንቅላታችን ከተወለድን ጀምሮ የሚሰማውንና የሚያየውን ነገር ሁሉ ይመዘግባል። እኛ ማስታወስ ስላቃተን ባዶ ይመስለናል እንጂ አእምሮ እጅግ ውስብስብ ተፈጥሮ ነው ይላሉ። ምናልባት ሮሪ ፈረንሳይኛው ከጭንቅላቱ የቋንቋ ቋት ተዘርግፎበት ቢሆንስ? ሮሪ የመኪና አደጋው ከደረሰበት በኋላ በሙከራ ላይ የነበረ የሆርሞን መድኃኒት ወስዷል። ያ መድኃኒት የሰው ልጅ ላይ ሲሞከር ሮሪ በዓለም ሁለተኛው ሰው ነበር። መድኃኒቱ ጭንቅላታቸው አካባቢ ከፍተኛ አደጋ ደርሶባቸው ለተጎዱ ሰዎች እንዲያገግሙ የሚረዳ ነበር። በአሜሪካ ሐኪሞች የተመራው ይህ የመድኃኒት ሙከራ ሲናፕሴ (Synapse) ይባላል። በከፊል ፕሮግሬስትሮን የተሰኘ የሴቶችን ሆርሞን ነበር የተወጋው። ሐኪሞቹ በየሦስት ወራት ሮሪን ይመለከቱት ነበር። ቤተሰቡ ለእሱ በተአምር መትረፍ ይህ መድኃኒት ዋናው እንደሆነ ያስባል። እሱን ይከታተሉት ከነበሩት ሀኪሞች አንዱ የሆኑት ኒውሮሎጂስቱ ዶ/ር አንቶኒ ቤሊ ግን መድኃኒቱ ለእርሱ እንዳልሰራለት ነው የሚናገሩት። ከዚያ ይልቅ የልጁ ጥንካሬና ዘረመሉ ሊሆን ይችላል ለተአምሩ መፈጠር ምክንያት የሆነው። ሮሪ ሙሉ በሙሉ ይዳን እንጂ አሁንም ድረስ ራሱን አግንኖ የማየት ነገር አለበት። ""ፍጹም ነኝ ብዬ የማመን ስሜት ይሰማኛል"" ይላል። ሮሪ በእግር ኳሱ ብዙ ተስፋ እንደሌለው ሲያስብ ወደ አስተማሪነት ከዚያም ወደ ጸጉር አስተካካይነት ገባ። ""እናቴ 6 እህቶች አሏት። ሁሉም አስተማሪዎች ናቸው። እኔም ለምን በጸጉር ሙያ አስተማሪነት አልሞክርም ብዬ ተነሳሁ። አባቴ ዘርማንዘሮቹ ሁሉ ጸጉር አስተካካዮች ነበሩ። ለምን እሱን አልሞክረውም አልኩኝ"" ይላል። የአባቱ ድርጅት ቻርሊ ፓርከር ጸጉር ቤት ይባላል። ከ1980ዎቹ ጀምሮ ቤተሰቤ በጸጉር ሥራ ነው ሲተዳደር የኖረው። ""ስለዚህ ከእናቴ ቤተሰቦች አስተማሪነትን ከአባቴ ደግሞ ጸጉር አስተካካይነትን ወሰድኩ።"" ሮሪ በኋላ ላይ ተምሮ ከተመረቀ በኋላ በበርሚንግሀም ሳውዝ ኤንድ ሲቲ ኮሌጅ ሌክቸረር ሆኖ ተቀጠረ። ጥቂት እንደሰራ ግን የልቡ አልደርስ አለ። ስለዚህ ለምን የራሴን ጸጉር ቤት አልከፍትም ብሎ ""ቻርሊ ፓርከርስ ከት ትሮት ኤንድ ኮፊ"" የሚባል የውበት ሳሎን ባለፈው ዓመት ከፈተ። ���ጀመርያ በ11 ዓመቱ፣ በኋላ ደግሞ በ22 ዓመቱ ሞትን በቆረጣ ጎብኝቶ የመጣው ሮሪ ጭንቅላቱ ላይ በደረሰው አደጋ የዓለም መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። እሱ ደግሞ ከጭንቅላት በላይ በሚበቅል ጸጉር መተዳደር ጀምሯል። ስለመጪው እሱም፣ ሐኪሞቹም የሚያውቁት ነገር የለም። እንኳን ስለመጪው ስላለፈውስ መቼ በቅጡ አወቁና. . ." https://www.bbc.com/amharic/news-52913458 +sports ባርሴሎና አሰልጣኝ ሮናልድ ኩማንን አሰናበተ "ሮናልድ ኩማን በኑካምፕ ለ14 ወራት ከዘለቀው የባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ሥራቸው ተባረዋል። ባርሳ በላሊጋው ካደረጋቸው 10 ጨዋታዎች 15 ነጥቦችን ብቻ ሰብስቧል። በዘንድሮው የቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎችም ሁለት ጊዜ ተሸንፏል። ረቡዕ በራዮ ቫሌካኖ ከተሸነፉ በኋላ ከመሪዎቹ በስድስት ነጥብ ርቀው በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ለባርሳ ሽንፈቱ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ሦስተኛው ነው። ባለፈው እሁድ በኤል ክላሲኮ በሪያል ማድሪድ መሸነፋቸው ይታወሳል። የስፔኑ ክለብ ባወጣው መግለጫ ""የክለቡ ፕሬዝዳንት ጆአን ላፖርታ ከራዮ ቫሌካኖ ሽንፈት በኋላ ስለ ውሳኔው ለኩማን አሳውቀውታል"" ብሏል። ""ሮናልድ ኩማን ሐሙስ ዕለት ቡድኑን ይሰናበታሉ።"" የ58 አመቱ የቀድሞ የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን፣ የኤቨርተን እና የሳውዝሃምፕተን አሰልጣኝ የአምስት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮናዎቹን ባለፈው የውድድር ዓመት በሊጉ ሦስተኛ ደረጃ ይዘው እንዲጨርሱ አድረጓል። ክለቡ ያጋጠመው ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ሆላንዳዊውን አልረዳውም። በዚህ ምክንያት ሊዮኔል ሜሲ ወደ ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን እንዲዘዋወር ሆኗል። በክረምቱ ባርሴሎና ለአዳዲስ ፈራሚዎች ምንም ገንዘብ ማውጣትም አልቻለም። ሜምፊስ ዴፓይ፣ ሰርጂዮ አጉዌሮ እና ኤሪክ ጋርሲያ በነጻ ዝውውር ኑ ካመፕ ደርሰዋል። አጥቂው ሉክ ዴ ዮንግ ከሲቪያ በውሰት ተቀላቅሏል። ከረቡዕ ሽንፈት በኋላ ኩማን ""[የባርሴሎና ሊግ አቋም] ደህና አለመሆኑን ያሳያል"" ብሏል። ""ይህ የሚያሳየው ቡድኑ ሚዛኑን አጥቷል፣ በጣም ውጤታማ የሆኑ ተጫዋቾችን አጥቷል። ሌላው የሚያሳየው ደግሞ በቅርብ ዓመታት ሌሎች ክለቦች ሲጠናከሩ እኛ ይህን አላደረግንም።"" የኳታሩ ክለብ አል ሳድ አሰልጣኝ የሆነው የቀድሞ የባርሳ አማካይ ዣቪ ኩማንን ለመተካት ከተመረጡት አንዱ ነው። ከእአአ 1987 ወዲህ ባርሳ በተከታታይ ሦስት ጨዋታዎች ከሜዳው ውጪ ጎል ሳያስቆጥር ሲሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ኩማን በመጀመሪያው የውድድር ዘመን የኮፓ ዴልሬይ ዋንጫን ቢያሸንፍም ባርሳ በአትሌቲኮ ማድሪድ እና ሪያል ማድሪድ በላሊጋው ከመበለጡም በላይ ከ2008 በኋላ ዝቅተኛውን ነጥብ ሰብስቦ አጠናቋል። የቀድሞው የኔዘርላንድ የመሃል ተከላካይ እአአ ከ1989 እስ 1995 ለስፔኑ ክለብ ተጫውቶ አራት የሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል። በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆሴፕ ማሪያ ባርቶሜው ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ወደ ክለቡ እአአ ነሐሴ 2020 ተመልሷል። አዲሱ ፕሬዝዳንት ላፖርታ ግን የሆላንዳዊው ሹመቱ የሳቸው ውሳኔ አለመሆኑን ደጋግሞ ተናግረዋል። ግንኙነታቸው መሰናክል የበዛበት ሲሆን ኩማን ሜሲ እና አንቶንዮ ግሪዝማን ካጣ በኋላ እንደገና ቡድኑን ለመገንባት ጊዜ እንዲሰጠው በመጠየቅ መስከረም ላይ መግለጫ አውጥቷል። ከእሁዱ የማድሪድ ሽንፈት በኋላ የኩማን መኪና በአንዳንድ የባርሴሎና ደጋፊዎች ተከቦ የነበረ ሲሆን አሰልጣኙ በኋላም ""ያልተማሩ ሰዎች"" ሲል አጣጥሏቸዋል። ወደ ራዮ ቫሌካኖ ከማቅናታቸው በፊትም ""ማህበራዊ ችግር ነው። ደንቦችን እና እሴቶችን ያልተረዱ ያልተማሩ ሰዎች"" ሲል ተናግሯል።" https://www.bbc.com/amharic/59074458 +politics ጠ/ሚንስትሯ በመኖሪያ ቤታቸው ሁለት ሴቶች ከፊል እርቃናቸውን ፎቶ ከ���ነሱ በኋላ ይቅርታ ጠየቁ የፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን በመኖሪያ ቤታቸው ሁለት ሴቶች ከወገባቸው በላይ እርቃናቸውን ሆነው ፎቶግራፍ ከተነሱ በኋላ ይቅርታ ጠየቁ። በጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤት ካናቴራ ሳይለብሱ እየተሳሳሙ ፎቶ የተነሱት ሁለት ሴቶች ተዋቂ ሰዎች ናቸው ተብሏል። ሁለቱ ሴቶች ፎቶውን የተነሱት ባለፈው ሐምሌ በጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤት በእንግድነት ተጋብዘው ሳለ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ባለፈው ሳምንት ሲደንሱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል መውጣቱን ተከትሎ ወቀሳ በዝቶባቸው እንደነበር ይታወሳል። የአደንዛዥ እፅ ምርመራ እንዲያደርጉ ተጠይቆ፣ እጽ አለመውሰዳቸው ተረጋግጧል። የሁለቱ ዕውቅ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሴቶች ፎቶ በስፋት በማኅበራዊ ሚዲያ ተዘዋውሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ “ፎቶዎቹ አግባብ አይደሉም” ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ እንዳሉት ሐምሌ ላይ ከሩስሮክ የሙዚቃ ፌስቲቫል በኋላ ሄልሲንኪ በሚገኘው ቤታቸው ድግስ አዘጋጅተው እንደነበረና ፎቶውም ድግሱ ላይ እንደተነሳ ተናግረዋል። ፎቶው የተነሳው ለእንግዶች በተዘጋጀ መጸዳጃ ቤት እንደሆነ የፊንላንድ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። አንድ ሌላ ፓርቲ ላይ ሲጨፍሩ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል ከወጣ በኋላ የፓርቲያቸው አባሎች እንዲሁም ተቀናቃኞቻቸውም ትችት እየሰነዘሩ ነው። በፓርቲው ላይ አደንዛዥ እፅ ወስደው ሊሆን ይችላል ያሉ አንድ ተቀናቃኝ ፖለቲከኛ ጠቅላይ ሚኒስትሯ እንዲመረመሩ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ የተወሰነ አልኮል ከመጠጣታቸው ውጪ ድግሱ ላይ አደንዛዥ እፅ እንዳልወሰዱና ወስደውም እንደማያውቁ ተከራክረዋል። ምርመራ ከተደረገላቸውም በኋላ ከአደንዛዥ እፅ ነጻ ሆነው ተገኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አኒካ ሳሪኮ፣ በጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤት የተነሳው ፎቶ በኑሮ ውድነት የሚንገላቱ የፊንላንድ ዜጎችን ሕይወት እንደማይወክል ገልጸዋል። ሆኖም ግን የሰዎችን የሞራል ዝቅታም ይሁን ከፍታ መተንተን “ቦታዬ አይደለም” ብለዋል። ፊንላንድ ከሩሲያ የሚጓዙ ቱሪስቶች ላይ እንደ አብዛኞቹ የአውሮፓ አገራት ገደብ ጥላለች። ጠቅላይ ሚኒስትሯን ዝነኛ እያደረጋቸው የመጣው ግን ከፖሊሲያቸው በላቀ የአኗኗር ዘያቸው ሆኗል። ፊንላንዳውያን ስለ መሪያቸው የተደበላለቀ ስሜት አላቸው። ተራው የፊንላንድ ዜጋ፣ ጠቅላይ ሚኒስሯ እንደ ማንኛውም በእሳቸው የዕድሜ ክልል ያለ ሰው ዘና ማለታቸውን ይደግፋል። ጫና ከሚበዛበት ሥራቸው ውጪ መደነስና መዝናናት መውደዳቸው የተለመ ነው የሚሉም አሉ። እንዲያውም አብዛኛው ወጣት ከጠቅላይ ሚኒስሯ ጋር የሚያመሳስለኝ ነገር አለ ብሎ እንዲያምን ያደርጋል ሲሉ ይከራከራሉ። እነዚህ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትሯን ለመደገፍም እየደነሱ ቪድዮ ለጥፈዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cyx8xw7rrj4o +health የኮሮናቫይረስ በአንዳንድ ምግቦች ላይ ለቀናት እንደሚቆይ ጥናት አረጋገጠ የኮሮናቫይረስ በተለይም ታሽገው በሚሸጡ ምግቦች ላይ እንደሚቆይ የዩናትድ ኪንግደም ተመራማሪዎች ገለጹ። የአገሪቱ የምግብ ጥራት ኤጀንሲ ባሰራው ጥናት ሳይንቲስቶች ቫይረሱን ሆነ ብለው በተወሰኑ የምግብ ማሸጊያዎች ላይ በማድረግ ሙከራውን አድረገዋል። ይህም በአትክልት እና ፍራፍሬ፣ ኬክ እና ዳቦ እንዲሁም የታሸጉ መጠጦች ሙከራው ተደርጎባቸዋል። ሳይንቲስቶቹ ሳይታጠቡ ወይም ሳይበስሉ ሊበሉ የሚችሉ ምግቦችን በመምረጥ ነው ጥናቱን ያካሄዱት። ነገር ግን ይህ ሸማቾች ላይ የሚያመጣው አደጋ ያነሰ መሆኑን ገልጸዋል። በአብዛኛው የምግብ ምርቶች ላይ ሳይንቲስቶቹ ያስቀመጡት የቫይረስ መጠን በ24 ሰአት ውስጥ ከፍተኛ ማሽቆልቆል ታይቶበታል። ነገር ግን በአንዳንድ ማሸጊያዎች ��ይ ቫይረሱ ለአንድ ሳምንት ያህል እንደሚቆይ የሳውዝ ሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ተናግረዋል። ሳርስ ኮቭ 2 የተሰኘውን የቫይረስ አይነት ወስደው ምርምሩን ያደረጉት አጥኚዎች እንደሚሉት ''እንደዚህ ያለ በንክኪ ብቻ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭ የቫይረስ አይነትን በተመለከተ ያገኘነው ግኝት ትኩረት የሚገባው ነው'' ሲሉ ተናግረዋል። ሳይንቲስቶች ሸማቾች በተለይም ምግብ በሚያዘጋጁበት ወቅት እጃቸውን እንዲታጠቡ እና በጥሬው የሚበሉ ምግቦችን አጥበው እንዲመገቡ አሳስበዋል። ተመራማሪዎች በጥናታቸው የኮሮናቫይረስ በንክኪ ከሚተላለፈው ይልቅ በምራቅ ፍንጣቂዎች በአየር አማካይነት የበለጥ እንደሚተላለፍ አረጋግጠዋል። ጥናቱ እንዳረጋገጠው ቫይረሱ በተለይም ሸካራ ገጽ ባላቸው እንደ ብሮኮሊ ባሉ አትክልቶች ላይ እንደ ፖም ባሉ ልሙጥ ከሆኑት በበለጠ እንደሚቆዩም አረጋግጧል። ጥናቱ አክሎም ፖም በቅርፊቱ ላይ በያዘው ኬሚካል አማካኝነት በቂቃዎች ወይም በሰዓታት ውስጥ በላዩ ላይ ያረፈውን ቫይረስ መግደል እንደሚጀምርም አረጋግጧል። በኬክ እና ዳቦ ላይ በተደረጉ ሙከራዎችም በአንዳንድ ደረቅ ገጽ በላቸው ኬኮች ላይ ቫይረሱ በሰአታት ውስጥ ቁጥሩ መቀነሱን ተናግረዋል። ለዚህም ምናልባት ኬኮቹ በሚበስሉበት ወቅት እንቁላል ስለሚቀቡ እና ይህም እንቁላል ውስጥ ካለ አሲድ አማካኝነት ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል። በቺዝ እና ቀዝቃዛ ስጋ ቫይረሱን ለቀናት አንዳንዴም ለሳምንት ሊያቆዩ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ኮቪድ በፕላስቲካ እቃዎች ላይ እስከ አንድ ሳምንት ድረስ ሊቆይ ይችላል። በካርቶን ላይ ለተወሰኑ ቀናት ብሎም በአልሙኒየም ማሸጊያዎች ላይ የተወሰኑ ሰአታትን ሊቆይ እንደሚችል ሳይንቲስቶቹ ተናግረዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0j54rpdryo +sports የዓለም ዋንጫ፡ አፍሪካን ስለሚወክሉ አገራት ስድስት ወሳኝ ነጥቦች በኳታር የዓለም ዋንጫ የሚካፈሉ የአፍሪካ አፍሪካ አገራት አዲስ ታሪክ ጽፈዋል። አምስቱም አገራት በራሳቸው ዜጎች ነው የሚሰለጥኑት። አራቱ አሰልጣኞች በዚህ ውድድር ሲካፈሉ የመጀመሪያቸው ነው። የሴኔጋሉ አሉ ሲሴ ብሔራዊ ቡድኑን ሩሲያ ላይም መምራት ችለዋል። በ2018 አምስቱም የአፍሪካ ተወካዮች ከምድባቸው ማለፍ አልቻሉም። ቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ከእነዚህ ቡድኖች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ወሳኝ ጥያቄዎችን ይመልሳል። የአፍሪካ ተወካዮች ፈተና ከየምድባቸው ይጀምራል። ሞሮኮ፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዝያ፣ ግብጽ እና ናይጄሪያ ከ2018 የዓለም ዋንጫ ምድብ ጨዋታዎች አልዘለሉም። ካሜሮን እና ጋና ርዕስ ከነበሩበት የ2014 የዓለም ዋንጫ በኋላ ለዘንድሮው ውድድር በቅተዋል። የካሜሮን ተጫዋቾች ሜዳ ላይ ቡጢ ተሰናዘሩ። ጋናዎች ከቦነስ ክፍያ ጋር በተያያዘ ተጋጩ። ሴኔጋሎች ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካ ሻምፒዮን ከሆኑ በኋላ የሚሳተፉበት የዓለም ዋንጫ ነው። የዓለም ኮከብነትን በሁለተኛነት ያጠናቀቀው ሳዲዮ ማኔ በጉዳት ከቡድኑ ርቋል። ሞሮኮ አዲስ አስልጣኝ ከሾመች ሁለት ወር ብቻ ሆናት። ቤልጂየም፣ ክሮሽያ እና ካናዳ በምድቧ ይገኛሉ። ካሜሮን ፍጥነት እና ጉልበት የቀላቀለ አጨዋወት ስትመርጥ ይስተዋላል። የቀድሞ ኮከቧ እና የአገሪቱ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ኃላፊ ሳሙኤል ኤቶ ዋንጫውን ማን ያነሳል ተብሎ ተጠይቆ ሞሮኮ እና ካሜሮን ለፍጻሜ ይደርሳሉ ብሏል። ዋንጫው በሪጎበርት ሶንግ የሚመሩት የማይበገሩት አንበሶች ይሆናል ማለቱ ቡድኑ ላይ ጫና እንዳይፈጠር ተሰግቷል። ሦስት የአፍሪካ አገራት የዓለም ዋንጫው የሩብ ፍጻሜ ደርሰዋል። አሁን ቀዳሚው ዓላማ ግማሽ ፍጻሜ ነው። ሴኔጋል ኮከቧን እና በ34 ጎሎች የብሔራዊ ቡድኑ ጎል አግቢነትን የሚመራውን አጥቂዋ�� ሳዲዮ ማኔን በጉዳት አጥታለች። ጆርጅ ዊሃ የዓለም ኮከብ የተባለው እአአ በ1995 ነው። ከዚያ ወዲህ በዓለም ኮከብነት ምርጫ ከሦስተኛ በላይ ያለውን ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ የቻለው ማኔ ብቻ ነው። ሴኔጋል አሁን ተስፋ ያደረገችው በዋትፎርዱ ኢስማሊያ ሳር እና በአላንያስፖሩ አጥቂ ፋማራ ዲድሁ ላይ ነው። ቡላዬ ዲያም ሌላው ተስፋዋ ነው። ሲሴ ከሴኔጋል ወርቃማ ትውልድ አባላት አንዱ ናቸው። ቡድኑ በጃፓን እና ኮሪያው የ2002 የዓለም ዋንጫ ስምንት ውስጥ መግባት ችሏል። አሰልጣኙ ለዓመታት ያካበቱትን ልምድ ተጠቅመው አዲስ ዕቅድ እንደሚነድፉ ይጠበቃል። ሞሐመድ ሳላህ እና ሪያድ ማህሬዝ ለትልቁ ውድድር ለመብቃት አልቻሉም። አሁን አዲስ አፍሪካ ኮከብ ፍለጋ መውጣት ግድ ይላል። ከአያክስ ጋር በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እየፈካ የሚገኘው ጋናዊው አማካኝ ሞሐመድ ኩዱስ ከዕጩዎቹ አንዱ ነው። ካሜሮን ምርጥ የአጥቂ ስብስብ አላት። ኤሪካ ማክሲም ቹፖ-ሞቲንግ፣ ካርል ቶኮ ኤካምቢ እና ቪንሰንት አቡበከር ይጠቀሳሉ። ቱኒዚያውያን ድንቅ በአማካኛቸው አይሳ ላይዱኒ ይተማመናሉ። ሞሮኮ በበኩሏ ሃኪም ዛይችን ይዛለች። ዛይች ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር ባለመግባባቱ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ቢያገልም አዲስ አስልጣኝ ሲሾም ሃሳቡን ቀይሮ ለቡድኑ መከታ ለመሆን ተዘጋጅቷል። ይህ ዓለም ዋንጫ እንደ ቀደሞዎቹ ሁሉ ሰኔ ላይ አይካሄድም። ይህም በሞቃታማ ወቅት የሚከናወን የዓለም ዋንጫ ያደርገዋል። የኳታር የአየር ሁኔታ ለአውሮፓዊያን የሚቻል አይመስልም። ምሽት ላይ አየሩ ቀዝቀዝ ይላል። የስታዲየሞች አየር ተመጣጣኝ እንዲሆን ኳታር ተዘጋጅታለች። አፍሪካ ቡድኖች ለማጣሪያው በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች እጅግ ሞቃታማ የሆኑ ስታዲየሞችን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ለመጫወት ይገደዳሉ። ታዲያ ይህ ለኳታሩ ውድድር ይጠቅማቸው ይሆን? ኳታር አረብ ዋንጫን ባለፈው ዓመት አዘጋጅታ ነበር። ለፍጻሜ ቱኒዝያ እና አልጄሪያ ደረሱ። ዋንጫው ወደ አልጀርስ አቀና። ቱኒዝያ ብዙ ደጋፊ ኳታር ላይ እንዳላት ያወቀችበት ውድድር ነው። ከዴንማርክ፣ አውስትራሊያ እና ፈረንሳይ ጋር ስትጫወት በሜዳዋ የመጫወት ያህል ስሜት ትጠብቃለች። ሰሜን አፍሪካ አገራት ወደ ጥሎ ማለፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማለፍ ይህን ድጋፍ ይሻሉ። “የአፍሪካ በተለይም የአረብ አገራት በኳታር መጫወት ይጠቅመናል” ያለው የቱኒዝያው አምበል ዋህቢ ካዚር ነው። “በተመሳሳይ ድባብ ውስጥ ነው የምንጫወተው። ብዙ ቱኒዝያውያን ዲያስፖራዎች ኳታር ይኖራሉ። በአረብ ዋንጫ ወቅት ቀዩን ማልያ በለበሱ ደጋፊዎች ስታዲየሞች መሞላታቸውን አስተውለናል። ይህም ይረዳናል” ብሏል። ይህ ለሞሮኮም ይሠራል። አፍሪካ በራሷ ልጆች አሰልጣኝነት በዓለም ዋንጫ የተወከለችው ከ40 ዓመት በፊት አንድ የአህጉሪቱ ተወካይ ብቻ በነበረበት፣ በስፔኑ የዓለም ዋንጫ ወቅት ነበር። ረዥም ጊዜ ያገለገሉት የሴኔጋሉ ሲሴ ሲሆኑ የተሾሙት እአአ በ2015 ነው። ሌሎቹ ዓመትም አልደፈኑም። ቱኒዝያ (ጃሌል ካድሪ)፣ ጋና (ኦቶ አዶ) እና ካሜሩን (ሶንግ) ከአፍሪካ ዋንጫ መልስ ሹመቱን ያገኙ ናቸው። ሞሮኮ ደግሞ ነሐሴ ላይ ነው ኃላፊነቱን ለዋሊድ ሬግራጉይን ሰጠችው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c03nz6g2rndo +sports ብራዚል ለሴት የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከወንዶች እኩል መክፈል ጀመረች የብራዚል ሴት ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋቾች ከእንግዲህ ከወንድ እግር ኳስ ተጨዋቾች እኩል እንደሚከፈላቸው የብራዚል እግር ኳስ ማኅበር አስታወቀ። ይህ ብቻም ሳይሆን ሁሉም ተጨዋቾች፣ ጉርሻ እና የሽልማት ገንዘብ እንዲሁም በልምምድ ላይ ሳሉ የሚሰጣቸው የኪስ ገንዘብ በሙሉ ከወንዶች ጋር እኩል እንዲሆን ተወስኗል። የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ሮጄሪዮ ካቦክሎ እንዳሉት ይህ ውሳኔ የተላለፈው ባለፈው መጋቢት ወር ነው። ብራዚል የወሰችውን ዓይነት እርምጃ እንግሊዝም ከባለፈው ጥር ጀምሮ ተግባራዊ አድርጋለች። የእንግሊዝ እግር ኳስ ማኅበር ቃል አቀባይ እንዳሉት ሴቶች ከወንዶች እኩል ደመወዝም ሆነ ጥቅማ ጥቅም ያገኛሉ። ብራዚል ለዓለም ዋንጫም ሆነ ለኦሎምፒክ ተወዳዳሪዎቿ በክፍያ ረገድ የጾታ መድልዎን አስቀርታለች። እስካሁን አውስትራሊያ፣ ኖርዌይ እና ኒውዚላንድ ለሴት ተጨዋቾች ከወንዶች እኩል እንዲከፈላቸው ቀድመው የወሰኑት አገራት ናቸው። የብራዚል የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከባለፈው መጋቢት ጀምሮ ምንም ዓይነት ውድድር አላደረገም። ምክንያቱ ደግሞ የኮሮና ወረርሽኝ እየተስፋፋ በመሄዱ ነው። ብራዚል በተህዋሲው የተያዙ ዜጎቿ ቁጥር ከአሜሪካና ከሕንድ ቀጥሎ ከዓለም 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። https://www.bbc.com/amharic/54054552 +sports ሹራ ቂጣታ፡ “የለንደን ማራቶንን ያሸነፍኩት በቀነኒሳ ምክር ነው” "ከትናንት በስቲያ እሁድ ዕለት በተካሄደው የለንደን ማራቶንን በማሸነፍ ዓለምን ያስደነቀው አትሌት ሹራ ቂጣታ የድሉ ምክንያት የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ምክር መሆኑን ለቢቢሲ ተናገረ። ሹራ ከውድድሩ በፊት ከአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ጋር ልምምድ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሶ፤ ቀነኒሳ እግሩ ላይ ባጋጠመው ጉዳት በውድድሩ ሳይሳተፍ መቅረቱን ያስታውሳል። ""ከውድድሩ በፊት ቀነኒሳ ብዙ ምክር ለግሶኛል። ቀድመህ ወጥተህ እንዳትመራ፣ እራስህን እየጠበክ እሩጥ፣ ከፊት ሆነህ ከንፋስ ጋር አትጋፈጥ፣ ውሃም በደንብ ውሰድ፣ ውሃ ልታነሳ ስትል ደግሞ ከሌሎች ሯጮች ጋር እንዳትጋጭ ተጠንቀቅ ብሎ መክሮኛል"" በማለት ከአትሌት ቀነኒሳ ያገኘውን ምክር ያስረዳል። • ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት ከለንደን ማራቶን ራሱን አገለለ • ኢትዮጵያዊው ሹራ ቂጣታ በለንደን ማራቶን ማሸነፍ ዓለምን አስደመመ • ''ምን እንደተፈጠረ አልገባኝም"" አትሌት ሃጎስ ገ/ሕይወት ""እኔም እሱ እንዳለኝ ነበር ያደረኩት። ወደፊትም የወጣሁት እሱ በነገረኝ ኪሎ ሜትር ላይ ነው። በዚህ ምክንያት ነው ውድድሩን ማሸነፍ የቻልኩት"" በማለት አትሌት ሹራ ውድድሩን በድል ለማጠናቀቅ የአትሌት ቀነኒሳን ምክር ወሳኝ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግሯል። የዚህ ዓመቱ የለንደን ማራቶን ላይ በኢትዮጵያዊው ቀነኒሳ በቀለና በበኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ መካከል የሚደረገውን ፉክክር ዓለም በጉጉት እየተጠባበቀ በነበረበት በመጨረሻው ሰዓት ላይ ቀነኒሳ ባቱ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በውድድሩ ዋዜማ ከውድድሩ መውጣቱ ይታወሳል። ከውድድሩ በፊት የለንደን ማራቶንን ያሸንፋል ተብሎ በስፋት ተጠብቆ የነበረው የርቀቱ የክብረ ወሰን ባለቤት ኬኒያዊው ኤሊዩድ ኪፕቼጌ ነበር። ይሁን እንጂ የተጠበቀው ሳይሆን ቀርቶ ኪፕቼጎ 8ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል። ""ሚዲያው ሲያወራና ሲያስተላልፍ የነበረው ስለ እነኪፕቾጌ ነበር"" ያለው ሹራ፤ ይህን ውድድር ለማሸነፍ እልህ አስጨራሽ ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበረ ለቢቢሲ ገልጿል። ""ወድድሩ ከባድ ነበር። የአየር ሁኔታውም ዝናባማ ነበር። ጠንካራ አትሌቶችም ነበሩበት፤ ይሁን እንጂ 80 በመቶ ውድድሩን እንዳሸንፍ የሚያስችለኝን ጠንካራ ዝግጅት አድርጌ ስለነበረ ለድል በቅቻለሁ"" ሲል አትሌት ሹራ ቂጣታ ያደረገውን ዝግጅት ተናግሯል። ኬኒያዊው አትሌት ኪፕቾጌ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ በውድድሩ ለመሸነፉ ዋነኛ ምክንያት በውድድሩ ላይ እያለ በጆሮው ላይ ባጋጠመው እክል ምክንያት መሆኑን አስፍሮ ነበር። ""ከ25ኛው ኪሎ ሜትር በኋላ ጆሮዬ ተደፍኖ አልከፈት አለኝ። ስፖርት እንዲህ ነው። ሽንፈ���ን ተቀብለን በቀጣይ ለማሸነፍ ማተኮር አለብን"" ያለው አትሌት ኪፕቾጌ ለተደረገለት ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቧል። አትሌት ኪፕቾጌ በውድድሩ ለመሸነፉ ዋነኛው ምክንያት ጆሮው መደፈኑ መሆኑን በገለፀበት ጽሁፉ አስተያየት መስጫ ሥር በአትሌት ሹራ ስም በተከፈተ ገጽ ምክንያቱን የሚያጣጥል ምላሽ ተሰጥቶ በርካቶች ሲጋሩት ነበር። ይህንን በተመለከተ በቢቢሲ የተጠየቀው አትሌት ሹራ፤ ውድድሩ ከተጠናቀቀ በኋላም ከኪፕቾጌ ጋር እንዳልተገናኙ እንዲሁም ከኪፕቾጌ የፌስቡክ ጽሑፍ ሥር በስሙ የተሰጠው አስተያየት የእርሱ አለመሆኑን ተናግሯል። የ2018 ለንደን ማራቶን በ2ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው አትሌት ሹራ ቂጣታ የዚህ ዓመቱ የማራቶን ድል ""ትልቅ ደስታ እና መነሳሳትን ፈጥሮልኛል"" ብሏል። ""በሽልማት በኩል ለውድድሩ አሸናፊው የተሰጠው ከነበረው የሽልማት መጠን የዘንድሮ በ50 በመቶ ቀንሷል። 30 ሺህ ዶላር አካባቢ ነው የተሸለምኩት። ሌሎች ሽልማቶችም ይኖራሉ"" ሲል አትሌት ሹራ ቂጣታ ለቢቢሲ ተናግሯል። በሹራ ቂጣታ አሸናፊነት የተጠናቀቀው የለንደኑ የወንዶች ማራቶን ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያን ሯጮች በበላይነት አጠናቀዋል። በዚህም መሰረት በውድድሩ ሁለተኛ ከወጣው ኬንያዊው ቪንሰንት ኪፕቹምባ ውጪ ከአንድ አስከ ስድስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቁት ኢትዮጵያውያን ናቸው። አሸናፊው ሹራ ቂጣታ፣ ሦስተኛ ሲሳይ ለማ፣ አራተኛ ሞሰነት ገረመው፣ አምስተኛ ሙሌ ዋሲሁን እና ስድስተኛ ታምራት ቶላ ተከታትለው በመግባት አሸናፊ መሆናቸው ይታወቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54424934 +business አበባ ምርት፡ በዘንድሮው የፍቅረኞች ቀን ከአበባ ምርት ከፍተኛ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ በዘንድሮው የፍቅረኞች ቀን ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከላከችው የአበባ ምርት ከፍተኛ ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ። የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማኅበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ኢትዮጵያ በዘንድሮው የፍቅረኞች ቀን 3 ሺህ ቶን አበባ ወደ ውጭ መላኳንና ከዚህም 55 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በዋጋም በመጠንም ጭማሬ ማሳየቱን የገለጹት ዳይሬክተሩ በዘንድሮው ገበያ የአበባ ዋጋ የ20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል። ለዚህ የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል። በአውሮፓ ባጋጠመው የነዳጅ ዋጋ መጨመር ብዙ አበባ አምራቾች የሚጠበቀውን ያህል ማምረት አለመቻላቸው እንዲሁም ከአፍሪካ በተለይ ከኬንያ የሚላከው አበባ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ በገጠመው የካርጎ ችግር ምክንያት ብዙ አበባ አለመላኩ የኢትዮጵያ አበባ ተጠቃሚ እንዲሆን ካስቻሉ ምክንያቶች ዋና ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ወደ ውጭ ከላከችው የአበባ ምርት 530 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ያገኘች ሲሆን ይህም አገሪቷ ወደ ውጭ ከምትልከው አጠቃላይ ገቢ 15 በመቶ የሚሆነውን እንደሚይዝ አቶ ቴዎድሮስ አስታውሰዋል። በየዓመቱ በአውሮፓውያኑ ፌብሩዋሪ 14 የሚከበረው የቫላንታይንስ ቀን (የፍቅረኞች ቀን) ሰዎች ለፍቅረኛቸው፣ ለትዳር አጋራቸው፣ ለእጮኛቸው አበባ እና ሌሎች ስጦታዎችን በማበርከት ፍቅራቸውን የሚገልጹበት ዕለት ነው። ይህንን ዕለት ጨምሮ እስከ ሰኔ ያሉት ጊዜያት የእናቶች፣ የሴቶች እና የአባቶች ቀን የሚከበሩበት በመሆኑ ከፍተኛ የአበባ ሽያጭ የሚከናወንበት ወቅት ነው። በመሆኑም ከፍቅረኞች ቀን በኋላ ባሉት ጊዜያት ከፍተኛ የአበባ ሽያጭ እንደሚከናወን ይጠበቃል ብለዋል ዳይሬክተሩ። የኢትዮጵያ አበባዎች የሚላኩት ወደየትኞቹ አገራት ነው? የኢትዮጵያ የአበባ ምርቶች በአጠቃላይ ወደ ኢ��ዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻ አገራት ይላካሉ። በአሁኑ የፍቅረኞች ቀን በብዛት የተላኩት ወደ አውሮፓ ነው። ኔዘርላንድስ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን ፣ ጣሊያን እና ሌሎችም አገራት። ወደ ሰሜን አሜሪካ እና ካናዳ ፣ ወደ ሩቅ ምሥራቅ ደግሞ ጃፓንና ኮሪያ እንዲሁም አውስትራሊያም ተልከዋል። በዋናነት የኢትዮጵያ የአበባ ምርት ትልቁ መዳረሻ ግን የዓለም የአበባ ንግድ ማዕከል የምትባለው ኔዘርላንድስ እና ጀርመን መሆናቸውን አቶ ቴዎድሮስ ገልጸዋል። ኔዘርላንድስ በዓለም አቀፍ ደረጃ አበባ ከሚያመርቱ እና ከሚልኩ አገራት ግንባር ቀደም ናት። ኔዘርላንድስ ብዙ አበባ ባታመርትም ወደ ውጭ በመላክና ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ቀዳሚውን ሥፍራ ትይዛለች። ከዚያም ኮሎምቢያ፣ ኢኳዶር፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ ይከተላሉ። ኢትዮጵያ ከአምስቱ የአበባ አምራችና ላኪ አገራት ተርታ የገባችው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ነው የሚሉት ዳይሬክተሩ ምቹ የግብርና አካባቢ፣ በቂ አምራች ኃይል እና የውሃ ኃብት መኖሩ እንዲሁም ለመካከለኛው ምሥራቅ እና ለአውሮፓ ገበያ ምቹ ቦታ ላይ መገኘቷ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድም በማጓጓዙ በኩል ትልቅ ሥራ መስራቱ እዚህ ደረጃ ውስጥ እንድትካተት ያስቻሏት ምክንያቶች ናቸው ብለዋል። አሁን ላይ ያለው የመሬት አቅርቦት ችግር ከተፈታ ከዚህም በላይ የአበባ ምርት ንግዱን ማሻሻል እንደሚቻል ጠቁመዋል። በዚህ ዘርፍ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬም በአገሪቷ ውስጥ ያለውን የወጪ እና የገቢ ንግድ ጉድለት ለመሙላት እንደሚያግዝም አክለዋል። ለፍቅረኞች ቀን የሚፈለጉት አበባዎች ምን ዓይነት ናቸው? ለፍቅረኞች ቀን በዋናነት የሚላከው ቀይ አበባ [ ጽጌሬዳ አበባ] ነው። ተፈላጊነቱም ሆነ ዋጋው ከሌሎች የበለጠ ነው። ዘንድሮ 20 በመቶ የዋጋ ጭማሬ አለው። ካርኔሽን እና የበጋ አበባም በዚህ ወቅት ተፈላጊ ሲሆኑ የእነርሱ ግን ጭማሬያቸው 10 በመቶ ነው። አሁን አሁን የፍቅረኞች ቀን በኢትዮጵያ በተለይ በከተሞች አካባቢ በድምቀት እየተከበረ ቢሆንም በአገር ውስጥ ያለው የአበባ ገበያ ግን በዋጋም በመጠንም እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑን አቶ ቴዎድሮስ ገልጸዋል። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ተቀዛቅዞ የነበረው የኢትዮጵያ የአበባ ንግድ ከግንቦት 2020 ወዲህ ገበያው ተነቃቅቶ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መምጣቱን አቶ ቴዎድሮስ አክለዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-60377982 +health ኮቪድ ያሰራጨው የቬትናም ዜጋ አምስት ዓመት ተፈረደበት አንድ ቬትናማዊ ግለሰብ የኮቪድ-19 መመሪያዎችን በመጣስ እና ቫይረሱን በማሰራጨት ወንጀል ተከስሶ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የአምስት ዓመት እስር ተፈረደበት። ሊ ቫን ትሪ አደገኛ እና ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ የሚተላለፍ በሽታን በስምንት ሰዎች ላይ በማሰራጨት ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑን ተከትሎ ነው ፍርድ ቤቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈበት። ግለሰቡ ኮቪድ ካስያዛቸው ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ ህይወቱ አልፏል ተብሏል። እስከ ቅርብ ጊዜያወት ድረስ ቬትናም የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በመቆጣጠርና ጥብቅ መሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ስኬታማ አገር ነበረች። ነገር ግን ከባለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ አዲሱ ዴልታ የተሰኘው የቫይረሱ ዝርያ በአገሪቱ መከሰቱን ተከትሎ በርካቶች በቫይረሱ እየተያዙ ነው። እስካሁን ድረስም በቬትናም ከ530 በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 13ሺህ 300 ሰዎቸው ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል። ነገር ግን ከዚህ ቁጥር አብዛኛው የተመዘበው ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ መሆኑ ነገሮች ምን ያክል አሳሳቢ ስለመሆናቸው ማሳያ ነው ተብሏል። በስርጭት ደረጃ ደግሞ ሆ ቺ ሚኒ ከተማ ውስጥ በርካቶች በቫይረሱ ተይዘዋል። በሰኔ ወር መጀመሪያ አካባቢ ጥፋተኛ ���ተባለው የ28 ዓመቱ ሊ ከሆ ቺ ሚኒ ከተማ ተነስቶ ወደ ትውልድ አካባቢው ካ ማው ግዛት በሞተር ሳይክል ተጉዟል። ካ ማው ከደረሰ በኋላ ደግሞ ስለ ጉዞ ታሪኩ እና ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ለተጠየቀው ጥያቄ ሀሰተኛ መረጃ ሰጥቷል፤ በተጨማሪም እራሱን መለየት ሲገባው ይህንን መመሪያ ተግባራዊ አላደረገም። የአካባቢው ባለስልጣናት ከወራት በፊት እንዳስታወቁት ማንኛውም ተጓዥ ወደ ካ ማው ግዛት ሲገባ እራሱን ለ21 ቀናት ላይቶ ማቆየት ግዴታ ነው። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ሊ የኮቪድ19 ምርመራ ሲደረግለት በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሲሆን በወቅቱም ቫይረሱን ለቤተሰቡ አባላት እንዲሁም ለህክምና የሄደበት የጤና ማዕከል ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችን አስይዟል። ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ከሰማ በኋላ ሊ አምስት ዓመት እስራት እና 880 ዶላር መቀጮ ፈርዶበታል። https://www.bbc.com/amharic/58463475 +politics የአሜሪካ ምክር ቤት አባሉ ከአንድ አፍሪካዊ ባለሀብት ገንዘብ መቀበላቸው ተረጋገጠ "ከአንድ አፍሪካዊ ቢሊየነር የገንዘብ ድጋፍ ስለማግኘታቸው ዋሽተዋል የተባሉ የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ከእንደራሴነታቸው ሊባረሩ እንደሚችሉ ተነገረ። ጄፍ ፎርተንቤሪ የተባሉት የኔብራስከካ ግዛት የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይ፣ ከስኬታማው ናይጄሪያዊ የንግድ ሰው ጊልበርት ቻጉሪ ሕገወጥ የገንዘብ ድጋፍ ስለመቀበላቸው ለአገር ውስጥ የምርመራ ተቋም ኤፍቢአይ መዋሸታቸውን የፌደራል ዳኞች ደርሰውበታል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በሦስት ጥፋቶች አስከ 15 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ለፈረድባቸው ይችላል። ይህ ጉዳይም የውጭ ተጽእኖ ፈጣሪዎች በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ሊያሳድሩ የሚችሉትን ጫና በተመለከተ ከዚህ በፊት የነበረውን ክርክር መልሶ ቀስቅሶታል። ምንም እንኳን የውጭ ዜጎች ለፖለቲካ ጉዳዮች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ባይፈቀድላቸውም የ75 ዓመቱ ናይጄሪያዊ ቢሊየነር በርካታ የገንዘብ ስጦታዎችን ማበርከታቸው ይነገራል። በዚህም ከአራት ዓመት በፊት ጊልበርት ቻጉሪ የ1.8 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት በአሜሪካ መንግሥት የተጣለባቸው ሲሆን፣ የገንዘብ ስጦታውን የተቀበሉ አንዳንድ ሰዎች ላይም ምርመራ ተደርጎባቸዋል። ግለሰቡ እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 አሁን ጥፋተኛ ሆነው ለተገኙት የምክር ቤት አባል ጄፍ ፎርተንቤሪ በአንድ ዝግጅት ላይ በሌሎች ለጋሾች በኩል በሕገወጥ መንገድ የ30,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ሰጥተዋል ተብሏል። መቀመጫቸውን ፈረንሳይ ፓሪስ ያደረጉት የኢንደስትሪዎች ባለቤት የሆኑት ናይጄሪያዊው ባለሀብት ከፍ ያለ ዝና አላቸው። በአንድ ወቅት ከእስላማዊው ታጣቂ ቡድን ሔዝቦላህ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው አሜሪካ እንዳይገቡ ቪዛ ተከልክለው ነበር። ባለሀብቱ በ1990ዎቹ የናይጄሪያ ወታደራዊ መሪ የነበሩትና በኋላም በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ከአገሪቱ ካዝና ዘርፈዋል የሚባሉት የጄነራል ሳኒ አባቻ ዋነኛ አማካሪ ነበሩ። ጊልበርት ቻጉሪ ለምን እንደራሴ ጄፍ ፎርተንቤሪን ኢላማ እንዳደረጉ የታወቀ ነገር ባይኖርም የምርመራ ሰነዱ ባለሀብቱ ""ብዙም ትኩረት ከማያገኙ ግዛቶች ለሚመጡ ፖለቲከኞች የገንዘብ ድጋፍ እንዲሰጡ"" መመከራቸውን ያመለከተ ሲሆን ምክንያቱም ድጋፉ ""ትኩረት ያገኛል"" የሚል ነው። እንደራሴው 30,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያገኙ የሚገልጽ የተቀረጸ የስልክ ውይይት የተገኘ ቢሆንም፣ ለኤፍቢአይ መርማሪዎች ግን ስለገንዘቡ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ክደዋል። ዐቃቤ ሕግ ክሱን ባስረዳበት ጊዜ የምክር ቤት አባሉ ""ሥራቸውን፣ ዝናቸውንና የቅርብ አጋሮቻቸውን ለመከላከል ሲሉ በተደጋጋሚ"" ስለገንዘብ ስጦታው ደብቀዋል ብሏል። ሐሙስ እለት ሎስ አንጀለስ ውስ��� ለሁለት ሰዓታት ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኞች፣ ጄፍ ፎርተንቤሪን ሐሰተኛ ቃል በመስጠትና እውነትን ከፌደራል መርማሪዎች በመደበቅ ጥፋተኛ ብለዋቸዋል። የምክር ቤት አባሉ ላይ የቅጣት ውሳኔ የሚሰጠው ከወራት በኋላ ሰኔ ላይ ሲሆን፣ አስከዚው ድረስ ግን እንደራሴው በውሳኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል። ይህንን ተከትሎ በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራቲክና የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት እንደራሴው በፈቃዳቸው ሥራቸውን እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል። ነገር ግን ጄፍ ፎርተንቤሪን በፈቃዳቸው ከምክር ቤቱ አባልነታቸው የማይለቁ ከሆነ ከእሳቸው በፊት ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ የምክር ቤቱ አባላት እንዳጋጠማቸው ከኮንግረሱ ሊባረሩ ይችላሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-60881984 +health 'በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ህሙማን መጨመርን ተክትሎ ኦሚክሮን መግባቱን ለማረጋገጥ የናሙና ምርመራ እየተደረገ ነው' ጤና ሚኒስቴር "በኢትዮጵያ በያዝነው ሳምንት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ አዲሱ የቫይረሱ ዝርያ ኦሚክሮን ገብቶ ከሆነ ለማረጋገጥ የናሙና ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ለቢቢሲ ገለጹ። ባለፈው ሳምንት ከተመረመሩ 53 ሺህ ሰዎች መካከል 8500 በቫይረሱ ሲያዙ፣ 34 ሰዎች ሞተዋል። በተጨማሪም 440 ሰዎች የጽኑ ሕሙማን ክፍል ገብተዋል። ካለፉት ሳምንታት በተለየ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ ኦሚክሮን ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ መሆኑን ለማወቅ የናሙና ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝና ውጤቱ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይፋ እንደሚደረግ ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል። ""እስካሁን የነበረው አካሄድ ጥሩ ነበር። ነገር ግን ከታኅሳስ 7/2014 ዓ. ም. ወዲህ ባሉት ቀናት በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው"" ብለዋል። የዛሬ ሳምንት ገደማ ከሚመረመሩ ሰዎች 3% ብቻ ቫይረሱ ይገኝባቸው የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት ግን ቁጥሩ ወደ 28% እንዳደገ ገልጸዋል። ""በሌሎች አገሮች የሚታየው ኦሚክሮን ዝርያ በኢትዮጵያም ምልክቶቹ ታይተዋል። በአስጊ ሁኔታ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል። አሁን ናሙና እየመረመርን ነው። በናሙና እስክናረጋግጥ ድረስ ኦሚክሮን መግባቱን በይፋ ለመናገር ያስቸግራል"" ሲሉ ዶ/ር ደረጄ አብራርተዋል። በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመርምረው 382 ሺህ ቫይረሱ ሲገኝባቸው፤ 6880 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ሕዝቧ ወደ 10 ሚሊዮን ገደማ ዜጎችን ከትባለች። ዶ/ር ደረጄ እንዳሉት፤ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት ዜጎች ክትባት እንዲወስዱ ከማበረታታት ባሻገር ከዚህ ቀደም የተከተቡ ሰዎች ማጎልበቻ (ቡስተር) እንዲወስዱ እንደሚደረግም ጠቁመዋል። ከ100 በላይ አገሮች ውስጥ የተገኘው የኦሚክሮን ዝርያ በፍጥነት በመሰራጨት ላይ ነው። በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ ትናንት ከተመረመሩ 13147 ሰዎች መካከል 3793 ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ጤና ሚኒስትር ገልጿል። ""በቫይረሱ በድጋሚ የመያዝ ዕድል አለ። ማኅበረሰቡ ወረርሽኙ 'ውሸት ነው' ወይም 'ለፖለቲካ ነው' ሳይል ክትባት ይውሰድ። ስለ ክትባት ሐሰተኛ ወሬ ማሰራጨት ያቁም። ከዚህ ቀደም እንደነበረው ለሕሙማን አልጋ የጠፋበት ደረጃ እንዳንደርስ ተጠንቀቁ"" ሲሉ አሳስበዋል። የጤና ሚኒስቴር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ከሚወስዳቸው እርምጃዎች መካከል፤ የጤና ባለሙያዎች በአስገዳጅ ሁኔታ ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ እንዲሁም ያልተከተቡ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የመንግሥት የነጻ ሕክምና ተጠቃሚ እንይሆኑ ማድረግ መሆኑን ዶ/ር ደረጄ ጠቅሰዋል። ""አሁን ላይ ከሚመረመሩት ሰዎች አንድ ሦስተኛ��� ቫይረሱ እየተገኘባቸው ስለሆነ የጥንቃቄ እርምጃ መወሰድ አለበት። ማኅበረሰቡ ማስክ ማድረግ፣ ክትባት መከተብም ይገባዋል"" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የጤና ሚኒስቴር የወረርሽኙን ስረጭት ለመከላከል የሚያወጣቸውን ሕጎች በማስተግበር ረገድ ሕግ አስፈጻሚው አካል ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል። በተጨማሪም የጥንቃቄ እርምጃዎችን ማኅበረሰቡ እንዲተገብር ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እስከ ቀበሌ የሚወርድ ንቅናቄ እንደሚደረግ ጠቁመዋል። ለገና በዓል ከሚመጡ ዳያስፖራዎች ጋር በተያያዘ የምርመራ ውጤት እና የክትባት ሰርተፍኬት ከማረጋገጥ አንስቶ ክትባቱን አገር ውስጥ እስከማቅረብ ድረስ እንደሚዘጋጁ ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59778547 +business በፈረንሳይ ሲኒማዎች ላይ የሲጃራ ጭስ ለምን ያለቅጥ ይንቦለቦላል? "ሰፊ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የፈረንሳይ ፊልም ኢንዱስትሪ በሲጃራ ጭስ የታፈነ ይመስላል። የጸረ ትምባሆ አቀንቃኞች ይህ ሁኔታ ይከነክናቸዋል። አንዳንድ ጊዜም ያስቆጣቸዋል። እውነት አላቸው። በምድራችን ላይ ሲጃራ በፈረንሳይ ሲኒማ የሚታየውን ያህል በየትኛውም ዓለም አይታይም። ሆሊውድንም ቦሊውድንም ጨምሮ። በቁጥር እናስደግፈው? በአማካይ በማንኛውም የፈረንሳይ ሲኒማ ውስጥ የማጨስ ትዕይንት 2 ደቂቃ ከ6 ሰኮንዶች ይይዛል። ይህ አማካይ አሐዝ ነው። ይህ ማለት ስድስት ራሳቸውን የቻሉ ማስታወቂያዎች የሚሄድበት ሰዓት ማለት ነው። በሌላ አነጋገር የፈረንሳይ ሲኒማ በጭስ ተደብቆ ያለ ነው የሚመስለው። የፈረንሳይ ጸረ ካንሰር ማኅበር ነው እዚህ ስሌት ላይ ደምሮና ቀንሶ የደረሰበት። ብቻ ምን አለፋችሁ ትምባሆ ለፈረንሳይ ሲኒማ ደምና አጥንት ሆኗል ይላሉ አንድ የማኅበሩ ባልደረባ። ይህ የሲጃራ ትዕይንቶች ድግግሞሽ በተለያየ መልኩ የሚገለጽ ነው። ለምሳሌ በቀጥታ ተዋንያን ሲያጨሱ መታየት፣ ወይም በሲጃራ ዙርያ ሲወያዩ መስማት፣ ወይም በሌላ። አደጋው ሥነ ልቦናዊ ነው። በሁሉም ሲኒማዎች ቅንጡና ዘናጭ አጫሽ ተዋንያን በቄንጥ ትምባሆ ሲያንበለብሉ የሚያዩ ሰዎች ቀስ በቀስ ነገሩን የዝመና መገለጫ አድርገው ሊወስዱት ይችላሉ። የቀድሞ የፈረንሳይ ሲኒማ ሴት ከዋክብት የነበሩት ጂን ሞሪ እና ብሪጊት ባርዶት ሲጃራቸውን በቄንጥ ሲያጨሱ ማየት ለዓመታት የቀጠለ ከትዝታ የማይጠፋ ምሥል ነው። ከ2015 እስከ 2019 ብቻ በተሠሩ ፊልሞች ላይ በተሠራ አንድ መደበኛ ጥናት 150 ፊልሞች ላይ በቄንጥ የማጤስ ትዕይንት ይታያል። ይህ ታዲያ ማጨስን ብቻ ሳይሆን ትንባሆን የሚያጅቡ ቁሳቁሶች ለምሳሌ እንደ አሽትሬይና መለኮሻ ላይተርን ሊያካትት ይችላል። ለምሳሌ ተዋናዮች ስለ ሲጃራ በአንድም ሆነ በሌላ አመጻድቀው ሲያወሩ የሚያሳዩ ትዕይንቶችን የሚጨምር ነው። ለመሆኑ ተመልካቾች የሲጃራ ትዕይንቶችን ሲመለከቱ ምን ይሰማቸዋል? አንድ የቅርብ ጊዜ ጥናት እንዳመለከተው በነዚህ ፊልሞች ላይ 60 ከመቶ የሚሆኑ ተመልካቾች በትዕይንቱ እንደተማረኩ አምነዋል። በፈረንሳይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአንጻራዊ ሁኔታ ሲጃራ አጫሽ ቀንሷል። ያም ሆኖ ሲጃራና ሲጃራ ማጨስ በሲኒማዎች ውስጥ አሁንም እንደ ትኩስ ፋሽን እየተንሰራፋ ነው። በፈረንሳይ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከአንድ ሚሊዮን ዜጎች በላይ ማጨስ እንዳቆሙ በቅርብ ጊዜ ተዘግቦ ነበር። ሲኒማው ግን ይህን አያንጸባርቅም። አንዳንድ ጊዜ ፊልሞች መሬት ላይ ካለው እውነታም በላይ ሲጃራና ማጨስን በልዩ ሁኔታ ሲያዳንቁት መታየቱ አስገራሚ የሆነውም ለዚሁ ነው። ""ይህ ሁኔታ ማጨስን ጤናማ አድርገው ሰዎች እንዲረዱት የሚያደርግ ነው"" ይላሉ የማኅበሩ ባልደረባ። አሁን የጸረ ትንባሆና የጸረ ካንሰር ማ��በራት እየጠየቁ ያሉት የፈረንሳይ መንግሥት የሲጃራ ትዕይንት ያለቅጥ የሚያሳዩ ሲኒማዎችን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ አደብ እንዲያሲዛቸው ነው። አንዱ አደብ ማስያዣ መንገድ በርካታ የሲጃራ ማጨስና ከዚያ ጋር ተያያዥ የሆኑ ትዕይንቶች ላሉባቸው ፊልሞች ለሲኒማ የሚሰጠውን ድጎማ እየቆረጡ መቅጣት ሊሆን ይችላል። ማቲው ካዞቪትዝ በፈረንሳይ ሥመ ጥር የፊልም ዳይሬክተር ናቸው። ይህን ሐሳብ ፈጽሞ አይቀበሉትም። ""ፊልሞች የኅብረተሰብ ተምሳሌት ለመሆን አይደለም የሚሠሩት። ፊልሞች የሚሠሩት የኅብረተሰቡን ኑሮ ለማንጸባረቅ ነው"" ይላሉ። የሲጃራ ትዕይንት በሲኒማ ላይ ይቀነስ የሚለው ሐሳብ ከንቱና ጸረ ኪናዊ እንደሆነ ተሟግተዋል። በተለያዩ ጊዜ የተጠኑ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከየትኛውም አገር በላይ በፈረንሳይ ሲኒማዎች የትምባሆ ትዕይንቶች ይስተዋላሉ። በአሜሪካ ከ2010 እስከ 2018 ብቻ በወጡ ሲኒማዎች 46 ከመቶ የሚሆኑት አንድ ገጸ ባህሪ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ሲያጨስ ወይም ከሲጃራ ጋር የተያያዘ ተግባር ሲከውን ይታያል። የፈረንሳይ የፊልም ፕሮዲውሰሮች ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት ዣቪየር ሪጎልት የሲጃራ ትዕይንት በሚያሳዩ ፊልሞች ላይ መንግሥት ቁጥጥር ያድርግ የሚለው ዘመቻ መስመር ያለፈ ነው ብለዋል። ""መስመር ያለፈ ብቻ ሳይሆን የፈጠራ ነጻነትንም የሚጋፋ ነው"" ይላሉ። ዣቪየር ጨምረው ሲኒማ ስለ ኅብረተሰቡ ምናገባው፤ ኅብረተሰብ ለማስተማር አይደለም ፊልም የምንሠራው ብለዋል። በ60ዎቹ የገነነው የፈንሳይ ሲኒማ በጭስ ተደብቆም ተወዳጅነቱ ቀጥሏል። በሲጃራም ያለ ሲጃራም።" https://www.bbc.com/amharic/news-57271010 +politics ኢራናውያን አዲስ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ድምጽ እየሰጡ ነው "ሐሰን ሩሃኒን የሚተኩ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ኢራናውያን ዛሬ አርብ ድምጽ እሰጡ ነው። ከሕዝብ በተሰበሰበ አስተያየት መሠረት የፍትህ ሥርዓቱን በበላይነት የሚመሩት ወግ አጥባቂ የሺአ መሪ ኢብራሂም ራይሲ ያሸንፋሉ ተብሎ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል። የቀድሞው ማዕከላዊ ባንክ ገዥ አብዶልናስር ሄማቲ ተቀናቃኛቸው ናቸው። በርካታ ተፎካካሪዎች እንዳይወዳደሩ መታገዳቸው ራይስን ያለ ከባድ ተፎካካሪ እንዳስቀራቸው በመጥቀስ ተቃዋሚዎች እና አንዳንድ የለውጥ አራማጆች ሕዝቡ እንዳእመርጥ ጥሪ አቅርበዋል። ሐይማኖታዊው መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ አርብ ማለዳ ዋና ከተማዋ ቴህራን ውስጥ ድምጻቸውን ከሰጡ በኋላ ሰዎች እንዲመርጡ አበረታተዋል። ""እያንዳንዱ ድምጽ ዋጋ አለው። ይምጡና ፕሬዝዳንትዎን ይምረጡ። ይህ ለአገርዎ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አስፈላጊ ነው"" ብለዋል። አሜሪካ ከሦስት ዓመት በፊት ከኢራን ጋር የደረሰችውን የኒኩሌር ስምምነትን ወደ ጎን አድርጋ ማዕቀቦችን ወደነበሩበት ከመለሰችበት ጊዜ ጀምሮ በደረሰው የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት በኢራናውያን ዘንድ ሰፊ ቅሬታ አለ። ከተፎካካሪዎቹ አንዱ ቢያሸንፉ በኢራን እና በዓለም ኃያላን መካከል ስምምነቱን እንደገና ለማደስ ዓላማ ያደረገው ድርድር ያደናቅፋል ተብሎ አይታሰብም። ለዘብተኛው ሩሃኒ ከምዕራባውያን ጋር ለመግባባት ይፈልጉ የነበረ ቢሆንም ለሁለት ተከታታይ አራት ዓመታት የሥልጣን ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸውን በድጋሚ መወዳደር አይችሉም። ዕጩዎቹን ማን አፀደቀ? 40 የሚሆኑ ሴቶችን ጨምሮ ወደ 600 የሚጠጉ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ዕጩ ሆነው ተመዝግበዋል። የዕጩ ተወዳዳሪዎችን ብቃት በተመለከተ የመጨረሻ ውሳኔ ያለው ያልተመረጠ አካል ሲሆን 12 የሕግ ባለሙያዎች እና የሐይማኖት ምሁራንን የያዘ ነው። በዚህ አካል ሰባት ዕጩዎች ለፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ ፈቃድ ሰጠቷል። እንዲወዳደሩ ካልተፈቀደላቸው ታዋቂ ዕጩዎች መካከል የሩሃኒ የመጀመሪያው ምክትል ፕሬዝዳንት ኢሻቅ ጃሃንጊሪ እና ወግ አጥባቂውና የፓርላማ አፈ ጉባኤ የነበሩት አሊ ላሪጃኒ ይገኙበታል። ሐሙስ ድረስ እንዲወዳደሩ ከተፈቀደላቸው ዕጩዎች መካከል ሦስቱ (የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ጸሐፊው ሰዒድ ጃሊሊ፣ የፓርላማ አባሉ አሊሬዛ ዛካኒ እና የለውጥ አራማጁና የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ሞህሰን መህላራሊዛዴህ) ራሳቸውን አግልለዋል። ጠንካራ አቋም ያላቸው ጃሊሊ እና ዛካኒ ሁለቱም ራይስን ደግፈው የቆሙ ሲሆን መህላራሊዛዴህ ደግሞ የውጥ ኃይሉን ""አንድ ለማድረግ"" እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ይህም ለሔማቲ ግልጽ ድጋፍ መስጠት ነው ተብሏል። አንድ ተወዳዳሪ በአንደኛው ዙር ከ50 በመቶ በላይ ድምጽ ካላገኘ ሁለተኛ ዙር ምርጫ ይካሄዳል። በውድድሩ እነማን ይሳተፋሉ? ኢብራሂም ራይሲ የ60 ዓመቱ ሐይማኖታዊ መሪ አብዛኛውን የሥራ ዘመናቸውን በዐቃቤ ሕግነት አገልግለዋል። ባለፈው ምርጫ በሩሃኒ ከተሸነፉ ከሁለት ዓመታት በኋላ እአአ በ2019 የፍትህ ዋና ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። ራይስ ሙስናን ለመዋጋት እና የኢራንን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት የተሻሉት ሰው እንደሆኑ እያስረዱ ነው። ብዙ ኢራናውያን እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በ1980 ዎቹ በፖለቲካ እስረኞች የጅምላ ግድያ ላይ ሚና አለቸው በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል። አብዶልናሰር ሔማቲ የ64 ዓመቱ ባለሙያ እአአ በ2018 የኢራን ማዕከላዊ ባንክ ገዢ የነበሩ ሲሆን ዕጩ ከሆኑ በኋላ ግን ከኃላፊነት ተነስተዋል። በሩሃኒ እና በቀድሞው ፕሬዝዳንት መሐሙድ አህመዲነጃድ ስር መሾማቸው በኢራን ያሉትን ሁሉንም አንጃዎች በጋራ የማሠራት ብቃት እንዳለቸው ማስረጃ ተደርጎ ታይቷል። የአሜሪካ ማዕቀብ የኢራን ገንዘብ ምንዛሬ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለማቃለል ባለመቻላቸው ከሌሎቹ ዕጩዎች ትችት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል። ሞህሲን ረዛይ የ66 ዓመቱ ረዛይ መንፈሳዊውን መሪ በበላይነት የሚያማክሩና በሕግ ጉዳዮች ላይ በሚነሱ አለመግባባቶች የመጨረሻ የመዳኘት ስልጣን ያላቸው የምክር ቤት ጸሐፊ ናቸው። እአአ ከ1988-88 በኢራን እና ኢራቅ ጦርነት ወቅት የእስላማዊው አብዮታዊ ዘብ ቡድን አዛዥ ነበሩ። መከላከያ ኃይሉን ከለቀቁ በኋላ ለሦስት ጊዜያት ለፕሬዝዳንትነት ዕጩ ሆነው ተወዳድረዋል። አሚርሆሴን ቀዚዛዴህ ሃሸሚ አሚርሆሴን ቃዚዛዴህ ሃሸሚ የአንገት በላይ የቀዶ ጥገና ሐኪም ናቸው። ከ2008 ጀምሮ የፓርላማ አባል የነበሩ ሲሆን ከግንቦት ወዲህ ደግሞ ተቀዳሚ አፈ-ጉባኤ ናቸው። የ50 ዓመቱ ዕጩ ከተወዳዳሪዎቹ መካከል በዕድሜ ትንሹ ናቸው። የሕዝብ ተሳትፎ ለምን አስፈላጊ ሆነ? 80 ሚሊዮን ሕዝብ ባላት ኢራን 59 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ድምጽ ለመስጠት ብቁ ናቸው። በ2017ቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተሳታፊዎች 73 በመቶ ቢሆንም በመንግሥት በሚደገፈው የኢራን ሰቱደንትስ ፖሊንግ ኤጀንሲ ባደረገው ጥናት ግን በአርቡ ምርጫ 42 በመቶዎቹ ብቻ ሊሳተፉ እንደሚችሉ ጠቁሟል። ይህ እአአ ከ1979ቱ እስላማዊ አብዮት በኋላ በኢራን ከተደረጉት ምርጫዎች ይህ ዝቅተኛ ተሳትፎ የሚኖረው ሲሆን ተመራጩም የመራጮች ቁጥርን እንደ ድጋፍ ስለሚያየው ችግር ሊደቅን ይችላል። ሩሃኒ ሐሙስ ለኢራናውያንን ""የተቋም ወይም የቡድን ጉድለቶች"" ድምጽ ከመስጠት እንዳያስቆሟቸው ነግረዋቸዋል። ""ለጊዜው ስለነገ ለቅሬታዎች አናስብ"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57519045 +business ለላይቤሪያው ፕሬዚዳንት ልደት ትልልቅ ሰሌዳዎች መሰቀላቸው አነጋጋሪ ሆኗል የላይቤሪያው ፕሬዘዳንት ጆርጅ ዊሃ 55ኛ ልደት በአል መቃረብን ተከትሎ ዋና ከተማዋ ሞኖሮቪያ በትልልቅ የመልካም ልደት መግለጫ ቢልቦርዶች ተሞልታለች። ከሁለት ቀናት በኋላ ልደታቸው የሚያከብሩት ፕሬዘዳንቱ እነዚህ ሰሌዳዎች እየቆሙላቸው የሚገኘው በሞኖሮቪያ ከተማ ምክርቤት ሲሆን በተለይም በማዕከላዊ ሞኖሮቪያ በብዛት ተሰቅለው ታይተዋል። አሁንም በርካታ ቢልቦርዶች በመሰቀል ላይ ሲሆኑ ሁሉም ሰሌዳዎቹ ተመሳሳይ መልክት ይዘዋል። «ሁሉም መሪዎች እርስዎን መሆን አለባቸው። ምክኒያቱም እርስዎ የብቃት ፍጹም ምሳሌ ስለሆኑ። መልካም ልደት አለቃ። በልቦት ውስጥ የተሸሸጉት ህልሞችዎ እውን ይሁንልዎት» ሲል በቢልቦርዶቹ ላይ የተከተበው መልዕክት ይነበባል። የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ፕሬዚዳንቱ ይህ ይገባቸዋል የሚሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። የመሪያቸውን ፎቶ በመላው ከተማዋ በመመልከታቸው ደስተኞች ናቸው። ነገር ግን የፕሬዘዳንቱ ተቺዎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። በኢኮኖሚ ቀውሶች ውስጥ የምትገኘው ላይቤሪያ አብዛኛው ህዝቧ ድሀ ሆኖ እያለ ቢልቦርዶቹ ይዘውት የወጡት መልዕክት ግን ግዴለሽነትን ያንጸባርቃል ሲሉም ተችተዋል። የሞኖሮቪያ ከንቲባ ጄፈርሰን ኮጄም ቢሆኑ በቅርቡ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ልደታቸውን ድል አድርገው አክብረዋል። ደጋፊዎቻቸው የአደባባይ ትርኢት ጭምር አቅርበዋል። የእርሳቸውም ምስሎች በትልልቅ ሰሌዳዎች በሞኖረቪያ ጎዳናዎች ላይ ተሰቅለው ታይተው ነበር። https://www.bbc.com/amharic/news-58716167 +health በዩናይትድ ኪንግደም በኦሚክሮን የተያዙ ሰዎች ከ10 ሺህ በላይ ሆነ "አዲሱ የኮሮናቫይረስ ልውጥ ኦሚክሮን ወረርሽኝ ከቀን ወደ ቀን በጨመረባት ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እስካሁን ባለው ከ10 ሺህ ሰዎች በላይ በኦሚክሮን መያዛቸው ተገልጿል። ይህንንም ተከትሎ በለንደን 'ትልቅ ክስተተት' የተሰኘ አዋጅ ተደንግገጓል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ ባገረሸባት ዩናይትድ ኪንግደም ከቀናት ከፍተኛ የቁጥር ጭማሪ በኋላ ቅዳሜ ዕለት ብቻ 90 ሺህ 418 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጣለች። የጤና ዘርፉ አማካሪዎች ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉና አዳዲስ እርምጃዎች ካልተወሰዱ በየቀኑ ሆስፒታሎች የሚተኙ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። የለንደኑ ከንቲባ ሳዲቅ ካን በመዲናይቱ የታወጀው ትልቅ ክስተት ""ነገሮች ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆኑ"" ያሳያል ብለዋል። ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ሚኒስትሮች ስለ አዲሱ የኮቪድ መረጃ አጭር መግለጫ ተሰጥቷቸዋል። ከዚህ ቀደም ከነበረው ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ገደቦች እስካልተጣሉ ድረስ በሆስፒታሎች የሚተኙ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ እንደማይቻልና እንደ ከዚህ ቀደሙም ሊያሻቅብ እንደሚችልም የመንግሥት አማካሪዎች ተናግረዋል። በእንግሊዝ ካለው የ'ፕላን ቢ' ሕግ ውጪ ጣልቃ መግባት ካልተቻለ በሆስፒታል የሚተኙ ሰዎች ቁጥር ወደ 3 ሺህ ሊያሻቅብ ይችላል ሲሉ የድንገተኛ አደጋ ሳይንሳዊ አማካሪ ቡድን (ሴጅ) አባላት ገልጸዋል። የቅርብ ጊዜ ዕለታዊ መረጃ እንደሚያሳየው 900 የኮቪድ-19 ህሙማን በእንግሊዝ ሆስፒታል ተኝተዋል። የሴጅ አማካሪዎች የኦሚክሮንን ስርጭትን ለመግታት ""በአንድ ላይ የሚሰበሰቡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ፣ አካላዊ ርቀትን መጨመር፣ አካላዊ ግንኙነቶችን ማስወገድና ከፍተኛ ስጋት ያላቸውን ቦታዎች መዝጋት"" እንደ አማራጮች አቅርበዋል። አዲሱ የኮሮናቫይረስ ልውጥ አሚክሮን በዓለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ከሰሞኑ አስጠንቅቋል። ይህ ልውጥ ዝርያ በ77 አገራት ውስጥ መኖሩ ተረጋግጧል። ኦሚክሮን የተሰኘው ልውጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በደቡብ አፍሪካ በኅዳር ወር ላይ ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር አሳይቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59716727 +health ኮሮናቫይረስ፡ በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን በአካላዊ ርቀት ምክንያት ለማፅናናት ያልቻለው ግለሰብ "በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን ለማፅናናት አቅፏት የነበረው እንግሊዛዊ አካላዊ ርቀትህን ጠብቅ መባሉ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳበሳጨው ገልጿል። ክሬይግ ቢክኔል ይህ የተነገረው ክራውንሂል በተባለው የቀብር ስነ ስርአት አስፈፃሚ ሰራተኛ ነው። ክሬይግም ሆነ ወንድሙ ወንበራቸውን ራቅ አድርገው እንዲቀመጡ ከመንገር በተጨማሪም የኃዘን ስነ ስርአቱም እንዲቋረጥ ተደርጓል። በኃዘን ልቧ ተሰብራ ከነበረው እናቱ ጎን ተቀምጦም በማፅናናትም ላይ እንደነበረ ተናግሯል። የሚልተን ኬይንስ ምክር ቤት በበኩሉ በተፈጠረው ሁኔታ ማዘኑንና ለወደፊቱም የተሻለ አማራጭ እንጠቀማለንም በማለት ምላሽ ሰጥቷል። የ43 አመቱ ክሬይግ በበኩሉ ""እናቴን ማፅናናት እንደምፈልግ ለሁሉም ተናግሬ ነበር። በከፍተኛ ሁኔታ ሃዘኗም ጨምሮ ስብርብር ስትል አቀፍኳት"" ብሏል። በአባቱ የኃዘን ስርአት ላይ ወንበሮቹ አካላዊ ርቀትን በሚያስጠብቅ መልኩ ተራርቀው የነበረ ሲሆን የናቱንም የበረታ ኃዘንም ተመልክቶ ወደናቱ የተጠጋ ሲሆን ወንድሙም ተከትሎት እናታቸውን ማፅናናት ጀመሩ። የቀብር አስፈፃሚ ሰራተኞቹም ወንበሮቹን በየቦታቸው እንዲመልሱና ማንቀሳቀስ አትችሉም ተብለዋል። በዚህ ሃዘን ላይ እያሉ እንዲህ መባላቸው ከፍተኛ ንዴትና ሃዘን እንደፈጠረበትም ገልጿል። ""በከፍተኛ ሁኔታ የባዶነት ስሜት እንዲሰማኝ አድርጓል"" ያለው ክሬይግ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልና በሰላም እንዲጠናቀቅም ከራሱ ጋር ትግል ማድረግ ነበረበት። ""ፈታኝ ነበር። የአባቴ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልም ውሳኔ ላይ መድረስ ነበረብኝ"" ያለው ክሬይግ አክሎም ""በጣም ያዘንኩበትና የፈራሁበትም ወቅት ነው፤ እንዲህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም"" ብሏል። የሚልተን ኬይነስ ምክር ቤት በበኩሉ ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ሁኔታ ተፈፅሞ እንደማያውቅና ቤተሰቡንም በማሳዘናቸው ይቅርታ ጠይቀዋል። የኃዘንም ሆነ የቀብር አስፈፃሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት ሰብሰብ ብለው ቢቀመጡም ችግር እንደሌለው ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በኃዘንም ሆነ በቀብር ስርአት ላይ መገኘት ያለባቸው 30 ሰዎች መሆናቸው በመመሪያው ላይ የተቀመጠ ሲሆን እነሱም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆኑንም አስፍሯል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54460664 +politics መፈንቅለ መንግሥት በተሞከረባት ሱዳን ሲቪል መሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ "መፈንቅለ መንግሥት መካሄዱ እየተነገረ ባለበት ጊዜ የሱዳን ሽግግር መንግሥት እና ሌሎች የሲቪል መሪዎች በቁጥጥርስ ስር መዋላቸው ተነገረ። ማንነታቸው ባልተገለጸ ወታደሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል ከተባሉት መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ እንደሚገኙበት ከካርቱም የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ምን እየተካሄደ እንደሆነ ምንም አይነት አስተያየት ያልሰጠ ሲሆን፣ የዴሞክራሲ እንቅስቃሴ ደጋፊ ቡድኖች ግን ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ እንዲቃወም ጥሪ አቅርበዋል። በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ በምትገኘው ሱዳን በሁለት ወር ውስጥ ሁለተኛው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እየተካሄደ መሆኑ የተነገረው ዛሬ ሰኞ ማለዳ ነው። በዚህም የታጠቁ ወታደሮች በርካታ የአገሪቱ የሽግግር መንግሥት አባላትን በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው እና የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን መኖሪያ ቤትን በወታደሮች መከበቡ ተዘግቧል። ባለሥልጣናቱን በቁጥጥር ስር ያዋለው ወታደራዊ አካል ማን እንደሆነ አስካሁን በይፋ የታወቀ ነገር የለም። በአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገጽ ላይ የወጣ መግለጫ እንዳለው ባለሥልጣናቱን በቁጥጥር ስር የማዋል ድርጊት የተፈጸመው ""በጥምር ወታደራዊ ኃይሎች"" መሆኑንና የተያዙት ሰዎች ያሉት ""በማይታወቅ ስፍራ"" መሆኑን አመልክቷል። ጨምሮም ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ መፈንቅለ መንግሥቱን እንዲደግፉ ግፊት ቢደረግባቸውም መቃወማቸውንና ሕዝቡ በሰላማዊ ተቃውሞ ""አብዮቱን እንዲከላከል"" ጥሪ አቅርበዋል ብሏል። ከዋና ከተማዋ ካርቱም አቅራቢያ በምትገኘው ኦምዱርማን ከተማ ውስጥ ያለውን የአገሪቱን የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና መሥሪያ ቤትን ወታደሮች ጥሰው እንደገቡ የሱዳን ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታውቋል። በተጨማሪም ወታደራዊ ኃይሎቹ በርካታ ቁጥር ያላቸው የተቋሙን ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አመልከቷል። በከባድ ሁኔታ የታጠቁ ወታደሮች እና የፀጥታ ኃይሎች በካርቱም ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ የተሰማሩ ሲሆን የነዋሪዎችን እንቅስቃሴ ገድበዋል። ኤኤፍፒ እንደዘገበው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እየተካሄደ መሆኑ ከተሰማ በኋላ የሲቪል አስተዳደሩን የሚደግፉ ሰዎች ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ ለመውጣት መሞከራቸውን ተከትሎ ወደ ዋና ከተማዋ የሚያስገቡ ዋና መንገዶችን ወታደሮች ዘግተዋል። የሱዳን መገናኛ ብዙኀን እንደዘገቡት በዋና ከተማዋ ካርቱም ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል። ልዩ መልዕክተኛዋን ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደ ሱዳን ልካ የነበረችው አሜሪካ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥትን በተመለከተ የሚወጡ ዘገባዎች ""በጽኑ እንዳሳሰባት"" ገልጻለች። በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ መንግሥት መልዕክተኛ ሆኑት ጄፍሪ ፌልትማን በሱዳን ውስጥ የሚካሄድ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ""ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እና አሜሪካን የምትሰጠውን ድጋፍ አደጋ ላይ የሚጥል ነው"" ሲሉ ትዊተር ላይ ጽፈዋል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር ከሥልጣን እንዲወርዱ ያደረገውን ሕዝባዊ ተቃውሞ የመራው የሱዳን የሠራተኞች ማኅበር፣ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ወታደራዊ መፈንቀለ መንግሥትን እንዲቃወም ጥሪ አቅርቧል። የሱዳንን የሽግግር መንግሥትን በጋራ በሚመሩት ወታደራዊ እና የሲቪል ባለሥልጣናት መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ወራት ተቆጥረዋል። ባለፉት ሳምንታት ወታደራዊ መሪዎቹንና የሲቪል አስተዳደሮቹን የሚደግፉ ሰልፎች በአገሪቱ ውስጥ ሲካሄዱ ነበር። ወታደራዊውን መሪዎች የሚደግፉት ሰልፈኞች ጦር ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ የሲቪል አስተዳደሪዎችን ከሥልጣን እንዲያስወግድ ጥሪ አቅርበዋል። በተመሳሳይ ባለፈው ሐሙስ ዕለት የሲቪል አስተዳደሩን የሚደግፉ ሱዳናውያን አደባባይ ወጥተው አገሪቱ ወደ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እንድተሸጋገር ለሲቪል መሪዎቹ ድጋፋቸውን ገልጸው ነበር። ዛሬም ሰልፈኞች ሠራዊቱ ሥልጣን ለመያዝ የሚያደርገውን ሙከራ በመቃወም እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን በመደገፍ ወደ ጎዳናዎች ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ትናንት እሁድ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ጄፍሪ ፌልትማን ከጦር ኃይሉ እና ከሲቪል መሪዎቹ ጋር ተገናኝተው አገሪቱን ወደ ሲቪል አስተዳደር አንዲያሸጋግሩ ጥሪ አቅርበዋል። ባለፈው መስከረም ወር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተሞክሮ መክሸፉ የሚታወስ፣ ይህንንም ተከትሎ የሽግግር አስተዳደሩን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ��ድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል። በዚህም ሲቪሉን በመወከል የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን አብደላ ሐምዶክ የያዙ ሲሆን ከሠራዊቱ በኩል ደግሞ የአገሪቱ ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆን ሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሐን ከፍተኛውን ቦታ ይዘዋል። ነገር ግን የሱዳንን የሽግግር አስተዳደር በሚመሩት ወታደራዊና የሲቪል ባለሥልጣናት መካከል ያለው ግንኙነት የሰከነ ሳይሆን ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የደኅንነት ሁኔታ እየተዳከመ የመጣ ሲሆን፣ ምክንያቱም ወታደራዊ መሪዎቹ ሥልጣን የሚያስረክቡበት ወቅትን ለማስተጓጎል ነው ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። በሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የሚመራው ኃያሉ የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ለሲቪሎች ሥልጣኑን በመጪው ኅዳር እንዲያስተላልፍ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59027282 +business እስያ፡ የሲንጋፖር አየር መንገድ የቆሙ አውሮፕላኖቹን ምግብ ቤት አደረገ ሲንጋፖራውያን ምሳቸውን ለመመገብ ወደ አየር መንገድ ጎራ ብለው አንድ ጥግ የቆመ A380 ኤርባስ አውሮፕላን ውስጥ መሰየም ብቻ ይጠበቅባቸዋል። በአውሮፕላኑ ውስጥ ምሳቸውን ለመመገብ የቋመጡ ሰዎች ለሁለት ቀን የተዘጋጀውን ወንበር ሙሉ በሙሉ ይዘውታል። በዚህ አውሮፕላን ውስጥ ገብቶ ለመመገብ 496 የአሜሪካ ዶላር መክፈል ይጠበቃል። አየር መንገዱ አገልግሎቱን ፈላጊዎች ስለበዙበት ሁለት ተጨማሪ ቀናትን ምሳና እናት ለማስተናገድ በማሰብ መጨመሩን አስታውቋል። የሲንጋፖር አየር መንገድ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ገበያ አጥተው ፈተና ውስጥ ከወደቁ እና ሌሎች አማራጭ ከሚፈልጉ አየር መንገዶች መካከል አንዱ ነው። አየር መንገዱ በአሁን ሰዓት ሁለት A380 ኤር ባስ አውሮፕላኖችን ለሶስት ሰዓት የምግብ መስተንግዶ እንዲሰጡ ለመጠቀም አቅዷል። ሁለቱም አውሮፕላኖች አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ በሚያስችል መልኩ ተደራጅተው በግማሽ አቅማቸው ብቻ ደንበኞችን ያስተናግዳሉ። ተመጋቢዎች እየተመገቡ ፊልም መመልከት ቢፈልጉ ወይንም ደግሞ በምቾት በተንቆጠቆተው ክፍል ውስጥ መስተናገድ ከፈለጉ መምረጥ ይችላሉ ተብሏል። አውሮፕላኑ ግን ተመጋቢዎቹን ጭኖ መሬት ለቅቆ አይበርም ተብሏል። የሲንጋፖር አየር መንገድ ምግቦቹን ፍላጎት ላላቸው ቤታቸው ድረስ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። ይህ ደግሞ የአየር መንገዱ የጥንቃቄ ኪቶችንና የጠረጴዛ ሽፋኖች ያካትታል። የሲንጋፖር አየር መንገድ በኮቪድ-19 ከተጎዱ የአየር መንገዶች መካከል አንዱ ነው ባለፈው ወር አየር መንገዱ 4300 ሰራተኞቹን እንደሚያሰናብት ገልጾ ነበር። ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበርም በሺዎች የሚቆጠሩ የአቪየሽኑ ስራዎች በኮቪድ-19 ምከንያት እንደሚጎዱ አስጠንቅቆ ነበር። 290 አየር መንገዶችን የሚወክለው ይህ ተቋም በረራዎችን ከባለፈው አመት ጋር በማነጻጸር በ 66 በመቶ ቀንሷል ብሏል። https://www.bbc.com/amharic/news-54520081 +politics በመርዓዊ ከተማ ሐሙስ ዕለት ተከሰተ ስለተባለው ሁኔታ "በምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ በትናንትናው ዕለት ሐሙስ ግንቦት 12/2013 ዓ.ም በተካሄደ ሰልፍ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በቅርቡ ለሚደረገው ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ በስፍራው ሰልፍ እንደነበረ ቢቢሲ ካገኘው መረጃ መረዳት ተችሏል። በሰልፉ ላይ የህይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት እንደደረሰ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ""ድምፃቸውን በሰላማዊ መንገድ ባሰሙ ተማሪዎች ላይ የጸጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ የሕይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት ደርሷል"" በማለት አስፍሯል። አብን ዛሬ��� በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ በተማሪዎቹ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በጥብቅ አወግዛለሁ ብሏል። በተጨማሪም ለጥቃቱ ትዕዛዝ የሰጡና የፈፀሙ አካላት ላይም መንግሥት አስቸኳይ ምርመራ እንዲያደርግና ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንዲሁም ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግም ጠይቋል። ፓርቲው አክሎም ""ገዥው የብልጽግና መንግሥት ሕዝቡ የሚሰጠውን ፖለቲካዊ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ተቃውሞንም በአግባቡ ለማዳመጥ መዘጋጀት አለበት"" ብሏል። የመርዓዊ ከተማ ኮምዩኒኬሽን ስለጉዳዩ የሰሜን ሜጫ ወረዳ ሰላምና ደኅንነት ጽህፈት ቤትን ጠቅሶ እንዳለው ፖሊስ በንጹሃን ዜጎች ላይ ተኩሶ ገድሏል እየተባለ በሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ ፍጹም ሐሰት ነው ብሏል። የሰሜን ሜጫ ወረዳ ሰላምና ደኅንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ተስፋ፤ ""በብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ወቅት ሰልፉ በሰላም እንዳይጠናቀቅ ፍላጎት ያላቸው አካላት ሁከት ለመፍጠር ሙከራ አድርገዋል"" ብለዋል። የመርዓዊ ከተማ ኮምዩኒኬሽን ኃላፊውን ዋቢ አድርጎ እንዳሰፈረው ""ሰልፉን ለማደናቀፍ የተጠቀሙባቸው ምንም የማያውቁ የአገር ተረካቢ ተማሪዎችን ነው"" ብሏል። ኃላፊው ሰልፉን ለማደናቀፍ ተማሪዎችን በሽፋንነት ተጠቅመዋል ያሏቸውን አካላት አልጠቀሱም። ነገር ግን ""የችግሩ ፈጣሪዎች አላማ በተለያየ ወንጀል ተጠርጥረው ፖሊስ ጣቢያ ማረፊያ ቤት ያሉ ሰዎችን የማስለቀቅ ነበር"" ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ተመስገን ፖሊስ ""ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል"" ያሉ ሲሆን በዚህም የድብደባ እና የአካል ማጉደል ደርሶባቸዋል ብለዋል። በፖሊስ ደረሰ ስለተባለውም ጉዳት ሲያስረዱ አንድ የፖሊስ አባል ላይ የአካል ድብደባ ሲደርስ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ሽጉጥ ተወስዷል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሰልፉን ለመደገፍ የመጡ አርሶ አደሮች ላይ ደብደባ ማጋጠሙንና በንብረት ላይ ጉዳትና ዘረፋ መፈጸሙን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት የችግሩን ፈጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን ምርመራው ከተጠናቀቀ በኋላ መረጃው እንደሚሰጥም ኃላፊው ተናግረዋል። ቢቢሲ ያናገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከድጋፍ ሰልፉ ጋር ተያይዞ ተኩስና አለመረጋጋት እንደነበር አረጋግጠው ደረሰ ስለተባለው ጉዳት የተለያየ መረጃ ሰጥተዋል። ቢሆንም ግን በሰዎች ላይ ስለደረሰ ጉዳት ከጸጥታ ኃላፊዎችና ከህክምና ተቋማት ቢቢሲ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።" https://www.bbc.com/amharic/news-57198405 +health ኮሮናቫይረስ፡ የውጭ አገር ተጓዦች የኮቪድ-19 ምርመራ ለማድረግ ፈተና ሆኖባቸዋል "አገራት ድንበሮቻቸውን በጥንቃቄ እየከፈቱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የአየር በረራ መጀመርን ተከትሎ በወጡ አዳዲስ ደንቦች ምክንያት ተጓዦች ከኮቪድ-19 ተህዋሲ ነጻ መሆናቸውን በምርመራ እንዲያረጋግጡ ይገደዳሉ። በኢትዮጵያ ይህንን ምርመራ በማድረግ ውጤት ከሚሰጡ ተቋማት መካከል የሆነውና አብዛኞቹ የውጭ አገር ተጓዦችን የሚያስተናግደው ተቋም የምርመራ ፈላጊዎች ቁጥርና አገልግሎቱ ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ተገልጋዮች እየተናገሩ ነው። የአየር በረራ አገልግሎት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ በመቆየቱ ለወራት ሲጠባበቁ የነበሩ ተጓዦች ይህንን ምርመራ ለማድረግ ከባድ ፈተና ሆኖብናል ይላሉ። ምክንያቱ ደግሞ ምርመራውን የሚያከናውነው ተቋም የወሰደውን ናሙና ውጤት ለማሳወቅ ቢያንስ 48 ሰዓታትን ይፈልጋል። አገራት ደግሞ ተጓዦች ከመሳፈራቸው በፊት ምርመራ እንዲያደርጉ የሚፈልጉበት የሰዓት ገደብ ከ48 ሰዓት እስከ 96 ሰዓት እንደየአገሩ ይለያያል። ምርመራውን ከብዙ ጥበቃ በኋላ ��ለፈው አርብ ዕለት ማድረግ የቻሉ ተጓዦች ውጤት አልደረሰም በመባላቸው በረራቸውን ለመሰረዝ እንደተገደዱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ክሊኒኩ ለተመርማሪዎች ውጤት የሚሰጠው የጉዞው ዕለት ወይም ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ በ10 ሰዓት ብቻ ነው። በዚህም ምክንያት የጉዞ ቀን፣ የሚጓዙበት አገር የምርመራ ደንብና የክሊኒኩ ውጤት መስጫ ዕለት ለማጣጣም ፈታኝ እንደሆነ ተጓዦቹ ጠቅሰዋል። ቢቢሲ ሰኞ ማለዳ ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ምርመራ በሚሰጠው ተቋም ደጃፍ ላይ ተሰልፈው ያገኛቸው ተጓዦች ተቋሙ ስለምርመራው በቂ መረጃ እንዳልሰጣቸው፣ በረራቸውን በተደጋጋሚ ለመሰረዝ እንደተገደዱና ላልተጠበቀ ወጪና መጉላላት እንደተዳረጉ ገልጸዋል። አገልግሎቱን ፈልገው ወደተቋሙ የሄዱ ሰዎች ለቢቢሲ እንደገለጹት ምርመራውን የሚያደርገው ላቦራቶሪ ሥራውን የሚያስኬድበት ግልጽ አሰራር እንዳልዘረጋም ተናግረዋል። አገልግሎት ፈላጊዎች የሚስተናገዱት በቅድሚያ በኢሜይልና በስልክ ከተመዘገቡና የጉዞ ትኬታትና የፓስፖርታቸውን ቅጂ ከሰጡ በኋላ ነው የሚል ማስታወቂያ በክሊኒኩ ደጃፍ ላይ የተለጠፈ ቢሆንም፤ በክሊኒኩ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የተጠቀሱት የስልክ መስመሮች ከአገልግሎት ወጪ ናቸው አልያም ተዘግተዋል። የኢሜይል ምላሽም ከክሊኒኩ ማግኘት አልተቻለም። የቢቢሲ ዘጋቢዎችም ይህንኑ ማረጋገጥ ችለዋል። የክሊኒኩ ሠራተኞች በበኩላቸው ሰዎች ከተመዘገቡ በኋላ በራሳቸው ምክንያት ሊቀሩ ስለሚችሉ ይህንን የቅድመ ምዝገባ አሰራር ትተን ሰዎች እንደ አመጣጣቸው ማስተናገድ ጀምረናል ይላሉ። ሰኞ ማለዳ በስፍራው ተሰልፈው ከነበሩ ተጓዦች ቢቢሲ እንደተረዳው አንዳንዶቹ ተገልጋዮች እሑድ ከቀትር ጀምሮ ለረዥም ሰዓት አገልግሎቱን ለማግኘት በዝናብ ተሰልፈው የጠበቁ ቢሆንም ""አሁን ደክሞናል ከዚህ በላይ አናስተናግድም"" በሚል እንዲበተኑ ተደርገዋል። ሌሎች ደግሞ ነገ በአዲስ መልክ አንሰለፍም በሚል ቅሬታ በማንሳታቸውና የክሊኒኩን በር አናዘጋም በማለታቸው ስም ዝርዝራቸው ተጽፎ በቀጣይ ቀን ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እንደሚስተናገዱ ቃል እንደተገባላቸው ተናግረዋል። ክሊኒኩ በዚህ መንገድ ተገልጋዮቹን ካሰናበተ በኋላ የተወሰኑ ሰዎችን ""አሾልኮ እንዳስገባና አገልግሎት እንደሰጣቸው"" በቦታው ነበርኩ ያሉ እማኝ ተናግረዋል። በአካባቢው የሚገኙ የመኪና አስተናባሪዎችና የጎዳና ተዳዳሪዎች የችግሩን ስፋት በመረዳት በጠዋት ወረፋ በመያዝ ሰልፋቸውን እስከ 200 ብር እየሸጡ እንደሚገኙ ተገልጋዮች ይናገራሉ። የምርመራ አገልግሎት ሰጪው ተቋም በርካታ ለምርመራ የሚመጡ ሰዎች በሚስተናገዱበት በአንደኛው ቅርንጫፉ በሁለት ነርሶችና በሁለት ናሙና ሰብሳቢዎች ብቻ አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሆነና የሚሰጠው ምርመራው አገልግሎቱን ከሚፈልገው ሰው ጋር ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ቢቢሲ ለመታዘብ ችሏል። የቢቢሲ ዘጋቢ ሰኞ ማለዳ በስፍራው እንደተመለከተ የአገልግሎት ደረሰኝ ወረቀት ማተሚያ ማሽን ብልሽት ገጥሟል በሚልም ክሊኒኩ ለግማሽ ሰዓት ያህል ሥራውን አቁሞ ነበር። ክሊኒኩ ምንሊክ ሆስፒታል አካባቢና ቡልጋሪያ ባሉት ቅርንጫፎቹ የምርመራ አገልግሎት ይሰጣል ቢባልም የሌሎች ቅርንጫፎቹ ተገልጋዮች ከሌሎች ቅርንጫፎች ይልቅ ወደ አንደኛው ክሊኒክ በብዛት ሄደው ምርመራ ለማግኘት እየጣሩ ነው። ""ወደ ሌላ ቅርንጫፍ ሄደን እድላችንን እንሞክር ስንላቸውም መልስ አይሰጡንም፣ መረጃ እንኳን ማግኘት ብርቅ ነው"" ይላሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ተገልጋይ። ሰኞ በዚህ ቅርንጫፍ ረዣዥም ሰልፎች የነበሩ ሲሆን በምንሊክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው የክሊኒኩ ቅርንጫፍ ግን የተገልጋዩ ቁጥር ��ነስተኛ ሆኖ ታይቷል። ክሊኒኩ ተመርማሪዎችን አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ብር ለአገልግሎቱ ካስከፈለ በኋላ ውጤቱን የሚሰጠው ከ48 ሰዓታት በኋላ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ቅርንጫፉ ብቻ ነው። ጠዋት በረራ ያላቸው ሰዎች ውጤት ስለማይደርስላቸው በብዛት ለድጋሚ የትኬት ማስቀየሪያ ወጪ፣ እንዲሁም ለሌላ አዲስ ምርመራ ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸውን ቢቢሲ ካናገራቸው ሰዎች ለመረዳት ችሏል። ቢቢሲ ምርመራውን ከሚሰጠው የኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላቦራቶሪስ ምላሽ ለማግኘት በማስታወቂያ ሰሌዳቸው ላይ ባሰፈሩት የስልክ አድራሻ በተደጋጋሚ ቢደውልም ቁጥሩ ስለማይሰራ መልስ ማግኘት አልቻለም።" https://www.bbc.com/amharic/news-53638908 +politics የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ያስከተለው ጥርጣሬ እና መስዋዕትነት "ባለፈው ሳምንት አንድ ምሽት ላይ በመዲናዋ አዲስ አበባ ብዙ በጎ ፈቃደኛ ዜጎች ተሰባስበው አካባቢያቸውን እየጠበቁ ነበር። መኪኖችን አስቁመው ይፈትሻሉ። አስፈላጊ ሰነዶችንም ይመለከታሉ። ፍተሻውን እያስተባበሩ የነበሩት የዕድሜ ባለ ፀጋ ""ሰፈራችን ውስጥ ያቋቋምነው ኮሚቴ 180 አባላት አሉት። ብዙ ሰዎችን ይዘናል። ሽጉጥ እና ፈንጂን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ አጠራጣሪ ቁሳቁሶችን አግኝተናል"" ብለዋል። በጎ ፈቃደኞቹ በአገር አቀፉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት የትግራይ አማጺያን እና ደጋፊዎቻቸውን ነው የሚፈልጉት። ተቺዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገቢ ባልሆነ መንገድ መታሰራቸውን ቢናገሩም፤ በመዲናዋ ግን እስሩ ሰፊ ድጋፍ ያለው ይመስላል። ምሽት ላይ ሰፈራቸውን ይጠብቁ ከነበሩት አንዱ ""ሊያመልጥ እየሞከረ ነው፤ ፍጠኑ"" እያለ በስልኩ ሲነጋገር ይደመጣል። ከእሱ በቅርብ ርቀት በብዛት አረጋውያን በጎ ፈቃደኞች ለሥልጠና ተሰብስበዋል። የሚሰጣቸውን ትዕዛት ተከትለው ይለማመዳሉ። በመዲናዋ ያለው አጠቃላይ ድባብ ሰላማዊ ይመስላል። ሆኖም ግን ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በርካታ አገራት በኢትዮጵያ ያለው ደኅንነት ሁኔታ ""እያሽቆለቆለ"" ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ማስጠንቀቂያው የተሰጠው የትግራይ ኃይሎች ወደ አዲስ አበባ የመዝመት ፍላጎት እንዳላቸው ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነው። የሩሲያ ኤምባሲ በበኩሉ ""የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኢትዮጵያ መዲና የዕለት ተዕት ሕይወት ላይ ያመጣው ለውጥ የለም"" ሲል በማኅበራዊ ገጹ አስፍሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ጦር ሜዳ ዘምተው ሠራዊቱን እንደሚመሩ ካሳወቁ በኋላ አፋር ግንባር ላይ ሆነውን የሚያሳይ ቪድዮ ተላልፏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደራዊ ልብስ ለብሰው፣ በወታደሮች ተከበው ይታያሉ። ""አሁን አካባቢውን መቆጣጠር ችለናል። የሠራዊቱ ሞራል በጣም የሚያስደስት ነው። የኢትዮጵያ ነጻነት እስከሚረጋገጥ ወደ ኋላ አንልም"" ብለዋል። በህወሓት ተይዘው የነበሩ ብዙ ከተሞችን መከላከያ እየተቆጣጠረ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በእነዚህ ውጊያ እየተካሄደባቸው ባሉ አካባቢዎች የስልክ መስመሮች ስለማይሠሩ የተባለውን ለማረጋገጥ ከባድ ነው። በተጨማሪም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የወጣው አዲስ መመሪያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እና የጦር ሜዳ ውጤቶችን ከተፈቀደለት አካል ውጪ ማንም እንዳይገልጽ ይከለክላል። የህወሓት አመራሮች በቅርቡ በድሮን በተቀረጸ ቪድዮ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ናቸው ያሏቸውን ምርኮኞች አሳይተዋል። በተለያዩ ግንባሮች ወደ ፊት እየገፉ እንደሆነም ተናግረዋል። አሁን ላይ ዋነኛ ትኩረት የሆነችው የደብረ ብርሃን ከተማ ናት። ከተማዋ ከአዲስ አበባ ውጭ መከላከያ በከፍተኛ ተጠንቀቅ የሚገኝባት እንደሆነች ይታመናል። አንዳንድ ተንታኞች፤ የትግራይ ኃ���ሎች ለመልሶ ማጥቃት እንደሚጋለጡ፣ ኤርትራም ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችልና ሠራዊቱ ከአቅሙ በላይ ውጥረት ሊገትመው እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ። ሰዎች በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ የትኛውም ወገን እያሸነፈ ቢሆን የውጊያው መስፋፋት ሰብዓዊ ቀውሱን አባብሶታል። የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያ 9.4 ሚሊዮን ሰዎች እርዳታ እንደሚፈልጉ ገልጿል። የድርጅቱ የአዲስ አበባ ኃላፊ ክሌር ነቪሊ ""ግጭቱ በሰሜን ኢትዮጵያ መስፋፋቱን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ለአስከፊ ችግር እየተጋለጡ ነው"" ብለዋል። በትግራይ አማጽያን የሚደርሰው ጥቃት፣ የፌደራል መንግሥቱ ቢሮክራሲ እንዲሁም አለመረጋጋቱ ሰብዓዊ እርዳታን እያደናቀፈ እንደሚገኝም ተናግረዋል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ባሉ ሁለት የአማራ ክልል ከተሞች በቅርቡ እርዳታ ማድረስ ችሏል። ጦርነት ከ'ካህዲዎች' ጋር መሪው ብልጽግና ፓርቲ በጎ ፈቃደኛ ዘማቾችን ለማመስገን ሕዝባዊ ክንውኖች አዲስ አበባ ውስጥ ማካሄዱን ቀጥሏል። የከተማ ምክር ቤት አባሉ ኢቲሳ ደሜ ""ከአገር ውስጥ አሸባሪዎች እና ከውጭ ደጋፊዎቻቸው ጋር ጦርነት ውስጥ ነን"" ይላል። የ22 ዓመቱ ባቡሽ ስጦታው ""ለአገሬ ክብር እንድዋጋ ተጠርቻለሁ። ቤተሰብ ቢሞት በአገር ይለቀሳል፤ አገር ከሌለ ግን ወዴት ይደረሳል? ሕይወቴን ለመስጠት ዝግጁ ነኝ። ገና ሥልጠና አለመውሰዳችን አያሰጋኝም"" ይላል። አዛውንቷ ድንቅነሽ ንጋቱም ለተሰበሰበው ሕዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል። ""አገሬን እወዳታለሁ። መዝመት እፈልግ ነበር። ግን ባለቤቴ እና ልጄ አንቺ አትዝመቺ እኛ እንዘምትልሻለን አሉኝ።"" አዛውንቷ አክለውም ""በበጎ ፈቃደኛነት ሰልጥኛለሁ። ልጄና ባለቤቴ ጦር ግንባር ሲዋጉ እኔ አካባቢዬን እጠብቃለሁ። መንገድ ላይ የማየውን ሰው ሁሉ ዝመቱ እላለሁ። ጠላት መጥቶ እስከሚገድለን መጠበቅ የለብንም"" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከብልጽግና ፓርቲ አመራሮች አንዷ አይዳ አወል ""ጀግና ናቸው። ለሁላችሁም ተስፋ ይሆናሉ"" ስትል ድንቅነሽን አቅፋ ተናግራለች። ""በርካታ ወጣቶች የእሳቸውን አርአያ እንደሚከተሉ እንጠብቃለን። የኢትዮጵያ መንፈስ ከመቼውም በላይ አሁን ጠንክሯል። ከአራዳ ክፍለ ከተማ ከሰባት ሺህ በላይ ሰዎች አገራቸውን ለመርዳት ለመዝመት ወስነዋል"" ብላለች አይዳ። የ 'ኒዮ-ኮሎኒያሊዝም' ክስ የኢትዮጵያ መንግሥት የምዕራቡ ዓለም መንግሥታት እና መገናኛ ብዙኃን የግጭቱን እውነተኛ ገጽታ የሚያዛባ መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ ሆነ ብለው ከፍተዋል ሲል ይከሳል። በርካታ ኢትዮጵያውያን በዚህ አስተያየት የሚስማሙ ይመስላል። አገሪቱን ለማጣጣል እና የህወሓትን ድል ለማጋነን ""ቅኝ ግዛታዊ"" ሙከራ ተደርጓል ሲሉ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አስተያየት ይሰጣሉ። የፖለቲካ ተንታኙ አቻምየለህ እውነቱ ""በሁለት ግንባሮች ጥቃት ተከፍቶብናል። አንደኛው ቢቢሲን ጨምሮ ሌሎችም ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን የከፈቱብን ኒዮ ኮሎኒያል የሆነ የተሳሳተ መረጃ ስርጭት ነው። ሌላው ህወሓት የከፈተው የዘር ጭፍጨፋ ጦርነት ነው"" ይላል። የኢትዮጵያ መንግሥትን እንደሚተች የሚናገረው አቻምየለህ፤ ቢሆንም ግን የአገሩን ሉዓላዊነት ከመከላከል ወደኋላ እንደማይል ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለቃለ መጠይቅ ከቢቢሲ በተደጋጋሚ የቀረበለትን ጥያቄ አልተቀበለም። ሆኖም ግን የኢትዮጵያ መንግሥት በአገር ውስጥና በውጭ መገናኛ ብዙኃን ላይ ጫና በማሳደር በስፋት ይተቻል። መገናኛ ብዙኃንን የተመለከተ አደገኛ ትርክት በማስነገር እና መረጃ እንዳይገኝ በመገደብም ይኮነናል። ከጦርነቱ በፊት የፖለቲካ እስረኞችንና ጋዜጠኞ���ን ከእስር በመፍታት ሲሞገሱ የበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዳግመኛ መገናኛ ብዙኃንን የሚያፍን እና የሚያስፈራራ ሁኔታ በመፍጠር እየተተቹ ነው። ቢቢሲ በበኩሉ ስለ ኢትዮጵያ እና የተቀረው ዓለም ገለልተኛ፣ ትክክለኛ እና ወገንተኝነት የሌለው ዘገባ በማቅረብ እንደሚቀጥል ይገልጻል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59456795 +health ኮሮናቫይረስ፡ የአፍሪካ አገራት የኮቪድ-19 አንቲቦዲ ምርመራ ሊጀምሩ ነው "ሰባት የአፍሪካ አገራት የኮሮናቫይረስ አንቲቦዲ ምርመራ ሊጀምሩ መሆኑን የአፍሪካ በሽታ መቆጣጣርና መከላከል ማዕከል አስታወቀ። ምርመራው ወረርሽኙ በአፍሪካ ውስጥ ምን ያህል እንደተሰራጨ ለማወቅ የሚደረግ ጥረት አካል ነው ተብሏል። ድርጅቱ በሰተው ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ""ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ፣ ካሜሮን፣ ናይጄሪያ፣ ሞሮኮ ምርመራውን ቀድመው ለማድረግ የተዘጋጁ አገራት ናቸው"" ያሉት የአፍሪካ በሽታ መቆጣጣርና መከላከል የበላይ ኃላፊ ጆን ኬንጋሶንግ ናቸው። ኃላፊው አህጉሪቱ እስካሁን ድረስ 9.4 ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረጓን ገልፀው፤ 10 ሚሊዮን ምርመራዎችን ለማከናወን የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካት ከአገራት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። ዶ/ር ንኬንጋሶንግ አፍሪካ በክትባት ምርመር ረገድም ጥሩ መንገድ ላይ መሆኗን ተናግረዋል። አክለውም በአህጉር ደረጃ ለሚደረግ ክሊኒካል ሙከራ ጥምረት ለማቋቋም ስትራቴጂ መቀረፁን ገልፀው፣ ለክትባቱ የሚያስፈልጉ አቅርቦቶችን ለመግዛት እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ይጀመራል ብለዋል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ከሆነ በአፍሪካ እስካሁን ድረስ 1,084,904 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በአፍሪካ በብዛት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ካደረጉ አገራት መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የምትይዘው ደቡብ አፍሪካ ነች። ደቡብ አፍሪካ አህጉሪቱ ከመረመረቻቸው አጠቃላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎች መካከል 80 በመቶውን መርምራለች ሲል የአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል አስታውቋል። ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ሞሮኮ፣ ጋና፣ ግብጽ፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ሞሪሺየስ፣ ኬንያ፣ ናይጄርያ እና ሩዋንዳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችን መርምረዋል። ደቡብ አፍሪካ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥርም ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ስትሆን ከዓለም ደግሞ አምስተኛዋ ነች። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት አንጻር ሲታይ በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በደቡብ አፍሪካ በጣም ትንሽ ነው። በርግጥ በአገሪቱ የሚገኝ አንድ በሕክምና ምርምር ላይ የተሰማራ ተቋም በአገሪቱ የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊልቅ እንደደሚችል አስታውቋል። የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል የቫይረሱ ስርጭትን በቅርበት ከሚከታተልባቸው አገራት መካከል ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ዛምቢያ፣ ካሜሮን፣ ጋቦን፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ጋና፣ አይቮሪ ኮስት፣ ሴኔጋል ፣ ግብጽ፣ ሞሮኮ እና አልጄሪያ ይገኙበታል። በመካከለኛው እና ምሥራቅ አፍሪካ ባሉ የአህጉሪቱ አገራት በጣም ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን በሌሎች አገራት ደግሞ በአንጻራዊነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎ መያዛቸው ተመዝግቧል። እንደ አፍሪካ በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል መረጃ ከሆነ በአህጉሪቱ የሚገኙ አምስት አገራት በአጠቃላይ በአህጉሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው ከተገለፀው 75 እጁን ያህል መዝግበዋል። ይህም በመላ አህጉሪቱ የቫይረሱ ስርጭት ምን እንደሚመስል ለማወቅ ያለውን ሁኔታ አዳጋች ማድረጉን የማዕከሉ ኃላፊዎች ይገልፃሉ።" https://www.bbc.com/amharic/53775413 +sports ዛሬ በሚካሄደው የ5ሺህ ሜትር ፍጻሜ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተጠባቂ ናቸው ዛሬ ከሰዓት በሚካሄዱ ሁለት የፍጻሜ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከሰዓት 9፡40 ላይ የሚጀምረው የሴቶች 5ሺ ሜትር የፍጻሜ ውድድር በጉጉት የሚጠበቅ ነው። በዚህ የፍጻሜ ውድድር ጉዳፍ ጸጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና ሰንበሬ ተፈሪ ተጠባቂ ናቸው። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሐሰን ደግሞ ዋነኛ ተፎካካሪ ነች። ጉዳፍ ፀጋይ በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይ በፈረንሳይ በተካሄደ የ1ሺህ 500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ክብረ ወሰን ማሻሻል ችላለች። ሰንበሬ ተፈሪ ደግሞ በአውሮፓውያኑ 2015 ላይ ቻይና ቤጂንግ በተካሄደው የ5ሺ ሜትር ውድድር ሁለተኛ ሆና መጨረስ ችላለች። ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት እጅጋየሁ ታዬ በበኩሏ ከዚህ በፊት በኦሎምፒክ ተሳትፋ የማታውቅ ሲሆን በ2018ቱ የታዳጊዎች የዓለም ሻምፒዮና ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች። በዚህ ምድብ ኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና አግነስ ቲሮፕ እንዲሁም ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው ሲፋን ሐሰን ቀንደኛ ተፎካካሪዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል። ከሴቶች የፍጻሜ ውድድር ቀደም ብሎ ደግሞ የወንዶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ውድድር ከቀኑ 9፡15 ላይ ይጀምራል። ከቀናት በፊት በተካሄደው ማጣሪያ ግርማ ላሜቻ እና ዋለ ጌትነት ለፍጻሜ ማለፋቸውን ያረጋገጡ ሲሆን የሜዳሊያ ዝርዝር ውስጥ እንደሚገቡ ይጠበቃል። ዋሌ ጌትነት በዳይመንድ ሊግ ውድድር በ3 ሺ ሜትር መሰናክል ማሸነፍ የቻለ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሲሆን በኦሎምፒክ ሲሳተፍም የመጀመሪያው ነው። እሁድ ሌሊት ከ9፡35 ጀምሮ በተካሄደ የሴቶች 1500 ሜትር ማጣሪያ ደግሞ ከሶስቱ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ሁለቱ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። አትሌቶቹም ፍሬወይኒ ኃይሉ እና ለምለም ኃይሉ ናቸው። ሌላኛዋ አትሌት ድርቤ ወልተጂ ደግሞ 12ኛ ሆኗ በማጠናቀቋ ማጣሪያውን ሳታልፍ ቀርታለች። በ3ሺ ሜትር የሴቶች መሰናክል ውድድር በተለያየ ምደብ ተደልድለው ውድድራቸውን ካደረጉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ሁለቱ ማጣሪያውን ማለፍ ችለዋል። አትሌቶቹም መቅደስ አበበ እና ዘርፌ ወንድማገኝ ሲሆኑ አትሌት ሎሚ ሙለታ ደግሞ 10ኛ ሆና በማጠናቀቋ ማጣሪያውን ሳታልፍ ቀርታለች። ማጣሪያውን ያለፉት ሁለቱ አትሌቶችም የፊታችን ረቡዕ በሚካሄደው የፍፃሜ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ። https://www.bbc.com/amharic/58022665 +politics የክልል እንሁን ጥያቄ፡ በጉራጌ ከተሞች የሥራ ማቆም አድማ ተደረገ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የተካተተው የጉራጌ ሕዝብ እራሱን በቻለ ክልል እንዲዋቀር ጥያቄ ሲቀርብ ቆይቷል። ይህን ጥያቄ በተለይ ከአራት ዓመት በፊት የዞኑ ምክር ቤት ጭምር ለፌደራል መንግሥቱ ማቅረቡ ይታወሳል። ነገር ግን ይህ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ለጥያቄው ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ የዞኑ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጉራጌ ዞን በክልል የመደራጀት ጥያቄን ተከትሎ ማክሰኞ ዕለት በዞኑ መዲና ወልቂጤ እና በሐዋርያት ከተማ የሥራ ማቆም አድማ ተደርጓል። ይህን ነሐሴ 03/2014 ዓ.ም. የተካሄደውን የሥራ ማቆም አድማ ማን እንደጠራው በትክክል ባይታወቅም ሰኞ ነሐሴ 02/2014 ወረቀት ከተበተነ በኋላ ወልቂጤ ከተማ ከሥራ እንቅስቃሴ ውጪ ሆና መዋሏን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በጉራጌ ጉዳዮች ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሐሳቦችን የሚያቀርበው አቶ ተስፋ ነዳም የሁለቱ ከተሞች ነዋሪዎች ከቤቱ መዋላቸውን “ከዳቦ ቤት እና ከሕክምና ተቋማት ውጪ ሙሉ በሙሉ የንግድ እንቅስቃሴ ቆሞ ውሏል” ሲሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። እንደ አቶ ተስፋ ከሆነ በዞኑ ባሉ አንዳንድ ���ካባቢዎች የመንግሥት አስተዳዳሪዎች ነዋሪዎችን ለውይይት ቢጠሩም ነዋሪዎች ለመሰብሰብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው የታቀዱት ስብሰባዎች ሳይካሄዱ ቀርተዋል ብለዋል። የሥራ ማቆም አድማ የተደረገው የጉራጌ ዞን ከሌሎች ማኅበረሰቦች ጋር በመሆን በክላስተር መደራጀት ሳይሆን በክልልነት እንዲዋቀወር የቀረበው ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ጫና ለማሳደር መሆኑን አቶ ተስፋ ያስረዳሉ። ጨምረውም ከሦስት ዓመታት በፊት የጉራጌ ዞን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት ጥያቄውን ለክልሉ በይፋ አቅርቦ እንደነበረ በማስታወስ፣ የዞኑ አስተዳደርም በአሁን የቀረበውን የአወቃቀር አማራጭን አይቀበልም ሲሉ ይናገራሉ። የጉራጌ ሕዝብ እራሱን በክልልነት የማደረጀት ሙሉ ሕገ-መንግሥታዊ መብት እንዳለው የሚናገሩት አቶ ተስፋ፤ “መንግሥትም ቢሆን በዚህ አደረጃጀት ተደራጁ ወይም የምፈቅደው ይህ ነው የማለት መብት የለውም” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጉራጌ ዞን ራሱን ችሎ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ማቅረብ ከጀመረ ዓመታት መቆጠራቸውን የሚናገሩት ደግሞ የጉራጌ ባህላዊ ሸንጎ መሥራችና ሰብሳቢ ወ/ሮ ዛይዳ ግዛው ናቸው። “ለውጡ ከመምጣቱ በፊት ህወሓት አገር ሲመራ ከሌሎች ጋር በክልል አልዋቀርም ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞ ያሰማው የጉራጌ ማኅብረሰብ ነው” በማለት ይናራሉ። ለዘመናት የዘለቀው ጥያቄ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ምላሽ አላገኘም የሚሉት ወ/ሮ ዛይዳ፤ “ሕዝቡ ቁጭት ውስጥ ገብቷል። የፖለቲካ አሻጥርም በዝቶበታል” በማለት ወ/ሮ ዛይዳ ያስረዳሉ። ጉራጌ አሁን ተደራጅቶ የሚገኝበት ሁኔታ “የራሱን ቋንቋ፣ ማንነቱን፣ ባህሉን ማሳደግ እናመጠበቅ አልቻለም። የጉራጊኛ ቋንቋ ሊጠፋ ከጫፍ ድርሷል። ቋንቋው ለመማሪያነት አልበቃም እነዚህ ሁሉ መስተካከል ስላለባቸው ነው የክልል ጥያቄ የተነሳው” ይላሉ አቶ ተስፋ። ጉራጌ በክላስተር የሚደራጅ ከሆነ ሕዝቡ ከሁለት በላይ ወደ ሆኑ ዞኖች ተከፋፍሎ ስለሚገባ የጉራጌ ማንነትን ሊያሳጣ ይችላል በማለት ስጋታቸውንም ጨምረው ይናገራሉ። ወ/ሮ ዛይዳ በበኩላቸው፤ ክላስተሩ የሕገ-መንግሥት መሠረት የሌለው እና ሕብረተሰቡ ሳይቀበለው በግድ የሚጫንበት ሃሳብ በመሆኑ አንቀበለውም ይላሉ። “የጉራጌ ማኅብረሰብን ቋንቋ፣ ባህል የሚያጠፋ ነው። እስከ ዛሬ ድረስ በቋንቋው ማስተማር እና አካባቢውን ማልማት ያልቻለ፣ የፖለቲከኖች አሻጥር አድክሞት የኖረ ማኅብረሰብ ከአሁን በኋላ በክላስተር ይደራጅ ቢባል በፍጹም ሊያንሰራራ የማይችልበት ደረጃ ላይ ይገባል” ሲሉ ወ/ሮ ዛይዳም ስጋታቸውን ይገልጻሉ። “በትግል የማይለወጥ ነገር የለም” የሚሉት ደግሞ አቶ ተስፋ፤ “የተቀረውን ሕዝብ የሚጎዳ ነገር ሳይኖር አሁንም ቢሆን ሕጋዊ መስመሩን በመከተል የዞኑ ምክር ቤት ጥያቄ እንዲከበረ ጥረታችንን እንቀጥላለን” ሲሉ አቶ ተስፋ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/czv81ngnk08o +politics """ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሱዳን ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ ግዛት እንድታስወጣ ያሳስብ"" የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር" "የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ ሱዳን ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ ግዛት እንድታስወጣ ዓለም አቀፉ ማሳሰብ እንዳለበት ተናገሩ። አምባሳደር ዲና ሳምንታዊ የመገናኛ ብዙኃን መግለጫቸውን ዛሬ ሲሰጡ፤ ሱዳን እአአ በ1972 በሁለቱ አገሮች መካከል የተደረገውን ስምምነት እንድትከተል አሳስበዋል። የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ድልድዮችን እና ወታደራዊ ሰፈሮችን ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ይህንንም ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እያሳወቁ መሆኑን አክለዋል። ሱዳን ከዚህ እንቅስቃሴ መታቀብ እንዳለባት ��ልጸው፤ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው አለመግባባት መፈታት ያለበት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሆነም ተናግረዋል። ሱዳን እና ኢትዮጵያ በድንበር ጉዳይ ውዝግብ ውስጥ ከገቡ ወራት ተቆጥረዋል። አምባሳደር ዲና በዛሬው መግለጫቸው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ይጠቀሳል። ኢትዮጵያ፤ ከግብጽ እና ከሱዳን ጋር 2015 ላይ በደረሰችው የሦስትዮሽ ስምምነት መሠረት የግድቡን ግንባታ መቀጠሏን አንስተዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት በተመለከተ፤ የፌደራል መንግሥቱ የተኩስ አቁም ቢያደርግም የህወሓት ኃይሎች ""በአማራ እና በአፋር ክልሎች ጥቃት መሰንዘራቸው የተኩስ አቁሙን ውሳኔ የሚፈትን"" መሆኑን ጠቁመዋል። ""ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ህወሓት የተኩስ አቁሙን እንዲያከብር ጫና ማሳደር አለበት"" ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ካነሷቸው ነጥቦች መካከል በግጭት ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች ጉዳይ ይጠቀሳል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በግጭት ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል ለጂሌ ጢሙጋ እና ኤፍራታ ግድም ወረዳዎች መልሶ ግንባታ እንዲውል ለእያንዳዳቸው 200,000 ብር መስጠቱም ተጠቁሟል። የሳዑዲ ተመላሾች ጉዳይ ኢትዮጵያ በአንድ ወር ውስጥ 42,000 ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገር ቤት መመለሷ ተገልጿል። ይህም 84 በመቶ ወንዶች እና 16 በመቶ ሴቶችን ያካተተ ነው ተብሏል። ከስደት ተመላሾች ወደ ትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚደረግ ሲሆን፤ አሁን ላይ በትግራይ ባለው ቀውስ ሳቢያ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ከስደት ተመላሾችን ወደ አካባቢው ለመመለስ አዳጋች እንደሆነ ተገልጿል። አዲስ አበባ ውስጥ ስምንት የስደተኞች መቀበያ ማዕከሎች እንደተቋቋሙና፤ የሳዑዲ ተመላሾች ወደ መዳረሻቸው እስኪሄዱ ድረስ በማዕከሎቹ እንደሚቆዩ ተነግሯል። ከስደት የተመለሱ ዜጎች የአካላዊ ጤናና የሥነ ልቦና ክትትል እንደሚደረግላቸው ተጠቁሟል። ከዚህ በተጨማሪ ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ ልጆች፣ ልጆች ያላቸው እናቶች፣ የሕገ ወጥ የሰው ዝውውር ሰለባ የሆኑ ሰዎች ልዩ ክትትል የሚያገኙባቸው ማዕከሎች እንዳሉ ተገልጿል። ኢትዮጵያ እአአ ከ2017 ወዲህ ከሳዑዲ ያስመለሰቻቸው ዜጎች ባጠቃላይ 415,000 ይደርሳሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-58014959 +sports የእግር ኳሱ ዓለም ሐዘን በአርጀንቲናዊው ኮከብ ዲያጎ ማራዶና ሞት "የእግር ኳሱ ዓለም በአርጀንቲናዊው ኮከብ ድንገተኛ ሞት ሐዘን ውስጥ ገብቷል። ማራዶናን በተጫጨችነትም ሆነ በአሰልጣኝነት ዘመኑ የሚያውቁት ሰዎች ለቢቢሲ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የሊቨፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ""እንኳን ጨዋታው ሲያሟሙቅ የሚያደርገው እንቅስቃሴም ልዩ ነው"" ብለውታል። የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ፈረንሳያዊው ዚነዲን ዚዳን ደግሞ ""በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የዓለማችን ወጣቶች አርዓያ መሆኑን የመንገር ዕድሉ ገጥሞኝ ነበር"" ይላል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55145183 +politics ፖላንድ የተመታችው በዩክሬን ሚሳኤል እንደሚሆን ኔቶ ገለጸ ፖላንድ ውስጥ ሁለት ሰዎችን የገደለው ሚሳኤል የዩክሬን ሊሆን እንደሚችል የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) ዋና ጸሐፊ የሆኑት ጀነራል ጄን ስቶልንበርግ ለቢቢሲ ገለጹ። በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ስለተተኮሰው ሚሳኤል ምርመራ እየተደረገ ሲሆን፣ ዋና ጸሐፊው “ሚሳኤሉ የዩክሬን የአየር መከላከያ የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው” ብለዋል። ሚሳኤሉ የዩክሬን ቢሆንም፣ ለአጠቃላይ ሁኔታው ተጠያቂ ወረራ ያካሄደችው ሩስያ እንደሆነች ተናግረዋል። ሚሳኤሉ የተተኮሰው በሩሲያ እንደሆነ ዩክሬን ገልጻለች። “ይሄ የኛ ሚሳኤል እንዳልሆነ ቅንጣት አልጠራጠርም። ወታደራዊ ሪፖርቶቻችን ��ንደሚያሳዩት ሚሳኤሉ የሩሲያ ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ተናግረዋል። ከዩክሬን ድንበር በስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፣ በፖላንድ፣ ፕርዝዎዶ በተባለ የእርሻ ቦታ የወደቀው ሚሳኤልን በተመለከተ በሚደረገው ምርመራ ለመሳተፍ ዩክሬን ጠይቃለች። ሩሲያ ባለፈው ማክሰኞ ከዘጠኝ ወራት በፊት የዩክሬን ወረራ ከተጀመረ ወዲህ ትልቁ የተባለ ተከታታይ የሚሳኤል ድብደባ ዩክሬን ላይ ፈጽማለች። ይህንን ተከትሎም ማክሰኞ የዩክሬን የአየር መከላከያዎች አልግሎት እየሰጡ ነበር። ሩሲያ በርካታ ሚሳኤሎችን ብትተኩስም ዩክሬን መታ እንደጣለቻቸው አስታውቃለች። የቡድን 20 አገራት ጉባዔ በኢንዶኔዥያ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው ሩሲያ ጥቃቱን የፈጸመችው። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ጥቃቱን አውግዟል። የኔቶ አባል በሆነችው ፖላንድ ውስጥ ሚሳኤል መተኮሱ ጦርነቱ በአስጊ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ይጠቁማል ተብሎም ተፈርቷል። የኔቶ ዋና ጸሐፊ እንዳሉት፣ ኔቶ ዘመነኛ የአየር መከላከያዎችን ለዩክሬን ለመስጠት ቃል ገብቷል። “ዩክሬንን ከሚደግፉ የኔቶ አጋሮች ጋር ባደረግነው ውይይት ዘመናዊ የአየር መከላከያ መሣሪያዎችን ለመስጠት ተስማምተናል። መሣሪያዎቹ የሩሲያን ሚሳኤል መተው ይጥላሉ” ብለዋል። ዘላቂ መፍትሄ የሚሆነው ግን ጦርነቱን ማቆም እንደሆነ ዋና ጸሐፊው አስምረውበታል። የፖላንድ ፕሬዝዳንት አንድርዜጅ ዱዳ፣ ከጥቃቱ ጀርባ ያለው S-300 የተባለው የሩሲያ ሚሳኤል እንደሆነ ተናግረዋል። ሆኖም ግን የተሰነዘረው ከሩሲያ እንደሆነ ማስረጃ አልተገኘም። ዩክሬን እና ሩሲያን ለማስታረቅ ስለሚደረገው ጥረት የተጠየቁት የኔቶ ዋና ጸሐፊ “ፑቲን ለመደራደር ፈቃደኛ አልሆኑም። ፑቲን ጦርነቱን ለማቆም ከፈቀዱ ሰላም ይሰፍናል። ዩክሬን ራሷን መከላከል ካቆመች ግን ውድመት ይጠብቃታል” ብለዋል። ሩሲያ ከዩክሬን መውጣቷ ለጦርነቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ ወደመስጠት ሊያመራ እንደሚችል አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ጄነራል ተናግረዋል። ሆኖም ግን ሌላኛው ወታደራዊ ጀነራል ማርክ ሚሊ እንዳሉት፣ ዩክሬን አጠቃላይ ግዛቶቿን አስመልሳ ድል የምትቀዳጅበት ጊዜ ሩቅ ሊሆን ይችላል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c03nwl2w295o +sports ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች አርሰናል ክለቡን ለ18 ወራት ያሰለጠኑት ስፔናዊው ኡናይ ኤምሪን ከስራቸው አሰናብቷል። ፓሪሴንት-ጀርሜይን ጋር የፈረንሳይ ሊግ ዋንጫ እና ከሲቪያ ጋር ሶስት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን ማንሳት የቻሉት ኡናይ ኤምሪ በአርሰናል አመርቂ ውጤት ማምጣት ባለመቻላቸው ዛሬ የክለቡ አስተዳደር እንዳሰናበታቸው ገልጿል። • የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ ሊያግድ ነው • ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ ክለቡ ቋሚ አሰልጣኝ እስኪያገኝ ድረስ፤ በረዳት አሰልጣኝ እና በቀድሞ የአርሰናል አማካይ ፍሬዲ ሉንበርግ በግዜያዊነት ይሰለጥናል ተብሏል። መድፈኞቹ ባለፉት 7 ጨዋታዎች ማሸነፍ ሳይችሉ የቀሩ ሲሆን፤ ትናንት ምሽት የዩሮፓ ሊግ የምድብ ጨዋታ በሺዎች በሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ፊትና በሜዳቸው በጀርመኑ ክለብ ኢንትራ ፍራክፈርት 2 ለ 1 ተሸንፈዋል። ለመሆኑ ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ማን ሊተካቸው ይችላል? 1. ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶስ ኡናይን ይተካሉ ተብለው ከተገመቱ አሠልጣኖች መካከል በዋነኛነት ስማቸው እየተነሳ ያለው የወቅቱ የዎልቨርሃምፕተን አሠልጣኝ ኑኖ ኤስፔሪቶ ሳንቶስ ናቸው። ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶስ ዎልቭስን ይዘው በፕሪሚየር ሊጉ ሰንተረዥ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ። 2. ማሲሚላኖ አሌግሪ ስካይ ስፖርት እንደዘገበው ኡናይ ኤምሪ ከአርሰናል ከተለያዩ በኋላ በማሲሚላኖ አሌግሪ እና በአርሰናል ክለብ መካከል ግንኙነቶች ተጀምሯል። በቅርቡ ከጁቬንቱስ የተለያዩት አሌግሪ ከአሮጊቷ ጋር ውጤታማ የሚባል ጊዜን አሳልፈዋል። አሌግሪ ከጁቬንቱስ ጋር አምስት የሴሪያአ እና አራት ኮፓ ኢታሊያ ዋንጫዎችን ከማንሳታቸውም በተጨማሪ ሁለት ጊዜ ለቻምፒያንስ ሊግ ፍጻሜ መድረስ ችለዋል። 3. ካርሎ አንቾሎቲ ናፖሊን እያሰለጠኑ የሚገኙት ካርሎ አንቾሎቲ ሌላው ኡናይ ኤምረን ይተካሉ ተብለው ከተገመቱት አሰልጣኞች መካከል ይገኙበታል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ ጣሊያናዊው አንቾሎቲ የውድድሩ ዘመን እስኪናቀቅ ድረስ ከናፖሊ ጋር ኮንትራት ቢኖርባቸውም፤ አሰልጣኙ ወደ ኤምሬትስ ሊያቀኑ እንደሚችል በስፋት እየተዘገበ ነው። 4. ብሬንዳን ሮጀርስ ሌስተር ሲቲዎች ዘንድሮ ደንቅ የሚባል የውድድር ዘመን እያሳለፉ ይገኛሉ። በብሬንዳን ሮጀርስ የሚመሩት ቀበሮዎቹ ካለፉት 10 ጨዋታዎች አርሰናልን ጨምሮ በድንቅ ጨዋታ 9 ግጥሚያዎችን በድል ማጠናቀቅ ችለዋል። ብሬንዳን ሮጀርስ ወደ ኢሚሬትስ እንዲያቀኑ የበርካታ የአርሰናል ደጋፊዎች ምኞት ነው። ኡናይ ኤምሪ አርሰናልን እንዲያሰለጥኑ ከመሾማቸው በፊት፤ ክለቡን ለማሰልጠን ስሙ በስፋት ሲነሳ የነበረው ማይክል አርቴታ ነበር። የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ባለፉት ሶስት ዓመታት ከከማንችሰተር ሲቲው ፔፕ ጋርዲዎላ ሥር ሆኖ የአሰልጠኝነትን ክህሎት ሲማር ቆይቷል። ረዳት አሰልጣኙ አርቴታ፤ ማንችሰተር ሲቲ ሁለት የፕሪሚር ሊግ ዋንጫ፣ ሁለት የሊግ ዋንጫዎችን እና ኤፍ ኤ ዋንጫዎች እንዲያነሳ የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል። ሌላው የቀድሞ የአርሰናል ባለታሪክ አማካይ ፓትሪክ ቪዬራ ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ ሊሆን እንደሚችል እየተጠቀሰ ነው። • የሆንግ ኮንግን የዘር መድልዎ የሚፋለሙ አፍሪካዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ቪዬራ የማይረሳውን የአርሰናል ወርቃማ የ2003/4 የድል የውድድር ዘመን አንበል በመሆን ክለቡን መርቷል። የፈረንሳዩን ኒስ እግር ኳስ ክለብ እያሰለጠነ የሚገኘው ቪዬራ የሚፈለገውን ውጤት እያስመዘገበ ባይሆንም፤ መድፈኞቹ የቼልሲን አርዓያ የሚከተሉ ከሆነ፤ ቪዬራ የአርሰናል አሰልጣኝ ሆኖ ሊሾም እንደሚችል እየተጠቆመ ነው። 7. ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በቅርቡ ከፖተንሃም አሰልጣኝነት የተነሱት ፖቸቲኖ፤ ሌላው ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ ይሆናሉ ተብለው ከተገመቱ አሰልጣኖች መካከል ይገኙበታል። የቶተነሃም ባላንጣ የሆነው አርሰናልን ለማሰልጠን ፍላጎት ይኖራቸው ይሆን? ሲሉ የሚጠይቁም አልጠፉም። ፖቸቲኖ ከአርሰናል ውጪ፤ የባየር ሚዩኒክ፣ ሪያል ማድሪድ ወይም ባርሴሎና አሰልጣኝ ለሆኑ እንደሚችሉ በስፋት እየተገመተ ይገኛል። https://www.bbc.com/amharic/news-50597494 +business 'በርሜል ሙሉ ገንዘብ ተገኘ የተባለው ሐሰት ነው' - አ/አ ፖሊስ "የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአራዳ ክፍለ ከተማ በልመና በሚተዳደሩ አንዲት ግለሰብ ቤት ውስጥ ከ45 ሺህ በላይ ብር ማግኘቱን ሲያረጋግጥ፤ በርሜል ሙሉ ገንዘብ ተገኘ የሚለውን ዘገባ ሐሰት ሲል አስተባብሏል። በክፍል ከተማው በተለምዶ አትክልት ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በልመና የሚተዳደሩት ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው ገንዘቡ የተገኘው። ኮሚሽኑ ግለሰቧ ረዳትም ሆነ ልጅ በአጠገባቸው የሌላቸው የአእምሮ ህመም ያለባቸው ናቸው ያለ ሲሆን፤ ገንዘቡ የተገኘው በተለያዩ ፌስታሎች ነው ይላል ኮሚሽኑ በፌስቡክ ገፁ ያሰፈረው ዜና። የአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ወደ ስፍራው በማምራት ገንዘቡን እንዳገኘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል። ""በቦታው ��ይ በተደረገው የማረጋገጥ ሥራ በግለሰቧ መኖሪያ ቤት ውስጥ በርካታ የተቋጠሩ ፌስታሎች እና ሌሎች ቆሻሻ ዕቃዎች ተከማችተው የተቀመጡ ሲሆን ከተቋጠሩት ፌስታሎች መካከል ገንዘብ ያለባቸው"" ይላል የኮሚሽኑ ገለፃ። በልብስ መዘፍዘፊያ ፕላስቲክ የተወሰነ ብር እንደተገኘ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከአካባቢው ነዋሪዎች ታዛቢዎችን በመጨመር ፖሊስ እና የወረዳው አስተዳደር ባደረጉት ቆጠራ የተገኘው ገንዘብ 45 ሺህ 858 ብር መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል። ፖሊስ ኮሚሽኑ ጨምሮ እንደገለጸው ከተገኘው ገንዘብ ውስጥ አንድ ሺህ ብር ግለሰቧ ለዕለት ወጪያቸው እንዲጠቀሙበት የተሰጣቸው ሲሆን፤ ቀሪው ብር ደግሞ በግለሰቧ ስም የባንክ የሂሳብ ተከፍቶ ገቢ ተደርጎላቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በርሜል ሙሉ ገንዘብ ተከማችቶ ተገኘ በሚል በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች እየተላለፈ ያለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታዉቋል። ማክሰኞ ረፋዱ ላይ አራዳ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ኢንፎኔት ኮሌጅ አካባቢ አንድ በርሜል ገንዘብ ወድቆ ተገኝቷል ሲሉ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበው ነበር። የተገኘው ገንዘብ የኢትዮጵያ ብር እና ዶላር እንደሆነና ገንዘቡን ማን እንደጣለው ያልተተረጋገጠ መሆኑን በመግለጽ የአካባቢው ፖሊስ በመኪና ጭኖ እንደወሰደውም ተዘግቦ ነበር። ኮሚሽኑ ግን ይህ ዘገባ የተሳሳተ ነው ሲል አስተባብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54977501 +sports እግር ኳስ፡ ቲየሪ ኦንሪ በዘረኝነት ምክንያት ራሱን ከማኅበራዊ ሚዲያ አገለለ "የቀድሞው የአርሰልና የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ቲዬሪ ኦንሪ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰነዘሩ የዘረኝነትና ሌሎች መሰል የበይነ መረብ ጥቃቶችን በመቃወም ራሱን ከማኅበራዊ ሚዲያዎች እንዳገለለ አስታውቋል። የ43 ዓመቱ ኦንሪ 2.3 ለሚሆኑት የትዊተር ተከታዮቹ አርብ ዕለት ባስተላለፈው መልዕክት ችግሩ በጣም አሳሳቢ እንደሆነና ችላ ለማለት እንኳን ከባድ እንደሆነ ገልጿል። ወደ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚመለሰው የማኅበራዊ ሚዲያዎች ባለቤቶች ኮፒራይት (የባለቤትነት መብት) ላይ የሚከተሉትን አይነት ጠበቅ ያለ ክትትልና እርምጃ በዘረኝነት ላይም ሲያደርጉት ብቻ እንደሆነ ገልጿል። በጉዳዩ ላይ የተሻለ እርምጃ መወሰድ እንዲጀመርም ጠይቋል። ''በማኅበራዊ ሚዲያዎች በቀላሉ ገጽ መክፈት ይቻላል፤ ሌሎችን ማስፈራራትና የዘረኝነት መልዕክቶችን ማስተላለፍም እንዲሁ። የሚያስገርመውና የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ እኚህ ሰዎች ማንነታቸው እንኳን በትክክል አይታወቅም'' ብሏል ፈረንሳያዊው እግረ ኳሰኛ። ''በማኅበራዊ ሚዲያዎቹ የሚታዩት ጥቃቶችና የዘረኝነት መልዕክቶቸ ችላ ለማለት እንኳን ጊዜ የሚሰጡ አይደሉም'' ብሏል። ቲዬሪ ኦንሪ ከእንግሊዙ ክለብ አርሰናል ጋር በመሆን በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1999 እስከ 2007 ባሉት ዓመታት ሁለት ጊዜ የፕሪምየር ሊጉ አሸናፊ መሆን የቻለ ተጫዋች ነው። ለአርሰናልና ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በሚጫወትበት ወቅት አንዳንድ የዘረኝነት ጥቃቶች አጋጥመውት እንደነበር ባሳለፍነው መስከረም መግለጹ የሚታወስ ነው። ''እኛ ጥቃት የሚደርስብን ሰዎች ህመም ላይ እንደሆንን ሌሎች እንዲረዱ እንፈልጋለን። ሲበቃ ይበቃል'' ብሏል ኦንሪ። አርብ ዕለት በትዊተር ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት አክሎም ''ከነገ ጠዋት ጀምሮ እራሴን ከማኅበራዊ ሚዲያዎች አግልያለው። ከዚህ በኋላ ወደ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የምመለሰው የነዚህ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ባለቤቶች ልክ የኮፒራይት መብት ላይ የሚከተሉትን አይነት ጠበቅ ያለ ክትትልና እርምጃ በዘረኝነት ላይም ሲያደርጉት ብቻ ነው'' ብሏል። ''ይህ ሁኔታ እስከሚቀየር ድረስ ሁሉ��ም የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቼን አጠፋቸዋለው። ለውጡ ቶሎ እንደሚመጣም ተስፋ አደርጋለው።"" ብሏል። ማኅበራዊ ሚዲያን የሚያስተዳድሩት ድርጅቶች ችግሩን ለመቆጣጠር በርካታ ሥራዎችን እያከናወኑ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገልጹ ነበር። ትዊተር በቅርቡ መሰል የማኅበራዊ ሚዲያ ጥቃቶችን ለመቆጣጠር 'ኪክ ኢት አውት' (Kick It Out) የተሰኘ አሰራር መጀመሩን አስታውቋል። በፌስቡክ ስር የሚገኘው ኢንስታግራም በበኩሉ ባለፈው ዓመት ብቻ 6.6 ሚሊየን የጥላቻ ንግግሮችን እንዳስወገደ ገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56547572 +business የአሜሪካው አየር መንገድ ያልተከተቡ ሰራተኞቹን 200 ዶላር በየወሩ ሊቀጣ ነው "ዴልታ አየር መንገድ የአሜሪካ ሦስተኛው ትልቁ አየር መንገድ ሲሆን የኮቪድ-19 ላይ ክትባት ባልወሰዱ ሠራተኞች ላይ በየወሩ 200 ዶላር እንዲከፍሉ ሊያደርግ ነው። ሁለቱንም ክትባቶች ወስደው በበሽታው ለተያዙ ለኮቪድ ህመምተኞች ብቻ የሕመም ክፍያ እከፍላለሁ ብሏል። የቫይረሱ ስርጭት በመላው አሜሪካ እየጨመረ ባለበት ሁኔታ ውሳኔው የኮሮናቫይረስን ""በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋት"" ለመግታት ይረዳል ብለዋል ኃላፊው ኢድ ባስቲያን። እርምጃው አንድ ትልቅ ኩባንያ ሠራተኞቹ እንዲከተቡ ለማድረግ የተወሰደ ሙከራ ነው። ባስቲያን ለሠራተኞች በላኩት በማስታወሻ ላይ የዴልታ ተጨማሪ ክፍያ ከታህሳስ ጀምሮ በጤና እንክብካቤ መድን ዕቅዱ በተመዘገቡ ሠራተኞቹ ላይ እንደሚተገበር ገልጸዋል። ይህም አብዛኛዎቹን 75 ሺህ ሠራተኞቹን የሚመለከት ይሆናል። ዴልታ ለኮቪድ-19 የሆስፒታል ቆይታ በአንድ ሰው በአማካይ 50 ሺህ ዶላር ዋጋ ይከፍላል ብለዋል። ""ክትባቱን ያለመውሰድ ውሳኔው ለኩባንያችን እየፈጠረ ያለውን የገንዘብ አደጋን ለመቅረፍ ይህ ተጨማሪ ክፍያ አስፈላጊ ይሆናል"" ብለዋል። ""B.1.617.2 የተባለው አዲስ ዝርያ ከተስፋፋ ወዲህ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ሆስፒታል የገቡ የዴልታ ሠራተኞች ሙሉ በሙሉ ያልተከተቡ ናቸው።"" ከመስከረም 30 ጀምሮ ደግሞ ያልተከተቡ የዴልታ ሠራተኞች በየሳምንቱ የኮቪድ ምርመራዎችን ማድረግ እና በዴልታ የቢሮ ውስጥ ጭምብል ማድረግ አለባቸው። ሁሉም የአሜሪካ አየር መንገድ ሠራተኞች በአውሮፕላን ውስጥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል መልበስ ቢኖርባቸውም በቢሮዎች ውስጥ ግን አይተገበርም። ዴልታ የተሰኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ በአሜሪካ መስፋፋቱን ተከትሎ የሃገሪቱ ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸው ክትባት እንዲወስዱ ለማበረታታት የተለያዩ ዘዴዎች እየሞከሩ ነው። እንደ ዩናይትድ አየር መንገድ፣ ጎልድማን ሳክስ፣ ማይክሮሶፍት እና ጉግል ያሉ ኩባንያዎች ወደ ሥራ ለመግባት ሙሉ በሙሉ መከተብ እንዳለባቸው ለሠራተኞቻቸው ነግረዋል። የኢንቨስትመንት ኩባንያው ቫንጋርድ ለክትቡ ሠራተኞቹ የ 1 ሺህ ዶላር ጉርሻ ሰጥቷል። አማዞን እና አፕል ግን በዚህ ረገድ ምንም ፖሊሲ አላወጡም። የኢንቨስትመንት ባንኩ ክሬዲት ሱይስ ሁሉም ክትባት ያልሰጣቸው ሠራተኞች ከመስከረም 7 ጀምሮ ከቤት እንዲሠሩ እንደሚጠይቅ ረቡዕ ዕለት አስታውቋል። እንደ ሌሎቹ ኩባንያዎች ሁሉ ወደ ቢሮ ሙሉ ለሙሉ መመለሻ ጊዜን እስከ ጥቅምት ድረስ አዘግይቷል። በወረርሽኙ ወቅት ከፍተኛ የፍላጎት መቀዛቀዝ ተከሰቶ የአሜሪካ አየር መንገዶች በራስ መተማመንን ለመመለስ በሚታገሉበት ጊዜ ነው ዴልታ አየር መንገድ በአዲስ እርምጃ የመጣው። የአየር መንገዱ የመንገደኞች እስከ ሰኔ 30 ድረስ ያለው የሦስት ወራት ገቢ 5.3 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ቀውሱ ከመጀመሩ በፊት በ 2019 ከነበረው ተመሳሳይ ጊዜ ከ 50 በመቶ በላይ ቀንሷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58333315 +sports የተለያዩ አገራት አትሌቶች ከቶኪዮ ወደ አገራቸው ሲመለሱ የሚጠብቋቸው ���ስደናቂ ሽልማቶች በኦሊምፒክ መድረክ አገርን ወክሎ አሸናፊ መሆን ከሚያስገኘው ትልቅ ሐሴት፣ ክብርና ታዋቂነት በተጨማሪ በርካታ አይነት ሽልማቶችም ይዞ ይመጣል። የተለያዩ አገራትም በኦሊምፒክ ተሳትፎ ያደረጉ ተወዳዳሪዎችን የተለያዩ አይነት ሽልማት ይሰጣሉ። ነገር ግን አንዳንድ አገራት ለስፖርተኞቹ ከሚሰጡት ማበረታቻዎች መካከል ከገንዘብ እስከ መኖሪያ ቤት፤ አንዳንዴ ደግሞ ከብት ጭምር ይበረከታል። በኢትዮጵያም ቢሆን መጠኑ ይለያይ እንጂ በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች ሽልማት ሲበረከት ቆይቷል። በኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ አትሌቶች በመሳተፋቸው ብቻ ዓለማ አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የሚሰጣቸው ገንዘብ ባይኖርም በርካታ አገራት ግን ባንዲራቸውን ላውለበለቡላቸው ስፖርተኞች ጠቀም ያለ ገንዘብና ማበረታቻ ይሰጣሉ። በዚህም መሠረት በቶክዮ ኦሊምፒክ ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች በአገራቸው የሚያገኙትን ሽልማትና ማበረታቻ እናስቃኛችሁ። ሁለት ድንቅ መኖሪያ ቤቶች የፊሊፒንሷ ስፖርተኛ ዲያዝ በሴቶች 55 ኪሎግራም ክብደት ማንሳት ማሸነፏን ተከትሎ በአገሪቱ እንደ ጀግና እየተሞካሸች ነው። መሞካሸት ብቻ አይደለም ሕይወቷን የሚቀይሩ ሽልማቶችና ማበረታቻዎች እየጎረፉላት ይገኛሉ። የፊሊፒንስ ስፖርት ኮሚሽን እና የአገሪቱ ፕሬዝዳንት በጥምረት ገንዘብ በማዋጣት ለዚህች ስፖርተኛ 600ሺህ የአሜሪካ ዶላር (27 ሚሊየን ብር አካባቢ ማለት ነው) እንደሚሰጧት ቃል ግበተውላታል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሁለት እጅግ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ተሰጥተዋታል። የፊሊፒንስ አየር ኃይል ውስጥ በወር 500 ዶላር እየተከፈላት ታገለግል የነበረችው ዲያዝ እነዚህ ሽልማቶች ሕይወቷን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀይሩትና ብርታት እንደሚሰጣት መገመት ከባድ አይሆንም። ይህች ስፖርተኛ በሚያስገርም ሁኔታ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ስትዘጋጅ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል ውስጥ እንኳን የመሰልጠን እድል አላገኘችም ነበር። እንደውም በአካባቢዋ ያገኘቻቸውን ብረቶች እንዲመቻት አድርጋ ነበር ክብደት ማንሳት ስትለማመድ የቆየችው። የገንዘብ ሽልማት የገንዘብ ሽልማት መጠን ከአገር አገር ይለያያል። በርካታ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ የሚታወቁትና አትሌቶቻቸውን እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ማዕከላት የሚያሰለጥኑ አገራት ለስፖርተኞቹ የሚሰጡት ቀጥተኛ ሽልማት ብዙ ጊዜ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። አንዳንዴም አትሌቶች ምንም ሽልማት ላያገኙ ይችላሉ። ነገር ግን በስንት ጊዜ አንዴ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ የሚገቡ አገራት አልያም በውስን የውድድር አይነቶች ብቻ ሜዳሊያ የሚያሰገኙ አገራት ስፖርተኞቻቸውን ለማበረታታት ጠቀም ያለ ገንዘብ በሽልማትነት ያቀርቡላቸዋል። ለምሳሌ ማሌዢያ በ13 የኦሊምፒክ ተሳትፎዋ ማግኘት የቻለችው 11 ሜዳሊያዎችን ብቻ ሲሆን በቶክዮ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ለሚያመጣ ስፖርተኛ 241 ሺህ ዶላር፣ ነሐስ ለሚያመጣ ደግሞ 150 ሺህ ዶላር እንዲሁም ብር ለሚያመጣ ስፖርተኛ ደግሞ 24 ሺህ ዶላር እንደምትሸልም አስታውቃለች። በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ደግሞ ማሌዢያ በወንዶች የጥንድ ባድሜንተን ውድድር የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ለሚገቡ አትሌቶቻቸውን ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ከሚሰጡ አገራት መካከል የተወሰኑት። ሽልማቱ በአሜሪካን ዶላር ነው። አንጸባራቂ፣ ውድ እና አዲስ መኪናዎች ቻይና እና ሩሲያ ደግሞ በሜዳሊያ ከሚጥለቀለቁት አገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አገራቱ ለስፖርተኞቻቸውን ጠቀም ካለ የገንዘብ ሽልማት በተጨማሪ በአዳዲስ መኪኖች ያንበሸብሿቸዋል። ለምሳሌ ሩሲያ በኦሊምፒክ መድረክ የአገራቸውን ባንዲራ ማውለብለብ ለቻሉ ስፖርተኞች በጣም ውድ የሚባሉ መኪናዎችን እና ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን ታበረክታለች። አንዳንድ ሽልማቶች ደግሞ ለየት ያሉና አስገራሚም ናቸው። ደቡብ አፍሪካውያኑ ሲዝዌ ንዶቩ፣ ማቲው ብሪቴይን፣ ጆን ስሚዝ እና ጄምስ ቶምሰን በወንዶች ቀላል ክብደት በአውሮፓውያኑ 2012 ለንደን ኦሊምፒክ ላይ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ምርጥ ላሞች በሽልማት መልክ ተበርክቶላቸው ነበር። የተሻለ ሥራ እና ከአስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት ነጻ መሆን በአንዳንድ አገራት ደግሞ በኦሊምፒክ አሸናፊ መሆን የተሻለ ሥራና የተሻለ ክፍያ የሚያስገኝ ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ ከአስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት እስከመቅረትም ያደርሳል። የሕንዷ ክብደት ማንሳት ተወዳዳሪ ሚራቢ ቻኑ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ 350 ሺህ ዶላር ሽልማት የተበረከተላት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የምትሰራበት መስሪያ ቤት የሆነው 'ኢንዲያን ሬልዌይ ሰርቪስ' የደረጃ እድገትና የደሞዝ ጭማሪ ቃል ገብቶላታል። በደቡብ ኮሪያ ደግሞ ሜዳሊያ ማምጣት የቻሉ ስፖርተኞች ጠቀም ያለ የገንዘብ ሽልማት የሚሰጣቸው ሲሆን ዋነኛው ሽልማታቸው ግን ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ የአገሬው ዜጎች መቅረት የማይችሉበት የ18 ወራት ወታደራዊ አገልግሎት እንዲቀርላቸው መደረጉ ነው። ነገር ግን ለበርካታ አትሌቶች በመንግሥታቸው የሚሰጣቸው ገንዘብና ማበረታቻ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ምክንያቱም አብዛኛዎቹ ስፖርተኞች በቂ የሆነ ስልጠና ለማግኘት እንኳን የሚያስችላቸው የገንዘብ አቅም የላቸውም። ለምሳሌ ሳትጠበቅ በኦሊምፒክ መድረክ በሴቶች ጂምናስቲክስ ሁለት ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ የቻለችው ብራዚላዊት ሬቤካ አርናልዴ በብራዚል መንግሥት ድጎማ ነበር የምትኖረው። ባለፈው ኅዳር ወር አንድ ዓለመ አቀፍ የጥናት ተቋም ከ48 አገራት የተወጣጡ 500 የሚሆኑ ትልልቅ አትሌቶችን በማነጋገር በሰበሰበው መረጃ መሠረት 60 በመቶ የሚሆኑት በገንዘብ እራሳቸውን መደገፍ እንደማይችሉ ገልጸዋል። አንዳንድ አትሌቶች እንደውም በቶኪዮ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ገንዘብ ለማግኘት 'ጎ ፈንድ ሚ' ላይ ጭምር በመሄድ እርዳታ ሲያሰባስቡ ነበር። ታዲያ እንዲህ ባሉ አስቸጋሪ ጊዜያት አገራት ለስፖርተኞቻቸው መሰል የገንዘብ፣ መኖሪያ ቤት፣ መኪና አንዳንዴም ከብቶች መሸለማቸው በርካታ ታዳጊዎች ለወደፊት መነሳሳትን እንደሚፈጥርባቸው ይታመናል። https://www.bbc.com/amharic/news-58142401 +health ኮሮናቫይረስ፡ በርካታ የአውሮፓ አገራት በታላቋ ብሪታኒያ ላይ የጉዞ እቀባ እያደረጉ ነው በርካታ የአውሮፓ አገራት በታላቋ ብሪታኒያ ላይ የጉዞ እቀባ እያደረጉ ነው። ምክንያቱ ደግሞ በዚያች አገር አዲስ ዓይነት የኮቪድ ዝርያ መገኘቱ ነው። አዲሱ ዝርያ ገና በስፋት ያልተጠና ቢሆንም ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ ከሰው ወደ ሰው ይዛመታል የሚለው ፍርሃት በርካታ አገራትን ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸዋል። እስከ አሁን ባለው ብቻ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ኔዘርላንድስ እንዲሁም ቤልጂየም ሁሉም ወደ ታላቋ ብሪታኒያ የአየር በረራን አቋርጠዋል። ዛሬ ሰኞ የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች ስብሰባ ስለሚቀመጡ ከዚህ የባሰ የእቀባ ውሳኔ ሊኖር እንደሚችል እየተጠበቀ ነው። አዲሱ ኮቪድ-19 ዝርያ በለንደንና በደቡብ ምሥራቅ ኢንግላንድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው በስፋት የተሰራጨው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ቅዳሜ በሰጡት አስቸኳይ ትእዛዝ ደረጃ 4 የጥንቃቄ ደንቦች እንዲከበሩ አዘዋል። ለፈረንጆች ገናና አዲስ ዓመት የእንቅስቃሴ ገደቦች ይላላሉ ተብሎ ታስቦ የነበረውን ሐሳብ ሰርዘዋል። የጤና ባለሙያዎች አዲሱ የተህዋሲው ዝርያ ��በልጥ ገዳይ ስለመሆኑም ሆነ ለክትባት እጅ የማይሰጥ ስለመሆኑ ገና እርግጠኛ አልሆኑም። ሆኖም ግን ከለመድነው የኮሮናቫይረስ በ70 በመቶ በይበልጥ የመሰራጨት አቅም አለው መባሉ ማን ይተርፋል እንዲባል አድርጓል። የታላቋ ብሪታኒያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይህ አዲስ ዝርያ ቫይረስ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖብናል፤ በቁጥጥራችን ልናውለው ይገባል ብለዋል። ታላቋ ብሪታኒያ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ይፋ ባደረገች በሰዓታት ውስጥ ኔዘርላንድ ማንኛውም በረራ ከታላቋ ብሪታኒያ እንዳይመጣብኝ ብላለች። ፈረንሳይ በተመሳሳይ ከባድ መኪና ተሽከርካሪ፣ መርከብ፣ ጀልባዎች፣ እግረኛና በበራዎችን ከእንግሊዝ በኩል ወደ አገሯ እንዳይገቡብኝ ብላለች። አየርላንድና ጀርመንም ተመሳሳይ ውሳኔን አሳልፈዋል። ጣሊያን እስከ ጃንዋሪ 6 ማንም ከታላቋ ብሪታኒያ አይምጣብኝ ብላለች። በአዲሱ የቫይረስ ዝርያ የተጠቃ አንድ ሰው በጣሊያን መገኘቱም ድንጋጤን ፈጥሯል። ቱርክ፣ ቡልጋሪያና ኦስትሪያም ከታላቋ ብሪታኒያ ጉዞ እቀባ አድርገዋል። የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በተመለከተ ከዩናይትድ ኪንግደም ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየተነጋገረ እንደሆነ በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ድርጅቱ እንዳለው ዩናይትድ ኪንግደም አዲሱን የቫይረስ ዝርያ በተመለከተ እየተካሄዱ ስላሉ ጥናቶች መረጃዎችን ስታጋራ እንደነበር ጠቅሶ፤ ድርጅቱ ስለአዲሱ ቫይረስ ባሕርይ እና አደጋው የደረሰበትን ለአባል አገራቱ እና ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል። ምንም እንኳን የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፤ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከቀድሞው እስከ 70 በመቶ ያህል የመዛመት እድሉ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ ባለሥልጣናት አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከፍተኛ ሞት ስለማስከተሉ አሊያም እስካሁን በተዘጋጁት የኮሮናቫይረስ ክትባቶች እና ሕክምናዎች ሊበገር ስለመቻሉ የሚያሳይ መረጃ እንደሌለ ተናግረዋል። ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ ፋይዘርና በባዮንቴክ የበለጸገውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቻቸው መስጠት መጀመራቸው ይታወሳል። 95 በመቶ ኮሮናቫይረስን ይከላከላል የተባለለት ይህንን ክትባት ለዜጎች በመስጠት ዩናይትድ ኪንግደም ቀዳሚዋ አገር ሆና ነበር። https://www.bbc.com/amharic/news-55391881 +sports ጋና ወደ ድል ስትመለስ ሮናልዶ አስቆጠርኩት ያለው ጎል ለፈርናንዴዝ ተቆጥሯል ደቡብ ኮሪያ ከጋና ያደረጉት ጨዋታ በጎሎች የተንበሸበሸ፣ የስሜት መለዋወጥ እና ካርድ ያስመዘዘ ሆኖ አልፏል። በመጀመሪያው ጨዋታ በፖርቹጋል የተሸነፈችው ጋና በ24ኛው ደቂቃ በሞሐመድ ሳሊሱ ጎል ቀዳሚ ሆነች። ሞሐመድ ኩዱስ ያስቆጠራት ሁለተኛ ጎል ጋናዊያን በቀላሉ አሸነፉ አስብሎ ነበር። የደቡብ ኮሪያ ሊግ ኮከብ ጎል አስቆጣሪው ቾ ጉ-ሱንግ በተከታታይ ያስቆጠራቸው ጎሎች ጨዋታውን ቀየሩት። ደበብ ኮሪያ 2-2 ጋና። ጋናዎች በፍጥነት በኩዱስ ባስቆጠሩት ጎል ምላሽ ሰጡ። ደበብ ኮሪያ 2-3 ጋና። ደቡብ ኮሪያ አቻ ለመሆን ያደረገችውን ተደጋጋሚ ጥረት ግብ ጠባቂው አቲ ዚጊ አክሽፎታል። ጨዋታው በዚሁ ውጤት ተጠናቀቀ። ጋናዎች ሲጨፍሩ የደቡብ ኮሪያው አምበል ሰን ሁንግ-ሚን ሲያለቅስ ታይቷል። የኮሪያው አሰልጣኝ ፓውሎ ቤንቶ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ከዳኛው ጋር በነበራቸው እሰጥ አገባ ቀይ ካርድ ተመልክተዋል። በምድቡ ሌላኛ ጨዋታ ፖርቹጋል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። የጨዋታው መልክ የተቀየረው 54ኛው ደቂቃ ላይ ነው። ቡርኖ ፈርናንዴዝ ያሻማው ኳስ ከመረብ ላይ ያርፋል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ ኳሱን ማስቆጠሩን በመተማመን ከቡድን አጋሮቹ ጋር ደስታውን ገልጿል። ጎሏ ሮ���ልዶን በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለፖርቹጋል በርካታ ጎል ካስቆጠረው ኡሴቢዮ የምታስተካክለው ነበረች። በኋላም ሮናልዶ ኳሷን አልነካትም በሚል ጎሏ በፈርናንዴዝ ስም እንድትመዘገብ ተደርጓል። ውሳኔው ሲገለጽ አጥቂው በምጸት ፈገግ ሲል ታይቷል። ጨዋታው መገባደጃ ላይ የተገኘችውን ፍጹም ቅጣት ምትም ፈርናንዴዝ አስቆጥሯል። ምድቡን በስድስት ነጥብ የምትመራው ፖርቹጋል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። ጋና በሦስት ነትብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ደቡብ ኮሪያ እና ኡራጓይ አንድ አንድ ነጥብ አላቸው። በምድብ ሰባት ጨዋታ ካሜሮን እና ሰርቢያ 3 ለ 3 በሆነ ውጤት አቻ ተለያይተዋል። ጂን-ቻርለስ ካስቴሌቶ በ29ኛው ደቂቃ ካሜሮንን ቀዳሚ ያደረገች ጎል አስቆጠረ። ስታርሂንጃ ፓቭሎቪች እና ሰርጌይ ሚሊንኮቪች-ሳቪች በተከታታይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሰርቢያ 2 ለ 1 እየመራች እረፍት ወጡ። አሌክሳንደር ሚትሮቪች ያስቆጠራት ጎል ሦስቱን ነጥቦች ሰርቢያ ለመውሰድ የቻለች አስመስሏት ነበር። በካሜሮን በኩል ተቀይሮ የገባው ቪንሰንት አቡበከር የጨዋታውን መልክ ቀየረው። አቡበከር አንድ ጎል በስሙ ሲያስመዘግብ ኤሪክ ማክሲም ቹፖ-ሞቲንግ ያስቆጠራትን ኳስ ደግሞ አመቻችቶ አቀብሏል። በዚህም ጨዋታው ሦስት አቻ ተጠናቋል። ለዋንጫው ትልቅ ግምት የተሰጣት ብራዚል ከስዊዘርላንድ ጋር ያደረገችው ጨዋታ ቅዝቅዝ ያለ ነበር። በፊፋ ሃገራት ደረጃ ቀዳሚ የሆነችው ብራዚል ያለ ኮከብ ተጫዋቸዋ ኔይማር ነበር ወደ ሜዳ የገባችው። ብራዚል በ83ኛው ደቂቃ ጎል ለማስቆጠር ችላለች። የማንቸስተር ዩናይትዱ አማካይ ካሰሚሮ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ አሳርፏል። ጨዋታው በዚሁ ውጤት ሲጠናቀቅ ብራዚል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። ብራዚል በስድስት ነጥብ ምድቡን ትመራለች። ስዊዘርላንድ ሦስት ነጥብ አላት። ካሜሮን እና ሰርቢያ በአንድ ነጥብ ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የኳታር የዓለም ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ መከናወን ይጀምራሉ። ምድብ አንድ ሁለት ጨዋታዎች በተመሳሳይ 12 ሰዓት ይከናወናሉ። አዘጋጇ ኳታር ኔዘርላንድስን አል ባይት ስታዲየም ትገጥማለች። ኻሊፋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ላይ ኢኳዶር እና ሴኔጋል ይገናኛሉ። ኔዘርላንድስ ምድቡን በአራት ነጥብ ስትመራ ኢኳዶርም በተመሳሳይ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ሴኔጋል ሦስት ነጥብ አላት። ኳታር ያለምንም ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛለች። በምድብ ሁለት እንግሊዝ ከዌልስ እና ኢራን ከአሜሪካ ምሽት አራት ሰዓት ይጫወታሉ። ምድቡን እንግሊዝ በአራት ነጥብ ትመራለች። ኢራን በሦስት ነጥብ ትከተላለች። አሜሪካ ሁለት ነጥብ ሲኖራት ዌልስ አንድ ነጥብ አላት። https://www.bbc.com/amharic/articles/c3g53x5d2dlo +business በፍራሹ ስር 137ሺ ብር ያስቀመጠው ኬንያዊ ገንዘብ ከመቀየሩ ጋር ተያይዞ ከሰረ "ኬንያ የመገበያያ ገንዘብ መቀየሯን ተከትሎ አንድ ግለሰብ 137 ሺ ብር (4ሺ 800 ዶላር) ከጥቅም ውጭ ሆኖበታል። ጁሊየስ ኦዲንጋ ምቦጋ የተባለው ግለሰብ 137 ሺ ብር የሚገመት ባለ አንድ ሺ የኬንያ ሺልንግ ገንዘብ ፍራሹ ስር አስቀምጦ የነበረ ሲሆን ገንዘብ ለመቀየር የተቀመጠበት ቀነ ገደብም በማለፉ ነው ለዓመታት ያጠራቀመው ገንዘብ ከጥቅም ውጪ የሆነበት። •ኬንያ ገንዘብ ከመቀየሯ ጋር ተያይዞ ከሰባት ቢሊዮን ሺልንግ በላይ ጥቅም አልባ ሆነ •ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት የገንዘብ ቅየራው በሃገሪቷ ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስና ለማስቀረትና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርንም ለመቆጣጠር እንዲያስችል እንደሆነ ተገልጿል። ግለሰቡ ከመንደሩ ሲያያ ግዛት ስልሳ ኪ.ሜትር ርቀት በሚገኘው የማዕከ���ዊ ባንክ በመገኘት አሮጌ የመገበያያ ገንዘቡን በአዲስ መልኩ ለመቀየር ሙከራ ቢያደርግም የገንዘብ መቀየሪያ ቀነ ገደቡ መጠናቀቁን ተከትሎ ለኪሳራ ተዳርጓል። •""የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም"" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመካኒክነት ስራ ሲተዳደር የነበረው ግለሰብ ለጡረታ ብሎ ያጠራቀመው ገንዘብ እንደሆነም ለደይሊ ኔሽን ተናግሯል። የማዕከላዊ ባንክ አስተዳደር እንዳሳወቁት አዲስ የመገበያያ ገንዘብ የታወጀው ሰኔ አንድ ቀን ሲሆን ከመስከረም ሃያ ጀምሮ አሮጌው የመገበያያ ገንዘብ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። •""ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው"" መስፍን ነጋሽ አፍሪካ ታክስ ጀስቲስ ኔትወርክ የተባለ ድርጅት እንዳሳወቀው በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት ኬንያ በየአመቱ 400 ሚሊዮን ዶላር እንደምታጣ አስታውቋል። ባንኩ እንዳስታወቀውም የገንዘብ ቅይይሩ መሳካቱንና ከዚህ በኋላ ስርአት ባለው መንገድ የገንዘብ ዝውውር እንደሚከናወን ነው።" https://www.bbc.com/amharic/50084810 +health ፋይዘር የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒቱን ታዳጊ አገራች እንዲያመርቱት ፈቀደ "ፋይዘር በሙከራ ደረጃ ያለውን የኮሮናቫይረስ ማከሚያ እንክብል መድኃኒቱን ታዳጊ አገሮች እንዲሠሩት እና እንዲያከፋፍሉት ፈቀደ። የአሜሪካው መድኃኒት አምራች ፋይዘር በ95 ታዳጊ አገራት እንክብል መድኃኒቱ እንዲመረት የተስማማው የተባበሩት መንግሥታት ከሚደግፈው ሜድስንስ ፔሸንት ፑል ድርጅት ጋር በመጣመር ነው። ድርጅቱ የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒቱን ከሠራ በኋላ 53 በመቶ ለሚሆነው የዓለም ሕዝብ ያዳርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ስምምነቱ እንደ ብራዚል ያሉ በከፍተኛ ሁኔታ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው አገራትን አያካትትም። መድኃኒቱ ለሕመም ተጋላጭ የሆኑ ጎልማሶች በጽኑ በሽታ እንዳይያዙ እንደሚከላከል ፋይዘር አስታውቋል። መድኃኒቱ በታዳጊ አገራት እንዲመረት መፍቀዱ ""የመድኃኒቱን ተደራሽነት ያሰፋዋል"" ሲል ገልጿል። በታዳጊ አገራት ከሚመረተው መድኃኒት ፋይዘር የባለቤትነት (ሮያሊቲ) ክፍያ አይወስድም። ወረርሽኙ ለዓለም አስጊ ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ በሁሉም አገራት ትርፍ እንደማይሰበስብም ይፋ አድርጓል። ፋይዘር ለኮቪድ-19 ማከሚያ እየሠራ ያለው ፓክሎቪድ የተባለ መድኃኒት ነው። ይህም በከፍተኛ ሁኔታ ለሕመም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ሞትና ሆስፒታል የመግባት እድልን በ89 በመቶ ይቀንሳል ተብሏል። የሜድስንስ ፔሸንት ፑል ኃላፊ ቻርልስ ጎሬ እንዳሉት መድኃኒቱ በታዳጊ አገራት እንዲመረት ፍቃድ መሰጠቱ መልካም ነው። ""ይህ መድኃኒት በተለይም አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ሕይወት ያድናል"" ብለዋል። መድኃኒቱን እንዲሠሩ ፈቃድ ካገኙ አገራት አብዛኞቹ በአፍሪካ እና እስያ ይገኛሉ። እንደ ብራዚል፣ ቻይና፣ ሩስያ፣ አርጀንቲና እና ታይላንድ ያሉ ክፉኛ በወረርሽኙ የተጎዱ አገራት በስምምነቱ አልተካተቱም። የኮሮናቫይረስ ሕክምና እንዲሁም ክትባቱን ተደራሽ ለማድረግ ይህ እርምጃ በቂ እንዳልሆነ ባለሙያዎች ተችተዋል። ፋይዘርን ጨምሮ ሌሎችም የኮቪድ-19 ክትባት አምራቾች የባለቤትነት መብታቸውን አንስተው፤ ክትባቱ በሌሎች አገራት እንዲመረት ፈቃድ እንዲሰጡ ቢጠየቁም አሻፈረኝ ብለዋል። ዶክተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ ባወጣው መግለጫ፤ ፋይዘር ለታዳጊ አገራት የሰጠው ፈቃድ የኮሮናቫይረስ መድኃኒት በመላው ዓለም እንዲደርስ እንደማይረዳ ተችቷል። ""ወረርሽኙን መግታት ከፈለግን የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒት ለሁሉም ሰው፣ በሁሉም አገር መዳረስ አለበት"" ሲሉ የድርጅቱ የሕግ አማካሪ ዩአንክዮንግ ሁ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም መርክ የተባለ�� መድኃኒት አምራች ድርጅት ሞልኑፒራቪር የተባለ የኮሮናቫይረስ መድኃኒቱ ከሜድስንስ ፔሸንት ፑል ጋር በጥምረት ለማምረት ተስማምቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59315766 +health 'በኮሮናቫይረስ ምክንያት የማስታወስ ችሎታዬን አጥቻለሁ' በኮሮናቫይረስ ለረጅም ጊዜ ከተሰቃዩ ሚሊዮን የዓለማችን ሰዎች መካከል ሮቼሌ ዴቪድ አንዷ ነች። ሮቼሌ ከቫይረሱ ካገገመች 10 ወራት ቢቆጠሩም አንድን ነገር ለማስታወስ ከአንድ ክፍል ወደ ሌላ ክፍል እየተራመደች መሆኗን ሐኪሟ ይናገራሉ። የኮቪድ-19 ሕመም የሚያስከትለው ጉዳት ለረጅም ጊዜ የሚቆይበት አንደኛው ምክንያት ድካም ነው። የራስ ምታት፣ የፀጉር መሳሳት፣ የትኩረት ማጣት፣ ጠረን እና ጣዕም መለየት አለመቻል የመሳሰሉት ምልክቶቹ ናቸው። https://www.bbc.com/amharic/news-59206703 +politics ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ከስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ባለው የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በቅን ልቦና በሚካሄድ ንግግር ከስምምነት እንዲደረስ የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው የቻይና-አረብ አገራት ጉባኤ ላይ ባደረጉት አገራቸውን እና የአረቡን ዓለም በሚመለከተው ንግግራቸው ነው። ወደ መጠናቀቁ የተቃረበውን የታላቁ ሕዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌትና የሥራ ሂደት በሚመለከት ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በተለይ ባለፉት አምስት ዓመታት ድርድር ቢያደርጉም ከስምምነት ላይ ሳይደርሱ መቅረታቸው ይታወሳል። ግድቡ ከዓባይ ወንዝ የማገኘውን የውሃ መጠን ይቀንስብኛል የሚል ስጋት ያላባት ግብፅ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በተለያዩ መድረኮች እንደሚያደርጉት ሁሉ አሁንም ከኢትዮጵያ ጋር ከስምምነት መድረስ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። አል ሲሲ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ እና የአረብ አገራት መሪዎች በታደሙበት ስብሰባ ላይ ባድረጉት ንግግር፣ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን አስገዳጅ ሕጋዊ ስምምነት እንዲደረስ ጠይቀዋል። “ለአሁኑ እና ለመጪው ትውልድ የመልማት መብትን የሚያረጋግጥ እና ትብብራቸውን፣ መረጋጋታቸውን እንዲሁም ደኅንነታቸውን ከስጋት የሚጠብቅ በቅን ልቦና ላይ የተመሠረተ ንግግር በማድረግ አሳሪ ሕጋዊ ስምምነት ላይ እንዲደረስ ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቼ በድጋሚ ጥሪዬን አቅርባለሁ” ብለዋል ፕሬዝዳንት አል ሲሲ። በተያያዘ ዜና የግብፅ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት እንዳሳወቀው ከቻይና-አረብ አገራት ጉባኤ ጎን ለጎን አል ሲሲ የስብሰባው ተሳታፊ ከሆኑት የሱዳን የሽግግር ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን ጋር ተወያይተዋል። በሁለቱ መሪዎች ንግግር ወቅት ውሃ የሕዝባቸው ብሔራዊ ደኅንነት ዋነኛ ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ፣ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ አሳሪ ሕጋዊ ስምምነት መድረስ አስፈላጊ መሆኑን አንስተው አል ቡርሐን የሱዳንን አቋም ማንጸባረቃቸው ተመልክቷል። ይህ የፕሬዝዳንት አል ሲሲ ጥሪ ከዚህ ቀደምም በራሳቸውን በበርካታ የግብፅ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አማካይነት ሲቀርብ የቆየ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ የግድቡ ጉዳይ አስከ መንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ድረስ ቀርቦ ነበር። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በሕዳሴው ግድብ ላይ ከስምምነት እንዲደርሱ ለማድረግ በአሜሪካ መንግሥት እና በአፍሪካ ኅብረት አማካይነት ተከታታይ ድርድሮች ሲካሄዱ ቢቆዩም፣ በግብፅ በኩል አስገዳጅ ሕጋዊ ስምምነት እንዲደረስ ያለው ፍላጎት በዓባይ ውሃ የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብቴን የሚጋፋ ነው በሚል ኢትዮጵያ ሳትቀበለው ቆይታለ��። ግንባታው አሥር ዓመታትን ያስቆጠረውና ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢትዮጵያን ያስወጣው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ከስምምነት ሳይደረስ እንዳይካሄድ ከግብፅና ከሱዳን ከፍተኛ ተቃውሞ ቢገጥመውም ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ እንዲይዝ ተደርጓል። በአፍሪካ ከውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጭት ከተገነቡ ግድቦች ሁሉ ግዙፉ እንደሆነ የሚነገረው ይህ የኢትዮጵያ ግድብ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በተወሰነ ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወቃል። ቢሆንም ግን ግብፅ አሁንም ከወንዙ የምታገኘውን የውሃ መጠን ለማስጠበቅ የሚያስችላትን በግድቡ አጠቃላይ የሥራ ሂደት ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ሕጋዊ ስምምነት እንዲደረግ ትፈልጋለች። አል ሲሲ ለመጀመሪያ ጊዜ በቻይና እና በአረብ አገራት መካከል በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ባድረጉት ንግግር ላይ የውሃ ደኅንነት ጉዳይ ከአገራቸው በተጨማሪ ሌሎች የአረብ አገራትንም የሚመለከት መሆኑን ጠቅሰዋል። በዚህም ወደፊት በቻይና እና በአረብ አገራት መካከል በሚኖረው ትብብር ውስጥ የአረብ አገራት የውሃ ደኅንነት ጉዳይ ቅድሚያ ከሚሰጠቸው ጉዳዮች መካከል ከፊት ሊሆን እንደሚገባው አል ሲሲ ተናግረዋል። የግብፁ ፕሬዝዳንት ንግግር ያደረጉበት በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የሚካሄደው የቻይና እና የአረብ አገራት ጉባኤ፣ ቻይና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ካሉ አገራት ጋር ያለትን ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ትስስሯን ለማጠናከር ከምታካሂደው ዘመቻ ጋር የተያያዘ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cv270n6lpzvo +health "ኮሮናቫይረስ ፡ ""ኮቪድ-19 የሚያስከትለው የአእምሮ ጤና ችግር ለብዙ አስርት ዓመታት ሊቀጥል ይችላል""- ፕ/ር መስፍን አርዓያ" "እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ ከኮሮናቫይረሰ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ በአፍሪካ የአእምሮ ጤና መታወክ እየተከሰተ መጥቷል። ድርጅቱ ባለፈው ሐሙስ እለት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተባለው፤ በአፍሪካ የአእምሮ ጤና መታወክ ከኮቪድ-19 በኋላ መጨመር አሳይቷል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሕክምና አገልግሎቶችን በማስተጓጎሉ ሁኔታውን የበለጠ ፈታኝ አድርጎታል። በዛምቢያ የአእምሮ ጤና ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሪም ዳላል እንዳሉት፤ በአህጉሪቱ ከወረርሽኙ በኋላ የአእምሮ ጤና ችግሮች ስለመባባሳቸው መረጃዎች አሉ። በዚህ ሳምንት በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1.5 ሚሊዮን ያለፈ ሲሆን ቢያንስ ከ36,787 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። በኢትዮጵያም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 82,662 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,271 ደርሷል። ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአእምሮ ህክምና ትምህርት ክፍል መምህር እና ሐኪም ናቸው። ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ የሚችሉ የአእምሮ ህመሞች በጣም ሰፊ መሆናቸውን ይናገራሉ። ወረርሽኙ በራሴ፣ በቤተሰቤና በአካባቢዬ ላይ ይከሰታል የሚለው ስሜት ከፍተኛ ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ድብርት እንዲያም ከፍተኛ ወደ ሆነ የአእምሮ መረበሽ ሊያደርስ ይችላል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኮቪድ-19 በአካል ላይ በሚያደርሰው ጉዳት ምክንያት በአካባቢያችንና በቤተሰባችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ከዚህም ጋር በተያያዘ የሚከሰተው ሰርቶ ያለማደርና ቤት ውስጥ ተዘግቶ መዋል ከፍተኛ ጭንቀትና ድብርት እንደሚያስከትል ይናገራሉ። ሕጻናትና ሴቶች በቤት ውስጥ ወይንም በአንድ አካባቢ ብቻ መዋላቸው ከሚያደርስባቸው የአእምሮ ጤና ችግር በላይ በተቃራኒ ጾታ የሚደርስባቸው ጥቃት መስተዋሉን ፕሮፌሰሩ ያነሳሉ። ላለፉት ሰባት ወራት ከመዋዕለ ሕጻናት ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድረስ ከትምህርት ገበታ ርቀው በቤት ውስጥ መቆየታቸውን በማስታወስም፤ ይህ የአእምሮ ጤና ላይ ጫና እንዳለው ያብራራሉ። ልጆች እየተሯሯጡ፣ ከእኩዩቻቸው ጋር ሲጫወቱ አካላቸው ብቻ ሳይሆን ማኅበራዊ መስተጋብራቸውም እያደገ እንደሚመጣ የሚያስረዱት ፕሮፌሰሩ፤ እነዚህ ሕጻናት በጋራ ሲጫወቱ አንዳቸው ከሌላኛቸው የሚማሩት እውቀትና ክህሎት ከፍተኛ መሆኑን በማንሳት፤ ለረዥም ወራት በአንድ አነስተኛ ግቢ ወይንም ቤት ውስጥ ተገድቦ መቀመጥ ለሕጻናቱ ከፍተኛ ጫና መሆኑን ያነሳሉ። ከዚህም የተነሳ ሕጻናቱ በከፍተኛ ሁኔታ ሊሰላቹ፣ ሊጨናነቁ፣ ሊወጣጠሩ ይችላሉ ብለዋል። ሕጻናቱ እንደ አዋቂዎች የሚሰማቸውን መናገር አለመቻላቸው ሌላው ችግር በመሆኑ ለተለያዩ የሕጻናት የአእምሮ ጤና ችግር ሊጋለጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል። በተለይ በከተማ የሚኖሩ እና የተማሩ የሚባሉት ወላጆች ልጆችን ከኤሌክትሮኒክስ ጋር ስለሚያጋፍጧቸው ለኮምፒውተር ጌም ሱስ እንደሚያጋልጧቸው ይገልፃሉ። በዚህም የተነሳ ትምህርት በሚከፈትበት ወቅት ከእኩዮቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዳ እንደሚችል ጨምረው አብራርተዋል። ወረርሽኞች የአእምሮ ጤና ችግር ያስከትላሉ? ""የሚገድሉ ሕመሞች በጣም ያስጨንቃሉ"" የሚሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ተላላፊ በሽታዎች ግለሰቦች ላይ ባይደርስ እንኳን ገና ለገና 'ይመጣብኛል' የሚለው ስጋት እንደሚያሳቅቅ ይናገራሉ። እንደ ኮሌራና ኢቦላ ያሉ ወረርሽኞች ተመሳሳይ ተጽዕኖ እንዳላቸው የሚገልፁት ፕሮፌሰሩ፤ የኮሮናቫይረስ ባህሪ በየጊዜው ይበልጥ በታወቀ ቁጥር የሚፈጥረው ስጋትና ጭንቀት እየጨመረ እንደሚመጣ ገልፀዋል። መጀመሪያ ላይ በእድሜ የገፉ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው የሚለው መረጃ ከተሰማ በኋላ፣ ወጣቶችና ሕጻናትም ተጋላጭ መሆናቸው መታወቁ፣ ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው የሚለው መረጃ ከተሰራጨ በኋላ፣ የሌለባቸውም ተጋላጭ መሆናቸው መታየቱ፤ ""ጭንቀት በሰው ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንዲመጣ"" ማድረጉን ይናገራሉ። ገና ለገና በሽታው ይመጣብኛል የሚለው አስጨናቂ መሆኑን ተናግረው፤ ጭንቀትን የሚያባብሰው ከራስ አልፎ ለቅርብ ቤተሰብ የሚኖረው ስጋት ነው ይላሉ። ቤተሰቦቼ ይያዙ ይሆን? ምልክት ሳላሳይ ቫይረሱን ይዤ እየዞርኩ ይሆን? በእድሜ የገፉ ወላጆቼን፣ ታማሚ ቤተሰቦቼን፣ ልጆቼን አስይዝ ይሆን? የሚሉት የበለጠ ያስጨንቃሉ። ከዚህ በሽታ ጋር ተያይዞ መጀመሪያ የሚከሰተው የጤና ችግር ጭንቀት የሚባለው መሆኑን ፕሮፌሰር መስፍን ይናገራሉ። ይህ ከቀላል ጭንቀት ጀምሮ እስከ ከፍተኛው እንደሚደርስ ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል። በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው በቤተሰብ ውስጥ ሲገኝ ደግሞ ሕመሙ በመከሰቱ ለበለጠ ጭንቀት መጋለጥ እንደሚኖር እንዲሁም ሊባባስ እንደሚችልም ያብራራሉ። በቫይረሱ የተያዘ የቤተሰብ አባል በሞት ሲታጣ ደግሞ ወደ ተራዘመ ሐዘንና ጭንቀት፣ ባስ ሲልም ወደ ድብርት ሊያስገባ ይችላል ይላሉ። ፕሮፌሰር መስፍን፤ ቫይረሱ በአካል ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ አንጎል ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖና ሊከሰቱ የሚችሉ አእምሮ ጤና ችግሮች ገና እየተጠኑ መሆኑን ይናገራሉ። አንዳንድ ጊዜ አንጎል ሲመረዝ ከፍተኛ የሆነ የመርሳት ችግር (ዲሜንሺያ) ወይንም ከፍተኛ የአእምሮ ሕመሞች ሊከሰቱ የሚችሉበት እድል አለ ይላሉ ፕሮፌሰሩ። እንደ አእምሮ ጤና ባለሙያ፤ ""ኮቪድ 19 በአካል ላይ ከሚያደርሰው ችግር በላይ፤ ከወረርሽኙ መረጋጋት በኋላ የሚመጣው የአእምሮ ጤና ችግር ለብዙ ዓሥርት ዓመታት ይቀጥላል ብለን እናምናለን"" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በኮቪድ -19 ተይዘው ሕመም የጠናባቸውና የትንፋሽ ማገዣ መሣሪያ ላይ ያሉ ሰዎች በ���ብዛኛው የመትረፍ እድላቸው አነስተኛ መሆኑን ያስታወሱት ፕሮፌሰር መስፍን፤ በመተንፈሻ ታግዘው ጤናቸው ሲመለስ ደግሞ ለከፍተኛ ጭንቀት እንደሚዳረጉ ማስተዋላቸውን ገልፀዋል። እነርሱ በመሣሪያ እየታገዙ ተንፍሰው ሲድኑ፤ ሌሎች ግን ከጎናቸው በመሣሪያ እየተረዱም መትረፍ ሳይችሉ ቀርተው ሲመለከቱ የሚደርስባቸው ሥነ ልቦናዊ ጫና እንዳለ ገልፀዋል። እነዚህ ሰዎች በመትረፋቸው ተመስገን ቢሉም ጭንቀትም ሆነ ድብርት ሊታይባቸው እንደሚችል ከልምዳቸው በመነሳት ያስረዳሉ። ፕሮፌሰሩ አክለውም በተለይ የሕክምና ባለሙያዎች ራሳቸውን መስዋዕት አድርገው ስለሚሠሩ ከራሳቸው አልፎ በእድሜ ለገፉ ወላጆቻቸው፣ ለቅርብ ቤተሰቦቻቸው ተጨንቀው ማስተዋላቸውንም ገልፀዋል። በኮሮናቫይረስ ዘመን ጭንቀትን መቆጣጠር አለመቻል፣ መቼም ቢሆን እርግጠኛ አለመሆን በሰዎች ዘንድ ተፈጥሯል። ጥርጣሬው የሚጀምረው ""ንፁህ ነኝ?"" ከሚል ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ትንሽ ቆይቶ ""ወደ ቀደመው ሕይወቴ መመለስ እችል ይሆን?"" ወደሚለው ያመራል። አካላዊ ርቀታችንን መጠበቅ ከቻልን፣ በተደጋጋሚ እጃችንን ከታጠብን፣ አገራት ያሳለፏቸውን ቤት የመቀመጥ መመሪያዎች ከተከተልን በቫይረሱ እንደማንያዝ እርግጠኛ ነን። ነገር ግን አእምሯችንን የሚነዘንዘን ጥርጣሬና እርግጠኛ አለመሆን፤ ከዚያም ጋር ተያይዞ የሚመጣው ጭንቀት ሕይወታችንን ሞልቶታል። የሚመላለሱት ሐሳቦች መጥፎ ስሜቶች ናቸው። ምናልባት ጭንቀቱ በትንሹም ቢሆን እንድንጠነቀቅ ያደርገን ነበር፤ ችግሩ ግን ከቁጥጥራችን ውጪ ይሆናሉ። ""ከመጠን በላይ መፍራት ለተለያዩ የእምሮ ጤና ችግሮች ይዳርጋል"" ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ አንዳንድ ሰዎች ከልክ ባለፈ ፍርሃት ተውጠው ማስተዋላቸውንም ጠቅሰዋል። ቤታቸውን ዘግተው የተቀመጡ እና እንቅስቃሴያቸውን የገደቡ፣ በተደጋጋሚ እጃቸውን በሳሙናና በውሃ የሚታጠቡ አልያም ሳኒታይዘር የሚጠቀሙ ሰዎች ከኮቪድ-19 በኋላ በሕክምና ቋንቋ ኦሲዲ (Obsessive-compulsive disorder) ለሚባለው ችግር እንደሚጋለጡ ይተነብያሉ። የማይፈለግና ለመቆጣጠር የሚያስቸግር ሐሳብ በሰዎች አእምሮ ሲመላለስ ኦሲዲ (ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር) ይባላል። አንድን ነገር ሱስ በሚባል ሁኔታ በተደጋጋሚ ከማድረግ ጋር ይገናኛል። ከፍተኛ ፍርሃት የሚመጣው ስለ ቫይረሱ ያለው ግንዛቤ እና እውቀት አነስተኛ ወይንም ቁንጽል ከመሆኑ የተነሳ ነው በማለት በየጊዜው የሚሰጡ የጤና መረጃዎችን ባለሙያዎች ማዳረስ እንዳለባቸው ይመክራሉ። ሐዘንን እና መረበሽን የመቋቋም አቅም ከሰው ወደ ሰው ስለሚለያይ ስለኮሮናቫይረስ የሚተላለፉ መረጃዎች በማያስፈራራና በማይረብሽ መንገድ በአግባቡ መሰጠት እንደሚኖርበት ይናገራሉ። ሰዎች በሚሰሙት መረጃ ተረብሸው ወደ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ራስን ወደመጥላት እና ከዚያም ወደ ከፋ እርምጃ እንዳይሄዱ የመገናኛ ብዙኀን፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ ወጣቶች ትክክለኛውን መረጃ ማድረስ እንደሚያስፈልጋቸው ይመክራሉ። የአእምሮ ጤናን መጠበቅ የሚቻለው ልክ ሌላው የአካል ክፍል ጤና እንደሚጠበቀው መሆኑን ፕሮፌሰር መስፍን ያስታውሳሉ። ንጹሕ አየር መተንፈስ፣ አመጋገብን ማስተካከል፣ መንፈሳዊ ሕይወትን ማጠናከር፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ጥሩ እንቅልፍ መተኛት፣ ከሱስ መጠበቅ ጠቃሚ መሆናቸውን በማንሳት፤ ለአካላዊ ጤና የሚጠቅሙት እነዚህ ነገሮች ለአእምሮም እንደሚያስፈልጉት ይገልፃሉ። በዚህ ወቅት ከጭንቀት እና ውጥረት ራስን መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ። እርስ በእርስ መተሳሰብ እንዲሁም መደጋገፍ አስፈላጊ መሆኑንም ያስታውሳሉ።" https://www.bbc.com/amharic/54485207 +sports በአውሮፓ ��ቦክስ ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው ትውልደ ኢትዮጵያዊ በዚህ ዓመት አርሜኒያ ውስጥ በተካሄደው የአውሮፓ የቦክስ ሻምፒዮና ላይ አየርላንድን ወክለው በቡጢው መድረክ ለመፎካከር ከተሰለፉ መካከል ጋብርኤል ዶሰን አንዱ ነበር። ትውልደ ኢትዮጵያዊው ጋብርኤል በዚህ ስፖርት በአየርላንድ ውስጥ ዝናው ከፍ ያለ ነው። በአርሜኒያ በተካሄደው የቦክስ ሻምፒዮና ላይም ስለብቃቱ መገናኛ ብዙኃን በአንድ ድምጽ ተርከዋል። የዶሰን ፈጣን ቡጢዎች፣ ተጋጣሚዎቹን ለመከላከልም ሆነ ለማጥቃት ፋታ ነስተው መታየታቸው ተመስክሯል። እነርሱ ጋብርኤልን፣ ጋቢ እያሉ ያቆላምጡታል። የጋልዌዩ ቡጢኛም የሚሉትም አሉ። መኖሪያ አካባቢውን በማጣቀስ። ጋብርኤል ለአገሩ አየርላንድ ወርቅ በማምጣት ባንዲራዋ ከፍ ብሎ አንዲውለበለብ፣ ስሟ በቡጠኞች እና በሻምፒዮናው አዘጋጆች ዘንድ እንዲናኝ አድርጓል። የ22 ዓመቱ ጋቢ፣ የወርቅ ሜዳልያውን ያጠለቀው እንግሊዛዊው ሉዊስ ሪቻርድሰንን አሸንፎ ነው። ሉዊስ ከጋቢ በቀኝ በኩል የሚሰነዘርበትን ፈጣን ቡጢ መቋቋም አለመቻሉን በቦክስ ሜዳው ላይ እና ዙሪያ የነበሩ ሁሉ ታዝነበዋል። ቢቢሲ ጋብሬል ዶሰንን ስለ ድሉ ሲጠይቀው፣ “ጥቁር አፍሪካዊ የኢትዮጵያ ልጅ፣ ሆኜ በቦክስ የአውሮፓ ሻምፒዮና በመሆኔ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል” ብሏል። በዚህ ድል በኩራት ልባቸው ሐሴት ካደረገ ሰዎች መካከል ደግሞ እናቱ ምሥራቅ ተስፋዬ አንዷ ነች። “ልጄ እኔን እና ቤተሰቦቼን ብቻ ሳይሆን፣ . . .አጠቃላይ ጥቁር አፍሪካውያንን አኩርቷል። የአውሮፓ ሻምፒዮና መሆኑ ለየት ያለ ስሜት አለው” ትላላች። ጋብርኤል በዚህ ውድድር ላይ የወርቅ ሜዳልያ በማጥለቅ ሻምፒዮና ለመሆን በመጀመሪያ የስፔን ተወዳዳሪውን፣ በመቀጠል የቡልጋርያን፣ ወደ ፍጻሜ ለማለፍ ደግሞ የኖርዌይ ተጋጣሚዎቹን በዝረራ አሸንፏል። “አሁን እኔ በቦክስ የአውሮፓ ሻምፕዮን ነኝ። ነገር ግን ያሸነፍኩ ቀን ለማመን ደቂቃዎች ፈጅቶብኛል። ጥቁር አፍሪካዊ፣ የአየርላንድ ዜጋ ሆኜ፣ ደግሞም ከኢትዮጵያ የተገኘሁ ሆኜ በአውሮፓ መድረክ ላይ ሻምፒዮና መሆኔ፣ በጣም አስገርሞኛል። በዚያ ቅጽበት የተሰማኝን መግለጽ ከባድ ነው” ይላል ጋብርኤል። እናቱ ምሥራቅ ተስፋዬ ደግሞ፣ ውድድሩ መክፈቻ ላይ ጋብርኤል ከተጋጣሚው ጋር ሲገናኝ አየርላንዳውያን በአጠቃላይ በጉጉት ሲጠብቁ እንደነበር አስታውሳለች። ሲያሸንፍ የተሰማቸውንም ስትናገር  “ዜጎቻቸውን በሙሉ ይወዳሉ። ጥቁር ነጭ ሳይሉ። እርሱ ሲያሸንፍ መላ አገሪቱ ላይ ትልቅ ደስታ ነበር” ብላለች። ጋብርኤል የተወለደው አይቮሪኮስት ውስጥ ነው። አባቱ የላይቤሪያ ዜግነት ያለው ሲሆን በእናቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነው። ከዓመታት በፊት እናቱ በአይቮሪኮስት በስደተኝነት ትኖር ነበር። ያኔ ነው የዶሰን አባት እና ምሥራቅ የተገናኙት። ዶሰን እና ምሥራቅ ተጋብተው ጋብርኤል በተወለደ በሁለት ዓመቱ ወደ አየርላንድ አመሩ። ጋብርኤል ዘጠኝ ዓመት ሲሞላው ደግሞ የቦክስ ሥልጠና መውሰድ ጀመረ። በ16 ዓመቱ ለአየርላንድ ታዳጊ ቡድን ተመርጦ፣ በአውሮፓ መድረክ አገሩን አየርላንድን በመወከል ለንደን ላይ ተወዳደረ። እኤአ በ2019 የአየርላንድ ብሔራዊ ቦክስ ውድድር ላይ ተሳትፎ በአንደኝነት ማሸነፍ ችሏል። ጋቢ ገና ስፖርት ሲጀምር ‘በኪክ ቦክሲንግ’ እንደነበረ ይናገራል። ከቦክስ በተጨማሪ ዋና፣ እግር ኳስ እንዲሁም ቴክዋንዶ የእርሱ የስፖርት ምርጫዎች ናቸው። በቴክዋንዶ ስፖርትም የጥቁር ቀበቶ ማግኘቱን ለቢቢሲ ገልጿል። እድሜው 19 ሲሞላ፣ ወደ ቦክስ አመዝኖ ለብሔራዊ ቡደን ተመረጠ። ጋብርኤል በቦክስ ቡድን ውስጥ ታቅፎ ሥልጠና ሲያደርግ መቆየቱን ይና��ራል። ከአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን ጋር በመሆን ደግሞ ከማክሰኞ እስከ አርብ ልምምድ ያደርግ ነበረ። ጋብርኤል ለቤቱ የመጀመሪያ ልጅ ሲሆን፣ አረን ዶሰን የሚባል ታናሽ ወንድም አለው። አረን በእግር ኳስ ብቃቱ ይታወቃል። የእንግሊዙ ቼልሲ እግር ኳስ ቡድን ለታዳጊ ክለቡ መልምሎት እንደነበር እናቱ ምሥራቅ ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ ወቅት ተናግራለች። “እኔም ከእርሱ ጋር መሄድ ስለነበረብኝ ለሌሎች ልጆቼ ብዬ መሄድ አልቻልኩም። በዚህ ምክንያት ይህ ዕድል አመለጠው። ለሌሎቹ በማሰብ ነው እዚህ የቀረሁት” ትላለች። ነገር ግን አረን፣ በአሁኑ ወቅት ለጎልዌይ ከተማ ስለሚጫወት “አሁንም ዕድል አለው ብዬ አምናለሁ”  ስትል ተስፋዋን ተናግራለች። የጋብርኤል እህት ኢቭ ዶሰን ደግሞ 17 ዓመቷ ሲሆን፣ በእግር ኳስ ለአየርላንድ ከ19 ዓመት በታች የእግር ኳስ ቡድን ተመርጣለች። አንድ የስኮትላንድ እግር ኳስ ቡድን ሊያስፈርማት ጠይቋት የነበረ ሲሆን፣ ትምህርቷን መጨረስ እንዳለባት ቤተሰቡ በመወሰኑ እናቷ ወደ ስኮትላንድ እንዳትሄድ እንደከለከለቻት ለቢቢሲ ተናግራለች። እናታቸው ምሥራቅ ልጆቿ ለስፖርት ስላላቸው ፍቅር ስትጠየቅ፣ “በአንድ ሳምንት ሰባቱንም ቀን መኪና ውስጥ ነው ውለን የምናድረው፣ መኪናችንን እንደ ቤት ነው የምንጠቀመው፣ ቀን ቀን ትምህርት ቤት ይውላሉ። አድርሼያቸሁ እመልሳቸዋለሁ። “ከዚያ በኋላ ደግሞ ለሥልጠና ወደ ተለያዩ ቦታዎች አደርሳቸዋለሁ። በየሁለት ሳምንቱ ደግሞ ወደ ተለያዩ ቦታዎች እወስዳቸዋለሁ። እኔ ደግሞ እነርሱን ለማሳደግ እና ለማስተማር ሥራ እሰራለሁ። ሕይወታችን ይህንን ነው የሚመስለው” ትላለች። ጋብርኤል እዚህ ስኬት ላይ ለመድረስ ከ10 ዓመት በላይ ወስዶበታል። አሁን የልፋቱን ውጤት በማየታቸው ቤተሰቡ ደስተኞች ናቸው። ጋቢ ከአርሜኒያ ወርቅ አሸንፎ ወደ አየርላንድ ሲመለስ ቤተሰቦቹ እና የእግር ኳስ ቡድኑ ደማቅ አቀባበል አድርጎለታል። ይህ ግን ለእናቱ ምሥራቅ ተስፋዬ ስሜት የሚበርዝ ነበር። ኢትዮጵያ ወገኖቹ መካከል ቢሆን ይሄኔ ደስታውና ሆታው የተለየ ነበር ስትል አስባ እንደ ከፋት ለቢቢሲ ተናግራለች። እናት ምሥራቅ ለላለፉት 11 ዓመታት ልጆቿን ብቻዋን ማሳደጓን ትናገራለች። “የልጆቼን ሕልም ለማሳካት ቀንና ሌሊት ነው የምሰራው። አንዳንዴ ማሽን አልያም ሰው መሆኔን እጠራጠራለሁ፤ እራስ ደካማ ሆኖ ልጆችን በርቱ ማለት አይቻልም። ሰርቶ ለልጆችህ ማሳየት ያስፈልጋል።” ከአየርላንድ ምንም እርዳታ እንደሌላት የምትናገረው ምሥራቅ፣ ከፍተኛ ሥራ ዕድል ስላለ ሰርታ ያሰበችው ደረጃ መድረስ እንደምትችል ትናገራለች። ጋብርኤል ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የእናቱን የትውልድ ስፍራ ማየት ሕልሙ ነው። “የእናቴ ትውልድ ቦታ ሐረጌ ስለሆነ አንድ ቀን ሄጄ ብጎበኝ ብዬ አስባለሁ።” ጋብርኤል በቶኪዮ ኦሊምፒክ በቦክስ ውደድድር ለመሳተፍ እየተዘጋጀ ሳለ በደረሰበት ጉዳት የተነሳ ሳይሳካለት ቀርቷል። ቀጣዩ የኦሊምፒክ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ግን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cpdn44d94klo +politics ተቃዋሚዎች 'ስላቅ' ነው ያሉት ምርጫ በሶሪያ እየተካሄደ ነው "በሶሪያ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ እየተደረገ ባለው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሽር አል አሳድ ለ4ኛ ጊዜ ለ7 የስልጣን ዓመታት ለመምራት አሸናፊ እንደሚሆኑ እርግጥ እየሆነ ነው። የፕሬዝዳንት አሳድ ተፎካካሪዎች ሆነው የቀረቡት ብዙም የማይታወቁ አብደላ ሳልሙንና ማህመድ አህመድ የተባሉ ፓለቲከኞች ናቸው። ምርጫው ከተካሄደባቸው በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ አካባቢዎችን የተቆጣጠሩ ተቃዋሚዎች ምርጫውን ቀልድ ነው ያሉት ሲሆን የአሜሪካና አውሮፓ ፓለቲከኞች ደግሞ ፍትሀዊና ነፃ ያልሆነ ምርጫ ነው ሲሉ ገልፀዋል። ፕሬዝዳንት አሳድ ድምፃቸውን በሰጡበት ወቅት በሰነዘሩት አስተያየት የምዕራባውያን አስተያየት ""ዜሮ"" ተብሎ ተቆጠረ ብለዋል። በአውሮፓውያኑ የዘመን ስሌት በ2011 ዲሞክራሲን እንፈልጋለን ያሉ ተቃዋሚዎች ላይ የበሽር አል አሳድ መንግስት የኃይል እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ የተቀሰቀሰ ግጭት 10 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ሶሪያን 'እንዳልነበረች' አድርጓታል። የ55 ዓመቱ በሽር አል አሳድ እንደ አውሮፓውያኑ 2000 ላይ ነበር ከሩብ ምዕተ ዓመት ለሚልቅ ጊዜ ሀገሪቱን የመሩትን አባታቸውን ተክተው ፕሬዝዳንት የሆኑት። ከሰባት ዓመታት በፊት ሀገሪቱ በግጭት ውስጥ ሆናና ተቃዋሚዎች ለመሳተፍ ባልተስማሙበት ምርጫ ፕሬዝዳንት አሳድ 88 በመቶ የሚሆነውን ድምፅ በማሸነፍ ለ3 ጊዜ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠው ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-57264684 +politics የተመሠረተው አዲሱ መንግሥት ከከዚህ ቀደሞቹ በምን ይለያል? ዛሬ ሰኞ መስከረም 24/2014 ዓ.ም አዲሱ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥራውን በመጀመር ለቀጣይ አምስት ዓመታት አገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚመራውን ግለሰብ ይሰይማል። ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የሥራ አስፈጻሚ መዋቅርና በካቢኔው ውስጥ ሆነው በሚኒስትርነት የሚያገለግሉ ዕጩዎችን በምክር ቤቱ አስሹሞ በይፋ ሥራውን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት ሰኔ 14 በተካሄደው ምርጫ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሊቀመንበርነት የሚመራው የብልጽግና ፓርቲ ምርጫው በተካሄደባቸው አከባቢዎች ከፍተኛ የበላይነትን በፌደራልና በክልል ምክር ቤቶች ውስጥ ለማግኘት ችሏል። ይህም ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለፓርቲያቸው ተጨማሪ አምስት የሥልጣን ዘመናትን የሚጨምር ሲሆን፤ ዛሬ ሥራውን በሚጀምረው ምክር ቤት ውስጥም ይኸው ይንጸባረቃል ተብሎ ይጠበቃል። በሁለት ዙር ተከፍሎ በተካሄደው ምርጫ ውስጥ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም የተደረገው የመጀመሪያው ዙር በአብዛኞቹ የአገሪቱ ከፍሎች ድምጽ የተሰጠበትና ውጤቱም የታውቆ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አዲሱን አስተዳደር ዛሬ ይመሰርታሉ። ባለፈው ሳምንት የተካሄደው ሁለተኛው ዙር የምርጫ ውጤት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጸድቆ ይፋ ባይደረግም፤ ቀደም ባለው ምርጫ አብዛኞቹ የምክር ቤት መቀመጫዎች ውጤት በመታወቁ በሕጉ መሠረት በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት አዲሱ መንግሥት ይመሰረታል። ዛሬ የመጀመሪያ ጉባኤውን የሚያካሂደው ስደስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት 547 መቀመጫዎች ውስጥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርቲ 410 ወንበሮችን እንዳሸነፈ ይፋ መደረጉ ይታወሳል። ባለፉት ሁለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዘመናት ገዢው ኢህአዴግ ከ547ቱ መቀመጫዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ፓርላመውን ተቆጣጥሮት እንደነበር ይታወሳል። ምርጫው ዘግይቶ በተካሄደባቸው ክልሎችና አካባቢዎች የሚገኘው ውጤት ገና የሚታወቅ ቢሆንም፤ ምንም እንኳን የተጠበቀውን ያህል ባይሆንም በተወሰነ ደረጃ ተቃዋሚዎችና የግል ዕጩዎች ምክር ቤቱን ተቀላቅለዋል። በአዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ ግልጽ የበላይነትን በመያዝ አብዛኛውን መቀመጫ ይያዝ እንጂ፤ አሁን ባለው መረጃ መሠረት 11 መቀመጫዎችን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ሲያሸንፉ፣ አራት መቀመጫዎች ደግሞ በግል በተወዳደሩ ዕጩዎች ተይዘዋል። በምርጫው ከተሳተፉት 47 ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ሦስቱ አስራ አንድ መቀመጫዎችን ያገኙ ሲሆን እነሱም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) 5፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 4 እና የጌዲዮ ሕዝብ ዴሞክራሲኣ�� ድርጅት (ጌህዴድ) 2 መቀመጫዎችን አግኝተዋል። በተጨማሪም በግል ቀርበው ከተወዳደሩት 125 በዕጩነት መካከል አራቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውክልናን አግኝተዋል። እነዚህም የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የኦነግ ቀደምት መስራቾችና አባላት የነበሩት አቶ ዲማ ነገዎና አቶ ገላሳ ዲልቦ እንዲሁም ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ናቸው። ምርጫው ዘግይቶ በተደረገባቸው የሶማሌና የሐረሪ ክልሎች አጠቃላይ ውጤት ገና ባለመታወቁ በአዲሱ ምክር ቤት ምስረታ ላይ እንደራሴዎቻቸው አይገኙም። እንዲሁም ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ጦርነት በተቀሰቀሰበት ትግራይ ክልል ውስጥ ምርጫው ባለመካሄዱ የክልሉ 38 ውክልናዎች ባዷቸውን ይቆያሉ። ዛሬ በሚመሰረተው ምክር ቤት ውስጥ ከፍተኛውን የበላይነት የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ይሰይማል። በዚህም መሠረት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን ላይ እንደሚቆዩ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት አስተዳደራቸውን የመሰረቱት ክልሎች ላይ እንደተስተዋለው በአዲሱ የፌደራል መንግሥቱ ካቢኔ ውስጥ ተቃዋሚዎች ቦታ እንደሚያገኙ ይጠበቃል። በኦሮሚያ፣ በአዲስ አበባ፣ በአማራና በደቡብ ምክር ቤቶች ምስረታ ወቅት እንደታየው በተወሰነ ደረጃ ተቃዋሚዎች ሥልጣን እንዲጋሩ ተደርገዋል። ቀደም ሲል ብልጽግና ፓርቲ ሲል እንደነበረው አዲስ በሚመሰረተው ካቢኔ ውስጥ ተቃዋሚዎች ሊካተቱ ይችላሉ። አንዳንዶች እንደሚገምትቱም ብልጽግና ከተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆነ በግል ከሚሳተፉ ግለሰቦች መካከል ጉልህ የሚባሉ የሥልጣን ቦታዎችን ሊያጋራ ይችላል። ከእነዚህ መካከልም በምርጫው ከፍ ያለ ውጤትን ያገኛል ተብሎ የተጠበቀው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ከፍተኛ ግምት ተሰጠው ተቃዋሚ ነው። ከመንግሥት ምስረታው ቀናት ቀደም ብሎ ጉባኤውን ያካሄደው ኢዜማ ከብልጽግና ፓርቲ አብሮ የመስራት ጥያቄ እንደቀረበለት የገለጸ ሲሆን፤ ይህንንም ጥያቄ ተወያይቶበት መቀበሉን አሳውቋል። ምናልባትም ይህ ጥያቄ በፓርቲው ውስጥ ካሉ ፖለቲከኞች መካከል መሪውን ጨምሮ አንዳንዶቹን በፌደራል መንግሥቱ የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለመሾም ዕድል ሳይፈጥር እንደማይቀር ተገምቷል። በተመሳሳይም በግል ተወዳድረው የምክር ቤት መቀመጫዎችን ካገኙት እንደራሴዎች መካከልም በአዲሱ መንግሥት ካቢኔ እና በሌሎች የሥልጣን ቦታዎች ላይ ሊመደቡ የሚችሉበት ዕድልም አለ። ይህ ሁሉ የሚሆነው ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሰብስቦ ከአባላቱ መካከል ቀጣዩን ጠቅላይ ሚኒስትር ከሰየመ በኋላ የተለያዩ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን የሚመሩ ሚኒስትሮችን አቅርቦ ይሁንታን ሲያገኝ ነው። በምክር ቤቱ የሚመረጠው ጠቅላይ ሚኒስትር አገሪቱ አሁን ያለችበትን ሁኔታ እንዲሁም በቀጣይ አምስት ዓመታት የሚያከናውናቸውን ዋነኛ ተግባራቱን በተመለከተ ንግግር ያደርጋል። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የፌደራል አስተዳደር ከዚህ ቀደም ከነበሩት የተለየ የሚያደርገው ሥነ ሥርዓት እንደሚኖር እየተነገረ ነው። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ከሚካሄደው የመጀመሪያው የእንደራወሴዎች ስብሰባ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር መሰየምና የካቢኔ ሚኒስትሮች ሹመት በኋላ በመስቀል አደባባይ ሌላ ዝግጅት እንዳለ የአገር ውስጥ መገኛኛ ብዙኃን እየዘገቡ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞም በአዲሱ መንግሥት ምስረታ ላይ ለመታደም የውጪ አገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ወደ አዲስ አበባ እየገቡ መሆናቸውን ከቅዳሜ ጀምሮ እየተነገረ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-58756172 +business ሎተሪ በአንድ ጀንበር ሚሊዬነር ያደረጋቸው ሰዎች ምን አሉ? "ይበለውና ዛሬ ድንገት ዝሆን ሎተሪ ቢደርስዎ ምን ያደርጉበታል? የሀብታሞች አገሮቹ ዝሆን ሎቶሪ። ምናልባት እንደ ዝሆን ጎምለል እያሉ ዓለምን ይዞሩ ይሆናል። ምናልባት ቀሪ ሕይወትዎን በተድላ ይመሩ ይሆናል። ምናልባት ከዚያ በኋላ በደስታ ሕንድ ውቅያኖስ ጠልቀው በሐሴት ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ብቅ የሚሉ ይመስልዎት ይሆናል። ነገሩ እንደዚያ ላይሆን ይችላል ብለው አስበው ያውቃሉ? በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ መናጢ ጋዜጠኛ ከሚዘባርቅ የደረሳቸው ቢናገሩት ሳይሻል አይቀርም። አዲ ጉድቻይልድ ባለፈው ዓመት የ71 ሚሊዮን ፓውንድ ሎተሪ አሸነፈ። ዩሮ ሚሊዮንስ የሚባለውን ዝሆን ሎቶሪ ነበር ያሸነፈው። ከዚህ በኋላ ጡረታ ወጥቼ ቁጭ ብዬ እበላለሁ ብሎ ነበር። ቁጭ ብሎ መብላት ደስታን የሚያመጣ ነገር እንዳልሆነ የተረዳው ግን ዘግይቶ ነው። አዲ ብቻውን አይደለም። ጄን አለች። ""ሎተሪ ማሸነፌ ሕይወቴን አተራማምሶታል"" ጄን ሬስቶሪክ ሎተሪ ሳይደርሳት በፊት ጄን ፓርክ ነበር ስሟ። ስሟን እንድትቀይር ብቻም ሳይሆን ሕይወቷም እንዲቀየር ያደረጋትን ሎተሪ ያሸነፈችው የዛሬ 4 ዓመት ግድም ነበር። በብሪታኒያ ታሪክ ሎተሪን በማሸነፍ ልጅ አግሯ እሷ ናት፤ ጄን። ሎተሪው ሲደርሳት የሆነ አስተዳደር ቢሮ ውስጥ ትንሽዬ ሥራ ነበረቻት። በኤደንብራ በትንሽዬ አፓርታማ ውስጥ ከእናቷ ጋር ትኖር ነበር። ጄን አንድ ሚሊዮን ዶላር ሎተሪው እንደደረሳት በፌስቡክ አወጀች። ከዜናው ጋር የመደነቅ ኢሞጂ የሚሉትን (እኛ ለዚህ የሎቶሪ አዝናኝ ታሪክ ደቂቀ ገጽታ ብለን የምንጠራውን የማኅበራዊ ሚዲያ አሻንጉሊት ሳቅ) አስከተለች። መጀመሪያ ያደረገችው ውድ የቺኋሄ ቡችላ ዝርያን (Chihuahua dog) የሳሎን ውሻ መግዛት ነበር። ፕሪንሰስ ብላ ጠራቻት። ከዚያ ውድ የንግድ ስም ያለውን አንድ ቦርሳ መግዛት ህልሟ ነበር። እንዳሰበችውም የሉዊ ቪቶ (Louis Vuitton) ቅንጡ ፋሽን የእጅ ቦርሳ ገዛች። በእነዚህ ሁለት ወጪዎች ብቻ 10 ሺህ ፓውንዶች እልም ብለው ሄዱ። ከዚያ በኋላ ግን ግራ ገባት። ሕይወቴ እላዬ ላይ ሲፈርስ ነበር የሚታየኝ ብላለች ከሦሰት ዓመት በፊት በሰጠችው አንድ ቃለ ምልልስ። በየቀኑ ስነሳ የማስበው ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነገር ነበር። ያ ስሜት ደስ አይልም ትላለች። ይህን ሐሳቧን ከአእምሮዋ ማውጣት ግን አልቻለችም። ""ምነው ይሄ ሎተሪ ጭራሽ ባልደረሰኝ"" ብላ እስከመመኘት ደርሳም ነበር። የአንድ ሚሊዮን ፓውንድ ሎተሪ ለ17 ዓመት ልጅ አደገኛ ነገር ነው። ይሄ ምንም አጠራጣሪ አይደለም። ""ምን ማድረግ ነው ትክክል የሚለውን ነገር የሚመራኝ ሰው አልነበረም"" ትላለች። ሎተሪው ከደረሳት በኋላ ወዳጅ ዘመዶቿ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ዓይን ዓይኗን ማየት ጀመሩ። ይቺ ልጅ ""የገንዘብ ችግራችንን የምትቀርፍልን"" በሚል መነጽር ብቻ ያይዋት ጀመረ። ""ሰዎች እኔን የሚፈልጉኝ ከሎተሪ ገንዘቡ ጋር በተያያዘ ብቻ መሆኑን ስረዳ ጭንቀት ውስጥ ገባሁ"" ትላለች። የሎተሪው ድርጅት ኃላፊ ካሜሎት በበኩላቸው ""ለልጅቷ የሥነ ልቦና ደጋፍ ብቻም ሳይሆን ገንዘቧን እንዴት ማስተዳደር እንዳለባት የሚያማክራት ሰው በነጻ አቅርበንላት ነበር"" ሲሉ ጥፋቱ ከእነሱ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ""ሚሊየነር ብሆንም ሥራዬን እወደዋለሁ"" ሱ ሪቻርድስ በ2016 ወደ ቤት እየሄደች ነበር። እግረ መንገዷን ሱፐር ማርኬት ገብታ ፈጣን ሎተሪ ገዛች። ነገሩን ከቁብም አልቆጠረችውም ነበር። እንደጨዋታ ነበር የገዛችው። ቤት ገብታ ፋቀችው። 3 ሚሊዮን ፓውንድ አሸናፊ አደረጋት። ደስታዋ ወደር አልነበረምው። ከባሏ ጋር ወደ ኢሴክስ ከተማ ሄደው ቤት ገዙ። አራት መኪኖችን እላዩ ላይ መረቁበት። ከዚያ በኋላ ደግሞ ዓለምን ዞር ዞር ብለው ማየት ጀመሩ። ���ልጆቻቸውም የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ አሟሉ። ባለፈው ዓመት ሚስ ሪቻርድ ከባለቤቷ ጋር ሆና ሎተሪ ያሸነፉበትን አራተኛ ዓመት አከበሩ። የቤታቸው ግቢ አፀድ ውስጥ በርከት ያለ ብር አውጥተው በሻምፓኝ ነበር ያከበሩት። ሚስ ሪቻርድስ ሚሊየነር ብትሆንም ቅሉ በሳምንት 90 ሰዓት አዛውንት ተንከባካቢ ሆና ትሰራለች። ምን በወጣሽ ትለፊያለሽ? ስትባል ""ሥራዬን እወደዋለሁ"" ነው መልሷ። ምናልባት ከሚሊዮን ዶላሩ ባሻገር የደስታዋ ምንጭ ሥራዋ ሳይሆን አልቀረም። ""ሚሊየነር መሆን ያን ያህልም አልደነቀኝም"" በታኅሣስ 2017 ሜሊሳ ኤድ ወደ ሐል ነዳጅ ማደያ ገባች። እሷም እንዲሁ የሚፋቅ ሎተሪ ገዛች። ፈጣኑን። በሦስተኛው ቀን ባንክ ደብተሯ አብጦ ሊፈነዳ ደርሶ አገኘችው። 5 ሚሊዮን ፓውንድ ገብቶበታል። ""በአንድ ጀንበር የባንክ ደበተሬ ከአንደ ፓውንድ ወደ 5 ሚሊዮን ፓውንድ ተመነደገ"" ብላ ነበር ለቢቢሲ። ሜሊሳ ሚሊየነር ከመሆኗ በፊት ማታ ማታ የታክሲ ሾፌር ነበረች። ቤሳ ቤስቲን አልነበራትም። ""ሕይወት በጣም ፈተና ሆናብኝ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ገንዘብ ስለማይኖረኝ እራት እንኳን የማልበላበት ጊዜ ነበር"" ትለላች። ካሸነፈች በኋላ 3 ሚሊዮን ፓውንዱን ኢንቨስት አደረገችው። ቤት ገዛች። የቤተሰቧንና የጓደኞቿን እዳቸውን ከፋፈለች። ሕይወታቸውን ለወጠች። ይህን ሁሉ አሳክታም እንዲህ ትላለች። ""ሰዎች ሎተሪ ሁሉን ነገር የሚቀይር ይመስላቸዋል። ያን ያህልም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም። ከጊዜ በኋላ ሁሉም ነገር ወደነበረበት ይመለሳል"" ትላለች። ""ብዙ ሰዎቸ ገንዘብ ሁሉንም ችግር የሚቀርፍ ይመስላቸዋል። ውሸት ነው። ሚሊየነር መሆን ደስተኛ መሆን ማለት እንዳልሆነ እኔ ህያው ምስክር ነኝ"" ብላ ነበር ለቢቢሲ። ""በኬክ ላይ የተንሸራተትኩ ያህል ተሰማኝ"" ሪቻርድና ካቲ ብራውን ጋዜጠኞች ነበሩ። ሳያስቡት 6 ሚሊዮን ፓውንድ አሸነፉ። ለነገሩ ሎተሪ ማን አስቦት አሸንፎ ያውቃል። እነ ሪቻርድ ወዲያውኑ ዓለምን መዞር ጀመሩ። በበረዶ ወደተሸፈነው የአንታርክታካ አህጉር ሄደው በረዶ ሸርተቴ ተጫውተዋል። ህልማቸውም እሱ ነበር። ""በኬክ ላይ የመንሸራተት ያህል ነው"" ይላሉ የሕይወታቸውን መቃናት ሲያሰምሩበት። ባልና ሚስቱ አሁን ጡረታ ወጥተዋል። በሰሜን ዋልታ በባህር ቀዘፋ እየተጫወቱ ዓመቱን ሙሉ ሽር ብትን እያሉ ለማሳለፍ ነው ያቀዱት። ""በሎተሪ ያገኘነው ገንዘብ በሕይወታችን ከሚያስፈልገን የገንዘብ መጠን እጅግ የበዛ ነው። ስለዚህ በተቻለ መጠን ቤተሰባችን ከእኛ መልካም ዕድል ተጋሪ ማድረግ ነው የምንሻው"" ብለዋል ለቢቢሲ። ሚሊየነር መሆን የገንዘብ ችግርን ይቀርፍ ይሆናል እንጂ በራሱ የደስታ ምንጭ እንዳልሆነ ግን ያሰምሩበታል። ባልና ሚስቱ።" https://www.bbc.com/amharic/news-55156381 +business ሕንዳውያን የስኳር ምርት ስለተትረፈረፈ አብዝተው እንዲጠቀሙ ተነግሯቸዋል ሕንድ በጣም የበዛ ስኳር በማምረቷ ሕዝቧ ስኳር አብዝቶ እንዲጠቀም እየመከረች ነው። የሕንድ ስኳር ምርት ማሕበር ስኳር ጤና ላይ ጉዳት ያመጣል የሚባለውን ችላ ብለው ሰዎች አብዝተው እንዲጠቀሙ መክሯል። ሕንዳውያን በአማካይ በዓመት 19 ኪሎ ግራም ስኳር ይጠቀማሉ። ይህ ደግሞ ከተቀረው ዓለም ሲነፃፀር አነስተኛ ነው። ቢሆንም ሕንድ ካላት ሕዝብ አንፃር ከፍተኛ ስኳር ተጠቃሚዋ ሃገር ናት። . ሕንዳውያን ከልጅና የልጅ ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩት ለምንድን ነው? . ትራምፕ ስለ ሕንድ የአየር ብክለት የተናገሩት በርካቶችን አስቆጣ . የቶልስቶይ መፅሐፍ ህንዳውያን 'አክቲቪስቶች' ላይ መዘዝ አምጥቷል የሕንድ የስኳር ምርት መጠን በዚህ ዓመት በ13 በመቶ አድጎ 31 ሚሊዮን ቶን ምርት እንደሚመረት ይጠበቃል። ነገር ግን መንግሥት ���ንደ ሌላ ጊዜው በገፍ ለውጭ ገበያ ማቅረቡን ትቶ ለሕዝብ ሊያከፋፍል ይችላል ተብሏል። የስኳር ምርት ማሕበሩ ድረ-ገፁ ላይ ስኳር መጠቀም እንደማይጎዳ የሚጠቁም ማስታወቂያ ለቋል። ማሕበሩ ሰዎች ለሚሰሯቸው ምግቦች ሌላ ዓይነት ማጣፈጫ ከሚጠቀሙ ስኳር ቢጠቀሙ የተሻለ እንደሆነ የሚጠቁሙ ማስታወቂያዎች እየለቀቀ ነው። የሕንድ የምግብ ሚኒስቴር ሱዳንሹ ፓንዴይ የሕንድ ማሕበረሰብ ለስኳር ያለው አስተሳሰብ የተዛባ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። እርግጥ ነው በሌሎች ሃገራት ሰዎች የስኳር አጠቃቀማቸውን እንዲያስተካክሉና ቀነስ እንዲያደርጉት ነው የሚመከሩት። ስኳር ከመጠን ላለፈ ክብደትና በተለምዶ ስኳር በሽታ ተብሎ ለሚታወቀው ዳያቢቲስ ሊያጋልጥ ይችላል ይላሉ ባለሙያዎች። የዓለም ጤና ድርጅት የተለያዩ ምግቦች ውስጥ፤ በተለይ ደግሞ ማርና የፍራፍሬ ጭማቂ ላይ የሚታከል ስኳር ለጤና አሳሳቢ ነው ይላል። ሕንድ ውስጥ 50 ሚሊዮን ገደማ ገበሬዎች ሸንኮራ አገዳ ያመርታሉ። ሚሊዮኖች ደግሞ ስኳር በሚያመርቱ ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው ይሠራሉ። ሕንድ የተረፈ የስኳር ምርቷን ወደ ውጭ ለመላክ ማቀዷ በሌሎች ስኳር አምራች ሃገራት ዘንድ ቅራኔ ፈጥሯል። ሌላኛው የተረፈ የስኳር ምርትን ማስወገጃ መንገድ ወደ ኢታኖል ቀይሮ መጠቀም ነው። የሕንድ ስኳር ምርት ማሕበር የኢታኖል ምርት አሁን ካለው 1.9 ቢሊዮን ሊትር ምርት በሚቀጥለው ዓመት ወደ 3 ቢሊዮን ሊያድግ እንደሚችል ገምቷል። https://www.bbc.com/amharic/news-54791680 +politics አሜሪካ በአፋር ክልል አዲስ ጦርነት መቀስቀሱ እንዳሳሰባት ገለጸች "የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ በአፋርና በትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች አዲስ ጦርነት መቀስቀሱ አሳስቦኛል አለ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ትናንት ሐሙስ ጥር 18/2014 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ""በአፋር ክልል ጦርነት እንደ አዲስ መቀስቀሱ እጅግ አሳሳቢ ነው"" ብለዋል። ከቀናት በፊት የህወሓት ኃይሎች ከትግራይ ክልል አዋሳኝ የሆኑ በአፋር ክልል ዞን ሁለት ውስጥ የሚገኙ ሦስት ወረዳዎችን መቆጣጠራቸውን የአፋር ክልል መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ለቢቢሲ መናገራቸው ይታወሳል። የህወሓት ኃይሎች ደግሞ ከአፋር ኃይሎች በኩል የሚሰነዘርባቸውን ጥቃት ሲከላከሉ መቆየታቸውን በመግለጽ ሰኞ ጥር 16/2014 'ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ' መውሰዳቸውን ገልጸዋል። ኔድ ፕራይስ በመግለጫቸው፤ የአሜሪካ መንግሥት ግጭት እንዲቆም እና በሁሉም አካላት ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከ ገለልተኛ የሆነ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ከቀናት በፊት አዲሱ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ኔድ ፕራይስ ገልጸዋል። በተጨማሪም ቃል አቀባዩ፤ ጦርነቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ ደኅንነት እና ፀጥታ ስጋት መሆኑን በመጥቀስ፣ በግጭቱ አካባቢ ላሉ ሰዎች ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲመቻች እና ግጭቱ በድርድር እንዲጠናቀቅ የመንግሥታቸው ፍላጎት መሆኑን አመልክተዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኔድ ፕራይስ ጨምረውም የኢትዮጵያ መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከቀናት በፊት ላለፉት ሦስት ወራት ያህል በመላው አገሪቱ ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ውሳኔ ማሳለፉ የአሜሪካ መንግሥት በበጎ እንደሚመለከተው ገልጸዋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ረቡዕ ጥር 17/2014 ዓ.ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ያሳለፈው ውሳኔ ���ድቆ ተግባራዊ እንዲሆን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቷል። ""ይህ ውሳኔ [የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ መወሰኑን] በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይጸድቃል ብለን ተስፋ እንዳርጋለን"" ሲሉ ኔድ ፕራይስ ተናግረዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት ተባብሶ በበርካታ የአማራ እና የአፋር አካባቢዎች በሚካሄድበት ወቅት ነበር በአገሪቱ ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል በሚል ነበር ሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት ወር ማጠናቀቂያ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገገው። ኔድ ፕራይስ ጨምረውም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ሰዎች እንዲፈቱም በመግለጫቸው ጠይቀዋል። ቃል አቀባዩ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ማስቆም የሚቻለው በድርድር ግጭት ሲቆም፣ የታሰሩ ሰዎች ሲፈቱ፣ የሰብዓዊ እርዳታ ሲፈቀድ እና ሁሉን አካታች የሆነ ብሔራዊ ምክክር ለማድረግ መሠረት ሲጣል ነው ብለዋል። አሜሪካ በትግራይ ክልል ውስጥ ተጀምሮ ወደ አጎራባቾቹ የአፋርና የአማራ ክልሎች የተዛመተው ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ መንግሥት ከአማጺያኑ ጋር ድርድር አድርጎ ጦርነቱ እንዲቋጭ ግፊት ስታደርግ የቆየች ሲሆን፣ ልዩ መልዕክተኛ ሰይማም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣንት ጋር ውይይት ሲደረግ ቆይቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60133594 +business በማዳበሪያ ዋጋ መናር “መሬታችን ጦም ሊያድር ይችላል” ሲሉ አርሶ አደሮች ስጋታቸውን ገለጹ "በማዳበሪያ ዋጋ መናር ምክንያት "" መሬታችን ምንም አዝዕርት ሳይዘራበት ሊከርም ይችላል"" ሲሉ አርሶ አደሮች ስጋታቸውን ለቢቢሲ ገለጹ። የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ዘንድሮ ከ150 በመቶ በላይ ጨምሯል። ይህም ለአርሶ አደሩ ራስ ምታት ከሆነ ሰነባብቷል። በባለፈው ዓመት በኩንታል 1700 ብር ይሸጥ የነበረው ማዳበሪያ ዘንድሮ ዋጋው ከእጥፍ በላይ ጨምሮ 4200 ብር ገብቷል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች የዋጋ ንረቱ በምርታቸው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ይናገራሉ። ""የእኔ እቅድ በዚህ ዓመት ለማዳበሪያ እስከ 25 ሺህ ብር ድረስ አወጣለሁ የሚል ነበር። አሁን ግን ከእጥፍ በላይ ሆኖ ከ50 ሺህ ብር በልጧል። ታዲያ እንዴት አድርጌ እዘራለሁ?!"" ሲሉ ይጠይቃሉ አርሶ አደር ጌቴ። የዋጋ ንረቱ ማዳበሪያ የማይፈልጉ እና ዋጋ የማያወጡ ሰብሎችን መዝራትን እንደ አንድ አማራጭ እንዲያስቡም አስገድዷቸዋል። አርሶ አደር ጌቴ ""እስካሁን አንድም ማዳበሪያ አልገዛሁም፤ ለበጋ መስኖ ቀደም ብሎ ከሰው ተበድሬ የዘራሁትንም እንዴት እንደምከፍል ጭንቅ ሆኖብኛል"" ይላሉ። የሌላኛው አርሶ አደር ሹመት ጭንቀትም ተመሳሳይ ነው። ""የመንደራችን የማለዳና የምሽት ወግም የማዳበሪያ ጉዳይ ከሆነ ሰንብቷል"" ይላሉ። መሬታቸውን በአዝዕርት ለመሸፈን ቢያንስ 8 ኩንታል ኤንፒኤስ እና 4 ኩንታል ዩሪያ ማዳበሪያ እንደሚያስፈልጋቸው የገለፁት አርሶ አደሩ፣ ይህንን ለመግዛት አቅማቸው ስለማይፈቅድ የተሻለ መፍትሔ ካልተሰጠ ጭራሽኑ ማምረት እንደማይችሉ ይናገራሉ። ""እኔ ደሃ አርሶ አደር ነኝ። በተባለው ዋጋ ገዝቼ ማምረት አልችልም። እንደው ልጄቼ የሚቆርጡት እሸት እንዳያጡ ጥቂት በቆሎ እዘራ እንደሁ እንጂ ሌላማ ምኑን አመረትኩት"" ይላሉ። ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት 12.8 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መፈፀሟን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። እስካሁን ወደ አገር ውስጥ መግባት የቻለውንም ለክልሎች የማሰራጨት ሥራ መጀመሩን በሚኒስቴሩ የኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ሶፊያ ካሳ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የማ���በሪያ ዋጋው ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ150 በመቶ በላይ መጨመሩን የገለጹት ዶ/ር ሶፊያ፣ የግዥ ስምምነቱ ቀድሞ ስለተፈፀመ እንጂ አሁን ባለው የገበያ ዋጋ ጭማሪው ከዚህ የበለጠ ሊሆን ይችል ነበር ብለዋል። ለመሆኑ የማዳበሪያ ዋጋ ለምን ጨመረ? ሚኒስትር ዲኤታዋ ለዋጋ ጭማሪው እንደ ዋና ምክንያትነት የሚያነሱት በዓለም አቀፍ ደረጃ የማዳበሪያ ዋጋ መናርን ነው። "" እንደ አገር ቀድመን ጨረታ አውጥተን ውል ስለገባን ነው አሁንም የተሻለ የሚባል ዋጋ ያገኘነው"" ይላሉ። ትላልቅ የማዳበሪያ አምራች አገራት በኮቪድ-19 ምክንያት ምርታቸውን በመቀነሳቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ እጥረት መከሰቱን ሚኒስቴር ዲኤታዋ ያስረዳሉ። በተለይ ደግሞ ዩሪያ ለተባለው ማዳበሪያ ማምረቻ የሚያገለግል የተፈጥሮ ጋዝ ዋጋ በመጨመሩ እና ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚያመርቱት አገራት ከምርት ውጭ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። እንዲሁም ቻይና እና ሩሲያ ወደ ውጭ የሚልኩትን ማዳበሪያ ውስን አድርገውት ስለነበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሆነ እጥረት መከሰቱን ሚኒስቴር ዲኤታዋ ለዋጋው መናር አስተዋጽኦ ያደረጉ ነገሮችን በምክንያትነት ይዘረዝራሉ። በግዥ አፈጻጸሙ መዘግየት የተስተዋለውም በዚሁ ምክንያት ተደጋጋሚ ጨረታ ለማውጣት በመገደዳቸው እንደሆነ ያክላሉ። ይሁን እንጂ አሁን እየገባ ያለውን ማዳበሪያ ቀድመው የሚዘሩ አካባቢዎችን በመለየት ክልሎች በአግባቡ እንዲያደርሱ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዲኤታዋ ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ አርሶ አደሮች የሰው ሰራሽ ማዳበሪያ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ማዳበሪያ እየተጠቀሙ ማምረት እንዲችሉ ክልሎች በከፍተኛ ንቅናቄ እየሰሩም ነው ብለዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች ግን የተፈጥሮን ማዳበሪያ እምብዛም እንደማይጠቀሙ እና መሬታቸው ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ እንደተለማመደ በመግለጽ ያለውን ችግር ያስረዳሉ። በመሆኑም መንግሥት የሚራዘሙ ፕሮጀክቶችን እያራዘመ አርሶ አደሩ በተመጣጣኝ ዋጋ ማዳበሪያ እንዲያገኝ ድጎማ እንዲያደርግ የተሻለ ነው ያሉትን የመፍትሔ ሃሳብ ሰንዝረዋል። ይህንኑ የአርሶ አደሮቹን ጥያቄ ያቀረብንላቸው ሚኒስትር ዲኤታዋ ""በቀጣይ ታይቶ መንግሥት የሚወስደውን አቅጣጫ እናሳውቃለን። አሁን መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ያለው አቅርቦት ላይ ነው"" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ሚኒስትር ዲኤታዋ አክለውም ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ከፈፀመችው 17 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ የዘንድሮው ከ5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ያነሰ መሆኑን ጠቅሰው ""አጠቃላይ ከነበረው ፍላጎት 70 በመቶ ግዥ ነው የተፈፀመው ፤ በበልግ ወቅት ተጨማሪ ግዥ ሊኖር ይችላል "" ብለዋል። ኢትዮጵያ በዋናነት የማዳበሪያ ግዥ የምትፈጽመው ከአፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ መሆኑንም ዶ/ር ሶፊያ ገልጸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60985422 +politics የፈረንሳዩ ማክሮን 'ፑቲን ሁኔታዎችን ለማርገብ ቃል ገብተውልኛል' አሉ "ለከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት ወደ ሩሲያና ዩክሬን ያቀኑት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ቭላድሚር ፑቲን ሁኔታዎችን እንደሚያረግቡ ቃል እንደገቡላቸው ተናገሩ፡፡ ""ድንበር አካባቢ ሁኔታዎች እንደማይባባሱ፣ አዳዲስ ትንኮሳዎች እንደማይኖሩ ማረጋገጫ አግኝቻለሁ"" ብለዋል ማክሮን ለጋዜጠኖች፡፡ ኢማኑኤል ማክሮን ይህን ያሉት የዩክሬንኑን አቻቸውን ከማግኘታቸው ቀደም ብሎ ነው፡፡ ሩሲያ ዩክሬን ድንበር ላይ መቶ ሺህ ወታደሮቸን ማስፈሯ ሲነገር ነበር፡፡ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ሩሲያ ወረራውን ለመፈጸም ከሚያስፈልጋት ኃይል 70 ከመቶው በዩክሬን ድንበር ላይ መስፈሩን አረጋግጠናል ያሉት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ይህ በዩክሬን፣ ሩሲያና ምዕራብ አገራት መካከል ከፍተኛ የጦርነት ስጋትና ውጥረት የተከሰተው ሩሲያ በደቡብ ዩክሬን የክሪሚያን ባሕረ ገብ በኃይል ከያዘች ከ8 ዓመት በኋላ ነው፡፡ ሞስኮ፣ ዩክሬን የሚንስክ ስምምነትን ልታከብርልኝ አልቻለችም ስትል ትወቅሳታለች፡፡ የሚንስክ ስምምነት የሚባለው ጀርመንና ፈረንሳይ ያሸማገሉትና በሩሲያና ዩክሬን መካከል የተደረሰ የሰላም ስምምነት ነው፡፡ ሩሲያ የምትደግፋቸው አማጺያን በሚቆጣጠሩት አካባቢ ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ 14ሺህ ሰዎች መገደላቸው ይነገራል፡፡ ማክሮን ትናንት ማክሰኞ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪያቭ የተገኙ ሲሆን ወደዚያ ያመሩት ሰኞ ዕለት ከፑቲን ጋር ቢያንስ ስድስት ሰዓታትን የፈጀ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ ይህ የተራዘመ ውይይት የተደረገው በእራት ግብዣ ታጅቦ ነበር፡፡ ማክሮን ከፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር በሰጡት የጣምራ መግለጫ ይህን ውጥረት ለማርገብ ወደ ተጨባጭ መፍትሄ ማምራት አለብን ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በበኩላቸው ፑቲን በተጨባጭ ጦርነቱን የማርገብ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳስበዋል፡፡ ""ቃላትን ብዙም አላምናቸውም፤ ፖለቲከኞች የሚጨበጥ እርምጃዎችን በግልጽ ሲወስዱ ነው የሚሻለው"" ሲሉ ከባላንጣቸው ፑቲን የሰላም ተግባር እንደሚጠብቁ ጠቁመዋል፤ ዘለንስኪ፡፡ ማክሮን ከዚህ በኋላ ወደ ጀርመን ያቀኑ ሲሆን በዚያ ጀርመንና ፖላንድ ለዩክሬን ሉአላዊነት ያላቸውን ቀናኢነት ገልጠውላቸዋል፡፡ እነዚህ መሪዎች በጀርመን የተገኙት የዌይማር ትሪያንግል ቡድን ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ነው፡፡ ይህ ቡድን የተመሠረተው የዛሬ 31 ዓመት ገደማ ሲሆን የቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃትን ተከትሎ አውሮጳን የሚገጥማትን አዳዲስ ፈተናዎች ለማርገብ የተፈጠረ ስብስብ ነበር፡፡ የአሜሪካው ጆ ባይደን በበኩላቸው ከትናንት በስቲያ ሰኞ አንጌላ መርክልን የተኩትን የጀርመኑን መራሒ መንግሥት ሾልዝን በዋሺንግተን ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል፡፡ ሁለቱ መሪዎች ዋንኛ አጀንዳ ያደረጉት የሩሲያን የወረራ ስጋት ሲሆን ፑቲን እንደተፈራው ዩክሬንን የሚወሩ ከሆነ ወደ ጀርመን የተዘረጋውና ከፍተኛ መዋእለ ነዋይ ፈሶበታል የሚባለውን የኖርድ ስትሪም2 የጋዝ መስመርን ለመዝጋት ዝተዋል፡፡ ይህ የሚፈራው ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጀርመን ወታደር እንደማታዋጣ ቀደም ብላ ማሳወቋ በወዳጅ አገራትን ዘንድ ቅሬታን ፈጥሮ ነበር፡፡ ቭላድሚር ፑቲን ይህ የጦርነት ስጋት ጨርሶውኑ እንዲቀለበስ ያቀረቡት ቅድመ ሁኔታ በብዙ የምዕራብ አገራት ዘንድ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ሞስኮ፣ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዩክሬንን አባል ላለማድረግ እንዲወስን፣ እንዲሁም በምሥራቅ አውሮጳ አካባቢ ዝር እንዳይል ትፈልጋለች፡፡ አሁን በማክሮን የዲፕሎማሲ ሩጫ የሩሲያና የዩክሬን የድንበር ጦርነት የረገበ ቢመስልም ዘለንስኪ ግን ጥርጣሬ እንዳላቸው ተስተውሏል፡፡ ዘለንስኪ ከማክሮን ጋር በሰጡት የጋራ መግለጫ ላይ ፑቲን የሚናገሩትን እምብዛምም እንደማያምኑ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ""ግልጽነት በመሪዎች ዘንድ ሲታይ ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ማዘናጊያ ቁማር መሆን የለበትም"" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ በዚህ መግለጫ ላይ ያልተጠበቀ ሐሳብ የሰነዘሩት ማክሮን የዩክሬንና የኔቶ ግንኙነት የፊንላድን ሊመስል እንደሚችል ጥቁምታን ሰጥተዋል፡፡ ""ፊንላንድ የኔቶ አባል ባትሆንም ቅርብ ናት"" ብለዋል፡፡ ይህ ሐሳብ ዘለንስኪን ቅር ሳያሰኛቸው አልቀረም፡፡ ማክሮን በዲፕሎማሲ ጥረታቸው ከፑቲን ቃል አግኝቻለሁ ቢሉም ክሬምሊን ይህን ሐሳብ ለማስተባበል ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ""ማክሮን የኔቶ መሪ አይደሉም፡፡ የተደረሰ ስምምነትም የለም"" ሲል መግለጫ አውጥ��ል፡፡ አሁንም በአገራት መካከል በየአቅጣጫው ንግግሩ የቀጠለ ሲሆን ሩሲያም ወደ ድንበር ወታደሮችና ቁሳቁስ ማስጠጋቷን ገፍታበታለች፡፡ ኔቶም ወደ ምሥራቅ አውሮጳ መስፋፋቱንና ለጦርነት የተጠንቀቅ መሰናዶ ማድረጉን ቀጥሎበታል፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-60314312 +politics ሩሲያ የኔቶ አባል በሆነችው ሊቱዌኒያ ላይ ጠንካራ ዛቻ ሰነዘረች "ሩሲያ የቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት ግዛትና የኔቶ አባል በሆነችው ሊቱዌኒያ ላይ ጠንካራ ዛቻ ሰነዘረች። ሩሲያ ዛቻውን የሰነዘረችው ሊቱዌኒያ የጭነት ዕቃዎች በድንበሯ በግዛቷ በኩል የሩሲያ ይዞታ ወደ ሆነችው ካሊኒንግራድ እንዳያልፉ ካገደች በኋላ ነው፡፡ ሊቱዌኒያ በበኩሏ ለሩሲያ ዛቻ ምላሽ ሰጥታለች፡፡ ""እኛ የአውሮፓ ሕብረትን ማዕቀብ መሠረት አድርገን ነው ክልከላ የጣልነው"" ብለዋል የሊቱዌኒያ ባለሥልጣናት፡፡ ካሊኒንግራድ፣ በፖላንድና በሊቱዌኒያ መካከል ያለ አንድ የሩሲያ ግዛት ነው፡፡ ግዛቱ የሩሲያ ይሁን እንጂ ከዋናው የሩሲያ ፌዴሬሽን ጋር ድንበር አይጋራም፡፡ ሆኖም ካሊኒንግራድን የአውሮፓ አባል የሆኑት ፖላንድና ሊቱዌኒያ ያዋስኑታል፡፡ ይህ ግዛት ለሩሲያ ወሳኝ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ነው፡፡ ሩሲያ ለሊቱዌኒያ ባስተላለፈችው በዚህ ማስጠንቀቂያ ሊቱዌኒያ ጭነቶቹ እንዲያልፉ የማታደርግ ከሆነ ""ብርቱ ቅጣት"" ይጠብቃታል ብለዋል፡፡ ""ሩሲያ ለዚህ ጸብ አጫሪነት ሊቱዌኒያን ትቀጣለች"" ብለዋል ኒኮሊያ ፓትሮቭ የተባሉ አንድ ከፍተኛ የሩሲያ ባለሥልጣን፡፡ ሊቱዌኒያ በበኩሏ የእኔ ሚና የአውሮፓ ሕብረትን የማዕቀብ ውሳኔ ተፈጻሚ ማድረግ ብቻ ነው ብላለች፡፡ ከባልቲክ ባሕር ኩታ ገጠም የሆነው ካሊኒንግራድ ግዛት ከሩሲያ ርቆ የሚገኝ የሩሲያ ስትራቴጂክ ግዛት ከመሆኑ ባሻገር የሩሲያ የጦር ሰፈር የሚገኝበት ነው፡፡ ይህ የምዕራብ ግዛት የ2ኛው የዓለም ጦርነትን ተከትሎ ከጀርመን ለሩሲያ የተሰጠ ሲሆን፣ በኔቶ አባል አገራት የተከበበ ነው፡፡ አንድ ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩበት ካሊኒንግራድ በብዛት ከሩሲያና ከአውሮፓ ሕብረት በሚመጡ ጥሬ ዕቃዎች ላይ ጥገኛ የሆነ አካባቢ ነው፡፡ ትናንት ማክሰኞ ካሊኒንግራድን የጎበኙት ሚስተር ፓትሮቭ ""ይህ ምዕራቡ ዓለም የተነኮሰው ተግባር ነው፤ …ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጻረር ተግባር ነው፤ …ሊቱዌኒያ ለዚህ ድርጊቷ ትቀጣለች"" ብለዋል፡፡ ይህ ሩሲያ ደጋግማ የምትሰነዝረው የቅጣት ዛቻ ምጣኔ ሃብታዊ ይሁን ወታደራዊ  የተባለ ነገር የለም፡፡ ሆኖም የሊቱዌኒያ ዕቀባ ተከትሎ ሩሲያ በአገሯ የሚገኙትን የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደርን ጠርታ ማብራሪያ ጠይቃለች፡፡ ምናልባት ሩሲያ እንደዛተችው ሉቲኒያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት ከሰነዘረች የኔቶ አባል አገራት ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡ የኔቶ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 5፣ 'የየትኛውም አባል አገር ጥቃት የሁሉም አገር ጥቃት ነው' ይላል፡፡ አሜሪካ በሊቱዌኒያ ላይ የሚሰነዘር ማንኛውም ጥቃት አጸፋ እንደሚኖረው ይፋ አድርጋለች፡፡" https://www.bbc.com/amharic/articles/clmxg0vn0x4o +health የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዶ/ር ቴድሮስን ዳግም ዕጩ አድርጎ አቀረበ "የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅቱን ዳግም ለቀጣይ አምስት ዓመታት በዳይሬክተርነት እንዲመሩ ዕጩ አደረገ። ድርጅቱን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት ዶ/ር ቴድሮስ ያለተፎካካሪ ብቸኛ ዕጩ ሆነው የቀረቡ ሲሆን የመጨረሻው ውጤትም ግንቦት 2014 ዓ.ም. ላይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ኃላፊነታቸውን ከአምስት ዓመት በፊት ከመረከባቸው ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የጤና ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል። ዶ/ር ቴድሮስ ከአምስት ዓመታት በፊት ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ የኢትዮጵያ ድጋፍ አልተለያቸውም ነበር። ይሁን እንጂ የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴድሮስ ኃላፊነታቸውን ተጠቅመው ለህወሓት ድጋፍ ያደርጋሉ ሲል በተደጋጋሚ ከሷቸዋል። የዓለም ጤና ደርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በጄኔቭ ለስበሰባ ከመቀመጡ በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት በዶ/ር ቴድሮስ ገለልተኝነት ላይ ምርመራ እንዲያካሂድ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ቦርዱ በዳይሬክተሩ ላይ ምርመራ እንዲደረግ የቀረበውን የኢትዮጵያ ጥያቄ ወደ ጎን በመግፋት ሳይመለከተው ቀርቷል። ዶ/ር ቴድሮስ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ጤና ድርጅትን ለመምራት ዕጩ በሆኑበት ጉዳይ ላይ ለመወያየት በተጠራ የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ስብሰባ ላይ የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ አሞት አቤቱታውን ያልተመለከቱበትን ምክንያት ገልጸዋል። ""ይህ ጉዳይ በጣም የተወሳሰበና ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው፤ ከዚህ ኮሚቴ የአስራር ማዕቀፍ ውጪ ነው"" አሞት ያሉ ሲሆን፤ የቦርዱ 34 አባላት በሙሉ የምርመራ ጥያቄውን ሳይቀበሉት ቀርተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በጉዳዩ ላይ በተወያየበት ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካይ የአገራቸውን አቤቱታ ለማብራራት በመከሩበት ጊዜ እንዲያቋርጡ ተደርገው ነበር። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ንግግር እንዳያደርጉ መከልከሉ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ተቃውሞውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ ውሳኔው የዓለም ጤና ድርጅት በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ አለመሆኑን ማሳያ ነው ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ቃል አቀባዩ የዓለም ጤና ድርጅት በዶ/ር ቴድሮስ ላይ ምርመራ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ይጠይቃልም ሲሉ ለሮይተርስ ጨምረው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት የድርጅቱን ነፃነት፣ ገለልተኝነት መርህ ጥያቄ ውስጥ እንደከተቱት በመጠየቅ ምርመራ እንዲደረግ አቤቱታ አቅርቦ ነበር። በትግራይ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሲቪልና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓመታት አባልና አመራር የነበሩበትን ህወሓት የሚደግፉ ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ሲሉ ሲከሱ ቆይተዋል። ዶ/ር ቴድሮስ እና የዓለም ጤና ድርጅት የቢቢሲ የጄኔቭ ዘጋቢ ኦሞጂን ፉክስ እንዳለችው የትኛውም የከዚህ ቀደም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር እንደ ዶ/ር ቴድሮስ አልተፈተነም። የኮቪድ-19 ወረርሸኝ፣ ቻይና ስለ ወረርሽኑ መረጃ እንድታጋራ ጫና ማድረግ፣ ከቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የተፈጠረው እሰጣገባ፣ የአሜሪካ ድጋፍ ማቆም እና ከድርጅቱ አባልነት መውጣት በቀዳሚነት የሚወጠቀሱ ሲሆን። ለአንድ ዓመት የዘለቀው የትግራዩ ጦርነት በግል ያደረሰባቸው ጫና እና ከትውልድ አገራቸው መንግሥት ጋር የገቡት ቅሬታ የዶ/ር ቴድሮስ ፈተናዎች ከነበሩት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አሁንም ቢሆን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዝርያውን እየቀረ ዓለም ማሸበሩን አላቆመም፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሁንም የኮቪድ ክትባትን አልወሰዱም። የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኞች በዲሞክራቲክ ኮንጎ ፈጽመውታል በተባለው የጾታ ጥቃት የድርጅቱን የከበረ ስም አጉዱፏል። በሌላ በኩል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የትራምፕን ውሳኔ በመቀልበስ አሜሪካን ወደ የዓለም ጤና ድርጅት አባልነት መልሰዋል። አሜሪካ ለድርጅቱ የምታደርገው ከፍተኛ ድጋፍም ቀጥሏል። በውጣ ውረዶች ውስጥ ያለፉት ዶ/ር ቴድሮስ ግዙፉን የጤና ድርጅት ለሌላ አምስት ዓመታት የመምራት ጽኑ ፍላጎት አላቸው ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60133588 +politics የጋዜጠኞቹ እስርና በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ዘመቻ "በማህበራዊና በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥትን በመተቸት የምትታወቀው መስከረም አበራ ቅዳሜ እለት፣ ግንቦት 13 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር መዋሏን ባለቤቷ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በአዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህር የነበረችው መስከረም በቁጥጥር ስር የዋለችው በአዲስ አበባ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲሆን ያለችበትንም ስፍራ እንደማያውቁ ባለቤቷ ተናግረዋል። ይህም በሳምንቱ የታሰሩትን የጋዜጠኞች እና የሚዲያ አካላት ቁጥር ሰባት ያደረሰው ሲሆን ሁኔታውም የተችዎን ድምጽ በማፈኑ ረገድ አዲስ እርምጃ ሊኖር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። በያዝነው ሳምንት ሐሙስ ግንቦት 11፣ 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል ተቀማጭነቱን ያደረገውና የቅርብ ዘገባቸው በፋኖ ላይ ያተኮረው አሻራ ሚዲያ አምስት ጋዜጠኞቹ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል። ጋዜጠኞቹ የአማራ ልዩ ኃይል፣ የአማራ ፖሊስና የአድማ በታኝ የደንብ ልብስ በለበሱ የጸጥታ አካላት እንደተወሰዱ ""ሽንት ቤት ውስጥ ተደብቄ ነበር"" ያለ የስራ ባልደረባቸው ለሮይተርስ ተናግሯል። ግለሰቡ በባህርዳር ከተማ የሚገኘው የአሻራ ጽህፈት ቤት መዘጋቱንም ተናግሯል። በተጨማሪም በሃገሪቱ የተካሄደውን ጦርነት በመቃወምና የሰላምና ድርድር መንገዶች የተሻሉ አማራጮች እንደሆኑ በተደጋጋሚ አፅንኦት በመስጠት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬም መታሰሩ ተዘግቧል። ቢቢሲ የአዲስ አበባን ሆነ የፌደራል ፖሊስን ለማግኘት ቢሞክርም ባለመሳካቱ ምላሻቸውን ለማካተት አልተቻለም። ጋዜጠኞቹ በቁጥር ስር የዋሉት መንግሥት በተለያዩ ክልሎች ህግን የማስከበር ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን ባስታወቀ ማግስት ነው። የፌደራል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አርብ ምሽት በአማራ ክልልና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ የሕግ የበላይነትን ማስከበር የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት እንዲሁም የአገርን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ብቸኛው መፍትሔ ነው ብሏል። በተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ሕገ ወጥነትና የሰላም መደፍረስን መንግሥት እንዲቆጣጠር ሕዝቡ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ነበር ያለው መግለጫው፣ ብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤት አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ መወሰኑን አስታውሷል። የተቃዋሚው አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዘጠኝ አባላትም እንዲሁ በያዝነው ሳምንት ግንቦት 10፣ 2014 ዓ.ም በሁለት ከተሞች መታሰራቸውን ሮይተርስ በአሜሪካ የሚገኘውን የአማራ ማህበር ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። በተጨማሪም የአብን ፓርቲ አባላትና አመራሮች እስር ተጠናክሮ መቀጠሉን የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አምስት የአብን አባላት አርብ ዕለት፣ ግንቦት 12፣ 2014 ዓ.ም ባወጡት መግለጫ ""መንግሥት እገታና ስወራ"" እየፈጸመ ነው ሲሉ ከሰዋል። ""በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን አባላትና አመራሮች፣ በፋኖ አባላት፣ በሕጋዊ ታጣቂዎችና ወጣቶች እንዲሁም አገራቸውንና ሕዝባቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያገለገሉ የጦር መኮንኖችንና የጸጥታ አመራሮች ላይ የሚፈጸመው መንግስታዊ እገታና ስወራ በአስቸኳይ እንዲቆምና በዚህ ሰበብ በማንነታቸው ብቻ የታገቱ አካላትም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን፡፡"" ብሏል። ከቀናት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ መሰወራቸው የተነገረው የቀድሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ኃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ ሞክረዋል በሚል ተጠርጥረው እንደተያዙና በባህርዳር ጠቅላይ ፍርድ ቤት አርብ እለት መቅረባቸው ይታወቃል። ሮይተርስን ጨምሮ ሌሎች ሚዲያዎች ከሰሞኑ ባወጡት ዘገባ በተለያዩ ከተማዎች የሚገኙ የፋኖ አባላት መታሰራቸውንና ሌሎቹንም በቁጥጥር ስር ለማዋል ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ዘግበዋል። መግለጫው አክሎም ""ህግ ማስከበርን ሰበብ በማድረግ የፌደራል የፀጥታ መዋቅር በሕገ መንግሥቱ ለክልልና ለፌድራል ተለይቶ የተሰጠውን ኃላፊነት እና ሚና በደፈጠጠ መልኩ ክልሉን በሕገ-ወጥ መንገድ ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም"" ጠይቋል። የአማራ ክልል ባለስልጣናት በግለሰቦች እጅ የሚገኝ የጦር መሳሪያ እንዲመዘገብ ያደረጉት ጥሪ ትጥቅ ለማስፈታታት ነው ከሚሉ ወጣቶች ጋር ለግጭት መነሻ ሆኗል። ""መነሻው ፋኖዎችን ትጥቅ እናስፈታለን በሚሉ የፀጥታ አካላት የተጀመረ ነው። በዚያ ውጥረት ሳቢያ ፋኖዎቹም ትጥቅ አንፈታም በሚል ቦታ ይዘው ነበር"" ነበር ያሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ እማኝነታቸውን ሰጥተው፣ ነዋሪዎችም ፋኖ ትጥቅ መፍታት የለበትም በሚል ተቃውሞ አሰምተዋል ብለዋል። በሞጣ ከተማ በጸጥታ ኃይሎች እና በአካባቢው ወጣቶች መካከል በተፈጠረ ግጭት በትንሹ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህንንም ተከትትሎ የከተማው አስተዳደር በእንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ ከመጣል በተጨማሪ የሰዓት እላፊ አዋጅ ጥሏል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ቅዳሜ በሰጠው መግለጫ ""የሕግ ማስከበር ሥራውን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ማንኛውም ድርጊቶች ላይ አስፈላጊው የሕግ እርምጃ"" እንደሚወሰድ አስታውቋል። ቢሮው በመግለጫው ካለፉት ቀናት ጀምሮ ተጠርጣሪዎች ያለምንም ግጭት እጃቸውን ለህግ እንዲሰጡ እየተደረገ እንደሆነና ፈቃደኛ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ ጉዳት የመቀነስን ስራ ከህዝቡ ጋር እየተሰራ ነው ብሏል። ህግ ማስከበር ብሎ የጠራው ተግባር ለህዝቡ ሰላም እና ደህንነት፣ ለክልሉ እና ሃገሪቱ የሰላም ዋስትናን ዓላማ አድርጎ እየተከናወነ ባለበት ወቅት የተለያዩ ግለሰቦች ""ዋና ጠላቶች"" ብሎ ከጠራቸው ጋር በመተባበር ክልሉንና ሃገሪቱን ለማፍረስ የሚሰሩ አካላት እንቅፋት እየሆኑ ይገኛሉ ብሏል። ""በአሁኑ ወቅት ከዋና ጠላቶታችን ጋር በማበር ክልላችንን እና ሀገራችንን ለማፍረስ የሚሠሩ አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ባለቤቶች እና ግለሰቦች በአንዳንድ የክልላችን አካባቢዎች ሰልፍ መጥራት እና ለሰላም ማስከብር ሥራው እንቅፋት የኾኑ ቅስቀሳዎችን እያደረጉ ይገኛሉ"" ያለው መግለጫው በክልሉ የትኛውም አካባቢ ህጋዊ ጥያቄ ያቀረበም ሆነ ለሰልፍ ፈቃድ ያገኘ እንደሌለም ገልጿል። የክልሉ መገናኛ ብዙኃን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)ን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ""ህግ ማስከበሩ ዋና ዓላማው የክልሉ ህዝብ በሰላም ወጥቶ የመግባትና የመስራት መብት ለማረጋገጥ ነው"" ብለዋል። አክለውም ""ክልሉ ከወንጀለኞች የፀዳ ኾኖ እና አንድነቱ የተጠበቀ ሕዝብ ኖሮት ሊመጣ የሚችልን ጠላት ኹሉ በብቃት ለመመከት ነው"" ማለታቸውን አስፍሯል። በክልሉ አፈና፣ ዝርፊያ፣ ግድያ፣ በሃይማኖት ሰበብ ግጭት ቀስቃሽነት እና ሌሎችም ወንጀሎች በርከት ብለው እንደተስተዋሉና ይህንንም ለመቅረፍ ወደተቀናጀ የሕግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራ መገባቱንም ተናግረዋል። ክልሉ የሕግን የበላይነት እንዲረጋገጥና በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን እያደረግኩ ነው ባለው ዘመቻም የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ በተቀናጀ አሠራር እየተሳተፉ መሆኑንም አስረድተዋል። የአማራ ክልል በግለሰቦች እጅ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ምዝገባ እንዲካሄድ ባዘዘው መሰረት ከግንቦት 9፣ 2014 እየተካሄደ ይገኛል። ይህንንም ጥሪ ተከትሎ በርካቶች የጦር መሳሪያ ማስመዝገባቸውን የገለጹት ሰማ ጥሩነህ ምዝገባው በተሰጠው ቀነ ገደብ መጠናቀቅ ባለመቻሉ እስከ ረቡዕ ግንቦት 17፣ 2014 ዓ.ም በሁሉም አካባቢዎች እንዲቀጥል መወሰኑንም አስረድተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61540238 +business ኢትዮጵያ ኢንትርኔትን ስታቋርጥ በየቀኑ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ታጣለች "ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎትን በምታቋርጥባቸው እያንዳንዱ ቀናት በትንሹ ከአራት ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደምታጣ የኢንተርኔት ነጻነትና ተደራሽነትን የሚቆጣጠረው ኔትብሎክስ የተባለው ድርጅት ዳይሬክተር ለቢቢሲ ገለጹ። ዳይሬክተሩ እንዳሉት ""ኢትዮጵያ ኢንትርኔትን ለአንድ ቀን ስታቋርጥ ከገቢ አንጻር ቢያንስ 4.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ታጣለች።"" ይህም ሌሎች ኪሳራዎችን ሳይጨምር የሚከሰት ጉዳት ሲሆን በተጨማሪ ደግሞ ለኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ የሆኑት የመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች ዘንድ እምነት ማጣትን ያስከትላል። ከሁለት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ በኢንትርኔት መቋረጥ ሳቢያ በቀን 500 ሺህ ዶላር ታጣ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኢንተርኔት የሚንቀሳቀሰው የኢኮኖሚ ክፍል እየሰፋ በመሆኑ የኪሳራው መጠን ከፍ እንዲል እንዳደረገው ይታመናል። • 'የማለዳ ወፍ' ነዎት ወይስ 'የሌሊት'? • ባቡር ላይ የተወለደችው ህጻን ለ25 ዓመታት ነጻ የባቡር ትኬት ተሰጣት • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፊቱን ወደ ቻይና እያዞረ ይሆን? የኢንተርኔት አገልግሎትን የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በዋናነት የሚጠቀሙ በመሆኑ በርካታ የአፍሪካ ሃገራት በዚሁ ቴክኖሎጂ ላይ ጥገኛ እየሆኑ እንደሆነ የኢንተርኔት ነጻነትና ተደራሽነትን የሚቆጣጠረው ኔትብሎክስ የተባለው ድርጅት ዳይሬክተር አልፕ ቶከር ተናግረዋል። የአፍሪካ ሃገራት በግለሰብ ደረጃ የሚደረግ የገንዘብ ዝውውርን ጨምሮ ከፍ ያሉ ቁልፍ እንቅስቃሴዎችን ኢንተርኔትን በመጠቀም የሚከውኑ በመሆናቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ የአገልግሎቱ መቋረጥ በሚከሰትባቸው ሃገራት ላይ ከፍ ያለ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዳለው አልፕ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመታት በፊት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተከስቶ የነበረውን ጸረ መንግሥት ተቃውሞ ለመግታትና የፈተና መሰረቅን ለመቆጣጠር ስትል ለ36 ቀናት ያህል የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጧ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንዳጣች የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የመረጃ ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ትብብር የተሰኘው ተቋም አሳውቆ ነበር። በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ የተለያዩ ችግሮች በተለይ ደግሞ ፖለቲካዊ ቀውሶች ሲያጋጥሙ መንግሥታት በቀዳሚነት የኢንተርኔት አገልግሎት በማቋረጥ ችግሮችን ለመቆጣጠር ጥረት ያደርጋሉ። • ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በመዝጋቷ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ አጣች ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በመዝጋት ከሚታወቁ የአፍሪካ ሃገራት መካከል አንዷ ለመሆን ችላለች። የኢትዮጵያ መንግሥት ለውጥ እንዲያደርግ ያስገደደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ካበቃ በኋላ ሆን ተብሎ የተደረገ ሃገር አቀፍ የኢንተርኔት መቋረጥ አላጋጠመም ነበር። በዚህ ሳምንት ግን ሃገር አቀፉ ፈተና ከተጀመረ ከአንድ ቀን በኋላ የኢንትርኔት አገልግሎት በመላው ሃገሪቱ ተቋርጧል። ብልጭ ድርግም እያለ ቆይቶ ባለፉት ሁለት ቀናት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል። ይህንን በተመለከተም ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት አቅ���ቢው መንግሥታዊው ኢትዮቴሌኮምም ሆነ ሌላ የሚመለከተው የመንግሥት አካል የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠበትን ምክንያት በይፋ ለመናገር አልደፈሩም። አሁንም ድረስ ለአገልግሎቱ መቋረጥ በርካቶች የሚጠቅሱት ሀገር አቀፉን ፈተና ነው። ቀነኒ ሂኮ በአሰላ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ዓመት የፋርማሲ ተማሪ ነች። በዩኒቨርስቲ ውስጥ ትምህርት ነክ መረጃዎችን ለመለዋወጥ ያስችላለቸው ዘንድ የትምህርት ክፍሏ ተማሪዎች የቴሌግራም ቡድን አቋቁመው ነበር። በዚህ ቡድን መምህሩ ክፍለ ጊዜ ቢሰርዝ፣ የቤት ሥራ ቢሰጥ ወይንም የተከታታይ ምዘና መምህሩ ቢያቅድ መልእክት ይለዋወጡበታል። አሁን ግን የኢንተርኔት አገልግሎቱ ስለተቋረጠ ምንም ዓይነት መረጃ መለዋወጥ አልቻሉም። ይህ በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ለሆነው መሐመድ ቃሲምም ተመሳሳይ ነው። የመማር ማስተማሩን ሂደት ያለ ያለኢንትርኔት አገልግሎት ማሰብ ከብዶታል። መረጃ ለመለዋወጥ፣ የተለያዩ የሚሰጡ ሙከራዎችን ለመስራትና በአጠቃላይ ከኢንተርኔት መኖር የሚያገኛችው ጥቅሞች፣ መፅሀፍት ከኢንተርኔት ለማግኘት እንዲሁም የሌክቸር ቪዲዮዎችን ማየት ስላልቻለ ከእለት እቅዱና ትምህርቱ መደናቀፉን ይናገራል። ቀነኒም አክላ በመምህራንና በተማሪዎች መካከል የነበረው ግንኙነት ስለተቋረጠ መቸገራቸውን ትናገራለች። በኢንተርኔት እና የሞባይል አጭር መልዕክት መቋረጥ በባንኮች ላይ ያደሳደረውን ተፅዕኖ ለመጠየቅ የደወልንባቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኦሮሚያና የዳሸን ባንኮች ስልኮች ባለመስራታቸው ምላሽ ማግኘት አልቻልንም። የአቢሲኒያ ባንክ የማርኬቲንግ፣ የኮሙኑኬሽንና ኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አስቻለው ታምሩ የኢንተርኔት መቋረጡ የእኛ አገልግሎት ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ የለም ሲሉ ነግረውናል። ""ኢንተርኔቱን በተመለከተ ባንኩ የሚጠቀምበት ቲ24 የተባለ የተለየ የኢንተርኔት መስመር ስላለ እርሱ በአግባቡ እየሰራልን ነው"" ብለዋል። ነገር ግን ከባህር ማዶ ገንዘብ ለሚላክላቸው ሰዎች ገንዘቡን በባንካቸው ቅርንጫፍ እንደገባ የሞባይል አጭር መልዕክት የእጣ ቁጥር ይልኩ እንደነበር ያስረዳሉ። አሁን ግን ይህንን ማድረግ ተቸግረናል በማለት የሞባይል የአችር መልዕክት ባለመስራቱ መቸገራቸውን ነግረውናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-48633098 +health የአውሮፓ ዕለታዊ የኮቪድ ሞት ካለፈው ሳምንት አንጻር 40 በመቶ ከፍ ብሏል "በአውሮፓ በየቀኑ የሚመዘገበው የሞት መጠን ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በ40 በመቶ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ለቢቢሲ ገለጸ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ዶ/ር ማርጋሬት ሃሪስ እንደተናገሩት ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ እንግሊዝ፣ ኔዘርላንድስ እና ሩሲያ በአንድ ሦስተኛ ባደገው ቁጥር ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል። ""በሆስፒታሎች ውስጥ የጽኑ ህሙማን የህክምና ክፍሎች በጣም በታመሙ ሰዎች መሞላት ጀምረዋል"" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ በቀን 320 የሆነ ከፍተኛ ሞት በማስመዝገብ በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ26ሺህ በላይ አድርሶታል። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በ 221 ሰዎች ሞት ምክንያት በጣሊያን ውስጥም እንዲሁ ከፍተኛ ጭማሪ ታይቷል። በአጠቃላይ በኦስትሪያ የሟቾች ቁጥር ማክሰኞ ከ 1000 በላይ ሆኗል። ጣሊያን ውስጥም ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ወደ 22,000 ደርሰዋል። አዲስ የተጣለውን ገደብ በመቃወም ሰኞ አመሻሽ ላይ የተቃውሞ ሰልፎች በጣሊያን ተካሂደዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ምን አለ? ከቢቢሲ ወርልድ ጋር ቆይታ ያደረጉት ያደረጉት ዶ/ር ሃሪስ ""በመላው አውሮፓ የከፋ እና አስደንጋጭ በሆነ መልኩ በቫይረሱ የሚያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ጭማሪ እያየን ነው"" ብለዋል። ከቀደመው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በየቀኑ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንድ ሦስተኛ ሲጨምር የሚመዘገበው የሞት መጠን በ40 በመቶ ከፍ ብሏል። ""የሆስፒታሎችን አቅም በተሻለ መንገድ ማስተዳደር ቢቻልም በበርካታ አገራት የሚገኙ ሆስፒታሎች አልጋዎች በፍጥነት እየተያዙ ነው"" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ""በተወሰኑ የአውሮፓ አገራት ውስጥ የተጣሉ አዳዲስ ገደቦች ውጤታማነት የሚታወቀው በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው"" ብለዋል። ሩሲያ ከዛሬ ጀምሮ ሰዎች በሚበዙባቸው እንደ ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ታክሲ እና አሳንሰር ያሉ ቦታዎች ላይ የአፍና አፍኝጫ መሸፈኛዎችን ማድረግን አስገዳጅ አድርጋለች። የፈረንሳይ መንግሥት በፓሪስ እና በሌሎች ከተሞች ውስጥ ቀድሞ የተጣሉትን እገዳዎች ማራዘምን ጨምሮ ጥብቅ እርምጃዎችን በመተግበር ላይ እየተወያየ ነው። ጣሊያን ካለፈው አርብ ጀምሮ ምግብና እና መጠጥ ቤቶች፣ የስፖርት መዝወተሪያ ስፍራዎች ና ሲኒማዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መዘጋታቸውን በመቃወም በቱሪን ሰልፍ ያደረጉ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው ፖሊስ በሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ለመተኮስ ተገዷል።" https://www.bbc.com/amharic/54708506 +politics የሱዳንን 'አደገኛ' ፖለቲካዊ ቀውስ ለማርገብ አብደላ ሐምዶክ ኮሚቴ አቋቋሙ "ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ በሱዳን ለተከሰተው ፖለቲካዊ ቀውስ መፍትሄ ለመፈለግ የሚያስችል ""የቀውስ ጊዜ ኮሚቴ"" ማቋቋማቸው ተነገረ። ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሁለት ዓመት በፊት ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገሪቱን የገጠማት ""በጣም አደገኛ"" ፖለቲካዊ ቀውስ ነው ያሉትን ችግር ለመፍታት ነው ቡድኑን ያዋቀሩት ሲል የአገሪቱ ዜና ወኪል ሱና ዘግቧል። ትናንት ሰኞ ካርቱም ውስጥ በተካሄደው አስቸኳይ የካቢኔ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ነው የቀውስ ጊዜ ኮሚቴውን ማቋቋማቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ ያስታወቁት። ሱዳን ለገጠማት ከባድ ፖለቲካዊ ቀውስ መፍትሄ ለማፈላለግና የተጀመረውን የሽግግር ሂደት ለማሳካት በተዋቀረው ኮሚቴ ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮችም መካተታቸው ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር የሚደረገውን ጥረት ወደኋላ የመመለስ ስጋትን ፈጥሯል ያሉትን ለሳምንታት የዘለቀ ፖለቲካዊ ውጥረትን ለማርገብ ሁሉም ችግሩን ከሚያባብሱ እርምጃዎች ተቆጥበው ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። ሐምዶክ ይህንን ያሉት በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ጠንካራ ተጽእኖ ባለውን የአገሪቱ ጦር ሠራዊት የተደገፈና የሽግግር አስተዳደሩ እንዲወገድና ጦሩ አገሪቱን እንዲመራ የሚጠይቁ ሰልፍ በፖሊስ መበተኑን ተክትሎ ነው። ባለፈው ቅዳሜ የጀመረው የተቃዋሚዎቹ ሰልፍ በርካታ የጦር ኃይሉ ደጋፊ የሆኑ ሱዳናውያን የተሳተፉበት ሲሆን፣ በፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት አካባቢ በመሰባሰብ ጦር ሠራዊቱ ሥልጣን እንዲጨብጥ ጥሪ አድርገው ነበር። ከኦማር አልበሽር ከሥልጣን መወገድ በኋላ በአሁኑ ጊዜ ሱዳን በሲቪልና በወታደሮች ጥምረት በተመሰረተ ሉአላዊ ምክር ቤት አማካይነት በሽግግር መንግሥት እየተመራች ትገኛለች። ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የአገሪቱን የሽግግር ሂደት ለማደናቀፍ ሙከራ የሚያደርጉ ያሏቸውን አካላት አስጠንቅቀው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት የአገሪቱን የሽግግር አስተዳደር በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት ውስጥ ባሉ ወታደራዊና ሲቪል መሪዎች መካከል ያለው አለመግባባት እየተባባሰ ባለበት ጊዜ ነው። ነገር ግን አገሪቱን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት ውስጥ ሱዳን በታቀደው መሰረት ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሸ���ገር የምታደርገውን ጥረት ለመቀልበስ ከፍተኛ ጥረት የሚያደርጉ የጎላ ተጽእኖና ተሰሚነት ያላቸው የሠራዊቱ አባላት መኖራቸው ይነገራል። ባለፈው መስከረም ወር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ ተሞክሮ ከከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ የሽግግር አስተዳደሩን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ቡድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል። በዚህም ሲቪሉን በመወከል የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን አብደላ ሐምዶክ የያዙ ሲሆን ከሠራዊቱ በኩል ደግሞ የአገሪቱ ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆን ሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሐን ከፍተኛውን ቦታ ይዘዋል። ነገር ግን የሱዳንን የሽግግር አስተዳደር በሚመሩት ወታደራዊና የሲቪል ባለሥልጣናት መካከል ያለው ግንኙነት የሰከነ ሳይሆን ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የደኅንነት ሁኔታ እየተዳከመ የመጣ ሲሆን፣ ምክንያቱም ወታደራዊ መሪዎቹ ሥልጣን የሚያስረክቡበት ወቅትን ለማስተጓጎል ነው ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። በሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የሚመራው ኃያሉ የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ለሲቪሎች ሥልጣኑን በመጪው ኅዳር እንዲያስተላልፍ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58966846 +sports እግር ኳስ ፡ ለጡረታ እየተዘጋጁ ያሉት የ80 ዓመቱ እግር ኳስ ተጫዋች "ለእግር ኳስ ጥልቅ ፍቅር ያላቸው የ80 አመቱ የእድሜ ባለፀጋ እግር ኳስ ተጫዋች ከሰሞኑ የመጨረሻ ጨዋታዬን አደርጋለሁ ብለዋል። በአውስትራሊያ ነዋሪነታቸውን ያደረጉት እንግሊዛዊው ፒተር ዌብስተር ለጡረታም መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። በባለፉት ጥቂት አመታት አቅማቸው ደክሞ ከዚህ ቀደም በነበራቸው የሰውነት አቋም ባለመሆናቸውም ከሚወዱት የእግር ኳስ ጨዋታ ለመገለልም ምክንያት ሆኗቸዋል። ""ለባለፉት ጥቂት አመታት በእንደዚሁ አይነት ሁኔታ የነበርኩት። የምለብሰውንም ማልያ እያባከንኩ መሰለኝ"" በማለትም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፒተር ዌብስተር የተወለዱት በጎሮጎሳውያኑ አቆጣጠር 1948 በእንግሊዟ ፕሬስተን ነው። በህፃንነታቸው ራግቢና እግርኳስ ይጫወቱ የነበረ ሲሆን በተለይም ከአስራ አምስት አመታቸው በኋላ ዝንባሌያቸው ወደ እግር ኳስ ሆነ። በፕሮፌሽናል ተጫዋችነትም በዌልስ ለሚገኙ ክለቦች በሃያዎቹና በሰላሳዎቹ እድሜያቸው ተጫውተዋል። በ1981ም ከባለቤታቸውና ከሶስት ልጃቸው ጋር ወደ አውስትራሊያ የሄዱ ሲሆን እዚያም ባለው የእግር ኳስ ደረጃ ከፍተኛ መሆን አድናቆትን እንደፈጠረባቸውም ከሰሞኑ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል። ለአስርት አመታትም በአውስትራሊያ ፊግትሪ የእግር ኳስ ክለብም ተጫውተዋል። የመጨረሻ ጨዋታቸውንም በያዝነው ሳምንት አርብ እለት እንዳደረጉም ተዘግቧል። በክለቡም ሆነ በአካባቢው ከፍተኛ ዝናን ያተረፉት ፒተር በሳቸውም ስም ውድድር ተሰይሞላቸዋል- ፒተር ዌብስተር ካፕ የሚባል። ""እንዲህ አይነት ውድድሮች በስም የሚሰየሙት አንድ ሰው ገንዘብ ከከፈለ ወይም ከሞተ ነው። እኔ አልሞትኩምም አልከፈልኩም፤ እስቲ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ እሞክራለሁ"" ብለዋል። ለረዥም አመታት በእግር ኳስ ተጫዋችነታቸው ለመቆየት ሚስጥሩ ሳያቋርጡ መጫወታቸውና ከፍተኛ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጋቸው ነው። ለአመታትም ሩጫ፣ ሳይክል መንዳትን ያዘወትሩ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ከእድሜ ጋር ተያይዞ የልጅ ልጃቸውን ውሻ ይዘው ለመራመድ ይወጣሉ��� ምንም እንኳን እግር ኳስ ከመጫወት ራሳቸውን ቢያገሉም የልጅ ልጆቻቸው እግር ኳስ ሲጫወቱም እመለከታለሁ ብለዋል። ከዚህ ቀደም ራሳቸው ጨዋታ ስለነበራቸው የነሱን ጨዋታ መመልከት አልቻሉም ነበር። ባለቤታቸውም በቤት ስራዎች እንዲያግዙዋቸው ጡረታ የሚወጡበትን ቀን በጉጉት እየጠበቀች እንደሆነም ተናግረዋል። የፊግ ትሪ የእግር ኳስ ክለብ ፕሬዚዳንት ማይክ ዶድ የእድሜ ባለፀጋው እግር ኳስ ተጫዋች አስተዋፅኦ ""ከቃላት በላይ ነው"" በማለትም አሞግሰዋቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54406746 +sports ኢትዮጵያዊው የእግር ኳስ ኮከብ አቡበከር ከደቡብ አፍሪካ ክለብ ጋር ከስምምነት መድረሱ ተነገረ ወጣቱ ኢትዮጵያዊ የእግር ኳስ ኮከብ አቡበከር ናስር ለደቡብ አፍሪካው ክለብ ለመጫወት ከስምምነት መድረሱ ተነገረ። ያለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ኮከብ ግብ አግቢ የሆነው የኢትዮጵያ ቡና አጥቂው አቡበካር ናስር ከስምምነት የደረሰው ከደቡብ አፍሪካው ኃያል ቡድን ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ነው። አቡበካር በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ለታዋቂው ኢትዮጵያ ቡና ቡድን ከመጫወቱ ባሻገር ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተመርጦ ካሜሩን እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በሦስት ጨዋታዎች ተሰልፏል። የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ፕሬዝደንት የሆኑት ፈቃደ ማሞ ትናንት ምሽት በአንድ ዝግጅት ላይ አቡበከር 'ብራዚላውያኑ' በሚል ቅጽል ስያሜ ወደ ሚታወቁት ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ክለብ ዝውውር ያደርጋል የተባለውን ዜና አረጋግጠዋል። አቡበካር ወደ ደቡብ አፍሪካው እግር ኳስ ክለብ በምን ያህል ክፍያ እንደሚያቀና አስካሁን የተባለ ነገር የለም። የክለቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ ገዛኸኝ ወልዴ ተጫዋቹ የተዘዋወረበትን የገንዘብ መጠን ይፋ ባያደርጉም ክፍያው ከፍተኛ እንደሆነ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፕሪሚዬር ሊግን እየመራ የሚገኘው ኃያሉ ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ስለአቡበካር ዝውውርና ሌሎች ጉዳዩን የሚመለከት ዝርዝር መረጃ አስካሁን አላወጣም። 'ብራዚላዊያኑ' አቡበከርን እስከውድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ለቡና በውሰት መልሰው ሊሰጡት እንደሚችሉም ተዘግቧል። የ21 ዓመቱ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋች አቡበከር ናስር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ መሰናበቱን ተከትሎ ከደቡብ አፍሪካው ቡድን ጋር የሙከራ ጊዜ ማሳለፉ ይታወሳል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጎል የተሰኘው ታዋቂ የእግር ኳስ ድረ-ገፅ ሌላኛው የደቡብ አፍሪካ ቡድን ካይዘር ቺፍስ አቡባካርን ለማስፈረም እንደሚፈልግ አስነብቦ ነበር። ከዚህ በፊት ጌታነህ ከበደና ፍቅሩ ተፈራ ለደቡብ አፍሪካ ክለቦች መጫወታቸው አይዘነጋም። https://www.bbc.com/amharic/news-60227690 +health ኢንስታግራም 'ክብደት ጨማሪ ክኒን' በማስተዋወቁ ውግዘት ገጠመው ኢንስትግራም ክብደትን የሚጨምሩ መድሃኒቶችን በሚያስተዋውቁ ተጠቃሚዎቹ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ። ኢንስታግራም ወጣት ሴቶችን አላማ አድርገው ፍቃድ የሌላቸውና 'አደገኛ' የሆኑ ክብደት ለመጨመር የሚያግዙ መደሃኒቶችን የሚሸጡ ተጠቃሚዎቹን አደብ እንዲያስገዛ የእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት አሳሰበ። 'አፒታሚን' የተሰኘው የሰውነትን ክብደት የሚጨምር እንክብል በእንግሊዝ ምድር የታገደ ቢሆንም በበይነ መረብና ሱቆች ውስጥ እንደሚሸጥ ቢቢሲ 3 አጋልጧል። እናም የሀገሪቱ የጤና አገልግሎት እንክብሎቹ ማስተዋወቅ አካላዊና አዕምሯዊ ጤንነት ላይ ያለውን ስጋት ይፋዊ በሆነ ደብዳቤ ገልፃል። ኢንስታግራም ደግሞ ህመሞችን ለመፈወስ ከሚውሉ በስተቀር መድሃኒቶችን መሸጥ 'ከፓሊሲያችን ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው' ብሏል። የምግብ ፍላ���ትን በመጨመር የሰውነት ክብደትን የሚየጨምረው 'አፒታሚን' የጉበት ስራ ማቆምን ጨምሮ ለተለያዩ የጤና እክሎች እንደሚዳርግ የጤና ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ሆኖም ይህ መድሃኒት በርከት ያሉ ተከታዮች ባሏቸው የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች በቋሚነት እየተዋወቀ ይገኛል ተብሏል። ኢንስታግራም በበኩሉ ይህን መድሃኒት ያስተዋወቁና የሸጡ ተጠቃሚዎቹን አካውንት ዘግቻለሁ ሲል ይህንን ጉዳይ ላጋለጠው ቢቢሲ 3 ገልጿል። ሆኖም የእንግሊዝ የጤና አገልግሎት በርከት ያሉ አካውንቶች አሁንም አሉ ያለ ሲሆን ሪፓርት ቢደረግም ኢንስታግራም እርምጃ አይወስድም ነበር ሲል ከሷል። https://www.bbc.com/amharic/news-56972154 +sports የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በቶኪዮ አየር ማረፊያ ያጋጠመው ምን ነበር? "በቶኪዮ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ቡደን ቶኪዮ አየር ማረፊያ ከደረሰ በኋላ ለሰዓታት በአየር ማረፊያ እንዲቆይ መደረጉ ተገልጿል። በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ማክስኞ አመሻሽ ወደ ቶኪዮ የበረረው ቡድኑ፤ የኮቪድ-19 ምርመራ ሰርተፊኬቶች ሲመረመሩ እና በአየር ማረፊያ የተደረገው ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት እስኪመጣ ድረስ ለሰዓታት በአየር ማረፊያ ለመቆየት መገደዱ ተነግሯል። ከቡድኑ ጋር አብራ የተጓዘችው ጋዜጠኛ አርያት ራያ የኢትዮጵያ ልዑክ በበረረበት አውሮፕላን ውስጥ ተሳፋሪ ከነበሩት አትሌቶች መካከል የአንጎላ ዜግነት ያለው አንድ አትሌት በኮቪድ-19 መያዙ መረጋገጡን ተከትሎ ለሌላ ተጨማሪ ሰዓት በአየር ማረፊያው ለመቆየት መገደዳቸውን ለቢቢሲ አስረድታለች። በረራው ረዥም ነበር የምትለው ጋዜጠኛ አርያት፤ በደቡብ ኮሪያ በኩል ትራንዚት አድርገው ቶኪዮ ለመድረስ ከ15 ሰዓታት በላይ መውሰዱን ታስረዳለች። ""ብዙ ነበርን። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ብቻ አልነበረም። የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን፣ የማደጋስካር፣ የታንዛኒያ፣ የአንጎላ ብሔራዊ ቡድን አባላትም ከእኛ ጋር ነበሩ። ብዙ ስፖርተኛ ነበር። ያ ሁሉ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ነበረበት"" ያለችው አርያት፤ የኤርፖርቱ ኃላፊዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረጉ ስለነበረ የኮቪድ-19 ምርመራውን በፍጥነት እያከናወኑ አልነበረም ትላለች። ""ፓስፖርት አይተው እስኪያጣሩ፤ ይዘን የሄድነውን የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት እስኪያረጋግጡ እና የኮቪድ-19 ውጤታችን እስኪመጣ ድረስ ረዥም ሰዓት ነው የወሰደው። ወደ ሰባት ሰዓት ያህል አየር ማረፊያ ውስጥ ቆይተን ነበረ። ምርመራ ጨርሰን፤ ውጤታችንን አይተን ልንወጣ ስንልን አንድ የአንጎላ አትሌት ውጤቱ ፖዘቲቭ ሆነ ተብሎ እንደገና ትንሽ ቆይታ አድርገን ነው የወጣነው"" ብላለች። በመጀመሪያ ዙር ወደ ቶኪዮ ካቀኑት መካከል የኢፌድሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር፤ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ይገኙበታል።" https://www.bbc.com/amharic/57931331 +health አዘውትሮ ምሽት አራት ሰዓት አካባቢ መተኛት ለልብ ችግር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል- ጥናት "ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ባለው ጊዜ አዘውትሮ መተኛት ለተሻለ የልብ ጤንነት እንደሚረዳ በ88 ሺህ በጎ ፈቃደኞች ላይ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች አስታወቁ። በዩናይትድ ኪንግደም ባለ አንድ ቡድን በተደረገ ጥናት እንቅልፍ ከውስጣዊው የሰውነት ክፍላችን የጊዜ አቆጣጠር ጋር እንዲጣታም ማድረግ ለልብ ድካም እና ለስትሮክ የመጋለጥ እድልን እንደሚቀንስ ጠቁሟል። የሰውነት ተፈጥሯዊ የ24-ሰዓት ምት ለደኅንነት እና ንቁ ለመሆን አስፈላጊ መሆኑን የሚገልጸው ጥናቱ እን��� የደም ግፊት ባሉ ሂደቶች ላይም ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ይላል። በአውሮፓ የልብ ጤና ጆርናል ላይ በታተመው በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ በሰባት ቀናት ውስጥ በእንቅልፍ እና በእንቅልፍ ጊዜ ላይ ከጥናቱ ተሳታፊዎች መረጃን ለማሰባሰብ የእጅ ሰዓት የሚመስል መሳሪያ እንዲያጠልቁ አድርገዋቸዋል። በመሳሪያው አማካኝነት በአማካይ በስድስት ዓመታት ውስጥ በልብ እና በደም ዝውውር ጤና ላይ ያለውን ሁኔታ ተከታትለዋል። በዚህም ከ3,000 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች የልብ ችግር [የካርዲዮቫስኩላር] በሽታ ተገኝቶባቸዋል። በጥናቱ መሰረት ለዚህ ችግር የተጋለጡት ከምሽቱ 4 ወይም 5 ሰዓት ቀደም ብለው ወይም ዘግይተው ወደ አልጋ የማምራት ልምድ ያላቸው ሰዎች ላይ ነው። ተመራማሪዎቹ እንደ ዕድሜ፣ የሰውነት ክብደት እና የኮሌስትሮል መጠን ያሉ የአንድን ሰው ለልብ ስጋት የሆኑ ሌሎች ነገሮችን ለማየት ሞክረዋል። ነገርግን ጥናታቸው መንስኤውንና ውጤቱን ማረጋገጥ አልቻለም። ተመራማሪዎቹ እንደ ዕድሜ፣ የሰውነት ክብደት እና የኮሌስትሮል መጠን ያሉ አንድን ሰው ለልብ ችግር የሚያጋልጡ ሌሎች ነገሮችን ለማየት የሞከሩ ሲሆን ጥናታቸው መንስኤና ውጤቱን ማረጋገጥ እንዳልቻለ አስረድተዋል። ""በጥናታችን መንስኤው ላይ መደምደሚያ መስጠት ባንችልም በውጤቱ መሰረት ከመደበኛው የመኝታ ሰዓት ቀደም ብሎ ወይም ዘግይቶ መተኛት የሰውነትን አቆጣጠርን ሊያስተጓጉል ስለሚችል የልብና የደም ሥር ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያስከትል ጥናቱ አመላክቷል"" ሲሉ አጥኚው ዶ/ር ዴቪድ ፕላን ገልጸዋል። ""በጣም ችግር የማስከተል ዕድል ያለው የእንቅልፍ ጊዜ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ያለው ነው። ምክንያቱ ዘግይቶ የተኛው ሰው የጠዋት ብርሃንን የማየት እድሉን ሊቀንስ ስለሚችል የሰውነት አቆጣጠር እንደገና ይጀምራል"" ሲሉም አክለዋል። በብሪቲሽ የልብ ፋውንዴሽን ከፍተኛ የልብ ነርስ የሆኑት ራይጃና ጊብሊን ""ይህ ትልቅ ጥናት እንደሚያመለክተው ከምሽቱ 4 እስከ 5 ሰዓት መተኛት ለብዙ ሰዎች ልባቸው ለረጅም ጊዜ ጤናማ እንዲሆን ምቹ ሊሆን ይችላል"" ብለዋል። ""ሆኖም ይህ ጥናት መንስኤውን እና ውጤቱን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ማስታወስ አስፈላጊ ነው። የእንቅልፍ ጊዜ እና ቆይታ ከልብ እና ደም ዝውውር በሽታዎች ጋር ስላለው ተያያዥነት ምርምሮች ያስፈልጋሉ"" ሲሉ ገልጸዋል። ነርሷ በቂ እንቅልፍ ማግኘታችን ለአጠቃላይ ጤንነታችን ብሎም ለልባችን እና ለደም ዝውውር ጤናማነት ጠቃሚ ነው። አብዛኞቹ ጎልማሶች ከሰባት እስከ ዘጠኝ ሰዓታት መተኛት ይጠበቅባቸዋል ሲሉም አስረድተዋል። ""ይህ ማለት ግን እንቅልፍ የልብ ጤና ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር የሚችል ብቸኛው ምክንያት ነው ማለት አይደልም። የደም ግፊት እና የኮሌስትሮል መጠንን ማወቅ፤ ጤናማ ክብደትን መጠበቅ እና በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ የጨው እና አልኮል መጠጦችን በመቀነስ የአኗኗር ዘይቤን ማጤን በጣም አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም የተመጣጠነ ምግብ መመገብ የልብን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል"" ሲሉ ነርስ ራይጃና ጠቅሰዋል።" https://www.bbc.com/amharic/59230351 +health ኮሮናቫይረስ: 'ልጆቼ እናታቸው በኮቪድ እንደሞተች ስለማያውቁ ትመጣለች ብለው ይጠብቃሉ' "ሕንድን ያመሰው ሁለተኛው የኮቪድ ሞገድ በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦችን የማይነገር ሃዘን ጥሎባቸዋል። መከራ፣ ቸልተኝነት፣ አለመዘጋጀት እና በደንብ ያልታሰበበት የክትባት ዕቅድ ለብዙዎች ሞት ምክንያት ሆኗል። አልቱፍ ሻምሲ ሐዘንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕንዳውያ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ከገጠማቸው ልብን የሚሰብር ሐዘን መካከል አንዱ ነው። ሚያዝያ መጀመሪያ ላይ ቤተሰቤ እንደተለመደው ደስተኛ ነበር። እኔና ባለቤቴ ሪሃብ ሦስተኛ ልጃችንን እየጠበቅን ነበር። የማህጸን ሐኪሟ ከሚያዝያ 22 በፊት ሆስፒታል እንድንመጣ መክሮናል። ሪሐብ በእርግዝናዋ 38ኛ ሳምንት ውስጥ ስለነበረች በሚቀጥለው ቀን ለማዋለድ ነበር ዕቅዱ። ነፍሰጡር ሴቶች ከመውለዳቸው በፊት ኮቪድ እንዲመረመሩ መመሪያ ወጥቷል። ተመረመረች። ኮሮና እንዳለባት ስናውቅ ደነገጥን። ሆስፒታሉ ኮሮና ያለባቸውን አይቀበልም። ሪሃብ ጊዜ ስለነበራት ሐኪሟ ሌላ ቀጠሮ ሰጠን። ኮቪዱ ላይ እንድናተኩርም ነገረችን። ከጥቂት ቀናት በኋላ ሪሃብ ከፍተኛ ትኩሳት አጋጠማት። ሚያዝያ 28 በሐኪሟ ምክር መሠረት የኮቪድ ህክምና ወደሚሰትበት ሆስፒታል አስገባናት። ሆስፒታል ከገባች ሁለት ቀን ሆናት። ሪሃብ ጠንካራ መድኃኒት እየወሰደች በመሆኑ ህጻኑን እንደምናጣ ሐኪሙ ነገረን። አመሻሹ ላይ ህመሟ ተባብሶ የኦክስጂን ድጋፍ አስፈለጋት። ዶክተሮችም ህጻኑን በድንገተኛ ቀዶ ጥገና እንዲወለድ ወሰኑ። ሆስፒታሉ በከፍተኛ ደም መፍሰስ ምክንያት እስከሞት የሚደርስ ከፍተኛ ዕድል እንዳለ የሚገልጹ ሰነዶችን እንድንፈርም አደረገ። ከገደል አፋፍ ዘሎ በሠላም የማረፍ ተስፋ ዓይነት ነው። ከቀዶ ጥገናው በኋላ ሪሃብ ከፍተኛ የህክምና ክትትል ስለሚያስፈልጋት ሌላ ሆስፒታል የጽኑ ህሙማን አልጋ እንድፈልግ ተነገረኝ። የተሟላ የኮቪድ ህክምና ቢያስፈልጋትም እነሱ ሊያሟሉ አልቻሉም። በዚህ ጊዜ ልጅ እንደወለድን ረስቻለሁ። በአዕምሮዬ የሚመላለሰው ብቸኛው ነገር ሪሃብን ማዳን ነበር። ለቀዶ ህክምናው አእምሮዬን እያዘጋጀሁ እያለ መጥፎ ዜና መጣ። ባለቤቴ ኮሮና እንዳለበት ያወቅነው አባቴም ዴልሂ በሚገኝ ሌላ ሆስፒታል የገባ ጊዜ ሲሆን ጤንነቱ እያሽቆለቆለ ነበር። እናቴም ኮሮና የተገኘባት ሲሆን በአነስተኛ የኦክስጂን ድጋፍ በቤት ውስጥ ነበረች። ባለቤቷ እና የልጇ ሚስት ህይወታቸውን ለማትረፍ እየታገሉ እንደሆነ እንኳን አታውቅም። ዓለም በዙሪያዬ ሊፈርስ ከጫፍ የደረሰ መሰለ። እንዲድኑ እየጸለይኩኝ የጽኑ ህሙማን አልጋ ፍለጋዬን አጧጡፍ ጀመር። ሚያዝያ 29 ሴት ልጄ ተወለደች። አልጋ ማግኘት ስላልቻልኩ ሪሃብ ወደ ጊዜያዊ የጽኑ ህሙማን ክፍል እንድትዛወር ተደረገ። ሆስፒታሉ በቂ ነርሶች አልነበሩትም። እኔም በኮሮና ተያዝኩኝ። የራሴን ትቼ ከሪሃብ ጎን ለመቆም ወሰንኩ። ስለመድኃኒቷ ያለማቋረጥ ነርሶችን ማሳሰብ ነበረብኝ። እነሱ ደግሞ ወደ ሌላ ቦታ እንድወስዳት በተደጋጋሚ ይነግሩኛል። አጋዥ መተንፈፈሻ መሣሪያ (ቬንትሌተር) ያለው አልጋ ካገኘሁ በሚል የማውቃቸው ሰዎች ሁሉ ጋር ደዋወልኩኝ። በመጨረሻም የየጽኑ ህሙማን አልጋ አገኘሁላት። እሷን የሚወስዳት የህይወት ድጋፍ መሣሪያ ያለው አምቡላንስ ግን አልነበረም። ሆስፒታሉ ህክምናውን እንዲቀጥልላት ተማጸንኩኝ። እነሱም እሷን ለማዳን የቻሉትን ሁሉ አደረጉ። ግንቦት አንድን መቼም አልረሳውም። በርካታ ሆስፒታሎች ከፍተኛ የኦክስጂን እጥረት እንደገጠማቸው ይገልጹ ነበር። ሪሃብ የምትታከምበት ሆስፒታል ያሉ ሠራተኞችም ኦክስጂን ሊያልቅባቸው እንደሆነ ነግረውኝ ሲሊንደሮችን እንዳዘጋጅ ጠየቁኝ። አመሻሹ ላይ አባቴ ከሚታከምበት ሆስፒታል ተደውሎልኝ ጤንነቱ በፍጥነት እያሽቆለቆለ እንደሆነ ተነገረኝ። እዚያ ስደርስ አባቴ ህይወቱ አልፏል። ደንዝዤ ነበር። አስከሬኑን እያየሁ ከሪሃብ ሆስፒታል ስለኦክስጅን እጥረት የሚደርሰኝን መልዕክት እያነበብኩ ነበር። እናቴም በጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለችም። የሰባት እና የአምስት ዓመት ሴት ልጆቼ እናታቸው እና አዲሷ እህታቸው ቃል በተገባው መሠረት ለምን ቤት እንዳልመጡ ይጠይቁ ነበር። ለእናቴ የ42 ዓመት የትዳር አጋሯን ሞት መንገር ከባድ ነበር። እሱ የቤተሰቡ ጠባቂ ነበር። የእሱ ማለፍ የበለጠ ተጋላጭ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ አደረገኝ። እሱን ቀብሬ በፍጥነት ወደ ሪሃብ ሆስፒታል ተመለስኩ። የእሷም ጤንነት አሽቆልቁሏል። በቀጣዮቹ 11 ቀናት በተስፋ እና በተስፋ መቁረጥ መካከል ስወዛወዝ ቆየሁ። ሪሃብ በየቀኑ በመጠኑ እየተሻላት እንደሆነ ቢነገረኝም በከፋ ሁኔታ ውስጥ ነበረች። ከሁለት ቀናት በኋላ ኩላሊቶቿ ድጋፍ አስፈለጋቸው። በማሽን የተደገፈ የደም እጥበት [ዲያሊሲስ] ጀመረች። የኦክስጂን መጠኗ መሻሻል ሲጀምር ከህክምና ክፍሉ እንድወጣ ተነገረኝ። ከሁለት ቀን በኋላ ቬንትሌተሩን ሲነቅሉላት እንደማያት ተነግሮኛል። የዚያኑ ዕለት ምሽት 2 ሰዓት ገደማ ሪሀብን እንድትንከባከብ የቀጠርኳት የግል ነርስ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለች ነገረችኝ። እናቴን እና ሴት ልጆቼን ለማየት ወደ ቤት ተመለስኩኝ። ከምሽቱ 5 ሰዓት ገደማ ከሆስፒታሉ ተደውሎ በፍጥነት እንድመለስ ተጠራሁኝ። ተጣድፌ ሆስፒታል ስደርስ ልቤ በአፌ ልትወጣ ደረሳ ነበር። ሪሃብ ግን በህይወት አልቆየችኝም። የሆስፒታሉ ሠራተኞች ""የልብ ችግር"" እንደነበር ነግረውኛል። ሙሉ በሙሉ ተሰበርኩኝ። እኔ ጠንካራ ለመሆን እየሞከርኩ ነበር። ቤተሰቦቼን ተንከባክቤ በሚቀጥለው ቀን ባለቤቴን ለማየት እና ላወራት ተስፋ አድርጌ ነበር። ሊደረመስ ከቋፍ ደርሶ የነበረው ዓለሜ ፈረሰ። የነበረኝ ብቸኛው ጭንቀት እናታቸው ወደ ቤት መቼም እንደማትመለስ ለልጆቼ እንዴት እንደምነግራቸው ነው። እስካሁንም አልነገርኳቸውም። እንዴት ማድረግ እንዳለብኝም አላውቅም። በየቀኑ ስለ እሷ ይጠይቁኛል። አሁንም ሆስፒታል መሆኗን እነግራቸዋለሁ። እህቴ አዲሷን ሕፃን በመጠበቅ እየረዳችኝ ነው። ሪሃብ አስደናቂ ሴት ብቻ አይደለችም። አፍቃሪ እና አሳቢ እናት፣ ሚስት፣ ሴት እና ምራትም ነበረች። ደፋር እና በራስ መተማመን የነበራት ስለነበረች ነው የታገለችው። አዲስ የተወለደችውን ልጃችንን ለማየት አልታደለችም። የሪሃብ ስጦታ አድርጌ ስለምወስዳት እንከባከባታለሁ። ለልጆቼ አባት እና እናት ለመሆን እየሞከርኩ ነው። ሪሃብ በህይወታችን የፈጠረችው ክፍተትን ግን በጭራሽ መሙላት አልችልም። እሷን ለማዳን ከዚህ በላይ ማድረግ የምችለው ሌላ ነገር ይኖር ይሆን? እያልኩ አስባለሁ። የተሻለ ሆስፒታል ባገኝ ኖሮ በህይወት ትኖር ነበር? እላለሁ። ቀላል መልሶች የሉትም። በእርግጠኝነት ግን የኮቪድ ክትባቶች እንደ ሪሃብ ያሉ ብዙ ሴቶችን ማዳን ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ። ክትባት ብታገኝ ኖሮ በሕይወት ትኖር ይሆናል። ለእርሷ ምንም ክትባት አልተገኘም። በከባድ የኮቪድ በሽታ ለተያዙ እርጉዝ ሴቶች መንግሥት ክትባቱን ገና አላጸደቀም። የህይወቴን አንጸባራቂ ብርሃን አጥቻለሁ። ባለፍኩበት መንገድ ሌላ ሰው እንዲያልፍ አልፈልግም። በሌኛው ዓለም እስከማይሽ ደህና ሁኚ ሪሃብ።" https://www.bbc.com/amharic/news-57534543 +politics ኢሰመኮ በኮንሶ ያሉ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ መብት አያያዝ የከፋ ነው አለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኮንሶ ያሉ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ መብት አያያዝ የከፋ ነው አለ። ኢሰመኮ ይህን ያለው በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞን እና በሦስት ልዩ ወረዳዎች በሚገኙ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታን በተመለከተ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ነው። የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ በኮንሶ ዞን፣ በአሌ ልዩ ወረዳ፣ በደራሼ ልዩ ወረዳ እና በአማሮ ልዩ ወረዳ በአጠቃላይ የተመዘገቡ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ከ145 ሺህ በላይ መሆኑን ገልጿል። ኮሚሽኑ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮቹ ሰብዓዊ ድጋፍ እን��ማያገኙ እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጿል። የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ተቋሙ ክትትል ባደረገባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች “በቂ የሰብዓዊ ድጋፍ ባለማግኘታቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ከመሆኑም ባሻገር፣ በተለያዩ ጊዜያት በዚህ አካባቢ የሚያገረሹ ግጭቶች የተፈናቀሉ ሰዎችን ለተደራራቢ ጉዳት እና መፈናቀል እየዳረጉ ነው” ብለዋል። ስለዚህም የሚመለከታቸው አካላት ለመፈናቀል መንስዔ የሆኑ ግጭቶችን ማስወገድ፣ በቂ የሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ እና ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ይህን ሪፖርት ያወጣው የአገር ውስጥ ተፈናቃዮቹ በሚገኙባቸው መጠለያ ጣቢያዎች እና ተቀባይ ማኅበረሰብ ጋር በመዘዋወር ተፈናቃዮችን፣ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችን እና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በማነጋገር እና የሰነድ ማስረጃዎች በማሰባሰብ ነው። ተፈናቃዮች ቀያቸውን ጥለው እንዲሄዱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛው ግጭት መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሟል። የአካባቢውን ነዋሪዎች ለግጭት ከሚዳርጉ ምክንያቶች መካከልም የእርሻ፣ የግጦሽ መሬት እና የደን ሃብት ይዞታ ይገባኛል የሚለው ምክንያት አንዱ ነው። ሌሎች ጉዳዮች ደግሞ የአስተዳደር መዋቅር በሚጠይቁ እና መዋቅሩን በሚቃወሙ እንዲሁም የአስተዳደር ወሰን ግጭት በምክንያት ነት ይጠቀሳል። ኢሰመኮ የክልሉ እና ብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለተፈናቃዮች በቂ እና ጊዜውን የጠበቀ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያቀርቡ እና እንዲያስተባብሩ ጠይቋል። ለመፈናቀል መንስኤ የሆኑ የአስተዳደር መዋቅር እና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄዎችን የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መልኩ አፋጣኝ መፍትሔ ሊሰጥ ይገባልም ብሏል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ አካባቢ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ምክንያቶች በማኅበረሰቦች መካከል በተደጋጋሚ በሚከሰቱ ግጭቶች ከሚፈናቀሉት በተጨማሪ፤ የበርካታ ሰዎች ሕይወት የጠፋ ሲሆን፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረትም ለውድመት ተዳርጓል። https://www.bbc.com/amharic/articles/ckv27jv55xjo +business ኮሮናቫይረስ፡ ሳኡዲ ለዜጎቿ የምትሰጠውን ድጎማ በማቋረጥ ተጨማሪ ዕሴት ታክስን በሦስት እጥፍ ጨመረች "የሳኡዲ አረቢያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የደቀቀውን ኢኮኖሚዋን ለመደገፍ በተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ ሦስት አጥፍ ጭማሪ ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች። የአገሪቱ መንግሥት ከዚህ በተጨማሪም ለዜጎቹ ይሰጠው የነበረውን የኑሮ መደጎሚያ ገንዘብ እንደሚያቋርጥም አስታውቋል። የኮሮናቫይረስ ባስከተለው ዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በመቀነሱ በነዳጅ ሀብት የበለጸገችው ሳኡዲ አረቢያ የገቢ መጠኗ በእጅጉ አሽቆልቁሏል። ሳኡዲ አረቢያ ከሁለት ዓመታት በፊት ነበር ኢኮኖሚው በነዳጅ ላይ ብቻ እንዳይንጠለጠል በሚል ተጨማሪ እሴት ታክስን ያስተዋወቀችው። የሳኡዲ አረቢያ ዜና ተቋም እንደዘገበው ተጨማሪ እሴት ታክሱ ከፈረንጆቹ ሰኔ ወር ጀምሮ ከ5% ወደ 15% ከፍ ይላል። ""እነዚህ እርምጃዎች በጣም ከባድ ነገር ግን አሁና ካለው ሁኔታ አንጻር እጅግ አስፈላጊ ናቸው። የአገሪቱን የገንዘብና ኢኮኖሚያዊ ደኅንነትን ለማረጋገጥ ነው እርምጃዎቹ የተወሰዱት"" ብለዋል የገንዘብ ሚኒስትሩ ሞሐመድ አል ጃዳን። ይህ ውሳኔ የተላለፈው አገሪቱ የምታወጣው ወጪ ከምታስገባው ገቢ በማነሱ ምክንያት መንግሥት ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ የ9 ቢሊዮን ዶላር የበጀት ጉድለት ማጋጠሙን ተከትሎ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌ��� ውስጥ ከነዳጅ የሚገኝ ትርፍ 22 በመቶ በመቀነሱ አገሪቱ ማግኘት የቻለችው 34 ቢሊዮን ዶላር ብቻ በመሆኑ ነው። በነዚሁ ሦስት ወራትም የሳኡዲ አረቢያ ማዕከላዊ ባንክ እንዳስታወቀው የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዝቅ ብሏል። ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን የሳኡዲ አረቢያ ኢኮኖሚን ለማነቃቃትና አጠቃላይ የአገሪቱን ገጽታ ለመቀየር እየወሰዱት የነበረውን እርምጃ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ፈተና እንደሚሆንበት ይጠበቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-52613715 +business የኮሮናቫይረስ መከሰትን ተከትሎ የዓለም ምጣኔ ሃብት ወደቀ ወይስ ደቀቀ? የኮሮናቫይረስ ጥምር ኪሳራ እያስከተለ ነው። በመላው ዓለም በሚባል ደረጃ በሰዎች ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ቫይረሱን ለመከላከል ሲባል የሚዘጉ ምርት፣ የንግድና የመዝናኛ ተቋማት ምንም ዓይነት የግብይት እንቅስቃሴ እንዳይኖር በማድረግ ምጣኔ ሃብቱ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ደቅኗል። https://www.bbc.com/amharic/news-51978777 +sports የቀነኒሳ በቀለ ክብረ ወሰን በኡጋንዳዊው ወጣት ተሰበረ ኡጋንዳዲው ጆሹዋ ቼፕቴጌ በፈረንሳይ ሞናኮ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለ16 ዓመታት በቀነኒሳ በቀለ ተይዞ የነበረውን የ5000 ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን በሁለት ሰከንድ ማሻሻል ችሏል። የ23 ዓመቱ ወጣት ባላፈው ዓመት በዶሃ የዓለም ሻምፒዮና ላይ የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ በሆነበት ወቅት የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንን ለማሻሻል እቅድ እንዳለው ገልጾ የነበረ ሲሆን በቅርብ ዓመታት ያሳካዋል ተብሎ ግን አልተገመተም ነበር። ነገር ግን በትላንቱ የሞናኮው ውድድር ላይ 5 ሺህ ሜትሩን 12 ደቂቃ 35.36 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመጨረስ ቀነኒሳን ክብረ ወሰን መስበር ችሏል። ቀነኒሳ በቀለ የዛሬ 16 ዓመት ክብረ ወሰኑን ሲያስመዘግብ ውድድሩን የጨረሰው በ12 ደቂቃ 37 ሰከንድ ከ35 ማይክሮ ሰከንድ ነበር። በሚያስገርም ሁኔታ ቼፕቴጌ በዚህ ዓመት ክብረ ወሰን ሲሰብር ይሄ ሁለተኛው ነው። ባለፈው የካቲት ወር ላይ ደግሞ በተካሄደ የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ሰዓት ማሻሻል እንደቻለ ተነግሯል። ''ሞናኮ በጣም ልዩ ቦታ ናት፤ የዓለም ክብረ ወሰኖችን ልሰብርባት የምችልባት ከተማ ናት'' ሲል በደስታ ተውጦ ቼፕቴጌ ተናግሯል። ''በዚህ ዓመት በእውነቱ ሞራልን ሰብሰብ አድርጎ ለመስራት ትንሽ ይከብዳል፤ ምክንያቱም በወረርሽኙ ምክንያት ሰዎች ከቤታቸው አይወጡም፤ ብዙ ነገሮችም በፊት እንደነበሩት አይደሉም፤ ተቀይረዋል። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ በማሸነፌ በጣም ደስተኛ ነኝ።'' በሌሎች ውድድሮች የዓለም ሻምፒዮኑ ኖዋህ ሊይስ የ200 ሜትር ውድድሩን በ19 ሰከንድ ከ72 ማይክሮሰከንድ በሆነ ሰዓት በማሸነፍ አይበገሬነቱን አሳይቷል። ታናሽ ወንድሙ ጆሴፈስ ደግሞ በመጀመሪያው የዳይመንድ ሊግ ተሳትፎው እሱን ተከትሎ ሁለተኛ ሆኖ መጨረስ ችሏል። ኖርዌያዊው ዓለም ሻምፒዮን ካርስተን ዋርሆልም ደግሞ በ400 ሜትር መሰናክል ውድድር በአውሮፓውያኑ 1992 በኬቨን ያንግ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን መስበር ችሏል። ለብቻው ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ሲሮጥ የነበረው ካርስተን ውድድሩን በ47 ሰከንድ ከ10 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ ደግሞ የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ ሲፋን ሀሰን ደግሞ ጥቂት ዙሮች ሲቀሩት ውድድሩን አቋርጣ ወጥታለች። 5 ሺህ ብቻ ሰዎች እንዲመለከቱት በተፈቀደው የሞናኮው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ተመልካቾች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታቸው ሲሆን አካላዊ ርቀትም መጠበቅ ነበረባቸው። https://www.bbc.com/amharic/news-53789764 +sports ወደፊት እግር ኳስ ተጫዋቾች 'ቴስታ' መምታት ይከለከሉ ይሆን? "ቴስታ ወይም የጭንቅላት ኳስ ወደፊት ከእግር ኳሱ ዓለም ሊወገድ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መነጋገሪያ ሆኗል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ጤና ነው። ተመራማሪዎች ኳሰን በጭንቅላት መግጨት ጣጣ አለው እያሉ ነው። እንግሊዝ ይህን በማስመልከት ሕፃናት እግር ኳስ ሲጫወቱ ቴስታ እንዳይመቱ የሚከለክል ሕግ እያወጣች ነው። አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው የቀድሞ ተጫዎቾች ከሌሎች በተለየ በጭንቅላት ሕመም የመሞት ዕድላቸው በሦስት እጥፍ የጨመረ ነው። በዚህ ሃሳብ እግር ኳስ ተጫዎቾችም ይስማማሉ። የቀድሞው የቶተንሃምና የሃል ሲቲ ተጫዋች ራያን ሜሰን ቴስታ በሚቀጥሉት ከ10 አስከ 15 ዓመታት ባለው ጊዜ ሊቀር ይችላል ይላል። ሜሰን በ2017 ጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት በጊዜ ከእግር ኳስ ሕይወት ራሱን አሰናብቷል። የ29 ዓመቱ ሜሰን ""በሚቀጥሉት ዓመታት ቴስታ ከእግር ኳስ ዓለም መወገድ አለበት ቢባል አልደነቀም"" ሲል ለቢቢሲ ይናገራል። ሜሰን እንደሚለው ቴስታን በተመለከተ የሚሠሩ ጥናቶች ከዚህም በላይ በጣም አስደንጋጭ ውጤቶች ይዘው ሊመጡ ይችላሉ። ""እኔ እግር ኳስ ተጫዋቾች ቴስታ የሚያመጣውን ተፅዕኖ በቅጡ ያወቁት አይመስለኝም። ለዚህ ነው ተጨማሪ ጥናቶች ያስፈልጋሉ የምለው።"" ""በጣም አስጨናቂ ጉዳይ ነው"" ይላል ሜሰን ስለጭንቅላት ኳስ ሲያወራ። ""ችግሩ የቴስታን ጉዳት አሁን አናየውም። ጉዳቱ የሚመጣው ከዓመታት በኋላ ነው።"" ቴስታ በእግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ የሚያመጣው ጉዳት ምንድነው የሚለውን ያጠኑት ዶ/ር ዊሊ ስቴዋርት ቴስታ የጭንቅላት ሕመምና የመርሳት በሽታ ሊያስከትል ይችላል ይላሉ። በፈረንጆቹ 1966 ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫ ያነሳው ኖቢ ስታይልስ ባለፈው ጥቅምት ከመሞቱ በፊት በተደጋጋሚ ኳስን በጭንቅላቱ በመምታቱ ለመርሳት በሽታ እንደተጋለጠ ተናግሮ ነበር። ከቴስታ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው ጉዳይ የአየር ላይ ኳስ በጭንቅላት ለመግጨት በሚደረግ ፍልሚያ የሚከሰተው አደጋ ነው። ከጥቂት ሳምንታት በፊት አርሰናልና ዎልቭስ በነበራቸው ጨዋታ የአርሴናሉ ዴቪድ ሉዊዝና የዎልቭሱ ራዉል ሂሜኔዝ ለጭንቅላት ኳስ ሲሻሙ ተጋጭተው ሂሜኔዝ ክፉኛ ተጎድቶ ነበር። በወቅቱ ሂሜኔዝ በቃሬዝ ነበር ከጨዋታው የወጣው። ሉዊዝ ደግሞ ጭንቅላቱን በፋሻ አስሮ ጨዋታውን ቀጥሎ ነበር። እንግሊዛዊው የቀድሞ የፕሪሚዬር ሊግ ኮከብ አለን ሺረር አርሴናል ሉዊዝን ከሜዳ ማስወጣት ነበረበት ብሎ ትችት መሰንዘሩ አይዘነጋም። የቀድሞው የቶተንሃም ተጫዋች ያን ቬርቶንገን ከሁለት የውድድር ዘመን በፊት በቻይምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የጭንቃላት አደጋ አጋጥሞት ነበር። ተጫዋቾ የዚህ አደጋ ሕመም ለዘጠኝ ወራት ያህል ይሰማው እንደነበር ከጥቂት ሳምንታት በፊት ተናግሮ ነበር። ሜሰን ከቼልሲው ተከላካይ ጋሪ ካሂል ጋር ተጋጭቶ ባጋጠመው አደጋ ነው ጉዳት የደረሰበት። ""በሕይወቴ መቆየቴ በራሱ ዕድለኛነት ነው"" ይላል። ከሚቀጥለው ጥር ወር ጀምሮ ክለቦች የጭንቅላት አደጋ ሲያጋጥም ከመደበኛው ቅያሪ በተጨማሪ ሁሉት ተጫዋቾችን መቀየር እንዲችሉ ይፈቀድላቸዋል። አሁን የቶተንሃም አካዳሚ አሠልጣኝ ሆኖ የሚያገለግለው ሜሰን ግን ይህ ከሚሆን የጭንቅላት ኳስ ሕግ ሙሉ በሙሉ መቀየር አለበት ብሎ ያምናል። ቴስታ ወደፊት ከእግር ኳስ ዓለም ይወገድ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ግን አከራካሪነቱ እንደቀጠለ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-55445728 +business ኢኮኖሚ፡ የብር የምንዛሪ ዋጋ በገበያ መወሰኑ ምን ይዞ ይመጣል? "ብሔራዊ ባንክ የብር የውጭ ምንዛሪ ፍላጎትን መሠረት በማድረግ የብር ዋጋ በገበያ ተመን እንዲወሰን ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፤ ኢትዮጵያ በሦስት ዓመታት ውስጥ ብርን ወደ ፍሎቲንግ ካረንሲሥርዓት (የገንዘብን ተመን በገበያ ዋጋ ላይ መመስረት) እንደምትሸጋገር ተገልጿል። ለመሆኑ ፍሎቲንግ ካረንሲ ምንድነው? ኢትዮጵያ ፊቷን ወደዚህ ሥርዓት ማዞሯ ምን ያስከትላል? በንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ላይ የሚያሳድረሰው ተጽዕኖ ምንድነው? በተራው ዜጋ ህይወት ላይስ ምን አንድምታ አለው? ለእኒዚህ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡን የምጣኔ ሃብት ባለሙያ የሆኑቱን እዮብ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) እና አቶ ዋሲሁን በላይን ጠይቀናል። የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቶች የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ የተለያዩ አይነት የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቶች እንዳሉ ይጠቅሳሉ። የገንዘብን ዋጋ በገበያ መሠረት መተመን (Floating Exchange Rate)፣ የገንዘብ ዋጋ መጠን በማዕካለዊ ባንክ የሚወሰንበት (Fixed Exchange Rate) እና ማዕከላዊ ብንኩ እንደ አስፈላጊነቱ ጣልቃ የሚገባበት (Managed Floating Exchange Rate) ይጠቀሳሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ ሁሉም አይነት የውጪ ምንዛሪ ሥርዓቶች የራሳቸው የሆነ አውንታዊና አሉታዊ ውጤቶች እንዳላቸው ይስማማሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ፤ አገራት የተወሰነ የውጪ ምንዛሪ ሥርዓትን ስለመረጡ ብቻ ውጤታማ ይሆናሉ ማለት አይደለም ይላሉ። እንደምሳሌም ሳዑዲ አረቢያ ምንዛሪው በማእከላዊ ባንክ የሚወሰን የተመን ሥርዓትን እየተከተለች ውጤታማ መሆኗን በማስታወስ፤ ""ዋናው ቁምነገሩ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቱን በነጻ ገበያ ወይም በመንግሥት የሚወሰን አይደለም። የአገር ውስጥ ምርታማነትን በማሳደግ ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ማሳደግ ነው"" ይላሉ። በገበያ ከሚወሰነው ምንዛሪ ኢትዮጵያ ምን ታተርፋለች? ብር በአሁኑ ወቅት ከሚገባው በላይ ዋጋ እንዳለው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ስለዚህም የብር ዋጋ በገበያ ወደሚተመንበት ሥርዓት ሲሸጋገር ዋጋው አሁን ካለው እንደሚቀንስ ወይም በብር እና በዶላር መካከል ያለው ልዩነት እንደሚሰፋ ይታመናል። አቶ ዋሲሁን የብር የመግዛት አቅም ሲቀንስ ኢትዮጵያ የምታመርታው ምርት ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ርካሽ ይሆናል ይህም የአገር ውስጥ አምራቾችን ተወዳዳሪ ያደርጋቸዋል ይላሉ። ""ለምሳሌ 1 የአሜሪካ ዶላር 25 ብር ነው ብለን እናስብ። አንድ አሜሪካዊ 1 ዶላር ይዞ ቢመጣ፤ 25 ብር ዋጋ ያለውን እቃ በ1 ዶላር ይገዛናል። የብር የመግዛት አቅምን በቀነስን ቁጥር ከውጪ የሚመጣ ሰው በርካሽ ዋጋ እንዲገዛን እያደረግን ነው። የዚህ እሳቤ ምንድነው ብዙ ምርት ለገበያ ባቀረብን ቁጥር ብዙ ዶላር እናገኛለን ማለት ነው።"" አቶ ዋሲሁን በሌላ በኩል ደግሞ የዚህን ተገላቢጦሽ እንመልከት ይላሉ። ""የ1 ዶላር ወደ 33 ከፍ ተደረገ ብለን እናስብ። አሁን የ1 ዶላር እቃ ለመግዛት 33 ብር መያዝ ያስፈልገናል። በፊት ግን 25 ብር ነበር የሚያስፈልገው"" ብለዋል። በዚህም ይህ የሚያሳየን ብር ከዶላር ጋር ያለውን ልዩነት በሰፋ ቁጥር ኢትዮጵያዊ እቃ ከውጪ ለመግዛት ይወደድበታል። የአገር ውስጥ ምርትን ግን ውጪ ለመሸጥ ተወዳዳሪ ይሆናል። ይህ ማለት የአገራችን የውጪ ምንዛሪ ክምችት ያድጋል፤ ምርትና ምርታማነት ይጨምርልናል ሲሉ ሊኖረው የሚችለውን ውጤት ይናገራሉ። ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት ሊያስከትል ይችላል በአሁኑ ጊዜ ብር ከሚገባው በላይ ዋጋ እንደተሰጠው የሚናገሩት እዮብ (ዶ/ር)፤ የብር የዋጋ በገበያው መሠረት ሲተመን ከውጪ አገራት ገንዘብ ጋር የሚኖረው ልዩነት እንደሚሰፋ ይገልጻሉ። ለምሳሌ አንድ የአሜሪካ ዶላር ዛሬ ላይ በባንኮች 35 ብር የሚመነዘር ከሆነ፤ በትክክለኛው የገበያ ዋጋ ይተመን ቢባል አንድ ዶላር እስከ 45 ብር ድረስ ሊመነዘር ይችላል። ""በዚህም ወደ በገበ��� ዋጋ በሚወሰን የምንዛሪ ተመን ስንሸጋገር የብር ዋጋ በከፍተኛ ዋጋ ሊያሽቆለቁል ይችላል፤ ይህም የዋጋ ግሽበትን ይከሰታል። ሌሎች እክሎችም ሊከሰቱ ይችላሉ"" ይላሉ እዮብ (ዶ/ር)። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ወደዚህ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓት ሽግግር ሲደረግ ከሚያጋጥሙ አሉታዊ ተጽዕኖዎች መካከል ዋነኛው የዋጋ ግሽበት ሊሆን ይችላል ይላሉ። ""ለምሳሌ ከሰሞኑ መንግሥት የ1 ዶላር ምንዛሬን ከ32 ወደ 35 ብር ከፍ ብሏል። ይህ ከ5 እና 6 ወራት በኋላ እስከ 24 በመቶ ድረስ በእቃዎች ላይ ጭማሪ ያመጣል"" ሲሉ ይናገራሉ። አለማየሁ (ዶ/ር) በሱዳን የተከሰተውን እንደምሳሌ ያነሳሉ። 1 የአሜሪካ ዶላር 29 የሱዳን ፓወንድ ሳለ ሱዳን የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቷን በገበያ ወደ ሚወሰነው አሰራር መቀየሯን ያስታወሳሉ። ""በዚህም ሱዳን ውስጥ የ1 ዶላር ምንዛሪ 48 የሱዳን ፓወንድ ገባ። በሕገ-ወጡ ገበያ ደግሞ 1 ዶላር 58 የሱዳን ፓወንድ ደረሰ። በዚህን ጊዜ ሰዎች በሱዳን ፓወንድ ላይ እምነት አጡ"" በዚህም ሁሉም ሰው ወደ ኤቲኤም በመሄድ ገንዘብ ማውጣት ላይ ተረባረበ፤ ባንኮች ደግሞ የሚከፍሉት ማጣታቸውን አለማየሁ (ዶ/ር) ይናገራሉ። ""ከዚያም ችግሩ ተባብሶ ሄዶ እንደ ዳቦ ባሉ መሠረታዊ ፍጆታዎች ላይ ጭማሪ ታየ። ተቃውሞ ተቀስቅሶ አሁን ለመጣው የመንግሥት ለውጥ ምክንያቶች መካከል አንዱ ሆነ "" ይላሉ። የውጪ ምንዛሬ ስርዓት ከ3 ዓመት በኋላ ይቀየራል መባሉ 'ግራ አጋቢ ነው' ብሔራዊ ባንክ የብር ዋጋ በገበያው የሚተመነው በሦስት ዓመት ውስጥ ነው ማለቱ ይታወሳል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቷን በዚህ ጊዜ ውስጥ መቀየር ይቻላታል? እዮብ (ዶ/ር) በበለጸጉ አገራት ዘንድ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓታቸውን በሦስት ዓመት ውስጥ የመቀየር ልምድ እንዳለ አውስተው፤ በብሔራዊ ባንክ በኩል ግን ቅድሞ ሊታሰብባቸው የሚገቡ ጉዳዮች እያሉ ""ከሦስት ዓመት በኋላ የተባለው ከምን ተነስቶ እንደሆነ 'ግራ አጋቢ' ነው"" ይላሉ። በኮቪድ-19 ምክንያት የዓለምና የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እድገት እየተጓተት መሆኑን ያስታወሱት እዮብ (ዶ/ር)፤ በወረርሽኙ ሳቢያ የተወሰነው የአገሪቱ ኢኮኖሚ ክፍል ክፉኛ መጎዳቱን ይናገራሉ። ""ከእነዚህ ጫናዎች ሳንላቀቅና የኮቪድ-19ን ሙሉ ጫና ሳንረዳ ከአሁኑ ሦስት ዓመት ብሎ መወሰን ለእኔ ግራ አጋቢ ነው። በበኩሌ የምቀበለው ነገር አይደለም"" ሲሉ ይሞግታሉ። እዮብ (ዶ/ር) እንደሚሉት ወደዚህ አይነት የውጪ ምንዛሬ አስተዳደር ለማምረት የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እንደሚያስፈልጉ በማውሳት፤ ኢትዮጵያ ወደዚህ ከመሸጋገሯ በፊት ""የማክሮ ኢኮኖሚውን ማረጋጋት ያስፈልጋል፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር ያስፈልጋል፣ በቂ የውጪ ምንዛሬ ክምችት መኖር ይኖርበታል እንዲሁም የንግድ ሚዛን ጉድለት መጥበብ ይኖርበታል"" ሲሉ ይመክራሉ። እንደ እዮብ (ዶ/ር) አመለካከት በገበያ ወደሚወሰን የምንዛሪ ሥርዓት ከመሸጋገራችን በፊት የዋጋ ግሽበት መጠንን ወደ አንድ አሃዝ ማምጣት ""እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።"" ""በገበያው ላይ በቂ የሆነ የውጪ ምንዛሪ መኖር ይኖርበታል። ይህ እንዲሆን ደግሞ በቂ የውጪ ምንዛሪ ክምችት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያም የውጪ ምንዛሪ የምታገኘባቸውን መንገዶች መጨምር ይኖርባታል። ከውጪ የሚላክ ገንዘብ እንዲጨምር ማበረታቻ ማድረግ፣ ቱሪዝምና ኤክስፖርት ማደግ ይኖርባቸዋል"" ይላሉ። ይህን የውጪ ምንዛሬ ሥርዓት ለመተግበር የተማረ ሰው ኃይልና ተቋማዊ ለውጥ የግድ እንደሚልም እዮብ ተስፋዬ (ዶ/ር) ያሳስባሉ። አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ ግፊት ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ገንዘቧ በገበያ ዋጋ እንዲተመን ግፊት እንደሚያሳድሩ ይነገራ���። እዮብ (ዶ/ር) ለዚህ አንዱን ምክንያት ሲያስረዱ፤ አይኤምኤፍ ከተመሰረተባቸው ምክንያቶች አንዱ የዓለም አገራት የመገበያያ ገንዘብ ዋጋ እንዲረጋጋ ለማድረግ በመሆኑ ነው። ""በእነሱ ፍልስፍና የምንዛሪ ተመን የተረጋጋ የሚሆነው ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሲሆን ነው። ምክንያቱም ምንዛሪ እንደማንኛውም ሸቀጥ ዋጋ አለው። እንደ ሌሎች ሸቀጦች ሁሉ ይህ ዋጋ በገበያ ኃይል መወሰን አለበት ብለው ያምናሉ"" ሲሉ ያስረዳሉ። አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ከምትልከው ምርት በላይ ከውጪ የምታስገበው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ በመሆኑ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ይህንን ልዩነት ለማጥበብ የብር ዋጋ በገበያ ቢወሰን በተሻለ መልኩ የውጪ ምንዛሪ እንዲገኝ ይረዳል የሚል እሳቤ ስላለ አገሪቱ ወደዚህ ሥርዓት እንድትገባ ጫና እንደሚደረግ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ አለማየሁ (ዶ/ር) እንደሚሉት በኢትዮጵያዊያን ላኪዎች እንደችግር ከሚቀርቡት መካከል የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት እጥረት ትልቁ ራስ ምታት አይደለም ባይ ናቸው። ""እኔ ከመቶ በላይ ላኪዎችን አነጋግሬ የደረስኩበት ነገር፤ ለእኛ አገር ላኪዎች መሠረታዊ ችግር የሆነው የጥሬ እቃ አቅርቦት እጥረት፣ የመሬትና የፋይናንስን አቅርቦት ችግር፣ ሙስናና ጉምሩክ ላይ ያለው ውጣ ውረድ ነው እንጂ የዶላር እጥረት የላኪዎች ትልቁ ችግር አይደለም"" ይላሉ። ""ዋናው ጉዳይ መሆን ያለበት በትይዩ ገበያ [ጥቁር ገበያ] እና በባንክ መካከል ያለው ልዩነት እንዲሁም ወደ አገር በሚገባውና ወደ ውጪ በሚላከው መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ ነው።"" በእነዚህ መካከል ልዩነቱ የሰፋበት ዋነኛ ምክንያት ወደ ውጪ የሚላከው ምርት ስላላደገ እንደሆነ የሚናገሩት አለማየሁ (ዶ/ር) ""በእኔ ስሌት ወደ አገር በሚገባውና ከውቺ በሚመጣው መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ወደ ውጪ የምንልካቸው ምርቶች በአማካይ በዓመት 20 በመቶ ለስምንት ተከታታይ ዓመት ማደግ ይኖርበታል"" ይላሉ። ስለዚህም የመንግሥት ትኩረት መሆን ያለበት ""ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች የሚጨምሩበትን መንገድና ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት አምራቾችን ማበረታት ላይ ነው"" ይላሉ አለማየሁ (ዶ/ር)። አዋጭ ነው? የባለሙያዎቹ ጠቅላላ ግምገማ ኢትዮጵያ ከሦስት ዓመታት በኋላ የብር የዋጋ ተመን በገበያ እንዲወሰን ብታደርግ ያዋጣታል? የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ ማጠቃለያ ሃሳብ የሚከተለው ነው። እዮብ (ዶ/ር) - የምንዛሪ ሥርዓት መቀየርና በገበያ ዋጋ መወሰን እንዳለበት አምናለሁ። አካሄዱ ግን ቀስ በቀስ በሂደት መሆን አለበት። ብሔራዊ ባንክ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ መከናወን ያለባቸው ነገሮችን መሰራት ይኖርበታል፤ ለዚህ ደግሞ የዘርፉ ባለሙያና ተቋም ያስፈልጋል። አለማየሁ (ዶ/ር) - ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። የውጪ ምንዛሪ ሥርዓታችንን ከመቀየራችን በፊት ቀድሞ መከናወን ያለባቸው የቤት ሥራዎች አሉ። አቶ ዋሲሁን - በጠቅላላው አዋጭ ነው ብዬ አስባለሁ። ሥርዓቱ በራሱ ጊዜ ወደ ዚያው እየወሰደን ይገኛል። በመጪው ሦስት ዓመታት ውስጥ የሚጠበቅብንን የቤት ሥራዎች ማከናወን የምንችል ከሆነ የሚየቀሩ ነገሮች ቢኖሩም ከሦስት ዓመታት በኋላ የብር ዋጋ በገበያ እንዲተመን ማድረጉ ትክክለኛ አካሄድ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-53634447 +politics የዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት በኤፍቢአይ የተበረበረበት ምክንያት ይፋ ሊደረግ ነው "የኤፍቢአይ ወኪሎች የቀድሞውን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ቤት የበረበሩበት የፍተሻ ማዘዣ ይፋ እንዲደረግ የአገሪቱ ፍትህ ቢሮ የፍሎሪዳውን ፍርድ ቤት ጠየቀ። ያልተለመደ ነው የተባለለት ጥያቄ ፈቃድ ካገኘ የትራምፕ መኖሪያ ቤት እንዲፈተሽ የተደረገበት ምክንያት ለሕዝብ ይፋ ይሆናሉ ተብሏል። ዶናልድ ትራምፕ በተመሳሳይ የብርበራ ፍቃዱ ሰነድ ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን ፍላጎታቸው እንደሆነ ገልጸዋል። የፍትህ ቢሮ ፍተሻው ለምን እንደተካሄደ እስካሁን ይፋ አላደረገም። የአሁኑ ጥያቄ ግን ለዚህ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ሰኞ ዕለት በኤፍቢአይወኪሎች የተደረገው ብርበራ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጥብቅ እና ሚስጢራዊ ሰነዶች አያያዝ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ተብሎ ነበር። ስማቸው ያልተገለጸ አንድ ምንጭን ጠቅሶ ዋሽንግተን ፖስት እንዳስነበበው የኤፍቢአይ ወኪሎች ከኒውክለር መሣሪያዎች ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ጭምር በትራምፕ መኖሪያ ቤት ስፈልጉ ነበር። ወኪሎቹ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕን ቁም ሳጥን እና የግል ቁሳቁሶቻቸውን መበርበራቸውን ትራምፕ ገልጸዋል። ቀደም ሲል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ሜሪክ ጋርላንድ በትራምፕ መኖሪያ ቤት ላይ ፍተሻው እንዲካሄድ መፍቀዳቸውን ገልጸዋል። ከፍርድ ቤት ፍተሻ ማዘዣ ጋር የተገናኙ ሰነዶች ለሕዝብ ጥቅም ሲባሉ ይፋ እንዲሆኑ እየጠየቁ መሆኑን ጋርላንድ ተናግረዋል። የፍትህ ቢሮ ሁሌም መደበኛ ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ እንደሚያደርገው ዝምታ የመምረጥ ልምዱን እየተከተለ ነው። የፍትህ ቢሮ ጠበቆች ሐሙስ ዕለት በፌዴራል ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ""በዚህ ሁኔታ የተከሰተውን ነገር ለመረዳት የሕዝቡ ግልጽ እና ከፍተኛ ፍላጎት ስላለው ይፋ መሆኑ ይጠቅማል” ብለዋል። የቀድሞ ፕሬዝዳንት መኖሪያ ቤት ከወንጀል ምርመራ ጋር በተያያዘ ሲፈተሽ የሰኞው በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያው ነው። ትራምፕ እና ሌሎች ሪፐብሊካኖች እርምጃውን ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ሲሉ አውግዘዋል። ሐሙስ ዕለት በጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ጋርላንድ የኤፍቢአይ ወኪሎችን እና የፍትህ ክፍል ኃላፊዎችን ተከላክለዋል። ጠቅላይ ዓቃቤ ህጉ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ታማኝነታቸው ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሲጠቃ በዝምታ አላይም” ብለዋል። የፍተሻ ማዘዣውን ለማስፈጸም መወሰኑም ቀላል እንዳልነበር ተናግረዋል። የትራምፕ ጠበቃ የሆኑት ሊንሴይ ሃሊጋን ፍርድ ቤት ውሳኔ ከማስተላለፉ በፊት የህግ ቡድናቸው ማዘዣውን በመልቀቅ ጉዳይ ላይ እየተወያ ነው። የብርበራውን ፎቶ እና ቪዲዮ ይፋ ለማድረግም እያሰቡ ነው። የኤፍቢአይ ወኪሎች የማር-አ-ላጎ የሲሲቲቪ ካሜራዎች እንዲጠፉ ጠይቀው ነበር። የትራምፕ ሠራተኞች ግን ይህንን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆኑም ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c80qyv0xrwqo +business "ኮሮናቫይረስ፡' 'ጨለምተኛው' ፕሮፌሰር ""ዓለም ለ10 ዓመታት ትማቅቃለች"" አሉ" "ኖሪኤል ሮቢኒ ስመ ጥር የምጣኔ ሃብት ፕሮፌሰር ናቸው። መጪውን ዘመን በመተንበይ ይታወቃሉ። ሆኖም ሰውየው በጎ በጎው ስለማይታያቸው 'ጨለምተኛው ኢኮኖሚስት' የሚል ቅጽል ተበጅቶላቸዋል። ትንቢታቸው ጠብ አይልም የሚባሉት ፕሮፌሰር ሮቢኒ ከዚህ በፊት ባንኮችና የቁጠባ ቤት ገዢዎች በፈጠሩት ሀሳዊ የቢዝነስ ሽርክና የዓለም ኢኮኖሚ ይናጋል ብለው ከማንም በፊት ተንብየው ነበር፤ እንዳሉትም ሰመረላቸው። ይህ የሆነው በፈረንጆች 2008 የዛሬ 12 ዓመት ነበር። ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ቀድመው ያዩት እኚህ ሰው ታዲያ ከሰሞኑ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኮቪድ-19 የፈጠረው ምስቅልቅል ቢያንስ ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ዓለምን ያናጋታል፤ የዓለም ምጣኔ ሃብትም ለ10 ዓመታት ይማቅቃል ብለዋል። ሰውየው እንደሚሉት ይህ ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር ውሎ በዓመት ውስጥ ምጣኔ ሃብቱ ማንሰራራት ቢጀምርም ነቀርሳው ግን ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ይቆያል። እንዲያውም አንዳንድ የሥራ ዘርፎ��� ጨርሶውኑ ላያንሰራሩ እንደሚችሉም ተንብየዋል። ወረርሽኙን ከ2008ቱ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ጋር ሲወዳደርም ሆነ በ1930ዎቹ ከተከሰተው የዓለም ክፉው የምጣኔ ሃብት ድቀት ጋር ሲተያይ የአሁኑ የከፋ እንደሆነ ሮቢኒ ያብራራሉ። ያን ጊዜ ምርት በዓለም ላይ እንዲቀንስ ወይም የቀውሱን ምልክቶች በተግባር ለማየት ከችግሩ በኋላ ዓመታትን ወስዶ ነበር። ኮሮናቫይረስ ግን ከእነዚህ ሁለቱ ቀውሶችም በላይ ነው። በባህሪው ይለያል። ያስከተለውን የምርት ማሽቆልቆልን በግላጭ ለማየት ዓመታት ወይም ወራት አልወሰደበትም። በሳምንታት ውስጥ በመላው ዓለም ምርት ተንኮታክቷል። ይህ የሚነግረን መጪው ዘመን ፍጹም ጭጋጋማ መሆኑን ነው ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ""በዚያ ዘመን 3 ዓመት የወሰደው የምርት መንኮታኮት በዚህ ዘመን 3 ሳምንት ነው የወሰደበት።"" ፕሮፌሰሩ ከምጣኔ ሃብት ቀውስ በኋላ የማገገሙን ሂደት ሲያስረዱ በሁለት የእንግሊዝኛ ሆሄያት ይመረኮዛሉ። ዩ እና ኤል [""U"" እና ""L""]። ዩ በእኛ ሀሌታው 'ሀ' ብለን ልንተረጉመው እንችላለን። የሀሌታው ሀ የማገገም ሂደት የሚያሳየው አንድ ምጣኔ ሀብት በአንዳች መጥፎ አጋጣሚ ሲንኮታኮት ቀስ በቀስ መሬት ይነካል። ከዚያ ወደነበረበት ለመመለስ የሀሌታው ሀ ቅርጽን ይዞ ሲንፏቀቅ ቆይቶ፣ በብዙ አዝጋሚ ሂደት ምጣኔ ሃብቱ ይመለሳል። ይህ ሂደት ዓመታትን የሚወስድ ነው። ከዚህ የተሻለው ደግሞ በቪ ""V"" ይወከላል። ቶሎ ወድቆ ቶሎ የሚያንሳራራ ምጣኔ ሃብት። አሁን የገጠመን ይላሉ ፕሮፌሰሩ፤ ኮቪድ-19 ያስከተለው የምጣኔ ሃብት ድቀት የሀሌታው ሀ ቅርጽን ሳይሆን የእንግሊዝኛው ሆሄ ""L""ን ወይም በእኛ የ""ረ"" ቅርጽ የያዘ ነው። ይህም ማለት በአንድ ጊዜ ዘጭ ያለው ምጣኔ ሃብት ጨርሱኑ አያንሰራራም ወይም ለማንሰራራት አሥር ዓመት ይወስድበታል። 'ጨለምተኛው' ፕሮፌሰር እንዲያውም የኮቪድ-19 ተጽእኖ የመጪውን ዘመን ምጣኔ ሃብት በአይ ሆሄ ""I"" የሚወከል እንዳይሆን ይሰጋሉ። እንደወደቀ የሚቀር ኢኮኖሚ። በፕሮፌሰሩ ትንቢት መሠረት በዚህ ወረርሽኝ ሥራ ያጡ ዜጎች ወደ ሥራቸው የመመለስ ዕድላቸው አነስተኛ ነው። ከተመለሱም በጊዝያዊ ሠራተኝነት እንጂ ቋሚ ሥራ የሚያገኙት በጣም ጥቂቶች ናቸው። ከደመወዝ ውጭ ያሉ ጥቅማጥቅሞች ከዚህ በኋላ የሚታሰቡ አይሆኑም። በዝቅተኛና መካከለኛ የቅጥር ሥራ ላይ ያሉ ሰዎችም ቢሆን የሥራ ዋስትና አይኖራቸውም። ይህ በብዙ የምርት ዘርፎች ላይ ይታያል ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ከዚህ በኋላ ምርት አይጨምርም፤ የአገራትም ሆነ የኩባንያዎች እድገት ባለበት እርገጥ ይሆናል፣ ሰዎች ገቢያቸው ይደቃል፤ ገበያ ይተናል፣ ፍላጎት ይከስማል። ""ሰዎች ስለ ቢዝነስ መልሶ መከፈት ያወራሉ፤ ቢከፍቱስ ማን ይገዛቸዋል? ጀርመን ሱቆችን ከፈተች፤ ገዢ ግን የለም። ቻይና ትልልቅ የንግድ መደብሮቿ ክፍት ናቸው፤ ማን ይገዛቸዋል? ከፍተው ነው የሚዘጉት፤ በረራዎች ተስተጓጉለዋል…ይህ ሁኔታ ለዓመታት የሚቀጥል ነው የሚሆነው"" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ፕሮፌሰር ሮቤኒን ከበለጸጉ አገራት ይልቅ ታዳጊ የእሲያ ምጣኔ ሃብት በሁለት እግሩ ለመቆም የተሻለ እድል እንዳለውም ተናግረዋል። ፕሮፌሰር ኖሪኤል ሮቢኒ ሌላው ትንቢታቸው ዓለም ልክ እንደ ቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን በሁለት ግዙፍ እድሮች እንደሚሰባሰብ ነው። የእድሮቹ አባቶች የሚሆኑትም ቻይናና አሜሪካ ይሆናሉ ይላሉ። ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸው እየሻከረ እንደሚሄድና የራሳቸውን የምጣኔ ሃብት አጋሮች ማሰባሰብ እንደሚጀምሩ አስምረውበታል። አብዛኛዎቹ የእሲያና ታዳጊ አገራት ከእነዚህ ሁለት አገሮች ወደ አንዱ እድር እንዲገቡ የሚገደዱበት ሁኔታ እንደሚፈጠርም ፕሮፌሰሩ ተንብየዋል። ""ሁለቱ የእድር አ��ቶች ወይ ከእኔ ጋር ነህ፣ ከእኔ ካልሆንክ ደግሞ ከጠላቴ ጋር ነህ ማለት ይጀምራሉ። ይህ ማለት ወይ የእኔን 5ጂ ትጠቀማለህ፣ አልያም የጠላቴን፤ ወይ የእኔን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትጠቀማለህ ወይም የጠላቴን…እየተባለ ሁለት ዓለም ይፈጠራል። ታዳጊ አገራትም በሁለት ቢላ መብላት አይፈቀድላቸውም"" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ከኒውዮርክ ቤታቸው ሆነው ቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት ፕሮፌሰር ሮቢኒ ጨለምተኛው ፕሮፌሰር ስለመባላቸው አስተያየት ሲጠየቁ ""ከዚያ ይልቅ እቅጩን ነጋሪው ፕሮፌሰር የሚለው ስም ይመጥነኛል"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-52796482 +sports """እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል?' ተብሎ ነበር"" ኢንስትራክተር መሠረት ማኒ" "ውልደቷ ድሬዳዋ ነው፤ ልዩ ስሙ አንደኛ መንገድ ከሚባል ሥፍራ፤ ደቻቱ ግድም ማለት ነው። ይህ ሠፈር ደግሞ ለአሸዋው ቅርብ ነው። ኳስ እያንቀረቀቡ ለማደግ የሰጠ ነው። አንደኛ ደረጃ ትምህርቷን በለገሃሬ፤ ሁለተኛውን ደግሞ በድሬዳዋ አጠቃላይ ትምህርት ቤት ተስተምራለች። ፊፋ በ1983 የዓለም የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫን በይፋ ከማካሄዱ በፊት ሴቶቹ በይፋ እግር ኳስ እንዲጫወቱ አይፈቀድም [አይፈለግምም] ነበር። ነገር ግን ይህ ኳስ ከመጫወት አላገዳትም [በፕሮፌሽናል ደረጃ ባይሆንም]። ማንም ከተጫዋችነት ወደ አሠልጣኝነት ወደ መምጣት የከለከላት አልነበረም፤ በኢትዮጵያ [በአፍሪካም] ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የወንዶች እግር ኳስ ቡድን አሠልጣኝ ከመሆን ሊመልሳት የቻለም አልተገኘም. . . እርሷም ማንም ወደኋላ እንዲጎትታት አልፈቀደችም. . . መሠረት ማኒ። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ «አሠልጣኝነትን የጀመርኩት ገና በልጅነቴ ነው ። ልጅ እያለሁ ራሱ 'የሊደርሺፕ' ተሰጥዖ ነበረኝ። ከዚያ ጓደኞቼን ሰብስቤ 'ድል በትግል' የሚባል ቡድን መሠረትኩ። ከዚያ የሕንፃ ቡድን፤ ቀጥሎ የመድህን ድርጅት የተወሰነ ድጋፍ እያደረገልኝ ማሠልጠን ጀምርኩ። ከዚያ የ'ሴቭ ዘ ቺልድረን' የሴቶች እና ወንዶች ቡድንን መሥርቼ ማሠልጠን ያዝኩ።» መሠረት የምታሠለጥነው የእግር ኳስ ቡድኖችን ብቻ አልነበረም። የቴኒስ እና መረብ ኳስ ቡድኖችንም ታሠለጥን ነበር። 'ማቴሪያል' ስለነበር ፍላጎቱ ያላቸው የድሬዳዋ ልጆች እንዲሠለጥኑ አደርግ ነበር። 1970 ዎቹ ላይ እነ ማክዳ፣ ታጠቅ፣ አየር ኃይል እና መሰል የሴት እግር ኳስ ቡድኖች፤ የሴቶች እግር ኳስ ሲቋረጥ በዚያ ከሰሙ። ከዚያ 1986 ላይ የመጀመሪያውን የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በማቋቋም በታሪክ መዝገብ ስሟን አሰፈረች። 2004 ላይ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ሲጀመር መሠረት የከተማዋን ሴቶች ቡድን ይዛ ተቀላቀለች። 2007 ላይ ድሬዳዋ ከነማ የፕሪሚዬር ሊጉ ታናሽ በሆነው የሊግ ውድድር ላይ ተሳታፊ ነበር። ይሄኔ ነው መሠረት ማኒ የወንዶቹን ቡድን ተረክባ ለፕሪሚዬር ሊግ ለማሰለፍ ቃል በመግባት ሥራ የጀመረችው። «እርግጥ በጣም 'ቻሌንጂንግ' ነበር። ቢሆንም ለእኔ ብዙ ያልከበደኝ፤ ከልጅነቴም ጀምሮ ወንዶችን እያሠለጠንኩ ማደጌ ነው። ትላልቆቹም ሳሰለጥናቸው የሚሠጡኝ አክብሮትና ፍቅር እንዲሁም ኃላፊነታቸውን የሚወጡበት መንገድ አቅም ሆኖኝ ነበር። በፆታ መለካቴ ግን አልቀረም። 'እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል? ቀልድ ነው እንዴ የያዙት?' ያሉ አልጠፉም ነበር። አንዳንዶቹም እንደውም ይሄ ለፖለቲካ 'ኮንሳምፕሽን' ነው ብለው ከንቲባው [የድሬዳዋ] ድረስ ይሄዱ ነበር። ነገር ግን ለኔ የበለጠ አቅም ነበር የሆነኝ። ምክንያቱም ይህንን መቀየር አለብኝ አልኩኝ፤ በምን? በውጤት።» ከውጭ ብዙ ፈተና የገጠማት መሠረት ከውስጥም መንገዱ አልጋ 'ባልጋ አልሆነላትም። በዚያ ላይ የመጀ��ሪያው ዙር ለመሠረት ቀላል የሚባል አልነበረም፤ ሦስት ነጥብ ማግኘት። «ተጨዋቾቼን ማሳመን አንዱ ፈተና ነበር። በሴት ሠልጥነው አያውቁም፤ ትልልቅ ተጨዋቾች ናቸው። 'እንዴት ነው አሁን እሷ እኛን የምትመራን?' የሚል ጥያቄ ነበራቸው። አንዳንዶቹ የመሥራት ፍላጎታቸው ውርድ ያለም ነበር። ነገር ግን ልጆቼን በሥራ ማሳመን ቻልኩኝ። በተለይ ሁለተኛው ዙር ላይ በውጤት በጣም አሪፍ ነበርን። እንደውም ከ12 ጨዋታ 11 አሸንፈን በአንዱ ብቻ ነው አቻ የተለያየነው።» ጉዞ ወደፕሪሚዬር ሊግ ድሬዳዋ ከነማ በአሠልጣኝ መሠረት ማኒ እየተመራ ፕሪሚዬር ሊግ ገባ። ሁሉም 'ሴት የወንዶች አሠልጣኝ?' ሲል መጠየቅ ጀመረ። አድኖቆት ጎረፈላት። ተጫዋቾች፣ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይ ደግሞ ድሬዎች ቆመው አጨበጨቡላት። ፕሪሚዬር ሊግ ከብሔራዊ ሊግ ሲነፃፀር ከበድ [በጥራት] ያለ ቢሆንም መሠረትን የሚያቆም ግን አልተገኘም። ክለቧ ትልቁ ዓላማው የነበረው ከፕሪሚዬር ሊጉ ተመልሶ አለመውረድ ነበር። መሠረት ግን አለመውረድ አላስጨነቃትም፤ ውጤቱ የበለጠ እንዲያምር ጣረች። «ስንጀምረው አራት ጨዋታ ማሸነፍ አልቻልንም ነበር። ከአምስተኛው ጨዋታ በኋላ ግን ሁሉንም እያስተካከልን መጣን። እንደውም በአንደኛው ዙር አምስተኛ ሆነን ጨረስን፤ ይሄ ደግሞ ትልቅ ድል ነው። በተለይ ከብሔራዊ ሊግ ለመጣ ቡድን ሊያውም በሴት አሠልጣኝ ለሚሠለጥን።» ቢሆንም ሁለተኛው ዙር የድሬዳዋ ውጤት ዕለት ተ'ለት ያሽቆለቁል ያዘ። በመጀመሪያዎቹ አምስት ጨዋታዎች ጥሩ ውጤታ ማምጣት የቻለው ድሬዳዋ ከነማ ሦስት ነጥብ ብርቁ ሆነ። ምን ተፈጠረ? «እኔ እስከዛሬም ድረስ ሳስበው ግራ ይገባኛል። ምንድን ነው ነገሩ ብዬ ልጆቼን ጠየቅኩ፤ ግን አጥጋቢ ምላሽ አላገኘሁም። አንድ የማላውቀው እና ውጤታችንን እንዲያሽቆለቁል ያደረገ ነገር እንዳለ አሁንም ድረስ ይሰማኛል። አሁን ራሱ አንዳድንድ ተጨዋቾችን ሳገኝ እጠይቃለሁ፤ ግን ብዙም አይነግሩኝም። የሆነ ነገር እንዳለ ግን ይሰማኛል፤ ከውጭም ከውስጥም። ወደፊትም መጠየቄን አላቆምም።» • ሴት እግር ኳሰኞች ስንት ይከፈላቸው ይሆን? ከዚያ «በዚህ መንገድ መቀጠል አልቻልኩም ትላለች» መሠረት። «ገንዘብ ፈልጌ አይደለም የመጣሁት እኔ። እኔ መሥራት ነው የምፈልገው። በዚህ መንገድ መቀጠል ደግሞ አልፈልግም። ጫናዎች በዝተዋል። እግር ኳስ ደግሞ ነፃነት ይፈልጋል። እኔ በቃኝ 'ቴንኪው' ብዬ፤ ልጆቼን እና 'ስታፉን' ተሰናብቼ ቡደኑን ለቅቄ ወጣሁ።» ይህ የሆነው እንግዲህ 2008 ላይ ነው። መሠረት 2002 ላይ ሉሲዎችን ተረክባ ታሪክ ፅፋለች፤ ታሪኩ ምንድን ነው? ብሎ ለሚጠይቅ 'ቡድኑ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴት አሠልጣኝ የተመራበት ወቅት በመሆኑ [የተሰጣት ኮንትራት የ3 ወራት ብቻ ቢሆንም]' መልሷ ነው። መሠረት ከዚያ በኋላ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በቀረበላት ግብዣ ወደ አሜሪካ አቀናች። ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ ከአሜሪካ ኤምባሲ በቀረባለት ግብዣ አሜሪካ ደርሳ ተመልሳለች። ወደ አሜሪካ ከማቅናቷ በፊት ሉሲዎችን እንደገና ተረክባ ነበር [2009]። ስትመለስ ግን የአሠልጣኝነት ቦታው በሌላ ሰው ተይዞ ጠበቃት። እንደገና ሉሲዎችን ተረክባ ወደ ኡጋንዳ አቀናች፤ በሴካፋ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ። ኳስ ይዞ በማጥቃት የአጨዋወት ስልት የምትታወቀው መሠረት ውድድሩን ሦስተኛ ሆና በማጠናቀቅ የነሃስ ሜዳሊያ ይዛ ተመለሰች [የራሳችን ድክመት ነው እንጂ ዋንጫ ማምጣት ይገባን ነበር ትላለች]። ቢሆንም ኮንትራቷ ከመጠናቀቁ በፊት ሉሲዎች ሌላ አሠልጣኝ ተሾመላቸው። መሠረት አዲሱን መፅሐፏን ለማስመረቅ ጉድ ጉድ በማለት ላይ ትገኛለች። 'የስኬት ተምሳሌት' የተሰኘ ርዕስ ሰጥታዋለ��። ያለፈችበትን ውጣ ውረድ የሚያትት 198 ገፆች ያሉት መፅሐፍ ነው። «ይሄኔ ነው ጀምሬው የነበረውን መፅሐፍ ልጨርስ ብዬ ትኩረቴን ወደዚያ ያደርግኩት» ብላናለች። መሠረት ድሬዳዋ ከነማ እያለሽ ምን ያህል ነበር የሚከፈልሽ? እንደው ፈቃደኛ ከሆንሽ ብትነግሪን? «ኧረ በደንብ ነው ምነግርህ [ፈገግታ]. . . እንግዲህ እኔ ፕሪሚዬር ሊግ እያለሁ 14 ክለቦች ነበሩ። በወቅቱ ዝቅተኛው የአሠልጣኝ ክፍያ የኔ ነበር። ተቆራርጦ እጄ ላይ 'ሚደርሰኝ 13ሺህ 500 ብር ነበር። ያኔ የወረዱት ዳሸንና የሆሳዕና ቡድን አሠልጣኞች ከኔ የተሻለ ክፍያ ያገኙ እንደነበር አውቃለሁ። ምክንያቱም እኔ ብዙ ጊዜ በፆታዬ ነው 'ምለካው። እንጂ ባለኝ አቅም አልነበረም። ይሄን ሳስብ ያመኛል ግን በቃ ፍቅር ነው፤ ኳሱን እወደዋለሁ፤ እሠራዋለሁ። አሠልጣኞች እና ተጨዋቾች በድህረ-ጨዋታ መጨባበጥና ማልያ መቀያየር የተለመደ ነው። እርግጥ አሁን አሁን በሰላም ጨዋታን መጨረስ በራሱ ትልቅ ድል እየሆነ ቢመጣም። እንደው በመሠረት እንዴት እንሸነፋለን ያሉ አሠልጣኞች እና ተጫዋቾች እጅ ነስተዋት ያውቁ ይሆን? «የነፈጉኝን እንኳ ብዙም አላስታውስም፤ ግን እኔ አንድ ጊዜ በደስታ ውስጥ ሆኜ ሳልጨባበጥ በመቅረቴ ተከስሻለሁ። እዚሁ ድሬዳዋ ላይ ነው። ከሙገር ሲሚንቶ ጋር እየተጫወትን ነበር። ደርቢ በመሆናችን ጨዋታው ደመቅ ያለ ነበር። 0-0 ነበርንና ባለቀ ሰዓት አገባንና አሸነፍን። በቃ በጣም ደስተኛ ስለነበርኩ የሙገር አሠልጣኝን ሳልጨብጠው ቀረሁ። ከዚያ እስከ ክስ ደረጃ ደርሶ ነበር።» ሰዎች አሠልጣኝ መሠረትን ሲያስቡ ቀድሞ ትዝ የሚለቸው ከድሬዳዋ ከነማ ጋር የተጎናፀፈችው ስኬት ነው። እርሷም ከማትረሳቸው ድሎች መካከል አንዱ እርሱ ነው። ግን ከዚያም በላይ የማልረሳው ትላለች መሠረት. . . «የማልረሳቸው ሁለት ቀናት አሉ። አንደኛው ከአዲስ አበባ ከነማ ጋር አራት ውስጥ ለመግባት የተጫወትነው ነው። 1 ለ 0 እየመራን ነበር፤ ከዚያ አቻ ሆንን። አንድ ጨምረን መምራት ያዝን፤ ግን መልሶ ተቆጠረብን። በስመዓብ አሁን በቃ 2 ለ 2 ሆነን ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ልንሄድ ነው። ከምክትሌ ጋር ተነጋገርኩና 'ቤንቹ' በረኛ 'ፔናሊቲ' ጎበዝ ስለሆነ ብለን አስገባነው። በረኛችን ሦስት ጎል አዳነልንና አሸነፍን።» «ሁለተኛው ቅዱስ ጊዮርጊስን የረታንበትን ነው። እንግዲህ ጊዮርጊስ በጣም ትልቅ ቡድን ነው። እኔ ደግሞ ፕሪሚዬር ሊጉ አዲሴ ነው። እና በሜዳዬ ሊያውም በጨዋታ ብልጫ ማሸነፌ ፍፁም አልረሳውም። በጣም ልዩ ነበር። መሠረት አሁን ላይ የአዲስ አበባ ሴቶች እግር ኳስ ቡድንን በማሠልጠን ላይ ትገኛለች። አንደኛ ዲቪዚዮን ላይ እየተጫወተ የሚገኘው አ.አ. ስድስተኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዘመኑን አጠናቋል። መሠረት ስለወደፊቱ ዕቅዷ እጅጉን እያሰበችበት እንደሆነ አልደበቀችንም። «ብዙ ዕቅዶች አሉኝ። የሕፃናት አካዳሚም አለኝ [120 ሕፃናት ያሉት]። እሱን ከፍ ማድረግም ሕልሜ ነው። የአሠልጣኝነት ጥያቄዎችም ይመጣሉ። እውነት ለመናገር ብዙ 'ፍራስትሬት' የሚያደርጉ አጋጣሚዎች ገጥመውኛል። ሙያውን ለመተው ሁላ አስቤ አውቃለሁ፤ ግን ደግሞ ብዙ ሰዎች ይህን ውሳኔዬን ሲቃወሙ አያለሁ። በተለይ ያሠለጠንኳቸው ልጆች 'ኖ መቀጠል አለብሽ' የሚል አስተያየት ይሰጡኛል። ስለዚህ ቁጭ ብዬ ማሰብ አለብኝ ብያለሁ።» በኢትዮጵያም ሆነ በአህጉረ አፍሪካ ከመሠረት ሌላ ሴት የወንዶች እግር ኳስ ክለብ አሠልጣኝ እንዳለች አልሰማንም፤ አላየንም። ይህንን ክብር መጎናፀፍ ምን ዓይነት ስሜት ይሰጥ ይሆን? «በጣም ነው ደስ የሚለኝ። ሌላ ሴት አለመኖሯ ሳይሆን፤ ስኬታማ መሆን መቻሌ ደስ ያሰኘኛል። ሴት ልጅ ይህንን ማድረግ እንደምትችል ደግሞ ���ሳየት መቻሌ እጅግ ያኮራኛል። እንጂ ብቸኛ ስለሆንኩኝ አይደለም፤ በቃ ይቻላል የሚለውን መንፈስ ማንገስ መቻሌ ነው። ሁሌም የምለው ሴቶች በፆታቸው ሳይሆን በአቅማቸው ቢለኩ ነው።» «አንዲት ሴት አናጢም መሆን ትፈልግ፣ ኢንጅነር ወይም ኤሌክትሪሺያን ለዚያ ሙያ የሚሆን ዕውቀት ያስፈልጋታል። ይህ ደግሞ እንዲሁ አይገኝም፤ ልፋት ይጠይቃል፤ ጥረት ያስፈልጋል፤ ድካም ያስፈልጋል፤ በቀላሉ የሚገኝ ነገር የለም። እኔ ሴት ስለሆንኩ እንደው እንደ ገፀ-በረከት እንዲሰጠኝ አልፈልግም። በራሴ ልክ፤ ባለኝ አቅም እንጂ። የማይቻል ምንም ነገር የለም። ሕልም ይኑረን።» እኛም ምክር ያፅና ብለናል፤ ለመሠረትም መልካም ዕድል! • ""የናንዬ ሕይወት"" የአይዳ ዕደማርያም ምስል ከሳች መፀሐፍ" https://www.bbc.com/amharic/news-48715607 +health ሕንዳውያን የስኳር ምርት ስለተትረፈረፈ አብዝተው እንዲጠቀሙ ተነግሯቸዋል ሕንድ በጣም የበዛ ስኳር በማምረቷ ሕዝቧ ስኳር አብዝቶ እንዲጠቀም እየመከረች ነው። የሕንድ ስኳር ምርት ማሕበር ስኳር ጤና ላይ ጉዳት ያመጣል የሚባለውን ችላ ብለው ሰዎች አብዝተው እንዲጠቀሙ መክሯል። ሕንዳውያን በአማካይ በዓመት 19 ኪሎ ግራም ስኳር ይጠቀማሉ። ይህ ደግሞ ከተቀረው ዓለም ሲነፃፀር አነስተኛ ነው። ቢሆንም ሕንድ ካላት ሕዝብ አንፃር ከፍተኛ ስኳር ተጠቃሚዋ ሃገር ናት። . ሕንዳውያን ከልጅና የልጅ ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩት ለምንድን ነው? . ትራምፕ ስለ ሕንድ የአየር ብክለት የተናገሩት በርካቶችን አስቆጣ . የቶልስቶይ መፅሐፍ ህንዳውያን 'አክቲቪስቶች' ላይ መዘዝ አምጥቷል የሕንድ የስኳር ምርት መጠን በዚህ ዓመት በ13 በመቶ አድጎ 31 ሚሊዮን ቶን ምርት እንደሚመረት ይጠበቃል። ነገር ግን መንግሥት እንደ ሌላ ጊዜው በገፍ ለውጭ ገበያ ማቅረቡን ትቶ ለሕዝብ ሊያከፋፍል ይችላል ተብሏል። የስኳር ምርት ማሕበሩ ድረ-ገፁ ላይ ስኳር መጠቀም እንደማይጎዳ የሚጠቁም ማስታወቂያ ለቋል። ማሕበሩ ሰዎች ለሚሰሯቸው ምግቦች ሌላ ዓይነት ማጣፈጫ ከሚጠቀሙ ስኳር ቢጠቀሙ የተሻለ እንደሆነ የሚጠቁሙ ማስታወቂያዎች እየለቀቀ ነው። የሕንድ የምግብ ሚኒስቴር ሱዳንሹ ፓንዴይ የሕንድ ማሕበረሰብ ለስኳር ያለው አስተሳሰብ የተዛባ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። እርግጥ ነው በሌሎች ሃገራት ሰዎች የስኳር አጠቃቀማቸውን እንዲያስተካክሉና ቀነስ እንዲያደርጉት ነው የሚመከሩት። ስኳር ከመጠን ላለፈ ክብደትና በተለምዶ ስኳር በሽታ ተብሎ ለሚታወቀው ዳያቢቲስ ሊያጋልጥ ይችላል ይላሉ ባለሙያዎች። የዓለም ጤና ድርጅት የተለያዩ ምግቦች ውስጥ፤ በተለይ ደግሞ ማርና የፍራፍሬ ጭማቂ ላይ የሚታከል ስኳር ለጤና አሳሳቢ ነው ይላል። ሕንድ ውስጥ 50 ሚሊዮን ገደማ ገበሬዎች ሸንኮራ አገዳ ያመርታሉ። ሚሊዮኖች ደግሞ ስኳር በሚያመርቱ ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው ይሠራሉ። ሕንድ የተረፈ የስኳር ምርቷን ወደ ውጭ ለመላክ ማቀዷ በሌሎች ስኳር አምራች ሃገራት ዘንድ ቅራኔ ፈጥሯል። ሌላኛው የተረፈ የስኳር ምርትን ማስወገጃ መንገድ ወደ ኢታኖል ቀይሮ መጠቀም ነው። የሕንድ ስኳር ምርት ማሕበር የኢታኖል ምርት አሁን ካለው 1.9 ቢሊዮን ሊትር ምርት በሚቀጥለው ዓመት ወደ 3 ቢሊዮን ሊያድግ እንደሚችል ገምቷል። https://www.bbc.com/amharic/news-54791680 +politics ሩሲያ በነዳጅ ማከማቻዋ ላይ ዩክሬን ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች "ከዩክሬን በስተሰሜን በምትገኘው የሩሲያ ከተማ የሚገኝ የነዳጅ ማከማቻ ላይ ጥቃት መፈጸሙን የከተማዋ አስተዳዳሪሪ አስታወቁ። ጥቃቱ የተፈጸመው በዩክሬን ሁለት የጦር አውሮፕላኖችም ነው ተብሏል። ዩክሬንና ሩሲያ በሚዋሰኑበት ድንበር 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቤልጎሮድ ከተማ ውስጥ በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ቃጠሎ መነሳቱንም በትዊተር የተጋራ ቪዲዮ ያሳያል። እንዲሁም አንዳንድ ቪዲዮች የነዳጅ ዲፖው በሮኬቶች ሲመታም አሳይተዋል። ይሁን እንጂ የዩክሬን አውሮፕላኖች ቀደም ሲል በሩሲያ ኢላማዎችን መምታት አልቻሉም ነበር። የከተማዋ አስተዳዳሪ ቪያቼስላቭ ግላድኮቭ ጥቃት ደርሷል ቢሉም የዩክሬን ባለስልጣናት ምላሽ አልሰጡም። የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቃለ አቀባይም ለቃጠሎው ተጠያቂው ዩክሬን መሆኗን ተናግረው ይህ ክስተት ከዩክሬን ጋር ያለውን ""ውይይት ለመቀጠል ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል ተብሎ ሊታሰብ አይችልም"" ብለዋል። እስካሁን እየተደረጉ ያሉ የሰላም ድርድሮች እምብዛም መሻሻል አላሳዩም። የሩሲያ ባለስልጣናት የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለቱን እንደገና ለማስቀጠል እንዲሁም በቤልጎሮድ የኃይል አቅርቦት እንዳያስተጓጉል የተቻላቸውን እያደረጉ መሆናቸውን ቃለ አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል ። በሩሲያ ጦር ከፍተኛ ውድመትና በአሁኑም ወቅት ተከባ ከምትገኘው ከዩክሬን ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ካርኪቭ በስተሜን የምትገኘው ይህች የሩሲያ ከተማ ከ370 ሺህ በላይ ነዋሪ አላት። የከተማዋ አስተዳዳሪ ግላድኮቭ በቴሌግራም ባስተላለፉት መልእክት ""በዝቅተኛ ከፍታ ላይ ወደ ሩሲያ ግዛት የገቡት ሁለት የዩክሬን ጦር ሄሊኮፕተሮች ባደረጉት የአየር ድብደባ ምክንያት በነዳጅ ማከማቻው ላይ የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል"" ብለዋል። በዚህ ጥቃትም የተገደለ ሰው የለም ብለዋል። የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች እሳቱን በተቻለ ፍጥነት ለመቆጣጠር እየሞከሩ እንደሆነ እና በነዋሪዎች ላይ ምንም አይነት ስጋት እንደሌለም ተናግረዋል። የድንገተኛ አደጋ ሚኒስቴር የእሳቱን ቪዲዮ በቴሌግራም ገጹ አስፍሯል። የሩሲያው ኢንተርፋክስ የዜና ወኪል እንደዘገበው በአቅራቢያው ያሉ ነዋሪዎችን ማስወጣት እንደተቻለና በዲፓው ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎችም መቁሰላቸውን አስነብቧል። ስምንት የነዳጅ ታንኮች በእሳት መያያዛቸውን እና ወደ 200 የሚጠጉ የእሳት አደጋ ተከላካዮች በቦታው ላይ እየተረባረቡ እንደሆነም ዘገባው አክሎ ገልጿል። ዲፖው የሚተዳደረው በሩሲያ መንግሥት የነዳጅ ኩባንያ ሮስኔፍት ነው። ቃጠሎውን ተከትሎ የመኪና ወረፋዎች በአካካቢው የነዳጅ ማደያዎች ላይ የታየ ቢሆንም ነገር ግን አስተዳዳሪው በከተማዋ የነዳጅ አቅርቦት እጥረት የለም ብለዋል። የሩሲያው አርአይኤ ኖቮስቲ የዜና ወኪል እንደገለጸው በዲፖው በሚገኘው ሶስት የነዳጅ ታንኮች ላይ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ቢጠፋም አሁንም እሳቱ የመስፋፋቱ ስጋት አልተቀረፈም ብሏል። ከሁለት ቀናት በፊት በቤልጎሮድ ዲፖት አቅራቢያ በሚገኝ የጥይት መጋዘን ላይ በርካታ ፍንዳታዎች ተዘግበዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60956542 +business ባለ 14 ካራት ትንሽዬ አልማዝ በ26 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠች "ለማግኘት በጣም ከባድና ውድ የተባለ አንድ ሐምራዊ አልማዝ ክብረ ወሰን በሚባል ዋጋ ተሸጠ። ይህ አልማዝ የተሸጠው በጨረታ ሲሆን ጨረታው ስዊዘርላንድ አገር ነው የተካሄደው። 14.8 ካራት የሚመዝነው ይህ አልማዝ ""ዘ ስፕሪት ኦፍ ሮዝ"" የሚል ስም ተሰጥቶታል። እስከዛሬም ለጨረታ ከቀረቡ አልማዞች ትልቁ ነው። 99 ከመቶ የሚሆኑ የሐምራዊ ሮዛማ ቅይጥ ቀለም ያላቸው አልማዞች የካራት መጠን ከ10 በታች እንጂ 14 ካራት አይደርሱም። ይህን አልማዝ ልዩ የሚያደርገውም መጠኑና የቀለም ስብጥሩ ነው ተብሏል። ይህን ውድ አልማዝ በጨረታ አሸንፎ የገዛው ግለሰብ ማንነት ይፋ አልተደረገም። ሐምራዊውን አልማዝ ለጨረታ ያቀረበው ግን የሩሲያ የማዕድን ኩባንያ አልሮሳ ነው። ""ዘ ስፕሪት ኦፍ ዘ ሮዝ"" የተሰኘው ይህ ሐምራዊው አልማዝ ከድፍድፍ የ���ልማዝ ድንጋይ ነጥሮ የወጣው በሩሲያ በጎሮጎሳውያኑ 2017 ድፍድፍ አልማዙ ያን ጊዜ ሲወጣ ኒጂንስኪ የሚል የክብር ስም ተሰጥቶት ነበር። አልማዙ በዚህ ስም የተሰየመው የሩሲያ ፖሊሽ የባሌት ዳንስ ጥበበኛ ክብር ለመስጠት ነው። ቮስላቭ ኒጂንስኪ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ወደር ያልተገኘለት የባሌት ዳንሰኛ ነበር። በዓለም ላይ እስከዛሬ ለፒንክ (ሮዝ) አልማዝ የተከፈለው ትልቁ ሽያጭ 71 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይህም በ2017 በሆንግ ኮንግ በተደረገ ጨረታ የተሸጠው 59 ካራት አልማዝ ነው። አልማዞች ብዙውን ጊዜ 150 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ውስጥ የኖሩና ወደላይኛው የምድር ክፍል በእሳተ ጎመራ አማካኝነት የወጡ ውድ የከበሩ ደንጋዮች ሲሆኑ እነዚህን ውድ የከበሩ ድንጋዮች ፈልጎ አግኝቶና አጽድቶ ለገበያ ለማቅረብ በአማካይ እስከ 20 ዓመት ሊወስድ ይችላል። የተፈጥሮ አልማዝ እስከ 3 ቢሊዮን ዓመት ያህል እድሜ ያለው በብዙ የእሳት ጎመራና የመልከዓ ምድር ለውውጦች የተቀየጠ እንደሆነ ይታመናል። ከከበሩ ድነጋዮች ውስጥ እንደ አልመዝ ጠንካራ ማዕድን የለም።" https://www.bbc.com/amharic/news-54913705 +health ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 ምን እንደሆነ አናውቅም የሚሉት 10 አገራት ኮቪድ ዓለምን አምሷል፡፡ እኛ ግን አናውቀውም የሚሉ 10 አገሮች አሉ ብንላችሁስ፡፡ ለመሆኑ እነዚህ አገሮች እነማን ናቸው? የማያውቁት ኮቪድ እንዴት እያደረጋቸው ይሆን? 1.ፕላው (Palau) ይቺ አገር የት ያለች ትመስልዎታለች? ሩቅ ምዕራብ ፓስፊክ ነው የምትገኘው፡፡ ማይክሮኒዢያ ሪጂን በሚባለው አካባቢ ከነ ፊሊፒንስ እና ኢንዶኒዢያ ነጠል ብላ በባትሪ ተፈልጋ የምትገኝ ጢኒጥ ደሴት ናት፡፡ እዚያ ፕላው የሚባል ሆቴል አለ፡፡ ድሮ በ1982 ነበር የተከፈተው፡፡ ያኔ የአገሩን ስም የያዘው ይኸው እስከዛሬ አለ፡፡ በአገሩ ሌላ ሆቴል የሌለ ይመስል፡፡ በፓስፊክ ውቅያኖስ ሰማያዊ ቀለም ውሀ ውስጥ ጠብ ያለች ነጥብ የምትመስለው ይቺ አገር የቱሪስት አገር ናት፡፡ ያለፈውን ዓመት ብቻ አሐዝ ብንወስድ፣ ወደ ፕላው ደሴት 90ሺህ ቱሪስት ገብቷል፡፡ ይህ አሐዝ ከፕላው ጠቅላላ ሕዝብ አምስት እጥፍ ይበልጣል ብንላችሁስ? 40 ከመቶ የአገሪቱ ጥቅል አገራዊ ምርት ገቢ በቱሪዝም የሚታለብ ነው፡፡ ይህ ግን ከኮቪድ በፊት ያለ ታሪክ ነው፡፡ ኮቪድ ድንበሯን ሲያዘጋት ፕላው ደሴት ጉሮሮዋ ተዘጋ፡፡ እንኳን ሌላው መዝናኛ ይቅርና የአገሪቱን ስም የያዘው ሆቴል ሳይቀር ተዘጋ፡፡ ‹‹ለውድ ደንበኞቻችን፡- ኮቪድ የሚባል በሽታ በተቀረው ዓለም ስለተከሰተ ፕላው ሆቴል ለጊዜው ዝግ መሆናችንን ለውድ እንገልጻለን›› ብለው በር ላይ ሳይለጥፉ አልቀሩም፡፡ ፕላው አገር አንድም ዜጋ በቫይረሱ ባይያዝባትም ቫይረሱ ግን ቱሪዝማዊ ኢኮኖሚዋን ደም እያስተፋው ነው፡፡ 2. የማርሻል ደሴቶች 4ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀው በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ መሀል፣ ከምድር ወገብ ሰሜን፣ ብጥስጥስ ብለው ከሚገኙት የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ውስጥ የማርሻል ደሴቶች ይገኙበታል፡፡ በሀዋይ እና በፊሊፒንስ መሀል ነው የሚገኙት፡፡ በውስጣቸው 1200 ጥቃቅን ደሴቶችና የጎመራ ፍንጥቅጣቂ የሆኑ የሰመጡ ደቂቀ ደሴቶች (ኮራል አቶልስ) ይገኛሉ፡፡ ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ የአሜሪካ የሩቅ ግዛት ሆነው የቆዩ ቢሆንም ከ1986 ወዲህ ራሳቸውን ችለዋል። ደህንነቱና መከላከያን እንዲሁም ጠቀም ያለ ድጎማን ግን አሁንም ከአሜሪካ ነው የሚያገኙት። የሕዝብ ብዛት 55ሺህ ሲሆን ዋና ከተማቸው ማጁራ ትባላለች፡፡ እነዚህ ደቂቀ ደሴቶችና የቱሪስት መዳረሻ የሆኑ ስብስቦች ማርሻል ደሴቶች ተብለው ይጠራሉ፡፡ ኮቪድ ምን እንደሆነ ባያውቁም ምጣኔ ሀብታዊ ቁንጥጫው ግን ፓሲፊክን አቋርጦ ተሰምቷቸዋል። ታዲያ አንድ ፕላው በቱሪዝም በኩል አይደለም ቁንጥጫው፡፡ በዓሣ ማጥመድና መላክ ጥሩ ገንዘብ ያገኙ ነበር፡፡ ኮቪድ ይህንን አስተጓጎለባቸው፡፡ በኮቪድ ምክንያት 700 ሰዎች ሥራ አጥተዋል፡፡ ይህ ትንሽ ሕዝብ ላላት ማርሻል አይላንድስ ብዙ ቁጥር ነው፡፡ የሕዝብ ብዛቷ 300ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ዋና ከተማዋ ፖርትቪላ ይባላል፡፡ በ1ሺህ 300 ኪሎ ሜትር ላይ የተሰፉ የሚመስሉ 80 ደሴቶች የፈጠሯት አገር ናት፡፡ ከፈረንሳይና እንግሊዝ ቅኝ ነጻ የወጣችው ገና በ1980 ነበር፡፡ አብዛኛው ሕዝቧ ገጠር የሚኖር ገበሬ ነው፡፡ የብዙ አገር ህዝቦች ድንበር ክፈቱልን ሥራ እንስራበት እያሉ ነው የሚያስቸግሩት፡፡ ቫኑዋቱ ብትሄዱ ግን በተቃራኒው ነው የምትሰሙት፡፡ ዶ/ር ሌን ታሪቮንዳ የኅብረተሰብ ጤና ዳይሬክተር ናቸው፣ የቫኑዋቱ ደሴት፡፡ ዶ/ር ሌን የመጡባት ደሴት አምባኡ ደሴት ትባላለች፡፡ 10ሺ ሰዎች ይኖሩባታል፡፡ ‹‹እኔ የመጣሁበት ደሴት ሄዳችሁ ድንበሩ ይከፈት ወይ ብትሏቸው አረ እንዳታስጨርሱን ነው የሚሏችሁ›› ይላሉ ለቢቢሲ፡፡ መታመም አንፈልግም ነው የሚሉት፡፡ 80 ከመቶ የታሪቮንዳ አገር ሕዝብ ገጠር ነው የሚኖር፡፡ የኮቪድ ሕመም ብዙም አልተሰማቸውም፡፡ እርሻ እንጂ ቱሪዝም ላይ ስላልተንጠላጠሉ ሊሆን ይችላል፡፡ ዶር ሌን ድንበር ለመክፈት አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ጎረቤት ፓፓዎ ጊኒ ለወራት ከቫይረሱ ነጻ ሆና ቆይታ ሐምሌ ላይ እንዴት ጉድ እንደሆነች ሰምተዋል፡፡ ስለዚህ ድንበር መክፈቱ ይቆየን ብለዋል፡፡ 4. ቶንጋ ቶንጋን የፈጠሩት ደግሞ 170 ደቂቀ ደሴቶች ናቸው፡፡ እዚያው ደቡባዊ ፓስፊክ ነው የሚገኙት፡፡ ቶንጋ ደሴቶቿን ብትሰበስብ በስፋት ከጃፓን አታንስም፡፡ ለ165 አመታት ንጉሣዊ የፊውዳል አስተዳደር ነበራት፡፡ ከዚህ ፊውዳላዊ ሥርዓት የወጣችው በ2010 ዓ. ም ነበር፡፡ ጥብቅ ክርስቲያን አማኞች ያሏት ቶንጋ ከእንግሊዝ ነጻ የሆነችው በ1970 ዓ.ም ነበር፡፡ ቶንጋ ምን አይነት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ የሌላት አገር ተደርጋ ትታያለች፡፡ ማዕድን አልባም ናት ይባላል፡፡ ይህ ነው የሚባል የተፈጥሮ ማዕድን ሀብት ባይኖራትም በዓሣ ሀብት ራሷን ትደጉማለች፡፡ ሌላው የገቢ ምንጭ እርሻ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ቶንጋዊያውን ከውጭ አገር የሚልኩት ገንዘብ ነው፡፡ ብዙዎቹ ቶንጋዊያን ያሉት በኒዊዚላንድ ነው፡፡ በአገሪቱ የሥራ አጥ ቁጥር ከፍ ያለ ነው፡፡ ያም ሆኖ የውጭ ምንዛሬዋን የምታገኝበት አንዱ ቀዳዳ ቱሪዝም ስለነበር ኮቪድ ባይደርስባትም ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት አድርሶባታል፡፡ 5. ሰሙዋ በፓስፊክ ውቅያኖስ የምትገኘው ሰሙዋ እስከ 1961 ዓ. ም ድረስ በኒውዚላንድ ሥር ነበር የምትተዳደረው፡፡ 9 የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ነው የፈጠሯት ይቺን አገር፡፡ ሆኖም 99 ከመቶ ሕዝቧ የሚኖረው በኡፖሉና ሳቫይ ደሴቶች ነው፡፡ ዋና ከተማዋ አፒያ ይባላል፡፡ ምጣኔ ሀብቷ በእርሻና በዓሣ ሀብት የተንጠለጠለ ነው፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቱሪዝም ሞቅ ደመቅ ብሎላት ነበር፡፡ በተለይ ያማሩ የባሕር ዳርቻዎቿ ተወዳጅ ሆነውላታል፡፡ ከቱሪዝም ጋር የባሕር ማዶ ዓለም አቀፍ ኦፍሾር የባንክ አገልግሎት በማሳለጧ ሀብታሞች ሸሸግ ማድረግ የፈለጉትን ገንዘብ ይዘው እዚያ ይሄዳሉ፡፡ አንድም ለመዝናናት፣ አንድም ለባንክ አገልግሎት፡፡ 200ሺህ የማይሞላው ሕዝቧ የወግ አጥባቂ ባህልና የጥብቅ ክርስትና ተከታይ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ዜጎቿ ወደ ኒውዚላንድና ሌሎች አገሮች እየተሰደዱ ገንዘብ ወደ ቤተሰብ ይልካሉ፡፡ ኮሮና በሌሎች አገሮች ያደረሰው ጉዳት ሕመሙ ተሰምቷል፣ ሩቅ በምትገኘው በሰሙዋ ደሴት፡፡ 6.ቱቫሉ ቱቫሉን የፈጠሩት 9 ደሴቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ 5ቱ እሳተ ገሞራ ወልዶ፣ አሳብጦ፣ በድጋሚ አስምጦ ዳግም የወለዳቸው (ኮ��ል አቶልስ) ናቸው፡፡ የተቀሩት አራቱ ደግሞ ሕዝብ በደንብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቱቫሉ በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ ነው የምትገኘው፡፡ ፉናፉቲ ይባላል ዋና ከተማዋ፡፡ በቱቫሉ ተራራ አይታሰብም፡፡ ከባሕር ጠለል በላይ ከ4.5 ሜትር ከፍ ያለ ቦታ የለም፡፡ የአየር ንብረት በቱቫሉ ትልቁ ጉዳይ ቢሆን የማይገርመውም ለዚሁ ነው፡፡ የባሕር ጠለል ከፍታ ከምድረ ገጽ ከሚያጠፋቸው አገሮች አንዷ ቱቫሉ ነው የምትሆነው፡፡ በቱቫሉ ወንዝም ምንጭም ስለሌለ ኑሮ የዝናብ ጥገኛ ነው፡፡ የኮኮናት ተክል የአገሪቱ ገቢ ምንጭ ነው፡፡ ይህ ገቢ እንዲታወክ ምክንያት በመሆኑ ኮቪድ ቱቫሉ ባይገባም ገብቷል፡፡ 7. ናውሩ በዓለም ትንሽዋ አገር ናውሩ ናት፡፡ ይቺ ደሴት ስሟ በቅርብ ጊዜ ይነሳ የነበረው አውስትራሊያ አገሪቱን እንደ ጓሮ እየተጠቀመቻት ነው በሚል ነው፡፡ ናውሩ ስደተኞች ማጎርያ አለ፤ ንብረትነቱ የአውስትራሊያ የሆነ፡፡ ይሄ ማጎርያ ታዲያ ለናውሩ አንድ የገቢ ምንጭ መሆኑ ይገርማል፡፡ ናውሩዎች አንዱ ሥራ ቀጣሪ ኢንደስትሪያችሁ ምንድነው ቢባሉ የአውስታራሊያ የስደተኛ ካምፕ ብለው ሊመልሱ ይችላሉ፡፡ ከ2013 ጀምሮ አውስትራሊያ በጀልባ ወደ አገሯ ሊገቡ የሚሞክሩ ስደተኞችን በሙሉ ወደ ናውሩ ነው የምትወስዳቸው፡፡ ካልሆነም ፓፓው ኒው ጊኒ፡፡ ከአውስትራሊያ 3ሺህ ኪሎ ሜትር ርቃ በሰሜን ምሥራቅ ፓስፊክ አቅጣጫ የምትገኘው ናውሩ የዜጎቿ ብዛት 10 ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ናውሩን የሚያኖራት እርዳታ ነው፡፡ ሌላው ብቸኛ ሀብቷ ፎስፌት ማዕድን ነው፡፡ በናውሩ የውጭ ጋዜጠኛ ሄዶ መዘገብ አይችልም፡፡ ምክንያቱም በካምፖቹ ውስጥ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ያጋልጣል፡፡ ይህ ደግሞ ናውሩ የገቢ ምንጬን ሊጎዳብኝ ይችላል ትላለች፡፡ ናውሩን በዓመት የሚጎበኛት ሰው ከ200 አይበልጥም ይባላል፡፡ ቴሌግራፍ በአንድ ዘገባው በናውሩ እስከዛሬ የገባው ቱሪስት ቢደመር ከ15ሺህ አይበልጥም ሲል ጽፏል፡፡ በስፋት ቫቲካን ሲቲና ሞናኮ ብቻ ናቸው የሚበልጧት፤ ለዚህም ነው የዓለም ትንሽዋ ሪፐብሊክ ደሴት የምትባለው፡፡ ቱሪስት የአገሪቱ ገቢ ምንጭ አለመሆኑ በኮቪድ-19 አልተጎዳችም ማለት ግን አይደለም፡፡ ለጊዜው ከ10ሺህ ዜጎቼ አንድም ሰው ኮቪድ-19 አልያዘውም ብትልም ሕመሙ ግን ናውሩም ደርሷል፡፡ 8. ኪሪባቲ ኪሪባቲ የብጥስጣሽ ደሴቶች አገር በመሆኗ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ 4ሺህ ኪሎ ሜትር፣ ከሰሜን ደቡብ ደግሞ 2ሺህ ኪሎ ሜትር ታስኬዳች፡፡ ይህ ማለት ግን ይህ ሁሉ ርቀት ሰው የሚኖርበት ደረቅ መሬት ነው ማለት አይደለም፡፡ ነጻነቷን ያገኘችው ከእንግሊዝ በ1979 ዓ.ም ነው፡፡ በ1960ዎቹ ይቺ አገር አንዳንድ ደሴቶቿ ለእንግሊዝ የኑክሌር መሞከሪያ ሆነው አገልግለዋል፡፡ እንደ ብዙዎቹ የፓስፊክ ደቂቀ ደሴቶች ሁሉ ኪሪባቲም የዓለም ሙቀት መጨመር ከምድረ ገጽ ሊያጠፋት እንደሚችል ይገመታል፡፡ ኪሪባቲ ከፊጂ ደሴት መሬት ተከራይታ ምግብ ታመርታለች፡፡ ኢኮኖሚዋ ደካማ ሲሆን ኮኮናትና ኮፕራ በመላክ ነው የምትታወቀው፡፡ የዓሣ ማጥመድ ፍቃድ ለውጭ ኩባንያዎች እየቸበቸበች ኢኮኖሚዋን በከፊል ትደጉማለች፡፡ 9ኛ የሰለሞን ደሴቶች፤ 10ኛ ማይክሮኒዢያ በዝርዝሩ 9ኛ እና 10ኛ ላይ ያሉት የሰለሞን ደሴቶች እና ማይክሮኒዢያ ናቸው፡፡ ሁለቱም አገራት በዓሣ ምርትና በቱሪዝም ይታወቃሉ፡፡ ሁሉም በኮቪድ-19 የተጠቃ ዜጋ የለባቸውም፡፡ ይህ ዝርዝር ታዲያ ሰሜን ኮሪያና ቱርከሜኒስታን አላካተተም፡፡ ሆኖም እነዚህ ሁለት አገራት በይፋ ከኮቪድ-19 የያዘው ዜጋ አለም የለምም ብለው አያውቁም፡፡ ወይም አይታመኑ ይሆናል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-53864759 +sports የ105 ዓመቷ እማማ ራምባይ በሩጫ ክብረ ወሰን ሰበሩ ወ/ሮ ራምባይ 105 ዓመታቸው ነው። 100 ሜትርን በ45.40 ሰከንድ በመጨረስ በአዛውንቶች የተያዘውን የሕንድን ክብረ ወሰን ሰብረዋል። ይህንን ውድድር የሚያዘጋጀው አካል እስካሁን ትልቁ የውድድር ተሳታፊ የ85 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cglrkjmrvngo +business ሕዳሴ የግድብ 3ኛ ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ ተገለጸ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ተጠናቆ በግድቡ አናት ላይ ውሃ መፍሰስ መጀመሩ ተገለጸ። የ3ኛው ዙር የግደቡ የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት በስፍራው ተገኝተዋል። ባለፉት ሁለት የክረምት ወቅቶች የመጀመሪያው እና ሁለተኛው የግድቡ የውሃ ሙሌት መካሄዱ ይታወሳል። የ3ኛው ዙር የግደቡ የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ የተገለጸው ትናንት ነሐሴ 5/2014 ዓ.ም. የሁለተኛው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተርባይን ሥራ መጀመሩ ከተገለጸ በኋላ ነው። ትናንት ኃይል ማመንጨት የጀመረው የግድቡ 2ኛው ተርባይን ዩኒት ዘጠኝ የተባለው ሲሆን 270 ሜጋ ዋት የአሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው ተብሏል። የካቲት 2014 ዓ.ም. ወደ ሥራ የገባው ዩኒት 10 ተርባይን በተመሳሳይ 270 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል። በዚህም መሠረት ሁለቱ ኃይሎች በድምሩ 540 ሜጋ ዋት የአሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላቸው ተመልክቷል። የግድቡ ግንባታ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የግድቡ የሲቪል ሥራዎች ግንባታ 95 በመቶው መጠናቀቁን የገለጹ ሲሆን፤ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ግንባታና እና ተከላ ወደ 61 በመቶ ከፍ ማለቱንና የውሃ ማስተላለፊያ የብረታ ብረት ሥራዎችን ደግሞ 73 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል። ዋና ሥራ አስኪያጁ የግድቡ ሁለተኛው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተርባይን ኃይል የማመንጨት ሥራን ለማስጀመር በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር የግድቡ አጠቃላይ የግንባታ ሥራ 83.3 በመቶ ደርሷል ብለዋል። ግንባታው ሲጠናቀቅ በአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ እንደሚሆን የሚጠበቀው የሕዳሴ ግድብ ከፍታው 145 ሜትር ሲሆን፤ ርዝመቱ ደግሞ 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ነው። ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ፈሶበት ከአምስት ሺህ በላይ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል የተባለው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአካባቢው አገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። የግንባታው መሠረተ ድንጋይ መጋቢት 24/2003 ዓ.ም የተጣለው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ በስተምዕራብ ከሱዳን ጋር በምትዋሰንበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በጉባ ወረዳ እየተገነባ ይገኛል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cqqdgz7ydg0o +business የኑሮ ውድነት፡ በኢትዮጵያ የዋጋ ጭማሪ እንጂ ቅናሽ የማይታየው ለምን ይሆን? "በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት እና በኑሮ ውድነቱ የተማረሩት የቤተሰብ አስተዳዳሪ ሁሌም ለሸቀጦች ዋጋ መጨመር ነጋዴው ምክንያት የሚሰጣቸው የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና የዶላር ምንዛሬ ዋጋ መናርን እንደሆነ ለቢቢሲ ይናገራሉ። ""ፈሳሹ ዘይት ተፈልጎ አይገኘም"" የሚሉት እኚህ የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ ከዚህ ቀደም አንድ እንጀራ በ10 ብር ይገዙ እንደነበር አስታውሰው 12 ብር መግባቱን በምሬት ይናገራሉ። የኑሮ ውድነቱ ግን አዲስ አበባን መኖሪያቸው ያደረጉትን ብቻ አይደለም የተጫነው፣ በሐረር ከተማ የሚኖሩት ወ/ሮ ሽርካ አሕመድ ዘንድሮ የገጠማቸው የዕቃዎች ዋጋ መጨመር ከዚህም በፊት ከነበረው ሁሉ የተለየ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""ኑሮ እጅግ ተወዶብናል። ለምሳሌ አንድ ኪሎ ቲማቲም 12 ብር የነበረው በአሁኑ ሰዓት 25 ብር ገብቷል። ከጥቂት ቀናት በፊት ��265 ብር ይገዛ የነበረው ዘይት 430 ገብቷል። ከሶስት ወራት ወዲህ ያልጨመረ አንድም ነገር የለም። ከአቅማችን በላይ ሆኗል"" ሲሉ ተስፋ በመቁረጥ ይናገራሉ።። ወ/ሮ ሽርካ በሁሉም እቃዎች ላይ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ 'ዶላር ስለጨመረ ነው' ሲባል ከመስማት ውጪ ምክንያቱ ይህ ነው ብሎ ያስረዳቸው የለም።። በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩት የአጋሮ ከተማ ነዋሪ ወ/ሮ እመቤት ከድር በበኩላቸው፣ በገበያ የሚታየው የዋጋ ንረት ""ጠዋትና እና ከሰዓት በኋላ የዋጋ ልዩነት ማሳየት ጀምሯል"" ይላሉ። ""እኔ የችርቻሮ ነጋዴ ነኝ፤ ከኅብረተሰቡ ጋር በቀጥታ እገናኛለሁ፤ እኛ ደግሞ ከጅምላ አከፋፋዮች እንገዛለን። እኛ እነርሱን ስንጠይቅ፣ የጨመረው ከላይ ነው ይሉናል፤ ግልጽ የሆነ ምክንያት የለም። እኔ አሁን ይህንን የሕዝብ ምሬት መስማት አቅቶኝ ሥራዬን እያቆምኩ ነው"" ይላሉ ወ/ሮ እመቤት። አክለውም ""አንድም ዋጋው አልጨመረም የምንለው ነገር የለም። አንተ ጠዋት አንድ እቃ ከሸጥክ፣ ከሰዓት በኋላ ዋጋው ጨምሯል። እቃው ግን ያው ጠዋት የነበረው ነው። ተገቢ ቁጥጥር መደረግ አለበት"" ሲሉ ለመፍትሄው የመንግሥትን እጅ ይማፀናሉ። በዚህ ወር ውስጥ ዋጋቸው ከጨመረ ነገሮች መካከል የነዳጅ ዘይት አንዱ ነው። በዚህም ምከንያት የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል። ኢትዮጵያ ከውጪ የምታስገባው የነዳጅ ዘይት በሁለት አቅጣጫዎች፣ በሱዳን እና ጅቡቲ በኩል የነበረ ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በሱዳን በኩል የሚገባው መቋረጡን የቢሮው ኃላፊዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አለማየሁ ፀጋዬ በሱዳን በኩል የሚገባው ነዳጅ ቢቋረጥም፣ አገሪቷ ከውጪ በምታስመጣው ነዳጅ ላይ ግን የታየ ለውጥ የለም ይላሉ። ""በነዳጅ አቅርቦት ላይ ከዚህ በፊት በነበረው ላይ ልዩነት የለም። በሱዳን በኩል ይገባ የነበረው ቤንዚን ብቻ ነው። እንደውም በጥገና ምክንያት ይገባ ከነበረው የቀነሰ እና ለተወሰኑት ከተሞች ብቻ ሲቀርብ የነበረ ነው። በኮሮናቫይረስ ምክንያት ደግሞ ይገባ የነበረው ራሱ ተቋርጦ ነው የቆየው"" መሆኑን ገልፀዋል። በሱዳን በኩል ይቀርብ የነበረው ነዳጅ፣ ቀድሞ የተቋረጠ እና በሁለቱ አገራት መካከል ካለው የድንበር ውዝግብ ጋር የማይገናኝ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ነዳጅን ከመካከለኛው ምስራቅ፣ በጅቡቲ በኩል እያስገባች መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው የሚናገሩት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው፣ በሱዳን በኩል የነበረው አቅርቦት ከተቋረጠ ወዲህም የአቅርቦት እጥረት አልተፈጠረም ብለዋል። በኢትዮጵያ ከሰላሳ በላይ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች ከውጪ የሚገባውን ይህንን ነዳጅ ለተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያቀርባሉ። በነዳጅ ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪም ከዓለም ገበያ ዋጋ ጋር የተያያዘ እንጂ በአቅርቦት መቀነስ ምክንያት እንዳልሆነ ኀብረተሰቡ ሊረዳ ይገባል ሲሉ አቶ አለማየሁ ፀጋዬ ያስረዳሉ። የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን የሚወስነው የንግድ ሚኒስቴር በመሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የጨመረበትን ምክንያት ለማጣራት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የምጣኔ ኃብት ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ጉቱ ቴሶ አሁን በኢትዮጵያ ለገጠመው የኑሮ ውድነት ምክንያቶቹ በርካታ መሆናቸውን ያስረዳሉ። ቀዳሚዎቹ ግን ከዓመት ዓመት መጨመር እንጂ መቀነስ የማያሳየው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አንዱ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ይህ በየዓመቱ መጨመር ብቻ የሚያሳየው የዋጋ ግሽበት መንስዔው መሠረታዊ የሆኑ የምጣኔ ኃብት መዋቅሮች አለመስተካከል ጋር ተያይዞ መሆኑን ገልፀዋል። ቀሪዎ�� ደግሞ ወቅታዊ የሆኑ እና የአገሪቱን ምጣኔ ኃብት ፈተና ውስጥ የሚጥሉ ክስተቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፥። ዶ/ር ጉቱ የምርት አቅርቦት እየቀነሰ መምጣት፤ የሰላም መታጣት፣ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ መፈናቀሎች ለገበያው ዋጋ መናር ምክንያቶች መሆናቸውንም ይጠቅሳሉ። በአገሪቱ ውስጥ የተካሄዱ ሕዝባዊ አመጾች፣ የተደረጉ ተከታታይ የገበያ እቀባዎች፣ የንግድ ሰንሰለቱን በተጋጋሚ መሰበራቸውን፣ በተለይ ደግሞ ትርፍ አምራች በሆኑ አካባቢዎች በሰላም እጦት ምክንያት ተደራራቢ ጫና መፍጠሩን ያስረዳሉ። ገበሬው በሰላም እጦት ምክንያት ቢያርስ እንኳ አልጎለጎለም የሚሉት ባለሙያው፣ የጎለጎለው መዝራት ሳይችል ሲቀር፣ የዘራ ደግሞ መሰብሰብ አለመቻሉ የእርሻ ምርቶች አቅርቦት እየቀነሰ እንዲመጣ ማድረጉን ይገልጻሉ። የምጣኔ ኃብት ባለሙያው አክለውም በርካታ ኢንደስትሪዎችም ከውጪ አገር ግብዓት ስላላገኙ ወይንም በሰላም እጦት ፍራቻ ምክንያት ምርት መቀነሳቸው ወይንም ማቆማቸው ሌላው ለኑሮ ውድነቱ አስተዋጽኦ ካደረጉ ነገሮች መካከል አንዱ ነው። እነዚህ ማምረት የሚያቆሙ ኩባንያዎች በበዙ ቁጥር ለኑሮ ውድነቱ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ የሚገልጹት ዶ/ር ጉቱ፣ የውጪ ምንዛሬ እጥረት እና የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ተደራርበው የኑሮ ውድነትን ማክበዳቸውን ይገልጻሉ። ""ከ2017 እስከ 2021 (እኤአ) የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም በ54 በመቶ ወርዷል፤ በአጠቃላይ ሲታይ በአስር ዓመታት ውስጥ የኢትዮጰያ ብር የመግዛት አቅም በመቶ እጅ ወድቋል"" የሚሉት ዶ/ር ጉቱ፣ የምግብ አቅርቦትና ሌሎች የዕለት ፍጆታ የሆኑ ምርቶች የብር የመግዛት አቅም በወደቀበት በዚህ ጊዜ ከውጪ ሲገቡ የኑሮ ውድነትን እንደሚያባብሱ ይናገራሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ምርት የሚያመርቱ አብዛኞቹ ኢንደስትሪዎች ከውጪ በሚገባው ግብዓት ላይ የተንጠለጠሉ በመሆናቸው ይህንን ችግር ለመፍታት ያላቸውን ሚና ማሳነሱንም ይገልጻሉ። በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የኑሮ ውድነት ዘላቂ መፍትሄ ሳያገኝ ከቀጠለ አገሪቷን ውስብስብ ወደ ሆነ ችግር ሊመራት እንደሚችል ባለሙያው ይመለክታሉ። ""ሰው በኢኮኖሚ ሲዳከም ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ይሰደዳል። እንደዚህ ዓይነት ስደት ደግሞ በከተሞች ላይ ማህበራዊ ቀውስን ያስከትላል። የሚበላው ያጣ ሕብረተሰብ ደግሞ ወደ ተቃውሞ እና ሽብር ይሄዳል። ይህ ደግሞ አሁንም ምልክቱ እየታየ ነው"" ብለዋል። የሥራ ማጣት፣ የኑሮ ውድነት እና ሌሎች ምክንያቶች ችግሮች፣ መጀመሪያውኑ አሁን ካለንበት አዙሪት ውስጥ እንዳንወጣ ያደርጉናል የሚል ስጋት እንዳላቸው ጨምረው ይናገራሉ። የኑሮ ውድነትን ጨምሮ ለበርካታ የአገሪቱ ችግሮች መነሻ የሆነው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት የመጀመሪያው ምርጫ መሆን እንዳለበት ዶ/ር ጉቱ ያመለክታሉ። ""ሰላም ከሌለ ኢንቨስትመንት የለም፣ ወደ ውጪ መላክ የለም፣ ምርትን አጓጉዞ ማከፋፈል የለም። ሰላም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መኖር ያለበት ጉዳይ ነው። ለዚህ ደግሞ መንግሥትና ሌሎች ድርጅቶች አብረው ሆነው መወያየት አለባቸው። ግጭት ከሁሉም ወገን መቆም አለበት"" ሲሉ ይመክራሉ። የውጪ ምንዛሬ ላይ በፍጥነት ማስተካከያ መደረግ አለበት የሚሉት የምጣኔ ኃብት ባለሙያው፣ በዚህ ሁኔታ አገሪቱ ከቀጠለች አስቸጋሪ የምጣኔ ኃብት ቅርቃር ውስጥ ልትገባ እንደምትችል ገልፀዋል። ብር የመግዛት አቅሙ ከቀን ወደ ቀን መቀነሱ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም እንዳለበትም ይመክራሉ። አሁን ያለው የውጪ ምንዛሬ ከዚህም ባነሰ በ30 እጅ ወደ ኋላ መመለስ አለበት ይላሉ። አሁን የብርን ዋጋ እንዲወርድ ማድረግ በኢንቨስትመንትም ሆነ በውጪ ንግድ አንጻር ለኢትዮጵያ የሚያመጣው ፋይዳ የለውም ብለዋል። የአገሪቷን ኢኮኖሚ እንዲያገግም ለማድረግ፣ የባህልና ማህበረሰባዊ እንቅስቃሴ ማካሄድ አለበትም የሚሉት ዶ/ር ጉቱ፣ የህዝቦች የሥራ ባህልም ላይ መሻሻል መደረግ አለበት በማለት ሃሳባቸውን ያጠናቅቃሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-56136264 +sports ማኔ፣ ኬሲ. . . የአምስቱ ቀዳሚ አፍሪካውያን ተጫዋቾች ዝውውር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ወደ ሁለት ቢሊዮን ፓውንድ የሚጠጋ ገንዘብ አውጥተዋል። እንደዚህም ሆኖ ሊጉ ከኮከቦቹ አንዱ የሆነውን ሳዲዮ ማኔን አጥቷል። የዝውውር እንቅስቃሴው ከኮቪድ በፊት ወደ ነበረበት ተመልሷል። ስም ካላቸው ዝውውሮች በተጨማሪ ብዙ ክለቦች የክፍያ ክብረ ወሰናቸውን ሰባብረዋል። በዝውውር መስኮተቱ የመጨረሻ ቀን ፒየር-ኤሜሪክ ኦባሚያንግ ወደ ለንደን መመለሱን አረጋግጧል። በባርሴሎና ከነበረው የስድስት ወራት ቆይታ በኋላ ቼልሲን ተቀላቅሏል። የዝውውር መስኮቱ ተጠናቋል። ተጫዋቾች ለአዳዲስ ቡድኖቻቸው መፋለም ጀምረዋል። ዛሬ አምስቱን የአፍሪካ ትልልቅ ተጨዋቾችን ዝውውር እንመልከት። የማኔ ከሊቨርፑል ወደ ባየር መዛወሩ በሴኔጋላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ላይ ጫና ፈጥሮ ነበር። አሁን ለለባሎንዶር ዕጩ ለሆነው ተጫዋች ነገሮች ፈር እየያዙ ይመስላል። ጀርመናዊው ጋዜጠኛ ራፋኤል ሆኒግስቴይን ለቢቢሲ እንደተናገረው ባየርን “ጥሩ ዝውውር ለማከናወን ከፍተኛ ጫና ገጥሞት ነበር።” የ30 ዓመቱ ተጫዋች ወደ ቡንደስ ሊጋው ማቅናቱ ደረጃውን ዝቅ አያደርገውም ይላል። በየካቲት ወር የአፍሪካ ዋንጫን ያነሳው ማኔ በመጀመሪያዎቹ ሰባት ጨዋታዎች አምስት ግቦችን በማስቆጠር ምላሽ ሰጧል። በመጀመሪያዎቹ 4 የቡንደስሊጋ ጨዋታዎች ተጨማሪ ጎሎችን ቢያስቆጥርም ተሰርዘውበታል። ሮበርት ሌዋንዶውስኪን እንዲተካ ስለሚጠበቅ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ይቆያል። ፖላንዳዊው በ374 የባየር ሙኒክ ጨዋታዎች 344 ጎሎችን አስመዝግቧል። የሴኔጋል አምበል ካሊዱ ኩሊባሊ ከብዙዎቹ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ ቆይቷል። በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው ተከላካዩ በመጨረሻም ማረፊያው ቼልሲ ሆኗል። በለንደኑ ክለብ የአራት ዓመት ውል ፈርሟል። ቼልሲ ከቶተንሃም ጋር 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ሲለያይ የ31 ዓመቱ ተጫዋች በሜዳቸው ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ጎል አስቆጥሯል። ከናፖሊ የመጣው ተጫዋች በሊድስ 3 ለ 0 ሲሸነፉ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። አንጋፋው ቲያጎ ሲልቫ፣ አዲስ ፈራሚዎቹ ዌስሊ ፎፋና እና ማርክ ኩኩሬላ ጋር እንዴት ተጣጥሞ ውጤታማ እንደሚሆን በጉጉት ይጠበቃል። ከሁለት ዓመት በፊት ባሲ በሌስተር ሲቲ ተጠባባቂ ቡድን ውስጥ ነበር። አሁን አያክስን ከተቀላቀለ በኋላ በቻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታው ለማከናወን እየተዘጋጀ ነው። የ22 ዓመቱ ናይጄሪያዊ ያለፈው የውድድር ዓመት የዩሮፓ ሊግ ጉዞ ድንቅ ነበር። ከሬንጀርስ ጋር አስከ ፍጻሜው መጓዝ ችሏል። ዋንጫውን በኢንትራክት ፍራንክፈረት መነጠቃቸው ይታወሳል። ተከላካዩ የኔዘርላንድን ሕይወቱን በአሳዛኝ መልኩ ጀምሯል። በሱፐር ካፕ በፒኤስቪ አይንድሆቨን 5 ለ 2 ተሸንፈው ዋንጫውን አጥተዋል። ቡድኑ ከዚያን በኋላ ያደረጋቸውን ሦስት የኤርዲቪዜ ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፏል። ያለፈው የውድድር ዘመን ባሲ ምን ማድረግ እንደሚችል ያሳየ ነው። አያክስ ትልልቅ ክለቦች የሚመኟቸውን ተጫዋቾች ለማብቃት እና ለማሻሻል ጥሩ ቦታ ነው። ኬሴ ከኤሲ ሚላን ወደ ባርሴሎና በነጻ ነው የተዘዋወረው። ይህም በአይቮሪ ኮስታዊው ተጫዋች በሜዳም ሆነ ከሜዳ ውጪ ፈተና ፈጥሮበታል። ምክንያት ከተባለ ደግሞ የስፔኑ ኃያላን ቡድኖች የገንዘብ ችግር ነው። የ25 ዓመቱን ተጫዋች ቡድኑ ማስፈረሙን ለማረጋገጥ የውድድር ዘመኑ ማስጀመሪያ ዋዜማን መጠበቅ ከነበረባቸው የባርሳ ፈራሚዎች አንዱ ነበር። የመጫወት ፈቃድ ያገኘበትን ወረቀት ያገኘው ከራዮ ቫልካኖ ጨዋታ ትንሽ ቀደም ብሎ ነው። በተቀያሪ ወንበር ላይ የጀመረው አማካዩ ከጋቪ፣ ፔድሪ ወይም ሰርጂዮ ቡስኬትስ አንዱን ለማስቀመጥ ይፎካከራል። ባለፉት አራት ጨዋታዎችም ተቀያሪ ወንበር ላይ ለመቀመጥ ተገዷል። የመሐል አማካዩ የጨዋታ ዘመኑን በአታላንታ ጀመረ። እአአ በ2019 ሳን ሲሮ ያቆየውን ቋሚ ዝውውር ከማጠናቀቁ በፊት በሚላን ሁለት የውሰት ዓመታትን አሳልፏል። ከሮሶነሪዎች ጋር ባለፈው የውድድር ዓመት የሴሪአውን ዋንጫ እንዲያነሳ አስችሎታል። የቼልሲ በዝውውር መስኮቱ የመጨረሻ ቀን ፊቱን ወደ ፒየር-ኤምሪክ ኦባሚያንግ ማዞሩ ለሁሉም አካላት ጥሩ ይመስላል። ግን ጋቦናዊው አጥቂ በቦርሺያ ዶርትሙንድ ለቶማስ ቱሄል የተሳካለትን ያህል ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል? ቱሄል የዶርትሙንድ አሰልጣኝ እያሉ ነበር የፊት አጥቂውን ወደ መሐል አጥቂነት የቀየሩት። ውጤቱ እአአ በ2018 ኦባሚያንግ በ56 ሚሊየን ፓውንድ ወደ መድፈኞቹ እንዲዛወር እገዛ አድርጓል። የ33 ዓመቱ ተጫዋች በነበረው አለመግባባት በጥር ወር ከሰሜን ለንደኑ ቡድን ለቅቆ ወደ ካታላኑ ክለብ አመራ። ለባርሴሎና በ24 ጨዋታዎች 13 ጎሎችን አስቆጠረ። በኋላም በ10.3 ሚሊየን ፓውንድ ወደ ቼልሲ ተዛወረ። የኦባሚያንግ የፕሪሚየር ሊግ ልምድ ስላለው የተከፈለው ዋጋ ጥሩ ነው። ዋናው ጥያቄ ግን ሮሜሉ ሉካኩ እና ቲሞ ወርነር የወደቁበትን ስፍራ እሱ ይሳካት ይሆን የሚለው ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cg3187dvd0wo +sports እውቁ የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ቱጃር 'ደላላ' በሞት ተለየ """ሚኖ"" በሚለው በመጀመሪያ ስሙ የሚጠራው እውቁ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ወኪል ሚኖ ራዮላ በ54 ዓመቱ ሕይወቱ አልፏል። የሆላንድ እና ጣሊንያን ጥምር ዜግነት ያለው ሚኖ፤ እንደ የዶርትመንዱ የፊት መስመር ተጫዋች ሃላንድ፣ የማንችስተር ዩናይትዱ ፖል ፖግባ፣ ዝላታን ኢብራሂሞቪች፣ ሄንሪክ ሚኪታሪያንና ዴ ሊት የመሳሰሉ ተጨዋቾች ወኪል ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ሚኖ እውቅ የተጫዋቾች ወኪሎችን የሚወክለው 'ፉትቦል ፎረም' ፕሬዝደንት ነበር። ሕልፈተ ሕይወቱን ተከትሎ፤ 'ሚኖ ሁሌም ይናፈቃል' ሲሉ የሚኖ ቤተሰብ መግለጫ አውጥተዋል። ሚኖ ማን ነበር? ጣልያን ተወልዶ በኔዘርላንድስ ሃርለም ከተማ እንዳደገ የሚነገርለት ራዮላ ሁሉም የሚስማሙለት 'ምርጥ ደላላ' ነው። በልጅነቱ አባቱ በከፈቱት ሬስቶራንት ውስጥ ደፋ ቀና ብሎ አስተናግዷል። በጎንዮሽ ደግሞ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በሕግ ተመርቋል። ጣልያንኛ፣ ጀርመንኛ፣ ስፓኒሽ፣ ፈረንሳይኛ፣ ፓርቹጊዝ፣ ደች እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፎ የሚናገረው ራዮላ ገና የ18 ዓመት ለጋ ሳለ ነበር ኔዝርላንድስ ውስጥ የሚገኝ አንድ የታዳጊዎች እግር ኳስ ኃላፊ ሆኖ ራሱን ያገኘው። ከዚያም የነብስ ጥሪው ወደሆነው የወኪልነት ሥራ ገባ፤ ለአንድ ወኪል ድርጅት ተቀጥሮ ይሠራም ጀመር። የመጀመሪያው ሥራ የሆነው ደግሞ ተስፋ የሚጣልባቸውን ታዳጊ ደች ተጫዋቾችን ለጣልያኑ ሴሪ ኤ ማሻሻጥ። በታዳጊነታቸው በራዮላ ደላይነት ወደ ጣልያን ብሎም ወደ እንግሊዝ ገብተው ስማቸውን በጉልህ መፃፍ ከቻሉ ተጫዋቾች መካከል ዴኒስ ቤርግካምፕ የሚጠቀስ ነው። ምንም ቢሆን የራሥ የራሥ ነው ያለው ራዮላ ተቀጥሮ ይሠራበት የነበረበትን ድርጅት ለቆ የራሱን የውክልና ድርጅት ሊያቋቁም ቻለ። አሁን ላይ አውሮፓ ውስጥ ከሚጫወቱ እግር ኳሰኞች ስም ያላቸው በርካታ ተጨዋቾች ውክልናቸውን ለሚኖ ሰጥተው ነበር። እንደ አውሮፓዊያኑ 2016 ላይ ራዮላ 'ታሪክ ሠራ'። ያኔ የዓለም ሬከርድ በነበረ ዋጋ ፖል ፖግባን ከዩቬንቱስ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ እንዲዛወር አደረገ፤ ዋጋው ደግሞ 105 ሚሊዮን ዩሮ። ጉደኛው ራዮላ ከዚህ ዝውውር 25 ሚሊዮን ዩሮ ገደማ ወደ ኪሱ እንዳስገባ ይነገራል። ከዚያ በኋላ ወደ አሜሪካዋ የባህር ዳርቻ ግዛት ማያሚ አቅንቶ 9 ሚሊዮን ዩሮ ማፍሰስ ቤተ-መንግሥት የሚያስንቅ መኖሪያ 'መንደር' ሸመተ። ሚኖ ከፈጸማቸው ውድ የተጫዋቾች ዝውውሮች መካከል ፎርብስ እአአ 2018 ላይ ባወጣው ዘገባ ሚኖ 69 ሚሊዮን ዶላር የተጣራ ገቢ ያለው ሲሆን በእርሱ ውክልና ሥራ ያሉ 70 ተጫዋቾች 629 ሚሊዮን ዶላር ሊያወጡ ይችላሉ ሲል አትቷል። ሰውየው ያሻውን ከመናገር ወደኋላ የሚልም አይደለም። በአትንኩኝ ባይነቱ የሚታወቀው ራዮላ በእርሱ ውክልና ሥር ያሉ ተጨዋቾችን የሚተቹ የቀድሞ እግር ኳሰኞችም ሆነ ተንታኞችን በመወረፍ ይታወቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61283418 +politics የኡጋንዳ ምርጫ 2021፡በኡጋንዳ ምርጫ ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ እየመሩ ነው ተባለ "ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ ሐሙስ ጥር 6/2013 ዓ.ም ብሔራዊ ምርጫ አካሂዳለች። በዚህ ምርጫ አገሪቷን ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የመሯት ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒና ሙዚቀኛና ፖለቲከኛው ቦቢ ዋይን ዋነኛ ተፎካካሪ ሆነዋል። በምርጫ ቅስቀሳውም ወቅት ከፍተኛ ሁከትን ባስተናገደችው ኡጋንዳ ከ50 ሰዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል። በምርጫው ሰሞንም ማህበራዊ ሚዲያዎችን ያገደች ሲሆን ከዋዜማውም ጀምሮ ኢንተርኔት ተቋርጧል። የምርጫ ውጤቱ በነገው ዕለት፣ ቅዳሜ የሚገለፅ ይሆናል። በትናንትናው ዕለት በኡጋንዳ በተደረገው ምርጫ ዩዌሪ ሙሴቪኒ የመሪነት ቦታውን ጨብጠዋል ተባለ። በዛሬው ዕለት የምርጫ ኮሚሽኑ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤቱ ይፋ ባደረገበትም ዕለት እስካሁን ባለው ቆጠራ የመጪውን ፕሬዚዳንትነት ቦታ ሙሴቪኒ እየመሩ መሆኑን አሳውቋል። ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ 1 ሚሊዮን 536 ሺህ 205 ድምፅ (65.02 በመቶ) በማግኘት እየመሩ ሲሆን፣ ዋነኛ ተቃናቃኙ ሮበርት ክያጉላንያ በመድረክ ስሙ ቦቢ ዋይን በበኩሉ 647 ሺህ 146 ድምፅ (27.39) በማግኘት እየተከተለ መሆኑንም የምርጫ ኮሚሽኑ መረጃ ያሳያል። ውጤቱ የተሰበሰበው ከ8 ሺህ 310 የምርጫ ጣቢያዎች ነው። በአጠቃላይ በአገሪቱ 34 ሺህ 684 የምርጫ ጣቢያዎች አሉ። ቦቢ ዋይን በበኩሉ ትናንትና በተደረገው ምርጫ ከፍተኛ ማጭበርበርና በግጭቶች የተሞላ ነው ቢልም ውንጀላውን አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የኡጋንዳ መንግሥት በበኩሉ ምርጫው ሰላማዊ ነበር ብሏል። በትናንትናው ዕለት ብሔራዊ ምርጫዋን ባካሄደችው ኡጋንዳ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ቢዘጋም የምርጫ ውጤቶቹ ወደ ዋናው ማዕከል እየተላኩ እንደሆነ የአገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል። የኮሚሽኑ ኃላፊ ሲሞን ብያባካማ የምርጫውን ውጤትም ለማስተላለፍ ሌሎች ውስጣዊ መንገዶችን እየተጠቀሙ እንደሆነ ቢናገሩም ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥበዋል፥ ""የምርጫውን ውጤት ለመላክ ኢንተርኔት እየተጠቀምን አይደለም። የራሳችንን ስርአት እየተጠቀም ነው። አትጨነቁ፣ ኢንተርኔቱ ቢቋረጥም ውጤቱ መድረሱ አይቀርም፤ ይፋም ይሆናል"" በማለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ዛሬ ጥዋትም ኮሚሽኑ ከ330 የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ ሰበሰብኩት ባለው መረጃ መስረት የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ያሳወቀ ሲሆን በዚህም መሰረት አገሪቷን ከሶስት አስርት አመታት በላይ የመሯት ዩዌሪ ሙሴቪኒ እየመሩ ነው ማለቱንም ደይሊ ሞኒተር ጋዜጣ አስነብቧል። አገሪቷ በአጠቃላይ 34 ሺህ 684 የምርጫ ጣቢያዎች አሏት። በኡጋንዳ ህግ መስረት ምርጫው በተካሄደ በ48 ሰዓታት ውስጥ የምርጫው ኮሚሽን ከሁሉም ግዛቶች ���ምፆችን ሰብስቦ ውጤቱን ማሳወቅ አለበት። የፓርላማ መቀመጫ ያሸነፉ አባላት በተለያዩ ግዛቶች በሚገኙ ማዕከላት ዝርዝራቸው የሚገለፅ ሲሆን በሌላ በኩል የፕሬዚዳንትነቱ አሸናፊ በመዲናዋ ካምፓላ በሚገኘው ማዕከል ይፋ ይሆናል። ሮበርት ክያጉላንይ ወይም በመድረክ ስሙ ቦቢ ዋይን ተብሎ የሚታወቀው ሙዚቀኛና ፖለቲከኛ የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ዋነኛ ተቀናቃኝም ሆኖ ወጥቷል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ባለስልጣናቱ የትኛውንም ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲሁም ቪፒኤኖችም እንዲዘጉ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55672696 +health የአፍሪካ አገራት ግዜው ያለፈበት የኮቪድ ክትባትን እንዳያስወግዱ ተጠየቁ "የዓለም ጤና ድርጅት የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈ የኮሮናቫይረስ ክትባት በእጃቸው የሚገኝ የአፍሪካ አገራት ክትባቱን ከማስወገድ እንዲቆጠቡ አሳሰበ። አገራቱ ቀጣይ መመሪያዎች እስኪሰጡ ድረስ የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶችን ይዘው እንዲያቆዩ ተጠይቀዋል። ማላዊ እና ደቡብ ሱዳን በሚያዚያ ወር አጋመሽ ላይ 70 ሺህ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ክትባቶችን ለማስወገድ ማሰባቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው የዓለም የጤና ድርጅት ይህን ማሳሰቢያ የሰጠው። ማላዊ 16 ሺህ የአስትራ ዜኔካ ብልቃጦችን፤ ደቡብ ሱዳን ደግሞ 59 ሺህ ተመሳሳይ ብልቃጦችን ለማስወገድ አስበዋል። የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ (ሲዲሲ) ግን ምንም እንኳን ክትባቶቹን ለመጠቀም የተቀመጠው ግዜ ቢያልፍም ክትባቶቹ ጥቅም ላይ መዋል እንደሚችሉ ገልጾ ነበር። በዓለማችን ያሉ ሌሎች ክትባቶች ከተመረቱ ጀምሮ እስከ 36 ወር ድረስ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆን የኮቪድ ክትባት ግን አዲስ መሆኑን ተከትሎ ነው ለምን ያህል ግዜ ውጤታማ ሆኖ መቆየት እንደሚችል ገና ያልተለየው። እነዚህ ግዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶች ጥቅም ላይ የማዋል ውሳኔ የሚሰጠው በብሔራዊ የመድሃኒት ተቆጣጣሪዎች እንደሆነ የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ ርሆዳ ኦዲያምቦ ታብራራለች። የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ዋና ዳይሬክተር ማክሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫቸው ላይ፤ ""ለአባል አገራት የማቀርበው ጥሪ ቢኖር፤ እኛ ክትባቱን አስተባብረን ለማቅረብ የራሳችንን ድርሻ እየተወጣን ነው፤ እናንተም ክትባቶቹን በመጠቀም የድርሻችሁን ተወጡ"" ሲሉ ተማጽነዋል። የኮሮናቫይረስ ክትባትን በአፍሪካ በሚፈለገው ፍጥነት እስካሁን ማድረስ ያልተቻለ ሲሆን፤ ለዚህም የአቅርቦት እጥረት እንዲሁም ስለ ክትባቱ ጥርጣሬዎች መኖራቸው እንደ ምክንያት ይነሳሉ።" https://www.bbc.com/amharic/56855661 +health በአውስትራሊያ አረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት በየሳምንቱ 50 ወሲባዊ ጥቃቶች ይደርሳሉ ተባለ "በአውስትራሊያ የሚገኙ የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት ውስጥ በየሳምንቱ አምሳ ያህል ወሲባዊ ጥቃቶች እንደሚደርሱ ከሰሞኑ ብሔራዊ አጣሪ ኮሚቴ ይፋ አድርጓል። ለሁለት አመታት ያህልም በአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶችንና መንገላቶችን ይፋ ባደረገበት መረጃ ነው ሮያል ኮሚሽን ይህንንም ያካተተው። መርማሪዎቹ እንዳሉት በጎሮጎሳውያኑ 2018-2019 ጊዜ 2 ሺህ 520 አረጋውያን ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። ""ይህ ሁኔታ ብሔራዊ እፍረት ነው"" ብለውታል የምክር ቤት አባሉ ፒተር ሮዝን ኪው ሲ ለአጣሪው ኮሚቴ ""ቁጥሮቹ የሚረብሹትን ያህል እነዚህን መረጃዎች ያገኘው የመንግሥት አካል ክትትትልና ቁጥጥር አለማድረጉ የበለጠ የከፋ ነው"" ብለዋል። በአረጋውያኑ የእንክብካቤ ማዕከል ላይ የሚታየው ቸልተኝነት ከፍተኛ ውዝግብና ጥያቄ ያስነሳ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በአውስትራሊያ በኮሮናቫይረስ ከሞቱት አብዛኛዎቹ በአረጋውያን ማዕ���ል የሚገኙ ናቸው። አውስትራሊያ በኮሮናቫይረስ ሞተዋል ብላ ከመዘገበችው 903 ሰዎች መካከል 75 በመቶ በነዚህ ማዕከላት የሚገኙ ናቸው። በእነዚህ ማዕከላት ላይ የሚደርሱ ወሲባዊ ጥቃቶች የቀደመ ስጋት ሆነው የቆዩ መሆናቸውን ያመኑት ፒተር ሮዝን ቁጥሩም በአገሪቱ ያሉትን 13-18 በመቶ ጥቃት እንደደረሰባቸው ያሳያል። በርካቶች በዕድሜያቸው የበለፀጉ ወይም ተጋላጭ የሆኑ ቤተሰቦቻቸውን በአረጋውያኑ ማዕከል የሚያስገቡት ደህንነታቸው ይጠበቃል በሚል ዕምነትም እንደሆነም የምክር ቤት አባሉ አስረድተዋል። ""በአረጋውያን ማዕከላት የሚገኙ ሰዎች ከማህበረሰቡ በበለጠ ለወሲባዊ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸው ተቀባይነት የለውም"" ብለዋል ፒተር ሮዝን በአጠቃላይ መርማሪዎች እንደሚገምቱት 32 ሺህ ያህል ወሲባዊ፣ አካላዊና የስነልቦናዊ ጥቃቶች መድረሳቸውን ነው። ይህም ቁጥር በአንድ አመት ያህል እንደደረሰ መረጃው ጠቁሟል። ወሲባዊ ጥቃቱ እንክብካቤ በሚሰጡ ግለሰቦች እንዲሁም እዛው ባሉ ነዋሪዎች እንደሚፈፀምም መረጃው ይፋ አድርጓል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54637492 +politics ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ 44 የአማፂያን ታጣቂዎችን መግደሏን አሳወቀች የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የጦር መኮንኖች መዲናዋ ባንጉይን ከበው ነበር ያላቸውን 44 የአማፂያን ታጣቂዎችን መግደላቸውን አሳውቀዋል። አማፂያኑ በቅርቡ የተመረጡትን ፕሬዚዳንት ፎስ አርቸንግ ቱዋዴራ በኃይል ለመገልበጥ በሚል ከተማዋን እንደከበቡ ተነግሯል። የመንግሥት ቃለ አቀባይ ለፈረንሳዩ ዜና ወኪል እንደተናገሩት ወታደሮቹ ከሩሲያ ልዩ ኃይል ጋር በመተባበር ቦዳ የተባለችውን ከተማ መቆጣጠር እንደቻሉ ነው። ከመንግሥት በኩል የሞተ ሰው ባይኖርም ከአማፂያኑ በኩል ግን ከቻድ፣ ሱዳንና ፉላኒ ብሔር የተውጣጡ ቅጥር ወታደሮች እንደተገደሉ መንግሥት በፌስቡክ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ከመንግሥት የወጣውን መረጃ የሚያጣራ ነፃ አካል አልተገኝም። አማፂው ቡድን ሶስት አራተኛውን የአገሪቱን ክፍል በቁጥጥር ስሩ ያለ ሲሆን በቅርቡም ቡድኑን ለመታገል በሚል የአገሪቱ መንግሥት ለአስራ አምስት ቀናት የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተላልፏል። በአገሪቱ ያሉ ስድስት ከፍተኛ ታጣቂ ቡድኖች በታህሳስ ወር ኃይላቸውን በማጣመር 'ኮኦሊሽን ኦፍ ፓትሪየትስ ፎር ቸንጅ' የሚባል አንድ ቡድን መስርተዋል። ነገር ግን መዲናዋ ከ12 ሺህ በሚበልጡ ከተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ የተውጣጡ ወታደሮች፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወታደሮችና የሩሲያና ሩዋንዳ ልዩ ኃይሎች በመተባበር በከባድ ጦር መሳሪያ እየጠበቋት ይገኛሉ። የተባበሩት መንግሥታት አማፂ ቡድኖቹ ዋና መዲናዋን ለመቆጣጠር በሚል ከከተማዋ ጋር የሚያገናኙ ሶስት ዋና መንገዶችን ዘግተዋል በማለት አስጠንቅቋል። አገሪቱ ባለፈው ወር ባደረገችው ምርጫ ለሁለተኛ ጊዜ ያሸነፉት ፕሬዚዳንት ፎስ አርቸንግ ቱዋዴራ ማሸነፋቸውን አማፂው ቡድን አይቀበለውም። ከዚህም ጋር ተያይዞ በግጭት እየተናጠች ባለችው የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿም ወደ ጎረቤት አገር ተሰደዋል። https://www.bbc.com/amharic/55807194 +business ሶማሊያ በዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ከፍተኛ የብድር ስረዛ ተደረገላት "የዓለም ባንክና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ሶማሊያ ብድር እንዲቃለልላት የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰዷን ማስታወቃቸውን ተከትሎ የአበዳሪዎችን ድጋፍ አግኝታለች። እንደ መግለጫው ከሆነ ሶማሊያ አጠቃላይ ብድሯ ከ5.2 ቢሊዮን ዶላር በከፍተኛ ደረጃ ዝቅ ይደረግላታል። ይህም የሚሆነው በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ነው። በሶማሊያ የዓለም ባንክ ተወካይ ሁግ ራይደል ለቢቢሲ እንደገለጹት የሶማሊያን የብድር መጠን ለማቃለል ከሚወሰደው የተቀናጀና ሰፊ ሂደት መካከል ይህ የመጀመሪያው እርምጃ ነው ብለዋል። ሶማሊያ ከ30 ዓመት በፊት ከነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ጀምሮ ብድሯን ከፍላ አታውቅም፤ በዚህ ምክንያትም ሶማሊያ ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት እንደገና ብድር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ከባድ አድርጎባታል። አሁን ግን ይህ የብድር ስረዛ ስለተደረገላት መንግሥት በመላ አገሪቱ ለሚያከናውናቸው አገልግሎቶች ብድር ለመጠየቅ ያስችለዋል። የሶማሊያው ጠቅላይ ሚንስትር ሃሰን አሊ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ""ይህ ከነጻነት በኋላ ያገኘነው ሁለተኛው ነጻነት ነው"" ብለዋል፤ ከቅኝ ግዛት ነጻ የወጡበትን ሁኔታ በማጣቀስ። ""አሁን ያለንበት ጊዜ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ በመሆኑ በአበዳሪ ተቋማቱ በተወሰደው እርምጃ መሰረት ልናገኘው የምንችለው የበጀት ድጋፍ በመላ አገራችን ለሕዝቡ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ እገዛ ያደርጋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁላችንንም እያሸበረን ያለውን ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት ይረዳናል"" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። እንደ ሶማሊያ ባለ በሽብርተኞች በተደጋጋሚ ጥቃት ለሚደርስበት አገርም ሽብርተኝነትን ማሸነፍ የሚቻለው ምጣኔ ሃብትን በማሳደግ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ወጣቶችንና ሴቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። አክለውም ፍትሃዊና ግልጽ የሃብት ክፍፍል በመፍጠር ሽብርተኝነትን ማሸነፍ ስለሚቻል የብድር ቅነሳ ውሳኔው ለሶማሊያ ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚያመጣ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር ሃሰን ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-52046300 +business አዲሱ የኬንያ ፕሬዝደንት መሠረታዊ ድጎማዎችን አነሱ "በምርጫ ቅስቀሳቸው የመደበኛ ኬንያዊያንን ህይወት አሻሽላለሁ፣ የስራ ዕድል ፈጥራለሁ እና የኑሮ ውድነትን እቀንሳለሁ በማለት ቃል የቡት ዊልያም ሩቶ፣ የነዳጅ ድጎማን ማንሳታቸው በርካታ ኬንያውያንን እያነጋገረ ነው። በመላው ዓለም በተለያዩ ምክንያቶች እየናረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ዜጎች እንዲቋቋሙ በማሰብ መንግሥታት ድጎማዎችን እያስተዋወቁ ባሉበት በዚህ ወቅት አዲሱ የኬንያ መሪ ግን ቀዳሚ ባደረጉት የፖሊሲ ማስተካከያ የነዳጅ ድጎማን አንስተዋል። በዚህ ኬንያውያንን ባስገረመ ውሳኔ የነዳጅ ዋጋ በአገሪቱ ታሪክ ከፍተኛው የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ እንዲደርስ የሚያደርግ ነው። በርካቶች በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ቅሬታቸውን እየገለጹ ሲሆን የኢኮኖሚ ተንታኞች በበኩላቸው ምርጫውን እጅግ ጠባብ በሆነ ልዩነት ያሸነፉት ዊልያም ሩቶ ገና በስልጣን ዘመናቸው መጀመሪያ ላይ ድጋፍ ሊያሳጣቸው የሚችል ውሳኔ ነው ያሳለፉት ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የናይሮቢ ነዋሪ የሆኑት ጆን ማና ""ከወራት በፊት ወደ ስራ ለመሄድ መኪና መንዳት አቁሜያለሁ። አሁን ደግሞ ማታቱዎች (የሕዝብ ታክሲዎች እና አውቶብሶች) የታሪፍ ጭማሪ አድርገው ይህንንም ጉዞ የበለጠ ውድ ይሆንብኛል ብዬ እየሰጋሁ እገኛለሁ’’ ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፕሬዚደንት ሩቶ በምርጫ ቅስቀሳቸው የመደበኛ ኬንያውያንን ህይወት አሻሽላለሁ፣ የስራ ዕድል ፈጥራለሁ እና የኑሮ ውድነትን እቀንሳለሁ በሚል ቃል የገቡ ሲሆን ለዚህም ራሳቸው ከዝቅተኛ ኑሮ ተነስተው አሁን ያሉበት ደረጃ መድረሳቸውን በማጉላት አስተጋብተዋል። በምርጫ ዘመቻው ከገቡት ቃል ውስጥ አንዱ የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ፣ በነዳጅ ላይ የሚጣለውን ግብር ማንሳት እና ይህንንም ተከትሎ የመሰረታዊ ሸቀጦችን ዋጋ ዝቅ ማድረግ ነበር። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ በበዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ንግግር የድጎማ ፕሮግራሙ ማብቃቱን አስታውቀው ድጎማው ቢቀጥል እስከ መጪው ሰኔ ወር ድረስ ኬንያ 2.3 ቢሊየን ዶላር ታወጣ እንደነበር ተናግረዋል። ""ይህ ከጠቅላላው የአገሪቱ የመንግሥት የልማት በጀት ጋር ሲነጻጸር እኩል ነው"" ያሉት ፕሬዘዳንቱ ድጎማው የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ የታለመለትን ዓላማ ማሳካት አልቻለም ብለዋል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ድጎማ ለኬንያ ዘላቂነት የሌለው መፍትሄ ብሎም ለአጭበርባሪዎች ዕድል ከመስጠት ባሻገር ለመደበኛው ዜጋ ያን ያህል ፋይዳ እንደሌለው ይናገራሉ። ነገር ግን የነዳጅ ዋጋ በ13 በመቶ ጨምሮ 1.49 ዶላር ወይም 78 ብር መግባቱ ጫና መፍጠሩ አይቀሬ ነው ሲሉ ይስማማሉ። ""ተፅዕኖው በእርግጠኝነት መሰማቱ አይቀርም። ምክንያቱም የሁሉም ነገር ዋጋ ከነዳጅ ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ መጨመሩ ስለማይቀር’’ ሲሉ ተንታኙ ኸርማን ማንዮራ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንዲህ ያለ ትልቅ ውሳኔ ገና አዲስ መንግሥት ሳይቋቋም በፊት መደረጉ አላስፈላጊ ብሎም “ከታሰበበት የመንግሥት ውሳኔ ይልቅ የአንድ ሰው ውሳኔ እንዲመስል አድርጓል’’ ሲሉም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ሩቶ የካቢኔ አባላቶቻቸውን አዋቅረው ብሎም የፓርላማውን ይሁንታ የሚሹ የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውን አላሾሙም። ተንታኙ ጃቫስ ቢጋምቦ በበኩላቸው ፕሬዘዳንቱ ጉዳዩን በቅድሚያ ለኬንያውያን ማስረዳት ብሎም የድጎማውን ገንዘብ በምን ላይ ሊያውሉት እንዳሰቡ ለማስረዳት ተጨማሪ ጊዜ ወስደው እርምጃውን ህዝባዊ ድጋፍ እንዲያገኝ ማድረግ ነበረባቸው ብለዋል። ፕሬዘዳንት ሩቶ የኬንያውያን የዕለት ተዕለት ተቀዳሚ ምግቦችን ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ የሚውለውን  የበቆሎ ዱቄትዋጋ በግማሽ የቀነሰውን ድጎማ ግዜው ማብቃቱን ተከትሎ ለተጨማሪ ግዜ አላራዝምም ብለዋል። ኬንያ በከፍተኛ እዳ ውስጥ የምትገኝ አገር ስትሆን ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ጋር ባላት የብድር ውል መሠረት ድጎማውን ማንሳቷ አስፈላጊ ተብሎ የተቀመጠ ነበር። ""እነዚህ ድጎማዎች ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች ይልቅ ከፍተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች የበለጠ የማገዝ አዝማሚያ አላቸው"" ሲሉ የአይኤምኤፍ የአፍሪካ ዳይሬክተር አበበ ሥላሴ ተናግረዋል። ፕሬዚደንት ሩቶ በናፍጣ እና ኬሮሲን ላይ አነስተኛ ድጎማ አድርገዋል። ናፍጣ በአብዛኛው የሕብ ትራስፖርት አግልግሎት ሰጪዎች እና ፋብሪካዎች ጥቅም ላይ ይውላል። እንዲሄም ኬሮሲን በተለይም የገጠር ቤተሰቦች ምግብ ለማብሰል እና በምሽት ብርሃን ለማግኘት የሚጠቀሙበት ነው። በነዳጅ እና በቆሎ ዱቄት ላይ የሚደረገው ድጎማ ተቀንሶ በምትኩ የማዳበሪያ ወጪን ለመቀነስ መታሰቡም ይፋ ሆኗል። በኬንያ የማዳበሪያ ዋጋ፣ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት ከከፈተች በኋላ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። ኬንያ ራሷን ለመመገብ የሚያስችል በቂ በቆሎ ስለማታመርት በአገር ውስጥ ምርት ፍላጎትን ማሟለት ካስፈለጋት አገራዊ ምርትን ማሳደግ ይጠበቅባታል። በኬንያ አርሶ አደር ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ ያላቸው አዲሱ ፕሬዘዳንት ሩቶ ""የኑሮ ውድነት ዝቅ የማድረግ ስትራቴጂያችን አምራቾችን በማብቃት ላይ የተመሰረተ ነው"" ብለዋል። በመሆኑም አዲሱ አስተዳደር ከመጪው ሰኞ ጀምሮ 1.4 ሚሊዮን ባለ 50 ኪሎ ግራም ማዳበሪያ የያዙ ከረጢቶችን አሁን ከሚሸጥበት 54 ዶላር ወደ 29 ዶላር ዝቅ ለማድረግ ማሰባቸውን ፕሬዝደንቱ ይፋ አድርገዋል። ፕሬዝደንቱ የወሰዷቸው እነዚህ ውሳኔዎች በሚቀጥሉት ወራት የኑሮ ውድነቱን ጋብ ካላደረጉት የሩቶ ተቀባይነት ላይ ትልቅ ጫና ሊያመጣ እንደሚችል ተንታኙ ቢጋምቦ አስጠንቅቀዋል። ""በሚቀጥሉት ስድስት እና ስምንት ወራት ውስጥ የሚደረጉት ውሳኔዎች የኑሮ ውድነቱን ካልቀነሱት የዜጎች ደስታ ብዙም አይቆይም"" ሲሉ ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c2j41x59zpko +sports የሳዑዲ አረቢያ ድል በአርጀንቲና ላይ፣ የዓለም ዋንጫው ቀዳሚ ያልተጠበቀ ውጤት በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ይህ ነው የሚባል የጎላ ስም የሌላት ሳዑዲ አረቢያ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለፍጻሜው ከሚጠበቁ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነውን የአርጀንቲናን ቡድን ድል አድርጋለች። እሁድ ዕለት በተጀመረው በዚህ የዓለም ዋንጫ ከማይጠበቁ ክስተቶች ሁሉ ቀዳሚ በሆነ ውጤት፣ የሳዑዲ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከመመራት ተነስተው የሁለት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ባለቤት የሆነችውንና ሜሲን ጨምሮ በባለ ዝናዎች የተዋቀረውን የአርጀንቲናን ቡድን አሸንፈዋል። ሳዑዲዎች በሉሳይል ስታዲየም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታቸው አንድ ለባዶ ከመመራት በመነሳት ሁለት ግቦችን አስቆጥረው የምድብ ሐ መሪነት ቦታን ተቆናጠዋል። በዓለም የእግር ኳስ ደረጃ ላይ 51ኛ የሆነችው ሳኡዲ አረቢያ በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ የተሰጠባትን የፍጹም ቅጣት ምት ሊዮኔል ሜሲ አስቆጥሮ ነው ጨዋታውን እየተመራች የጀመረችው። በአርጀንቲና በኩል በርካታ ግቦችን ለማስቆጠር ተደጋጋሚ ጥረቶች ተደርገው ተጨማሪ ሦስት ግቦችን ማስቆጠር ቢችሉም ዕድለኛ ሳይሆኑ ቀርተው ከጨዋታ ውጪ በመሆናቸው ሳይመዘገቡላቸው ቀርተዋል። የጨዋታው ግማሽ ድረስ አርጀንቲና በአንድ ለባዶ ውጤት መሪ ሆና እረፍት ከተደረገ በኋላ፣ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሮ በ10 ደቂቃ ውስጥ ሳዑዲ ውጤት ቀያሪውን ግብ አስቆጠረች። የመጀመሪያው ግብ በሳሌህ አል-ሼህሪ ሲመዘገብ፣ ተከትሎ ደግሞ ሳሌም አል ዳወሳሪ ያስቆጠራት ግብ ለአርጀንቲና ድንጋጤን ለሳዑዲዎች ደግሞ ፈንጠዝያን አጎናጸፈች። አርጀንቲናዎች በመጀመሪያው ጨዋታቸው ተጨማሪ ግቦችን በማስቆጠር ድልን በእጃቸው አሊያም አቻ ለመውጣት ቢጥሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል። በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ላይ በአሸናፊነት የተመዘገበላት አራተኛ ጨዋታ ብቻ ያላት ሳዑዲ አረቢያ፤ አርጀንቲናን በመርታት ሜክሲኮ እና ፖላንድ ያሉበትን ምድብ አጓጊ አድርጋዋለች። የሊዮኔል ሜሲው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በዚህ ውድድር ለዋንጫ ከሚጠበቁጥ መካከል ሲሆን፣ ቡድኑ ከዓለም ዋንጫ ቀደም ብሎ ባደረጋቸው 36 ጨዋታዎች ምንም ሽንፈት ካለማስተናገዱ በተጨማሪ፣ ባለፈው ዓመት የአህጉራዊው ኮፓ አሜሪካ ባለድል ነው። አርጀንቲና ከአውሮፓውያኑ 1986 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫ ለማንሳት ያላት ተስፋ አሁንም የጨለመ ባይሆንም ከባድ ፈተና ይጠብቃታል። ይህ የዓለም ዋንጫ ለታዋቂው ሊዮኔል ሜሲ የመጨረሻው ሊሆን ይችላል እየተባለ ሲሆን፣ ቡድኑ በሳዑዲ የገጠመውን የሽንፈት ጥላ በመግፈፍ ወደ ቀጣይ ዙሮች አልፎ እንደተጠበቀው ዋንጫ ካነሳ ለሜሴ የክብር ስንብት ይሆንለታል እየተባለ ነው። አሁን ግን ሳዑዲ አረቢያ በምድብ ሐ ከተመደቡት ቡድኖች ሙሉ ሦስት ነጥብ ከአንድ ንጹህ ጎል ጋር በመያዝ መሪ ሆናለች። አርጀንቲና ደግሞ ካለ ነጥብ በአንድ የግብ ዕዳ ለጊዜው ከምድቡ ግርጌ ተቀምጣለች። ቅዳሜ ኅዳር 17/2015 ዓ.ም ሳዑዲ አረቢያ ከፖላንድ፣ አርጀንቲና ደግሞ ከሜክሲኮ ቀጣይ ጨዋታ ያደርጋሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c2vqle7png2o +politics የኢሕዲሪ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ አረፉ "ከሰላሳ ዓመታት በፊት በነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቀድሞው መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማሪያም ምክትል በመሆን የኢሕዲሪ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ፣ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ለ20 ዓመታት ያህል በእስር ቆይተዋል። ቢቢሲ ከቤተሰባ��ው ለመረዳት እንደቻለው ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ የልብ ሕመም የነበረባቸው ሲሆን ለዚህም በአገር ውስጥና በውጪ ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት የነበሩት ፍሰሐ ሕይወታቸው ያለፈው አርብ ሚያዚያ 28/2014 ዓ. ም. እኩለ ሌሊት አካባቢ ሲሆን የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው እሁድ ሚያዚያ 30/2014 ዓ. ም. በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል። ከእስር ከወጡ በኋላ በሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ስላለፉባቸው ሁኔታዎች የሚተርክ ""አብዮቱና ትዝታዬ"" የሚል መጽሐፍ ያበረከቱ ሲሆን፣ በዚህም ""ደርግ በወሰዳቸው በጎ ዕርምጃዎች እንደምደሰት ሁሉ በማወቅ፣ በድፍረት፣ ባለማወቅና በስህተት ለተፈጸሙት ደግሞ ሙሉ ኃላፊነት በመውሰድ በበኩሌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ"" ብለው ነበር። ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ከመጀመሪያው መጽሐፋቸው በተጨማሪ ሁለተኛ መጽሐፍ በማዘጋጀት ላይ እንደነበሩ ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ትግራይ አድዋ ውስጥ የተወለዱት ሌፍተናንት ኮሎኔል ፍሰሐ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአደዋ ንግሥተ ሳባ እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃን አዲግራት ውስጥ በሚገኘው አግአዚ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። በተጨማሪም አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ኮተቤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሩ ሲሆን፣ ከዚያም በኋላ ወደ ሐረር ጦር ትምህርት ቤት ገብተው ከሰለጠኑ በኋላ በክብር ዘበኛ ውስጥ ገብተው በንጉሡ ቤተ መንግሥት ውስጥ ተመድበው አገልግለዋል። ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ወደ አሜሪካ በመሄድ ከፍተኛ ወታደራዊ ሥልጠና ወስደዋል። ከዚህ በሻገርም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት ተከታትለዋል። ንጉሡን ከሥልጣን ያስወገደው ሕዝባዊ አብዮት ሲፈነዳና በደርግ አማካይነት ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ሲመሠረት ከጦር ኃይሉ ተወጣጥተው የአመራርነት ቦታውን ከያዙት የወቅቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል አንዱ ነበሩ። ከዓመታት ቆይታ በኋላ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ሲመሠረት የቀድሞው ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪም ምክትል በመሆን የአገሪቱ ሁለተኛ ሰው ለመሆን በቅተው ነበር። ከአማጺያኑ ጋር ለ17 ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የቆየው አስተዳደራቸው እየተዳከመ መጥቶ ፕሬዝዳንቱ አገር ለቀው ከተሰደዱ በሳምንታት ውስጥ የአማጺያኑ ስብስብ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የኢሕዲሪ መንግሥት ፍጻሜ ሆነ። ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐን ጨምሮ በአገር ውስጥ የተገኙት የቀድሞው መንግሥት ባለሥልጣናት በአገሪቱ ውስጥ በተፈጸሙ ጭፍጨፋዎችና በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ተከሰው ለዓመታት በተካሄደ የፍርድ ሂደት እስር ተፈርዶባቸዋል። ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታም ለ20 ዓመታት በእስር ካሳለፉ በኋላ ከ10 ዓመት በፊት በይቅርታ መለቀቃቸው ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61361343 +business ኢትዮጵያን ጨምሮ ባፈለው ዓመት ኢንተርኔት በመዝጋት የከሰሩ ሃገራት "ባፈለው የፈረንጆቹ ዓመት ኢንተርኔት በመዝጋት የከሰሩ ሃገራትን ዝርዝር ይፋ ያደረገ አንድ ጥናት ""ዓለም በዚህ ምክንያት 8 ቢሊዮን ዶላር ከስራለች"" ብሏል። ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ኢንተርኔትን በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት የዘጉ ሃገራት ቁጥር ከምን ጊዜውም የላቀ ነው ሲል ኔትብሎክ የተባለው አጥኚ ድርጅት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ ላይ እንደተጠቀሰው በተለያዩ ሃገራት 122 ጊዜ ኢንተርኔት የተቋረጠ ሲሆን በጠቅላላ 22 ሺህ ሰዓታትን እነዚህ ሃገራት ያለ ኢንተርኔት አሳልፈዋል ብሏል። ባለፉት 12 ዓመታት ጥናቱ ውስጥ የተካቱት መንግሥታት በሃገር ደረጃ ወይም በክልል ደረጃ ኢንተርኔትን ሆን ብለው አጥፍተዋል፤ ዋነኛው ዓለማው ደግሞ ተጠቃሚውን ፌስቡክ ከመሳሰሉ ከማህበራዊ ድር አምባዎች ለማገድ ነው። ድርጅቱ የኢንተርኔት አዘጋግ ሂደቱን በሁለት ይከፍለዋል። አንደኛው ሙሉ በሙሉ የኢንተርኔቱን ባልቦላ መቁረጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ማሕበራዊ ድር-አምባዎችን ከጥቅም ውጭ ማድረግ ነው። ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ፣ ትዊተር፣ ዩቲዩብ እና መሰል ድር አምባዎች ቢታገዱም ተጠቃሚዎች 'ቪፒኤን' በመጠቀም ሊያገኟቸው ይችላሉ። ጥናቱ ይፋ ባደረገው መሠረት አብዛኛዎች የኢንተርኔት መቋረጦች ከተቃውሞ እና አለመረጋጋት እንዲሁም ምርጫ ጋር የተያያዙ ናቸው። የባልቦላው መዘጋት በተለይ 'በደሃ' ሃገራት በልማዳዊው ገበያ ላይ ያለው ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን ጥናቱ ደርሶበታል። ይህ ማለት ጥፋቱ ጥናቱ ላይ ከተቀመጠው በላይ ሊሆንም ይችላል ማለት ነው። የኢንተርኔት መዘጋቱ የሰው ልጅ የመናገር ነፃነትን የሚገፍ ነው የሚለው ድርጅቱ ኢንተርኔት መዝጋቱ ለበለጠ አመፅ እንደጋበዘ ታዝቤያለሁ ይላል። በዚህ ረገድ መካከለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪቃ ኢንተርኔት በመዝጋት የሚስተካከላቸው አልተገኝም። ከሰሃራ በታች ያሉ ሃገራት ደግሞ ተከታዩን ደረጃ ይእዛሉ። እስያ በሶስተኛ ደረጃ የምትገኝ ሲሆን የደቡብ አሜሪካ ሃገራት በአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ድርጅቱ ኢንተርኔት የዘጉ ሃገራትን ዝርዝር፤ ያጡትን ገንዘብ [በዶላር] እንዲሁም የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ቁጥር ከዚህ እንደሚከተለው አስቀምጧል። ዚምባብዌ፣ ሞሪታኒያ፣ ፓኪስታን፣ ግብፅ፣ ካዛኪስታን፣ ቤኒን፣ ጋቦን፣ ኤርትራ እና ላይቤሪያ ሌሎች በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ሃገራት ናቸው። ከማሕበራዊ ድር-አምባ አንፃር ሲታይ ደግሞ ዋትስአፕ የተሰኘው መልዕክት መላላከያ ብዙ ሃገራት የዘጉት ሆኖ ተመዝግቧል። ፌስቡክ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ኢንስታግራም ትዊተር እና ዩቲዩብ ተከታትለው ይመጣሉ። ኢራቅ፣ ሱዳን፣ ሕንድ እና ቬንዝዌላ ኢንተርኔት በመዝጋታቸው ምክንያት 1 ቢሊዮንና ከዚያ በላይ ያጡ ሃገራት ሆነው ተመዝግበዋል። ይህም ምጣኔ ሃብታቸው ላይ ከፍተኛ ድቀት እንዳደረሰ የድርጀቱ መረጀ ያመለክታል። አራቱም ሃገራት ሕዝባዊ ተቃውሞን ለማብረድ ሲሉ ነው የኢንተርኔታቸውን ባልቦላ የቆረጡት። ኢትዮጵያ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ኢንተርኔቷን ለ274 ሰዓታት ዘግታለች። በተለይ ወርሃ ሰኔ ላይ [አማራ ክልል እና አዲስ አበባ ላይ ከተከሰተው የባለሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ] ኢንተርኔት በሃገሪቱ ለተወሰኑ ቀናት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ነበር። ከዚያ ባለፈ ሃገር አቀፍ የተማሪዎች ፈተና በሚኖርበት ወቅት ኢንተርኔት በበርካታ የሃገሪቱ ክፍሎች ተቋርጧል። ነገር ግን ኢንተርኔቱን የሚያስተዳድረው ኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ መንገሥት ይፋዊ መግለጫ አልሰጡም። ከሃገር አቀፍ የኢንተርኔት መቋረጦች ባለፈ በተመረጡ አካባቢዎችም ተጠቃሚዎች ለቀናት ከኢንተርኔት ጋር ተቆራርጠው ቆይተዋል። ይህም ኢትዮጵያን ባላፈው ዓመት ብቻ 2 ቢሊዮን ብር ገደማ አሳጥቷታል።" https://www.bbc.com/amharic/51166093 +health ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ ለኮቪድ-19 ጽኑ ህሙማን የኦክስጂንና የቬንትሌተር እጥረት ማጋጠሙ ተነገረ "በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የጽኑ ህሙማን ህክምናና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠመ መሆኑ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ። ተቋሙ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ የባለሙያ ድጋፍና እንክብካቤ የሚሹ ሰዎች ቁጥር ""የህክምና ማዕከላት ማስተናገድ ከሚችሉት አቅም በላይ"" እየሆነ መም���ቱን ጨምሮ ገልጿል። በዚህም ሳቢያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ ታምመው በህክምና ተቋማት ድጋፍ ለማግኘት ለሚመጡ ህሙማን አገልግሎት የሚውሉ ""የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እና የኦክስጅን እጥረት እያጋጠመ ነው"" ሲል ገልጿል። በኢትዮጵያ እስከ ትናንት እሁድ ድረስ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 175,467 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ 2,550 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። የኮሮናቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ ለተጠቁ ጽኑ ህሙማን ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን ህይወታቸውን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስፈላጊ ናቸው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ ቬንትሌተሮች ቁጥር ከ500 ብዙም የበለጠ አይደለም። ስለዚህም በበሽታው የሚያዙት ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ የህክምና ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎችን መጠን በመጨመር በህክምና ተቋማቱ ላይና በባለሙያዎች ላይ ጫናን በመፍጠር ከአቅም በላይ ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል። በተለይም በወረርሽኙ በጽኑ ታምመው የቬንትሌተርና የኦክስጂን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህሙማን ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የነፍስ አድን አገልግሎቱን መስጠት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ከደረሰ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ሊያሻቅብ ይችላል። በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ በየዕለቱ የሚመዘገበው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የገለጸው ኢንስቲትዩቱ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በወረርሽኙ ሳቢያ የጽኑ ህሙማን የህክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ህሙማንና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር ""አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል"" ይገኛል ብሏል። የኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ይፋ ከተደረገ ባለፈው ቅዳሜ አንድ ዓመት የሞላው ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ እስካሁን ድረስ በወረርሽኙ ሳቢያ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 2550 ደርሷል። በኮቪድ-19 ለሞት ከተዳረጉት ሰዎች መካከል 74 በመቶ የሚሆኑት በህክምና ማዕከላት ውስጥ ሲሆን 24 በመቶዎቹ ደግሞ በአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ ምርመራ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል። ኢንስቲቲዩቱ እንደሚለው ባለፉት ጥቂት ቀናት እየተመዘገበ ያለው የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው። እስካሁን ድረስ በየዕለቱ ከተመዘገቡት ሞቶች ሁሉ ከፍተኛው በእነዚህ ቀናት ውስጥ ተመዝግቧል። በወረርሽኙ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በተለያዩ የአገሪቱ ከፍሎች የተመዘገቡ ሲሆን በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ውስጥ የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር ከሌሎቹ ቦታዎች አንጻር በእጅጉ ከፍተኛ ነው። በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ 1,852 ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ለህልፈት ሲዳረጉ ይህም ከአጠቃላዩ የሟቾች ቁጥር 73 በመቶውን ይይዛል። በተከታይነት በኦሮሚያ ክልል 256 ሰዎች (10 በመቶ)፣ በአማራ ክልል 105 ሰዎች (4 በመቶ)፣ በሲዳማ ክልል 75 ሰዎች (3 በመቶ) የሚሆኑት በበሸውታው ህይወታቸው አልፏል። በየዕለቱ በሚደረገው ምርመራ ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥርም በፍጥነት እየጨመረ መሆኑ ተገልጿል። ቬንትሌተር ምንድን ነው? ቬንትሌተር የሰውነታችንን የአተነፋፈስ ሥርዓት ተክቶ የሚሠራ ማሽን ነው። የህሙማን ሳምባ እክል ሲገጥመው ቬንትሌተር የመተንፈስ ተግባር ስለሚያከናውን ህይወትን ይታደጋል። በኮቪድ-19 በጽኑ ከታመሙ ስድስት ህሙማን መካከል ቢያንስ አንዱ የመተንፈስ ችግር ይገጥመዋል። ይህም የሚሆነው ቫይረሱ ሳምባን ስለሚያውክ ነው። በዚህ ወቅት ቬንትሌተር ከሌለ ግለሰቡን ማዳን አዳጋች ነው። ሁለት ዓይነት የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያዎች (ቬንትሌተር) አሉ። አንዱ መካኒካል ቬንትሌተር ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ቱቦ-አልባ ቬንትሌተር ይባላል። መካኒካል ቬንትሌተር የአየር ቱቦ በአፍ በኩል እንዲገባ ተደርጎ ታማሚው ካርቦንዳይኦክሳይድ እንዲያስወጣና ኦክስጂን እንዲያስገባ የሚያደርግ ነው። ቱቦ-አልባው ቬንትሌተር ወይም በእንግሊዝኛው ግን ወደ ሳምባ የሚወርድ ቧንቧ ሳይኖረው አፍና አፍንጫ ላይ በሚደረግ ጭምብል ብቻ የሚሰራ ነው። ቬንትሌተሮቹ ሂሙዲፋየር [እርጥበት የሚፈጥር] ክፍል አላቸው። ይህም ማለት ወደ ሰውነት የሚገባን ሙቀትና እርጥበት የሚቆጣጠርና ህመምተኛው የሚተነፍሰው አየር ለሰውነት ሙቀት ተስማሚ በሆነ መጠን እንዲሆን የሚያደርግ ነው። በዚህ ወቅት በሽተኞች የመተንፈሻ አካል ጡንቻዎች ዘና እንዲሉላቸው የሚያስችል መድኃኒት ይሰጣቸዋል። መጠነኛ የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን የሚያሳዩ በሽተኞች ግን የፊት ጭምብል ቬንትሌተር ብቻ ሊሰጣቸው ይችላል። ይህም በአፍና አፍንጫ በኩል በግፊት አየር ወደ ሳምባ እንዲገባ የማድረግ ዘዴ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-56359828 +sports ብሔራዊ ቡድኑን ወደ የአፍሪካ መድረክ ለመመለስ የሚመኘው ሽመልስ በቀለ ትውልድ እና እድገቱ አዋሳ ከተማ ኮረም ሰፈር ነው። እንደ አብዛኛው የኢትዮጵያ ልጆች ኳስ እና ሽመልስ በቀለን ያስተዋዋቃቸው ትምህርት ቤት ነው። በእረፍት ጊዜ ባለችው ትንሽ ክፍተት ኳስን መጫወት የጀመረው ሽመልስ ወደ ሰፈሩ ሲመለስም ከሰፈር ጓደኞቹ ጋር ከማታ ጥናት በፊት ያለችውን የ አንድ ሰዓት ክፍተት ኳስ በመጫወት ያሳልፋ ነበር። ዛሬ ላይ በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ ተወዳዳሪ ለሆነው ሚሰረ ሌል ማካሳ እየተጫወተ ይገኛል። ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለማለፍ ከማደጋስካር አቻዋ ለምታደርገው ጨዋታ ቁልፍ ሚና ከሚኖራቸው መካከል አንዱ የሆነው እግር ኳሰኛው ሽመልስ በቀለ ስለ 'ፕሮፌሽናል' የእግር ኳስ ሕይወቱ ለቢቢሲ የሚከተለውን አጋርቷል። በግብፅ ሊግ የመጫወት እድል ግብፅ ሄጄ የመጫወት እድል የተፈጠረልኝ፤ በቅድሚያ ሊቢያ እና ሱዳን ሄጄ የነበረኝ አጭር ቆይታ ብሎም በኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩኝ እንቅስቃሴዎች ናቸው። በሱዳን ለስድስት ወር ያክል ተጫውቼ ነበር። ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ለ ሁለት ወር ያክል ዝግጅት ላይ እያለሁ አሁን ያለው ወኪሌ ቪዲዮዎችን እንድልክለት ይጠይቀኝ ነበር። እኔም በውጪ የነበረኝን እና በአገር ውስጥ የነበሩኝን ቆይታ የሚያሳዩ ምስሎች ላኩለት። በተጨማሪም አጭር ግዜ ቢሆንም ወጥቼ የመጫወት ሪከርድ ስላለኝ አሱ ያገዘኝ ይመስለኛል። ፔትሮጅክት የሚባል ክለብ ቪዲዮዎቹን ተመልክቶ ነበር። አሰልጣኞቹ ደስተኛ ነበሩ። በተለይ ምክትል አሰልጣኙ የበለጠ በእኔ ደስተኛ ነበር። ከቪዲዮ በተሸለ በአካል መጥተው ለማየት ተነጋገሩ እኔም ደስተኛ ነበርኩ። አዲስ አበባ ላይ ከአልጄሪያ ጋር በነበረን ጨዋታ መጥተው ተመለከቱኝ፤ ምንም እንኳን ሁለት ለአንድ ብንሸነፍም በእንቅስቃሴዬ ደስተኛ ስለነበሩ ለክለቡ ለመፈረም እድሉን አገኘሁ ማለት ነው። በፕሮፌሽናል የኳስ ህይወትህ ወርቃማ የምትለው ጊዜ የቱ ነው? በፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወቴ ወርቃማ ብዬ የማስበው ከሁለት አመታት በፊት ፔትሮጄት የነበርኩበት ነው። ይህም በእግር ኳስ ህይወቴ አምበል ሆኜ ቡድን መርቼ አላውቅም ነበር። በወቅቱ አምበል ሁኜ ነበር። ይህ ከአገር ወጥቼ ለመጀመሪያ ክለቤ ፔትሮጄት መሪ መሆኔ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው። የብሔራዊ ቡድኑን አቋም እንዴት አገኘኸው? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አቋም ከዓመት ዓመት ልዩነት አለው። እኔ በሄድኩበት ግዜ በተለይ በመጨረሻው ዓመት በፕሪሚ��ር ሊጉ 18 ጠንካራ ክለቦች ነበሩ። በዚህ ዓመት እንደሚታወቀው 13 ክለቦች ነው ያሉት። ይሄ በራሱ በብሔራዊ ቡድኑ አቋም ላይ የራሱ ጫና አለው። ነገር ግን አሁን ላይ ሊጋችን በቀጥታ ለዓለም መታየቱ [በዲኤስቲቪ አማካኝነት] ደግሞ የራሱ የሆነ በጎ ነገር ያመጣል ብዬ አስባለሁ። እግር ኳስና የኮሮናቫይረስ እንዴት እየሄዱ ነው? ኮሮናቫይረስ ከመጣ በኋላ ፊፋ ባወጣው ሕግ መሰረት ሁል ጊዜ ጨዋታ ሲኖረን ከሁለት ቀን በፊት ምርመራ እናደርጋለን። ኮሮናቫይረስ ያለበት ሰው አይጫወትም። ይሄ በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ነው። ለአፍሪካ ዋንጫ እየተዘጋጃችሁ ነው። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ዋንጫ ካለፈች ዘጠኝ ዓመት አለፈ። አሁን ያለው ቡድን የሚያልፍ ይመስልሃል? አዎ ለአፍሪካ ዋንጫ እናልፋለን ብዬ አምናለሁ። ባፈው ሳምንት ከማላዊ ጋር ያካሄድነው የወዳጅነት ጨዋታ በብቃት ነው የተወጣነው። ጎበዝ ተጫዋቾች ከተለያዩ ክለቦች ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ተጠርተዋል። ሁሉም ተጫዋች ጥሩ አቋም ላይ ነው ያለው። ያለፈውን ሳምንት ጨዋታ በብቃት እንደጨረስነው ሁሉ ከማዳጋስካር ጋር የምናደርገውን ጨዋታም በድል እንወጣዋለን። ለዚህም ምክንያቱ አሪፍ ተጫዋቾች እና አሪፍ አሰልጣኞች ስላሉን ነው። ስለዚህ እነዚህን በድል ከቋጨን ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማናልፍበት ምን ምክንያት አለ? ያኔ አንተ የነበርክበት ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፍ በአገሪቱ የነበረው ስሜት እንዴት ታስታውሰዋለህ? ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ምንም የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳትፎ አላደረግንም። ይሄ በጣም ረጅም ጊዜ ነው። አሁን ግን ወደ 10ኛ ዓመት ከመግባታችን በፊት እኛ ቡድኑን አሳልፈን ያኔ እኛ የነበረንን ስሜት ድጋሚ ለሁለተኛ እንዲሰማን እፈልጋለሁ። የዚያን ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ካለፈው ቡድን ውስጥ አሁን ያለነው ሦስት ተጫዋቾች ብቻ ነን። እኛ ያለፍንበትን ስሜት አሁን ያሉት አዳዲስ ልጆች እንዲሰማቸው እንፈልጋለን። እሱ ጊዜ ሲነሳ በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ ተፈጥሮ ያለፈው ከፍተኛ መነቃቃት እና ደስታ ይታወሰኛል። ያ ስሜት እንዲደገም እፈልጋለሁ። ሕዝቡ ጋር የነበረው ስሜት ከባድ ነበር። ብዙ ነገሩን ትቶ ያኔ ኳስ ለመመለከት እና ለአገሩም የነበረው ትልቅ ስሜት ያንጸባርቅ ነበር። ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋችን የፈጠረው ደስታ በጣም ትልቅ ነበር። አገራችን አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ያ ስሜት እንደገና እንዲመጣ እንፈልጋለን። ከእግዚአብሔር ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ የምናልፍ ከሆነ ሁሉንም ነገር የምናስረሳበት ጊዜ ይመጣል ብዬ አስባለሁ። በፖለቲካ ምክንያት ሁሉም ቦታ ጭንቀት ነው የሚሰማው፤ ምንም ሰላም የለም። ሕዝቡ ሰላሙን እንዲያገኝ እና ያኔ የነበረው የደስታ ስሜት እንዲመጣ እፈልጋለሁ። በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ አዲስ እየመጡ ካሉ ጎበዝ ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ አቡበከር ናስር ተደጋግሞ ስሙ ይነሳል። ከእሱ ጋር ተጣምሮ መጫወትን እንዴት አገኘኸው? አቡበከር ናስር እና እኔ አሁን በብሔራዊ ቡድን ውስጥ አብረን የመጫወት እድል አግኝተናል። በእኔ አይን ባጭሩ ምርጡ ተጫዋች ነው። ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም። ጎበዝ ተጫዋች ነው። ልጁ ገና 21 ዓመቱ ነው፤ ትልቅ ደረጃ መድረስ የሚችል ነው። ከዚህ በኋላ ራሱን አጠንክሮ እና ታግሶ የሚሰራ ከሆነ የሚያሳየው ብቃት ተስፋ ያሳድራል። ራሱን ወደ ላይ ሳያደርግ የሚጫወት ልጅ ነው። እያደርም እኔ ካለሁበት ደረጃ የበለጠ ትልቅ ቦታ ላይ መድረስ የሚችል ልጅ ነው። የኳስ ተንታኞች የኢትዮጵያ ተጫዋቾች እድል አጥተው እንጂ የቴክኒክ ብቃት አላቸው ይላሉ። አንተ ከአገር ወጥተህ ስትጫወት ምን ታዘብክ? አዎ በቴክኒክ በኩል ጥሩ ተጫዋቾች አሉን ከኳስ ጋር የተያያዙ ብዙ እድሎች ግን የሉም። ኢት���ጵያ ውስጥ በጣም ብዙ ተሰጥኦ ያላቸው አግር ኳስ የሚችሉ ምርጥ ልጆች አሉ። ያሰልጣኝ ችግር፣ የቁሳቁስ ችግር እና የመሳሰሉት ነው ጎልተው እንዳይወጡ ያደረጋቸው። እነዚህ እድል ቢሰጣቸው የኢትዮጵያ ተጫዋቾች በጣም ስኬታማ መሆን እና ወደ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ መምጣት ይችላሉ። ሰባት ዓመት በግብጽ ስትኖር ሕዝቡን እንዴት አገኘኸው? ብዙ ግብጻዊያን ጓደኞች አሉኝ። ከክለብ አጋሮቼ ባሻገርም በምኖርበትም አከባቢ ግብጻዊያን ጓደኞች አሉኝ። በደንብ እንነጋገራለን ጥሩ ጓደኝነት አለን። በኳስ ህይወቴ ላይም ምንም ያደረሰብኝ ጫናም የለም። ፖለቲካዊ ጉዳዮችን አንስተን ብዙም ተነጋግረን አናውቅም፤ ያው ግን ሁሉም ለአገሩ አይደለ፤ በተረፈ ግን አሪፍ ባህሪ አላቸው። በታዳጊነት እድሜህ ላይ ብትሆን እና አሁን ባለው እውቀትህ ላይ ሆነህ የእግር ኳስ አካዳሚ ብትገባ የትኛው ክህሎትህን ታሻሽል ነበር? ያለኝን የኳስ ክህሎት ላይ በደንብ ብሰራ ደስ ይለኛል። ነገር ግን ዋናው የአካል ብቃት ጥንካሬ ላይ በጣም አተኩሬ የምሰራ ይመስለኛል። ምክኒያቱም አንድ ሰው ምንም ያህል የቴክኒክ ብቃት ቢኖረው ጥንካሬው ዝቅተኛ ከሆነ መቋቋም ይከብዳል። ምን አልባት ተመልሼ በልጅነት አካዳሚ ብገባ የአካል ጥንካሬዬ ላይ በጣም የምሰራ ይመስለኛል። ብዙ ግዜ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ከአገር ሲወጡ ሳይሳካላቸው በቶሎ ይመለሳሉ። ምክንያቱ ምድነው? የሥነ ልቦና ጉዳይ በእግር ኳስ ህይወት ላይ ከባድ ችግር ነው። ሌላው ከአገር ቤት ይዘን የምንሄደው ብቃትን እዚያ ሄደን ከፍ ማድረግ ያስፈለጋል። እንደዛ ካልሆነ ብቃት ይወርዳል፤ ያኔ ተፈላጊነት ይቀንሳል። ብዙ ትንንሽ የሚመስሉ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥሩ ፈተናዎች አሉ። ለምሳሌ ተጫዋች ቤቱ ነው መመገብ ያለበት። እኔ ደግሞ ማብሰል አልችልም ነበር። ከፍተኛ ፈተና ሆኖብኝ ነበር። አገርም ይናፍቃል። እና እመለሳለሁ እያለ የሚጫወት ሰው ደግሞ ወዲያው ተመልሷል። ለሥራ እስከወጣን ድረስ ዋናው የሥነ ልቦና መጠንከር እና ትዕግስተኛ መሆን ለስኬት ቁልፍ ነው። በጣም ብዙ ችግሮች አሉ እነዚያን መቋቋም እና ዲሲፕሊንም ይጠይቃል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በቴሌቪዝን መታየቱ የሚጨምረው ፋይዳ አለ? አሁን ያለው ፕሪሚያር ሊግ በቀጥታ በቴሊቪዥን መቅረቡ ከፍተኛ የመታየት እድል መፍጠሩ አይቀርም። ቅድም እንዳልኩት ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ የኳስ ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች አሉ። ክለቦች ተጫዋቾቻው ወጥተው እንዲጫወቱ ማበረታታት አለባችው። ክለብ ብቻ ሳይሆን ፌዴሬሽኑ የራሱ ኃላፊነት አለበት። ፌዴሬሽኑ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ ትልቅ ነገር መስራት ይጠበቅበታል። ለምሳሌ ሌሎች አገራት ለተጫዋቾቻቸው ነፃ ቪዛ ስለሚያመቻቹ ሄደው ይሞክራሉ። ብዙ ግንኙነት ማድረግ እና ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ጋር መነጋገር አለበት። ባለሞያዎች እንደሚሉት አንድ ቡድን ከተገነባ ከ 4 እስከ 10 ዓመት ዋና ቡድን ውስጥ ያሉ ሰዎች ሳይቀያየሩ በተመሳሳይ ብቃት መቀጠል ይችላል ይላሉ። ያኔ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈው ቡድን ወዲያውኑ ለምን ደከመ? ወይስ ያኔ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፋችሁት በአጋጣሚ ነበር? ጠንካራ ክለብ ያለመኖሩ ነው ብሔራዊ ቡድኑን ያደከመው። ቡና እና ጊዮርጊስን ጨምሮ ብዙ ጠንካራ የክልል ክለቦች ነበሩ። አሪፍ ብሔራዊ ቡድን የተሰራው በዕድል ሳይሆን በጥንካሬ ነው። ተጫዋቾችም በትንሽ ነገር እንሸወዳለን። ትንሽ ድል ያታልለናል። በዚያ ውስጥ እንጠፋለን። ተጫዋቾች ትንሽ ድል ስናገኝ ብዙ ነገር የሰራን ይመስለናል። የዓለም ዋንጫን ደጋግመው የወሰዱት እንደ ጀርመን እና ብራዚል እንኳን በዚያው ነው ጠንክረው የሚቀጥሉት። https://www.bbc.com/amharic/news-56471330 +health በዓ��ም የመጀመሪያ የሆነው ሰው ሰራሽ ደም በሰዎች ላይ መሞከር ተጀመረ በቤተ ሙከራ ውስጥ የዳበረ ሰው ሰራሽ ደም ለመጀመሪያ ጊዜ በሚደረግ ክሊኒካዊ ሙከራ ለሰዎች መሰጠቱን የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ተመራማሪዎች አስታወቁ። አሁን ለሙከራ ለሰዎች የተሰጠው ሰው ሰራሽ ደም መጠኑ ትንሽ ሲሆን፣ የተወሰነ የሻይ ማንኪያ መጠን እንደሆነ ተገልጿል። በዚህም ደሙ በሰው አካል ውስጥ ገብቶ ምን ውጤት እንደሚኖረው ለማወቅ ሙከራ ይደረጋል። አስካሁን በዓለም ዙሪያ ደም ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ከሌሎች በልገሳ የተገኘ ደምን በመስጠት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል። ይህ በቤተ ሙከራ የተሰራው ደም ስኬታማ ከሆነ፣ በተለይ ለማግኘት አስቸጋሪ የሆኑ የተለዩ የደም አይነቶችን በማምረት ላይ ትኩረት ይደረጋል። በተለይ የደም ካንሰር እና ሲክል ሴል አኒሚያ ላለባቸው እንዲሁም መደበኛ የደም ለውጥ ለሚያስፈልጋቸው ህሙማን ይህ አዲሱ ሰው ሰራሽ ደም ስኬታማ ከሆነ ችግራቸውን ያቀላል ተብሏል። በደም ልገሳ ወቅት ተቀባዩ ግለሰብ በትክክል ተመሳሳይ የደም አይነት የማያገኝ ከሆነ ሰውነቱ ሊቆጣና ህክምናው ሊሰናከል ይችላል። ይህም የደም አይነት ተመሳሳይነት በስፋት ከሚታወቁት የደም አይነት ከሆኑት ኤ፣ ቢ፣ ኤቢ እና ኦ ባሻገር ዝርዝር ልዩነቶችን መለየትን የሚጠይቅ ነው። አንዳንድ የደም አይነቶች ከተጠቀሱት በተለየ “በጣም፣ በጣም የተለዩ ከመሆናቸው ባሻገር፤ በአንድ አገር ውስጥ የዚያ አይነት ደም ያላቸው ሰዎች 10 ሰዎች ብቻ ሊሆኑ ይችላሉ” ይላሉ የብሪስቶል ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር አሽሊ ቶዬ። ሰው ሰራሹን ደም ለማዳበር የብሪስቶል፣ የኬምብሪጅ፣ የለንደን እና የዩኬ ብሔራዊ የጤና አግልግሎት የምርምር አባላት እየተሳተፉ ነው። የፕሮጀክቱ ትኩረት ከሳንባ ወደ ቀሪው የሰውነት ክፍል ኦክስጂን በሚወስደው ቀይ የደም ህዋስ ላይ ነው። ሰው ሰራሽ ደሙን ለመሞከር ቢያንስ 10 ጤናማ በጎ ፈቃደኞች የሚያስፍልጉ ሲሆን፣ አሁን የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰዎች በሙከራው ላይ እየተሳተፉ ነው። በዚህም ሙከራው የሚደረግባቸው ሰዎች በአራት ወራት ልዩነት ውስጥ ከ5 አስከ 10 ሚሊ ሊትር የሚሆን ደም በመጀመሪያ ትክክለኛ ደም፣ ቀጥሎ ደግሞ በቤተ ሙከራ የዳበረ ደም ይሰጣቸዋል ተብሏል። ይህ በቤተሙከራ የዳበረው ደም ስኬታማ ከሆነ በወጪ ረገድ አሳሳቢ እንደሚሆን ባለሙያዎቹ የተናገሩ ሲሆን፣ ከለጋሾች ተፈጥሯዊ ደምን ለማግኘት የሚወጣው ወጪ፣ ሰው ሰራሽ ደሙን ለማምረት ከሚያስፈልገው ያነሰ ነው። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ብሔራዊው የጤና አገልግሎት እንደሚለው ተፈጥሯዊው የደም ልገሳ በአማካይ 130 ፓወንድ ያክል ያስወጣል። ምርምሩን የሚያካሂደው ቡድን ባይገልጸውም በቤተ ሙከራ ውስጥ ሰው ሰራሽ ደም ማዳበር ከፍተኛ ወጪን ይጠይቃል ተብሏል። በተጨማሪም በቤተሙከራ ውስጥ የስቴም ህዋሳትን ለማዳበር በሚከናወነው ሂደት ውስጥ ሌሎች ተግዳሮቶች ስለሚኖሩ በምርቱ ወቅት የተለያዩ ችግሮች መግጠማቸው እንደማይቀር ተገልጿል። ነገር ግን ይህ በቤተ ሙከራ የሚዳብረው ደም መደበኛ የደም ዝውውር ለሚፈልጉ እና እጅግ ለየት ያለ የደም አይነት ላላቸው ሰዎች የሚሆን ደም በማምረት በኩል ትልቅ መፍትሔ እንደሚሆን ባለሙያዎች ይናገራሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c06xl7dg58go +business አሁን ባለው የዋጋ ግሽበት ገንዘብ መቆጠብ ያዋጣል? በአጠቃላይ ገንዘብ ቆጠብን ስንል ወደ ወጪ ያልተቀየረ ገንዘብ አለን ወይንም ወጪያችንን በመቀነስ የምናስቀምጠው ገንዘብ ማለታችን ነው። በምጣኔ ኃብት ቋንቋ ደግሞ ገቢያችን የወጪያችን እና የቁጠባችን ድምር ነው። የምጣኔ ኃብት ባለሙያው ተሾመ ተፈራ (ዶ/ር) በመርህ ደረጃ ከወጪ የሚተርፍ ገንዘብ መቆጠብ አለበት። ይሁን እንጂ ቁጠባ ከሰዎች ባህሪ ጋር የሚገናኝ ጉዳይ ነው ይላሉ። “አንዳንድ ሰዎች ከወጪያቸው ቆጥበው ለወደፊት ኑሯቸው፣ ለጡረታ ዘመናቸው ወይንም ለልጆቻቸው ይቆጥባሉ። ሌሎች ደግሞ ከወጪያቸው እንደፈለጉ አውጥተው የሚተርፋቸውን ያስቀምጣሉ፤ ሌሎች ዛሬን ብቻ መኖር የሚፈልጉ አይቆጥቡም። ስለዚህ ቁጠባ ሌሎች ነገሮች ላይ ከምናሳየው ከባህሪያችን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው” ይላሉ። የምጣኔ ኃብት ባለሙያው እንደሚሉት በግለሰብ ደረጃ የምናደርገው የሀብት አጠቃቀም ውሳኔ አንድ ሰው ደስታ ያመጣልኛል ብሎ በሚያምነው ነገር ላይ የተመሰረተ ነው። “ለምሳሌ አንድ ሰው ዛሬ ደስ የሚለውን ልብስ መግዛት ያስደስተኛል ካለ፣ ሊቆጥብ የሚገባውን ገንዘብ እዚያ ላይ ያወጣዋል። ሌላው ሰው ደግሞ ለወደፊት መግዛት ለሚፈልገው ደስታ አሁን ብሩን ይቆጥባል ማለት ነው” ተሾመ (ዶ/ር) እንደሚሉት ገንዘብ የሚቆጥበውም ሆነ አባካኝ የሆነው፣ ሌላ ሰው ከውጪ ስም ይሰጣል እንጂ ሁለቱም በገንዘባቸው ደስታን የመግዛት ስራ እየሰሩ ነው ያሉት። በምንኖርባት አገር ውስጥ የምንቆጥበው ገንዘብ ጥቅም ሊያስገኝልን የሚችለው የገበያው የዋጋ ንረት እኛ በመቆጠብ ከምናገኘው ጥቅም በታች ከሆነ ብቻ ነው ይላሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው። ይህንንም በምሳሌ ሲያስረዱ “አንድ ሰው ያለፈው ዓመት አንድ መቶ ብር ባንክ ቢያስቀምጥ ከአመት በኋላ ቢበዛ ስድስት በመቶ ብቻ ነው ሊወልድለት የሚችለው። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የዋጋ ግሽበቱ ከ34 በመቶ በላይ ሆኗል።” የምጣኔ ኃብት ምሁሩ እንደሚሉት አምና የቆጠብነው አንድ መቶ ብር ዘንድሮ የመግዛት አቅሙ በ34 በመቶ ይወርዳል። “ስለዚህ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት ባለበት አገር ገንዘብ ዝም ብሎ ማስቀመጥ አዋጭ አይደለም። ከዚህ የዋጋ ግሽበት የቆጠቡትን ገንዘብ ለማስመለጥ ሰዎች መሬት እና የመሳሰሉ ሀብቶችን በመግዛት ገንዘባቸውን የተሻለ ነገር ላይ ቢያውሉት ተመራጭ ነው” ይላሉ። አክለውም “ግን በአጠቃላይ ቁጠባ ጥቅም ሊያስገኝ የሚችለው የአንድ አገር የዋጋ ንረት ከባንክ ወለድ በታች ከሆነ ብቻ ነው። በዚህ ሁኔታ ገንዘብ መቆጠብን እንደ መነሻ ተጠቅመን ገንዘባችንን ኢንቨስት ማድረግ የተሻለ አማራጭ ነው። ገንዘብ ኢንቨስት ማድረግ ማለት፣ ገንዘብ ማስቀመጥ ሳይሆን እንዲያድግ ማድረግ ነው፝ ይህንንም በምሳሌ ሲያስረዱ፣ የባንክ ሼር በመግዛት እና በተለያዩ ሌሎች አማራጮች ተግባር ላይ ማዋል እንደሚቻል በመጥቀስ ይመክራሉ። ለምሳሌ ይላሉ ዶ/ር ተሾመ፣ “ የኢትዮጵያ ባንኮች ለአንድ አክስዮን ከ20 በመቶ በላይ ትርፍ ይከፍላሉ። ስለዚህ ከምንቆጥበው ገንዘብ በላይ እንጠቀማለን ማለት ነው።” እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ኢንቨስትመንት ስላልተስፋፋ ከኢንቨስትመንት ላይ የምናገኘው ጥቅም ትልቅ ሊሆን ይችላል። እንደ ጃፓን ያሉ አገራት ውስጥ ግን ያለው የዋጋ መውረድ (ዲፊሌሽን) በመሆኑ ገንዘብ መያዝ ኢንቨስት ከማድረግ የተሻለ አማራጭ የሚሆንብት አጋጣሚ መኖሩን አቶ ተሾመ ያስረዳሉ። የተረጋጋ ምጣኔ ሀብት ባለበት አገር ገንዘባቸንን ስራዬ ብለን ብንቆጥብ ሀብት ማካበት እንችላለን የሚል ጥያቄ ለምጣኔ ኃብት ምሁሩ አቅርበን ነበር። ባለሙያውም የአንዳንድ አገራትን ልምድ በማንሳት ይህንን ጉዳይ ያብራራሉ። እንደ ቤልጂየም ያሉ አገራት ቁጠባን አያበረታቱም። ስለዚህ የቁጠባ የባንክ አካውንት ለሚከፍቱ ሰዎች ዓመታዊ ክፍያ ያስከፍላሉ። ይህንንም የሚያደርጉት ብሩ እንዳይቀመጥ እና ስራ ላይ እንዲውል ስለሚፈልጉ ነው። በአገራችን ግን ባንኮች እነርሱ ጋር አንድንቆጥብ በዘመቻ የሚያበረታቱን ከ��ጠቃሚው የሚሰበስቡትን ገንዘብ ለኢንቬስተር አበድረው ጥቅም ማግኝት ስላለባቸው ነው ይላሉ። ስለዚህ እንደ ምሁሩ ገለጻ፣ ገንዘብ መቆጠብ እድል የሚከፍት ቢሆን እንጂ ብቻውን ወደ ሀብት ማካበት አያደርሰንም። ለምሳሌ አንድ ተቀጥሮ የሚሰራ ሰራተኛ ገንዘቡን ቢቆጥብ በግሽበት እየተበላበት ነው የሚሄደው። በተለይ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ እና የሰራተኞች ማህበራት ጠንካራ ባልሆኑበት አገር፣ የዋጋ ግሽበት በመጣ ቁጥር የሰራተኛው ደመወዝ ስለማይስተካከል መቆጠብ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ። ነገር ግን አንድ ሱቅ ያለ ሰው ከተቀጣሪ ራሱን በተሻለ ሁኔታ ማስተዳደር ይችላል። ምክንያቱም የሽያጭ እና ግዢ ሁኔታው ከዋጋ ግሽበቱ ጋር ማስተካከል ስለሚችል ነው። እንዲሁ በአጠቃላይ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ባለበት አገር ገንዘብ መቆጠብ ኢንቨስት ለማድረግ መንገድ ሊከፍት እና ሊያሳድግ ይችላል። ነገር ግን በራሱ መቆጠብ ወደ ሀብት ማካበት አያደርስም። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት የቁጠባ እና የኢንቨስትመንት ዋና ልዩነት ገንዘብን ለአጭር እና ለረዥመ ጊዜ ማስቀመጥ ነው። በተጨማሪም ሌሎች እነዚህ ሁለቱ ሀሳቦች የሚለያዩበት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1v20381w3o +politics የባይቶና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ ክብሮም በርኸ መታሰራቸው ተነገረ የብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ ወይም ባይቶና የሚባለው የፖለቲካ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ክብሮም በርኸ አዲስ አበባ ውስጥ በፀጥታ ኃይሎች መታሰራቸው ተነገረ። በትግራይ ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የባይቶና ከፍተኛ አመራር አንዱ የሆኑት አቶ ክብሮም በቅርቡ “ምጽአት” የሚል ርዕስ ያለው በትግራዩ ጦርነት ላይ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ለንባብ አቅርበዋል። አቶ ክብሮም እሑድ ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ በፀጥታ ኃይሎች መያዛቸውን ለቢቢሲ የተናገሩት የፓርቲው የቁጥጥር ኮሚሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ዮሴፍ ኃይለሥላሴ ናቸው። ምሽት ከአንድ ሰዓት እስከ ሁለት ሰዓት ባለው ጊዜ ሲቪል የለበሱ ሰዎች በቅድሚያ የአቶ ክብሮም ባለቤትን መያዛቸውን የተናገሩት አቶ ዮሴፍ “ባለቤትሽን አምጪ ብለው ጠይቀዋት፣ ከዚያ በኋላ እርሱ ሲሄድ በቁጥጥር ስር አዋሉት” ብለዋል። ጦርነቱ በተስፋፋበትና የትግራይ ኃይሎች ወደ አፋርና አማራ ክልሎች በገቡበት ወቅት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ፣ የባይቶና ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ክብሮም ተይዘው በአፋር ክልል ውስጥ ለወራት በእስር ላይ ቆይተው እንደነበር ተነግሯል። አቶ ክብሮም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት ስልክ በመወደል ባለቤታቸው መያዛቸውንና እሳቸውም በፖሊስ እንደሚፈለጉ እንደተነገሯቸው የጠቀሱት አቶ ዮሴፍ፣ አቶ ክብሮም በአሁኑ ጊዜ በቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኝ እስር ቤት እንዳሉም ጨምረው ገልጸዋል። የአቶ ክብሮም ባለቤት እሳቸው በቁጥጥር ሥር ሲውሉ መለቀቃቸውን የተናገሩት አቶ ዮሴፍ፣ የባይቶና የውጭ ጉዳይ ኃላፊው አቶ ክብሮም በርኸ ለምን እንደታሰሩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለና ፍርድ ቤትም አለመቅረባቸውን አመልክተዋል። የአቶ ክብሮም እስርን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ስልክ በመደወል ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ ለጊዜው አልተሳካለትም። ከቅርብ ወራት ወዲህ መንግሥት ሕግ ማስከበር ባለው ዘመቻ በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ውስጥ ጋዜጠኞችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c97pw1q3gqno +sports ኦሌ ጉና ሶልሻየር፡ አራተኛ ሆኖ መጨረስ በቂ አይደለም "ኦሌ ጉና ሶ���ሻየር ማንችሰተር ዩናይትድ በቀጣዩ የውድድር ዘመን ''አራተኛ ሆኖ ከመጨረስ በላይ ነው የሚያልመው'' ሲሉ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጡ። የ46 ዓመቱ አስልጣኝ ማንችስተር ዩናይትድን ከጆሴ ሞሪኒሆ መቀበላቸው ይታወሳል። ሶልሻየር የቀያይ ሴጣኖቹ ቋሚ አሰልጣኝ ሆነው ከመሾማቸው በፊት ካደረጉት 19 ጨዋታዎች 14ቱን ማሸነፍ ችለው ነበር። ኦሌ ቋሚ አሰልጣኝ ሆነው ከተሾሙ በኋላ ግን ካደረጓቸው 10 ጨዋታዎች ሙሉ ነጥብ መሰብሰብ የቻሉት ከሁለት ጨዋታዎች ብቻ ነው። ዩናይትዶች አዲሱ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት የሚከናወኑ ጨዋታዎችን ለማድረግ አውስትራሊያ የሚገኙ ሲሆን፤ ኦሌ ጉና ሶልሻየር ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ የቀጣዩ የውድድር ዘመን እቅዳቸውን ጨምሮ ስለ አሌክሲስ ሳንቼዝ እና ፖል ፖግባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። • ""እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል?' ተብሎ ነበር"" መሠረት ማኒ ኦሌ ጉና ስለቀጣዩ የውድድር ዓመት ሲናገሩ፤ በሊጉ ሰንጠረዥ የመጀመሪያዎቹ አራት ውስጥ ለመጨረስ ከሚደረገው ጥረት በላይ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል። ""ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች አሉን በተጨማሪም ለቡድኑ በትክክል የሚመጥኑ ተጨዋቾችን በማስፈረም ከምንፈልገው ቦታ ላይ መድረስ እንችላለን። የሚጠበቅብን ወጥ የሆነ አቋም ላይ መገኘት መቻል ነው። በየቀኑ ጠንክረን እየሰራን ከእቅዳችን ዘንበል ማለት የለብንም።"" የዩናይትዶቹ አሰልጣኝ ኦሌ ጉና ሶልሻየር ለቡድኑ ስኬት የፖል ፖግባ አሰተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ። ኦሌ ''ፖል ድንቅ ተጫዋች እና የሚደንቅ ሰው። በሞልዴ ክለብ እያለሁ፤ 'ፖል በቡድን ውስጥ ካለ፤ በእሱ ላይ በመመስረት ቡደን መመስረት ይቻላል' እል ነበር። አሁንም ተመሳሳይ እምነት ነው ያለኝ። የዩናትድ ደጋፊዎች የቡድናቸውን አጨዋወት ያውቃሉ። ፖልን የሚተቹ ብዙ ቢሆንም በበርካቶች ግን ይወደዳል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ ከአርሰናል ወደ ማንችስተር የተዘዋወረው አሌክሲስ ሳንቼዝ በክለቡ ውስጥ ትልቅ ስም እና ክፍያ ካላቸው ቀዳሚ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። ይሁን እንጂ ሳንቼዝ ወደ ማንችስትር ከተዘዋወረ በኋላ በክለቡ ወጥ አቋም ማሳየት አልቻለም። ''የአሌክሲስን አቅም ሳስብ ትልቅ እረፍት ይሰጠኛል። ማድረግ የሚችለውን እናውቃለን። ምን ማድረግ እንዳለብን ነው መለየት ያለብን። ምክንያቱም አሌክሲስ በቀላሉ 20 ጎሎችን ሊሰጠን የሚችል ተጫዋች ነው። በኮፓ አሜሪካ ላይ ይህን አይተናል። ወጥ አቋም ማየት አልቻለንም በተጨማሪም ጎዳቶች ሲያጋጥሙት ነበር። ወደ ድንቅ አቋሙ ይመለሳል ብለን እናስባለን'' በማንችሰተር ዩናይትድ ቤት ውስጥ የተጫዋቾች ዝውውር ስትራቴጂን በሚመለከት ''እዚህ የማልፈልጋቸው ተጫዋቾች የሉም። አሁንም አንድ ወይም ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም እየሞከርን ነው። ክለቡን የሚለቁ ተጫዋቾች ካሉ እነሱን ለመተካት ሌሎች ተጫዋቾችን የማስፈረሙ ስራ ይኖራል'' ሲሉ መልሰዋል። ኦሌ ጉና ስለ ወጣቱ ሜይሰን ግሪንውድ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ''ተፈጥሯዊ የእግር ኳስ ክህሎት ያለው ተጫዋች ነው። በቀኝ እግሩም ሆነ በግራ እግሩ ጎል ያስቆጥራል። ሁለቱንም እግሮቹን በሚገርም ብቃት ይጠቀማል። ቀኝ ወይም ግራኝ ስለመሆኑ እርሱ እራሱ የሚያውቀው አይመስለኝም። መቶ በመቶ እርግጠኛ የምሆነው በዚህ የውድድር ዘመን ጎሎችን ያስቆጥራል'' ከቀድሞ የክለቡ አልጣኝ ሰር አሌክ ፈርጉሰን ጋር ስላላቸው ግነኙነት የተጠየቁት ኦሌ ''ለ14 ዓመት ከፈርጉሰን ጋር አብሬ ሰርቻለሁ። አብዛኛው የእግር ኳስ ህይወቴ ከእርሱ ጋር ነው ያሳለፍኩት። ከፈርጉሰን ብዙ ትመሬያለሁ ይህ እውነት ነው። ከጨዋታ በኋላ አልፎ አ���ፎ እንነጋገራለን፣ የጽሁፍ መልዕክት እንላላካለን ከዚህ ውጪ ሌሎች ብዙ የሚባሉት ነገሮች ግን ስህተት ናቸው። • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ ኦሌ ጉና በስተመጨረሻም ቡድን እንደ አዲስ ማዋቀር ጊዜ የሚወስድ መሆኑን በመጠቀስ የዩናይትድ ደጋፊዎች ትዕግስት እንዲኖራቸው ጠይቀዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-49013411 +politics በኢትዮጵያ መንግሥትና በትግራይ አመራሮች መካከል ንግግር መቀጠሉን ተመድ አስታወቀ "በኢትዮጵያ መንግሥት እና በትግራይ አመራሮች መካከል ያለው ውይይት መቀጠሉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ ረቡዕ የካቲት 02/2014 ዓ.ም ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው ይህንን የተናገሩት። ምክትል ዋና ፀሐፊዋ በጦርነቱ የተጎዱትን የትግራይ፣ የአማራና የአፋር ክልሎችን ከጎበኙ በኋላ ለሰላም ተስፋ እንዳለ የገለጹ ሲሆን ""በእርግጥከጥቂት ወራት በፊት ከነበረው አንፃር አነስተኛ ግጭቶች ናቸው የሚታዩት"" ብለዋል። ምክትል ዋና ፀሐፊዋ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ""በአሁኑ ወቅት በእርግጠኛነት የተሻለ ቦታ ላይ ነን። ተጨማሪ ውይይቶችም አሉ"" በማለት አስረድተዋል። ከትግራይ አመራሮች፣ ከአማራ እንዲሁም ከፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደረጉት አሚና መሐመድ ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። ለአስራ አምስት ወራት የዘለቀውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ ወገኖች በቅርቡ ለሰላም ያሳዩትን እርምጃ በበጎ እንደሚያዩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከቀናት በፊትም መግለጻቸው ይታወሳል። ሰላም ለማስፈን ግጭቱን እንዲሁም ተኩስ ማቆም ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ የተናገሩት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተፋላሚ ወገኖች ይህንን እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከዚህ ቀደምም ጦርነቱን ለማብቃትና ሰላም ለማውረድ የሚያስችል የሚታይ ጥረት እየተደረገ መሆኑ እንዳስደሰታቸው መግለጻቸው ይታወሳል። ዋና ፀሐፊው የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ከሆኑት ከኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት እያደረጉት ስላላው ጥረት ከሕብረቱ ተወካይ መረዳታቸውን በወቅቱ አስታውቀው ነበር። በአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ዋና ፀሐፊውን በመወከል የመንግሥታቱ ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ የተገኙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በጦርነቱ የተጎዱ የአማራና የትግራይ ክልል ከተሞችን ጎብኝተዋል። እንዲሁም ከክልል አመራሮችም ጋር ተገናኝተዋል። ምክትል ዋና ፀሐፊዋ በክልሎቹ ከሴቶችና ተማሪዎች ጋር ባደረጉት ቆይታ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወሲባዊ እንዲሁም ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን እንደማይታገስ አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል። ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች አጋርነታቸውን የገለጹት አሚና፣ በጦርነቱ ሳቢያ በሴቶች ላይ የደረሰውን ግፍና በደል እንዲሁም አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ለማቃለል ድርጅታቸው መፍትሄ በማፈላለግ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። ሴቶች ካለባቸው ህመም እንዲፈወሱ በተሃድሶ እና በመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ውስጥ እንዲካተቱም አመራሮቹን አሳስበዋል። በተጨማሪም ተመድ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሰላም ጥረትም ይደግፋል ብለዋል። ከአሚና በተጨማሪ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ሰኞ ዕለት በአማራ ክልል የኮምቦልቻ ከተማን እንዲሁም ወደ ትግራይ እና አፋር ክልሎችም በመሄድ ጉብኝት አድርገዋል። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከቀናት በፊት ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በትግራይ ክልል ውስጥ 40 በመቶ የሚጠጉ ሰዎች በአስከፊ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጿል። ከአስራ አምስት ወራት በላይ ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ ኬንያና ሌሎች አገሮች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ የተጓዙ ሲሆን የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴንጎ ኦባሳንጆም የትግራይ መሪዎችን አነጋግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥታቸው ከትግራይ ኃይሎች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን መናገራቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ወኪል (ኤፒ) ዘግቦ ነበር። የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሪ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በህወሓትና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር እየተደረገ መሆኑን ለቢቢሲ ከሳምንት በፊት ተናግረዋል። ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ይህ እየተደረገ ያለው ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት የተወሰነ ውጤት እያሳየ መሆኑንና የመሻሻል ምልክቶች እንዳሉ አመልክተው ነበር። እየተካሄደ ነው ስለተባለው ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይትን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል አስካሁን የተባለ ነገር የለም።" https://www.bbc.com/amharic/news-60319702 +politics ለሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ ለማግኘት ያሉ እድሎችና ተግዳሮቶች "በትግራይ አማፂያን ላይ ድል መቀዳጀቱ የሚገልጸው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ወደ ትግራይ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ ዕቅድ እንደሌለውና በያዛቸው ቦታዎች ተወስኖ እንዲሚቆይ ካሳወቀ ሰነባብቷል። የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው፣ ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረውና ከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ ላስከተለው የእርስ በርስ ጦርነት የሰላም ዕድል ለመስጠት በሚል ከአፋርና ከአማራ ክልሎች ጠቅልለው መውጣታቸውን ይናገራሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፋር ክልላዊ መንግሥት የህወሓት አማፂያን በሰላማዊ የክልሉ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት መክፈታቸውን እና የተወሰኑ አካባቢዎችን መቆጣጠራቸውን አሳውቋል። ይህንንም ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱ የህወሓት አማፂያን የሚያደርጉትን ትንኮሳ ለመከላከል የመከላከያ እና የክልል ፀጥታ ኃይሎች እርምጃ እንዲወስዱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በትግራይና በተለያዩ አዋሳኝ አካባቢዎች ውጊያዎች መኖራቸው የሚገጸው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በበኩሉ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ እና ሊተነበይ የማይችል እንደሆነ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ተንታኞች አንዱ ወገን የሌላውን የማድረግ አቅም ለማደከም ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው ነገር ግን በሁለቱም በኩል በጦርነት የመቀጠል ፍላጎታቸው መቀነሱን ያስረዳሉ። ያገረሹ ግጭቶች የትግራይ ኃይሎች ከሁለቱም ክልሎች መውጣታቸው የኢትዮጵያ መንግሥትም፣ ወደ ትግራይ ክልል አልዘልቅም ማለቱ በተወሰነ ደረጃ ጦርነቱ ረገብ እንዲል አድርጎታል። በአንዳንድ ድንበር አካባቢዎች ያለው አለመረጋጋት ግን ተጨማሪ ስጋት እያስከተለ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ያነሱታል። ""የሰላም ምልክት ያለ ቢመስልም አሳሳች ድምዳሜ ላይ መድረስ ግን አይገባም። ምክንያቱም ጦርነቱ ረገብ ���ልም፣ በአንዳንድ የትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ውጊያ የቀጠለበት ሁኔታ አለ። በአላማጣ፣ በማይ ጸብሪና በዓዲ ዓርቃይ አካባቢዎች ከባድ ውጊያ መካሄዱን ሰምተናል"" ይላሉ የክራይስ ግሩፕ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዊልያም ዴቪሰን። ከዊሊያም ዴቪሰን ሃሳብ ጋር የሚስማሙት የፖለቲካ ተንታኙ አደም ካሴ (ዶ/ር)፤ በበኩላቸው በአንዳንድ የድንበር አካባቢዎች የሚስተዋለው ግጭት እየታየ ያለውን የሰላም ተስፋ የሚያጨልም እንዳይሆን ስጋት እንደሆነ ይናገራሉ። ""ግጭቱን ማነው ያስነሳው የሚለው ለማወቅ ከባድ ነገር ቢሆንም፣ በትግራይ ኃይሎች በኩል ግን ወደ ሰላም ድርድር መግባታችን ስለማይቀር በምንችለው መጠን አቅሙን እናዳክመው የሚል እሳቤ ሊኖር ይችላል"" ሲሉም ያክላሉ። ""ያም ሆነ ይህ በሁለቱም በኩል በጦርነት ዓላማቸውን ለማሳካት ያለው ፍላጎት የቀነሰ ይመስላል። ሁለተኛው ነገር ስምምነት ላይ እስኪደረስ በቻሉት መጠን አንደኛው የሌላኛውን አቅም የማዳከም ጥረት እያደረጉ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ።'"" እስከ አሁን ድረስ ከፌደራል መንግሥቱ በኩል የተሰማ ነገር ባይኖርም የሰላም ዕድል መኖሩን ግን ዶክተር አደም ይገልጻሉ። ""ድምዳሜ ለመስጠት ልንቸኩል አይገባም። ምክንያቱም በትግራይ በኩል አንድ ድርጅት ነው ያለው፤ በፌዴራል በኩል ግን ብዙ ተሳታፊዎች አሉ፣ ብዙ ፍላጎቶች አሉ። በፓርቲቹ በኩል የአስተሳሰብም የአካሄድም ልዩነትም አለ"" በማለት አደም (ዶ/ር) ሁኔታውን ያስረዳሉ። የሰላምጭላንጭል ዊልያም ዴቪሰን ሁኔታው በሁለቱም ወገኖች መካከል የሰላም ፍላጎት እንዳለ የሚያመለክት ሁኔታ መኖሩን ያምናሉ። ከማሳያዎቹም ""የትግራይ ኃይሎች ከአፋርና ከአማራ ክልሎች መውጣታቸው አንዱን የፌዴራል መንግሥት ፍላጎት አሟልቷል ማለት ይቻላል።"" የፖለቲካ ተንታኙ አደም ካሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው ሁለቱም ተፋላሚ ኃይሎች አላማቸውን በጦርነት ለማሳካት ያላቸውን ፍላጎት እየተዉ መምጣታቸውን ያስረዳሉ። ""የፌዴራል መንግሥቱ ወደ ትግራይ ክልል ዘልቆ አለመግባት፣ የትግራይ ኃይሎች ደግሞ ተገድደውም ይሁን ፈቅደው ወደ ኋላ መመለሳቸው፤ ሁለቱም 'የምንፈልገውን ዓላማ በጦርነት ብቻ እናሳካለን የሚለውን ነገር ያቆሙ ይመስለኛል"" ይላሉ። ዊሊያም አክለውም የትግራይ አማፂያን ከአማራ እና ከአፋር ክልል መውጣታቸውን ተከትሎ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለተባበሩት መንግሥታት በጻፉት ደብዳቤ፤ የአማራ እና የኤርትራ ኃይሎች ከምዕራብ ትግራይ እንዲወጡና እርምጃ እንዲወሰድ መጠየቃቸው፣ በትግራይ አመራር በኩል የአስተሳሰብ ለውጥ መኖሩ የሚያመላክት ነው ይላሉ። እንዲሁም፣ በፌዴራል መንግሥት በኩል የተቃውሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራር እና አባል የሆኑ እሰረኞቹን መፍታቱ በአገሪቱ ያለው ቀውስ በሰላማዊ ድርድር እንዲያልቅ ፍላጎት እንዳለ የሚሳይ መሆኑን ይናገራሉ። አደም ካሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው ""በሥርዓትና ይፋዊ በሆነ መልኩ የተኩስ ማቆም ስምምነት እስካልታወጀ ድረስ ያለው ሁኔታ አስተማማኝ አይደለም"" በማለት ያለውን የታየውን ለውጥ ይገልጹታል። ""በእኔ እምነት ያንን ግምት ውስጥ በማስገባት ይመስላል የፌዴራል መንግሥቱ የአየር ላይ ጥቃት እያካሄደ ያለው፤ ከመደራደራችን በፊት በተቻለ መጠን የትግራይ ኃይሎች የመደራደር አቅም ማዳከም አለብን የሚል እሳቤ ያለ ይመስለኛል"" ሲሉም ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። ስጋቶችና እንቅፋቶች በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 9.4 ሚሊዮን እንደደደረሰ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ካለፈ�� ዓመት ሰኔ ወር አጋማሽ ጀምሮ ከትግራይ ለቅቆ ቢወጣም ክልሉ ""ይፋዊ ባልሆነ የሰብዓዊ እርዳታ እቀባ"" ውስጥ በመሆኑ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የማቅረቡ ሥራ አስቸጋሪ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል። ምንም እንኳ የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ የሰብዓዊ እርዳታ እንዳይደርስ ምንም አይነት እቀባ አለማድረጉን ቢገልፅም፣ በክልሉ የሚገኙ አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትም ቢሆኑም ከመድኃኒት እና አስፈላጊ ቁሳቁሶች ውጪ መሆናቸውን በመጥቀስ በቀላል ሕክምና የሚድኑ ሕሙማን ህይወታቸውን እያጡ መሆኑን ይናገራሉ። በቅርቡም በአፋር ክልል በአባላ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የተነሳ ምንም ዓይነት የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ መኪኖች ማለፍ አለመቻላቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድርጅቶች ገልጸዋል። ዊልያም ዴቪሰን በአጭር ጊዜ የሰላም ድርድር ካልተጀመረ የትግራይ ኃይሎች ይህንን 'የሰብዓዊ እርዳታ ዕቀባ' ለማስከፈት እና የትግራይ ክልልን ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት ለመመለስ፣ በተለይ በምዕራብ ትግራይ ጦርነት መክፈታቸው አይቀርም ይላሉ። ""የትግራይ ኃይሎች ወደ ኋላ ሲመለሱ ብዙ ጉዳት ደርሶባቸው ሊሆን ይችላል"" የሚል ግምት ያላቸው ዳቪሰን፣ አሁንም ድረስ ግን ከፍተኛ የጦር ኃይል እንዳለቸው ያምናሉ። ""የትግራይ ኃይሎች በማናቸውም መመዘኛ አሁንም ከፍተኛ ጦር ነው ያላቸው። እነርሱ ሕዝባቸው ላይ ተከፍቶበታል ከሚሉት 'የዘር ማጥፋት' ዘመቻ ለመከላከል የህልውና ትግል እያደረጉ እንደሆነ በጽኑ ያምናሉ።"" በተጨማሪም ""አዲስ አበባ እና አሥመራ ያሉት መንግሥታት ደግሞ የትግራይ ኃይሎች ለራሳቸውና ለሕዝባቸው ዋነኛ ስጋት አድርገው ነው የሚመለከቷቸው"" ይላሉ ዴቪሰን። ይህ በሁለቱም ወገን ያለው አመለካከት ደግሞ ለሚታሰበው የሰላም ሂደት ""ከባዱ እንቅፋቱ"" ሊሆን እንደሚችልና ""በመካከላቸው ካለው አለመተማመንና መጠራጠር አንጻር የትግራይ ኃይሎች ሠራዊታቸውን ለመበተን የሚስማሙ አይመስለኝም"" ይላሉ። አደም (ዶ/ር) በበኩሉ፣ በተለይ በአፋርና በአማራ ክልል በኩል ጦርነቱ በሰላም የማያልቅ ከሆነ መልሶ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ተጨባጭ ስጋት እንዳለ ይገምታሉ። በትግራይ በኩልም፣ የፌዴራል መንግሥቱ ወደ ትግራይ ክልል ገፍቼ 'አልሄድም' ቢልም ጥርጣሬዎች እንደሚፈጠሩ ያስገነዝባል። ለዚህ ደግሞ ""በትግራይ፣ በአፋርና በአማራ ክልል አንዳቸው ወደሌላኛው በኩል ዘልቆ የመግባት ዕቅድ እንደሌላቸው ሁሉም ማሳየት አለባቸው።"" የእስረኞች መፈታት በቅርቡ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለን ገርባ እንዲሁም አቶ እስክንደር ነጋን ጨምሮ ከፍተኛ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከእስር ተፈትተዋል። ዊልያም ዴቪሰን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የወሰዱት እሰረኞችን የመፍታት እርምጃ፣ በተለይ ሊካሄድ ለታቀደው አገራዊ ውይይት አሳታፊ እንዲሆን ለማድረግ ጉልህ ሚና እንዳለው ያምናሉ። አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ ስድስት ነባር የህወሓት አመራሮች መፈታታቸውን በተመለከተ ግን ""እምብዛም ፖለቲካዊ ትርጉም የለውም"" ይላሉ ዴቪሰን። ""እነዚህ የህወሓት የፖሊት ቢሮ አባላት ያልሆኑትን መፍታት እንደ ትልቅ ጉዳይ አድርጌ አላየውም፤ ሰላማዊ ድርድር እንዳይደርግ እንቅፋት የሆኑት ጉዳዮችን ከመቀነስ አንጻር፤ እምብዛም ለውጥ የሚያመጣ እርምጃ መስሎም አይታየኝም።"" ይህ ብቻ ሳይሆን ህወሓትና ኦነግ-ሸኔ በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአሸባሪነት መዝገብ መስፈራቸው ለሚደረጉ የሰላም ንግግሮች እና ድርድሮች እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል ሁለቱም ተንታኞች ይስማማሉ። ድርጅቶቹ ከዚህ ፍረጃ ካልወጡ በስተቀር፣ የሰላም ድርድር እንዳይደርግ እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚል ስጋትም እዚህም እዚያም ይደመጣል። ይህንን በተመለከተ ዊሊያም ዴቪሰን፣ ድርጅቶቹ ከዚህ ፍረጃ ወጥተው፣ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርጎ፣ የአገር አቀፍ መድረኩ ውስጥ እንዲሳተፉ ካልተደረገ፣ አገራዊ ውይይቱ ውጤት አያመጣም የሚል እምነት እንዳላቸው ያስረዳሉ። ማምለጥ የሌለበት ዕድል የዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ተቋማት እንዲሁም አገራት ትግራይ ውስጥ ተጀምሮ ወደ አጎራባች ክልሎች ተዛምቶ ከፍተኛ ቀውስ ያስከተለው ጦርነት በሰላማዊ መገድ እንዲፈታ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ሻክሮ የነበረው የኢትዮጵያና የአሜሪካ መንግሥታት ግንኙነት መሻሻል ሰላም ለማውረድ አዎንታዊ ሚና ሊኖረው እንደሚችል ይታመናል። ዊልያም ዴቪሰን የሰላም ሂደቱ ውጤት እንዲያመጣና ጦርነቱ እንዲቆም ግን በተለይ በትግራይ ያለውን 'የሰብዓዊ እርዳታ እቀባ' በአስቸኳይ መፈታት አለበት ይላሉ። ""ሁለቱም ወገኖች የሰላም ዕድሉ ሊያመልጣቸው አይገባም"" የሚሉት ዳቪሰን፤ ስልክ፣ መብራትና ባንክን የመሳሰሉ መሠረታዊ አገልግሎቶች መከፈት እንዳለባቸው እንደ መፍትሄ ሃሳብ ያቀርባሉ። አደም ካሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው የምዕራብ ትግራይን ጉዳይ በማንሳት በሁለቱም የፖለቲካ ተፋላሚ ወገኖች በኩል ""አስቸጋሪ የፖለቲካ ጭቅጭቅ"" ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። ""ሁለቱም ወገኖች ቢያንስ የሕግ ሥርዓቱን መከተል አለባቸው"" ነገር ግን ችግሩ የመጨረሳውን ዕልባት የሚያገኘው በፖለቲካዊ መንገድ በመሆኑ ይህም ወደተሻለ መተማመን እንደሚያደርስ በመግለጽ ሃሳባቸውን ያጠናቅቃሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-60182998 +health ኮሮናቫይረስ፡ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ እና ጭምብል ማድረግ ለዓመታት ሊዘልቅ እንደሚችል ተጠቆመ በእግሊዝ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን ማድረግ ብሎም ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ ለዓመታት ሊቀጥል እንደሚችል የአገሪቱን የክትባት ዘርፍ የሚመሩ ባለሙያ ገለፁ። በእንግሊዝ የጤና ሚኒስቴር ውስጥ የክትባት ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሜሪ ራምሴ ሌሎች አገራት የክትባት ዘመቻቸውን በስኬት እስከሚያጠናቅቁ እና ይህንንም ተከትሎ ወደ መደበኛ ህይወት ለመመለስ እነዚህ ገደቦች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም ብዙ ሰው የሚታደማቸው ዝግጅቶች ጥንቃቄ የተሞላበት የደህነንት መመሪያዎች ትግበራ እና ክትትል እንደሚያስፈልጋቸውም ተናግረዋል። ዶክተር ራምሴ እንዳሉት በተለይም ጭምብሎችን እንደማድረግ ያሉ ገደቦች በማህበረሰቡ ውስጥ ተቀባይነትን እያገኙ የመጡ ሲሆን ይህም በተለይ ኢኮኖሚው እንዲንቀሳቀስ እድል ከፍቷል ብለዋል። ‹‹ሰዎች ከእንዲህ ያሉ ገደቦች ጋር እየተለማመዱ አብረዋቸው መኖር ይችላሉ። ኢኮኖሚውም ከባድ ካልሆኑ ክልከላዎችን ጋር መንቀሳቀስ ይችላል›› ብለዋል። ‹‹የኮሮናቫይረስ ቁጥር በሌላው ዓለም እስከሚቀንስ እና ክትባት በበቂ ሁኔታ እስከሚዳረስ ድረስ እነዚህ ገደቦች በእርግጠኝነት ለተወሰኑ ዓመታት የሚቀጥሉ ሲሆን ቀስ በቀስ ወደ መደበኛ ህይወት እንመለሳለን›› ሲሉም ጨምረው ገልፀዋል። ዶክተር ራምሴ ጨምረው ቫይረስ በቀላሉ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ሊያጠቃ ስለሚችል ‹‹በችኮላ ወደ መዘናጋት መግባት የለብንም›› ሲሉም አሳስበዋል። የእንግሊዝ መንግሥት ዋና የጤና አማካሪ ፕሮፌሰር ክሪስ ዊቲ በያዝነው ወር መጀመሪየ ላይ ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ እጅ መታጠብ፣ ጭምብል ማጥለቅ፣ ምርመራ በማድረግ መለየት እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ክትባት መጀመር ቫይረሱን ከበጋው ወራት በፊት ለመቆጣጠር ያግዛል የሚል ተስፋ ተጥሎ ነበር ብለዋል። መንግሥትን የሚያማክሩ የሳይንትስቶች ቡድንም የቫይረሱን ስርጭት ሊቀንሱ የሚችሉ መሰረታዊ የሆኑ ፖሊሲዎችን መተግበር ለተወሰነ ግዜ አስፈላጊ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው ነበር። እነዚሁ ባለሙያዎች በምርመራ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መለየት፣ ራስን በለይቶ ማቆያ ውስጥ ማቆየት፣ በፈቃደኘነት የሚደረጉ እና በሽታውን አደጋዎች ለመቀነስ የሚያበረታቱ ሕዝባዊ መልዕክቶች ሊቀጥሉ እንደሚችሉም ተናግረው ነበር። የእንግሊዝ መንግሥት የእንቅስቃሴ ገደቦችን ቀስ በቀስ ለማንሳት ያዘጋጀው ፍኖተ ካርታ እንደሚለው ማህበራዊ መራራቅን የሚያስገድዱ ሕጋዊ ግዴታዎች ከሰኔ 14 በፊት እንደማይነሱ ያስረዳሉ። https://www.bbc.com/amharic/56484252 +politics ሙሴቪኒ ከአሜሪካዋ ዲፕሎማት ጉብኝት አስቀድመው ‘ማንም ትዕዛዝ አይሰጠንም’ አሉ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር የኡጋንዳ ጉብኝትን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ማንም ትዕዛዝ አይሰጠንም ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ። አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝታቸው ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም. ከኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። አምባሳደሯ ከዋሽንግተን ዲሲ መመሪያዎችን ይዘው ይመጡ እንደሆነ የተጠየቁት ሙሴቬኒ፤ “ማንም ትዕዛዝ አይሰጠንም” ሲሉ መልሰዋል። ሙሴቬኒ አገራቸው ኡጋንዳ ከምዕራባውያን የሚላከውን እርዳታ በመልካም ጎኑ እንደምትመለከተው ጠቅሰው፤ አገራቸው ያለ እርዳታ መኖር እንደምትችልም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ኡጋንዳ በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ የያዘችውን አቋም ለማስቀየር የተደረገ ጥረት እንደሌለ ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ወረራ እንድታቆም ያወጣውን ምክር ሃሳብ በድምጸ ታዕቅቦ ካለፉት 16 የአፍሪካ አገራት መካከል ኡጋንዳ አንዷ መሆኗ ይታወቃል። አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪን ፊልድ ወደ ካምፓል የሚያመሩት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኡጋንዳ ጉብኝት ካደረጉ ከቀናት በኋላ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በቅርቡ ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ አገራት ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል። ሙሴቬኒ፤ “ጥሩ ጓደኛ” ሲሉ የገለጿቸው አምባሳደር ቶማስ-ግሪንፊልድን ሁሌም ወደ ኡጋንዳ እንዲመጡ በራችን ከፍት ነው ካሉ በኋላ፤ አስተዳደራቸው ለምዕራባውያን ጫና እንደማይበረከክ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ አቋማቸው ምን እንደሆነ ሲጠየቁ፤ ጦርነቱን ከ1962ቱ የኩባ ሚሳኤል ቀውስ ጋር አነጻጸረውታል። ሙሴቪኒ ዛሬ ላይ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በሩሲያ ዙሪያ መገኘትን ሶቪየት ሕብረት አሜሪካ አፍንጫ ስር ኩባ ውስጥ ሚሳኤል ከመትከሏ ጋር አነጻጽረውታል። የኩባ ሚሳኤል ቀውስ ተብሎ የሚታወቀው ክስተት የወቅቱ የዓለማችን ኃያላንን ወደ ኒውክሌር ጦርነት እንዲገቡ ከጫፍ አድርሶ ነበር። በወቅቱ ሶቪየት ሕብርት የኩባን ደኅንነት ከአሜሪካ ጥቃት ለመጠበቅ በሚል፣ ኩባ ውስጥ የአሜሪካ ከተሞችን መምታት በሚያሰችሉ ስፍራዎች ላይ የኒውክሌር አረሮችን ማስወንጨፍ የሚችሉ ሚሳኤሎችን ተክላ ነበር። ሙሴቬኒ ይህ ክስተት የአሜሪካንን የደኅንነት ስጋት ውስጥ ከትቶ እንደነበረ ተናግረው፤ በወቅቱ አገራቸው ለአሜሪካ ድጋፏን መሽጠቷን አስታውሰዋል። ሙሴቬኒ ዛሬም ተመሳሳይ መርኅ ማረመድ አለብን ብለዋል። ሙሴቬኒ ኔቶ በሩሲያ ዙሪያ መክተሙ፤ የሩሲያን እርምጃ እንዲገነዘቡ ያደርግዎታል ወይ ተብለው ሲጠይቁ፤ “በትክክል” ሲሉ መልሰዋል። “ታሪክ የምትሉትን፤ እኔ ወቅታዊ ጉዳይ እለዋለሁ” ብለዋል ሙሴቬኒ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cl57jk5n4jeo +politics ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ወደ ሥልጣናቸው ተመለሱ "ጥቅምት ወር ላይ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው የተወገዱት የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ወደ ሥልጣናቸው መመለሳቸው ተገለጸ። በቤታቸው ውስጥ በቁም አስር ላይ የሰነበቱት ሐምዶክ ከመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን ጋር አዲስ የሥልጣን መጋራት ስምምነት ለመፈራረም ዛሬ እሁድ በአገሪቱ ቴሌቪዥን ቀርበው ታይተዋል። ከሁለት ዓመት በፊት አብደላ ሐምዶክን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የሾመው የሲቪል ፖለቲከኞች ስብስብ ግን ከወታደሮች ጋር የሚደረግን ማንኛውንም አይነት አዲስ ስምምነት እንደማይቀበለው አሳውቋል። ""የሱዳን የወደፊት ዕጣ የሚወሰነው በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ወጣቶች ነው"" ሲል የነጻነትና የለውጥ ኃይሎች የተባለው ጥምረት ቃል አቀባይ የሆነው ሲዲቅ አቡ ፋዋዝ ለቢቢሲ ተናግሯል። ከመፈንቅለ መንግሥቱ መካሄድ በኋላ የተቀሰቀሰውና ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። በዋና ከተማዋ ካርቱም ጦር ሠራዊቱ ከአገሪቱ ፖለቲካ ሙሉ ለሙሉ እንዲወጣ የሚጠይቁ ሰልፈኞች ወደ ፕሬዝዳንታዊው ቤተመንግሥት በሚያመሩበት ጊዜ የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጋዝ እንደተኮሱባቸው ተዘግቧል። በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ የሲቪል አስተዳደሩን አመራሮች ከበተነና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ መፈንቅለ መንግሥቱን ተቃውመው አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል ቢያንስ 40 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው አብደላ ሐምዶክ ""የሱዳናውያን ደም ውድ ነው፣ ደም መፋሰሱን እስቁመን ወጣቱን ኃይል ወደ ግንባታና ልማት እንምራው"" በማለት ግጭቶች እንዲቆሙ ከስምምነት መድረሳቸውን ተናግረዋል። ወደ ሥልጣን የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክና ሲቪል ሚኒስትሮቻቸው ምን ያህል ሥልጣን እንደሚኖራቸው ግን ግልጽ አይደለም። ከሥልጣናቸው የተወገዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ የተደረገው የሱዳን ጦር፣ ሲቪል መሪዎች እንዲሁም የቀድሞ አማጺያን ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ነው ሲሉ አሸማጋዮች አስታውቀዋል። ይህ ስምምነት ቅዳሜ ምሽት የተደረሰ ሲሆን እሁድ ከሰዓት በኋላ ነው ተግባራዊ የተደረገው። ምሁራን፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም ፖለቲከኞች የተካተቱበት አሸማጋይ ቡድን የስምምነቱን ይዘት ለሕዝብ ይፋ አድርጓል። ይዘቱ እንደሚያትተው በቁጥጥር ሥር የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክና የካቢኔ አባሎቻቸው ይለቀቃሉ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደግሞ ወደ ሥልጣናቸው ይመለሳሉ። አክሎም ሱዳን ወደ ዲሞክራሲ የምታደርገው ሽግግር እንደሚቀጥል ይዘቱ ያትታል። የሱዳን ሲቨል መሪዎችና የአገሪቱ ጦር ላለፉት ሁለት ዓመታት በሥልጣን ክፍፍል ሳቢያ እሰጥ-አገባ ውስጥ ነበሩ። የሱዳን ጦር ወደ ሥልጣን የመጣው ለረዥም ዓመታት ሱዳንን የመሩት ፕሬዝደንት ኦማር አል-ባሽር ከመንበራቸው ከተወገዱ በኋላ ነው። አገሪቱን በጋራ ለመምራት ሥልጣን የተረከቡት ወታደራዊው ኃይልና የሲቪሉ መንግሥት በበርካታ ጉዳዮች ሊስማሙ አልቻሉም ነበር። ባለፈው ወር የጦር ኃይል ጄኔራል የሆኑት አብደል ፋታህ አል ቡርሐን ሲቪሉን መንግሥት መበተናቸውንና ባለሥልጣናቱን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው ይታወሳል። ጄኔራሉ ክስተቱ ""መፈንቅለ መንግሥት አይደለም የእርስ በርስ ጦርነትን ለማስቀረት እንጂ"" ካሉ በኋላ አዲስ ምክር ቤት አቋቁመው ራሳቸውን የበላይ አድርገው ሾመው ነበር። ከዚህ የፖለቲካ ውጥንቅጥ በኋላ ዋና ከተማዋ ካ���ቱምን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሕዝባዊ አመጽ የተቀጣጠለ ሲሆን ይህንንም ለመመከት የተሰማራው የአገሪቱ ጦር ሰልፈኞች ላይ ተኩሷል ተብሎም ተወቅሷል። ሱዳናዊያን ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እሑድ ቀነ ቀጠሮ ይዘው ሰልፍ ከመውጣታቸው በፊት ነው ስምምነቱ ይፋ የሆነው። ወታደራዊው መንግሥት ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ አገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንዲመልሳት ከባድ ጫና ሲደረግብት የቆየ ሲሆን፤ የአፍሪካ ሕብረት አገሪቱን ከአባልንት ሲያግድ የዓለም ባንክ ደግሞ ለሱዳን ሊሰጥ ያቀደውን ድጋፍ አግዷል። ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን ተወግደው የሽግግር አስተዳዳር ከተመሰረተ በኋላ በሠራዊቱ መሪዎችና በሲቪል ባለሥልጣንት መካከል አለመግባባት የቆየ ሲሆን፤ በዚህ ወር አል ቡርሐን ሥልጣናቸውን ለሲቪል መሪ ያስርክባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነው መፈንቅለ መንግሥት ያካሄዱት።" https://www.bbc.com/amharic/news-59365382 +sports ዋልያዎቹ በቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ወሳኝ 90 ደቂቃዎች ቀራቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማደጋስካርን በሰፊ የግብ ልዩነት ካሸነፈ በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለመግባት አንድ ቀጣይ ጨዋታ ብቻ ቀረው። ብሔራዊ ቡድኑ በአሁኑ ጊዜ የምድቡን መሪነት የያዘ ሲሆን በቀጣይ ከኮትዲቯር ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ከዓመታት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የመሳተፍ እድል ይኖረዋል። ዋልያዎቹ ረቡዕ መጋቢት 15/2013 ዓ.ም ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በባሕር ዳር ላከተማ ባደረገው ጨዋታ የማደጋስካር አቻቸውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ በቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ የመሳተፍ እድላቸው ከፍ ብሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትናንት ከሰዓት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታ ማዳጋስካርን 4 ለ 0 በማሸነፍ የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት ጀምሯል። ግቦቹን አማኑኤል ገብረሚካኤል ፣ጌታነህ ከበደ፣ አቡበከር ናስር እና ሽመልስ በቀለ አስቆጥረዋል። በዋሊያዎቹ ምድብ ውስጥ የሚገኙት ኮትዲቯር እና ኒጀር ነገ የሚጫወቱ ሲሆን፤ የጨዋታው ውጤት እስከሚታወቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደረጃ ሰንጠረዡን በ9 ነጥብ መምራቱን ይቀጥላል። በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኮትዲቯር፣ ማደጋስካር እና ኒጀር ጋር የተመደበችው ኢትዮጵያ፤ በመጀመሪያው ጨዋታ በማደጋስካር አንድ ለባዶ ተሸንፋ የነበረ ሲሆን በቀጣይ በባሕር ዳር በተደረገ ጨዋታ ኮትዲቯርን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። በመቀጠል ዋልያዎቹ ወደ ኒጀር ተጉዘው፤ አንድ ለባዶ ቢሸንፉም በመልሱ ጨዋታ ሦስት ለባዶ ማሸነፍ ችለዋል። በወዳጅነት ጨዋታ በቀላሉ ማላዊን በሰፊ የጎል ልዩነት ያሸነፉት ዋልያዎቹ ከማደጋስካር ጋር በነበራቸው የምድብ ጨዋታ ደግሞ አራት ለባዶ በማሸነፍ ነው ምድቡን በዘጠኝ ነጥብ መምራት የቻሉት። በምድቡ ወሳኝ ጨዋታ ነገ አርብ ኮትዲቯር ከኒጀር የሚያደርጉት ሲሆን ጨዋታው በኮትዲቯር አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ ኢትዮጵያ በምድቡ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ ትላለች። ጨዋታው በኒጀር አሸናፊነት አልያም አቻ የሚጠናቀቅ ከሆነ ደግሞ ዋልያዎቹ መሪነታቸውን አስጠብቀው ወደ መጨረሻው የምድብ ጨዋታ ይጓዛሉ ማለት ነው። ዋልያዎቹ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታቸውን መጋቢት 21/2013 ዓ.ም ወደ ኮትዲቯር ተጉዘው የሚያደርጉ ሲሆን ማደጋስካር ከኒጀር የሚያደርጉትም ጨዋታ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። ኢትዮጵያ ኮትዲቯርን የምታሸንፍ ከሆነ በካሜሩን አዘጋጅነት በሚካሄደው ጨዋታ ተሳታፊነቷን የምታረጋግጥ ሲሆን፤ ማደጋስካር ከኒጀር የሚያደርጉት ጨዋታ በኒጀር አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ ደግሞ ሰፊ የማለፍ እድል ይኖራታል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ዓመት በተራዘመው 33ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ከወዲሁ አምስት አገራት ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። እነዚህም አገራት አዘጋጇ ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ማሊ እና አልጄሪያ ናቸው። https://www.bbc.com/amharic/56520048 +politics ቶማስ ሳንካራ፡ 'የአፍሪካውን ቼ ጉቬራ' ማን ገደለው? "ከሠላሳ አራት ዓመት ገደማ በፊት የወቅቱ የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ቶማስ ሳንካራ አስደንጋጭ ግድያ የተፈጸመበት። እነሆ አሁን ከ34 ዓመት በኋላ ""የአፍሪካው ቼ ጉቬራ"" በመባል በሚታወቀው ሰው ግድያ ተባባሪ በመሆን 14 ሰዎች ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት ቀርቡ። የባለግርማ ሞገሱ የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ እአአ ጥቅምት 15/1987 በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት በወታደሮቹ ነበር በጥይት ተገደለው። ይህን ተከትሎ የቅርብ ጓደኛው ብሌዝ ኮምፓዎሬ ወደ ሥልጣን መጣ። ከግድያው ከአራት ዓመት ቀድም ብሎ ሳንካራና ካምፓዎሬ ሳንካራን ፕሬዝዳንትነት ያበቃውን መፈንቅለ መንግሥት መርተዋል። ኮምፓዎሬም ከ14ቱ ተከሳሾች መካከል ነበር። በጎረቤት አይቮሪ ኮስት በግዞት የሚገኘው ኮምፓዎሬ እአአ በ2014 በተካሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሥልጣኑን ለቆ ነው የተሰደደው። ነገር ግን በሳንካራ ግድያ ውስጥ እጁ እንደሌለበት በተደጋጋሚ አስተባብሏል። በፍርድ ሂደቱ እንደማይገኝም አስታውቋል። ምንም እንኳን ጊዜው ቢቆይም ሳንካራ በመላው አፍሪካ እንደ ተምሳሌት ሆኖ ይታያል። በምዕራብ አፍሪካ ታክሲዎችን በምስሉ ያስጌጣሉ። የደቡብ አፍሪካው የተቃዋሚ መሪ ጁሊየስ ማሌማ ከምሳሌዎቹ አንዱ አድርጎ ሳንከራን ይጠቅሳል። ሳንካራ ለምን እንደ ጀግና ይታያል? የቶማስ ሳንካራ የመታሰቢያ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ ሉክ ዳሚባ ""ለእኛ ሳንካራ ጀግናችን ነበር። ሕዝቡን ይወዳል። አገሩን ይወዳል። አፍሪካን ይወዳል። ሕይወቱን ለእኛ ሰጥቷል"" ብለዋል። አገሪቱ በእሱ የስልጣን ዘመን ነበር ከአፐር ቮልታ ወደ ቡርኪና ፋሶ ስያሜዋን የቀየረችው። ትርጉሙ ""የቀና ሰዎች ምድር"" ማለት ነው። ሳንካራ ቅንጡ የሚባል የአኗኗር ዘይቤ አልነበረውም። የራሱን እና የመንግሥት ሠራተኞችን ደመወዝ ሁሉ ቀንሷል። የመንግሥት ሹፌሮችን እና አንደኛ ደረጃ የአየር መንገድ ትኬቶች እንዳይጠቀሙም አግዷል። ለትምህርት ቅድሚያ ይሰጥ ነበር። ሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ በአገሪቱ ማንበብ እና መጻፍ የሚችሉ ሰዎች በ1983 ከነበረበት 13 በመቶ በ1987 ወደ 73 በመቶ አድጓል። እንዲሁም ግዙፍ ብሔራዊ የክትባት ዘመቻን በበላይነት መርቷል። ከፊውዳል ባለንብረቶችም መሬት በቀጥታ ለድሃ ገበሬዎች አከፋፍሏል። ይህም የስንዴ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርጓል። ተባበረችው አፍሪካ የ""ኒዮ-ቅኝ አገዛዝ"" ተቋማት ብሎ ከጠራቸው እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ተቃራኒ እንድትቆም ጥሪ ያቀርብ ነበር። አንድ ጊዜ ""የሚያበላህ ይቆጣጠርሃል"" ሲል መናገሩ ይጠቀሳል። አፍሪካ ውስጥ እንደ ቡርኪና ፋሶ ባሉ በርካታ ቅኝ ግዛቶቿ ከፍተኛ ተጽዕኖ የነበራትን የፈረንሳይን የበላይነት የሚገዳደር የፀረ-ኢምፔሪያሊስት የውጭ ፖሊሲን ይፋ አደረገ። ፈረንሳይን እሱን ለመግደል ፊታውራሪ ነበረች ስትል ባለቤቱ ማሪያም ትከሳለች። በኡጋዱጉ የሚገኘው የቶማስ ሳንካራ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ለቢቢሲ እንደተናገረው ""እሱ ፕሬዝዳንቴ ሆኖ ይኖራል። ለሕዝቡ ያደረገው ነገር እኛ ወጣቶች እሱ ያደረገውን እንድናደርግ ያበረታታናል"" ብሏል። በዋና ከተማዋ ኡጋዱጉ በሚገኘው ቶማስ ሳንካራ የመታሰቢያ ፓርክ ውስጥ ስድስት ሜትር ርዝማኔ ያለው የነሐስ ሐውልት እ.ኤ.አ. በ2019 ይፋ ተደርጓል። የመጀመሪያው ሐውልት ላይ ቅሬታዎች በመነሳታቸው ባለፈው ��መት በድጋሚ ተሠርቷል። ዳሚባ እንዳሉት ፓርኩን ለማስፋፋት ዕቅድ ተይዟል። ኦዋጋዱጉን ወደታች የሚመለከት 87 ሜትር ከፍታ ያለው ማማ ደግሞ አንዱ ነው። ለሳንካራ መቃብር ቤት፣ የሲኒማ አዳራሽ እና በስሙ የተሰየመ የሚዲያ ቤተ መጽሐፍትም ይኖራል። እነዚህ ማስታወሻዎች የሳንካራን አብዮታዊ ሃሳቦች ለትውልድ ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ተቺዎቹስ? የሳንካራ አክራሪ የግራ ክንፍ ፖሊሲዎች በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተተችቷል። እአአ በ 1986 አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ዘገባ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ናቸው የተባሉ ሰዎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባቸዋል። በሳንካራ መንግሥት ውስጥ የመረጃ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ሰርጌ ቴኦፊል ባልማ ""የብዝሃነት ዴሞክራሲ ሃሳብን ለመቀበል በጣም የዘገየ ይመስለኛል። ተቃዋሚዎቹን ለማናገርና እና ሊያዳምጣቸው አልቻለም"" ብለዋል። ፕሮፌሰር ባሊማ አክለውም ""ለሕዝብ ሥልጣን መስጠት ስለፈለገ የሕዝቡን ግላዊና ሕዝባዊ የህይወት ዘይቤ በተገቢው መንገድ ለመምራት ለተመለመሉት የአብዮቱ መከላከያ ኮሚቴዎችን [ሲዲአር] ለሚመሩት ሠርቶ አደሮች ሥልጣን ሰጠ። በእውነቱ እነሱም የእሱን ሥልጣን ያጠለሹ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ ተገኝተዋል።"" እአአ በ 2020 ከአፍሪካ ሪፖርት ድርገጽ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት እና በሳንካራ ከስልጣን የተባረሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዣን-ባፕቲስት ኦውድራጎ ""በግል ፍላጎት እና የፖለቲካ ማኪያቬሊያኒዝም"" በባህሪው ውስጥ ቦታ እንዳላቸው ገልጸዋል። የፍርድ ሂደቱ ለምን ረዥም ጊዜ ፈጀ? ወንድሙ ፖል ሳንካራ ""የ27 ዓመታቱ የብሌዝ ኮምፓዎሬ አገዛዝ ተጨምሮበት ረዥም ጊዜን ጠብቀናል። በእሱ አገዛዝ ዘመን ፍርድ አለ ብለን እንኳን ማለም አልቻልንም"" ብሏል። ሚስቱ ስለባለቤቷ ግድያ እአአ በ1997 የወንጀል ቅሬታ ብታቀርብም ምርመራው ሊቀጥል ይችላል የሚለውን ለመወሰን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ 15 ዓመት ፈጅቶበታል። ሆኖም ኮምፓዎሬ እአአ በ2014 ከስልጣን እስኪወርዱ ድረስ ብዙም ፈቀቅ አላለም ነበር። በቀጣዩ ዓመት የእሱ ነው የተባለ አስከሬን ተቆፍሮ ቢወጣም በዘረመል (ዲኤንኤ) ምርመራ የእሱ መሆኑን ማረጋገጥ አልተቻለም። እአአ በ2016 የቡርኪናፋሶ ባለሥልጣናት የፈረንሳይ መንግሥት ስለ ሳንካራ ግድያ ያለውን ወታደራዊ ሰነዶችን እንዲለቅን በይፋ ጠይቀዋል። እነዚያ ሰነዶች በሦስት ደረጃ ወደ ቡርኪና ፋሶ ተዛውረዋል። የመጨረሻው ኦጋዱጉ የደረሰው እአአ ሚያዝያ 2021 ነው። በፍርድ ሂደቱ ላይ ሌላ ማን ይቀርባል? የኮምፓዎሬ የቀድሞው አዛዥ ጄኔራል ጊልበርት ዲንዴሬ እና ሌሎች 11 ሰዎች በወታደራዊው ፍርድ ቤት እንደሚገኙ ይጠበቃል። ""የመንግሥትን ደኅንነት በማጥቃት""፣ ""በግድያ ተባባሪነት"" እና ""አስከሬን በመደበቅ"" ክስ ይቀርብባቸዋል። እአአ በ2015 ባልተሳካው መፈንቅለ መንግሥት ሚና ነበረው በሚል ዲንዴሬ 20 ዓመት ተፈርዶበት በእስር ላይ ይገኛል። ከተከሳሾቹ መካከል የሞት የምስክር ወረቀቱን የፈረመው ዶክተር ዲቤሬ ዣን ክሪስቶፍ ይገኝበታል። ሐኪሙ የቀድሞው ፕሬዚዳንት በተፈጥሯዊ ምክንያቶች ሞተዋል ሲል ፈርሟል። ሐኪሙ የሕዝብ ሰነድ በማጭበርበር ክስ ቀርቦበታል። በሌለበት የሚከሰሰው የኮምፓዎሬ የቀድሞ የደኅንነት ኃላፊ ሂያሲን ካፋንዶ ነው። ዓለም አቀፉ የእስራት ማዘዣ ወጥቶበታል። ሳንካራን እና ሌሎች 12 ሰዎችን የገደለውን ቡድን በመምራት ክስ ተመስርቶበታል። የፍርድ ሂደቱ ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል? ከአልቃይዳ እና ከእስላማዊ መንግሥት ቡድን ጋር የተቆራኙ የጂሃዲስት ቡድኖች የሚያደርሱባትን ተደጋጋሚ ጥቃቶች እየታገለች ያለችው ቡርኪና ፋሶ የፍርድ ሂደቱ የበለጠ እንዳ��ረጋጋ ሊያደርጋት ይችላል የሚል ሥጋት አለ። ኮምፓዎሬ አሁንም በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያለው ሲሆን የእሱ ታማኝ የሆኑ የወታደር ክፍሎች ችግር ሊቀሰቅሱ እንደሚችሉ አንዳንድ ተንታኞች አስጠንቅቀዋል። ይህ ስለመሆኑ ግን ትንሽ ምልክት ነው ያለው። በተቃራኒው ፕሬዝዳንት ሮች ማርክ ካቦሬ የፍርድ ሂደቱ ውጥረትን አቃሎ ብሔራዊ ዕርቅን ያጠናክራል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። በኢንተርናሽናል ክራይወሲስ ግሩፕ የሳህል ተንታኝ የሆነው ማቲው ፔሌሪን ""እንዲህ ዓይነቱ ፍርድ አለመረጋጋትን ሊያዳብር ይችላል ብዬ አላምንም"" ሲል እአአ በ2020 ለፈረንሳዩ መጽሔት ጁን አፍሪክ ተናግሯል። አክሎም ""ያለ ፍትህ ዕርቅ እምብዛም አይገኝም"" ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58867138 +sports ላሚን ዲያክ፡ የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚደንት በሙስና ወንጀል የ4 ዓመት እስር ተፈረደባቸው "የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (አይኤኤኤፍ) የቀድሞ ፕሬዚደንት ላሚን ዲያክ፤ በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው አራት ዓመት በእስር እንዲያሳልፉ ውሳኔ ተላለፈባቸው። ሌሎች ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ከሥራ መታገዳቸው ተገልጿል። የ87 ዓመቱ ሴኔጋላዊ ከአበረታች መድሃኒት ጋር ተያይዞ በሙስናና በገንዘብ ዝውውር ነው ክስ የቀረበባቸው። ዲያክ አበረታች መድሃኒት ይጠቀማሉ ተብለው ከተጠረጠሩ አትሌቶች የምርመራ ውጤታቸውን ለመደበቅ እና የ2012ቱ የለንደን ኦሎምፒክን ጨምሮ ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ ጉቦ በመቀበል ጥፋተኛ ተብለዋል። የቀድሞ ፕሬዚደንቱ የ500 ሺህ ዩሮ ቅጣትም ተጥሎባቸዋል። ዲያክ የአትሌቶቹን ጉዳይ ለመሸፋፈን ከ3 ሚሊየን ዩሮ በላይ ገንዘብ ተቀብለዋል የሚል ክስ ከቀረበባቸው በኋላ የፈረንሳይ ባለሥልጣናት ለ አራት ዓመታት ምርመራ ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ውሳኔውን ያስተላለፉት ዳኛም የቀድሞ ፕሬዚደንቱን ድርጊት ""የአትሌቲክስን እሴትና አበረታች መድሃኒት ላይ የሚደረገውን ትግል የጣሰ "" ብለውታል። ዲያክ ከህዳር 2015 ጀምሮ በፓሪስ በቁም እስር ላይ ነበሩ። የቀድሞ ፕሬዚደንቱ በዓለም ስፖርት የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ግለሰቦች አንዱ የነበሩ ሲሆን በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌደሬሽኖች ማህበር በአሁኑ የዓለም አትሌቲክስ ለ16 ዓመታት አገልግለዋል። በእንግሊዛዊው ሎርድ ሴባስቲያን ኮ የተተኩትም ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-54181586 +business ማኅበራዊ ሚዲያ፡ ኡጋንዳውያን ለሚጠቀሙት የኢንተርኔት አገልግሎት ታክስ መክፈል ጀመሩ ኡጋንዳውያን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ከዛሬ ሐሙስ ዕለት ጀምሮ የሞባይል ዳታ 12 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ መክፈል ጀመሩ። ይህ ታክስ እአአ በ2018 የተዋወቀውና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጣለውን የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ዕለታዊ ታክስ [ኦቲቲ] ን ተክቷል። አዲስ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ ተግባራዊ መሆን የጀመረው አዲስ የበጀት ዓመት መጀመሩን ተከትሎ ነው። ኤክሳይዝ ታክስ በተመረጡ እቃዎች ወይም አገልግሎቶች፤ በተለይም የቅንጦት ተብለው በሚታሰቡት ላይ የሚጣል ቀጥተኛ ያልሆነ የታክስ ዓይነት ነው። ይህ ታክስ የተዋወቀው በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ ምክር ቤት ማሻሻያ ከተደረገበት በኋላ ነው። ለሕክምና እና ለትምህርት አገልግሎት ለሚገዛ የሞባይል ዳታ ላይ ታክሱ አይጣልም ተብሏል። ይሁን እንጅ ይህንን አገልግሎት ከሌላው እንዴት መለየት እንደሚቻል ግልፅ ያለ ነገር የለም። እአአ ሐምሌ 2018 የማኅበራዊ ሚዲያ ታክስ ተቃውሞን ቀስቅሶ ነበር። ተቃውሞው በተቃዋሚው ፖለቲከኛውና ሙዚቀኛ ሮበርት ክያጉላኒ ወይም ቦቢ ዋይን የተመራ ነበር። በወቅቱ ተቃውሞው የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እር��ጃ ተበትኗል። አብዛኞቹ ኡጋንዳውያን ቪፒኤን የተባለውንና እገዳውን ለማለፍ የሚያስችሉ መተግበሪያዎችን ኢንተርኔትን ለመጠቀም አማራጭ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የሚጠበቀውን ያህል ግብር መሰብሰብ ሳይቻል ቀርቷል። የአገሪቷ የገቢዎች ባለሥልጣን በ2018 - 2019 የበጀት ዓመት ለመሰብሰብ አቅዶ ከነበረው 80 ሚሊየን ዶላር፤ መሰብሰብ የቻለው 14 ሚሊየን ዶላር መሆኑን በዚያው ዓመት አስታውቆ ነበር። ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ላይ ታክስ መጣል በኡጋንዳ፤ በተለይም አነስተኛ ንግዶችን ለመጀመር በብዛት ኢንተርኔትን የሚጠቀሙ ወጣቶችን አስቆጥቷል። https://www.bbc.com/amharic/news-57682386 +politics በአሜሪካ ምክር ቤት መሪዎች መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ "በአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲና የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት የብዙሃን መሪው ሚች ማኮኔል መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ። ካሊፎርኒያ ውስጥ ከሚገኘው የናንሲ ፔሎሲ ቤት ውጪ አንገቱ የተቆረጠ አሳማና ደም የሚመስል ቀለም የተገኘ ሲሆን ግድግዳውም በተለያየ ጽሁፍ ተበላሽቶ ተገኝቷል። ኬንተኪ ውስጥ በሚገኘው የሪፐብሊካኑ ማኮኔል ቤት ግድግዳ ላይ ደግሞ ""ገንዘቤ የታለ"" የሚል ጽሁፍና የስድብ ቃላት ተጽፈው ተገኝተዋል። ይህ በባለስልጣናቱ መኖሪያ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የተከሰተው በኮሮናቫይረስ ምክንያት ያጋጠመውን ችግር ለመቅረፍ በቀረበው የድጋፍ ዕቅድ ላይ በምክር ቤት ከባድ ፖለቲካዊ ውዝግብ መካሄዱን ተከትሎ ነው። ባለፈው ማክሰኞ በዲሞክራቶች በሚመራው የአሜሪካ ምክር ቤት የ40 ሪፐብሊካን አባላት ድጋፍን በማግኘት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ገቢያቸው ለተጎዳ ዜጎች እንዲሰጥ ሐሳብ ቀርቦበት የነበረውን የ600 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ወደ 2000 ዶላር ከፍ እንዲል ተወስኖ ነበር። ምንም ችንኳን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን ረቂው የምክር ቤት አባላቱ እንዲያጸድቁ ቢጠይቁም በሪፐብሊካኖች የሚመራው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ከፍተኛ የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀውን በጀት ሳይቀበለው ቀርቷል። ረቡዕ ዕለት ሚች ማኮኔል እንደተናገሩት በሚደረግ ማንኛውም ጫና ""በብድር የሚገኘውን ገንዘብ ድጋፉ ለማያስፈልጋቸው ለዲሞክራት ሐብታም ወዳጆች በጥድፊያ እንዲሰጥ አናደርግም"" ሲሉ ተደምጠው ነበር። ሚች ማኮኔል ቅዳሜ በቤታቸው ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ባወጡት መግለጫ ላይ ""ቢስማሙም ባይስማሙም"" በምክር ቤቱ የሥራ ሂደት ወቅት የተሳተፉትን በሙሉ አመስግነዋል። ጨምረውም ""ይህ የተለየ ጉዳይ ነው"" በማለት የተፈጸመውን ጥቃት በመቃወም ""ንብረት ማውደምና ጉዳት ማድረስ እንዲሁም ፍርሃት ለመፍጠር የሚደረገው ፖለቲካም በማኅበረሰባችን ውስጥ ቦታ የለውም"" ብለዋል። የሳንፍራንሲስኮ ፖሊስ በአፈጉባኤዋ ቤት ላይ በተፈጸመው ጥቃት ዙሪያ ምርመራ እያደረጉ ሲሆን ፔሎሲ ግን እስካሁን ምንም አስተያየት አልሰጡም። ባለፈው አርብ የአሜሪካ ምክር ቤት በፕሬዝዳንት ትራምፕ የስልጣን ዘመን አጋጥሞ በማያውቅ ሁኔታ የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። በቅርቡ በተደረገው ምርጫ ለአሜሪካ ምክር ቤት አባልነት የተመረጡ የኮንግረስ አባላት ዛሬ እሁድ ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-55516801 +politics ጦርነት እንዲቆም የሰላም ጥሪ ለማቅረብ የተጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ታገደ በአገሪቱ ባሉ በርካታ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲቆም የሰላም ጥሪ ለማስተላለፍ የተጠራ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይካሄድ በፀጥታ ኃይሎች መታገዱ ተገለጸ። ጋዜጣዊ መግለጫውን ከጠሩት 35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የመብቶች እና የዴሞክራሲ እድገት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ኃይሉ፤ መግለጫ ሊሰጥበት በነበረው ሆቴል ሲቪል የለበሱ የመንግሥት የፀጥታ ኃይል አባላት ነን ያሉ ግለሰቦች መግለጫውን መስጠት አይቻልም በማለት ከልክለዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “የትኛው የመንግሥት አካል ክልከላውን እንደፈጸመ አልተነገረንም። እንዲሁ በጥቅሉ ይህን መግለጫ መሰጠት የለባችሁም የሚል መልዕክት ብቻ ነው የተላለፈልን” ብለዋል አቶ በፈቃዱ። ቢቢሲ ስለጉዳዩ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ምላሽ ጠይቆ ኮሚሽኑ ስለክልከላው የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የገለጸ ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊስ ምላሽን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ግን አልተሳካም። የመንግሥት የፀጥታ ሰዎች ነን ያሉት ግለሰቦች ጋዜጣዊ መግለጫውን ለመዘገብ በሆቴሉ ተገኝተው የነበሩ ጋዜጠኞችም መግለጫው እንደማይካሄድ በመግለጽ እንዲያሰናብቱ ለሆቴሉ ሠራተኞች ተናግረዋል ሲሉ አቶ በፍቃዱ ተናግረዋል። “ለማካሄድ አቅደን የነበረው የአደባባይ ስብሰባ ስላልነበረ ቀድመን ማሳወቅ አይጠበቅብንም ነበር” ያሉት አቶ በፍቃዱ፤ ወደፊት ማን ለምን እንደከለከለን ለማጣራት እንሞከራለን ብለዋል። 35ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሊሰጡት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ መከልከሉን ተከትሎ “ይህ ዓይነቱ አሠራር የሕግ የበላይነትን የሚፃረር ከመሆኑ ባሻገር የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለሰላም ሊጫወቱ የሚገባቸውን ድርሻ ይነፍጋል” በማለት ደርጊት እንዲታረም ጠይቀዋል። 35ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአንድ ስፍራ ተገኝተው ሊያስተላልፉት የነበረውን መልዕክት በጋዜጣዊ መግለጫ አሰራጭተዋል። በዚህም በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልል የተዛመተው ጦርነት አገሪቷን እና ሕዝቧን ለሰብዓዊ እና ቁሳዊ ከፍተኛ ኪሳራ ዳርጓል ብለዋል ሲቪል ማኅብራቱ። አክለውም ተፋላሚ ወገኖች ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ አቁም ማድረጋቸው እና ለሰላም ድርድር ፍላጎት ማሳየታቸው ትልቅ ተስፋ እንዲሰንቁ አድርጓቸው እንደነበር አመልክተው፣ ይሁንና ጦርነቱ ዳግም ማገርሸቱ በእጅግ እንዳሳዘናቸው ግልጸዋል። ከሰሜኑ ጦርነት ባሻገር በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በአንዳንድ የደቡብ ክልል አካባቢዎች ግጭቶች እየተካሄዱ ነው ያሉት ማኅበራቱ፤ ግጭቶቹ በሕይወት የመኖር መብትን ጨምሮ መሠረታዊ የዜጎችን መብቶችን ከመንፈጋቸው ባሻገር የአገርን ኅልውናን የሚፈታተኑበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ብለዋል። ስለሆነም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያለው ጦርነት እና በሌሎችም አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ ቆመው፤ “ሐቀኛ፣ ሰላማዊና የግጭቶቹ ተሳታፊ አካላትን በሙሉ ያካተቱ የእርቅ ንግግሮች እንዲጀመሩ” ጠይቀዋል። በትግራይ እና ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች የተቋረጡ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች በአፋጣኝ እንዲጀመሩ እና ሰብዓዊ ዕርዳታ ያለ እንቅፋት እንዲደርስ የጠየቁ ሲሆን፤ በጦርነት ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ያደረሱ አካላት ላይ ምርመራ ተደርጎ የተጠያቂነት እርምጃ ይወሰድ ሲሉ ጠይቀዋል። ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ለአምስት ወራት ያህል ጋብ ብሎ ከቆየ በኋላ ከሁለት ሳምንት በፊት ዳግም ተቀስቅሷል። ቀደም ባለው ጦርነት ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመትን ያስከተለው ግጭት፣ ዳግም ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ መንግሥትና የትግራይ ኃይሎች በአስቸኳይ ድርድር እንዲጀምሩ ጥሪ እያደረጉ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cjqvwwxyljjo +business ዛፍ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይረዳል? ዛፍ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይረዳል? https://www.bbc.com/amharic/news-49165027 +health ኮቪድ-19: በእ��ራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ለተከታታይ 10 ወራት ሞት አልተመዘገበም "ፈጣን የክትባት ዘመቻ እያካሄደች ያለችው እስራኤል ለ10 ተከታታይ ወራት በኮቪድ-19 ምክንያት ሞት አለመመዝገቧን አስታወቀች። በአገሪቱ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች አሃዝ 6ሺህ 346 ሆኖ ሳይቀየር ለወራት መዝለቁን የእስራኤል ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። በእስራኤል በጥር ወር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረው የወረርሽኙ ስርጭት አሁን ላይ ቅናሽ አሳይቷል። የኮቪድ-19 ክትባት በሰፊው መሰጠቱን ተከትሎ የእስራኤል መንግሥት የእንቅስቃሴ ገደቦችን እያላላ ይገኛል። በርካታ ዜጎቻቸውን ከከተቡ አገራት መካከል እስራኤል ተጠቃሽ ናት። እስከ ሐሙስ ብቻ አምስት ሚሊዮን የኮቪድ -19 ክትባቶችን ሰጥታለች። ዘጠኝ ሚሊዮን ገደማ ከሚሆነው የሃገሪቱ ህዝብ ቁጥር ከ53 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሁለት ዙር ክትባቶችን እንደወሰዱ የጤና ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ሚኒስትሩ ጁሊ ኤደልስቴይን አርብ ዕለት በትዊተር ገጻቸው ""ይህ ለጤናው ስርዓት እና ለእስራኤል ዜጎች ትልቅ ስኬት ነው። በጋራ የኮሮናቫይረስን እናጠፋለን"" ብለዋል። በእስራኤል ትልቅ በሆነው የሼባ ሕክምና ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ኤያል ሌሸም እንዳሉት አገሪቱ ወደ ""ሄርድ ኢሙኒቲ"" ልትደርስ ተቃርባለች ብለዋል። ከፍተኛ መጠን ያለው ሕዝብ በሽታውን የመከላከል አቅም ሲያዳብሩ የቫይረሱ ስርጭት ይገታል፤ ይህም 'ሄርድ ኢሙኒቲ' ይባላል። የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች 'ሄርድ ኢሙኒቲ' ደረጃ ላይ ለመድረስ አገራት ከ65-70 በመቶ የሚሆነው ሕዝባቸውን መከተብ ይኖርባቸዋል ይላሉ። ተጨማሪ ገደቦች መነሳታቸውን ተከትሎ በእስራኤል የቫይረሱ ስርጭት መቀነስ ብቸኛው ምክንያት 'ሄርድ ኢሙኒቲ' ነው ብለዋል ሌሸም። እስራኤል ፋይዘር እና ባዮንቴክ የተሠራውን እና ሁለት ጊዜ የሚሰጠውን ክትባት እየሰጠች ነው። የእስራኤል ጤና ሚኒስቴር በየካቲት ወር እንደገለጸው ሁለቱንም ዙር የፋይዘር ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ የቫይረሱ ህመም በ95.8 በመቶ ቀንሷል።" https://www.bbc.com/amharic/56870712 +politics ቦሪስ ጆንሰን የካቢኔ አባሎቻቸው ሥራ መልቀቃቸውን ተከትሎ ጫና በረታባቸው የዩናይትድ ኪንግድም (ዩኬ) ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው አስተዳደራቸውን ተችተው ሥራ መልቀቃቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብተዋል። የገንዘብ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እና የጤና ሚኒስትር የነበሩት ሳጂድ ጃቪድ በ10 ደቂቃ ልዩነት ሥራቸውን በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ተቺዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ ሕይወት “አብቅቶለታል” ያሉ ሲሆን ሌበር ፓርቲ ደግሞ የቦሪስ ጆንሰን አስተዳደር በብልሹ አሰራር የተሞላ ነው ብሏል። በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ እያለፉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 29/2014 ዓ.ም. ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በፓርላማ ይገኛሉ። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የመተማመኛ ድምጽ የተሰጠባቸው ቦሪስ ጆንሰን፤ ምንም እንኳ ተቃውሞ ቢበዛባቸውም በሥልጣናቸው እንደሚቆዩ ገልጸዋል። ሥልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው በለቀቁት ሁለቱ የካቢኔ አባላት ምትክም ሌሎች ፖለቲከኞችን ሾመዋል። የጤና ሚኒስትር የነበሩት ሳጂድ ጃቪድ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተዳደር ብሔራዊ ጥቅምን ባማከል ሁኔታ አገር እየመራ አይደለም ሲሉ፤ የገንዘብ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ሕዝቡ መንግሥት አገሪቱን በአግባቡ እንዲያገለግል ይጠብቃል ብለዋል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የቦሪስ ጆንሰን ካቢኔ አባላት ሁለቱን ግለሰቦች በመከተል ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ እየጠየቁ ይገኛሉ። ወግ አጥባቂው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አንድር ሚሼል የቦሪስ ጆንሰን ጉዳይ “አብቅቶለታል” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ምንም እንኳ የምክር ቤት አባሉ ይህን ይበሉ እንጂ፣ አሁንም በርካታ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔ አባላት ድጋፋቸውን ለቦሪስ ጆንሰን እንደሰጡ ናቸው። ከእነዚህም መካከል ቦሪስ ጆንሰንን በመተካታ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ የመሆን ዕድል አላቸው የሚባሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሯ ሊዝ ትረስ ይገኙበታል። ሚንስትሯ፤ 100 ፐርሰንት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፌን እስጣለሁ ብለዋል። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶሞኒክ ራብ እና መከላከያ ሚኒስትሩ ቤን ዋላስ በሥራቸው እንደሚቀጥሉ ከገለጹት መካከል ይገኙበታል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c6pw4q7p371o +sports ክርስቲያኖ ሮናልዶ በከፍተኛ ደረጃ 800 ግቦችን ያስቆጠረ ብቸኛው ተጫዋች ሆነ "የፖርቹጋል እና የማንስችተር ዩናይትድ አጥቂው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በከፍተኛ ደረጃ በታሪክ 800 ጎሎችን ያስቆጠረ ተጫዋች ሆነ። ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትላንት ማንቸስተር ዩናይትድ አርሰናልን 3 ለ 2 ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለቱን ግቦች በማግባቱ 800 ግቦች ያስቆጠረ በታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል። ሮናልዶ ለአገሩ እና ለተጫወተባቸው ክለቦች 1097 ጊዜ ተሰልፎ 801 ግቦች ያስቆጠረ ተጫዎች መሆን ችሏል። ሮናልዶ ለዩናይትድን በሁለት የተጫዋችነት ዘመናት 130 ግቦችን ሲያስቆጥር ለስፖርቲንግ ሊዝበን 5፣ ለሪያል ማድሪድ 450፣ ለጁቬንቱስ 101 እና ለፖርቹጋል 115 ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል። ይህም ተጫዎቹን በወንዶች አለም አቀፍ እግር ኳስ፣ በሻምፒዮንስ ሊግ እና በሪያል ማድሪድ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እንዲሆን አድርጎታል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አግቢ አላን ለሮናልዶ ያለውን አድናቆት ለሺረር ለአማዞን ፕራይም ተናግሯል። ""ይህ የእርሱ ቁርጠኝነት ነው። ከፍተኛ ደረጃ መድረስ በጣም ከባድ ነው። እንደገና ከፍ ብሎ መቆየትም አለ። በጠዋት ተነስተህ እንደገና መጎዝ አለብህ። ዓለም ሁሉ በየሳምንቱ ስትጫወት ማየት ይፈልግል። ይህን አስደናቂ ነገር ነው ያደረገው።"" የሮናልዶ ዩናይትድ እና ፖርቱጋል የቡድን አጋር ብሩኖ ፈርናንዴዝ ደግሞ ""አስደናቂ ነው። ሁላችንም ከዓመት ዓመት ከጨዋታ ጫዋታ እያሻሻለ እንደሆነ እናውቃለን። ምርጥ ሆኖ መቀጠል ይፈልጋል፤ ያደረገውም ያንን ነው"" ብሏል። የብራዚል ስመ ገናና ተጫዋቾች ፔሌ እና ሮማሪዮ በየግላቸው ከ1ሺህ በላይ ጎሎችን አስቆጥረዋል ይላል። ይሁን እንጂ ይፋዊ ባልሆኑ እና በዋዳጅነት ጨዋታዎች ላይ ያስቆጠሯቸው ጎሎች ቢቀናነሱ ያስቆጠሩት የጎል መጠን ወደ 700ዎች ይወርዳል። ሊዮኔል ሜሲ 756 ጎሎችን ለአርጀንቲና፣ ባርሴሎች እና ፓሪስ አስቆጥሯል።" https://www.bbc.com/amharic/59515621 +business ኬንያ በአንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር የሰራችውን የባቡር መንገድ ልትመርቅ ነው "ኬንያ የባቡር መንገዷ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን የኬንያ ባቡር መንገድ በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል። አዲሱ የኬንያ የባቡር መስመር ከመዲናዋ ናይሮቢ ወደ ናይቫሻ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል። መስመሩ ለጊዜው አገልግሎት የሚሰጠው ለሰዎች ሲሆን የጭነት ማጓጓዝ አገልግሎት ደረቁ ወደብ እስኪገነባ ድረስ ይጠበቃል ተብሏል። •የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል? •""ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው"" መስፍን ነጋሽ ግንባታውም ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚወስድም ተገምቷል። ለዚህም በአካባቢው የሚኖሩ የማሳይ ማህበረሰብ ግንባታውን በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ በመውሰዳቸው እንደሆነ ተገልጿል። በቻይና ኮሚዩኒኬሽንና ግንባታ ኩ���ንያ የተገነባው ይህ መስመር 120 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው ሲሆን 1.4 ቢሊዮን ዶላር ፈጅቷል። የተጓዦች አገልግሎት ከአስራ ሁለቱ ጣቢያዎች በአራቱ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀመር ዘ ቢስነስ ደይሊ ኒውስፔፐር የኬንያ የባቡር አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት ፊሊፕ ማይንጋን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። የመጀመሪያው የባቡር መንገድ ከመዲናዋ ናይሮቢ ወደ ሞምባሳ ከሁለት አመት በፊት በተመረቀበት ወቅት ከፍተኛ ደስታና ፈንጠዝያ የነበረ ሲሆን ይህ መስመር ግን እንደ መጀመሪያው አልሆነም ተብሏል። በወቅቱም ኬንያ ለምርጫ ስትዘጋጅ ነበር። •በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የሞቱ ሰዎች አጽም ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው • በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ የአዲሱ የባቡር መንገድ ዋጋ ከአለም አቀፉ ስታንዳርድ አንፃር ጋር ሲታይ ሶስት እጥፍ እንዲሁም መጀመሪያ ያወጣል ተብሎ ከተገመተው አራት እጥፍ ነው ተብሏል። መንግሥት ዋጋው እንዲህ ለምን ናረ ለሚለው የሰጠው ምክንያት የመልክአ ምድሩ አስቸጋሪነት ድልድዮችንና ቱቦችን በመገንባት ላልታሰበ ወጪ እንደተዳረጉ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ለመሬት ካሳ ተከፍሏል ተብሏል። ከዚህ ወጪ ውስጥ 80% የተገኘው ከቻይና በተገኘ ብድር ነው። የባቡር መስመሩ የመጀመሪያ እቅድ ከሞምባሳ- ኪሱሙን በመሻገር ኡጋንዳ ይደርሳል ተብሎ ነበር። አገሪቷ ይህንን የባቡር መስመር ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ብድር ያስፈልጋታል ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-50065673 +health ሐሰተኛ መድኃኒት በግብፅ ሕጻናትን ገደለ በግብፅ ሐሰተኛ አንቲባዮቲክስ የተሰጣቸው በርካታ ልጆች መሞታቸው ተገለጸ። አንድ የሁለት ዓመት ሕጻን ከፍተኛ ሙቀት ገጥሞት ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ሐኪሞች መርፌ ወግተውት ሕይወቱ አልፏል። ልጁ የተወጋው መድኃኒት ሐሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል። የግብጽ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፣ ባለፈው ወር ብቻ 160 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ሐሰተኛ መድኃኒቶች ተይዘዋል። የሐሰተኛ መድኃኒት ስርጭት በተለያዩ አገራት እየተስፋፋ ይገኛል። የአሜሪካው ‘ጆርናል ኦፍ ትሮፒካል ሜድስን ኤንድ ሀይጅን’ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት መሠረት በሐሰተኛ መድኃኒቶች በዓመት 300 ሺል ሕጻናት ይሞታሉ። የግብፅ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ ሴፍትሪአግዞን የተባለው አንቲባዮቲክስ ጥቅም ላይ እንዳይውል እያሳሰቡ ነው። ካፍር ዚያት በተባለው ከተማ ፈቃድ የሌላቸው ፋብሪካዎች ላይ ፍተሻ ተደርጓል። ሐሰተኛ መድኃኒት ከሚበዛባቸው የመድኃኒት ዓይነቶች መካከል አንቲባዮቲክስ ይጠቀሳል። ጥቅምት ላይ በጋምቢያ ወደ 70 የሚጠጉ ሕጻናት የሕንድ ምርት የሆነ የሳል መድኃኒት ወስደው ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ፣ የሕንድ የጤና ባለሥልጣናት የሕጻናቱ ሕይወት እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል የተባለውን የሳል መድኃኒት የሚያመርተው ተቋም ምርቱን እንዲያቆም ማገዷ ይታወሳል። ከዚያ በኋላ ግን መድኃኒቶቹ ምንም ብክለት እንደሌላቸው ሕንድ ገልጻለች። የዓለም ጤና ድርጅት ግን አራት መድኃኒቶች ላይ ተቀባይነት የሌለው የተበከለ ኬሚካል እንደተገኘ አሳውቋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/czdy794z1nvo +politics የአማራ እና አፋር ክልላዊ መንግሥታት ሕዝቡ የህወሓት አማፂያንን 'እንዲመክት' ጥሪ አቀረቡ "የአፋር ክልላዊ መንግሥት ነዋሪዎች ታጥቀው የትግራይ አማፂያንን እንዲመክቱ ጥሪ አቅርቧል ሲል ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘገበ። ""እያንዳንዱ አፋር መሬቱን በተቻለው መንገድ ሊጠብቅ ይገባል። በጥይትም ይሁን፣ በዱላ አሊያም በድንጋይ"" ሲሉ የክልሉ ፕሬዝደንት አዎል አርባ ተናግረዋል ሲል ኤኤፍፒ አስነብቧል። ""የ��ኛውም መሣሪያ ዝቅ እንድንል ሊያደርገን አይችልም። ይህንን ጦርነት በጠንካራ ኃይላችን እንረታዋለን።"" የአማራ ክልል ብሔራዊ መንግሥት የህወሓት አማጺያንን ለመውጋት የክተት አዋጅ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል። የህወሓት አማፂያን ትግራይ እና አፋር ድንበር አቅራቢያ ጥቃት ስለመክፈታቸው በስፋት ተዘግቧል። የአፋር ክልል አደጋ መከላከል ኃላፊ ባለፈው ሳምንት ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች በግጭቱ ተፈናቅለዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ኤኤፍፒ ደግሞ አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ከ20 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል ሲል ዘግቧል። የአማፂያኑ ቃል አቀባይ ግታቸው ረዳ በአፋር ክልል ያለውን ኦፕሬሽን ለመንግሥት ወግነው አፋር ክልል ውስጥ በሚዋጉ የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች ላይ የተሰነዘረ ""በጣም የተገደበ"" ጥቃት ነው ብለው ነበር። ነገር ግን የአፋር ክልል ፕሬዝደንት ይህ ሃሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል። ""አንዳንድ ሰዎች አማፂያኑ የወረሩን የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን ስላስጠለልን ነው ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ይህ ከእውነት የራቀ ነው። እነሱ ከኢትዮጵያ በኃይል ሊገነጥሉን ይፈልጋሉ"" ብለዋል። በተያያዘ ዜና የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ሕዝቡ መሣሪያውን በመታጠቅ የሕወሓት ኃይሎችን ""እንዲመክት"" ጥሪ አቅርበዋል። ፕሬዝደንቱ በክልሉ ቴሌቪዥን ቀርበው ባወጁት ክተት ""በመንግሥትም ሆነ በግላቸው መሣሪያ የታጠቁ ሰዎች ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ"" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ፕሬዝደንት አገኘሁ ተሻገር ""ከተሠለፈብን ጠላት አኳያ ብዙ ኃይል የምናሰልፍበትና ሎጅስቲክስ የሚያስፈልግ ነው"" ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። በተያያዘ ዜና በ6ኛው አገራዊ ምርጫ የፖርላማ መቀመጫ ካሸነፉ ጥቂት ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በአማራ ክልል መንግሥት የታወጀውን የክተት አዋጅ ጥሪን ተቀብያለሁ ብሏል። ፓርቲው "". . . በጠላትነት የተፈረጀውን ህዝባችን ለመታደግ የአወጀውን የክተት ጥሪ በሙሉ ልብ የምንቀበለውና ለተግባራዊነቱም የበኩላችን ከፍተኛ ጥረት የምናደርግ መሆኑን እየገለፅን የክልሉ መንግስትም አልፎ አልፎ የሚታዩ አስተዳደራዊ ችግሮችን በመፍታት የመሪነት ሚናውን በተገቢው መንገድ እንዲወጣ እንጠይቃለን"" ብሏል ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ። የድጋፍ ሰልፎች ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በበርካታ የአገሪቱ ከተሞች ሰልፎች ተካሂደዋል። የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ፣ በዳንሻ ከተማ፣ በጎንደር እና እንጅባራ ለአገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፉ እና ህወሓትን የሚቃወሙ ሰልፎች መካሄዳቸውን ዘግቧል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ለአገር መከላከያ ሠራዊት አጋርነትን ለማሳየት ያለመ ህዝባዊ ሰልፍ በአፋር ክልል ሰመራ-ሎግያ፣ አይሳኢታና አበአላ ከተሞች መካሄዱን ዘግቧል። በሠመራ-ሎግያ ከተማ በተካሄው ሰልፍ ላይ በከተማው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ተሳትፈውበታል ሲል ኢዜአ ጨምሮ ዘግቧል። ከቀናት በፊት በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ የተካፈለበት የአገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ እና ህወሓትን የሚቃወም ሰልፍ መካሄዱ ይታወሳል። ስምንት ወራት የዘለቀው በሕወሓትና በመንግሥት መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት ከትግራይ አልፎ ወደ ሌሎች ክልሎች እየተስፋፋ ነው። የተባበሩት መንግሥታት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ ግጭት ሞተዋል፤ በመቶ ሺዎች የሚሆኑ ደግሞ ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል ይላል። የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም አዋጅ አውጆ ከትግራይ አካባቢዎች ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ የህወሓት አማጺያን የክልሉን በርካታ ስፍራዎች መልሶ መያዝ ችሏል��" https://www.bbc.com/amharic/news-57966979 +politics ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የመረጧቸው ተተኪ ባለማሸነፋቸው እንዳዘኑ ገለጹ "የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሥልጣናቸውን ለቀጣዩ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በደስታ እንደሚያስረክቡ ቢናገሩም የመረጧቸው ተተኪ ራይላ ኦዲንጋ አገሪቱን ለመምራት የተሻሉ ነበሩ ብለዋል። “ሥልጣኔን ፈገግ ብዬ አስረክባለሁ ምክንያቱም ሕገ መንግሥታዊ ግዴታዬ ነው፤ ነገር ግን መሪዬ ባባ ናቸው።"" ሲሉ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ራይላ ኦዲንጋን በቅፅል ስማቸው በመጥራት አሞካሽተዋቸዋል። አክለውም “ አገሪቱን ወደ አንድነት ለማምጣት የነበረውን ዕድል ነው የተከላከላችሁት እንጂ ራይላን አይደለም የከለከላችሁት” በማለት በምርጫው ውጤት የተሰማቸውን ኃዘን ገልጸዋል። ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ያቀረቡት ተቃውሞ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርጓል። በመሆኑም ቀጣዩ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን ያረጋገጡት ዊሊያም ሩቶ በመጪው ማክሰኞ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ እስካሁን ለምክትላቸው የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት ባያስተላልፉም የሥልጣን ሽግግሩን በተመለከተ በትናንትናው ዕለት ውይይት አድርገዋል። ሁለቱ መሪዎች ሐሙስ ፓርላማው ከመከፈቱ  በፊት ከየፓርቲዎቻቸው ጋር ተገናኝተዋል። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ፣ ራይላ ኦዲንጋን እጩ ፕሬዚዳንት አድርጎ የነበረው የአዚሚዮ ጥምረት ሊቀመንበር ናቸው። ሁለቱም ወገኖች የሁለቱን ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤነት እንዴት ማሸነፍ እንደሚችሉ ስትራቴጂ እየነደፉ ነው። ሁለቱም ፓርቲዎች በፓርላማ ውስጥ አብላጫ ድምፅ አላገኙም። ተመራጩ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ ወሳኝ የሆኑ ፖሊሲዎችን ለማሳለፍ፣ የካቢኔ እጩዎችን፣ ዋና ጸሐፊዎችን፣ አምባሳደሮችን እና ከፍተኛ ኮሚሽነሮችን ለመሾም አብላጫ ድምጽ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c251x3vr8jzo +business "አየር መንገዶች ""ከምድራችን ይልቅ ጥቅማቸውን ያስቀድማሉ"" የሚል ክስ ቀረበባቸው" "በብሪቲሽ አየር መንደገድ ውስጥ የሚሰራ አንድ የዘርፉ ባለሙያ እንዳጋለጠው፤ በአየር መንገድ ኢንዱስትሪ ውስጥ ሆነ ተብሎ አውሮፕላኖች ብዙ ነዳጀ ጭነው እንዲጓዙ ይደረጋል። ይህም አውሮፕላኑ በሚይዘው ክብደት ልክ ብዙ ነዳጅ ተቃጥሎ አየር እንዲበከል እየተደረገ ነው ተብሏል። አየር መንገዶች አውሮፕላኖቻቸው ከመነሻቸው ብዙ ነዳጅ ጭነው የሚነሱት በመዳረሻ አየር መንገዶች ለነዳጅ የሚጠየቁትን ብዙ የነዳጅ ገንዘብ ለማስቀረት ነው። ብሪቲሽ አየር መንገድ ""ለደህንነት እና ከዋጋ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች"" ተጨማሪ ነዳጅ ይዞ መብረር የተለመደ ነው ብሏል። ቢቢሲ ፓኖራማ የተሰኘው የቢቢሲ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ባለፈው ዓመት የብሪቲሽ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ተጨማሪ ነዳጅ ይዘው በመብረራቸው ተጨማሪ 18ሺህ ቶን ካርበን ዳይኦክሳይድ አመንጭተዋል ሲል መዘገቡ ይታወሳል። አንድ ጥናት እንዳረጋገጠው ደግሞ አውሮፓ ውስጥ ከሚደረጉ ከአምስት በረራዎች ቢያንስ በአንዱ አውሮፕላኑ ተጨማሪ ነዳጅ ይዞ ወደ መዳረሻው ይበራል። ተቺዎች እንደሚሉት ይህ ተግባር አየር መንገዶች የአየር ብክለትን ለመቀነስ እንሰራለን የሚሉትን ቃል ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው። ከተቺዎቹ መካከል አንዱ የሆኑት ጆህን ሳኡቨን አየር መንገዶች ""ከምድራችን ይልቅ ጥቅማቸወን ያስቀድማሉ"" ለምንለው ይህ ትክክለኛ ማሳያ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-50371705 +politics ተጭበርብሯል ተብሎ በተተቸው የሩስያ ምርጫ የፑቲን ፓርቲ አሸነፈ "የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፓርቲ በምክር ቤት አብላጫ ድምጽ በማግኘት ምርጫውን አሸነፈ። ምንም እንኳን ምርጫው ተጭበርብሯል ተብሎ ቢተችም በፑቲን የሚመራው ዩናይትድ ራሽያ ፓርቲ ወደ 50% ድምጽ አግኝቷል። የፑቲን ቀንደኛ ተቺዎች በምርጫው እንዳይሳተፉ ከመታገዳቸው ባሻገር መራጮች ድምጽ እንዲሰጡ እንደተገደዱና የምርጫ ኮሮጆ ውስጥ የተጭበረበሩ ድምጾች እንደተገኙ ተገልጿል። የሩስያ ምርጫ ኮሚሽን በበኩሉ ምርጫው ተጭበርብሯል በማሉን አስተባብሏል። ከፑቲን ፓርቲ ጋር በዋነኛነት የተፎካከረው ኮምኒስት ፓርቲ 19% ድምጽ አግኝቷል። ስለዚህም የፑቲን ፓርቲ ከምክር ቤቱ 450 መቀመጫዎች መካከል ከሁለት ሦስተኛው በላይ የሚሆኑትን ይቆጣጠራል። እአአ በ2016 በተካሄደው ምርጫ ፓርቲው 54% ድምጽ ነበር ያገኘው። ዘንድሮ ያገኘው ድምጽ በመጠኑም ቢሆን ቀንሷል። ምክር ቤት ውስጥ የፑቲንን ፓርቲ ሐሳብ ከሞላ ጎደል የሚደግፈው ኮምኒስት ፓርቲ ባለፈው ምርጫ 6% ድምጽ አግኝቶ ነበር። ዘንድሮ ግን የመረጡት ሰዎች ቁጥር ከፍ ብሏል። አሶሽየትድ ፕረስ እንደዘገበው፤ የኮምኒስት ፓርቲ መሪ ጌንዳይ ዚጋኖቭ ምርጫው በተለያዩ አይነት የማጭበርበሪያ መንገዶች የተሞላ ነበር ሲሉ ተችተዋል። የምርጫ ኮሚሽን ኃላፊ ኤላ ፓምፊቮላ የፊታችን አርብ አጠቃላይ ውጤት ይፋ ይደረጋል ብለዋል። ሩስያ ውስጥ ያለው ፈታኝ የኑሮ ሁኔታ እንዲሁም አስተዳደሩ በሙስና ተዘፍቋል የሚሉ ክሶች የፑቲን ደጋፊዎች ቁጥር እንዲቀንስ ማድረጋቸውን ተንታኞች ይናገራሉ። በተለይም እስር ላይ የሚገኘው የፑቲን ተቺ አሌክሲ ናቫልኒ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። በሌላ በኩል ፑቲን ለምዕራባውያን ጫና የማይንበረከኩ እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስቀድሙ ናቸው የሚለው አመለካከት ብዙ ሩስያውያን ፕሬዝዳንቱን እንዲደግፉ አድርጓቸዋል። ትላንት በቴሌቭዥን የቀረቡት ፑቲን መራጩን ሕዝብ አመስግነዋል። ፓርቲያቸው ምርጫውን ያሸነፈው በነጻና ፍትሐዊ የምርጫ ሂደት እንደሆነ ያምናሉ። የናቫንሊ ደጋፊዎች ደግሞ ምርጫውን እንደማይቀበሉት ገልጸው ተቃውሞ ጠርተዋል። የናቫንሊ ደጋፊዎችን ጨምሮ ፑቲን ላይ የሰላ ሂስ ያሰሙ የነበሩ ተቃዋሚዎች በምርጫው እንዲሳተፉ አልተፈቀደላቸውም። በምርጫ ሂደቱ መራጮች ላይ ጫና እንደተደረገ፣ የምርጫ ታዛቢዎች ማስፈራሪያ እንደደረሳቸው እና የምርጫ ኮሮጆ ውስጥ የተጭበረበሩ ድምጾች እንደተገኙ ተገልጿል። መራጮች ከአንድ በላይ የድምጽ መስጫ ወረቀት ኮሮጆ ውስጥ ሲከቱ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችም ሾልከው ወጥተዋል። እንደ መዲናዋ ሞስኮ ባሉ ከተሞች የድምጽ መስጫ ሰዓት ሲቃረብ ድምጽ የሚሰጠው በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ነው በማሉም ጥያቄ አስነስቷል። ሚካሂል ሎባኖቭ የተባለ የኮምኒስት ፓርቲ አባል የፑቲን ፓርቲ ""እንዲህ ያለው ውጤት ሊያገኝ እንደማይችል አውቃለሁ"" ሲል ትዊት አድርጓል። ሰኪውሪቲ ኤንድ ኮኦፕሬሽን ኢን ዩሮፕ የተባለው ተቋም ምርጫውን እንዳይታዘብ በሩስያ መንግሥት እገዳ ተጥሎበታል። ተቋሙ ከ1993 ወዲህ የሩስያን ምርጫ ሳይታዘብ ሲቀር የዘንድሮው የመጀመሪያው ነው። የአውሮፓ ሕብረት ቃል አቀባይ ምርጫው በተገቢው ሁኔታ ቁጥጥር አልተደረገበትም ብለው ተችተዋል። የዩናይድት ኪንግደም፣ የጀርመን እና የአሜሪካ መንግሥታትም ምርጫው ነጻና ፍትሐዊ አልነበረም ብለዋል። ገለልተኛው እና ጎሎስ የተባለው ምርጫ ታዛቢ ቢያንስ 5,000 የተጭበረበሩ ድምጾች እንዳሉ ሪፖርት ደርሶኛል ቢልም የሩስያ መንግሥት ድርጅቱን ""የውጪ ኃይሎች ተላላኪ"" ሲል አጣጥሎታል። የናቫልኒ ቃል አቀባይ ኪራ ያራምሽ ""2011 ላይ እንዳደረጉት ሁሉ አሁንም ምርጫውን አጭበረበሩ"" ስትል ቃሏን ሰጥታለች። አንድ የጸጉር ቤት ሠራተኛ ""ድምጽ የመስጠት ጥቅሙ አይታየኝም። እነሱ እንደሆነ ምርጫውን እንደሚያሸንፉ ቀድመው ያውቃሉ"" ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች።" https://www.bbc.com/amharic/58634883 +sports ኮቢ ብራያንት ሕይወቱን ያጣበት ሄሊኮፕተር አደጋ የምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ ታዋቂው አሜሪካዊ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብራያንትና ታዳጊ ሴት ልጁን ጨምሮ 9 ሰዎች አሳፍሮ የተከሰከሰው ሄሊኮፕተር አደጋ ሪፖርት ይፋ ሆኗል። ሪፖርቱ ዘጠኙም ተሳፋሪዎች ለሞት የበቁት ሰውነታቸው ላይ በደረሰ ከባድ ግጭት ሳቢያ ነው ብሏል። 180 ገፆች ያሉት ይህ ሪፖርት የሄሊኮፕተሯ አብራሪ የ50 ዓመቱ አራ ዞባያን አደንዛዥ ዕፅም ሆነ የአልኮም መጠጥ አልወሰደም ሲል ደምድሟል። ባለፈው ጥር በአሜሪካዋ የካሊፎርኒያ ግዛት የተከሰተው የሄሊኮፕተር አደጋ መንስዔ ምን እንደሆነ አሁንም እየተጣራ ነው። አነስተኛዋ ሄሊኮፕተር ስትከሰከስ የአየር ሁኔታው ደመና እንደነበር ይታወሳል። ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብራያንትና የ13 ዓመት ልጁ ጂያና ከዘጠኙ ተሳፋሪዎች መካከል ነበሩ። ከእነሱ በተጨማሪ ሁለት የጂያና እኩያ ሴት ቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች፣ ቤተሰቦቻቸውና አሠልጣኛቸው ሄሊኮፕተሯ ውስጥ ነበሩ። ተሳፋሪዎቹ ለታዳጊ ሴቶች የቅርጫት ኳስ ፍልሚያ ነበር ታውዘንድ ኦክስ ወደ ተሰኘው ሥፍራ ሲያቀኑ የነበረው። ዘጠኙንም ሰዎች ያሳፈረችው ሄሊኮፕተር በሰሜናዊ ሎስ አንጀለስ የሚገኝ ተራራ ላይ የተከሰከሰችው። ሪፖርቱ የሁሉም ሟቾች የሞት ምክንያት አደጋ ነው ሲል ደምድሟል። የድህረ-አደጋ ምርመራው በከተማዋ ጤና ጉዳዮች ድረ-ገፅ ላይ በይፋ ተሰቅሏል። አምስት ጊዜ የአሜሪማካ ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮን መሆን የቻለው ኮቢ ብራያንት ዕድሜውን ሙሉ ኤልኤ ሌከርስ ለተበላው ቡድን ነው የተጫወተው። በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ማሕበር [ኤንቢኤ] ታሪክ ከታላላቅ ተጫዋቾች መካከል የሚመደብ ነው። ለ20 ዓመታት ቅርጫት ኳስ የተጫወተው ኮቢ በፈረንጆቹ ሚያዝያ 2016 ነበር ቅርጫቱን የሰቀለው። የኮቢ ብራያንት ባለቤት ቫኔሳ ብራያንት ጠበቆች የሄሊኮፕተር አብራሪውን ድርጅት ከሰዋል። ክሱ፤ አብራሪው ለበረራ ከመነሳቱ በፊት የአየር ሁኔታውን አላጣራም ይላል። የሎስ አንጀለስ ከተማ ፖሊስ መርማሪዎች በአደጋው ሥፍራ ተገኝተው እጅግ አሰቃቂ ፎቶዎች ማንሳታቸውን አምነው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ፎቶዎቹን ከማሕህሮቻቸው እንዲያጠፉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-52689130 +politics የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ስለታይዋን ምንም ነገር ሳይሉ ጉብኝታቸውን ጀመሩ የአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት ናንሲ ፔሎሲ የቻይናን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ታይዋን የጉብኝታቸው አካል ትሁን አትሁን ምንም ነገር ሳይገለጽ ወደ እስያ ተጓዙ። ፔሎሲ በጉዟቸው ሴንጋፖርን፣ ማሌዢያን፣ ደቡብ ኮሪያን እና ጃፓንን እንደሚጎበኙ ጽህፈት ቤታቸው የገለጸ ሲሆን፣ ቻይና የግዛቴ አካል ናት የምትላትን ታይዋንን ግን ሳይጠቅስ አልፏታል። አፈ ጉባኤዋ ጉብኝት እንደሚያደርጉ በተገለጸበት ጊዜ ወደ እራስ ገዟ ታይዋን ሊጓዙ እንደሚችሉ በስፋት ሲወራ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ታይዋን የግዛቴ አካል ናት የምትለው ቻይና፣ ፔሎሲ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ “ከባድ መዘዝ” እንደሚከተል አስጠንቅቃለች። ባለፉት 25 ዓመታት አንድም ከፍተኛ ሥልጣን ያለው በሕዝብ የተመረጠ የአሜሪካ ባለሥልጣን ታይዋንን ጎብኝቶ አያውቅም። የዲሞክራቲክ ፓርቲ ተመራጯ ናንሲ ፔሎሲ ጉብኝታቸውን በተመለከተ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት፣ የአገሪቱ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን ስድስት አባላት “በአካባቢው ላሉ ወዳጆቻችንና አጋሮቻችን አሜሪካ ያላትን የማይወላውል አቋም የምናጸናበት ነው” ብለዋል። የአፈ ጉባኤዋ ጽህፈት ቤት ጉዞውን በተመለከተ እንዳለው፣ ጉብኝቱ “ሴን���ፖር፣ ማሌዢያ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓንን ጨምሮ የኢንዶ-ፓሲፊክ አካባቢን” የሚመለከት ነው ብሏል። ቻይና ታይዋን ወደ እናት አገሯ መመለስ ያለባት አፈንጋጭ ግዛቷ እንደሆነች ትመለከታታለች። ይህንንም ለማሳካት ወደፊት ቤይጂንግ ኃይል መጠቀምን እንደ አንድ አማራጭ ታየዋለች። የቻይና ባለሥልጣናት አሜሪካ ከታይዋን ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እያደረገች ነው በሚል ቁጣቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል። ባለፈው ሚያዚያ ወርም ስድስት የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት በታይዋን ድንገተኛ ጉብኝት አድርገው ነበር። አሜሪካ ከቻይና ጋር እንጂ ከታይዋን ጋር መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት የላትም። ናንሲ ፔሎሲ በቻይና የሰብአዊ መብት አያያዝ የተነሳ የአገሪቱን መሪዎች ለረጅም ጊዜ ሲተቹ ቆይተዋል። በተጨማሪም ከዲሞክራሲ ደጋፊ ቻይናውያን ጋር የተገናኙ ሲሆን፣ የታይናሚን አደባባይ ጭፍጨፋ ሰለባዎችን ለማስታወስ አደባባዩን ጎብኝተዋል። አፈ ጉባኤዋ ታይዋንን ለመጎብኘት አቅደው የነበረው ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ የነበረ ቢሆንም፣ በኮቪድ በመያዛቸው ጉዟቸውን አዘግይተውት ቆይተዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት “ለታይዋን ያለንን ድጋፍ ማሳየት ለእኛ አስፈላጊ ነገር ነው” ብለው ተናግረውም ነበር። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአሜሪካ ጦር ኃይል ፔሎሲ ወደ ታይዋን ሊያደርጉ ያሰቡት ጉብኝት “በአሁኑ ወቅት ጥሩ ሃሳብ አይደለም” ብሎ እንደሚያምን ተናግረዋል። ከአፈ ጉባኤዋ ጽህፈት ቤት ዛሬ እሁድ የወጣው መግለጫ ጉዞው “በኢንዶ-ፓሲፊክ አካባቢ ስላላው የጋራ የደኅንነት፣ ምጣኔ ሀብታዊ አጋርነት እና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ላይ የሚያተኩር ይሆናል” ብሏል። በውይይቱ ላይ ንግድ፣ የአየር ፀባይ ለውጥ እና የሰብአዊ መብት ጉዳዮችም እንደሚነሱ ተነግሯል። ከፔሎሲ ጋር በጉዞው የሚሳተፉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋነኛ አባላት የሆኑት ግሪጎሪ ሚክስ፣ ማርክ ታካኖ፣ ሱዛን ዴልቤኔ፣ ራጃ ክሪሽናሙርቲ እና ኤንዲ ኪም ናቸው። ታይዋንን የጎበኙ የመጨረሻው የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሪፐብሊካኑ ኒውት ጊንግሪች ሲሆኑ፣ እሱም በአውሮፓውያኑ 1997 ነበረ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1jlkx1lzro +business በኢትዮጵያ ከባንኮች በሚወጣ የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ተጣለ "ኢትዮጵያ ከባንኮችና ከማክሮ ፋይናንስ ተቋማት በሚወጣ የጥሬ ገንዘብ ላይ ገደብ መጣሏን አስታወቀች። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ይፋ ባደረገውና ተግባራዊ በሚሆነው መመሪያው መሰረት ተቋማትና ግለሰቦች ከባንኮች በቀንና በወር ውስጥ ከባንኮች በሚያወጡት የጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ተጥሏል። በዚህም መሰረት አንድ ግለሰብ በቀን እስከ 200 ሺህ ብር እንዲሁም በወር እስከ 1 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ከባንኮች ማውጣት የሚችል ሲሆን፤ ተቋማት ደግሞ በቀን እስከ 300 ሺህ ብር እና በወር እስከ 2.5 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ይህንን እርምጃ በተመለከተ እንደተናገሩት ""የገንዘብ ዝውውርን ሥርዓት በማስያዝ ወንጀልንና የግብር ስወራን ለመከላከል ይረዳል"" ማለታቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በጥሬ ገንዘብ ዝውውር ላይ የተጣለውን የመጠን ገደብ በተመለከተ የወጣው መመሪያ እንዳመለከተው ግን ከተቀመጠው መጠን በላይ ለማንቀሳቀስ ለሚፈልጉ በገንዘብ ተቋማቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች በኩል የሚያቀርቡት ምክንያት ተመርምሮ እንደሚፈቀድላቸው ተገልጿል። በተጨማሪም የመጠን ገደብ ከተጣለበት በላይ ጥሬ ገንዘብ ለሚያንቀሳቅሱ ግለሰቦችና ተቋማት ከአንድ ሒሳብ ወደ ሒሳብ፣ በቼክ፣ወይም በሲፒኦ ተጨማሪ ገንዘብ ማዘዋወር እንደሚችሉም ተመልክቷል። ከዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 11/2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የተነገረው መመሪያን ተግባራዊነትን በተመለከተ ብሔራዊ ባንክ ጥብቅ ክትትል እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን፤ ባንኮችም በየሳምንቱ የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴያቸውን ለማዕከላዊው ባንክ ሪፖርት እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል። ይህ መመሪያም በአገሪቱ ያሉትን ሁሉንም ባንኮችና አነስተኛና ጥቃቅን የገንዘብ ተቋማትንም የሚመለከት መሆኑ ተገልጿል። ይህንን የብሔራዊ ባንኩን መመሪያ ተላልፈው የተገኙ የገንዘብ ተቋማት ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልባቸውም ተመልክቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-52703739 +politics በአርባ ምንጭ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት የባልደራስ አመራሮች ተፈቱ "በትላንትናው ዕለት ሚያዝያ 12፣ 2014 ዓ.ም ማምሻውን በአርባ ምንጭ ከተማ ካረፉበት ሆቴል ተወስደው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አራት የባልደራስ አመራሮች በዛሬው ዕለት መፈታታቸውን የፓርቲው ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም ለቢቢሲ ገልጸዋል። ሃላፊዋ ባልደራስ አሁን ክልል አቀፍ ፓርቲ መሆኑን ገልጸው ወደ ሀገር አቀፍ ፓርቲነት ለማደግ የሚያስችለውን የደጋፊዎች ፊርማ ለማሰባሰብ እና ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ የመጀመሪያ ጉዞውን ወደ አርባ ምንጭ ማድረጉን ተናግረዋል። ""ምርጫ ቦርድ ሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ክልሎች ተዘዋውረን ህዝባዊ ስብሰባ እንድናደግ፣ ፊርማ እንድናሰባስብ፣ ቢሮም እንድንከፍት የሚያግዙ የትብብር ደብዳቤዎችን"" ጽፎልናል የሚሉት ወ/ሮ ቀለብ በአርባ ምንጭ ከተማ ስብሰባ ለማድረግ ፓርቲው ከከተማ አስተዳደሩ ቀደም ብሎ ፍቃድ ተሰጥቶት እንደነበርም ተናግረዋል። ""ስለዚህ ዋናው ዓላማው የህዝብ ስብሰባ ለማድረግ እና እዛው ቢሮ ለመክፈት ታስቦ ነው ጉዞ የተደረገው"" ሲሉም አክለዋል። በዚህ መሰረት የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን እና ሌሎች ሶስት አመራሮች ትላንት ጠዋት ወደ አርባ ምንጭ መጓዛቸውን ጠቅሰዋል። ሆኖም ፓርቲው ቀደም ብሎ ከተሰጠው ፍቃድ በተቃራኒ ማድረግ እንዳይችል መከልከሉን ሃላፊዋ ገልጸዋል። ""እንዴት ልትከለክሉን ቻላችሁ? ብለው ሲጠይቁ 'ከላይ በመጣ ትእዛዝ ነው' የሚል መልስ ነው የሰጧቸው"" ብለዋል። ወ/ሮ ቀለብ ስብሰባው ከተከለከለ በኋላ ግን አመራሮች ሀገር አቀፍ ፓርቲ ለመመስረት የሚያስችለውን ፊርማ በከተማው የተለያዩ አከባቢዎች እየተዘዋወሩ እየሰባሰቡ መዋላቸውን እና ማምሻውን ወደ ሆቴል ከሄዱ በኋላ በፖሊስ መያዛቸውን ገልጸዋል። ""አቶ እስክንድር ስልኬ ላይ ደውለው በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ነገሩኝ"" ብለዋል። አመራሮቹ ለሊቱን 'በማይመች ሁኔታ' ፖሊስ ጣቢያ ማደራቸውን የገለጹት ሃላፊዋ የነበሩበት ፖሊስ ጣቢያ ቃላቸውን ሊሰጡ የነበረ ቢሆንም ወደ ጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ መወሰዳቸውን ጠቁመዋል። ሆኖም በዛሬው እለት መፈታታቸውንና ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ማቅናታቸውን ቢቢሲ መረዳት ችሏል። የባልደራስ አመራሮችን በቁጥጥር ስር ለምን ዋሉ የሚለውን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት የጋሞ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ስልክ ባለማንሳታቸው ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም።" https://www.bbc.com/amharic/news-61172477 +health ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በመጪው ሚያዚያ ወር እንደምታስገባ ገለጸች ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በመጪው ሚያዚያ ወር ወደ አገር ውስት እንደምታስገባ ገለጸች። የሚገባው የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ቢያንስ 20 ከመቶ ለሚሆኑ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚዳረስ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህንን የክትባት ሥራ የሚያስተባብር ግብረሃይል በብሄራዊ ደረጃ መቋቋሙም ተገልጿል። በጤና ሚኒስቴር የክትባትና ተያያዥ ጉዳዮች የሚኒስትሯ ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ሙሉቀን ዮሃንስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት መረጃ መሰረት፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር እና ከፕሬዚዳንት ፅ/ት ቤቶች ጋር በመቀናጀት የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባትን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው፡፡ ክትባቱን ለመውሰድ ቅድሚያ የሚያገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መስፈርት መሰረት የጤና ባለሙያዎች፣ እድሜያቸው የገፉ፣ ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎችና መጪውን ምርጫ ተከትሎ ተደራራቢ ስራና ሃላፊነት ያለባቸው የጥበቃ ኃይሎች መሆናቸውን ተገልጿል። የክትባቱ ብዛት እየታየም ለአውቶብስና የባቡር አሽከርካሪዎች እንዲሁም በመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚሰሩ መምህራን እንዲዳርስ የሚደረግ መሆኑን ተመልክቷል። ኢትዮጵያ ክትባቱን ወደ ሃገር ውስጥ የምታስገባው ‹‹ኮቫክስ›› በተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት ሸማች ማህበር መሆኑንም ዶክተር ሙሉቀን ተናግረዋል። የመጀመሪያው ዙር ክትባት እስከ መጪው ሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባና በፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ 2021 መጨረሻ ድረስ ደግሞ ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገባም አማካሪው ጠቁመዋል። ኮቫክስ (COVAX) ምጣኔ ኀብታቸው ደካማና መካከለኛ ለሆኑ አገራት ክትባቱን ለማቅረብ ያለመ፣ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የተመሰረተ ኢኒሼቲቭ ነው። ሁሉም የአፍሪካ አገራት ይህንን ኢኒሼቲቭ ተቀብለውታል። ይህም ማለት አፍሪካ በዚህ ኢኒሼቲቭ በኩል ክትባቱ ፍቃድ ካገኘና ከፀደቀ በኋላ፣ 220 ሚሊዮን ክትባቶችን ታገኛለች። እኤአ በ2021 መጨረሻ ላይ ኮቫክስ 2 ቢሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመግዛት እቅድ ይዟል።አፍሪካ ለአህጉሩ የሚሰራጭ ለጊዜው 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' (መጠን) የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ሕብረት በኩል ማግኘቷ ተገለፀ። አጠቃላይ የተገኘው ክትባት በዚህ ዓመት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሕብረቱ መሪ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል ገብተዋል። ይህ ክትባት ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው 600 ሚሊየን 'ዶዝ 'ተጨማሪ ቢሆንም አሁንም ግን ሙሉ አህጉሩን ለመከተብ በቂ አይደለም። በዚህም የዓለማችን ድሃ አገራት ከሃብታም አገራት ይልቅ ክትባቱን ለመከተብ ረዥም ጊዜ ሊጠብቁ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ምንም እንኳን በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በንፅፅር ዝቅተኛ ቢሆንም በአንዳንድ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በድጋሜ እየጨመረ ነው። አፍሪካ ለአህጉሩ የሚሰራጭ ለጊዜው 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' (መጠን) የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ሕብረት በኩል ማግኘቷ መገለፁ ይታወሳል። አጠቃላይ የተገኘው ክትባት በዚህ ዓመት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሕብረቱ መሪ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል ገብተዋል። ይህ ክትባት ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው 600 ሚሊየን 'ዶዝ 'ተጨማሪ ቢሆንም አሁንም ግን ሙሉ አህጉሩን ለመከተብ በቂ አይደለም። በዚህም የዓለማችን ድሃ አገራት ከሃብታም አገራት ይልቅ ክትባቱን ለመከተብ ረዥም ጊዜ ሊጠብቁ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ምንም እንኳን በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በንፅፅር ዝቅተኛ ቢሆንም በአንዳንድ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በድጋሜ እየጨመረ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-55883638 +business የዓለማችን ውዱ የመኪና ማቆሚያ ቦታ በ1.3 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ ሆንግ ኮንግ ውስጥ አንድ የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት የሚሰጥ ቦታ በዓለማችን ውድ በሆነ 1.3 ሚሊየን ዶላር ዋጋ መሸጡ ተሰም��ል። የሆንግ ኮንግ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት በከተማዋ በጣም ምርጥ በሚባለው መኖሪያ አካባቢ የሚገኘው የመኪና ማቆሚያ እጅግ ቅንጡ ከሚባሉት መካከል ነው። 'ማውንት ኒኮልሰን' የተባለው የግንባታና የቤቶች ሽያጭ ድርጅት እሲያ ውስጥ በጣም ውድ የሆኑ መኖሪያ ቤቶችን የሚያስተዳድር ሲሆን፤ በሆንግ ኮንግም 'ቪችቶሪያ ሃርበር' የተባለውን ውድ አካባቢም ያስተዳድራል። ይሄው ድርጅት ነው ታዲያ በዓለማችን ውድ የተባለውን የመኪና ማቆሚያ ቦታ የሚያስተዳድረው። ሆንግ ኮንግ በጣም የተጨናነቀች ከተማ መሆኗን ተከትሎ በ1.3 ሚሊየን ዶላር ዋጋ የተሸጠው ቦታ ለመኖሪያም ሆነ ለመኪና ማቆሚያ አገልግሎት ቢውል የበርካታ ሰዎችን ቀልብ መሳብ እንደሚችል ከወዲሁ ተገምቷል። በዓለማችን ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር ከሚካሄድባቸው ከተሞች አንዷ የሆነችው ሆንግ ኮንግ በጣም ውድ የሚባሉ መኖሪያ ቤቶች እንደሚገኙባት ይገመታል። ከተማዋ ለኑሮ ምቹ ብትሆንም የኑሮ ዋጋ ግን በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል። ከዚህ በፊት ለመኪና ማቆሚያ ቦታ ከፍተኛው ዋጋ የተከፈለው በዛው ሆንግ ኮንግ ውስጥ ሲሆን፤ በወቅቱ በአውሮፓውያኑ 2019፤ 980 ሺህ ዶላር ነበር ወጪ የተደረገበት። ለማውንት ኒኮልሰን የሽያጭ ሥራውን የሚያከናውንለት 'ዊሎክ ፕሮፐርቲስ' በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ከቢቢሲ የተጠየቀ ቢሆንም እስካሁን ምላሽ አልሰጠም። በቅርብ ወራት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጫት በመጠኑም ቢሆን መቀነሱን ተከትሎ በሆንግ ኮንግ የንግድ እንቅስቃሴዎች እየደሩ ነው። ገዢዎችም ቢሆኑ በርካታ ሚሊየኖችን እያወጡ ቅንጡ ቤቶችና ሌሎች ቦታዎችን እየገዙ ነው። ባለፈው ወር በከተማዋ የሚገኝ አንድ ቅንጡ መኖሪያ ቤት የዓለም ሪከርድ በሆነ 210 ሺህ ዶላር በወር ተከራይቷል። https://www.bbc.com/amharic/57354351 +politics ዩክሬን ፡ ዩኬ በዩክሬን ያለውን ውጥረት ተከትሎ በርካታ ወታደሮችን ለማሰማራት እያሰበች ነው "ዩናይትድ ኪንግደም በምሥራቅ አውሮፓ የምታሰማራውን ወታደሮቿን በእጥፍ ለማሳደግ እያሰበች መሆኑ ተገለጸ። ይህ የተሰማው ሚኒስትሮች በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ሩሲያ ላይ ጫና ለማሳደር አማራጮችን እያሰላሰሉ ባሉበት ወቅት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ወታደሮችን ለማሰማራት መታሰቡ ""ለክሬምሊን ግልጽ መልእክት ያስተላልፋል"" ብለዋል። በሌላ በኩል የመከላከያ እና የውጭ ጉዳይ ኃላፊዎች ውጥረቱን ለማርገብ በሞስኮ ከሚገኙ አቻዎቻቸው ጋር ለመገናኘት በዝግጅት ላይ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስም በቀጣይ ቀናት ከሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ ሳምንት ምሥራቅ አውሮፓን የሚጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ዩኬ ""የሩሲያን የጥፋት እንቅስቃሴ እንደማትታገስ"" እና ሁል ጊዜም ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት [ኔቶ] አጋሮቻቸው ጋር እንደሚቆሙ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም ፕሬዚደንት ፑቲን የደም መፋሰስ እና የጥፋት መንገድን ከመረጡ ለአውሮፓ አሳዛኝ ነው የሚሆነው። ዩክሬን የራሷን መጻኢ እድል ለመምረጥ ነጻ መሆን አለባት "" ብለዋል። "" የኔቶ አጋሮቻችንን በየብስ፣ በባህር እና በአየር ለመደገፍ ወታደሮቻችን በሚቀጥለው ሳምንት በአውሮፓ ለመሰማራት እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ"" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ። ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ 100 ሺህ ወታደሮችን፣ ታንኮችን፣ ከባድ መሳሪያዎችን እና ሚሳይሎችን አስፍራለች። ይሁን እንጂ ከአውሮፓ እና ከሩሲያ ጋር የምትዋሰነውን የቀድሞዋን ሶቭየት ሪፐብሊክ ለመውረር አቅዳለች መባሉን አስተባብላለች። ዩናይትድ ኪንግደም በኢስቶኒያ የሰፈሩ ከ900 በላይ የጦር መኮንኖች ያሏት ሲሆን ከ100 በላይ የሚሆኑት ለሥልጠና ተልዕኮ ዩክሬን ይገኛሉ። 150 የሚጠጉ የጦር ፈረሰኞች ቡድን ደግሞ ወደ ፖላንድ ተሰማርቷል። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሰኞ ዕለት በሩሲያ ስትራቴጂያዊ እና የፋይናንስ ፍላጎቶች ላይ ጠንካራ ማዕቀብ ላይ ፓርላማው ያሳለፈውን ውሳኔ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ኪንግደም ባለሥልጣናት አገሪቷ ያቀረበችው ሃሳብ በዝርዝር ተነጋግሮ ለመቋጨት ወደ ብራስልስ ያቀናሉ ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60187251 +politics እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ከሦስት ሳምንት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት በአካል ቀረቡ "በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ የሚነገረው እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ዛሬ ረፋድ ላይ ፍርድ ቤት ለነበራቸው ቀጠሮ ሲቀርቡ አካላቸው ደክሞ እና ከስተው ታዩ። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱ የ24 ሰዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ዛሬ ጠዋት ላይ ቀጠሮ ይዞ ነበር። ከእነዚህ መካከል እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 21 ሰዎች በፍርድ ቤት ተገኝተው ነበር። ይኹን እንጂ ጠበቆች ደንበኞቻቸው እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነ እና ደጀኔ ጣፋ የረሃብ አድማ ከጀመሩ 33 ቀናት እንዳለፋቸው ለፍርድ ቤት ተናግረው፤ ደንበኞቻቸው አሁን ባሉበት ሁኔታ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠት አይችሉም በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ዐቃቤ ሕግም ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጥ እንደማይቃወም ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። በዚህም መሠረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብርና ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች አንደኛ ችሎት የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለመጋቢት 6/2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ከድምጻዊ ሃጫሉ ግድያ በኋላ በቁጥጥር ስር የዋሉት እና ክስ ተመስርቶባቸው በእስር የሚገኙት እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሸምሰዲን ጠሃ እና ሃምዛ አዳነ በፖለቲከኞች እና በቤተሰብ አባላቶቻቸው ላይ የሚደርሰውን እስር እና ወከባ በመቃወም የረሃብ አድማ ማድረግ ከጀመሩ ከ33 ቀናት በላይ እንዳስቆጠሩ ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። የተከሳሽ ጠበቆች ምን አሉ? የተከሳሽ ጠበቆች ""መንግሥት እና ሕግ ባለበት አገር ደብዳቤ ስናመላልስ ደንበኞቻችን ሕይወታቸው ሊያልፍብን ነው"" በማለት የደንበኞቻቸው በሕይወት የመኖር መብት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ከደንበኞቻቸው መካከል አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ አራት ተከሳሾች በጠና ታምመው እንደሚገኙ በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ጠበቆች ለችሎቱ አስረድተዋል። ተከሳሾች የሚገኙበት ሁኔታ የቢቢሲ ሪፖርተር እንደተመለከተው ዛሬ ጋዜጠኞች ወደ ፍርድ ቤቱ ሲገቡ፤ አቶ በቀለ ገርባ ጭንቅላታቸውን በተከሳሽ አረፋት አቡበከር ላይ እንዲሁም እግራቸውን ደግሞ በአቶ ጃዋር መሐመድ ላይ አድርገው በአግዳሚ ወንበር ላይ በጀርባቸው ተኝተው ነበር። አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነ ሰውነታቸው እጅጉን ከስቶ እና ጸጉራቸውን ተላጭተው ታይተዋል። አቶ ሐምዛ አዳነ በሰዎች ድጋፍ ወደ ችሎቱ ሲገቡ የቢቢሲ ሪፖርተር ተመልክቷል። ችሎቱ ሲጀመር አቶ በቀለ ገርባ በሰዎች ድጋፍ በጀርባቸው ተኝተው ከነበሩበት አግዳሚ ወንበር ተነስተው ተቀምጠዋል። የተከሳሽ ቤተሰብ አባላት መካከል አንዳንዶቹ በችሎት ውስጥ ሲያለቅሱ ሪፖርተራችን ተመልክቷል። እነ አቶ ጃዋር ለመጨረሻ ጊዜ ጋዜጠኞች እና ታዳሚዎች በተገኙበት በፍርድ ቤት ቀርበው የታዩት ጥር 27/2013 ዓ.ም ነበር። በዕለቱ የችሎት ውሎውን ለመዘ��ብ እና ለመከታተል በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞች እና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ተቋም ሠራተኞች ተፈትሸው ወደ ችሎቱ ከገቡ በኋላ በጸጥታ አስከባሪዎች ከችሎቱ እንዲወጡ ተደርገው ነበር። 'የደረሰብን ክፍት ከፍተኛ ነው' በዛሬው የችሎት ውሎ ከተከሳሾች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ከተቀመጡበት ሳይነሱ እንዲናገሩ ተፈቅዶላቸዋል። አቶ በቀለ ለፍርድ ቤቱ ክብር እንዳላቸው ተናግረው፤ ለሕክምና ወደ ላንድማርክ ሆስፒታል እየተወሰዱ ሳለ፤ መንገድ ተዘግቶባቸው በኃይል ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ""ይህ ቡድን የፍርድ ቤት ትዕዛዝን የማያከብር ነው"" ያሉት አቶ በቀለ ገርባ፤ ""ጨካኝ የሆነውን ሥርዓትን መታገል እንፈልጋለን። እኛ ላይ የደረሰው ክፋት ከፍተኛ ነው"" ብለዋል። አሁን ባሉበት ሁኔታ ወደፊት በችሎት መቅረብ እንደማይገባቸው የተናገሩት አቶ በቀለ፤ ወደፊት ጤናቸው የሚመለስ ከሆነ ለጤና መቃውስ ዳርገውናል ያሉትን አካል ካሳ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል። አቶ በቀለ ደብዳቤ በመጻፍ ላንድማርክ በተሰኘው የግል ሕክምና ተቋም እንዳይታከሙ የከለከሉት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ እንደሆነም ቢቢሲ ከጠበቆቻቸው ለመረዳት ችሏል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የረሃብ አድማው ተከሳሾችን የከፋ አደጋ ላይ እንዳይጥል የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ኮሚሽኑ ባሳለፍነው አርብ ባወጣው መግለጫ አስነብቧል። ""ለታሳሪዎች ምክንያታዊ የሆኑ ጥያቄዎች ተገቢውን አፋጣኝ ምላሽ መስጠትና የእስረኞች ጠያቂዎችን በማረሚያ ቤቱም ሆነ በፍርድ ቤቶች በአግባቡ ማስተናገድ ይገባል"" ስለማለታቸው በመግለጫው ሰፍሯል። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በቁጥጥር ሥር የዋሉት እነ አቶ ጃዋር ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ መወሰኑ ይታወሳል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ፤ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ፤ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ የመተላለፍ ክሶች ከተመሰረቱባቸው ክሶች መካከል ሲሆኑ፤ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 ጋር የተያያዙ ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/news-56240090 +politics የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከሴት ልጃቸው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ታዩ ለረዥም ጊዜ ሴት ልጅ እንዳላቸው ሲወራ የቆዩት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለመጀመሪያ ጊዜ አብረዋት በአደባባይ ታዩ። ስለ ኪም ሴት ልጅ እስካሁን በዝርዝር የሚታወቅ ምንም ነገር የሌለ ሲሆን፣ ስሟም ኪም ቹ-ኢ እንደሆነ ይታመናል። ሴት ልጃቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ከአባቷ ጋር የታየችው ኪም ጆንግ ኡን ለዓመታት ከምዕራባውያን ጋር በሚወዛገቡበት የጦር መሣሪያ ፕሮግራም ሙከራ ወቅት ነው። የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ትናንት አርብ የአገሪቱ ትልቁ ነው የተባለው አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ በተደረገበት ሥነ ሥርዓት ላይ ነው ከሴት ልጃቸው ጋር የተገኙት። አሜሪካ ባወገዘችው የሚሳኤል ሙከራ ላይ አባት እና ሴት ልጃቸው እጅ ለእጅ ተያይዘው ታድመው ነበር። በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግባትን አገር ስለሚመሩት ኪም ጆንግ ኡን የግል ሕይወት የሚታወቀው ነገር እጅግ በጣም ጥቂት ነው። ከሴት ልጃቸው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የታዩትን የአባት እና ልጅን የተለያዩ ፎቶዎችን የሰሜን ኮሪያው የዜና አገልግሎት ኬሲኤንኤ አሰራጭቷል። የኪም ጆንግ ኡን ሴት ልጅ የሆነችው ቹ-ኤ ለሕዝብ በይፋ መታየቷ ትልቅ ነገር ነው፣ ሲሉ በዋሽንግተን በሚገኘው የስቲምሰን ማዕከል የሰሜን ኮሪያ ተንታኝ የሆኑት ማይክል ማደን ይናገራሉ። ሰሜን ኮሪያን በመምራት ከቤተሰባቸው ሦስተኛው ትውልድ የሆኑት ኪም፣ አሁንም በአገራቸው የመሪነት ሥልጣን ላይ ጠንካራ ቁጥጥር እንዳላቸው እያሳዩ መሆናቸውን ተንታኙ ያምናሉ። ማደን እንደሚሉት ኪም ከሴት ልጃቸው ጋር መታየታቸው “አገሪቱን የሚመራው አራተኛው ትውልድ ከእሳቸው የቤተሰብ ግንድ እንደሚመጣ ለማሳየትም ሊሆን ይችላል” ብለዋል ለቢቢሲ። መሪው ከልጃቸው ጋር የታዩት “በኪም እና በአመራሩ ከፍተኛ ሰዎች መካከል ባለፈው ዓመት ግጭት መኖሩን የሚያመለክት ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ ነው” ይላሉ። በዚህም ኪም ለተቀናቃኞቻቸው ማስተላለፍ የፈለጉት መልዕክት “የምትገዳደሩኝ ከሆነ፣ ቦታችሁን ትለቃላችሁ” የሚል ነው። ማደን እንደሚያምኑት የኪም ሴት ልጅ በአሁኑ ወቅት ዕድሜዋ በ12 እና በ13 መካከል ነው፣ በዚህም ከአራት እና ከአምስት ዓመታት በኋላ ወደ ዩኒቨርስቲ ወይም ወደ ወታደራዊ አገልግሎት ለመግባት ትዘጋጃለች። ቹ-ኤ በይፋ ስትታይ የአሁኑ የመጀመሪያዋ አይደለም የሚሉት በርካታ የሰሜን ኮሪያ ጉዳይን የሚከታተሉ ባለሙያዎች፣ ቹ ባለፈው መስከረም ላይ በተከበረው የአገሪቱ ብሔራዊ ቀን ክብረ በዓል ላይ በተቀረጹ ቪዲዮዎች ላይ ታይታለች። ነገር ግን ይህ ከግምት ባለፈ ማረጋገጫ አልተገኘለትም። የሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣናትም በቪዲዮው ላይ የታየችው የመሪው ሴት ልጅ ስለመሆኗ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ አልሰጡም። ኪም ጆንግ ኡን ሴት ልጅ እንዳላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የተገለጸው ከዘጠኝ ዓመት በፊት የቀድሞው የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ኮከብ ዴኒስ ሮድማን አወዛጋቢ ጉዞ ወደ ሰሜን ኮሪያ ባደረገበት ጊዜ ነው። ሮድማን በወቅቱ ከኪም ቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፉን በመጥቅስ፣ በባሕር ዳርቻ ላይ ዘና ማለቱንና የመሪውን ሕጻን ልጅ ቹ-ኤን ማየቱን በገለጸበት ወቅት ነበር። የሰሜን ኮሪያን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉ ባለሙያዎች እንደሚያምኑት ኪም ሦስት ልጆች ያሏቸው ሲሆን፣ ሁለቱ ሴቶች አንዱ ወንድ ናቸው፤ ቹ-ኤ ደግሞ የመጀመሪያ ልጅ ናት ይላሉ። ኪም ጆንግ ኡን ቤተሰባቸውን በሚመለከት ሁሉንም ነገር በጥብቅ ምስጢርነት የያዙ መሪ ናቸው። ባለቤታቸው ሪ ሶል-ጁን ካገቡ በኋላ እንኳን እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ጋብቻቸውን በምስጢር ይዘውት ቆይተዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cv27nlz2225o +politics ማግዳሊና አንደርሰን፡ የስዊድን የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሥልጣናቸው ተመለሱ ባለፈው ሳምንት በፖለቲካ ውዥንብር በተሾሙ በሰዓታት ውስጥ ሥልጣናቸውን የለቀቁት የስዊድን የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሥልጣናቸው ተመለሱ። የፓርላማ አባላት ሰኞ ዕለት በሰጡት አዲስ ድምጽ የሶሻል ዲሞክራቲክ መሪ ማግዳሊና አንደርሰንን በጠባብ ልዩነት ደግፈዋል። በዚህም መሠረት ማግዳሊና በሚቀጥለው ዓመት መስከረም ወር እስከሚካሄደው ምርጫ ድረስ የአንድ ፓርቲ መንግሥት ይመራሉ ተብሏል። ማግዳሊና ባለፈው ረቡዕ ዕለት ከርሳቸው ፓርቲ ጋር ጥምረት የፈጠረው የፖለቲካ ድርጅት ከጥምረቱ በመልቀቁና የሳቸው ፓርቲ ሶሻል ዲሞክራት ያቀረበው የበጀት ጥያቄ በምክር ቤቱ ሊያልፍ ባለመቻሉ ነበር ከተሰጣቸው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት የለቀቁት። ማግዳሊና ሥልጣን ከመልቀቃቸው ከሰዓታት በፊት ነበር የስዊድን የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በፓርላማው የተመረጡት። ነገር ግን የ54 ዓመቷ ዓመቷ የምጣኔ ሐብት ምሁር ከግሪን ፓርቲ ጋር አዲስ ጥምር መንግሥት ለመመስረት ይዘውት የነበረው እቅድ የበጀት ረቂቃቸው ባለመጽደቁ ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ይልቁኑ ፓርላማው የቀኝ አክራሪዎቹን የስዊድን ዲሞክራቶችን ጨምሮ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ቡድን ያዘጋጁትን በጀት ተቀብሏል። ግሪን ፓርቲ በቀኝ አክራሪዎቹ የረቀቀውን በጀት እንደማይቀበል ገልጿል። ማግዳሊና በዚህ ሁኔታ ለመቀጠል እንደማይፈልጉና የገዛ ፓርቲያቸው አብላጫ ድምጽ አግኝቶ መንግሥት ሲመሰርት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መመረጥ እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር። ሰኞ ዕለት በተካሄደው የስዊድን ፓርላማ ድምጽ አሰጣጥ ግን ሪክስዳግ የተባለው የስዊድን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት 349 አባላቱ 101 የድጋፍ ፣ 75 ድምጸ ታቅቦ፣ 173 ደግሞ የተቃውሞ ደምጽ ሰጥተዋል። በስዊድን የፖለቲካ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ለመሾም አንድ እጩ አብላጫ የተቃውሞ ደምጽን ማግኘት የለበትም። ከድምጽ አጣጡ ሥርዓት በኋላ ማግሊንዳ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በደህንነት ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በወንጀል ላይ ያተኮረ ፕሮግራም በመዘርጋት ስዊድንን ወደ ፊት ለማራመድ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረው ነበር። ነገር ግን አሁንም የሌሎች ፓርቲዎችን ድጋፍ ካላገኙ ሴንተር ሌፍት ሶሻል ዲሞክራቶች ከ349፣ 100 መቀመጫ ባላቸው ፓርላማ ሕግ ለማጽደቅ ይቸገራሉ ተብሏል። ማግዳሊና በዩኒቨርስቲ ሲቲ ኡፕሳላ የአዳጊዎች የውሃ ዋና ሻምፒዮን የነበሩ ሲሆን ፖለቲካ ውስጥ የገቡት በ1996 የጠቅላይ ሚኒስትር ጎራን ፐርሰን አማካሪ በመሆን ነበር፡፡ ላለፉት ሰባት ዓመታትም በገንዘብ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡ ማግደሊና አንደርሰን በሕዝብ እንደራሴዎች ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ድምጽ ከማግኘታቸው በፊት ስዊድን ከኖርዲክ አገሮች ሁሉ ብቸኛዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ኖሯት የማያውቅ አገር ሆና ቆይታለች፡፡ ስዊድን የጾታ እኩልነት ከፍ ባለ ደረጃ የምታከብር አገር ናት፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-59472445 +sports ወደ አገሬ አልመለስም ያለቸው የቤላሩስ አትሌት ወደ ቪዬና አቀናች "ወደ አገሯ እንድትመለስ የተሰጣትን ትዕዛዝ አልቀበልም ያላችው የቤላሩስ አትሌት ከቶኪዮ ወደ ኦስትሪያ፣ ቪዬና አቀናች። የ24 ዓመቷ ክሪስቲሲና ትሲማኑስካያ ረቡዕ ጠዋት ወደ ፖላንድ ትሄዳለች ተብሎ የነበረ ቢሆንም ቪየና በሚያቀና አውሮፕላን ተሳፍራለች ተብሏል። ፖላንድ ቪዛ ስለሰጠቻት በቀጥታ ወደ ፖላንድ መዲና ዋርሶ ትጓዛለች ተብሎ ቢጠበቅም በመጨረሻው ሰዓት መዳረሻዋ ተቀይሯል ሲሉ አንድ የአየር ማረፊያው ባለሥልጣን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። አትሌቷ ወደ አገሬ አልመለስም ያለቸው በፖለቲካዊ ምክንያት እንዳልሆነ ለቢቢሲ ተናገረች። ""አገሬን እወዳለሁ፤ አገሬን አልከዳሁም"" ብላለች። አትሌቷ ለውሳኔዋ ምክንያቱ ""በኦሎምፒክ ባለሥልጣኖቻችን የተፈጠሩ ስህተቶች ናቸው"" ብላለች። አትሌቷ ባለፈው ሳምንት አሰልጣኞቿን በመተቸቷ ዕቃዎቿን ጠቅልላ ወደ ቶኪዮ ሃኔዳ አውሮፕላን ማረፊያ ብትወሰድም ለደኅንነቴ እሰጋለሁ በሚል ወደ ቤላሩስ አልጓዝም ብላ ነበር። በቶኪዮ ወደሚገኘው የፖላንድ ኤምባሲ ከመዛወሯ በፊት የፖሊስ ጥበቃ የተደረገላት ሲሆን ረቡዕ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ እስክትጓዝ ድረስ በኤምባሲው ቆይታለች። የቤላሩስ አትሌቲክስ ቡድን አትሌቷ ከአዕምሮ ዝግጁነት ጋር በተያያዘ ከብሔራዊ ቡድኑ እንደተቀነሰች አስታውቋል። ማክሰኞ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረገችው ክሪስቲሲና ትሲማኑስካያ ግን ምንም ዓይነት የአዕምሮ ጤና ችግር እንዳልነበራት እና በኦሎምፒክ መ��ደሩ ከሐኪሞች ጋር ምንም ውይይት እንዳላደረገች ተናግራለች። ""የፖለቲካ ነገር ስላልተናገረች"" ከውድድሩ እንደምትወጣ ሲነግሯት በጣም እንደተገረመች ተናግራለች። ደኅንነቷ የተጠበቀ መሆኑን ስታውቅ ወደ ቤላሩስ መመለስ እንደምትፈልግ ገልጻለች። ምናልባት ከአምስት ወይም ከ10 ዓመታት በኋላ መመለስ ይቻላል ብላለች። ቤላሩስ ክሪስቲሲና ትሲማኑስካያን ወደ አገሯ እንድትመለስ ለማስገደድ ሞክራለች በሚለው ክስ ላይ የዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) ምርመራ ጀመሯል። የአይኦሲው ቃል አቀባይ ማርክ አዳምስ ""ሙሉ እውነታውን ማግኘት አለብን። ያ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። እስከዚያ ድረስ የእኛ የመጀመሪያ ጉዳይ አትሌቷ ናት"" ብለዋል። የቤላሩስ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሪፖርቱን እስከ ማክሰኞ ድረስ እንዲያቀርብ አይኦሲ ጠይቋል።" https://www.bbc.com/amharic/58079204 +business ኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ምጣኔ ሐብታዊ ጫና ትተርፋለች? እስከ ሚያዝያ አንድ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ስድሳ አምስት ሰዎችን አጥቅቶ፣ ሦስቱን ለሞት ያበቃው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፤ እንደሌሎች የዓለም ክፍሎች ሁሉ ተያያዥ የሥነ ጤና፣ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ኃብታዊ ጠንቆችን እንደሚያስከትል ይጠበቃል። ወረርሽኙ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ አኳኋን በፍጥነት መዛመት፤ ይዟቸው የሚመጣቸውን ጣጣዎችም በዚያው ልክ የገዘፉ እንዲሁም በዓለም ዙርያ የተሰራጩ አድርጓቸዋል። በዚያውም ልክ መጭውን ለመተነብይም አዳጋች ሆኗል። ይሁንና በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሞያዎች የጉዳቱን መጠን ለመስፈር፤ የድኅረ-ወረርሽኝ አቅጣጫዎችንም ለመቀየስ መሞከራቸው አልቀረም። ወረርሽኙ በሰዎች የሥራ እና የገቢ ሁኔታ ላይ የሚያሳርፈውን ጡጫ በተመለከተ ጥናት ያደረገው ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (አይ.ኤል.ኦ) እ.ኤ.አ መጋቢት 18 ቀን 2020 ባሳተመው ግምገማው ምንም እንኳ የኮሮናቫይረስ በዕድሜ የገፉትን እና ቀደም ሲል በሽታ የነበረባቸውን ግለሰቦችን የማጥቃት ከፍ ያለ ዕድል ቢኖረውም፤ ከወረርሽኙ በኋላ የሚከሰት የሥራ አጥነት ቀውስ ወትሮውኑም ሥራ ማጣት የሚያበረታባቸው ወጣቶች ላይ ሊጠነክር ይችላል ይላል። በአገልግሎት ዘርፍ በብዛት ተሰማርተው የሚገኙት ሴቶች፣ ዋስትና አልባ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች (ለምሳሌ የራሳቸውን ሥራ የሚሰሩ እና በጊዜያዊነት የተቀጠሩ) አንዲሁም ስደተኛ ሠራተኞች አንዲሁ ክፉኛ በሥራ አልባነት ማዕበል ክፉኛ ሊደቆሱ ይችላሉ ይላል የአይ.ኤል.ኦ ግምገማ። በምጣኔ ኃብት ያልጠነከሩ አገራት ኢትዮጵያም ወረርሽኙ የሚያስከትለውን የጤና ቀውስ ለመቋቋም ከምታደርጋቸው ጥረቶች ባሻገር ይዞት የሚመጣው የምጣኔ ኃብት ጡጫ ያሳሰባት ይመስላል። ከሳምንታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የበለፀጉ አገራት ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ የአፍሪካ አገራት የዕዳ ቅነሳ እና የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸው ይታወሳል። ባገባደድነው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ በተደረገ የድረ ገፅ ላይ ውይይት የሥራ ፈጠራ ኮሚሽነሩ ኤፍሬም ተክሌ ሌማንጎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሥራዎቻቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ መናገራቸው ተዘግቧል። የሥራ ዕጦቱ በአገሪቱ ትልቁ ኩባንያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጀመረ ይመስላል። የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ድርጅታቸው ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ 550 ሚሊዮን ዶላር ማጣቱን በገለፁበት መገለጫቸው ላይ ቋሚ ያልሆኑ ሠራተኞችን ለጊዜው ሥራ እንዲያቆሙ መደረጋቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የምጣኔ ኃብት ማኅበር ያሳተመው የአራት ባለሞያዎች ምልከታ ከወረርሽኑም በፊት ለብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን መሠረታዊ ግልጋሎቶችን ማግኘት አዳጋች ነበር፤ ይህም ወረርሽኙን ለመከላከል መ��ረግ ያለባቸውን እርምጃዎች ቀላል እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል ይላል። እንደአብነትም ከጠቅላላው ሕዝብ መካከል ስድስት በመቶ የሚሆነው ያህል በመኖርያው አቅራቢያ የመታጠቢያ ውሃ አለው ይላል። • “ገደቦችን በአጭር ጊዜ ማንሳት ወረርሽኙ በአስከፊ ሁኔታ እንዲሰራጭ ያደርጋል” ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም • ኮሮናቫይረስ ካለበት ሰው ጋር ንክኪ ላደረጉ ሰዎች ጥቆማ የሚሰጥ መሣሪያ እየተሠራ ነው ባለሞያዎቹ ብሔራዊው የስታትስቲክስ ድርጅት በማጠቀስ ከአራት ዓመት በፊት በተጠናቀረ መረጃ መሠረት አገሪቱ ውስጥ ካሉ ቤቶች ሰማንያ አምስት በመቶው ባለአንድ ወይንም ባለሁለት ክፍል መሆናቸውን አስታውሰው በኮቪድ 19 በሽታ ጥርጣሬ ቤት ውስጥ ተነጥሎ መቀመጥ አዋጭ አማራጭ ያለመሆኑን ይናገራሉ። ወረርሽኑ የሚፈጥረው የምጣኔ ኃብት ንዝረት የአገልግሎት ዘርፉን፣ ቱሪዝምን እና የመስተንገዶ ኢንዱስትሪውን፣ የውጭ ንግድን እና የመጓጓዣ ዘርፍን ሊጎዳ እንደሚችል የሚገምተው የባለሞያዎቹ ምልከታ ግብርናም ቢሆን ከዚህ የሚተርፍ አይደለም ይላል- በተለይ በቀላሉ የሚበላሹ ምርቶች አብቃዮች እና አከፋፋዮች ለጉዳት ተጋላጭ መሆናቸው አይቀርም። ወረርሽኙ የአቅርቦት ሰንሰለትን ያውካል። የሥራ መቀዛቀዝ በሚፈጥረው የገቢ እጥረት እንዲሁም የሚመጣው አይታወቅም በሚል ስጋት ምክንያት ሰዎች ገንዘብ ከማውጣት ስለሚቆጠቡ የፍላጎት እጥረትን ያስከትላል፤ አንዲሁም የንግድ ተቋማት የመንቀሳቀሻ ገንዘብ እጥረት እንዲያጋጥማቸው፣ ዕዳ መክፈል እንዲሳናቸውም ሊያደርግ ይችላል የባለሞያዎቹ ግምገማ እንደሚያመላክተው። እነዚህ ችግሮች እርስ በእርስ እየተመጋገቡ የምጣኔ ኃብት እንቅስቃሴው በአዝጋሚነት ዘለግ ላለ ጊዝ የሚዘልቅ ከሆነ ምጣኔ ኃብታዊ መኮማተር (ሪሰሽን) ሊከተልም ይችላል። ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂ.ዲ.ፒ.) ሰላሳ ዘጠኝ በመቶውን ድርሻ የሚይዘው የአገልገሎት ዘርፍ በወረርሽኙ ከሌሎች ዘርፎች በበለጠ ሊጎሳቆል ይችላል። ሰላሳ ሦሰት በመቶውን ድርሻ የሚይዘው ግብርና ግን ቢያንስ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአንፃራዊነት ያነሰ ጉዳት ሊደርስበት ይችላል። በባለሞያዎቹ ግምት መሠረት ወረርሽኙ አነስ ባለ የጉዳት ለሦስት ወራት ያህል ቢቆይ እንኳ ምጣኔ ኃብቱ እስከ 44 ቢሊዮን ብር የሚደርስ እጦትን ሊያስተናግድ ይችላል። ወረርሽኙ ለስድስት ወራት ቢቆይና የከፋ ጉዳት የሚያደርስ ቢሆን የእጦቱ መጠን ከሁለት መቶ ቢሊዮን ብር ይሻገራል። ኮሮናቫይረስ ሠራተኞች ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ የተሠራ አንድ ጥናት 3 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ሥራ-አጥ ሊሆኑ ይችላሉ ይላል። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ማኅበር ያሳተመው ጥናት ቫይረሱ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ከሆነ በርካቶች ሥራ-አጥ ሊሆኑ ይችላሉ ባይ ነው። በቅርቡ የኢትዮጵያ ሥራ ፈጠራ ኮሚሽን በሠራው ጥናት እንደሚጠቁመው ቫይረሱ ለስድስት ወራት የሚቆይ ከሆነ በማኒዩፈክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ 60 በመቶ ሰዎች ሥራቸውን ሊያጡ ይችላሉ።በተመሳሳይም በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ 74 በመቶ ሰዎች ሥራ-አጥ ይሆናሉ። ጥናቱ አክሎም ከ9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተሰማርተውበታል በሚባለው የአገልግሎት ዘርፍ ብቻ 3 ሚሊዮን ሰዎች ሥራቸውን ሊያጡ ይችላሉ ይላል። ቫይረሱ በኅብረተሰቡ ውስጥ ከተንሰራፋ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ጥናቱ ያስጠነቅቃል።ጥናቱ የተሠራው የቫይረሱን ቆይታ በሁለት በመከፋፈል ነው። የመጀመሪያው ለሦስት ወራት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ስድስት ወራት ነው። የቫይረሱ ተፅዕኖ የከፋ ከሆነ ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ችግር ላይ ሊወድቁ ይችላሉ ይላል። https://www.bbc.com/amharic/52254173 +health ህንድ፡በሬሳ ማቀዝቀዣ ውስጥ በህይወት የተገኙት ህንዳዊ ከቀናት በኋላ ሞቱ በስህተት ሞተዋል ተብለው 'ሬሳቸው' ማቀዝቀዣ ውስጥ እንዲገባ የተደረጉት ህንዳዊ ከቀናት በኋላ ህይወታቸው አልፏል። ባላስቡራማንያም የተባሉት የ74 አመቱ ህንዳዊ ታሚል ግዛት ውስጥ በሚገኝ የግል ክሊኒክ ውስጥ ሞተዋል ተብለውም የሬሳ ማቀዝቀዣ ውስጥ አስገብተዋቸዋል። በነገታውም የቀብር ስነ ስርአታቸውን ለመፈፀም ማቀዝቀዣውን ከፍተው በሚያዩበት ወቅት ሰውነታቸው እየተንቀጠቀጠና በህይወት መኖራቸውም ታወቀ። ሆስፒታል እንደገና ቢወሰዱም ከአምስት ቀናት በኋላ ህይወታቸው እለፏል። ተመልሰው የተወሰዱበት የመንግሥት ሆስፒታል ኃላፊ ዶክተር ባላጂናታን እንደተናገሩት ህመምተኛው በከፍተኛ ሁኔታ ደክመው እንደነበርና ከሳንባ ጋር በተገናኘ እክልም ህይወታቸው ማለፉን ለቢቢሲ ታሚል ተናግረዋል። በሬሳ ማቀዝቀዣው ውስጥም ምን ያህል ሰዓታትን እንዳሳለፉ የተገለፀ ነገር የለም። ሰኞ እለት ሞተዋል ብሎ ዶክተሩ ከተናገረ በኋላ ቤተሰቡ አስከሬኑን ይዘው ወደቤታቸው ከወሰዱ በኋላም በአካባቢው የሚገኝ የጤና ባለሙያም ማቀዝቀዣ እንዲልክላቸው ጠየቁ። ለወዳጅ፣ ዘመድ አዝማዱም በነገታው የቀብር ስነ ስርአታቸውም እንደሚፈፀም ተነግሮም ነበር። የቀብር ስነ ስርአት አስፈፃሚ ድርጅቱም የባላስቡራማንያም ወንድም በጤና ባለሙያ የተፈረመ የሞት ሰርቲፊኬት እንዳላቸውም መነገራቸውን አስረድተዋል። ሆኖም የፖሊስ ኃላፊው ሴንቲል ኩማር እንዳሉት ከሆነ ቤተሰቡ የሞት ሰርቲፊኬቱን ማምጣት አልቻሉም። ፖሊስም ቤተሰቡ በመጣደፍና ችላ በማለት የሰውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለዋል በማለትም ወንጅሏቸዋል። ግለሰቡ በነርቭ ህመም ችግርም ይሰቃዩ እንደነበር ቤተሰቡ ለፖሊስ ማሳወቃቸውን ኃላፊው አክለው ተናግረዋል። ባላስቡራማንያም ከባለቤታቸው፣ ሁለት ልጆቻቸውና ወንድማቸው ጋር ይኖሩ ነበር። በአስከሬን ማቀዝቀዣው ውስጥ ለሰዓታት ያህል በዚያ ቅዝቃዜ ውስጥ በህይወት እንዴት ቆዩ የሚለው ሚስጥራዊ ሆኗል። ከዚህም በተጨማሪ መጀመሪያ ግለሰቡን ሞቷል ያለው የግል ሆስፒታል እንዲሁም ዶክተር ምርመራ ተከፍቶባቸዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54554015 +sports የፕሪሚየር ሊግ ተጫዋቾች የኮቪድ ክትባት እንዲወስዱ በመንግሥትና በሊጉ ተጠየቁ "የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እና የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) መንግሥት የእግር ኳስ ተጫዋቾች የኮቪድ-19 ክትባትን እንዲወስዱ አሳሰቡ። በሳምንቱ መጨረሻ ሊደረጉ የነበሩት የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ግማሾቹ ክለቦች ላይ እንደ አዲስ በተቀሰቀሰው ወረርሽኝ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። 25 በመቶ የሚሆኑ ተጫዋቾች ክትባት የማግኘት ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለጻቸው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ቅዳሜ ሊደረጉ የታቀዱ 19 ጨዋታዎች ተሰርዘዋል። የዩኬ የስፖርት ሚኒስትር ኒጄል ሃድልስተን ""ክትባት መውሰድ ማኅበራዊ ኃላፊነት ያለበት ተግባር ነው"" ብለዋል። ""እግር ኳስ ተጫዋቾችን ጨምሮ ማንኛውም ሰው እራሱን፣ ባልደረቦቹን እና የሚወዳቸውን ሰዎች ከቫይረሱ ለመጠበቅ ማድረግ የሚችለው እና በጣም ወሳኙ ነገር ክትባት መውሰድ እና ማጠናከሪያ ክትባት ማግኘት ነው"" ብለዋል ሚኒስትሯ። ""አንዳንድ ተጫዋቾች ለምን ክትባት ለመውሰድ እንደሚያመነቱ ለመረዳት የእግር ኳስ አመራሮች ከተጫዋቾች ጋር እየሰሩ መሆናቸውን አውቃለሁ"" ሲሉም አክለዋል። የሊቨርፑሉ አስልጣኝ የርገን ክሎፕ ክትባቱን መውሰድ ግዴታ መሆን አለበት ብለው የሚያምኑ ሲሆን ""ከሥነ ምግባር አንጻር"" 99 በመቶ የሚሆኑት የቡድናቸው አባላት ሁለቱንም ዙር ክትባት ወስደዋል። ዋናው ""የማሳመን ጉዳይ ነው"" ነው የሚሉት አሰልጣኙ ""በዙሪያዬ ያ��ትን ሰዎች የሚረዳ አንድ ነገር ካደረግኩ እንደ ግዴታዬ እወስደዋለሁ። አንዳንድ ሰዎች ግን ይህንን በተለየ መንገድ እንደሚያዩት ግልጽ ነው"" ሲሉ ተናግረዋል። ""እኔ 54 ዓመቴ ነው እናም ሰዎችን ስለ ትክክለኛ ነገሮች ማሳመን እንደምችል በትልቁ አምናለሁ። ነገር ግን በዚህ ልዩ ጉዳይ ላይ ሰዎችን ማሳመን እንደምችል እርግጠኛ አይደለሁም"" ሲሉም አክለዋል። በጥቅምት ወር የታተመ አንድ የፕሪሚየር ሊግ መረጃ 81 በመቶ የሚሆኑት የሊጉ ተጫዋቾች ቢያንስ አንድ ጊዜ የተከተቡ ሲሆን 68 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ሁለት ዙር ክትባት አግኝተዋል። በመላው ዩናይትድ ኪንግደም 89 በመቶ የሚሆኑት ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች የመጀመሪያውን ክትባት ወስደዋል፣ 82 በመቶዎቹ ደግሞ ሁለተኛውን ዙር የወሰዱ ሲሆን 44 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የማጠናከሪያ ክትባት አግኝተዋል። በዩኬ ያልተከተቡ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ካላቸው ለ10 ቀናት ራሳቸውን ማግለል እንዳለባቸው መንግሥት ያወጣው ሕጋዊ መመሪያ ያዛል። የፕሪሚየር ሊጉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሪቻርድ ማስተርስ ሁሉም የሊጉ ክለቦች ተጫዋቾቻቸውን እንዲከተቡ ""አበክረው እንዲያበረታቱ"" በደብዳቤ ጠይቀዋል። ""የክትባትን አስፈላጊነት በጋራ አስምረንበታል እናም ከዚህ የበለጠ አስፈላጊ የሆነ ነገር የለም"" ሲሉ አስፍረዋል። ጨምረውም ኃላፊው ""እባካችሁ ሙሉ በሙሉ ያልተከተቡት ክትባቱን እንዲወስዱ አጥብቃችሁ አበረታቷቸው። የኦሚክሮን ዝርያን ብቸኛው የመከላከያ ሽፋን የሆነውን ማጠናከሪያ እንዲያገኙም አበረታቷቸው"" ሲሉ ጠይቀዋል። አንዳንዳንዶች በክትባቱ ውጤታማነት ላይ እምነት በማጣት፣ ሌሎች ደግሞ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ወይም መርፌን መፍራትን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶችን በመጥቀስ አለመከተብን ይመርጣሉ። በቁጥር አነስ ያሉ ሌሎች ደግሞ ከኢንተርኔት በተለይም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚያገኟቸው የተሳሳቱ መረጃዎች እና የሴራ ትንታኔዎች ምክንያት ክትባት አይወስዱም።" https://www.bbc.com/amharic/news-59708916 +politics ኦፌኮ በብሔራዊ ውይይቱ የታጠቁ ቡድኖች እንዲካተቱ እና ጦርነት እንዲቆም ጠየቀ "በኢትዮጵያ ሊደረግ የታቀደው ብሔራዊ ውይይት የታጠቁ ተቃዋሚ ቡድኖችን ማሳተፍ ጨምሮ ሌሎች አራት ቅድመ ሁኔታዎች ሊያሟሉ እንደሚገባ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አስታወቀ። እውነተኛ፣ ሐቀኛ እና ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይቶች ማካሄድ አገሪቱ የገባችበትን ፖለቲካዊ ቀውስ መፍታት እንደሚያስችልም ፓርቲው ጥቅምት 15/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኦፌኮ እንደ ቅድመ ሁኔታዎች ካስቀመጣቸው መካከል በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የአገሪቱን ሁለንተናዊ ህልውና አደጋ ላይ በመጣሉ ሊቆም እንደሚገባና ተፋላሚ ወገኖችም ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት ማድረግ አለባቸው ብሏል። ""በጦርነቱ አሸናፊና ተሸናፊ የለም"" በማለትም የኦፌኮ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""ጦርነትን በማወጅ የምናመጣው ነገር የለም። ጠመንጃን የሚያነሱና በዚህ የሚያመልኩ ሰዎች ይህንን ጉዳይ ትተው ወደ ጠረጴዛ እንዲመጡ ነው። ዕልባት ሊሆን የሚችለው በጠረጴዛ ዙሪያ አንድ ላይ ሆነን ችግሮቻችን አንድ ላይ ስንማከር ነው። ወደ ውይይት መምጣት ታላቅነት ነው፣ ጀግንነት ነው። መዋጋቱና መገዳደሉ ዋና መፍትሔ አይሆንም"""" ብለዋል አቶ ሙላቱ። ብሔራዊ ውይይቱ የአገሪቱን አንገብጋቢ ጥያቄ ሰላምን ትርጉም ባለው መልኩ ለመፍታትም ተቃዋሚ ታጣቂ ቡድኖችን ጨምሮ ሁሉንም የፖለቲካ አካላት ባሳተፈ መልኩ ሊሆን እንደሚገባው ፓርቲው አሳስቧል። መግለጫው ተቃዋሚ ታጣቂ ያላቸውን ቡድኖች በስም ባይጠቅስም ነገር ግን የሁሉንም ቡድኖች ውክልና ለማስጠበቅ የሕግ እና የደኅንነት እንቅፋቶች ሊወገዱም እንደሚገባም በቅድመ ሁኔታው አስቀምጧል። እነዚህን ታጣቂ ኃይሎች ማንነት በተመለከተ ቢቢሲ ለአቶ ሙላቱ ጥያቄ ያቀረበላቸው ሲሆን የኦሮሞ ነፃነት ጦርን ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት የሚያካሂዱና ስማቸው የማይነሳ አካላት እንዳሉም ይናገራሉ። ከእነዚህም መካከል ""በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ያለው የጉሙዝ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂ ኃይል፣ በሰሜን በኩል ባለው ጦርነት የሚሳተፉ አካላት፣ በአፋርና በሶማሌ በኩል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ያሉ ታጣቂዎችና፣ በአማራ ክልል ውስጥ መንግሥትን የሚገዳደሩና ለመብት የሚታገሉ ታጣቂ ኃይሎች"" እንዳሉና በርካታም እንደሆኑ ያስረዳሉ። ""እኛ ከጥይት የሚመጣ ምንም ነገር የለም። ከጠመንጃ አፈሙዝ ለጊዜው ሰላም ቢያመጣም ቋሚ አይደለም። ጊዜያዊ ነው"" የሚሉት አቶ ሙላቱ አገሪቱ በጦርነት አዙሪት ውስጥ ለዘመናት መቆየቷ ወደ ኋላ እንደጎተታትና ብዙም መስዋዕነትም አስከፍሏል ይላሉ። ህወሓትን ጨምሮ መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለው የኦሮሞ ነፃነት ጦር ሽብርተኛ ተብለው በኢትዮጵያ መንግሥት ከመፈረጃቸው አንፃር በምን መንገድ ድርድሩ ሊካሄድ ይችላል? ተብሎም ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ሙላቱ ሲመልሱ፡ ""ሁሉንም በሆደ ሰፊነት ችሎ ለሰላም መንበርከክ መቻል አለብን። ሁሉም ወገኖች ኢትዮጵያውያን ናቸው። ማንም ሰው ለዚህ አገር ለብቻው ሰርቲፊኬት የያዘ የለም። ሰርቲፊኬት ሰጪና ነሽ የለም። የአንዱ ቃል ለአንዱ የሚጎረብጠው ቢሆን ቁጭ ብለን መነጋገሩ ነው ዋናው እንጂ አንዱ ኢትዮጵያዊ ሌላውን ኢትዮጵያዊ መግደሉ ጀግንነት አይደለም"" ብለዋል። ""በጠላት ተፈራርጆ እንዴት ነው አገር የሚፈርሰው? ወደየት እየሄድን ነው ተብሎ አይታሰብም? ""በማለትም አቶ ሙላቱ ጨምረው ይጠይቃሉ። አንዳንዶች የሰላምና የድርድር ሃሳብ ሲያነሱ በህወሓት ወገንተኝነት የሚፈርጇቸው እንዳሉ አቶ ሙላቱ ጠቅሰው ""ከማን ጋር ነው የምንደራደረው?"" ብለው ጥያቄ ለሚያቀርቡ ሰዎችም አቶ ሙላቱ ምላሽ አላቸው። ""የፈለገ ጠላትም ቢሆን በኢትዮጵያዊነቱ ቁጭ ብለን መደራደር አለብን። ለሰላም ስንል ወንበራችንንም ለቀን መሬት ቁጭ ብለን ተደራድረን አገራችንን ሰላም ማድረጉ አዋቂነት እንዲሁም ጀግንነት ነው"" ይላሉ። አክለውም ""የምናካሂደው የእርስ በርስ ጦርነት ነው። ትውልድ የሚገደልበት፣ የሚያልቅበት፣ በጠቅላላው ሲታይ ወጣት አሰልጥነን፣ ድሮን ከውጭ አምጥተን፣ በሌለን የውጭ ምንዛሬ ጥይት ገዝተን ሄደን አንደኛውን መግደል እብድነት ነው"" በማለትም ያስረዳሉ። አቶ ሙላቱ ከጦርነቱ በተጨማሪ የተፈጥሮ ሁኔታና ረሃብም አገሪቱን እያቆረቆዛት ይገኛል በማለትም በትግራይና በአማራ ክልሎች ጦርነቱን ተከትሎ ከተከሰቱ ረሃቦች በተጨማሪ በጉጂና አካባቢው፣ ቦረናና ደቡብ በኩል ከፍተኛ ድርቅ መኖሩንና በየአቅጣጫው በተፈጠረው ችግር አገሪቱ እየተጎዳች መሆኑ አሳሳቢ መሆኑንም ያስረዳሉ። ሆኖም መፍትሄውና የአገሪቱ የመዳን እጣ ፈንታ በኢትዮጵያውያን ላይ መሆኑንም ጠቅሰው ""ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገሪቱ የገባችበትን እልቂት፣ ረሃብና አዘቅት በማት ልንታደጋት ይገባል። ሕዝቡም ቢሆን ይህ እልቂት የሚፈጠረው ለምንድን ነው ብሎ ሊጠይቅ ይገባል"" በማለትም መፍትሄውም ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት እንደሆነም አስምረዋል። የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ፣ ብልፅግና ያቀረበው ብሔራዊ ውይይት አንዳንዶች ዘግይቷል ሲሉ ማጣጣላቸውን የጠቀሰው መግለጫው ኦፌኮ በበኩሉ ዘግይቶም ቢሆን መካሄዱም እንደ ጥሩ እመርታ እንደሚያየው አስታውቆ ሆኖም እውነተኛና በሃ��ኛ መንገድ ሊካሄድ እንደሚገባውም አመልከቷል። ብሔራዊ ውይይቱ በሁሉም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ባለው እንዲሁም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውቅና እና ድጋፍ ባለው ገለልተኛ አካል ሊካሄድም እንሚገባም ፓርቲው እንደ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል። ""አገሪቱ ካለችበት የፖለቲካ ሁኔታ አንፃር ሲታይ በአገር ውስጥ ገለልተኛ እና በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው ታማኝ አካል ማግኘትም አስቸጋሪ መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል"" በማለትም አትቷል። ከዚህም በተጨማሪ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና በዚህም ሂደት ተሳታፊ እንዲሆኑም ኦፌኮ በመግለጫው ጠይቋል። በቅርቡ በመስቀል አደባባይ የአዲስ መንግሥት ምስረታና በዓለ ሲመት ወቅት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፤ በአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል መግባባትን ለመፍጠር ሁሉን አካታች ውይይት እንደሚካሄድ አመልክተው ነበር። የኢትዮጵያ ፖለቲካ አሸናፊ ብቻውን የሚገንበት ሳይሆን የመግባባትና በጋራ የመሥራት እንደሚሆን በንግግራቸው ጠቁመዋል። እንዲሁም የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሁሉን አካታች የሆነ ብሔራዊ ውይይት እንደሚካሄድ በመንግሥት ምስረታው ወቅት መናገራቸው የሚታወስ ነው። ሆኖም ከአገሪቱ መሪዎች ከተናገሩት ውጪ ብሔራዊ ውይይቱ እንዴት እንደሚካሄድ፣ ማንን እንደሚያሳትፍ እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን በተመለከተ መረጃ እንዳልደረሳቸው አቶ ሙላቱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፉት ሦስት ዓመታት እና ከዚያም በፊት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የኢትዮጵያን ስር የሰደደ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የፖለቲካ ቀውስ ለመፍታት የሚያግዝ ትርጉም ያለው አገራዊ ውይይት እንዲደረግ በተደጋጋሚ መጠያቁን አቶ ሙላቱ ያስታውሳሉ። ከዚያን ጊዜም ጀምሮ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የኦፌኮ አመራሮች በስብሰባዎችም በአካልም ሆነ በመገናኛ ብዙኃን ""ደካማውን ሽግግር"" ለመታደግ እና አገሪቱን ወደከፋ ትርምስ ውስጥ እንዳትገባ የውይይት እና የድርድር ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱንም መግለጫው ጠቅሷል። ለአብነትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ኦፌኮ የአገሪቱን አንገብጋቢ የፖለቲካዊ ጉዳዮች የሚወያይበት የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሽግግር የሚረጋገጥበት የጋራ ፍኖተ ካርታ የሚቀረጽበት አገር አቀፍ የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅ ተማፅኗል በማለትም ጠቅሶ ሆኖም እስካሁን ባለው ሁኔታ ሰሚ እንዳላገኙም አትቷል። በኦፌኮ ግምምገማ መሰረት በአገሪቱ በልሂቃን መካከል ያለው አለመተማመን ለወቅታዊው ቀውስ ትልቅ አስተዋፅኦ ካደረጉት መካከል አንዱ ነው በማለት ""በብሔራዊ ውይይት ስም ሁሉን አቀፍ ያልሆነ ስብሰባ ማድረግ መተማመንን የበለጠ እንደሚሽርና ግጭቶች በሚፈጠሩበት ወቅት በውይይት መፍታት እንኳን የማይቻል ያደርገዋል"" በማለት አስፍሯል። ስለዚህ ኦፌኮ ከዚህ ቀደምም እውነተኛ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ በመጥራት ግንባር ቀደም የነበረ ቢሆንም የመጪው ብሔራዊ ውይይት ኦፌኮ ያስቀመጣቸውን ቅድመ ሁኔታዎች እስካላሟላ ድረስ ""በግማሽ ልብ የሚደረግ ተሳትፎ ትርጉም የለሽ እና አጠቃላይ ሁኔታው ከንቱ ነው"" በማለትም አስቀምጧል። መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት በዚህ ዓመት እንደሚካሄድ የገለጸ ሲሆን ይህ ውይይት ማንን እንደሚያካትና መቼ እንደሚካሄድ አስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር ለም።" https://www.bbc.com/amharic/news-59046893 +politics የህወሓትና በትግራይ ያሉ ተቃዋሚዎች ውዝግብ "በቅርቡ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በትግራይ ክልል ስለተካሄደው ጦርነት እና ስለ ክልሉ አስተዳደር ላይ በጋራ መግለጫ ያወጡ ሲሆ���፣ በክልሉ ሁሉን አቀፍ የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋምም ጠይቀዋል። በክልሉ ሥልጣን ላይ ህወሐት ለዘመናት የበላይ ሆኖ መቆየቱን የሚቃወሙት ሦስቱ ፓርቲዎች ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት)፣ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ (ውናት) እንዲሁም ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ናቸው። እነዚህ ፓርቲዎች ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበውን ጦርነት ለማብቃት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ይካሄዳል በተባለው ድርድር ላይ ህወሓት ትግራይን ወክሎ የመደራደርም ሆነ ክልሉን በብቸኝነት የማስተዳደር ህጋዊምና ሞራላዊ መብት የለውም ይላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ከማዕከላዊው መንግሥት ፖለቲካ የተገፋው ህወሓት፣ በፌደራል መንግሥቱ ተቀባይነት ያላገኘ ክልላዊ ምርጫዎች በማካሄድ ‘የሕዝብ ተቀባይነት’ አግኝቻለሁ በማለት ሥልጣኑን ለማጠናከር የሚያስችለው ሁኔታ ፈጥሮ ነበር። ነገር ግን በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም. የተቀሰቀሰን ጦርነት ተከትሎ ህወሓት ከክልላዊ ሥልጣኑ ተወግዶ በሕዝቡ ዘንድ ብዙም ተቀባይነት ያላገኘ በገዢው ብልጽግና ፓርቲ መሪነት በትግራይ ለአጭር ጊዜ የቆየ ጊዜያዊ አስተዳደር ተመስርቶ ነበር። ጦርነቱን ተከትሎ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጅምላ ግድያ፣ ዘረፋ፣ ጾታዊ ጥቃት እና የመሠረተ ልማቶች ውድመት ደርሷል። የተባበሩት መንግሥታት እና ሌሎችም የመብት ተቋማት ለተፈጸሙት ጥፋቶች ህወሓትን ጨምሮ ሁሉንም ተጻራሪ ኃይሎች ተጠያቂ ያደርጋል። የሳልሳይ ወያነ ትግራይ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኃይሉ ከበደ “በልጆቹና ባለቤቱ፣ በእናቱ እና በእህቶቹ ላይ ግፍና በደል የተፈጸመበት የትግራይ ሕዝብ የታገለው ለሉአላዊነቱ እና ለደኅንነቱ እንጂ ለህወሓት አልነበረም” ይላሉ። “ህወሓት በሕግ ይሁን በሞራል ከሥልጣን በኃይል ተወግዷል። በዚህ መካከልም ሌላ አስተዳደር ተመስርቶ ነበር። ትግላችን የትግራይን መንግሥትነት መመለስ ነበር” ሲሉ ያስረዳሉ። የባይቶና ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ክብሮም በርኸ ከመታሰራቸው ከቀናት በፊት ለቢቢሲ እንደተናገሩት “ህወሓት ከፕሮፓጋንዳ በዘለለ ተገቢውን ወታደራዊ ዝግጅት ባለማድረጉ የትግራይ ሕዝብን ለአደጋ እንዲጋለጥ ስላደረገ ከሕዝቡ ጋር የነበረው ውል ፈርሷል” ይላሉ። በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በክልሉ ውስጥ ለተፈጸተው ክፈተት ተጠያቂ የሚያደርጉት ህወሓትን ነው። በአዲስ መልክ የተደራጁት የትግራይ ኃይሎች ሰኔ 21/2013  ዓ.ም. ላይ መቀለን ከተቆጣጠሩ በኋላ የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የቀድሞ የክልሉ አስተዳደር ወደ ቦታው መመለሱን አስታውቀዋል። ነገር ግን በትግራይ ሁሉን አሳታፊ አስተዳደር መመስረትን በተመለከተ ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበሩት የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአዲሱ መንግሥት ውስጥ ምንም ቦታና እውቅና አልተሰጣቸውም። የሦስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሊቀመንበሮችን ጨምሮ በርካታ አባሎቻቸው በትጥቅ ትግሉ የተሳተፉ ቢሆንም ህወሓት ግን ከበረሃ ተመልሶ ሥልጣኑን ብቻውን መቆጣጠር ነው የመረጠው ይላሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አንዳንዶች የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ሲጠይቁ ሌሎች ደግሞ ጥምር ክልላዊ ምክር ቤት እንዲቋቋም ጠይቀዋል። ሆኖም ከህወሓት ምንም አይነት አዎንታዊ ምላሽ አላገኙም። ለአቶ ኃይሉ ከበደ በትግራይ ሁሉን አሳታፊ መንግሥት መመስረት ማለት በሕዝባዊ ተቋማቱ በኩል አዲስና አሳታፊ ሕዝባዊ አስተዳደርን ማወቀር ማለት ነው። “ሕዝባዊ ትግል ነው ያካሄድነው፤ ስለሆነም ሕዝባዊ መንግሥት መመስረት አለበት የሚል እምነት ነበረን” ይላሉ። አያይዘውም “እኛ የምንታገለው የትግራይ መንግሥትነት እንዲመለስ እንጂ ህወሓት እንዲመለስና ብቻውን ያለፉትን 30 ዓመታት እንዲደግም አይደለም” በማለት ያስረዳሉ። የትግራይ ነፃነት አገርነት አላማው አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የትግራይ ነፃነት ፓርቲ (ውናት) ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር ደጀን መዝገበ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ “ጥምር መንግሥት መሥርተን በጋራ ለመሥራት ተስፋ አድርገን ነበር” ብለዋል። ህወሓትን “ህገወጥ” የሚሉት የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጋራ አቋም በመያዝ ባወጡት የጋራ መግለጫ ህወሓትን ያካተተ ሕዝባዊ የሽግግር መንግሥት በክልሉ እንዲመሰረት ጠይቀዋል። ነገር ግን በአሜሪካ የህወሓት ተወካይ የሆኑት አቶ ዮሐንስ አብረሃ “ከዚህ ቀደም ሕጋዊ ክልላዊ መንግሥት ወደ ቦታው ይመለስ ብለው ሲጠይቁ ቆይተው፣ ዛሬ ደግሞ ተመልሰው የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ማቅረባቸው ልክ አይደለም” ብለዋል። አክለውም “የትግራይ መንግሥትን ሕገወጥ ነው” በማለት መክሰሳቸው፣ ፓርቲዎቹን እሳቸው ‘የጠላት ኃይሎች’ ሲሉ ከሚገልጿቸው አካላት ነጥለው ለማየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ተቃዋሚዎችን “ቀበጦች” ሲሉ በማኅበራዊ ሚድያ ላይ የወረፏቸው ሲሆን ለዚህ አባባላቸውም ከብዙዎች ዘንድ ጠንካራ ትችት ቀርቦባቸዋል። በውጭ አገራት የሚኖሩ ሌሎች የህወሓት ‘ቀንደኛ’ ደጋፊዎች በበኩላቸው ተቃዋሚዎቹን ‘የዐቢይ ተላላኪዎች’ በማለት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቀዋል። ‘የሥልጣን ጥመኞች’ ሲሉም የሚከሷቸው አሉ። ክብሮም በርኸ “ሥልጣን ፈላጊዎች ይሉናል። ሥልጣን ብንፈልግም ሃጢአት አይደለም። እኛ ፖለቲከኞች ነን፤ ምንም የሚያሳፍር ነገር የለውም። ሊያፍሩ የሚገባቸው እነዚያ በመጠቃቀምና በስብስብ ሥልጣን የተቆጣጠሩ ሰዎች ናቸው” ብሏል። ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲያበቃ በተለይም በአሜሪካ፣ በኬንያ እና በአፍሪካ ኅብረት የሚመሩ የድርድር ጥረቶች እየተሞከሩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ ተደራዳሪ ኮሚቴ መሰየሙን አስታውቀዋል። የህወሓት መሪዎችም በኬንያ መንግሥት ለሚመራ ውይይት ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ተደራዳሪዎቻቸውን ግን እስካሁን ይፋ አላደረጉም። ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ቀውስ ያስከተለው ጦርነት ብዙዎች በሰላማዊ መንገድ ይፈታ ይሆን በሚል ተስፋ ቢያደርጉም ሌሎች ደግሞ “ጊዜ መግዣ ነው” የሚል ጥርጣሪ አላቸው። በሰሜን አሜሪካ የህወሓት ተወካይ አቶ ዮሐንስ አብረሃ “በእኛ በኩል በውይይት መፍትሄ ሊመጣ ይችላል ብለን እናምናለን” በማለት ከሌላኛው ወገን በኩል ግን ጥርጣሬ እንዳላቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። አቶ ኃይሉ ከበደ ግን “የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንዴ ፈርሷል። ለቀጣይ አቅጣጫም መነሻ ሊሆን አይችልም። የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ሊያስከብር አይችልም። በእሱ ተደራድረን የምናሳካው ጥቅምም የለም” ይላሉ። ተቃዋሚ ፓርቲዎቹም ከዚህ በመነሳት ነው ህወሓት የመደራደር ውክልና የለውም በማለት “የትግራይን ሕዝብ ለዚህ ውርደት አጋልጦ ትንሽ መፀፀት ያስፈልግ ነበር። እነዚህ ግን በድርቅና አድራጊ ፈጣሪ እኛ ነን እያሉ ነው” በማለት አቶ ኃይሉ ህወሓትን ይወቅሳሉ። ዶ/ር ደጀን በበኩላቸው ይህንን ተቃዋሚዎች አለ የሚሉትን የሕግ ክፍተት በመጥቀስ “ህወሓት ብቻውን ለመደራደርም ሆነ ትግራይን ለመምራት ምንም አይነት የሕግ መሰረት የለውም” ሲሉ ይቃወማሉ። ይህን ያሉበት ምክንያት ሲያስረዱም “በየትኛው ሕግ ነው ሠራዊት ሊገነባ እና ዲፕሎማሲን ማስቀጠል የሚችለው?” በማለት በሕገ መንግሥቱ መሰረት እነዚህ የፌደራል መንግሥት ተግባራት መሆናቸውን ያስታውሳሉ። አክለውም “ከሕገ መንግሥቱ ውጪ የሆነ ኃላፊነት የያዘ መንግሥት አለ። ይህን መስራት የሚችል ኃላፊነት ያለው ፓርቲ የለም።። የወደፊት የትግራይ ዕጣ ለዘላለም ብቻውን እንዲወስን የተመረጠ ፓርቲ የለም። የህወሓት ስርወ መንግሥትንም ለመመስረት የመረጠ ሕዝብም የለም” ይላሉ። “ህወሓት ለረጅም ጊዜ በሥልጣን ላይ ቆይቷል ለማለት ከሆነ ይገባኛል” በማለት የሚናገሩት አቶ ዮሐንስ ነገር ግን ፓርቲው በሕግ አግባብ መመረጡን ይጠቅሳሉ። ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በመላ ትግራይ ተንቀሳቅሰው የህዝቡን ቀልብ መሳብ የሚችሉበትን ሁኔታ ፈጥረው፣ ሕዝቡ ህወሓትን በቃህ የሚለው ከሆነ የሕዝቡን ፍላጎት እንደሚያከብሩ አቶ ዮሐንስ ያስዳሉ። ነገር ግን ፓርቲዎቹ ሕዝባዊ ስብሰባ እንኳን እንዳያካሂዱ መከልከላቸውን እና እንቅስቃሴያቸውም መገደቡን በማስመልከት ስለሚያርቡት አቤቱታ ከቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ዮሐንስ በጉዳዩ ላይ መረጃ እንደሌላችው በመግለጽ “እንደዚያ የተደረገ ግን አይመስለኝም” ብለዋል። የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከህወሓት ጋር በጋራ ለመሥራት ‘የፓርቲዎች የጋራ መድረክ’ ተቋቁሞ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በጋራ መወያየት ጀምረው እንደነበረ ያስታውሳሉ። “የፓርቲዎች ፎረምን የልጆች መጫወቻ አድርገውታል” የሚሉት አቶ ኃይሉ ከበደ፣ ህወሓት ሲፈልግ ብቻ እንደሚሰበሰቡና ወታደራዊ ድሎች ሲገኙ ግን እንደሚረሱ ጠቅሰዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ግን የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ከስምንት ጊዜ በላይ ከዶ/ር ደብረፂዮን ጋር  መወያየታቸውን በማኅበራዊ ሚድያ ጽሁፋቸው ላይ አስፍረው ነበር። አቶ ኃይሉ ከበደ ግን “ከኅዳር ወር በኋላ ‘መከበብና መዘጋት’ ወደ ሚለው ግልፅ ወዳልሆነ ፖለቲካ ገባን። የትግራይ ሕዝብ እየጠፋና እየረገፈ ነው። በህወሓት ምክንያት ዲፕሎማሲያዊ ሥራ መሥራት አልተቻለም። የትግራይ ሕዝብ ትግል ዲፕሎማሲያዊ አጋር አላገኘም” ይላል። ተቃዋሚዎቹ ትግራይ ውስጥ በተካሄደው ጦርነት ምክያት ሕገ መንግሥቱ በአገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ ፈርሷል ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ። የህወሓት ተወካይ አቶ ዮሐንስ ግን “ሕገ መንግሥቱ ፈርሷል ካልን እነሱስ በየትኛው አሰራር ነው ሕጋዊ ተቃዋሚ የሆኑት?” ሲሉ ይጠይቃሉ። “ሕገ መንግሥታዊ ቀውስ ነው ያጋጠመው” የሚለው ፖለቲከኛ ክብሮም በርኸ በበኩሉ አዲስ ውል ማሰር እንደሚያስፈልግ ያምናል። ""ለዓላማችን ስንል ሠራዊት ልንገነባና ዲፕሎማሲ መሥራት ስላለብን የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት ፓርቲዎችና ሌሎች ግለሰቦች የሚሳተፉበት የጋራ መድረክ ሊኖር ይገባል” ይላሉ ዶክተር ደጀን በበኩላቸው። በአሜሪካ የህወሓት ተወካይ የሆኑት አቶ ዮሐንስ አብርሃ “ሕገ መንግሥቱ ተሸራርፏል እንጂ ፈርሷል” ብለው እንደማያምኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""ሕገ መንግሥቱ ፈርሷል ካልን ያለሱ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለመንቀሳቀስ ይከብደናል” ሲሉም ይሞግታሉ። “አሁን የሽግግር መንግሥት ቢቋቋም ተቃዋሚ ኃይሎቹ ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ነበር?” የሚል ጥያቄ በማንሳትም የቀረበው ሐሳብ መፍትሔ እንደማያመጣ ይናገራሉ። የምዕራብ ትግራይ ጉዳይ እና ሌሎች የትግራይን ሕዝብ ዕጣ ፈንታን ሊወስኑ የሚችሉ ሁኔታዎች ሕገ መንግሥቱን መሰረት በማድረግ ሊፈቱ እንደሚችሉ ነው የሚያምኑት። እሳቸው ይህን ቢሉም፣ ተቃዋሚዎቹ ግን በአንድ ድምፅ “ህወሓት በኢትዮጵያ ውስጥ መኖርን ነው የሚመርጠው። ከሕዝባችን የነፃነት ምኞት ጋር አልተስማማም” በማለት ይከሱታል። ‘ሕዝበ ውሳኔ’ የሚለው ቃልም ማደናገሪያና በተደጋጋሚ የትግራይን ህዝብ ጥቅም አሳልፎ የሰጠ መሆኑን ይገልፃሉ።። ይህንን ክስ የማይቀበሉት አቶ ዮሐንስ በበኩላቸው “የእኛ ምርጫ የሕዝባችን ውሳኔ ነው የሚሆነው። ሕዝባችን ምን እንደሚፈልግ ለመወቅም ለድርድር የማይቀርብ መድረክ እናዘጋጃለን” ብለዋል። የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ዙሪያ በአሁኑ ወቅት የህወሓት አቋሙ ምን እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ዮሐንስ፣ ፓርቲው በቅርቡ ጠቅላላ ጉባኤ ካካሄደ በኋላ ግልጽ እንደሚሆን ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c8vqvgr8gjlo +business የነዳጅ ዋጋ እንዲንር ወይም እንዲቀንስ የሚያደርገው ምንድን ነው? የሚወስነውስ ማን ነው? ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ማብቂያ ላይ የዓለማችን ቀዳሚ ነዳጅ ላኪ አገራት ስብሰባ አድርገው ነበር። አጀንዳቸው የነበረውም የድፍድፍ ነዳጅን ዋጋ ለመቀነስ ያለመ ነበር። በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ዋጋ ካለፉት ስምንት ዓመታት የበለጠ ሆኗል። ነዳጅ ከውጭ አስመጥተው የሚጠቀሙ አገራት፣ ነዳጅ አምርተው የሚልኩ አገራት ስብስብ የኦፔክ ፕላስ (Opec+) የነዳጅ ምርትን እንዲጨምሩ ተማጽነዋል። ዋነኞቹ ነዳጅ ላኪ አገራት እምብዛም ተማጽኖውን የሰሙ አይመስልም። ይልቁንም በቀን የሚመረተውን ነዳጅ በሁለት ሚሊዮን በርሜል ለመቀነስ ተስማምተዋል። ሩሲያን ጨምሮ የኦፔክ ፕላስ አባል አገራት የነዳጅ ዋጋን ለመጨመር እርምጃ እየወሰዱ ነው። የነዳጅ ዋጋ ባለፈው ዓመት የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም፤ ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ ዋጋው ንሯል። ዋነኞቹ የዓለማችን የነዳጅ ዘይት አምራች አገራት የምርታቸውን መጠንና ዋጋን ለመቆጣጠር ኦፔክ ፕላስ በተባለ ማኅበር ተሰባስበዋል። አባላቱም 23 አገራት ናቸው። በዓለም ገበያ ድፍድፍ ነዳጅ በስንት ይሸጥ የሚለውን ለመወሰን ውይይት ያካሂዳሉ። በዚህ ስብስብ ውስጥ ካሉት አገራት መካከል 13ቱ ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከአፍሪካ ናቸው። ከኦፔክ ፕላስ በፊት በ1960ዎቹ ኦፔክ ሲመሠረት አላማው የዓለምን የነዳጅ ዘይት ገበያ ፈር ማስያዝ ነበር። ዛሬ ላይ የዓለም 30 በመቶ ነዳጅ የሚመረተው በኦፔክ አገራት ነው። ሳዑዲ አረቢያ በቀን ከ10 ሚሊዮን በርሜል በላይ ነዳጅ በማምረት የአንበሳውን ድርሻ ትይዛለች። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2016 የነዳጅ ዋጋ እጅግ አሽቆልቁሎ ነበር። ኦፔክ ከሌሎች 10 ነዳጅ አምራቾች ጋር ተዋህዶ ኦፔክ ፕላስ የተፈጠረውም የዚያን ጊዜ ነበር። ኦፔክ ፕላስ የዓለምን 40 በመቶ ድፍድፍ ነዳጅ ያመርታል። በኢነርጂ ኢንስቲትዩት የምትሠራው ኬት ዶውሪን “ኦፔክ ፕላስ ገበያውን ለማረጋጋት አቅርቦት እና ፍላጎትን ያመጣጥናል” ትላለች። “የነዳጅ ፍላጎት ሲቀንስ፣ የነዳጅ አቅርቦትን ዝቅ በማድረግ ዋጋውን ይጨምራሉ” ስትልም ታስረዳለች። በርከት ያለ ነዳጅ ገበያው ላይ በማቅረብ ዋጋ እንዲቀንስ ማድረግም ይችላሉ። የኦፔክ ፕላስ አባል አገራት ከሁለት ዓመት በፊት ኦስትሪያ፣ ቪየና ውስጥ ከተገናኙ በኋላ፣ ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ በቀን የሚመረተውን ነዳጅ በሁለት ሚሊዮን በርሜል በመቀነስ ምርታቸውን ከ42 ሚሊዮን በርሜል በታች ለማድረግ ወስነዋል። ይህ ውሳኔም ካለንበት ጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል። በዚህም የሚደረገው ቅነሳ ከዓለም አጠቃላይ የነዳጅ ምርት ሁለት በመቶውን ሲይዝ፣ ከሚጠበቀውም በላይ ነው። ከአውሮፓውያኑ 2020 ወዲህ የኦፔክ ፕላስ አባላት ነዳጅ ምርት ላይ ያደረጉት ከፍተኛው ቅነሳ እንደሆነም ተገልጿል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት ጊዜ የነዳጅ ምርትን በቀን ከዘጠኝ ሚሊዮን በርሜል በላይ ለመቀነስ ወስነው ነበር። ውሳኔው የተላለፈው የነዳጅ ዋጋን ለመጨመር ነው። በወቅቱ የነዳጅ ዋጋ ከነበረበት 122 ዶላር ወደ 90 ዶላር ዝቅ ብሎ ነበር። የነዳጅ ምርትን ለመቀነስ ውሳኔ ሲተላለፍ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል። የነዳጅ ዋጋ መጨመር በመላው ዓለም የዋ�� ንረትን አስከትሏል። አሜሪካ ኦፔክ ፕላስ የነዳጅ ምርትን እንዳይቀንስ ጠይቃለች። የነዳጅ ዋጋ አነስተኛ ከሆነ ሩሲያ የምታገኘው ገቢም ያንሳል ማለት ነው። ዋይት ሐውስ የኦፔክ ፕላስን ውሳኔ “የረጅም ጊዜ ሁኔታን ያላጋዘበ” ሲል ተችቷል። ያለፈው ሐምሌ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ሳዑዲ አረቢያ ተጉዘው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን የነዳጅ ምርትን እንዲጨምሩ ጠይቀው ነበር። ነገር ግን ጥያቄውን አልተቀበሉትም። የቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንም በተመሳሳይ ሳዑዲ አረቢያ እና ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የነዳጅ ምርት እንዲጨምሩ ቢጠይቁም አልተሳካላቸውም። ከሁለት ዓመት በፊት ኮሮናቫይረስ ሲነሳ፣ አገራትም በራቸውን ሲዘጉ፣ ድፍድፍ ነዳጅ ገዢ አጥቶ ዋጋው አሽቆልቁሎ ነበር። “ነዳጅ አምራቾች ምርታቸውን ለመሸጥ ለገዢዎች ገንዘብ እየከፈሉ ነበር። አምራቾቹ ነዳጁን የሚያከማቹበት ቦታ አጥተውም ነበር” ስትል በኢነርጂ ኢንስቲትዩት የምትሠራው ኬት ዶውሪን ታስረዳለች። የኦፔክ ፕላስ አባላት የነዳጅ ምርትን በቀን በአስር ሚሊዮን በርሜል ለመቀነስ የወሰኑት የነዳጅ ዋጋ እንዲያንሰራራ ነበር። ከዚያ ወዲህ ኦፔክ ፕላስ የነዳጅ ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ ቀስ በቀስ ምርቱን እያሳደገ መጥቷል። ሩሲያ ዩክሬንን ስትወር ግን የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ ሆነ። በሩሲያ ላይ የተጣሉ ዓለም አቀፍ ማዕቀቦች የሩሲያ ነዳጅ ምርት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ ተብሎ ተሰግቷል። እየቀነሰ ያለው የነዳጅ ዋጋ እንዲያንሰራራ ኦፔክ ፕላስ አምራች አገራት ምርታቸውን ለመቀነስ መወሰናቸው ተጠቁሟል። ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ በርካታ አገራት ከሩሲያ የሚገዙትን የነዳጅ መጠን ቀንሰዋል። የሩሲያ ነዳጅ ዋጋ እየቀነሰም መጥቷል። የሩሲያ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል ከ30 ዶላር በላይ የተሸጠበት ጊዜም ነበር። መስከረም መጨረሻ ላይ ወደ 20 ዶላር ወርዷል። ሩሲያ ላይ ማዕቀብ ከጣሉት ምዕራባውያን አገራት ጋር ያልተባበሩት ሕንድ እና ቻይና፣ አሁን ላይ ከአገሪቱ ምርት ከግማሽ በላዩን ይረከባሉ። በዚህም ሩሲያ የቻይና ትልቋ ነዳጅ አቅራቢ ሆናለች። ከዚህ ቀደም ወደ ቻይና ነዳጅ በዋናነት የምትልከው ሳዑዲ አረቢያ ነበረች። መጋቢት ላይ ቻይና እና ሕንድ ከሩሲያ የገዙት ነዳጅ ከ27ቱ የአውሮፓ ኅብረት አባላት ይበልጣል። በዚህ በጥቅምት ወርም የአውሮፓ ኅብረት በሩሲያ የድፍድፍ ነዳጅ ምርት ላይ ማዕቀብ ለመጣል አቅዷል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1v5xnn3e2o +business ከጎጃም እናቶች አንገት ላይ ስለማይታጣው ማርትሬዛ ምን ያክል ያውቃሉ? "በኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ የጎጃም እናቶች አንገታቸው ላይ ለመዋቢያነት የሚያደርጉት 'ማርትሬዛ' ወይም 'ጠገራ' ተብሎ የሚጠራው ሳንቲም ምንጩ ከወዴት እንደሆነ ጠይቀው ያውቃሉ? ከየት መጣ? እንዴት መጣ? እንዴትስ ለመዋቢያነት ጥቅም ላይ ዋለ? ጠገራውን ለመዋቢያነት ከአንገቷ ላይ አኑራ በባህር ዳር ከተማ ገብያ መሃል ያገኘናት ወ/ሮ እሙዬ ጓዴ ""በባህላችን ሴት ልጅ ስትዳር ይሄ ይሰጣታል። ለእርሷ የሚቀርባት ሰው ነው የሚሰጣት። ይሄ የቀድሞ ጠገራ ነው፤ የትም አይገኝም"" ትላለች። • ከፕላስቲክ የጫማ ቀለም የሚያመርቱት የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች • እሷ ማናት? የበለስ ማርማላታ ወደ ውጪ የምትልከው ኢትዮጵያዊት ወ/ሮ እሙዬ ጠገራው ከየት እንደመጣ እርግጠኛ ባይሆኑም፤ ከቀደመ ትውልድ እንደወረሱት ይናገራሉ። ""ጠገራው የአያቴ ነበር። አያቴ ለእናቴ ሰጠቻት። እናቴ ደግሞ ለእኔ ሰጠችኝ። አሁን አንገቴ ላይ ካኖርኩት ከ40 ዓመት በላይ ይሆነዋለ"" ብላለች። ""የሃገር ባህል ነው። ሴቶች ሲዳሩ እንደ ጥሎሽ ��በር የሚሰጣቸው። ጠገራው ከብር ስለሚሰራ ብዙ ገንዘብ ያወጣል። ስለሚያምር ለመዋቢያነት ይውላል"" የሚሉት ደግሞ እዚያው ገብያ መሃል ያገኘናቸው አቶ አማረ ናቸው። ሙሉ መጠሪያው ማሪያ ቴሬሳ ቴለር ሲሆን ለመገበያያነት ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ሳንቲም ነው። መጠሪያውን ያገኘው ከኦስትሪያ-ሃነጋሪ ንግስት ስም ማሪያ ቴሬዛ ታለር ነው። ይህ ለመገበያያነት ይውል የነበረው ሳንቲም በአውሮፓዊቷ ሃገረ ኦስትሪያ ከ1730ዎቹ እስከ 1770ዎቹ ድረስ ባሉት የማሪያ ቴሬዛ ታለር ንግስና ዓመታት ታትሟል። ማሪያ ቴሬሳ ቴለር በዓለም ላይ በስፋት ከሚታወቁት መገበያያ ሳንቲሞች መካከል አንዱ የነበረ ሲሆን፤ የአረብ ሃገራት ነጋዴዎች ከአውሮፓ ሃገራት ጋር ለሚያደርጉት ግብይት የሚቀበሉት ማሪያ ቴሬሳ ቴለርን ብቻ ስለመሆኑ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የታሪክ ጥናት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳምጤ ደምሴ፤ ''ማርትሬዛ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል"" ይላሉ። አቶ ዳምጤ ""የጎንደሩ ዳግማዊ አጼ እያሱ የንግስና ዘመን ማብቂያ አካባቢ ሳንቲሙ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ነበር። ነጋዴዎች፣ አውሮፓውያን አሳሾች እና ተጓዦች ወደ ሃገራችን ይዘውት መጥተዋል"" ብለውናል። • ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . . ክርስቲያን ጎቲች የተባሉ ክሮሺያዊ የታሪክ ተመራማሪ ''ዘ ቴለር ኦፍ ማሪያ ቴሬዛ'' በተሰኘው ጽሁፋቸው፤ በአውሮፓ በተለይ ደግሞ በቪዬና ከተማ ከተቀረጹ 245 ሚሊዮን ከሚሆኑት ማሪያ ቴሬሳ ቴለር ሳንቲሞች መካከል 20 በመቶ ያክሉ ወደ ኢትዮጵያ ስለመወሰዳቸው አትተዋል። ይህ ሳንቲም ደግሞ በስፋት ወደ ኢትዮጵያ የገባው፤ በአጼ ቴዎድሮስ II ወቅት ወራሪው የእግሊዝ ጦር በፊልድ ማርሻል ሮቤርት ናፒየር እየተመራ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ፤ ለጉልበት ሥራ ለሚያሰማራቸው ሰዎች በክፍያ መልክ ይህን የጠገራ ሳንቲም ለመክፈል በብዛት ይዞ በመምጣቱ እንደሆነ ሪቻርድ ፓንክረስት ''ዘ ማሪያ ቴሬሳ ዶላር ኢን ፕሪ-ዋር ኢትዮጵያ'' በተሰኘው ጥናታዊ ጽሁፋቸው ላይ ጠቅሰዋል። ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በአውሮፓ እና መካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ውስጥ ይህ ሳንቲም በስፋት እንደሚገኝ ይነገራል። ከብር የተቀረጹት እኚህ ሳንቲሞች በኢንተርኔት ገበያዎች ላይ በመጠን እና በተቀረጹበት ዓመት ልዩነት መሰረት ከ15 እስከ 500 የአሜሪካ ዶላር ይሸጣሉ። በኢትዮጵያም ከብር የተሰሩ ጠገራዎች እስከ 1500 ብር ይጠየቅባቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-50781921 +business በአሜሪካ ከጭነት መኪና ላይ ቲማቲም ተደፍቶ ለትራፊክ አደጋ ምክንያት ሆነ በአሜሪካዋ የካሊፎርኒያ ግዛት ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ባለበት መንገድ ላይ አንድ የጭነት መኪና 150 ሺህ ቲማቲም አስፓልት ላይ ከደፋ በኋላ የትራፊክ አደጋ አጋጠመ። ቲማቲም ጭኖ የነበረው የደረቅ ጭንት ተሽከርካሪ አደጋ ካጋጠመው በኋላ ነው ግዛቶችን በሚያገናኘው አውራ ጎዳና ላይ ቲማቲሙ የተደፋው። መንገዱ ላይ የተደፋው ቲማቲም አራት መኪኖች እንዲጋጩ እና የተለያዩ ግዛቶችን የሚያገናኘው አውራ ጎዳና አብዛኛው የመንገዱ ክፍል እንዲዘጋ ምክንያት ሆኗል። ባጋጠመው የመኪና አደጋ ሦስት ሰዎች ቀላል ጉዳት ያጋጠማቸው ሲሆን፣ አንድ ሰው ደግሞ የእግር መሰበር አደጋ ደርሶበት በሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት መሆኑን የካሊፎርኒያ የመንገድ ተቆጣጣሪ ፖሊስ አስታውቋል። የቲማቲም ምርት ከተሰበሰበ በኋላ አሸከርካሪዎች ምርቱን ወደ ሌሎች ግዛቶች ለማጓጓዝ ይህን አውራ ጎዳና ይጠቀማሉ። ቲማቲም ጭኖ የነረበው የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪ ተንሸራቶ ከመንገድ ሲወጣ የደፋው ቲማቲም 200 ጫማ የመንገዱን ክፍል ሸፍኖታል። መጠናቸው ከፍ ያሉ 150 ሺህ ቲማቲሞች ተጨ��ላልቀው እስከ 60 ሳንቲ ሜትር ከፍታ ያለው “ቀይ ስልስ” ፈጥረው ነበር ሲሉ የመንገድ ተቆጣጣሪ ፖሊስ አባሉ ጄሰን ታይረስት ተናግረዋል። መኪኖች የተጨፈላለቁ ቲማቲሞች ላይ ሲሄዱ እየተንሸራተቱ አደጋ ማጋጠሙም የፖሊስ አባሉ ተናግረዋል። “የቲማቲም ልጣጭ አስፓልት ከደረሰ በረዶ ላይ እንደመራመድ ነው” ሲሉ ጄሰን ታይረስት ለኒዮርክ ታይምስ ተናግረዋል። አደጋው ካጋጠመ ከበርካታ ሰዓታት በኋላ ዳግም የተሽከርካሪ አደጋ እንዳያጋጥም መንገዱ እንዲጸዳ ተደርጎ ዳግም ለትራፊክ ክፍት ሆኗል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cyrxd87m5rdo +health ሁለቴ የተከተቡ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሊያስተላልፉ ይችላሉ ተባለ ሁለት ጊዜ የኮቪድ-19 ክትባትን የወሰዱ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ እንደሆነ እና አብረዋቸው የሚኖሩ ሰዎችንም እያስያስያዙ እንደሚገኙ ባለሙያዎች ተናገሩ። ይህንን ያሳወቁት በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ቤተሰቦች ላይ ጥናት ያካሄዱ ባለሙያዎች ናቸው። እንደ ባለሙያዎቹ ከሆነ፤ ክትባቱን ሁለት ጊዜ የወሰዱ ሰዎች ክትባቱን ካልወሰዱ ሰዎች ባልተለየ መልኩ ቫይረሱን ወደ ሌሎች ሰዎች ያስተላልፋሉ። በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ምልክቶችን ቢያሳዩም ባያሳዩም፤ ቫይረሱን ክትባቱን ወዳልወሰዱ ሰዎች የማስተላለፍ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል። ይህም ከአምስት ሰዎች ሁለቱ እንደማለት ነው ይላሉ ባለሙያዎቹ። በሌላ አገላለጽ ደግሞ ቫይረሱን የማስተላለፍ ዕድላቸው 38 በመቶ ነው። ነገር ግን ሁሉም የቤተሰብ አባላት ክትባቱን ወስደው ከሆነ ቁጥሩ የሚቀንስ ሲሆን፤ ከአራት ሰዎች አንድ ሰው ቫይረሱን ያስተላልፋል። በመቶዎች ሲሰላ ደግሞ ሁለቱንም ዙር ክትባት ከወሰዱ ሰዎች መካከል 25 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ቫይረሱን ያስተላልፋሉ ማለት ነው። የላንሴት ተላላፊ በሽታዎች ምርምር ማዕከል እንደሚለው፤ ሁሉንም ሰው እንዲከተብ ማድረግ ከሰዎች ወደ ሰዎች የመተላለፍ እድሉን ስለሚቀንሰው አሁንም ክትባቱ ላይ ማተኮር ጠቃሚ ነው። ክትባቱን ያልወሰዱ ሰዎች በቫይረሱ ያለመያዝ እድላቸውን ከፍ ለማድረግ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች መከተባቸውን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን እራሳቸውም ክትባቱን ቢወስዱ ይመረጣል ሲሉ ተመራማሪዎቹ ያስጠነቅቃሉ። ክትባቶች በኮቪድ-19 ምክንያት የሚከሰት ከፍተኛ ህመምን እና ሞትን ለማስቀረት ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ ምንም ጥርጥር የለውም። ነገር ግን የቫይረሱን ስርጭት መቀነስ ላይ አሁንም ብዙ የሚቀሩት ነገሮች አሉ። በተጨማሪ ደግሞ እንደ ዴልታ ያሉ አዳዲስ ዝርያዎች መምጣት ክትባቶቹ የታሰበላቸውን ያክል ውጤታማ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል። በጊዜ ብዛት ደግሞ የክትባቶቹ የመከላከል አቅም እየቀነስ ስለሚመጣ ተጨማሪ ድጋፍ የሚሰጡ ክትባቶችን (ቡስተር) መውሰድ ግድ እያለ ነው። በአሁኑ ሰዓት በተለይ በአውሮፓ አገራት ከፍተኛው የቫይረሱ ስርጭት እየተከሰተ ያለው በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ መሆኑን ተከትሎ በተቻለ መጠን ክትባቱን መውሰድ የሚችል የቤተሰብ አባል በሙሉ ቢከተብ ይመረጣል ይላሉ ባለሙያዎቹ። እንግሊዝ ውስጥ በተሠራ አንድ ጥናት መሠረት ሁለት ጊዜ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ካልተከተቡት ጋር ሲነጻጸር በአዲሱ የዴልታ ቫይረስ የመያዝ ዕድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ እንደሆነ ተመልክቷል። ሆኖም በቫይረሱ የተያዘ ሰው በሰውነቱ ውስጥ ያለው የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ በሚሆንበት ወቅት የቫይረስ ክምችት እና የተከተበ ሰው የሚኖረው የቫይረስ ክምችት ተመሳሳይ ነው። ለዚህም ነው ምንም እንኳን የተከተቡት ሰዎች ምንም አይነት ምልክት ባያሳዩም ወደ ሌሎች ሰዎች ግን የሚያስተላልፉት። https://www.bbc.com/amharic/59086852 +health ኮሮናቫይረስ፡ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ልጅ ���ቪድ-19 ተገኘበት የዶናልድ ትራምፕ ልጅ ዶናልድ ትራምፕ ጁንየር ኮሮናቫይተስ እንደተገኘበት ቃል አቀባዩ ተናገረ። የ42 ዓመቱ ትራምፕ ጁንየር በሳምንቱ መባቻ ላይ ነው በቫይረሱ መያዙ የታወቀው። አሁን ራሱን ለይቶ ይገኛል። እስካሁን የበሽታውን ምልክቶች እንዳላሳየና በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጠውን መርህ እየተከተለ መሆኑ ተገልጿል። ሌላው የትራምፕ ልጅ የ14 ዓመቱ ባሮን ትራምፕ ባለፈው ወር በወረርሽኙ ተይዞ በፍጥነት ማገገሙ ይታወሳል። ትራምፕ ጁንየር በአባቱ የምርጫ ቅስቀሳ ጉልህ ሚና ተጫውቷል። የፖለቲካ ዝንባሌ እንዳለውና ምርጫ መወዳደር እንደሚፈልግም ይነገራል። የትዳር አጋሩ ኪምበርሊ ጉይልፎይ ሐምሌ ላይ በቫይረሱ ተይዛ አገግማለች። በትራምፕ ዙሪያ ካሉ ሰዎች ሌላው ቫይረሱ የተገኘበት አንድሪው ጁሊያኒ የተባለው አማካሪያቸው ነው። አንድሪው የትራምፕ የግል ጠበቃ ሩዲ ጁሊያኒ ልጅ ነው። ሲቢኤስ እንደሚለው ቢያንስ አራት የዋይት ሐውስ ሠራተኞች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ትራምፕ ቫይረሱ ሲይዛቸው ሦስት ቀን ሆስፒታል ቆይተው መውጣታቸው አይዘነጋም። ልጃቸው ትራምፕ ጁንየር አንድ ቃለ ምልልስ ላይ መገናኛ ብዙኃን የሞቱ ሰዎችን ቁጥር አጋነው እንደሚገልጹና ያገገሙ ሰዎች ቁጥር እንደሚበልጥ ተናግረው አሜሪካ ቫይረሱን እየተቆጣጠረችው እንደሆነ ገልጸዋል። እስካሁን 11.8 ሚሊዮን አሜሪካውያን በቫይረሱ ተይዘው 253,000 ሞተዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-55026686 +business የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዦች ቁጥር ከኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ መጨመሩ ተገለጸ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞች ቁጥር ከዓለም አቀፉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ጭማሪ ማሳየቱን የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተናገሩ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ኩባንያው የበጀት ዓመቱ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ማብቂያ ላይ የተጓዦች ቁጥር ወረርሽኙ ከመከስቱ በፊት ወደነበረበት ይመለሳል ብለዋል። ሮይተርስ አቶ መስፍን ጣሰውን ጠቅሶ እንደዘገበው አየር መንገዱ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 12.7 ሚሊዮን መንገደኞችን አጓጉዛለሁ ብሎ ይጠብቃል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው ዓመት 8.6 ሚሊዮን ሰዎችን ያጓጓዘ ሲሆን፣ የኮሮናቫይረስ ከመቀስቀሱ በፊት ደግሞ ያጓጓዛቸው የደንበኞቹ ቁጥር 12.1 ሚሊዮን ነበር። ዓለም አቀፍ ስጋት የነበረው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከፍተኛ የሆነ ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስን አስከትሎ የነበረ ሲሆን በተለይ ደግሞ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ ጉዳትን አስከትሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን በወረርሸኙ ስርጭት ወቅትም የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ወደ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላኖች በመቀየር በመንገደኞች መቀነስ ያጣውን ገቢ ማካካስ ችሏል። ሮይተርስ በዘገባው ከወረርሽኙ በኋላ አየር መንገዱ የተጓዦቹን ቁጥር ከፍ ማድረግ አስችለውታል ያላቸውን ምክንያቶች የኩባንያውን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጠቅሶ ዘግቧል። አየር መንገዱ አዳዲስ አውሮፕላኖች መግዛቱ፣ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን መጨመሩ እና የሰሜን ኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ለማብቃት የሰላም ስምምነት መፈረሙ ለስኬቱ እንደምክንያት ተጠቅሰዋል። ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ኩባንያው በአሁኑ ወቅት 141 አውሮፕላኖች አሉት። ከእነዚህ መካከል እጅግ ዘመናዊ እና ግዙፍ የሆኑት 19 ኤርባስ ኤ350-900 እና 19 ቦይንግ ቢ787-8 እና 8 ቦይንግ ቢ787-9 የመንገደኞች አውሮፕላኖች ይገኙበታል። ዘመናዊዎቹን 4 ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላኖችን ጨምሮ 21 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች ደግሞ አንዲቀርቡለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። አየር መንገዱ ተጨማሪ አውሮፕላ��ችን ለመግዛት ከአሜሪካው ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ ኦፍ ዘ ዩናይትድ ስቴትስ የጠየቀው ብድር ዋስትና በዚህ ሳምንት ሊፈቅድለት እንደሚችል የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዋና ሥራ አስኪያጁን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። አየር መንገዱ ባንኩን የጠየቀው የብድር ዋስትና በሰሜን ኢትዮጵያ ሲካሄድ በነበረው የርስ በርስ ጦርነት እና በፖለቲከኞች ጫና ምክንያት መዘግየቱን መስፍን ጣሰው ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የብድር ሂደቱን የማጽደቅ ሂደት መጀመሩን እና በተያዘው ሳምንት ፍቃዱ ሊገኝ እንደሚችል ተዘግቧል። አየር መንገዱ ለስኬቱ እንደ ምክንያት የተጠቀሰው ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን መጨመሩ ነው። ኩባንያው በአውሮፓውያኑ 2035 የአውሮፕላን ቁጥሮችን እና መዳረሻዎችን ከፍ በማድረግ ዓመታዊ ገቢውን በ400 ፐርሰንት እንዲሁም የተጓዦቹን ቁጥር ደግሞ በ440 ፐርሰንት የመጨመር ዕቅድ እንዳለው ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርብ ከጀመራቸው ወይም ከሚጀምራቸው አዳዲስ መዳረሻዎች መካከል የስዊትዘርላንዷ ዙሪክ፣ ሕንዷ ቺናይ፣ ጆርዳን አማን እና የዚምባብዌዋ ቡላዋዮ ተጠቃሽ ናቸው። ከወራት በኋላ ደግሞ ወደ ሲንጋፖር የሚያደርገውን የቀጥታ በረራ ዳግም ይጀምራል። “በተመሳሳይ ጊዜ የመንገደኞች ቁጥር እና የዕቃ ጫኝ በረራዎችን እየጨመርን ነው” ሲሉ ለዜና ወኪሉ የተናገሩት መስፍን፤ የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ አገራት ጥለው የነበሩትን የጉዞ ገደቦችን እያላሉ እና እያነሱ በሄዱ ቁጥር የመንደኖች ቁጥር እንዲጨምር ይፈቅዳል ሲሉ ተናግረዋል። የ2022 የስካይትራክስ የዓለም አየር መንገዶች ውድድር ላይ በርካታ ሽልማትን የተቀበውለው አየር መንገድ ሥራ አስኪያጅ፤ ኩባንያው ካላደገ በቅር ተልዕኮውን ማሳካት አይችልም ያሉ ሲሆን ይህን ለማድረግም የአየር መንገዱን ኦፕሬሽን ማስፋፋት እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ መንገደኞችምን ይሁን የዕቃ ማጓጓዝ ሥራ ላይ ቁልፍ መዳረሻ በሆነችው ቻይና የአገሪቱ መንግሥት የኮቪድ ስርጭትን ለመቆጣጠር ሲባል እየተገበራቸው ያሉት ጥብቅ ቁጥጥሮች ለአየር መንገዱ ፈተና ሊሆን እንደሚችል ተመላክቷል። ከሦስት ወራት በፊት በተካሄደው የስካይትራክስ የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ አየር መንደጉ ለተከታታይ አምስት ዓመታት የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ፣ የአፍሪካ ምርጥ ቢዝነስ ክላስ፣ የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክለስ ተብሎ ተመርጧል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cw0w008g05wo +business በኢትዮጵያ ሚሊዮኖች ሥራ ሊያጡ እና የአገር ውስጥ ምርት እድገት 11.2 በመቶ ሊቀንስ ይችላል "የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ ከበድ ያለ ነው። ግዙፍ የምጣኔ ሃብት አላቸው የሚባሉት እንደ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንገድደም እና ሕንድ ባሉ አገራት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎቻቸው ቫይረሱ ባመጣው ሰበብ ሥራ ፈላጊ ሆነዋል። ወረርሽኙ በአገራችንም ምጣኔ ሃብት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው ግልጽ ነው። ወረርሽኙ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ክፍል መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጥናት ሠርተዋል። • ""ጆርጅ ፍሎይድን አንቆ የገደለው ፖሊስ 'አስቦና አቅዶ' ነው"" የፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጥናት እንዳሳየው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የአገሪቱን ምጣኔ ሃብት 5.6 በመቶ ሊጎዳው እንደሚችል ይጠቁማል። ""ልክ አውሮፓ እና አሜሪካ እንደተስፋፋው፤ ቫይረሱን እኛም አገር ቢሰራጭ ኢኮኖሚያችን እሱን የሚሸከምበት አቅም የለውም። ከሚጠበቀው በላይ ነው የሚጎዳን። ምክንያቱም እነሱ [ምዕራባውያን አገራት] የተሻለ ኢኮ��ሚ፣ የሰው ኃይል እና ቁጠባ አላቸው። እኔ ባሰላሁት መሠረት ኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ እጅግ ትልቅ ነው"" ይላሉ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰሩ አለማየሁ ገዳ። የፕሮፌሰሩ ጥናት እንደጠቆመው ኢትዮጵያ በ2020 (በአውሮፓውያን አቆጣጠር) የበጀት ዓመት የአገር ውስጥ ምርት እድገት (ጂዲፒ) በአማካይ 11.2 በመቶ ሊላሽቅ ይችላል። ፕሮፌሰር አለማየሁ እንደሚሉት ከሆነ፤ ከሐምሌ 2012 እስከ ሰኔ 2013 በሚዘልቀው የበጀት ዓመት ላይ ቫይረሱ የሚያስከትለው ጉዳት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሚገታ ከሆነ፤ የአገር ውስጥ ምርት እድገቱ ሊቀንስ የሚችለው በ5.6 በመቶ ነው። ቫይረሱ የሚስከትለው ጉዳት ግን እስከ ሶስተኛው ሩብ ዓመት የሚዘልቅ ከሆነ የአገር ውስጥ ምርት እድገቱ የሚቀንሰው በ16.7 በመቶ ይሆናል። • “ሚድያውን ደፍረን ማስተካከል ካልቻልን፤ ይህቺን አገር ነገ ላናገኛት እንችላለን” ዘነበ በየነ (ዶ/ር) ፕሮፌሰሩ የቫይረሱ ስርጭት የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ ድቀት ለመቀነስ ""ያለ ኃይልን በማሰባሰብ ቫይረሱ ወደ ህብረተሰቡ ከመሰራጨቱ በፊት በቁጥጥር ሥር ማድረግ ነው"" ሲሉ ይመክራሉ። ፕሮፌሰር አለማየሁ ዘመዶቻችን ከውጪ በባንክ በኩል የሚልኩት ገንዘብ አገሪቱ ምርት ወደ ውጪ ልካ ከምታገኘው ዶላር በላይ መሆኑን ይናገራሉ። ""የመንግሥት አሃዞችን ብንመለከት እንኳ፣ አገሪቱ ወደ ውጪ አገራት ምርት ልካ የምታገኘው ገቢ 2.8 እስከ 3 ቢሊዮን ነው። እንደውም ወደ ውጪ የሚላከው ምርት እየቀነሰ ነው። ከውጪ የሚላከው ገንዘብ ግን ከ4.5 እስከ 6 ቢሊዮን ዶላር ነው"" ይላሉ። ""መንግሥት ወደ ውጪ እንደሚላኩ ምርቶች ሁሉ ከውጪ ወደ አገር በሚላክ ገንዘብ ላይ በቂ አትኩሮት አይሰጥም የሚሉት ፕሮፌሰሩ፣ ""ምርት ወደ ውጪ ልከን የምንሸጠው 3 ቢሊዮን ነው። የምናስገባው ደግሞ 17-18 ቢሊዮን ዶላር ነው"" በማለት ይሄን የንግድ ክፍተት ለመሸፈን 'ሬሚታንሱ' ከፍተኛውን ሚና እንደሚጫወት ይናገራሉ። • የደረሱበት ያልታወቀው ተማሪዎች ስድስት ወር ሆናቸው በኮቪድ-19 ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ይልኩ የነበሩ ሰዎች እንደ ከዚህ ቀደም መላክ ባለመቻላቸው አገሪቱ ከ'ሬሚታንስ' ወይም ከውጪ ይላክ ከነበረ ዶላር ታገኝ ነበረውን ገንዘብ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ አድርጓል ይላሉ። ዓለም አቀፍ ትንበያዎች ከሃብታም አገራት ወደ ትውልድ አገራት የሚላክ ገንዘብ መጠን በ26 በመቶ እንደሚቀንስ ማሳየታቸውን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ይናገራሉ። ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአሜሪካ እና አውሮፓ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ሥራ አጥ አድርጎ የመንግሥት ድጎማን እንዲጠብቁ አስገድዷል። ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳም፤ በአገራችንም ኮቪድ-19 ቢያንስ እስከ 2.5 ሚሊዮን ሰዎች ሥራ አጥ ሊያደርግ እንደሚችል በጥናታቸው አመላክተዋል። ""1.8 ሚሊዮን ሰው የመንግሥት ሰራተኛ ነው። የመንግሥት ሰራተኛው በወረርሽኙ ሳብያ ከሥራው ይፈናቀላል ብለን አንጠብቅም"" የሚሉት ፕሮፌሰሩ፤ ""የግል ሴክተሩ ደግሞ 1.5 ሚሊዮን ሰዎችን ቀጥሯል። ከእነዚህም መካከል ግማሽ ያክሉ ሥራ አጥ ሊሆኑ ይችላሉ"" ይላሉ። ከእነዚህ በተጨማሪ ""ራሱን ቀጥሮ የሚያሳድር ደግሞ 3.1 ሚሊዮን አለ። እነዚህም ተጋላጭ ናቸው። ሥራቸውን በቀላሉ ሊያጡ ይችላሉ"" ይላሉ። ""የእርሻው ክፍለ ኢኮኖሚ ብዙ አይጎዳም። ብዙ የሚጎዱት የአገልግሎት እና ኢንደስትሪ ዘረፎች ናቸው። ስለዚህ ያለ የሌለ አቅማችንን በእርሻው ላይ ማድረግ አለብን። ግብርናው የሚወድቀውን ኢኮኖሚያችንን ሊታደግልን ይችላል"" በማለት እንደመፍትሄ ካስቀመጧቸው የመጀመሪያውን ነጥብ ያነሳሉ። ለዚህም በሽታው ወደ ገጠር እንዳይገባ ጥንቃቄ መድረግ እንዳለበት ፕሮፌሰር አለማየሁ ያሳስባሉ። መንግሥት ከግል ሴክተሩ ጋር በመነጋገር ሊታገዙ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ እቅድ ማውጣት ያስፈልጋል ሲሉም ያክላሉ። • በምዕራብ ወለጋ የአራት ልጆች እናት የሆኑትን ግለሰብ ማን ገደላቸው? ፕሮፌሰር አለማየሁ እንደሚሉት በቫይረሱ ስርጭት እጅጉን ከሚጎዱት መካከል ራሳቸውን ቀጥረው የሚገኙት 3.1 ሚሊዮን ዜጎች እና ቤተሰቦቻቸው ናቸው በማለት ""ሥራ በሌለበት የሥራ ቦታ እና የመኖሪያ ቤት ኪራይ እየከፈሉ ነው። መንግሥት እያለ ያለው 'እባካችሁ ቤት ኪራይ ቀንሱላቸው' ነው። እንደዛ ብቻ መሆን የለበትም። መንግሥት የቤት ኪራይ የማይከፍሉበትን መንገድ ቢፈልግ እና ለአከራዮች ደግሞ እንደ ቼክ ወይም ቦንድ ባሉ ሰነዶች ማረጋገጫ ቢሰጥ ይረዳል ብዬ አስባለሁ"" ብለዋል። የግል ዘርፉም ከመንግሥት ድጋፍ ማግኘት እንዳለበትም ሃሳባቸውን ኣቀርባሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-52831184 +sports አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ኮቪድ-19 ተገኘበት ሊዮኔል ሜሲ ኮቪድ-19 ከተገኘባቸው አራት የፓሪስ ሴይንት-ዠርሜይን ተጫዋቾች አንዱ እንደሆነ ታወቀ። አርንቲናዊው አጥቂ እንዲሁም የቡድን አጋሮቹ የሆኑት ሁዋን በርናት፣ ናታን ቢቱማዛላ እንዲሁም ሰርጂዮ ሪኮ ናቸው ኮቪድ-19 እንደተገኘባቸው የተገለጸው። ተጫዋቾቹ ቡድናቸው ፒኤስጂ በፍሬንች ካፕ ፍልሚያ ከቫኔስ ጋር ሊጫወት ሲሰናዳ ነው ውጤታቸው የተነገራቸው። አራቱም ተጫዋቾች ራሳቸውን አግልለው የጤና ሁኔታቸውን እየተከታተሉ ነው። የፒሴስጂው አሠልጣኝ ሞሪሲዮ ፖቼቲኖ እንዳሉት ሜሲ ለበዓል እረፍት ወደ አገር ቤት ስለሄደ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤቱ ኔጋቲቭ እስኪሆን ድረስ እዚያው ይቆያል። ከጨዋታው በፊት እንደተለመደው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ፖቼቲኖ አክለው ሜሲ መቼ ሊመለስ ይችላል የሚለውን መገመት እንደሚያዳግታቸውም ተናግረዋል። ፒኤስጂ ከፍሬንች ካፕ ሲመለስ ከበዓል እረፍት በኋላ በሚቀጥለው እሑድ ሊዮንን ይገጥማል። ሌላኛው የክለቡ አጥቂ ብራዚላዊው ኔይማር ካጋጠመው ጉዳት ስላላገገመ በዚህ ጨዋታ የመሳተፉ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል። ፒኤስጂ የ29 ዓመቱ ኔይማር በሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት ወደ ሜዳ ሊመለስ ይችላል ተብሏል። የፈረንሳይ ሊግን እየመራ የሚገኘው ፒኤስጂ በቻምፒዬንስ ሊግ ፍልሚያ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከሪያል ማድሪድ ጋር ይፋለማል። አርጀንቲናዊው አጥቂ ሜሲ በፈረንሳይ ሊግ ብዙም እየተሳካለት አይደለም። ሜሲ እስካሁን በሊጉ ያስቆጠረው አንድ ጎል ነው። በቻምፒዬንስ ሊግ ደግሞ በምድብ ጨዋታ አምስት ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል። https://www.bbc.com/amharic/news-59856473 +health ኮሮናቫይረስ፡ ሳኡዲ አረቢያ የኡምራ ጉⶋን በመስከረም ወር መጨረሻ ልትጀምር ነው "በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለሰባት ወራት ያህል ተቋርጦ የነበረው የኡምራ ሃይማኖታዊ ጉዞ በዚህ ወር እንደሚጀመር ሳዑዲ አረቢያ አስታወቀች። ከመስከረም 24፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮም ስድስት ሺህ የሳዑዲ ዜጎች በየቀኑ የኡምራ ጉዞ እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸዋል። ከሌላ አገር የሚመጡ የኡምራ ፀሎተኞችም ከጥቅምት 22፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ መምጣት ይችላሉ ተብሏል። የየቀኑም ተጓዦች ቁጥር ወደ 20 ሺህ ያድጋል እንደሚያድገም ሳዑዲ አስታውቃለች። ከእስልምና እምነት መሰረቶች አንዱ የሆነው የኡምራ ጉዞ በየትኛውም ወቅት ማከናወን ቢቻልም የሃጂ ጉዞ ግን የእስልምና እምነት ተከታዮች በህይወት ዘመናቸው አንዱ ሊያደርጉት የሚገባ የተቀደሰ ተግባር ነው። በመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የሃጅ ጉዞ በዘንድሮው እክል ገጥሞታል። ከዚህ ቀደም ከሁለት ሚሊዮን በላይ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከየአገሩ ተሰባስበው ቢመጡም በዚህ አመት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሳዑዲ አረቢያ የፈቀደችው ጥቂት ሺዎች እንዲታደሙ ነው። ከሃጅ ጉዞ በተለየ መልኩ በየዓመቱ የትኛውም ጊዜ ላይ መደረግ ለሚችለው ለኡምራ ጉዞ ቢያንስ በዓመት ስምንት ሚሊዮን የሚሆኑ ወደ መካ ያቀኑ ነበር። በየቀኑ 20 ሺህ ተጓዦችን ለመቀበል ያቀደችው ሳዑዲ አረቢያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል የሚለው በይፋ እስኪነገር የምትቀበለው ተጓዦች ቁጥር ተወስኖ እንደሚቆይም የሳኡዲ ዜና ወኪል የአገር ውስጥ ሚኒስትሩን ዋቢ አድርገው ዘግበዋል። ""ከሌላ አገራት የሚመጡ የኡምራ ፀሎተኞችና ተጓዦችን የምንቀበለው ቀስ በቀስ ሲሆን፤ ከወረርሽኙ ነፃ የሆኑ አገሮችንም ቅድሚያ እንሰጣለን"" ማለታቸውም ተዘግቧል። ተጓዦች የኮሮናቫይረስ ወርርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎች እንደ የፊት ጭምብል፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅን ፅዳትን መጠበቅ እንደሚኖርባቸውም የዜና ወኪሉ አስነብቧል። በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ እስካሁን ባለው 330 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 4 ሺህ 452 ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54276747 +sports ትምህርት፡ አራት ሜዳሊያ እና ዋንጫ የተሸለመችው ቆንጂት "ቆንጂት ሐብታሙ ትባለላች። ተወልዳ ያደገችው በሰሜን ሸዋ ጊዳ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርቷን ያጠናቀቀችው ዘንድሮ ነው። ቆንጂት በመቱ ዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቧ ሶስት ሜዳሊያ እና አንድ ዋንጫ ለመሸለም በቅታለች። ለስኬቷ ምክንያት የሆነውንና የወደፊት እቅዷን በማስመልከት ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ባደረገች ወቅት "" ፊደል ካልቆጠሩ የገጠር ቤተሰብ መገኘቴ ለስኬቴ እንቅፋት አልሆነብኝም"" ብላለች። ""ተወልጄ ያደግኩት ገጠር ነው። ቤተሰቦቼም ፊደል የቆጠሩ አይደሉም። እኔ እንድማር ግን አብረውኝ ለፍተዋል። ከተማረ ቤተሰብ ይልቅ ተምሬ ትልቅ ሰው እንድሆንላቸው ያስቡልኛል"" በማለት ቤተሰቦቿ ያደረጉላትን ትገልጻለች። ቆንጂት ከመቱ ዩኒቨርስቲ በአፕላይድ ባዮሎጂ የትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቧ የተለያዩ ሽልማቶችን ለማግኘት በቅታለች። ""ያስመዘገብኩት ውጤት 3.96 ነው"" የምትለው ቆንጂት፣ በመቀጠልም ""እንደ ኮሌጅ አንደኛ በመውጣቴ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሜያለሁ። እንዲሁም ከሴቶች አንደኛ በመሆን ሌላ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸለምኩ"" በማለት ታስረዳለች። ሶስተኛ ወርቅ ያገኘችው ደግሞ ከአጠቃላይ መቱ ዩኒቨርስቲ ሴት ተማሪዎች አንደኛ በመውጣት መሆኑን ገልጻለች። ከዚህ በተጨማሪ ከአጠቃላይ ዩኒቨርስቲው በሶስተኛ ደረጃ በመገኘቷ የነሐስ ሜዳሊያ እና በአጠቃላይ በዩኒቨርስቲው ካሉ ተማሪዎች በመላቋ ደግሞ ዋንጫ አግኝታለች። በዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ያበቋትንም ነገሮች ስታስረዳ "" ዩኒቨርስቲ እንደገባሁ እቅድ በማውጣት ጊዜዬን በአግባቡ ተጠቅሜ ነበር። ክፍልም በአግባቡ እከታተል ነበር። አጠቃላይ ትኩረቴ በትምህርቴ ላይ በማድረግ ነበር ስከታተል የነበረው"" ትላለች። በመቀጠልም ""የተማርነውን መከለስ ብቻም ሳይሆን ወደ ፊት ልንማራቸው የምንችላቸውን ቀድሜ በማንበብ እዘጋጅ ነበር።"" በማለት ልምዷን መለስ በማለት ታስታውሳለች። የዩኒቨርሰቲ ቆይታ በራስ ሕይወት ላይ ትኩረት በማድረግ ከተሰራ የወደፊት ሕይወት መስመር የሚይዝበት ነው የምትለው ቆንጂት፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ የተወጣበት ዓላማ ከተዘነጋ ግን የወደፊት ሕይወት የሚጠፋበት ስፍራም መሆኑን ታስረዳለች። ""እኔ ዩኒቨርስቲ እንደገባሁኝ ከኔ በፊት የነበሩትን ሰዎች ምክር አግኝቼ ነበር። ለምሳሌ በዩኒቨርስቲ ሕይወት ምን ማድረግ እንዳለብኝና እንደሌለብኝ አስመልክቶ ከኔ በፊት ከነበሩት ተማሪዎች ጥሩ ምክር አግኝቻለሁ"" በማለት የቀድሞ ተማሪዎች የሰጧት ምክር ለዛሬ ውጤቷ ማማር ድርሻ እንዳለው ትናገራለች። ሕይወት በርካታ እንቅፋቶች አለው የምትለው ቆንጂት "" ያጋጠሙኝን እንቅፋቶችና ፈተናዎች በትዕግሥትና በዓላማዬ ላይ ትኩረቴን በማድረጌ ስኬታማ ለመሆን በቅቻለሁ"" ትላለች። "" እኛ ሴቶች በዓላማችን ላይ ጠንክረን ከሰራን ላንደርስበት የምንችለው ስፍራ የለም። በሴትነት የሚደርሱብን ፈተናዎችን ደግሞ በትዕግሥት ማለፍ በጣም አስፈላጊ ነው በማለት ምክሯን ትለግሳለች። በዩኒቨርስቲ ሕይወት ሴት ተማሪዎች በተለያዩ ነገሮች ሊታለሉ ይችላሉ በማለትም፣ ይኹን እነጂ ለወጡለት ዓላማ ቅድሚያ መስጠት ለወደፊት ዓላማ መመቅናት ወሳኝ ነው በማለት ሃሳቧን ታካፍላለች። ተማሪዎእ ዩኒቨርስቲ መግባትን የዓለም መጨረሻ አድርጎ መውሰድ እንደሌለባቸውም ትናገራለች። ""ሌሎች ሕይወቶች የወጣንበትን ዓላማ ካሳካን በኋላ የሚደረሱ ናቸው።"" ቆንጂት ስለወደፊት ሕይወቷ ስትናገር የከፍተኛ ትምህርቷን በመቀጠል አቅም ሲኖራት ደግሞ ለሴቶች ድጋፍ የሚያደርግን ተቋም አቋቁማ ለመስራት እቅድ እንዳላት ገልጻለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-55883438 +politics ሰሜን ኮሪያ አዲስ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል ሙከራ አደረገች "ሰሜን ኮሪያ ሐሙስ ዕለት አዲስ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን የገለጸች ሲሆን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አራተኛ የጦር መሣሪያ ሙከራዋ ሆኖ ተመዝግቧል። ሰሜን ኮሪያ አዲሱን ሙከራዋን ያደረገችው የኒውክሌር አቅም እንዳለው የሚታመነውን አዲስ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ ካደረገች ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሙከራዎቹ ""አለመረጋጋትን እና አለመተማመንን የበለጠ ይፈጥራሉ"" ብለዋል። ፒዮንግያንግ የጦር መሣሪያው ራስን ለመከላከል የሚያስፈልጉ መሆናቸውን በመግለጽ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያን ""ፍትሐዊ ያልሆነ አቋም ይዘዋል"" በማለት ወንጅላለች። ሙከራዎቹ ምንም እንኳን ጥብቅ ማዕቀቦች ቢኖሩም ፒዮንግያንግ የጦር መሣሪያ መሥራቷን ለማዘግየት ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳይ ግልፅ ምልክት ተደርገው ተወስደዋል። በመንግሥታዊው የዜና ማሰራጫ ኬሲኤንኤ መሠረት አዲሱ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል ""አስደናቂ አፈፃፀም"" ያሳየ ሲሆን ""አዳዲስ ቁልፍ ቴክኖሎጂዎችን"" አካቷል ሲል ዘግቧል። ሙከራው የተደረገው የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ወደነበረበት መመለስ እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው። ኪም የአሜሪካን ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎን ከሰዋል። "" አሜሪካ ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ በማታለል የጥላቻ ድርጊቱን ለመደበቅ ሞክራለች"" ብለዋል። አንዳንድ ተንታኞች ፒዮንግያንግ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ግንኙነቷን በማስቀጠል አሜሪካን በማስወጣት ዋሽንግተን እና ሴኡልን ለመለያየት እንደምትፈልግ አመላካች ነው ብለው ያምናሉ። ሆኖም ሰሜን ኮሪያ የማዕቀብ እፎይታን እና ሌሎች ድጋፎችን አሜሪካ እንድታደርግላት የደቡብ ኮሪያን ድጋፍ ትፈልጋለች። ሰሜን ኮሪያ ከዓለም ተቆራርጣ ከአንድ ዓመት በላይ አሳልፋለች። ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ከቅርብ አጋሯ ከቻይና ጋር አብዛኛውን ንግዶች አቋርጣለች። በዚህም ምክንያት ኢኮኖሚው በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ በመሆኑ የምግብ እጥረት አሳሳቢ ነው ተብሎ ይታሰባል። በመጋቢት ወር አገሪቱ ማዕቀቦችን ወደ ጎን በማለት የባልስቲክ ሚሳኤሎችን ሞክራለች። ይህም ከአሜሪካ፣ ከጃፓን እና ከደቡብ ኮሪያ ጠንካራ ወቀሳ አስነስቶባታል። ባለፈው ወር የተባበሩት መንግሥታት የአቶሚክ ኤጀንሲ ሰሜን ኮሪያ ""በጣም አሳሳቢ"" ያለውን ለኒዩክሌር መሣሪያዎች የሚረዳ ፕሉቶኒየም ማምረት የሚችል ማብላያዋን እንደገና እን���ጀመረች ገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58730483 +politics ካዛኪስታን፡ የተባባሰውን አለመረጋጋት ተከትሎ የካዛኪስታን መንግሥት የሩስያን ድጋፍ ጠየቀ "ካዛኪስታን ውስጥ ፀረ-መንግሥት ሰልፎች በተጧጧፈበት በአሁኑ ወቅት አገሪቱን ""ለማረጋጋት"" በሩሲያ የሚመሩ ወታደሮች ሊሠማሩ ነው። ፕሬዝደንት ካሲም-ጆማርት ቶካዬቭ በአገር አቀፍ ደረጃ የተባባሰውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ሴኩሪቲ ትሪቲ ኦርጋናይዜሽን (ሲኤስቲኦ) ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። በነዳጅ ዋጋ መናር የተቀጣጠለው ተቃውሞው በሂደት የፖለቲካ ጥያቄዎችን በማካተት ተባብሷል። ፕሬዚደንት ቶካዬቭ ብጥብጡን በውጭ የሰለጠኑ ""የአሸባሪ ቡድኖች"" ተግባር ነው ብለውታል። በለንደን የሚገኘው ቻታም ሐውስ የመካከለኛው እስያ ኤክስፐርት የሆኑት ኬት ማሊንሰን በበኩላቸው የተቃውሞ ሰልፎቹ ""የካዛኪስታን መንግሥት አገቱን ለማዘመን እና ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ ከፍተኛ ብስጭት እና ቁጣን ማሳያ ነው"" ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ የሌሊት ሰዓት እላፊ ገደብ እና መሰባሰቦችን ጨምሮ ሌሎች ክልከላዎችን የሚጥል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት ለተቃውሞ ሰልፎቹ ጠንከር ያለ ምላሽ እንደሚሰጡም ቃል ገብተዋል። ሐሙስ ማለዳ ላይ በቴሌቭዥን የተላለፈ ንግግራቸው ሲኤስቲኦ [ሩሲያ እና አምስት የቀድሞ የሶቪየት መንግሥታትን ያቀፈ ወታደራዊ ኅብረት ነው] አገሪቱን ለማረጋጋት እርዳታ እንዲያደርግላቸው መጠየቃቸውን ገልጸዋል። የሲኤስቲኦ ሊቀመንበር የሆነችው አርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን ረቡዕ ዕለት በፌስቡክ በሰጡት መግለጫ ኅብረቱ የሠላም አስከባሪ ኃይሎችን ""ለተወሰነ ጊዜ"" እንደሚልክ አረጋግጠዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በካዛክስታን ያለውን ሁኔታ ""በቅርበት እየተከታተለ"" መሆኑን ጠቅሶ ቃል አቀባዩ ባለሥልጣናት እና ተቃዋሚዎች ካላስፈላጊ ድርጊት እንዲታቀቡ አሳስቧል። ፕሬዚደንት ቶካዬቭ ካዛኪስታንን እአአ በ1991 ነጻነቷን ካወጀች በኋላ አገሪቱን እየመሩ ያሉ ሁለተኛው ግለሰብ ናቸው። እአአ በ2019 ሲመረጡ ዴሞክራሲያዊ መስፈርቶች በዝቅተኛ ደረጃ የተከበሩበት ነበር ሲል በአውሮፓ የደኅንነት እና ትብብር ድርጅት (ኦኤስሲኢ) ሂደቱን አውግዟል። አደባባይ የወጡት ዜጎች አብዛኛው ቁጣቸው ያነጣጠረው ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ በብሔራዊ ደኅንነት ቢሮ ቁልፍ ሚና በያዙት የቀድሞው መሪ ኑርሱልታን ናዛርባይቭ ላይ ይመስላል። እየጨመረ የመጣውን አለመረጋጋት ለማርገብ በማሰብ ረቡዕ ከሥራ እንዲሰናበቱ ተደርጓል። ተቃዋሚዎች የናዛርቤዬቭን ስም ሲጠሩ የነበረ ሲሆን የቀድሞውን መሪን ግዙፍ የነሐስ ሐውልት ለማፍረስ ሲሞክሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በማኅበራዊ ድር አምባ ላይ ተሰራጭቷል። እንደ ቢቢሲ ሞኒተሪንግ ዘገባ ከሆነ አሁን የፈረሰው ሐውልት የናዛርባይቭ የትውልድ ክልል በሆነችው ታልዲኮርጋን የቆመ ይመስላል። የካዛክስታን ትልቁ አየር ማረፊያ ሠራተኞች የመንግሥት ህንጻዎችን ዒላማ ካደረጉት የፀረ-መንግሥት ተቃዋሚዎችን ሲሸሹ ታይተዋል። ተቃዋሚዎች በአልማቲ በሚገኘው የከንቲባ ጽህፈት ቤት ከተሰባሰቡ በኋላ ወረራ ፈጽመውበታል። በማኅበራዊ ድር አምባዎች ላይ የተለቀቁ ቪዲዮዎች ከህንጻው ከፍተኛ ጭስ ሲወጣ ያሳዩ ሲሆን የተኩስ ድምጽም ይሰማ ነበር። የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ካናት ታይመርዴኖቭ በበኩላቸው ""ጽንፈኞች እና አክራሪዎች 500 ሠላማዊ ዜጎችን በማጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ የንግድ ድርጅቶችን ዘርፈዋል"" ብለዋል። በምዕራብ አክቶቤ ከተማ በተቃዋሚዎች ላይ የአድማ መበተኛ ውሃ ጥቅም ላይ ውሏል። በአንዳንድ ቦታዎች የጸጥታ ኃይሎች ከተቃዋሚዎች ጋር መወገናቸውን የሚ���ልጹ መረጃዎችም እየወጡ ነው። በመካከለኛው እስያ በምትገኘው ካዛኪስታን እየሆነ ስላለው ነገር ግልጽ የሆነ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። የአገር ውስጥ ሚኒስቴር በጸጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሚገልጹ መረጃዎችን ይፋ ቢያደርግም በተቃዋሚዎች ስለደረሰው የአካል ጉዳት እና ሞት ምንም አልተባለም። ""በአገር አቀፍ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ"" መኖሩም ተገልጿል። እሑድ የጀመረውን ተቃውሞ ለማስቆም መንግሥት ብዙ ሰዎች ለመኪናቸው የሚጠቀሙበት የጋዝ ዋጋ ጭማሪ እንዲቀር አድርጓል። ከናዛርባይቭ ከኃላፊነት መነሳት በተጨማሪም ሁሉም የካቢኔ አባላት ከሥራ ለቀዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59891093 +sports የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ ጎተይቶም ዕቅዴን አሳክቻለሁ አለች "በማራቶን ውድድር ለመጀረሚያ ጊዜ ተወዳድራ የ2021 የበርሊን ማራቶን ያሸነፈችው አትሌት ጎተይቶም ገብረ ስላሴ በውድድር መድረኩ ያሰብኩትን አሳክቻለሁ አለች። አትሌት ጎተይቶም ጀርመን በርሊን ላይ በተካሄደው የማራቶን ውድድር የጠበቀችውን ሰዓት ማሳካት መቻሏንም ተናግራለች። ""የመጀመሪዬ ስለሆነም 2፡20 እሮጣለሁ ብዬ ነው የመጣሁት። ያሰብኩትን ነው የሮጥኩት"" ብላለች። ጎተይቶም በውድድሩ በ2፡20፡09 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው አሸናፊ በመሆን ያጠናቀቀችው። ትናንት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን በተለይ በወንዶች የማራቶን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ሳይሻሻል የቀረው በበርሊን የነበረው የአየር ሁኔታ ሞቃታማ መሆኑ በአትሌቶች እንደምክንያት ተነስቷል። አትሌት ጎተይቶም ግን ይህ የማራቶን ውድድሯ የመጀሪያዋ መሆኑን በማስታወስ፤ ""የመጀመሪያዬ እንደመሆኑ ማራቶን ውስጡ ምን እንደሆነ እራሱ አላወኩም ነበረ። . . . ከ35ኛው ኪሎ ሜትር በኋላ ድካምም ስለነበር የዛኔ ነው ሙቀት እንደነበር የታወቀኝ"" ብላለች። የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ ጎተይቶም ገብረ ስላሴ ከትናንት ውድድሯ የማራቶን ውድድር ልምድ ማግኘቷን በመጥቀስ ወደፊት ከ02፡20፡00 በታች ለመሮጥ እቅዷ እንደሆነ ተናግራለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-58704716 +politics 'ሁላችንን ሊገድሉን አይችሉም'-የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት ተቃዋሚዎች "በሱዳን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ ከሁለት ሳምንት በኋላ የዋና ከተማዋ ካርቱም ጎዳናዎች በየቦታው በተተከሉ ጊዜያዊ አጥሮች ተጨናንቀዋል። በአብዛኛዎቹ ቦታዎች ድንጋዮች እና የተቃጠሉ ጎማዎች መኪና እንዲተላለፍ ለማድረግ ተነስተዋል። ምክንያቱ ደግሞ ከመጋረጃ ጀርባ የሚደረገው የፖለቲካ ድርድር መፈንቅለ መንግሥቱን ሊፈታ ይችላል በሚል ነው። የመንገዱ መዘጋት፣ ተቃውሞዎች እና የሠራዊቱ አጸፋዊ ምላሽ በማንኛውም ጊዜ ሊባባስ ይችላል የሚል ሰፊ እምነት አለ። በሽግግር መንግሥቱ ውስጥ ሴቶችን እና ህጻናትን ከጥቃት የመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠው ክፍል መሪ የሆኑት ሱሌማ ኤልካሊፋ ""ከንግግር እና ከድርድር ውጪ መውጫ መንገድ የለም"" ይላሉ። ""ሰዎች አሁን የበለጠ ቆራጥ ናቸው። የበለጠም ፖለቲካዊ ግንዛቤ አላቸው። ከ30 ዓመታት ወታደራዊ አምባገነንነት በኋላ ድጋሚ አንገዛም። ወጣቱ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነውን አገሪቱን ይወክላል። ስለዚህ ይህንን መንግሥት እንደማንፈልግ ግልጽ ነው። ሁላችንንም ሊገድሉን አይችሉም። ይህንን ህልምም መግደል አይችሉም"" ብለዋል። ""ወታደሮቹ እንደ እንስሳት ናቸው"" በመፈንቅለ መንግሥቱ ወቅት በወታደሮች ተይዘው በቁም እስር ላይ የሚገኙት የሽግግር መንግሥቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ሰፊ ድጋፍ ያላቸው ይመስላል። ""ሐምዶክ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው መሆኑን አሳይቷል። [የኢኮኖሚ ችግር ቢኖርም] ለዚያም ነው ሰዎች በእሱ የሚተማ��ኑት። ግብፆች፣ ሳዑዲዎች እና ሌሎችም ሃሳባቸውን እንደሚቀይሩ ተስፋ እናደርጋለን"" ሲሉ ኤልካሊፋ መፈንቅለ መንግሥቱን እንደሚደግፉ በሰፊው የሚታመኑባቸውን አገራት ጠቁመዋል። በካርቱም የሚገኘው እና የግል በሆነው የሮያል ኬር ሆስፒታል መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ በተፈጠረው የወታደራዊ ምላሽ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና የሚከታተሉትም ተመሳሳይ ቁርጠኝነት አላቸው። የ18 ዓመቱ ተማሪ ሙሃየድ ፋይሰል በቅርቡ በነበረው ተቃውሞ እግሩ ላይ ሁለት ጊዜ በጥይት ተመትቷል። ""ከዘጠኝ ሰዎች ጋር በጥይት ተመታሁ። ምንም አይነት የማስጠንቀቂያ ተኩስ አልነበረም፣ በቃ በቀጥታ መተኮስ ጀመሩ። ወታደሮቹ… እንደ እንስሳት ናቸው። ምናልባት እንስሳት የተሻሉ ሊሆኑ ይችላሉ"" ብሏል። በቀኝ እግሩ ላይ ሦስት ቀዶ ህክምና ተደርጎለታል። ""ምክንያታችን አልተለወጠም። ወታደሩ አይገዛንም"" ሲል ሐኪም እግሩን እየነካካ ሲያክመው ተናገሯል። በአቅራቢያው ባለ አልጋ ላይ ልብስ ሰፊውና የ54 ዓመቱ ያይር መሐመድ አሊ አብደላ በዘመዶችቹ ተከቧል። በመፈንቅለ መንግሥቱ ወቅት ተቃዋሚዎችን ለመቀላቀል ሱቁን ትቶ ወጣ። በካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ መኪና ላይ የተጫኑ ወታደሮች ሆን ብለው በመኪና እንደገጩት ተናግሯል። ""ከዚያ በኋላ አምስት እና ስድስት ሰዎች ያለ ርህራሄ ጀርባዬ እና ደረቴ ላይ ደበደቡኝ። ወደ ሰልፉ የሄድኩት ነጻነትን፣ ሰላምንና ፍትህን ለመጠየቅ ነው። ሠራዊቱ ያንን ማድረግ ካልቻለ መወገድ አለበት። መለዮዋችሁን አስረክቡ የሚሉ መጥተው ኃላፊነቱን እንዲወስዱ ያድርጉ"" ብሏል። እአአ በ2019 ሱዳንን ለረዥም ጊዜ የመሩትን ኦማር አልበሽርን በመቃወም ከስልጣን እንዲወርዱ ተደረገ። ከዚያ በኋላ ነበር የሽግግር መንግሥት የተቋቋመው። በጦር ኃይሉ እና በሽግግር መንግሥት ውስጥ በሚሳተፉ የተለያዩ አካላት እና ድርጅቶች መካከል ሊደረግ የሚችለው ስምምነት እና ዕጣ ፈንታ ላይ መላምት አለ። ነገር ግን በካርቱም የሚገኙ የዲፕሎማቲክ እና ሌሎች ምንጮች ድርድሩ በጠንካራ ዓለም አቀፍ ጫና እየተካሄደ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያሻው በመጥቀስ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። መፈንቅለ መንግሥቱን የመሩት አብደል ፋታህ አል-ቡርሐን እንዳሉት ወታደሮቹ የእርስ በርስ ጦርነትን ለማስወገድ ጣልቃ መግባታቸውን ጠቅሰው በ2023 ምርጫ እንደሚካሄድ ቃል ገብተዋል። ቢሊዮኖች ጠፍተዋል መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ በወታደሮች በፍጥነት የተዘጋው ተቋም በሽግግር መንግሥቱ የተቋቋመው አፍራሽ ኮሚቴ ነው። ኮሚቴው በአሮጌው ሥርዓት ኃያላን ሰዎች ተዘርፏል የተባለውን ንብረት ለመንጠቅ የተቋቋመ ድርጅት ነው። መፈንቅለ መንግሥቱ ከመደረጉ ከጥቂት ወራት በፊት ከኮሚቴው ከፍተኛ ባለሥልጣናት አንዱ የሆኑት ዋጅዲ ሳሌህ ለቢቢሲ ሥራውን አስጎብኝተዋል። ለወንጀለኝነት ማስረጃ ነው ያሉትንም ክምር አሳይተዋል። ""እነዚህ በዓለማችን ትላልቁን ሕገወጥ የገንዘብ ማሸሽን ያደራጁ ሰዎች ነበሩ። የጠፉትን በቢሊዮኖች እያደነን ነው። የድሮው አገዛዝ [አብዮቱን ለማደናቀፍ] እየሞከሩ ቢሆንም በጭራሽ አይሳካላቸውም"" ብለዋል። እሳቸው በመፈንቅለ መንግሥቱ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በሽግግር መንግሥቱ ውስጥ ተፅዕኖ ካላቸው በርካታ ሰዎች ጋር በእስር ላይ ይገኛሉ። ""በአፍራሽ ኮሚቴው በቅርቡ የተደረገው ምርመራ በወታደራዊው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘንድ ጭንቀት መፍጠሩ በሰፊው ይታመናል። ኮሚቴው ከወርቅ ዝውውር እስከ ገንዘብ ሽያጭ እና ኮሚሽኖች ድረስ የተለያዩ ጉዳዮችን በማጣራት ላይ ሲሆን ይህም በከፍተኛ መኮንኖች መካከል ከፍተኛ የሆነ ሙስና መኖሩን ያ��ያል"" ሲል ከአብዮቱ ጀምሮ ለሱዳን መንግሥት ሲሠራ የነበረው የቀድሞ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ሞሃናድ ሃሺም ገልጿል። ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ የቁልፉ ወደብ እገዳ ተነስቷል። ወታደሮቹ እገዳውን ያቀነባበሩት በሽግግር መንግሥቱ ላይ ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመፍጠር ነው ተብሎ በሰፊው ይጠረጠራል። በዚህም በካርቱም ብዙ የምግብ አቅርቦቶች እንዲኖር እና አንዳንድ ዋጋዎች እንዲቀንሱ ረድቷል። የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪዎች በወሰዱት ጥንቃቄ ለድርጊታቸው መሰረት ያዘጋጁ ቢመስሉም አብዮቱን ተከትሎ የመጣውን የኢኮኖሚ ችግር ተቋቁመው ለውጡን ለመደገፍ የቆረጡትን ""ሰልፈኞች"" በተሳሳተ መንገድ የተረዱ ይመስላል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59196274 +health ኦሚክሮን፡ በፍጥነት በሚዛመተው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ? "እንሆ ሁለት ትላልቅ ጥያቄዎች፡ ኦሚክሮን በምን ያህል ፍጥነት ሊዛመት ይችላል? በኦሚክሮን ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ? እኒህን ሁለት ጥያቄዎች መልስ አገኘንላቸው ማለት ኦሚክሮን የተሰኘው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምን ያህል አደገኛ ነው የሚለውን መለስን ማለት ነው። የምድራችን ሳይንቲስቶች እኒህን ጥያቄዎች ለመመለስ ደፋ ቀና እያሉ ነው። ትንሽ ፍንጭ የሚሰጥ ነገር ያገኙም ይመስላል። የመከላከል አቅም በጣም አስፈላጊ ነው። ኦሚክሮን ሁሉን ነገር ወደኋላ መልሶ እንደአዲስ እንድንድህ ሊያደርገን ነው ባይባልም አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ምን ያህል አስጊ ነው የሚለውን መመልስ ጥቂት ሳምንታትን ሊጠይቅ ይችላል። ኦሚክሮን በምን ያህል ፍጥነት እየተዛመተ ይሆን? መልሱ ""በፍጥነት"" የሚል ነው። ይህ ዝርያ በክትባትም ይሁን በርካታ ሰዎች በመያዛቸው ምክንያት የተሻለ የመከላከል አቅም አዳብረዋል በሚባሉ ሥፍራዎችም በፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል። ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ ከአንድ ወር በፊት ዴልታ ከተሰኘው የኮቪድ ዝርያ ጋር ተላምዳ በቀን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 300 ወርዶ ነበር። አሁን ግን አራተኛው የኮቪድ ማዕበል ከ10 ሺህ በላይ ሰዎችን አዳርሷል። ዩናይትድ ኪንግደምም ብትሆንም ኦሚክሮን እንደሰደድ እሣት እየተዛመተባት ይገኛል። ሳይንቲስቶች የኦሚክሮንን ዱካ እያገኙ ያሉት ዝርያው የኮቪድ ምርመራ በሚደረግበት ወቅት ትቶ በሚያልፋቸው አሻራዎች አማካይነት ነው። ይህ አሻራ ኤስ-ጂን ይሰኛል። ይህ ከኮቪድ ምርምራ ላይ የሚገኝ ቅንጣት ባለፈው ወር መጨረሻ ወደ 0.1 በመቶ ወርዶ ነበር። አሁን ግን ወደ 5 በመቶ አድጓል። ይህ በቁጥር ሲገለጥ በቀን 2500 ሰዎች በአዲሱ ዝርያ ይያዛሉ ማለት ነው። ይህ ስሌት ሙሉ በሙሉ ትክክል ነው ማለት ባይቻልም በአራተኛው የኮቪድ ማዕበል የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ የማይታበይ ሐቅ ነው። ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም የኦሚክሮን ቁጥር በየሦስት ቀኑ እጥፍ እየሆነ እንደሚሄድ መረጃዎች ጠቋሚ ናቸው። ኦሚክሮን የሚዛመትበት ፍጥነት ዴልታ ከተሰኘው ዝርያ በላይ ሲሆን ኮሮናቫይረስ ባለፈው ዓመት መባቻ ሲጀምር ሲስፋፋ የነበረውን ዓይነት ፍጥነት እንዳለው ተደርሶበታል። በዚህ ፍጥነቱ መዛመቱን ከቀጠለ በቀን 2500 የነበረው ቁጥር ከአንድ ወር በኋላ በቀን 100 ሺህ ይሆናል ማለት ነው። እኔን ይይዘኝ ይሆን? በሽታው ምን ያህል ከባድ ነው? ሳይንቲስቶች እስካሁን ድረስ ባደረጉት ጥናት ጭንቀት ውስጥ የከተተታቸው የኦሚክሮን ዝርያ የኮቨድ ክትባትን የመቋቋም አቅሙ ነው። ኦሚክሮን አሠራሩ ክትባቱ እንዲከላከል ከተሠራለት የመጀመሪያው የኮቪድ ዝርያ ለየት ያለ ነው። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የኮቪድ ክትባት ሁለት ጊዜ የወሰዱ ሰዎች አዲሱን ዝርያ የመከላከል አቅማቸው ከ20 እስከ 40 እጥፍ ሊቀንስ ይችላል። እርግጥ ነው እስካሁን በአዲሱ ዝርያ ዙሪያ አጠንጥነው የተሠሩ ጥናቶች ቁጥር ትንሽ ነው። ነገር ግን እኒህ ጥናቶች የአዲሱን ዝርያ የመዛመት ኃይል የሚያሳዩ ናቸው። ቢሆንም ስለ አዲሱ ዝርያ መልካም ዜናም አልጠፋም። ፋይዘር-ባዮንቴክ የሠራው ሙከራ እንደሚያመለክተው ማጠናከሪያ ክትባት [ሦስተኛ ክትባት] የወሰዱ ሰዎች ኦሚክሮንን የመከላከል አቅማቸው ከፍ ይላል። ለኦሚክሮን ሦስት ዙር መከተብ ማለት ለዋናውና የቀደመው ቫይረስ ሁለት ዙር እንደመከተብ ማለት ነው። የኤደንብራ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ኤሌኖር ራይሊ ይህን ሙከራ ""አበረታች"" ሲሉ ይገልፁትና ""ማጠናከሪያው ክትባት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚያሳይ ነው"" ይላሉ። ኦሚክሮን ምን ያህል ከባድ የኮሮናቫይረስ ዝርያ እንደሆነ ግን እስካሁን የምናውቀው ጥቂት ነው። በዝርያው ተይዘው ሆስፒታል የገቡ ሰዎች ጥናት እስኪደርግባቸው ድረስ ስለበሽታው ኃያልነት ያለው እውቀት እፍኝ አይሞላም። እርስዎ ሁለት ጊዜ ክትባት ወሰዱ ማለት አሊያም ከዚህ በፊት ኮቪድ ይዞዎት ነበር ማለት ኦሚክሮንን የመከላከል አቅምዎ የተሻለ ነው ይላሉ ሳይንቲስቶች። እና ወደፊት ምን ሊሆን ይችላል? ኮሮናቫይረስን እንዲከላከሉ ተብለው የተዘጋጁት ክትባቶች ኦሚክሮንን ሊከላከሉ እንደሚችሉ ግምት አለ። ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ጤና ብንሆን እንኳ ሁላችንም ደህና ላንሆን እንችላለን። አንዳንድ ሰዎች የመከላከል አቅማቸው እጅግ የደከመ ነው። አንዳንዶች ቢከተቡም ላይከላከሉ ይችላሉ። አንዳንዶች ክትባት መውሰድ አይችሉ ይሆናል። አንዳንዶች ደግሞ በውዴታ ክትባት አንወስድም እያሉ ነው። በዴልታ ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ሆስፒታል እስከመግባት ደርሰዋል። አዲሱ ዝርያ ብዙ ሰዎች በአንድ ጊዜ ወደ ሆስፒታል እንዲገቡ ካደረገ ችግር ሊፈጠር ይችላል። የዋርዊክ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ማይክል ቲልደስሊ ""ማዕበል ትልቅ ከሆነ ባለፈው ጥር እንደተመለከትነው ዓይነት ሊሆን ይችላል። ሆስፒታሎችም ሊጨናነቁ ይችላሉ"" ባይ ናቸው። ነገር ግን አሁን ያለን መረጃ ጥቂት ስለሆነ ይህ ነው ብሎ መናገር እንደሚከብድ ያስረዳሉ። የዓለም ሳይንቲስቶች የተስማሙበት ይህ ነው የሚባል ኦሚክሮን እየተዛመተበት ያለ ፍጥነት የለም። በሽታው ምን ያህል ከባድ ሊሆን እንደሚችልም በውል አይታወቅም። ክትባቱን ሊፈታተነው ይችላል ወይ የሚለውም ምላሽ አላገኘም። ማድረግ የሚቻለው ራስን ከበሽታው እየጠበቁ በቀጣይ ሳምንታት የሚሆነውን በቅርበት መከታተል ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-59596054 +health ሕክምና ፡ ቁመት ለመጨመር ምን አይነት ቀዶ ሕክምና ነው የሚደረገው? "ሳም ቤከር የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ ሳለ የክፍሉ ረዥም ልጅ ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆነው ጓደኞቹ ሁሉ ዘለግ ዘለግ ያሉ ሲሆኑ የእሱ ቁመት ግን አልጨመረም። ""ኮሌጅ ስገባ ከሌሎች ወንዶችና ሴቶች ያጠርኩ መሆኔን አስተዋልኩ። ሴቶች ከእነሱ ከሚያጥር ሰው ጋር ፍቅር አይጀምሩም። እናም ሚስት አላገኝም ብዬ እሰጋ ነበር"" ይላል። የ30 ዓመቱ የኒው ዮርክ ነዋሪ ሳም እረዝማለሁ ብሎ ቢጠብቅም ቁመቱ አልጨምር አለው። ""ቁመትና ስኬትን አስተሳስሬ ነው የማየው"" የሚለው ሳም ቁመት ለመጨመር አማራጮች ያስስ ጀመር። ከፍ ያለ ጫማ ማድረግ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ወዘተ. . . የሚሉት አማራጮች አላሳመኑትም። እግር ስለሚያረዝም ቀዶ ሕክምና ሲያነብ ግን ትኩረቱን ሳበው። ""ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ"" በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቁመታቸውን ለመጨመር ቀዶ ሕክምና ያደርጋሉ። ቀዶ ሕክምናው ብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሳም ስለ ቀዶ ሕክምና��� ከእናቱ ጋር ከተወያየ በኋላ የጎንዮሽ ጉዳት ቢኖርም እንኳን ለማካሄድ ወሰነ። ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ሲሆን፤ ይህም ከ162 ሴንቲ ሜትር ወደ 170 ሴንቲ ሜትር ከፍ እንዲል አስችሎታል። ""ሐኪሙ መጀመሪያ ሲያገኘኝ ቀዶ ሕክምናው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ነግሮኛል። ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ።"" ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሆስፒታል ውስጥ የማገገሚያ ሕክምና ተደርጎለታል። ለስድስት ወራት፣ በሳምንት ለአራት ቀን ሕክምና ይሰጠው እንደነበር ያስታውሳል። ""እንደ አዲስ መራመድ መማር ነበረብኝ"" ይላል። ብዙ አገሮች እግር ለማርዘም ቀዶ ሕክምና ይሰጣሉ። እስከ አምስት ኢንች ወይም 13 ሴንቲ ሜትር ድረስ ቁመት መጨመርም ይቻላል። አሜሪካ፣ ጀርመን እና ደቡብ ኮርያ የሚገኙ ሆስፒታሎች በዓመት ከ100 እስከ 200 ቀዶ ሕክምናዎችን ያደርጋሉ። ስፔን፣ ሕንድ፣ ቱርክ እና ጣልያን ውስጥ በዓመት ከ20 እስከ 40 የሚደርሱ ቀዶ ሕክምናዎች ይካሄዳሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ደግሞ በዓመት 15 ጊዜ ቀዶ ሕክምናው ይደረጋል። ቀዶ ሕክምናውን የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ቀዶ ሕክምናው እንዴት ይካሄዳል? ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ቀዶ ሕክምናው እስከ 50 ሺህ ፓውንድ ያስከፍላል። አሜሪካ ውስጥ ደግሞ ከ75 ሺህ እስከ 280 ሺህ ዶላር ያስወጣል። ቀዶ ሕክምናው ውድ ነው። ረዥም ሰዓታት ይወስዳል። ያማልም። በሕክምናው ፈር ቀዳጅ የሆኑት የሶቪየቱ ጋቪል ሊዝሮቭ ናቸው። ሕክምናውን የጀመሩት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተረፉ ወታደሮችን ለማከም ነበር። ቀዶ ሕክምናው ባለፉት 70 ዓመታት ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል። ሕክምናው የሚካሄደው የእግር አጥንትን ቦርቡሮ ለሁለት ከከፈሉ በኋላ አነስተኛ ብረት በክፍተቱ በመክተት ነው። ግለሰቡ የሚፈለገው ርዝመት ላይ እስኪደርስ ብረቱ በየቀኑ አንድ ሚሊ ሜትር ከፍ እንዲል ይደረጋል። ታካሚው ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ለወራት የማገገሚያ ሕክምና ይሰጠዋል። ቀዶ ሕክምናው ነርቭ ሊጎዳ፣ የደም ዝውውር ሊገታም ይችላል። የእግር አጥንትን መልሶ ለመግጠም የሚያስቸግርበትም ጊዜ አለ። ""ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር"" ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከአምስት ዓመት በፊት ጣልያን ሲሆን፤ 3 ኢንች ጨምሯል። የእግር ቀዶ ሕክምና እንዲያደርግ የታዘዘው በሐኪሞች ምክር ነበር። ""ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር። የእግሬ አጥንት መልሶ ሊገጥም አልቻለም። የሦስት ኢንች ክፍተት ተፈጥሮ ነበር"" ይላል። ቀዶ ሕክምናው ምቾት ነስቶት እንደነበር ይናገራል። ""እያንዳንዱ የእግሬ ነርቭ እንደተወጠረ ይሰማኝ ነበር። ህመሙ ቀላል አልነበረም።"" የብሪትሽ የአጥንት ሕክምና [ኦርቶፒዲክ] ማኅበሩ ፕሮፌሰር ሀሚሽ ሲምሰን እንደሚሉት፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሕክምናው እየተሻሻለ መጥቷል። ""ሂደቱ አስተማማኝ እየሆነ ቢመጣም ከአጥንት በተጨማሪ ጡንቻ፣ ነርቭ፣ የደም መዘዋወሪያ እና ቆዳን ማሳደግም ስለሚያስፈልግ ሂደቱ ውስስብ ነው"" ይላሉ። በዩናይትድ ኪንግደም የሚሠሩት ዶ/ር ዴቪድ ጎደር፤ አንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ለማዳን ብለው ደኅንነቱ በማያስተማምን ቦታ ቀዶ ሕክምናውን እንደሚያገኙ ይናገራሉ። ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ካካሄደ ከአምስት ዓመታት በኋላ ነው የመጨረሻውን የሕክምና ደረጃ ያጠናቀቀው። በስተመጨረሻ እግሩ ውስጥ የቀረው ብረት እንዲወጣ ተደርጓል። ""የአንዳንዶች ቀዶ ሕክምና በስኬት ይጠናቀቃል። እኔ ግን ለማገገም ገና ጊዜ ይወስድብኛል። ሆኖም ቀዶ ሕክምናውን ማድረጌ አይጸጽተኝም። አጭር ሰዎች ከሚገጥማቸው መድልዎ ነጻ ሆኜ ሕይወቴ��� እንድገፋ እድል ሰጥቶኛል"" ይላል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55198053 +sports የቀድሞው የሊቨርፑል አጥቂ የጠፋ ውሻውን ላገኘለት ራፐር 30 ሺህ ዶላር እንዲከፍል ተፈረደበት "የቀድሞው የሊቨርፑል ተጫዋች ዳንኤል ሰተሬጅ ከሁለት ዓመታት በፊት ጠፍታ የነበረቸውን ሉሲ የተሰኘች ውሻውን ላገኘለት ግለሰብ 30 ሺህ ዶላር እንዲከፍል ፍርድ ቤት ወሰነበት። አሁን በአውስትራሊያ ላለ ክለብ የሚጫወተው ዳንኤል፤ ሉሲ የተሰኘች ውሻው በሎስ አንጀለስ ከሚገኘው ቤቱ መሰረቋን ተከትሎ ነበር ላገኛት ሰው ወረታውን ለመክፈል ቃል የገባው። ኪላ ፌም በሚለው የመድረክ ስሙ የሚታወቀው ፎስተር ዋሽንግተን የተሰኘው ራፐር ውሻውን አግኝቶ ለዳንኤል ቢሰጠውም ቃል የተገባው ክፍያ ግን እንዳልተፈጸመለት ተናግሯል። ይህንን ማመልከቻ ተከትሎም ችሎቱ ለዋሽንግተን ፈርዶለታል። ፒኤ በተሰኘው የዜና ወኪል እጅ የገቡት የችሎቱ ሰነዶች እንደሚያሳዩት ፍርዱ ዳንኤል ወደ ችሎት ቀርቦ ምላሽ ሳይሰጥበት በፊት ነው የተሰጠው። ዳኛው እግር ኳስ ተጫዋቹ ለራፕ ሙዚቃ አቀንቃኙ ከ30 ሺህ ዶላሩ ክፍያ በተጨማሪ ደረሰብኝ ያለው የመገፋት ስሜት ላደረሰበት ጉዳት የ85 ዶላር ካሳ እንዲከፍለውም አዟል። ""ገንዘቡን እንደሚከፍል እና ወደ ይግባኝ እንደማይሄድ ተስፋ አደርጋለሁ። በጣም ደስ ብሎኛል። ለዚህ የፍርድ ቤት ጉዳይ ከአንድ ዓመት በላይ ስከራከር ቆይቻለሁ። ውሻውን ሳገኝ ሕይወቴ የተወሰነ ይሻሻላል ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር"" ሲልም ዋሽንግተን ተናግሯል። በእግር ኳስ ተጫዋቹ የሆሊዉድ ቤት ውስጥ ተገጥመው በነበሩ የደኅንነት ካሜራ ቪዲዮዎች ኮፍያ ያለው ሹራብ ያደረጉ ሦስት ሰዎች ውሻዋ በጠፋችበት ጊዜ ላይ ታይተው ነበር። ""ለውሻዋ ማንኛውንም ነገር እንከፍላለን"" ሲል ዳንኤል ስተርጅ ተናግሮ ነበር። ""ማንም ይሁን ማን ውሻዬን ካመጣልኝ ከ20 እስከ 30 ሺህ ዶላር እከፍላለሁ"" ሲልም ገልጾ ነበር። ይህንን ካለ ከሁለት ቀን በኋላ ነበር ውሻውን ያገኘው። የቀድሞው የሊቨርፑል ቡድን ተጫዋቹ ወኪሎች በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59788736 +health ''ኮሮናቫይረስ በሁለት ዓመታት ውስጥ ሊጠፋ ይችላል'' ደ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ገለጹ። ትላንት በሲዊዘርላንድ ጄኔቫ ባደረጉት ንግግር ዳይሬክተሩ ስፓኒሽ ፍሉ በጎርጎሮሳውያኑ 1918 በተከሰተበት ወቅት ለመጥፋት የወሰደበት ጊዜ ሁለት ዓመት ነበር ብለዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም ዓለም አሁን ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ መራቀቅና ከፍተኛ ምርምሮች አንጻር የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ገልጸዋል። ''በሌላ በኩል ደግሞ አሁን ባለው ከፍተኛ የሰዎች ማህበራዊ ትስስር ምክንያት የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ሊሆንም ይችላል'' ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። ''ነገር ግን የሰው ልጅ የደረሰበት የቴክኖሎጂ ርቀት ቫይረሱን ለማስቆም የሚረዳ እውቀት በቶሎ እንዲያዳብር ይረዳዋል'' ካሉ በኋላ አሁንም ቢሆንም ግን ብሄራዊ አንድነትና ዓለማቀፍ ትብብር ላይ ከፍተኛ አጽንኦት ሰጥተው አልፈዋል። የ1918ቱ ስፓኒሽ ፍሉ ቢያንስ 50 ሚሊየን ሰዎችን የገደለ ሲሆን ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን ቁጥር 800 ሺህ ነው። በአጠቃላይ ደግሞ 22.7 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ዶክተር ቴዎድሮስ በመግለጫቸው ላይ የግል መከላከያ መሳሪያዎች ወይም 'ፒፒኢ' ስርጭት በተመለከተ ሙስና እየተስተዋለ እንደሆነ ለቀረበላቸውም ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ጉዳዩን ''ወንጀል'' ነው በማለት ገልጸው���ል። ''ማንኛውም አይነት ሙስና ተቀባይነት የለውም'' ብለዋል። ''ነገር ግን ከፒፒኢ ጋር የተያያዘ ሙስና ለእኔ በግሌ እንደ ነብስ ማጥፋት ነው የምቆጥረው። ምክንያቱም የጤና ባለሙያዎች ፒፒኢ የማያገኙ ከሆነ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ እየጣልን ነው። በተጨማሪም የሚያገለግሏቸው ሰዎችን ሕይወትም ነው ስጋት ውስጥ የምንከተው'' ብለዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-53872753 +business ኮሮናቫይረስ ፡ ኮቪድ-19 ኒውዚላንድን ለዓመታት አጋጥሟት ለማያውቅ የኢኮኖሚ ውድቀት ዳርጓታል ተባለ "የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ በተከሰተ በመጀመሪያዎቹ ወራት በርካቶችን እንደ ቅጠል ሲያረግፍ፤ ኒው ዚላንድ ግን በሌሎች የአውሮፓና አሜሪካ አገራት የሆነው አልገጠማትም። ይህ የሆነው የአገሪቷ መንግሥት ቀድሞ በወሰዳቸው ጥብቅ እርምጃዎች ምክንያት ነው። ኒው ዚላንድ ለወረርሽኙ ምላሽ በመስጠት ከተወደሱ አገራት መካከል አንዷ ናት። ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርንም በዚህ ሥራቸው ተሞግሰዋል። ነገር ግን አገሪቷ ኮቪድ -19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የጣለቻቸው ጥብቅ ገደቦች ባለፉት አስርት ዓመታት አጋጥሟት ወደማያውቅ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እንደከተታት ተገልጿል። በአገሪቷ የእንቅስቃሴ ገደቡ በተጣለባቸውና ድንበር በዘጋችበት ከሚያዚያ እስከ ሰኔ ባሉት ጊዜያት የኢኮኖሚ እድገቷ በ12̀.2 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገልጿል። ይህም ኒው ዚላንድ ዓለም አቀፉን የኢኮኖሚ ቀውስ ተከትሎ በጎርጎሮሳዊያኑ 1987 ከገጠማት የመጀመሪያው የኢኮኖሚ ድቀት ነው ተብሏል።. ይሁን እንጅ መንግሥት ለወረርሽኙ የሰጠው ምላሽ ኢኮኖሚው በፍጥነት ወደማንሰራራት እንደሚያመራው ተስፋ አድርጓል። 5 ሚሊየን የሚጠጋ የሕዝብ ብዛት ያላት ኒው ዚላንድ ከቫይረሱ ነፃ መሆኗን ያወጀች ቢሆንም አሁንም ግን በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ይገኛሉ። አገሪቷ በቫይረሱ ሳቢያ ያስተናገደችው ሞትም 25 ብቻ ነው። የኢኮኖሚው ጉዳይም ነሐሴ ወር ላይ ባልተጠበቀ መልኩ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ የተራዘመውና በሚቀጥለው ወር በሚደረገው ምርጫ ላይም ዋነኛ ጉዳይ ሆኖ እንደሚነሳ ይጠበቃል። የኒው ዚላንድ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ቃል አቀባይ ፖል ፓስኮ፤ ወረርሽኙን ተከትሎ ከመጋቢት ወደ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረጉ ገደቦች በተወሰኑ የኢኮኖሚው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደነበረው ተናግረዋል። ""በኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ፣ በሆቴሎችና ሬስቶራንቶች እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ የሆነ መዳከም ታይቷል። እነዚህ ዘርፎች በዓለም አቀፉ ጉዞ እገዳ እና በአገሪቷ ተጥሎ በነበረው ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ በቀጥታ ተጎጅ ሆነዋል"" ብለዋል ቃል አቀባዩ ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን መንግሥትም ቫይረሱን በመቆጣጠር የተገኘው ውጤት ኢኮኖሚው እንዲያንሰራራ ያግዛል ብለዋል። የአገሪቷ የገንዘብ ሚኒስትር ግራንት ሮበርትሰን በበኩላቸው፤ የኢኮኖሚ እድገት [ጂዲፒ] አሃዝ ከተጠበቀው የተሻለ መሆኑን በመጥቀስ ወደ ፊት ኢኮኖሚው እንደሚሻሻል አስተያየታቸው ሰጥተዋል። አንዳንድ የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎችም ኒው ዚላንድ ቫይረሱን ለመቆጣጠር ጠንካራ ምላሽ በመስጠቷ ኢኮኖሚዋ በፍጥነት እንደሚያገግም ተንብየዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54193966 +business ከኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ኩባንያ ሕንጻ ላይ የወደቀ መኪና ሁለት ሰዎችን ገደለ ከቻይናው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያ ኒዮ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ ላይ አንድ መኪና ወድቆ ሁለት ሰዎችን ገደለ። ሻንጋይ ከሚገኘው የኒዮ ዋና መሥሪያ ቤት ሦስተኛ ፎቅ ላይ መኪና መውደቁን ተከትሎ ነው ሰዎቹ ለህልፈት የተዳረጉት። ኒዮ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ሲሆን፣ ከሞቱት ሰዎች አንደኛው ���ድርጅቱ ተቀጣሪ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የኒዮ አጋር ድርጅት ሠራተኛ ናቸው ተብሏል። ሟቾቹ መኪናው ሲወድቅ ውስጡ እንደነበሩ ተገልጿል። ከመንግሥት አመራሮች ጋር በመጣመር ክስተቱን እየመረመረ እንደሚገኝ የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ኒዮ አስታውቋል። የዋና መሥሪያ ቤቱ ሦስተኛ ፎቅ መኪኖች ለዕይታ የሚቀርቡበት ሲሆን፣ መኪኖች ከመሸጣቸው በፊት የሚሞከሩትም በዚህ የሕንጻው ክፍል ነው። መኪና አምራቹ ባወጣው መግለጫ “ከአገር ውስጥ ደኅንነት ጋር ድርጅታችን ተጣምሮ ስለ አደጋው መንስኤ ምርመራ ጀምሯል። እስካሁን ባገኘነው መረጃ ክስተቱ ድንገተኛ ነው። የተፈጠረውም በመኪናው ምክንያት አይደለም” ብሏል። ለሟቾች ቤተሰቦች መጽናናትን የተመኘው ድርጅቱ፣ ቤተሰቦቻቸውን የሚደግፍ ቡድን እንዳቋቁመ አክሏል። ኒዮ ባወጣው መግለጫ፣ አደጋው ከመኪናው ጋር የተያያዘ አይደለም ማለቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቁጣን ቀስቅሷል። “ይህ መግለጫ የካፒታሊዝምን አደገኛነትን ያሳብቃል” ሲል አንድ የቻይና ማኅበራዊ ሚዲያ ዌቦ ተጠቃሚ ተናግሯል። “ይህ አባባል ግድየለሽነታቸውን ነው የሚያሳየው። ሹፌሮች መኪኖችን እንዲሞክሩ እያደረጉ ክስተቱ ከመኪናው ጋር የማይገናኝ አደጋ ነው ይላሉ” ሲል ሌላ የዌቦ ተጠቃሚ ተችቷል። ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ “አደጋ ነበር ወይስ አልነበረም የሚለውን መወሰን ያለበት የአገር ውስጥ ደኅንነት ቢሮ ነው” ብሏል። መኪና አምራቹ መጀመሪያ ላይ የለጠፈውን መግለጫ አሻሽሎ ‘አደጋው የተከሰተው በመኪናው ምክንያት አይደለም’ የሚለውን አረፍተ ነገር በቅንፍ ውስጥ አስቀምጦታል። ከዚያ በኋላ የተሰጡት አስተያየቶች “ነፍስ ይማር” የሚሉ ናቸው። ኒዮ በኤሌክትሮኒክ ተሽከርካሪዎች ምርት ቻይና ውስጥ ግንባር ቀደም ከሚባሉት መካከል ይጠቀሳል። ኩባንያው መኪኖችን በተደጋጋሚ ቻርጅ ማድረግ ለጉዞ መሰናክል እንዳይሆን ተለዋጭ ባትሪ በማዘጋጀትም ይታወቃል። ሌላው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች፣ የኤሎን መስክ ቴስላ ሻንጋይ ውስጥ ቅርንጫፍ አለው። ኒዮ የቴስላ ተቀናቃኝ እንደሆነም ይታመናል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cye9w6rl475o +sports የዓለም ዋንጫ፡ ብሔራዊ ቡድናቸው በመሸነፉ ደስታቸውን ሲገልጹ ከነበሩ ኢራናዊያን መካከል አንድ ሰው ተገደለ ብሔራዊ ቡድናቸው ከዓለም ዋንጫ በጊዜ በመሰናበቱ ደስታቸውን ሲገልጹ ከነበሩ የኢራን መንግሥት ተቃዋሚዎች መካከል አንድ ሰው በጸጥታ አካላት መገደሉ ተገለጸ። ማከሰኞ ምሽት የህብረተሰብ አንቂ የሆነው ሜህራን ሳማክ በባንዳር አንዛሊ የመኪናውን ጥሩምባ ሲነፋ ግንባሩ ላይ በጥይት መመታቱ ተነግሯል። ከሌሎች ከተሞች የተገኙ ምስሎች እና ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት በርካታ ሰዎች መንገዶች ላይ ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል። ብሔራዊ ቡድኑ የኢስላሚክ ሪፐብሊክ ምልክት ነው በማለት ብዙ ኢራናዊያን ድጋፋቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል። የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በሃገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ኃይሎች በአሜሪካ 1 ለ 0 በተሸነፈበት የመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ወቅት ጫና እንዳሳደሩበት ገልጸዋል። በእንግሊዝ 6 ለ 1 በተሸነፉበት ጨዋታ ደግሞ ተጫዋቾችቹ ብሔራዊ መዝሙር አልዘመሩም። ይህም ለተቃዋሚዎች ያላቸውን ድጋፍ ያሳያል ተብሏል። ዌልስን 2 ለ 0 ባሸነፉበት እና ፖለቲካዊ ውጥረት በነበረው የአሜሪካ ጨዋታ ወቅት ግን ብሔራዊ መዝሙሩን ዘምረዋል። የቡድኑ አባላት በጸጥታ ሃይሎች ጫና ደርሶባቸው ነው ቢባልም አንዳንድ ተቃዋሚዎች ቡድኑ ብሔራዊ መዝሙሩን በመዘመሩ ከድቶናል የሚል ስሜት ፈጥሮባቸዋል። በኢራን አለመረጋጋት የጀመረው ከአስር ሳምንታት በፊት ነው። የ22 ዓመቷ ማህሳ አሚኒ የሂጃብ አለባበስ ደንብ ጥሳለች ���ሚል በስነ ምግባር ፖሊሶች እጅ ህይወቷ ማለፉ ቁጣውን ቀስቅሶታል። ባለስልጣናት “አመጹን” በውጭ ሃይላት የሚደገፍ ሲሉ ይገልጻሉ። መቀመጫውን ኖርዌይ ያደረገው የኢራን የሰብዓዊ መብት ቡድን 60 ህጻናትን ጨምሮ በትንሹ 448 ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል። ከ18 ሺህ በላይ ሰዎች መታሰራቸውም ተነግሯል። ኢራን ብሔራዊ ቡድን ሽንፈትን በደስታ ለማክብር የመኪናውን ጥሩምባ ሲነፋ የነበረው የ27 ዓመቱ ሜህራን ሳማክ በጸጥታ ሃይሎች መገደሉን የኢራን ሰብዓዊ መብት ሪፖርት አድርጓል። ቢቢሲ ፐርዢያ ረቡዕ ጠዋት የተደረገለትን የቀብር ስነ ስርዓት ቪዲዮ ለመመልከት ችሏል። ሃዘንተኞች “ቆሻሻ ናችሁ፣ ሞራል የላችሁም፣ እኔ ነጻ ሴት ነኝ” የሚሉና በተቃዋሚዎች የሚዘወተሩ መፈክሮችን አሰምተዋል። የኢራን ጸጥታ ኃይሎች ሠላማዊ ተቃዋሚዎችን አልገደልንም ሲሉ ያስተባብላሉ። ሌሎች ቪዲዮዎች ደግሞ ቴህራንን ጨምሮ በተለይም በኩርዲስታን ከተሞች የብሔራዊ ቡድኑን ከዓለም ዋንጫ መሰናበት ደስታቸውን የገለጹ በርካታ ናቸው። በቅርቡ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዷቸው እርምጃዎች በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። በማህሳ አሚኒ የትውልድ ከተማ ሳቄዝ ስካርፋቸውን በማውለብለብ ደስታቸውን ከመግልጽ ባለፈ ርችትም ሲተኩሱ ታይተዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c979d3z0e2no +health አዲሱ ኮሮናቫይረስ ኦሚክሮን ምን ያህል አሳሳቢ ነው? "የዓለም ጤና ድርጅት ኦሚክሮን ብሎ የሰየመው አዲሱ የኮሮረናቫይረስ ዝርያ እንደ አዲስ ዓለምን ማስጨነቅ ከጀመረ ሰነባብቷል። በርካታ አገራትም ከወዲሁ ስርጭቱን በመስጋት በራቸውን እየዘጉ ይገኛሉ። ኦሚክሮን እራሱን የሚለውጥበትና የሚስፋፋበትን መንገድ የተመለከቱ ተመራማሪዎችም በጣም አስፈሪ እንደሆነ እየገለጹ ነው። ይህ የቫይረስ ዝርያ በብዙ የለውጥ ሂደት ውስጥ ያለፈ ሲሆን ማስረጃዎች ቀደም ሲል ተይዘው የነበሩ ሰዎች በቫይረሱ የመያዝ ምጥኔን እንደሚጨምር ይጠቁማሉ ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። አዲሱ ኦሚክሮን እስካሁን ከ30 በላይ አገራት ውስጥ የተገኘ ሲሆን ሰዎች በክትባትም ሆነ የኮሮረናቫይረስ ሲይዛቸው የሚያዳብሩትን በሽታ የመከላከል አቅም በቀላሉ ማለፍ የሚችል ነው። ነገር ግን ከዚህ በፊት ከነበሩት የኮሮረናቫይረስ አይነቶች አንጻር እስካሁን ቀላል የሚባሉ ምልክቶችን ብቻ ነው ያሳየው። በዚህም ምክንያት ስለ ቫይረሱ፣ ስለ ስርጭቱ እና ስለሚያደርሰው ጉዳት በርካታ መላ ምቶች እየተሰነዘሩ ነው። እስካሁን እኛ የምናውቀውን እናካፍላችሁ ኦሚክሮን እስከዛሬ ከታዩት የኮሮናቫይረስ አይነቶች በሙሉ በፍጥነት እራሱን ማሻሻሻልና መቀየር የቻለው የቫይረስ አይነት ነው። በበርካታ የዘረመል ለውጥ ውስጥ በማለፉ በአንድ ሳይንቲስት ""አሰቃቂ"" ተብሎ ሲገለጽ ሌላው ደግሞ እስካሁን ከታዩት ""የከፋ"" ዝርያ ነው ብለዋል። አዲሱ ዝርያ በምን ያህል በፍጥነት እንደሚሰራጭ እና ክትባቶችን በመቋቋም አቅሙ ዙሪያ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ። ይህ የዝርያ ለውጥ ቫይረሱን ማሸነፍ ካልቻለ አንድ ታካሚ የመጣ ሳይሆን አይቀርም ተብሏል። አሳሳቢው ነገር ይህ ቫይረስ በቻይና ዉሃን ከተፈጠረው የመጀመሪያው ቫይረስ በእጅጉ የተለየ ነው። ይህም ማለት የመጀመሪያውን ቫይረስ ከግምት በማስገባት የተመረቱት ክትባቶች ለዚህ አዲስ ዝርያ ያን ያህል ውጤታማ ላይሆኑ ይችላሉ። በደቡብ አሜሪካ የሚገኘው የተላላፊ በሽታዎች መካለከያና ምላሽ ሰጪ ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ቱሊዮ ዴ ኦሊቬራ እንደሚሉት፣ ኦሚክሮን ከዚህ በፊት ከታዩት ቫይረሶች በሙሉ በተለየ መልኩ እራሱን መቀያያርና እንደ ሁኔታዎች መለዋወጥ የሚችል ነው። ""ይህ ዝርያ አስገርሞናል። ለውጡ በከፍተኛ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን ከምንጠብቀው ብዙ ለውጥ አለው"" ብለዋል። ፕሮፌሰር ዴ ኦሊቬራ አክለውም አዲሱ ቫይረስ በአጠቃላይ 50 የዘረ መል ለውጦች አሉት። የብዙዎቹ ክትባቶች ዒላማ ከሆነው ከስፔክ ፕሮቲን ከ30 በላይ ለውጥ ታይቷል። ይህም ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ህዋሳት መግቢያ በር ለመክፈት የሚጠቀምበት ቁልፍ ነው። ቫይረሱ ከሰውነታችን ህዋሳት ጋር የመጀመሪያ ግንኙነት ሲያደርግ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው ዴልታ ዝርያ ሁለት ሲሆን አዲሱ ዝርያ ደግሞ 10 እጥፍ ለውጥ አለው። ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ የዝርያ ለውጥ ቫይረሱን ማሸነፍ ካልቻለ አንድ ታካሚ የመጣ ሳይሆን አይቀርም። አሳሳቢው ነገር ይህ ቫይረስ በቻይና ዉሃን ከተፈጠረው የመጀመሪያ ቫይረስ በእጅጉ የተለየ መሆኑ ነው። ይህም ማለት የመጀመሪያውን ቫይረስ ከግምት በማስገባት የተመረቱት ክትባቶች ለዚህ አዲስ ዝርያ ያን ያህል ውጤታማ ላይሆኑ ይችላሉ። አንዳንዶቹ ለውጦች በሌሎች ዝርያዎች ውስጥ ከዚህ ቀደም ታይተዋል። ይህም በዚህ ለውጥ ውስጥ ያለውን ሚና የተወሰነ ግንዛቤ ይሰጣል። ለምሳሌ ኤን501ዋይ የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ቀላል የሚያደርግ ይመስላል። የሰውነት የበሽታ መከላከያ ቫይረሱን እንዳያውቁ የሚያከብዱበት እና ክትባቶች ውጤታማ እንዳይሆኑ የሚያደርጉ ሌሎች ዝርያዎች አሉ። በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ተመራማሪዎች ቀደም ብለው እንደገለጹት ኦሚክሮን የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅም በቀላሉ ማለፍ ይችላል። በደቡብ አፍሪካ የኩዋዙሉ-ናታል ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ሌሰልስ ""ይህ ቫይረስ የመተላለፍ ችሎታውን ከፍ አድርጎ ከሰው ወደ ሰው ከመተላለፍ ባለፈ የበሽታ ተከላካይ ክፍሎችን ማካለል ይችላል የሚል ስጋት አሳድሮብናል"" ብለዋል። በወረቀት ላይ አስፈሪ የሚመስሉ ነገር ግን ጉዳት ያላደረሱ ብዙ የዝርያ ምሳሌዎች ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ የቤታ ዝርያ የበሽታ መከላከል ሥርዓትን ሊያመልጥ ይችላል በሚል በሰዎች ዘንድ ስጋት ፈጥሮ ነበር። በደቡብ አፍሪካ ኦሚክሮን በእጅጉ እየተስፋፋ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ባሳለፍነው ወር አጋማሽ አካባቢ በየቀኑ እስከ 250 የሚደርሱ አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ ነበር። ሌሎች የኮሮረናቫይረስ አይነቶች እያስቸገሯት በምትገኘው ደቡብ አፍሪካ አሁን ላይ በኦሚክሮን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በቀን እስከ 8 ሺህ ይደርሳል። አሁን ላይ ሰዎች ስለአዲሱ ቫይረሰ አይነት ያላቸው እውቀት ውስን ነው። በዚህም ምክንያት ተመራማሪዎችም ሆነ ሌሎች ሰዎች አዲሱን ቫይረስ በንቃት ሊከታተሉትና አካሄዱን በደንብ ሊያውቁት ይገባል። በተለይ የዘርፉ ተመራማሪዎች በዚህ ዙሪያ በርካታ ሥራዎች ይጠብቋቸዋል። ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ የተማርነው አንድ ነገር ቢኖር፤ ለጥያቄዎቻችን በሙሉ መልስ እስከምናገኝ ድረስ ዝም ብለን መቀመጥና መጠበቅ እንደሌለብን ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-59594592 +politics የኢትዮጵያ መንግሥት በሱዳን ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ አስታወቀ የኢትዮጵያ መንግሥት በሱዳን የተፈጠረውን ቀውስ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግሥት በሱዳን የሽግግር መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በወታደሮች ቁጥጥር ስር ውለው በአገሪቱ ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ጄነራል አል ቡርሐን አስቸኳይ ጊዜ ማወጃቸውን ተከትሎ ነው መግለጫውን ያወጣው። በሱዳን በተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክና ሚኒስትሮቻቸው በወታደሮች የተያዙ ሲሆን የአገሪቱ የሽግግር ምክር ቤት ተበትኗል። ሚኒስቴሩ በመግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ ከዚህ ቀደሙ ከሱዳን ሕዝብ ጎን እንደሚቆም ገልጿል። ይህም የሁለቱ አገራት ሕዝቦች ለዘመናት ካላቸው ጠንካራ ትስስር የመነጨ ነው ብሏል። በሱዳን ሲቪልና ወታደራዊ አባላትን ያካተተ የጥምር መንግሥት እንዲመሰረት እንዲሁም ለሽግግር ጊዜ የሚሆን ሕገ መንግሥታዊ ሰነድ በማዘጋጀት የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ሚና እንደነበረው መግለጫው አስታውሷል። በመሆኑም ሁሉም ወገኖች በመረጋጋት እና ሁኔታዎችን በማርገብ የተፈጠረው ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የተቻላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። መግለጫው አክሎም የኢትዮጵያ መንግሥት ሱዳን ወደ ዲሞክራሲ የምታደርገውን ሽግግር እንደሚደግፍ እንዲሁም ለሽግግር ጊዜ ያለውን ሕገ መንግሥታዊ ሰነድ እንደሚያከብር ገልጿል። ኢትዮጵያ የሱዳን ሕዝብ የሚፈልገውን ሉዓላዊነት እንዲከበር ፍላጎት እንዳላት የገለፀች ሲሆን በሱዳን የውስጥ ጉዳይ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ አለመግባታቸው አስፈላጊ እንደሆነ አፅንኦት ሰጥታለች። የኢትዮጵያ መንግሥት የሱዳን ሕዝብ የገጠመውን ተግዳሮት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አቅሙ እንዳለው እምነት እንዳለውም ገልጿል። የሱዳን ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፍላጎት እንዲሟላ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከጎናቸው እንደሚቆሙም መግለጫው አስታውቋል። በሱዳን በወታደሮችና በሲቪሎች የሚመራ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም እና አገሪቱ እንድትረጋጋ ኢትዮጵያ በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ የሱዳን ሠራዊት በኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ተይዘው የነበሩትን የድንበር አካባቢዎች ወሮ ከያዘ በኋላ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ሻክሮ ቆይቷል። በሕዳሴው ግድብ ግንባታ እና ውሃ ሙሌት ዙሪያ በቆየው አለመግባባትም ሁለቱ አገራት ሲወቃቀሱ መቆየታቸው ይታወሳል። ባለፈው መስከረም ወር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተሞክሮ መክሸፉ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህንንም ተከትሎ የሽግግር አስተዳደሩን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ቆይቷል። ዛሬ ሰኞ ጠዋት የአገሪቱ ጦር ሠራዊት የሽግግር መንግሥቱን ጠቅላይ ሚኒስትርና ሲቪል አባላትን በቁጥጥር ስር በማድረግ አስተዳደሩን የበተነ ሲሆን የአስቸኳይ ጊዜ አውጇል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ቡድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/news-59042599 +politics በግብፅ የተገኙት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ኢትዮጵያ ሊጓዙ ነው "ከዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በግብፅ ጀመሩ። ላቭሮቭ ከግብፅ ጉብኝት በኋላ ወደ ኮንጎ ብራዛቪል አቅርንተዋል። በማስከተልም ወደ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ እንደሚጓዙ ተገልጿል። ጉዟቸውን በካይሮ የጀመሩት ላቭሮቭ ከግብፁ አቻቸው ሳሚ ሹኩሪ ጋር ተገናኝተው የተነጋገሩ ሲሆን፤ ሩሲያ ለግብፅ የምታቀርበውን ስንዴ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ጦርነት የአረቡ ዓለም አገራት እና አፍሪካ በእህል አቅርቦት እጥረት ክፉኛ ተጎድተዋል። በግብፅ ለአረብ ሊግ አምባሳደሮች ንግግር ያደረጉት ላቭሮብ፣ በአገራቸው ላይ የተጣለው ማዕቀብ በዓለም የምግብ ዋስትና ላይ እያሳደረ ስላለው ተጽእኖ የምዕራባውያን አገራት እውነታውን እያጣመሙ ነው ብለዋል። ""ምዕራባውያን አገራት የበላይነታቸውን በሌሎች ላይ ለመጫን እየሞከሩ ነው"" ሲሉም ከሰዋል። እንዲሁም ሞስኮ የዓለምን የምግብ ቀውስ አስከትላለች የሚለውን ወቀሳ አጣጥለውታል። ምዕራባዊያኑ በሩሲያ ላይ እያደረሱ ያሉትን ዲፕሎማሲያዊ ጫናን ለመመከት ወደ አፍሪካ ጉዞ ማድረግ የጀመሩት ላቭሮቭ፤ ጨምረውም በአገራቸው ላይ የጣሏቸው ማዕቀቦች ዓላማቸው ""ስለ ዩክሬን ሳይሆን ወደፊት ዓለምን ስለመቆጣጠር ነው"" ሲሉ ተናግረዋል። \n\n""እያንዳንዱ ሰው ሕግን መሠረት ያደረገ የዓለም ሥርዓትን መደገፍ አለበት'' ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ሕጎቹም የተፃፉት የምዕራባውያንን ፍላጎት በሚጠቅም መልኩ እና ልዩ ሁኔታዎች ላይ በመመስረት ነው ብለዋል። ዩክሬን እና ሩሲያ ከ40 በመቶ በላይ የሚሆነውን የአፍሪካን ስንዴ ፍላጎት እንደሚያቀርቡ የአፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ ያሳያል።\n\nግብፅ ከፍተኛ የዩክሬን ስንዴ ተጠቃሚ ስትሆን እ.ኤ.አ. በ2019 ከማንኛውም አገር በበለጠ 3.62 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ከዩክሬን ገዝታለች።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cyd43de07jzo +business ኢትዮጵያ ስንዴ ከውጭ ማስገባት ትታ ወደ ውጭ መላክ ትችላለች? በምሥራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ መምሬ መሠረት፣ ከዚህ በፊት ስንዴ ያመርቱ የነበረው በክረምት ዝናብ ብቻ ተጠቅመው ነበር። ማሳቸው ውሃ የሚገባው በመሆኑ በበጋው ወራት ሽንኩርት እና ቲማቲም እያመረቱ ለገበያ ያቀርቡ እንደነበረም ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከሦስት ዓመት በፊት ግን ‘ለምን አዲስ ነገር አልጀምርም’ በማለት በበጋ መስኖ ስንዴ ዘርተው ለማየት ወሰኑ። “ይህ ነገር መሆን አለበት ብዬ በራሴ ተነሳሽነት የበጋ ስንዴ ማምረት ጀመርኩ። በዚያን ወቅት አንድም ሰው በበጋ ስንዴ መዝራት የጀመረ የለም። ፈጣሪ ይመስገን ተሳክቶልኛል” ይላሉ አቶ መምሬ። ይህ የበጋ ስንዴ ምርት ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ እና እየሰፋ እየመጣ መሆኑን አቶ መምሬ አክለው ተናግረዋል። ልክ እንደ አቶ መምሬ ሁሉ የሉሜ ወረዳው አርሶ አደር አቶ እንግዳ ብሩ፣ በበጋ መስኖ ተጠቅመው ጥሩ የስንዴ ምርት እንዳገኙ ይገልጻሉ። እኚህ አርሶ አደር በዚህ ዓመት ብቻ ከስድስት ሄክታር መሬት 320 ኩንታል ስንዴ ማግኘታቸውን ጠቅሰው፣ አዲስ ነገር ስለሆነ በፍርሃት እንደጀመሩት በመግለጽ አቶ እንግዳ “ያገኘነው ምርት ሸጋ ነው”  ብለዋል። ይህ የበጋ ስንዴ ከክረምቱ ወቅት ምርት በላይ ትርፋማ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ እንግዳ ግሪሳ (የወፍ መንጋ)፣ የማዳበሪያ ወጪ እና ነዳጅ መፍትሔ ቢያገኝ ስንዴን በበጋ ማምረት “በጣም ትርፋማ” መሆኑን ገልፀዋል። በመጀመሪያ የምርት ዓመት በአንድ ሄክታር ላይ ብቻ ስንዴ ዘርተው የነበሩት አቶ መምሬ፣ መንግሥት ያቀረበላቸውን ድጋፍ በማየት በዚህ ዓመት ወደ 5 ተኩል ሔክታር አሳድገውታል። የበጋ ስንዴ በክረምት ወቅት ከሚመረተው በተሻለ ምርታማ እንደሆነ የሚናገሩት አርሶ አደሩ፣ ከአንድ ቀርጥ (የሄክታር አንድ አራተኛ) ከ16 ኩንታል በላይ ማግኘት እንደሚቻል ይናገራሉ። አቶ መምሬ እንደሚሉት ከአንድ ሄክታር እስከ 64 ኩንታል ይገኛል። ሽንኩርት እና ቲማቲም ማምረት አቁመው ወደ ስንዴ በመግባታቸው ያለውን ልዩነት ሲገልጹ “ይህ የበጋ ስንዴ ምርት ሥራው አድካሚ አይደለም። ትንሽ ማዳበርያ ብቻ ይፈልጋል እንጂ ሌሎች ብዙ ወጪዎች ስለሌሉበት ትርፋማ ነው” ብለዋል። አቶ መምሬ ካገኙት የበጋ ስንዴ ምርት 250 ኩንታል ያህሉን መንግሥት በጥሩ ዋጋ (በኩንታል 3680) እንደተረከባቸው ጨምረው አስረድተዋል። እንደ አሜሪካ ግብርና ቢሮ መረጃ ከሆነ በኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ዘርፍ ትልቅ እመርታ እያሳየ እና ምርታማነቱ እየጨመረ ነው። የአሜሪካ የውጭ ግብርና ቢሮ ሪፖርት ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2022/2023 ዓመት ውስጥ 5.7 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ታመርታለች ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክቷል። ይህም ካለፈው የምርት ዘመን በ3.26 በመቶ ከፍ ያለ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ሦስት ዓመታት የስንዴ ምርት እንዲጨመር በርካታ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ያስታወሰው ይህ ሪፖርት፤ የኤክስቴንሽን ድጋፍ፣ የመስኖ ልማት፣ በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ የእርሻ ሥርዓት እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶች እንደሚያቀርብም ዘርዝሯል። ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት 70 በመቶ ያህል የአገር ውስጥ ፍላጎቷን የምታመርት ሲሆን፣ 30 በመቶ ያህሉን ደግሞ ከውጭ እንደምታስገባ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከውጭ ከምታስገባው የተወሰነውን ስንዴ የውጭ ምንዛሬ በማውጣት የምትገዛ ሲሆን፣ ቀሪውን ደግሞ ከአሜሪካ በእርዳታ እንደምታገኝ የአሜሪካ የውጭ ግብርና ምርት ቢሮ መረጃ ያሳያል። ኢትዮጵያ በ2023 (እኤአ) ያላትን የስንዴ ፍላጎት በአገር ውስጥ ምርት ለሟሟላት እና ከባሕር ማዶ የምታስገባውን ለማስቀረት አቅዳ እየሰራች መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። ይህንንም ለማሳካት በመላ አገሪቱ ባለፉት ሦስት ዓመታት 1.3 ሚሊዮን አርሶ አደሮች በ30 ሺህ ክላስተር ተደራጅተዋል። እያንዳንዱ ክላስተርም የተሻሻለ ዘር እንዲሁም ለአካባቢው ተስማሚ የሆነ ማዳበርያ እንዲጠቀም ይደረጋል። እንዲሁም የኤክስቴንሽን ሠራተኞች ክትትል እና ድጋፍ በምርት ስብሰባ ወቅትም ብክነት ለመቀነስ የማሽን ድጋፍ ተደርጓል። በኦሮሚያ ግብርና ቢሮ የስንዴ ምርት ጉዳይን የሚከታተሉት ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ፣ ክልሉ በስንዴ ምርት ላይ ዕቅድ አውጥቶ እየሰራ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ጌቱ ገመቹ በበኩላቸው የስንዴ ምርትን ለመጨመር የተያዙትን አራት መሠረታዊ እቅዶች ሲያብራሩ “በምግብ ራስን መቻል፤ ከውጭ የሚገባውን ምርት በአገር ውስጥ ማምረት፣ በአገር ውስጥ የሚመረተውን ደግሞ ወደ ውጪ መላክ እና በእነዚህ ውስጥ የሥራ ዕድል መፍጠር” መሆናቸውን ገልፀዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ጀምሮ እየተሰራ መሆኑን የሚናገሩት ኃላፊው፣ በመጀመሪያው ዓመት ላይ ከምርምር ተቋማት ጋር በመሆን ውጤታማነቱን በምርምር ለማረጋገጥ ተችሏል ይላሉ። ግንቦት 2022 እኤአ የቡድን ሰባት አገራት ሚኒስትሮች በጀርመን ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የተገኙት የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት፣ አክንዊሚ አዲሲና ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ስንዴ ከውጪ እንደማታስገባ ተናግረዋል። የአፍሪካ ልማት ባንክ ለአፍሪካ በሚያቀርበው የግብርና ቴክኖሎጂ ፕሮግራም አማካኝነት የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ለኢትዮጵያ አድርጓል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ምርት በመጨመሯ በዓመት 26 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ምርቷ ማደግ ችሏል ብለዋል። ካለፈው ዓመት ጀመሮ ኢትዮጵያ ከውጭ አለማስገባቷን የሚናገሩት ፕሬዝዳንቱ፣ ለሚቀጥለው ዓመት በ2 ሚሊዮን ሄክታር ላይ ለማምረት ዕቅድ ስላላት ይህንን ምርት በ2023 ለጎረቤት አገራት ጅቡቲ እና ኬንያ ለመሸጥ ማሰቧን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዝብ ተወካዮች በበጋ ስንዴ ከፍተኛ ምርት መገኘቱን ገልፀው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ የስንዴ ምርት እንዴት እንደተገኘ ሲያብራሩ መስኖ እንዲሁም የክላስተር ግብርናን በአስረጂነት ጠቅሰዋል። ምንም እንኳ ኢትዮጵያ የምታመርተውን ስንዴ ብትጨምርም በአገሪቱ ውስጥ በተከሰቱ የተለያዩ ግጭቶች የተነሳ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው የዕለት እርዳታ የሚጠብቁ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው። እንዲሁም ለ19 ወራት የቀጠለውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የምግብ እህል እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥርን ከፍተኛ አድርጎታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን መረጃ እንደሚያሳየው በ2022/2023 ብቻ 10 ሚሊዮን ያህል ሰዎች የዕለት እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን ስንዴ አቁማ ወደ ውጭ መላክ ለመጀመር የያዘችው ዕቅድ አጣብቂኝ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል የሚል ስጋት አጭሯል። ኢትዮጵያ እኤአ በ2023 ከባሕር ማዶ የምታስገባውን ስንዴ ለማቆም ማቀዷን ያስታወሰው የአሜሪካ ግብርና ቢሮ ሪፖርት በበኩሉ ባለው ውስን ሀብት እና ቴክኖሎጂ አንዲሁም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሳካት ያለውን ተግዳሮት ሲገልጽ “ከተጨባጭ እውነታው የራቀ እና ሊሳካ የማይችል” ብሎታል።። ኢትዮጵያ በእርዳታ የምትቀበለውን ስንዴ ጨምሮ በየዓመቱ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ከውጭ ታስገባለች። ለዚህ የስንዴ ግዢም በየዓመቱ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደምታደርግ መረጃዎች ያሳያሉ። የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ኃላፊው አቶ ጌቱ እንደሚሉት በክልላቸው የስንዴ ምርት ከዚህ በፊት ከነበረው ከ42 እስከ 45 በመቶ ጨምሯል። ባለፈው የምርት ዓመት የተገኘው ውጤት በመነሳትም በዚህ ዓመት 607 ሺህ ሄክታር የሚሆነውን በሁለት ዙር ለማምረት እንዳቀዱ የሚናገሩት አቶ ጌቱ፣ በዚህም በክልሉ 17 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ቃል ኪዳን ሽፈራው ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን፣ በዚህ ዓመት ከ40 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን በልዩ ትኩረት በማልማት በበጋ መስኖ ስንዴ እንዲሸፈን መደረጉን ገልፀዋል። አክለውም በ35 ሺህ ሄክታር ላይ የደረሰ ሰብል ተሰብስቦ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል የሚሆን ስንዴ ምርት ተገኝቷል ብለዋል። “ከዚህ በመነሳት ስንዴን ስለወደድን ብቻ ሳይሆን ይህ ሰብል በተለያዩ የአገራችን የተለያዩ አየር ንብረቶች ሁሉ የሚመረት መሆኑን ስተለተረዳን በምግብ ራስን መቻል ብቻ ሳይሆን ወደ ውጭ ለመላክ አንደምንችል አረጋግጠናል” ይላሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cn432yp5rlvo +sports ሮናሊዲኒሆ ሃሰተኛ ፓስፖርት በመያዝ ተጠርጥሮ በፓራጓይ በቁጥጥር ስር ዋለ "እውቁ የቀድሞ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሮናልዲንሆ ወደ ፓራጓይ ለመግባት ሃሰተኛ ፓስፖርት ተጠቅሟል በሚል ጥርጣሬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል። በዚህም ምክንያት የፓራጓይ ፖሊስ ሮናልዲንሆ እና ወንድሙ በፓራጓይ መዲና ያረፉበትን ሆቴል በርብሯል። የፓራጓይ አገር ውስጥ ሚኒስትር ሮናልዲንሆና ወንድሙ እንዳልታሰሩ ነገር ግን ፖሊስ ምርመራ እያደረገባቸው እንዳለ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ እንዳሉት ወንድማማቾቹ የተጠረጠሩበትን ወንጀል ክደዋል፤ በሚደረገው ምርመራ ላይ ግን አስፈላጊውን ትብብር እያደረጉ ነው። ሮናልዲንሆ ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት በታክስ ጉዳይ እንዲሁም በሕገወጥ ግንባታ የተጣለበትን ቅጣት ባለመክፈል የብራዚልና የስፔን ፓስፖርቱን ተነጥቆ ነበር። የፓራጓይ የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ""በእግር ኳስ ችሎታው አደንቀዋለሁ ነገር ግን ማንም ሁን ማን ሕግ ደግሞ መከበር አለበት"" ሲሉ ለአዣንስ ፈራንስ ፕሬስ ተናግረዋል። የ39 ዓመቱ ሮናልዲንሆ ወደ ፓራጓይ ያቀናው አንድ መፅሃፍን ለማስተዋወቅና ስለ ችግረኛ ህፃናት ዘመቻ ለማካሄድ እንደሆነ ተገልጿል። ሮናልዲንሆ እአአ በ2004 እና በ2005 የዓለም ምርጥ የዓመቱ እግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ ተመርጦ ነበር። የሮናልዲንሆ አጠቃላይ ሃብት ከ80 እስከ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ይገመታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-51764736 +politics የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሥልጣናቸውን ማራዘማቸውን ተቃወመ "የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን ማራዘማ��ውን ተቃወመ። ሕብረቱ ልዩ መልዕክተኛ ወደ ሞጋዲሾ በመላክ የፖለቲካ ውጥንቅጡን ለመፍትታ እንደሚሞክርም አስታውቋል። የአፍሪካ ሕብረት ሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ለሰዓታት ዝግ ስብሰባ ካካሄደ በኋላ ነው የሶማሊያን ፖለቲካዊ ችግር እፈታለሁ ያለው። ሐሙስ ዕለት ከተካሄደው ስብሰባ በኋላ የተለቀቀው መግለጫ ሁሉም በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲመክሩ አሳስቧል። ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት መስከረም የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥትና ክልላዊ አስተዳደሮች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች መክረው ነበር። በዚህ ውይይት ወቅት በሶማሊያ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲደረግ ተስሰማምተው ነበር። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት ፕሬዝደንት ፎርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን እንዲራዘም የሚያትት ረቂቅ አፅድቀዋል። የፕሬዝደንቱ አወዛጋቢ ውሳኔ ከብዙዎች ዘንድ ተቃውሞ እንዲገጥማቸው አድርጓል። ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታኒያ፣ የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ሕብረት የፕሬዝደንቱን እርምጃ ከተቃወሙ መካከል ናቸው። ""የመስከረም 2020 ስምምነት ለወደፊቱ ሶማሊያ አዋጭ የሆነ ዕቅድ ይዟል። ይህም ተዓማናኒ ነፃ ምርጫ ማድረግ ነው"" ይላል ሕብረቱ የለቀቀው መግለጫ። የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት የሶማሊያ ፖለቲካዊ አመራሮች ነገሮች የበለጠ የሚያከሩ ድርጊቶች ከመፈፀም እንዲቆጠቡም አሳስቧል። ምክር ቤቱ ይህ ሆነ ማለት የሶማሊያ፣ የአፍሪካ ቀንድና የመላው አፍሪካ ሰላም ደፈረሰ ማለት ነው ሲል በመግለጫ አትቷል። የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት በዝግ ባካሄደው ስብሰባ በቻድ ስላለው ሁኔታም ቢመክርም ለጊዜው ምንም ዓይነት ውሳኔ ላይ አልደረሰም። የቻዱ ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ ከታጣቂዎች ጋር በተደረገ ውጊያ ሕይወታቸው ማለፉን ይታወሳል። የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች በዴቢ ቀብር ላይ ለመገኘት ወደ ቻድ እያመሩ ይገኛሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-56855691 +politics ታሊባን ከምዕራባውያን አገራት ባለሥልጣናት ጋር በኦስሎ ንግግር ጀመረ "ታሊባን ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ምድር ከምዕራባውያን አገራት ባለሥልጣናት ጋር ንግግር ጀመረ። ታሊባን እና ምዕራባውያኑ ባለሥልጣናት ለሦስት ቀናት በሚዘልቅ ውይይታቸው ስለ ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን በተመለከተ ይነጋገራሉ ተብሏል። የተባበሩት መንግሥታት 95 በመቶ የሚሆኑት አፍጋናውያን በቂ ምግብ የላቸውም ይላል። በአሁኑ ወቅት በአፍጋኒስታን የሥራ አጥ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። የምግብ ዋጋ ንሯል፤ የአገሪቱ መገበያያ ገንዘብ ዋጋ እያጣ ነው። ባንኮችም ወጭ በሚደረግ የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ጥለዋል። የተባበሩት መንግሥታት 55 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ለረሃብ ተጋላጭ ነው ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር። ዛሬ ሰኞ ጥር 16/2014 ታሊባን እና ምዕራባውያኑ ጥብቅ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ታሊባን በአሜሪካ ባንኮች ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ የታገደው በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ እንዲለቀቅለት ይጠይቃል ተብሏል። ""ለአፍጋን ሕዝብ ገንዘብ እንዲለቁ እየጠየቅናቸው ነው። በፖለቲካ ልዩነት የአፍጋኒስታን ዜጎች ሊጎዱ አይገባም"" ሲሉ የታሊባን ተወካዩ ሻፊኡላህ አዛም ለአሶሺዬትድ ፕሬስ ተናግረዋል። ተወካዩ በአፋጋኒስታን ተጋርጧል በተባለው ረሃብ እና በአገሪቱ ባለው ከባድ ቅዝቃዜ ምክንያት ዓለም አቀፉ ማሕብረሰብ አፍጋኒስታንን መርዳት እንጂ መቅጣት የለበትም በማለት ጨምረው ተናግረዋል። ታሊባን እና ምዕራባውያኑ በሚያደርጉት ውይይት ላይ የምዕራባውያኑ ተወካዮች ቡድኑ የበለጠ አካታች እንዲሆን እና የሰብዓዊ መብት ጥበቃዎች ላይም ትኩረት ያደርጋሉ። ታሊባን አፍጋኒ���ታንን መልሶ ከተቆጣጠረ ወዲህ ሴት ሠራተኞች በቤት እንዲቆዩ ማዘዙ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪም ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤቶች ለወንድ ተማሪዎች እና ለወንድ መምህራን ብቻ ከፍት ሆነዋል። ይህን የታሊባን ሥርዓት የተቃወሙ በርካታ ሴቶች በቡድኑ ዒላማ ተደርገዋል። አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ አድራሻቸው የጠፉ ሴቶች አሉ። ታሊባን በበኩሉ ከሴቶቹ መጥፋት ጋር የሚያገናኘኝ የለም ይላል። ከመብት ተከራካሪ ሴቶች በተጨማሪ ጋዜጠኞችም በታሊባን ዒላማ ሲደረጉ ቆይተዋል። እስካሁን ድረስ የትኛውም አገር ለአዲሱ የታሊባን መንግሥት እውቅና አልሰጠም። የኖርዌይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አኒከን ሁኢትፌልደት ምዕራባውያን ከታሊባን ጋር የሚያደርጉት ውይይት ቡድኑ ለመሠረትው መንግሥት እውቅና መስጠት አይደለም ብለዋል። የታሊባን እና ምዕራባውያን አገራት ባለሥልጣናት ለውይይት መቀመጥ በአፍጋኒስታን የተከፋፈለ ስሜትን ፈጥሯል። አንዳንዶች ምዕራባውያኑ ከቡድኑ ተወካዮች ጋር መነጋገራቸው መልካም ነው ሱሉ ገሚሱ ደግሞ ታሊባን ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ በአውሮፓ ከተሞች ላይ ለውይይት መጋበዙ ትክክል አይደለም ይላሉ። የውይይቱን መካሄድ የሚቃወሙ ሰልፎች በአውሮፓ ከተሞች ተካሂደዋል።" https://www.bbc.com/amharic/60107886 +politics የደቡብ ሱዳን አመራሮች በሕገወጥ ገንዘብ ዝውውር ተዘፍቀዋል-ተመድ "በደቡብ ሱዳን ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና የንግዱን ዘርፍ እየመሩ ያሉ ግለሰቦች በሕገወጥ መንገድ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በማዘዋወር በአገሪቱ ውስጥ ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው በማለት የተባበሩት መንግሥታት የባለሙያዎች ቡድን ከሰሰ። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እንዳስታወቀው በደቡብ ሱዳን ከአውሮፓውያኑ 2018 ጀምሮ ""የመንግሥት ባለስልጣናትና ከእነሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት ቢያንስ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በሕገወጥ መንገድ አዘዋውረዋል እንዲሁም አጭበርብረዋል"" ብሏል። ይህ ግን በአገሪቱ ውስጥ እየተፈፀመ ያለውን ሕገወጥ ገንዘብ ዝውውር ደረጃን አያሳይም ተብሏል። በአገሪቱ ውስጥ የተንሰራፋው ሙስና ያለውን የሰብዓዊ መብትና የፀጥታ ሁኔታን ያዳክማል ብሏል ሪፖርቱ። ከአውሮፓውያኑ 2018 ጀምሮ 73 ሚሊዮን ዶላር በሕገወጥ መንገድ ተዘዋውሯል። ኮሚሽኑ ይህ አሃዝ ከተዘረፈው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ባጣም ጥቂቱ ነው ብሏል። ""የብዝበዛውንና ዘረፋውን ሁኔታ በምናይበት ወቅት ፖለቲከኞች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ዓለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖች፣ ወታደራዊ አመራሮች እና ዓለም አቀፍ ባንኮች መሳተፋቸውን በግኝታችን ማረጋገጥ ችለናል"" በማለት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ያሲሚን ሱካ ሪፖርቱን በሚያቀርቡበት ወቅት አስረድተዋል። ሪፖርቱ በተጨማሪም የደቡብ ሱዳን የነዳጅ ኢንዱስሪ ""ተጠያቂነት በሌለው የነዳጅ ጥምረት ቡድን"" በበላይነት የሚመራ ሲሆን በዚህም አካቢውን መበከል ጨምሮ ለማኅበረሰቡ ጤና ጠንቅ ሆኗል ብሏል። እንዲህ አይነት ብዝበዛዎችና ዘረፋዎች እየተፈፀሙባት ያለችው ደቡብ ሱዳን ሁለት ሦስተኛ ወይም 7.2 ሚሊዮን የሚሆነው ሕዝቧ ምግብ ለማግኘት በየቀኑ እየታገለ ይገኛል። የባለሙያዎቹን ሪፖርት በተመለከተ የደቡብ ሱዳን መንግሥት የሰጠው ምላሽ የለም።" https://www.bbc.com/amharic/news-58680865 +politics በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የሚደረግ ጫናን የሚቃወሙ ሰልፎች በበርካታ አገራት ተደረጉ "ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በሰሜን አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና እስራኤልን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የምዕራብ አገራትን ጫና በመቃወም ለኢትዮጵያ መንግሥት ያላቸውን ድጋፍ አደባ���ይ በመውጣት ገለጹ። ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት አማጺያን ጋር በሚያደርገው ጦርነት ምዕራባውያን አገራት ለፌደራሉ መንግሥት ድጋፍ እንዲሰጡ ጠይቀዋል። መንግሥታዊው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በ27 ከተሞች የድጋፍ ሰልፉ መካሄዱን ዘግቧል። የድጋፍ ሰልፉ ከተደረገባቸው ከተሞች መካከል፤ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ኒው ዮርክ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ኦስቲን፣ ሂውስተን፣ ቶሮንቶ፣ ኦታዋ፣ ካልጋሪ፣ ዊኒፒግ እና ለንደን ተጠቃሽ ናቸው። የካናዳው ሲቢኤስ ኒውስ በካናዳዋ ማኒቶባ ግዛት ዊኒፒግ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋር በሚያደርገው ጦርነት የካናዳ መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግ አደባባይ ወጥተው ጠይቀዋል ሲል ዘግቧል። በዊኒፒግ ከተማ የተዘጋጀውን የድጋፍ ሰልፍ ካስተባበሩት መካከል አንዱ የሆኑት ማርቆስ ተገኝ፤ ""በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ በተለይ አሜሪካ ጣልቃ መግባት ማቆም አለባት፤ ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው እንዲፈቱ መፍቀድ አለባት"" ሲሉ ሲቢኤስ ኒውስ ተናግረዋል። በሌላኛዋ የካናዳ ከተማ ካልጋሪ ተመሳሳይ የድጋፍ ሰልፍ መካሄዱን ሲቲቪ ኒውስ ካልጋሪ ዘግቧል። ለፌደራሉ መንግሥት ድጋፍ ለመስጠት በተጠራው ሰልፍ ላይ ሰዎች #NoMore (ከአሁን በኋላ ይብቃ) እንዲሁም #Handsoff (እጃችሁን አንሱ) የሚሉ መፈክሮችን ይዘው መውጣታቸው ሲቲቪ ኒውስ ካልጋሪ አሳይቷል። በተመሳሳይ በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ኦስቲን ከተማ ተመሳሳይ ድጋፍ አድርገዋል። ""እነዚህ በኢትዮጵያ ያሉ ጉዳዮች ናቸው፤ እራሳችን መፍታት እንችላለን። እዚህ የተገኘነው እባካችሁ አቁሙ፤ የራሳችንን ጉዳይ እራሳችን እንፈታዋለን ለማለት"" በማለት የኦስቲን ሰልፍ ተሳታፊ የሆነው ቴድ ኃይሉ ለሲቢኤስ ኦስቲን ተናግሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በተለያዩ ከተሞች የተካሄዱ ሰልፎችን የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን በማጋራት ""...ለእውነት ለቆሙ ኢትዮጵያውያን እና የአፍሪካ ቀንድ ዳያስፖራዎች አድናቆቴን እገልጻለሁ"" ብለዋል። በየአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በኢትዮጵያውያን መንግሥትን በመደገፍ ሰልፍ የተደረገበትን የትናንቱን ቀን ""በኢትዮጵያ የዲያስፖራ ታሪካዊ ቀን ነው"" ሲሉ ትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። በአውሮፓ እና አሜሪካ በሚገኙ ከተሞች ከተደረጉት የድጋፍ ሰልፎች በተጨማሪ፤ በትዊተር ላይ ሰዎች ደምጻቸውን ለማሰማት አደባባይ ይዘው የወጡት #Handsoff መፈክር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ጊዜ ሪትዊት ተደርጓል። የውጭ ጣልቃ ገብነት የፌደራሉ መንግሥት ከህወሓት አማጺያን ጋር እያደረገ ያለው ጦርነት በድርድር እንዲፈታ ምዕራባውያን አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። የአሜሪካ መንግሥት አስተዳደር ጦርነቱ ይቁም ከማለት ባሻገር በጦርነቱ ተሳታፊ ናቸው አልያም ጦርነቱ እንዲራዘም ምክንያት ናቸው ባለቸው ግለሰቦች ላይ እቀባ መጣሉ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል ያለቻቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያን ብዙ ከምትጠቀምበት ከአጎዋ የንግድ ስምምነት ለማገድ መወሰኗ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ወደ ትግራዩ ጦነርት ተገዶ መግባቱን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ምዕራባውያን በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት እንዲቆምና ሰብአዊ እርዳታ በችግር ላይ ላሉ ሰዎች ያለገደብ እንዲደርስ ጫና እያደረጉ መሆናቸውን ቢገልጹም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ለአማጺያን ድጋፍ በማድረግ የመንግሥት ለውጥ እንዲመጣ እየሞከሩ ነው ሲል ይከሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59370730 +health ኮሮናቫይረስ፡ የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት በህጻናት ላይ ሊሞከር ነው የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት በህጻናት ላይ ምን ያህል ውጤታማ ይሆናል የሚለውን ለማጣራት አዲስ የክትባት ሙከራ መጀመሩ ተገልጿል። የመጀመሪያዎቹ ዙር የክትባት ሙከራዎች በያዝነው ወር መጨረሻ አካባቢ የሚጀመሩ ሲሆን በነዚህ ሙከራዎችም እስከ 300 የሚደርሱ በጎ ፈቃደኛ ህጻናት ይሳተፋሉ ተብሏል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ይህ ሙከራ እድሜያቸው ከ6 እስከ 17 የሆኑ ህጻናት የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባትን ከወሰዱ በኋላ ምን ያህል የመከላከል አቅማቸው ይጠነክራል የሚለውን ለማወቅ ወሳኝ ነው። ይህ ክትባት ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በኮሮረናቫይረስ ምክንያት የሚከሰት ከፍተኛ ህመምን አልያም ሞትን ለመቀነስ ጥቅም ላይ እየዋለ ሲሆን የፋይዘር-ባዮንቴክ ክትባትም ቢሆን ለተመሳሳይ አገልግሎት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። በህጻናቱ ላይ በሚደረገው ሙከራ እስከ 240 የሚደርሱት ተሳታፉዎች የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባትን እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ የማጅራት ገትር መድሀኒት በተመጠነ መልኩ እንዲወስዱ ይደረጋሉ ተብሏል። የክትባት ሙከራው በሚደረግባቸው አራት ማዕከላት፤ ዩኒርሲቲ ኦፈ ኦክስፎርድ፣ ሴንት ጆርጅ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል፣ ለንደን፣ ሳውዝሀም[ፕተን ዩኒቨርሲቲተ ሆስፒታል እና ብሪስቶል የህጻናት ሆስፒታል አቅራቢያ የሚኖሩ በጎ ፈቃደኞች በቶሎ እንዲመዘገቡ ተጠይቀዋል። ለመሳተፍ በጎ ፈቃደኛ የሆኑት ህጻናት ሙከራው ከመጀመሩ በፊት ግን ለይቶ ማቆያ መግባት ግዴታ እንደሆነ ተነግሯል። በዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባትን ለህጻናት ለመስጠት ምንም የታሰበ ነገር እንደሌለ የተገለጸ ሲሆን ለጊዜው ግን እድሜያቸው ከ28 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው ክትባቱን እየወሰዱ የሚገኙት። የፋይዘር-ባዮንቴክ ክትባት ደግሞ እድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች ተፈቅዷል። በክትባቱ አሰጣጥ ስርአት መሰረት እድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችና ህጻናት በጠና ቢታመሙ እንኳን ክትባቱ አይሰጣቸውም። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ እድሜያቸው ከ6 እስከ 17 ለሆኑ ህጻናት ክትባቱን መስጠት ምን አይነት አሉታዊና አዎንታዊ ተጽዕኖዎች እንደሚኖሩት ለማወቅ የሚደረገው ይህ ሙከራ የመጀመሪያው ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ በርካታ ሙከራዎች እንደሚደረጉ አስታውቋል። https://www.bbc.com/amharic/news-56059659 +sports ቼልሲ አሰልጣኙን ቶማስ ቱህልን አሰናበተ የእንግሊዙ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ ቼልሲ አሰልጣኙን ቶማስ ቱህልን አሰናበተ። አሰልጣኝ ቱህል የተሰናበቱት በ2022/23 የውድድር ዓመት በመጀመሪያ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ከተሸነፉ በኋላ ነው። የጀርመናዊው አሰልጣኝ ቡድን ቼልሲ ትናንት ማክሰኞች ጳጉሜ 2/2014 ዓ.ም. ወደ ክሮሺያ ተጉዞ በዳይናሞ ዛግሬብ 1 ለ 0 ተሸንፏል። አሰልጣኙ በቼልሲ ቆይታቸው ቻምፒንስ ሊግ፣ ሱፐር ካፕ እና የክለቦች የዓለም ዋንጫን ማንሳት ችለዋል። ክለቡ የቱህልን መሰናበት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ለቼልሲ አዲስ አሰልጣኝ እስኪሰየም ድረስ የልምምድ እና ወደፊት የሚካሄዱ ጨዋታዎች ዝግጅትን የክለቡ አሰልጣኞች ቡድን ይመራዋል ብሏል። ቱህል 100ኛ የቼልሲ ጨዋታቸውን ነበር ትላንት ምሽት ያከናወኑት። ባለፉት 7 ጨዋታዎች ሦስቱን አሸንፈው በአንዱ አቻ ሲለያዩ በቀሪዎቹ ተሸንፈዋል። ቡድኑ በመጪው ቅዳሜ ከፉልሃም ጋር ይጫወታል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cldz5xk91g2o +business ኮሮናቫይረስ፡ 300ሺህ አፍሪካውያን በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ-የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን "የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ያለበቂ መከላከያ 300ሺህ አፍሪካውያን በኮሮና ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ይገመታል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ አስታወቀ። የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካውያን ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት በገመመገመበት በዚህ መግለጫ ከሰው ህይወት በተጨማሪ የአህጉሪቷን ምጣኔ ኃብት እያሽመደመደው እንደሆነም አስፍሯል። በዚህ አመት የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በ3.2 በመቶ ያድጋል ተብሎ የተገመተ ቢሆንም ቫይረሱ ባደረሰው ጫና ምክንያት ምናልባት 1.8 በመቶ ሊያድግ ይችላል ብሏል። ይህም ሁኔታ 27 ሚሊዮን ህዝብን ለረሃብ እንደሚያጋልጥ የኮሚሽኑ መግለጫ ጠቁሟል። • መንግሥታት ከተሜውን ከኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዲታደጉ ጥሪ ቀረበ • ኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ምጣኔ ሐብታዊ ጫና ትተርፋለች? • አገራትን ጭምብል እስከመሰራረቅ ያደረሳቸው የኮሮናቫይረስ ዲፕሎማሲ ኮሚሽኑ ነገ ይፋ በሚያደርገው ሪፖርት ቫይረሱ ካስተለው ቀውስ ጋር ተያይዞም ደካማ የሚባለው የአህጉሪቷጤና ስርዓት ለተጨማሪ ወጪ እንደሚዳረግም አስገንዝቧል። እስካሁን ባለው መረጃ በአህጉሪቷ ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16 ሺ ሲሆን 800 ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ይህ ቁጥር እየጨመረ ሊሄድ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የአህጉሪቱ የጤና ስርአትም ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ መግለጫው አመላክቷል። ይህንንም ለመታደግ የመንግሥታት ቁርጠኝነት እንዲሁም ድጋፍ እንደሚገባም የኮሚሽኑ ዋና ፀሐፊ ቬራ ሶንግዌ ገልፀዋል። "" የአህጉሪቱን የጋራ ብልጽግና ለመከላከልና ለመንባት፤ መንግሥታት ለዜጎቻቸው በአስቸኳይ መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ማቅረብ እንዲችሉ 100 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል"" ብለዋል "" የወረርሽኙ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ቫይረሱ በቀጥታ ከሚያደርሰው ጉዳት የበለጠ ነው"" ያሉት ፀሐፊዋ በአፍሪካ አገራት በአጠቃላይ ምጣኔ ሃብታቸው ቫይረሱ እንደተከሰተ መጎዳት መጀመሩን ገልጠዋል። ""ወረርሽኙን ለመከላከል ተብሎ የተቀመጠው አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን እግር ተወርች አስሯል"" ሲሉ አስረድተዋል የኮሚሽኑ ሪፖርት አክሎም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ካልተደረገላቸው በስተቀር ሙሉ በሙሉ እንደሚዘጉ አትቷል። የአፍሪካን ምጣኔ ሃብት 40 በመቶ የሚሸፍነው ዘይት በግማሽ ዋጋው መቀነሱን፣ በዋነኝነት አፍሪካ ወደውጪ የምትልካቸው የጨርቃ ጨርቅና አበባ ምርቶችም መውደቃቸውን ጠቅሷል። ቱሪዝም የአንዳንድ የአፍሪካ አገራት አጠቃላይ ብሔራዊ ምርትን 38 በመቶ ቢይዝም አየር መንገዶች ስራቸውን በማቋረጣቸው ምክንያት ሙሉ በሙሉ ቆሟል ሲል ያትታል። የአፍሪካ ምጣኔ ሃብት የተሳሰረ ነው ያለው ሪፖርቱ ለቀውሱም የምንሰጠው ምላሽ "" ወደ አንድ ሊያመጣን ይገባል"" ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/52293148 +health እስካሁን በኮሮናቫይረስ ያልተያዙ ሰዎች ለምን ሳይያዙ ቆዩ? የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተከስቶ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በሁሉም አገራት የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህመም፣ ከተወሳሰበ የጤና ችግር እና ለሞት ዳርጓል። ይህ በሽታ ከተከሰተ ሁለት ዓመት ያለፈው ሲሆን ከመተላለፊያ መንገዶቹ አመቺነት የተነሳ በአጭር ጊዜ መላውን ዓለም አዳርሷል። አንዳንዶች እንዲያውም አብዛኛው የዓለም ሕዝብ በበሽታው የመያዝ ዕድል አለው ይላሉ። ከወረርሽኙ የስርጭት ፍጥነት እና ስፋት አንጻር በርካቶች ለቫይረሱ የተጋለጡ ቢሆንም፣ ተጋላጭ ቢሆኑም በርካቶች አስካሁን በሽታው አልያዛቸውም ይባላል። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው? https://www.bbc.com/amharic/articles/ce9ne2g26qeo +politics ትግራይ፡ የትግራይ ቴሌቪዥን ���ዜጠኛ ዳዊት ከበደና ጓደኛው በመቀለ ከተማ ተገደሉ "የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደ አርአያ ወደ ሥራው ከተመለሰ ከቀናት በኋላ በመቀለ ከተማ ውስጥ ተገድሎ መገኘቱ ተዘገበ ። የሥራ ባልደረቦቹ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በሚያስተዳድረው ቴሌቪዥን ጣቢያ በጋዜጠኝነት ይሰራ የነበረው ዳዊት ተገድሎ የተገኘው ረቡዕ ዕለት ጥር 12/ 2013 ዓ.ም በመኪና ውስጥ ነው። ከዳዊት ከበደም አርአያ በተጨማሪ አንድ ሌላ ጓደኛውም መቀሌ ውስጥ በምትገኝ አዲ ሃውሲ በምትባል ሰፈር መገደላቸውን ባልደረቦቹ ተናግረዋል። የቀይ መስቀል ሠራተኞች የዳዊትንና አብሮት የነበረውን ግለሰብ አስከሬን ካነሱ በኋላ በትግራይ ቴሌቪዥን ለሚሰሩ የሥረራ ባልደረቦቹ ማሳወቃቸውም ተጠቅሷል። ስለ ግድያው እስካሁን ድረስ ክልሉን ከሚያስተዳድሩት ባለስልጣናት የተሰጠ መረጃ የለም። አዲስ በተቋቋመው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የደኅንነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዋልታ ሐረጎትን ስለ ጋዜጠኛው አሟሟት ቢቢሲ በጠየቃቸው ወቅት ምንም መረጃ እንደሌላቸውና፤ መረጃዎችን ሰብስበውና አጠናቅረው ይፋ እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል። ስሜ አይጠቀስ ያለ አንድ የዳዊት የሥራ ባልደረባ ለቢቢሲ ትግርኛ እንደተናገረው ሁለቱ ግለሰቦች የተገደሉት በተተኮሰባቸው ጥይት ነው። ይህንን መረጃ ከአካባቢው የፀጥታና ደኅንነት ኃላፊዎች ማረጋገጥ አልተቻለም። ሁለተኛው የተገደለው ግለሰብ ማንነትንም በተመለከተ ቢቢሲ ባደረገው ማጣራት በትግራይ ቴሌቪዥን የሚሰራ ሌላ ጋዜጠኛ ወንድም መሆኑን መረዳት ችሏል። ወደ ሥራ መመለስ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት በተፋፋመበት በኅዳር ወር ሥራ አቋርጦ እንደነበር የተነገረው ዳዊት ከበደ አርአያ በቅርቡ ወደ ሥራው ተመልሶ ነበር ተብሏል። የመከላከያ ሠራዊት መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ተቋርጦ የነበረውም የክልሉ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ስርጭት መተላለፍ የጀመረ ሲሆን ሠራተኞቹም ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አድርጓል። ዳዊት ወደ ሥራ ተመልሶ ቢሮ በገባበት ወቅት ተይዞ ለቀናትም ያህል በቁጥጥር ስር የነበረ መሆኑን አንድ በቴሌቪዥን ጣቢያ የሥራ ባልደረባው አሳውቀዋል። እስሩን በተመለከተ የአካባቢው ባለስልጣናት ያሉት ነገር ባይኖርም የሥራ ባልደረባው ግን ከመገደሉ በፊት ለሦስት ቀናት በእስር ላይ እንደነበረ ተናግረዋል። ""የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳዳሪዎች የቀድሞ ጋዜጠኞችንና የካሜራ ባለሙያዎችን እያናገሩ ነበር። ካናገሩዋቸው ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ዳዊት ነው"" በማለትም ባልደረባው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከህዳር 19/2013 ዓ.ም ጀምሮ በመከላከያ ቁጥጥር ስር ባለችው መቀለ የምሽት ሰዓት እላፊ የተጣለ ሲሆን በዚያ ሰዓትም በከተማው ማንኛውም እንቅስቃሴ የተከለከለ ነው። ዳዊት ከበደ አርአያ ማን ነው? ዳዊት በትግራይ ቴሌቪዥን ተቀጥሮ ከመስራቱ በፊት ለበርካታ ዓመታት በብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢቲቪ ሰርቷል። ኢቲቪን ከለቀቀ በኋላ የራሱን የትግርኛ መፅሔት በማቋቋም ለበርካታ ዓመታት ፅሁፍ ሲያበረክት ነበር። በኋላም ባለፈው ዓመት እስከ ተዘጋበት ድረስ አዲስ አበባ በሚገኘው የትግራይ ቴሌቪዥን ቅርንጫፍ ውስጥ እያገለገለ ነበር። የአዲስ አበባ ቅርንጫፉን መዘጋት ተከትሎ መቀለ ወደሚገኘውም ዋና ጣቢያ በመመለስ በቴሌቪዥን ጣቢያው ሲሰራ ነበር። የሁለቱ፣ የዳዊትና አብሮት የነበረው ግለሰብ የሥርዓተ ቀብር በትናንትናው ዕለት ጥር 12/ 2013 ዓ.ም አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55745102 +politics "ሩሲያ፡ የፑቲን ባላንጣ አሌክሴ አገሩ ሲገባ ""የእስር አቀባበል"" ተደረገለት" "የሩሲያው ቭላድሚር ��ቲን የሰላ ተቺ ነው የሚባለው አሌክሴ ናቫልኒ ታሰረ። አሌክሴ የታሰረው ከጀርመን ወደ ሩሲያ በገባበት ቅጽበት ነው። አሌክሴ በአደገኛ መርዝ የግድያ ሙከራ ተደርጎበት በተአምር ከተረፈ ወዲህ ነው በድጋሚ ወደ አገሩ ሩሲያ የተመለሰው። ብዙዎች አሌክሴ ወደ ሩሲያ ከተመለሰ ሊገደል ስለሚችል ሐሳቡን እንዲቀይር ቢወተውቱትም እሱ ግን አሻፈረኝ ብሏል። የ44 ዓመቱ አሌክሴ ናቫልኒ ልክ ሼርሜትዯቮ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርስ፣ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎታል። አብራው የነበረችው ሚስቱን ጉንጮቿን ስሞ በፖሊስ ታጅቦ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስዷል። አሌክሴ ወደ ሩሲያ ለመመለስ ሲወስን በሺህ የሚቆጠሩ ደጋፊዎቹ በሞስኮ አየር ማረፍያ በጉጉት ሲጠብቁትና ደማቅ አቀባበል ሊያደርጉለት ነበር። ሆኖም እሱ የተሳፈረበት ከጀርመን የተነሳው አውሮፕላን አቅጣጫውን እንዲቀይር ተገዷል። ይህም ከደጋፊዎቹ ጋር እንዳይገናኝ የሩሲያ ባለሥልጣናት ያደረጉት ነው። የቭላድሚር ፑቲን ተቀናቃኝ አሌክሴ ከ5 ወራት በፊት የመረዙኝ እሳቸው ናቸው ይላል። ክሬምሊን በበኩሉ እጄ የለበትም ሲል ያስተባብላል። አሌክሴ በአደገኛ የነርቭ መርዝ መመረዙን የጀርመን ሐኪሞች አረጋግጠዋል። ይህን ሊያደርጉ አቅሙ ያላቸው ቭላድሚር ፑቲንና አስተዳደራቸው ብቻ ስለመሆኑ ደግሞ በርካታ የምርመራ ጋዜጠኞች አረጋግጠዋል። የአሌክሴ ናቫልኒ ወደ ሩሲያ መመለስ ዓለምን ያስገረመ ጉዳይ ሆኖ የሚጠበቀው እስሩ እንደተሰማ ግን የአውሮጳ ኅብረት፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ሌሎች በርካታ አገሮች ድርጊቱን አውግዘዋል። ከሰሞኑ ነጩ ቤተ መንግሥት የሚገቡት 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ተመራጭ ጆ ባይደን የመረጧቸው የደኅንነት አማካሪ ጃክ ሰሊቫን፣ የሩሲያ ድርጊት ያፈጠጠ የሰብአዊ መብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን የሩሲያን ሕዝብ ድምጽ የማፈን ተግባር ነው ሲሉ ኮንነዋል። አሌክሴ ባለፈው ነሐሴ ወር የአገር ውስጥ በረራ ላይ ሳለ አውሮፕላን ውስጥ ራሱን ሲስት፣ በሰርቢያ ሕክምና ከጀመረ በኋላ ወደ ጀርመን ለተሻለ ሕክምና ተወስዶ ነበር። በርካቶች ግን ሕይወቱ ትተርፋለች አላሉም። ሆኖም ውጤታማ ሕክምና አድርጎ ነፍሱ ከተመለሰች በኋላ ትናንት እሑድ ወደ ሩሲያ ሲሳፈር ብዙዎችን አስደንግጧል። እሱ ወደ ሩሲያ የተሳፈረበት አውሮፕላን በርካታ ጋዜጠኞች ተሞልቶ ነበር። የኛ የቢቢሲ ዘጋቢ አንድሬ ኮዜንኮ ከተሳፋሪዎቹ አንዱ ነበር። ልክ አውሮፕላኑ ሊያርፍ ሲቃረብ ግን ፓይለቱ ""የቴክኒክ ችግር ስለገጠመን"" በሚል ከቭኑኮቮ አየር ማረፍያ ወደ ሼርሜትየቮ መዳረሻችንን ቀይረናል ሲል አስታውቋል። አሌክሴ አየር ማረፍያው እንደደረሰ ፖሊሶች ሲከቡት ""ብዙ አስጠበቅኳችሁ እንዴ ሲል መቀለዱ ተዘግቧል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55700764 +politics የጀርመን አካል ሆና ለጀርመን ዕውቅና ያልሰጠቸው 'ቀበሌ' ሰሞኑን በጀርመን መፈንቅለ መንግሥት ሴራ ተጎንጉኗል በሚል በርካቶች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ይህ የአፍሪካ ብቻ ዜና የሚመስለው ነገር እንዴት በጀርመን ተሰማ ያሉ ብዙ ናቸው። በምሥራቅ ጀርመን የምትገኘውን ‘ደችላንድ’ ስለማያውቋት ነው እንደዚያ ያሉት። የዚህ መንደር ልብ ተራራ ነው። ይቺ ትንሽ ቀበሌ ራሷን 'የጀርምን ሥርወ መንግሥት' እያለች ነው የምትጠራው። የሰሞኑ መፈንቅለ መንግሥት ጎንጓኞች የዚህች ቀበሌ አማኞች እንደሆኑ ይጠረጠራል። ወደዚች መንደር ስትጠጉ ያልተሰመረ ድንበር አለ፤ የማይታይ። በሰዎች ልብ ውስጥ ብቻ የሚኖር። ቀበሌዋ መግቢያ ላይ የተሰቀለው ማስታወቂያ ‘እንኳን ወደ ጀርመን ግዛት በሰላም መጡ’ ይላል። በአገሬው ቋንቋ እንዲህ ይላል። Königreich Deutschland- የደቾች አገር፤ የደቾች ምደር እንደማለት ነው። የጀርመ�� ሥርወ መንግሥት ብለው ራሳቸውን ሲጠሩ በታላቅ ኩራት ነው። ይህ ለብዙዎች ፌዝ ሊሆን ይችላል፤ ለቀበሌዋ ነዋሪዎች ግን የምር ነው። የራሳቸው ንጉሥ ሁሉ አላቸው። የንጉሡ ስም ‘ቀዳማዊ ንጉሥ ጴጥሮስ” ይባላል። ይህ ንጉሥ የቢቢሲ ጋዜጠኞች መሆናችንን አውቆ በታላቅ አክብሮት ጣሪያና ግድግዳው በጣውላ በተሠራ አዳራሽ ተቀበለን። ልብ ልትሉ የሚገባው ታዲያ 'ቀዳማዊ ጴጥሮስ' በዚህች ጠባብ አዳራሽ ነበር ከ12 ዓመት በፊት በዓለ ሲመቱ የተከናወነው። በዓለ ሲመቱን ያከናወኑለት መቶ የማይሞሉ የቀበሌዋ ነዋሪዎች ናቸው። በቃ ንጉሣችን አንተ ነህ አሉት። 'ዓለምን የተሻለች ላደርጋት ቃል ገብቻለሁ' አላቸው። ከዚያ ወዲያ ባሉ ዓመታት ታዲያ ለዋናዋ አገር ለጀርመን ብዙም ዕውቅና ሳይሰጥ፣ ብዙም ፊት ሳይሰጥ ራሱን 'ንጉሥ' አድርጎ ቀበሌዋን ቀጥ አድርጎ እየመራት ይገኛል። የራሱን መገበያያ ገንዘብ ሁሉ ማተም ጀምሯል። የቀበሌዋ ነዋሪዎች የራሳቸው ባንዲራ አላቸው። የራሳቸው የዜግነት መታወቂያም ማተም ጀምረዋል። ወደየትም ባይወስድም። ብዙዎቹ ጀርመናዊያን 'ቀዳማዊ ንጉሥ ጴጥሮስንና ተከታዮቹን የቀልድና ቧልት ምንጫቸው አድርገው ነበር የሚያይዋቸው። እስከባለፈው ሳምንት ድረስ። በጀርመን ሊፈጸም የነበረው መፈንቅለ መንግሥት ሴራው የተጠነሰሰው ከዚህ ንጉሥ ተከታዮች መካከል ባሉ ሴረኞች እንደሆነ ከተነገረ በኋላ ግን ከባድ ድንጋጤ ተፈጥሯል። ‘ንጉሥ ቀዳማዊ ጴጥሮስ’ ግን በነገሩ የለሁበትም፤ እጄ ንጹሕ ነው ብሏል። ይህ መንደርና ተከታዮቹ ዓለም በውሸታሞችና ገንዘብ አምላኪዎች እየተሽከረከረች ነው ብሎ ያምናል። በዓለም ላይ የሚመረቱ መድኃኒቶች ዉሸት ናቸው ብለው ያምናሉ። ለምሳሌ በመንደሪቱ ያሉ ‘ዜጎች’ አንዳቸውም የኮቪድ-19 ክትባት አልወሰዱም። እንዲያውም በካፒታሊዝም ሥርዓት በፍጹም አያምኑም። ቀዳማዊ ጴጥሮስ አሁን 'ዜጎቼ' የሚላቸው ተከታዮቹ 5ሺህ ደርሰውልኛል ይላል። የጀርመን ፖሊስ ግን እነዚህ ሰዎች አሻጥረኞች ናቸው ይላቸዋል። በሳይንስ አያምኑም። አሁን ዓለም ላይ በቆመው የአስተዳደር ሥርዓት አያምኑም። ካፒታሊዝም ጥቂቶችን ለማበልጸግ፤ ሰፊውን ሕዝብ ለማቆርቆዝ ነው የተዋቀረው ይላሉ። እነዚህ የማይጨበጥ ‘አሻጥር ሽረባ’ አማኞች 21ሺህ ደርሰዋል ይላል ፖሊስ። ባለፈው ሳምንት ፖሊስ 25 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አውሏል። የጀርመን ፓርላማን ለማውደም፤ መራሔ መንግሥቱንና ሚኒስትሮቻቸውን ለመግደል ሲያሴሩ ነበር ይላል ፖሊስ። የቢቢሲ ጋዜጠኞች ራሱን ‘ንጉሥ ጴጥሮስ ቀዳማዊ’ ብሎ ከሚጠራው ሰው ጋር ጉብኝት እያደረጉ ነው። ሆኖም አንድ ሰው እየተከታተለ ሁሉን ነገር ይቀርጻል። ለምን ሁሉ ነገር እንደሚቀረጽ ሲጠየቅ ቀሪው ዓለም ስለኛ የሚያሰራጨውን የሐሰት መረጃ ለመቋቋም ነው ይላል። የራሱን የቴሌቪዥን ጣቢያ ለመጀመርም እየተሰናዳ ነው። የዚህ ንጉሥ ነኝ ባይ ዕውነተኛ ስም ፒተር ፊዘር ነው። ከዚህ ቀደም ከንቲባ ለመሆን ተወዳድሯል። ፓርላማ ለመግባት ተወዳድሯል። አልተሳካለትም። ያልተሳካልኝ የተገነባዋው ሥርዓት እኔን ለመቀበል ዝግጁ ስላልሆነ ነው፤ ዓለም ለለውጥ ግዝጁ አይደለም ይላል። ከዚያ ወዲያ ነበር የራሱን 'ጀርመን' በራሱ አምሳያ ለመፍጠር የተነሳው። ለእሱ ትክክለኛዋ የጀርመን ሥርወ መንግሥት እሱ የመሠረታት መንደር ናት። እርግጥ ነው ጀርመን እንዲህ ዓይነት ራሱን የቻለ ትንሽ መንግሥት መመሥረትን አትፈቅድም። ነገር ግን መንደሪቱ የሕግ ክፍተቶችን በመጠቀም፣ የራሷ የጤና ሥርዓት እስከመመሥረት ደርሳለች። ፒተር መኪና ሲያሽከረክር ያለ መንጃ ፍቃድ በመሆኑ ብዙ ጊዜ ተከሷል። ለዓመታት እስር ቤት ተወርውሯል። ‘���ጎቼ’ የሚላቸው ተከታዯቹን አጭበርብሯል በሚልም ዘብጥያ ወርዷል። ይህን ሁሉ አልፎ አዲስ ሥርዓት- አዲስ ግዛት ለመመሥረት ይታትራል። አሁን ቀን ተሌት የጀርመን ፖሊስ ይከታተለዋል። እሱ ግን የንግሥና ክብሩን ጠብቆ ‘ዜጎቼ’ ለሚላቸው፤ ለሚያምኑትና ለሚያምናቸው ሰዎች ማገልገሉን ቀጥሎበታል። ዜጎቼ የሚላቸው በካፒታሊዝም ሥርዓት ማመን የተውትን ነው። በተለይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተከታዮቹን ብዛት እጥፍ አድርጎለታል። ሰዎች ክትባት መከተብ እንደሌለባቸው ይመክራል። አሁን ባለው ገንዘብ ሰፋፊ መሬት እየገዛ 'የጀርመን ሥርወ መንግሥትን' እያፋፋ ነው። አዲሱ የጀርመን ሥርወ መንግሥት ሰዎች የማይበዘበዙበት፤ ደስታና ፍሰሐ የሚዘንብበት ይሆናል ይላል። ከነዚህ ግዛቴ ከሚላቸው አንዱ ባርዋልዴ መንደር ይባላል። ከበርሊን ወደ ደቡብ የአንድ ሰዓት የመኪና ጉዞ ነው። ቤቶቹ አሮጌና ጥንታዊ ናቸው። ሆኖም ነዋሪዎች ደስተኞችና ተስፈኞች ይመስላሉ። ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት አይልኩም። ግብር አይከፍሉም። በጀርመን ሁለቱም ከባድ ወንጀሎች ናቸው። እንዴት እንደሚያመልጧቸው እንጃ። 'ንጉሥ ጴጥሮስ ቀዳማዊ’ እንደሚለው አሁን የራሳቸውን የጤናና የሕግ ሥርዓት እያበጁ ነው። የርሱ አስተዳደር ለ 'ዜጎቹ' አስፈላጊውን ምግብ ያቀርባል። አሁን በቀጣይነት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ዘላቂ አረንጓዴ ልማት ለማምጣት፤ የራሳቸውን መድኃኒት ለማምረት ዕቅድ አላቸው። “እኛን ብዙ ሰው የሴራ ተንታኞች አድርጎ እያሰበ ያወግዘናል፤ ስለ ዓለም በተጨነቅን፤ ስለ ሕዝብ ባሰብን እንወገዛለን፤ ነገር ግን ብዙዎቻችን ማታ ሲያቃዠን የሚውለው የግል ጉዳያችን ሳይሆን የኅብረተሰብ ችግር ነው” ይላል። እነ ‘ንጉሥ ጴጥሮስ ቀዳማዊ’ና ተከታዮቹ ለጀርመን ብሔራዊ ቧልቶች ሆነው ቆይተዋል። ከዚህ ወዲያ ግን እንዲያ አይቀጥልም። ምክንያቱም ሁሉም ነገር ሲጠነሰስ እንዲያ ነበር። ሒትለርም ከአንድ ስብሰባ ተነስቶ ነው ዓለምን በእሳት የቀቀለው። ይህ ደግሞ ለጀርመናዊያን የ80 ዓመት መጥፎ ትዝታ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c6p6l5064pyo +health ኮሮናቫይረስ፡ የሱዳን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸው አለፈ የሱዳን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አል ማህዲ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሦስት ሳምንታት ያህል በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሆስፒታል ገብተው ሕክምና ሲደረግላቸው እንደነበር ቤተሰቦቻቸውና ብሔራዊው ኡማ ፓርቲያቸው ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። እዚያው ሕክምና ሲከታተሉ በነበሩበት ነው ሐሙስ ዕለት ሕይወታቸው ያለፈው። ማህዲ ሆስፒታል የገቡት በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ የአል ማህዲ 21 የቤተሰብ አባላት በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነበር። የ84 ዓመቱ ማህዲ በአውሮፓውያኑ 1989 በቀድሞው የአገሪቷ ፕሬዚደንት ኦማር ኣል በሽር በተመራ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ሲወገዱ የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ የመጨረሻው ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ። እርሳቸው ይመሩት የነበረው ኡማ ፓርቲም በፕሬዚደንት አልበሽር አስተዳዳር ሥር ከነበሩ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዱ ነበር። ማህዲ ምንም እንኳን አልበሽር ባለፈው ዓመት በተነሳ ሕዝባዊ ተቃውሞ ከሥልጣን ቢወገዱም በአገሪቷ ተፅእኖ ፈጣሪ ሰው እንደነበሩ ይነገርላቸዋል። ሕልፈታቸውን ተከትሎም አገሪቷን እያስተዳደረ ያለውና በሲቪልና ወታደራዊ የሥልጣን ከፍፍል የተቋቋመው የሽግግር መንግሥት የሦስት ቀናት የሃዘን ቀን ማወጁን ሮይተርስ ዘግቧል። እንደ ጆንስ ሆ��ኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ በሱዳን እስካሁን 16 ሺህ 052 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 1 ሺህ 197 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-55079316 +sports """40 ዓመትም ቢሆን ለማራቶን ውድድር ትልቅ አይደለም"" ቀነኒሳ በቀለ" "ኢትዮጵያዊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በእሁዱ የበርሊን ማራቶን ሦስተኛ ሆኖ ካጠናቀቀ በኋላ ከስፖርቱ የመውጣት ዕቅድ እንደሌለው አፅንኦት በመስጠት ተናግሯል። ሰኔ ወር ላይ 39 ዓመቱን ያከበረው ቀነኒሳ በኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌ የተያዘውን ሁለት ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከ 39 ሰኮንድ የማራቶን ክብረ ወሰን ለመስበር እንዳቀደም ይናገራል። ሆኖም በባለፈው ሳምንት መጨረሻ በበርሊን በተደረገው ውድድር ከኪፕቾጌ የክብረ ወሰን ሰዓት ከአምስት ደቂቃዎች በላይ ዘግይቶ እንዲሁም ውድድሩን ካሸነፈው እና ከአገሩ ልጅ ጉዬ አዶላ አንድ ደቂቃ ዘግይቶ ነበር ውድድሩን በሦስተኛነት ያጠናቀቀው። የሦስት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና ቀነኒሳ በአሁኑ ወቅት ትኩረቱ በሚቀጥለው ዓመት በጀርመን መዲና በርሊን በሚካሄደው የማራቶን ውድድር ክብረ ወሰኑን መስበር ቢሆንም በፓሪስ የሚደረገውን የ2024 ኦሎምፒክም እንደሚሳተፍ ፍንጭ ሰጥቷል። ""ከበርካታ አትሌቶች በዚህ ዕድሜ፣ 40 ጥሩ ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ መረጃ አለኝ። ለማራቶን ውድድር ትልቅ አይደለም"" ብሏል። ""ጤነኛ ከሆንኩ እና ከተዘጋጀሁ በበርሊን በሚደረገው የማራቶን ውድድር ክብረ ወሰን ለማሻሻል እሮጣለሁ"" በማለት ተናግሯል። ከወራት በፊት በኮሮናቫይረስ ተይዞ ያገገመው ቀነኒሳ የበርሊኑ ማራቶን ውድድር ላይም ህመሙ ጥሎብት ባለፈው ጫና ያሰበውን ሳያሳካ እንደቀረም አስረድቷል። በአሁኑ ወቅት የኮሮናቫይረስ ህመም ምልክቶች ባይኖሩትም ከህመሙ በተጨማሪ በአጠቃላይ ከወረርሸኙ ጋር ተያይዘው የተከሰቱ ጉዳዮች በአትሌቱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጥረዋል። ""ለኔ ዋነኛው ችግር በወረርሽኙ ምክንያቱ ስልጠና አለመኖሩ ነው"" በማለት ወረርሽኙ የደቀነውን ጉዳት አስረድቷል። በአትሌቲክስ ዘርፍ ምርጥ የረጅም ርቀት ሯጮች አንዱ የሆነው ቀነኒሳ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለመመረጡ ብዙዎችን ባስገረመ መልኩ ያለፉት ሁለት የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ አልተወዳደረም። ቀነኒሳና ፌዴሬሽኑ ጥሩ ግንኙነት የሌላቸው ሲሆን በቅርቡም በነበረው የምርጫ ሂደት ላይ በማራቶን ውድድር ሁለተኛው ፈጣን አትሌት ቢሆንም ችላ ተብሏል። ቀነኒሳ ከሁለት አመት በፊት በበርሊን በተደረገው የማራቶን ውድድር ከኪፕቾጌ ክብረ ወሰን ጥቂት በሚባል፣ ሁለት ሰኮንዶችን ዘግይቶ በመግባት አሸናፊ ሆኗል። ""በእርግጠኝነት ከሦስት አመት በኋላ በሚደረገው ፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ መሮጥ እፈለጋለሁ፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ ፌዴሬሽን መሰረት መወሰን ከባድ ነው"" በማለት ተናግሯል። ""እኔ ያለኝ አንድ አገር ብቻ ነው። ወደ ፖሪስ መሄድ ብፈልግ እንኳን የፌዴሬሽኑን መስፈርቶች ስለማላውቅ አስቸጋሪ ይሆናል"" ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58696684 +health በጎርፍ የተጥለቀለቁ የለንደን ሆስፒታሎች ታካሚዎችን 'አትምጡ' አሉ "ሁለት በምሥራቅ ለንደን የሚገኙ ሆስፒታሎች ድንገተኛ ክፍሎቻቸው በጎርፍ በመጥለቅለቃቸው ሳቢያ ታካሚዎች ወደ ሆስፒታሎቹ እንዳይሄዱ አስጠነቀቁ። ሁለቱ ሆስፒታሎች የጎርፍ አደጋ የደረሰባቸው ትላንት ነው። ዊፐርስ ክሮስ የተባለው ሆስፒታል የኤሌክትሪክ አቅርቦቱ ተቋርጧል። 100 ተኝተው የሚታከሙ ሰዎችን ከሆስፒታሉ ለማስወጣትም ተገዷል። ኒውሀም የተባለው ሆስፒታል ደግሞ ታካሚዎች ወደ ሌሎች የድንገተኛ ክፍሎች እንዲሄዱ ጠይቋል። የለንደን እሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ እንዳለው፤ ከ1,000 በላይ ከጎርፍ አደጋ ጋር የተያያዙ የስልክ ጥሪዎች ደርሰውታል። መኪና ውስጥ ሳሉ የጎርፍ አደጋው የገጠማቸውን ጨምሮ በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከአደጋው ማምለጥ የተሳናቸው ሰዎችንም መታደግ ተችሏል። ሁለቱን ሆስፒታሎች የሚያስተዳድረው ማኅበር ቃል አቀባይ ""ታካሚዎች ከኛ ሆስፒታሎች ውጪ ያሉ የሕክምና መስጫ አማራጮችን እንዲጠቀሙ እንጠይቃለን"" ብለዋል። ለንደን ውስጥ የሚገኙ አውራ ጎዳናዎች በጎርፍ አደጋው ምክንያት ተዘግተዋል። ሴንት ፓርክ የተባለው ፓርክ ውስጥ የዝናቡ መጠን 41.6 ሚሊ ሜትር እንደደረሰና፤ ይህም ለንደን ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ በጎርፍ ከተጥለቀሉ ቦታዎች ቀዳሚ እንደሚያደርገው ተገልጿል። በምሥራቅ ለንደን የሚኖሩ ዜጎች ትላንት ጎርፉ ወደ ቤታቸው እንዳይገባ በመጥረጊያ ወይም የእንጨት ከለላ በመሥራት ሲከላከሉ ነበር። የሬስቶራንት አስተዳዳሪዋ ማርያ ፔቫ የጎረቤቷ መኝታ ቤት በጎርፍ እንደተዋጠ ተናግራለች። ልጇ ጎረቤቶቿን ከጎርፉ ለመታደግ እየሞከረ እንደነበረም ታክላለች። ""ልጄ ምግብ ሊገዛ ወጥቶ ሲመለስ ሰፈራችን በጎርፍ ተጥለቅልቆ ጠበቀው። ጎርፉ ቤታችን ሊገባም ነበር"" ብላለች የ46 ዓመቷ ማርያ። ሆስፒታሎቹ በመዘጋታቸው አምቡላንሶች ህሙማንን ወደ ሌሎች ሕክምና መስጫዎች ለመውሰድ ተገደዋል። ኒውሀም የተባለው ሆስፒታል አሁን አገልግሎት እየሰጠ ያለው በእናቶችና ሕፃናት ክፍሉ ነው። ይህ ክፍል በጎርፍ አልተጠቃም። የሆስፒታሉ ሬዚደንት ክሪስ ዴት ""የጎርፍ ውሃው አስፋልቱን አጥለቅልቆት ነበር። መራመድም አይቻልም። ውሃው እስከ ጉልበቴ ድረስ ሞልቶ ስለነበር አውቶብስ ውስጥ ለመግባት ተቸግሬ ነበር"" ሲል በትዊተር ገጹ ጽፏል። የ28 ዓመቱ የለንደን ነዋሪ ኤዲ ኤልየት ""እንደዚህ አይነት ነገር ለንደን ውስጥ አይቼ አላውቅም። አውቶብሶች በጎርፍ ተይዘው ቆመው ነበር"" ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57972780 +sports ለተሰንበት ግደይ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ ሆነች ለተሰንበት ግደይ በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ባለው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ ሆነች። የ24 ዓመቷ አትሌት በዚህ ውድድር 30፡09፡94 ሰዓት በማስመዝገብ ነው የአንደኛነት ስፍራን በማግኘት የወርቅ ሜዳሊያዋን ያጠለቀችው። ፍጻሜው ላይ ከፍተኛ ትንቅንቅ በታየበት በዚህ ውድድር፣ ለተሰንበትን ተከትለው ኬንያውያን አትሌቶች ሄለን ኦቢሪ በሁለተኝነት እና ማርጋሬት ቼሊሞ ኪምኬምቦይ በሦስተኛነት አጠናቀዋል። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና ለሆላንድ የምትወደዳረው ሲፋን ሐሰን በዚህ ውድድር ላይ በአራተኝነት አጠናቃለች። በዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶቹ እጅጋዬሁ ታዬ 6ኛ፣ ቦሰና ሙላቴ 8ኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩን አጠናቀዋል። ቀደም ሲል በ10 ሺህ ሜትር፣ በ5 ሺህ ሜትር እና በግማሽ ማራቶች ሦስት የዓለም ክብረ ወሰኖችን የያዘችው አትሌት ለተሰንበት በዚህ ዓለም አቀፍ ከፍተኛ ውድድር ላይ በመሳተፍም አሸናፊነቷን አስጠብቃለች። ለተሰንበት በቶኪዮ ማራቶን የአሸናፊነት ቦታ ትልቅ ግምት የተሰጣት ሲሆን 3ኛ በመሆን የነሐስ ተሸላሚ ሆናለች። እንዲሁም በአውሮፓውያኑ 2019 በኳታር ዶሃ በነበረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለተሰንበት በሁለተኝነት አጠናቃለች። ለተሰንበት ከውድድሩ በኋላም ለመገናኛ ብዙኃ በሰጠችው አስተያየት “ይህንን ውድድር ማሸነፍ ትልቁ አላማዬ ነበር። ህልሜም እውን ሆነ። ይህ ድል ከዓለም ክብረ ወሰን በበለጠ ለእኔ ትልቁ ነው። በውድድሩ በጣም ደስተኛ ነኝ” ብላለች። አትሌቷ በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ስፔን ቫሌንሺያ በተካሄደው ግማሽ ማራቶን ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰን መ��በሯ ይታወሳል። ለተሰንበት በኬንያዊቷ ሩት ቼፕንጌቲክ በ1 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ02 ሰኮንድ ተይዞ የነበረውን የግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በማሻሻል 1 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ52 ሰኮንዶች በመግባት ክብረ ወሰን ጨብጣለች። በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር የሚካሄድ ሲሆን በሪሁ አረጋዊ፣ ሰለሞን ባረጋና ታደሰ ወርቁ እንደሚወዳደሩ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። ሰለሞን ባረጋ በጃፓን ቶኪዮ ኦሊምፒክ በ10 ሺህ ሜትር በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቱ ይታወሳል። ሰለሞን በዚህ ውድድር ያስመዘገበው ሰዓት 27፡43፡22 ሲሆን የዓለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነውንም ጆሹዋ ቼፕቴጊን አስከትሎ ነው የገባው። በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ጉዳፍ ፀጋይ፣ ፍረወይኒ ኃይሉና ሂሩት መሸሻ ማጣሪያውን አልፈዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cy7q9vn5pwyo +health በኒው ዚላንድ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው "በኒው ዚላንድ በጠና የታመሙ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው። ባለፈው ወር በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ 65.2% መራጮች የፍቃድ ሞትን ደግፈዋል። ዩትኔዝያ ወይም የፈቃድ ሞት በጠና የታመሙ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖሩ የተነገራቸው ሰዎች በህክምና እርዳታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ የሚደረግበት ሂደት ነው። ሕጉ በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ጸድቆ ይተገበራል ተብሎ ይጠበቃል። ኒው ዚላንድ ሕጉን ካጸደቀች የፈቃድ ሞት ከሚተገበርባቸው ጥቂት አገሮች አንዷ ትሆናለች። ዩትኔዝያ ከተፈቀደባቸው አገሮች ኔዘርላንድ እና ካናዳ ይጠቀሳሉ። ኒው ዚላንዳውያን ባለፈው ወር መሪያቸውን ሲመርጡ ስለ ፈቃድ ሞት እና ዕጸ ፋርስ ሕዝበ ውሳኔ አድርገዋል። ዕጸ ፋርስን ለመዝናኛ መጠቀም ሕጋዊ እንዲሆን ድምጽ የሰጡት 46.1% ብቻ ሲሆኑ፤ 53.1% ተቃውመዋል። የፈቃድ ሞትን ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደን እንዲሁም ተቀናቃኛቸው ጁዲት ኮሊንስም ይደግፉታል። ሕዝቡም ሕጋዊ ይሁን ብሎ እንደሚመርጥ ይጠበቅ ነበር። ባለቤቱ የሞተችበት ማት ቪከርስ ""ርህራሄ እና ደግነት አሸንፈዋል። በጠና የታመሙ ኒው ዚላንዳውያን ሕይወታቸውን ማሳለፍ ስለሚችሉ ደስ ብሎኛል"" ሲል የተሰማውን ገልጿል። ጠበቃ የነበረችው ባለቤቱ የአንጎል እጢ ሲገኝባት በፈቃዷ ለመሞት ክስ ብትመሠረትም ሳታሸንፍ በጠና ታማ ከአምስት ዓመታት በፊት ሞታለች። ""ባለቤቴ መሞት አትሻም ነበር። ማንም ሰው መሞት አይፈልግም። ነገር ግን መኖር የምርጫ ጉዳይ ነው። ስቃይ እየበረታ ሲሄድ መሞት አንዱ ምርጫ መሆን አለበት"" ብሏል። አንድ ሰው በፈቃዱ ለመሞት በጠና የታመመ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖር የተረጋገጠ መሆን አለበት። ሰውነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ እንደሄደና ውሳኔው ላይ ለመድረስ በቂ መረጃ እንዳለው ማረጋገጥም ተገቢ ነው። ሂደቱ የሚመራው በዶክተር ወይም በነርስ ነው። አንድ ሰው እድሜው ስለገፋ፣ የአእምሮ ህመም ስላለበት ወይም የአካል ጉዳት ስላለበት የፍቃድ ሞት ሕግን መተግበር አይችልም። ሕጉን የሚቃወሙ ሰዎች ""እንድንኖር እንጂ እንድንሞት አትርዱን"" ሲሉ ምክር ቤት ሄደው ተቃውሞ አሰምተዋል። ሕጉ ለማኅበረሰቡ አስጊ እንደሆነ እና ራስን ማጥፋትን ለመግታት ከወጣ መርህ ጋር እንደሚቃረን ይናገራሉ። ሌላው መከራከሪያ ነጥብ በጠና የታመሙ ሰዎች የቤተሰብ ሸክም ላለመሆን ብለው በፈቃዳቸው ሊሞቱ ይችላሉ የሚለው ነው። ዩትኔዝያን አጥብቆ ሲተች የነበረ ቡድን ""የኒው ዚላንድ ዜጎች የተሳሳተ ሕግ እንዲጸድቅ ድምጽ በመስጠታቸው አዝነናል"" ሲል መግለጫ አውጥቷል። የፈቃድ ��ትን ሕጋዊ ያደረጉ አገሮች የኒው ዚላንድን ሕዝበ ውሳኔ በቅርበት ሲከታተሉ ነበር። ከነዚህ መካከል ቤልጄም፣ ካናዳ፣ ኮሎምቢያ፣ ሉግዘምበርግ እና ኔዘርላንድስ ይጠቀሳሉ። በኔዘርላንድስ በህክምና ታግዞ ራስን ማጥፋት ይቻላል። በአሜሪካ ያሉ ብዙ ግዛቶች እና የአውስትራሊያዋ ቪክቶሪያ በህክምና የታገዘ ሞትን ፈቅደዋል።" https://www.bbc.com/amharic/54744271 +business አንበጣ ፡ ኢትዮጵያ የአንበጣ መንጋን ለመቆጣጠር ምን ያህል አውሮፕላኖች አሏት? "የምሥራቅ አፍሪካ አገራትን በማዳረስ በተለይ የኢትዮጵያን ሰሜናዊና ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎችን ክፉኛ እያጠቃ የሚገኘውን ግዙፍ የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመከላከል ከአየር ላይ ጸረ ተባይ መድኃኒት የሚረጩ ጥቂት አውሮፕላኖች ተሰማርተው ጥረት እየተደረገ ነው። የአንበጣ መንጋው ክፉኛ ባጠቃቸው አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች ብዙም ውጤታ ያልሆነውን ባህላዊ አንበጣን የመከላከያ መንገድ ጥረት እያደረጉ ሲሆን፤ ከዚሁ ጎን ለጎን አውሮፕላኖችም ተሰማርተው ጸረ ተባይ መድኃኒቶችን እየረጩ ቢሆንም እክል እየገጠማቸው የመከላከሉ ሥራ ላይ እክል እያጋጠመ ነው። ባለፈው የመስከረም ወር ሁለት የጸረ ተባይ መርቻ አውሮፕላኖች በሰሜንና በምሥራቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ አካበቢዎች ተሰማርተው በነበረበት ጊዜ ወድቀው ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል። የመጀመሪያው አውሮፕላን በአማራ ክልል ወረባቦ ወረዳ ፍራንጉል በሚባል ቦታ ወድቆ የተከሰከሰ ሲሆን የወረዳው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሳዳም ሽመልስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በአብራሪው ላይ ከደረሰው መጠነኛ ጉዳት ውጪ በሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። ነገር ግን በአደጋው በአውሮፕላኑ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የተነገረ ሲሆን በዚህም ሳቢያ አውሮፕላኑ ከአገልግሎት ውጪ ሊሆን ይችላል ተብሏል። ሁለተኛው አውሮፕላን ደግሞ በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጃርሶ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ኬሚካል በመርጨት ላይ በነበረበት ጊዜ ጊደያ በሃ በምትበል ቀበሌ ውስጥ ነው የመውደቅ አደጋ የገጠመው። የወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አብዱል ቃድር ደዚ ለቢቢሲ በአደጋው ወቅት በአውሮፕላኑ ውስጥ አብራሪው ብቻ የነበረ ሲሆን እሱም ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰበትና በአውሮፕላኑ ላይም ቀላል ጉዳት እንዳጋጠመ ተናግረዋል። ስለዚህም የአንበጣው መንጋ ጥፋት የሚያደርስባቸውን አካባቢዎች እያሰፋ ባለበት በዚህ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉት የጸረ አንበጣ መድኃኒት መርጫ አውሮፕላኖች ሁለቱ በአንድ ወር ውስጥ ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል ማለት ነው። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ስንት አውሮፕላኖች አሏት? የአፍሪካ ቀንድንና ደቡብ እስያን እያካለለ ያገኘውን ሰብል በማውደም የአካባቢውን ሕዝብ የምግብ አቅርቦትና ህይወት አደጋ ላይ ጥሎ የሚኘውን በ25 ዓመት ውስጥ ካጋጠሙት ሁሉ የከፋው ነው የተባለለትን የአንበጣ መንጋ ወረርሽን ለመከላከል ኢትዮጵያ ከምድር እና ከአየር ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። የአንበጣ መንጋው ጥቃት ሰፊ ቦታን በሚሸፍን ቦታ ላይ እንደተከሰተ የግብርና ሚኒስቴር ግብርና ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ማንደፍሮ ንጉሤ (ዶ/ር) የገለጹ ሲሆን፤ በአፋር፣ ሶማሊ፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ተከስቷል። ባለፉት ወራት በኢትዮጵያ ውስጥ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ስድስት አውሮፕላን እና ሁለት ሄሊኮፕተሮች ተሠማርተው የነበሩ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በገጠማቸው አደጋና ለጥገና ወደ ውጭ የሄዱ በመኖራቸው በሥራ ላይ የሚገኘው አንድ አውሮፕላን ብቻ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ���አንበጣ መንጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከዚህ ቀደም አውሮፕላኖቹ ተሰማርተው ባከናወኑት አንበጣውን የመከላከል ሥራ ""በጣም ውጤታማ ነበሩ"" የሚሉት ማንደፍሮ (ዶ/ር)፤ ""በሰባት ክልሎች እና በአንድ ከተማ መስተዳድር የበረሃ አንበጣው ሲከሰት በተቀናጀ መልክ ተሠማርተው በመከላከል በሁለት ክልሎች ብቻ ሲቀር የሌሎቹን መቆጣጠር ችለው ነበር"" ይላሉ። ነገር ግን ከወራት በፊት የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ በመቆጣጠር ""የቀረውንም ተረባርበው ለማጥፋት ሲቃረቡ አዲስ የበረሃ አንበጣ መንጋ ከውጭ ገባ"" የሚሉት ሚኒስትር ዲኤታው ሌላ ጫና መፈጠሩን አመልክተዋል። ስለዚህም አሁን የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ውስጥ ሁለቱ እክል ገጥሟቸው የወደቁ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በጥገና ላይ በመሆናቸው የቀረው አንድ አውሮፕላን ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ካጋጠመው የአንበጣ መንጋ ወረራ አንጻር ከአቅም በላይ መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚሁ ተግባር የሚውሉ አዳዲስ አውሮፕላኖች ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል። አዲሶቹ የጸረ አንበጣ መድኃኒት መርጫ አውሮፕላኖች ስምንት ሲሆኑ የሚመጡትም በኪራይ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ማንደፍሮ (ዶ/ር) አመልክተው፤ ተባዩን ለመቆጣጠር በግብርና ሚኒስትሩ የሚመራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ከአውሮፕላን በተጨማሪ በሰው ኃይልና በተሸከርካሪ በመታገዝ የጸረ ተባይ ርጭት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አውሮፕላኖቹ ምን አጋጠማቸው? የአንበጣ መንጋው ወረራ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ባለፈው የመስከረም ወር ላይ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ጸረ አንበጣ መድኃኒት ለመርጨት ተሰማርተው የነበሩት አውሮፕኖች ላይ በተከታታይ የደረሰው አደጋ በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን የጸረ ተባይ መርጫ አውሮፕላኖች ቁጥር አንድ ብቻ አድርጎታል። ለአደጋው መከሰት ምክንያቱ ምን እንደሆነ የተገለጸ ነገር ባይኖርም ሚኒስትር ዲኤታው ማንደፍሮ (ዶ/ር) ግን ""ከፍ ብሎ ለመብረር መቸገራቸው ምክንያት ሳይሆን አይቀርም"" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አደጋው የደረሰባቸው ሁለቱም አውሮፕላኖች በኪራይ የመጡና ንብረትነታቸውም የደቡብ አፍሪካ ሲሆኑ፤ አብራሪዎቹም ኢትዮጵያዊያን አለመሆናቸው ተገልጿል። አውሮፕላኖቹ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ የመጡ ሲሆን የአደጋና የኢንሹራንስ ጉዳይ የግብርና ሚኒስቴርን የሚመለከት እንዳልሆነ ተጠቅሷል። አደጋው መድረሱ እንዳሳዘናቸው ነገር ግን ""እኛ በውላችን መሠረት ኪራይ መከፈል እንጂ አደጋ ሲደርስ እንከፍላለን የሚል ውል የለም"" ሲሉ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ተናግረዋል። የግብርና ሚንስቴር የራሱ እንዲህ አይነቱ የተፈጥሮ ችግር በሚያጋጥምበት ጊዜ ፈጥነው በመሰማራት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ሄሊኮፕተርም ሆነ አውሮፕላን እንደሌለው የጠቆሙት ሚንስትር ዲኤታው ""አውሮፕላኖች ቢኖሩን ኖሮ አንበጣውን በፍጥነት ለመከላከል ይቻል ነበር"" ብለዋል። ከዚህ አንጻርም የጎረቤት አገር ሱዳን የግብርና ሚንስቴር የአንበጣ እና የወፍ መከላከያ እንዲሁም ለሌሎች ሥራዎች የሚያገለግሉ ዘጠኝ አውሮፕላኖች እንዳሉት ጠቅሰው በኢትዮጵያም ""ተመሳሳይ አቅም መገንባት"" አስፈላጊነትን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ምን ያህል አውሮፕላኖች ያስፈልጓታል? በተለይ በኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኙ ክልሎች ላይ ተከስቶ ከባድ ውድመት እያስከተለ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ያመለከተውን የአንበጣ መንጋ ወራረ ለመከላከል ከአየር ላይ የሚደረገው የጸረ ተባይ ርጭት ወሳኝ መሆኑን ከዓለም የምግብ ፕሮግራም መረጃ ያመለክታል��� በተለይ ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ተራራማ አገራት ውስጥ ከአየር ላይ የሚደረገው የጸረ አንበጣ መድኃኒት ርጭት አንበጣው የሚያደርሰውን ጉዳት በቶሎ ለመቆጣጠር ያስችላል። ነገር ግን አውሮፕላን ወይም ሄሊኮፕተር ለመግዛትም ሆነ ለመከራየት የሚያስፈልገው ገንዘብ ቀላል የሚባል አይደለም። ሚኒስትር ዲኤታው እንደሚሉት አንድ ሄሊኮፕተር ለመግዛት የሚያስፈልገው ገንዘብ ሁለት ሚሊዮን ዶላር እንደሚገመት ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ አስር ብትገዛ ወደ 20 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል። አንበጣው በአገሪቱ ግብርና ላይ ከሚያደርሰው ጉዳትና ለተለያዩ ችግሮች ከሚያጋልጣቸው የአገሪቱ ዜጎች አንጻር የአውሮፕላኖቹ አስፈላጊነት አጠያያቂ አይደለም ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታው። ""በአገሪቱ ከዚህ በሚበልጥ ወጪ የሚሠሩ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን እና በተመሳሳይ ለዚህም ግዢ ትኩረት ያስፈልጋል"" ብለዋል። አንድ አውሮፕላን የአንበጣ መንጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በአንድ ጉዞ አንድ ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ኬሚካል የመርጨት አቅም ሲኖረው፤ አንድ አውሮፕላን በቀን እስከ አምስት ምልልስ በማከለናወን የጸረ አንበጣ መድኃኒት መርጨት ከቻለ አምስት ሺህ ሄክታር መሬትን መሸፈን ይችላል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በአንበጣ መንጋው የወረራ ስጋት ውስጥ ይሆናል ተብሎ እንደሚገመት ሚኒስትር ዲኤታው አመልከተው፤ ይህንንም ስፋት የጸረ ተባይ መድኃኒት ለመርጨት በትንሹ 10 አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ። የበረሃ አንበጣ መንጋው እስካሁን ስላደረሰው ጉዳት ጥናት ባለመደረጉ የተረጋገጠ መረጃ አለመኖሩን የተናገሩት ማንደፍሮ (ዶ/ር) አሁን ዋነኛ ትኩረት የተደረገው በመከላከል ሥራው ላይ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። ሚኒስትር ዲኤታው ጨምረውም የበረሃ አንበጣውን ወረራ ለመከላከል ከአውሮፕላኖች በተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ መኪኖች ጉዳቱ በከፋባቸው አካባቢዎች ተሰማርተዋል። ከ25 ዓመታት ወዲህ የከፋ ነው የተባለለት የበረሃ አንበጣ ለወራት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምሥራቅ አፍሪካ ያሉ አገራት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ አስካሁን በተከታታይ ለተከሰተው የአንበጣ መንጋ ምክንያቱ እንደ አውሮፓዊያኑ በ2018 እና 2019 ያጋጠመው ከባድ ነፋስና ዝናብ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንዳመለከተው ከሁለት ዓመት በፊት በደቡባዊ የአረብ ልሳነ ምድር ላይ የነበረው እርጥብና አመቺ የአየር ሁኔታ የአንበጣው ሦስት ትውልድ ሳይታወቅ እንዲራባ እድል ፈጥሮ በአካባቢው አገራት ላይ የሚታየውን የአንበጣ መንጋ ወረራ አስከትሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54495523 +politics የፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ‘ፓርቲ’ ላይ ሲጨፍሩ መታየታቸው ትችት አስከተለባቸው "የፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ሾልኮ በወጣ ቪዲዮ ‘ፓርቲ’ ላይ ሲጨፍሩ መታየታቸው ትችት አስከትሎባቸዋል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት እየተጋራ ባለው ተንቀሳቃሽ ምስል ጠቅላይ ሚኒስትሯ እና ዝነኛ ፊላንዳውያን ጓደኞቻቸው ሲጨፍሩ እና ሲዘፍኑ ታይተዋል። ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል ከወጣ በኋላ የአገሬው መገናኛ ብዙኃን መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ከፍተኛ ትችት ተሰንዝሮባቸዋል። ይባስ ብሎም አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ""የአደንዛዥ እጽ ምረመራ ይደረግላቸው"" ሲሉ ጠይቀዋል። የ36 ዓመቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ግን አደንዛዥ እጽ አልወሰድኩም ካሉ በኋላ፣ አልኮል መጠጣታቸውን እና በሙሉ ኃይላቸው በፓርቲው ላይ መጨፈራቸውን ግን ተናግረዋል። የዓለማችን ወጣቷ ጠቅላይ ሚኒስ��ር ለጭፈራ ወደ ፓርቲ ቦታ ማቅናትን በምስጢር የሚይዙት ጉዳይ አይደለም። ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሙዚቃ ፌስቲቫሎች ላይ በይፋ ታይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ባለፈው ዓመት እራሳቸውን ለኮቪድ-19 አጋልጠው ወደ ጭፈራ ቤት በመሄዳቸው ይቅርታ ጠይቀው ነበር። ባለፈው ሳምንት ተዋቂው የጀርመን መጽሔት ቢልድ ሳና ማሪን ""የዓለማችን ምርጧ ጠቅላይ ሚኒስትር"" ብሏቸው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቪዲዮ እየተቀረጹ መሆኑን እንደሚያውቁ ገልጸው ለሕዝብ ዕይታ መቅረቡ ግን ያበሳጫል ሲሉ ሾልኮ ስለወጣው ተንቀሳቃሽ ምስል አስተያየታቸውን ሲጥተዋል። ""ደንሻለሁ፣ ዘፍኛለሁ እንዲሁም ፓርቲ አድርጊያለሁ ሁሉም ሕጋዊ ናቸው። እኔ ወይም በአካባቢዬ አደንዛዥ እጽ በሚወሰድበት ቦታ ሆኜ አላውቅም"" ብለዋል የፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር። ጠቅላይ ሚኒስትሯ እራሳቸውን ሲከላከሉ፤ ""የቤተሰብ ሕይወት አለኝ፣ የሥራ ሕይወት አለኝ፣ እንዲሁም ከጓደኞቼ ጋር የማሳለፈው ነጻ የምሆንበት ጊዜ አለኝ። በእኔ የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ከሌሎች ሰዎች ጋር ተመሳሳይ ነው"" ብለዋል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ሪካ ፑራ ጠቅላይ ሚኒስትሯ በገዛ ፍቃዳቸው የአደንዛዥ እጽ ምርመራ ያደርጉ ሲሉ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፤ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ደግሞ ሌሎች አንገብጋቢ አገራዊ ጉዳዮች እያሉ ስለ ጭፈራ ማውራቱ ጊዜው አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሯን እና የአገሪቱን መገናኛ ብዙኃን ተችተዋል። መሪን ከእአአ 2019 መጨረሻ ጀምሮ ፊንላንድን ሲመሩ የቆዩ ሲሆን አሁንም ድረስ ከፓርቲያቸው ጠንካራ ድጋፍ አላቸው።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cmj3g8pezj1o +business መካከለኛ አፍሪካ ሪፓብሊክ ቢትኮይንን ይፋዊ መገበያያ አደረገች "መካከለኛ አፍሪካ ሪፓብሊክ ቢትኮይንን ይፋዊ መገበያያ በማድረግ ሁለተኛዋ አገር ሆነች። ቢትኮይንን አገር አቀፍ መገበያያ በማድረግ ኤል ሳልቫዶር የመጀመሪያዋ ናት። የሴንትራል አፍሪካን ሪፐብሊክ ሕግ አውጭዎች በሙሉ ድምጽ ቢትኮይን መገበያያ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፈዋል። ""ውሳኔው አገሪቷን ከዓለም ባለ ራዕይ አገሮች አንዷ ያደርጋታል"" ብለዋል። ከአለማችን ድሃ አገራት አንዷ ብትሆንም በአልማዝ፣ ወርቅና ዩራንየም የበለጸገች ናት። የሩሲያ የቅርብ ወዳጅ የሆነችው መካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ (ካር) ለዓመታት በግጭት ስትናጥ ቆይታለች። የሩሲያ ቅጥረኛ ወታደሮች በአገሪቱ አማጽያንን እየተዋጉ ነው የሚለው ዜና ከወራት በፊት መውጣቱ አይዘነጋም። ኤል ሳልቫዶር እአአ መስከረም 2021 ላይ ቢትኮይንን መገበያያ ስታደርግ አይኤምኤፍን ጨምሮ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ውሳኔውን ተችተዋል። ቢትኮይንን ይፋዊ መገበያያ ማድረግ የፋይናንስ ሥርዓት አለመረጋጋት ይፈጥራል፣ ወንጀለኞች ሕገ ወጥ ገንዘብን ወደ ሕጋዊ መስመር እንዲያስገቡ መንገድ ይከፍታል፣ ሂደቱ በርካታ የኤሌክትሪክ ኃይል ስለሚወስድም አካባቢ ይበክላል ብለው ነበር የነቀፉት። የ2019 መረጃ እንደሚያሳየው፣ ሴንትራል አፍሪካን ሪፐብሊክ ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ከአጠቃላይ ሕዝቡ 4 በመቶ ናቸው። ይህም ቢትኮይንን ለመጠቀም ፈታኝ ያደርገዋል። በአገሪቱ ጥቅም ላይ የሚውለው በፈረንሳዩ ሲኤፍኤ ባንክ የሚደገፈው ፍራንክ ነው። ባንኩ በማዕድን የበለጸገችው አገር ላይ የበለጠ ጫና እንዳያሳድር በሚል አገሪቱ ወደ ቢትኮይን ፊቷን አዙራለች የሚሉ አሉ። ቴሪ ቪርኮሉን የተባሉ ተንታኝ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት፣ በአገሪቱ ያለው መዋቅራዊ ሙስና እንዲሁም የአገሪቱ ወዳጅ አገር ሩሲያ ከሰሞኑ በምዕራባውን ማዕቀብ ሥር መውደቋ፣ ቢትኮይንን መገበያያ ለማድረግ እንዲወሰን ሳይገፋፉ አልቀሩም። በመዲናዋ ባኑጊ የሰዎች ስሜት የተደ��ላለቀ ነው። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ያን ዳውሮ፣ በቢትኮይን መገበያየት ሕይወትን ቀላል ያደርጋል ሲሉ ለቢቢሲ አስተያየት ሰጥተዋል። ""ነጋዴዎች ከዚህ በኋላ የሲኤፍኤ ፍራንክ ይዘው መጓጓዝ የለባቸውም። በቢትኮይን በስልክ መገበያየት ይቻላል። ቢትኮይንን ወደ ሌላ መገበያያ ገንዘብ በቀላሉ መቀየርም ይቻላል"" ብለዋል። ሲኤፍኤ አፍሪካን የሚጠቅም አሠራር እንዳልዘረጋ ባለሙያው ይናገራሉ። ሌሎች የፈረንሳዩ ባንክ ጥገኛ የሆኑ የአፍሪካ አገራት መገበያያውን እንዲተውት የሚጠይቁም አሉ። መገበያያው ከቅኝ ግዛት የተወረሰና ፈረንሳይ ምጣኔ ሀብታዊ ጫና እንድታደርግ የሚረዳት ነው በሚል ይተቻል። ኮምፒውተር ሳይንቲስቷ ሲድኒ ቲካያ በበኩሉ፣ ቢትኮይንን መገበያያ ማድረግ ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው ሲል ይከራከራል። ""የኢንተርኔት ዝርጋታ ውስን ነው። ቢትኮይን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት ላይ የተመሠረተ ነው። ወደ ቢትኮይን የመሸጋገሪያው ጊዜ አሁን አይደለም"" ብሏል። አገሪቱ እንደ ትምህርት እና ንጹህ የመጠጥ ውሃ ያሉ መሠረታዊ አቅርቦቶችን ማሟላት ላይ ብታተኩር እንደሚሻልም ይመክራል። ሴንትራል አፍሪካን ሪፐብሊክ ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣት በኋላ ከ1960ዎቹ ወዲህ በግጭት ስትናጥ ቆይታለች። በ2013 ሙስሊም አማጽያን በብዛት የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የሚገኙባትን አገር ተቆጣጠሩ። ይህንን በመቃወም ሚሊሻዎች መደራጀት ጀመሩ። ይህም በሃይማኖት የተከፋፋለ ግጭትን አስከተለ። 2016 ላይ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን አርቻንጌ ቶዋድራ ሥልጣን ከያዙ በኋላ አገሪቱ ከፈረንሳይ ወደ ሩሲያ ወዳጅነት ተሻግራለች።" https://www.bbc.com/amharic/61253742 +politics አዲሷ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ ማን ናቸው? የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ ሆነው የተመረጡት ሊዝ ትረስ ከንግሥት ኤልዛቤጥ ጋር ከተገናኙ በኋላ በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል። ሊዝ ከየት ተነስተው አሁን ካሉበት ደረሱ? * * ሊዝ ትረስ ገና በ7 ዓመታቸው የቀድሞዋን ዝነኛ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርጋሬት ታቸርን በመወከል ተማሪ ሳሉ ተውነው ነበር። ሊዝ ትረስ ከ39 ዓመታት በኋላ በእውኑ ዓለም የወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ መሆን ችለዋል። እስካሁን ድረስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ ያሉት ሊዝ ትረስ፣ በተቀናቃኛቸው ሪሲ ሱናክ ለአምስት ዙሮች ሲመሩ ቢቆዩም በወግ አጥባቂ ፓርቲ አባላት ምርጫ በመጨረሻ አሸናፊ መሆናቸው ታውቋል። ሜሪ ኤልዛቤት ትረስ በሚለው ሙሉ የመዝገብ ስማቸው የሚታወቁት ፖለቲከኛዋ፣ ከሂሳብ ሊቁ አባታቸው እና ከነርስ እናታቸው እአአ 1975 በኦክስፎርድ፤ ኢንግላንድ ነበር የተወለዱት። የሊዝ ትረስ መሠረታዊ መረጃዎች ሊዝ ገና በልጅነት እድሜያቸው የዩናይትድ ኪንግደም አካል በሆነችው ስኮትላንድ መዲና ግላስጎ ውስጥ ኖረዋል። ከዚያም የቤተሰብ አባላቱ ወደ ሊድስ ተዘዋውሯል። ሊዝ ትረስ በወጣትነት እድሜያቸው ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ገብተው፤ ፍልስፍና፣ ፖለቲካ እና ምጣሄ ሃብት አጥንተዋል። በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በተማሪዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁ ተሳትፎን ያደርጉ ነበር። አሁን ላይ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ሆነው የተመረጡት ሊዝ ትረስ፤ በተማሪነት ዘመናቸው ግን ሊብራል ዴሞክራት ነበሩ። ሊዝ በፀረ ንጉሣዊ አስተዳደር ላይ በሚያንጸባርቁት ጠንካራ አቋም ይታወቁ ነበር። እአአ 1994 ላይ በሊብራል ፓርቲ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ “እኛ ሊብራል ዴሞክራቶች ለሁሉም መሰጠት ስላለበት ዕድል እናምናለን። ሰዎች ለመምረት ይወለዳሉ ብለን አናምንም” ሲሉ ተናግረው ነበር። ሊዝ ገና በኦ���ስፎርድ ሳሉ ነበር የፖለቲካ አቋም ለውጥ በማድረግ ፊታቸውን ወደ ወግ አጥባቂ ፓርቲ ያዞሩት። ከዩኒቨርሲቲ ከወጡ በኋላ ለሼል እንዲሁም ኬብል ኤንድ ዋየርለስ ለሚባል ኩባንያ የሂሳብ ባለሙያ ሆነው እያገለገሉ ሳለ ከሙያ አጋራቸው ጋር እአአ 2000 ላይ ትዳር መስርተዋል። ጥንዶቹ በእስራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሴት ልጆች ወላጆች ናቸው። ትረስ እአአ 2001 ላይ በምዕራብ ዮርክሻየር የወግ አጥባቂ ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የነበረ ቢሆንም፣ ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል። በተመሳሳይ 2005 ላይ በነበረ ምርጫም ተሸናፊ ነበሩ። ሊዝ ትረስ ከአንድም ሁለቴ ሽንፈት ቢገጥማቸውም ለፖለቲካ እጅ አልሰጡም። እአአ 2006 ላይ በደቡብ ምሥራቅ ለንደን ካውንስለር ሆነው ተመርጠው ነበር። እአአ 2010 ለነበረው ምርጫ የወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ ዴቪድ ካሜሩን ሊዝ ትረስን ለፓርቲው አጋርነት የመጀመሪያ ተመራጭ ዕጩ ዝርዝሮች ውስጥ ቢያካትቷቸውም፤ ወጣቷ ፖለቲከኛ ማርክ ፊልድ ከተባሉ የፓርላማ አባል ጋር የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸው ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከፓርቲ አባላቶች ጫና በዝቶባቸው ነበር። ይሁን እንጂ የቀረበባቸውን ፈተና በማለፍ ተመራጭ ሆነው ነበር። ሊዝ ትረስ እአአ 2010 ላይ ከሌሎች አራት የወግ አጥባቂ ፓርቲ አባላት ጋር በመሆን ‘ብሪታኒያ አንቼንድ’ የተሰኘ ብዙ ያነጋገረ መጽሃፍ አሳትመው ነበር። በዛ መጽሐፍ ላይ ብሪታኒያውያን ሠራተኞችን፤ “በዓለማችን ካሉ ሰነፍ ሠራተኞች” ብለው መግለጻቸው ብዙ ያስተቻቸው ሲሆን፤ በቅርብ በነበሩ የክርክር መድረኮች ላይ ሊዝ ትረስ ይህን አስተያየት እንዳልጻፉ ተናግረዋል። ሊዝ የፓርላማ አባል በሆኑ በሁለት ዓመታት ውስጥ የትምህርት ሚንስትር ሆነው ተሾሙ። ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ በእድገት የአካባቢ ጥበቃ ሚንስትር በመሆን ሌላ ሹመት አግኝተዋል። ምናልባትም እአአ 2015 ከአውሮፓ ኅብረት የመውጣት ሕዝበ ውሳኔ በዚህ የዩኬ ትውልድ ትልቁ የፖለቲካ ክስተት ሊሆን ይችላል። ሊዝ ትረስ በብሬክዚት ላይ የነበራቸው አቋም ዩናይትድ ኪንግደም በአውሮፓ ኅብረት ውስጥ መቆየት አለባት የሚለው ነበር። ዘ ሰን ጋዜጣ ላይ አስፈረውት በነበረው መከራከሪያቸው፤ ዩኬ ከአውሮፓ ኅብረት ብትለይ ምርቶችን ለአውሮፓ ኅብረት ማቅረብ ፈታኝ ይሆናል ብለው ነበር። በሕዝበ ውሳኔው ዩኬ ከአውሮፓ ኅብረት ከተለየች በኋላ ሊዝ ትረስም አቋማቸውን በመቀየር፤ ዩኬ ከኅብረቱ መውጣቷ በበጎ መልኩ የአሰራር ሂደቶችን ቀይሯል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ አስተዳደር ውስጥ የፍትሕ ሚኒስትር፣ ከዚያም ደግሞ የግምጃ ቤት ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል። እአአ 2019 ላይ ቦሪስ ጆንሰን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ወደ ሥልጣን ሲመጡ ደግሞ ሊዝ ትረስ የዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር ሆነው ማገልገል ጀምረዋል። ሊዝ የ46 ዓመት ጎልማሳ ሳሉ ነበር ትልቁን የመንግሥት ኃላፊነት የተረከቡት። እአአ 2021 ከዶሚኒክ ራብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሥልጣንን ተረክበዋል። የሊዝ ትረስ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ያደረጉት ጉዞ አልጋ ባልጋ አልነበረም። ከተቀናቃኛቸው ሪሺ ሱናክ ጋር በነበሯቸው ክርክሮች ላይ ባቀረቧቸው መከራከሪያዎች ሲተቹ ነበር። ይሁን እንጂ የምርጫ ውጤቱ ሊዝ ትረስ ከሪሺ ሱናክ ይልቅ በፓርቲ አባላት ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት እንዳላቸው አሳይቷል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1557wx3qyo +politics የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዊሊያም ሩቶን አሸናፊነት አጸና የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ነሐሴ 09/2014 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ ላይ የቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ የዊሊያም ሩቶን በፕሬዝዳንትነት መመረጥ አጸደቀ። ምርጫውን ተከትሎ ተፎካካሪ ዕጩ የነበሩት ራይላ ኦ���ንጋ በምርጫው ሂደት ላይ ማጭበርበር መከሰቱን በመግለጽ ያቀረቡትን ክስ ተከትሎ ነው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው። ሰባት አባላት ያሉት የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ክስ ሲመለከት ቆይቶ ዊሊያም ሳሞይ ሩቶ አምስተኛው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡበት ሂደትን ተቀብሎታል። ተቀናቃኙ ራይላ ኦዲንጋ እና አጋሮቻቸው በምርጫው ሂደት የውጤት መለወጥን ጨምሮ ከፍተኛ የማጭበርበር ድረጊቶች ተፈጽመዋል በማለት ነው ለአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡት። ከፍተኛ ፉክክር በተካሄደበት ምርጫ 50.5 በመቶ የመራጮችን ድምጽ አግኝተው በጠባብ የድምጽ ብልጫ ነበር ዊሊያም ሩቶ ማሸነፋቸው የታወጀው። በአወዛጋቢው ምርጫ አሸናፊነታቸው በድጋሚ በፍርድ ቤት የጸናላቸው ዊሊያም ሩቶ የኬንያ አምስተኛው ፕሬዝዳንት በመሆን በሚቀጥለው ሳምንት ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ነሐሴ መጀመሪያ ላይ የተካሄደውን የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተከትሎ በቀረበለት ቅሬታ ዙሪያ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚሰጠውን ውሳኔ በርካታ ኬንያውያን በጉጉት ሲጠበቅ ነበር። በምርጫው ሂደት ላይ ተፈጽመዋል የተባሉ የማጭበርበር ድርጊቶችን በተመለከተ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰብሳቢ ማርታ ኮምቤ የቀረቡት ማስረጃዎች “ሐሰተኛ እና በስሜት ላይ የተመሰረቱ ናቸው” በማለት የሰባቱን ዳኞች ውሳኔ ይፋ አድርገው ውጤቱን አጽንተዋል። የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ውሳኔ ተከትሎ በምርጫው የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ እና ምክትላቸው ማርታ ካሩዋ በተሰጠው ብይን ደስተኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል። ኦዲናጋ ባወጡት መግለጫ ካሩዋ ደግሞ ትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ሁለቱም በተመሳሳይ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደሚያከብሩ ነገር ግን “ፈጽሞ እንደማይስማሙበት” ገልጸዋል። ይህ ውሳኔ በምርጫው ውዝግብ ላይ የመጨረሻው ብይን በመሆኑ የዊሊያም ሩቶ ፕሬዝዳንትነት እውን ሆኗል። የአገሪቱ የምርጫ እና ድንበር ኮሚሽን የወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳን ዊሊያም ሩቶን አብላጫ ድምጽ አግኝተዋል በማለት ተመራጭ ፕሬዝዳንት ሲል ማወጁ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የሩቶ ተቀናቃኝ ራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ውጤቱን በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል። የራይላ ኦዲንጋ ጠበቆች በምርጫው ሂደት ተአማኒነት የጎደላቸው አሠራሮች በማጋጠማቸው ፍርድ ቤቱ የምርጫ ውጤቱን ውድቅ እንዲያደርገው ጠይቀው ነበር። ለቀናት የሁለቱንም ወገን መከራከሪያ ሲያዳምጥ የነበረው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በሰጠው ውሳኔ የቀደመውን ውጤት አጽድቆታል። የዊሊያም ሩቶ እና የምርጫ ኮሚሽኑ ጠበቆች በበኩላቸው ምርጫው ስለመጭበርበሩ ምንም ማስረጃ አልቀረበም በሚል ውጤቱ እንዲጸና ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ እስካለፍነው አርብ ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም. ድረስ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር ሲያዳምጥ ቆይቶ፤ ዳኞች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት የጋራ ውሳኔ ለማሳለፍ በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሲሰሩ ቆይተዋል። ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት የፀጥታ ኃይሎች ዋና ከተማዋ ናይሮቢን ጨምሮ በበርካታ የአገሪቱ ግዛቶች ውስጥ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ተሰማርተው እንደሚገኙ ታይቷል። ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በናይሮቢ ውስጥ በሚገኘው በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ህንጻ ዙሪያ ያሉ ዋና ዋና መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ሆነዋል። ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ጋር በተያያዘ የአደባባይ ተቃውሞ ሊከሰትባቸው ይችላሉ ተብለው በተለዩ አካባቢዎችም የፀጥታ ጥበቃው ጥብቅ እንዲሆን መደረጉን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ከአምስት ዓመት በፊት በነበረው ምርጫ ተመሳሳይ ውዝግብ ተከስቶ የአሁኑ ከሳሽ ራይላ ኦዲንጋ ጉዳዩን ወደ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መውሰዳቸው ይታወሳል። በወቅቱም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አሁን የሚሰናበቱት የፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን የአሸናፊነት ውጤትን ውድቅ አድርጎ ምርጫው እንዲደገም ወስኖ ነበር። በተደገመው ምርጫም ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በድጋሚ አሸናፊ ሆነው ለሁለተኛ ዙር አምስት ዓመታት አገሪቱን ሲመሩ ቆይተዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cgl00v5ymv7o +health ኮሮናቫይረስ፡ በዩናይትድ ኪንግደም ከ10ሺህ በላይ ተጨማሪ ሰዎች በኮቪድ -19 መያዛቸው ተገለፀ ዩናይትድ ኪንግደም በስፋት ምርመራ ማካሄድ ከጀመረች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ10 ሺህ ሰዎች በላይ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን አስታወቀች። በአገሪቷ ላለፉት 28 ቀናት በተደረገ ምርመራ 12 ሺህ 872 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተገኙ ሲሆን፤ የ49 ሰዎች ሕይወትም አልፏል። በቴክኒክ ችግር ምክንያት በዚህ ሳምንት የተወሰኑ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ያልተመዘገበ ቢሆንም በቅዳሜ ዕለቱ መረጃ ላይ እንደተካተተ መንግሥት ገልጿል። መንግሥት ይህን ያለው በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የወጣው መረጃ የቫይረሱ ስርጭት ቀድሞ ከነበሩት ሳምንታት ቀስ በቀስ ሊጨምር እንደሚችል ካመላከተ በኋላ ነው። መረጃው በኢንግላንድ ምን ያህል ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ለማወቅ ከማሕበረሰቡ ውስጥ በተወሰደ የአጋጣሚ ናሙና ላይ በተደረገ ሳምንታዊ ምርመራ ላይ የተመሰረተ ነበር። የአገሪቷ መንግሥት በየዕለቱ የሚወጡ መረጃዎችም የቫይረሱ ሥርጭት ያለበትን የቅርብ ሁኔታ ስለሚያሳዩ በየዕለቱ የሚመዘገቡ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥርም በቅርበት እየተከታተልኩ ነው ብሏል። ይሁን እንጅ በሚቀጥሉት ቀናት የሚወጣው መረጃ በቀደመው ሳምንት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን እንደሚያካትት አሳስቧል። የጤና መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ መረጃው በዚህ መልኩ መውጣቱ ሰዎች የምርመራ ውጤታቸውን ከመቀበል አያግዳቸውም ብለዋል። ውጤታቸውም በተለመደው አግባብ እንደሚገለፅላቸው ቃል አቀባዩ አክለዋል። በዩናይትድ ኪንግደም እስከ ቅዳሜ እለት ድረስ 480 ሺህ 017 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በዩናይትድ ኪንግደም የታየው የቫይረሱ ሥርጭት መስፋፋትም በሌሎች የአውሮፓ አገራት ላይ ታይቷል። ፈረንሳይ ቅዳሜ ዕለት 16 ሺህ 972 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ይህም አዲስ የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው ተብሏል። በኔዘርላንድስ እና ቤልጂየም በቅደም ተከተል 3ሺህ 967 እና 3ሺህ 175 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ለአገራቱ ይህ በአንድ ቀን የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር መሆኑ ተገልጿል። በአውሮፓ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት ሩሲያም ከግንቦት ወዲህ ከፍተኛ የተባለውን 9 ሺህ 859 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መዝግባለች። በተለይ በአውሮፓ ወረርሽኙ እንደገና እያገረሸ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-54407550 +politics ኢራናዊው የዶናልድ ትራምፕ አማካሪን ለመግደል በማሴር ተከሰሰ "ኢራናዊው የዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጆን ቦልተንን ለመግደል በማሴር በአሜሪካ ክስ ቀረበበት። የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ (አይአርጂ) አባል የሆነው ሻህራም ፑርሳፊ በአሁኑ ወቅት ኢራን ውስጥ እንደሚገኝ እና በተጠረጠረው የግድያ ሴራ እንደሚፈለግ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ግለሰቡ ግድያውን ያሴረው በአሜሪካ ጥቃት ለተገደሉት የኢራን ኃያል ወታደራዊ አዛዥ ቃሴም ሶለይማኒ የበቀል ምላሽ ሳይሆን እንዳልቀረም ተናግረዋል። ሶለይማኒ በመካከለኛው ምስራቅ የነበረውን የኢራን ወታደራዊ ዘመቻን መርተዋል። የ62 አመቱ ወታደራዊ አዛዥ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃን ቡድን ኃይል የመሩ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2020 በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በ���ራቅ፣ በባግዳድ አየር ማረፊያ መገደላቸው ይታወሳል። የግለሰቡን ክስ አስመልክቶ የኢራን መንግሥት ቃል አቀባይ “ክሱ መሰረተ ቢስ ነው” ሲሉ ለመንግሥት ሚዲያ ተናግረዋል። የአሜሪካ የፍትሕ ዲፓርትመንት ክሱን ይፋ ባደረገበት ወቅት እንዳሳወቀው መህዲ ሬዛይ በመባል የሚታወቀው የ45 አመቱ ፑርሳፊ በዋሽንግተን ዲሲ ወይም ሜሪላንድ ግድያው እንዲፈጸም አሜሪካ ላሉ ግለሰቦች 300 ሺህ ዶላር ከቴህራን ሆኖ ለመክፈል ሞክሯል። በተጨማሪም በክሱ ላይ ፑርሳፊ በኢንተርኔት ላይ ላገኘው አንድ አሜሪካዊ የቀድሞ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጆን ቦልተንን ፎቶ እንዲያነሳው የጠየቀ መሆኑም ቀርቧል። ለዚህም እንደ ሽፋንነት የተጠቀመው ""መጽሐፍ እየጻፍኩ ነው"" የሚል እንደሆነ ተገልጿል። ይህ ስሙ ያልተጠቀሰ አሜሪካዊ ፑርሳፊን ሌላ ግለሰብ ጋር እንዳስተዋወቀው ያተተው ክሱ፣ ይህ ግለሰብ ጆን ቦልተንን እንዲገድል ለግድያው ማስረጃም ቪዲዮ እንዲልክ ተጠይቋል ብሏል። ጆን ቦልተን ኤፍ ቢ አይን እና የፍትሕ ክፍሉን ለዚህ ተግባራቸው አመስግነው መግለጫ አውጥተዋል። ""የፍትሕ ክፍሉ ዜጎቻችንን ሊጎዱ ወይም ሊገድሏቸው ከሚፈልጉ ከጠላት መንግሥታት የመጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት አለበት"" በማለት ረዳት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ማቲው ጂ ኦልሰን መናገራቸው ተዘግቧል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c90lvej7dq4o +sports ዓለም ዋንጫ፡ በሜሲ ድንቅ ጎል ታግዛ አርጀንቲና ወደ ድል ተመለሰች ሜሲ የተለመደበትን ድንቅ ብቃት አሳይቶ ጎል ባስቆጠረበት ምሽት አርጀንቲና ከፍተኛ ውጥረት የነበረበትን ጨዋታ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድሏን አለምልማለች። በሳዑዲ አረቢያ ከደረሰባት አስደንጋጭ ሽንፈት በኋላ አርጀንቲና ሌላ ሽንፈት ቢያጋጥማት ከጥሎ ማለፉ ውጭ መሆኗን ታረጋግጥ ነበር። ሜክሲኮዎች በተለይም በመጀመሪያው አጋማሽ ሜሲን እና ጓደኞቹ ተጭነው ለመጫወት ችለዋል። ሜሲ በ64ኛው ደቂቃ ያገኛትን የግብ ዕድል ተጠቅሞ በተዓምረኛ ግራ እግሩ ኳሷን ጉሌርሞ ኦቾአ መረብ ላይ አሳርፏል። ሜሲ በተለይም በመጀመሪያው አጋማሽ በጨዋታው ውስጥ ያለው ተሳትፎ ዝቅ ብሎ ነበር። ሃይል የተቀላቀለበት ጨዋታ መረጋጋት ሲጀመር አጥቂው ተጽዕኖውን ማሳየቱን የጀመረው። ኤንዞ ፈርናንዴዝ ጨዋታው መገባደጃ ላይ ለቡድኑ እፎይታ የሰጠች ጎል አስቆጥሯል። አርጀንቲና ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን ለማረጋገጥ ከፖላንድ ጋር ጠንካራ ፍልሚያ ይጠብቃታል። በሌላ የምድቡ ጨዋታ ፖላንድ ሳዑዲ አረቢያን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋዋን አሳድጋለች። ጨዋታው በፖላንድ 2 ለ 0 አሰናፊነት ተጠናቋል። ፒዮትር ዚየለንስኪ በመጀመሪያው አጋማሽ ፖላንድ ቀዳሚ ማድረግ ቻለ። በሁለተኛው አጋማሽ የሳዑዲ ተጫዋቾች የሰሩትን ስህተት ተጠቅሞ አምበሉ ሮበርት ሌዋንዶꬅውስኪ ሁለተኛ ኳስ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ይህቺ ጎል ለጎል ቀበኛው ሌዋንዶውስኪ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ጎሉ ሆና ተመዝግባለች። የፖላንዱ አጥቂ ከጎሏ በኋላ ደስታውን በእንባ ታጅቦ ገልጿል። ሳዑዲዎች ያገኙትን ፍጹም ቅጣት ምት  ወደ ጎል መቀየር ሳይችሉ ቀርተዋል። ከሁለት ጨዋታ በኋላ ፖላንድ ምድብ ሦስትን በአራት ነጥብ መምራት ጀምራለች። አርጀንቲና እና ሳዑዲ አረቢያ በእኩል ሦስት ነጥብ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በሚቀጥለው ሳምንት የሚደረጉ የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታዎች ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያልፉ ሃገራትን ይለያል። በምድብ ሦስት ደግሞ ፈረንሳይ ዴንማርክን በማሸነፍ ለጥሎ ማለፉ መብቃቷን አረጋግጣለች። ፈረንሳይ ዴንማርክን 2 ለ 1 በማሸነፍ ነው ሦስት ነጥብ ያሳካችው። ክሊያን ምባፔ የሰማያዊዎቹን ሁለት ጎሎች ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። የሁለቱ ቡድኖ�� ጨዋታ እስከ 61ኛው ደቂቃ ድረስ ጎል አላስተናገደም። ምባፔ በ61ኛው ደቂቃ ፈረንሳይ ቀዳሚ አደረገ። አንድሪያስ ክርስቲያንሰን ከሰባት ደቂቃዎች በኋላ ዴንማርክን አቻ ማድረግ ቻለ። ጨዋታው በዚህ ውጤት ሊጠናቀቅ ነው ተብሎ ሲጠበቅ ምባፔ በ86ኛው ደቂቃ ሁለተኛዋን ጎል ከመረብ አሳርፎ ቡድኑን አሸናፊ ማድርግ ችሏል። በሌላ የምድቡ ጨዋታ ቱኒዝያ አውስትራሊያ ተሸንፋለች። ሚቼል ዱክ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ አሳርፏል። በበርካታ ደጋፊዎች ታጅባ ወደ ሜዳ የገባችው ቱኒዝያው ውጤቱን መቀልበስ ሳትችል ቀርታለች። ከዚህኛው ምድብ ፈረንሳይ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። አውስትራሊያ በሦስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። ዴንማርክ እና ቱኒዝያ አንድ አንድ ነጥብ አላቸው። ፈረንሳይ ከቱኒዝያ እና ዴንማርክ ከአውስትራሊያ በሚያደርጉት ጨዋታ የምድቡ ሁለተኛ አላፊ ቡድን ይለያል። የዓለም ዋንጫው ዛሬም ቀጥሎ ይከናወናል። ዛሬ የምድብ አምስት እና የምድብ ስድስት ጨዋታዎች ይከናወናሉ። ጃፓን ከኮስታሪካ በሚያደርጉት ጨዋታ የምድብ አምስት ጨዋታ ውድድሩ ይቀጥላል። ስፔን ከጀርመን የሚያድርጉት የምድቡ ሌላኛው ጨዋታ በጣም ተጠባቂ ነው። ጀርመን ጨዋታውን ከተሸነፈች ከምድቡ መውደቋን ታረጋግጣለች። በምድብ ስድስት ደግሞ ቤልጂየም ከሞሮኮ እና ክሮሽያ ከካናዳ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/crgzzdpnpkxo +health ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት ገበያ እንዲወጣ የተባለው የአፕል ጭማቂ "በደቡብ አፍሪካ የሚመረተው ሲረስ የተባለው ታሸገ ጭማቂ ከፍተኛ መጠን ያለው ለጤና ጎጂ የሆነ ንጥረ ነገር በውስጡ በመገኘቱ ከሰባት የአፍሪካ አገራት ገበያ እንዲሰበሰብ መደረጉ ተዘግቧል። የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በበኩሉ ሲረስ አፕል ጁስ የተሰኘው ጭማቂ ""በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት"" ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ አውጥቷል። ባለስልጣኑ ስለተገኘው መርዛማ ንጥረ ነገር በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በኩል በሰጠው ማብራሪያ በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰት ማይኮቶክሲን ከሚባል ከሻጋታ የሚመነጭ መሆኑን አመልክቶ ኅብተሰቡ የተጠቀሰውን ምርት እንዳይጠቀም መክሯል። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተመርቶ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚሰራጨው ሲረስ የአፕል ጭማቂ በመበስበስና በመሻገት የሚከሰተው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር ስለተገኘበት ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ ነው። በጭማቂው ላይ በተደረገ ቤተ ሙከራ ፍተሻ እንደተረጋገጠው ሲረስ በተባለው የአፕል ምርት ላይ በአንድ ሊትር ውስጥ እንዲኖረው ከተፈቀደው 50 ማይክሮ ግራም ከፍ ያለ መጠን መገኘቱ ተገልጿል። ይህ የማይኮቶክሲን ውጤት የሆነው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር በአፕል እና በአፕል ምርቶች ውስጥ በሚከሰቱ በተለያዩ ሻጋታዎች አማካይነት የሚፈጠረው። በጭማቂው ውስጥ የተገኘው ንጥረ ነገር ፓቱሊን በተጠቃሚዎች ላይ ማቅለሽለሽና ማስታወክን በማስከተል ጤናን ሊያውክ ይችላል ተብሏል። ይህ ሲረስ የተባለው የአፕል ጭማቂ በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አመልክቶ ኅብረተሰቡ እንዳይ ጠቀመውና በገበያ ላይ ከተገኘም ጥቆማ እንዲሰጠው ጥሪ አቅርቧል። ምርቱ በተጨማሪም በኬንያ፣ በዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ በዛምቢያ፣ ዚምብብዌ፣ ኡጋንዳ፣ ሲሸልስ እና ሞሪሺየስ ገበያዎች ውስጥ ተሰራጭቶ እንደሚገን ተነግሯል። የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ የንግድ ቀጠና (ኮሜሳ) የንግድ ውድድር ኮሚሽን በአገራቱ ውስጥ ያሉ የምርቱ ተጠቃሚዎች ባለፈው ሰኔ ወር ተመርተው የተሰራጩ የሲረስአፕል ጭማቂ ምርቶችን ከገበያ አስወጥተው ለአምራቹ እንዲመልሱ ጥሪ አቅርቧል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58919812 +politics የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት በዕድል የተረፉበት የግድያ ሙከራ ቪዲዮ የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት ክርስቲና ፈርናንዴዝ ዴ ኪሪችነር ባለፈው ሐሙስ ምሽት ከተሞከረባቸው ግድያ ለጥቂት አምልጠዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቷ በጥይት ከመመታት የዳኑት የተኳሹ መሳሪያ በመንከሱ ነው ተብሏል። ዴ ኪሪችነር ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ሰላምታ በመስጠት ላይ ሳሉ ነበር አንድ ግለሰብ ከሕዝቡ መካከል ወጥቶ ፊታቸው ላይ ሽጉጡን አነጣጥሮ ለመተኮስ የሞከረው። ቪዲዮውን ይመልከቱ . . . https://www.bbc.com/amharic/articles/cxwrnvrj481o +politics ትግራይ፡ በአድዋ 'የኤርትራ ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ' ነዋሪዎች መገደላቸው ተገለጸ "በአድዋ ከተማ ሚያዚያ 04/2013 ዓ.ም፣ ሰኞ ረፋድ አካባቢ የኤርትራ ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ ነዋሪዎች እንደተገደሉና እንደቆሰሉ ተገለጸ። በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱምና የማዕከላዊ ዞን ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እንዳሉት ተኩሱ በኤርትራ ወታደሮች መከፈቱን ለቢቢሲ አረጋግጠው፤ በዚህም ሳቢያ ቢያንስ አንድ ሰው እንደሞተ ሲናገሩ ነዋሪዎች ግን ቁጥሩ ስምንት ነው ብለዋል። ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ደግሞ በክስተቱ ሦስት ሰዎች በኤርትራ ወታደሮች መገደላቸውንና ቢያነስ 19 ሰዎች መቁሰላቸውን ማረጋገጡን ለቢቢሲ ገልጿል። ድርጅቱ ጨምሮም ይህ ሁኔታ የኤርትራ ወታደሮች አሁንም በትግራይ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ያመለክታል ብሏል። ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀው የአክሱም ሆስፒታል ዶክተር ከትናንት ረፋድ ጀምሮ እስከ ከሰዓት በኋላ ድረስ 20 የቆሰሉ ሰዎች ከአድዋ እንደመጡ ለቢቢሲ ተናግሯል። ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ማኅበር (ኤምኤስኤፍ) እንዳለው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን ከአድዋ ሆስፒታል እንዳመጣቸው የሚናገረው ይህ ዶክተር ""ሁለት ሴቶች የሚገኙባቸው 20 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እያከምን ነው"" ብሏል። ኤምኤስኤፍ በበኩሉ ትናንት በትዊተር እንደገለጸው ሰኞ እለት 18 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አድዋ ኪዳነምህረት ሆስፒታል እንደመጡና እርዳታ እንደተደረገላቸው በመጥቀስ፤ 11 ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለከፍተኛ ህክምና ወደ አክሱም ሆስፒታል ተልከዋል ብሏል። ""ወታደሮቹ ጥቃት በደረሰባቸው ሰዎች ላይ መተኮሳቸው ነግረውኛል"" ብሏል። የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው ስድስቱ ከፍተኛ ጉዳት ስለ ደረሰባቸው በጽኑ የህክምና ክትትል ውስጥ ሲሆኑ፤ ከእነዚህ አንዷ ሴት እንደሆነች ቢቢሲ ያነጋገረው ሐኪም ገልጿል። የህክምና ባለሙያው እንደሚለው አንዳንዶቹ ሆዳቸው ላይ፤ የተቀሩት ደግሞ በተለያየ የሰውነታቸው ክፍል ጉዳት ደርሶባቸዋል። እነዚህ በ20ዎቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል የሚገኙ ሲሆን አንድ በ60ዎቹ የሚገኙ ግለሰብ እንደሆኑ ለማወቅ ችለናል። ጥቃቱ በአድዋ መናኽሪያ በመባል በሚታወቀው አካባቢ እንደሆነ ያረጋገጡልን በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱምና የማዕከላዊ ዞን ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስገዶም ስዩም፤ በመኪና ተጭነው ሲሄዱ የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች ""አንድ የባጃጅ አሽከርካሪ መንገድ ዘጋብን"" በሚል ጥቃት እንደፈጸሙ ተናግረዋል። ""ባለ ባጃጁ ጉዳት ደርሶበታል፤ አንድ ሰው እንደሞተም መረጃው ደርሶኛል። ሌሎች አምስት ሰዎች ደግሞ ተመትተው አክሱም ሪፈራል ሆስፒታል ይገኛሉ"" ብለዋል። በተጨማሪም ""የአክሱም ሕዝብም ሲሮጥ ነው የዋለው፤ የኤርትራ ወታደሮች ያገኙትን ሰው እየገደሉ እየመጡ ነው የሚል ስልክ ወደ አክሱም ተደወለ። ሕዝቡም ንብረቱን ትቶ፣ የከፈተው ሱቅ ሳይዘጋ ሸሸ"" ሲሉ አቶ አስገዶም ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ የኤርትራ መንግሥት የሰጠው ማብራሪያ የለም። በጉዳዩ ላይ የትግራይ ግብረ ኃይል ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ዮሐንስ ገብረመስቀልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማብራሪያ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ባለፈው ሳምንት ግን የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው የገቡት የኤርትራ ወታደሮች መውጣት እንደጀመሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ገልጾ ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ተጠቂዎችና ኗሪዎች እንደሚሉት የኤርትራ ወታደራዊ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች ጥቃት እንደፈፀሙ ነው። የአካል ጉዳት ደርሶበት አክሱም ሆስፒታል ላይ ከሚገኙት ታካሚዎች አንዱ የሆነው በጸጉር ሥራ ላይ የተሰማራው ወጣት፤ ሰኞ ጠዋት ወደ ሥራ እየሄደ ዲጋዲግ ተብሎ በሚጠራው የአውቶብሶች መናኽሪያ መኪና ላይ ሆነው የሚተኩሱ የኤርትራ ወታደር ልብስ የለበሱ ወታደሮች በጥይት እንደመቱት ለቢቢሲ ገልጿል። ""ሁለት የኤርትራ ሠራዊት የጫኑ የጭነት መኪኖች አንበሳ ባንክ አካባቢ ሲደርሱ መተኮስ ጀመሩ። አጋጣሚ አጠገቤ አንድ ሱቅ ነበርና ወደ እዚያ ልገባ ስሮጥ ሦስት ጊዜ ተኮሱብኝ። ሁለት ከጀርባዬ አንድ ደግሞ ሆዴ ላይ መታኝ።"" ተመሳሳይ ቆስሎ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው ሌላ ታካሚ አምስት ጥይት እንደተተኮሰበት በመግለጽ ""አንዱ አንገቴ አካባቢ፣ ሦስት ከጀርባዬ፣ አንድ ደግሞ እጄን መቶኛል"" ብሏል። ሰኞ እለት ጥቃቱ ሲፈጸም አካባቢው ላይ ማን ነበር ብሎ ቢቢሲ የጠየቀው ሌላ የአድዋ ከተማ ኗሪ በበኩሉ"" ወታደሮቹ ወደ ከተማዋ ሲገቡ፣ ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት አድዋ ላይ ምንም አይነት ጦርነት አልነበረም"" ብሏል። ከሰሞኑ የኤርትራ ሠራዊትን አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከትግራይ ክልል ግጭት ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ሲነሳ ለነበረው የኤርትራ ሠራዊት ተሳትፎ ምላሽ ሰጥተዋል። በዚህም የኤርትራ ሠራዊት በድንበር አካባቢ ""የደኅንነት ስጋት እንዳለበት"" ገልጾ በዚያው አካባቢ ሠራዊቱ እንዳለ ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፣ ለዚህም ምክንያቱ ""በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ በህወሓት የተፈጸመው ጥቃት እንደሆነ"" ተናግረው ነበር። በዚሁ ወቅት በተጨማሪ ትግራይ ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰትና በደሎች መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች መኖራቸውን ጠቅሰው መንግሥታቸው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል። ""እኛ ወታደሩን የላክነው ወንጀለኞችን እንዲቆጣጠር እንጂ እንዲደፍር አይደለም። በዚህ ወንጀል የተሰማራ ወታደር ካለ በሕግ ተጠያቂ ይደረጋል"" ማለታቸው የሚታወስ ነው። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀው መቃቃርና አለመግባባት ተካሮ የህወሓት ኃይሎች የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የፌደራሉን ጦር ወደ ትግራይ ማዝመታቸው ይታወሳል። በትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አሃዙ በበርካታ ሺዎች ሊሆን እንደሚችል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገርም በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ኃይሎች ግድያዎች፣ ጾታዊ ጥቃቶች፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ዘረፋና የንብረት ውድመቶች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ አመልከተዋል። በተጨማሪም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳለው በግጭቱ ሳቢያ ከሁለት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ለመፈናቀል የተዳረጉ ሲሆን፤ ከአራት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የ���ብአዊ እርዳታ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/news-56745429 +politics የእስራኤል ምርጫ ቅድመ ውጤት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ  እየመሩ እንደሆነ አመላከተ የቀድሞ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ትላንት ማክሰኞ በሀገራቸው በተከናወነው  ምርጫ  እየመሩ መሆናቸውን የቅድመ ምርጫ ውጤቶች አመላክተዋል። ከይፋዊ የምርጫ ውጤት በፊት ይፋ የሆኑ ቅድመ ውጤቶች እሳቸው የሚመሩት የቀኝ አክራሪ ፓርቲ በአነስተኛ አብላጫ ድምጽ እየመራ እንደሚገኝ አመላክቷል። ውጤቱም ለተከታታይ 12 ዓመታት በስልጣን ከቆዩ በኋላ ሃላፊነታቸውን ለቀው የነበሩትን ኔታንያሁ ወደ ፖለቲካው መድረክ የመለሰ ነው ተብሏል። በእየሩሳሌም ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግርም “ለታላቅ ድል ተቃርበናል” ብለዋል። ምርጫው ኔታንያሁን መደገፍ ወይመ አለመደገፍ ተደርጎ በስፋት ሲታይ ቆይቷል። ከሰዓታት በኃላ ይፋ እንደሚሆን የሚጠበቀው ዋናው ውጤት ከተጠበቀው በተቃራኒ ሊሆን የሚችልበት ዕድል አለ ተብሏል። ዋነኛ ተፎካካሪያቸው እና የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ያይር ላፒድ እስካሁን የተወሰነ ነገር የለም ብለዋል። የቅድመ ውጤቱ ይፋ ሲሆን በእየሩሳሌም ከሚገኘው የኔታናንያሁ ፓርቲ ቢሮ የተከፈተ ከፍ ያለ ሙዚቃ ተሰምቷል። የ73 ዓመቱ ኔታንያሁ በእስራኤል ፖለቲካ ውስጥ በአወዛጋቢነት ከሚነሱ ፖለቲከኞች አንዱ ናቸው። ጠንካራ ተቺዎች እንዳሏቸው ሁሉ ሰፊ ድጋፊም አላቸው። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1967 ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በኃላ እስራኤል በተቆጣጠረችው ዌስት ባንክ ላይ የዘረጉት የሰፈራ ፕሮግራም ጠንካራ ድጋፍ አስገኝቶላቸዋል። ምንም እንኳን እስራኤል ባትቀበለውም ይህ የሰፈራ ፕሮግራም ከዓለም አቀፍ ህግ አንጻር ህገ ወጥ እንደሆነ ይገመታል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በዌስት ባንክ እና በጋዛ ሰርጥ የፍልስጤምን እንደ ሀገር መመስረት የእስራኤል እና ፍልስጤምን ግጭት ለመፍታት የቀረበውን እና የባይደን አስተዳደርን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ድጋፍ የሚሰጠውን የመፍትሄ ሃሳብ ይቃወሙታል። ኔታናንያሁ በጉቦ፣በማጭበርበር እና የተጣለባቸውን እምነት በማፍረስ ተከሰው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ ሲሆን የሚቀርብባቸውን ክስ በሙሉ አይቀበሉትም። በእስራኤል ቴሌቪዥን የተላለፉ የቅድመ ምርጫ ውጤቶች በሀገሪቱ ፓርላማ ካለው 120 መቀመጫ የሳቸው ፓርቲ 61 ወይም 62ቱን እንዳገኘ ይፋ አድርገዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c84g3yj3x3lo +health የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የ3ዲ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ አደረጉ "በእንግሊዝ የ11 ዓመት ታዳጊ የ3ዲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኩላሊት ቀዶ ህክምና ተደረገላት። በአገሪቷ የ3ዲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኩላሊት ቀዶ ህክምና ሲደረግ የዚች ታዳጊ የመጀመሪያው ነው። በእንግሊዟ ዋቼት ግዛት ነዋሪ የሆነችው ሊቢ በኩላሊት እና በፊኛ ችግሮች እየተሰቃየች የነበረች ሲሆን ለረዥም ጊዜም በከፋ ህመም ትሰቃይ ነበር። ከሰሞኑም የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች የ3ዲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ትንሽ ቀዳዳ አበጅተው ፈጣን በሆነ እና በተሳካ መንገድ ቀዶ ህክምና በሊቢ ላይ ማድረግ ችለዋል። በመላ አገሪቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ልጆች በቀጣዩ ፈጣን የቀዶ ህክምና ሊደረግላቸው እንደሚችል ተነግሯል። ከ200 ህፃናት መካከል አንዱ ከተለጠጡ ኩላሊቶች ጋር የሚወለዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ቀዶ ህክምና የተደረገላት ሊቢ አደግ እስክትል ድረስ ሁኔታዋ አልታወቀም ነበር። ኩላሊቷን ከፊኛዋ ጋር የሚያገናኘው የሽንት ቱቦ በመዘጋቱም ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ገብታ ነበር። ህመሟም እየከፋ በመጣ ቁጥር የሊቢ ሁኔታ ለቤተሰቡ ""በጣም ��ስጨናቂ ነበር"" ሲሉ እናቷ ተናግረዋል። 4 ሚሊሜትር ስፋት ያለው እና ለአእምሮ ቀዶ ህክምና በአብዛኛው ጥቅም ላይ የሚውለውን የ3ዲ ቴክኖሎጂን መሳሪያ በመጠቀም ያለባት እክል ተስተክሏል። ቀዶ ህክምናው የተደረገላት በብሪስቶል የህጻናት ሆስፒታል ነው። ሊቢ ላይ ቀዶ ህክምና ያደረጉላት ዶክተር ማርክ ዉድዋርድ እንደተናገሩት 20 ሺህ ፓውንድ የሚያወጣው የ3ዲ መሳሪያ በቀዶ ጥገናው ወቅት ትክክለኛ ምስል እንዲያገኙና እንዲሁም በተቀላጠፈና በተሳካ መንገድ ቀዶ ህክምናውን ለማካሄድ አስችሎኛል ብለዋል። ዶክተሩ አክለውም የ3ዲ መሳሪያው በትክክል ቀዶ ህክምና ማድረግ የሚያስችል ሲሆን ሰልጣኝ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎችም በፍጥነት እንዲማሩ ያግዛል ብለዋል። የሊቢ ቀዶ ህክምና በተለምዶ ከሁለት እስከ ሶስት ሰአታት ይወስድ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን 3ዲ መሳሪያዎችን በመጠቀም ዶክተሮች በ 20 በመቶ መቀነስ እንደሚቻልም ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59782208 +politics አሜሪካ ፡ የፕሬዝደናት ዶናልድ ትራምፕን መከሰስ የፓርቲያቸው አባላት ጭምር እየደገፉ ነው "ዲሞክራቶች ፕሬዝዳንት ትራምፕን ጥቂት ቀናት ከቀረው ሥልጣናቸው ለማባረር የሚያደርጉት ጥረት ከሪፐብሊካን ፓርቲ አባላትም ድጋፍ እያገኘ መሆኑ ተነገረ። የፓርቲያቸው አባል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሥልጣን እንዲባረሩ የሚጠይቀው ክስ እንዲመሰረትባቸው ድጋፋቸውን ከገለጹት መካከል በተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛዋ የሪፐብሊካን ፓርቲ እንደራሴ ሊዝ ቼኒ፤ ባለፈው ሳምንት ዋሺንግተን ውስጥ ከነበረው ግርግር ጋር በተያያዘ ፕሬዝዳንቱ እንዲከሰሱ ድምጽ እንደሚሰጡ በይፋ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ለሳምንት ያህል ድምጻቸውን አጥፍተው ከቆዩ በኋላ ማከስኞ ምሽት በሰጡት ቃል ደጋፊዎቻቸው በአገሪቱ ምክር ቤት ላይ ለፈጸሙት ጥቃት ኃላፊነቱን እንደማይወስዱ ገልፀዋል። የዛሬ ሳምንት በአዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት የሚተኩት ዶናልድ ትራምፕን ከቀሯቸው የሥልጣን ቀናት በውርደት እንዲባረሩ ዲሞክራቶች ግፊት እያደረጉ ነው። የአገሪቱ ምክር ቤት በፕሬዝዳንቱ ላይ አመጽ በማነሳሳት በሚቀርብባቸው ክስ ላይ ዛሬ ረቡዕ ድምጽ የሚሰጥ ሲሆን፤ በዚህም ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ በስልጣን ዘመናቸው ሁለት ጊዜ የተከሰሱ መሪ ይሆናሉ። የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዲክ ቼኒ ሴት ልጅ የሆኑት ሊዝ ቼኒ በማለት የአንድ ፓርቲ መሪ የእራሳቸውን አባል ለመክሰስ መስማማታቸው በርካቶችን አስደንቋል። ባወጡት መግለጫ ላይ ትራምፕ ""በሕገ መንግሥቱና በገቡት ቃል ላይ ክህደት ፈጽመዋል"" ብለዋል። የዋዮሚንግ ግዛት ተወካይ የሆኑት ሊዝ ጨምረውም ፕሬዝዳንቱን ""አመጸኞቹን ጠርተው በማሰባሰብ የጥቃቱን እሳት ለኩሰዋል"" ሲሉ ከሰዋቸዋል። ሁለት ተጨማሪ የፕሬዝዳንቱ ፓርቲ አባላትም በትራምፕ ላይ የሚከፈተውን ክስ በመደገፍ ድምጻቸውን እንደሚሰጡ ተናግረዋል። በምክር ቤቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ የሆኑትና የትራምፕ ወዳጅ ኬቭን ማካርቲ ክሱን እንደሚቃወሙት የገለጹ ሲሆን፤ ነገር ግን የፓርቲያቸው አባላት በሙሉ በምክር ቤቱ ውስጥ የተቃውሞ ድምጽ እንዲሰጡ ጥሪ እንደማያደርጉ ተናግረዋል። ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ የሆኑት ሚች ማኮኔል ለቅርብ ሰዎቻቸው ተናገሩት ብሎ እንደዘገበው፤ ፕሬዝደንቱን በዲሞክራቶች መከሰሳቸው ትራምፕን ከፓርቲው ለማስወገድ ይረዳል ብለው እንደሚያምኑ አመልክቷል። ማኮኔል ለተባባሪዎቻቸው ጨምረው እንደተናገሩት ፕሬዝደንት ትራምፕ ሊያስከስስ የሚችል ጥፋት ፈጽመዋል ብለው እንደሚያምኑ ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55631984 +business የዩናይትድ ኪንግደም ፓውንድ የመግዛት አቅም ከዶላር አንጻር ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ዝቅ አለ ከአውሮፓውያኑ 1971 በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የዩናይትድ ኪንግደም ፓወንድ ከአሜሪካ ዶላር ጋር ሲነጻጸር ያለው ዋጋ ማሽቆልቆሉ ተነገረ። ፓውንድ ስተርሊንግ በእስያ ገበያ ያለው የመግዛት አቅም በ4 በመቶ የወረደ ሲሆን አንዱ ፓውንድ ዋጋ ቀደም ሲል ከነበረው ከ1.05 ወደ  1.0327 ዶላር ዝቅ ብሏል። ይህ የተሰማው የዩናይትድ ኪንግደም ቻንስለር ካዋሲ ከዋርቴነግ በከፍተኛ የብድር ድጋፍ የታገዘ ታሪካዊ የታክስ ቅነሳን ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው። በአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ እየተደረገ ያለው ዶላርን የማጠናከር እና የወለድ ምጣኔ ጭማሪ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ፓወንድ ከዶላር አንጻር ያለው የመግዛት አቅም ጫና ውስጥ እንዲገባ ምክንያት ሆኗል። በተጨማሪም ከዶላር አንጻር የዩሮ የመግዛት አቅም ከ20 ዓመት ወዲህ በእስያ ገበያ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ዝቅ ብሏል። ይህም በዩክሬን የተቀሰቀሰው ጦርነት ያስከተለው የነዳጅ ቀውስ መቼ እንደሚፈታ ምልክት አለማሰየቱ ባለሃብቶችን አሳስቧል ተብሏል። በአሁኑ ወቅት ሁሉም የመገበያያ ገንዘብ አይንቶች ከዶላር አንጻር ያላቸው አቅም እየተዳከመ ነው። ስለዚህ የአሜሪካ ዶላር ከፍተኛ ጥንካሬ እያሳየ ነው። ፓውንድን በታክስ ቅነሳ ለመደፍ መታሰቡ ማሽቆልቆሉን እንዲባባስ ያደርገዋል ሲሉ የአንድ የንግድ ተቋም ተባባሪ መስራች የሆኑት ፒተር ኢስኮ ተናግረዋል። “የኃይል አቅርቦት ላይ በቅርቡ የተደረገው ድጎማ እና የዩኬ ባንክ የአደጋ ጊዜ የዋጋ ጭማሪ ሊኖር እንደሚችል የሚጠቁመው ዜና የፍርሃት ምልክት ነው” ሲሉም አክለዋል። ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ የፌደራል ጠባባቂያ እና የዩኬ ባንክን ጨምሮ የበርካታ አገራት ማዕከላዊ ባንኮች የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል የወሰዱት የወለድ ምጣኔን የመጨመር እርምጃ የዓለም ገበያን እንዲቀዘቅዝ አድርጓል። ፓውንደ ከዶላር በታች ሀኖ የሚቆይ ከሆነ ጋዝ እና ነዳጅ ዘይትን ጨምሮ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ አሁን ካለው በላይ ሊወደደዱ ይቸላሉ። ከአሜሪካ ወደ ዩኬ የሚገቡ ሌሎች ምርቶችም ሊወደዱ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ሲሆን በበአላት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ የብርታኒያ ቱሪስቶች ቁጥር ከዚህ ቀደም ከነበረው ሊወርድ ይችላል ተብሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cv21qlrlx4po +politics በጦርነቱ ከአፋር ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ከ112 ሺህ በላይ መድረሱ ተገለጸ በአፋር ክልል ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ112 ሺህ በላይ መሆኑን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አስታውቋል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ከአፋር ክልል እና ከፌደራል መንግሥት ጋር በመሆን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እያደረስኩ ነው ብሏል። እስካሁን ድረስ ባለው 30 ሺህ ለሚሆኑና በአምስት ወረዳዎች ላሉ ቤተሰቦች ስንዴ፣ የጥራጥሬና የአትክልት ዘይት ማድረስ መቻሉንም የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስፍሯል። በትግራይ ኃይሎችና በፌደራሉ መንግሥት መካከል የተነሳው ጦርነት አስረኛ ወሩን ያስቆጠረ ሲሆን ወደ አጎራባች ክልሎችም ተዛምቶ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን አፈናቅሏል። የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ ባደረጉት ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችና ቁጥራቸው የማይታወቅ ተዋጊዎች ተገድለዋል። ከወራት በፊት የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም በማወጅ ወታደሮቹን ከመዲናዋ መቀለ እንዳስወጣ ቢገልፅም ህወሓት በበኩሉ መቀለን በኃይል እንደተቆጣጠረ ተናግሯል። የፌደራሉ መንግሥት የተኩስ አቁም በማወጅ ከትግራይ ለቆ ከወጣበት ምክንያቶች መካከል አብዛኛዎቹ የህወሓት የፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪዎች በመገደላቸውና በመታሰራቸው እንዲሁም የቀሩትን ጥቂት የህወሓት አመራሮች ለመያዝ ሲባል ጦርነቱን መቀጠል አስፈላጊ ባለመሆኑ ነው ተብሏል። በክልሉ ያሉ ነዋሪዎች የግብርና ወቅታቸውን እንዳይስተጓጎል፣ የረድዔት ድርጅቶች የበርካቶችን ህይወት እንዲያድኑ እድል ለመስጠት ነው የሚል መሆኑንም አስታውቋል። ህወሓት በስምምነት ላይ የተደረሰ የተኩስ አቁም እንደሚቀበል ያስታወቀ ሲሆን ካስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ከክልሉ የኤርትራ ወታደሮችና የአማራ ክልል ኃይሎች ወጥተው ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት እንዲመለሱ የሚጠይቀው ይገኝበታል። ባለፉት ወራት ጦርነቱን ተከትሎ በክልሉ ውስጥ ተፈጽመዋል የተባሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ ወገን እንዲመረመሩ እንዲሁም ቴሌኮም፣ መብራትና የአውሮፕላን በረራን ጨምሮ የተቋረጡ የመሠረተ ልማት አገልግሎቶች እንዲጀመሩም ጠይቋል። በአሁኑ ወቅት የጦርነት ክተት ጥሪ በየቦታው በሚቀርብበት በዚህ ወቅት ግጭቱ ወደ አዲስ እና ይበልጥ ደም አፋሳሽ ወደ ሆነ ምዕራፍ ሊያመራ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። https://www.bbc.com/amharic/news-58391134 +health ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ ኮሪያ በስፖርት ማዘውተሪያዎች ውስጥ ፈጠን ያሉ ሙዚቃዎች መጫወትን አገደች በደቡብ ኮሪያ የሰውነት ማጎልመሻ ማዕከላት ወይም በጂም ውስጥ የሚከፈቱ ሙዚቃዎች ለስለስ ያሉ እንዲሆኑ ደንብ ተላለፈ፡፡ ይህም የሆነው ፈጣን ምት ያላቸው ሙዚቃዎች ላብ እንዲፈጠር ስለሚያደርጉ፣ እንዲሁም ሰዎች ቶሎ ቶሎ እንዲተነፍሱ ምክንያት ስለሚሆኑ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በዋናነት የኮቪድ ሥርጭትን ሊያስፋፋ ስለሚችል ለስላሳ ሙዚቃዎች ማጫወት በተዘዋዋሪ ኮቪድን ሊገታ ይችላሉ ተብሎ የተዘየደ መላ ነው ተብሏል፡፡ በዚህ መመርያ መሰረት 120 ቢት በደቂቃ እና ከዚያ በታች የሆነ ምት ያላቸው ሙዚቃዎች ናቸው ተገቢ የሚሆኑትና በሰውነት ማጎልመሻዎቹ ውስጥ መጫወት የሚችሉት፡፡ ተንቀሳቃሽ ያልሆነ የመሮጫ መም (ትሬድሚል) ደግሞ ቢበዛ በሰዓት 6 ኪሎ ሜትር ብቻ እንዲፈጥን እንዲደረግ ታዟል፡፡ የጤና ባለሞያዎች እንደሚሉት ይህ መመሪያ ተግባራዊ ሲደረግ በስፖርት ማጎልመሻ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች አተነፋፈሳቸው ከልክ በላይ እንዳይሆን፣ ላባቸውም እንዳይንቆረቆር ያስችላል፡፡ ይህም የኮቪድ ስርጭትን ይቀንሳል ብለዋል፡፡ ደቡብ ኮሪያ ከትናንት በስቲያ እሑድ አንድ ሺህ አንድ መቶ አዳዲስ ሰዎች በኮቪድ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ድንጋጤ ተፈጥሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አርብ ዕለት እንዳስጠነቀቁት አገሪቱ በኮቪድ ምክንያት ትልቅ ምስቅልቅል ውስጥ ገብታለች፡፡ ከዚህ በላይ ጭንቅ መሸከም አትችልም፡፡ በዚህም የተነሳ መመርያዎቹ በጥብቅ እንዲተገበሩ አዘዋል፡፡ በዚህ መመሪያ ይበልጥ ተጸእኖ የሚደርስባቸው የዙምባና የኤሮቢክስ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የእንቅስቃሴ አይነቶች ፈጠን ያለ ሙዚቃን የሚሹ በመሆናቸው፡፡ በአዲሱ መመሪያ መሰረት ሰውነት ማጎልማሻ ማዕከላት ገብተው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያዘወትሩ ሁሉ ቢበዛ መቆየት የሚችሉት ለሁለት ሰዓታት ብቻ ሲሆን ገላቸውን መታጠብ የሚችሉት ደግሞ ቤታቸው ሄደው ነው፡፡ የጂም ባለቤቶች በበኩላቸው አዲሱ መመሪያ ግራ እንደሆነባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡ እንዴት ነው ለስላሳ ሙዚቃ ማጫወት ኮቪድን የሚከላከለው ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ ጨምረውም፣ በርካታ ሰዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ‹ጂም› ውስጥ በሚሰሩ ጊዜ በግል ድምጽ ማጫወቻ ነው ሙዚቃ የሚሰሙት፡፡ እነዚህ ሰዎች ታዲያ መንግሥት ያዘዘውን ለስላሳ ሙዚቃ እየሰሙ እንደሆነ መከታተል የሚችለውስ እንዴት ነው ሲሉ መሰ��ታዊ ጥያቄን አንስተዋል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-57796207 +business የአውሮፕላን በረራ የሚጀመረው መቼ ይሆን? የአውሮፕላን በረራ የሚጀመረው መቼ ይሆን? የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አገራት ከወሰዷቸው እርምጃዎች መካከል አንዱ በሆነው በአየር ትራንስፖርት እገዳ ምክንያት ዘርፉ ክፉኛ ተዳክሟል። በየዕለቱ በዓለም ዙሪያ ይደገሩ የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ በረራዎች በመሰረዛቸው የንግድ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በአብዘኛው ተቋርጧል። በዚህ ዓመት በዓለም ደረጃ የአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ 84 ቢሊዮን ዶላር ይከስራል ተብሎ ተገምቷል። በዚህም ሳቢያ አየር መንገዶች እከሰሩ ሠራተኞቻቸውን ከመቀነስ በተጨማሪ የተዘጉም አሉ። ለወራት በወረርሽኙ ምክንያት የተስተጓጎለው የአየር ትራነስፖርት መቼ ይጀምራል? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው። ባለሙያዎች በረራዎችን መልሶ ለማስጀመር የሚያስፈልጉ ያሏቸውን ጉዳዮች ያነሱበትን ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ። https://www.bbc.com/amharic/52891046 +politics ሶማሊላንድ ሕገ ወጥ ስደተኞች እንዲወጡ ቀነ ገደብ አስቀመጠች፣ ኢትዮጵያውያን ሰግተዋል ዓለም አቀፍ እውቅና የሌላት እና ከሶማሊያ ተነጥላ የወጣችው ሶማሊላንድ ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ ዜጎች አገሪቱን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች። የአገሪቱ የኢሚግሬሽን አገልግሎት ሐምሌ 21/2014 ዓ.ም. ባወጣው ማሳሰቢያ እስከ መጪው ነሐሴ 11/2014 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ያሳስባል። በተጨማሪም ሕገ ወጥ ስደተኞችን በሚያሰሩ ዜጎች ላይም እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል። ከሌሎች አገራት ዜጎች በተለየ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሶማሊላንድ ውስጥ በተለያዩ መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ በመሆናቸው ይህ ውሳኔ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል። በሶማሊላንድ የኢትዮጵያ ወኪል የሆኑት አቶ ሰኢድ መሐመድ ጂብሪል ጉዳዩን ቆንስላ ጽህፈት ቤታቸው እየተከታተለው እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “ከሶማሊላንድ መንግሥት ጋር እየተነጋገርን ነው። በመጪው ሦስት ቀናት ውስጥ ለውጥ ይኖራል ብለን እንገምታለን። እስካሁን ድረስ ግን በቁጥጥር ስር የዋለ ኢትዮጵያዊ የለም” ብለዋል። ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ በቀጥታ እውቅና ባትሰጥም ተጎራባች ግዛት በመሆኗ ግንኙነት ካላቸው ጥቂት አገራት መካከል አንዷ ናት። የሶማሊላንድ አምባሳደር በአዲስ አበባ እንዲሁም ኢትዮጵያም በሃርጌሳ ቆንስላ ጽህፈት ቤት አላቸው። ይህንን ተከትሎም ኢትዮጵያ የሶማሊላንድ የቅርብ አጋሮች ዝርዝር ውስጥ ትገኛለች። ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት ከዱባዩ ዲፒ ወርልድ ጋር የበርበራ ወደብን ለማልማት የሚያስችላትን 19 በመቶ ድርሻ መውሰዷ ብሎም ስምምነቱን የሶማሊላንድ ፓርላማ እንዳጸደቀው ይታወሳል። ይህ ስምምነት በያዝነው ዓመት ኢትዮጵያ ያላት ድርሻ መቋረጡን የሚያሳዩ መረጃዎች ከሶማሊላንድ መንግሥት ዘንድ የወጡ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሂደቱን አስተባብሏል። ጉዳዩም ገና መቋጫ ያልተበጀለት እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልጾ ነበር። መቀመጫቸውን በሶማሊላንድ ያደረጉት እና ከሚሰሩበት ተቋም ፖሊሲ ጋር ተያይዞ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈቀዱት ተንታኝ እንደሚሉት፣ ይህ አዲስ እርምጃ እንዳልሆነ እና ከአራት ዓመት በፊት ተመሳሳይ ውሳኔ ተላልፎ እንደነበር ለቢቢሲ ገልጸዋል። አክለውም ይህ የሶማሊላንድ ውሳኔ ከጫት ንግድ እና ከሌሎች የደኅንነት እንዲሁም የፀጥታ ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ነው ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ። “በሶማሊላንድ ያሉ ስደተኞች” ሲል የኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤቱ በድፍን ይናገር እንጂ ኢትዮጵያውያንን ኢላማ ያደረገ ነው በማለት፣ ለዚህም በአገሪቱ ከኢትዮጵያውያን ውጪ ያሉ የሌሎች አገራት ስደተኞች ጥብቅ የሰነድ ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው ጠቅሰዋል። “ለምሳሌ ፓኪስታኖች አሉ። ነገር ግን ቪዛቸው ጊዜው ካለፈ ራሱ ይቀጣሉ” ሲሉ ያክላሉ። “በሶማሊላንድ ያሉ ኢትዮጵያዊውን እንደ መደራደሪያ ናቸው። በሁለቱ መንግሥታት መካከል የጫት ንግድን የተመለከቱ ያለመግባባቶች አሉ። ከዛም ባሻገር በቅርቡ የተፈረመው የደኅንነት ስምምነት ለችግሩ ምክንያት ነው ብዬ አምናለሁ” ሲሉ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ ልማት ላይ የወሰደችው ድርሻ መሰረዙ ከተሰማ ወዲህ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን የያዘ ልዑክ ወደ ሃርጌሳ ተልኮ ነበር። የትራንስፖርት ሚንስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን ልዑኩን በሐምሌ ወር መጀመሪያ መርተው ተጉዘውም ነበር። በዚህ ሳምንት አጋማሽም በአገር መከላከያ የደኅንነት ሹም የተመራ ልዑክ ሃርጌሳ መግባቱን የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ታዲያ እነዚህ የንግድ ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ሁለቱ አገራት በቅርቡ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን በሃርጌሳ መቀመጫቸውን ያደረጉት የሰላም እና የደኅንነት ተንታኝ የሆኑት ግለሰብ ይናገራሉ። የሶማሊላንድ እና የኢትዮጵያ ድንበር በቀጭን ገመድ የሚለይ እና ሰፊ የንግድ እና ማኅበራዊ ልውውጦች ያሉበት ነው። እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ያለጥብቅ የድንበር ቁጥጥር ሶማሊላንድ ገብተው ይወጣሉ፤ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉትም በተለያዩ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ይኖራሉ። በተለይም የቤት ውስጥ ሥራ፣ ፀጉር ቤቶች እንዲሁም አነስተኛ ምግብ ቤቶችን ከፍተው ይሰራሉ። በቶግ ወቻሌ ከተማም በርካታ የኢትዮጵያ ባንኮች ቅርጫፎቻቸውን ከፍተው ይሰራሉ። በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ አዋሳኝ አካባቢዎችና ድንበር ተሻግሮ ባሉ ስፍራዎች ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግ ሲሆን፣ በሁለቱም በኩል ተንካራ የሆነ ግንኙነት እንዳለ ይታመናል። የሶማሊያ ታጣቂ ቡድን አል ሻባብ ከሳምንት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ በመግባት ጥቃት ከፈጸመ በኋላ የኢትዮጵያ ሠራዊት እና የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በቡድኑ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውና ከፍተኛ አመራሮቹ መገደላቸው መነገሩ ይታወሳል። ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ ድንበር በኩል አስካሁን ይህ ነው የሚባል የፀጥታ ስጋት ያልገጠማት ሲሆን፣ ይህንንም ለማጠናከር የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ባለፉት ቀናት በሃርጌሳ ጉብኝት ማድረጋቸው ተዘግቧል። https://www.bbc.com/amharic/articles/clmk47ley75o +politics የዩክሬን የህዋ ሮኬቶች ፋብሪካ መመታትና የአሜሪካ ተጨማሪ የሳዑዲን ነዳጅ ፍለጋ ባለፈው አርብ አመሻሽ ላይ ሩሲያ በማዕከላዊ ዩክሬን በምትገኘው ዲኒፕሮ ከተማ ላይ በፈጸመችው የረዥም ርቀት የሚሳኤል ጥቃት ሦስት ሰዎች ተገድለዋል። የአከባቢው ባለሥልጣናት እንዳሳወቁት ሚሳኤሎቹ የጠፈር ሮኬቶችን እና ሳተላይቶችን የሚያመርት ፋብሪካን እንዲሁም በአቅራቢያው የሚገኝ ጎዳናን መትተዋል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ይህ ፋብሪካ ለዩክሬን የሚሳኤል ግብአቶችን እና የተለያዩ ክፍሎችን ይሰራ ነበር ብሏል። የዲኒፕሮ ከተማ ሩሲያ ኃይሏን ባሰባሰበችበት ምሥራቃዊ ክፍል ጦርነቱን ሸሽተው የመጡ ዩክሬናውያን መጠለያም መሆኑ ተነግሯል። ክላቭዲያ የተባለች ነዋሪ አንድ ሮኬት ከመስኮቷ ፊት ለፊት እንደወደቀ ተናግራለች። “እንደዚህ ያሉ ጥቃቶችን ለማምለጥ የት መጠለል እንዳለብን ማወቅ ፈታኝ ነው። በቤታችን በታችኛው ክፍል፣ በቤቶች ጀርባ ሁሉም ነገር በጥቃቱ ይወድቃል፣ ይፈራርሳል” ስትል ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግራለች። ሩሲያ በምሥራቅ ዩክሬን ዶንባ��� አካባቢ የምታደርገው የምድር ጥቃት ቀዝቀዝ እያለ በአየር ላይ የምታደርሰው ጥቃት እየጨመረ መጥቷል። እነዚህ ጥቃቶች አብዛኛውን ጊዜ እየደረሱ ያሉት በከተሞች ማዕከላት ላይ ነው ተብሏል። ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ከኪዬቭ በስተምዕራብ በምትገኘው ቪኒትሲያ ከተማ ሩሲያ ባደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት 24 ሰዎች ተገድለዋል። ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዚዳንትነቱን መንበር በተቆጣጠሩበት የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት የሳዑዲ አረቢያን ገዥ ልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማንን ለማነጋገር ፈቃደኛ አልነበሩም። የአሜሪካ የደኅንነትና የስለላ ድርጅት ልዑል አልጋ ወራሹ በሳዑዲው ተቃዋሚ ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ እጃቸው አለበት ብሎ ያምናል። የጋዜጠኛው ግድያ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ድንጋጤን እንዲሁም ውግዘት ማስከተሉ ይታወሳል። ነገር ግን ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ጦርነት ያስከተለው ከፍተኛ መዘዝ ማሳያ የፕሬዚዳንቱ በመካከከለኛው ምሥራቅ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ሳዑዲ አረቢያ መጓዛቸው ነው። ሁለቱ መሪዎች በጀዳ በሚገኘው ንጉሣዊ ቤተ መንግሥት ግቢ ውስጥ ወዳጅነት ባለው መልኩ በጡጫ ሲነካኩ የሚያሳይ ፎቶ ወጥቷል። እንዲህ ፕሬዚዳንቱን ውሳኔያቸውን ያስቀለበሰው ጉዳይ ምንድን ነው? ዋነኛ ማጠንጠኛው የነዳጅ ዋጋ ነው። የዘይት፣ የነዳጅ በአጠቃላይ የኃይል ዋጋ በተወሰነ መልኩ ከዩክሬን ባለው ጦርነት  ምክንያት እያሻቀበ መጥቷል። አሜሪካ ያንን ዋጋ ዋጋ ለማውረድ ሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ምርቷን እንድትጨምር ፍላጎት አላት። https://www.bbc.com/amharic/articles/cjq9ev834l0o +health ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥን ያበረታቱት የሲሪሊንካ ሚኒስትር በቫይረሱ ተያዙ ከዕፅዋት የተሰራ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥን አገራቸው እድትጠቀም ያበረታቱት የሲሪላንካ የጤና ሚኒስትር በቫይረሱ ተያዙ። የጤና ሚኒስትሯ ፓቪትራ ዋኒያራቺቺ በዚህ ሳምንት በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን የመስሪያ ቤታቸው ሚዲያ ዘርፍ ፀሐፊ ለቢቢሲ አስታውቀዋል። የአገሪቱ የባህል ህክምና አዋቂ ለህይወት ዘመን የሚሆን የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥ ማምረታቸውን ተከትሎ ሚኒስትሯም አገራቸው እንድትጠቀም ሲያበረታቱ ነበር። ፓቪትራ ዋኒያራቺቺ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጡን በይፋ ሲጠጡም ታይተዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ በሲሪሊንካ 56 ሺህ 76 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 276 ዜጎቿንም አጥታለች። በቅርብ ወራትም በከፍተኛ ሁኔታ እያገረሸ ነው ተብሏል። የጤና ሚኒስትሯ በኮሮቫይረስ የተያዙ አራተኛ ሚኒስትር ሆነዋል። የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጡ ማርና ገውዝን ጨምሮ ከሌሎች ንጥረ ነገሮች የተቀመመ ሲሆን ውህዱም በህልም እንደተሰጣቸው የባህል ሃኪሙ ተናግረዋል። የአገሪቱ የጤና ባለሙያዎች የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያው ፍቱንነት አልተረጋገጠም ቢሉም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የባህል ሃኪሙ ወደሚገኝበት መንደር ይጎርፉ ነበር ተብሏል። የጤና ሚኒስትሯ ሁለት የኮቪድ-19 ምርመራ ቢያደርጉም ሁለቱም በቫይረሱ መያዛቸውን እንደሚያሳይ የሚዲያ ፀሃፊው ቪራጅ አብይሲንጌ ተናግሯል። ሚኒስትሯ ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩና የቅርብ ቤተሰባቸውም እንዲሁ ራሳቸውን እንዲያገሉ ተጠይቀዋል። ሲሪላንካ ለድንገተኛ ጊዜ የሚሆነውን የኦክስፎርዱን አስትራዜኔካ ክትባት ዜጎቿ እንዲከተቡ ፈቃድ ሰጥታለች። የመጀመሪያ ዙር ክትባት በሚቀጥለው ወር ይደርሳል ተብሏል። ፍቱንነቱ ያልተረጋገጠ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥ የአንድ አገር ባለስልጣን ሲያበራታቱ እሳቸው የመጀመሪያ አይደሉም። ባለፈው አመት የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆሊና ከዕፅዋት የተቀመመ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ ተገኝቷል ማለታቸው ከፍተኛ ትችትን እንዲያስተናግዱ አድርገዋቸዋል። በመዲናዋ መጠጡን ሲያከፋፍሉ ታይተዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ የአለም መሪዎች፣ ሚኒስትሮችና ባለስልጣናት በቫይረሱ ተይዘዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንና ዶናልድ ትራምፕ በቫይረሱ ተይዘው ማገገማቸው ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/news-55785136 +politics ፕሬዝዳንት ባይደን የ6 ትሪሊየን ዶላር ዕቅድ አውጡ "የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የ2022 የበጀት ዕቅዳቸው 6 ትሪሊየን ዶላር እንዲሆን ሲያረቁ፤ በዕቅዱ በዓመቱ ከፌዴራል በጀት ጉድለት ጋር በተያያዘ በየዓመቱ ከአንድ ትሪሊየን ዶላር በላይ ይጨምራል፡፡ ባለፈው ዓመት በዶናልድ ትራምፕ ከቀረበው የ4.8 ትሪሊየን ዶላር ዕቅድ የሚበልጥ ሲሆን የመሰረተ ልማት ማዘመኛ እና የተስፋፋ ማኅበራዊ የደኅንነት መረብን እንደሚያካትት ተስፋ ተደርጓል፡፡ ሐሳቡ ለኮንግረሱ የሚሰጥ ሲሆን እንዲተገበር ድጋፍ ይፈልጋል፡፡ ከጸደቀም አሜሪካን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ወጪዋን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍ ያደርገዋል፡፡ በጀቱ ፕሬዚዳንቱ ቅድሚያ የሚሰጡትን ነገሮች የሚያሳይ ፍንጭ ይሰጣል፡፡ በዚህም ባይደን ያቀረቡት ሐሳብ ተዛማጅ የሆነ የወጪ ደረጃዎች እና የተስፋፋ መንግሥት ራዕይ እንዳላቸው የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ ባይደን በጀቱ ""በቀጥታ በአሜሪካ ሕዝብ ላይ የሚውል እና የአገራችንን ኢኮኖሚ የሚያጠናክር እና በረዥም ጊዜም አጠቃላይ ኢኮኖሚውን የሚያሻሽል ነው"" ብለዋል፡፡ የፕሬዚዳንት ባይደን ዕቅዶች ለመንገዶች፣ ድልድዮች፣ የብሮድባንድ ኢንተርኔት እና የውሃ ዘርፍ ተጨማሪ ገንዘብን ያካትታሉ፡፡ የአዲሱ የወጪ ጭማሪ በመጪዎቹ 10 ዓመታት ለሦስት እና ለአራት ዓመት ሕጻናት ነጻ የቅድመ ትምህርት ቤት ለማቅረብ 200 ቢሊዮን ዶላር ይመድባል። 109 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ሁሉም አሜሪካውያኖች የሁለት ዓመት ነጻ የኮሚኒቲ ኮሌጅ እንዲያገኙ ያግዛል፡፡ ዴሞክራቱ ፕሬዝዳንት በርካታ የግብር ጭማሪዎችን እና ሌሎች ገቢ ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘዴዎችን ቢያቀርቡም ዕቅዱ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የብድር ዕዳውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል፡፡ በሪፐብሊካኖች ከፍተኛ ነው የተባለለት በጀት በኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ""ከጊዜ በኋላ በተሻለ የፋይናንስ ደረጃ ላይ ያደርሰናል"" ተብሎለታል፡፡ ኮንግረሱ አዳዲስ የወጪ ሒሳቦችን ለማፅደቅ እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ጊዜ አለው፡፡ አዲሱን በጀት ማሳለፍ ካልቻሉ የመንግሥት ሥራ በከፊል ሊዘጋ ይችላል፡፡ ዴሞክራቶች በምክር ቤቱ ውስጥ ጠባብ የአብላጫ ድምፅ አላቸው።" https://www.bbc.com/amharic/57291564 +health ኮሮናቫይረስ፡ ኩባ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማምረት የምታደርገው ጥረት ይሳካ ይሆን? "በኩባዋ ዋና ከተማ ሃቫና የሚገኘው ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት ምናልባት ከሌሎች የዓለማችን ማዕከላት አንጻር ሲታይ ያረጀና ጊዜ ያለፈበት ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በዚህ ማዕከል የሚሰራው የምርምር ሥራ እጅግ ዘመናዊ ነው። የአገሪቱ ከፍተኛ ተመራማሪዎች እረፍት አልባ ረጅም ፈረቃዎችን ጭምር በመስራት ለኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ መፍትሄ ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ነው። የክትባቱ ስም 'ሶቤሬና 2' የሚባል ሲሆን በኩባ ተመራማሪዎች ኩባ ውስጥ የተሰራ ነው። ይህ ክትባት በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፈቃደኞች ላይ ይሞከራል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ባለፉት ሳምንታት በተደረጉ ክሊኒካዊ ሙከራዎች በጣም አመርቂ የሚባል ውጤት የተመዘገበ ሲሆን ይህ አገሪቱ ክትባቱን ለማግኘት በምታደር��ው ጥረት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የኢንስቲትይቱ ዳይሬክተር ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ ቤንኮሞ ገልጸዋል። በኩባ መንግሥት እቅድ መሰረት ክትባቱ ክሊኒካዊ ሙከራውን ከጨረሰ በኋላ በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ አካባቢ ለሁሉም ዜጎች መሰጠት ይጀመራል። ""የእኛ እቅድ በመጀመሪያ ሕዝባችንን መከተብ ነው'' ይላሉ ዶክተር ቪሴንቴ። ""ከሕዝባችን በኋላ ምናልባት ለሌሎች አገራት መላክ ልንጀምር እንችላለን። ከ2021 መጨረሻ በኋላ ምናልባት 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን አምርተን ሕዝባችን ሙሉ በሙሉ ለመከተብ እቅድ ይዘናል።"" ይህ ክትባት የአሜሪካም ሆነ የየትኛውም አገር እርዳታ አልተደረገለትም። ኩባ በባዮቴክኖሎጂ ከ30 ዓመታት በላይ ልምድ ያላት አገር እንደመሆኗ ይህ ምንም የሚገርም ነገር አይደለም። በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ የኩባ ሳይንቲስቶች ለማጅራት ገትር ቢ (ሚኒንጃይተስ) ክትባት ካመረቱ የመጀመሪያዎቹ ሲሆኑ የወቅቱ የአገሪቱ መሪ ፊደል ካስትሮ መሰል ሥራዎችን ለማበረታታት ነበር ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት እንዲቋቋም ያደረጉት። በአሜሪካ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የሚሰሩ መድኃኒቶች ወደ ኩባ እንዳይገቡ ሲደረግ አገሪቱ በራሷ መንገድ መድኃኒቶቹን ማምረት ትችላለች በማለት ፊደል ካስትሮ ይከራከሩ ነበር። ነገር ግን አሁን ባለው ቴክኖሎጂ እና ዘመናዊ አሰራር እንኳን ያለ ሌሎች አገራት ድጋፍና እርዳታ 100 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦችን አምርቶ ሕዝቡን መከተብ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ""ክትባቱን በማምረት ሂደቱ ላይ ግንኙነት የፈጠርነው ከአውሮፓ አገራትና እና ካናዳ ጋር ነው። ከጣልያን እና ፈረንሳይ የመጡ ተመራማሪዎችም በሂደቱ ላይ ይሳተፋሉ"" ብለዋል ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ። አክለውም ""በሚያሳዝን ሁኔታ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የአሜሪካ ተሳትፎ የለም። ምናልባት ወደፊት በመሰል ሂደቶች ላይ ትብብር ሊኖረን እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን"" ብለዋል። እንደ ፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን መሰል ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኩባ ለኮሮረናቫይረስ የሚሆነውን ክትባት በማግኘት የመጀመሪያዋ የላቲን አሜሪካ አገር እንደምትሆን ተስፋ ያደርጋሉ። ""ኩባ ክትባቱን እንደምታገኝ ተስፋ እናደርጋለን'' ይላሉ በኩባ የድርጅቱ ተወካይ ዶክተር ሆዜ ሞቫ። ''የሶብሬና 2 ክትባት ሁለተኛ ደረጃ ሙከራ ውጤትን ከሰማን በኋላ ሂደቱን በቅርበት ስንከታተለው ነበር። ካለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ ኩባ የክትባቱን ውጤታማነትና ደኅንነት ስትመረምር እንደነበርም እናውቃለን።'' በአሁኑ ጊዜ በክትባቱ ዙሪያ ያለው ጉጉት ትልቅ ነው። በመጀመሪያ አገሪቱ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው። ወረርሽኙ በጀመረበት የመጀመሪያዎቹ ወራት ውስጥ በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ የነበረ ሲሆን ከብራዚልና ሜክሲኮ ጋር ሲነጻጸር ግን ቁጥሩ ብዙም አስፈሪ አይደለም። ነገር ግን የአገሪቱን የጤና ሥርዓት በእጅጉ ፈትኖታል። ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ ዓመት አጋማሽ ላይ ኩባ የወረርሽኙን ስርጭት መግታት ችላ ነበር። በዋነኛነት አየር ማረፊያዎችን በመዝጋትና የማኅበረሰቡን እንቅስቃሴ በመገደብ ነበር ይህንን ማሳካት የቻለችው። ሐምሌ እና ነሐሴ ላይ በጣም ዝቅተኛ የሚባል ስርጭትና ሞት ነበር የተመዘገበው። የፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን ተወካዩ በአሁኑ ጊዜ ያለው የቫይረሱ ስርጭት መቆጣጠር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ አልደረሰም ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ኩባ ውስጥ በወረርሽኙ ምክንያት በርካታ እንቅስቃሴዎች በመገደባቸው በጣም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ መላሸቅ አጋጥሟታል። እንደውም ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ ከፍተኛው የኢኮኖሚ መድቀቅ ነው እየተባለ ነው። ክትባቱ በአገር ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ደግሞ ሕዝቡን ከመክተብ ባለፈ ከሽያጭ ሊገኝ የሚችለው ገቢ ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ሁኔታ ሊረዳው ይችላል ተብሎ ይታመናል። በተጨማሪም ከትባቱን ከሌሎች አገራት ማስመጣት ሊያስከትለው የሚችለውን ወጪ ይቀንሳል። ኮሮረናቫይረስን ተከትሎ በኩባ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ባለፈው ዓመት ብቻ ኢኮኖሚው 11 በመቶ ኪሳራ አጋጥሞታል። በተጨማሪም የምግብ ሱቆችና ሱፐር ማርኬቶች አካባቢ ከፍተኛ ሰልፍና ግፊያም ታይቷል። በዚህ ወቅት ሁሉም ህጻናት ከትምህርት ቤት ቀርተዋል፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች በእጅጉ ተቀዛቅዘዋል፣ የእንቅስቃሴ ገደቦችም ቢሆን የዜጎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ አስቸጋሪ አድርጎታል። ስለዚህ የክትባቱ ዜና በርካቶች በጉጉት እንዲጠብቁት አድርጓቸዋል። የዚህ ክትባት ውጤታማ መሆን የዜጎችን ጤንነት ከመጠበቅ ባለፈ ለጎረቤት አገራት ከሚደረገው ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ኢኮኖሚውን እንደሚያነቃቃው ይታመናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56088539 +sports ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓራሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ በትዕግስት ገዛኸኝ አገኘች ትዕግስት ገዛኸኝ በፓራሊምፒክ ውድድር ላይ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት ታሪክ አስመዘገበች። ይህ በአትሌት ትዕግስት የተገኘው የወርቅ ሜዳሊያ በኢትዮጵያ የፓራሊምፒክ ተሳትፎ ታሪክ ውስጥ አገሪቱ ያገኘችው የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳልያ ነው። በጃፓን፣ ቶኪዮ እየተካሄደ ባለው የፓራሊምፒክ ውድድር ላይ በአንድ ሺህ አምስት መቶ ሜትር የሩጫ ውድድር ላይ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳሊያ ተመዝግቧል። በዚህ ውድድር ከትዕግስት በመከተል አሜሪካዊት አትሌት ሁለተኛ እንዲሁም ከአፍሪካ ቱኒዚያዊት ደግሞ በሦስተኛነት አጠናቀዋል። በዘንድሮው ፓራሊምፒክ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ሦስት አትሌቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ባለፈው ማክሰኞ ነሐሴ 18/2013 ዓ.ም በተጀመረው በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ በትዕግስት ገዛኽኝ ባገኘችው የወርቅ አማካይነት በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ላይ ከተወዳዳሪ አገራት መካከል የ35ኛ ደረጃን ለጊዜው ይዛለች። በዚህም በቶኪዮው የፓራሊምፒክ ውድድር ላይ ከሚሳተፉ የአፍሪካ አገራት ከደቡብ አፍሪካ፣ ከአልጄሪያ፣ ከቱኒዚያ እና ከናይጄሪያ በመቀጠል አምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓራሊምፒክ የተሳተፈችው እስራኤል፣ ቴል አቪቭ ውስጥ እ.አ.አ በ1968 በተካሄደው ውድድር ላይ ነበር። በ2012 በተካሄደው ፓራሊምፒክ ላይ አትሌት ወንድዬ ፍቅሬ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የብር ሜዳልያ አስመዝግቦ ነበር። ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የብር ሜዳልያ ያገኘችው በ2016 በሪዮ ደ ጄኔሮ የወንዶች 1500 ሜትር ሩጫ በአትሌት ታምሩ ደምሴ አማካይነት ነው። የቶኪዮ ኦሊምፒክን ጨምሮ ኢትዮጵያ በፓራሊምፒክ ውድድር እስካሁን ስምንት አትሌቶችን አሳትፋለች። ዛሬ ትዕግስት ገዛኸኝ ያስመዘገበችው የወርቅ ሜዳልያ በፓራሊምፒክ ታሪክ ለኢትዮጵያ ትልቁና ቀዳሚው ውጤት ነው። ማክሰኞ ነሐሴ 18/2013 ዓ.ም የተጀመረው የቶኪዮ ፓራሊምፒክ ውድድር ለ13 ቀናት ይካሄዳል። ኢትዮጵያን በፓራሊምፒክ ውድድር የሚወክሉት አትሌት ታምሩ ከፍያለው፣ አትሌት ገመቹ አመኑ እና አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ ናቸው። ቱኒዚያ ላይ በ1500 ሜትር በተደረገው የማጣሪያ ውድድር አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ 4:31:53 በመግባት አንደኛ በመሆን ማጠናቀቋ ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/58366879 +business ሩሲያ ቢትኮይንን ለውጭ ንግድ ግብይት ለመቀበል እያሰበች መሆኑ ተነገረ "ሩሲያ ወደ ውጭ አገራት ለምትልካቸው የነዳጅ ዘይ��ና ጋዝ ምርቶች ክፍያዎችን በቢትኮይን ለመቀበል እያሰበች መሆኑን አንድ የአገሪቱ ከፍተኛ የሕግ አውጪ ምክር ቤት አባል ገለጹ። ፓቬል ዛቫልኒይ እንዳሉት የሩሲያን የኃይል ምርቶች የሚገዙ ""ወዳጅ"" አገራት ክፍያቸውን በክሪፕቶከተንሲ ወይም በራሳቸው የመገበያያ ገንዘብ እንዲከፍሉ ሊፈቀድላቸው ይችላል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ""ወዳጅ ያለሆኑ"" አገራት የአገራቸውን የጋዝ ምርት ሲገዙ በሩሲያ ገንዘብ (ሩብል) እንዲከፍሉ ለማድረግ እንደሚፈልጉ ገልጸው ነበር። ይህ እርምጃቸውም በዚህ የፈረንጆች ዓመት ብቻ ከ20 በመቶ በላይ ዋጋውን ያጣውን ሩብል ጥንካሬ ለመመለስ እንደሆነ ተገምቷል። በዚህም ሩብል በከፍተኛ ሁኔታ ማንሰራራት አሳይቷል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን ተከትሎ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሕብረት የተጣሉባት ማዕቀቦች በአገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ ላይ ጫናን የፈጠረ ሲሆን የኑሮ ውድነትንም አንሮታል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ሩሲያ ለዓለም ገበያ ከፍተኛ መጠን ያለው የተፈጥሮ ጋዝን በማቅረብ ቀዳሚ ስትሆን በነዳጅ ዘይትም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በሩሲያ ምክር ቤት ዱማ ውስጥ የኢነርጂ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ፓቬል ዛቫልኒይ እንዳሉት፣ አገራቸው ወደ ውጪ ለምትልካቸው የነዳጅና የጋዝ ምርቶች መገበያያ አማራጭ የክፍያ መንገዶችን እያፈላለገች እንደሆነ አመልክተዋል። ጨምረውም ቻይናና ቱርክ በሩሲያ ላይ እየተደረገ ባለው ""የማዕቀቦች ጫና ውስጥ ያልተሳተፉ ወዳጅ"" አገራት ናቸው በማለት ጠቅሰዋል። ""ለረጅም ጊዜ ከቻይና ጋር የሚደረገውን የንግድ ልውውጥ በየአገሮቻችን መገበያያ ገንዘብ በሩብል እና በዩዋን እንድናደርገው ሃሳብ ስናቀርብ ቆይተናል"" ያሉት ዛቫልኒይ ""ከቱርክ ጋር በሊራ የምንገበያይ ይሆናል"" ብለዋል። ባለሥልጣኑ ጨምረውም ከአገራቱ የመገበያያ ገንዘብ በተጨማሪ ""በቢትኮይንም መገበያየት ይቻላል"" ብለዋል። ተንታኞች እንደሚሉት ግን አደጋዎች ሊኖሩት ቢችሉም ሩሲያ በታዋቂ ክሪፕቶከረንሲዎች መገበያየት ከጀመረች ተጠቃሚ ልትሆን ትችላለች። ነገር ግን ከተለመዱት የግብይት ገንዘቦች በተቃራኒ የቢትኮይን ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ተለዋዋጭ በመሆኑ የራሱ የሆነ አደጋን ሊያስከትል እንደሚችል በኢነርጂው ዘርፍ ባለሙያ የሆኑት ዴቪድ ብሮድስቶክ ይናገራሉ። የሩሲያ ከበርቴዎች በምዕራባውያን የሚጣሉ ማዕቀቦችን ለማምለጥ ሲሉ እነዚህ ክሪፕቶከረንሲዎች ሊጠቀሙ ይችላሉ በሚል የዩክሬን፣ የአሜሪካና የአውሮፓ ፖለቲከኞች የክሪፕቶከረንሲ የመገበያያ መድረኮች የሩሲያ ተጠቃሚዎችን እንዲያግዱ ጠይቀዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ ይህንን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60871774 +business ከ20 ሺህ ብር በላይ የሚወጣበት የኢትዮጵያ ዘመናዊ የንቅሳት ገበያ "ሰውነታቸው ላይ ንቅሳት ለማሳረፍ ወደ ንቅሳት ቤቶች ጎራ ከሚሉ ሰዎች መካከል በፍቅር ወይም በትዳር የተጣመሩ ጥንዶች ይገኙበታል። ""ጥንዶቹ ፍቅራቸውን ለመግለጽ ሴቷ የወንዱን፣ ወንዱ ደግሞ የሴቷን ስም አሊያም የስም መጀመሪያ ፊደላትን መነቀስ የተለመደ ሆኗል"" ይላል የንቅሳት ባለሙያው (ታቱ አርቲስት) ሔኖክ ጥላሁን። ሆኖም በጥንዶቹ መካከል ንፋስ ገብቶ መራራቅ ሲመጣ ""ለየብቻ ይመጡና ንቅሳቱን ቀይርልኝ"" ብለው እንደሚጠይቁት ይናገራል። ይህንን በመሰሉ አጋጣሚዎች የተሞላውን የንቅሳት ሥራ፤ ሰዎች ሐሳባቸውን ለማንጸባረቅ ያውሉታል። ዮሴፍ ተስፍዬ ይባላል። 28 ሺህ ብር አውጥቶ በሁለቱም እጆቹ ከትከሻው እስከ መዳፉ አንጓ 'የውስጤን ሐሳብ ይገልጹልኛል' ያላቸውን የተለያዩ ምስሎችና ጽሁፎች ��ነቅሷል። ለእሱ የደስታ ምንጭ የሆነው ንቅሳቱ በተመልካቾች ዘንድ ሁለት ዓይነት አስተያየት ይቀርብበታል። አንዱ ""ምን ነካህ?"" ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ""ያምራል"" የሚል ነው ይላል። ነገር ግን በሚሠራበት አካባቢ ንቅሳቱ እንዳይታይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግም ይናገራል። ሳምራዊት ተስፋዬ እና ኤልኤዘር ሙሴም በተመሳሳይ መነሻ የተለያዩ የሰውነት ክፍላቸውን ተነቅሰዋል። ለመሆኑ በአዲስ አበባ ምን አይነት ንቅሳቶች ይዘወተራሉ? ምን ያህል ገንዘብስ ይወጣባቸዋል? የንቅሳቶች ይዘት እና ምክንያት የንቅሳት ባለሙያው ሔኖክ ጥላሁን ቀደም ሲል ሥዕሎችን ይስል እንደነበር ይናገራል። እንደ ባለሙያው ገለጻ ንቅሳትም አንድ የጥበብ ዘርፍ በመሆኑ 'ሄና ታቱ' የሚል ድርጅት በመክፈት ንቅሳትን መተዳዳሪያው ካደረገ ከስምንት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል። ንቅሳት የሚፈልጉ ሰዎች ከተዘጋጀ የንቅሳት ዝርዝር ውስጥ መርጠው ወይም የፈለጉትን ማንኛውንም አይነት ምስል አሊያም ጹሁፍን ወደ ንቅሳት መቀየር ይቻላል ይላል። በብዛት ወደ እሱ የሚመጡ ሰዎች ሰውነታቸው ላይ እንዲያርፍ የሚርጡት ይዘት ሐይማኖታዊ መሆኑን ይናገራል። በተጨማሪም ጥንዶች ፍቅራቸውን ለመግለጽ ተመሳሳይ ንቅሳት ወይም አንዱ የሌላውን ስም ይነቀሳሉ። የእናታቸውን ወይም የአባታቸውን ምስል ወይም ስም የተነቀሱ ደንበኞች እንዳሉት የሚጠቅሰው ሔኖክ፤ በሌላ በኩል መስቀል፣ የቅዱሳን ሥዕሎችና መሰል ሐይማኖታዊ ይዘቶች በብዛት እንደሚዘወተሩ ያስረዳል። ብዙዎች ንቅሳትን ""የሚወዱትን ነገር መግለጫና ማሳያ አድርገው ነው የሚያዩት"" ሲል ይጠቅሳል። ሳምራዊት የግራ እጇ ከክንዷ በታች ያለው ክፍል ሙሉ በሙሉ በንቅሳት የተሸፈነ ነው። ""ስለ ወደደኝ አዳነኝ"" እና ""Be Happy"" የሚሉ ጽሁፎች፣ ሳቅን የሚገልጽ የስሜት ነጸብራቅ ምስል (emoji)፣ አበባ እንዲሁም ሌሎች ምስሎች አሉ። ደረቷ ላይ ""blessed"" የሚል ጽሁፍና አንገቷ ላይ ደግሞ መስቀል ተነቅሳለች። ኤልዜር የደረቱ አብዛኛው ክፍል ንቅሳት ያረፈበት ሲሆን፤ የነብርና ንስር ምስሎችን ነው የተነቀሰው። ዮሴፍ ደግሞ ሰዓት፣ አበባ፣ ኮምፓስና መሰል ምስሎችን በቀይና ጥቁር ቀለሞች በእጆቹ ላይ ተነቅሷል። ሳምራዊት ለሐይማኖቷ ያላትን ፍቅር ለመግለጽና ውስጧ ያለውን የተለያየ ሰሜት ለማንጸባረቅ እንደተነቀሰች ትገልጻለች። ዮሴፍ እና ኤልኤዘር ውስጣቸው የሚያምንበትና የሚወዱት ሐሳብ ሰውነታቸው ላይ እንዲታይ በማለም ነው አካላቸውን በንቅሳት የሸፈኑት። በተለይ ኤልኤዘር ለቤተሰቦቹ ያለውን ፍቅር ለመግለጽ መነቀሱን ተናግሯል። እነ ሳምራዊት በጠቀሷቸው ምክንያቶች ይነቀሱ እንጂ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጠባሳን ለመሸፈን ወይም ባህላዊ ንቅሳቶችን ወደ ዘመነኛ ለመቀየር ወደ ንቅሳት ቤቶች የሚያመሩ ሰዎች እንዳሉም ሔኖክ ይገልጻል። የንቅሳት ገበያ ኤልኤዘር ንቅሳቱን በተለያየ ጊዜ ማድረጉን ያስረዳል። ለዚህም እስከ 20 ሺህ ብር አውጥቷል። ሳምራዊት ደግሞ 15 ሺህ ብር በመክፈል ነው ንቅሳቷን ያሠራችው። ዝቅተኛው የንቅሳት ርዝመት አምስት ወይም ስድስት ሴንቲ ሜትር እንደሚረዝምና 500 ብር እንደሚያስወጣ ሔኖክ ይገልጻል። ንቅሳቱ ከፍ እያለ ሲሄድ ዋጋ እንደሚጨምር እንዲሁም ጀርባ ላይ የሚሠሩ ንቅሳቶች በአንድ ጊዜ እንደማያልቁና እስከ ሦስት ቀናት ሊፈጁ እንደሚችሉ ተናግሯል። ይህም እስከ 15 ሺህ ብር የሚወጣበት ነው። ታዲያ ይህ ሥራ ዋና የገቢ ምንጬ ነው የሚለው ሔኖክ ""በየቀኑ ሥራ አለ"" ሲል አስረድቷል። ንቅሳት ለመሥራት የሚውሉ መሣሪያዎች ከዘመኑ ጋር እየተጓዙ ነው የሚለው የንቅሳት ባለሙያው፤ ግብዓቶችን አገር ውስጥ ማግኘት ግን ፈታኝ መሆኑን እና የንቅሳት ��ርፌ ሳይቀር ከውጪ አገራት እንደሚገባ ይገልጻል። ""ንቅሳት ላይ ከቴክኖሎጂው በላይ የአርቲስቱ ጉዳይ [የባለሙያው አቅም] ነው ትልቁ ነገር"" ሲልም ጨምሯል። የተመልካቾች አስተያየት እና ልዩ ገጠመኞች ዮሴፍ ንቅሳቴን ሲያዩ ""የሚያማትቡ አሉ"" ይላል። ኤልኤዘር ደግሞ ""አንዳንድ ሰው የሚያየኝ እንደ ዱርዬ ነው። ባንክ ስገባ አንዳንድ ሰዎች ቦርሳቸውን የሚደብቁበት ጊዜ አለ"" ሲል ገልጾታል። ""ሁሉም ሰው አንድ አይደለም። ወጣቶቹ ይወዱታል። 'በጣም ያምራል' ይላሉ። ሌላው ደግሞ 'ኔጌቲቭ' አስተያየት ነው የሚሰጠው። 'ለምን እንዲህ አደርግሽ?' 'በሐይማኖት አይፈቀድም' ይላሉ"" ያለችው ደግሞ ሳምራዊት ናት። የንቅሳት ባለሙያው ሔኖክም በሥራው ብዙ ነገሮች እንደሚገጥሙት ይገልጻል። ፍቅረኞች ወይም ባለትዳሮች ፍቅራቸውን 'ለማጠንከር' በማሰብ ለመነቀስ ወደኛ ይመጣሉ የሚለው ሔሄኖክ፤ ከተሠራላቸው በኋላ ግን ተመልሰው የሚመጡ እንዳሉ ጠቅሷል። ""ይመጡና ይሄን ነገር አልፈለኩትም። የዚያን ጊዜ በደንብ አላሰብኩበትም። ይሄን ነገር ማጥፋት እፈልጋለሁ ይላሉ። ያው ማጥፋት ከባድ ስለሆነ በሌላ ዲዛይን ይሸፈናል።"" በሌላ በኩል ፊታቸው ላይ ንቅሳት ለማሠራት መጥተው እድሜያቸው ትንሽ ከሆነ ""በኋላ እንዳይጸጽታቸው"" ብለን እንመክራለንም ብሏል። ""አንዳንዴ ሰዎች ንቅሳተቱን ሳይጨርሱ የሚሄዱበት አጋጣሚ አለ - አመመኝ በሚል"" ሲልም ተናግሯል። አንዱን አጋጣሚ ሲያስታውስ፤ አንድ ደንበኛው ""የቅዱስ ሚካኤልን ምስል ጀርባው ላይ ለመነቀስ መረጠ"" ይላል። እናም ንቅሳቱ ተጀመረ። ""ሥዕሉ መልአኩ ሰይጣኑን ሲረግጥ የሚያሳየው ነው። እኛ ከሥር እየሠራን ነው ወደ ላይ የምንሄደው። ሰይጣኑን ወደ ማገባደድ ደርሰን ወደ ላይ እየወጣን ስንሄድ 'በቃ አልቻልኩም ይቅርብኝ' አለ። ለመጨረስ በተከታታይ ብደውልለትም አልመጣም። እስካሁን ሰይጣኑን ይዞ ነው የሚዞረው"" ሲል ያስታውሳል። ንቅሳቱ ሲሠራ በሚፈጠረው ህመም ምክንያት ንቅሳት ጀምረው ከሚያቋርጡ በተቃራኒው የንቅሳቱ መሣሪያ በሚፈጥው መጠነኛ ህመም 'እንደሚደሰት' ዮሴፍ አስረድቷል። ኤልኤዘር ደግሞ ""አንድ ጊዜ ፀበል ለጠመቅ ሄጄ ቄሱ አልጠምቅህም ብለውኝ ነበር [ንቅሳቱን አይተው]"" ብሏል። በሌላ በኩል ዮሴፍ ""ሰዎች እንደ ቁም ነገረኛ ስለማይቆጥሩኝ፤ ሥራ ቦታ 'ታቱ' እንዳለኝ የማያውቅ ብዙ ሰው አለ"" ሲል ገልጿል። ሳምራዊት በመነቀሷ ከቤተሰቧ አሉታዊ አስተያየት እንዳልገጠማትና እንዲያውም ስትነቀስ 15 ሺህ ብሩን ቤተሰቧ እንደከፈለላት ስትናገር፤ ከዚህ በተቃራኒ ኤልኤዘርና ዮሴፍ ቤተሰቦቻቸው ብዙም በአወንታዊ መንገድ አልተቀበሏቸውም። ንቅሳት እና ጤና የቆዳና የአባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ሐኪሙ ዶክተር ድጋፌ ጸጋዬ ""ዘመናዊም ይሁን ባህላዊ ንቅሳት ሹል በሆኑ ነገሮች እየወጉ ቀለምን ቆዳ ውስጥ በመጨመር ጌጦችን የመፍጠር ልምድ ነው ብለን ልንገልጸው እንችላለን"" ሲሉ ያስረዳሉ። ታዲያ ይህ ልምድ ከጤና አኳያ ሊታዩ የሚችሉ ጉዳዮች አሉትም ብለዋል። እንደ ዶ/ር ድጋፌ ገለጻ፤ ንቅሳት ቋሚ ሲሆን ሰዎች ግን ቀድመው ለንቅሳት የተነሱበት ፍላጎትና ስሜት በጊዜ ብዛት ሊቀየር ይችላል። በዚህም ምክንያት የተነቀሱ ሰዎች ከ40 ዓመታቸው በኋላ የሚጸጸቱበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል። በሌላ በኩል ""ንቅሳት ያለበት ሰው ደም እንዲሰጥ አይመከርም"" ያሉት ሀኪሙ፤ ለዚህም ምክንያቱ የንቅሳት መሣሪያዎች ለተላላፊ በሽታ ስለሚያጋልጡ ነው ብለዋል። ንቅሳት የቆዳ መቆጣት [allergic reactions] ሊፈጥር እንደሚችል ዶ/ር ድጋፌ ጠቅሰዋል። ""የሰውነት አለርጂው ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመጣል። ከተነቀሱ ከሳምንታት ብሎም ከ10 ወይም ከ15 ዓመታት በኋላ የቆዳ መቆጣት፣ የማሳከክ ወይም የማበጥ ስሜትን ሊያመጣ ይችላል"" ብለዋል። ንቅሳት የሚደረግበት ስፍራና የመሣሪያው ንጽህና ካልተጠበቀ ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ሊዳርግም ይችላል። ""ንቅሳት ያደረገ ሰው ኤምአርአይ የሚባለውን ምርመራ ማድረግ ቢፈልግ እንደ ንቅሳቱ አይነትና የቀለም አይነት ንቅሳቱ ባለት ቦታ ላይ የቃጠሎ ቁስል ሊያጋጥም ይችላል"" ሲሉም ያክላሉ። ቋሚ ንቅሳት መጥፋት ይችላል? አዎ መጥፋት ይችላል። ""አብዛኛውን ንቅሳት በሌዘር [በጨረር] ማሽን ማጥፋት የሚቻልበት ዕድል አለ"" ሲሉ ገልጸዋል - ዶ/ር ድጋፌ። ሕክምናው የብርሃንን ኃይል ወደ ሙቀት በመቀየር የሚሠራ መሆኑን የሚስረዱት ሐኪሙ፤ ጨረሩ ቆዳው ውስጥ ያለውን ቀለም በመሰባበር በደም አማካይነት እንዲወገድ ያደርጋል ብለዋል። ሕክምናው ተከታታይ ሲሆን፤ ለዘመናዊ ንቅሳት ከ6 እስከ 10 ጊዜ ቢሰጥ ""ከፍተኛ ለውጥ ሊመጣ የሚችልበት አጋጣሚ አለ"" ብለዋል - ቆዳን ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት ባይመልሰውም። ሕክምናው በእያንዳንዱ የክትትል ዙር እስከ 2500 ብር ሊያስወጣ እንደሚችል የሚገልጹት ሐኪሙ፤ ሰዎች ንቅሳት ከማሠራታቸው በፊት ደጋግመው እንዲያስቡበት መክረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57390536 +politics የጤና እክል ገጥሟቸዋል የተባሉት የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ከፈረንሳይ ተመለሱ የጂቡቲው ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ ከፈረንሳይ ወደ ጂቡቲ መመለሳቸውን ንብረትነቱ የመንግሥት የሆነው ቴሌቪዝን ጣቢያ አርቲዲ ጂቡቲ ዘገበ። ፕሬዝደንቱ ወደ ፈረንሳይ የሄዱት የጤና እክል ገጥሟቸው ነው የሚል ጭምጭምታ ለሳምንታት ሲሰማ ነበር። ነገር ግን የጂቡቲ መንግሥት ጭምጭምታውን አጣጥሎታል። የ73 ዓመቱ እስማኤል ኦማር ጉሌህ ፈረንሳይ ውስጥ እየታከሙ ነው የሚለውን የማኅበራዊ ሚዲያ ወሬ መንግሥት ሐሰት ነው ሲል አስተባብሎት ነበር። ትላንት ፕሬዝደንቱ ከአውሮፕላን ሲወርዱ እንዲሁም አቀባበል ላደረጉላቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ሰላምታ ሲሰጡ በብሔራዊው ቴሌቭዥን ጣቢያ ታይቷል። እንደ አርቲዲ ጂቡቲ ዘገባ፤ ፕሬዘደንቱ ወደ ፈረንሳይ ያቀኑት ለግል ጉብኝት ነው። ተቃዋሚ ፓርቲው ራሊ ፎር አክሽን ዴሞክራሲ ኤንድ ኢኮሎጂካል ዴቨሎፕመንት (አርኤዲዲኢ) ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ ከሳምንት በላይ ለሆነ ጊዜ ከሕዝብ ዕይታ መጥፋታቸው አጠራጣሪ ነው ብሏል። መሪው ከዕይታ ከመጥፋታቸው ባሻገር ስለ ጤና ሁኔታቸው ግልጽ መረጃ አለመሰጠቱንም ተቃዋሚ ፓርቲው ተችቷል። እአአ ከ1999 አንስቶ ሥልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዝደንቱ ለአምስተኛ ጊዜ የተመረጡት ባለፈው ግንቦት ወር ላይ እንደነበር ይታወሳል። ተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ተቀባይነት የለውም ብለውም ነበር። ጂቡቲ ለወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ የወጪና ገቢ ንግድ ዋነኛ መተላለፊያ ስትሆን ከወደብ ኪራይ ከፍተኛ ገቢን ታገኛለች። የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የሆነችው ጂቡቲ ቁልፍ በሚባለው የቀይ ባሕር ስልታዊው ስፍራ ላይ የምትገኝ ሲሆን በርካታ የዓለማችን ወታደራዊ ኃያል አገራት በአገሪቱ ውስጥ ወታደራዊ ሰፈር አላቸው። https://www.bbc.com/amharic/news-58628570 +politics ምርጫ 2013፡ የድምጽ መስጫ ቀን ላይ ለውጥ ሊኖር ይችላል ተባለ "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ በርቱካን ሚደቅሳ የ2013 አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ድምጽ መስጫ ቀን ላይ ለውጥ ሊደርግ እንደሚችል ተናገሩ። የቦርዱ ሰብሳቢዋ የስድሰተኛው ሃገራዊ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ""አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል"" ይችላል ሲሉ ተናግረዋል። ሰብሳቢዋ ቦርዱ በጉዳዩ ላይ እስካሁን የወሰነው ምንም ዓይነት የቀን ለውጥ አለመኖሩን አረጋግጠው፤ በመራጮች ምዝገባ እና በድምጽ መስጫ ቀናት መ���ከል መከናወን ያለባቸው ተግባራት መኖራቸውን አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በአንድ ዓመት የተራዘመውን አጠቃላይ ምርጫ ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 ለማድረግ አቅዳለች። ባሳለፍነው ቅደሜ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት፤ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚደቅሳ የሎጂስቲክ እና የደህንነት ጉዳዮችን እንደምክንያት በመጥቀስ፤ የድምጽ መስጫው ቀን ""አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል ይችላል ብዬ እገምታለሁ"" ሲሉ ተናግረዋል። ቦርዱ እስካሁን ድረስ ከ31 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። የምርጫ ቁሳቁሶችን ማከፋፈል፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ እና ስልጣና እንዲሁም የፓርቲዎች ግብዓት ማግኘት የሚሉት ተግባራት የመራጮች ምዝገባ ተጠናቆ እስከ ድምጽ መስጫ እለት የሚተገበሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። ""እነዚህን አይተን በሁለቱ መካከል ለማስገባት እንሠራለን። የሚያስፈልገው ነገር የሚወስደው ጊዜ ከታወቀ በኋላ አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል ይችላል ብዬ እገምታለሁ"" ብለዋል። በአዲስ አበባ እና በሌሎች ህዝብ በብዛት የሰፈረባቸው ቦታዎች የምርጫ ጣቢያ አለመኖሩን ያረጋገጡት የቦርዱ ሰብሳቡቢ ""ይህ የአሰራር ክፍተት ነው። ችግር በመሆኑ ኃላፊነትም የወሰድንበትም ጉዳይ ነው"" ብለዋል። የሕዝብ ቆጠራ አለመደረጉ እና ያለው መረጃ የቆየ መሆኑ የመራጮች ምዝገባ ግምት አስቸጋሪ ማድረጉን በምክንያትነት አስቀምጠዋል። ችግሩን ለመቅረፍ እየተሠራ መሆኑን በመጠቆም ""አዲስ አበባ ላይ ብዙ ቦታዎች ላይ በተለይም ኮንዶሚኒየም አካባቢዎች ላይ ከህዝብ ቁጥር አንጻር ያለመመጣጠን ነበር። በቀረው ጊዜ ብዙ ሰው እንመዘገባል ብለን እንገምታለን። የተሻለ ምዝገባ እንጠብቃልን"" ብለዋል። የመራጮች ምዝገባ የተራዘመባቸው ስፍራዎች የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን፤ በደህንነት ስጋት የመራጮች ምዝገባ ዘግይቶ በነበረባቸው አካባቢዎች የመራጮች ምዝገባ መጀመራቸውን ተናግረዋል። በኦሮሚያ በአራቱ የወላጋ ዞኖች፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ካማሺ እንዲሁም በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ምዝገባ መጀመሩን ተናግረዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን በተመለከተም ""በመተከል ዙሪያ ቦርዱ በትኩረት እየተከታተለው ነው። የደህንነት እና የተፈናቃዮች ሁኔታን ከግምት በማስገባት ምዝገባ ለማስጀመር እያየነው እንገኛለን"" በማለት እስካሁን መተከል ላይ የመራጮች ምዝገባ አለመጀመሩን ተናግረዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ 3 የምርጫ ክልሎችም አሁንም ምዝገባ አልመጀመሩን ጠቅሰው ከአባቢው የተፈናቀሉ ወደቦታቸው ስላልተመለሱ እና የደህንንነት ስጋት በመሆኑ ምዝገባ አለመጀመሩን አስረድተዋል። በደቡብ ክልል ደግሞ የሱርማ ልዩ እና ዲዚ ልዩ እስካሁን ምዝገባ አለመጀመሩ እንዲሁም በሶማሌ ክልል የምርጫ ምዝገባ ግድፈት ተፈጸሞባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች ቦርዱ ምዝገባውን መታገዱን አስታውቀዋል። የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎቸን አልክም ስለማለቱ የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መግባባት በለመቻሉ የምርጫ ታዛቢዎቹን እንደማይልክ ባሳለፍነው ሳምንት ማስታወቁ ይታወሳል። የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎችን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ""የውጭ ታዛቢዎች ሁለት ደረጃዎች አሉት። የመጀመሪያው ከመንግሥት ጋር የሚያልቅ ነው። . . . በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የሚጠናቀቅ ነው። [ሁለተኛው] በውጭ ጉዳይ ማረጋገጫ መሠረት ዕውቅና በመስጠት እናሰማራለን። አውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ባለመላኩ ቦርዱ አዝኗል። ከእኛ በፊት ከመንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ሳይጨርስ ነው ይህ ነገር የተፈጠረው��� ቢመጡ እንደምንወድ ለሂደቱም የሚጨምረው ነገር እንዳለ አረጋግጠንላቸው ነበር። በእነሱም በኩል ተመሳሳይ ግምት እና እምነት ነበር። . . . ቢመጡ መልካም ነበር። ከዚህ ያለፈ ሃሳብ መስጠትል አልችልም"" ብለዋል። ኢትዮጵያ ምርጫ ለመታዘብ ካቀደው የአውሮፓ ሕብረት ጋር ያልተስማማቸው ሕብረቱ ሉዓላዊነትን የሚጻረር ጥያቄን በማቅረቡ ነው ሲሉ የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መናገራቸው ይታወሳል። ሕብረቱ ኢትዮጵያ የሌላትን የኮሚኒኬሽን ስርዓት ወደ አገር ውስጥ ይዞ መግባትን እንደ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡ እና የምርጫ ውጤትን ይፋ የማድረግ እኔ ነኝ ማለቱን ተከተሎ ከስምምነት መድረስ አለመቻሉን የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/57056780 +sports ቡልጋሪያ ከ እንግሊዝ፡ የዩሮ 2020 ማጣሪያ ውድድር በደጋፊዎች ዘረኛ ስድብ የተነሳ ሁለቴ መቋረጡ ተሰማ "እንግሊዝ ለዩሮ 2020 ማጣሪያ በቡልጋሪያ፤ ሶፊያ ከተማ እያደረገች የነበረው ግጥሚያ ላይ የታደሙ የቡልጋሪያ ደጋፊዎች ዘረኛ የሆኑ ምልክቶችን በማሳየታቸውና ድምጾችን በማሰማታቸው የተነሳ ጨዋታው ሁለት ጊዜ መቋረጡ ተሰማ። በስታዲየሙ የነበሩት ደጋፊዎች የናዚ ሰላምታ ምልክት ያሳዩ ሲሆን እንደ ዝንጀሮ ይጮሁ እንደነበርም ተነግሯል። ጨዋታው መጀመሪያ የተቋረጠው እንግሊዝ 2 ለ 0 እየመራች ሳለ በ28ኛው ደቂቃ ላይ ነበር። • ዕድሜያችን የማቱሳላን ሲሶ እንኳ መሄድ የተሳነው ለምን ይሆን? • አሜሪካ ቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች • ""የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም"" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ በዚህ መካከል ስታዲየሙ ውስጥ በድምፅ ማጉያ ደጋፊዎች ከእንደዚህ አይነት ተግባራቸው እንዲታቀቡ መልዕክት የተላለፈ ቢሆንም፤ ነውጠኛ ደጋፊዎቹ ግን በድርጊታቸው ገፍተውበታል። በ43ኛው ደቂቃ ላይ ጨዋታው በድጋሚ ተቋርጧል። በዚህ ጨዋታ እንግሊዝ 6 ለ 0 የረታች ሲሆን ምድብ ሀ ላይ በመሪነት ስፍራውን ይዛ ትገኛለች። የእንግሊዝ የእግር ኳስ ማህበሩ ሊቀመንበር ግሬክ ክላርክ በስፍራው የነበሩ ሲሆን የተፈጠረውንም መታዘብ ችለዋል። የቡልጋሪያ ደጋፊዎች ተግባር በርካታ እንግሊዛዊያን ተጫዋቾችንና የቡድኑን አባላት ያስቆጣ ነው ብለዋል። ""በርካታ ዘረኛ የሆኑ ድምጾችን ሰምቻለሁ"" ካሉ በኋላም ""50 የሚሆኑ ሰዎች በቡድን በመሆን ጥቁር ለብሰው የፋሺስት ምልክት ሲያሳዩ ተመልክቻለሁ፤ እርግጠኛ መሆን ባልችልም ካለሁበት በ100 ሜትር ርቀት ላይ ነበር ምልክቱን የሚያሳዩ ደጋፊዎች የነበሩት"" ብለዋል። አክለውም የአውሮፓ እግር ኳስን የሚያስተዳድረው አካል በእለቱ ስለተፈጠረው ጉዳይ ጥልቅ ምርመራ ማድረግ እንዳለበትም ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። በጨዋታው ወቅት የተፈጠረው ምን ነበር? የእንግሊዙ ተከላካይ በቁጥጥሩ ስር የነበረውን ኳስ ካሻገረ በኋላ ከደጋፊዎች የሰማው ድምፅ ምን እንደሆነ ለማጣራት ዞረ፤ ከዚያም በደቂቃዎች ውስጥ ጨዋታው ቆመ። አጥቂው ሀሪ ኬን ከጨዋታው ዳኛ ኢቫን ቤቤክ ጋር ከተነጋገረ በኋላ በስታዲየሙ ውስጥ የተሰማውን ዘረኛ ንግግር የሚያወግዝ መልዕክት በድምፅ ማጎያ ተላለፈ። በዚሁ ሰዓት የቡድኑ ኃላፊ የተወሰኑ ተጫዋቾችን እያነጋገሩ ነበር። ከዚያም ጨዋታው እንዲቀጥል ቢደረግም የእረፍት ሰዓት ከመድረሱ አስቀድሞ በድጋሚ ሊቋረጥ ችሏል። ጨዋታው እንደገና ከመጀመሩ በፊት የቡድኑ ኃላፊ ከተጫዋቾቹ ጋር ተነጋግረዋል። የተወሰኑ ፊታቸውን የሸፈኑና ጥቁር የለበሱ የቡልጋሪያ ቡድን ደጋፊዎች፤ ጨዋታው ከእረፍት ከመመለሱ በፊት ስታዲየሙን ጥለው ወጥተዋል። ቢቢሲ ሬዲዮ 5 እንደዘገበው የተወሰኑት ዘረኛ እና የቀኝ ክንፍ አክራሪ ምልክቶችን ���ያሳዩ ነበር። እንግሊዝ በ2020 የአውሮፓ ማጣሪያ ጨዋታ ወቅት ዘረኛ መልዕክቶችን ስታስተናግድ ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። ከሞንቴኔግሮ ጋር በነበራትና 5 ለ 1 ባሸነፈችበት ጨዋታም እንዲሁ ዘረኛ የሆኑ መልዕክቶች በእንግሊዝ ተጫዋቾች ላይ ተሰንዝሯል። በዚህም የተነሳ ሞንቴኔግሮ 20ሺህ ዩሮና ሁለት ጨዋታዎችን ደጋፊዎቿ በሌሎበት ዝግ ስታዲየም እንድታካሄድ ተቀጥታለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-50052020 +business መካከለኛው ምሥራቅ ፡ ከእስራኤል ወደ አረብ ኤምሬትስ የመጀመሪያው የንግድ በረራ ሊደረግ ነው ከእስራኤል ወደ አረብ ኤምሬትስ ለመጀመሪያ ጊዜ የንግድ በረራ ሊካሄድ ነው። ይህም በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነት ጤናማ እየሆነ ስለመምጣቱ ጠቋሚ ነው ተብሏል። የእስራኤሉ ኤል አል አየር መንገድ የእስራኤል ልዑካንን እንዲሁም የአሜሪካ ባለሥልጣኖችን ይዞ የሦሰት ሰዓት በረራ ያካሂዳል። አውሮፕላኑ በሳዑዲ አየር ክልል እንዲበር ይፈቀድለታል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የእስራኤል አውሮፕላን በአየር ክልሉ ማለፍ አይችልም ነበር። በመካከለኛው ምሥራቅ፤ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እስራኤል ከተመሠረተች ወዲህ እውቅና የሰጠ ሦስተኛው የአረብ አገር ናት። አረብ ኤምሬትስ እስራኤል ላይ ከ1972 አንስቶ ተጥሎ የነበረውን ገደብ ቅዳሜ አንስታለች። በወሩ መባቻ ላይ ቀጥታ የስልክ መስመር ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል። በእስራኤል እና በአረብ ኤምሬትስ መካከል ያለው ግንኙነት የተለሳለሰው በአሜሪካ አሸማግይነት ሲሆን፤ ነሐሴ 13 ነበር ወዳጅነታቸውን ይፋ ያደረጉት። በአብዛኛው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ይህ ዜና በመልካም ቢወሰድም፤ ፍልስጤም ግን ተቃውሞዋን ገልጻለች። በተለይም የአረብ ኤምሬትስ ለፍልስጤም እውቅና ካልሰጠችው እስራኤል ጋር ግንኙነት መፍጠራቸው፤ ፍልስጤምን መክዳት ነው ተብሏል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ ከአረብ ኤምሬትስ ጋር ዳግመኛ መወዳጀታቸውን አስታከው በወረራ የተያዘውን ዌስት ባንክ በግዳጅ የእስራኤል ይዞታ የማድረግ እቅዳቸውን ለማዘግየት ተስማምተዋል። ፍልስጤም ይዞታው አገር የምመሠርትበት ነው ትላለች። https://www.bbc.com/amharic/news-53972550 +sports የኢራን ብቸኛዋ ሴት የኦለምፒክ ሜዳሊያ ባለቤት ሃገር ጥላ መሸሿን አሳወቀች የኢራን ብቸኛዋ ሴት የኦለምፒክ ሜዳሊያ ባለቤት ኪሚያ አሊዛዴህ ሃገር ጥላ እንደሸሸች አሳወቀች። የ21 ዓመቷ አሊዛዴህ በማሕበራዊ ድር-አምባ ገጿ ይፋ እንዳደረገችው፤ 'ሃገሬን ጥዬ የሸሸሁት በዋናነት ኢራን ውስጥ ያለው ግብዝነት፣ ውሽትና ኢ-ፍትሃዊነት አካል መሆን ባለመፈለጌ ነው' ብላለች። አሊዛዴህ ራሷን ኢራን ውስጥ ከሚገኝ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጨቋኝ ሴቶች አንዷ ስትል ትገልፃለች። አሊዛዴህ ያለችበትን ሥፍራ በይፋ ባታሳውቅም ኔዘርላንድስ ውስጥ ልምምድ ታደርግ እንደነበር ተነግሯል። 2016 ብራዚል በተካሄደው የሪዮ ኦለምፒክ ላይ በቴኳዋንዶ የስፖርት ዓይነት ብር በማምጣት ታሪክ ሠርታለች። ነገር ግን የኢራን ባለሥልጣናት ድሌን ለፕሮፖጋንዳቸው ተጠቅመውባታል ስትል በማሕበራዊ ገጿ መልዕክት ላይ አስፍራለች። ኢራን፤ በስህተት የዩክሬን አውሮፕላንን መትቼ ጥያለሁ ብላ ካመነች በኋላ ይህ ያበሳጫቸው ኢራናውያን አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ማሰማት በጀመሩበት ወቅት ነው አሊዛዴህ ሃገር ጥላ መሸሿን ያሳወቀችው። «ልበሽ ያሉኝን ለብሻለሁ፤ በይ ያሉኝን ብያለሁ። እያንዳንዷን ቃል አነብንብያለሁ። እኛ ማለት ለእነሱ [ለኢራን ባለሥጣናት] ግዑዝ ነን።» ምንም እንኳ መንግሥት የሷን ድል ለፕሮፖጋንዳ ቢያውለውም ባለሥልጣናቱ 'ሴት ልጅ እግሯን ማንሳት የለባትም' በማለ�� ያንጓጥጧት እንደነበር ይፋ አድርጋለች። አሊዛዴህ ወደ የትኛው ሃገር እንደሸሸች ይፋ ማድረግ አልፈቀደችም፤ አውሮጳ ናት ተብሎ የተነገረውንም አስተባብላለች። የኢራናውያን የአሊዛዴህን መሸሽ ሲሰሙ መደናገጣቸው አልቀረም። ፖለቲከኛው አብዶልካሪም ሆሴንዛዴህ 'አቅም የሌላቸው ፖለቲከኞች የሰው ኃይል እንዲሸሽ እያደረጉ ነው' ሲል ወቀሳውን አሰምቷል። አሊዛዴህ ቶክዮ በሚካሄደው ኦለምፒክ ላይ እንደምትሳተፍ ይጠበቃል። የኢራንን ባንዲራ ማውለብለቧ ግን እርግጥ አልሆነም። ሃገር ጥላ የሸሸችው አሊዛዴህ ስለ ወደፊት ዕቅዷ ምንም ያለችው ነገር ባይኖርም 'ሁልጊዜም የኢራን ልጅ ነኝ' ስትል መልዕክቷን ቋጭታለች። https://www.bbc.com/amharic/51087784 +sports "ሰሜን ኮሪያ ለቶክዮ ኦሎምፒክ ""እንዳትጠብቁኝ አልመጣም"" አለች" ሰሜን ኮሪያ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በሚደረገው የቶክዮ ኦሎምፒክ አልሳተፍም ብላለች፡፡ የማልሳተፈውም ‹ስፖርተኞቼ በኮቪድ ይለከፉብኛል ብዬ ስለምሰጋ ነው› ብላለች፡፡ ይህ የሰሜን ኮሪያ ውሳኔ ከየትኛው አገር በላይ ልቧን የሰበረው የደቡብ ኮሪያን ነው፡፡ ምክንያቱም ደቡብ ኮሪያ ይህን የኦሎምፒክ ጨዋታዎችን አጋጣሚ በመጠቀም ከባላንጣዋ ጋር የመቀራረብ ፍላጎትና ተስፋን አሳድራ ስለነበረ ነው፡፡ በ2018 ሁለቱ አገሮች ለዊንተር ኦሎምፒክ የጋራ ቡድን ማሰለፋቸው አይዘነጋም፡፡ ያ አጋጣሚ ሁለቱን አገሮች እንዲቀራረቡ ረድቷቸው ነበር፡፡ ፒዮንግያንግ አሁንም ድረስ ቫይረሱ ወደ አገሬ ድርሽ አላለም ብላ ትሟገታለች፡፡ የወረርሽኝና ተያያዥ የጤና ጉዳዮችን በውል የሚያውቁ ባለሙያዎች ግን ይህ የማይመስል ነገር ነው ይላሉ፡፡ የሰሜን ኮሪያ ቴሌቪዥን ይህን ‹ከኦሎምፒክ ወጥተናል› ውሳኔ ይፋ ያደረገው በመጋቢት 25 የሰሜን ኮሪያ የኦሎምፒክ ኮሚቴው ያደረገውን ስብሰባ ተከትሎ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት የወረርሽኙን መቀስቀስ ተከትሎ ሰሜን ኮሪያ ጥብቅ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምራ ነበር፡፡ ድንበሮቿን የዘጋችው ቀደም ብላ በጥር ወር ነበር፡፡ ወደ አገሯ የሚገቡ የውጭ ዜጎችንም ለይታ ማዋል ማሳደርም ጀምራ ነበር፡፡ በርካታ ድንበር ተሻጋሪ ባቡሮችና የሕዝብ ማመላለሻ መኪናዎች ወደ አገሯ እንዳይገቡ እግድ አስቀምጣ ነበር፡፡ በሁለቱ ወንድም-እህት ሕዝቦች መካከል በ1953 የኮሪያዎች ጦርነት ሲያበቃ የሰላም ስምምነት ባለመደረሱ ሰሜን ኮሪያ አሁንም ከደቡብ ኮሪያ ጋር በጦርነት ላይ እንዳለች ነው የምታምነው፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-56645978 +health የዓለም ጤና ድርጅት ለደሃ አገራት ክትባቱ እስኪዳረስ ሶስተኛው የኮቪድ ክትባት እንዲገታ ጠየቀ የዓለም ጤና ድርጅት ቫይረሱን የመከላከለል አቅም መጠን ለመጨመር በሚል የማበረታቻ ወይም ሶስተኛ የኮቪድ-19 ክትባት ቢያንስ እስከ መጪው መስከረም መገባደጃ ድረስ ገታ እንዲደረግ ጠይቋል። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም እንዳሉት መሰል እርምጃ ቢያንስ 10 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ ክትባቱን እንዲያገኝ ያስችላል። እንደ እስራኤልና ጀርመን ያሉ አገራት ደግሞ ሶስተኛ የኮቪድ-19 ክትባት ለዜጎቻቸው ለመስጠት ማሰባቸውን ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው። ነገር ግን ኃላፊው ደሃ የሚባሉት አገራት በክትባት ሂደቱ ወደኋላ እየቀሩ እንደሆነ አሳስበዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣው መረጃ መሰረት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራት ካለው የክትባት እጥረት አንጻር ለእያንዳንዱ 100 ሰው 1.5 ክትባቶችን ብቻ ማቅረብ እንደሚችሉ ያሳያል። ዶክተር ቴድሮስ ክትባቶቹ ተመልሰው መሰብሰብ እንዳለባቸውና ከተሰበሰበው ክትባት አብዛኛው ደግሞ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገራት መሰራጨት እንዳለበት አሳስበዋል። አክለውም ''��ሉም መንግስታት ዜጎቻቸውን ከአዲሱ የዴልታ ዝርያ ለመከላከል እያደረጉ ያሉትን ነገር እረዳለሁ። ነገር ግን በዓለማችን ያለውን አብዛኛውን ክትባት የተጠቀሙት አገራት መልሰው አሁንም ክትባቱን እንዲጠቀሙት መፈቀድ የለበትም'' ብለዋል። ከፍተኛ ገቢ ባላቸውና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት መካከል ያለውን የክትባት ልዩነት ለመቀነስ እየሰራ የሚገኘው የዓለም ጤና ድርጅት የአሁኑ ጥያቄው ከበድ ያለ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ድርጅቱ በሁሉም አገራት ከሚገኙ ዜጎች መካከል ቢያንስ 10 በመቶ የሚሆኑት እስከሚቀጥለው ወር መጨረሻ ድረስ ክትባቱን እንዲያገኙ እቅድ ያወጣ ቢሆንም ነገሮች አሁን እየሄዱበት ካለው ፍጥነት አንጻር ግን ላይሳካ እንደሚችል ተገምቷል። እንደ ሄይቲ እና ዴሞክራቲክ ኮንጎ ባሉ አገራት እስካሁን ድረስ ሁለተኛውን ዙር ክትባት የወሰደ ሰው የለም። ኢንዶኔዢያ ውስጥ ደግሞ ባለፈው ወር እንደ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን አገሪቱ ግን መከተብ የቻለችው 7.9 በመቶ የሚሆነውን ህዝቧን ብቻ ነው። በሌላ በኩል እስራኤል እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ አዋቂዎች ተጨማሪ ክትባት እንዲያገኙ እያሰራጨች ሲሆን ጀርመን ደግሞ ሞደርና እና ፋይዘር ክትባቶችን ለሶስተኛ ዙር ለማሰራጨት ማሰቧን ማክሰⶉ ዕለት አስታውቃለች። ከዚህ በተጨማሪ በዩናይትድ ኪንግደም ተጋላጭ ናቸው ተብለው የተለዩ ዜጎች ከመጪው ወር ጀምሮ ማጠናከሪያ ክትባቶችን እንደሚያገኙ ተገልጿል። አሜሪካ እስካሁን የማጠናከሪያ ክትባቶችን በተመለከተ ምንም ያለቸው ነገር ባይኖርም ዋይት ሃውስ ግን ረቡዕ ዕለት አሜሪካውያን በሙሉ እንዲከተቡ የሚያስችልና ለሌሎች አገራት ጭምር የሚላክም ክምችት እንዳለ አስታውቋል። ዶክተር ቴድሮስ ሀብታም አገራት ክትባቶችን ወደ ድሃ አገራት መላክ እንዲጀምሩ ሲጠይቁ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ግንቦት ወር ላይ ሀብታም አገራት ለህጻናትና ለታዳጊዎች ሚሰጡትን ክትባት ቀነስ አድርገው ወደ ደሃ አገራት ክትባቶቹን መላክ እንዲጀምሩ ጠይቀው ነበር። ኃላፊው ያደጉት አገራት ኮቫክስ በተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት በኩል በፍትሀዊነት ክትባቶቹን ለማድረስ እንዲሰሩ ቢጠይቁም እንደ ዩኬ ያሉ በርካታ አገራት ግን ህጻናትና ታዳዊቾን የመከተብ እቅዳቸውን በፍጥነት እየገፉበት ይገኛሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-58089449 +business ኢትዮጵያ ያለባት ዕዳ ስንት ነው? ዕዳዋን ባትከፍልስ ምን ይከተላል? የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በፍጥነት እያደገ መምጣት ይዟል። የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው ደርግ ከሥልጣን ሲወርድ የኢትዮጵያ ዕዳ 9 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ነገር ግን በ2006 የፈረንጆቹ ዓመት ይህ ዕዳ ወርዶ 2.2 ቢሊዮን ወርዶ የነበረ ቢሆንም፣ ከዚያ በኋላ ግን የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በቢሊዮን ዶላሮች ይጨምር ያዘ። የዓለም ባንክ በፈረንጆቹ 2020 ባወጣው መረጃ የአገሪቱ ዕዳ 30.36 ቢሊዮን ዶላር ነበረ። እነሆ ከሁለት ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ ከአገር ውስጥና ከውጭ የወሰደችው ብድር 56.6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ይላል የገንዘብ ሚኒስቴር። የኢትዮጵያ ዕዳ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት ግማሽ ያክል መሆኑን ተከትሎ ባሉ ወቅታዊ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ምክንያት አበዳሪዎች በኢትዮጵያ እና በሌሎች አገራት የብድር አከፋፈሉ ዙሪያ ውይይት ይዘዋል። ከኢትዮጵያ የውጭ አበዳሪዎች የአንበሳውን ድርሻ የምትይዘው ቻይና እንዲሁም ፈረንሳይ ናቸው ስብሰባውን የሚመሩት። የኢትዮጵያ አበዳሪዎች ዕዳ ስለማሸጋሸግ ውይይት ማድረግ የጀመሩት ባለፈው ዓመት ነበር። ነገር ግን በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት ጉዳዩን ���ጓተተው። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ)፣ የዓለም ባንክ፣ ሌሎች የገንዘብ ተቋማት ቻይና እና ሌሎች አበዳሪዎች ኢትዮጵያ፣ ቻድ እና ዛምቢያ ላለባቸው ዕዳ አስተያየት እንዲያደርጉ በመወትወት ላይ ናቸው። የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ዕዳ ኖሮባቸው ተጨማሪ ፈተና እየገጠማቸው ላሉ አገራት መፍትሔ መበጀት አለበት ሲሉ ለሮይተርስ ዜና ወኪል ተናግረዋል። ለመሆኑ ዕዳ ማሸጋሸግ ምንድን ነው? ኢትዮጵያ ዕዳዋን መክፈል ባትችል ምን ይፈጠራል? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2010 ዓ.ም. ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ኢትዮጵያ የነበረባት ዕዳ 28 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ነበር ይላሉ አየለ ገላን (ዶ/ር)። የምጣኔ ሃብት ተንታኙ እንደሚሉት በወቅቱ የተፈጠረውን የፖለቲካ ለውጥ የተመለከቱ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ልገሳና ብድር ሰጥተዋል። “ሁኔታው የተበላሸው ከተፈጠረው ትልቅ ተስፋ አንፃር መንግሥት የተበደረውን ገንዘብ ጥቅም ላይ አለማዋሉ ነው” ይላሉ ተንታኙ። “ብድሩን ተጠቅሞ ተጨማሪ ገቢ ማስገባት አለመቻሉ፤ በቂ ሥራ አለመፈጠሩና ገንዘቡ የውጭ ምንዛሬ አለማምጣቱ ችግር ፈጥሯል።” ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት በፊት የነበረው አስተዳደር የወሰደው ብድር ሳይመለስ እስከ 2012 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ቢያንስ ተጨማሪ 10 ቢሊዮን ዶላር ብድር መንግሥት መውሰዱ የዕዳውን መጠን እንዳሻቀበው ያምናሉ። “ብድር መክፈል ከዚህ ቀደም ከነበረው ይልቅ አሁን አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል።” ለኢትዮጵያና ሌሎች በርካታ የአፍሪካ አገራት ብድር ከሚሰጡ መካከል አንዱ የሆነው አይኤምኤፍ፣ በፈረንጆቹ 2020 ለኢትዮጵያ 3 ቢሊዮን ዶላር ብድር አፅድቋል። ሌሎች አበዳሪዎችና የዓለም ባንክም እንዲሁ ተጨማሪ 6 ቢሊዮን ዶላርመስጠታቸውን ተከትሎ አሁን ኢትዮጵያ ያለባት ዕዳ መጠን ከ38 ቢሊዮን ዶላር አያንስም ይላሉ ተንታኙ። አይኤምኤፍ ብድሩን ከማፅደቁ በፊት በ2019 ኢትዮጵያ ብድር ለመመለስ ከሚቸገሩ አገራት መካከል እንደሆነች ገልጦ ነበር። “ይህ ማስጠንቀቂያ የኢትዮጵያ ዕዳ መጠን በ2 ቢሊዮን ዶላር ቀንሶ በነበረ ጊዜ የወጣ ነው።” የዐቢይ አሕመድ መንግሥት አበዳሪዎች ለኢትዮጵያና ለሌሎች የአፍሪካ አገራት የዕዳ ሽግሽግ [ዴት ሪስትራክቸሪንግ] እንዲያደርጉ ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርብ ቆይቷል። ከሰሞኑ አበዳሪዎችና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ውይይት ጀምረዋል። የምጣኔ ሃብት ሙያተኛው አየለ ገላን፣ መንግሥት የ2015 ዓ.ም. በጀትን አስመልክቶ ባቀረበው ሪፖርት በቀዳሚነት ያሰፈረው ጉዳይ ብድር መመለስ መሆኑን ያወሳሉ። ኢትዮጵያ ከሰሜኑ ጦርነት በፊት ጀምሮ የዕዳ ሽግሽግ ጥያቄ ስታቀርብ ብትቆይም በጦርነቱ ወቅት ከአበዳሪዎች ጋር የነበራት የሻከረ ግንኙነት ችግር እንደፈጠረ ተንታኙ ይገልጣሉ። “መንግሥት በበጀት ድልድል ውስጥ ብድር መክፈልን ከላይ ሲያስቀምጥ አይቼ አላውቅም” የሚሉት ተንታኙ፤ ይህ የዕዳ ጫናው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያሳያል ባይ ናቸው። “አሁን የቀረበው የዕዳ ሽግሽግ ጥያቄ በአጭሩ ‘ብድሩ ከአቅም በላይ ስለሆነብኝ ማሻሻያ ይደረግልኝ’ ማለት ነው።” እንደ ተንታኙ ገለፃ ሽግሽጉ በዋናነት ሦስት መንገዶች አሉት። “አንደኛው ብድሩ ከአቅሜ በላይ ስለሆነ ይሰዘርልኝ ብሎ አበዳሪን ለማስማማት መሞከር ነው። ሁለተኛው፤ የብድሩ ወለድ ከፍተኛ ስለሆነብኝ ይቀነስልኝ የሚል ሊሆን ይችላል፤ ሦስተኛው ደግሞ ብድሩን ከፍዬ የምጨርስበት ጊዜ ይራዘም የሚል ነው።” አየለ (ዶ/ር) በዓለም አቀፍ ደረጃ ብድር ወስዶ በጊዜው አለመመለስ ወንጀል ነው ይላሉ። “ከዚህ ለመራቅ አገራት አበዳሪዎቻቸው ብድሩን እንዲሽሩላቸው የ��ቻላቸውን ያደርጋሉ። ይህ ካልሆነ ጥቁር መዝገብ ውስጥ ይገባሉ። ይህ ደግሞ ችግሩን የከፋ ያደርገዋል።” ከዚህ ቀደም ብዙ ጊዜ አበዳሪ ድርጅቶች የኢትዮጵያን ብድር እንደ ሰረዙ የሚያስታውሱት ተንታኙ በአሁኑ ድርድር ሊሆን የሚችለው የክፍያ ጊዜን ማራዘም እንደሚሆን ግምት አላቸው። የመሳካት ዕድል የሚያገኘው የክፍያውን ጊዜ ማርዘም ነው። “የክፍያ ጊዜን በማራዘም የሚደረግን ሽግሽግ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ መልካም ዜና ቢያየውም አደጋ አለው። ጊዜያዊ መፍትሔ ሊሆን ቢችልም የክፍያ ጊዜው በረዘመ ቁጥር የወለድ መጠኑም እየጨመረ ይመጣል። ይህ ለበለጠ ድህነት የሚዳርግ ነው። ‘ሾርት ተርም ጌይን፤ ሎንግ ተርም ፔይን’ (አጭር ጊዜ ጥቅም፤ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ጉዳት) ይሆናል።” በርካታ የልማት ተቋማት 40 በመቶ የሚሆኑ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ከባድ የብድር ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ይገልጻሉ። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) በፈረንጆቹ 2018 ባወጣው መረጃ አፍሪካ የዕዳ ቀውስ ውስጥ እየገባች ነው ሲል አስጠንቅቆ ነበር። ተቋሙ እንደሚለው ባለፉት አምስት ዓመታት የዕዳ ስጋት ያለባቸው የአፍሪካ አገራት ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል። ቻይና ለአፍሪካ አገራት ብድር ከሚሰጡ መካከል ቁንጮዋ ናት። ከአፍሪካ መንግሥታት መካከል 20 በመቶው የቻይና ዕዳ አለባቸው። 35 በመቶ ብድር የሚገኘው እንደ ዓለም ባንክ ካሉ ተቋማት ሲሆን፣ 32 በመቶ ደግሞ ከግል አበዳሪዎች ነው። ባለፉት 11 ወራት [እስከ ግንቦት ወር 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ] መንግሥት 330 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 309 ቢሊዮን ብር ብቻ መሰብሰቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ተናግረው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ እንደራሴዎች ፊት ቀርበው ባሰሙት ንግግር መንግሥት 500 ቢሊዮን ዶላር ወጭ አድርጓል ብለዋል። የኢትዮጵያ ወጪ ከገቢዋ አንጻር ያለው ልዩነት እንደህ እንዲሰፋ ያደረገው አገሪቱ ያለባት ዕዳ ነው። “በዚህ ዓመት 1.7 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ከፍለናል። ይህ መቶ ቢሊዮን ብር አካባቢ ማለት ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ የ2015 በጀት እንዲሆን የመደበው ገንዘብ 786.6 ቢሊዮን ብር ነው። በወቅቱ ከዚህ ገንዘብ መካከል አብዛኛው ለዕዳ ክፍያ፣ ለመልሶ ማቋቋምና ለመከላከያ ግንባታ የሚውል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ጠቅሶ ነበር። የምጣኔ ሃብት ሙያተኛው አብዱልመናን አሕመድ ኢትዮጵያን ወደ ኋላ ከሚጎትቱ ፈተናዎች መካከል አንደኛው አገሪቱ ያለባት ዕዳ ነው ይላሉ። አብዱልመናን መንግሥት የግል ዘርፉን የሚያበረታታ ፖሊሲ ካልቀረፀ ምጣኔ ሃብቱን ማሳደግ ሊከብደው ይችላል ብለው ያምናሉ። “የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ፣ የማክሮ ኢኮኖሚው ጉዳይ [ለምሳሌ የዋጋ ግሽበት] እና መንግሥት ያለበት የተጠራቀመ ዕዳ ማነቆ ሆነዋል።” ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት ያለበትን የዕዳ መጠን እንዲሁም ከአገሪቱ በጀት ገዘፍ የሚለው ለዕዳ ክፍያ መሆኑን ባስረዱበት ወቅት በርካታ እንደራሴዎች ጥያቄ አንስተው ነበር። የመንግሥት የበጀት አጠቃቀም ችግርና ብክነት እንዲሁም የአገር ውስጥ ገቢ የመሰብሰብ አቅም አለመጎልበት ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ይላሉ እንደራሴዎቹ። የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ከ2011-13 ዓ.ም. ባለው ዘመን ከዕቅድ በታች የሆነ 7.1 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል። ኢትዮጵያ ካለባት ዕዳ 97 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ የሚይዘው የረጅም ጊዜ ብድርና ‘ፐብሊክና ፐብሊክሊ ጋራንቲንድ’ የተሰኘ የብድር ዓይነት እንደሆነ ኢኮኖሚስቱ አየለ ገላን ይተነትናሉ። “የረጅም ጊዜ ብድር ማለት ክፍያው ከ30 እስከ 50 ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚከፈል ነው። ይህ ማለት ብድሩን መመ��ስ አሁን የተበደረው መንግሥት ኃላፊነት ላይሆን ይችላል ማለት ነው።” ‘ፐብሊክና ፐብሊክሊ ጋሪንቲንድ’ [በሕዝብ ንብረት ዋስትና የተገኘ ብድር] የተሰኘው ደግሞ ክፍያው መመለስ ባለበት ሰዓት የመመለስ ኃላፊነት ያለበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲሆን፣ ብድሩን የሚመልሰው የአሁኑ ትውልድ አይሆንም ማለት ነው ይላሉ ተንታኙ። ዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ሲያበድሩ ብድሩ በጊዜው የማይመለስ ከሆነ እንደ ዋስትና የሚይዙት ሃብት አሊያም ንብረት ይኖራል። አገራት ብድራቸውን መከፍል ሲሳናቸው ፕሮጀክቶቻቸው እንደ መያዣ ሲያዙ መስማት የተለመደ ሆኗል። ለምሳሌ ብቸኛው የዚምባቡዌ አየር መንገድ ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት መክፈል የነበረበትን ዕዳ ባለመክፈሉ እስከ 2019 ተይዞ ቆይቷል። አየር መንገዱ በ2019 በረራ ሲጀምር 2017 በተከማቸበት ከፍተኛ ውዝፍ ዕዳ ምክንያት ከግማሽ በላይ ሠራተኞቹን ለማሰናበት ተገዶ ነበር። ይህ ሳያንሰው ኤይር ዚምባብዌ በደኅንነት ስጋት ምክንያት በአውሮፓ አገራት አየር ክልል የመብረር ፈቃዱን ተነጥቋል። አንጎላ ደግሞ መክፈል ያለባትን 100 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ በገንዘብ መመለስ ባለመቻሏ ለቦትሰዋና ከብቶች በመስጠት ጭምር እየከፈለች መሆኑን በ2020 የአገሪቷ ጋዜጣ አስነብቦ ነበር። የምጣኔ ሃብት ተንታኙ አየለ ገላን እንደሚሉት ኢትዮጵያ ምን አስይዛ ብድር እንደምትወስድ እስካሁን በግልፅ አይታወቅም። የሌሎች አገራትም ልምድ ተመሳሳይ መሆኑን የሚገልጡት ባለሙያው አገራት ምን አስይዘው ብድር እንደሚወስዱ የሚታወቀው በተበዳሪውና በአበዳሪው መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ወደ ሕግ ሲያመሩ እንደሆነ ያስረዳሉ። “መንግሥት ሲበደር በእጁ የሚገኘውን የትኛውንም ሃብት አስይዞ ነው። ምንድነው የሚለው ግን ምስጢር ነው።” ተንታኙ በኬንያ እና ቻይና መካከል የተፈጠረውን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። “ኬንያ ከቻይና ወስዳ በነበረው ብድር ዙሪያ አለመግባባት ተፈጥሮ የሞምባሳ ወደብ እንደ ዋስትና ተይዞ እንደነበር ግልፅ የሆነው ቻይና ወደቡ የእኔ ነው ማለት ስትጀምር ነው። “ዛምቢያም እንዲሁ ከቻይና ተበድራ ለነበረው ገንዘብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተቋሟን ማስያዣ አድርጋ እንደ ነበር አለመግባባት ሲፈጠር ነው ያወቅነው።” ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎቿ ጋር ግልፅ የሆነ አለመግባባት ውስጥ ስላልገባች ምን እንዳስያዘች ማወቅ አዳጋች ነው ይላሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0gy1yvdpzo +health ከሥነ ልቦና አማካሪ ጋር የተወራ ሚስጥርን ለማጋለጥ የሚያስፈራሩት መዝባሪዎች "ፊንላንድ ውስጥ የሥነ ልቦና ምክር የሚወስዱ ሰዎች ለሀኪማቸው የተናገሩት ሚስጥር እየተሰረቀ ነው። የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች ይህን ሚስጥር ሰርቀው፤ ገንዘብ ካልተከፈላቸው ሚስጥሩን አደባባይ እንደሚያወጡት ያስፈራራሉ። በፊንላንድ የሚገኝ ትልቅ የሥነ ልቦና አማካሪ ክሊኒክ ውስጥ ህክምና ይከታተሉ የነበሩ ሰዎች ግላዊ መረጃ ተመዝብሯል። ቫስታሞ የተባለው ክሊኒክ ከ20 በላይ ቅርንጫፎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ታካሚዎች አሉት። የግል መረጃቸው የተመዘበረባቸው ሰዎች ለፖሊስ እንዲያስታውቁም ክሊኒኩ አሳስቧል። የክሊኒኩ የመረጃ ቋት የተመዘበረው በጎሮጎሳውያኑ በኅዳር 2018 እና በሚያዝያ 2019 እንደሆነ ይገመታል። ""መረጃ መዝባሪዎቹ ሀፍረተ ቢስ ናቸው"" ክሊኒኩ ከፖሊስ ጋር ተባብሮ እየሠራ እንደሆነ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። አሁን ላይ የመገናኛ ብዙኃን ክፍሉ የኢሜል አድራሻ አይሠራም። እስካሁን የ300 ታካሚዎች ግላዊ መረጃ ተሰርቆ በስውሩ ድረ ገጽ 'ዳርክ ዌብ' መታተሙን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል። ክሊኒኩ የታካሚዎች መረጃ መመዝበሩ ""ከባድ ቀውስ ነው"" ብሏል። ቫስታሞ፤ ታካሚዎች እርዳ��� የሚያገኙበት ነጻ የስልክ መስመር ከፍቷል። ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች አንድ ነጻ የምክር አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፤ የምክር አገልግሎቱ እንደማይቀረጽ አስታውቋል። የፊንላንድ መንግሥት ባለፈው እሑድ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል። የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ማርያ ኦሳሎ ""ልዩ ሁኔታ ነው"" ብለዋል። የበይነ መረብ ደህንነት ድርጅት የሆነው ኤፍ-ሰክዩር ሠራተኛ ሚኮ ሀፖነን ""መረጃ መዝባሪዎቹ ሀፍረተ ቢስ ናቸው። አንዳንዶቹ ታካሚዎች 18 ዓመት እንኳን አልሞላቸውም"" ሲል ተናግሯል።። ግላዊ መረጃቸው ከተሰረቀባቸው አንዱ የሆነው ጄሪ ለቢቢሲ እንደገለጸው፤ 'ዘ ራንሰም ጋይ' በሚል ራሱን የሚጠራ ሰው በቢትኮይን (ዲጂታል ገንዘብ) ጉቦ እንዲከፍል ጠይቆታል። መጀመሪያ ላይ የተጠየቀው 40 ዩሮ ቢሆንም፤ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ስላልከፈለ 200 ከዛም 500 ዩሮ ክፈል ተብሏል። ክፍያውን ካልፈጸመ ግን ወጣት ሳለ ከሥነ ልቦና ሀኪም ጋር ያደረገው ንግግር ይፋ እንደሚወጣም ተነግሮታል። ""ከሥነ ልቦና አማካሪዬ ያደረግኳቸው ንግግሮችን የያዘ ጽሑፍ በመረጃ መዝባሪዎች እጅ መግባቱ አስጨንቆኛል"" ብሏል ጄሪ። አያይዞም ""በጽሑፍ የተቀመጡትን ነገሮች ከተቀረው ዓለም ጋር ለመጋራት ዝግጁ አይደለሁም"" ሲል ስሜቱን ገልጿል። ከሀኪሙ ጋር ያወራው ነገር በማስታወሻ ደብተር ላይ ነበር የተጻፈው። ጽሑፉ ወደ ኮምፒውተር እንደሚሸጋገር አልተነገረውም ነበር። መረጃ መዝባሪው እንዲከፍል ያዘዘውን ገንዘብ የመክፈል አቅም እንደሌለው የሚናገረው ጄሪ፤ ""ብከፍልም እንኳን የግል መረጃዬ አደባባይ እንደማይወጣ ማረጋገጫ የለኝም"" ብሏል። መረጃቸው የተጋለጠባቸው 300 ሰዎች እጣ ፈንታ ይደርሰኛል ብሎ ይሰጋል። ግላዊ መረጃቸው ከመነበቡ ባሻገር ለማንነት ስርቆት ሊጋለጡ እንደሚችሉም ስጋት አለ።" https://www.bbc.com/amharic/54703285 +health እንግሊዛዊው 35 ኪሎግራም የሚመዝኑ ኩላሊቶቹ በቀዶ ህክምና ተወገዱለት "በአንግሊዝ ነዋሪ የሆነ አንድ ግለሰብ ሁለቱም ኩላሊቶች በከፍተኛ ደረጃ ትልቅ መሆናቸውን ተከትሎ እንዲወጡለት መደረጉን ሐኪሞች ተናገሩ። የ 54 ዓመቱ ዋረን ሂግስ በአጠቃላይ 35 ኪሎ ግራም የሚመዝኑትን የአካል ክፍሎቹን ለማስወገድ የሁለት ሰዓት ቀዶ ጥገና አድርጓል። ግለሰቡ ኩላሊቶቹ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ትልቅ ከመሆናቸው የተነሳ ክብረ ወሰንም ይዟል ተብሏል የአንድ ወድ ልጅ አባት የሆነው እና ፖሊሲስቲክ የተባለ የኩላሊት በሽታ ያለበት ግለሰቡ ""በየትኛውም መንገድ ቢለካ"" ትልቅ ኩላሊት ያለው በመሆን ክብረ ወሰን እንደሚሰብር ሐኪሞቹ እንደነገሩት አስታውቋል። በሆዱ መጠን ላይ ያለውን ልዩነት ""አስገራሚ ነው"" ብሏል። ከእንግሊዟ ዊንድሶር የመጣው ሂግስ ትልቁ የቀኝ ኩላሊቱ 15 ኪሎ ሲመዝን ተጨማሪ 5 ኪሎ የሚመዝን ፈሳሽም በላዩ ላይ ነበር ብሏል። ቀደም ሲል በዓለም ላይ ትልቅ የነበረው ኩላሊት በሕንድ በቀዶ ጥገና የተወገደው እና 7.4 ኪ.ግ የሚመዝነው እንደሆነ ይታመን ነበር። ""የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ሁሉንም አረጋግጦ ነበር። እናም አዎ በእያንዳንዱ መለኪያ ክብረ ወሰኑን አሻሽለነዋል።"" ብሏል። ""ርዝመቱ በሚለካበት ጊዜ፣ ከያዘው ፈሳሽ ጋር ሲመዘን እና ፈሳሹ ከተወገደ በኋላም አሻሽዬዋለሁ።"" ያለው ግለሰቡ ሆኖም ""ይህ የምኮራበት ነገር አይደለም።"" ይላል ፒኬዲ በኩላሊት ውስጥ ሲስቲክ የሚባሉ ትናንሽ ፈሳሽ የተሞሉ ከረጢቶች እንዲፈጠሩ ያደርጋል። ከአምስት ዓመት በፊት በውርስ የሚመጣው ህመም ኩላሊቶቹ ከሚገባው በላይ አምስት እጥፍ እንዲያድጉ አድርጓቸዋል ሲሉ ዶክተሮቹ ተናግረዋል። ኩላሊቶቹ ሳንባውን፣ ሆዱን እና ልቡን መጉዳት ስለጀመሩ ""ሕይወት አድን"" ቀዶ ጥገና መደረጉ አስፈ��ጊ መሆኑ እንደተነገረው ሂግስ አስታውቋል። በተጨማሪ ትልቅ የሆድ እብጠት እንዲኖረው ምክንያት ሲሆን እብጠቱ ከሐምሌው ቀዶ ጥገና በኋላ ""አስደናቂ"" ለውጥ አምጥቷል ብሏል። ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት ወደ ጂምናዚየም የተመለሰ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመትም በኤሌክትሪክ ብስክሌት ትሪያትሎን (ሩጫ፣ ዋና እና ሳይክልን ያካተት ውድድር) ላይ ለመወዳደር በጉጉት እየተጠበቀ ነው። የቀድሞው የሂሳብ ባለሙያው በየሁለት ቀኑ የዲያሊሲስ ማድረጉ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰበት መሆኑን ጠቅሷል። ""በዲያሊሲስ ማለፍ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መግለጽ አልችልም"" ብሏል። በሚቀጥለው ዓመት ለኩላሊት ንቅለ ተከላ ብቁ ለመሆን በመዝገቡ ውስጥ እንደሚገባ ተስፋ ያደርጋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58825476 +sports አንጋፋው የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔ ሲታወሱ በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፖርቶች ውስጥ አሻራቸውን ካሳረፉ ሰዎች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ። በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያውን የእግር ኳስ ግጥሚያ በሬዲዮ ከማስተላለፍ አንስቶ፣ በሬዲዮና በጋዜጣ ላይ ስፖርትን የሚመለከቱ ዘገባዎች ቦታ እንዲያገኙ አድርገዋል። በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት ውስጥ ጉልህ ሚና ካላቸው ጥቂት ኢትዮጵያውያን መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። በ87 ዓመታቸው ያረፉት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ እንዴት ይታወሳሉ? በኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኝነት ሙያ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ግጥሚያ በሬዲዮ ከማሰራጨት እስከ ፀሐፊ እና የስፖርት ሕትመቶች ዋና አርታዒነት ደርሰዋል። በስፖርት እውቀታቸው ዓለም አቀፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ሴክሬታሪያት ፀሐፊ ሆነው አገልግለዋል። በዘረፉ ለስመዘገቡት አስተዋጽኦ በዓለም አቀፉ የስፖርት ፕሬስ ማኅበር የሕይወት ዘመን ስኬት ሽልማትን ተቀብለዋል። ጥቅምት 01/2015 ዓ.ም. ፈረንሳይ ውስጥ በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን አንጋፋውን የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔን ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛው ገነነ መኩሪያ “የሕይወት ዘመናቸውን በሙሉ ለኢትዮጵያ ስፖርት ያዋሉ” ሲል ይገልጻቸዋል። አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ እአአ 2016 ላይ ለሲቢሴስ አማርኛ ሲናገሩ፤ በኢትዮጵያ የሕትመት ውጤቶች እና የሬዲዮ ስርጭት ውስጥ የስፖርት ፕሮግራሞች እንዲከፈቱ ጥረት ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። አቶ ፍቅሩ እርሳቸው በጀመሩት የመጀመሪያው የሬዲዮ ፕሮግራም የኢትዮጵያ እና የሱዳን ብሔራዊ ቡድኖችን የእግር ኳስ ግጥሚያ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሰተላለፋቸውን ይገልጻሉ። አቶ ፍቅሩ ይህን ጨዋታ እንዴት በሬዲዮ እንዲያስተላለፉ የተደረገው በድንገትና ሳያስቡት ነበር። ይህም ጨዋታውን ለሕዝብ ጆሮ እንደሚያደርሱ ሳይነገራቸው እና ምንም አይነት ዝግጅት ሳያደርጉ ነበር የመጀመሪያውን የቀጥታ ሥርጭት ያስተላለፉት። አቶ ፍቅሩ ይህን ጨዋታ እንዴት በሬዲዮ እንዲያስተላለፉ የተደረገው በድንገትና ሳያስቡት ነበር። ይህም ጨዋታውን ለሕዝብ ጆሮ እንደሚያደርሱ ሳይነገራቸው እና ምንም አይነት ዝግጅት ሳያደርጉ ነበር የመጀመሪያውን የቀጥታ ስርጭት ያስተላለፉት። ሱዳኖች የእግር ኳስ ጨዋታውን ከአዲስ አበባ በቀጥታ በሬዲዮ እንደሚያስተላልፉ የተረዱት አቶ ይደነቃቸው ተስማ፣ እኛስ ለምን አናስተላልፍም? በማለት ሐሳቡን በድንገት እንዳመጡት ጋዜጠኛ ገነነ ይናገራል። ከዚያም ከኢትዮጵያ ሬዲዮ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር የቀጥታ ሥርጭቱ በመፈቀዱ ጨዋታው ከመጀመሩ ከደቂቃዎች በፊት አቶ ፍቅሩ እንደሚፈለጉ በድምጽ ማጉያ ተጠርተው ነበር በድንገት ተጠርተው የቀጥታ ሥርጭት ማይክሮፎን የቸበጡት ይላል ገነነ። አቶ ፍቅሩም “ጨዋታው ሊጀመር 10 ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት ትፈለጋለህ ተብዬ ተጠርቼ ስሄድ፣ አቶ ይድነቃቸው አንተ እኮ ነው የምትፈለገው ብሎ የተጫዋቾችን አሰላለፍ ሰጥቶ ጨዋታውን እንዳስተላልፍ ነገረኝ” ሲሉ አስታውሰዋል። “ጨዋታው ሊጀመር 10 ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት ትፈለጋለህ ተብዬ ተጠርቼ ስሄድ፣ አቶ ይድነቃቸው አንተ እኮ ነው የምትፈለገው ብሎ የተጫዋቾችን አሰላለፍ ሰጥቶ ጨዋታውን እንዳስተላልፍ ነገረኝ።” ከዚያ በኋላ በኢትዮጵያ የስፖርት ውድድር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ስታዲዮም (በ1948 ዓ.ም.) የእግር ኳስ ጨዋታ በሬዲያ በቀጥታ በሬዲዮ በማስተላከፍ አቶ ፍቅሩ ቀዳሚው ሆኑ። በሕትመት ውጤቶች ላይም ቢሆን ስፖርታዊ ጉዳዮችን መዘገብ የተጀመሩት በአቶ ፍቅሩ ጥረት ነበር። ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ለቢቢሲ ሲናገር፤ “በጋዜጦች ላይም ስፖርት የሚባል አይታወቅም ነበር። ከ1950 በኋላ ፍቅሩ ነበር መጻፍ የጀመረው።” ገነነ እንደሚለው በባዶ እግሩ የኢሊምፒክ ማራቶንን በማሸነፍ የሚታወቀው የዓለማችን ታላቁ የማራቶን ሯጭ አበበ ቢቂላ በጫማ እንዲሮጥ ያደረጉት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ናቸው። “ፍቅሩ ከአንድ ጫማ አምራች ድርጅት ጋር ተነጋግሮ ለአበበ በነጻ የመሮጫ ጫማ እንዲሰራለት አስደርጓል። ጫማ አምራቹም በአበበ ስም ታዋቂነትን ለማግኘት ችሏል።” በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ሲሰሩ የቆዩት አቶ ፍቅሩ፣ ወታደራዊው መንግሥት ወደ ሥልጣን በመጣበት ጊዜ እንደወጡ ቀርተው ለበርካታ ዘመናት በተለያዩ አገራት ውስጥ ኖረዋል። ነገር ግን ባሉበት ሆነው በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፖርቶች እንዲጎለብቱ የሚችሉትን አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ ቆይተው፤ አብዛኛውን እድሜያቸውን በቆዩባቸው የውጭ አገራት ውስጥ ሆነው እንኳን ለኢትዮጵያ ስፖርት ሲሰሩ እንቆዩ ገነነ ገልጿል። አቶ ፍቅሩ በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፖርቶች ውስጥ ፍቅሩ ያልገቡበት ዘርፍ የለም የሚለው ገነነ፣ አሁን ትኩረትን እየሳበ ያለው የሴቶች እግር ኳስ እንዲጎለበት የአቶ ፍቅሩ ሚና ጉል እንደነበር ይጠቅሳል። ፍቅሩ ከእግር ኳስ ባሻገር በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ውስጥ ኢትዮጵያ ውክልና እንዲኖራት በግሉ የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ እንደቆየ የሚናገረው ጋዜጠኛ ገነነ፤ ብዙም አቅም የሌላቸው የስፖርት ፌዴሬሽኖችን በመወከል በእራሱ ወጪ በዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ላይ ይሳተፍ ነበር። እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ የነበረውን የዘር መድልዎ (አፓርታይድ) ሥርዓት በመቃወም አገሪቱ ከዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች እንድትታገድ ከአቶ ይድነቃቸው ተሰማ ጋር ከፍተኛ ጥረት ከማድረግ ባሻገር፤ በዓለም አቀፍ ሕትመቶች ላይ ፀረ አፓርታይ የቅስቀሳ ጽሁፎችንም ያቀርብ እንደነበር ገነነ አስታወሷል። አቶ ፍቅሩ ስፖርት በመገናኛ ብዙኃን ላይ ቦታ እንዲያገኝ ከመጣራቸው ባሻገር፣ ቴሌቪዥን ባልተስፋፋበት በዚያ ዘመን ከአዲስ አበባ ውጪ ያለው ስፖርት አፍቃሪ ታላላቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን እንዲመለከትም አስችለዋል። ለዚህም እአአ 1958 በስዊዲን አገር ተካሂዶ የፔሌ ትውልድን የያዘው የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ዋንጫ የወሰደችበትን ግጥሚያ አቶ ፍቅሩ በክፍለ አገር ከተሞች እየተጓዙ በፕሮጀክተር ጨዋታውን ያሳዩ እንደነበረ ጋዜጠኛ ገነነ ይናገራል። “እኛ ፔሌ፣ ጋሪንቻ የሚባሉትን በስም እንኳ አናውቃቸውም ነበር። እሱ በየክፍለ አገሩ ዞሮ ካሳየ በኋላ ነው ተጫዋቾቹ ኢትዮጵያ ውስጥ የታወቁት።” አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ በስፖርት ጋዜጠኝነት ሙያ ከማገልገላቸው በተጨማሪ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ፣ የማስታወቂያ ባለሙያ ሆነውም ሠርተዋል። በተጨማሪም በመንግሥታቱ ድርጅት በኩል ኢትዮጵያ ወደ ኮንጎ ጦሯን ባሰማራችበት ወቅት ጦሩን የሚመሩት የኢትዮጵያ ጄኔራሎች ፈረንሳይኛ የሚናገር ወጣት በመ��ለጋቸው፣ ፍቅሩ የመቶ አለቃ ማዕረግ ይዘው ወደ ኮንጎ መዝመተውም ነበር። ይህ አጋጣሚ ነበር አቶ ፍቅሩ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ የሥራ ዕድል በር ከፍቶላቸው የማስታወቂያ ባለሙያ ሆኖ የመስራት ዕድልን እንደከፈተላቸው ጠቅሰው ነበር። አቶ ፍቅሩ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ስለኦሊምፒክ ጨዋታዎች ያለው እውቀት እምብዛም ባልነበረበት ወቅት ውድድሩን ለአገሬው ለማስተዋወቅ መጽሐፍ እስከ ማሳተም ደርሰው ነበር። “የኦሊምፒክ ጨዋታ የሚል መጽሐፍ በ1960 አሳተምኩ። ይህን መጽሐፍ ያዘጋጀሁት ሕዝቡ ስለ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች እውቀት እንዲኖረው ነው።” ይህን መጸሐፍም ለትምህርት ሚኒስቴር በመስጠት በአገሪቱ ባሉ ትምህርት ቤቶች እንዲታደሉ በማድረግ ወደ ወጣቶች እንዲደርስ አድርገዋል። አቶ ፍቅሩ ከስፖርት ጋር በተቆራኘው ሕይወታቸው በበርካታ ኃላፊነቶች ላይ አገልግለዋል። በኢትዮጵያ የወቅቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ ተቀጥተው የኢትዮጵያ የብስክሌት ፌዴሬሽን፣ የቴኒስ ፌዴሬሽን፣ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። አቶ ፍቅሩ የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበርን አቋቁመው የማኅበሩ ፕሬዝዳንት በመሆንም ሠርተዋል። ከኢትዮጵያም ውጪ አቶ ፍቅሩ ከኦሊምፒክ ውድድር ጋር ባላቸው ቁርኝት ትልቅ የሥልጣን ደረጃ ላይ መድረስም ችለው ነበር። ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ አቶ ፍቅሩ የመጀመሪያው ጥቁር የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እና የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ ሆነው ተሹመው እንደነበረ ይገራሉ። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ፣ የአፍሪካ የሰፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር ዋና ፀሐፊ በመሆን አገልግለዋል። የፊፋ የፕሬስ ኮሚቴ አባል የነበሩ ሲሆን እንደ ቢቢሲ፣ የአሜሪካ ድምጽ፣ ሬዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል ላሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችን ይሰሩም ነበር። https://www.bbc.com/amharic/articles/cx76v13n28eo +sports በሩዋንዳ መንግሥት ስፖንሰር በሚደረገው የአርሰናል ክለብ ሽንፈት ፕሬዚዳንት ካጋሜ ብስጭታቸውን ገለፁ "የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት እና የአርሰናሉ ደጋፊ ፖል ካጋሜ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን መክፈቻ ቀን በክለቡ አስደንጋጭ ሽንፈት ብስጭታቸውን ገልፀዋል። ለ74 ዓመታት ያህል በከፍተኛ ሊጎች ውስጥ ያልነበረው ብሬንትፎርድ አርሰናልን 2-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በሩዋንዳ መንግሥት ስፖንሰር የሚደረገው አርሰናል ክለብን በተመለከተ ፕሬዚዳንት ካጋሜ ስለ መድፈኞቹ በርካታ ጊዜ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። አርብ ዕለት ከተደረገው ጨዋታ በኋላ ፕሬዚዳንት በትዊተር ገፃቸው ""ለሁኔታዎች ይቅርታ እያደረግን ወይም የማይረቡ ነገሮችን መቀበል የለብንም። አንድ ቡድን መገንባት ያለበት ለማሸነፍና ለማሸነፍ ዓላማ ብቻ ነው"" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በሁለት ተጨማሪ የትዊተር መልዕክቶቻቸው ክለቡ ስኬታማ የሚያደርገውን ዕቅድ እንዲያመጣ የጠየቁ ሲሆን ""አድናቂዎች እንዲህ አይነት ሁኔታዎችን መልመድ አይገባቸውም"" ብለዋል። ከአውሮፓውያኑ 2018 ጀምሮ የሩዋንዳ መንግሥት ከ 42 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ከክለቡ ጋር አድርጓል። ይህም በአርሴናል የመለዮ ሸሚዝ እጀታ ላይ የሚታየውን ""ሩዋንዳን ጎብኙ"" አርማ ያካትታል። ተቺዎች ለሀብታም የእግር ኳስ ክለብ ድጎማ የሚሰጡ የደሃ አፍሪካዊት ሀገር አምባገነናዊ መሪ ምሳሌ ናቸው ቢሉም ነገር ግን የሩዋንዳ መንግሥት በበኩሉ የስፖንሰር ገቢው በቀጥታ ከሚገኘው በቱሪዝም ገቢው ነው በማለት ይከራከራል። በፕሬዚዳንት ካጋሜ አገዛዝ ዘመን ወደ�� አልባዋ አገር በአውሮፓውያኑ 1990 ዎቹ ከተከሰተው የብሔር ግጭትና ዘር ማጥፋት አገግማለች። በአውሮፓውያኑ 2018 የዓለም ባንክ ሃገሪቱ እያከናወነች ያለውን ""አስደናቂ የልማት ስኬቶች"" አመስግኗል። ነገር ግን ፕሬዚዳንቱ በፖለቲካ እና በሰብአዊ መብቶች አያያዝ በአገር ውስጥ እና በውጭ ትችት ይገጥማቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58220075 +health አዘውትሮ ምሽት አራት ሰዓት አካባቢ መተኛት ለልብ ችግር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል- ጥናት "ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ባለው ጊዜ አዘውትሮ መተኛት ለተሻለ የልብ ጤንነት እንደሚረዳ በ88 ሺህ በጎ ፈቃደኞች ላይ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች አስታወቁ። በዩናይትድ ኪንግደም ባለ አንድ ቡድን በተደረገ ጥናት እንቅልፍ ከውስጣዊው የሰውነት ክፍላችን የጊዜ አቆጣጠር ጋር እንዲጣታም ማድረግ ለልብ ድካም እና ለስትሮክ የመጋለጥ እድልን እንደሚቀንስ ጠቁሟል። የሰውነት ተፈጥሯዊ የ24-ሰዓት ምት ለደኅንነት እና ንቁ ለመሆን አስፈላጊ መሆኑን የሚገልጸው ጥናቱ እንደ የደም ግፊት ባሉ ሂደቶች ላይም ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ይላል። በአውሮፓ የልብ ጤና ጆርናል ላይ በታተመው በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ በሰባት ቀናት ውስጥ በእንቅልፍ እና በእንቅልፍ ጊዜ ላይ ከጥናቱ ተሳታፊዎች መረጃን ለማሰባሰብ የእጅ ሰዓት የሚመስል መሳሪያ እንዲያጠልቁ አድርገዋቸዋል። በመሳሪያው አማካኝነት በአማካይ በስድስት ዓመታት ውስጥ በልብ እና በደም ዝውውር ጤና ላይ ያለውን ሁኔታ ተከታትለዋል። በዚህም ከ3,000 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች የልብ ችግር [የካርዲዮቫስኩላር] በሽታ ተገኝቶባቸዋል። በጥናቱ መሰረት ለዚህ ችግር የተጋለጡት ከምሽቱ 4 ወይም 5 ሰዓት ቀደም ብለው ወይም ዘግይተው ወደ አልጋ የማምራት ልምድ ያላቸው ሰዎች ላይ ነው። ተመራማሪዎቹ እንደ ዕድሜ፣ የሰውነት ክብደት እና የኮሌስትሮል መጠን ያሉ የአንድን ሰው ለልብ ስጋት የሆኑ ሌሎች ነገሮችን ለማየት ሞክረዋል። ነገርግን ጥናታቸው መንስኤውንና ውጤቱን ማረጋገጥ አልቻለም። ተመራማሪዎቹ እንደ ዕድሜ፣ የሰውነት ክብደት እና የኮሌስትሮል መጠን ያሉ አንድን ሰው ለልብ ችግር የሚያጋልጡ ሌሎች ነገሮችን ለማየት የሞከሩ ሲሆን ጥናታቸው መንስኤና ውጤቱን ማረጋገጥ እንዳልቻለ አስረድተዋል። ""በጥናታችን መንስኤው ላይ መደምደሚያ መስጠት ባንችልም በውጤቱ መሰረት ከመደበኛው የመኝታ ሰዓት ቀደም ብሎ ወይም ዘግይቶ መተኛት የሰውነትን አቆጣጠርን ሊያስተጓጉል ስለሚችል የልብና የደም ሥር ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያስከትል ጥናቱ አመላክቷል"" ሲሉ አጥኚው ዶ/ር ዴቪድ ፕላን ገልጸዋል። ""በጣም ችግር የማስከተል ዕድል ያለው የእንቅልፍ ጊዜ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ያለው ነው። ምክንያቱ ዘግይቶ የተኛው ሰው የጠዋት ብርሃንን የማየት እድሉን ሊቀንስ ስለሚችል የሰውነት አቆጣጠር እንደገና ይጀምራል"" ሲሉም አክለዋል። በብሪቲሽ የልብ ፋውንዴሽን ከፍተኛ የልብ ነርስ የሆኑት ራይጃና ጊብሊን ""ይህ ትልቅ ጥናት እንደሚያመለክተው ከምሽቱ 4 እስከ 5 ሰዓት መተኛት ለብዙ ሰዎች ልባቸው ለረጅም ጊዜ ጤናማ እንዲሆን ምቹ ሊሆን ይችላል"" ብለዋል። ""ሆኖም ይህ ጥናት መንስኤውን እና ውጤቱን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ማስታወስ አስፈላጊ ነው። የእንቅልፍ ጊዜ እና ቆይታ ከልብ እና ደም ዝውውር በሽታዎች ጋር ስላለው ተያያዥነት ምርምሮች ያስፈልጋሉ"" ሲሉ ገልጸዋል። ነርሷ በቂ እንቅልፍ ማግኘታችን ለአጠቃላይ ጤንነታችን ብሎም ለልባችን እና ለደም ዝውውር ጤናማነት ጠቃሚ ነው። አብዛኞቹ ጎልማሶች ከሰባት እስከ ዘጠኝ ሰዓታት መተኛት ይጠበቅባቸዋል ሲሉም አስረድተዋል። ""ይህ ማለት ግን እንቅልፍ የልብ ጤ�� ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር የሚችል ብቸኛው ምክንያት ነው ማለት አይደልም። የደም ግፊት እና የኮሌስትሮል መጠንን ማወቅ፤ ጤናማ ክብደትን መጠበቅ እና በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ የጨው እና አልኮል መጠጦችን በመቀነስ የአኗኗር ዘይቤን ማጤን በጣም አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም የተመጣጠነ ምግብ መመገብ የልብን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል"" ሲሉ ነርስ ራይጃና ጠቅሰዋል።" https://www.bbc.com/amharic/59230351 +health ኢትዮጵያ የጤናማ አመጋገብ መመሪያን ይፋ ልታደርግ ነው "በኢትዮጵያ የጤናማ አመጋገብ መመሪያ [dietary guideline] ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በኋላ ይፋ እንደሚሆን በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የምግብ ስርዓት እና ስነ ምግብ ምርምር ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ ለቢቢሲ ገለጹ። ሃላፊው ለሶስት ዓመታት ሲዘጋጅ የቆየው የጤናማ አመጋገብ መመሪያ ወደ መጠናቀቁ መደረሱን ገልጸው በጤና ሚኒስቴር እና በሌሎች ሚኒንስቴር መስሪያ ቤቶች የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል። ዶ/ር ማስረሻ የመመሪያውን አስፈላጊነት ሲገልጹ ""ህብረተሰቡ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንድን ነው መብላት ያለብኝ? በሚል ብዙ ሰው ይጠይቃል የተማረም ያልተማረም ሰው ስለዚህ ይህንን በዘላቂነት ለመመለስ"" የተዘጋጀ መሆኑን አስረድተዋል። መመሪያው ለማዘጋጀት 'ሰፊ ጥናት' እንደተደረገበትም ገልጸዋል። እድሜያቸው ከሁለት ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች የተዘጋጀ ሲሆን ምን አይነት ምግቦች እና አመጋገቦች ለጤናማ ህይወት እንደሚረዳ የሚያመላክት ነው ብለዋል። በተጨማሪም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን እንዲሁም በሀገሪቱ ዙሪያ ያሉ ባህላዊ እሴቶችን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ነው ሲሉ አክለዋል። ጤናማ የአመጋገብ መመሪያ ምንድን ነው? እንደ ዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት ትርጓሜ ጤናማ የአመጋገብ መመሪያ በሀገራት ውስጥ ጤናማ የአመጋገብ እና የኑሮ ዘይቤም ለመገንባት የሚወጡ ናቸው። በውስጣቸውም ከስነ ምግብ አኳያ ጠቃሚ የሆኑ ምግቦችን እና አመጋገቦችን በተለያዩ የእድሜ ክልል ለሚገኙ ዜጎቻቸው በምክረ ሃሳብ መልክ የሚያቀርቡበት ነው። በተጨማሪም እርሻና የምግብ ዝግጅትን በተመለከተ የሚያትት ነው። በሌላ በኩል ጤናን ለማጎልበት እና አሳሳቢ በሽታዎችን ለመከላከል የሚረዱ ንጥረ ነገርን ያዘሉ ምግቦች የአመጋገብ ዘይቤዎች ላይ ምክር ሃሳብ ይሰጣሉ። እንደ ድርጅቱ መረጃ በዓለም ከአንድ መቶ በላይ ሀገራት የጤናማ አመጋገብ መመሪያ አላቸው። በአፍሪካ ሰባት ሀገራት ይህ መመሪያ ያላቸው ሲሆን ከሌሎች አህጉራት አንጻር ዝቅተኛው ነው። በአህጉሪቱ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሲሼልስ፣ ናይጄሪያ፣ ቤኒን፣ ናሚቢያና ሴራሊዮን የአመጋገብ መመሪያ አላቸው። ከሁለት ወር በታች በሆነ ጊዜ የጤናማ አመጋገብ መመሪያን ይፋ ለማድረግ ያቀደችው ኢትዮጵያ 8ኛዋ የአፍሪካ ሀገር እንደምትሆን ይጠበቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60101546 +business በ2012 ጎልተው የወጡ ምጣኔ ኃብታዊ ጉዳዮች ከሁለት ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ወደ ስልጣን ያመጣው ለውጥ ይፋ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ከፖለቲካው በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችም እንደሚደረጉ ሲነገር ቆይቷል። እነዚህን ማሻሻያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላሉ የተባሉ እርምጃዎች እየተጠናቀቀ ባለው 2012 የተወሰደ ሲሆን፤ የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ግን ከተለያዩ ፈተናዎች አሁንም አልተላቀቀም። በዓመቱ በአገሪቱ ውስጥ የተከሰቱ አለመረጋጋቶች፣ ዓለም አቀፉ የኮሮናወረርሽኝ እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶች በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይና በሕዝቡ የዕለት ከዕለት ህይወት ላይ ቀላል የማይባል ጫናን አሳድረዋል። በተጠናቀቀው ዓመት በኢትዮጵያ የምጣኔ ���ብት ገጽታ ላይ ጎልተው ከታዩ ጉዳዮች መካከል ከጊዜ ወደ ጊዜ እጠነከረ የመጣው የዋጋ ግሽበት፣ የብር የምንዛሪ ዋጋ በገበያ ይወሰናል መባል እንዲሁም የግል ባንኮች ከውጪ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ እንዲበደሩ መፈቀዱን መልስ ብለን ለመቃኘት እንሞክራለን። በአገሪቱ በተከታታይ ከፍ እያለ የመጣው የዋጋ ግሽበት ከመስከረም እስከ ሐምሌ 2012 ባሉት 11 ወራት ውስጥ የመቀነስ ምልክት እንዳልታየበት ከማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የሚወጡት መረጃዎች ይጠቁማሉ። ለዋጋ ግሽበት መጠን አለመቀነስ እንደ ዋነኛ ምክንያት የሚቀመጠው በፍላጎት እና በአቅርቦት መካከል ያለው ልዩነት ሰፊ መሆኑ እንደሆነ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ሃቅ ነው። ከማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠኑ በ18.6 በመቶ እና በ22.9 በመቶ መካከል ሲዋዥቅ ቆይቷል። የምግብ ዋጋ ግሽበት ደግሞ ከ20 በመቶ ሳይወርድ ቆይቷል። ዝቅተኛ የምግብ ዋጋ ግሽበት የተመዘገበው በጥር 2012 ሲሆን የምግብ ግሽበት መጠኑም 20 በመቶ ነበር። መጋቢት 2012 ደግሞ የዋጋ ግሽበቱ ዋጋ 26.7 በመቶ በመሆን በዓመቱ የምግብ ግሽበት ዋጋ ጣራ የነካበት ወቅት ወር ሆኖ አልፏል። ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበትም ቢሆን ባለፉት 11 ወራት ከ10.3 በመቶ እስከ 19.7 በመቶ መካከል ሆኖ ተመዝግቧል። ከብሔራዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በተገኘው አሃዝ መሰረት ከመስከረም እስከ ሐምሌ 2012 ድረስ የተመዘገበው የምግብ የዋጋ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ እና አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠኑ እንደሚከተለው ቀርቧል። ሌላ በዚህ ዓመት አነጋጋሪ ሆኖ ያለፈው ብሔራዊ ባንክ ከሦስት ዓመታት በኋላ የብር የምንዛሪ ዋጋ ተመን በገበያ ዋጋ ይወሰናል ማለቱ ነበር። ባንኩ የብር የውጭ ምንዛሪ ፍላጎትን መሠረት በማድረግ የብር ዋጋ በገበያ ተመን እንዲወሰን ማድረግ ተገቢ ነው በማለት ኢትዮጵያ በሦስት ዓመታት ውስጥ ብርን ወደ ፍሎቲንግ ካረንሲ ሥርዓት (የገንዘብን ተመን በገበያ ዋጋ ላይ መመስረት) እንደምትሸጋገር ሐምሌ ወር ማገባደጃ ላይ ገልጿል። ብር በአሁኑ ወቅት ከሚገባው በላይ ዋጋ እንዳለው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ስለዚህም የብር ዋጋ በገበያ ወደሚተመንበት ሥርዓት ሲሸጋገር ዋጋው አሁን ካለው እንደሚቀንስ ወይም በብር እና በዶላር መካከል ያለው ልዩነት እንደሚሰፋ ይታመናል። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የምንዛሪ ሥርዓት በገበያ ዋጋ መወሰን እንዳለበት ይሚስማሙበት ጉዳይ ሆኖ፤ አካሄዱ ግን ቀስ በቀስ መሆን እንደሚገባው አመልክተዋል። ብሔራዊ ባንክም በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ መከናወን ያለባቸው ነገሮችን መሰራት እንደሚኖርበትና ለዚህ ደግሞ የዘርፉ ሙያተኞችን የያዘ ተቋም ያስፈልጋል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። የብር የዋጋ በገበያው መሠረት ሲተመን ከውጭ አገራት ገንዘብ ጋር የሚኖረው ልዩነት እንደሚሰፋ ሙያተኞች ይናገራሉ፤ ለምሳሌ አንድ የአሜሪካ ዶላር ዛሬ ላይ በባንኮች 35 ብር የሚመነዘር ከሆነ፤ በትክክለኛው የገበያ ዋጋ ይተመን ቢባል አንድ ዶላር እስከ 45 ብር ድረስ ሊመነዘር ይችላል። ይህም የዋጋ ግሽበትን ያስከትላል። በሌላ በኩል ብር በአሁኑ ወቅት ከሚገባው በላይ ዋጋ እንዳለው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ስለዚህም የብር ዋጋ በገበያ ወደሚተመንበት ሥርዓት ሲሸጋገር ዋጋው አሁን ካለው እንደሚቀንስ ወይም በብር እና በዶላር መካከል ያለው ልዩነት እንደሚሰፋ ይታመናል። በዚህም ኢትዮጵያ የምታመርታው ምርት ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ርካሽ ይሆናል፤ ይህም የአገር ውስጥ አምራቾችን ተወዳዳሪ እንደሚ��ደርግ በመጥቀስ መልካም አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ። ባንኮች በውጭ ምንዛሪ እንዲበደሩ መፈቀዱ ብሔራዊ ባንክ ከሳምንታት በፊት ይፋ ካደረጋቸው መመሪያዎች መካከል የግል ባንኮች በራሳቸው ጊዜ በውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ይበደሩ የሚለው ይገኝበታል። ይህ የባንኩ ውሳኔ ኢትዮጵያ ጥብቅ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደሯን እያላላች ስለመምጣቷ የሚያመላክት ሲሆን፤ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ ከአገር ውጭ እንዲበደሩ መፍቀዱ ለላኪዎች መልካም አጋጣሚን ይዞ የሚመጣ እንደሆነ እየተነገረ ነው። የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንዲጎለብትም ይህ ውሳኔ ከፍተኛ አስተጽኦ ይኖረዋል ተብሏል። የውጭ ኢንቨስተሮች በአንድ አገር ኢንቨስት ለማድረግ ከመሰናቸው በፊት ኢንቨስት በሚያደርጉበት አገር ግብዓቶችን ከውጭ ለማስገባት እንዲሁም ትርፋቸውን ይዘው ለመውጣት በቂ የውጪ ምንዛሬ መኖሩን ቀድመው ያረጋግጣሉ። ከፍተኛ የሆነ የውጪ ምንዛሪ እጥረት ባለባት ኢትዮጵያ ሌላ የውጭ ምንዛሪ ማግኛ መንገድ መኖሩ ምልካም አጋጣሚ እንደሚሆን በአንዳንድ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይታመናል። በሌላ በኩል ደግሞ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ የሚበደሩትን ገንዘብ ከእነ ወለዱ በውጭ ምንዛሪ እንደመመለሳቸው የምንዛሪ ተመን መዋዠቅ በአገር ውስጥ ባንኮች ላይ አሉታዊ ጫና ሊፈጥር ይችላል። https://www.bbc.com/amharic/news-54084794 +business የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ ተነስቶ ወደ ነፃ ገበያ አሰራር እንዲገባ ተወሰነ "በሲሚንቶ ግብይት ላይ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታትና፣ የዋጋ ንረት እንዳይከሰትና የተረጋጋ የሲሚንቶ ግብይት እንዲኖር ለማድረግ በሚል ወጥቶ የነበረው የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ ላልተወሰነ ጊዜ መነሳቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። መንግሥት የሲሚንቶ አቅርቦት እና ግብይት መመሪያን ማውጣቱን ተከትሎ ከፌደራል ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ በገበያው ላይ የዋጋ ቁጥጥር ሥራን እንዲሁም ያለውን ተደራሽነት ክትትል ይሰራ ነበር። ከረቡዕ ሐምሌ 7/2013 ዓ.ም ጀምሮ የወጣው መመሪያና ከዚያ ጋር ተያይዘው የወጡ የሰርኩላር ማስፈጸሚያ ደብዳቤዎች እንዲነሱና ወደ ቀደመው የግብይት ሥርዓት፣ የነፃ የገበያ አስራር እንዲመለስ ተወስኗል ተብሏል። የሲሚንቶ ግብይትን በተመለከተ ከዚህ በፊት መንግሥት ከፌደራል ጀምሮ እስከ ወረዳ ያለውን የተደራሽነትና የዋጋ ቁጥጥር ተቋርጦ ፋብሪካዎች ራሳቸውና በሰንሰለቱ የሚገኙ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎችን በመቆጣጠር ራሳቸው ማስፈፀም እንደሚችሉ ከፋብሪካ ባለቤቶችና ሥራ አስኪያጆች ጋር ስምምነት መደረሱም ተገልጿል። የፋብሪካዎች የምርት መሸጫ ዋጋ ከሚኒስቴሩ ጋር በመተባበር በተጠና መልክ እንዲሆን ስምምነት ላይ መደረሱ ተነግሯል። ""ፋብሪካዎች የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋቸውን ከመሥሪያ ቤቱ ጋር በመነጋገር በተጠናና ባልተጋነነ ዋጋ እንዲወስኑና እንዲያቀርቡ ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ሙሉ ኃላፊቱን ለፋብሪካዎችና በተለያየ ደረጃ ላይ ላሉ የንግድ አካላት እየተቆጣጠሩ እንዲያሰሩ ተወስኗል"" ብለዋል በሚኒስቴሩ የንግድ እቃዎች ዋጋ ጥናት፣ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት። ቀድሞ በነበረው የግብይት ሥርዓት እንዲሆን የተወሰነበትንም ምክንያትም አቶ ካሳሁን አስረድተዋል። በክረምት ወቅት የግንባታ ሁኔታ ዝቅተኛ ስለሚሆን የሲሚንቶ ፍላጎትም ማነስ ስለሚከሰት፣ አምራች ኢንዱስትሪዎች አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች ሲሚንቶ ባልተጋነነ ዋጋ ለመሸጥ በመስማማታቸው እንደሆነም ጠቅሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ ፋብሪካዎች የበኩላቸውን ቁጥጥር ከደንበኞቻቸው ጋር እንደሚያደርጉ ስምምነት ላይ በመደረሱ እንዲሁም በአቅርቦትና በፍላጎት ያለውን ክፍተት ለመሸፈን በአገር ውስጥ ያሉ ፋብሪካዎችን አቅም አሁን ካለው በበለጠ በማጠናከር ምርታቸውን እንዲጨምሩ በማድረግና በተለይም እንደ አስፈላጊነቱ ከውጭ ተጨማሪ የሲሚንቶ ምርት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት መንግሥት በመወሰኑ ነው። መመሪያው ከነሐሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረ ሲሆን የአምራች፣ የአስመጪ፣ የአከፋፋይ፣ የቸርቻሪ ግዴታዎችን የያዘ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የተከለከሉ ተግባራትንም በዝርዝር አስቀምጧል። የሲሚንቶ አምራቾች ያለበቂ ምክንያት ከእቅድ በታች ማምረት፣ ከመደበኛው የግበይት ሰንሰለት ውጪ የሲሚንቶ ምርትን ማከፋፈል፣ አከፋፋይ ለአከፋፋይ እና ለቸርቻሪ የሚደረግ የጎንዮሽ ግብይትን ይከለክል ነበር። ከዚህም በተጨማሪ የዋጋ ንረት እንዲፈጠር ማድረግ፣ የሲሚንቶ ምርትን መደበቅ፣ ማከማቸት እና በሕገ ወጥ መንገድ ማዘዋር፣ በዝምድና የሚከናወን የሲሚንቶ ንግድንም ይከለክልም ነበር። ከዚህ ቀደም መንግሥት ካስቀመጠው የሲሚንቶ የዋጋ ተመን በላይ የሚሸጡ አከፋፋዮች እንዲሁም ምርት በመደበቅ፣ በማከማቸት፣ አየር በአየር በመሸጥ፣ ከንግድ አድራሻ ውጪ በመሸጥ፣ እንዲያከፋፍሉ ወይም እንዲሸጡ ከተፈቀደላቸው ውጪ ለሌላ አካል በመሸጥ የተገኙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰደ ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57837774 +health ኮሮናቫይረስ፡ ዶናልድ ትራምፕ በፍጥነት ያገገሙበት መድሃኒት እውቅና ተሰጠው አሜሪካ በኮቪድ-19 ታምመው ሆስፒታል ለሚገቡ ግለሰቦች ሬምዴስቪር የተሰኘውን ፀረ ቫይረስ መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደች። የአሜሪካ ምግብና መድሃኒት አስተዳደር (ኤፍዲኤ) እንዳለው መድሃኒቱ በክሊኒክ ውስጥ ሙከራ ላይ ባለበት ወቅት በቫይረሱ የተያዙ ሕሙማንን ማገገሚያ ጊዜ በአምስት ቀናት ውስጥ ያሳጥራል። በቅርቡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ መድሃኒቱ የተሰጣቸው ሲሆን በፍጥነትም እንዲያገግሙ ረድቷቸዋል መባሉ ይታወሳል። ይህ ቬክለሪ በሚል የብራንድ ስያሜ የሚታወቀው መድሃኒት የአሜሪካ መድሃኒትና ምግብ አስተዳደር ፈቃድ ሲያገኝ የመጀመሪያው መድሃኒት መሆኑን በመግለጫው ላይ ተመልክቷል። ባለፈው ሳምንት የዓለም ጤና ድርጅት ሬምዴሲቪር በቫይረሱ ተይዘው የታመሙ ግለሰቦች ላይ ያለው ውጤት አነስተኛ ነው ብሎ ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት በሰራው ጥናት እዚህ ድምዳሜ ላይ መድረሱን ቢናገርም የመድሃኒት አምራቹ ገሌድ ግን ውጤቱን ሊቀበለው አልፈለገም። ሬምዴሲቪር በአሜሪካ ከግንቦት ወር ጀምሮ ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል ተፈቅዶ ነበር። እንደ አሜሪካ መድሃኒት እና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን ከሆነ መድሃኒቱ ለአዋቂዎችና እድሜያቸው 12 ለሞላ ሕጻናት እንዲሁም ክብደታቸው 40 ኪሎ ግራም ለሆነ ግለሰቦች በሆስፒታል የኮቪድ-19 ሕክምና በሚከታተሉበት ወቅት ለማከም ጥቅም ላይ መዋል ይችላል። የባለስልጣኑ ኮሚሽነር የሆኑት ስቴፈን ሃሃን እንዳሉት ተቋሙ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ተደጋጋሚ የክሊኒክ ሙከራዎችን ካደረገ እና በሚገባ ከፈተሸ በኋላ ነው። ከተደረጉ የተለያዩ ጥናቶች መካከል አንዱ የማገገሚያ ቀናቱ ከ15 ቀናት 10 ማድረሱ ተገልጿል። https://www.bbc.com/amharic/news-54612591 +politics ፕሬዚዳንት ባይደን የሱዳን የሲቪል አገዛዝ በአስቸኳይ እንዲመለስ አሳሰቡ "የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሱዳን ወታደራዊ መሪዎች የሲቪል አገዛዙን በአስቸኳይ እንዲመልሱ እና ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ አሳስበዋል። በጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የተመራውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም አደባባይ ላይ የወጡ ሰልፈኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንዲቆምም ፕሬዚዳ��ቱ ጠይቀዋል። ""ለሱዳን ወታደራዊ ባለስልጣናት የምናስተላልፈው መልእክት በርካታ እና ግልፅ ነው። የሱዳን ህዝብ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን እንዲያሰማ እና በሲቪል የሚመራ የሽግግር መንግስት ወደነበረበት መመለስ አለበት"" ሲሉም በመግለጫቸው አስተላልፈዋል። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሱዳንን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በመቃወም የአረብ ሊግ እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡን ውግዘት ተቀላቅለዋል። በሱዳን በቅርብ ጊዜ የተከሰቱት ክስተቶች ሃገሪቷን በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ኋላ የሚጎትቱ ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንት ባይደን ነገር ግን ""የሱዳንን አብዮት አላማ ለማራመድ ከሱዳን ህዝብ እና ከሰላማዊ ትግል ጋር እንቆማለን"" በማለት የመንግሥታቸውን አቋም ገልጸዋል። በተቃውሞው የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 11 መድረሱንም የህክምና ምንጮች ገልጸዋል። በአውሮፓውያኑ 2019 ለአስርት ዓመታት ሱዳንን አንቀጥቀው የገዙት ኦማር አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በሲቪል መሪዎች እና በወታደራዊ አቻዎቻቸው መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል። በሲቪል እና በወታደራዊ መሪዎች መካከል የተደረገው የሥልጣን ክፍፍል ስምምነት ሱዳንን ወደ ዲሞክራሲ ለመምራት የተነደፈ ቢሆንም ከባለፈው አንድ ወር በፊት የተደረጉ በርካታ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች ግን በተፃራሪው አገሪቷ በተቃራኒው አቅጣጫ እየሄደች እንደሆነ ያመላከተ ነው። የስልጣን መጋራት ምክር ቤት መሪ የነበሩት ጄኔራል ቡርሐን ሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሸጋገር ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀው ምርጫው በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2023 ሐምሌ ወር ሊካሄድ እንደታቀደም ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59078937 +sports ነጥብ የተቀነሰበት የዋይኒ ሩኒ ቡድን ወደ ሶስተኛው ሊግ ወረደ "አንጋፋው እንግሊዛዊ እግር ኳስ ተጫዋች ዋይኒ ሩኒ የሚያሠልጥነው ደርቢ ካውንቲ ወደ ሶስተኛው ሊግ ወረደ። ራምስ በተሰኘው ቅጥል ስማቸው የሚታወቁት ደርቢዎች በኪውፒአር ተረተው ወደ ሶስተኛው ሊግ ወርደዋል። ደርቢ ካውንቲ በፈረንጆቹ 1986 ወደ ላይኛው ሊግ ከወጣ በኋላ ወደ ሶስተኛው ሊግ ሲወርድ ይህ የመጀመሪያው ነው። ደርቢ ካውንቲ ለዚህ ቀውስ የተዳረገው የቀድሞው ባለቤቱ ሜል ሞሪስ ክለቡን ማስተዳደር አልችልም ብለው ለመንግሥት አሳልፈው ከሰጡት በኋላ ነው። ወደ ሶስተኛው ሊግ የወረደው ዋይኒ ሩኒ ""መቼም ባለቤቱ ይህን እያዩ እንቅልፍ ባይነሳቸው ነው የሚገርመኝ"" ሲል መረር ያለ አስተያየት ሰጥቷል። ደርቢ ካውንቲ ባለፈው መስከረም 12 ነጥብ ተቀንሶበት ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ ወራጅ ቀጣና መውረዱ ይታወሳል። ነገር ግን የዋይኒ ሩኒ ልጆች ከረዥምና አድካሚ ትግል በኋላ እጅ ሰጥተዋል። ""ክለቡን አመሰቃቅሎት ነው የሄደው። ሜል ሞሪስ የደርቢ ደጋፊ እንደሆነ አውቃለሁ። በብስጭት እየጨሰ እንደሆነ አልጠራጠርም"" ሲል ሩኒ ቃሉን ለቢቢሲ ሰጥቷል። ""ይህ እንዳይሆን የቻልነውን ሁሉ አድርገናል። ከሚገባው በላይ ለፍተናል። ብስጭታችን የሚበርድ አይደለም።"" ደርቢ ካውንቲ መስከረም ላይ ከተጣለበት የ12 ነጥብ ቅጣት በተጨማሪ ባለፈው ኅዳር ተጨማሪ 9 ነጥብ ተቀንድቦበታል። የዋይኒ ሩኒ ቡድን 21 ነጥብ ባይቀነስበት ኖሮ 24 ቡድኖች ባሉት ሁለተኛው የእንግሊዝ ሊግ 17ኛ ደረጃ ላይ ይቀመጥ ነበር። ""በዚህኛው ሊግ የሚያቆየን ነጥብ ነበረን። በዚያ ላይ በጣም ጥሩ ብቃት ያላቸው እዚሁ ያደጉ ተጫዋቾች አፍርተን ነበር"" ሲል ውጤቱ ያንገበገበው ሩኒ ተናግሯል። ""በጣም ተበሳጭቻለሁ። እጅግ አዝኛለሁ። ነገር ግን በክለቡ በጣም እኮራለሁ። ተስፋ ያለው ቡድን ሠርተናል።"" የእንግሊዝና ማንችስተር ዩናይት ቁጥር አንድ ጎል አስቆጣሪው ሩኒ ጫማ የሰቀለው ባለፈው የውድድር ዘመን ነበር። ሩኒ ወደ ደርቢ ካውንቲ የመጣው በአሠልጣኝነትና ተጫዋችነት ቢሆንም ሙሉ በሙሉ የአሠልጣኝነት ወንበሩን ተቆጣጥሮ ክለቡን ሲመራ ቆይቷል። ባለፈው የውድድር ዘመን እንዲሁ ከመውረድ ያዳነውን ክለብ ታሪክ ዘንድሮ ግን ሊደግመው አልቻለም። ነገር ግን ቀውስ ያለ ቡድንን መንፈሰ ጠንካራና ታጋይ እንዲሆን በማድረጉ ብዙዎች ያወድሱታል። ያደገበት ክለብ ኤቨርተን ባለፈው ጥር አሠልጣኝ አድርጎ ይቀጥረዋል ተብሎ ቢታማም ሩኒ ግን ከደርቢ ጋር መቆየትን መርጧል። የአንጋፋው ተጫዋች ስም አሁን ደግሞ አሠልጣን ሾን ዳይሽን ካሰናበተው በርንሊ ጋር እየተያያዘ እየተነሳ ነው። ነገር ግን አዲሱ የደርቢ ካውንቲ ባለቤት ክሪስ ክሪችነር ሩኒ ከክለባቸው ጋር እንደሚቆይ ተናግረዋል። ከደርቢ ጋር የአንድ ዓመት ውል የሚቀረው ሩኒም በሚቀጥለው ዓመት ለሚገጥመው ፈተና እንደተዘጋጀ ጠቆም አድርጓል። አሜሪካዊው አዲሱ የደርቢ ባለቤት ክሪስ ክሪችነር ከጥቂት ሳምንታት በፊት ክለቡን ለመግዛት የተስማሙት። የደርቢ ካውንቲ ሜዳ የሆነው ፕራይድ ፓርክ አሁንም ባለቤትነቱ በሜል ሞሪስ እጅ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-61151826 +sports የእንግሊዝ ክለቦች ለተጫዋች ግዥ 1.6 ቢሊዮን ዶላር አወጡ "ትናንት ብሪታኒያ ውስጥ ሁለት ክስተቶች በተመሳሳይ ሰዓት እልባት አግኝተው በብዙዎች ዘንድ ግርምትን አጭሯል። ሁለቱም የተጠናቀቁት በየራሳቸው መንገድ ቢሆንም ትናንት እኩለ ሌሊት ስፖርትና ፖለቲካ ተመሳሳይ ሰዓት ላይ ተገጣጥመዋል፤ በእንግሊዝ ሰዓት አቆጣጠር 23፡00 ላይ። ለሦስት ዓመታት ሲንከባለል የነበረው የብሪታኒያ ከአውሮፓ ሕብረት የመውጣት ሂደት ፍጻሜውን አግኝቶ በመላዋ ብሪታኒያ ሲበሰር፤ በዚያችው ቅጽበትም የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ የጥር የዝውውር መስኮት ተዘግቷል። የዝውውር ወሩ ስም ያላቸው ተጫዋቾችን ብዙም ሳይዳፈር በአብዛኛው አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ፕሪሜር ሊጉ በማምጣት ተጠናቋል። • አሠልጣኝ አብርሃም መብራህቱ፡ ""የመጣውን በጸጋ መቀበልና መዘጋጀት ነው"" በማጠናቀቂያ ሰዓቱ ላይ የፈረሙት ጃሮድ ቦውን እና ኦዲዮ ኢጋሎ በመጨረሻዋ ቀን በከፍተኛ የዝውውር ገንዘብ የተገዙ ተጫዋቾች ናቸው። በመጨረሻዋ ቀን ዌስትሃም ዩናይትድ የሃል ሲቲውን አጥቂ ጃሮድ ቦውን በ18 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈርሟል። በውድድር ዘመኑ በጥር የዝውውር የመዝጊያ ዕለት ብቻ የወጣ ከፍተኛ ገንዘብ ሆኖም ተመዝግቧል። ይሁን እንጂ በጥር የዝውውር ወር የመጨረሻ ቀን እስከዛሬ ከወጣው ከፍተኛ ገንዘብ ጋር ሲነጻጸር ከ2010 እ.አ.አ ወዲህ ትንሹ ገንዘብ ሆኖ ተመዝግቧል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ በወሩ አጠቃላይ የእንግሊዝ ክለቦች 230 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ አድርገው ተጫዋቾችን የገዙ ሲሆን በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ገንዘብ ነው። ከዚህ ገንዘብ መካከል ታዲያ በመጨረሻዋ ቀን 25 ሚሊዮን ፓውንድ ብቻ ነው ወጪ የተደረገው። እንደአጠቃላይ ደግሞ በዚህ የውድድር ዘመን የእንግሊዝ ክለቦች ተጫዋች ለመግዛት 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ፓውንድ አውጥተዋል። ይህም 1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ፓውንድ ከወጣበት የ2017/18 የውድድር ዘመን ቀጥሎ በታሪክ ከፍተኛ ገንዘብ የወጣበት ሁለተኛው የውድድር ዘመን ያደርገዋል። ከዚህ የውድድር ዘመን ውጪ በጥር የዝውውር ወር በዝውውሩ የመዝጊያዋ ዕለት ከ30 ሚሊዮን ፓውንድ በታች ወጪ የተደረገበት የውድድር ዘመን 2010 እ.አ.አ ነው። 10 ሚሊዮን ፓውንድ ብቻ ነበር ወጪ የተደረገበት። • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ' ከፍተኛው ደግሞ 2018 እ.አ.አ ሲሆን በመዝጊያው ዕለት ብቻ 180 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ተደርጎበታል። በዚህ የዝ��ውር ወር ቼልሲ ምንም ተጫዋች ባለማስፈረም ብቸኛው ክለብ ነው። ማንችስተር ዩናይትድ የስፖርቲንግ ሊዝበኑን ብሩኖ ፈርናንዴዝን በ47 ሚሊዮን መነሻ ዋጋ ያሰፈረመ ሲሆን በሂደት ግን የተጫዋቹ ዋጋ እስከ 67.7 ሚሊዮን ፓውንድ ያድጋል ተብሏል። ሸፊልድ ዩናይትዶች ሳንዴር በርግን በ22 ሚሊዮን ፓውንድ በማስፈራም የራሳቸውን ክብረወሰን አሻሽለዋል። • ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ? በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች የዝውውር ጊዜያቸውን አጠናቅቀዋል። ስፔን፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ፈረንሳይና ሆላንድ እንደ እንግሊዝ ሁሉ የዝውውር ጊዜያቸውን በፈረንጆቹ ጥር 31 ትናንት ሌሊት የብሪታኒያ ከአውሮፓ ሕብረት መውጣት ጋር እኩል የዘጉ ናቸው። የፖርቱጋል ክለቦች ደግሞ በገበያው እስከ ፈረንጆቹ የካቲት ሁለት (በኢትዮጰያ እስከ ጥር 24) ድረስ ይቆያሉ። በተጨማሪም የሩሲያ፣ የቻይናና የአሜሪካ ክለቦች አሁንም አዲስ ተጫዋቾችን መቀበል ከሚችሉት መካከል ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/sport-51338567 +sports አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ ሲታወስ "በዛሬው ዕለት ጥቅምት 25 ታዋቂው የማራቶን ሯጭ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ 41 ዓመታትን አስቆጥሯል። አትሌቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካውያን በአትሌቱ ዘርፍ በር ከፋች ነበር። የዚህ ታላቅ ሰው መካነ መቃብር አዲስ አበባ በሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስትያን ይገኛል። ድሉ ደግሞ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ታትሟል። የአበበን ታሪክ የታሪክ ሰነዶች፣ የስፖርት መዛግብት፣ የዓለም መገናኛ ብዙኀንና ኢትዮጵያውያን በጉልህ ያስታውሱታል። ከድሎቹ ሁሉ ደምቆ የሚታወሰው ደግሞ በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ ሮጦ ለአገሩ ኢትዮጵያ እና ለጥቁር ህዝቦች ያስመዘገበው ድል ነው። 17ኛው የዓለም ኦሎምፒክ ውድድር እኤአ በ1960 በጣልያን መዲና ሮማ ነበር የተካሄደው። በዚህ ውድድር ከ83 ሀገራት የተወጣጡ ከ5 ሺህ በላይ ስፖርተኞች መሳተፋቸው ይነገራል። በሮም ኦሎምፒክ ከተሳተፉ ጥቁሮች መካከል ግን ሌላ ባለድልም አለ። መሐመድ ዓሊ በቀላል ሚዛን የወርቅ ሜዳልያ ተጎናፅፎ ነበር። ቢሆንም ኦሎምፒኩ በመሐመድ ዓሊ ወርቅ ሜዳልያ እምብዛም የደመቀ አልነበረም። በወቅቱ ታሪክ የሚያስታውሰው ሌላ ክስተትም ነበር። ጊዜው ደቡብ አፍሪካ በአህጉራዊ ውድድሮች ለመጨረሻ ግዜ ተሳትፋ የታገደችበት ነበር። የእገዳዋ ምክንያት ደግሞ ትከተለው በነበረ የአፓርታይድ ስርአት መሆኑ ነው። ቢሆንም የያኔ የሮሙ ኦሎምፒክ በመሐመድ ዓሊ የወርቅ ሜዳልያም ብሎም በደቡብ አፍሪቃ መታገድ አይደለም የሚታወሰው። ታድያ በምን ይታወሳል ያሉ እንደሆነ በውድድር ዘመኑ የማራቶን ሩጫ ያለ ጫማ ሮጦ የርቀቱ አዲስ ክብረወሰን ባስመዘገበው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሻምበል አበበ በቂላ ነው። በወቅቱ በርካታ ሊጠቀሱ የሚችሉ ነገሮች ቢከናወኑም አበበ ግን ታሪኮችን ሁሉ ልቆ የሚታወስ ድንቅ ታሪክ አስመዘገበ። ያኔ፣ አይደለም አበበ በቂላ የሚባል አትሌት፣ ኢትዮጵያ ተብላ ስለምትጠራ ሀገርም የሚያውቅ የውጭ ዜጋ ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም። ይሁን እንጂ ውድድሩ በጣልያን መካሄዱ እና የጣልያን ወረራ በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት ተጠናቅቆ ነጻነቷን የማግኘቷ ወሬ ገና ከዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የወሬ አጀንዳነት ባለመረሳቱ፣ የአበበ ቢቂላ ድል ገነነ። የዓለም አቀፍ ሚድያዎች ሳይቀር ባልተጠበቀው የአትሌት አበበ በቂላ ድል ተደምመው ደጋግመው፣ በባዶ እግር ሮጦ የወርቅ ሜዳልያ ስላገኘው ኢትዮጵያዊው አትሌት ተናገሩ። ""ሙሶሎኒ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች አሰልፎ እና መድፍ እና መርዛማ ጋዝ ተጠቅሞ ኢትዮጵያን ሲወር፣ አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር ግን ጣልያንን ብቻ ሳይሆን መላውን አለም አሸነፈ"" የሚል ዘገባዎች ተሰራጩ። የኦሎምፒክ ውድድር እየተካሄደ በነበረበት ግዜ ጥቂት ኢትዮጵያውያን በጣልያን ሮም ይኖሩ ነበር። እነዚህ ኢትዮጵያውያን በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን አማካኝነት የሥነ መለኮት ትምህርት እንዲማሩ ተብለው ከኢትዮጵያ የተላኩ ናቸው። እኤአ በ1960 አንዲት እናት በስራ ምክንያት ከአስመራ ወደ ሮም ተጉዘው ነበር። እኚህ ወ/ሮ ሳራ ሰለባ፣ የተሰኙ እናት ""የጥቁሮች ፊት ሳላይ እኖራለሁ፣ ያቺ ተወልጄ ያደግኩባት አስመራም በምናቤ ትመላለስ ነበር። አልፎ አልፎ እነዛ የተባረኩ የሥነ መለኮት ተማሪዎች ብቸኝነቴ ተረድተው እየመጡ ይጠይቁኝ ነበሩ"" ብለው ያጫውቱት እንደነበር ልጃቸው ያስታውሳል። ወ/ሮ ሳራ፣ አበበ በቂላ ሮጦ ድል ያደረገበ ዕለት ውደድሩ በቴሌቭዥን መስኮት ተከታትለዋል። አብረዋቸው የነበሩ ነጮች ተሰብስበው ""የሀገርሽ ልጅ አሸንፏል"" እያሉ ይጮሁ እንደነበር ያስታውሳሉ። ታድያ ወ/ሮ ሳራ አብረዋቸው ከመደሰት ይልቅ ማልቀስን መረጡ። ለወ/ሮ ሳራ የለቅሶ ምክንያት የነበረው ደግሞ የአበበ ባዶ እግር መሮጥ ነበር። አበበ ቢቂላ ነሐሴ 30 ቀን 1925 ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በደብረ ብርሃን አውራጃ፣ ደነባ ልዩ ስሟ ጃቶ በምትባል ሥፍራ ከአባቱ አቶ ቢቂላ ደምሴና ከእናቱ ከወይዘሮ ውድነሽ መንበሩ ተወለደ። ወጣቱ አበበ እንደአካባቢው ልምድ በእረኝነት ቤተሰቡን አገልግሏል። በአሥራ ሁለት ዓመቱም የቄስ ትምህርቱን አጠናቋል። በዚህ በጨቅላ ዕድሜው ስመ ጥር የገና ተጫዋች እንደነበር ይነገርለታል። በ1944 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በክብር ዘበኛ ሰራዊት በወታደርነት ተቀጥሮ በገና ጨዋታ እና በስፖርት እየዳበረ ቆየ። ስዊድናዊው ኦኒ ኒስካነን [1910-1984] የክብር ዘበኛ ስፖርት ክፍል አስልጣኝ ነበር። በወቅቱ የስፖርት ክፍሉ ባልደረቦች ከነበሩት መካከል የሁለቱ አበበዎች የሩጫ ልምድ ትኩረቱን ስቦት እንደነበር ትቶት የሄደው ማስታወሻ ያሳያል። አበበ በቂላ ወደ አትሌቱ መንደር የተቀላቀለው በ24 አመቱ ነበር። ኦኒ ኒስካነን አበበን ወደ ሩጫ እንዲገባ ባያደፋፍረው አትሌትም ላይሆን ይችል እንደነበር ይነገራል። እርግጥ ነው አበበ እግር ኳስ እና ቅርጫት መጫወት ይወድ ነበር። አስለጣኝ ኦኒ ኒስካነን አበበ የሩጫ ውድድር እንዲሞካክር ይገፋፋው ነበር። በአራራጡ እና በራስ መተማመኑ ይወድለት ስለነበር በክቡር ዘበኛ ውድድሮች ሲያሳትፈው ጥሩ ውጤት ያመጣ ጀመር። ኒስካነን የአበበ በቂላ እና አበበ ዋቅጅራ የሩጫ ልምድ አይቶ ሮም ላይ በተካሄደው የዓለም ኦሎሚፒክ ውድድር እንዲሳተፉ አዘጋጃቸው። አበበ ዋቅጅራ ከአበበ ቢቂላ በ10 ዓመት ያህል የሚበልጥ ሲሆን በሮም ኦሎምፒክ ላይ እንደ አበበ ሁሉ በባዶ እግሩ ሮጦ ሰባተኛ መውጣቱን ድርሳናት ያሳያሉ። በሮም ኦሊምፒክ አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ የሮጠበት ምክንያት በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች ሲንፀባረቁ ተሰምተዋል። በርካታ መዛግብት ለአበበ የሚስማማ ጫማ መጥፋቱን፣ የሞከረውም ጫማ ስለጠበበው ያለጫማ መሮጥን መምረጡን ጽፈዋል። እነዚህ መዛግብት አበበ ዋቅጅራም በባዶ እግሩ ስለመሮጡ ያነሱት አንዳች ነገር የለም። ይሁን እንጂ እውነታውን በተመለከተ የአበበ ቢቂላ ልጆች እንዲሁም አሰልጣኙ ትተዋቸው ያለፉ ድርሳናትና የይድነቃቸው ተሰማ እሸቴ ማስታወሻዎች ይህንን ይናገራሉ። ኦኒ ኒስካነን እነ አበበን ይዞ ወደ ሮም ከተጓዘ በኋላ እዚያው ሮም የሩጫ ልምምድ ያደርጉ ነበር። ልምምዱ የሚካሄደውም ጫም ተጫምተው እና በባዶ እግር ነበር። ኦኒ ኒስካነን በልምምዱ ሂደት ታድያ አንድ ነገር አስተዋለ። ሁለቱም አትሌቶች በባዶ እ��ር ሲሮጡ የተሻለ ፍጥነት ማስመዝገብ ችለው ነበር። ውድድሩን በድል ያጠናቅቁ እንጂ እንደ ፍላጎታቸው መሮጥ እንዲችሉ ፈቀደላቸው። አበበ ቢቂላ ጫማ ተጫምቶ ሲሮጥ በአንዲት ደቂቃ ከ5-6 ስንዝር ይዘገይ እንደነበርም አሰልጣኙ ኦኒ ኒስካነን መስክሯል። ከውድድሩ በኋላ ስለ ሁኔታው የተጻፉት እውነታነት እንዳልነበራቸውም ኒስካነን ተናግሮ ነበር። 'ጫማ ስላልተገዛላቸው ነው' እና 'የተገዛላቸው ጫማ ስለጠበባቸው ነው' የሚሉ ሀሳቦች ሀቅ አይደሉም ብሏል ኒስካነን። ኦኒ ኒስካነን እንደሚተርከው ሁለቱም ተወዳዳሪዎች ወደ ሮም ከመሄዳቸው በፊት ስለ ውድድሩ በቂ መረጃ ተሰጥቷቸው ነበር። በውድድሩ የተሻለ ፍጥነት ያላቸው ተወዳዳሪዎች እነማን ሊሆኑ ይችላሉ ከሚለው ጀምሮ እስከ የመወዳደርያ ማልያ ቁጥራቸው በሚገባ ተነግሯቸዋል። እነ አበበ ቢቂላን ከሚፎካከሩት መካከል ደግሞ ሞሮኳዊው ሯጭ ራዲ ቢን አብደልሰላም ይገኝበታል። ስለራዲ እነ አበበ መረጃ ቢኖራቸውም የመወዳደሪያ ቁጥሩ መቀየሩን ግን አያውቁም ነበር። ራዲ ቀድሞ የተሰጠው የመወዳደርያ ቁጥር ስላልተገኘ ነበር ሌላ አዲስ ቁጥር የተሰጠው። እነ አበበ ግን ራዲ አዲስ ቁጥር እንደተሰጠው መረጃው የላቸውም። አበበ ከቀሪዎቹ ተወዳዳሪዎች በሰፊ ርቀት ፈንጠር ብሎ በሚሮጥበት ግዜ ሞሮኳዊው ራዲ ግን በቅርብ ርቀት ይከተለው ነበር። በወቅቱ ሞሮኮ በውድድሩ ሶስት ተወዳዳሪዎች አሰልፋ ስለነበር፣ አበበ ከሶስቱ አንዳቸው ይሆናሉ በሚል ሮም የሚገኘው የአክሱም ሀውልት እስኪደርሱ ድረስ ብዙም ግምት አልሰጠውም ነበር። አበበ በውድድሩ በአስልጠኙ እንዲያደርጋቸው ከተነገሩት ነገሮች መካከል አንዱ የአክሱም ሀውልት ሲደርስ ፍጥነቱ እንዲጨምር ነበር። አበበም በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ውድድሩ ሊያልቅ 2 ኪሎ ሜትር ሲቀረው ሮም ፒያሳ በተተከለው አክሱም ሀውልት ሲደርስ በፍጥነት ተፈተለከ። አበበ ያኔ ለጥቂትም ቢሆን ቢዘናጋ ኖሮ ራዲ የማሸነፍ እድል እንደነበረው ይነገራል። እንደ አስልጣኙ ኦኒ ገለጻ ከሆነ አበበ 40 ኪሎ ሜትር ድረስ አብሮት የተጓዘው ራዲ መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ ቀድሞት ሊሮጥ ምናልባትም ያስመዘገበው ክብወሰን በተሻለ ያሻሽለው ነበር ይላል። ሻምበል አበበ በቂላ በ1964 በቶክዮ ጃፓን በተካሄደው ውድድርም የራሱን ክብረወሰን በማሻሻል አሸናፊ ሆነ። ከውድድሩ አንድ ወር በፊት ግን ቀዶ ጥገና ተደርጎለት የነበረ ቢሆንም ውድድሩ በአስደናቂ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ችሏል። በ1968 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ36 ዓመቱ በኦሎሚፒክ ውድድር ለ3ኛ ግዜ የተሳተፈ ቢሆንም በጉዳት ምክንያት ሳይጨርስ የቀረ ሲሆን፣ ውድድሩ በሌኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ማሞ ወልዴ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። አለምን በባዶ እግር ሮጦ በማሸነፍ አንቱታ ያተረፈውን ሻምበል አበበ በቂላ በገጠመው የመኪና አደጋ ምክንያት በ41 ዓመቱ ከዚህ አለም ተለየ።" https://www.bbc.com/amharic/news-54672466 +politics የኔዘርላንድሷ ልዕልት በደኅንነት ስጋት ከትምህርት ቤት ወጣች የኔዘርላንድስ ንጉሥ እና ንግሥት የ18 ዓመት ልጃቸው ጥቃት ሊደርስባት ስለሚችል ከአሁን በኋላ በነጻነት መንቀሳቀስ እንደማትችል ገለጹ። ልዕልት አማሊያ አምስተርዳም ከሚገኘው የተማሪዎች መኖሪያ በመውጣት ዘ ሄግ ወደሚገኘው ቤት ተመልሳለች። ወላጆቿ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በስዊድን ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ነው በስሜታዊነት ዝርዝር ጉዳዮችን የገለጹት። ንግሥት ማክስማ “አስቸጋሪውን ሁኔታ” ሲገልጹ ዐይኖቻቸው በእምባ ተሞልቶ ነበር። “ለእሷ የተማሪነት ሕይወት እንደሌሎቹ ተማሪዎች አይደደለም” ብለዋል። ልዕልት አማሊያ እና የኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት ከተደራጁ ወንጀለኞች የተ���ኘ መረጃ ዒላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አመልክቷል። ባለፈው ወር በተሰራጨ ኦፊሴላዊ ፎቶ  ልዕልት አማሊያን በመጀመሪያ የትምህርት ቀን በፈገግታ ተሞልታ ትታያለች። ወጣቷ ወደ ተማሪዎች መኖሪያ ቤት መግባቷ እና በአምስተርዳምስ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ፣ በሥነ ልቦና፣ በሕግ እና በምጣኔ ሀብት የመጀመሪያ ዲግሪዋን መማር መጀመሯ በብዙዎች አድናቆት አትርፎላታል። ታኅሳስ ላይ 19 ዓመት የምትደፍነው አማሊያ ኔዘርላንድስ ውስጥ ብዙዎች በአንፃራዊነት ወደ ኅብረተሰቡ የቀረበች የንጉሣዊ ቤተሰብ ነች ሲሉ ይገልጿታል። ሞሂቶ የሚባል ፈረስ ያላት ሲሆን፤ በበጋ ወራት በሼቨኒንገን የባሕር ዳርቻ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ መሥራቷ 'የኮክቴይል ንግሥት' የሚል ቅጽል ስም አስገኝቶላታል። ልዕልት አማሊያ ለ18ኛ ዓመት ልደቷ  ባሳተመችው የሕይወት ታሪኳን በያዘው መጽሐፍ ስለ አእምሮ ጤንነቷ ተናግራ ብዙ ጊዜ የሥነ ልቦና ባለሙያዎችን እንደምትጎበኝ ተናግራለች። የመጀመሪያው የትምህርት ዘመንን በቅጡ ሳታጋምስ ነው የስለላ ተቋም ዘገባን ተከትሎ ልዕልት አማሊያ የምትወደውን እና የሚያስደስታትን የተማሪነት ሕይወት ለመተው የተገደደችው። የደኅንነት ጥንቃቄዎቹ ጊዜያዊ ብቻ እንደሆኑ ቤተሰቦቿ ተስፋ ያደርጋሉ። ንግሥት ማክስማ በስዊድን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ልዕልት አማሊያ ነገሩን የተቋቋመችበትን መንገድ እና ለጀግንነቷ ክብር እንደሚሰጡ ተናግረዋል። የአርጀንቲና ተወላጅና የቀድሞ ኢኮኖሚስት አባቷ አማሊያ አሁንም ዩኒቨርስቲ እንደምትማር ጠቁመው እንዲያውም ጥሩ ውጤት እያስመዘገበች ሊሆን ይችላል በማለት ቀልደዋል። ንጉሥ ቪለም-አሌክሳንደር እንደ አባት ጉዳዩን እንዲገልጹ ሲጠየቁ “ከባድ ሁኔታ” መሆኑን አምነው ተጽዕኖውን መግለጽ እንዳልቻሉ ተናግሯል። ለንጉሣዊው ቤተሰብ አባላት ወይም ለመንግሥት ባለሥልጣናት ስለደኅንነት ጉዳዮች ማውራት አልተለመደም። ፖሊስ፣ የሕዝብ ዐቃቤ ሕግ እና የመንግሥት ሚኒስቴር በንጉሣዊያኑ ጥንዶች መግለጫ ላይ አስተያየት ይሰጣሉ ተብሎ አይጠበቅም። https://www.bbc.com/amharic/articles/c5164w2wxdqo +sports “በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነኝ” አትሌት ገብረእግዚአብሔር "አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም ተወልዶ ያደገው በትግራይ ክልል በቀድሞዋ ሐውዜን፣ በአሁኗ ሳዕሲዕ ጻዕዳ እምባ ወረዳ ነው፤ ልዩ ስሟ ጻንቃኔት በተባለች አካባቢ ነው። በ1976 ዓ.ም. የተወለደው ገብረእግዚኣብሄር፤ ገና ታዳጊ እያለ በ16 ዓመቱ ጊዜውም በ1992 ዓ.ም ሩጫን ሀ ብሎ የጀመረው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመጀመርያ ጊዜ 2003 ኒው ዮርክ በተካሄደው ማራቶን ላይ ተሳትፎ የወርቅ ሜዳልያ አገኘ። •""ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል"" ኃይሌ ገብረሥላሴ ለቁጥር በሚያዳግቱ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ውድድሮች በግሉም እንዲሁም በሃገርም ደረጃ ተሳትፎ ብዙ ወርቆችን ያስገኘ አትሌት ነው። በአሁኑ ወቅት ከሩጫው ባሻገር በአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በኦሎምፒክ ኮሚቴ ምክትል ኃላፊነት እያገለገለ ሲሆን፤በይፋ ጫማ ባይሰቅልም እምብዛም በሩጫ መድረክ ላይ ሲሳተፍ እየታየ አይደለም። ለዚህም ገብረእግዚአብሔር ምላሽ አለው ""ሩጫ እንደሚታውቀው ብዙ ትኩረት የሚጠይቅ ነው። ቢዝነስን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እሳተፋለሁ። ከዚህ በተጨማሪም በዕድሜም እየገፋሁ ነው። በይፋ ጫማ ባልሰቅልም አሁን ወደዛው ነኝ።"" በዚህና ወቅታዊ ስፖርታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ቢቢሲ ከገብረእግዚአብሄር ጋር ቆይታ አድርጓል። አትሌት ገብረእግዚአብሄር ሩጫ በጀመረበት ወቅት ሩጫ በአለም አቀፍ ደረጃ በውድድር ደረጃ ስላለው ስፍራ የጠለቀ እውቀት አልነበረውም። ትምህርቱን የተማረው እንደ ብዙው የኢትዮጵያ የገጠር ልጅ በእግሩ እየሄደ ነበር፤ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ ርቀቷን በሩጫ ፉት ይላታል። •ስለ አቶ ዱቤ ጅሎ ሽልማት ምን እናውቃለን? ""እኔ የአርሶ አደር ልጅ ነኝ። ወላጆቼ ያዘዙኝን በሙሉ ሰርቼ በሰዓቱ ትምህርት ቤት ለመድረስ ስለማልችል እየሮጥኩ ነበር የምሄደው። ከትምህርት ቤት ስመለስም እንዲሁ በሩጫ ነበር።"" ይላል ይሄ የአብዛኛው የአርሶ አደር ልጆች ታሪክ ቢሆንም ለገብረ እግዚአብሄር ግን የተለየ ዕድል እንደፈጠረለት ይናገራል። ""አጋጣሚው ተፈጥሯዊ አቅምን ፈጥሮልኛል።"" ሩጫን ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ በፍጥነት ለመድረስ እንጂ በስፖርቱ አለም ያለውን ስፍራም አልተረዳውም ነበር። ""በስፖርት ይሄን ያህል ታዋቂነት እንደሚገኝም አላውቅም ነበር"" ይላል። ውድድር ማካሄድ የጀመረው በትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት ሲሆን፤ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሆኖ በትምህርት ቤቱ በተጀመረው ውድድር ለመጀመርያ ጊዜ አንደኛ ወጥቶ የምስክር ወረቀትም አግኝቷል። •ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ፡ «ስለተተከሉት ዛፎች ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ የለም» ከትምህርት ቤቱ በተጨማሪ ሌሎችን ውድድሮችን ማካሄድ የጀመረው ገብረእግዚአብሔር በ1993 ዓ.ም. የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሆኖም አዲግራት አቅራብያ በምትገኘው ዕዳጋ ሐሙስ ከተማ ትምህርት ቤቱን ቀጢን ቃላይ' ወክሎ ነበር የተወዳደረው፤ አንደኛም ወጣ። ቀጥሎም ወረዳውን ወክሎ 1500 ኪሜ ተወዳደሮ ማሸነፉን ያስታውሳል። ለመጀመርያ ግዜ ከምስክር ወረቀት በተጨማሪ ሽልማት ያገኘበት መሆኑም ልዩ ያደርገዋል። አትሌት ገብረእግዚአብሄር አትሌት ገብረ እግዚአብሄር በተለይ ለእነዚህ ሶስቱ ድሎች [የአየርላንድ፣ የኒው ዮርክና አፍሪካ ሻምፒዮን] የተለየ ቦታ አለው። በተለይ ደግሞ የአፍሪካ ሻምፕዮን በኢትዮጵያ የተካሄደ በመሆኑና ከፍተኛ ዝናብ የጣለበት ፈታኝ ውድድርም ስለነበር ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠዋል። •""የት ይቀርልሃል!? አፈር ድሜ ትበላለህ...!"" ጋሽ አበራ ሞላ ""በኢትዮጵያ የመጀመርያ ውድድርም ስለ ነበር ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወርቅ እንዲያመጡ ጉልበት የሆናቸው ይመስለኛል"" የሚል እምነት አለው። የአትሌት ገብረ እግዚአብሄር አርአያ ማን ነው? ገብረእግዚአብሄር ሩጫን በአጋጣሚ ቢጀምርም በትምህርት ቤት ስለ እነ አትሌት ምሩጽ ይፍጠርና አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ የሩጫ ገድል ሲሰማ በሩጫ ላይ የተለየ ፍላጎት እንዳደረበት ይናገራል። አበበ ቢቂላም ሌላኛው የገብረእግዚአብሄር አርአያ ነው። ለሶስቱ አትሌቶች የተለየ ክብርና አድናቆት እንዳለው ነው የሚናገረው ገብረእግዚአብሄር፤ ""ሩጫን ለዓለም በደንብ ያስተዋወቅነው እኛ ኢትዮጵያውያን ነን"" የሚል አቋም አለው። ገብረእግዚአብሄር ከሁሉም በላይ ለኃይሌ ገብረ ስላሴ ያለው ቦታ ከፍ ያለ እንደሆነ ይናገራል። በሩጫ ማሸነፉ ብቻ ሳይሆን በሩጫው ለረዥም ግዜ የቆየበት ፅናቱን እንደ ምሳሌ ይቆጥረዋል። እንዲሁም ደግሞ ከሩጫው በተጨማሪ በቢዝነስ የሚያደርገው እንቅስቃሴና ስኬትም ሌላ የሚያደንቅበት ጉዳይ ነው። አትሌት ምሩጽ ይፍጠር በአንድ ኦሎምፒክ ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት መሆኑን ከፍተኛ ስፍራ ከመስጠቱ በተጨማሪ ለመጀመርያ ጊዜ ሩጫን በውድድርነት ሲሰማ የአትሌት ምሩጽ ይፍጠርን ድል ነበር የሰማው። የስድስተኛ ክፍል የሳይንስ መምህሩ ስለ አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ማርሽ ቀያሪነት በሚነግሯቸው ወቅት መጀመርያ የሚያወሩት ስለመኪና ማርሽ ይመስለው እንደነደበር በፈገግታ ያስታውሰዋል። ""ምሩጽ ስሙም ምርጥ ማለት ነው፤ ተግባሩም ምርጥ ነበር። በአካል ሳላውቀው ለረዥም ግዜ በውስጤ ይመላለስ ነበር፤ ምን ዓይነት ሰው ይሆን ብዬ ሁሌ አስብ ነበር"" ይላል። በኋላም በአካል ተገናኝተው ከተዋወቁ በኋላ ያላቸው ግንኙነት ጠንክሮ እንደ ልጅና አባት ይተያዩ እንደነበር ይናገራል። • ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ ""በህይወት ሳለ እንደ አብሮ አደጎችም ነበር የምንቀራረበው። እንደ አባቴ ነበር የማየው። የሃገሪቱም ሆነ ዓለም ክብር ነበር"" በማለት በኃዘኔታ ያስታውሳል። ለተወሰኑ ዓመታት አሰልጣኙ እንደነበርም ይናገራል። በተለያዩ ማሕበራዊ ጉዳዮችም ያማክረው እንደነበር ገብረእግዚአብሄር ያስታወሳል። ተተኪ አትሌቶችን ከማፍራት ባለፈ የመቀሌ ከተማና ሌሎች በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅ አላማ ያለው 'ናትና ስፖት' በሚል ከባለቤቱ ከአትሌት ወርቅነሽ ኪዳነ ጋር ባቋቋሙት ተቋም አማካኝነት ሶስተኛው 'ናትና' የጎዳና ሩጫ ባለፈው ወር መቀሌ ላይ ተከናውኗል። ""ትግራይ ክልል በደንብ ከተሰራበት ለስፖርት አመቺ የሆነ ሁኔታ አለ"" የሚለው ገብረእግዚአብሄር ከሩጫው በሚገኘው ገቢ ሶስት የአትሌቲክስ መንደሮች ለማቋቋም አስቧል። የመቀሌ ሰብዓ እንደርታ እግር ኳስ ቡድን ዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫን ሲያነሳ በክልሉ የታየው መነቃቃትና መነሳሳት ደግሞ ስፖርት ምን ያህል ጉልበት እንዳለው የሚያሳይ እንደሆነም ያስረዳል። የስፖርት መርህ ሰላምና ፍቅር መሆኑን የሚናገረው አትሌት ገብሬ በተለያዩ ምክንያቶች የሚነሱ ግጭቶችና አለመግባቶች ስለስፖርት ምንነት ጠንቅቆ ካለማወቅ የመነጨ እንዳሆነ ይገልጻል። ከአትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አገኘኋት በሚለው ተሞክሮ ባገኛት ""ሳንቲም"" ኢንቨስት ማድረጉን ይናገራል። አዲስ አበባ ውስጥ ሁለት ሕንጻዎች ሲኖሩት መቀሌ ከተማ ውስጥ ደግሞ ለሆቴል የሚሆን ሕንፃ እያስገነባ እንደሆነ ነግሮናል። ከዚህም በተጨማሪ የስፖርት አልባሳትን ከውጭ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት የተሰማራው ገብረእግዚአብሄር የመቀሌ ሰብዓ እንደርታ ማልያ በእርሱ ኩባንያ በኩል እንደሚመጣ ይናገራል። አትሌት ገብረ እግዚአብሄር በተለያዩ ሃገራዊ ኃላፊነቶችም በማገልገል ላይ ይገኛል። በአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በኦሎምፒክ ኮሚቴ ውስጥ በአመራርነት ይሳተፋል። •በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ቢሆንም ""በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መሳተፌ ውጤታማነቴ ላይ ድክመት እንዳያስከትልብኝ እፈራለሁ"" ይላል። ""ሆኖም በምሰራቸው ስራዎች ደስተኛ ነኝ። ሃገራዊ ግዴታዬን መወጣቴ ደስ ያሰኘኛል። የአንድ ሰው ህይወትም ቢሆን ከቀየርኩ ደስተኛ ነኝ።"" ፖለቲካ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ጥያቄ የቀረበለት ገብረእግዚአብሄር ምላሹ አጠር እና ፈርጠም ያለ ነበር፤ ""በፍጹም ፍላጎት የለኝም"" የሚል። ""ሆኖም"" ይላል ገብረእግዚአብሄር ""ሰዎች ለውጥ ያመጣል ብለው ካመኑብኝ እሠራለሁ። የወከለኝን ሰው አላሳፍርም። አቅም አለኝ ብየ ግን አይደለም።"" 'ወርቄ' እያለ አቆላምጦ የሚጠራት ባለቤቱ ወርቅነሽ ኪዳኔም ከሩጫውም ከሚድያውም ርቃለች። ""ወርቄ ለሀገሯ ብዙ ሠርታለች። ለዛውም ከፍተኛ መስዋዕትነትን እየከፈለች። አሁን ግን እኔም እሷም ወደ መተው ደረጃ ደርሰናል። የምንችለውን አድርገናል ብየ ነው የማስበው።"" በተለያዩ የአትሌቲክስና ኦሎምፒክ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን በቡድን ስራ የተዋጣ ስራ ሲሰሩ እንደነበር አትሌት ገብረ እግአዚአብሄር ይናገራል። ሆኖም ወርቅ ላመጣ ብቻ የሚሰጠው እውቅናና ክብር ግን ያንን የቡድን ስራ ዋጋ እንዳይቀንሰው ይሰጋል። ""እኛ፤ እኔም ሆነ ቀነኒሳ፤ ጥሩነሽ ሆነች ወርቅነሽ ሁላችንም የምንሰራው ኢትዮጵያ ወርቅ እንድታገኝ ነው። በእኛ ምክንያት ሃገር ማፈር የለባትም ብለ�� ነው። ስለሆነም ቀነኒሳ ወርቅ አምጥቶ ባንዲራ አንስቶ ሲሮጥ፤ ሁላችንም ተነስተን በደስታ እንጨፍራለን።""ይላል። ነገር ግን ወርቅ ያመጣው ላይ ብቻ ከፍተኛ ትኩረት ስለሚሰጥም በመንግሥትና በሚድያዎች ላይ መጠነኛ ቅሬታ እንዳለው ግን አልደበቀም። ""ወደ አገር ስትመጣ ለእንዲህ ዓይነት የቡድን ስራ ክብር ሲሰጥ አይታይም። ወርቅ ላመጣ ብቻ ክብር መስጠት ራሱን የቻለ ችግር አለበት። ይህንን ደጋግመን ነግረናቸዋል"" ይላል። አክሎም ""በእርግጥ እኛ ተሰምቶን አያውቅም። የምንችለውን አድርገናል። መስዋዕትነት ነበር የምንከፍለው። ይሄ ከየት የመጣ ነው - ካልከኝ ከወከለን ህዝብ አደራ ነው።"" ""በአምስት የአለም ዋንጫዎች ተሳትፌያለሁ። በአምስቱም ወርቅ አላመጣሁም። ወርቅ እንዲመጣ ግን ምክንያት ነኝ። በሁለት ኦሎምፒክ ተሳትፌያለሁኝ። በሁለቱም ወርቅ እንዲገኝ ምክንያት ነኝ። ወርቄ [ወርቅነሽ] ደግሞ በተመሰሳይ በስድስት የዓለም ዋንጫና በሶስት የኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ተሳትፋለች። እሷም እንደዚሁ። ወርቅ እንዲመጣ የመጀመርያ ተጠሪ እሷ ነች። 'ዘ ካንትሪ ዉማን' ይሉዋታል። ወደፊት ወጥታ ለሁለትና ለሶስት ቆርጣ ደረጃ ታወጣባቸዋለች። ከተሸላሚዎቹ በላይ ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነች። እነሱም ያምናሉ። ወደ መንግሥት ስትመጣ ግን ሌላ ነው፤ ይሄ የአስተሳሰብ ጠባብነት ነው የሚመስለኝ።"" ይላል በሩጫ ውድድር ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ሌሎች አገራዊ ዘርፎችም እንደዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ችግር እንዳለና መስተካከል እንዳለበት ያሳስባል ገብረእግዚአብሄር ""ለሁሉም በተለይ ደግሞ መስዋዕትነት ለሚከፍለው ዕውቅና መስጠት አስፈላጊ ነው። ጥቅም አይፈልግም"" በማለት ሃሳቡን ይቋጫል።" https://www.bbc.com/amharic/49306146 +health የኮሮናቫይረስ ታማሚው ሆስፒታል ውስጥ ሌላ ታማሚን ገደለ "አሜሪካ፣ ካሊፎርንያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ተይዞ ሆስፒታል የነበረ ግለሰብ ሌላ ቫይረሱ ያለበትን ታማሚ ገደለ። የ37 ዓመቱ ግለሰብ ባለፈው ሳምንት ታማሚውን የገደለው በኦክስጅን መያዣ ታንክ ደብድቦት ነው። ግለሰቡ በግድያ እና በጥላቻ ወንጀል ተከሷል። ጀሲ ማርቲኔዝ የተባለው ግለሰብ የ82 ዓመት አዛውንት በኮሮናቫይረስ ተይዘው እሱ የሚገኝበት የሆስፒታል ክፍል ውስጥ ከገቡ በኋላ ነው ግድያውን የፈጸመው። ለሎስ አንጀለስ ፖሊስ በሰጠው ቃል መሠረት አዛውንቱ የሆስፒታሉ ክፍል ውስጥ እየጸለዩ ስለነበረ ተበሳጭቶባቸዋል። አዛውንቱ በኦክስጅን ታንክ ከተመቱ በኋላ በቀጣዩ ቀን ሕይወታቸው አልፏል። ፓሊስ እንዳለው፤ ሁለቱ ግለሰቦች በተመሳሳይ የሆስፒታል ክፍል ውስጥ ሕክምና ሲደረግላቸው ነበር። ከዚያ በፊትም አይተዋወቁም። አንቲሎፕ ቫሊ በተባለውና በደቡብ ካሊፎርንያ በሚገኝ ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግለት የነበረው ጀሲ ""አዛውንቱ ሲጸልዩ ተበሳጨና በኦክስጅን ታንክ ገደላቸው"" ሲል ፖሊስ መግለጫ አውጥቷል። ከግድያ በተጨማሪ የጥላቻ ወንጀል እና አረጋውያንን የማሰቃየት ክስም ተመስርቶበታል። ካሊፎርንያ ውስጥ በስድስት ሳምንት ብቻ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ሆስፒታሎች ህሙማንን ለማስተናገድ እየተጣጣሩም ነው። ወረርሽኙ ከጀመረ ወዲህ በግዛቲቱ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ሆስፒታሎች የጤና ባለሙያዎች እጥረት ስለገጠማቸው ከአውስትራሊያ እና ታይዋን 3000 ባለሙያዎች ለመውሰድ አቅደዋል። የካሊፎርንያ የጤና ቢሮ ጸሐፊ ዶ/ር ማርክ ጋሊ በዚህ ወር መጨረሻ ለህሙማን አልጋ ላይኖር እንደሚችል ተናግረዋል። አገረ ገዢው ጋቪን ኒውሰም ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ አዘዋል። እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ አገልግሎቶች ውጪ ያሉ ተቋሞችም ተዘግተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/55438467 +politics ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የመተማመኛ ድምጽ ሊሰጥባቸው ነው የዩናይትድ ኪንግደሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ዛሬ የመተማመኛ ድምፅ ሊሰጥባቸው ነው። መሰል ጉዳዮችን የሚመረምረው የላይኛው ምክር ቤት ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሰር ግራሃም ብሬዴ ይህን ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ሥልጣን ይልቀቁ የሚሉ ድምፆች እየበረከቱ መጥተዋል። ቦሪስ የመተማመኛ ድምፅ ሊሰጥባቸው እንደሆነ የእንግሊዝ መገናኛ ብዙሃን ከውስጥ አዋቂዎች ሰምተናል ሲሉ ነው የከረሙት። ቦሪስ የመተማመኛ ድምፅ የሚሰጥባቸው 54 የገዥው ወግ አጥባቂ አባላትና የሕዝብ እንደራሴዎች [ቶሪስ] በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያለን እምነት ተሟጧል የሚል ደብዳቤ ካስገቡ ነው። ባለፈው ሰንበት የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ግራንት ሻፕስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመተማመኛ ድምፅ ቢወጣባቸውም ምንም እንደማይሆኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፉት 10 ቀናት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከገዛ ፓርቲያቸው ያለመተማመን ድምፅ ሊሰጥባቸው እንደሚችል ሲነገር ቆይቷል። እስካሁን 28 ቶሪዎች [የገዥው ፓርቲ አባላትና የሕዝብ እንደራሴዎች] ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን እንዲለቁ በይፋ ጠይቀዋል። ቦሪስ በንግሥት ኤልሳቤጥ 70ኛ ዓመት የፕላቲኒዬም ኢዩቤልዩ ክብረ በዓል ላይ ሲገኙ ሕዝቡ ቁጣን ገልጦባቸዋል። በገዥው ወግ አጥባቂ ፓርቲ ሕግ መሠረት ቢያንስ 15 በመቶ የፓርቲው አባላትና የሕዝብ እንደራሴዎች ድምፅ መስጠት አለባቸው። ገዥው ፓርቲ በአሁኑ ወቅት በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት 54 አባላት አሉት። እኒህ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩን አንደገፍም ብለው ደብዳቤ መፃፍ አለባቸው። እስካሁን ምን ያህል አባላት ደብዳቤ እንዳስገቡ ግልፅ አይደለም። 54ቱም አባላት ደብዳቤ ካስገቡ ከፍተኛ ቶሪዎች በመሪያቸው ላይ በድብቅ የተማመኛ ድምፅ ይሰጣሉ። ይህ ከሆነ በኋላ ጉዳዩ ወደ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አምርቶ 180 አባላት አንተማመንም የሚል ድምፅ መስጠት አለባቸው። ቦሪስ ይህን የመተማመን ድምፅ ማለፍ ከቻሉ ሌሎችንም ፈተናዎች የማለፍ ዕድላቸው የሰፋ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cgxyx74n2llo +business አሜሪካ የዓለም ንግድ ድርጅት ለመምራት የታጩትን አፍሪካዊት ልታግድ መሞከሯ ተገለፀ "የናይጄሪያ የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር የዓለም ንግድ ድርጅትን እንዲመሩ መሾማቸው የአሜሪካ መቃወምን ተከትሎ ጥርጣሬ ውስጥ ወድቋል ፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅት እጩዎች ኮሚቴ ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዊላ እንዲሾሙ ሀሳብ ያቀረበው ረቡዕ ነበር። የዓለም ንግድ ድርጅት የመሩ የመጀመሪያዋ ሴት እና የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ይሆናሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር ፡፡ ነገር ግን የዓለም ንግድ ድርጅት የዓለም ንግድን የመራበትን መንገድ አጥብቃ የነቀፈችው አሜሪካ ሌላ ሴት እያሰበች ነው- የደቡብ ኮሪያዋን ዮ ሚንግ ሂን፡፡ ኦኮንጆ-ኢዊላ በሹመቱ ""እጅግ እንደተደሰቱ""ገልጸው ነበር፡፡ ለድርጅቱ አዲስ መሪ ለመፈለግ ለአራት ወራት የተደረገው ጉዞ ዋሺንግተን የደቡብ ኮሪያን የንግድ ሚኒስትርን እንደምትደግፍ በመናገሯ እንቅፋት አጋጠመው፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅትን በመተቸት የአሜሪካ የንግድ ጽሕፈት ቤት ድርጅቱ ""በእውነተኛ እና በመስኩ ልምድ ባለው ሰው መመራት አለበት"" ብሏል ፡፡ ዮ ""የድርጅቱን ውጤታማ መሪ ለመሆን የሚያስፈልጉ ብቃቶች ሁሉ አሏት"" ይላል መግለጫው ፡፡ አክሎም ""ይህ ለዓለም ንግድ ድርጅት እና ለዓለም ዓቀፍ ንግድ በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነው። በ 25 ዓመታት ውስጥ ሁለገብ የታሪፍ ድርድሮች አልተካሄዱም፤ የአለመግባባቶች መፍትሄ አሰጣጡ ሥርዓት ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል። ግልፅነትን በተመለከተም በጣም ጥቂት አባላት ብቻ ግዴታቸውን ���የተወጡ ነው፡፡ ደርጅቱ ትልቅ ለውጥ የሚያስፈልገው ነው"" ብሏል። መግለጫው ኦኮንጆ-ኢያላ አልተጠቀሰም ፡፡ የድርጅቱ ቃል አቀባዩ ኪት ሮክዌል ስለውሳኔው ላይ ለመወያየት የዓለም ንግድ ድርጅት ልዑካን ከተሰበሰቡ በኋላ አንድ አባል ሀገር ብቻ ኦኮንጆ-ኢዊላን እንዳልደገፈ ተናግረው ነበር ፡፡ ""ከአንድ ልዑክ በስተቀር ሁሉም ልዑካን ለሂደቱ ... ለውጤቱ ጠንካራ ድጋፍ አድርገዋል"" ብለዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ የዓለም የንግድ ድርጅትን ""አስፈሪ"" እና ለቻይና ያደላ አድርገው የገለጹ ሲሆን በድርጅቱ ውስጥ ቁልፍ የተባሉ አንዳንድ ሹመቶች ቀድሞውኑም ታግደዋል ፡፡ የዓለም የንግድ ድርጅት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ከአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ ስብሰባ ጠርቷል ፡፡ የአሜሪካ መቃወም ናይጄሪያዊቷ እንዳይሾሙ ያግዳል ማለት አይደለም። ሆኖም ዋሽንግተን በውሳኔው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር ትችላለች ፡፡ የ66 ዓመቷ ኦኮንጆ-ኢዊላ የናይጄሪያ የመጀመሪያዋ ሴት የገንዘብ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በዓለም ባንክ ኢኮኖሚስት ሆነውአገልግለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54729315 +business በዩኬ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ቀውስ ለማቃለል የሀገሪቱ ሰራዊት ዝግጁ ነው ተባለ በዩኬ የተፈጠረውና አራተኛ ቀን ባስቆጠረው የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ምክንያት የተፈጠሩ ረጃጅም ሰልፎችንና መሰል ችግሮችን ለማቃለል ሰራዊቱ ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ። በሀገሪቱ በተከሰተው የነዳጅ አቅርቦት ችግር የነዳጅ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች እጥረትም ገጥሟል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እስከ 150 የሚደርሱ የወታደር ነዳጅ ጫኝ አሽከርካሪዎች ሥልጠና በመሰጠት ማሰማራት እንደሚቻልም ተጠቅሷል። በርካታ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች የነዳጅ አቅርቦት ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት በርካታዎች በነዳጅ ማደያዎች በማጣሪያዎች በቁጥር በዝተው ይታያሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ከ100 ሺህ በላይ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች ያስፈልጋታል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ባለፉት ወራት የምግብ አቅራቢዎችን እና ሱፐርማርኬቶችን ጨምሮ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ችግር አጋጥሟቸዋል። የሀገሪቱ ባለስልጣን በነዳጅ ማደያዎች ለሚታዩት ረጃጅም ሰልፎች ነዳጅ ሳያስፈልጋቸው ወደ ማደያዎች የሚሄዱ ሰዎችን ተጠያቂ አድርገዋል። ኤኤሲሲ የተባለ ኩባንያ እንዳስታወቀው ከዓርብ ጀምሮ የአንድ ሊትር ነዳጅ ዋጋ በአንድ ሳንቲም ጨምሯል ይህም ከስምንት ዓመት በኋላ የታየ ነው። ከፍተኛ ሰዎች በሚታዩባቸው ማደያዎች አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቸርቻሪዎች ዋጋውን ከዚህም በላይ እየጨመሩ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ ብሏል። በሌላ በኩል እንደ ጤና እና ማህበራዊ እንክብካቤ ላሉ ወሳኝ ሠራተኞች ቅድሚያ የነዳጅ ተደራሽነት እንዲያገኙ ጥሪዎችን እያደረጉ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-58716168 +health ጤና፡ የወጣቶች የወገብ ህመም መንስዔ እና መፍትሔው "አሁን አሁን የወገብ ህመም አጋጥሟቸው የህክምና ተቋማትን የሚጎበኙ ወጣቶች እየተበራከቱ ነው። በተለይ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ለወገብ ህመም የሚጋለጡ ወጣቶች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጥናቶች ያመለክታሉ። ለመሆኑ ለዚህ መንስዔው ምንድን ነው? መፍትሔውስ? በዚህ ላይ በፓራጎን የፊዚዮቴራፒና ስፓርት ህክምና ስፔሻሊቲ ልዩ ክሊኒኮች ውስጥ ሥራ አስኪያጅ እና ሜዲካል ዳሬክተር ከሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ ወ/ገብርኤል ጋር ቆይታ አድርገናል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ሦስቱንም ድግሪያቸውን የተከታተሉት በአሜሪካ ሲሆን በፊዚዮቴራፒ በተለይ በስፖርት ህክምና እና ኦርቶፔዲክስ ህክምና ዶክትሬታቸውን አግኝተዋል። በሙያቸው በአሜሪካ ለ10 ዓመታት የሰሩ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ላለፉት 12 ዓመታት እያገለገሉ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት ውስጥ ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው። በጥቁር አንበሳ ህክምና ትምህርት ቤት በፊዚዮቴራፒ ዶክትሬት ፕሮግራም በመምህርነት ሠርተዋል። ብዙውን ጊዜ ወጣቶች ለወገብ ህመም ያጋለጣቸውን መንስዔ በውል አያውቁትም። እንዲሁ በደፈናው ድንገት አመመኝ ሲሉ ነው የሚሰማው። ለመሆኑ የወገብ ህመም መንስዔዎች ምንድን ናቸው? የሰውነት ማጎልመሻ እንቅስቃሴዎች፣ የምንጫማቸው ጫማዎች ፣ የምንተኛበት ፍራሽ ፣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈፀምበት መንገድ ( Sex position) . . . ለወገብ ህመም ይዳርጉ ይሆን? ወደዚህ ዝርዝር ከማለፋችን በፊት ስለወገብ እና የወገብ ህመም ምንነት እናንሳ። ወገብ ቀበቷችን ወይም መቀነታችን የሚያርፍበት የሰውነታችን ክፍል ሲሆን በዚህ ላይ የሚከሰት ህመም የወገብ ህመም ይባላል። የወገብ ህመም ጽንሰ ሃሳቡ ሰፊና ጥልቅ ቢሆንም በቀላል አገላለጽ በወገብ አካባቢ በሚገኙ ጡንቻዎች ፣ የነርቭ ሥሮች፣ የአከርካሪ አጥንቶች፣ የጎን አጥንቶች እና ጅማቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው። ይህ ጉዳት ጊዜያዊ ወይም ዘለቄታዊ ሊሆን ይችላል። የወገብ ህመም ዓይነቶች እንደ መንስዔያቸው ይለያያሉ። ዋና ዋናዎቹ ግን እነዚህ ናቸው፦ ከመጨረሻው ነጥብ እንጀምር። የሰውነት በሽታ ተዋጊ ሂደት በመዛበት የሚከሰተው የወገብ ህመም የሚያጋጥመው ሰውነት በሽታን የሚከላከልበት ሂደት ሌሎች የሰውነት አካላትን ሲያጠቃ ነው። በእንግሊዝኛ አጠራሩ Ankylosing spondylitis ይባላል። የሰውነት የውስጥ ቁስለትን በመፍጠር ዘለግ ላለ ጊዜ የሚቆይ ህመም ነው። የዚህ ህመም ምክንያቱ ምን እንደሆነ በውል አይታወቅም። በተለይ በመገጣጠሚያዎች እና በአከርካሪ አጥንቶች መጋጠሚያ መካከል ቁስለትን ያስከትላል። ህመሙ እየጨመረ ሲሄድም የአከርካሪ አጥንቶች እንዲንቀሳቀሱ እንደ ሃዲድ የሚያገለግለው የሰውነት ክፍል ላይ አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸውን ትተው እርስ በእርሳቸው እንዲጣበቁ ያደርጋል። በዚህ ምክንያት አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸው ቀርቶ አንድ አካል ይሆናሉ። በዚህ ህመም የተጠቃ ሰው ማጎንበስ፣ ወደ ኋላ አሊያም ወደ ጎን መንቀሳቀስ አይችልም። የሌሎቹ የወገብ ህመም ዓይነቶች መንስዔዎችስ? ለወገብ ህመም የሚዳርጉን መንስዔዎች በርካታ ቢሆኑም ዶ/ር ቴዎድሮስ በ21 ዓመት የህክምና ልምዳቸው የተመለከቷቸውንና ዋና ዋና ያሏቸውን መንስዔዎች ያስረዳሉ። ከባድ ነገር ማንሳት፡ ማንኛውም ሰው በዕለት ተዕለት ክንውኑ ጥንቃቄ ካላደረገ ወገቡን ሊታመም ይችላል። በባልዲ ውሃ ቀድቶ ፎቅ ላይ መውሰድ፣ ክብደት ያላቸውን ሰዎች ከአልጋ ማንሳት እንዲሁም ማንኛውንም ከአቅም በላይ የሆነ ክብደትን ማንሳት ለወገብ ህመም ሊዳርግ ይችላል። ከልክ በላይ የሆነ የሰውነት ክብደት መኖር፡ በተለይ በአንድ ጊዜ የሚጨምር የሰውነት ክብደት የወገብ ህመም እንደሚያስከትል ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። ""በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት አካላዊ እንቅስቃሴ የሌለው ሥራ በመዘውተሩ በዚህ ሳቢያ የሚከሰት ህመም ተበራክቶ ነበር"" ይላሉ። ረዘም ላለ ጊዜ ቆሞ፣ ተቀምጦ ወይም ቆሞ ጎንበስ ብሎ መስራት፡ ረዘም ላለ ጊዜ ቆመው፣ ተቀምጠው አልያም ቆመው ከአንገታቸው ተጎንብሰው በሚሰሩ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለወገብ ህመም የመጋለጣቸው ዕድል ሰፊ ነው። ዶ/ር ቴዎድሮስ አንድ ሰው ቆሞ ከአንገቱ ጎንበስ ብሎ በሚሰራበት ጊዜ በሁለት አከርካሪ አጥንቶች መካከል ወደ 270 ኪሎ ግራም ግፊት እንዳለው ጥናቶችን ያጣቅሳሉ። ይህን በየቀኑ ማድረግ ደግሞ ከጊዜ በኋላ የከፋ ጉዳት ያስከትላል። ብዙ ጊዜ የቀዶ ህክምና ሐኪሞች በዚህ ሳቢያ ለሚከሰት የወገ�� ህመም ሲጋለጡ ይስተዋላል። ብዙ መንገጫገጭ ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር፡ ብዙ ንዝረት ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር ወይም ምቹ ባልሆኑ መንገዶች ላይ መኪና ማሽከርከር ከጊዜ በኋላ የወገብ ህመም ያስከትላል። የዝላይ እና የሩጫ እንቅስቃሴዎች፡ በተለይ ከልክ በላይ የሰውነት ክብደት ያላቸው ሰዎች ሩጫ ወይም የመዝለል እንቅስቃሴ የሚያዘወትሩ ከሆነ ወገባቸው ሊጎዳ ይችላል። እንደ አስፓልት ያለ ጠንካራ የሆነ ቦታ ላይ የሚሮጡ ሰዎችም መሬቱ ላይ እግራቸውን በጣሉ ቁጥር መሬትም በአጸፋው ስለሚመታቸው ለጉዳት ሊዳርጋቸው ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ወጣ ገባ የሆነ መሬት ላይ የሚሮጡ ሰዎች እግራቸው በሚያርፍበት ሰዓት ሚዛናቸው እኩል ስለማይሆን ወገብ ላይ ጫና ይፈጠራል። ሰውነት ሳይለምድ በአንድ ጊዜ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት፡ አሁን አሁን በወጣቶች ዘንድ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እየተለመደ መጥቷል። የሚሰሯቸው እንቅስቃሴዎችንም ዩቲዩብ በማየት የሚመርጡም አሉ። ይህ ብቻም ሳይሆን ስፖርቱን ለምን ዓላማ እንደሚሰሩ የማያውቁ በርካቶች ናቸው። በዚህ ሳቢያ ተጎድተው ወደ ክሊኒካቸው የሚመጡ ወጣቶች መኖራቸውን ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። ""ችግሩ አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ የተከሰተ ሳይሆን ሰውነት ሳይለማመድ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት ነው"" ይላሉ። ""ጂምናዚየም ውስጥ ለአሰልጣኝ ጉርሻ መስጠት የተለመደ ሆኗል"" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳንድ አሰልጣኞች ጉርሻዋን ለማግኘት ደንበኞቻቸው የሚፈልጉት የሰውነት ለውጥ ላይ ቶሎ ማድረስ ላይ ብቻ ትኩረት እንደሚያደርጉ ይናገራሉ። አሰልጣኞቹ ስለስፖርታዊ እንቅስቃሴው እንጂ ስለጤና እውቀት ላይኖራቸውም ይችላል። አንዳንድ ሰልጣኞችም በአንድ ጊዜ በሰውነታቸው ላይ የሚፈልጉት ለውጥ እንዲመጣ ባልተገባ መልኩ ከልክ በላይ የሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ ይህንን ሲገልጹት ""ምንም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጎ የማያውቅ ሰው ቅዳሜ እና እሁድ ጂምናዚየም ገብቶ አገር ይያዝልኝ እንደ ማለት ነው"" ይላሉ። ዲስክ መንሸራተት፡ የዲስክ መንሽራተት ስሙ ለብዙዎቻችን ጆሮ እንግዳ አይደለም። ዶ/ር ቴዎድሮስም የዲስክ መንሸራተት ያለ ስሙ ብዙ ስም የተሰጠው በሽታ ነው ይላሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ እንደሚሉት የዲስክ ችግር ተብለው ወደ ክሊኒካቸው ከሚመጡት 100 ሰዎች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ችግራቸው ሌላ ነው። በተለምዶ የህክምና ባለሙያዎች ህሙማንን ለዲስክ መንሸራተት ተዳርገዋል የሚሉት 'ኤምአርአይ' መመርመሪያ የሚያሳየው ውጤት ላይ ተመርኩዘው ነው። ይሁን እንጂ ዶ/ር ቴዎድሮስ ""10 ሰዎችን እንዲሁ ከመንገድ ላይ በግምት ተመርጠው ኤምአርአይ ቢነሱ ቢያንስ 7ቱ የዲስክ መንሸራተት ሊያሳዩ ይችላሉ"" ይላሉ። ይህ ማለት ግን ህመም አለባቸው ማለት አይደለም። ""የዲስክ መንሸራተት ታይቷል ማለት የተዛባ ዲስክ አላቸው፤ ግን ዲስኩ ነርቩን ጨፍልቆ ህመም የሚያመጣበት ደረጃ ላይ አይደለም ማለት ነው"" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። በዚህ የምርመራ ውጤት ላይ ተመስርተው ቶሎ ቀዶ ህክምና አድርጉ ወደሚል ድምዳሜ የሚደርሱ የህክምና ባለሙያዎች መኖራቸውን የሚናገሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ ይህ ግን ስህተት ነው ብለዋል። ለመሆኑ ዲስክ ምንድን ነው? የሚገኘውስ የት ላይ ነው? ዲስክ በአከርካሪ አጥንቶች መካከል የሚገኝ በውስጡ ፈሳሽ ያለው ለስላሳ የሆነ እንደ ጎሚኒ (ሾክ አብሶርቨር) የምንጠቀምበት የአካል ክፍል ነው። ታዲያ ሰውነታችን ጫና በሚበዛበት ጊዜ በዲስኩ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ሊወጣ ይችላል ወይም ደግሞ ፈሳሹ ሳይወጣ ዲስኩ ወደ አንድ በኩል አመዝኖ መውጣ�� ወደማይገባበት ቦታ ሊወጣ ይችላል። ዲስክ ያለበት አካባቢ የተጨናነቀ በመሆኑ አፈትልኮ በሚወጣበት ጊዜ ከጭንቅላታችን በሚወርደውና ህብለ ሰረሰር በሚባለው የነርቭ ግንድ እና ቅርንጫፎች ላይ በመተኛት ጫና ይፈጥራል። የዲስክ መንሸራተት በሚያጋጥምበት ጊዜ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ከመጣደፍ በፊት ዲስኩ ተንሸራቶ ምን ሆነ? ወዴት አቅጣጫ ነው የተንሸራተተው? ምን ያህል ነው የተንሸራተተው? እየነካ ያለውስ ነርቭ የትኛውን ነው? ሊያስከትል የሚችለው የህመም ስሜት አለ ወይ? የሚሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር ቴዎድሮስ ያሰምሩበታል። ወጣቶችን ለወገብ ህመም የሚያጋልጣቸው የተለየ ምክንያት ይኖር ይሆን? ከምንጊዜውም በላይ ብዙ ወጣቶች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ እየተሠማሩ መሆናቸው አንዱ ምክንያት ነው ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ወጣቶች ረዘም ያለ ጊዜ መቆምን፣ መቀመጥን አሊያም ጎንበስ ብሎ መቆምን እንዲሁም ከባድ ነገር ማንሳትን፣ መሸከምን የሚጠይቁ ሥራዎችን ይሠራሉ። በሌላም በኩል ከዚህ ቀደሙ በተሻለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተርም ሌላኛው ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። ""ስለምንሰራው አካላዊ እንቅስቃሴ ጠለቅ ያለ እውቀት ከሌለን በስተቀር የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ጥቅም እንዳላቸው ሁሉ ጉዳት አላቸው።"" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። በተቃራኒው ደግሞ የሰውነት እንቅስቃሴ ማነስ ለወገብ ህመም መንስዔ ነው። የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለወገብ ህመም ያጋልጣል? የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሳይንስ እንደ ወገብ ህመም መንስዔነት ወይም እንደ ወገብ ህመም መነሻነት አይታወቅም ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ይሁን እንጂ የወገብ ህመም ያለባቸው ሰዎች የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙበት መንገድ ህመማቸውን ሊያባብስባቸው ወይም የተሻላቸውን ህመም እንደገና ሊያስነሳባቸው እንደሚችል ይናገራሉ። ""በተለይ በሴቶች ዘንድ ይህንን ለሐኪም የማስረዳት ልምድ የለም"" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳንዶች ግን በስልክም ቢሆን ምክር የሚጠይቁ መኖራቸውን አልሸሸጉም። ""እንደ የወገብ ህመማቸው ዓይነትም ለተወሰነ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደራረግ (Sex position) እንዲቀይሩ፣ እንዳያደርጉ ወይም ሊያደርጓቸው ስለሚችሉ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደራረግ ዓይነቶች ምክር የሚሰጣቸው ታማሚዎች አሉ"" ይላሉ። የምንጫማው ጫማስ? የወገባችንን ጤንነት ለመጠበቅ የምንጫማው የጫማ ዓይነት ወሳኝነት አለው። ይህ ግን በአብዛኛው የሚገናኘው ከሴቶች ጋር ነው። ምክንያቱም በተለይ በፋሽንና መዝናኛ ኢንደስትሪው ሴቶች መንቀሳቀስ እስከሚቸገሩ ድረስ ረጃጅም ታኮ ያላቸውን ጫማዎች ተጫምተው ማየት የተለመደ ነው። ይህ ደግሞ በሰውነት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። እንዴት? ዶ/ር ቴዎድሮስ ለዚህ ሳይንሳዊ ምላሽ አላቸው። ሰውነት የራሱን ሚዛን የሚጠብቅበት መንገድ አለው። ይህ የስበት ማዕከል (Center of gravity) ይባላል። ስንራመድ የማንወድቀው ወይም ደግሞ ቁጭ ብለን ስንነሳ ከግድግዳ ጋር የማንጋጨው ይህ የመሬት ስበት ማዕከል ሚዛናችንን ስለሚጠብቅልን ነው። ታዲያ ከፍ ያሉ ታኮዎች ያሏቸውን ጫማዎች ስንጫማ ሰውነት ተፈጥሯዊ የሆነውን የሰውነት ሚዛን ይለቃል። የሰውነታችን የመሬት ስበት ማዕከልም ይቀየራል። በመሆኑም ሰውነት ይህንን የስበት ማዕከል መልሶ ወደ ማዕከሉ ላይ ለማምጣት (ሚዛኑን ለመጠበቅ) የሚያደርጋቸው ማስተካከያዎች ወገብ ላይ ጫና ይፈጥራሉ። ጫናው ወገብ ላይ ብቻ ሳይሆን ጉልበት፣ እግርና የእግር መዳፍ ላይም ነው። ከዓመታት በፊት በዩናይትድ ኪንግደም በፖዲያትሪ ኮሌጅ የተሠራ ጥናት ሴቶች ህመም እንደተሰማቸው ሳይናገሩ ከፍ ያለ ታኮ ጫማ ተጫምተው መቆየት የሚችሉት በአማካይ ለአንድ ሰዓት ያህል ነው ይላል። በዚህ ጥናት ተሳታፊ የነበሩ ሴቶች ጫማውን ከተጫመቱ ከ10 ደቂቃ በኋላ በእግራቸው ላይ ህመም እንደተሰማቸው ተናግረዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሰው የተፈጠረው በባዶ እግሩ ለመሄድ ነው በማለት ሰዎች በባዶ እግራቸው እንዲሄዱ የሚያበረታታ ሳይንስ አለ። በዚህም ምክንያት ሆነ ብለው በባዶ እግራቸው የሚሄዱ ሰዎች አሉ። በእርግጥ ዶ/ር ቴዎድሮስ በባዶ እግር መሄድ አሊያም በጣም አነስተኛ ታኮ ያላቸው ጫማዎች ማድረግ ጉዳት አለው ብለው አያምኑም። ይሁን እንጂ በተፈጥሮ 'የእግራቸው ቅርጽ ለየት ያለ' ሰዎች ከተረከዝ ሁለት ሴንቲ ሜትር ከፍ ያለ ታኮ ያለው ጫማ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። ""ተረከዝ በጫማ መሄድ ከለመደ በኋላ በባዶ እግር በብዛት መሄድ በተረከዝ ላይ አጥንት መብቀልን (Bone Spur) ሊያስከትልም ይችላል"" ይላሉ። ይህ አጥንት የተረከዝን ስጋ እንደ ጩቤ የሚወጋ ነው። በመሆኑም በተለይ በባዶ እግር መሄድ ያልለመደ እና ተረከዝ ላይ በቂ የስብ ንጣፍ (Fat pad) የሌለው ሰው በባዶ እግሩ ቢሄድ ለእንዲህ ዓይነት ችግር ሊጋለጥ እንደሚችል ያሳስባሉ። ይህ ግን በስፋት የሚከሰት አይደለም። የወገብ ህመም እንዳጋጠመን እንዴት ማወቅ እንችላለን? እንደማንኛውም ህመም የወገብ ህመም ሲያጋጥም የሚታዩ ከቀላል እስከ ከባድ ምልክቶች አሉ። የህመም ማስታገሻ መድሃኒት የማያስወስዱ፣ ቁጭ ስንል የሚያስታውሱን፣ መድሃኒት እስከ መውሰድ የሚያደርስ የማቃጠልና መቆጥቆጥ ስሜት፣ ጎንበስ ብሎ ቀና ለማለት መቸገር፣ ለመነሳት ድጋፍ መፈለግ፣ የጡንቻ መኮማተር፣ ለመንቀሳቀስ መቸገር፣ ተኝቶ ለመገላበጥ ማቃት የተወሰኑት ምልክቶቹ ናቸው። የሚታዩት ምልክቶች ግን እንደ ህመሙ መንስዔዎች ይለያያሉ። ለምሳሌ ረዘም ላለጊዜ በመቆም ወይም በመቀመጥ የሚመጣ ህመም ከሆነ ተቀምጠን ቆይተን ድንገት ስንነሳ የሰውነት መያዝ ፣ ስንቀመጥ ወይ ስንቆም ህመም መሰማት፣ የመቀመጫ አካባቢ ህመም፣ መጠዝጠዝና ንዝረት ያጋጥማል። ንዝረቱ ከመቀመጫ አለፍ ብሎ ቁርጭምጭሚት ፣ ጣቶች እና የእግር መዳፍ ድረስ የሚሰማ የመደንዘዝና የማቃጠል ህመሞች እየባሰ ሲመጣም የእግር መክዳትና ደረጃ ለመውጣት አቅም እስከማጣት ሊደርስ ይችላል። እግርን ማዘዝ፣ ጣቶችን ወደ ላይ ቀና ማድረግ ካቃተን ግን ህመሙ የከፋ ደረጃ ደርሷል ማለት ነው። ምን አልባት ይህ ቀዶ ሕክምና የሚያስፈልግበት ደረጃ ሊሆን ይችላል። ያጋጠመንን የወገብ ህመም ለማስታገስ በቤት ውስጥ ምን ማድረግ እንችላለን? በአቅራብያ የህክምና ተቋም ከሌለ ለጊዜው የህመም ማስታገሻዎችን መውሰድ ይመከራል። ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን ሌላ የሚወስዱት መድሃኒት ከሌለ እና ከሚወስዱት መድሃኒት ጋር የማይጋጭ ከሆነ ነው። ዘላቂ መፍትሔ ግን አይደለም። የወገብ ህመሙ የተከሰተው በድንገተኛ አደጋ [መውደቅ] ከሆነ ደግሞ በመጀመሪያ ህክምና እርዳታ በረዶ ማድረግ ጥሩ ነው። ""የቁስለት ሂደቱን ለመቀነስ፣ እብጠት እና ውስጥ የደም መፍሰስ እንዳይኖር ይረዳል"" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ከዚህ በኋላም የጡንቻ መኮማተር የሚኖር ከሆነ ሙቀት ሰውነትን የማፍታታት ባህርይ ስላለው ሙቀት ማድረግ የተሻለ መሆኑን ይመክራሉ። እረፍት ማድረግም ህመማችንን በተወሰነ ደረጃ ሊያስታግስልን ይችላል። ይህን ሁሉ አድርገን የማይሻል ከሆነ ግን ሥር ሳይሰድ እንደ ምንም ወደ ህክምና ቦታ ሄዶ ትክክለኛ ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው። ""አንዳንድ ሰዎች ባህላዊ ቦታ ሄደው ባልተገባ ሁኔታ ህክምና ወስደው ተጎድተው የሚመጡ አሉ"" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። እንደዚህ ያሉ ቦታዎችን ከሚያዘወትሩ ሰዎች መካከል የተማሩ ሰዎችም ጭምር እንደሚገኙበት በመግ��ጽም ይህ ተገቢ አለመሆኑን ይናገራሉ። ህመሙን ለማስወገድ ሲባል ያልተገባ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግም ጉዳቱን ሊያባብሰው እንደሚችል ዶ/ር ቴዎድሮስ ያስጠነቅቃሉ። ወገባችንን በህክምና ቀበቶ ወይም በመቀነት ብንደግፈውስ? የወገብ ህመም የተለያዩ ደረጃዎች አሉት። መጀመሪያ አካባቢ ችግሩ እንደተፈጠረ፣ ከዚያ ከሁለት እስከ ሦስት ወር እና ከሦስት ወር በላይ የቆየ ህመም ናቸው። ህመሙ ከሦስት ወር በላይ የቆየ ከሆነ ሥር የሰደደ ችግር ይባላል። በመሆኑም ህመሙ እንደ ጀመረ አካባቢ እረፍት ማድረግን ጨምሮ በመቀነት ማሰር ወይም በቀበቶ መደገፍ ያገዘን ስለሚመስል በሥነ ልቦናም ሆነ አካላዊ በሆነ መልኩ ሊደገፍ ይችላል ይላሉ- ዶ/ር ቴዎድሮስ። ሆኖም ይህ ለረዥም ጊዜ የሚደረግ ከሆነ ችግር እንደሚያስከትል ይናገራሉ። ምክንያታቸውን ሲያስረዱም ""ቀበቶ ተደረገ ወይም መቀነት ታሰረ ማለት እዚያ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች እረፍት ወጡ ማለት ነው።"" ይላሉ። በዚህ ሳቢያም የጡንቻ መክሳት ችግር ይከሰታል። በመሆኑም ጡንቻችን ያለ ድጋፍ ሥራውን መሥራት ይቀንሳል፤ አልያም ያቆማል። ይህም ሰዎች በቀበቶ አሊያም በመቀነት ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። ""በኢትዮጵያ በህክምና ባለሙያዎች ዘንድ የአንገት መደገፊያ [ኮላር] እና የወገብ መደገፊያ ቀበቶ የማዘዝ ችግር ጎልቶ እየታየ ነው"" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የችግሩ መንስዔ ሳይታወቅ እነዚህን ቁሶች ማዘዝ ተገቢ እንዳልሆነ ይናገራሉ። አንዳንድ ጊዜ ሐኪሞች ቀበቶ ማዘዛቸውን ሊዘነጉት የሚችሉበት አጋጣሚም ስለሚኖር ታማሚዎቹ ለረዥም ጊዜ ቀበቶውን ሊያደርጉት ይችላሉ። ይህ ደግሞ ጉዳት ያስከትላል ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ምን ዓይነት ፍራሽ እና ትራስ ላይ እንተኛ ? መቼም በወገብ ህመም ሳቢያ ፍራሽ ያልቀያየረ፤ ከአልጋ መደብ ፣ ከመደብ አልጋ ያላለ አይኖርም። ትራስም ቢሆን እንዲሁ። ምን ዓይነት ፍራሽ ላይ እንተኛ ? ምን አይነት ትራስ እንጠቀም የበርካቶች ጭንቀት ነው። ለወገብ ህመም ፍቱን ናቸው የተባሉ ፍራሾችም ይቸበቸባሉ። በሰለጠነው ዓለም የተለያዩ ዓይነት ዘመናዊ ፍራሽና ትራሶች እየተመረቱ ነው። በአንድ አልጋ ላይ ባልና ሚስትን በመረጡት ፍራሽ ላይ የሚያስተኛ ቴክኖሎጂም ተፈልስፏል። ታዲያ የትኛው ላይ ብንተኛ የተሻለ ነው? ዶ/ር ቴዎድሮስ ""ታማሚዎቹ ተመቸን ያሉትን ፍራሽ ትክክል አይደለም ማለት አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም ሰውነታቸው ከመረጡት ፍራሽ ጋር ተመቻችቶ ሊሆን ይችላል"" ይላሉ። ቢሆንም ግን ደረቅ ፍራሽ ላይ መተኛትን አይመክሩም። እርሳቸው የሚመክሩት ሰውነት ቅርጹን በጠበቀ መልኩ የሚያሳርፍን ፍራሽ ወይም ትራስ ነው። ""ራቁታችንን በመስታዎት ብንመለከት ሰውነታችን እጥፋቶች (Curves) አሉት። ስንተኛ እነዚያ እጥፋቶች ቅርጻቸውን ጠብቀው በትክክል ማረፍ አለባቸው"" ይላሉ። ለዚህም ነው በሰለጠነው ዓለም 'ሚሞሪ ፎም' የተመረተው። ሚሞሪ ፎም ስንተኛ የሰውነትን ቅርጽ ይዞ ስንነሳ ወደ ነበረበት መመለስ የሚችል ፍራሽ ነው። 'ስሊፕ ነምበር ቤድ' የሚባልም ባልና ሚስት አልጋቸውን ሳይለዩ ለየራሳቸው የሰውነት ቅርጽ በሚመቻቸው መልኩ ማስተካከል የሚችሉት ሳይንሳዊ ፍራሽም ተሰርቷል። በኢትዮጵያ ለወገብ ህመም ተብለው የሚሸጡ ፍራሾችስ? ዶ/ር ቴዎድሮስ እነዚህ ፍራሾች ሳይንሳዊ አይደሉም ይላሉ። ""ሱቅ የተሰቀለን ልብስ በግምት አንስቶ ግባ ብሎ እንደመታገል ነው"" ሲሉም በምሳሌ ያስረዳሉ። ""በሰለጠነው ዓለም 30 ደቂቃ ፍራሹ ላይ እረፍት ወስደን ነው ፍራሽ የምንገዛው"" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ በኢትዮጵያ አንዳንድ መሸጫዎች ውስጥ 'ፍራሾቹ ላይ መተኛት ክልክል ነው!' የሚልም ማስታወቂያ በመለጠፍ ምቾቱን ሞክሮ ለመግዛት የሚደረገውን ክልከላንም ተችተዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ትራስን በተመለከተም ተመሳሳይ ሃሳብ ነው ያላቸው። ትራስ በጭንቅላታችን እና በአንገታችን ሥር መካከል ያለውን ክፍተት የሚሞላ መሆን አለበት ይላሉ። ነገር ግን ሰዎች ትራሳቸውን በአግባቡ ሲጠቀሙበት አይስተዋልም። በእርግጥ የሚመቸንንና ልካችንን ለማወቅ አዳጋች ነው። ገንዘባቸውን ትራስ በመግዛት የሚጨርሱም ጥቂት አይደሉም። ይህንን ችግር ለመፍታትም ይመስላል በሰለጠነው ዓለም 'ዎተር ፒሎው' [በውሃ የሚሞላ ትራስ] የተሰራው። ይህ የውሃውን መጠን በመቀነስ ወይም በመጨመር ትራሱን በልክ ለማሳነስና ለማተለቅ ያስችላል። በመሆኑም የምንጠቀመውን ትራስ ልክ ማወቅ እና በተገቢው መንገድ መጠቀም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ይመክራሉ። የአኗኗር ዘይቤያችን ምን ይምሰል? የሰውነት ክብደታችንን መቆጣጠር ወሳኝ ነው። ይህን ማድረጋችን ከወገብ ብቻም ሳይሆን ከሌሎች በሽታዎችም ራሳችንን ለመጠበቅ ያስችለናል። ""በሰውነታችን ላይ አንድ ኪሎ በጨመርን ቁጥር በእያንዳንዱ ኪሎ አንዱ ጉልበታችን ላይ 4 ኪሎ ጫና ይፈጠራል"" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የሰውነታችንን ክብደት መቆጣጠርን ቸል ልንለው እንደማይገባ ይመክራሉ። የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በአቅማችን ልክ እና ቀስ በቀስ በተደረገ የሰውነት ልምምድ መስራት ሌላኛው ነው። የውሃ ዋና እና በሳምንት ለአራት ወይም ለሦስት ቀናት ለ45 ደቂቃ ያህል በእግር ፈጠን ያለ እርምጃ መሄድም ጥሩ ነው። የሥራ ሁኔታን ምቹ ማድረግም አስፈላጊነቱ የሚያጠያይቅ አይደለም። ቆመው የሚሰሩ ሰዎች እቃ ሲያነሱ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለባቸው ማወቅ፣ የሚመች ጫማ ማድረግ እንዲሁም ብዙ የሚቆሙ ሰዎች አንድ እግራቸውን አንድ ነገር ላይ አሳርፈው (ሰቅለው) መቆም ለወገብ ህመም የመጋለጥ እድላቸውን ይቀንሳል። ከዚህም ባሻገር የወገብ ህመም መንስዔ ከሆኑ ድርጊቶች ራስን መጠበቅ እንደሚገባ ዶ/ር ቴዎድሮስ ይመክራሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-60278142 +sports ለተሰንበት ግደይ የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰንን ሰበረች ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ስፔን ቫሌንሺያ ዛሬ በተካሄደው ግማሽ ማራቶን ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰንን ሰበረች። ቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን ትሪኒዳድ አልፎንሶ ኢዲፒ የተሰኘ ስያሜ በተሰጠው የዘንድሮው ውድድር ላይ የተሳተፈችው ለተሰንበት 1 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ52 በመግባት ነው ክብረ ወሰን የሰበረችው። ባለፈው ዓመት የ5 ሺህ ክብረ ወሰንን በሰበረችበት መድረክ ላይ ነው ለተሰንበት ዛሬ በኬንያዊቷ አትሌት የተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ለማሻሻል የቻለችው። ኬንያዊቷ ሩት ቼፕንጌቲክ በያዝነው ዓመት ነበር የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰንን 1 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ02 ሰኮንድ መግባት የያዘችው። የቶኪዮ ኦሊምፒክስ የነሐስ ባለቤቷ ለተሰንበት በዛሬው ውድድር ላይ የመጀመሪያውን 5 ኪሎ ሜትር በ15 ደቂቃ ነበር የሮጠችው። ለተሰንበት የውድድሩን 10 ኪሎ ሜትር በ29 ደቂቃ ስታጠናቅቅ ይህም በግማሽ ማራቶን ታሪክ ሦስተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል። ለተሰንበት በአስደናቂ ፍጥነት ቀጣዩን 5 ኪሎ ሜትር በመሮጥ 15 ኪሎ ሜትር በ44 ደቂቃ 29 ሰኮንድ ማጠናቀቅ ችላለች። ነገር ግን በመጨረሻው ሲሶ ፍጥነቷ በተነፃፃሪ ቢቀንስም በመጀመሪያዎቹ ኪሎ ሜትሮች ያስመዘገበችው ፈጣን ሰዓት ክብረ ወሰኑን እንድትሰብር አስችሏታል። በስተመጨረሻም 1 ሰዓት ከ02 ደቂቃ በ52 ሰኮንድ በመግባት በስሟ ሦስተኛውን ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ችላለች። ለተሰንበት ግደይ በአሁኑ ወቅት የ10 ሺህ ሜትር፣ የ5 ሺህ ሜትርና ዛሬ ባስመዘገበችው ውጤት መሠረት ደግሞ የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ናት። በውድድሩ ላይ ተሳታፊ የነበረችው ሌላኛዋ ኢትዮጰያዊት የዓለምዘርፍ የኋላው ለተሰንበትን ተከትላ በ1 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ52 ሰኮንድ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች። https://www.bbc.com/amharic/news-59027278 +business ቲክቶክ ስደተኞች ለምነው ከሚያገኙት ገንዘብ ከፍተኛ ኮሚሽን እየሰበሰበ መሆኑ ተጋለጠ "በሶሪያ መጠለያዎች ውስጥ ያሉ ስደተኞች በቲክቶክ ላይ ድጋፍ እየለመኑ ከሚያገኙት ገቢ ኩባንያው እስከ 70 በመቶውን እንደሚወስድ የቢቢሲ ምርመራ አረጋገጠ። ልጆች ወደ ገንዘብ የሚቀየሩ ዲጂታል ስጦታዎችን ለማግኘት በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ለሰዓታት በቀጥታ ስርጭት ሲማጸኑ ይቆያሉ። ስደተኞቹ ከቀጥታ ስርጭቶቹ በሰዓት እስከ 1,000 ዶላር እንደሚያገኙ ቢቢሲ ተመልክቷል። ስደተኞቹ ኪስ የሚገባው ግን በጣም ጥቂት ነው። ቲክቶክ ""በልመና"" ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ ተናግሯል። ኩባንያው በልመና ገንዘብ መሰብሰብን እንደማይፈቅድ ገልጾ ከዲጂታል ስጦታዎች የሚቀበሉ ደርሻ ከ70 በመቶ ያነሰ ነው ቢልም ትክክለኛውን መጠን ከመግለጽ ግን ተቆጥቧል። በፈረንጆቹ 2022 መጀመሪያ ላይ የቲክቶክ ተጠቃሚ ገጾች ከሶሪያ ካምፖች በሚገኙ የስደተኖች የቀጥታ ስርጭቶች ተሞልተው ነበር። በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በሚገኙ መጠለያዎች ውስጥ ይህን ሁኔታ የሚያመቻቹ ‘የቲክቶክ ደላሎች’ መኖራቸውን ቢቢሲ አረጋግጧል። ለስደተኞቹ የቀጥታ ስርጭት የሚያገለግሉ ተንቀሳቃሽ ስልክ እና ቁሳቁስ እነዚህ ደላሎች ያቀርባሉ። ደላላዎቹ በበኩላቸው በቻይና እና በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙና ከቲክቶክ ጋር ግንኙነት ካላቸው ድርጅቶች ጋር በመሥራት ስደተኞቹ የቲክቶክ አካውንት እንዲያገኙ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። እነዚህ ድርጅቶች የቀጥታ ስርጭቶችን ለማስፋት እና ተጠቃሚዎች በመተግበሪያው ላይ ተጨማሪ ጊዜ እንዲያሳልፉ ለማበረታታት ቲክቶክ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጀመረው ስትራቴጂ አካል ናቸው። ቲክቶክ የሚሰራበት ሁኔታ (አልጎሪዝም) ይዘትን ይበልጥ የሚያስተዋውቀው የተጠቃሚውን የስልክ ቁጥር ጂኦግራፊያዊ አቀመጣጥ መሠረት በማድረግ ነው። በዚህም ደላላዎቹ የእንግሊዝ ሲም ካርዶችን መጠቀም እንደሚመርጡ ተናግረዋል። የዩናይትድ ኪንግደም ሰዎች በጣም ለጋሾች ናቸው ይላሉ። ሞና አሊ አል-ካሪም እና ስድስት ሴት ልጆቿ በየቀኑ በቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፉ ቤተሰቦች ናቸው። በድንኳናቸው ለሰዓታት ተቀምጠው የሚያውቁትን ጥቂት የእንግሊዘኛ ሐረጎች ይደጋግማሉ። ""እባክዎ የመውደድ ምልክቱን ይጫኑ፣ ያጋሩ፣ እባክዎን ስጦታ ይስጡን"" የሚሉ ቃላት ይደጋገማሉ። ሞና ባለቤቷ በአየር ድብደባ ወቅት ነው የተገደለው። የቀጥታ ስርጭቱን ተጠቅማ ማየት ለተሳናት ልጇ ሸሪፋ ቀዶ ህክምና የሚሆን ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ ትገኛለች። የሚጠይቋቸው ስጦታዎች ምናባዊ ናቸው። ተመልካቾችን ግን እውነተኛ ገንዘብ ያስከፍላሉ። ከመተግበሪያውም በጥሬ ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ። የቀጥታ ስርጭቱ ተመልካቾች ስጦታዎቹን ይልካሉ። ጥቂት ሳንቲሞችን ከሚያስወጡ ዲጂታል ጽጌረዳዎች እስከ 500 ዶላር ገደማ የሚያወጡ ምናባዊ አንበሶችን በስጦታ መልክ ይሰጣሉ። ለአምስት ወራት ያህል ቢቢሲ ከሶሪያ የስደተኞች ካምፖች በቀጥታ የሚተላለፉ 30 የቲክቶክ አካውንቶችን ተከታትሏል። ለዚሁ የሚሆን የኮምፒዩተር ስለተ ቀመር አዘጋጅቶ ባገኘው መረጃ እያንዳንዱ አካውንት በሰዓት እስከ 1,000 ዶላር የሚያወጡ ዲጂታል ስጦታዎችን እንዳገኘ ያሳያል። በካምፑ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች ግን በጣም ትንሽ ብቻ እያገኙ እንደሆነ ተናግረዋል ። ቲክቶክ ከስጦታዎች ምን ያህል እንደሚያገኝ አልገለጸም። ቢቢሲ ገንዘቡ የት እንደሚገባ ለማወቅ ሙከራ አድርጓል። በሶሪያ የሚ���ኝ አንድ ጋዜጠኛ በመጠለያ ጣብያ ውስጥ የሚኖር ስደተኛ መስሎ ከቲክቶክ ጋር ግንኙነት ወዳለው አንድ ኤጀንሲ ይቀርባል። አካውንት ይሰጠውና ቀጥታ ስርጭት ይጀምራል። በለንደን የሚገኙ የቢቢሲ ሠራተኞች በሌላ አካውንት 106 ዶላር የሚያወጣ የቲክ ቶክ ስጦታዎችን ላኩለት። የቀጥታ ስርጭቱ መጨረሻ ላይ በሶሪያው አካውንት ላይ ያለው ቀሪ ሒሳብ 33 ዶላር ነበር። ቲክቶክ ከስጦታዎቹ ዋጋ 69 በመቶውን ወስዷል። የቲክቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪው እና የቀድሞው የራግቢ ተጫዋች ኪት ሜሰን በአንድ ቤተሰብ የቀጥታ ስርጭት ወቅት 330 ዶላር ለገሰ። አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮቹም በተመሳሳይ አንዲለግሱ አበረታቷቸዋል። አብዛኛው ገንዘብ በማህበራዊ ድር አምባው ኩባንያ እንደሚወሰድ ከቢቢሲ ሲነገረው በሶሪያ ውስጥ ላሉ ቤተሰቦች ላይ የሚደረግ ""አስገራሚ"" እና ""ፍትሃዊ ያልሆነ"" ነገር ነው ብሏል። ""ግልጽነት ሊኖር ይገባል። ለእኔ ይህ በጣም ስግብግብነት ነው። ስግብግብነት” ብሏል። ከቢቢሲ 106 ዶላር ስጦታ የቀረው 33 ዶላሩ ነው ብለናል። ይህን ገንዘብ ሲቀበሉ የሃገር ውስጥ የገንዘብ አስተላላፊዎች ደግሞ 10 በመቶ ይቀንሳሉ። የቲክ ቶክ ደላላዎቹ ደግሞ 35 በመቶውን ይወስዳሉ። ከዚህ ሁሉ በኋላ የስደተኛ ቤተሰቦቹ 19 ዶላር ብቻ ያገኛሉ። በካምፑ ውስጥ ከሚገኙ የቲክ ቶክ ደላላዎች አንዱ የሆነው ሃሚድ ከብቶቹን ሸጧል። በገንዘቡ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ሲም ካርድ እና ዋይ ፋይ ገዝቷል። ይህንንም የቀጥታ ስርጭት ከሚያሰራጩ ቤተሰቦች ጋር ይሠራበታል። አሁን በቀን ለበርካታ ሰዓታት ከ12 የተለያዩ ቤተሰቦች ጋር ይሠራል። ሃሚድ እነዚህ ቤተሰቦች ለመተዳደሪያ የሚሆን ገቢ እንዲያገኙ ለመርዳት ቲክቶክን እንደሚጠቀም ይሞግታል። የራሱን ኮሚሽን ቀንሶ አብዛኛውን ገቢ እንደሚከፍላቸውም ገልጿል። ቻይና ውስጥ በቀጥታ ከቲክቶክ ጋር የሚሠሩ “ኤጀንሲዎች” ይደግፉናል ሲል ሃሚድም ሌሎችን ደላላዎች ሃሳብ ይጋራል። ""በመተግበሪያው ላይ ችግር ካጋጠመን ይረዱናል። የታገዱ አካውንቶችን ያስከፍታሉ። የአካውንቱን ስም እና ምስል ስንሰጣቸው አካውንቱን ይከፍታሉ"" ሲል ሃሚድ ያስረዳል። “የቀጥታ ስርጭት አጋዥ ” በመባል የሚታወቁት እነዚህ ኤጀንሲዎች በመላው ዓለም ይገኛሉ። ተጠቃሚዎች ይበልጥ ማራኪ የቀጥታ ስርጭቶችን እንዲያዘጋጁ ለመርዳት ከቲክቶክ ጋር የተስማሙ ናቸው። ቲክ ቶክ በቀጥታ ስርጭት የቆይታ ጊዜ እና በተቀበሉት ስጦታዎች ዋጋ መሠረት ኮሚሽን ይከፍላቸዋል ሲሉ ኤጀንሲዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የቆይታ ጊዜውን ለማሳደግ በሶሪያ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ያሉ ህጻናትን ጨምሮ ሌሎችም ቲክቶክ ላይ ለሰዓታት ይጣዳሉ። የዲጂታል መብቶች ድርጅት አክሰስ ናው ባለደረባ የሆኑት ማርዋ ፋፍታታ እነዚህ የቀጥታ ስርጭቶች  ከቲኪ ቶክ ፖሊሲዎች ጋር የሚቃረኑ ናቸው ብለዋል። በተለይም ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህጻናትን “ከጉዳት፣ አደጋ ወይም ብዝበዛ መከላከል” ከሚለው ፖሊሲ ጋር ይቃረናል ይላሉ። ""ቲክቶክ ተጠቃሚዎቹ በግልጽ ስጦታዎችን እንዲጠይቁ እንደማይፈቀድላቸው ይናገራል። ስለዚህ ይህ የራሱን የአገልግሎት ውሎች እና የሰዎችን መብት መጣስ ነው"" ይላሉ። ሰዎች ""ድጋፍ እና ርህራሄን ለማግኘት"" ታሪኮቻቸውን የማካፈል መብት እንዳላቸው ይገልጻሉ። እነዚህ የቀጥታ ስርጭቶች ግን ""ክብር የሌላቸው እና የሚያዋርዱ ናቸው"" ይላሉ። የቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት ከመጀመር በፊት 1,000 ተከታዮች ሊኖሩዎት ይገባል ይላል። ስጦታዎችን በቀጥታ መጠየቅም አይፈቀድም። ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን “ከጉዳት፣ አደጋ ወይም ብዝበዛ መከላከል” አለብዎትም ይላል። ቢቢሲ መተግበሪያውን ተጠቅሞ ህፃናት የሚለምኑባቸውን 30 አካውንቶች ሪፖርት ቢያደርግም ቲክቶክ ፖሊሲው እንዳልተጣሰ ተናግሯል። ቢቢሲ አስተያየት ለማግኘት በቀጥታ ቲክቶክን ካነጋገረ በኋላ ኩባንያው ሁሉንም አካውንቶች አግዷል። በመግለጫውም “ቢቢሲ ያቀረበልን መረጃ እና ውንጀላ በጣም አሳስቦናል። ፈጣን እና ጥብቅ እርምጃም ወስደናል” ብሏል። ""ይህ ዓይነት ይዘት በእኛ መድረክ ላይ ፈጽሞ አይፈቀድም። በበዝባዥ ልመና ዙሪያ ዓለም አቀፋዊ ፖሊሲያችንን የበለጠ እያጠናከርን ነው።"" ቲክቶክ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበ የሚገኝ ማህበራዊ ድር አምባ ነው። ሴንሰር ታወር እንደተባለ አጥኚ ኩባንያ ከሆነ እአአ በ2017 ከተመሠረተ በኋላ 6.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል። በቲክቶክ ቀጥታ ስርጭት ገንዘብ ማግኘትን እንደ አማራጭ ከመውሰድ  በሶሪያ ውስጥ የሚሠሩ በጎ አድራጊ ድርጅቶች በመጠለያዎች ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችን እንዲደግፉ ቢቢሲ ጠይቋቸዋል። ታካፉል አልሻም የተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ልጆቹ ትምህርት እንዲያገኙ የትምህርት ወጪያቸውን በመሸፈን ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት መሠረታዊ ቁሳቁሶችን እንደሚያቀርብ ተናግሯል። በካምፑ ውስጥ ላሉ ብዙ ቤተሰቦች ግን በቀጥታ ስርጭት ከመለመን ውጪ ገንዘብ የማግኛ ጥቂት አማራጮች ነው ያላቸው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች በየቀኑ በቀጥታ ስርጭት መቅርባቸውን ቀጥለዋል። ከተለገሰው ገንዘብ አብዛኛውም ቲክቶክ መግባቱን ቀጥሏል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c725qj2l2gko +business ኢትዮጵያ ለመጀመር ያቀደችው ‘ስቶክ ማርኬት’ ምን ይዞ ይመጣል? ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኢትዮጵያ የስቶክ ማርኬት ማስጀመር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል። ‘ኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ’ (ESX) የተሰኘውን የአክሲዮን ገበያ በኢትዮጵያ ለማስጀመር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት የተፈረመው በኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በኤፍኤስዲ አፍሪካ መካከል ነው። አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ የፌርፋክስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ሊቀ መንበር ናቸው። የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮችም በቅርበት ይከታተላሉ። ለስቶክ ማርኬት ‘የድርሻ ገበያ’ የሚል አቻ የአማርኛ ትርጉም ልንሰጠው እንችላለን ይላሉ። ኩባንያዎች የኩባንያውን የባለቤትነት ድርሻ ለገበያ ያቀርባሉ። ሰዎችም ይህን ድርሻ ከገዙ በኋላ ኩባንያው ትርፋማ በሆነ መጠን ያላቸውን ድርሻ መልሰው በመሸጥ ወይም ከትርፍ ክፍፍል ትርፋማ የሚያደርግ አሠራር ነው። ስቶክ ማርኬት ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣል? አቶ ዘመዴነህ ኢትዮጵያ የስቶክ ገበያ ለማቋቋም በዝግጅት ላይ ብትሆነም የስቶክ ገበያ ጽንሰ ሐሳብ ለአገሪቱ ገበያ አዲስ አይደለም ይላሉ። በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ ጥምረት የሚቋቋመው የስቶክ ገበያ በዋናነት የሚከተሉትን ጥቅሞች ለኢትዮጵያ ይዞ እንደሚመጣ ይገልጻሉ። በርካታ የአገር ውስጥ ባንክ እና ኢንሹራንሶች ሲመሠረቱ እና ከምሥረታቸውም በኋላ የአክሲዮን ድርሻዎችን ሲሸጡ መቆየታቸውን በማስታወስ፤ የስቶክ ገበያን ከዚህ የተለየ የሚያደርገው፤ ይፋዊ በሆነ መልኩ ተደራጅቶ ቁጥጥር እየተገደረገበት በግልጽ መገበያየት ማስቻሉ ነው ይላሉ። የኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ (ኢኤስኤክስ) እውን ሲሆን፤ ባንኮች እና ኢንሹራንሶች ሲቋቋሙም ሆነ ማስፋፋት ሲፈልጉ አክሲዮኖቻቸውን ለመሸጥ ይከተሉት የነበረውን ረዥም መንገድ እንደሚያሳጥርላቸው ያክላሉ። “እነዚህ ኩባንያዎች ሲቋቋሙ ስቶክ ኤክስቼንጅ ስላልነበረ በጣም ረዥም ሂደት በማለፍ ለእያንዳንዱ ሰው እየዞሩ ነው ሼር የሚሸጡት። ይህ ረዥም ጊዜ እና ገንዘብ ይወስዳል። አዋጭም አይደለም” ይላሉ ዘመዴነህ። የኢት��ጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ መመሥረት አንዱ ጥቅም አዲስ ለመሚሠረቱም ሆነ ለነባር ኩባንያዎች የካፒታል ገበያን መፍጠሩ ነው ይላሉ። ካፒታል ማሰባሰብ ለሚፈልጉም ስቶክ ገበያ መልካም አማራጭ እንደሆነ አቶ ዘመዴነህ ያስረዳሉ። “ጥሩ ሐሳብ ኖሯቸው የካፒታል እጥረት ላለባቸው ሰዎች ይጠቅማል። ዛሬ ላይ ከባንክ ብድር ማግኘትም ቀላል አይለደም። ለዘመድ ወይም ለጓደኛ ሼር የመሸጥ ሂደት ቀላል አይደለም። ስቶክ ማርኬት አዲስ ለሆኑም ይሁን መስፋፋት ለሚፈልጉ ኩባንያዎች የካፒታል ገበያን ይፈጥራል።” የስቶክ ገበያ፣ ፍትሐዊ እና ተመጣጣኝ በሆነ ሁኔታ ሀብት ማከፋፈል የሚችል ሥርዓት እንደሆነ አቶ ዘመዴነህ ይገልጻሉ። በአሁኑ ጊዜ ግዙፍ መንግሥታዊ ኩባንያዎች ወደ ግሉ ዘርፍ እየተሸጋገሩ እንደሆነ በማስታወስ፣ እነዚህ ከመንግሥት ወደ ግሉ የሚዘዋወሩት ግዙፍ ኩባንያዎችን ሲገዙ የቆዩት ጥቂት ግለሰቦች እና ኮርፖሬሽኖች መሆኑን ይጠቅሳሉ። ኢኤስኤክስ ሲመጣ ግን መንግሥት የሕዝብን ሀብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ማከፋፈል ይችላል። “ስቶክ ማርኬት ላይ አንድ ሼር በአምስትም፣ በአሥርም ዶላር ሲሸጥ ሁሉም የየአቅሙን በመግዛት ኢትዮጵያ ያካበተችውን ሀብት ማከፋፈል ይቻላል” ሲሉ ያብራራሉ። እነዚህ ወደ ግሉ ዘርፍ የሚዘዋወሩ ኩባንያዎች ወደ ስቶክ ገበያው ሲገቡ፣ ሁሉም የአቅሙን ያህል ባለቤት እንደሚሆንና ይህም የሀብት ክፍፍልን እንደሚያመጣ ያክላሉ። የኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ እውን ሲሆን የቁጠባ ባህልን ከፍ እንደሚያደርግ አቶ ዘመዴነህ ይናገራሉ። ሰዎች በአሁኑ ጊዜ ኪሳራ አያስከትልም ብለው በሚያስቡት ዘርፍ ላይ ብቻ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ ይገኛሉ። “ገንዘብ ያላቸው ሰዎች የቤት ልማት ላይ ብቻ ትኩረት ሲያደርጉ ይታያል። የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ደግሞ ተጎድቷል። ይህም ኢንቨስት የሚደረግባቸው ዘርፎችን ውስን በማድረግ የቁጠባ አለመመጣጠን ይፈጥራል። ስቶክ ማርኬቱ ግን ውጤታማ በሆነ መንገድ ካፒታል በሁሉም ዘርፎች ላይ ማሰራጨት ያስችላል” በማለት ያስረዳሉ። ሌላኛው መልካም አጋጣሚ የድርሻ ገበያዎችን በቀላሉ፣ ግልጸኝነት በሰፈነበት መልኩ መግዛት እና መሸጥ ማስቻሉ ነው። ምን ያህል ሼር በምን ያህል ዋጋ ለገበያ እንደቀረበ ግልጽ ነው። “ሰዎች ስልካቸው ላይ በሚጭኑት መተግበሪያ በቀላሉ የገበያ ድርሻዎችን መግዛት እና የገዙትንም መሸጥ ይችላሉ” ይላሉ አቶ ዘመዴነህ። የባንክ ባለ አክሲዮኖች ዓመት ጠብቀው ትርፍ ከመከፋፈል ውጪ በቀላሉ ያላቸውን አክሲዮን መሸጥ አይቻላቸውም። ኢኤስኤክስ እውን ሲሆን ግን በቀላሉ አክሲዮን የመሸጥ ዕድል ይዘረጋል። ከበርካታ አሥርት ዓመታት በፊት የተቋቋመው የኬንያው ‘ናይሮቢ ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ’ ወደ 60 ገደማ የአገር ውስጥ እና የውጭ ኩባንያዎችን ይዟል። አቶ ዘመዴነህ የኢትዮጵያው ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ በሁለት ዓመታት ውስጥ ከ50 ያላነሱ ኩባንያዎችን በውስጡ ይይዛል የሚል ተስፋ አላቸው። እሳቸው እንደሚሉት፣ የስቶክ ገበያውን ሊቀላቀሉ የሚችሉ ኩባንያዎችን ስናስብ በብሔራዊ ባንክ ጠንካራ ቁጥጥር የሚደርግባቸውን 18 ባንኮች እና ከ18 የማያንሱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች መዘንጋት የለብንም ይላሉ። “ሁሉም የስቶክ ገበያውን ላይቀላቀሉ ይችላሉ። . . . ቁጥሩን 30 ብለን እንያዘው። 20ው ከየት ይመጣል? ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ባለቤትነታቸው በቤተሰብ ደረጃ የሆነ ግዙፍ ኩባንያዎች ስቶክ ማርኬት ላይ ለመግባት ዝግጁ የሆኑ ይኖራሉ። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ዓለም አቀፍ የሆኑ የውጭ ኩባንያዎች አሉ። ኮካ ኮላ፣ ሃይኒከን፣ ዩኒሊቨር እና ቶታልን ማንሳት ይቻላል። የእኔ ግምት ከ40 አስከ 70 ነው” በማለት ሐሳባቸውን ያጠናክራሉ። ይህ ማለት ግን ሁሉም ኩባንያዎች በአንድ ቀን ይገባሉ ማለት አይደለም። ቁጥራቸው በጊዜ ሂደት የሚጨምር ይሆናል። ይህንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ስቶክ ገበያ ምንድን ነው? እንዴትስ መሸጥ እና መለወጥ ይቻላል? የሚለውን እንመልከት። ስቶክ ገበያን በቀላል ቋንቋ ለመረዳት የምጣሄ ሀብት ባለሙያዎች አዘወትረው የሚጠቀሙትን ቀላል ምሳሌ እንውሰድ። 'ሀ'፣ 'ለ' እና 'ሐ' የሚባሉ ሦስት ምናባዊ የሞባይል ስልክ አምራች ኩባንያዎችን አሉ አንበል። እርስዎ 6 ዶላር አውጥተው ከእያንዳንዱ ኩባንያ የሁለት ዶላር የገበያ ድርሻ ይገዛሉ። 'ሀ' ለገበያ ያቀረበው ሞባይል ስልክ ባትሪው እየፈነዳ ሰዎችን ለጉዳት እየዳረገ መሆኑን የሚያመለክት ሪፖርት መውጣት ይጀምራል። የ'ለ' ኩባንያ የሆነው ምርት ደግሞ ባትሪው በፍጥነት እያለቀ ከተጠቃሚዎች ቅሬታ ይደርሰዋል። የ'ሐ' ምርት የሆነው ሞባይል ስልክ ግን በአግባቡ ይሠራል። ይህ በገበያ ላይ ያጋጠመው ክስተት በሦስቱ ኩባንያዎች ስቶክ ገበያ ዋጋ ላይ ለውጥ ያመጣል። የአንድ ኩባንያ ምርት ጥራት ሲወርድ የዚያ ኩባንያ ፈላጊዎች ይቀንሳሉ። በተቀራኒው አንድ ኩባንያ ትርፍማ የሚያደርገውን ውሳኔ ወስኖ ትርፍ ሲያጋብስ፣ የትርፉ ተቋዳሽ መሆን የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከፍ ይላል። በዚህ መሠረት ባትሪው እየፈነዳ ሰዎችን ለአደጋ እያጋለጠ ያለው የሞባይል ኩባንያ ድርሻ በከፍተኛ መጠን ሊወርድ ይችላል። በሁለት ዶላር የገዙትን ድርሻ መልሰው መሸጥ ቢፈልጉ ከግማሸ ባነሰ ዋጋ እንኳን የሚገዛዎትን ላያገኙ ይችላሉ። ይህ ሞባይል አምራች ኩባንያ ሲከስር እርስዎም የኩባንያው ባለድርሻ እንደመሆንዎ ኪሳራ ያጋጥምዎታል። ስለዚህ በኩባንያ 'ሀ' ላይ ያደረጉት ኢንቨስትመንት ኪሳራን ያስከትላል። የ 'ሐ' ምርት የሆነው ስልክ ግን በገበያ ተፈላጊነቱ ሲጨምር የኩባንያው ዋጋም ከፍ ይላል። ምናልባት በሁለት ዶላር የገዙትን የኩባንያውን ድርሻ፣ አሁን ላይ በ4 ዶላር ሸጠው ትርፍ ሊያገኙ ይችላሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2re4ddxgvo +politics ለ2ኛ ጊዜ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ማክሮን ሕዝቡን አንድ ለማድረግ ቃል ገቡ ኢማኑኤል ማክሮን ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ በድጋሚ ተመረጡ፡፡ ማክሮን ትናንት በተደረገ አገር አቀፍ ምርጫ ተቀናቃኛቸውን ማሪን ሌ ፔንን በሰፊ ልዩነት አሸንፈዋቸዋል፡፡ የቀኝ አክራሪዋ፣ ስደተኛ ጠል ናቸው የሚባሉት ማሪን ሌ ፔን ሊያሸንፉ የሚችሉበት ዕድል ስለነበረ የፈረንሳይ ምርጫ በተለይ በመላው አውሮጳ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ነበር፡፡ ሌ ፔን ሙስሊም ሴቶች ሒጃብ በአደባባይ እንዳይለበሱ ሕግ የማውጣት ፍላጎት ነበራቸው፡፡ ስደተኞችን የማባረር፣ ለአገሬው ሕዝብ በሁሉም ረገድ ቅድሚያ የመስጠት ፖሊሲም እንደሚከተሉ ቃል ገብተው ነበር፡፡ በተጨማሪም ፈረንሳይ ከኔቶ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት እንዲሁም ከአውሮጳ ኅብረት የምትወጣበትን ሁኔታ እንደሚያፈላልጉ ለደጋፊዎቻቸው ቃል ገብተው ነበር፡፡ ይህም በመሆኑ ነው የሳቸው አለመመረጥ በአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ዘንድ እፎይታን የፈጠረው፡፡ ማክሮን በድጋሚ ፕሬዝዳንትነቱን ያሸነፉት ከድምጽ ሰጪው ሕዝብ 58.55 ከመቶ በማግኘት ነው፡፡ ሌ ፔን ድምጽ ማግኘት የቻሉት ግን 41.45 የሚሆነውን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና ለአንድ ቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ይህን ያህል ድምጽ ማገኘት እጅግ ከፍተኛ የሚባል ሲሆን አገሪቱ ምን ያህል እንደተከፋፈለች የሚያመላክት ነው ይላሉ ተንታኞች፡፡ ማክሮን ከድል በኋላ ባደረጉት ንግግር የተከፋፈለውን የፈረንሳይ ሕዝብ አንድ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡ ኢማኑኤል ���ክሮን በተለይ ለመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ደንታ የላቸውም፣ እሳቸው የሃብታም ፈረንሳዊያን ፕሬዝዳንት ናቸው በሚል ሲወቀሱ ቆይተዋል፡፡ ማክሮን የኑሮ ውድነትን መቆጣጠር አለመቻላቸውም ከፍተኛ ተቃውሞን አስነስቶባቸዋል፡፡ የምርጫ ውጤቱ ይፋ ከሆነ በኋላ ሌ ፔን ሽንፈታቸውን የተቀበሉ ሲሆን ያገኙት ድምጽ በራሱ ግን ለፓርቲያቸው ትልቅ ድል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በአውሮጳ ከሚንቀሳቀሱ ቀኝ አክራሪ ብሔርተኞች ሌ ፔን ከፍ ያለ ስምና ዝና ያላቸው ቢሆንም እሳቸውም እንደ ወላጅ አባታቸው በተደጋጋሚ ተወዳድረው ድል ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ በተለይ በዚህኛው ዙር የሳቸው ፓርቲ ከሩሲያ ባንክ ብድር መውሰዱ፣ እሳቸውም ሩሲያ ክሪሚያን ጠቅልላ በወረራ ስትወስድ ድጋፍ ማሳየታቸውና ከቪላድሚር ፑቲን ጋር የተለየ ቅርበት ማሳየታቸው በምርጫ ክርክር ወቅት ከፍተኛ ነጥብ እንዲጥሉ ሳያደርጋቸው አልቀረም፡፡ የምርጫው ውጤት ከተሰማ በኋላ የአውሮጳ አባል አገራት ከፍተኛ እፎይታ ተሰምቷቸዋል፡፡ ምክንያቱም ሌ ፔን ምርጫውን አሸንፈው ቢሆን ሁነኛ የኔቶ አባልና የአውሮጳ ኅብረት አባል ፈረንሳይ ከኅብረቶቹ ልትወጣ የምትችልበት አጋጣሚ ይኖር ስለነበረ ነው፡፡ ሌ ፔን የፑትንን ወረራ የመደገፍ አዝማሚያ ማሳየታቸው የአውሮጳ ኅብረት አባላትን አስቆጥቶ ነበር፡፡ የማክሮንን ድል ተከትሎ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የአውሮጳ ኅብረት ፕሬዝዳንት ቮን ደር ሌዮን እንዲሁም የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ ዘለንስኪ ከምርጫው ቀደም ብሎም ቢሆን ፈረንሳዊያዊን በፍጹም ለማሪን ሌ ፔን ድጋፍ እንዳያሳዩ፣ ይለቅ ለማክሮን ድምጽ እንዲሰጡ ተማጽነው ነበር፡፡ ይህም የሆነው ተቀናቃኛቸው ማሪን ሌ ፔን ከፑቲን ጋር ያላቸው ቅርበት ስጋት ስለፈጠረባቸው ነበር፡፡ የመራጮች ቁጥር በታሪክ ዝቅተኛ ከሚባሉት አንዱ ሆኖ የተመዘገበ የትናንቱ ድምጽ አሰጣት፣ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ መራጮች ባዶ ወረቀት ምርጫ ኮሮጆ ውስጥ ዶለዋል ተብሏል፡፡ ይህም የሚያመላክተው በርካታ መራጮች በሁለቱም እጩዎች ደስተኛ እንዳልነበረ ነው ይላሉ ተንታኞች፡፡ ማክሮን በ20 ዓመታት የፈረንሳይ የቅርብ ታሪክ ለ2ኛ ጊዜ የተመረጡ የመጀመርያው ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-61213148 +sports ታላቁ ሩጫ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ተራዘመ ህዳር 5/ 2014 ለ21ኛ ጊዜ ሊካሄድ የነበረው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከቀናት በፊት በታወጀው የአስቸኳያ ጊዜ አዋጅ ምክንያት መራዘሙን የውድድሩ አዘጋጅ አስታውቋል። 'ቶታልኢንርጂስ' የሚል ስያሜ የተሰጠው የ2014 ታላቁ ሩጫ መቼ እንደሚካሄድ አዘጋጁ ወደፊት እንደሚያሳውቅም በድህረ ገጹ ትናንት ማምሻውን አስታውቋል። ከ10 ቀናት በኋላ እንዲካሄድ ታቅዶ በነበረው ውድድር 25ሺ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ባለፈው ዓመት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከተለመደው ጊዜ ውጪ ጥር ላይ በተከናወነው ታላቁ ሩጫ 12 ሺህ 500 ተሳትፈው ነበር። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላለፉት 20 ዓመታት ሲካሄድ የቆየ እና በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት የስፖርት ፌስቲቫል ነው። በዓለም የአትሌቲክስ ውድድር የገዘፈ ስም ባለው አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ 1994 የተመሰረተው ታላቁ ሩጫ፤ እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ በድምሩ ወደ 600 ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎችን አስተናግዷል። የመጀመሪያው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ10 ሺህ ያነሱ ተሳታፊዎች የነበሩት ሲሆን ባለፉት ዓመታት ውድድሩ ከ40 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን አስተናግዶ ነበር። በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ውድድር፤ ከኢትዮጵያውን ባሻገር ከተለያዩ ዓለም ክፍሎች የሚመጡ የውጪ አገራት ዜጎ���ም የሚሳተፉበት ሆኗል። ታላቁ ሩጫ ለጤና ከሚደረገውና አስር ሺዎች ከሚሳተፉበት ሩጫ በተጨማሪም፣ ለአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት የሚያበርክትበት መደበኛ የውድድር ዘርፍም አለው። የዘንድሮ ታላቁ ሩጫ ሊካሄድ 11 ቀናት ሲቀሩት መራዘሙ የተገለጸው ባለፈው ማክሰኞ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በስሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ተከትሎ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሚቀጥሉት 6 ወራት ተፈጻሚ የሚሆን ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-59174005 +health ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስጅን እጥረት በምትታመሰው ዴልሂ ህይወት ምን ይመስላል? "የዴልሂ ሆስፒታሎች ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር የኦክስጂን እጥረት ያጋጥማቸው የጀመረው። ቀውሱ የመቀነስ ምልክት አላሳየም። ቅዳሜ ብቻ በአንድ ታዋቂ ሆስፒታል ኦክስጅንን በማለቁ ሐኪምን ጨምሮ ቢያንስ 12 ታካሚዎች ሞተዋል። ከሆስፒታሎች ውጭ አልጋ ማግኘት የማይችሉ የሕመምተኞች ቤተሰቦች ተንቀሳቃሽ ሲሊንደሮችን ለማግኘት እየታገሉ ነው። አንዳንድ ጊዜ ለ12 ሰዓታት ድረስ ወረፋ ለመጠበቅ ይገደዳሉ። የዴልሂ ትልልቅ ሆስፒታሎች በየቀኑ በሚታደል የኦክስጅን እደላ ነው እየሰሩ የሚገኙት። አንድ ዶክተር ሁኔታውን አስፈሪ እንደሆነ ገልጸዋል። ""ዋናውን ሲሊንደር አንዴ ከተጠቀሙ በኋላ የሚቀየርበት ምንም ነገር የለም"" ብለዋል፡፡ የማጠራቀሚያ ታንከሮች በሌላቸው እና በትላልቅ ሲሊንደሮች በሚሠሩ አነስተኛ ሆስፒታሎች ሁኔታው የከፋ ነው። እሁድ ዕለት በዴልሂ ብቻ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 412 ሰዎች መሞታቸውን ተዘግቧል። ሕንድ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ 400ሺህ በላይ አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን በማስመዝገብ የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። 'የዕለት ተዕለት ውጊያ ነው' የሽሪ ራም ሲንግ ሆስፒታልን አስተዳዳሪው ዶ/ር ጋውታም ሲንግ 16 የጽኑ ህሙማን እና 50 የኮቪድ ህሙማን አልጋዎች እንዳላቸው ገልጸዋል። የኦክስጅን አቅርቦት ዋስትና ስለሌላቸው ህሙማንን ለመቀበል ግን ፈቃደኛ አይደሉም። ሕይወት ለማትረፍ ኦክስጅን እንዲሰጣቸው በማሰብ ባለፉት ጥቂት ቀናት በርካታ የድረሱልን ጥሪዎችን አድርገዋል። ""በየዕለቱ የምናደርገው ውጊያ ነው። ግማሾቹ የሆስፒታል ሠራተኞች ከቦታ ወደ ቦታ በመሄድ ሲሊንደሮች ለመሙላት በየቀኑ ሲንገላቱ ይውላሉ።"" በሆስፒታሉ በኦክስጅን እጥረት የሚሞቱ ህመምተኞች ጉዳይ እንቅልፍ እንደሚነሳቸው ዶ/ር ሲንግ ይገልጻሉ። ""ታካሚዎቼን ስለማከም እንጂ ኦክስጅን ለማግኘት መንገላታት አልነበረብኝም"" ብለዋል። የሌሎች የሆስፒታሎችም እጣ ፈንታ ተመሳሳይ ነው። ቤተሰቧ ዴልሂ ውስጥ ሆስፒታል ያላቸው አንዲት ግለሰብም ቀውሱ ሲጀመር በባለስልጣናት መካከል ቅንጅት እንደሌለ ትናገራለች። ""በእነዚያ ጥቂት ቀናት ውስጥ የሚመለከተው አካል ማን እንደሆነ እና ጉዳዩን የሚፈታው ማን እንደሆነ አናውቅም ነበር"" ትላለች። ሁኔታው ""አሁን በመጠኑ ተሻሽሏል"" ትላለች። ይሁን እንጂ የኦክስጅን አቅርቦቱ ላይ እርግጠኛ መሆን ስለማይቻል ሆስፒታሎች ብዙ ታካሚዎችን የመቀበል አቅማቸው ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል። ""የኦክስጅን አልጋ አለሽ ወይ ብለው ሲጠይቁኝ የለኝም በማለት ስመለስ በጣም ይሰማኛል"" ትላለች። ኦክስጅን የሚያከፋፍለው የፌደራል መንግስት ነው። የደልሂ ዋና ሚኒስትር አርቪንድ ኬጅሪዋል ከተማዋ በቂ ኦክስጅንን እያገኘች አይደለም ሲሉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል። የፌዴራል ባለሥልጣናት ደግሞ የኦክስጅን እጥረት የለም የቸገረን የትራንስፖርቱ ጉዳይ ነው ይላሉ። 'ሰዎች ዋጋ እየከፈሉ ነው' በመሬት ላይ ያለው ሁኔታ ግን አሁንም አስከፊ ነው። ""በግዛቶች እና በፌዴራል መንግሥት መካከል በተፈጠረው የፖለቲካ ውዝግብ ሰዎች ዋጋ እየከፈሉ ነው። አንዳንድ ጊዜ ህይወታቸውን ነው የሚከፍሉት"" ብለዋል አንድ ተንታኝ። በኦክስጅን እጥረት ምክንያት አልጋ ያገኙ ቤተሰቦችም በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ናቸው። ያለፉት 48 ሰዓታቶች ለአልታፍ ሻምሲ አሰቃቂ የሚባሉ ናቸው። እሱ እና መላው ቤተሰቡ ባለፈው ሳምንት ተመርምረው ኮቪድ -19 አለባችሁ ተባሉ። ነፍሰ ጡር ሚስቱ በጠና ታማ ሆስፒታል ተወሰደች። አርብ ዕለት ሴት ልጅ ተገላገለች። በተወሳሰበ ወሊድ ምክንያት ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በመታመሟ ቬንትሌተር የተገጠመላት ሲሆን አሁን በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች። አልታፍ አባቱ በሌላ ሆስፒታል ህይወታቸው እንዳለፈ ተነገረው። በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ የሚገኙት ሚስቱ እና ሕጻኗ የሚገኙበት ሆስፒታል ኦክስጅን እያለቀ ነው ሲል አሳውቋቸዋል። ሆስፒታሉ ለአንድ ቀን የሚሆን ኦክስጅን ቢያገኝም አልታፍ ግን ዘላቂ መፍትሔ ባለመሆኑ እንደተጨነቀ ነው። ""ነገ ምን እንደሚፈጠር ማን ያውቃል?"" ይላል። ከኦክስጅን እጥረቱ በተጨማሪ ሆስፒታሉ በቂ የሰው ኃይል የለኝም በሚል ባለቤቱን ወደ ሌላ ተቋም እንዲያዛውር እየጠየቀው ነው። በዚህም ራሱ የባለቤቱን የኦክስጅን መጠን እና ትኩሳት ለመከታተል ተገደደ። ""እያሳለፍኩ ያለሁትን ስቃይ መገመት እንኳን አትችሉም"" ይላል። 'የአባቴ ኦክስጅን እያለቀ ነው' በዴልሂ በከባድ ሁኔታ ውስጥ ላሉት ታካሚዎች የሆስፒታል አልጋ ካላገኙ በቤታቸው ተንቀሳቃሽ የኦክስጂን ሲሊንደሮች መጠቀማው ብቸኛው መንገድ ነው። የአቢሼክ ሻርማ አባት የኦክስጅን መጠን ከቅዳሜ ጀምሮ እየወረደ ነው። ሲሊንደር ለመግዛት ወደ ገበያ በፍጥነት አቀና። ከደርዘን በላይ ሱቆችን ጎብኝቶ ለስድስት ሰዓታት ብቻ የሚቆይ ሲሊንደር አገኘ። በኋላ አንድ ትልቅ ሲሊንደር በ944 ዶላር ቢገዛም ባዶ ነበር። ሲሊንደሩን ለማስሞላት ወደ ብዙ መሙያ ጣቢያዎች ወስዶ አንዱ ብቻ ሊረዳው ፈቃደኛ የነበረ ቢሆንም ወረፋው በጣም ረጅም ነበር። ""በወረፋው በቆምኩበት እያንዳንዱ ደቂቃው አባቴ ኦክስጂን እያለቀ ነበር። ሁሉም ሰው በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ስለነበረ እንዲያስቀድሙኝ ማንንም መጠየቅ አልቻልኩም ነበር። ሲሊንደሩን ከስድስት ሰዓታት በኋላ አስሞላሁ። ነገም ደግሞ ደጋሚ መሰለፍ አለብኝ"" ይላል። የህዝብ ፖሊሲ እና የጤና ስርዓት ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ቻንድራካንት ላሃሪያ መንግስት ""ሊመጣ ስለሚችለው ቀውስ"" ሕዝቡን ቢያስጠነቅቅም ምንም እርምጃ አልተወሰደም ይላሉ። የአገሪቱ ፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ በህዳር ወር ስለ ኦክስጅን አቅርቦት እና ""በቂ ስላልሆነው የመንግሥት ሆስፒታል አልጋዎች ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር። እንደ ዶ/ር ላሃሪያ ከሆነ በሕንድ የተከሰተው የህክምና ኦክስጅን ቀውስ፤ የስርጭት እና የትራንስፖርት ኔትወርክን የማስተካከል ዕቅድ ባለመኖሩ ነው። 'የጦርነት ክፍል አዘጋጅተናል' በችግር ወቅት ዜጎች በችግር ውስጥ ያሉትን ለመርዳት ቅድሚያ ይሰጣሉ። ድጋፍ ከሰጡት ታዋቂ ሰዎች መካከል ማህበራዊ ጉዳይ ተሟጋች እና ፖለቲከኛው ተህሴን ፖናዋላ፣ ፖለቲከኛው ዲሊፕ ፓንዴይ፣ አክቲቪስት እና ፖለቲከኛ ስሪኒቫስ ቢ ቪ እና ተዋናይ ሶኑ ሶድ ይገኙበታል። ፖናዋላ መለስተኛ ሆስፒታሎች ኦክስጂን ሲያልቅባቸው ሲያግዙ ቆይተዋል። ""የቸገራቸውን ለመርዳት ከሚችሉ ጋር እያገናኘሁ ነው"" ብለዋል። ""አንድ ትንሽ ቡድን ከእኔ ጋር አብሮ የሚሰራበትን የውጊያ ክፍል አቋቁመናል። የማውቃቸውን ሰዎች ጋር ብቻ እየደወልኩ ነው። አንዳንዶቹ በሌሎች ግዛቶች ቢኖሩም ለመርዳት ዝግጁ ናቸው"" ይላሉ። ""በእያንዳንዱ ቀን ሁኔታው ይበልጥ አስከፊ እየሆነ ነው። እንደ እኔ ያሉ ሰዎች እያንዳንዱን ሰው ወይም የተቸገረን ሆስፒታል ለማገዝ የሚረዳ ሃብት ስለሌላቸው መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ኃላፊነቱን መውሰድ አለበት"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56968683 +sports ኔይማር በማጭበርበር ተከሶ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው ታዋቂው ብራዚላዊ እግር ኳስ ተጫዋች ኔይማር ጁኒየር በዝውውሩ ወቅት ተፈጽመዋል ከተባሉ ሕገ ወጥ ድርጊቶች ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ተከሶ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው። አሁን ለፈረንሳዩ ፓሪ ሴን ዠርመን (ፒኤስጂ) የሚጫወተው ኔይማር፤ ለዓመታት በዘለቀ የፍርድ ቤት ጉዳይ በማጭበርበር እና በሙስና ክስ ቀርቦበታል። የኔይማር ጉዳይ በፍርድ ቤት የሚታየው ለሁለት ሳምንታት በመጪው ጥቅምት ወር የዓለም ዋንጫ ውድድር ኳታር ውስጥ መካሄድ ከመጀመሩ በፊት ነው። ከኔይማር በተጨማሪ ሌሎች ታዋቂ ሰዎችም ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል። ሁለት የቀድሞዎቹ የባርሴሎና እግር ኳስ ቡድን ፕሬዝዳንቶች ጆሴፍ ማሪያ ባርቶሙ እና ሳንድሮ ሮሴል እንዲሁም የኔይማር ወላጆች በተመሳሳይ ክስ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የስፔን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። በዚህ ክስ ውስጥ ስማቸው የተነሳው ግለሰቦች በሙሉ የቀረበባቸውን ውንጀላ አስተባብለዋል። ክሱን ያቀረበው ተቋም ኔይማር ከዓመታት በፊት ከብራዚሉ ሳንቶስ ክለብ ሲዘዋወር 40 በመቶ ገንዘብ ይገባኛል ብሏል። ኔይማር የተዘዋወረበት የገንዘብ መጠን እንዳይገለጽ በመደረጉ ከሳሽ ከዝውውሩ ሊያገኝ ከሚገባው ገንዘብ ያነሰ መቀበሉን ጠቅሷል። በጣም ከፍተኛ ነው የሚባለው የኔይማር የዝውውር ገንዘብ መጠን በሕጋዊ ውዝግብ የተከበበ እንደሆነ ይነገራል። ባርሴሎናን የተሰናበተው ኔይማር ከፍርድ ቤት ውጪ በሆነ ስምምነት በ222 ሚሊዮን ዩሮ ወደ ፒኤስጂ ነበር ያቀናው። ከዚህ ቀደም በነበረ የፍርድ ቤት ክርክር ባርሴሎና ኔይማርን ከሳንቶስ ባዘዋወረበት ሂደት ሕጋዊ ጉዳዮች ተጥሰዋል በሚል ባርሴሎና 5.5 ሚሊዮን ዩሮ እንዲከፍል ተፈርዶበት ነበር። https://www.bbc.com/amharic/articles/cg3255v7pe4o +sports የኮንጎ ተወላጁ የስቱትጋርት አጥቂ በሐሰተኛ ስም ሲጫወት ነበር ተባለ "የዓመቱ ምርጥ አዲስ ተጫዋች በሚል ሽልማት የተቀበለውና በጀርመን ቡንደስሊጋ የሚሳተፈው የስቱትጋርት እግር ኳስ ክለብ ተጨዋች የሆነው ሲላስ ዋማንጊቱኪያስ በሐሰት መዝገብ ሲንቀሳቀስ ነበር ተባለ። የዴሞክራቲክ ኮንጎ ተወላጁ ሲላስ ዋማንጊቱኪያስ ትክክለኛ ስሙ ሲላስ ካቶምፓ ምቩምፓ ሲሆን የተወለደው ደግሞ በአውሮፓውያኑ ጥቅምት ወር 1998 ነበር። ይህ መረጃ ደግሞ እሱ ከተናገረውና መረጃ ካቀረበበት ጋር ሲነጻጸር በአንድ ዓመት እድሜውን ከፍ ያደርገዋል። ተጫዋቹ እንደሚለው ከሆነ እድሜውን ቀንሶ እንዲናገር ከፍተኛ ጫና ያደረሰበት የቀድሞ ወኪሉ ነበር። በዚህም ምክንያት 'በከፍተኛ ፍርሀት' ውስጥ እንደቆየ ተናግሯል። ስቱትጋርት እግር ኳስ ክለብ ደግሞ ጉዳዩን ካረጋገጠ በኋላ ከቡንደስሊጋ እና የጀርማን እግር ኳስ ማሕበር ጋር ንግግር ማድረግ ጀምሯል። ክለቡም ከ22 ዓመቱ ወጣት ተጨዋች እና አዲሱ ወኪሉ ጋር ንግግር እያደረገ እንደሆነና ጉዳዩን በጥልቀት እየመረመረው እንደሆነ አስታውቋል። ክለቡ ጨምሮም ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ይፋዊ መረጃዎችን ከጥቂት ቀናት በፊት ማግኘቱን ገልጿል። ሲላስ ዋማንጊቱኪያስ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በጀርመን ቡንደስሊጋ 13 ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ክለቡ ስቱትጋርትም ዘጠነኛ ሆኖ ማጠናቀቅ እንዲችል ረድቷል። በአውሮፓውያኑ 2017 ለቤልጂየሙ አንደርሌክትም ተጫውቶ የነበረ ሲሆን በቀድሞ ወኪሉ ገፋፊነት ደግሞ በፈረንሳይ ሁለተኛ ሊግ ወደ���ጫወተው ፓሪስ እግር ኳስ ክለብ ተዘዋውሯል። 2019 ላይ ደግሞ ስቱትጋርትን በመቀላቀል ቡድኑ ወደ ጀርመን ቡንደስሊጋ እንዲያድግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ""ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኮንጎ ለሚገኙት ቤተሰቦቼ ጭምር እሰጋ ነበር"" ብሏል ተጨዋቹ። ""የግል ታሪኬን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ መወሰን በጣም ከባድ ነገር ነበር። ነገር ግን ስቱትጋርት እግር ኳስ ክለብ እንደ ቤቴ የምቆጥረውና የማምነው ክለብ በመሆኑ ድፍረቱን አግኝቻለሁ"" ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57401439 +politics ሕዝቡ የማይመርጥበት የሶማሊያው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ "የሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ጎዳናዎች እሁድ በሚካሄደው ምርጫ በሚወዳደሩት ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ትላልቅ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ተንቆጥቁጣለች። በመኪኖች በተጨናነቀው የትራፊክ እንቅስቃሴም አላፊው አግዳሚው ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው ምርጫ ከመድረሱ በፊት የተሰቀሉትን ፖስተሮችን ይቃኛሉ። ነገር ግን ሕዝቡ አይመርጥም። ሕዝብ የማይመርጥበት ምርጫ እንዴት? ልትሉ ትችላላችሁ። ለዚህም ምክንያቱ ሶማሊያ ውስብስብ እና ቀጥተኛ ያልሆነ የፖለቲካ ሥርዓት ስለምትከተል እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ስለማይወዳደሩ ነው። ይልቁንም 275 አባላት ያሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሚመረጡት በክልል ባለሥልጣናት በተሰየሙ የጎሳ የአገር ሽማግሌዎችና የሲቪክ ማኅበራት አባላት ነው። በተጨማሪም የሶማሊያን አምስት ክልላዊ መንግሥታት የሚወክል 54 አባላት ያሉት ከፍተኛ ምክር ቤት (ሴኔት) አለ። ከዚያም የሁለቱም ምክር ቤቶች የፓርላማ አባላት 16.3 ሚሊዮን የሚሆነውን የሶማሊያን ሕዝብ የሚመራውን ፕሬዚዳንት ይመርጣሉ። ፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎቹ እነማን ናቸው? ሶማሊያ ለረጅም ጊዜ የተጓተተውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዛሬ እሁድ ግንቦት 07/2014 ዓ.ም. ታካሂዳለች። ይህም መጀመሪያ ሊደረግ ከታቀደው ከአንድ ዓመት በላይ ዘግይቶ ነው። በሥልጣን ላይ የሚገኙትን መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ወይም ፋርማጆን ጨምሮ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ለመወዳደር 39 ዕጩዎች ቀርበዋል። በአውሮፓውያኑ 1991 በሲያድ ባሬ የሚመራው የሶሻሊስት መንግሥት ከተገረሰሰ ወዲህ ከፍተኛው ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ቁጥር ነው ተብሏል። ከዕጩዎቹ መካከል ሁለቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች፣ ሻሪፍ ሼህ አህመድ እና ሐሰን ሼክ መሐሙድ እንዲሁም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሰን አሊ ኬሬ ይገኙበታል። ሌላኛዋ ዕጩ ፋውዚያ ዩሱፍ አደም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉ ሲሆን፣ ብቸኛዋ ሴት ዕጩ ተወዳዳሪ ናቸው። የወቅቱ የሶማሊያ ከፊል ራስ ገዝ የፑንትላንድ ክልል ፕሬዝዳንት ሰኢድ አብዱላሂ ዴኒም ውድድሩን ተቀላቅለዋል። የሚመረጠው ፕሬዚዳንት ለአራት ዓመታት የሚያገለግል ሲሆን እንደገና መመረጥም ይችላል። ይሁን እንጂ ቀጥተኛ ባልሆነ የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት በአውሮፓውያኑ 2000 ከተጀመረ ወዲህ አንድም የሶማሊያ ፕሬዝዳንት በድጋሚ አልተመረጠም። ለምን ተራ ዜጎች አይመርጡም? ይህ ሁኔታ በሶማሊያ ያለውን የጎሳ ኃይል የሚያሳይ ነው። የምዕራባውያን አይነት ዲሞክራሲ ባልሰፈነበት ማኅበረሰብም የጀርባ አጥንት ናቸው። በአውሮፓውያኑ 1991 በሶማሊያ የማዕከላዊ መንግሥት መውደቅን ተከትሎ አገሪቱ መንግሥት አልባ ሆና የቆየች ሲሆን ይህንንም ክፍተት የጎሳ መሪዎች ሞልተውታል። በሶማሊያ ጎሳዎች መካከል ከፍተኛ ፉክክር ስላለ ሥርዓቱ በሥልጣን ክፍፍል ቀመር ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ አራቱ ትላልቅ ጎሳዎች እኩል ቁጥር ያላቸው የፓርላማ መቀመጫዎችን ሲይዙ ቀሪዎቹ ጎሳዎች አንድ ላይ ተጣምረው ግማሹ የፓርላማ መቀመጫ ይሰጣቸዋል። ይህም ሁኔታ የሶማሊያ ጎሳ ተወካዮች በአገሪቱ አድራጊ ፈጣሪ እንዲሁም የአገሪቱን መሪ ወደ ሥልጣን የሚያመጡ ኃያላን ያደርጋቸዋል። የሁለቱን ምክር ቤቶች ምርጫ ተከትሎ ወደ 300 የሚጠጉ የፓርላማ አባላት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። ምርጫዎቹ መጠነ ሰፊ ሙስና፣ ሥልጣንን አላግባብ የተጠቀሙበት እና የምርጫ ሕግጋት ችላ የተባሉበት ነው ተብሏል። በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ልዑካንን ለመግዛት በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወጪ ተደርጓል ተብሎ ይታመናል። እንደ አለመታደል ሆኖ አገሪቱ ሙስናን የሚቆጣጠሩ ተቋማት የሏትም። ኳታር በሶማሊያ ፖለቲካ መድረክ ዋና ተዋናይ ነች። ተንታኞች እንደሚናገሩት በአውሮፓውያኑ 2017 የፕሬዚዳንት ፋርማጆ የምርጫ ዘመቻን ወቅት ኳታር በብቸኝነት ከፍተኛ ድጋፍ ያደረገች ሲሆን ከአስተዳሩም ጋር ጠበቅ ያለ ግንኙነት ነበራት። ለምን ይህን ያህል ጊዜ ዘገዬ? የፕሬዚዳንት ፋርማጆ የሥልጣን ወቅት በአውሮፓውያኑ የካቲት 2021 ቢጠናቀቅም በነበረው የፖለቲካ አለመግባባት በሥልጣን ላይ ቆይተዋል። ለፓርላማ አባላት የነበረው ምርጫ ዝግጅት አለመኖር ምርጫውን ያዘገየው ሲሆን እሳቸውም ሆነ ሕግ አውጪዎች የመምራት ሥልጣን ባይኖራቸውም እየመሩ እንዲቆዩ አድርጓቸዋል። የፓርላማ ምርጫው በመጨረሻ የተካሄደው በምዕራባውያን ለጋሾች ግፊት ነው። አሜሪካ የምርጫውን ሂደት እያዘገዩ ነው ያለቻቸውን ባለሥልጣናት ቪዛ አግዳለች ። ምርጫው ከታኅሣሥ እስከ መጋቢት ድረስ አራት ወራትን አስቆጥሯል። በግንቦት ወር አጋማሽ ምርጫው ካልተጠናቀቀ ለሶማሊያ የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ሊያቆም እንደሚችል ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) አስታውቋል። አዲሱ መንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ድርቅን ጨምሮ የሶማሊያን ተግዳሮቶች መፍታት ይኖርበታል። ድርቁ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የተባባሰ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የረድዔት ድርጅቶች ረሃብ ሊከሰት እንደሚችል እያስጠነቀቁ ነው። በአሁኑ ወቅት ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን 1.4 ሚሊዮን ህጻናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል። ምዕራባውያን በሶማሊያ ያላቸው ፍላጎት ምንድን ነው? ምዕራባውያን ዋናው ጭንቀታቸው የታጣቂ እስላማዊ ቡድን እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ማንሰራራት ነው። ሶማሊያ የአል-ሸባብ ማዕከል ስትሆን የአልቃይዳ አጋር የሆነው አልሸባብ በአፍሪካ ውስጥ በጣም አደገኛ ነው ተብሎ ይታሰባል። ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በአሜሪካ የሚደገፉ የኢትዮጵያ ወታደሮች የእስልምና ፍርድ ቤቶች ሕብረትን ከሥልጣን ለማውረድ ዋና ከተማይቱን ሞቃዲሾን ከወረሩ በኋላ የታጣቂ እስልምና እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ተንሰራፍቶ ይገኛል። የእስልምና ፍርድ ቤቶች ሕብረት መሸነፍ አልሸባብን እንዲጠናከር ረድቶታል፤ የአልሻባብ ታጣቂዎች ""ወራሪዎቹን"" ለማባረርም ቃል ገቡ። በአሁኑ ወቅት አልሸባብ በርካታ የሶማሊያ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ የሚገኝ ሲሆን መንግሥትን ለመጣል እና እስላማዊ አገዛዝ ለመመስረት በማለም ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ይፈጽማል። በአውሮፓውያኑ 2012 እና 2016 ምርጫ አልሸባብ የጎሳ ሽማግሌዎችን ከእስልምና እምነት ውጪ በሆነው ምርጫ ተሳትፈዋል በሚል ካወገዛቸው በኋላ የዛተባቸው ሲሆን አልፎ ተርፎም የታገቱም ነበሩ። በአሁኑ ምርጫ የአልሸባብ ድምጽ ያልተሰማ ሲሆን ምክንያቱ አባላቱ ወይም ደጋፊዎቹ በድብቅ የፓርላማ መቀመጫ ፈልገው ከውስጥ ሆነው ሥርዓቱን ለመናድ ሊገቡ ስለሚችል ስጋት እንዳይፈጠር በሚል ነው። ይህንንም ጉዳይ የጎረቤት አገር ጂቡቲ ፕሬዝዳንት ኦማር ጉሌህ ስጋታቸውን በይፋ ገልጸዋል ""አልሸባብ በተዘዋዋሪ የሚቆጣጠረው ፓርላማ እንዳይኖር እሰጋለሁ፤ ምክን���ቱም የአንዳንድ የፓርላማ አባላትን ድጋፍ ሊገዙ ይችላሉ"" ብለዋል። አንዳንድ ተንታኞች ፕሬዚዳንት ጉሌህ አልሸባብ ፓርላማውን በተዘዋዋሪ ይቆጣጠረዋል ማለታቸው የተጋነነ ነው ያሉ ሲሆን፣ ነገር ግን በሶማሊያ ውስጥ ትልቅ የፖለቲካ ኃይል ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ሶማሊያ ዲሞክራሲያዊ አገር ልትሆን ትችላለች? በሶማሊያ የፖለቲካ ሥልጣን ክፍፍል ሂደት ውስጥ ተጽእኖ ያላቸው ወገኖች በዚህ ዓመት ሕዝብ የሚመርጥበት ሥርዓት በዘንድሮው ምርጫ እንደሚዘረጉ ከረጅም ጊዜ በፊት ተስማምተው የነበረ ቢሆንም ቃላቸውን ሳይፈጽሙ ቀርተዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና አዲስ ሕገ መንግሥት በሕዝበ ውሳኔ ማጽደቅን ጨምሮ ለዚህ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና መስፈርቶች ባለሟሟላታቸው ይህ የሚያስደንቅ አልነበረም። በርካታ ግዙፍ ፈተናዎች የሚገጥሙት የቀጣዩ መንግሥት ቀዳሚ ጉዳይ ምን ያህል እንደሚሆን ግልጽ አይደለም።" https://www.bbc.com/amharic/news-61441549 +sports በኮሮናቫይረስ ስጋት ካናዳ እራሷን ከጃፓኑ የኦሊምፒክ ውድድር አገለለች "በዚህ ዓመት ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው የጃፓን ኦሊምፒክ ካናዳ እራሷን አገለለች። የጨዋታው ዋነኛ ተሳታፊ ከሚባሉት መካከል የሆነችው ካናዳ እራሷን በማግለሏ በውድድሩ መካሄድ ላይ ተጨማሪ ጥርጣሬ ጥሏል። ካናዳ ይህንን ውሳኔዋን ያሳወቀችው የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦሊምፒክ ውድድሩ ለሌላ ጊዜ ሊተላለፍ ይችላል በማለት ከተናገሩ በኋላ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውስትራሊያ የኦሊምፒክ ቡድን እንዳለው አሁን ባለው ሁኔታ ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ እንደማይካሄድ ""ግልጽ እየሆነ በመምጣቱ"" ተሳታፊ አትሌቶች ለቀጣዩ ዓመት እንዲዘጋጁ ተነግሯቸዋል። ጃፓን ለማስተናገድ ለዓመታት ስትዘጋጅለት የነበረው የ2020ው ኦሊምፒክ ውድድር ከአራት ወራት በኋላ በሐምሌ ወር ላይ ነበር የሚካሄደው። የካናዳ የኦሊምፒክና ፓራኦሊምፒክ ኮሚቴ ውሳኔውን በተመለከተ እንዳለው፤ ከውድድሩ ለመውጣት ""አስቸጋሪ"" ካለው ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ከአትሌቶች፣ ከስፖርት ቡድኖችና ከካናዳ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር መመካከሩን ገልጿል። ኮሚቴው ጨምሮም ለዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ለዓለም አቀፉ የፓራኦሊምፒክ ኮሚቴና የዓለም የጤና ድርጅት የኦሊምፒክ ውድድሩ በአንድ ዓመት እንዲዘገይ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። ""ውድድሩን ለሌላ ጊዜ በማሸጋገር ሂደት ውስጥ የሚያጋጥመውን ውስብስብ ሁኔታን ብንረዳውም፤ ምንም ነገር ከአትሌቶቻችንና ከዓለም ሕዝብ ጤናና ደኅንነት የሚበልጥ አይሆንም"" ብሏል የካናዳ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ላይ።" https://www.bbc.com/amharic/news-52000794 +politics የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ የሰላም ተደራዳሪዎች ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸው ተገለጸ "በሰሜን ኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት እየተፋለሙ ያሉት የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች ወኪሎች ዛሬ ጥቅምት 14፣ 2015 ዓ.ም ለሚጀመረው የሰላም ንግግር ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸው ተገለጸ። የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት፣ በአፍሪካ ኅብረት በሚመራው የሰላም ንግግር ላይ የሚሳተፈው የትግራይ ልዑክ ቡድን ደቡብ አፍሪካ ደርሷል ሲሉ ትናንት እሁድ ጥቅምት 13 ምሽት ላይ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል። በተመሳሳይ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ረፋድ ጥቅምት 14/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በሰላም ንግግሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል ብሏል። ሁለቱ ኃይሎች ልዩነቶቻቸውን በንግግር ለመፍታት በጠረጴዛ ዙሪያ የሚቀመጡት በትግራይ የሚካሄደው ጦርነት ተጠና��ሮ በቀጠለበት ወቅት ነው። ባለፉት ቀናት የፌደራሉ መንግሥት ጥምር ኃይሎች በርካታ ከተማዎችን እና የትግራይ አካባቢዎችን ከትግራይ ኃይሎች አስለቅቋል የሚሉ ዘገባዎች እየወጡ ነው። ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 14/2015 ዓ. ም. ጀምሮ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት በፌደራል መንግሥቱ እና በሕወሓት አመራሮች መካከል የሰላም ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። የአፍሪካ ኅብረት ተፋላሚ ኃይሎች ግጭት አቁመው ልዩነቶቻቸው በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች ሊደራደሩባቸው የሚችሏቸውን ጉዳዮች በይፋ ባይገልጹም፤ የአፍሪካ ኅብረት እና ምዕራባውያን ግን ለግጭቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ፕሮፌሰር ክንደያ፣ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በሚደረገው ውይይት የትግራይ ኃይሎች የሚያነሷቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች ግጭት በአስቸኳይ ማስቆም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ እና የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ማስወጣት የሚሉት መሆናቸውን አስታውቀዋል። የፌደራል መንግሥት ግን ከዚህ ቀደም ""ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ"" ለንግግር ዝግጁ መሆኑን ሲገልጽ ቆይቷል። ዛሬ በደቡብ አፍሪካ የሚጀመረው የሰላም ንግግር ለሁሉም ዜጎች መረጋጋትን የሚመልስ ነው ስትል አሜሪካ ያላትን ተስፋ ገልጻለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ጥቅምት 11፣ 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የሰላም ውይይቱን አሜሪካ እንደምትደግፍ ገልጾ፤ ድርድሩ በኢትዮጵያ ያለውን ውጊያ ይገታል ሲል ያለውን ተስፋ ጨምሮ ገልጿል። “ደቡብ አፍሪካ ይህንን ውይይት ለማስተናገድ በመፍቀዷ እናመሰግናለን። የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ልዑክ ኦሉሴጎን ኦባሳንጆን እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት ፓናል አባል የሆኑትን ፑምዚሌ ማልምቦ ንግቹካ እና ኡሁሩ ኬንያታ የሰላም ስምምነት ላይ እንዲደረስ የሚያደርጉትን ጥረት እንደግፋለን” ይላል መግለጫው። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ድረ ገጽ ላይ የወጣው መግለጫ “ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መስከረም ላይ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዳሉት፣ በአፍሪካ ኅብረት ፓናል አባላቱ አማካይነት የሚደረሰው የሰላም ስምምነት፣ በኢትዮጵያ ያለውን ውጊያ ይገታል። ለሁሉም ዜጎች መረጋጋትንም ይመልሳል” ሲልም አክሏል። የፌደራሉ መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር የሚነጋገሩ አባላት ከዚህ ቀደም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይህ ተደራዳሪ ቡድን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን የሚመራ ሲሆን ሰባት አባላትን ያካተተ ነው። ከአቶ ደመቀ በተጨማሪ የፌደራል መንግሥቱን የሚወክሉት የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)፣ ብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንት ጉዳዮች አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የመከላከያ ሠራዊት የመረጃ ደኅንነት ኃላፊ ሌ/ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ጌታቸው ጀምበር (ዶ/ር) እና በብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ማዕከል ዘርፍ ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት እየሰሩ የሚገኙት አምባሳደር ሐሰን አብዱልቃድር ናቸው። የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው ሁለት ተወካዮቻቸውን ለድርድር እንደሚልኩ ከዚህ ቀደም ገልጸው ነበር። የመጀመሪያው የህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የፓርቲው ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ የትግራይ ኃይሎችን ከሚመሩት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መካከል አንዱ የሆኑት ጀኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cgxv4qge5e2o +sports እውቁ የቴኒስ ተጫዎች ጆኮቪች ከአውስትራሊያ ተባረረ "የዓለማችን ቁጥር አንድ የሜዳ ቴኒስ ኮኮብ ኖቫክ ጆኮቪች በአውስትራሊያ ለመቆየት ባደረገው የመጨረሻ ፍርድ ቤት ክርክር ተረትቶ አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ። ክትባት ለመቀበል አሻፈረኝ ያለው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቹ፤ የአገሪቱ መንግሥት ""በጤና እና ባልተገባ ስነምግባር"" ምክንያት ቪዛውን መሰረዙን ተከትሎ ጆኮቪች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ቢወስደውም ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ውድቅ አርጎበታል። በውሳኔው ""በጣም ቅር ብሎኛል"" ያለው ጆኮቪች ውሳኔው ተቀበሎ ወደ ዱባይ አቅንቷል። አገሩ ሰርቢያ 'በአውስትራልያ ኦፕን' የቴኒስ ውድድር ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ያደረገችው ጥረትም ፍሬ አልባ ሆኗል። የጆኮቪች ደጋፊዎች ከውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታውን አንድ ቀን ቀደም ብሎ የተወሰነውን ውሳኔ ከችሎቱ ውጪ ሆነው በቁዘማ ተከታትለዋል። ከደጋፊዎቹ መካከል አንዷ በውድድሩ ላይ የዚህ ዝነኛ ተጫዎች አለመኖር የእረፍት ጊዜዋን ""ባዶ"" እንደሚያደርግባት ተናግራለች። የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ""ድንበሮቻችንን ለማጠናከር እና አውስትራሊያውያንን ለመጠበቅ የተደረገ ውሳኔ ነው"" ሲሉ ውሳኔውን በአውንታ መቀበላቸው ገልጸዋል። ሆኖም ጠቅላይ ሚንስትሩ እና አስተዳደራቸው የጆኮቪችን ጉዳያ የያዙበት መንገድ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ እያስተቻቸው ነው። የጆኮቪች ጉዳይ መነሻ የአውስትራሊያ ኢሚግሬሽን ሚኒስትር አሌክስ ሃውክ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ቪዛውን ከሰረዙ በኋላ ነው። ምክንያት ያሉት ደግሞ በአገሪቱ የፀረ-ክትባት እንቅስቃሴን ሊያስፋፋ የሚችል ስሜት አንጸባርቋል በሚል ነው። ትላንት እሁዱ በተደረገው የፍርድ ቤት ችሎት የጆኮቪች ጠበቃ ተጫዋቹን ቪዛ ለመቀማት በመንግስት የተሰጡት ማብራሪያዎች ምክንያታዊ አይደሉም ያሉ ሲሆን የቴኒስ ኮከቡን ከአገር ማባረር የፀረ-ክትባት እንቅስቃሴን ያባብሳል ሲሉ አስረድተዋል። ዕውቁ ጆኮቪች በመጀመሪያ በፈረንጆቹ ታህሳስ ወር አጋማሽ ላይ በኮቪድ መያዙ ተረጋግጦ ነበር። ሆኖም ከዛ በኋላ በአውስትራሊያ የቴኒስ አስተዳደር እና በቪክቶሪያ የግዛት አስተዳደር ወደ አውስትራሊያ መግባት እንዲችል ፍቃድ ተሰጥቶት ነበር። ሆኖም የአውስትራሊያ የድንበር ዘብ የፌደራል የኮሮናቫይረስ መስፈርቶችን አላሟላም በሚል በፈረንጆቹ ጥር መግቢያ ላይ ቪዛው ተሰርዟል። የጠቅላይ ሚኒስትር ሞሪሰን መንግሥት ""የአገሪቱን የግዛት አንድነት ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎች እና እርምጃዎችን ለመውሰድ ተዘጋጅቷል"" ብሏል። ሆንም የተቃዋሚው ሌበር ፓርቲ አመራር እና ሴናተር የሆኑት ክሪስቲና ኬኔሊ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጆኮቪች ጉዳይን በተሳሳተ መንገድ በመምራት እራሳቸውን ""በዓለም ፊት መሳቂያ"" አድርገዋል ሲሉ ተችተዋቸዋል።" https://www.bbc.com/amharic/60020796 +sports ለቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ዝግጅት ምን ይመስላል? ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ከአትሌቲክሱ በተጨማሪ በውሃ ዋና፣ በብስክሌት ውድድር እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በቴኳንዶ ውድድር ትወከላለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 35 አትሌቶችን ይዞ ወደ ቶኪዮ የሚያመራ ሲሆን አትሌቶች በ7 የተለያዩ ርቀቶች ተወዳዳሪ ሆነው ይቀርባሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-57913705 +sports “ኢትዮጵያውያን በኳታሮች ዘንድ ይከበራሉ” - የዓለም ዋንጫ ዶሃ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዐይን "ግሩም ሰይፉ ጋዜጠኛ ነው። አዲስ አድማስ ለተሰኘው ጋዜጣ ስፖርታዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን በመፃፍ ይታወቃል። ግሩም የኳታር የዓለም ዋንጫ ዝግጅትን ለመታደም ወደ ዶሃ ያቀናው ከመክፈቻው ጥቂት ቀናት ቀድሞ ነው። ዶሃ ከአዲስ አበባ 2200 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ትገናለች። የኢትዮጵያ አየር መንገደ እና ኳታር ኤርዌይስ በየቀኑ መንገደኞችን ያመላልሳሉ። ግሩም፤ ነፋሻማዋን አዲስ አበባ ለቆ ወደ ዶሃ ሲያመራ የጠበቀው የግንቦት ሃሩር ነው። ነገር ግን ይህ ወቅት ለኳታሮች ቀዝቃዛው ወር ነው። “ዶሃ የቀትር ፀሐይ የሚባል የለም” ይላል። ምክንያቱም ቀኑን ሙሉ የዶሃን አሸዋማ መሬት የሚቀጠቅጠው ፀሐይ ሃሩር ነው። ኳታር፤ በሜትሬዎሎጂ ዘገባ አገላለፅ “በአብዛኛው ፀሐያማ” ናት። በአብዛኛው ከማለት ከንጋት እስከ ምሽት ማለት ሳይቀል አይቀርም። አሁን ባለው የአገሪቱ የአየር ሁኔታ ዝቅተኛው የሚባለው 23 ድግሪ ሴንትግሪድ የሚጀምረው ለሊት 10 ሰዓት ገደማ ነው። ዎርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው የተሰኘው ድረ-ገፅ የኳታር ሕዝብ ብዛት በዚህ ዓመት 2.7 ሚሊዮን ይገመታል ይላል። ከእነዚህ መካከል ካታሪ የሚባሉት አረቦች 15 በመቶውን ይይዛሉ። ሕንዳዊያን፣ ፊሊፒናውያን እንዲሁም ሌሎች የእስያ አገራት ዜጎች ኑሯቸውን በኳታር ይኖራሉ። ከዚህ ባሻገር በርካታ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እና ኬንያዊያን በዋና ከተማዋ ዶሃ እንዲሁም በአር ራያን ይገኛሉ። በነዳጅ ሃብት የበለፀገችው ኳታር እነሆ በአረቡ የዓለም ሲዘጋጅ የመጀመሪያው የሆነውን የዓለም ዋንጫ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች። ግሩም፤ ካሜሩን ከሰርቢያ የሚያደርጉትን የቀን 7 ሰዓት የምድብ ጨዋታ ታድሞ ለመዘገብ እየተጓዘ ሳለ ነው በስልክ ያገኘነው። በየገባህበት ሥፍራ ሁሉ የአየር ማጤዣ ተገጥሟል የሚለው ግሩም፣ ይህ ቴክኖሎጂ ባይኖር ኳታር ለኑሮ ከባድ ትሆን እንደነበር ያምናል። “አሁን ለምሳሌ በአገሩ ሰዓት አቆጣጠር 5 ሰዓት ከምናምን ነው። እኛ አገር ግንቦት ወር ላይ ያለው የሚያማርረው ሙቀት ነው አሁን እዚህ ያለው።” ግሩም የኳታር ነዋሪዎችን ስለአየር ሁኔታው ሲጠይቃቸው “በብርድ ወቅት መጣህ” በሚል ዓይን እያዩት “ኧረ እንዲያውም ይሄ እኮ ቀዝቃዛው ጊዜ ነው” ይሉታል። ኳታር፤ ለዚህ ነው ይህንን ወቅት ለዓለም ዋንጫ የመረጠችው እንጂ ለወትሮው የዓለም ዋንጫ በሰኔ ነበር  የሚዘጋጀው። ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ የሚነሳው ነፋስ የኳታር ምሽትን ቀዝቀዝ አድርጎታል። ኳታር፤ ይህን የዓለም ዋንጫ ስታዘጋጅ ከምዕራቡ ዓለም ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባት ነበር። አገሪቱ የሰብዓዊ መብት አይከበርባትም፣ ስታድየሞቹ ሲታነፁ በርካታ የጉልበት ሠራተኞች ሞተዋል፣ የአየር ሁኔታው ምቹ አይደለም. . . ብቻ ብዙ ነቀፋ አስተናግዳለች። ነገር ግን ጋዜጠኛ ግሩም ይህ ነቀፋ ተጋኗል የሚል እምነት አለው። “የኳታር ዜጎች በጣም ሰላምተኞች ናቸው። እንግዳ ተቀባይነታቸውን ማየት ችያለሁ። በአረቡ ዓለም መዘጋጀቱ የአረቡ የዓለም ለእግር ኳስ ያለውን ፍቅር ለማሳየት ልዩ አጋጣሚ ነው” ይላል። እንደሱ አመለካከት ዶሃ ወደፊት ልክ እንደ ዱባይ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚመጡ ጎብኚዎች የምታስናግድ መናኸሪያ እንደምትሆን አምነት አለው። ግሩም፤ በዶሃ በተዘዋወረባቸው ቦታዎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ኑሮን ለማሸነፍ በተለያየ ሥራ ተሠማርተው ሲተጉ አይቷል። “ስታድየሞች ውስጥ በጎ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን አግኝቻለሁ። አንድ የሥነ-ጥበብ ባለሙያ ኢትዮጵያዊም ተዋውቄያለሁ። በዓለም ዋንጫው ከትላልቅ የብሮድካስት ኩባንያዎች ጋር የሚሠራ ኢትዮጵያዊም ማግኘት ችያለሁ።” ጋዜጠኛው ባለኝ መረጃ መሠረት ከ20 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ኳታር ውስጥ ይኖራሉ ይላል። ስለአገሪቱ የተለያዩ መረጃዎችን የሚያወጣው ‘ኦንላይን ካታር’ የተሰኘው ገፅ ቢያንስ 25 ሺህ ኢትዮጵያዊያን እንደሚገኙ አስፍሯል። “በቤት ሠራተኝነት የሚሠሩ አሉ። የሚማሩ አሉ። የሕንፃ ግንባታ ባለሙያዎች፤ የታክሲ ሾፌሮች አሉ። በርካታ የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች ያሉበት አንድ አካባቢ አለ። አዲስ አበባ የሚል ስ���ሜ ያለው ፀጉር ቤት አይቻለሁ። እኔ ከጎበኘኋቸው ሬስቶራንቶች በአንዱ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ተሰባስበው አይቻለሁ።” ግሩም፤ “ኢትዮጵያውያን በኳታሮች ዘንድ ይከበራሉ። “የሥራ ሰዎች ናቸው ይባላሉ” ይላል። ጋዜጠኛ ግሩም ከዚህ ቀደም ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ሩሲያ ተጉዞ የዓለም ዋንጫን መታደም ችሏል። ነገር ግን የዶሃው በብዙ መልኩ እንደሚለይ ይገልጻል። አንደኛው ምክንያት ስታድየሞቹ የተቀራረቡ በመሆናቸው እሱና የሙያ አጋሮቹ በአንድ ቀን የተለያዩ ጨዋታዎችን መታደም መቻላቸው ነው። ለምሳሌ በሩሲያው የዓለም ዋንጫ ከዋና ከተማዋ ሞስኮው ወደ ሶቺ ለመሄድ 72 ሰዓታትን በባቡር ተጉዞ ነበር። አልፎም ከዚህ በፊት ከተመለከታቸው የዓለም ዋንጫዎች በተለየ በምድብ ጨዋታዎች የታየው ፉክክር፣ ተመልካቾች ብዛት፣ የስታድየሞቹ ልዩ ‘ዲዛይን’ ይህንን የዓለም ዋንጫ “ለየት አድርጎብኛል” ባይ ነው። መስከረም ዘውዴ በኳታር ከ15 ዓመታት በላይ ኖራለች። ዋና ከተማዋ ዶሃን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተዘዋውራ ሠርታለች። አሁን ዶሃ ውስጥ አቢሲኒያ-ቢሾፍቱ የተሰኘ የቤተሰብ ሬስቶራንት ታስዳድራለች። የመስከረም ሬስቶራንት ከሰሞኑ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት በሚመጡ ተጠቃሚዎች መሞላቱን “ዕድሜ ለዓለም ዋንጫ” በሚመስል አንድምታ ትናገራለች። በርካታ ኢትዮጵያውያን እንግዶች፣ ኤርትራውያን፣ ሱዳናውያንን ጨምሮ የበርካታ አገራት ዜጎች ምግብ ቤቷን እንደሚጎበኙ ጠቅሳለች። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች የሌሎች አገራት ዜጎች ጓደኞቻቸውን ይዘው መጥተው የአገራቸውን ገበታ ሲቋደሱ ስታይ ደስ ይላታል። መስከረም ለአራት ዓመታት ያክል ያስተዳደረችው አቢሲኒያ-ቢሾፍቱ ሬስቶራንት፣ ዶሃ ውስጥ ኔአዘር የተሰኘ አካባቢ ይገኛል። ይህ መንደር በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበት ነው። መስከረም የዓለም ዋንጫ መጣ ሲባል ምናልባት አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከመጠን በላይ መጨናነቅ ይኖራል የሚል ፍራቻ ነበራት። ነገር ግን ይህ በየአራት ዓመት የሚዘጋጅ ውድድር ደስታን ይዞላት ብቅ ብሏል። “ሰዉ በጣም ደስተኛ ነው። በነፃነት ነው የሚንቀሳቀሰው። ከዚህ በፊት ከምናውቀው የተለየ ነገር እያየን ነው። ሁሉም ሰው በሥነ-ሥርዓት ይስተናገዳል። ስሜቱም ለየት ይላል።” አቢሲኒያ-ቢሾፍቱ ሬስቶራንት የ32 አገራት ባንዲራዎች ይውለበለቡበታል። በዓለም ዋንጫ እየተሳተፉ ያሉ 32 አገራትን የሚወክል ነው። ሬስቶራንቱ ካለበት ቦታ ራቅ ብሎ ያለው ድባብ ልዩ እንደሆነ የምትናገረው መስከረም፣ እግር ኳስ እንዲህ ሰውን ሲያቀራርብ ማየቷ አስደንቋታል። “በቃ ኳስ ማለት ይሄ ነው። እግር ኳስ የዓለም ሰዎችን የሚያቀራርብ እንደሆነ ነው የገባኝ። በግሌ የተረዳሁት ይህንን ነው። በጣም ነው ደስ የሚለው። በጣም!” መስከረም፤ ሬስቶራንቱ ከሰሞኑ በደንበኞች በመጨናነቁ እንጂ በስታድየሞች ዙሪያ የኢትዮጵያ ገበታ ለተጠቃሚዎች አስባ ነበር። ለወትሮው ሙቀቷ ነፍስን የሚያስጨንቀው ኳታር ከሰሞኑ ቀዝቀዝ ማለቷ ለመስከረም አስደንቋታል። እንጂ የዶሃ ሙቀት የሚቋቋሙት አይደለም ትላለች። ለበርካታ ዓመታት በባሕረ ሰላጤዋ አገር የኖረችው መስከረም ኳታር ወግ አጥባቂ የአረብ አገር እንደመሆኗ እግር ኳስ ለመታደም የሚመጡ ሰዎች እንደልባቸው ላይዝናኑ ይችላሉ የሚል ስጋት ነበራት። ኳታር ስታዲዬሞች ውስጥ የአልኮል መጠጥ እንዳይሸጥ ከልክላለች። ነገር ግን በምሽት ክለቦች ሜክሲኮ እና የብራዚል ዜጎች ሲጨፍሩ ነው የከረሙት ትላለች መስከረም። ከሌሎች አገራት የሚመጡ ሰዎች የተለያየ ባሕርይ ይዘው ነው የሚመጡት። ነገር ግን አብዛኛዎቹ ጎብኚዎች ደስተኛ ሆነው በ���ፃነት ሲንቀሳቀሱ፣ ሲጫወቱ፣ ሲጨፍሩ ተመልክታለች። “አይቼው የማላውቀው ነው። በእውነት የተለየ ስሜት ፈጥሮብኛል።” ኢትዮጵያዊው አብዱልሃኪም አብዱልራህማን፤ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ መኖር ከጀመረ አምስት ዓመታት አልፎታል። አብዱልሃኪም፤ ከዓለም ዋንጫው በጎ ፈቃደኞች አንዱ ነው። ወጣቱ፤ ከዶሃ ግዙፍ ስታዲዮሞች አንዱ በሆነው ኻሊፋ ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። አብዱልሃኪም ዋነኛ ሥራው ጨዋታ ለመታደም ለሚመጡ ተመልካቾች አቅጣጫ መጠቆም፣ የሚያስፈልጋቸውን ነገር በመርዳት የበኩሉን ይወጣል። አልፎም በአገሪቱ ሕግ መሠረት የማይቻሉ ነገሮችን ጎብኚዎች ሲፈጽሙ ከተገኙ በማስረዳት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን ይወጣል። እያወቁ የሚያጠፉ ሰዎችን ደግሞ ለበላይ አካል ያሳውቃል። አብዱልሃኪም ይህን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት ከመጀመሩ በፊት የአጭር ጊዜ ሥልጠና ወስዷል። ወደ ስታዲዬም ጨዋታ ለመመልከት የሚመጡ ሁሉም ሰዎች ምግባረ-መልካም አይደሉም፣ የሚለው ወጣቱ አንዳንድ ጎብኚዎች በጎ ፈቃደኞችን እንደሚያንጓጥጡ ይናገራል። ""ኳታር ሁለተኛ አገሬ ናት"" የሚለው አብዱልሃኪም በዓለም ዋንጫው ብዙም ላልተሳካለት የኳታር ብሔራዊ ቡድን ድጋፉን ሲሰጥ ነበር። በምድብ አንድ ከኔዘርላንድስ፣ ከሴኔጋል እና ከኤኳዶር ጋር የተደለደለችው ኳታር ሦስቱንም ጨዋታዎች ተረትታ ተሰናብታለች። ቢሆንም አብዱልሃኪም እንደሚለው “ኳታር በብዙ ነገር አሸንፋለች።” “ከዓለም አገራት ብዙ መልክ እና ፍላጎት ያላቸው እንግዶችን ተቀብላ ማስተናገዷ እንደ አንድ ትልቅ ድል ነው የማየው።”" https://www.bbc.com/amharic/articles/cj59y335yj6o +politics """ጀዋር መሐመድ እናቱ ሊጠይቁት ሄደው ሊያውቃቸው አልቻለም"" ኦፌኮ" "የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) በረሀብ አድማ ላይ የሚገኙት እነ አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ አሐምዛ አዳነ እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጾ መንግሥት ""በአስቸኳይ ሕይወታቸውን አድኖ ግዴታውን ይወጣ"" ሲል መግለጫ አውጥቷል። ""ለሚጠፋው የዜጎቻችንና አባሎቻችን ሕይወት መንግሥት ኃላፊነቱን ይወስዳል"" በማለት ሕዝቡ እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድርም ፓርቲው አሳስቧል። የኦፌኮ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ የረሀብ አድማ ላይ የሚገኙት እስረኞች ""ታመዋል። ከዚያም በላይ ሰው መለየት አይችሉም። መቆም አይችሉም። ሕይወታቸው አስጊ ደረጃ ነው"" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፊርማ በማሰባሰብ፣ አቤቱታ በማሰማት፣ ሰልፍ በማድረግ ወይም መንግሥታቸው በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድር በማድረግ የእስረኞቹን ሕይወት እንዲያድን ጠይቀዋል። ያሳለፍነው ሰኞ፣ የካቲት 1/2013 ዓ.ም እስረኞቹን እንደጎበኟቸው የጠቀሱት አቶ ጥሩነህ፤ ""ምንም ቃል ማውጣት አይችሉም። የሕክምና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል"" ብለዋል። አያይዘውም አቶ ጀዋር መሐመድን ሊጠይቋቸው የሄዱ እናታቸውን መለየት እንዳልቻሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ""ሰኞ እለት አይቻቸዋለሁ። ቃል ማውጣት አይችሉም። መቆም አይችሉም። ጀዋር መሐመድን እናቱ ሊጠይቁት ሄደው ሊለያቸው አልቻለም። ጀዋር መሬት ይዞ እየዳኸ ነው ወደ እስር ክፍሉ የሄደው። አልቅሼ ነው የተለየሁት"" በማለት ሁኔታውን ገልጸዋል። አቶ ጥሩነህ ዐቃቤ ሕግ፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶችና ሌሎችም አካላት እስር ቤት ሄደው እነ አቶ ጀዋርን እንዲያዩና መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድሩም ጠይቀዋል። ""በኢትዮጵያ ታሪክም ጥቁር ነጥብ መሆኑን በመገንዘብ ለመንግሥት ���ስፈላጊውን ማስጠንቀቂያ ምክርም መስጠት ይችላሉ"" ብለዋል። የኦፌኮ አባላት በጅማ፣ በምዕራብ አርሲ ዞን፣ በምዕራብ ወለጋ፣ በምሥራቅ ወለጋ እና በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እንደሚታሰሩ፣ ታስረውም ፍርድ ቤት ያልቀረቡ እንዲሁም እንግልት የደረሰባቸው እንዳሉ ተናግረዋል። ""ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ አባሎቻችንና ሌላው ሕዝብም መታሰሩ ያሳስበናል። ነገሮች ካልተሻሻሉ በሚደርስብን ጫና፣በግድያና በማስፈራሪያው ሳቢያ ኦፌኮ ሊዳረከም ሊፈርስም ይችላል"" ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። እነ አቶ ጀዋር በረሃብ አድማ ላይ ለረዥም ቀናት በመቆየታቸው የተነሳ የጤና ችግር እየተስተዋለባቸው መሆኑን የጤና ክትትል ከሚያደርጉላቸው ሐኪሞች መካከል አንዷ የሆኑት ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ለቢቢሲ መግለጻቸው አይዘነጋም። የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚሄዱ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ እንደሆነና ከ15 ቀናት በላይ እንዳለፋቸው ቢቢሲ ከጠበቆቻቸው ለመረዳት ችሏል። እነ አቶ ጃዋር እና አቶ በቀለን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች መካከል ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ ቤት ጥር ወር ላይ መወሰኑ ይታወሳል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ፣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ፣ የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ የመተላለፍ ክሶች ከተመሰረቱባቸው ክሶች መካከል ሲሆኑ፤ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሣሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 የተያያዙ ሲሆኑ በወቅቱ ውሳኔ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 የተያያዙ መሆናቸውም የሚታወስ ነው። የቀሩት አራት ክሶች ""በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 240 በመተላለፍ ብሔርን እና ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ አንዱ ወገን በሌላው ወገን ላይ እንዲነሳሳ በማድረግ""፣ የፀረ ሽብር አዋጅ 1176/2012 እና የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅን 7061/2004 የሚመለከቱ ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/news-56041932 +business “የኑሮ ውድነቱ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልገዋል” "ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ ከተማ የሆነውና መካከለኛ ገቢ ካለቸው ሰዎች ሊመደብ የሚችለው ግለሰብ በተለይ የኮቪድ-19 ወረረሽኝ ስጋትን ከመጣበት ከወርሃ ሚያዚያ አንስቶ የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ መጨመር ህይወቱ ላይ የሚጨበጥ ተፅዕኖ ማምጣቱን ለቢቢሲ ይገልፃል። ""ሃገር ውስጥ የሚመረቱ እንደ ሽንኩርት፣ ጤፍ፣ ቲማቲም የመሳሰሉት ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል፤ ከዚያ ባሻገር ከውጭ የሚገቡ እንደ መዋቢያ ምርቶች፣ አልባሳት የመሳሰሉትም ከፍተኛ ጭማሪ ታይቷል"" የሚለው ይሄው ግለሰብ ምናልባትም ከዓለም አቀፍ ወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የንግድ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዛቸው፣ እንደ ወትሮውም በቀላሉ መጓጓዝ ባለመቻሉ የአቅርቦት እጥረት ማጋጠሙ ለዋጋ ጭማሪ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር ግምቱን ሰንዝሯል። ""ሽንኩርት በአስራዎቹ ብር ደረጃ ነበር የምንገዛው፥ አሁን ወደ አርባ ብር ደርሷል፤ ቲማቲምም እንደዚሁ ከፍ ብሏል፤ እንደዚሁ ሃያ ስምንት ብር ሃያ ዘጠኝ ብር [ገደማ] እየተሸጠ ነው ያለው በኪሎ"" የሚለው ይህ ሰው ከዚህም የተነሳ እርሱና በማኅበራዊ ከባቢው የሚያውቃቸው ሌሎች ሰዎች አጠቃቀማቸውን ለማስተካከል መገ���ዳቸውን ይናገራል። የፍቼ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ዘውዲቱ አሰፋም ከአዲስ አበባው ነዋሪ ጋር ተመሳሳይ ሃሳብ ነው ያላት። የኑሮ ውድነቱ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መሆኑን ለቢቢሲ ስትገልጽ፤ ""ለምሳሌ ሽንኩርት ከ45 እስከ 50 ብር እየተሸጠ ይገኛል። ሁሉም ነገር ጨምሯል። ጤፍ ከ4300 በላይ እየሆነ ነው። ዘይት ድሮ መንግሥት ያቀርብ ነበር፤ አሁን ግን አያቀርቡም፤ ስለዚህ ከነጋዴ እየገዛን ነው። ዋጋው ጨምሯል። የመንግሥት ሰራተኛ የሆነ፣ ደሞዙ አነስተኛ የሆነ፣ ቤተሰብ ያለው በጣም እየተቸገረ ነው።"" ብላለች። የኑሮ ውድነቱ መናር በአኗኗሩ ላይ ያመጣውን ለውጥ የሚገልፀው የአዲስ አበባ ነዋሪ "". . .በምንጠቀማቸው ምግቦች ውስጥ ቲማቲም የምናዘወትር ከሆነ እርሱን እንተዋለን ማለት ነው፤ ሽንኩርትም የምንገዛውን እየቀነስን ሄደናል""፤ ስለዚህ ""የምታገኘው ገቢና ለፍጆታዎችህ የምታወጣው ካልተመጣጠነልህ ፍጆታውን ወደ መቀነስ ብሎም ወደ ማቆም ነው የምንሄደው"" ብሏል። ይኼው ሰው የኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ እርግጥ የሆነበት ሰሞን በርካታ ሰዎች፣ የተለያዩ ምርቶችን በጅምላ ይሸምቱና ያከማቹ እንደነበር አስታውሶ፣ በወቅቱ አጋጣሚውን ለመጠቀም በፈለጉ አንዳንድ ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ይጠቅሳል።

""እኛ አገር የተለመደው ነገር ደግሞ ዋጋ አንድ ጊዜ ከፍ ካለ በኋላ ተመልሶ የመውረድ ዕድሉ በጣም አናሳ ስለሆነ"" በዚያው ከፍ ብሎ ቀርቷል ይላል። የአርባምንጭ ነዋሪ የሆኑ ሌላ ግለሰብ ለቢቢሲ ሲናገሩ ገበያው ""እሳት ነው"" ይላሉ። ዋጋውን ለማነጻጸር ሩቅ መሄድ አልፈለጉም፤ ""በቅርቡ እንኳ ቲማቲም እንገዛ የነበረው 20 ብር ነው አሁን ግን 30 ገብቷል"" ካሉ በኋላ ሽንኩርት ደግሞ 30 ብር መግባቱን፣ ድንች በኪሎ 15 ብር፣ ነጭ ሽንኩርት 150 መሆኑን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ነጋዴዎችም እንደ ከዚህ ቀደሙ ደፍረው የሚገዙ ደንበኞቻቸው እየቀነሱ መምጣታውን ለቢቢሰ ተናግረዋል። በላሊበላ የሚኖሩት ሌላው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ግለሰብ ኑሯቸው የተመሰረተው ከተማዋን ለመገብኘት በሚመጡ ቱሪስቶች ላይ እንደነበር ተናግረው አሁን ግን በኮቪድ-19 ምክንያት ጎብኚ በመጥፋቱ ኑሯቸው ፈተና ውስጥ መውደቁን ለቢቢሲ አልሸሸጉም። ከዚህ ቀደም 30 እና 40 ብር ይገዙት የነበረውን ሽንኩርት አሁን 120 ብር እንደሚሸጥም አስረጅ በመጥቀስ ተናግረዋል። ""ጤፍ ከ4000 ብር በላይ ገብቷል"" በማለትም ኑሮ ከእለት ወደ እልት እየከበደ መምጣቱን ለቢቢሲ በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆነው አስረድተዋል። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር ጉቱ ቲሶ በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሸቀጣሸቀጥ ዋጋ መጨመሩን ይገልፃሉ። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በኮቪድ-19 እና በተጓዳኝ ችግሮች ምክንያት ምርትና አቅርቦት ላይ መስተጓጎል በመፈጠሩ መሆኑን ያስረዳሉ። ምሁሩ አክለውም ከየካቲት ወር ጀምሮ ይህ መከሰቱን እና እስካሁን መቀጠሉን ይናገራሉ። ዶ/ር ጉቱ በተለይ ደግሞ የአለማቸችን የሸቀጣሸቀጥ እቃዎች ዋነኛ አቅራቢ ቻይና በኮሮናቫይረስ ክፉኛ መጎዳቷ ምርቶችን ማስተጓጎሉንና በዚህም የተነሳ የዋጋ ንረት መከሰቱን ገልፀዋል። ""አቅርቦት ሲቀንስ ዋጋ ይጨምራል"" የሚሉት ባለሙያው፤ በተፈጠረው የአቅርቦት እጥረት ገበያ ውስጥ ያለውን መቀራመት በመፈጠሩ የምርት ዋጋ መናሩን አብራርተዋል። ሌላኛው ምርቶችን ከውጪ አገራት ገዝቶ ለማምጣት የውጭ ምንዛሬ በማስፈለጉ እና በበቂ ሁናቴ የውጪ ምንዛሬ ማግኘት አለመቻል ለዋጋ ግሽበቱ መናር አንዱ አስተዋጽኦ እንደሆነ ያስረዳሉ። በኮሮናቫይረስ ምክንያት አምራቾች የግብአት እጥረት ስለሚገጥማቸው የዋጋ ንረት ይከሰታል የሚሉት ዶ/ር ጉቱ፣ አምራ���ች የማምረት ወጪያቸው ሲጨምር አብሮ የምርት ዋጋ ይጨምራል ይላሉ። አምራቹ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከትራንስፖርትና ከማምረት ጋር የተገናኘ የግብአት አቅርቦት እየተገታና እጥት እየተፈጠረ በመምጣቱ ለምርት እጥረቱ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልፀዋል። ""ግብአት አቅርቦት ቀነሰ ማለት፣ የግብአት ዋጋ ጨመረ ማለት ነው"" በማለትም ናገራሉ። የማምረቻ ዋጋ ሲጨምር፣ በተዘዋዋሪ አምራቹ ዋጋውን ወደ ሸማቹ እንደሚያዞር የሚያስረዱት ዶ/ር ጉቱ፤ ዋጋው ወደ ተጠቃሚ ሲዞር ምርቱ ላይ ጭማሪ ያሳያል ሲሉ ይተነትናሉ። ከእነዚህ በተጨማሪ የስርጭት መሰተጓጎል መኖሩን ባለሙያው ጨምረው አስድተዋል። ""በአንድ ቦታ የተመረተ ምርት በሚፈለግበት ወቅት ወደ ተለያየ የአገሪቱ ክፍል ማሰራጨት ሲያቅት፣ እጥረት ስለሚፈጠር ለተጨማሪ ወጪ ይዳረጋል፤ የዋጋ ጭማሪ ይከሰታል።"" በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የሰላምና መረጋጋት ጥያቄ ትልቅ ፈተና ውስጥ መውደቁን በማስታወስ፣ ይህ ሁሉ በምርት ሰንሰለት፣ በግብዓት አቅርቦት፣ በምርት ስርጭቶች ላይ ትልቅ መስተጓጎል መፍጠሩን ይናገራሉ። በሰላም እና መረጋጋት እጦቱ ፋብሪካዎች ምርታቸውን መቀነሳቸውን፣ ምርት ስርጭት ላይ የተሰማሩም መስተጓጎል ገጥሟቸዋል ሲሉ ይገልጻሉ። መኪናዎች ጭነት ጭነው መንገድ ላይ ከአንድ ቀን በላይ ተስተጓጉለው መቅረት፣ ለተጨማሪ ወጪ እና ኪሳራ ሲዳርጋቸው በተዘዋዋሪ ሸማቹ ላይ የምርቱ ዋጋ ከተገቢው በላይ ዋጋ እንዲጫን እንደሚያደርጉ ጨምረው ያስረዳሉ። እነዚህ ነገሮች በጥቅሉ ሲታዩ የሸቀጣ ሸቀጥ ዋጋ ላይ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም አገልግሎቶችና አቅርቦቶች ላይ የዋጋ ንረት እንደሚያሳዩ ዶ/ር ጉቱ ገልፀዋል። ለዋና ዋና ከተሞች የምግብ ፍጆታ ምርቶች የሚመጡት በከተሞቹ አቅራብያ ከሚገኙ የክልል ከተሞች መሆኑን በማስታወስ እነዚህ የግብርና ምርቶች ከየትኛውም ጊዜ ይልቅ የዋጋ ንረት ማሳየታቸውን ገልፀዋል። እነዚህ የፍጆታ እቃዎች አሳሳቢ በመባል ደረጃ ዋጋቸው እየጨመረ ነው የሚሉት ምሁሩ፣ ለዋጋ መናር ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሲያስረዱም እነዚህ የእለት ፍጆታ ምርቶች ( እንደ ጥራጥሬ ያሉት) ለገበያ የሚቀርቡት ባለፈው አመት የተመረቱ መሆናውን በመጥቀስ ነው። ባለው አመት በተለያየ የአገሪቱ ክፍል አካባቢዎቹ የነበሩበት ሁናቴ የነበረውን ሁኔታም በማስታወስ፣ ለማምረት፣ ለመሰብሰብ፣ ለማሰራጨት አስቸጋሪ በሆነ ሁናቴ ውስጥ ማሳለፋቸውን ይጠቅሳሉ። በዚህ የተነሳ የምርት ማሽቆልቆል ተከስቶ ዘንድሮ ለገበያ ሲደርስ የዋጋ መናር መፈጠሩን ያስረዳሉ። ባለፉት ወራት የተከሰተውንም በተመለከተ ሲያስረዱም፣ ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዳሴ ግድያ በኋላም ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ምርቶች ትልቅ መስተጓጎል እንደገጠማቸው ያብራራሉ። በተጨማሪም ነጋዴዎች ባለፈው አመት የገዙት ምርት እንኳ ቢሆን በእንዲህ አይነት ወቅት ዋጋ ከመጠን በላይ ጨምረው እንደሚሸጡ ሸማቾችም በገፍ ገዝው እንደሚያከማቹ ይህም ለዋጋ ንረቱ አስተዋጽኦ እንዳለው ይገልጻሉ። ወደ 80 በመቶ የሚጠጋው አትዮጵያዊ መደበኛ ባልሆነ ስራ ውስጥ ተሰማርቶ፣ ከእጅ ወደአፍ ገቢ እንደሚያገኝ የሚናገሩት ምሁሩ፤ በዚህም ለበርካታው ኢትዮጵያዊ ኑሮን ማክበዱን ይገልፃሉ። ገንዘብ ያለውም ቢሆን የፍጆታ እቃዎች ዋጋ በናረበት ቁጥር ያለውን ገቢው በአጠቃላይ ወደ ሚመገበው ነገር ለማዞር ይገደዳል ይላሉ። ይህም ቁጠባን፣ የወደፊት የማደግ ተስፋውንና ጥረቱን እንደሚያመክን ገልፀው፣ ይህ እንደ ግለሰብ ቢሆንም እንደ አገር ማህበረሳባዊ እድገትንም ፈተና ውስጥ እንደሚጥል ይገልፃሉ። እንደ ዶ/ር ጉቱ ከሆነ ለዋጋ ግሽበቱ መፍትሄ ለመስጠት ችግሩ ከምን መነጨ የሚለውን መለየት አስፈላጊ ነው። አንዳንድ ጊዜ ለምጣኔ ሃብት ችግር የምጣኔ ሃብት መልስ መስጠት ያስቸግራል የሚሉት ምሁሩ፣ የችግሩ መንስኤ ምጣኔ ሃብታዊ ሳይሆን ማህበራዊ አልያም ፖለቲካዊ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ የተከሰተን የዋጋ ንረት በፍጥነት በሽታውን በቁጥጥር ስር በማዋል፣ ህብረተሰቡ ወጥቶ ሰርቶ መግባት እንዲችል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ይናገራሉ። ለዚህ ደግሞ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉም አካላት ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። ይህን በፍጥነት መቆጣጠር ካልተቻለ የምጣኔ ሃብቱን ቀውስ እያባባሰው እንደሚሄድ ይናገራሉ። ሌላው በየዓመቱ ያለው የሰላም መደፍረስ ምክንያቱ ተጠንቶ እውነተኛ፣ አሳታፊ እና ግልጽ የሆነ ውይይት ተደርጎ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባ ይመክራሉ። በሶስተኛ ደረጃ እንደ ህዝብ ያሉትን ፖሊካዊ ብሶቶችና ጥያቄዎችን የምንገልፅበት መንገድን ቆም ብሎ መመልከት ተገቢ መሆኑን ይመክራሉ። ሁል ጊዜ የምጣኔ ሃብት ተቋማትን በማውደም፣ ምርትና ምርታማነትን በማስተጓጎል ብቻ ሳይሆን ሌሎች በተዘዋዋሪ ጫና መፍጠር የተፈለገው አካል ላይ ጫና መፍጠር የሚያስችሉ አማራጮችን መመልከትና መፈተሽ ተገቢ መሆኑን ያስታውሳሉ። ካልሆነ ግን አሁን የዋጋ ንረቱ እየሄድንበት ያለው ፍጥነትና መንገድ ከምጣኔ ሃብት አንፃር ሲታሰብ አገሪቷን መጥፎ ደረጃ ላይ እያደረሰ መሆኑን ለቢቢሲ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53657254 +politics በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ለለውጥ ጎዳና ላይ ወጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ፖለቲካዊ ለውጥን በመሻት በተለያዩ ከተሞች ጎዳናዎች ለተቃውሞ ወጥተዋል። ባለፈው አመት የሱዳኑን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣን መገርሰስ ተከትሎ ቃል የተገቡ ማሻሻያዎችና ለውጦች ምን ላይ እንደደረሱ ተቃዋሚዎች በመጠየቅ ላይ መሆናቸውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አስታውቀዋል። በመዲናዋ ኻርቱምን ጨምሮ በአጎራባች ከተሞችና ወደ ጦር ኃይሉ ዋና መቀመጫ የሚያመሩ ጎዳናዎች ላይ የፀጥታ ኃይሎች ተሰማርተዋል። ተቃዋሚዎችም የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ እንዲሁም በዘፈኖች፣ የመኪና ጥሩምባ በማሰማት ተቃውሟቸውን እየገለፁ ነው። በአሁኑ ሰዓት እየተደረጉ ያሉ ተቃውሞዎች ባለፈው አመት ከነበረው፣ ለወራት ከዘለቀውና የኦማር አልበሽርን ረዥም የስልጣን ዘመን ማብቂያ ከሆነው አብዮትም ጋር ይመሳሰላል ተብሏል። የኦማር አልበሽር ከስልጣን መውደቅ ተከትሎም የሲቪልና ወታደራዊ ጥምር መንግሥት ተመስርቷል። ነገር ግን እውነተኛ የሲቪል መንግሥት እንዲሁም ፖለቲካዊ ለውጦች ይመጣሉ ወይ ለሚለው በርካቶች ስጋት አጭሮባቸዋል። በትናንትናው ዕለት በተደረጉ ተቃውሞችም የተንሰራፋው ሙስና እንዲጠፋ፣ በአልበሽር አገዛዝ ወቅት የተገደሉ ሰዎች ፍትህ እንዲያገኙ እንዲሁም ቃል የተገባው ፓርላማ እንዲመሰረት የሚጠይቁ ነበሩ። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክም በበኩላቸው ቁልፍ የሚባሉ ማሻሻያዎችና ለውጦች በሃገሪቱ እንደሚካሄዱ ጠቅሰው በመጪዎቹ ቀናቶችም ይፋ ይሆናሉ ብለዋል። ሃገሪቱ በተፈጠረው የገበያ ግሽበት ምክንያት የምግብ እንዲሁም የነዳጅ ዋጋ መጨመር ጫናን ፈጥሮባታል። ከዚህም በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ቀጥ ማለትም ድቀትን እንዳይፈጥር ፍራቻን ደቅኗል። https://www.bbc.com/amharic/53243266 +politics ትግራይ፡ የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ በቂ እርዳታ ባይቀርብም የመንግሥት ጥረት የሚበረታታ ነው አለ "የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል በቂ የሰብዓ�� እርዳታ ባይቀርብም የኢትዮጵያ መንግሥት ጥረት ግን የሚበረታታ ነው አለ። ምክር ቤቱ ኢትዮጵያን በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጣው መግለጫ፤ በክልሉ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አሳስቦኛል ያለ ሲሆን፣ የምክር ቤቱ አባል አገራት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የፖለቲካ ነጻነትን ያከብራሉ ብሏል። የመግለጫውን መውጣት ተከትሎ የተመድ የኢትዮጵያ ተወካይ፤ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ለሰጡት 'ገንቢ ምልከታ እና ድጋፍ' አድናቆቱን ገልጿል። የጸጥታው ምክር ቤት ምን አለ? የጸጥታው ምክር ቤት ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ፤ የምክር ቤቱ አባል አገራት በትግራይ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ እንዳሳሰበው ገልጾ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እና የሰብዓዊ እርዳታ እንዲቀርብ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ ነው ብሏል። የጸጥታው ምክር ቤት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በተባበሩት መንግሥታት መርህ መሠረት መቀጠል አለበትም ብሏል። በትግራይ ያለው የደኅንነት እጦት የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሥራ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረም ነው ብሏል። ጾታዊ ጥቃቶችን ጨምሮ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ያሳስቡኛል ያለው ምክር ቤቱ፤ ጥሰቶቹ በገለልተኛ አካል እንዲመረመሩ እና ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል። በዚህ ረገድም የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን በጋራ የሚያደርጉትን ምርመራ በበጎ ጎኑ ተቀብሎታል። የጸጥታው ምከር ቤት ዓለም አቀፍ ሕግጋቶች መከበር አለባቸው ብሏል። ምክር ቤቱ እንደ የአፍሪካ ሕብረት እና ኢጋድ የመሳሰሉ አህጉራዊ እና ቀጣናዊ ተቋማት ለችግሩ መፍትሄ ለማምጣት ለሚኖራቸው ተሳትፎ ጠንካራ ድጋፍ እንዳለው ገልጿል። በመጨረሻም ምክር ቤቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ነጻናትና የግዛት አንድነትን እንደሚያከብር ገልጿል። የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤቱ ኢትዮጵያን በተመለከተ መግለጫ ለማውጣት በርካታ ጊዜ ቢሰበሰብም ከስምምነት ሳይደርስ መቅረቱ ይታወሳል። የካቲት 25/2013 ዓ.ም የጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያን በተመለከተ ያደረገው ውይይት ከስምምነት ላይ ሳይደርስ መቅረቱን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። የዜና ወኪሉ የጸጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ባረጋገጠ መልኩ በትግራይ አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ እና ግጭት እንዲቆም የሚጠይቅ መግለጫ ለማውጣት ያደረገው ስብሰባ በሩሲያ እና በቻይና ተቃውሞ ሳይወጣ ቀርቷል። ሩሲያ እና ቻይና መግለጫው በኢትዮጵያ ""ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው"" በማለት ነበር ተቃውሟቸውን ያሰሙት። በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ አሜሪካ በሉአላዊ አገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ ጠይቆ ነበር። ሩሲያና ቻይና በተቃወሙት ሰብሰባ ላይ ሌሎች አባላት ምን ብለው ነበር? የካቲት 25/2013 ዓ.ም ተካሂዶ በነበረው ውይይት ላይ በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ለሁለት ሰዓት ያህል የዘለቀ ውይይት ተካሂዶ እንደነበረ ቢቢሲ ያናገራቸው በውይይቱ ላይ የታደሙ አንድ ዲፕሎማት አስታውሰዋል። አስራ አምስቱም የጸጥታው ምክር ቤት አባላት በተገኙበት በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ሁሉም በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ በተመለከተ ሐሳባቸውን ሰንዝረዋል። በዝግ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት ሊባል በሚችል ደረጃ በትግራይ ክልል ውስጥ ያለው የሰብአዊ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው መግለጻቸውን ዲፕሎማቱ ተናግረዋል። ኬንያ፣ ቱኒዚያና ኒጀር እንዲሁም ሴንት ቪንሰንት እና ግሪናዲስ የኢትዮጵያ መንግ��ት የእርዳታ ፈቃድ የመስጠት ሂደቱን በማፋጠንና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመመርመር በኩል እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው ነበር። በስብሰባው ላይ በትግራይ ውስጥ ያለው ሁኔታ ለቀጠናው ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፍ ሰላም እና ደኅንነት ጉዳያ ሊሆን ይችላል ያለችው ፈረንሳይ ናት። ስለዚህም ምክር ቤቱ መፍትሔ ለማምጣት የሚደረጉ ቀጠናዊ ጥረቶችን ከመደገፍ በተጨማሪ ለመፍትሔው አስተዋጽኦውን እንዲያበረክት ጠይቃ ነበር። ዩናይትድ ኪንግደም በስበሰባው ላይ ፖለቲካዊ መፍትሔ ማማጣት ባለመቻሉ ውጥረቱ እየተባባሰ እንዲሄድ ምክንያት መሆኑን ጠቅሳ፤ የጸጥታው ምክር ቤት ይህ ቀውስ እንዲያበቃ ለማድረግ ተገቢውን ሚና መጫወት ይኖርበታል ብላለች። አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ እርዳታና የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ እንደሚያሳስባት ገልጻ ይህም ለቀጠናው ሰላምና ጸጥታ ቀጥተኛ ስጋት ስለሆነ በቶሎ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል ብላ ነበር። ሩሲያ፣ ቻይና፣ ሕንድና ቬትናም ያለው የሰብአዊ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው የገለጹ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ ረገድ እርዳታ ለማቅረብ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው የኢትዮጵያ ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም እነዚህ አገራትና የምክር ቤቱ አባል የሆኑ የአፍሪካ አገራት ለችግሩ መፍትሔ ለመፈለግ ኢጋድንና የአፍሪካ ሕብረትን የመሳሰሉ ተቋማት ሚና እንደሚደግፉ ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ግድያዎችን በተመለከተ የሚወጡት ሪፖርቶች አሳሳቢ እንደሆኑ ገልጾ፤ የሰብአዊ ሁኔታውን በተመለከተ ያለው መረጃ መሬት ላይ ያለው እውነታ ነጸብራቅ እንደሆነ ገልጿል። በተጨማሪም አስፈላጊውን እርዳታ ለማቅረብ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፉ ከፍ እንዲል ተጨማሪ ሐብት እንደሚያስፈልግም አመልክቷል። የጸጥታው ምክር ቤት አባል አገራት የትኞቹ ናቸው? የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት 15 አባል አገራት አሉ። ከ15ቱ አባል አገራት አምስቱ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸው ቋሚ አባል አገራት ሲሆኑ፤ አስሩ ደግሞ በየዓመቱ የሚቀያየሩ እና ድምጽን በድምጽ የመሻር አቅም የሌላቸው አባል አገራት ናቸው። ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸው የምክር ቤቱ አባላት አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ዩናይትድ ኪንግድ፣ ፈረንሳይ እና ቻይና ናቸው። ኢስቶኒያ፣ ሕንድ፣ አየርላንድ፣ ኬንያ፣ ሜክሲኮ፣ ኒጂር፣ ኖርዌይ፣ ሴንት ቪንሰንት ኤንድ ዘ ግሬናዲንስ፣ ቱኒዚያ እና ቬትናም ደግሞ አስሩ ተለዋዋጭ የምክር ቤቱ አባላት ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/news-56855668 +sports የአፍሪካ ዋንጫ ፈር ቀዳጆቹ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ ሲታወሱ "ከተጀመረ ሳምንት በሞላው የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ በሜዳ ላይ ይህ ነው የሚባል ድምቀት ባይታይበትም የውድድር ፈር ቀዳጅ የሆኑት አገራት በአንድ ላይ ተሳታፊ በመሆናቸው በታሪካዊነቱ እየተጠቀሰ ነው። ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በአውሮፓውያኑ 1957 የተጀመረውን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ የጠነሰሱና የጀመሩ አገራት ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ታሪክ ይዘክራቸዋል። ከ52 ዓመታት በኋላም የውድድሩ ሦስት የመጀመሪያ ተፎካካሪ አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በአንድ ላይ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆኑት። ""የሦስቱም አገራት ቡድኖች በዚህ ውድድር አንድ ላይ መመለሳቸው ኩራትን እንዲሁም ጥልቀት ያለውን የውድድሩን ባህልን የሚያንጸባርቅ ነው"" በማለት የስፖርት ጋዜጠኛው ባደርልዲን ባከይት ተናግሯል። በአፍሪካ ዋንጫ ቀዳሚ ስፍራ ያላቸው ሦስቱ አገራት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን ዋንጫ አሸናፊ ቢሆኑም ግብፅ ሰባት ጊዜ በማሸነፍ ክብረ ወሰንን ጨብጣለች። ኢትዮጵያና እና ሱዳን ደግሞ አንዳንድ ዋንጫዎችን በስማቸው አስመዝግበዋል። እግር ኳስ በምሥራቅ አፍሪካ አገራቱ ኢትዮጵያና ሱዳን ከፍተኛ ተወዳጅነት ቢኖረውም እንዲሁም ከፍተኛ ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች እንዳላቸው ቢነገርም ከነበራቸው ከ1960ዎቹና 70ዎቹ ታላቅነት ወደ ኋላ ቀርተዋል። ከምሥራቅ አፍሪካ አገራት በብቸኝነት ዋንጫውን ያነሱት ጎረቤት አገራቱ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በጨዋታው ተመሳሳይ ታሪክ አላቸው። በአፍሪካ ዋንጫ ቀደምት ስፍራ ቢኖራቸውም ሁለቱም ድሎቻቸውን ያገኙት በአገራቸው መሬት ነበር። ኢትዮጵያ ለ31 ዓመታት ያህል ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ማለፍ አቅቷት በአውሮፓውያኑ 2013 ነበር ወደ ውድድሩ መመለስ የቻለችው፤ በተመሳሳይ ሱዳንም እንዲሁ ለ32 ዓመታት ያህል ርቃ በአውሮፓውያኑ 2008 ነበር ተሳታፊ የሆነችው። ""በእግር ኳሱ ዘርፍ ሱዳንና ኢትዮጵያን ወደ ኋላ በመመለስ ረገድ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ሚና ተጫውተዋል"" በማለት የሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰርና 'አፍሪካን ሶከርስኬፕስ፡ ሀው ኤ ኮንቲነንት ቼንጅድ ዘ ወርልድ'ስ ጌም' መጽሐፍ ደራሲ ፒተር አሌጊ ይናገራሉ። ""ነገር ግን የአፍሪካ ዋንጫ እየተስፋፋና የዓለም ዋንጫ 2026 ማጣሪያ ባለበት በአሁኑ ወቅት የሁለቱ አገራት ቡድኖች አዎንታዊ ሁኔታዎችን እያሳዩ ያሉ ይመስላል"" ሲሉ ያስረዳሉ። በሁለቱም አገራት የተራዘሙ የእርስ በርስ ጦርነቶች፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ውድቀት እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ተደማምረው በእግር ኳስ ጨዋታው እድገትና ሂደት ላይ በአሉታዊ መልኩ ተጽዕኖ አሳድረዋል። ይሁን እንጂ ሁለቱም አገራት ቀደም ባለው ስኬታቸው የተነሳ የሰፈነው ኩራት ለትውልዶች እንደ አስጨናቂ ማስታወሻና ማበረታቻ ሆኖም አገልግሏል። ኢትዮጵያ ካሜሩን እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ባደረገቻቸው ሁለቱም ጨዋታዎች ሽንፈትን ማስተናገዷን ተከትሎ ለቀጣዩ ዙር የማለፊያ ዕድሏን አጥብቦታል። ነገር ግን ሱዳን ከጊኒ ቢሳዎ ጋር በነበረው ጨዋታ አቻ መውጣቷን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር ልታልፍ ትችላለች። በናይጄሪያ ሽንፈት ያጋጠማት ግብፅም በቀጣዩ ከዚህ ማገገም አለባት። የአፍሪካ ዋንጫ ውልደት በአውሮፓውያኑ 1956 የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን ባለሥልጣናት ከደቡብ አፍሪካ ተወካይ ጋር በመሆን የአፍሪካ አህጉራዊ ውድድርን ለመመስረት በፖርቹጋል በነበረው የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ ፊፋ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ተገኙ። የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በአውሮፓውያኑ 1957 በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የተካሄደ ሲሆን ሲሆን የደቡብ አፍሪካ ፌደሬሽን ከተለያዩ ዘሮች የተውጣጣ ቡድን ለመላክ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ከውድድሩ ተገለለች። ሱዳንን የረታችው ግብፅ፣ ኢትዮጵያንም በፍፃሜው ጨዋታ 2 ለ 1 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነች። ነገር ግን የኢትዮጵያ ቡድን በአውሮፓውያኑ 1962 በተካሄደው በሦተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ያኔ አረብ ሪፐብሊክ ትባል የነበረችውን ግብፅ 4 ለ 2 በመርታት ሻምፒዮን በመሆን ድሏን አጣጣመች። የቡድኑ አምበል ኤርትራዊው ሉቺያኖ ቫሳሎ ዋንጫውን ከአፄ ኃይለሥላሴ እጅ የተቀበለ ሲሆን ይህ ውድድር ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀችው ነበር። ""ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ዘርፍ በጣም ታዋቂ ናት፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ በጣም ተወዳጅ ስፖርት እግር ኳስ ነው"" በማለት በአዲስ አበባ የሱፐር ስፓርት ተንታኝ ሰይድ ኪያር ይናገራል። በመጀመሪያዎቹ ሁለት ውድድሮች ተሳታፊዎች የነበሩት የሦስት አገራት ቡድኖች ነበሩ ቀስ በቀስም ሌሎች አገራት መቀላቀል ጀመሩ። ይህንን በተመለከተ ሰይድ ኪያር እንደሚያምነው ያለፉትን ድሎችንም ቢሆን በጥልቀት ልንመረምረው ይገባል ይላ���። ""በተጫዋቾቻችን፣ በአሰልጣኞች፣ በታሪክ ሰሪዎቻችን ኩራት እና ክብር ይሰማናል። ነገር ግን እንደ አይቮሪኮስት፣ ናይጄሪያና ቱኒዝያ በርካታ የአፍሪካ አገራት በቅኝ ግዛት ውስጥ ነበሩ። ብሔራዊ ቡድኖቻቸውም አልነበሩም"" በማለት የወቅቱን ፖለቲካዊና ታሪካዊ ዳራ ማጥናት እንደሚያስፈልግ ያስረዳል። ለሱዳን እክል የሆነው የአገር ውስጥ ፖሊሲ ሱዳን በአውሮፓውያኑ 1970 እነ አሊ ጋጋሪ፣ ጃክሳ በመባል የሚታወቀው ናስር ኤዲን ባካተተው ወርቃማ በሚባለው የእግር ኳስ ትውልዷ ጋናን 1 ለ ምንም በመርታት ብቸኛዋን ዋንጫ አሸንፋለች። የሱዳን ቡድን በዚያው ዓመት በሜክሲኮ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ተቃርቦ ነበር። ከሁለት ዓመት በኋላ ቡድኑ በአውሮፓውያኑ 1972 ሙኒክ ኦሊምፒክ ተሳትፎ በአንፃራዊነት ጥሩ አፈጻጸም አሳይቷል። ነገርግን በቀጣዮቹ ዓመታት 'ዘ ሴክሬታሪ በርድስ' ቡድን ውድቀት ገጠመው። ""በወቅቱ አገሪቱ ውስጥ የነበረው መረጋጋት ለእግር ኳስ ማደግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቶ ነበር። ነገር ግን የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የምጣኔ ሀብት ችግሮች አገሪቱ በሌሎች ጉዳይ ላይ እንድታተኩር አድርጓታል"" በማለት የወርቃማው ትውልድ ቡድን አባል የነበረው በአሁኑ ወቅት የ77 ዓመት እድሜ አዛውንቱ ጃክሳ ያስረዳል። በርካታ የመንግሥት ፖሊሲዎች በእግር ኳሱ ላይ የራሳቸውን ጥላ አጥልተውበታል። ከእነዚህም መካከል የ1976ቱ አል-ሪያዳ አል-ጃማሂሪያ ወይም የቀድሞው አምባገነን ጃፋር ኒሜሪ የብሔራዊ ሊግን በማገድ እግር ኳስን ወደ አካባቢያዊ ውድድር ያወረዱበት ""ስፖርት ለሰፊው ሕዝብ"" ፖሊሲዎች ይጠቀሳሉ። በምላሹም የሱዳን ታዋቂ ተጫዋቾች ወደ ጎረቤት አገራት እና ሊጎች በተለይም ወደ አረብ ባሕረ ሰላጤ አቀኑ። ከአንድ ዓመት በኋላ ፖሊሲው እንዲቀር ቢደረግም ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰ በኋላ ነበር። ""ሱዳን ማገገም ያልቻለችበት የትውልድ መቆራረጥ አጋጠመ"" በማለት የኩራ ዶት ኮም ድረ ገፅ ጋዜጠኛ ባኬት ይናገራል። ጨዋታዎቹ አካላዊ እንዲሁም የታክቲክ ለውጦች በመጡበት ወቅት የምሥራቅ አፍሪካ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ከዘመኑ ጋር መራመድ ወይ መላመድ አለመቻላቸው ከምዕራብ እና ሰሜን አፍሪካ አገራት ጋር መፎካከር አዳጋች እንዲሆን ያደረጉባቸው ሌሎች ምክንያቶችም ሊታሰብባቸው ይገባል። ""የእኛን የአጨዋወት ዘይቤ ከአካላዊ ወደ አእምሯዊ መለወጥ ከቻልን ኳስን በመቆጣጠር፣ በአጫጭር ቅብብሎች፣ በቴክኒክ ችሎታዎች ጥሩ ነን"" ሲል ሰይድ ያስረዳል። ከሜዳ ውጭ ያለው አደረጃጀት መስተከካል የተሻሻለ የጨዋታ አያያዝ እና የረጅም ጊዜ ስልቶችን መንደፍ ያስፈልጋል። ለምሳሌም ያህል እንደ ስፔን የማለፊያ ስታይል መተግበር ወይም በአውሮፓ ሻምፒዮና ደካማ ውጤቶችን ተከትሎ ጀርመን የታዳጊዎች የእግር ኳስ ፕሮግራሞችን ማዋቀር የመሳሰሉትን አይነት ፕሮግራሞች ልንከተል ያስፈልጋል። ""ገንዘብ ማግኘት ወይም ጥሩ ተጫዎቾች እንዲኖረን ማድረግ ብቻ ሳይሆንን ይህንንም በአግባቡ ማስተዳደር እና ማቀድ ያስፈልጋል"" ሲል የሞደርን ስፖርት ባልደረባ ሀሰን ኤል ሚስታዊ ይናገራል። አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ አሁንም ግብፅ ለመሻሻል ቦታ እንዳላት ያምናል። ለዚህም በአፍሪካ ዋንጫ በመሳተፍ ክብረ ወሰንን መጨበጥ ብቻ ሳይሆን ከአውሮፓውያኑ 2006-2010 ባለው ሦስት ተከታታይ ዋንጫዎችም ድሎችን በማስመዝገብ እንዲሁም በዓለም ዋንጫም ሦስት ጊዜ መሳተፏን ይጠቅሳል። ሌላኛው ባክሄት የሚጠቅሰው የሱዳን ትልልቅ ክለቦች የበላይነትን ሲሆን ይህም የሌሎችን ጉዳዮችንም እድገት የሚነካ ጉዳይ ነው። አል-ሂላል እና አል-ሜሪክ የተሰኙት ቡድኖች በአህጉር አቀፍ ውድድር በአንፃራዊነ��� ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ ቢሆንም ከሀብታም ደጋፊዎች የሚያገኙት ድጋፍ ውድድሮችን እያደናቀፈ ይገኛል። የምዕራብ እና የሰሜን አፍሪካ አገራትም ተጫዋቾቻቸው በከፍተኛ የአውሮፓ ክለቦች እና ሊጎች መጨዋታቸው ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው ሲሆን ኢትዮጵያ እና ሱዳን በበኩላቸው በአብዛኛው በአገር ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዎች ነው ያሏቸው። በካሜሮንም ለሚደረገው ውድድር እነዚህኑ ተጫዋቾችን ነው ይዘው የቀረቡት። ""ለአውሮፓ ክለቦችና ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋቾቹ ልምዳቸውን ወደ አገራቸው ብሔራዊ ቡድኖቻቸው ያመጣሉ"" ይላል ኤል ሚስታካዊ። ኢትዮጵያና ሱዳን ከአፍሪካ ዋንጫ ተፎካካሪነት ርቀው ቢገኙም በኢትዮጵያ በቀጠለው የርስ በርስ ጦርነትና በሱዳን ባለው መፈንቅለ መንግሥት ተመሳሳይ የፖለቲካ ፈተና ላይ ያሉት አገራት ደጋፊዎቻቸው በጨዋታቸው እንደሚያስደንቁ ተስፋን ሰንቀዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59977329 +politics ቦሪስ በኮቪድ ወቅት ስላዘጋጁት ግብዣ ከእንደራሴዎች ጥያቄ ሊቀርብላቸው ነው "የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ነምበር ቴን በሚባለው መሥሪያ ቤታቸው ኮቪድ-19 ባየለበት ወቅት ስላዘጋጁት ድግስ ከሕዝብ እንደራሴዎች ጥያቄ ሊቀርብላቸው ነው። ነባር የእንግሊዝ መንግሥት ባለሥልጣን የሆኑት ሱ ጌሪ፤ ቦሪስ ጆንሰንን የተለመከተ አንድ ሪፖርት ያወጣሉ ተብሎ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። ነገር ግን ሪፖርቱ ይፋ ከመደረጉ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ከሕዝብ እንደራሴዎች ጋር ፍጥጫ ይጠብቃቸዋል። ፖሊስ በበኩሉ የራሱን ምርምራ አድርጎ ውጤቱን ማክሰኞ ዕለት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። የሜት ፖሊስ ኮሚሽነር ክሬሲዳ ዲክ እንዳሉት የቦሪስ አስተዳደር ኮቪድ-19ን ተከትሎ የእንቅስቃሴ ገደብ በጣለበት ወቅት በተለያዩ የመንግሥት ሕንፃዎች የመጠጥ ድግሶች ነበሩ። ይህ የፖሊስ የምርመራ ውጤት ለቦሪስ ጆንሰን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባቸዋል። ዳውንኒንግ ስትሪት በተሰኘው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና መሥሪያ የሚገኝበት ሥፍራ በኮቪድ-19 ምክንያት ሰዎች ቤታቸው ሳሉ እሳቸው ግን የመጠጥ ድግስ አዘጋጅተዋል የተባሉት ቦሪስ ከሰሞኑ ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈረንጆቹ ግንቦት 20/2020 የመጀመሪያው የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለበት ወቅት አንድ ""ሥራ ነክ"" ድግስ ተዘጋጅቶ በመገኘቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለው ነበር። ነገር ግን ሰኔ 2020ም በተመሳሳይ የልደት ድግስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ተዘጋጅቶ ነበር የሚሉ ዘገባዎች ብቅ ማለት ጀምረዋል። አንዳንድ ወግ አጥባቂ የሕዝብ እንደራሴዎች ቦሪስ ከሥልጣን እንዲወርዱ ቢጠይቁም ሚኒስትሮች ደግሞ የሱ ጌሪ ምርመራ ውጤት ይፋ እስኪሆን እንጠብቅ እያሉ ነው። ወግ አጥባቂው ቶሪ ፓርቲ ምርመራው ይፋ ከተደረገ በኋላ በቦሪስ መንግሥት ላይ እምነት የለንም የሚል ደብዳቤ ሊፅፉ አቅደዋል። ይህ ደግሞ ቀጣዩ የዩኬ መንግሥት ማነው ወደሚል ሽኩቻ ሊያስገባ ይችላል። ኮመንስ ለተሰኘው የታችኛው ምክር ቤት አባላት መግለጫ የሚሰጡት ቦሪስ የምርመራውን ውጤት እየተጠባበቁ ሲሆን ውጤቱ ለሕዝብ መች ይፋ እንደሚሆን ግን አልታወቀም። ሌበር ፓርቲ በበኩሉ መንግሥት የሕዝብ እንደራሴዎች የምርመራውን ውጤት አንብበው እንዲያገናዝቡ ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቋል። የታችኛው ምክር ቤት አባላት ኃላፊ የሆኑት ጃኮብ ሪስ-ሞግ የአሁኑ የእንደራሴዎችና የቦሪስ ፍጥጫ ከሌላው ጊዜ የተለየ እንደሚሆን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጃኮብ አክለው የካቢኔው አባላት በሙሉ ቦሪስን የደገፉት ""ያልደገፉ ሚኒስትሮች ሥልጣን እንዲለቁ ስለሚገደዱ ነው"" ብለዋል። ትይዩ [ሻዶው] ዋና አቃቤ ሕግ የሆኑት ኤሚሊ ቶርንቤሪ እንደሚሉት ጠቅላይ ሚ���ስትሩ ድግሶቹን በተለመከተ የቀረበባቸውን ወቀሳ ችላ ማለታቸው ትክክል አልነበረም። ኤሚሊ አክለው ቦሪስ ስለተካፈሏቸው ድግሶች በመዋሸታቸው ምክንያት አሁን ስላለው የኑሮ ውድነትም ሆነ ስለ ሩሲያ ወደ ዩክሬን መገስገስ የመወሰን ሥልጣን የላቸውም። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከአንድም ሁለት ሶሥት አራቴ በቢሯቸው ድግሶች አዘጋጅተዋል ተብለው መወቀስ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። የዩናይት ኪንግደም ሕዝብን ያስቆጣው ጉዳይ ጠቅላዩ ድግስ ሲደግሱ ሕዝቡ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎበት ቤቱ መከርቸሙ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-60136737 +politics 2020 በፎቶ ፡ ከኮሮናቫይረስ ጨረቃ ላይ ሰንደቅ አላማ እስከማስቀመጥ ዓለም በኮሮናቫይረስ የተፈተነበት የፈረንጆቹ 2020 ሊያበቃ ነው። ዓመቱን ወደኋላ መለስ ብለን በፎቶ ስብስብ እንዲህ ቃኝተናል። ከጥር ወር እንጀምር። ጥር ቻይና ዉሃን ውስጥ የተቀሰቀሰው ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ የግድ ነው። ከወራት በፊት በመላው ዓለም የጭምብል እጥረት ተከስቶ ነበር። የካቲት በከዋክብት ሳይንስ እጅግ አስደናቂ የሆነው ሙሉ ጨረቃ ቱርክ በሚገኘው ሰልሚዬ መስጂድ አቅራቢያ የታየው በዚህ ዓመት ነው። መጋቢት አብዛኛው ሰው ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ጓደኛ ለማግኘት እንደ ዙም ያሉ የተለያዩ መተግበሪያዎችን ለመጠቀም ተገዷል። ይህ ፎቶ ሆንግ ኮንግ ውስጥ የሚገኝ መምህር ለተማሪዎቹ በበይነ መረብ ትምህርት ሲያስተላልፍ የተነሳ ነው። ሚያዝያ ወረርሽኙን ለመከላከል አካላዊ ርቀትን የመጠበቅ መርህ በዓለም ዙሪያ ተግባራዊ ሆኗል። አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ የካቶሊክ ቄስ ጸበል ለመርጨት ፈጠራ የተሞላበት መንገድን ተጠቅመዋል። ግንቦት ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ እጅ መገደሉ በአሜሪካና በሌሎች አገራትም ዘረኝነትን የሚቃወም ንቅናቄ አስነስቷል። ሰኔ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ከመጣሉ በፊት ባርሴሎና ውስጥ በሚገኘው ግሬን ቴትሬ ደል ሊሲዮ ከሁለት ሺህ ለሚበልጡ ችግኞች ሙዚቃ ቀርቧል። ሐምሌ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎችም የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች እንዲሁም በሕንድ፣ በፓኪስታን እና በኢራን ውስጥ የተስፋፋው የአንበጣ መንጋ ስጋት የሆነበት ዓመት ነው። በምስሉ ኬንያ ውስጥ አንዲት ሴት ሰብል በአንበጣ መንጋ ተወሮ ስትመለከት ይታያል። ነሐሴ በሊባኖስ መዲና በቤይሩት የተከሰተው ፍንዳታ ኒውክሌር ነክ ካልሆኑ ፍንዳታዎች ሁሉ ትልቁ ነው። ከ200 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፎቶው የሚያሳየው ፒያኖ ተጫዋቹ ሬይመንድ ኢሳያም ከደረሰበት ጉዳት ባሻገር ቤቱን አጥቷል። መስከረም የብራዚል አማዞን ጫካ እጅግ በሚያስፈራ ሁኔታ የእሳት አደጋ ደርሶበታል። የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ቃጠሎው አሳስቧቸዋል። አንድ ጃጓር መዳፉ ተቃጥሎ ከእሳቱ ተርፏል። ጥቅምት ኮሮናቫይረስ ከፍተኛ ተጽዕኖ ካሳደረባቸው መካከል ነጋዴዎች በዋነኛነት ይጠቀሳሉ። በጣሊያን መዲና ሮም የሚገኘው ሬስቶራንት የንግዱ መቀዛቀዝ ተምሳሌት እንዲሆን አጽም አስቀምጧል። ኅዳር በታይላንድ ተቃውሞ ከሚሳተፉ አንዱ ሚትሬ ቺቲንዳ ነው። ጸጉሩን የተቆረጠው ተቃውሞውን እንደሚደግፍ በሚጠቁም የሦስት ጣት ምልክት ነው። ይህ ምልክት 'ሀንገር ጌምስ' ከተባለው ፊልም የተወሰደ ነው። ታኅሣስ ቻይና ጨረቃ ላይ ሰንደቅ አላማዋን በመትከል ከዓለም ሁለተኛዋ አገር ሆናለች። በተጨማሪም ቼንጅ-5 የተባለው የሕዋ ጉዞ ከ44 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጨረቃ አለት አምጥቷል። https://www.bbc.com/amharic/news-55472951 +business ኢትዮጵያ አይኤምኤፍን አዲስ የተራዘመ የብድር አቅርቦት ስምምነት ጠየቀች ኢትዮጵያ ዓለም አ��ፉን የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) አዲስ የተራዘመ የብድር አቅርቦት (ኤክስቴንድድ ክሬዲት ፋሲሊቲ) ስምምነት መጠየቋን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። በአሁኑ ወቅት የተራዘመው የብድር አቅርቦት ጊዜው ያለቀ ቢሆንም የተራዘመ የፈንድ አቅርቦት (ኤከስቴንድድ ፈንድ ፋሲሊቲ) የተባለው የተቋሙ የድጋፍ ማዕቀፍ ቀጥሏል ተብሏል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ለኢትዮጵያ አገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ድጋፍ የተራዘመ የብድር አቅርቦት እና የተራዘመ የፈንድ አቅርቦት በተባሉ ማዕቀፎች በኩል በአውሮፓውያኑ 2019፣ 2.9 ቢሊዮን ዶላር ማፅደቁ የሚታወስ ነው። አገሪቷ የተራዘመ የብድር አቅርቦት (ኤክስቴንድድ ክሬዲት ፋሲሊቲ) ማዕቀፍ ውስጥም ቃል ከተገባላት 1.7 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ እስካሁን የተቀበለችው ወደ 200 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን 1.5 ቢሊዮን ዶላር ሳታገኝ ነው ጊዜው ያበቃው። ኢትዮጵያም የተራዘመው የብደር አቅርቦት በአዲስ ስምምነት እንዲቀጥልና የተፈጸመውን እንዲተካና ተመሳሳይም የገንዘብ መጠን እንዲሆን ተስፋ ተደርጎበታል። አዲሱ የተራዘመው የብድር አቅርቦት የቀድሞውን በመተካት በድህነት ቅነሳና የእድገት ፕሮግራሞች (PRGT)ን እንድታገኝም ጠይቃለች ተብሏል። የገንዘብ ሚኒስቴርም በመግለጫው የተራዘመ የብድር አቅርቦት እና የተራዘመ የፈንድ አቅርቦት ማዕቀፎች በኩል በኩል ለኢትዮጵያ የማሻሻያ ሂደት ያበረከተውን ድጋፍም እውቅና ሰጥቷል። አገሪቷ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋምን ጨምሮ ለሌሎች ተቋማትና አገራት ያላትን ዕዳ ለማሸጋሸጝ የአበዳሪዎች ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን የመጀመሪያውን የአበዳሪዎች ኮሚቴ ስብሰባ መስከረም 12/2014 ዓ.ም ተካሂዷል። የአበዳሪዎቹ ኮሚቴ የጋራ ሊቀመንበሮች የሆኑት ፈረንሳይና እና ቻይና ሲሆኑ ኮሚቴውን ለማቋቋም ያደረጉትን ያላሰለሰ ጥረት እንዲሁም አገሪቷ በስብሰባው ላይ ተገኝታ ጥያቄዋን እንድታቀርብ ለተመቻቸላት እድል ሚኒስቴሩ አመስግኗል። ኢትዮጵያ በቡድን 20 አገራት የጋራ ማዕቀፍ (G20's Common Framework) ያለባትን 30 በሊዮን ዶላር እዳ ማቃለያ በጊዜው ታሳካ ዘንድ በአበዳሪዎች ኮሚቴ የተወሰዱ አስፈላጊ እርምጃዎችን በበጎ መልኩ እንደምታያቸው አስታውቃለች። በዚህ ማዕቀፍ መሰረት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የደቀቀውን የዓለም ኢኮኖሚ እንዲያገግም በተለይም ለሚያድጉ አገራት የብድር እፎይታ ጊዜ የሰጡ ሲሆን ከዚህም ኢትዮጵያ አንዷ ተጠቃሚ ናት። የአበዳሪዎች ኮሚቴ የአገሪቱ የእዳ ሽግሽግ በአገሪቱ ካለው የምጣኔ ሀብት ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲሁም በመሠረታዊነት የማክሮ ኢኮኖሚውን መረጋጋትን ለማረጋገጥ ያደረገውን ጥረት አገሪቱ ደስተኛ መሆኗም ተገልጿል። በተለይም እርምጃዎቹ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከተፈጠረው ምጣኔ ሀብታዊ ተግዳሮቶች የመፍትሄ እፎይታን እንደሚሰጥና አገሪቷ ለልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ይውል ዘንድ የገንዝብ ፍሰት ቦታን በመፍጠር እንዲሁም የአገሪቱን የእዳ መጠንም ለማሸጋሸግ ሚና ይጫወታል ተብሏል። አገሪቷ የእዳዋንም ሽግሽግ ሁኔታ ዝርዝሮችን ለማጠናቀቅ ከአበዳሪዎቿ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ ናት ብሏል። የሃገር በቀሉን የኢኮኖሚ ማሻሸያ እየደገፈ ያለው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አገሪቷ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጫና እንድታገግም የሚያደርገውን የምጣኔ ሀብት ድጋፍ እንዲሁም ለተጋላጭ ማኅበረሰቦች አቅርቦትም ቀጣይ ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነም ሚኒስቴሩ አፅንኦት ሰጥቷል። ተቋሙ የገንዘብ እና እና የፋይናንስ ዘርፍ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን የሚደግፍ የቴክኒክ ድጋፍ የኢኮኖሚያችንን አፈፃፀም በማጠናከር ረገድም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ተብሏል። ከጥቂት አመታት በፊት የሃገር ��ቀል የምጣኔ ኃብት ማሻሻያ እየተገበረች ሲሆን ይህም የተረጋጋ የእድገት ጎዳና የማይናወጥ ምጣኔ ሀብት እንዲፈጠር እያደረገ መሆኑም ተገልጿል። ማሻሻያውም የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር ሥርዓት፣ የግሉ ዘርፍ በተሻለ ሁኔታ የሚሳተፍበት ከባቢ መፍጠር፣ የመንግሥት ልማቶች ድርጅቶች የተሻሻለ አፈፃፀም፣ የተሻሻለ የወጪ ንግድ እንዲሁም ገቢን መጨመርና ወጪዎችን ማስተካከል መቻሉንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ የሚባሉ የገንዘብ ተቋማት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ብድር ለመልቀቅ እያንገራገሩ ነው ተብሏል። በዋነኝነትም የነዚህ ተቋማት ስጋት ተጨማሪ ብድር ለአገሪቱ መስጠት የበለጠ ጫና ውስጥ ይከታታል እንዲሁም መክፈል አቋሟን የበለጠ ሊያዳክም ይችላል ከሚል ስጋት ጋር የተያያዘ ነው። የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጰያ ለመስጠት ቃል የገባውን 339 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑ ተነግሯል። ከዚህም በተጨማሪ የዓለም ባንክ አንድ አካል የሆነው የዓለም አቀፉ የልማት ትብብር ማኅበር (ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን) 3.3 ቢሊዮን ዶላር፣ የዓለም የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) 2.7 ቢሊዮን ዶላር፣ የኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ ቻይና 1.4 ቢሊዮን ዶላርና ሌሎችም አበዳሪዎች ባለፈው አመት እስከ መጋቢት ድረስ ይሰጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም እስካሁን አልተለቀቀም። https://www.bbc.com/amharic/news-58638143 +sports ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ከተሞች የተካሄዱ ውድድሮችን አሸነፉ በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ የተለያዩ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል። በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድር በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያዊው አትሌት ጫሉ ዴሶ ገልሜሳ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ7 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸናፊ መሆን ችሏል። አትሌቱ ሰይፉ ቱራ ደግሞ 2ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ በፓሪሱ ማራቶን የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል። በሴቶች ምድብ ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፋንቱ ጂማ የቦታውን ሪከርድ ያሻሻለችውን ኬንያዊቷን አትሌት ጁዲት ጄፕቱምን ተከትላ በመግባት የብር ሜዳሊያ ስታሸንፍ አትሌት በሱ ሳዶ ደግሞ ውድድሩን በሦስተኝነት በማጠቀቅ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች። ስፔን ባርሴሎና ውስጥ በተደረገ የወንዶች ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሐፍቱ ተክሉ እና አትሌት ጫላ ረጋሳ አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው በመጨረስ የወርቅ እና የብር ሜዳሊያውን ወስደዋል። በተመሳሳይ በሴቶች ምድብ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጌጤ ዓለማየሁ ሁለተኛ፣ አትሌት አስናቀች አወቀ ሶስተኛ እና አትሌት ረድኤት ዳንኤል ደግሞ አራተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በሌላ ውድድር በ2022 የኮሪያ ዴጉ ዓለም አቀፍ ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ሽፈራው ታምሩ 2:06:31 በሆነ ሰዓት አንደኛ በመውጣት አሸንፏል። በሴቶች ዴጉ ዓለም አቀፍ ማራቶን ኤርትራዊቷ ናዝሬት ወልዱ አሸናፊ ሆናለች። በጣልያን በተካሄደው የሚላኖ 2022 ማራቶን ውድድርም ኢትዮጵይውያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። በሴቶች ምድብ አትሌት ስንታዬሁ ጥላሁን 2ኛ ሆና ስታጠናቅቅ ሌላኛዋ የአገሯ ልጅ አትሌት አታለል አንሙት የ3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች። ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ያለውን ደረጃም ቢሆን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ናቸው የያዙት። https://www.bbc.com/amharic/news-60979076 +health ኮሮናቫይረስ ፡ የካናዳው ሚኒስትር በኮቪድ-19 ወቅት ሽርሽር በመሄዳቸው ምክንያት ሥልጣናቸውን ለቀቁ "የካናዳዋ ኦንታሪዮ ግዛት የገንዘብ ሚኒስትር የሆኑት ግለሰብ በኮቪድ-19 ወቅት ለመዝናናት ወደ ካሪቢያን በመጓዛቸው ምክንያት ሥራ ለቀዋል። የግዛቲቱ ገዥ ዶግ ፎርድ የገንዘብ ሚኒስትራቸው ሥልጣን እንዲለቁ ያደረጉት ኦንታሪዮ የእንቅስቃሴ ገደብ ላይ እያለች ሽርሽር ብለው በመጓዛቸው ነው። ሚኒስትር ሮድ ፊሊፕስ ይቅርታ ጠይቀዋል። ጉዟቸውንም ""የሞኝ ሥራ"" ብለውታል። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ እንዳሉት ""የፋይናንስ ሚኒስትሩ ሥልጣን መልቀቃቸው መንግሥታቸው ኃላፊነትን በአግባቡ የማይወጡ ሰዎችን እንደማይምር ማሳያ ነው"" ብለዋል። በካናዳ ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት የኦንታሪዬ ግዛት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ጠበቅ ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሏ ይታወቃል። የፕሮግረሲቭ ኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ አባል የሆኑት ሚኒስትር ሴይንት ባርትስ ወደ ተሰኘችው የካሬቢያን ደሴት ለሽርሽር የሄዱት በዚህ በታኅሣስ ወር ነው። በወቅቱ የኦንታሪዮ የጤና ባለሥልጣናት በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁትሩ በመጨመሩ ምክንያት ነዋሪዎች ከቤታቸው ንቅንቅ እንዳይሉ አዘው ነበር። ኦንታሪዮ ከቀናት በፊት እንደ አዲስ ጠበቅ ያለ የኮቪድ-19 ሕግ አውጥታለች። ባለፈው ሐሙስ ብቻ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከገባ በበሽታው የተያዙ ከፍተኛው የተባለው ቁጥር [3328] ተመዝግቧል። 56 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ በካናዳ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ582 ሺህ በላይ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 15 ሺህ 600 ደርሷል። ሚኒስትሩ ከሽርሽር ሲመለሱ ሥራቸውን ለመቀጠል አስበው የነበረ ቢሆንም የግዛቲቱ አስተዳደር ሥልጣናቸውን ቢለቁ የተሻለ እንደሆነ ነግረዋቸዋል። ""እንምታዩት በጣም ከባድ ስህተት ፈፅሜያለሁ። ተጠያቂ መሆን ደግሞ አለብኝ። መሄድ በሌለብኝ ወቅት ነው የተጓዝኩት። ምንም ምክንያት መደርደር አይጠበቅብኝም"" ብለዋል ስልጣናቸውን የለቀቁት ሚኒስትር። የኦንታሪዮ አስተዳዳሪ ሥልጣን በለቀቁት ሚኒስትር ምትክ ሌላ ሰው በጊዜያዊነት ሾመዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55505118 +sports ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ድልድሉን ተቀላቀለች በ2022 ኳታር ለምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በአፍሪካ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ ተካሂደዋል። ከቀናት በፊት በባህር ዳር ስታዲየም ከሌሴቶ አቻዋ ጋር ያለምንም ግብ የተለያየችው ኢትዮጵያ፤ የመልስ ጨዋታዋን በሌሴቶ አድርጋ አንድ አቻ ተለያይታለች። ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ህግ መሰረትም ወደቀጣዩ ዙር በማለፍ የምድብ ድልድል ውስጥ መግባቷን አረጋግጣለች። ሃያ ተጫዋቾችን ይዘው ወደ ሌሴቶ ያቀኑት አሰልጣኝ አብራሃም መብራቱ በተቻለ መጠን አጥቅቶ በመጫወት ከሜዳቸው ውጪ ግብ ለማስቆጠር እንደሚጥሩ ገልጸው ነበር። በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ተጠንቅቀው የተጫወቱ ሲሆን ዋልያዎቹ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ነበራቸው። ነገር ግን ብዙም የግብ ዕድሎችን መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። በአንጻሩ ሁለተኛው አጋማሽ ፈጣንና ብዙ የግብ ሙከራዎች የታዩበት ነበር። 50ኛው ደቂቃ ላይ በቀኝ መስመር የሚጫወተው ቢንያም በላይ ያሻማውን ኳስ የሌሴቶው ንካይ ኔትሮሊ ሲመልሰው ኳሷ አቅጣጫዋን ቀይራ በራሱ መረብ ላይ ግብ አስቆጥሮ ኢትዮጵያ መምራት ጀመረች። ነገር ግን ከአምስት ደቆቃዎች በኋላ ሌሴቶዎች አቻ የምታደርጋቸውን ግብ በሴፖ ሴትሩማንግ አማካይነት ማግኘት ችለዋል። ጨዋታው በዚሁ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ቢጠናቀቅም ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ኢትዮጵያ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ አሥመራ ላይ ናሚቢያን አስተናግዳ በደጋፊዎቿ ፊት 2ለ1 የተሸነፈችው ኤርትራ ደግሞ የመልስ ጨዋታዋን የፊታችን ማክሰኞ ���ንድሆክ ላይ ታደርጋለች። • ሳሙኤል ኤቶ እግር ኳስ ሊያቆም ነው • 'አምብሮ' ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር የአቅርቦት ውል ተፈራረመ ባለፈው ሐሙስ 1ለ0 በሆነ ጠባብ ውጤት ዚምባብዌን በማሸነፍ አስደናቂ ድል ያስመዘገቡት የሶማሊያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች፤ ለሁለተኛው ዙር ጨዋታ የፊታችን ማክሰኞ ወደ ሃራሬ ያቀናሉ። በሌላ በኩል ከአርብ ጀምሮ የአውሮፓ ቻምፒየንሺፕ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ተከሂደዋል። በዚህም መሰረት ሆላንድ ጀርመንን 4 ለ2 በማሸነፍ ጥሩ አጀማመር ያደረገች ሲሆን ቤልጂየም ሳን ማሪኖን 4 ለምንም አሸንፋለች። ክሮሺያም በተመሳሳይ ስሎቫኪያን 4 ለምንም ፤ አውስትራሊያ ደግሞ ላቲቪያን 6 ለባዶ ረምርማለች። ቅዳሜ በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ እንግሊዝ ቡልጋሪያን 4 ለምንም፣ ፖርቹጋል ሰርቢያን 4 ለ2 እንዲሁም ፈረንሳይ አልባኒያን 4 ለ1 ማሸነፍ ችለዋል። ዕሁድ በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ ጣልያን ፊንላንድን 2 ለ1 ፣ ስፔን ፋሮ አይላንድስን 4 ለምንም ሲያሸንፉ ጆርጂያና ዴንማርክ 0 ለ0 እንዲሁም ስዊድን እና ኖርዌይ 1 ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። https://www.bbc.com/amharic/49625537 +business ሲሪላንካ ወሳኝ ላልሆኑ አገልግሎቶች ነዳጅ መሸጥ አቆመች "በአስር ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ እያጋጠማት የምትገኘው ሲሪላንካ ወሳኝ ላልሆኑ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ መሸጥን አቁማለች። በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ለህክምና አገልግሎት እና ምግብ ለማጓጓዝ የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች፣ አውቶቡሶች፣ ባቡሮች እና ተሽከርካሪዎች ብቻ ነዳጅ እንዲሞሉ ተፈቅዶላቸዋል። መንግሥት በከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ያደረገ ሲሆን፣ የአገሪቱ 22 ሚሊዮን ነዋሪዎች ከቤት እንዲሠሩ በባለሥልጣናት ተነግሯቸዋል። የደቡብ እስያዋ አገር እንደ ነዳጅ እና ምግብ ያሉ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች ክፍያ ለመፈጸም የሚያስችላትን ገንዘብ ለማግኘት እየተነጋገረች ነው። “በ1970ዎቹ የነዳጅ ቀውስ ተፈጥሮ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ያለውን ፍላጎት ለመቀነስ የተሽከርካሪዎች የፍጥነት ገደብ እና የኮታ አቅርቦት ከተዋወቀ ወዲህ ስሪላንካ ለተራው ሰው የነዳጅ ሽያጭን በማስቆም ከባድ እርምጃ የወሰደች የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች” ሲሉ በኢንቨስቴክ የጋዝና ነዳጅ ምርምር ኃላፊው ናታን ፓይፐር ለቢቢሲ ተናግረዋል። እገዳው በሲሪላንካ ያለውን ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና የውጭ ምንዛሪ ክምችት ውስን መሆኑን በግልጽ አሳይቷል። ብዙዎቹ የደሴቲቱ ነዋሪዎች ያለ ነዳጅ ኑሯቸውን እንዴት እንደሚገፉ ግራ ተጋብተዋል። ለወራት በስሪላንካ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ረዣዥም ሰልፎች ይታዩ ነበር። በዋና ከተማዋ ኮሎምቦ የታክሲ አሸከርካሪ የሆነው የ29 ዓመቱ ቺንታካ ኩማራ እገዳው “በሰዎች ላይ የበለጠ ችግር ይፈጥራል” ብሎ ያስባል። ለቢቢሲ ሃሳቡን ሲገልጽ “እኔ የቀን ደሞዝተኛ ነኝ። ወረፋ ይዤ ለሦስት ቀናት ቆይቻለሁ። መቼ ቤንዚን እንደማገኝ አላውቅም"" ብሏል። አሽከርካሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ የተነገረ ሲሆን የቀረ የነዳጅ ክምች ካለ ይከፋፈላል በሚል ቁጥር ተሰጥቷቸዋል። አንዳንዶቹ መሰለፋቸውን ቢቀጥሉም ሌሎች ግን ተመልሰዋል። የ52 ዓመቱ ኤስ ዊጄቱንጋ በበኩላቸው ""ለሁለት ቀናት ወረፋ ይዤ ነበር። 11 ቁጥር ተሰጥቶኛል ግን ነዳጅ መቼ እንደምወስድ አላውቅም” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""አሁን ወደ ሥራ መሄድ ስላለብኝ ተሽከርካሪዬን እዚህ ትቼ በባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ከመሄድ ውጪ ምንም አማራጭ የለኝም"" ብለዋል። ኮሎምቦ ውስጥ ኮታሄና በሚባለው መንደር ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪ ያለው ኬናት እንደ እሱ ያሉ ሰዎች “ይበልጥ መጎዳታቸውን” ገልጿል። ""ቤተሰባችን በቀን ሦስ�� ጊዜ ይመገብ ነበር። አሁን የምንበላው በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ ነው። በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ አንድ ጊዜ ወደ መብላት ይወርዳል"" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ""ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ"" በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት የኢኮኖሚ ቀውስ ሌላ የነደዳጅ ዋጋ መጨመር እና የታክስ ቅነሳ መደረጋቸው ተደማምረው ስሪላንካ አስፈላጊ ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የሚያስችላትን በቂ የውጭ ምንዛሪ እንድታጣ ምክንያት ሆኗል። ከፍተኛ የነዳጅ፣ የምግብ እና የመድኃኒት እጥረት የአገሪቱን የኑሮ ውድነት እንዲንር አድርጎታል። ብዙዎች ገቢያቸውን ከግል ሞተር ሳይክሎቻቸው ያገኛሉ። ሰኞ ዕለት የአገሪቱ መንግሥት እስከ ሐምሌ 10 ድረስ የግል ተሽከርካሪዎች ቤንዚን እና ናፍታ እንዳይገዙ እንደሚከለክል ተናግሯል። የአገሪቱ ካቢኔ ቃል አቀባይ ባንዱላ ጉኔዋርዴና በበኩላቸው ስሪላንካ “በታሪኳ እንደዚህ ያለ ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ገጥሟት አያውቅም” ብለዋል። በገንዘብ ችግር የተሸበሸበችው አገር ርካሽ የነዳጅ አቅርቦት ለማግኘት ባለሥልጣናትን ወደ ነዳጅ አምራቾቹ ሩሲያ እና ኳታር ልካለች። በሳምንቱ መጨረሻ ባለሥልጣናቱ እንዳስታወቁት፣ በአገሪቱ በመጪዎቹ ቀናት አስፈላጊ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል 9,000 ቶን ናፍጣ እና 6,000 ቶን ቤንዚን ብቻ ነው ያለው። ክምችቱ በመደበኛ መንገድ ከተሰራጨ ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚያልቅ ተገምቷል. የኃይል እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ካንቻና ዊጄሴኬራ እሑድ ዕለት ለጋዜጠኞች “ተጨማሪ ክምችት ለማግኘት የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው። ይህ መቼ እንደሚሆን ግን አናውቅም” ሲሉ ተናግረዋል። አገሪቱ በግንቦት ወር በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለም አቀፍ አበዳሪዎች መክፈል ያለባትን ዕዳ ሳትከፍል ቀርታለች። ይህም በፕሬዚዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ መንግሥት ላይ ለሳምንታት የዘለቀውን ተቃውሞ ተከትሎ የተፈጠረ ነበር። የፕሬዝዳንቱ ወንድም ማሂንዳ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ቦታ ለቀዋል። ፕሬዝዳንቱ አሁንም ሥልጣን እንዲለቁ ግፊት እየተደረገባቸው ነው። በዋና ከተማው ነዳጅ ለመግዛት የሚጠባበቀው ካናን የተባለ አሸክርካሪ “መንግሥት ምንም ዓይነት እርምጃ የሚወሰድ አይመስልም” ሲል ለቢቢሲ ታሚል ተናግሯል። “እንድንታገስ እየጠየቁን ነው። ዶላር የለንም ይላሉ። እኔ ግን ለዚህ ተጠያቂው ማነው? ስል መንግሥትን እጠይቃለሁ” ብሏል። በምትኩ ""የተማሩ ወጣቶች"" አገሪቱን መምራት እንዳለባቸው ጠቁሟል። ባለፈው ሳምንት የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ቡድን በሦስት ቢሊዮን ዶላር  የእርዳታ ስምምነት ላይ ለመነጋገር ወደ ሲሪላንካ አቅንቶ ነበር። መንግሥትም አስፈላጊ እቃዎች ለማስገባት ከሕንድ እና ቻይና እርዳታ እየጠየቀ ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ራኒል ዊክሬሜሲንጌ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ እንደገለጹት እንደ ምግብ፣ ነዳጅ እና ማዳበሪያ ላሉ አስፈላጊ ዕቃዎች ለመክፈል አገሪቱ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ቢያንስ 5 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል። የምግብ እጥረት ሊከሰት ይችላል በሚልም ባለፉት ሳምንታት ሚኒስትሮች ገበሬዎች ብዙ ሩዝ እንዲያመርቱ ጠይቀዋል። መንግሥት በሲሪላንካ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከሚያስገኙት አንዱ የሆነው የቱሪስት ዘርፍ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መጎዳቱን ለቀውሱ ተጠያቂ አድርጓል። ብዙ ባለሙያዎች ግን የመልካም አስተዳደር እጦት ለኢኮኖሚው ውድቀት ዋነኛው መንስኤ ነው ይላሉ።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2rdzdnevro +health ጤና፡ የወጣቶች የወገብ ህመም መንስዔ እና መፍትሔው "አሁን አሁን የወገብ ህመም አጋጥሟቸው የህክምና ተቋማትን የሚጎበኙ ወጣቶች እየተበራከቱ ነው። በተለይ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ለወገብ ህመም የሚጋለጡ ወጣቶች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጥናቶች ያመለክታሉ። ለመሆኑ ለዚህ መንስዔው ምንድን ነው? መፍትሔውስ? በዚህ ላይ በፓራጎን የፊዚዮቴራፒና ስፓርት ህክምና ስፔሻሊቲ ልዩ ክሊኒኮች ውስጥ ሥራ አስኪያጅ እና ሜዲካል ዳሬክተር ከሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ ወ/ገብርኤል ጋር ቆይታ አድርገናል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ሦስቱንም ድግሪያቸውን የተከታተሉት በአሜሪካ ሲሆን በፊዚዮቴራፒ በተለይ በስፖርት ህክምና እና ኦርቶፔዲክስ ህክምና ዶክትሬታቸውን አግኝተዋል። በሙያቸው በአሜሪካ ለ10 ዓመታት የሰሩ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ላለፉት 12 ዓመታት እያገለገሉ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት ውስጥ ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው። በጥቁር አንበሳ ህክምና ትምህርት ቤት በፊዚዮቴራፒ ዶክትሬት ፕሮግራም በመምህርነት ሠርተዋል። ብዙውን ጊዜ ወጣቶች ለወገብ ህመም ያጋለጣቸውን መንስዔ በውል አያውቁትም። እንዲሁ በደፈናው ድንገት አመመኝ ሲሉ ነው የሚሰማው። ለመሆኑ የወገብ ህመም መንስዔዎች ምንድን ናቸው? የሰውነት ማጎልመሻ እንቅስቃሴዎች፣ የምንጫማቸው ጫማዎች ፣ የምንተኛበት ፍራሽ ፣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈፀምበት መንገድ ( Sex position) . . . ለወገብ ህመም ይዳርጉ ይሆን? ወደዚህ ዝርዝር ከማለፋችን በፊት ስለወገብ እና የወገብ ህመም ምንነት እናንሳ። ወገብ ቀበቷችን ወይም መቀነታችን የሚያርፍበት የሰውነታችን ክፍል ሲሆን በዚህ ላይ የሚከሰት ህመም የወገብ ህመም ይባላል። የወገብ ህመም ጽንሰ ሃሳቡ ሰፊና ጥልቅ ቢሆንም በቀላል አገላለጽ በወገብ አካባቢ በሚገኙ ጡንቻዎች ፣ የነርቭ ሥሮች፣ የአከርካሪ አጥንቶች፣ የጎን አጥንቶች እና ጅማቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው። ይህ ጉዳት ጊዜያዊ ወይም ዘለቄታዊ ሊሆን ይችላል። የወገብ ህመም ዓይነቶች እንደ መንስዔያቸው ይለያያሉ። ዋና ዋናዎቹ ግን እነዚህ ናቸው፦ ከመጨረሻው ነጥብ እንጀምር። የሰውነት በሽታ ተዋጊ ሂደት በመዛበት የሚከሰተው የወገብ ህመም የሚያጋጥመው ሰውነት በሽታን የሚከላከልበት ሂደት ሌሎች የሰውነት አካላትን ሲያጠቃ ነው። በእንግሊዝኛ አጠራሩ Ankylosing spondylitis ይባላል። የሰውነት የውስጥ ቁስለትን በመፍጠር ዘለግ ላለ ጊዜ የሚቆይ ህመም ነው። የዚህ ህመም ምክንያቱ ምን እንደሆነ በውል አይታወቅም። በተለይ በመገጣጠሚያዎች እና በአከርካሪ አጥንቶች መጋጠሚያ መካከል ቁስለትን ያስከትላል። ህመሙ እየጨመረ ሲሄድም የአከርካሪ አጥንቶች እንዲንቀሳቀሱ እንደ ሃዲድ የሚያገለግለው የሰውነት ክፍል ላይ አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸውን ትተው እርስ በእርሳቸው እንዲጣበቁ ያደርጋል። በዚህ ምክንያት አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸው ቀርቶ አንድ አካል ይሆናሉ። በዚህ ህመም የተጠቃ ሰው ማጎንበስ፣ ወደ ኋላ አሊያም ወደ ጎን መንቀሳቀስ አይችልም። የሌሎቹ የወገብ ህመም ዓይነቶች መንስዔዎችስ? ለወገብ ህመም የሚዳርጉን መንስዔዎች በርካታ ቢሆኑም ዶ/ር ቴዎድሮስ በ21 ዓመት የህክምና ልምዳቸው የተመለከቷቸውንና ዋና ዋና ያሏቸውን መንስዔዎች ያስረዳሉ። ከባድ ነገር ማንሳት፡ ማንኛውም ሰው በዕለት ተዕለት ክንውኑ ጥንቃቄ ካላደረገ ወገቡን ሊታመም ይችላል። በባልዲ ውሃ ቀድቶ ፎቅ ላይ መውሰድ፣ ክብደት ያላቸውን ሰዎች ከአልጋ ማንሳት እንዲሁም ማንኛውንም ከአቅም በላይ የሆነ ክብደትን ማንሳት ለወገብ ህመም ሊዳርግ ይችላል። ከልክ በላይ የሆነ የሰውነት ክብደት መኖር፡ በተለይ በአንድ ጊዜ የሚጨምር የሰውነት ክብደት የወገብ ህመም እንደሚያስከትል ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። ""በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት አካላዊ እንቅስቃሴ የሌለው ሥራ በመዘውተሩ በዚህ ሳቢያ የሚከሰት ህመም ተበራክቶ ነበር"" ይላሉ። ረዘም ላለ ጊዜ ቆሞ፣ ተቀምጦ ወይም ቆሞ ጎንበስ ብሎ መስራት፡ ረዘም ላለ ጊዜ ቆመው፣ ተቀምጠው አልያም ቆመው ከአንገታቸው ተጎንብሰው በሚሰሩ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለወገብ ህመም የመጋለጣቸው ዕድል ሰፊ ነው። ዶ/ር ቴዎድሮስ አንድ ሰው ቆሞ ከአንገቱ ጎንበስ ብሎ በሚሰራበት ጊዜ በሁለት አከርካሪ አጥንቶች መካከል ወደ 270 ኪሎ ግራም ግፊት እንዳለው ጥናቶችን ያጣቅሳሉ። ይህን በየቀኑ ማድረግ ደግሞ ከጊዜ በኋላ የከፋ ጉዳት ያስከትላል። ብዙ ጊዜ የቀዶ ህክምና ሐኪሞች በዚህ ሳቢያ ለሚከሰት የወገብ ህመም ሲጋለጡ ይስተዋላል። ብዙ መንገጫገጭ ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር፡ ብዙ ንዝረት ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር ወይም ምቹ ባልሆኑ መንገዶች ላይ መኪና ማሽከርከር ከጊዜ በኋላ የወገብ ህመም ያስከትላል። የዝላይ እና የሩጫ እንቅስቃሴዎች፡ በተለይ ከልክ በላይ የሰውነት ክብደት ያላቸው ሰዎች ሩጫ ወይም የመዝለል እንቅስቃሴ የሚያዘወትሩ ከሆነ ወገባቸው ሊጎዳ ይችላል። እንደ አስፓልት ያለ ጠንካራ የሆነ ቦታ ላይ የሚሮጡ ሰዎችም መሬቱ ላይ እግራቸውን በጣሉ ቁጥር መሬትም በአጸፋው ስለሚመታቸው ለጉዳት ሊዳርጋቸው ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ወጣ ገባ የሆነ መሬት ላይ የሚሮጡ ሰዎች እግራቸው በሚያርፍበት ሰዓት ሚዛናቸው እኩል ስለማይሆን ወገብ ላይ ጫና ይፈጠራል። ሰውነት ሳይለምድ በአንድ ጊዜ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት፡ አሁን አሁን በወጣቶች ዘንድ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እየተለመደ መጥቷል። የሚሰሯቸው እንቅስቃሴዎችንም ዩቲዩብ በማየት የሚመርጡም አሉ። ይህ ብቻም ሳይሆን ስፖርቱን ለምን ዓላማ እንደሚሰሩ የማያውቁ በርካቶች ናቸው። በዚህ ሳቢያ ተጎድተው ወደ ክሊኒካቸው የሚመጡ ወጣቶች መኖራቸውን ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። ""ችግሩ አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ የተከሰተ ሳይሆን ሰውነት ሳይለማመድ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት ነው"" ይላሉ። ""ጂምናዚየም ውስጥ ለአሰልጣኝ ጉርሻ መስጠት የተለመደ ሆኗል"" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳንድ አሰልጣኞች ጉርሻዋን ለማግኘት ደንበኞቻቸው የሚፈልጉት የሰውነት ለውጥ ላይ ቶሎ ማድረስ ላይ ብቻ ትኩረት እንደሚያደርጉ ይናገራሉ። አሰልጣኞቹ ስለስፖርታዊ እንቅስቃሴው እንጂ ስለጤና እውቀት ላይኖራቸውም ይችላል። አንዳንድ ሰልጣኞችም በአንድ ጊዜ በሰውነታቸው ላይ የሚፈልጉት ለውጥ እንዲመጣ ባልተገባ መልኩ ከልክ በላይ የሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ ይህንን ሲገልጹት ""ምንም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጎ የማያውቅ ሰው ቅዳሜ እና እሁድ ጂምናዚየም ገብቶ አገር ይያዝልኝ እንደ ማለት ነው"" ይላሉ። ዲስክ መንሸራተት፡ የዲስክ መንሽራተት ስሙ ለብዙዎቻችን ጆሮ እንግዳ አይደለም። ዶ/ር ቴዎድሮስም የዲስክ መንሸራተት ያለ ስሙ ብዙ ስም የተሰጠው በሽታ ነው ይላሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ እንደሚሉት የዲስክ ችግር ተብለው ወደ ክሊኒካቸው ከሚመጡት 100 ሰዎች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ችግራቸው ሌላ ነው። በተለምዶ የህክምና ባለሙያዎች ህሙማንን ለዲስክ መንሸራተት ተዳርገዋል የሚሉት 'ኤምአርአይ' መመርመሪያ የሚያሳየው ውጤት ላይ ተመርኩዘው ነው። ይሁን እንጂ ዶ/ር ቴዎድሮስ ""10 ሰዎችን እንዲሁ ከመንገድ ላይ በግምት ተመርጠው ኤምአርአይ ቢነሱ ቢያንስ 7ቱ የዲስክ መንሸራተት ሊያሳዩ ይችላሉ"" ይላሉ። ይህ ማለት ግን ህመም አለባቸው ማለት አይደለም። ""የዲስክ መንሸራተት ታይቷል ማለት የተዛባ ዲስክ አላቸው፤ ግን ዲስኩ ነርቩን ጨፍልቆ ህመም የሚያመጣበት ደረጃ ላይ አይደለም ማለት ነው"" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። በዚህ የምርመራ ውጤት ላይ ተመስርተው ቶሎ ቀዶ ህክምና አድርጉ ወደሚል ድምዳሜ የሚደርሱ የህክምና ባለሙያዎች መኖራቸውን የሚናገሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ ይህ ግን ስህተት ነው ብለዋል። ለመሆኑ ዲስክ ምንድን ነው? የሚገኘውስ የት ላይ ነው? ዲስክ በአከርካሪ አጥንቶች መካከል የሚገኝ በውስጡ ፈሳሽ ያለው ለስላሳ የሆነ እንደ ጎሚኒ (ሾክ አብሶርቨር) የምንጠቀምበት የአካል ክፍል ነው። ታዲያ ሰውነታችን ጫና በሚበዛበት ጊዜ በዲስኩ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ሊወጣ ይችላል ወይም ደግሞ ፈሳሹ ሳይወጣ ዲስኩ ወደ አንድ በኩል አመዝኖ መውጣት ወደማይገባበት ቦታ ሊወጣ ይችላል። ዲስክ ያለበት አካባቢ የተጨናነቀ በመሆኑ አፈትልኮ በሚወጣበት ጊዜ ከጭንቅላታችን በሚወርደውና ህብለ ሰረሰር በሚባለው የነርቭ ግንድ እና ቅርንጫፎች ላይ በመተኛት ጫና ይፈጥራል። የዲስክ መንሸራተት በሚያጋጥምበት ጊዜ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ከመጣደፍ በፊት ዲስኩ ተንሸራቶ ምን ሆነ? ወዴት አቅጣጫ ነው የተንሸራተተው? ምን ያህል ነው የተንሸራተተው? እየነካ ያለውስ ነርቭ የትኛውን ነው? ሊያስከትል የሚችለው የህመም ስሜት አለ ወይ? የሚሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር ቴዎድሮስ ያሰምሩበታል። ወጣቶችን ለወገብ ህመም የሚያጋልጣቸው የተለየ ምክንያት ይኖር ይሆን? ከምንጊዜውም በላይ ብዙ ወጣቶች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ እየተሠማሩ መሆናቸው አንዱ ምክንያት ነው ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ወጣቶች ረዘም ያለ ጊዜ መቆምን፣ መቀመጥን አሊያም ጎንበስ ብሎ መቆምን እንዲሁም ከባድ ነገር ማንሳትን፣ መሸከምን የሚጠይቁ ሥራዎችን ይሠራሉ። በሌላም በኩል ከዚህ ቀደሙ በተሻለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተርም ሌላኛው ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። ""ስለምንሰራው አካላዊ እንቅስቃሴ ጠለቅ ያለ እውቀት ከሌለን በስተቀር የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ጥቅም እንዳላቸው ሁሉ ጉዳት አላቸው።"" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። በተቃራኒው ደግሞ የሰውነት እንቅስቃሴ ማነስ ለወገብ ህመም መንስዔ ነው። የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለወገብ ህመም ያጋልጣል? የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሳይንስ እንደ ወገብ ህመም መንስዔነት ወይም እንደ ወገብ ህመም መነሻነት አይታወቅም ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ይሁን እንጂ የወገብ ህመም ያለባቸው ሰዎች የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙበት መንገድ ህመማቸውን ሊያባብስባቸው ወይም የተሻላቸውን ህመም እንደገና ሊያስነሳባቸው እንደሚችል ይናገራሉ። ""በተለይ በሴቶች ዘንድ ይህንን ለሐኪም የማስረዳት ልምድ የለም"" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳንዶች ግን በስልክም ቢሆን ምክር የሚጠይቁ መኖራቸውን አልሸሸጉም። ""እንደ የወገብ ህመማቸው ዓይነትም ለተወሰነ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደራረግ (Sex position) እንዲቀይሩ፣ እንዳያደርጉ ወይም ሊያደርጓቸው ስለሚችሉ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደራረግ ዓይነቶች ምክር የሚሰጣቸው ታማሚዎች አሉ"" ይላሉ። የምንጫማው ጫማስ? የወገባችንን ጤንነት ለመጠበቅ የምንጫማው የጫማ ዓይነት ወሳኝነት አለው። ይህ ግን በአብዛኛው የሚገናኘው ከሴቶች ጋር ነው። ምክንያቱም በተለይ በፋሽንና መዝናኛ ኢንደስትሪው ሴቶች መንቀሳቀስ እስከሚቸገሩ ድረስ ረጃጅም ታኮ ያላቸውን ጫማዎች ተጫምተው ማየት የተለመደ ነው። ይህ ደግሞ በሰውነት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። እንዴት? ዶ/ር ቴዎድሮስ ለዚህ ሳይንሳዊ ምላሽ አላቸው። ሰውነት የራሱን ሚዛን የሚጠብቅበት መንገድ አለው። ይህ የስበት ማዕከል (Center of gravity) ይባላል። ስንራመድ የማንወድቀው ወይም ደግሞ ቁጭ ብለን ስንነሳ ከግድግዳ ጋር የማንጋጨው ይህ የመሬት ስበት ማዕከል ���ዛናችንን ስለሚጠብቅልን ነው። ታዲያ ከፍ ያሉ ታኮዎች ያሏቸውን ጫማዎች ስንጫማ ሰውነት ተፈጥሯዊ የሆነውን የሰውነት ሚዛን ይለቃል። የሰውነታችን የመሬት ስበት ማዕከልም ይቀየራል። በመሆኑም ሰውነት ይህንን የስበት ማዕከል መልሶ ወደ ማዕከሉ ላይ ለማምጣት (ሚዛኑን ለመጠበቅ) የሚያደርጋቸው ማስተካከያዎች ወገብ ላይ ጫና ይፈጥራሉ። ጫናው ወገብ ላይ ብቻ ሳይሆን ጉልበት፣ እግርና የእግር መዳፍ ላይም ነው። ከዓመታት በፊት በዩናይትድ ኪንግደም በፖዲያትሪ ኮሌጅ የተሠራ ጥናት ሴቶች ህመም እንደተሰማቸው ሳይናገሩ ከፍ ያለ ታኮ ጫማ ተጫምተው መቆየት የሚችሉት በአማካይ ለአንድ ሰዓት ያህል ነው ይላል። በዚህ ጥናት ተሳታፊ የነበሩ ሴቶች ጫማውን ከተጫመቱ ከ10 ደቂቃ በኋላ በእግራቸው ላይ ህመም እንደተሰማቸው ተናግረዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሰው የተፈጠረው በባዶ እግሩ ለመሄድ ነው በማለት ሰዎች በባዶ እግራቸው እንዲሄዱ የሚያበረታታ ሳይንስ አለ። በዚህም ምክንያት ሆነ ብለው በባዶ እግራቸው የሚሄዱ ሰዎች አሉ። በእርግጥ ዶ/ር ቴዎድሮስ በባዶ እግር መሄድ አሊያም በጣም አነስተኛ ታኮ ያላቸው ጫማዎች ማድረግ ጉዳት አለው ብለው አያምኑም። ይሁን እንጂ በተፈጥሮ 'የእግራቸው ቅርጽ ለየት ያለ' ሰዎች ከተረከዝ ሁለት ሴንቲ ሜትር ከፍ ያለ ታኮ ያለው ጫማ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። ""ተረከዝ በጫማ መሄድ ከለመደ በኋላ በባዶ እግር በብዛት መሄድ በተረከዝ ላይ አጥንት መብቀልን (Bone Spur) ሊያስከትልም ይችላል"" ይላሉ። ይህ አጥንት የተረከዝን ስጋ እንደ ጩቤ የሚወጋ ነው። በመሆኑም በተለይ በባዶ እግር መሄድ ያልለመደ እና ተረከዝ ላይ በቂ የስብ ንጣፍ (Fat pad) የሌለው ሰው በባዶ እግሩ ቢሄድ ለእንዲህ ዓይነት ችግር ሊጋለጥ እንደሚችል ያሳስባሉ። ይህ ግን በስፋት የሚከሰት አይደለም። የወገብ ህመም እንዳጋጠመን እንዴት ማወቅ እንችላለን? እንደማንኛውም ህመም የወገብ ህመም ሲያጋጥም የሚታዩ ከቀላል እስከ ከባድ ምልክቶች አሉ። የህመም ማስታገሻ መድሃኒት የማያስወስዱ፣ ቁጭ ስንል የሚያስታውሱን፣ መድሃኒት እስከ መውሰድ የሚያደርስ የማቃጠልና መቆጥቆጥ ስሜት፣ ጎንበስ ብሎ ቀና ለማለት መቸገር፣ ለመነሳት ድጋፍ መፈለግ፣ የጡንቻ መኮማተር፣ ለመንቀሳቀስ መቸገር፣ ተኝቶ ለመገላበጥ ማቃት የተወሰኑት ምልክቶቹ ናቸው። የሚታዩት ምልክቶች ግን እንደ ህመሙ መንስዔዎች ይለያያሉ። ለምሳሌ ረዘም ላለጊዜ በመቆም ወይም በመቀመጥ የሚመጣ ህመም ከሆነ ተቀምጠን ቆይተን ድንገት ስንነሳ የሰውነት መያዝ ፣ ስንቀመጥ ወይ ስንቆም ህመም መሰማት፣ የመቀመጫ አካባቢ ህመም፣ መጠዝጠዝና ንዝረት ያጋጥማል። ንዝረቱ ከመቀመጫ አለፍ ብሎ ቁርጭምጭሚት ፣ ጣቶች እና የእግር መዳፍ ድረስ የሚሰማ የመደንዘዝና የማቃጠል ህመሞች እየባሰ ሲመጣም የእግር መክዳትና ደረጃ ለመውጣት አቅም እስከማጣት ሊደርስ ይችላል። እግርን ማዘዝ፣ ጣቶችን ወደ ላይ ቀና ማድረግ ካቃተን ግን ህመሙ የከፋ ደረጃ ደርሷል ማለት ነው። ምን አልባት ይህ ቀዶ ሕክምና የሚያስፈልግበት ደረጃ ሊሆን ይችላል። ያጋጠመንን የወገብ ህመም ለማስታገስ በቤት ውስጥ ምን ማድረግ እንችላለን? በአቅራብያ የህክምና ተቋም ከሌለ ለጊዜው የህመም ማስታገሻዎችን መውሰድ ይመከራል። ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን ሌላ የሚወስዱት መድሃኒት ከሌለ እና ከሚወስዱት መድሃኒት ጋር የማይጋጭ ከሆነ ነው። ዘላቂ መፍትሔ ግን አይደለም። የወገብ ህመሙ የተከሰተው በድንገተኛ አደጋ [መውደቅ] ከሆነ ደግሞ በመጀመሪያ ህክምና እርዳታ በረዶ ማድረግ ጥሩ ነው። ""የቁስለት ሂደቱን ለመቀነስ፣ እብጠት እና ውስጥ የደም መፍሰስ እንዳይኖር ይረዳል"" ይ��ሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ከዚህ በኋላም የጡንቻ መኮማተር የሚኖር ከሆነ ሙቀት ሰውነትን የማፍታታት ባህርይ ስላለው ሙቀት ማድረግ የተሻለ መሆኑን ይመክራሉ። እረፍት ማድረግም ህመማችንን በተወሰነ ደረጃ ሊያስታግስልን ይችላል። ይህን ሁሉ አድርገን የማይሻል ከሆነ ግን ሥር ሳይሰድ እንደ ምንም ወደ ህክምና ቦታ ሄዶ ትክክለኛ ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው። ""አንዳንድ ሰዎች ባህላዊ ቦታ ሄደው ባልተገባ ሁኔታ ህክምና ወስደው ተጎድተው የሚመጡ አሉ"" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። እንደዚህ ያሉ ቦታዎችን ከሚያዘወትሩ ሰዎች መካከል የተማሩ ሰዎችም ጭምር እንደሚገኙበት በመግለጽም ይህ ተገቢ አለመሆኑን ይናገራሉ። ህመሙን ለማስወገድ ሲባል ያልተገባ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግም ጉዳቱን ሊያባብሰው እንደሚችል ዶ/ር ቴዎድሮስ ያስጠነቅቃሉ። ወገባችንን በህክምና ቀበቶ ወይም በመቀነት ብንደግፈውስ? የወገብ ህመም የተለያዩ ደረጃዎች አሉት። መጀመሪያ አካባቢ ችግሩ እንደተፈጠረ፣ ከዚያ ከሁለት እስከ ሦስት ወር እና ከሦስት ወር በላይ የቆየ ህመም ናቸው። ህመሙ ከሦስት ወር በላይ የቆየ ከሆነ ሥር የሰደደ ችግር ይባላል። በመሆኑም ህመሙ እንደ ጀመረ አካባቢ እረፍት ማድረግን ጨምሮ በመቀነት ማሰር ወይም በቀበቶ መደገፍ ያገዘን ስለሚመስል በሥነ ልቦናም ሆነ አካላዊ በሆነ መልኩ ሊደገፍ ይችላል ይላሉ- ዶ/ር ቴዎድሮስ። ሆኖም ይህ ለረዥም ጊዜ የሚደረግ ከሆነ ችግር እንደሚያስከትል ይናገራሉ። ምክንያታቸውን ሲያስረዱም ""ቀበቶ ተደረገ ወይም መቀነት ታሰረ ማለት እዚያ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች እረፍት ወጡ ማለት ነው።"" ይላሉ። በዚህ ሳቢያም የጡንቻ መክሳት ችግር ይከሰታል። በመሆኑም ጡንቻችን ያለ ድጋፍ ሥራውን መሥራት ይቀንሳል፤ አልያም ያቆማል። ይህም ሰዎች በቀበቶ አሊያም በመቀነት ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። ""በኢትዮጵያ በህክምና ባለሙያዎች ዘንድ የአንገት መደገፊያ [ኮላር] እና የወገብ መደገፊያ ቀበቶ የማዘዝ ችግር ጎልቶ እየታየ ነው"" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የችግሩ መንስዔ ሳይታወቅ እነዚህን ቁሶች ማዘዝ ተገቢ እንዳልሆነ ይናገራሉ። አንዳንድ ጊዜ ሐኪሞች ቀበቶ ማዘዛቸውን ሊዘነጉት የሚችሉበት አጋጣሚም ስለሚኖር ታማሚዎቹ ለረዥም ጊዜ ቀበቶውን ሊያደርጉት ይችላሉ። ይህ ደግሞ ጉዳት ያስከትላል ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ምን ዓይነት ፍራሽ እና ትራስ ላይ እንተኛ ? መቼም በወገብ ህመም ሳቢያ ፍራሽ ያልቀያየረ፤ ከአልጋ መደብ ፣ ከመደብ አልጋ ያላለ አይኖርም። ትራስም ቢሆን እንዲሁ። ምን ዓይነት ፍራሽ ላይ እንተኛ ? ምን አይነት ትራስ እንጠቀም የበርካቶች ጭንቀት ነው። ለወገብ ህመም ፍቱን ናቸው የተባሉ ፍራሾችም ይቸበቸባሉ። በሰለጠነው ዓለም የተለያዩ ዓይነት ዘመናዊ ፍራሽና ትራሶች እየተመረቱ ነው። በአንድ አልጋ ላይ ባልና ሚስትን በመረጡት ፍራሽ ላይ የሚያስተኛ ቴክኖሎጂም ተፈልስፏል። ታዲያ የትኛው ላይ ብንተኛ የተሻለ ነው? ዶ/ር ቴዎድሮስ ""ታማሚዎቹ ተመቸን ያሉትን ፍራሽ ትክክል አይደለም ማለት አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም ሰውነታቸው ከመረጡት ፍራሽ ጋር ተመቻችቶ ሊሆን ይችላል"" ይላሉ። ቢሆንም ግን ደረቅ ፍራሽ ላይ መተኛትን አይመክሩም። እርሳቸው የሚመክሩት ሰውነት ቅርጹን በጠበቀ መልኩ የሚያሳርፍን ፍራሽ ወይም ትራስ ነው። ""ራቁታችንን በመስታዎት ብንመለከት ሰውነታችን እጥፋቶች (Curves) አሉት። ስንተኛ እነዚያ እጥፋቶች ቅርጻቸውን ጠብቀው በትክክል ማረፍ አለባቸው"" ይላሉ። ለዚህም ነው በሰለጠነው ዓለም 'ሚሞሪ ፎም' የተመረተው። ሚሞሪ ፎም ስንተኛ የሰውነትን ቅርጽ ይዞ ስንነሳ ወደ ነበረበት መመለስ የሚችል ፍራሽ ነው። 'ስሊፕ ነምበር ቤድ' የሚባልም ባልና ሚስት አልጋቸውን ሳይለዩ ለየራሳቸው የሰውነት ቅርጽ በሚመቻቸው መልኩ ማስተካከል የሚችሉት ሳይንሳዊ ፍራሽም ተሰርቷል። በኢትዮጵያ ለወገብ ህመም ተብለው የሚሸጡ ፍራሾችስ? ዶ/ር ቴዎድሮስ እነዚህ ፍራሾች ሳይንሳዊ አይደሉም ይላሉ። ""ሱቅ የተሰቀለን ልብስ በግምት አንስቶ ግባ ብሎ እንደመታገል ነው"" ሲሉም በምሳሌ ያስረዳሉ። ""በሰለጠነው ዓለም 30 ደቂቃ ፍራሹ ላይ እረፍት ወስደን ነው ፍራሽ የምንገዛው"" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ በኢትዮጵያ አንዳንድ መሸጫዎች ውስጥ 'ፍራሾቹ ላይ መተኛት ክልክል ነው!' የሚልም ማስታወቂያ በመለጠፍ ምቾቱን ሞክሮ ለመግዛት የሚደረገውን ክልከላንም ተችተዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ትራስን በተመለከተም ተመሳሳይ ሃሳብ ነው ያላቸው። ትራስ በጭንቅላታችን እና በአንገታችን ሥር መካከል ያለውን ክፍተት የሚሞላ መሆን አለበት ይላሉ። ነገር ግን ሰዎች ትራሳቸውን በአግባቡ ሲጠቀሙበት አይስተዋልም። በእርግጥ የሚመቸንንና ልካችንን ለማወቅ አዳጋች ነው። ገንዘባቸውን ትራስ በመግዛት የሚጨርሱም ጥቂት አይደሉም። ይህንን ችግር ለመፍታትም ይመስላል በሰለጠነው ዓለም 'ዎተር ፒሎው' [በውሃ የሚሞላ ትራስ] የተሰራው። ይህ የውሃውን መጠን በመቀነስ ወይም በመጨመር ትራሱን በልክ ለማሳነስና ለማተለቅ ያስችላል። በመሆኑም የምንጠቀመውን ትራስ ልክ ማወቅ እና በተገቢው መንገድ መጠቀም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ይመክራሉ። የአኗኗር ዘይቤያችን ምን ይምሰል? የሰውነት ክብደታችንን መቆጣጠር ወሳኝ ነው። ይህን ማድረጋችን ከወገብ ብቻም ሳይሆን ከሌሎች በሽታዎችም ራሳችንን ለመጠበቅ ያስችለናል። ""በሰውነታችን ላይ አንድ ኪሎ በጨመርን ቁጥር በእያንዳንዱ ኪሎ አንዱ ጉልበታችን ላይ 4 ኪሎ ጫና ይፈጠራል"" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የሰውነታችንን ክብደት መቆጣጠርን ቸል ልንለው እንደማይገባ ይመክራሉ። የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በአቅማችን ልክ እና ቀስ በቀስ በተደረገ የሰውነት ልምምድ መስራት ሌላኛው ነው። የውሃ ዋና እና በሳምንት ለአራት ወይም ለሦስት ቀናት ለ45 ደቂቃ ያህል በእግር ፈጠን ያለ እርምጃ መሄድም ጥሩ ነው። የሥራ ሁኔታን ምቹ ማድረግም አስፈላጊነቱ የሚያጠያይቅ አይደለም። ቆመው የሚሰሩ ሰዎች እቃ ሲያነሱ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለባቸው ማወቅ፣ የሚመች ጫማ ማድረግ እንዲሁም ብዙ የሚቆሙ ሰዎች አንድ እግራቸውን አንድ ነገር ላይ አሳርፈው (ሰቅለው) መቆም ለወገብ ህመም የመጋለጥ እድላቸውን ይቀንሳል። ከዚህም ባሻገር የወገብ ህመም መንስዔ ከሆኑ ድርጊቶች ራስን መጠበቅ እንደሚገባ ዶ/ር ቴዎድሮስ ይመክራሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-60278142 +sports በደማቅ መክፈቻ እና በሜዳ ላይ ውዝግብ የጀመረው የኳታር የዓለም ዋንጫ ኳታር ያዘጋጀችው የ2022 የዓለም ዋንጫ በአል-ባይት ስታዲም በድምቀት ተጀምሯል። አሜሪካዊው ፊልም ተዋናይ ሞርጋን ፍሪማን እና በዩቲዩብ ታዋቂነትን ያተረፈው ኳታራዊው ጋኒም አል-ሙፍታህ የመድረኩ ፈርጦች ነበሩ። የውድድሩ ዘፈን የሆነውን ድሪመርስ (ህልመኞቹ) የተሰኘውን ሙዚቃ ደቡብ ኮሪያዊው ፖፕ ኮከብ ጆንግ ኩክ እና የኳታሩ ፋሃድ አል ኩባሲ በስታዲየሙ ተገኝተው እየተቀባበሉ አቀንቅነዋል። ሞርጋን ፍሪማን በመከፍቻው ሥነ ሥርዓት ላይ እግር ኳስ ሰዎችን ለማቀራረብ ያለውን ኃይል ተርኳል። የዓለም ዋንጫ በመካከለኛው ምሥራቅ የሙስሊም አገር ሲዘጋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፣ ኳታር የሠራተኞችን መብት ጨምሮ በብዙ ጉዳዮች ስትብጠለጠል ቆይታለች። በድንኳን ቅርጽ በተሠራው ስታዲየም ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊን ጨምሮ የቱርክ፣ የግብፅ እና የአልጄሪያ መሪዎች ታድመዋል። ለ30 ደቂቃ የዘለቀው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በርችት ደምቆ በመጠናቀቅ ሜዳውን ለዓለም ዋንጫው መጀመሪያ ጨዋታ ለቋል። ኳታር የደቡብ አሜሪካዋን ኢኳዶርን አስተናገደች። የዳኛው ፊሽካ ከተሰማበት ቅጽበት ጀምሮ የኳታር ብሔራዊ ቡድን ተበልጦ አምሽቷል። በደቂቃዎች ውስጥ የኢኳዶሩ ኤነር ቫሌንሽያ ኳስን እና መረብን ማገናኘት ቻለ። በቪዲዮ ምስሎች ድጋፍ ረዳት ዳኞች ኳሱ ከጨዋታ ውጪ ነው በሚል ሽረውታል። እፎይታ ለኳታር። ይህ ጎል የተሻረበት መንገድ ትክክል ነው አይደለም በሚል በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መነጋጋሪያ ሆኗል። ነገሮች ግን አልተሻሻሉም። ቫሌንሽያ ከፍጹም ቅጣት ምት እና በጭንቅላት ባስቆጠራቸው ጎሎች ኢኳዶር ጨዋታውን 2 ለ 0 በመምራት ወደ መልበሻ ክፍል አመሩ። ከእረፍት መልስ ተጨማሪ ጎል ሳይቆጠር ጨዋታው ተጠናቀቀ። አሰልጣኝወ ሳንቼዝ ከጨዋታው በኋላ “ይህ የጠበቅነው ነገር አይደለም” ሲሉ ለስድስት ወር ካምፕ ገብተው ያደረጉትን ዝግጅት ውሃ እንደበላው ገለጹ። በመጀመሪያው አጋማሽ ብዙ ደጋፊዎች ሜዳውን ለቀው ወጥተዋል። ሳንቼዝ ተከፍቶ ከሜዳ ለወጣው የአገሬው ሰው በሚቀጥለው ጨዋታ “እንክሳችኋለን” ቢሉም ቀላል አይመስልም። በመጪው አርብ የአፍሪካ ሻምፒዮናዋ ሴኔጋልን ነው የሚገጥሙት። የምድቡን የመጨረሻ ጨዋታ ደግሞ ከብርቱካናማዎቹ ኔዘርላንድሶች ጋር። ኳታር በውዝግብ የጀመረችው የዓለም ዋንጫ በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ድምቀት የተሸፈነ ቢመስልም፣ ደጋፊዎች ሜዳ ውስጥ ባዩት ነገር አንገታቸውን ደፍተው ተመልሰዋል። የዓለም ዋንጫው ዛሬ በሚከናወኑ ሦስት ጨዋታዎች ይቀጥላል። በምድብ ለ ጨዋታዎች ውድድሩ ሲቀጥል አስር ሰዓት ላይ እንግሊዝ እና ኢራን ይጫወታሉ። በፖለቲካ ጉዳይ የሚቆራቆዙት ሁለቱ አገራት የሚያደርጉት ጨዋታ ከሜዳ ውጪ ባለው ጉዳይ ተጠባቂ ሆኗል። አህጉረ አፍሪካ ተወካይ ሴኔጋል በምድብ ሀ ከኔዘርላንድስ ጋር አንድ ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። በምድብ ለ ሁለተኛ ጨዋታ አሜሪካ እና ዌልስ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c1dg5g1zr5no +business ‘የክሪፕቶው ንጉሥ’ ሳም ባንክማን በባሃማስ በቁጥጥር ስር ዋለ ግዙፉ የክሪፕቶከረንሲ ልውውጥ ኩባንያ 'ኤፍቲኤክስ' መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ሳም ባንክማን ፍራይድ በባሃማስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። ኩባንያው መክሰሩን በቅርቡ በይፋ አውጆ ወጣቱ ቢሊየነር ከስልጣኑ ለቅቄያለሁ ማለቱ ይታወሳል። ‘የክሪፕቶው ንጉስ’ በባሃማስ በሚገኘው ፍርድ ቤት ማክሰኞ እለት እንደሚቀርብም ባለስልጣናቱ ገልጸዋል። ሳም ባንክማን በቁጥጥር ስር የዋለው የአሜሪካ እና የባሃማስ ህጎችን ተላልፎ “የፋይናንስ ጥፋቶች” በመፈጸሙ መሆኑን ፖሊስ ይፋ አድርጓል። ኤፍቲኤክስ በዓለም ላይ ግዙፍ ከሚባሉ የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት ኩባንያዎች አንዱ የነበረ ሲሆን እንዳልነበር ሆኖም በመንኮታኮቱ ባለፈው ወር ኪሳራ በይፋ መዋጁ ይታወሳል። በርካታ የክሪፕቶ ደንበኞች ዲጂታል ገንዘባቸውን በአንዳች ቁስ ወይም መደበኛ ገንዘብ ለመቀየር ሳይችሉ ቀልጦባቸው ቀርቷል። ኩባንያው ኪሳራ ማወጁን ተከትሎ በሚካሄደው የፍርድ ሂደት ምን ያህሎቹ ገንዛባቸውን እንደሚያገኙ ግልጽ አይደለም። ባለሙያዎች በበኩላቸው ካላቸው ገንዘብ ጥቂት ሊሆን እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል። ኤፍቲኤክስ ክሪፕቶን በመሸጥ፣ ዲጂታል ገንዘብን የማለዋወጥ ሥራን የሚሠራ የዲጂታል ግብይት አሳላጭ ኩባንያ ነው። ኤፍቲኤክስ ኪሳራ ከመግጠሙ በፊት ሳም 'የክሪፕቶ ዋረን በፌት' ተብሎ ይወደስ ነበር። በኪሳራ የተንኮታኮተው ኤፍቲኤክስ የክሪፕቶ ግብይት ኩባንያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እና 15 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት ነበረው። የ30 ዓመቱ ሳም በዓለም ላይ ሁለተኛውን ግዙፉን የክሪፕቶከረንሲ ልውውጥ ኩባንያን በበላይነት ሲያስተዳድር ነበር። “ዛሬ አመሻሽ ላይ የባሃማስ ለስልጣናት በአሜሪካ መንግሥት ጥያቄ ከደቡብ ኒውዮርክ በታሸገ የክስ መዝገብ መሰረት ሳሙኤል ባንክማን ፍራይድን በቁጥጥር ስር አውለዋል። የክስ መዝገቡን ጥዋት ከፍተን የምናየው ይሆናል በወቅቱም የበለጠ የምንለው ነገር ይኖራል” በማለት በማንሃተን የሚገኘው የአሜሪካ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት በትዊተር ገፁ አስፍሯል። የዋል ስትሪት ተቆጣጣሪዎችም እንዲሁ በሳሙኤል ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል። ባንክማን ፍራይድ በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ በአሜሪካ ኮንግረስ ኤፍቲኤክስ ስላጋጠመው መንኮታኮት ምስክርነቱን ይሰጣል ተብሎ ነበር። ሆኖም በአሁኑ ወቅት ምስክርነቱን መስጠት እንደማይችል የምክር ቤት አባሏ ማክሲን ዋተርስ አስረድተው በቁጥጥር ስር መዋሉም እንዳስገረማቸው ተናግረዋል። የሳሙኤል ባንክማን ፍሪድ ጠበቃ ቢቢሲ ላቀረባላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም። https://www.bbc.com/amharic/articles/cz9yen17mzlo +business “የሚላስ የሚቀመስ እንኳን አልነበረንም” ብራዚላዊው ኮከብ ሪቻርሊሰን ብራዚላዊው አጥቂ ሪቻርሊሰን እየተካሄደ ባለው የዓለም ዋንጫ ሰርቢያ ላይ ‘በመቀስ ምት’ ያስቆጠራት ጎል ስያሜ ታጥቶላታል። ብዙዎቹ ዐይናቸው ሌላኛው ብራዚላዊ የእግር ኳስ ማግኔት ኔይማር ላይ ነበር። ነገር ግን በዚህ ጨዋታ የሰዎችን ቀልብ የገዛው የ25 ዓመቱ ሪቻርሊሰን ነው። ሪቻርሊሰን፤ የሰርቢያ ብሔራዊ ቡድንን መረብ ሁለት ጊዜ በመጎብኘት የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። የቶተንሃሙ አጥቂ፣ ብራዚል በኳታሩ የዓለም ዋንጫ የጎል መዝገቧን የከፈተችባቸውን ሁለት ግቦች አስቆጥሯል። ይህ አጥቂ ሜዳ ላይ በሰራው ታሪክ ብቻ ሳይሆን ከሜዳ ውጪ በፈጸመው በጎ ምግባርም ስሙ ሲነሳ ከርሟል። ለመሆኑ ሪቻርሊሰን ማነው? ከሌሎች ብራዚላዊ ከዋክብትስ ምን ይለየዋል? ምንም እንኳ ሪቻርሊሰን ከአብዛኞቹ ብራዚላውያን ጋር የሚያመሳስለው ነገር ቢኖርም፣ እሱን ልዩ የሚያደርጉት ብዙ ነገሮች አሉት። ከአንዲት ትንሽዬ መንደር ኪሳቸው ካልዳበረ ወላጆች የተወለደው ሪቻርሊሰን በ16 ዓመቱ ትምህርት አቋርጦ ኳስ ማዘውተርን መረጠ። ሪቻርሊሰን ከሁሉ ትሻለኛለች ብሎ የመረጣ እግር ኳስ ወላጆቹን፣ ወንድም እና እህቶቹን ትደጉም ጀመር። ወደ እንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ከማምራቱ በፊት ለአትሌቲኮ ሚኔይሮ እና ለፍሉሚኒሴ ተጫውቷል። ወደ እንግሊዝ ከመጣ በኋላ መጀመሪያ ለዋትፈርድ ለጥቆ ደግሞ ብዙ ስምና ዝና ላተረፈረበት ኤቨርተን ተሰልፏል። እየተጠናቀቀ ባለው በዚህ የፈረንጆቹ ዓመት ለለንደኑ ክለብ ቶተንሃም የፈረመው ሪቻርሊሰን፣ ሳይንስና ተፈጥሮ ላይ ያተኮሩ ሥራዎች በመሥራት አልፎም ዘረኝነትን በመፋለም ይታወቃል። ተጫዋቹ በትውልድ አገሩ በሠራው የበጎ አድራጎት ተግባርም በፈረንጆቹ 2020 ከእንግሊዝ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋቾች ማኅበር ሽልማት ተበርክቶለታል። ብራዚል ውስጥ “እግር ኳስ እና ፖለቲካ አንድ ላይ አይሄዱም” የምትል ከብዙዎች አፍ የማትይጠፋ አባባል አለች። ምንም እንኳ ብራዚላውያን የእግር ኳስ ጥበበኞች ፖለቲካን እንደተላጠ የኤሌክትሪክ ገመድ ቢፈሯትም ኔይማር የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጃይር ቦልሶናሮን በግልጽ ደግፎ ነበር። ሪቻርሊሰንም ሐሳቡን በይፋ ከመግለጽ ያገደው አንዳችም ኃይል አልነበረም። ብራዚል በኮቪድ ወረርሽኝ ትናጥ በነበረበት ወቅት ስለክትባት ጥቅም ለማወጅ የቀደመው አልተገኘም። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ 700 ሺህ ያህል ብራዚላውያንን ቀጥፏል። የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት የኮቪድ ክትባትን ሲነቅፉ በነበረበት ወቅት፣ ሪቻርሊሰን በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የማኅበራዊ ሚድያ ተከታዮቹ ይህን መልዕክት አስተላልፎ ነበር፡ “እባካችሁ! ከልቤ ልማፀናችሁ። ክትባት መውሰዳችሁን እንዳትዘነጉ. . . ክትባቱ የእናንተ ነው። መብታችሁ ነው። ይህ ዕድል እንዳያመልጣችሁ።” ሪቻርሊሰን፤ የሳኦ ፖሎ ዩኒቨርሲቲ አምባሳደር ከሆነ በኋላ የእግር ኳስ ጫማውን ለጨረታ አቅርቦ ገንዘቡን ለቤተ-ሙከራዎች ለግሷል። የብራዚልን የአካባቢ ሳይንስ ፖለሲ በጽኑ በመንቀፍ የሚታወቀው ሪቻርሊሰን በአገሩ ብራዚል የተነሳው እሣት የአገሪቱ ዋነኛ የብዘሃ ሕይወት መገኛ የሆነውን አካባቢ 30 በመቶውን ሲያወድም ድምፁን አሰምቷል። ይህ ስፍራ ፓንታናል የሚባል ሲሆን፣ በብራዚል የሚገኝ እጅግ ጠቃሚ የሥነ-ምኅዳር አካል ነው። አንድ ቃለ-መጠይቅ ሲያደርግ በእሣት ወደተጎዱት ሥፍራዎች ሄዶ በዐይኑ ያየውን ማመን እንዳቃተው ተናግሯል። ሪቻርሊሰን፤ ሰኔ 2022 ብሪታኒያዊው ጋዜጠኛ ዶም ፊሊፒስ ወደ አማዞን ጫካ ተጉዞ ደብዛው ከጠፋ በኋላ ባለሥልጣናት ፍለጋቸው እንዲያጠናክሩ ጠይቆ ነበር። ባለፈው መስከረም ብራዚል ከቱኒዚያ ጋር ፓሪስ ላይ በነበራት የወዳጅነት ግጥሚያ ላይ ጎል ያስቆጠረው ሪቻርሊሰን ደስታውን ሲገልጽ ሙዝ ይወረወርበታል። ዘረኝነትን ለመግታት “ሥልጣኑ ያላቸው ሰዎች ወሬ ብቻ ከሆኑ፤ ይህ ድርጊት ይቀጥላል” ሲል በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል። “ዘረኝነት ሁሌም አብሮን የሚኖር ነገር ነው። በቃላት እና በድርጊት ብቻ ሳይሆን በማይታይ መልኩ ይገለጣል” ሲል በፈረንጆቹ 2020 ተናግሮ ነበር።” “ልጅ እያለሁ ከጓደኞቼ ጋር እግር ኳስ ስጫወት አንድ ሰው ምንም ሳላጠፋ ሽፍታ ሲል ሰደበኝ። ይህ ዘረኝነት ነው። ሰዎች ከፊት ለፊታቸው ጥቁር ሰው ሲመጣ አቅጣጫ ከቀየሩ ይህም ዘረኝነት ነው።” “እኒህ የማይታዩ የሚመስሉ ጉዳዮች ዘረኝነት ምን ያህል እንደሰረጸ ያሳያሉ” ሲል ድምፁን አሰምቷል። ሪቻርሊሰን፤ ጆርጅ ፍሎይድ የተሰኘው ጥቁር አሜሪካዊ አንድ ነጭ ፖሊስ አንገቱን በጉልበቱ ረግጦ ከገደለው በኋላ የተቃውሞ ድምፃቸውን ካሰሙ እግር ኳሰኞች መካከል አንዱ ነው። ሪቻርሊሰን፤ ኤስፒሪቶ ሳንቶ ከተባለችው ግዛት ድህነት ከደቆሳቸው ወላጆች ነው የተወለደው። ታዳጊ ሳለ ከረሜላ እና ማስቲካ እየሸጠ ወንድ አያቱ የቡና እርሻቸውን እንዲገፉበት ያግዛቸው ነበር። “አንዳንድ ጊዜ. . .” ይላል ሪቻርሊሰን፤ “የሚላስ የሚቀመስ እንኳን አልነበረንም።” ትምርህርቱን አቋርጦ ወደ እግር ኳስ ያመራበት ዋነኛው ምክንያት ቤተሰቡን ለመደጎምና ጠረጴዛቸው ላይ ምግብ ለማቅረብ ነው። “ይህ የእኔ ታሪክ ብቻ አይደለም። እኔ ባደግኩበት ከተማም ሆነ በሌሎች የብራዚል ከተሞች ያሉ ሕፃናትም ነው” ሲል ተናግሮ እንደነበር ይታወሳል። “ብዙዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ሥራ ፈልገው ቤተሰቦቻቸውን ያግዛሉ። ትምህርት ያቋረጠ ሕፃን ሳይ ልቤ ይሰበራል። ራሴን በእነሱ ውስጥ አየዋለሁ።” ቲክቶክ፣ ትዊተር፣ ኢንስታግራም እና ፌስቡክ በተሰኙት የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረኮች ላይ 19 ሚሊዮን ተከታዮች ያሉት ሪቻርሊሰን ከእግር ኳስ ሜዳ ውጪ ብዙዎችን ማነቃቃት ይፈልጋል። “የእግር ኳስ ሕይወቴን ከተመለከትኩ በኋላ በጣም ትልቅ ነገር ማድረግ እንደምችል እየገባኝ መጣ” ሲል ለኤቨርተን እየተጫወተ ሳለ ተናግሯል። “ይህ የገንዘብ ጉዳይ አይደለም። መጀመሪያ ለቤተሰቦቼ ቤት ሠርቶ መስጠት ነበር ዓላማዬ። አሁን ግን ከዚህ የተሻለ ብዙ ነገር ማድረግ እንደምችል አመንኩ።” https://www.bbc.com/amharic/articles/c4nrv477vg4o +health በዲሞክራቲክ ኮንጎ አንዲት ሴት በኢቦላ በሽታ ሕይወቷ አለፈ ��ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ በኢቦላ በሽታ የሰው ሕይወት ማለፉን የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር አስታወቀ። በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ቡቴምቦ በምትሰኝ ከተማ ነዋሪ የነበረች ሴት በኢቦላ በሽታ ከተያዘች በኋላ ሕይወቷ ማለፉ ተገልጿል። ቡቴምቦ ከዚህ ከቀደም የኢቦላ በሽታ ተቀስቅሶ በርካቶች ሕይወታቸውን ያጡባት ከተማ ነች። በኢቦላ በሽታ ሕይወቷ ያለፈው ይህች ሴት ከዚህ ቀደም በበሽታው ተይዞ ያገገመ ሰው ባለቤት ነች ተብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት በበሽታው ሕይወቷን ካጣችው ሴት ላይ የተወሰደው ናሙና በኢቦላ በሽታ መያዟን አረጋግጧል ብሏል። የኢቦላ በሽታ ምልክትም ይታይባት ነበር ተብሏል። የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር የጤና ባለሙያዎች ቡድን ወደ ሥፍራው መላኩን አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅትም ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ይሁን እንጂ በአከባቢው ያለው የደህንነት ስጋት የበሽታ መቆጣጠሩ ሥራ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ለ10ኛ ጊዜ ተቀስቅስቅሶ የነበረው እና ለሁለት ዓመታት በዘለቀው የኢቦላ ወረርሽኝ 3481 ሰዎች በበሽታው ተይዘው 2299 ሰዎች ሞተዋል። በአገሪቱ የኢቦላ በሽታ ሲመዘገብ ይህ ለ12ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም በበሽታው የተያዘ ሰው የተገኘው ከወራት በፊት በምዕራባዊ የአገሪቱ ክፍል ነበር። ኢቦላ ቫይረስ ሲሆን ድንገተኛ እና አደገኛ የሆነ ትኩሳት፣ ድካም፣ የጡንቻ እና የጉሮሮ ሕመም ያስከትላል። በሽታው እየጠና ሲሄድ ትውከት፣ ተቅማጥ ይጀምራል። ባስ ሲል ውስጥ እና ወደ ውጪ መድማትን ያስከትላል። በበሽታው የሚያዙ ሰዎች በድርቀት እና የሰውነት አካላት መስራት ማቆም ምክንያት ሕይወታቸው ያልፋል። የዓለም ጤና ድርጅት በኢቦላ የሚያዝ ሰው በበሽታው የመሞቱ እድል 50 በመቶ ነው ይላል። አንድ ሰው በኢቦላ በሽታ ሊያዝ የሚችለው በኢቦላ በሽታ የተያዘ ሰው ደም፣ ትውከት፣ ሰገራ እና ፈሳሽ ወደ አፍና አፍንጫ አልያም ቁስለት ያለበት ቆዳ ላይ ካረፈ ነው። https://www.bbc.com/amharic/55976626 +business 45 ሺህ ሹፌሮች ያሉት ኡበር የሎንዶን የሥራ ፍቃዱን ተነጠቀ ኡበር የተሰኘው የታክሲ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት በእንግሊዝ ከተማ ሎንዶን እንዲሠራ የተሰጠው ፈቃድ ተነጠቀ። 'ትራንስፖርት ፎር ሎንዶን' የተሰኘው የታክሲ አገልግሎት ኩባንያዎች ፈቃድ ሰጭ መሥሪያ ቤት ኡበር ሎንዶን ውስጥ ለመሥራት አቅምና አግባብነት የለውም ሲሉ ነው ፈቃዱን የነጠቁት። ኡበር፤ በግሪጎሪ አቆጣጠር 2017 ላይ በተመሳሳይ የሎንዶን የሥራ ፈቃዱን ተነጥቆ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ የተጠቃሚዎች ደህንነት ነው። በጊዜው ይግባኝ የጠየቀው ኡበር የ15 ወራት ፈቃድ ተሰጥቶታል። ይህ ፈቃድ በ21 ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቀው ኡበር የሥራ ፈቃዱ ድጋሚ እንደማይታደስ ያሳወቁት የትራንስፖርት ፎር ሎንዶን የሥራ ፈቃድ ሰጭ ሊቀመንበር ሄለን ቻፕማን ናቸው። «ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ምንም እንኳ ኡበር በጎ ለውጦችን ቢያመጣም ማንነታቸው የማይታወቅ ሰዎች ሹፌር ሆነው እንዲቀጠሩ መፍቀዱ አግባብ አይደለም» ሲሉ ኃላፊዋ ፈቃድ የነሱበትን ምክንያት ያስረዳሉ። ኡበር ይግባኝ እንደሚጠይቅ ይጠበቃል። 45 ሺህ ገደማ አሽከርካሪዎች ለኡበር ይሠራሉ። የኡበር የሥራ ፈቃድ ለዘለቄታው የሚሠረዝ ከሆነ እኒህ ሹፌሮች ከሥራ ውጭ ይሆናሉ የሚል ስጋት አለ። ነገር ግን ከዓለም አቀፍ ኡበር ጋር የተመሳሰለ ሥራ የሚሠሩ በርካታ ድርጅቶች በሎንዶን መኖራቸው ይታወቃል። 'ትራንስፖርት ፎር ሎንዶን' ለድርጅቶች ብዙ ጊዜ የአምስት ዓመት ፈቃድ በመስጠት ይታወቃል። ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፈቃድ መስጠት ላይ ቆጠብ ያለ ይመስላል። ድርጅቱ 'የተጠቃሚዎች ደህንነት' አደጋ ላይ ሊወድቅ እንዳይችል ነው ፈቃድ የነሳሁት ይላል። ውሳኔው ከሎንዶን ከንቲባ ሳዲቅ ካህን ድጋፍ አግኝቷል። ኡበር ሎንዶን ውሰስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ከተሞችም ተቃውሞ ይገጥመዋል። ብዙ ቦታዎች ተቃውሞ የሞመጣው በባሕላዊ መንገድ የታክሲ ግልጋሎት ከሚሰጡ ሰዎች ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-50545277 +sports የእግር ኳስ ኮከቡ ቦአቲንግ ፍቅረኛው ላይ ጥቃት በመፈጸም ጥፋተኛ ተባለ ጀርመንናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ዤሮም ቦአቲንግ የቀድሞ ፍቅርኛው ላይ ጥቃት በመፈጸም ጥፋተኛ ተባለ። የቀድሞ ፍቅረኛውን በማጥቃት ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው ጀርመናዊው እግር ኳስ ተጫዋች ዤሮም ቦአቲንግ 1.8 ሚሊዮን ዩሮ ቅጣት እንዲከፍል ተበይኖበታል። ተጫዋቹ እአአ በ2018 በተፈጠረ አለመግባባት መንትያ ሴት ልጆቹን እናት ሼሪን ኤስን መጎዳቱን አስተባብሏል። የቀድሞው የባየርን ሙኒክ ተከላካይ እና የ2014 የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ከሳሽ ለፍርድ ቤቱ በቡጢ በከፍተኛ ሁኔታ እንደመታት እና ለአፍታ እስትንፋሷን አጥታ እንደነበር ተናግራለች። በምስክርነቱ ወቅት ቦአቲንግ የተለየን የክስተቶች ሂደት ገልጿል። በጀርመን የቤት ውስጥ ጥቃት ሕጎች መሠረት እስከ አምስት ዓመት ድረስ በእስር ሊቆይ ይችል ነበር። ቦአቲንግ ጥቁር ሰማያዊ ሙሉ ልብስ ለብሶ በግል ጠባቂዎቹ እና በጠበቃው ካይ ዋልደን ተከቦ ነበር ፍርድ ቤት የደረሰው። ከችሎቱ በፊት ዐቃቤ-ሕግ በቦአቲንግ በሐምሌ 2018 በካሪቢያን ደሴት እረፍት ላይ በነበሩበት ወቅት በቀድሞው ፍቅረኛውአነስተኛ የማቀዝቀዣ ሣጥን በመወርወር ሆን ብሎ አካላዊ ጉዳት አድርሷል ብሏል። የቀድሞ ፍቅረኛው በፍርድ ቤት ምስክርነቷን ስትሰጥ በግጭቱ ወቅት ቦአቲንግ በቡጢ እንደመታት፣ ፀጉሯን መጎተቱን፣ ጭንቅላቷን መንከሱን እና እሷ እንደሰደበችው ተናግራለች። ቦአቲንግ በሰጠው ቃል በካርድ ጨዋታ ወቅት ውጥረቱ መባባሱን አምኗል። ጠበኛ መሆኗን እና እንደሰደበችው፣ እንደመታችው እና ከንፈሩን እንደጎዳችው ተናግሯል። ከላዩ ላይ ሲገፈትራትም መውደቋን ተናግሯል። ችሎቱ በታህሳስ ወር ሊካሄድ የነበረ ቢሆንም ምስክር ሊቀርብ ባለመቻሉ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። በእግር ኳስ ዓለም እና በማህበራዊ ሚዲያ ታዋቂ የሆነው ቦአቲንግ በክለብ እና በሀገር ደረጃ የተለያዩ ሽልማቶችን አንስቷል። ሁለት የሻምፒዮንስ ሊግና ዘጠኝ የቡንደስሊጋን ዋንጫን ጨምሮ ከሙኒክ ጋር 22 ዋንጫዎችን አንስቷል። በሙኒክ የነበረው ኮንትራት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ፈረንሳዩ ሊዮን በነጻ ዝውውር ተዛውሯል። ሌላኛዋ የቦአቲንግ የቀድሞ ፍቅረኛ የ25 ዓመቷ ሞዴል ካሲያ ሌንሃርትት በየካቲት ወር በርሊን ውስጥ በሚገኝ አንድ አፓርታማ የራሷን ሕይወት አጥፍታለች። https://www.bbc.com/amharic/58507469 +business የዚምባብዌ አልማዝ ማዕድን ቁፋሮ በጉልበት ብዝበዛ ይሆን የሚካሄደው? "የአሜሪካ መንግሥት ከዚምባብዌ የሚመጣውን ያልተጣሩ የአልማዝ ምርቶችን በማዕድን ቁፋሮው ወቅት የጉልበት ብዝበዛን ይጠቀማሉ በሚል አግጃለሁ ብሏል። ዚምባብዌ ጉዳዩን ተራ ውንጀላ ነው በማለት አጣጥለዋለች። የመረጃ ሴክሬታሪው ኒክ ማንግዋና እንደሚሉት አሜሪካ ምንም ዓይነት መረጃ የላትም ""መረጃ የላቸውም፤ ወይም ያሳሳታቸው አካል አለ"" ብለዋል። • ""የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም"" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ •የቀድሞው ፕሬዝደንት ልጅ በጉልበት ብዝበዛ ወንጀል ተፈረደባቸው የማዕድን ቁፋሮው በምስራቃዊቷ አገሪቷ ክፍል ማራንጅ ግዛት አካባቢ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዓለም ላይ ካሉ ከፍተኛ የአልማዝ ምርት የሚገኝበት ሲሆን በኢ���ኖሚ ቀውስ ለምትንገዳገደው ዚምባብዌም የውጭ ምንዛሬን በማስገኘት አገሪቷን የሚያንቀሳቅሳት ነው። የአሜሪካ ውንጀላ ምንድን ነው? የአሜሪካ ከተሞች የሥራ ልምዶችን የሚፈትሸው ድርጅት እንዳሳወቀው በማዕድን ቁፋሮ ሥራ ለመሰማራትና በተከለለው ቦታ ላይ ፍቃድ ለማግኘት ለፀጥታ ኃይሎች ጉቦ መክፈል ነበረባቸው። የአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ኤጀንሲ ተወካይ ብሬንዳ ስሚዝ እንደተናገሩት ሠራተኞች ያለ ፈቃድ የማዕድን ቁፋሮ አካባቢውን ለቀው መሄድ እንደማይችሉና፤ እምቢተኝነትን ያሳዩት ደግሞ አካላዊና ወሲባዊ ቅጣቶች እንዲሁም ለእስር ይዳረጋሉ ተብሏል። የአሜሪካ መንግሥት እንዳሳወቀው እንዲህ ዓይነት ጥቃቶችን በመረጃ አጠናቅረን ይዘናል ብለዋል። •ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ረቂቅ ህግ የሞት ቅጣት ተካቶበታል •""ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው"" መስፍን ነጋሽ መረጃው ምንድን ነው? ጋዜጠኞችም ሆነ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ቡድን አካባቢውን እንዲጎበኙ የማይፈቀድላቸው ሲሆን፤ አካባቢውን ለማየትም ልዩ የሆነ ፍቃድ ያስፈልጋል። በማራንጌ የአልማዝ ቁፋሮ ቦታ ላይ የሥራ ሁኔታዎችን የሚቆጣጠረው ቡድን እንዳሳወቀው የጉልበት ብዝበዛ በተለይም የግዳጅ ሥራ እንደሚከናወን አሳውቋል። የቦቻ ዳይመንድ ትረስት ኩባንያ ሊቀመንበር ሞሰስ ሙክዋዳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የአካባቢው ሰዎች ተገደው በማዕድን ቁፋሮው ሥራ እንደተሰማሩ አጋልጠዋል። አንዳንድ ኩባንያዎች የግዳጅ ሥራ አለ ለማለት አልደፈሩም። ለማዕድን ቁፋሮ ሰራተኞች መብት የሚታገለው ዘ ሴንተር ፎር ናቹራል ሪሶርስስ ገቨርናንስ የተባለው ድርጅት ከአስራ ስምንት ዓመት በታች ያሉ ታዳጊዎች አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ቢገልፅም ሰራተኞች በግዳጅ ተሰማርተዋል ከሚለው አስተያየት ተቆጥቧል። ""ሰራተኞች በግዳጅ ተሰማርተዋል የሚለውን ሃሳብ ሙሉ በሙሉ አናጣጥለውም፤ ከአሜሪካ መንግሥትም ሆነ ከየትኛውም አካል በግዳጅ የተሰማሩ ሰራተኞች እንዳሉ መረጃ አልደረሰንም። ማን ማንን እያስገደደ ነው የሚለውንም የበለጠ ማወቅ እንፈልጋለን"" በማለት የድርጅቱ ቃል አቀባይ ሲሚሶ ምሌቩ ተናግረዋል። በማራንጄ የማዕድን ቁፋሮ ቦታ ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ውንጀላዎች ሲቀርቡ የመጀመሪያው አይደለም። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተደጋጋሚ እንዳሳወቁት ከአካባቢው የሚመጣው አልማዝ ""ከግጭት አካባቢ የተገኘ አልማዝ"" ስለሆነ ወደ ውጭ የሚላከው የአልማዝ መጠን ሊገደብ ይገባል በሚል አሳውቀው ነበር። በጎርጎሳውያኑ 2011 ቢቢሲ ባደረገው ምርመራ በአካባቢው የከፋ ድብደባና ወሲባዊ ጥቃት እንደሚደርስም መረጃ ሰብስቧል። ""በማራንጌም ሆነ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የአልማዝ ምርቶች በከፍተኛ ሁኔታ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ቢያጠላባቸውም ወደ አለም አቀፉ ገበያ መድረሳቸው አልቀረም"" በማለት ዘ ሴንተር ፎር ናቹራል ሪሶርስስ ገቨርናንስ አስታውቋል። ሰራተኞች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች እንዲሁም ባለው የከፋ ሁኔታ አርባ ሰዎች በየአመቱ ይሞታሉ ተብሏል። •ቤይሩት፡ ባለፉት 7 ወራት 34 ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን አጥተዋል •ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት የሰራተኞች መብት በዚምባብዌ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚለው ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች ባለፈው ዓመት ባወጣው ሪፖርት በሃገሪቷ በሚገኙ የትምባሆ እርሻዎችም የግዳጅ ሥራ እንደተንሰራፋ ይፋ አድርጓል። የአሜሪካ መንግሥትም እንዲሁ ባለፈው አመት የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ እንደሚከናወን አንድ መረጃ አውጥቶ ነበር። ዚምባብዌ በበኩሏ የተባበሩት መንግሥታት የጉልበት ብዝበዛን ለማስቀረት ያፀደቃቸው��� ሕጎች በዚህ ዓመት እንደተቀበለችና የግዳጅ ሥራ ልምድንም ለማስቀረት እየሞከሩ እንደሆነ ገልፃለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-50114465 +sports ሞ ፋራህ በኃይሌ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሸለ ትውልደ ሶማሊያዊው ሞ ፋራህ በኃይሌ ገብረስላሴ ለ13 ዓመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሸለ። ለግሬት ብሪቴን የሚሮጠው የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ሞ ፋራህ የአንድ ሰዓት የዓለም ክብረ ወሰንን በዳይመንድ ሊግ ውድድር ነው ትናንት ምሽት ማሻሻል የቻለው። ፋራህ በአንድ ሰዓት ውስጥ 23.33 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ነው የሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴን 21.285 ኪሎ ሜትር ርቀት ያሻሻለው። “የዓለም ክብረ ወሰንን መስበር ቀላል ነገር አይደለም። ይህን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። ይህ ክብረ ወሰን ለረዥም ጊዜ ሳይሰበር ቆይቷል” ሲል ከውድድሩ በኋላ ሞ ፋራህ ተናግሯል። በዚህ ውድድር አትሌቶች በአንድ ሰዓት ውስጥ በተቻላቸው መጠን ረዥም ርቀትን ለመሸፈን ይወዳደራሉ። ከዛ ቀደም ብሎ በተካሄደ ተመሳሳይ የሴቶች ውድድርም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሃሰን በተመሳሳይ የዓለም ክብረ ወሰንን ማሻሻል ችላለች። ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፈን ያሻሻለችው ክብረ ወሰን በኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድሬ ቱኔ ተይዞ የነበረውን ነው። ሲፈን በአንድ ሰዓት ውስጥ 18.930 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ከ14 ዓመታት በፊት ድሬ ቱኔ አስመዝግባ የነበረውን 18.517 ኪሎ ሜትር ማሻሻል ችላለች። https://www.bbc.com/amharic/news-54039364 +sports በቅጣት ከቼልሲ ጨዋታ ውጪ የሆነው ሮናልዶ ምላሽ ሰጠ "በዲስፕሊን ምክንያት ማንቸስተር ዩናይትድ ከቼልሲ ከሚያደርገው ጨዋታ ውጭ የታደገው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ምላሽ ሰጠ። ሮናልዶ ከትናንት በስቲያ ጨዋታ ሳይጠናቀቅ ስታዲየም ለቅቆ የወጣው “በወቅቱ በነበረው ሁኔታ” ምክንያት ነው ብሏል። የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ቡድኑ ረቡዕ ምሽት የነበረው ጨዋታ ሳይጠናቀቅ ስታዲየሙን ለቆ መሄዱ ይታወቃል። ሮናልዶ በወቅቱ የነበረው ሁኔታ ስታዲየም ጥሎ እንዲወጣ እንዳደረገው ኢንስታግራም ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሑፍ አመላክቷል። በተቀያሪ ወንበር ላይ የነበረው ፖርቹጋላዊ ቡድኑ ማንቸስተር ዩናይትድ ቶተነሃምን 2-0 እየመራ 89ኛው ደቂቃ ላይ ከተቀያሪ ወንበር ተነስቶ ሲወጣ ታይቷል። ሮናልዶ ከተቀያሪ ወንበር ተነስቶ በቀጥታ ወደ ልብስ መቀየሪያ ከሄደ በኋላ ከስታዲየሙ መውጣቱ ተገልጿል። ""በወከልኳቸው ቡድኖች ውስጥ ላሉ ወጣቶች ራሴን አርአያ ለማድረግ ሁልጊዜ እሞክራለሁ"" ሲል ሃሙስ ምሽት በኢንስታግራም ገጹ አስፍሯል። ""ይህ ግን ሁል ጊዜም የሚቻል አይደለም። . . . አንዳንድ ጊዜ የወቅቱ ሁኔታ ያሸንፈናል” ሲል አክሏል። “በካርሪንግተን (የዩናይትድ የልምምድ ቦታ) ጠንክሬ መሥራት እንዳለብኝ ይሰማኛል፣ የቡድን አጋሮቼን መደገፍ እና በማንኛውም ጨዋታ ዝግጁ መሆን እንዳለብኝ ይሰማኛል።"" ""ለግፊቱ መልስ መሰጠት አማራጭ አይደለም፤ በጭራሽ አልነበረምም። ይህ ማንቸስተር ዩናይትድ ነው። እናም ሁሌም አንድ ሆነን መቆም አለብን። በቅርቡ እንደገና አብረን እንሆናለን።"" ብሏል የዩናይትድ የፊት መምመር ተጫዋቹ። ማንችስተር ዩናይትድ የ37 ዓመቱ ተጫዋች አሁንም የቡድኑ ወሳኝ አባል እንደሆነ ገልጿል። ተጫዋቹ ከቼልሲው ጨዋታ ውጭ የሆነው በዲሲፕሊን ጉዳይ መሆኑን ጠቁሟል። በስታምፎርድ ብሪጅ የማይሳተፍበት ጨዋታ ትልቅ ሲሆን ዩናይትድ አራተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ቼልሲ በአንድ ነጥብ ብቻ ዝቅ ብሎ ይገኛል። በስፐርስ ጨዋታ በመጠናቀቂያ ደቂቃዎች ተቀይሮ እንዲገባ ቢጠየቅም ፈቃደኛ አለመሆኑን በርካታ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ነው። ዩናይትዶች ከተፈቀደላቸው 5 ቅያሬዎች ውስጥ ሦስቱን ብቻ ቢያደርጉም  በ89ኛው ደቂቃ ሮናልዶ ከተቀያሪ ወንበር ተነስቶ ወደ መልሻ ክፍል አቅንቷል። ቀጥሎም በፍጥነት ከስታዲየም መውጣቱ ታውቋል። አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ሐሙስ ዕለት ጉዳዩን ""እንደሚፈቱት” ተናግረው ነበር። ሮናልዶ ማንቸስተር እሑድ ዕለት በሜዳው ከኒውካስትል ጋር 0 - 0 ሲለያይ ተቀይሮ በመውጣቱ የተሰማውን ቅሬታ አሳይቷል። የቀድሞው የእንግሊዝ አጥቂ ጋሪ ሊንክከር የሮናልዶ ባህሪ ዩናይትድ በስፐርስ ላይ ያሳየውን አስደናቂ ብቃት ትኩረት እንዳሳጣ ተናግሯል። ""ይህ ተቀባይነት የሌለው ነው።  በጣም ደካማ ነው"" ሲልም ሊንከር በቢቢሲ ማች ኦፍ ዘ ዴይ ፕሮግራም ላይ ተናግሯል። የቀድሞው የዌልስ አምበል አሽሊ ዊሊያምስ “ለማንቸስተር ዩናይትድ ታላቅ ምሽት ነበር። ተሰልፎ ባይጫወትም አሁንም ስለ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እንናገራለን” ብሏል። የቀድሞ የእንግሊዝ ተከላካይ ሚካህ ሪቻርድስ “ቡድንህ ሲያሸንፍ ከስፖርቱ ታላላቆች አንዱ ይህን ማድረጉ ተስፋ አስቆራጭ ነው” ብሏል። ሪቻርድስ አክሎም የሮናልዶ ባህሪ ""አክብሮት የጎደለው ነው"" እና በጥር የዝውውር መስኮትም እንዲለቅ ሊፈቀድለት ይገባል ብሏል። ሪቻርድስ ለቢቢሲ ሬድዮ 4 እንደተናገረው “አሰልጣኙ በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ከእሱ ጋር ችግር ውስጥ ገባ። በቅድመ-ውድድር ዘመንም ቀጠለ።  አሁንም ያው ነው። እኔ እንደማስበው ይህ መፈታት ያለበት በአንድ መንገድ ብቻ ነው” ብሏል። ""በጥር የዝውውር መስኮት ሊለቁት ይገባል።  የአሰልጣኙን ሥራ እያበላሸ በመሆኑ መለያየቱ  ጥሩ ይመስለኛል።"" ብሏል። የቀድሞው የዩናይትድ ግብ ጠባቂ ፒተር ሽሚሼል ሮናልዶ እንደዚህ አይነት ባህሪው “ርዕሰ ዜና"" እንደሚሆን ያውቅ ነበር ብሏል። ""በእሱ ቅር እንደተሰኘሁ መናገር የምችልበት የመጀመሪያ አጋጣሚ ነው። ስደግፈው ቆይቻለሁ። ያለበትንም ሁኔታ ተረድቻለሁ"" ሲል ሽማይክል ለቢቢሲ ሬዲዮ 5 ቀጥታ ስርጭት ወቅት ተናግሯል። ""እኛ በሽግግር ላይ ነን። ማንቸስተር ዩናይትድ ከአሌክስ ፈርጉሰን መልቀቅ በኋላ አምስት አሰልጣኞች ቀያይሯል።” ""እኛ እንደዚህ አይነት ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮች አያስፈልጉንም። ይህ ተስፋ አስቆራጭ ነው” ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cgeg92p8epdo +health ኢትዮጵያ የምታከናውነው ድንበር ተሻጋሪ የእንስሳት ክትባት ምንድነው? "በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር አካባቢዎች ድንበር ተሻጋሪ ተዛማች የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁለተኛው ዙር የእንስሳት ክትባት ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል። የክትባት ዘመቻው በኢትዮጵያ በኩል በቦረና ዞን፣ ሞያሌ ወረዳ የተለያዩ እንስሳትን በመከተብ የተጀመረ ሲሆን በመቀጠል ደግሞ በኬንያ በኩል ይካሄዳል። ይህ ከአጎራባች አገራት ጋር በመቀናጀት የሚካሄደው ድንበር ተሻጋሪ የክትባት ዘመቻ በደቡብ ኦሞ ዞን፣ በሀመር ወረዳም በይፋ ተጀምሯል። አርብቶ አደሮች ግጦሽና ውሃ ፍለጋ ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ አጎራባች አገራት ተቀናጅተው ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን በጋራ መከላከልና መቆጣጠር ካልቻሉ በድንገት የሚከሰቱ በሽታዎች የእንስሳትን ምርታማነት ከመቀነሰ አልፎ ቁጥራቸውንም በጊዜ ብዛት ይቀንሰዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር እንደሚለው የእንስሳት ሀብት ልማት ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ዝሪያን በማሻሻል፣ በቂ መኖን በማቅረብ እና ገበያን በማመቻቸት ብቻ ሳይሆን ከጤናማ እንስሳት ጤናማ ምርት ማቅረብ ሲቻል ነው። በአርብቶ አደሩ አካባቢ የእንስሳት በሽታዎችን በመካለከል እና በመቆጣጠር ጥራት ያለውን የእንስሳት ምርት በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ በሆነ መልኩ ማቅረብ ዋነኛ አላማው ነው። የ��ንበር ዘለል የእንስሳት በሽታ ክትባትን በጋራ የመተግበር ሥራ በተለይ በአራት ዋና ዋና በሽታዎች ላይ ያተኮረ እንደሆነ በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒትር ዴኤታ አማካሪ የሆኑት ዮሐንስ ግርማ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ገልጸዋል። ""ከኬንያ ጋር በተለይ አራት ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን ለመቆጣጠር ስምምነት ላይ ደርሰናል። የመጀመሪያው የበጎችና የፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ ክትባት ነው። ሁለተኛው ደግሞ የበጎችና የፍየሎች የሳምባ በሽታ ክትባት፣ የከብቶች የሳምባ በሽታ እንዲሁም በግመሎች ላይ የሚከሰቱ ዋና ዋና በሽታዎችን ነው አንድ ላይ የምንከትበው"" ይላሉ። በአውሮፓውያኑ 2019 የተጀመረው ይህ ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን በጋራ የመከላከል ሥራ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፤ በያዝነው ዓመት ደግሞ በአዲስ መልኩ ነው እየተሠራ የሚገኘው። ምንም እንኳን የግብርና ሚኒስቴር በተለይ ከኬንያ መንግሥት ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት ከሁለት ዓመት በፊት የድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን ክትባት መስጠት ቢጀምርም፤ ባለፈው ዓመት ግን ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ በተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች ምክንያት ሥራውን ማስቀጠል አልተቻለም። ነገር ግን በያዝነው ዓመት ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ በኩል በቦረና ዞን፣ ሞያሌ ወረዳ ክትባቱን ያካሄደ ሲሆን በኬንያ በኩል ደግሞ በመርሳቢት ካውንቲ ተካሂዷል። በመቀጠል በደቡብ ኦሞ ዞን፣ በሐመር ወረዳ እንዲሁም በሰሜን ኦሞ ዞን የእንስሳት ክትባቱ ተካሂዷል። በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል ካለው የንግድ ትስስር አንጻር እና በሁለቱም አገራት የሚገኙ አርብቶ አደሮች ከብቶቻቸውን ይዘው መንቀሳቀሳቸው እንስሳቱን ለድንበር ተሻጋሪ በሽታዎች ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። ዮሐንስ (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ ""ምናልባት እኛ በራሳችን በኩል ያሉትን እንስሳት ብቻ ከትበን ብንተውና በሌላኛው በኩል በተመሳሳይ እንስሳቱን ባይከትቡ የበሽታዎቹን ስርጭት መቆጣጠር አንችልም።"" ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ እንስሳቱ ከአንዱ አገር ወደሌላኛው መንቀሳቀሳቸው ነው። ይህ የክትባት ስምምነት የተደረገው ከኬንያ ጋር ብቻ ሳይሆን ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ እና ከሱዳን ጋር ነው። ከዚህ በፊት በተደረጉ ድንበር ተሻጋሪ ተዛማች የእንስሳት ክትባት ዘመቻዎች በርካታ እንስሳት መከተባቸውን የገለጹት ዶ/ር ዮሐንስ፤ በዚህኛውም ዙር የተሻለ ውጤት እንደሚጠብቁ ገልጸዋል። ""በዋነኛነት የምናተኩረው እነዚህ በሽታዎች በድንገት እንዳይከሰቱ ማድረግ ላይ ነው። አብዛኞቹ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክም ሆነ በሌላ መልኩ የሚከሰቱባቸው ወቅቶች አሉ። እነሱን ተንተርሰን ከመከሰታቸው ቀደም ብለን ዘመቻዎች እናደርጋለን። አሁን ካለው የድርቅ ክስተት ጋር ተያይዞ እንስሳት ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም የበሽታዎች ክስተት ግን በብዛት እየታየ አይደለም"" ይላሉ። በአጠቃላይ በዚህ ዓመት ኢትዮጵያን በሚያዋስኑና ስምምነት ካደረጉ አገራት ጋር አጎራባች በሆኑ አካባቢዎቸ እስከ 5.4 ሚሊየን እንስሳትን ለመከተብ ዕቅድ መያዛቸውን አማካሪው ይናገራሉ። በያዝነው ዓመት የሴንትራል ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በሠራው ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ ወደ 61 ሚሊየን የሚጠጉ የቀንድ ከብቶች አሏት። ከ40 ሚሊየን በላይ ፍየሎችና ከ50 ሚሊየን በላይ በጎች እንዲሁም 8 ሚሊየን የሚደርሱ ግመሎችም አሏት። አርብቶ አደሩ የሚያረባቸውና የሚጠቀማቸው አብዛኛዎቹ የእንስሳት ዝርያዎች በተፈጥሯቸው በሽታን የመቋቋምና አስቸጋሪ የአየር ፀባይን መቋቋም የሚችሉ ናቸው። የግብርና ሚኒስቴር እንደሚለው እነዚህ ዝርያዎች በሽታና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋም ቢችሉም ምርትና ም���ታማነት ላይ ግን ችግር አለባቸው። ይህንኑ ከግምት ውስጥ በማስገባትም ሚኒስቴሩ ከክትባቶች በተጨማሪ በአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኙት እንስሳት ላይ ማሻሻያ በማድረግ የተሻለ ምርት መስጠት እንዲችሉ እየሠራ መሆኑን ዮሐንስ (ዶ/ር) ይናገራሉ። ""በቦረና ዞን የሚገኘው የዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ውስጥ የቦረና ዝርያዎችን በማባዛት፣ በማሻሻልና በመጠበቅ ሥራዎችን ይሠራል። ቁጥራቸው ሲበዛ ደግሞ ለአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲከፋፈሉ ይደረጋል። ወደሌሎች የአገሪቱ አርብቶ አደር አካባቢዎችም እንዲደርሱ ይደረጋል"" ብለዋል። በድንበር አካባቢዎች ላይ ከሚደረገው የክትባት ዘመቻ በተጨማሪ በመላው አገሪቱ የሚገኙ እንስሳት ላይ ክትባቱ ይቀጥላል። ነገር ግን በድንበር አካባቢዎች ላይ የሚገኙ እንስሳት ቁጥራቸው ላቅ ያለ መሆኑ እና ከቦታ ቦታ ስለሚንቀሳቀሱ ቅድሚያ ተሰጥቶ ይከተባሉ። እነዚህ በሽታዎች ቀስ በቀስ ሲጠፉና የእንስሳቱን ደኅንነት መጠበቅ ከተቻለ በዓለም አቀፍ ደረጃ የገበያ ተወዳዳሪነትን ለመጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ""እነዚህ በሽታዎች በኢትዮጵያ አሉ ተብሎ ከታሰበ ምርታችንን ማንም አይገዛም፤ አልያም ቁጥሩ ዝቅተኛ ይሆናል። በተለይ በርካታ ያደጉ አገራት እነዚህን በሽታዎች ማጥፋት በመቻላቸው በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃሚ ሆነዋል። እኛም እነዚህም በሽታዎች ማጥፋት ስላልቻልን ወደ አውሮፓ እና እስያ ገበያዎች መድረስ አልቻለንም"" ሲሉ ያስረዳሉ። ዓለም አቀፍ የእንስሳት ጤና ድርጅት የሚባለውና 182 አባል አገራት ያሉት ተቋም በየጊዜው የአገራትን የእንስሳት ጤና የሚከታተልና የአገራቱን ደረጃ የሚያወጣ ነው። ኢትዮጵያም የዚህ ድርጅት አባል እንደመሆኗ የእንስሳቶቿን ጤንነት ከጠበቀች የምታገኘው ተቀባይነት ከፍተኛ እንደሆነም ይናገራሉ። ይህ ክትባት የዓለም አቀፍ ገበያውን ከመድረስ ባለፈም አርብቶ አደሮች በበቂ ሁኔታ ከእንስሳቶቻቸው ተገቢውን ምርት እንዲያገኙ እና የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/59252309 +business አውሮፓ በሩሲያ ላይ በጣለችው ማዕቀብ ከ400 ቢሊየን ዶላር በላይ ታጣለች፡ ፑቲን "የአውሮፓ ሕብረት በሩሲያ ላይ ማዕቀብ በመጣሉ ምክንያት በመቶ ቢሊዮኖች የሚገመት ኪሳራ ሊያጋጥመው እንደሚችል የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ። ሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ በተዘጋጀ ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የምጣኔ ሀብት መድረክ ላይ ፑቲን እንዳሉት አገራቸው ላይ በተጣለው ማዕቀብ ሳቢያ የአውሮፓ ሕብረት ከ400 ቢሊየን ዶላር በላይ ምጣኔ ሀብታዊ ኪሳራ ሊገጥመው ይችላል ብለዋል። በ27ቱ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት ውስጥ የዋጋ ግሽበት እየጨመረ መሆኑንና ቡድኑ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ በሚጥልበት ጊዜ የአገራቱን ዜጎች ትክክለኛውን ጥቅም ወደጎን ገፍቷል ሲሉ ፑቲን ወቅሰዋል። ጨምረውም የምጣኔ ሀብት ጫናው ዕቀባው ከተጣለባት ሩሲያ ይልቅ፣ ዕቀባውን በጣሉት አገራት ላይ “የበለጠ ጉዳትን ያስከትላል” ሲሉም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ""በሩሲያ ላይ እየተካሄደ ያለው ምጣኔ ሀብታዊ ዕቀባ ከመነሻው አንስቶ ምንም አይነት የመሳካት እድል የለውም” ብለዋል። ምዕራባውያን ከዩክሬን ወረራ በኋላ በሩሲያ ላይ የጣሏቸው ማዕቀቦች “እብደትና የሚያስከትሉትን ጉዳት ያላገናዘቡ ናቸው” ሲሉም ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተችተዋል። ምዕራባውያን መንግሥታት የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ሩሲያ ላይ ጫናን በመፍጠር እና የራሳቸውን የምጣኔ ሀብት ጥቅም በማስጠበቅ መካከል ሚዛን ለመጠበቅ ሲጥሩ ቆይተዋል። ነገር ግን አንድ የሩሲያ ባለሥልጣን በአገ��ቸው ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች በምጣኔ ሀብቷ ላይ ከባድ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን አመልክተዋል። የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ገዢ ኤልቪራ ናቡሊና ሐሙስ ዕለት እንደተናገሩት “የአገሪቱ 15 በመቶ አገራዊ ምርት” በማዕቀቦቹ ምክንያት ስጋት ላይ ወድቋል። የጦርነቱን መቀስቀስ ተከትሎ በርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በሩሲያ ያሏቸውን ተቋማት እየለቀቁ ቢወጡም ፑቲን ግን በራቸው ለመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች አሁንም ክፍት እንደሆነ ጥሪ አቅርበዋል። ፑቲን በተጨማሪም ዩክሬን ውስጥ በቀጠለው ጦርነት ምክንያት የተፈጠረውን ዓለም አቀፋዊ የምግብ አቅርቦት ቀውስን በተመለከተም፣ ሩሲያ ለዓለም ገበያ የሚቀርበውን የእህል ምርትና ማዳበሪያ በከፍተኛ ደረጃ ልትጨምር እንደምትችል ተናግረዋል። በዚህም አገራቸው የእህል ምርት አቅርቦቷን በ50 ሚሊዮን ቶን ከፍ ለማድግ አቅሙ አላት ብለዋል። ዩክሬን እና ሩሲያ ለዓለም ከፍተኛውን የእህል ምርት የሚያቀርቡ አገራት ሲሆኑ ከወራት በፊት በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት የጥቁር ባሕር ወደቦቿ በመዘጋታቸው ዩክሬን ምርቷን ለዓለም ገበያ ማቅረብ አልቻለችም። አሁንም በተለያዩ የዩክሬን አካባቢዎች ከፍተኛ ውጊያዎች እየተካሄዱ ሲሆን ምዕራባውያንም በሩሲያ ላይ ከጣሏቸው ምጣኔ ሀብታዊ ዕቀባዎች በተጨማሪ፣ ዩክሬን እራሷን እንድትከላከልና በጦርነቱ አሸናፊ እንድትሆን ቢሊዮን ዶላሮችን የሚያወጡ ዘመናዊ የጦር ማሳሪያ ድጋፍ እያደረጉላት ይገኛሉ።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cm5vy3ejd3no +politics ፑቲን ቅንጡ ቤተ መንግሥት ማስገንባታቸውን 'የሚያጋልጠው' ቪድዮ "የሩስያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቅንጡ ቤተ መንግሥት ለመገንባት በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ማፍሰሳቸውን የሚያሳየው የምርመራ ቪድዮ በተለቀቀ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተመልካች አግኝቷል። ቪድዮው የተለቀቀው በሩስያዊው ተቃዋሚ አሌክሴ ናቫልኒ ቡድን ነው። ናቫልኒ ሩስያ፣ ሞስኮ ሲደርስ በቁጥጥር ስር የዋለው ከቀናት በፊት ነበር። የምርመራ ቪድዮው እንደሚያሳየው፤ ቤተ መንግሥቱ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር ወጥቶበታል። ""በታሪክ ትልቁ ጉቦ ነው"" በማለት በቪድዮው ተገልጿል። ክሬምሊን ቤተ መንግሥቱ የፑቲን አይደለም ብሏል። በደቡብ ሩስያ ብላክ ሲ አካባቢ የሚገኘው ቤተ መንግሥት የሞኖኮ 39 እጥፍ ስፋት እንዳለው ተገልጿል። ቪድዮው የተለቀቀው ናቫልኒ ከጀርመን ወደ ሩስያ ከሄደ ከሁለት ቀን በኋላ ነበር። ናቫልኒ በቅድመ ምርመራ ለ30 ቀናት የታሰረ ሲሆን፤ ገንዘብ በመበዝበር የቀረበበትን ክስ በመጣሱ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። እሱ ግን እስሩ ፖለቲካዊ ነው ይላል። የ44 ዓመቱ ተቃዋሚ ባለፈው ነሐሴ ተመርዞ ለሞት ተቃርቦ ነበር። ለመመረዙ ተጠያቂው ፑቲን እንደሆኑ ቢናገርም፤ የሩስያ መንግሥት እጁ እንደሌለበት አስታውቋል። ቪድዮው ምን ያሳያል? የምርመራ ቪድዮው እንደሚያሳው ቤተ መንግሥቱ የተሠራው በፑቲን የቅርብ ሰዎች ሕገ ወጥ የገንዘብ ድጋፍ ነው። የነዳጅ ምርት ባለሥልጣኖች እና ቢሊየነሮች ከነዚህ መካከል ናቸውም ተብሏል። ናቫንሊ በቪድዮው ""በዚህ ገንዘብ ለአለቃቸው ቤተ መንግሥት ሠርተዋል"" ብሏል። የሩስያ ብሔራዊ የምርመራ ተቋም ቤተ መንግሥቱ ዙርያ ያለው 27 ስኩዌር ማይል መሬት ባለቤት እንደሆነም በቪድዮው ተጠቁሟል። ሕንጻው ውስጥ ካዚኖ (መቆመሪያ)፣ የበረዶ ሆኪ መጫወቻና ወይን ማቀነባበሪያ ይገኛል ተብሏል። ""ለመጣስ የሚከብድ አጥር አለው። ራሱን የቻለ ወደብና ቤተ ክርስቲያን አለው። በረራ ማድረግ ክልክል ነው። የድንበር ላይ ጥበቃ ኃይልም አለው። ሩስያ ውስጥ ያለ ራሱን የቻለ አገር ነው"" ሲል ናቫንሊ ተናግሯል። ናቫንሊ በጸረ ሙስና ንቅናቄ��� ይታወቃል። እአአ 2018 ላይ ፑቲን ተቀናቃኝ ሆኖ ምርጫ ሊወዳደር ሲል ገንዘብ የመበዝበዝ ክስ ተመስርቶበታል። ታዋቂው ሩስያዊ ተቃዋሚ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮች አሉት። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፐስኮቭ በቪድዮው ላይ የተባሉት ነገሮች ""ሐሰት ናቸው"" ብለዋል። ፕሬዘዳንቱ ""ምንም ቤተ መንግሥት የላቸውም"" ሲሉም ቃል አቀባዩ አስተባብለዋል። 22 ሚሊዮን ተመልካቾች ያገኘው የምርመራ ቪድዮ የሚገባደደው፤ ሕዝቡ ተቃውሞውን በአደባባይ እንዲገልጽ በማሳሰብ ነው። ""ከተበሳጩ ሰዎች 10 በመቶው እንኳን የተቃውሞ ሰልፍ ቢያደርጉ መንግሥት ምርጫውን ለማጭበርበር አይደፍርም"" ሲል ናቫንሊ ተናግሯል። ናቫንሊ የተመረዝኩት በፑቲን ነው ብሎ ወደ ሩስያ መመለሱ በርካቶችን አስገርሟል። ሆኖም ግን ማረሚያ ቤት ሆኖ ቪድዮው ከተለቀቀ በኋላ ደጋፊዎቹ ተቃውሞ እንዲካሄድ እያነሳሱ ነው። የናቫንሊ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? የካቲት 2 ናቫንሊ ፍርድ ቤት ይቀርባል። 2014 ላይ በፍርድ ቤት የተወሰነበት የሦስት ዓመት ተኩል እስር ስለመጽናቱም ውሳኔ ይተላለፋል። ከሦስት ቀናት በኋላ በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀርቦ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ጀግኖችን ስም የማጥፋት ክሱ ይታያል። ናቫንሊ ከተመረዘ በኋላ ጀርመን ውስጥ ህክምና ሲከታተል ነበር። ወደ ሩስያ ከተመለሰ እንደሚታሰር ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ወደ አገሩ ከመመለስ ወደኋላ አላለም። የቀረበበትን ክስ ""ፍትሕ ላይ መቀለድ ነው። ሕገ ወጥነት መንሰራፋቱን ያሳያል"" ሲል ተችቷል። 2018 ላይ የአውሮፓ የሰብአዊ መብት ፍርድ ቤት፤ የናቫንሊ ክስ ""የዘፈቀደ ነው"" ብሎ ነበር። መታሰሩ ከዚህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ጋር የሚቃረን ነው የሚል ጥያቄ ተነስቷል።" https://www.bbc.com/amharic/55735400 +sports "ሲፈን ሐሰን፡ ""ፈይሳ ሌሊሳ የእኔ ጀግና ነው''" "ሲፈን ሐሰን፡ ""ፈይሳ ሌሊሳ የእኔ ጀግና ነው''" https://www.bbc.com/amharic/50697605 +politics የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ድምጻቸውን አሰሙ "በአዲስ አበባ ""ብሔራዊ ክብር በሕብር"" በሚል በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ኢትዮጵያውያን በያሉበት ድምጻቸውን አሰሙ። በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ""እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ"" ፣ ""ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ የአገርን ሉዓላዊነት የሚጥስ ነው""፣ ""ግድቡ የኔ ነው"" የሚሉና መሰል መልዕክቶች በመኪናዎች ላይ በመለጠፍና በእጃቸው በመያዝ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል። ከአስተባባሪዎቹ አንዷ የሆኑት ክብሬ ተስፋዬ ድምጽ የማሰማቱ መርሃ ግብር ዓላማ በቀጥታ ጣልቃ ገብነትን የሚመለከቱ መግለጫዎችን ለሚያወጡ አካላት 'እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲያነሱ' ለመጠየቅ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ""የሕዳሴ ግድብ፣ በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጋር የሚነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ምርጫን ተከትሎ የውጭ ተጽዕኖ ኢትዮጵያ ላይ እየበረታ ነው"" ያሉት አስተባባሪዋ፤ የውጭ አካላት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ ለመጠየቅ መርሃ ግብሩ መካሄዱን ተናግረዋል። ""'ለኢትዮጵያ እናውቅላታለን' የሚል የውጭ ኃይል ሲመጣ፤ እኛ ደግሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ እናውቀዋለን፤ ስለዚህ እጃችሁን አንሱልን ነው ያልነው"" ብለዋል አስተባባሪዋ። የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለ ማለት ምን ያስቆጣል ተብለው የተጠየቁት አስተባባሪዋ፤ ተቃውሟቸው 'ለእናንተ እኛ እናውቅላችኋለን' ብለው ውሳኔና መፍትሔ ካልፈለግን ለሚሉት እንደሆነ ተናግረዋል። ""የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም መንግሥትም ያመናቸው እንዳሉና እኛም እያለቀስንበት ያለ ጉዳይ ነው"" በማለት ""የውስጥ ጉዳይን መፍታት ያለብን እኛው ነን"" ብለዋል። አስተባባሪዋ አክለውም ዛሬ በነበረው የመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ""በቀጥታ ጣልቃ ገብነትን የሚመለከቱ መግለጫዎችን ለሚያወጡት እጃቸውን እንዲያነሱ፤ አብረውን ለቆሙ ለተረዱን አገራት ደግሞ የምስጋና ደብዳቤ የማስገባት እቅድ ነበረን"" ብለዋል። ይሁን እንጂ አንዳንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች 'የጸጥታ ስጋት' በሚል መሥሪያ ቤታቸውን በመዝጋታቸው ይህንን ማድረግ እንዳልቻሉ አስረድተዋል። ድምጽ የማሰማት መርሃ ግብሩ አዲስ አበባ በሚገኘው ከአሜሪካ ኤምባሲ ውጪ ተቃውሞ እንደሚካሄድ ቀደም ብሎ የተገለጸ ቢሆንም በዛሬው ዕለት ይህ እንዳልተከናወነ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ገልጿል። ከሲቪክ ማኅበራት፣ ከሐይማኖት ተቋማት፣ እንዲሁም መንግሥታዊ ካልሆኑ አካላት የተዘጋጀ የተቃውሞ ደብዳቤ ወደ ኤምባሲዎች ለማስገባት ታቅዶ እንደነበርና ዛሬ ኤምባሲዎቹ ዝግ በመሆናቸው አለመሳካቱን ከመርሃ ግብሩ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ዐብይ ታደለ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል። ኮሚቴው ኤምባሲዎቹን ቀጠሮ እንዲሰጠው መጠየቁንና ቀጠሮውን በሚሰጣቸው ጊዜ ደብዳቤውን በአካል እንደሚያቀርቡ አስተባባሪው አክለዋል። የአሜሪካ ኤምባሲ ትናንት ባወጣው መግለጫ በማኅበራዊ የትስስር ገጾች በኤምባሲው አካባቢ ተቃውሞ ሊኖር እንደሚችል በመግለጽ አርብ መሥሪያ ቤቱ ዝግ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል። በትግራይ ውስጥ የህወሓት ኃይሎች በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ በተቀሰቀሰው ግጭት ሳቢያ እንዲሁም በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ምዕራባዊያንና ዓለም አቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር እየሞከሩ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ቅሬታውን ሲያሰማ ቆይቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ሌሎች የአገሪቱ ባለሥልጣናት በተለያዩ መድረኮች ላይ ምዕራባዊያን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት እየሞከሩ መሆናቸውን፤ ነገር ግን ይህ ተቀባይነት እንደሌለው ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይህ ""ብሔራዊ ክብር በሕብር"" የተሰኘው በታዋቂ ሰዎች የተዘጋጀው እንቅስቃሴም ዜጎች የውጭ አገር መንግሥታት በኢትዮጵያ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት እያደረጉ ነው ያሉትን ጥረት ለመቃወም የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57184359 +sports የሳዑዲ አረቢያ የሴቶች እግር ኳስ ሊግ ተጀመረ "በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ተጓትቶ የነበረው የሳዑዲ አረቢያ የሴቶች እግር ኳስ ሊግ ተጀምሯል። 600 እግር ኳስ ተጫዋቾች በ24 ቡድኖች ተከፍለው በሪያድ፣ ጅዳና ዳማም ከተሞች ለቻምፒየንሺፕ ዋንጫ ይፋለማሉ። ማክሰኞ አመሻሹን የተደረገው የመጀመሪያው ጨዋታ በቴሌቪዥን ባይተላለፍም የሳዑዲ መገናኛ ብዙሃን የሊጉ መጀመር ለሴቶች ተሳትፎ እመርታ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ሳዑዲ፤ ሴቶች ስታድየም ገብተው እግር ኳስ ጨዋታዎችን እንዲመለከቱ የፈቀደችው በፈረንጆቹ 2018 ነበር። ለዘመናት የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ባሕላዊና ኃይማኖታዊ እሴቶችን በማጣቀስ ሴቶች በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዳይሳተፉ ሲከለክሉ ቆይተዋል። ወግ አጥባቂዎች ሴቶች በስፖርት ጨዋታዎች መሳተፋቸው ወደ ኢ-ሞራላዊነት ይመራል ይላሉ። በመክፈቻው ቀን የሳዑዲ ሴቶች እግር ኳስ ሊግ ጨዋታዎች በዋና ከተማዋ ሪያድና በቀይ ባህሯ ጅዳ ከተማዋ ተከናውነዋል። ታይገርስ ጅዳ ቻለንጅን 11 ለባዶ፤ አል ሪያድ ዩናይትድ ናጅድ ሪያዲን 10 ለ 1 ያሸነፉበት ጨዋታ በርካታ ጎሎች የተቆጠሩበት ሆኗል። አሸናፊዋ ቡድን 500 ሺህ የሳዑዲ ሪያል ወይም 133 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ትሆናለች። የሳዑዲ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ��ጉን ያስጀመረው ሴቶች በስፖርትና ሌሎች ማሕበራዊ እንቅስቃሴዎች የጎላ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ነው ብሏል። አረብ ኒውስ ለሰተኘው ጣቢያ ድምጿን የሰጠችው የ16 ዓመቷ ናጂላ አሕመድ በፈረንጆቹ 2021 ከትምህርት ቤት አልፋ ለሊጉ ቡድን ለመጫወት እንደምትሻ ተናግራለች። ""የዚያኔ 17 ዓመት ይሆነኛል። ለመጫወት ብቁ እሆናለሁ ማለት ነው። ማን እንደሚያቆመኝ አያለሁ።"" በተያያዘ በዓለም የመጀመሪያው የሴቶች የጎልፍ ጨዋታ ሳዑዲ አራቢያ የተካሄደው በዚህ ሳምንት ነው። የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ተቺዎች ግን ሃገሪቱ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመሰል ክንውኖች እየሸፋፈነች ነው ሲሉ ይተቻሉ። በርካታ የሴቶች መብት ተሟጋቾች አሁንም በሳዑዲ እሥር ቤቶች ይገኛሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-54993325 +health """በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ የጤና ባለሙያዎች አሉ"" አይደር ሪፈራል ሆስፒታል" "በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ የሚገኘው ዋነኛ የሕክምና ተቋም አይደር ሪፈራል ሆስፒታል በቀን ከ4 እስከ 6 አስክሬኖች የሚሸኝበት ደረጃ እንደደረሰ ለቢቢሲ ገለጸ። በመድኃኒትና ሕክምና አገልግሎት እጥረት ከሞቱት መካከል የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች እንደሚገኙበትም አስታውቋል። ቢቢሲ ያነጋገረው የሆስፒታሉ የነርሲንግ አገልግሎት ኃላፊ ቴዎድሮስ ካህሳይ ከጦርነቱ በፊት ከትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ሆስፒታል አሁን ግን እጅግ መዳከሙን ገልጿል። ከአንድ ዓመት በላይ በሆነው የሰሜኑ ጦርነት ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል እና ከዓለም ተቆራርጣ ባለችው ትግራይ ክልል በሕክምና ቁሳቁሶች፣ መድሃኒቶችን እና የሰብዓዊ እርዳታዎች እጥረት በርካቶች ለከፋ ችግር መዳረጋቸው ሲዘገብ ቆይቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ የጤና ማዕከላት በአስፈላጊ መድኃኒት እጥረት ሳቢያ ሥራ ማቆማቸውን ያስታወቀ ሲሆን በትግራይ ክልል የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች በበኩላቸው ህፃናትን ጨምሮ ህሙማን በከፍተኛ መድኃኒት እጥረት ምክንያት እየሞቱ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማድረስ ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን አስታውቆ፤ የትግራይ ኃይሎች ከማንኛውም ጥቃት እንዲታቀቡና በኃይል ከያዟቸው የአጎራባች አፋር ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ ጠይቆ ነበር። ይህንን ተከትሎም የትግራይ ኃይሎች የተኩስ አቁም እንዳደረጉና ከአፋር ክልል ኤረብቲ መውጣታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ሳምንት ደግሞ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ህወሓት ከአፋር ክልል ሙሉ ለሙሉ ለመውጣት ዘላቂ፣ ያልተገደበ፣ ወቅታዊ እና በቂ የሆነ እርዳታ ማቅረብን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል። ቀደም ሲል የተደረገውን ስምምነት ተከትሎም ከሁለት ሳምንት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም 47 ምግብና ነዳጅን ጨምሮ የተለያዩ ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ ማድረሱን ገልጿል። አለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያዎችና የምግብ እርዳታ የጫኑ መኪኖቹ ከስድስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሜ መጋቢት 24፣ 2014 ወደ ትግራይ መግባታቸውን አስታውቋል። አሜሪካም በሰሜን ኢትዮጵያ ለተከሰተው ችግር የሚውል 313 ሚሊየን ዶላር የሚገመት የሰብዓዊ እርዳታ ማድረጓን ከትናንት በስቲያ አስታውቃለች። የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል የነርሲንግ አገልግሎት ኃላፊው ቴዎድሮስ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ ለሆስፒታሉ ሲሰጥ የነበረው ድጎማ እና የሕክምና ቁሳቁስ አነስተኛ እንደነበር አስታውሰው ላለፈው ���ንድ ዓመት ግን ሆስፒታሉ ካለምንም በጀት እየሠራ እንደሆነ ተናግሯል። "" በአሁኑ ሰዓት 30 በመቶ በሚሆን አቅም ነው አገልግሎት እየሰጠን ያለነው፤የመድሃኒት ክምችታችን ወደ 10 በመቶ ወርዶ ነበር። ከዓለም ጤና ድርጅት የመጣ እርዳታ ተጨምሮበት ክምችቱ ወደ 20 በመቶ ደርሶ ነበር። ነገር ግን ይህ ለሆስፒታሉ የተሰጠው መድሃኒት ያለቀው በሁለት ሳምንት ውስጥ ነው"" ይላል። ኃላፊው እንደሚሉት ድጋፍ የተደረጉላቸው መድሃኒቶች በዓይነትም እጅግ አነስተኛ እንደነበር ጠቁመዋል። ኃላፊው እንደ ካንሰር፣ ደም ግፊት ላሉ ስር የሰደዱ በሽታዎች ምንም ዓይነት መድሃኒት አለመግባቱን በመግለፅም ለሳንታት ታይቶ የነበረው የሆስፒታሉ አገልግሎት መሻሻል ተመልሶ መውረዱን አክለዋል። ለላብራቶሪ የሚውሉ ግብዓቶች ፣ መድሃኒቶች፣ ማሽኖችን ማንቀሳቀሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ፣ ተኝተው ለሚታከሙ የሚቀርብ ምግብ ፣ ለሠራተኞች የሚከፈል በሌለበት መስራትም አስቸጋሪ አንደሆነ ቴዎድሮስ ገልጿል። ""በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ ባልደረቦቻችን አሉ"" በሆስፒታሉ ድንገተኛ ክፍል ውስጥ ነርስ የሆነው ገብረይ አቢዩ "" ሰዎች ለሕክምና መጥተው እያየናቸው ሕይወታቸውን ሲያጡ እጅግ እናዝናለን"" ይላል። የሆስፒታሉ ሠራተኞች በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ሆነው እየሠሩ እንደሆነ የሚናገረው አቶ ገብረይ ""በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ ባልደረቦቻችን ግን አሉ"" ይላል። ""ከባድ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው ሰዎች ሙያዊ ድጋፍ ፈልገው ሲመጡ ምንም ሳይደረግላቸው ሲቀር ሥራ ቦታ ብቻ ሳይሆን ቤት ሄደህም ሰላም አታገኝም። ለሊት ተኝተህ ወደ ህሊናህ የሚመጣ ብዙ ነገር አለ። ሕጻናት መጥተው በኦአርኤስ ወይም በሌላ ትንሽ ነገር ሕይወታቸውን ማትረፍ እየተቻለ ይህ ባለመኖሩ ስታጣቸው በጣም ከባድ ነው። እጆችህን አጣጥፈህ ነው ቆመህ የምታየው። ልብህን የሚያደማ እንጂ ደስ ብሎህ የምትሠራው ሥራ አይደለም።"" ሲሉ በሆስፒታሉ ያለውን ችግር ያስረዳሉ። ችግሩ ይህ ብቻ አይደለም፤ ድርብርብ ነው። የትራንስፖርት አገልግሎት ባለመኖሩም ለ11 ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው ሠራተኞች እስከ 2 ሰዓት የሚወስድ መንገድ በእግር ተጉዘው ሆስፒታሉ እንደሚደርሱ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የጤና ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ""የጤና ባለሙያዎችም በሕክምና አገልግሎት እጦት ሕይወታቸው አልፏል"" ቴዎድሮስ እንደሚለው የመድኃኒትና የሕክምና አገልግሎት እጥረት የታካሚዎችን ሕይወት ብቻ ሳይሆን የጤና ባለሙያዎችንም ሕይወት እየቀጠፈ ነው። ""በዚህ ሁለት ወር 2 ነርሶች ሞተውብናል። መዳን ይችሉ ነበር፤ ግን መድኃኒት ማግኘት አልቻሉም። በተለይ አንደኛዋ ነርስ ኤምአርአይ ማሽኑ እየሠራ ስላልሆነ በሽታዋን በግልጽ ማወቅ አልተቻለም። በዚህ ምክንያት ሕመሟ ጸንቶ ሞታለች። ሁለተኛው ነርስ ደግሞ ሊወስደው የሚገባ መድኃኒት እዚህ ሆስፒታል ስለሌለ ያጣነው ባልደረባችን ነው። አሁን በቀን እስከ 4 አልፎም እስከ 6 አስክሬን ከዚህ ሆስፒታል ይሸኛል። ከዚህ በፊት ግን በሁለት ወይም ሦስት ቀን አንድ ሬሳ ነበር የሚወጣው"" ይላል። በሕክምና እጦት ምክንያት ሕይወታቸው ከሚያልፍ የጤና ባለሙያዎች መካከል አብዛኞቹ የክሮኒክ በሽታዎች ተጠቂ መሆናቸውንም ኃላፊው ገልጿል። ትግራይ ባለው የጥሬ ገንዘብ እጥረት ምክንያት ሆስፒታሉ ለሚሰጠው አግልግሎት ከታካሚዎች የሚጠይቀው ገንዘብም እጅግ ዝቅተኛ ክፍያ [ከቀድሞው ከ90 በመቶ ያነሰ) ነው። ""በሆስፒታሉ የማይገኙ መድኃኒቶችን ከውጭ ለመግዛት የተቸገሩ ሰዎች፣ ከሩቅ የትግራይ አካባቢ መጥተው መመለሻ ያጡ ሰዎች፣ የሞቱ ቤተሰቦቻቸውን አስክሬን ለመውሰድ የሚቸገሩ ሰዎችን ማየት የሠራተኞቹን ልብ በሐዘን ይሰብራል"" ብሏል። ለታካሚዎችና ለተወሰኑ ሠራተኞች ይቀርብ የነበረ ምግብ ላለፉት 10 ቀናት ውስጥ ስለተቋረጠ እስከ 240 ታካሚዎች ወደ ቤታቸው እንደተሸኙም አክሏል። ከዚህ ቀደምም የአይደር ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ባወጡት መግለጫ በቀዶ ህክምና ወቅት የሚያስፈልጉ በደም ስር የሚሰጡ (intravenous fluids) እና የሰመመን መስጫ መድኃኒቶች ባለመኖራቸው ቀዶ ህክምና ማድረግ አለመቻላቸውን ነው። በተደጋጋሚ የሚከሰተው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና ያልተሟላ የኦክስጂን አቅርቦት ለታካሚዎች ሞት ምክንያት ነው ብለዋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶች መብራት፣ ውሃ፣ ስልክ፣ ትራንስፖርትና የባንክ አገልግሎቶች ተቋርጠው ይገኛሉ። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልገው ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ገልጿል። አስራ ስምንት ወራት ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ የአፍሪካ ሕብረትና ሌሎች አጋሮች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ከሰሞኑ የኢትዮጵያ መንግሥትና የትግራይ ኃይሎች ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ አቁም ያወጁ ሲሆን ይህም ለሰላም በር ሊከፈትና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማብቃት ወደሚያስችል ውይይት መሄድ እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61132952 +health ከበርካታ ሕጻናት ሞት በኋላ በ4 የሕንድ ምርት በሆኑ ሽሮፖች ላይ ማስጠንቀቂያ ወጣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሕጻናት ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ የሕንድ ምርት በሆኑ አራት የሽሮፕ አይነቶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ። የዓለም ጤና ድርጅት ዓለም አቀፍ ማስጠንቀቂያውን ያወጣው በአፍሪካዊቷ ጋምቢያ የ66 ሕጸናት ሕልፈት ከሽሮፖቹ ጋር ሳይገናኝ አይቀርም ከተባለ በኋላ ነው። ሽሮፖቹ ለከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት እና ለ66 የሕጻናት ሞት ምክንያት ሳይሆኑ አይቀርም ብሏል የዓለም ጤና ድርጅት። የዓለም ጤና ድርጅት ወላጆች ለልጆቻቸው ከመስጠት መቆጠብ አለባቸው ያላቸው ሽሮፖች ፕሮመታዚን ኦራል ሶሉሽን (Promethazine Oral Solution)፣ ኮፌክስማሊን ቤቢ ካፍ ሲረፕ (Kofexmalin Baby Cough Syrup)፣ ማኮፍ ቤቢ ካፍ ሲረፕ (Makoff Baby Cough Syrup) እና ማግሪፕ ኤን ኮልድ ሲረፕ (Magrip N Cold Syrup) የሚባሉት ናቸው። እነዚህ የሕጻናት ሽሮፖችን ያመረተው ማይደን ፋርማሱቲካልስ የሚባል የሕንድ ኩባንያ ሲሆን፤ ለሽሮፖቹ የደኅንነት ማስረጃ ማቅረብ አለመቻሉን የዓለም ጤና ድርጅት ጨምሮ አስታውቋል። አምራቹ ኩባንያ በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም። ቢቢሲም ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም። የሕንድ ባለሥልጣናት በበኩላቸው ሽሮፖቹ ለሕጻናቱ ሞት ምክንያት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲሰጣቸው የዓለም ጤና ድርጅትን መጠየቃቸው ተገልጿል። ሽሮፖቹን መጠቀም በተለይ በሕጻናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ወይም ሞትን ሊያስከትል እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ሽሮፖቹ የጤና ጉዳት እንደሚያስከትሉ ማወቅ የቻለው የጎብኚዎች መዳረሻ በሆነችው በጋምቢያ በተለይ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት የሚያጋጥማቸው ሕጻናት ቁጥር መጨምሩን ተከትሎ ነው። ይህን ተከትሎ የአገሪቱ መንግሥት ዜጎች ፓራሲታሞል ሽሮፖችን መጠቀም በማቆም በምትኩ የሚዋጥ ኪኒኒ ��ንዲጠቀሙ አሳስቧል። የጋምቢያ ጤና ኃላፊዎች ባለፈው ወር ትክክለኛውን ቁጥር ሳይጠቅሱ በርካታ ሕጻናት ሕይወታቸው አልፏል ብለው ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት በሽሮፖቹ ላይ በተደገረ ምርመራ ዳይታይለን ግላይኮል እና ኢታይለን ግላይኮል የተሰኙ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ንጥረ ነገሮች ተገኝተዋል። እነዚህ ንጥረ ነገሮች መርዛማ ሲሆኑ የሆድ ሕመም፣ ትውከት፣ ተቅማጥ፣ ራስ ምታት እና ለሞት የሚዳርግ ከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ረቡዕ መስከረም 25/2015 ዓ.ም. በጄኔቭ ንግግር ሲያደርጉ፤ “የእነዚህ ጨቅላ ሕጻናት ሕልፈት ለወላጆቻቸው ልብ የሚሰብር ነው” ብለዋል። የሕንድ ማዕከላዊ የመድኃኒት ጥራት ተቆጣጣሪ ድርጅት ሽሮፖቹ ለጋምቢያ ብቻ መላካቸውን ለዓለም ጤና ድርጅት መግለጹን ኤአፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ምንም እንኳ እነዚህ አራት የሕጻናት ሽሮፕ አይነቶች የተሰራጩት በጋምቢያ ብቻ ነው ቢባልም መደበኛ ባልሆነ የገበያ ስንሰለት ወደ ተቀሩት ጎረቤት አገራትም ሳይሰራጩ አይቀርም ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም የዓለም ጤና ድርጅት አምራቹ ሽሮፖቹ ውስጥ የተገኙትን መርዛማ ኬሚካሎች በሌሎች ምርቶቹ ላይ በመጠቀም ሕንድ ውስጥ እና ወደተቀረው ዓለም ልኮ ሊይሆን ይችላል ብሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c29eg84k0gko +sports ባሎንዶር፡ እውን ሜሲ የዘንድሮው ሽልማት አይገባውም? "የዘንድሮው የባሎን ዶር ሽልማት አከርካሪ ሆኗል። ሽልማቱ ለፖላንዳዊው ሌቫንዶቭስኪ ነው የሚገባው ከሚለው ወቀሳ ጀምሮ ሞሐመድ ሳላህ ሰባተኛ መውጣቱ አግባብ አይደለም የሚሉ ደምፆች እየተሰሙ ነው። አርጀንቲናዊው ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ሽልማቱን ለሰባተኛ ጊዜ በማንሳት ታሪክ ፅፏል። ነገር ግን እንደዚህ ቀደሙ የይገባዋል ድምፅ ሳይሆን ሌቫንዶቭስኪ እያለ እንዴት በሚሉ ትችቶች የታጀበ ሆኗል። እርግጥ ነው የ34 ዓመቱ ሜሲ ያሳለፈው የውድድር ዘመን የከፋ የሚባል አልነበረም። ሜሲ በ2021 40 ጎሎች አስቆጥሯል። 28 ለባርሴሎና፤ 4 ለፒኤስጂ እንዲሁም 8 ለሃገሩ አርጀንቲና። ሜሲ በእግር ኳስ ሕይወቱ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ዋንጫ ያነሳው በዚህ ዓመት አርጀንቲና የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ አሸናፊ ስትሆን ነው። እና ለምን ሽልማቱ አይገባውም የሚሉ ድምፆች በረከቱ? በርካታ የእግር ኳስ ተንታኞች የባየር ሚዩኒክና ፖላንድ የፊት መስመር ተጫዋች የሆነው ሮበርት ሌቫንዶቭስኪ የዘንድሮው ባለን ዶር ሽልማት አሸናፊ ሊሆን በተገባ ነበር ይላሉ። የ33 ዓመቱ አጥቂ ዘንድሮ ለባየርን በሁሉም ውድድሮች 53 ጎሎች በማስቆጠሩ የዓመቱ ምርጥ አጥቂ የተሰኘ ሽልማት ተበርክቶለታል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተሰረዘው የባለፈው ዓመት የባለን ዶር ሽልማት ተዘጋጅቶ ቢሆን ኖሮ አሸናፊው ሌቫንዶስኪ እንጂ ሌላ ማንም ሊሆን አይችልም የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ሌቫንዶቭስኪ ከባየርን ጋር ባለፈው ዓመት የጀርመን ዋንጫ፣ ቡንደስሊጋ እንዲሁም ቻምፒዮንስ ሊግ ማንሳት ችሏል። በ2021 ባየርን ቡንደስሊጋ ለዘጠነኛ ተከታታይ ጊዜ ሲያነሳ ሌቪ በቡንደስሊጋው በአንድ የውድድር ዘመን በርካታ ጎሎች በማግባት በ41 ጎሎች የገርድ ሙለርን ክብረ ወሰን መስበር ችሎ ነበር። እግር ኳስ ተጨዋቾች፣ አሠልጣኞች እንዲሁም ተንታኞች ትላንት አመሻሹን ከተከናወነው የባለን ዶር ሽልማት በኋላ ሐሳባቸውን ሰጥተዋል። የሪያል ማድሪዱ አማካይ ቶኒ ክሩስ ""ሜሲ ሽልማቱ በጭራሽ አይገባውም"" ብሏል። ሜሲና ሮናልዶ ያለፈውን 10 ዓመት በበላይነት መያዛቸው የማያከራክር ቢሆንም ዘንድሮ ግን ሽልማቱ የሚገባው ለሌላ ሰው ነበር። ሌላው ቀርቶ ሜሲ እንኳ ሳይቀር ሽል��ቱን ሲቀበል ሌቪ ባለን ዶር ይገባው እንደነበር ተናግሯል። በሌላ በኩል የወቅቱ የዓለማችን ድንቅ ተጫዋች እየተባለ እየተሞካሸ ያለው ግብፃዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሞ ሳላህ ሰባተኛ መውጣቱ ብዙዎችን አስከፍቷል። የሊቨርፑል አሠልጣኝ ዩርገን ክሎፕ ሞ ሳላህ የተሻለ ድምፅ ማግኘት በተገባ ነበር ሲሉ ማክሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ክሎፕ አክለው ሜሲ የሕይወት ዘመን ሽልማት ቢሆን ኖሮ ወርቃማው ኳስ ይገባው ነበር ሲሉ የሽልማቱን አዘጋጆች ሸንቆጥ አድርገዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59483014 +business በቅርቡ ከወጣው ኮንዶሚኒየም ዕጣ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ አዲስ አበባ ውስጥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለማግኘት ለተመዘገቡ ሰዎች በተካሄደው የዕጣ ሂደት ላይ ከታዩ ጉድለቶች ጋር በተያያዘ የከተማው አስተዳደር ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ። ባለፈው ሳምንት አርብ ሐምሌ 01/2014 ዓ.ም. 25ሺህ 491 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በ20/80 እና የ40/60 የቁጠባ መርሃ ግብር አማካይነት ለባለ ዕድሎች እንዲደርስ ዕጣ መውጣቱ አስታውቆ ነበር። ይህንን ሂደት ተከትሎም የተለያዩ ወገኖች በዕጣ አወጣጡና በዕጣው ውስጥ በተካተቱ ሰዎች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያነሱ ቆይተው፣ የከተማው አስተዳደር አደረግኩት ባለው ማጣራት ችግሮች እንዳሉ አረጋግጧል። በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ያሉ ምንጮች ለቢቢሲ እንደገለጹት ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቢያንስ ሁለት ኃላፊዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል። ሰኞ ዕለት የከተማው አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ላይም ቤቶቹን ለማስተላለፍ ከተከናወነው የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች መቅረባቸውን አመልክቷል። ይህንንም ተከትሎ በዕጣው ውስጥ በተካተተው መረጃ ላይ በተደረገው ማጣራት “በባንክ የተላከውና ለዕጣ እንዲውል ወደ ኮምፒውተር የተጫነው ዳታ ላይ ልዩነቶች ተግኝተዋል” ሲል ተፈጠረ ያለውን ችግር አመልክቷል። ጨምሮም ባለፈው አርብ በወጣው የቤቶች ማስተላለፍ የዕታ ሂደት ላይ በተደረገው ማጣራት “ላልቆጠቡ ሰዎች ዕጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል” ሲል ገልጿል። የከተማው አስተዳደር የተዓማኒነት ጉድለቶች ያላቸውን ጉዳዮች ዝርዝር እንዲሁም ጉድለቱ የታየው ምን ያህል ቤቶች ላይ መሆኑን አላሳወቀም። በዚህም ምክንያት የቤት ማስተላለፍ ሂደቱ ላይ ተከስተዋል የተባሉ “የተዓማኒነት ጉድለቶች” ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት ተጨማሪ የማጣራት ሥራ በመከናወን ላይ ነው ብሏል የከተማው አስተዳደር ባወጣው መግለጫ። ከተከሰተው የአሰራር መዛባት ጋር በተያያዘም “የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገባቸው” እንደሚገኝም አረጋግጧል። ምርመራው ስለደረሰበትም ሂደት ሆነ ስለተጠረጠሩ አመራሮችን በተመለከተ ቢቢሲ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚመለከታቸውን የአስተደዳሩን ኃላፊዎች ለማግኘት በተደጋጋሚ ቢሞክርም ምላሽ ማግኘት አልቻለም። የከተማዋ ነዋሪዎችን ባለቤት ለማድረግ በማቀድ በ1997 ዓ.ም. የተጀመረው የጋራ መኖሪያ ቤት ከዓመት ወደ ዓመት እየናረ ያለውን የቤት ኪራይ ጫናንም ለበርካቶች ያቃልላል የሚል ተስፋ ተሰንቆበት ነበር። ነዋሪዎች የተወሰነውን ቆጥበው በዓመታት ይከፍሉታል በተባለው 20/80 እንዲሁም 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮጀክት እንደታሰበው የግንባታው ሥራ ሊከናወን አልቻለም። ለዓመታት በርካቶች ቆጥበው ቤቶች እንዳልደረሳቸው የሚናገሩ ሲሆን በተጨማሪም ሳይወረራዱ የቀሩ ብሮች፣ ሕገወጥ የመሬት ይዞታዎችና የሌሎች ውዝግቦች ምንጮች ሆነዋል። በባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ በአ���ስ አበባ 21 ሺህ 695 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሕገ-ወጥ ተይዘው መገኘታቸውን ከንቲባዋ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ማስታወቃቸው ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cw53zpx3wx3o +business ከአዲስ አበባ ኮምቦልቻ ተቋርጦ የነበረው በረራ ሊጀመር ነው ከአዲስ አበባ ወደ ኮምቦልቻ/ደሴ ተቋርጦ የነበረው በረራ ከታኅሣሥ 27/2014 ዓ.ም ሊጀመር መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ። አየር መንገዱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አክሎ እንዳሰፈረው ከተጠቀሰው ዕለት ጀምሮ በየቀኑ በረራዎች እንደሚኖሩ ነው። የደቡብ ወሎ ከተሞች የሆኑት ደሴና ኮምቦልቻ በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ነበር አየር መንገዱ ወደ ኮምቦልቻ የሚያደርገውንና ሁለቱን ከተሞች የሚያገለግለውን በረራ አቋርጦ የነበረው። አየር መንገዱ በኮምቦልቻ አየር ማረፊያ የሚያደርጋቸውን የየቀኑ በረራዎች ለሁለት ወራት ያህል አቋርጦ ነበር። ከኮምቦልቻ በተጨማሪ በላሊበላ ለወራት ተቋርጦ የነበረው በረራም በትናንትናው ዕለት ታኅሣሥ 25/2014 ዓ.ም መጀመሩን አየር መንገዱ በተጨማሪ ገልጿል። በህወሓት ቁጥጥር ስር በነበሩ ከተሞች የመብራት፣ ውሃና ስልክ አገልግሎት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን መንግሥት እነዚህን ከተሞች በስሩ ማድረጉን ተከትሎ የመብራትና፣ ውሃና ስልክ አገልግሎት ተመልሷል። በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞችም እንዲሁ ተቋርጦ የነበረው ኢንተርኔት አገልግሎት (ዳታ) መመለሱንም ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም የባንክ አገልግሎቶች በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች የተመለሱ ሲሆን ትራንስፖርት በአንዳንድ አካቢዎች መጀመሩም ተነግሯል። የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ ትምህርት ቤቶች መከፈታቸውንም ቢቢሲ ከነዋሪዎች በሰበሰው መረጃ መረዳት ችሏል። ከጦርነቱና ትራንስፖርት መገደብ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ ንሮ የነበሩ መሰረታዊ ሸቀጣሸቀጦች ዋጋም በተወሰነ መልኩ መቀነስ እንዳሳየም ነዋሪዎች ገልጸዋል። ሆኖም በአሁኑ ወቅትም በአማራ ክልል አንዳንድ ከተሞች ለምሳሌ በሰቆጣ ከተማና አካባቢው የመብራትና ውሃ አገልግሎት አሁንም እንዳልተመለሰ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶች መብራት፣ ውሃ፣ ስልክና የባንክ አገልግሎቶች አሁንም እንደተቋረጡ ናቸው። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች በተለያየ ደረጃ እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠሩ የሚችሉ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግና የስደተኛ ሕግ ጥሰቶችን መፈፀማቸውን የመብት ተቆርቋሪዎች ያወጧቸው ሪፖርቶች ያመለክታሉ። ከአስራ አራት ወራት በላይ ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ የአፍሪካ ሕብረት እንዲሁም የሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ እና ሌሎች አጋሮች ጥረት ቢያደርጉም ፍሬ አላፈራም። https://www.bbc.com/amharic/news-59864724 +health በሽታን በሚከላከሉ ክትባቶች መካከል ለምን ልዩነት ተፈጠረ? የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት አንድን ሰው እስከ ምን ያህል ጊዜ ከበሽታው ሊከላከል እንደሚችል ማንም እርግጠኛ አይደለም። አንዳንድ ክትባቶች እስከ እድሜ ልክ በሽታን የመከላከል አቅም ሲኖራቸው ሌሎች ደግሞ በተወሰነ ጊዜ የተገደበ የመከላከል አቅምን ያዳብራሉ። ይህ ልዩነት እንዴት ሊፈጠር ቻለ? ይህ ቪዲዮ ምላሽ አለው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cyrdrpjd6d2o +politics መሪዋን ከቀናት በፊት በድምጽ ብልጫ ያነሳችው ፓኪስታን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መረጠች የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን እሁድ ዕለት ያለመተማመን ድምጽ [አንድ በሥልጣን ላይ ያለ ግለሰብ በኃላፊነቱ ለመቀጠል ብቁ ነው ወይስ አይደለም በሚል የሚሰጥ ድምጽ] ብልጫ ከሥልጣናቸው ከተነሱ በኋላ የፓኪስታን ፓርላማ ሼህባዝ ሻሪፍን የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መረጠ። ካንን ከሥልጣን ለማውረድ ሲሰሩ የነበሩ የተቃዋሚዎች ጥምረት መሪ የፓርላማውን አብላጫ ድጋፍ ማግኘት ችለዋል። በመሆኑም ሼህባዝ ሻሪፍ ነሐሴ 2023 ምርጫ እስከሚደረግ ድረስ ሥልጣን ላይ የሚቆይ አዲስ መንግሥት ይመሰርታሉ። የ69 ዓመቱ ካን ከሥልጣናቸው የተነሱት ቀናትን ካስቆጠረና ከብዙ የፖለቲካ ድራማ በኋላ አነስተኛ ድምጽ በማግኘት ነበር። ካን ከዚህ ቀደም ፓርላማውን በመበተን እና በአስቸኳይ ምርጫ እንዲካሄድ በመጠየቅ በእርሳቸው ላይ ሊካሄድ የነበረውን ያለመተማመን ድምጽ አሰጣጥ እንዲዘገይ ሙከራ አድርገው ነበር። ይሁን እንጂ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድርጊቱ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይቃረናል በማለት የተቃዋሚዎችን አቤቱታ በማጽደቅ ያለመተማመን ድምጽ አሰጣጡ እንዲቀጥል አዝዟል። በመሆኑም ሰኞ ዕለት ሻሪፍ ያለምንም ተቀናቃኝ በፓርላማው የተመረጡ ሲሆን የፓኪስታን 23ኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ። የተቀናቃኝ እጩ ሸህ ማህሙድ ቁረይሺ በካን የሚመራው የፓኪስታን 'ተህሪክ ኢ ኢንሳፍ' ፓርቲ የፓርላማውን ድምጽ እንደማይቀበለው በመግለጽ አዳራሹን ጥሎ መውጣቱን አስታውቀዋል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፓርቲያቸው አብዛኞቹ የምክርቤት አባላት ከድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ቀደም ብሎ ከምክር ቤት አባልነታቸው ለቀዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-61020768 +sports ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ተጋጣሚዎቻቸውን በብቃት በመርታት ሩብ ፍጻሜን ተቀላቀሉ ኳታር እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ዋንጫ ትናንት የጥሎ ማለፍ ጨዋታቸውን ያደረጉት ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ተጋጣሚዎቻቸውን በመርታት ወደ ቀጣይ ዙር አለፈዋል። ፈረንሳይ ከፖላንድ ተገናኝታ 3 ለ 1 ያሸነፈች ሲሆን እንግሊዝ ደግሞ ሴኔጋልን 3 ለ 0 ረትታለች። ትናንት ታጋጣሚዎቻቸውን በብቃት ያሸነፉት ሁለቱ ቡድኖች በሩብ ፍጻሜው እርስ በርስ የሚገናኙ ሲሆን ገና ከአሁኑ በርካቶች ጨዋታውን ከፍጻሜ በፊት ለዋንጫ የሚደረግ ጨዋታ ነው እያሉት ይገኛል። የፈረንሳይ እና እንግሊዝ ግጥሚያ የፊታችን ቅዳሜ ምሽት 4 ሰዓት ይካሄዳል። 12 ሰዓት ላይ ቀድሞ በተካሄደው ጨዋታ ኦሊቪዬ ጂሩድ ቡድኑን ቀዳሚ ያደረገች ጎል ሲያስቆጥር ጎሏ ደግሞ ለእርሱ የምንግዜም የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ አድርገዋለች። የቀድሞ የአርሰናል እና ቼልሲ የአሁን የኤሲ ሚላን አጥቂው የ36 ዓመቱ ጂሩድ ለአገሩ እስካሁን ድረስ 52 ጎሎችን አስቆጥሯል። ከጁሩድ ጎል በኋላ ትናንት ድንቅ ሆኖ ያመሸው ካሊያን ምባፔ ሁለቱ ቀሪ ጎሎችን አስቆጥሯል። ምባፔ ትናንት ያስቆጠራቸውን ሁለት ጎሎች ጨምሮ በውድድሩ አምስት ጎሎችን በማስቆጠር እየመራ ይገኛል። በምድብ ጨዋታቸው ኳታር እና ኤኳዶርን አሸንፈው ወደ ጥሎ ማለፉ የገቡት ሴኔጋሎች፤ እንግሊዝ ላይ ያልተጠበቀ ውጤት ሊያስመዘግቡ ይችላሉ የሚል ግምት ነበር። ሆኖም ግን ሴኔጋሎች አንድ ግዜ ብቻ ዒላማውን የጠበቀ ሙከራ አድርገው ከተሸነፉ በኋላ ከውድድሩ ተሰናብተዋል። በአሁኑ ወቅት በውድድሩ ላይ ያለችው አፍሪካዊት አገር ሞሮኮ ብቻ ናት። ሞሮኮ ነገ ኃያሏን ስፔንን ትገጥማለች። እንግሊዞች ሴኔጋልን 3 ለ 0 ያሸነፉት ከፍጽም የበላይነት ጋር ነበር። የእንግሊዝን የማሸነፊያ ጎሎች ጆርዳን ሄንደርሰን፣ ሃሪ ኬን እና ቡካዮ ሳካ ሲያስቆጥሩ ኮከብ ሆኖ ያመሸው ግን አማካዩ ጁድ ቤሊንግሃም ነበር። የቦሪሺያ ዶርትመንዱ አማካይ የመጀመሪያውን ጎል አመቻችቶ ከመስጠቱም በላይ እንግሊዝ ሁለተኛውን ጎል ማስቆጠር እንድትችል የመልሶ ማጥቃት ሥራ በበላይነት ሲከወን የነበረው ይህ የ19 ዓመት ወጣት ነበር። https://www.bbc.com/amharic/articles/cnlgk9zex0ro +sports የአየር ትራንስፖርት፡ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የአየር ትራንስፖርተ ዘርፍ ሥራዎች አሁንም አደጋ ላይ ናቸው ተባለ "በኮሮናቫይረስ ምክንያት በመቶ ሺዎቹ የሚቆጠሩ የአየር መጓጓዣ ሥራዎች አሁንም አደጋ ላይ እንደሚገኙ ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር አስታወቀ። 290 አየር መንገዶችን የሚወክለው ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር የአየር ትራፊክ በ2019 ከነበረው ከ2020 ጋር ሲነጻጸር በ66 በመቶ ይቀንሳል ሲል ተንበያውን አሳውቋል። በማኅበሩ ቅድመ ግምት መሠረት ከወረርሽኙ በኋላ የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ወደቀደመ ደረጃው የሚመለሰው ከአራት ዓመታት በኋላ በ2024 ይሆናል ብሏል። በበርካታ አገራት የኮሮናቫይረስ ሁለተኛ ዙር ስርጭት መከሰቱ እና መንግሥታት አሁንም የጉዞ ክልከላዎችን መጣላቸው ኢንዱስትሪ የሚፈለገውን ያክል ለውጥ እንዳያስመዘግብ ምክንያት ሆኗል ተብሏል። ኮሮናቫይረስ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ ከፍ ባለበት ወቅት የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው በከፍተኛ መጠን መጎዳቱ ይታወሳል። ግዙፍ አየር መንገዶች፣ አየር ማረፊያዎች እና አስጎብኚ ደርጅቶች በሺህዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቻቸውን ለመቀነስ መገደዳቸውን አሳውቀው ነበር። ""አየር መንገዶች ከመንግሥት ድጋፍ አለማግኘታቸው እና ደንበሮች ዝግ ሆነው መቆየታቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሥራቸውን እንዲያጡ ምክንያት ይሆናል"" ብለዋል የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሌክሳንደር ዲ ጁኒአካ። ""መንገደኞች ያለ ስጋት እንዲጓዙ፤ መንግሥታት ደግሞ ደንበሮቻቸውን እንዲከፍቱ ለማበረታታት አየር መንገዶች ተጓዦች ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ይዘው እንዲቀርቡ ማደረግ ይኖርባቸዋል"" ብለዋል ዋና ሥራ አስፈጻሚው። ከዚህ ቀደም 3 ሺህ 500 ሠራተኞቹን የቀነሰው ቨርጅን አትላንቲክ አሁንም ተጨማሪ 1 ሺህ 150 ሰዎችን ሊቀንስ መሆኑን አስታውቋል። አየር መንገዱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በሥራ ላይ የሚቆይበትን ጊዜ በ18 ወራት ለማራዘም አቅዶ ነው ተብሏል። የዓለማችን ግዙፉ አየር መንገድ አሜሪካን ኤርላይንስ በበኩሉ ባለፈው ወር 19 ሺህ ሠራተኞቹን እንደሚቀንስ አስታውቆ ነበር። አየር መንደጉ በወረርሽኙ ሳቢያ 30 በመቶ ሠራተኞቹን እንዲቀንስ መገደዱ ተጠቅሷል። ሌላኛው የአሜሪካ ግዙፍ አየር መንገድ ዩናይትድ ኤርላይንስ በበኩሉ 36 ሺህ ሠራተኞቹ ሊቀንስ እንደሚችል አስታውቆ ነበር። የጀርመኑ ሉፍታንዛ 22 ሺህ ሠራተኞችን ሊቀንስ እንደሚችል አስታውቋል። ብሪቲሽ ኤርዌይስ ደግሞ 13 ሺህ ሠራተኞችን ቀንሷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54351583 +health በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተመዘገቡ በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረጉ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተገለጸ። በየዕለቱ የሚደረጉ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎችን መሠረት በማድረግ ማክሰኞ ታኅሣሥ 13/2014 ዓ. ም በጤና ሚኒስቴር በኩል የወጣው መረጃ እንዳመለከተው 2,323 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ይህ አሐዝም ከዚህ በፊት በአንድ ቀን ከተመዘገቡት በጣም ከፍተኛው ነው። በየዕለቱ በ24 ሰዓት ይፋ የተደረጉ ቀደም ያሉ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ዕለታዊ አሐዝ ከ500 እስከ 1000 ባለው መካከል የቆየ ነበር። የማክሰኞ ዕለቱ ሪፖርት እንዳመለከተው 2,323 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው በዕለቱ ምርመራ ካደረጉ 10,016 ሰዎች መካከል ነው። እስካሁን በአገሪቱ በወረርሽኙ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 379,379 የደረሰ ሲሆን፣ ትናንት ለተመዘገበው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ምክንያቱ ምን እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር እስካሁን የሰጠው መረጃ የለም። እስካሁን በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ከነበሩ መካከል 351,168 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ 6,877 ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በዓለም ዙሪያ ክትባት እየተሰጠ ቢሆንም፤ በቅርቡ የተከሰተው ኦሚክሮን የተባለው አዲስ ዓይነት ዝርያ የበሽታውን የመስፋፋት ፍጥነትና አደገኝነት እንዳባባሰው የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል። ይህ መጀመሪያ ላይ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መገኘቱ የተነገረው ኦሚክሮን በርካታ ሰዎች ላይ እየተገኘ ሲሆን አገራት በሽታውን ለመቆጣጠር ጥብቅ እርምጃ እየወሰዱ ነው። ይህ የወረርሽኙ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመገኘቱ በጤና ባለሥልጣናት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም። https://www.bbc.com/amharic/news-59730317 +politics የናንሲ ፔሎሲ ባለቤት ጠጥቶ በማሽከርከር ጥፋተኛ ተባሉ የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ባለቤት ጠጥተው መኪና በማሽከርከር ብሎም ጉዳት በማድረስ ጥፋተኛ ተበለው የአምስት ቀን እስር ተፈረደባቸው። የ82 ዓመቱ ፖል ፔሎሲ በግንቦት ወር ካሊፎርኒያ ናፓ ካውንቲ ውስጥ በመጠጥ ኃይል ውስጥ ሆነው ፖርሽ መኪናቸውን ማጋጨታቸውን እና ጉዳት ማድረሳቸውን አምነዋል። ሚሊየነሩ ፖል ከዐቃቤ ሕግ ጋር በሚደረግ ድርድር አነስተኛ ፍርድ ይቀበሉ እንጂ ወንጀሉ ከዚህም ለከፋ ጥፋት ይዳርጋቸው ነበር። በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ከፍተኛ  መሪ የሆኑት ናንሲ ፔሎሲ እ.ኤ.አ. ከ1963 ጀምሮ ከፖል ፔሎሲ ጋር በትዳር ቆይተዋል። ፖል ከዐቃቤ ሕግ ጋር ባደረጉት ድርድር መሠረት ከአምስት ቀኑ በተጨማሪ ሌላ የእስር ቅጣት አይጠብቃቸውም። ከአደጋውበኋላ በእስር ቤት ሁለት ምሽት አሳልፈው መውጣታቸውም ታውቋል። ይህንንም ተከትሎ ከአምስት ቀኑ ቅጣት ላይ የሚቀነስ ይሆናል። ለመልካም ሥነ ምግባር ሁለት ተጨማሪ ቀናት የተቀነሰላቸው ሲሆን የመጨረሻው አንድ ቀን የማኅበረሰብ አገልግሎት በመስጠት ይካካሳል። በፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማሩት ፖል ሌሎች ቅጣቶችም ይጠብቃቸዋል። ለሦስት ዓመት በዕግድ ላይ የሚቆዩ ሲሆን ለሦስት ወር የሚቆይ እና ስለጠጥቶ ማሽከርከር የሚያስተምር ትምህርት ወስደው ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም 7,000 ዶላር የገንዘብ ቅጣትም ይጠብቃቸዋል። ፖል መንጃ ፈቃዳቸውን ባይነጠቁም የመኪናቸው ሞተር ከመነሳቱ በፊት በትንፋሽ የአልኮል መጠናቸውን የሚለከውን መሳሪያ መጠቀም ይኖርባቸዋል። ናንሲ ፔሎሲ ባለቤታቸው ላይ የቅጣት ውሳኔ በተላለፈበት ወቅት በችሎት አልተገኙም። ፖል ፔሎሲ ኦክቪል ካሊፎርኒያ ውስጥ የረዥም ጊዜ ጓደኛቸው እና የዴሞክራቲክ ፓርቲ ለጋሽ ከሆኑት ግለሰብ ቤት ለቀው በወጡበት ወቅት ነበር አደጋው ያጋጠመው። የፖሊስ መዝገብ እንደሚያመለክተው የ2021 ሞዴል የሆነው ጥቁር ፖርሽ መኪናቸውን በቤታቸው አቅራቢያ ከሚገኝ ጂፕ መኪና ጋር አጋጭተዋል። ሁለቱም ተሽከርካሪዎች ውድመት ደርሶባቸዋል። ፖል ፔሎሲ የካሊፎርኒያ ሀይዌይ ጠባቂ የፖሊስ መኮንኖችን የሚደግፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት አባል መሆናቸውን የሚያሳይ ካርድ አደጋውን ተከትሎ በስፍራው ለተገኙ መኮንኖች አሳይተዋል ሲል ፖሊስ ቅሬታውን አቅርቧል። ናንሲ ፔሎሲ በወቅቱ በሌላኛው የአሜሪካ ጥ��� ሮድ አይላንድ ውስጥ ብራውን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የምረቃ ንግግር ለማቅረብ ተጉዘው ነበር። ጽሕፈት ቤታቸውም ይህ “የግል ጉዳይ ነው” በማለት ተጨማሪ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cprlrv7q9geo +health ኮሮናቫይረስ፡ አንዳንድ ሰዎች ለምን ቶሎ ከኮቪድ-19 አያገግሙም? ብዙዎች ከኮሮናቫይረስ በቀላሉ፣ በአጭር ጊዜ ያገግማሉ። አንዳንዶች ላይ ግን በሽታው ይበረታል። ለወራት መተንፈስ የሚቸገሩ፣ የሚደክማቸውም አሉ። አጭር ርቀት ተጉዘው በጣም እንደሚደክማቸው የተናገሩ ሰዎች አሉ። በሽታው ዘለግ ላለ ጊዜም ይቆይባቸዋል። ኮቪድ-19 አንዳንዶች ላይ ለወራት የሚቆይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው ለምንድን ነው? ለሚለው ገና ግልጽ መልስ አልተገኘም። ኮሮናቫይረስ ለምን ረዥም ጊዜ ይቆያል? በሽታው ረዥም ጊዜ የቆየባቸው ሰዎች በአጠቃላይ ተመሳሳይ ምልክት አያሳዩም። ሆኖም ሁሉም እንደሚደክማቸው ይናገራሉ። ትንፋሽ ማጠር፣ ሳል፣ የጡንቻ ህመም፣ የስሜት ህዋሳት ህመም፣ ራስ ምታት እንዲሁም የልብ፣ ኩላሊት፣ አንጀት እና ሳምባ በሽታ የሚገጥማቸውም አሉ። በተጨማሪም ድብርት፣ ጭንቀት እና በግልጽ ለማሰብ መቸገር ይስተዋላል። ጄድ ግሬይ ክርስቲ “እንዲህ አይነት ድካም ተሰምቶኝ አያውቅም” ስትል ስሜቱን ገልጻለች። ፕ/ር ዴቪድ ስትሬይን “በሽታው አንዳንዶች ላይ እንደሚቆይ አንጠራጠርም” ብለዋል። በሮም ሆስፒታል 143 ታማሚዎች ላይ የተሠራ ጥናት፤ 87 በመቶ የሚሆኑት ከሁል ወራት በኋላ ከምልክቶቹ ቢያንስ ሁለቱ እንደታዩባቸው ይጠቁማል። ከግማሽ በላዩ ይደክማቸዋል። ዩኬ ውስጥ የሚሠራ መተግበሪያ እንደሚያሳየው፤ 12 በመቶ ህሙማን ከ30 ቀናት በኋላ የበሽታው ምልክት ታይቶባቸዋል። ከ50 ሰዎች አንዱ ከ90 ቀናት በኋላ ምልክት አሳይተዋል። ዘለግ ላለ ጊዜ የሚታመሙት በሽታው ከመጀመሪያውም የበረታባቸው ሰዎች ብቻ አይደሉም። ደብሊን ውስጥ የተሠራ ጥናት በበሽታው ከተያዙ ከአሥር ሳምንት በኋላ ድካም የገጠማቸው እንዳሉ ያሳያል። አንድ ሦስተኛው ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ አልቻሉም። ፕ/ር ክሪስ ብራይትሊንግ እንደሚናገሩት፤ ሳምባቸው የተጎዳ ሰዎች ለኒሞኒያ ተጋልጠዋል። ቫይረሱ ከሰውነት ቢወጣም አንዳንድ አካል ላይ እንደሚቀር ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ፕ/ር ቲም ስፔክተር “ዘለግ ላለ ጊዜ ተቅማጥ ከተከሰተ ቫይረሱ አንጀት ውስጥ ቀርቷል ማለት ነው። ማሽተት ካቀተ ደግሞ ቫይረሱ በህዋሳት ውስጥ ቀርቷል” ይላሉ። ቫይረሱ ህዋሳትን ሲያጠቃ፤ ሰውነት በሽታውን ለመከላከል ከመጠን በላይ ሲሞክር፤ አካላችን ይጎዳል። በሽታው የሰውነታችንን እንቅስቃሴም ያስተጓጉላል። የደም ዝውውር ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር የስኳር መጠናቸውን ለመቆጣጠር የተቸገሩ ህሙማን አሉ። የአንጎል መዋቅር ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የሚጠቁም መረጃ ቢኖርም እስካሁን አልተረጋገጠም። ህመሙ የተለመደ ነው? በቫይረስ ከተያዙ በኋላ መድከም ወይም ማሳል የተለመደ ነው። ከአሥር ሰዎች አንዱ ለወራት የሚቆይ የህዋሳት ህመም ሊገጥመው ይችላል። እአአ በ1918 ከተከሰተው ወረርሽኝ ወዲህ ጉንፋን የፓርኪንሰን በሽታን የሚመስል ምልክት ያለው ህመም እንደሚያስከትል ታይቷል። ኮቪድ-19ን ተከትሎ የተለያዩ የህመም ምልክቶች ሊስተዋሉ እንደሚችሉ ፕ/ር ክሪስ ያስረዳሉ። “ቫይረሱ የተለያዩ ሰዎችን በተለያየ መንገድ ይጎዳል። ህዋሳት ላይ የሚያስከትለው ችግርም ይለያያል። አንዳንዶች ላይ ሲበረታ፣ ለሌሎች ይቀላል” ይላሉ። ሙሉ በሙሉ ማገገም ይቻላል? ኮሮናቫይረስ ለረዥም ጊዜ የሚቆይባቸው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ይመስላል። ሆኖም ግን በሂደት የሚከሰተው አይታወቅም። ፕ/ር ክሪስ ሰዎችን ለ25 ዓመታት ለመከታተል እንደወሰኑና ህመሙ ከአንድ ዓመት በላይ ይቆይባቸዋል ብለው እንደማያምኑ ይናገራሉ። ሆኖም ግን ሰዎች አሁን ቢያገግሙም በሽታው ዘላቂ ተጽዕኖ ሊያሳድርባቸው የሚችልበት እድል አለ። በጣም የሚደክማቸው ሰዎች ስሜቱ ዘለግ ላለ ጊዜ ሊቆይባቸው ይችላል። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ወጣቶችም ሳይቀር ለልብ ህመም ሊጋለጡ ይችላሉ። ስለዚህም ከኮሮናቫይረስ በማገገም ላይ ያሉ ሰዎች ራሳቸው ላይ ጫና እንዳያሳድሩና እንዲያርፉ ይመከራል። አድካሚ ሥራ ካለባቸው በተከታታይ ከማከናወን ይልቅ በተለያየ ሰዓት መተግበር አለባቸው። በተጨማሪም በጠበቁት ፍጥነት ካላገገሙ ወደ ህክምና መስጫ መሄድ ይጠበቅባቸዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54441793 +sports 91 ለ 1 በማሸነፍ የታገደው የአፍሪካ እግር ኳስ ክለብ ወደ ውድድር እንዲገባ ተፈቀደለት በሴራሊዮን የሚገኘው የሁለተኛ ደረጃ የእግር ኳስ ክለብ፣ ገልፍ ኮኖ 91 ለ 1 በሆነ ውጤት በተጠናቀቀው የእግር ኳስ ጨዋታ የማጭበርበር  ወንጀል ምርመራ እየተደረገበት ቢሆንም ወደ አገሪቱ ፕሪሚየር ሊግ ለማለፍ በሚደረገው ውድድር እንዲሳተፍ ተፈቀደለት። ገልፍ ኮኖ የተሰኘው ክለብ ኮኪማ ሌባኖን በማሸነፍ ወደ ሱፐር 10 የፕሪሚየር ሊግ ምዕራፍ ማለፉን ሲያረጋግጥ የቅርብ ተፎካካሪው ካሁንላ ሬንጀርስ እሁድ በተደረገው የመልስ ጨዋታ በሉምቤቡ ዩናይትድ 1 ለ 0 ተሸንፏል። ባለፈው ወር ካሁንላ ሌንጀርስ ሉምቤቤ ዩናይትድን 95 ለ0 በማሸነፍ ገልፍ ኮኖ ደግሞ ኮኪማ ሌባኖንን 91 ለ 1 በማሸነፍ አለም አቀፍ መነጋገሪያ ሆነው ነበር። በነዚህ ሁለት ጨዋታዎች 187 ጎሎች በመቆጠራቸው የሴራሊዮን እግር ኳስ ማህበር በጨዋታ ማጭበርበር ክስ ሰርዟቸዋል እንዲሁም ምርመራም ተከፍቷባቸዋል። ሁለቱ ቡድኖች ከፍተኛ ወደሆነው የአገሪቱ ፕሪሚየር ሊግ ለማለፍ ተጋጣሚዎቻቸውን ማመን በማይቻል ውጤት ቢያሸንፉም የሁለቱም ጨዋታ ውጤቶች ተሰርዘዋል። በነዚህ ጨዋታዎች የተሳተፉት አራት ቡድኖች በጨዋታዎቹ አዘጋጆች አካላት ታግደው ነበር። ይሁንና እገዳው የጨዋታው አዘጋጅ የሆነውና የሴራሊዮን እግር ኳስ ማህበር አካል የሆነው የምስራቃዊ ክልል የእግር ኳስ ማህበር ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተነሳ ሲሆን ይህም የዲሲፒሊን ኮሚቴው ያደረገው ጥናት ተከትሎ ነው። ጥናቱ እስካሁን ለህዝብ ይፋ አልሆነም። “ከምስራቃዊ ክልል የእግር ኳስ ማህበር ባገኘነው ሪፖርት መሰረት የፕሪሚየር ሊጉን የጊዜ ሰሌዳ እንዳያልፍ ግጥሚያዎቹ እንዲደገሙ ፈቅደናል” ሲሉ የሴራሊዮን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ቶማስ ዳዲ ብሪማ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ተናግረዋል። “ነገር ግን ይህ ማለት ምርመራውን ዘግተነዋል ማለት አይደለም። ፊፋ እና ካፍ (የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን) እንዲመለከቱት እና በዚያም መሰረት እንዲመክሩበት ልከናል” ብለዋል። “ ገልፍ በሱፐር 10 ውስጥ እንዲሳተፍ መፈቀዱን አረጋግጣለሁ” ብለዋል ሆኖም ማህበሩ የቀደመ ውጤቱን በተግባር የማይቻል እንደሆነም በዚህ ወቅት አስምሯል። “ማንም ሰው ቢሆን ይህንን ውጤት ከቁም ነገር አይወስደውም። በማንኛውም መስፈርት በ90 ደቂቃ ውስጥ 90 ግቦች ሊቆጠሩ አይችሉም ብሏል። ማህበሩ ከአራቱም ክለቦች የተውጣጡ ተጫዎቾችን እንዲሁም ኃላፊዎችን እንደሚመረምሩ ተናግረዋል። ሆኖም ገልፍ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በምዕራብ አፍሪካ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ለመግባት ቅዳሜ በሱፐር 10 የመጀመሪያ ግጥሚያው ላምቦይን ይገጥማል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cyxk9pwnklro +business ለወንዶች የተተወ የሚመስለውን ሥራ የደፈረችው ሴት የታክሲ ረዳትነት እየሰራች መንጃ ፈቃድ አወጣች። እንዳሰበችው ስራ ስላላገኘች በቀን ሰራ���ኝነት ተቀጠረች። በኋላም የከባድ መኪና አሽከርካሪ በመሆን በየበረሃው ሰርታለች። https://www.bbc.com/amharic/50832947 +health የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት ላይ የተደረገ ሙከራ ከፍተኛ ውጤት አሳየ "በኦክስፎርድ የኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እና በቡርኪናፋሶ ሳይንቲስቶች በጋራ የተሰራ አዲስ የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት በተደረገለት ሙከራ ውጤታማ መሆነ ተገለጸ። በክትባቱ ላይ በተደረጉት መጀመሪያ ሙከራዎች 77 በመቶ በሆነ ውጤት ስኬታማ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ይህም አሁን ለህክምና ከሚውሉ መድኃኒቶች አንጻር ውጤታማነቱ በእጅጉ የላቀ ነው ተብሏል። የህክምና ጉዳዮች መጽሔት በሆነው 'ላንሴት' ላይ የታተመው የጥናቱ ውጤት 450 ከቡርኪናፋሶ የተወጣጡ ህጻናት የተሳተፉበት ሲሆን ከዚህ በኋላ በርከት ያሉ ሰዎች የሚሳተፉበት ሙከራ ይደረግበታል። በቀጣዩ የሙከራ ሂደትም 4,800 ህጻናት የሚሳተፉ ሲሆን እነዚህም ከቡርኪናፋሶ፣ ከማሊ እና ከኬንያ ናቸው። ""ይህ ሙከራ በጣም አስደሳች የሆነ ውጤታማነት ነው ያሳየው። ክትባቱ ከዚህ በፊት ከነበሩ ህክምናዊች አንጻር የተሻለ የመከላከል ብቃት አሳይቷል። ""በመቀጠል የምናካሂዳቸውን ሁለተኛና ሦስተኛ ዙር ሙከራዎች እየተጠባበቅን ነው። በእነዚህ ሙከራዎች በርከት ያሉ ሰዎች የሚሳተፉ ሲሆን በስፋት ቢመረት ምን አይነት ውጤት እንደሚኖረው ለማወቅ ይረዳናል"" ብለዋል በቡርኪናፋሶ የጤና ሳይንስ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ሃሊዶ ቲንቶ። ለወባ በሽታ የሚሆን ክትባት ማግኘት በህክምና ምርምር ውስጥ እግጅ ትልቅ ዜና ነው የሚሆነው። ሙከራው በስኬት የሚጠናቀቅ ከሆነ ትልቅ ግኝት እንደሚሆን ይጠበቃል። የወባ በሽታ በዓመት ከ400 ሺህ በላይ ሰዎችን የሚገድል ሲሆን አብዛኛዎቹ ከሰሀራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገራት ውስጥ የሚኖሩ ህጻናት ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ለወባ በሽታ የሚሆን አንድ ክትባት ያለ ሲሆን ውጤታማነቱ ደግሞ 50 በመቶ ብቻ ነው። በአዲሱ ክትባት የመጀመሪያ ዙር ሙከራ ላይ 77 በመቶ ውጤታማነት የታየ ሲሆን በሌሎች አገራትም ላይ ለመሞከር ታቅዷል። በጊዜ ብዛት ደግሞ ቢያንስ በአራት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ይሞከራል። በሙከራው የሚሳተፉት 5 ሺህ የሚሆኑ ህጻናት ደግሞ እድሜያቸው ከሦስት ዓመት በታች የሆኑ ናቸው። አሁን በሙከራ ላይ የሚገኘው አዲሱ ክትባት ሙሉ ፈቃድ አላገኘም። ነገር ግን ውጤታማነቱ በሙከራዎች በተገቢ ሁኔታ የሚረጋገጥ ከሆነ የበርካቶችን ህይወት የማትረፍ ትልቅ አቅም አለው ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56827450 +politics ምርጫ 2013 ፡ ኦፌኮ እና ባልደራስ በመጪው ምርጫ የመሳተፋቸው ነገር እንደሚያሳስባቸው ገለጹ "የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ወደ ምርጫ መግባት ያሳስበናል ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ። ሁለቱ ፓርቲዎች ይህንን ያሉት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ዓመት ለሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ማስፈጸሚያ የሚሆን ረቂቅ የጊዜ ሠሌዳን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው። የኦፌኮ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ፤ ""ከከፍተኛ እስከ መካከለኛ የፓርቲያችን አመራሮች መታሰር እና የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ለምርጫ የምናደርገውን ዝግጅት አስቸጋሪ ያደርገዋል"" ሲሉ ተናግረዋል። በተመሳሳይ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ፤ የባልደራስ አመራሮች በተራዘመ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ እንዳሉ በመጥቀስ ""የምንገባበት ምርጫ እጅግ አሳስቦናል"" ብለዋል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቃል አቀባይ ሶሊያና ሽመልስ ከቀናት በፊት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ""ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው መካሄድ አለበ��� ነው ያሉት። ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ስጋት ይሆናል ያሉት ሁለት ነገር ነው። አንዱ የአገሪቱ የጸጥታ ችግር ነው። አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ቢሯቸው እንደሚዘጋ እና አባሎቻቸው ችግር እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል"" ብለዋል። ፓርቲዎች ለሚያነሷቸው መሰል ችግሮች መፍትሄ መስጠት የሚችለው የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ አካል እንጂ ምርጫ ቦርድ አለመሆኑንም ተናግረዋል። የምርጫ ቦርድ ረቂቅ የምርጫ የጊዜ ሠሌዳውን አርብ እለት ይፋ ባደረገበት መድረክ ላይ የብልጽግና ፓርቲን ወክለው የተሳተፉት አቶ ዛዲግ አብረሃ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እየደረሰብን ነው ያሉት ጫናን በተመለከተ ምላሽ ሰጥተው ነበር። በዚህም መሰረት የቀረቡ ቅሬታዎች ላይ ማጣራት እንደተደረገና አንዳንዶቹ የተጋነኑ መሆናቸውን ገልጸው፤ የቀረቡትን አቤቱታዎችን ፓርቲያቸው እንደማያጣጥላቸውና ለማረም አስፈላጊውን ነገሮች ሁሉ እንደማያደርግ እንዲሁም ቀጣዩ ምርጫ ትክክለኛ ፉክክር የሚደረግበት እንዲሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል። በዚህ ዓመት ለሚካሄደው ስድስተኛው ዙር አገራዊና ክልላዊ አጠቃላይ ምርጫ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ በተደረገው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የድምጽ መስጫው ቀን ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 መሆኑ ገልጿል። አቶ ጥሩነህ በርካታ አባሎቻቸው መታሰራቸውን፣ የቀሩትም ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን እና በዞንና በወረዳ ደረጃ ያሉ ጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋታቸውን በመጥቀስ፤ ""በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት ቢኖረንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን"" ብለዋል። ይህንንም ስጋታቸውን ከዚህ ቀደም መግለጫ በማውጣት ማስታወቃቸውን አስታውሰዋል። ትናንት ምርጫ ቦርድ ባካሄደው ስብሰባ ላይም ተገኝተው ይህንኑ ስጋታቸውን ማስረዳታቸውን የተናገሩት አቶ ጥሩነህ፤ ""ችግሮችን ለማስተካከል ጥረት እናደርጋለን"" የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል። ""ነገር ግን አንዳንድ ከአቅማቸው በላይ የሆኑ ነገሮች መኖራቸውንም ተገንዝበናል"" ብለዋል አቶ ጥሩነህ። እንደ ኦፌኮ እስካሁን በምርጫው አንሳተፍም የሚል ውሳኔ ላይ ባይደርሱም፤ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ በሚያስችል አቅም ላይ አለመሆናቸውን ግን አስረግጠው ተናግረዋል። ለዚህም የጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋት፣ የአባላቶቻቸው እስር፣ ስደትና ማስፈራሪያ እንዲሁም በአገሪቷ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ችግሮችን እንደ ምክንያት ጠቅሰዋል። ""በዚህ ሁኔታስ መንግሥትና ምርጫ ቦርድ ምርጫ ማካሄድ ይችላሉ ወይ?"" ሲሉም ጠይቀዋል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥትና ጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የባልደራስ ፓርቲ ሊቀመንበር በሆኑት በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ዐቃቤ ሕግ ምስክር እንዲያሰማ ለመጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል። በትናንቱ የፍርድ ቤት ውሎ ማዘናቸውን የገለፁት የፓርቲው ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው፤ ""በእነአቶ እስክንድር ነጋ ላይ የተሰጠው ቀጠሮ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች በውድድሩ ውስጥ ሳይገቡ መንግሥት ብቻውን ሮጦ 'አሸናፊ ነኝ' ለማለት የተደረገ ይመስላል"" ሲሉ ኮንነዋል። አቶ ገለታው ""ምርጫው በህወሓት ዘመን የተለመደ የምርጫ ዓይነት ሊሆን ነው"" በማለትም በእነርሱ በኩል ተስፋ እየታያቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል። ""አባላቶቻችን ወከባ አለባቸው። መንግሥት በየጊዜው ምህዳሩን እያጠበበ ነው፤ ባልሰፋ ምህዳር ውስጥ ታሪካዊ ምርጫ ሊደረግ እንደማይችል እያረጋገጠ ነው"" ሲሉም ወቅሰዋል። ይህ እንደ ፓርቲ ብቻም ሳይሆን እንደ አንድ ግለሰብ እንደሚያሳስባቸውም አልሸሸጉም። አቶ ገለታው ""ይህ ምርጫ እንደ በፊቱ ተጭበርብሮ እንራመድ ቢባል የማያራምድ ሕዝብ የ���ነሳበት ወቅት ስለሆነ፤ ድህረ ምርጫ አገሪቷን ወደ ብጥብጥ እንዳይወስዳት ያሳስባል"" ብለዋል። መንግሥት ሁኔታዎችን በፍጥነት ማስተካከል ካልቻለም ምርጫው ታሪካዊ መሆኑ ቀርቶ፤ አደጋዎችን ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቃል አቀባይ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ""ፓርቲዎች ችግር ገጥሞናል ባሉት ጉዳይ ላይ ለክልል አስተዳደር፣ ለፖሊስ ኮሚሽን ወይም ሌላ ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ቦርዱ ያሳውቃል"" በማለት የመሥሪያ ቤታቸው የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት አስረድተዋል። በዚህም መሰረት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ካላቸው ለቦርዱ በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ተጠይቆ፤ 11 ፓርቲዎች የሚገጥማቸውን ችግር ለቦርዱ ማሳወቃቸውን የጠቀሱት ሶሊያና፤ ቦርዱም ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔ ያስፈልጋል ብሎ ለመንግሥት ማሳወቁን ገልጸዋል። በየክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የሚገጥማቸውን ችግር በተመለከተ ከገዢው ፓርቲ፣ መንግሥትና ምርጫ ቦርድ ጋር የሦስትዮሽ ውይይት የሚካሄድበት አሠራር መዘርጋቱንም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። የኦፌኮ እና ባልደራስ ፓርቲዎች አመራር እና አባላት የሆኑት ጀዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እንዲሁም እስክንድር ነጋ፣ አስቴር ስዩምና ስንታሁ ቸኮል በሽብር ወንጀል ተከሰው በእስር እንደሚገኙ ይታወቃል። ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ከየካቲት 8 ጀምሮ የእጩዎች ምዝገባ እንደሚያከናውኑ እና የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ በትናንትናው ዕለት ገልጿል። ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 21 ድረስ ደግሞ የመራጮች ምዝገባ የሚከናወን ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የድምጽ መስጫ ቀን በአንድ ሳምንት ዘግይቶ ሰኔ 5/2013 ዓ.ም እንደሚከናወን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊዮን የሚደርሱ መራጮች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠብቅ ማስታወቁ ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55447033 +sports አትሌት ሲፋን ሐሰን ለኢትዮጵያ ባለመሮጤ ፀፀት አይሰማኝም አለች "በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሜዳሊያ ""ሦስታ"" በመሥራት ዓለምን ያስደነቀችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ ሯጭ ሲፋን ሐሰን ኢትዮጵያን ወክላ ባለመሮጧ አንዳችም ፀፀት እንደማይሰማት ተናገረች፡፡ አትሌት ሲፋን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጦርነት አገሪቱን ድምጥማጧን እያጠፋት ነው ብላለች፡፡ በፖለቲካ ሥልጣን መጋራት የተሻለ ሁኔታ ሊያመጣ እንደሚችልና ይህም ሌሎች በርካታ ሯጮች ወደፊት ለሌሎች አገሮች መሮጥ ትተው ለኢትዮጵያ እንዲሮጡ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁማለች፡፡ አትሌት ሲፋን ለኔዘርላንድስ በ5ሺህ እና በ10ሺህ ወርቅ አስገኝታለች፡፡ በ1ሺ 500 ደግሞ ነሐስ አግኝታለች፡፡ አትሌት ሲፋን ከኢትዮጵያ ወደ ኔዘርላንድስ የወጣችው ገና በ14 ዓመቷ ነበር፡፡ የ28 ዓመቷ ሲፋን በኦሮሚያ ክልል ነው ያደገችው፡፡ በወቅቱ የራስ ገዝ ጥያቄ ይነሳ የነበረበት ሲሆን ለነጻነት የሚዋጉ ኃይሎች ጥቃት ይፈጽሙ ነበር ብላለች፡፡ ሲፋን በ10ሺህ ሜትር ያሸነፈቻት በርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ያላትን ኢትዮጵያዊቷን ለተሰንበት ግደይን ጭምር በመምራት ነው፡፡ ለተሰንበት የተገኘችው ደግሞ አሁን በጦርነት እየታመሰች ከምትገኘው ትግራይ ነው፡፡ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ሐሳቧን የሰጠችው ሲፋን ሐሰን ያን ወቅት በኦሮሚያ የነበረው የሰዎች ግድያ ልብ የሚሰብር እንደነበር አስታውሳለች፡፡ ‹‹ከዚያች አገር በመሰደዴ አንዳች ቅሬታ የለኝም፡፡ መመለስም አልፈልግም፡፡ ማሰቡ ራሱ ያመኛል፡፡›› ብላለች፡፡ ሲፋን በፈረንጆቹ እስከ 2007 ደስ የሚል የልጅነት ጊዜ እንዳሳለፈችና ከዚያ በኋ�� ግን በኦሮሚያ በነበረው ውጊያ ነገሮች እየተበላሹ መምጣታቸውን አስታውሳለች፡፡ በቶኪዮ የ10ሺህ ሜትር የሜዳሊያ አሸናፊዎች ሥነ ሥርዓት መድረኩ በትውልደ ኢትዮጵያዊያን ነበር የተሞላው፡፡ሆኖም ለተሰንበት ብቻ ናት ኢትዮጵያን የወከለችው፡፡ የብር ሜዳሊያ ያገኘችው ቃልኪዳን ገዛኸኝ ባህሬንን ትወክል እንጂ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ናት፡፡ በሕዝብ ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛ የሆነችው ኢትዮጵያ በብሔር ግጭት ውጥረት ስሟ የሚነሳ ሲሆን ይህ ሁኔታ አገሪቱ በርካታ አትሌቶችን እንድታጣ ምክንያት ሆኗል ብላለች ሲፋን ሐሰን፡፡ ‹‹ትዝ ይለኛል በፊት ወጣቱ እርስ በእርስ ይዋደድ ነበር፡፡ አሁን ግን እርስ በእርሱ የሚጠላላ ሆኗል፡፡ በፊት ሁሉም ራሱን ኢትዮጵያዊ ብሎ ይጠራ ነበር፡፡ አሁን ግን እርግጠኛ ነኝ ብዙ ትግራዊያን ራሳቸውን ኢትዮጵያዊ ብለው አይጠሩም›› ብላለች ሲፋን፡፡ በሰኔ ወር ለተሰንበት በ10ሺህ ሜትር ሁለት ቀናት ብቻ የቆየውን የሲፋንን የዓለም ክብረ ወሰን በርቀቱ ስትወስድ በርካታ የስፖርት ወዳጆች ወደ ዓለም አቀፉ የትሌቲክስ ማኅበር ማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ በመሄድ ክብረ ወሰኑ የትግራዋይት እንጂ የኢትዮጵያ አይደለም ሲሉ ይጽፉ ነበር፡፡ በዚህ ወር መጀመርያ የተባበሩት መንግሥታት አፋጣኝ የሰብአዊ እርዳታ በኦሮሚያ እንደሚያስፈልግ የጠቀሰ ሲሆን በትግራይ ደግሞ አራት ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ እርዳታን ይሻሉ ሲሉ መግለጫ አውጥቶ ነበር፡፡ ‹‹ለተሰንበት ድንቅ አትሌት ናት፡፡ የመጣችበት ቦታ ግን ሕጻናት ይደፈራሉ፤ አስቀያሚ ሁኔታ ነው ያለው፤ ያሳዝናል›› ብላለች ሲፋን ለቢቢሲ፡፡ ""አስበሽዋል! ልክ እንደኔው ሕልም የነበራቸው ስንትና ስንት ሴቶች እንደተደፈሩ?"" ስትል ሁኔታውን ምን ያህል እንደሚያውክ አብራርታለች፡፡ ከኦሮሚያ የተገኙት የአሁን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ተቺዎች ለክልሎች የራስ ገዝ አስተዳደርን ከመስጠት ይልቅ ማዕከላዊ መንግሥትን አጠናክሮ አሀዳዊ መንግሥት ለመፍጠር ይሞክራሉ ሲሉ ይወቅሷቸዋል፡፡ ‹‹እኔ እሱን ብሆን ዘወር እል ነበር፡፡ ሥልጣኑን ለሕዝቦች እሰጥ ነበር፣ የሚፈልጉትን እንደሚርጡ አደርግ ነበር፡፡›› ብላለች ሲፋን ሐሰን፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-58176592 +politics ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት አሜሪካን ተጠያቂ አደረጉ "የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ 31ኛው የነጻነት በዓልን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ለሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት አሜሪካን ተጠያቂ አድርገዋል። በእርሳቸው አገላለጽ፣ ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም በኋላ ""በአሜሪካ የሚመራው የምዕራባውያን ኃይል፣ የአሜሪካ ሕዝብንም ይሁን የምዕራቡ ዓለምን የማይወክል አደገኛ አካሄድ ጀምሯል።"" ""ዓለም የኛ ይሆናል፣ በሁሉም ዘርፍ ያለን ኃያልነት ተገዳዳሪ አይኖረውም"" ብለው ምዕራባውያኑ እንደተነሱ ጠቅሰው በዚህም ኤርትራ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ከመተቸት አልፈው ለሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት አሜሪካን ተጠያቂ እስከማድረግ ደርሰዋል። በተባበሩት መንግሥታት ውይይት ሩሲያ ዩክሬንን በመውረሯ ማዕቀቦች እንዲጣሉ የተነሱ ሐሳቦችን ከተቃወሙ አገራት አንዷ ኤርትራ እንደሆነች አይዘነጋም። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ባደረጉት ንግግር በዋነኛነት አሜሪካ ሊገዳደሯት የሚችሉ ኃይሎች ላይ ""የአፈና ፖሊስ"" እንደምትከተልና፣ ይህንን ፖሊሲዋን ሩሲያን ""ለመቆጣጠር"" እንዳዋለችው ጠቅሰዋል። የሩሲያ የቅርብ ጎረቤቶች የሆኑ የምሥራቅ አውሮፓ አገራት ""እንደ እጅ አዙር መጠቀሚያ"" እንደዋሉ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ይህ ""የአፈና ፖሊሲ"" እንደሆነ ገልጸው፣ የዩክሬን ሕዝብ የዚህ ��ለባ ሆኗል ሲሉ ተችተዋል። ፕሬዝዳንቱ ባለፉት 30 ዓመታት ይህ አካሄድ ""አልሠራም"" ሲሉም አክለዋል። ""ማስፋራራት፣ መቅጣት፣ መውረር፣ ስም ማጠልሸት፣ ማዕቀብ መጣል፣ ሰብአዊ መብትን እንደ መሣሪያ መጠቀም አልሠራም።"" በእጅ አዙር የምጣኔ ሀብት ጫና ለማሳደር ከሩሲያ በተጨማሪ ቻይና ላይም ""እንደተቃጣ"" ገልጸዋል። ""ታይዋን እና ሆንግ ኮንግን እንዲሁም በአጠቃላይ እስያ ያሉ አገራትን እንደ መሣሪያ ለመጠቀም ተሞክሯል። ይህም ከሩሲያ ቢበልጥ እንጂ የማይተናነስ ቀውስ ያስከትላል።"" ጠቅለል አድርገውም ዓለም አቀፍ ሕግጋት የሚከበሩበት፣ ማዕቀቦች የሚቀለበሱበት፣ ዓለም አቀፍ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል የሚረጋገጥበት፣ ሉዓላዊ አገሮች የማይገረሰሱበት እንዲሁም አገራዊ፣ ቀጠናዊና አህጉራዊ ትብብር የሚደረጅበት ዓለም መገንባትን እንደ አማራጭ አቅርበዋል።የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለኤርትራ 31ኛው የነጻነት በዓል ባደረጉት ንግግር፣ የአፍሪካ ቀንድን ""መረጋጋት ማረጋጋጥ"" የኤርትራ አገረ ግንባታ ዋነኛ ማጠንጠኛ እንደሆነ ተናግረዋል። በንግግራቸው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት፣ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እንዲሁም ""የምዕራባውያን ጫና"" ይገኙበታል። ""የቀጠናውን መረጋጋት ማስጠበቅ፣ የጋራ ትብብርን ማጠናከር እና በሉዓላዊ አገራት መካከል ትስስርና እድገትን ማረጋገጥ የአገር ግንባታው ዋነኛ ማጠንጠኛ ነው፣ ሆኖም ይቀጥል"" ብለዋል። ""የውስጥ እና የውጭ አፍራሽ አጀንዳዎች"" ባሏቸው ጉዳዮች ""የጎረቤት አገራት ዜጎች"" እንደሚፈተኑም አያይዘው ጠቅሰዋል። ከቀጠናው ባለፈ አፍሪካን እንደ አህጉር ቀጠናዊ ትስስሮችን ማጠናከር እንዳለባት ጠቅሰው ""ይህ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን እጅግ አስፈላጊ ነው"" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተውታል። የኤርትራ መንግሥት ""ለቀጠናዊ ትስስር ግብዓት እንዳፈሰሰ"" ከዚህ ባሻገርም ለጋራ የምጣኔ ሀብት እድገት፣ ለጸረ ሽብር ትግል እና ብሔራዊ ደኅንነት ስጋትን ለመቀልበስም ""እንደሚታጋ"" ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። ለ30 ዓመታት የተካሄደውን የትጥቅ ትግል የመራው የኤርትራ ነጻ አውጪ ግንባር (ሻዕቢያ) የኤርትራ መዲና አሥመራን የተቆጣጠረበት ቀን በኤርትራ ተከብሮ ውሏል። የነጻነት ቀንን አስመልክተው ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፣ በዓሉ የአገሪቱ ""አሁናዊ፣ የቀድሞ እና የወደፊት ሁኔታ የሚቃኝበት"" ብለውታል። በቀጠናውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ""ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት"" የኤርትራን ሉዓላዊነት እና ነጻነት ለመጠበቅ የተደረገው ትግል አልፎም አገሪቱ ለወደፊት ማሳካት የምትሻው የሚቃኝበት ዓመት እንደሆነም ጠቅሰዋል። ስለ ኤርትራ ፕሬዝዳንቱ የኤርትራ ሕዝብ ነጻነቱን ለመቀዳጀት ለ50 ዓመታት ያደረገውን ትግል አሞግሰዋል። ኤርትራን በሃይማኖት ለመከፋፈል፣ በምጣኔ ሀብት ለማዳከም እንዲሁም የተለያዩ አሉታዊ ሙከራዎች ቢደረጉም የኤርትራን ሕዝብ ""ፖለቲካዊ ንቃተ ሕሊና ያዳበሩ"" እንጂ ያወኩ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። ""ለ50 ዓመታት ከተደረገው ትግል የተገኘው ተሞክሮና ትምህርት"" ከትውልድ ወደ ትውልድ እንደተሸጋገረ በንግገራቸው ጠቅሰዋል። ኤርትራ ""ሽብርን ትደግፋለች"" በሚል ሽፋን የተጣሉባትን ማዕቀቦች ሳይኮንኑም አላለፉም። ኤርትራ ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሃይማኖት፣ የፖለቲካ ነጻነት እንደተሸረሸረ እና ሰብአዊ መብትን የሚጥሱ አፈናዎች በመንግሥት እንደሚፈጸሙ የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ የተለያዩ የመብት ተሟጋቾች ቢተቹም፣ የኤርትራ መንግሥት ግን እነዚህን ውንጀላዎች አይቀበላቸውም።" https://www.bbc.com/amharic/news-61579468 +health በኢንዶኔዥያ አውሮፕላ�� ማረፊያ ውስጥ የኮቪድ ናሙና መሰብሰቢያዎችን በድጋሚ የተጠቀሙ ግለሰቦች ተያዙ በኢንዶኔዥያ የሚገኝ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ ሠራተኞች ያገለገሉ የኮቪድ መመርመሪያ መሣሪያዎችን አጥበው ድጋሚ በመሸጥ ወንጀል በቁጥጥር ስር ውለዋል። በሜዳን በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ በኩል የተጓጓዙ እስከ 9000 የሚደርሱ መንገደኞች እንደገና ጥቅም ላይ በዋሉት መሣሪያዎች ተመርምረው ሊሆን እንደሚችል ፖሊስ ገልጿል። በመንግሥት የሚተዳደረው ኪሚያ ፋርማ በተጓዦቹ ስም በተመሠረተ ክስ ፍርድ ቤት ሊቆም እንደሚችል ተዘገቧል፡፡ በኮቪድ ወረርሽኝ በተጠቁ በርካታ አገሮች ውስጥ ከአፍንጫ ፈሳሽ በመውሰድ መመርመር የተለመደ ሆኗል፡፡ ካለፈው ታህሳስ ጀምሮ በሰሜን ሱማትራ ሜዳን በሚገኘው ኳላናሙ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ማጭበርበሩ ሲፈጸም እንደነበር ይታመናል ብሏል ፖሊስ፡፡ ተሳፋሪዎች ለመብረር ከፈለጉ ከተህዋሲው ነጻ መሆን ይጠበቅባቸዋል። አየር ማረፊያው ፈጣን ውጤት ለሚፈልጉ በቦታው የምርመራ አማራጭ ይሰጣል። የአውሮፕላን ማረፊያው ባለሥልጣናት ኪሚያ ፋርማ የሚያቀርበውን አንቲጂን ፈጣን የመመርመሪያ መሣሪያዎችን ይጠቀሙ ነበር ተብሏል፡፡ በስህተት ተህዋሲው እንዳለባቸው የሚያሳይ የምርመራ ውጤት ማግኘታቸውን ተከትሎ ከተሳፋሪዎች ቅሬታ ቀርቧል። ባለፈው ሳምንት ፖሊስ ተሳፋሪ አስመስሎ በህቡዕ መኮንኑን በመላክ ጉዳዩን ማጣራቱን ዴቲክ የተሰኘው የአካባቢው የዜና አውታር ዘግቧል፡፡ ፖሊሱ ከአፍንጫው ናሙናው ተወስዶ ተህዋሲው እንዳለበት ሲነገረው ሌሎች ባልደረቦቹ ወደ ላቦራቶሪው በመግባት እንደገና ጥቅም ላይ የዋሉ የመመርመሪያ መሣሪያ አግኝተዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የሜዳንን ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ አምስት የኪሚያ ፋርማ ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከአፍንጫ ናሙና መውሰጃ የጥጥ ዘንጎችን በማጠብ እና በማሸግ ለሽያጭ አቅርበዋል በሚል የጤና እና የሸማቾች ህጎችን በመጣስ ወንጀል ተከሰዋል፡፡ የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣናት ከ 23 ምስክሮች ሪፖርቶችን አጠናቅረዋል ብለው ዘግበዋል። በጉዳዩ የተጠረጠረው አንዱ ግለሰብ በ124,800 ዶላር ገደማ የገነባው ቅንጡ ቤት ገንዘብ የዚሁ የማጭበርበር የውጤት ስለመሆኑ እየመረመሩ ነው። መቀመጫውን በዋና መዲናዋ ጃካርታ ያደረገው ኪሚያ ፋርማ በድርጊቱ የተሳተፉ ሠራተኞችን ያባረረ ሲሆን አሠራሩን እንደሚያጠብቅ ቃል ገብቷል፡፡ ባለፉት ወራት በኳላናሙ አውሮፕላን ማረፊያ በተደጋጋሚ በረራ ያደረጉ ሁለት ጠበቆች ኪሚያ ፋራማን ለመክሰስ ማቀዳቸውን የደቡብ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል፡፡ በጋራ ክስ በመመስረት ለእያንዳንዱ ተጎጂ ተሳፋሪ 1 ቢሊዮን ሩፒያ እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል፡፡ የኢንዶኔዥያ ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በሕንድ የታየው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ በሁለት ሰዎች ላይ መገኘቱን ገልጸው ነበር፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-56980753 +business በአዲስ አበባና አካባቢዋ ባለፉት 9 ወራት በደረሰ ድንገተኛ አደጋ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ውድመት መድረሱ ተገለጸ "ባለፉት 9 ወራት ብቻ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ በደረሰ የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የንብረት ውድመት መድረሱ ተገለጸ። የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቢቢሲ እንደገለጸው ባለፉት 9 ወራት በመዲናዋ እና አካባቢዋ በደረሱ 377 ድንገተኛ አደጋዎች 511 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል። የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በተከሰቱት ድንገተኛ አደጋዎችም የ104 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ154 ሰዎች ላይ ድግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልጸው፣ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ድንገተኛ አደጋ የእሳት አደጋ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ኮሚሽኑ መረጃ ከሟቾቹ ውስጥ በእሳት አደጋ የሞቱት 13 ሲሆኑ ሌሎቹ በጎርፍ፣ በኤሌክትሪክ አደጋ፣ ጉድጓድ ውስጥ በመግባት እና በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ በደረሰ አደጋ ሕይወታቸው ያለፉ ናቸው። አቶ ንጋቱ፣ በመዲናዋ እና አካባቢዋ በደረሰው አደጋ የደረሰው ጉዳት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ጭማሬ አሳይቷል ብለዋል። አደጋዎቹን በመቆጣጠር ሂደት ላይ ጉዳት የደረሰባቸው የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ቢኖሩም የተጠቀሰው አሃዝ ይህንን እንደማያካትት አክለዋል። ከዚህ ቀደም በአደጋ ሕይወታቸውን ያጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መኖራቸውንም ባለሙያው አስታውሰዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራትም 47 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት አጋጥሟቸዋል። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞቹ በ55 ሰዎች ላይ ሊደርስ የሚችልን አደጋ ማስቀረታቸውንና 3.7 ቢሊየን ብር የሚገመት የንብረት ውድመትን ማዳን ችለዋል ብለዋል። ለመሆኑ እዚህም እዚያም እየተከሰቱ ላሉ የእሳት አደጋዎች ምክንያቱ ምንድን ነው? በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ድንገተኛ አደጋዎች አጋጥመዋል። በዚህም የሰዎች ሕይወት አልፏል፤ በንብረት ላይም ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመዲናዋ አዲስ አበባ መካኒሳ አካባቢ የደረሰው የጎርፍ አደጋ የቤተሰብ አባላት ሕይወት አልፏል። በኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ አካባቢ ተለኩሶ በተረሳ ሻማ ሳቢያ የተነሳ የእሳት አደጋ አባትን ከአራት ልጆቹ ጋር በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል። ቦሌ ቡልቡላ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የጋዝ ሲሊንደር ፈንድቶ የ10 እና የ6 ህጻናት ሕይወት አልፏል። በቅርቡም በአዲስ አበባ ቃሊቲ ኢንደስትሪ መንደር ኤሊያስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ350 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል። በመዲናዋ እና አካባቢዋ ለተከሰቱ እነዚህ ድንገተኛ አደጋዎች ዋነኛ ምክንያቶች የከተሞች እያደገ መምጣት እና የሕዝብ ቁጥር መጨመር እንዲሁም የጥንቃቄ ጉድለት ናቸው ይላሉ ባለሙያው። በከተሞች ያለው የሕዝብ ቁጥር መጨመር በእሳትና በኤሌክትሪክ የሚገለገሉ ሰዎች ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት ነው ያሉት ባለሙያው፣ ነዋሪው ለመረጃ ቅርብ የሆነ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ ቢከተልም ለጥንቃቄ የሚሰጠው ዋጋ ግን አነስተኛ ነው ብለዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ካጋጠሙት የእሳት አደጋዎች ውስጥም ከ90 በመቶ በላይ ለሚሆኑት መነሻው የጥንቃቄ ጉድለት ሲሆን 10 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከአቅም በላይ በሆነ ችግር የተከሰቱ መሆናቸውን ባለሙያው ጠቅሰዋል። በጥንቃቄ ጉድለት ከተፈጠሩት ውስጥ ደግሞ ወደ 85.5 በመቶ የሚሆኑት ከኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ጋር የተያያዙ ናቸው። ወደ ኮሚሽኑ ሪፖርት ያልተደረጉ አደጋዎች እንደሚኖሩ የተናገሩት ባለሙያው፣ እነዚህ አሃዞች ያልተሰሙና ሪፖርት ያልተደረጉ አደጋዎችን አያካትትም ብለዋል። እነዚህ ቢካተቱ በአደጋው የደረሰው ጉዳት ከተጠቀሰው ከፍ ሊል እንደሚችል ተናግረዋል። ኮሚሽኑ የእሳት አደጋን ለመቆጣጠር ምን ያህል ብቁ ነው? ኮሚሽኑ በመዲናዋ እና አካባቢዋ የሚደርሱ ድንገተኛ አደጋዎችን ለመቆጣጠር ፈጥኖ ባለመድረስ እና የሰዎችን ሕይወትና ንብረትን ለማታደግ አስፈላጊ መሳሪያዎች እና ማሽኖች ባለመኖሩ ይተቻል። ለዚህም በከተማው ውስጥ ቤቶች ተጠጋግተው መሰራት፣ የመንገዶች ምቹ አለመሆን፣ የህንጻዎችና የመኖሪያ ቤቶች ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ምቹ ተደርገው አለመሰራታቸው፣ ስለድንገተኛ አደጋዎች በቂ ግንዛቤ አለመኖር አፋጣኝ ምላሽ ላለመስጠቱም እንደ ���ክንያትነት ይጠቀሳሉ። ይህንኑ ያነሳንላቸው ባለሙያው፣ ኮሚሽኑ በዘጠኝ ቅርንጫፍ ጣቢያዎችና በአንድ ማዕከል እንደሚመራና በእያንዳንዱ ጣቢያ አራት የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን ገልጸው፣ ይህ ግን እየተስፋፋ ላለው ከተማ በቂ አይደለም ብለዋል። ባለሙያው እንዳሉት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንጻ ላይ እሳት ቢነሳ ኮሚሽኑ ይህንን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሳሪያ የለውም። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ህንጻ በመዲናዋ ከሚገኙ ረጃጅም ህንጻዎች አንዱ ሲሆን ከመሬት 209 ነጥብ 15 ሜትር ከፍታ እና 53 ወለሎች አሉት። ""ህንጻዎች ከፍታቸው እየጨመረ በመጣ ቁጥር ለእንዲህ ዓይነት አደጋዎች የመጋለጥ እድላቸውን የሚቀንሱበትና የሚቆጣጠሩበት መንገድ መዘርጋት ህንጻዎቹን የሚገነቡት ግለሰቦች፣ ተቋማት፣ ድርጅቶች እና መንግሥት ኃላፊነት ነው"" ይላሉ። በመሆኑም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ህንጻ አደጋ ከመድረሱ በፊት መረጃ የሚሰጥና በቀላሉ ለመቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ በመጠቀም የተገነባ መሆኑን ይናገራሉ። ሆኖም በከተማዋ የሚሰሩ የመኖሪያ ህንጻዎች ፣ የንግድ ተቋማት፣ የአደጋ ጊዜ መውጫ እና ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያስችል መልኩ የተገነቡ አለመሆናቸውን ባለሙያው ይተቻሉ። በህንጻዎቹ ላይ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያ የተገጠመላቸው ቢኖሩም አብዛኞቹ አገልግሎት የሚሰጡ እንዳልሆኑና ባለሙያም እንደሌላቸው ጠቁመዋል። አዲስ አበባ ከተማ የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር ለምን የላትም? የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት ሲገነባ ሁለት ሄሊኮፕተር እንዲያሳርፍ ተደርጎ የተሰራ ቢሆንም አንድም ሄሊኮፕተር የለውም ይላሉ። በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በርካታ ጥብቅ ፓርኮች እንዳሉና በመዲናዋም የጉለሌ የእፅዋት ማዕከል እና የእንጦጦ ፓርክ መኖራቸውን ያነሱት ባለሙያው፣ በእነዚህ ፓርኮች እሳት ቢነሳ በከተማ ባሉ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ተሽከርካሪዎችን ብቻ በመጠቀም ሊጠፋ እንደማይችል ይናገራሉ። በመሆኑም ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀ የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር መኖሩ የግድ ነው ይላሉ። ባለፉት ዓመታት በርካታ የደን ቃጠሎዎች አጋጥመው አቻ ከሆኑ የአፍሪካ ከተሞች ማለትም ከኬንያ ፣ ደቡብ አፍሪካ ድጋፍ መጠየቁንና በሌሎች አገራት ድጋፍ እሳቱን ለማጥፋት መሞከሩን ባለሙያው አስታውሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ የጎርፍ አደጋ ሲያጋጥም የሰዎችን ሕይወት ለመታደግ ጀልባዎች እንደሚያስፈልጉም ጠቁመዋል። ክልሎች የራሳቸውን የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች ለማሟላት ቢሞክሩም ብዙም የተጠናከረ አቅም ስለሌላቸው በርካታ ጉዳቶች ደርሰዋል። ምንም እንኳን ኢንደስትሪ ፓርኮች ባሉበት አልፎ አልፎ የእሳት አደጋ ማጥፊያዎች በተሻለ ሁኔታ ቢኖሩም፣ በፌደራል ደረጃ የእሳት አደጋ መከለከያና መቆጣጠሪያ ተቋም ቢዋቀር ለሕብረተሰቡ የቀረበ አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ባለሙያው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የእሳት አደጋ ከመድረሱ በፊትና ከደረሰ በኋላ ምን ማድረግ አለብን? በኮሚሽኑ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ማካተትና ትግበራ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት እመቤት ኃይለሚካኤል፣ የእሳት አደጋን ለመከላከል በመኖሪያ መንደርም፣ በተቋምም ደረጃ በሕብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ መፍጠር ቀዳሚው ነው ይላሉ። ከዚህም ባሻገር እያንዳንዱ ተቋም ከሚሠራው ሥራ አንጻር አደጋ የሚከላከልበትን ጥንቃቄዎችና እርምጃዎችን ሊወስድ ይገባል። ይህንን ለማድረግ እንዲያስችልም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡና ህንጻዎች ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር አደጋን ለመከላከል የሚያስችል የ��ሰጣቸው መለያ (ኮድ) አለ። በዚህም መሠረት አደጋን የመከላከል ሥራው ህንጻዎች ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር የሚገነቡበትን ጥሬ እቃ ከመምረጥ ይጀምራል። ምክንያቱም ህንጻዎቹ የሚገነቡበት ጥሬ እቃ እሳትን የመቋቋም አቅማቸው ተመሳሳይ ስለማይሆን ነው። በመሆኑም ፋብሪካዎች ፣ ባንኮችና ሌሎች ተቋማት የሚገነቡበት ጥሬ እቃ ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር የተለያየ መሆን አለበት። ከዚህም በተጨማሪ ህንጻዎች በሚገነቡበት ጊዜም የእሳት ማጥፊያ ሥርዓት ዝርጋታ፣ የእሳት ማጥፊያ፣ የእሳት ሃይድራንት፣ አደጋ አነፍናፊ መሣሪያዎች [ሴንሰር] መገጠም አለባቸው። የጭስ፣ የሙቀት፣ የጋዝ እና የጨረር አነፍናፊ መሣሪያዎችን መግጠም፣ በተገቢው ሁኔታ እንዲሰሩ ማድረግ እና የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ማዘጋጀትና በየጊዜው መስራታቸውን መከታተል ያስፈልጋል። የአደጋ ጊዜ መውጫ ቦታዎችን ማለትም በሮችን፣ መንገዶችንና ኮሪደሮችን መገንባት ማዘጋጀት፣ ተንቀሳቃሽ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎችን ማደራጀት እና እሳትን መቋቋም የሚችሉ በሮችን መግጠም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ባለሙያዋ ይመክራሉ። ይህም ብቻ ሳይሆን የአደጋ ጊዜ መውጫ በሮች አዘጋግና አከፋፈታቸውን ለመውጣት አመቺ እንዲሆኑ ማድረግ ወሳኝ ነው። በመጋዘኖች አሊያም በቤት ውስጥ እቃዎችን ስናስቀምጥ በዓይነት በዓይነታቸው እንዲቀመጡ ማድረግ፣ በእቃዎቹ መካከል ክፍተት እንዲኖረው ማድረግ፣ ተቀጣጣይ ነገሮች ካሉ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲከማቹ ማድረግም ሊደርስ የሚችልን አደጋ በመከላከልና አደጋውን በመቀነስ ረገድ አስተዋጽኦ አለው። በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ ያለውን ጥግግት ማስቀረት ፣ የኤሌክትሪክ ዝርጋታን በባለሙያ ማከናወንና የጋዝ ሲሊንደር አጠቃቀምን ጥንቃቄ የተሞላበት ማድረግ፣ ያረጁትን መቀየር፣ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን ከተጠቀሙ በኋላ መንቀል፣ የኤሌክትሪክ ገመዶችን በእቃዎች ሥር እና ህጻናት በሚደርሱበት ቦታ አለማስቀመጥ፣ የጋዝ ሲሊንደርን ሙቀት ካለበት ቦታ ማራቅ፣ የማያገለግሉ እቃዎችንና ደረቅ ተቀጣጣይ ነገሮችን ግቢ ውስጥ አለማከማቸት የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ለማድረግ ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው። አደጋ ከደረሰ በኋላስ ምን መደረግ አለበት? የእሳት አደጋ ከደረሰ በኋላ እሳቱን በተገኘው ነገር ለማጥፋት ከመሞከር በፊት እሳቱ የተነሳበትን መንስዔ ማወቅ አስፈላጊ ነው። በትልልቅ ተቋማት የተገጠሙ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎች ህንጻዎቹ በሚሰጡት አገልግሎት ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው እሳት ሲከሰት መሣሪያዎቹን በተገቢው መንገድ በባለሙያ በመጠቀም ማጥፋት ወሳኙ እርምጃ ነው። ""የተከሰተ አደጋ ሁሉ ተመሳሳይ የእሳት አደጋ አይደለም"" የሚሉት ባለሙያዋ፣ ሁሉንም እሳት በተመሳሳይ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያ ማጥፋት አይቻልም ይላሉ። የእሳት ማጥፊያ መንገዶች ውሃ፣ ፎም፣ ካርቦንዳኦክሳይድ እና ደረቅ ኬሚካል ዱቄት ናቸው። እነዚህ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎችን የምንጠቀመውም እንደ የእሳት አደጋው መንስኤ ነው። ለምሳሌ የነዳጅ ዴፖ፣ የአልኮል መጠጦች፣ የኮስሞቲክስ፣ ዘይት ፣ ቀለም የሚመረቱበትና የሚሸጡበት ቦታ ላይ የተነሳን የእሳት አደጋ በውሃ ለማጥፋት መሞከር እሳቱን ያባብሰዋል። በመሆኑም ተቀጣጣይ ፈሳሾች ባሉበት ቦታ የተነሳን እሳት ማጥፋት የሚቻለው በፎም ነው። ፎም 90 በመቶው ውሃ ሲሆን 10 በመቶው ውሃ ነው። ደረቅ ተቀጣጣይ ነገሮች ባሉበት ደግሞ ውሃን መጠቀም አስፈላጊ ነው። የፋይናንስ ተቋሞች፣ ባንኮች ፣ ቤተ መጽሐፍት ፣ ቤተ መዛግብት፣ ሙዚየም እና የሰነዶች መቀመጫ ቦታዎች ደግሞ በውሃ ቢረጩ ሊበላሹ ስለሚችሉ እሳት ቢነሳ ካርቦንዳ ኦክሳይድን በመጠ���ም ማጥፋት ይቻላል። እሳትን ማጥፋት ያለበት ማን ነው? የእሳት አደጋ ሲከሰት ማንኛውም ሰው እሳቱን ለማጥፋት መረባረብ አለበት? በምን ዓይነት ደረጃ ላይ ያለ እሳት ነው ያለ ባለሙያ ድጋፍ ሊጠፋ የሚችለው? እሳቱ የተነሳበት ተቋም ወይም ቤት ውስጥ ያሉ ሰዎችስ ምን ማድረግ አለባቸው? ባለሙያዋ እንደሚሉት ሦስት የእሳት ደረጃዎች አሉ። አንደኛው ጅምር ሲባል ቀሪዎቹ በማደግ ላይ ያለ እና የሞተ እሳት ይባላል። በመሆኑም በተቋም ወይም በመኖሪያ ቤት ያሉ ሰዎች ሊያጠፉት የሚችሉት ጅምር በተባለው ደረጃ ላይ ያለን እሳት ነው። እሳቱ በማደግ ላይ ወይም በመስፋፋት ላይ ካለ ግን ሰዎች ቤቱንም ሆነ ህንጻውን ለቀው በመውጣትና በአንድ ላይ በመሰባሰብ ለአደጋ መቆጣጠሪያ ተቋም መደወል ነው የሚጠበቅባቸው። በዚህ ደረጃ ላይ ያለ እሳት መጥፋት የሚችለው በተሽከርካሪ በታገዘ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያ አማካይነት ነው። ሰዎች እንዲህ ዓይነት አደጋ በሚያጋጥም ጊዜም ወደ ቤቱ የሚገባውን የኦክስጅን መጠን ለመቀነስ እና ወደ ውጭ እሳቱ እንዳይስፋፋ ለማድረግ በርና መስኮት ዘግቶ መውጣትም ይመከራል። አደጋ በሚከሰትበት ሰዓት ሰዎች በድንጋጤ ይዋጣሉ። ምን አልባት የሚያደርጉት ሊጠፋቸው ይችላል። በዚህም ጊዜ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ ሊወስኑ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ግን ሰዎች ማድረግ ያለባቸው ቤታቸውን ወይም ተቋሙን ወዲያውኑ ለቀው በመውጣት ለአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መደወል እንዳለባቸው ባለሙያዋ ይመክራሉ። "" በአደጋ ጊዜ ለሰው ሕይወት ነው ቅድሚያ መሰጠት ያለበት"" የሚሉት ባለሙያዋ፣ ተቀጣጣይ ነገሮች የሚለቁት መርዛማ ጋዞች ስላሉ ለእርሱ ሊጋለጡ ስለሚችሉ ቤት ውስጥ የቀረ ሰው ቢኖርም እንኳን ለባለሙያዎች መተው አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዋ ይመክራሉ። አደጋው የተከሰተበት ቦታ የቀረ ሰው ካለም መረጃዎች በመስጠት፣ የቤቱን ወይም የተቋሙን መግቢያ መውጫ በማመላከት የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን ማገዝ እንደሚገባም ባለሙያዋ ተናግረዋል። አሁን አሁን በተለይ በከተሞች አካባቢ የሚገነቡ ህንጻዎች እና የመኖሪያ መንደሮች እየተበራከቱ ነው። ይሁን እንጂ በርካታ ማሕበረሰብ የሚኖርባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ መንግሥት ህንጻዎች ሲገነቡ ለደህንነት ጥንቃቄ የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ከግምት አያስገቡም። አብዛኞቹ የአደጋ መውጫ ጊዜ መውጫ ኮሪደርና በሮች የሏቸውም። የተገጠመላቸው የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎችም እንዲሁ የተገጠመላቸው አይደሉም። በተለይ ዝቅተኛ የገቢ ምንጭ ያላቸው ነዋሪዎች የሚኖሩባቸው መንደሮች የተጠጋጉና አደጋን ለመቆጣጠር የሚያመቹ የውስጥ ለውስጥ መንገድ የላቸውም። አንድ ህንጻ ሲገነባ ከዲዛይኑ ጀምሮ ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ ደንቦችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚያስችል ሕግ ቢኖርም አፈጻፀም ላይ ግን ችግር እንዳለ ባለሙያዋ ይናገራሉ። ይህም በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዲባባስ አድርጎታል። አንዳንድ ህንጻዎችና ተቋማት ቁሳቁሶቹን ለደንቡ ቢያሟሉም ባለሙያ የሌላቸውና በየጊዜው ፍተሻ እንደማይደረግላቸውም ባለሙያዋ ተችተዋል። አሁን ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተሳሰር ይህንን ክፍተት ለመሙላት እየተሰራ ቢሆንም ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ባለሙያዋ አሳስበዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61435709 +health በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከአምስት ሺህ ተሻገረ "በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ቀናት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ከ70 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተመዘገበ። ከጤና ሚንስቴር እና ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ማክሰኞ መስከ��ም 4/2014 ዓ.ም. ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የ34 ሰው ሕይወት አልፏል። ሰኞ መስከረም 3/2014 ዓ.ም. ደግሞ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የ38 ሰዎች ሕይወት አልፎ፤ በሁለቱ ቀናት ውስጥ ብቻ 72 ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል። በወረርሽኙ ምክንያት ሕይወታቸው ከሚያልፍ ሰዎች በተጨማሪ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እንዲሁ በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ እያሳየ ነው። ከሰሞኑ በቫይረሱ ምክንያት የሚሞቱ እና የሚያዙ ሰዎች ቁጥር የጨመረው 'ዴልታ' በተባለው አዲስ አይነት የቫይረሱ ዝርያ ስርጭት ምክንያት መሆኑን የጤና ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። ሦስተኛ ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንደተከሰተ መልክት በታየባት ኢትዮጵያ፤ ""ዴልታ"" የተሰኘው አዲስ የኮቪድ ዝርያ መገኘቱንም የጤና ሚንስቴር ባለፈው ሳምንት አስታውቆ ነበር። የአሜሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል እንደሚለው ይህ 'ዴልታ' የኮቪድ ዝርያ ከሌላው የቫይረሱ ዝረያ ሁለት እጥፍ የመስፋፋት አቅም ያለው ሲሆን የሚያስከትለው ህመምም ከፍ ያለ ነው። 'ዴልታ' የተባለው ይህ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ሁሉንም የዕድሜ ክልል የሚያጠቃ፣ ለከባድ ህመምና ሞት የሚዳርግ በተለይም ባልተከተቡ ሰዎች ላይ የሚበረታ መሆኑ ተነግሯል። የጤና ሚንስቴር ዲኤታው እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ 'ዴልታ' በተሰኘው የቫይረሱ ዝርያ የሚያዙ፣ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው። ሕብረተሰቡ የኮቪድ-19 ቅድመ ጥንቃቄ መመሪያዎችን አለመከበር የቫይረሱ ስርጭት እንዲስፋፋ ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። ከዚህ ቀደም ለመጨረሻ ጊዜ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ከ30 በላይ የሞት መጠን የተመዘገበው ባለፈው ዓመት 2013 ሚያዝያ ወር የመጨረሻ ሳምንታት ላይ ነበር። ሚያዝያ 19 ላይ 35 ሰዎች፣ ሚያዝያ 20 ላይ 34 ሰዎች እንዲሁም ሚያዝያ 25 እና 30/2013 ዓ.ም. ላይ ከበሽታው ጋር በተያያዘ 31 ሰዎች መሞታቸውን የጤና ሚንቴር አስታውቆ ነበር። አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ 'ዴልታ' ከቀናት በፊት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ ቀደሞ ካለው የከፋ መሆኑን ተናግረዋል። 'ዴልታ' የተሰኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ የኮቪድ-19 ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ የሚኖረው ጉዳት ዝቅተኛ ስለሆነ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባቶችን እንዲወስዱ ይመከራሉ። መንግሥት የኮሮናቫይረስ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋት በመቀጠሉ የጤና ሚኒስቴር ከጥቂት ሳምንት በፊት በሽታውን ለመከላከል መወስድ ስላለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ያወጣውን መመሪያ በማሻሻል በጥብቅ ተግባራዊ እንዲሆን አዟል። ከዚህ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰጣቸው ዜጎች የዕድሜ ገደብ ዝቅ ከመደረጉ በተጨማሪ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲካተቱ ተደርጓል። የኮሮናቫይረስ ክትባት በኢትዮጵያ መሰጠት ሲጀምር ክትባቱ በቀዳሚነት ለጤና ባለሙያዎች፣ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ50 እስከ 60 ሆኖ ተጓዳኝ ህመም ላለባቸው እንዲሰጥ ቅድሚያ ተሰጥቶ ነበር። በአሁኑ ወቅት ደግሞ በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ በተስፋፋባት በመዲናዋ በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ እድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች እንዲሁም በሌሎች የአገሪቱ ክልሎችና የከተማ አስተዳደር እድሜያቸዉ ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ዜጎች እንደሚሰጥ የጤና ሚኒስተሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀው ነበር። በኢትዮጵያ የወረርሽኙ መከላከያ ክትባት መሰጠት ከጀመረ አንስቶ አስከ ትናንት መስከረም 4 2014 ዓ.ም. ድረስ 2.3 ሚሊዮን ሕዝብ ክትባት ወስዷል። የአሜሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል በኮቪድ ስርጭት ምክንያት ኢትዮጵያን ""ደረጃ ሦስት"" በሚል የጉዞ ማስጠንቀቂያ ከሰጠባቸው አገራት ውስጥ ትናንት አካቷል። የአሜሪካ መንግሥት ዜጎቹ ""ደረጃ ሦስት"" ውስጥ ወደ ተመደቡ አገራት አስገዳጅ ያልሆነ ጉዞ እንዳያደርጉ ይመክራል። የኮቪድ-19 የበለጠ የከፋባቸው አገራት ደግሞ ""ደረጃ አራት"" ውስጥ የሚካተቱ ሲሆን፤ የአሜሪካ መንግሥት ዜጎቹ ወደነዚህ አገራት እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። የክትባት ፍትሐዊነት የዓለም ጤና ድርጅት አፍሪካ ከቀሪው ዓለም ጋር ስትነጻጸር በኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት አቅርቦት ""ወደኋላ ቀርታለች"" ሲል አስጠነቀቀ። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የዓለም ጤና ድርጅት ባስቀመው ግብ መሠረት ባለንበት የፈረንጆች ዓመት 40 በመቶ የሚሆነውን ሕዝባቸውን መከተብ የሚችሉት የአፍሪካ አገራት ሁለት ብቻ ናቸው። ይህም ከሌሎች የዓለም አህጉራት ሁሉ በጣሙን ዝቅተኛው ነው ብለዋል፤ ዶ/ር ቴድሮስ። ዳይሬክተሩ እንዳሉት እስካሁን በዓለም ዙሪያ ከ5.7 ቢሊየን በላይ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች የተሰጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለአፍሪካ የደረሰው ግን 2 በመቶው ብቻ ነው። ዶ/ር ቴድሮስ ጨምረውም ክትባቶቹ በፍትሐዊ ሁኔታ ካልተከፋፈለ ቫይረሱ ባህሪዩን እንዲቀይር የሚያደርግ ከፍተኛ ዕድል እንዳለ አስጠንቅቀዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58567895 +business """አገሪቷ ስለተረጋጋች ኢንተርኔቱ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚከፈት ተስፋ አደርጋለሁ""-ቢልለኔ ስዩም" "በአገሪቱ ከተቋረጠ ቀናት የተቆጠሩት የኢንትርኔት አገልግሎት በቀጣይ ሳምንት ሊመለስ እንደሚችል በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የሆኑት ቢልለኔ ስዩም ለቢቢሲ ኒውስዴይ ተናገሩ። ቢልለኔ እንዳሉት የኢንተርኔት አገልግሎት የብሔር ጥላቻን ለማስፋፋት ጥቅም ላይ በመዋሉ መንግሥት አገሪቱንና ሕዝቡን የመጠበቅ ኃላፊነት ስላለበት ለማቋረጥ መገደዱን ተናግረዋል። ኢንተርኔት መቼ ይለቀቃል ተብለው ሲጠየቁ ነገሮች ወደ ቀደመው ሁኔታ እየተመለሱ መሆኑን ገልጸው በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ተናግረዋል። ቃል አቀባይዋ ለኒውስዴይ እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባም ሆነ በኦሮሚያ ውስጥ ሁኔታዎች ወደ ቀደሞው መረጋጋታቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል። ቢልለኔ ስዩም የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ግጭት 80 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋው፤ አንዳንድ ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓቱን በማስተጓጎል ችግር ለመፍጠር ቢሞክሩም ፖሊስ ግን በሰዎች ላይ አልተኮሰም ብለዋል። ጨምረውም ካለመረጋጋት ታሪክ ውስጥ እየወጣች ያለችውን አገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ዲሞክራሲ ለመውሰድ ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጽ ከጥቂት ዓመታት በፊት የማይቻል የነበረው በአሁኑ ሰዓት በርካታ ወገኖች ድምጻቸውን ማሰማት ችለዋል ሲሉም ተናግረዋል። ከሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተያዙ ሰሰዎች መኖራቸውን የተናገሩት ቃል አቀባይዋ፤ ነገር ግን ጉዳዩ በምርመራ ላይ ያለ በመሆኑ አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ አስታውቀዋል። በተያያዘ ዜና የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአዲስ አበባ ቢሯቸውን ከፍተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሦስት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታወቋል። እነዚህም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አስራት፣ ድምጺ ወያኔ እንዲሁም ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) ሲሆኑ ኦኤምኤን የአዲስ አበባ ቢሮው መዘጋቱ ታውቋል። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እንዳለው ለድምጺ ወያኔ እና ለትግራይ ቲቪ ጠንከር ያለ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መጻፉን ገልጿል። ቢቢሲ ስማቸው ከተጠቀሱት የቴሌቪዥን ጣቢ���ዎች ከእራሳቸው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እየሞከረ ቢሆንም እስካሁን አልተሳካም። ምላሻቸውን ለማግኘት ጥረታችን ይቀጥላል። የድምጺ ወያኔ ዋና ቢሮ መቀሌ የሚገኝ ሲሆን አስራትና ኦኤምኤን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ደግሞ ዋና ስቱዲዮዋቸው በአሜሪካ መሆኑ ይታወቃል። በትናንትናው ዕለት ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በሰጡት መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከጥምር የፀጥታ ኃይል ጋር በመሆን የከተማዋን ሰላምና ሥርዓት ማስከበር መጀመሩንም ተናግረው ነበር። ""ማናችንም ብንሆን ከአገር በታች ነን፣ ከሕግ በታች ነን"" በማለት አገርንና ትውልድን ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ጠቅሰው፤ አገር የማስተዳደር ሂደትን ለማደናቀፍ የሚሞክር የትኛውም አካልን ""ትዕግስት ልክ አለው"" በማለት ""ከዚህ በኋላ በየትኛውም ሚዲያ፤ በየትኛውም ጽሁፍ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ፤ ግለሰብን ማዕከል ያደረገ፤ ሕዝብን ማዕከል ያደረገ የጥላቻ፤ የፕሮፖጋንዳ ሥራ አንታገስም"" ማለታቸው ይታወሳል። ሲፒጄ በበኩሉ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ መዘጋቱ ከተሰማ በኋላ ባወጣው መግለጫ ""የመንግሥት ባለስልጣናት በአስቸኳይ ኢንተርኔቱን እንዲመልሱት"" ጠይቆ ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/53274906 +politics በርካቶች ስፔናውያን ለካታላን ተገንጣዮች የሚሰጥ ምህረትን በመቃወም አደባባይ ወጡ "በእስር ላይ ለሚገኙት የካታላን ተገንጣዮች ለማድረግ የታሰበውን አከራካሪ የይቅርታ ዕቅድ በመቃወም በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በስፔን ዋና ከተማ ማድሪድ የተቃውሞ ሰልፎችን አካሄዱ። የስፔን የቀኝ ክንፍ ፓርቲ አመራሮች እአአ በ2017 ያልተሳካውን የነጻነት ሙከራ የመሩ 12 ተገንጣዮች ምህረትን በመቃወም ሰልፉን ተቀላቅለዋል። በሶሻሊስት ፓርቲ የሚመራው የስፔን መንግሥት ዕቅዱን የፖለቲካ ድጋፉን ለማጎልበት ተጠቅሞበታል ሲሉ ሰልፈኞቹ ይከሳሉ። መንግሥት በበኩሉ በምህረቱ በካታሎኒያ ላይ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ለማርገብ ይረዳል ብሏል። የከፊል ራስ ገዟ ክልል ካታሎኒያ የእአአ 2017 የነፃነት እንቅስቃሴ ስፔንን በ40 ዓመታት ውስጥ ትልቁ ወደ ተባለው የፖለቲካ ቀውስ ከቷታል። ዘጠኝ የካታላን ተገንጣይ መሪዎች በሕገወጥ የነፃነት ሪፈረንደም ውስጥ ከነበራቸው ሚና ጋር ተያይዞ ጥፋተኛ ተብለዋል። ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙም በቁጥጥር ስር አልዋሉም። እንደሰልፈኞቹ ከሆነ ይቅርታው ለብሔራዊ አንድነት አደጋ ነው። በማዕከላዊ ማድሪድ ኮሎን አደባባይ ሲሰበሰቡ ብዙዎች ቀይ እና ቢጫ ብሔራዊ ባንዲራዎችን ያውለበለቡ ነበር። ካርሎስ ባንዴቻ የተባሉ ሰልፈኛ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ""ይህንን ማስቆም አለብ። ምክንያቱም ይቅር ለማለት ይቅርታ መጠየቅ አለበት። ተገንጣዮቹ ግን ያን አያሳዩም።"" የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እርምጃውን ካታሎኖችን እና ስፔናውያንን ይበልጥ ያቀራርባል በሚል ውሳኔውን ተከላክለዋል። ሳንቼዝ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ""የስፔን ማኅበረሰብ ካለፈው መጥፎ ታሪክ ወደ ተሻለ የወደፊት ኑሮ መሸጋገር ይኖርበታል"" ብለዋል። የስፔኑ 'ኤል ሙንዶ' ጋዜጣ ባደረገው አንድ ጥናት መሠረት 61 በመቶ የሚሆኑት ስፔናውያን በይቅርታው አይስማሙም፣ 29.5 በመቶዎቹ ደግሞ ደግፈውታል። የስፔን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ካርመን ካልቮ ይቅርታው ""ቅርብ"" መሆኑን ጠቁመዋል። የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ወር አስገዳጅ ባልሆነው ሪፖርት ለካታላን ተገንጣይ መሪዎች መንግሥት ሊሰጥ የሚችለውን ይቅርታ እንደሚቃወም ገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57455831 +politics ሺንዞ አቤ እና አበበ ቢቂላ ሺንዞ አቤ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር። የዛሬ ሰባት ዓመት ገደማ። በወርሃ ጥር 2007 ዓ.ም. ኢት���ጵያ መጥተው ምን አደረጉ? ከአበበ ቢቂላ ልጅ የትናየት አበበ ጋር ተገኛኙ። የትናየት የአባቱን የአበበ ቢቂላን ፎቶ አበረከተላቸው። ለመሆኑ አበበ ቢቂላና ሺንዞ አቤ ምንና ምን ናቸው? ከሟቹ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አንደበት እንደተሰማው ከሆነ እሳቸው አበበ ቢቂላን አይረሱትም። አበበ ከ58 ዓመት ገደማ በፊት በቶኪዮ ማራቶን በባዶ እግሩ ሮጦ ድል ሲያደርግ እሳቸው ትንሽ ልጅ ነበሩ። ተማሪ ቤት ነበሩ። የአበበ ቢቂላ ስምና ዝና ደግሞ በመላዋ ጃፓን እጅግ ናኝቶ ነበር። ሺንዞ አቤ ደግሞ መጠሪያ ስማቸው አቤ ነው። ‘አቤ’ በሰሜን ጃፓን ሆካይዶ ደሴት ውስጥ ከሚነገር ‘አይኑ’ ቋንቋ የተገኘ ስያሜ ነው። አቤ በጃፓን ውስጥ የበርካታ ሰዎች መጠሪያ ስም ከመሆኑ በተጨማሪ ብዙ ቦታዎችም ይህንን ስያሜ ይጋራሉ። በዚህም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ከዝነኛው አበበ ቢቂላ ጋር ባላቸው የስም ምስስሎሽ ትምህርት ቤት መቆሚያ መቀመጫ አጡ። የክፍል ልጆች አስቸገሯቸው። አበበ እያሉም ይጠሯቸው ነበር። በአበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ የቶኪዮ ማራቶንን ባሸነፈበት ወቅት እሳቸው ገና 10 ዓመታቸው ነበር። ቢሆንም የአበበ ቢቂላ ድል ልክ ትናንት የሆነ ያህል ትዝ ይለኛል፣ ሲሉ ነበር ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት በመጡበት ጊዜ የተናገሩት። በጉዟቸው አቤ የስመ ጥሩ ሞክሺያቸውን ፍቅር ለመግለጽ፣ የልጅነት ጊዜያቸው ጀግና ወደ ሆነው ሰው አገር ከመጡ አይቀር ቤተሰቡን እና አትሌቶችን አግኝተዋል። የአበበ ቢቂላን የሙያ ልጆች ፈለጉ አስፈለጉ። ደራርቱን፣ ኢብራሂም ጀይላንን፣ ቲኪ ገላና እና መሰረት ደፋርን አገኙ ኤኤፍፒ በወቅቱ እንደዘገበው። የአበበ ቢቂላ ልጅ የትናየት አበበም ለሺንዞ አቤ አባቱ ከ50 ዓመት በፊት ቶኪዮ ላይ ታሪክ ሰርቶ የመጨረሻውን የማራቶን መስመር በማለፍ ድል ያደረገበትን ጊዜ የሚያስታውስ ፎቶ በስጦታ አበረከተላቸው። ሺንዞ አቤ አበበ ቢቂላ ቶኪዮ ላይ ሲያሸንፍ የነበረውን ሁኔታ እያስታወሱ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት አድናቆታቸውን ገልጸው ነበር። “በርካታ ጃፓናውያን ተወዳዳሪዎች ሩጫውን ጨርሰው ተዘርረው ሲወድቁ፣ አበበ ግን ከባዱን ሩጫ ጨርሶ እዚው ሰውነቱን ያፍታታ ዱብ፣ ዱብ ይል ነበር” በማለት የ10 ዓመት ልጅ ሳሉ ያዩትን አበበን አስታውሰዋል። አበበ ቢቂላ በኦሊምፒክ ታሪክ ስሙ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም በደማቁ የተጻፈ አትሌት ነው። በተጨማሪ ደግሞ ሺንዞ አቤን ጨምሮ አሁን ድረስ በበርካታ ጃፓናውያን የሚጠቀስ ኮከብ ሯጭ ነው። ሐሙስ ዕለት የዓለም መገናኛ ብዙኃን በብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ላይ ዐይኑን ጥሎ ነበር። አርብ ዕለት ከማለዳው ጀምሮ ደግሞ ዓለም በሺንዞ አቤ በጥይት መመታት ከዚያም መሞት በእጅጉ ደንግጧል። እሳቸው ሥልጣን በቃኝ ካሉ ዓመታት ተቆጥረዋል። ነገር ግን ለጃፓን የላይኛው ምክር ቤት የሚወዳደር ዕጩን ወክለው ቅስቀሳ እያደረጉ ነበር። በኋላ ላይ የተመረመሩ ፎቶግራፎች እንዳሳዩት ተጠርጣሪው ገዳይ ከአቤ ኋላ በቅርብ ርቀት ቆሞ ንግግራቸውን ያዳምጥ ነበረ። ከዚያም ከጀርባቸው አከታትሎ ተኮሰባቸው። በቀኝ በኩል አንገታቸውና ጀርባቸው ላይ በጥይት ተመቱ። ተዝለፍልፈው ወደቁ። ደም ፈሰሳቸው። ሄሌኮፕተር ተጠራ። ሆስፒታል ገቡ። የጃፓን ስመጥር ሐኪሞች ነፍስ ለማዳን የቻሉትን ሁሉ አደረጉ። አልተሳካም። እሳቸው ይቺን ምድር ሲሰናበቱ ገና 67 ዓመታቸው ነበር። ረጅም ዕድሜን ለሚኖሩት ጃፓኖች ይህ ዕድሜ በአጭር የመቀጨት ያህል ነው። የጦር መሣሪያ ጥቃት እምብዛም ባልተለመደባት ጃፓን ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ የሚለው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ጃፓን ጥብቅ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ያለባት አገር ነች። እንደ አሜሪካ ጃፓን ውስጥ የጦር መሣሪያ ከሱቅ እንደሸቀጥ እንደልብ አይገዛም። በአውሮፓውያኑ 2014 አሜሪካ ውስጥ 33,599 የጦር መሣሪያ ጥቃቶች ሲፈጸሙ፣ ጃፓን ውስጥ ግን ስድስት ብቻ ነበረ። መሣሪያ ለመታጠቅ የሚፈለግ ጃፓናዊ በመንግሥት የሚሰጥን ጥብቅ ፈተና እና የአእምሮ ጤና ምርመራን በብቃት ማለፍ ይጠበቅበታል። ለዚህም በጃፓን የጦር መሣሪያ ፍቃድ ለማግኘት ከመሞከር መሣሪያ መፈብረክ ይቀላል። ጃፓኖች ደግሞ ቁስ በማምረት ማን አህሏቸው፤ ከወዳደቀ ቁሳቁስም ቢሆን የጦር መሣሪያ ሊፈበርኩ ይችላሉ። በቁጥጥር ሥር የዋለው ገዳያቸው መሣሪያውን ቤቱ ውስጥ ራሱ ጠፍጥፎ እንደሰራው እየተዘገበ ነው። ፖሊስ የአቤ ገዳይ ለምን ግድያውን እንደፈጸመና ለድርጊቱ ተባባሪ እንዳለው ለማወቅ ምርመራ እያደረገ ነው። ቤቱ ላይ በተደረገው ፍተሻም ከጦር መሳሪያ በተጨማሪ ፈንጂዎች መገኘታው ተነግሯል። ሺንዞ አቤን በመግፈል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው ቴተሱያ ያማጋሚ የሚባል ሥራ አጥ የ41 ዓመት ጎልማሳ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል። ያማጋሚ ጡረተኛውን ጠቅላይ ሚኒስርት ለመግደል ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከግምት በስተቀር የተነገረ ጉዳይ የለም። ሺንዞ አቤ፣ የአበበ ቢቂላ አድናቂና ሞክሼ፣ 20 ሺህ ጃፓናውያንን የጨረሰውን ሱናሚ አልፈው፣ እንደ መሪ የሚደረገውን ሁሉ አድርገው በአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ቤት ሠራሽ ጥይት ላይመሱ አሸልበዋል። የፈሩት የአንጀት ቁስለት፣ ሥልጣን የለቀቁለት በሽታ ሳይገድላቸው፤ በቤት ሠራሽ ጥይት እስከወዲያኛው አሸልበዋል። ዓለም በተለይም ጃፓናውያን በእጅጉ ደንግጠዋል፣ ግድያውን ተከትሎም “ዴሞክራሲ እንጂ ፖለቲካዊ ጥቃትን አንፈልግም” የሚል የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻን ከፍተዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cv29dpr543go +business ከ1600 በላይ የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ እንዲገቡ ቻይና ፈቀደች ኢትዮጵያ ምርታቸውን ወደ ቻይና ከቀረጥ እና ከኮታ ነጻ እንዲያስገቡ የገበያ ዕድል ከተፈቀደላቸው አገራት መካከል አንዷ መሆኗን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ። የቻይና መንግሥት አብዛኞቹ ከአፍሪካ ከሆኑ አገራት ጋር ያለውን የንግድ ትስስር ለማጠናከር በሚል ባቀደው መርሃ ግብር መሠረት ነው ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ምርቶች ያለ ቀረጥ እንዲገቡ የፈቀደው። ኢትዮጵያ በዚህ ነጻ ዕድል ለመጠቀም የሚያስፈልጉትን መረጃዎችን በወቅቱ ሳታሟላ በመቅረቷ በመርሃ ግብሩ ውስጥ ሳትካተት ቀርታለች ተብሎ ነበር። ነገር ግን በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር ቁምነገር እውነቱ፣ የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ ቻይና እንዲገቡ መፍቀዱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህም መሠረት ቻይና ከ1600 በላይ የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ እንዲገቡ መፍቀዷን ገልጸዋል። ይህም አሐዝ በአጠቃላይ የንግድ ልውውጥ ከሚደረግባቸው 6,422 ምርቶች መካከል 1,644ቱን ምርቶች ከቀረጥ እና ከኮታ ነጻ ማስገባት እንደሚቻል ተገልጿል፡፡ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዳለው ይህ የገበያ ዕድል ከቻይና በኩል ብቻ የተሠጠ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በዚህ ዕድል ተጠቃሚ ስትሆን የሚጠበቅባት ምንም ዓይነት ግዴታ የለም። ከዚህ ቀደም ቻይና 10 አገራት ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ ምርቶች እንዲያስገቡ ዕድል ስትሰጥ ኢትዮጵያ በዝርዝሩ ውስጥ አለመካተቷ ጥያቄ ሲያስነሳ እንደነበር የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሯ፣ አሁን 1644 ምርቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ መፈቀዱን ለቢቢሲ አስረድተዋል። “ኢትዮጵያ ብዙ ሀብትና ምርት እያላት እንዴት ልትገለል ቻለች? የሚሉ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ሲነሱ ነበር። እኛም ስንጠባበቅ ነበር። አሁን 1644 ምርቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ተፈቅዷል” ሲሉ አብራርተዋል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ እነዚህን ሁሉ ምርቶች በአጠቃላይ ወደ ቻይና ትልካለች ማለት ሳይሆን “ከዝርዝሮቹ መካከል በእጇ ላይ የሚገኙትን ምርቶች” እንደምትልክ አክለዋል። ለምሳሌ የብረታ ብረት እጥረት እያለ እንዴት ወደ ውጭ መላክ ይቻላል? የሚሉ ጥያቄዎች እየተነሱ እንደሆነ የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሯ፣ “ኢትዮጵያ ወደ ቻይና መላክ የምትችለው የታወቁ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ይሆናል” ብለዋል። እነዚህም ኢትዮጵያ እስካሁን ለተለያዩ የዓለም ገበያዎች በማቅረብ የምትታወቅባቸው ከቁም እንስሳት፣ ከቅባት እህሎች እና ከግብርና ምርቶች ጋር የተያያዙ ሲሆኑ፣ በተጨማሪም በቻይና ፈቃድ ከተሰጣቸው ምርቶች ውስጥም ሌሎች ከኢትዮጵያ ወደ ቻይና የሚላኩ እንደሚኖሩ ኃላፊዋ ተናግረዋል። ቻይና ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ እንዲገቡ ከፈቀደቻቸው በርካታ ዓይነት የምርቶች ዝርዝር ውስጥ አሁን ለመላክ የምትችላቸውን በቀዳሚነት የምታቀርብ መሆኑም ተገልጿል። ነገር ግን በሂደት ለኢትዮጵያ ከተፈቀዱት ምርቶች ውስጥ በስፋት አምርታ ለገበያ ማቅረብ ከቻለች የተሻለ የውጭ ምንዛሪ ለማስገባት ዕድል እንዳላት ዳይሬክተሯ አመልክተዋል። “በዚህም ወደ ውጭ ምርቶችን በላክን ቁጥር እኛም ከቻይና ምርት የማስገባታችን ዕድል ሰፊ ይሆናል” ሲሉ በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚያመጣውን አዎንታዊ ተጽዕኖ ተናግረዋል። ይህ ፈቃድ ከተሰጠበት ዕለት አንስቶ በቀረጥ ነጻ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ምርቶችን መላክ እንደሚቻልም አያይዘው ገልጸዋል። ቻይና ይህንን ነጻ የንግድ ዕድል እንዲጠቀሙ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአስር አገራት ነው በአሁኑ ጊዜ ፈቃድ የሰጠችው። ቀደም ሲል ለረዥም ጊዜ የቆየ ተመሳሳይ ዕድልን አሜሪካ አጎዋ በሚል ስያሜ ኢትዮጵያም ለተካተተችባቸው በማደግ ላይ ላሉ አገራት ሰጥታ ምርቶችን ከቀረጥና ከታሪፍ ነጻ እያስገቡ ይገኛሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ በትግራይ ውስጥ ሲካሄድ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ ከዚህ የነጻ ንግድ ዕድል ካለፈው ዓመት ጥር ጀምሮ መታገዷ ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cpvnp01eyx9o +politics የሶማሊያ ፕሬዚዳንት አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር ሾሙ የሶሚሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር ሾሙ። የፕሬዝዳንቱ ፓርቲ አባል እና የህዝብ እንደራሴ የሆኑት ሐምዛ አብዲ ባሬ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ሹመት ተሰጥቷቸዋል። ፕሬዝዳንቱ ምርጫውን ለማከናወን ጊዜ ወስደው መወሰናቸውን ገልጸው ባሬም ጥሩ ዕጩ ሆነው ማግኘታቸውን ገልጸዋል። ሹመቱን ተከትሎ አስተያየታቸውን የሰጡት አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር የሶማሊያን አንድነት በማስጠበቅ ሃገሪቱን የማዳን ተግባር ላይ እንደሚያተኩሩ አስረድተዋል። ሐምዛ አብዲ ባሬ በሶማሊያ መንግሥት ውስጥ የተለያዩ የስልጣን እርከኖች ላይ ሠርተዋል። እአአ ከ2019 እስከ 20220 ድረስ የጁባላንድ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ባገለገሉበትም ወቅት ነው ስማቸው የገነነው። እአአ ከ2014 እስከ 2015 የቤናዲር ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የሞቃዲሾ ከንቲባ ለሆኑት ሐሰን መሐመድ ሁሴን አማካሪ ሆነው አገልግለዋል። የሕገ መንግሥት ጉዳዮችና የፌደራሊዝም ጉዳዮች ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ሆነውም አገልግለዋል። ከሠላሳ ቀናት በፊት ሶማሊያ ሐሰን ሼክ መሀመድን የሶማሊያ 11ኛው ፕሬዝዳንት አድርጋ መርጣለች።  ለረዥም ጊዜ ዘግይቶ የተካሄደው ምርጫ በቀድሞው ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ እና በጠቅላይ ሚኒስትራቸው መሀመድ ሁሴን ሮብሌ መካከል አለመግባባት ፈጥሮ መቆየቱ ይታወሳል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመታቸው በፓርላማው ከጸደቀ በ���ላ መንግሥት ይመሰርታሉ ተብሎ ይጠበቃል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c87j5lnjjmno +business ለቀናት ባሕር ላይ ቆመው የነበሩ መርከቦች በሱዊዝ ቦይ ማቋረጥ ጀመሩ የዓለማችን ዋነኛው የንግድ መርከቦች መተላለፊያ የሆነው የሱዊዝ ቦይን ዘግታው የነበረችው ግዙፍ መርከብ እንድትነሳ ከተደረገ ከአንድ ቀን በኋላ ለቀናት ቆመው የነበሩ መርከቦች ጉዟቸውን ጀመሩ። በአሁኑ መተላለፊያው በተዘጋበት ጊዜ ወደ ማቋረጫው ገብተው ባሉበት ቆመው የነበሩ 37 የጭነት መርከቦች ቅድሚያውን አግኝተው እንዲያልፉ የተደረገ ሲሆን፤ ሌሎች 70 መርከቦች ደግሞ ዛሬ ማክሰኞ በሱዊዝ ቦይ በኩል ያልፋሉ ተብሏል። የመተላለፊያው ባለስልጣናት የባሕር መስመሩ በተዘጋባቸው ባለፉት ቀናት ውስጥ ባሉበት ቆመው ለመጠበቅ ተገድደው የነበሩትን ከ300 በላይ መርከቦች አስተላልፎ ለመጨረስ ሦስት ቀን ተኩል ይፈልጋል ብለዋል። ከእነዚህ መርከቦች መካከል ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ከሞሮኮ ማዳበሪያና ከቱርክ ደግሞ የተለያዩ ሸቀጦችን የጫኑ ሁለት መርከቦች በሜዲትራኒያን ላይ ቆመው እንደቆዩ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለቢቢሲ መግለጹ ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በመተላላፊያው የሚያቋርጡ መርከቦች ለባሕር ጉዞ ብቁ መሆናቸው በባለሙያዎች ይመረመራሉ ተብሏል። 400 ሜትር ርዝመትና 200 ሺህ ቶን የምትመዝነው ኤቨር ጊቭን የተባለችው መርከብ ባለፈው ማክሰኞ ጠዋት በመተላለፊያው በኩል እያቋረጠች ሳለ አሸዋ በቀላቀለ ከባድ ንፋስ ሳቢያ መስመሯን ስታ ነበር አግድም የባሕር ማቋረጫውን የዘጋችው። መስመሩ ከተዘጋ ከሰባት ቀናት በኋላ በአሸዋ መቆፈሪያ ከባድ መሳሪያዎችና በጎታች ጀልባዎች እየተረዳች ግዙፏ መርከብ ተቀርቅራበት ከነበረው የባሕሩ ዳርቻ አሸዋ ውስጥ ሰኞ ዕለት ለማውጣት ተችሏል። የሱዊዝ መተላለፊያ ቦይ በግብጽ ግዛት ውስጥ 193 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤ የዓለማችን 12 በመቶ የንግድ ጭነት የሚያልፍበት መስመር ነው። የባሕር ላይ መስመሩ የሜዲትራንያንና የቀይ ባሕርን በማገናኘት ከእስያ ወደ አውሮፓ የሚደረግን ጉዞ አጭር አድርጎታል። በመተላለፊያው ላይ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች እንዳሉት እስከ ማክሰኞ ጠዋት ድረስ 306 መርከቦች ለማለፍ እየተጠባበቁ ናቸው። ከእነዚህም ውስጥ 163 በቦዩ ደቡባዊ የቀይ ባሕር ክፍል ላይ ሲገኙ ቀሪዎቹ 137ቱ ደግሞ በሰሜን በኩል ሜዲትራኒያን ባሕር ላይ ይገኛሉ ተብሏል። በሱዊዝ መተላለፊያ ቦይ በኩል ለማለፍ ተሰልፈው እየተጠባበቁ ያሉትን መርከቦች በማስተናገድ እንዲያልፉ ለማድረግ ረጅም ሠዓት የሚጠይቅ ሲሆን ሁሉም አልፈው እስኪያበቁ ድረስ ከሦስት ቀን በላይ እንደሚፈጅ ይጠበቃል። https://www.bbc.com/amharic/news-56569253 +health ለሁለት ዓመት ድንበሯን ዘግታ የቆየችው ኒው ዚላንድ በሯን ልትከፍት ነው "በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከሁለት ዓመታት በላይ ድንበሯን ዘግታ የቆየችው ኒው ዚላንድ በስተመጨረሻ በሮቿን ልትከፍት እንደሆነ ይፋ አድርጋለች። ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ አውስትራሊያዊያን ምንም ዓይነት በለይቶ ማቆያ መቆየት ሳያስፈልጋቸው በነፃነት መግባት ይችላሉ። ከ60 ሃገራት የሚመጡ ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች ደግሞ ከግንቦት ወር ጀምሮ መግባት እንዲችሉ ይፈቀድላቸዋል። ከእነዚህ ሃገራት መካከል ዩናይትድ ስቴትስ እና ዩናይት ኪንግደም ይገኙበታል። ሁሉም ወደ ኒው ዚላንድ የሚመጡ ተጓዦች ከኮቭድ ነፃ መሆናቸውን የሚያሳይ ወረቀት ማሳየት አለባቸው። ኒው ዚላንድ ድንበሯን ሙሉ በሙሉ ዝግ በፈረንጆቹ መጋቢት 2020 ነበር። ኒው ዚላንድ ለአውስትራሊያ ከሰጠችው ለአጭር ጊዜ የቆየ የጉዞ ፈቃድ ውጭ ድንበሯን ለማንም ሳትከፍት ቆይታለች። አሁን ላይ ወደ ሃገሪቱ መግባትና መውጣት የሚችሉት የኒው ዚላንድ ዜጎች ብቻ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደን እንዳሉት ኒው ዚላንድ ""ዓለምን ለመቀበል ዝግጁ ናት።"" ""አሁን በተሰጠን መመሪያ መሠረት ድንብራችንን ለመክፈት ሁሉም ነገር ምቹ ይመስላል። ቱሪስቶቻችንም ይመለሳሉ"" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ። ወደ ኒው ዚላንድ ለመግባት ቪዛ ቀድሞ ያላቸው ሰዎች ከግንቦት ወር ጀምሮ እንደልባቸው መንቀሳቀስ ይችላሉ። ኒው ዚላንድ ጠንካራ የሚባል የእንቅስቃሴ ገደብ በመጣሏ የኮቪድ-19 ስርጭትን በመቆጣጠር ስሟ በተደጋጋሚ ይነሳል። ከኒው ዚላንድ ነዋሪዎች 95 በመቶው ተከትበዋል። ወረርሽኙ ከጀመረ ወዲህ በኮቪድ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 115 ብቻ ነው። ያልተከተቡ ሰዎች ሥራ አያገኙም መባሉን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ዌሊንግተን ተቃውሞ ተቀስቅሶ እንደነበር አይዘነጋም። ምንም እንኳ ኒው ዚላንድ ድንበሯን ከፍታ፤ እጇን ዘርግታ እንግዶች ለመቀበል ብትዘጋጅም አሁንም ቢሆን በርከት ብሎ መሰባሰብም ሆነ ያለጭንብል መንቀሳቀስ ክልክል ነው።" https://www.bbc.com/amharic/60761357 +sports ''በኳታር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሙቀቱ ተቸግሯል'' የቡድኑ መሪ "በኳታር የሚገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሀገር ቤት ከነበረው ቀዝቃዛ የአየር ጸባይና ከፍተኛ ዝናብ አንጻር ወደ ኳታር ሲሄድ በሙቀት ምክንያት መቸገሩን የቡድኑ መሪ የሆኑት ዶክተር በዛብህ ወልዴ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ''ሙቀቱ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ገምተን ነበር፤ ነገር ግን የአየሩ ሁኔታ ከገመትነው በላይ ሆኖ እንኳን ለሩጫ ውድድር ቆሞ መራመድ አስቸጋሪ ሆኖ ነው ያገኘነው። በዚሁም ምክንያት የማራቶኑ ሃሳባችን አልተሳካም፤ የአስር ሺውም ቢሆን መጥፎ ባይባልም እንዳሰብነው አልሆነም።'' በማራቶን ውድድር ወቅት በሙቀቱ ምክንያት አቋርጠው የወጡት ሦስቱም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም የቡድን መሪው አክለዋል። ''ሯጮቹ በሰውነታቸው ውስጥ የውሃ ማነስ ነበር ያጋጠማቸው፤ ይሄን ያህል ለአደጋ የሚሰጣቸው ግን አይደለም።"" • በዶሃ የሴቶች ማራቶን ሦስት ኢትዮጵያውያን ሯጮች አቋርጠው ወጡ • ሁሌም አብሮን ያለው 'የመስቀል ወፍ' በኳታር ካለው ከፍተኛ ሙቀት አንጻር ቡድኑ ከፍተኛ ሙቀት ባለባቸው አካባቢዎች ሄዶ ልምምዱን እንዲሰራ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በብዙ ምክንያቶች ሳይሳካ መቅረቱንም የቡድን መሪው ጨምረው አስረድተዋል። ''እንደዚህ አይነት ነገር ለመተግባር ከባድ ነው። ወደታች በወረድን ቁጥር ከሙቀቱ ጋር አብረው የሚመጡ ብዙ ነገሮች አሉ"" ያሉት ዶ/ር በዛብህ ሙቀት ቦታ ልምምድ መስራት ለእንደዚህ አይነት ውድድሮች ጠቃሚ ቢሆንም ብዙ ጉዳቶችም እንዳሉት ጠቅሰዋል። አትሌቶች በምን አይነት ሁኔታ ልምምድ መስራት አለባቸው ለሚለው ጥያቄ አሰልጣኞች ወደፊት ብዙ መነጋገርና ሃሳብ ማቅረብ እንዳለባቸውም ዶክተር በዛብህ ወልዴ ጠቁመዋል። በካታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ከትራንስ ኢትዮጵያ ክለብ በተገኘቸው ለተሰንበት ጊደይ አማካይነት አግኝታለች። ለተሰንበት ጊደይ ውድድሩን 30 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ ከ23 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰአት በማጠናቀቅ የሁለተኛ ደረጃን ይዛ መጨረስ ችላለች። ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ኔዘርላንድስን ወክላ የተወዳደረችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሃሰን የወርቅ ሜዳሊያውን ወስዳለች። በውድድሩ ኬንያዊቷ አትሌት አግኔስ ትሪፖ ሦስተኛ ደረጃን ስትይዝ፤ በውድድሩ የተሳተፈችው ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ ስድስተኛ ደረጃ��� ይዛ አጠናቃለች። ከቢቢሲ ጋር አጭር ቆይታ ያደረገችው ለተሰንበት ''ውድድሩ በጣም አሪፍ ነበረ፤ አየሩም ቢሆን ከውጪ ነው የሚሞቀው እንጂ ስታዲየም ውስጥ ብዙም አላስቸገረኝም'' ብላለች። በመጨረሻዎቹ ዙሮች አንደኛ ከወጣችው ሲፈን ሃሰን ጋር የነበረው ፉክክር ምን እንደሚመስልና እንዴት ልታሸንፋት እንደቻለች ስትጠየቅ ለተሰንበት ይህንን ብላለች። ''በዚህ ውድድር ሜዳሊያ አግንቼ ስለማላውቅ አዲስ ሆኖብኝ ነበር፤ በቀጣይ ብዙ የማስተካክለው ነው። እስከመጨረሻው ድረስ ሄጄ ነበር ግን እሷ በአቅም ትንሽ በልጣኛለች'' ስትል በቁጭት ተናግራለች። ውድድሩ ሲጀመርም ኢትዮጵያዊያን በቡድን ተጋግዘው ለማሸነፍ ተመካክረው እንደነበር የገለጸችው ለተሰንበት ''በመጀመሪያዎቹ ዙሮች ሌሎች አትሌቶች መምራት ሲጀምሩ ደስ ብሎን እየጠበቅናቸው ነበር'' ብላለች። ''ወደ መጨረሻ ላይ ግን እንዳሰብነው ሳይሆን ተበታተንን''። ውድድሩ በተካሄደበት ግዙፉ ካሊፋ ስታዲየም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድንን ለመደገፍ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን ለአትሌቶቹ ሞቅ ያለ ድጋፍ በመስጠት ምሽቱን አድምቀውት እንደነበር የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል። የኢትዮጵያ ደጋፊዎች ጎላ ብሎ የሚሰማ ዝማሬ ሌሎች ታዳሚዎችንም ጭምር ስቦ ነበር። በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ያጌጡት ደጋፊዎች ግዙፋ የስታድየም ስክሪን ላይም ተደጋግመው ሲታዩ አምሽተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-49869494 +health ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተገለፀ "የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችና በተለያዩ መስኮች ላይ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ለኮሮናቫይረስ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል። ይህንን በተመለከተም ባለፈው ሐምሌ ወር ላይ የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለው በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 ከተያዙት ሰዎች መካከል 10 በመቶዎቹ የጤና ሠራተኞች ሲሆኑ በአፍሪካም ከ10 ሺህ በላይ የህክምና ባለሙያዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ወረርሽኙ መኖሩ ከታወቀ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘ ተነግሯል። ይህንን በተመለከተ ቢቢሲ በአገሪቱ ውስጥ አንዳንድ አካባቢዎች ያሉ የጤና ባለሙያዎች ስላሉበት ሁኔታ ለማወቅ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በሲዳማ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የዳሰሳ ቅኝት አድርጓል። በዚህም በሁሉም ክልሎች የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ለኮቪድ-19 ያላቸው ተጋላጭነት አሳሳቢ መሆኑን ተገንዝቧል። በተጨማሪም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ዘንድ እየተስፋፋ መሆኑን ያነጋገርናቸው ክልሎች የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የጤና ቢሮ ኃላፊዎቹ ለቢቢሲ እንዳሉት ባለሙያዎቹ በተለያየ ምክንያት ለቫይረሱ የተጋለጡ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ከጥንቃቄ ጉድለት፣ ለመከላከያነት የሚያገለግሉ የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት እጥረት መኖር እና በሌሎች ስፍራዎች በሚኖር የቫይረሱ ተጋላጭነት ምክንያት መያዛቸውን ተናግረዋል። በትግራይ ክልል እስካሁን ድረስ ከ30 በላይ በኮቪድ-19 የተያዙ የህክምና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች መኖራቸውን የክልሉ የኮሮናቫይረስ ሎጀስቲክስ አስተባባሪ አቶ ጣዕመ አረዶ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ባለሙያዎቹ ከሥራ ቦታ ውጪ በነበራቸው ተጋላጭነት፣ ከቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር በነበራቸው ንክኪ፣ በጤና ተቋማት ውስጥ የኮሮናቫይረስ መከላከያ በቂ አቅርቦት ባለመኖሩ ምክንያት መያዛቸውን ጨምረው ተናግረዋል። በማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል ለይቶ ��ቆያ የሚሰሩት ዶ/ር ሳምሶን ነጋሲ የቫይረሱ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ""በአላማጣ በላብራቶሪ ቴክኒሺያንነት የሚሰሩ ሰባት ባለሙያዎች በቫይረሱ ተይዘዋል"" ያሉት ዶ/ር ሳምሶን፣ በአይደር ሆስፒታል ሦስት ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ በርካታ የህክምና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል ሲሉ ይናገራሉ። በዚህም የተነሳ ሆስፒታሉ ከድንገተኛ፣ ማዋለጃ እና አንዳንድ ህክምናዎች ውጪ ሌላው ክፍል ህክምና እየሰጠ አለመሆኑን ገልፀዋል። ዶ/ር ሳምሶን በህክምና ማዕከላቱ የሕክምና እቃዎች አቅርቦት ችግር መኖሩንም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ለክልሉም ሆነ ለፌደራል አካላት ያለባቸውን ችግር ቢያቀርቡም እስካሁን መፍትሄ አለማግኘታቸውን ጨምረው አስረድተዋል። በአማራ ክልል በአሁኑ ሰዓት በስፋት በኮሮናቫይረስ ከተያዙት የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል የህክምና ባለሙያዎች እንደሚገኙበት የገለፁት ደግሞ የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኅብረተሰብ ጤና ኢመርጀንሲ ማኔጅመንት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ አሌ አያል ናቸው። ጨምረውም ለወረርሽኙ ተጋላጭ ናቸው የሚባሉት የህክምና ባለሙያዎች በክልሉ በተለየ ሁኔታ ተጠቅተዋል ባይባልም፤ አሁን ግን ቁጥሩ እየጨመረ በመምጣት 23 ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መረጋገጡን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ አስተዳደር 21 የሕክምና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የከተማዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለቢቢሲ ማረጋገጡ ይታወሳል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ስንታየሁ ደበሳ እንደተናገሩት በሕክምና ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው እተደረገ ያለውን ወረርሽኙን የመከላከል ሥራን ያዳክመዋል የሚል ስጋት አለ ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። ""የጤና ባለሙያዎቻችን በቫይረሱ እየተያዙ መምጣት ወረርሽኙን ለመከላከል የምናደርገውን ጥረት ያዳክማል"" ሲሉም በአስተዳደሩ በኩል ያለውን ስጋት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። በሽታውን ለመከላከል አስፈጊ የሆኑ አቅርቦቶችን አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ ማቅቡንና ገልጸው ""እስካሁን ድረስ እጥረት የለብንም"" ብለዋል። ነገር ግን በሕክምና ተቋማቱ የሚኖሩ ንክኪዎች ባለሙያዎቹን ለቫይረሱ ማጋለጡን የሚናገሩት አስተባባሪዋ፤ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገ ውይይት ለቫይረሱ የተጋለጡት በየትኛው ጊዜ እንደሆነ ለማለየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። በህክምና ተቋማቱ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ግን ይላሉ ባለሙያዋ ""በሕክምና ሥራ ላይ እያሉ ተጋላጭ መሆናቸውን ነው"" በማለት ባለሙያዎቹ እየወሰዱ ያሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግም ለቢቢሲ ተናግረዋል። በኦሮሚያ ክልል በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን በሁሉም የክልሉ ዞኖችና ከተሞች ቫይረሱ መከሰቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል። በክልሉ እስካሁን ድረስ 1827 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል 34 የሚሆኑት የጤና ባለሙያዎች መሆናቸውን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረጃ አብደና ለቢቢሲ ገልጸዋል። የጤና ባለሙያዎች በብዛት የተገኙት መደበኛ ህክምና በሚሰጡ ሆስፒታሎችና ጤና ጣብያዎች ውስጥ መሆናቸውን አቶ ደረጀ ጨ���ረው ተናግረዋል። የሲዳማ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ማቴ መንገሻ በበኩላቸውእስከ ዛሬ ድረስ በሲዳማ ክልል 13 የሕክምና ባለሙያዎች እና ሁለት ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተናግረዋል። በኮቪድ-19 ከተያዙት የህክምና ባለሙያዎች መካከል ወደተለያየ ስፍራ ሄደው ራሳቸውን ለቫይረሱ ያጋለጡ፣ በሚሰሩባቸው ተቋማት አካባቢ ባለ የጥንቃቄ ጉድለት እንዲሁም የህክምና ቁሳቁስ እጥረት በመኖሩ የተነሳ የተጋለጡ እንደሚገኙበት አብራርተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53742959 +business በምዕራብ ኦሮሚያ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መስተጓጎሉን ነዋሪዎች ገለፁ "በምዕራብ ኦሮሚያ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ምክንያት የትራንፖርት እንቅስቃሴ መስተጓጎሉን ነዋሪዎች እና የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ለቢቢሲ ገለፁ። በቄለም ወለጋ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ምክንያት ዋና መንገዶች በመዘጋታቸው ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ሲናገሩ የአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት ደግሞ ችግሩ የተፈጠረው በስጋት ምክንያት ነው ብለዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ከዚህ በፊት አጋጥሞ በማያውቅ ሁኔታ ከግምቢ ነጆ፣ ከግምቢ ደምቢ ዶሎ፣ ከጊዳሚ አሶሳ የሚወስዱ መንገዶች መዘጋታቸውን ተናግረዋል። መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጀው የሸኔ ጦር አዛዥ ኩምሳ ድሪባ ሰሞኑን ለቢቢሲ እንደተናገረው በምዕራብ ኦሮሚያ በርካታ የገጠር አካባቢ እና ትንንሽ ከተሞችን በእጃቸው ማስገባታቸውን ተናግሯል። የምዕራብ ወለጋ እና የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው የተዘጋ መንገድም ሆነ በአማጺያኑ ቁጥጥር ስር የገባ ስፍራ የለም ሲሉ አስተባብለዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሁለቱ ዞኖች አስተዳዳሪዎች የትራንስፖርት መስተጓጎል የተፈጠረው ታጣቂዎች በኃይል ከሾፌሮች ላይ ቁልፍ እየተቀበሉ ተሽከርካሪዎችን እየወሰዱ ስለሆነ ነው ይላሉ። የምዕራብ ወለጋ አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ ባለፉት ቀናት የሸኔ ታጣቂዎች ወደ ዋና መንገድ በመውጣት ከሾፌሮች ቁልፍ እየተቀበሉ መኪና ከቀሙ በኋላ ወደ ጫካ እየተመለሱ በመሆኑ በአንዳንድ አካባቢዎች የትራንስፖርት መስተጓጎሎች ተፈጠረ እንጂ መንገድ ሙሉ በሙሉ አልተዘጋም ብለዋል። ቢቢሲ በሁለቱ የወለጋ ዞኖች የሚኖሩ ነዋሪዎችን ያነጋገረ ሲሆን፣ መንገድ ከመዘጋቱ ጋር ተያይዞ በወለጋ ዩኒቨርስቲ በሚካሄደው የተማሪዎች ምርቃት ላይ ለመገኘት አለመቻላቸውን ተናግረዋል። አቶ ኤልያስ ኡመታ ""የተዘጋ መንገድ አናውቅም፤ በእኛ ትዕዛዝ የተዘጋ መንገድ የለም፤ አንዳንድ ቦታዎች የፀጥታ ችግር ስላለ ብቻ ይህንን መስመር ለማስያዝ የሚሰራ ሥራ ይኖራል እንጂ የተስተጓጎለ መንገድ የለም"" ብለዋል። አስተዳዳሪው አክለውም፣ ኦነግ ሸኔ የሚሏቸው ታጣቂዎች ኋላ ቀር መሳሪያዎችን እንዲሁም ባዶ እጃቸውን በመሆን ሹፌሮችን በማስፈራራት ቁልፍ እየተቀበሉ እነደነበር ገልጸዋል። በዚህ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው መኪኖች መኖር አለመኖራቸው ለጊዜው እንዳልተጣራ ተናግረዋል። በዚህ ሳምንት ውስጥ በቄለም እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሲካሄድ እንደነበር የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ይናገራሉ። የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ገመቹ ጉርሜሳ በበኩላቸው ዞኑን አቋርጦ በሚያልፈው መንገድ፤ ትራንስፖርት የተስተጓጎበትን ምክንያት ሲያስረዱ ""እነዚህ ታጣቂዎች ከሾፌሮች ቁልፍ እየተቀበሉ መኪኖችን እየወሰዱ ትራንስፖርት እንዲስተጓጎል ስላደረጉ እንጂ እንደ ከዚህ ቀደሙ መንገድ ተዘግቶ አይደለም"" ብለዋል። ከሁለት ቀናት በፊት በሃዋ ገላን ወረዳ በተለምዶ የሱ��� ተብሎ በሚጠራው ቦታ ታጣቂዎች ከሾፌሮች ቁልፍ በመንጠቅ ሦስት መኪኖችን እንደወሰዱ አቶ ገመቹ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በዞኑ አንዳንድ ወረዳዎችም በድንጋይና በእንጨት መንገድ ለመዝጋት ተሞክሯል የሚሉት አስተዳዳሪው፣ ይህ ሙከራም በፍጥነት እንደከሸፈ እና በዚህ መልኩም የተዘጋ መንገድ እንደተከፈተም ገልጸዋል። የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ""በአሁኑ ወቅት የእነዚህን ታጣቂዎች እንቅስቃሴ ለማስቆም መፈተሽ ያለበት ስፍራ ተፍሾ፣ መታየት ያለበት ቦታ ታይቶ የኅብረተሰቡ እንቅሰቃሴ ወደ ቀድሞው ተመልሷል"" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንድ ቢቢሲ ያነጋገረው እና ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ነዋሪ በሳምንቱ መጨረሻ፣ ዘመድ ጥየቃ ከጊዳሚ ወደ ጊምቢ መምጣቱንና መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ወደ ቀየው ለመመለስ እንደተቸገረ ይናገራል። መንግሥት አሸባሪ በማለት የፈረጀውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር በማለት የሚጠራው አማጺ ቡድን ምዕራብ ወለጋ ዞን የሚገኙ አውራ መንገዶችን መቆጣጠሩን ማክሰኞ ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ አስፍሯል። የአማጺያኑ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ኦዳ ተርቢ ከግምቢ ነጆ፣ ከግምቢ ደምቢ ዶሎ፣ ከነቀምቴ ባሕር ዳር እና ከግዳሚ አሶሳ የሚወስዱ መንገዶች በቁጥጥራቸው ስር መግባቱን አስፍሮ ነበር። ከነቀምት ባሕር ዳር ከሚወስደው መንገድ በስተቀር ሌሎቹ በእነዚህ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መግባቱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በእነዚህ ሁለት ዞኖች ውስጥ የተለየ ጦርነት አለ? ሁለቱ የወለጋ ዞኖች ውስጥ እንደከዚህ ቀደሙ ከአማፂያኑ ጋር ግጭት መኖሩን የሁለቱ ዞኖች አስተዳዳሪዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መንግሥት አሸባሪ በማለት የፈረጀው ሸኔ፣ በቅርቡ ለገሰ ወጊ በሚል ስም የጥቃት ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን እና ትልልቅ መንገዶች፣ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ካምፖችን እና አንዳንድ አካባቢዎችን መያዙን እየገለጸ ይገኛል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር በማለት የሚጠራው አማጺ አዛዥ፣ ኩምሳ ድሪባ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ባለፉት ቀናት በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ መጠነ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ መክፈታቸውን ተናግሯል። ""የኦሮሞ ነጻነት ጦር አንድም ቀን ጦርነት አቋርጦ አያውቅም፤ የአሁኑን ለየት የሚያደርገው በራሳችን በሦስት አቅጣጫ ጦርነት ከፍተን ነው ያለነው።"" አክሎም በምዕራብ ኦሮሚያ ብዙ የገጠር አካባቢ እና ትንንሽ ከተሞች አማጺ ቡድኑ፣ ከዚህ ቀደምም በእጁ አስገብቶ እንዳለ ተናግሯል። በተጨማሪም ""በአገሪቱ ሰሜን አቅጣጫ ትልቅ ጦርነት ስላለ የእኛ እንቅስቃሴ ትኩረት አልተሰጠውም እንጂ ብዙ ቦታዎችን ተቆጣጥረን ነው ያለነው"" ሲል አክሏል። ይሁን እንጂ የቄለም እና የምዕራብ ወለጋ ዞኖች አስተዳዳሪዎች የሸኔ ታጣቂ ቡድኖች ቀበሌን እና ወረዳን ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም የላቸውም ሲሉ ይናገራሉ። ቦታዎችን በቁጥጥራችን ስር አውለናል የሚሉት ""ውሸት ነው"" ሲሉም አጣጥለውታል። አቶ ኤልያስ ጥቂት ኃይሎች የፀጥታ ችግርን ከመፍጠር ባለፈ፣ ቀበሌን እና ወረዳን ለመቆጣጠር የሚችል ኃይል በዞናችን ውስጥ የለም ሲሉ ይናገራሉ። የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ገመቹ፣ የእነዚህ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ አንዳንድ ወረዳ ውስጥ ይታያል ግን ከመንግሥት አቅም በላይ የሆነ እንቅስቃሴ የለም ሲሉ ያስረዳሉ። ""ጦርነት የሚካሄድበት እና ገፍተው የሚወጡበት ስፍራን በሙሉ ተቆጣጥረናል ይላሉ እንጂ የተቆጣጠሩት አንድም ቀበሌ እና ወረዳ የለም። አይቻልምም"" ይላሉ አቶ ገመቹ። በምዕራብ ኦሮሚያ እንደሚንሳቀስ የሚነገረው ታታቂ ቡድኑ በተለያዩ ወቅቶች በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ እና በአካባቢ ባለሥል���ናት ላይ ጥቃቶችን በመፈጸም ክስ ይቀርብበታል። በቅርቡ መንግሥት በሽብርተኛ ቡድንነት የፈረጃቸው ህወሓትና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን ከኢትዮጵያ መንግሥት አንጻር በወታደራዊ መስክ ለመተባበር መስማማታቸውን ይፋ አድርገዋል። ኦነግ-ሸኔ በሚል መንግሥት የሚጠራው ቡድንን ቀደም ሲል በምዕራብ ኃይል አዛዥ የነበረውና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአጠቃላዩ የኦሮሞ ነጻነት ጦር መሪ እንደሆነ የሚነገረው ኩምሳ ድሪባ ወይም መሮ ለቢቢሲ ""ሁለቱም ቡድኖች የጋራ ጠላት ስላለን በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ ለመደጋገፍ ከስምምነት ላይ ደርሰናል"" ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58206435 +business የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ በረራ መለሰ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሦስት ዓመታት ለሚተጋ ጊዜ ከበረራ አግዶት የነበረውን ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ወደ አገልግሎት መለሰ። አየር መንገዱ ዛሬ ጥር 23/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ አውሮፕላኑ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የቦይንግ እና የአየር መንገዱ ቦርድ አባላትን አሳፍሮ ወደ በረራ ተመልሷል ብሏል። አየር መንገዱ ባጋጠሙ አስከፊ አደጋ ምክንያት ከበረራ አግዷቸው የነበሩት አራት ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖቹን ወደ መደበኛ የመንገደኞች በረራ በያዝነው ሳምንት እንደሚመልስ አስታውቆ ነበር። ከአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉትን ዘመናዊ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች ከበረራ ውጪ ካደረገ ሁለት ዓመት አልፎታል። መጋቢት 01 ቀን 2011 ዓ.ም ጠዋት ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 149 ሰዎችን ይዞ ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ET302 መከስከሱን ተከትሎ ነበር አውሮፕላኖቹ በመላው ዓለም ከበረራ ውጪ የሆኑት። በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ከደረሰው አደጋው ቀደም ብሎ በኢንዶኔዢያው ላየን ኤየር አየር መንገድ ተመሳሳይ ቦይንግ አውሮፕላን ላይ አደጋ አጋጥሞ የ181 ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል። ከሁለቱ አደጋዎች በኋላ በመላው ዓለም የሚገኙ በርካታ አየር መንገዶች ቦይንግ 737 ማክስን 8 አውሮፕላኖችን ማብረር አቁመው ነበር። አየር መንገዱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የሚሰጠው ለደኅንነት ነው ብሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረማሪያም አየር መንገዱ አውሮፕላኑን ወደ አገልግሎት ለመመለስ ከውሳኔ ላይ የደረሰው በዓለም ዙሪያ ያሉ የበረራ ደኅንነት ተቆጣጠሪ አካላት አውሮፕላኑ አስተማማኝ መሆኑን አረጋግጠው አስፈላጊውን ፈቃድ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በዓለም ዙሪያ ያሉ ሌሎች 36 አየር መንገዶች አውሮፕላኑን ወደ በረራ መመለሳቸውን ተከትሎ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። አየር መንገዱ አውሮፕላኑን ወደ መደበኛ አገልግሎት ከመመለሱ በፊት 'የሙከራ' ናቸው የተባሉ በራራዎችን አካሂዷል። አየር መንገዱ አውሮፕላኑን ወደ አገልግሎት ከመመለሱ በፊት ያደረጋቸውን የሙከራ በረራዎችን ከፍላይት ራዳር24 እና ፍላይት አዌር ድረ-ገጾች በተገኘው መረጃ መሠረት አውሮፕላኑ በቅርቡ ጥር 17 እና ዛሬ ጥር 24/2014 ዓ.ም በረራዎችን አድርጓል። እንደ ፍላይት አዌር ድረ-ገጽ ከሆነ ማክሰኞ ጥር 17 ረፋድ 5፡20 ላይ ለበረራ የተነሳው የበረራ ቁጥር ET9301 ለ53 ደቂቃዎች አየር ላይ ቆይቶ እኩለ ቀን 6፡13 ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተመልሶ አርፏል። ፍላይት ራዳር24 ላይ እንደተመለከተው ደግሞ አየር መንገዱ ሌላ በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኑ ዛሬ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ሌላ የሙከራ በረራ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ እ�� በኢንዶኔዚያው አየር መንገድ ላይ አውሮፕላኖች ላይ በበረራ መቆጣጠሪያው እክል ገጥሞት ባስከተለው አደጋ ከበረራ ውጪ እንዲሆን የተደረገው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን እጅግ ዘመናዊ ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል አንዱ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አራት ቦይንግ 737 ማክስ 8 ያሉት ሲሆን ከአደጋው ቀደም ብሎ ተጨማሪ 25 ተመሳሳይ አውሮፕላኖችን ለመግዛት አዝዞ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ይረከባል ተብሎ ይጠበቃል። በአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ተከትሎ በርካታ አየር መንገዶች ለኪሳራ ሲዳረጉ አየር መንገዱ ግን ትርፋማነቱን ስለማስቀጠሉ ብዙ ተብሎለታል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአምስት አህጉራት በመቶዎች ወደሚቆጠሩ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን 130 አውሮፕላኖች አሉት። እነዚህም እጅግ ዘመናዊ የሚባሉትን 16 ኤይርባስ ኤ350-900 እና 19 ቦይንግ ቢ787-8 ይጨምራሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-60218470 +politics በአሜሪካ - አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ምን አይነት ጉዳዮች ይነሳሉ? የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የ49 አገራት መሪዎች የሚሳተፉበት ሁለተኛው የአሜሪካ- አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ታኅሣሥ 04/2015 ዓ.ም. ይጀመራል። ከማክሰኞ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ዓለማችንን እየፈተኗት ያሉ ተግዳሮቶች የአየር ንብረት ቀውስ፣ መልካም አስተዳደር፣ የምግብ ዋስትና እና የዓለም ጤናን የሚጨምር ሲሆን፣ እንዲሁም የአሜሪካ-አፍሪካ የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማጠናከር ላይ ያተኩራል። “ጉባዔው… አፍሪካ ቁልፍ የጂኦፖለቲካል ተጫዋች እንደሆነች ዕውቅና በመስጠት ላይ የተመሠረተ ነው። አህጉሪቱ የአፍሪካን ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የአለምን የወደፊት ሁኔታ ትቀርፃለች” ሲሉ የአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ሰኞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መናገራቸው ተዘግቧል። በጉባኤው አርባ ዘጠኝ የአፍሪካ መሪዎች እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት ተጋብዘዋል ሲሉ ሱሊቫን በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። በዚህ ሳምንት በሚካሄደው የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ፕሬዝዳንት ባይደን በቡድን 20 ውስጥ የአፍሪካ ኅብረት ቋሚ ቦታ እንዲያገኝ ድጋፍ እንደሚሰጡ ይጠበቃል ተብሏል። በተጫማሪም የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ከአፍሪካ አገራት መካከል “ቋሚ አባል እንዲያካትት” ድጋፍ መስጠትን ጨምሮ ማሻሻያ እንዲያደርግ ፕሬዝዳንት ባይደን ቁርጠኛ ናቸው በማለት ሱሊቫን ተናግረዋል። የመሪዎቹ የመክፈቻ ጉባኤ የአፍሪካውያን እና የዲያስፖራ ወጣት መሪዎች ላይ የሚያጠነጥን ይሆናል። “ድምጾችን ማጉላት፡ ዘላቂ የሆነ ሽርክና መፍጠር” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ፣ ከአህጉሪቱ ጋር የጠበቀ ትስስር ያላቸው አፍሪካውያን እና ዲያስፖራዎች ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያጠናክር እንደሆነም ተገልጿል። የአሜሪካ-አፍሪካ ስትራቴጂያቸውን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ፕሬዝዳንት ባይደን እንዳስታወቁት “የአፍሪካ ዲያስፖራች የጥንካሬያችን ምንጭ ናቸው” ብለዋል። አህጉሪቷን በመገንባት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱትን በባርነት ከአህጉሪቷ ተግዛው አሜሪካ የደረሱ አፍሪካውያን የልጅ ልጆች፣ ከአፍሪካ ጋር የጠበቀ ቤተሰባዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ያላቸው ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ አፍሪካውያን ስደተኞችን ያጠቃልላል። የአፍሪካ እና የዲያስፖራ ወጣት መሪዎች ጉባኤ፣ በፈጠራ ኢንዱስትሪዎች እና በአካባቢ ፍትሃዊነት ላይ ያተኮረ እንደሆነም ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው ማስረጃ ያስረዳል። ���ሜሪካ ለአፍሪካውያን አገራት ከቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት ዕድል (አጎዋ) ጋር በተያያዘ ከተጠቃሚ አገራቱ ንግድ ሚኒስትሮች ጋር የሚካሄደው ጉባኤም በዛሬው ዕለት ቀጠሮ ተይዞለታል። ። የአሜሪካ የንግድ ፖሊሲ ከፍተኛ ባለሥልጣን በሆኑት በአምባሳደር ካትሪን ታይ የሚመራው ይህ ጉባኤ፣ የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት፣ የአሜሪካ መንግሥት እና የአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ሴክሬታሪያት፣ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና ክልላዊ የኢኮኖሚ ማኅበረሰቦችን የሚያሳትፍ ነው። በዚህ ጉባኤም በዋነኝነት የኢኮኖሚ ትብብርን ማጠናከር፣ የሁለትዮሽ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት፣ ቀጣናዊ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን መደገፍ እና የአሜሪካ-አፍሪካ ንግድን በሚመለከቱ ሌሎች የጋራ ተጠቃሚነት ጉዳዮች እና አጎዋ ትግበራ ላይ ይወያያል። አሜሪካ ከትግራዩ ጦርነት ጋር በተያያዘ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተፈፅመዋል በሚል አጎዋ ከተሰኘው የቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት ኢትዮጵያ መታገዷ ይታወሳል። ከኢትዮጵያ በተጨማሪም ከሰብዓዊ መብት እና ከዲሞክራሲ ስጋቶች ጋር በተያያዘም ማሊ እና ጊኒም እንዲወገዱ ተደርገዋል። በወቅቱም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለአሜሪካ ኮንግረስ በጻፉት ደብዳቤ ኢትዮጵያ “በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈፅማለች” ማለታቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያን ከቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት እድል፣ አግዋ ማስወጣትም ከ200 ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ቤተሰቦች ላይ ተፅእኖ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚነስቴር የገለጸ ሲሆን፣ በተለይም ከግጭቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሴቶች ላይ ጉዳቱ ይበረታል ብሎ ነበር። ከሰሞኑም ኢትዮጵያ ከቀረጥ ነጻ ንግድ አጎዋ እንድትመለስ በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት የተፈጸሙ ጥሰቶችን ለሚያጣረው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የሰብዓዊ ባለሙያዎች ቡድን ፍቃድ ስትሰጥ መሆኑ ተዘግቧል። ሪፖርተር እንግሊዝኛው ጋዜጣ እንደዘገበው የባለሙያዎቹ ቡድን ወደ አገር ውስጥ ገብተው መመርመር እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ባለሥልጣን መናገራቸውን ነው። ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባወጣው የ19 ገጽ ሪፖርት የጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መፈጸማቸውን አካቶ ጦርነቱ ወደተካሄደባቸው የትግራይ ክልል አካባባቢዎች እንዲሄዱ አለመፈቀዱን መግለጹ ይታወሳል። በተጨማሪም የሲቪል ማኅበረሰቦች፣ የአፍሪካ ጠፈር፣ የሰላም፣ የፀጥታ እና አስተዳደር፣ የጤና ትብብር ጉባኤዎች በዛሬው ዕለት ይካሄዳሉ። ታኅሣሥ 05/2015 ዓ.ም. የሚካሄዱት ጉባኤዎች  በአሜሪካ- አፍሪካ ቢዝነስ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ይሆናል። በዚህም ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ባይደን ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የአሜሪካ- የአፍሪካ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት የወደፊት ዕጣፈንታ፣ ለአፍሪካ መሠረተ ልማት እና የኃይል ሽግግርን ለመገንባት ሽርክናን መፍጠር፣ የምግብ ዋስትናን የማጠናከር አጋርነት፣ የዲጂታል ግንኙነትን ማሳደግ እና በቴክኖሎጂ ሁሉን አቀፍ ዕድገት የማስቻል ትብብር የሚሉ ውይይቶችንም ያካተተ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ-ገጹ አውጥቷል። በማጠቃለው ሐሙስ ታኅሣሥ 06/2015 ዓ.ም. የመሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል። በዚህም  “መልካም አስተዳደር፣ ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባት፣ ፍትህ እና የሕግ የበላይነት የሰፈነባት አፍሪካ”፤ “ሰላምና አስተማማኝ የሰፈነባት አፍሪካ”፤ “በአካታች ዕድገት እና ዘላቂ ልማት ላይ በመመስረት የበለጸገች አፍሪካ” በሚልም በሦስት ክፍሎች ይካሄዳል። ጉባኤው አሜሪካ እንደ ዋና ዓለም አቀፍ ተፎካካሪዋ የምትመለከታት ቻይና በአፍሪካ ያላት ኢንቨስትመንቶች ከፍተኛ ብልጫ ባለበት ወቅት ነው። ከቻይና በተጨማሪ ሩሲያ በዩክሬን እያደረገችው ያለውን ጦርነት አህጉሪቷ ድጋፍ እንድትሰጣት እየጣረች ትገኛለች። በባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር የባይደን አስተዳደር ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራትን በተመለከተ አዲስ የስትራቴጂ ሰነድ አውጥቷል። ይህም ሰነድ የአህጉሪቷን ጠቃሚነት በማጉላት የአሜሪካን እሳቤ ከሚጋሩ አገራትም ጋር የመከላከያ ትብብርንም አስፈላጊነት ጠቅሷል። ፕሬዝዳንት ባይደን አገራቸው የተባበሩት መንግሥታትን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ጨምሮ ከሌሎች አገራት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመገንባት እየጣሩ ይገኛሉ። በተለይም ከእሳቸው በፊት የነበሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ ፖሊሲያቸው “ቀዳሚዋ አሜሪካ” በማለት ላይ የተመሠረተ እና የአፍሪካ አገራትንም በመዝለፍና በማንቋሸሽ ለአራት አመታት መስራታቸውንም ተከትሎ ፕሬዚዳንት ባይደን ይህንን ለማስተካከል ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። የመጀመሪያው የአሜሪካ አፍሪካ ጉባኤ የተካሄደው በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የሥልጣን ዘመን ከስምንት ዓመታት በፊት ሲሆን ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ አሜሪካ በአፍሪካ ውስጥ ያላት ሚና ማሽቆልቆሉም ተነግሯል። የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣናት በአፍሪካ ካሉ አገራት ጋር አሜሪካ ያላትን ግንኙነት ማጠናከርም እንደሚያስፈልግ ሲያሳስቡም ይሰማል። “ከኮንግረሱ (ምክር ቤቱ) ጋር በቅርበት በመሥራት አሜሪካ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ 55 ቢሊዮን ዶላር ለአፍሪካ ትሰጣለች” ሲል ሱሊቫን ሰኞ ዕለት ተናግረዋል።። https://www.bbc.com/amharic/articles/cn3zk02kp0vo +business የቻይናዋ ቤይጂንግ አሽከርካሪ አልባ የታክሲ አገልግሎት መስጠት ጀመረች የቻይናዋ ቤይጂንግ ከተማ ባለሥልጣናት ለመጀመሪያ ጊዜ አሽከርካሪ አልባ የታክሲ አገልግሎት እንዲሰጥ ፈቃድ ሰጥተዋል። ይህም በርካታ የሮቦት ታክሲዎች በቤይጂንግ ጎዳናዎች ላይ እንዲታዩ አድርጓል። ለጊዜው አሸከርካሪ አልባ ታክሲዎቹ በመዲናዋ ደቡባዊ ክፍል በ60 ኪሎ ሜትር ውስጥ ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ተወስኗል። በሂደት ብዙ ቦታዎች ተደራሽ ይሆናሉ ተብሎ ይታሰባል። https://www.bbc.com/amharic/news-59682113 +sports የቶኪዮ 2020 የፓራሊምፒክ ሜዳሊያ ዝርዝር በጃፓን ቶኪዮ የተካሄደው የኦሊምፒክ ውድድርን ማብቃት ተከትሎ ማክሰኞ ነሐሴ 18/2013 ዓ.ም ሌላኛው ውድድር ፓራሊምፒክ መካሄድ ጀምሯል። የአሁኑ የፓራሊምፒክ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ተመሳሳይ ውድድሮች በበለጠ 4,400 ስፖርተኞች በ22 የስፖርት አይነቶች አማካይነት 540 ውድድሮች ይካሄዱበታል። ይህ የቢቢሲ አማርኛ ገጽም በፓራሊምፒክ ውድድር ላይ ስፖርተኞች የሚያገኟወቸውን የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያዎች ዝርዝር ወክለው ከተወዳደሩባቸው ብሔራዊ የፓራሊምፒክ ቡድን ጋር ያቀርባል። ይህ ገጽ በየ10 ደቂቃው የሚኖሩ በፓራሊምፒክ ውድድር የተገኙ የሜዳሊያ ለውጦችን እየተከታተለ ያቀርባል። https://www.bbc.com/amharic/news-58328997 +sports በፈረንሳይ ሊግ የውሃ ኮዳ ተጫዋች ላይ በመወርወሩ ጨዋታው ተቋረጠ "በፈረንሳይ ሊግ የውሃ ኮዳ ተጫዋች ላይ በመወርወሩ ኒስ እና ማርሴ ሲያደርጉት የነበረው ጨዋታ እንዲቋረጥ ሆነ። የማርሴ ተጫዋች ዲሚቲሪ ፓዬ በውሃ ኮዳ ተመትቶ ኮዳውን ወደ ደጋፊዎች መልሶ መወርወሩን ተከትሎ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባታቸው ጨዋታ እንዲቋረጥ ተደርጓል። የማርሴው ፓዬ የማዕዘን ምት ሊመታ ሲሰሰናዳ በባለሜዳዎቹ ኒስ ደጋፊዎች በውሃ ኮዳ ጀርባውን ተመቷል። ተጫዋቹ ኮዳውን መልሶ መወርወሩን ተከትሎ ወደ ሜዳ የገቡ ደጋፊዎችን ጠባቂዎች እና ተጫዋቾች ሊያስቆሟቸው አልቻሉም። ከረዥም ቆይታ በኋላ የኒስ ተጫዋቾች ጨዋታውን ለመጨረስ ወደ ሜዳ ቢገቡም የማርሴይ ተጫዋቾች ግን ፍቃደኛ አልሆኑም። በዚህ ምክንያት ጨዋታው ተቋርጧል። በካሴፐር ዶልበርግ የመጀመሪያ አጋማሽ ግብ ባለ ሜዳው ኒስ 1-0 እየመራ ነበር። አንዳንድ የማርሴይ ተጫዋቾች በተፈጠረው ግርግር ምክንያት ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል። የማርሴይ ፕሬዝዳንት ፓብሎ ሎኖሪያ ""የእኛ ተጫዋቾች ጥቃት ደርሶባቸዋል"" ብለዋል። ""በሜዳ ወረራው ወቅት ጥቃት ለደረሰባቸው ተጫዋቾቻችን እና ለሌሎቹም ደህንነት ዋስትና ስላልነበረ ጨዋታው እንዳይቀጥል ወስነናል"" ብለዋል። ትርምሱ ተጫዋቾች ከሜዳ ለመውጣት ሲሞክሩ ቀጥሏል። የማርሴይ አሰልጣኝ ጆርጅ ሳምፓሊ በሥራ ባልደረቦቻቸው ሲገላገሉ ታይተዋል። ጨዋታው እየተካሄደም የማርሴይ ተጫዋቾች በማዕዘን ምቱ መምቻ አካባቢ የውሃ ኮዳ ሲወረወርባቸው የነበረ ሲሆን አንዱ ፓዬን በመታቱ አማካዩ ወድቋል። ይህን ተከትሎ በተፈጠረው አለመግባባት የቡድን ባልደረቦቹ አልቫሮ ጎንዛሌዝ እና ማቲዮ ጉንዶዚ ደጋፊዎቹን ለመጋፈጥ ሲሮጡ የኒሱ ግብ ጠባቂ ዳንቴ ደግሞ ደጋፊዎቹን ለማረጋጋት ሲሞክር ታይቷል። ማርሴይ ከሁለት ሳምንት በፊት ሞንትፔሊየን 3-2 ባሸነፈችበት ጨዋታም ደጋፊዎች ወደ ሜዳው የውሃ ኮዳዎችን በተመሳሳይ ሲወረውሩ ታይተዋል። በስታዲየሙ ድምጽ ማጉያ ደጋፊዎች እንዲረጋጉ የጠየቁት የኒሱ ፕሬዝዳንት ዣን ፒዬር ሪቭሬ ለአንዳንድ ጥፋቶች ማርሴዮችን ተጠያቂ አድርገዋል። ""ጨዋታው በዚህ መልኩ መጠናቀቁ ያሳዝናል"" ብለዋል። ""ሁሉም የተከሰተውን አይቷል። የውሃ ኮዳዎች እንደተወረወሩ መካድ አንችልም። ግጭቱን ያቀጣጠለው የበቀል እርምጃ በወሰዱት ሁለት የማርሴይ ተጫዋቾች ምላሽ ነበር። ከዚያ በኋላ የማርሴይ የደህንነት ሠራተኞች ጣልቃ ገብተው ተጫዋቾቻችንን መምታታቸው በጣም የሚያሳዝን ነው።"" ሲሉ ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/58302235 +health ኮሮናቫይረስ፡ ቫይታሚን ዲ ከኮቪድ-19 ይከላከለን ይሆን? ተመራማሪዎች ቫይታሚን ዲ ሰውነታችን የበሽታ መከላከል ስርዓት ብርታትን በመስጠት ከኮቪድ-19 ጋር ለሚያደርገው ፍልሚያ እገዛ ያደርጋል ወይ? የሚለውን ለማረጋገጥ የሚያስችላቸውን ሙከራ ለማድረግ በጎ ፈቃደኞችን እየፈለጉ መሆኑ ተገልጿል። በጎ ፈቃደኞቹ ከጸሀይ ብርሀን የሚገኘው ቫይታሚን ዲ እጥረት ካለባቸው ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት በፖስታ ቤት በኩል የቫይታሚን ዲ እንክብሎች ወደቤታቸው ይላክላቸዋል። የዩናይትድ ኪንግደም ዜጎችና ነዋሪዎች ደግሞ የብርዱ ወቅት እየመጣ መሆኑን ተከትሎ የቫይታሚን ዲ እጥረት በሰውነታችሁ ውስጥ ሊፈጠር ስለሚችል እንክብሎቹን ብትወስዱ ጥሩ ነው ተብለዋል። የቫይታሚን ዲ እንክብሎቹ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ በሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ ለማድረግና ኢንፌክሽኖችን ለመቀነስም በእጅጉ ጠቃሚ ነው ተብሏል። የቫይታሚን ዲ እጥረት የሚታይባቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ እድሜያቸው የገፋና የአፍሪካ አልያም የእሲያ ዝርያ ያለባቸው ሰዎች ሲሆኑ እነዚህ ሰዎች ለኮቪድ-19 ተጋላጭ መሆናቸውም ሌላ አሳሳቢ ነገር ነው። በለንደን ኩዊን ሜሪ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እየተደረገ የሚገኘው ምርምር በባርትስ በጎ አድራጎት ድጋፍ ይደረግለታል። በምርምሩም የቫይታሚን ዲ እንክብሎች ለሰዎች ይታደላሉ። የምርምሩ መሪ የሆኑት ዴቪድ ጆሊፍ እንደሚሉት ''ሙከራው በዚህ ረገድ ጠንከር ያለ ምላሽ ይሰጠናል ብለን እናምናለን'' ብለዋል። አክለውም ''ቫይታሚን ዲ ኮቪድ-19ኝን የመከላከል አቅም ከፍ የሚያደርግ ከሆነ ትልቅ ዜና ይሆናል'' ብለዋል። ''የቫይታሚን ዲ እንክብሎች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ የሚገኙ ናቸው፤ በተጨማሪም የጎንዮሽ ጉዳታቸው ዝቅተኛና በቀላሉ መገኘት የሚችሉ ናቸው። ወረርሽኙን ለመዋጋት እየተሰራ ያለው ዓለማ አቀፍ ሰራ በደንብ ሊያግዝ ይችላል'' ምንም እንኳን የቫይታሚን ዲ እንክብሎችን መውሰድ ለጤና ጠቃሚ ቢሆንም ከህክምና ባለሙያዎች ምክር ውጪ መውሰድ ግን የጎንዮሽ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ባለሙያዎቹ ገልጸዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54569305 +politics ታጣቂዎች በሙገር ሲሚንቶ የሠራተኞች አውቶቡስ ላይ ተኩስ ከፍተው ሰዎች ተገደሉ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ ታጣቂዎች በሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የሠራተኞች ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ተኩስ ከፍተው በፈጸሙጥ ጥቃት ቢያንስ ሁለት ሰዎችን ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ። ቢቢሲ ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች እና ከአካባቢው ነዋሪዎች እንዳረጋገጠው ጥቃቱ የተፈጸመው ዛሬ ሰኞ መስከረም 23/2015 ዓ.ም. ንጋት 12 ሰዓት አካባቢ ነው። ነዋሪዎችና ሠራተኞች እንዳሉት ጥቃቱን የፈጸመው መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጀውና በአካባቢው እንደሚንቀሳቀስ የሚነገረው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ወይም ሸኔ ነው። በሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች ላይ ጥቃት የተፈጸመው የሠራተኞች ማመላለሻ አውቶቡስ የሲሚንቶ ግብዓት ወደሚወጣበት አካባቢ እየተጓዘ ሳለ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ነው። በዚህ ጥቃት ቢያንስ ሁለት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከ12 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል። በአውቶብሱ ምን ያክል ሰዎች ተሳፍረው እንደነበረ ግን ግልጽ አይደለም። ቢቢሲ ጥቃቱን በማስመልከት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኦሮሚያ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ከፍያለው ተፈራን ቢጠይቅም መረጃ እንደሌላቸው ሲገልጹ፤ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ እና የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ እና አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ መልሰን እንድንደውል ነግረውናል። በተጨማሪም ስለደረሰው ጉዳት ለመጠየቅ ተሽከርካሪው ላይ ጥቃት የተፈጸመበትን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን አስተያየት ለማካተት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። ቢቢሲ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች እንደተረዳው ከሆነ ሠራተኞቹ በአውቶቡሱ እየተጓዙ ሳለ አድፍጠው ይጠብቁ የነበሩት ታጣቂዎች የተሸካርካሪውን ጎማ ጨምሮ የተለያየ የመኪናውን አካል በጥይት መትተዋል። ተሳፋሪዎች እና ተሸከርካሪው በጥይት ይደብደቡ እንጂ የአውቶብሱ አሸከርካሪ መኪናውን ሳያቆም የፊት ጎማው በጥይት የተመታ መኪናውን እያሸከረከረ የሲሚንቶ ግብዓት ከሚወጣበት ቦታ ላይ ደርሷል። ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪ በርካታ ሰዎች ከወገባቸው በታች ያለ የሰውነት ክፍላቸው በጥይት ተመትቶ መቁሰላቸውን እማኞች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ቢቢሲ ከሲሚንቶ ፋብሪካው ሠራተኞች እንደተረዳው በአካባቢው ያሉ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ለምርታቸው ግብዓት የሚሆናቸውን ላይምስቶን የተሰኘ የድንጋይ አይነት ከፋብሪካው በጥቂት ኪሎ ሜትር ርቆ ከሚገኝ አካባቢ ይወስዳሉ። ለሲሚንቶ ምርት ግብዓት የሚወጣበት አካባቢ በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ጥበቃ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ ከታጣቂዎች ተኩስ ያመለጠው የሠራተኞች ማመላለሻ አውቶብስ ከጥቃቱ በኋላ የፀጥታ አስከባሪዎች እስካሉበት ቦታ ድረስ በቸርኬ ተጉዞ መድረሱን ቢቢሲ ከፋብሪካው ሠራተኛ እና ከነዋሪዎች ለማውቅ ችሏል። መንግሥት ሸኔ የሚለውና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን በስፋት ከሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ በርካታ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚገኙበት ምዕ���ብ ሸዋ አድአ በርጋ ወረዳ እና ዙሪያው ነው። በዚህ አካባቢ ታጣቂ ቡድኑ የፋብሪካ ሠራተኞች እና ነዋሪዎችን በማገት የማስለቀቂያ ገንዘብ መጠየቅ የተለመደ ይሁን እንጂ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ መክፈት የተለመደ አይደለም። ይሁን እንጂ በዚህ አካባቢ ሰላማዊ ሰዎች ከመንግሥት ወይም ከታጣቂዎች ጋር ተባብራችኋላ በሚል ምክንያት በታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በዚሁ አደአ በርጋ ወረዳ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት በታጣቂዎች ከተገደሉ በኋላ አርብ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም. የፖሊስ አባላቱ በወሰዱት እርምጃ በርካታ ንጹሃን ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ነዋሪዎች በዚህ ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥርን ከ21 እስከ 40 አድርሰውት ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ለመንግሥት የፀጥታ ኃይል አባላት ወደውም ሆነ ተገደው የትራንስፖርት አገልግሎት የሰጡ ሰላማዊ ሰዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸው ያውቃል። ከምዕራብ ሸዋ ባሻገር በሌሎች የወለጋ ዞኖች ባለፉት ወራት ውስጥ ተፈጽመው በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆኑ ጥቃቶችን ፈጽሟል ተብሎ ታጣቂው ቡድን ይከሰሳል። ቡድኑ ግን እነዚህ ጥቃቶች አልፈጸምኩል በማለት ሲያስተባብል ቆይቷል። ዛሬ ስለተፈጸመው ጥቃት ግን አስካሁን በቡድኑ በኩል የተባለ ነገር የለም። https://www.bbc.com/amharic/articles/ck5855y03gro +business ግብጽ ስዊዝ ቦይን ዘገቶ የነበረውን መርከብ ለመልቀቅ ተስማማች "ከመርከቡ ባለቤትና መድህን ሰጪ ጋር ከስምምነት ከደረሰች በኋላ ግብጽ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ የስዊዝ ቦይ እንቅስቃሴ ለመስተጓጎሉ ምክንያት የነበረችውን መርከብ ለመልቀቅ ፍቃዷ ሆኗል። ግብጽ ለድርድር በመያዣነት ያቆያቻትና 'ኤቨር ጊቭን' የሚል ስያሜ ያላት መርከቧ ነገ [ረብዕ] ወራትን ከቆየችበት ቦዩ ለቃ እንደምትወጣ ከሁለቱም ወገን ተሰምቷል። በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረሰው ስምምነት ጭብጥ ባይታወቅም ግብጽ ግን 550 ሚሊዮን ዶላር ካሳ መጠየቋ ታውቋል። 400 ሜትር የምትረዝመው 'ኤቨር ጊቭን' በከፍተኛ ንፍስ ከተመታች በኋላ ነበር አቅጣጫዋን ስታ በመቀርቀር ቦዩን የዘጋችው። እናም መርከቧን ከተቀረቀረችበት በማላቀቅ ቦዩን ወደ መደበኛ ስራው ለመመለስ ስድስት ቀናትን የፈጀ ሲሆን በሂደቱ አንድ ሰው ሞቷል። 193 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የሜዲትራንያንን ባህር ከቀይ ባህር ጋር የሚያገናኘው እና በእስያ እና በአውሮፓ መካከል አጭሩን የባህር ላይ መንገድ የሆነው ሲዊዝ ቦይ በተዘጋበት በመቶዎች የሚቆጠሩ መርከቦች ለመቆም በመገደዳቸው የዓለም ንግድ አስተጎጉሎት ነበር። የ'ኤቨር ጊቭን' ሶስተኛ ወገን መድህን ሰጪ የሆነውና 'ዩኬ ክለብ' የተባለው ኢንሹራንስ ባለቤት ሾይ ኪሰን ከሱዊዝ ቦይ ባለስልጣን ጋር በመነጋገር ጉዳዩን እልባት ለመስጠት ""መደበኛ መፍትሄ"" ላይ መደረሱን አስታውቋል ፡፡ መርከቡን ለመልቀቅ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም አንስተዋል። የቦዩ አስተዳደር ስምምነቱ ረብዕ ይደረጋል ያለ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን መርከቡ ሊወጣ እንደሚችል አስታውቋል። የትኛውም ወገን በ'ኤቨር ጊቭን' የተፈጠረውን መጉላላላትና ኪሳራ ለመተካት የሚቀርበውን የካሳ ክፍያ መጠን ይፋ ባያደርጉም የቦዩ አስተዳደር ሊቀመንበር ኦሳማ ራቢ የስምምነቱ አካል የሆነ ተጎታች ጀልባ ግብጽ እንደምታገኝ ተናግረዋል። የቦዩ አስተዳደር ቀደም ብሎ ከ900 ሚሊዮን ዶላር ባላይ ካሳ ጠይቆ እንደነበር ተሰምቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57731706 +politics የንግሥቲቷን ሞት ተከትሎ አንቲጓ ሪፓብሊክ ለመሆን ሕዝበ ውሳኔ ልታደርግ ነው የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት የነበረችው አንቲጓ እና ባርቡዳ የንግ���ት ዳግማዊት ኤልዛቤጥ ሞትን ተከትሎ ሪፓብሊክ ለመሆን ሕዝበ ውሳኔ ልታካሂድ ነው። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ጋስቶን ብራዎን ሕዝበ ውሳኔው ከሦስት ዓመታት በኋላ እንደሚከናወን ገልጸው፤ ሕዝበ ውሳኔ የማካሄድ እቅዱ “የጠላትን ድርጊት አይደለም” ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ አገራቸው ሪፓብሊክ ብትሆን “ነጻ እና ሉዓላዊ” መሆናችንን የምናገረጋግጥበት የመጨረሻው እርምጃ ይሆናል ብለዋል። ንግሥት ዳግማዊት ኤልዛቤጥ እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ የአንቲጓ እና ባርባዱ ርዕሰ ብሔር ነበሩ። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አንቲጓ ሕዝበ ውሳኔ እንደምታደርግ የተናገሩት ንጉስ ቻርልስ ሳልሳዊ  የካሪቢያኗ አገር አንቲጓ እና ባርባዱ ርዕሰ ብሔር መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ነው። ጋስቶን ብራዎን በቀጣይ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ካሸነፉ ሕዝበ ውሳኔውን እንደሚያስፈጽሙ ገልጸዋል። ንግስት ኤልዛቤጥ ከካረቢያኗ አገር በተጨማሪ አውስትራሊያ፣ ካናዳ እና ኒው ዚላንድን ጨምሮ የበርካታ የቀድሞ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ርዕሰ ብሔር ናቸው። የንግስቲቱ ሞት በአውስትራሊያ ሪፓብሊክ የመሆን እንቅስቃሴን ዳግም አጋግሎታል። በአሁኑ ወቅት ንጉስ ቻርልስ ሳልሳዊ ከዩናይትድ ኪንግደም በተጨማሪ የ14 አገራት ርዕሰ ብሔር ናቸው። እነዚህም አንቲጓ እና ባርባዱ፣ አውስትራሊያ፣ ባህማስ፣ ቤሊዝ፣ ካናዳ፣ ግሬናዳ፣ ጀማይካ፣ ኒው ዚላንድ፣ ፓፐዋ ኒው ጊኒ፣ ሴንት ኪትስ እና ኔቪስ፣ ሴንት ሉሺያ እና ዘ ግሬናዲኢስ፣ ሰለሞን ደሴቶች እና ቱቫሉ ናቸው። ከአንድ ዓመት በፊት ባርባዶስ ንግስት ኤልዛቤጥን ከርዕሰ ብሔርነት አንስታ ተመራጭ ፕሬዝዳንቷን ርዕሰ ብሔር በማድረግ ሪፓብሊክ መሆኗን አውጃ ነበር። ሌላኛዋ የካረቢያን አገር ጀማይካ ገዢ የሠራተኞች ፓርቲ ሕዝበ ውሳኔ አካሂዶ ሪፓብሊክ መሆኑን ለማወጅ ማቀዱን አስታውቋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cpr2v5rgq7ro +business ልዑል ሃሪና ሜጋን ከዚህ በኋላ የገቢ ምንጫቸው ምን ይሆናል? "ልዑል ሃሪ ንጉሣዊው ቤተሰቡ ለሱና ለባለቤቱ ይሰጡትን የነበረውን የገንዘብ ድጎማ ማቋረጣቸውን ይፋ አድርጓል። ይህ የሆነው ልዑሉና ባለቤቱ ሜጋን ከነባር የንጉሣዊያን ቤተሰብ አባልነት 'ራሳቸውን አግልለው' ወደ ካሊፎርኒያ በማቅናታቸው ነው። እና አሁን የገቢ ምንጫቸው ምን ይሆናል? ልዑል ሃሪና ሜጋን ከንጉሣዊው ቤሰተብ ገንዘብ የሚያገኙበት መንገድ ይኖር ይሆን? የሰሴክስ ዱክና ደችስ በመባል የሚታወቁት ሜጋንና ሃሪ ባለፈው ዓመት ጥር ነበር የንጉሣዊ ቤተሰብ አባልነት በቃን ብለው የወሰኑት። በወቅቱ ራሳቸውን በገንዘብ ለመቻል ቃል ገብተውም ነበር። ነገር ግን በጊዜው ጥንዶቹ በገቡት ስምምነት መሠረት ከሃሪ አባት የገንዘብ ድጎማ ይደረግላቸው እንደነበር ይነገራል። የሃሪ አባት የሆኑት ልዑል ቻርልስ የሒሳብ መዝገብ እንደሚያሳየው ሃሪና ሜጋንን ጨምሮ የካምብሪጅ ዱክና ደችስ ተብለው ለሚታወቁት ጥንዶች የሚሆን 5.6 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ ተደርጓል። ይህ ወጪ እስከ መጋቢት 2020 ያለውን ጊዜ የሚያሳይ ነው። ነገር ግን ልዑል ሃሪ ከዚህ ወቅት ጀምሮ የገንዘብ ድጎማ ተቋርጦብኛል ሲል ለጉምቱዋ አሜሪካዊት ቃለ-ምልልስ አድርራጊ ኦፕራ ዊንፍሬይ ነግሯታል። ቢሆንም ልዑሉ እያወራ ያለው ከአባቱ ኪስ ስለሚሰጠው ገንዘብ ይሁን አሊያም ከግብር ከፋዩ ማሕበረሰብ ወይም ከሁለቱ ግልፅ አይደለም። ከመጋቢት ጀምሮ ያለው የልዑል ቻርልስ ሒሳብ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልደተረገም። ቤተ-መንግሥቱም በዚህ ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። ሃሪና ሜጋን ሃብታም ናቸው? የሰሴክስ ዱክና ደችስ በመባል የሚታወቁት ሃሪን ሜጋን የማይናቅ ሃብት አላቸው። ልዑል ዊሊያምና ልዑል ሃሪ በድምሩ 13 ሚሊዮን ዩሮ ከእናታቸው ልዕልት ዳያና ወርሰዋል። ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ አሜሪካ እንደመጡ ለኦፕራ የነገራት ሃሪ ""እናቴ ትታልኝ የሄደችው ነገር ባይኖር ኖሮ ይሄን ማድረግ አንችልም ነበር"" ብሏል። የቢቢሲው የንጉሣዊያን ቤተሰብ ተንታኝ ኒክ ዊቼል ደግሞ ልዑል ሃሪ ከአያቱ [ንግሥት ኤሊዛቤት] ሚሊዮን ፓውንዶች ወርሷል ይላል። በሌላ በኩል ሜጋን ተዋናይት በነበረችበት ወቅት ሱትስ በተሰኘው ተከታታይ ድራማ ላይ ስትተውን በአንድ ክፍል 50 ሺህ ዶላር ይከፈላት እንደነበር ይነገራል። ሜጋን ከዚህ በተጨማሪ 'የላይፍስታይል' መጦመሪያ [ብሎግ] እና ለአንድ የካናዳ ልብስ አምራች የሚሸጥ የፋሽን ዲዛይን አላት። ሌላ የገቢ ምንጫቸው ምንድነው? አሁን ጥንዶቹ ከንጉሣዊው ቤተሰብ ጋር ያላቸው ውል ስለተቀደደ ያሻቸውን ነገር መሥራት ይችላሉ። ጥንዶቹ ከኦፕራ ጋር ያደረጉት ቆይታ በክፍያ አልነበረም። ነገር ግን ኔትፍሊክስና ስፖቲፋይ ከተሰኙት ድርጅቶች ጋር ውል ገብተዋል። እነዚህ ስምምነቶች በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደሚያስገቡላቸው ይታመናል። ሜጋንና ሃሪ አርችዌል የተሰኘ ተቋም አላቸው። ይህ ድርጅት ከአንድ ሌላ የእርዳታ ድርጅት ጋር ይሠራል። ጥንዶቹ ዩናይትድ ኪንግደም እያሉ ጥበቃ ይመድብላቸው ነበር። የጥበቃው ሒሳብ ምን ያክል እንደሆነ አይታወቅም። የካናዳ መንግሥት ለጥንዶቹ የሚያደርገውን ጥበቃ እንደሚያቆም ሲያሳውቅ ነው ሜጋንና ሃሪ ወደ አሜሪካ ያቀኑት። ይሄኔ አሜሪካዊው ቢሊየነር ታይለር ፔሪ እስኪደላደሉ ድረስ መኖሪያ ቤትና ጥበቃ እንዳበረከተላቸው ጥንዶቹ ተናግረዋል። ""ለኔ ዋናው ነገር የቤተሰቤን ደህንነት ለመጠበቅ በቂ የሆነ ገንዘብ ማግኘት ነበር"" ሲል ሃሪ ለኦፕራ ነግሯታል። ጥንዶቹ የንጉሣዊው ቤተሰብ ኃላፊነት ይብቃን ከማለታቸው በፊት 95 በመቶ የገቢያቸው ምንጭ የሃሪ አባት ልዑል ቻርልስ ነበሩ። ለምሳሌ በፈረንጆቹ 2018-19 ብቻ ለሜጋንና ሃሪ እንዲሁም ለካምብሪጅ ዱክና ደችስ ከ25 ሚሊዮን በላይ ዩሮ ፈሰስ ተደርጓል። ከግብር ከፋዩ የሚገኘው ገቢ ደግሞ 5 በመቶ የሚሆነው ወጪ ይሸንፋል። ጥንዶቹ ከቤተሰቡ በወጡ ጊዜ በታክስ ከፋዩ ገንዘብ አሳደሱት የተባለውን ቤት ወጪ 2.4 ሚሊዮን ዩሮ መመለሳቸው አይዘነጋም።" https://www.bbc.com/amharic/news-56356832 +business ''የአሰብና ምፅዋ ወደቦችን አገልግሎት ለማሻሻል እየሰራን ነው'' ፕሬዚዳንት ኢሳያስ "የምፅዋና የአሰብ ወደቦች የሚሰጡትን አገልግሎት የማሻሻል ስራዎች እየሰሩ እንደሆነ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትናንትናው ዕለት ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት ከኃገሪትዋ ውስጣዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በትናንትናው ዕለት ከመንግስት መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው። የነዚህን ወደቦችን አገልግሎት ውጤታማነት ለመጨመር የማደስ፣ የማስፋትና የማሳደግ ስራዎች ለማከናወን እቅድ መያዙን ፕሬዚዳንቱ አብራርተዋል። • ""የኤርትራ መሬት ያልተመለሰው በህወሓት እምቢታ ነው"" ፕ/ት ኢሳያስ • ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን ያህል ያውቃሉ? ""ወደቦቹን ስናሻሽል ኢትዮጵያን ብቻ እያሰብን አይደለም፤ ዋነኛ ትኩረታችን ቀይባሕር በቀጠናው ላይ ያላትን ቦታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሰፋ ያለ አገልግሎት እንዲሰጡ ያለመ እቅድ ነው"" ብለዋል ፕሬዚዳንቱ ""ከተጋገዝን የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ስለምንችል በአካባቢው ኢኮኖሚያዊ ውህደት መፍጠር"" አንዱ የመንግስታቸው ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከወደቦች በተጨማሪ ከመንገድ ግንባታ ጋር የተያዙ እቅዶችም ላይ መረጃ የሰጡ ሲሆን፤ በዚህም ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚያገናኙ መንገዶችም የሚያስፈልጋቸውን ጥገናም ሆነ ግንባታ ለመስራት መንግሥታቸው አቅዷል ብለዋል። በዚህም መሰረት ከአሰብ በደባየሲማ ኢትዮጵያን የሚያገናኘውን መንገድ የማስፋት፤ ከምጽዋ በደቀመኃሪ አድርጎ ዛላምበሳ፤ ከአስመራ በመንደፈራ፣ ራማን የሚያገናኙት የአስፋልት መንገዶች ደግሞ የማሻሻል ስራዎች በዚህ አመት እንደሚጀመሩና፤ የተጀመሩትም እንደሚጠናቀቁ ገልፀዋል። ፕሬዚዳንቱ በሃገሪቱ ውስጥ ያሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን፣ ኢንቨስትመንት፣ የኑሮ ውድነት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ከዚህም መካከል ለሁለት አስርት አመታት ሲንከባለል የመጣው የመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ ማስተካከያ ጥያቄ ላይ ምላሽ የሰጡት ፕሬዚዳንቱ ሰራተኞች አስፈላጊውን የኑሮ ወጪ የሚሸፍንላቸው በቂ ደመወዝ እንዳልነበራቸው አምነዋል። መንግሥታቸው ይህንን ችግር ለመፍታት ከሁለት አመታት በፊት የደመወዝ ማስተካከያ ማድረግ መጀመሩን ጠቁመው፤ በደመወዝ ማስተካከያው ሂደት እስከ አሁን ጭማሪው ያልደረሳቸው የመንግስት ሰራተኞች የሁለት ዓመት ድምር እንደሚደርሳቸው ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል። መንግሥት የደመወዝ ማስተካከያ አሰራሩንም ለመተግበር እክሎች እንደገጠሙት የገለፁት ፕሬዚዳንቱ ይህም በሃገሪትዋ ""ተገቢ ባልሆኑ ምክንያቶች"" የሸቀጦች ዋጋ ንረት በመፈጠሩ ነው ብለዋል። ""መንግሥት ይህ ኢ-ምክንያታዊ የሆነ የዋጋ ንረትን በቸልታ አያልፈውም ፤ እርምት ይወስዳል"" በማለት አስጠንቅቀዋል ያለውን የዋጋ ንረት ለማስተካከልም ባለፉት ዓመታት መንግሥት የቤት ኪራይ፣ ስጋ እና የታሸገ ውሀ ላይ የዋጋ ተመን ማድረግ እንደጀመረ ምንጮች ይገልጻሉ። የመኖርያ ቤቶች ግንባታ ዋነኛው የሀገሪትዋ ቁልፍ ችግር እንደሆነ ያወሱት ፕሬዚዳንቱ መንግሥት ይህንን ችግር ለመፍታት ብሎ የጀመራቸው የቤቶች ግንባታ ቢጀምርም፤ ያላለቁ ቤቶች ግን በርካታ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች • ኤርትራ በዶይቼ ቬለ ዘገባ ሳቢያ የጀርመን አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቀች በሂደትም መንግሥት ጥናት አካሂዶ አዋጪ ሆኖ ከተገኘ በቤቶች ግንባታ የውጪ ተቋራጮች ጭምር ለማሳተፍ ሀሳብ እንዳለ የገለጹት ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፤ ያላለቁ እቅዶች ስላሉ በዚህ አመት የሚሰሩ ስራዎችን ለማስቀመጥ ትንሽ ከባድ እንደሆነ በመጠቆም ዝርዝርም ሆነ ቀነ ገደብ ከማስቀመጥ ተቆጥበዋል። ፕሬዚዳንቱ አንዳንድ ሃገሪቷ ያሉባትን ችግሮች በግልፅ ከመናገር ወደኋላ ያላሉ ሲሆን በተለይም ባለፉት 20 ዓመታት ""አክስሮናል"" ያሉትን የትምህርት ዘርፍ ፖሊሲ ለሀገሪትዋ ኢኮኖሚ ዋነኛው ምሰሶ በመሆኑ ስር ነቀል ለውጥ ሊመጣ ይገባል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከቀይ ባህር በዓመት እስከ 100 ሺ ቶን የአሳ ሀብት ማግኘት እየታቸለ ባለፉት 20 ዓመታት ግን አስር ሺ ቶን ብቻ እንደነበረ ገልጸዋል። ይህንን የአሳ ሀብት ለማሳደግም አስፈላጊውን የመሰረተ ልማት ስራዎች ለማከናወን እቅድ መያዙን አብራርተዋል። ፕሬዚዳንቱ መንግሥታቸው በዚህ አመት ከያዟቸው ሌሎች እቅዶች መካከል በአሰብ፣ ምጽዋ እና አስመራ ከተሞች 60 ሜጋ ዋት ኤሌትሪክ ከታዳሽ ኃይል ለማመንጨት የተለያየ መጠን ያላቸው የውሀ ግድቦች የሚገነቡ ሲሆን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን ለማበረታት አስፈላጊ የመሰረተ ልማት ስራዎች እንደሚሰሩም አስረድተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-51440267 +politics የማሊው ወታደራዊ መሪ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር መነጋገራቸውን ገለጹ የማሊ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል አሲሚ ጎኢታ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ መነጋገራቸውን ገለጹ። በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የያዘ�� ጁንታ መሪ የሆኑት ኮሎኔሉ፤ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በስልክ የተነጋገሩት ትናንት ረቡዕ ነሐሴ 04/2014 ዓ.ም. መሆኑን አመልክተዋል። “ለማሊ ፖለቲካዊ ሽግግር የሩሲያ ፌዴሬሽን ድጋፍ ላይ ተነጋግረናል” ያሉት ኮሎኔል ጎኢታ፤ የማሊን ሉዓላዊነት ያከበረ እና የሕዝቡን ፍላጎት የሚረዳ የሁለቱ አገራት ወዳጅነት ጠንካራ መሆኑን ለፕሬዝዳንት ፑቲን መገለጻቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፈረዋል። ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ኮሎኔል አሲሚ ጎኢታ በተገኙበት ሥነ ሥርዓት ላይ ማሊ ከሩሲያ የተረከበቻቸውን በርካታ ተዋጊ አውሮፕላኖችን በዋና ከተማዋ ባማኮ አየር ማረፊያ ለዕይታ አቅርባ ነበር። ሞስኮ በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ከጨበጠው ከማሊ ጦር ሠራዊት ጋር ያላንትን የጠበቀ ወዳጅነት ለማሳየት በሶቪየት ሕብረት የተመረቱ የጦር አውሮፕላኖችን ለማሊ ሰጥታለች። ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኀወላ የማሊ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት ከምዕራባውያን አገራት በተለይ ደግሞ ከፈረንሳይ ጋር የነበረው ግንኙነት በእጅጉ ሻክሯል። ፈረንሳይ የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን ዋግነር በምዕራባ አፍሪካዊቷ አገር መገኘቱን ከተቃወመች በኋላ ከጊዜያዊው ወታደራዊ መንግሥት ጋር ያላት ግንኙነት ተበላሽቶ ወደታደሮቿን ከአገሪቱ አስወጥታለች። የፈረንሳይ እና ሌሎች የአውሮፓ አገራት ጥምር ጦር ወታደሮች በማሊ ተሰማርተው ጸንፈኛ እስላማዊ ቡድኖችን ሲወጋ ቆይቷል። ለምዕራባውያን ጀርባዋን ሰጥታ ፊቷን ወደ ሩሲያ ባዞረችው ማሊ፣ በጽንፈኛ ቡድኖች የሚፈጸሙ ጥቃቶች ተበራክተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት በእስማላዊ ታጣቂ ቡድን በተፈጸመ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 42 መድረሱ ተገልጿል። ባለፈው እሁድ ነሐሴ 01/2014 ዓ.ም. ከኢስላሚክ ስቴትስ (አይኤስ) ጋር ግንኙነት አለው የተባለ ቡድን በፈጸመው ጥቃት በርካታ ወታደሮች መገደላቸው እና መቁሰላቸው ተዘግቦ ነበር። ቡድኑ ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር በሚዋሰኑበት የማሊ ግዛት ውስጥ በፈጸመው ጥቃት የሟቾች ቁጥር 42 መድረሱን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ደግሞ መኖሪያቸውን ጥለው መሰደዳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ገልጸዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cnl1z2e1lk9o +sports የሳዑዲ አረቢያን ቡድን ለመደገፍ 1600 ኪሎ ሜትር በእግሩ የተጓዘው ደጋፊ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በውድድሩ ታሪክ በአረብ አገር አስተናጋጅነት ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በዚህም ትንሽየዋ ነገር ግን ባለፀጋዋ አገር ኳታር ቢሊዮኖችን አፍስሳ ውድድሩን እያካሄደች ነው። ይህ በኳታር የሚካሄደው የዓለም ዋንጫ በአረብ የእግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በልዩ ሁኔታ እየታየ ነው። ከመላው ዓለም ወደ አገሪቱ ካቀኑት በተጨማሪ በርካታ ሰዎች ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከባሕረ ሰላጤው አረብ አገራት ውድድሩን ለመታደም በተለያዩ መንገዶች ከስፍራው ደርሰዋል። ከእነዚህም መካከል አብዱላህ አል ሳልሚ ለዘመናት ሲያልመው የነበረውን ፍላጎቱን ለማሳካት በኳታር የሚስተናገደው የዓለም ዋንጫ ዕድሉን ፈጥሮለታል። አብዱላህ በመጀመሪያ ጨዋታው የእግር ኳስ ታላቅ አገር የሆነችውን አርጀንቲናን በማሸነፍ ዓለምን ያስደመመውን የአገሩን ቡድን  ለመደገፍ ከሳዑዲ አረቢያ ጅዳ እስከ ኳታር ዶሃ ያለውን 1600 ኪሎ ሜትር በእግሩ ተጉዟል። ጉዞው አስቸጋሪ ቢሆንም ኳታር ከደረሰ በኋላ ግን አብዱላህ ዝነኛ ሆኗል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cnd5438x5j9o +politics ጃዋር መሐመድ፡ በቢጫ ለባሾቹ ምክንያት የእነ ጃዋር ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት "ቢጫ ቀለም ልብስ በለበሱ ግለሰቦች ምክንያት የእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የዛሬ ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብርና ሕገመንግሥታዊ አንደኛ ችሎት ዛሬ ማለዳ የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሊቀበል ቀጠሮ ይዞ ነበር። ይህን ተከትሎ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ በዚህ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ተከሳሾች ፍርድ ቤትየቀረቡ ቢሆንም ችሎቱ ግን ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት አሰናብቷቸዋል። ይሀህ ሊሆን ቻለው የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል ቢጫ ልብስ ለብሰው በፍርድ ቤት የተገኙ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤቱ እንዳይገቡ በፖሊስ መከልከላቸውን ተከትሎ ተከሳሾች እና ጠበቆች ባሰሙት አቤቱታ ነው። ከተከሳሾች መካከል አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አዳነ ሰዎች ቢጫ ቀለም ያለው ልብስ በመልበሳቸው ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መደረጉ አግባብ አይደለም፤ ቢጫ ልብስ በመልበሳቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ አሉ ሲሉ ቅሬታቸውን ለፍርድ ቤት አቅርበዋል። ከሰሞኑ በማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ በርካቶች ቢጫ ልብስ የመልበስ ዘመቻ ሲያከናውኑ ቆይተዋል። ይህም ተከሳሾች በማረሚያ ቤት እና ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የሚለብሱትን ባለ ቢጫ ቀለም ቱታ ለመወከል ነው። ተከሳሾች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፤ ለተከሳሾች የሞራል ድጋፍ ለመስጠት ቢጫ ቀለም ያላቸውን ልብሶች በመልበስ በፍርድ ቤት እንደሚገኙ የዘመቻው አካል የሆኑት ይናገራሉ። ባለፉት ሁለት ቀጠሮዎች በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥራ የተከሰሱ ተከሳሾች ፍርድ ቤት በቀረቡብት ወቅት ቢጫ ቀለም ያለው ልብስ ለብሳ ከፍርድ ቤት የተገኘችው መሠረት ዳባ፤ ይህ ዘመቻችንን ለተከሳሾች የሞራል ብርታትን ለመስጠት ነው ትላለች። ""እነሱ ከሚለብሱት የልብስ ቀለም ጋር ተመሳሳይ ልብስ በመልበስ 'እኛም ከእናንተ ጋር ነን'፣ 'ከእናንተ ጋር ታስረናል' የሚል መልዕክት ማስተላለፍ ፈልገን ነው"" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። ባለ ቢጫ ቀለም ልብስ የመልበስ ዘመቻ አስተባባሪ የሆነው ወቢ ቡርቃሳ የጀመሩት ዘመቻ በርካቶችን በማሳተፍ ከታሰበው በላይ ብዙ ሰዎች ጋር መድረሱን ይናገራል። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ #oromoyellowmovement የሚል መሪ ቃል ሲጠቀሙ ቆይተዋል። በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ላይ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ የቤተሰብ አባላቶቻቸው እና ሌሎች ሰዎች በለበሱት የልብስ ቀለም ሳቢያ ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መደረጋቸውን እና ለእስር መዳረጋቸውን በመጥቀስ፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ ተደርጎ ባሉበት ሁኔታ ምንም ዓይነት አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል። አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐመዛ አዳነ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መከልከላቸው እንዳሳዘናቸው እና ቢጫ በመልበሳቸው የታሰሩት ይፈቱ ሲሉ ጠይቀዋል። የተከሳሾች ጠበቆችም ችሎቱ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ሳለ ሰዎች በለበሱት የልብስ ቀለም ሳቢያ ወደ ችሎት እንዳይገቡ መከልከላቸው አግባብ አይደለም በማለት የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱን ጠይዋል። ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠት የፍርድ ሂደቱን ያጓትታል ሲል ተከራክሯል። የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመስማት ለጥር 27፣ 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ሰዎች በለበሱት የልብስ ቀለም ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መደረጉ አግባብ አይደለም ያለ ሲሆን፤ ታዳሚዎች በሙሉ ግን ቢጫ ቀለም ያለው ልብስ ለብሰው በፍርድ ቤት የሚገኙ ከሆነ በችሎቱ ላይ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ከግምት ማስገባት አለበት ብሏል። በሰኔ ወር፣ 2012 ዓ.ም ከሙዚቀኛው ሃጫሉ ግድያ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉት አቶ ጃዋር መሐመድና በክስ መዝገባቸው ውስጥ የሚገኙ ሌሎች 24 ሰዎች ተደራራቢ አስር ክሶች እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል። በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ ��ቀረቡ ተደራራቢ አስር ክሶች ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ ቤት ጥር 14/2013 ዓ.ም ውሳኔ አስተላልፏል። አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ ዶ/ር ብርሃነ መስቀል አበበና ፀጋዬ ረጋሳ አገር ውስጥ የሌሉና በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ውስጥ ከተከሰሱት መካከል ናቸው። የድምጻዊ ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ ከነበረ ሁከት ጋር ተያይዞ ነበር እነ አቶ ጃዋር መሐመድ በቁጥጥር ሥር የዋሉት።" https://www.bbc.com/amharic/news-55825409 +sports 'ሴቶች ብዙ ያወራሉ' ያሉት የቶክዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ይቅርታ ጠየቁ "የቶክዮ ኦሊምፒክስ አዘጋጅ ኪሚቲ ኃላፊ የሆኑት ግለሰብ ሴቶችን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ምክንያት ሥልጣናቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። የ83 ዓመቱ ዮሺሮ ሞሪ 'ምንም ሳያሰላስሉ' ለሰጡት አስተያየት ይቅር በሉኝ ብለዋል ሲሉ የጃፓን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የኮሚቲው ኃላፊ 'ሴቶች በጣም ብዙ ያወራሉ፤ ሴት የቦርድ ኃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል' ሲሉ ተናግረዋል ተብለው ተወቅሰዋል። ሰውዬው ትላንት [ረቡዕ] በተካሄደው የጃፓን ኦሊምፒክ ኮሚቲ ስብሰባ ላይ ይህን ያሉት። የኦሊምፒክ ኮሚቲው በአሁኑ ወቅት 24 አባላት ያሉት ሲሆን አምስቱ ሴቶች ናቸው። የጃፖን ኦሊምፒክ ተሳታፊዎችን የመመረጥ ኃላፊነት ያለበት ይህ ኪሚቲ በፈረንጆቹ 2019 ሴት የቦርድ ኃላፊዎችን ድርሻ 40 በመቶ ለማድረስ ቃል ገብቶ ነበር። ""ሴት የቦርድ አባላትን ቁጥር ለመጨመር ካሰብን ለሚያደርጉት ንግግር የሚሰጣቸው ሰዓት የተወሰነ ሊሆን ይገባል። እነሱ እንደሆነ ቶሎ ተናግሮ የመጨረስ ችግር አለባቸው። በጣም ያናድዳል"" ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል በማለት አሳሂ ሺምቡን ጋዜጣ ዘግቧል። በፈረንጆቹ ከ2000 እስከ 2001 ለአንድ ዓመት ብቻ ጃፓን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያስተዳደሩት ዮሪ ዲፕሎማሲ በራቃቸው አስተያየቶቻቸው ይታወቃሉ። ሴቶችን በማስመልከት የሰጡት አስተያየትም ከማሕበራዊ ድር አምባ ተጠቃሚዎች ዘንድ ተቃውሞ አስነስቶባቸዋል። በርካታ የትዊተር ተጠቃሚዎች ዮሪ ሥልጣን ይልቀቁ በማለት ላይ ናቸው። ሰውዬው ቤት ሲገቡ ባለቤታቸው ጭምር በሰጡት አስተያየት እንደተቀየሟቸው መናገራቸውን አልደበቁም። ""ትላንት ምሽት ቤት ስገባ ባለቤቴ፤ አሁን ደግሞ ሌላ የማይሆን ነገር ተናገርክ አይደል? ሴቶችን የሚያፀይፍ ነገር በመናገርህ እኔ ነኝ የምሳቀቀው"" ብለዋል። ""ዛሬ ጥዋት ደግሞ ሴት ልጄ፣ ሴት የልጅ ልጄ ወቀሳ ሰንዝረውብኛል"" ብለዋል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል። የቶኪዮ ኦሊምፒክስ አዘጋጅ ኮሚቲ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለአንድ ዓመት የዘገየውን የቶኪዮ ኦሊምፒክና ፓራሊምፒክ በተሳካ ሁኔታ ለማዘጋጀት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል። ኮሚቲው 36 ከፍተኛ የቦርድ አባላት ያሉት ሲሆን ከዚህ ቀድም ጃፓን ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሠሩ ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/55930694 +sports "ከካሜሩን ጋር በሚደረገው የዛሬው ጨዋታ ""እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ለመፋለም ዝግጁ ነን""- አሰልጣኝ ውበቱ" "ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ከአዘጋጇ ካሜሩን ጋር ለምታደርገው ለዛሬው ጨዋታ ቡድኑ ጥሩ ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ገልጸዋል። በአፍሪካ ውስጥ ስመ ጥር ከሆኑት ቡድኖች የሆነው የካሜሩን ቡድንም ጠንካራና ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች እንደሆኑ እንደሚያውቁ በትናንትናው ዕለት በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ የተናገሩት አሰልጣኝ ውበቱ ሆኖም ቡድናቸው ከዚህ ጨዋታ አንድ ነገር ለማግኘት ዝግጁዎች ነን ብለዋል። ካሜሩን የዘንድሮው አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ በመሆኗ በዛሬው ዕለትም ኢትዮጵያ የምታደርገው ጨዋታ በደጋፊዎቿ ፊት ከምትጫወት ሃገር ጋ��� ከመሆኑም ቀላል ባይሆንም ""ጥቃቅን ስህተቶችን አስወግደን እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ለመፋለም ዝግጁ ነን።"" ይላሉ አሰልጣኙ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ በነበራት ጨዋታ በኬፕቨርዴ አንድ ለምንም ተረታለች። በዚህ ጨዋታ አንድ ተጫዋች በቀይ ካርድ በመውጣቱ አብዛኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአንድ ሰው ጎዶሎ እንደተጫወቱም የጠቀሱት አሰልጣኙ ይህም በዋልያዎቹ ላይ ተፅእኖ ፈጥሯል ብለዋል። ""ይህ በተጨዋቾቻችን በአካልና በመንፈስ ጠንካራ እንዳይሆኑ ያደረገ ክስተት ነበር።"" ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ አክለውም ቡድኑ በጥሩ አቋም ላይ አለ ብለዋል። ""ቢሆንም አሁን ወደ አቋማችን ተመልሰናል። ይህንንም በልምምድ ሜዳና በካምፕ ማየት ችለናል። ከዛሬው ጨዋታ የተሻለ ነገር እንደምናገኝ ተስፋ አለኝ።"" በማለት አስረድተዋል። ውበቱ አክለው በካሜሩን ጋር በሚኖራቸው ጨዋታ ብሔራዊ ቡድኑ የሚታወቅበትን ጨዋታ ለማሳየት እንደሚሞክሩ ጠቁመዋል። የመጀመሪያው ጨዋታ ለቡድናቸው ፈታኝ እንደነበር ጠቁመው የተሸነፈውም በአንድ ጎል ነው ይላሉ። ቡድናቸው ጎል የተቆጠረበት በመጀመሪያ አጋማሽ መገባደጃ ላይ መሆኑንም ጠቅሰው ""ይህ የሆነው በትኩረት ማነስ ሊሆን ይችላል።"" ብለዋል። ለዚህም እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ኢትዮጵያ ያደረገቻቸውን ያለፉትን ስድስ ሰባት ጨዋታዎችን በመጥቀስ ነው። ""ያለፉትን ስድስት ሰባት የኢትዮጵያ ጨዋታዎች ብንመለከት ኳስን በመቆጣጠር ከተጋጣሚዎቻችን የተሻልን ነበርን። ጋናን ብናነሳ፣ ደቡብ አፍሪካ አሊያም ዚምባብዌ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ነበረን።"" ይላሉ። በመጀመሪያው ጨዋታ ያሬድ ባየህ ቀይ ካርድ ከተመለከተ በኋላ ተቀይሮ የወጣው አማካዩ መሱድ ሞሐመድ ካሜሩንን ብናከብራትም ውጤት ለማግኘት መፋለማችን ግን አይቀርም ብሏል። ""ካሜሩን ጠንካራ ቡድን እንደሆነች እናውቃለን። አፍሪካን ወክላ በዓለም ዋንጫ ስትጫወት እኛ ኢትዮጵያዊያን ስንደግፋት ነበር። አልፎም የሳሙዔል ኤቶ ሃገር በመሆኗ ክብር እንሰጣታለን። ነገር ግን ዛሬ ከፈጣሪ ጋር ጥሩ ፍልሚያ እንደምናደርግ አስባለሁ።"" ብሏል መሱድ በትናንትናው ዕለት በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ከቡድኑ አባላት በኮቪድ ምክንያት አሊያም በጉዳት የማይሰለፍ አለ ወይ ተብለው የተጠየቁት አሠልጣኙ ኮቪድን በተለመከተ ተጫዋቾችን ጨምሮ ሁሉም የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ከኮቪድ-19 ነፃ መሆናቸውን ተናግረዋል። ""ይህ ለኛ መልካም ዜና ነው"" ብለዋል ጉዳትን በተመለከተ ለግብፅ ሊግ የሚጨዋተውና ልምድ አላቸው ከሚባሉት ተጫዋቾች አንዱ ሽመልስ በቀለ በጉዳት ምክንያት እንደማይሰለፍ ተናግረዋል። ከሃገር ውጭ ከሚጫወቱት ሁለት ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ሽመልስ ከትናንት በስቲያ ጉዳት እንዳጋጠመው አሰልጣኝ ውበቱ ገልጸዋል። ""ከሃገር ውጭ ከሚጫወቱ ሁሉት ተጫዎቾቻችን አንዱ ነው። ቢሆንም ልምዱን ልንጠቀምበት አልቻልንም። ከትናንት በስቲያ እንደገና ጉዳት አጋጥሞታል። ከሱ በቀር ሁሉም ተጫዋቾቻችን ለዛሬው ፍልሚያ ዝግጁ ናቸው።"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59967701 +health ኮሮናቫይረስ፡ የለንደን ፖሊስ ክልከላዎችን በመተላለፍ ሰልፍ የወጡ ሰዎችን አሰረ በለንደን ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ለመቃወም ከወጡ ሰዎች መካካል 18 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ውሳኔውን የተቃወሙ በርካታ ሰዎች ከዩናይትድ ኪንግደም ንጉሳውያን መኖሪያ በሆነው ባኪንግሃም ቤተ-መንግስት ፊትለፊት ተሰባስበው ነበር። በመቀጠል ተቃዋሚ ሰልፈኞች ወደ ትራፋልጋር አደባባይ አምርተዋል። ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች በኮቪድ ምክንያት የተነጠቅነው ነጻነት ይመለስልን ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል። የሜትሮፖሊታን ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ እንዲበተኑ የተደረገ ቢሆንም ዜጎች ግን አሁንም ቢሆን አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል። በዌስትሚኒስተር ድልድይ ላይ ደግሞ ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ለመበተን ጥረት በሚያደርግበት ወቅት አንዳንድ ችግሮች ተፈጥረው ነበር ተብሏል። የፖሊስ አባላት ቀላል የሚባል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፖሊስ ሰልፈኞቹ በቁጥጥር ሥር ያዋልኩት የተለያዩ ሕግጋቶችን በመተላለፍ ነው ብሏል። ከጥፋቶቹ መካከልም የኮሮረናቫይረስ ሕጎችን በመጣስ፣ የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ ላይ ጉዳት ማድረስና ነውጠኝነት በዋነኛነት ተጠቃሽ ናቸው። ለንደን በያዝነው ሳምንት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ጠበቅ ያሉ ገደቦች ተጥለውባታል። ''ሰዎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ሲገኙ አካላዊ ርቀታቸውን አለመጠበቃቸውና የተቀመጡ ሕግና ደንቦችን አለማክበራቸው በእጅጉ አሳስቦናል'' ብለዋል የሜርሮፖሊታን ፖሊስ አዛዡ ኮማንደር አዴ አዴሌካን። አክለውም ''የተቃውሞ ሰልፉ አዘጋጆች የሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በቂ ዝግጅት አላደረጉም። በዚህ ሰአት ነው የህብረተሰቡን ደህንነት ለማረጋገጥ በማሰብ ፖሊሶች የተሰበሰቡትን ሰዎች ለመበተን የተንቀሳቀሱት'' ብለዋል። ''አብዛኛዎቹ የተሰበሰቡት ሰዎች የፖሊስ አባላቱ የነገሯቸውን በመስማታቸውና አካባቢውን ቶሎ በመልቀቃቸው ደስተኞች ነን። ነገር ግን ጥቂቶች ተባባሪ ለመሆን ፈቃደኛ አልነበሩም። ሆነ ብለው ፖሊሶች የሚነግሯቸው ነገር ችላ ሲሉ ነበር። ዌስትሚኒስተር ድልድይንም ዘግተው ነበር'' ብለዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54681599 +sports እንግሊዝ ከአለም ዋንጫ ውድድር ውጭ ስትሆን፣ ፈረንሳይ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች ከፍተኛ ግምት የተሰጣት እንግሊዝ ከአለም ዋንጫ ውድድር ውጭ ሆነች። በኳታሩ አልባይት ስታዲየም ከፈረንሳይ ጋር ትናንት ታህሳስ 1፣ 2015 ዓ.ም ባደረገችው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ እንግሊዝ ጥሩ እንቅስቃሴ ብታሳይም ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ ተስኗታል። በተለይም የሃሪ ኬን ፍጹም ቅጣት ምት መሳት የእንግሊዝን መሸነፍ ያመላከተ ነበር። ሃሪ ኬን በጨዋታው ላይ ስሪ ላየንስን እኩል ያደረገበትና ለእንግሊዝ 53 ጎሎች በማስቆጠር ክብረወሰን የያዘውን ዋይኒ ሩኒን የተስተካከለበትን ግብ በፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሎ ነበር። ፈረንሳይ በ17ኛው ደቂቃ በኦሬሊየን ቹአሚኒ ጎል የመሪነቱን ስፍራ ተቆጣጥራ ነበር። እንግሊዝ በጨዋታው የበላይነት ቢኖራትም የተሻሉ የጎል እድሎችን መፍጠር አልቻለችም። ኦሬሊዮን ቹአሚኒ በእንግሊዙ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ ላይ ጥፋት በመፈጸሙ የተገኘችውንም የፍጹም ቅጣት ምት ሃሪ ኬን በመምታት ግብ በማስቆጠር እኩል መሆን ችለው ነበር። ጨዋታው ሊጠናቀቅ 12 ደቂቃ ሲቀረው አንትዋን ግሪዝማን ያሻገረለትን ኳስ ኦሊቪየር ጂሩድ በግንባሩ በመግጨት ባስቆጠራት ጎል ፈረንሳይ የመሪነቱን ቦታ ዳግም ተቆናጠጠች። ሆኖም እንግሊዝ ባገኘችው የፍጹም ቅጣት ምት እኩል የምሆንበትን እድል ብታገኝም አባክናዋለች። ፍጹም ቅጣት ምቱን የመታው ኬን ለሃገሩ ታሪክ ለማስመዝገብ እድሉን ቢያገኝም ነገር ግን ባልተለመደ መልኩን ኳሷን ወደላይ ጠልዟት ግቡን ስቷል። በዚህም የእንግሊዝ የአለም ዋንጫ ግስጋሴና ህልም የተገታ ሲሆን ፈረንሳይ ወደቀጣዩ የግማሽ ፍጻሜም አልፋለች። በቀጣዩም ፈረንሳይ ከሞሮኮ ጋር የምትፋለም ይሆናል። የሁለቱ አገራት ብሔራዊ ቡድኖች በተለያዩ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ከዓለም ዋንጫ ውጪ በጥሎ ማለፍ ግጥሚያ ሲገናኙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በዓለም ዋንጫም ከአውሮፓውያኑ 1982 ወዲህ በጥሎ ማለፍ ውድድር የተገናኙት በዚህ ጨዋታ ነ��። https://www.bbc.com/amharic/articles/c7215x0grmjo +politics የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ካለ ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ ኮሚሽነሩ አሳሰቡ "መንግሥት በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይ ጣልቃ የሚገባ ከሆነ ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው እንደሚለቁ ከቀናት በፊት የኮሚሽኑ ዋና ሰብሳቢ ሆነው የተሰየሙት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ተናገሩ። የኮሚሽኑ ዋና ሰብሳቢ ይህንን ያሉት የካቲት 16/2014 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን የሥራ መጀመሪያ ትውውቅ ፕሮግራም በተካሄደበት ወቅት መሆኑን ምክር ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። በዚህ ኮሚሽን አባል ሆነው እንዲሰሩ ኃላፊነት የሰጣቸው ሕዝቡ መሆኑን የተናገሩት ዋና ሰብሳቢው ኃላፊነት በተሞላው መንፈስ ለመስራትና ከሚዲያውና ከሌሎች አጋላት ጋር በጋራ እንደሚሰሩም መናገራቸው ተገልጿል። አክለውም ባደረጉት ንግግር የአስፈፃሚው አካል ወይም የመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንደማይኖር እምነታቸው መሆኑን ጠቁመዋል። ሆኖም በኮሚሽኑ አሰራር ውስጥ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት የሚኖር ከሆነ ግን ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው እንደሚለቁ ማሳሰባቸውን ከምክር ቤቱ ካገኘነው መግለጫ መረዳት ተችሏል። በአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የትውውቅ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ሥራውን በገለልተኝነት በመስራት የተሰጠውን ሕዝባዊ ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል። ""ፖለቲካ ከአገር በላይ ስላልሆነ"" ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት የተሰጠውን ኃላፊነት ገለልተኛ በመሆን ታሪካዊ ሥራ ሰርቶ ማለፍ እንደሚገባው ማስገንዘባቸው ተገልጿል። በምክክሩ የሚሳተፉት የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ አንድ አካል ሊታዩ እንደሚገባ ያብራሩት አፈ ጉባኤው የምክክሩ ባለቤት ሕዝቡ በመሆኑም ትክክለኛ ውሳኔ የሚጠበቀውም ከሕዝብ ነው ማለታቸውም ሰፍሯል። በዚህ ትውውቅ ፕሮግራም ላይ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ተሞክሮዎችን በማካተት እና በሕዝቡ መካከል በርካታ የባህል ትስስሮች ስላሉ እድሉን ለሕዝቡ መስጠት ይገባል ሲሉ የኮሚሽኑ አባላት መናገራቸው ተገልጿል። በተጨማሪ ሕዝቡን በማወያየት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አለመግባባቶች በውይይት በሚፈቱበት ሁኔታም ላይ አበክረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል ሂደትን የሚመራና የሚያስተባብር አካል ለማቋቋም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካይነት ጥቆማ መካሄዱ ይታወሳል። ከጥቂት ወራት በፊት ለሕዝብ በቀረበ ጥሪ መሠረት 632 ዕጩዎች ለኮሚሽኑ አባልነት በተለያዩ ወገኖች ተጠቁመው ከእነዚህ መካከልም ኮሚሽኑን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ መስፈርቶች መሠረት 42ቱ ተለይተው ኅብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ዝርዝራቸው ይፋ ሆኖ ነበር። ከዚህ ሂደት በኋላም በተጠቋሚ ዕጩዎቹ ላይ በተዘጋጀው መስፈርት መሠረት ከሕዝብ የሚቀርበው አስተያየት ተገምግሞ የመጨረሻዎቹ 11 ዕጩ ኮሚሽነሮች ተለይተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ እንዲሾሙ አድርጓል። ኮሚሽኑ በአገሪቱ ለዘመናት የቆዩ ናቸው በተባሉ የተለያዩ አወዛጋቢና ጉዳዮች ላይ የሚመለከታቸው ወገኖችንና ኃይሎችን በማቀራረብ ውይይት ተደርጓ መግባባት ላይ እንዲደረስ ለማድረግ የሚያስችሉ ምክክሮችን ይመራል ተብሎ ይጠበቃል። ከሰሞኑ በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም የመንግሥታቸው የስድስት ወራት አፈጻጸም በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው ብሔራዊ ውይይቱና ምክክሩ የሚደረገው በቆሰሉ ታሪኮችና ነገ በምንገነባት ኢትዮጵያ ላይ ፟እንደሆነ ""የምንገነባው አገር ከሥልጣናችን በላይ ስለሆነ ነው፤ ለወደፊቱ ትውልድ ስለሆነ ነው"" ሲሉም አስረድተዋል። የውይይቱ ሂደት በዋነኝት ሊያካትታቸው የሚገባ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህም ግልፅ፣ የሚገለል ማኅበረሰብ የሌለበትና ሁሉንም ሕዝብ አሳታፊ ሊሆን እንደሚገባም አንስተዋል። እንደ ምሳሌ የጠቀሱት በሕገ መንግሥቱ ላይ ያለውን አንቀፅ 39፣ በርካታ ጥያቄ የሚያነሱ ፓርቲዎችን ጉዳይ እንዲሁም የሰንደቅ አላማ ጉዳይን ሲሆን በአሁኑ ወቅት አገሪቱን የሚያከራክሩና የሚያጣሉ ጉዳዮች መቋጫ ሊያገኙ የሚችሉበት ነው ብለዋል። ውይይት የሚያስፈልገው ሽኩቻ፣ ጦርነትና የፖለቲካ ሽግግር ሲኖር መሆኑን ጠቅሰው አገሪቷ እያተዘጋጀችበት ያለችውም ምክክር አራት ምዕራፎች እንዳሉት ጠቅሰዋል። እስካሁን የተካሄደው ቅድመ ዝግጅት ሲሆን እስካሁን ያለው ብሔርና ፆታን ባሳተፈ መልኩ የተዋቀረ በመሆኑ ጥሩ ጅማሮ ነው ብለዋል። ""በውይይትና በድርድር የሚፈታ ችግር ካለ መንግሥት ለማንም በሩ ክፍት ነው። እኛ የምንጠላው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚነካ ሲሆን ነው"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60504072 +sports ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ አለፈች ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት የምእራብ አፍሪካ አገሯ ካሜሮን ለምታዘጋጀው የአፍሪካ እግረ ኳስ ዋንጫ ማለፏ አረጋገጠች። ኢትዯጵያ ለአፍኮን 2021 ያለፈችው ከስምንት ዓመት በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚገኝበት ምድብ ወስጥ ያሉት የኒጀርና የማዳጋስካር አቻ መውጣታቸውን ተከትሎ ነው 9 ነጥብ በመያዝ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መቀላቀሉን ያረጋገጠው። ዛሬ በምድብ ኬ የሚገኙት ኢትዮጵያ ኮትዲቯርና ማዳጋስካር ኒጀር የመጨረሻ ቀሪ ጨዋታቸውን አካሄደው ነበር። በዚህ ውጤት መሰረት ኢትዮጵያና ኮትዲቯር ባደረጉት ጨዋታ ኮትዲቯር ሦስት ለአንድ ኢትዮጵያን እየመራች ሳለ በዳኛው ሕመም ምክንያት ጨዋታው ተቋርጧል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ማለፏን ያረጋገጠችው በተመሳሳይ ምድብ የሚገኙት ማዳጋስካርና ኒጀር ባዶ ለባዶ መለያየታቸውን ተከትሎ ነው። ሰባት ነጥብ የነበራት ማዳጋስካር ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ኒጀርን አሸንፋ 9 ነጥብ ያላትን ኢትዮጵያን መብለጥ ይጠበቅባት ነበር። የዋሊያዎቹን ድል ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በሚቀጥለው ዓመት ታኅሣሥ ወር ላይ በካሜሮን አዘጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ላይ 24 አገራት ተሳታፊ ይሆናሉ። እስካሁን ድረስ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ጊኒ፣ አልጄሪያ፣ ዚምባብዌ፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ማሊ፣ ግብጽ፣ ኮሞሮስ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ማላዊ፣ጋና ፣ሱዳን ፣ጋምብቢ፣ ሞሮኮ እና ጋቦን ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-56582175 +health ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ-19 ሞት መዘገበች "የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በምታደርገው ጥረት የምትመሰገነው እስያዊቷ አገር ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ -19 ሞት መዘገበች። ይህም እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ሞት ላልመዘገበችው ቬትናም አሳዛኝ ክስተት ሆኗል። በበሽታው የሞቱት የ70 ዓመቱ ግለሰብ ከሆይ አን ከምትባል ግዛት መሆናቸውንም የአገሪቷ ሚዲያ ዘግቧል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ ሪዞርት አቅራቢያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከመመዝገባቸው በፊት ከሦስት ወራት ለሚበልጥ ጊዜ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። 95 ሚሊየን ሕዝብ ያላት ቬትናም፤ ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ እስካሁን 509 በቫይረሱ ተይዘውባታል። ይህም ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ ቁጥ�� ነው። በእርግጥ አገሪቷ ከሌሎች አገራት በተለየ ቫይረሱን ለመከላከል እርምጃ መውሰድ የጀመረችው አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሳይኖር ነበር። ድንበሮቿንም ወደ አገራቸው ከሚገቡ ዜጎቿ በስተቀር ለተጓዦች ዝግ ያደረገችው ቀድማ ነበር። ከዚህም ባሻገር ወደ አገሪቷ የሚገባ ማንኛውም ግለሰብ መንግሥት ባዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ለ14 ቀናት መቆየትና መመርመር ግድ ነው። እነዚህ የጥንቃቄ እርምጃዎችም ውጤት አሳይተው ከሚያዚያ ወር አጋማሽ ጀምሮ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። በዚህ በወቅት በሽታውን ለመቆጣጠር ባደረገችው ጥረት እንዲሁም በቫይረሱ ተይዞ ሁለት ወራትን በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ላሳለፈው ስኮትላንዳዊ አብራሪ ላደረገችው እንክብካቤም አድናቆት ተችሯታል። ይሁን እንጂ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በታዋቂው ዳ ናንግ ሪዞርት አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የመገኘታቸው አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል። በዚህ ወቅትም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአገሪቷ ጎብኝዎች በከተማዋ ውስጥ ነበሩ ተብሏል። መንግሥት ረቡዕ ዕለት በከተማዋ ሙሉ ለሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣሉ በፊትም ከተማዋን ለጎብኝዎች ዝግ አድርጎ ነበር። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ የተከሰተውን ወረርሽኝ ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስተር ጉየን ዡዋን ፑክ ""ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በፍጥነትና በትጋት እርምጃ መውሰድ አለብን"" በማለት በአገሪቷ ያሉ ግዛቶችና ከተሞችን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቃቸውን የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል።" https://www.bbc.com/amharic/53610860 +politics ሴኔቱ ዶናልድ ትራምፕ ላይ ክስ የመመስረቱ ሂደት ሕገ መንግሥታዊ ነው አለ "የአሜሪካ ሴኔት የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ክስ መመስረቱ ሕገ መንግሥታዊ ነው በማለት የክስ ሂደቱን አስቀጠለ። የትራምፕ ጠበቆች በበኩላቸው ዶናልድ ትራምፕ ዋይት ሃውስን ከለቀቁ በኋላ መሰል ክስ ሊቀርብባቸው አይችልም ሲሉ ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ 56-44 በሆነ የድምጽ ብልጫ የቀድሞ ፕሬዝደንት ላይ ክስ የመመስረቱ ሂደት ድጋፍ አግኝቷል። ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ወር ደጋፊዎቻቸው በካፒቶል ሂላ ላይ ጉዳት እንዲያደርሱ አመጽ ቀስቅሰዋል በሚል እየተወነጀሉ ነው። ትራምፕ ምንም አይነት ማረጋገጫ ሳያቀርቡ ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ መቆየታቸው ይታወሳል። ትራምፕን እየከሰሱ የሚገኙት ዲሞክራቶች ሂድቱን በኤግዚቢትነት ያቀረቧቸውን ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማሳየት ጀምረዋል። በተንቀሳቃሽ ምሰሉ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው ወደ ካፒቶል ሂል እንዲሄዱ 'ሲያነሳሱ' እና በሺዎች የሚቆጠሩ የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሂልን ሰብረው ሲገቡ፤ በንብረት እና በጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ጉዳት ሲያደርሱ ያሳያል። ዴሞክራቶች ባቀረቡት ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው 'እስከመጨረሻው እንዲታገሉ' መልዕክት ሲያስተላልፉ፤ ይህን ተከትሎም በካፒቶል ሂል ላይ ጉዳት ሲደርስ አስመልክተዋል። ዲሞክራቱ ጄሚ ራስኪን፤ ይህ ተግባር ትራምፕን በወንጀል ማስጠየቅ አለበት ብለው ተከራክረዋል። ""ይህ የአሜሪካ የወደፊት እጣ መሆን የለበት። በመንግሥታችን ላይ አመጽ የሚቀሰቅስ ፕሬዝደንት ሊኖረን አይገባም"" ብለዋል። የቀድሞ ፕሬዝደንት ትራምፕ ጠበቆች በበኩላቸው፤ ዶናልድ ትራምፕን በዚህ ሂደት ውስጥ ማሳለፍ ሕገ መንግሥታዊ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። ዲሞክራቶችም ይህን እያደረጉ ያሉት ፖለቲካዊ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ነው ብለዋል። 56-44 የሚለው የድምጽ ውጤት ስድስት የትራምፕ ፓርቲ አባላት የሆኑ ሪፐብሊካኖች ከዲሞክራቶች ጎን በመሆን ድምጽ መስጠታቸውን ያመላክታል። በትራምፕ ላይ ክስ ለመመስረት 100 መቀመጫ ባሉት ሴኔት ውስጥ 2/3ኛ ድጋፍ ያስፈልጋል። ትራምፕ ላይ ክስ እንዲመሰረት ከተወሰነ ዶናልድ ትራምፕ ወደፊት የፖለቲካ ተሳትፎ አድርገው ስልጣን እንዳይዙ ሊደረጉ ይችላሉ። በትራምፕ ላይ ክስ እንዲመሰረት የሚጠይቁት ዴሞክራቶችም ሆኑ የትራምፕ ጠበቆች ለአንድ ተጨማሪ ቀን መከራከሪያ ነጥቦቻቸውን ማቅረባቸውን ይቀጥላሉ። በሴናተሮች በኩል ለሚነሱ ጥያቄዎች ዴሞክራቶች እና የትራምፕ ጠበቆች ምላሽ ይሰጣሉ። ዴሞክራቶቹ የዓይን ምስክሮችንም ቃል ሊያሰሙ ይችላሉ። እስከ መጪው ሰኞ ድረስ ትራምፕ ክስ እንዲመሰረትባቸው አልያም ነጻ እንዲወጡ ሴኔቱ ውሳኔ ማስተላለፉ አይቀርም ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55976634 +politics የሚንስትሮች ምክር ቤት 'ሕወሓት እና ሸኔ' በሽብርተኛነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ አስተላለፈ "የሚንስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና ሸኔ በሽብርተኛነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ማስተላለፉን የጠቅላይ ሚንስትሩ ጸ/ቤት አስታወቀ። ሁለቱ ቡድኖች ባለፉት ሦስት ዓመታት የመጣውን ለውጥ ለመቀልበስ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ሲፈጸሙ ቆይተዋል ብሏል ጸ/ቤቱ። ""በዚህም የበርካታ ዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፣ አካላቸው ጎድሏል፤ ንብረታቸው ወድሟል፤ ከቀዬአቸውም ተፈናቅለዋል። ጥቃቶቹ ህብረተሰቡ ቀጣይነት ባለው ሥጋት እና ፍርሐት ውስጥ እንዲኖር በማድረግ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ፣ ዜጎች እርስ በእርስ እንዳይተማመኑ አድርጓ።"" ""እነዚህ ሁሉ የሀገረ መንግሥቱን ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል ታቅደው ሲፈጸሙ የነበሩ መሆኑን ከተለያዩ ማስረጃዎች ለመረዳት ተችሏል"" ብሏል በመግለጫው። የጠቅላይ ሚንስቴሩ ጸ/ቤት በተለያዩ አካባቢዎች ሲፈጸሙ የቆዩት ጥቃቶች በተለያዩ አካላት ቢፈጸሙም ""በዕቅድ፤ በገንዘብ፣ በሐሳብ እና በሰው ኃይል ሥልጠና በመደገፍ፤ የሚዲያ ሽፋን እና እገዛ በመስጠት ረገድ የመሪነት ሚናውን ሲጫወቱ የነበሩ ቡድኖች አሉ"" ብሏል። ""ኢትዮጵያን የማመሰቃቀል፤ የማዳከም እና የማፍረስ ፍላጎት ያላቸው"" ናቸው ያላቸው 'የውጭ ኃይሎች' ቡድኖቹን እየተጠቀሙባቸው ነው ሲልም አስታውቋል። ""ድርጅቶቹ ሲፈጸሙና ሲያስፈጽሙ የቆዩዋቸው የጥፋት ተግባራት የሽብር ወንጀል ተግባራት ናቸው። እነዚህ ተግባራት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አወጅ 1176/2012 አንቀጽ 3 ሥር ስለሽብር የወንጀል ድርጊት የተሰጠውን ትርጓሜ ሙሉ ለሙሉ የሚያሟሉ ተግባራት እንደሆኑ በቀላሉ ለመገንዘብ ይቻላል"" ብሏል። የሽብር ተግባራቱን የፈጽሙ ድርጅቶች አባላትና እና ደጋፊዎቻቸውን በግለሰብ ደረጃ በተናጠል በሽብር ወንጀል ተጠያቂ ከማድረግ ""ድርጅቶቹን የሽብርተኛ ድርጅት አድርጎ በመሰየም በሕጉ በተቀመጠው አግባብ የሽብር ወንጀል ድርጊትን በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር እና ለመከላከል ይችላል"" ብሏል በመግለጫ። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 18 እና 19 በመጥቀስ ""ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት)"" እና ""ሸኔ"" የሽብር ወንጀልን ዓላማቸው አድርገው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑና የድርጅቶቹ የሥራ አመራር ወይም ውሳኔ ሰጭ አካላት ወንጀሉን አምነው የተቀበሉት ወይም አፈጻጸሙን እየመሩት በመሆኑ፤ የሽብር ተግባር መፈጸምም የድርጅቶቹ ጠቅላላ መገለጫ በመሆኑ፤ ድርጅቶቹ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ቀርቧል"" ብሏል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 23 መሠረትም ""በተመሳሳይ ተግባር በተሰማሩ እና በዚህ ውሳኔ ሐሳብ መሠረት ከተሰየሙት የሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ትብብር፤ ትሥሥር ወይም የሐሳብ እና የተግባር ዝምድና ያላቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም ይህ ውሳኔ ሐሳብ ተፈጻሚ ይሆናል"" ሲል አጠናቋል።" https://www.bbc.com/amharic/56954704 +politics ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የባህር ድንበርን ያቋረጠ ሚሳኤል ተኮሰች ሰሜን ኮሪያ ከጎረቤቷን ደቡብ ኮሪያ ጋር የሚለያትን የባህር ድንበር አቋርጣ ሚሳኤል ተኩሳለች። ይህም ሀገሪቱ ባህረ ገብ መሬቱን ከተካፈሉት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የተተኮሰው የአጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤል በደቡብ ኮርያ ሶኮቾ ከተባለች ከተማ 60 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ ስፍራ ላይ አርፏል። ይህም ደቡብ ኮሪያ ኡሌንጉዶ በተባለው ደሴቷ የሚገኘው አየር ሃይሏ በተጠንቀቅ እንዲቆም ያደረገ ነው። ደቡብ ኮሪያ በአጸፋው ሶስት ሚሳኤሎችን አከታትላ ተኩሳለች። የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክይሉ የፒዮንግኣንግን ድርጊት “የድንበር ወረራ” ስትል ጠርታዋለች። ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ጠዋት ቢያንስ 10 ሚሳኤሎችን እንደተኮሰች የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታውቋል። ቀጥሎም ጦሩ ሶስት ከአየር ወደ ምድር የሚተኮሱ ሚሳኤሎችን ወደ ሰሜን በአጸፋ እንደተኮሰ አስታውቋል። ጦሩ “ በሰሜን ኮሪያ የሚፈጸሙ እንዲህ አይነት ጽብ አጫሪ ድርጊቶችን አይታገስም። በደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ መካከል ባለው ትብብር ጥብቅ ምላሽ ይሰጣል” ብሏል። የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክይሉ ለተፈጸመው ጸብ አጫሪ ድርጊት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ማዘዛቸውም ተጠቁሟል። ሰሜን ኮሪያን ድርጊት ተከትሎ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ብሄራዊ የድህንነት ምክክር ጠርተዋል። ሁለቱ ሀገራት የድንበር ወሰን ያቋረጠውን ሚሳኤል ጨምሮ የተተኮሱ ሚሳኤሎችን መዝግበዋል። ወሰኑን ያቋረጠ ሌላ ሚሳኤል ከደቡብ ኮሪያዋ ምስራቃዊ ከተማ ሶኬቾ 57 ኪሎ ሜትር ርቀት እና በሰሜን ምዕራብ ከምትገኘው ኦልንጎዴ ደሴት 167 ኪሎ ሜትር ርቀት ውሃማ አካል ላይ አርፏል። ይህ ድርጊት “እጅግ ያልተለመደ እና ተቀባይነት የሌለው” ሲሉ የተናገሩት የጥምር ጦር ዘመቻው መሪ ካንግ ሺንቹል ባህረገብ መሬቱ ከተከፈለ በኋላ በግዛት ውስጥ ላለ የውሃ አካል የቀረበ ተኩስ መሆኑን ተናግረዋል። ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤሎቹን ከማስወንጨፏ ቀድም ብሎ ፒዮንግያንግ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ከባህረ ገቡ መሬት አቅራቢያ የሚያደርጉትን የጋራ ልምምድ እንዲያቆሙ አስጠንቅቃ ነበር። ትላንትና ሰሜን ኮሪያ ጥምር ጦሩ ልምምዱን የማያቆም ከሆነ “ሃይለኛ” እርምጃ እንደምትወስድ ዝታ ነበር። ፒዮንግያንግ ባለፈው ወር አሜሪካ፥ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ላደረጉት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አጸፋ ሚሳኤል ተኩሳ ነበር። ይህ ተኩስ ወደ ደቡብ ኮሪያ የተደረገ የኒውክሌር ጥቃት “አምሳያ” ነው ትብሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c2xz2z2n8m6o +health በቱርክ የድንጋይ ከሰል ማውጫ ላይ በተከሰተ ፍንዳታ 40 ሰዎች ሲሞቱ፣ 11 ቆሰሉ በሰሜናዊ ቱርክ ውስጥ በሚገኝ አንድ የድንጋይ ከሰል ማውጫ ላይ በተከሰተ ፍንዳታ 40 ሰዎች መሞታቸውን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታወቁ። የቱርክ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሱሌይማን ሶይሉ እንዳሉት ከአደጋው ስፍራ 58 ሰዎችን በሕይወት ማትረፍ ሲቻል፣ 11 ደግሞ የመቁሰል አደጋ ሲደርስባቸው አንድ ሰው የደረሰበት አልታወቀም። በጥቁር ባሕር ዳርቻ በምትገኘው አምሳራ በምትባለው ስፍራ አርብ ዕለት በድንጋይ ከሰል ማውጫ ላይ ፍንዳታው ሲከሰት 110 ሰዎች በስፍራው ነበሩ። ሁሉም ቢያንስ ከምድር በታች 300 ሜትር ወርደው እየሠሩ ነበር። በፍንዳታው ከመሬት በታች የተቀበሩ ሰዎችን ከዋሻው ለማውጣት የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሌሊቱን ሙሉ ቁፋሮ ሲያካሂዱ ነበር ያደሩት። የድንጋይ ከሰል አውጭ ሠራተኞች በጥቁ��� ጭስ ተሸፍነው እና ዐይናቸው ቀልቶ ወደ ሕክምና መስጫ ሲወሰዱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል ወጥቷል። የሠራተኞቹ ቤተሰቦች እና ወዳጆች ሠራተኞቹ ከዋሻው እስከሚወጡ በቦታው ሲጠባበቁም ታይቷል። የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ በተካሄደው ፍለጋ 40 አስከሬኖች የተገኙ ሲሆን 58 ሠራተኞች በራሳቸው እና በነፍስ አድን ሠራተኞች ከማዕድን ጉድጓዱ ወጥተዋል፤ በዚህም “ግዙፉ የነፍስ አድን ሥራ ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል” ብለዋል። ፍንዳታው ከመሬት 300 ሜትር ጥልቀት ላይ እንደተከሰተ ይታመናል። እስካሁን የፍንዳታው መንስኤ ምን እንደሆነ ባይታወቅም፣ የቱርክ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ምርመራ ጀምሯል። የቱርክ የኢነርጂ ሚኒስትር እንዳሉት፣ በድንጋይ ከሰል ማውጫ ውስጥ ተቀጣጣይ ኬሚካል በመፍጠር በሚታወቀው ፋየርዳምፕ ሳቢያ ፍንዳታው ተከስቶ ሊሆን ይችላል። ፍንዳታው የተከሰው አንድ ጊዜ እንደሆነም ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን አደጋው የተከሰተበት ባርቲን ግዛትን ዛሬ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የአማስራ ግዛት ከንቲባ ሬሳይ ካኪር፣ ከፍንዳታው የተረፉ ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል። አንድ ከፍንዳታው የተረፈ ሠራተኛ “ጭስ እና አቧራ አካባቢውን ሞልቶት ነበር። ምን እንደተከሰተ አልገባንም” ብሏል። የድንጋይ ከሰል ማውጫው በቱርክ መንግሥት የሚተዳደር ነው። በአገሪቱ የከፋ የድንጋይ ከሰል ማውጫ ቦታ አደጋ የተከሰተው እአአ በ2014 ሲሆን 301 ሰዎች ሞተዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c6pxz1ge16wo +politics ቻይና በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አወገዘች "በኤርትራ የሁለት ቀናት ጉብኝት ያደረጉት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አወገዙ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአንድ ፓርቲ በብቸኝነት በምትተዳደረውና በምዕራባውያን ዘንድ በተገለለችው ኤርትራ ያደረጉትን ጉብኝታቸውን ረቡዕ ከሰዓት በኋላ አጠናቀዋል። ዋንግ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መወያየታቸውን እና ""ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን"" ለማጠናከር ፕሬዝዳንቱ በቻይና ጉብኝት እንዲያደርጉ መጋበዛቸውንም የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከስብሰባው በኋላ በጋራ በሰጡት መግለጫ ""በዲሞክራሲና በሰብአዊ መብት ሰበብ በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ የሚደረግ ጣልቃገብነትን"" አውግዘዋል። ""ቻይና በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማንኛውንም ማዕቀብ ትቃወማለች"" ማለታቸውም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ የአሜሪካ መንግሥት በአራት የኤርትራ ተቋማትና በሁለት ኤርትራውያን ላይ በያዝነው ዓመት ማዕቀብ ጥሏል። ማዕቀቡ የኢትዮጵያን መረጋጋትና አንድነት እያናጋ ነው ባለው ቀውስና ግጭት ውስጥ አስተዋጽኦ አላቸው ያላቸውን የኤርትራ ተቋማትና ዜጎችን ኢላማ ያደረገ መሆኑን የአሜሪካ የፌደራል ግምጃ ቤት በወቅቱ አመልክቷል። በዚህም መሠረት ዕቀባው የተጣለባቸው ተቋማት የኤርትራ መከላከያ ኃይል፣ የኤርትራ ገዢ ፓርቲ ህዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ለፍትህ፣ ህድሪ ትረስ እና ሬድ ሲ ትሬዲንግ ኮርፖሬሽን ሲሆኑ ግለሰቦቹ ደግሞ አብረሃ ካሳ ነማሪያም እና ሐጎስ ገብረሕይወት ወልደኪዳን የተባሉት ናቸው። ኅዳር ወር መጨረሻ አካባቢ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው የነበሩት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነትን ተቃውመዋል። ""ኢትዮጵያውያን ውስጣዊ ችግሮቻቸውን መፍታት ስለሚችሉ ቻይና በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳዮች ጣልቃ ገብነትን ትቃወማለች"" ማለታቸውንም የ���ጭ ጉዳይ ሚንስቴር በወቅቱ አስታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአዲስ አበባ ጉብኝታቸውንም በተመለከተ ቻይና በኢትዮጵያ ላይ ያላትን መተማመን እንደሚያሳይ እና ቻይና ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ያላትን ድጋፍ የሚገልጽ ነው ማለታቸውም የሚታወስ ነው። ቻይና በቅርብ ወራት በተለይ ደግሞ ከትግራዩ ጦርነት ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ መድረኮች ላይ ድጋፏን ስትገልጽ ቆይታለች። የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል የሆነችው ቻይና፤ የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ መክሮ የውሳኔ ሐሳብ እንዳያወጣ ሲቃወሙ ከነበሩ አገራት መካከል አንዷ ነች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኤርትራው ጉብኝታቸው በተጨማሪ ቻይና ለአገሪቱ የምትሰጠውን የ100 ሚሊዮን ዩዋን ተጨማሪ ድጋፍ ማስታወቃቸውንም የማነ በትዊተር ገጻቸው ጠቅሰዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በበኩላቸው ቻይና በባለፉት 100 ዓመታት ላስመዘገበችው ትልቅ እድገት እንዲሁም ለቻይና ሕዝቦች እና ለዓለም ሁሉ ያበረከተችውን አስተዋፅኦ አድንቀው መናገራቸውም ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ ቻይና ዓለም አቀፍ ሕግን በማክበር ላይ የተመሰረተ ሚዛናዊ የሆነ ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት እንዲመጣ ላበረከተችው ጉልህ ሚናም አመስግነዋል ተብሏል። የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ከኤርትራ ጉዟቸው ተከትሎ ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ረቡዕ ኬንያ ናይሮቢ የገቡ ሲሆን በቆይታቸው፣ ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመገናኘት በተለያዩ መስኮች የትብብር ስምምነቶችን እንደሚፈርሙ ይጠበቃል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኬንያ በኋላ ቀጣይ ጉብኝታቸውን ለማድረግ ወደ ሕንድ ውቅያኖሷ ደሴት ኮሞሮስ ያቀናሉ ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/59884251 +sports አሜሪካ የቅርጫት ኳስ ጀግናዋን ለማስፈታት ‘የሞት ነጋዴውን’ ከእስር ፈታች "ሩሲያና አሜሪካ ወራትን ባስቆጠረ ድርድር የተሳካ የእስረኛ ልውውጥ አድርገዋል። በቅርጫት ኳስ የኦሎምፒክ ጀግና የሆነችው አሜሪካዊቷ ብሪትኒ ግራይነር ላለፉት 9 ወራት በሩሲያ እስር ቤት ቆይታ ነበር። የአሜሪካ መንግሥት ይህችን ዝነኛ ለማስፈታት ከፍተኛ የደኅንነት ሰዎችን ያሳተፈ ድርድር ሲካሄድ ቆይቶ በመጨረሻ ተሳክቶለታል። ሩሲያ ይቺን የቅርጫት ኳስ ጀግና የምቀይረው በቪክቶር ቡት ብቻ ነው በማለቷ ይኸው ተፈጻሚ ሆኗል። ቪክቶር ቡት ሩሲያዊ ዜጋ ሲሆን እጅግ አደገኛ የተባለ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ነጋዴና አዘዋዋሪ ነው። ሆሊውድ በርሱ ሕይወት ላይ ‘ሎርድ ኦፍ ዎር’ የተሰኘ ፊልም እስከመሥራት ደርሷል። ቪክተር ቡት ላለፉት 12 ዓመታት በአሜሪካ እስር ቤት ነበር። 25 ዓመታት ጽኑ እስር ተፈርዶበት የነበረው ይህ ዓለም አቀፍ የሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ነጋዴ ቡት በመጨረሻ ዝነኛዋን ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ ግራይነርን ለማስፈታት ሲባል ተለቋል። ሁለቱ እስረኞችን ለማስፈታት ሁለት  የግል አውሮፕላኖች ከሞስኮና ከዋሺንግተን እስረኞችን ይዘው ወደ አቡ ዳቢ የበረሩ ሲሆን በአቡዳቢ አየር ማረፊያ እስረኞቹ ሲለዋወጡ የሚያሳይ ቪዲዮ ወጥቷል። የእስረኛ ልውውጡ እንዲሰምር የሳኡዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማንና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት መሐመድ ቢን ዛይድ አል ነህያን ሁነኛ ሚና ተጫውተዋል ነው የተባለው። በተለይ ከፑቲን ጋር ጥብቅ ወዳጅ ናቸው የሚባሉት ልዑል ቢን ሰልማን ከዚህ የእስረⶉች ልውውጥ በሻገር የዩክሬንና የሩሲያ የጦር ምርኮኞችን ልውውጥ ያሳለጡ ሰው እንደሆኑ ይነገራል። ጆ ባይደን የእስረኛ ልውውጡ ተደርጎ ብሪትኒ ወደ አገሯ አሜሪካ በማቅናት ላይ ሳለች ከዋይት ሐውስ በሰጡት አጭር መግለጫ “ጀግኒትን በስልክ አወራኋት። ጥሩ ስሜት ላይ ናት። ለማገገ��� ጊዜ ያሻት ይሆናል’ ሲሉ ለአሜሪካዊያን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። የዚች ቅርጫት ኳስ ተጫዋች የፍቅር አጋር የሆነችው ቼሬል ግራይነር “ባለቤቴ በመፈታቷ ወደር የሌለው ደስታ ተሰምቶኛል’ ብላለች። በተመሳሳይ ‘የሞት ነጋዴው’ በሚል ቅጽል የሚታወቀው ቪክቶር ቦት ሞስኮ መድረሱ ተሰምቷል። ቦት ሞስኮ ሲደርስ ለሩሲያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን እንደተናገረው፣ ""ድንገት ሌሊት ላይ መጥተው ተነስ ሻንጣህን ሸክፍ አሉኝ፤ በቃ ይኸው ነው” ብሏል። ቦት ከአውሮፕላኑ ደረጃዎች ሲወርድ እቅፍ አበባ ለእናቱና ለባለቤቱ ሲያበረክት ታይቷል። ይህ ግለሰብ የዛሬ 12 ዓመት አካባቢ ነበር በአሜሪካ ደኅንነቶች ሲታደን ቆይቶ በታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ በቁጥጥር ሥር የዋለው። ቦት ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያን ለድሃ አገራትና ለአሸባሪዎች በማስተላለፍ የሩሲያ ቀኝ እጅ ነበር ትላለች አሜሪካ። ሩሲያ ይህ ሰው በአሜሪካ በቁጥጥር ሥር መዋሉ አበሳጭቷት ቆይቷል። የቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ ግራይነር በበኩሏ በቁጥጥር ሥር የዋለችው በሞስኮ አየር መንገድ የካናቢስ ዘይት በሻንጣዋ ይዛ በመገኘቷ ነበር። ይህቺን አሜሪካዊት ለማስፈታት ድርድር ሲጀመር አሜሪካ የቀድሞውን የባሕር ኃይል ባልደረባ ፖል ዊላንን ከርሷ ጋር አብሮ እንዲፈታላት ጠይቃ ነበር። ነገር ግን ሩሲያ ይህን ሰው ለመልቀቅ አልፈቀደችም። ፖል የታሰረው በፈረንጆች 2008 ለአሜሪካ ሲሰልል በመገኘቱ ነው። የ32 ዓመቷ ብሪትኒ ግራይነር በቅርጫት ኳስ የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ አሸናፊ ለፊኒክስ ሜርኩሪ የምትጫወት ዕውቅ ስፖርተኛ ናት።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c19vgxrgxreo +sports ናኦሚ ኦሳካ ለመገናኛ ብዙሃን አልናገርም በማለቷ ከውድድሮች ልትታገድ ትችላለች ተባለ "የዓለም ቁጥር ሁለቷ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ናኦሚ ኦሳካ ለመገናኛ ብዙሃን ለመናገር ፈቃደኛ አለመሆኗን ከቀጠለች የፈረንሣይ ኦፕንን ጨምሮ ወደፊቱ ከሚደረጉ የግራንድ ስላም ውድድሮች እንደምትባረር አዘጋጆቹ ተናግሩ። ጃፓናዊቷ ኦሳካ ባለፈው ሳምንት የአዕምሮ ጤንነቷን ለመጠበቅ ስትል በሮላንድ ጋሮስ (የፈፈረንሳይ ኦፕን ሌላኛው ስም) ውድድር ወቅት ምንም ዓይነት መግለጫ እንደማትሰጥ ገልጻለች። እሑድ ሮማኒያዊቷን ፓትሪሺያ ማሪያ ቲግን በውድድሩ የመጀመሪያ ዙር አሸንፋ መግለጫ ባለመስጠቷ 15,000 ዶላር ተቀጥታለች፡፡ የዓለም ቁጥር ሁለቷ ውድድሩን 6-4 7-6 (7-4) አሸንፋለች፡፡ የአራቱ ግራንድ ስላም አዘጋጆች በጋራ በሰጡት መግለጫ ኦሳካ፤ “ተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት እና ወደፊቱ ከግራንድ ስላም ውድድሮች ልትታገድ ትችላለች” ብለዋል፡፡ ኦሳካ እሁድ ዕለት “ለውጥ ሰዎችን ምቾት እንዳይኖራቸው ያደርጋል” ስል በትዊተር ገጿ አስፍራለች። ኦሳካ ሃሳቧን ማስታወቋን ተከትሎ አዘጋጆቹ የ23 ዓመቷ የቴኒስ ተጫዋች ሃሳቧን እንደገና እንድታጤን የጠየቁ ሲሆን የጤንነቷን ሁኔታ ለመፈተሽ ያደረጉት ሙከራም አልተሳካም፡፡ ከኦሳካ “የምላሽ አለማግኘት” በኋላ ድጋፍ እንደሚሰጣት እና “ግዴታዋንም አስታሰውሰው” የጽሑፍ መልዕክት ሰደውላታል፡፡ “ከግራንድ ስላም ህጎች ዋነኛው ተጫዋቾች ምንም ውጤት ያስመዝግቡ ከሚዲያ ጋር የመሠራት ሃላፊነታቸው ነው። ይህም ተጫዋቾቹ ለስፖርቱ፣ ለደጋፊዎች እና ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የሚወስዱት ሃላፊነት ነው” ብሏል መግለጫው፡፡ . “ናኦሚ ኦሳካ በውድድሩ ወቅት የሚዲያ ግዴታዎቿን ችላ ማለቷን ከቀጠለች ለተጨማሪ የሥነ ምግባር ጥሰት መዘዞች ራሷን ታጋልጣለች” ብሏል። “ተደጋጋሚ ጥሰቶች ከውድድሩ መታገድን ከባድ የወንጀል ምርመራን ጨምሮ ከፍተኛ ቅጣቶችን ያስከትላል። ለወደፊቱም ከግራንድ ስላም ውድድሮች እገዳን ሊያስከትል ይችላል።“ አክሎም ህጎች ያሉት “ሁሉም ተጫዋቾችን በአንድ ዓይን እንዲታዩ ለማድረግ” ነው ብሏል፡፡ እንዴት እዚህ ደረጃ ተደረሰ? የመገናኛ ብዙሃን መግለጫዎች በተጫዋቾች የአዕምሮ ጤንነት ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ በመጥቀስ በፈረንሣይ ኦፕን ወቅት መግለጫ እንደማትሰጥ ኦሳካ ረቡዕ ዕለት አሳወቀች፡፡ ተጫዋቾች ከሽንፈት በኋላ ለጥያቄዎች መልስ እንዲሰጡ መጠበቁን “እየወደቀ ያለን ሰው ከኋላ የመርገጥ ያህል ነው” ስትል አስረድታለች፡፡ በማህበራዊ ድር አምባር ባስተላለፈችው መግለጫ “ብዙ ጊዜ ሰዎች ለአትሌቶች የአዕምሮ ጤንነት ምንም እንደማይጨነቁ ይሰማኛል። ይህ እውነት መሆኑን ጋዜጣዊ መግለጫ ስመለከት ወይም ስሳተፍ ያየሁት ነው” ብላለች፡፡ “ብዙ ጊዜ እዚያ ቁጭ ብለን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የተጠየቅነውን ጥያቄዎች ወይም በአዕምሯችን ጥርጣሬን የሚጭሩ ጥያቄዎችን እንጠየቃለን። እናም እኔ ለሚጠራጠሩኝ ሰዎች ራሴን አላስገዛም፡፡“ በግራንድ ስላም ህግ ተጫዋቾች የመገናኛ ብዙሃን ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው እስከ 20,000 ዶላር ሊቀጡይችላሉ። የሴቶች ቴኒስ ማህበር እንደሚለው በውድድር ወቅት ተጫዋቾቹ ለመገናኛ ብዙሃን የመናገር “ስፖርታዊ እና የአድናቂዎቻቸው ኃላፊነት አለባቸው።"" የቴኒስ ተጫዋቾችን ጨምሮ ሌሎች ስፖርተኞች ብዙዎቹ ለመገናኛ ብዙሃን መናገር “የሥራው አካል” መሆኑን ቢቀበሉም የኦሳካን አቋም አድንቀዋል። ኦሳካ ከድሏ በኋላ የተለመደውን የሜዳ ላይ ቃለ-መጠይቅ አድርጋለች፡፡ “በአሸዋ ሜዳ ያለኝ እንቅስቃሴ እየተሻሻለ ያለ ነው፡፡ ብዙ ግጥሚያዎችን ካደረኩኝ የተሻለ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ” ብላለች፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-57304051 +politics የሰላም ስምምነቱ አፈጻጸምን በተመለከተ እየተሰሙ ያሉ ልዩነቶች የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የሰላም ስምምነቱ የሚጠይቀውን ሁሉ ተግባራዊ እያደረኩ ነው እያለ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ከትግራይ በኩል ግን መንግሥት ቃሉን ሙሉ ለሙሉ እያከበረ አይደለም የሚል ወቀሳ እየተሰነዘረ ነው። መንግሥት ቅዳሜ ታኅሣሥ 08/2015 ዓ.ም. በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎቱ በኩል ባወጣው መግለጫ ላይ የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ በህወሓት በኩል ግን ከዚህ የሚቃረን ሃሳብ ተሰንዝሯል። መንግሥት በመግለጫው “ለአገር እና ለሕዝብ ሲባል በተደረሰው የሰላም ስምምነት የገባውን ቃል ሳይውል ሳያድር እና ሳያንጠባጥብ በመፈጸም ላይ ይገኛል” ብሏል። ነገር ግን የህወሓት ሊቀመንበር እና የክልሉ ፕሬዝዳንት ዶክተር ድብረጽዮን ገብረሚካኤል መቀለ በተካሄደ ጉባኤ ላይ ሲናገሩ የሚጠበቅባቸውን እየፈጸሙ ቢሆንም በመንግሥት በኩል የሚጠበቀው ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እየሆነ አይደለም ማለታቸውን የትግራይ ክልል መገኛኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ዕሁድ ታኅሣሥ 09/2015 ዓ.ም. ዶ/ር ደብረጽዮን በትግራይ ክልል ምክር ቤት በተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የሰላም ስምምነት የአንድ ወር አተገባበርን በተመለከተ አቀረቡት በተባለው ሪፖርት ላይ፣ ስምምነቱ በሚጠበቀው መጠን እየተተገበረ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ደብረጽዮን (ዶ/ር) የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ ወዲህ በትግራይ በኩል ሁሉም የሰላም ስምምነቱ ጥያቄዎችን እየፈጸሙ መሆናቸውን ጠቅሰው “በፌደራል መንግሥት በኩል ከሰብአዊ እርዳታ አንፃር አበረታች ጉዳዮች ቢኖሩም በተቀሩት የሰላም ስምምነቱ ነጥቦች ዙርያ ግን መንግሥት በቃሉ መሠረት አልፈጸመም” ብለዋል። ሁለት ዓመት ያስቆጠረውን የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም በመንግሥት እና በህወሓት አመራሮች መካከል በመጀመሪያ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተደረገውን ድርድር ተከትሎ ዘላቂ ግጭት የሚያስቆ��� እና ትጥቅ የመፍታት ስምምነት ተደርሶ ነበር። በማስከተልም ኬንያ ውስጥ በሁለቱም ወገኖች ወታደራዊ አመራሮች መካከል የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለመተግበር በሚያስችል አጠቃላይ የትግበራ ሰነድ ላይ ስምምነት መፈረማቸው ይታወሳል። በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት በተደረሰው ስምምነት ግጭት ማቆም፣ የሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ፣ መሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ፣ የህወሓት ተዋጊዎች ትጥቅ እንዲፈቱ እና ከፌደራሉ ሠራዊት ውጪ የሆኑ ኃይሎች ከክልሉ እንዲወጡ ስምምነት ተደርሷል። ከሁለት ሳምንት በፊት ደግሞ የሰላም ስምምነቱን አፈጻጸም በተመለከተ በሁለቱም ወገኖች ወታደራዊ አመራሮች መካከል ትግራይ ሽረ ከተማ ውስጥ ውይይት መደረጉ እና የትግራይ ኃይሎች ከውጊያ ግንባሮች እየወጡ መሆናቸው ተዘግቧል። በተጨማሪም ሰላም ወርዶ ጦርነት ከቆመ በኋላ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ወደ ተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ያለችግር እየደረሰ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት እና ሌሎች የእርዳታ ተቋማት ገልጸዋል። ከዚህ ጎን ለጎን በጦርነቱ የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን በመጠገን ጥቂት በማይባሉ የትግራይ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት መጀመሩ የተዘገበ ሲሆን፣ የስልክ አገልግሎትም የተመለሱባቸው ቦታዎች እንዳሉ፣ በሌሎቹም ቦታዎች አገልግሎት ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል። በፌደራሉ መንግሥት እና በህወሓት ኃይሎች መካከል ከተፈረመ ከአንድ ወር በላይ የሆነውን ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ እስካሁን ያለበትን ሂደት በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከአሸማጋዮቹም ሆነ ከሁለቱም ወገን በይፋ የተሰጠ መረጃ የለም። ከዚህ አንጻር ባለፉት ቀናት ሁለቱም ወገኖች በተናጠል የሰላም ስምምነቱን በተመለከተ ያለበትን ደረጃ በየበኩላቸው ገልጸዋል። የፌደራሉ መንግሥት በሰላም ስምምነቱ የሚጠበቅበትን ሁሉ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን እየገለጸ ያለ ቢሆንም፣ ደብረጽዮን ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ደግሞ ከእርዳታ አቅርቦት ውጪ ተግባራዊ ያልሆኑ ጉዳዮች እንዳሉ አንስተዋል። ዶክተር ደብረጽዮን ጨምረውም “በተደረሰው የሰላም ስምምነት ውል መሰረት የኤርትራ ሠራዊት እና የአማራ ታጣቂዎች በወረራ ከያዙት የትግራይ መሬት ለቀው ሊወጡ ሲገባ አሁንም በትግራይ መሬት ላይ ሆነው የትግራይ ሕዝብን እየጨፈጨፉ ይገኛሉ” ብለዋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት በክልሉ ውስጥ ያሉ ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ውጪ የሆኑ ኃይሎች ለቀው እንዲወጡ እና የህወሓት ተዋጊዎችም ትጥቅ እንዲፈቱ ይጠበቃል። ነገር ግን ይህ ስምምነት ተግባራዊ ስለመሆኑ እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ሁለት ዓመት የደፈነው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የኤርትራ ሠራዊት የፌደራል መንግሥቱን በመደገፍ በግጭቱ ውስጥ ሲሳተፍ መቆየቱ ሲዘገብ የቆየ ቢሆንም፣ በሁለቱ ወገኖች በተደረሰው ስምምነት ላይ ግን የኤርትራ ስም በግልጽ አልተጠቀሰም። ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘው የሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ውጪ ያሉ ኃይሎች መውጣት በተጨማሪ የትግራይ ኃይሎች ትጥቅ እንዲፈቱ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የፌደራሉ ሠራዊትም መቀለን ጨምሮ ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች እንደሚገባ ያመለክታል። የፌደራል መንግሥቱ ከቀናት በፊት እንዳሳወቀው የመከላከያ ሠራዊት ባልደረሰባቸው መቀለን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የተደራጀ የዝርፊያ ድርጊቶች እየተፈጸሙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ መንግሥት የሕዝቡን ደኅንነት ለመጠበቅ ያለበትን ኃላፊነት ለመፈጸም አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አመልክቷል። ይህንን በተመለከተ ደብረጽዮንም ሆኑ ህወሓት ���ይፋ የሰጡት ምላሽ ባይኖርም፣ ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ግን የመንግሥት መግለጫን አያይዘው በትዊተር ገጻቸው አጭር አስተያየት አስፍረዋል። “እኛ ልንፈታው የማንችለው፣ ሕዝባችን ሊፈታው የማይችለው ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት፣ ማንም ሊፈታው አይችልም” በማለት ጽፈዋል። በሁለቱም ወገኖች በኩል ስምምነት ተደርጎ አስካልተራዘመ ድረስ ስምምነቱ በአንድ ወር ውስጥ ወደ ተግባር እንደሚሸጋገር ተገልጾ ነበር። ነገር ግን ከእነዚህ ወሳኝ ጉዳዮች አንጻር የተደረጉ ተግባራዊ እርምጃዎች ስለመኖራቸው ከየትኛውም ወገን የተባለ ነገር የለም። ከባድ ሰብአዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስን ያስከተለው የእርስ በእርስ ጦርነት ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ፣ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መሪዎች መካከል በተደረሰ ስምምነት ከቆመ ወደ ሁለት ወራት እየተቃረበ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cj7zmyn3x44o +politics የአሜሪካ እና የታሊባን ስምምነት የአፍጋኒስታንን ውድቀት አፋጥኖታል ተባለ "የአሜሪካ የመከላከያ ባለሥልጣናት ታሊባን አፍጋኒስታንን በቁጥጥሩ ሥር ማድረጉ በቡድኑ እና በትራምፕ አስተዳደር መካከል በተደረገው ስምምነት ላይ የተመሠረተ ነው ሲሉ ገለጹ። የዶሃ ስምምነት ተብሎ የሚጠራው ውል እአአ የካቲት 2020 የተፈረመ ሲሆን አሜሪካ ወታደሮቿን ከአፍጋኒስታን የምታስወጣበትን ቀን አስቀምጧል። ጄነራል ፍራንክ ማክኬንዚ ስምምነቱ በአፍጋኒስታን መንግስት እና በወታደሮች ላይ ""አስከፊ ውጤት"" አለው ብለዋል። የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስቲንም በሃሳቡ ተስማምተው ስምምነቱ ታሊባን ""እንዲጠናክር ረድቷል"" ሲሉ ገልጸዋል። የዶሃው ስምምነት ቀን ገደብ ከማስወቀመጥ በተጨማሪ እንደ አልቃይዳ ያሉ ቡድኖች የአሜሪካን እና የአጋሮቿን ደህንነት አደጋ ላይ እንዳይጥሉ እርምጃዎችን እንዲወስድ ታሊባን ሰፊ ግዴታዎችን ተጥሎበታል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መንበሩን ከተቆጣጠሩ በኋላ የሠራዊቱን የማስውጣት ዕቅዱን ቀጥለውበታል። ቀነ ገደቡ ግን ከግንቦት ይልቅ ነሐሴ መጨረሻ ሆነ። የአሜሪካ የመከላከያ ባለሥልጣናት ሐሳባቸውን የተናገሩት ረቡዕ በተወካዮች ምክር ቤት የመከላከያ አገልግሎት ኮሚቴ ፊት ቀርበው ነበር። ባለስልጣናቱ ሐሳባቸውን የሰጡት የውጭ ኃይሎች ዜጎቻቸውን ሲያስወጡ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ተስፋ የቆረጡ አፍጋኒስታኖች እንዲታደጓቸው ሲለምኑ በካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ሁከት ከተነሳ ከሳምንታት በኋላ ነው። በወቅቱ በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት 182 ሰዎች ተገድለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ መሪ የሆኑት ጄነራል ማክኬንዚ ከአፍጋኒስታን መውጣቱን በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር። ሥራው አሜሪካ በሃገሪቱ የነበራትን የ 20 ዓመታት ቆይታ እና ረዥሙ ጦርነት ያበቃበት ነበር። ጄነራል ማክኬንዚ ለኮሚቴው እንደገለጹት የዶሃው ስምምነት በአፍጋኒስታን መንግሥት ላይ ""ሁሉም ዕርዳታ ይጠናቀቃል ብለው የሚጠብቁበትን ቀን"" ያስቀመጠ ጠንካራ የስነ-ልቦና ተፅእኖ አሳድሯል። ዩናይትድ ስቴትስ በአፍጋኒስታን የሚገኙትን ወታደራዊ አማካሪዎቿን ከ 2500 በታች ዝቅ ካደረገች የአፍጋኒስታን መንግስት እና ወታደሩ መውደቃቸው የማይቀር መሆኑን ካመኑ ""የተወሰነ ጊዜ"" ማለፉን ገልጸዋል። ከዶሃ ስምምነት በኋላ በሚያዝያ ወር በፕሬዚዳንት ባይደን የታዘዘው የወታደራዊ ቅነሳ ችግሩን ያባባሰው ነው ብለዋል። ኦስቲን በበኩላቸው አሜሪካ በታሊባን ላይ የአየር ድብደባን ለማስቆም በዶሃው ስምምነት በመግባባታቸው ""እስላማዊ ቡድኑ ተጠናከረ፣ በአፍጋኒስታን የጸጥታ ኃይሎች ላይ የማጥቃት ሥራቸውን ጨምሯል። አፍጋኒስታኖች በየሳምንቱ ብዙ ሰዎችን እያጡ ነበር።"" የመከላከያ ባለሥልጣናቱ ማክሰኞ ከሴኔቱ የጦር መሣሪያ አገልግሎት ኮሚቴ ጋር ተነጋግረዋል። በወቅቱ ጄነራል ሚሌይ እና ጄኔራል ማክኬንዚ በነሐሴ ወር አሜሪካ ጦሯን ከማሰወውጣቷ በፊት በአፍጋኒስታን የ 2500 ወታደሮች እንዲቆዩ ምክረ ሃሳብ አቅርበው እንደነበር ገልጸዋል። ጄኔራል ሚሌይ አክለውም ቡድኑ አሁንም ከአልቃይዳ ጋር ያለውን ግንኙነት ያላቋረጠ አሸባሪ ድርጅት በመሆኑ አሜሪካውያንን ከአሸባሪ ጥቃቶች ለመጠበቅ ከባድ ያደርገዋል ብለዋል። የታሊባኑ ቃል አቀባይ ዛቢሁላህ ሙጃሂድ ረቡዕ ዕለት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ታጣቂዎች ""ከአፍጋኒስታን በመነሳት አሜሪካንን ጨምሮ ለማንኛውም ሃገር ምንም ዓይነት ስጋት እንደማይኖር ለዓለም ዋስትና ሰጥተዋል"" ብለዋል። ""በአፍጋኒስታን እስላማዊ ኢሚሬት እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል በዶሃ ለተፈረመው ስምምነት መተግበር ቁርጠኛ ነን። አሜሪካና እና አጋሮቿም ለስምምነቱ ቁርጠኝነት እንዲሆኑ እንፈልጋለን። አሉታዊ አስተያየቶችን ከመስጠት ይልቅ የዲፕሎማሲን እና የትብብርን መንገድ ቢመርጡ ለእነሱ የተሻለ ይሆናል""ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58716791 +sports ሦስት የጂቡቲ እግር ኳስ ተጫዋቾች በፈረንሳይ ጥገኝነት ጠየቁ "ሦስት የጂቡቲ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላት በፈረንሳይ ጥገኝነት የጠየቁ ሲሆን ከመካከላቸውም ለአንድ ሳምንት በአየር መንገድ ውስጥ የቆየው ተጫዋች በመጨረሻ መውጣት ችሏል። ነስረዲን አብዲ የተሰኘው ይህ ተጫዋች በፓሪስ በኩል በ2022 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ላይ ለመሳተፍ ሊሳፈር የሚገባውን አውሮፕላን በመተው እዚያው ጥገኝነት ጠይቋል። ሁለቱ የቡድን አጋሮቹ ቢላል ሐሰን እና አቦቡካሪ ኤልሚ ረቡዕ ከአውሮፕላን ማረፊያው የወጡ ሲሆን ጉዳያቸውን ለፈረንሳይ መንግሥት እንዲያቀርቡ ሦስት ወር ተሰጥቷቸዋል። ሦስቱም ተጫዋቾች በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ሳሉ በ72 ሰዓታት ውስጥ ጉዳያቸውን የሚያስረዳ ሰነድ እንዲያቀርቡ ጊዜ ተሰጥቷቸው ነበር። ተጫዋቾቹን በማገዝ ላይ የሚገኘው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅትም ለጂቡቲ መንግሥት የሚሠሩት ሐሰን እና ኤልሚ ጥገኝነት ተከልክለው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ከተገደዱ እስር ቤት ሊገቡ ይችላሉ የሚል ሥጋት እንዳለው ገልጾ ነበር። ኤልሚ በፖሊስ አገልግሎት ተቀጥሮ የሚሠራ ሲሆን፤ ሐሰን በጂቡቲ ሪፐብሊካን ዘብ ውስጥ በሚሠራበት ወቅት መፈጸም የማይፈልገውን ትዕዛዝ ለመከተል እንደሚገደድ ተናግሮ ጥገኝነት ጠይቋል ተብሏል። ""ትክክል ያልሆነ ነገር በተናገሩ ቁጥር በመንግሥት ይዋከባሉ"" ሲሉ የጂቡቲ የሰብአዊ መብቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዣን-ሎፕ ሻል ተናግረዋል። ""ሐሰን የቤተሰቡን አባላት እንዲያስር ይገደድ ነበር። ይህንን እያደረገ ለመቀጠል አልፈለገም"" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። የሁለቱም የትዳር አጋሮች አንዲሁም ቤተሰቦች በጂቡቲ ውስጥ ይገኛሉ ያሉት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት የሐሰን ባለቤት በመጨረሻው የእርግዝናዋ ወራት ውስጥ እንደምትገኝም አስታውቀዋል። ቡድኑ ከአራት ቀናት በፊት በአፍሪካ ሻምፒዮና በኒጀር 8 ለ 0 ተሸንፎ ከአልጄሪያ ወደ ሞሮኮ በቀጥታ መብረር ባለመቻሉ በፓሪስ አድርጎ ለመጓዝ ወደ ፈረንሳይ ተጉዞ ነበር። ተጫዋቾቹ በቪዛ ብሎም በኮቪድ ሰነዶች መጓደል ምክንያት ከፓሪስ ወደ ሞሮኮ የሚሄደው በረራቸው አምልጧቸዋል። ቀጥሎም ጥገኝነት ስለሚጠይቁበት መንገድ እቅድ ማውጣታቸው ተነግሯል። ሌሎች የቡድን አባላቶቻቸው ፓሪስን ለቀው ሲበሩ ሦስቱ የቡድን አባላት ግን ተደብቀው ቀርተዋል። ""በሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፈው ወደ አ���ራቸው መመለስ በጣም ፈርተዋል"" ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ መሪ ተናግረዋል። ከቀናት በፊት የፈረንሳይ ችሎት ሐሰን እና ኤልሚ ከአውሮፕላን ማረፊያው እንዲወጡ እስከሚፈቅድበት ጊዜ ድረስ ሦስቱም የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጣቢያው ትራንዚት ዞን ውስጥ ቆይተዋል። በምሽትም በዚያው በአየር ማረፊያው ውስጥ ባለ ሆቴል ውስጥ እንዲያርፉ ሲደረግ አንደነበረም ተገልጿል። የተጫዋቾቹ ጥያቄ በፈንሳይ የስደተኞች ተቋም መልስ ካገኘ በፈረንሳይ ውስጥ እንዲኖሩ ሊፈቀድላቸው ይችላል። ቢቢሲ ከጂቡቲ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን መልስ ለማግኘት ሞክሮ ሳይሳካ ቀርቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58527743 +health ኮሮናቫይረስ፡ሪፐብሊካኖች በሚያደርጉት እጩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሚዲያዎች እንዳይሳተፉ ተወሰነ "የአሜሪካ የሪፐብሊካን ፓርቲ በዚህ ወር እጩ ፕሬዚዳንቱን በይፋ ለመምረጥ እቅድ ይዟል። ይህ ምርጫም ሚዲያዎች እንዳይሳተፉበትና በዝግም እንደሚካሄድ ተገልጿል። የሪፐብሊካን ቃለ አቀባይ እንደተናገሩት ሚዲያ እንዳይሳተፍ የተወሰነው ከኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ጋር በተያያዘ መሆኑንም አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። በሰሜን ካሮላይና የሪፐብሊካን ልዑካን ተሰባስበውም እጩ ፕሬዚዳንቱን ዶናልድ ትራምፕን በይፋ እንደገና ይመርጣሉ። 336 የሚሆኑ ልዑካን በሰሜን ካሮላይና ግዛት፣ ቻርሎቴ ከተማ በዚህ ወር ይሰባሰባሉ። እነዚህ ልዑካን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቁጥሩ በመገደቡ መገኘት ያልቻሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ አባላትን ወክለው ይገኛሉ። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፓርቲያቸው ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ሲሆኑ፤ እንደገና በይፋ መመረጣቸውም የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸውንም እንዲሁ በይፋ መጀመሩን የሚያበስር ነው ተብሏል። ""ፓርቲያችን በፌደራል እንዲሁም በተለያዩ ግዛቶች የወጡ የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን በመከተልም ነው ስብሰባውን የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥርን የወሰንነው"" በማለት ቃለ አቀባይዋ ተናግረዋል። ይህ ውሳኔ ከዚህ በፊት ይደረጉ የነበሩ ስብሰባዎቸን አካሄድ የቀየረ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነቱ ስብሰባ የበርካታ ሚዲያዎችን ቀልብ የሚስብና ለህዝቡም መልዕክቶች ይፋ የሚሆኑበት ነበር። የሰሜን ካሮላይና አስተዳዳሪ በሚገኙት ሰዎች ብዛትና አካላዊ ርቀት ጋር ተያይዞ ስብሰባውን ወደ ሌላ ቦታ እንዲያደርጉት መጠየቀቻውን ተከትሎ ግንቦት ወር ላይ ወደ ጃክሰን፣ ፎሎሪዳ እንደሚደረግ ትራምፕ ተናግረው ነበር። ነገር ግን ወደ በኋላ ፍሎሪዳ ሊደረግ የነበረውን ስብሰባ በመሰረዝ ወደቀደመው እቅድ በመመለስ ሰሜን ካሮላይና እንዲካሄድ ተወስኗል።ግዛቲቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ያለምክንያት እያቀጣጠሉ ነው በማለት ወንጅለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53627157 +politics ባለፈው ሰኔ በጋምቤላ የፀጥታ ኃይሎች የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ 50 ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸው ተገለጸ በጋምቤላ ከተማ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና በጋምቤላ ነጻነት ግንባር የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ ቢያንስ 50 ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሸን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። በጋምቤላ ክልል ያጋጠመውን ቀውስ በተመለከተ ኢሰመኮ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 18/2014 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት በጋምቤላ ከተማ በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ከሕግ ውጪ ግድያ የፈጸሙ ኃላፊዎች ላይ የሕግ ተጠያቂነት እንዲኖርም ጠይቋል። በከተማዋ በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ እና በአማጺያኑ ታጣቂዎች መካከል የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ የተፈጸሙ ግድያዎችን፣ የአካል ጉዳቶችን እና ዘረፋዎችን በተመለከተ ኢሰመኮ ምርመራ ማድረጉን ገልጿል። ይህንንም በተመለከተ ኮሚሽኑ ይፋ ባደረገው 13 ገፅ ሪፖርት ከሰኔ 07 እስከ 09 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ ግድያ፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ዘረፋ  በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ኃይሎች መፈጸሙን አመልክቷል። እነዚህን አካላት ይፋ ያደረገው ኢሰመኮ የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል፣ ፖሊስ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ የጋምቤላ ነጻነት ግንባር፣ ሚሊሻዎች እና ተባባሪ ወጣቶች ድርጊቱን በመፈጸም፣ በመምራት እና በማስፈፀም ተሳትፈዋል ብሏል። በሦስቱ ቀናት ውስጥ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ሴቶችና የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ ቢያንስ 50 ሰላማዊ ሰዎችን በተናጠል እና በጅምላ ከፍርድ ውጪ መግደላቸውን ኮሚሽኑ አረጋግጧል። ታጣቂዎቹ ከተማዋን ለቀው ከወጡ እና ከተማው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ከገባም በኋላ ግድያዎቹ የተፈፀሙ ሲሆን ለዚህ የክልሉ  የጸጥታ ኃይሎች ተጠያቂ መሆናቸው ሰፍሯል። ኮሚሽኑ የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ብሎ የጠራቸው የክልሉ ልዩ ኃይል፣ መደበኛ ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎች ሲሆኑ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር የተባበሩ የተወሰኑ ወጣቶች መኖራቸው ተጠቅሷል። የጸጥታ ኃይሎቹ ባደረጉት አሰሳ ቢያንስ 50 ሰዎችን በመኖሪያ ቤታቸው ግቢ እና ውጪ፣በመንገድ ላይ እና በህግ አስከባሪዎች ቁጥጥር ስር የነበሩ ሰዎችን ጭምር ከህግ አግባብ ውጭ መግደላቸውን ኮሚሽኑ በምርመራ አረጋግጫለሁ ብሏል። በተጨማሪ 25 በሚሆኑ ሰዎች ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት፣ ቁጥራቸው ያልተጠቀሱ በርካቶች ላይ ደግሞ ድብደባ እና የማሰቃየት ተግባር መፈጸሙን የኢሰመኮ ሪፖርት ያስረዳል። ለዚህም የፀጥታ ኃይሎቹ “የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እና መሳሪያ በቤታችሁ እንዳለ ተጠቁመናል፤ የደበቃችሁትን መሳሪያ አውጡ” የሚል ምክንያትም እየሰጡ ነበር ብሏል። በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሰላማዊ ነዋሪዎች አስከሬን በክልሉ ልዩ ኃይሎች እና ፖሊሶች አማካይነት በጭነት መኪና ተሰብስበው ወዳልታወቀ ቦታ እንደተወሰደና በጅምላ እንዲቀበሩ መደረጉን ኮሚሽኑ የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ ነዋሪዎችና የዓይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ አስፍሯል። በተጨማሪም አስከሬን እንዲሰጣቸው ጥያቄ ያቀረቡ የሟች ቤተሰቦችም መከልከላቸውን አረጋግጧል። የሟቾች አስከሬን ለምን ለቤተሰቦች እንዳልተሰጠና የተቀበሩበት ቦታ ለምን ለቤተሰቦች እንዳልተገለጸ ኢሰመኮ የክልሉን ፖሊስ ጠይቆ፣ አስከሬን እንዲሰጠው ያመለከተ የከተማው ነዋሪ የለም የሚል መልስ ማግኘቱን ገልጿል። የከተማው ማዘጋጃ በበኩሉ ፌደራል ፖሊስን እንዲያነጋግሩ ለኢሰመኮ ምላሽ የሰጠ ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊስ በበኩሉ አስከሬኖች ተሰብስበው የተቀበሩት በማዘጋጃ ቤቱ መሆኑን መግለጹ ተጠቅሷል። ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ሌላ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎችም ውጊያው በተካሄደበት ዕለት “ተኩሳችሁብናል” በሚል ምክንያት በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ ያገኟቸውን ቢያንስ ሰባት ሰዎች መግደላቸውን ያትታል። ከግድያው በተጨማሪ በበርካታ ነዋሪዎች ላይ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት ማድረሳቸውንም ተገልጿል። የፀጥታ ኃይሎቹና ታጣቂ ኃይሎቹ ከገደሏቸው በተጨማሪ በተኩስ ልውውጡ ወቅት በየትኛው አካል እንደተገደሉ ያልታወቁ ስድስት ሰዎች ሕይወታችው ማለፉንም ሪፖርቱ አመልክቷል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም በበኩሉ ከውጊያው በኋላ ባደረገው ማጣራት የክልሉ ልዩ ኃይሎች ሰኔ 8 እና ሰኔ 9/2014 ዓ.ም. በከተማዋ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገልጾ፣ በተጨማሪ መወሰድ ያለባቸውን ሕጋዊ እርምጃዎችም መጠቆማቸውን ገልጸዋል። “የመብት ጥሰቶችን የፈጸሙ ሰዎችና ቡድኖችን ተጠያቂነት ለ���ረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ፣ ተጎጂዎች ፍትሕ እና ተገቢውን የካሳ እና መልሶ የመቋቋም ድጋፍ እንዲያገኙና” ተፈጻሚነቱንም እንደሚከታተል ኢሰመኮ አሳስቧል። ሰኔ 07 ከጥዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መንግሥት በሽብርተኛነት የሰየመው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እና የጋምቤላ ነጻነት ግንባር በጋራ ወደ ጋምቤላ ከተማ ገብተው ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ከክልሉ ልዩ ኃይሎች፣ ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎች እና ፌደራል ፖሊስ ጋር ውጊያ ተደርጓል። ታጣቂዎቹ የከተማዋን የተወሰነ ክፍል ተቆጣጥረው የነበረ ሲሆን ውጊያውንም ተከትሎ  የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች የጋምቤላን ከተማ መልሰው መቆጣጠራቸው ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cy67z0d35q2o +health ኮሮናቫይረስ ፡ የ90 ዓመቷ አዛውንት የፋይዘር/ባዮንቴከ ክትባትን በመከተብ በዓለም የመጀመሪያዋ ሆኑ "ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ዛሬ ለዜጎቿ መስጠት ስትጀምር የዘጠና ዓመቷ አዛውንት የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባትን በመውሰድ በዓለም የመጀመሪያዋ ሆኑ። በሰሜን አየርላንድ ኢኒስኪለን ነዋሪ ሆኑት የዘጠና ዓመቷ የእድሜ ባለጸጋ ማርግሬት ኪናን የፋይዘር/ባዮንቴክ የኮቪድ-19 ክትባትን ከሙከራ ውጪ በመውሰድ በምድራችን የመጀመሪያዋ ሰው ሆነዋል። አዛውንቷ ማርግሬት በመርፌ የሚሰጠውን ክትባት ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ በኮቬንትሪ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሚገኘው የክትባት ማእከል ተገኝተው ነው የወሰዱት። አሁን መሰጠት የተጀመረው የኮቪድ-19 ክትባት በዋናነት ትኩረት ያደረገው ለበሽታው በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑትን ሰዎች ሲሆን በቀጣይም ለሌሎች እንደሚዳረስ ተነግሯል። በመላው ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የሚገኙ ከ70 በላይ የሚሆኑ ሆስፒታሎች እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ ለሆኑ አዛውንቶች እና ለጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ለመስጠት መዘጋጀታቸው ተገልጿል። የአሜሪካ እና የጀርመን ኩባንያ የሆኑት ፋይዘር እና ባዮንቴክ ያበለጸጉት ክትባት ዩናይትድ ኪንግደም ለዜጎቿ እንዲሰጥ የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መፍቀዱ ይታወሳል። በዚህም ዩኬ ይህን ክትባት በመጠቀም የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። ክትባቱን ዛሬ ከሚወስዱት መካከል የ87 ዓመቱ ዶ/ር ሃሪ ሹክላ አንዱ ናቸው። ዶ/ር ሃሪ ክትባቱን ከባለቤታቸው ጋር በመሆን ኒውካስትል በሚገኝ ሆስፒታል እንደሚወስዱ ገልጸው በዚህም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የክትባት አሰጣጥ መረሃ ግብሩ ቅድሚያ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑትን በማስቀደም ሕይወት ወደቀደመ መልኩ እንድትመለስ ይረዳል ተብሏል። ""ቪ-ዴይ"" ወይም የድል ቀን የሚል ስያሜ በተሰጠው ዕለት የሚጀመረው የክትባቱ መርሃ ግብር፤ ዜጎች ክትባቱን የመከተብ ግዴታ አይኖርባቸውም ተብሏል። ጠቅላይ ሚንሰትር ቦሪስ ጆንሰን፤ ""ዩናይትድ ኪንግደም ከኮሮናቫይረስ ጋር በምታደርገው ትግል የዛሬዋ ቀን ሌላ ምዕራፍ ከፍታለች"" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ክትባቱን ለዜጎች ለማዳረስ ወራትን ሊፈጅ እንደሚችል አስታውሰው እስከዚያው ድረስ ግን መንግሥት ያስተላለፋቸው የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን ዜጎች እንዲተገብሩ አስታውሰዋል። እስካሁን በዩናይትድ ኪንግደም ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ከ60ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። መንግሥት በአሁኑ ወቅት 800 ሺህ የክትባት ብልቃጦችን ዝግጁ ያደረገ ሲሆን ተጨማሪ 40 ሚሊዮን ክትባቶችንም አዟል። ይህም ለ20 ሚሊዮን ሕዝብ በቂ ነው። 95 በመቶ ቫይረሱን የመከላከል አቅምን ያጎለብታል የተባለለትን ክትባት ሰዎች በ21 ቀናት ልዩነት ሁለት ጊዜ መወጋት ይኖርባቸዋል። ሰዎች ከቫይረሱ እራሳቸውን መከላከያ የሚጀምሩ��� ሁለተኛውን ክትባት ከወሰዱ ከሰባተኛው ቀን በኋላ ነው ተብሏል። ባለፉት ሁለት ቀናት ክትባቱን የያዙ ማቀዝቀዣዎች ከሚመረቱበት ቤልጄየም ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ሲገቡ ቆይተዋል። በቀጣይ ሦስት ሳምንታት ውስጥም ተጨማሪ 10 ሚሊዮን የክትባት ብልቃቶች ወደ ዩኬ ገብተው ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ይሰራጫሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከሳምንታት በኋላ ደግሞ በስታዲየሞች እና በግዙፍ መሰብሰቢያ አዳራሾች ለበርካታ ሰዎች በአንድ ጊዜ ክትባት መስጠት ይጀመራል ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55226540 +sports የዓመቱ የአፍሪካ ምርጥ ስፖርተኛ ዕጩዎች ይፋ ሆኑ በአፍሪካዊያን እና ዩናይትድ ኪንግደም በሚገኙ ጋዜጠኞች የተመለመሉት ስድስቱ የቢቢሲ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኞች ዝርዝር ይፋ ሆኗል። የጋዜጠኞቹ ጉባዔ ስድስት ዕጩዎችን ይፋ ያደረገ ሲሆን ስፖርተኞች በ2021 በዓለም አቀፍ መድረክ አፍሪካን ያስጠሩ ናቸው። እነሆ የዕጩዎቹ ዝርዝር፡ እርስዎም የዘንድሮው ሽልማት ይገባዋል ለሚሉት ዕጬ ድምፅዎን እዚህ መስጠት ይችላሉ። ድምፅ መስጫው ሰዓት የሚያበቃው ታኅሣሥ 11 ከሌሊቱ 9 ሰዓት ሲሆን የሽልማቱ አሸናፊ ታኅሣሥ 29 በፎከስ ኦን አፍሪካ ቴሌቪዥንና ራድዮ እንዲሁም በቢቢሲ ስፖርት ድረ-ገፅ ላይ ይፋ ይደረጋል። ዕጩዎቹን በዝርዝር ስንመለከት ኢሊዩድ ኪፕቾጌ አገር፡ ኬንያ ዕድሜ፡ 37 የሩጫ መስክ፡ ማራቶን ኪፕቾጌ በማራቶን ሩጫ እስከዛሬ ከታዩ አትሌቶች ምርጡ ነው ሲባል ይደመጣል። ኪፕቾጌ በሁለት ተከታታይ ኦሊምፒኮች በማራቶን ውድድር ወርቅ ማምጣት ችሏል። ኬንያዊው አትሌት በኦሊምፒክ ታሪክ በተከታታይ ማራቶን ያሸነፈ ሦስተኛው ሯጭ ሲሆን በዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምርጥ ወንድ አትሌት ተብሎም ተመርጧል። በቶኪዮ ኦሊምፒክ ድል ያስመዘገበው ኪፕቾጌ 15 ጊዜ ማራቶን ሮጦ 13 ጊዜ ድል ማድረግ ችሏል። ከእነዚህ መካከል የርቀቱን ክብረ ወሰን በ2 ሰዓት ከ1 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ የያዘበት የበርሊን ማራቶን ተጠቃሽ ነው። ፌይዝ ኪፕዬጎን አገር፡ ኬንያ ዕድሜ፡ 27 የሩጫ መስክ፡ መካከለኛ ርቀት ፌይዝ በቶኪዮ ኦሊምፒክስ በ1500 የውድድሩን ክብረ ወሰን መስበር ችላለች። በዚህ ርቀት በሪዮ የመጀመሪያዋን ወርቅ ማምጣቷም አይዘነጋም። በወሊድ ምክንያት ከ21 ወራት በኋላ ወደ ሩጫ መድረክ የተመለሰችው ፌይዝ ከወሊድ በኋላ በተመሳሳይ ርቀት ያሸነፈች በታሪክ ሦስተኛዋ አትሌት ሆናለች። ባለፈው ሐምሌ ሞናኮ በተረገ ውድድር በታሪክ አራተኛውን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገቧ ይታወሳል። የፌይዝ ቀጣይ ዓላማዋ የርቀቱን የዓለም ክብረ ወሰን መጨበጥ ነው። ኡንታንዶ ማሽላንጉ አገር፡ ደቡብ አፍሪካዊ ዕድሜ፡ 19 የስፖርት መስክ፡ ዝላይና 200 ሜትር ሩጫ ማሽላንጉ በፓራሊምፒክ ውድድር የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያገኘው የ14 ታዳጊ ሳለ ነበር። በያዝነው ዓመት በ200 ሜትር [ቲ61] እና በዝላይ [ቲ63] ውድድሮች ወርቅ ማምጣት ችሏል። ደቡብ አፍሪካዊው አትሌት በ7.17 ሜትር ዝላይ የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብሯል። ወደፊት ብዙ ስኬቶች የሚጠብቁት ወጣቱ አትሌት የ10 ዓመት ታዳጊ ሳለ ነበር እግሮቹን ያጣው። ማሽላንጉ ባለፈው ሚያዚያ በ22.94 ሰከንድ የ200 ሜትር የዓለም የወንዶች ክብረ ወሰንን ጨብጧል። ክሪስቲን ምቦማ አገር፡ ናሚቢያ ዕድሜ፡ 18 የስፖርት መስክ፡ አጭር ርቀት በ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳታፊ የነበረችው ክሪስቲን በኦሊምፒክ የአሸናፊዎች መድረክ ላይ በመቆም የመጀመሪያዋ ናሚቢያዊት ሆናለች። በ25 ዓመታት የናሚቢያ ኦሊምፒክ ታሪክ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያስገኘችው ክሪስቲን በ200 ሜትር ርቀት የጃማይካዋ ኦሊምፒክ ቻምፒዮን ኢለይን ቶምፕሰን-ሄራንን ተከትላ በመግባት ብር አግኝታለች። ክሪስቲን የገባችበት 21.81 ���ከንድ በርቀቱ ከ20 ዓመት በታች ፈጣኑ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦላታል። ባለፈው መስከረም ዙሪክ በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ በ21.78 ሰከንድ ከማሸነፏም በላይ የአፍሪካ ክብረ ወሰንን ሰብራለች። የ18 ዓመቷ ታዳጊ በ400 ሜትር በዓለም አትሌቲክስ እንዳትሳተፍ የታገደች በተፈጥሮ ባላት ከፍተኝ ቴስቴስትሮን ምክንያት ነው። ኤድዋርዶ ሜንዲ አገር፡ ሴኔጋል ዕድሜ፡ 29 የስፖርት መስክ፡ እግር ኳስ ኤድዋርድ ሜንዲ ከፈረንሳዩ ክለብ ሬኔስ ወደ ቼልሲ ከተዛዋረ በኋላ በስታንፈርድ ብሪጅ ብቃቱን ማሳየት ችሏል። ባለፈው ግንቦት ደግሞ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ በማንሳት ታሪክ ፅፏል። ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ባደረገው ግስጋሴ ስምንት ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት በመጠበቁ ታሪክ ተጋርቷል። ሜንዲ በቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ የተጫወተ የመጀመሪያው ግብ ጠባቂም መሆን ችሏል። ከዚህ በፊት በአውሮፓ አህጉራዊ ዋንጫ ታሪክ በፍፃሜ የተሰለፈው የመጀመሪያው ግብ ጠባቂ ዚምባብዌያዊው ብሩስ ግሮብላር ሲሆን ይሄም በ1985 በአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ የተጻፈ ታሪክ ነው። ሜንዲ ባለፈው ውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 19 ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት በመጠበቁ የአውሮፓ የ2020-21 ምርጡ ግብ ጠባቂ ተብሎ ተሸልሟል። ሜንዲ በፍራንስ ፉትቦል የሚዘጋጀው የባለንዶር ሽልማት የያሺን ሽልማትን ባያገኘም ከዕጩዎቹ መካከል አንዱ ነበር። ታቲያና ስኩንማርከር አገር፡ ደቡብ አፍሪካ ዕድሜ፡ 24 የስፖርት መስክ፡ ውሃ ዋና ታቲያና በቶኪዮ ኦሊምፒክ በውሃ ዋና የወርቅና የብር ሜዳሊያ ለአገሯ ደቡብ አፍሪካ ከማስገኘቷም በላይ በ200 እና 100 ሜትር የዓለምና የኦሊምፒክ ክብረ ወሰንን መስበር ችላለች። ታቲያና በሪዮ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ባደረገችው ውድድር በሽራፊ ማይክሮሰከንድ ተሸንፋ በመውደቋ ከስፖርቱ ዓለም ራሷን ለማግለል ጫፍ ደርሳ ነበር። ነገር ግን ተስፋ ባለመቁረጥ ወደፊት በመግፋት በርካታ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ድሎችን ተጎናፅፋለች። https://www.bbc.com/amharic/news-59546277 +health ኮሮናቫይረስ፡ በኖርዌይ የአንዲት መርከብ ተሳፋሪዎችና ሠራተኞች በቫይረሱ ተያዙ "በኖርዌይ የመዝናኛ መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ቢያንስ 40 መንገደኞችና ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ኤምኤስ ሮልስ አሙንድሰን በተባለችው መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች መንገደኞች ደግሞ ለይቶ ማቆያ ገብተው የምርመራ ውጤታቸውን እየተጠባበቁ እንደሆነ የመርከቧ ባለንብረት ተናግረዋል። ሁርቲግሩትን የተባለ የኖርዌይ ድርጅት ንብረት የሆነችው መርከብ በትሮምሶ ወደብ ያረፈችው ባሳለፍነው አርብ ነበር። በዚህም ሳቢያ ድርጅቱ ሁሉንም የመዝናኛ መርከቦቹን እንዳይንቀሳቀሱ አግዷል። የድርጅቱ ኃላፊ ዳንኤል ስካይልዳም ""አሁን ትኩረት ያደረግነው ባልደረቦቻችንና እንግዶቻችንን ለመንከባከብ የምንችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ነው"" ሲሉ በመግለጫቸው ተናግረዋል። አራት የመርከቡ ሠራተኞች የኮሮናቫይረስ ምልክት ታይቶባቸው አርብ ዕለት መርከቧ ወደብ ላይ ካረፈች በኋላ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በኋላ ላይ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ158 ሠራተኞች መካከልም ሌሎች 32ቱ በቫይረሱ መያዛቸው የምርመራ ውጤታቸው አመላክቷል። ይሁን እንጂ 180 የሚሆኑ መንገደኞች ከመርከቧ እንዲወጡ የተፈቀደላቸው ሲሆን በባለሥልጣናት ቁጥጥር እንዲመረመሩ ተደርጓል። ሁሉም መንገደኞች ራሳቸውን እንዲለዩ መደረጉንም የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ከሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ በመርከቧ ጉዞ ላይ ከነበሩ 387 ተሳፋሪዎች መካካልም እስካሁን በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠው አምስት እንደሆኑ ተገልጿል። የጤና ባለሥልጣን የሆኑት ሊን ቮልድ ���ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት አሁን ከተከሰተው የቫይረስ ሥርጭት ጋር ተያይዞ በርካታ ሰዎች ቫይረሱ ሊገኝባቸው እንደሚችል ገልፀዋል። መርከቧ በአርክቲክ በሚገኘው ስቫልባርድ ለአንድ ሳምንት የቆየች ሲሆን በኢንግላንድና ስኮትላንድ የሚገኙ ወደቦችን ደግሞ መስከረም ላይ ለመጎብኘት እቅድ ይዛ ነበር ተብሏል። ይሁን እንጂ ኢንዱስትሪው በወረርሽኙ በመመታቱ ሁሉም የወደፊት ጉዞዎች ስለመኖራቸው የታወቀ ነገር እንደሌለ ተገልጿል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ወረርሽኙ በመርከቦች ላይ በመዛመቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በባሕር ላይ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ መቆየታቸው ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/53640749 +sports ስቴቨን ጄራርድ የአስተን ቪላ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ "የቀድሞ የሊቨርፑል እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አማካይ ስቴቨን የአስቶን ቪላ ክለብ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ። ጄራርድ ክለቡን ለሦስት ዓመት ተኩል ለማሰልጠን ውል መያዙ አስተን ቪላ ክለብ ይፋ አድርጓል። የ41 ዓመቱ ጄራርድ የአስተን ቪላ ክለብ ኃላፊነትን ከመቀበሉ በፊት ለሦስት ዓመታት የስኮትላንድ ክለብ የሆነውን ሬንጀርስን ሲያሰለጥን ቆይቷል። ጄራርድ ሬንጀርስ በባለፈው የውድድር ዘመን ከ10 ዓመታት በኋላ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሰ ረድቶ ነበር። ዕሁድ ዕለት አስተን ቪላ አምስት ዓመት በክለቡ የቆዩትን አሰልጣኝ ዲን ስሚዝን ከሥራ ማሰናበቱ ይታወሳል። አስተን ቪላ በአሁኑ ወቅት በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ከወራጅ ቀጠና በሁለት ነጥቦች ብቻ ርቀው 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ""አስተን ቪላ በእንግሊዝ እግር ኳስ ውስጥ ብዙ ታሪክ እና ባህል ያለው ክለብ ነው፤ አሰልጣኝ በመሆኔ ትልቅ ክብር ተሰምቶኛል"" ብሏል ጄራርድ ከሹመቱ በኋል። ጄራርድ የበላይ የአሰልጣኝነት ሥራውን የጀመረው የኮቲሹን ሬንጀርስ ክለብ እአአ 2018 ላይ ማሰልጠን በጀመረበት ወቅት ነው። ጄራርድ ወደ ቪላ መሄዱን ተከትሎ አስተን ቪላ ለስኮትላንዱ ክለብ 4.5 ሚሊዮን ፓዎንድ ካሳ እንደሚከፍል ተዘግቧል። በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን እና በሊቨርፑል ክለብ ውስጥ ትልቅ ስም የገነባው ጄራርድ፤ ለሊቨርፑል 710 ጊዜ ተሰልፎ ተጫውቷል። ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ 114 ጊዜ ተሰልፎ ተጫውቷል። ጄራርድ የአስተን ቪላ አሰልጣኝነት ሥራውን ከተረከበ በኋላ ብራይተንን በሜዳው ያስተናግዳል። ቀጥሎም ኃያሎቹን ማንችስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል እና ቼልሲን ይገጥማል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59249764 +health በኢትዮጵያ የጠፋ መድኃኒት የሚያፈላልገው መተግበሪያ ቤዛዊት በዕድሜ የገፉ እናቷ የደም መርጋት በሽታ ያሰቃያቸዋል፡፡ በጤና እንዲቆዩ ሪቫሮክሳባን የሚባል መድኃኒት ሳያቋርጡ መውሰድ ነበረባቸው፡፡ ይህ መድኃኒት እየተገባደደ ሲመጣ ቤዛዊት እንደተለመደው ለመግዛት ወጣች፡፡ ወትሮ በቀላሉ ታገኘው የነበረው ሪቫሮክሳባን ከየት ይምጣ፡፡ ዮሐንስ-አራት መንታ-ሰባራ ባቡር አካባቢ ይገኛል አሏት፡፡ አልሆነም፡፡ ቀይ መስቀል ሞክሪ ተባለች፡፡ አልሆነም፡፡ ከነማ ተሰለፈች፡፡ አልሆነም፡፡ ወጣች ወረደች፡፡ ጠዋት ወጥታ፣ ማታ ገባች፡፡ አልሆነም፡፡ የመድኃኒት ደላሎችን ሳይቀር ተማጸነች፡፡ ከየትም ሊገኝ አልቻለም፡፡ መድኃኒቱ ግን የት ገባ? ምንም አማራጭ አልነበራት፤ አውስትራሊያ የሚገኝ የሩቅ ዘመድ ማስቸገር የግድ ሆነ፡፡ ለካንስ መድኃኒት ከውጭም ቢሆን ለማስገባት ቀላል አልነበረም፡፡ ዲኤችኤል፣ ፌዴክስ እና ሌሎች የጥቅል ዕቃ ተላላኪ ኩባንያዎች፣ በነርሱ በኩል መድኃኒት ለማስላክ ከመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ደብዳቤ ይፈልጋሉ፡፡ ሌላ መከራ፡፡ ሌላ ስቃይ፡፡ ቀን እየገፋ ሲመጣ ቤዛዊት ተጨነቀች፡፡ ምክንያቱም ���ድኃኒቱ ከተገባደደ እናቷ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ፡፡ መፍጠን አለባት፡፡ በመጨረሻ በሰው በሰው፣ ከብዙ የስልክ ልውውጦች በኋላ፣ ከብዙ ተማጽኖ በኋላ፣ ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ እየበረረች በነበረች አንዲት በጎ ፈቃደኛ በኩል መድኃኒቱ ደረሰላት፡፡ የእናቷን ሕይወትም ታደገች፡፡ ይህ የመድኃኒት ፍለጋ እሽክርክሪት የቤዛዊት ብቻ አይደለም፡፡ በርካቶች በየቀኑ ይኖሩታል፡፡ የሚሰወሩት መድኃኒቶች በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከውጭ ምንዛሬ መመናመን ጋር ተያይዞ መድኃኒቶች ድንገት ይሰውሩ ይዘዋል፡፡ መንግሥት ለምግብና መድኃኒት የውጭ ምንዛሬን አይሰስትም፡፡ ኾኖም ግን ይህ መድኃኒቶች እንደልብ እንዲገኙ አላስቻለም፡፡ ደላሎች ደብቀው አስወድደው ይሸጧቸዋል ይባላል፡፡ የጨነቀው ቤተሰብ የትኛውንም ዋጋ ከፍሎ እንደሚገዛቸው ያውቃሉ፡፡ በሰው ችግር ያተርፋሉ፡፡ አሁን አሁን የጠፉ መድኃኒቶች ብቻ አይደሉም፣ የሚገኙትም የት እንደሚገኙ ማወቅ ጊዜና ጉልበትን ይጠይቃል፡፡ በአዲስ አበባ ሺህ ፋርማሲዎች አሉ፡፡ የሚፈልጉት መድኃኒት ወይ ቦሌ ወይም ጉለሌ አንድ ፋርማሲ መደርደሪያ ላይ ቁጭ ብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ሁሉን ፋርማሲ አዳርሶ ይሆናል እንዴ? በዚህ ሕዝብ ጤፍ በሆነበት ከተማ ከጦር ኃይሎች-ሲኤምሲ፣ ከቦሌ-ሸጎሌ ለመድረስ ግማሽ ቀን አይበቃም፡፡ ይህን ችግር መነሻ አድርጎ ታዲያ አንድ የጤና ድርጅት መፍትሄ ፍለጋ ተነሳ፡፡ መድኃኒቶችን የሚያፈላልግ ድረ ገጽ ፀነሰ፡፡ ድረ ገጹ የስልክ መተግበሪያን ወለደ፡፡ የስልክ መተግበሪያው የጥሪ ማዕከልን ፈጠረ፡፡ ለምን ሁሉንም መድኃኒቶች ወደ አንድ ቋት አስገብተን የሕዝብን እንግልት አንታደግም ያለው ይህ ድርጅት ማን ነው? የመድኃኒት ዝርዝሮችን በስልክ ‹‹ጤናዎ›› የሞባይል መተግበሪያ የጤና ጥበቃ ከፍተኛ ተጠሪ በተገኙበት በሸራተን አዲስ የተመረቀው ከወራት በፊት ነበር፡፡ ኬ.ኤም.ኤስ ሄልዝ ትሬዲንግ ይባላል ድርጅቱ፡፡ ባለአክሲዮኖቹ በኢትዮጵያ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝና አሜሪካ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮያዊያን ናቸው፡፡ ገሚሶቹ የድርጅቱ መሥራቾች ታዲያ አገር ቤት በዚሁ የጤና ዘርፍ የተሠማሩ ባለሙያዎች መሆናቸው ለዚህ ትርምስምሱ ለወጣ የጤና ሥርዓት መፍትሄ እንዲሹ ሳይገፋፋቸው አልቀረም፡፡ ይህም ካለፉበትና በየቀኑ ከሚያስተውሉት ችግር ተነስተው ለማኅበረሰብ መፍትሄ ለመስጠት አግዟቸዋል፡፡ የዚህ ሐሳብ አፍላቂና የድርጅቱ መሥራች ዶ/ር ሲሳይ አበበ፣ በሠሩባቸው ሐኪም ቤቶች ሁሉ በተደጋጋሚ አንድ ነገር አስተዋሉ፡፡ ‹‹ታማሚዎች ተመልሰው መጥተው ያዘዝኩላቸውን መድኃኒት ማግኘት እንዳልቻሉ ይነግሩኝ ነበር›› ይላሉ፡፡ ይህ ሁኔታ መደጋገሙ ታዲያ ዶ/ር ሲሳይ የመተግበሪያውን ሐሳብ እንዲያብሰለስሉ ምክንያት ሆናቸው፡፡ ለመሆኑ የጤናዎ መተግበሪያ ተግባር ምንድነው? በአጭሩ ለማስቀመጥ ደንበኛው የሚፈልገው መድኃኒት የት እንዳለ ይጠቁመዋል፡፡ ይህን የሚያደርገው በስልክ መተግበሪያ በመጠቀም ነው፡፡ መተግበሪያው አሠራሩ ከነ ኡበር፣ ራይድ ወዘተ የታክሲ ማሰሻ መተግበሪያዎች ጋር ተመሳሳይ ይመስላል፡፡ መጀመርያ ለደንበኛው፣ ካለበት በ500 ሜትር ራዲየስ ያሉ መድኃኒት ቤቶችን ያሳየዋል፡፡ ወይም ደግሞ መድኃኒት ፈላጊዋ ካለችበት ሆና በከተማው ያሉ መድኃኒት ቤቶቹን እያማረጠች በመተግበሪያው በምናብ ፋርማሲዎች ውስጥ ትዘልቃለች፡፡ የመድኃኒት ዝርዝራቸውን መመልከት ትችላለች፡፡ የምትፈልገው መድኃኒት መኖሩን ስታረጋግጥ ደግሞ ዋጋቸውን ማመሳከር ይቻላታል፡፡ ይህ ነው ‹‹የጤናዎ የስልክ መተግበሪያ›› ተግባር፡፡ ይህ መተግበሪያ በከፊል ሥራ ጀምሯል፡፡ የመረጃ ቋቱን ብዛ���ና ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ ነው፡፡ ‹‹የተገልጋዩን ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ ከብክነት መታደግ ነው ቀዳሚው ፍላጎታችን›› ይላሉ ዶ/ር ሲሳይ አበበ፡፡ ዶ/ር ሲሳይ የኬ.ኤም.ሲ ሄልዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ ጤናዎ መተግበሪያ ታዲያ በስልክ ብቻ የሚገኝ አገልግሎት አይደለም፡፡ ዘመናዊ ስልክ ላልታደሉና ከቴክኖሎጂ ላልተዋወቁ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሌላ አማራጭ አለው፡፡ 24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ 9456 የጥሪ ማዕከል፡፡ ሐኪምና ታካሚን ማገናኘት የጤናዎ መተግበሪያ ዋናው ተግባሩ የትኞቹ መድኃኒቶች በየትኛው ፋርማሲ ውስጥ ይገኛሉ የሚለውን መጠቆም ይሁን እንጂ ሌሎች ተጓዳኝ አገልግሎቶችም አሉት፡፡ ለምሳሌ በግል ጤና ጣቢያ ለመታከም የሚፈልግ ተገልጋይ የት ሆስፒታል ማን የሚባል ስፔሻሊስት መቼ እንደሚገኝ ማወቅ ቢፈልግ ይህን መረጃ ከዚሁ ማግኘት ይችላል፡፡ በዚህ መተግበሪያ ውስጥ 80 የሚሆኑ ሐኪሞች፣ በተለያየ ስፔሻላይዜሽን ያሉ፣ ማንነታቸውና የሥራ ልምዳቸው ተካቷል፡፡ በቀጣይ ዓመታትም በርካታ ሐኪሞች የዚሁ መተግበሪያ አባል ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ማለት አንድ ታካሚ ሐኪሙን ከተገቢ ምክር ጋር የመምረጥ፣ ካለበት ሆኖ ቀጠሮ የማስያዝ ዕድልን ይሰጠዋል፡፡ ዶ/ር ሲሳይ እንደሚሉት በአሁኑ ጊዜ ድርጅታቸው በየትኛውም የግል ሆስፒታል የታካሚና የሐኪም ቀጠሮን የማስያዝ ተጨማሪ ሥራን ይሠራል፡፡ ‹‹ታካሚዎች የትኛውን ሐኪም፣ መቼ፣ የት ክሊኒክ ማግኘት እንደሚችሉ ማማከር ብቻ ሳይሆን ቀጠሮም እንይዝላቸዋለን፡፡ በሆስፒታል እየሄዱ ወረፋ መያዝ፣ መንገላታትን ለማስቀረት ነው እየሞከርን ያለነው›› ይላሉ፡፡ አገር ውስጥ የሌሉ መድኃኒቶችን ፍለጋ በቀድሞ ጊዜ የምሽት ተረኛ መድኃኒት ቤቶች በየቀኑ በብሔራዊ ራዲዮ ይነገሩ ነበር፡፡ ልክ ዛሬ የአየር ትንበያና ስፖርት ዘገባዎች ከዜና በኋላ እንደሚታወጁት ሁሉ፡፡ ዛሬ ይህ ነገር መኖሩን እንጃ፡፡ ዜጎች አጣዳፊ የመድኃኒት ጥያቄ ቢገጥማቸው እንግልታቸውን ለማስቀረት ያለመ ነበር ነገሩ፡፡ ያን ጊዜ ጥቂት ፋርማሲዎች ነበር በከተማው የነበሩት፡፡ አሁን መድኃኒት ቤቶች እንደ አሸን በፈሉበት ዘመን፣ ኮንዶሚንየም ግቢ ድረስ ዘልቀው የነዋሪዎች ጎረቤት መሆን በቻሉበት ዘመን ነገሩ ያን ያህልም አልተቃለለም፡፡ ለምን? መድኃኒት ቤቶችን እንጂ መድኃኒቶችን ማግኘት አልተቻለም፡፡ ይህ ሀቅ የጤናዎ መተግበሪያ ፈጣሪዎችም የሚክዱት አይደለም፡፡ በቂ መድኃኒቶች በሌሉበት ፋርማሲ መጠቆም ምን ይፈይዳል? በገበያ የሚገኙት መድኃኒት ቤቶችማ ወትሮም የትም የሚገኙ ናቸው፡፡ የማይገኙት ደግሞ የትም አይገኙም፡፡ ዶ/ር ሲሳይ ይህን ሁኔታ ድርጅታቸው እንደሚረዳ ለቢቢሲ አስረድተው ለዚህም ሲባል መድኃኒት ከውጭ የማስመጣት ፍቃድ መውሰዳቸውን አብራርተዋል፡፡ ለጊዜው ሰዎች ከገበያ ያጧቸውን መድኃኒቶች በተናጥል ጥያቄ ሲያቀርቡልን ከውጭ ለማስመጣት ዝግጅት ጨርሰናል ይላሉ፡፡ ዶ/ር ሲሳይ እንደሚሉት ታዲያ የጤና ድርጅቱ ሥራ በመድኃኒት አድራሻና ዋጋ ጥቆማ የሚቆም አይደለም፡፡ ለምሳሌ ኤምአርአይ ወይም ሌላ የኢሜጂንግ ወይም የላቦራቶሪ አገልግሎት የሚፈልግ ደንበኛ በአቅራቢያው ይህን አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ስለመኖር አለመኖሩ፣ የዋጋ ዝርዝሩን እና ለአገልግሎቱ የሚጠየቀውን ተያያዥ መረጃ ሁሉ አቀናጅቶ አስቀድሞ መረጃ የማቀበል ተግባርም በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ በጤና ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ መልካሙ ይህ አዲስ የጤና መተግበሪያ የተገልጋይ እንግልትን፣ ጊዜና ጉልበትን በመቆጠብ ሁነኛ ሚና እንደሚጫወት መተግበሪያው በተመረቀበት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው አድናቆታቸውን ገልጠው ነበር፡፡ ይህ መተግበሪያ፣ የጥሪ ማዕከልና የጤና ድረ ገጽ ኅብረተሰብን በማገዝ ረገድ ሁነኛ ሚና ስላለው መሥሪያ ቤታቸው አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንደሚያደርግም ቃል ገብተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ብቅ ጥልቅ እያሉም ቢሆን የጤና ዘርፉን ለማዘመን የተሞከሩ ሙከራዎች እንደነበሩ የጠቀሱት ዶ/ር ሲሳይ በበኩላቸው ጤናዎ መተግበሪያ አስተማማኝና ዘላቂ አገልግሎት ለመስጠት ከሐኪሞችና ከጤና ተቋማት ጋር መጠነ ሰፊ ግንኙነት መፍጠሩንና፣ በእስካሁኑ አጭር ተሞክሮም ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች እንዳዩም ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡ የዚህ አገልግሎት ልዩ ባህሪም የግል ዘርፉን የጤና አገልግሎት በአንድ ጥላ ጠቅልሎ መያዙ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ይህም ማለት ሐኪም ቀጠሮ ከማስያዝ ጀምሮ እስከ መድኃኒት ዋጋ ድረስ ዲጂታል በሆነ አሠራር ቀላል ማድረግን፣ በዚህም የጤና ሥርዓቱን ማዘመንን ያካተተ ነው፡፡ የዲጂታል ነገር፣ እስኪዘልቅና ዘላቂነቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዳዲስ ይበል የሚያሰኙ ሐሳቦች ይመነጫሉ፡፡ ወዲያው ይከስማሉ፡፡ አንዱ ምክንያት የኅብረተሰቡ ለውጡን ለመቀበል ዳተኛ መሆን ነው፡፡ ወደ ሕዝብ አይዘልቁም፡፡ ቢዘልቁም ዘላቂነት አይኖራቸውም፡፡ በዚህ ረገድ ጤናዎ መተግበሪያ የት ርቀት ይሄድ ይሆን? ዶ/ር ሲሳይ አንዱ ፈተና ይኸው መሆኑን አውስተዋል፡፡ ወደ ዲጂታል ሄልዝ ለመሸጋገር ለብዙ ሰዎች ቀላል እንዳልሆነ በዚህ አጭር ቆይታ ራሱ የተረዱት ዶ/ር ሲሳይ፣ ድርጅታቸው ታዲያ ሕዝቡን ከአግልግሎቱ ጋር በቀላሉ ለማስተዋወቅ በማሰብ ለጊዜው ማንኛውንም ክፍያ አየጠየቁ አለመሆኑን አብራርተዋል፡፡ ‹‹ለጊዜው ከመቶ በላይ መድኃኒት ቤቶች ከኛ ጋር ለመሥራት ተመዝግበዋል፡፡ እነዚህ መድኃኒት ቤቶች አዲስ መድኃኒት ሲያስገቡም ሆነ ነባር መድኃኒቶችን ሽጠው ሲጨርሱ በኛ ሲስተም እየገቡ አሁናዊ መረጃን ለኅብረተሰቡ ያቀብላሉ፡፡ ሌሎችንም ለማሳመን እየሞከርን ነው›› ይላሉ ዶ/ር ሲሳይ፡፡ በኢትዮጵያ ከ60 ሚሊዮን የሚልቅ ሞባይል ተጠቃሚ ቢኖርም፣ የኢንተርኔት ተደራሽነቱና ዘመናዊ ስልክ ተጠቃሚው ቁጥር የዚህ ሲሶውን እንኳ አይሞላም፡፡ እርግጥ በአሁን ዘመን ብዙ አገልግሎቶች ወደ ሞባይል እየገቡ ነው፡፡ ገንዘብ ዝውውርም ከወረቀት ወደ ሞባይል እየተሸጋገረ ነው፡፡ ይሁንና የሕዝብን እምነት ማግኘት በቀላል የሚገኝ እሴት አይደለም፡፡ ዶ/ር ሲሳይም ይህን አይክዱም፤ ‹‹ወደ ዲጂታል ሽግግር ጉዞው ቀላል እንደማይሆን አውቀን ነው የተነሳነው፤ በኛ አገር ዲጂታል ቴክኖሎጂ ገና እያደገ ነው፡፡ ሰዎች እምነት ገና አላዳበሩም፡፡ ይህ ነገር ጊዜ ሊወስድ ይችላል›› ብለዋል፡፡ ይህን ለማገዝም ነው የሚመሩት ድርጅት ለሁሉም አገልግሎቶቻቸው ለጊዜው ክፍያን ላለመጠየቅ የወሰነው፡፡ ፈውስን ፍለጋ ወጥቶ በሽታን መሸመት ወደ ዲጂታል ዓለም ለመግባት እዚያ እዚህም የሚታዩት ሙከራዎች ከብዙ በጥቂቱ ይሁንታን ያገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ካየነው ሁሉ ለጊዜው በትራንስፖርት ዘርፍ የሰመረ ይመስላል፡፡ በፋይናንስ ዘርፍም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተስፋ ሰጪ ምልክቶች ታይተዋል፡፡ በጤና ዘርፍ ግን እምብዛም አይደለም፡፡ እርግጥ የሰዎች የጤና ሰነድ ከገንዘብም በላይ ከለላን ይሻል፡፡ ደኅንነቱ የተጠበቀ የመረጃ አያያዝን መከተል ይፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ ብዙ ከተሠራ ከብዙ ትዕግስት ጋር ወደፊት መንፏቀቅ ይቻል ይሆናል፡፡ በተለይ የኅብረተሰብን ችግር ለመፍታት ያለሙ፣ መፍትሄ ላይ መሠረት ያደረጉ መተግበሪያዎች ሲሳኩም የዛኑ ያህል ሕይወት ዘዋሪ ናቸው፡፡ የኬ.ኤም.ኤስ ሄልዝ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሲሳይ አበበ ደጋግመው እንደሚሉት፣ ሰዎች ፈውስ ፍለጋ ወጥተው፣ በሽታን ሸምተው መመለስ የለባቸውም፡፡ ‹‹ጤናዎ ሁለገብ መተግበሪያ›› የጤናው ዘርፍ ዲጂታል ሽግግር ረዥሙ ጉዞ አንድ እርምጃ ይሆን? https://www.bbc.com/amharic/61218340 +politics የቀድሞ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት በአንድ ጉባኤ ላይ 'ከሃዲ' ተባሉ "የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት በአንድ ሃይማኖታዊ ጉባኤ ላይ በሚናገሩበት ወቅት ከተሳታፊዎች ስድብ ተወርውሮባቸዋል። አንዳንዶች ""ከሃዲ"" በሚል የሰደቧቸው ሲሆን ""ነፃነት"" የሚሉ ቃሎችም ተሰምተዋል። ፖለቲከኛው በያዝነው ሳምንት አርብ በኦርላንዶ ግዛት በነበረው የፌይዝ ኤንድ ፍሪደም ኮሊሸን ንግግር እያደረጉ በነበረ ወቅት ነው ይሄ የደረሰባቸው ተብሏል። የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ለአሸናፊው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዕውቅና መስጠታቸውንም ተከትሎ ነው ይህንን ያስተናገዱት ተብሏል። በተሳዳቢዎቹ ምክንያት ፖለቲከኛው ንግግራቸውን እንዳላቆሙና ለ28 ደቂቃም የቆየ ንግግርም አድርገዋል። ተሳዳቢዎቹም መሃል ላይ በፖሊስ እንዲወጡ ተደርገዋል። በዚህ ንግግግራቸው ወቅት የዲሞከራቱን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፖሊሲዎች በመተቸት የተሰናባቹን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን አወድሰዋል። በጥር ወር ላይ ፕሬዚዳንት ትራምፕን ጨምሮ በርካታ ደጋፊዎቻቸው በወቅቱ የምክር ቤቱ የበላይ የነበሩትን ማይክ ፔንስን ፕሬዚዳንት ባይደን ያሸነፉበትን ሰርቲፊኬት በኮንግረሱ እውቅና እንዳይሰጡት ጠይቀዋቸው ነበር። ማይክ ፔንስ ይህንን ለማድረግ ስልጣኑ የለኝም ቢሉም በርካታ የትራምፕ ደጋፊዎች ተናደውባቸዋል። በምርጫው ውጤት የተናደዱ የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች በጥር ወር ላይ በካፒቶል ህንፃ ሰብረው በመግባት ከፍተኛ ሁከት ማስከተላቸው ይታወሳል። ጥር 6፣ በተለምዶ ""የካፒቶል ሒል ነውጥ"" ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የሁለቱ ምክር ቤቶች መሰብሰብያና በርካታ የመንግሥት አስተዳደር ቢሮዎችን ሰብረው በመግባት የዲሞክራሲ ተምሳሌት ተደርጎ የሚታየውን ስፍራ እንዲሁም የአገሪቱን ስምና ክብር የሚያጎድፍ ተግባር የፈጸሙበት ዕለት ነው። በካፒቶል የደረሰውንም ጥቃት ተከትሎ ማይክ ፔንስ ከትራምፕ ራሳቸውን አግልለዋል። የካፒቶሉን ጥቃት ተከትሎ ትራምፕ በምክር ቤቱ ያለመከሰሰስ መብታቸው እንደተገፈፈ ይታወሳል። በአሜሪካ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ በመከሰስ የመጀመርያ ሆነው የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ አመጽን ቀስቅሶ ከመምራት ክስ ነጻ መደረጋቸው ይታወሳል። ማይክ ፔንስ ነውጠኞቹን የተቃወሙ ሲሆን የፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን በዓለ ሲመት ላይ ተገኝተዋል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመቱ ላይ አልተገኙም። ነገር ግን አርብ እለት በነበረው ንግግራቸው ማይክ ፔንስ የቀድሞ አለቃውን በስልጣን ላይ ያሳኩዋቸውን ነገሮች ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57534153 +sports ዩሮ 2020፡ እግር ኳስ ተጫዋቾች በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የማስታወቂያ መጠጦችን ካነሱ ሊቀጡ ይችላሉ "በቅርቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ፖል ፖግባ እንዳደረጉት ተጫዋቾች በጋዜጣዊ መግለጫዎች ወቅት የስፖንሰሮችን መጠጦች ከጠረጴዛ አንስተው ከካሜራ ካራቁ በዩሮ 2020 የሚሳተፉ ቡድኖቻቸው የገንዘብ ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላል ተባለ። ሰኞ ዕለት የፖርቹጋሉ አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሁለት የኮካ ኮላ ጠርሙሶችን ከፊቱ በማንሳት ሰዎች ውሃ እንዲጠጡ አበረታቷል። በቀጣዩ ቀን ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታይ ሆነው ፈረንሳዊው አማካይ ፖግባ የሄኒከን ቢራ ጠርሙስን ከጠረጴዛው ላይ አንስቷል። ጣሊያናዊው ማኑዌል ሎካቴሊ ደግሞ ረቡዕ ዕለት ኮካ ኮላ አንስቶ በውሃ ተክቶታል። ሐሙስ ዕለት ""የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (ዩኤፋ) ተሳትፊ ቡድኖች ስፖንሰር አድራጊዎች ለውድድሩ መካሄድ ሚና እንዳላቸው አስታውሶ በመላው አውሮፓ ወጣቶችን እና ሴቶችን ጨምሮ የእግር ኳስ ዕድገትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው"" ብለዋል የውድድሩ አዘጋጆች። የዩኤፋ የዩሮ 2020 የውድድር ዳይሬክተር ማርቲን ካለን በበኩላቸው ተጫዋቾች ""የውድድር ደንቦችን ለመጠበቅ በፌዴሬሽናቸው በኩል"" የውል ግዴታቸው አለባቸው ብለዋል። ሆኖም እንደ ፖግባ ያሉ ተጫዋቾች በሐይማኖታዊ ምክንያቶች ያደረጉት በመሆኑ እንደሚረዱት ተናግረዋል። ቡድኖች የውል ደንቦቻቸውን እንዲያስታውሱ የተደረገ ሲሆን ካለን እንዳሉት ደግሞ የዲሲፕሊን እርምጃም ሌላው ""አማራጭ"" ነው። ዩኤፋ በቀጥታ ተጫዋቾችን የመቅጣት ፍላጎት የሌለው ሲሆን ማንኛውም ቅጣት የብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ውሳኔ ነው። ""ዩኤፋ ተጫዋቾችን በቀጥታ እየቀጣ አይደለም። ይህን ሁሌም በተሳታፊ ብሔራዊ ማኅበር በኩል ይከናወናል። ከዚያ በኋላ እነሱ ወደ ተጫዋቾቹ የሚሄዱ ከሆነ ማየት ይችላሉ። ለጊዜው በቀጥታ ወደ ተጫዋቾቹ አንሄድም"" ብለዋል ካለን። ""በተሳታፊ ፌደሬሽኖች የተፈረሙ ደንቦች አሉን"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57519046 +health በዓለማችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የመንትዮች ቁጥር ጨምሯል "ዓለማችን ከዚህ በፊት አይታው በማታውቀው መጠን በመንትዮች እየተሞላች እንደሆነ አጥኚዎች አረጋገጡ። በየዓመቱ 1.6 ሚሊዮን መንታ ልጆች ይወለዳሉ። ይህ ማለት ከ42 ሕፃናት መካከል መንታዎች አሉ ማለት ነው። ዘግይቶ ማርገዝና አንዳንድ የሕክምና መላዎች ከ1980ዎቹ በኋላ የመንታ ልጆች የውልደት መጠንን በሦስት እጥፍ እንዲያድግ አድርጎታል። ነገር ግን የመንታ ልጆች ውልደት መጠን ከዚህ በኋላ እንደሚቀንስ ይገመታል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት አንድ ልጅ ብቻ ወልዶ ማሳደግ አዲሱ የሕይወት ዘይቤ እየሆነ መምጣቱ ነው። ሂዩማን ሪፕሮዳክሽንስ የተሰኘው ጋዜጣ ላይ የወጣ ዘገባ እንደሚያሳየው ባለፉት 30 ዓመታት የመንታ ልጆች ዕድገት እስያ ውስጥ 32 በመቶ ሲጨምር ሰሜን አሜሪካ በ71 በመቶ ተመንድጓል። አጥኚዎቹ በፈረንጆቹ ከ2010-15 ባለው ጊዜ ከ165 አገራት የሰበሰቡትን ጥናት ከ1980-85 ካለው ጋር አነጻጽውታል። በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ከአንድ ሺህ አዲስ የሚወለዱ ሕፃናት የመንታዎች ቁጥር ጨምሯል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከአንድ ሺህ ሕፃናት መካከል 12 መንታዎች ይወለዳሉ። በአፍሪካ የሚወለዱ የመንታ ልጆች መጠን በፊትም ባለፉት 30 ዓመታት ከፍተኛ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የሕዝብ ብዛት ነው ይላሉ አጥኚዎች። አፍሪካና እስያ በዓለማችን ካሉ መንታዎች 80 በመቶውን በመያዝ ቀዳሚዎቹ አህጉራት ናቸው። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ክርስቲያን ሞንደን ለዚህ አንድ ምክንያት አሉ ይላሉ። ""በአፍሪካ የመንታ ልጆች ቁጥር እየጨመረ ያለበት አንዱ ምክንያት ከሁለት የተለያዩ እንቁላሎች መወለዳቸው ነው።"" ""ይህ የሚሆንበት አንደኛው ምክንያት በአፍሪካ ሕዝብና በሌላው ሕዝብ መካከል ያለው የዘረ-መል (ጄኔቲክ) ልዩነት ሊሆን ይችላል።"" የመንታ ልጆች ውልደት መጠን በአውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካና ኦሺኒክ አገራትም ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ ነው። ለዚህ እንደምክንያት የሚቆጠረው ከ1970ዎቹ በኋላ እየተለመደ የመጡት ሳይንሳዊ መላዎችን ተጠቅሞ መንታ ልጆች መውለድ መለመዱ ነው። ሴቶች ዘግይተው ልጅ መውለዳቸው፣ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች መበራከት፣ እንዲሁም የውልደት መጠን መቀነስ ለመንታ ልጆች ውልደት መጠን መጨመር አስተዋፅዖ እያበረከቱ ነው። ነገር ግን አሁኑ ትኩረቱ አንድ ልጅ ብቻ ወደማሳደግ እየዞረ መጥቷል፤ ይህ ተመራጭ ነው ይላሉ ፕሮፌሰር ሞንደን። ፕሮፌሰር አንድ ልጅ ብቻ ለመውለድ መሞከር መልካም ነው ብለው የሚያስቡት መንታ ልጆችን የሚያረግዙ እናቶች በእርግዝና ወቅት፣ በወሊድ ጊዜና እንዲሁም ከወሊድ በኋላ ብዙ ችግር እንደሚያጋጥማቸው ጥናቶች ስለሚጠቁሙ ነው። ከወሊድ በኋላም ቢሆን በተለይ ደግሞ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት መንታ ልጆችን ማሳደግ ቀላል አይደለም። ለምሳሌ ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ክፍል ውስጥ በርካታ መንታ ልጆች በመጀመሪያው ዓመት አብረዋቸው የተወደለዱ ልጆችን ያጣሉ። ወደፊት ለሚታየው የመንታ ልጆች ውልደት መጠን ቻይናና ሕንድ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚችል ይታመናል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56372875 +business የባንክና የኢንሹራንስ ዘርፍ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ የተተዉ ይሆናል "ኢትዮጵያ የባንክና የኢንሹራንስ ተቋማትን ለውጪ ባለሃብቶች ተሳትፎ ክፍት እንደማታደርግ ሮይተርስ ጉዳዩን በሚመለከት የተዘጋጀን ረቂቅ ሕግን ዋቢ አድረጎ ዘገበ። ኢትዮጵያ የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ለውጪ ባለሃብቶች ክፍት ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነች ቢሆንም የባንክና የኢንሹራንስ ዘርፎች ግን አሁንም ዜጎቿ ብቻ የሚሳተፉባቸው መስኮች ሆነው እንዲቆዩ ልታደርግ መሆኑን ሮይተርስ አየሁት ባለው ረቂቅ ሕግ ላይ ሰፍሯል ብሏል። የተለያዩ የውጪ ባለሃብቶችና ተቋማት ኢትዮጵያ ክፍት ታደርጋቸዋለች ተብለው የሚጠበቁ ተቋማትን ለመግዛትና በመንግሥት እጅ ስር ብቻ ተይዘው በነበሩ ዘርፎች ላይ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት እየገለጹ ነው። • እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት • ""ኢስላማዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል?"" የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግና ኢትዮጵያን ወደ መካከለኛ ገቢ ለማሳደግ በመንግሥት ቁጥጥር ስር የነበሩ ዘርፎች ላይ የውጪ ባለሃብቶች ክፍት እንደሚሆኑ ተገልጾ ነበር። ሮይተርስ የጠቀሰው ረቂቅ የኢንቨስትመንት ሕግ ላይ እንዳመለከተው የባንክ፣ የኢንሹራንስ፣ አነስተኛ የቁጠባና የብድር የገንዘብ ተቋማት ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ የተተዉ ዘርፎች ይሆናሉ። የአገሪቱ የባንክ ዘርፍ በአፍሪካ በመንግሥት ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግ ነው። ባለፈው ሐምሌ የአገሪቱ ምክር ቤት አምስት ሚሊዮን ለሚሆኑ የሌላ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የባንኮችን አክሲዮን ለመግዛት እንዲችሉ የሚፈቅድ ሕግ ሲያወጣ፤ በበርካቶች ዘንድ ቀስ በቀስ ዘርፉ ለውጪ ባለሃብቶችም ክፍት ሊደረግ ይችላል የሚል ተስፋን ፈጥሮ ነበር። • በስህተት የተሰጣቸውን 1 ሚሊየን ብር የመለሱት መምህር • እውን ድህነትን እየቀነስን ነው? በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተወሰዱ ካሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች መካከል ትላልቆቹን የስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎች ወደ ግል ይዞታነት የማዘዋወሩ እርምጃ ከወራት በኋላ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም መንግሥት ለሁለት የሞባይል ስልክ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች ፈቃድ ለመስጠትና የመንግሥት ንብረት ከሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ላይ ደግሞ የተወሰነ ድርሻን ለባለሃብቶች ለመሸጥ ዕቅድ አለው። በሮይተርስ የተጠቀሰው ረቂቅ የኢንቨስትመንት ሕግ በቀጣዮቹ ሁለት ወይም ሦስት ሳምንታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮጵያ በፍጥነት እየጨመረ የሚሄድና ወጣት ሕዝብ ያላት ሲሆን ኢኮኖሚዋም ከአስር ዓመታት በላይ በሁለት አሃዞች ሲያድግ ቆይቷል። ነገር ግን በአገሪቱ የሚስተዋለው ብሔርን መሰረት ያደረገ ውጥረትና ግጭት ኢኮኖሚው ላይ ስጋትን ፈጥሯል።" https://www.bbc.com/amharic/news-50641297 +sports ሩሲያ ያሰረቻትን የቅርጫት ኳስ ተጫዋች አሜሪካ ባለእስረኛ የመለዋወጥ ፍላጎት እንዳላት ተነገረ "ሩሲያ ጉዳይዋ በፍርድ ቤት እየታየ የምትገኘውን ታዋቂ አሜሪካዊት የቅርጫት ኳስ ተጫዋችን አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ እስረኛ ለመለዋወጥ ፍላጎት እንዳላት ተነገረ። አደንዛዥ ዕጽ ይዛ ተገኝታለች በሚል ከወራት በፊት ሩሲያ ውስጥ በእስር ላይ የምትገኘውን የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ ግሪነር፣ በሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ተፈርደቦት አሜሪካ ውስጥ በሚገኘው ቪክቶር ባውት የመቀየር ፍላጎት በሩሲያ በኩል እንዳለ ስማቸው ያልተጠቀሰን ባለሥልጣን ጠቅሶ የሩሲያ የዜና ወኪል ዘግቧል። በቀጠሮ ፍርድ ቤት ቀርባ የነበረችው የቅርጫት ኳስ ተጨዋቿ ተጨማሪ የአንድ ወር የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባታል። የ31 ዓመቷ ብሪትኒ ግሪነር በሩሲያ ከነበራት ጨዋታ በኋላ ወደ አገሯ ስትመለስ ካናቢስ የተባለ ዕጽ ሻንጣ ውስጥ ተግኝቶባታል በሚል ነበር በቁጥጥር ስር የዋለችው። የአሜሪካ ባለሥልጣናት የስፖርተኛዋ እስር ተገቢ አይደለም፤ መለቀቅ አለባት በማለት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርጥ ሴት የቅርጫት ኳስ ተጨዋች ከሚባሉት አንዷ የሆነችው ግሪነር በቀረበባት ክስ ጥፋተኛ ከተባለች እስከ 10 ዓመት የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃታል ተብሏል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ተጨዋቿ ከሞስኮ ወጣ ብላ በምትገኝ ከተማ በነበራት ችሎት ላይ የቆንስላ ኃላፊዎች መታደማቸውን እና እርሷንም እንዳነጋገሯት ገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሩሲያ በእስር ላይ ያለችውን ብሪትኒ ግሪነር አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ እስር ቤት ባለ ሩሲያዊ ታሳሪ የመቀየር ፍላጎት እንዳላት ተሰምቷል። ""የሞት ነጋዴው"" በሚለው መጠሪያ በስፋት የሚታወቀው ቪክቶር ባውት በሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ነበር የተፈረደበት። ቦውት እንደ አውሮፓውያኑ በ2008 ታይላንድ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሎ ነው ለአሜሪካ ተላልፎ የተሰጠው። ግለሰቡ በኮሎምቢያ የሚገኙ አማጽያንን በማስታጠቅ የአሜሪካ ዜጎች ላይ ጥቃት እንዲያደርሱ አድርጓል የሚል ክስ ቀርቦበት ነበር እንደ አውሮፓውያኑ በ2012 በኒው ዮርክ ውስጥ የ25 ዓመታት እስር የተፈረደበት። ባለፈው የካቲት ወር ሩሲያ ውስጥ በተካሄደ የቅርጫት ኳስ ውድድር ላይ ተሳትፋ ወደ አገሯ ልትመለስ ስትል አየር ማረፊያ ውስጥ የተያዘችው አሜሪካዊቷ ግሪነር፣ ይዛው በነበረው ሻንጣዋ ውስጥ ቅባታማ ሃሺሽ በአነፍናፊ ውሻ እንደተለየ በወቅቱ የሩሲያ ባለሥልጣናት ገልጸው ነበር። ባለሥልጣናቱ የቅርጫት ኳስ ተጨዋቿን መታሰር ያረጋገጡትም ከሳምንታት በኋላ ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-61448051 +health በርካቶች የኮቪድ-19 መከላከያ ላለመከተብ የሚያቀርቧቸው ምክንያቶችና መልሶቻቸው በመላው ዓለም የኮቪድ ክትባት አሰጣጥ ላይ ትልቅ ልዩነት አለ። የክትባት አቅርቦት አሁንም በብዙ አገራት ትልቅ ችግር ነው። ነገር ግን ክትባቱ ኖሮም ብዙዎች ለመከተብ ያመነታሉ ወይም ፈቃደኛ አይደሉም። እርስዎ ተከትበዋል? ካልተከተቡ ምክንያትዎ ምንድን ነው? በበርካታ ሰዎች ዘንድ ላለመከተባቸው በስፋት እንደምክንያት የሚነሱ ነገሮችን በማንሳት ይህ ቪዲዮ ምላሽ ይሰጣል። https://www.bbc.com/amharic/news-60140221 +politics """አን ሳን ሱቺ ጥሩ እንክብካቤ እያገኙ ነው""- የምያንማር ጦር" "በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የጨበጠው የምያንማር ወታደራዊ መንግሥት አን ሳን ሱቺ በደል እየደረሰባቸው ነው መባሉን አስተባብሏል። የ76 ዓመቷ የቀድሞው የአገሪቱ መሪ፣ ወታደራዊው አገዛዝ ሥልጣን ከያዘበት ካለፈው ዓመት የካቲት ጀምሮ በአደባባይ አልታዩም። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት የወታደራዊው ኃይል ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ዛው ሚ��� ቱን ናቸው ሱቺ ሰላም ናቸው ያሉት። የምያንማር መንግሥት አሜሪካዊውን ጋዜጠኛ ዳኒ ፎስተርን በ11 ዓመታት እሥር ከቀጣ በኋላ በቀናት ልዩነት በነፃ እንዲለቀቅ መወሰኑ ይታወሳል። ከመፈንቅለ መንግሥቱ ወዲህ በርካታ ጋዜጠኞችና በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በአገሪቱ ለእሥር ተዳርገዋል። ሜጀር ጄኔራል ዛው ሚን ቱ እንደሚሉት አን ሳን ሱቺ ባሉበት እሥር ቤት እንክብካቤ እየተደረገላቸው ነው። ""ከራሷ ሰዎች ጋር ቤት ውስጥ በአንድነት እንድትኖር እኮ ነው የፈቀድንላት። ነገር ግን የቁም እሥር ላይ ትገኛለች"" የሚሉት ቃል አቀባዩ ""የፈለገችውን እንድታገኝና የፈቀደችውን እንድትመገብ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን"" ሲሉ አክለዋል። ሳን ሱቺ በቅኝት ግዛት ዘመን ተግባራዊ ይደረግ በነበረ ሕግ ነው ተከሰው በቁም እሥር ላይ የሚገኙት። አልፎም የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል፤ ዋኪ ቶኪ የተሰኘውን የርቀት መነጋገሪያ ይዘው ተገኝተዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ምንም እንኳ ችሎት ፊት ይቅረቡ እንጂ ክሳቸውን በተለመከተ ያሉት ዘርዘር ያለ ነገር የለም። ለቢቢሲ ቃለ ምልልስ የሰጡት ሜጀር ጄኔራል ዛው ቱን ሚን ጨምረው ባለሥልጣናት አሜሪካዊውን ጋዜጠኛ ለመልቀቅ ሲያስቡ ነበር ብለዋል። ዳን ፌስተር፤ የኢሚግሬሽን ሕግን በመጣስ፣ ከሕገ-ወጥ ሰዎች ጋር በማበርና ወታደራዊው አገዛዝ ከሚያዘው ውጪ በመንቀሳቀስ የ11 ዓመት እሥር ከተጣለበት ከቀናት በኋላ ሰኞ ዕለት ተለቋል። በተጨማሪ ጋዜጠኛው በሽብር ወንጀልና ሥልጣን ላይ ያለን ኃይል ለመጣል በማሴር ተጠርጥሮ ፍርዱን እየተጠባበቀ ነበር። ጄኔራሉ፤ አሜሪካው ጋዜጠኛው ነፃ መሆኑን ተከትሎ ምያንማር በምትኩ የምታገኘው ነገር ይኖር ይሆን ተብለው ተጠይቀው ""ምንም እንደሌለ"" ተናግረዋል። ባለፈው ወር የምያንማር ወታደራዊ አገዛዝ መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወማቸው ምክንያት ለእሥር የተዳረጉ 5 ሺህ ሰዎችን ለመፍታት ቃል ገብቶ ነበር። ቢያንስ 7291 ሰዎች ለእሥር የተዳረጉ ሲሆን የተወሰኑት የተበየነባቸው የተቀሩት ደግሞ ክስ ያለባቸው ናቸው።" https://www.bbc.com/amharic/news-59284875 +politics በቱኒዚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከስልጣናቸው ተነሱ "በመላው ቱኒዚያ የተቀሰቀሰውን ከፍተኛ አመጽ ተከትሎ ፕሬዝደንቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከስልጣና አንስተው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ደግሞ አገዱ። በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች መንግሥት ወረርሽኙን ለመግታት የወሰደውን እርምጃ በመቃወም አደባባይ ወጥተው ቁጣቸውን የገለጹ ሲሆን እሁድ ዕለት ደግሞ ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውም ተገልጿል። ፕሬዝደንት ካኢስ ሳኤድ በአገሪቱ መረጋጋትን ለመፍጠር እሰራለሁ ካሉ በኋላ አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር እንደሚሾሙ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ተቃዋሚዎች ፕሬዝደንቱ ጠቅላይ ሚንሰትሩን ማሰናበታቸው እና ምክር ቤቱን ማገዳቸው ከመፈንቅለ መንግሥት ተይቶ አይታይም እያሉ ነው። ""እነዚህን እርምጃዎች የወሰድነው በአገሪቱ ሰላም እስከሚመለስና አገሪቱን ማዳን እንድንችል በማሰብ ነው"" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት። ትናንት ዕሁድ ምሽት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ሂኬም ሚቺቺ ከኃላፊነታቸው የመነሳት ዜና ከተሰማ በኋላ ዜጎች አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን በዋና ከተማዋ ቱኒዝ ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ተቃዋሚዎችን ተቀላቅለው ታይተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች በተለያዩ ከተሞች ዋና ዋና ጎዳናዎች በመሰባሰብ የገዢው ፓርቲ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ሲገልጹ ተስተውለዋል። በርካቶችም የፓርቲዎው አመራሮች ይውጡልን በማለት ፓርላማውም እንዲፈርስ ጠይቀዋል። የጸጥታ ኃይሎች ተቃዋሚዎች ወደ ፓርላማው ቅጥር ግቢ እንዳይጉ ሲከለክሉና ወደ 'ቦርጊባ' አደባባይ እንዳይሄዱ መንገድ ሲዘጉ ተስተውለዋል። ይህ ጎዳና በአውሮፓውያኑ 2011 ለተቀጣጠለው ጸረ መንግሥት ተቃውሞ ዋነኛ ማዕከል ሆኖ አገልግሎ ነበር። ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ጭምር የተጠቀመ ሲሆን አንዳንድ ሰዎችን ደግሞ በቁጥጥር ስር አውሏል። ይህን ተከትሎም ተቃውሞውም ወደ አብዛኛው የአገሪቱ ከተሞች ተስፋፍቷል። ተቃዋሚዎችም የገዢው ፓርቲ ቢሮዎችን ሰብረው በመግባት ንብረቶችን የሰባበሩ ሲሆን 'ቶውዙር' ውስጥ የሚገኘው ያርቲው አካባቢያዊ ዋና ቢሮም በእሳት አያይዘውታል። ፓርቲው በበኩሉ የሰልፈኞቹን ተግባር በማውገዝ ይህንን አጋጣሚ ወንጀለኛ ዘራፊዎች አገሪቱን ወደ ብጥብጥና መፈራረስ ለመውሰድ እየተጠቀሙበት ነው ብሏል። ምንም እንኳን በዋና ከተማዋ ወጥተው ከተቃዋሚ ሰልፈⶉች ጋር አብረው ቢታዩም ፕሬዝዳንቱ ከዚህ በኋላ አላስፈላጊ አመጽ የሚቀጥል ከሆነ መከላከያ ኃይል ጣልቃ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል። ""ማንኛውም ዜጋ የጦር መሳሪያ የሚጠቀም ከሆነ፣ ጥይት የሚተኩስ ከሆነ የመከላከያ አባላት በጥይት ምላሽ ይሰጣሉ"" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ከአስር ዓመታት በፊት በቱኒዚያ የተቀሰቀሰው አብዮት ተስፋፍቶ የአረብ አገራትንም ያዳረሰ ሲሆን በወቅቱም ከለውጡ በኋላ በርካታ ነገሮች እንደሚቀየሩ ተስፋ ተደርጎ ነበር። ነገር ግን ቱኒዚያ አሁንም ድረስ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በአፍሪካም በኮሮረናቫይረስ በእጅጉ ከተጠቁት አገራት መካከል ትገኝበታለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-57967516 +politics የሕዳሴው ግድብ፡ ኢትዮጵያ ከሕዳሴው ግድብ ሙሌት የሚያደናቅፋት ኃይል እንደሌለ ገለጸች "ኢትዮጵያ በመጭው የክረምት ወራት በታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሙከራ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ኢትዮጵያ ይህን ያለችው በመጭው ክረምት ለሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት ነው። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ከግድቡ ሙሌት እና ግንባታ ጋር ተያይዞ የአሠራር ሂደቱን ""ምንም ዓይነት ኃይል እንደማያደናቅፈው"" ገልጿል። ኢትዮጵያ ትናንት ረቡዕ የግድቡ ግንባታ 80 በመቶ መድረሱን አስታውቃለች። የግድቡ ተደራዳሪዎች ቴክኒክ ቡድን አባል በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር) ለብሔራዊ ጣቢያው በሰጡት አስተያየት የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 80 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል። የግድቡ የሲቪል ግንባታ 91.8፣ የኤሌክትሮ መካኒካል ግንባታው 54.5 በመቶ እንዲሁም የኃይድሮሊክ ስትራክቸር ሥራው ደግሞ 55.2 በመቶ መድረሱንም አስረድተዋል። በመሆኑም ግድቡን ለማጠናቀቅ የሚቀረው 20 በመቶ ግንባታ እንደሆነ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ በቀጣዩ ክረምት ኢትዮጵያ የምታከናውነው የውሃ ሙሌት አገራቸው ላይ የጎላ ተጽዕኖ እንደማይኖረው መናገራቸው የግብጽ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ታላቁ የአስዋን ግድብ በቂ ውሃ በመያዙ የሕዳሴ ግድቡ በመጪው ክረምት ውሃ መያዙ ግብጽን አይጎዳም ሲሉ ነው ሳሚ ሽኩሪ የተናግሩት። የሕዳሴ ግድቡ በመጪው ክረምት ውሃ ከመያዝ በተጨማሪ በተያዘው ዓመት መገባደጃ ላይ ቅድመ ኃይል እንደሚያመነጭም በለጠ (ዶ/ር) ገልጸዋል። በተያዘው ዓመት የሕዳሴው ግድብ 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እንደሚይዘ መንግሥት የገለጸ ሲሆን ይህም ባለፈው ዓመት ካቆረው 4 ነጥብ 9 ቢሊዮን ኪዮቢክ ሜትር ውሃ ጋር በዓመቱ መጨረሻ የውሃውን መጠን ወደ 18 ቢሊዮን ከፍ ያደርገዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበርና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ሴሸዴኪ በሕዳሴ ግድቡ ዙሪያ ሦስቱን አገራት ሊያግባባ የሚችል አዲስ ሃሳብ ማቅረባቸው ተስምቷል። የሦስቱን አገራት መሪዎች ተዘዋውረው ያነጋገሩት ፕሬዝዳንቱ ላመነጩት ሀሳብ ውጤታማነት የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ሕብረት ድጋፋ እንደሚያደርጉ አል ሞኒተር የተባለ የዜና ተቋም ዘግቧል። ሀሳቡ በግድቡ ሙሊት ዙሪያ ኢትዮጵያ የጊዜ ሰሌዳዋንና የውሃውን መጠን መረጃ የምትሰጥበት ሆኖ አገራቱ ከሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ያስችላል ነው የተባለው። በአባይ ወንዝ ላይ የተመሠረቱት ግብጽ እና ሱዳን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ውሃ ሙሌትና ግንባታ በፊት በቅድሚያ ከስምምነት ላይ መደረስ እንደሚገባ በተደጋጋሚ አቋማቸውን ገልጸዋል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ10 ዓመታት በፊት ሲጀመር የጀመረው ይኸው የሕዳሴው ግድብ ድርድር ለበካታ ጊዜያት ያለስምምነት መቋረጡ በቀጠናው ስጋት ፈጥሯል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57167688 +sports የእንግሊዝ ተጫዋቾች በድጋሚ የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ ሆኑ "እንግሊዝ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሀንጋሪን 4ለባዶ ባሸነፈችበት ጨዋታ ጥቁር ተጫዋቾች ላይ የደረሰውን የዘረኝነት ጥቃት እንደሚያወግዙ የቡድኑ አባላት አስታውቀዋል። ለማንችስተር ሲቲ የሚጫወተው ረሂም ስተርሊንግ እና ለጀርመኑ ዶርትመንድ የሚጫወተው ጁድ ቢሊንግሀም ናቸው የዘረንነት ጥቃት የደረሰባቸው። የሀንጋሪ ደጋፊዎች በአውሮፓ ዋንጫ ወቅት ያሳዩትን ተገቢ ያልሆነ ባህሪ ተከትሎ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ብሄራዊ ቡድኑ በሜዳው የሚያደርጋቸውን ሶስት ጨዋታዎች ያለ ተመልካች በዝግ ስታዲየም እንዲያደርግ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር። ነገር ግን ከእንግሊዝ ጋር በነበረው ጨዋታ 67 ሺ ተመልካቾችን ማስተናገድ በሚችለው የቡዳፔሽቱ ፑሽካሽ አሬና ውስጥ ጥቂት ተመልካቾች እንዲገቡ ተፈቅዶላቸው ነበር። ምከንያቱ ደግሞ ውድድሩን በበላይነት የሚቆጣጠረው ፊፋ ስለሆነ ነው። የእንግሊዝ ተጫዋቾች ገና ጨዋታው ሊጀመር ሲል ተንበርክከው ዘረኝነትን የሚቃወም መልእክት ሲያስተላልፉ የሀንጋሪ ደጋፊዎች በጩሀት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ነበር። ምንም እንኳን የሀንጋሪ ተጫዋቾችና አሰልጣኙ ማርኮ ሪሲ ደጋፊዎቻቸው የአንግሊዝ ተጫዋቾች ማስተላለፍ የፈለጉትን መልእክት እንዲያከብሩ ቢጠይቁም የሚሰማቸው ግን አላገኙም። ""ዘረኝነትን በመቃወም ተጫዋቾቹ ሲንበረከኩ ጀምሮ ተቃውሞ እንደሚገጥመን አውቀን ነበር። ነገር ግን ይህን ማድረግ ለእኛ ትክክለኛው ነገር ነው'' ብለዋል የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኙ ጋሬት ሳውዝጌት። የጨዋታው መጀመሪያ አጋማሽ ምንም ግብ ያልተቆጠረበት ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ ግን ራሂም ስተርሊንግ ለእንግሊዝ የመጀመሪያዋን ግብ ሲያስቆጥር የሀንጋሪ ደጋፊዎች በከፍተኛ ሁኔታ የፕላስቲክ ብርጭቆዎችን ጭምር ወርውረዋል። የማንችስተር ዩንይትዱ ተከላካይ ለእንግሊዝ ሶስተኛዋን ግብ ሲያስቆጥር ደግሞ የሀንጋሪ ደጋፊዎች ተቀጣጣይ ነገር ወደ ሜዳው ሲወረውሩ ተስተውለዋል። የእንግሊዙ አሰልጣኝ ጋሬት ሳውዝጌትም ቢሆን ከዚህ አላመለጠም ነበር። ከጨዋታው በኋላ አሰልጣኙ ለጋዜጠኞች መልስ በሚሰጥበት ወቅት የበረዶ ስባሪ ከተመልካቾች ተወርውሮበታል። ""እንደ ቡድን ለየትኛው ጉዳይ አንድ ላይ መቆም እንዳለብን እናውቃለን። የተፈጠረው ነገር በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም። የቡድናችን የደህንነት ኃላፊው ሁሉንም ተጨዋቾች አነጋግሮ መረጃ ሰብስቧል። ከዚህ በኋላ ማድረግ የሚገባንን ትክክለኛውን ነገር እናደርጋለን'' ብለዋል አሰልጣኙ። ""አንዳንድ ተመልካቾች በተንቀሳቃሽ ስልክ ጭምር ተገቢ ያልሆነ ነገር ሲያደርጉ እና ሲናገሩ ተቀርጸዋል። በተገቢው መንገድ እንርም��� እንደሚወሰድ ተስፋ አደርጋለው'' ሲሉም አክለዋል። የእንግሊዙ አምበል ሃሪ ኬን በበኩሉ ''ጓደኞቼን አነጋግራቸዋለሁ። በትክክል ሪፖርት እናደርገዋለን። በተገቢው መንገድ ጠንከር ያለ እርምጃ እንደሚወሰድ ተስፋ አደርጋለሁ'' ብሏል። የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ባወጣው መግለጫ ደግሞ ""የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ቡዳፔሽት ውስጥ የዘረኝነት ሰለባ መሆናቸው በጣም አሳዝኖናል'' ብሏል። ""ፊፋ ጉዳዩን በደንብ እንዲመረምረው እንጠይቃለን። ተጫዋቾቻችን እና የቡድ አባላት በሙሉ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። እኛም ይህንኑ እናደርጋለን። ዘረኝነትንም እየተቃወምን እስከመጨረሻው ድረስ እንታገላለን።''" https://www.bbc.com/amharic/news-58424831 +business የዓለማችን ዋነኛ ቱጃር ጄፍ ቤዞስ ናሳን ሊከስ ነው "የጄፍ ቤዞስ የሕዋ ምርምር ተቋም ብሉ ኦሪጂን፤ ናሳ የተሰኘው የአሜሪካው የሕዋ ተቋምን ሊከስ እንደሆነ ተሰምቷል። ናሳ ሉናር ላንደር የተሰኘ ቴክኖሎጂ እንዲሠራለት ጨረታ አውጥቶ ለኢላን መስክ ድርጅት የ2.9 ቢሊዮን ብር ኮንትራት መስጠቱን ተከትሎ ነው ብሉ ኦሪጂን ክስ ሊመሠርት የተሰናዳው። የቤዞስ ብሉ ኦሪጂን በሁለቱ ድርጅቶች መካከል የተገባው ስምምነት ""ችግሮች አሉበት""፤ አልፎም ፍትሃዊ አይደለም ሲል ወቅሷል። ናሳ ቅድሚያ አቅዶ የነበረው ሥራውን ለሁለት ድርጅቶች ለመስጠት ነበር። ነገር ግን ባለፈው ሚያዚያ ጨረታውን ካወጣ በኋላ በበጀት እጥረት ምክንያት ለአንድ ድርጅት መስጠቱን ተናግሮ ነበር። ምንም እንኳ ናሳ እስካሁን በክሱ ዙሪያ አስተያየት ባይሰጥም አንድ ብሔራዊ ተቋም ይደግፈዋል እየተባለ ነው። ባለፈው አርብ ክሱን የመሠረተው ብሉ ኦሪጂን ሁለት ተቋማት ቴክኖሎጂውን ለመገንባት ያስፈልጋሉ የሚል እምነት እንደነበረው በክስ መዝገቡ ላይ አስፍሯል። ናሳ ሊያሠራ ያሰበው ቴክኖሎጂ የጠፈር ተመራማሪዎችን ይዞ ወደ ጨረቃ የሚያቀና መንኩራኩርን ለማሳረፍ የሚውል ነው። የአሜሪካ ሕዋ ምርምር ተቋም ናሳ ይህን ቴክኖሎጂ በፈረንጆቹ 2024 ለመሞከር አቅዷል። ነገር ግን ብሉ ኦሪጂን በጨረታው ሂደት ናሳ ""ሕጋዊ ያልሆነ ግምገማ አድርጎብናል"" ሲል ከሷል። ናሳ ጨረታውን ማን እንዳሸነፈ ይፋ ባደረገበት ወቅት የተቋሙ 'ሂዩማን ኤክስፕሎሬሽን' አለቃ የሆኑት ካቲ ሉደርስ ናሳ ሁለት ኩባንያዎችን ከመቅጠር የተቆጠበው በበጀት እጥረት ምክንያት ነው ብለው ነበር። ናሳ ለፕሮጀክቱ ማስኬጃ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ከመንግሥት ቢጠይቅም ኮንግረሱ 850 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው የፈቀደው። ስፔስኤክስ የተባለው የኢላን መስክ ተቋም የተሳኩ የኦርቢት [ምህዋር] ሚሽኖች ማካሄዱ እንዲመረጥ እንዳደረገው ናሳ ተናግሮ ነበር። ነገር ግን ስፔስኤክስ ከሌሎች ተቋማት ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስ ያለ ገንዘብ ማቅረቡ ጨረታውን እንዲያሸንፍ እንዳገዘው እየተነገረ ነው። ባለፈው ወር ጄፍ ቤዞስ ናሳ ያጠረውን 2 ቢሊዮን ዶላር ከፍሎ በፕሮጀክቱ መካተት እንደሚፈልግ ቢናገርም ሐሳቡ ተቀባይነት አላገኘም። የመንግሥት ተጠያቂነት ቢሮ የተሰኘው የአሜሪካ ፌዴራላዊ ተቋም ግን የብሉ ኦሪጂንና ዳይኔቲክ የተሰኘውን ሌላ የሕዋ ተቋም ክስ አጣጥሎታል። ናሳ እስከ ጥቅም 2/2015 ባለው ጊዜ ውስጥ ምላሽ መስጠት አለበት። የኢላን መስክ ስፔስኤክስ እካሁን ምንም አስተያየት አልሰጠም። ናሳ በአዲሱ ቴክኖሎጂ ታግዞ ከፈረንጆቹ 1972 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጨረቃ ለመመለስ አቅዷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58240626 +health ኮሮረናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ጽኑ ህሙማን ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት አሻቀበ "የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጽኑ ታማሚዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ ማለፉን ተገለጸ። የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ሐሙስ ሚያዝያ 07/2013 ዓ.ም ባወጣው ዕለታዊ የወረርሽኙ መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በበሽታው በጽኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 031 መድረሱን አመልክቷል። ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ ከአንድ ዓመት በኋላ ባሉት ሦስት ወራት፤ ማለትም ባለፉት ጥር፣ የካቲትና መጋቢት ውስጥ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ቀስ በቀስ እያሻቀበ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን የኢትዮጵያ የጤና ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ነበር። የወረርሽኙ በማኅበረሰብ ደረጃ መስፋፋቱ አሳሳቢ ከመሆኑ በተጨማሪ በወረርሽኙ ሳቢያ በጽኑ የሚታመሙና ለሞት የሚዳረጉ ሰዎችም ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከወራት በፊት ምርመራ ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል ቫይረሱ ይገኝባቸው የነበሩት ከአምስት መቶ ብዙም ሳይርቅ በመቶዎቹ የሚቆተሩ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘው ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም በበሽታው ክፉኛ ታመው የጽኑ ህሙማን ክትትልና ድጋፍን የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከአምስት መቶ በታች ሆኖ ለረጅም ጊዜ የቆየ ሲሆን፤ ባለፉት ሁለት ወራት ግን አሃዙ ከአምስት መቶ አልፎ አሁን ከአንድ ሺህ በላይ ደርሷል። በተመሳሳይ በየቀኑ በበሽታው ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአስራዎቹ የሚቆጠር ሆኖ ለረጅም ጊዜ ቆይቶ አሁን ግን ከሃያዎቹ አስከ ሰላሳዎቹ የሚደርሱ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ እየተመዘገበ ነው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የጽኑ ህሙማን ህክምናና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠመ መሆኑ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጾ የነበረ ሲሆን ቁጥሩ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ችግሩን የበለጠ ያባብሰዋል። ተቋሙ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ የባለሙያ ድጋፍና እንክብካቤ የሚሹ ሰዎች ቁጥር ""የህክምና ማዕከላት ማስተናገድ ከሚችሉት አቅም በላይ"" እየሆነ መምጣቱን ጨምሮ ገልጿል። በዚህም ሳቢያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ ታምመው በህክምና ተቋማት ድጋፍ ለማግኘት ለሚመጡ ህሙማን አገልግሎት የሚውሉ ""የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እና የኦክስጅን እጥረት እያጋጠመ ነው"" ሲል ገልጿል። የኮሮናቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ ለተጠቁ ጽኑ ህሙማን ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን ህይወታቸውን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስፈላጊ ናቸው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ ቬንትሌተሮች ቁጥር ከ500 ብዙም የበለጡ እንዳልሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል። በየዕለቱ በበወረርሽኙ በጽኑ ታመው ድጋፍ የሚሹት ህሙማን ቁጥር በመቶዎች ከመቆጠር አልፎ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሺህ በላይ መድረሱ የጤና ተቋማት ለህሙማኑ እንክብካቤና ድጋፍ ለመስጠት ችግር እየገጠማቸው መሆኑ ቀደም ሲል መገለጹ ይታወሳል። በተለይም በወረርሽኙ በጽኑ ታመው የቬንትሌተርና የኦክስጂን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህሙማን ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የነፍስ አድን አገልግሎቱን መስጠት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ከደረሰ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ሊያሻቅብ ይችላል። በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ በየዕለቱ የሚመዘገበው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የገለጸው ኢንስቲትዩቱ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በወረርሽኙ ሳቢያ የጽኑ ��ሙማን የህክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ህሙማንና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር ""አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል"" ይገኛል ብሏል። ሐሙስ ዕለት በወጣው የበሽታው ዕለታዊ ሪፖርት መሠረትም 33 ሰዎች በኮቪድ-19 በሽታ ምክንያት መሞታቸው ተገልጿል። በዕለቱ 8 ሺህ 878 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው 2 ሺህ 149ኙ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ቀደም ሲል በበሽታው ተይዘው ከነበሩት መካከል ደግሞ 1 ሺህ 288 አገግመዋል። አስካሁን በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ 236 ሺህ 554 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3 ሺህ 285 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 175 ሺህ 879 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56755324 +politics የአሜሪካ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ከትራምፕ መኖሪያ ቤት ጥብቅ ምስጢራዊ ሰነዶችን ወሰደ "የአሜሪካ የፌደራል ወንጀል ምርመራ (ኤፍ.ቢ.አይ) በፍሎሪዳ  በሚገኘው የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት በተካሄደ ብርበራ ጥብቅ ምስጢራዊ ሰነዶች መውሰዳቸውን የፍተሻ ማዘዣው አመለከተ። በዚህም የኤፍቢአይ ወኪሎች በአገሪቱ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደገኛ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ቲ.ኤስ/ ኤስ.ሲ.አይ በሚል ስያሜ የተለዩ እና ምልክት የተደረገባቸው አስራ አንድ ሰነዶችን መያዝ ችለዋል። በአሜሪካ ታሪክ በወንጀል ምርመራ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ቤት ብርበራ ሲካሄድ ይህ የትራምፕ ቤት የመጀመሪያው ነው። የሰነዶቹ ዝርዝር አርብ ለሕዝብ ይፋ የሆነው ዳኛው፣ ማር አ ላጎ የሚገኘውን የትራምፕ መኖሪያ ቤት ለመፈተሽ የሚያስችል የማዘዣ ዝርዝር ያካተተ ባለ ሰባት ገጽ ሰነድ ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው። ሰነዱ እንደሚለው የፎቶግራፍ አልበም፣ በእጅ የተጻፈ ማስታወሻ፣ ያልተገለጸ፤ ነገር ግን ስለ ""የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት"" መረጃ እና የረጅም ጊዜ የትራምፕ አጋር የሆነውን ሮጀር ስቶንን ወክለው የተጻፈ የምህረት ደብዳቤን ጨምሮ ከ20 ሳጥን በላይ ሰኞ ዕለት በወንጀል መርማሪዎቹ ተወስደዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ ምስጢራዊ ሰነዶችን የያዙ አራት ፋይሎች የተገኙ ሲሆን፣ በፋይሎቹ ውስጥ ሦስት ምስጢራዊ ሰነዶች እና ምስጢራቸው የተጠበቀ ቁሳቁሶች ተገኝተዋል። ማዘዣው እንዳመለከተው የኤፍቢአይ ወኪሎች፣ አደገኛ ሊሆኑ የሚችሉ የብሔራዊ ደኅንነት መረጃዎችን መያዝ ወይም ማስተላለፍ ሕገ ወጥ የሚያደርገውን የሕግ ጥሰትን እየተመለከቱ ነው። በምስጢራዊነታቸው ተለይተው የተቀመጡ ሰነዶች እና ቁሳቁሶችን መውሰድ በሕግ የተከለከለ ነው። ትራምፕ በሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜም በዚህ ወንጀል የሚያስቀጣውን ቅጣት ጨምረውታል። ድርጊቱ አሁን ላይ እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እስር ሊያስቀጣ ይችላል። የማዘዣው ማስታወሻ እንደሚለው ማር አ ላጎ የተካሄደው ፍተሻ በትራምፕ መኖሪያ ቤት ብቻ የተገደበ አልነበረም። ‘45 ኦፊስ’ እና የሰነዶች ማከማቻ ክፍሎችን ያካተተ ሲሆን፤ ነገር ግን ትራምፕ እና ባልደረቦቻቸው ይጠቀሙበት የነበረውን የግል የእንግዳ ክፍሎችን አይጨምርም። የአሜሪካ ፍትሕ መሥሪያ ቤት  ጉዳዩ ሐሙስ ዕለት ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ጉዳዩ በምርመራ ላይ ባለበት ወቅት ይፋ እንዲደርግ መጠየቁም ያልተለመደ ነው ተብሏል። የትራምፕ ጽህፈት ቤት በበኩሉ አርብ ምሽት ላይ ባወጣው መግለጫ፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት በሥልጣን ዘመናቸው፣ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ምስጢራዊ የነበሩ ሰነዶችን ምስጢራዊነታቸው እንዲያበቃ (Declassify) አድርገዋል ብሏል። “ሰነዶቹን ከቢሯቸው ወደ መኖሪያ ቤታቸው መወሰዳቸው ለዚህ ማሳያ ነው” ሲልም መግለጫው አክሏል። ""ሰነዶቹን የመለየትና የመከፋፈል ሥልጣኑም የፕሬዝዳንቱ ብቻ ነው” ብሏል መግለጫው። የሕግ ባለሙያዎች ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን እነዚህ ክርክሮች በፍርድ ቤት ይቀጥሉ አይቀጥሉ ግልጽ አይደለም ብለዋል። ቀደም ብሎ በፍትሕ መሥሪያ ቤት ሲያገለግሉ የነበሩት የሕግ ባለሙያ ቶም ዱፕሪ፣ “ፕሬዝዳንቶች ሰነዶችን መለየት ይችላሉ፤ ነገር ግን የአሠራር ሂደቶችን መከተል አለባቸው” ይላሉ። “ፎርሞችን መሙላት አለባቸው። ፈቃድ መስጠት አለባቸው። ዝም ብሎ እነዚህ ሰነዶች ተለይተዋል ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ሂደቶችን መከተል አለባቸው። ትራምፕ ይህን ስለመከተላቸው ግልጽ አይደለም” ብለዋል። የትራምፕ ቃል አቀባይ ታይለር ቡዶዊች፣ የጆ ባይደንን አስተዳደር በዋና የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸው ላይ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማውጣት ይከሳሉ። የትራምፕ አጋሮችም ትራምፕ በ2024 ምርጫ ለመወዳደር እያሰቡ በመሆናቸው በቤታቸው ላይ የተፈጸመው ፍተሻ ፖለቲካዊ ነው ሲሉ አውግዘውታል። የሕግ አስፈጻሚ ወኪሎችም የኤፍቢአይ ብርበራን ተከትሎ በመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ በኦንላይን የሚደርሰውን ማስፈራሪያ እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል። ማዘዣውን በግል ያጸደቀው የአሜሪካ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሜሪክ ጋርላንድ፣ ሐሙስ ዕለት “ቁርጠኛ እና አገር ወዳድ የሕዝብ አገልጋዮች” ሲሉ የፌደራል የወንጀል ምርመራ ወኪሎችን ተከላክለዋል። “ታማኝነታቸው ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ ሲጠቃ ዝም ብዬም አልመለከትም” ሲሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c04k0e03905o +politics በኦሮሚያ ክልል አደአ በርጋ ወረዳ በርካታ ሰዎች በኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት መገደላቸው ተነገረ "በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አደአ በርጋ ወረዳ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት በርካታ ንጹሃን ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። ዛሬ ከሰዓት ቢቢሲ ያነጋገራቸው የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በበኩላቸው፣ ""ይህ ውሸት ነው"" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። እንደ ነዋሪዎች ከሆነ የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት ትናንት አርብ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም. በነዋሪዎች ላይ ግድያ የፈጸሙት ከአንድ ቀን በፊት ታጣቂዎች የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላትን ከገደሉ በኋላ ነው። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለት የአካባቢው ነዋሪዎች ትናንት አርብ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 21 ይሆናሉ ሲሉ ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ የሟቾች ቁጥር ወደ 40 ይጠጋል ብለዋል። በአካባቢው በስፋት የሚንቀሳቀሰው እና ከመንግሥት ኃይሎች ጋር ጦርነት ውስጥ የሚገኘው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ቡድን ትናንት በመንግሥት ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 46 መሆኑን ጠቅሶ ከተገደሉት መካከል የ15 ሰዎችን ስም ዝርዝር አውጥቷል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በበኩሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአደአ በርጋ ወረዳ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች 15 ንጹሃን ዜጎችን ገድለዋል ብሏል። ከተገደሉት ንጹሃን ዜጎች መካከል የ70 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መግለጫው ጠቁሞ ""የታጠቁት ኃይሎች ገንዘብ፣ ጌጣጌጥ እና ሌላም ቁሳቁስ እየዘረፉ እንዲሁም የሰዎችን መኖሪያ እያቃጠሉም ነው"" ሲል አክሏል። የአካባቢው ነዋሪዎች በአሁን ወቅት ሕይወታቸውን ለማዳን ወደ ጫካ እየሸሹ እንደሆነም የኦነግ መግለጫ ያመለክታል። ሐሙስ እና አርብ ያጋጠመው ምንድን ነው? ሐሙስ ሚያዚያ 20/2014 ዓ.ም. የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት በወረዳው በሚገኝ ገጠራማ ስፍራ በፒክ አፕ መኪና ተጭነው ሲጓዙ ድንገተኛ ጥቃት በታጣቂዎች ተፈጽሞባቸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በዚህ ጥቃት ከ10 የማያንሱ የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት መገደላቸውን እና ቢያንስ 3 ሰዎች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረ��ል። በልዩ ኃይል አባላቱ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ በቀጣይ ቀን ማለትም አርብ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም. በወረዳው በሚገኙ ኢንጪኒ፣ ሙገር፣ ሬጂ እና ጂማታ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ነበር ይላሉ ነዋሪዎች። ""በጂማታ ቤት ለቤት እየዞሩ ፍተሻ እያደረጉ ሰዎችን መግደል ጀመሩ"" ሲሉ አንድ ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ""ሬሳ በቤት ውስጥ፣ በየጓሮ፣ ከዋናው መንገድ ዳር ሁሉ ይታይ ነበር"" ሲሉ በጂማታ ከተማ የነበሩ እና አሁን በሆለታ ከተማ የሚገኙ ነዋሪ ነግረውናል። የፖሊስ አባላቱ በነዋሪዎች ቤት ላይ ብርበራ ሲፈጽሙ እና ሲገድሉ፤ 'ሸኔን የምትደብቁት እናንተ ናችሁ' ሲሉ እንደነበረ በቦታው ካለ ነዋሪ እንደሰሙ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪ ይናገራሉ። የኢንጪኒ ከተማ ነዋሪ ደግሞ ከሰዎች መኖሪያ ቤት የወጡ ታጣቂዎች በልዩ ኃይል አባላቱ ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ የፖሊስ አባላቱ በቀጣይ ቀን በነዋሪዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸውን ተናግረዋል። ነዋሪው ትናንት አርብ ምሽት በከተማዋ በሚገኝ ሆስፒታል ""ብዙ ግርግር ነበር"" ብለዋል። ""ሁሉም ስለሚፈራ ወደዛ ሄደን ምን እየተካሄደ እንደሆነ አልጠየቅንም"" ሲሉ ተናግረዋል። ከግድያው በተጨማሪ በጂማታ በርካታ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ከነዋሪዎች መረዳት ተችሏል። የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ፣ ""ይህ ውሸት ነው። እንደዚህ ዓይነት ሪፖርት አልደረሰንም"" ሲሉ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ሌሎች ጥያቄዎች ብናቀርብም ""ሐሰት ነው"" ከሚለው በዘለለ የገለጹልን ነገር የለም። ስለ ጉዳዮ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ መንግሥት ኮምንኬሸን አገልግሎት ዶ/ር ለገሰ ቱሉ እንዲሁም ሰላማዊት ካሳ ብንደውልም ስልክ ስላልተነሳ ምላሽ ማካተት አልቻልንም። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ስለተፈጠረው ነገር መረጃ እንዳለው ለመጠየቅ ወደ ሕዝብ ግንኙት ባልደረባዎች ብንደውልም አልተሳካም። ከሰሞኑ መንግሥት 'ሸኔ' ብሎ የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን ""የማጽዳት ዘመቻ"" ጀምሬያለሁ ካለ በኋላ በሁለቱ አካላት መካከል የሚደረገው ውጊያ ተጠናክሮ ቀጥሏል። እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው እና የፌደራሉ መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጀውን 'ሸኔ' ቡድን ለማጥፋት ለአንድ ወር የሚዘልቅ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩን የክልሉ መንግሥት ከጥቂት ሳምንታት በፊት አስታውቆ ነበር። ይህን ተከትሎ ባለፉት ሳምንታት በተለይ በምዕራብ ሸዋ ዞን የፌደራሉ መንግሥት በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የታዘገ ጥቃት ሲያካሂድ መቆየቱ ተዘግቧል። ክልሉ ከቀናት በፊት ""ሸኔን የማጽዳት"" ዘመቻው ተጠናክሮ መቀጠሉን እና ይህ ወታደራዊ ዘመቻ የተፈለገለትን ዒላማ እያሳካ እንደሆነ በመግለጫ አውጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ፤ ""ወታደሮቻችን እየተዋጉ ነው። ድል እንጂ ሽንፈት አልገጠመንም። . . . ከ400 በላይ ወታደር ማርከናል። የተለያዩ ጦር መሣሪያዎችን ማርከናል"" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/61283409 +health በቀጣይ በዓለም ላይ የሚከሰቱ ወረርሸኞች ከኮቪድ በላይ ገዳይ ሊሆኑ ይችላሉ ተባለ "በዓለማችን ከዚህ በኋላ የሚከሰቱ ወረርሽኞች ከኮሮረናቫይረስ በላይ የከፉ ገዳይ ሊሆኑ እንደሚችሉ የኦክስፎርድ አስትራዜኔካ ክትባትን ከፈጠሩት ተመራማሪዎች መካከል አንዷ ባለሙያ ተናገሩ። ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት እንደሚሉት ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ዝግጁነት ለመደገፍ መንግሥታት በቂ ድጋፍ ማድረግ ያለባቸው ሲሆን አሁን የተገኙ ስኬቶችንም ማስቀጠል አስፈላጊ ነው። ፕሮፌሰሯ አክለውም ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት ክትባቶች አዲሱን የቫይረስ አይነት ኦሚክሮን ለመከላከል ብዙም አቅም ላይኖራቸው እንደሚችልም ጠቁመዋል። ስለአዲሱ ቫይረስ በቂ መረጃ እስከሚገኝ ድረስ ሰዎች በጥንቃቄ እንዲንቀሳቀሱም መክረዋል። ""ወረርሽኝ ሕይወታችንን እና አኗኗራችንን አደጋ ላይ ሲጥል ይህ የመጨረሻው የሚሆን አይመስለኝም። እውነታው ቀጣዩ ወረርሽኝ በጣም ከባድ ሊሆን እንደሚችል ነው። በፍጥነት የሚዛመት፣ በከፍተኛ ሁኔታ ገዳይ አልያም ሁለቱንም ያጣመረ ሊሆን ይችላል"" ብለዋል። ""በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ያለፍነውን ችግር መርሳት የለብንም። ወረርሽኙ በምጣኔ ሀብታችን ላይ ያሳደረው ጫና ወደፊት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን እንዳንቆጣጠር ሊያደርገን አይገባም'' ሲሉ ያሳስባሉ። ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት ስለአዲሱ ኦሚክሮን ቫይረስ ሲናገሩ ""አዲሱ ቫይረስ እራሱን አሻሽሎ ስለመጣ በክትባት መልክ ወይም በኮሮረናቫይረስ ስንያዝ የምናዳብረው በሽታ የመከላከል አቅም ብዙም ላይጠቅመን ይችላል"" ብለዋል። አክለውም ስለአዲሱ ቫይረስ በቂ መረጃ እስከሚገኝና ምርምሮች እስከሚደረጉ ድረስ ሰዎች ስርጭቱን ለመቀነስ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። በኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የተገኘው ትምህርትና ክትባቶችን በፍጥነት የማድረስ ልማድ ሊቀጥል እንደሚገባ ያሳሰቡት ፕሮፌሰሯ ከዚህ በኋላ መሰል እርምጃዎች የተለመዱ መሆን አለባቸው ብለዋል። የኦሚክሮን ስርጭትን ለመቆጣጠር እንዲቻል በማለት ቅዳሜ ዕለት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚጓዙ ሰዎች ከበረራቸው አስቀድመው የኮሮረናቫይረስ ምርምራ እንዲያደርጉ መንግሥት አሳስቧል። በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እስካሁን 246 ሰዎች በአዲሱ ኦሚክሮን መያዛቸው የተረጋተጠ ሲሆን ትናንት ዕሁድ ዕለት ብቻ 86 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መንግሥት አስታውቋል። ነገር ግን የዩኬን መንግሥት የሚያማክሩ አንድ ተመራማሪ የጉዞ እገዳውና ሌሎች መመሪያዎች የዘገዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕሮፌሰር ማርክ ዉልሐውስ እንደሚሉት የመንግሥት ውሳኔ የዘገየ ሲሆን እዚህ ግባ የሚባል ለውጥ ያመጣል ብለው እንደማያምኑም ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59545549 +politics የአሜሪካ ሕዝብ እንደራሴዎች 'አክራሪዋን' የምክር ቤት አባል ለማስወገድ ድምፅ ሰጡ "የዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ እንደራሴዎች አክራሪዋን የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል ከሁለት ኮሚቲዎች ለማስወገድ ድምፅ ሰጡ። ማርጆሪ ግሪን የተሰኙት የምክር ቤቱ አባል መሠረት የሌላቸው የሴራ ትንተናዎችን በማሰራጨት ይታወቃሉ። አልፎም እንደራሴዋ ዴሞክራቶች ላይ በሚሰንዝሯቸው ጠብ አጫሪ አስተያየቶቻቸውም ይታወቃሉ። ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ሁሉም ዴሞክራቶች ሴትዬዋ ከኮሚቴ አባልነታቸው ይነሱ ብለው ድምፅ ሲሰጡ፣ 11 ሪፐብሊካኖችንም አብረዋል። በአጠቃላይ 230 ለ199 በሆነ ድምፅ የአሜሪካ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሴትዬዋን ለመቅጣት ወስኗል። አሜሪካ ውስጥ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና የ9/11 የሽብር ጥቃት የተቀነባበረ ነው ብለው የሚያምኑት እንደራሴዋ፣ ድምፅ ከመሰጠቱ በፊት ባደረጉት ንግግር ይህ ድርጊታቸው የሚያስወቅሳቸው እንደሆነ አልካዱም። በአሜሪካ ፖለቲካ መሰል ክስተቶች እምብዛም አይስተዋሉም። ብዙ ጊዜ አባላት አልባሌ ድርጊት ሲፈፅሙ ፓርቲው ነበር የሚቀጣቸው። እንደራሴዋ ድርጊታቸው የሚያስኮንናቸው እንደሆነ ይናገሩ እንጂ ይቅርታ ከመጠየቅ ተቆጥበዋል። እነዚህ ድርጊቶች የሕዝብ ተወካይ ከመሆኔ በፊት የፈፅምኳቸው ናቸው ሲሉም ተከራክረዋል። ""እኒህ ያለፉ ድርጊቶች ናቸው። እነዚህ ነገሮች እኔን አይወክሉኝም"" ብለዋል እንደራሴዋ በባልደረቦ��ቸው ፊት ቀርበው ባደረጉት ንግግር። የ46 ዓመቷ የግዛተ ጆርጂያ ተወካይ የሴራ ትንተና ከሚያራምዱ እኩል መገናኛ ብዙሃንም ውሸትን በማራገብ ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል። ሴትዬዋ በበይነ መረብ ዓለም እጅግ ታዋቂ ናቸው። ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ በንቃት ይሳተፋሉ። የዶናልድ ትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊ ናቸው። አንድ ፌስቡከኛ የአሜሪካ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ""ጭንቅላታቸውን በጥይት ይመቱ"" ብሎ የለጠፈውን መልክት በመውደዳቸው [ላይክ በማድረጋቸው] ምክንያት ብዙ ወቀሳ አስተናግደዋል። ""ባራካ ኦባማ ይሰቀሉ"" የሚል መልዕክት ሥር ገብተው ደግሞ ""መድረኩ ተዘጋጅቷል"" ሲሉ ኮምተው ነበር። ከአንድ ጅምላ ግድያ ያመለጠን ታዳጊ መንገድ ላይ አግኝተው 'አውሬ' ብለው ሲስደቡት የሚያሳይ ምስል ተለቆ አጃኢብ አሰኝቶ እንደነበር አይዘነጋም። በፈረንጆቹ 2018 ደግሞ በየሁለት ዓመቱ የሚደረገው የአሜሪካ የምክር ቤት ምርጫ ""መንግሥታችን በሙስሊሞች እንዲወረር እያደረገ ነው"" የሚል አስተያየት ሰንዝረው ነበር። ማርጆሪ በቅርቡ የተደረገውን የአሜሪካ ምርጫ ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው ብለው ያምናሉ። እንደራሴዋ ባደረጉት ንግግር ስለነዚህ ጉዳዮች አንዳችም ነገር አላሉም።" https://www.bbc.com/amharic/55945222 +sports ጉዳፍ ፀጋይ የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰንን አሻሻለች "ጉዳፍ ፀጋይ ፈረንሳይ ሌቪን በተካሄደው የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰንን በማሻሻል አሸነፈች። ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ የዓለም ክብረ ወሰን በ2 ሴኮንድ በማሻሻል 3፡53፡09 በሆነ ሰዓት ውድድሩን አጠናቃለች። ጉዳፍ ያሻሻለችው ክብረ ወሰን በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ገንዘቤ ዲባባ በ2014 (እአአ) ካርልስሩሄ ላይ የተያዘ ነበር። ""የዓለምን የቤት ውስጥ ሩጫ ክብረ ወሰን በማሻሻሌ እጅግ ደስተኛ ነኝ"" ያለችው አሸናፊዋ ጉዳፍ፤ ""ጠንከራ ልምምድ ሰርቼ ስለነበር የዓለምን ክብረ ወሰን ለመስበር ራሴን አዘጋጅቼ ነበር"" ብላለች። ትናንት ምሽት በወንዶች በተደረገ የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫም ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎቻቸውን በፍጹም የበላይነት አሸንፈዋል። ኢትዮጵያውያኑ ከአንድ እስከ አራት ያለውን ደረጃ ይዘው ሲያጠናቅቁ የዓለም ሁለኛው ፈጣን ሰዓትም በውድድሩ ተመዝግቧል። በመሰናክል ሩጫ ጌትነት ዋለ በ3 ሺህ ሜትር ሩጫ በአንደኝነት ሲያሸንፍ ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም ተከታትለው በመግባት ድሉን አድምቀውለታል። ሩጫውንም በ7፡24፡98 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ የወርቅ ተሸላሚ ሆኗል። ጌትነት የገባበት ሰዓት የዓለም ሁለተኛው ፈጣን ሰዓትም ሆኖ ተመዝግቦለታል። የ20 ዓመቱ ጌትነት ለረጅም ጊዜ ክብረወሰኑን 7፡24፡90 በሆነ ሰዓት ለያዘው ዳንኤል ኮሜን ትልቅ ስጋት ፈጥሯል። የዓለም ሻምፒዮና የ5 ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊው ሰለሞን ባረጋ ደግሞ በእዚሁ ወድድር 7፡26.10 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቅቋል። ለሜቼ ግርማ በ7፡27፡98 ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ በሪሁ አረጋዊ ደግሞ በ7፡29፡24 አራተኛ በመሆን ውድድሩን ጨርሷል። ከአሁን በፊት በ3 ሺህ ሜትር ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ ከ00፡07፡30 በታች መግባት የቻሉት 6 ሯጮች ብቻ ነበሩ። አሁን ግን እድሜያቸው ከ19 እስከ 21 የሆኑ አራት ሯጮች ከ00፡07፡30 በታች ይህንን ውድድር ማጠናቀቅ ችለዋል። ይህም ክብረወሰኑን በቅርቡ ለማሻሻል ተስፋ የታየበት ነው ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/56006574 +sports የጆርጅ ፍሎይድን ሞት የቀረጸችው ሴት ምን አለች? "ሰዎች ስለ ሟች ጆርጅ ፍሎይድ ያወራሉ። ሰዎች ስለ ጨካኙ ፖሊስ ዴሪክ ያወራሉ። ሰዎች ይህን ሁሉ ጉድ በስልኳ ቀርጻ ለዓለም ስላጋራችው አንዲት ትንሽ ልጅ ���ን አያወሩም። የእርሷ የስልክ ቪዲዮ ባይኖር ዛሬ ስለ ጆርጅ ፍሎይድ የሚያወሩት ቤተሰቦቹ ብቻ በሆኑ ነበር። ማን ያውቃል? አንዳንድ ወንጀሎች ወንጀል የሚሆኑት ለአደባባይ ሲቀርቡ ነው። ስርቆት ሌብነት ሆኖ የሚያስከስሰው ሲደረስበት ብቻ ነው። በጆርጅ ፍሎይድ የደረሰው ሳይቀረጽ ቀርቶ ቢሆንስ? በዚህ ዘመን የማኅበራዊ ሚዲያ ጉልበት ኃያል ነው። ሰደድ እሳት ነው። ዓለምን ለማዳረስ ሰከንዶች ይበቁታል። አማዞን ጫካ ላይ የምትጫር ክብሪት…እንደማለት ነው። ዳርኔላ ፍሬዘር ገና 17 ዓመቷ ነው። ገና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መግባቷ ነው። የአክስቷን ልጅ ወደ ሰፈራቸው ምግብ ቤት ይዛት እየሄደች ነበር። የአክስቷ ልጅ ደግሞ ገና 9 ዓመቷ ነው፡። ልክ ምግብ ቤቱ አካባቢ ስትደርስ የሆነ ጥቁር ሰውዬ ፖሊሶች ሲያስጨንቁት አይታ ቆመች፤ ቆመችና እንደ ዋዛ ስልኳን ከኋላ ኪሷ መዘዝ አድርጋ አወጣች። 'ሪከርድ' የሚለውን ቀይ ምልክት ተጫነች። እርሷ መቅረጽ ስትጀምር ጆርጅ ፍሎይድ አየር አጥሮት ያቃስት ጀምሯል። ""እባካችሁ! እባካችሁ"" እያለ። የእርሱ እስትንፋስ እስከወዲያኛው ልትቋረጥ የመጨረሻ ቃሉ ""I can't breathe,"" [መተንፍስ አልቻልኩም] ነበር። ይቺን ""መተንፈስ አልቻልኩም"" የምትለዋ ቃል ለመጨረሻ ጊዜ ከእስትንፋሱ ስትወጣ የዳርኔላ ስልክ ባትሪው አላለቀም። እርሷም መቅረጽ አላቆመችም። ከዚህ በኋላ ጆርጅ ፍሎይድ ምንም አላለም። እስከወዲያኛው አሸልቧል። የ44 ዓመቱ የፖሊስ መኮንን ዴሪክ ቾቪን ግን እጁን ኪሱ አድርጎ በጉልበቱ የፍሎይድን አንገት እንደተጫነው ነበር። ከዴሪክ ጋር ሦስት ፖሊሶችም ለዚህ ተግባሩ ተባባሪ ነበሩ። የ17 ዓመቷ ዳርኔላ ስልኳ መቅረጹን እንዲያቆም ያደረገችው ፖሊስ ዴሪክ በእግሩ ወደ ግራ፣ ጆርጅ ፍሎይድ በቃሬዛ ወደ ቀኝ ሲሄዱ ነበር። ዳርኔላ በድምሩ 10 ደቂቃ ከ9 ሰከንዶች ቀርጻለች። ድርጊቱን አጠናቃ ስልኳን ወደ ኪሷ ስትከት ግን በስልኳ ቋት ያኖረችው ተንቀሳቃሽ ምስል ዓለምን ሊንጥ እንደሚችል በፍጹም አልተከሰተላትም። በወቅቱ ምን እንዳደረገች፣ ምስሉ ከተሰራጨ በኋላ ምን እንደተሰማት ለቢቢሲ ለመናገር ፍቃደኛ አይደለችም። ለጊዜው ለቢቢሲም ሆነ ለሌላ ሚዲያ አስተያየት መስጠት ትታለች። ዕድሜዋም አንድ ምክንያት ይሆናል። የእርሷ ጠበቃ ሚስተር ኮቢን ግን ለምን ክስተቱን መቅረጽ እንደፈለገች ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል። ""የዜግነት ግዴታዋን የመወጣት ስሜት ተሰምቷት ሊሆን ይችላል።"" ""ያም ሆነ ይህ በእርሷ ቪዲዮ የመብት ትግል እቅስቃሴ ድጋሚ ተወልዷል ብዬ አምናለሁ"" ይላሉ ጠበቃዋ። የ2ኛ ደረጃ ተማሪዋ ዳርኔላ ከዚህ ክስተት በኋላ መጠነኛ የአእምሮ መታወክ ደርሶባት ሕክምና ጀምራለች። በሕይወቷ እንዲያ ያለ ሰቅጣጭ ነገር አይታ አታውቅም። ያን ቪዲዮ በፌስቡክ ሰሌዳዋ ላይ ከሰቀለችው በኋላ የነበረው ምላሽ በእርሷ ዕድሜ ለመቋቋም የሚቻል አልነበረም። በፖሊስ ድርጊት የተቆጡ እንዳሉ ሁሉ በእርሷ ድርጊት የተቆጡም ቁጥራቸው ትንሽ አልነበረም። ያመሰገኗት እንዳሉ ሁሉ ""ጫካኝ፣ አውሬ"" ሲሉ የሞለጯትም ጥቂት አይደሉም። የጆርጅ ፍሎይድ አሰቃቂ ሞት በግንቦት 25 ነበር፤ እርሷ ወደ ፌስቡክ ገጽ ያመራቸው ግን ከ2 ቀናት በኋላ በግንቦት 27 ነው። ወዲያውኑ እሳት ተቀጣጠለ። ነደደ፣ ጨሰ…። የእርሷ ቪዲዮ የእርሷ መሆኑ ቀረ። ሚሊዮኖች ቤት ገባ። መጀመርያ አካባቢ በፌስቡክ ሰሌዳዋ ስር ለተሰጧት አስተያየቶች ምላሽ ትሰጥ ነበር። አንዱ አስተያየት ሰጪ እርሷን ዝና ናፋቂ አድርጎ ይከሳታል። እንዲያ ባይሆን ኖሮ ሞባይልሽን አስቀምጠሸ የሚሞተውን ሰው ታድኚው ነበር ብሎ ይከሳታል። እርሷም ዝም አላለችም። የሚከተለውን መለሰችለት። ""እኔ ያን ��ስተት ባልቀርጽ ኖሮ፣ አራቱ ፖሊሶች ዛሬ በሥራ ላይ ነበሩ። ምናልባትም ሌላ ሰው እያነቁ…"" ዳርኔላን 'ያን ያደረግሽው ዝና ፍለጋ ነው' የሚሏት ሰዎች ከምር ያበሳጯት። ""ምን? ለዝና ነው ያደረግሽው ነው የምትሉኝ? ለገንዘብ ነው ያደረግሽ ነው የምትሉኝ? እናንተ ሰዎች ደደብና ደንቆሮዎች ሳትሆኑ አትቀሩም።"" በዳርኔላ ላይ የደረሰው ትችት፤ አደጋ እየደረሰ ቪዲዮ መቅረጽ ጽድቅ ነው ኩነኔ የሚል ሌላ ዙር የክርክር ምዕራፍ ከፍቷል። ለመሆኑ እንዲህ ማድረግ ተገቢ ነው? በሞራል ሕግ እንዴት ይሰፈራል? ራስ ወደድነታችን ይሆን ሰው እየሞተ እኛ ቪዲዮ እንድንቀርጽ የሚያስችለን? በምንቀርጽበት ቅጽበት እየሞተ ላለው ሰው የምር ሐዘኔታ ይሰማናል? ነው ወይስ የሚያስጨንቀን በእኛ የሚቀረጸው የቪዲዮ ጥራትና ቀጥሎ የሚመጣው እውቅና? ዳርኔላ በእርሷ የተቀረጸው ተንቀሳቃሽ ምስል ዓለምን ከናጠ በኋላ ሽልማት አልጠበቃትም። እንዲያውም ነገሩ ሕይወቷን ረብሾታል። አሁን የአእምሮ ሐኪም እየተንከባከባት የሚገኘው ያለምክንያት አይደለም። ከዚህ ቀደም ቪዲዮ በመቅረጽ ወንጀል ያጋለጡም ቢሆኑ ሽልማት አልጠበቃቸውም። ሕይወታቸው በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ተረባብሿል። 1.ዴኒስ ፍሎረስ ይሄን ቪዲዮ እየቀረጹ የፖሊስን ጭካኔ ማጋለጥ የጀመረው ሰው ዴኒስ ፍሎረስ ሳይሆን አይቀርም። የኒው ዮርክ ሰው ነው። የኒው ዮርክ ከተማ ፖሊስን እንደሱ የቀረጸ የለም። ፖሊስ 70 ጊዜ አስሮታል። ከ90ዎቹ ጀምሮ እንደቀረጻቸው ነው ያለው። ዛሬ 'ፖሊስ አደብ ይግዛ፣ ዘረኝነቱን ይተው' የሚሉ እንቅስቃሴዎች እንዲጀመሩ ምክንያት የሆነው እርሱ ነው። ሞባይል ሳይጀመር እርሱ የፖሊስ ግፍ መቅረጽ ጀምሯል። ይህ ድርጊቱ ሕይወቱን እንዴት እንዳከበደው ወደኋላ ላይ ይነግረናል። ፍሎረስ የጀመረውን ተግባር ግን በብዙዎች ይተገበር ጀመር። 2.ቧንቧ ሠራተኛው ጆርጅ ሆሊዴይ ከፍሎረስ በኋላ በ1991 አካባቢ አንድ ጆርጅ ሆሊዴይ የሚባል የቧንቧ ሠራተኛ ከአፓርትመንቱ በርንዳ ላይ ሆኖ የቀረጸው ነገር ምናልባትም እንደ ወረርሽኝ የተዛመተ የመጀርመያ ቪዲዮ ሳይሆን አይቀርም። ያን ጊዜ እንደዛሬው ፌስቡክ የለ፣ ቅንጡ ሞባይል የለ! ምን የለ፣ ምን የለ! እርሱ ቀረጻ ያደረገውም በተለምዶ የልደት ካሜራ መቅረጫ በምንላት ትንሽ ሶኒ ቪዲዮ ካሜራ ነበር። ከበረንዳው ቀርጾ ያስቀረው ምስል ከባድ ውጤትን አስከተለ። በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ሮድኒ ኪንግ የሚባልን አንድ ጥቁር ወጣት በርከት ያሉ ነጭ ፖሊሶች ከበውት እየተቀባበሉ ሲያዳፉት የሚያሳይ አሰቃቂ ቪዲዮ ነበር። ጆርጅ ሆሊዴይ ያን ጊዜ ይህን ክስተት ሲቀርጽ ሞባይል አልነበረም ብለናል። 5ጂ ኢንተርኔትም አልተፈጠረም፤ ፌስቡክ የለም። ታዲያ እንዴት ተዛመተ? ይህንን የቀረጸውን አሰቃቂ የቪዲዮ ቴፕ ወስዶ እዚያ ሰፈሩ ለሚገኝ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰጠ። ጣቢያው ተንቀሳቃሽ ምስሉን በዜና እወጃ ሰዓት ላይ አስተላለፈው፤ አገሪቱም በተቃውሞ ተናጠች። ከዓመት በኋላ ያንን ድርጊት የፈጸሙ ፖሊሶች ፍርድ ቤት ነጻ ናችሁ ሲላቸው ደግሞ ደም አፋሳሽ ተቃወሞ በመላው አሜሪካ ዳግም ተከሰተ። ""ይሄ ሰው የቀረጸው ምስል ነው በአሜሪካ ምድር የፖሊስን ግፍ መቅረጽ እንዲለመድ ምክንያት የሆነው"" ይላል በዚህ ተግባር ጥርሱን የነቀለው የኒው ዮርኩ ፍሎርስ፣ ለቢቢሲ። በአሜሪካ ሕገ መንግሥት ዜጎች በፖሊስ የሚፈጸምን ተግባር ቆመው የመቅረጽ መብት አላቸው። 3.ራምሴ ኦርታ ከዚህ ክስተት በኋላ የመጣው የኤሪክ ጋርነር ጉዳይ ነው። ሚስተር ጋርነር የ43 ዓመት ጥቁር አሜሪካዊ ነበር። በኒው ዮርክ ከተማ በ2014 ልክ እንደ ጆርጅ ፍሎይድ ሁሉ በነጭ ፖሊሶች አንገቱን ታንቆ ነበር የሞተው። ፖሊሶቹ አንገቱን አንቀው የያዙት የምትሸጣቸው ሲጃራዎች ሕጋዊ አይደሉም በሚል ምክንያት ነበር። ልክ እንደ ጆርጅ ፍሎይድ ሁሉ ሚስተር ጋርነርም ፖሊሶቹ አንገቱን ጠምልለው ሲያስጨንቁት፤ 'እባካችሁ መተንፈስ አቃተኝ፣ እባካችሁ!' እያለ ይጮኽ ነበር። ""I can't breath"" የሚለው ንግግርም የትግል መፈክር መሆን የጀመረው ከእርሱ በኋላ ነበር። በእርሱ የደረሰው የሞት አደጋ ፍርድ ቤት የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ነው ቢልም ድርጊቱን የፈጸመው ፖሊስ ግን ነጻ ሆኗል። ያ ፖሊስ ስሙ ዳንኤል ፓንታሊዮ ይባል ነበር። ሟችና ገዳይን ለጊዜው ትተን ያን ድርጊት በቪዲዮ ስላስቀረው ሰው ትንሽ እናውራ። ራምሴ ኦርታ ይባላል። የእርሱ ጉዳይም እንደ ሌሎቹ ቀራጮች ሁሉ ሲያወዛግብ ነው የኖረው። ""ይህን ክስተት ከቀረጽኩ በኋላ ፖሊሶች ሲከታተሉኝ ነው የኖርኩት"" ብሏል ከዚህ በፊት በሰጠው አንድ ቃለ ምልልስ። በ2016 ራምሴ ኦርታ በአደገኛ እጽና በሕገ ወጥ መሳሪያ ዝውውር ክስ ተመሰረተበት። አራት ዓመትም ዘብጥያ ወረደ። እርግጥ ነው የተመሰረተበት ክስ የፖሊስን ድርጊት በቪዲዮ ከመቅረጽ ጋር የሚያገናኘው አንዳችም ነገር ባይኖርም ጓደኛው ሚስተር ፍሎረስ እንደሚያምነው ግን ፖሊስ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሲከታተለውና የሚታሰርበትን ሰበብ ሲፈልግለት፣ እንዲሁም ቀን ሲጠብቅለት ነበር። ""ፖሊስን ማጋለጥ ለአደጋ መጋለጥ እንደሆነ ሊያስረዳ የሚችለው የራምሴ ኦርታ ጉዳይ ነው"" ይላል ፍሎረስ። የሚገርመው ራምሴ ኦርታ ከእስሩ በኋላ ምነው ያን ጊዜ ፖሊስን ባልቀረጽኩ ኖሮ ሲል ተጸጽቷል። ያም ሆኖ ግፍ ሲፈጸም ዝም ብሎ ማለፍም ከባድ የሕሊና ጸጸት እንደሚተርፍ የፈይዲን ሳንታናን ታሪክ ማየት በቂ ነው። 4.ፈይዲን ሳንታና ፈይዲን ሳንታና በ2015 በሳውዝ ካሮላይና ግዛት፣ ቻርልስተን ከተማ ወደ ሥራ እየሄደ ነበር። አንድ ነጭ ፖሊስ ዋልተር ስኮት የሚባል አንድ ጥቁርን መኪናው ውስጥ ሳለ ሲያስቆመው ያያል። ነገሩ እንዲሁ ስላላማረው ወይም ልማድ ሆኖበት ይሆናል ስልኩን አውጥቶ መቅረጽ ይጀምራል። ፖሊሱ ትንሽ ዘወር ባለበት ቅጽበት ጥቁሩ ዋልተር ስኮት ድንገት ከመኪናው ወርዶ እግሬ አውጪኝ ይላል። ሳንታና ይህ ሁሉ ሲሆን በግማሽ ልብም ቢሆንም እየቀረጸው ነበር። በዚህ ቅጽበት ፖሊሱ ያደረገው ነገር ግን ፍጹም ያልጠበቀው ነበር። ፖሊሱ ሽጉጡን አውጥቶ እየሮጠ የነበረውን ጥቁሩን ዋልተር ስኮትን 8 ጥይቶችን ከጀርባ ለቀቀበት። አከታትሎ። ዋልተር ስኮት መሬት ላይ ወደቀ። ሳንታና እንደቀልድ የቀረጸው ነገር በኋላ ላይ ለከፍተኛ የአእምሮ መረበሽ ዳረገው። ""ድንጋጤ ውስጥ የከተተኝ ምንም ያልታጠቀ አንድ ጥቁር ሰውዬ እንዲሁ ለማምለጥ ሲል ብቻ ስለሮጠ 8 ጥይት ከጀርባው ይዘንብበታል ብዬ አላሰብኩም ነበር"" ብሏል ለቢቢሲ። ሳንታና ከዚህ ክስተት በኋላ ለሦሰት ቀናት ያህል ከቤት መውጣት አስጠላው። እርሱ ራሱ ስደተኛ ነው፣ በዚያ ላይ ከዶሚኒካን ሪፐብሊክ መጥቶ በፀጉር አስተካካይነት ነበር የሚተዳደረው። በስልኩ ያስቀረውን ነገር ለማንም አላሳየም። ለማንም አላጋራም። እንዲያ ቢያደርግ በኋላ ጣጣው ብዙ ነው ብሎ አሰበ። እንዲያውም ያስቀረውን ተንቀሳቃሽ ምስል እስከ ወዲያኛው ሊሰርዘውና ቻርለስተን ከተማን ጥሎ ለመሄድም አስቦ ነበር። በዚህ መወዛገብ ውስጥ ሳለ ታዲያ አንድ ቀን የፖሊስን ሪፖርት ተመለከተ። ያየውን ማመን አቅቶት ደርቆ ቀረ። በዚህ ሪፖርት 8 ጥይት በጥቁሩ ሰው ላይ ከጀርባው የለቀቀበት ራሱን ለማዳን ነው ይላል። ""ፖሊስ ያን ያደረኩት ሰውየው መሳሪያ ይዞ ስለነበረ ሕይወቴ ላይ አደጋ እንዳያደርስ ፈርቼ ነው"" የሚል ነገር ሳነብ ደነገጥኩ፤ ""በዚህ ጊዜ ውሳኔዬን ቀለበስኩ"" ይላል ሳንታና። ""በዚያ ጊዜ ይህን ጭልጥ ያለ ውሸት ለማጋለጥ በምድር ላይ ያለሁት ብቸኛው ሰው እኔ እንደሆንኩ አውቃለሁ፤ ፍርሃቴን ለመጋፈጥ ወሰንኩ"" ይላል ለቢቢሲ። ሳንታና ጨክኖ ያን ቪዲዮ ወስዶ ለሟች ቤተሰብ አስረከበ። ቪዲዮው ፖሊስ መዋሸቱን አጋለጠ። ""እኔ የቀረጽኩት ቪዲዮ በቅጽበት እንደ ሰደድ እሳት ይዛመታል አላልኩም ነበር"" ይላል ሳንታና። ከዚያ ቪዲዮ በኋላ የሳንታና ሕይወት እስከ ወዲያኛው ተቀየረ። ""የእንገድልሀለን ዛቻ፣ ዘረኛ ስድቦች ሁሉ ይዘንቡብኝ ጀመር። ፍርሃቴን ለመጋፈጥ እኔም ነገሩን መጋፈጥ ፈለኩ…"" ዕድሜ ለሳንታናና ለዚያ ቪዲዮ የፖሊስ መኮንንኑ ሚስተር ስላገር ክስ ተመሰረተበት። ፍርድም አገኘ። ""አንዳንድ ጊዜ ዝም ማለት የወንጀል ተባባሪነት ነው። ላመንኩበት ነገር መታገል ጀመርኩ። ፍርሃቴንም እያሸነፍኩ መምጣት ጀመርኩ"" ይላል ሳንታና፤ ለቢቢሲ በሰጠው አስተያየት። ሞባይል ስልክና ኢንተርኔት በሌለበት ዘመን የተወለደው የፖሊስን ግፍ የማጋለጥ ተግባር ዛሬ ቀላል ሆኗል። በርካታ ሰዎች ግፍ የመሰላቸውን ተግባር በስልካቸው እየቀረጹ በማኅበራዊ ድረ አምባው ያጋራሉ። ይህም ወንጀሎች ቸል እንዳይባሉ፣ ማኅበረሰቡ በአካባቢው ለሚፈጠሩ ነገሮች ዐይኑን እንዲገልጥ ምክንያት ሆነዋል። ወንጀል ፈጻሚዎችም ግፍ ሲፈጽሙ ዓለም እየተመለከታቸው እንደሆነ ማገናዘብ ጀምረዋል። ለሀቀኛ መርማሪዎችም ነገሩ ሥራ አቅልሎላቸዋል። ለምሳሌ የጆርጅ ፍሎይድን ክስተት ከወጣቷ ዳርኔላ ስልክ ወስደው አስቀምጠውታል። ""ወደፊት ደግሞ ዳርኔላ ፍርድ ቤት ቀርባ እንድትመሰክር መደረጉ አይቀርም"" ይላሉ ጠበቃዋ ሚስተር ኮቢን። ምንም እንኳ ገና የ2ኛ ደረጃ ጀማሪ ተማሪ ብትሆንም ድርጊቱን በመቅረጽዋ ለአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ቃሏን ሰጥታለች። ቃሏን በምትሰጥበት ወቅት የነበራት ስሜት በዚህ ድርጊት ውስጥ መሳተፍ ተራ ተግባር እንዳልሆነ ማሳያ ነው። ጠበቃዋ ዳርኔላ ቃሏን ስትሰጥ የነበረውን ሁኔታ በዚህ መልኩ ገልጸውታል። ""ያለማቋረጥ ታለቅስ ነበር። የደረሰባት ነገር ከባድ ነው። ለመርማሪዎች እንደገለጸቸው በማንኛው ሰዓት ዐይኗን ስትጨፍን የሚመጣባት ምስል ፖሊስ ጆርጅ ፍሎይድን አንቆ ሲገድለው ነው። የሚሰማት ድምጽ 'እርዱኝ መተንፈስ አልቻልኩም' የሚለው ነው። ጆርጅ ፍሎይድ እየሞተ ሳለ የነበረው ፊቱ ይመጣባታል። ዐይኗን ስትገልጥ ግን ምስሉ የለም። ዐይኗን ስትጨፍን ጆርጅ ፍሎይድ ነው የሚታያት።"" ወጣቷ ዳርኔላ በዚህ ጉዳይ ፍርድ ቤት ቀርባ ባትመሰክር ምርጫዋ ነው። ይህን ቪዲዮ በፌስቡክ ሰሌዳዋ ላይ ባትሰቅለው ትመርጥ ነበር። ምንም የመታወቅ ፍላጎት አልነበራትም። በዚህ ረገድ ጠበቃዋ ሚስተር ኮቢን ለቢቢሲ ያቀረበው የታሪክ ምስስሎሽ መጠቀስ የሚገባው ነው። ""ዳርኔላ ልክ እንደ ሮዛ ፓርክስ ነው የሆነችው፤ ሮዛ ፓርክስ በ1955 ዓ.ም በአላባማ ባቡር ተሳፍራ ሳለ ወንበር ለነጭ እንድትለቅ ስትጠየቅ እምቢ አለች፡፡… ይህ ድርጊቷ በጥቁር መብት ትግል ታሪክ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው፡፡ ነገር ግን እርሷ ያን ስታደርግ ወደፊት ማን እንደምትሆን አላሰበችውም። ማርቲን ሉተር ኪንግን ወይም ማልኮም ኤክስን ለመሆን አልነበረም እምቢ አልነሳም ያለችው። በቃ በዚያ ሰዓትና ሁኔታ ለነጭ ወንበሯን መልቀቅ ትክክል እንዳልሆነ ተሰማት አደረገችውም፡፡ የእኔ ደንበኛ ዳርኔላም እንዲያ ናት። መጥፎ ተግባር አየች፤ ስልኳን አውጥታ ቀረጸች።"" ዳርኔላስ ልጅ ናት፤ አንድ አዋቂ ሰው እየሞተ ያለን ሰው መርዳት ሲገባው ካሜራውን አውጥቶ ቢቀርጽ ድርጊቱ ጽድቅ ነው ኩነኔ?" https://www.bbc.com/amharic/news-53004401 +politics የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በጦር ኃይሉ ተሹመው የነበሩ አስተዳዳሪዎችን አሰናበቱ የሱዳን ጦር መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ ሹመት ሰጥቷቸው የነበሩ የክልል አስተዳዳሪዎችና ሚኒስትሮች በጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ። ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ በቁም እስር ላይ የነበሩት እና ዳግም ወደ ሥልጣን የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ከክልል አስተዳዳሪዎች በተጨማሪ በጦሩ ተሹመው የነበሩ ሚኒስትሮችንም አንስተዋል። አብደላ ሐምዶክ ከሥልጣን ያነሷቸው ሚኒስትሮች ከቀድሞው የሱዳን የረዥም ጊዜ መሪ ኦማር አል በሽር መንግሥት ጋር ቁርኝት የነበራቸው ናቸው ተብሏል። ከጥቂት ወራት በፊት የሱዳን ጦር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የሚመራውን የሲቪል መንግሥት ገልብጦ ሥልጣን ተቆጣጥሮ እንደነበረ ይታወሳል። አብደላ ሐምዶክ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ ሥልጣናቸው የተመለሱት በጄነራል አብድል ፈታ አል ቡርሐን ከሚመራው መፈንቅለ መንግሥት አድራጊ ኃይል ጋር ባደረጉት ስምምነት ነው። ጄነራል አል-ቡርሐን ወደ ሥልጣናቸው እንዲመለሱ ከተደረጉት የሲቪል መንግሥቱ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጋር አብሮ ለመሥራት እና ምርጫ እስኪከናወን ድረስ አብደላ ሐምዶክ ለሚመሰርቱት የሽግግር መንግሥት ድጋፍ እንደሚሰጡ ገልጸዋል። ሱዳናውያን ግን የወታደራዊ ሥርዓቱ አሁንም በአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ ያለው ሚና መቀጠሉ እንዳስቆጣቸው በመግለጽ ተጨማሪ የአደባባይ ላይ ተቃውሞዎች ይቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ድምጻቸውን በአደባባይ ለማሰማት የሚወጡ ሰዎች በሱዳን ጦር መሪዎች ላይ ያላቸው ተቃውሞ እና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ያላቸውን ድጋፍ ሲገልጹ ቆይተዋል። በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ የሲቪል አስተዳደሩን አመራሮች ከበተነና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ መፈንቅለ መንግሥቱን ተቃውመው አደባባይ ከወጡ መካከል ቢያንስ 40 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ምዕራባውያን አገራት እና የአፍሪካ ሕብረትን ጨምሮ በርካቶች መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወም፤ የአገሪቱ ዜጎች ሱዳን ወደ ሰላማዊ የዲሞክራሲ ሽግግር እንድትመለስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ሲጠይቁ ነበር። https://www.bbc.com/amharic/news-59633484 +health የአየር ንብረት ለውጥ ተላላፊ በሽታዎች የበለጠ እንዲስፋፉ ምክንያት እየሆነ ነው ሳይንቲስቶች እንደሚሉት 50 በመቶ የሚሆኑትን የምድራችንን ተላላፊ በሽታዎች የሚያባብሰው የአየር ንብረት ለውጥ ነው። የአየር ንብረት ሞቃታማ መሆኑን ተከትሎ እንስሳት እና ትንኞች ከቦታ ቦታ ስለሚዘዋወሩ በሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ ይስፋፋሉ። ይህ ቪዲዮ የአየር ንበረት ለውጥና የተላላፊ በሽታዎችን መስፋፋት በተመለከተ በአጭሩ ይዳስሳል። https://www.bbc.com/amharic/articles/ceqyqzg71y4o +politics በሙስና ሲከሰሱ የነበሩት ሲሪል ራማፎሳ በኤኤንሲ መሪነታቸው እንዲቀጥሉ ተመረጡ በሙስና ክስ ሲብጠለጠሉ የነበሩት እና በፓርቲያቸው መሪነት ላይ ጥያቄ የተነሳባቸው የደብብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲን) መሪነታቸው እንዲቀጥሉ የመተማመኛ ድምጽ አገኙ። ራማፎሳ ተፎካካሪያቸው የሆኑትን የቀድሞ የጤና ሚኒስትራቸው የነበሩትን ዝዌሊ ምኺዜን ያሸነፉት 2,476 ለ 1,897 በሆነ ድምጽ ነው። ፕሬዝዳንት ራማፎሳ የፓርቲው መሪነትን ያሸነፉት ባለፉት ሳምንታት ስማቸው በሙስና ሲነሳ ከሰነበተ በኋላ ነው። ተቀናቃኛቸውም በተመሳሳይ በሙስና የሚከሰሱ ቢሆንም ለመሪነት ቦታው ሲወዳደሩ ቀላል ያማይባል ድጋፍን አግኝተዋል። ሁለቱም ፖለቲከኞች ግን የሚቀርብባቸውን ክስ አይቀበሉትም። ሲሪል ራማፎሳ በኤኤንሲ የመሪነት መንበር ላይ ለመቀጠል መመረጣቸው ከሁለት ዓመት በኋላ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ለመወዳደር ቀዳሚ ቦታ ላይ ያስቀምጣቸዋል። ነገር ግን ራማፎሳ አሁንም ከቤታቸው ሶፋ ውስጥ በሌቦች ተዘርፏል ስለተባለው 580,000 ዶላር ምንጭ ጋር በተያያዘ በፖሊስ ምርመራ ይደረግባቸዋል እየተባለ ነው። በአገሪቱ ፓርላማ አፈጉባኤ የተቋቋመው የሕግ ባለሙያዎች ቡድን ራማፎሳ ሕገ መንግሥቱን እና የፀረ ሙስና ሕግን በመጣስ ከሥልጣን የሚያስነሳ ክስ እንዲመሰረትባቸው ሃሳብ አቅርቦ ነበር። ነገር ግን ኤኤንሲ በፓርላማው ያለውን የበላይነት በመጠቀም የሕግ ባለሙያዎች ያቀረቡትን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ በማድረጉ ነው ለፓርቲው መሪነት የተወዳደሩት። የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የገዢው ፓርቲ መሪ ሆኖ ለመቀጠል ከዝዌሊ ምኺዜ ብርቱ ፉክክር ነው የገጠማቸው። ፕሬዝዳንቱ ለገዢው የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ፓርቲ መሪነት ጠንካራ ፉክክር የገጠማቸው ከሙስና ጋር በታያያዘ ሥልጣን እንዲልቁ ካስገደዷቸው ከቀድሞው የጤና ሚኒስትራቸው ዝዌሊ ምኺዜ ነው። የቀድሞ የጤና ሚኒስትር በጆሃንስበግ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ በመጨረሻዎቹ ሰዓታት ላይ ከፍተኛ ድጋፍ ለማግኘት ችለው ነበር ተብሏል። ሁለቱ ዕጩዎች የኤኤንሲ መሪ ለመሆን እንዲችሉ 4 ሺህ 426 ተሳታፊዎች ከታደሙበት የፓርቲው ጉባኤ ድጋፍ ለማግኝት ተፎካክረዋል። ራማፎሳ በግል የእርሻ ስፍራቸው ላይ ባለ ቤት ውስጥ የተሰረቀ የውጭ አገር ገንዘብ ሶፋ ስር ተገኝቷል መባሉን ለመሸፋፈን ሞክረዋል በሚል ክስ ከፓርቲው ጉባኤ በፊት ከሥልጣን እንዲለቁ ጫና እየተደረገባቸው ነበር። በአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ በኩል የቀረበው ገለልተኛ ሪፖርት ራማፎሳ ሕግ ተላልፈው ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል። ሆኖም ፕሬዝዳንቱ የፈጸምኩት ነገር የለም ብለዋል። ባለፈው ማክሰኞ የገዢው የኤኤንሲ ፓርቲ የፓርላማ አባላት ራማፎሳን ከሥልጣን ለማስነሳት የሚደረገውን ጥረት ለፕሬዝዳንቱ ድጋፍ በመስጠት እንዲያከሽፉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር። ባለፈው አርብ የተወሰኑ የጉባኤው ተሳታፊዎች ራማፎሳን ሲቃመው እና ገንዘብ የተሰረቀበትን ፓላፓላ የተባለውን የእርሻ ቦታ ስያሜ በጽሁፍ ይዘው ታይተዋል። የማካዚህ ደጋፊዎች “ለውጥ” የጠየቁ ሲሆን ራማፎሳ “ተመልሶ አይመጣም” ሲሉ ተደምጠዋል። የቀድሞ የጤና ሚኒስትር በኮቪድ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ አንድ የኮሚኒኬሽን ኩባንያ ከቤተሰባቸው ጋር በጥቅም የተሳሰረ ውል ፈጽሟል ከተባለ በኋላ ነበር ከሥልጣን ለመውረድ የተገደዱት። እሳቸው ግን ይህንን የቀረበባቸውን የሙስና ክስ አይቀበሉትም። https://www.bbc.com/amharic/articles/crgzypzj4jpo +politics የዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል የመሆን ጥያቄ አስርት አመታትን ይወስዳል ተባለ "ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ አስርት አመታትን እንደሚወስድ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስታወቁ። ፕሬዚደንቱ በስትራስቡርግ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ዩክሬን ውሳኔውን እየጠበቀች በምትኩ ወደ ትይዩው የአውሮፓ ማህበረሰብ ልትቀላቀል እንደምትችል ጠቁመዋል። ይህም ሁኔታ የአውሮፓ ህብረት አባል ያልሆኑ አገራት የአውሮፓን የደህንነት መዋቅር በሌላ መንገድ እንዲቀላቀሉ ያስችላቸዋል ብለዋል ፕሬዚዳንት ማክሮን። የፕሬዚዳንቱ ንግግር የተደመጠው ሩሲያ ምስራቃዊ ዶንባስን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ፍልሚያ እያደረገችበት ባለችበት ወቅት ነው። አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ መከላከያ ባለስልጣን የሩሲያን ግስጋሴ ""አንድ አሃዝ ያለው የኪሎ ሜትር እርምጃ"" ሲሉ ገልጸውታል። በሉሃንስክ ግዛት የሚገኙ የዩክሬን ባ��ስልጣን በበኩላቸው ከባድ ጦርነቶች እየተካሄዱ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዩክሬን ለአውሮፓ ህብረት አባልነት ጥያቄ ያቀረበችው በዚህ አመት የካቲት ወር ላይ ከሩሲያ አራት ቀናት ወረራ በኋላ ነው። ""ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል እንድትሆን የመፍቀድ ሂደት ብዙ አመታትን ምናልባትም በርካታ አስርት ዓመታትን እንደሚወስድ ሁላችንም በሚገባ እናውቃለን"" ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። አክለውም "" የአባልነት መስፈርቶችን ዝቅ ለማድረግ ካልወሰንን በስተቀር እውነታው ይህ ነው። የአውሮፓ አንድነትን በሌላ መልኩ ልናስበው ይገባል"" ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ዩክሬንን የአውሮፓ ህብረት አባል ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት ጥብቅ የአባልነት መስፈርቶችን ከማስተካከል ይልቅ ""ትይዩ የአውሮፓ ማህበረሰብ"" ሊታሰብበት እንደሚገባ ገልጸዋል። ይህ ትይዩ የአውሮፓ ማህበረሰብ ""በአውሮፓ ውስጥ ያሉና የእኛን እሴቶች የሚጋሩትን አንድ ላይ የማምጣት መንገድ ነው"" ብለዋል። የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌር፣ በሰኔ ወር በዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባልነት ጥያቄ ላይ የህብረቱ ስራ አስፈጸሚ የመጀመሪያ ምላሹን በጽሁፍ ይሰጣል ብለው ነበር። የዩክሬን ባለስልጣናት ሰኞ እለት እንዳረጋገጡት ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት የአባልነት ማመልከቻ ሁለተኛውን ጥያቄ ለብራሰልስ ማቅረቧን አስረድተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61369470 +politics በቻይና የሚደገፈው የአፍሪካ ቀንድ የሰላምና የደኅንነት ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን የሚያደርግና የአካባቢውን አገራት የሚያሳትፍ በቻይና የሚደገፍ ስብሰባ ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይጀመራል። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነ ስብሰባ የተሰናዳው በቻይና መንግሥት ድጋፍ እንደሆነ ተነግሯል። ስብሰባው በቻይና መንግሥት ድጋፍ መደረጉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቻይና በአካባቢው ሁነኛ ተጽዕኖ እንዲኖራት መፈለጓ እንደ አንድ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። ቻይና የአካባቢው ድኅንነት ሁኔታ ያሳሰባትም በእነዚህ አገራት ከፍ ያለ መዋዕለ ነዋይ በማፍሰሷ ነው የሚሉ አልጠፉም። በዚህ የሁለት ቀናት ኮንፈረንስ ከምሥራቅ አፍሪካ አገራት የሚወከሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል። እነዚህ ብዙዎቹ አገራት በአህጉሪቱ ከፍተኛ የሚባል የቻይናን የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ናቸው። የኮንፈረንሱ አሰናጅ ኢትዮጵያም ከቻይና መንግሥት ከፍተኛ የሚባል የገንዘብ ድጋፍ እና መዋዕለ ነዋይ የምታገኝ አገር ናት። ይሁንና ባለፉት ዓመታት በአገሪቱ እየተባባሰ የመጣው አለመረጋጋትና የእርስ በእርስ ጦርነት ቻይናን ሊያሳስብ የሚችል እንደሚሆን ተገምቷል። በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መባቻ በኬንያ ጉብኝት ላይ የነበሩት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ለሰላም በሚደረገው ጥረት አገራቸው “ትልቅ ሚና” መጫወት እንደምትፈልግ ተናግረው ነበር። ይህን ካሉ በኋላ ብዙም ሳይሰነብት ቤይጂንግ ባልተለመደ ሁኔታ ለአካባቢው ልዩ መልዕክተኛ መሰየሟ አይዘነጋም። ምንም እንኳ ዛሬ የሚጀመረውን ኮንፈረንስ በቻይና ድጋፍ የሆነ ቢሆንም በኢትዮጵያ ተዋጊ ወገኖችን ለማደራደር ቻይና ያሳየችው ይፋዊ ፍላጎት የለም ። ኮንፈረንሱ ቻይና በአካባቢው ያላትን የኢንቨስትመንትና የውጭ ፖሊሲ ፍላጎቶች እየጨመረ ስለመምጣቱ እንደ አንድ ማሳያ የወሰዱት አልጠፉም። ቻይና ለአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሾመችው ባለፈው የካቲት ወር ነበር። አንጋፋ ዲፕሎማት ናቸው የሚባሉት ዡ ቢንግ ለዚህ ሹመት ከመታጨታቸው በፊት በፓፓዎ ኒው ጊኒ አምባሳደር ሆነው ማገልገላቸው ተጠቅሷል። ያም ብቻ ሳይሆን ግለሰቡ አገራቸውን ወክለው በአፍሪካ፣ በአሜሪካና በኦሽኒያ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሠሩ ናቸው። ቤይጂንግ በምሥራቅ አፍሪካ ሰፊ የሆነ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች ያሏት ሲሆን በጂቡቲ ያቋቋመችው ግዙፍ የባሕር ኃይል ሰፈርም የሚጠቀስ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ በቀጠናው ለሚገኙ አገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር ከመስጠቷ በተጨማሪ በአገራቱ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ታከናውናለች። በኢትዮጵያ ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት፣ የደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ አስተማማኝ መረጋጋት ሊሰፍን አለመቻሉ እንዲሁም አሁንም እልባት ያላገኘው የሱዳን ፖለቲካዊ ቀውስ ለቀጠናው ደኅንነት ፈተና የሆኑ ጉዳዮች ናቸው። ከቻይና በተጨማሪ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ አገራት ጉዳይን በቅርበት የሚከታተሉ ልዩ መልዕክተኞች እንዳሏቸው ይታወቃል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cnexwjz3xx8o +business 5 ጥያቄዎች ለስድስት ኢትዮጵያውያን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለሙያ ሴቶች አዲሱን ዓመት 2015 ዓ.ም. ምክንያት አድርገን በተለያየ የሳይንስ ዘርፍ ያሉ ስድስት ኢትዮጵያውያን ሴቶችን አምስት ጥያቄዎች ጠይቀናል። ዶ/ር ሶስና ኃይሌ- በአሜሪካ፣ ኢሊኖይ ግዛት፣ በኖርዝዌስተርን ዩኒቨርስቲ የማቴሪያልስ ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰር እንዲሁም ኬሚስት በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ሥራዬ ከኢነርጂ ሳይንስ ጋር ይገናኛል። ዋናው ትኩረቴ ደግሞ ኤሌክትሮኬሚካል ኢነርጂ ትራንስፎርመሮች ናቸው። በሙያዬ እጅግ ያስገረመኝ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ነው። ይህም አሜሪካ የሰው ልጅን ጨረቃ ላይ ከላከችበት የስኬት ታሪክ ጋር ተመሳሳይ ነው። የሕዳሴ ግድቡን ጨረቃ ላይ ከመውጣት የሚለየው ዓለምን በሳይንስ ከማሳመን አልፎ የአየር ንብረት ቀውስን ሳያባብስ በአፍሪካ ቀንድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከኃይል ድህነት (Energy Poverty) መንጭቆ ማውጣቱ ነው። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? ያለፈው ዓመት ትልቁ ስኬቴ ከአሜሪካ የኢነርጂ ክፍል በተመደበ ገንዘብ የጥናት ቡድን አሰባስቤ ‘ኢነርጂ ፍሮንቲርስ ሪሰርች ሴንተር’ የተባለ የጥናት ማዕከል መቋቋሙ ነው። ሥራችን፣ ሀይድሮጅን ከጠጣር አካሎች ጋር ስለሚያደርገው ግንኙነት የዓለምን መረዳት የሚያሳድግ ነው። ለአራት ዓመት 10 ሚሊዮን ዶላር አግኝተናል። ጥናታችን፣ በኤሌክትሪካል ኢነርጂ አማካይነት ውሃን በመክፈል ሃይድሮጅን ለማምረት መሠረት ይጥላል። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? ኧረ ዕቅዶቼ ብዙ ናቸው! ያለው ጊዜም አጭር ነው! ዕቅዶችሽን ያለ ተጨባጭ ግብ በአደባባይ መናገር ደግሞ ወደ ውድቀት ሊያመራም ይችላል። እኔና የጥናት ቡድኔ፣ ኤሌክትሪሲቲ በመጠቀም ውሃን ለመክፈል የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፉ መሰናክሎችን መፍታት ነው ዕቅዳችን። ልክ እንደ ሕዳሴ ግድቡ፣ የኤሌክትሪክ ኃይልን ከካርበን ነጻ ከሆኑ ምንጮች ማመንጨት ነው ሐሳቡ። ኤሌክትሪኩን ኋላ ላይ ለመጠቀም ሀይድሮጅን ማምረት ቁልፉ ነው። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? አይ ምንም የለኝም! የዳንኤል ካህንማን “Thinking, Fast and Slow” ማንበብ ፈልጌ ነበር ግን ገና ጊዜ አግኝቼ አልጀመርኩትም። ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? የዌብ ስፔስ ቴሌስኮፕ ምሥሎች እጹብ ድንቅ ናቸው። አስትሮፊዚሲስቶች 13.7 ቢሊዮን ዓመታት ወደኋላ ተጉዘው ማየት ችለዋል። እንዴት ወደዚች ምድር እንደመጣን ለ��ወቅ መመራመራችን ከሌሎች የምድራችን ፍጡራን የተለየን ያደርገናል። እነዚህ ስለጋላክሲዎች አፈጣጠር የሚነግሩን ምሥሎች አንዳች መንፈሳዊ ኃይል አላቸው። ምድራችንን ጠብቀን ለልጅ ልጆቻችን እንደምናወርስ ተስፋ አደርጋለሁ። ቤተልሔም ደሴ- የአይኮግ ኤኒዋን ካን ኮድ ዋና ኃላፊትና ኮምፒውተር ሳይንቲስት በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ቃላት፣ ሐረግና ዓረፍተ ነገር ተሰጥቶት ወደ ምሥል የሚቀይረው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሠራሽ ልኅቀት) አስደናቂ ነው። ኤአይ የሥዕል ውድድርም አሸንፏል። ይህ እውን ሆኖ ስናይ፣ ሳናስበው ወዴት እየሄድን ነው? የሚል ጥያቄም ያጭራል። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? የ2014 ዓ. ም. ከፍታዬ ‘Rebel Girls’ የተባለው መጽሐፍ ላይ መውጣቴ ነው። ከድሮም የልጆች መጽሐፍ ላይ መውጣት አልም ነበር። እኔ ባለሁበት መጽሐፍ እነ ቢሊ አይሊሽ፣ እነ ቴይለር ስዊፊት አሉበት። ስለዚህ ይገዙታል ማለት ነው። ሲገዙት ደግሞ እነሱ ጋር ደረስኩ ማለት ነው። መጽሐፉ እስካሁን 5 ሚሊዮን ኮፒ ተሸጧል። ትልቁ የሰው ልጅ ከፍታ ሌሎች ሰዎችን ማነሳሳት ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? የ2015 ዓ. ም. ዕቅዴ ከ13 ዓመቴ ጀምሮ ያለምኩትን ማሳካት ነው። ይህም ተንቀሳቃሽ የኮምፒውተር ማዕከል  ነው። ‘ዲጂ ትራክ ኢትዮጵያ’ ይባላል። ይህም 40 ጫማ ኮንቴነር ሲሆን በፀሐይ ይሠራል። በየከተማው እየዞረ ኮዲንግ እና ሮቦቲክስ ያስተምራል። በጣም በጣም በጉጉት የምጠብቀው እሱን ነው። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ Shoe Dog [ፊል ናይት] 21 Lessons for the 21st Century [ዮቫል ኖሀ ሀሪሪ] The Thing Around Your Neck [ቺማማንዳ ንጎዚ አዲቺ] ቢታዩ የምላቸው ፊልሞች ደግሞ The Gentlemen፣ Rick and Morty እና Love, Death & Robots ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሸል? ለምን? ኢንተርኔት! ምንም ጥያቄ የለውም። ኢንተርኔትን የመሰለ ፈጠራኮ የለም። ሕይወት ለውጧል። የዕውቀት ሽግግርን አስችሏል። ተደራሽነቱ በመስፋቱና በመላው ዓለም በመዳረሱ በተለይም በወጣቶች ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አለው። ዶ/ር ሩት ድሪባ- የላስት ማይል ኸልዝ ቴክኒካል አማካሪና የሕክምና ባለሙያ በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ከመቶ ዓመታት በላይ ለወባ በሽታ ክትባት ለማግኘት ሲሞከር ነበር። ክትባቱ ተገኝቶ በቅርቡ ይፋ ተደርጓል። እስከ 80 በመቶ የወባ በሽታን የመከላከል አቅም ስላለው በበሽታው ሕይወታቸውን የሚያጡ ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ ተስፋ ሰጥቷል። በ2014 ዓ. ም. በጣም ያስገረመኝ እና ተስፋ የሰጠኝም ግኝት ነው። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? ትልቁ ስኬቴ፣ በዓይነቱ ልዩ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ በጤና ጥበቃ እንዲሁም በላስት ማይል ኸልዝ የተተገበረው ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሥልጠና የሚሰጥበት (Blended Learning) ዲዛይን እና ትግበራ ላይ መሳተፌ ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ፣ በ2015 ዓ. ም. የሕጻናትን ጤና የሚያሻሽል ሥራ ላይ የመሳተፍ፣ ማኅበረሰቡን እንዲሁም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን ያማከለ ሥራም የመሥራት እቅድ አለኝ። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ Winning with People [ጆን ማክስዌል] The Checklist Manifesto [በአቱል ጋውንዴ] Our Iceberg is Melting [ሆልገር ራታግበር እና ጆን ኮተር] ቢታዩ የምላቸው ፊልሞች ደግሞ Fractured፣ Unforgivable እና Sweet girl ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? የሚደንቀኝ ፈጠራ ክትባት ነው። በሽታን፣ በበሽታ አምጭ ተሕዋስ ወይም ባለው ንጥረ ነገር ሰውነትን አለማምዶ በሽታን እንዲከላከል ቀድሞ ማዘጋጀት እና ስቃይን ብሎም ሞትን መቀነስ በጣም ትልቅ ፈጠራ ነው። ብርሃን ታዬ- የቴክኖሎጂ ፖሊሲ አጥኚ እና ተንታኝ በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ያስገረመኝ ዶትፕሎት (DotPlot) መተግበሪያ ነው። ይሄ መተግበሪያ ስልክ ላይ ተጭኖ ሴቶች የጡት ካንሰርን ቀድመው ማወቅ እንዲችሉ ጡታቸው ላይ የሚታይ ለውጥን ይከታተሉበታል። ገና በሕክምና ፈቃድ ሰጪዎች ይሁንታ እስከሚሰጠው እየጠበቀ ቢሆንም፣ እንዲህ ያለ መተግበሪያ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሴቶች የጡት ካንሰርን እንዲከላከሉ ይረዳል። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? ትልቁ የ2014 ዓ. ም. ስኬቴ በቋሚነት የአካል ብቃት እየሠራሁ 10 ኪሎ ሜትር መሮጤ ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? ዕቅዴ ዋጋ ከምሰጣቸው ሰዎች ጋር ውብ ጊዜ ማሳለፍና በበይነ መረብ ላይ የማሳልፈውን ጊዜ ቀንሼ ከሰዎች ጋር የበለጠ መነጋገር ነው። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ Do Not Disturb: The Story of a Political Murder and an African Regime Gone Bad [ሚሼላ ሮንግ] Seven and a half Lessons about the Brain [ሊሳ ፌልድማን] Race after Technology [ሩሀ ቤንጃሚን] ፊቸር ፊልም እንኳን ብዙ አላይም። ግን ተከታታይ ፊልሞች ልጠቁም። እነዚህም Paper Girls፣ Veep እና The office ናቸው። ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? ኅትመትን የሚበልጥ ፈጠራ ያለ አይመስለኝም። ሕይወት የሰጠን ኅትመት ነው። ቤተልሔም ላቀው- የሊሄም ኒውትሪሽን መሥራች፣ የቤኑ ፉድስ አጋር መሥራችና ኃላፊት፣ የአክት ፎር ፉድ አክት ፎር ቼንጅ ንቅናቄ መሪ እንዲሁም ኒውትሪሽኒስት በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ኢትዮጵያ ውስጥ ስብ መምጠጥ [Fat Removal] ተጀምሯል። ይሄ ሂደት እኛ አገር እንዲህ በቅርብ ጊዜ ይገባል ብዬ አልገመትኩም ነበር። በጣም ነው ያስደነቀኝ። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? የዓለም አቀፉ ‘አክት ፎር ፉድ አክት ፎር ቼንጅ’ ንቅናቄ የኢትዮጵያ ወጣቶች ተወካይ ሆኜ የተለያዩ ሥራዎችን እሠራ ነበር። 2014 ዓ. ም. በጣም ስኬታማ የሆንበት ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? ሊሄም በትንሽ ደረጃ ነበር የሚሠራው። በ2014 ዓ. ም. ግን አድጎ፣ ቢሮ ተከራይተን መሥራት ጀምረናል። ቢዝነሱ ከተጀመረ እንኳን ቆይቷል። እና በ2015 ዓ. ም. ከአጋሮቻችን ጋር ተጣምረን ወደ ክሊኒክ የማሳደግ ዕቅድ ይዘናል። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ ትንሿ ቤተክርስቲያን [ገብረእግዚአብሔር ኪዳን] Zero to One [ፒተር ታይል] ሕክምና በቤታችን [በቀለች ቶላ] ፊልም እንኳን አላይም። በምትኩ ቢጎበኙ ብዬ የማስባቸውን ሦስት ቦታዎች ልንገርሽ። ላሊበላ፣ አክሱም እና የሩዋንዳው ‘ኪጋሊ ጄኖሳይድ ሜሞሪያል’ ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? የኢንዶስኮፒ ምርመራ መደረግ መቻሉ ያስገርመኛል። በእርግጥ ውስብስብ ሳይንስ አይደለም። አሁን ባለው መሣሪያ በቀላሉ የትኛውም ሆስፒታል ውስጥ ሊሠራ ይችላል። አንድን ግለሰብ ሳናፈርሰው ስላለበት ሂደት እንድናውቅ ያስችላል። የላብራቶሪ ምርመራና የደም ሕዋስ ማየት መቻል አሁን ላለንበት ዘመን ትልቅ ግኝት ነው። ሕሊና ኃይሉ ንጋቱ- በአሜሪካ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ፣ በርክሌ የኮምፒውተር ሳይንስ የፒኤችዲ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? በ2014 ዓ. ም. ካስደመሙኝ ፈጠራዎች አንዱ በኤአይ ሞዴል የሚፈጠሩ ምሥሎች የጥራት ደረጃ ነው። እነዚህ ሞዴሎች በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ። በአንድ በኩል እንደ ቤኖ ሳሙኤል ያሉ ባለሙያዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥነ ጥበብ ሲሠሩ ያስገርመኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ተገቢው ቁጥጥር ያልተደረገበት ቴክኖሎጂ ጉዳቱ ያሰጋኛል። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? ትልቁ ስኬቴ በአሶሴሽን ፎር ኮምፒውቲንግ ማሽነሪ ተቋም የኮምፒውቴሽናል እና ዳታ ሳይንስ ፌሎሺፕ ማሸነፌ ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? በ2015 ዓ. ም. በዩሲ በርክሌይ ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ዓመት ፒኤችዲ ትምህርቴን እከታተላለሁ። ዕቅዴም ከአፍሪካውያን አጋሮቼ ጋር ተጣምሬ ማኅበረሰባችንን የሚጠቅም ሥራ ማከናወን ነው። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ All about Love [ቤል ሁክስ] Race After Technology [ሩሀ ቤንጃሚን] Shadow King [መዓዛ መንግሥቴ ] ቢታዩ የምላቸው ፊልሞች Queen of Katwe፣ Us እና እረኛዬ ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? አንድ ፈጠራ መምረጥ ካለብኝ፣ የተለያዩ የሰውነት አካላትን በቀዶ ሕክምና መለወጥ (Organ Transplant) ይደንቀኛል። ለምን? የሚለው ግልጽ ነው። የሰዎችን ሕይወት ስለሚያተርፍ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c0wzew2yx90o +politics """ህይወቴን እንዳጣ የሚደረግ ሙከራ ነው"" አቶ ልደቱ አያሌው" "ለሦስተኛ ጊዜ ህክምና ለማግኘት ወደውጪ አገር እንዳይሄዱ የተከለከሉት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ድርጊቱ በህክምና እጦት ""ህይወቴን እንዳጣ የሚደረግ ሙከራ ነው"" አሉ። አቶ ልደቱ አያሌው ለቢቢሲ ይህንን የተናገሩት ለህክምና ወደ ውጪ አገር ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ ለሦስተኛ ጊዜ ከተስተጓጎለና ፓስፖርታቸው ከተወሰደ በኋላ ነው። ያለባቸው የጤና ችግር በአገር ውስጥ ሊታከም የማይችል ""የልብ ጉዳይ ነው። ከልብም የደም ቧንቧ መዘጋት [አርተሪ ብሎኬጅ] ነው። ስለዚህ ተገቢውን ህክምና ካላገኘሁ ለህይወቴ የሚያሰጋ ነው"" ነው ሲሉ ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ልደቱ ከዓመት ከስምንት ወር በፊት ተመሳሳይ ህክምና ማግኘታቸውን ገልጸው፤ በአሁኑ ጉዟቸው የተደረገላቸው ህክምና በትክክል ስለመስራቱ ለማረጋገጥና ተጨማሪ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ነበር። የጤና ችግራቸው ያለህክምና የሚድን ስላልሆነ እንዲሁም የሚያስፈልጋቸው ህክምና ደግሞ በአገር ውስጥ ስለሌለ ያሉበት ሁኔታ ""ለህይወቴ አስጊ"" ነው ብለዋል። በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው ለወራት በእስር ላይ የቆዩት አቶ ልደቱ አያሌው ባለባቸው የጤና ችግር ምክንያት እራሳቸውን ከዚህ በፊት ሲያደርጉት ከነበረው ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ ማግለላቸውን በቅርቡ መግለጻቸው ይታወሳል። የተደረገባቸውን ተደጋጋሚ የጉዞ ክልከላ በተመለከተ ""ምን ያህል ያለአግባብ ህይወቴን እንዳጣ እየተሞከረ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። እኔም ከዚህ የተለየ ትርጉም ልሰጠው አልችልም"" ብለዋል። አቶ ልደቱ ካለባቸው የልብ ህመም ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊ�� የተደረገላቸው ህክምና ያለበት ሁኔታን ለማወቅና ተጨማሪ ተከታይ ህክምና ለማግኘት ነበር ወደ አሜሪካ ሊጓዙ የነበረው። ሐሙስ ዕለት ወደ አሜሪካ ለመሄድ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ያቀኑት አቶ ልደቱ ሻንጣቸውን አስረክበው ወደ አውሮፕላን ለመሳፈር የመጨረሻ ፓስፖርት በሚያሳዩበት ጊዜ ከአገር እንዳይወጡ እገዳ እንዳለባቸው በመግለጽ እንደመለሷቸው ተናግረዋል። በዚህ ጊዜ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት የተጻፈ ደብዳቤን ቢያሳዩም ""የፍርድ ቤት እገዳ ስላለብህ መውጣት አይችሉም"" እንደተባሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ልደቱ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ ከአገር እንዳይወጡ በኢሚግሬሽን ሠራተኞች ተከልክለው እንደነበር መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ሁለቱንም ጊዜ ጉዞ እንዳያደርጉ የተከለከሉት በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መሆኑን ገልጸዋል። ከአገር እንዳይወጡ በተከለከሉበት ጊዜ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አቤቱታ አቅርበው የነበሩት አቶ ልደቱ፤ ክልከላው በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አለመፈጸሙን መግለጹ ይታወሳል። የደኅንነት መሥሪያ ቤቱን ምላሽ ተከትሎም የነበረው ችግር ተፈትቷል በሚል ጉዞ ለማድረግ መነሳታቸውን የሚጠቅሱት አቶ ልደቱ፤ ነገር ግን ውጤቱ ቀደም ካሉት ጉዞዎች ጋር ተመሳሳይ ሆኗል ብለዋል። ሐሙስ ዕለት ጉዞ ማድረግ እንደማይችሉ በተነገራቸው ጊዜም ለኮሚሽኑ ዋና ኃላፊ ለዶክተር ዳንኤል በቀለ በስልክ እንዳሳወቁና እሳቸውም የኢሚግሬሽን ባለስልጣናትን ለማነጋገር መሞከራቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዶ/ር ዳንኤልም ያገኙት መልስ ""መውጣት አይችልም፤ የፍርድ ቤት እገዳ አለበት "" የሚል ነበር ያሉት አቶ ልደቱ ከዚህ በኋላ ለጉዞ አስረክበው የነበረውን ሻንጣቸውን በመቀበል መመለሳቸውን ገልጸዋል። ቀደም ባለው የጉዞ ክልከላ ወቅት ""የመለሱኝ ብሔራዊ ደህንነቶች ናቸው። ሁለቱንም ጊዜ ሲመልሱኝ የፍርድ ቤት እገዳ አለብህ፤ መውጣት አትችልም እያሉ ነው። የት ነው የፍርድ ቤት እገዳ ያለብኝ ስላቸው የሚነግሩኝ ነገር የለም።"" ብለዋል። ለሦስተኛ ጊዜ ለህክምና የሚያደርጉት ጉዞ በማያውቁት ምክንያት መስተጓጎሉን የሚናገሩት አቶ ልደቱ፤ ""ሁለት ጊዜ ከአገር እንዳልወጣ የከለከለኝ ብሔራዊ ደኅንነት ነበር"" ብለዋል። ቢቢሲ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት እንዲሁም ከኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለአሁን አልተሳካም። በአንደበተ ርቱዕነታቸው የሚታወቁት አቶ ልደቱ አያሌው ለረጅም ዓመታት በተቃውሞው ፖለቲካ ውስጥ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ፤ በተለይ በአወዛጋቢው የ1997 ምርጫ ወቅት በነበራቸው ሚና ከፍ ያለ እውቅና አግኝተዋል። አቶ ልደቱ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ የተለያዩ ክሶች ቀርበውባቸው በኦሮሚያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ለበርካታ ወራት የቆዩ ሲሆን በመጨረሻም ከቀረቡባቸው ክሶች ነጻ ተብለው መለቀቃቸው ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56778226 +health ሕንድ በኮቪድ-19 ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች ካሳ ልትከፍል ነው "የሕንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መንግሥት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸው ላለፈ ሰዎች ቤተሰቦች እከፍለዋለው ያለውን ካሳ ማጽደቁ ተሰምቷል። ለእያንዳንዱ ሟች የሚከፈለው የካሳ መጠን ደግሞ 50 ሺ ሩፒ ወይም 647 ዶላር መሆኑ ተገልጿል። በሕንድ እስካሁን ባለው ይፋዊ መረጃ መሰረት 447 ሺ ዜጎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። ነገር ግን ባለሙያዎች እንደሚሉት የሟቾች ቁጥር መንግስት ከሚለው በአስር አጥፍ ሊበልጥ ይችላል። የሕንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኃላፊው ኤምአር ሻህ ሰኝ ዕለት ''የሟቾች ወራሽ አልያም የቅርብ ዘመ�� ካሳውን ያገኛል'' ብለዋል። ፍርድ ቤቱ አክሎም የሟቾች ቤተሰቦች ተገቢውን ማስረጃና ሰነድ ለመንግሥት ካስገቡ በኋላ በሚቀጥሉት 30 ቀናት ውስጥ የካሳ ክፍያውን ከመንግስት ማግኘት ይችላሉ ብሏል። ባለፈው ሰኔ ወር ጠበቆችና የመብት ተቆርቋሪዎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ እንዲሳተፍና በኮቪድ-19 ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሰዎች ካሳ እንዲከፈል ፊርማ አሰባስበው ነበር። በወቅቱም የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ብሄራዊ አደጋ ተብሎ ከታወጀ ለተጎጂዎች መንግሥት ካሳ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት የብሄራዊ አደጋ አመራር መመሪያን በመጥቀስ ተከራክረዋል። መመሪያው እንደሚለው በማንኛው ብሄራዊ አደጋ ወቅት ተጎጂዎች ከመንግስት እስከ 400 ሺ ሩፒ የሚደርስ ካሳ ሊከፈላቸው እንደሚገባ ተጠቅሷል። ""መንግስት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ገንዘብ እንዳወጣ እናውቃለን። ነገር ግን በመመሪያው መሰረት መንግስት 400 ሺ ሩፒ ለተጎጂዎች መክፈል ነበረበት። ወይም ደግሞ ለደሃ ማህበረሶች ከፍተኛውን የገንዘብ መጠን መስጠትና ደህና ኑሮ ላላቸው ደግሞ ዝቅተኛውን መስጠት ይቻል ነበር"" ብለዋል ፊርማውን ሲያሰባስቡ ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ጋወራቭ ባንሳል። የፌደራል መንግስት እንደሚለው የካሳ ክፍያው የሚፈጸመው በኮቪድ-19 ምክንያት የቤተሰብ አባል ለሞተባቸው ሰዎች ሲሆን ግለሰቡ አልያም ግለሰቧ በቫይረሱ ምክንያት ስለመሞታቸው ደግሞ ተገቢው ማስረጃ መቅረብ አለበት። የካሳ ክፍያውን የሚፈጽሙት ደግሞ የግዛት መንግስታት ናቸው ተብሏል። ኬራላ እና ራጃስታን የተባሉት ግዛቶች ደግሞ የካሳ ክፍያው ከፍተኛ ጫና እንደሚያደርስባቸው በመግለጽ የፌደራሉ መንግስት ክፍያውን እንዲፈጽም ጠይቀዋል። እንደ ካርናታካ ያሉት ግዛቶች ደግሞ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች እስከ 100 ሺ ሩፒ የሚደርስ የካሳ ክፍያ ለመፈጸም መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። እስካሁን 16 ቤተሰቦች የካሳ ክፍያውን እንዳገኙ የአካባቢው ገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-58799031 +health "ኮሮናቫይረስ ፡ 'በጦርነት አድጌ በወረርሽኝ አልሞትም""" """በጦርነት ነው ያደግኩት፤ በወረርሸኙ አልሞትም።"" ማርጋሬት አልኮክ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ጀርመን በእንግሊዝ ላይ ያደረሰችው ""ዘ ብሊትዝ"" ተብሎ የሚጠራው የቦምብ ጥቃት በመጠለያ ውስጥ ሆነው ያን ፈታኝ ጊዜ አልፈውታል ። ከዚያም ባሕር፣ ውቅያኖስ ተሻግረው ወደ አውስትራሊያ ተወሰዱ። ላኪ ማርቲን እባላለሁ፤ የ89 ዓመቷ ማርጋሬት አያቴ (ናና) ናት ያንን የጦርነት ጊዜ በጨለምተኝነት አታወሳውም፤ በተቻለ መጠን ሳቅና ቀልድ በተሞላበት መልኩ ነው ጦርነትን የመሰለ አስከፊ ነገር የምታወራው። ስለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝም እንዲሁ በቀልድ ነው የምታወራው። ""አንዳንዴ በምን ተአምር ነው እንዲያው እዚህ ወረርሽኝ ላይ የጣለኝ፤ እንዴት በህይወት እያለሁ ይሄን አየሁ"" ትለኛለች ስደውልላት። ከዚያም ትቀጥልና ""የከፋ ነገር ስላየሁ ወረርሽኙ ብዙም አያስጨንቀኝም"" ትለኛለች። በጥር ወር ላይ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአውስትራሊያ ሲያጋጥም አያቶቼ የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከል በመሆናቸው ወላጆቼም ሆነ እኔ ከበሽታው እንደሚጠበቁና ምንም እንደማይነካቸው እርግጠኛ ነበርን። ነገር ግን ግምታችን የተሳሳተ ነበር በአምስት ወራት ውስጥ በአውስትራሊያ ከተከሰተው 247 ሞቶች መካከል 156ቱ በአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በርካታ አረጋውያንም ሊያልቁ የቻሉበት ምክንያትም የጤና ሥርዓቱ እነዚህን ተጋላጭ የኅብረተሰቡ ክፍሎችን ችላ በማለቱ ነው ተብሎ እየተተቸ ነው። በተለያየ የስልጣን እርከን ደረጃ ላይ የሚገኙ ኃላፊዎችም ለዚ�� ክፍተት መፈጠር ጥያቄዎች እየቀረቡላቸው ነው። በአውስትራሊያ ውስጥ 180 ሺህ ያህል አረጋውያን በእንክብካቤ ማዕከል ውስጥ ይኖራሉ። እነዚህ ማዕከላት በእርዳታ ድርጅቶች፣ በግል ኩባንያዎችና በመንግሥት መስሪያ ቤቶች የሚተዳደሩ ናቸው። የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ እነዚህም ማዕከላት በፍጥነት ነው ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያስገቧቸው። አንዳንዶቹም መንግሥት ካስተላለፈው መመሪያም በማፈንገጥ እንግዶች እንዳይጎበኙ አረጋውያኑም በክፍላቸው ብቻ እንዲቆዩና ሌሎች እንቅስቃሴዎችንም እንዳያደርጉ ሲከለክሉ ቆይተዋል። ማርጋሬት ያሉበት ማዕከል ለተወሰነ ጊዜ ጎብኚዎችን ቢከለክሉም በግቢው ውስጥ እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱና መውጣትም ስለፈቀዱላቸው እድለኛ ናቸው። ሌላኛዋ የ87 ዓመቷ አያቴ፤ የእሷም ስም በሚገርም ሁኔታ ማርጋሬት ነው፤ ከመጋቢት ጀምሮ በክፍሏ ውስጥ ናት። ማዕከሉ በሜልቦርን የሚገኝ ሲሆን፤ ይህች ከተማም የወረርሽኙ ማዕከል ሆናለች። አያቴ በክፍሏ ተወስና ነው ያለችው፤ የሚፈቀድላት በኮሪደሩ ላይ እንድትራመድ ብቻ ነው። ለወራትም ያለ ጎብኚ ብቻዋን ትበላለች፤ ወንበሯ ላይ ቁጭ ብላ ነው የምታሳልፈው። እንዲያም ሆኖ በዚህ አስጨናቂ ሰዓት በማዕከሉ እያገለገሉ ላሉ ሠራተኞች ምስጋናዋ ከፍ ያለ ነው። ""እንዲህ ተዘግቶ መቀመጥ ከባድ ቢሆንም ተቀብየዋለሁ፤ ከሁሉ በላይ ለእኔ ደኅንነትም ነው"" ትለናለች። ""ብዙም አልጨነቅም። ቤተሰቦቼን አለማየቴ ከባድ ቢሆንም እዚህ አይደሉም ማለት ግን አይወዱኝም ማለት አይደለምም"" በማለት ስሜታችንን ትነካዋለች። እሷ ያለችበትን ማዕከል የሚያስተዳድረው ኩባንያ በሁሉም ነገር ዝግጁ እንደሆነ አሳውቆናል። ጥብቅ የሆነ የጽዳት ቁጥጥርን ጨምሮ፣ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በከፍተኛ መጠን አከማችቷል። ነገር ግን በተለያዩ ሁለት ግዛቶች የሚገኙ ማዕከላት የቫይረሱን መዛመት መቆጣጠር አቅቷቸው በርካታ አረጋውያን ረግፈዋል፤ ይህም ሁኔታ ለቤተሰቦቻቸው ልብ ሰባሪ ሆኗል። እነዚህ አረጋውያን በቫይረሱ በቀላሉ እንደሚጠቁና፣ ተጋላጭም እንደሆኑ ማወቅ የሮኬት ሳይንስ አይደለም። በርካታዎቹ አረጋውያን ሌላ ተደራራቢ ህመሞች ያሉባቸው ሲሆኑ በማዕከላቱም ውስጥ ያለው የህክምና አገልግሎት የተወሰነ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የማዕከሉ ሠራተኞችም በተለያዩ ቦታዎች ከመስራታቸውም አንፃር ቫይረሱን በቀላሉ ያዛምታሉ። በየካቲት ወር ላይ በአውሮፓ በሚገኙ ማዕከላት ውስጥ ያሉ አረጋውያን በሚያሰቅቅ ሁኔታ እንደ ቅጠል እየረገፉ እንደሆነ ታሪኮች መውጣት ጀመሩ። ይህም ሁኔታ በአውስትራሊያ ሊያጋጥም እንደሚችል አገሪቷ ማወቅ ነበረባት የሚሉት በሞናሽ ዩኒቨርስቲ የጤና ሕግ ክፍል ኃላፊ ጆ ኢብራሂም ናቸው። ""የአውስትራሊያ ምላሽ በቂ አልነበረም። ለሚመጣው ነገር በሙሉ ዝግጁ አልነበረችም እናም አሁን የተፈጠረው ክስተት ሊያስደንቀን አይገባም"" ይላሉ ። ""ብዙ ሰዎች ይህ መሆኑ አይቀሬ ነበር ሲሉ ይሰማል። ይሄ ግን ትክክለኛ አይደለም፤ ምክንያቱም ምንም ማድረግ አንችልም ነበር የሚለውን ትርጉም ስለሚሰጥ ነው። የኮሮናቫይረስ በአረጋውያን ላይ ምን ያህል አደጋ እንደደቀነ ከግምት ውስጥም አላስገባነውም። በሌሎች አገሮች ላይ እያለቁ የነበሩትንም አረጋውያን መረጃዎች አላጤንነውም"" ይላሉ። በመጋቢት ወር ላይ በሲድኒ የሚገኝ ዶሮቲ ሄንደርሰን ሎጅ የተባለ የአረጋውያን ማዕከል ሠራተኛ በኮሮናቫይረስ መያዟ ተረጋገጠ፤ በግንቦት ወርም 21 በማዕከሉ የሚኖሩ አረጋውያንና ሠራተኞችም ተያዙ። ከእነዚህም ውስጥ ስድስቱ ሞቱ። ሌላ እንዲሁ በሲድኒ ውስጥ የሚገኝ ኒውማርች የተባለ ማዕከልም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ህሙማንን ወደ ጤና ማዕከል ከመላክ ይልቅ ክፍላቸው ውስጥ እንዲዘጉ አደረገ። ማዕከሉ የሠራተኞች ዕጥረት እንዲሁም የኮሮናቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችም በበቂ ሁኔታ አልነበሩትም። ይህንንም ተከትሎ 19 አረጋውያን ሲሞቱ በርካቶችም በቫይረሱ ተያዙ። የአረጋውያኑ መሞት በርካታ ጥያቄዎችን ቢያጭርም ይህ ለምን እንደተከሰተ አጥጋቢ ምላሽ የሚሰጥ አካል አልተገኘም። አሁንም ከክስተቱ ያልተማረችው አውስትራሊያ አረጋውያኗን በኮሮናቫይረስ እያጣች ነው። የቪክቶሪያ ግዛት እንደ አዲስ ወረርሽኙ እያገረሸባት ሲሆን ከማህበረሰቡ ስርጭት በተጨማሪ የአረጋውያኑ የእንክብካቤ ማዕከላት በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠቁ ነው። በአሁኑ ወቅትም 1 ሺህ 200 የሚሆኑ አረጋውያን በ97 ማዕከላት ውስጥ መያዛቸው ተረጋግጧል። ፕሮፌሰር ኢብራሂም እንደሚሉት የእንቅስቃሴ ገደቦች ብቻቸውን ቫይረሱን መግታት አይችሉም። ""በሽታው ቢያጋጥም ምን ማድረግ አለብን የሚለው ላይ የተቀመጠ ግልጽ ያለ ፖሊሲም ሆነ ይህንንም መቆጣጠር የሚችል መዋቅር አልተዘረጋም"" ይላሉ። የአረጋውያኑን የእንክብካቤ ማዕከላት በቀጥታ የሚመለከተው የፌደራል መንግሥቱን ቢሆንም ወረርሽኙን ደግሞ በየግዛቱ ያሉ የኅብረተሰብ ጤና ኃላፊዎች በበላይነት ይቆጣጠሩታል። ""በዚህም ምክንያቱ ኃላፊነቱ የማን ነው በሚል መወዛገብ ተፈጠረ። ይሄ ብቻ አይደለም የኮሮናቫይረስ ህሙማን ህክምናው መሰጠት ያለበት ሆስፒታል ወይስ ቤታቸው ውስጥ የሚለውም ላይ ውሳኔ ሳያገኝ እንዲሁ እያወዛገበ ነበርም"" በማለት ያስረዳሉ። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አንቶኒ አልባኔዝ በዚህ ሳምንት ሰፋ ያለ ምርመራና ኃላፊነት ሊወስዱ የሚባቸውም አካላት እንዲጠየቁ ተናግረዋል። ""በኒውማርች እንክብካቤ ማዕከል ካጋጠመን ክስተት ለምን አልተማርንም? ይህ የተከሰተው ከወራት በፊት ነበር"" በማለትም ይጠይቃሉ። በሜልቦርን የግዛቲቷና የፌደራል ኤጀንሲዎች ተጣምረውም በቪክቶሪያ የተከሰተውን የወረርሽኝ ቀውስ ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ነው። ለፕሮፌሰር ኢብራሂም ግን ዋናው ነገር ብሔራዊ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ በአውስትራሊያ የሚገኙ የእንክብካቤ ማዕከላት ሁኔታ ሊገመገም እንዲሁም ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል ይላሉ። ""በዚህም መንገድ ነው የትኞቹ ማዕከላት አደጋ ውስጥ እንዳሉ የምንረዳው"" የሚሉት ፕሮፌሰሩ አክለውም ""ከዚያ በመቀጠልም ያለምንም ማንገራገር ፈጣንና የማያዳግም እርምጃ ሊወሰድ ይገባል"" በማለትም ምክራቸውን ለግሰዋል። በእንክብካቤ ማዕከላቱ የተፈጠረውንም ሁኔታ የሚያጣራ የመንግሥት ቡድንም ተቋቁሟል። ከተለያዩ ቦታዎች የተገኙ መረጃዎች እንደሚያስረዱትም ለእነዚህ አረጋውያን መሞት ዋነኛ ምክንያቶች በማዕከላቱ የሚገኙ ሠራተኞች እጥረት እና በቂ ስልጠና አለማግኘት የሚጠቀሱ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ የመከላከያ ቁሳቁሶች እጥረትና የጤና ኃላፊዎች ምላሽ መዘግየት ይገኙበታል። የአውስትራሊያ ህክምና ማኅበር በበኩሉ መንግሥትን ተጠያቂ አድርጓል፤ ጥብቅ ምርመራም ያስፈልጋል እያለ ነው። በቪክቶሪያ የሚገኘው ቅርንጫፉ ፕሬዚዳንት ጁሊያን ራይት ለናይን ጋዜጣ እንደተናገሩት ቀውሱ ""የተገመተውን አሳዛኝ ክስተት ጥሎ አልፏል"" እንዳሉ አስነብቧል። በቪክቶሪያ የሚገኙ በርካታ አረጋውያን በኮሮናቫይረስ መሞታቸው አይቀሬ እንደሆነ የአውስትራሊያ ጤና ቢሮ ፀሐፊ ብሬንዳን መርፊ ከሰሞኑ ተናግረዋል። ውድ አያቶቼ በእነዚህ ማዕከላት አለመገኘታቸው እድለኛ ነኝ። አሁንም የሚገኙባቸው የእንክብካቤ ማዕከላት ከኮሮናቫይረስ ነፃ ናቸው። አንደኛዋ አያቴ ማርጋሬት ጎብኚም አያያትም፤ ሌላኛዋ አያቴ ��ርጋሬትን ግን በሳምንት አንዴ እንድናያት ተፈቅዶልናል፤ እናቴም ቅዳሜ እለት ሄዳ ነበር። ለረዥም ጊዜያት ሳቁ፣ ተቃቀፉ፣ ቀልድም ጣል እያደረጉ ኮሮናቫይረስ እንዳለ ዘነጉት። አያቴ ናና ቫይረሱ ከያዛት መሞቻዬ ነው ብትልም እንዲህ በቀላሉ እጅ አልሰጥም ትላለች። ""ህፃን እያለሁ ዳክዬዎች አባረሩኝ ግን አልደረሱብኝም፤ አሁንም ኮሮናቫይረስ ይይዘኛል የሚል ግምት የለኝም"" ብላ አስቃናለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-53680615 +sports ሞሮኮ ለዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ በመድረስ ታሪክ ሰራች ሞሮኮ ፖርቹጋልን በመርታት ለዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያዊት አፍሪካዊት ጋር በመሆን ታሪክ ሰራች። ሰሜናዊ አፍሪካዊቷ ሃገር ሞሮኮ ትናንት ታህሳስ 1፣ 2015 ዓ.ም ፖርቹጋልን በኳታር የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ 1ለ0ም በመርታት ነው ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፈችው። በዚህም ጨዋታ ከፍተኛ ስፍራ ተሰጥቷት የነበረውን ፖርቹጋልን እንዲሁም መሪ ተጨዋቿን ክርስቲያኖ ሮናልዶን ግስጋሴ ገትታለች። የሞሮኮው አጥቂ ዩሴፍ ኤን ኔሲሪ በመጀመሪያው አጋማሽ የማሸነፊያውን ጎል በማስቆጠር የአል ቱማማ ስታዲየምን ታዳሚዎች እንዲሁም የአረቡን አለምና አፍሪካውያንን አስፈንጥዟል። የአትላስ አናብስቱ ደጋፊዎች ስታዲየሙን ሞልተውት የነበረ ሲሆን በዓለም አቀፉ የስፖርት መድረክ ሞሮኮን ከፍ ያደረጋትንም ድል በከፍተኛ ደስታ ገልጸውታል። በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ጨዋታዎች 196 ጊዜ በመጫወት ክብረ ወሰኑን የተቆጣጠረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ50ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ቢገባም ጎል ሊቀናው አልቻለም። አገሩንም ወደ ግማሽ ፍጻሜ ሊያሳልፋት አልቻለም። በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ፈረንሳይን የምትፋለመው ሞሮኮ ከእረፍት በፊት ኤን ኔሲሪ፣ ያህያ አቲያት አላህ ያሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ጎል አስቆጥሯል። የፖርቹጋሉ አጥቂ ብሩኖ ፈርናዴዝ ከደቂቃዎች በኋላ አስደናቂ ጎል ለማስቆጠር ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም የጎሉ ብረት መልሶበት አገሩን እኩል የማድረግ እድሉ ለጥቂት ከሽፏል። በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታ ሞሮኮ ተጨዋቾች ቢጎዱባትም እንዲሁም እንዲሁም አጥቂዋ ዋሊድ ቼዲራ በስምንት ደቂቃ ተጨማሪ ጊዜ ውስጥ ሁለተኛውን ቢጫ ካርድ በማየቱ ከጨዋታው ቢሰናበትም ፖርቹጋል ጎል ማስቆጠር አልቻለችም። ሶስት የአፍሪካ ሃገራት ከዚህ ቀደም በነበሩ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ሩብ ፍጻሜ ደረጃ ላይ ቢደርሱም አንዳቸውም ቢሆን ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፍ አልቻሉም ነበር። ድንቅ ጨዋታን ላሳዩት የሞሮኮ ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች ኤን ኔሲሪ በቴስታ ያስቆጠራት ግብ ሃገሪቱን በታሪክ መዝገብ እንድትሰፍር በማድረግ ደስታቸውን ሌላ ደረጃ ላይ አድርሶታል። https://www.bbc.com/amharic/articles/czq32x0wl8eo +sports የፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች መለያ በስማቸው ምትክ የጥቁሮች ፍትህ ጥያቄ ሊሰፍርበት ነው "የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች ቀሪዎቹን 12 ጨዋታዎች ሲያደርጉ ከመለያቸው ጀርባ ላይ በስማቸው ፈንታ 'ብላክ ላይቭስ ማተር' [የጥቁሮች ህይወት ዋጋ አለው] የሚለውን ጽሁፍ እንደሚያሰፍሩ ተገለጸ። ከዚህ በተጨማሪም ፕሪምየር ሊጉ ከጨዋታ በፊትም ሆነ በኋላ የጥቁሮች የፍትህ ጥያቄ መለያ በሆነው ተንበርክኮ ድጋፋቸውን ለመግለጽና መልዕክት ማስተላለፍ የሚፈልጉ ተጫዋቾች አይከለከሉም ብሏል። ቀድሞ በተጀመረው የጀርመን ቡንደስሊጋ የሚጫወቱ እግር ኳስ ተጫዋቾች ነበሩ የጆርጅ ፍሎይድን ሞት አስመልከቶ ሜዳ ውስጥ ቀድመው መልዕክት ያስተላለፉት። የፕሪምየር ሊጉ 20 ቡድኖች ባወጡት የአቋም መግለጫ ላይ ""እኛ እንደ እግር ኳስ ተጫዋች በህብረት በመቆም የዘር መድሎን ለማስወገድ አብረን እንቆማለን"" ብለዋል። አክለውም ሁሉንም ያካተተ፣ መከ��በር ያለበትና በቀልም እንዲሁም በጾታ ሳይለይ ሁሉም እኩል እድል የሚያገኝበት ዓለም አቀፋዊ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። ‘ብላክ ላይቭስ ማተር’ የሚለውን መልዕክት የዘንድሮው የውድድር ዓመት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሁሉም ተጫዋቾች በጀርባቸው ላይ የሚያደርጉ ሲሆን በተጨማሪም በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን የሚያመሰግን መልዕክትም ያስተላልፋሉ። በርካታ የፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች በስልጠና ሜዳዎች ላይ በመንበርከክ ዘረኝነትን ያወገዙበትን ምስል ቀደም ሲል በማኅበራዊ መገናኛ መድረክ ላይ አጋርተዋል። ባለፈው ወር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሳል ህይወቱ ባለፈቸው የ46 ዓመቱ ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ሞት ምክንያት ዘረኝነት ይቁም በማለት ሜዳ ውስጥ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ አራት የጀርመን ቡንደስሊጋ ተጫዋቾች በእግር ኳስ ማኅበሩ ምርመራ ተደርጎባቸው ነበር። በመጨረሻ ግን የትኛውም ተጫዋች ቅጣት እንዳልተጣለበትና ተጫዋቾች በሚቀጥሉት ሳምንታት ዘረኝነትን በመቃወም መልዕክታቸውን ማስተላለፍ እንደሚችሉ የጀርመን እግር ኳስ ማኅበር አስታውቋል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከሦስት ወራት በኋላ በዝግ ስታዲየሞች በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ የሚጀመር ሲሆን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በርካታ ጥንቃቄዎች ይደረጋሉ ተብሏል። የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንና የኒውካስል እንዲሁም የቶተንሀም አማካይ ጀርሜይን ጄናስ ለቀሪዎቹ 12 ጨዋታዎች የሚተላለፈው መልዕክት በዘላቂነት ቢታሰብበት ጥሩ ነው ብሏል። ""ሁሉም ክለቦችና ተጫዋቾች በዚህ ጉዳይ ላይ ተስማምተው ዘረኝነትን ለመዋጋት ማሰባቸው በጣም ደስ የሚል ሀሳብ ነው። ቀላል ለማይባሉ ሰዎች መልዕክቱ እንደሚደርስም እርግጠኛ ነኝ። ፕሪምየር ሊጉ በመላው ዓለም በርካታ ተከታታዯች ያሉት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት ጠንከር ያሉ መልዕክቶች ለወደፊቱም ቢቀጥሉ ጥሩ ነው"" ብሏል ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ። አክሎም ""በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጥቁር አሰልጣኞች እንደሌሉ በስፋት ይነገራል፤ አሰልጣኞችና ሌሎች አባላት ሲመለመሉ ብዝሃነትን ባማከለ መልኩ መደረግ ያለባቸው ይመስለኛል’’ ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-53033059 +politics ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፖሊስ ድብደባ እንደተፈጸመበት ጠበቃው እና ወንድሙ ተናገሩ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ድበደባ እንደተፈጸመበት ጠበቃው እና ወንድሙ ለቢቢሲ ተናገሩ። የጋዜጠኛው ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ በተመስገን ላይ ድብደባው የተፈጸመው ሐሙስ ረፋድ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም. ታስሮ በሚገኘበት 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ መሆኑን ገልጿል። ታሪኩ ጋዜጠኛ ተመስገንን ለመጠየቅ ሄዶ በመካከላቸው ባለው ርቀት ምክንያት ሲነጋገሩ መደማመጥ ባለመቻላቸው ጋዜጠኛ ተመስገን ወደ እርሱ ለመጠጋት መሞከሩን ተከትሎ፣ ከጠባቂ የፖሊስ አባላት ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ ድብደባ እንደተፈጸመበት አስረድቷል። “በጠያቂ እና በተጠያቂ መካከል ያለው ርቀት ሰፊ ነው። በአንድ ጊዜ ከ10 ሰው በላይ ነው የሚያወራው። መጯጯህ ነው። ከዚህ በፊት በእስር ላይ ሳለ ጆሮው ላይ ጉዳት አጋጥሞት ነበር። በዚህ ሁኔታ መደማመጥ ይከብደዋል” የሚለው ታሪኩ፤ ለመጠጋት ጥያቄ ካቀረበ በኋላ ድበደባ እንደተፈጸመት ተናግሯል። “ዓይናችን እያየ በጫማ ጥፊ እና በቦክስ መቱት። . . . ከዚያ ወደ እስረኛ ክፍል ሳይሆን ወደ ሌላ ክፍል ይዘውት ሄዱ። ‘ካላየነው’ ብለን አስቸገርን። ይሄ ከሆነ ከ40 ደቂቃ በኋላ ለሁለት ደቂቃ ያክል አሳዩን። ከግራ ዓይኑ በታች አብጧል። ለብሶት ያለው ካናቴራ ተቀዷል። ምንም ነገር ማድረግ አልቻልንም። ለጠበቃው ተናግረን ወጣን” ብሏል የነበረውን ሁኔታ ሲያስረዳ። በተመሳሳይ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጠበቃ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ጋዜጠኛው በመንግሥት ፀጥታ ኃይል አባላት ድበደባ እንደተፈጸመበት ከቤተሰብ አባላት መስማታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጠበቃ ሄኖክ ከቀናት በፊት ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደነበሩ አስታውሰው፣ ተመስገንን ባያገኙትም ስለደረሰበት ጉዳት ከቤተሰብ አባላት ሰምቻለሁ ብለዋል። ታናሽ ወንድሙ ሊጠይቀው ሄዶ መደማመጥ ባለመቻላቸው ለጠጋት በሚሞክርበት ጊዜ አለመግባባት ተፈጥሮ “በጥበቃ ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላት ተመስገንን ጎትተው በማውጣት በጥፊ እና በእርግጫ ድብደባ ፈጸሙበታል” ሲሉ ጠበቃ ሄኖክ ተናግረዋል። “ይህ ሰው ፊት የተፈጸመ ድርጊት ነው። ኋላ ደግሞ ወደ ውስጥ አስገብተው ድብደባ ፈጽመውበታል። ቆይቶ ቤተሰብ ተመስገንን ሲያገኘው ልብሱ ተቀዳዶ እና ብዙ ጉዳት ደርሶበታል” ብለዋል። ጠበቃ ሄኖክ እንደሚሉት ጋዜጠኛ ተመስገን በመንግሥት ቁጥጥር ስር ሳለ ድበደባ ቢፈጸምበትም ለፍርድ ቤትም ሆነ ለሚመለከተው አካል ቅሬታ ማቅረብ ስላልፈለገ የቅሬታ ማመልከቻ አላስገባንም ብለዋል። ከአንድ ሳምንት በፊት በቁጥጥር ሥር የዋለው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት ተጠርጥሮ ግንቦት 19/2014 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ እንደነበር ይታወሳል። በዕለቱ ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገንን ገንዘብ ተከፍሎት በተለያዩ ሚዲያዎች እየቀረበ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት መጠርጠሩን ተናግሯል። ጠበቃ ሄኖክ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን እና መስከረም አበራ ጉዳያቸው ቀርቦበት ለነበረው ፍርድ ቤት ክሱ መታየት ያለበት በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እንጂ በመደበኛ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ መሆን የለበትም ብለው ያቀረቡት ክርክር በፍርድ ቤቱ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ዛሬ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረባቸውን ተናግረዋል። የፍትህ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ግንቦት 18/2014 ዓ.ም. ከሥራ ቦታው በሁለት መኪና ተጭነው በመጡ የፀጥታ ኃይሎች ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መወሰዱ ይታወሳል። የጋዜጠኛው ቤት እንዲሁም ቢሮው በፖሊስ የተፈተሸ ሲሆን፣ በተለያየ ጊዜ የታተሙ የፍትህ መጽሔቶች፣ ሃርድ ዲስኮችና ሌሎች ፖሊስ ለምርመራ ያስፈልገኛል የሚላቸውን ሰነዶች መውሰዳቸውን ጠበቃ ሄኖክ አስረድተዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c90qeld9lzjo +politics ኬንያዊው ፖለቲከኛ ለአዲስ ተጋቢዎች ብድር ለመስጠት ቃል ገቡ "ከወራት በኋላ በሚደረገው የኬንያ ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ፖለቲከኛ፤ ከተመረጡ ከ4,400 እስከ 8,800 ዶላር የሚደርስ ብድር ለአዲስ ተጋቢዎች ለመስጠት ቃል ገብተዋል። ፕሬዝዳንታዊ ማኒፌስቷቸውን እሑድ ይፋ ያደረጉት ማቻኮስ የተባለው ግዛት አገረ ገዢ አልፍሬድ ሙቱዋ፤ በ20 ዓመት የሚከፈልና ዝቅተኛ ወለድ ያለው ብድር ጥንዶች ""ሕይወታቸው በክብር እንዲጀምሩ"" ይረዳል ብለዋል። ""የዚህ ሁሉ ውጤት ምንድን ነው?"" ብለው በመጠየቅ የጀመሩት ሙቱዋ ""ለሁላችንም ክብር ነው። የኑሮ ደረጃን ከማሻሻል እና በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የመኖሪያ ቤቶችን ጥራት ከማሳደግ ባለፈ የጭቃ ቤቶችን ያስቀራል"" ብለዋል። ችግኝ ተከላ እንደ ጥሎሽ እንዲቆጠር መንግሥታቸው እንደሚያበረታታም ተናግረዋል። በቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ በተላለፈው የማኒፌስቶ ማስተዋወቂያ ዝግጅት ላይ ""ጥሎሽ ለመክፈል ስትሄዱ ምን ያህል ዛፎች እንደተከላችሁ መናገር አለባችሁ"" ሲሉ ተደምጠዋል። ይህ የፖለቲከኛው ሃሳብ ግን ከሁሉም ���ንድ አውንታዊ ምላሽ አላገኘው፣ ከአንዳንድ የማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ተጠቃሚ ኬንያውያን በኩል የሰላ ትችት እና ፌዝ አስተናግዷል። የ10 ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው መገባደጃ ወራት ላይ የሚገኙትን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ለመተካት 10 የሚጠጉ ፖለቲከኞች በዕጩነት ለመቅረብ ከወዲሁ ዘመቻ ጀምረዋል። ነሐሴ 2022 በሚካሄደው ምርጫ ዋና ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው ከተገመቱት አንጋፋው የተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ እና የአሁኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ይገኙበታል። ምጣኔ ሀብት፣ የወጣቶች ሥራ አጥነት እና ሙስናን መዋጋት የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ በሚሹ ሰዎች ቁልፍ አጀንዳዎች ሆነው ብቅ ብለዋል። ያለፉት ምርጫዎች የሚያሳዩት ግን ኬንያውያን ከፖሊሲ ጉዳዮች ይልቅ በጎሳ ወይም ሕብረት ፈጥረው ለሚመጡ ድምጻቸውን እንደሚሰጡ ታይቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59549852 +business ኢትዮጵያ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከቀናት በኋላ ልትጀምር ነው ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገር ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ኅዳር 5/2015 ዓ.ም ልትጀምር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኤሌክትሪክ የማስተላለፍ የሙከራ ሥራ ጥቅምት 29/2015 ዓ.ም በስኬት መከናወኑን ተከትሎም ወደ ኬንያ የሚደረገው የኤሌክትሪክ ኃይል የወጪ ንግድ ሊጀመር እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ መለስ ዓለም ገልጸዋል። አገራቱን በሚያገናኘው 500 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ላይ የኃይል ማስተላለፍ የሙከራ ሥራ በይፋ መጀመሩን ያስታወቁት የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ አያሌው ናቸው። ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ ሙከራው በስኬት መከናወኑን ያስታወቁት ሥራ አስኪያጁ ይህም በቅርቡ አገሪቱ የምታደርገው የኃይል ሽያጭ በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሚሄድ አመላካች ነው ማለታቸውን ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ከዚህ ቀደም የተለያዩ የኤሌክትሮ ሜካኒካል መሳሪያዎች ፍተሻዎች እንዲሁም ከቀናት በፊት የመገናኛ ሲግናል በመላክ ከኬንያ ኔትወርክ ጋር ማገናኘት መቻሉን ሥራ አስኪያጁ ማስታወቃቸው ተጠቅሷል። የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፉ በይፋ ሲጀመርም በሕብረተሰቡ ላይ አደጋ እንዳይደርስ መስመሩ ከሚያልፍባቸው ዞኖች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መካሄዱም ተገልጿል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የኃይል ማስተላለፍ ሙከራው በሚከወንበትም ወቅት ምንም አደጋ አለመድረሱንም አቶ ቴዎድሮስ መናገራቸው ተጠቁሟል። የግንባታ ሥራው በ2008 የተጀመረው የኢትዮ- ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር 334.5 ሚሊዮን ዶላር እንደፈጀ ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ የግንባታ ሥራ ከአራት ዓመት በፊት መጠናቀቁ ይታወሳል። ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ በኩል የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ግንባታ እና የፍተሻ እንዲሁም የሙከራ ሥራዎች ቢጠናቀቁም በኬንያ በኩል ቀሪ የዝርጋታ እና የግንባታ ሥራዎች እንዳሉ እየተነገረ መጀመር ከነበረበት ወቅት እየተጓተተ ረዘም ያሉ ወራት ተቆጥረዋል። የማስተላለፊያ መስመር የግንባታ ሥራው ሲኢቲ በተሰኘ የቻይና ኩባንያ ሲከናወን የኮንቨርተር ጣቢያውና ሌሎች ተግባራት ደግሞ ሲመንስ በተሰኘ ኩባንያ መከናወኑ ተገልጿል። ለምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ከፍተኛ ስፍራ ያለው ይህ ፕሮጀክት 1.3 ቢሊዮን ዶላር ፈጅቷል። አገራቱን የሚያገናኘው የኤሌክትሪክ መስመር 500 ኪሎ ቮልትና ከኢትዮጵያ በኩል 440 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ በአጠቃላይ ከ1 ሺህ ሜትር በላይ ርዝማኔ ያለው ነው። ወጪውም ከዓለም ባንክ በተገኘው ብድር 684 ሚሊዮን ዶላር፣ ለኢትዮጵያ 441 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለኬንያ 27.4 ቢሊዮን ዶላር የተሸፈነ ነው። የአፍሪካ ልማት ባንክም ይህንኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የግልገል ጊቤ ሦስት ግድብ ጋር የሚያገናኘውን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ድጋፍ ለኢትዮጵያ 232 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለኬንያ 116 ሚሊዮን ዶላር አጽድቋል። ለኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ እና ለሌሎች ሥራዎች በብድር ከተገኘው በተጨማሪ አገራቱም ይህንን ትልቅ ፕሮጀክት ለመስራት የራሳቸውን ወጪ አድርገዋል። ፕሮጀክቱ በምሥራቅ አፍሪካ ባሉ አገራት መካከል ድንበር ዘለል የኃይል ንግድ እንዲሁም ትስስርን ለማስተባበር በአውሮፓውያኑ 2005 የተቋቋመው ቀጠናዊ ተቋም ኢስተርን አፍሪካ ፓወር ፑል አካል ነው። በአጠቃላይ የኃይል ልማት እና ተግባር የማስተባበር ሥልጣን የተሰጠው ተቋም ዋና ጽህፈቱ በአዲስ አበባ የሚገኝ ሲሆን፣ አስራ አንድ አባል አገራት አሉት። እነሱም ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ታንዛንያ፣ ኡጋንዳ እና ሊቢያ። ኮንጎ (ዲአርሲ)፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ናቸው። ፕሮጀክቱ እነዚህንም አገራት በኃይል የማስተሳሰርና የማዋሃድ አቅም እንዳለው ይነገራል። በሁለቱ አገራት የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመርም እስከ 2000 ሜጋ ዋት የመሸከም አቅም ያለው ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c4nr1py1j72o +business በለንደን በሕግ ዘርፍ የተሰማራ ኩባንያ ሠራተኞች በደመወዝ ቅናሽ በቋሚነት ከቤት እንዲሠሩ ፈቀደ "በለንደን የሚገኝ እና በሕግ ዘርፍ የሚሰራ አንድ ኩባንያ ሠራተኞች በቋሚነት ከቤት የሚሰሩበትን አማራጭ ይፋ አድርጓል። ሆኖም ይህንን አማራጭ የሚወስዱ ሠራተኞች ሙሉ ደመወዛቸውን አያገኙም። በለንደን የሚገኘው ስቴፈንሰን ሃርውድ የተባለው በሕግ የሥራ ዘርፍ ላይ የታወቀ ስም ያለው ድርጅት ያስቀመጠውን በቋሚነት ከቤት የመስራት አማራጭ የሚፈልጉ ሰዎች ከደመወዛቸው 20 በመቶው ይቆረጣል። የኮሮና ወረርሽኝ ይዟቸው ከመጡ ጉዳዮች አንዱ ከቤት መስራትን ነው። ሆኖም ከቤት መስራት ማንን ይጠቀማል? ማንን ይጎዳል? በሚል ሲያከራክር ቆይቷል። ከቤት በመስራት አሰሪም፣ ሠረተኛም እየተጠቀሙ ነው። ሠራተኞች ገንዘብ እና ጊዜያቸውን እንዲቆጥቡ ሲያግዝ አሰሪዎችን ደግሞ ለቢሮ ቦታ እና ሥራ ማስኬጂያ የሚያወጡትን ወጪ ቀንሷል። ሆኖም ሠራተኞች ከቤት ሲሰሩ የሚሰሩበት መጠን ወይም ምርታማነታቸው ዝቅ ይላል በሚል የሚከራከሩም አሉ። ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ሰዎች ወደ ሥራ ቦታቸው ለመሄድ የሚያጠፉትን ጊዜ በመቆጠብ በምሽት እና በእረፍት ሰዓት ብዙም ሳይረበሹ እንዲሰሩ ያስችላል የሚሉም አሉ። በቅርቡ በዩኬ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊ የሆኑት ጃኮብ ሪስሞግ ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ከቤት መስራቱን ያቁም ማለታቸውን ተከትሎ ውዝግብ ተፈጥሮ ነበር። በጉዳዩ ላይ በትምህርት ተቋማት የተደረጉ ጥናቶች ከቤት መስራት የሠራተኞችን ውጤታማነት ከፍ እንደሚያደረግ ያሳያሉ። በርካታ የግል ኩባንያዎች ደግሞ ከቤት እና ከቢሮ እያቀያየሩ ማሰራት ሰፋ ያለ የሥራ ቦታ እንዲኖር እንደሚያስችል እና ሠራተኞችንም እያስደሰተ መሆኑን ጠቁመዋል። ስቴፈን ሃርውድ የኮሮና ወርሽኝ በተከሰተበት ጊዜ ከቤት የሚሰሩ እና ከለንደን ውጪ ያሉ ሠራተኞችን በዝቅተኛ ደመወዝ መቅጠር መቻሉን ለቢቢሲ ገልጿል። ሆኖም እነዚህ ሠራተኞች ከቢሮ መስራት ቢፈልጉ የመጓጓዣ ወጪ መጠየቅ እንደሚችሉ ተናግሯል። የስቴፈን የሕግ ኩባንያ አሁን ያቀረበው አማራጭ ያላቸው ሠራተኞች ከቤት ለመስራት ማመልከት እንደሚችሉ ያስታወቀ ሲሆን ከቤት እና ከቢሮ የሚሰሩ ሰዎች በሁለት ዓይነት የደመወዝ ማዕቀፍ የሚሰሩበትን አሰራርም ዘርግቷል። በአጋርነት ከሚሰሩት ውጪ ሁሉም ሠራተኞች ቢሮ መምጣት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት የመስራት አማራጭ ተሰጥቷቸዋል። ኩባንያው ብዙ ሠራተኞች ከቤት የመስራት አማራጭን ይወስዳሉ ብሎ እንደማይጠብቅም ገልጿል። በዚህ አሰራር መሰረት ለድርጅቱ የተቀጠረን አንድ ሠራተኛ እንደ ምሳሌ ብንወስድ ደመወዙ 90 ሺህ ፓውንድ ቢሆን ከቤት ለመስራት ቢወስን ደመወዙ ወደ 72 ሺህ ፓውንድ ዝቅ ይላል ማለት ነው። አሁን ላይ ሠራተኞች በሳምንት እስከ ሁለት ቀን መስራት የሚችሉበት አማራጭ የተዘረጋ ሲሆን ይህ ቤት ከቤት እና ቢሮ እየቀያየሩ የመስራት አሰራር በድርጅቱ ሥር ላሉ በለንደን ፣ ፓሪስ ፣ ግሪክ ፣ ሆንግኮንግ ፣ ሲንጋፖር እና ደቡብ ኮሪያ ለሚገኙ 1 ሺህ 100 ሠራተኞች እየተተገበረ ነው። ""ለአብዛኛው ሠራተኞቻችን ይህ ፖሊሲያችን በአግባቡ እየሰራ ነው"" ሲሉም የድርጅቱ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ኒኮላስ ብሉም ከኮሮና ወርርሽኝ ማክተም በኋላ 10 በመቶ የሚሆነው ሠራተኛ ከቤቱ ይሰራል የሚል ግምት አስቀምጠዋል። እንደሳቸው ገለጻ ከሆነ ከቤት መስራት የሠራተኞችን ውጤታማነት ለመጨመር፤ እኩልነትን መሰረት ያላደረገን አሰራር ለማጥበብ እና ከበድ ያለ ሥራ የሚሰሩ ሰዎች በተሻለ ነጻነት እንዲሰሩ ያግዛል። የተወሰኑ ተቋማት ሠራተኞች በተቀየጠው አሰራርም ቢሆን ወደ ቢሮ መመለስን እየተቃወሙ ይገኛሉ። አፕል በሳምንት ሦስት ቀን ከቢሮ ለመስራት ያቀደ ሲሆን ይህ አሰራሩ ተቋሙን ""የወጣቶች፣ የነጮች እና የወንዶች የበላይነት"" የሚታይበት ያደርገዋል የሚል አስተያየት ቀርቦበታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61277155 +sports እግር ኳስ፡ ዛሬ የሚጀምረውን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ማን ያሸንፍ ይሆን? በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ2020/21 እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ፉልሃም ከአርሰናል በሚያደርጉት ጨዋታ 8፡30 ሲል ይጀምራል። ዛሬ ከሚደረጉ 4 ጨዋታዎች መካከል፣ ያለፈው ዓመት የውድድር ዘመን አሸናፊዎቹ ሊቨርፑሎች፣ ፕሪምየር ሊጉ ከተቀላቀሉት ሊድስ ዩናይትድ ጋር በአንፊልድ የሚያደርጉት ጨዋታ አንዱ ነው። ማንችስተር ሲቲ፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ቼልሲና ዎልቭስ ፕሪምየር ሊጉ ከተጠናቀቀ በኋላ በአውሮፓ የውድድር መድረኮች ሲሳተፉ ስለነበር ጨዋታቸውን የሚጀምሩት በሚቀጥለው ሳምንት ነው። በዘንድሮ ፕሪሚየር ሊግድ ውድድር ፉልሃም፣ ሊድስ ዩናይትድ እና ዌስት ብሮም አልቢን አዲስ ተሳታፊ ቡድኖች ናቸው። ሊድስ ዩናይትድ ከ16 ዓመታት ጥበቃ በኋላ ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መመለሱን ሲያረጋግጥ፣ ዌስት ብሮም ደግሞ በቻምፒየንሺፕ ውድድር እስከመጨረሻው ጨዋታ ድረስ ጠብቆ ወደ ፕሪምየር ሊግ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ፉልሀም ደግሞ በመጨረሻው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ብርንትፎርድን በዌምብሌይ ስታዲየም በማሸነፍ በዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ መሳተፍ የሚያስችላቸው ዕድል አግኝተዋል። ኖርዊች፣ ዋትፎርድና ቦርንማውዝ ወደ ቻምፒየንሺፑ በመውረድ ከላይ ለተጠቀሱት ሶስት ክለቦች ቦታቸውን የለቀቁ ቡድኖች መሆናቸው ይታወሳል። ደጋፊዎች ወደ ስታዲም መቼ ይመለሱ ይሆን? የዘንድሮው የውድድር ዓመት በዝግ ስታዲየሞች የሚጀመር ሲሆን የኮሮናቫይረስ ስርጭትና ሁኔታዎች እየታየ ተመልካቾች ቀስ በቀስ ወደ ስታዲየሞች መግባት እንደሚጀምሩም ተስፋ ተደርጓል። ምናልባትም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በዝግ ስታዲየም የሚካሄዱት እስከ ጥቅምት ወር ድረስ ብቻ ሊሆን ይችላል። አርሰናል ከሼፊልድ በኢሚሬትስ በሚያደርጉት ጨዋታ ታዳሚዎች በአነስተኛ ቁጥር ወደ ስታዲየም ሊመለሱ ይችላሉ የሚል ቅድመ ዝግጅት አለ። እንደውም አንዳንድ ቡድኖች በሙከራ ደረጃ የቅድመ ውድድር ጨዋታዎችና የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታዎች በተመልካቾች ፊት እንዲካሄድና ሁኔታዎች እየታዩ ማስተካከያዎች እንዲደረጉ ሀሳብ አቅርበው ነበር። አዲስ ፈራሚዎች በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ከፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች እንደ ቼልሲ ድንቅ ተጫዋቾችን የሰበሰበ የለም። ፍራንክ ላምፓርድ እስካሁንም ስድስት ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ለማምጣት ቸልሲዎች ደፋ ቀና እያሉ ነው። የተከላካይ መስመር ተጫዋቹን ቲያጎ ሲልቫ ከፈረንሳዩ ፒኤስጂ፣ የግራ መስመር ተመላላሹ ቢን ቺልዌልን ከሌስተር ሲቲ፣ የአያክሱን የክንፍ መስመር አጥቂ ሃኪም ዚዬክ፣ የአርፒ ሌፕሲዥ የጎል አነፍናፊው ቲሞ ቨርነር፣ የባየር ሊቨርኩሰን የጨዋታ አቀጣጣዩ ኪያ ሃርቭዝ እንዲሁም ወጣቱን ተከላካዩ ማላንግ ሳር ከኒስ አስፈርመዋል። በዘንድሮው የዝውውር መስኮት በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ደግሞ ኤቨርተኖች ናቸው። በካርሎ አንቸሎቲ የሚመሩት ኤቨርተኖች አብዱላዬ ዱኩሬን ከዋትፎርድ፣ ሃመስ ሮድሪጌዝን ከሪያል ማድሪድ እንዲሁም አላንን ከናፖሊ አስፈርመዋል። አርሰናል እስካሁን የሊሉን ተከላካይ ጋብሪኤል ማጋሊያስ እንዲሁም የቼልሲውን ዊሊያን ያስፈረመ ሲሆን ማንቸስተር ዩናይትዶች ደግሞ የአያክሱን የመሃል ሜዳ ተጫዋች ቫን ደ ቢክን አስፈርመዋል። ማን በበላይነት ያጠናቅቃል? የዘንድሮውን የውድድር ዓመት የትኛው ቡድን በአሸናፊነት ያጠናቅቃል የሚለው ጥያቄ ደግሞ የዘርፉ ባለሙያዎችን ለሁለት ከፍሏል። አንደኛው ጎራ ሊቨርፑሎች በድጋሚ ሻምፒዮን ይሆናሉ ሲል በሌላኛው ጎራ ደግሞ ዘንድሮ ማንቸስትር ሲቲዎች የሚያቆማቸው የለም ይላሉ። በርካታ አቋማሪ ድርጅቶች ግን ዘንድሮ ማንቸስተር ሲቲ እንደሚያሸንፍ ግምታቸውን እያስቀመጡ ነው። ነገር ግን የሲቲዎች ደካማ የተከላካይ መስመር ብዙ ጎሎችን የሚያስተናግድ ከሆነ አሁንም ለሊቨርፑል ዋንጫውን አሳለፈው ሊሰጡ እንደሚችሉ ተገምቷል። ሊቨርፑሎችም ቢሆኑ በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ቡድኑን ሊቀይር የሚችል ተጫዋች እስካሁን አለማስፈረማቸው ጨዋታዎቻቸውን ከባድ ሊያደርግባቸው እንደሚችል ባለሙያዎቹ አስጠንቅቀዋል። በተጨማሪም ቡድኖች ከዚህ በኋላ ለሊቨርፑል የሚሆን አይነት አጨዋወት ይዘው እንደሚመጡ መገመት አይከብድም። ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ደግሞ ቡድናቸውን በማጠናከር ስራ ላይ እንደመሆናቸው መጠን ከአንድ እስከ አራት ውስጥ ይጨርሳሉ አይጨርሱም የሚለው እንጂ የሊጉ ሻምፒዮን እንደማይሆኑ ግልጽ ነው ብለዋል አቋማሪዎቹ ድርጅቶች። አርሰናል፣ ቶተንሃም፣ ሌስተር ሲቲና ኤቨርተን ደግሞ ከአምስተኛ በታች ያለውን ቦታ ይዘው እንደሚጨርሱ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54115494 +business በሊባኖስ የኢኮኖሚ ቀውሱን ተከትሎ ተቃውሞዎች እየተባባሱ ነው "ሊባኖስ ያጋጠማትን የመገበያያ ገንዘቧ መድከምን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል፡፡ የሊባኖስ መገበያያ ገንዘብ ዋጋ በታሪኳ ዝቅተኛ ወደሚባል ደረጃ በመውረዱና 70 በመቶ የሚሆነውን አቅሙን በማጣቱ ከጥቅምት ወር ጀምሮ አገሪቷ ተቃውሞዎችን እያስተናገደች ነው፡፡ ቁጣዎችም ተባብሰዋል፡፡ የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስተርም የኢኮኖሚ ቀውስ ላይ ውይይት ለማድረግ አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡ ተቃውሞዎቹ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ሳቢያ ጋብ ብሎ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ እንደገና ተጀምሯል፡፡ የሊባኖስ ፓውንድ ዋጋ መውደቅ አገሪቷን በአስርት ዓመታት ውስጥ አስከፊ ወደ ሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ ከቷታል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ምንዛሬ ላይ የተሰማሩ አብዛኞቹ ሊባኖሳዊያንም ለድህነት ተዳርገዋል��፡ በወረርሽኙ ወቅትም ችግራቸው ተባብሷል፡፡ በሊባኖሷ ከተማ ቤሩት የቢቢሲ ዘጋቢ ሊና ሲንጃብ እንደገለጸችው፤ ሐሙስ ዕለት ምሽት በከተማዋ እንብርት ላይ ተሰባስበው የነበሩ ተቃዋሚዎች እሳት በማቀጣጠል እና መንገዶችን በመዝጋት ቁጣቸውን ገልጸዋል፡፡ ምንም እንኳን የአኮኖሚ ቀውሱን ተከትሎ በመጀመሪያዎቹ ወራት በነበሩት ተቃውሞዎች ፖለቲካዊ ለውጥ ለመጠየቅ የተደረጉ ቢሆንም የአሁኑ ግን መነሻው ርሃብ ነው፡፡ በአገሪቷ የሥራ አጦች ቁጥር ከፍተኛ ሆኗል፡፡ አብዛኞቹ ሊባኖሳዊያንም ለሰሩበት የሚከፈላቸው ዋጋው በወደቀው የአገሪቷ ገንዘብ ነው፡፡ በመሆኑም ለአብዛኞቹ ቤተሰቦች ምግብና መሰረታዊ ፍላጎትን ማሟላት ፈታኝ ሆኗል፡፡ ከተቃዋሚዎቹ መካከል አንዷ ""ሊባኖስ ሁል ጊዜ በተቃውሞ ውስጥ ነው ያለችው ፤ ይህ ማለት ጥረታችን እና ጩኸታችን ለውጥ ማምጣት አልቻለም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ በበለጠ ተቃውሞ ማሰማት አለብን"" ብለዋል፡፡ ይሁን እንጅ አብዛኞቹ አሁን እየታየ ያለው ችግር እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ 1975 ሊባኖስ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ቀድሞ የነበረውን ጊዜ እንደሚያስታውሳቸው እና ተቃውሞው በዚህ ሁኔታ እየቀጠለ ከሄደ ወዴት ሊያመራ እንደሚችል አሳስቧቸዋል፡፡ ሌላኛው ተቃዋሚም ""ዛሬ የአንድ ዶላር ምንዛሬ 7ሺህ የሊባኖስ ፓውንድ ደርሷል፡፡ የቤት ኪራይ ለመክፈልም ሆነ ምግብ ለመመገብ አልቻልንም ፤ በመሆኑም የዶላር ምንዛሬው ዝቅ ካላላ በስተቀር እና ጥያቄዎቻችን ካልተመለሱ እዚሁ እንቆያለን ፤ ያገኘነው ጠቅላይ ሚኒስተርም ከዚህ ቀደም ከነበረው የባሰ ነው"" ብለዋል፡፡ ከቤሩት ውጭ ያሉ በርካታ መንገዶች አሁንም እንደተዘጉ ናቸው፡፡ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽን ቀድሞም ሌባኖስ በታሪኳ አጋጥሟት የማያውቅ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ገብታለች፡፡ ይህም ባለፈው ዓመት ጸረ መንግሥት ተቃውሞዎችን አስነስቷል፡፡ ምንም እንኳን የአገሪቷ መንግሥት የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በሰጠው ምላሽ ቢመሰገንም ግማሽ የሚሆነው ሕዝብ የሚኖረው ከድህነት ወለል በታች ነው፡፡ የመገበያያ ገንዘብ ዋጋው መውደቅም የዋጋ ግሽበት በማስከተሉ የገቢ ንግድ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ የንግድ ተቋማት ኪሳራ አጋጥሟቸዋል፡፡ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ህዝቧም ሥራ አጥ ሆኗል፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-53025567 +sports ትናንት ፍጹም ቅጣት ምት በሳቱት ጥቁር እንግሊዛውያን ላይ የዘረኝነት ጥቃት ደርሷል ተባለ "ትናንት ጣሊያን እንግሊዝን በፍጹም ቅጣት ምት አሸንፋ ሻምፒዮን ስትሆን ሦስት ፍጹም ቅጣት ምት በሳቱት ጥቁር እንግሊዛውያን ላይ የዘረኝነት ጥቃት መድረሱ ተነገረ። ጣሊያ እና እንግሊዝ በመደበኛው እና በተጨማሪ ሰዓት 1ለ1 በማጠናቀቃቸው አሸናፊውን ለመለየት ቡድኖቹ ወደ መለያ ምት ተሸጋግረው ነበር። ይሁን እንጂ ማርከስ ራሽፎርድ የመታት ፍጹም ቅጣት ምት በግቡ ብረት ሲመለስ ጄደን ሳንቾ እና ቡካዮ ሳካ የመቷቸው ኳሶች በጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ ተመልሰዋል። ይህን ተከትሎ በሦስቱ ተጫዋቾች ላይ በማህበራዊ ድር አምባ የዘረኝነት ጥቃት ደርሶባቸዋል። በጉዳዩ ላይ የእንግሊዝ እገር ኳስ ማህበር ያተገቢ ያልሆነ ሲል ፖሊስ ደግሞ ምርመራ ጀምሬያለሁ ብሏል። እንግሊዝ ለትልቅ ክብር ለመብቃት ከ55 ዓመት በላይ ያደረገች ጥበቃ ሳይሳካለት ቀርቷል። የማንቸስትር ዩናይትዱ ሉክ ሾው በሁለተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል እንግሊዝ ባለ ክብር ለመሆን በትክክለኛው መንገድ ላይ እንደሆነች አስመስሎ ነበር። በ33 ጨዋታዎች ያልተሸነፈችው ጣሊያን ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታው በመመለስ በ67ኛው ደቂቃ በተከላካዩ ሊዮናርዶ ቦኑቺ ጎል አቻ ለመሆን በ���ች። ጨዋተው ወደ ተጨማሪ ሰዓት ቢያመራም ጎል መቆጠር ሳይችል ቀርቷል። ጨዋተው በፍጹም ቅጣት ምት ሲጠናቀቅ ሦስት እንግሊዝ ተጨቻዋቾች ዕድሎቻቸውን ሳይጠቀሙ ቀርተዋል። አምበሉ ሃሪ ኬን እና ተከላካዪ ሃሪ ማጓየር ከፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር የቻሉ የእንግሊዝ ተጫዋቾች ናቸው። የእንግሊዙ ግብ ጠባቂ ፒክፎርድ በበኩሉ የአንድሪያ ቤሎቲ እና የጆርጂንሆን ኳሶች በማዳን የቡድኑን ተስፋ ማለምለም ችሎ ነበር። ዶሜኒኮ ቤራዲ፣ ሊዮናርዶ ቦኑቺ እና ፌደሪኮ በርናርዴስኪ ደግሞ ፍጹም ቅጣት ምቱን ወደ ጎልነት የቀየሩ ተጫዋቾች ናቸው። ራሽፎርድ እና ሳንቾ በጨዋታው መገባደጃ ላይ ተቀይረው የገቡ ሲሆን የአንግሊዙ አሰልጠኝ ጋሬት ሳውዝጌት ለፍጹም ቅጣት ምት ብለው ቀይረው እንዳስገቧቸው ቢገመትም ሳይሳካለቸው ቀርቷል። ጣሊያኖችም ያለመሸነፍ ክብራቸው ወደ 34 ጨዋታዎች ባሳደጉበት ምሽት የዩሮ 2020 ክብርን ለመጎናጸፍ በቅተዋል። አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ በዕድሜ የገፉ ተጫዋቾችን ከወጣቶች ጋር በማቀናጀት ምርጥ የሚባል ውድድር ለማሳለፍ ችለዋል። ቡድናቸው በውድድሩ ላይ እንደ ቤልጂም እና ስፔን ያሉ ቡድኖችን በማሸነፍ ነው ለፍጻሜ የበቃው። ለ2018ቱ የሩሲያ የዓለም ዋንጫ ማለፍ ተስኗት ለነበረችው ጣሊያን ድሉ የማንቺኒ እና የቡድኑ ጠንካራ ሥራ ውጤት ተደርጎ ተወስዷል። ጣሊያን በትላንት ምሽቱ ጨዋታ በኳስ ቁጥጥርም ሆነ በጎል ሙከራ ከእንግሊዝ የተሻለች ሆና አምሽታለች። ""ሽንፈቱ የሚያሳምም ነው"" ሽንፈቱን ""የሚያሳምም""? ያሉት አሰልጣኝ ሳውዝጌት ተጫዋቾቻቸው ""ማድረግ የሚችሉትን በሙሉ ማድረጋቸውን"" ተናግረዋል። ""ሁላችንም በህብረት ቆመን ነበር። ተጫዋቾቹ ለሃገራቸው የማይታመን አስደሳች ጊዜን ሰጥተው ነበር"" ብለዋል። የ22 ዓመቱ ጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል። ስፔናዊው የ18 ዓመቱ አማካይ ፕድሪ የውድድሩ ወጣት ኮከብ ተጫዋች ለመባል በቅቷል። ፑርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአምስት ጎሎች እና አንድ ለጎል አመቻችቶ ኳስ በማቀበሉ የውድድሩ ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ አጠናቋል።" https://www.bbc.com/amharic/57774763 +business ሩሲያ ወደ አውሮፓ ጋዝ የሚያስተላልፈውን ዋና መስመር እንደገና ዘጋች "ሩሲያ ለጥገና በሚል ወደ አውሮፓ የሚሄደውን ኖርድ ስትሪም 1 የተሰኘውን የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧን እንደገና ዘጋች። በዚህም ለአውሮፓ የሚደርሰው የጋዝ አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ቆሟል። በሩሲያ መንግሥት ባለቤትነት የሚተዳዳረው ግዙፉ የኃይል ማመንጫ ጋዝፕሮም ኖርድ ስትሪም የነዳጅ ማስተላለፊያ ላይ የተጣለው ገደብ ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት ይቆያል ብሏል። ሩሲያ ቀደም ሲልም በቧንቧው በኩል ወደ ውጪ የሚላከውን ጋዝ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሳለች። በምዕራባውያን አገራት ላይ የኃይል አቅርቦትን እንደ መሳሪያ ተጠቅማለች የሚለውን ክስም ውድቅ አድርጋለች። የኖርድ ስትሪም የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ከሩሲያ ባሕር ዳርቻ ሴንት ፒተርስበርግ ተነስቶ በባልቲክ ባሕር ስር 1 ሺህ 200 ኪሎሜትር ሸፍኖ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ጀርመን ድረስ የሚዘልቅ ነው። በአውሮፓውያኑ 2011 አገልግሎት መስጠት የጀመረው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧው  በቀን ከፍተኛውን 170 ሚሊዮን ኪዪቡክ ሜትር ጋዝ ከሩሲያ ወደ ጀርመንም መላክ ይችላል። ከዚህ ቀደም ሩሲያ በየዓመቱ ለምታካሂደው የጥገና ሥራ ለአስር ቀናት ዘግታው የነበረ ሲሆን፣ ከተከፈተ በኋላም በ20 በመቶ አቅም ብቻ እየሰራ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ ሩሲያ ችግር ያለባቸው መሳሪያዎች ስላሉ ነው ብላለች። የጀርመን የኔትወርክ ተቆጣጣሪ ፕሬዝዳንት ሩሲያ በሚቀጥሉት ቀናት አቅርቦት ከጀመረች አገሪቱ ባላት ክምችት መ���ቋም እንደምትችል ተናግረዋል። ""ችግሩን ለመቋቋም እንደምንችል እገምታለሁ፤ ሩሲያ በመጪው ቅዳሜ ወደ 20 በመቶ መላክ እንደምትጀምር አምናለሁ፤ ነገር ግን ማንም በትክክል ይህንን በእርግጠኛነት መናገር አይችልም"" በማለት  ክላውስ ሙለር ለሮይተርስ ተናግረዋል። ነገር ግን የጀርመኑ ኢኮኖሚ ሚኒስትር ሮበርት ሃቤክ ለፋይናንሺያል ታይምስ እንደተናገሩት እርምጃው ከወዲሁ አንዳንድ የጀርመን ኩባንያዎች ምርታቸውን እንዲያቆሙ አስገድዷቸዋል፣ በአሁኑ ወቅት የተፈጠረው ጉዳይ  ""አሳዛኝ ነው"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cw9d8x9lz9do +health ኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ በበሽታ የሚሞቱ ሰዎችን መጠን ለማወቅ መመሪያ አዘጋጀች ኢትዮጵያ በአገር አፍ ደረጃ በበሽታ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎችን መጠን ለማወቅ የሚያስችል የቅኝት መመሪያ ማዘጋጀቷን ቢቢሲ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ካገኘው መረጃ መረዳት ችሏል። በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የሞት መጠን ለማወቅ የሚያስችል የቅኝት መመሪያ ለማዘጋጅት መነሻ የሆነው የኮሮኖቫይረስ ወረርሽኝ መሆኑም ተገልጿል። መመሪያወው በማህበረሰቡ ውስጥ በበሽታ የሚሞቱ ሰዎችን ጭምር ማካተት እንደሚኖርበት ታምኖ የአገሪቱን የሞት መጠን የሚያሳውቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል ተብሏል። በተለይም እንዲህ አይነት ወረርሽኞች ሲከሰቱ የሞቱን መጠን በትክክል ለማወቅ፣ ከዚህ ቀደም የነበረውን የሞት መጠን ለመገምገም፣ በሽታው የትኛውን የማህበረሰብ ክፍል በፆታ፣ በእድሜና ሌሎች መስፈርቶች አስመልክቶ የትኛውን አካል ነው እያጠቃ ነው የሚለውን በተመለከተ መመሪያው ምላሽ ይሰጣል ተብሏል። መመሪያው ይፋ የተደረገው ግንቦት 11፣ 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ነው። መመሪያው ይፋ መሆኑን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የጤና ክስተቶች ቅኝትና ምላሽ መስጠት ዳይሬክቶሬት የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ሞት ዳሰሳ እና ምላሽ መስጠት ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ ሮዚና ታሪኩ ከመረጃዎች አሰባሰብና መለኪያ ጋርም ተያይዞ ወሳኝ የሚባሉ ጉዳዮች በመመሪያው መካተታቸውን አስታውቀዋል። መመሪያው መጠናቀቁን አስመልክቶ አዳማ በነበረው ዝግጅት ላይ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እንደተናገሩት መመሪያው የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ጉዳት ሳያደርሱ ለመከላከልና ለመቆጣጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል። መመሪያውን በማዘጋጀቱ በኩል የጤና ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ የክልሎች የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር እና የአጋር ድርጅት ተወካይ ባለሙያዎች ተሳትፎ ማድረጋቸውም ከመረጃው መረዳት ተችሏል። https://www.bbc.com/amharic/news-57188529 +health ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 ውጤትን በ30 ደቂቃ ውስጥ ማወቅ ሊቻል ነው "ኮቪድ-19ን በደቂቃዎች ውስጥ የሚለይ ምርመራ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመለየት ስራን በእጅጉ ያሳድጋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ተናገረ። አምስት ዶላር ብቻ የሚያስወጣው ይህ ምርመራ ሃብታም ባልሆኑ እና የጤና ባለሙያዎችና የላብራቶሪ እጥረት ባለባቸው አገራት የኮቪድ-19 ሕሙማንን ለመለየት በእጅጉ ይረዳል ተብሏል። መመርመሪያውን ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር የተደረገ ስምምነት በስድስት ወር ውስጥ 120 ሚሊዮን መመርመሪያዎችን ለማምረት ያስችላል። ይህንን እርምጃ የጤና ድርጅቱ የበላይ ኃላፊዎች ""ጉልህ ሚና የሚጫወት"" ብለውታል። በበርካታ አገራት ምርመራ ከተደረገ በኋላ ውጤት ለማወቅ የሚፈጀው ጊዜ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የሚያርጉትን ትግል ጎድቶት ቆይቷል። እንደ ሕንድና ሜክሲኮ ባሉ ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ በተሰራጨባቸው አገራት በፍጥነት መርምሮ ውጤቱን ማወቅ አለመቻል የወረር��ኙን የመስፋፋት ፍጥነት ትክክለኛ ምስል ማሳየት አልቻለም ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ይህ አዲሱ ""ተንቀሳቃሽ እና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ"" መመርመሪያ ውጤትን ከ15 እስከ 30 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ሰኞ እለት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ግን የኮሮናቫይረስን ውጤት ለማወቅ ሰዓታት ካልሆነም ቀናት እንደሚፈጅ ይታወቃል። አቦት እና ኤስዲ ባዮሴንሰር የተባሉ መድሃኒት አምራቾች ከቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን 120 ሚሊዮን መመርመሪያዎችን ለማምረት ስምምነት መድረሳቸውን ዶ/ር ቴድሮስ ጨምረው ገልፀዋል። በዚህ ስምምነት መሰረት የሚመረቱ መመርመሪያዎች በቫይረሱ በጣም የተጎዱ የላቲን አሜሪካ አገራትን ጨምሮ ለ133 አገራት ይሰጣል ተብሏል። ""ይህ በተለይ ከፍተኛ ስርጭት ባለባቸው አካባቢዎች የመመርመር አቅም ላይ ትልቅ እመርታ የሚፈጥር ነው"" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። አክለውም ""ላቦራቶሪ በሌላቸውና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ወይንም ምርመራውን ለማካሄድ በቂ የሰለጠነ ባለሙያ በሌለበት አካባቢ የመመርመር አቅምን ያሰፋል።''" https://www.bbc.com/amharic/54336434 +health በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አለፈ "በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አለፈ። በበርካታ አገራት በኮቪድ-19 የሚያዙ ከፍተኛ ቁጥር መመዝገቡን ተከለትሎ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አልፏል። እንደጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ ከ1.25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። በብዙ አገራት በቂ ምርመራ ባለመደረጉ እንጂ ይህን አሃዝ ከፍ ያለ ነው ተብሎ ይገመታል። ሮይተር በበኩሉ ቫይረሱ ሁለተኛ ዙር ማገርሸቱ ከተመዘገበው ቁጥር ውስጥ ሩብ ለሚሆነው ድርሻ አለው ሲል ዘግቧል፡፡ ቀደም ሲል የቫይረሱ ስርጭት ማዕከል የነበረችው አውሮፓ 12.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙባት 305,700 ደግሞ ህይወታቸው አልፎፋባት በድጋሚ የቫይረሱ ስርጭቱ ማዕከል ሆናለች፡፡ በአሜሪካ 10 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በቀን ከ125,000 በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የችግሩን መጠን ከማሳነስ ባለፈ የአፍና የአፍንጫ ጭምብል ማድረግ እና አካላዊ ርቀት ማስጠበቅን ባይቀበሉም ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሙሉ ሃይላቸው እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል። ባይደን በጥቂት ቀናት ከፍተኛ የሳይንስ ሊቃውንትን ያካተተ የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል ለማቋቋም ቃል ገብተዋል። ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድረግ እና ሁሉም አሜሪካዊያን ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ሲሆኑ የአፍና የአፍንጫ ጭንብል እንዲያደርጉ ለመጠየቅ አቅደዋል። ባይደን ወረርሽኙ በአገሪቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ ኃላፊነታቸውን ሊረከቡ ይችላሉ ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር ኮሚሽነር ዶ/ር ስኮት ጎትሊብ ገልጸዋል። እንደ ዶ/ር ጎትሊብ ከሆነ የቫይረሱ ስርጭት ጥር መጨረሻ ድረስ መቀነስ ይጀምራል። ""ብቸኛው ጥያቄ በዚህ ጊዜ ውስጥ ስንት ሰዎች ይሞታሉ እና ምን ያህል ሰዎች ይያዛሉ የሚለው ነው"" ብለዋል፡፡ በአውሮፓ ፈረንሳይ እሁድ 38,619 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባለች። ቅዳሜ ከፍተኛ ሆኖ ከተመዘገበው የ86,852 ቁጥር ግን በጣም ያነሰ ነው፡፡ ሆኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ መረጃ የመሰብሰብ ችግሮች እንደነበሩበት በመግለጽ ሰኞ እርማት እንደሚያደረግ ገልጿል ፡፡ ህንድ እና ብራዚልም እንዲሁ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡" https://www.bbc.com/amharic/54869295 +health መፀዳ��� ቤት ስንጠቀም በምናያቸው ምልክቶች የምንለየው የካንሰር ዓይነት በአንጀት ካንሰር የሞተችው የአርባ ዓመቷ ጎልማሳ ዴሚ ዴብራ ጄምስ በሽታውን ቀድሞ ለማወቅ ሁሉም ሰው ሰገራው ላይ ያሉ ለውጦችን ትኩረት እንዲሰጥ ስትመክር ቆይታለች። ታዲያ እንዴት የአንጀት ካንሰርን ልንለይ እንችላለን? ከዚህ የጤና ችግር ጋር በተያያዘ ሦስት ነገሮችን ልብ ማለት ይኖርብናል፡ እነዚህ ብቻ ሳይሆኑ በአንጀት ካንሰር የተያዘ ሰው የሚከተሉት አይነት ሌሎች ምልክቶችም ሊኖሩት ይችላሉ። የክብደት መቀነስ፣ መፀዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ በደንብ ያልተጻዳዱ ያህል መሰማት፣ ከተለመደው በተለየ የሰውነት መድከምና የመዛል ስሜት ያጋጥማል። እነዚህ ምልክቶች ታዩ ማለት ግን የአንጀት ካንሰር አለ ማለት ላይሆን ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ምልክቶች ለሦስት ሳምንታትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከታዩ እንዲሁም የሚሰማን ነገር ትክክል ካልሆነ ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል። በዚህም ተገቢው ምርመራ በፍጥነት ተደርጎ ካንሰር ከሆነ እና በመጀመሪያው ደረጃ ላይ ከተደረሰበት ለማከም ቀላል ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ የአንጀት ካንሰር ሰገራ በተገቢው መስመር እንዳይወገድ በማድረግ መዘጋትን ሊፈጥርና ይህም ከባድ የሆድ ቁርጠት፣ ድርቀት እና ህመምን ሊያስከትል ይችላል። እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥምም ችላ ሳይሉ ወደ ሐኪም ዘንድ በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው። መፀዳጃ ቤት በሚጠቀሙ ጊዜ የሚወጣውን ሰገራ ይመልከቱ፣ የተለየ ነገር ሲያጋጥምዎት የሕክምና ባለሙያ ለማማከር በወደ ኋላ አይበሉ። በተለይ ሰገራ ላይ የደም ምልክትና መፀዳጃ ቤት ሲጠቀሙ የመድማት ሁኔታ ካጋጠመ በቀላሉ መታለፍ የለበትም። አንዳንድ ጊዜ በሰገራ መተላለፊያ አካል ላይ ባሉ የደም ስሮች እብጠት ሳቢያ ቀይ ደም ሊወጣ ይችላል፤ ነገር ግን ይህ በአንጀት ካንሰር ሳቢያ የተከሰተ ሊሆን ይችላል። ጠቆር ያለ ደም ወይም ጥቁር ደም ሰገራ ላይ ከታየ ይህ የተከሰተው በአንጀት ወይም በጨጓራ ላይ ባጋጠመ የጤና ችግር ስለሚሆን አሳሳቢ ሊሆንም ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ቀጠን ያለ ሰገራ መኖር ወይም ከወትሮው በተለየ ቶሎ ቶሎ መፀዳዳት ሊኖር ይችላል። ወይም ደግሞ አንጀት ውስጥ የተከማቸው ሰገራ ያልወጣ መስሎ መሰማት አሊያም በበቂ ሁኔታ አለመፀዳዳት ያጋጥማል። በዩናይትድ ኪንግደም ስለ አንጀት ካንሰር መረጃ የሚሰጠው ድረ ገጽ ወደ ሐኪም ዘንድ ከመሄድ በፊት በየዕለቱ የሚታዩ ምልክቶችን በመከታተል መመዝገብ እንደሚገባ ይመክራል። ይህንንም ለሐኪምዎ መናገር ያለብዎትን ሳይዘነጉ አንድ ባንድ መናገር እንዲችሉ ይረዳል። ሐኪሞች በተለያዩ የአንጀት ጤና እክሎች ያሉባቸው በርካታ ሰዎችን ስለሚመለከቱ በእራሳችሁ ላይ ያያችሁትን ለውጥ ወይም መድማት ካለ መናገራችሁ የበሽታውን መንስዔ ማወቅ እንዲችሉ ያግዛል። በአብዛኛው የአንጀት ካንሰር በዘር አይተላለፍም። ይሁን እንጂ የቅርብ የቤተሰብ አባል ከአምሳ ዓመት ዕድሜ በፊት በበሽታው ተይዘው ሕክምና አድርገው የሚያውቁ ከሆነ፣ ይህንን ለሐኪም መናገር አስፈላጊ ነው። እንደ ሊንቺ ሲንድረም ያሉ አንዳንድ በዘር የሚተላለፉ ካንሰሮች ለአንጀት ካንሰር የመጋለጥ እድል እንዲሰፋ ያደርጋል። ስለዚህ ሁኔታ ሐኪም ማወቅ ከቻለ በሽታውን ቀድሞ ለመከላከል ያስችላል። ከሚከሰቱት የአንጀት ካንሰሮች ግማሽ ያህሉ ጤናማ የሕይወት ዘይቤን በመከተል ቀድመን ልንከላከላቸው የምንችላቸው እንደሆኑ ተመራማሪዎች ይናገራሉ። በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ፣ በብዛት አሰር ያላቸውን ምግቦችን በመመገብ እና ስብን በመቀነስ እንዲሁም በቀን ውስጥ ከስድስት እስከ ስምንት ብርጭቆ ውሃ በመጠጣት የአንጀት ካንሰርን ቀድሞ መከላከል ይቻላል። ነገር ግን የሚያሳስብ ምልክት ከተከሰተ የጤና ባለሙያን ማማከር እና የካንሰር ምርመራ ማድረግ ይመከራል። የአንጀት ካንሰር ምልክቶች ከታዩ ፈጠን ብሎ ሐኪም ማማከር በሽታውን ለመቆጣጠር ወሳኝ ነው። ምርመራውም ቱቦ በመጠቀም ሁሉንም የአንጀት ክፍሎች በካሜራ በሚያሳይ መሣሪያ (ኮሎኖስኮፒ) ይደረጋል። ወይም ደግሞ የተወሰነውን ክፍል ለማየት በሚያስችል መሣሪያ (ሲግሞዶስኮፒ) በተባለ ተጣጣፊ መሣሪያ ምርመራው ይካሄዳል። በመጀመሪያው የአንጀት ካንሰር ደረጃ ላይ ምርመራ ያደረጉ ሰዎች በሽታውን በቶሎ በመለየት አስፈላጊው ሕክምናን በወቅቱ ማግኘት ስለሚችሉ የሚከሰተውን ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ይቻላል። የካንሰር በሽታ በብዛት የሚከሰተውና ገዳይ የሚሆነው እድሜያቸው በገፉ ሰዎች ላይ በመሆኑ ልክ እንደ ሌሎች የካንሰር በሽታዎች ሁሉ በአንጀት ካንሰር የተያዙ ከ15 እስከ 40 ባለው የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች በሕይወት የመቆየታቸው ዕድል ሰፊ ነው። ሆኖም አጠቃላይ በሕይወት የመቆየት እድል ከሌሎች የአውሮፓ አገራት ጋር ሲነጻጸር በዩኬ ያለው ጥሩ የሚባል አይደለም። የአንጀት ካንሰር በተለይ ቀድሞ ሕክምና ማድረግ ከተቻለ የሚድን በሽታ ነው። በሽታውን ቀድሞ ለመከላከል ያለው ሕክምና በአብዛኛው በግል የሚከናወን ሲሆን፣ የዘረ መል ምርመራ ቀድሞ ማድረግ የተከሰተውን ካንሰር ለማከም ያስችላል። ይህ ዘዴ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ተጨማሪ ዓመታትን በሕይወት እንዲቆዩ ይረዳል። በየትኛውም የዕድሜ ክልል በበሽታው ለተያዘ ሰው ሕክምናው ይሰጣል። ሕክምናው ቀዶ ሕክምና፣ ኬሞቴራፒ፣ ራዲዮቴራፒ ወይም ደግሞ እንደየግለሰቡ የካንሰር ሁኔታ ሌሎች ሕክምናዎች ሊሰጡ ይችላሉ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c885exp9rexo +health ኮሮናቫይረስ: እስራኤል የፋይዘር ክትባት ውጤታማ ሆኖ ማግኘቷን ገለፀች "ከእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የፋይዘር ክትባት የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን 94 በመቶ የመከላከል አቅም አለው። ይህም ክትባቱ በክሊኒክ ውስጥ በተደረጉለት ሙከራዎች ወቅት የነበረውን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ባለው ህዝብ ውስጥም ውጤታማ መሆኑን ያሳያል፡፡ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ከፍተኛ ውጤታማነት እያስገኘ መሆኑን የማህበረሰብ ጤና ሐኪሙ ፕሮፌሰር ሀጋይ ሌቪን ተናግረዋል። ""በጣም ተጋላጭ ለሆኑት ቡድኖች ከፍተኛ የክትባት ሽፋን መስጠት ወሳኝ"" ነበር ብለዋል፡፡ የእስራኤል ትልቁ የጤና ፈንድ ክላሊት በተመሳሰይ ዕድሜ እና የጤና ሁኔታ በሚገኙ 600,000 ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ መልካም የሚባል ውጤት መገኘቱን፣ ክትባት ካልወሰዱ ሰዎች አንጻር እንደታየባቸው አመልክቷል፡፡ ክትባቱን በወሰዱት ዘንድ 94% ያነሰ ኢንፌክሽኖችን አግኝቷል፡፡ በተጨማሪም ክትባቱ ሁሉንም ማለት በሚቻል ሁኔታ ከባድ ህመሞችን ተከላክሏል፡፡ ውጤቱ ከ70 ዎቹ በላይ የሆኑትን ጨምሮ በሁሉም የዕድሜ ቡድኖች ውስጥ ተመሳሳይ ነበር፡፡ ይህ ""እንደ እንግሊዝ ላሉት ሌሎች ሀገሮች"" ስለ ክትባቱ ጠቃሚ መልዕክት ከማስተላለፉም በተጨማሪ፣ በቫይረሱ በጣም ሊታመሙ የሚችሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች ""በከፍተኛ"" ሁኔታ ክትባቱን እንዲያገኙ ያግዛል ብለዋል ፕሮፌሰር ሌቪን፡፡ ፕሮፌሰሩ አክለውም የእንቅስቃሴ ገደቦችን ከማላላት በፊት ምን ያህል ቁጥር መከተብ እንደሚያስፈልግ መናገር አልችልም ብለዋል፡፡ ""በመተላለፍ ላይ ያለው ተጽዕኖ ምን እንደሆነ እስካሁን አናውቅም"" ብለዋል፡፡ ሆኖም ቢያንስ ""ክትባቱ ግለሰብን ለመጠበቅ ጠቃሚ ነው"" ሲሉም አክለዋል፡፡ የእስራኤል ጤና ጥበቃ ሚኒ��ቴር መረጃን በመተንተን ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር ኤራን ሴጋል በበኩላቸው ክትባቱ በኮቪድ -19 ጉዳዮች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመረዳት ሃገሪቱ ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ ከሆኑት መካከል 80 በመቶውን መከተብ እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ እስራኤል የክትባት መርሃግብሩ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመመልከት በዓለም ላይ የመጀመሪያዋ ሀገር ብትሆንም፣ ወደዚህ ደረጃ ለመድረስ ከፍተኛ የሆነ ህዝብን ማዳረስ እና በርካታ ሳምንታትን ሊፈጅባት ይችላል፡፡ በመጀመሪያ ክትባት በተወሰዱ እና ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ በሆናቸው እና ከዚያ ቀደም ነዋሪዎቻቸውን ባስከተቡ ከተሞች ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት ሲቀንስ ታይቷል። ይህም ቀደም ባሉት የእንቅስቃሴ ገደቦች ወቅት ያልታየ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ከእገዳው ይልቅ ክትባቱ ለቁጥሩ መቀነስ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠንካራ ማስረጃ ይሰጣል፡፡ ፕሮፌሰር ሴጋል እንደሚያስጠነቀቁት ከሆነ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በላይ በዝግታ የቀነሰ ሲሆን ምናልባትም በእስራኤል ውስጥ ዋነኛው የቫይረሱ ዝርያ በሆነው እና በብሪታንያ በተገኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ""በጣም ፈጣን"" በሆነው በእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር እንኳን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊከላከሉት የማይችሉ ሲሆን በበሽታው ከተያዙም በጠና ሊታመሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ""አሁንም ቢሆን ከእንቅስቃሴ እገዳው ለመውጣት በጥንቃቄ መውጣት አለብን"" ወይም ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሆስፒታል መተኛት ሊገደዱ ይችላሉ ይላሉ፡ እስራኤል ከፍተኛ የሆነ የኢንፌክሽን ማዕበል እያጋጠማት እና በጥብቅ እገዳዎች ውስጥ ብትቆይም ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆኑ ሁሉ የመከተብ መብት ስላላቸው ትምህርት ቤቶች የመከፈት ተስፋ አላቸው ተብሏል፡፡ በፍልስጤም ግዛቶች ክትባቱን ማን መስጠት አለበት በሚለው ጥያቄ ሃገሪቱ ትችት ደርሶባታል፡፡ ለጤና ሠራተኞች እንዲደርስ እስራኤል በዌስት ባንክ እና በጋዛ ላሉት ፍልስጤሞች የተወሰነ መጠን ያለው ክትባት ማሳለፍ የጀመረችው ገና አሁን ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከነዋሪዎቿ ለሩብ ያህሉ ሁለቱንም ዙር ክትባት ሰጥታለች፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-56073530 +sports """የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም"" ዱቤ ጂሎ" የኢትዮጵያ የማራቶን ውድድር ሯጮች ላይ ምንም አይነት የእገዳ ውሳኔ እንዳልተላለፈ ከአትሌቶቹ ጋር ካታር የሚገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክትር ዱቤ ጂሎ ለቢቢሲ ተናገሩ። በካታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በማራቶን ውድድር ላይ የተሳተፉት አትሌቶች ለቀጣዮቹ ሦስት ወራት እረፍት አድርገው እንዲያገግሙ እንጂ እገዳ አለመሆኑን ገልጸዋል። • ቀነኒሳ 'ከሞት እንደመነሳት' ነው ባለው ሁኔታ ማራቶንን አሸነፈ • በዶሃ የሴቶች ማራቶን ሦስት ኢትዮጵያውያን ሯጮች አቋርጠው ወጡ ውሳኔው ከ42 ኪሎሜትሮች በላይ በሚሮጥበት ከባድ በሚባለው የማራቶን ውድድር ላይ የሚሳተፉ ሯጮችን ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰድ ተቀባይነት ያለው እረፍት ነው ብለዋል ዱቤ ጅሎ። አትሌቶች የሦስት ወራት የማገገሚያ ጊዜ እንዲያገኙ ማድረግ በዓለም አቀፍ የውድድር ሕግና ደንብ ውስጥ ተቀባይነት ያለውና በሌሎችም ሃገራት የሚሰራበት እንደሆነ አመልክተዋል። ለሦስት ወራት ከውድድር እርቆ የሚወሰደው እረፍት ሁሉንም በማራቶን ውድድር የተሳተፉ አትሌቶችን የሚመለከት መሆኑን የጠቀሱት የቴክኒክ ዳይሬክተሩ፤ በተለይ በዶሃ ያለው ከባድ ሙቀት ላይ ለተወዳደሩ አትሌቶች እረፍቱ በጣም አስፈላጊያቸው ነው ብለዋል ለቢቢሲ። ባለፈው አርብ ሌሊት በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ላይ ተሳታፊ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ሯጮች በነበረው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ውድድሩን አቋርጠው መውጣታቸው የሚታወስ ሲሆን እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ በርካቶችም ለማቋረጥ ተገደው ነበር። • ''በኳታር የኢትዮጵያ ቡድን በሙቀቱ ተቸግሯል'' የቡድኑ መሪ • የሞ ፋራህ የቀድሞ አሠልጣኝ ከአትሌቲክስ ታገዱ ስለዚህም የማራቶን ሯጮቹ ከነበሩበት ከባድ ሁኔታ እንዲያገግሙ በፌዴሬሽኑ ደንብ መሰረት ለሦስት ወራት ልምምድ እየሰሩ እረፍት እንዲያደርጉና ከውድድር እንዲርቁ መደረጉን አመልክተዋል። በሴቶቹ የማራቶን ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበሩትና አቋርጠው ለመውጣት የተገደዱት ሯጮች የጤንነት ሁኔታን በተመለከተ በስፍራው የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ዱቤ ጅሎን ጠይቆ ባገኘው መረጃ መሰረት አንዷ ከገጠማት ቀላል ችግር በስተቀር ሁሉም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ታውቋዋል። በዶሃ ባለው ከባድ ሙቀት ምክንያት በእኩለ ሌሊት ጎዳና ላይ በሚደረጉት የማራቶንና የእርምጃ ውድድሮች ተሳታፊዎች ላይ ከባድ ጫናን የሚያሳድር እንደሆነ የተናገሩት የቴክኒክ ዳይሬክተሩ ስታዲየም ውስጥ የሚደረገው ግን ብዙም አስቸጋሪ እንዳልሆነ ገልጸዋል። https://www.bbc.com/amharic/49897069 +sports የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅ ኳታር ከምድብ ጨዋታ ባሻገር መሄድ ሳትችል መሰናበቷ ተረጋገጠ ኳታር ከሴኔጋል ጋር በነበራት ጨዋታ በገጠማት ሽንፈት ሳቢያ እያስተናገደችው ካለው የዓለም ዋንጫ ውድድር ከምድብ ጨዋታው ባሻገር ሳትሄድ መሰናበት የግድ ሆኖባታል። ኳታር በውድድሩ የመክፈቻ ዕለት ከኢኳዶር ጋር በነበራት ጨዋታ ሁለት ለዜሮ በሆነ ውጤት ተሸንፋ ነበር ውድድሩን የጀመረችው፣ ትናንት አርብ ደግሞ ከአፍሪካዊቷ ሴኔጋል ጋር ገጥማ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረትታለች። በዚህም ሳቢያ ኳታር ማድረግ ካለባት ሦስት የምድብ ግጥሚያዎች ሁለቱን በመሸነፏ ወደ ቀጣይ ዙር የማለፍ እድሏን በሌሎች ቡድኖች ጨዋታ ላይ የተንጠለጠለ አድርጎት ነበር። ነገር ግን የምድኑ ኃያላን ኢኳዶር እና ኔዘርላንድ ነጥብ ተጋርተው በመውጣታቸው ኳታር የሚቀራትን የመጨረሻ ጨዋታ አድርጋ ውጤቱ ምንም ቢሆን ከውድድሩ ለመሰናበት ተገዳለች። ኳታር የምድብ ጨዋታ መረሃ ግብሯን ብቻ ለማሟላት የአውሮፓ የእግር ኳስ አንጋፋ ከሆነችው መካከል አንዷ ከሆነችው ከኔዘርላንድስ ጋር በሚቀጥለው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዋን አድርጋ ትሰናበታለች። ኳታር በሴኔጋል ከተሸነፈች በኋላ በውድድሩ ውስጥ ለመቆየት በመጀመሪያ ጨዋታዋ ካሸነፈቻች ኢኳዶር አስቸጋሪ ውለታን ማግኘት ነበረባት። ነገር ግን ከኔዘርላንድ ጋር የገጠመችው የደቡብ አሜሪካዋ አገር ኢኳዶር አንድ አቻ በመውጣቷ፣ ኳታር ከምድብ ውድድሩ ለመሻገር ሳትችል ቀርታለች። በዚህ ምድብ በመጀመሪያ ጨዋታቸው በኔዘርላንድስ 2 ለ 0 የተሸነፉት የአፍሪካ ሻምፒዮኖቹ ሴኔጋሎች፣ ከሽንፈታቸው አገግመው ኳታርን በማሸነፍ በምድብ ውድድሩ ውስጥ ተፎካካሪነታቸውን አጠናክረዋል። ኳታር አረቡ ዓለም የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫን ከማስተናገዷ በተጨማሪ ብሔራዊ ቡድኗም በዓለም ዋንጫ ውድድር ሲሳተፍ የመጀመሪያው ነው። ከውድድሩ የመክፈቻ ዕለት አንሰቶ ባሉት ስድስት ቀናት ውስጥ ሁለት ጨዋታዎችን ያደረገችው ኳታር፣ አምስት ግቦች ተቆጥረውባት አንድ ግብ አስቆጥራ በጨዋታዎቹ ተሸንፋለች። ቀሪ ጨዋታዋን በመጪው ማክሰኞ ከኔዘርላንድስ ጋር የምታደርግ ሲሆን፣ ቀላል ይሆንላታል ተብሎ አይጠበቅም። ኳታር ቢሊዮኖችን አፍስሳ ዘመናዊ ስታዲየሞችን በመገንባት ለአረቡ ዓለም የመጀመሪያ የሆነውን ዓለም አቀፉን እግር ኳስ ውድድር በማስተናገድ ታሪክ አስምዝገባለች። ነገር ግን በውድድሩ ላይ ብሔራዊ ቡድኗ በ��ከታታይ ጨዋታዎቹ ሽንፈት ስለገጠመው በዙር ውድድሩ ላይ በመሰናበቷ ከሆነ፣ የዓለም ዋንጫን አስተናግዳ በምድብ ጨዋታ ከውድድሩ ውጪ በመሆን ከደቡብ አፍሪካ ቀጥላ ሁለተኛዋ አገር ሆናለች። ከሁለት ጨዋታዎች ተመሳሳይ አራት ነጥብና ሁለት የግብ ልዩነቶች ይዘው የምድቡን የመሪነት ስፍራ የያዙት ኢኳዶር እና ኔዘርላንድስ በአንደኝነት ወደ ቀጣይ የጥሎ ማለፍ ውድድር ለመግባት ተጋጣሚዎቻቸውን ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል። በዚህም መሠረት በአውሮፓ ሊጎች ውስጥ በሚሰለፉ ተጫዋቾች ከተገነባችው ሴኔጋል ጋር የምትገጥመው ኢኳዶር ከባድ ፈተና የሚጠብቃት ሲሆን፣ ከወዲሁ ከውድድሩ መውጣቷን ካረጋገጠችው ከኳታር ጋር የምትገጥመው ኔዘርላንድስ ግን በአሸናፊነት የምድቡን የበላይነት ትይዛለች ተብሎ ይጠበቃል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c2e99pgn9j2o +politics አሜሪካዊቷን ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ለማስለቀቅ የተደረገው የእስረኞች ልውውጥ እንዴት ተካሄደ? ሩሲያ ውስጥ ለወራት ታስራ የነበረችውን አሜሪካዊቷ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ ግሪነርን እንዲያስፈቱ እና ወደ አገሯ እንዲመልሱ የሕዝብ ግፊት በርትቶባቸው የነበሩት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመጨረሻ ተሳክቶላቸዋል። እንደ ጀግና የምትታየው ስፖርተኛዋ ተፈትታ ወደ አገሯ እንድትመለስ ደከመች ሰለቸኝ ሳትል ከፊት ሆና ዘመቻውን ስትመራም የነበረችው የትዳር አጋሯም ቼሪል እፎይ ብላለች። “ደህና ናት። በአውሮፕላን ውስጥ ናት። ወደ አገሯ፣ ወደ ቤቷ እየመጣች ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ባይደን ለሕዝባቸው ንግግር አድርገዋል። ግሪነር በሩሲያ የቆየችበትንም ሰቆቃ የተሞላበት ወቅት “የገሃነም ወራት” ሲሉ ጠርተውታል። አጋሯ ቼሬልም ፈገግ ብላ የታየች ሲሆን ለጋዜጠኞች “በከፍተኛ ስሜት ላይ ነኝ። [ፕሬዝዳንቱ] ሳቄን መልሰውልኛል” ብላለች። በእስረኛ ልውውጥ የተፈታችውን ብሪትኒን ለመመለስ ዘጠኝ ወራት ወስዷል። ምንም እንኳን በርካቶች ደስታቸውን ቢገልጹም የባይደን አስተዳደር በእስር ላይ ያለውን ሌላኛውን የአሜሪካ ዜጋ ፖል ዊላን ማስፈታት አለመቻሉ ደስታውን ሙሉ አላደረገውም። ብሪትኒ በቁጥጥር ስር የዋለችው ሩሲያ ዩክሬንን ከመውረሯ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ በሞስኮ አየር ማረፊያ ላይ ነበር። ትንሽ መጠን ያለው የካናቢስ (ዕጸ ፋርስ) ዘይት በሻንጣዋ ውስጥ መገኘቱ ነበር ለእስር የዳረጋት። ብሪትኒ ጥፋተኛ መሆኗን ብታምንም፣ ሆን ብላ ያደረገችው እንዳልሆነ ገልጻለች። የባይደን አስተዳደር በስህተት እንደታሰረች በተደጋጋሚ ሲገልጽም ቆይቷል። እነዚህን እስረኞች እንደታገቱባት ስትገልጽ የቆየችው አሜሪካ ቅድሚያ እነዚህን ታጋቾች ለማስለቀቅም ልዩ ልዑክ እስከማቋቋም ደርሳለች። ሆኖም የብሪትኒ የመለቀቅ ጉዳይ ውስብብ ሁኔታዎችን ያስተናገደ ነበር። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት አሜሪካ ዩክሬንን እያስታጠቀች እና ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገችበት ባለበት ወቅት መሆኑ ነው። ሆኖም የአሜሪካ መንግሥት በሩሲያ በእስር ላይ የነበረውን አሜሪካዊ የባሕል ኃይል አባል ትሬቨር ሪድን በሚያዝያ ወር ማስለቀቅ ችሏል። ሁለቱ አገራት ፖለቲካዊ ውጥረታቸውን ወደ ጎን ማድረግ እንደሚችሉ ባሳየ ድርድር በአሜሪካ በኮኬይን ዕፅ ማዘዋወር ወንጀል ታስሮ በነበረውን ሩሲያዊ አብራሪ መቀያየር ቻሉ። የትሬቨር መለቀቅ እንዲሁም የብሪትኒ እስር የዓለምን ቀልብ መሳብ ሌሎች የታሰሩባቸውም ቤተሰቦች በአንድነት እንዲቆሙና በዋይት ሐውስ ላይ ጫና እንዲያሳድሩ አድርጓቸዋል። ሐምሌ ወር ላይ ብሪትኒ በሩሲያ ላልተወሰነ ጊዜ ልታሰር እችላለሁ የሚል ፍራቻ እንዳላት እና እንዳይረሷትም በመለመን ለፕሬዝዳንት ባይደን በእጅ የተጻፈ ደብዳቤ ላከች��� ከቀናት በኋላ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን የሩሲያ አቻዎቻቸው በእስረኞች ልውውጥ እያቀረቡ ያሏቸውን ተጨባጭ ነገሮች ሊቀበሉ እንዳልቻሉ በመግለጽ ብስጭታቸውን በአደባባይ ገለጹ። የብሊንከን በይፋ እንዲህ መናገር በዲፕሎማሲው ዓለም ያልተለመደ ነው ተብሏል። የታጋቾቹም ሆነ የእስረኞች ልውውጥ ምስጢራዊ በሆነ ሁኔታ ነበር የሚካሄደው። ሩሲያውያን ነውጠኛውን የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ እና በአሜሪካ 25 ዓመት እስር የተፈረደበትን ቪክቶር ቦውት እንደሚፈልጉ ግልጽ ሆነ። ግለሰቡ ሩሲያ አደገኛ በሆኑ የአየር ጉዞዎች አደጋ ወደተሞላባቸው ስፍራዎች የሚሄድ ነጋዴ ነው የሚል ስም አትርፏል። ቪክቶር ከሩሲያ የስለላ ድርጅት ጋር ግንኙነት እንደነበረው ግልጽ ባይሆንም፣ የሩሲያ እና የአሜሪካ ተንታኞች የሚስማሙበት ጉዳይ በደኅንነት መረጃ የካበተ ስለመሆኑ ነው። ለዚህም ነው ሩሲያ አጥብቃ እንዲመለስላት ስትሟገት የቆየችው። ይህም ለአሜሪካ ፈታኝ ጥያቄ በመሆኑ፣ ለዚህም ነበር አስተዳደሩ በድርድሩ ውስጥ ለአራት ዓመታት ያህል በእስር ላይ የሚገኘውን የኮርፖሬት ደኅንነት ሥራ አስፈጻሚ ዊላንን ለማካተት አጥብቆ የጠየቀው። ግለሰቡ በስለላ ወንጀል ተከሶ የ16 ዓመት እስራት ተፈርዶበት በሩሲያ እስር ላይ ይገኛል። ድርድሮቹም ለተወሰነ ወራት ፍሬ ሊያፈሩ ያልቻሉ ሲሆን፣ ብሪትኒም የዘጠኝ ዓመት አስር ተፈረደባት። የጠየቀችውም ይግባኝ ውድቅ ተደርጎ ራቅ ወዳለ እስር ቤትም ተላከች። ለቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ ሁኔታዎች ጨለሙባት። ድንገትም ነው የእስረኛ ልውውጡ ዜና ይፋ የሆነው። በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ሁለቱም የሩሲያ እና የአሜሪካ ባለሥልጣናት ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ተስፋ እንዳለ ቢጠቁሙም የእስረኛ ልውውጡ ጉዳይ ድንገት ነው የተነገረው። አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን እንደተናገሩት ስምምነቱ ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ መደረሱን ነው። ዋነኛው የስምምነቱ ነጥብም ሁለት እስረኞችን በአንድ መለወጥ የሚል ቢሆንም፣ ሩሲያ ብሪትኒን ብቻ እንደምትለቅ አስታወቀች። “ይህ ስምምነት የትኛው አሜሪካዊ ነው ወደ አገሩ መምጣት ያለበት የሚል ምርጫ አልነበረም” በማለት የተናገሩት አንቶኒ ብሊንከን “ምርጫው አንድ ወይም ምንም ነበር” ብለዋል። ፕሬዝዳንት ባይደን በጣም አሳዛኝ ውሳኔን መቀበል ነበረባቸው፤ ይህም ብሪትኒን በቦውት መለወጥ። በዚህም ሁለቱ እስረኞችም አቡ ዳቢ አውሮፕላን ማረፊያ መንደርደሪያ ላይ እንዲተላለፉ በማድረግ ልውውጡ ተካሄደ። ብዙም ሳይቆይ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ሳዑዲ አረቢያ የጋራ ሽምግልና ጥረታቸው ብሪታትኒ እንድትፈታ ረድቷል ሲሉ መግለጫ አወጡ። ፕሬዝዳንት ባይደን ለልውውጡ የሚሆን ቦታ ስላቀረበች የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን ቢያመሰግኑም፣ ነገር ግን ዋይት ሐውስ መደበኛ አደራዳሪ የሚለውን ሚና ሀሳብ ዝቅ አድርጎታል። የዋይት ሐውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሪን ዣን ፒየር ሳዑዲ አረቢያ ጉዳዩን ከሞስኮ ጋር በማንሳት ቢያመሰግኑም ድርድሩ በአሜሪካ እና በሩሲያ ብቻ የተካሄደ ነው ብለዋል። የአሜሪካ ባለሥልጣናት ዊላን በስምምነቱ ውስጥ አለመካተቱ እንዳሳዘናቸው እና ከእስር እንዲፈታ ጥረታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል። ከዊላን ጋር ተያይዞ ያለው ዋነኛ ችግሮች “ሐሰተኛ የስለላ ወንጀል ክስ” ነው ሲሉ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ተናግረዋል። በግልጽ እንደሚታየው ለሩሲያውያን ከሰላይ ይልቅ የስፖርት ኮከብን መለወጥ እንደ ትልቅ ጉዳይ አይተውታል ብለዋል። ብሪትኒ ታዋቂ በመሆኗ እስሯ የሚዲያ ቀልብን የሳበ ቢሆንም ከዘጠኝ ወራት በላይ በእስር ላይ የቆዩ ሌሎች አሜሪካውያንም እንዳሉ ማስታወስ ይገባል ተብሏል። በተጨማሪም አሜሪካ እንደ ልዕለ ኃያል አገርነቷ ሳይሆን ልታሳካ የምትችለው ጉዳይ ውስንነትና ከፍተኛ ዋጋ መክፈል እንደነበረባት አስታዋሽ ነው ተብሏል። “ሌላኛው ወገን ሁልጊዜም ተጠቃሚ ይሆናል” ሲሉም የአሜሪካ እስረኞች ተወካይ ሮጀር ካርስተንስ በቅርቡ ተናግረዋል። በአሁኑ ስምምነት አሜሪካ “የሞት ነጋዴ” በመባል የሚታወቀውን የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ከአንድ ግራም ያነሰ የካናቢስ ዘይት ይዛ በተገኘችው የስፖርት ኮከብ ለመለወጥ ተገደደች። ሁለቱ አገራት ያካሄዱት የእስረኞች ልውውጥ በዚህ ዓመት ሁለተኛው ነው። ሆኖም ይህ የእስረኞች ልውውጥ ሩሲያ እና አሜሪካ ግንኙነታቸው እንደሸከረ፣ ከመጋረጃ ጀርባ ያሉ ድርድሮች እና ንግግሮችን እንደሚቀጥሉ ያሳያል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1vkyy6v93o +sports ኮሮናቫይረስ፡ የሜዳ ቴኒሱ ኮከብ ሰርቢያዊው ጆኮቪች በኮቪድ-19 ተያዘ ሰርቢያዊው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ጆኮቪች 33 ዓመቱ ሲሆን በቤልግሬድ አንድ የቴኒስ ውድድር አሰናድቶ ነበር ሰሞኑን፡፡ ውድድሩ የተሰናዳው ሁለት ዓላማ አንግቦ ነበር፡፡ አንደኛው በደቡም ምሥራቅ አውሮጳ የሚገኙ ቴኒስ ተጫዋቾች ከውድድር ርቀው ስለነበር ለቀጣይ ውድድር እንዲዘጋጁ ለማድረግ ሲሆን ሁለተኛው የሚገኘው ገቢ ከኮሮና ጋር በተያያዘ የሚውል ለበጎ አድራጎት እንዲሰጥ ነበር፡፡ ይህ ውድድር ገና ከመጀመሩ ታዲያ አሳዛኝ ዜና አጋጥሞታል፡፡ ቢያንስ አራት የሚሆኑ ዕውቅ የቴኒስ ተጫዋቾች በኮሮና መያዛቸው ታውቋል፡፡ ከነዚህም መሐል ክሮሺያዊው ቦርና ኮሪክ እና ሰርቢያዊው ቪክተር ትሮይኪ እንዲሁም ቡልጋሪያዊው ግሪጎር ዲሚትሮቭ ይገኙበታል። • ኢትዮጵያ መሰረታቸውን ግብጽ ባደረጉ ቡድኖች የመረጃ መረብ ጥቃት ተሞከረብኝ አለች • የናይጄሪያ ፖሊስ በሩዝ ፋብሪካ ተቆልፎባቸው እንዲሰሩ የተገደዱ 300 ሰራተኞችን ነፃ ማውጣቱን ገለፀ • በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ሊደረግ ነው ‹‹ይህንን የቴኒስ ውድድር ያሰናዳሁት ከቅን ልቦና ተነስቼ ነበር፡፡ ሁሉንም የጤና መመርያዎች ለመከተል ሞክረናል፡፡ ይህ አሳዛኝ ዜና በመምጣቱ ከልብ አዝናለሁ›› ብሏል ቾኮቪች፡፡ የእንግሊዙ እውቅ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች አንዲ ሙሬይ በበኩሉ ‹‹ይህ ለኛ ትልቅ ትምህርት ነው›› ሲል ትዊተር ሰሌዳው ጽፏል፡፡ ይህንን ውድድር በዚህ ወቅት ማሰናዳት አደጋ ሊኖረው ይችላል የሚል ሐሳብ ቀድሞውንም ሲንጸባረቅ ነበር፡፡ የቴኒስ ውድድሩ በጆኮቪች ሐሳብ አመንጪነት ሲሰናዳ እውቅ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾች ራሳቸውን ከውድድር በማራቃቸው እንደ ማነቃቂያ ሊሆናቸው ይችላል፤ በዚያውም የበጎ አድራጎት ሥራ ይሆናል በሚል ነበር፡፡ ጆኮቪች በድረገጹ እንደጻፈው መጀመርያ ቤልግሬድ እንደደረሰ በኮሮና መያዙ ይፋ የተደረገው ኖቫክና ቤተሰቡ ነበር፡፡ ሆኖም ምንም ምልክት አያሳይም ነበር፡፡ ይህ በሰርቢያ የተሰናዳው ውድድር 4ሺህ ሰዎች ታድመውታል፡፡ ሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾችም ከውድድር በኋላ መሸታ ቤት ሲደንሱ የሚያሳይ ፎቶ ወጥቷል፡፡ በመጀመርያው ቀን ውድድር የቡልጋሪያው ዲሚትሮቭ ከክሮሺያው ኮሪክ ጋር ቅዳሜ እለት ተጫውተው ነበር፡፡ ጆኮቪች ከዚህ ቀደም የኮሮናቫይረስ ክትባት ቢኖር እንኳ ክትባቱን ለመወጋት ፍቃደኛ እንደማይሆን በትዊተር ገጹ በመጻፉ የሴራ ንድፈሐሳብ አራማጆች ክትባቱ በቢልጌትስ የተቀነባበረ ስለመሆኑ እንደ አንድ ማስረጃ የርሱን ጽሑፍ ሲያጋሩ ነበር፡፡ ሚስቱ ጄሌና ከዚህ ቀደም ኮሮናቫይረስ የመጣው በ5ጂ ቴክኖሎጂ ነው የሚል ይዘት ያለው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ማጋራቷ ሲታይ ቤተሰቡ በወረርሽኙ ምንነት ላይ ጥርጣሬ እንደነበረው እንዲገመት በር ከፍቷል። https://www.bbc.com/amharic/news-53160664 +health ሊሞት የተቃረበ አባታቸውን ሊሰናበቱ የፈለጉ አራት ልጆች ለለይቶ ማቆያ 600 ሺህ ብር ክፈሉ ተባሉ "በአውስትራሊያ በህይወትና በሞት መካከል ያለ አባታቸውን ሊሰናበቱ ከሌላ ከተማ ሊመጡ የፈለጉ አራት ልጆች ለሚያርፉበት ለይቶ ማቆያ ሆቴል አስራ ስድስት ሺህ ዶላር (600 ሺህ ብር) መክፈል አለባችሁ ተብለዋል። የ39 አመት አባታቸው በካንሰር ህመም በፀና የታመመ ሲሆን ኩዊንስላንድ በምትባለው ከተማ ቤቱ ውስጥ ይገኛል። አራቱ ልጆቹ ደግሞ በሌላኛዋ ከተማ ሲድኒ ናቸው ያሉት። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አውስትራሊያ ከከተማ ወደ ከተማ የሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ የጣለች ሲሆን የኩዊንስላንድ ባለስልጣናትም ለዚህ ሲሉ ህጉን እንዲያላሉት ብዙዎች ተማፅነዋቸዋል። ሁኔታው ቁጣን በመቀስቀሱም ከ200 ሺህ ዶላር በላይም ገንዘብ ተዋጥቷል። መጀመሪያ ላይ ህመምተኛው ማርክ ኪንስ አንድ ልጅ ብቻ ሊያየው እንደሚችልና ከልጆቹም መምረጥ እንዳለበት ተነግሮት ነበር። በኋላም የግዛቲቷ አስተዳደር ሁኔታውን አሻሽለው ሁሉም ልጆቹ መጥተው እንዲያዩትና እንዲሰናበቱት ፈቀዱ። ሆኖም ልጆቹ ለሁለት ሳምንታት ያህል በራሳቸው ወጪ በሆቴል ለይቶ ማቆያ እንዲገቡም እንደ ቅድመ ሁኔታ ተቀመጠላቸው። ከዚህም በተጨማሪም ልጆቹ አባታቸውን በሚጎበኙበት ወቅት ሰውነታቸው በሙሉ በመከላከያ መሸፈን አለበት። ""ባለቤቴ እሱን ለማየት ይህን ያህል ክፍያ ክፈሉ እያላችሁን ነው? ለመቅበርስ ምን ያህል ሊያስወጣን ነው? አለችኝ"" በማለት የልጆቹ አያት ብሩስ ላንግቦርን ለ7 ኒውስ ተናግረዋል። ልጆቹን አባታቸውን እንዲያዩና እንዲሰናበቱም ለማስቻል በጎ ፈንድ ሚ ገንዘብ እየተሰባሰበ ነው። መጀመሪያ ታቅዶ የነበረው 30 ሺህ ዶላር ለመሰብሰብ ቢሆንም ባልተጠበቀ ሁኔታም 200 ሺህ ዶላር ተዋጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰንም አንድ ሺህ ዶላር አዋጥተዋል። በገንዘብ ማሰባሰቢያው ድረገፅም በርካቶች ቤተሰቦቹን ያፅናኑ ሲሆን፤ የኩዊንስላንድ አስተዳደርም ከፍተኛ ትችትን እያስተናገደ ነው። በርካቶችም ""ሊሞት የተቃረበ አባታቸውን እንዳያዩ እንዴት ይከለከላሉ? እንዲህ አይነት ገንዘብ ክፈሉ ማለትም አሳፋሪና ጨካኝነት ነው""ብለውታል። የኩዊንስላንድ የጤና ኃላፊዎች በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት አለም አቀፍ ወረርሽኝ እየታገሉ ከመሆናቸው አንፃር ህዝቡን በተለይ ተጋላጭ ማህበረሰቡን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስምረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54119251 +business በዚምባብዌ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ ሰዎችን ገደለ "በዚምባብዌ የወርቅ ማዕድን ሲያወጡ የነበሩ ሰዎች የመደርመስ አደጋ ደርሶባቸው ሕይወታቸውን አጡ። የአገሪቱ ሄራልድ ጋዜጣ እንዳስነበበው ከሆነ በደረሰው የመሬት መደርመስ ምክንያት ሁለት ሰዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል። 20 የሚሆኑት ደግሞ በተደረመሰው አፈር ተቀብረው እስካሁን መውጣት አልቻሉም። ማዕድን አውጪዎቹ ከመዲናዋ ሐረሬ በስተምዕራብ በኩል 120 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቃ በምትገኘው ክዌክዌ ከተማ ነው ማዕድን ሲያወጡ የነበረው። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣንን ውሳኔን ተከትሎ የማዕድን ማውጫ ስፍራው በ2007 እ.አ.አ እንዲዘጋ ተደርጎ ነበር። ነገር ግን ሰዎች በሕገ ወጥ መልኩ ወደቦታው በማምራት በምሽት ማዕድን ሲያወጡ ቆይተዋል። ""ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ እየሰራን እያለ በሌላኛው የማዕድን ማውጫ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የጩኸት ድምጽ ሰማን፤ ከዚያ ወጥተን ስንመለከት የተደረመሰ ድንጋይ ጓደኞቻችን ላይ እየተጫነ መሆኑን አየን"" በማለት በቦታው የነበረ አንድ የማዕድን ሠራተኛ ምስክርነቱን ሰጥቷል። ""አን��ን ጓደኛችንን ተረባርበን በሕይወት ማትረፍ ብንችልም ሁለቱ ግን ወዲያው ነበር የሞቱት። ከተቀበሩበት ለማውጣት ብንሞክርም የተጫናቸው አለት ከባድ በመሆኑ እርሱን ማንሳት አልቻልንም። ከሟቾቹና በሕይወት ከተረፉት ተጎጂዎች በተጨማሪ 20 የማዕድን ሠራተኞች ከመሬት በታች መውጫ አጥተዋል"" ብሏል። ከአደጋው የተረፉት ተጎጂዎች ወደ አካባቢው ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው ነው። ባለፈው ዓመት 22 የማዕድን ሠራተኞች በተመሳሳይ አደጋ በዚምባብዌ ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአገሪቱ መንግሥትም በአሁኑ ወቅት በሕገ ወጥ ማዕድን ማውጣት ሥራ ተሰማርተዋል ያላቸውን ግለሰቦች በብዛት እያፈሰ በማሰር ላይ ይገኛል።" https://www.bbc.com/amharic/news-51410600 +business ኩባ በህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ለአነስተኛ እና መካከለኛ የግል ንግዶች ፍቃድ ሰጠች ግለሰቦች ለሚያስተዳድሯቸው አነስተኛና መካከለኛ ንግዶች ለአመታት ፍቃድ ከልክላ የነበረችው ኩባ ባለፈው ወር በተካሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ይህንን ህግ ሽራለች። የኩባ ኮሚኒስት መንግሥት ሕዝባዊ ተቃውሞን ተከትሎ አነስተኛና መካከለኛ የግል ንግዶችን ሕጋዊ እንዲሆኑ አድርጓል። በአዲሱ ህግ መሰረት እስከ 100 ሰራተኞች ያሉት የንግድ ድርጅቶችን ግለሰቦች እንዲያቋቁሙ ተፈቅዷል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሚጌል ዲአዝ-ካኔል ኩባ የኢኮኖሚ ሞዴሏን ለማዘመን ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው ብለዋል። ሆኖም ሺዎች የኢኮኖሚውን ሁኔታ በተመለከተ አደባባይ መውጣታቸው መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ በፍጥነት እንዲደርስ ምክንያት ነው የሚሉ አስተያየቶች ተደምጠዋል። ሰልፈኞቹ የሀገሪቱ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን የያዘበትን መንገድ ያወገዙ ሲሆን የፖለቲካ ለውጥ እንዲደረግ ጠይቀዋል። ሀገሪቱ በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ባለችበት ጊዜ በተነሳው በዚህ ተቃውሞው ምክንያት በአገር አቀፍ ደረጃ በርካቶች ለእስር የተዳረጉ ሲሆን ባስከተለው አለመረጋጋት ቢያንስ አንድ ሰው መሞቱ ተዘግቧል። ታዲያ ባለፈው አርብ አነስተኛና መካከለኛ ንግድን በተመለከተ መንግስት ያሳለፈው ውሳኔ በሀገሪቱ የተደረገ ትልቅ የፖሊሲ ለውጥ ነው ተብሏል። ኢኮኖሚዋ እየላሸቀ ነው የምትባለው ኩባ በሐምሌ ወር ባለሥልጣናቱ ወደ አገሪቱ የሚመጡ ተጓዦች ግብር መክፈል ሳይጠበቅባቸው ምግብ ፣ መድኃኒት እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን እንዲያመጡ ፍቅዳለች። በሀገሪቱ አለ የሚባለውን የመድኃኒት እና የምግብ እጥረትን ለማቃለል አንዳንድ ኩባንያዎች ከውጭ የሚያስገቡበትን ግብር እስከመሻር ደርሳለች። ለኩባ ኢኮኖሚ ወሳኝ ከሆኑት ዘርፎች አንዱ የሆነው ቱሪዝም በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት በዓለም አቀፍ የጉዞ ገደቦች ምክንያት ክፉኛ ተጎድተውባታል። የስኳር ምርትን ወደ ውጭ መላክ ሌላኛው የኩባ ቁልፍ ገቢ ነው። ሆኖም የዘንድሮው ምርት ግን ከተጠበቀው እጅግ የወረደ ሆኗል። የዚህም ድምር የመንግስት የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዲሞጠጥ ምክንያት በመሆኑ እጥረትን ለማሟላት ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎችን መግዛት ለሀገሪቱ ፈተና ሆኗል። ኩባ በቅርቡ ለተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞው እና ለሰፊ ችግሮቿ አሜሪካን እና የጣለችባትን የኢኮኖሚ ማዕቀቦ ዋነኛ ምክንያት አድርጋ ትከሳለች። https://www.bbc.com/amharic/news-58135227 +sports ሴኔጋላዊያን የብሬክ ዳንሰኞች የኦሎምፒክ ተሳታፊ ለመሆን ተስፋ ሰንቀዋል ሴኔጋላዊያን የብሬክ ዳንሰኞች የኦሎምፒክ ተሳታፊ ለመሆን ተስፋ ሰንቀዋል https://www.bbc.com/amharic/sport-50210682 +sports 'ፌክ' ፓስፖርት ይዞ ተገኝቷል የተባለው ሮናልዲንሆ ፍርድ ቤት ቀረበ ብራዚላዊ የእግር ኳስ ጠቢብ ሮናልዲንሆና ወንድሙ ፓራጓይ ለመግባት ሃሰተኛ ፓስፖርት ተጠቅመዋ��� ተብለው በመጠርጠራቸው ፍርድ ቤት ቀረቡ። አቃቤ ሕግ፤ ወንድማማቾቹ ባለፈው ረቡዕ የፓራጓይ ዋና ከተማ አሱንሲዮን ሲደርሱ ሃሰተኛ ሰንዶች ተሰጥቷቸዋል ሲል ይከሳል። አቃቤ ሕግ ወንድማማቾቹ ቀለል ያለ ቅጣት ይቀጡ የሚል ሃሳብ ቢያቀርብም ዳኛው ግን የኋሊት ጠፍራችሁ አምጡልኝ ሲሉ አዘዋል። ሮናልዲንሆና ወንድሙ አርብ ዕለት ነው የካቴና ሲሳይ የሆኑት። አቃቤ ሕግ ሮናልዲንሆና ወንድሙ በቀጣፊዎች ተታለዋል ይላል። ወንድማማቾቹም 'እኛ የምናውቀው ነገር የለም' ይላሉ። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ያረፉበትን ሆቴል ከበረበረ በኋላ ምርመራ አድርጎባቸዋል። ሮናልዲሆንና ወንድሙ 'ፖስፖርቱ ሲሰጠን የክብር መገለጫ መስሎን ነበር' ይላሉ። ፓርጓዊው ዳኛ ሮናልዲንሆም ሆነ ወንድሙ ፍርድ እስኪሰጣቸው ድረስ ማቆያ እንዲሰነብቱ አዘዋል። ዓለም ካየቻቸው ድንቅ እግር ኳሰኞች አንዱ የሚባለው ሮናልዲንሆ ባለፈው ሐምሌ ግብር አልከፈለም ተብሎ የብራዚልና የስፔን ፓስፖርቱን መነጠቁ አይዘነጋም። አልፎም ብራዚል ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ የተፈጥሮ ሃብት መጠበቂያ ሥፍራ ገንብቷል ተብሎ ክስ ቀርቦበት ነበር። «ቃዋቂ እግር ኳሰኛ ነው። አከብረዋለሁ። ነገር ግን ሕግ ሕግ ነው» ሲሉ የፓራጓይ ሃገር ውስጥ ሚኒስቴር ለሃገራቸው ጋዜጠኞች ተናግረዋል። የ39 ዓመቱ ሮናልዲንሆ ወደ ፓራጓይ ያቀናው አዲስ የታተመ መፅሐፉን ለማስተዋወቅና እርዳታ ለሚሹ ሕፃናት ድጋፍ ለማሰባሰብ ነው። ሁለት ጊዜ የዓለም ኮከብ ተብሎ የተሸለመው ሮናልዶ የ2002 ዓለም ዋንጫ አሸናፊ ነው። አልፎም ከባርሴሎና ጋር ስኬታማ ጊዜ አሳልፏል። ብራዚላዊው የኳስ ቀማሪ 100 ሚሊዮን ፓውንድ የተጣራ ሃብት እንዳለው ይገመታል። https://www.bbc.com/amharic/51789011 +health ትግራይ ውስጥ ከባድ የጤና ስጋት የፈጠሩ 3 ተላላፊ በሽታዎች "በትግራይ ክልል ወባ፣ ኮሌራ፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ እንዲሁም አባ ሠንጋ በወረርሽኝ መልክ መከሰታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ። የክልሉ ጤና ቢሮ እንደሚለው ከሆነ ከእነዚህ በሽታዎች መካከል ውስጥ ሶስቱ በከፍተኛ ደረጃ ስጋት ሆነዋል። ቢሮው ለቢቢሲ በላከው መረጃ መሰረት የእብድ ውሻ በሽታ፣ አባ ሠንጋ እንዲሁም ወባ ጦርነቱን ተከትሎ በተፈጠረ የመድሃኒት እጥረት፣ የጤና ተቋማት መዳከም እንዲሁም የመገናኛ መንገዶች መቋረጥና የአቅርቦት እጥረት ከተያያዥ ችግሮች ጋር ተደማምረው ለበሽታዎቹ መስፋፋት ዋና ምክንያቶች ሆነዋል። ትግራይ ውስጥ የተከሰቱ ሶስት ከባድ የጤና ስጋቶች የትኞቹ ናቸው? አባ ሠንጋ ትግራይ ውስጥ ‘መገረም’ በሚል የሚታወቅ ሲሆን በቀላሉ ማወቅና ለጤና ባለሙያዎች ማሳወቅ ከሚቻሉ በሽታዎች መካከል አንዱ ነው። በዚህ ዓመት (2022) ማእከላዊ ዞን ናዕዴር ዓዴት ወረዳ ውስጥ 10 ሰዎች መያዛቸውን የሚያመላክት ሪፖርት ቀርቧል። ከዚያ ወዲህ ወደ ክልሉ ጤና ቢሮ ሪፖርት የላኩ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በበሽታው የተጠቁ በርካታ ሰዎች መኖራቸው ታውቋል። የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ "" ሰኔ10/2022 ዓ.ም በታሕታይ ቆራሮ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ  የዓዲ-ገሽቲን ዓዲ-ሓበሳይን ጣብያዎች  እንዲሁም ሰሜን ምዕራብና  ምስራቅ ዞኖች ውስጥ ሞት ሲያጋጥም ሰዎችና እንስሳት መያዛቸው የሚያሳይ መረጃ አለኝ"" ብሏል። ይህን ተከትሎ ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO)፣ ከእርሻና ገጠር ልማት ቢሮ፣ እንዲሁም ከጤና ቢሮ የተውጣጣ ቡድን ሰኔ 22 2022 ሁኔታውን መርምሮ የመከላከል ስራ እንዲሰራ ተልኳል። ቡድኑ ከእንስሳት ጋር ንክኪ ከነበራቸውና ስጋ ከበሉ 120 ሰዎች መካከል 34 በበሽታው እንደተያዙ እና ሁለት ደግሞ ህይወታቸው እንዳለፈ አረጋግጧል። በበሽታው መያዛቸውከተጠረጠሩ 30 የቤት እንስሳት (ከብቶት፣ ፍየሎችና አህዮች) ውስ�� 23 ሞት እንዳጋጠመ ተገንዝቧል። ""በዳሰሳቸው 12 ወረዳዎችን ለማዳረስ የሞከሩ ሲሆን በመንገዳቸው ላይ 13 በአባ ሠንጋ የተያዙ ሰባት [አንድ ላዕላይ ማይጨው 12 ደግሞ ቆላ ተምቤን ውስጥ] አግኝተዋል"" ይላል የክልሉ ጤና ቢሮ ለቢቢሲ የላከው መረጃ። ክልሉ አክሎም በመገናኛ እጥረት ሳብያ ግን የህዝብ ጤና ስጋት አስተዳደር [Public health Emergency Management (PHEM)] ቡድን ከሁሉም ወረዳዎች የጤና ተቋማት ሙሉ መረጃ ማግኘት እንዳልቻለ ገልጿል። ከመጋቢት 2022 መጨረሻ ጀምሮ በማእከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅና ምስራቅ ዞኖች ውስጥ በጠቅላላ በአባ ሠንጋ መያዛቸው የተጠረጠሩ 116 ሰዎችና 7 ሞት እንደተመዘገበ የጤና ቢሮ ሪፖርት ያመለክታል። ከጦርነቱ በፊት የእብድ ውሻ በሽታ ቁጥጥርና መከላከል ስራ በማህበረሰቡ፣ በመጀመርያ ደረጃ የጤና ክትትል ቡድን እንዲሁም ሆስፒታሎች ይሰራ ነበር። በወቅቱ በርካታ የጤና ተቋማት በበሽታው ስለተጠረጠሩና ስላጋጠመ ሞት የሚያሳይ ሪፖርት ያቀርቡ ነበር። የውሾች ክትባት፣ ባለቤት የሌላቸው ውሾች አስተዳደር፣ በበሽታው ለተያዙ ሰዎች የሚደረግ ህክምና እንዲሁም የህዝብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቀጣይነት ስኬታማ በሆነ መልኩ ይካሄዱ ነበር። እስከ 2030 በእብድ ውሻ በሽታ የሚያጋጥም ሞት ዜሮ ለማድረስ እየተሰራ እንደነበር የትግራይ ክልል የጤና ቢሮ ያመለክታል። ""ይሁን እንጂ ጦርነቱን ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስና ከበባ በአሁኑ ወቅት በውሻ መነከስንና በበሽታው መያዝን የሚመለከት ሪፖርት ከ12 በመቶ በታች በሆኑ የጤና ተቋማት ብቻ ተገድቦ እንደሚገኝ"" የትግራይ ክልል የላከው ሪፖርት ያሳያል። ""በአሁኑ ወቅት በውሻ መነከስና ያጋጠመ ሞትን የሚመለከቱ ይፋ የሆኑና ያልሆኑ ሪፖርቶች ወደ ቢሮው እየመጡ ነው” የሚለው የትግራይ የጤና ቢሮ፣ በጦርነቱ ምክንያት ባለፉት ሁለት ዓመታት ለውሾች የሚሆን ክትባት፣ ባለቤት የሌላቸው ውሾችን ለማስወገድ የሚውል ‘ስትሪክኒን’ የሚባል ኬሚካል እንዲሁም የተያዙ ሰዎችን ለማከም የሚረዳ የመድሃኒት አቅርቦት እንደሌለ አስረድቷል። በዚህም ምክንያት በ11 የትግራይ ወረዳዎች 41 ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። እንዲሁም በበሽታው የታመሙ ሰዎች ለማከም የሚረዳ መድሃኒት ባለመኖሩ በበሽታው የተያዙ ሰዎች በቤታቸው በባህላዊ መንገድ አልያም ወደ ባህላዊ ሐኪም በመሄድ መፍትሔ ለማግኘት እንዲጥሩ እያስገደዳቸው ነው። በትግራይ ክልል የወባ ወረርሽኝ ከመስከረም -እስከ ታሕሳስ ባለው ወቅት እጅግ ስፋት ባለው ሁኔታ የሚታይ ሲሆን፤ በሚያዝያ እና ግንቦት ወራትም ያጋጥማል። በክልሉ ለመጨረሻ ጊዜ ወረርሽኝ የተከሰተው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 ከመጋቢት እስከ ሚያዝያ ሲሆን አካባቢውም አሕፈሮም የሚባል ወረዳ ነበረ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የወባ በሽታ የመከላከል እና የቁጥጥር ስትራቴጂዎች በተገቢው መንገድ በመተግበራቸው የበሽታው ወረርሽኝ አጋጥሞ አያውቅም። አሁን ላይ በጦርነቱ ሳቢያ ተገቢ የህክምና አገልግሎት፣ የህክምና አቅርቦቶች እና መደበኛ ክትትል ባለመኖሩ የበሽታው መስፋፋትና በበሽታው ምክንያት የሚያጋጥም ሞት እየተመዘገበ መሆኑ የክልሉ ቢሮ ለቢቢሲ ገልጿል። ወረርሽኙን ለመከላከል እና ህይወትን ለማዳን ቀድሞ ስለበሽታው መስፋፋት ማወቅ እና የታካሚ መረጃ ማግኘት ወሳኝ መሆኑን የጤና ቢሮው ይገልጻል። ነገር ግን በትግራይ የመገናኛ ዘዴዎች አገልግሎት በመቋረጡ እና ከየአካባቢው የሚቀርቡ መረጃዎች ያልተሟሉ በመሆናቸው የበሽታው መስፋፋት በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት እንዳዳገተው ገልጿል። ወባ ከሰኔ 2020 ሁለተኛ ሳምንት ጀምሮ በወረርሽኝ መልክ እየተዛ��ተ መሆኑን የትግራይ ጤና ቢሮ ያስረዳል። የበሽታውን ሁኔታ የሚያጠና የባለሙያዎች ቡድን ወደ ተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እንደተላኩ የሚገልፀው ጤና ቢሮው ""ለቡድኑ ጉዞ የቀረበ የነዳጅ እና የገንዘብ ድጋፍ መቀለ በሚገኘው የዓለም ጤና ድርጅት ፅህፈት ቤት የተሸፈነ ነው። ሆኖም ግን በነዳጅ እና በጊዜ እጥረት የበሽታውን ዋና መንስኤ መለየት አልቻሉም” ብሏል። እ.ኤ.አ. እስከ ሐምሌ 23 ቀን 2022 ባለው ጊዜ በትግራይ ውስጥ ከ10 በላይ ወረዳዎች የወባ በሽታ መስፋፋት ታይቷል። በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የፀረ ወባ መድሐኒት እና ሌሎች የህክምና አቅርቦቶች ባለመኖሩም ሁኔታው ተባብሷል። ወረርሽኙን በጊዜ መቆጣጠር ካልተቻለ ወደ ብዙ የትግራይ አካባቢዎች ሊዛመት እንደሚችል ነው የትግራይ ጤና ቢሮ ያስጠነቀቀው።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c72wzeg612do +health ኮሮናቫይረስ፡ ዋይት ሀውስ በዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ንግግር ተቆጣ ዋይት ሀውስ፤ ከፍተኛ የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ፤ ስለ ኮሮናቫይረስ ያደረጉት ንግግር ፖለቲካዊ አላማ ያለው ነው ሲል ከሰሰ። ዶ/ር ፋውቺ ከዋሽንግተን ፖስት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ አሜሪካ “ከፍተኛ ጉዳት ገጥሟታል” ብለዋል። አሜሪካ ከየትኛው አገር በበለጠ በወረርሽኙ ሳቢያ ዜጎቿን አጥታለች። በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ መሠረት ከ230,000 በላይ ሰዎች ሞተዋል። ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ደግሞ በቫይረሱ ተይዟል። ዶ/ር ፋውቺ በቃለ ምልልሱ ላይ “ወደቀዝቃዛው ወቅት ስንገባ ነገሮች ይባባሳሉ” ብለዋል። በተያያዥም ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን ስለ ወረርሽኙ ያላቸውን አቋም ገምግመዋል። ባይደን ለቫይረሱ ተገቢውን ትኩረት እንደሰጡት “ከሕብረተሰብ ጤና እና ከምጣኔ ሀብት አንጻርም በቁምነገር እየተከታተሉት ነው” በማለት ገልጸዋል። አሜሪካ የሕብረተሰብ ጤናን በተመለከተ ለውጥ ማምጣት እንዳለባት አሳስበዋል። በዚህ የዶ/ር ፋውቺ አስተያየት ዋይት ሀውስ ደስተኛ አልሆነም። ባይደን ምርጫውን እንዲያሸንፉ የሚገፋ ምላሽ ነው በማለትም ዶክተሩን ተችተዋል። ቃል አቀባዩ ጁድ ደሬ፤ “አስተያየቱ ተቀባይነት የለውም። ከመርህ ውጪ ነው። ዶ/ር ፋውቺ የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል አባል እንደመሆናቸው ለለውጥ መገፋፋት ነበር የሚጠበቅባቸው። እሳቸው ግን ፕሬዘዳንቱን በመተቸት ለተቀናቃኛቸው ወገንተኝነት አሳይተዋል” ብሏል። የወረርሽኙ ጉዳይ በትራምፕ እና በባይደን መካከል ዋነኛ ከሆኑት መከራከሪያ ነጥቦች አንዱ ነው።ባይደን “ውሳኔያችን ሳይንስን የተመረኮዘ መሆን አለበት” ብለው፤ ምርጫውን ካሸነፉ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል። ትራምፕ በበኩላቸው፤ ባይደን እንቅስቃሴ ላይ ገደብ በመጣል አሜሪካውያንን የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ ይከታሉ ብለዋል። “ባይደንን ከመራጥችሁ ትምህርት ቤት አይከፈትም። ተማሪዎች አይመረቁም። ሠርግ አይኖርም። ገና አይከበርም” ብለዋል። ባይደን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የወጡ መርሆችን ተከትለው ነው። በሌላ በኩል ትራምፕ አካላዊ ርቀት ሳይጠበቅ በርካታ ዜጎች የተገኙባቸው የምረጡኝ ቅስቀሳዎች አካሂደዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54776092 +business መንግሥት ስምንት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመሸጥ ጨረታ አወጣ የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ስምንት የስኳር ፋብሪካዎችን በጨረታ ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች መሸጥ እንደሚፈልግ አስታወቀ። የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የጨረታ ጥሪ ላይ እንደተመለከተው የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች በስኳር ፋብሪካዎቹ ግ�� ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል። በመንግሥት ይዞታ ስር የሚገኙት እና ለሽያጭ የቀረቡት ስኳር ፋብሪካዎች፡ ኦሞ ኩራዝ 1፣ 2፣ 3 እና 5፣ አርጆ ደዴሳ፣ ከሰመ፣ ጣና በለስ እና ተንዳሆ ናቸው። የገንዘብ ሚኒስቴር ጨረታውን ያወጣው በዘርፉ ተወዳዳሪነትን ከፍ ለማድረግ እና የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ለማሟላት ያለመ መሆኑን አስታውቋል። ኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ፍጆታን ለመሸፈን በከፍታኛ የውጭ ምንዛሪ ስኳር ከውጪ አገራት እንደምታስገባ ያመላከተው የገንዘብ ሚኒስቴር፤ ስምንቱ ፋብሪካዎች ወደ ግል ይዞታ መሸጋገራቸው ተወዳዳሪነትን እና ምርትን ይጨምራል ብሏል። የስኳር ምርት ዘርፍ ማደግ የስኳር ሸንኮራ አገዳ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ላሉ የማኅብረሰብ ክፍሎች ሕይወት እና ገቢ መሸሻል ያስገኛሉም ተብሏል። የአገር ውስጥ የውጪ ባለሃብቶች ወደ ስኳር ዘርፉ መግባታቸው ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል ስኳር ከማምረት በተጨማሪ የተለያዩ የስኳር አይነቶችን ወደ ውጪ በመላክ የውጭ ምንዛሪ ያስገኛሉ ብሏል የገንዘብ ሚኒስቴር። የገንዘብ ሚኒስቴር ለጨረታ ያቀረብኳቸው የስኳር ፋብሪካዎች በቅርቡ የተገነቡ እና የሚገኙባቸው ስፍራዎችም ለሸንኮራ አገዳ ምርት ምቹ፣ ከፍተኛ የውሃ ሃብት ያለበት፣ መሠረተ ልማት የተሟላላቸው መሆናቸውን ገልጿል። ይህንን ፋብሪካዎቹን ወደ ግል የማዞር ሂደት ኧርነስት ኤንድ ያንግ ያተባለውን አማካሪ ተቋም በአማካሪነት ሂደቱ ግልጽ እና የተሳካ እንዲሆን ሥራውን እንደሚያካናውን ተገልጿል። የስኳር ፋብሪካዎቹን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው የአገር ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ ወይም ጥምር ተቋማት ፍላጎታቸውን የሚገልጽ ሰንድ እንዲያቀርቡ የገንዘብ ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል። ከአራት ዓመት በፊት የውቅቱ ገዢ ፓርቲ የነበረው ኢህአዴግ ግምገማ አድርጎ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል፣ ለአስርታት በመንግሥት ብቸኛ ቁጥጥር ስር የነበሩ እና በግንባታ ላይ ያሉ ማምረቻ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ባለቤትነት እንዲዘዋወሩ መወሰኑ ይታወሳል። በዚህም መሠረት በመንግሥት ይዞታ ሥር ያሉ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙትም ሆነ በግንባታ ላይ የሚገኙ የባቡር፣ የስኳር ልማት፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የሆቴልና የተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በአክሲዮን ሽያጭ ወደ ግል ዘርፍ እንዲተላለፉ ተወስኖ ነበር። ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትዮ ቴሌኮም በከፊል ወደ ግል የማዞር ሃሰብ እንዲሰረዝ ሲደረግ፣ ይህ የስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል የማዞሩ ጥሪ ውሳኔው ከተላለፈ ከዓመታት በኋላ የቀረበ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c6p6qr2p579o +politics በአለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት የተከሰሰው ኬንያዊ ጠበቃ ሞቶ ተገኘ በአለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) በምስክሮች ጣልቃ ገብነት ክስ ቀርቦበት የነበረው ኬንያዊው ጠበቃ ፖል ጊቼሩ ሞቶ ተገኘ። ፖሊስ እንዳስታወቀው ጠበቃው ፖል ጊቼሩ ሰኞ ምሽት በመዲናዋ ናይሮቢ በሚገኘው ቤቱ ሞቶ መገኘቱን አረጋግጧል። ጠበቃው በአውሮፓውያኑ 2007 ምርጫ ማግስት ከተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ ለምስክሮች ጉቦ በመስጠት ነው ክስ የቀረበበት። ምስክሮቹ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በአይሲሲ ተከሰው በነበረበት ወቅት ምስክርነት የሚሰጡ ግለሰቦች ምስክርነት የሚሰጡ ግለሰቦች እንደነበሩም ተገልጿል። በዚህ ሁከት ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።ጠበቃው የቀረበበትን ክስ አስተባብሏል። ጠበቃው የአይሲሲ የእስር ማዘዣ ካወጣበት ከአምስት ዓመት በኋላም በአውሮፓውያኑ 2020 ራሱን አሳልፎ ሰጥቷል። አቃብያነ ህ�� እንደሚሉት ጠበቃው ፈጸመው በተባለው ተግባር ምክንያት ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በፍርድ ቤቱ የቀረቡባባቸውን ክሶች ውሃ እንዳይቋጥር አድርጎታል ብለዋል። ዊሊያም ሩቶ በኬንያ ምርጫ ማግስት በተቀሰቀው ሁከት በተፈጸሙ ግድያዎች፣ ስወራ እና ማፈናቀል በአለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት ተከሰው ነበር። ዊሊያም ሩቶ  እነዚህን ወንጀሎች አልፈጸምኩም በማለት በተደጋጋሚ ተናግረዋል። አይሲሲ በዊሊያም ሩቶ ላይ በቂ ማስረጃ ባለማግኘቱ ክሱን አቋርጧል። በጠበቃው አሟሟት ላይ አንዳንድ ዝርዝር መረጃዎች እየወጡ ባለበት በአሁኑ ወቅት በአሟሟቱ ላይ ፖሊስ ፈጣን እና የተረጋጋጠ ምርመራ እንዲያደርግ የኬንያ የመብት ተቋማት ጠይቀዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c97e8q53xewo +business የሱዊዝ መተላለፊያ ለመርከቦች እንቅስቃሴ ክፍት ሆነ "ለሳምንት ያህል የስዊዝ ቦይን ዘግታ የነበረችው መርከብ ከቦታው ላይ መነሳቷንና መስመሩም ለእንቅስቃሴ ክፍት መደረጉን የግብጽ ባለሥልጣናት ተናገሩ። ከማክሰኞ ጀምሮ በአንዲት መርከብ የተዘጋው የሱዊዝ መተላለፊ መስመር ለመክፈት የተደረገው ጥረት ውጤት አስገኝቶ መርከቧ ከመተላለፊያው ላይ እንድትንቀሳቀስ ተደረጓል። ባለስልጣናት ለቀናት የተዘጋው የሱዊዝ ቦይ ቅዳሜ ወይም እሁድ ይከፈታል በማለት ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቆይቶ ዛሬ ጠዋት መስመሩን ለማስከፈት ችለዋል። በዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ መስተጓጎልን ያስከተለው የመተላለፊያው መዘጋት ለተጨማሪ በርካታ ቀናት ሊቆይ ይችላል ተብሎ ቢሰጋም በተደረገው ጥረት ግዙፏ የጭነት መርከብ እንድትንቀሳቀስ ተደርጎ መተላለፊያው ሊከፈት ችሏል። ከማክሰኞ ጀምሮ የባሕር መተላለፊያ መስመሩን በአግድሞሽ ዘግታ የቆመችውን ግዙፏን የጭነት መርከብ ለማንቀሳቀስ ጥረት ሲደረግ ነበር። በዚህም ሳቢያ በመተላለፊያው የሰሜንና የደቡብ መግቢያ መስመር ላይ የሱዊዝ ቦይ መከፈትን በሚጠብቁ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው መርከቦች መጨናነቅ መፈጠሩ ተገልጿል። ጆ ሬይኖልድስ የታዋቂው የመርከብ እቃ አመላላሽ ድርጅት ሚርስክ ዋና ኢንጂነር ናቸው። ለቢቢሲ ሲገልጹ ''በቦዩ ደቡባዊ መግቢያ በኩል መንገዱ በመዘጋቱ በርካታ መርከቦች ለማለፍ እየተጠባበቁ ነው። ይህ ደግሞ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ፈጥሯል'' ብለዋል። ''በመላው ዓለም የተዘረጋው የመርከቦች የጉዞ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል'' ሲሉም አስጠንቅቀዋል። ማክሰኞ ጠዋት አካባቢ 400 ሜትር ርዝማኔና 59 ሜትር ስፋት ያለው መርከብ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አሁንም ድረስ መንገድ እንደዘጋ ይገኛል። የሱዊዝ ቦይ በመባል የሚታወቀው የግብፅ መተላለፊያ ሜድትራኒያን እና ቀይ ባሕርን በማገናኘት በእስያና አውሮፓ መካከል አጭሩ የሚባለውን የውቅያኖስ መንገድ ይፈጥራል። በታይዋኑ ኤቨርግሪን ማሪን ሥር ያለው ኤቨር ጊቭን መርከብ በዓለም ትልቁ ኮንቴነር ጫኝ ሲሆን፤ 200,000 ቶን የሚመዝን እንዲሁም 20,000 ኮንቴነር ማጓጓዝ የሚችል ነው። ኤቨር ግሪን የተሰኘው ግዙፍ መርከብ ከቻይና ተነስቶ ወደ ኔዘርላንድስ እያቀና ነበር። የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት መርከቡ ባጋጠመው ቴክኒካዊ ችግር ምክንያት ነው መሀል ላይ ቆሞ የቀረው። በፈረንጆቹ 2018 የተሠራው ይህ የፖናማ መርከብ ኤቨርግሪን ማሪን በተሰኘው የትራንስፖርት ኩባንያ ባለቤትነት ነው የሚንቀሳቀሰው። በእንደዚህ አይነት ችግሮች ብዙ ልምድ አላቸው የተባሉ ድርጅቶች የሱዊዝ ቦይ ትራፊክ መጨናነቅን ለመፍታት ቢጥሩም እስካሁን መፍትሄ አልተገኘም። የግብፅ ፕሬዝዳንት አማካሪ ችግሩ በቀናት ውስጥ እንደሚፈታ ገልጸው ነበር። ነገር ግን ባለሙያዎቹ ትልቋን መርከብ ለማንቀሳቀስና ወደቀደመው እንቅስቃሴ ለመመለስ ሳምንታት ሊፈጅ እንደሚችል ሲሉ ቆይተዋል። መተላለፊያው በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ምርቶች የሚተላለፉበት ሲሆን፤ የጦፈ ንግድ የሚካሄድበት መስመር ነው። ከመላው ዓለም የባሕር ንግድም 12 በመቶው የሚያልፈውም በዚሁ የግብፅ የባሕር ላይ ማቋረጫ መስመር በኩል ነው። በሱዊዝ ቦይ ምትክ እንደ አማራጭ የቀረበው የኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ መንገድ ደግሞ ከሱዊዝ ቦይ ጋር ሲነጻጸር ተጨማሪ ሁለት ሳምንታት ይፈጃል። ይህ ደግሞ ለበርካታ የመርከብ ድርጅቶች አዋጪ አይደለም። የግብፅ ሱዊዝ ቦይ በመዘጋቱ ምክንያት እስካሁን በየቀኑ 9.6 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መተላለፍ አልቻሉም። ሎይድስ ሊስት የተባለው የመርከብ ጉዞ ድርጅት እንደሚለው፤ በቀን ውስጥ ከምዕራብ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩ 5.1 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መጓጓዝ አልቻሉም። ከምሥራቅ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩና የተስተጓጎሉ ምርቶች ደግሞ 4.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ናቸው። ሎይድስ ሊስት ባወጣው አሃዝ መሠረት፤ በአሁኑ ጊዜ 160 መርከቦች በሱዊዝ ቦይ በኩል ለማለፍ እየጠበቁ ነው። ከእነዚህ መካከል 41 የሚሆኑት የተለያዩ ምርቶች ሲይዙ 24 ደግሞ ነዳጅ ጫኝ ናቸው። ቢአይኤምሲኦ የተባለው ዓለም አቀፍ የመርከበኞች ማኅበር እንደሚለው መተላለፊያው ተዘግቶ ከቆየ የምርት አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። በተጨማሪም በሱዊዝ የመተላለፊያ መስመር ላይ ቆማ የባሕር ላይ ጉዞን ባስተጓጎለችው መርከብ የተነሳ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ታይቷል። በመተላለፊያ መስመሩ መዘጋት ሰበብ የድፍድፍ ነዳጅ አቅርቦት ሊስተጓጎል ይችላል በሚል ስጋት ነው ረቡዕ ዕለት የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የታየበት። በሰሜናዊ ምሥራቅ አፍሪካ የሚገኘውን ወሳኝ የባሕር ላይ መተላለፊያን ዘግታ የምትገኘው የጭነት መርከብ ባለቤት የሆነው ጃፓናዊ በመርከቧ ምክንያት በዓለም የንግድ ልውውጥ ላይ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ መጠየቁ ተነግሯል። በከባድ ንፋስ ምክንያት መስመሯን ስታ መተላለፊያውን የዘጋችውን መርከብ ለማንቀሳቀስ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ የገለጸው የመርከቧ ባለቤት ""ነገር ግን የተቻላቸውን ጥረት በማድረግ"" ላይ መሆናቸውን ገልጿል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56547974 +politics የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ሳርኮዚ ለምርጫ ቅስቀሳ ባወጡት ወጪ አንድ ዓመት ተፈረደባቸው የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ዳግም ለመመረጥ በሕግ ከሚፈቀደው በላይ ለምርጫ ቅስቀሳ ገንዘብ ወጪ አድርገዋል ተብለው የአንድ ዓመት እስር ተፈረደባቸው። ሳርኮዚ እአአ 2012 ላይ ፈረንሳይን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት ዳግም ቢወዳደሩም በምርጫው ሳይሳካላቸው መቅረቱ ይታወሳል። የ66 ዓመቱ የቀድሞው ፕሬዝደንት ለምርጫ ቅሰቀሳ ከሚፈቀደው በላይ ወጪ አድርገዋል ሲል ፓሪስ የሚገኝ ፍርድ ቤት ዛሬ ብይን ሰጥቷል። ሳርኮዚ በሕግ ከሚፈቀደው በላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዩሮ ወጪ አድርገዋል ብሏል ፍርድ ቤቱ። ሳርኮዚ የአንድ ዓመት እስር ቢፈረድባቸውም ፍርዳቸውን በእስር ቤት ሆነ መጨረስ አይጠበቅባቸውም። የሳርኮዚን እንቅስቃሴ መከታተያ በቀድሞው ፕሬዝደንት እግር ላይ ከታሰረ በኋላ ሳርኮዚ የአንድ ዓመት እስራቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ማሳለፍ ይችላሉ ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል። የቀድሞ ፕሬዝደንት ምንም ጥፋት የለብኝም የሚሉ ሲሆን የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ይላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሳርኮዚ በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ሲባሉ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ሳርኮዚ ኅዳር ወር ላይ በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው ነበር። ሳርኮዚ የአንድ ዓመት እስር በተፈረደባቸው ክስ ላይ ፓርቲያቸው ለምርጫ ቅስቀሳ ከሚፈቀው 22.5 ሚሊዮን ዩሮ እጥፍ ለምርጫ ቅስቀሳ ወጪ አድርጓል ተብሏል። ፓርቲያቸው ለምርጫ ቅስቀሳ ያወጣውን ወጪ ለመደበቅ የሕዝብ ግንኙነት ተቋም ቀጥሮ ለምርጫ ቅስቀሳ የወጣውን ገንዘብ ለድርጅቱ ክፍያ የተፈጸም አስመስሏል። የፓሪሱ ፍርድ ቤት ዛሬ በሰጠው ብይን ላይ ምንም እንኳ የቀድሞ ፕሬዝደንት በፓርቲው የተፈጸመውን ማጭበርበር በዝርዝር ሊያውቁ ባይችሉም፤ ለምርጫ ቅስቀሳ በሕግ ከሚፈቀደው በላይ ወጪ ስለመሆኑ እያወቁ ምንም አይነት እርምጃ አልወሰዱም ብሏል። ሳርኮዚ በቀድሞ ፕሬዝደንት ፍራንሷ ኦላንዴ እስከተተኩበት ጊዜ ድረስ ከእአአ 2007 እስከ 2012 ድረስ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት በመሆን ለአንድ የስልጣን ዘመን አገልግለዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-58751353 +sports ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሴቶች እና ወንዶች የተለያየ ሰዓትን መምረጥ እንዳለባቸው ጥናት አመለከተ "አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ለጤና ጠቃሚ እንደሆነ አጠያያቂ አይደለም። ነገር ግን ከምንሰራቸው አካላዊ እንቅስቃሴዎች ተገቢውን ጥቅም እንድናገኝ የምንሰራበትን ሰዓት ከግምት ውስጥ ማስገባት ወሳኝ ነው። አንድ በቅርቡ የተካሄደ ጥናት፤ ወንዶችና ሴቶች አካላዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት ሰዓት የበለጠ ውጤታማ ሊያደርጋቸው እንደሚችል አመላክቷል። እንደ ጥናቱ ከሆነ ሴቶች ጠዋት ላይ አካላዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በሰውነታቸው ውስጥ የሚገኘውን የስብ ክምችት በፍጥነት ማጥፋት የሚችሉ ሲሆን፣ ወንዶችን ደግሞ የበለጠ ውጤታማ የሚያደርገው ምሽት ላይ ስፖርት መስራታቸው ነው። በሁለቱም ጾታ ውስጥ የሆርሞን መለያየት፣ የእንቅልፍ ሰዓት እና ተፈጥሯዊ አወቃቀር በጠቅላላው ልዩነት የሚያመጣ መሆኑ በጥናቱ ላይ ተገልጿል። ዕድሜያቸው ከ25 እስከ 55 የሆኑና በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ 30 ወንዶችና 26 ሴቶችን ያሳተፈው ይህ ጥናት፤ ለ12 ሳምንታት ነው የተካሄደው። በእነዚህ ሳምንታት የጥናቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ አይነት የማሳሳብ፣ የፍጥነት፣ የጥንካሬ እንዲሁም የዝላይ አቅማቸውን ከፍ የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ ነበር። የሴቶቹ ቡድን ከጠዋቱ 2 ሰዓት ተኩል ጀምሮ እነዚህን አካላዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሰሩ የተደረገ ሲሆን፤ የወንዶቹ ቡድን ደግሞ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ሁለት ሰዓት እንቅስቃሴዎቹን እንዲሰሩ ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የጥናቱ ተሳታፊዎች በልዩ ሁኔታ የተዘጋጁ ምግቦችን እንዲመገቡ ተደርጓል። ተሳታፊዎቹ በዚህ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ውስጥ ለ12 ሳምንታት የሰነበቱ ሲሆን ተመራማሪዎቹ ደግሞ የደም ዝውውራቸውን፣ በሰውነታቸው ውስጥ ያለውን የስብ መጠን፣ አካላዊ ብቃት እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን ሲመዘግቡና ሲያወዳድሩ ቆይተዋል። መጀመሪያ ላይ ተመራማሪዎቹ ይፋ ያደረጉት ውጤት ሁሉም የጥናቱ ተሳታፊዎች በተለያየ ሰዓት አካላዊ እንቅስቃሴያቸውን ቢያደርጉም ሁሉም በጣም ጥሩ የሚባል አካላዊ ለውጥ አሳይተዋል። ""አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ሰዓት መምረጥ ላያስፈልግ ይችላል። ነገር ግን ከሴቶችና ወንዶች አንጻር ስናየው ግን አካላዊ እንቅስቃሴ የምንሰራበት ሰዓት በምናገኘው ጥቅም ፍጥነትና ውጤታማነት ላይ ልዩነት አለው’’ ይላሉ የጥናቱ መሪ የሆኑት ዶ/ር ፖል አርሴሮ። በጥናቱ መሠረት በሰውነታቸው ውስጥ ያለውን የስብ መጠን መቀነስና የደም ግፊታቸውን ለማውረድ የሚፈልጉ ሴቶች ጠዋት ላይ አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ የበለጠ ጥቅም እንደሚያገኙ ዶ/ር ፖል ያስረዳሉ። በሌላ በኩል ደግሞ አካላዊ ጡንቻቸውን ማሳደግና ጥንካሬያቸውን መጨመር የሚፈልጉ ሴቶች ወደ ማታ አካባቢ አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ እንደሚመረጥ ጥናቱ ጠቁሟል። ወ��ዶች ደግሞ በጥናቱ መሰረት ጠዋትም ሆነ ማታ አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ አጠቃላይ አካላዊ ብቃታቸውን መጨመር የሚችሉ ሲሆን፤ የልባቸውን ጤንነት መጠበቅና ማሻሻል እንዲሁም የአእምሮ ጤና ማሻሻል የሚፈልጉ ከሆነ ግን ማታ አካባቢ አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ ጥሩ ነው። ወንዶች እና ሴቶች በተለያዩ ሰዓታት አካላዊ እንቅስቃሴን ማድረጋቸው ለምን ልዩነት እንደሚያመጣ ተመራማሪዎቹ እስካሁን አልደረሱበትም። ነገር ግን ተጨማሪ ጥናቶች እንደሚያስፈልጉ ጠቁመዋል።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cy6ne5zdx93o +politics ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በዕጩነት የተለዩ የ42 ግለሰቦች ዝርዝር ይፋ ሆነ ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ከሕዝብ ከተጠቆሙ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ግለሰቦች መካከል በዕጩነት የተለዩ የ42ቱን የስም ዝርዝር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፋ አደረገ። በቀጣይ ሂደትም ከ42ቱ መካከል ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኮሚሽነርነት የሚሰየሙትን ለመለየት በቀረቡት ዕጩዎች ላይ ሕዝብ አስተያየት እንዲሰጥ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል ሂደትን የሚመራና የሚያስተባብር አካል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካይነት ለማቋቋም ጥቆማ መካሄዱ ይታወሳል። ለሕዝብ በቀረበ ጥሪ መሠረት 632 ዕጩዎች በተለያዩ ወገኖች ተጠቁመው ከእነዚህ መካከል ኮሚሽኑን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ በተቀመጡት መስፈርቶች አማካኝነት 42ቱን መለየታቸውን ከሳምንት በፊት የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አስታውቀው ነበር። ከተጠቆሙት 632 ዕጩዎች ውስጥ የተለዩት 42ቱ ዕጩ ተጠቋሚዎች የትምህርት ሁኔታና የሥራ ልምድ ላይ ከአማካሪዎች ጋር ምክክር ከተደረገበት በኋላ ለሕዝብ ቀርበው አስተያየት እንደሚሰበሰብ ተገልጾ ነበር። በዚህም መሠረት አብዛኞቹ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በማስተማርና በምርምር ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ምሁራን የተካተቱበት የ42 ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ የተደረገ ሲሆን ሕዝቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸውም ተጠይቋል። በቀረበው ጥሪ መሠረት ከተለያዩ ወገኖች ከተጠቆሙት ዕጩዎች መካከል የተለዩት 42ቱ ዕጩ ተጠቋሚዎች የሚከተሉት ናቸው፡ 1. ሎሬት ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈራ 2. ፕሮፌሰር አፈወርቅ በቀለ ስመኝ 3. ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ 4. ፕሮፌሰር ባዬ ይማም 5. ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ 6. ፕሮፌሰር ያእቆብ አርሳኖ 7. ፕሮፌሰር ካሳሁን ብርሃኑ ዓለሙ 8. ፕሮፌሰር ህዝቅያስ አሰፋ 9. ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ ጀቤሳ 10. ፕሮፌሰር ዶክተር ዳንኤል ቅጣው 11. ፕሮፌሰር ዘካሪያስ ቀነአ ተስገራ 12. ፕሮፌሰር ክፍሌ ወ/ሚካኤል ሐጀቶ 13. ዶክተር በድሉ ዋቅጅታ 14. ዶክተር ሰሚር የሱፍ 15. ዶክተር አብዲሳ ዘርዓይ በማኖ 16. ዶክተር ሀብታሙ ወንድሙ 17. ዶክተር ታከለ ሰቦቃ 18. ዶክተር ዮናስ አዳዬ 19. ዶክተር ወዳጆ ወ/ጊዮርጊስ 20. ዶክተር ሙሉጌታ አረጋዊ 21. ዶክተር ነጋልኝ ብርሃኑ ባዬ 22. ዶክተር አበራ ዴሬሳ 23. ዶክተር አይሮሪት መ/ድያሲን 24. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌጡ መንገሻ 25. ዶክተር ዳዊት ዮሐንስ 26. ዶክተር ተካለ ሰቦቃ 27. ኢንጂኒየር ጌታሁን ሁሴን ሽኩር 28. አምባሳደር ታደለች ኃይለሚካኤል 29. አምባሳደር ምዑዝ ገብረ ሕይወት ወልደ ሥላሴ 30. አምባሳደር ማህሙድ ድሪር 31. አቶ ዘገየ አስፋው አብዲ 32. ወ/ሮ ዘነብወርቅ ታደሰ ማርቆስ 33. አቶ ኢብራሂም ሙሉ ሸዋ እሸቴ 34. አቶ መላኩ ወልደማሪያም 35. አቶ አንዳርጋቸው አሰግድ 36. አቶ ገመቹ ዱቢሶ ጉደና 37. አቶ ሳሙኤል ጣሰው ተፈራ 38. አቶ አህመድ ሁሴን መሐመድ 39. ወ/ሮ ሂሮት ገ/ሥላሴ ኦዳ 40. አቶ ንጉሡ አክሊሉ 41. አቶ ተስፋዬ ሐቢሶ 42. አቶ አባተ ኪሾ የሕ���ብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የተጠቆሙትን 42ቱን ግለሰቦች ዝርዝር ከአጭር የትምህርትና የሥራ መግለጫ ጋር በድረ ገጹ ላይ ይፋ ያደረገ ሲሆን ሕዝቡም አስተያየት እንዲሰጥባቸው ጥያቄ አቅርቧል። ከዚህ ሂደት በኋላም በተጠቋሚ ዕጩዎቹ ላይ ከሕዝብ የሚቀርበው አስተያየት ተገምግሞ የመጨረሻዎቹ 11 ዕጩ ኮሚሽነሮች ተለይተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሹመት እንደሚቀርቡ ተገልጿል። https://www.bbc.com/amharic/news-60260831 +health የኮሮናቫይረስ ክትባት መገኘት ተስፋ የዓለም ገበያን እያነቃቃው ነው "ኮቪድ-19ን ለመከላከል ይረዳሉ የተባሉ ክትባቶች ወደመጨረሻ ደረጃቸው ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ የዓለም ገበያ እንደ አዲስ እየተነቃቃ መሆኑ ተዘግቧል። ፋይዘር የተባለው መድሀኒት አምራች ኩባንያ ኮሮናቫይረስን የመከላከል አቅሙ 90 በመቶ ነው ያለውን ክትባት ይፋ ካደረገ በኋላ የድርጅቱ ድርሻ በዓለም ገበያ በ9 መቶ ከፍ ማለቱ ተስተውሏል። በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊው ጆ ባይደን መሆናቸው ከተነገረ ወዲህ መነቃቃት እያሳየ የነበረው ዓለም ገበያ አሁን ደግሞ ክትባቱን ተከትሎ ሌላ እሽቅድድምን ፈጥሯል። የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአክስዮን ገበያ ከአውሮፓውያኑ የ2008 የዓለም የገንዘብ ቀውስ ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ መቀነሱ የሚታወስ ነው። በሞዛምቢክ ከ50 በላይ ሰዎች በጽንፈኞች 'አንገታቸው ተቀላ' አርሜኒያ ""እጅግ በጣም የሚያም"" ያለችውን የሰላም ስምምነት ከአዘርባጃን ጋር ለመፈረም ተገደደች 90 በመቶ ውጤታማ ነው የተባለ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ተሰራ በአሜሪካ የሚገኙ ድርጅቶች የአክሲዮን ዋጋቸው ከ1.1 በመቶ እስከ 5.6 በመቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍ ያለ ሲሆን በእሲያና አውሮፓ የሚገኙ ድርጅቶችም ድርሻቸው በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ አሳይቷል። ክትባቱን ይፋ ያደረጉት ፋይዘርና ባዮኤንቴክ ክትባቱን በሶስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል። በቁጥር የበዙ ክትባቶች የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን ይህ ክትባት ተስፋ ከተጣለባቸው ውስጥ ቀዳሚው ነው። ከዚህ ቀደም የተደረገው ሙከራ ክትባቱ ሰውነታችን ከበሽታው ጋር እንዲለማመድና አንቲቦዲዎችን እንዲያዳብር መርዳቱ የተስተዋለ ሲሆን ሌላው ደግሞ ቲ-ሴል በመባል የሚታወቀው የመከላከል አቅምን የኮሮናቫይረስን መዋጋት እንዲችል አድርጎታል ተብሏል። በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኘው 'ኤፍቲኤስኢ 100' የወረርሽኙ ዜና ከተሰማበት መጋቢት ወር ጀምሮ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በዓለም አቀፍ ገበያ ድርሻው ላይ የ82 ቢሊየን ፓውንድ ጭማሪ አግኝቷል። የተለያዩ መድሃኒት አምራች ኩባንያዎች እየሞከሯቸው ባሉት የክትባት ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያገኙ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ መግለጻቸውን ተከትሎ የዓለም አቀፍ ገበያው ከዚህም በበለጠ ሊያድግ እንደሚችል ተጠቁሟል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54884202 +politics በማህተማ ጋንዲ ገዳይ ዙሪያ ያለው ምስጢር "ጥር 30/1948 ምሽት ማህተማ ጋንዲ ወይም በሙሉ ስማቸው ሞሃንዳስ ካራምቻንድ ጋንዲ በሕንድ መዲና ደልሂ ከፀሎት ሲወጡ በሽጉጥ ተገደሉ። ከቅርብ ርቀት ሽጉጥ ተኩሶ የገደላቸውም ናታሁራም ቪናያክ ጎድሴ ይባላል። የ38 ዓመቱ ገዳይ ሂንዱ ማሃሳብሃ ተብሎ የሚጠራው የአክራሪው ቀኝ ክንፍ ፓርቲ አባል ነው። ጋንዲ ሙስሊሞችን ይደግፋሉ እንዲሁም ለፓኪስታን ገር የሆነ ልብ በማሳየት ሂንዲዎችን ክደዋልም ሲል ከሷቸዋል። ከብሪታንያ ቅኝ ግዛት ነፃ መውጣታቸውን ተከትሎ በአንድ ግዛት ስር የነበሩት ሕንድና ፓኪስታን በሚል ለሁለት በመከፈል በ1947 ለተፈጠረው ደም መፋሰስም ጋንዲ��� ተጠያቂ አድርገዋቸዋል። ማህተማ ጋንዲ ከተገደሉ ከዓመት በኋላ ጎድሴ የሞት ቅጣት ተፈረደበት። ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔውን ካረጋገጠ በኋላ በኅዳር 1949 ዓ.ም ግለሰቡ በስቅላት ተቀጣ። በግድያው ተባባሪ የነበረው ናራያን አፕቴም በሞት ሲቀጣ፣ ሌሎች እጃቸው አለበት የተባሉ ስድስት ግለሰቦች ደግሞ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል። የጎድሴን የኋላ ታሪክ ስናይ የሂንዱ ማሃሳብሃን ከመቀላቀሉ በፊት የሕንድ ገዢ ባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲ (ቢጄፒ) ርዕዮተ ዓለም መስረት የሆነው የራሽትሪያ ስዋያምሴቫክ ሳንግ (ብሔራዊ የበጎ ፈቃደኞች ድርጅት) አባል ነበር። አገሪቱን በአሁኑ ወቅት እየመሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲም ቢሆኑ በሕንድ ውስጥ በሂንዱ ብሄርተኝነቱ ፈር ቀዳጅ የሆነው የ95 ዓመቱ ባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲን (ቢጄፒ) የተቀላቀሉት ከረጅም ዓመታት በፊት ነው። የራሽትሪያ ስዋያምሴቫክ ሳንግ (አርኤስኤስ) በሕንድ ባለው አገዛዝ እንዲሁም በውጭው ዓለም ከፍተኛ ሚናን በመጫወት የሚጠቀስ ነው። ለአስርት ዓመታትም አርኤስኤስ ""የሕንዳውያን አባት"" ተብለው የሚጠሩትንና በድንቅነታቸው ታሪክ የሚዘክራቸውን ማህተማ ጋንዲ ገዳይን ጎድሴን ሲያወግዝ ይሰማ ነበር። ሆኖም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሂንዱ ቀኝ አክራሪ ቡድን ጎድሴን በጀግንነት በማወደስና የጋንዲን መገደል በይፋ አክብረዋል። በባለፈው ዓመትም የገዢው ፓርቲ ባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲ የፓርላማ አባል የሆኑ ግለሰብ ጎድሴን ""አርበኛ"" ሲሉ አሞካሽተውታል። እነዚህ ክስተተች በርካታ ሕንዳውያንን ቢያበሳጩም አርኤስኤስ ጎድሴ ጋንዲን ከመግደሉ በፊት ከድርጅት አባልነቱ ተሰናብቷል በሚል አቋሙ እንደጸና ነው። ነገር ግን በቅርቡ የወጣ መጽሐፍ የአርኤስኤስን አለኝ የሚለውን እውነት የሚያፈርስ ነው። ጎድሴ ዓይነ አፋር፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያቋረጠና ማሃሳብሃን ከመቀላቀሉ በፊትም በልብስ ስፌትና ፍራፍሬ በመሸጥ ይተዳደር ነበር። ማሃሳብሃን ከተቀላቀለ በኋላ የጋዜጣ አርትዖት ሥራ ተሰማራ። በፍርድ ሂደቱ ወቅት 150 አንቀፆች ያሉትን መግለጫ ይዞ የቀረበ ሲሆን ለአምስት ሰዓት ያህልም አንብቧል። ጋንዲን ለመግደል ምንም አይነት የተቀነባበረ ሴራ የለም በማለትም ተባባሪዎቹን ከቅጣት ለማዳንም ሞክሯል። የሂንዱትቫ ወይም የሕንዳዊነት ማንነትን እሳቤ በወለደው በመሪያቸው ቪናያክ ዳሞዳር ሳቫርካር መሪነት ተቀነባብሮ የተፈጸመ ግድያ ነው የሚለውን ክስም ውድቅ አደረገው። መሪው ሳቫርካር ከሁሉም ክሶች ነፃ ቢወጣም ተቺዎች ጋንዲን የሚጠላው የአክራሪው ቀኝ ክንፍ ከግድያው ጀርባ እጁ አለበት ብለው ያምናሉ። ጎድሴ ጋንዲን ከመግደሉ ከረጅም ጊዜ በፊት ከአርኤስኤስ ጋር መቆራረጡን ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። የጋንዲ ገዳይ መጽሐፍ ደራሲ የሆኑት ድሪንደርድራ ጃሃ ጎሴ በበኩላቸው ከፖስታ ሠራተኛ አባትና ከቤት እመቤት እናት የተወለደው ጎድሴ በአርኤስኤስ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ሠራተኛ እንደነበርም አስፍረዋል። በተጨማሪም ከአርኤስኤስ ስለመባረሩ ምንም አይነት መረጃ የለም ይላሉ። ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት ቃሉን በሚሰጥበት ወቅትም የሂንዱ ማሃሳብሃ አባል ከሆነ በኋላ ከአርኤስኤስ ስለመውጣቱ ያለው ነገር የለም። ሆኖም ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት አርኤስኤስን ከተሰናበተ በኋላ የሂንዱ ማሃሳብሃ አባል እንደሆነ ቢናገርም መቼ ከድርጅቱ እንደወጣም ሊያስረዳ አልቻለም። ከዚህም ጋር ተያይዞ የጎድሴ ህይወት አከራካሪ ሆኖ መቀጠሉንም ጃሃ ይናገራሉ። የአርኤስኤስ ደጋፊ ጸሐፊዎች ጎድሴ ጋንዲን ከመግደሉ ከአስር ዓመት በፊት ድርጅቱን እንደተሰናበተና ከዚያም ሂንዱ ማሃሳብሃን ተቀላቅሏል የሚል ���ጀንዳን ለመግፋት ተጠቅመውበታል ይላሉ ጃሃ። አሜሪካዊው ተመራማሪ ጄኤ ኩራን ጁኒየር ጎድሴ አርኤስኤስን በ1930 እንደተቀላቀለ እና ከአራት ዓመት በኋላ መሰናበቱን ያስረዳል፣ ነገር ግን ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም። ጎድሴ የፍርድ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት ለፖሊስ በሰጠው ለሁለቱም ድርጅቶች ይሰራ እንደነበር አምኗል ሲሉ ጃሃ ጽፈዋል። የጎድሴ የቤተሰብ አባላት የዚህ ክርክር አካል ሆነዋል። በ2005 የሞተው የናቱራም ጎድሴ ወንድም ጎፓል ጎድሴ በበኩሉ አርኤስኤስን እንዳልተሰናበተ ተናግሯል። የጎድሴ ታላቅ ወንድም ልጅ በ2015 ከጋዜጠኞች ጋር ባደረገው ቆይታ ጎድሴ አርኤስኤስን በ1932 እንደተቀላቀለና ከድርጅቱም እንዳልተባረረ ራሱም እንዳልወጣ ተናግሯል። የተለያዩ መዛግብትን ያገላበጡት ጃሃ ሁለቱ የሂንዱ ድርጅቶች ግንኙነት እንደነበራቸው ያስረዳሉ። የሂንዱ ማሃሳብሃ እና አርኤስኤስ ተመሳሳይ ግብና ለየት ያለ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን ሲንቀሳቀሱ የነበሩት በተመሳሳይ ርዕዮተ ዓለም ነው ሲሉ ጽፈዋል። ሁለቱም ድርጅቶች ጋንዲ እስከሚገደሉበት ጊዜ ድረስ የቅርብ ጊዜ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን የሁለቱም ድርጅቶች አባል የሆኑ ግለሰቦች ነበሯቸው። ጋንዲ ከተገደሉ በኋላ አርኤስኤስ ከአንድ ዓመት በላይ ታግዷል። አርኤስኤስ ጎድሴ በፍርድ ቤት የተናገረውን ድርጅቱን በ1930ዎቹ አጋማሽ ለቅቆ መውጣቱን በመጥቀስ እንዲሁም የፍርድ ቤት ውሳኔውን ከአርኤስኤስ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ማሳያ ነው ሲልም ይከራከራል። የአርኤስኤስ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ራም ማድሃቭ ጎድሴ በግድያው ወቅት ""የአርኤስኤስ አባል ነበር ማለት ፖለቲካዊ ጥቅም ለማግኘት የተፈጠረ ውሸት ነው"" ብለዋል። በአርኤስኤስ በጣም ተደማጭነት ካላቸው መሪዎች አንዱ የሆኑት ኤም ኤስ ጎልዋልከር የጋንዲን ግድያ ""ወደር የለሽ አሳዛኝ ሁኔታ"" ሲሉ በመግለጽ በጣም አስደንጋጭ የሚያደርገውም ግድያውን ያቀነባበረው የአገሪቱ ዜጋና ሂንዱ መሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በቅርብ ጊዜም እንደ ኤምጂ ቫይድያ ያሉ የአርኤስኤስ አመራሮች ""የሕንድን ታላቅ ሰው በመግደል የሂንዱትቫን ፅንሰ ሃሳብ ያንቋሸሸ ነፍሰ ገዳይ"" ሲሉ ጎድሴን ጠርተውታል። እንደ ቪክራም ሳምፓት ያሉ ደራሲዎች በበኩላቸው አርኤስኤስ እና የሂንዱ ማሃሳብሃ የሚሞቅና የሚቀዘቅዝ ግንኙነት እንደነበራቸው ያምናሉ። የሳቫርካርን የህይወት ታሪክ በሁለት ጥራዝ የፃፉት ቪክራም ሳምፓት ""የሂንዱዎችን ጥቅም ለማስጠበቅ"" በሚል የሂንዱ ማሃሳብሃ የበጎ ፈቃደኞች ቡድንን ከ""አብዮታዊ ምስጢራዊ ማኅበር"" ጋር በማዋቀር ያደረገው ውሳኔ አሳዝኖታል፣ ከአርኤስኤስ ጋር የነበረውንም ግንኙነት አሻክሮታል። ሳምፖት እንዳሉት ""በጀግንነት አምልኮ የተጠመደ እና የተጋነነ አድናቆት ""እሳቤን "" ከሚከተለው ከማሃሳብሃ መሪ ሳቫርካር በመለየትም አርኤስኤስ ግለሰቦችን ጣኦት ከማድረግ ተቆጥቧል። አርኤስኤስ 'ኤ ቪው ቱ ዘ ኢንሳይድን' የጻፉት ዋልተር ኬ አንደርሰን እና ሽሪድሃር ዲ ዳም በመጽሐፋቸው የቀድሞው አባል ናቱራም ጎድሴ በጋንዲ ግድያ ላይ መሳተፉ ድርጅቱን በከፍተኛ ሁኔታ አጠልሽቶታል፤ ጎድቶታልም ብለዋል። ድርጅቱ የፋሽስት፣ አምባገነን፣ አጭበርባሪዎችን ከመደገፍ ጋር መያያዙ ስሙ ጠፍቷል። ነገር ግን ጎድሴ የአርኤስኤስ አካል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥርጣሬዎች መቼም ደብዝዘው አያውቁም። ጎድሴ በኅዳር 15/1949 ወደ መሰቀያው ስፍራ ከመወሰዱ በፊት የአርኤስኤስ ፀሎት የመጀመሪያዎቹን አራት ዓረፍተ ነገሮች ሲያነበንብ ነበር። ""ይህም የድርጅቱ ንቁ አባል እንደነበረ በድጋሚ ያሳያል"" ሲሉ ጃሃ ያስረዳል። ""አርኤስኤስን ከጋ���ዲ ገዳይ ማግለል የታሪክ ፈጠራ ነው"" ይላሉ ጃሃ። ማስታወሻ፦ በፅሁፉ የተጠቀሱት የቀን አቆጣጠሮች በሙሉ በአውሮፓውያኑ ነው" https://www.bbc.com/amharic/news-60172567 +health ተጨማሪ ዘጠኝ የኮቪድ-19 ምልክቶች ይፋ ሆኑ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች ላይ ተጨማሪ ዘጠኝ ምልክቶች ተጨመሩ። እነዚህ ምልክቶች ከዚህ በፊት የነበሩትን የሚያሰፉና ተጨማሪ ነገሮችን ከግምት ውስጥ የሚያስገቡ ናቸው። የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ ባዘጋጀው አዲስ መመሪያ ውስጥ የጉሮሮ ህመም፣ የጡንቻ ህመም እና 'ተቅማጥ' ከተካተቱት አዳዲስ የኮሮረናቫይረስ ምልክቶች መካከል ናቸው። ይህ መመሪያ የወጣው ወረርሽኙ ከተከሰተ ሁለት ዓመታት ካለፈው በኋላ ሲሆን እንግሊዝ ውስጥ ደግሞ ይደረግ የነበረው የነጻ ምርመራ ከተቋረጠ ከቀናት በኋላ ነው። ነገር ግን የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልእክት አዳዲሶቹ ምልክቶች ከጉንፋን ብዙም ያልተለዩ መሆናቸውን አሳስቧል። ከዚህ በፊት የሚታወቁት የኮቪድ-19 ምልክቶች ትኩሳት፣ የማያቆም ሳል፣ የሽታ እና የመቅመስ ስሜቶቻችን መጥፋት እንዲሁም ድካም የሚጠቀሱ ናቸው። ወረርሽኙ ባጋጠመበት የመጀመሪያዎቹ ወራት ወቅት የስርጭቱን አካሄድ መረዳትና ምልክቶቹን መለየት ከባድ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን ዓለም ስለቫይረሱ ማወቅ ከሚገባው አብዛኛውን ነገር አውቋል። የዓለም ጤና ድርጅትም ቢሆን ከረጅም ጊዜ በፊት ምልክቶች ብሎ ያስቀመጣቸው ነገሮች በርካታ ናቸው። ነገር ግን ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ትክክለኛ ምልክቶቹ የትኞቹ ናቸው እንዲሁም ምን አይነት ምልክቶችን የሚያሳይ ሰው ነው ምርመራ ማድረግ ያለበት የሚሉት ጥያቄዎች መከራከሪያ ሆነው ቆይተዋል። ለምሳሌ ራስ ምታት የኮሮናቫይረስ ምልክት ተደርጎ ሊቆጠር የሚችል ቢሆንም ራሱን ያመመው ሰው በሙሉ ግን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ አይችልም። ምክንያቱም ራስ ምታት ከኮሮናቫይረስ ውጪ በበርካታ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። ትኩሳት፣ ሳል፣ ማሽተት ማቆም አልያም ጣእም ማጣት በርካቶችን የማያከራክሩ ምልክቶች ሲሆኑ አሁን ላይ ደግሞ ዘጠኝ ተጨማሪ ምልክቶች እንዲጨመሩ ተደርጓል። እነዚህም ትንፋሽ ማጠር፣ ድካም፣ የሰውነት መላሸቅ፣ ራስ ምታት፣ የጉሮሮ ሕመም፣ ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ [ንፍጥ]፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ተቅማጥ እና አጠቃላይ የጤንነት ስሜት ማጣት ናቸው። ዩኬ ውስጥ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4.9 ሚሊየን የደረሰ ሲሆን መንግስት በነጻ ሲያከናውነው የነበረው ምርመራም ባሳለፍነው ሳምንት ተጠናቋል። የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ እንደሚለው ሰዎች አሁንም ቢሆን በተቻላቸው መጠን ከቤታቸው ላለመውጣት መሞከርና ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላቸውንም ንክኪ መቀነስ አለባቸው። በተለይ ደግሞ እነዚህን ምልክቶች የሚያሳይ ሰው ምርመራ ማድረግና እራሱን ከሰዎች መለየት እንዳለበት ኤጀንሲው አሳስቧል። https://www.bbc.com/amharic/news-60992822 +sports ስለ አቶ ዱቤ ጅሎ ሽልማት ምን እናውቃለን? "በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቴክኒካል ዳይሬክተርነት እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ዱቤ ጅሎ ለኢትዮጵያዊ የመጀመሪያ ነው የተባለውን ሽልማት ሊያገኙ ነው። የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (አይኤኤፍ) 'ቬተራን ፒን' የሚል ስያሜ ያለው ይህ ሽልማት ዜና ከአይኤኤፍ ፕሬዝዳንት ከጥቂት ቀናት በፊት እንደደረሳቸው አቶ ዱቤ ለቢቢሲ ገልፀዋል። •""ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል"" ኃይሌ ገብረሥላሴ •በታላቁ ሩጫ ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ላይ የአበረታች መድኃኒት ምርመራ ሊካሄድ ነው ይህንን ሽልማት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያዊ አግኝቶ��� እንደማያውቅም አቶ ዱቤና ሌላ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተጠባባቂ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ብስራት ገልፀዋል። ሽልማቱ ከዚህ ቀደም አትሌት የነበሩና ለስፖርቱ ዕድገትና ልማት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሚሰጥ ሲሆን ከዚህም በፊት ኬንያዊው አትሌት ፖል ቴርጋት ተሸልሟል። የአፍሪካው አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን መርጦ ወደ ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመላክ የሽልማቱ ሂደት ይከናወናል። ሽልማቱ መስከረም ወር ላይ ዶሃ በሚዘጋጀው የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ሻምፒዮን በመስከረም ወር የሚሰጥ ይሆናል። •ታይላንዳዊው ቦክሰኛ በውድድር ሳቢያ ሕይወቱ አለፈ ሽልማቱን ያገኙበት ምክንያት ሽልማቱ ዕውቅና መስጠት ነው የሚሉት አቶ ዱቤ ""ከአስር አመታት በላይ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ እድገት አስተዋፅኦ ላደረግኩት የሚበረከት ነው። ""በወቅቱም ውጤታማ አፈፃፀሞች ላሳየሁባቸው እውቅና መስጠት ነው"" ብለዋል። በሽልማቱ መደሰታቸውን ገልፀው የበለጠ ለስራ እንደሚያነሳሳቸው ይናገራሉ። ""ከዚህም ቀደም ቬተራን (የአንጋፋነት) ፒን የሚባል ሽልማት የተሸለመ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ"" የሚናገሩት አቶ ዱቤ ለአመታት የአትሌቶች ተወካይና ቴክኒካል ዳይሬክተር ሆነው ማገልገላቸው ለዚህ እንዳበቃቸው ገልፀዋል። ከአይኤኤፍ ፕሬዝዳንት ጆን ሪድጌዎን የተላከላቸው ደብዳቤም 'ለረዥም ጊዜ ለሽልማት የሚገባ ስራ በአትሌቲክሱ ስለሰሩ ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል' የሚል ነው። አቶ ስለሺ ብስራት በበኩላቸው ""የተሸለሙት ፈጣን የሆነ ኮሚዩኒኬሽን ስላላቸው ነው"" ብለዋል። ""በጥሩ ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያ የተመረጠች ሲሆን"" ይህንን ደግሞ የሚመሩት አቶ ዱቤ ጅሎ መሆናቸውን አቶ ስለሺ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሁለቱም ኃላፊዎች ሽልማቱ ትልቅ እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ዱቤ በአሁኑ ወቅት በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ የአትሌቲክስ ጥናት ውድድርና የአትሌቲክስ ልማት ይመራሉ። አቶ ዱቤ ጅሎ ማናቸው?" https://www.bbc.com/amharic/news-49102031 +health በሳይንስ የበለፀገ የአሳማ ልብ ተገጥሞለት የነበረው ግለሰብ ሕይወቱ አለፈ "በሳይንሳዊ መንገድ የበለፀገ የአሳማ ልብ ቀዶ ጥገና የተደረገለት የዓለማች የመጀመሪያው ግለሰብ የተባለው ሰው ሕይወቱ አለፈ። ዴቪድ ቤኔት የልብ በሽተኛ ነበር። የአሳማ ልብ ከተገጠመለት በኋላ ለሁለት ወራት ቆይቶ ነው የሞተው። ግለሰቡ ጤናው መቃወስ የጀመረው ከጥቂት ቀናት በፊት እንደነበር ዶክተሩ ተናግረዋል። ዴቪድ በዶክተሮች ጥብቅ ክትትል ሲደርግለት ቆይቶ በፈረንጆቹ ማርች 8 ይህችን ዓለም ተሰናብቷል። ሰውዬው የመጀመሪያው የአሳማ ልብ በቀዶ ጥገና እንዲገጠምለት የፈቀደው ሂደቱ ለሞት ሊዳርገው እንደሚችል በመረዳት ነው። በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የጤና ማዕከል ያሉ ዶክተሮች ቀዶ ጥገናውን እንዲያደርጉ ከአሜሪካ መንግሥት ሰዎች ፈቃድ አግኝተዋል። ዴቪድ የሰው ልብ በቀዶ ጥገና ሊገጥምለት ስለማይችል ነው የአሳማ ልብ የሞከረው። ከቀዶ ጥገናው በፊት ለስድስት ሳምንታት በማሽን እርዳታ ነበር ሲተነፍስ የከረመው። ታኅሣሥ 29 ቀን ቀዶ ጥገና ተደርጎለት ዓለም አጀብ ካለ በኋላ የቀሩትን ቀናት ከቤተሰቡና ወዳጆቹ ጋር አሳልፏል። ነገር ግን እየቆየ ጤናው ይቃወስ መጣ። ዶክተሮቹም ተደናገጡ። ""በጣም ጀግና እና ልዩ የሆነ ሰው ነው። እስከ መጨረሻው ነው የተፋለመው"" ይላል የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ባርትሊ ግሪፊዝ። የሰውዬው ልጅ የሆነው ዴቪድ ጁኒዬር የአባቱ ቀዶ ጥገና ለሌሎች የተስፋ ጭላንጭል እንዲሆን ይመኝ እንደነበር ኤፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ዶክተር ግሪፊዝ ከዚህ ቀደም ቀዶ ጥገናው መሳካቱ የሚለገስ የሰውነት አካል አጥተው ለሚሞቱ ሰዎች ተስፋ ሰጭ ነው ብለው ነበር። ዩናይትድ ስ��ትስ ውጥ የሚለገስ የሰውነት አካል በማጣት በየቀኑ 17 ሰዎች ይሞታል። 100 ሺህ ገደማ ሰዎች ደግሞ መጠባበቂያ መዝገብ ላይ ስማቸው ሰፍሯል። የአሳማ ልብን ለሰው ልጅ በቀዶ ጥገና መግጠም የሚለው ሐሳብ ለረዥም ጊዜ ጥናት ሲደርግበትና ሲብላላ የቆየ ጉዳይ ነው። ባለፈው ዓመት ጥቅምት ኒው ዮርክ የሚገኙ ዶክተሮች የአሳማ ኩላሊት በተሳካ ሁኔታ ለሰው እንደገጠሙ ተናግረው ነበር። ምንም እንኳ ያኔ ይህ ቀዶ ጥገና አዲስ ነገር ቢሆንም ቀዶ ጥገና የተደረገለት ግለሰብ አእምሮው መሥራት ያቆመና የመዳን ተስፋው የመነመነ ነበር። ከዚያ በኋላ የተሰማው የአሳማ ልብ ቀዶ ጥገና በሕክምናው ዘርፍ ትልቁ ዜና ሆኖ ቆይቷል። የእንስሳትን አካል ለሰው መግጠምን አስቸጋሪ የሚያደርገው ""ሃይፐርኪዩት ሪጄክሽን"" የተባለ ሂደት ነው። ሰውነታችን ከሌላ ዝርያ አካል ሲገጥምለት ባዕድ ነገር እንደመጣበት አውቆ የተገጠመውን አካል በደቂቃዎች ውስጥ ይገድለዋል። ነገር ግን ለአሳማው የሰውነት አካል አስር ጊዜ በሳይንሳዊ መንገድ በልፅጎ ሰውነታችን እንዲቀበለው ማድረግ ተችሎ ነበር። ቢሆንም ይህንን ሰው ላይ ሞክሮ ሰውነት የተለገሰውን አካል ይገድለዋል አይገድለውም የሚለውን መጠባበቅ ለዶክተሮች በጣም አስጨናቂ ሂደር ነበር። የልብ ቀዶ ጥገናውን ያደረጉት ዶክተሮች ልቡን ከገጠሙ ከአንድ ወር በኋላም ሁሉም ነገር ሰላም መሆኑን ተናግረው ነበር። ሰውዬው የሞተበት ትክክለኛው ምክንያት ምን እንደሆነ እስካሁን ግልፅ አይደለም።" https://www.bbc.com/amharic/news-60687786 +politics ሱዳን መፈንቅለ መንግሥት፡ የሱዳን ፖለቲካዊ ቀውስ በሕዳሴው ግድብ ድርድርና በሰሜኑ ጦርነት ላይ ምን ተፅዕኖ ይኖረዋል? "ሲንገዳገድ የቆየው የሱዳን የሽግግር አስተዳደር ለይቶለት በጦር ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዶበት ከኃላፊነቱ ተወግዶ የሽግግሩ መንግሥት አባል የነበሩት ጄነራል አል ቡርሐን መሪነቱን ጠቅልለው ይዘዋል። የአፍሪካ ሕብረትና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም መፈንቅለ መንግሥቱን ያወገዙ ሲሆን ዓለም አቀፍ ተቋማትም ለሱዳን የሚሰጡትን እርዳታ ከማገድ በተጨማሪ የመንግሥት ግልበጣውን ላደረጉት መሪዎች እውቅና ከመስጠት ተቆጥበዋል። ኦማር ሐሰን አልባሽር ከስልጣን መባረር በኋላ በአገሪቱ ጦር ሠራዊትና በሲቪል ፖለቲከኞች መካከል የነበረው ውዝግብ ሰላም ነስቷት የቆየችው ሱዳን ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ ሰላም የማግኘቷ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል። የመንግሥት ግልበጣ ዜናው ከተነገረበት ሰዓት አንስቶ አገሪቱ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንድትሸጋገር የሚፈልገው ሕዝቧ፣ የሙያ ማኅበራትና ፖለቲከኞች በየእለቱ አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። በሱዳን ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣን መቆጣጠሩና በአገሪቱ የተከሰተው አከመረጋጋት በታላቁ ሕዳሴ ግድብና በድንበር ይገባኛል ምክንያት እየተወዛገበቻት ካለችው ኢትዮጵያ አንጻር ምን ውጤት ይኖረዋል? የሱዳንን መፈንቅለ መንግሥት የመሩት ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን የሱዳኑ አልሲሲ ይሆናሉ የሚል ስጋት አለ። ጄነራሉ ከግብፁ መሪ አልሲሲ ጋርም መልካም ግንኙነት እንዳላቸው ይነገራል። መቀመጫቸውን ለንደን ያደረጉት የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አጥኚ አብዱራህማን ሰኢድ አቡሃሽም የጄነራል አል ቡርሐን የሱዳን መንግሥትን ሥልጣን መጠቅለል በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ይናገራሉ። ""ባለፉት ሁለት ዓመታት የአልቡርሐን መንግሥት ከግብፅ ጋር የጋራ ስምምነት ተፈራርሞ በአባይ ጉዳይ ላይ አንድ ዓይነት ፖሊሲ ሲያራምዱ ቆይተዋል"" ይላሉ አቡሃሽም። በዚህም የተነሳ የድንበር ውዝግቦችን እያስነሱ ኢትዮጵያን ሲተናኮሱና ወደ ጦር��ት እንድትገባ ሲገፋፉ መቆየታቸውን አጥኚው ጠቅሰዋል። ""ይህም በኢትዮጵያ መንግሥት ትዕግስት ነው የታለፈው"" ይላሉ። አቡሃሽም እንደሚሉት የሱዳን መንግሥት ሲቪል አባላት ጄነራል አል ቡርሐን በሚያደርጓቸው ትንኮሳዎች አይስማሙም ነበር። ሱዳናውያንም ቢሆኑ ኢትዮጵያን እንደ ባለውለታና ወንድም ሕዝብ ስለሚያዩ ውዝግቡን አይደግፉትም። በመሆኑም ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣኑን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠረና በአገሪቱ ዲሞክራሲ ከጠፋ ጄነራል አልቡርሐን ለሥልጣናቸው ሲሉ ወደ አሉታዊ አማራጮች ሊያዘነብሉ እንደሚችሉ አቡሃሽም አስረድተዋል። ""ይህ ከሆነም በቀጥታ ወደ ጦርነት ሊያመራ ስለሚችል ኢትዮጵያን ያሰጋታል"" በማለት፤ ይህ ካልሆነም አልቡርሐን ከግብፅ ጋር በሚኖራቸው ቅርበት የተነሳ ኢትዮጵያን ለጦርነት ሊገፋፉ እንደሚችሉ ይናገራሉ። የሱዳኑ ቀውስ በሰሜኑ ጦርነት ላይ የሚኖረው አንድምታ እንደ ፖለቲካ ተንታኙ አቡሃሽም ከሆነ የአልቡርሐን ኃይል አይሎ በቀጥታ ወደ ጦርነት ካልገባ በስተቀር የሱዳን ቀውስ በሰሜኑ ጦርነት ላይ ብዙ ለውጥ አያመጣም። ምክንያታቸው የሱዳን ኃይል የህወሓት ኃይሎችን ለመደገፍ ሲሞክር በመቆየቱ አዲስ ነገር አይፈጠርም የሚል ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ሱዳን በሚገኝ ስደተኞች ካምፕ ውስጥ ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ የህወሓት ኃይሎች እንደተደራጁ እና ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ሲሞክሩ እንደቆዩ ክስ ሲያቀርብ እንደነበርም ተንታኙ አስታውሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሱዳን መንግሥታት ስትራቴጂያዊ የሆነ አቋም ስለሌለው በኢትዮጵያ ላይ ተቃዋሚ ኃይሎች በሚመጡበት ጊዜ እንደየ ሁኔታው አቋማቸውን ሊለዋውጡ እንደሚችሉ አቡሃሺም ያስረዳሉ። በመሆኑም ""ህወሓትን እንደ አንድ ስትራቴጂያዊ ተባባሪ አድርጎ ሲሸነፍ የሚያግዘው፤ ሲወድቅ የሚያነሳው ሊሆንለት የሚችል አይመስለኝም"" ብለዋል አጥኚው። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ግንባታውና በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብፅ መካከል የሚካሄደው ድርድር አስር ዓመታትን ቢያስቆጥርም ከስምምነት ሳይደርሱ አስካሁን ቆይቷል። ጉዳዩ ወደ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ድረስ አምርቶም ባለፈው ሐምሌ ወር ላይ ምክር ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ በሕዳሴው ግድብ ላይ መክሮ ጉዳዩ በአፍሪካ ሕብረት አመቻችነት መፍትሔ እንዲያገኝ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ድርድሩ ሳይጀመር በሱዳን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዶ የአገሪቱ ካቢኔ መበተኑ የሕዳሴው ግድብ ድርድርን ወዴት ይወስደው ይሆን? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል። የምሥራቅ ናይል ቴክኒካዊ አህጉራዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፈቅ አሕመድ ነጋሽ በኢትዮጵያ የተፈጠረው ሁኔታ፤ በተለይ ደግሞ ሱዳን ውስጥ የተፈጠረው ቀውስ ተፅእኖ በመፍጠሩ ድርድሩ እስካሁን አለመጀመሩን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የፀጥታው ምክር ቤት በሁለተኛው ስብሰባው አገራቱ በተወሰነ የጊዜ ገደብ አስገዳጅ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳለባቸው ውሳኔ አስቀምጦ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ፈቅ አሕመድ፤ ይህንን ግን ማድረግ አልተቻለም ብለዋል። ድርድሩን ለማመቻቸት ኃላፊነት የወሰደው የአፍሪካ ሕብረትም ሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር እስክትመለስ ድረስ ከአባልነት ማገዱን አስታውቋል። ጄነራል ቡርሐን ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ ካቢኔውን ሲበትኑ በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ ላይ የሱዳን ተደራዳሪ የሚባሉት የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የውሃና መስኖ ሚኒስትርም እንቅስቃሴያቸው ታግዷል። በመሆኑም ""የተደራዳሪዎቹ የወደፊት እጣ ፋንታ ባልታወቀበት ሁኔታ ስለድርድር ማውራት አስቸጋሪ ነው"" ይላሉ አቶ ፈቅ አሕመድ። ""የፖሊሲ ለውጦችም ይኖራሉ፤ ሱዳ��� በአሁኑ ሰዓት የምትከተለው ፖሊሲም ምን እንደሆነ አልታወቀም። የአፍሪካ ሕብረት ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴ ላይም ሱዳን አትሳተፍም። በመሆኑም የሕዳሴው ግድብ ድርድር ተንጠልጥሎ የሚቆይ ይመስለኛል"" ብለዋል። የሱዳን ወታደራዊ ኃይልና የግብፅ መንግሥት ግንኙነት በሕዳሴው ግድብ ላይ አልባሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ወታደራዊውና ሲቪል መሪዎች ሥልጣን ተጋርተው አገሪቱን ሲመሩ ቢቆዩም በይበልጥ ሥልጣኑን የያዘው ወታደራዊው ኃይል እንደነበር ያስታወሱት አቶ ፈቅ አሕመድ፤ ወታደራዊው ኃይል ከካይሮ ጋር እንዳበረ ተናግረዋል። በመሆኑም ወታደራዊው መንግሥት ሥልጣን ላይ ቢቆይም ባይቆይም እስከ አሁን የነበራቸውን አቋም ይለውጣል የሚል እምነት የላቸውም። ""ብቸኛው አማራጭ ድርድር በመሆኑም ድርድሩ ይቀጥላል። ይህንንም እነርሱም ጠንቅቀው ያውቁታል"" ብለዋል። አቶ ፈቅ አሕመድ የዓለም ባንክ፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ አሜሪካ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ላይ እየፈጠሩ ያሉት ጫና ውጤት እያሳየ መሆኑን ይናገራሉ። በቁጥጥር ስር የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውንም ለዚህ እንደ አብነት ጠቅሰዋል። ጫናው ከበረታበት ወታደራዊ ኃይል የሲቪል መንግሥቱን ወደ ሥራው ይመልሳል አሊያም በአጭር ጊዜ ምርጫ አካሂዶ ሌላ የሲቪል አስተዳደር ያቋቁማል የሚል ግምት እንዳለ የተናገሩት አቶ ፈቅ አሕመድ፤ ይህ ከሆነ ቶሎ ወደ ድርድር የመመለስ ሁኔታ ይኖራል ብለዋል። ካልሆነስ? ""ይህ የማይሆን ከሆነ አገራቱ ሌላ አማራጭ የሚፈልጉ ይመስለኛል"" ይላሉ አቶ ፈቅ አሕመድ። የሱዳን መንግሥት ተዳራዳሪዎቹን [የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የውሃና መስኖ ሚኒስትር] ወደ ሥራ መልሶ ወደ ድርድሩን እንዲመለሱ ማድረግ ባለሙያው ያስቀመጡት አንደኛው አማራጭ ነው። ከዚህም ባሻገር ሌላ ጊዜያዊ ተደራዳሪ በመሰየም ሦስቱ አገራት የሚደራደሩበትን ሁኔታ መፍጠር እንደሚቻልም ተናግረዋል። በወሰን ተሻጋሪ ወንዞች የሚወዛገቡ አገራት ድርድር የሦስተኛ አገር ጣልቃ ገብነት ባይደገፍም፤ የተሻለ፣ የተለየ ፍላጎት እና ወገንተኝነት የሌለው ሦስተኛ አካል በማስገባት መደራደርም ሌላኛው አማራጭ ነው ብለዋል። አቶ ፈቅ አሕመድ እንደሚሉት የአፍሪካ ሕብረት በድርድሩ አልቀጥልም ቢል እንኳን አገራቱ ፍላጎት ካላቸው ተነጋግረው ልዩነቶቻቸውን መፍታት ይችላሉ። ግብፅ ከሕዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አማራጮችን ስትሞክር እንደቆየች የሚናገሩት አቶ ፈቅ አሕመድ ""ሙርሲ ፕሬዝዳንት እያሉ ለውዝግቡ ስድስት የመፍትሔ ሃሳቦችን አቅርበው ነበር። ከስድስቱ ተግባራዊ ያልተደረገው 'ቀጥተኛ ጦርነት መክፈት' የሚለው ብቻ ነው"" ይላሉ። ይሁን እንጂ ወደ ቀጥታ ጦርነት መግባት ራሳቸውንም ሰለባ ስለሚያደርጋቸው አሁን ባሉበት ይቀጥላሉ የሚል እምነት እንዳላቸው አቶ ፈቅ አሕመድ አክለዋል። የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኙ አቡሃሽምም ይህንኑ ሃሳብ ይጋሩታል። ""የአባይ ጉዳይ በይበልጥ ሊፈታ የሚችለው በኢትዮጵያና በግብፅ ነው"" ያሉት አቡሃሽም፤ ግብፆችም ሆኑ ሱዳኖች የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ኃይሎች ለመደገፍ ወይም ላለመደገፍ የሚወስኑት ለአባይ ሲሉ ነው ብለዋል። ነገር ግን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከ80 በመቶ በላይ ተገንብቶ ያለቀ በመሆኑና የሚቀለበስ ጉዳይ ባለመሆኑ በተለይ ግብፆቹ ምን ዓይነት መፍትሔ ነው የሚፈልጉት የሚለው ጉዳይ እስካሁን ግልጽ አለመሆኑን አቡሃሽም ተናግረዋል። ""ግብፅ ግድቡን አፈርሳለሁ ብትል እንኳን በራሷ ላይ ይዞት የሚመጣው መዘዝ ከባድ በመሆኑ፤ ይህም ዘላቂ መፍትሄ አይሆንም"" ብለዋል። በኢትዮጵያ በኩል በድርድር መቀጠሉ ጥሩ ነው የሚሉት አቶ ፈቅ አሕመድ፤ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በማስጠበቅ የሌሎችንም ጥቅም ሳትነካ፤ በአሜሪካ ተጀምሮ የነበረውን የስምምነት መርሆዎችና ይዘቶችን በመተው በአዲስ ስልት ድርድር በማካሄድ ወደ ተሻለ ስምምነት መምጣት እንደምትችል ተናግረዋል። ቀጠናው ውስብስብ ችግር ውስጥ ይገባ ይሆን? በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የሰሜኑ ጦርነት፣ የአልፋሽቃ ድንበር ውዝግብ፣ የግብፅ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ውዝግብ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ፍላጎቶች፣ የአረብ አገራት ሚና ቀጠናውን ወደ ውስብስብ ችግር ያመሩታል የሚል ስጋት አለ። የፖለቲካ ተንታኙ አቡሃሽም ግን ይህ የሰሜኑ ጦርነት በሰላም ወይም በወታደራዊ መንገድ በቶሎ መጠናቀቁ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአካባቢው ጠቃሚ ነው ይላሉ። ""የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርነቱን የውስጥ ጉዳዩ አድርጎ ሊጨርሰው እየሞከረ ነው"" የሚሉት ተንታኙ ጦርነቱ ሙሉ በሙሉ አለመጠናቀቁ ለሌሎች አገራት ጣልቃ መግባት በር ሊከፍት ይችላል ብለው ያምናሉ። ይሁን እንጅ ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይዋ እየተተራመሰች የአባይና የግድቡ ጉዳዮችን የሚያዘናጉ እና የሚያደናቅፉ ሁኔታዎች ከተፈጠሩ ለግብፆች አመቺ ይሆናል ይላሉ። በሌላ በኩል ኤርትራ ህወሓትን እንደ ጠላት እንደምታይ የጠቀሱት ተንታኙ፤ የህወሓት ጥንካሬ እያየለ ከሄደ ኤርትራ በቀጥታ ጦርነቱ ውስጥ ልትገባ የምትችልበት ዕድል እንዳለ ይጠቅሳሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-59066437 +business በኢትዮጵያ ለሚታየው የነዳጅ እጥረት ምክንያቱ ምንድን ነው? በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለመቅዳት ለሰዓታት ረጅም ሰልፍ ለመጠበቅ ከተገደዱ ቀናት ተቆጥረዋል። በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩን ተከትሎ መንግሥት ለዓመታት ለነዳጅ ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ ቀስ በቀስ ለማቋረጥ ወስኖ ተግባራዊ ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው። ኢትዮጵያ ለነዳጅ የምታደርገው ድጎማ ነዳጅ ለሁሉም ተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ አስችሎ ቆይቷል፤ ነገር ግን ይህ ድጎማ ከዚህ በኋላ ዘላቂ እንደማይሆን በነዳጅና ፔትሮሊየም ባለሥልጣን ውስጥ የሚሰሩ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ስታንዳርድ ጥናት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ቱሉ እንደሚሉት መንግሥት ለነዳጅ በሚያደርገው ድጎማ ምክንያት በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ወጪ ያደርጋል። በግንቦትና በሰኔ መካከል ባሉ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ብቻ መንግሥት 16 ቢሊዮን ብር ወይም 268 ሚሊዮን ዶላር ነዳጅን ለመደጎም ሲል ወጪ ማድረጉን አቶ ለሜሳ ተናግረዋል። ከዋጋ ጭማሪው ባሻገር በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚከሰቱት ግጭቶች የትራንስፖርት መስመሮችን በማስተጓጎል በቅርብ ወራት ውስጥ የነዳጅ አቅርቦት ችግር በአገሪቱ ውስጥ እንዲከሰት ምክንያት እየሆኑ ነው። ነገር ግን አሁን ለተከሰተው የነዳጅ እጥረት መባባስ ከጂቡቲ ወደ አገር ውስጥ የሚገባውን ነዳጅ መድረስ ካለባቸው ቦታ ውጪ መውሰድና የነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ትራንስፖርት መዘግየት ምክንያት እንደሆነ አቶ ለሜሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንዳንድ አከፋፋዮችም መንግሥት በተወሰነ ደረጃ ድጎማውን በማንሳት አዲስ የነዳጅ ታሪፍ ይፋ በሚያደርግበት ጊዜ በተጨማሪ ዋጋ ለመሸጥ ሲሉ ነዳጅ ያከማቻሉ ሲሉም ባለሥልጣኑ ይከሳሉ። ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል ነዳጅ ጭነው ተደብቀው የነበሩ 15 ቦቴዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበው ነበር። የተሽከርካሪዎችን መዘግየት ለማስቀረትም ከአዋሽ ጀምሮ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎ�� መመደባቸው ተገልጿል። አንዳንድ ሪፖርቶች ወደ አገሪቱ ከሚገባው ነዳጅ ውስጥ የተወሰኑት ቦቴዎች በጦርነት ምክንያት ዝግ ወደ ሆነችው ትግራይ ክልል እንዲገባ እንደሚደረግ ቢያመለክቱም፣ ባለሥልጣኑ ግን ይህንን የሚያረጋግጥ በቂ መረጃ እንደሌለ ይናገራሉ። “እስካሁን የምናውቀው አንዳንድ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ይዘው ከሚጠበቁበት ቦታ ላይ አለመድረሳቸውን ነው” ሲሉ አቶ ቱሉ ስላልታወቁት ቦቴዎች ተናግረዋል። ስለዚህም በአገሪቱ ውስጥ ለሚስተዋለው የነዳጅ እጥረት፣ በተለያዩ ጊዜያት በነዳጅ ማመላለሻ መስመሮች አካባቢ የሚከሰቱ የፀጥታ መደፍረሶች፣ ተሽከርካሪዎች አቅርቦታቸውን በሚፈለጉበት ቦታ ዘግይተው ማድረስ፣ ነዳጅ መድረስ ካለባቸው ቦታዎች ውጪ ወደ ሌሎች ቦታዎች መሸጋገር እንዲሁም አከፋፋዮች ነዳጅን ደብቆ ማስቀመጥ ምክንያት ናቸው ብለዋል። በተለይ ነዳጅ ለመቅዳት ተሽከርካሪዎች የታሪፍ ክለሳ ከሚደረግባቸው የወራት መጨረሻ ቀናት ቀደም ብሎ መኪናቸውን ሙሉ ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ሰልፎች እንዲበራከቱ ያደርጋሉ። ከቀጣዩ ሐምሌ ወር ጀምሮ መንግሥት በነዳጅ ላይ የሚያደርገውን ድጎማ ለማንሳት ለሚወስደው እርምጃ የመጀመሪያው ደረጃ በመሆኑ ካሉት ተደራራቢ ችግሮች በተጨማሪ የነዳጅ ሰልፉን እንዳባበሰው አሽከርካሪዎች ይናገራሉ። የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች የነዳጅ ድጎማ መነሳቱ ላይ የተለያየ ሃሳቦችን ያንጸባርቃሉ። አንዳንዶች የተቀናጀ ቁጥጥር እና በቂ ግንዛቤ ለሕብረተሰቡ ከደረሰ የከፋ ጫና አያስከትልም ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ባለው የኑሮ ውድነት ላይ መሠረታዊ የሆነውን የነዳጅ ድጎማን ማንሳት “ እየነደደ ባለ እሳት ላይ ነዳጅ ማርከፍከፍ ነው” ሲሉ ውሳኔውን ተቃውመውታል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c726xp15vy6o +sports ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተደረጉ የእግር ኳስ ጨዋታዎች እነማን አሸነፉ? በአውሮፓ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ኦሚክሮን በስፋት መሰራጨት መጀመሩን ተከትሎ በርካታ የእግር ኳስ ጨዋታዎች እየተስተጓጎሉ ነው፤ ነገር ግን ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ፣ በጣልያን ሴሪ እንዲሁም በስፔናን ላሊ ጋ በርካታ ጨዋታዎች ተካሂደዋል። በእንግሊዝ ፕሪምየር ምንም እንኳን ጥቂት የማይባሉ ወሳኝ ጨዋታዎች በኦሚክሮን ስርጭት ምክንያት ለሌላ ጊዜ ቢተላለፉም በሊጉ ከአንድ እስከ ሦስት የሚገኙት ቡድኖች ግን ጨዋታቸውን አድርገዋል። ማንቸስተር ሲቲ ኒውካስልን አራት ለዜሮ በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን ያረጋገጠ ሲሆን ቼልሲዎች ደግሞ ከዎልቭስ ያደረጉትን ጨዋታ ያለምንም ግብ አቻ ጨርሰዋል። ቼልሲዎች በአራት ጨዋታ ለሦስተኛ ጊዜ ነው አቻ የወጡት። ትናንት ምሽት ደግሞ ሊቨርፑል በአዲሱ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ የሚመሩት ቶተንሀሞችን ገጥሟል። ጨዋታው ምንም እንኳን በሙከራዎችና በግቦች የታጀበ ቢሆንም ውጤቱ ግን አቻ ነበር። ጨዋታውም 2 ለ 2 ተጠናቋል። ይህንን ተከትሎ ማንቸስተር ሲቲዎች በ18 ጨዋታዎች ሊጉን በ44 ነጥብ መምራት የጀመሩ ሲሆን ሊቨርፑል ደግሞ በ41 ነጥብ የሁለተኛውን ቦታ ይዟል። ቼልሲ በ38 ነጥብ ሦስተኝነቱን አሁንም ማስጠበቅ ያለ ሲሆን አርሰናል፣ ዌስት ሀም፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቶተንሀም ለአራተኛው ቦታ እየተፎካከሩ ይገኛሉ። በርንሌይ ኒውካስል እና ኖርዊች ሲቲተ ደግሞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች ናቸው። በጣልያን ሴሪ አ የሊጉ መሪ ኢንተር ሚላን ከሳሌኒታና ያደረገውን ጨዋታ 5 ለባዶ በሆነ ውጤት በማሸነፍ በ48 ነጥብ መሪነቱን ማረጋገጥ ችሏል። በጉጉት የተጠበቀው የናፖሊ እና የሚላን ጨዋታ ደግሞ በናፖሊ አንድ ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል። ይህን ተከትሎ ናፖሊ በ39 ነጥብ ከኢንተር ሚላን በመቀጠል ሁለተኝነቱን ያረጋገጠ ሲሆን ኤሲ ሚላኖች ደግሞ ምንም እንኳን ቢሸነፉም በተመሳሳይ 39 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጠው ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኙት ጁቬንቱሶች ደግሞ ቅዳሜ ዕለት ቦሎኛን ሁለት ለምንም በማሸነፍ በ25 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በስፔን ላሊጋ ቅዳሜ ዕለት የቀድሞ ተጫዋቻቸውን በአሰልጣኝነት የቀጠሩት ባርሴሎናዎች ከኤልቼ ያደረጉትን ጨዋታ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። ከቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ማለፍ ያቃታቸው ባርሴሎናዎች በሊጉም ቢሆን ወደ ቀድሞ ቦታቸው ለመመለስ ብዙ ይቀራቸዋል። በአሁኑ ሰዓት በ28 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኙት። ያለፈው ዓመት የላሊጋው አሸናፊ አትሌቲኮ ማድሪድ ደግሞ በሲቪያ ሁለት ለአንድ መሸነፉን ተከትሎ በ29 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሲቪያ ደግሞ አንድ ቀሪ ጨዋታ እየቀረው በ37 ነጥብ ሁለተኛ ነው። የሊጉ መሪ ሪያል ማድሪድ ትናንት ምሽት የነጥብ ልዩነቱን ማስፋት የሚችልበትን ዕድል ሳይጠቀም ቀርቷል። እሁድ ምሽት ከካዲዝ የተገናኙት ሪያል ማድሪዶች ጨዋታውን ያለምንም ግብ ዜሮ ለዜሮ በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-59708923 +business ብሔራዊ ባንክ ክሪፕቶከረንሲዎች በኢትዮጵያ ዕውቅና የላቸውም አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደ ቢትኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎች በአገሪቱ ውስጥ ለግብይት መጠቀም ዕውቅና አልተሰጣቸውም በማለት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከለከለ። ብሔራዊ ባንክ በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን አማካይነት ባወጣው መግለጫ፤ በክሪፕቶከረንሲዎች ግብይት መፈጸም ሕገ ወጥ ተግባር በመሆኑ ኅብረተሰቡ እራሱን ከመሰል ተግባራት ይጠብቅ ብሏል። ክሪፕቶከረንሲ በአጭር ቋንቋ የማይዳሰስ ዲጂታል ገንዘብ ማለት ነው። ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ክሪፕቶከረንሲን፤ የገንዘብ ልውውጦችን ደኅንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ፣ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ ነው ሲል ይገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በርካታ ዓይነት ክሪፕቶካረንሲዎች አሉ። በስፋት ከሚታወቁት መካከል ቢትኮይን፣ ኤቴሪያም፣ ካርዳኖ እና ዶጅኮይን ተጠቃሽ ናቸው። ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሰዎች እንደ ቢትኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎችን በመጠቀም ለምርት እና አገልግሎት ክፍያ እየፈጸሙ እንደሆነ ጠቁሟል። ምንም እንኳን ባንኩ ይህን ይበል እንጂ በኢትዮጵያ ለሚሰጡት ምርት እና አገልግሎት ክፍያ በክሪፕቶከረንሲ የሚቀበሉ ድርጅቶች ስለመኖራቸው ግልጽ አይደለም። እንዲህ ዓይነቶቹ የዲጂታል መገበያያ ዘዴዎች በአገሪቱ እየተስፋፉ መምጣታቸውን በመግለጽ በአገሪቱ ተቀባይነት የሌለው ሕገ ወጥ ድርጊት መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት በበርካታ አገራት ሰዎች ለሚያገኟቸው ምርት እና አገልግሎቶች በክሪፕቶከረንሲዎች አማካይነት ክፍያ መፈጸም እየተለመደ መጥቷል። ማይክሮሶፍት፣ ፔይፓል፣ የጉዞ ወኪሉ ኤክስፔዲያን ከመሳሰሉ ባለብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ኩባንያዎችን አንስቶ እስከ ሆቴሎች እና ካፊቴሪያዎች ቢትኮይንን በክፍያ መልክ ይቀበላሉ። ብሔራዊ ባንክ የኢትዮጵያ ይፋዊ መገበያያ ገንዘብ ብር መሆኑን አስታውሶ፤ “በየትኛውም የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድም ሆነ ሥርዓት ያለ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የገንዘብ ዝውውርም ሆነ ገንዘብ ነክ አገልግሎት መስጠት አይቻልም” ብሏል። በክሪፕቶከረንሲ ግብይት ላይ መንግሥታት ቁጥጥር ለማድረግ ያዳግታቸዋል። በክሪፕቶከረንሲ በሚደረጉ ግብይቶች ላይም የሻጭ እና ገዢ ማንነት ይፋ ሳይደረግ ግብይት ማድረግ ይቻላል። በዚህም ምክንያት ሕገ ወጥ ቡድኖች/ግለሰቦች የተከለከሉ ቁሶች ሊገዙ እና ሊሽጡ ይቻላሉ። በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አድርገው ሊጠቀሙም ይችላሉ። ይህም ለአገራት ስጋት ሆኖ ቀጥሏል። ብሔራዊ ባንክም በዛሬው መግለጫው ክሪፕቶከረንሲዎች “በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል” ብሏል። “ይህን ፈጽመው በሚገኙ አካላት ላይ ብሔራዊ ባንክ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል” ካለ በኋላ ኅብረተሰቡም በዚህ “ሕገ ወጥ ተግባር” ላይ የተሰማሩትን አካላትን ለብሔራዊ ባንክ እና ለሚመለከታቸው ሕግ አስከባሪ አካላት እንዲጠቁም ጥሪውን አስተላልፏል። ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እንዱሁም ኤል ሳልቫዶር በቅርቡ ቢትኮይንን ሕጋዊ መገበያያ አድርገዋል። ይህ ማለት ሰዎች በእነዚህ አገራት ለሚያገኙት አገልግሎት ክፍያ በቢትኮይን መፈጸም ይችላሉ። በተቀሩት አገራት በተለይ ደግሞ በምዕራባውያን አገራት ሕገ ወጥ ነው ማለት ግን አይደለም። አንደ ቦሊቪያ፣ ቻይና፣ ኢራን እና ኮሎምቢያ ያሉ አገራት ግን ቢትኮይን ላይ ክልከላ ጥለዋል ወይም ሕገ ወጥ አድርገውታል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cw0g085dpwno +business በኢትዮጵያ ያለው የነዳጅ ዋጋ ከአንዳንድ የአፍሪካ አገራት ጋር ሲነጻጸር ምንም እንኳን በዓለም ገበያ ላይ ዋጋው ቢጨምርም ለወራት ባለበት የቆየው የኢትዮጵያ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቋል። በዚህም መሠረት በመላው አገሪቱ በታኅሣሥ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ የተደረገ ሲሆን፤ በዚህም በተለያዩ የነዳጅ እምርቶች ላይ ቀላል የማይባል ጭማሪ ታይቷል። በዚህ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ካስፈለገባቸው ምክንያቶች መካከል፤ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መኖሩና ከጎረቤት አገራት ጋር ሲነጻጸር በኢትዮጵያ ያለው የነዳጅ ዋጋ ዝቅተኛ በመሆኑ የነዳጅ ምርቶች ለከፍተኛ ኮንትሮባንድ መጋለጡ ተጠቅሷል። የኮሮናቫይረስ ክስተትን ተከትሎ የነዳጅ ፍላጎት ዝቅ በማለቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ቅናሽ አሳይቶ የቆየ ቢሆንም፣ ከአንድ ዓመት በኋላ ዋጋው ቀስበቀስ እየጨመረ አሁን ካለበት ላይ ደርሷል። ባለፉት ወራት ጭማሪው ያለመቋረጥ የቀጠለ ሲሆን፣ በወረርሽኙ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው የዓለም ምጣኔ ሀብት ለማንሰራራትና ወደነበረበት ለመመለስ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የነዳጅ ፍጆታ ከፍ እያለ መሆኑ ለዚህ ተጠቃሽ ነው። በኢትዮጵያ የተደረገው የዋጋ ክለሳ ለወራት በሊትር 25 ብር ከ85 ሳንቲም ይሸጥ የነበረው ቤንዚን፤ አሁን በተደረገው የዋጋ ማስተካከያ አንድ ሊትር ቤንዚን 31 ብር ከ74 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል። ይህም ከስደስት ብር በላይ ጭማሪን በአንድ ሊትር ላይ ያስከተለ ሲሆን፣ ጭማሪው በሌሎችም ሸቀጦችና አገልግሎቶች ላይ ሊንጸባረቅ እንደሚችል ከዚህ ቀደም የታዩት ልምዶች ያመለክታሉ። ነጭ ናፍጣ 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣ ነጭ ጋዝ 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 23 ብር ከ73 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ 58 ብር ከ77 ሳንቲም በሊትር ከኅዳር 30 ቀን 2014 ጀምሮ እንደሚሸጥ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴሩ አስታውቋል። የኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከጎረቤት አገራት ሲነጻጸር በየጊዜው እየተደረገ ካለው የዋጋ ጭማሪ ጋር ቢሆንም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚገኙ አገራት ነዳጅ በአነስተኛ ዋጋ ከሚሸጥባቸው አገራት መካከል ተጠቃሽ ነች። በዓለም ዙሪያ ባሉ አ��ራት ውስጥ የነዳጅ መሸጫ ዋጋን እንደሚያቀርበው 'ስታቲስታ' መረጃ ከሆነ ኢትዮጵያ ነዳጅ አምራች ከሆኑት አንጎላ፣ ናይጄሪያ እና አልጄሪያ በመቀጠል በአፍሪካ ውስጥ በአስተኛ ዋጋ የነዳጅ ምርቶች ለሕዝቧ የምታቀርብ አገር ናት። የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆነችው ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬንያ በቀጠናው ካሉ አገራት ነዳጅ በውድ የምታቀርብ አገር እንደሆነች ይነገራል። በስታቲስቲክስታይምስ መረጃ መሠረት በኬንያ 1 ሊትር ነዳጅ 1.19 ዶላር ይሸጣል። ከኬንያ በመከተል በአካባቢው ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ያላቸው አገራት ሱዳን እና ኡጋንዳ ሲሆኑ፤ ነዳጅ የምታመርተው ሱፋን በሊትር 1.03 ዶላር ስታስከፍል፣ በቅርቡ የነዳጅ ዘይት ያገኘችው ኡጋንዳ ደግሞ አንድ ሊትር በ1.09 የአሜሪካ ዶላር ታቀርባለች። በዓለም ላይ ዜጎቿን አነስተኛ የነዳጅ ዋጋ የምታስከፍለው ነዳጅ አምራች የሆነችው እና ምጣኔ ሀብቷ ክፉኛ የተጎሳቆለባት ቬንዙዌላ ነች። እንደ ግሎባል ፔተሮል ፕራይስ ከሆነ በቬንዙዌላ በ1 የኢትዮጵየ ብር (0.02 የአሜሪካ ዶላር) አንድ ሊትር ነዳጅ መሸመት ይቻላል። በአፍሪካ ነዳጅ በከፍተኛ ዋጋ ከሚሸጡባቸው አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ ተጠቃሽ ናት። በመረጃው መሠረት በደቡብ አፍሪካ አንድ ሊትር ነዳጅ የሚሸጠው በ1.25 ዶላር ነው። የበለጸጉት እንደ ኔዘርላንስ፣ ኖርዌይ፣ ጣሊያ እና ሆንግ ኮንግ ለአንድ ሊትር ነዳጅ ከ2 የአሜሪካ ዶላር በላይ (ወደ 95 ብር ገደማ) ይጠይቃሉ። ነዳጅ የማታመርተው ኢትዮጵያ፤ ነዳጅ አምራች ከሆኑ አገራት በላይ በአነሰ ዋጋ ነዳጅ ለዜጎች ታቀርባለች። ይህ የሆነውም መንግሥት ለዘረፉ በሚያደርገው ድጎማ ምክንያት ነው። አገሪቱ ከዓመታዊ በጀቷ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ መድባ ነዳጅ ታቀርባለች። ኢትዮጵያ ነዳጅ የምታስገባው ከየት ነው? ኢትዮጵያ ለፍጆታዋ የሚውለውን ነዳጅ ከተለያዩ ነዳጅ አምራች አገራት የምታስገባ ሲሆን፣ በዋናነት ከመካከለኛው ምሥራቅና የባሕረ ሰላጤው አገራት ታገኛለች። በዚህም መሠረት በአሁኑ ጊዜ አገሪቱ የሚያስፈልጋትን የነዳጅ ዘይት ከሳዑዲ አረቢያ እና ከኩዌት በማስመጣት ላይ እንደምትገኝ የነዳጅ ድርጅት መረጃ ያመለክታል። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት እንደሚለው በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚገባበት ብቸኛው መንገድ በጂቡቲ ወደብ በኩል ባለው መስመር ነው። ከአራት ወራት በፊት ቢቢሲ ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ባገኘው መረጃ መሠረት ለአገሪቱ ፍጆታ በየዕለቱ 2.5 ሚሊዮን ሊትር ቤንዚን እና 8 ሚሊየን ሊትር ናፍጣ ይቀርባል ። ይህንንም ለማሟላት በየዓመቱ ለአገሪቱ ፍጆታ የሚያስፈልገውን የነዳጅ መጠን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን፣ ኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በዓመት ምን ያህል የነዳጅ አቅርቦት እንደሚያስፈልግ የተለያዩ መረጃዎችን በመመርኮዝ ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ያቅዳል። ። ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸው የነዳጅ ምርቶች አምስት ዓይነት ናቸው። እነዚህም ቤንዚን፣ ናፍጣ፣ የአውሮፕላን ነዳጅና ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውሉ ሁለት ዓይነት ናፋጣዎች ናቸው። በዚህም መሠረት ቤንዚን በዓመት እስከ 700 ሺህ ሜትሪክ ቶን፣ 2.8 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ናፍጣ፣ 600 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአውሮፕላን ነዳጅና እስከ 70 ሺህ ሜትሪክ ቶን የተለያየ አይነት የኢንዱስትሪ ናፍጣ በየዓመቱ እንደሚገባ ታደሰ ኃይለማርያም ተናግረው ነበር። https://www.bbc.com/amharic/news-59594066 +politics ፖሊስ ኢትዮ-እስራኤላውያንን ጨምሮ ዜጎችን ሰልሏል መባሉን እስራኤል ልታጣራ ነው "የእስራኤል ፖሊስ ከኢትዮጵያ የሄዱ ቤተ እስራኤላውያንን ጨምሮ የታዋቂ ዜጎችን ስልክ ያለሕጋዊ ፈቃድ ጠልፏል የሚለውን ክስ የሚያጣራ ኮሚሽን በእስራኤል መንግሥት እንደሚቋቋም ተገለጸ። የስልክ ግንኙነትን የሚፈትሽ መተግበሪያ (ስፓይዌር) ያለ ፈቃድ በመጠቀም የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ልጅን ጨምሮ የባለሥልጣናትን፣ ተቃዋሚዎችን እና የጋዜጠኞችን ስልክ መሰለሉ 'ካልካስት' በተባለ ጋዜጣ ተዘግቧል። የኔታንያሁ የሙስና ክስ ውስጥ የተካተተ ምስክር ስልክም እንደተጠለፈ ተገልጿል። የኔታንያሁ ልጅ እና በሙስና ክስ ላይ ምስክር የሆኑም ስልካቸው መጠለፉ ቢገለጽም፤ በስለላ የተገኘው መረጃ በፍርድ ቤት እንደማስረጃ ስለመቅረቡ አልታወቀም። ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት ""ይህ ዘገባ እውነት ከሆነ ከባድ ጥፋት ነው የተፈጸመው"" ብለዋል። ጋዜጠኞች እንደሚሉት የእስራኤል ፖሊሶች ፔጋሰስ የተባለውን የስለላ መተግበሪያ ነው የተጠቀሙት። በእስራኤሉ ጋዜጣ በወጣው ዘገባ መሠረት የበርካታ እስራኤላውያን ስልክ በፖሊስ ያለ ፈቃዳቸው ተጠልፏል። ሕጋዊ ምርመራ ባልተከፈተባቸው ሰዎች እንዲሁም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስለላው መከናወኑም ተጠቁሟል። ስለላ ሲካሄድባቸው ነበር ከተባሉት መካከል የአገሪቱ የትራንስፖርት፣ የገንዘብና የፍትሕ ሚኒስትሮች ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን-እስራኤላውያን እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች መብት ተሟጋቾችም እንደተሰለሉ ተገልጿል። በእስራኤል ውስጥ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ብሎም የኔታንያ፣ መቫስረት ዛየን፣ ኪርያት አታ እና ሆሎን ከንቲባዎችም ያለ ፈቃዳቸው እየተሰለሉ ነበር ተብሏል። ፔጋሰስ መተግበሪያን ያመረተው የእስራኤሉ ኤንኤስኦ ሲሆን፤ ተቋሙ በመላው ዓለም ለአምባገነን መሪዎች የስለላ መተግበሪያ በመሸጥ ይወነጀላል። ድርጅቱ በበኩሉ መተግበሪያውን አንዴ ከሸጠ በኋላ ክትትል እንደማያደርግና የእስራኤል ዜጎችን ለመሰለል እንደማይውል ገልጿል። የእስራኤል ፖሊስ ያለ ዜጎች ፈቃድ ሰልሏል የሚለውን ዘገባ በተመለከተ ግን እስካሁን ምላሽ አልሰጠም። ፔጋሰስ የተባለው መተግበሪያ ከግለሰቦች ስልክ አጭር የጽሑፍ መልዕክት፣ ምስል፣ ኢሜል፣ የተቀረጸ ድምጽ እና የስልክ ንግግር መጥለፍ ያስችላል። ""ፔጋሰስ ሽብርና ሌሎች ወንጀሎችን ለመዋጋት ከሚያስችሉ መተግበሪያዎች አንዱ ነው። ነገር ግን መተግበሪያው የእስራኤል ዜጎችንና ባለሥልጣናትን እንዲሰልል አልተሠራም"" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት። ምክትል ዐቃቤ ሕግ አሚት ሜሪ ጉዳዩን እየተከታተሉት እንደሚገኙና ለሕዝቡ ምላሽ እንደሚሰጥም አክለዋል። ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ""ዴሞክራሲያችንን ልናጣ አይገባም። ፖሊሳችንን ልናጣ አይገናም። ሕዝባችንም በፖሊስ ላይ እምነት እንዲያጣ አንፈልግም"" ብለዋል። የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስትር ኦማር ባርሊዝ፤ ጉዳዩን የሚመረምረው ኮሚሽን ጡረታ በወጡ ዳኛ እንደሚመራና ማንኛውንም ሰው ለምስክርነት የመጥራት መብት እንዳለው አስረድተዋል።" https://www.bbc.com/amharic/60291117 +health የምግብ ፍላጎት የሚቀንሰው መድኃኒት ከመጠን በላይ ውፍረትን እንደሚቀንስ ተነገረ "የምግብ ፍላጎትን የሚቀንሰው መድኃኒት አንዳንድ ሰዎች ከአንድ አምስተኛ በላይ የሰውነት ክብደታቸውን እንዲቀንሱ አድርጓቸዋል ሲል አንድ ዓለም አቀፍ ጥናት አስታወቀ፡፡ ሴማግሉታይድ የተሰኘው እና በየሳምንቱ የሚሰጠው መድኃኒት ከአመጋገብ እና ከአካል ብቃት ምክሮች ጎን ለጎን ተሰጥቷል፡፡ ወደ 2,000 የሚጠጉ ሰዎች ላይ በተደረገው ጥናት በአማካይ 15 ኪሎ ግራም ክብደት በ15 ወር የሙከራ ጊዜ መቀነሱ ታይቷል፡፡ ባለሙያዎች ውጤቱ ከመጠን በላይ ውፍረትን ለማከም ""የአዲስ ምዕራፍ"" ምልክት ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡ ከኬንት የመጣችው ጃን ከሰውነት ክብደቷ ከአንድ አምስተኛው በላይ የሚሆነውን 28 ኪሎ ግራም ቀንሳለች፡፡ ""መድኃኒቱ ሕይወቴን የቀየረ ሲሆን ለምግብ ያለኝን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ቀይሯል"" ብላለች፡፡ ምግብ መቀነስ ለጉዳት እንደዳረጋት ተናግራ፤ ረሃብ ስለማይሰማት መድኃኒቱን መውሰድ ""ፍፁም የተለየ ነበር"" ስትል ገልጻለች፡፡ 'ጥረት የማይፈልግ' ጃን አሁን ከሙከራው ስለወጣች የምግብ ፍላጎቷ ተመልሶ ክብደቷ እየጨመረ ይገኛል። ""በሙከራው ጊዜ ክብደት መቀነስ ምንም ጥረት እንደማይፈልግ ቢሰማኝም አሁን ግን ከምግብ ጋር የማያቋርጥ ወደሚመስል ውጊያ እንደመመለስ ነው"" ብላለች፡፡ ሴማግሉታይድ ለሁለተኛው ዓይነት የስኳር በሽታ ሕክምና ይውል ስለነበር በአንዳንድ ሰዎች ቀድሞውኑ ቢታወቅም በዚህ ሙከራ ግን በከፍተኛ መጠን መሰጠቱ ተመልክቷል፡፡ መድኃኒቱ የሚሠራው የሰውነትን የምግብ ፍላጎት በመቀነስ እና ምግብ ከተመገቡ በኋላ ሆድ መሙላቱን የሚያሳውቀውን ሆርሞን የሚለቅበትን ሂደት በማስመሰል ነው፡፡ በኒው ኢንግላንድ ጆርናል ኦፍ ሜዲስን ይፋ በተደረጉት ውጤቶች መሠረት በሴማግሉታይድ የታገዙት ሰዎች በአማካይ 15 ኪሎ ግራም ክብደት የቀንሰዋል፡፡ 'አዲስ ዘመን' ከተመራማሪዎቹ አንዷ የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቼል ባተርሃም ለቢቢሲ እንደተናገሩት ""የሚያስከትለው የክብደት መቀነስ መጠን በዘርፉ ለውጥ ያመጣል።"" ""ላለፉት 20 ዓመታት ከመጠን ባለፈ ውፍረት ዙሪያ ጥናት ሳካሂድ ቆይቻለሁ። እስከ አሁን ከቀዶ ህክምና ውጭ ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ለመከላከል ውጤታማ ህክምና አላገኘንም"" ብለዋል። ክብደትን መቀነስ የልብ ህመም፣ የስኳር እና የኮቪድ -19 ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ተናግረዋል፡፡ ሴማግሉታይድ ለመድኃኒት ተቆጣጣሪዎች እየቀረበ ስለሆነም በመደበኛነት ሊታዘዝ አይችልም፡፡ እንደ ፕሮፌሰር ባተርሃም ከሆነ መድኃኒቱ መጀመሪያ ላይ በስፋት ለገበያ ከመቅረቡ በፊት በልዩ ባለሙያ ክብደት መቀነስ ላይ በሚሠሩ ክሊኒኮች ጥቅም ላይ እንደሚውል ይጠበቃል፡፡ በሕክምናው ላይ ማቅለሽለሽ፣ ተቅማጥ፣ ማስታወክ እና የሆድ ድርቀት የመሳሰሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ነበሩ፡፡ በተጨማሪም ክብደት መቀነሱ በረዥም ጊዜ ውስጥ ሊቆይ የሚችል መሆኑን ለመመልከትም የአምስት ዓመት ጥናቶች አሉ፡፡ የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ስቴፈን ኦራሂሊይ እንደተናገሩት ""የተገኘው የክብደት መቀነስ መጠን ፈቃድ ከተሰጠው የፀረ ውፍረት መድኃኒት አንጻር ውጤቱ ትልቅ ነው"" ብለዋል፡፡ ""ወደፊት የጎንዮሽ ጉዳቶቹ ያነሱ የክብደት መቀነስ ደረጃዎችን ለማሳካት የአዲስ ዘመን ጅማሬ ነው"" ሲሉ ገልጸዋቀል፡፡ የሥነ ምግብ ባለሙያው እና የአስቶን ሜዲካል ትምህርት ቤቱ ዶ/ር ዱአን ሜሎር ""ሰዎች ክብደታቸውን እንዲቀንሱ የሚያግዝ አማራጭ መኖሩ ጠቃሚ ነው። ክብደትን ለመቀነስ አሁንም ግን የአኗኗር ለውጥ ይፈልጋል። ማንኛውም መድኃኒት ወይም የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን እና የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል"" ብለዋል። ""ስለዚህ ክብደት ለመቀነስ ከመሞከርዎ በፊት ከጤና ባለሙያ ጋር መነጋገሩ ሁል ጊዜም ብልህነት ነው"" ሲሉም አስረድተዋል፡፡" https://www.bbc.com/amharic/56027723 +politics የጣሊያኗ ጆርጂያ ሜሎኒ የቀኝ አክራሪ መንግሥት ሊመሠርቱ ነው "የጣሊያን ቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ጆርጂያ ሜሎኒ መንግሥት ለመመሥረት በይፋ ፍቃደኝነታቸውን ገለጹ። አንድ ቀኝ አክራሪ ብሔርተኛ ፓርቲ በጣሊያን መንግሥት ሲመሠርት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። ፕሬዝዳንት ሰርጊዮ ማታሬላ ጆርጂያ ሜሎኒ መንግሥት እንዲመሠርቱ የጠየቁት ፓርቲያቸው ‘ብራዘለርስ ኦፍ ኢታሊ’ ምርጫ ማሸነፉነት ተከትሎ ነው። ጆርጂያ ሜሎኒ የመጀመርያዋ የ���ሊያን ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በይፋ ቃለ መሐላ የሚፈጽሙት በመጪው ቅዳሜ ነው። ሥልጣን የሚረከቡት ደግሞ ጣሊያንን በአስቸጋሪው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጊዜ ከመሯት ማሪዮ ድራጊ ነው። የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል የሆነችው ጣሊያን በአውሮፓ ኅብረት አባላት ሦስተኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ናት። ጆርጂያ ሜሎኒ በውጭ ፖሊሲ ረገድ ምንም ለውጥ እንደማያደርጉ ቃል ገብተዋል። ሜሎኒ በነጭ ፊያት መኪና ወደ ፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት ተጉዘው ለአንድ ሰዓት ያህል ከፕሬዝዳንቱ ጋር ከተወያዩ በኋላ ከቤተ መንግሥት ወጥተው ካቢኔያቸውን አሳውቀዋል። በካቢኔዋ ውስጥ የማቴዎ ሳልቪኒ ቀኝ አክራሪ ሊግ ፓርቲ እና የ86 ዓመቱ ሲልቪዮ በርለስኮኒ ፓርቲ ፎርዛ ኢታሊያ ተካቶበታል። አወዛጋቢው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጋዳፊ ወዳጅ የነበሩት ሲልቪዮ በርልስኮኒ የፑቲን ቀንደኛ ደጋፊ መሆናቸውን የተናገሩበት የድምጽ ቅጂ ሾልኮ ከወጣ በኋላ በጣሊያን ጆርጂያ ሜሎኒ ሊመሠረቱት የነበረው መንግሥት መጠነኛ መንገጫገጭ ተፈጥሮበት ነበር። የፓርቲዎቹ መሪዎች ከፕሬዝዳንት ማታሬላ ጋር አርብ ለ11 ደቂቃዎች ያህል ከተወያዩ በኋላ ጆርጂያ በሰጡት መግለጫ ጣሊያናዊያን በአዲሱ መንግሥት ሊተማመኑ ይገባል ብለዋል። ጨምረውም፣ ""አዲሱ መንግሥት በብቃት ችግሮችን የሚጋፈጥና መፍትሄ የሚሰጥ ይሆናል"" ብለዋል። ጆርጂያ ካዋቀሩት ካቢኔ ከ24 ሚኒስትሮች ውስጥ ስድስቱ ብቻ ሴቶች ናቸው። ከነዚህም መሀል የቤተሰብና የወሊድ ምጣኔ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ኡጌንያ ሮሴላ ይገኙበታል። እኚህ ሴት ጽንስ ማቋረጥን የሚቃወሙ ናቸው። አዲሱ የአካባቢ ጉዳዮች ሚኒስትር ሮቤርቶ ካልዴሮሊ በዘረኛ ንግግራቸው የሚታወቁ ሲሆን ከዚህ ቀደም የመጀመርያ ጥቁር የካቢኔ አባል የነበሩን ሰው ‘ዝንጀሮ’ ብለው የተሳደቡ ናቸው። ሲልቪዮ በርልስኮኒ ምንም እንኳ በካቢኔው ባይካተቱም ይህን ጥምር መንግሥት ችግር ውስጥ ከተውት ቆይተዋል። ይህም የሆነው የፑቲን ቀንደኛ ደጋፊ መሆናቸውን የተናገሩበት ድምጽ ቅጂ ሾልኮ መውጣቱን ተከትሎ ነው። የ86 ዓመቱ በርልስኮኒ ቪላድሚር ፑቲን ""20 ጠርሙስ ምን የመሰለ ቮድካ ለልደቴ ልኮልኛል"" ካሉ በኋላ ""እኔ ከፑቲን አምስት ምርጥ ወዳጆቹ አንዱ ነኝ"" ሲሉ ተሰምቷል። ከዚህም ሌላ በርልስኮኒ የዩክሬንን ፕሬዝዳንት ሲያወግዙ፤ ምዕራባዊያንን ሲያንቋሽሹና ፑቲንን ሲያንቆለጳጵሱ በሾለከው የድምጽ ቅጂ ይሰማል። ሆኖም በርልስኮኒ ነገሩ ከአውድ ውጭ ተወስዶብኛል፤ ጣሊያንና ምዕራቡ በዩክሬን ጉዳይ የያዘውን አቋም እደግፋለሁ ሲሉ አስተባብለዋል። ሌላው በጆርጂያ ሜሎኒ ካቢኔ ውስጥ የተካተቱት ማቴዎ ሳልቪኒም የረዥም ጊዜ የፑቲን አድናቂ ናቸው። ሆኖም ጆርጂያ ሜሎኒ ጥምር መንግሥት ለመመሥረት የግድ እርሳቸውን ማካተት ነበረባቸው። ጆርጂያ ሜሎኒ የ45 ዓመት ሴት ሲሆኑ በጸረ ስደተኛ አቋማቸው የሚታወቁ ናቸው። የመጀመርያ ሥራቸው የሚሆነው ጣሊያናዊያን የኃይል ወጪያቸውን ዝቅ ማድረግ ነው። ከሊቢያ ወደ ጣሊያን የሚገቡ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ለማቆም በሜዲትራኒያን የባሕር ኃይል አዘምታለሁ ብለዋል ሜሎኒ። የሜሎኒ ፓርቲ መሥራችና አዲስ የሴኔቱ አፈ ጉባኤ የሆኑት ሰው፣ የፋሺስት ቤኒቶ ሞሶሎኒ ከፍተኛ አፍቃሪ ናቸው። የጆርጂያ ሜሎኒ ፓርቲ፣ ብራዘርስ ኦፍ ኢታሊ ራሱ ከፋሽስቱ ሞሶሎኒ ዘመን የሚመዘዝ ታሪክ አለው።" https://www.bbc.com/amharic/articles/c16xn3wrk44o +sports ጋና ከኢትዮጵያ ጋር አቻ በመለያየቷ ለዓለም ዋንጫ የማለፍ እድሏ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ ጋና ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያካሄደችውን ጨዋታ አንድ አቻ መለያየቷን ተከትሎ ኳታር ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ውድድር የማለፍ እድሏ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። የጋና ብሔራዊ ቡድን አምበል አንደሬ አዩ በመጀመሪያው አጋማሽ ከቅጣት ምት አስደናቂ ጎል ያስቆጠረ ሲሆን በሁለተኛ አጋማሽ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አምበል ጌታነህ ከበደ ኢትዮጵያን አቻ ማድረግ ችሏል። በመድቡ 4 ነጥብ ብቻ ያላቸው ዋሊያዎቹ ቀድሞውኑ ከውድድሩ ውጪ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ 9 ነጥብ የነበራት ጋና ግን ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን ጨዋታ አሸንፋ ለዓለም ዋንጫ ውድድር ተሳታፊነት ግስጋሴዋን የምታቀናበት ጨዋታ ይሆናል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ስታዲየም የላትም ተብላ በደቡብ አፍሪካ ለመጫወት የተገደደችው ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ነጥብ ተጋርታለች። ጋና እና ኢትዮጵያ በሚገኙበት ምድብ ደቡብ አፍሪካ አንድ ጨዋታ እየቀራት 10 ነጥብ ያላት ሲሆን፤ ዚምባብዌ በተመሳሳይ አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለት በ1 ነጥብ መጨረሻ ላይ ተቀምጣለች። ደቡብ አፍሪካ ዛሬ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ዚምባብዌን በሜዳዋ የምታስተናግድ ሲሆን፤ ደቡብ አፍሪካ ይህን ጨዋታ የምታሸንፍ ከሆነ ምድቡን በአንድኛነት ትጨርሳለች። የአፍሪካ አገራት በ10 ምድብ ሲጫወቱ የቆዩ ሲሆን፤ ከየምድቡ አንደኛ ሆነው የሚጨርሱት ከአራት ወራት በኋላ በደርሶ መልስ ተለይተው አምስት አገራት ኳታር ለምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ አፍሪካን ወክለው ይቀርባሉ። እስካሁን ድረስ ማሊ፣ ግብፅ፣ ሴኔጋል እና ሞሮኮ ከምድባቸው በአንደኛነት ማለፋቸውን ያረጋገጡ አገራት ናቸው። https://www.bbc.com/amharic/news-59249766 +health የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዶ/ር ቴድሮስን ዳግም ዕጩ አድርጎ አቀረበ "የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅቱን ዳግም ለቀጣይ አምስት ዓመታት በዳይሬክተርነት እንዲመሩ ዕጩ አደረገ። ድርጅቱን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት ዶ/ር ቴድሮስ ያለተፎካካሪ ብቸኛ ዕጩ ሆነው የቀረቡ ሲሆን የመጨረሻው ውጤትም ግንቦት 2014 ዓ.ም. ላይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ኃላፊነታቸውን ከአምስት ዓመት በፊት ከመረከባቸው ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የጤና ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል። ዶ/ር ቴድሮስ ከአምስት ዓመታት በፊት ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ የኢትዮጵያ ድጋፍ አልተለያቸውም ነበር። ይሁን እንጂ የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴድሮስ ኃላፊነታቸውን ተጠቅመው ለህወሓት ድጋፍ ያደርጋሉ ሲል በተደጋጋሚ ከሷቸዋል። የዓለም ጤና ደርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በጄኔቭ ለስበሰባ ከመቀመጡ በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት በዶ/ር ቴድሮስ ገለልተኝነት ላይ ምርመራ እንዲያካሂድ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ቦርዱ በዳይሬክተሩ ላይ ምርመራ እንዲደረግ የቀረበውን የኢትዮጵያ ጥያቄ ወደ ጎን በመግፋት ሳይመለከተው ቀርቷል። ዶ/ር ቴድሮስ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ጤና ድርጅትን ለመምራት ዕጩ በሆኑበት ጉዳይ ላይ ለመወያየት በተጠራ የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ስብሰባ ላይ የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ አሞት አቤቱታውን ያልተመለከቱበትን ምክንያት ገልጸዋል። ""ይህ ጉዳይ በጣም የተወሳሰበና ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው፤ ከዚህ ኮሚቴ የአስራር ማዕቀፍ ውጪ ነው"" አሞት ያሉ ሲሆን፤ የቦርዱ 34 አባላት በሙሉ የምርመራ ጥያቄውን ሳይቀበሉት ቀርተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በጉዳዩ ላይ በተወያየበት ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካይ የአገራቸውን አቤቱታ ለማብራራት በመከሩበት ጊዜ እንዲያቋርጡ ተደርገው ነበር። ይህንንም ��ከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ንግግር እንዳያደርጉ መከልከሉ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ተቃውሞውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ ውሳኔው የዓለም ጤና ድርጅት በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ አለመሆኑን ማሳያ ነው ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ቃል አቀባዩ የዓለም ጤና ድርጅት በዶ/ር ቴድሮስ ላይ ምርመራ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ይጠይቃልም ሲሉ ለሮይተርስ ጨምረው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት የድርጅቱን ነፃነት፣ ገለልተኝነት መርህ ጥያቄ ውስጥ እንደከተቱት በመጠየቅ ምርመራ እንዲደረግ አቤቱታ አቅርቦ ነበር። በትግራይ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሲቪልና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓመታት አባልና አመራር የነበሩበትን ህወሓት የሚደግፉ ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ሲሉ ሲከሱ ቆይተዋል። ዶ/ር ቴድሮስ እና የዓለም ጤና ድርጅት የቢቢሲ የጄኔቭ ዘጋቢ ኦሞጂን ፉክስ እንዳለችው የትኛውም የከዚህ ቀደም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር እንደ ዶ/ር ቴድሮስ አልተፈተነም። የኮቪድ-19 ወረርሸኝ፣ ቻይና ስለ ወረርሽኑ መረጃ እንድታጋራ ጫና ማድረግ፣ ከቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የተፈጠረው እሰጣገባ፣ የአሜሪካ ድጋፍ ማቆም እና ከድርጅቱ አባልነት መውጣት በቀዳሚነት የሚወጠቀሱ ሲሆን። ለአንድ ዓመት የዘለቀው የትግራዩ ጦርነት በግል ያደረሰባቸው ጫና እና ከትውልድ አገራቸው መንግሥት ጋር የገቡት ቅሬታ የዶ/ር ቴድሮስ ፈተናዎች ከነበሩት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አሁንም ቢሆን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዝርያውን እየቀረ ዓለም ማሸበሩን አላቆመም፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሁንም የኮቪድ ክትባትን አልወሰዱም። የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኞች በዲሞክራቲክ ኮንጎ ፈጽመውታል በተባለው የጾታ ጥቃት የድርጅቱን የከበረ ስም አጉዱፏል። በሌላ በኩል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የትራምፕን ውሳኔ በመቀልበስ አሜሪካን ወደ የዓለም ጤና ድርጅት አባልነት መልሰዋል። አሜሪካ ለድርጅቱ የምታደርገው ከፍተኛ ድጋፍም ቀጥሏል። በውጣ ውረዶች ውስጥ ያለፉት ዶ/ር ቴድሮስ ግዙፉን የጤና ድርጅት ለሌላ አምስት ዓመታት የመምራት ጽኑ ፍላጎት አላቸው ተብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60133588 +sports ኢትዮጵያ የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በታሪኳ ከፍተኛ የተባለውን ውጤት አስመዘገበች በኮሎምቢያ ካሊ ለስድስት ቀናት ከሐምሌ 25- ሐምሌ 30 2014 ዓ.ም በተካሄደው የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ12 ሜዳሊያዎች ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም ሶስተኛ ሆና አጠናቀቀች። ኢትዮጵያ በስድስት ወርቅ፣ በአምስት ብር እና አንድ ነሃስ ሜዳሊያ በአጠቃላይ በ12 ሜዳሊያዎች አሜሪካንና ጃማይካንም ተከትላ ነው በሶስተኛነት ያጠናቀቀችው። ይህም ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታሪክ የተመዘገበ ውጤት ከፍተኛው እንደሆነ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። “ዘንድሮ የተመዘገበው ውጤት ከፍተኛው ሲሆን ከተሳተፍንበት ውስን የውድድር ተግባራት አንፃር እጅግ የሚያኮራ ውጤት ነው” ብሏል ፌዴሬሽኑ በትናንትናው ዕለት በተጠናቀቀው በዚህ ውድድር አሜሪካ በሰባት ወርቅ፣ በአራት ብርና በአራት ነሐስ ሜዳሊያ በ15 ሜዳሊያዎች በአንደኛነት አጠናቃለች። እሷንም ተከትላ ጃማይካ በስድስት ወርቅ፣ በሰባት ብርና በሶስት ነሃስ በአጠቃላይ 16 ሜዳሊያዎ��� በማግኘት ከፍተኛውን የሜዳሊያ ቁጥር ብትይዝም በአሜሪካ በወርቅ ተበልጣ በሁለተኛነት አጠናቃለች። አፍሪካዊቷ አገር ኬንያ ሶስት ወርቅ፣ ሶስት ብርና አራት ነሐስ በማግኘት በአጠቃላይ በአስር ሜዳሊያዎች በአራተኛነት ውድድሩን ማጠናቀቋን ከአለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘው መረጃ ያሳያል። በዚህ በተካሄደው የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ የሻምፒዮና ውድድር ላይ ኤርምያስ ግርማ በ800 ሜትር ወርቅ በማግኘት እንዲሁም በ1500 ሜትር ብር በማግኘት የጥምር ሜዳሊያዎች ባለቤት ሆኗል። በአንድ ሺህ ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ውድድር ብርቄ ሃየሎም የሻምፒዮኑንሺፕ ክብረ ወሰን በማሻሻል በአንደኛነት ወርቅ አስመዝግባለች። ሴት አትሌቶች በደመቁበትና በቅርቡ በተደረገው የኦሪጎን አትሌቲክሽ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በአስር ሜዳሊያዎች በታሪኳ ከፍተኛውን ሜዳሊያ ማስመዝገቧ ይታወሳል። ኢትዮጵያ በ4ወርቅ፣ በ4ብርና በ2 ነሃስ ከአዘጋጇ አሜሪካ በመቀጠል ከዓለም 2ኛ ደረጃ ከአፍሪካ አንደኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወሳል። የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ወይም የአለም  ጁኒየር የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ከ20 አመት በታች ባሉ አትሌቶች የሚደረግ አለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ነው። ባለፈው አመት በነበረው ውድድር ኬንያ በስምንት ወርቅ በአጠቃላይ በአስራ ስድስት ሜዳሊያ በአንደኛነት ነበር ያጠናቀቀችው፣ ኢትዮጵያ በወቅቱ ሶስት ወርቅ፣ ሰባት ብር፣ ሁለት ነሐስ በአጠቃላይ 12 ሜዳሊያ በማግኘት ውድድሩን በአራተኝነት ነበር ማጠናቀቋ ይታወሳል። በዘንድሮው አመት በ5000 ሜትር ብር ያስገኘችው መልክናት ውድ ባለፈው አመት ሁለት ሜዳልያዎችን አስገኝታ ነበር። ከ20 አመት በታች ለተደረገው የሻምፒዮንሺፕ ውድድር ኢትዮጵያ 19 አትሌቶችን መላኳን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ የሚያስረዳ ሲሆን በሁለቱም ጾታዎች በአስር አይነት ውድድሮች ተሳትፈዋል። ለስድስት ቀናት በካሉሊ ኮሎምቢያ በተደረገው ውድድር በአጠቃላይ 41 ሃገራት ቢያንስ አንድ ሜዳሊያ ሲያሸንፉ 24 ሃገራት ደግሞ ቢያንስ አንድ ወርቅ ማግኘታቸውን ከአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cyrgemvd2y3o +sports የኦስካር ሽልማት፡ ዊል ስሚዝ በታላቁ የሽልማት መድረክ ላይ ክሪስ ሮክን በጥፊ ተማታ "ተዋናይ ዊል ስሚዝ ኦስካርስ በተሰኘው የፊልም ጥበብ የሽልማት መድረክ የሚስቱን ስም አንስቶ ያብጠለጠለውን ታዋቂውን ኮሜዲያን ክሪስ ሮክን በጥፊ ተማታ። ክሪስ ሮክ፤ የዊል ስሚዝ ሚስት ጄዳ ፒንኬት ስሚዝን የፀጉር ቁርጥ በቀልድ ወረፍ ካደረገ በኋላ ነው ይህ የተከሰተው። ዊል ስሚዝ ከመቀመጫው በመነሳት ወደ መድረኩ አቅንቶ ክሪስ ሮክን በጥፊ አጋጭቶ ሲመለስ ብዙዎች ጉዳዩ ቀልድ ነው ብለው አስበው ነበር። ነገር ግን ወደ ወንበሩ ከተመለሰ በኋላ ""የሚስቴን ስም በ. . . አፍህ አታንሳ"" ብሎ ሲጮህ ነው ብዙዎች ተዋናዩ ማምረሩን የተረዱት። ስሚዝ ከዚህ ብዙዎችን ካስበረገገ ድርጊት በኋላ የኦስካር ሽልማቱን ሲያነሳ ለድርጊቴ ይቅርታ በሉኝ ብሏል። ""አካዳሚውን [ኦስካር ሸላሚው ኮሚቴ] እንዲሁም ለሽልማት የታጩ የተውኔት አጋሮቼን ይቅርታ መጠየቅ እሻለሁ"" ሲል ተማፅኗል። ዊል ስሚዝ፤ ኪንግ ሪቻርድ በተሰኘው ፊልም ላይ የቴኒስ ከዋክብቱን ቬነስና ሰሪና ዊሊያምስ አባት ሆኖ በመተወኑ ነው በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለስም የከበደውን የኦስካር ሽልማት ያገኘው። ""ጥበብ የሕይወት ቅጂ ናት። ልክ እንደ ተወንኩት ሪቻርል ዊሊያምስ የእብደት ሥራ ሠርቻለሁ። ነገር ግን ፍቅር የእብድ ሥራ እንድትሠሩ ያደርጋችኋል።"" ባለቤቱ ፒንኬት ስሚዝ ከዚህ በፊት የፀጉር መነቀል የሚያስከትል 'አላፒሺያ' የተሰኘ በሽታ እንዳለባት ተናግራ ነበር። የዊል ስሚዝ ጥፊ ሰላባ የሆነው ክሪስ ሮክ በሁኔታው እጅግ ተደናግጦ ""በቴሌቪዥን ታሪክ እጅግ አስደናቂውን ክስተት ታድመናል"" ሲል ተደምጧል። ክሪስ ሮክ ወደ መድረክ የወጣው በምርጥ የዘገባ ፊልም ዘርፍ አሸናፊ ለሆነው ግለሰብ ሽልማት ለመስጠት ነበር። ሎስ አንጀለስ በሚገኘው ዶልቢ ቲያትር በተባለው ግዙፍ መድረክ ላይ ዊል ስሚዝ የፈፀመው ድርጊት ብዙዎችን አጀብ አሰኝቷል። ብዙዎች ዊል ስሚዝ የሙያ አጋሩን በጥፊ ያጋጨው እየቀለደ እንዳልሆነ የገባቸው ወደ መቀመጫው ተመልሶ አፀያፊ ቃል ከተጠቀመ በኋላ ነው። የሽልማት ሥነ ሥርዓቱን በቴሌቪዥን ሲያሰራጭ የነበረው ኤቢሲ የተሰኘው ጣቢያ ይህን የዊል ስሚዝ ንግግር ከማስተላለፍ ተቆጥቧል። ፒንኬት ስሚዝ ፌስቡክ ላይ በምታሰራጨው ሬድ ቴብል ቶክ በተሰኘው ዝግጅት ላይ ፀጉር የሚያሳጣ በሽታ እንዳለባት ይፋ ያደረገችው ከአራት ዓመታት በፊት ነበር። ""ለመጀመሪያ ጊዜ ፀጉሬን እየታጠብኩ ተነቅሎ ሲወድቅ በጣም ደንግጬ ነበር። ለዚህ ነው ብዙውን ጊዜ ፀጉሬን የምላጨው።"" ዊል ስሚዝ የባለቤቱ ስም ተነስቶ ሲብጠለጠል ሊዋጥለት ባለመቻሉ ከኦስካርስ ሽልማት ታሪክ የማይፋቅ ድርጊት ፈፅሟል። ከዚህ ድርጊት ለጥቆ ደግሞ በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦስካር ሽልማት በማንሳት ሌላ ታሪክ ፅፏል። ሽልማቱን ለመቀበል ወደ መድረኩ ድጋሚ ካቀና በኋላ የይቅርታ ቃሉን አሰምቶ ንግግር ሲያደርግ አምላኩን አመሰግኗል። ""በዚህ ቢዝነስ [የፊልም ዓለም] ውስጥ እስካለን ድረስ ሰዎች ስለኛ የማይሆን ነገር ሲያወሩ ሰምቶ እንዳልሰሙ ማለፍን መቀበል እንዳለብኝ አውቃለሁ። ሰዎች እኛን የሚያንቋሽሽ ነገር ሲያደርጉ ፈገግ ብለን ማለፍ እንዳለብን እረዳለሁ"" ብላል ስሚዝ። ""መቼም በቀጣይ ዓመትም እንደምትጋብዙኝ ተስፋ አለኝ"" በማለት ነው ዊል ስሚዝ ንግግሩን የቋጨው።" https://www.bbc.com/amharic/news-60897684 +sports ኢትዮጵያ፡ የቴኳንዶ ሦስተኛ ዳን ባለቤቱ የአካል ጉዳተኛ ከማል ቃሲም ነዋሪነቱ በባሕርዳር ከተማ የሆነው ከማል ቃሲም አንድ እግሩን ያጣው በልጅነቱ ከቆመ ታንክ ላይ ሲጫወት ነበር። በአንድ ወቅት ጓደኞቹ ቴኳንዶ ሲሰሩ አይቶ ምነው እንደ እነሱ ሁለት እግር ኖሮኝ ስፖርቱን ሙያዬ ባደረግኩት ብሎ ተመኘ። ቅን አሳቢ ጓደኞቹ ግን በአንድ እግርም ህልሙን እውን ማድረግ እንደሚችል ነገሩት። ለመሞከር አላመነታም። ያኔ እንደዋዛ የጀመረው የቴኳንዶ ስፖርት ዛሬ ሦስተኛ ዳን እንዲደርስ አስችሎታል። በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችንም አሰልጥኗል። https://www.bbc.com/amharic/news-54325094 +business ኬንያ በጥራት ስጋት ምክንያት ታዋቂ የምግብ ዘይት ምርቶችን አገደች ኬንያ ከጤናና ጥራት ጋር በተያያዘ ስጋት ምክንያት 10 ታዋቂ የምግብ ዘይት ምርቶች ገበያ ላይ እንዳይውሉ እገዳ ጣለች። የኬንያ ደረጃዎች ተቆጣጣሪ ኬብስ በችርቻሮ ለሚሸጡ ሱቆች እና መገበያያ መደብሮች በጸፈው ደብዳቤ ላይ እነዚህ ምርቶች መደበኛ የጥራት ፈተናዎችን ማለፍ አልቻሉም ብሏል። እነዚህ ምርቶች ከሽያጭ መደርደሪያዎች በአስቸኳይ እንዲወርዱ ትዕዛዝ ተላልፏል። ተቋሙ የተላለፈው ትዕዛዝ ሙሉ እገዳ ሳይሆን አምራቾቹ የተወሰኑ የጥራት መስፈርቶችን እስካሟሉ ድረስ ጊዜያዊ እገዳ መሆኑን አብራርቷል። ትልልቅ የመገበያያ መደብሮችንና ትላልቅ ቸርቻሪዎችን ላቀፈው የኬንያ የችርቻሮ ነጋዴዎች ማህበር ተቋሙ በጻፈው ደብዳቤ የተጠቀሱት የምግብ ዘይት ምርቶች ወደ ገበያ ከመመለሳቸው በፊት የጥራት ማረጋገጫ ማግኘታቸው ሊረጋገጥ እንደሚገባም አሳስቧል። እነዚህ 10 የምግብ ዘይት ምርቶች የሚመረቱ በኬንያ የሚጠቀሱ አራት ትልልቅ የምግብ ዘይት ኩባንያዎች ሲሆኑ እነሱም ቢድኮ አፍሪካ፣ ፕዋኒ የዘይት አምራች፣ ካቻ የዘይት ማጣሪያ እና ሜኔንጋይ የዘይት ማጣሪያ ናቸው። ቢቢሲ ሁለቱን ኩባንያዎች ምላሽ የጠየቃቸው ሲሆን እስካሁን ድረስ ምላሽ አልሰጡም። ጉዳዩን ለመፍታት ተቋሙ እና ዘይት አምራቾቹ በዛሬው ዕለት አርብ እንደሚገናኙም የኢንዱስትሪ ምንጮች ገልጸዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cw4g29l2ey7o +business መንግሥት ያጋጠመውን ተጨማሪ ወጪ ለመሸፈን የ122 ቢሊዮን ብር የበጀት ጥያቄ አቀረበ የገንዘብ ሚኒስቴር በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ተጨማሪ ወጪ በማስፈለጉ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ጥያቄ አቀረበ። ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ተጨማሪ ገንዘብ በማስፈለጉ እና መንግሥት በሚሰበስበው ገቢ ያለውን የክፍያ ጥያቄ መመለስ አዳጋች በመሆኑ እንዲሁም ያለውን የተጨማሪ ወጪ በበጀት ሽግሽግ መሸፈን ባለመቻሉ ተጨማሪ በጀት ማዘጋጀት አስፈልጓል። ይህ ተጨማሪ በጀት ለአገር ደኅንነት ማስጠበቂያ፣ ለሰብአዊ እርዳታ፣ በጦርነትና ግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ማቋቋሚያ እንዲሁም ለሌሎች አስፈላጊ የመንግሥት ሥራዎች ማስፈጸሚያነት የሚውል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አመልክቷል። ትግራይ ውስጥ ተቀስቅሶ አንድ ዓመት በላይ የሆነው ጦርነት ወደ አማራና አፋር ክልሎች በመስፋፋት ከፍተኛ ውድመትን ያስከተለ ሲሆን መንግሥትን ከፍተኛ ወጪ በማስወጣት በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩ ይነገራል። ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ያጋጠሙ ወጪዎችን ለመሸፈን ባለፈው ዓመትም 26.4 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት መጽደቁ ይታወሳል። በወቅቱ እንደተገጸው በ2013 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት ያስፈለገው በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከተከሰተው ጦርነት ጋር ተያይዞ ላጋጠሙ ወጪዎች፣ በድርቅ ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ እና ለተመላሾች የእለት እርዳታ አቅርቦት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል፣ ለማዳበሪያ አቅርቦት ድጎማ፣ ለጎርፍ መከላከል ነበር። በዚህ ዓመት በገንዘብ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ የቀረበው የተጨማሪ በጀት ጥያቄ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከአራት እጥፍ በላይ ጨምሮ 122 ቢሊዮን ብር ደርሷል። ይህ የተጨማሪ በጀት ጥያቄው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ታይቶ ለሕህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚቀርብ ሲሆን፣ ተቀባይነት ካገኘ በቀጥታ ሥራ ላይ እንደሚውል የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። ባለፈው ዓመት፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ2014 ዓ.ም ከፍተኛውን ዓመታዊ በጀትን ማጽደቋ ይታወሳል። የአገሪቱ ዓመታዊ በጀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመሄድ ላይ ሲሆን የዚህ ዓመት በጀት ግን 561 ቢሊዮን ብር ሆኖ በሚኒስትሮች ምክር ቤትና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል። ይህም በጀት ከ2013 ዓ.ም በ85 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሎ በአገሪቱ መንግሥት የበጀት ታሪክ ከፍተኛው ለመሆን ችሏል። አሁን የተጠየቀው ተጨማሪ በጀት ሲታከልበት ደግሞ አጠቃላይ የዓመቱ በጀት ከ680 ቢሊዮን ብር በላይ ይሆናል። https://www.bbc.com/amharic/news-59827779 +politics “ጃል አብዲ ረጋሳ ከአገር ሳልወጣ ያየሁትን እንዳልናገር አስጠንቅቆኛል” ታምራት ነገራ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ከታዩት የህትመት ሚዲያዎች መካከል ከፍ ያለ ተነባቢነት እና ዝናን አትርፋ የነበረችው የ“አዲስ ነገር” ጋዜጣ ባልደረቦች ከነበሩት መካከል አንዱ የሆነው ታምራት ነገራ ዳግም ለስደት ተዳርጓል። ታምራት ነገራ እና የአዲስ ነገር ባልደረቦች በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ይመራ ከነበረው መንግሥት በገጠማቸው ጫናና ስጋት ከአገር ተሰደው ለዓመታት መቆየታቸው ይታወሳል። ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐ���ይ አሕመድ አስተዳደር ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎ ባካሄዱት ለውጦች ተበረታተው ወደ አገር ቤት ከተመለሱት የጋዜጣዋ ባልደረቦች መካከል ታምራት ነገራ አንዱ ነው። ለዓመታት ከቆየባት አሜሪካ የተመለሰው ታምራት ባለፉት አራት ዓመታት በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ላይ ወቅታዊ ፖለቲካዊ ትንታኔዎችን በመስጠት እና በመንግሥት ላይ ጠንካራ ትችቶችን በመሰንዘር ይታወቃል። ኋላ ላይም “ተራራ ኔትወርክ” የተባለውን የራሱን የዩቲዩብ ቻናል በመጀመር ዜና እና ትንታኔዎችን ሲያርብ ቆይቷል። ነገር ግን ባለፈው ዓመት ታኅሣሥ መጀመሪያ ላይ በፀጥታ ኃይሎች ከቤቱ ተወስዶ ለአራት ወራት ያህል በእስር ከቆየ በኋላ በዋስ መፈታቱ ይታወሳል። ታምራት መጋቢት ወር ማብቂያ ላይ ከእስር ከተፈታ በኋላ ወደ ሥራው ሳይመለስ ለወራት ድምጹ ሳይሰማ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ከባለቤቱ ጋር ዳግም ወደ ስደት ተመልሷል። ታምራት አሁን እንዳይጠቀስ ከፈለገው በስደት ካለበት ስፍራ ስለእስሩ፣ በዝምታ ስለቆየበት ምክንያት፣ ስለወደፊት ዕቅዱና ስለሌሎች ጉዳዮች በተለይ ከቢቢሲ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ቢቢሲ፡ መሰደድህን የሚገልጥ ዜና ባሳለፍነው ሳምንት ተመልክተናል። በርግጥም ስደትን መርጠሃል? ለምን? ታምራት ነገራ፡ አዎ መሰደዴን የሚገልጸው ዜና እውነት ነው። ለመሰደድ የወሰንኩባቸው ምክንያቶች ግልጽ ናቸው። የታሰርኩበት ሁኔታ፣ ከታሰርኩ በኋላ ብሎም በዋስ ከተለቀቅሁ በኋላ ወደ ጋዜጠኝነት ለመመለስ የሚያስፈልጉ ነገሮች አልተሟሉም። እንዲያውም አደጋዎች እየጨመሩ መጡ። የኦሮሚያ ፖሊስ ስታስር የወሰዳቸው ከ32 በላይ የስቱዲዮ እቃዎችን አልመለሰልኝም። ይሄ የእኔ ብቻ ሳይሆን የተራራ ኔትወርክ ሠራተኞች ንብረት የሆኑም ይገኙበታል። ባለቤቴ ሰላም በላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ፍርድ ቤት፣ ፖሊስ ኮሚሽን በመሄድ “ታምራት ላይ ክስ ትመሰርታላችሁ ወይ፣ ምርመራ ጨርሰናል ብላችኋል፣ ንብረታችንን ትመልሳላችሁ ወይ?” የሚሉ ጥያቄዎችን በማመልከቻ ጭምር አቅርባ ነበር። ያገኘችው ምላሽ ግን “አይበቃችሁም ወይ?”፣ ወደ ሥራም ለመመለስ ታስባላችሁ ወይ?” በሚል ማስፈራሪያው ከእኔ አልፎ ቤተሰቤ ላይ እና ሠራተኞች ላይ መምጣቱ ሌላው የመሰደዴ ምክንያት ነው። ማስፈራሪያው እየጨመረ መጥቶ ለቅሶ ቤት፣ ሠርግ ወይም በአደባባይ ከተገኘሁ “ለምን ዐይንህን እናያለን?” የሚሉ የደኅንነት እና የፖሊስ ኃይሎች እየታዩ ስለመጡ አገር ውስጥ መኖር አሳሳቢ እየሆነ መጣ። ከእኔ ባሻገር ግን ሌሎች ጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው እስር እና እንግልት ብሎም በአጠቃላይ ሚዲያ ላይ የሚደረገው አፈና እየበረታ መምጣቱ በቀጣይነት ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ የሚዲያ ሥራ መስራት ይቻላል የሚለውን እምነቴን ሙሉ ሉሙሉ ስለዘጋው፣ የሚዲያ ሥራውንም ለመስራት ብሎም በሰላም ለመኖር ከአገር መውጣት አስገዳጅ ሆኖ ስላገኘነው እኔ እና ባለቤቴ ወጥተናል። ባለፉት ወራት ታስሬ በነበረበት ብሎም ከተፈታሁ በኋላ ከፍርድ ቤት፣ ከዐቃቤ ሕግ፣ ከፖሊስ ብሎም ተራራ ኔትወርክን ማስተዳደርን ጨምሮ ይህንን የሕይወት ጉዞ ያለ ባለቤቴ ሰላም በላይ እገዛ እና አብሮነት ላልፈው አልችልም ነበር። ብዙዎች ከሚያውቁት በላይ ነው የሰላም ሚና። ተራራ እንዲቋቋም ብሎም በእግሩ እንዲቆም ያደረገችው። አንደኛው እንድሰደድ ምክንያት የሆነኝም ባለቤቴን ወደ እነዚያ 7 ቀናት [ፍርድ ቤት ሳይቀርብ፣ ያለበት ሳይታወቅ የቆየባቸው] መልሶ ለመውሰድ የሚያስችል ጭካኔ ስለሌለኝ ነው። ከብዙ የቤተሰብ እና የግል የኑሮ ጫና ጋር በፖሊስ፣ በፌደራል ብሎም በክልል ዐቃቤ ሕግ፣ በፍርድ ቤት ምን አይነት እንግልት እንደደረሰባት ለመናገር አልችልም። ስለዚ�� አንዱ ለመሰደድ እንድመርጥ ያደረገኝ በእሷ ትከሻ ላይ የነበረው ጫና ነው። አብረን እንድንሰደድ ያደረገው አንዱ ምክንያትም እሱ ነው። ቢቢሲ፡ በቁጥጥር ስር ከዋልክ በኋላ ያለህበትን ለማወቅ እና ፍርድ ቤት እስከምትቀርብ ድረስ 7 ቀናት ጠይቋል። የት ነበር የተወሰድከው? እዚያ የነበረህ ቆይታ ምን ይመል ነበር? ታምራት ነገራ፡ በቁጥጥር ስር ከዋልኩ በኋላ ለ7 ቀናት ፍርድ ቤት አልቀረብኩም፣ ቤተሰብም የት እንዳለሁ ማወቅ አልቻለም ነበር። በወቅቱ ወደ ገላን ከተማ ተወስጄ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ነበር የቆየሁት። ካምፕ መሆኑን ያወቅሁት በቁጥጥር ስር ያዋሉኝ ፖሊሶች ዩኒፎርማቸውን በማየት ነው። ይህ ካምፕ የኢትዮጵያ መንግሥት ብሎም የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የግድያ እና የስቅይት ካምፕ ነው። ለሰባት ቀናትም ለብቻዬ ከሌሎች ታሳሪዎች ጋር በማልገናኝበት ክፍል ውስጥ ነበር የታሰርኩት። በእነዚህ ቀናት ለእኔ የጮሁ ሰዎችን በሙሉ በዚህ አጋጣሚ በእግዚአብሔር ስም ማመስገን እፈልጋለሁ። ይህ ጫና ባይኖር ኖሮ ምን አልባትም በሕይወት ላልኖር እችል ነበር። ቢቢሲ፡ ከተፈታህ በኋላ ዝምታን መርጠህ ነበር። ለምን? ከዚያ ስለምን ተመልሰህ ወደ ሚዲያህ አልመጣህም? ታምራት ነገራ፡ ዝምታን የመርጥኩበት ብዙ ምክንያቶች አሉ። አንደኛው እንደተፈታሁ ለመናገር ያሰብኳቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ። በተለይም እስር ቤት ውስጥ ያገኘኋቸው በፖለቲካም፣ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትም ሆነ የፖለቲካ አቅጣጫ ላይ የማልስማማቸው ብዙ ሰዎችን አግኝቻለሁ። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች አጽንተው የተናገሩት እዚህ እስር ቤት ያየኽውን ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነህ እንድትናገር አንፈቅድልህም ነው ያሉኝ። ከቤተሰቤም በፊት ማለት ነው። በተለይም ጃል አብዲ ረጋሳ [የኦነግ ከፍተኛ አመራር እና በእስር ላይ ያሉ ፖለቲከኛ] በዐቢይ አሕመድ አስተዳደር በግሉም ሆነ በቤተሰቡ ላይ ብዙ መከራ፣ ስቃይ ብሎም ከፍተኛ የሚባለውን ግፍ ካዩ ሰዎች አንዱ ይመስለኛል። እርሱ አጥብቆ ያስጠነቀቀኝ ነገር፣ “ከኢትዮጵያ ሳትወጣ የምንነግርህንም ሆነ ያየህውን ነገር እንዳትናገር” ብሎ ነው። ሁለተኛው የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይም በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ በተቀበሩ የጨለማ እስር ቤቶች ውስጥ የሚፈጽመውንና ያየሁትን ሳልናገር ወደ ሚዲያ ሥራው መመለስ አልችልም። እንደ ጋዜጠኛም ሆነ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ይህንን ሳልናገር ሚዲያ መስራት አልችልም። ይህንን የምናገርበት ቀን ይመጣል። ብዙ መረጃዎች የያዘዝኩት አለ። ይህንንም በቅርቡ ይፋ አደርጋለሁ። ያንን እንዳላደርግ የእነ ጃል አብዲ ማስጠንቀቂያ ብሎም ቤተሰብ አለ። ሦስተኛው ደግሞ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነታ ለሚዲያ የሚመች አይደለም። ስለዚህ የምናገር ከሆነ፣ የምናገረው እውነት መሆን አለበት። እውነትን ለመናገር ደግሞ እውነትን ለመናገር የሚቻልበት ቦታ ላይ መሆን ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት እውነትን ለመናገር የሚቻልበት ቦታ ናት ብዬ አላምንም። ሁኔታዎች ከተቀየሩ ብዬ 7 ወር ያህል ቆየሁኝ። ያለው ነገር ይበልጥ እየባሰ መጣ። ቢቢሲ፡ በስደት ከምትኖርበት አሜሪካ ስትመለስ ይዘህ የመጣህውን ተስፋ እና አሁን ለዳግም ስደት ስትዳረግ ያለህን ስሜት አነጻጽረህ ንገረኝ እስቲ? ታምራት ነገራ፡ የዛሬ አራት ዓመት ከስደት ተመልሼ ስመጣ እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙዎቻችን ተስፋ ነበረን። አሁን ተስፋ አስቆራጭ ነገር አለ። ተስፋ የቆረጥኩት አሁን ባለው መንግሥት እና አገዛዝ እንጂ በኢትዮጵያ አይደለም። ሥርዓቱ ተስፋ የሚቆረጥበት ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያ ላይ ተስፋ አልቆርጥም። በአሁኑ ወቅት ኢት���ጵያ ውስጥ የሚዲያ ሥራ ለመስራት አስቸጋሪ ነው። ሚዲያ አንዱ ጎኑ ንግድ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የትኛውንም ንግድ ለማንቀሳቀስ ያለው ሕገ መንግሥት፣ ብሔርተኝነት እና ዘረኝነት እየታየ ሥራ ለመስራት የሚቻልበት ሆኖ አይታይም። ስለዚህ ከአራት ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲታይ አሁን ያለው ነገር ተስፋ ያስቆርጣል፤ ተስፋ የምንቆርጠው ግን በገዢዎቹ ላይ እንጂ በኢትዮጵያ ላይ አይደለም። ቢቢሲ፡ ከዚህ በኋላ ወደ መገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ትመለሳለህ? ታምራት ነገራ፡ የመገናኛ ብዙኃን ሥራ በውስጤ ስለሆነ የትም ብሄድ፣ ምንም ቋንቋ ብናገር ከውስጤ የማይቀር ሥራ ስለሆነ አይቀርም። ስለዚህ ወደ መገናኛ ብዙኃን ሥራ እመለሳለሁ። እመለሳለሁ ብቻ ሳይሆን የተራራ ኔትወርክ የኢትዮጵያዊነት ድምጽ መሆኑን ይቀጥላል። ተጠናክረን እና ከባለፈውም በበለጠ ነጻ በሆነ ሁኔታ ይቀጥላል። ስለኢትዮጵያ ተስፋ መስጠታችንን፣ ማስተማራችን እና ድምጽ መሆናችን አይቀርም። ቢቢሲ፡ በቆይታህ ካከናወንከው ውስጥ ማድረግ አልነበረብኝም እና ሳላደርግ የቀረሁት የምትለው? ታምራት ነገራ፡ ከመታሰሬ አንድ ቀን በፊት ሦስት አዲስ ተመራቂ ልጆችን ቀጥረን ጨርሰን ነበር። ሙሉ ሂደቱን ጨርሰን ነበር። እና በጣም የሚቆጨኝ ወጣቶችን እና የሚቀጥለውን ትውልድ አገሬ ውስጥ ሆኜ ያለችኝን መጠነኛም ብትሆን የጋዜጠኝነት እውቀት ላሳያቸው እፈልግ ነበር። የዲጂታል ጋዜጠኝነትን በአዲስ መልኩ መስራት ፈልጌ ነበር። የተራራ ኔትወርክን ለመደገፍ በተሰበሰበ ገንዘብ የተገዙ የስቱዲዮ እቃዎች በመንግሥት እጅ ውስጥ ወድቀዋል። ነገር ግን እሱ አይደለም የሚያሳስበኝ። የሚያሳስበኝ ለወጣት ጋዜጠኞች በአገሬ ውስጥ ሆኜ ጋዜጠኝነትን ለማሳየት ባለመቻሌ ነው። ቢቢሲ፡ ወደ ኢትዮጵያ መቼ እመለሳለሁ ብለህ ታስባለህ? ኢትዮጵያ እንዴት ሆና እንድትጠብቅህ ትፈልጋለህ? ታምራት ነገራ፡ ወደ ኢትዮጵያ ልመለስ እችላለሁ፤ ሁኔታዎች ከተቀየሩ። ዋናው የሚያሳስበኝ ግን መመለስ ያለመመለስ አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ውጪ ላለው የምትሆን አገር እንዴት ነው ማድረግ የሚቻለው የሚለው ጥያቄ ነው የሚያሳስበኝ። ይሄ ደግሞ የእኔ ብቻ ጥያቄ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ነው። በዚህ ላይ ያለኝን አስተዋጽኦን ከውጪም ሆኜ ቢሆን አበረክታለሁ ብዬ አምናለሁ። ኢትዮጵያውያን የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ እስከምናይ ድረስ አናቆምም። አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ለማንም የምትሆን አይደለችም። ሁልጊዜ እንደምለው እስራኤላዊያን እስራኤል ከፈረሰች ከሁለት ሺህ ዓመት በኋላ መልሰው ገንብተዋታል። ኢትዮጵያ የመፍረስ አደጋ እንዳለባት ሁላችንም እናውቃለን። ኢትዮጵያ እንድትቆም የምንፈልገው ሰዎች ብንችል በዘመናችን እናቆማታለን፤ ባንችል በቃል አቁመናት ያ ቃል ነገ ከሺህ ዓመታትም በኋላ ይሁን ኢትዮጵያን መልሶ የሚሰራ እንዲሆን ማድረግ ግዴታ አለብን ባይ ነኝ። ቢቢሲ፡ በቅርቡ ከኢሠፓ መልሶ ምሥረታ ጋር ስምህ በተደጋጋሚ ተነስቶ ነበር። በዚህ ዙሪያ ምን ምላሽ አለህ? ታምራት ነገራ፡ ከኢሠፓ ምሥረታ ጋር ስሜ መነሳቱ ለእኔም ዜና ነው። ምንም የማውቀው ነገር የለም። እኔ የኢሠፓ አባልም ደጋፊም አይደለሁም። በወቅቱ ግን ይህንን ማስተባበል አስፈላጊ ስላልነበረ አላስተባበልኩም። ከዚህ በተጨማሪ ግን ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ግንኙነት እንዲኖረኝ አልፈልግም። በወጣትነት ዘመኔ ከቅንጅት ጋር ተሳትፌያለሁ፤ ተመራጭ ነበርኩ። ፖለቲካ ፓርቲን ከምሥረታው በቅርብ ርቀት አይቼዋለሁ። ቅንጅትን ያፈረሱትም ሆነ ለማሰቀጠል የሞከሩት አመራሮች ጋር በቅርበት ሰርቼ የፖለቲካ ፓርቲን አሰራር ኢትዮጵያ ��ስጥ ምን እንደሆነ አይቼዋለሁ። እኔ የፖለቲካ ፓርቲ ኢትዮጵያን ያድናል የሚል እምነትም የለኝም። ለዚህም ነው ወደ ሚዲያ ሥራ የማተኩረው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c165znkrl12o +health እስራኤል 5 ሺህ አዕዋፋትን የገደለውን 'የአቪያን ፍሉ' ወረርሽኝ ለመቆጣጠር እየጣረች ነው "በእስራኤል ከባዱና የአዕዋፋት ዝርያን የሚያጠቃው የአቪያን ፍሉ ወረርሽኝ መቀስቀሱን ተከተሎ አገሪቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተርኪ የተባሉ የዶሮ ዝርያዎችን እያስወገደች ነው። የአገሪቱ አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ታማር ዛንድበርግ፤ በእስራኤል ታሪክ ውስጥ ""በዱር እንስሳት ላይ የከፋ ጉዳት"" ሲሉ በገለጹት ወረርሽኝ ሳቢያ በሁላ የተፈጥሮ ጥብቅ ስፍራ ከ5,000 በላይ የሚሆኑ እና የሚፈልሱ 'ክሬንስ' ተብለው የሚታወቁ የአዕዋፋት ዝርያዎች ሞተዋል። የአገሪቱ አርሶ አደሮችም ወረርሽኙን ለመከላከል በሚል ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ተርኪ ዶሮዎችን እንዲያስወግዱ እየተገደዱ ሲሆን፤ ይህም በእስራኤል የእንቁላል እጥረት ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። እስካሁን ይህ አዕዋፋቱን የሚያጠቃው ቫይረስ ወደ ሰው ስለመተላለፉ አልተረጋገጠም። ሆኖም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናታሊ ቤኔት በሽታው ወደ ሰዎች እንዳይተላለፍ በሚደረገው ጥረት ዙሪያ ለመወያየት ሰኞ ዕለት የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪያቸውን እና ሌሎች ባለሙያዎችን ማነጋገራቸው ተሰምቷል። በበሽታው ከተያዙ አዕዋፋት ጋር የቅርብ ግንኙነት ወይም ንክኪ የነበራቸው ሰዎች የመከላከያ ሕክምና እየተደረገላቸው ነው። አቪያን ፍሉ ከአዕዋፋት ወደ ሰው የመተላለፍ ዕድሉ ጠባብ ቢሆንም እንደ አውሮፓውያኑ ከ2003 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ 456 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አሳውቋል። ከእስራኤል ተፈጥሮ እና ፓርኮች ባለሥልጣን የወጡ ምስሎች፣ ሌሎች የዱር እንስሳት በወረርሽኙ እንዳይያዙ ለመጠበቅ ከሁላ ሐይቅ የሞቱ ክሬኖችን ለማንሳት የተሰማሩ ባለሙያዎችን ያሳያል። ሁላ በተሰኘው ጥብቅ ስፋራ ዙሪያ ባለው ሸለቆ ውስጥ የ250 ክሬኖች ቅሪቶች መታየታቸውን እና 30ዎቹ ደግሞ ታመው በአገሪቱ ሌላ ስፍራ መታየታቸውንም ባለሥልጣኑ ገልጿል። ከአውሮፓ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እነዚህ አዕዋፋት በሁላ የተፈጥሮ ጥበቅ ስፍራ ላይ ሲከርሙ ማየት ብዙውን ጊዜ ለወፍ አድናቂዎች አስደሳች ክስተት ነው። ነገር ግን ጣቢያው ባለፈው ሳምንት ለጎብኝዎች ዝግ የተደረገ ሲሆን ምክንያቱ ድግሞ ከባድ እንደሆነ የተገለጸው በአቪያን ፍሉ ወረርሽኝ ነው። ምልክቶች የማይታዩበት አቪያን ፍሉ በባሕርያቸው ከቦታ ቦታ በሚፈልሱ ወፎች ላይ የሚከሰት ነው። በአገር ውስጥ ያሉ ወፎች ለዚህ ወረርሽኝ ያላቸው ተጋላጭነት ዝቅተኛ ቢሆንም ቫይረሱ ለሽያጭ በቀረቡ ወይም በቤተሰብ ውስጥ በሚራቡ የአዕዋፍ ዝርያዎች ላይ ከተገኘ ግን ሁሉንም በፍጥነት ማስወገድ ይመከራል። በሰሜን እስራኤል 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሞሻቭ ማርጋዮት በተሰኘው የጋራ ማርቢያ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ እንቁላል የሚጥሉ ዶሮዎች ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እና በሰዎች ላይ ያለውን አደጋ ለመቀነስ እየተገለሉ መሆኑን የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ሞሻቭ በእስራኤል ውስጥ ጥቅም ላይ ከሚውሉ እንቁላሎች 7 በመቶውን ያቀርባል። ታይምስ ኦፍ እስራኤል የተሰኘው ሚዲያ እንደዘገበው በእስራኤል የመጀመሪያው የአቪያን ፍሉ ወረርሽኝ እንደ አውሮፓውያኑ ጥቅምት 18 ተመዝግቧል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59815430 +sports ማንቸስተር ሲቲ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አደጋ? "እጅግ ድንቅ ፉክክር የታየበት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ያለፈው ወድድር ዘመን እነሆ በአዲሱ ተተክቷል። አውሮፓ ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ የዓለማችን ልጥጥ ክለቦች የሚገኙበት ቢሆንም አደጋ የተጋረጠበት ይመስላል። አደጋው ደግሞ የባለፈው ውድድር ዘመን ቻምፒዮና - ማንቸስተር ሲቲ፤ ይላል የቢቢሲ ስፖርት ተንታኙ ቤን ሱዘርላንድ። •ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ፡ «ስለተተከሉት ዛፎች ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ የለም» •""የት ይቀርልሃል!? አፈር ድሜ ትበላለህ...!"" ጋሽ አበራ ሞላ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ተወዳጅ እንዲሆን ካደረጉት ጉዳዮች መካከል ዋነኛው ልብ-አንጠልጣይ ፉክክር የሚታይበት መሆኑ ነው። ፈጣን፣ ፈታኝ እና የማይጠበቁ ውጤቶች የሚመዘገቡበት ሊግ ነው። ቢሆንም ይህ ምስል አደጋ ላይ ይመስላል። በዓመታት ሂደት ሊጉ ስድስት ኃያላን ክለቦች ተብለው የሚታወቁትን አምርቷል። ዩናይትድና ሲቲ፣ ሊቨርፑል፣ አርሴናል እና የከተማ ተቀናቃኙ ቶተንሃም እንዲሁም የምዕራብ ለንደኖቹ ቼልሲ። አደጋው እዚህ ጋ ነው። በሂደት ስድስቱ ኃያላን ቀርቶ አንድ ኃያል እንዳይሆን የሚል ስጋት። ያለፈው ውድድር ዘመን እጅግ ተወዳጅ ያደረገው ሊቨርፑል የሲቲን እግር እየተከተለ ዋንጫ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ነበር። ነገር ግን ሁለቱም ክለቦች የቋመጡለትን ዋንጫ ተቀያይረው አግኝተዋል። ፕሪሚዬር ሊግን የቋመጠው ሊቨርፑል ቻምፒዮንስ ሊግ ሲያነሳ፤ ቻምፒዮንስ ሊግን ለማንሳት የሻተው ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ወስዷል። •ታዳጊዎችን በወሲብ ንግድ በማሰማራት ተከሶ የነበረው ቱጃር አሟሟት ጥያቄን ፈጥሯል ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ ካነሳ ሶስት አስርት ዓመታት ተቆጥረዋል፤ በአቡ ዳቢ ቱጃሮች የተያዘው ሲቲ ደግሞ ቻምፒዮንስ ሊግ አንስቶ አያውቅም። ሲቲ ዘንድሮ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ከቻለ ሌላ ታሪክ ይፅፋል። በአንድ ውድድር ዘመን በርካታ ጎሎች በማስቆጠር እና በርካታ ነጥቦች በማምጣት ሲቲ ሪከርዱን ይዟል። በኤፍ ኤ ዋንጫ ዋትፈርድን 6-0 በመርታት ተመልካችን አጀብ አሰኝተዋል። ይህን ያዩ የኳስ ተንታኞች 'እግር ኳስ ከስማለች' እስከማለት ደርሰዋል። የፈርናንዲሆ ምትክ ያስፈልጋቸዋል እየተባሉ ሲታሙ የነበሩት ሲቲዎች ባለተሰጥዖው ሮድሪን አስፈርመዋል። በዘመናዊ እግር ኳስ ምርጡ አሰልጣኝ የሚል ስያሜ የተሰጠው ፔፕ ጉዋርዲዮላን የያዙት ሲቲዎች ወደፊትም ተፅዕኖዋቸው እንደሚቀጥል ይገመታል። የተሻለ የእረፍት ጊዜ ያሳለፉት ሲቲዎች በኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ሊቨርፑልን መርታት ችለዋል። በአቋምም ሆነ በስነልቡና ጥንካሬ ከሊቨርፑል የተሻሉ ሆነው ነበር የታዩት። በሌላ በኩል ሌሎች ኃያላን ሲቲን ተቋቁመው የሊጉን ዋንጫ ያነሳሉ ማለት ከባድ ነው። አርሴናሎች ፔፔን ቢያስፈርሙም፤ ተከላካይ መስመሩ አሁንም ጥገና የሚያሻው ይመስላል። ኪዬራን ቲየርኒን ከሴልቲክ፣ ዴቪድ ልዊዝን ደግሞ ከቼልሲ ማስፈረማቸው ሳይዘነጋ። አዲስ አሰልጣኝ የቀጠሩት ቼልሲዎች ኤደን ሃዛርድን ለቼልሲ ቢሸጡም በተጣለባቸው ቅጣት ምክንያት ተጫዋች መግዛት አልቻሉም። ይህ ደግሞ ለአዲሱ አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ሁኔታዎችን የሚያከብድበት ይመስላል። የዩናይትዱ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ቡድኑን የተቀበለ ሰሞን ድንቅ አቋም ቢያሳይም ወደ መጨረሻ ከበድ ያለ ጊዜ አይቷል። ዩናይትዶች ሊጉን ያሸንፋሉ ተብሎ የተሰጣቸው ግምት ከእስከዛሬው እጅግ ዝቅ ያለ ነው። •ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ ታድያ የእነዚህ ኃያላን ቡድኖች እንደ ሲቲ ዝግጁ አለመሆን ለሊጉ አደጋ መሆኑ አይቀርም። እንደ ጣልያን [ጁቬንቱስ ለ8 ተከታታይ ዓመታት ዋንጫ ያነሳበት]፤ እንዲሁም ጀርመን [ባየርንሚዩኒክ ለሰባት ተከታታይ ዓመታት] ሊጎች አጓጊነቱ የወረደ እንዳይሆን ነው ዋነኛው ���ጋት። በየወሩ ክፍያ እየከፈሉ የሚመለከቱ ተመልካቾች ክፍያቸውን ሊያቋርጡ ይችላሉ፤ በተለይ ደግሞ እንግሊዝ የሚገኙቱ የሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ማሽቆልቆል ከማሳየቱ ጋር በተያያዘ። በዓለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን ፉክክር የማይታይበት ሊግን ለማዬት ተመልካቾች ብዙም ጉጉት ላያሳዩ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ጣልያን እና ጀርመን የአፍሪቃ እና እስያ ተመልካቾችን ለመመለስ ብዙ ትግል እያደረጉ እንዳለ ልብ ይሏል። አውሮፓ ሱፐር ሊግ እውን ከሆነ አደጋው ለፕሪሚዬር ሊግም ጭምር ነው። ሲቲ በገንዘቡ ነው ዋንጫ እየገዛ ያለው የሚለው ትላልቅ የሊጉ ክለቦች ጭምር ሊቀላቀሉ ይችላሉ። 500 ሚሊዮን ዩሮ ደግሞ የሱፐር ሊግ ዓመታዊ ገቢ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው። ምንም እንኳ የሱፐር ሊግ ሃሳብ ከ98 የአውሮፓ ክለቦች በ94ቱ ተቃውሞ ቢገጥመውም። •በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ግን ዕቅዱ እንዳለ ነው። ማን ያውቃል ከጊዜ ወደ ጊዜ የደጋፊዎች ቁጥር እየጨመረ ሊመጣ ይችል ይሆናል። ቶተንሃም፣ ቼልሲ እና አርሴናል ባለፈው ዓመት አንድ ወቅት ላይ ለሊጉ ለዋንጫ ያሰፈሰፉ ቡድኖች ነበሩ። ቢሆንም ከተስፋ ውጭ ምንም የተጨበጠ አልነበረም። ይህ ደግሞ ደጋፊዎቻቸው በጊዜ ሂደት እየሸሹ እንዲመጡ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው። ደጋፊዎች ሁሉንም የቀጥታ ሥርጭት ጨዋታዎች ከፍለው መመልከት አይችሉም። አውሮፕ ሊግ ጨዋታዎች ግን ክፍያቸው እንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ያነሰ ነው። ይህ ደግሞ ትልቅ አደጋ ነው። ማንቸስተር ሲቲ መቆም ካልቻለ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ዕጣ ፈንታ ከሴሪ ኤ፣ ቡንደስሊጋ እና የስኮቲሽ ፕሪሚዬርሺፕ የተለየ የሚሆን አይመስልም፤ የአንድ ቡድን ፍፁም ተፅዕኖ የሚታይበት ሊግ። የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አሁን ላይ አጓጊና እና ኃያል ይመስላል፤ በዚህ ከቀጠለ ግን አወዳደቁ የሚያምር አይሆንም።" https://www.bbc.com/amharic/news-49310398 +business የቱርክ የዋጋ ግሽበት በ24 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ በቱርክ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው የተባለለት የዋጋ ግሽበት አጋጠመ። በአገሪቱ ያለው የዋጋ ግሸበት 83 በመቶ መድረሱ ተገልጿል። ትራንስፖርት፣  ምግብ እና የቤት ዘርፎች ደግሞ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። ኢንፍሌሽን ሪሰርች ግሩፕ የሚባለው ገለልተኛ የአጥኚዎች ቡድን ዓመታዊውን የዋጋ ግሽበት 186.7 በመቶ ያደርሰዋል። ባለፈው ዓመት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት በሚል ባልተለመደ ሁኔታ የወለድ ምጣኔውን ቀንሰው ነበር። በርካታ ባንኮች ደግሞ የዋጋ ግሽበቱን ለመከላከል የወለድ መጠናቸውን ከፍ አድርገው ነበር። የትራንስፖርት ዘርፉ 117.66 በመቶ የዋጋ ግሽበት በማስመዝገብ ቀዳሚ ነው። ምግብ እና ከአልኮል ነጻ የሆኑ መጠጦች በ93 በመቶ ይከተላሉ። የምጣኔ ሃብት ፖሊሲያቸው በውጭ ምንዛሪ ገበያ ውስጥ ጣልቃ መግባትን የሚያካትተው ኤርዶሃን፤ የወለድ ምጣኔን “የሁሉም ሴጣኖች እናት እና አባት ነው” ሲሉ ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት የወለድ ምጣኔ ከ19 በመቶ ወደ 14 በመቶ መቀነሱ የአገሪቱን መገበያያ ገንዘብ ሊራን ዋጋ ቀንሶታል። ይህም አገሪቱ ከውጭ የምታስገባቸው ዕቃዎችን በከፍተኛ ዋጋ እንድትገዛ ያስገድዳታል። ሊራ ከዶላር አንጻር ያለው ልዩነት ክብረወሰን በሆነ ደረጃ ቀንሶ 1 የኤሜሪካ ዶላር በ18.56 ሊራ እየተመነዘረ ነው። የአሜሪካው ባንክ ጂፒ ሞርጋን እንዳለው የቱርክ የዋጋ ግሽበት “የፖሊሲ ለውጥ ካልተደረገ ባልተለመደ መልኩ ከፍተኛ ይሆናል።” ሰኞ ምሽት ቴሌቭዥን ፊት የቀረቡት ፕሬዝዳንት አርዶሃን “ይህንን የዋጋ ግሽበት ችግር አራግፈን በጋራ ጠንካራዋ�� ቱርክ እንገነባለን” ብለዋል። ይህ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ጭማሪ የተከሰተው ከሁለተኛው የዓለም ጦርንት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ሲሉ የቀድሞው የቱርክ ማዕከላዊ ባንክ ዋና ኢኮኖሚስት ሃካን ካራ ተናግረዋል። ከሚቀጥለው ሃገራዊ ምርጫ በፊት የዋጋ ግሽበት እና የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ የኤርዶሃንን ፓርቲ ፈተና ይሆናል ተብሏል። ከኮቪድ-19 ስርጭት ጋር በተያያዘ በተከሰተ የአቅርቦት መስተጓጎል በመፈጠሩ እና የነዳጅ እና የምግብ ዋጋን ካናረው የዩክሬን ጦርነት ጋር ተያይዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዋጋ ጭማሪ እየተከሰተ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cpey3qdzd08o +politics በኢራቅ የሺዓ መሪው ራሳቸውን ከፖለቲካ ማግለላቸውን ተከትሎ በተነሳ ብጥብጥ 15 ሰዎች ተገደሉ በኢራቅ የሺዓ መሪው ሙክታዳ አል ሳድር ከፖለቲካ ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ በተነሳ ግርግር አስራ አምስት ሰዎች ተገደሉ። በኢራቋ መዲና ባግዳድ የተነሳው ሁከት በጸጥታ ኃይሎችና በፖለቲከኛው ደጋፊዎች መካከል በተነሳው ግጭት ነው። የኢራቅ ባለስልጣናት እንደሚሉት የሙክታዳ አል ሳድር ደጋፊዎች ተቃውሟቸውን ለማሰማት የፕሬዚዳንቱን ቤተ መንግሥት ጥሰው ከገቡ በኋላ በርካቶች መቁሰላቸውን ተናግረዋል። አለመረጋጋቱ የተቀሰቀው ሙክታዳ አል ሳድር ከፖለቲካው አለም ራሳቸውን ማግለላቸውን ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነው። የኢራቅ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚንስትር መረጋጋት እንዲሰፍን ጥሪ ያደረጉ ሲሆን በሌሎች ከተሞች በተፈጠረውም አለመረጋጋት ጦሩ ብሔራዊ የሰዓት እላፊ አውጇል። የኢራቅ ጎዳናዎች በተዋጊዎች የተኩስ ልውውጥ የተሞሉ ሲሆን በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከታየውም አስከፊው ነው ተብሏል። እነዚህ ውጊያዎች የተካሄዱት በከተማው አረንጓዴ ዞን ተብሎ በሚጠራውና የመንግሥት ህንፃዎች ችና የውጭ ኤምባሲዎች በሚገኙበት አካባቢ ነው። ግጭቱ የተፈጠረው ለሙክታዳ አል ሳድር ታማኝ በሆኑት ፒስ ብርጌድስ በተሰኘው ሚሊሻ እና በኢራቅ ጦር አባላት መካከል እንደሆነ የኢራቅ ደህንነት ባለስልጣናት አስታውቀዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋሩ ቪዲዮዎች አንዳንድ ተዋጊዎች በሮኬት የሚንቀሳቀሱ የእጅ ቦምቦችን ጨምሮ የከባድ መሳሪያ ልውውጥ እንደነበር ያሳያሉ። ይህንንም ተከትሎ ኢራን ከኢራቅ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር የዘጋች ሲሆን ኩዌት ዜጎቿ አገሪቷን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ አሳስባለች። የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት 15 የሙክታዳ አል ሳድር ደጋፊዎች በጥይት ተመትተው ህይወታቸው ሲያልፍ ወደ 350 የሚጠጉት  ተቃዋሚዎች ቆስለዋል ሲል ኤኤፍኢ ዘግቧል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃለ አቀባይ በኢራቅ የተከሰቱት ሁነቶች አስደንጋጭ መሆናቸውን ገልጻው “ሁከቱን ለማረጋጋት አፋጣኝ እርምጃዎች እንዲወሰዱ” ጥሪ አቅርበዋል ። ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሙክታዳ አል ሳድር አጋር የሆኑት ሙስጠፋ አል ካዲሚ የካቢኔ ስብሰባዎች እንዲታገዱ ውሳኔ አሳልፈው ተጽዕኖ ፈጣሪ የሃይማኖት አባቶች ጣልቃ እንዲገቡ እና ብጥብጡን እንዲያቆሙ ተማጽነዋል። የሙክታዳ አል ሳድር ከፍተኛ ረዳት  ለኢራቅ መንግስት የዜና ወኪል ኢ ኤን ኤ እንደተናገሩት ሁከቱ እና የጦር ውጊያው እስኪቆም ድረስ የረሃብ አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ሙክታዳ አል ሳድር ራሳቸውን ከፖለቲካ ህይወት ለማግለል ውሳኔ ያስተላለፉትተቀናቃኝ የሺአ መሪዎች እና ፓርቲዎች የኢራቅን የፖለቲካ ስርዓት ለማሻሻል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው። በጥቅምት ወር፣ ለሙክታዳ አል ሳድር ታማኝ የሆኑ እጩዎች በኢራቅ ፓርላማ ብዙ መቀመጫዎችን ቢያሸንፉም ነገር ግን መንግስት ለመመስረት በቂ መቀመጫዎችን ማግኘት አልቻሉም። ���ዚያን ጊዜ ጀምሮ በኢራን ከሚደገፉ የሺዓ ቡድኖች ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ ባለመሆናቸውም ለአንድ አመት ያህል የፖለቲካ አለመረጋጋት አስከትሏል። ሙክታዳ አል ሳድር የኢራቅ ፖለቲከኛ እና የሚሊሺያ መሪ ሲሆኑ የሳድሪስት ንቅናቄ መሪ እንዲሁም ቀደም ሲል የአሜሪካ ጦር ኢራቅ ውስጥ በነበረበት ወቅት ይመሩት የነበረው ሚሊሻ  ማህዲ ጦር ተተኪ የሆነው  የሰላም ኩባንያዎች መሪ ናቸው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cw0gevzxzqwo +health ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማቅረብ የሃብታምና ድሃ አገራት ፍጥጫ ስለ ኮቪድ-19 ክትባት ስናወራ አንድ ጥያቄ ብዙዎቻችንን ሰቅዞ መያዙ አያጠራጥርም - መቼ ይሆን እኔ የምከተበው? የሚለው። ጥቂት አገራት የኮቪድ-19 ክትባት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ የማሕበረሰብ ክፍሎች ብለው ለይተዋል። የዓለማችንን ሰዎች ፀረ-ኮሮናቫይረስ መከተብ የሞትና የሕይወት ጉዳይ ነው። ነገር ግን እንዲህ ቀላል አይደለም። ጉዳዩ በርካታ ግዙፍና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት፣ መንግሥታት የማይፈፅሙትን ቃል የሚገቡበት፣ በቢሮክራሲ የታጠረና ቁጥጥር የበረታበት ነው። ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት የተሰኘው ተቋም ባልደረባ የሆኑት አጋተ ዳማራይስ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ጥናት ሠርተዋል። ተቋሙ ዓለማችን ምን ያክል ክትባት ማምረት እንደምትችልና ያለው የጤና መሠረተ ልማት ምን ያህል በቂ ነው? የሚለውን አጥንቷል። የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው ፍጥጫው የሃብታምና የድሃ ነው። ዩናይትድ ኪንግደምና ዩናይትድ ስቴትስ በአሁኑ ወቅት በቂ የሆነ የክትባት አቅርቦት አላቸው። ምክንያቱም ክትባቱን መግዛት የሚያስችል ገንዘብ አላቸውና። ሌሎች እንደ ካናዳና የአውሮፓ ሕብረት አባላት ያሉ አገራት የመግዛት አቅሙ ቢኖራቸውም ክትባት ላይ ብዙ እየተሯሯጡ ያሉ አይመስሉም። ካናዳ ሕዝቧ ከሚያስፈልገው የክትባት መጠን አምስት እጥፍ ከፍ ያለ ክትባት ብታዝም ክትባቱ በታሰበው ጊዜ የደረሰላት አይመስልም። ካናዳ ክትባቱ በፈለገችው ሰዓት ያልደረሰላት ምናልባት የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የውጭ ገበያን እንዳይከለክል በመፍራት ፊቱን ወደ አውሮፓውያን ክትባት አምራቾች በማዞሯ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ሳትሆን የአውሮፓ ሕብረት ነው ክትባት ወደ ውጭ መላክ የለበትም የሚል አቋም እያንፀባረቀ ያለው። አብዛኛዎቹ ገቢያቸው አነስተኛ የሆኑ አገራት ገና ዜጎቻቸውን መከተብ አልጀመሩም። ነገር ግን በተለይ መሃል ላይ አንዳንድ ሃገራት አስደናቂ ውጤት እያስመዘገቡ ነው። ለምሳሌ ሰርቢያ በአሁኑ ወቅት ከሕዝቧ በመቶኛ ሲቆጠር በርካታ ሰው በማስከተብ ከዓለም ስምንተኛ ናት። እርግጥ ሰርቢያ ከቻይናና ሩስያ ብዙ ተጠቅማለች። ሁለቱ ሃያላን አገራት በምስራቅ አውሮፓ ያላቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ ሰርቢያን ወዳጅ አድርገው ይዘዋል። የሩስያ ስፓትኒክ 5 የተሰኘው ክትባትና የቻይናው ሲኖፋርም ሰርቢያ ውስጥ እንደልብ ይገኛሉ። ምንም እንኳ ሰርቢያዊያን የክትባት ቅፅ ሲሞሉ ከፋይዘር፣ ስፓትኒክ አሊያም ሲኖፋርም ምረጡ ቢባሉም በርካቶች ሲኖፋርም ነው የሚሰጣቸው። ዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስም ሲኖፋርም በተሰኘው የቻይና ክትባት ላይ ጥገኛ ናት። አገሪቱ ለዜጎቿ እየሰጠችው ካለው ክትባት 80 በመቶው ሲኖፋርም ነው። አልፎም በአገሯ የሲኖፋርም ማምረቻ ፋብሪካ እየገነባች ትገኛለች። አንድ አገር የዓለማችን ከፍተኛ የክትባት አምራች ሆነች ማለት ዜጎቿን በሙሉ ቀድማ ትከትባለች ማለት አይደለም። አይኢዩ የተሰኘው ተቋም ሠራሁት ባለው ጥናት መሠረት የዓለማችን ከፍተኛ ክትባት አምራች የሚባሉት ቻይናና ሕንድ እስከ ፈረንጆቹ 2022 ድረስ ዜጎቻቸውን በበቂ ሁኔ��� ላይከትቡ ይችላሉ። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት አገራቱ ያላቸው የሕዝብ ብዛትና የጤና ሠራተኞች ቁጥጥር አለመመጣጠኑ ነው። ሕንድ የዓለማችን ከፍተኛው የክትባት አምራች ኩባንያ የሆነችው በአንድ ሰው ምክንያት ነው። አንዳር ፑንዋላ። የዚህ ሰው ኩባንያ የሆነው ሴረም በዓለማችን ከፍተኛው የክትባት አምራች ድርጅት ነው። ነገር ግን ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት አጋማሽ ቤተሰቦቹ ሰውዬው አብዷል እስኪሉ ድረስ በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች እየመዠረጠ ለክትባት ምርምር ያውል ነበር። ቢሆንም ቁማሩ ተሳክቶለት ክትባቶቹ ውጤታማ መሆን ችለዋል። አሁን የዚህ ሃብታም ኩባንያ በቀን 2.4 ሚሊዮን ክትባቶች ያመርታል። የፑንዋላ ኩባንያ ለሕንድ፣ ብራዚል፣ ሞሮኮ፣ ባንግላዴሽ እና ደቡብ አፍሪካ ክትባት በዋናነት በማቅረብ ላይ ይገኛል። የዚህ ሰው ኩባንያዎች ከሌሎች የሚለያቸው የኮቪድ-19 ክትባት ማምረት የጀመሩት ቀድመው መሆኑ ነው። ለምሳሌ የኮቪድ-19 ክትባት አሁን ማምረት የጀመሩ ፋብሪካዎች ክትባቱ ታሽጎ እስኪወጣ ወራት ሊፈጅባቸው ይችላል። ፑናዋላ መጀመሪያ የምሰጠው ለሕንድ ነው ይላል። ቀጥሎ ደግሞ ለአፍሪካ። ይህ የሚሆነው በኮቫክስ አማካይነት ነው። ኮቫክስ በዓለም ጤና ድርጅት አማካይነት የተቋቋመ ፕሮግራም ሲሆን ለዓለማችን አገራት ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ ክትባት ለማቅረብ ያልማል። ክትባት የመግዛት አቅም የሌላቸው አገራት ደግሞ በነፃ እንዲያገኙ ይመቻችላቸዋል። የኮቫክስ ፕሮግራም በሚቀጥለው ወር ለአገራት ክትባት ማድረስ ለመጀመር አቅዷል። ነገር ግን የመግዛት አቅም የሌላቸው አገራት በጎን በኩል ከኃያላኑ ጋር ውል ለመፈፀም ደፋ ቀና ማለታቸው የዚህን ፕሮግራም ተፈፃሚነት አጠራጣሪ አድርጎታል። ፑናዋላ እንደሚለው አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት መሪዎች እርሱን በአንድ በሌላም መንገድ አግኝተውት ክትባት እንዲሰጣቸው ጠይቀውታል። ባለፈው ሳምንት ዩጋንዳ ከሴረም ኩባንያ 18 ሚሊዮን ክትባት በ7 ዶላር ሒሳብ ማግኘቷን አሳውቃለች። 4 ዶላር የሚችለው ኮቫክስ ነው። ሴረም የተሰኘው ተቋም ከዩጋንዳ ጋር ንግግር ላይ እንደሆነ ቢያሳውቅም ስምምነት ላይ ግን አልደረስንም ብሏል። የፑናዋላ ተቋም ከዓለም ጤና ድርጅት ፈቃድ ካገኘ 200 ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባቶችን ለኮቫክስ ፕሮግራም ለማቅረብ ዝግጁ ነው። ሃብታሙ ሕንዳዊ ለኮቫክስ ፕሮግራም 900 ሚሊዮን ተጨማሪ ክትባቶች ለማቅረብ ቃል ገብቷል። ጥናቱን የሠራው ተቋም አንዳንድ አገራት በፈረንጆቹ 2023 እንኳ ሙሉ በመሉ ክትባት ላያገኙ ይችላሉ ሲል ይተነብያል። በተለይ ደግሞ በርካታው የሕዝብ ክፍል ወጣት የሆነባቸውና የቫይረሱ ተፅዕኖ ጎልቶ ያልወጣባቸው አገራት ክትባቱ በጊዜ ላይደርሳቸው ይችላል ይላል ግምቱ። እርግጥ ነው ክትባቶች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መጠን እየተመረቱ ነው። ነገር ግን እኛስ መች ይደርሰናል? የሚል ጥያቄ ምላሽ በብዙ ኹነቶች ላይ የተመሠረተ ነው። https://www.bbc.com/amharic/news-56096274 +politics ባይደን ከኢራን ጋር ለመነጋገር ብለው ማዕቀብ እንደማያነሱ ገለጹ "የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ኢራን እአአ በ2015 የተፈረመውን የኒውክሌር ስምምነት ካልተገበረች ማዕቀብ እንደማያነሱላት ተናገሩ። አሜሪካ ኢራን ላይ የጣለቻቸውን ማዕቀቦች ከኢራን ጋር ለመነጋገር ስትል እንደማታነሳ ከሲቢኤስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል። የኢራኑ መሪ አያቶላ አሊ ካምኒ በበኩላቸው ኢራን ስምምነቱን የምታከብረው አሜሪካ ማዕቀቡን ስታነሳላት ነው ብለዋል። 2015 ላይ የኢራንን የኒውክሌር ምርት የሚገድብ ስምምነት ተፈርሞ ነበር። የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካንን በ2018 ከስምምነቱ አስወጥተዋል። ስምምነቱ ሲፈረም ላልተው የነበሩ ማዕቀቦችን ትራምፕ በድጋሚ አጥብቀውም ነበር። ኢራን ማዕቀቦቹ እንደ አዲስ መጣላቸውን ተከትሎ ከስምምቱ ውጪ የሆኑ ድርጊቶች መፈጸም ጀምራለች። ኒውክሌርን ለሰላማዊ ተግባር ነው የማውለው የምትለው ኢራን የተጣራ ዩናንየም ምርቷን እያሳደገች ነው። የተጣራ ዩናንየም የኒውክሌር ቦምብ ለመሥራት ይውላል። ስምምነቱ ለምን ፈረሰ? ኢራን፣ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሩስያ እና ዩናይትድ ኪንግደም በ2015 የኒውክሌር ስምምነት ፈርመው ነበር። በስምምነቱ መሠረት ቴህራን የምታበለጽገውን ዩራንየም እንደምትቀንስና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የምርት ሂደቱን እንዲከታተሉ እንደምትፈቅድ ተገልጿል። ኢራን እነዚህን እርምጃዎች ከወሰደች በምላሹ ማዕቀቦች እንደሚነሱላት ቃል ተገብቶም ነበር። ሆኖም ግን ትራምፕ አሜሪካን ከስምምነቱ አስወጥተው ኢራን አዲስ ስምምነት እንድትፈርም ጫና ለማሳደር ሞክረዋል። ኢራን በአዲሱ የትራምፕ እቅድ አልስማማም ብላ ዩራንየምን በ20% ጥራት ወደ ማምረት እንደምትመለስ አስታውቃለች። የጦር መሣሪያ መሥራት የሚቻለው 90% የምርት ጥራት ላይ ሲደረስ ነው። ባይደን ኢራንን ወደቀደመው ስምምነት ለመመለስ ሲሉ ምጣኔ ሀብታዊ ማዕቀቦችን ያነሱ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ ""በፍጹም ማዕቀብ አላነሳም"" ብለው ምላሽ ሰጥተዋል። ኢራን ግን ወደቀደመው ስምምነት ለመመለስ ያስቀመጠችው ቅድመ ሁኔታ የማዕቀቦችን መነሳት ያካትታል። የኢራኑ መሪ በብሔራዊ ቴሌቭዥን ""ሁሉንም ማዕቀቦች ያንሱ። ከዚያ ወደ ስምምነቱ እንደመለሳለን"" ሲሉ ተደምጠዋል።" https://www.bbc.com/amharic/55976536 +business ኢትዮጵያ በዓለም ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር እድገት ከሚያሳዩ አገራት መካከል ተካተተች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በመጪው 30 ዓመታት የዓለምን ግማሽ የሕዝብ ቁጥር ይይዛሉ ያላቸውን ስምንት አገራት ይፋ ያደረገ ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኮንጎ፣ ናይጄሪያ እና ታንዛኒያ ከአፍሪካ አገራት በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል። እንዲሁም በሚቀጥለው ዓመት ቻይናን በመብለጥ በዓለም ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት አገር የምትሆነው ሕንድ እንዲሁም ፓኪስታን ከስምንቱ አገራት መካከል ናቸው። ሕንድ 1.4 ቢሊዮን ሕዝብ በመያዝ ነው በሕዝብ ብዛቷ ለዓመታት የዓለም ቁንጮ ሆና የቆየችውን ቻይናን የምትበልጠው። በቀጣይ ዓመት ኅዳር ወር ውስጥም የዓለም ሕዝብ ቁጥር 8 ቢሊዮን የሚደርስ ቢሆንም፣ የዓለም የሕዝብ ቁጥር እድገት ቁጥር እስከ ዛሬ ከነበረው የእድገት መጠን ያነሰ እንደሆነም የመንግሥታቱ ድርጅት ይፋ አድርጓል። በስልሳ ዓመታት ውስጥም ዝቅተኛ የተባለው የሕዝብ ቁጥር እድገት መመዝገቡን ይፋ ያደረገው የተባበሩት መንግሥታት፣ ከ40 ዓመታት በኋላ በድጋሚ ከፍተኛ እድገት ላይ ሊደርስ እንደሚችል እና ቁጥሩም 10.4 ቢሊዮን እንደሚደርስ ትንበያው ያሳያል። እ.ኤ.አ. በ2050፣ 61 አገራት የሕዝብ ቁጥራቸው ቢያንስ በአንድ በመቶ መቀነስ ያሳያል ተብሎ ይገመታል። በአሁኑ ወቅትም በተወሰኑ ታዳጊ አገራት ውስጥ እድገቱ በአንድ ሴት 2.1 በመቶ አካባቢ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህ ምጣኔ ያለውን የሕብ ብዛት ቁጥር የመተካት እንጂ እድገት እንዳልሆነ ተመድ አስታውቋል። ቻይና 1.15 ልጅ በአንድ ሴት በማስመዝገብ በዓለም ዝቅተኛ የሕዝብ ቁጥር እድገት ካስመዘገቡ አገራት መካከል ስትሆን፣ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ደግሞ የሕዝብ ቁጥሯ መቀነስ እንደሚጀምር አስታውቃለች። ቻይና ጥንዶች ከአንድ ልጅ በላይ መውለድ እንዳይችሉ የሚከለክለውን ሕጓን በማንሳት ብሎም ሁለት እና ከዚያ በላይ ለሚወልዱ ዜጎቿ ማበረታቻዎችን መስጠት ብትጀምርም እድገቱን ከመቀነስ አላስቆመውም። ምንም እንኳን አን�� ሴት የምትወልደው ልጅ ቁጥር ቢቀንስም የሕዝብ ቁጥር እድገት በተለይም ከሕክምና ሳይንስ መሻሻል ጋር ተያይዞ የሚሞቱ ሕጻናት ቁጥር በመቀነስ፣ እንዲያድጉ በማስቻሉ ምክንያት እድገቱ ቀጥሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/ce4l8rdzp0no +business አንድ ኪሎ ቡና ከ47 ሺህ ብር በላይ የሸጠው ኢትዮጵያዊ ለገሠ በጦሳ 2014 ዕድል ፊቷን ካዞረችላቸው ኢትዮጵያውያን አንዱ ሆኗል። ነዋሪነቱ አዲስ በተቋቋመው ሲዳማ ክልል ነው። ሲዳማ ክልል አርቤጎና ወረዳ ቡርሳ ቀበሌ። ቡርሳ ከክልሉ ዋና መዲና ሐዋሳ 80 ኪሎ ሜትር ያህል ትርቃለች። እድገቱና ውልደቱም በዚያ ነው። በሠላሳዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘው ለገሠ የሚተዳደረው በግብርና ነው። “ከቀድሞ ጀምሮ በግብርና ነው የምተዳደረው” የሚለው ለገሠ በቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ እና የመሳሰሉትን እያመረትኩ ነበር የምንኖረው” ሲል ያክላል። እንሰት ከጓሮው እና እንስሳት ከደጁ አይጠፉም። የእሱ፣ የባለቤቱ እና የአራት ልጆቻቸው መተዳደሪያም ይህ ነው። በቅርቡ ግን ፊቱን ወደ ሌላ ዘርፍ አዞረ፤ ቡና ወደ ማብቀሉ። ቡና አዲሱ መተዳደሪያው ከሆነ አምስት ዓመት ሆነው። በፊት ለምን ቡና አታመርቱም ነበር ሲባል “ቀዬው ቡና እንደሚያመርት አናውቅም ነበር” ይላል። እውነትም አካባቢው ለቡና ምቹ መሆኑን ሳያውቁ ቆይተዋል። አሁንም በአካባቢው ቡና በስፋት እየተመረተ አይደለም። ጥቂቶች ናቸው ቡና የሚያመርቱት። ለገሠ ፊቱን ወደ ቡና ሲያዞርም ከሌላው ይልቅ ቡና ውጤታማ ሆነለት። “ከሌላው እርሻ የቡናው በገቢ የተሻለ ነው” ሲል ለገሠ ይገልጻል። ግማሽ ሔክታር መሬት ላይ ከአንድ ሺህ ኪሎ በላይ ቡና በየዓመቱ ይሰበስባል። የሚያመርተውን ቡና በአካባቢው ለሚገኙ ቡና ነጋዴዎች ይሸጣል። በዓመት ‘ከ70 እስከ 100 ሺህ ብር’ ያገኝ ነበር። በዚህ መካከል ደግሞ ቡና ለዓለም አቀፍ ገበያ በውድድር እንደሚቀርብ ይሰማል። ሌሎች ከእነሱ አካባቢ ያመረቱትን እና የገዙትን ቡና 'ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ' አቅርበው በዓለም አቀፍ ገበያ እንደሚሸጥ ሰምቷል። ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ የቡና የጥራት ውድድር ነው። ባለፉት 20 ዓመታት የጥራት ውድድር በዋና ዋና የቡና አብቃይ አገራት ውስጥ ይካሄድ ነበር። በኢትዮጵያ ውድድሩ የተጀመረው ከሁለት ዓመት በፊት ነው። ዓላማው ከቡናዎች መካከል የተሻለውን መርጦ በዓለም አቀፍ ጨረታ ለታላላቅ ገዢዎች መሸጥ ነው። በተጨማሪም ገበሬዎችን እንዲሁም ልዩ ጣዕም ያላቸውን ቡናዎች እና አምራቾችን ማስተዋወቅም ሌላኛው ዓላማው ነው። በዚህ ውድድር አሸናፊ የሆኑ ሻጮች ቡናቸው በከፍተኛ ዋጋ ይቸበቸባል። ለገሠ ይህንን ሰምቶ ‘እኔስ ለምን በግሌ አልወዳደርም?’ አለ። በአካባቢያቸው ለሚገኙ ነጋዴዎች ቡናውን ማስረከብ አቆመ። “የማውቃቸው ሰዎች ከዚህ ቀደም [በውድድሩ] ቡናቸው እየሸጡ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሲወጡ ተመልክቻለሁ” ይላል። ለገሠ ለውድድሩ አንድ ሺህ ኪሎ ያህል አቀረበ። ውድድሩ አዘጋጅ ከቀረበለት ቡና የተሻለውን መምረጥ እና ቀንሶ ለውድድሩ የማቅረብ መብት አለው። ከዚህ ውስጥ ተጣርቶ 480 ኪሎ ያህሉ ለውድድሩ ፍጻሜ ቀረበ። ውድድሩ ላይ እስከ 40 ባለው ደረጃ ውስጥ ብገባ ሲል ለገሠ ተመኘ። ውጤቱ ሲመጣ ግን ከተመኘውም በላይ ሆነ። ቡናው አንደኛ ወጣ። የአምስት ዓመት ልፋቱ ፍሬ አፈራ። ያውም ጥሩ ፍሬ። የለገሠ አንድ ኪሎ ቡና በውድድሩ ከፍተኛ በሚባል 884.10 ዶላር ተሸጠ። 47 ሺህ 236 ብር ገደማ ማለት ነው። አንድ ኪሎ ቡና 47 ሺህ 236 ብር። ይህም በኢትዮጵያ የቡና ታሪክ በከፍተኛ ዋጋ የተሸጠ ሆኖ ተመዘገበ። ያቀረበው ቡና አጠቃላይ ዋጋ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አስገኘለት። ውጤቱን ከሁለት ሳምንት በፊት ገደማ ነበር የሰማው። “መረጃውን በወንድሜ በኩል ነው የሰማሁት። በጣም ነው ደስ ያለኝ” ብሏል ዜናውን የሰማበትን አጋጣሚ ሲገልጽ። “ቡናው አንደኛ ይወጣል ብዬ አልጠበቅኩም። ግን ተመረጠ። ሌሎች ሲወዳደሩ እና ሲያሸንፉ አይቼ ቡናውን አጥቤ በሚፈለገው መንገድ ለውድድሩ አቀረብኩ። እስከ 40 ባለው ደረጃ ውስጥ ቢገባ ብዬ ነበር ያሰብኩት” ብሏል። ለመሆኑ ይህ ቡና ምን ቢሆን ነው እንደዚህ ውድ በሆነ ዋጋ የተሸጠው? አካባቢው ደጋማ ነው። ቡና ማምረት ያልተለመደበት አካባቢ። “የቡናው ጥራቱ ለመሬቱ አዲስ በመሆኑ ይመስለናል። መሬቱ ኦርጋኒክ [ተፈጥሯዊ] ሲሆን ከቡና ጋር በተያያዘ ብዙም አልተጠቀምንበትም። ለብዙ ዓመታት ቢታረስም ቡና ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ነው የተተከለበት። ስለዚህ ቦታው ኦርጋኒክ ስለሆነ ቡና የሚፈልገውን ነገር ከመሬቱ ያገኘ ይመስለኛል” ሲል ይመልሳል። ከዚህ ውጪ ይህ ነው ብሎ የሚያቀርበው ሌላ ምክንያትም አለ። “አማኝ ነን” የሚለው ለገሠ “አማኝ ነን። ቡናውን ምርጥ ያደረገልኝ ፈጣሪ ነው” ይላል። “እኔ ወደ ቡና ሥራ እንደገባሁ የተሳካላቸው እንዴት እንደሚሠሩ እከታተል ነበር። እኔም ቡናውን አድርቄ ነው የሸጥኩት። 40 ውስጥም እገባለሁ ብዬ አላሳብኩም። እግዚአብሔር ረዳኝ።” ለገሠ ቡናውን ከመትከል ጀምሮ እስከ መንከባከብ ድረስ ይሳተፋል። “(አንዳንዴ) ሠራተኛ ቀጥሬ አሠራለሁ። እኔም እየገባሁ እሠራለሁ። ሙሽራው ቡና ሲመጣ ስሩ ማዕድን ይዞ ስለሚመጣ እንዳይነካ እያደረኩ እየኮተኮትኩ እንከባከበዋለሁ። ከማሳዬ አልጠፋም።” ለገሠ አሁን ሚሊየነር ሆኗል። ብሩ እስካሁን እጁ ባይገባም፤ ከአሁኑ ግን ዕቅድ ተጀምሯል። “ቡና ውስጥ ያልገመትኩት ነው የገጠመኝ። ሐዋሳ ከተማ ቤት ገዝቼ ለመግባት አስባለሁ። ሥራውን ማስፋፋትም እፈልጋለሁ። ቡና ዓለም ውስጥ በስፋት እገባለሁ” ይላል። ጎረቤት፣ ዘመድ . . . በለገሠ ውጤት ማን ያልተደሰተ አለ? በፊት ‘አቅም ያላቸው ናቸው የሚወዳደሩት’ በሚል ወደ ኋላ ያሉትንም እንዳነቃቃ ለገሠ ያስባል። “አሁን ሌሎችም ለመወዳደር ፍላጎት አላቸው” ሲል በአካባቢው የፈጠረውን መነሳሳት ይገልጻል። አልፎ አልፎ የግብርና ባለሙያዎች እየመጡ ‘እንዲህ ብታደርጉ እንዲህ ቢሆን ይህ ቢጨመር ይህ ቢቀነስ ይሏቸዋል።’ በውጤቱም ደስተኞች ሆነዋል። መሬቱ ‘ለቡና’ አዲስ ስለሆነ ‘በደንብ ሥሩ’ ሲሉ ሌሎችንም እየመከሩ ነው። አቶ ለገሠ በፊት እርጥብ ቡና ነበር ለገበያ የሚያቀርበው። አሁን አድርቆ መሸጥ ችሏል። የሚሸጠውም በአካባቢው ላሉ ነጋዴዎች ነበር። አሁን በዓለም አቀፍ መድረክ መሸጥ ችሏል። በዓመት እስከ መቶ ሺህ ብር ብቻ ያገኝ ነበር። በአሁኑ ወቅት ሚሊዮኖችን ማግኘት ችሏል። አሁን ጉዞውን ጀምሯል። ዓይኑንም በቀጣዩ ውድድር ላይ ጥሏል። “ከዚህ በሚበልጥ ሁኔታ ከዚህ በተሻለ ሁኔታ ተዘጋጅቼ ለውድድር እቀርባለሁ” ሲል ያጠናቅቃል። ይህ የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ውድድር ስፔሻሊቲ (ባለ ልዩ ጣዕም ቡና) ብቻ ሳይሆን ለየት ያለ ቡና ገዢዎች የሚገዙበት ነው። ቡናውም ከመሸጡ በፊት በተለያየ ደረጃ እና አገራት ተቀምሶ፣ ደረጃ ወጥሎት ነው ለሽያጭ የሚቀርበው። በውድድሩ ማሸነፍ እውቅና ይዞ ይመጣል። ለገሠ ከዚህ በኋላ በተመሳሳይ ዋጋ ባይሸጥ እንኳን ቡናው ከሌሎች አምራቾች እኩል ዋጋ አይሰጠውም። ከውድድሩ የሚገዛው ቡናም በተለየ ቡና መሸጫ በድንቅ ባለሙያ ተዘጋጅቶ በውድ ዋጋ ለገበያ ይቀርባል። ሦስተኛው የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ውድድር የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ከአሊያንስ ኮፊ ኤክሰለንስ እና ዩኤስኤይድ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው። በዘንድሮው ውድድር የኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ ከፍተኛ በሚባል ዋጋ ተሽጧል። የለ���ሠን አንድ ኪሎ ቡና በ884.10 ዶላር (47236 ብር) የገዛው የቻይናው ኤልኤንኬ ኮፊ ትሬዲንግ ነው። ቀሪው ቡና ደግሞ ሳዛ ኮፊ ለሚባል ድርጅት ተሽጧል። ዋጋው የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ሽያጭ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል። በዘንድሮው ውድድር ከ23 አገራት የተወጣጡ 170 ገዢዎች ተሳታፊ ሆነዋል። ከውድድሩ በኋላ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ “አርሶ አደሮቻችን አገራቸውን አኩርተዋል። የዘንድሮው ውድድር በብዙ ስኬት እና አስደናቂ ክብረ ወሰን ተጠናቋል” ብለዋል። የዩኤስኤይድ ዳይሬክተር ሴን ጆንስ በበኩላቸው “በዚህ በዩኤስኤይድ ድጋፍ በሚካሄደው ውድድር በተለይም የቡናው ዘርፍ እንዲቀየር በማገዛችን ኩራት ይሰማናል። አነስተኛ ቡና አምራቾችን ከቡና ገዢዎች ጋር በማገናኘት አምራቾች ገቢያቸው እንዲያድግ ማድረግ ችለናል” ብለዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cpwe404n806o +health ኮሮናቫይረስ ፡ ክትባቱን ቀድሞ የሚያገኘው ማን ይሆን? እንዴትስ ይከፋፈላል? "ተመራማሪዎች ለኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ የሚሆን ክትባት ማግኘት ሲችሉ በፍጥነት ለመላው ዓለም በሚበቃ መልኩ ማዘጋጀት አዳጋች ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም። የምርምር ላብራቶሪዎችና ትልልቅ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ከዚህ በፊት አንድን ክትባት ለማዘጋጀት፣ ለመፈተሽ፣ ለማምረትና ውጤታማነቱን ለማረጋገጥ የሚወስደውን ጊዜ በመሻር በፍጥነት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ክትባቱ በእርግጠኝነት ሲገኝም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማከፋፈልም የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው። ነገር ግን በሀብታም አገራት መካከል ክትባቱን ለማግኘት በሚደረገው እሽቅድድም ተጋላጭ የሆኑት የዓለማችን ማኅበረሰቦቸ ተጎጂ ይሆናሉ። ክትባቱን ማነው ቀድሞ የሚያገኘው? ምን ያህል ያስወጣ ይሆን? የእንቅስቃሴ ገደቦች ተጥለው በሚገኙበት በዚህ ወቅት ክትባቱን እንዴት በፍጥነት በሁሉም ቦታ ማዳረስ ይቻላል? የሚሉት ወሳኝ ጥያቄዎች አልተመለሱም። ከዚህ ቀደም በነበረው ተሞክሮ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውሉ ክትባቶችን ለማዘጋጀት፣ ለመሞከርና ለማሰራጨት ዓመታትን ይወስድ ነበር። እንደዚያም ሆኖ ክትባቶች ስኬታማ የማይሆኑበት አጋጣሚዎች አሉ። የሰው ልጅ የፈንጣጣ በሽታን ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት 200 ዓመታት ወስዶበታል። ምንም እንኳን ክትባት ቢገኝላቸውም እንደ ፖሊዮ፣ ቲታነስ፣ ቲቢ እና የመሳሰሉ በሽታዎች ደግሞ አሁንም ድረስ አብረውን ይኖራሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያሳትፉ የሙከራ ሥራዎች በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በሚገኙ የምርምር ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተከናወኑ ይገኛሉ። በደህናው ዘመን ከአምስት እስከ አስር ዓመታት ይወስድ የነበረው ፍቱን ክትባት የማግኘቱ ሥራ አዋጪ እንደማይሆን የተገነዘቡት አንዳንድ አገራት፤ ደርሰንበታል ያሉት የክትባት አይነትን በብዛት ለማምረት በዝግጅት ላይ ናቸው። አምራቾችም ለክትባቱ የሚረዳ በቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ፈሰስ ለማድረግ ተዘጋጅተው እየጠበቁ ነው። ባሳለፍነው ወር ደግሞ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ ማግኘቱን ተናግረው ነበር። በአገራቸው ላለፉት ሁለት ወራት በሰዎች ላይ ሙከራ እየተደረገበት የነበረው ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል መፈቀዱን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል። ክትባቱ አስፈላጊውን የምርመራ ሂደት ማለፉን የገለጹት ፑቲን፤ ልጃቸው ክትባቱን እየወሰደች እንደምትገኝም ተናግረዋል። ጥቅምት ወይም ኅዳር ላይ ክትባቱን በጅምላ የመስጠት እቅድ እንዳለ የአገሪቱ አመራሮች ቢናገሩም፤ ባለሙያዎች የሩሲያ የክትባት ምርምር እየሄደ ያለበት ፍ���ነት ላይ ጥያቄ አንስቷል። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ሩሲያ ክትባት ስታመርት ዓለም አቀፍ ሕግጋትን እንድትከተል ማሳሰቡም አይዘነጋም። የሩሲያ ክትባት ድርጅቱ በሦስተኛ ደረጃ ሙከራ ላይ ይገኛሉ ብሎ ከዘረዘራቸው ክትባቶች መካከል አደይለም። እነዚህ ክትባቶች በሰዎች ላይ ተሞክረው ተጨማሪ ምርምር መካሄድ አለበት። ፕሬዘዳንት ፑቲን ግን፤ በሞስኮው ጋማሊያ ተቋም ውስጥ የተሠራው ክትባት ቫይረሱን “በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል” ነው ብለዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ክርስቲያን ሊንድሜር ""አንዳንዴ በግላቸው ምርምር የሚያካሂዱ ሰዎች ውጤታም እንደሆኑ ይናገራሉ። ይህም እጅግ መልካም ዜና ነው"" ብለዋል። ቃል አቀባዩ አያይዘውም፤ ውጤታማ ክትባት በማግኘት እና በምርምር ደረጃዎች በማለፍ መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለም አስምረውበታል። በመላው ዓለም ክትባቱን ለማግኘት ሙከራ በማድረግ ላይ የሚገኙት ቀሪዎቹ ተቋማት ደግሞ ክትባታቸው በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት ፈቃድ እንደሚገኝ ተስፋ አድርገዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ግን እስከ ፈረንጆቹ 2021 አጋማሽ ድረስ በርከት ያሉ ለኮቪድ-19 የሚሆኑ ክትባቶችን ላንመለከት እንችላለን ሲል ተደምጧል። የእንግሊዙ ግዙፍ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ አስትራዜኔካ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየበለጸገ የሚገኘውን ክትባት ለማምረት ፈቃድ ያገኘ ሲሆን ለዩናይትድ ኪንግደም 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን ለማምረት ተስማምቷል። ለተቀረው ዓለም ደግሞ 2 ቢሊየን የክትባት ብልቃጦችን አምርቶ ለማከፋፈል አቅሙ እንዳለው አስታውቋል። ፋይዘር እና ባዮንቴክ የተባሉት ሌሎች ግዙፍ ኩባንያዎች ደግሞ ለኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት እስካሁን ድረስ 1 ቢሊየን ዶላር ወጪ ማድረጋቸውን በመግለጽ በያዝነው ዓመት የፈረንጆቹ ጥቅምት ወር ላይ የማምረት ፈቃድ እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል። ፈቃድ የሚያገኙ ከሆነ ደግሞ የፈረንጆቹ 2020 ከማለቁ በፊት ቢያንስ 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን እንዲሁም ከዚያ በኋላ ደግሞ በ2021 ተጨማሪ 1.3 ቢሊየን ብልቃጦችን ማምረት አለባቸው። ከእነዚህ ትልልቅ ድርጅቶች በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ 20 የሚሆኑ መድኃኒት አምራቾች ክሊኒካል ሙከራቸውን በማከናወን ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን ሁሉም ስኬታማ እንደማይሆኑ ይታወቃል፤ ብዙ ጊዜ ክትባት ለመስራት ላይ ታች ከሚሉት ድርጅቶች መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ተሳክቶላቸው ማምረት የሚጀምሩት። የእንግሊዙ አስትራዜኒካ በቅልጥፍና ያመርተዋል የተባለው ይህ የኮሮናቫይረስ ክትባት መድኃኒት በዋናነት እንዲደርስ የታሰበው ደግሞ መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገሮች ነው። አስትራዜኒካ በበኩሉ ለፍጥነት እንዲረዳው ከሌሎች ሁለት ኩባንያዎች ጋር ስምምነት አድርጓል። ከእነዚህ መካከል የመጀመሪያው የሕህንዱ ሴሩም ኢንዲያ አንዱ ሲሆን፤ ይህ መድኃኒት አምራች በዓለም ላይ መድኃኒትን በከፍተኛ መጠን በማምረት አቅሙ ተስተካካይ የለውም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባስተላለፉት መልዕክት ''እየጠበቅን ያለው ክትባት ለሁሉም የሰው ልጆች በእኩል የሚደርስ የሕዝብ ክትባትን ነው'' ካሉ በኋላ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በየአቅሙ ርብርብ እንዲያደርግም ተማጽነዋል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ለጊዜው ስማቸው ካልተጠቀስ ስድስት መድኃኒት አምራቾች ጋር ስምምነት መፈረሙ ተሰምቷል። አሜሪካም ብትሆን እስከ ጥር ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 300 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን ለማግኘት እየሰራች ነው። ነገር ግን ሁሉም የዓለማችን አገራት በዚህ ፍጥነት ክትባቶቹን ማግኘት አይችሉም። ከዚህ ቀደም ከትባቶችን በማከፋፈል የሚታወቁት እንደ 'ሜድሲንስ ሳንስ ፍሮንቲርስ' ያሉ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ደግሞ አገራት ከመድኃኒት አምራች ድርጅቶቹ ጋር የሚያደርጉት ድርድር የክትባት ፉክክር እንዳይፈጥር ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። በዚህም ድርጅቶቹ የሚያመርቱትን ክትባት በሙሉ ሃብታም አገራት የሚቀራመቱት ከሆነ ደሃዎቹ አገራት ሊዘነጉ ነው ማለት ነው። ከዚህ በፊት በነበሩ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት የሕይወት አድን ክትባቶች ስርጭት ጉዳይ በርካታ አገራት ህጻናትን ከተላላፊ በሽታዎች መከላከል እንዳይችሉና ለሚሊየኖች ሞት ምክንያት ሆኗል። አንዲት ብልቃጥ ክትባት ምን ያክል ይጠየቅባት ይሆን? በአሁኑ ጊዜ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ክትባት ለማግኘት እና ለማምረት ፈሰስ እየተደረገ ነው። ለዚህም ወጪውን ከሞላ ጎደል እየሸፈኑ የሚገኙት ባለጸጋ አገራት ናቸው። እያደጉ ያሉ አገራት ክትባቱን በርካሽም ሆነ በነጻ ለማግኘት ድርድር ላይ ናቸው። የክትባቶች ዋጋ አገራት በሚያዙት መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። ለምሳሌ ሞደርና የተባለው መድኃኒት አምራች ኩባንያ ለኮቪድ-19 ይሆናል ያለውን ክትባት በብልቃጥ ከ32 እስከ 37 ዶላር ድረስ እንደሚሸጥ ገልጿል። አስትራዜኒካ ደግሞ ክትባቱን ባመረተበት ዋጋ እንደሚሸጠው አልያም እጅግ በጣም በረከሰ ዋጋ እንደሚያከፋፍለው አስቃውቋል። በሕንድ የሚገኘው በዓለማችን ትልቁ የክትባት አምራች ኩባንያ ሴረም ኢንስቲትዩት ደግሞ ከጋቪ እና ከቢልና ሜሊንዳ ፋውንዴሽን የ150 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ያገኘ ሲሆን እስከ 100 ሚሊየን ክትባቶችን ለዝቅተኛ ገቢ አገራት ለማቅረብ ተስማምቷል። የዓለም ጤና ድርጅት፣ ዩኒሴፍ እና ሌሎች ድርጅቶች ክትባቱ ከተገኘ በአግባቡ ማሰራጨት የሚያስችል ሥርዓት ቀደም ብለው ዘርግተዋል። ማቀዝቀዣ ያላቸው መኪኖች፣ በፀሐይ የሚሰሩ ማቀዝቀዣዎች እና ማከማቻ መጋዘኖች ከዚህ በፊት ለነበሩ ክትባቶች ጥቅም ላይ ሲውሉ ነበር። እነዚሁ መገልገያዎችም ለኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ይጠበቃል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54114328 +health ኮሮናቫይረስ ፡ ታዋቂው የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ በኮቪድ-19 ተይዞ ሆስፒታል ገባ ታዋቂው የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ ኮሮናቫይረስ እንዳለበት በመረጋገጡ ሎስአንጀለስ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገለት መሆኑን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ለላሪ ኪንግ ቤተሰብ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለኤቢሲ ኒውስና ቀድሞ ይሰራበት ለነበረው ሲኤንኤን ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ላሪ ሆስፒታል ከገባ ከሳምንት በላይ ሆኖታል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የልብ ህመምን ጨምሮ በርካታ የጤና እክሎች ሲያጋጥሙት የነበረው ላሪ፤ ከ60 ዓመት በላይ በዘለቀው የቴሌቪዥን አቅራቢነት ሙያው በርካታ ሽልማቶችናና እውቅናዎችን አግኝቷል። የ87 ዓመቱ ላሪ ተወካዮች እስካሁን በይፋ ወጥተው ሆስፒታል ስለመግባቱና አሁን ስላለበት ሁኔታ ምንም አይነት መግለጫ ስላልሰጡ ዝርዝር መረጃ የለም። ላሪ ኪንግ መጀመሪያ ላይ እውቅናን ያገኘው በ1970ዎቹ በሬዲዮ ያቀርበው በነበረ ዝግጅቱ ነበር። ከዚያም ከ1985 እስከ 2010 (እአአ) በሲኤንኤን ቴሌቪዥን ላይ በተለያዩ መስኮች የዓለማችን ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆኑ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር በሚያደርገው ቃለ ምልልስ እውቅናን አትርፏል። ላሪ ኪንግ ከሬዲዮና ከቴሌቪዥን ሙያው በተጨማሪ በአሜሪካ ታዋቂ ለሆነው 'ዩኤስኤ ቲዴይ' ለተባለው ጋዜጣ ለ20 ዓመታት አምደኛ ሆኖ ጽሁፎችን ሲያርብ ቆይቷል። በቅርቡም በሩሲያ መንግሥት በሚተዳደረው የስርጭት ተቋም ስር ለሚቀርቡት 'ሁሉ' እና 'አርቲ' ለተባሉት ቴሌቪዥኖች 'ላሪ ኪንግ ናው' የተሰኘ ዝግጅትን ያቀርብ ነበር። ታዋቂው ቃለ መጠይቅ አድራጊ ላሪ ኪንግ ሙያውን እያከናወነ ባለበት ዘመን ውስጥ የስኳር፣ የልብ ህመምና የሳምባ ካንሰርን ጨምሮ በርካታ ከባድ የጤና ችግሮች ገጥመውት ነበር። በተጨማሪም ካሉት አምስት ልጆች ውስጥ ሁለቱ በልብ ህመምና በሳንባ ካንሰር በሳምንት ልዩነት ውስጥ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ሞተውበታል። ላሪ ኪንግ ከ30 ዓመት በፊት የልብ ህሙማን ሆነው የገንዘብ አቅምም ሆነ የጤና መድን የሌላቸውን ሰዎች የሚረዳ የበጎ አድራጎት ድርጅት በስሙ በማቋቋም ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። https://www.bbc.com/amharic/news-55516800 +health በሺዎች የሚቆጠሩ ሀሰተኛ የበይነ መረብ መድሃኒት መደብሮች ተዘጉ በግንቦት ወር በዓለም ዙሪያ ባሉ ሀሰተኛ የ'ኦንላይን' (በይነ መረብ) መድሃኒት መደብሮች ላይ የተወሰደው ይህ እርምጃ እስካሁን ከነበሩት ከፍተኛው ነው ተብሏል። ዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም [ኢንተር ፖል] እያደረገ ያለው ዘመቻ አካል በሆነው በዚህ እርምጃ በበይነ መረብ አማካኝነት ህገ ወጥ መድሃኒቶች የሚሸጡ ከ100 ሺህ በላይ የ'ኦንላየን' (በይነ መረብ) ገበያዎች እንዲወገዱ ተደርገዋል። በዚህ ዘመቻ በዩኬ 13 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ህገ ወጥ መድሃኒት በቁጥጥር ስር ውሏል። እንድ አውሮፓውያኑ የዘመን ስሌት በ2008 ዘመቸው ከተጀመረ በኃላ የተመዘገበ ከፍተኛ ውጤት ሲሆን እርምጃው ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ ህገ ወጥ የ'ኦንላየን' የመድሃኒት ግብይት በተጦጦፈበት ጊዜ የተወሰደ ነው። እንደ አውሮፓውያኑ በዘመቻው ከግምቦት 18 እስከ 25 ድረስ በነበሩት ቀናት በ92 ሀገራት 277 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 20 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ህጋዊ ያልሆነ መድሃኒትና ከህክምና ጋር የተያያዙ መሰራያዎች በመንግስታቱ ተወርሷል። በቁጥጥር ከዋሉት ቁሶች አብዘኞቹ ለኮሮና ቫይረስ ምርመራ የሚውል ሀሰተኛና ትክክለኝነታቸው ያልተረጋገጠ ኪቶች መሆናቸም ተዘግቦል። በዩኬ ከ3 ሺህ በላይ ህገ ወጥና ፍቃድ የሌላቸው የህክምና ምርቶችን የሚያስተዋውቁ የኢንተርኔት ማስታወቂያዎች የተወገዱ ሲሆን 43 ድረ ገጾች ደግሞ ተዘግተዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-57417538 +business በደቡብ አፍሪካው ዝርፊያ ከአርባ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ደቡብ አፍሪካውያን ሥራችንን ወስደበውናል ያሏቸውን ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት ዜጎች ላይ ጥቃት አድረሰዋል። አመፀኞቹ የውጭ ሃገር ዜጎች ሱቆችንና ንብረቶችን በመዝረፍ እና በማቃጠል ላይ እንዳሉ ከሥፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ። ይህንን ተከትሎም ከአርባ በላይ ደቡብ አፍሪካውያን ትናንት ማምሻውን ጀምሮ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ፖሊስ አመጸኞቹን ለመቆጣጠር አስለቃሽ ጭስ የተጠቀመ ሲሆን ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ መሆን ሲጀምሩ ደግሞ የጎማ ጥይቶችንም ጭምር ተጠቅሞ ነበር ተብሏል። • በደቡብ አፍሪካ እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ • ደቡብ አፍሪካ በወሮበሎች ላይ የጦር ሠራዊቷን አዘመተች ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጂፒ በተሰኘው የደቡብ አፍሪቃ ግዛት የሬስቶራንት ባለቤት የሆነው አቶ ተከስተ ሹምዬ ስለሁኔታው ጠይቀነው ነበር። ''የሌላ ሃገር ዜጎች የሆኑ አፍሪካውያን ላይ ነው ጥቃቱ የተሰነዘረው። በተለይ ደግሞ የመኪና ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ናይጄሪያውያን ላይ ከእሁድ ጀምሮ ጥቃት ተፈጽሟል። እስካሁን በሰማሁት ዜና ከ50 በላይ መኪና ተቃጥሏል''በማለት ሁኔታውን ያስረዳል። እሁድ ጠዋት ላይ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን እና አንድ ህንጻ እንደተቃጠለ ሁኔታው እስካሁን እንዳልተረጋጋ ተከስተ ይናገራል። ተከስተ እንደሚለው በግምት ከአስር ቀናት በፊት ፕሪቶሪያ በተባለችው ከተማ የሃገሬው ታክሲ ሾፌሮች ከናይጄሪያውያን ሾፌሮች ጋር ተጋጭተው በናይጄሪያውያን በተተኮሰ ጥይት አንድ ደቡብ አፍሪካዊ መሞቱን ተከትሎ ትልቅ ብጥብጥ ተነስቶ ነበር። በዚህም ምክንያት ላለፉት ቀናት ናይጄሪያውያንን ጨምሮ ከሌላ ሃገራት የመጡ ዜጎችን ንብረት መዝረፍና ማቃጠል ተበራክቶ እንደነበር ተከስተ ይናገራል። ''ይህ ዝርፊያና አመጽ ወደ ጆሃንስበርግ ተዛምቶ መጥቷል። እሁድ ዕለት ዝርፊያና ማቃጠሉ ተጀመረ። ቀደም ብሎ ግን ከሌላ ሃገራት የመጡ ዜጎችን እናስወጣለን የሚል ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ ደርሶን ነበር''። • ትሬቨር ኖዋ የዓለማችን አራተኛው ቱጃር ቀልደኛ ሆነ ብዙ ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት ጂፒ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኢትዮጵያን ላይ የደረሰ ጉዳት አለ ወይ? ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ተከስተ ሲመልስ፤ '' ጂፒ አካባቢ እስካሁን ምንም የደረሰ ነገር የለም። ግን ፕሪቶሪያ ውስጥ ሱቆች ሲቃጠሉ የአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ሱቆችም አብረው ወድመዋል። ግን እዚህ ጆሃንስበርግ የፖሊስ ቁጥሩ ከፍ ስላለ ብዙ ደፍረው አልመጡም'' ብሏል። በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በበኩላቸው ደቡብ አፍሪካውያን ወጣቶች ከሌላ ሃገራት የመጡ ዜጎች ስራችንን ቀምተውናል በሚል መነሻ እራሳቸውን በማደራጀት ሱቆች ላይ የመዝመት ሁኔታ ታይቷል ይላሉ። ''ከዚህ ጋር በተያያዘ ዜጎቻችን በስነልቦናም ይሁን ከዝርፊያው ጋር በተገናኘ የሚያጋጥማቸው ችግር አለ፤ ይህንንም ለመፍታት ከሃገሪቱ የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር የሚቻለውን ሁሉ እየተደረገ ነው''። አክለውም ''በእኛ ማህበረሰብ በኩል በቂ የሆነ ከለላ በማድረግ ላይ እና የዜጎች ንብረት እንዳይዘረፍ በመከላከል በኩል የተሟላ አይደለም በሚል ቅሬታ አለ'' ብለዋል። • ደቡብ አፍሪቃዊቷን የቦክስ ቻምፒዮን የገደለው ተያዘ ብዙ ናይጄሪያውን እና የናይጄሪያውያን ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ የናይጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆፍሪ ኦንዬማ ''ማሰብ የተሳናቸው ወንጀለኞች'' የፈጸሙት ተግባር ነው በማለት መሰል ተግባራት በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስበዋል። የውጭ ሃገር ዜጎች ንብረት የሆኑ ሱቆች መዘረፍና ማቃጠል የደቡብ አፍሪካ የዕለት ተዕለት አጋጣሚ እየሆነ መጥቷል። በቅርቡም መፍትሄ የሚያገኝ አይመስልም። ብዙዎችም እንዴት ደቡብ አፍሪካውያን የሌላ አፍሪካ ሃገር ዜጎች ላይ ጥቃት ያደርሳሉ? ብለው ቢጠይቁም ጉዳዩ በቀላሉ ምላሽ የሚያገኝ ነገር አይደለም። ምናልባት ስራ አጥ የሆነው የደቡብ አፍሪካ 28 በመቶ የሚሆነው ወጣት ስራ ቢያገኝ ይሄ ሁሉ ነገር በአንዴ ይቆም ነበር የሚሉም አልጠፉም። https://www.bbc.com/amharic/49561141 +politics “ለተራቡ ቤተሰቦቼ ገንዘብ መላክ አልቻልኩም” ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም "የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም፣ ትግራይ ለሚገኙ “የተራቡ ቤተሰቦቻቸው” ገንዘብ መላክ እንዳልቻሉ ተናገሩ። “ቤተሰቦቼ ትግራይ ናቸው። ብር ልልክላቸው እፈልጋለሁ። ግን ገንዘብ ልልክላቸው አልቻልኩም” ብለዋል ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ባደረጉት ንግግር። ዶ/ር ቴድሮስ አክለውም “ማን እንደሞተ ማን በሕይወት እንዳለ አላውቅም” ሲሉ ተደምጠዋል። ጦርነቱ ከተነሳ ወዲህ ትግራይ እንደ ባንክ፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ መብራት ያሉ መሠረታዊ አገልግሎቶች ተቆራርጣ ቆይታለች። ለወራት ጋብ ብሎ የነበረው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ነሐሴ 18/2014 ዓ.ም. ዳግም አገርሽቷል። ግጭቱን በመጀመር አንደኛው ወገን ሌላኛውን እየከሰሰ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና መንግሥታት የፌደራል መንግሥቱ እና የህወሓት ኃይሎች ግጭቱን አቁመው ለድርድር እንዲቀመጡ ጥሪ እያቀረቡ ነው። በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ግጭት ሦስተኛ ቀኑን ይዟል። እስካሁን ግን በአካባቢው ስላለው ጦርነት ከሁለቱም ወገን የሚወጣ መረጃ የለም። የኢትዮጵያ መንግሥት ሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዳይገባ ዕቀባ በማድረግ ይከሰሳል። የፌደራል መንግሥቱ በምላሹ ጦርነቱንና የትግራይ ኃይሎችን እንደ ምክንያት ያቀርባል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች በጦርነቱ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚጠብቁ ሲሆን፣ ለረሃብ መጋለጣቸውንም ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ያወጧቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከትግራይ ሕዝብ ግማሽ ያህሉ “አሳሳቢ የምግብ እጥረት” ገጥሞታል ብሏል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትርና የአሁኑ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ ጦርነቱ ስላሳደረባቸው የከፋ ተጽዕኖ ሲናገሩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ባለፈው ሳምንት፣ በትግራይ ያለው ሁኔታ “ከዩክሬን የባሰ ነው። ዓለም ለዩክሬን እና ትግራይ በእኩል መጠን ምላሽ የማይሰጠው፣ እርዳታም በበቂ ደረጃ ለትግራይ የማይቀርበው ዘረኝነት ስለሰፈነ ነው” ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። “ያለ ምንም ማጋነን የትግራይ ሰብአዊ ቀውስ ከዩክሬን የባሰ እንደሆነ ልነግራችሁ እወዳለሁ። ከወራት በፊትም ይሄንን ተናግሬዋለሁ። የትግራይ ሕዝብ የቆዳ ቀለሙ ነው [ትኩረት ለመነፈጉ] ምክንያቱ” ብለዋል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴድሮስ ለትግራይ ኃይሎች መሣሪያ በማቀበል ተባብረዋል ሲል ቢከስም፣ ዋና ኃላፊው ክሱን አጣጥለዋል። “ወገንተኝነት እንዳሳየሁ የሚጠቁሙ ሪፖርቶች ሐሰተኛ ናቸው” ብለዋል። ዛሬ አርብ ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም. ሦስተኛ ቀኑን የያዘውን ጦርነት በመቀስቀስ አንደኛው ወገን ሌላኛውን እየከሰሰ ሲሆን፣ ባለፉት ሁለት ቀናት ስላለው ሁኔታ የትኛውም ወገን መግለጫ አልሰጠም። ረቡዕ ዕለት ጥቃት እንደተከፈተባቸው በትግራይ ቴሌቪዥን ያሳወቁት የትግራይ ኃይሎች፤ የአማራ ሚሊሻ፣ ፋኖ እና የአገር መከላከያ ሠራዊት ጥምር ኃይል በትግራይ ደቡብ አቅጣጫ መጠነ ሰፊ ጥቃት ጀምረዋል ብሎ ነበር። ህወሓት ለጦርነት ሲዘጋጅና ከሰላም ድርድሩ ለመራቅ ሰበብ ሲፈልግ ቆይቶ ነበር ያለው መንግሥት ደግሞ፣ ረቡዕ ማለዳ ላይ ጥቃት ፈጽሟል ሲል ከሷል። የህወሓት ከፍተኛ አመራሩ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ አሁንም ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ እንደሆነና የትግራይ ሕዝብ እየተሰቃየ እንደሚገኝ ገልጸዋል። “አዲስ አበባ ባሉት አመራሮች በተጣለው ዕቀባ ምክንያት ሰዎች እየተራቡ ነው። ሰብአዊ እርዳታ በአፋጣኝ ሕዝቡ ያስፈልገዋል። ሕዝባችን ሰብአዊ እርዳታ እያስገለገው ጦርነት ብንጀምር ሞኝነት ይሆንብናል” ብለዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ምላሽ ለማግኘት ቢቢሲ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል ከሚዋሰኑበት እንዲሁም በፌደራሉ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ግጭት እየተካሄደባቸው እንደሆነ ከሚነገሩት አካባቢዎች 20 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ቆቦ ከተማ ያሉ ነዋሪዎች ረቡዕ ጀምሮ የከባድ መሣሪያ ተኩስ ድምፅ እንሚሰማ ሐሙስ አመሻሽ ላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ ሲሆን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የሚሰማው የተኩስ ድምፅ ስጋት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል። አንዲት ነዋሪ “የከባድ መሣሪያ ተኩስ እየሰማን ነው። አሁንም ድረስ ተኩሱ አልተቋረጠም። ጦርነቱ ተባብሷል። ተጨማሪ ኃይልም ወደ አካባቢው እየገባ ነው” ስትል ያለውን ሁኔታ ለቢቢሲ ገልጻለች። አንድ ሌላ ነዋሪ የከባድ መሣሪያ ተኩስ መሰማቱ እንደቀጠለና ይህም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ግራ መጋባትን እንደ��ጠረ ገልጿል። አንዳንዶችም ""በአቅራቢያ ወደሚገኝ ከተማ” መሄዳቸውን ለቢቢሲ ተናግሯል። በትግራይ ተነስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተስፋፋው ጦርነት በሺዎች ሕይወታቸውን ያጡበት፣ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉበት እንዲሁም በአሜሪካ ባለሥልጣናት አሐዝ መሠረት 700,000 ዜጎች “ለረሃብ” የተጋለጡበት ነው።" https://www.bbc.com/amharic/articles/cnl10pdgrrro +business ቤንዚን በሊትር 11 ብር ጨምሮ 48 ብር ገደማ ሊሸጥ ነው መንግሥት ለነዳጅ የሚያውለውን ድጎማ ሂደት ለማንሳት በያዘው ዕቅድ መሠረት በመጀመሪያው ዙር የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ክለሳ ከፍተኛ ጭማሪ ተደረገ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከነገ ረቡዕ ሰኔ 29/2014 እስከ ሐምሌ 30/2014 ዓ.ም. ድረስ የሚያገለግል አዲስ የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ዝርዝር ይፋ አድርጓል። በዚህም መሠረት በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረው ቤንዚን፤ 10 ብር ከ96 ሳንቲም ጨማሪ በማሳየት ከነገ ጀምሮ በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም ይሸጣል። ነጭ ናፍጣ ደግሞ ባለፉት ጥቂት ወራት 14 ብር ገደማ ጭማሪ አሳይቷል። ከሚያዚያ 30/2014 ጀምሮ በሊትር 35.43 ብር ሲሸጥ የነበረው ነጭ ናፍጣ በአንድ ግዜ 13.59 ብር ጨምሮ ከነገ ጀምሮ በሊትር 49.02 ብር ለገበያ ይቀርባል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባወጣው የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ክለሳ አስመልክቶ ማከስኞ ምሽት ባወጣው የዋጋ ዝርዝር መሠረት ከነገ ሰኔ 29/2014 ዓ.ም. ጀምሮ ነጭ ናፍጣ 49.02፣ ኬሮሲን 49.02፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 53.10፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 52.37 እና የአውሮፕላን ነዳጅ 98.83 በሊትር ዋጋ እንደተቆረጠላቸው አስታውቋል፡፡ በአሁኑ በነዳጅ ምርቶች ላይ የተደረገው ጭማሪ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ጭማሪዎች ሁሉ ከፍተኛው ቢሆንም፣ አሁንም መንግሥት ለነዳጅ ምርቶች ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል። ምንም እንኳን መንግሥት ለነዳጅ ምርቶች በአጠቃላይ ድጎማ ሲያደርግ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን የታለመለት የነዳጅ ድጎማ በተባለ ሥርዓት አማካይነት ለሕዝብ የትራንስፖርት መገልገያዎች ድጎማ ይደረጋል ተብሏል። ባለፉት ጥቂት ወራት የኢትዮጵያ መንግሥት በነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ላይ ተከታታይ ጭማሪን አድርጓል። ለማሳያም ከሚያዝያ 30/2014 ዓ.ም. ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ በተደረገው ለውጥ ቤንዚን የ15 በመቶ ጭማሪ በማድረግ ከ31.74 ወደ 36.87 ብር ከፍ እንዲል ተደርጎ ነበር። ለዚህ ከፍተኛ ጭማሪ የሚነሱት ምክንያቶች ደግሞ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ምርት ዋጋ መጨመር እና መንግሥት ለነዳጅ ምርቶች እያደረገ ባለው ድጎማ ምክንያት በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ወጪ ማድረጉ ጫና እየፈጠረበት በመሆኑ ነው። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ስታንዳርድ ጥናት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ቱሉ እንደሚሉት መንግሥት ለነዳጅ በሚያደርገው ድጎማ ምክንያት በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ወጪ ያደርጋል። በግንቦትና በሰኔ መካከል ባሉ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ብቻ መንግሥት 16 ቢሊዮን ብር ወይም 268 ሚሊዮን ዶላር ነዳጅን ለመደጎም ሲል ወጪ ማድረጉን አቶ ለሜሳ ተናግረዋል። የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ላይ ጭማሪ ሲደረግ እንደሚስተዋለው በሌሎች ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በስከተል የኑሮ ውድነቱን ያባብሰዋል የሚል ስጋት በበርካቶች ዘንድ አስከትሏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cxen371z51eo +politics የካፒቶል ሂል ሁከት፡ የአሜሪካ ፍርድ ቤት የትራምፕን ጥያቄ ውድቅ አደረገ "የዩናይትድ ስቴትስ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካፒቶል ሁከት መርማሪዎች የዋይት ሃውስ መዝገቦቻቸውን እንዳይመለከቱ ለማገድ ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አደረገው። ትራምፕ በዋይት ���ውስ መዝገቦቻቸው የፕሬዝደንቶችን ማህደር በሚስጥር እንዲቀመጥ በሚፈቅደው መብት ሊጠበቅ ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል። ሆኖም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሰነዶቹ ላይ የነበረውን መብት አንስተዋል። ትራምፕ ጥር 6 ስለተፈጠረው የካፒቶል ሂል ሁከት አስቀድመው ያውቁ እንደሆነ ለማወቅ ምርማሪዎች በምርመራ ላይ ይገኛሉ። የአሜሪካ ኮንግረስ የጆ ባይደንን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ለማረጋገጥ በስብሰባ ላይ ባለበት ወቅት የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ህንጻን መውረራቸው ይታወሳል። ትራምፕ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ምንም ማስረጃ ሳያቀርቡ መጨበርበር ነበር በሚል በባይደን መሸነፋቸውን ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የሐሙሱን ውሳኔን በመቃወም ይግባኝ ያቀርባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ጉዳዩም ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያመራል። ውሳኔውን ያሳወቁት የኮሎምቢያ አካባቢ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኞች የባይደንን ትዕዛዝ በመሻር የቀድሞው ፕሬዝዳንት ያቀረቡትን ጥያቄ የሚያስቀብል ""ምንም ምክንያት"" አላቀረቡም ብለዋል። አክለውም ሁለቱም የመንግሥት አካላት ከጥቃቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው መዝገቦች ልዩ የህግ ፍላጎት እንዳለው ተስማምተዋል ብለዋል። ጥያቄው በፕሬዝዳንት ባይደን ፓርቲ በሆነው ዴሞክራቶች የበላይነት በተያዘው በተወካዮች ምክር ቤት በተቋቋመ ኮሚቴ የተካሄደ ነው። ኮሚቴው በኮንግረሱ ላይ ጥቃት ከመሰንዘሩ በፊት ስለነበረው ሁኔታ ፍንጭ ይሰጠኛል በሚል የስልክ ልውውጦችን፣ የጎብኝዎች መዝገቦችን እና ሌሎች የዋይት ሃውስ ሰነዶችን ለማየት ይፈልጋል። ""በቀድሞው እና በአሁኑ ፕሬዝዳንቶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሙሉ በሙሉ የመደመጥ ሕገ መንግሥታዊ እና ህጋዊ መብታቸው በመከልከልከሉ ሊጠገን የማይችል ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል"" ሲሉ የትራምፕ ጠበቆች ደንበኛቸው ቀደም ሲል ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አቤት ብለዋል። የካፒቶሉን ግርግር ተከትሎ አመጽ አነሳስተዋል በሚል ትራምፕ በኮንግረሱ የታችኛው ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳ ቢሆንም በወቅቱ ሪፐብሊካን በበላይነት በተቆጣጠሩት የላይኛው ምክር ቤት (ሴኔት) ውድቅ ሆኗል። ከካፒቶል ሂልን አመጽ ጋር በተያያዘ ከ670 በላይ ሰዎች ታስረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59594067 +sports ሜሲ ከባርሴሎና ጋር ይቆያል፡ ፔፕ ጋርዲዮላ "በርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች ሰሞኑን አንድ ነገር ላይ ስምምነት ነበራቸው። የስድስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ ከባርሴሎና ጋር ሰሞኑን የፈጠረው ቅራኔ መዳረሻውን ማንችስተር ሲቲ ያደርጋል የሚል። ""ሜሲ የእግር ኳስ ዘመኑን በባርሳ የሚያጠናቅቅ ይመስለኛል፤ የማምነውም እንደዚያ እንደሚሆን ነው"" በማለት የማንቺስትር ሲቲው አለቃና የቀድሞው የሜሲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ግን የበርካቶችን ግምት ከግምት እንዳያልፍ አድርጎታል። የ32 ዓመቱ አርጀንቲናዊ የኮከብ የእግር ኳስ ሕይወቱን ያሳለፈው ከባርሴሎና ጋር ነው። ነገር ግን በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ ክለቡን በነጻ ዝውውር መልቀቅ የሚያስችል ስምምነት አለው። የአሁኑ የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከ2008 እ.አ.አ ጀምሮ እስከ 2012 ድረስ ለአራት ዓመታት ያክል ሜሲን አሰልጥኖታል። በአራት ዓመት ጊዜውም ሦስት የላሊጋና ሁለት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል። በአንድ ወቅትም ""እኔ በጣም እድለኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ቢያንስ የዓለማችንን ምርጡን ተጫዋች ሌዮኔል ሜሲን አሰልጥኜዋለሁ"" በማለት ጋርዲዮላ ለሜሲ ያለውን አድናቆት ገልጿል። ይህ ወደጅነታቸውም አሁን እንደገና ሊያገናኛቸው ይችላል የሚለውን ግምት በበርካቶች ዘንድ አሳድሯል። ነገር ግን ጋርዲዮላ የማይታ���ብ ነው ብሏል። ""እዚያው [ባርሴሎና] ይቆያል፤ የእኔ ፍላጎት ይህ ነው"" በማለት። ጋርዲዮላ ባርሴሎናን ለቆ ወደ ባየር ሙኒክ ሲያመራ ባርሴሎናን በዋንጫ አንበሽብሾት ነበር። የክለቡም በጣም ስኬታማው አሰልጣኝ የነበረ ሲሆን በአራት ዓመት ቆይታው 14 ዋንጫዎችን ለስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ገቢ አድርጓል። ከዚያም ወደ ጀርመን አቅንቶ ጋርዲዮላ ከባየር ሙኒክ ጋር ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የቡንደስ ሊጋውን ዋንጫ ማሸነፍ ችሏዋል። ወደ እንግሊዝ በማምራትም ማንችስተር ሲቲን በማሰልጠን ያለፉትን ሁለት ተከታታይ የውድድር ጊዜያት በበላይነት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ አሸፏል። በዚህኛው የውድድር ዘመን ግን ጋርዲዮላ የሚደግመው አይመስልም፤ አንድም ጨዋታ ያልተሸነፈው ሊቨርፑል 13 ጨዋታዎች ብቻ እየቀሩት ማንችስተር ሲቲን በ22 ነጥብ ርቆ ሊጉን እየመራ ይገኛል። የባርሴሎናው የምንጊዜም ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ስድስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊ በመሆን የምድራችን ብቸኛ ተጫዋች ሲሆን በባርሳ ቆይታው 10 የላሊጋና አራት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን አሸንፏል። እስከ ፈረንጆቹ 2021 በባርሳ የሚያቆየው ኮንትራትም አለው። ነገር ግን የባርሴሎናው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ኤሪክ አቢዳል ተጫዋቾች በቀድሞው የክለቡ አሰልጣኝ ኧርኔስቶ ቫልቨርዴ ጊዜ ""ጠንክረው አይሰሩም ነበር"" የሚል ክስ ማንሳቱን ተከትሎ ሜሲ የአጸፋ መልስ ሰጥቷል። በእንደዚህ አይነት ጠንካራ ንግግሩ ለዓመታት የማይታወቀው ሜሲ አሁን መልስ መስጠቱ ክለቡ ጋር መለያየትን ስለመረጠ ሊሆን ይችላል በማለት ተንታኞች ግምታቸውን አስቀምጠዋል። አሁን በአቢዳልና በሜሲ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ጋርዲዮላ ማራገብ አልፈለገም። ሁለቱንም በአንድ ወቅት ባርሳ ውስጥ ያሰለጠኑት ጋርዲዮላ ""ስለሌላ ክለብ ተጫዋቾች ማውራት አልፈልግም፤ ሜሲ ግን የእግር ኳስ ዘመኑን እዚያው ባርሴሎና ውስጥ የሚያጠናቅቅ ይመስለኛል"" ብሏል።" https://www.bbc.com/amharic/sport-51425052 +politics የአዲሱ ካቢኔ አምስቱ ቁልፍ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ስድስተኛውን ዙር ብሔራዊ ምርጫን ተከትሎ ብልጽግና ፓርቲ አብዛኛውን የፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መቀመጫዎች ካሸነፈ በኋላ ሰኞ መስከረም 24/2014 ዓ.ም አዲስ መንግሥት መስርቷል። በምክር ቤቱ የመጀመሪያ ቀን ስበሰባ የብልጽግና ፓርቲ ሊቀመንበርና ባለፉት ሦስት ዓመታት አገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ዐቢይ አሕመድ፣ ለቀጣይ አምስት ዓመት በመሪነት መንበር ላይ እንዲቆዩ መርጧቸዋል። የአስተዳደራቸውን ሥራ አስፈጻሚ ከፍተኛ ባለሥልጣንትን ይፋ ማድረግ ደግሞ ቀጣዩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥራ ነው። በዚህም በእሳቸው በሚመራውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውስጥ አባል የሚሆኑና በቁልፍ የሚኒስትርነት ቦታዎች ላይ የሚሰየሙ ግለሰቦችን በመምረጥ ለምክር ቤቱ አቅርበው እንዲሾሙ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩና ፓርቲያቸው ቀደም ሲል እንደገለጹት በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነት ቦታዎች ከብልጽግና ፓርቲ ባሻገር ከተፎካካሪ ፓርቲ አባላት መካከል እንዲካተቱ አድርገዋል። እስካሁን በነበሩት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ላይ የአወቃቀርና የስያሜ ለውጥ የተደረገባቸው ያሉ ሲሆን ነባርና አዳዲስ ሚኒስትሮች ተካተዋል። አዲሱ መንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚኖሩት ሁሉም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በሚመደቡባቸው መስኮች የየራሳቸው ቁልፍ ሚና ቢኖራቸውም አንዳንዶቹ ግን የሚኖራቸው ኃላፊነትና ተጽዕኗቸው የጎላ ነው። አገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ይኖራቸዋል ከሚባለው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት አኳያ አምስት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ቃኝተናል። • የገንዘብ ሚኒስቴር፡ ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ ከህወሓት አማጺያን ጋር አገሪቱ የገባችበትን ጦርነት ተከትሎ የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ክፉኛ እየተፈተነ ይገኛል። ይህ ጦርነት በርካታ የምጣኔ ሀብት አውታሮች እና መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመትን አድርሷል። ይህንን ጦርነት ተከትሎ ዋነኛ የአገሪቱ ድጋፍ ሰጪ ምዕራባውያን እጃቸውን የመሰብሰብ አዝማሚያ እያሳዩ ነው። በተጨማሪም በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሪ ዋጋ በተከታታይ እየጨመረ በመሄዱ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በጥቁር ገበያውና በመደበኛው የምንዛሪ ገበያ ያለው የምንዛሪ ተመን ልዩነቱ እጅጉን የሰፋ ሆኗል። ከዚህ በተጨማሪም በአገሪቱ ያለው የኑሮ ውድነት ባለፉት ወራት በመናሩ የሸቀጦችና አገልግሎቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። የምዕራባውያን አገራትና የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ለአገሪቱ በሚያቀርቡት ድጋፍ ላይ ለውጥ የሚኖር ከሆነ አሁን ባለው የዶላር እጥረት፣ የመሠረታዊ ፍጆታ እቃዎች ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ የአገሪቱን ምጣኔ ሀብት ሊፈትነው ይችላል ተብሎ ያሰጋል። • ሰላም ሚኒስቴር፡ በአገሪቱ ሠሜናዊ ክፍል ያለው ጦርነት፣ በምዕራብ እና ደቡብ ያለው አለመረጋጋት የአገሪቱን ሰላም እና ደኅንነትን አደጋ ውስጥ ከከተቱት ጉዳዮች መካከል ናቸው። ለውጥ ይደረግባቸዋል ከሚባሉት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች አንዱ የሆነው ይህ ተቋም ያጋጠሙ የሰላም መደፍረሶችን ለመፍታት እና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት መሥራት እንዳለበት፣ ይህም የአዲሱ መንግሥት ቁልፍ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የአዲስ መንግሥት ምስረታና በዓለ ሲመት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል መግባባትን ለመፍጠር ሁሉን አካታች ውይይት እንደሚካሄድ ተናግረዋል። • የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡ ትግራይ ውስጥ ከተከሰተው ግጭትና ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ሥራ ይጠብቃታል። በትግራይ ያለውን ጦርነት ተከትሎ ምዕራባውያንና ዓለም አቀፍ ተቋማት የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ግፊቶችን እያደረጉ ይገኛሉ። በትግራይ ያለውን ጦርነት ተከትሎ ምዕራባውያንና ዓለም አቀፍ ተቋማት የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ግፊቶችን እያደረጉ ይገኛሉ። የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ትግራይ ባለው የሰብአዊ ቀውስ እንዲሁም በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን ርዕስ በማድረግ ውይይት አድርጓል። በቅርቡ በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል በሚል ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ የተደረጉት የተባበሩት መንግሥታት ኃላፊዎች ጉዳይ ከመንግሥታቱ ድርጅት፣ ከምዕራባውያን በኩል ተቃውሞን አስከትሏል። ይህም ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ባላት ግንኙነት ላይ አሉታዊ ውጤት ሊኖረው የሚችል ሲሆን በዚህ በኩልም አገሪቱ ዋነኛ ሥራ ይጠብቃታል። በዚህ መካከል ኢትዮጵያ በመላው ዓለም ካሏት ከ60 በላይ ቆንስላዎች እና ኤምባሲዎች ገሚሱን ለመቀነስ ያላትን እቅድ ይፋ አድርጋ ወደ እርምጃ ገብታለች። • ዐቃቤ ሕግ፡ በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በሚነሱ ብሔር ተኮር ግጭቶች፣ ፖለቲካዊ ተቃውሞዎች የተነሳ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ግለሰቦች በፍትህ ሥርዓቱ ላይ ሲያማርሩ ይሰማል። በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ያለው የፍትህ አካል ገለልተኛ፣ ታማኝ እና ብቁ አይደለም የሚል የሰላ ትችት ሲቀርብ ይደመጣል። ከዚህ በተጨማሪም የተፋጠነ ፍትህ የሚሹ በርካታ ዜጎች ፍትህ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ከዚህ አንጻር የስያሜ ለውጥ ሊደረግበት ይችላል የተባለው የአገሪቱ ዋነኛ የፍትህ ተቋም ዐቃቤ ሕግ በርካታ ሥራዎች ይጠበቁበታል። • ገቢዎች ሚኒስቴር፡ የኮሮናቫይረስ ��ረርሽኝ በዓለም በመንሰራፋቱ ምክንያት የተከሰተው የንግድ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ገቢ ላይ ቀላል የማይባል ተጽእኖን አሳድሯል። የአወቃቀር ለውጥ እንደሚደረግባቸው ከተነገረካቸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች መካከል አንዱ የሆነው የገቢዎች ሚኒስቴር በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና ካላቸው ተቋማት መካከል አንዱ ነው። አገሪቱ ለተለያዩ ሥራዎቿ የምታውለውን መዋዕለ ነዋይ ከልዩ ልዩ ምንጮች የሚያሰባስበው ይህ ተቋም በተለያዩ ምክንያቶች ጫና ውስጥ ለወደቀው የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። የአገሪቱን የታክስና የገቢ መሠረት የማስፋቱ ሥራን የሚያከናውነው ይህተ ተቋም በምጣኔ ሀብቱ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጫና ለመቋቋም የሚያስችሉ ተግባራትን የማከናወን ኃላፊነት ተጥሎበታል። በተለያዩ ወቅቶች በአገሪቱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ብዛት፣ መዋቅርና ስያሜዎች ላይ በየጊዜው ለውጦች ሲካሄዱ የነበረ ሲሆን፤ ይፋ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የካቢኔ ሚኒስቴሮች ዝርዝር ላይም ይኸው ለውጥ እንደሚኖር በስፋት እየተነገረ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎችንም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሚመሩ ዕጩዎችን በማቅረብ እንዲሾሙላቸው ይጠይቃሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-58794356 +sports በአምላክ ተሰማ የዓለምን ቀልብ የገዙበት የአፍሪካ ዋንጫ ፍልሚያ "ኢትዮጵያዊው አርቢትር በአምላክ ተሰማ ትላንት ምሽት የስፖርቱ ዓለም መነጋገሪያ ሆነው አምሽተዋል። ለምን? ካሜሩን እያስተናገደችው የምትገኘው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ፍፃሜውን ቀጣይ እሑድ ሲያገኝ ሴኔጋል የዋንጫ ተፋላሚ መሆኗን አውቃለች። ረቡዕ ምሽት ከቡርኪና ፋሶ ፍፃሜ የተጫወተችው ሴኔጋል በኮከብ አጥቂዋ ሳዲዮ ማኔ ታግዛ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ፍልሚያውን ረታለች። ቢሆንም ከዚህ እልህ አስጨራሽ ጨዋታና ውጤት ትይዩ ኢትዮጵያዊው የመሃል ዳኛ በአምላክ ተሰማ መነጋገሪያ ሆነው አምሽተዋል። በአምላክ ተሰማ በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ሦስተኛ ጨዋታቸውን ረቡዕ ምሽት ዳኝተዋል። በአምላክ ከዚህ ቀደም ሴኔጋል ከጊኒ እንዲሁም አዘጋጇ ካሜሩን ከኮሞሮስ ያደረጉትን ጨዋታ በመሃል ዳኝነት ግብፅ ከናይጄሪያ እንዲሁም ከሱዳን ያደረገችውን ጨዋታ ደግሞ በአጋዥ ተንቀሳቃሽ ምስል [ቪኤአር] ዳኝነት መርተዋል። ነገር ግን ሴኔጋል ከቡርኪና ፋሶ ለዋንጫ ለማለፍ ያደረጉትን ፍልሚያ የመሩት 'ኢንተርናሽናል' አልቢትር የመገናኛ ብዙኃንና የማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆነዋል። በጨዋታው ምን ተፈጠረ? በደማቅ ፈገግታቸው የሚታወቁት በአምላክ ተሰማ ከተጫዋቾች ጋር እሰጥ አገባ መግባት የሚፈልጉ ዳኛ አይደሉም። የማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ አንዳንዴም ቀይ ካርድ ሲሰጡ በፈገግታ ታጅበው ነው። የወደቀ ተጫዋች ለማንሳት የሚቀድማቸውም የለም። በረቡዕ ምሽቱ ጨዋታ የሰኔጋሉ ኩያቴ ከቡርኪና ፋሶው ግብ ጠባቂ ኮፊ ጋር የተጋጨበትን ክስተት የተመለከቱት በአምላክ ለሴኔጋል ፍጹም ቅጣት ምት ይሰጣሉ። ሁለቱ ተጫዋቾች ክፉኛ በመጎዳታቸው ምክንያት ሕክምና እስኪያገኙ የጠበቁት ዳኛው ወደ ቪኤአር መስኮት በማቅናት ተሳስቻለሁ ፍጹም ቅጣት ምት አይደለም ሲሉ ይወስናሉ። የመጀመሪያው አጋማሽ መገባደጃ ገደማ ደግሞ የቡርኪናቤው ተከላካይ ኤድሞን ታፕሶባ ኳስ ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ነክቷል በማለት ዳኛው ለሴኔጋል 'ሪጎሬ' ይሸልማሉ። አልፎም ተጫዋቹ ለፈፀመው ቅጣት ማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ ይሰጡታል። ነገር ግን ውሳኔያቸውን ከማጽደቃቸው በፊት አጋዥ ተንቀሳቃሽ ምስል እንዲመለከቱ ረዳቶታቸው ይጠቁሟቸዋል። ከሜዳው ጠርዝ ወደቆመው የቪኤአር መስኮት ያቀኑት በአምላክ ፍጹም ቅጣት ምቱን ሽረው ወደ ታፕሶባ አቅንተው ቢጫ ካርድህ ተሰርዞልሃል ብለው ይቅርታ ሲጠይቁት በቴሌቪዥን መስኮት ታይተዋል። የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ያለምንም ግብ ቢጠናቀቅም የስፖርት ቤተሰቡ የበአምላክን ስም እያነሳ ሲያወድሳቸው ተስተውሏል። ሁለቱም የፍጹም ቅጣት ምቶች አሳማኝ አይደሉም ያሉ በርካታ የስፖርት ወዳጆች ዳኛው ቪኤአርን በአግባቡ መጠቀማቸውን ሳያደንቁ አላለፉም። ቁጥራቸው የበዛ አፍሪካዊያን የስፖርት ጋዜጠኞች በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የበአምላክን ስም እያነሱ ሲያንቆለጳጵሷቸው ታይተዋል። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የትዊተር ተከታዮች ያሉት ጋናዊው እውቅ የስፖርት ጋዜጠኛ ሳዲቅ አዳምስ ""ድንቅ ውሳኔ"" ብሎ ሲያሞግሳቸው ኬንያዊቷ ታዋቂ የስፖርት ጋዜጠኛ ካታሚ ሚሼል ደግሞ ""ሁሉም ውሳኔዎቹ አግባብ ናቸው"" ስትል ለዳኛው አድናቆቷን ገልፋለች። ደቡብ አፍሪካዊ የስፖርት ጋዜጠኛ ሊሬንዝ ኮለርም ለበአምላክ አድናቆታቸውን ከቸሩ ሰዎች መካከል ነው። ጎል ዶት ኮም የተሰኘው የእግርኳስ ድረ-ገፅ እስቲ ስለ በአምላክ ያላችሁን አስተያየን አጋሩን ብሎ በትዊተር ገፁ ከለጠፈው መልዕክት ሥር በርካታ የስፖርት ወዳጆች ለዳኛው አድናቆታቸውን ሲያጎርፉ ነበር። አልፎም በርካታ ኢትዮጵያውያንም የዳኛውን ብቃት በማድነቅ 'ኮርተንብሃል' ሲሉ ለዳኛ በአምላክ ያላቸውን ክብር አሳይተዋል። 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በበርካታ ክስተቶች የታጀበ፤ በዳኞች ቢጫና ቀይ ካርድ የተከበበ መሆኑን ተከትሎ በአምላክ ይህን ፈታኝ ጨዋታ በብቃት መዳኘታቸው ከበሬታ አጎናፅፏቸዋል። ጨዋታውን ሴኔጋል በሳዲዮ ማኔ፣ በአብዱ ዲያሎና በኢድሪስ ጉዬ ጎሎች በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ለፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች። ዛሬ ሐሙስ ምሽት ደግሞ ግብፅ አዘጋጇ ካሜሩንን ትገጥማለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-60241093 +health የአፍሪካ ሕብረት በኦሚክሮን ምክንያት በአባል አገራቱ ላይ የጉዞ እቀባ መደረጉን አወገዘ የአፍሪካ ሕብረት ምዕራባዊያን አገራት በአዲሱ የኮቪድ ዝርያ ኦሚክሮን ምክንያት በአፍሪካ አገራት ላይ የጣሉትን እቀባ ተቃወመ። ኦሚክሮን የሚል ስም የተሰጠው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በደበብ አፍሪካ መገኘቱን ተከትሎ ምዕራብ አገራት በአባል አገራት ላይ የጣሉት የጉዞ እቀባ ተቀባይነት እንደሌለው ሕብረቱ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል። ደቡብ አፍሪካ አዲሱን ቫይረስ ማግኘቷና በተገቢው ፍጥነት ለዓለም ማሳወቋ የሚደነቅ ነው ያለው የሕብረቱ መግለጫ፤ ነገር ግን ደቡብ አፍሪካ ይህን በምታደርግበት ጊዜ ቫይረሱ በሌሎች የአውሮፓ አገራት እንደነበረ ፍንጮች መኖራቸውን ገልጧል። ያም ሆኖ ደቡብ አፍሪካ ተህዋሲው መኖሩን በማጋለጧ መቀጣት አይገባትም ይላል መግለጫው። እንደ ዩናይትድ ኪንደግም፣ አሜሪካ እና ካናዳ ያሉ አገራት የኦሚክሮንን መገኘት ተከትሎ ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ሌሎች የደቡባዊ አፍሪካ አገራት ላይ ጉዞ እቀባ ጥለዋል። ምዕራባዊያን በደቡብ አፍሪካ አገራት ላይ የጣሉት የጉዞ እቀባ የምጣኔ ሀብት ፈተና እንደሚፈጥርም ሕብረቱ በመግለጫው ጠቅሷል። ኦሚክሮን እና የሚሰራጭበት ፍጥነትና ጠቅላላ ባህሪያቱ ገና በመጠናት ላይ ያለ ሆኖ ሳለ ሥርጭቱ አደገኛ ነው በሚል አባል አገራቱ ላይ እቀባ መጣል ተቀባይነት ስለሌለው በአስቸኳይ የጉዞ እገዳ ይነሳላቸው ሲል የአፍሪካ ሕብረት አሳስቧል። አሁን በአባል አገራት የተጣሉ የጉዞ ክልከላዎች ከምጣኔ ሀብት ተግዳሮቶች ባሻገር የሕክምና ቁሳቁሶች ወደ አፍሪካ እንዳይገቡ ሌላ ፈተና ይደቅናልም ብሏል። ይህም ብቻ ሳይሆን የደቡብ አፍሪካ ተመራማሪዎች ለምርምር የሚያስፈልጓቸውን ቁሳቁሶች እንዳያገኙም ያደርጋቸዋል። በዚህና ሌሎች ምክንያቶች የተነሳ የአፍሪካ አገራትን መርጦ የጉዞ እቀባ ማድረግ ተቀባይነት የሌለውና አሳፋሪም ነው ሲል መግለጫው ይቋጫል። የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት በተመሳሳይ ይህን በአፍሪካ አገራት የተጣለውን እቀባ መኮነናቸው ይታወሳል። https://www.bbc.com/amharic/news-59574507 +sports ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን አልተመለሱም ስለተባሉ ኤርትራውያን እስካሁን የሚታወቀው በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ኦሪገን ተጉዘው ጠፍተዋል ከተባሉ 5 ኤርትራውያን አትሌቶች መካከል ሦስቱ ለውድድር ወደ ሌሎች አገራት መሄዳቸውን ተነገረ። በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ከሄዱት የኤርትራ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት መካከል ወደ አገራቸው ያልተመለሱ ስለመኖራቸው ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ ተዘግቧል። ቀደም ሲል የኦሪገን ግዛት ፖሊስ የአምስት የአትሌቲክሱ ቡድን አባላት ስም ዝርዝርን በማውጣት የደረሱበት አልታወቀም ብሎ አሳውቆ ነበር። ይሁን እንጂ ኬፒቲቪ፣ ሪጅስታር-ጋርድ እና ኬዚ የተሰኙ የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ጠፍተዋል ተብለው የነበሩ አትሌቶች ተገኝተዋል ሲል የኦሬገን ዩኒቨርሲቲ ፖሊስ ገልጿል በማለት ዘግበዋል። እንደ የአካባቢው ሚዲያዎች ዘገባ ከሆነ፤ የአትሌቶቹን አድራሻ አግቻለሁ ብሎ ለኦሪገን ዩኒቨርሲቲ ፖሊስ ያስታወቀው የኤርትራ ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው። ዘገባዎቹ ይህን ይበሉ እንጂ አሁንም የአምስቱ ኤርትራውያን ስም በኦሬገን ግዛት ፖሊስ ድረ ገጽ ላይ አድራሻቸው በጠፉ ግለሰቦች ዝርዝር ላይ ይገኛል። በግዛቷ ፖሊስ ድረ ገጽ ላይ አድራሻቸው አይታወቅም ተብሎ ስማቸው የተዘረዘሩት ኤርትራውያን በሙሉ ጾታቸው ወንድ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል አንዱ አስልጣኝ ነው። የ44 ዓመቱ አሰልጣኝ በርሄ አስገዶም፣ ፊልሞን አንደ፣ ሃብቶም ሳሙኤል፣ መርሃዊ መብርሃቱ እና የማነ ኃይለሥላሴ በድረ ገጹ ላይ ጠፍተው እየተፈለጉ ካሉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተው ይገኛሉ። አድራሻቸው አይታወቅም ተብሎ ስማቸው ከረዘረዘሩት ኤርትራውያን አትሌቶች መካከል ሁለቱ፤ ማለትም መርሃዊ መብርሃቱ እና ሃብቶም ሳሙኤል ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ኮሎምቢያ ማቅናታቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል። የ18 ዓመት ወጣት የሆኑት ሁለቱ አትሌቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ትሻምፒዮና ላይ በ3 ሺህ እና 5 ሺህ ሜትር ውድድሮች እንደሚሳተፉ በይፋዊ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ሰነድ ላይ ስማቸው ተዘርዝሯል። ጠፍተዋል ከተባሉ አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው የማነ ኃይለሥላሴ ደግሞ ለሌላ ውድድር ወደ ስዊትዘርላንድ ማቅናቱን ለቢቢሲ ተናግሯል። ቢቢሲም የአትሌቱ የጉዞ ሰነድና ቪዛን ተመልክቷል። የዳይመንድ ሊግ አካል በሆነው እና በስዊትዘርላንድ ሎውዛን ከተማ በሚደረገው ውድድር ላይ ለመሳትፍ ወደ ስፍራው እንደሚያቀናም አትሌት የማነ ተናግሯል። ቀደም ሲል የኦሬገን ፖሊስ አድራሻቸው ጠፍቷል ካላቸው ልዑካን ቡድን አባላት መካከል የአሰልጣኝ በርሄ አስገዶም እና ፊሊሞን አንደ ያሉበት አልታወቀም። ኤርትራ 10 አትሌቶች በአራት ውድድሮች ተሳታፊ እንዲሆኑ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደተጠናቀቀው 18ኛው ኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ልካ ነበር። በውድድሩ ላይ የማነ ኃይለሥላሴ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል 7ኛ ሆኖ አጠናቋል። መርሃዊ መብራቱ በ5ሺህ ሜትር ማጣሪያውን ሳያልፍ የቀረ ሲሆን ሃብቶም ሳሙኤል በ10 ሺህ ሜትር 17ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ፊልሞን አንደ ደግሞ በማራቶን ለለመወዳደር ተመዝግቦ ነበር። https://www.bbc.com/amharic/articles/c9rq4l3yz36o +politics 'ምዕራባዊያን ሩሲያን እንዳያስቆጡ እመክራለሁ' በአውሮጳ የሩሲያ አምባሳደር "በአውሮጳ የሩሲያ አምባሳደር ቭላድሚር ቺዞፍ ምዕራባዊያን ሩሲያን እንዳያስቆጡ አሳሰቡ፡፡ አምባሳደሩ አሁን የተፈጠረውን ችግር ለማርገብ የዲፕሎማሲ ዕድል እንዳለም ጠቁመዋል፡፡ አምባሳደር ቭላድሚር ቺዞፍ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት ሁኔታዎችን በጥንቃቄና በብስለት ዲፕሎማሲን ተጠቅሞ ማርገብ እንጂ ሩሲያን ማስቆጣት አደጋው የከፋ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ ከተቆጣች ደግሞ የዲፕሎማሲ ሐሳቧን እርግፍ አድርጋ ልትተወው ትችላለችም ብለዋል፡፡ ባለፉት ቀናት በሩሲያና በምዕራብ አገራት መካከል ከፍተኛ ውጥረት እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ የፈረንሳዩ ኢማኑኤል ማክሮን ሰኞና ማክሰኞ ዕለት ኪያቭና ሞስኮ በመመላለስ ከዚያም ደግሞ ወደ በርሊን በመብረር ሁኔታዎችን ለማርገብ ሲተጉ ሰንብተዋል፡፡ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር 6 ሰዓታት የወሰደ ንግግርና ምክክር በማድረግም ወረራ እንደማይደረግ ፑቲን ቃል ገብተውልኛል ሲሉ ተስፋን ለዓለም ማብሰራቸው አይዘነጋም፡፡ አሜሪካ በበኩሏ ሩሲያ ዩክሬንን ለመውረር ድንበር ላይ 100ሺህ ወታደር ማሰለፏን በመጥቀስ ወረራው በማንኛውም ቅጽበት ሊደረግ ይችላል ስትል ማስጠንቀቋ ይታወሳል፡፡ ባለሥልጣናቷም ፑቲን ዩክሬንን ለመውረር ከሚያስፈልጋቸው የወታደር ኃይል 70 በመቶው በድንበር ሰፍሮ እንደሚገኝ ሲናገሩ ነበር፡፡ የደኅንነት ባለሥልጣናት በበኩላቸው ሩሲያ ወረራውን ተአማኒና ቅቡል ለማድረግ ሐሰተኛ ፊልም እየቀረጸች እንደሆነ መረጃ እንደደረሳቸው ለዓለም ይፋ ያደረጉት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ጆ ባይደን በበኩላቸው ሰኞ ዕለት አዲሱን የጀርመን መራሒ መንግሥት በዋሺንግተን ተቀብለው ያስተናገዱ ሲሆን ሩሲያ ወረራ ከቃጣት ምን ዓይነት ቅጣቶች ሊጣሉባት እንደሚችሉ መክረዋል፡፡ በተለይም ሩሲያን ክፉኛ ያሽመደምዳታል ብለው የገመቱትን የኖርዲክስ ስትሪም2 የጋዝ ማስተላለፊያ ለመዝጋት እንደማያመነቱ ሁለቱ መሪዎች ቃል ሰጥተው ነበር፡፡ ሩሲያ የዛሬ 8 ዓመት ግድም ነበር የዩክሬንን ደቡባዊ ክፍል፣ የክሬሚያ ባሕረ ገብን በወረራ የያዘቸው፡፡ ከሰኞ ወዲህ የዲፕሎማሲ ጥረቱ ተስፋ ሰጪ እየኾነ የመጣ ቢመስልም ዛሬ ሐሙስ ሩስያ ከሰሜናዊት ጎረቤቷ ቤላሩስ ጋር ወታደራዊ ልምምድ እንደምትጀምር አስታውቃለች፡፡ በዚህ ልምምድ 30ሺህ የሚኾኑ ወታደሮቿ እንደሚሳተፉ ተነግሯል፡፡ ቤላሩስ የፑቲን ቀኝ እጅ ናት፡፡ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት በአውሮጳ የሩሲያ አምባሳደር ቭላድሚር ቺዞፍ ግን የሩሲያ ወታደሮች ከቤላሩስ ጋር ልምምድ ካደረጉ በኋላ ወደ አገራቸው ቋሚ የጦር ሰፈር እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡ አሜሪካ ይህ ወታደራዊ ልምምድ ሁኔታዎችን ለማርገብ የሚደረግን ጥረት የማንኳሰስ ያህል ነው ስትል ተችተዋለች፡፡ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የጀመሩት የዲፕሎማሲ ጥረት ፍሬ ማፍራት እንደሚጀምር እየተጠበቀ ሲሆን በተለይ የሚኒስክ ስምምነት አሁን ለተፈጠረው ውጥረት እንደ መፍትሄ ሊወሰድ እንደሚችል ፍንጮች አሉ፡፡ ይህ ስምምነት በ2014 ሩሲያ ክሪሚያን ከተቆጣጠረች በኋላ የተደረሰ አዲስ ስምምነት ሲሆን የደቡባዊ ዩክሬን አካባቢ በሩሲያ በሚደገፉ አማጺያን እንዲተዳደር ያደረገ ስምምነት ነው፡፡ ይህን ስምምነት ፈረንሳይና ጀርመን ያሸማገሉትና የፈረሙበት ስምምነት ነው፡፡ የአሁኑ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ይህ ስምምነት ለሩሲያ ያደላ ነበር ሲሉ እምብዛምም አይቀበሉትም፡፡ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት አምባሳደር ቺዞፍ የዲፕሎማሲ ጥረቱ እንዳለ ሆኖ ሩሲያ ግን ለጊዜው ወታደሮቿን ከድንበር ፈቀቅ የማድረግ ��ላጎት እንደሌላት አረጋግጠዋል፡፡ ""ሁሉም ሚዲያ የሩሲያ ወታደሮች ወደ ዩክሬን ድንበር ስለመጠጋታቸው ያወራል፡፡ ወደ ሩሲያ ፊታቸውን ስላዞሩ የዩክሬን ወታደሮችስ ለምን አይወራም?"" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ሩሲያ ለምዕራብ አገራት ሰላም እንዲሰፍን በርካታ ቅድመ ሁኔታዎችን ያስቀመጠች ሲሆን ከነዚህ መሀል ዋነኞቹ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ወደ ምሥራቅ አውሮጳ መስፋፋቱን እንዲያቆም፣ በተለይ ደግሞ በፍጹም ዩክሬንን በአባልነት እንዳይቀበል የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ይህን የሩሲያን ጥያቄ ምዕራብ አገራት ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርገውታል፡፡ ከቢቢሲ ጋር ቆየታ የነበራቸው በአውሮጳ የሩሲያ አምባሳደር ይህ ጥያቄ ቁልፍ ጉዳይ ነው፤ ሩሲያ በኔቶ ላይ ያላትን ጥያቄ ከማንሳት አትቦዝንም ብለዋል፡፡" https://www.bbc.com/amharic/news-60329209 +politics የሩሲያ እና ዩክሬን ፍጥጫ በመባባሱ የነዳጅ ዋጋ እያሻቀበ ነው "የዩክሬን እና ሩሲያ ቀውስ በዓለም ዙሪያ የነዳጅ አቅርቦትን ያደናቅፋል በሚል ስጋት የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ ነው። የዓለም አቀፍ የገበያ መለኪያ በሆነው የብሬንት የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ዛሬ ማክሰኞ በበርሜል 97.76 ዶላር ደርሷል። ይህም በሰባት ዓመት ውስጥ ከፍተኛው ነው ተብሏል። ሩሲያ በምሥራቅ ዩክሬን በአማፅያን ቁጥጥር ስር ለሚገኙ ሁለት ክልሎች እውቅና ከመስጠት ባለፈ ወታደሮቿ ወደ አካባቢዎቹ እንዲገቡ ፈቅዳለች። የእስያ የአክሲዮን ገበያዎች ዝቅተኛ ሲሆኑ የአሜሪካ እና የአውሮፓ የአክሲዮን ሽያጮች ለኪሳራ ተጋልጠዋል። ከሳዑዲ አረቢያ ቀጥላ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ላኪ በሆነችው ሩሲያ ላይ ዩናይትድ ኪንግደም እና በርካታ የምዕራባውያን አገሮች ማዕቀብ ሊጥሉ እንደሚችሉ እየዛቱ ነው። ሩሲያ በተፈጥሮ ጋዝን ምርት ደግሞ ቀዳሚ ናት። ሩሲያ ወታደሮቿ ራሳቸውን የዶኔስክ እና ሉሃንስክ ሕዝቦች ሪፐብሊኮች ብለው ባወጁት አካባቢዎች ""የሠላም ማስከበር"" እንደሚሰማሩ አስታውቃለች። አሜሪካ ደግሞ የሠላም አስከባሪ መባላቸውን ""ከንቱ"" ስትል ገልጻ፣ ሩሲያ ለጦርነት ሰበብ እየፈጠረች ነው ስትል ተናግራለች። የማኑላይፍ ኢንቬስትሜንት ማኔጅመንት ባልደረባ የሆኑት ሱ ትሪን የዩክሬን እና የሩሲያ ቀውስ በነዳጅ ዋጋ ላይ ""ከፍተኛ እንድምታ"" አለው ብለዋል። ሩሲያ አነስተኛ ድፍድፍ ወይም የተፈጥሮ ጋዝ እንድታቀርብ የሚያስገድድ ማዕቀብ ""በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ተጽዕኖ ይኖረዋል"" ሲሉ አክለዋል። በፊደልቲ ኢንተርናሽናል የኢንቨስትመንት ዳይሬክተር የሆኑት ማይኪ ከሪ በበኩላቸው በዩክሬን ቀውስ፣ በአሜሪካ ያለው ቀዝቃዛ ክረምት እና በዓለም ዙሪያ በነዳጅ እና ጋዝ አቅርቦቶች ላይ ባለው የኢንቨስትመንት እጥረት ምክንያት ነዳጅ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ ሊወጣ ይችላል ብለዋል። ""ሩሲያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥቅም ላይ ከሚውለው 10 በርሜል ነዳጅ ዘይት አንዱን ታቀርባለች። በመሆኑም በነዳጅ ዋጋ ላይ ዋና ተዋናይ በመሆኗ የነዳጅ ተጠቃሚዎችን ይጎዳል"" ይላሉ። አሜሪካ እና አውሮፓ ሕብረት ሩሲያ ላይ ጥለውት ለዓመታት የዘለቁት ማዕቀቦች በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አሳድረዋል። በገንዘብ ተቋማት፣ በቴክኖሎጂዎች እና በግለሰቦች ላይ የሚጣሉ ማዕቀቦች ""ሊጠናከሩ"" እንደሚችሉ ከሪ ተናግረዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60476512 +business የወደፊቱ መገበያያ ይሆናል የሚባለው ቢትኮይን ምንድን ነው? በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አገራት የዲጂታል መገበያያ ገንዘብን [ቢትኮይን] ብዙ አገራት በከፊልና ሙሉ በሙሉ እየተጠቀሙበት ይገኛል። አንዳንዶቹ ምናልባትም ቢትኮይን የወደፊቱ የመገበያያ አማራጭ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ለመሆኑ ቢትኮይን ምንድን ነው? https://www.bbc.com/amharic/news-59459630 +politics የአሜሪካ ማዕቀብ በቀጣናው ስትራቴጂያዊ ለውጥን ያስከትል ይሆን? "ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ግንቦት 15/2013 የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ ካለው ግጭት ጋር እየተፈፀሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ጥቃቶች አገራቸው በተደጋጋሚ ስጋቷን ብታሰማም ትርጉም ያለው ምላሽ ባለመኖሩ አገራቸው የጉዞ እቀባ መጣሏን አስታውቀዋል። በዚህም በኢትዮጵያና በኤርትራ የቀድሞ እና የአሁን ባለስልጣናት፣ ወታደራዊ እና ደኅንነት ኃላፊዎች እንዲሁም የአማራ ክልል መደበኛና ኢ-መደበኛ የጸጥታ አባላትና ግለሰቦች፣ ሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን ባደናቀፉ የህወሓት አባላት ላይ የቪዛ እቀባ አሜሪካ ጥላለች። ይህ በግጭቱ ላይ እጃቸው ያለበት ወይም ተባባሪ የሆኑትን የሚመለከት ሲሆን እንዲሁም የቅርብ ቤተሰቦቻቸውም ጭምር እቀባው ተግባራዊ ሊሆንባቸው እንደሚችል የወጣው መግለጫ ጠቁሟል። ከጉዞ እቀባው በተጨማሪ አሜሪካ የምታደርገውን የምጣኔ ሀብትና የደኅንነት እገዛ እንዲቋረጡና ግጭቱ ካልቆመና መሻሻሎች ካልታዩ፤ ተጨማሪ እርምጃዎችን እንደምትወስድም አስጠንቅቃለች። ሌሎችም አገራት የአሜሪካን ፈለግ እንዲከተሉ ጥሪ አድርጋለች። ይህ የማዕቀብ ሁኔታ አሜሪካ በኢትዮጵያ የምታደርገው ያልተገባ ጫና አካል ነው በሚልም ኢትዮጵያን አሳዝኗል። ምንም እንኳን አሜሪካ ለግጭቱ መፍትሄ ለማምጣት ትርጉም ያለው እርምጃ ሊወሰድ አልተቻለም ብትልም ኢትዮጵያ በበኩሏ ከአሜሪካ አስተዳደር ጋር ገንቢ ግንኙነት በመፍጠር በጋራ እየሰራች ነበር ብላለች። ኢትዮጵያ በትግራይ የተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በጥምረት ሆነው ለመመርመር እየሰሩ መሆናቸውንና ተጠያቂ የሚሆኑበትንም ስራ እያከናወነች እንደሆነ አስታውቃለች። እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግሥት ግብዣ በአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ በመጥቀስ ቀውሱን ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝነት ገልጻለች። አሜሪካ ያሳለፈቻቸው እርምጃዎች የሁለቱንም አገራት የዘመናት ግንኙነት የሚጎዳ ነው ትላለች ኢትዮጵያ። የአሜሪካንን እርምጃዎች በውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ገብነት ነው የምትለው ኢትዮጵያ፤ አሜሪካ በዚሁ የምትቀጥል ከሆነ ግንኙነታቸውን የምታጤነው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። የማዕቀቡ አንድምታ፤ ስትራቴጂያዊ ለውጥ ይሆን? ኢትዮጵያና አሜሪካ በትግራይ ቀውስ ውስጥ እየተደረጉ ስላሉ እርምጃዎች ተመሳሳይ አረዳድ የላቸውም። በቀጣናው ከአልሻባብ መግነን ጋር ተያይዞ ሸብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል የአሜሪካ ቀኝ እጅ የነበረችው ኢትዮጵያና አሜሪካ በትግራይ ባለው ቀውስ ምክንያት ግንኙነታቸው ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። ለአስርት ዓመታት ኢትዮጵያ የአሜሪካ የደኅንነት አጋር ነበረች የሚሉት የአሜሪካ የቀድሞ ዲፕሎማትና በአትላንቲክ ካውንስል የደኅንነት ኃላፊ የሆኑት ካሜሮን ሀድሰን ናቸው። ለረጅም ጊዜያት ፖለቲካዊ ድርድሮችንና ሽምግልናዎችን በዋነኝነት በመምራት፣ በሰላም በማስከበር ስምሪት እንዲሁም በአጠቃላይ መረጋጋት በሌለባቸው የቀጣናው አካባቢዎች መረጋጋትን በማምጣት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና መጫወቷን ካሜሮን ይናገራሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ ራሷ መረጋጋት የሌለባት አገር ናት የሚሉት ዲፕሎማቱ፤ አሜሪካም ይሄንን ለመቆጣጠር የራሷን አስተዋፅኦ ማበርከት አለባት ይላሉ። በተለይም ከማዕቀቡ ጋር ተያይዞ በሁለትዮሽ ግንኙነቱ ላይ አዲስ የሆነ ግንኙነትን የሚያሳይ ነው፤ እን���ሁም አሜሪካ ስትራቴጂያዊ ለውጥን ማድረጓን ጠቋሚ ነው ይላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም ዳይሬክተርና መምህር ዶክተር ዮናስ አዳዬ በበኩላቸው በዲፕሎማቱ ሃሳብ አይስማሙም፤ የአሁኑን ማዕቀብ በአገራቱ መካከል መሰረታዊ የሚባል የርዕዮተ ዓለም ልዩነት የሌለበት ስለሆነ ""ጊዜያዊ ነው"" በማለት። ኢትዮጵያ ካላት መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ አንጻር ስትራቴጂክ ቦታ ላይ ከመሆኗም ጋር ተያይዞ አሁንም በምሥራቅ አፍሪካም ሆነ በቀጣናው ካሉ አገራት ከኢትዮጵያ የተሻለ ወዳጅ ለአሜሪካ ማግኘት ያስቸግራል ብለው እንደሚያምኑ ምሁሩ ይናገራሉ። ለዚህም እንደ ዋቢ የሚጠቅሱት የሶማሊያ በአልሻበብ ቁጥጥር ስር መውደቅ፣ የሶማሌላንድና የፑንትላንድ ዕውቅና አለማግኘት፣ በኬንያና በሶማሊያ መካከል ያለው የሻከረ ግንኙነት፣ የሱዳን የሽግግር መንግሥት ትርምስ ውስጥ መሆኑ ኢትዮጵያ አሁንም ለቀጣናው የተሻለች የአሜሪካ አጋር ናት እንዲሉ አስችሏቸዋል። በተለይም አሜሪካ የምጣኔ ሀብትና የደኅንነት ድጋፍ እቀባ ማድረጓን ተከትሎ አገራቱ ሽብርተኝነትን በጋራ እንዋጋለን የሚሉትን ፕሮጀክት እንዲቆም አያደርገውም ወይ? ብለው በርካቶች ጥያቄ ያነሳሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃል አቀባዩ ዲና ሙፍቲ በኩልም በሰጠው መግለጫ እርምጃው ቀጣናውን ችግር ላይ የሚጥል እንዲሁም ኢትዮጵያ በፀረ-አልሻባብ የሽብር መከላከል እና በሰላም ጥበቃ ላይ ያላትን ሚና በጉልህ የሚጎዳ ሲሉ ተችተውታል። ዶክተር ዮናስም በተመሳሳይ መልኩ ""ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ለአሜሪካ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ቀኝ እጅ ነበረች አሁንም ናት"" ብለው ያምናሉ። የዲፕሎማቱ ካሜሮን ሀድሰን እይታ ግን ከውጭ ጉዳይ መግለጫም ሆነ ከምሁሩ አስተያየት ለየት ይላል። አገሪቱ በአሁኑ ወቅት በውስጧ ካለው ቀውስ የተነሳ ለዓመታት የሚጠበቅባትን በቀጣናው የተጫወተችውን ሚና በአሁኑ ወቅት መጫወት አትችልም ይላሉ። ""ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ በሕዝቡ ላይ የምታደርገውን ጦርነት ለማካሄድ አዳዲስ የደኅንነት አጋሮችን እንደነ ሩሲያ፣ ቻይናና የባሕረ ሰላጤው አገራትን አገራትን አጋርነትን እየተመለከተች ነው። ሁኔታዎች በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ እነዚህን የመሳሰሉ የደኅንነት ግንኙነቶች በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የምዕራባውያን ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ስትራቴጂያዊ ለውጥ ያስከትላል"" ይላሉ። አሜሪካ ከዚህ ቀደም ከፀረ-ሽብር ጋር በተገናኘ ለኢትዮጵያ ስልጠናዎችን፣ እንዲሁም የደኅንነት መረጃዎችን በመለዋወጥ ይሰሩ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም የቀድሞው የሲአይኤ አባል የነበሩት ዲፕሎማት ሀድሰን እንደሚሉት አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር መሳሪያም አቀባይ ነበረች። በቅርቡ ያወጣችው የጉዞ እቀባና 'ዲፌንስ ትሬድ ኮንትሮል ፖሊሲ' ያለችውን ተግባራዊ እንደምታደርግም አሜሪካ አስታውቃለች። ይህ ፖሊሲ ምንን ያካትታል? ለዲፕሎማቱ ቢቢሲ ያቀረበላቸው ጥያቄ ነው። እሳቸውም በምላሹ የትኛውም እርምጃ በሕዝብ ላይ ጥፋት የሚፈፀምበት የቴክኖሎጂ ግብአት ላይ ከሚደረግ ቁጥጥር ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይናገራሉ። ሰፋ ያለ ይዘት ያለው ይህ ፖሊሲ የኮምፒውተር ቴክኖሎጂን ጨምሮ፣ ሶፍትዌሮች፣ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግባቸው ቁሳቁሶችና ረቀቅ ያሉ ወታደራዊ ቴክኖሎጂን ያካትታል። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የተለገሱ በአሜሪካ የተሰሩ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን መጠገን አስፈልጎ መለዋወጫ ቢያስፈልግ በዚህ እቀባ መሰረት ኢትዮጵያ ይሄንን ማካሄድ አትችልም ይላሉ። የሁለቱ አገራት ግንኙነት መበላሸት ኢትዮጵያና አሜሪካ ከመቶ ዓመታት በላይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ���ላቸው ሲሆን በሊግ ኦፍ ኔሽንም ሆነ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምስረታ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል የሚሉት ዶክተር ዮናስ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኢንዱስትሪዎችና ተቋማት ከአሜሪካ ጋር ትስስር አላቸው ይላሉ። የሁለትዮሽ አጋርነታቸውም ነፀብራቅ የሚባሉት በትምህርት ተቋማት እንዲሁም የአሜሪካ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የነበራትን ሚና እንደ ምሳሌ በማንሳት አሜሪካ ለዘመናት የኢትዮጵያ የልማት አጋር ሆና ቀጥላለች ይላሉ። ለዚያም ነው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማዕቀቡን የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት የማይመጥንና የመቶ ሃያ ዓመታቱንም ግንኙነት ""በዜሮ ያባዛው"" ያለው። በአገራቱ መካከል ያለውን ታሪካዊ ዳራ በምንመለከትበት ወቅት ሻክሮ የነበረው ደርግ ኢትዮጵያን ያስተዳድር በነበረ ወቅት ነበር። ኢህአዴግ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ግን ግንኙነታቸው ጠንካራ የሚባል እንደሆነ ይነገራል። ዲፕሎማቱም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እንዲህ አይነት እርምጃ ወስዳ አታውቅም ይላሉ። በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል የተወሰነ ውጥረት የነበረው የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት ተከትሎ በአሜሪካ የቀረበው የተባበሩት መንግሥታት የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በሁለቱ አገራት መጣሉን ተከትሎ እንደሆነ ያወሳሉ። አሜሪካ በማንኛውም በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን አጋርነት አልተወችም የሚሉት ዶክተር ዮናስ ይህ እቀባ ""ማስደንገጥ የለበትም"" ይላሉ። ለምሳሌ ያህልም ኢህአዴግ በ2002 ምርጫ መቶ በመቶ አሸንፌያለሁ ብሎ የፓርላማ ወንበሩን ከተቆጣጠረ በኋላ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ነው ብለው ማፅደቃቸውን በማውሳት ነው። ""ይህ ሁኔታ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ያሳዘነ ነበር"" ይላሉ። በአፍሪካ ውስጥ ""ኢትዮጵያ የአፍሪካ ፖለቲካ መዲና ናት"" የሚሉት ዶክተር ዮናስ ""ኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉት እቀባም አሜሪካንም ሆነ ኢትዮጵያን ይጎዳል"" ይላሉ። በተለይም ኢትዮጵያ የራሷን አፀፋዊ እርምጃዎች የምትወስድ ከሆነ ሁኔታዎች ሊጋጋሉና ቀጣናው የአሸባሪዎች መፈንጫ ሊሆን እንደሚችል ምሁራዊ እይታቸውን ይሰጣሉ። በተለይም በቀጣናው የደኅንነት ስጋት ቢፈጠር ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የአፍሪካ ቀንድም ሆነ ወደ ሌሎች አካካቢዎች አንደሚዛመትና ጉዳቱም ሰፋ ያለ መልክ ሊኖረው እንደሚችል በአፅንኦት ያስረዳሉ። ""በነገራችን ላይ የደኅንነትና የሰላም ጥናት ድንበር አይከፋፍልም። አንድ አካባቢ ያለው የደኅንነት ሁኔታ ከተጎዳ መላው ዓለም ነው የሚጎዳው። ለምሳሌ ከዓመታት በፊት በአሜሪካ ላይ ተፈጸመው የመስከረም 11ዱን ጥቃት ብንወስድ፤ ባደጉም ይሁን ባላደጉ አገራት ውስጥ ከፍተኛ ትርምስ ነው የፈጠረው"" የሚሉት ዶክተር ዮናስ የአንድ አገር ደኅንነት ወይም ሰላም የሚባል የለም በማለት የአገራቱ እጣ ፈንታ በከፍተኛ ሁኔታ የተሳሰረ እንደሆነ ይተነትናሉ። ዲፕሎማቱም በበኩላቸው ማዕቀቡ ኢትዮጵያ ከምዕራቡ ዓለም ጋር በነበራትን ግንኙነት ላይ ስትራቴጂያዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ጠቁመው፤ ይህም ሁኔታ አሜሪካ በቀጣናው ላይ ያላትን ስትራቴጂያዊ ፍላጎቶችም ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንደሚያደርስ አልደበቁም። በተለይም ኢትዮጵያ በውስጧ ሰላም ካልሰፈነባትና አጋርነቷ ከቀረ አሜሪካ በቀይ ባሕር ዙሪያ ደኅንነትንም ሆነ መረጋጋት ለማምጣትም እንዲሁም ተፅእኖ ለመፍጠር ፈተና እንደሚሆንባት ያስረዳሉ። የአሜሪካ ስጋት ምንድን ነው? በትግራይ ካለው ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ጥቃትና አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ችግር በተጨማሪ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ባወጣው መግለጫ፤ በትግራይ ክልል እንዲሁም በአገሪቱ ላይ የተጋረጡት የሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ አንድነትና የግዛት ጉዳይ ከፍተኛ ስጋት አሳድሮብኛል ይላል። የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች ጨምሮ ሌሎች ታጣቂዎች እርዳታ እንዳይደርስ እክል መፍጠር፣ በክልሉ ውስጥ ያሉ ግድያዎች፣ በአስገዳጅ ሁኔታ መፈናቀል፣ መዋቅራዊ የሆነ ወሲባዊ ጥቃት፣ ሆስፒታሎችና የህክምና ተቋማት መውደም አሜሪካ እንዳሳሰባት ትገልጻለች። እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ቀጥለዋል የምትለው አሜሪካ ተደጋጋሚ ጉትጎታዎችን ባደርግም ለቀውሱ ፖለቲካዊም ሆነ ሰላማዊ መፍትሄ መምጣት አልተቻለም ትላለች። በዚህም ምክንያት የወሰደችው እርምጃ አስፈላጊ ነው ትላለች። ዶክተር ዮናስ በበኩላቸው ሁለቱንም አገራት ይጎዳል ያሉት ይህን ማዕቀብ በተሳሳተና በደንብ ባልተጠና መረጃ ላይ ተመስርቶ የተወሰደ ነው ይላሉ። ምሁሩ በአውሮፓውያኑ 2003 አሜሪካ ኢራቅን መውረሯን እንደ ምሳሌ በማንሳትም በወቅቱ አሜሪካ ምክንያት ያደረገችው ኢራቅ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አላት የበሚል ነበር። ነገር ግን መሳሪያው አለመኖሩ የታወቀው ኢራቅ ከፈራረሰችና ከዘገዬ በኋላ መሆኑን ታሪክን ያጣቅሳሉ። በተመሳሳይም አፍጋኒስታንን በማንሳት ከቀደመ ስህተት መማርና ማገናዘብ እንደሚገባ ያወሳሉ። ""በስሜት የሚደረጉ ነገሮች የሚያሳዝኑ ይሆናሉ። በዚህ ትብብር ወቅት ኢትዮጵያን በግድ አንበረክካታለሁ ብሎ ማሰቡ በተለይም በጣም ካደጉ አገራት የሚጠበቅም አልነበረም። በተለይም የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት ረዥም ዘመናት ያስቆጠረ ከመሆኑ አንፃር። ይሄንን በድጋሚ ያጤኑታል ብዬ አስባለሁ"" ይላሉ። የኢትዮጵያ መንግሥትም በተለይም አሜሪካ ከምታወጣቸው መግለጫዎች ጋር በተያያዘ በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተው ጫና ለመሞከር የሚሞክሩ መንግሥታት ተቀባይነት አይኖረውም ሲል መደመጡ ይታወሳል፟። ከዚህም በተጨማሪ በትግራይ ክልል ቀውስና ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ምዕራባውያን እንዲሁም አሜሪካ ከፍተኛ ጫና እያሳደረች ነው ያሉ ተቃውሟቸውን በአዲስ አበባ እንዲሁም በሌሎች አገራት በበይነ መረብ አሰምተዋል። የኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን የውሃ ሚኒስትሮች እንዲሁም የሕግ እና የውሃ ጉዳይ የቴክኒክ ባለሞያዎች በዋሽንግተን ዲሲ ሲደራደሩ በነበረበት ወቅት፤ በዓመታት የተራዘመ ድርቅ እንዲሁም በተራዘመ ዓመታት አነስተኛ የውሃ ፍሰት ላይም መሰረታዊ መግባባት ተደርሷል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ያለምንም ውጤት መቋረጡ ይታወሳል። ኢትዮጵያ ዋሽንግተን ሲካሄድ የነበረውንም ድርድር ያቋረጠችበት ምክንያት በግብጽ ፍላጎት ታዛቢ እንዲሆኑ የገቡት አሜሪካና የዓለም ባንክ ለግብጽ ከመወገን አልፈው የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ላይ ጫና ለማሳደር ሞክረዋል በማለት ኢትዮጵያ መውቀሷ የሚታወስ ነው። አሜሪካ፣ የዓለም ባንክ ከግብጽ ጎን ቆመው ነበር በተባለው በዚህ ድርድር ላይ ከመጀመሪያው ሙሌት በኋላ ኢትዮጵያ ለምትጠቀመው ውሃ ለግብጽ የተጠራቀመ የውሃ ጉድለት ማካካሻ እንድትሰጥ የሚያስገድድ እንደሆነም ተገልጾ ነበር። ከዚህም ጋር በተያያዘ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሕዳሴ ግድቡ ድርድር ምክንያት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን 100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደማይሰጥ ገልፀው ነበር። ከዚህም ጋር ተያይዞ የአሜሪካ የአሁኑ ማዕቀብ የትግራይ ግጭት ብቻ አይደለም የሕዳሴ ግድብም ነው የሚሉ አልታጡም። ነገር ግን የአትላንቲክ ካውንስሉ ካሜሩን ሀድሰን በበኩላቸው ""የአሜሪካ ዋነኛ ስጋት በትግራይ ያለው ጦርነት እንዲሁም በአገሪቱ ያለው አለመረጋጋት አገሪቷን አንዳይበታትናት የሚል ፍራቻ ነው"" ይላሉ። ምንም እንኳን የተጣለው ማዕቀብ አገሪቱን የበለጠ እንዳያዳክማት አሜሪካ ��ትሰጋም ""በትግራይ ውስት እየተፈፀመ ካለው የመብት ጥሰት ክብደት አንፃር ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ሆና አግኝታዋለች"" ይላሉ። እቀባው ጣልቃ ገብነት ወይስ? ዲፕሎማቱ ጠንከር ያለ እርምጃ ቢሉም ለዶክተር ዮናስ በአገራት ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባትና በጉልበት ለመፍታት መሞከር ""ጊዜ ያለፈበት የፖለቲካ አካሄድ ነው"" ይላሉ። ""ሁላችንም እንደ መረብ የተያያዝን ዓለም ላይ ስለምንኖር አንዱ ሌላውን ገፍትሮ፣ አንዱ የሌላው የበላይ፣ አዛዥና ናዛዥ ሆኖ፤ ሌላኛው ታዛዥ ሎሌ ወይም ባርያ ሆኖ ለመኖር ጊዜው አልፏል"" የሚሉት ዶክተር ዮናስ ""21ኛው ክፍለ ዘመን አገራት ችግሮቻቸውን በአንድነት ተባብረው የሚፈቱበት ዘመን እንጂ አንዱ ሌላኛውን አስፈራርቶ ችግር ሊፈታ አይችልም"" ይላሉ። ይህንንም ከግምት ውስጥ በማስገባት ለዘመናት የቆየው ግንኙነት እንዳይበላሽና ዘላቂው ጥቅም እንዲጠበቅ ውሳኔው መጤን አለበት በማለትም ምክር ይለግሳሉ። ""አሜሪካ ለራሷም ጥቅም ለራሷም ክብር ሲባል የወሰደችውን አቋም እንደገና ማጤንና መገምገም አለባት"" በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ለመሆኑ አሜሪካ ኢትዮጵያ እቀባውን የጣለችውም ሆነ ምክር ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ አገሪቷ ምን እንድታደርግ የሚጠይቅ ነው? ጥሰቶችን በገለልተኛ አካላት ተጣርተው ጥፋተኞቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ ሰላማዊ ዜጎች እንዲጠበቁ፣ የሰብዓዊ ድጋፎች ያለምንም እክል እንዲደርሱ እንዲሁም የኤርትራ መንግሥትም ሠራዊቱን በአስቸኳይ ከክልሉ እንዲያስወጣና ዓለም አቀፍ እውቅና ወዳለው የኤርትራ ግዛት እንዲመለሱ የሚጠይቅ ነው። ግጭቱ እስካልቆመና ሰብዓዊ እርዳታዎችን ማቅረብ ካልተቻለ ያለው የምግብ ደኅንነት ስጋት ወደ ረሃብ ይቀየራል ይላል። የትግራይን ቀውስ ማስቆም የማይችሉ ከሆነ ከአሜሪካም ሆነ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሌሎች እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል የሚለው የአሜሪካ ሐሳብ በኢትዮጵያ ላለው ቀውስ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲመጣ አገራቸው እንደምትሰራ ዘርዝሯል። ኢትዮጵያ በበኩሏ በክልሉ ተፈፀሙ የተባሉ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመመርመር ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራች እንደሆነና በተመሳሳይም የሰብዓዊ እርዳታም ባልተገደበ ሁኔታ እርዳታ እንዲቀርብ እየሰራሁ ነው ብላለች። ነገር ግን ያላት አቅም ውስን መሆኑንም አስታውቃለች። ኢትዮጵያ ባወጣችው በዚሁ መግለጫ ላይ አሜሪካ በዋነኝነት ስለምትጠቅሰው የኤርትራ ሠራዊት መውጣት ጉዳይ የተጠቀሰ የለም። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራ ወታደሮች በቅርቡ እንደሚወጡ አስታውቆ ነበር። አሜሪካ የምታወጣው መግለጫዎችን በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው እያለ ሲወቅስ የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት እቀባውን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃል አቀባዩ በኩል በሰጠው መግለጫ ""የኢትዮጵያ ነፃነትና ሉዓላዊነት በገንዘብ የማይቀየር ቀይ መስመር ነው"" ብሎታል። በተለይም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑት ኃይሎች ወደ ድርድር መምጣት አለባቸው የሚለው ጥረት በመንግሥት በኩል ፍፁም ተቀባይነት እንደሌለው በተደጋጋሚ ተገልጿል። እቀባውንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ""ሽብርተኛ ተብሎ ከተሰየመው ህወሓት ጋር ድርድር ማድረግ እንደማይቻል ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል"" በማለት ቡድኑ መልሶ እንዲያንሰራራ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ አሉታዊ ውጤት የሚኖረውና የማይሳካ መሆኑ ተጠቅሷል። ዶክተር ዮናስም በበኩላቸው ከህወሓት ጋር ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በተለያዩ አካላት ወደ ድርድር ለማምጣት እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ከፍተኛ ጥረት መደረጉን አስታውሰው በወቅቱ አሜሪካም የ��ሷን ድርሻ መጫወት ትችል ነበር ይላሉ። ""የኢትዮጵያ ምክር ቤት ተሰብስቦ ህወሓትን በሽብርተኝነት ከፈረጀው በኋላ እንደገና ህወሓትን ከዚያ ውስጥ ለማውጣትና እንደ መንግሥት ሁለቱን እኩል አድርጎ ለድርድር ግቡ ማለት ቅንነት ያለው አይመስለኝም"" ብለዋል። የአሜሪካ መንግሥት በአገሪቱ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ""ሽብርተኛ ቡድን"" ተብሎ የተሰየመውን ህወሓት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በእኩል የመመልከት ዝንባሌ እንዳስቀየመው አስፍሯል።" https://www.bbc.com/amharic/news-57238327 +politics ከእስር እንዲለቀቁ ስለተወሰነላቸው ፖለቲከኞች ከምናውቀው በጥቂቱ "በኢትዮጵያ የተከሰቱ ሁለት ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ቀውሶችን ተከትሎ ከአንድ ዓመት በላይ በእስር ላይ የቆዩ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች እንዲፈቱ መወሰኑ ታኅሣሥ 29/2014 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል። በገና ዕለት አመሻሽ ላይ የፖለቲከኞቹ የመፈታት ዜና ከመሰማቱ በፊት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይቅርታና ምህረትን በተመለከተ ""ድላችን ዘላቂ ለማድረግ እንድንችል በአሸናፊ ምህረት ግጭቱ የፈጠረውን ውጥረት እናረግባለን"" በማለት ፍንጭ የሚሰጥ መግለጫ አውጥተው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም ""ያጠፋ እንዲቀጣ፣ የበደለ እንዲክስ የሚያደርግ ሁሉን አቀፍ ፍትሕ በሽግግር እና በተሃድሶ ፍትህ ዕይታ፣ አገራዊ ባህሎቻችን እና እሴቶቻችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ፍትህ እናሰፍናለን"" ብለዋል። በማስከተልም አመሻሽ ላይ መንግሥት በኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤቱ በኩል ስለውሳኔው መግለጫ ቢያወጣም፣ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ የተለያየ ምላሽን እያስተናገደ ከመሆኑ በተጨማሪ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርጓል። የምህረት ውሳኔውን በተመለከተ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ""ኢትዮጵያ ለዘላቂ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የትኛውንም መሥዋዕትነት ትከፍላለች"" በሚል ባወጣው መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ ችግሮችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ መፍታት እንደሚገባ መንግሥት በጽኑ እንደሚያምን አመልክቷል። ለዚህም መንግሥት አካታች አገራዊ ምክክር እንዲሳካ ከሚጠበቅበት ሞራላዊ ግዴታዎች አንዱ ምህረት መሆኑን በመጥቀስ ""ለተሻለ ፖለቲካዊ ምኅዳር ሲባል የተወሰኑ እሥረኞችን መንግሥት በምህረት ከእሥር ፈትቷል"" ብሏል። ይህ ምህረት ከዚህ በፊት በተፈጸመ ጥፋት የታሠሩትንም ሆነ በቅርቡ ከተፈጠረው ጦርነት ጋር በተያያዘ የታሠሩትን እንደሚጨምርም ጠቅሷል። ጨምሮም የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋትና ለአካታች አገራዊ ምክክር ሲባል በምህረት የተፈቱት ግለሰቦች ""ካለፈው የጥፋት መንገድ ተምረው፣ የተሻለ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አስተዋጽኦ በማድረግ፣ አገራቸውንና ሕዝባቸውን ይክሳሉ"" ብሎ መንግሥት እንደሚያምን ተገልጿል። መንግሥት ይህንን ውሳኔ የወሰነው ""የኢትዮጵያን ችግሮች ሰላማዊ በሆነ፣ ከእልህና ከመጠፋፋት በራቀ ሁኔታ፣ በአገራዊ ምክክር በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል መንገድ ለመክፈት"" መሆኑን ጠቅሶ፤ ለዘመናት የቆዩ ፖለቲካዊ ችግሮችን በአካታች ምክክር ለመፍታት እንዲቻል መንግሥት ገለልተኛ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም እየሰራ እንደሚገኝም አስታውሷል። የፍትሕ ሚኒስቴር በበኩሉ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሕገ መንግሥት እና የሽብር ችሎት እየታየ ከነበሩት መካከል በእነጃዋር መሐመድ እና በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ያሉ ተከሳሾች ክሳቸው እንዲነሳ መደረጉን አሳውቋል። ለዚህም ምክንያቱ በቀጣይ የሚደረገውን ""አገራዊ የምክክር መድረክ ሂደት ውጤታማነት እና አካታችነት ከፍ ለማድረግ"" መሆኑን አመልክቷል። በተጨማሪም የጤና እና የዕድሜ ሁኔታቸውን ከግምት በማስገባት በእነ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መዝገብ የተከሰሱ ስድስት የህወሓት አባላትና አመራሮች ክሳቸው እንዲነሳ መደረጉን የፍትሕ ሚኒስቴር ገልጿል። ለመሆኑ እነዚህ ከእስር እንዲለቀቁ የተወሰነላቸው ግለሰቦች እንማን ናቸው? በአጭሩ እነሆ. . . ጃዋር መሐመድ አቶ ጃዋር መሐመድ በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ ከሚጠቀሱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ ለበርካታ ዓመታት በውጭ አገር ቆይተው ወደ አገር የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ነበር። በውጭ አገር ቆይታቸው በአገር ውስጥ የሚካሄደውን ተቃውሞ በመምራትና በማስተባበር ጉልህ ሚና የነበራቸው አቶ ጃዋር ኦኤምኤን የተባለውን የሳተላይት ቴሌቪዥን በማቋቋምና በመምራት ጉልህ ሚና ነበራቸው። ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ወደ ፓርቲ ፖለቲካ ለመግባት በመወሰናቸው፣ ከመታሰራቸው ጥቂት ወራት ቀደም ብለው የነበራቸውን የአሜሪካ ዜግነት መመለሳቸው ይታወሳል። በዚህም በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ወደ'ሚመራው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በመግባት እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምረው የነበረ ሲሆን፣ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ በነበረው ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረጉ ነበር። ምርጫው ከተራዘመ በኋላ በ2012 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ አዲስ አበባ ውስጥ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል። በወቅቱም በአቶ ጃዋር መዝገብ ስር ከ20 በላይ ሰዎች የፀረ ሽብር አዋጅን፣ የቴሌኮም አዋጅን፣ የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅን በመተላለፍ ክስ ተመስርቶባቸው፣ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ከአንድ ዓመት በላይ ቆይቷል። አቶ ጃዋር በእስር ላይ በነበሩበት ጊዜ የተለያዩ የጤና እክሎች አጋጥሟቸው እንደነበር የተነገረ ሲሆን፣ በአንድ ወቅት ደግሞ እስራቸውን በመቃወም የረሃብ አድማ አድርገው የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ በመድረሱ ሆስፒታል እስከመግባት ደርሰው እንደነበር ይታወሳል። በቀለ ገርባ አቶ በቀለ ገርባ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የነበሩ ሲሆን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባልና ከፍተኛ አመራር ሲሆኑ በአቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ሥር ተመሳሳይ ክስ ከቀረበባቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ ናቸው። አቶ በቀለ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ከመምጣቱ በፊት ከሚያደርጉት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ተይዘው ለበርካታ ዓመታት በእስር ቤት ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ከእስር የተለቀቁት አቶ በቀለ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በእስር ቆይተው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ጊዜ ነው የተለቀቁት። አቶ በቀለ በእስር ላይ በነበሩበት ጊዜ ከአቶ ጃዋርና ከሌሎች ጋር መታሰራቸውን በመቃወም የረሃብ አድማ አድርገው የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ በመድረሱ ሆስፒታል እስከ መግባት ደርሰው ነበር። እስክንድር ነጋ አቶ እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛና ፖለቲከኛ ሲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት በነበረው አስተዳደር ከጋዜጠኝነት ሥራቸው ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ በእስር ላይ ቆይተዋል። አቶ እስክንድር የተለያዩ ጋዜጦችን በማዘጋጀትና በማሳተም የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው ሲሆን መንግሥትን በመተቸትም ይታወቃሉ። በዚህም ሳቢያ በተደጋጋሚ ለእስርና ለእንግልት የተዳረጉ ሲሆን ለረጅም ጊዜ በእስር ከቆዩ በኋላ ነበር ከሦስት ዓመት በፊት ነጻ የወጡት። አቶ እስክንድር በኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካዊ ለውጥ ተካሂዶ ከእስር እንደወጡ ወደ ጋዜጠኝነት ሥራቸው ተመልሰው ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ፣ በተለይ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የሚያተኩረውን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የተባለውን ፓርቲ መስርተው ሲመሩ ቆይተዋል። ሰኔ ወር 2012 ዓ.ም በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ እስክንድር የፀረ ሽብር አዋጅን በመተላለፍና ኃይልን በመጠቀም መንግሥትን ለመቆጣጠር ሙከራ በማድረግ ተከስሰው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል። አቶ እስክንድርና አብረዋቸው የታሰሩ የፓርቲያቸው አባላት ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ፣ ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት ባለማግኘታቸው ጉዳያቸውን ለፍርድ ቤት አቅርበው ተቀባይነት አግኝተው ነበር። በዚህም ቀደም ሲል ባልታየ ሁኔታ አቶ እስክንድርን ጨምሮ የባልደራስ ፓርቲ አመራሮች እስር ቤት ሆነው በምርጫው ዕጩ ሆነው በመቅረብ ለመወዳደር ቢችሉም ሳይመረጡ ቀርተዋል። በተጨማሪም አቶ እስክንድር በእስር ቤት ሳሉ በአንድ እስረኛ ጥቃት እንደደረሰባቸው የተነገረ ሲሆን ጉዳዩን ለፍርድ ቤትና ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አቅርበው እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀው ነበር። አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወ/ሮ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ የተባሉ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ታኅሣሥ 29/2014 ዓ.ም ከእስር ተለቅቀዋል። አስቴር ስዩም በኬሚስትሪ የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂ የሆነችው ወጣቷ ፖለቲከኛ ቀለብ (አስቴር) ስዩም ከዓመታት በፊት የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) የሰሜን ጎንደር ዞን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በመሆን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ታደርግ ነበረ። ከለውጡ በፊት በነበረው የኢህአዴግ አስተዳደር የፀጥታ ኃይሎች ተይዛ በሽብር ወንጀል ተከስሳ አራት ዓመታትን በማዕከላዊና በቂሊንጦ እስር ቤት ውስጥ ተፈርዶባት ቅጣቷን ጨርሳ ወጥታለች። የሁለት ልጆች እናት የሆነችው አስቴር ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሲመሰረት ፓርቲውን ተቀላቅላ በአመራርነት እያገለገለች የነበረ ሲሆን ሌሎቹ የፓርቲው አመራሮች በታሰሩበት ክስ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በላይ በእስር ላይ ቆይታ ነው አሁን የተፈታችው። አስቴር 'ሀገር ስታምጥ' እንዲሁም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የሚያጠነጥንና መሪዎችን የሚተች 'የመሪዎች ሴራ በኢትዮጵያ' የሚል መጽሐፍት ለንባብ አብቅታለች። አስቴር በተለያዩ ጊዜያት በፖለቲካዊ ተሳትፎዋ የተነሳ በእስር በቆየችበት ጊዜ በአጋጠማት አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ሰቆቃ ምክንያት የተለያዩ የጤና እክሎች እንዳጋጠሟት ይነገራል። ስብሐት ነጋ የህወሓት መስራች የሆኑት እና ኢህአዴግን በመምራት ሥልጣን ከያዘ በኋላ በኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ ቁልፍ ሰው የነበሩት አቶ ስብሐት ነጋ ባለፈው ዓመት በትግራይ ውስጥ ወታደራዊ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ መንግሥት ለግጭቱና ለቀውሱ ዋነኛ ተጠያቂ ናቸው በማለት የእስር ማዘዣ ካወጣባቸው ሰዎች መካከል አንዱ ነበሩ። ይህንንም ተከትሎ የ86 ዓመቱ አዛውንት አቶ ስብሐት ነጋ በኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊት ትግራይ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተነገረው የዛሬ ዓመት ታኅሣሥ 30/2013 ዓ.ም ነበር። አቶ ስብሐት ህወሓትን ከመመስረት በተጨማሪ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበሩ ሲሆን፣ በኢህአዴግና በኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ተደማጭነት የነበራቸው ፖለቲከኛ ነበሩ። አቶ ስብሐት ከፖለቲካው ባሻገር የህወሓት የምርትና የአገለግሎት ተቋማትን የሚያስተዳድረውና በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱ ተቋማትን በስሩ የያዘው ኤፈርትንም መርተዋል��� በተጨማሪም የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ ጥናት ተቋምን ጡረታ እስከ ወጡበት ጊዜ ድረስ በዋና ዳይሬክተርነት መርተውት ነበር። በትግራይ ክልል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ሲፈለጉ ከነበሩት የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች መካከል የሚገኙት አቶ ስብሐት፣ ባለፈው ዓመት ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በሆነ ገደላማ አካባቢ ከባለቤታቸውና ከእህታቸው ጋር ተይዘው ነበር ወደ አዲስ አበባ የመጡት። አቶ ስብሐት በአገር ክህደት፣ በትግራይ ይገኝ በነበረው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በማድረስና በመሳሪያ በታገዘ አመጽና ሁከት በማነሳሳት ወንጀሎች ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው እየታየ ነበር። ቅዱሳን ነጋ የህወሓት ነባር አባልና ከፍተኛ አመራር የነበሩት ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ በትግራይ ክልል ከተቀሰቀሰው ጦርነት ከወራት በኋላ በመከላከያ ሠራዊት በቁጥጥር ስር የዋሉት ከወንድማቸው ከአቶ ስብሐት ነጋ ጋር ነበር። ወ/ሮ ቅዱሳን በህወሓት ውስጥ ካላቸው ሚና በተጨማሪ የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ሆነው ሠርተዋል። ባለቤታቸው አቶ ፀጋይ በርሄ የህወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣን ከመሆናቸው በተጨማሪ የክልሉ ፕሬዝዳንት የፌዴራል መንግሥቱ ደኅንነት አማካሪ ነበሩ። ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር የህወሓት አባል ሲሆኑ በፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ አባል ከመሆናቸው በተጨማሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር ከአንድ ዓመት በፊት በፌደራሉ ኃይሎች ተይዘው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የነበረ ሲሆን አሁን እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው ግለሰቦች መካከል አንዷ ናቸው። ሌሎች ከጦርነቱ መቀስቀስ በኋላ በርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች በፌደራሉ የፀጥታ ኃይሎች መያዛቸው የሚታወቅ ቢሆንም አሁን በምህረት የሚለቀቁት ስድስቱ ብቻ መሆናቸውን ከመንግሥት በኩል የወጣው መግለጫ ያመለክታል። በዚህም መሠረት ከአቶ ስብሐት ነጋ፣ ከወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ ከወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር በተጨማሪ የቀድሞው የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ዓባይ ወልዱ፣ አምባሳደርና የክልሉ ባለሥልጣን የነበሩት አቶ አባዲ ዘሙና አቶ ኪሮስ ሐጎስ ይገኙበታል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59920859 +health ዕድሜያቸው 40 የሞላ እና ጥቁር ወንዶች ሊያውቁት የሚገባ የካንሰር ዓይነት ለበርካቶች ፕሮስቴት ሲባል ሁለቱ የወንድ ልጅ የዘር ፍሬዎች አካባቢ ወይም የዘር ፍሬ ከረጢቱ ውስጥ ያለ አካል እንደሆነ ነው የሚያስቡት። የኩላሊት፣ የፕሮስቴት፣ የሽንት ፊኛ እና ቧንቧ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ፍፁም ሠለሞን ግን ፕሮስቴት ከሽንት ፊኛ በታች ያለ አካል ነው ይላሉ። እንደ ዶ/ሩ ገለጻ ከሆነ ፕሮስቴት በወንድ ልጅ ብልት እና ፊኛ መካከል የሚገኝ እጢ ነው። ፕሮስቴት የዘር ፈሳሽ የማመንጨት ጥቅም አለው። የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ወደ ውጪ ሲፈስ ሰባ በመቶ ያህሉን የሚያመነጨው ፕሮስቴት መሆኑን ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ሀዋስ የሚዋኘው እንዲሁም ምግቡን የሚያገኘው ከዚህ ፈሳሽ መሆኑን አክለው ይጠቅሳሉ። ታድያ የፕሮስቴት ችግር ያለበት ወንድ የዘር ፈሳሹ ወደ ውጪ መፍሰሱን ትቶ የሚመለሰው ወደ ፊኛው ነው። ስለዚህ ይላሉ ዶ/ር ፍፁም ፕሮስቴት፣ የዘር ፈሳሹ ወደ ፊኛ እንዳይመለስ እና ወደ ውጪ እንዲወጣ ይረዳል። ፕሮስቴት ልክ እንደ ምራቅ አመንጪ እና ታይሮይድ እጢዎች ሁሉ እጢ (ግላንድ) ነው። የፕሮስቴት እጢ የሚገኘው ወንድ ላይ ብቻ ነው። እንደ ዶ/ር ፍፁም ገለጻ በየትኛውም የሰውነታችን ክልፍ ላይ ካንሰር ሊከሰት ይችላል፣ ስለዚህም ፕሮስቴትም ለካንሰር  ይጋለጣል። በዓለም ��ይ ከስምንት ወንዶች መካከል አንዱ በሕይወት ዘመኑ በፕሮስቴት ካንሰር ይያዛል። ፕሮስቴት አጥቢ እንስሳት ላይ በሙሉ የሚገኝ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስም ካንሰሩ ከሰው ውጪ የታየው ውሾች ላይ ብቻ ነው። 80 በመቶ ያህሉ ፕሮስቴት ካንሰር ቀስ ብሎ የሚያድግ እንዲሁም ህመም ሳያስከትል ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ነው። በብዛት የፕሮስቴት ካንሰር በመጀመሪያ ከፕሮስቴት እጢ ላይ ተወስኖ ይቆይና ከባድ ጉዳት በማያስከትል መልኩ ቀስ እያለ የሚያድግ ችግር ነው። ለፕሮስቴት ካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል አንዱ እድሜ ነው። እድሜያቸው ከ50 በላይ የሆኑ፣ ጥቁር ወንዶች እንዲሁም በቤተሰባቸው ውስጥ የፕሮስቴት ካንሰር የተያዘ ሰው የሚገኝ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ። የዩናይትድ ኪንግደም ተመራማሪዎችም እድሜያቸው 40 የሞላቸው ወንዶች በየዓመቱ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። ዶ/ር ፍፁም በበኩላቸው ፕሮስቴት ካንሰር ከ40 ዓመት በታች በሆኑ ሰዎች ላይ የመገኘት እድሉ እጅጉን በጣም አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ። እድሜያቸው ከ20 እስከ 30 የሆነ ወንዶች በፕሮስቴት የመያዝ እድላቸው አንድ በመቶ ብቻ ነው። ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው የፕሮስቴት ካንሰር የሚከሰተው እድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ በሆናቸው ወንዶች ላይ ነው ይላሉ ዶ/ር ፍፁም። አፍሪካውያን ከነጮች አንጻር ሲታይ በዚህ ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ተመሳሳይ የቤተሰብ ታሪክ ያላቸው ግለሰቦች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። ወንድም፣ አባት፣ አያት እንዲሁም አጎቱ በፕሮስቴት ካንሰር የተያዘበት ግለሰብ የተጋላጭነት ዕድሉ ሰፊ ነው። ከቅርብ ቤተሰብ መካከልም አባቱ በዚህ ካንሰር የተያዘ እና አያቱ የተያዘ ወንድ እኩል የተጋላጭነት ልክ እንደሌላቸው ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። አባቱ ወይንም ወንድሙ በፕሮስቴት ካንሰር የተያዘ ወንድ፣ ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከሁለት እና ሦስት እጥፍ በላይ ተጋላጭ ነው። ሌላኛው መታየት ያለበት በቤተሰብ ውስጥ ካንሰር የተያዘው ሰው በስንተኛው ዕድሜው ላይ ተገኘበት የሚለው ወሳኝ ነጥብ መሆኑን ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። ይህንንም ሲያብራሩ ከ65 ዓመት በታች የፕሮስቴት ካንሰር የተገኘበት አባት፣ ልጁ ለካንሰሩ የመጋለጥ ዕድሉ ከፍተኛ ይሆናል ሲሉ ያስረዳሉ። ይህም ማለት ልጁ እስከ 5 እጥፍ ድረስ የተጋለጠ ነው። ሌላኛው ደግሞ ይላሉ ዶ/ር ፍፁም፣ አባቱ እና አያቱ በፕሮስቴት የተጠቁ እና አባቱ ብቻ የተያዘ ልጅን ብናወዳድር፣ ይህ ሁለቱም የቤተሰብ አባላት የተያዙበት ግለሰብ የበለጠ ተጋላጭ ነው ይላሉ። የዘረመል እክል (ጄኔቲክ ሚውቴሽን) ላይ እክል ካለ የበለጠ ለዚህ ካንሰር ያጋልጣል። ካንሰር በአብዛኛው ሲታይ ህዋሱ በተነሳበት አካል ወይንም ስፍራ ከመጠን በላይ ይራባል። ከዚያም በመቀጠል ባለበት አካል ላይ ብቻ ተገድቦ ሳይቀመጥ ወደ ሌላ የአካል ክፍል ይሰራጫል። ፕሮስቴት ካንሰር ተገቢውን ሕክምና በተገቢው ሰዓት ካላገኘ የሽንት ፊኛን ሊያፍን ያችላል። የፕሮስቴት እጢ ከተራባ በኋላ ፕሮስቴት አጠገብ ያሉ የሽንት ቧንቧ እና ፊኛ ላይ ይዛመታል። ከዚያም አልፎ በደም ስር ተሰራጭቶ ወደ ጀርባ ይሄዳል። ፕሮስቴት ካንሰር ብዙ ጊዜ በደም ስር አድርጎ ወደ ጀርባ፣ አከርካሪ አጥንት እና ሆድ ውስጥ ወዳሉ ንፍፊቶች ይሰራጫል። የፕሮስቴት ካንሰርን ለመከላከል አመጋገብን ማስተካከል ዋነኛው መፍትሄ ነው። አትክልት እና ፍራፍሬ የበዛበት፣ ዓሳ፣ የዓሳ ዘይት፣ ኦሊቭ ኦይል ያለው ምግብ መመገብ ለመከላከል ይረዳል። ከእነዚህ በተጨማሪ አረንጓዴ ሻይ እነዲሁም ቫይታሚን ዲ መጠቀም የመከላከል አቅምን ያጎለብታል። የፕሮስቴት ካንሰር አብዛኛውን ጊዜ ቀስ ብሎ የሚያድግ በመሆኑ፣ ከጀመረበት አንስቶ ለመሰራጨት እና ሕይወትን አደጋ ላይ ለመጣል ረዥም ጊዜ ይወስድበታል። ስለዚህም ቢያንስ በዓመት ወይንም በሁለት ዓመት አንዴ ቅድመ ምርመራ ማድረግ ጠቃሚ ነው። በተለይ ለካንሰሩ የመጋለጥ ዕድላቸው የሰፋ የቤተሰብ ታሪክ ያላቸው፤ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ። ቅድመ ምርመራ ለመጀመር የተለያዩ አገራት፣ የተለያዩ መመርያዎች እንዳላቸው የሚናገሩት ዶ/ር ፍፁም፣ አንድ ሰው እድሜው ከ50 አስከ 55 ዓመት ሲሆን ቅድመ ምርመራ እንዲያደርግ ይመከራል። ተመሳሳይ የቤተሰብ ታሪክ ያለው ግለሰብ ደግሞ እድሜው ከ40 አስከ 45 ላይ እያለ ምርመራውን ቢጀመር መልካም መሆኑን ገልፀዋል። “ቢያንስ ቢያንስ በየሁለት ዓመቱ ቅድመ ምርመራ ማድረግ ይመከራል” ሲሉ ያክላሉ። ከሁሉ በፊት በቤተሰብ ውስጥ ያለን የፕሮስቴት ካንሰር ታሪክን ማወቅ እንዲሁም ወደ አርባዎቹ የእድሜ ክልል ሲገባም በተወሰ ጊዜው ውስጥ ምርመራ ማድረግ ችግሩ ካለ ስር ሳይሰድ ለማከም ይረዳል። ምርመራው ተደርጎ የፕሮስቴት ካንሰር መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ የተለያዩ ዓይነት ሕክምናዎች እንዳሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከእነዚህም ውስጥ በቀዶ ሕክምና ካንሰሩን ማውጣት፣ የጨረር ሕክምና ወይንም ደግሞ የወንድ ልጅ ቴስቴስትሮን ካንሰሩን በዋነኛነት ስለሚመግብ በሰውነት ውስጥ ያለውን የቴስቴስትሮን መጠንን ለመቀነስ ሕክምና ይሰጣል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cndxlne6nk9o +sports ጣሊያን ስፔንን በመርታት ለፍጻሜ መድረሷን አረጋገጠች በአውሮፓ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ጣልያን ስፔንን በፍጹም ቅጣት ምት በማሸነፍ ለፍጻሜ መድረሷን አረጋገጠች። በእንግሊዙ ዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዘጠና ደቂቃው እና ተጨማሪ ደቂቃ አንድ አቻ በመጠናቀቁ ሁለቱ ቡድኖች በፍጽም ቅጣት ምት እንዲለያዩ ሆኗል። የስፔኑ የፊት መስመር ተጫዋች አልቫሮ ሞራታ የስፔንን የመጨረሻውን ፍጹም ቅጣት ምት የሳተ ሲሆን የጣልያኑ ጆርጂንዮ ደግሞ ፍጹም ቅጣት ምቱን ወደ ግብ መቀየሩን ተከትሎ ጣልያን ዛሬ ምሽት ከእንግሊዝና ዴንማርክ አሸናፊ ጋር ለፍጻሜ በመጪው እሁድ ትጫወታለች። የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በፈጣን እንቅስቃሴና በስፔን የተበላይነት የተሞላ ቢሆንም ግብ ግን ሳይቆጠር ነበር የተጠናቀቀው። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ የጣልያኑ ፌደሪኮ ኪዬዛ አስገራሚ ግብ አስቆጥሮ ጣልያንን መሪ ማድረግ ችሏል። ነገር ግን ጨዋታው ሊጠናቀቅ እየተቃረበ በነረበት ሰአት የስፔን ተጫዋቾች በጥሩ ጨዋታ ጣልያን የግብ ክልል ውስጥ የተቀባበሏትን ኳስ ተቀይሮ የገባው አልቫሮ ሞራታ በግሩም ሁኔታ ወደ ግብነት በመቀየር አገሩን አቻ ማድረግ ችሎ ነበር። የጣልያኑ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ያዋቀሩት ቡድን እስካሁን ድረስ ብዙም ሳይቸገር ነበር ለግማሽ ፍጻሜው መድረስ የቻለው። ነገር ግን ከስፔን ጋር የተደረገው ጨዋታ ጣልያኖችን የፈተነ ነበር። የስፔኑ አሰልጣኝ ሊዊስ ኤነሪኬ የጣልያንን አጨዋወት በሚገባ አጥንተውና ኳስን መሰረት ያደረገ ጨዋታ ላይ አተኩረው ነበር የጀመሩት። በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ እንደ ሞራታ ብዙ ግብ የሚሆኑ እድሎችን ያባከነ የለም በሚል በርካቶች ሲወቅሱት የነበረ ሲሆን ስፔን ውስጥም ቤተሰቦቹ ዛቻ ደርሶባቸዋል። ነገር ግን በግማሽ ፍጻሜው አገሩን አቻ አድርጎ ነገሮችን መለወጥ ቢችልም ፍጹም ቅጣት ምቱን መሳቱ ደግሞ ተመልሶ ጫና ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ጣልያን ከምድብ ድልድል ጀምሮ ባልተለመደ መልኩ ማጥቃት ላይ መሰረት ያደረገና ብዙ ግቦችን ማስቆጠር የሚያስችል አጨዋወት ነበር ይዛ የመጣችው። ነገር ግን ከስፔን በነበረው ጨዋታ ወደቀድሞው መከላከልን ማዕከል ያደረገ አጨዋወት ተመልሰው ነበር። አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ብሄራዊ ብድኑን ከተረከቡ ወዲህ ለ2018ቱ የዓለም ዋንጫ እንኳን ጣልያንን ማሳለፍ አቅቷቸው የነበረ ቢሆንም በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ግን በደንብ የተደራጀና ውጤታማ ቡድን ሰርተው ለፍጻሜ መድረስ ችለዋል። ዛሬ ምሽት አራት ሰአት ላይ ደግሞ ሌላኞቹ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚዎች ዴንማርክና እንግሊዝ ይገናኛሉ። የዚህ ጨዋታ አሸናፊ የፊታችን እሁድ በሚካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ከጣልያን ጋር ይፋለማል። https://www.bbc.com/amharic/news-57737844 +health የሌሊት ወፍ ሳንድዊች የሚበላ ሰው የሚያሳየው ማስታወቂያ ላይ ምርመራ ተጀመረ "የሌሊት ወፍ ሳንድዊች ሲበላ የሚያሳይ ማስታወቂያ ላይ የአውስትራሊያው የማስታወቂያ ጥበቃ ድርጅት ምርመራ ጀመረ፡፡ ከቤት ውጭ መገልገያ አምራች የሆነው ቦቲንግ ካምፓኒ ፊሺንግ (ቢሲኤፍ) ያሠራው ይህ ማስታወቂያ በዩቲዩብ ከ 250,000 ጊዜ በላይ ታይቷል፡፡ በማስታወቂያው ለላይ ተዋናዩ ወረርሽኙ የተከሰተው አንድ ግለሰብ የሌሊት ወፍ በመብላቱ ነው ብሎ ይቀልዳል። የመጀመሪያዎቹ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች በቻይና ዉሃን ከተማ ከሚገኝ የእንሰሳት ገበያ ቢገኙም፣ ቫይረሱ እንዴት እንደጀመረ እና እንደተሰራጨ ትክክለኛ ማረጋገጫ የለም፡፡ የማስታወቂያ ደረጃዎች ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ""የማስታወቂያ ደረጃዎች በቢሲኤፍ የበጋ ዘመቻ ማስታወቂያ ላይ በርካታ ቅሬታዎች የደረሱት ሲሆን እነዚህን ቅሬታዎች በመገምገም ላይ ይገኛል"" ብለዋል። የቢሲኤፍ ቃል አቀባይ ቀደም ሲል ለአውስትራሊያ መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት ቀለል ብሎ በቀረበው ማስታወቂያ ብዙ አውስትራሊያውያን በክረምቱ ቤታቸውን እንዲቆዩ እና የራሳቸውን ጓሮ እንዲመረምሩ ያበረታታል፡፡ ""በእርግጥ የተከሰተውን ወረርሽኝ እና ስርጭት ምን ያህል እንደሆነ ተረድተናል። ይህ ግን ማስታወቂያ በተመሳሳይ መንፈስ የተቀረፀ መሆኑ ግልፅ ነው"" ብለዋል። ቢሲኤፍ ለአውስትራሊያ የማስታወቂያ ጥበቃ እንግዳ አይደለም- በጎርጎሮሳዊያኑ 2016 እና 2018 ባሠራቸው ማስታወቂያዎች ብዙ ቅሬታ ቀርቦበት ነበር፡፡ ""ባለፉት ዓመታት ቢሲኤፍ ተመሳሳይ ማስታወቂያዎችን የማስነገር ባህል መሥርቷል"" ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡ "" ማስታወቂያዎቹ ተቺዎች ቢኖራቸውም እኛም ግን ያንን እናውቃለን"" ሲሉም ያክላሉ። እንደባለሙያዎች ከሆነ በአውስትራሊያና በቻይና መካከል ያለው ግንኙነት ባለፈው ዓመት በአስርተ ዓመታት ውስጥ ከነበረበት ደረጃ ዝቅ ብሏል። ማስታወቂያው ውጥረቱ ይበልጥ እየተለጠጠ ስለመሆኑ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ አውስትራሊያ የኮሮናቫይረስ አመጣጥን ለማወቅ የሚያደረገውን ዓለም አቀፍ ምርመራን ደግፋለች፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የቻይና ተማሪዎች እና ቱሪስቶች ዘረኝነትን ፍራቻ ወደ አውስትራሊያ እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው የአውስትራሊያ ምርቶች የሚገቡትም በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ትኩረት ነበር፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ቻይና በአውስትራሊያ ወይን ላይ እስከ 212% የሚደርስ ግብር ጥላለች።" https://www.bbc.com/amharic/55547003 +politics መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ ለምን የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ አዳገተው? ከወለጋ ዞን ሆሮ ጉዱሩ ተፈናቅሎ አሁን አዲስ አበባ የሚገኘው የ37 ዓመቱ ግለሰብ፣ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ በቃላት መግለጽ ከባድ ነው ይላል። ለደኅንነቱ ሲል ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገው ይህ ግለሰብ በቅርቡ በአካባቢው የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በአንድ ቦታ ስምንት የቤተሰቡን አባላት እንዳጣ ለቢቢሲ ይናገራል። “ከቤተሰቦቼ ግማሹ ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ በሕይወት የተረፉት ደግሞ ተበታትነዋል፤ የት እንዳሉ የማይታወቁም አሉ።” በኦሮሚያ ክልል በተለይም በምዕራባዊው ክፍል የታጠቁ ኃይሎች ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠኑ እየጨመረ የሚደርሰውም ጉዳት እየበረታ መጥቷል። ቢቢሲ በተለያዩ ጊዜያት ያናገራቸው ነዋሪዎች ለጥቃቱ ተጠያቂዎች ‘ፋኖ’ የሚሏቸው ኃይሎች እንዲሁም መንግሥት ሽብርተኛ ነው ያለው ኦነግ/ሸኔ እንደሆነ ይናገራሉ። ምንም እንኳ ሁለቱ ኃይሎች ለሚደርሰው ጥቃት ኃላፊነት ወስደው ባያውቁም የፌዴራሉ መንግሥት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጣታቸውን ወደ ታጣቂዎቹ ይቀስራሉ። የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ‘ኦነግ/ሸኔ’ እንዲሁም ‘አክራሪ የአማራ ኃይሎች’ ለፖለቲካ ዓላማቸው ሲሉ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው ሲሉም ይወቅሳሉ። ላለፉት አራት ዓመታት በመንግሥትና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ሸኔ) መካከል በተደረጉ ግጭቶች ሳቢያ በርካታ ሰላማዊ ነዋሪዎች ሕይወታቸውንና ንበረታቸውን አጥተዋል፤ ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል። በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት ከመገናኛ ብዙኃን ዕይታ የተሸሸገ ይመስላል፤ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ትኩረት ተነፍጎታል። ይህ የሆነው ለምን ይሆን? መንግሥትስ የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ ለምን ተሳነው? በኦሮሚያ ክልል በተለይም በደቡባዊ እና በምዕራባዊ ክፍሎቹ ውስጥ የሚታየው ቀውስ ላለፉት አራት ዓመታት ዘልቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ የፖለቲካ ምሕዳሩ እንዲሰፋ በማለት በውጭ አገራት እና ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ ፈቀዱ። በዚህ ወቅት ወደ ፖለቲካው መድረክ ከተመለሱ ፓርቲዎች መካከል ለዘመናት የትጥቅ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አንዱ ነው። ይህንን ውሳኔ ተከትሎ ኦነግ ለሁለት ተከፈለ። አንደኛው ክንፍ የትጥቅ ትግሉን አቁሞ በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ የሚለው ሲሆን፣ ሌላኛው ክንፍ ደግሞ በጠመንጃ አላማውን ለማሳካት የሚታገል ነው። እነዚህ ጉዳዮች በአገር ቤት መገናኛ ብዙኃን ቢዘገቡም በዓለም አቀፍ ሚድያ ግን ችላ የተባሉ ነበሩ ይላሉ የአዲስ ስታንዳርድ መሥራች ፀዳለ ለማ። በተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በመቅረብ በኢትዮጵያ ስላሉ ሁኔታዎች ትንታኔ በመስጠት የሚታወቁት ፀዳለ፣ የኦሮሚያ ጉዳይ በተለያዩ ርዕሰ ዜናዎች ምክንያት ተቀብሮ ነበር ይላሉ። ከእነዚህ ምክንያቶች አንደኛው የትግራይ ጦርነት ነው። የትግራይ ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ በትግራይ ውስጥ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት፣ ኦነግ/ሸኔ እንዲሁም ህወሓት ሽብርተኛ ቡድኖች ናቸው ሲል ማወጁ ይታወሳል። ይህ የታጠቀ ኃይል በተለያዩ ጊዜያት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል በሚል በተደጋጋሚ ወቀሳ ቢደርስበትም ቡድኑ ለደረሱት ጥቃቶች ኃላፊነት ከመውሰድ ተቆጥቧል። ፀዳለ እንደሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የፖለቲካ ምሕዳሩን ሲከፍቱ፣ እሥረኞችን ሲፈቱ፣ የምጣኔ ሃብት ‘ሪፎርም’ እያካሄዱ ሳለ በኦሮሚያ ክልል ግጭት ነበር። “ምንም እንኳ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የመገናኛ ብዙኃን ችላ ቢሉትም፣ የኦሮሞ ነፃነት ኃይል ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሲገነጠል፤ ግጭቶች ሲጀማምሩ. . . የአገር ቤት ሚድያው ሲዘግብ ነበር።” አክለው እንደሚሉት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ለኦሮሞ ጥያቄ ምላሽ ናቸው” ብሎ ስለሚያስብ በኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ ትኩረት ተነፍጎታል። በሰሜን በኩል መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር ጦርነት ላይ በነበረበት ወቅት ጭምር ከኦሮሚያ ክልል የሚወጡ ዜናዎች መልካም አልነበሩም። የኦሮ�� ነፃነት ሠራዊት፣ ኦሮምያ ክልል ያሉ የአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እያደረሰ ነው መባሉን ተከትሎ ፋኖ የተባለው ኃይል ጥቃት እያደረሰ ነው የሚል ወሬ መሰማት ጀመረ። ተንታኟ እንደሚሉት ይህ ግጭት ከመገናኛ ብዙኃንና ከሰብዓዊ መብት ቡድኖች ዕይታ ውጪ የሆነበት ሌላኛው ምክንያት ጦርነቱ የሚካሄድበት ቦታ በጣም ራቅ ያለ መሆኑ ነው። “ደቡብ እና ምዕራብ ኦሮሚያ ጀምሮ ተስፋፍቶ አሁን ወደ ማዕከል የመቅረብም ነገር አለ። የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት መቋረጡ የሚድያ ሽፋን እንዳይሰጠው አስተዋፅዖ አድርጓል።” ቢቢሲ በተለያየ ጊዜያት ጥቃት ሲደርስ የሚያናግራቸው ሰላማዊ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ሰለባ እንደሆኑ፣ ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንደተፈናቀሉ ይናገራሉ። ከእነዚህም መካከል የ37 ዓመቱ የሆሮ ጉዱሩ ነዋሪ የመንግሥት ኃይሎችን ከደረሰበት ጥቃት ሊያስጥሉት እንዳልቻሉ ይናገራል። በተለይም በምዕራብ ወለጋ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በተደጋጋሚ ለሚደርስባቸው ጥቃት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ተወቃሽ በማድረግ፤ መንግሥት ተገቢውን ጥበቃ አላደረገልንም ይላሉ። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በበኩሉ “ጥቃቱን አልፈፀምንም፤ ተጠያቂው መንግሥት ነው” የሚል ምላሽ በመስጠት ክስተቱ በገለልተኛ አካል ይጣራ ይላል። “አሁን ያለው ሁኔታ ግጭት ከማለት ጦርነት ተብሎ ቢጠራ ይሻላል” ይላሉ በጄምስ ማዲሰን ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ታሪክ መምህር እና ተመራማሪው ፕ/ር ኢታና ሃብቴ። ተመራማሪው በተለያዩ ቦታዎች ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ጥቃት ሲደርስባቸው መንግሥት ደኅንነታቸውን  የመጠበቅ ኃላፊነቱን አልተወጣም ብለው ያምናሉ። ምሑሩ፤ መንግሥት ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ሁኔታውን የመቆጣጠር አቅም አለው፤ ነገር ግን ፍላጎት ይኑረው አይኑረው እርግጠኛ አይደሉም። በኦሮሚያ ክልል ግጭት በሚከሰትባቸው ቦታዎች ያሉ ነዋሪዎች የሚያቀርቡትን ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ እንዲሁም የፈደራል ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎትን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ኮሚሽናቸው በቅርቡ የተዘገቡ ጥቃቶችን በተመለከተ ምርመራ እያደረገ እንደሆነ የጠይቅናቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) “መረጃ እየሰበሰብን ነው። ምርመራችን ስናጠናቅቅ ውጤቱን ይፋ እናደርጋለን” ሲሉ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። በሌላ በኩል ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ወደ አካባቢው አቅንተው ጉዳዩን እየመረመሩት እንደሆነ  ለማጣራት ያናገርናቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዋች “ለጊዜው አስተያየት መስጠት አንችልም” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል። ፀዳለ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከሌሎች በተሻለ መረጃ የማግኘት ዕድል አለው ብለው ቢያምኑም “ድርጅቱ የሚያወጣው ሪፖርት አከራካሪ መሆኑ ተነሳሽነቱን ጎድቶታል” ብለው ያስባሉ። “ገለልተኛ የሆነ ሪፖርት ቢያወጡ እንኳ አወዛጋቢ ስለሚሆን ይህ ጉዳይ መነሳሳታቸውን የጎዳው ይመስለኛል። ይሄ ሊሆን ባይገባማ አስተዋፅዖ ግን ይኖረዋል።” ተንታኟ፤ ሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት የኦሮሚያን ግጭት ልክ እንደ ትግራይ ጦርነት ተከታትለው ባይመረምሩትም፣ ከዚህ ቀደም የተወሰኑ ምርምራ ማከናወናቸውን መዘንጋት አይፈልጉም። እርሳቸው እንደሚሉት ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ልክ እንደ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ሁሉ የሰብዓዊ መብት ተቋማትም ጉዳዩን ችላ እንዲሉት አስተዋፅዖ አድርጓል። ፕሮፌሰር ኢታና፤ “ይህን ጥያቄ ከ2018 በፊት ብጠየቅ ቀለል ያለ ምላሽ እሰጥ ነበር” በማለት፣ ጉዳዩ አሁን በጣም ከባድ እና የተወሳሰበ ደረጃ ላይ ስለደረሰ በቀላሉ ምላሽ የሚገኝበት አይመስልም። አዲስ ስታንዳርዷ ፀዳለ ለማ በበኩላቸው፣ ለችግሩ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲበጅለት “መንግሥት ዝግጁ አይደለም” የሚል ስጋት አላቸው። ፀዳለ፤ መንግሥት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ሽብርተኛ ተብሎ፤ እውቅና መንፈጉ፣ ጉዳዩ ከቁም ነገር እንዳይወሰድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል ይላሉ። “የኦሮሞ ፓርቲዎችን ጨምሮ አንዳንድ ፖለቲከኞች በመንግሥት ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል። ይህንን የተቃወሙ ሌሎች ፓርቲዎች ደግሞ ከፖለቲካ ምሕዳሩ ተገፍተዋል።” መንግሥት፤ ለኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እውቅና መስጠት በፍፁም አይሻም የሚሉት ፀዳለ፣ ይህ ካልሆነ ፖለቲካዊ መፍትሔ አይመጣም ብለው ያምናሉ። ፕ/ር ኢታና ደግሞ መጀመሪያ መቅደም ያለበት ጦርነቱ መቆሙ ነው ይላሉ። “ጦርነት ካልቆመ ንግግር ማድረግ አይቻልም።” “የሕዝብ ደኅንነት ተጠብቆ፤ የታጠቀው ኃይል እውቅና ተሰጥቶት፤ ጥያቄዎች ወደ ጠረጴዛ መጥተው ውይይት ሊደርግባቸው ይገባል።” ከዚህ ጋር በተያያዘ የኦሮምያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ መንግሥታቸው በክልሉ ለሚስተዋለው የፀጥታ ችግር መፍትሔ ለማበጀት እየሠራ ነው ሲሉ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። ነገር ግን አሁንም ሰላማዊ ዜጎች በስጋት ውስጥ መኖራቸውን ቀጥለዋል፤ በየትኛዋ ደቂቃ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ሊሰደዱ እንደሚችሉ አያውቁም፤ ብዙዎች ለቅሷቸውን ለፈጣሪያቸው ከማሰማት ውጪ አማራጭ ያላቸው አይመስልም። https://www.bbc.com/amharic/articles/czkd948zd7zo +politics ምዕራባውያን በሩሲያ እና በፑቲን ላይ ምን አይነት ማዕቀቦችን ሊጥሉ ይችላሉ? ምዕራባውያን አገራት ሩሲያ ዩክሬንን የምትወር ከሆነ በርካታ ማዕቀቦችን ሊጥሉባት እንደሚችሉ እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። ኃያላኑ ምዕራባውያን በሩሲያ እና በመሪያዋ ቭላድሚር ፑቲን ላይ ሊጥሉ የሚችሏቸው የማዕቀብ አይቶችን ይፋ ባያደርጉም፤ ተንታኞች ግን የሚከተሉት ማዕቀቦች በሞስኮ እና ፑቲን ላይ ሊተገበሩ ይችላሉ እያሉ ነው። የገንዘብ ዝውውር ዕቀባዎች በሩሲያ ላይ ሊጣሉ ከሚችሉ ማዕቀቦች መካከል አንዱ ሞስኮን 'ስዊፍት' ከተባለው የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ማገድ ነው። ስዊፍት ከ200 በላይ በሆኑ አገራት፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ኩባንያዎች የፋይናንስ መልዕክቶችን ለመለዋወጥ የሚጠቀሙት የየገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ነው። ሩሲያ ከስዊፍት ታገደች ማለት፤ ባንኮቿ ከአገር ውጪ ካሉ ባንኮች ጋር የገንዘብ ዝውውር ማድረግ በእጅጉን አዳጋች ያደርግባቸዋል። መሰል ማዕቀብ እአአ 2012 ላይ ኢራን ላይ ተጥሎ ነበር። ታዲያ ኢራን በዚህ ማዕቀብ ምክንያት ከነዳጅ ገበያ ማግኘት የነበረባትን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ሳትሰበስብ ቀርታለች። የዶላር ክልከላ ዋሽንግተን ሞስኮ የአሜሪካ ዶላርን ለግብይት እንዳትጠቀም መከልከል ትችላለች። ሩሲያ ዶላርን መጠቀም አትችልም ከተባለች፤ በምዕራባውያን አገራት የሚገኙ ባንኮች ከሩሲያ ባንኮች ጋር በዶላር ልውውጥ ቢያደርጉ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ይህ ደግሞ ሩሲያ ከተቀረው ዓለም ጋር የሚኖራት ግብይት እጅጉን የተገደበ ይሆናል። ሩሲያ የጋዝ አቅርቦቷ ለገበያ የሚቀርበው በአሜሪካ ዶላር እንደመሆኑ በምጣኔ ሃብቷ ላይ የሚኖረው አሉታዊ ተጽእኖ ከፍ ያለ ነው። የባንክ እገዳዎች አሜሪካ በቀላሉ የሩሲያ ባንኮችን ጥቁር መዝገብ ላይ ልታሰፍር ትችላለች። ይህ ማለት ማንኛውም አካል ከሩሲያ ባንኮች ጋር ግብይት መፈጸም ፍጹም እንዳይቻለው እንደማድረግ ይቆጠራል። ይህ በሞስኮ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት እንዲከሰት ያደርጋል። አሜሪካ በሩሲያ ባንኮች ላይ የምትጥለው እገዳ ጉዳቱ ለሞስኮ ብቻ አይተርፍም። ገንዘባቸው በሩሲያ ባንኮች ያስቀመጡ ምዕራ���ውያን ዲታዎችም የዚህ ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ። የኤክስፖርት ቁጥጥር ገደቦች ምዕራባውያኑ ሩሲያ ምን፤ በምን ያክል መጠን ወደ አገር ውስጥ ታስገባ የሚለውን መቆጣጠር ይችላሉ። ለምሳሌ አሜሪካ ኩባንያዎቿ የአሜሪካ ቴክኖሎጂ ወይም ሶፍትዌር ውጤት የሆኑ ምርቶች በሩሲያ ገበያዎች ላይ እንዳይሸጡ ልታግድ ትችላለች። የኃይል ሽያጭ ገደብ የሩሲያ ምጣኔ ሃብት መሠረቱን ካደረገባቸው ዘርፎች መካከል አንዱ የጋዝ እና የነዳጅ ሽያጭ ላይ ነው። ክሬምሊን ለምዕራባውያኑ ጋዝ እየሸጠች ከፍተኛ ገንዘብ ታገኛለች። ምዕራባውያኑ አገራት እና ኩባንያዎች ከሩሲያ ጋዝ እና ነዳጅ መግዛትን መከልከል ይችላሉ። ይህ ውሳኔ በተመሳሳይ በተለይ ለአውሮፓውያኑ አገራት ከባድ ኪሳራን ይዞ ሊመጣ ይችላል። አውሮፓውያኑ በብዛት የሚጠቀሙት ጋዝ ምንጩ ከሩሲያ እንደመሆኑ፤ በሩሲያ የኃይል አቅርቦት ላይ ዕቀባ ቢጣል በአውሮፓ የጋዝ ዋጋ ጣራ ይነካል። ግለሰቦችን ዒላማ ማድረግ አዳዲስ ማዕቀቦች ግለቦች ላይ ሊጣሉ ይችላሉ። ይህ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቅርብ አጋሮቻቸውን ሊጨምር ይችላል። የንብረት እና የጉዞ እገዳ ደግሞ ዋነኛዎቹ ግለሰቦች ላይ ሊጣሉ የሚችሉ ማዕቀቦች ናቸው። በተጽኖ ፈጣሪ ሩሲያውያን ላይ መሰል ማዕቀብ መጠል ምናልባት ንብረታቸውን እና አራሳቸውን ማንቀሳቀስ ያልቻሉ ግለቦች ፕሬዝደንት ፑቲን ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ የሚል ግምት በምዕራባውያን አገራት መንግሥታት ዘንድ ሊፈጠር ይችላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ለምዕራባውያኑ በቀላሉ የማይመለሰው ጥያቄ በሩሲያ ላይ መቼ እና ምን አይነት ማዕቀብ መጣል አለበት የሚለው ነው። ምዕራባውያን አገራትም በዚህ ላይ የተለያየ አቋም ሊያንጸባርቁ ይችላሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-60158165 +business ኢኮኖሚ ፡ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ሙዲስ ጠቆመ "ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫውን ማራዘሟን ተከትሎ የተፈጠረው አለመግባባት በአገሪቱ የሚከናወኑ የኢንቨስትመንት ውሳኔዎች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ሙዲስ የተሰኘው የአሜሪካ የቢዝነስና ፋይናንስ ተቋም ጠቆመ። አገራዊው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ቢራዘምም ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልላዊ ምርጫ ተካሂዷል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ምርጫውን “ሕገ ወጥ” ማለታቸው እንዲሁም የፌደሬሽን ምክር ቤት ""ምርጫው እንዳልተካሄደ ይቆጠራል"" እንደተባለ ይታወሳል። ሙዲስ እንዳለው፤ ባለፉት ዓመታት ፖለቲካዊ ውጥረቶች ያስከተሏቸው ግጭቶች የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ስጋት ከፍተኛ አድርጎታል። ሙዲስ ግንቦት ላይ የኢትዮጵያን ነጥብ ከቢ1 ወደ ቢ2 ዝቅ አድርጎታል። ለዚህም በምክንያትነት የተቀመጠው ከውጪ ምንዛሪ ገቢ ይልቅ እዳ ማመዘኑ ነው። ነሐሴ ላይ በኮቪድ-19 ምክንያት ኢትዮጵያ አሉታዊ ግምት ተሰጥቷታል። ወረርሽኙ በግብርና እና በመስተንግዶ ዘርፍ ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ እንዲሁም መንግሥት ገቢው ቢቀንስም ወጪው መናሩ እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ከግብጽና ከሱዳን ጋር ስምምነት ላይ ሳትደርስ ታላቁ ህዳሴ ግድብን መሙላት መጀሯም ተጠቅሷል። በተያያዥም አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎች ሳይወሰዱ ሙሌቱ መጀመሩ የውጪ አገራት ኢንቨስትመንቶች እንዲቀንሱ ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጿል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል አሜሪካ ለኢትዮጵያ ለመስጠት መድባ የነበረው እርዳታ ላይ እገዳ መጣሏን ይፋ አድርጋለች። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በጥሩ ሁኔታ ማስቀጠል መቻሏ ወደ አገሪቱ ኢንቨስትመንት እየሳበ መሆኑን ሙዲስ ገልጿል። ለዓመታት በመሠረተ ልማት ዝርጋታው ዘርፍ የውጪ ኢንቨስትመ��ት ከሳበች በኋላ፤ አይኤምኤፍ በፍጥነት ምጣኔ ሀብታቸው እያደገ ያሉ ካላቸው የአፍሪካ አገሮች ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ትገኝበታለች። ሙዲስ የተባለው ተቋም ዓለም አቀፋዊ በሆኑ በተለያዩ የፋይናንስና ምጣኔ ሃብት እንዲሁም የብድር ጉዳዮች ላይ ምርምሮችን በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በመነሳትም የአገራትን የብድር አዋጭነት ደረጃ ያወጣል። ሙዲስ በዓለም ላይ ካሉ ከሦስቱ ተሰሚነት ካላቸው ተመሳሳይ ተቋማት አንዱ ሲሆን አገራትና መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች ሙዲስን የመሳሰሉ የምጣኔ ሀብትና የፋይናንስ ተቋማት በሚያወጧቸው ትንተናዎችና ደረጃዎች ላይ በመመርኮዝ ቁልፍ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ።" https://www.bbc.com/amharic/news-54170608 +business አማዞን 'ከሂትለር ጋር ይመሳሰላል' የተባለውን የመተግበሪያ አርማውን ቀየረ "አማዞን የመገበያያ መተግበሪያው አርማ አዶልፍ ሂትለር ጋር ይመሳሰላል በሚል በርካቶች አስተያየታቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ አርማውን መቀየሩን አስታውቋል። ኩባንያው ይህንን የመተግበሪያ አርማ በቅርቡ ነው ያስተዋወቀው። ጥር ላይ የተዋወቀው ይህ አርማ የአማዞን የፈገግታ ምልክት ላይ ሰማያዊ የዕቃ ማሸጊያ ፕላስተር የተለጠፈበት ነው። ሆኖም አንዳንዶች የቀድሞውን የናዚ አምባገነን ሂትለር ፂም ጋር ይመሳሰላል በሚል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የቴክኖሎጂ ኩባንያው ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ዚግዛግ መስመር የነበረበትን ሰማያዊ ፕላስተር የታጠፈ እንዲሆን በማድረግ አሻሽሎታል። አማዞን ለቢቢሲ እንዳስታወቀው የመጀመሪያው ዲዛይን ሲቀየር በአንዳንድ አገራት መሞከሩን ነው። ኮሊ ፖርቴል ቤል የተባለው የማስታወቂያ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቪኪ ቡሌን በበኩላቸው ""በሚያሳዝን ሁኔታ ለአማዞን በመጀመሪያ አርማቸው ላይ የተለጠፈው ሰማያዊ ፕላስተር ከሂትለር ሪዝ ጋር ተመሳሳይ ሆኗል። ይሄ ቅርፅ በህሊናችን ውስጥ የማይረሳ ሆኗል። በተለይም በየቤቱ ዕቃ ለሚያደርስ ኩባንያ ይህ ጥሩ መመሳሰል አይደለም"" ብለዋል። ከዚህ ቀደም በተንቀሳቃሽ ስልኮችና ታብሌቶች ላይ የሚታየው የኩባንያው መተግበሪያ አርማ የዕቃ ጋሪ ነበር። አዲሱ ዲዛይን መነሻ ያደረገው የአማዞን ቡናማ የዕቃ መጠቅለያ ካርቶን፣ የኩባንያው ታዋቂ የፈገግታ ምልክትና ሰማያዊ ፕላስተር ነበር። ""አዲሱን አርማ ዲዛንይን ስናደርግ ደንበኞቻችን ዕቃቸው በራቸው በሚደርስበት ወቅት የሚያሳዩትን ደስታ በሚሸምቱበትም ወቅት ያንኑ እንዲያሳዩ ለማድረግ ነው"" ብሏል አንድ ደንበኛ እንዳለው ""ቤተሰቦቼ በየቀኑ በሚባል ሁኔታ ነው አማዞንን የሚጠቀሙት። በሚቀጥሉት ቀናትም ግራ የሚጋቡ ይመስለኛል። አማዞን የት ሄደ ሲሉኝ፤ የሂትለርን ምስል እንዲያዩ እነግራቸዋለሁ"" ብሏል ሌላ ደንበኛ በበኩሉ "" ዚግዛግ ምልክት ያለው ፕላስተር ስለሆነ አይደለም ነገር ግን ቅርፁም ሆነ አጠቃላይ ነገሩ የሚስቅ አዶልፍ ሂትለርን ነው የሚመስለው"" ብሏል። የኩባንያዎች ዲዛይንን በመስራት የሚታወቀው ስቱዲዮ ኤልደብልዩ ዲ መስራች ላውራ ዌልደን በበኩላቸው ""ኩባንያዎች አርማቸውን በተለያየ ጊዜ ይቀያይራሉ። አማዞን ደንበኞቹን መስማቱ መልካም ነገር ነው። ደንበኞችን ቅድሚያ በመስጠት ይህንን ማድረጋቸው የኩባንያውን ጥሩ አሰራር የሚያሳይ ነው"" ብለዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-56272133 +health ባለሙያዎች በኮቪድ ምክንያት የጠፋን የማሽተት ስሜት ለመመለስ 'የማሽተት ሥልጠና' ውሰዱ አሉ "በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተከትሎ የማሽተት ስሜታቸውን በፍጥነት መመለስ ያልቻሉ ሰዎች የማሽተት ሥልጠና እንዲወስዱ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ ሰጡ። ባለሙያዎቹ የማሽተት ስሜትን ለመመለስ የስትሮይድስ ህክምና ከመከታተል ይል�� 'የማሽተት ስልጠና' መውሰዱ የተሻለ እንደሆነ ገልጸዋል። ይህ የማሽተት ስልጠና ለወራት የተለያዩ ሽታዎችን በማሽተት አእምሮን እንደገና በማሰልጠን የተለያዩ ሽታዎችን እንዲለይ የማድረግ ሂደት ነው። የዓለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን እንደሚለው የማሽተት ስልጠና ዋጋው ርካሽ እና ሂደቱም ቀላል ነው። ከስቴሮይድስ ሕክምና ጋር ሲነጻጸርም፤ የማሽተት ስልጠናው የጎንዮሽ ጉዳቶች የሉትም። ከትኩሳት እና ከማያቋርጥ ሳል በተጨማሪ የመሽተት እና የጠዓም ስሜት ማጣት ከኮሮናቫይረስ ዋና ዋና ምልክቶች መካከል ተጠቃሾች ናቸው። ማሽተት አለመቻል ብዙውን ጊዜ ሕመሙ ካለፈ በኋላ በፍጥነት ይመለሳል። ሆኖም ከአምስት ሰዎች መካከል አንዱ ከህመሙ ከስምንት ሳምንት በኋላም የማሽተት ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ሪፖርት አድርገዋል። የኢስት አንግሊያ ዩኒቨርሲቲ ኖርዊች የሕክምና ትምህርት ቤት ባልደረባው ፕሮፌሰር ካርል ፊልፖት እንደሚሉት ኮርቲኮስትሮይድስ ማሽተትን የመመለስ አቅሙ በጣም ጥቂት ነው። ""የታወቁ የጎንዮሽ ጉዳቶች ስላሉት ከቫይረሱ በኋላ በሚመጣ የማሽተት ስሜት ማጣትን ለማከም መታዘዝ የለባቸውም ብለን እንመክራለን"" ብለዋል። ""እንደ ዕድል ሆኖ በኮቪድ-19 የተነሳ ሽታ ማጣት የሚገጥማቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች በፍጥነት የማሽተት ስሜታቸውን መልሰው ያገኛሉ"" ብለዋል። ከስቴሮይድ የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል የደም ግፊት እና የስሜት መለዋወጥ ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው። ዓለም አቀፍ የአለርጂ እና ሪህኖሎጂ ኦረም መጽሔት ላይ በወጣው ጽሑፍ መሠረት ተመራማሪዎቹ ""የማሽተት ሥልጠና""ን በአማራጭነት አቅርበዋል። ይህም ተለይተው የሚታወቁ እና በቀላሉ የሚለዩ ሽታ ያላቸውን አራት ነገሮችን ማሽተትን ያካትታል። ለምሳሌ ብርቱካን፣ አዝሙድ፣ ነጭ ሽንኩርት እና ቡናን በቀን ሁለት ጊዜ ማሽተት። ፕሮፌሰር ፊልፖት እንዳሉት ጥናቶች 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ከስድስት ወር በኋላ የማሽተት ስሜታቸውን ሙሉ በሙሉ መልሰው ያገኛሉ። በዚህ ጊዜ ካልተመለሰ ግን አእምሮ ሽታ እንዲለይ እና የተለያዩ ሽታዎችን እንደገና እንዲያውቅ ""የማሸተት ስልጠና"" ይረዳል።" https://www.bbc.com/amharic/56870718 +sports በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሚሳተፉ ቡድኖች ከ32 ወደ 36 ያድጋል ተባለ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2024/25 የውድድር ዓመት ጀምሮ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሚሳተፉ ክለቦች ቁጥር ከ34 ወደ 36 ከፍ እንደሚል የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አስታወቀ። በአዲሱ ሕግ መሰረት ተሳታፊ ቡድኖቹ በ10 የውድድር ሳምንታት ውስጥ ስምንት ጊዜ የሚጫወቱ ይሆናል። ነገር ግን ከየሊጉ ሁለት ተጨማሪ ቡድኖችን በውድድሩ ባላቸው ታሪክ አወዳድሮ ለማስገባት ታስቦ የነበረው እቅድ ተግባራዊ አይሆንም ተብሏል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማሕበር ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ሴፍሪን ስለ አዲሱ ሕግ ሲናገሩ ''ሁሉም ክለቦች የመሳተፍ ህልማቸውን ማሳካት ይችላሉ'' ብለዋል። በዚህም ቡድኖች ከዚህ በፊት ለዓመታት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ያላቸውን ታሪክ ከግምት ውስጥ ከማስገባት ይልቅ በየሊጋቸው ያላቸው ነጥብ እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሚኖራቸው ተሳትፎ እንደሚያስመርጣቸው ተገልጿል። ለምሳሌ ከ2024/25 ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው አዲሱ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ቢሆን ኖሮ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እና የሆላንድ ኤርዲቪሲ ተጨማሪ ሁለት ክለቦችን ማሳተፍ ይችላሉ። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ደግሞ ከሳምንታት በኋላ በሚጠናቀቀው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ብዙ ክለቦችን ያሳተፉትና ውጤታማ ሆነው መጓዝ የቻሉት ከእንግሊዝ እንዲሁም ከሆላንድ ሊግ የመጡ ክለቦች በመሆናቸው ነው። ስለዚህ አምስተኛ ሆነው የሚያጠናቅቁት ክለቦች በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የመሳተፍ እድል ይሰጣቸዋል ማለት ነው። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እንደሚለው አምስተኛ ሆነው ጨርሰው በቀጥታ ከሚያልፉት ሁለት ቡድኖች በተጨማሪ ቀሪዎቹ ሁለት ቡድኖች ደግሞ በውድድር ዓመቱ በሁሉም የአውሮፓ ሊጎች አምስተኛ ሆነው የሚያጠናቅቁት ተወዳድረው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግን እንዲቀላቀሉ የሚያደርግ አሰራር ይዘረጋል። ማሕበሩ መጀመሪያ ላይ አቅርቦት የነበረውን ቡድኖች ባላቸው ታሪክ ላይ የመመስረት ሀሳብ ትልልቅ ክለቦችን ብቻ ለማካተት የተደረገ ነው በሚል የቀረበበትን ከፍተኛ ተቃውሞና ትችት ተከትሎ ነው ሃሳቡ ውድቅ የሆነው። ይህ ሕግ ተፈጻሚ የሚሆን ቢሆን ኖሮ በአውሮፓ መድረክ ለዓመታት ጎልተው መታየት የቻሉ ትልቅ ክለቦች በሊጋቸው ደካማ አቋም ቢያሳዩ እንኳን በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የመሳተፍ ዕድል ያስገኝላቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በምድብ ድልድሉ ቡድኖች የሚያደርጉት ጨዋታ ከ6 ወደ 10 ከፍ እንዲል መደረጉን የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አስታውቋል። ምንም እንኳን እንደ ሊቨርፑል ያሉ ክለቦች የጨዋታዎች መደራረብ ተጫዋቾችን ለጉዳት እያጋለጠ ነው የሚል ቅሬታ ቢያሰሙም ማህበሩ ግን እንደውም የጨዋታዎችን ቁጥር እንደሚጨምር ገልጿል። አዲስ የቀረበው ሕግ በሁሉም በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ስራ አስፈጻሚ አባላት፣ የየአገራቱ ሊጎች እንዲሁም ብሄራዊ የእግር ኳስ ማህበራት በሙሉ ድምጽ ድጋፍ ማግኘቱን የማህበሩ ፕሬዝዳንት ገልጸዋል። በሌላ በኩል በቀድሞው ሕግ መሰረት ቡድኖች በስምነት ምድቦች ተደልድለው ከየምድቦቹ ከፍተኛ ነጥብ ያላቸው ሁለት ቡዶኖች ወደ ቀጣዩ ዙር እንዲያልፉ ነበር የሚደረገው። በአዲሱ ሕግ መሰረት ግን ይህ ይቀራል ተብሏል። በአዲሱ አሰራር ቡድኖች በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ተዘጋጅቶላቸው የሚወዳደሩ ይሆናል። ቡድኖቹ ስምንት ጨዋታዎችን የሚያደርጉ ሲሆን አራት በሜዳቸው አራት ደግሞ ከሜዳቸው ውጪ ማለት ነው። በመጀመሪያው ዙር ከአንድ እስከ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁት ቡድኖች በቀጥታ ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋሉ። በደረጃ ሰንጠረዡ ከዘጠነኛ እስከ 24ኛ ቦታ ይዘው የሚያጠናቅቁት ቡድኖች ደግሞ በደርሶ መልስ ተጫውተው አሸናፊዎቹ 8 ቡድኖች ደግሞ ቀጣዩን ዙር ይቀላቀላሉ። https://www.bbc.com/amharic/news-61404524 +business በአፍሪካ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ጀመረ "የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እሁድ የካቲት 13/2014 ዓ.ም የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ። ይህ ግንባታው አስራ አንድ ዓመታት ያህል ባስቆጠረው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ትልቅ ምዕራፍ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ ባለሥልጣናት በቤንሻንጉል ጉሙዝ በጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት መጀመሩ ተበስሯል። በባለፉት ሁለት ዓመታት ክረምት ወቅቶች ሙሌቱ የተከናወነውና ለዓመታት በቀጣናው የውዝግብ ምንጭ የሆነው ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በይፋ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀምሯል። ግድቡ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል አንዱ ተርባይን ነው ከተሳካ ተከላ እና ሙከራ በኋላ የመጀመሪያውን ኃይል የማመንጨት ሥራ የጀመረው። ይህ ሥራ የጀመረው ተርባይን 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል። የ13ቱም ተርባይኖች ግንባታ ሲጠናቀቅ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ አጠቃላይ የማመንጨት አቅም 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት እንደሚደርስ የተገለጸ ሲሆን ይህም በአፍሪካ ውስጥ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ አመንጪ ያደርገዋል። በኢትዮጵያውያን የቦንድ ግዥና በመንግሥት በጀት እየተገነባ ያለው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እስካሁንድ ደረስ 163 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበትም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። ግድቡ ግንባታ ጅማሮው ላይ በ80 ቢሊዮን ብር ወጪ ይገነባል የሚል ዕቅድም ተይዞ ነበር። ግድቡ 145 ሜትር ከፍታና ወደ ጎን ደግሞ 1 ሺህ 780 ሜትር ርዝመት ሜትር አለው። ግድቡ የሚይዘውን 74 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ሙሉ በሙሉ ሲይዝም ውሃው የሚተኛበት ስፍራ ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር እንደሚደርስም ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኃይል ማመንጨት ጅማሮውን አስመልክቶ ባስተላፉት መልዕክትም ""ዛሬ የአፍሪካ ትልቁ የኃይል ማመንጫ የሕዳሴ ግድብ ሥራውን ጀምሯል። ይህ ለአህጉራችን እንዲሁም አብረናቸው ሠርተን በጋራ ለመጠቀም ለምንሻ የታችኛው ተፋሰስ አገራት የምሥራች ነው። ""አባይ ወንዛችንን አገራችንን አልምቶ ጎረቤቶቻችንን ሊያረሰርስ ጉዞውን ቀጥሏል። ዛሬ ለኢትዮጵያ የብርሀን መባቻ ነውና መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አለን!"" ብለዋል። ለዓመታት ያህል በግብፅ፣ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል የሦስትዮሽ ድርድር የተካሄደበት ታላቁ ግድብ ጉዳዩ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እንዲፈታ ተመርቶ ነበር። በሦስቱ አገራት መካከል የነበረው የሦስትዮሽ ድርድር አፍሪካ ሕብረትን ጨምሮ በተለያዩ አሸማጋዮች እልባት እንዲያገኝ ቢሞከርም ሊቋጭ አልቻለም፤ አሁንም በእንጥልጥል ላይ ይገኛል። በተለይም ከሙሌቱ ጋር ተያያይዞ አሳሪ ስምምነት ሳይኖር መከናወን የለበትም በሚል ግብፅና ሱዳን ቢሞግቱም በ2012 እና በ2013 ክረምቶች ሙሌቱ በተሳካ ሁኔታ መከናወኑ ተገልጿል። ለግንባታው ከ4.5 ቢሊዮን ዶላር በጀት የተያዘለት ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በ2012 ዓ.ም 4.9 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መያዙ በወቅቱ ተገልጿል። የግድቡ ቁመትም ከባህር ጠለል በላይ 565 ሜትር ደርሶ ነበር። የሕዳሴ ግድብ አጠቃላይ የግንባታው ሂደት ወደ 84 በመቶ መድረሱም ተገልጿል። ግድቡ የውሃ የመያዙ አቅሙ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ሲሆን ለባለፈው ዓመት ክረምትም 13.5 ቢሊዮን ያህል ውሃ ሙሌት ታቅዶ ነበር። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ክረምት ላይም የውሃ ሙሌቱን በተመለከተ ግቧን ማሳካቷን አሳውቃለች ፤ ይህም ማለት ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል በቂ ውሃ አለ ማለት ነው። ይህም ውሃ በታችኛው ተፋሰሰስ አገራት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንደማያደርስና የመጀመሪያ ደረጃ የግድቡ የውሃ ሙሌት መመሪያም የተወሰደው ሦስቱ አገራት ከተስማሙበት የግድብ ትብብር መግለጫ ስምምነት መሆኑንም በወቅቱ ኢትዮጵያ ጠቅሳለች። ለዓመታት ያህል በግብፅ፣ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ሲደረግ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ፍሬ ሳያፈራ የቀረ ሲሆን ሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌቱን ተከትሎ ግብፅና ሱዳን ጉዳዩን ወደ ተመድ የፀጥታ ጉባኤ ምክር ቤት ወስደውት ነበር። በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር ሲደረግ የነበረው ድርድር ምንም ፍሬ አላፈራም ሲሉም ነበር ወደ ምክር ቤቱ ጉዳዩን የወሰዱት። ምክር ቤቱ የሕዳሴ ግድብን ውዝግብ ከተለያዩ ወገኖች ከሰማ በኋላ የታችኛው ተፋሰስ አገራት ወደ አፍሪካ ሕብረት እንዲመለሱ ምክር ለግሶ ልኳቸዋል። ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ግብፅ የቅኝ ግዛት ውሎችን ሙጥኝ እንዳለችና ኢ-ፍትሃዊና አግላይ የሆነውን ስምምነት ተቀባይነት እንዲያገኝ ጫና እያደረገች ነው በማለትም ትወቀሳለች። ባልነበረችበት የተፈረመ ስምምነት ለአባይ ወንዝ 77 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ለምታመነጨው ኢትዮጵያ ምንም ድርሻ የማይሰጥና ተፈጥሯዊም ሆነ ሕጋዊ መብቴን የሚነጥቅ ነው በማለትም ኢትዮጵያ ትከራከራለች። ግብፅ በጎርጎሳውያኑ 1959 የተፈረመውና፣ የአብዛኛውን የውሃ���ን ድርሻ የሚሰጣትን የቅኝ ግዛት ስምምነት አጥብቃ በመያዝ ታሪካዊ ተጠቃሚነት በሚል መርህ የወንዙን ውሃ ሙሉ በሙሉ በበላይነት ለብቻዋ የመጠቀም ፍላጎት አላትም ስትል ኢትዮጵያ ለተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ባስገባችው ደብዳቤ ወቅሳለች። ስምምነቱ ኢትዮጵያን ያላካተተ ከመሆኑ በተጨማሪ ግብጽ 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃን እንዲሁም ሱዳን 18.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃን እንድታገኝና 86 በመቶ የአባይን ውሃ የምትገብረውን ኢትዮጵያ ያለ ውሃ የሚያስቀር አግላይና ኢፍትሃዊ ስምምነት ነው፤ የኢትዮጵያንም ሉዓላዊነትንም ይጥሳል -ትላለች ኢትዮጵያ። ግብፅ ግድቡ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቴን ይቀንሰዋል እንዲሁም ለእርሻ የሚያስፈልገኝ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በየዓመቱ ይገባኛል ስትል የቆየች ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በበኩሏ አሜሪካ በነበረው ድርድር 31 ቢሊዮን ኪዩቡክ ውሃ በዓመት ለመልቀቅ ሃሳብ አቅርባ ነበር። ግብፅ በተጨማሪ ከምታነሳቸው ቅሬታዎች መካከል ኢትዮጵያ ግድቡን ሙሉ አቅም እየተጠቀመች ድርቅ ቢያጋጥም ችግሩ የሦስቱም አገራት ጉዳይ ነው የሚል አቋም ላይ መድረሷን ነው። ረዘም ላለ ጊዜ ድርቅ የሚከሰት ከሆነ ኢትዮጵያ የታችኛው ተፋሰስ አገራት ጥቅምን ለመጠበቅ ዋስትና ልትሰጠን ይገባል በማለትም ግብፅ ትከራከራለች። ኢትዮጵያ በበኩሏ የግብፅ ሃሳብ በአባይ ወንዝ ላይ ተፈጥሯዊ መብት እንዳይኖራት ወይም ምንም ዓይነት የውሃ ልማት ያልተገነባበት ፍሰት እንዲኖር የሚጠብቅ ነው በማለትም ተችታለች።" https://www.bbc.com/amharic/news-60413930 +politics የአልጄሪያው የቀድሞ መሪ አብደላዚዝ ቡቴፍሊካ አረፉ "የቀድሞው የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቡቴፍሊካ ከረጅም ጊዜ ሕመም በኋላ በ84 ዓመታቸው አረፉ። ቡቴፍሊካ ከ20 ዓመት በፊት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተካሄደውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ተከትሎ ሁለቱ አገራት የሰላም ስምምነት እንዲያደርጉ ጉልህ ሚና መጫወታቸው ይታወሳል። ቡቴፍሊካ አልጄሪያን ለ20 ዓመታት ገደማ ከመሩ በኋላ ለአምስተኛ የሥልጣን ዘመን ለመወዳደር መቅረባቸው ለከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ዳርጓቸው ነበር። ቡቴፍሊካ ከ1940 እስከ 1950ዎቹ አልጄሪያን ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ለማላቀቅ በተደረገው ጦርነት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። በመቀጠልም በ1991 የ200 ሺህ ያህል ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የእርስ በእርስ ጦርነት መገባደዱን ተከትሎ በመጣው ወታደራዊው ግፊት ለፕሬዝዳንትነት በቅተዋል። ፕሬዝዳንቱ በ2005 በስትሮክ ከተመቱ በኋላ ንግግር እና እንቅስቃሴ ማድረግ ላይ ከፍተኛ እክል ስላጋጠማቸው በአደባባይ እምብዛም አይታዩም ነበር። ቡቴፍሊካ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ የጀመሩት አገራቸው አልጄሪያ በ1954 ዓ.ም ነፃ ከወጣች በኋላ ነበር። ገና በ20ዎቹ አጋማሽ ላይ ሳሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው በወቅቱ የዓለም ወጣቱ ሚኒስትር ተብለውም ነበር። ለ16 ዓመታት በአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ነበራቸው። በ1966 የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት የነበሩት ቡቴፍሊካ የፍልስጤም መሪ የነበሩትን ያሲር አራፋት ለተባበሩት መንግሥታት ንግግር እንዲያደርጉ የጋበዙበት ሁኔት ታሪካዊ ነበር። በተጨማሪም ቻይና የተባበሩት መንግሥታት መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ በመሟገታቸው እንዲሁም በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ የነበረውን የአፓርታይድ አገዛዝን በይፋ በመቃወማቸውም ቡቴፍሊካ ይታወሳሉ። ለኔልሰን ማንዴላ ወታደራዊ ሥልጠና በመስጠታቸውም ይታወቁ ነበር። ቡተፍሊካ በ1970ዎቹ በቀረበባቸው የሙስና ክሶች ምክንያት በስደት የኖሩ ሲሆን በኋላ ላይ ክሶቹ ውድቅ መደረጋቸውን ተከትሎ በ1980ዎቹ ወደ አገራ��ው ተመልሰው ከሦስት አስርተ ዓመታት በኋላ የአልጄሪያ የመጀመሪያው የሲቪል መሪ ሆነው ተሹመዋል። የአገሬው ሰው ""ቡቴፍ"" እያለ የሚጠራቸው የቀድሞው ፕሬዘዳንት በመከላከያው እና በእስላማዊ ታጣቂ ቡድኖች መካከል ሰላም በማምጣት የአገሪቷን የእርስ በእርስ ጦርነት በዘላቂነት ለመፍታት ችለዋል። ቡቴፍሊካ በ2000 የፕሬዘዳንትነት ዘመንን ለሁለት ጊዜ የሚገድበውን የአልጄሪያን ሕገ-መንግሥት በማሻሻል ለተጨማሪ ሁለት የሥልጣን ዘመናት ቆይታቸውን አራዝመዋል። በመቀጠልም የአረብ አብዮት በመላው ሰሜን አፍሪካ ሲነሳ ቡተፍሊካ ሕዝባዊ ድጎማዎችን በፍጥነት ያሳደጉ ሲሆን ለረጅም ዓመታት የቆየውን የአልጄሪያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስተው ነበር። ለመጨረሻ ጊዜ ለሕዝብ የታዩትም ከአራት ዓመት በፊት በአልጄርስ የተገነባውን የባቡር ጣቢያ እና እድሳት ተድርጎለት የነበረው የኬቼዋ መስጊድን ባስመረቁበት ወቅት ሲሆን ይህም በስትሮክ ከተመቱ ከአራት ዓመት በኋላ ነበር። በወቅቱም ታናሽ ወንድማቸው ሰይድ ቡቴፍሊካ ከጀርባ አገሪቷን ይመራ እንደነበር ይታመን ነበር። በሕመም ላይ የነበሩት ፕሬዝዳንቱ ለአምስተኛ የሥልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ ሲሰማ መላው አልጄሪያ በአመጽ ተቀጣጠለች። ታይቶ በማይታወቅ መልኩም በአገር አቀፍ ደረጃ በየሳምንቱ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጉ ነበር። ይህንን ተከትሎም ምርጫውን ለሌላ ጊዜ በማስተላለፍ ብሎም በአንድ ዓመት ውስጥ ሥልጣን ለመልቀቅ ቃል ከገቡ በኋላ ቡቴፍሊካ ከሥልጣን ወርደዋል። ይህም አልጄሪያዊያን ቡቴፍሊካን ለመጨረሻ ግዜ ያዩበት ጊዜ ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-58554996 +sports ፕሪሚየር ሊግ፡ ማን ዋንጫ ያነሳል? ማንስ ከሊጉ ይወርዳል? "በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለዋንጫ ከሚደረገው ፉክክር በተጨማሪ በአውሮፓ መድረክ ለመሳተፍ እና ላለመውረድ የሚደረገው ትግል እስከ መጨረሻው ሳምንት ድረስ እንደሚዘልቅ እውን ሆኗል። 15 ጨዋታዎች ቀርተዋል። እሁድ የሊጉ ጨዋታዎች ከመጠናቀቃቸው በፊት ሰኞ (ዛሬ) ፣ ማክሰኞ እና ሐሙስ የሚከናወኑ ተስተካካይ ጨዋታዎች አሉ። የትኛው ቡድን ምን ይፈልጋል? ማክሰኞ፡ ሳውዝሃምፕተን ከሊቨርፑል እሑድ፡ ሊቨርፑል ከዎልቭስ እና ማንቸስተር ሲቲ ከአስቶን ቪላ ማንቸስተር ሲቲ ትላንት እሁድ ከዌስት ሃም ጋር ሁለት አቻ ተለያይቷል። አሁንም ግን ሊጉን በበላይነት ከመምራት አላገደውም። ቀሪ ጨዋታውን ካሸነፈ በአምስት ዓመት ውስጥ አራተኛ የሊግ ዋንጫውን ከፍ አድርጎ ይስማል። ሲቲ እስከ እሁድም ላይጠብቅ ይችላል። ማክሰኞ ሴንት ሜሪ ላይ ሊቨርፑል ከተሸነፈ ዋንጫው ኢትሃድ መድረሱ ይረጋገጣል። ዋንጫውን ለማንሳት ሊቨርፑል ቀሪዎቹን ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ ይገባዋል። ማንቸስተር ሲቲም በእሁዱ ጨዋታ ከአስቶን ቪላ ጋር ነጥብ መጣሉ መረጋገጥ አለበት። ""ሊቨርፑልን የመሰለ ቡድን እያለ አራት ጨዋታዎች እየቀሩ ዋንጫ ማንሳት ከባድ ነው። እስከመጨረሻው ፉክክሩ ይቀጥላል። እኛን የሚጠቅመን በሜዳችን መጫወታችን እና የሚወሰነውም በራሳችን መሆኑ ነው"" ያለው የሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ነው። ""ማንንም አንመለከትም። ራሳችን ጨዋታውን ለማሸነፍ እንሞክራለን። ኢትሃድ ስታዲም እንደሚሞላ እና ደጋፊው ከጎናችን እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ።"" ከማክሰኞው ጨዋታ በፊት ለሳውዝሃምፕተን መልዕክት ካለው ሲጠየቅም ""ሊቨርፑልን 4 ለ 0 አሸንፉ"" ብሏል። በቻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ የሚደረገው ፉክክር ሰኞ፡ ኒውካስል ከአርሴናል ሐሙስ፡ ቼልሲ ከሌስተር እሑድ፡ አርሴናል ከኤቨርተን፣ ቼልሲ ከዋትፎርድ እና ኖርዊች ከስፐርስ አርሴናል ቀሪዎቹን ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ ከቻለ ከ2016/17 በኋላ ለመጀመሪያ ጊ�� የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ይሆናል። ነጥብ ከጣለ ግን ስፐርስ መውረዱን ያረጋገጠውን ኖርዊችን ማሸነፍ ብቻ የአውሮፓ ትልቁ ውድድር ተሳታፊ ያደርገዋል። ""እንግሊዝ ውስጥ የቻምፒዮንስ ሊግ ቦታ በጣም ወሳኝ ነው። በሌላ ሊግ ትልቅ ዋንጫ እንደማንሳት ይቆጠራል"" ያለው ስፐርሱ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ነው። ""አርሴናል ዛሬ ይጫወታል። ለጊዜው በሁለት ነጥብ እንበልጣቸዋለን። ካላሸነፉ ዕጣችንን የምንወስነው ራሳችን ነን። ለጊዜው ግን ኳሱ ያለው በእነሱ እጅ ነው።"" ""የመጨረሻው ጨዋታ ለእኛ ወሳኝ ነው። እንግሊዝ ውስጥ ቀላል ጨዋታ የለም። ወደ ኖርዊች አቅንተን አሸንፈን ሦስት ነጥብ ማግኘት አለብን።"" ቼልሲ የቻምፒዮንስ ሊግ ቦታውን ሊያጣ ይችላል። ከሌስተር እና ከዋትፎርድ በሚቀሩት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ካገኘ በቂው ነው። ለዩሮፓ ሊግ እና ለኮንፈረንስ ሊግ የሚደረገው ፉክክር እሁድ፡ ብራይተን ከዌስት ሃም እና ክሪስታል ፓላስ ከማንቸስተር ዩናይትድ ዌስት ሃም እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው ዓመት በአውሮፓ መድረክ እንደሚሳተፉ አረጋግጠዋል። ጥያቄው በየትኛው መድረክ የሚለው ነው። ማንቸስተር ዩናይትድ በመጨረሻው ጨዋታ ክሪስታል ፓላስን ካሸነፈ የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊነቱን ያረጋግጣል። ዌስት ሃም ደግሞ በኮንፈረንስ ሊግ ይሳተፋል። ዌስት ሃም አሸንፎ ማንቸስተር ዩናይትድ ማሸነፍ ካልቻለ ግን የለንደኑ ክለብ ወደ ዩሮፓ ሊግ ዩናይትድ ደግሞ ኮንፈረንስ ሊግ ያመራሉ። ""ስድስተኛ ሆነን ካጠናቀቅን ትልቅ ስኬት ነው። ሰባተኛ መሆንም ትልቅ ነው። ስድስተኛ መሆን ከቻልን ግን የበለጠ ጥሩ ነው። በሚቀጥለው ሳምንት እንደምናሳካው ተስፋ አለኝ። ለማሳካትም እንሞክራለን።"" ሐሙስ፡ ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ እና አስቶን ቪላ ከበርንሌይ እሁድ፡ አርሴናል ከኤቨርተን፣ በሬንትፎርድ ከሊድስ እና በርንሌይ ከኒውካስል ሐሙስ ዕለት የሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች የሚወርዱ ቡድኖችን ዕጣ ይወስናል። ኤቨርተን፣ ሊድስ እና በርንሌይ በሁለት ነጥብ ተለያይተው ተቀምጠዋል። በርንሌይ በወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ተስተካካይ ጨዋታ ይቀረዋል። በዚህም የሊድስ ዕጣ ፈንታ በሌሎች ይወሰናል። የፍራንክ ላምፓርድ ቡድን ትላንት እሁድ ከብሬንትፎርድ ያደረገው ጨዋታ አሸንፎ ቢሆን እንደማይወርድ ያረጋግጥ ነበር። ሐሙስ ፓላስን ካሸነፉም በተመሳሳይ ያረጋግጣሉ። ""ሐሙስም ያለንን በሙሉ መስጠት አለብን። እስከመጨረሻው እንታገላለን። ዕጣችን እጃችን ነው"" ብሏል። በርንሌይ ሐሙስ ምሽት አስቶን ቪላን ገጥሞ ካሸነፈ ከወራጅ ቀጠና ይወጣል። ""በደጋፊያችን ፊት እንደምንጫወት እናውቃለን። ነጥብ ማግኘት አለብን"" ያለው የበርንሌይ ተጠባባቂ አሰልጣኝ የሆነው ማይክ ጃክሰን ነው። ""በጣም ግልጽ ነው። መሸፋፈን አያስፈልግም። ቀጣዩን ጨዋታ ማሸነፍ አለብን።"" የሊድስ እና የበርንሌይ ፉክክር እስከ መጨረሻው ሳምነት ይቀጥላል። ሊድስ በሬንትፎርድ ሲጫወት በርንሌይ ደግሞ ኒውካስልንን ያስተናግዳል። ቶፎዎቹ ሐሙስ ማሸነፍ ካልቻሉ በመጨረሻው ሳምንት ከአርሴናል ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ከባድ ይሆናል። ""በርንሌይ ተስተካካይ ጨዋታ አለው። ትላንት አንድ ነጥብ ማግኘታችን ተጽዕኖውን ወደ እነሱ ያዞረዋል"" ያለው የሊድሱ አሰልጣን ጄሲ ማርሽ ነው። ""ያለነው የሥነ-ልቦና ጦርነት ውስጥ ነው። በሚቀጥለው ሳምንት ያለንን ሁሉ ማውጣት አለብን። ለዚህም ተዘጋጅተናል። ያለንን በሙሉ ለመጨረሻው ጨዋታ አዘጋጅተናል።""" https://www.bbc.com/amharic/news-61462123 +health ኮሮናቫይረስ፡ ሐሰተኛ ዜና በዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ደቡብ እስያውያንን የኮቪድ-19 ክትባት እንዳይወስዱ እያደረገ ነው ተባለ "ሐሰተኛ ዜና በዩናይትድ ኪንግደም የሚኖሩ የተወሰኑ የደቡብ እስያ ማኅበረሰብ አባላት የኮሮናቫይረስ ክትባትን ላለመውሰድ እንዲያንገራግሩ እያደረገ ነው ሲሉ ሐኪሞች አስጠነቀቁ። ዶ/ር ሀርፕረት ሱድ በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የጤና አገልግሎት ዘርፍ የተሳሳቱ መረጃዎችን በሚያጣራው ቡድን ውስጥ ኃላፊ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባትን በሚመለከት የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች ""በጣም አሳሳቢ ናቸው"" ካሉ በኋላ ""ይህንን ለማስተካከል እየሰራን ነው"" ብለዋል። ለሐሰተኛ መረጃዎቹ መስፋፋት እንደምክንያት የተጠቀሰው የባህልና የቋንቋ ተግዳሮት መኖሩን ነው። በምዕራብ ሚድላንድስ የምትሰራ አንዲት ዶክተር ለቢቢሲ እንደተናገረችው የተወሰኑ ደቡብ እስያውያን የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባቱን አንወስድም ሲሉ አንገራግረዋል። በእንግሊዝ የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ውስጥ የሚሰሩት ዶ/ር ሱድ፣ እነዚህን ስለክትባቱ የሚነገሩ ሐሰተኛ መረጃዎች ለማስወገድ ከደቡብ እስያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ጋር እየሰሩ ነው። በርካቶቹ የሐሰተኛ መረጃዎች የሚያጠነጥኑት በክትባቱ ይዘት ዙሪያ ነው ተብሏል። እነዚህ የማኅበረሰብ አባላት የእንስሳት ተዋጽኦ እንደማይመገቡ ስለሚታወቅ ""ክትባቱ ከላምና ከአሳማ ሥጋ መሰራቱ"" እንደተወራ ዶ/ር ሱድ ያስረዳሉ። ""በሁሉም የእምነት አባቶች ክትባቱ ተቀባይነት ማግኘቱንና ተከታዮቻቸውም እንዲወስዱት መፍቀዳቸውን በግልጽ ለማኅበረሰቡ አባላት መንገር አለብን"" ብለዋል። አክለውም ለማኅበረሰቡ በሚናገሩት ቋንቋ ተተርጉሞ የሚሰራጨው መረጃ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል መድረሱን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ያስረዳሉ። ስለዚህም በየማኅበረሰቡ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪና አርአያ የሆነ ግለሰብ እየፈለግን፣ አንዳቸው ለሌላኛቸው ትክክለኛውን መረጃ በማስተላለፍ የተሳሳተውን መረጃ እንዲቀለብሱ እየሰራን ነው ብለዋል። ቢቢሲ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ ያያቸው የተወሰኑ የተሳሳቱ መረጃዎች ሐይማኖትን መሰረት ተደርገው የተሰራጩ ናቸው። እነዚህ መልዕክቶች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት የእንስሳ ተዋጽኦን ይዟል የሚሉ ሲሆን፣ የአሳማ ሥጋ በማይበሉ ሙስሊሞች እና የበሬ ሥጋ በማይበሉ ሂንዱዎች ረገድ ይህ መረጃ በስፋት ተሰራጭቶ ተቀባይነት አግኝቷል። ዶ/ር ሳማራ አፍዛል በምዕራብ ሚድላንድስ ዱድሊ ሰዎችን ስትከትብ ""ሁሉንም ሕሙማን ለክትባት ወረፋ እንዲይዙ እንዲደረግ ለሠራተኞቹ ቢነገርም፣ ነገር ግን የደቡብ እስያ ተወላጅ የሆኑ አንዳንድ ሕሙማን ክትባቱን አንወስድም ማለታቸውን ሰምተናል"" ""ቤተሰባቸውንና ጓደኞቻቸውን ባነጋገርንበትም ወቅት ያገኘነው መረጃም ተመሳሳይ ነው። እኔ ራሴ ጓደኞች አሉኝ፤ ቤተሰቦቹቼ ወይም አያቶቼ ክትባቱን እንዲወስዱ እንዳሳምንላቸው የሚጠይቁኝ"" ስትል የገጠማትን ተናግራለች። በሃምፕሻየር የውበት ባለሙያ የሆነችው ሬና ፑጃራ የሂንዱ እምነት ተከታይ ስትሆን በእንደዚህ አይነት ሐሰተኛ መረጃዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ገጿ መጥለቅለቁን ትናገራለች። ""ላልተማረ ሰው ግራ አጋቢ ነው። በዚያ ላይ ክትባቱ ከላም ሥጋ እንደተሰራ ሲገነጽ፤ ላም ደግሞ ለእኛ ቅዱስ በመሆኗ የሚረብሽ ነው"" ብላለች። 100 መስጂዶች በኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ላይ የሚናፈሱ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመመከትና ማኅበረሰቦቻቸው ክትባቱን እንዲወስዱ ለማሳመን ጥምረት ፈጥረዋል። እነዚህ መስጂዶች የአርብ ፀሎትን ለማስተማሪያነት ለመጠቀም ተስማምተዋል። በቅርቡ በሮያል ሶሳይቲ ኦፍ ፐብሊክ ሄልዝ በተደረገ ጥናት ግማሽ ያህል ጥቁሮች፣ እስያውያን እና ሌሎች በቁጥር ���ነስተኛ የሆኑ ሕዝቦች የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለመውሰድ ፈቃደኛ ናቸው ይላል። ከ79 በመቶ ነጮች መካከል ደግሞ 57 በመቶዎቹ ለመውሰድ ፈቃደኛ መሆናቸውን በጥናቱ ላይ ተመልክቷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-55677502 +politics ለኬንያው ምርጫ በሕይወት የሌሉ ሩብ ሚሊዮን ድምጽ ሰጪዎች ተመዝግበው ተገኙ ኬንያ ከሁለት ወራት በኋላ ለምታካሂደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሕይወት የሌሉ ከ250 ሺህ በላይ ድምጽ ሰጪዎች ተመዝግበው መገኘቱ ተገለጸ። ኢንዲፔንደንት ኤሌክቶራል እና ባውንደሪስ ኮሚሽን የተሰኘው የኬንያው ገለልተኛ ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ አስፈጻሚ ተቋም ባወጣው መግለጫ፤ የመራጮች ምዝገባ ላይ ባደረገው ምርመራ በሕይወት የሌሉ ሩብ ሚሊዮን ሰዎች ተመዝግበው አግኝቻለሁ ብሏል። ከዚህ በተጫማሪም ለፕሬዝደንታዊው ምርጫ ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገቡት መካከል ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉት ከአንድ ጊዜ በላይ ተመዝግበው ተገኝተዋል ብሏል። ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ አስፈጻሚ ተቋሙ 226 ሺህ ሰዎች ደግሞ የራሳቸው ባልሆኑ ሰነዶች ድምጽ ለመስጠት መመዝገባቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል። ድምጽ ለመስጠት ብቁ በማያደርጉ ሰነዶች የተመዘገቡ ድምጽ ሰጪዎች መኖራቸውንም ተቋሙ በመግለጫ አመላክቷል። በጠቅላላው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ድምጽ ሰጪዎች ሕጋዊ አሰራርን ባልተከተለ መልኩ ድምጽ ለመስጠት ተመዝገበው ተገኝተዋል። የተቋሙ ሊቀመንበር ዋፉላ ቼቡካቲ ሕጋዊ አሰራርን ባልተከተለ መልኩ መራጮች ተመዝግበው መገኘታቸው ተከትሎ ተቋማቸው የመጨረሻዎቹን መራጮች አረጋግጦ ይፋ የሚያደርግበትን ቀን ያራዝመዋል ብለዋል። ገለልተኛ የሆነው ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ አስፈጻሚ ተቋም የድምጽ ሰጪዎችን ዝርዝር አረጋግጦ ዛሬ ሐሙስ ይፋ ማድረግ ነበረበት። በኬንያ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ማጭበርበሮች፣ ምርጫን ተከትሎ ለሚከሰቱ ሁከቶች አንዱ ምክንያት ነበር። ኬንያ ነሐሴ 03/2014 ዓ.ም. ለምታካሂደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዲንጋ እና ሥልጣን ላይ ያሉት ምክትል ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ መካከል ጠንካራ ፉክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። በአሁኑ ወቅት አገሪቱን እያስተዳደሩ ያሉት ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ሁለት የሥልጣን ዘመን በማገልገላቸው በምርጫው ተሳታፊ አይሆኑም። https://www.bbc.com/amharic/articles/clkvg9ek0j3o +health ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮና ክትባትን በዓለም ለማሰራጨት 8ሺህ ግዙፍ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ ይበለውና የኮሮና ክትባት ቢሳካ በነገታው እንወጋዋለን ማለት አይደለም፡፡ በመላው ዓለም ማሰራጨቱ በራሱ ሌላ ትልቅ ፈተና ነው ሲል የአቪየሽን ኢንደስትሪ ማኅበር ተናግሯል፡፡ ምናልባትም በአውሮፕላን የካርጎ ታሪክ እጅግ ከባዱ ፈተና፣ እጅግ ከባዱ ኃላፊነት ይሆናል ተብሏል፡፡ የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር (IATA) እንደሚለው ምናልባት ክትባቱ ቢሳካ እያንዳንዳቸው የቦይንግ 747 አውሮፕላኖች አይነት ግዝፈትና ፍጥነት ያላቸው 8ሺህ ግዙፍ የካርጎ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ ብሏል፤ ክትባቱን ለማዳረስ፡፡ ምንም እንኳ ለጊዜው ክትባት ባይፈበረክም፣ መሳካቱ አይቀርም በሚል የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ነገሮችን ለማቀናጀት ከወዲሁ ተፍ ተፍ እያለ ነው፡፡ ማኅበሩ በጤና ዙርያ ከሚሰሩት በርካታ ድርጅቶች፣ ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከመድኃኒት አምራቾች፣ ከመድኃኒት አቀባባዮች፣ አከፋፋዮች፣ ከአውሮፕላን ካርጎ ሥራ ተሳታፊዎች ጋር በጥምረት መስራት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይህ 8ሺህ ቦይንግ ያስፈልጋል የተባለው ታዲያ አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ብቻ፣ አንድ ጠብታ ክትባት ብቻ ነው የሚያስፈልገው በሚል የተሰላ ሲሆን ይ��� ግምት ለምሳሌ በእጥፍ ቢጨምር እጥፍ ካርጎ አውሮፕላን ያሻል ማለት ነው፡፡ የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ አሌክሳንደር ዴ ጁኒያክ እንዲህ ተናግረዋል፣ ‹‹የኮቪድ 19 ክትባትን በጥንቃቄ ማጓጓዝ የዚህ ክፍለ ዘመን ትልቁ የካርጎ ኢንዱስትሪ ግብ ነው፡፡ ነገር ግን እንዲሁ በዘፈቀደ የሚጓጓዝ አይደለም፤ ከፍተኛ ዝግጅት ይፈልጋል፡፡ ለዝግጅቱ ትክክለኛው ጊዜ ደግሞ አሁን ነው›› በርካታ አየር መንገዶች በወረርሽኙ ጊዜ የሰዎች ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ በመታቀቡ ወደ ካርጎ ሥራ ገብተው ቆይተዋል፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይጠቀሳል፡፡ ነገር ግን ማንም እቃ የሚያጓጉዝ አየር መንገድ ክትባትን ማጓጓዝ ይችላል ማለት አይደለም፡፡ ክትባት ለማጓጓዝ ካርጎው ከ2 እስከ 8 ሴንትግሬድ የሙቀት መጠን ሊኖረው ይገባል፡፡ አንዳንድ ክትባቶች ደግሞ እጅግ ቀዝቃዛ (ከዜሮ በታች) የሆነ የሙቀት መጠንን ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ ይህን ማሟላት ለብዙ አየር መንገዶች ፈተና ሊሆን ይችላል፡፡ ዝግጅት ከወዲሁ የተጀመረውም ለዚሁ ነው፡፡ ይህንን ክትባት የማጓጓዙን ፈተና ለመቀነስ አንዱ መንገድ አገራት በየራሳቸው ክትባቱን እንዲያመርቱት ማድረግ ቢሆንም ይህ ለብዙ የዓለም አገራት የሚቻል አይሆንም፡፡ በተለይ በርካታ የካርጎ በረራዎች ወደ ደቡብ ምሥራቅ ኢሲያ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ሕዝብ ስለሚገኝና ክትባት የማምረት አቅም ያለው አገርም ባለመኖሩ ነው፡፡ ክትባቱን በቀላሉ ወደ አፍሪካ ለማጓጓዝም የሚቻል አይደለም ብሏል ማኅበሩ፡፡ ይህም በቂ የካርጎ አቅም ስለሌለ፣ አፍሪካ ሰፊ አህጉር በመሆኗና የድንበር ውስብስብነት መኖሩ ነው፡፡ የካርጎ ሥራው ልክ ወታደራዊ ጥንቃቄን የሚፈልግ ነው፤ ከተጓጓዘ በኋላም ቢሆን የሚቀመጥበት ቦታ መድኃኒቱን ለማስቀመጥ የሚሆን መሆን አለበት፡፡ ይህ ደግሞ ለበርካታ የአፍሪካ አገሮች ፈተና ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዓለም ደረጃ 140 ቤተ ሙከራዎች ክትባት ለመሥራት ተፍ ተፍ ማለት ጀምረው ነበር፡፡ አሁን 24 የሚሆኑት በሰዎች ላይ ሙከራ ጀምረዋል፡፡ ከነዚህ ሁሉ ትልቅ ተስፋ የተሰጠው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው የክትባት ሙከራ ነው፡፡. ሩሲያ ክትባቱ በእጄ ገብቷል ብትልም ዓለም በአገሪቱ ላይ እምነት በማጣቱ ይመስላል እምብዛምም የራሺያ ክትባት አይወራም፡፡ የጤና ባለሙያዎች የሩሲያ ክትባት ሳይንሳዊ ሂደትን የተከተለ አይደለም፣ ብሔራዊ ኩራተን ከጤና አስበልጧል ሲሉ ይተቹታል፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-54093179 +politics "ሩዋንዳ ""በዩኬ የጥገኝነት ስምምነት ላይ በሰዎች እየነገደች አይደለም"" ፕሬዚዳንት ካጋሜ" "የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ አገራቸው የዩኬ ጥገኝነት ጠያቂዎችን አስመልክቶ የገባችውን ስምምነት አስመልክቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት አስተያየት ሀገራቸው ""በሰው ልጅ አትነግድም"" ብለዋል። በስምምነቱ መሰረት በትንንሽ ጀልባዎች ወደ እንግሊዝ የተሻገሩ የጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ በማዛወር ጉዳያቸው በዚያ የሚታይ ይሆናል። በሩዋንዳና በዩናይትድ ኪንግደም ተደርሷል የተባለው አወዛጋቢው የ120 ሚሊዮን ፓውንድ ስምምነት በአለም አቀፉ ዘንድ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን የሁለቱም ሀገራት ባለስልጣናት ትችት ገጥሟቸዋል። ስምምነቱ ሲፈረም በኮንጎ ብራዛቪል፣ጃማይካ እና ባርባዶስ ጉብኝት ላይ የነበሩት ፕሬዚዳንት ካጋሜ - ሩዋንዳ ስደተኞችን ለመቀበል በምላሹ ገንዘብ እያገኘች ነው ብሎ ማሰብ ስህተት ነው ብለዋል። "" እኛ በሰው አንነግድም፣ እባካችሁ እርዳታ እየሰጠን ነው "" በማለት ከአሜሪካው ብራውን ዩኒቨርስቲ ጋር በበይነ መረብ በነበረ ሴሚናር ላይ ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ካጋሜ እንደሚሉት እንግሊዝ ሩዋንዳን የመረጠችበት ምክንያት በሊቢያ ለነበሩ ስደተኞች መጠለያ በመስጠታቸው መሆኑን ነው። በአውሮፓውያኑ 2018 የአፍሪካ ህብረትን ሲመሩ በነበረበት ወቅት ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩና በሊቢያ መሄጃ ላጡ ስደተኞች ሃገራቸው መጠለያ እንደምትሰጥ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን አስታውሰዋል። ይህንን እርምጃም ተከትሎ ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ የተወሰዱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 2/3ኛ የሚሆኑት ጉዳያቸው አልቆ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ካናዳ አቅንተዋል። ፕሬዚዳንት ካጋሜ አገራቸው እያደረገችው ያለችው ተግባር ""የስደት ችግር ላለባቸው"" እንደ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የተሳካ ሂደት ነበር ሲሉ አወድሰዋል። ሩዋንዳ ህገወጥ የስደተኞች ዝውውርን ለመግታት እየረዳች ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ካጋሜ ዩኬ የጥገኝነት ጥያቄያቸውን የምትቀበለውን ወይም የማትቀበላቸውን ግለሰቦች ጉዳይም እልባት እስኪገኝ በሩዋንዳ እንደሚቆዩ ጠቁመዋል። የሩዋንዳ ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስምምነቱን ""ከእውነታው የራቀ"" ከማለት በተጨማሪ የሩዋንዳ መንግሥት ""የበለጸጉ አገሮችን ሸክም"" ከመፍታት ይልቅ በአካባቢው ችግሮች ላይ እንዲያተኩር ጠይቀዋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-61192479 +business ባለሀብቱ በአሜሪካ ታሪክ ትልቁ በተባለ የታክስ ስወራ ተከሰሱ አሜሪካዊው ባለሀብት በአገሪቱ ታሪክ ትልቁ በተባለ የታክስ ስወራ ክስ ተመሰረተባቸው። ሮበርት ብሮክማን፤ ሬይኖልድስ ኤንድ ሬይኖልድ የተሰኘ የኮምፒዩተር ሶፍትዌር አምራች ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሲሆኑ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት፤ ያገኙትን 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ከአሜሪካ መንግሥት ደብቀዋል ተብሏል። ሮበርት ብሮክማን ከአሜሪካ መንግሥት 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ የሰወሩት ገንዘቡን በሌሎች አገራት ከሚገኙ ኩባንያዎቻቸው የተገኘ በማስመሰል ነው ተብሏል። ብሮክማን በቴሌኮንፍረስን አማካኝነት በሂውስተን ቴክሳስ በሚገኝ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ለቀረቡባቸውን ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም ብለው ተከራክረዋል። ባለሀብቱ በአጠቃላይ 39 ክሶች የተመሰረቱባቸው ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል የታክስ ስወራ እና በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ ማስመሰል የሚሉት ይገኙበታል። ብሮክማን ይህን የታክስ ስወራ ወንጀል ስለመፈጸማቸውን ለአሜሪካ መንግሥት ጥቆማ ያደሩት ደግሞ ሮበርት ስሚዝ የሚባሉ ሌላ ሚሊየነር የንግድ ሰው ናቸው። ሮበርት ስሚዝ በተመሳሳይ የገቢ ምንጮቻቸውን በመደበቅ ታክስ ሲያጭበረብሩ እንደነበረ ያመኑ ሲሆን፤ መንግሥት ክስ እንዳይመሰርትባቸው ብሮክማን ላይ ጥቆማ ሰጥተዋል ተብሏል። ሮበርት ስሚዝ ጥቆማውን ለአሜሪካ መንግሥት የሰጡት ለፈጸሙት የታክስ ማጭበርበር ክስ እንደማይሰመረትባቸው ከስምምነት ከደረሱ በኋላ ነው ተብሏል። ይሁን እንጂ ሮበርት ስሚዝ 139 ሚሊዮን ዶላር በቅጣት መልክ ለአሜሪካ መንግሥት ክፍያ ለመፈጸም ተስማምተዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54565664 +politics የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አነሳ "የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለስድስት ወራት በመላው ኢትዮጵያ ተጥሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በዛሬው ዕለት የካቲት 08/2014 ዓ.ም በይፋ አነሳ። የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛው ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ላለፉት ሦስት ወራት ያህል ተግባራዊ የሆነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል። በዚህም ስብሰባ ላይ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ የአገር ህልውና እና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማንሳት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በ63 ተቃውሞ በ21 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲያጥር ምክንያት የሆነውም ለአገሪቱ ስጋት የነበረው ""የአገር ህልውና እና ሉዓላዊነት አደጋ"" መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱ መሆኑም ተገልጿል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ህወሓት እና አጋሮቹ የአገር ህልውና እና ሉዓላዊነት ላይ የደቀኑትን አደጋን ለመከላከል እንዲያስችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014ን ያወጀ ሲሆን፣ ይህ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በአዋጅ ቁጥር 1264/2014 መጽደቁ ተገልጾ ነበር። አዋጁ በጸደቀበትም ወቅት በአገሪቱ የተደቀነውን የህልውናና እና የሉዓላዊነት አደጋ በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥራ መከላከል የማይቻል ሆኖ በመገኘቱም እንደነበር ተጠቅሷል። በአሁኑ ወቅት ያለውን ስጋት በመደበኛው የሕግ ማስከበር ተግባር መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ በመደረሱ ለስድስት ወራት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማሳጠር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱም ተገልጿል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስድስት ወራት የጊዜ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጅ ምክንያት የሆኑ ሁኔታዎች ከተቀየሩ እና በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥርዓት ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳዮችን መቆጣጠር ይቻላል ብሎ ካመነ የስድስት ወር ጊዜው ሳይጠናቀቅ ጊዜውን የማሳጠር ሥልጣን እንደተሰጠውም ተጠቅሷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ሥራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኗል። በሰሜን ኢትዮጵያ ይካሄድ የነበረው ጦርነት ከትግራይ ክልል ባሻገር ወደ አማራና አፋር ክልሎች መስፋፋቱን ተከትሎ በተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ በመንግሥት በአሸባሪነት ከተፈረጁት አማጺያን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ በርካታ ሰዎች መታሰራቸው ይታወሳል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60385017 +sports ታዋቂው አሜሪካዊ ስፖርተኛ ከነልጁ በሄሊኮፕተር አደጋ ሞተ "አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ኮቢ ብራያንት ከሴት ልጁ ጋር ካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ ሲጓዝበት የነበረው ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር ህይወቱ አለፈ። የ41 ዓመቱ ብራያንትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ላይ አደጋው የደረሰው ሲጓዙበት የነበረው የግል ሄሊኮፕተር ከተከሰከሰ በኋላ በእሳት ተያይዞ ነው። የሎስ አንጀለስ ፖሊስ እንዳስታወቀው ከአደጋ በህይወት የተረፈ ሰው የለም። • የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ለከባድ ጭንቀትና የልብ ህመም ተጋላጭ ናቸው ተባለ • የትራምፕን የክስ ሂደት በቀላሉ እንዲገነዘቡ የሚረዱ 5 ወሳኝ ጥያቄዎች • የአፍ ጭምብል ማጥለቅ ከቫይረስ ይታደገን ይሆን? ብራያንት ለታዋቂው ሎስ አንጀለስ ሌከርስ የቅርጫት ኳስ ቡድን በመጫወት አምስት ጊዜ ሻምፒዮን ለመሆን በመቻሉ በውድድሩ ታሪክ ውስጥም ታላላቅ ከሚባሉ ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀስ ስፖርተኛ ነበር። በርካቶች በብራያንት ድንገተኛ ሞት ድንጋጤያቸውን እየገለጹ ሲሆን ታዋቂ ግለሰቦችን ሃዘናቸውን እየገለጹ ነው። የስፖርተኛው ሞት እንደተነገረም በመላው አሜሪካ በሚካሄዱ የቅርጫት ኳስ ውድድሮች ላይ ለብርያንት የህሊና ጸሎት ተደርጎለታል። የአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ውድድር የበላይ አካል የሆነው ኤንቢኤ የብራያንትን ሞት ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ማህበሩ በስፖርተኛውና በ13 ዓመት ታዳጊ ልጁ ሞት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል። መግለጫው ""ላለፉት 20 የውድድር ወቅቶች ኮቤ ተሰጥኦንና ለስፖርቱ ያለውን ሁሉ በማ��ረግ አሸናፊ መሆን እንደሚቻል አሳይቷል"" ሲል ብራያንትን አስታውሶታል። ብራያንት ለ20 ዓመታት በዘለቀው የቅርጫት ኳስ ህይወቱ የተጫወተው ሎስ አንጀለስ ሌከርስ ለተባለው ቡድን ብቻ የነበረ ሲሆን ከአራት ዓመት በፊት መጫወት አቁሟል። በተለያዩ ጊዜያት በቅርጫት ኳስ ውድድር ባሳየው ችሎታው የኮከብነት ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን ሁለት ጊዜ በኦሊምፒክ ላይ ተሳትፎ የአሸናፊነትን ክብር ተጋርቷል። ብራያንት ከሁለት ዓመት በፊት 'ዲር ባስኬትቦል' በሚል ለቅርጫት ኳስ ስፖርት ያለውን ፍቅር በሚያሳየውና በእራሱ በተጻፈው አጭር ፊልም የኦስካር ሽልማትን ለማግኘት ችሎ ነበር። ኮቢ ብራያንት በአደጋው አብራው ህይወቷ ካለፈው ሴት ልጁ በተጨማሪ የሌሎች ሦስት ሴት ልጆች አባት ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-51260529 +business ኒውዮርክ ታይምስና መሰል ታላላቅ የዜና ምንጮች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንዲከፍሉ እየተፋለሙ ነው በበይነ መረብ ያሉ የዜና ድረገፆች ችግር ላይ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹም ኑሮ ከበደን ብለው ከገበያ ወጥተዋል፡፡ችግሩ የተፈጠረው ሰዎች በበይነመረቡ ዓለም ይዘቶቻቸውን በነጻ ማግኘታቸው ነው፡፡ ብዙ የተለፋባቸው የዜና ዘገባዎች ሰልባጅ ሆነዋል፡፡አሁን አዲስ ዘመቻ ጀምረዋል፤ አሳታሚዎች፡፡ ይከፈለን የሚል፡፡ እነ ጉጉል፣ እነ አፕልና እነ ፌስቡክ ቢሊዮን ዶላሮችን በትርፍ ሲዝቁ የዜና ድረገፆች ግን እየኮሰመኑ መሆኑ ፍትሐዊ አይደለም የሚሉ እንቅስቃዎች እዛም እዚም ብቅ ብቅ እያሉ ነው፡፡ ጋዜጣና መጽሔት አሳታሚዎች ለነ ጉገል አጭር ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ክፈሉን!ጉግልና ፌስቡክ ከዚህ በፊት ለተመረጡ ይዘቶች ክፍያ እንፈጽማለን ብለው ነበር፡፡ ይህንንም በተወሰነ ደረጃ ጀምረውታል፡፡ ይሁንና አታሚዎች እንደሚሉት ገቢው የልብ አያደርስም፡፡የዓለም ግዙፉ ጋዜጣ ኒውዮርክ ታይምስ አፕል ኩባንያ ትርፌን እየወሰደብኝ ነው ሲል ቅሬታ አቅርቧል፡፡ የአውስትራሊያ ጋዜጦችም ተመሳሳይ ጥያቄ ከማንሳት አልፈው ክስ ለመመስረት እየተዘጋጁ ነው፡፡አፕል ጋዜጦቹ በመተግበሪያ ቋቱ (አፕል ስቶር) በኩል ሲሸጡ ከእያንዳንዱ ሽያጭ 30 በመቶ ትርፍ ይወስዳል፡፡ ቢያንስ ይህን እንዲተው ወይም የትርፍ ህዳጉን እንዲቀንስ ነው አሳታሚዎቹ እየጠየቁ ያሉት፡፡በዚህ ሳምንት መጀመርያ ጉግል ከአውስራሊያ አሳታሚዎች ጋር ጠብ ውስጥ ገብቷል፡፡ አሳታሚዎቹ የሚሉት ጉግል የሚከፍለን ብር በጭራሽ የልብ አያደርስም፣ ይጨመር ነው፡፡ የበይነመረቡን ዓለም የተቆጣጠሩት አፕል፣ ጉጉልና ፌስቡክ ለአሳታሚዎች አጥጋቢ ክፍያ ለመፈጸም ዳተኛ ሆነዋል፡፡የአሜሪካ ግዙፎቹን ጋዜጦች ማለትም ኒውዮርክ ታይምስን፣ ዋሺንግተን ፖስትን እና ዎልስትሪት ጆርናልን በገበያና ንግድ ጉዳዮች የሚወክለው ዲጂታል ኮንቴንት ኔክስት የተባለው ኩባንያ ለአፕል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቲም ኩክ የቅሬታ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡ ቅሬታው አፕል ለምን ከትርፋችን 30 ከመቶ ይወስድብናል የሚል ነው፡፡ የአይፎን ስልኮች አምራቹ አፕል በመተግበሪያ ቋቱ (አፕ ስቶር) እነዚህ ጋዜጦች ሲሸጡ ከትርፋቸው ከ15 እስከ 30 ከመቶ ኮሚሽን ይበላል፡፡ ነገር ግን አማዞን ‹አንዳንድ ደንቦችና ግዴታዎችን ስለሚያሟላ› የዚህን ያህል የትርፍ ኮሚሽን አይወሰድበትም፡፡አሁን አሳታሚዎቹ እያሉት ያሉት አማዞን የሚያሟላቸውና እኛ የማናሟላው ደንብና ግዴታዎች ምንድን ናቸው፤ ይገለጽልን ነው፡፡ አፕል ከአሳታሚዎች ብቻ ሳይሆን ከጌም አምራቾችም ጋር ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ ገብቷል፡፡ኤፒክ ጌምስ በዓለም የዝነኛው ፎንትናይት ቪዲዮ ጌም አምራች ነው፡፡ ይህ ጌም ከአፕል ስቶር ሲገዛ አፕል የትርፉን 30 ከመቶ ይወስድበታል፡፡ ይህ ያበሳጨው ኤፒክ ጌምስ ኩባንያ ጉዳዩን ፍርድ ቤት ወስዶታል፡፡ በአውስትራሊያ የሸማቾች ውድድር ኮሚሽን አዲስ ሕግ አርቅቋል፡፡ ሕጉ እነ ጉግልና ፌስቡክ እንዲሁም ጉግል ፕሌይ ከገጾቻቸው በኩል ለሚለጥፏቸው ማናቸውም የጋዜጣና መጽሔት ይዘቶች ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚጠይቅ ነው፡፡ ጉግል በበኩሉ አሁን ከፍ ያለ የይዘት ጥራት ያላቸው ጋዜጦችና መጽሔቶችን ገንዘብ መክፈል ጀምሬያለሁ ብሏል፡፡ የአውስትራሊያ የገበያ ቁጥጥር ባለሥልጣን ‹‹አሳታሚዎች የሚከፈላቸውን ዋጋ መደራደር እንዲችሉ የመጫወቻ ሜዳው ፍትሐዊ እንዲሆን ጠይቋል፡፡ የቢዝነስ አዋቂዎች እንደሚገምቱት እነዚህ ግዙፍ ኩባንያዎች በበይነ መረብ ለታየ ነገር ሁሉ ክፍያ ሊፈጽሙ አይችሉም፡፡ ነገር ግን ሙያዊ ከፍታው ደርዝ ያለው፣ በጥራትና በትጋት የተሰራ የዜና ዘገባ ክፍያ ሊታሰብለት ይገባል ባይ ናቸው፡፡‹‹ርካሽ ነገር ርከሽ ነው፡፡ የትም በነጻ ሊገኝ ይችላል፡፡ ሙያውን የጠበቀና ብዙ የተለፋበትን ይዘት ግን እንደ መናኛ ነገር በበይነ መረብ ለጥፎ ምንም አለመክፈል በምንም መመዘና ተገቢ አይደለም፡፡ እነዚህ ይዘቶች በገንዘብ ካልተደገፉ ይጠፋሉ፡፡›› ይላሉ በስዊዘርላንድና በሲንጋፖር ቢዝነስ ትምህርት ቤቶች ፕሮፌሰር የሆኑት ማይክል ዋዴ፡፡ ‹‹ጉግል፣ ፌስቡክና ሌሎች የጋዜጦችን ምርት እየቦጨቁ በነጻ ሲዘሮት ኖረዋል፣ ለረዥም ጊዜ፤ ይህ ነገር ሊያበቃ ይገባል ብለዋል ፐሮፌሰሩ ለቢቢሲ፡፡ ጉግል በበኩሉ በአሁኑ ጊዜ ዓለም አቀፍ የፈቃድና የአከፋፈል ፕሮግራም ለማውጣት እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህ ሲጠናቀቅ ከፍ ላሉ የጋዜጣ ሥራዎች ክፍያ መፈጸም ይጀምል ብሏል፡፡ ይህ የክፍያ ፕሮግራም በዚህ ዓመት መጨረሻ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የጉግል ቃል አቀባይ ‹‹ሰዎች ግልብ መረጃዎች እንዳይነዷቸው፣ ጠለቅ ያለና ውስብስ ዜናዎችን ማግኘት አለባቸው፣ የሚያነቃ፣ የጠራ መረጃን ለሚሰጥ ነገር መጋለጥ አለባቸው፤ ይህ እንዲሆን አሳታሚዎች ገንዘብ ሊያገኙ ይገባል፡፡ ስለዚህ መክፈል እንጀምለን›› ብለዋል፡፡ዶ/ር ሪጫርድ ስሚዝ እንዲህ ይላሉ፡፡‹‹ጉጉልን የሚያኖረው አሳታሚው የፈጠረው መረጃኮ ነው፡፡ስለዚህ መረጃ ፈጣሪው ከሌለ ጉግል ራሱ የለም፡፡ ለራሱ ህልውና ሲል ትርፉን ማጋራት ይኖርበታል›› https://www.bbc.com/amharic/news-53863156 +health ኮሮናቫይረስ፡ አንዳንድ ሰዎች ለምን ቶሎ ከኮቪድ-19 አያገግሙም? ብዙዎች ከኮሮናቫይረስ በቀላሉ፣ በአጭር ጊዜ ያገግማሉ። አንዳንዶች ላይ ግን በሽታው ይበረታል። ለወራት መተንፈስ የሚቸገሩ፣ የሚደክማቸውም አሉ። አጭር ርቀት ተጉዘው በጣም እንደሚደክማቸው የተናገሩ ሰዎች አሉ። በሽታው ዘለግ ላለ ጊዜም ይቆይባቸዋል። ኮቪድ-19 አንዳንዶች ላይ ለወራት የሚቆይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው ለምንድን ነው? ለሚለው ገና ግልጽ መልስ አልተገኘም። ኮሮናቫይረስ ለምን ረዥም ጊዜ ይቆያል? በሽታው ረዥም ጊዜ የቆየባቸው ሰዎች በአጠቃላይ ተመሳሳይ ምልክት አያሳዩም። ሆኖም ሁሉም እንደሚደክማቸው ይናገራሉ። ትንፋሽ ማጠር፣ ሳል፣ የጡንቻ ህመም፣ የስሜት ህዋሳት ህመም፣ ራስ ምታት እንዲሁም የልብ፣ ኩላሊት፣ አንጀት እና ሳምባ በሽታ የሚገጥማቸውም አሉ። በተጨማሪም ድብርት፣ ጭንቀት እና በግልጽ ለማሰብ መቸገር ይስተዋላል። ጄድ ግሬይ ክርስቲ “እንዲህ አይነት ድካም ተሰምቶኝ አያውቅም” ስትል ስሜቱን ገልጻለች። ፕ/ር ዴቪድ ስትሬይን “በሽታው አንዳንዶች ላይ እንደሚቆይ አንጠራጠርም” ብለዋል። በሮም ሆስፒታል 143 ታማሚዎች ላይ የተሠራ ጥናት፤ 87 በመቶ የሚሆኑት ከሁል ወራት በኋላ ከምልክቶቹ ቢያንስ ሁለቱ እንደታዩባቸው ይጠቁማል። ከግማሽ በላዩ ይደክማቸዋል። ዩኬ ውስጥ የሚሠራ መ��ግበሪያ እንደሚያሳየው፤ 12 በመቶ ህሙማን ከ30 ቀናት በኋላ የበሽታው ምልክት ታይቶባቸዋል። ከ50 ሰዎች አንዱ ከ90 ቀናት በኋላ ምልክት አሳይተዋል። ዘለግ ላለ ጊዜ የሚታመሙት በሽታው ከመጀመሪያውም የበረታባቸው ሰዎች ብቻ አይደሉም። ደብሊን ውስጥ የተሠራ ጥናት በበሽታው ከተያዙ ከአሥር ሳምንት በኋላ ድካም የገጠማቸው እንዳሉ ያሳያል። አንድ ሦስተኛው ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ አልቻሉም። ፕ/ር ክሪስ ብራይትሊንግ እንደሚናገሩት፤ ሳምባቸው የተጎዳ ሰዎች ለኒሞኒያ ተጋልጠዋል። ቫይረሱ ከሰውነት ቢወጣም አንዳንድ አካል ላይ እንደሚቀር ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ፕ/ር ቲም ስፔክተር “ዘለግ ላለ ጊዜ ተቅማጥ ከተከሰተ ቫይረሱ አንጀት ውስጥ ቀርቷል ማለት ነው። ማሽተት ካቀተ ደግሞ ቫይረሱ በህዋሳት ውስጥ ቀርቷል” ይላሉ። ቫይረሱ ህዋሳትን ሲያጠቃ፤ ሰውነት በሽታውን ለመከላከል ከመጠን በላይ ሲሞክር፤ አካላችን ይጎዳል። በሽታው የሰውነታችንን እንቅስቃሴም ያስተጓጉላል። የደም ዝውውር ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር የስኳር መጠናቸውን ለመቆጣጠር የተቸገሩ ህሙማን አሉ። የአንጎል መዋቅር ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የሚጠቁም መረጃ ቢኖርም እስካሁን አልተረጋገጠም። ህመሙ የተለመደ ነው? በቫይረስ ከተያዙ በኋላ መድከም ወይም ማሳል የተለመደ ነው። ከአሥር ሰዎች አንዱ ለወራት የሚቆይ የህዋሳት ህመም ሊገጥመው ይችላል። እአአ በ1918 ከተከሰተው ወረርሽኝ ወዲህ ጉንፋን የፓርኪንሰን በሽታን የሚመስል ምልክት ያለው ህመም እንደሚያስከትል ታይቷል። ኮቪድ-19ን ተከትሎ የተለያዩ የህመም ምልክቶች ሊስተዋሉ እንደሚችሉ ፕ/ር ክሪስ ያስረዳሉ። “ቫይረሱ የተለያዩ ሰዎችን በተለያየ መንገድ ይጎዳል። ህዋሳት ላይ የሚያስከትለው ችግርም ይለያያል። አንዳንዶች ላይ ሲበረታ፣ ለሌሎች ይቀላል” ይላሉ። ሙሉ በሙሉ ማገገም ይቻላል? ኮሮናቫይረስ ለረዥም ጊዜ የሚቆይባቸው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ይመስላል። ሆኖም ግን በሂደት የሚከሰተው አይታወቅም። ፕ/ር ክሪስ ሰዎችን ለ25 ዓመታት ለመከታተል እንደወሰኑና ህመሙ ከአንድ ዓመት በላይ ይቆይባቸዋል ብለው እንደማያምኑ ይናገራሉ። ሆኖም ግን ሰዎች አሁን ቢያገግሙም በሽታው ዘላቂ ተጽዕኖ ሊያሳድርባቸው የሚችልበት እድል አለ። በጣም የሚደክማቸው ሰዎች ስሜቱ ዘለግ ላለ ጊዜ ሊቆይባቸው ይችላል። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ወጣቶችም ሳይቀር ለልብ ህመም ሊጋለጡ ይችላሉ። ስለዚህም ከኮሮናቫይረስ በማገገም ላይ ያሉ ሰዎች ራሳቸው ላይ ጫና እንዳያሳድሩና እንዲያርፉ ይመከራል። አድካሚ ሥራ ካለባቸው በተከታታይ ከማከናወን ይልቅ በተለያየ ሰዓት መተግበር አለባቸው። በተጨማሪም በጠበቁት ፍጥነት ካላገገሙ ወደ ህክምና መስጫ መሄድ ይጠበቅባቸዋል። https://www.bbc.com/amharic/news-54441793 +sports ሊዮኔል ሜሲ የነገሠበት የኳታር የዓለም ዋንጫ ዋና ዋና ክስተቶች ከመነሻው ክስና ውዝግብ የገጠመው የኳታር የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅነት ድንቅ ክስተቶችን አስተናግዶ ሁሉን አጀብ ባሰኘ ሁኔታ ለፍጻሜ በቅቷል። አርጀንቲናን ጨምሮ የዓለማችን ታላላቅ ቡድኖች ሽንፈት ሲገጥማቸው፣ ሞሮኮና ሌሎች ብዙም ትኩረት ያልተሰጣቸው ቡድኖች ደግሞ ታሪክ ሰርተዋል። በመጨረሻም የ35 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ሊዮኔል ሜሲን የዋንጫ ባለቤት በማድረግ ደማቅ ታሪክ እንዲጽፍ ያስቻለው የ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ሂደት ምን ይመስል ነበር? https://www.bbc.com/amharic/articles/c726pgwgxwjo +health ዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ-19 ከ80 እስከ 180 ሺህ የሚደርሱ የጤና ሠራተኞችን ሳይገድል አይቀርም አለ "የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የጤና ሠራተኞችን ክፉኛ መጎዳቱንና ከ80,000 እስከ 180,000 የ��ደርሱትን ግድሎ ሊሆን እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። የጤና ሠራተኞች ለክትባት ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፤ የክትባቱን ኢፍትሃዊ ስርጭትን ተችተዋል። ሞቱ የተመዘገበው በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ከጥር 2020 እስከ ግንቦት ባለው ጊዜ ነው። ቀደም ሲል ሌላ ከፍተኛ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣን የክትባት እጥረት ወረርሽኙ እስከሚቀጥለው ዓመት ድረስ ሊያስቀጥለው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። በዓለም ዙሪያ 135 ሚሊዮን የጤና ሠራተኞች እንዳሉ ይገመታል። ""ከ 119 አገራት የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአምስት የጤና ሠራተኞች በአማካይ ሁለቱ ሙሉ በሙሉ ክትባት አግኝተዋል"" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። ""ይህ ቁጥር በተለያዩ አገራት እና በኢኮኖሚ ቡድኖች ውስጥ ያለውን ትልቅ ልዩነት ይሸፍናል።"" በአፍሪካ ውስጥ ከ10 የጤና ሠራተኞች መካከል አንዱ ብቻ ሙሉ በሙሉ ክትባት ሲወስድ ከፍተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ስምንቱ ተከትበዋል። ቀደም ሲል ለድሃ አገራት በቂ ክትባት አለመስጠቱ የኮቪድ-19 ቀውስ ""በቀላሉ ወደ 2022 ሊጎትት ይችላል"" ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊ ዶ/ር ብሩስ አይልዋርድ ገልጸዋል። በአብዛኛዎቹ አህጉራት 40 በመቶ ሰዎች ክትባት ሲያገኙ ይህ ቁጥር በአፍሪካ ከአምስት በመቶ በታች ነው። አብዛኛው የኮቪድ-19 ክትባት ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ወይም በከፍተኛ መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ጥቅም ላይ ውሏል። አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተሰጡት ክትባቶች 2.6 በመቶውን ብቻ ትይዛለች። ክትባቶችን በፍትሃዊነት ለማሰራጨት በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈው ዓለም አቀፍ ፕሮግራም የሆነው የኮቫክስ የመጀመሪያው ሃሳብ ሃብታሞቹን ጨምሮ ሁሉም አገራት ከአንድ ማዕከል ክትባቶችን ማግኘት መቻላቸውን ለማረጋገጥ እንደነበር የቢቢሲ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዘጋቢ ኑሃሚን ግሪምሌይ ጽፋለች። ነገር ግን አብዛኛዎቹ የቡድን 7 አገራት ከአምራቾች ጋር የራሳቸውን አንድ ለአንድ ስምምነት ማድረግ ከጀመሩ በኋላ ከስምምነቱ ወደ ኋላ ለመመለስ ወሰኑ። የመድኃኒት አምራቾች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገራት ቅድሚያ እንዲሰጡ ሃብታም አገራት በክትባት ለመግዛት ያላቸውን ወረፋ እንዲተው ዶ/ር አይልዋርድ ጥሪ አቅርበዋል። ""በትክክለኛ በመንገድ ላይ እንዳሆንን ልንናገር እችላለሁ። በእርግጥ ማፋጠን አለብን። ካልሆነ ግን ምን እንደሚፈጠር ያውቃሉ? ይህ ወረርሽኝ ከሚያስፈልገው በላይ ለአንድ ዓመት ያህል ይቀጥላል"" ብለዋል። ዘ ፒፕልስ ቫክሲን የተባለው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሕብረት በመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች እና በሃብታም አገራት ቃል ከተገባው ከሰባት ክትባት አንዱ ለድሃ አገራት እየደረሰ መሆኑን የሚጠቁሙ አዳዲስ አሃዞችን አውጥቷል። ኦክስፋምን እና ዩኤንኤድስን ያካተተው ሕብረት በኮቫክስ በኩል ለራሳቸው ሕዝብ ክትባቶችን እየገዙ ነው በሚል ካናዳ እና እንግሊዝን ነቅፈዋል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ዩናይትድ ኪንግደም 539,370 የፋይዘር ክትባቶችን ከኮቫክስ የተቀበለች ሲሆን ካናዳ ከአንድ ሚሊዮን ገደማ የአስትራዜኔካ ክትባት ወስዳለች። ኮቫክስ በመጀመሪያ በዚህ ዓመት መጨረሻ ሁለት ቢሊዮን ክትባቶችን ለማድረስ ቢያቅድም እስካሁን ያሳካው 371 ሚሊዮን ብቻ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-58991731 +business ለ50 ዓመታት ሳይፈታ የቆየውን የሒሳብ እንቆቅልሽ በቀናት ውስጥ የፈታችው ተማሪ "አሜሪካዊቷ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለ50 ዓመት የበርካቶችን አእምሮ የፈተነውንና ሳይፈታ የቆየውን የሒሳብ ቀመር በቀላሉ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ፣ በትርፍ ሰዓቷ ፈትታዋለች። ሊሳ ፒኪሪሎ ሦስተኛ ዲግ��ዋን በዩኒቨርስቲ ኦፍ ቴክሳስ እየሰራች ነው። ከዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሯ ካሜሮን ጎርደን ጋር እያወራች በነበረበት ወቅት እግረ መንገዷን ለወሬያቸው ማጣፈጫ በሚል የሰራችውን የሒሳብ ስሌት፣ ያቃለለችውን የሒሳብ ቀመር አነሳች። ""መጮህ ጀመረ 'እንዴት በጣም ደስተኛ አልሆንሽም?'"" እንዳላት ፒኪሪሎ በኳንታ ለሚታተመው የሳይንስ ዜናን የሚሰራጨው ድረገጽ ተናግራለች። ""እብድ ነው የሆነው"" በማለትም የነበረውን ሁኔታ ያስታወሰችው። ወይዘሪት ፒኪሪሎ ሦስተኛ ዲግሪዋን ሳትይዝ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያሰጣት የሒሳብ ቀመር 'ኮንዌይ ኖት ፕሮብሌም' ይሰኛል። ኮንዌይ ኖት ፕሮፕሌም (Conway knot problem) በብሪታንያዊው ሒሳብ ሊቅ ጆን ሆርቶን ኮንዌይ በ1970 የተቀመረ ነው። ፒካሪሎ ግን ስለዚህ መልመጃ የሰማችው ለመጀመሪያ ጊዜ እአአ በ2018 በአንድ ሴሚናር ላይ መሆኑን ታስታውሳለች። ፕሮፌሰር ጎርደን ""ምን ያህል እድሜ ጠገብ ዝነኛ የሒሳብ መልመጃ መሆኑን ያወቀች አይመስለኝም"" ብለዋል። የወይዘሪት ፒኪሪሎ ሥራ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የታተመ ሲሆን እርሷም ይህንን የጥያቄ ጎምቱ፣ የመልመጃዎች አውራ በመፍታቷ በማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝታለች። ""የኮንዌይ ኖት መልመጃ ለረዥም ዓመታት በሒሳብ ሊቃውንት ሊፈታ ሳይችል ቆይቷል"" ያሉት ስፔናዊው ተመራማሪ ያቬር አራማዮና ናቸው። ይህ የሒሳብ ቀመር እንደምን ያለ ነው? ሒሳባዊ ቋጠሮ (Mathematical knots) የአንድ የሒሳብ ዘርፍ ሲሆን የሚመደብበትም ክፍል ቶፖሎጂ ይሰኛል። በቀላል ቋንቋ፣ ቶፖሎጂ የሚያጠናው ቁሶች ቅርጻቸውን ሲቀይሩ፣ ሲጎብጡ፣ ሲጠመዘዙ እና ሲወጠሩ-ነገር ግን ሳይሰበሩ እንዴት ያለ ጠባይ እንደሚያሳዩ ነው። ኖት ቲዎሪ (የጥልፍልልፎሽ ኀልዮት) የቶፖሎጂ አንዱ ዘርፍ ነው። ከእውኑ ዓለም ምሳሌዎች በተጻራሪው፣ ሒሳባዊ ቋጠሮ መጨረሻዎቹ የተሳሰረ ነው። በእርግጥ ቀላሉ ቋጠሮ የቀለበት ቅርጽ አለው፤ እናም ሊዋሃድ አይችልም። ነገር ግን የበለጠ ውስብስብ ይሆናል፤ ይህም አንዱ በአንዱ ላይ ሲጠላለፍና ሲቆላለፍ ነው። ይህንን በቀላሉ ለማስረዳት ገመድን ማሰብ በቂ ነው የሚሉት ማሪታኒያ ሲልቬሮ ናቸው። በሴቪሊ ዩኒቨርስቲ የሒሳብ ሊቅ የሆኑት እኚህ ምሁር ""የጥልፍልልፎሽ ኀልዮት በአንድ ገመድ ላይ የሚከሰትን ቅርጽ አልባነት ያጠናል"" ሲሉ ያክላሉ። ""በሌላ ቋንቋ፣ ገመዱን እንዴት አድርገን እንደምንጠመዝዝ፣ እንደምናጎብጠው፣ እንደምናጥፈው፣ እንደምንጨምቀው. . .ገመዱን ለመቁረጥ የማናደርገው ነገር ማለት ነው። ያ ክልክል ነው።"" ቶፖሎጂ ታዲያ በተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች ውስጥ ቁልፍ ቦታ አለው። የምጣኔ ሃብት ገበያዎችን እንዲሁም የዲኤንኤ ሞሎኪውልስን ቅርጽ ለማጥናት ይውላል። ከኖት ፕሮብሌም ጀርባ ያለው ሰው ጆን ሆርቶን ኮንዌይ በሚያዚያ ወር በተወለደ በ82 ዓመቱ በኮሮናበቫይረስ ምክንያት ሞቷል። ሊቨርፑል የተወለደው ይህ የሒሳብ ሊቅ በዘርፉ ምሁራን ዘንድ ተወዳጅ እንደነበር ይነገርለታል። ወይዘሪት ፒኪሪሎ 11 ጊዜ የተጠላለፈን የኮንዌይ ኖት ነው ተመሳሳዩን በመስራት ""አቻ ጥልፍልፍ"" መፍታት የቻለችው። እርሷ በአቻነት የሰራችው ጥልፍልፎሽን የእውቁን የሒሳብ ሊቅ የ50 ዓመት ሚስጥር ለመፍታት ተጠቀመችበት። ""ቀን ቀን ለመስራት አልፈልግም ነበር፤ ያ ለሒሳብ የሚመች አይመስለኝም. . . ልክ የቤት ሥራ እንደተሰጠኝ በማሰብ ቤት ወስጄ ነው የሰራሁት"" ብላለች። ወይዘሪት ፒኪሪሎ በአሜሪካ ማይን በምትባል ገጠራማ ስፍራ ተወልዳ ያደገች ሲሆን ሒሳብን ያጠናችው በቦስተን ኮሌጅ ነው።" https://www.bbc.com/amharic/news-53160666 +sports ቶኪዮ ኦሎምፒክ 2020፡ ለተሰንበት ከሲፈን፤ ስለ ሁለቱ ስመ ጥር አትሌቶች ሊታወቁ የሚገቡ ነጥቦች "በሁለት ቀን ልዩነት የ10ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንን ማሻሻል የቻሉት አትሌት ለተሰንበት ግደይ እና ሲፈን ሐሰን በትልቁ የአትሌቲክስ መድረክ ላይ በ10ሺህ ሜትር ተፋጠዋል። እነዚህ አትሌቶች በትልቅ የአትሌቲክስ መድረክ ላይ ሲገናኙ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በሪዮ ኦሎምፒክ የ10ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን በማሻሻል ወርቅ የወሰደችው አልማዝ አያና እና የወቅቱ ተፎካካሪዋ ቪቪያን ቼሪዩት በቶኪዮ ኦለምፒክ ተሳታፊ ባለመሆናቸው የፊታችን ቅዳሜ በሚደረገው የ10ሺህ ሜትር ፍጻሜ የወርቅ ሜዳሊያ ከሲፈን ወይም ከለተሰንበት እንደማያልፍ ይጠበቃል። በዚህ ውድድር ሌሎች ተጠባቂ ከሆኑት ተወዳዳሪዎች መካከል ኢትዮጵያውያኖቹ ጽጌ ገ/ሰላማ እና ጸሃይ ገመቹ እንዲሁም በርቀቱ ብዙ ልምድ ያላት ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ ተጠቃሽ ናቸው። እአአ 2019 ላይ በኳታር ዶሃ በተዘጋጀው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተገናኝተው ሲፈን ወርቁን ስትወስድ ለተሰንበት በሁለተኛነት አጠናቃለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሚሳተፍባቸው ርቀቶች በትውልድ ኢትዮጵያዊ እና የኔዘርላንድስ ዜጋ የሆነችው ሲፈን ዋነኛ ተፎካካሪ መሆኗን ገልጿል። ሲፈን በ1500 ሜትር፣ በ5ሺህ ሜትር እና በ10ሺህ ሜትር ወርቅ ለማምጣት ቆርጣ ተነስታለች። በ5ሺህ ሜትር እቅዷን ያሳካች ሲሆን በ1500 ሜትርም ማጣሪያውን አልፋለች። ብዙ ልምድ ያካበተችው የ28 ዓመቷ ሲፈን በቶኪዮ ኦሊምፒክ ታሪክ ለመስራት ወጥናለች። በሌላ በኩል ገና የ23 ዓመት ወጣት የሆነችው ለተሰንበት ግደይ በኦሊምፒክ መድረክ ስትወዳደር ይህ የመጀመሪያዋ ይሁን እንጂ የምትገኝበትን ወቅታዊ አቋም ከግምት በማስገባት የ10ሺህ ሜትር ድሉን ለለተሰንበት የሚሰጡ በርካቶች ናቸው። እአአ 1992 በባርሴሎና ኦሊምፒክ የየዛኔዋ የ23 ዓመት ወጣት፣ አትሌት ደራርቱ ቱሉ በ10ሺህ ሜትር ለአገሯ ወርቅ አስገኝታ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላም በሲድኒ ኦሊምፒክ በተመሳሳይ ርቀት ወርቅ አምጥታለች። በዘንድሮ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ለተሰንበት ኖሯት ሲፈን የማይኖራት ብቸኛው ነገር የደራርቱ ቱሉ ድጋፍ ነው። ""ሁለቱም ልጆች የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው። እንደ ዜጋችን ለተሰንበትን እንጠብቃለን። የምንደግፈውም ለተሰንበትን ነው። ይሁን እንጂ ሲፈንም የኛው ልጅ ነች። የምንኮራባት እና የምንወዳት ልጅ"" ትላለች አትሌት ደራርቱ ቱሉ። ደራርቱ ቱሉ ከለተሰንበት ጋር ልምምድ ስታደርግ እና ስታበረታታት ታይታለች። ለተሰንበት እና ሲፈን ለተሰንበት ተማሪ ሳለች በስፖርት ክፍለ ጊዜ 'አልሮጥም' በማለቷ 'ወላጅ አምጪ' ተብላ ነበር። ዛሬ ላይ ግን ለተሰንበት በሩጫው ሌላ ዓለም ውስጥ ነው ያለችው። የወቅቱ የ10ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን በእጇ ይገኛል። ሲፈን ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄዳው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን በ1500 ሜትር እና በ10ሺህ ሜትር ሁለት ወርቅ በመውሰድ ታሪክ ሰርታለች። ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፈን በኦሊምፒክ ስትሳተፍ ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። በሪዮ ኦሎምፒክ 800 ሜትር 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የፊታችን ቅዳሜ ለተሰንበት በርቀቱ የኢትዮጵያን የበላይነት ለማረጋገጥ፤ ሲፈን ደግሞ በአንድ የኦሊምፒክ መድረክ ሦስት ወርቅ የማግኘት ሕልሟን ለማሳካት ይሮጣሉ። ሲፈን ለለተሰንበት ስጋት ትሆን? ""አዎ ያሳስበናል፤ ለምን? በዓለም ቁጥር አንድ የምትባለ አትሌት ቀርቶ ሌላም አትሌት መናቅ የለበትም። ስለዚህ ጥንቃቄ ይፈልጋል። በቂ የሆነ ወድድር አድርጋለች [ለተሰንበት]። ጤንነቷ ጥሩ ነው። የአእምሮ ዝግጅቷም ጥሩ ነው። አስቀድመን በደንብ አዘጋጅተናታል"" በማለት ደራርቱ ትናገራለች። ለስደሰተኛ ጊዜ በኦ���ምፒክ የሚሳተፉት እና ለተሰንበትን በዋነኛነት የሚያሰለጥኑት አሰልጣኝ ኮማንደር ሁሴን ሸቦ፣ በለተሰንበት አሁናዊ አቋም ጥርጥር ባይገባቸውም ሲፈን ጠንካራ ተፎካካሪያቸው እንደምትሆን ያምናሉ። ሲፈንን ለማሸነፍ የተቀመጠው ስልት ኮማንደር ሁሴን አትሌት ሲፈን ለኢትዮጵያ አትሌቶች ስጋት ልትሆን የምትችልባቸውን ምክንያቶች እንዲህ ያስረዳሉ። ""በ5ሺህ እና በ10ሺህ ርቀቶች አሁን ባላት ልምድ እና ችሎታ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደምትሆን ምንም ጥርጥር የለውም""። ሌላኛው ደግሞ ሲፈን በመጨረሻ ዙር ላይ ፍጥነት እንዳላት አሰልጣኙ ይናገራሉ። ""ሲፈን በውድድር መጨረሻ ላይ ከለተሰንበት የበለጠ ፍጥነት አላት"" በማለት ያስረዳሉ። ለዚህም የአትሌቲክስ ቡድን ሲፈንን ለማሸነፍ መላ መዘየዱን አሰልጣኙ ይናገራሉ። ""እንደ ታክቲክ ለተሰንበት ማድረግ ያለባት እሷን [ሲፈንን] ከእራሷ ሳታርቅ ዙሩን አክርራ ሄዳ፣ አንድ ሁለት ዙር እስኪቀር ድረስ አኩል ከሮጡ ልትፈተን [ሲፈን] ትችላለች"" ሲፈን በዚህ ኦሊምፒክ በሦስት ውድድሮች ነው የምትካፈለው። የመጨረሻው ደግሞ የ10ሺህ ሜትር ውድድር ነው። በዚህ ውድድር ተሳታፊ በምትሆን ጊዜም ድካም ሊጫናት ይችላል። ""ይህ የሚሳካ ከሆነ አስደናቂ ነገር ነው [ሲፈን በሦስት ውድድር ወርቅ የማግኘት እቅድ]። ሁለት ውድድር አጠናቅቃ ሦስተኛው ላይ 10ሺህ ሜትር መሮጥ ይቅርና በዛ ሙቀት ቦታ፣ ሁለት ውድድር ማድረግ በራሱ በጣም ከባድ ነው። ሦስተኛው ውድድር ላይ በጣም ይከብዳታል የሚል ጥርጣሬ አለኝ"" በማለት ኮማንደር ሁሴን ይናገራሉ። በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚካሄድባት ጃፓን በአሁኑ ወቅት ያለው ሙቀት ከፍተኛ በመሆኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ሞቃታማ ወደሆኑ እንደ መተሃራ እና አዋሽ ከተሞች ልምምድ ሲያደርግ መቆየቱን ደራርቱ ቱሉ ለቢቢሲ ተናገራ ነበር።" https://www.bbc.com/amharic/news-58073431 +sports አትሌቲክስ፡ ለተሰንበት ግደይ የ5 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን ሰበረች "ኢትዮጵያዊቷ ሯጭ ለተሰንበት ግደይ በትናንትናው ዕለት የአምስት ሺህ ሜትር ርቀት ክብረ ወሰን ሰብራለች። ቫለንሺያ በተደረገው በዚህ ውድድር በጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት አመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሽላለች ተብሏል። የ22 ዓመቷ ሯጭ የገባችበትም ሰዓትም 14 ደቂቃ ከ6.62 ሰኮንዶች ሲሆን የጥሩነሸ ደግሞ 14 ደቂቃ ከ11.15 ሰኮንዶች ነበር። በትናንትናው ዕለት ከሷ በተጨማሪ ኡጋንዳዊው ጆሹዋ ቼፕተጊ በቀነኒሳ በቀለ ለአስራ አምስት ዓመታት ተይዞ የነበረውን የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በስድስት ሰኮንዶች በማሻሻልም ሰብሯል። የ24 ዓመቱ ሯጭ የገባበትም ሰዓት 26 ደቂቃ ከ11 ሰኮንዶች ነው ተብሏል። በስፔኗ ቫለንሺያ ከተማም ሁለት ክብረ ወሰኖች የተሰበሩበት እለትም ሆኗል። ""በጣም ተደስቻለሁ"" በማለትም ለተሰንበት ከሩጫው በኋላ ተናግራለች። ከዓመት በፊት በዶሃ ተካሂዶ የነበረውን የአለም ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ብር አግኝታ የነበረ ሲሆን "" ለረዥም ጊዜ ሳልመው የነበረ ነው። ለኔ በጣም ትልቅ ነው"" በማለትም ተናግራለች በቀነኒሳ በቀለ ተይዞ የነበረው 26፡ 17፡53 ሰዓት በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ለረዥም ጊዜ በመያዝ ታሪካዊ የተባለ ክብረ ወሰን ነው። ጆሹዋ በአስር ወራትም ውስጥ አራት የአለም ክብረ ወሰኖችን መጨበጥ ችሏል። በታህሳስ ወር የ10 ኪሎ ሜትር የመንገድና በየካቲት ወር እንዲሁም የ5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ክብረ ወሰኖችን ይዟል። ነሐሴ ወር ላይ በነበረው የሞናኮ ዳይመንድ ሊግም በቀነኒሳ በቀለ ለ16 አመታት ተይዞ የነበረውን የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንም በሁለት ሰኮንዶች በማሻሻል ሰብሯል። 'የዓለም ሬኮርድ (ክብረ ወሰን) ቀን' በተባለው በዚህ ውድድርም በቫለንሺያ ቱሪያ ስታዲየም 400 ሰዎች በተገኙበት ተካሂዷል።" https://www.bbc.com/amharic/news-54459888 +sports የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት የዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ ያለፈው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ተሰርዘው ነበር። ይህም ሕዳር ላይ ከሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ጋር ተደማምሮ ለፕሮግራም መጣበብ ተጨማሪ ራስ ምታት ሆኗል። የስምንተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት ይከናወናሉ። በዚህ ሳምንትም ሦስት ጨዋታዎች ለሌላ ጊዜ ተላልፈዋል። አርብ፣ ቅዳሜ እና እሑድ የሚካሄዱትን ሰባት ጨዋተዎች ግምት ቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ እንደሚከተለው ቃኝቷቸዋል። አስቶን ቪላ ከ ሳውዝ ሃምፕተን አሰልጣኝ ዤራርድ ጫና ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት ይህ ጨዋታ ለቪላ ትልቅ ትርጉም አለው። ሳውዝ ሃምፕተን ከቪላ የተሻለ ጥሩ አጀማመር አሳይቷል። የቪላ ደጋፊዎች ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ያገኛሉ። ጨዋታው ጥሩ ፉክክር የሚኖረው ሲሆን ቪላ ያሸንፋል ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 – 1 ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ፉልሃም 2-0 ከመምራት በበርንማውዝ ለተሸነፉት ፎረስቶች ይህ ጨዋታ ወሳኝ ነው። ሽንፈቱ ለቡድኑም ሆነ ለደጋፊዎቹ ጥሩ አይመስለኝም። ከፉልሃም ጋር በሚኖረው ጨዋታቸው የሚሰጡት ምላሽ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት ሁለቱ ቡድኖች በሻምፒዮንሺፑ ለይ ሲገናኙ ፉልሃም 4 ለ 0 አሸንፏል። አሌክሳንደር ሚትሮቪች ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል። ዘንድሮም የተለየ ውጤት አልጠብቅም። ግምት፡ 0 – 2 ዎልቭስ ከ ማንችስተር ሲቲ ባለፈው ሁለቱ ቡድኖች ተጫውተው ማንቸስተር ሲቲ 5 ለ 1 ሲያሸንፍ በሜዳው ውስጥ ነበርኩ። በዕለቱ ኬቪን ደ ብሩይን ድንቅ ነበር። ዎልቭሶች አሁን ኤርሊንግ ሃላንድንም እንዴት ማስቆም እንዳለባቸው ሊጨነቁ ይገባል። ዎልቭሶች ጎል እንደሚያስቆጥሩ ባስብም ሲቲ ያሸንፋል። ግምት፡ 1 - 3 ብራይትን ከ ክሪስታል ፓላስ ይህ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል። ኒውካስል ከ በርንማውዝ የኒውካስሉ አሰልጣኝ ኤዲ ሆዊ የቀድሞ ክለባቸውን ለማሸነፍ ይጫወታሉ። ማሸነፍ እንደሚችሉም ብዙ ምክንያት ማስቀመጥ ይቻላል። ኒውካስል በማጥቃት የሚጫወት ሲሆን የተወሰኑ ጎሎችንም ማስቆጠር አለባቸው። ብርንማውዞች ባለፈው ከፎረስት ጋር ከመመራት ተነስተው ባሸነፉበት መነሳሳት ለመቀጠል ይሞክራሉ። ብርንማውዞች ከዚህ ጨዋታ ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አላስብም። ቶተንሃም ከ ሌስተር ቶተንሃም በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በስፖርቲንግ ሊዝበን ተሸንፏል። ባለፉት ሳምንታት ውጤታቸው ሜዳ ውስጥ ያለውን አቋማቸውን ያሳያል ብዬ አላስብም። ሌስተሮች በማጥቃት መስመር ጥሩ ቢሆንም የተከላካይ ስፍራ ላይ ብዙ ክፍተት አለባቸው። ሶን ሁዩንግ ሚን በዚህ ጨዋታ ወደ ጎል ማስቆጠር ይመለሳል ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 4 – 1 ብሬንትፎርድ ከ አርሴናል ብሬንትፎርዶች ባለፈው ውድድር ዓመት ወደ ሊጉ እንደመጡ አርሴናልን በማሸነፍ ጥሩ አጀማመር አድርገዋል። በዚህ ጨዋታም ትልቅ ፉክክር ይኖራል። አርሰናሎች ባለፉት 12 ወራት ተሻሽለዋል። ብሬንትፎርዶች ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ሊድስ ጋር ያላቸውን አቅም ማሳየት ችለዋል። ስለዚህ በዚህ ጨዋታ አርሰናል የሚፈተንበት ይሆናል። ከዚህ ጨዋታ ብርንትፎርዶች ነጥብ እንደሚያገኙ ይሰማኛል። ግምት፡ 1 - 1 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሊድስ ይህ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል። ኤቨርትን ከዌስት ሃም ሁለቱም ቡድኖች ዕድለኞች አይደሉም እንጂ አሁን ካላቸው የተሻለ ነጥብ ማግኘት ነበረባቸው። ኤቨርተኖች በሊጉ የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ ይጫወታሉ። ከሊቨርፑል ጋር ጥሩ የነበሩ ሲሆን ለማሸነፍ የሚከብዱ ሆነዋል። ማሸነፍ የሁለቱም ቡድ��ች የውድድር ዓመት የሚያቃና ይሆናል። ዌስት ሃም ሦስት ነጥብ ያሳካል ብዬ አስባለሁ። ባለፈው ዓመት በሁለቱም ጨዋታዎች ዌስትሃሞች ያሸነፉ ሲሆን ዘንድሮም የተለየ አይሆንም። ግምት፡ 1 - 2 ቼልሲ ከ ሊቨርፑል ይህ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c9rkxzv0rn2o +sports በኢትዮጵያዊቷ መስከረም የተጠነሰሰው የአፍሪካ ሴቶች እግር ኳስ ቻምፒዮንስ ሊግ ተጀመረ "የመጀመሪያው ቶታልኤነርጂስ ካፍ የአፍሪካ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ባለፈው አርብ በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ተጀመረ። ይህ በአፍሪካ ታሪክ የመጀሪያው የሆነው ውድድር ለሁለት ሳምንታት የሚዘልቅ ነው። የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪ የሆነው ካፍ በማኅበራዊ ሚድያ ገፆቹ ውድድሩን በማስመልከት ሰፊ ዘገባ እያወጣ ይገኛል። የካፋ የሴቶች እግር ኳስ ክፍል ነባር ማኔጀር የሆኑት መስከረም ታደሰ ይህንን ውድድር ከጠነሰሱና ካሳኩ ሰዎች መካከል በመሆን ታሪክ መሥራታቸው እየተነገረላቸው ይገኛል። መስከረም ባለፈው ወር ከካፍ ድረ ገጽ ጋር ባደረጉት ቆይታ ""ይህ ውድድር እውን ሆኖ ማየቴ ትልቅ ደስታ ሰጥቶኛል"" ብለው ነበር። የቶታልኤነርጂስ ካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተሳታፊ ለመሆን 32 የአፍሪካ ክለቦች ቀጣናዊ የማጣሪያ ውድድር አድርገው ነበር። ይህንን ቀጣናዊ ውድድር ያሸነፉ ስምንት የአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ክለቦች በዚህ ታሪካዊ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ። የማሊ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ሞሮኮና የአስተናጋጇ ግብፅ ክለቦች በዚህ የ15 ቀናት ውድድር ላይ እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል። ያለፈው ዓመት የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ አሸናፊ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ኬንያ አቅንታ የማጣሪያ ውድድር ማድረጓ አይዘነጋም። ታድያ በዚህ ታሪካዊ ውድድር ኢትዮጵያን ለመወከል ከጫፍ ደርሳ የነበረችው የንግድ ባንክ ቡድን በማጣሪያው የፍፃሜ ጨዋታ በኬንያዋ ኢሂጋ ኩዊንስ ተሸንፋ መውደቋ ይታወቃል። ምንም እንኳን ንግድ ባንክ በዚህ ውድድር ላይ አገሯን መወከል ባትችልም ዋና ዳኛ ሊድያ ታፈሰ ወደ ግብፅ በማቅናት ኢትዮጵያን ትወክላለች። ዋና ዳኛ ሊድያ በውድድር ሁለተኛ ቀን [ቅዳሜ] በሞሮኮዋ አርሚ ሮያል ራባትና በናይጄሪያዋ ሪቨርስ አንግልስ መካከል የሚደረገውን ፍልሚያ ትዳኛለች። ሊድያን ጨምሮ በፈረንጆቹ 2023 አውስትራሊያ የሚደረገውን የሴቶች ዓለም ዋንጫ ለመዳኘት የተመለመሉ የአፍሪካ ሴት የእግር ኳስ ዳኞች ይህን ውድድር ይዳኛሉ። በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ አል-ሰላም ስታድዬም የሚደረገው ይህ ታሪካዊ ውድድር ለአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ቡድኖች ትልቅ መድረክ ሆኖ ታይቷል። ውድድሩ በሱፐር ስፖርት፣ በቤይን ስፖርት፣ በካናል ፕላስ፣ በካፍ ድረ-ገፅና በፊፋ የዩትዩብ ገፅ እንደሚተላለፍ ካፍ አስታውቋል።" https://www.bbc.com/amharic/news-59166789 +politics የዶናልድ ትራምፕ አዲሱ ማሕበራዊ ሚድያ ምን ዋጠው? "ባለፈው ዓመት ጥቅምት ላይ ነበር የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አብዮታዊ የቴክኖሎጂ ኩባንያ እከፍታለሁ ሲሉ ቃል የገቡት። ""ትሩዝ ሶሻልን ፈጥርያለሁ። ትላልቅ ኩባንያዎች በእውነት ስም ለመሞገት ስል"" ብለው ነበር። ""እንግዲህ የምንኖርበት ዘመን ታሊባን ትዊተር ላይ ብዙ ተከታዮች ያፈራበት፤ እናንተ የምትወዱት ፕሬዝደንታችሁ ግን ድምፁ የታፈነበት ነው"" ሲሉ ምሬታቸው ገልጠዋል በወቅቱ። ትራምፕ እንደፎከሩ አልቀሩም። ትሩዝ ሶሻል የተባለውን ማሕበራዊ ድር አምባ በፈረንጆቹ የካቲት 21 ይፋ አደረጉ። ነገር ግን ከስድስት ሳምንታት በኋላ የዶናልድ ትራምፕ አዲሱ ድር አምባ በችግር ተተብትቧል። ቢያንስ 1.5 ሚሊዮን ሰዎ��� ትራምፕን ብለው ይህን ድር አምባ ለመጠቀም ቢመዘገቡም በቀላሉ የቀድሞውን ፕሬዝደንት ማግኘት አልቻሉም። ይህን ማበራዊ ሚዲያ ለመጠቀም የተመዝጋቢዎች ቁጥር 1.4 ሚሊዮን ደርሷል። ትሩዝ ሶሻል በትዊተር አምሳል ነው የተሠራው። ትራምፕ ከዚህ በኋላ መተግበሪያዬን መጠቀም አይችሉም ብሎ እስከወዲያኛው ባሰናበተው ትዊተር አምሳል። ትዊተር ትራምፕን ከአምባው ያገደው ምርጫው በግድ ""ተጭበርብሯል"" ብለው ሃሳዊ ንግግር አሰራጭተዋል፤ አመፅም ቀስቅሰዋል በሚል ነው። ትራምፕ ከትዊተር በሞት ይፍታህ የተባረሩት በፈረንጆቹ ጥቅምት 8 ነበር። 'ትሩዝ ሶሻል' ትዊተርን ይምሰል እንጂ አንድሮይድ ስልክ ለሚጠቀሙ ሰዎች አልተሠራም፤ በድረ-ገፅም ማግኘት አይቻልም። አልፎም ይህ ድር አምባ ከአሜሪካ ውጭ ላሉ ተጠቃሚዎች ክፍት አይደለም። ""ትልቅ ውድቀት ነው"" ነው ይላሉ የኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል ሚድያና ፓለቲክስ ማዕከል ኃላፊው ጆሽዋ ታከር። ስማቸው እንዳይጠቀስ የሻቱ አንድ ሪፐብሊካን የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ ደግሞ ""ምን እየሆነ እንዳለ የሚያውቅ ሰው የለም"" ሲሉ ሹክ ብለዋል። የካቲት 21 ትሩዝ ሶሻል አፕ ስቶር ከተሰኘው የአይኦኤስ መተግበሪያ ማውረዳጅ ላይ ብዙ ሰዎች ያወረዱት መተግበሪያ ሆኖ ነበር። ነገር ግን ያወረዱት ሰዎች ሊጠቀሙበት አልቻሉም። ብዙዎች ችግሩ በጥቂት ቀናት ተቀርፎ ዶናልድ ትራምፕ እንደተለመደው አወዛጋቢ ፅሑፋቸውን ጣል ያደርጋሉ ተብሎ ቢጠበቅ ጠብ የሚል ነገር ጠፋ። እነ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ፣ ፌስቡክና እና ኢንስታግራም ብዙ ሰዎች ያወረዷቸው 10 መተግበሪያዎች ሆነው ታሪክ ሲፅፉ የትራምፕ ትሩዝ ሶሻል ከቁንጮ 100 ተርታ ውጭ ነው። አንደምንም ብለው ትሩዝ ሶሻልን መጠቀም የቻሉ ሰዎች ደግሞ ውስጥ ሲገባ ዝምታው ይጮኻል ይላሉ። አብዛኛዎቹ ቀኝ ዘመም የአሜሪካ ፖለቲከኞች እስካሁን ትሩዝ ሶሻልን ለመቀላቀል እያመነቱ ነው። አሁን ደግሞ መተግበሪያውን ከአፕ ስቶር የሚያወርዱት ሰዎች ቁጥርም እየቀነሰ ነው። ""ከሳምንታት በፊት ነበር ትሩዝ ሶሻልን ለመጠቀም የተመዘገብኩት። ነገር ግን እስካሁን ተጠባባቂ ወንበር ላይ ነኝ"" ሲል አንድ ግለሰብ ትዊተር ላይ ለጥፎ ነበር። የትሩዝ ሶሻል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴቪን ኑኔዝ ድር አምባው በመጋቢት ወር መጨረሻ ""ሙሉ በመሉ ሥራ ይጀምራል"" ብለዋል። ነገር ግን መተግበሪያው ለምን እንደዚህ በችግር እንደተበተበ ለብዙዎች ግራ የገባ ሆኗል። አንዳንዶች ትሩዝ፤ ራምብል ከተሰኘው በዩቲዩብ አምሳል ከተሠራው የተንቀሳቃሽ ምስል መጋሪያ ድር ጋር መጣመሩ ነው ያንቀራፈፈው ይላሉ። በወግ አጥባዊ አሜሪካዊያን ዘንድ ታዋቂ የሆነው ራምብል የትሩዝ የጀርባ አጥንት ይሆናል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ችግሩን በቀናት ልዩነት መፍታት አልተቻለም? የብዙዎች ጥያቄ ነው። ""በስድስት ሳምንታት ሳይሆን በጥቂት ቀናት ውስጥ ሊፈታ ይገባ ነበር"" ይላሉ ሪፐብሊካኑ የትራምፕ የቅርብ ሰው። ""ሁሌም ሲጀመር ችግር አያጣውም። ነገር ግን አሁን ተፈቶ ልንጠቀመው በተገባ ነበር። ምን እየሆነ እንዳለ የገባው ሰው የለም።"" ትራምፕ በዚህ የትሩዝ ቀርፋፋ አጓጓዝ ደስተኛ አይደሉም። ምንም እንኳ ከ750 ሺህ በላይ ተከታዮች ቢያፈሩም ከአንድ ወር በላይ ምንም ነገር አልጠፉም። የሲሊከን ቫሊይ ግዙፍ ድር አምባዎችን ይፎካከራል የተባለው ትሩዝ ለጊዜው ቆሞ መራመድ የተሳነው ይመስላል።" https://www.bbc.com/amharic/news-60979022 +sports የዓለማችን የሜዳ ቴኒስ ኮከብ ራፋኤል ናዳልን የገጠሙት የ97 ዓመቱ አዛውንት የሜዳ ቴኒስ ጨዋታን ከነፍሳቸው የሚወዱት ዩክሬናዊው ስታኒስላቭስኪ ለ50 ዓመታት ሜዳ ቴኒስ እየተጫወቱ ቆይተዋል። አሁን ዕድሜያቸው 97 ዓመት ደርሷል። ነገር ���ን አሁንም ጨዋታውን አላቆሙም። ሰሞኑን ከ20 ጊዜ በላይ የዓለማችንን ታላቁን የሜዳ ቴኒስ ውድድርን ካሸነፈው ስፔናዊ ኮከብ ራፋኤል ናዳል ጋር ያደረጉት ጨዋታ በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በእጅጉ መነጋገሪያ ሆኗል። https://www.bbc.com/amharic/news-59372312